Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የራያ ተወላጆች በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ

$
0
0
(ይህ ዜና ቪዲዮ አለው እዚህ ይጫኑ) በትግራይ ክልል መንግስት ላለፉት 27 ዓመታት በቅኝ ግዛት ውስጥ መሆናችን ይብቃ ያሉ የራያ ተወላጆች ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጽሕፈት ቤት ደጃፍ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ:: በቅድሚያ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ደጃፍ ላይ ተገኝተው የራያን ሕዝብ ብሶት ያሰሙት እነዚሁ የአዲስ አበባ እንዋሪ የራያ ተወላጆች ቀጥሎም ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ደጃፍ በማምራት […]

አቶ በረከት ስምዖን ለፍርድ እንዲቀርብ ተጠየቀ

$
0
0
(ይህ ዜና ቪዲዮ አለው እዚህ ይጫኑ)  በቅርቡ ከብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት የታገደው አቶ በረከት ስምዖን ለፍርድ እንዲቀርብ የጎንደር ሕዝብ ጠየቀ::: የጎንደር ሕዝብ ዛሬ አርቲስትና አክቲቭስት ታማኝ በየነን በጎንደር ቴዎድሮስ ስታዲየም ለመቀበል በወጣበት ወቅት ነው ይህን ጥያቄ ያቀረበው:: “በረከት ስምዖን በአማራ ሕዝብ ላይ ግፍ እና በደል ስላደረሰ ለፍርድ ይቅረብልን” ሲሉ መፈክር የያዙት እነዚሁ የጎንደር ነዋሪዎች ለታማኝ […]

ዶ/ር አብይ አህመድ አሰብ ገቡ

$
0
0
ቤጂንግ ከቻይና አፍሪካ የትብብር ፎረም ሲካፈሉ የሰነበቱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እግረመንገዳቸውን ለሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት  አሰብ መግባታቸው ታወቀ:: ስልጣን ላይ ከወጡ በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ኤርትራ ያቀኑት ዶ/ር አብይት በፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አቀባበል ተደርጎላቸዋል::   ከዶ/ር አብይ በተጫምሪም የሶማሊያው ፕሬዚዳንት  ሞሃመድ አብዱላሂ ፋርማጆም ኤርትራ የገቡ ሲሆን ሶስቱም ሃገራት የሶስትዮሽ ውይይት  እንደሚያደርጉ ተገልጿል:: በዚህ […]

የእነ ነውር ጌጡ መግለጫ በራያ ሕዝብ ላይ –አቻምየለህ ታምሩ

$
0
0
ሕወሓት የሚባለው የቅሚያና ግድያ ድርጅት በራያ ለተነሳውና «በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን» ለቀረበው የማንነት ጥያቄ መልስ የሚሆን መግለጫ አመሻሹን አውጥቷል። ነውር ጌጡ የሆነው ይህ የማፍያ ድርጅት በመግለጫው እንዳሰፈረው በራያ የተነሳውን ትግሬ አይደለንም የሚለውን የማንነት ጥያቄ አውግዞ ጥያቄው በማይመለከተው አካል የቀረበ «የትግራይ ማንነት ጥያቄ» አድርጎ አቅርቦታል። የትም ቦታ በተካሄደ የማንነት ጥያቄ ግን ትግሬዎችን ትግሬ አይደላችሁም ብሎ የጠየቀ የለም። ያልነበረ […]

ከዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲ እና ሉአላዊነት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

$
0
0
ዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲ እና ሉአላዊነት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የስድስት ወር መደበኛ ስብሰባው በሓምሌ 26 እና 27/2010 ዓ/ም በትግራይ ዋና ከተማ መቐለ አካሂደዋል። ዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲ እና ሉአላዊነት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባው ባለፉት ስድስት ወራት እንደ ፓርቲ የነበረውን የአፈጻጸም ስራ፣ ክልላዊ እና አገራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ የተወያየ ሆኖ የቀጣይ የስድስት ወራቶች ፓለቲካዊ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል። […]

ዲያስፖራውና የዜግነት ጥያቄ |ባይሳ ዋቅ-ወያ

$
0
0
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓቢይ ዲያስፖራዎች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው በመካሄድ ላይ በሚገኘው የለውጥ ሂደት እንዲካፈሉ ጥሪ ካደረጉበት ጊዜ ጀምሮ ብዙ ኢትዮጵያውያን ወዳገራቸው መመላሰቸውን ሳስተውል፣ እነዚህ ተመላሾች በተለይም የፖሊቲካ ድርጅት መሪዎችና አክቲቪስቶች ከብዙ ዓመታት በኋላ በሰላም መመለሳቸውን እንጂ ከተመለሱ በኋላ በፖሊቲካው እንቅስቃሴ ሂደት ውስጥ ሊያጋጥማቸው የሚችለውን መሰናከል በቅጡ ያስተዋሉት ስላልመሰለኝ፣ አንዳንድ ጠቃሚ ማስታወሻዎችን ለማስቀመጥ ወሰንኩ። ይህን ሆ […]

የ ዕለቱ አጫጭር ዜናዎች

$
0
0
____ የሶማሌው ፕሬዚዳንት መሐመድ ፈርማጆ ከኦጋዴን ነጻ አውጪ ግምባር መሪ አቶ መሐመድ ኦማር ኡስማን እና ከዋና ጸሐፊው አብድራሂም ማህዲ ጋር በኤርትራ ተገናኝተው መከሩ:: ሃሩን ማሩፍ በትዊተር ገጹ እንደዘገበው ፈርማጆ የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግምባር መሪዎችን ወደ መቋደሾ ጋብዘዋቸዋል:: ___ በትናንትናው እለት በአዲስ አበባ የተካሄደውን የራያ ተወላጆች ሰልፍ በተመለከተ የትግራይ ክልል መንግስት ትናንትናውኑ መግለጫ በማውጣት “በአዲስ አበባ […]

በኤርትራና ጅቡቲ መካከል ያለውን ውዝግብ ለመፍታት ኢትዮጵያ ሽምግልና ልትጀምር ነው

$
0
0
የኢትዮጵያ፣ የኤርትራና የሶማሊያ መሪዎች በተለያዩ መስኮች በጋራ ለመስራትና በኤርትራና በጂቡቲ መካከል ቆየውን አለመግባባት መፍትሄ እንዲያገኝ ለማድረግ እንደሚጥሩ ተስማምተዋል:: የሦስቱ ሃገራት መሪዎች አሥመራ ውስጥ ባደረጉት ውይይትና በደረሱት ስምምነት በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ፣ በባህል፣ በማህበራዊ እና በደህንነት ጉዳዮች በጋራ ለመስራት ከመግባባት ላይ ደርሰዋል። በተጨማሪም የቀጣናው አንድ አካል በሆነችው በጂቡቲና በኤርትራ መካከል ለረጅም ጊዜ የቆየው የድንበር ችግር መፍትሄ እንዲያገኝ ለማስቻል እንደሚጥሩም […]

ዶ/ር አብይ አህመድ ወደ አዲስ አበባ ከመመለሳቸው አስቀድሞ በኤርትራ የኢትዮጵያ ኢምባሲን መርቀው ከፈቱ

$
0
0
በኤርትራ ለሁለት ቀናት ጉብኝት ያደረጉት ዶ/ር አብይ አህመድ ዛሬ ወደ አዲስ አበባ ከመመለሳቸው አስቀድሞ በኤርትራ የኢትዮጵያ ኤምባሲን መርቀው ከፈቱ:: ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ኢምባሲውን መርቀው ሲከፍቱ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት ኤምባሲው ተገኝተው ነበር:: ከሃያ አመት በላይ ተዘግቶ የቆየው በኤርትራ የኢትዮጵያ ኢምባሲም በዛሬው ዕለት ሥራውን በይፋ ጀምሯል:: በአየርላንድ የኢትዮጵያ ባለ […]

የሃላባ አካባቢ ነዋሪዎች አዋሳ ድረስ በመሄድ የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

$
0
0
ደቡብ ኢትዮጵያ ሃላባ አካባቢ ሰሞኑን ሰላም አልነበረም:: የአካባቢው ነዋሪዎች መሐመድ ኑርና አካባቢውን ሕዝብ በመበደል የሚታወቁ ባለስልጣናት እንዲነሱና አስተዳዳሪዎች እንዲቀየሩ በመጠየቅ ከተማዋ ውስጥ ከፍተኛ ግጭት ተቀስቅሶ ነበር:: ቃጠሎዎች ነበሩ:: ቁጥሩ ያልታወቀ ንብረትም ወድሞ ነበር:: ዛሬ ደግሞ  «በሀገሪቱ የታየው ለውጥ ወደኛ አልደረሰም» ያሉ የሀላባባ አካባቢ ነዋሪዎች ወደ አዋሳ በመሄድ፣ በደቡብ ክልል ምክር ቤት ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ […]

ኢንጂነር ስመኘው በቀለን ሞት አስመልክቶ ሊሰጥ የነበረው መግለጫ ለ3ኛ ጊዜ ተራዘመ

$
0
0
(ዘ-ሐበሻ) የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 አዲስ አበባ A 29722 በሆነው ቶዬታ ላንድ ክሩዘር መኪና ውስጥ በአዲስ አበባ አብዮት አደባባይ አካባቢ መኪናቸው ውስጥ ሞተው የተገኙት የኢንጂነር ስመኘው ሕልፈት አሁንም በአነጋጋሪነቱ በቀጠለበት ወቅት ስለ ሞታቸው ምክንያት ፌዴራል ፖሊስ እና ጠቅላይ አቃቤር ህግ ይሰጡታል የተባለው መግለጫ ዛሬም ለ3ኛ ጊዜ መራዘሙ ጉዳዩን የበለጠ እያጦዘው ሄዷል:: ረቡዕ ግንቦት 8 ቀን […]

ፖሊስ ኢንጂነር ስመኘው ራሳቸውን ማጥፋታቸውን ገለጸ

$
0
0
ለሶስት ጊዜያት ሲራዘም የቆየው የኢንጂነር ስመኘው ሞት ምክንያት መግለጫ ዛሬ ተካሄደ:: የትናንቱ መግለጫ ሲሰረዝ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ብርሃኑ ጸጋዬ ስላልተመቻቸው ነው የሚል ምክንያት ተሰጥቶ የነበረ ቢሆንም በዛሬው ዕለት ጠቅላይ አቃቤ ህጉ ሳይገኙ መግለጫው መሰጠቱ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው:: ኢንጅነር ስመኘው በቀለ ራሳቸውን ማጥፋታቸውን የፖሊስ የምርመራ ውጤት እንደሚያሳይ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ያስታወቀ ሲሆን ሞተው የተገኙበት መኪና ውስጥ […]

በኢንጂነር ስመኘው ሞት ዙሪያ የፌደራል ፖሊስ መግለጫ

$
0
0
በኢንጂነር ስመኘው ሞት ዙሪያ የፌደራል ፖሊስ መግለጫ

የጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት ሁለተኛ ታሪካዊ ጉባኤውን በተሳካ ሁኔታ አጠናቀቀ

$
0
0
የጎንደር ሕብረት ጋዜጣዊ መግለጫ የጎንደር ህብረት ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ላለፉት አራት አመታት በግፍ ስርአት ሰቆቃ ለደረሰበት ህዝባችን በሁለንተናዊ መልኩ ለነፃነት፣ ለፍትህና ለዲሞክራሲ በሚደረገው ትግል እርዳታ በማድረግ የሚያኮራ ታሪካዊ ሥራ ሰርቷል፡፡ በተለይ በአሁኑ ሰአት ከአሰቃቂ የጨለማ አምባገነን ሥራዓት ተላቆ የኢትዮጵያ ህዝብ የተስፋ ጭላንጭል በማየቱ በደስታ በተሞላበት ወቅት ይህን ሁለተኛ ታሪካዊ ጉባኤውን ከነሃሴ 25/2010 ዓ.ም እስከ ነሃሴ […]

አጫጭር ዜናዎች

$
0
0
የአርበኞች ግንቦት 7 አመራር አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ቀለበት አሰሩ:: አቶ አንዳርጋቸው ቀለበት ያሰሩት ከልጆቻቸው እናት ከወይዘሮ የምስራች ኃይለማርያም ጋር ነው:: ወይዘሮ የምስራች አቶ አንዳርጋቸው በታሰሩበት ወቅት እንዲፈቱ ጸሐይም ብርዱም እየተፈራረቀባቸው ሲለፉ ነበር:: በመንገድ ላይ ፒትሽን ከማስፈረም አንስቶ የ እንግሊዝ ባለስልጣናት ድረስ በመግባት እንዳርጋቸው እንዲፈታ ታላቅ ሥራ ሰርተዋል:: አንዳርጋቸው እና ወ/ሮ የምስራች ለረዥም ጊዜ ተለያይተው የቆዩ […]

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ስያሜና ባንዲራው ተቀየረ

$
0
0
የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ሰንደቅ አላማ ወደ ቀድሞው ተቀየረ:: በቅርቡ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የሆኑት አቶ ሙስጠፋ ዑመር በፌስቡክ ገጻቸው የክልሉ ሰንደቅ አላማ መቀየሩን ገለጹ:: አቶ ሙስጠፋ “በሶማሌነታችንና በኢትዮጵያዊነታችን መሀከል ተቃርኖ የለም” ብለዋል። የቀድሞው ሰንደቅ አላማ ተመልሶ ሥራ ላይ መዋል መጀመሩን በተመለከተም “የሶማሌ ክልል ህዝቦች ነን፤ ከፊትም ከኋላም ቅጥያ የለም፤ የቀደመው ሰንደቅ አላማ ተመልሷል:: […]

ባቡር ወዲያ ማዶ ሃዲድ ወዲህ ማዶ |በዋሲሁን ተስፋዬ

$
0
0
የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ሃዲድ የማንጠፍ ስራ ወደመጠናቀቁ በተቃረበበት ሰአት ላይ ሜቴክና የምድር ባቡር ድርጅት ሃይለኛ ውዝግብ ውስጥ ገቡ ። የውዝግቡ መነሻ ሜቴክ ለአዲስ አበባ ቀላል ባቡር የሚሆኑ ሰው ማጓጓዣ ፉርጎዎችን ማምረት ያለብኝ እኔ ነኝ አለ ። ምድር ባቡር ደግሞ እነዚህ ሰው ማጓጓዣ የከተማ ባቡሮች ኢንተርናሽናል ደረጃቸውን የጠበቁና የሰው ማመላለሻ ፉርጎዎችን በመስራት ልምድ ባለው ድርጅት […]

እዉነት ቁጥሩ ስንት ይሆናል? መምሰል እና መሆን ይለያያል! –ታዬ ደንደአ

$
0
0
አዉነት አንድ ቢሆንም በተለያዬ ቅርፅ ይገለፃል። ከወንጀል ምርመራ ጋር ተያይዞ እዉነትን በሦስት ከፍሎ ማዬት ይቻላል። አንደኛዉ ህዝባዊ እዉነት ነዉ። ይህ እዉነት አብዘኛዉ ህዝብ “እዉነት” ብሎ የሚየምንበት ድምዳሜን ይመለከታል። ለምሳሌ በልብ ድካም የሞተ ሰዉ “ቡዳ በልቶት ሞተ” ሊባል ይችላል። ሶቅራጤስ፣ ታላቁ የግሪክ ፈላስፋ በሞት የተቀጣዉ በህዝባዊ እዉነት ነዉ። በቅርቡ ሻሻመኔ ከተማ ላይ ያገጠመዉም ለዝህ ጥሩ ማሳያ […]

የዕለቱ አጫጭር ዜናዎች

$
0
0
__ ኤርትራ መቀመጫውን አድርጎ ሲታገል የከረመው የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደህሚት) ወደ ኢትዮጵያ ጉዞውን መጀመሩን ምጽዋ ቱብ በፎቶ አስደግፎ ዘግቧል:: ከኦነግ ጋር ለመደራደር ለማ መገርሳና ወርቅነህ ገበየሁ; ከአማራ ዴሞክራሲዊ አንድነት ንቅናቄ ጋር ለመደራደር ንጉሱ ጥላሁን ወደ አስመራ ሄደው የነበሩ ሲሆን ከደህሚት ጋር ለመደራደር ግን የሕወሃት ሰዎች አለመሄዳቸው በተለይም ለውጥ የማይፈልገው የሕወሃት አንጃ ቡድን ተከፋይ ወገኖችን […]

ኢንጂነር ስመኘው ራሳቸውን ነው ያጠፉት ሲል ምርመራ ያደረገው ኮማንደር ዓለማየሁ በቂሊንጦ እስር ቤት ገራፊ እንደነበር ተጋለጠ

$
0
0
አግባው ሰጠኝ በ1996 የኢዴፓ- መድህን አባል… በ1997 ምርጫ ቅንጅትንችወክሎ በመተማ እና ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ አሸንፎ የፓርላማ አባል ነበር፡፡ ከዚያም አንድነት ፓርቲን ከመሠረቱት አንዱ የነበረ ሲሆን ከአንድነት ወጥተን ሠማያዊን መስርቶ የሠማያዊ ፓርቲ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የሠሜን ጎንደር ዞን የፓርቲው ሰብሳቢ በነበረበት ወቅት የኢትዮጵያ ድንበር ተቆርሶ ለሱዳን እየተሸጠ ነው በማለቱ ብቻ በሽብር ተከሶ እስር ቤት ገብቶ ሲሰቃይ […]
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>
<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596344.js" async> </script>