Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የዕለቱ አጫጭር ዜናዎች

$
0
0
አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ዙምባቤ በሄዱበት ወቅት ከኮለኔል መንግስቱ ሃይለማርያም ጋር ፎቶ የተነሱበት ቦታ ጀርባ ያለውን መኖሪያ ቤት የመንግስቱ ሃይለማርያም ነው ተብሎ በአንዳንድ የማህበራዊ ድረገጾች የሚወራው ውሸት መሆኑን የኮ/ል መንግስቱ ሃይለማርያም ልጅ አስተባበለች:: ትዕግስት መንግስቱ የተወራውን ስታስተባብል ” ይህንን ቆንጆ ቤት ለቤተሰባችን ስለተመኛችሁልን እናመሰግናለን:: መጥተው ያዩ ይመስክሩ:: ይህ አይደለም የመንግስቱ መኖሪያው :: አንዳርጋቸው ፅጌና ገነት አየለ […]

የአዋሳ ከተማ ከንቲባ ፍርድ ቤት ቀረቡ

$
0
0
በአዋሳ ከተማና አካባቢዋ በአንዳንድ የሲዳማና የወላይታ ብሄረሰብ መካከል ግጭት እንዲፈጠር በማድረግ፥ የበርካታ ሰዎች ህይወት እንዲጠፋና ዜጎች እንዲፈናቀሉ በማድረግ እጃቸው አለበት በሚል  ተጠርጥረው የታሰሩት የአዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ቴዎድሮስ ገቢባና የቀድሞውን የሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ አዱላን ጨምሮ 100 ግለሰቦች ላይ ክስ ተመሰረተ። በአዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፌደራል ተዘዋዋሪ ችሎት  እየታየ ያለው ይኸው ክስ በሁለት […]

ቢቢሲ ለአና ጎሜዝ “ከዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር የፍቅር ግንኙነት እንዳልዎ ይታማሉ፡፡”የሚል ጥያቄ አቀረበ

$
0
0
ከምርጫ 97 ጋር ተያይዞ ከኢትዮጵያውያን ጋር ጥሩ ወዳጅነትና ትውውቅ ያላቸው አና ጎሜዝ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ የቢቢሲ ጋዜጠኛ “ከዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር የፍቅር ግንኙነት እንዳልዎ ይታማሉ” የሚል ጥያቄ አቀረበላቸው:: አና ጎሜዝ  ዘለግ ካለ ሳቅ በኋላ ሲመልሱም “ይሄ ፌዝ መሆን አለበት። ብርሃኑን አውቀዋለሁ። ባለቤቱን ዶክተር ናርዶስም አውቃታለሁ። ኢትዮጵያ እያለሁ ነው የማውቃት። እሷም ታውቃለች። አሁን የምነግርህን ታሪክ […]

ራያ በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ነች |ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሚኒሻና መከላከያ ሠራዊት በከተማዎች ተበትኗል

$
0
0
የዶ/ር ደብረጽዮን  የትግራይ አስተዳደር በራያ ዋጃ ጥሙጋ ከተማ ከፍተኛ የሆነ የመከላከያ ሠራዊት እና የትግራይ ሚኒሻዎችን በማሰማራት ሕዝቡን በማሸበር ላይ መሆኑ ታወቀ:: የራያ ሕዝብ የማንነት ጥያቄ ከ እለት ወደ ዕለት እየተጋጋለ በመሄዱ የደብረጽዮን አስተዳደር በተለይም በራያ የተለያዩ ከተሞች የራያ ተወላጆች መሬታቸውን ለትግራይ ተወላጆች እንዲሸጡ በማግባባት ላይ ይገኛል:: በትግራይ ቴሌቭዥን ሳይቀር መሬታቸውን ለሚሸጡ የራያ ተወላጆች ከፍተኛ ገንዘብ […]

በኢንጂነር ስመኘው አሟሟት ዙሪያ ሊሰጥ የነበረው መግለጫ ለሁለተኛ ጊዜ ተራዘመ

$
0
0
በአፍሪካ ትልቁ የኃይል ማመንጫ እንደሚሆን የሚነገርለት ግዙፉ የአባይ ግድብ ሥራ አስኪያጅ መሃንዲስ ስመኘው በቀለ አሟሟት ዙሪያ ዛሬ አርብ ይሰጣል የተባለው መግለጫ ለሁለተኛ ጊዜ ተራዘመ:: ዘ-ሐበሻ ከሶስት ቀን በፊት ስለኢንጂነር ስመኘው አሟሟት ዛሬ አርብ ይሰጣል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው መግለጫ የኢንጂነሩ አሟሟት በተመለከተ የሚሰጠው ምክንያት ብዙዎችን ላያሳምን እንደሚችል የዘ-ሐበሻ ምንጮችን ጠቀሰን መዘገባችን ይታወሳል:: የፌዴራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ […]

ታማኝ በየነ ዳግም ተዘፈነለት

$
0
0
ታማኝ በየነ ከ22 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነገ ቅዳሜ ጠዋት አዲስ አበባ የሚደርስ ሲሆን ዛሬ ወዳጆቹና የሙያ አጋሮቹ ከዋሽንግተን ዲሲ አሸኛኘት አድርገውለታል:: በተጨማሪም ታማኝ ላበረከተው ታላቅ አስተዋጽኦ ይገባዋል ታማኝ የተሰኘ ነጠላ ዜማ ዝነናው ድምጻዊ መሐሪ ደገፋው ለቆለታል:: ይመልከቱት::

በጠለምት ሰላማዊ ሰልፍ ተደረገ

$
0
0
በሰሜን ጎንደር ዞን የጠለምት ወረዳ ነዋሪዎች የመልካም አስተዳደር እና የመሰረተ ልማት ችግሮች እንዲፈቱ በሰልፍ ጠየቁ። የአቶ ገዱ አንዳርጋቸውን እና የዶ/ር አብይን ምስል የያዙት እነዚሁ ሰልፈኞች የሚያወራልን ሳይሆን የሚሰራልን መሪ እንፈልጋለን ብለዋል:: የዶ/ር አብይ አመራርን እንደሚደግፉ የገለጹት እነዚሁ የጠለምት ነዋሪዎች ከተከዜ ሃይድሮ ፓወር 90% መጠቀም ይገባናል የሚል ጥያቄም አንስተዋል:: እኛ ጠለምቶች የልማት ተደራሽነታችንን ለማግኘትት ከማንነታችን በላይ […]

የዕለቱ አጫጭር ዜናዎች

$
0
0
አርበኞች ግንቦት 7 በኤርትራ ያለውን ወታደራዊ ካምፕ ዘግቶ ወታደሮቹ በወደ ኢትዮጵያ ጉዞ መጀመራቸው ታወቀ:: በሁመራ በኩል ወደ ሃገር ቤት በከባድ መኪናዎች ታጅበው ወታደሮቹ ጉዞ መጀመራቸውን የዘገቡት የኤርትራ ሚዲያዎች ናቸው:: አርበኞች ግንቦት 7 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ የትጥቅ ትግል ማቆሙን ማስታወቁ ይታወሳል። በትናንትናው ዕለት አስመራ የነበሩ የድርጅቱ የሚዲያ አባላት በአውሮፕላን አዲስ አበባ […]

የጭን ፈረስ ጉድጓድ እና የገረብ ሰገ የውሃ ግድብ በመበላሸቱ በመቀሌ ከ500 ሺህ በላይ ህዝብ ለውሃጥም፣ ለበሽታ ተጋልጧል

$
0
0
“የጭን ፈረስ ጉድጓድ እና የገረብ ሰገ የውሃ ግድብ በመበላሸቱ በመቀሌ ከ500 ሺህ በላይ ህዝብ ለውሃጥም፣ ለበሽታ ተጋልጧል” ሲሉ የቀድሞ የሕወሓት ታጋይ የነበሩት አቶ አሰገደ ገብረሥላሴ ገለጹ:: አቶ አሰገደ “የትግራይ ህዝብ በውሃ ጥምና በሌሎች ማህበራዊ ችግሮች እተሳቃዬ እነ ኣለም ገብረዋህድ ግን ለሆዳቸውና ለስልጣን ጥማቸው ለማርካት ይራራጣሉ ።” ሲሉ ከሰዋል:: “በመቀለ ከተማ የሚጠጣ እና ንጽህና ለመጠበቅ ውሃ […]

ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ ወደ አሜሪካ ሊመጡ ነው

$
0
0
(ዘ-ሐበሻ) የጠቅላይ ሚኒስተርነታቸውን በትረ ስልጣን ከያዙ አንድ መቶ ሃምሳ ቀናቸውን ያስቆጠሩት ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ በመስከረም ወር አጋማሽ ላይ ወደ አሜሪካ እንደሚመጡ የመረጃ ምንጮች ጠቆሙ:: ዶ/ር አብይ አህመድ በኒውዮርክ በሚደረገው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 73ኛ ጉባኤ ላይ የሚገኙ ሲሆን ከጉባኤው ጎን ለጎንም በኒውዮርክ እና አካባቢው ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጋር እንደሚገናኙ ተነግሯል:: በአሁኑ ወቅት በኒውዮርክ የኢትዮጵያ ኮንሱላ […]

ታማኝ በየነ ኢትዮጵያ ሲገባ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት |የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ መሪ ለታማኝ ‘ማስጠንቀቂያ’ጻፈ

$
0
0
ሕወሃትን ጫካ ውስጥ እያለ ጀምሮ ለኢትዮጵያ አንድነት የሚበጅ ድርጅት እንዳልሆነ በመግለጽ ሲቃወም የነበረው ታማኝ በየነ ከ22 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አዲስ አበባ ገባ::: ታማኝ አዲስ አበባ  ቦሌ አየር ማረፊያ ዛሬ ጠዋት ከባለቤቱ ድምጻዊት ፋንትሽ በቀለ ጋር ሲገባ በወዳጆቹና በሙያ አጋሮቹ ደማቅ አቀባበል አድርገውለታል:: ሃገሬ ከገባው መጀመሪያ መሄድ የምፈልገው ብሄራዊ ትያትር ነው ባለው መሰረት ቃሉን እንዲጠብቅ […]

“ያመነ ይድናል!”ሸፍጥ ለማይለየው ፖለቲካ አይሰራም። (ከይገርማል)

$
0
0
ሀገራችን ከአስከፊው የወያኔ አፋኝና ዘረኛ አገዛዝ ተላቃ በለውጥ ጸዳል ደምቃለች ብለው የሚያምኑ ኢትዮጵያውያን ብቻ አይደሉም። የተጀመረው ተስፋ ሰጪ ለውጥ እንዳስደሰታቸው በመግለጽ አሜሪካንን ጨምሮ ብዙ ሀገሮች ለውጡ እንከን ሳይገጥመው እንዲቀጥል ይጠቅማል የሚሉትን ምክር እየለገሱ ነው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ብድርና እርዳታ ፈቅዷል። በጠላትነት ይተያዩ የነበሩት ኢትዮጵያና ኤርትራ ካለሦስተኛ ወገን አደራዳሪ እርቅ አውርደው ያለፉት የመለያየት ግዚያት ብዙ የጎዱን […]

ትግራይ – የኢትዮጵያ ሰሜን ኮርያ –ነፃነት ዘለቀ

$
0
0
በአንድ “ፌዴራል” ሥርዓት ሥር በሚተዳደሩ ክልሎች መካከል ትግራይን እንደፈሳች ዝንጀሮ ተገልላ በባዕድነት እንድትኖር እያደረጉ ያሉ አኩራፊዎች አንድ ካልተባሉ  ማለትም ሽማግሌ ተገኝቶ ዕርቅና ሰላም እንዲወርድ ካልተደረገ አካሄዳችን ግንጥል ጌጥ እንደሆነ መቀጠሉ ነው፡፡ የትግራይ ሕዝብ ከቀሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ ተለይቶ መደሰትም ሆነ መሰቃየት እንደማይገባው የምንስማማ ይመስለኛል፡፡ እንደሀገር ሁላችንም የጋራ የሆነ የአሁንና መፃዒ ዕድል ያለን አንድ ሕዝብ ነንና በነዚህ […]

የስደት ጉዳያቸው ያላለቀላቸው በኢትዮጵያ ባለው የለውጥ ተስፋ ተያይዞ ለሚያነሱት ስጋት የጠበቃ ምላሽ

$
0
0
የስደት ጉዳያቸው ያላለቀላቸው በኢትዮጵያ ባለው የለውጥ ተስፋ ተያይዞ ለሚያነሱት ስጋት የጠበቃ ምላሽ

የዕለቱ አጫጭር ዜናዎች

$
0
0
  የብፁእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳስት ዘኢትዮጵያ የ30ኛ ዓመት ፕትርክናቸውን የኢትዮጵያ ፕሬዚደንት የነበሩት ግርማ ወልደጊዮርጊስ አከበሩላቸው:: ይህ በዓል “ዘንድሮ ለቤተክርስቲያናችን እጥፍ ድርብ ክብር አገኘንበት ዘመን በመሆኑ በድምቀት ሊከበር በተገባው ነበር” የሚሉት መል አከ ሰላም አባገብረሚካኤል “ከባለፉት ፓትርያርኮች እረጂም ዘመን የቆዩት ምንም እንኳን በስደት የሰማዕትነት ጊዜ ቢሆንም እግዚአብሔር ብዙ ሥራ በጸሎታቸው ሰርቷል:: በዓሉ […]

በጦር መኮንኖች ሲዘረፍ የከረመው ሜቴክ ለሁለት እንዲከፈል ዶ/ር አብይ ት ዕዛዝ ሰጡ

$
0
0
በኢትዮጵያ ታትሞ የሚወጣው የ እንግሊዘኛው አዲስ ፎርቹን ጋዜጣ ምንጮቼ ነገሩኝ ብሎ ባሰራጨው ዜናው ዶ/ር አብይ አህመድ በጦር መኮንኖች ሲዘረፍ ከርሟል የተባለውን ሜቴክን ከሁለት እንዲከፈል አዘዋል:: ካለ አግባብ ያለጨረታ የወሰዳቸውን ብሄራዊ ፕሮጀክቶች መዘግየት፣ በሀብት ብክነትና በሙስና ተጠያቂ ሲደረግ የቆየው ሜቴክ አሁን ያሉበትን ችግሮች ቀርፎ የተሰጠውን ሀላፊነት በአግባቡ እንዲወጣ በሚል ነው ለሁለት እንዲከፈል ትእዛዝ የተላለፈው፡፡ በመከላከያ ሚኒስትሩ […]

በሚኒሶታ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ቀን ፌስቲቫል ተከበረ

$
0
0
በፈረንጆቹ አቆጣጠር እሁድ ሴፕቴምበር 2, 2018 ዓ.ም በሚኒሶታ ደማቅ የሆነ የኢትዮጵያ ቀን ፌስቲቫል ተካሄደ:: አዘጋጆቹ ካወጡት መግለጫ መረዳት እንደተቻለው በሚኒሶታ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገው የኢትዮጵያ ቀን ፌስቲቫል እጅግ ያማረ፣ የደመቀ፣ እጅግ የተዋጣለት ነበር::  “የሚኒሶታ ኢትዮጵያውያን የሚያኮራ ታሪክ ጽፈናል:: በስታዲየሙ ውስጥ ይፈላ የነበረው ቡና ሽታ እና የዕጣኑ ማዕዛ ዝግጅቱን አውዳመት አስመስሎት ነበር:: ምግቦቹ ልዩ ነበሩ:: የኢትዮጵያው […]

በደቡብ ክልል በተከሰተ የመሬት መንሸራተት የአስራ ሁለት ሰዎች ሕይወት አለፈ

$
0
0
በደቡብ ክልል በዳውሮ ዞን ኢሰራ ወረዳ ኦፋ ቀበሌ ትናንት ማታ በግምት ዘጠኝ ሰዓት አከባቢ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት የ አስራ ሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ:: የወረዳዉ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃለፊ ሻምበል አልታዬ አለሙ እንደገለጹት ከሞቱት 12 ሰዎች መካከል የአስሩ አስከሬን ተገኝቷል; የሁለቱ ደግሞ በፍለጋ ላይ ነው ብለዋል:: በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸዉን አራት […]

Zehabesha Daily Ethiopian News September 5, 2018

$
0
0
Zehabesha Daily Ethiopian News September 5, 2018

የዕለቱ አጫጭር ዜናዎች

$
0
0
ሕይወቷን ከእናቷ ጋር በዶሮ መኖሪያ ቤት ስትመራ የነበረችው ታዳጊ አብስራ አማረ የ1 ሚሊዮን ብር ቤት ተገዝቶ ሊሰጣት ነው፡፡ በቅርቡ ቅርንጫፉን በኢትዮጵያ የከፈተው ዓለም አቀፉ ፒዛ ሀት የልጅቷን ህይወት በቴሌቭዥን ከተመለከተ በኋላ በአንድ ሚሊዮን ብር ቤት ገዝቶ እንደሚሰጣት ቃል ገብቷል::፡፡ እስከዚያው ድረስ ታዳጊዋንና እኗቷን በሆቴል እንደሚቆዩም ማድረጉንም ፒዛ ሃት አስታውቋል::፡፡ ለታዳጊዋ እናት ወ/ሮ ፋንታናሽ አማረም በፒዛ […]
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live