Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ባለስልጣናት ከተማ ውስጥ ቪ8 መኪናዎችን እንዳይሄዱ ተከለከሉ

$
0
0
ዶ/ር አብይ አህመድ በ2011 የኢትዮጵያ አመት እንደ እቅድ የያዙት የመንግስትን ወጪ መቆጠብ እንደሆነ በተደጋጋሚ ሲናገሩ ቆይተዋል:: በዚህም መሰረት ከዛሬ ጀምሮ ማንኛውም የመንግስት ባለስልጣን በከተማ ውስጥ ለሥራ በሚንቀሳቀስበት ወቅት ቪ8 መኪኖችን እንዳይጠቀም ተከልክሏል:: መንግስት አንድ ቪ8 መኪና ለመግዛት እስከ 5.5 ሚሊዮን ብር እንደሚያወጣ የተገለጸ ሲሆን መኪኖቹ ነዳጅ ስለሚበሉ ከመስክ ሥራ ውጪ ማንኛውም የመንግስት ባለስልጣን ለከተማ ውስጥ […]

በአዲስ አበባ አራት ቦታዎች ድንገተኛ የህገወጥ ገንዘብ ፍተሻ ተደረገ

$
0
0
የውጭ ምንዛሬ በህገወጥ መንገድ ይመነዘርባቸዋል ተብሎ በሚወራባቸው በጋንዲ ሆስፒታል፣ በኢትዮጵያ ሆቴል፣ በቴሌ ባር እና በአሜሪካን ጊቢ አካባቢ ባሉ ሱቆች ፖሊስ ድንገት ባደረገው ፍተሻ በርካታ የውጭ ና የሃገር ውስጥ ገንዘብ ተይዟል:: ዛሬ ድንገት በተደረገው ፍተሻ በርካታ ሱቆችም መታሸጋቸው ታውቋል:: የፌደራል ፖሊስ እንዳስታወቀው በዛሬው ድንገተና ፍተሻ 57 ሺህ የአሜሪካ ዶላር፣ ከ 2ሺ በላይ ዩሮ፣ ከ 5 ሚሊዮን […]

ጅምሩ ጥሩ ነው –ግን እነ በረከትና ካሣ ብቻ አይደሉም! –ነፃነት ዘለቀ

$
0
0
ነፃነት ዘለቀ (netsanetz28@gmail.com) ብዙ ከዘገዬ በኋላም ቢሆን ብአዴን ነፍስ እያወቀ መምጣቱን በግልጥ እያየን ነው፡፡ ከዘላለም ባርነት የአንድ ቀን ነፃነት እንደሚሻልም እየተገነዘበ እንደሆነ በአንዳንድ ያልተለመዱ መልካም ተግባራቱ እየገለጸ ነው፡፡ ለምሣሌ በድኩማኖቹ ወያኔዎች የማንአለብኝነት ግልጽ ጣልቃ ገብነት ምክንያት በመካከሉ ተሰግስገው በነበሩ የሕወሓት ተወካዮች በነበረከት ስምዖንና ካሣ ታደሰ (ጥንቅሹ) የፊጥኝ ታስሮ ሲሰቃይ መኖሩን ተገንዝቦ እንደተባለው እስከፊታችን መስከረም 2011 […]

ሀገራችን ከገባችበት አዘቅት እንድትወጣ ከሚያግዙ ነጥቦች ጥቂቶቹን እነሆ! –ምሕረት ዘገዬ (አዲስ አበባ)

$
0
0
ከአሁኑ የሕወሓት/ኢሕአዴግ መንግሥት ጋር ሲወዳደሩ የደርግና የቀ.ኃ.ሥላሤ መንግሥታት በአጋጣሚ ካልሆነ እንዳሁኑ ዘመን በመርህ ደረጃ በጎሣና በነገድ የተዋቀሩ እንዳልነበሩ ብዙዎች ይመሰክራሉ፡፡ ስለዚህ ከነዚህ ያለፉ መንግሥታት በሕይወት ያሉ የልዩ ልዩ ሙያ ባለቤቶችን አሁን ከያሉበት ጋብዞ ለውጡን እንዲቀላቀሉና እንዲሣተፉ ቢደረግ ሀገር ትጠቀማለች፡፡ ሙያቸውንና ሀገር ወዳድነታቸውን እያጣሩ በአግባቡ ቢገለገሉበት ሀገራችን አንድ እርምጃ ወደፊት ትራመዳለች – በተለይ በመከላከያና በደኅንነት ረገድ […]

አቶ ንጉሡ ጥላሁን ለበረከት ስምዖን ምላሽ ሰጡ |ይዘነዋል

$
0
0
ንጉሡ ጥላሁን ሰሞኑን የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ በርከትን እና አቶ ታደሰን ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነታቸው ማገዱን ተከትሎ አቶ በረከት ለተለያዩ ሚዲያዎች ውሳኔው:- => በስብሰባው ለመታደም ዋስትና ስላልተሰጠኝ መገኘት አልቻልኩም፣ => ውሳኔው መሰረተ ቢስ ነው፣ => የኤርትራ መንግስት እጅ እና ፍላጎት ስለላበት በኤርትራ መንግስት ትዕዛዝ የተፈፀመ ነው፤ እኔ እርምጃ የተወሰደብኝ ኤርትራዊ ዘር ስላለኝ ነው፣ => አቶ ደመቀ […]

የዕለቱ አጫጭር ዜናዎች

$
0
0
አቶ በርከት ስምዖን ስፖንሰር አፈላልጌ አሳተምኩት ያሉት ‘ትንሣኤ ዘ ኢትዮጵያ’ መጽሐፍ በረከት መጽሐፍ ጽፎ ትርፍ ማግኘት የለበትም ባሉ ግለሰቦች መጽሐፉ በፒዲኤፍ ተገልብጦ በኢንተርኔት በነጻ በሰፊው እየተሰራጨ ይገኛል:: ከዚህ ቀደም የኢህአፓ ድረገጾች የኮረኔል መንግስቱ ሃይለማርያምን መጽሐፍ በተመሳሳይ በፒዲኤፍ በነጻ ማሰራጨታቸው ይታወሳል:: —- የኢትዮጵያ እና የጅቡቲ የጦር ኃይል አዛዦች ዛሬ ስብሰባ ተቀምጠው ውለዋል:: የጅቡቲው መከላከያ ኢታማዦር ሹም […]

የአባይ ግድብ ሰራተኞች የሥራ ማቆም አድማ አደረጉ

$
0
0
(ዘ-ሐበሻ) የአባይ ግድብ ሥራ ላይ የተሰማሩት የጣሊያኑ ሳሊኒ ኩባንያ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞች የሥራ ማቆም አድማ አደረጉ:: ሠራተኞቹ አድማውን የመቱት ደሞዝ ስላልተከፈላቸው ነው:: ሳሊኒ ከሠራተኛ ተወካዮች ጋር እስከምወያይ ድረስ ወደ ሥራ ተመለሱ እያለ ነው:: የአባይ ግድብ ዋና መሃንዲስ የነበሩት ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ባልታወቀ መልኩ ሞተው ከመገኘታቸውን አስቀድሞ በጣልያኑ ተቋራጭ ሳሊኒ እና በመከላከያ ብረታብረትና ኢንጂነሪንግ (ሚቴክ) መካከል የከረረ አለመግባባት […]

በአዲስ አበባ ብሔር የማይጠየቅበት መታወቂያ ሊሰጥ ነው

$
0
0
(Reporter Amharic) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የነዋሪዎች ምዝገባና የመታወቂያ አሰጣጥ መመርያ ቁጥር 3/2010 በማሻሻል፣ ብሔር የማይጠቀስበት መታወቂያ ለነዋሪዎች መስጠት ሊጀምር ነው፡፡ የተሻሻለው መመርያ የከተማውን ነዋሪዎች የመታወቂያ አሰጣጥ ከማነዋል ወደ ዲጂታል የሚያሸጋግርና በአሻራ የተደገፈም ስለሚሆን፣ በሐሰተኛ ሰነድ መታወቂያ የያዙ ግለሰቦችን መለየት ያስችላል ተብሏል፡፡ ይህንን አሠራር ተግባራዊ ለማድረግ በክፍላተ ከተሞችና በወረዳዎች የሚገኙ አመራሮችና ሠራተኞችን ያካተተ ሥልጠና፣ ቅዳሜ […]

ለኢንጂነር ስመኘው አሟሟት የፊታችን አርብ የሚሰጠው ምክንያት ብዙዎችን ላያሳምን እንደሚችል ተጠቆመ

$
0
0
(ዘ-ሐበሻ) በአፍሪካ ትልቁ የኃይል ማመንጫ እንደሚሆን የሚነገርለት ግዙፉ የአባይ ግድብ ሥራ አስኪያጅ መሃንዲስ ስመኘው በቀለ መስቀል አደባባይ ላይ መኪናቸው ውስጥ ሞተው ተገኙ የሚለው ዜና ከተሰማ ወር አልፎታል:: አሟሟታቸውን በተመለከተ ለምን በአስቸኳይ ምላሽ አልተሰጠም በሚል ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ምርመራ ለማጣራት ጊዜ እንደሚፈጅ የግድያ ውጤትም ካለምንም ምርመራ ወዲያውኑ እንደማይገለጽ አስታውሰው ፖሊስ በቅርቡ የምርመራውን ውጤት ለሕዝብ […]

አቶ ንጉሡ ጥላሁን ለአቶ በረከት ስምዖን የሰጡትን የመልስ ምት በቪዲዮ አቀናብረነዋል ይመልከቱት

$
0
0
አቶ ንጉሡ ጥላሁን ለአቶ በረከት ስምዖን የሰጡትን የመልስ ምት በቪዲዮ አቀናብረነዋል ይመልከቱት

ዳግማዊ ቴዲ አፍሮ (ዳን አድማሱ) (ቃልኪዳን ኃይሉ)

$
0
0
“ከአቡነ በላይ ነው እያልሽ ክብሬና ማዕረጌ ፊትም አልተመለሽ ለአምስት ኪሎ እጨጌ” . ይህ ልጅ ያስደነቀኝ ዛሬ ሳይሆን “ዘመናይ” ብሎ በበኩር አልበሙ የመጣ ጊዜ ነበር፡፡ ዳን ዘፈኑ፣ አዘፋፈኑ ወይም ቅላጼው አይደለም ብቻ አይለም የሚደንቀው ይልቁንስ ሀሳቦቹም ጭምር እንጂ፡፡ ዳን ልዩ ሀሳብ አለው፡፡ ዳን ዝም ብሎ ድምጽ ስላለው አይዘፍንም ይልቁንስ ሀሳብ ስላለው ነው የሚያቀነቅነው፤ የሚለውና የሚያስተላልፈው ማኅበራዊና […]

የፓርቲ የንግድ ተቋማት የወደፊት ዕጣ ፈንታ – የግል ምልከታ –ግርማ ሰይፉ

$
0
0
የዛሬ ፅሁፍ መነሻ አቶ በረከት ስምዖን ጥረትን ከሃያ ሚሊዮን ብር መነሻ ወደ 11 ቢሊዮን አድርሼ ነው የለቀቅሁት የሚለው ጉዳይ ነው፡፡ ይህ መግለጫ እነዚህን ተቋማት ምን ያህል የዘረፋ ድርጅቶች እንደሆኑ ከማሳየት ውጭ አንድም እነ በረከት እና ታደሰ ጥንቅሹን ታማኝ ናቸው የሚያስብል ቁምነገር አላየሁበትም፡፡ በዚህ አጋጣሚ ብአዴን እነዚህ ድርጅቶች ከፓርቲ እጅ ወጥተው ወደ መንግሰት ይዛወሩ የሚል ውሣኔ […]

አሁንስ እኔም ወደ አገሬ የምገባበት ጊዜ ናፈቀኝ! – ይነጋል በላቸው (ከአዲስ አበባ)

$
0
0
ሆ! ከመኖሪያ ቤቴ 10 ኪሎ ሜትሮችን ያህል በሚርቀው ቤተ መንግሥቴ እየተካሄደ ያለው የለውጥ ማዕበል የዘመናት የራስ ምታቴን እያሻለው ከመምጣቱም ባሻገር እኔም ወደ ሀገሬ ለመግባት እንዳኮበኩብ አድርጎኛል (ወይ ጊዜ! ‹ቤተ መንግሥቴ› ለማለትም በቃሁ አይደል? ጌታ ይክበር፤ ይመስገን፡፡ በቀረችኝ ጥንጥዬ የሕይወት ዘመኔ ይሄን የመሰለ ለጊዜውም ቢሆን የሲዖልን ኑሮ የሚያስረሳ የእፎይታ ጊዜ አያለሁ ብዬ በጭራሽ አስቤው አላውቅም ነበር […]

የኢትዮጵያ አየር ሃይል ሄሊኮፕተር ተከሰከሰ

$
0
0
ከድሬደዋ ወደ ደብረዘይት (ቢሾፍቱ) በመብረር ክላይ የነበረ አንድ የኢትዮጵያ አየር ሃይል ወታደራዊ ሂሊኮፕተር ተከሰከሰ:: ሂሊኮፕተሩ የተከሰከሰው በምስራቅ ሸዋ ሎሜ ወረዳ ውስጥ መሆኑም ታውቋል:: ዛሬ ረፋድ ላይ ከድሬደዋ ወታደሮችን ጭኖ ወደ ደብረዘይት ሲመጣ የነበረው ይኸው ሄሌክፕፕተር የመከላከያ ሠራዊት አባላትን ጭኖ ነበር:: ከኢትዮጵያ አየር ኃይል ያገኘነው መረጃ እንደሚጠቁመው “የበረራ ቁጥሩ 808 የሆነ የኢትዮጵያ አየር ሃይል አውሮፕላን ዛሬ […]

አላሙዲ ይፈታ የሚሉ ቅስቀሳዎች በሜድሮክ መስሪያ ቤቶች እየተካሄዱ ነው

$
0
0
የልጅ አባት እንደሚሆኑ ሲነገራቸው ነብሰ ጡሯን የልጃቸውን እናት በደስታ ዱባይ ቫኬሽን ሄዱ::  ዱባይ እየተዝናኑ ባለበት ሰዓት ስልካቸው ጮኸ:: ከሳዑዲ አረቢያ ነበር:: ለአስቸኳይ ስብሰባ ስለምትፈለግ ሳዑዲ ና ተባሉ:: ሳዑዲ እንደሄዱ ለስብሰባ የተጠሩበት ሆቴል ከሌሎች የሳዑዲ ባለሃብቶችና ባለስልጣናት ጋር እስር ቤት ገቡ:: ይኸው ከታሰሩ አስር ወር ሊሞላቸው 5 ቀናት ብቻ ቀሩ – ሼክ መሐመድ አላሙዲ:: ከሦስት ወር […]

የአብዲ ኢሌ የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ሆነ

$
0
0
በሽተኛ ስለሆንኩ ዋስትና ይፈቀድልኝ ብለው የጠየቁት የቀድሞው የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ ኢሌ የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ ተደረገ:: የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ የወንጀል ችሎት ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሐመድ ዑመር ባቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ላይ ለመወሰን ዛሬ በዋለው ችሎት ባለፈው ሰኞ በቁጥጥር ስር የዋሉት አቶ አብዲ ኢሌን ጨምሮ 3 ተጠርጣሪዎች […]

የዕለቱ አጫጭር ዜናዎች

$
0
0
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሆነው እየሰሩ የሚገኙት የቀድሞው የሕወሃት ባለስልጣን ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም Royal Order of the Lion” የተሰኘው የክብር ሽልማት በሲኒጋሉ ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል ተበርክቶላቸዋል:: ይህ Royal Order of the Lion ሽልማት በሴኔጋል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ግለሰቦች የሚሰጥ ነው ተብሏል:: *** በአዲስ አበባ ከተማ በአፋን ኦሮሞ ሲያስተምሩ የነበሩ ት/ቤቶችን ማስተዳደር መጀመሩን የአዲስ አበባ […]

የአቶ በረከት ሴራ ብአዴንን ከማፍረስ እስከ ዶ/ር አብይ የጠ/ሚኒስትር ምርጫ |አያሌው መንበር

$
0
0
ወቅቱ ታህሳስ ወር ላይ ገደማ ነው።ኢህአዴግ ተሀድሶውን ገምግሞ አቅጣጫ አስቀመጠ።አሁን ሀገርም ድርጅቱም ቀውስ ውስጥ ናቸው።በ17 ቀን ግምገማው ይህንን ቀውስ ለማለፍ 4ቱም ብሄራዊ ድርጅቶች ግምገማ ይቀመጡ ብሎ ወሰነ።ህወሃት 35 ቀናትን አሴረ፣ መከረ ዘከረ። ብአዴንም እንዲሁ።. የበረከት ሴራ 1፦አሁን ያለውን የብአዴን አመራር አብዛኛውን ባለፈው ጥር ወር ላይ መበተን በዋናነት ብአዴንን በማሽከርከር የሚታወቁት እነ አዲሱ ለገሰ፣ በረከት ስምኦን፣ […]

ኣልማዝ አያና የጉልበት ቀዶ ጥገና አደረገች

$
0
0
በተደጋጋሚ የሃገራችንን ሰንደቅ አላማ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ያደረገችው አትሌት አልማዝ አያና በስዊዘርላንድ የጉልበት ቀዶ ጥገና አደረገች:: የቀዶ ጥገናው የተሳካ የነበረ ሲሆን ዶክተሮቿ ከሦስት ወር በኋላ ወደ ልምምድ እንድትመለስ ምክር እንደሰጡ ተገልጿል:: አልማዝ አያና በአሁኑ ወቅት ስዊዘርላንድ የምትገኝ ሲሆን የፊታችን ሰኞ አዲስ አበባ ትደርሳለች ተብሎ ይጠበቃል::

“ከብአዴን እና ከአብን ጋር እሰራለሁ….”

$
0
0
በኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን የላከው መላው አማራ ሕዝብ ድርጅት (መዐሐድ) ከብአዴን እና ከአብን ጋር እሰራለሁ ብሏል ያስቀመታቸው ጉዳዮችስ ምንድናቸው? ከፓርቲው ም/ል ሊቀመንበር አቶ መንግስቱ አስፋው ጋር ቆይታ አድርገናል
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live