Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

አረና በትግራይ ክልል ለሕወሓት ፈተና እየሆነበት ነው፤ የማእከላዊ ኮሚቴ አባሉ በዓዲግራት ታሰረ

$
0
0

ከመምህር አብርሃ በላይ መቀሌ

አብርሃ ደስታ

አብርሃ ደስታ

መምህር ፍፁም ግርሙ የተባለ የዓረና ፓርቲ የማእከላዊ ኮሚቴ አባል ዛሬ በዓዲግራት ከተማ በፖሊስ ታስረዋል። መምህር ፍፁም የታሰረው ባለፉት ሁለት ቀናት በዓረና አባላት ላይ የተፈፀመው ደብዳብ አስተባባሪ የነበረች ትርሓስ የተባለች የህወሓት ካድሬ “እሱ ካልታሰረ ለራሴና ለልጆቼ ደህንነት እሰጋለሁ” የሚል አቤቱታ ለፖሊስ በማሰማቷ ነው።

ትናንት ህወሓት ባደራጃቸው ዱርዬዎች፣ ሲቪል የለበሱ የፖሊስ አባላት፣ የከተማ አስተዳደር ባለስልጣናትና ሰላዮች መደብደባችን ይታወሳል። አቶ አስገደ ገብረስላሴ ሲታሰር ሌሎቻችን ደግሞ በፖሊስ ጣብያ ታግተን አምሽተናል። አቶ አስገደ ሌሊት ከእስር በዋስ ቢለቀቅም ፖሊስ በእሁዱ ስብሰባ ጥበቃ እንደማያደርግልን ስላሳወቀን የጠራነው ስብሰባ ሰርዘን ጉዳዩ ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ለማሳወቅ ዛሬ ጠዋት መቀሌ ገብተናል።

የዓዲግራት ተወላጆች የሆኑ አባላቶቻችን ግን ከሌላ ወረዳ በመጡ ቅጥረኞች “ከዓዲግራት ዉጥሉን” እያሉ ወደ ቤታችን ድንጋይ ሲወረዉሩ ዉለዋል። ድንጋይ ወርዋሪዎቹ የዓዲግራት ተወላጆች ሳይሆኑ በህወሓት አማካኝነት ከሌላ አከባቢ የመጡና የአከባቢው ሕብረተሰብ እያሰቃዩ ያሉ ናቸው። ቅጥረኞቹ ደብዳቢዎች ከዓዲግራት ህዝብ ጋር ሲጋጩ ነበር። የህወሓት ማፍያ ቡድን በሰለማዊ ዜጎች ላይ ድንጋይ በመወርወር የአምባገነንነት ሪከርድ ሰብሯል። ከዚህ በፊት አቶ አረጋዊ ገብረዮሃንስ የተባለ የዓረና አባል በባንዳዎቹ የህወሓት ቅጥረኞች መገደሉ ይታወሳል።

ዛሬ ከዓዲግራት ከተማ ህዝብ ባሰባሰብነው መረጃ መሰረት በህወሓት ተደራጅተው የዓረና አመራር አባላት እንዲደበድቡ ከተከፈላቸው ሰዎች አንድም የዓዲግራት ተወላጅ እንዳልነበረ ነው። የዓድግራት ኗሪዎች ህወሓት ማንነታቸው የማይታወቁ ዱርየዎች በመቅጠር የዓጋመ ህዝብን እንግዳ አክባሪነት ባህል ለማበላሸት መሞከሩ እጅግ አሳዝኗቸዋል። በመደብደባችን ክፉኛ ያለቀሱ እናቶች እንደነበሩም ለማወቅ ችለናል። እኛን ለማዳን ሲሉ ዱርየዎቹን ያባርሩ የነበሩ የዓዲግራት ወጣቶች ማምሻውን በፖሊስ መደብደባቸው ተሰምቷል።


የአገር አቋራጭ አውቶቡስ ተገልብጦ 17 ሰዎች ሕይወታቸው አለፈ፤ የ2 ዓመት ህፃን ሕይወቱ ተረፈ

$
0
0

Shashemene
(ዘ-ሐበሻ) ከሞያሌ ወደ ሻሸመኔ ተጓጓዦችን ጭኖ ይጓዝ የነበረ አንድ አገር አቋራጭ አውቶቡስ ተገልብጦ የ17 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰማ። የ2 ዓመቱ ህፃን ምንም ጉዳት ሳይደርስበት ሲተርፍ፤ ሌሎች 31 የሚሆኑ ሰዎች ግን ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ለዘ-ሐበሻ የደረሱት መረጃዎች አመልክተዋል።

ትናንት ማምሻውን ከሞያሌ ወደ ሻሸመኔ ሲጓዝ የነበረው ሃገር አቋራጭ አውቶቡስ የተገለበጠው በይርጋ ጨፌ ወረዳ ቆንጋ ቀበሌ እንደሆነ ሲገለጽ የአካባቢው የትራፊክ ፖሊስ በሰጠው መግለጫ ለአደጋው መንስኤ በፍጥነት ማሽከርከር ነው ተብሏል። ፖሊስ ጨምሮም መንገዱ ከፍተኛ ቁልቁለት የነበረው ሲሆን ሹፌሩ ሃላፊነት በጎደለው መልኩ በፍጥነት በማሽከርከሩ አደጋው ሊከሰት እንደቻለ ገልጿል።

በዚህ አካባቢ የተለያዩ የትራፊክ አደጋዎች በተለያየ ጊዜ እንደሚደርስ የጠቆሙት የአካባቢው ነዋሪዎች አደጋዎች በሹፌሮች አማካኝነት ይፈጠሩ እንጂ መንግስትም ተጠያቂ ነው ይላሉ። በተለይ ይህ ቦታ ብዙ የመኪና አደጋ የሚደርስበት ቢሆንም ትራፊክ ፖሊስ በሙስና በመጨማለቅ በፍጥነት በሚያሽከረክሩ ሰዎች ላይ ተገቢውን ቅጣት እንደማይጥሉባቸው የገለጹት እነዚሁ ታዛቢዎች ከአስተዳዳሪው ጀምሮ በሙስና የተጨማለቁ በመሆናቸውና ትራፊክ ፖሊስም የሚገባውን ሥራ ስለማይሰራ ለአደጋዎቹ መበራከትም ምክንያት ነው። በተለይ በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የአንድ ትራፊክ የወር ደመወዝ አንድ ሰው ለአንድ ምሽት በሬስቶራንት 2 ሰው ራት የሚጋብዝበት ሂሳብ መሆኑ ፖሊሶቹ በሙስና ላይ እንደሚሰማሩ ታዛቢዎች ለዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ገልጸዋል። በተጨማሪም በይርጋ ጨፌ ወረዳ በቂ የትራፊክ ምልክቶች አለመኖራቸው ለአደጋው መበራከት እንደምክንያት ያቀርባሉ።

በዚህ የመኪና አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል የታወቀ ሲሆን አብዛኞቹ በዲላ ሆስፒታል ህክምና ላይ እንደሚገኙ ጨምሮ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ከዚህ ቀደም በዘ-ሐበሻ ድረ ገጽ ላይ ይህን ጥናት ስለመኪና አደጋ አቅርበን ነበር። በድጋሚ እነሆ፦
በዓለም የጤና ድርጅት (WHO) የ2012 ሪፖርት መሰረት በዓለማችን በዓመት 1ሚሊየን 3 መቶ ሺ ህዝብ በትራፊክ አደጋ ህይወታቸው እንደሚያልፍ ሲታወቅ በኢትዮጵያ በተደረገ ጥናት ደግሞ በዓመት ክ2000 ሰዎች በላይ በመኪና አደጋ ሕይወታቸው ያልፋል።
ለመኪና አደጋ መንስኤ ተብለው ከሚጠቀሱት መካከል በፍጥነት ማሽከርከር፣ ለእግረኞች ቅድሚያ አለመስጠት፣ የሌሊት ጉዞ፣ ደርቦ ማለፍ፣ ከአቅም በላይ መጫን፣ አደንዛዥ ዕፅ መጠቀምና ጠጥቶ ማሽከርከር ከመንስኤዎቹን መሀል ዋነኞቹ እንደሆኑ ታውቋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የተሽከርካሪ የቴክኒክ ጉድለት ወይም ብልሽት፣ የእግረኛ ግራ መንገድ ይዞ አለመሄድና የማቋረጫ ምልክቶችን (ዜብራ) በአግባቡ አለመጠቀም፣ የመንገዶች በጥራት አለመሰራትና የመንገድ ላይ ምልክቶች ተሟልተው አለመዘጋጀት ለአደጋው እንደመንስኤ የቀረቡ ናቸው፡፡

ከዚህ ወዴት?

$
0
0

አንዱ ዓለም ተፈራ
የእስከመቼ አዘጋጅ

ወገንተኛው አምባገነን ሕገወጥ መንግሥት፤ ከዕለት ዕለት ሀገራችንን ወደባሰ አዘቅት እየከተታት ነው። ያለጥርጥር ከዚህ መንገድ ቀና የሚልበት የፖለቲካ አንጀት የለውም። እያሽቆለቆለ መሄዱ፤ የመሰንበት ዋስትናውና መጥፊያው ነው።

freedome
ሕዝቡ ተማሮ ሀገር እየለቀቀ፣ በየቦታው ሕይወቱን እያጣ ነው። ሕዝቡ መሪ አጥቶ በወገንተኛው አምባገነን ሕገወጥ መንግሥት ሥር እየማቀቀ ነው። ሀገሬ ብሎ መኩራት፣ ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ መዝናናት፣ በነገ ላይ ተስፋ መጣል በኖ ጠፍቷል። ሀገራችን፣ ኢትዮጵያዊያን በያለንበት፣ የነገ ሕልውናችን ብቻ ሳይሆን፤ ዛሬ የቆምንበትን መሬት መርገጥ አቅቶናል። እንዲህ ባለ የፖለቲካ ሀቅ ውስጥ እየዋተትን ነው።

በውጭ ሀገር ያለውን ኢትዮጵያዊ (ውጭሰው – ያራዳ ልጆች ለዲያስፖራ የሰጡት ስያሜና የወደድኩት ቃል ነው) ለመከፋፈልና ፀጥ ለማድረግ፤ ወገንተኛው አምባገነን ሕገወጥ መንግሥት ከፍተኛ ወጪ በማድረግ፤ የእምነት ቤቶችን፣ የአገልግሎት ማኅበረሰብ ድርጅቶችን፣ የስፖርት ድርጅቶችን ለመቆጣጠር በመሯሯጥ ላይ ነው። እኛም ተመችተነዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ የታጋዩ ክፍል ማዕከላዊ የሆነ ራዕይ፣ ተልዕኮና የዓላማ አንድነት የሌለው ነው። ኢትዮያዊነቱን የተቀበለ አለበት። ኢትዮያዊነቱን ያልተቀበለ አለበት። ታሪኬን እወዳለሁ የሚል አለበት። የታሪክ አንድነት የለኝም የሚል አለበት። በዚህ የትግል መስክ የተሠማሩት ድርጅቶች፤ በአብዛኛው የተዋቀሩትና ለሕልውናቸው ምክንያት የሚሠጡት፤ እኔ ሥልጣን መያዝ አለብኝ የሚል ምኞት ብቻ ነው። እኔ ከሌላው በአንድ ወይንም በሌላ ምክንያት የተሻልኩ ነኝ የሚል ነው።

በዚህ መሐከል፤ በውጭ ያሉ የታጋይ ድርጅቶችና በድርጅቶች ውስጥ የሌለን ግለሰቦች፤ ከተጨባጩ የሀገራችን እውነታ በጣም የራቅን ሆነናል። በሀገር ውስጥ ሆነው የሕዝቡን በደል አንስተው የሚታገሉ ድርጅቶች ደግሞ፤ የሚሠሩት በወገንተኛው አምባገነን ሕገወጥ መንግሥት ሥር በመሆኑ፤ እንዳይንቀሳቀሱ ጠፍሮ በያዛቸው ሕግ ሥር ተወጥረው፤ የነጠረና የተራቀቀ የትግል ዘዴ ፈጥረው ሕዝቡን መምራት ስላልቻሉና ወይንም ሕዝቡን ስላላስተባበሩ፤ ላለው መንግሥት ህጋዊነት ከመሥጠት ሌላ፤ ለፖለቲካ ትግሉ ፋይዳ የማይሠጡ ሆነዋል ማለት ይቻላል። ሆነም ቀረም ግን እነሱው ሆነዋል የወደፊቱ ተስፋዎች። አማራጭ ከማጣት ይሁን ወይንም እነሱ ካላቸው ጥንካሬ፤ ያሉት ተስፋ እነሱ ናቸው።

በሀገራችን ያለው ሀቅ ባጭር ጊዜ የሚያባራበት ቀዳዳ ብርሃን የለም። አሁንም ሕዝቡን ያሰቃያል፣ ሕዝቡ ፈርቶት በተለዋጩ ደግሞ መንግሥቱ ህዝቡን ፈርቶ ያለበት የፖለቲካ እውነታ ሠፍኗል። እናም ወገንተኛው አምባገነን መንግሥት በጉልበቱ ከቀን ወደ ቀን ሕልውናውን ለማራዘም፤ ያስራል፣ ያሳድዳል፣ ይገድላል። ታጋዩ ክፍል ደግሞ የዚህን ሕገወጥ መንግሥት ድርጊት ይዘረዝራል። በጦር የበላይነቱን ወገንተኛው አምባገነን ሕገወጥ መንግሥት ይዟል። የሕዝቡ ደም እየፈሰሰ ነው። ይኼን መንግሥት በጦር የሚያቸንፍ ኃይል ባሁን ሰዓት የለም። ተግባሩን መዘከሩ ደም ማፍሰሱን አያስቆመውም። ጥያቄው፤ በዚህ ሰዓት ምን መደረግ አለበት? ነው። የዚህ ሰዓት ውሳኔያችንስ፤ የነገውን ሕልውናችንን እንዴት ያደርገዋል? ነው። ደም ማፍሰሱን አሁን ማስቆም አልቻልንም። ታዲያ አሁን ካለንበት ወደ ማስቆም የምንችልበት እንዴት ልንጓዝ እንችላለን? በተናጠል ቆመን ነው? በየድርጅቶቻችን ተሽጉጠን ነው? ወይንስ ኢትዮጵያዊያን በአንድነት በኢትዮጵያዊነታችን ተሰልፈን? ምን እናድርግ? በተለይ በውጭ የምንገኝ ኢትዮጵያዊያን ምን ማድረግ አለብን?
ታዲያ ምን እናድርግ? ለሚለው፤ የሚከተለውን መፍትሔ አቀርባለሁ፤

፩ኛ፤ ውይይት ማድረግ አለብን፤

ስደተኞች ነን። ስደተኛነታችን የፍላጎት ጉዳይ አይደለም። የፖለቲካ ስደተኞች ነን። በሀገራችን ያለው ፖለቲካ ውጤት ነን። የሀገራችን ጉዳይ ያሳስበናል። ይኼ ጉዳይ ሁላችንም ይነካናል። ምን እናድርግ? በሚለው ላይ፤ የወገንተኛውን አምባገነን መንግሥት ግፍ ከመዘርዘር አልፈን፤ አብረን በአንድነት ሀገራዊ ውይይት ማድረግ አለብን።

፪ኛ፤ በሀገራችን ያለውን የፖለቲካ ሀቅና የትግሉን ምንነት በደንብ መተንተን አለብን፤

ምን ዓይነት መንግሥት ነው በሀገራችን ያለው? በምን መንገድ ይፈረጃል? መለወጥ አለበት ከተባለ፤ ለምን ይለወጣል? እንዴት ይለወጣል? በምን መንገድ ነው ለውጡ የሚካሄደው? እዚህ ላይ፤ በሁኑ ሰዓት ሠፍኖ ያለው፤ የዚህን መንግሥት ግፍ መዘርዘር ብቻ ነው። ይህ በቂ አይደለም። ትኩረቱ እኛ ምን እናድርግ ላይ ነው መሆን ያለበት።

፫ኛ፤
ዛሬ ዋና ዋና በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መሠረታዊ የሆኑ መግባቢያዎች ነጥቦች ላይ መድረስ አለብን፤

አሁን በሀገራችን ያለውን የአስተዳደር ዘይቤ በሚመለከት፣ የብሔር ጥያቄ፣ የሀገሪቱን የቋንቋ ምስቅልቅል አቀማመጥ በሚመለከት፣ የደንበር ጉዳይ፣ በልማት ስም በሀገር ውስጥ ለውጭ ሀገር ድርጅቶች የተሠጡ ለም መሬቶችና የተፈናቀሉ ሰዎችን በሚመለከት? የተፈናቀሉ አማራዎችን በሚመለከት፣ የሃይማኖቱን ውጥረት በሚመለከት፣ ወ. ዘ. ተ. አንድ ወጥ የሆነ አመለካከት ሊኖር ይገባል። አለበለዚያ ትግል በቀጠሮ ልናደርግ ነው።

፬ኛ፤ በትግሉ አይቀሬነት ስምምነት ላይ ከተደረሰ፤ ይህ ትግል የሚጠይቀው ዓይነት ድርጅት መመሥረት አለበት፤

በታጋዩ ክፍል የትግል አንድነት መኖሩ ግዴታ ነው። ይህ የትግል አንድነት ደግሞ ከትግሉ ራዕይ፣ የዓላማ ሂደት፣ ግብና ተልዕኮ ጋር የተያያዘ የአደረጃጀት ጥያቄ ነው። መሠረታዊ ጥያቄው የምንፈልገው ምንድን ነው? የሚለው ነው። የምንፈልገው ሥልጣን ነው? ሥልጣን ለማን? ለግላችን? ወይንስ ለሕዝቡ? የራሳችንን የግል ብልፅግና ለማራመድ? ለግለሰብ ዝናችን? ወይንስ ለሀገራችን ነፃነትና ለሕዝቡ አርነት? የግል ታሪካችንን ለማጉላት ወይንስ ሀገራችን በዓለም የሥልጣኔ ደረጃ ጎልታ እንድትታይ? የዴሞክራሲ በሀገራችን ሥር መስደድ በምን ይመሠረታል? የምንፈልጋቸውን ሰዎች ብቻ መርጠን በማቀፍ ሳይሆን፤ ሁሉን ኢትዮጵያዊያንን በሙሉ በአንድ ማየት ስንችል ነው። የምንወደውን ብቻ ሳይሆን የምንጠላውን በርጋታ አዳምጠን፤ የመስማቱ አቅል ኖሮንና ዕድሉን ሠጥተን ልዩነታችን አስምረን፤ በምንስማማባቸውና በከፍተኛ ሀገራዊ ጉዳዮች አብረን መሥራት ስንችል ነው። እኛ ራሳችን ዴሞክራሲያዊ አሠራርን ሥራዬ ብለን ሳንከተል፤ ለዴሞክራሲ ታጋዮችና የዴሞክራሲ ጠበቆች ልንሆን አንችልም። ለዲሞክራሲ ታጋዮች ነን ብንል ንፉቃን ነን። የሌሎች ድርጅቶችን መኖር አለመኖር ከዚህ አኳያ እንጂ፤ ስላሉ ወይንም ስለሌሉ በሚለው መነፅር መታየት የለበትም። ምን ዓይነት ድርጅት ነው አሁን ያለንበትን የፖለቲካ ምስቅልቅል ለውጦ፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ ለድል የሚያበቃ? ምን ዓይነት ትግል ነው ሁኔታው የሚጠይቀውና ለሕዝባዊ ትግሉ አስተማማኝ መንገድ የሚሆነው?

፭ኛ፤ ይህ ድርጅት፤ የትግሉን ራዕይና የትግሉን ተልዕኮ ማርቀቅና ማስፈር አለበት፤

ይህ ታጋይ ኢትዮጵያዊያንን ሁሉ የሚያሰባስብ ድርጅት ከተቋቋመ፤ ይህ ድርጅትና ይህ ድርጅት ብቻ የትግሉን ራዕይና ተልዕኮ ማስቀመጥ አለበት።ይህ ድርጅት የታጋይ ኢትዮጵያዊያን ድርጅት ስለሆነ፤ ለትግሉ ዓላማም የቆመ ነው። ሁሉንም ያቀፈ በመሆኑም፤ የትግሉን ራዕይና የትግሉን ተልዕኮ ለማርቀቅና ለማሳወቅ ገዴታና ኃላፊነት አለው።

፮ኛ፤ የዚህ ትግል ግብ፤ የኢትዮጵያን ህዝብ የሥልጣኑ ባለቤት ለማድረግ ነው፤

አዎን በውጭ የምንኖርና በሀገር ውስጥ ያሉት ወቅታዊ የትግል ድርሻችን የተለያዬ ነው። በውጭ ያለነው አንፃራዊ ነፃነት ስላለን፤ ሀገር ውስጥ ያሉት ይኼ ስለተነፈጋቸው፤ ለትግሉ የምናደርገው አስተዋፅዖ የተለያዬ ነው። እናም ይህ የሚቋቋመው ድርጅት፤ በሀገር ቤትና ከሀገር ውጭ የምንገኘውን ኢትዮጵያዊያን ማሰባሰብና፤ በተቻለው መንገድ ሁለቱን ክፍሎች፤ ትግሉን በሚጠቅምና በማይጎዳ መንገድ ሊያስተሣሥር የሚችል ተገቢ አደረጃጀት መንደፍ አለበት። በሀገር ውስጥ ወይም ከሀገር ውጪ መገኘት ለትግሉ ያለንን ተሳታፊነትን አያነጣጥልም። ወጣት መሆን ወይንም ሽማግሌ መሆን ሀገር ወዳድነትን አይለያይም። የክርስትና ወይንም የእስልምና ተከታይ መሆን፤ ከኦሮሞ ወይንም ከሶማሌ፣ ከሲዳማ ወይንም ከአማራ፣ ከሁለት ወይንም ከዚያ በላይ ከተለያዩ ቋንቋ ተናጋሪ ወላጆች መወለድ፤ ለኢትዮጵያዊያን የምናደርገውን ትግል አያሳንስም ወይንም አያጎለብትም። በማንኛውም መንገድ፤ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፤ እኩል ተሳትፎ የሚያደርግበትን መንገድ ድርጅቱ መተለም አለበት። እያንዳንዳችን ለትግሉ የምናቀርበው አለን። ሁላችን ካልተሳተፍንበት፤ ትግሉ እውነተኛ ግቡን መምታቱ አስተማማኝ አይደለም።

፯ኛ፤ ለሚያስፈልገው መስዋዕትነት የተዘጋጁት ብቻ በድርጅቱ ማዕከላዊ አካል መካተት አለባቸው፤

ይህ ትግል በጣም ረጂምና ብዙ እልህ አስጨራሽ ነው። የሆይ ሆይታ ፈጠዝያ ጨዋታ አይደለም። ሌሎች እስር ቤት እየታጎሩበት ነው። ሀገር ለቀው እየተሰደዱበት ነው። ደም እየፈሰሰበት ነው። ሕይወት እየጠፋበት ነው። ይህ የጊዜ ማሳለፊያ ተግባር አይደለም። ሙያዬ ብለው የሚታትሩ ታጋዮችን ይጠይቃል። ሌሎች ደጋፊዎች ናቸው። በሀገር ጉዳይ፤ ይሉኝታ ቦታ ሊኖረው አይገባም። ለሕዝብ ብለው የቆሙና ሁሉን ለዚህ ተግባር የሚያቀርቡ ብቻ ኃላፊነቱን መውሰድ አለባቸው። እንደገና፤ ይሉኝታ ቦታ ሊኖረው አይገባም። ለሀገር በአንድ እንነሳ።

በአረቡ ምድር በኳታር የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ልትሠራ ነው

$
0
0

ከዳንኤል ክብረት

በመካከለኛው ምሥራቅ ከእሥራኤል ቀጥሎ ሁለተኛዋ፣ በዐረቡ ምድር ደግሞ የመጀመሪያዋ የምትሆነው ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን በኳታር ምድር ልትታነጽ ነው፡፡

(በገልፍ ሃገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን) ፎቶ ፋይል

(በገልፍ ሃገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን) ፎቶ ፋይል


በኳታር ምድር የዛሬ አሥር ዓመት ለጸሎትና ለትምህርት መሰባሰብ በጀመሩ ወንድሞችና እኅቶች የተጀመረችው የኳታር ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ወደ አካባቢው ለሥራ የሚጓዙ ምእመናንን በማሰባሰብና በማገናኘት፣ ስብከተ ወንጌልን በማስፋፋትና ክርስቲያናዊ ማኅበራዊ ኑሮን በማጠናከር የምትታወቅ ናት፡፡ ቤተ ክርስቲያንዋ አገልግሎቷን የምትፈጽመው በግብጽ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሲሆን በዓረቡ ዓለም እንደተለመደውም ዘወትር ዓርብ ከሰዓት በኋላ የቅዳሴና የትምህርት አገልግሎት ይሰጣል፡፡ የኳታር ቅድስት ሥላሴ ምእመናን የሥራ ጫናውን ሁሉ ተቋቁመው ተግተው በማገልገል ብቻ ሳይሆን ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ጠብቀው በማስጠበቅም የሚታወቁ ናቸው፡፡

በአብዛኞቹ የዓረበ ሀገሮች እንዳሉት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ በኳታር ለነበረችው ቤተ ክርስቲያንም ዋና ፈተና የነበረው የራስዋ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን አለመኖር ነው፡፡ ይህም አገልግሎቷን በሳምንት ወደ ተወሰኑ ቀናትና ሰዓታት ከማሳነሡም በላይ፣ ምእመናን የሚፈልጓቸውን ሁሉን አገልግሎቶች ለመስጠት እንዳትችል አድርጓት ነበር፡፡ ለቤተ ክርስቲያንዋ የራስዋ ሕንጻ መሥሪያ ቦታ በመፈለግ ችግሩን ለመፍታት ጥረት ሲያደርግ የነበረው የሰበካ ጉባኤ ባሳለፍነው ሳምንት በዐረቡ ዓለም የመጀመሪያ የምትሆነውን ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ለመሥራት የሚያስችል መሬት ተረክቧል፡፡

እስካሁን ድረስ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በየመን፣ በዓረብ ኤምሬትስ፣ በባሕሬን፣ በኩዌት፣ በሊባኖስና በግብጽ የራስዋ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ቢኖሯትም በራስዋ ገንዘብ የተሠራና ንብረትነቷ የቤተ ክርስቲያኒቱ የሆነ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ግን አልነበራትም፡፡ የኳታር ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ከተሠራ ከእሥራኤል ቀጥሎ በመካከለኛው ምሥራቅ ሁለተኛው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ‹ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን› ይሆናል፡፡

በኳታር ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ መሠራት ዘርፈ ብዙ ጥቅም ይኖረዋል፡፡ በአንድ በኩል የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያኑን አገልግሎት ከሳምንት እስከ ሳምንት የማያቋርጥ እንዲሆን ሲያደርገው በሌላ በኩል ደግሞ በአካባቢው ላሉት ሌሎች አጥቢያዎችም አርአያነት ይኖረዋል፡፡ ከኳታር በፊት እንቅስቃሴ የጀመሩት እንደ አቡዳቢ መድኃኔዓለም ያሉትን አጥቢያዎች የጀመሩትን በርትተው እንዲፈጽሙ ያነሣሣቸዋል፡፡

በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የሐዋርያነት ታሪክ በዐረቢያ ፔኒዙኤላ የነበረው ቤተ ክርስቲያን ከ1400 ዓመታት በፊት በየመን ናግራን ታንጾ የነበረው የቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ነበር፡፡ እርሱ ከጠፋ ከ1600 ዓመታት በኋላ በዓረቢያ ፔኑዚኤላ ሁለተኛው ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን በቅድስት ሥላሴ ስም እንደገና በኳታር መታነጹ የታሪኩ ተገጣጣሚነት የሚያስደንቅ ነው፡፡

ይህ ቤተ ክርስቲያን በአንድ በኩል ታሪካዊ፣ በሌላ በኩል የቤተ ክርስቲያኒቱን ሐዋርያዊ ተልዕኮ ወደ አንድ ምዕራፍ የሚያሸጋግር፣ ሲሠልስም ለሌሎች አርአያነት ያለው በመሆኑ ሥራ በኳታር ለሚገኙ ብቻ የሚተው አይደለም፡፡ ግብጻውያን እንደዚህ ባሉ አካባቢዎች የሚታነጹ የተለየ ታሪክና ጠቀሜታ ያላቸውን አብያተ ክርስቲያናት በመተጋገዝ እንደሚገነቧቸው ሁሉ በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያንም እያንዳንዷን የሕንጻዋን ብሎኬት ተካፍለው በመገንባት በታሪክ ምዕራፍ ላይ አሻራቸውን ማስቀመጥና በረከት ማግኘት ይጠበቅባቸዋል፡፡

በሀገር ቤት፣ በአውሮፓ፣ በአሜሪካና በአውስትራልያ የሚገኙ ምእመናን በአካባቢያቸው ቤተ ክርስቲያን ባይኖር ነድተውም ሆነ ተሳፍረው ወደ ሌላ አካባቢ በመሄድ ቤተ ክርስቲያን መገልገል ይችላሉ፤ በዐረቡ ዓለም ግን በአንድ አካባቢ አንድ አጥቢያ ብቻ ስለሚገኝ ወጣ ብሎ በሌላ አጥቢያ መገልገል አይቻልም፡፡ በተለይ ደግሞ እንደ ኳታር ባሉ ሀገሮች ያለው ቤተ ክርስቲያን አንድ ነው፡፡ ይህን ቤተ ክርስቲያን ማነጽና አገልግሎቱን ማጠናከር፣ በዐረቡ ዓለም የሚገኙ ወገኖቻችን በመንፈሳ ሕይወታቸው በርትተው፣ ከመንፈስ ጭንቀት ተላቅቀው፣ የሚደርስባቸውን ፈተናም አሸንፈው ለሀገራቸውና ለወገኖቻቸው የሚጠበቅባቸውን እንዲያደርጉ የሚያስችል ነው፡፡ በመሆኑም በመላው ዓለም የተሠማሩ ኢትዮጵያውያን ሁሉ የሚታነጸው የራሳቸው አጥቢያ መሆኑን አስታውሰው ልባቸው ኳታር ሊሆን ይገባል፡፡

የገባው ክርስቲያን እግዚአብሔር ሲሠራ አብሮ ይሠራል፡፡

በአዲስ አበባ የካራሎ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ በፖሊስ ላይ ተኮሰ

$
0
0

በ ዳዊት ሰለሞን
Fnote Breaking News በአዲስ አበባ ካራሎ አካባቢ በሚገኘው ካራሎ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘጠነኛ ክፍል ተማሪ መሆኑ የተነገረለት ተሾመ አረጋ ታጥቆት ወደ ትምህርት ቤት እንደመጣ በተነገረለት ሽጉጥ አንድን ፖሊስ ለመምታት ተኩሶ ፖሊሱ መሬት ላይ በመተኛቱ ህይወቱ መትረፉን የፍኖተ ነጻነት የመረጃ ምንጮች አስታወቁ፡፡
በቅርቡ በተከበረው የጥምቀት በዓል በካራሉ ተፈጥሮ በነበረ የቡድን ጸብ በመደብደቡና በጩቤ በመወጋቱ ቂም ቋጥሮ የከረመው ተሾመ ለጊዜው በምን መንገድና ከማን እንዳገኘው ያልታወቀን ሽጉጥ በመያዝ ጉዳት ያደረሱበትን ወጣቶች ለመበቀል በማሰብ ወደ ትምህርት ቤቱ ይመጣል ፣ትምህርት ቤቱ ፈተና ለተማሪዎቹ በሚያዘጋጅበት ወቅት ሁልግዜም የተማሪዎቹን ደህንነት ለመጠበቅ የፖሊስ እርዳታን እንደሚጠይቅ የሚናገሩት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ጌታቸው ታምሩ በዛሬው ዕለትም በአካባቢው ፖሊሶች በመገኘታቸው ተሾመ በያዘው ሽጉጥ አደጋ ከመፍጠሩ በፊት ፖሊሶች ማክሸፋቸውን ለፍኖተ ነጻነት አስታውቀዋል፡፡
ተሾመ ወደ ትምህርት ቤቱ ከመግባቱ በፊት ግርግር በመፈጠሩ ፖሊሶች የግርግሩ ፈጣሪ እንደሆነ የተረዱትን ተማሪ ለመያዝ ሲጠጉ ተሾመ ሽጉጡን በማውጣት እንዳይጠጉት በማስጠንቀቅ ሩጫ ይጀምራል፣ ፖሊሶቹ ተማሪውን ለመያዝ በሩጫ ሲከተሉትም ተማሪው አንደኛውን ፖሊስ ለመምታት ይተኩሳል፣ በስፍራው የነበሩ የአይን እማኞች እንደተናገሩት ከሆነ ሽጉጥ የተተኮሰበት ፖሊስ መሬት ላይ በመውደቁ ከአደጋው ለማምለጥ ችሏል፡፡
የተማሪው ወላጅ አባት በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሚገልጹት ምንጮቻችን ተሾመም ከጥቂት ሰዓታት መሰወር በኋላ በፖሊስ መያዙን ገልጸዋል፡፡ክስተቱ በተማሪዎች ስነ ልቦና ላይ ጭንቀት የሚፈጥር በመሆኑ ፈተናቸውን በሌላ ጊዜ እንዲወስዱ ስለማድረጋቸው የተጠየቁት ምክትል ርዕሰ መምህሩ ‹‹በተማሪዎቻችን ላይ ምንም አይነት ጭንቀት ባለመፈጠሩ ፈተናቸውን እንዲወስዱ አድርገናል፡፡››ብለዋል፡፡

ስኬታማ ውድቀት (Successful Failure!)

$
0
0

ይሄይስ አእምሮ

ለውድቀት ስኬት “የምሥራች!” ወይም “እንኳን ደስ ያለን!” የማይባል ነገር ሆኖብኝ እንጂ ከነዚህ የደስታ ማብሠሪያ አባባሎች በአንደኛው ጽሑፌን መጀመር ቃጥቶኝ ነበር፡፡ ለማንኛውም ሀገራችን በማንኛውም ዘርፍ በገባችበት ውድቀትና ኪሣራ ምክንያት ልባችሁ ያዘነና ቅስማችሁ የተሰበረ ወገኖቼን “እግዚአብሔር ያጽናችሁ፤ የሀገራችሁን ትንሣኤም ፈጣሪ በአፋጣኝ እውን እንዲያደርግላችሁ የእግዚአብሔርን ልብ ያራራላችሁ” በሚለው የልመና ቃል ፈጣሪን እየተማጸንኩ ወሬየን ልቀጥል፡፡ ትንሽ በንዴት እንድትንጨረጨሩ ፈቃዳችሁ ይሁንልኝ፤ መልካም መንጨርጨር!
Success Failure
ሰሞኑን ለራሴ የጥሞና ጊዜ እንዲኖረኝ ፈለግሁና በንባባዊ አርምሞ ሰነበትኩ፡፡ በግሌ እንደብዙዎች ሰዎች ብዙ ጉድለት አለብኝ፡፡ ከነዚህ አንድኛው በመሸታ ቤቶችና በግል ግንኙነቶች ከጨዋታዎች ከምሰማው፣ ከመገናኛ ብዙኃን ከምከታተለው፣ በትምህርት ምክንያት ካገኘኋቸው አነስተኛ ግንዛቤዎችና ከጥቂት ንባቦች በስተቀር ስለሀገሬ ታሪክ ብዙም ዕውቀት አልነበረኝም፡፡ ይህን ትልቅ ክፍተት በተቻለ መጠን ለማጠጋጋት አንድ ሃሳብ መጣልኝ – ማንበብ፡፡ እርግጥ ነው የጥንታዊቷን ኢትዮጵያን ቀርቶ የትናንቷን አሜሪካን ታሪክም ቢሆን በንባብ ለመረዳት መሞከር አባይን በጭልፋ እንደማለት በመሆኑ ይህን መሰሉን ታላቅ ተግባር በአንድ ሰው ዕድሜ ማከናወን ከባድ ብቻም ሣይሆን ከነአካቴው የሚቻል አይደለም፡፡ ግን ከለዬለት ድንቁርና በተወሰነ ደረጃ መውጣት የሚቻለው ራስን በንባብ ማበልጸግ ሲቻል በመሆኑ ጊዜየ በፈቀደልኝ ጥቂት መጻሕፍትን – ከፊተኞችም ከአሁነኞችም – ባለፉት ሦስት ወራት ውስጥ ለማንበብ ሞከርኩ፡፡ ወደ አሥር ይጠጋሉ፡፡ ከነዚህ ግንዛቤ አስገኚ መጻሕፍት ውስጥ የርዕዮት ዓለሙ “የኢሕአዴግ ቀይ እስክርቢቶ” የሚለው አንዱ ነው፡፡ እመለስበታለሁ፡፡

የአለቃ ተክለኢየሱስ “የኢትዮጵያ ታሪክ” መጽሐፍ ሌላው ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ ዶክተር ሥርግው በሚባሉ ምሁር የአርትዖት ሥራ እንደተካሄደበት ተገልጾኣል፡፡ ግሩም እሳት ነው፤ ሲያነብቡት እያቃጠለ፣ እየለበለበና ኢትዮጵያዊነትንም እያስረገመ ተነብቦ ማለቁ አይቀርም ያልቃል፡፡ ከነዚህ መጻሕፍት ውስጥ ሥልጣን የማይወዱ መሆናቸውን በማስረዳት የሕይወት ዘመናቸውን እያገባደዱ የሚገኙት ፕሮፌሰር መስፍን የጻፉት “አገቱኒ”ም በስህተት ለሁለተኛ ጊዜ አንብቤዋለሁ፡፡ “ካረጁ አይበጁ ነው”ና ደግሜ እያነበብኩት መሆኔን እስክረዳ ብዙ ገፆችን ብጓዝም ጊዜና የማንበብ ፍላጎት ሞልቶ እንደተረፈው ሰው ጨረስኩት (በዚች መጽሐፍ ላይም በጨረፍታ ብመለስ ደስ ይለኛል)፡፡ ኢትዮጵያ የማያውቋት ሁሉ ዝናዋን ከሩቅ በመስማት ውዱን ሕይወታቸውን ሣይቀር ሊገብሩላት የፈቀዱ የዓለም ዜጎች እንደነበሩ “ጥቁር አንበሣ” በሚል መጽሐፍ ተጋድሎውን ካነበብኩለት ኩባዊ ሻምበል ልረዳ ችያለሁ፡፡ ይህን “ጉራ” የምቸረችርላችሁ ስለሁለት ምክንያት ነው፤ አንዱ ጉድለትን ለማስተካከል በግድ ወደንባብ መዞር እንደሚገባን በተለይ ለወጣቱ ትውልድ ለመጠቆም ነው፡፡ ሁለተኛውን ረሳሁት፡፡

የተሣካ ውድቀት ውስጥ መግባት እኛ ኢትዮጵያውያን ብርቃችን እንዳልሆነ ያነበብኳቸው መጻሕፍት ሁሉ በኩራት ይመሰክራሉ፡፡ እነዚህም ሆኑ ሌሎች በተለያዩ አጋጣሚዎች የማውቃቸው ታሪኮቻችን የሚነግሩኝ አንድ ነገር ቢኖር እኛ ኢትዮጵያውያን አንድ የሚጎድለን የተፈጥሮ ቅመም መኖሩን ነው፡፡ ይህ የጎደለን ቅመም እጅግ መሠረታዊ ከመሆኑ የተነሣ ፈልገን ካላገኘነውና ካላስተካከልነው ከአሁን በኋላ አምስት ሚሊዮን ዓመታትም በሀገርነትና በሕዝብነት ብንኖር በዬጊዜው ከምንገባባቸው የተሣኩ ውድቀቶች መውጣት ፈጽሞውን አይቻለንም፡፡ ብዙዎቻችን አዘውትረን እንደውዳሤ ማርያም እንደምንደጋግመው ምቀኝነትና የሥልጣን ጥም በደማችንና በመቅኒያችን የመሸጉብን ስለመሆናቸው የቀድሞና የአሁን ታሪካችን ነጸብራቅ የሆኑ እነዚህን መጻሕፍት በማንበብ መረዳት ይቻላል፡፡

አልጋ ለመቀማት ወይም አልጋውን ላለመቀማት ሲል ንጉሥ አባት ልዑል ልጅን በጦርና በጎራዴና ምግብን በመመረዝ ሣይቀር የሚገድልበት፣ ነገሥታት ከሀገራዊ ልማት ይልቅ ለሥልጣናቸው ሲሉ ለብዙ አሠርት ዓመታት በማያቋርጡ ጦርነቶች ራሳቸውንና ሕዝባቸውን የሚማግዱበት፣ ለሥልጣንና ለሹመት ሲባል አንዱ ሌላውን በመርዝና በሰይጣናዊ መተትና ድግምት የሚጨራረሱበት፣ የሥልጣን አራራን ለማስታገስ ሲባል የገዛ ሚስትን ሳይቀር ለከፍተኛ መሪዎች እያቀረቡ በትዳርና በ“ፍቅር” ጡር የሚሠራበት፣ ሃይማኖትን መሣሪያ በማድረግ ሕዝብ ከእውነተኛ የፈጣሪ መንገድ እንዲወጣና የነገሥታት ባሪያ እንዲሆን የሃይማኖት መሪዎችና ነገሥታት የሚመሣጠሩበት፣ በዕብድና ወፈፌ ነገሥታት የደንቆሮ አገዛዝ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በረባ ባልረባው ሚዛን የማይደፋ ምክንያት እጅ እግራቸው እንዲቆረጥና በ“እኔን ያዬህ ተቀጣ” ለመቀጣጫነት የሚዳረጉበት፣… አሣፋሪ ሁኔታ ከኢትዮጵያ ውጪ በሌላ ሀገር ስለመኖሩ በበኩሌ አላውቅም፡፡ የትናንቱ ድንቁርናችን ተባብሶ ዛሬም በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የምናስተውላቸው የውድቀታችን መንስኤዎች ከጥንቱ የተወረሱ እንደሆኑ መገንዘብ አይከብድም፡፡
ውድቀት ምንድነው? እንዴትስ ይታወቃል?

ብዙ መፈላሰፍ አያስፈልግም፡፡ በአጭሩ ውድቀት ማለት ኢትዮጵያ ማለት ነው፡፡ ኢትዮጵያና ውድቀት በፍቺ ይመሳሰሉ፤ አንዱ ቃል ሲጠራ ሌላው ይታወሳል፡፡ ይህን ለመገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ መምጣትና እየተዟዟሩ መጎብኘት ነው፤ በሁሉም ዘርፍ የተዘፈቅንበትን ኪሣራና ድቀት (Decadence) በአጭር ጊዜ ውስጥ ማየት ይቻላል፡፡ ልብ ማለት ያለብን ነገር ደግሞ ሕንጻና መንገድ የዕድገት ምልክት አለመሆናቸውን ነው፡፡ ኢትዮጵያ እንደዚህ ዘመን በተሣካ ውድቀት ውስጥ የገባችበት ዘመን የለም ማለት ይቻላል፡፡ የጥንት አባትና እናቶቻችን የጀመሩት ውድቀት ግዘፍ ነስቶ በአካል የታየው አሁን ባለንበት ዘመን ላይ ነው፡፡ ከታክ የማንማር፣ ጥፋትን እያሻሻልንና እያዘመንን ለሌላ ጥፋት ዝግጁ የምንሆን ዜጎች ብንኖር እኛ ኢትዮጵያውን ብቻ ነን፡፡ አሁን ያለንበት የውድመት ደረጃም ሲያንሰን ነው፡፡ የማንተዛዘን፣ አንዳችን በአንዳችን መከራ የምንደሰት፣ በአንዳችን መቃብር ላይ ሌላኛችን የሠርግ ዳስ የምንትል እጅግ ክፉዎች ነን፡፡ እውነት ቢነገር ምን ያመጣል? ምንም!!

ብዙ የውድቀት መከሰቻዎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ አንዱ የውድቀት ምልክት የአርአያሰብዕ (Iconic Figure(s)) መንጠፍ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት በተለይ ወጣቱ ትውልድ “ወደፊት እንደ እገሌ ነው የምሆነው!” ብሎ ከፊት ለፊቱ የሚያስቀምጠው ሰው እየጠፋ ነው፡፡ ዙሪያ ገባውን ብንቃኝ አርአያ የሚሆን ሰው ማግኘት እንቸገራለን፡፡ ይህ ዓይነቱ ድርቀት ዋና ሀገራዊ ኪሣራ ነው፡፡ የነበሩን መልካም ሰዎችና በሥራቸው አንቱ የተባሉ ዜጎች ብዙዎቹ ከመሬት ሥር ውለው ጥርኝ አፈር ሆነዋል፤ በጣት የሚቆጠሩ ቢኖሩም ዘመኑ ለነሱ አርአያነት ምቹ ባለመሆኑና በወቅቱ የወያኔ መንግሥት በጠላትነት ስለሚፈረጁ በሀገር ውስጥና በውጪው ዓለም ተደብቀዋል፡፡ በወቅቱ መንግሥት ትልቅ ዜጋ ማለት የወያኔን ዘረኛ መንግሥት ፖሊሲዎች ተቀብሎ በወንጀልና በኃጢኣት መመላለስን የመረጠ፣ በሰይጣናዊ ተግባራት ተጠምዶና በባዕድ አምልኮት ተጠምቆ ለሥጋው ድሎት ብቻ የቆመ ነው፡፡ ከዚያ ውጪ በአንጻራዊ አነጋገር የተሻለ በሚባል ኢትዮጵያዊ የአንድነት ዘመን ውስጥ በምርጥ ዜግነት የሚያሳውቁ ማኅበራዊና ምሁራዊ ተግባራትን በአሁኑ የወያኔ ዘመን ማከናወን ለእሥርና ለእንግልት እንዲሁም ለስደት ይዳርጋል፡፡ ሆዳምነትና ዋልጌነት በነገሠበትና የመንግሥት መታወቂያ በሆነበት ዘመን የሀገርና የሕዝብ አለኝታ ሆኖ ብቅ ማለት ሌላው ቀርቶ ባልተፈጸመ ወንጀል – የወያኔ የወንጀል መፈብረኪያ የደኅንነት መሥሪያ ቤት በሚሸርበው የፈጠራ ክስ – ወህኒ ሊያስወርድ ይችላል፡፡ የቴዎድሮስ ካሣሁንን መስዋዕትነት ያስታውሷል፡፡ ወሩ በገባ በ22ኛው ቀን የሞተን ዜጋ ወሩ በገባ በ23ኛው ቀን ከውጪ ሀገር በመጣው ቴዲ ላይ መላከኩ የገጪውና የተገጪው ግንኙነት ምናባዊ እንጂ እውናዊ መሆኑን እንኳንስ ‹ፍርድ ቤቱ›ና ከሳሾቹ እኛም እናውቅ ነበር – ማወቅ በራሱና ብቻውን ዋጋ የለውም እንጂ፡፡ ወያኔ መርዘኛ በቀለኛ ነው፡፡ ወያኔ ከመረዘ ሳያንፈራፍር በቀላሉ አይለቅም፡፡
በአሁኑ ወቅት ምሁር አለን ማለት ያስቸግራል፡፡ አድርባይና እበላ ባይ አስመሳይ ወይም በዘመኑ ቋንቋ ‹ፎርጅድ› ምሁር እንጂ ትክክለኛው ምሁር በመብራት ተፈልጎም አይገኝ፤ አሉ ከሚባሉት ጥቂት ወጣትና አንጋፋ ምሁራንም መካከል በትዕቢትና በትምክህት የማይወጣጠሩ ልሂቅነታቸው ያላሳወራቸው ትሁት የሕዝብ አገልጋዮችን ለማግኘት መቸገራችን አልቀረም – ከወደቁ አይቀር ውድቀቱ ሁለንተናዊ መሆን አለበትና ይህ የኢትዮጵያ ምሁራን መኮፈስ የማይጠበቅ አይደለም፡፡ ሁሉንም ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ወታደራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሃይማኖታዊ ዘርፎች ብናይ አርአያ ሊሆኑን የሚችሉ ድንቅ ዜጎችን ሣይሆን ለሆዳቸው ያደሩ አጋሰስና ግልብ ዜጎችን ነው የምናገኝ – በአብዛኛው፡፡ ሆድ ሰውነትን ሲገዛው ጭንቅላት ይጫጫና ከርስ/ቦርጭ ውስጥ ወርዶ ይወተፋል፡፡ ያኔ ኅሊና ትጠፋና ሆድአደርነት የማያፍሩባት ይልቁንም የሚኮሩባት የወቅቱ ፋሽን ትሆናለች፡፡ ሀቀኝነት እያሳፈረ ቅጥፈትና ዕብለት ያሾማል፤ ያሸልማል፡፡ በከንቱ ካልታበይንና ባለፈ የደግ ዘመን ጥቂት ታሪክ ተጀቡነን በተረት ተረት መኖርን ካልመረጥን በስተቀር ሀገራችን በዚህ አሣፋሪ ሂደት ውስጥ ትገኛለች – በችኮላ የ‹ደርግ ዘመን› ብላችሁ እንዳታነቡብኝ አደራችሁን፡፡ የሚብለጨለጨውን የቻይና ቴክኖሎጂና ሕንጻና መንገድ በዚህ ስሌት አናስገባውም፡፡ መጥፎ ነው ማለት ግን አይደለም፡፡ እነዚህ የሚታዩ ኳሻርኳራዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ውጤቶች በተወሰነ ደረጃ በሀገር ምስል ላይ አወንታዊ ሚና ስለሚጫወቱ መልካም ነገሮች ናቸው፡፡ ውድቀታችንን ግን ሊታደጉ ወይም ሊሸፍኑና እንዳልወደቅን ሊመሰክሩ ግን አይችሉም፡፡

ለእውነት ሲል የወያኔን ግፈኛ አገዛዝ በጥናታዊ ጽሑፉ አጋልጦ ሲመረቅ የለበሳትን ጥቁር ገዋን ያስመሰገነ ምሁር እንፈልግ – ካገኘን እሰዬው፡፡ በሚያገኘው ደሞዝ ብቻ እየኖረ ሕዝብን የሚያገለግል ባለሥልጣን እንፈልግ – ካገኘን እሰዬው፡፡ (እዚህ ላይ የአቶ ገብሩ አሥራትን ከሙስና የጸዳ ስብዕና ሳልጠቅስ ማለፍ አልፈልግም፡፡ አንድ ሰው የተለዬ ቆንጆ ምግብ ያምረውና ወደገብሩ ቤት በእንግድነት ይሄዳል – ቀደም ሲል ገብሩ የትግራይ ክልል ፕሬዚደንት በነበረበት ወቅት ነው፡፡ የቀረበለት ምግብ ግን የጠበቀው ሥጋና በአትክልትና ፍራፍሬ የታጀበ የሀብታም ብፌ ሣይሆን ተራ ቀይና አልጫ የሰላሱት ምግብ ይሆናል፡፡ ሰውዬው በግልጽነት “እዚህ ቤት እንዲህ ያለ ምግብ ነው እንዴ እሚዘጋጀው?” ብሎ ይጠይቃል፡፡ ያገኘው መልስ “የምንኖረው መንግሥት በሚከፍለን ደሞዝ ብቻ በመሆኑ ከዚህ የተለዬ ምግብ ማዘጋጀት አንችልም፡፡” የሚል ነበር፡፡ ይህችን እውነት ለመተንፈስ አጋጣሚ እፈልግ ነበር – ዛሬ ተሳካልኝ፡፡) በሚያገኘው ደሞዝ ብቻ እየኖረ የሀገርን ዳር ድንበር የሚያስከብር አንድም ቢሆን የመከላከያ ወይም የፖሊስ ሠራዊት መኮንን ብናገኝ ዕድለኞች ነን፡፡ የፈጣሪና የመንግሥት ሕጎች በሚያዙት መሠረት ነግዶ የሚከብር ቢያንስ አንድ ነጋዴ እንኳን ቢኖረን አሁንም ዕድለኞች በሆን፡፡ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት በቤተ መቅደስ እንደሚያንበለብለው ሁሉ በሕይወቱም ፈጣሪን የሚታዘዝ ቢያንስ አንድ ጳጳስ ቢኖረን ሎጥን ያገኘን ያህል በቆጠርነው ነበር፡፡ ቴዎድሮስ ካሣሁንንና ሻምበል በላይነህን ከመሳሰሉ በጣት የሚቆጠሩ የኪነ ጥበብ ሰዎች በስተቀር ከምንትስ ምንትስ በዘለለ የሕዝብን ብሶትና ችግር በፈጠራ ሥራዎቻቸው የሚያካትቱ የሥነ ጥበብና የኪነ ጥበብ ሰዎች ቢኖሩን መታደል ነበር፡፡ በተሠሩ በጥቂት ቀናት ወይም ወራት ውስጥ የሚፍረከረኩ የመንግሥት ቤቶችንና መንገዶችን የሚገነቡ በሙስና የተበከሉና በዕኩይ ሥነ ምግባር የተዘፈቁ ሀሳዊ መሃንዲሶች ሀገር ምድሩን ባይሞሉት ኖሮ ትምህርት ዋጋውን እንዳላጣ እንረዳ ነበር፡፡ ዘርዝረን በማንጨርሳቸው አጠቃላይ ችግሮች ውስጥ ተነክረናል፡፡ የትምህርት ጥራት አይነሳ፤ ሁሉም ዜሮ እየሆነ ነው፡፡ ለኅሊናቸው የሚታዘዙ ሠራተኞች፣ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ ወታደሮች፣ ባለሥልጣኖች፣ ነጋዴዎች፣ ዘፋኞች፣ ደራሲዎች፣ የሃይማኖት አገልጋዮች፣ዳኞች፣ ጠበቆች፣ ግምበኞች፣ ወዛደሮች፣ …. ጥቂት እንኳን ቢኖሩን ድቀታችን መልክ በኖረው ነበር፡፡ ይህ ሁሉ የሚያሳየን የተሣካ ውድቀት ውስጥ የመገኘታችንን የአደባባይ ምሥጢር ነው፡፡ ይህችን ሀገር እንደገና ገምብቶ ሀገር ለማድረግ ምን ዓይነት ጥረትና ስንትና ስንት ልፋት እንደሚጠይቀን ፈጣ ብቻ ነው የሚያውቀው፡፡ ብዙ ነገሮች ብቻ ሣይሆኑ ከሞላ ጎደል ሁሉም ነገሮች ከደንቡና ከሥርዓቱ ወጥተው በቀላሉ የማንወጣው አዘቅት ውስጥ ገብተናል፡፡

አንዳንዶቻችንን ሊያስከፋን ይችል ይሆናል፡፡ ግን እውነት ስለሆነ እዚህ ላይ ሳንጠቅስ ልንዘለው አንችልም፡፡ ወያኔ በሀገራችን ያነገሠው ዘረኝነት ከቃላት የመግለጽ አቅም በላይ ነው፡፡ትግሬን ተጠቃሚ ለማስመሰልና ከሌላው ሕዝብ ጋር ለማቃረን በእግረ መንገድም በእርግጥም የዘረኛውን ሥርዓት የጎሣ ተዋፅዖ በማጉላት በሥርዓቱ እምነት የሚጣልባቸውን ዜጎች ይበልጥ ለመጥቀም ሲባል እየታዬ ባለ የተንሻዋረረ ጎጠኛ አሠራር የማንታዘበው ጉድ የለም፡፡ ይህ እግዚኦ የሚያሰኝ ጉድ በማንም ሀገር በመቼም ዘመን አልታየም፡፡ የደቡብ አፍሪካው አፓርታይድም ይህን ያህል ግፍና በደል በጥቁሮች ላይ የፈጸመ አይመስለኝም፡፡ የኛ ዋና ችግርና ለአሣራችንም ቀጣይነት አስተዋፅዖ እያደረገ ያለው ክስተት የኛ ጨቋኞች በመልክና በቀለምም በባህልና በቋንቋም ከኛው ከተጨቋኞቹ ጋር በመመሳሰላቸው ጠላትን ከወዳጅ በቀላሉ መለየትና ዘረኛውን ከጤናማው ለይተን መተማመንን በመፍጠር ለነጻነት ትግሉ መትጋት አለመቻላችን ነው፡፡ አስቸጋሪ ነው ጓዶች፡፡ አንተን ከመሰለ ሰው ጋር ታግለህ ወደምትፈልገው ድል ለመብቃት ከባድና ጊዜንና ከፍተኛ ጥንቃቄን የሚጠይቅ ነው፡፡ አንዱና ትልቁ ችግር ይህ ስለሆነ እንጂ እነዚህን አረሞች ለመንቀል የማይቻል ሆኖ አይደለም፡፡ ግን ደግነቱ ይህም ያልፋል፡፡ ቆሞ ያለ የሚመስለው ግን ይጠንቀቅ!

ለአሁኑ ግን የዘረኝነቱ ዳፋ በሀገርህ ላይ ተቀምጠህ ሀገርህ እስኪናፍቅህ ድረስ፣ በወገንህ መካከል እየኖርክ ወገን እንደሌለህ እስኪሰማህ ድረስ፣ የጋራ እናት ሀገር እያለህ ምንም ዓይነት ዜግነት የሌለህና ባለቤት የሌለለው የመንገድ ላይ ውሻ የሆንክ ያህል እስኪሰማህ ድረስ ውስጥህን ዘልቆ በሚበረብር የሀገርና የወገን ርሀብ ትሰቃያለህ፡፡ ይህም ማለፉ ባይቀርም ለጊዜው ጭንቅላትህን ሊያፈነዳ በሚችል ሥነ ልቦናዊና እንደዬሁኔታውም ኢኮኖሚያዊ ችግር ልትወጠር ትችላለህ – በዚህ ያበዱና ለማበድም የተዘጋጁ እጅግ ብዙ ዜጎች አሉ፡፡ በ“ሰው ሀገር” እየኖርክ መብትህን መጠየቅ እንደማትችል፣ ብትሞክር ደግሞ ቢያንስ እንደሚሳቅብህና እንደሚፌዝብህ ስትረዳ ሀዘንህ ዕጥፍ ድርብ ይሆናል፡፡ ኬንያ ወይም ሆኖሉሉና ፊጂ ብትኖር የማይጓደልብህ ሰብኣዊ መብት የገዛ ሀገሬ በምትላት ኢትዮጵያህ ውስጥ ወደህና ፈቅደህ ባልሆንከው የዘርህ ማንነት ምክንያት ሲዳላብህ ስታይ አለመፈጠርህን ትመርጣለህ፡፡ ይህች ሀገር፣ ሀገር ተብላ ነው እንግዲህ እነሌንጮ ገብተው በ‹ሰላማዊ መንገድ ሊታገሉና ሕዝብን ነጻ ሊያወጡ› እንደሆነ እየተወራ ያለው፡፡ ተስፋ ስትቆርጥ አንድም ትወጣለህ አንድም ትገባለህ ማለት ነው፡፡ እኔ ተስፋ ቆርጬ መውጣት ፈልጌ መውጫ አጥቼ ቀረሁ፡፡ እነሌንጮ ተስፋ ቆርጠው ወጥተው ተስፋ ቆርጠው ሊመለሱ ነው፡፡ አንዳንዱ ደግሞ ተስፋ ቆርጦ ይወጣና ተስፋን ሰንቆ ይገባል – እንደአውራምባው ዳዊት ከበደ ያለው፡፡ ይሄ ‹ተስፋ› እሚሉት ግን መልኩ ምን ይመስል ይሆን?

ገባ ብለን በተጨባጭ እንየው፡፡ ትግሬዎች አትቀየሙኝ፡፡ እኔም ዋናው ትግሬ ነኝ፡፡ ዘመኑ ሲያልፍ ትግሬያዊ ማንነቴን እገልጣለሁ – ሊያውም አስፈላጊ ከሆነ፡፡ ያ ግን በመሠረቱ ምንም ማለት አይደለም፡፡ ቀዳሚው ሰውነት ነው፤ እናሳንሰው ካልን ደግሞ ኢትዮጵያዊነት፡፡ እነዚህ ሥልጣን ላይ ያሉ ሰዎችም – በነገራችን ላይ – ወደው አይደለም እንዲህ የሆኑት(አማራጭ አጥተው በገቡበት የወንጀል ዓለም የሚደሰቱበት አይመስለኝም)፡፡ ወደ እውነት ቢመጡ ሥልጣኑን እንደሚያጡት ለአእምሯቸው ነግረው ስላሳመኑት ነው – በዚያም ላይ ከጥንት ጀምረው የሠሯቸው ብዙ መጥፎ ተግባራት ስላሉባቸው በነዚያ ላለመጠየቅ ዋናው አብነት ሥልጣንን አጠናክሮ እስከሕይወት ፍጻሜ ወንበርን የፊጥኝ ማለት መሆኑን ያውቃሉ – በዚህ ረገድ እነሱ ስህተት የለባቸውም፤ ችግሩ የኛ የተጨቋኞች ነው – እነሱን በጋራ ትግል ላለመጣል የተዋዋልነው ፊርማ የለሽ ስምምነት ነው እየጠቀማቸው የሚገኘው፡፡ ጥቂቶች(minorities) “ተወዳድረን ሥልጣን መያዝ አንችልም፤ ብቸኛ አማራጫችን ኃይልና ጉልበት ነው” ብለው ካመኑ በየትኛውም ሁኔታ አስቸጋሪ ናቸው – የማይነቃነቁ ዓለቶች ሆነው ለብዙ ጊዜ ሊያስቸግሩ ይችላሉ፤ በሂደት ግን እንደጤዛ መርገፋቸው እንደጉምም መብነናቸው አይቀርም፡፡ እስከዚያው ግን ይሞቷታል አንጂ ሥልጣንን በፈቃዳቸው አይለቁም – “ሰላማዊ ትግል” የሚሉት ቀልድም እነሱ ዘንድ ከጨዋታነት ባለፈ በፍጹም የማይሞከር ነው፡፡ እነዚህን መሰል ጨቋኞች ዓለም የሠራቻቸውን ወንጀሎችና ሸሮች ሁሉ እያከናወኑ በሥልጣናቸውና ሥልጣናቸው በሚሰጣቸው ጥቅም ላይ እንደመዥገር ተጣብቀው ይኖራሉ፡፡ እናም የእነዚህን መዥገሮች ድርጊት ስናገር መጥፎ ድርጊት በደምና በዘር አይተላለፍምና ጤነኞች ትግሬዎች መናደድ አይገባንም፡፡ እውነቱ ባጭሩ እንግዲህ ይህን ይመስላል፡፡

ከትግሬዎች በስተቀር ሌሎች ኢትዮጵያውያን ድርሽ የማይሉባቸው የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ብዙ ናቸው፡፡ ከነዚህ መካከል የደኅንነትና መከላከያን የመሳሰሉ የፀጥታ መሥሪያ ቤቶች፣ ጅምሩክንና ማዕድናት የመሳሰሉ ከፍተኛ ጥቅም አስገኚ ቦታዎች በዋናነት ይገኙበታል፡፡ እነዚህን የመሰሉት ቦታዎች ከትግሬ በስተቀር ለሌሎች ጥብቅ ምሥጢር ናቸው – አጮልቀው እንኳን እንዲያዩዋቸው የማይፈቀድ፡፡ የማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት ከፍተኛ አመራር ሙሉ በሙሉ ማለት በሚያስችል ሁኔታ በትግሬዎች የተያዘ ነው – በስም ደግሞ አትመን (ወያኔ በስም የማታለልን ሸር የተካነበት ገና በረሃ ሳለ ነው- “ወርቅነህ በረደድ” ወይም “ደቻሣ ኩምሣ” ቢልህ እውነት አይምሰልህ – የዚህ ተጋዳላይ እውነተኛ ስም “ሐጎስ ግደይ” “ወዲ ዕንቋይ” ሊሆን ይችላል)፡፡ የትኛውንም የመንግሥት መሥሪያ ቤት አመራር ከላይ እስከታች ብንመለከት ሁሉም ትግሬ ነው፡፡ ውሸታም አትበሉኝ፡፡ እንዳልሆንኩ በተገቢ መረጃ አስደግፌ ልናገር ነው፡፡ ለምሳሌ የአንድ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ሚኒስትር እንደ ታሪካዊ ‹መጥፎ አጋጣሚ ሆኖ› ትግሬ አይደለም እንበል፡፡ ያ ሰው አማራ ነው እንበልና እንውሰድ – እዚህም ላይ ለሥርዓቱ ዕኩያንና ዕቡያን ትግሬዎች ይህ ክስተት እንደ ‹መጥፎ የታሪክ አጋጣሚ› ተቆጥሮ፡፡ አንተ አማራ ነህ ልበልህና ደስ አለህ አይደል አሁን? አዎ፣ ደስ ይበልህ እንጂ! “ወንድምህ” – ‹ዘርህ› – ተሾሞልህ ያልተደሰትህ መቼ ልትደሰት! ግን አይምሰልህ ወንድሜ፡፡ መሾምና መሻር በችሎታና በብቃት መሆኑን ዘንግተህና አንተም ወያኔ ሆነህ በደምና በአጥንት የምታመልክ ሰው ሆነህ ዘረኝነቱ ወዳንተም ተጋብቶ የኔ የምትለውን ሰው ሥልጣን ላይ ወጥቶ ያየኸው ከመሰለህና በዚያም ከተደሰትህ ተሳስተሃል ብቻ ሣይሆን ለወያኔው ወጥመድ ተመቻችተሃል እንደማለትም ነው፤ ያ ሚኒስትር የተቀመጠው ለስምና ለፖለቲካዊ ታይታ ብቻ ነው – ከግርጌውና ከራስጌው ታኮና ትራስ ሆኖ በዐይን ጥቅሻና በስልክ የሚያንቆራጥጠው ትግሬ አለ – ለዚህ ነው ሁሉም አዛዥ ናዛዥ ትግሬ ነው የምልህ፤ ለዚህ ነው የሀገሪቱ እስትንፋስ መቶ በመቶ በትግሬዎች ቁጥጥር ሥር መሆኑን በድፍረት የማረዳህ ማለትም የማስረዳህ – አንድም ቦታ ሳይቀር ሁሉም በነሱ እይታና ቁጥጥር ውስጥ ነው፤ ያ ቦታ ከመንግሥት ኅልውና ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ይኑረው አይኑረው ለነሱ ምንም ማለት አይደለም፡፡ የቆሻሻ ገንዳም ይሁን መጸዳጃ ቤት ጥበቃ፣ ስፖርት ኮሚሽንም ይሁን የዱር እንስሳት ጥበቃ ብቻ በአለቅነት ወይም በስለላ መልክ የሌሎች ወንድሞቹን እንቅስቃሴ የሚከታተል የሥርዓቱ ታማኝ እስከተቻለ ትግሬ አለዚያም የወያኔነት ሶፍትዌር የተገጠመለት ሌላ ሆድአደር ይመደባል፡፡ ለታይታ ከላይ የሚቀመጥ የሌላ ብሔር “ባለሥልጣን” ግን አሻንጉሊት ጉልቻ እንጂ ከራሱ አእምሮ አንቅቶ የሥልጣን ወንበሩ የሚፈቅድለትን ተግባራት ሊያከናውን የሚያስችል ቅንጣት የማዘዝ ሥልጣን የለውም ለዚህ ለዚህማ ጠቅላይ ሚኒስትርስ ከወላይታ ተሾሞልህ የለም እንዴ? ቲያትሩን እያስታወስኩህ እንጂ አዲስ ነገር እየነገርኩህ እንዳልሆነ አውቃለሁ፡፡ የምነግርህን ነገር ደግሞ ለራሴው ተግባራዊ ግንዛቤ ስል ራሴው በየመሥሪያ ቤቱ እየዞርኩ የተረዳሁት ነው፡፡ ያልሄድኩበት ቦታ የለም፡፡ ከብዙ ገጠመኞቼ አንድ ሁለቱን ያህል ብቻ ለአብነት እዚህ ላይ ልንገርህ፡፡ ወደጦር ኃይሎች ሆስፒታል ባለፈው ሰሞን ሄድኩ – አንድ ዘመድ ለማሳከም፡፡ ህክምናው አነስተኛ ቀዶ ህክምና ነበር፡፡ ዘመዴን ለማከም የቀረቡት ዶክተሩም ነርሶቹም ዕቃ አቀራራቢዎቹም አራቱም ትግሬዎች ናቸው፡፡ በዚህ ብቻ አይግረምህ፡፡ የከሰዓት ተቀያሪዎቹም ሦስቱም ትግሬዎች ናቸው፡፡ በሆስፒታሉ ተዘዋወርኩ፡፡ ከጥቂቶች በስተቀር ሁሉም የአስተዳደርና የህክምና ሠራተኞች ትግሬዎች ናቸው – የግቢው ብሔራዊ ቋንቋም ትግርኛ ነው – በዚህስ አልከፋኝም፡፡ ይህ ሁኔታ በአጋጣሚ ነው ከተባለ በትንሹ ሞኝነት ወይንም “አጋጣሚ” የሚለውን ቃል ካለመረዳት የሚመነጭ የዋህነት ነው፡፡ አንድ ወቅት አንድ ወታደራዊ ሰርቪስ መኪና ውስጥ በአጋጣሚ ተገኝቼ እንደታዘብኩት ከነበሩት አሥራ ምናምን ሰዎች ውስጥ ትግርኛ የማይናገረው ሾፌራችን ብቻ ነበር፡፡ እንዴ፣ እውነቱን እንነጋገር ካልንማ ጉዳችን ብዙ እኮ ነው፤ ለምን እንተፋፈራለን? ባይሆን እናውራውና ይውጣልን እንጂ፡፡

ወደ መንግሥት ባንኮችና ኢንሹራንሶች ሄድኩ፤ ወደ አየር መንገድ ሄድኩ፤ ወደ ዩኒቨርስቲዎችም ሄድኩ፡፡ ሁሉም በትግሬ ተጥለቅልቋል፡፡ የከተማዋ ጠረን ከዳር እዳር ወደትግሬነት ተለውጧል – ምናልባትም ‹መቐለ› ላይ ያለህ ሊመስልህ ቢችል አይፈረድብህም፡፡ አነጋገሬ ዘና ያለ እንዲሆን ያደረግሁት ሆን ብዬ ነውና ብዙም አይሰማችሁ፡፡ እናም ብዙ ቦታዎች ሄድኩ – ያው ነው፡፡ ሰዎች “ይህ ዘመን የትግሬዎች ብቻ ሆኗል” የሚሉትን ሃሜት ሊያስተባብልልኝ የሚችል አንዳች ነገር ባገኝ ብዬ ተመኘሁ፡፡ ነገር ግን አልተሳካልኝም፡፡ ትግሬ በአንዳች ምትሃታዊ ነገር እየተባዛ መላዋን የወያኔ ኢትዮጵያ በምልዓት ያዳረሳት ይህል ተሰማኝ – ማዳረሱ ለበጎ ነው ችግሬ የመድሎና የጥፋት ኃይል መሆኑ ላይ ብቻ ነው፤ ሌላውን ሕዝብ ምን በላው እስክትሉ ድረስ በትግሬዎች የመንግሥትን መሥሪያ ቤቶች በበላይነት መቆጣጠር ትገረማላችሁ – ትግሬ ስልህ ደግሞ በአባቱ ወይ በእናቱ ሊሆን ይችላል – እንዲያውም ትግርኛ የማያውቅና የማይናገርም ትግሬ ልታገኝ ትችላለህ – መሃል አገር የተወለደና ያደገ፡፡ “ትንሽ ሥጋ እንደመርፌ ትወጋ” የምትለዋ ብሂል በወያኔ ዘንድ ትልቅ ዋጋ አላት፤ ሌላውን ስለማያምኑ በተለይ ሹመት ላይ የሚያስቀምጡት ሰው ከነሱ ቁጥጥርና አመኔታ የማይወጣ እንዲሆን ይጠነቀቃሉ፡፡ አሁንም አንድ ነገር ግልጥ ላድርግ – ሌሎች ዜጎች በኃላፊነትም ሆነ በተራ ሠራተኛነት አይቀጠሩም ወይም የሉም ማለቴ አይደለም፤ እያልኩ ያለሁት ትርጉም ባለውና ወሳኝ በሆነ ደረጃ ፈላጭ ቆራጮቹ ትግሬዎች ናቸው ነው፡፡ ለምሳሌ በአንድ መሥሪያ ቤት ውስጥ ከመቶ ሠራተኞች መካከል አምስቱ ብቻ ትግሬዎች ቢሆኑ ዘጠና አምስቱ ሠራተኞች የሚሽቆጠቆጡትና የሚያሸረግዱት ለአምስቱ ትግሬዎች ነው – ከመስቀያው ነው – በጌታዋ የተማመነች ፍየል እኮ ቀንዷን በጎች መሃል ነው የምትሰካ፤ በዚህ ዓይነቱ አጋጣሚ ደግሞ እኛ ኢትዮጵያውያን ያለንን የማሸርገድ ብቃትና ለተሹዋሚ የማጎብደድ ተፈጥሯዊ ዝንባሌ መረዳት ይቻላል፡፡ ጊዜ ዘምበል ሲል ደግሞ እንዴት የመሰለ አክሮባት እንደምናሳይ ወደፊት የምናየው ይሆናል፡፡

በበኩሌ በትግሬ ሁሉንም የሥልጣን ቦታዎች መቆጣጠር ብዙም አልከፋም፡፡ የሚያስከፋኝ ባለሥልጣናቱ ቦታውን የሚያገኙት በችሎታና በትምህርት ሳይሆን በዘር ቁርኝት በመሆኑና ያም ሥራን ክፉኛ እያበላሸ በመሆኑ ነው፡፡ አለበለዚያ ሥራውን በሚችሉ የተማሩ ትግሬዎች ሁሉም ቦታ ቢያዝ ግዴለኝም፡፡ አሁን ያለው ችግር ግን አይነሳ፡፡ አንድም ትምህርት የሌለው ምናልባትም የሁለተኛና የአሥረኛ ክፍል ወያኔ ትልቅ ቢሮ ይይዝና የተማረው የሌላ ጎሣ አባል በሥሩ ሆኖ ከኅሊናው ባፈነገጠ አሠራር በዚህ ማይም ወያኔ እየተረገጠ ስታዩ የሥራው መበላሸት ብቻ ሣይሆን ዘረኝነት አንዲትን ሀገር በምን ዓይነት ደረጃ ድራሹዋን እያጠፋት እንደሆነ በመገንዘብ ታዝናላችሁ፡፡ ትግሬ መሆን ብቻውን ለሥልጣንና ለሀብት ካበቃ፣ አማራ መሆን ብቻውን ጉራን ለመቸርቸርና በትምክህት ለመወጠር ካበቃ፣ ጠምባሮ መሆን ብቻውን ለንቀትና ለተዋራጅ ኑሮ ከዳረገ … ሰብኣዊነትና የጋራ ብሄራዊ ማንነት አዲዮስ! በኢትዮጵያ እየታዘብን ያለነው ጉደኛ ትንግርት ዓይነቱ ብዙ ነው፡፡ ባለፉት 23 ዓመታት የጠፋውን ጥፋት ለማረም ስንት ዓመት እንደሚፈጅ ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቀው፡፡ በማይማን የተሞላውን በቅርጽ ያለ የሚመስል በይዘት ግን ደብዛው የጠፋውን የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የሰው ኃይል አደረጃጀት ለማስተካከል ራሱ ከሩብ ምዕተ ዓመት ያላነሰ ጊዜን መውሰዱ አይቀርም፡፡ የተማረ የሲቪል ሰርቪስ ሠራተኛ ለማግኘት፣ በሥነ ምግባር የታነጸና የሥራ ተነሳሽነት ያለው ዜጋ ለማፍራት ብዙ ጥረት ይጠይቃል፡፡ በአሁኑ ወቅት ለእስታቲክሳዊ ፍጆታ ካልሆነ በስተቀር የመንግሥት ሥራ በአግባቡ ይሠራል ማለት አንችልም፡፡ ከሞላ ጎደል ሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ሕይወት ያላቸው የሚመስሉት እዚህና እዚያ በለጣጠፏቸው የማይተገበሩ መፈክሮችና “ራዕይ፣ ዓላማ፣ ተልዕኮ፣…” በሚባሉ ትላልቅ የወረቀት ጀንዲዎች ላይ በጉልህ በተቀመጡ የሚያማምሩ ጽሑፎች አማካይነት ብቻ ነው፡፡ በተረፈ የዚህና የዚያ የሥራ ሂደት ባለቤት እየተባለ በሥሩም ዕውቀትና በቂ ሥልጠና የሌለው ሠራተኛ በዘመድና በፖለቲካ አመለካከቱ እየተመደበ አለተጨባጭ ሥራ ስላውደለደለና ሕዝብን በጉቦ ስላስለቀሰ ሀገር ትለማለች ብሎ መጠበቅ የሚቻል አይደለም፡፡ አዲስ የሚቋቋሙት መሥሪያ ቤቶችም በአብዛኛው የሥርዓቱን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የሚጠቅሙ የሀገር ሀብት አባባካኝ እንጂ ለሕዝብና ለሀገር ዕድገት የሚውሉ አይደሉም፡፡ ገመናችን ብዙ ነው፡፡

ንግዱን ያየን እንደሆነ አነስተኛና ጥቃቅን ከሚባሉት የሥርዓቱ ዕንባ ጠባቂዎች ጀምሮ የአንበሳውን ድርሻ ይዘው ያሉት ወያኔዎች ናቸው – ከአዲስ አበባ የንግድ ማዕከላትና ሱቆች ውስጥ፣ በአዲስ አበባ አስፋልት ከሚሽከረከሩ ዘመናዊ አውቶሞቢሎች ውስጥ፣ በየምሽቱ ዳንኪራ ከሚረግጡ ዜጎች ውስጥ፣ በየሉካንዳውና በየመጠጥ ቤቱ በጮማና ዊስኪ ከሚቀማጠሉ ‹ኢትዮጵያውያን› ውስጥ ስንቱ መቶኛ ኢ-ትግሬ ሊሆን እንደሚችል ገምቶ መናገሩ ሆድ ሊያስብስ ስለሚችል ሆድ በሆድ ይፍጀው ይቀመጥ፡፡ (እዚህ ላይ ቅድም በኢሳት የተከታተልኩት አንድ ቃለ መጠይቅ ትዝ አለኝ፡- አሥራት አብርሃም የተባለ ሰሜነኛ ከግዛው ጋር ሲነጋገር እንደሰማሁት የኢትዮጵያ ችግር እርሱና መሰል አመለካከተኞች እንደሚሉት የንግሥናው ነገር ከሸዋ ወደ ትግራይ ወይም ከትግራይ ወደሸዋ የመምጣት ጉዳይ አይደለም፡፡ እንደዚያ ያለው ንትርክ ጉንጭ አልፋ የሽፋን ተኩስ ዓይነት ነው፡፡ ዋናው ትግሬ ነገሠ ወይም አማራ ተሻረ የሚለው ሳይሆን የኅልውና ጉዳይ ነው፡፡ ትግሬና አማራ በሥልጣን መፈራረቃቸው እንግዳ ነገር አይደለም፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ወያኔ ባመጣው የዘር በሽታ መነደፉና በግፍ አገዛዝ ክፉኛ መሰቃየቱ ግን በታሪካችን ታይቶ የማይታወቅ እንግዳ ነገር ነው፡፡ ስለዚህ ችግሩን እስከዚህ አታሳንሱት – አታውርዱት፤ ችግራችን ከነገሥታት ምርጫ ጋር ፈጽሞውን የሚያያዝ አይደለም – ከጭቆና መግረር ጋር እንጂ፡፡ በከፊል አማራ ያልነበረው መንግሥቱ 17 ዓመታትን በገዛ ጊዜ የዘር ችግር እንዳሁኑ በፈጠጠ ሁኔታ አልነበረም፤ ሕዝቡም ‹ኦሮሞ ገዛን፤ የሸዋ አማራ ይሁንልን!› ብሎ አልጮኸም፡፡ አማራው መልካም ገዢ ካገኘ ሥልጣን ቀረብኝ ብሎ አካኪ ዘራፍ የሚል አይመስለኝም – ትግሬም ሆነ ሌላውም ሕዝብ እንዲሁ፡፡ ይቺ ማምታቻ ናት፡፡ እዬዬም ሲዳላ ነው ወገኖቼ፡፡ ጥድቁ ቀርቶብኝ አሉ …)

ትግሬ ሆኖ ፖለቲካን ከጠላ ወደንግዱ መግባትና ለሌሎች በተዘጋጋ ለርሱ ግን በተመቻቸ የጨዋታ ሜዳ “በመነገድ” በአንድ አዳር ሊከብር ይችላል፡፡ ንክኪ ከሆንክ አንድም ሳንካ ሳይገጥምህ የሀብት መንገድህ ሁሉ አልጋ በአልጋ ይሆንልሃል፡፡ ሌላ ከሆንክ ግን ሁሉም ይከረቸምብህና ብቸኛ አማራጭህ ስደትና ድህነት ይሆናል፡፡ አንዲት እህቴ አንድ ንግድ ትጀምራለች፡፡ ሰዎቹ ይመጡባትና እርሷ በወር የተጣራ ሁለት ሺህ ለማታገኝበት ንግድ በዓመት 62 ሺህ ብር ግብር ክፈይ ይሏታል – ወያኔ ጋ ማሰብ ብሎ ነገር የለም፡፡ በግልጽ ሂድ ላይሉህ ይችላሉ – እንድትሄድ ግን ያደርጉሃል፤ ውጣ አይሉህም እንድትወጣ ግን ያስገድዱሃል፡፡ ያቺ ዘመዴ ምን ከምን ታምጣና ትክፈል? ኪሣራዋን ተከናንባ የባሏን እጅ እያየች ተቀምጣለች፡፡ አንተን በእነሱነት ከጠረጠሩህ ምንም ምክንያት ሳያስፈልጋቸው እንዳትኖር ማድረግ ይችላሉ፡፡ በዚህ ሁኔታ ከንግድ ውጪ እያስወጡ ሙልጭ ድሃ ያደረጓቸውን ወገኖቻችንን ቤቱ ይቁጠራቸው፡፡ የምትሠራበት ቤት የመንግሥት ከሆነ ለነሱ አሸወይና ነው – ኪራይና ግብር ይቆልሉብህና ተማርረህ በራስህ ጊዜ ውልቅ ብለህ እንድትወጣ ያደርጉሃል፤ በማግሥቱ በጥንቱ አነስተኛ ኪራይና በዝቅተኛ የፍሬ ግብር ግምት የነሱን ሰው ያስገቡበታል፤ ስንትና ስንት የትግሬዎች ሱቅና ትላልቅ ንግድ ቤት በግልጽ ካለቫት ሲሸጡ እያየህ ባጠገባቸው የምትገኝ ሚጢጢዬ የሌላ ሰው ሱቅ ግን ካለቫት ስትሸጥ ብትገኝ አሣር ሲገጥማት ታያለህ – እነሱን ማንም አይቆጣጠራቸውም፤ በአንዲት ሀገር ውስጥ ብዙ ዓይነት ዜጎችና ሁለት መንግሥታት በግልጽ የሚታዩት ኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑን ስትገነዘብ በደረስንበት የዝቅጠት ደረጃ ታርር ትደብናለህ – ግን እውነትም ሰዎች ስንባል ከእንስሳትም የወረድን ምን ያህል ከንቱዎች ነን? የሚሠራውን ግፍ ስትሰማ ይሰቀጥጥሃል፡፡

ባለኝ መረጃ መሠረት በውድ ትምህርት ቤቶች ከሚማሩ ተማሪዎች መካከል ከ95 በመቶ በላይ የነሱ ልጆች ናቸው፤ ሌላው መንደር ያውደለድላል ወይም እንደሚፈጭ ጥሬ ጎዳና ላይ ተሰጥቶ ይውላል፡፡ የመንግሥት ት/ቤት ተብዬዎቹ ውሎ መግቢያ እንጂ ትክክለኛው የመማር -ማስተማር ሂደት የሚካሄድባቸው አይደሉም፡፡ በየቦታው የሚገነቡ ሕንጻዎችና የንግድ ተቋማት የነሱው እንደሆኑ ሁሉም ይናገራል፡፡ ከነሱ ውጪ ሌላው ነግዶም ሆነ ሠርቶ መብላት እንዳይችል በህግ የተገደበ ይመስላል፡፡ ለነገሩ ህግ የሚባል ነገር የለም፤ ሀገሪቱ በኳስ አበደች ዓይነት ጰራቅሊጦሳዊ ያልተለመደ የጉሽ ጠላ ስካር ውስጥ ትገኛለች፡፡ ለምሳሌ አትቀደም እንጂ ሰው ቢገድልህ ተከታትሎ በደለኛን ወደህግ የሚያቀርብ አካል ለማግኘት ትቸገራለህ፤ በኪነ ጥበቡ ይነጋል፤ ይመሻልም፡፡ የሙስናው ነገርም የጉድ ነው፡፡ በፖለቲካ አይሁን እንጂ ወንጀለኛን ወይም በሕግ ሥር የሚገኝን ሰው ለማስፈታት ጉቦ ከከፈልክ ባደረበት ወይም በዋለበት ማረፊያ ቤት አይውልም ወይም አያድርም ፡፡ ከሚነዳው የሕዝብ ትራንስፖርት መኪና አንድ ሰው በር ከፍቶ ዘልሎ ሲወርድ በመሞቱ ምክንያት የተከሰሰ አንድ ሾፌር ፍርድ ቤት በነጻ ካሰናበተው በኋላ ፖሊሶች አሥረው 17 ሺህ ብር ገደማ በሚስቱ በኩል አስመጥተው እንደተከፋፈሉ የሰማሁት በቅርቡ ነው፡፡ ሀገርህ ያለች ትመስላለች እንጂ በቁሟ ሞታልሃለች፡፡ ህግ ወደ ተራ ነገርነት ተለውጦ የምንተዳደረው በጉልበትና በሙስና ብቻ ሆኗል፡፡ በደሞዝ መተዳደር ስለማይቻልና ስለቀረም በሙስና የማይሠራ ነገር የለም፡፡ ቤተ ክርስቲያን እንኳን ብትሄድ ጥሩ የመቃብር ቦታ ለማግኘት፣ ረጂም የጸሎት ፍትሀት ለማግኘት፣ የሰበካ ጉባኤ አገልግሎት ለማግኘት፣ የልደት ሠርቲፊኬት ለማግኘት፣ አገልጋይ ከሆንክ ደህና ገቢ ወዳለው ደብር ለመዛወር፣ የድቁና ወይም የቅስና ማዕረግ ለማግኘት፣ በጠያፍ ድርጊት የክህነት ሥልጣንን ላለማጣት፣በቄሰ ገበዝነት ጥሩ ቦታ ለመሾም/ለመመደብ… ካለጉቦ አይሞከርም፡፡ ውድቀት ከዚህ በላይ ካለ እኔ አላውቅም፡፡ ሥርዓቱ የሞሰነ (የጠፋ) ስለሆነ የዚህ ሁሉ ጥፋት እስፖንሰሩ ወያኔ ነው፡፡ (በአንዲት ጨዋታ ለምን ፈገግ አላሰኛችሁም – አንድ ሦስት የሚሆኑ ሙስሊም ጓደኛሞች ሶላት ላይ ናቸው፡፡ አንድ በቅርባቸው የነበረ ሌላ ሙስሊም ሣንቲሞችን በብዛት ከኪሱ ያወጣና እየሰገዱ እንዳሉ ሆጨጭ አድርጎ አጠገባቸው ይበትናል፡፡ በተንቃጨለው የሣንቲም ድምፅ ሰጋጆቹ ከስግደቱ ተናጥበው ወደተንቃጨለበት ሥፍራ ሁሉም በአንዴ በደመ ነፍስ ዘወር ይላሉ፡፡ ያኔ ያ ተንኮለኛ ሰውዬ “ይህንን ዱኣ እንኳን አላህ እኔም አልቀበለውም” አላቸው ይባላል፡፡ ለምን ትዝ አለኝ ግን?አዎ፣ ልብንና ኩላሊትን የሚመረምር የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሞኝ የሚመስለን የሃይማኖት ሰዎች እጅግ ብዙ ነን፡፡ እርሱንና የርሱን እየረሳን ወደ ዓለም ብንጠፋና ከወንበዴዎች ጋር ብንወግን የወንበዴዎቹን የመጨረሻ ዕጣ እንጋራለን፡፡)
ትግሬዎች ተሳስተዋል፤ “የትኞቹ ትግሬዎች? “ በሚል ፀጉር አንሰንጥቅ፡፡ ኩይሃ ወይም እንደርታ ገጠር ውስጥ በላቡ አፈር እየገፋ የሚኖር ገበሬ መቼም ተሳስተሃል ልል አልችልም፡፡ ስለዚህ የተሳሳቱት ትግሬዎች ሕወሓትን አምልከውና አምነው ኢትዮጵያን ለማውደም ታጥቀው የተነሱትን እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ እነዚህኞቹ ትግሬዎች ይህን ያህል ገሃድ የወጣ ዘረኝነት ውስጥ መግባት አልነበረባቸውም፡፡ መሪዎች ሊሳሳቱ ይችላሉ፡፡ ተራዎቹ ዜጎች ግን ከትዝብት በሚያልፍ እስከዚህ ደረጃ ጭልጥ ብለው ወርደው በተሳሳቱ መሪዎች የጥፋት ጎዳና መትመም አይጠበቅባቸውም ነበር፡፡ ምክንያቱም “ነገ” የሚባል ጦሰኛ ቃል አለ፡፡ የትናንትን ታሪክ ማንበብ ያሰኘኝ – ቀደም ብዬ እንደተናገርኩት – ዛሬን ከትናንትና ትናንትንም ከዛሬና ከነገ ጋር በማስተያየት መጪው ጊዜ ምን ሊሆን እንደሚችል በመገመት ለመተንበይ ነው፡፡ እንደዚያም ይቻላል፡፡ እናም እተነብያለሁ – ነገ ለትግሬዎች ክፉ ቀን ይሆናል፡፡ አሁን ላይ ሆኜ እንደሚታየኝ የእኔን መሰል ደጋግ ትግሬዎች ሸክም ከባድ ነው፡፡ በትግሬነቴ ብዙ መሥራት የሚገባኝ አሁንና ለወደፊትም ብዙ የሥራ ጫና እንዳለብኝ ይሰማኛል፡፡ በወንድሞቼና በእህቶቼ ተላላነት ምክንያት እየሆነ ባለው ነገር ሁሉ አዝናለሁ፤ ማዘን ብቻውን ግን የታሪክን ቅጣት እንደማያስቀር እረዳለሁ፡፡ እናም በትግሬነቴ ሸክሜ ብዙና የሚያጎብጥም መሆኑን የምገነዘበው ከዚህ አኳያ ነው፡፡ ዶክተር ኃይሉ አርአያ፣ አብርሃ በላይ፣ ኤልያስ ክፍሌ፣ አብረሃም ደስታ፣ አስገደ ገ/ሥላሴ፣ ፀጋዬ ገብረ መድኅን፣ ጌታቸው ረዳ(የኢትዮሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)፣ … እና ሌሎችም ጥቂት የማይባሉ ብርቅዬ ትግሬዎች እየደከሙ ያሉት ሦስተኛውን ዐይናቸውን ፈጣሪ ስለከፈተላቸውና የነገን የፈጣሪና የታሪክ ፍርድ ከወዲሁ በማወቃቸው እንጂ እንደትግሬነታቸው ቢሆን ውጪ ያሉት ወደሲዖሊቱ ኢትዮጵያ በመግባት ቢፈልጉ ሚኒስትር ቢፈልጉ የናጠጠ ነጋዴ ሆነው በደናቁርት ወንድሞቻችን አገዛዝ ሥር ሥጋቸውን በምቾት ሊያኖሩ በቻሉ ነበር፡፡ ግን ግን “ከሰው መርጦ ለሹመት፣ ከእንጨት መርጦ ለታቦት” እንዲሉ ነውና እነዚህ በሁለት እሳት ውስጥ ሆነው እየተለበለቡ የሚገኙ ትግሬ ወገኖቻችን ሁሉንም እንዳመጣጡ እንዲቋቋሙ ፈጣሪ ትግስቱንና ችሎታውን ሰጥቷቸው ኢትዮጵያ የሁሉም ዜጎቿ እኩል ሀገር እንድትሆን እየተደረገ ባለው ሁለንተናዊ ትግል የበኩላቸውንና አቅማቸው የፈቀደላቸውን ያህል በመታገል ላይ ይገኛሉ፡፡ እግዚአብሔር ከነሱም ጋር ይሁን፡፡

የወደፊቱ ጊዜ ከአማራነት ስሜት፣ ከትግሬነት ስሜት፣ ከኦሮሞነት ስሜት፣ … በጥቅሉ ከጎጠኝነት ስሜት በአፋጣኝ መውጣት የሚጠበቅብንና የምንገደድበትም ጊዜ ነው፡፡ በተመሳሳይ የቂሎች ዘፈን ነጋሪት እየደለቅን በከንቱ የምንጠፋፋበት ዘመን ማብቂያው ላይ የደረሰ ይመስለኛል፡፡ ለዚህ አስከፊ አደጋ ያጋለጡን ብዙ ታሪካዊ አጋጣሚዎች መኖራቸው እውነት ቢሆንም የአሁኑ ትውልድ ከአንጋፋዎቹ ንዝህላልነት ብዙ የሚማርና የራሱን መፃኢ ዕድል የተቃና እንዲሆን ጥረት የሚያደርግ ይመስለኛል፡፡ በተቆፈረለት ጉድጓድ እየገባ ለማለቅ የቆረጠው ትውልድ በሂደት ለአዲሱ ትውልድ ሥፍራውን እየለቀቀ ይሄድና ወደመላው ዓለም የተበተነው ሥልጡኑ ኢትዮጵያዊ በአዲስ የአብሮነት ስሜት አዲሲቷን ኢትዮጵያ ገንብቶ እያንገሸገሸው ካለው የስደት ኑሮ ሊገላገል የወሰነ ይመስለኛል፡፡ አሮጌው ትውልድ ከነተንኮሉና ከነከፋፋይ ቅራቅንቦው ወደታሪክ መዝገብነት የሚከተት ይመስለኛል፡፡ በዘር መሳሳብና በአንድ ቅጽበት የናጠጠ ከበር የሚኮንት ጊዜ ተወግዶ በወዝና በላብ ተሠርቶ የሚከበርባት ኢትዮጵያ ልትፈጠር ዳርዳርታው የተጀመረ ይመስለኛል፡፡ (የአንድ ባለሥልጣን የዘመድ ልጅ አሠራ ሁለተኛ ክፍል እምቢዬው ይለዋል፡፡ በአንዲት ቀጭን ደብዳ ከሞሰበ ስሚንቶ በዱቤ ስሚንቶ እንዲወስድ ይደረጋል፡፡ ወዲያውኑ ያን ስሚንቶ ሸጦ ከወጪ ቀሪ 4 ነጥብ ምናምን ሚሊዮን ብር በከፈተው የባንክ አካውን ውስጥ ዘጭ ይልለታል – በድንጋጤ አለመሞቱ እሱው ሆኖ ነው – በአሁኑ ሰዓት ቢጠሩት የማይሰማ የልጅ ቱጃር ነው፤ እሱን መሰሎች ደግሞ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አሉ፡፡ እኔ ብሆን በደስታ ብዛት ሞቻለሁ፡፡ እኛ እንዲህ ነን፡፡ ወያኔ እንዲህ ነው፡፡ በአንድ ሌሊት ወገኑን ማክበርና በአንድ ሌሊት ተመሳሳይ ደግሞ የሚጠላውን ወደ አሰቃቂ ድህነት በማውረድ ማማቀቅ የሚችል ሕወሓት ብቻ ነው፡፡)

የሸዋ አማራ ለቀብራራው ጎንደሬ እንደባሪያ የሚቆጠርበት ዘመን ነበር፤ አማራነት እንደ ልዩ ትምክህት እየተቆጠረ በባዶው የሚኮፈሱበት፣ ከባዶ እግር ሳይወጡና ትከሻ ላይ ያለቀን መርዶፋና አቡጄዲ ሳይቀይሩ እንዲሁ በከንቱ በዘር የትውልድ ሐረግ የሚኩራሩበት ዘመን ነበር፡፡ በአማራነት ሥራ መያዝ ወይም አለመያዝ፣ በትግሬነት ሥራ መያዝ ወይም አለመያዝ፣ በኦሮሞነት ሥራ መያዝ ወይም መልቀቅ የገሃዱ እውነታ አሳዛኝ ነፀብራቅ ነበር፤ አሁንም በባሰ ደረጃ እንደቀጠለ ነው፡፡ ደረጃው ይለያይ እንጂ የአሁን ጥፋቶች አሁን አልተጀመሩም ቢባል ማጋነን አይደለም፡፡ እውነትን እንዳለ መቀበል የንስሃ መጀመሪያና የፅድቅ መንገድ ስንቅ ነው፡፡ የነበሩን ችግሮች ናቸው ግዘፍ ነስተው ኅልውናችንን እስከመፈታተን የደረሱት፡፡ ወያኔ የጀመረው ጥፋት የለም፤ ግን አራቀቀና ጫፍ አደረሳቸው፡፡ ስህተትን ወርሶ በዐዋጅ ማፅደቅና የመንግሥት መለያ ማድረግ የወያኔ ተፈጥሮ ሆነ እንጂ ቀድሞም ስህተቶች ነበሩብን፤ አልነበሩብንም ማለት ሞኝነት ይመስለኛል፡፡ የአሁኑ ትውልድ ግን ከራሱ ታሪክና ከየሚሰደድበት ሕዝብ ብዙ እየተማረ የወደፊት ሕይወቱን አስተካክሎ በዘልማድ ሳታጣ ያጣች የምትባለዋን ሀገሩን በቁጭትና በእልህ በጋራ ለመገንባትና በፍቅርና በመተሳሰብ ለመኖር የሚረባረብ ይመስለኛል – ነገ፡፡ ምን እስክንሆን እንጠብቃለን? በዓለም ፊት ከዕቃነት ከመቆጠር የበለጠ ምን ሊደርስብን ይችላል? ከአሁን ዘመን በበለጠ ብሔራዊ ክብራችን የተዋረደበት ዘመን የለም፡፡ እናም ሁሉም ነገር እንደሚፀነስና እንደሚወለድም፣ እንደሚያድግና አርጅቶም እንደሚሞት በወያኔ አድጎና ጎምርቶ ለአካለ መጠን የደረሰው የብሔራዊ ክብራችን ውድቀትና የጋራ ማንነታችን መደብዘዝ አሁን በማርጀቱ የማይቀርለትን ሞት እየሞተና በአንጻሩ የወደቀው ክብራችን ትንሣኤውን የሚቀዳጅበት ብሩኅ ዘመን እየመጣ ይመስለኛል፡፡ ብዙ እውን ሊሆኑ የሚችሉ የሚመስሉኝ ነገሮች እየታዩኝ ስለሆነ ወያኔዎች በተስፋ መቁረጥ አትውቀሱኝ፡፡ በል በል የሚለኝ አንዳች ነገር ስላለ ነው እንጂ እናንተን ለማስቀየም ፈልጌ አይደለም፡፡

ወደነማን እናንጋጥ? መሲሆቻችን እነማን ናቸው? ወጣቱ ምን ከነማን ይማር?

እመለስባቸዋለሁ ወዳልኳቸው ሁለት ነገሮች ልመለስ፡፡ ሰው በጠፋበት ዘመን አንዲት ሴት ልጅ ከርቸሌ ውስጥ ተገኘች፡፡ ይህች ልጅ ርዕዮት ዓለሙ ናት፡፡ አንድ የዐረብ ሀገር ተረት ባማርኛ ላስታውሳችሁ፡፡ “እከክ የሰጠ ጥፍር አይነሳም፡፡” ተፈጥሮም እግዜርም አንድ ተመሳሳይ ሕግ ያላቸው ይመስላል፡፡ በጨለማ ውስጥ ብርሃን እንዲጸነስ ያደርጋሉ፤ በብርሃንም ውስጥ ጨለማ፡፡ እነዚህ ነገሮች እየተፈራረቁ የሕይወትን ምንነት በአሉታዊና በአወንታዊ መልኮች ጎልተው እንዲታዩ ያደርጋሉ – አንዴ ይነጋል፤ አንዴ ይጨልማል፡፡ ምናልባት ባይነጋና ባይጨልም ኖሮ ማን ያውቃል ሕይወት ትርጉም አልባ ልትሆን ትችል ነበር፡፡ ስለዚህም ይመስላል እልም ባለ የተስፋ መቁረጥ ዘመን ውስጥ ተስፋን የሚያጭሩ ጥቂት ዜጎች ከወደቀው ትውልድ ውስጥ ብቅ የሚሉት፡፡ ስለዚህም ይመስላል ቆመናል የሚሉት በወደቁበት ሰዓት ከታናናሾች መካከል ታላላቆች የሚነሱትና የአርአያነትን መቅረዝ ከፍ አድርገው ይዘው እንደመጥምቁ ዮሐንስ በምድረ በዳ የነጻነትን ፋና የሚያበሩት፡፡ ስለዚህም ይመስላል ብዙዎች ወድቀው እንደዓሣማ የገማ ጭቃ ውስጥ ሲርመጠመጡ ጥቂቶች የኅሊናቸውን ጥሪ ተቀብለው በአካላዊ ስቃይ ለሚገኝ መንፈሣዊ ሃሴት የሚተጉትና ታሪካቸውን በወርቃማ ቀለም የሚጽፉት፡፡ ሕይወት ታላቅ ዩኒቨርስቲ ናት፤ ብዙ አየን – እያየንም ነው፡፡

ርዕዮት እግዚአብሔርና አላህ የሰጡን የኢትዮጵያ ዕንቁ ልጅ ናት፡፡ ርዕዮት በችግራችን ጊዜ ፈጣሪ የሰጠን እንስት ኤፍሬም ናት – “ኤፍሬም” ማለት “በመከራዬ ጊዜ የሰጠኸኝ ልጅ” ማለት ነው ሲባል ሰምቻለሁ፡፡ ርዕዮት ብዙ ያነበበች መሆንዋን ከመጽሐፏ መረዳት ይቻላል፡፡ መስዋዕትነት ከማወቅ ጋር ሲሆን የሠመረ ይሆናል፡፡ ማወቅ ብዙ ትናንሽ ግን አዘናጊ የሆኑ ዓለማዊ ነገሮችን እንድንንቅ፣ ታጋሽና አስተዋይ እንድንሆን፣ ከሚጠፋና ከሚጠወልግ ዝናና የዓለም ሀብት ይልቅ ለማይሞት የሀገርና የወገን ክብር እንድንተጋ… ያደርገናል፡፡ ይህን በርዕዮት፣ በእነእስክንድር ነጋና አንዱዓለም አራጌ አማካይነት እያየነው ነው፡፡ ብዙዎች ሊሸከሙት የከበዳቸውን ቀምበር እነሱ ተሸከሙት፡፡ የኛ ክርስቶሶች እነሱ ናቸው፡፡ የኛ ቤዛዎች እነሱ ናቸው፤ ብዙዎች ሲከዱን እነሱ ከጎናችን ሆነው ስለኛ የኛን መስቀል ተሸከሙ፡፡ ልደቱ አያሌውን የመሰለ ከሃዲ በወጣበት ማኅጸን እስክንድር ወጣበት፡፡ ሙሉጌታ አሥራተ ካሣ በወጣበት ማኅጸን አንዷለም አራገጌ ወጣበት፡፡ ገነት ዘውዴ በወጣችበት ማኅጸን ርዕዮት ዓለሙ ወጣችበት፡፡ ለጊዜው ማለት የምንችለው እንዲህ ብቻ ነው – ሌላ ምን ማድረግ እንችላለን? ምንም፡፡ እውነተኛ የሕዝብ ድምፅ የሚከበርበት ጊዜ ሲመጣ ግን በተለይ ይሁዳዎች ተገቢ ፍርዳቸውን እንዲያገኙ በፍትህ አደባባይ በግልጽ እንጮሃለን፡፡

ባነበብኩት የ204 ገጽ ስብስብ ሥራዎቿ ውስጥ ይህች ወጣት ሴት ጋዜጠኛና ለዜጎች መብት ተሟጋች ያልዳሰሰችው ማኅበራዊ ችግር የለም፡፡ ከይዘቶቹ በመነሣት ነው ልጂቱ ብዙ ያነበበች መሆንዋን የተገነዘብኩት፡፡ ለስኬታማው ውድቀታችን እንደ አንድ ማሳያ ይሆነኛል ብዬ ካሰብኩት ውስጥ የአንድ ዘምቦለል ኢትዮጵያዊን ታሪክ ከርዕዮት መጽሐፍ ጠቅሼ መናገር እፈልጋለሁ፡፡

“… በዘመናችን ከሚገኙ ታዋቂ ሰዎቻችን መካከል አንዱ የሆኑት አንጋፋው የማሰታወቂያ ባለሙያ አቶ ውብሸት ወርቃለማሁ በአንድ ወቅት ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ ይታወሰናል፡፡ በቃለ ምልልሳቸው ሴትና መኪናን ቶሎ ካልቀያየሩት ባሕርይው እንደሚበላሽ ሊያስረዱን የሞከሩት አቶ ውብሸት ሁሌም ለብሰው ከሚታዩት ካባ ጋር አብረው የጠቀስነውን ብቃት (የሕዝብ ሰው የመሆንን ብቃት ማለቷ ነው) አለመጎናጸፋቸውን እንረዳለን፡፡” (ገጽ 177)

ርዕዮት የጻፈችበት ርዕሰ ጉዳይ እንስታዊነት (ፌሚኒዝም) በኢትዮጵያ ያለበትን ችግር ነው፡፡ የጠቀሰችው ሰውዬ ታዋቂና ዝነኛ ነው – አርአያ ሊሆን ይገባው የነበረ ነገር ግን እንደኔ አመለካከት ኢትዮጵያዊ ጨዋነትን ገደል የከተተ ብኩን ዜጋ ነው – መፍረድ ቀላል ነው መቼም፡፡
ታዋቂነት ዕዳ ነው፡፡ ብዙ መዘዝ አለበት፡፡ አንድ ሰው ታዋቂ ከሚሆን ይልቅ የማይታወቅ ቢሆን ይሻለዋል፡፡ ከታዋቂነት ጋር የሚመጡ በርካታ ችግሮች አሉ፡፡ ውሎውና አዳሩ ሁልጊዜ በክትትል ውስጥ ነው – እሱ ተኝቶ የማይተኙለት ሰዎች አሉ፤ በበጎም በክፉም፡፡ ታዋቂ ሰው በባህርይው እንደ መላእክት የሆነ ያህል ወይም እንዲሆን የሚጠበቅበት መሆኑን የሚያመላክቱ ሁኔታዎች ሞልተዋል፡፡ ለአንዳንድ የዋህ ታዛቢ ታዋቂ ሰው የማይጠጣና የማይሰክር፣ የማይቆጣና የማይሳደብ፣ ከእንትን የራቀ ድንግላዊ፣ የማይዋሽና የማይቀጥፍ፣ … በጥቅሉ ፍጹም ሰው አድርጎ የማየት አዝማሚያ አለ፡፡ ግን ስህተት ነው፡፡ ሰዎች እንደመሆናቸው ሰው የሚሆነውን ይሆናሉ፤ ሰው የሚያደርገውን ያደርጋሉ፤ ሰው የሚኖረውም ይኖራቸዋል፡፡ ልዩነቱ ግን በነሱ ጎልተው እንዲወጡ የማንጠብቃቸው ብዙ ነገሮች መኖራቸው ነው፡፡ እነሱም መጠንቀቅ የሚገቧቸው እኛም ከነሱ የምንጠብቃቸው በአነስተኛው ማሟላት የሚገቧቸውን ሥነ ምግባራት ማሟላት ሲያቅታቸው ካስቀመጥናቸው ከፍ ያለ ቦታ አውርደን እንፈጠፍጣቸዋለን – እንደውብሸት፡፡ ለኔ ውብሸት ማለት አርአያ ሊሆን የማይችል እንዲሁ ተራና ቅሌታም ሽማግሌ ነው፤ ዕድሜውም ሆነ ያሳለፈው ተሞክሮ ያላስተማረው ከነማሙሽነቱ የሸበተ የእንጨት ሽበት ነው፤ ካባውን የሚያወልቅልኝ ሰው ስንት ጊዜ ፈልጌ አጣሁ፡፡ በባህል ማፌዝ ነው ሰውዬው የተያያዘው፡፡ ካባውን እንዲያወልቅ ብትነግሩልኝ ውለታ አለብኝ፡፡ ከ15 እና ከ16 ዓመት … ነውር ነው!

ይህን መሰል የእንጨት ሽበት በሞላባት ሀገራችን ውስጥ ነው እንግዲህ እነቴዲ አፍሮ ስለጨዋ ባህላችን እየዘመሩ እነውብሸት እያፈራረሱት የሚገኙትን ባህላችንን እየጠገኑ የሚገኙት፡፡ እግዚአብሔር የነዚህን ደጋግ ዜጎች ጸሎት ምህላቸውን ይቀበል ዘንድ፣ ምድራችንን ዳግም የጨዋዎች መፍለቂያ ያደርግልንም ዘንድ እንለምነው፡፡

ወደፕሮፌሰር መጽሐፍ ስመጣ፡

በዩንቨርስቲ ኮሌጅ የክፍል ኃላፊ የሆንኩት በመከራ ሰው ጠፍቶ ነው፤ ገፋፍቶ የክፍል ኃላፊ እንድሆን ያደረገኝ ዠቪ ያቬትዝ የሚባል እሥራኤላዊ ዲን ነበረ፤ ወደ አገሩ ለዕረፍት ሲሄድ ተጠባባቂ ሆኜ በሱ ቦታ እንድሠራም አግባባኝ፤ … (ገጽ 8)
የዩንቨርስቲው ሠላሳኛ ዓመት ሲከበር የአገልግሎት ሽልማት ስለሚሰጠኝ በበዓሉ እንድገኝ ፕሬዝደንቱ [ዶክተር]ዱሪ መሀመድ ነግሮኝ ነበር፡፡ በዩንቨርስቲ ኮሌጅ አንዲት ኤሊ አለችና እስዋ ትቀድመኛለች፤ ለስዋ ስጣት፤ አልመጣም፤ ስሜን አትጥራ ብዬው ነበር፡፡ ግን ባልነበርሁበት ስሜ ተጠራ፡፡ የደርግ አሥረኛ ዓመት ሲከበርም ልሻን እንደሚሰጠኝ ሰምቼ የጥሪ ካርዱ ላይ ባለ ስልክ ደውዬ እንደማልገኝ አስታውቄ ቀረሁ፤ በሌለሁበት አሁንም ስሜ ተጠራ፤ በጃንሆይ ዘመንም ወደ ፅሕፈት ሚኒስቴር ሄጄ ልሻን እንድቀበል ተነግሮኝ አልሄድኩም፡፡ … (ገጽ 13)

ፕሮፌሰር በነዚህ አባባላቸው ምን ማለት እንደፈለጉ ባውቅ ደስ ባለኝ፡፡ በመሠረቱ ሥልጣንን መውደድና መጥላት ግለሰባዊ ጉዳይ ነው፡፡ አያጣላም፡፡ ነገር ግን ሁሉም ሰው ሥልጣንን ቢጠላ ሀገርን የሚመራት ሰው እንደማናገኝ መረዳት ይገባል፡፡ ስለዚህም ሥልጣንን መጥላት ወይም ከሥልጣን መሸሽ ሁልጊዜ የጤናማነት ምልክት እንደሆነ ተደርጎ መወሰድ ያለበት አይመስለኝም፡፡ መተኮር ያለበት ሥልጣንን በአግባብ የመጠቀም ጉዳይ ላይ ነው፡፡ ሥልጣንና ሽልማትን መጥላትን ለመግለጥ የሚከድበት መንገድ ደግሞ የጨዋነትን ፈር የተከተለ ሊሆን ይገባዋል፡፡ አንድ ሰው አደረገው ተብሎ ለሚታመን መልካም ተግባር እንሸልምህ ሲሉት ለዔሊዋ ስጧት ብሎ ማጣጣል ከሞራል አንጻር ምን ሊባል እንደሚችል በበኩሌ ይጨንቀኛል፤ ለዚህም ነው በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ይህን ክፍል ሳነብ የሚገባኝ ነገር አጥቼ ወይም እንዲገባኝ የማልፈልገው ሊገባኝ ፈልጎ ሲፈታተነኝ ያን ጠልቼ በሃሳብ የናወዝኩት፡፡ ሰውን እንደመረዳት ያለ አስቸጋሪ ነገር የለም፤ ማለት በፈለገው ማለት ያልፈለገውን ወይም ማለት ባልፈለገው ማለት የፈለገውን ለመገንዘብ እንደመቃጣት የሚከብድ ነገርም የለም፡፡ በዚህ የፕሮፌሰር የሥልጣን አልወድም ገለጻ የገባኝ ነገር ሣይገባኝ ቢቀር እንደሚሻለኝ ተመኘሁ፡፡
በመሠረቱ ሹመትን ጠልቶ ዋና ትኩረቱ ከሹመት ጋር ስለሚያያዘው ፖለቲካ ማውራት አይቻልም፤ ሹመት በዓለም ብቻም ሳይሆን በገዳማትም አለ፡፡ ሀገርን ለማቅናትም ሹመት የግድ አስፈላጊ ነው፡፡ እውነተኛና ለሕዝብ በቀናነት የሚሠራበት ሹመት ሊጠላ አይገባም፡፡ በሌላም አነጋገር ሹመትንና ሥልጣንን አምርሮ መጥላት ባለሥልጣናትንና ሹሞችንም አብሮ እንደመጥላት ያህል ሊያስቆጥር ይችላል፡፡ ሥልጣንን በመጥላትና በማስጠላትም ተጨባጭ ቁም ነገር መሥራት የሚቻል አይመስለኝም፤ ዓላማው ግልጽ አይደለምም፡፡ ሥልጣንን የሚጠላ ሰው ደግሞ ስለሥልጣንና ስለፖለቲካ የሚናገረው ነገር ላይ የተወሰነ ጥላ ማሳረፉ አይቀርም፡፡ ያልተዛባና ፍትሃዊ አስተያየት ስለመስጠቱም አጠራጣሪ ነው፡፡ ቀድሞውን አወንታዊ እይታ የለውም ተብሎ ስለሚገመት ነጻና ገለልተኛ አስተያየት ይሰጣል ተብሎ አይገመትም፡፡ …

ላጠቃልል ነው፡፡ የሕዝብ ሰው መሆን ከፍ ሲል እንደጠቆምኩት ከባድ ነው፡፡ ሰውን ማክበር ያስፈልጋል፡፡ ትሁት መሆን ይገባል፡፡ ከአፈንጋጭ ስብዕና ለመራቅ ዘወትር መጠንቀቅ ያስፈልጋል፤ በዚህች ምድር የሚያኮራና እንድንታበይ ሊያደርገን የሚችል አንድም ነገር የለም፡፡ ሁሉም አላፊና ጠፊ ነው፤ ሀብትን ብል ይበላዋል፤ ዕውቀትን ‹ምሥጥ› ያነክተዋል፤ የዝናን ወርቃማ ቀለም ዘመን ያደበዝዘዋል፤ መልክና ውበት የዕድሜ ሽብሽባት ያጠወልገዋል፡፡ ምን ቀረን? ምንም! አንድ በትምህርትም ሆነ በሌላ ነገር ዕውቅናና ስመጥርነትን ያገኘ ሰው ከግል ሕይወቱ ሥምረት ጀምሮ ለሌሎች አርአያ ለመሆን መትጋት ይጠበቅበታል፡፡ ትዳርን ማክበር፣ ሃይማኖታዊ ትዕዛዛትን በተቻለው መጠን ማክበር፣ ሥነ ልሣናዊ የመግባባት ደረጃዎችን መለየትና በአግባቡ መጠቀምን መልመድ (ለምሳሌ አንተ እና አንቱ የሚባሉ አጠቃቀሞችን፣ የማዕረግ ስሞችን እንደዬሁኔታው መገልገልን ማወቅ …)፣ በወገን ችግር ጊዜ ቀድሞ መድረስንና ከልብ ለመርዳት መሞከር፣ ከምንም ዓይነት ዕብሪታዊና ትዕቢታዊ የአነጋገር ሥልት መለየት … ይጠበቅበታል፡፡ የተገነባ ስም እንደሚናድም መረዳት ተገቢ ነው፡፡ ብዙ አብነቶችን መጥቀስ ቢቻልም አላሙዲን ብቻ ይበቃናል፡፡ (ሰው ባጣንበት ዘመን ሰው የሆኑን እነቴዲ አፍሮና ታማኝ በየነ የሰይጣናዊ የልብ እብጠት ሰለባዎች እንዳይሆኑብንና እንዳይሰናከሉብን በበኩሌ እጸልያለሁ፤ ሁላችንም እነዚህን ወገኖች እንዲያበዛልን በአቋማቸው እንዲያጸናልንም እንጸልይላቸው፡፡ የሰው ዐይን ድንጋይ ይሰብራልና ከዐይን ያውጣልን፡፡ ሰው አልበረክትልን ብሎ ተቸግረናልና ይህን ሾተላይ ፈጣሪ እንዲያነሳልን ወደላይ እንማጠን፡፡)

እንዲያው ግን ሌላውን ነገር ሁሉ ልርሳውና አርአያ የሚሆን ሰው ጌታ በኪነ ጥበቡ አስተካክሎ ይስጠን – ከየዘርፉ፡፡ ደግሞም ይችላል፡፡ ከቁጣ የራቀ፣ ከትዕቢት የተቆራረጠ፣ ከትምክህት የተፋታ፣ ከጥበብ የተጋባ፣ አስተዋይነትና ትህትና ሞልቶ የተረፈው፣ ቅን አሳቢና ለሀገር ለወገን ተቆርቋሪ የሆነ የሕዝብ ሰው ይስጠን፡፡ ሁሉን ነገር ማድረግ የማይገደው የኢትዮጵያ አምላክ እኛንም ባሕርያችንን ገርቶ እንደገና ይፍጠረንና እርስ በርስ የምንተሳሰብ፣ ደገኞችና አስተዋዮች ያድርገን፡፡ ለዘመናት ከሚጨፍርብንና እግር ከወርች በማሰር ኮድኩዶ ከያዘን የምቀኝነት አባዜ ነጻ የወጣን እንሆን ዘንድም ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን፤ አሜን በሉ፡፡ ኧረ አቅላቀችንን ይመልስልን ወገኖች! ተበታትነን ቀረን እኮ፡፡ ብዙ ቢናገሩት ሆድ ባዶ ይቀራልና በነገር እንዳላሰለቻችሁ ነገሬን ሳላንዛዛ ባጭሩ እዚህ ላይ ልቋጭ፡፡

Hiber Radio: “የጎንደሩ የተቃውሞ ሰልፍ ለመሳተፍ ለሱዳን መሬታችን ከተሰጠበት አካባቢ ያሉ ጉዳዩን የሚያውቁ በርካቶች እንሳተፋለን ብለዋል”

$
0
0

የህብር ሬዲዮ ጥር 18 ቀን 2006 ፕሮግራም

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

>

አቶ አግባው ሰጠኝ የሰማያዊ ፓርቲ የጎንደር ተወካይ ለህብር ከሰጡት ቃለ ምልልስ የተወሰደ

>

ጋዜጠኛ ፍሬው አበበ የሰንደቅ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ተጠርቶ ቃል የሰጠበትን ጉዳይ በተመለከተ ከሰጠን ቃለ ምልልስ የተወሰደ

የአሜሪካ ዲፕሎማቶች የሰሞኑ የኢትዮ ኤርትራ ጉዳይ ላይ የተሰጠ አስተያየት ሲቃኝ

ታክስዎን ሲያሰሩ የኦባማ ኬርን እያሰቡ( አቶ ተካ የሰጡት ሙያዊ ማብራሪያ)

የአቶ ሌንጮ ለታ የተቃርኖ ፖለቲካዊ ተሳትፎና የአሜሪካ ዲፕሎማቶች ከህወሃት ጋር ስላላቸው ውስጣዊ ወዳጅነት ያረጋገጡበት የምስጡር መልዕክት ከዊክሊክስ ፋይል እና ከሃያ ዓመት በፊት ሌንጮ ማንነታቸውን ያጋለጡበት አጋጣሚ(ወቅታዊ ትንታኔ ካለፈው የቀጠለ )

ሌሎችም ዝግጅቶች

ዜናዎቻችን

ሰማያዊ ፓርቲ ለሱዳን የተሰጠውን መሬት በመቃወም በጎንደር ለጠራው ሰልፍ ቅስቀሳ እጀምራለሁ አለ

በኦሮሚያ ከ100 ሺህ በላይ ነዋሪዎች የዐይናቸውን ብርሃን ለማጣት ተቃርበዋል

አልሸባብ በኢትዮጵያ ጦር ላይ የተጠናከረ ጥቃት ለመፈጸም ዛተ

አረና በጫና በአዴግራት የጠራውን ስብሰባ ሰረዘ

ለሰልፉ ቅስቀሳ የሄዱ አመራሮችና አባላት በቅጥረኞች መደብደባቸው ተገለጸ

አገዛዙ አፈንኩት ያለው የሙስሊሞች ሰላማዊ እንቅስቃሴ በድጋሚ አገረሸ

ለኢትዮጵያዊቷ ሞት ተጠያቂ የሆኑ ባልና ሚስቶች በዱባይ ከፍተኛ ቅጣት ተጣለባቸው

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

ሞገደኛው ተክሌ ውስጡን አስነበበኝ –የስሞተኛው ብዕር።

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ sreate
ይድረስ ብለናል ከወደ ሲዊዘርላንድ ዙሪክ እኔና ብዕሬ ለሞገደኛው ብዕረ ተክሌ ….
ጭራሽ ተበዳይ ብዙኃኑ ተወቃሽ ሆነ? ይገርም! ጡር የሚባል ነገር አለ። በፈጠረህ ጡር ፍራ የስሞተኛው ብዕር …..
እንደምን አለህ ሞገደኛው ተክሌ? ደህና ነህ ወይ? ጠፍተህብኝ ጭንቅ ብዬ ሳለ የወጣት ጃዋር ዶክተሪን በመቃወም ከሰሞናቱ ፊርማ የማሰባሰብ ዘመቻን ተከትሎ ብዕርህን ብቅ አደረገችህና ደስ አለኝ። የእውነት ናፍቆትህ ግድል አድርጎኝ ነበር። እኔማ የኦሮሞና የአምራ ትዳር ፈርሶ የነገ ሀገር ተረካቢዎች እንዲበተኑ፤ እንዲሁም ከሁለት ብሄረሰብ የተወለዱ ወገኖች ጥግ አጥተው ሜዳ አደር እንዲሆኑ ሲታወጅባቸው፤ ያው በትንሹም በትልቁም የምታብጠለጥለው ብሄረሰብ ቁምጥና መላያው ተደርጎ ሲቀጠቀጥ፤ አንድ ታላቅ ማህበረሰብ ሞትና መፈናቀል ሲታወጅበት፤ መዲናች ተለቃ የንጹኃን አንድትሆን ሰባት አንቀፆች ያሉት ድንጋጌዎች ሲተረተረ፤ ኃያሉ ሚኒሊክ ሃውልታቸው ፈርሶ ፈረሱ ወደ ኦሮሚያ ሲጫን፤ ክብራቸው ትብያ ሲለብስ፤ የወሎይቱ ወርቂቱ አፄ ቴውድሮሰን አነጣጥራ የገደለች ስለመኋኗ ሲነገርላት፤ አፄ የኋንስም ጥላሸት ሲቀቡ፤ ተዋህዶ ተዘቅዝቆ ሲንጠለጠል፤ ብዕርህ ሃግ ትላለች ብዬ ሳሰብ እቴ እሷ አብራ ከበሮ ስትደልቅ ሰነባብታ ይሁን አይታወቅም፤ ብቻ ከመሼ ብቅ አለች። እኔማ እህትህ ሰርግና መልሱ፤ ቅልቅሉ አላዳርሳት ብሎ ይሁን ጣል ጣል ያደረገችን በጤና? ብዬ ነበር።
አሁን መልካም ሆነ ዕድሜ ለዘሃበሻ ከወደ ቶረንቶ ብቅ ማለታችሁ አስደሰተኝ። እጅም ነሳን ለጥ ብለን አደግድገን።
ግን ደህና ናችሁ? ብርዱና በረዶው እናንተን አልደረሰባችሁም …. ሞቅ ብሏችኋል „የፍቅር ጉዞ መደናቀፍ በደሌ ማዕቀብ እያጣጠምን ነው … ብሎን ነበር ወጣቱ …. ከፌስ ቡኩ ወደ ዘሀበሻ በተሻጋገረው ቅምሻ …
እኔ እንኳን ካንተው ከወዳጄ ጋር እንጂ በዛ ዙሪያ ምን መስራት እንዳለብኝ ስለማውቅ ቅጭጭም አይለኝ …. ቡጢ መግጠም አያስፈልግም። ሙያ በልብ … ይላል የጎሪጥ የምታዬው የጎንደር ሰው …
ለነገሩ ጎንደር ላይ ሆነ ጎጃም ላይ ስለነበረው የኦሮሞ ወራራስ ምን ይሰማህ ይሆን? የወተር የበደኖ የአርባጉጉ የጉራፈረዳ ጎሽ! ነው ወይንስ ሰቅጠጥ …. መሆን የማንችለውን የፈለገ ጫና ቢፈጠረም ማንነታችን ገላጫችን ነው – ኢትዮጵያዊነት። መወረድ የአባት አይደለም። ተግባባን? …. ጎሳ ከቤተሰብ ቀጥሎ ያለ ያላደገ የማህበረሰብ እስቤ በመሆኑ በግሌ ለእድሌም አላሳዬው። ሁኜም አላወቅም። መሆንም አልችልም። ሌላ የሚያርመጠምጠኝ መጠነ ሰፊ ሀገራዊ ጉዳይ አለብኝ። የሆነ ሆኖ ብዕራችን ጉጉስ ትጋጠም ዘንድ ወደደኩ። ደስ ስለምትለኝ ….

ዘሃበሻ ላይ ከአንተ ጹሑፍ ሥር የተሰጡ አስተያዬቶችን ሳነብ ደግሞ ጎሽ! ሞገደኛው ተብለኃል። ሜጫው አንተን ዘለል
አድርጎ ሽልማት ቢጤ ልታገኝ ስበሰባ ላይ መቀመጣቸውን አነበብኩ። ድምጽም ሰጡህ። ለነገሩ ወገኖቼ እውነት ብለዋል። እንዲህ ሁሉንም ፍላጎት በእኩልነት የሚስተናገድ ሚዲያን ነፃ ሊያሰኘው ስለመቻሉ በተግባር መገኘቱ ዘሃበሻ እኔም ምርቃቴ ይድረሳቸው እላለሁ። እኔንስ እኩል አድርገው ባለወግ አድርገውኝ የለ። ይባረኩ። በአንድ አቅጣጫ ብቻ የሚፈስ ወንዝ ውበቱ እንብዛም ነው … ህግጋትን ካልተላለፈ …. ትውልድን ለመናድ ካልተንጠራራ፤ ለዬት ያሉ አወያይ ሃሳቦች ጉልበት ይሰጣሉ። ቀዳዳም ይሸፍናሉ፤ ያልታዬትን ያስጎበኛሉ። እራስን ያርቃሉ። እንዲህም ያነጋግራሉ …

አንድ ትውስታ አለችኝ። ልጅ ተክሌ አንተ የኢሳት መደበኛ አዘጋጅ በነበርክበት ጊዜ አብዝቼ አደምጠው የነበረው „እፍታና የእሁድ ወግ„ ዛሬ የለሁበትም። ስለምን? አንተ በነበርክ ጊዜ የራስህን ዕይታ ይዘህ ከች ትልና አንተና ሲሳይ ማህል ዳኛው ደረጃ ስትፋተጉ፤ ሃሳብን በሃሳብ ስታፈጩ ትቆዩና ከዛም በሌላ ፕሮግራም ላይ ደግሞ በጋራ ማዕደኛ ስትሆኑ ገነት ነበር ለእኔ ለመንፈሴ። ምክንያቱም የእኔ ሃሳብ የእኔ ነው። እኔ ዬእምፈልገው እንደ አንተ ያለውን ወጣ ያለ የእኔን የማይመስለውን ስለነበር ጓጉቼ እታደም ነበር። የእውነት ውበት ነበረው። አዎን ዛሬ ዛሬ ግን የእኔን ሃሳብ ወይንም ዕይታ ደግሜ ለመስማት መታደሙ አላስፈለገኝም ማለት ቀርተህብኛል። የዛሬው ጹሑፍ ደግሞ ዋው! እራሰህን ያነበበው ሸጋ ነው። ማለፊያ ነው። አጋድመህ ከመጻፍ ግን እኔም ብሆን ብለህ ደፈር ብትል ማጣቀሻ ምሳሌዎችን ተረተረት ነገር ከምትነገረን የጭብጡን ተዋናይ አንተን አድርገኸው ቢሆን ገላጭ፤ ተራኪና ትዕይንታዊ በሆነ ነበር። እንዴት ባመረ ነበር። ካልጎሼ አይጠራም። የጠራ ደግሞ ጤና ነውና …. ከራስ መነሳት ደግሞ … አብነትነት ነው ….

ከቶ …. ወንድምዬ ብልህ ይሻልኃል ወይንስ ታናሼ …. በሞቴ በሥርጉት ሞት እንዲህ ካለ የአንድ ሀገር ምስረታ ታሪክን ከናደ ጠቀራ ሂደት ጋር ዶር. ኦባንግ ኢትዮጵያን ማነካካትህን አልወደድኩትም። እሙት ወንድምዬ የምር ክፍት ነው ያለኝ። “በኢትዮጵያዊነታችን ያጣነው ነገር ስላለ ብቻ ኢትዮጵያዊነታችን ይሰረዛል ማለት አይደለም”። „ውሃ ሲወስድ እያሳሳቀ“ እንዲሉ እንዳይሆን …። ምን ባደረገ …. ዶር. ኦባንግ እኮ ንጹህ ግን ብልህ ሰው ነው። ተቋማችንም ነው። ሞት ካወጀ ጋር ማዳበለህ ይቀፋል እሺ! ያው የፈረደበት ግንቦት ሰባት በትንሹም በትልቁም ጥርስ መፋቂያህ፤ ማጠቀሻህ፤ ማጣፈጫህ ስለሆነ አሁን ደግሞ አምጥትህ ማህል ላይ ድንቅር አደረከውም። ፍቅሩ ገደለህ አይደል የግንቦት ሰባት?!! …. ከትክት …. መስጠት ነበረበት ነው ማለም ነበረበት … እሱም እኮ ስደተኛ ነው የማከበርህ። ሥልጣን ኑሮት የነሳው ሲኖር ያን ጊዜ ቢተች …. በቀጠሮ …. ካለ ግንቦት 7 ብዕርህ ውቃቤዋ አይነሳም አይደል?

ከእርእስህ መነሳት ግድ ነው። „የእኛ ነገር የተሸነፈ ርእዮትናሀገር ገፊ ፖለቲካ“ የጹሑፍ ሆድ እቃ እንደ አመለከተኝ ከሆነ ኢትዮጵያዊነት ተሸንፎ አያውቅም ለወደፊቱም አይሸነፍም። ሀገረ ኢትዮጵያም በታሪኳ ስታሸንፍ እንጂ ስትሸነፍ ተሰምቶም ታይቶወም አይታወቅም። ጠላቶቿም አይመሰክሩባትም። እውነት እናትዬ ሞገደኛው ዬትኛው ፕላኔት ላይ ይሆን የከተምከው? ይህ የብሄር የምተለውም ፍትኃዊ ሥርዓት ስንገነባ ነው ተጠያቂነቱ …. „የተሸነፈ ርዕዮትናሀገር?!“ ይህ ታሪክን የመግደል ዕይታ የጤና ወንድምአለም? እርእሱ አራሱ እኮ ገዳይ ነው። አተጋፋት ሀገርህን ….

„ገፊ“ ለሚለውም ከሌላ ዕይታ አንጻር አቅርበኸው ቢሆን ሊያስማማን ይችል ነበር። አቅማችን በመሰብሰብ እረገድ ብትመጣ፤ ወይንም ይህ ሥልጣን በሚሉት ተወዳጅ አዚመኛ ብቅ ብትል ስምምነት በወረደ። ምን የመሰለ ድፎ ዳቦም በተቆረሰ። አንተ ላነሰኸው ነጥብ ግን የተገፋ ነገር አልበረም። በራሱ ጊዜ አጎጠጎጠ፤ በራሱ ጊዜ በቀለ፤ በራሱ ጊዜ ጥፋትን አወጀ፤ በቀለን ዘራ …. ለዛውም ብዙዎቻችን ዝም ብለን ነው እያየን ያለነው። የተማገዱት ጥቂቶች ናቸው … ፊት ለፊት ወጥተው „ኢትዮጵያዊነት“ ሲጠቃ … ዋቢ የሆኑት። ለነገሩ እንቅልፍ ሊኖረን ባልተገባ ….
ምንድን ነው የምትለን? ምን ሁኑ ነው የምንባለው? ከዛ በላይ ወጣቱ የፖለቲካ ተንታኝ፤ አክቲቢስት፤ የሰብዕዊ መብት ተሟጋች ምን ያልተባለው ነገር አለና? እኔ ከእሱ ይልቅ ጋዜጠኛ ሳዲቅ ቀልቤን ሳብ ያደርገው ነበር። ብቻ ከቁንጮጯችሁ ላይ ተሸክማችሁት ሂዱ ተብለን ነበር የታዘዝነው። ይገርምኃል እኔ እህትህ ሳይሞቀኝ ሳይቀዘቅዘኝ ጠርዝ ላይ ሆኜ እመለክት ነበር። በኋለም በዛ አጣብቂኝ ጥያቄ ከመንበሩ ዝቅ ማለት ሲጀምርም ኖርማል ነበር ለእኔ። ሰው ይወጣል ይወርዳል። በቃ!
ትእግስት አጣን ለምትለው ግን ኢትዮጵያዊ አይደለሁም ላላ ምን ቆራጣ ጊዜ ያስፈልገዋል ብለህ ነው። ይቅናው። መንገዱንም ጨርቅ ያድርግለት …. ከእኛ ተነጥሎ ህይወቱ አልባብ ባልባብ ሲሆን ይድላው … አይተናል ኤርትራን … ሚሊዮን ወጣቶች በርኃ ላይ ሲረግፉና ሲንጋፖር አፍሪካ ቀንድ ላይ ሲገነባ …. ከትከት!
ሌላው ግን ይህን አክቲቢስት የሚባል ሹመት አብዝቼ እታዘበው ነበር። መቼ እንደሚያቆምም እያነፈቀኝ ነው …የተያዘ የተረዘዘው ሁሉ „አክቲቢስቲ“ ሲባል የአውቶብስ ትኬት እንደ መግዛት ነው የቆጠርኩት። እንደ ወያኔ ሹሞች ዶክተሬትነት ….. ሳር ቅጠሉ ሁሉ ሆነ። ለነገሩ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ካለ ከፍተኛ ድግሪ ፍንክች አልልም ብሎ መልዕክት ልኳል አሉ?! ነጋሪትም ጎስሟል ይላሉ። ወይኔ! ሥርጉተ ብጣቂ ምንም የለ ከነፃነት በኋላ አስኮባ ማግኘትሽን እንጃ እያለ መንፈሴ ያጣድፈኛል። አንተ ድነሃል አሉ …. የእውነት ነውን? ቀለሜዋ ሳትሆን አትቀርም … በፈርንጅኛው ቃለ ምልስህን አዳምጬ ነበር። እኔ ስሜን መጣፉ አልሆነልኝም ….
ለማንኛውም የእኔ እናት ዘረኝነት በሽታ ነው። ጎጠኝነት ዲዲቲ ነው። ተመስጥሮ የተያዘ በሽታ ሲያዳልጥ በራስ ጊዜ ያፈናቅላል። ከእቅፍ …. አፈንጣሪው ንዑድ መንፈስ የማታውቀው እንደሆን ልንገርህ ወንድምዬ ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረው ሚስጢር „ኢትዮጵያዊነት“ ነው …. አሁን ደግሞ ከመቼውም በላይ በራሳቸው ቋንቋና የዕምነት ዶክተሪን ተሰልፈው የሚሟገቱለትን አፈራ። ልጆቹን እዬሰበሰበ ነው … ጎራ በልና በተቃራኒው በኩል ያሉትን ሲቢሊቲና ደብተራ ሩሞችም ሰንበት ላይ ሆነ በአዘቦት ታደምና ልኩን እወቅ። ልክን ማወቅ ከልክ ያደርሳል – አሁንም ጎንደሬ ይላል።

የከፋን፤ የኢሊባቡርን፤ የጋሙን፤ የሲዳሞን፤ የባሌን የሀረርን ወጣቶች በተለያዬ ኮርስ ምክንያት በቤተሰብ ደረጃ አውቃቸዋለሁ። ንጹህ ናቸው። በነገራችን ላይ አርሲን አወቀዋለሁ። ሮቤን በሙሉ። የጢቾ የአምኛ የሴሩ የዲክሲስ ቁርጡ ወተቱ ገንፎው ጭኮው ፍቅሩ ስስቱ ናፍቆቱ ከቶም ልክ የማይወጣለት ኢትዮጵያዊነቱ፤ እንግዳ ተቀባይነቱና አክባሪነቱ፤ ወደር የለሽ ናፍቆቴ ነው። አሁን አንተና ብዕርህ ጥብቅና የቆምክለት ዬሜጫም ፖለቲካ ያን ደግ ህዝብ ሊወክል የማይችል፤ በአብሮነትና በጨዋነት የሚኖር ስለሆነ …. ብጣቂ ስጋት የለኝም። ማን ወልቆ እንደሚቀር ፈጣሪ ያወቀዋል። እኔ ስዛውር ለአንድ ሳምንት ሥራ የገባ አንድም ሰው አልነበረም። ፍቅር ነው። ነፍሶቼ ናቸው እሺ!

የፈረደበትን ዲያሰፖራ ለማተራመስ ወያኔ በሙሉ ኃይሉ የሰራበት ዘመቻም እሳት የላሱ የእስልምና የተዋህዶ ኦሮሞዎች ሆኑ የሌላ ብሄረስብ አባላት ሁሉ እጅ እጅ ያላቸውን የጃዋር ዶክተሪን ፊት ለፊት እዬተዋጉት ነው። የምሥራቹ ደግሞ እንደምታወቀው በተዋህዶ ትንሳኤን ያበሰራቸው ቅድስት መግዳላዊት ናት። አሁን ደግሞ ሞገዱ የሴቶች ኃይል በመሆኑ ወዬ! ነው … እዬገፋህ ከማልፈልገው ነጥብ ጋር አለካለከኝ እግዚሩ ይይልህ። የእኔ አቅጣጫ ፈጽሞ ሌላ ነበር። የሚገርምህ ጆኖሳይድ ሩም ሲከፈት በተረጋጋ ስሜት ነበር የተቀበልኩት። „ኢትዮጵያዊነትን“ በሚመለከት ባላቤት የሌለው ስለሆነ በዚህ ዙሪያ ብዙ መስራት እንዳለብን ብቻ መንፈሴን አዘጋጀሁት። አሁን እንዲያውም በራሳቸው ጊዜ ጎርቦ የነበረው እብጠት ፈናዳ፤ የዋሆቹ ደግሞ ወደ ጡታቸው እናታቸው ተመለሱ ደስ አይልም? የምስራቹ ይህ ነው።

ትንሽ ከተረተረት የወጣውን የሰሞናቱን የሃቅ አናት መስማት ያሰኝኃልን? በምስክርነት ትንሽ ልበልለት
እንዲህ ሆነልህ …. ታናሼዋ …. „ሞት ለወያኔ“ በሚል ፓል ስም የምትታወቀው ዬእስልማና እምነት ተከታይ ብሄረሰቧ ኦሮሞ፤ ሀረር ተወልዳ ያደገች ብርቅዬ ውብ በ15.01.2014 ደብተራ ሩም ላይ እንዲህ አለችን። „ እኛ ተሰይፈን ሳናልቅ እናንተ ዘንድ አይደርሱም። አስተውል „እኛ ተሰይፈን ሳናልቅ“ እኛን ሳይጨርሱን ከእናንተ ዘንድ ድርሽ አይሉም። ቁምጥና በሽታ በመሆኑ ሀረር ላይም ድውያኑም ሆስፒታሉም አለ“ በማለት አብራ ቆመች ከማንነቷ ጋር አርበኝት።
… በ26.01.2012 ዛሬ ደግሞ ሲቢሊቲ በአባ መላ ሩም 1000 ታዳሚ ነበር። ቃለ ምልልስም ከዶር ጌታቸው ጋር ነበር። „ አጼ ሚኒሊክ ከወገኖቼ ጋር አገናኙን። እኔ የምጠይቀው በእሳቸው ዙሪያ የጀግኖች ሀውልት እንዲሰራ ነው። ከኢትዮጵያዊነታችን አንድ ኢንች ፈቀቅ አንልም።“ ድንቅ ውሳኔ! ሌላዋ እህቴም ሳራ አብዱ ትባባለች። እሷም „ጃዋር እኛን አይወክልም። ምን አለ የእስልምና ሊቃናትን አምጥታችሁ ቃለ ምልልስ ብታደርጉ። በኢትዮጵያዊነቴ እኮራለሁ።“ ሳርዬ ደግሞ የጉራጌ ብሄረሰብ አባል ናት። ለአምስት ዓመት አውቃት የነበረችው ናፍቆቴ አምርትዬ ደግሞ የሰላሌ አንበሲት „በረት ገልባጭ ጀግና ስትሉ ያሳፍራል። ቀመር ዮሱፍ ወይንም አገሪ ቱሉ ሽፍታ የነበረ በረት ገልባጭ ነው። 90 በመቶው ኦሮሞ እስልማና ነው ሲል ጃዋርን አዳመጥኩት። እኔስ የተዋህዶ ልጂት የት ልጣል ነው?! በሃይማኖቴ ቀልድ የለም። እሰዋለሁ። ለነገሩ የድርጅቱ የኦሮሞ ከፍተኛ መሪዎች እኮ ከ10 ጋሻ መሬት በላይ የነበራቸው አስገባሪዎች ነበሩ። አባቴን ጨምሮ፤ ዛሬ እነ አቶ ሌንጮ ስንት ደም አስፈስሰው ሀገር ሊገቡ ነው። እጅግ ያሳዝናል። መጀመሪያ እኔን ኦሮሞዋን ያሳምኑ። አባል ነበርኩ በድርጀቱ“ ሌላው እጅግ ድንቅ ነገር ዲነግዴ መቼም መብራት ነው። ከትናንት ወዲያ በ25.01.2014 ጋዲሳ በሚል ስም የሚጠሩ ፕሮፌሰርና ዳኛ ህይወት ሰጡን ብል ይቀላል። ዛሬ ደግሞ „ መምህሮቼ ስሄድ ይነሱልኛል ነበር ያከብሩኛል። በጀርባዬ ሀገሬ ኢትዮጵያ አለችና።“ አሉን ዘመናትን በትንግርት ያነገረ ሚስጢር ይሉኃል ይህ ነው። ክቡርነታቸው ደግሞ የጥቁር አንበሳ አንባ ጎሬ ላይ እትብታቸው የተቀበረ … ናቸው። ይህን ዘለቅ ብለህ ገባ እያልክ ዛቅ። ሥነ ጥበብ ከማህበረሰቡ ጓሮ ይታፈሳል። ምርት ደግሞ ከሃቅ አውድማ!

ማመሳካሪያዎችህን አብረን ….
1. ወይኔ! ይህ ማጣቀሻ ከሆነ „አከራዩ ደግ አማራ ሴት፤ ለጃዋር ምግብ ሰጥታ፤ እሳት አንድዳ እያሞቀችዉ፤ ከላዩ ላይ ጋቢ ደርባ “ለምን እስኪመሽ ቆየህ አሁን ከመንገድ አንድ ጋላ ቢያገኝህና አንገትህን ቢልሀስ” አለችው፡፡ የዚህን ልጅ ስሜትና ምላሽ ለመረዳት ኦሮሞ መሆን አያስፈልግም፡፡ ራስን በሱ ቦታ ማስቀመጥና ነገሩን የራስን ጎራ ያለስስት በመተቸት ፈቃደኝነት ማሰላሰል እንጂ፡፡”
1. “ልክ ጅሁርና ጋይንት፤ ቢቸናና አንኮበር እንደምትኖር አንዲት አማራ ኢትዮጵያዊት፤ ይህቺ ሴት ክፋት እንደሌላትና የንግግሩዋን ፖለቲካዊ አንድምታ፤ በዚህ ልጅ ቀጣይ ማንነት ውስጥ የሚኖረውንም ፋይዳ እንደማታውቅ አሳምሮ መገመት ይቻላል፡፡ ይሄንን አጋጣሚ የነገረን ጃዋር ግን የሚለው፤ ይህቺ የዋህ ሴት የኢትዮጵያ ገዢ መደብ አካላት ያሰራጩትንና ለገዢ መሳሪያነት የተጠቀሙበትን የተወሰነ የህብረተሰብ ክፍልን ዝቅ የማድረግ አመለካከት፤ ሳታውቀው ከነፍሱዋ አዋህዳዋለች ነው፡፡ ስለዚህም፤ በቀጥታ ይሄንን የተወሰነ ብሄርን ዝቅ የማድረግ ባህል በመፍጠርና በመቅረጽ ባትጠየቅም፤ የዚህ ባህል በረከት ተቁዋዳሽ በመሆንና አውቃም ሳታውቅም ይሄንን ባህል እድሜ በመስጠት ተሳታፊ ነች ሲል ተከራከረ፡፡ በላይኛው ጽሁፍ ላይ ሰፈርኩትን የኦባንግን ገጠመኝ ጨምረን ካየነው፤ የጃዋር መከራከሪያ ስሜት ይሰጣል፡”
ወይ ፈጣሪዬ! …. ስሜት ከሰጠህ የጆዋር ዶክተሪን መጠቃለል ምን ችግር አለው። በነፃነት ሀገር ልመና ዬለ … ፕሮቶኮል ሲናሪዮ ብሎ ነገር የለ ደጅ ጥናት የለ። አማረም ከፋም ፈርጆዋን በውልብልቢት ከማጣቀስ ዋና መልካም ነው …. ለነገሩ ቀዘፋ ታውቃለህን? ኧረ አስነካው ወንድም ጋሼ!

የገረመኝ የአማራር ብሄረሰብ ከቤንሻጉል ሲፈናቀል „አማራ ብሄረሰብ“ አይባልም ብለህ ሲሳይን የሞገትክ ጀግና አሁን አንተ የብሄረሰቦች ተቆርቋሪና አስታራቂ ሆነህ ጉብ ስትል ትዝብት ነው። …. እዬረሳኸው ይሆን? የሚመከት ነገር ጠፍቶ ይመስልኃልን? አይመስለህ። ሥልጡን ዕያታ ነው ያሳደገን ኢትዮጵያዊነት። ይህ በነጋ በመሼ ምክንያት እዬቆነጠርክ እያጣጣልክ የምትዘልፈው የተዋህዶ ሃይማኖት ሆነ መስጥረህ በጥርስህ የያዝከው ብሄረሰብ የወያኔን ማንፌስቶ የፈጠረ ስለሆነ ጎራው የት ላይ ሊያሰርፍ እንደሚችል ስለሚታወቅ አይደንቀንም ….. መሬትም ባለቤትም ጥግም አልባ ሆኖ የሚንከረተተው ድሃ …. ወገን። „የደላው ገንፎ ያላምጣል አሉ“ ብጣቂ አዘኔታ የለህም እኮ!

„አማራ ብሄረሰብ“ ለማለት አንደበትህ አልደፈረም። ከላይ ያነሰኃት ቅን ሴት የሰው ልጅ ከነነፍሱ ገደል ሲጣል በቅርብት የሰማች ናት …. በሙሉ መፈረጀህ ደግሞ እጅግ አሳዛኙ ገጠመኝ ነው። እኔ እኔን አውቀዋለሁ። በድፈረትም የመናገር አቅሙም ሆነ ብቃቱ አለኝ። ያሳደገኝ ማህበረሰም አሳምሮ ኢትዮጵያዊነትን አጠጥቶ በእሱ አቁርቦ ነው። ይህ ነው የጃዋር ዶክተሪን መሰረት …. የአንዲት ሴት ቀንጣ ዕይታ ታሪክና ሀገርን ለመበተን ያስነሳው። አንተም የምታጅበለት? አልተደመጠም? ምን? ሞትን ነው ማደማጥ የነበረብን ወይንስ 18000 ፊርማ ተሰብስቦ „የፍቅር ጉዞ መታገዱ“ …. እስኪ የበለጠህን ቴዲ ከአዲስ አድማስ ጋር የሰጠውን ቃለ ምልስ ከልብህ ሆነህ እንደ ለመድከው ምስባክ ገፋ አድርገህ ሂድበት ለቤትህ ቀናተኛ ነህ ብዬ ነው የማስበው። የትውልዱ መንፈስ ተነግሮኃል። „እግዚአብሄር በአንድም መንገድ በሌላም ይነገራል ሰው ግን አያስተውለውም“ ይላል አካል የሌለው የመዳህኒዓለም አገልጋይ ቃለ ወንጌል። ከአንተ ያነሰው ቴዲ ዘመኑን – የሚመራን ትእዛዝ ከአምላኩ ተላከለት። ለእኛ አቀበለን …. ካበቀልከው። የዕድሜ አቻውም ወጣቱ ጃዋር ካደመጠው ድህነቱ ከዛ ላይ አለለት …. ቂም በቀል ቋሳ የሌለበት የተረገጋ ንዑድ መንፈስ ….

2. “ወዳጄ ገረሱ ቱፋም፤ እንዲሁ ልጅ ሆኖ ሳለ፤ ጾም መሆኑን ረሳና፤ ወተት ጠጣ፡፡ እናቱ ወደንስሀ አባታቸው ላኩት፡፡ ቄሱ ቃል በቃል ምን ብለው እንደመለሱለትና ልቡን እንዳደሙት የነገረኝን በደንብ አላስታውሰውም፡፡ ብቻ፤ “ኤድያ ደግሞ፤ የጋላ ጹዋሚ ብሎ ነገር የለም” ብለው መለሱለት፡፡ “ለጋላ ንስሀ አባት ዲያቆን መች አነሰው” አይነት የሚለውን፤ የተለመደውን ክብረ-ነክ ተረት የሚያጠናክርና የሚያናንቅ መልስ ነው፡፡ በወቅቱ ገረሱ የሱ ጣፋት መስሎት ነበር፡፡ ነፍስ እያወቀ ሲመጣ ግን የሱ ጥፋት ሳይሆን ልክ እንደጃዋር ቀላቢ፤ አውቀውም ይሁን ሳያውቁ፤ በቄሱ ውስጥ የተተከለውን የሱን ብሄር ዝቅ የሚያደርግ ገዢው መደብ የፈጠረው ንቀትና ጥላቻ ተገለጸለት፡፡ ከአመታት በሁዋላ፤ እነሆ በገረሱ ነፍስ ውስጥ አብሮ የሚኖርና ዘወትር ቄሱ ስለወጡበት ህብረተሰብ ሲያስብና እኛ ጋር ክርክር በገጠመ ቁጥር ትዝ የሚለው መርዝ አጋጣሚ ሆነ፡፡ እንደውም ኢትዮጵያ ስትባል፤ የኚህን ቄስ ጋቢ የደረበች የአማሮች ፈጠራ መስላ ታየችው፡፡ጉርሶ አይደለም አንተን የጎረበጠህ” ኢትዮጵያ ስትባል የኚህ ቄስ ጋቢ የደረበች የአማሮች ፈጠራ መስላ ታዬው”
ሎቱ ስብኃት! ጉርሶ አይደለም አንተን የጎረበጠህ” ኢትዮጵያ ስትባል የኚህ ቄስ ጋቢ የደረበች የአማሮች ፈጠራ መስላ ታዬው” እግዚአብሄር ይቅር ይበልህ። ለምን እራስህን ማወረድ አስፈለገህ? ማንነትህ እኮ አለ “ኢትዮጵያ” ከምትባል ሀገር። ደፈጠጥከው። ሃዘን ቢጤ እኮ ፈለሰበት …. እናትዬ …. አቤት አቤት ማረን!
…. መጀመሪያ አፍሪካዊ ወይስ ኢትዮጵያዊ?
1. “ባለፈው ሰሞን፤ አልጀዚራ ላይ በቀጥታ ስርጭት ይመስለኛል፤ ጃዋር ፖለቲካዊ አጣብቂኝ ውስጥ የሚከተውን ጥያቄ ተጠየቀ፡፡ “መጀመሪያ ኦሮሞ ነህ፤ ኢትዮጵዊ?” የሚል፡፡ የሚቀጥለው ምሳሌ መቶ በመቶ ላይመሳሰል ይችላል፡፡ የተወሰነ መመሳሰል ግን አለው፡፡ አንድ ሰላሳ አመት ካናዳ ወይም አሜሪካ ውስጥ የኖረ ኢትዮጵያ፤ ወይንም እነዚህ አገር ውስጥ የተወለደ ናይጄሪዊ ይህንን ጥያቄ ቢጠየቅና፤ መጀመሪያ ናይጄሪያዊ ነኝ ብሎ ቢናገር፤ አሜሪካኖችን ወይንም ካናዳዎችን የሚያስቆጣ አይመስለኝም፡፡ ጃዋር ከኢትዮጵ በፊት መጀመሪያ ኦሮሞ ነኝ ብሎ ሲናገር ግን ብዙዎች አኮረፉ፡፡ ንትርክ ተጀመረ፡፡ የነቁና የበቁ የሚመስሉ የአንድነት አቀንቃኞች ራሱ ተቆጡ፡፡ አሁን በእመብርሀን ይሄ ምኑ ያበሳጫል? በዚህ መደንገጥም መቆጣትም የለብንም፡፡ ማድረግ ካለብን መጠየቅ ብቻ ነው፡፡ ችግሩ፤ እንድንሸመድድ እንጂ፤ እንድንጠይቅ በሚያበረታታ ባህል ውስጥ አላደግንምና፤ ከመጠየቅ ይልቅ፤ ልጁን ወደመዘልዘሉ ዘለልን፡፡”
አንደኛ፤ ከአገሬ በፊት ብሄሬን ነኝ የሚለው መልስ እንደየአመለካከታችን ትክክል ሊሆን ይችላል፡፡ በርግጥም ሰው ከአገሩ በፊት ብሄሩን ነው፡፡ አንድ ኢትዮጵያዊ መጀመሪያ ኢትዮጵያዊ ነህ አፍሪካዊ ቢባልና መጀመሪያ ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ ቢመልስ፤ ምንም ብዙ ቁጣ የሚቀሰቅስ አይመስለኝም፡፡ጥምር ዜግነት የሚሉትን ጽንሰሀሳብም ማስታወስ አይጎዳም፡፡ ኢትዮጵያዊ መሆንም ሙሉ በሙሉ የስራችንና የምርጫችን ውጤት ሳይሆን፤ የትውልድና የሕግ ጉዳይ ነው፡፡”
“ከሰደበኝ መልሶ የነገረኝ እንዳልባል እንጂ፤” አልከን ነገርከን እናመሰግንኃለን – ። ይህን ምሳሌ ዳር ዳር ከምትለው እኔ ብሆን ብለህ እንቅጩን ለምን አትነግረንም ነበር?! በብዕርህ ያለን ፍቅር እርሙን አውጥቶ ቦታ ፍለጋ ሊዝ ይገዛ ነበር። እርፍ ባልንም ነበር። እንዲህ በሺህ ምሳሌ ድርድር ከምታባካነን …. አናሳዝንህም ከቶ? … አንተም ወቅተህን፤ ወያኔም ቀጥቅጦን፤ … ዘረኛውም ደንፍቶብን – ዝቶብን – ቁምጥናችን ታቅፈን። ፈረደብን —- በህግ አምላክ!
„…. ነፍስ እንደዜግነት በህግ አትገደድም፡፡ ነፍስ ዜግነቱዋን ወይም ማንነትዋን ትመርጣለች እንጂ፡፡ ነፍሱ ማንነትዋን መረጠች፡፡ የኛ ስራ መሆን ያለበት፤ መናደድ ወይም ማበድ ሳይሆን፤” ማን ነው የተናደደው? ማን ነውስ ያአበደው? ሀቅ ላይ ተሁኖ … ንዴትም ማበድም የለም። በተከታታይ የወጡትን የኔን ጹሑፎች ስለማንነት አንብባቸው። እንኳንም ሩሙን ከፈቱት። ምን ያህል ምርት እንዳታፈሰ ጥንግ ገበሬዎች የተግባር ጀግኖች ያወቁታል። ይልቅ ያበደ ካለ አንተ የምታውቀው የቆምክለት ስሜትን አስረህ አስጠምቀው አንተው በነካ አፍህ …. “ ኢትዮጵያዊነት” የተረጋጋገ መንፈስ የረበበት ማንነት ነው። እሺ ወንድም ጋሼ! ተገፈቶ የማይገፋ ተንቆ የማይንቅ ገናና ተፈሪ ማንነት!

1. “እነዚህ ወጣቶችም ሆኑ የፖለቲካ ንስሀ አባቶቻቸው፤ በዚህ በአልጀዚራ ላይ የሰማነውን አይነት፤ ኢትዮጵዊነትን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ፤ ለኛ ለመቀበል የሚያስቸግረን ንግግር ሲናገሩ፤ የቆሰለውና እንዲህ ወዳለው ስሜት ውስጥ የሰነቀራቸውን ፖለቲካዊ ሕመም በማከም ፈንታ፤ እንደጠላት የሚፈርጅ አካሄዳችንና ራሳችንን የኢትዮጵያ አንድነት ጋሻዣግሬዎች አድርጎ የመሾም ባህላችንን ነው፤ እነዚህን ሰዎች ወደጽንፈንነት የሚመራቸው፡፡ ያ ደግሞ ለኛም ለኢትዮጵያም አይበጅም፡፡ በዚህ ረገድ ይሄን ያህል አመት በኢህአዴግ መበለጣችን ሁሌም ይገርመኛል፡፡ ምክንያቱም፤ ኢህአዴግ ለነጃዋር፤ የአንድነቱ ሀይል ለመቀበል የሚያዳግተውን፤ ኦሮሚያ የሚባል ክልል/ካርታ፤ ሙሉ ነጻነት ባይኖረውም በራሱ ቁዋንቁዋ የሚተዳደር መንግስት ሰጥቶዋቸዋልና፡፡ ስለዚህ ከአንድነት ሀይሉ ውግዘት ጋር ሲወዳደር ብቻ ሳይሆን፤ ራሱን ችሎም፤ ኢህአዴግ ለብሄር ፖለቲከኞች የሰጠው ፖለቲካዊ ገጸ-በረከት፤ ልብ የሚማርክ ነው፡፡”

ለነገሩ ባለፈው „ወያኔ ቀማን ሰልፋችን“ አልከን ዛሬ ደግሞ ወያኔ በለጠችሁ ትለናለህ …. ሀገር በማፈረስ፤ በመሸጥ በመለወጥ፤ ሰው በማጨረስ ጎሳና ጎሳ በማዋጋት፤ ሃይማኖት ሃይማኖትን በማጋጨት፤ በማፈን በመግደል በማሰረ አዎን በረኃብ በመቅጣት። ይበልጠናል። እኛ ስለ አብሮነት ስለ አንድነት ስለ ፍቅር ስለ ነፃነት ነው የሚያንገግበን … ከቶረንቶ ሽልማት ቢጤ ላክ አድርግለት ለሙጃው ወያኔ … ማንነትህን ለመቀማት እዬተጋለህ ነው።

1. “አማሮችና ትግሬዎች እየተፈራረቁ ይህቺን አገር መርተዋል፡፡ አሁን ደግሞ እኛ እንምራ ነው ነገሩ፡፡ በትግሬ ታኮ ወይንም በአማራ ጥላ ስር ሳይሆን፤ በራሳችን መታወቂያ፡፡ አገሪቱን መምራት ካልቻልንም፤ ቢያንስ የራሳችንን እጣ ፈንታ እንወስን ነው፡፡ የኛ ምላሽ …. “
እንዴት ከት ብዬ እንደሳቅኩኝ። ለመሆኑ መቼ ነው አማራ ብቻ ሀገር መርቶ የሚያውቀው? የትኛው ዘመን ላይ ነው ያለኸው? “ወያኔን” አዎን እያዬን ነው …. ይበቃኝ …. ናፍቆቱ ሳያባትለኝ ከች በልልኝና ምን አልባት ዳግም እንፋለም ይሆናል። …. በናፍቆት ይጠበቃል ቀጣዩ ዘላፈህ ደግሞ … “ችኮ” “ማነው ምንትስ” አለ ጋሼ ጸጋዬ “ማመናጨቅቅ” ቅብጥርስ የምትለው ፖለቲካና ፖለቲከኞችን፤ …. ለነገሩ … እስኪ ወኔው ካለህ ዘሀበሻን ጠይቃቸው ስጡት እላቸዋለሁ ኢሜሌንና ዲቤት ማደረግ እንችላለን። አንተ ሙሑር ነህ እኔ ግን መሃይም …… ደግመህ አንበበው። ጽንሰ ሃሳቡን ብቻ ተከተሎ አጠቃላይ እይታ ማቅረቡ ተመራጭ ነው …. ወደ ቀድሞዋ ውበት መልሳት ብእርህን በፈጠረህ። እኔ ለቀለማም ብዕር አብዝቼ ስስታም ነኝና።
ውዶቼ ይህ ኮበሌ እኮ አደከመን። በሉ ለነበረን መልካም የብዕር የጉጉሥ ትዕይንት በጎውን ሁሉ ተመኘሁላችሁ። መንፈሳችሁን ስለሸላማችሁኝ ወደድኳችሁ። አሁን ደግሞ በተክሌ ብዕር በነካ እጅ የተክሌ ደጋፊውች ውቁኝ። ይመቻችሁ ….
ልቦና ይስጠን። አሜን! ማስተዋልን እንደ ሰጠን እንጠቀምበት ዘንድ አዕምሯችን አምላካችን ያብራ። አሜን!
ኢትዮጵያዊነቴን የሰጠኝ አምላክ ክብሩ ይስፋ! ማህተም አለበት – የጸጋዬ ድህረ ገጽና ራዲዮ!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።


በልቡ የሸፈተ ህዝብ የካድሬውች ጋጋታና ሽብር አይገታውም

$
0
0

ሰሞኑን በትግራይ የህወሓት መሪዎችና ካድሬዎቻቸው ከየመንደሩ የተውጣጡ ነብሰ ገዳይ፣
ስብሰባ በታኝና አፋኝ የዱሪየ ቡድኖችን በተለያየ መልኩ በማደራጀት በአረና ትግራይ አባላትና
አመራር ላይ የከፈቱትን አዲስ የመንጥርና የድብደባ ዘመቻን አስመልክቶ

በዲያስፖራ የአረና ትግራይ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

ህወሓት/ኢሕአዴግ በትረ ስልጣኑን ከተጎናፀፈና ካደላደለ ወዲህ ከሱ የተለየ አመለካከትና ሃሳብ ያላቸው ወገኖች ሁሉ የተለያዩ ቀለማ
ቀለሞችን በመቅባት፣ የፈጠራ ስም በመለጠፍና ሰበብ አስባብ በመፈለግ በቀጥታም ሆነ በረቀቀ መንገድ የመመንጠር፣ የማፅዳት፣ የመሰወር፣
የማሰር፣ የመግደልና እርስ በርስ የማናቆር ስራ ዋነኛ የስርዓቱን ባህርይ መገለጫ ሆኖ መቆየቱ እሙን ነው። የእርምጃው ዋናው ምክንያትም
እውነት ተቃዋሚዎቹ የሀገርና የህዝብ ጠላቶች ስለሆኑ አይደለም። ነገር ግን ጥያቄያቸው “ስለ ሀገራችንና ህዝባችን ጉዳይ እኛም ያገባናል!!
አባቶቻችን ደም ከፍለው ያቆዩልንን ሀገር የመጠበቅ የኛም ግዴታ ነው!! ዘላቂ ልማትና ዕድገት የሚመጣው እውነተኛ ዲሞክራሲ፣ የሕግ
ልዕልና፣ ፍትሕ፣ ነፃነት፣ ሰላምና አንድነት ሲረጋገጥ እንጂ በጡንቻ አይደለም!! ሕገ መንግስቱ የሰጠንን የመናገር፣ የመፃፍ፣ የመደራጀት፣
የመንቀሳቀስ፣ የእምነት፣ የመምረጥና የመመረጥ ነፃነታችንን ይከበር!!” ብለው ሰላማዊና ሕጋዊ መንገድን ተከትለው በቆራጥነት ስለተንቀሳቀሱና
ስለጠየቁ ብቻ መሆኑን ማንም ቅን ህሊና ያለው ኢትዮጵያዊ ሊገነዘበው የሚችል ጉዳይ ነው።
ሰሞኑን የመድረክ አባል ከሆኑት የፓለቲካ ድርጅቶች አንዱ “በአረና ትግራይ ለሉዓላዊነትና ለዲሞክራሲ” አባላትና ከፍተኛ አመራር ላይ
እየደረሰ ያለው ግፍና አፈና ማየቱ በቂ ይመስለናል። የአረና ትግራይ ፈጣን ዕድገትና በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት እያገኘ መሄድ ያስደነጋጣቸው
የህወሓት ካድሬዎችና መሪዎቻቸው እንቅስቃሴውን ለመግታት የማይፈንቅሉት ድንጋይና የማይሸርቡት ተንኰል እንደሌለ በተደጋጋሚ
አይተናል። ዛሬም እንደለመዱት አዲስ የማጥቃት ስልት በመቀየስ ነብሰ ገዳይ፣ በታኝና አፋኝ የዱሩየዎች ቡድን በተለያየ መልኩ በሕቡእና
በግልፅ በማደረጃት በአረና አባላትና መሪዎች ላይ አዲስ የመንጥር ዘመቻና ጥቃት ጀምሯል።
የማጥቃት ዘመቻው ቀደም ብሎ በሽሬ እንዳስላሴ የተጀመረ ሲሆን ሰሞኑን ደግሞ በባሰ መልኩ በአዲ ግራት ከተማና በሌሎች አካባቢዎችም
በስፋት ቀጥሏል። በዚሁ ተከታታይ ዘመቻቸው ያነጣጠሩት አረና ትግራይ የጠራውን ስብሰባ እየተከታተሉ መበተን፣ ህዝቡን ወደ ስብሰባው
እንዳይሄድ በተለያዩ ዘዴዎች ማስፈራራትና ማሰናከል፣ በታኝ የዱሩየዎች በዱን በማደራጀት ለመበጥበጥና ለማወክ ያለ የሌለ ሀይላቸውን
በማንቀሳቀስ ስብሰባዎችን እንዲቋረጡ አድርጓል።
ጉዳዩን በቅርብ ተከታትለን እንዳረጋገጥነው የሚያሳዝነውና የሚያስገርመው ስብሰባውን መበተኑና መቋረጡ ብቻ ሳይሆን ህዝቡን ለመቀስቀስ
በአካባቢው የተሰማሩ በሶስት ከፍተኛ የአረና ትግራይ መሪዎች በአፋኝና በታኝ ቡድን እንዲደበደቡ ማደረጋቸውና ማሰራቸው ነው። የዚሁ
ጥቃት ሰለባ ከሆኑት ሰዎች ውስጥ አቶ አስገደ ገብረስላሴ የቀድሞ የህወሓት መስራችና አስልጣኝ የነበሩ፣ አቶ አብርሃ ደስታ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ
የፓለቲካ ሳይንስ መምህርና ተመራማሪ፣ አቶ ዓንዶም ገብረስላሴ የዓረና ማእከላይ ኮሚቴ አባልና የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ይገኙባቸዋል።
በአንጋፋ ወንድሞቻችን ላይ የደረሰባቸው ኢ ሰብኣዊ ጥቃት እጅጉን ያስቆጣንና ያስገረመን ቢሆንም በኛ እምነት ይህ ሁሉ ግፍና መሰሪ ተግባር
በድምር ሲታይ የሚከተሉትን ሓቆችንና ክስቶችን የሚያመላክቱ የስርዓቱን ባህርይ ገላጭ ናቸው ብለን እናምናለን።
1. ህወሓት ታሪክ፣ ባህልና ሕግ የማይገዛው፣ መሰረታዊ እውነታዎችንና ዲሞክራሲያዊ መርሆዎችን የሚፃረርና የህዝቡን ሉዓላዊ ህልውና
የሚያፈርስ የጥፋት መንገድ እየተከተለ በመሄድ ላይ እንደሆነ የሚያሳይ የቀቢፀ ተስፋ እርምጃ መሆኑን ራሱ በራሱ ጋሃድ እየሆነ መምጣቱ
የሚያመላክት ነው።
2. ይህ ዓይነቱ ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት የሚያሳየን ህወሓት ራሱን ከመንግስትነት ወደ ተራ ዘራፊነትና ማፊያነት በመቀየር የዜጎችን ድህንነት
ለመጠበቅ የማይችል ሕገ አልባና የሻገተ ስርዓት መሆኑን ራሱን በራሱ እያስመሰከረ ያለ ድርጅት መሆኑን እንገነዘባለን። አንድ መንግስት
በራሱ ህዝብና በገዛ ወገኑ ላይ ነብሰ ገዳይና አፋኝ ቡድንን በማደራጀት ዜጎቹን በአደባባይ ማስደብደብ ማለት የባዕድ ወራሪ እንኳን
ያላደረገው ከዚህ የባሰ ጭካኔ፣ ውድቀትና ዝቅጠት አለ ብለን አናምንም።
3. የህወሓት ፀረ ህዝብ ተግባር ለይስሙላ ስለዲሞክራሲና ስለየብዙሃን ፓርቲ ስርዓት ይናገር እንጂ በተግባር በህዝብ ፊት ቀርቦ ለመከራከርና
ለመዳኘት አቅምና ሞራል የሌለው፣ በህዝቡ ዘንድ ምን ያህል የተተፋና ጊዜ የጣለው ድርጅት መሆኑን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው።
ህወሓት የትግራይ ህዝብን ነፃነትና ደህንነት ጠባቂ ለመሆን ቀርቶ የነገ የሀገር ተረካቢና ተስፋ የሆነውን ወጣት በነፃነት አየር ተኰትኵቶና
የወገንና የሀገሩን ፍቅር ተላብሶ እንዳያድግ ወኔን የሚያኰላሽ ትውልድ ገዳይ ድርጅት መሆኑን ከተግባሩ በላይ ሌላ ምስክር የሚያሻ
አይደለም።
4. ህወሓት የትግራይ መንግስት ነኝ ይበል እንጂ ራሱ የፃፈውን ሕገ መንግስት እንኳ ጠንቅቆ የማያውቅ፣ በተግባር የሕገ መንግስቱን መሰረታዊ
መርሆዎችን የሚፃረር ስራ የሚሰራ አፍራሽ ድርጅት መሆኑን ራሱን በራሱ እያስመሰከረ ይገኛል። የትግራይ ህዝብ እየተዳደረ ያለው ራሱ
ባፀደቀው ሕገ መንግስት መሰረት ሳይሆን ገና በበረሃ የነበረው የደደቢት የካድሬ ሕግ መሆኑን ካለው ተጨባጭ ሁኔታና ከተግባራቸው
መረዳት ይቻላል።
5. ህወሓት የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ነኝ በማለት የትግራይ ህዝብ ነብዪ መስሎ ለመቅረብ ይሞክር እንጂ በተግባር ግን የታገለለትን አላማ
የሚፃረር ስራ የሚሰራና የህዝቡን ተስፋ እያጨለመ የሚገኝ ድርጅት መሆኑን ራሱ በራሱ እያስመሰከረ ይገኛል።
6. የጥቃቱ መንሲኤ ካድሬዎቹ እንደሚሉት የአረና ትግራይ አባላትና ደጋፊዎቻቸው የህዝብ ጠላት ስለሆኑ፣ ሕግ ስለጣሱ፣ የትምክሕተኞች
አመለካከት ስለሚያራምዱ ወይም የደርግ ስርዓትን ዳግም ለመመለስ የሚታገሉ ስለሆኑ አይደለም። አረና ትግራይ ሕገ መንግስቱ
የሚጠይቃቸው መመዘኛዎችን አሟልቶ በሕጋዊ መንገድ ተመዝግቦ በሰላማዊ መንገድ የሚታገል ድርጅት መሆኑን ይታወቃል። ይሁን
እንጂ “አያ ጅቦ ሳታማኸኝ ብላኝ” እንደሚባለው ሁሉ ከጥቃቱ በስተጀርባ ያለው ሚስጢር ግን ባንድ በኩል ገዢው ፓርቲ በሀገር ደረጃ
በተለይም በትግራይ ምድር እነሱ የማይቆጣጠሩት ትርጉም ያለው ነፃ የፓለቲካ ድርጅት እንዲፈጠር ፍፁም አይፈልጉም። በሌላ በኩል
ደግሞ በትግራይ ህዝብ ላይ ያላቸው ንቀትና ዝቅተኛ ግምት የሚያሳይ ነው። ሕብረተሰቡ በፓለቲካ ድርጅትና በህዝብ መካከል ያለው
ግንኙነትና ነፃነት፣ የዲሞክረሲ “ሀ ሁ”፣ ሕገ መንግስታዊ መብቱንና ታሪኩን በትንሹ ያውቃል ብለው ቢገምቱት ኖሮ እንዲህ ዓይነቱ ዓይን
ያወጣ አረሜናዊ ተግባር አይፈፁምም ነበር።
የተከበራችሁ በሀገር ውስጥና በውጭ የምትኖሩ ውድ ኢትዮጵያውያን!!
እኛ በዲያስፓራ የምንኖረው የአረና ትግራይ የድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴና መላ የትግራይ ተወላጆች በሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ በየማዕዝናቱ
በተለይም በበንሻንጉል፣ በጋምቤላ፣ በደቡብና በሌሎች ቦታዎች በወገኖቻችን ላይ የሚፈፀሙ አፈናዎችና እንግልት በቅርብ ስንከታተልና
በተለያየ መልኩ ድምፃችንን ስናሰማ ቆይተናል። በቅርቡ በሳውዲ ዓረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ላይ የደረሰው
ልብ ሰባሪ የሆነ አሳዛኝና አሳፋሪ ዜና ስንሰማም በቁጣ ስሜት በመነሳሳት በያለንበት ከሌሎች ወገኖቻችን ጎን በአደባባይ ቆመን ጭኾናል።
አውግዘናልም። ዛሬም በተመሳሳይ መልኩ እንደተለመደው በትግራይ በወገኖቻችን ላይ እየተካሄደ ያለው ጥቃትም ከዚሁ ተለይቶ የማይታይ
ስለሆነ አሁንም የተሰማንን ቁጣና ብሶት ይህንን የጋራ መግለጫ በይፋ እንድናወጣ ተገደናል። ያልታደለች ሀገር ሁሉጊዜ መርዶ ነውና!!………….
ትግራይ እንደነ አሉላ አባ ነጋና ዮሐንስ የመሳሰሉ የብዙ ጀግኖች ዓፅም የተቀበረባትና አኩሪ ታሪክ ያላት ምድር ብትሆንም ዛሬ ህዝብዋ በአንድ
ቤተሰባዊ ቡድን ለሚመራ ፓለቲካዊ ድርጅት በሞኖፓልና በንብረትነት ለማገልገል የተፈጠረ ህዝብ አድርገው በመቁጠር እንደ ህፃን ልጅ
አፍህን ያዝ እየተባለ በካድሬ ዱላ እየተኰረኰመ ሲኖር ማየች እጅግ የሚያሳዝን የታሪክ ጠባሳ ነው። ስለሆነም ህወሓት በህዝቡም ሆነ የተለየ
አመለካከት ይዘው በሚንቀሳቀሱ ወገኖቻችን ላይ የሚያካሂደው የስነ ልቦናና የአክል ጥቃት የዲሞክራሲ መርህ የሚፃረር ኢ ሰብኣዊ ተግባር
ብቻ ሳይሆን የዜጎች ሕገ መንግስታዊ መብት የሚጥስ ሕገ ወጥ ተግባር ስለሆነ ድርጊቱን እናወግዛን። እንዲሁም በግፍ የታሰሩ ወገኖቻችን
ከእስር እንዲፈቱና በነሱ ላይ ድብደባ ያደረሱ የማፊያና የነብሰ ገዳይ ቡድን አባላትም በአስቸኳ ለፍርድ እንዲቀርቡ አበክረን እንጠይቃለን።
በስልጣን ላይ ያለው ገዢው ፓርቲ ዜጎቻችንን ለያይተህ ግዛ በሚል ፈሊጥ በየተራ እንደ ፈለገ እያጠቃን እንዲኖር ምቹ ሁኔታ የፈጠርንለት
እኛው ራሳችን በተለያየ ጎራ የየራሳችን ጎጆ አበጅተን በረባም ባልረባም በመነጣጠላችን መሆኑን እሙን ነው። ህዝብ ከተባበረ ምን ዓይነት
ለውጥ ሊያመጣ እንደሚችል በሌሎች አጋጣሚዎች አይተናል። ስለዚህ በሀገር ቤትም በውጭም የምንኖር ኢትዮጵያውያን ሁሉ ለሀገርና ለወገን
ሲባል መለስተኛ ልዩነታችንን ወደ ጎን ትተን በዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ያለው አስነዋሪ ጥቃት በጋራ ልንቆምላቸው ይገባል። በመሆኑም ዛሬ
በትግራይ ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው በደል ነገ በሌሎች ክልሎችም የሚደርስ ጉዳይ ስለሚሆን ድርጊቱን በጋራ እንድናወግዘው ወገናዊ
ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ጀግናው ኩሩና ታጋሽ የትግራይ ህዝብም በአካል ይቆጣጠሩት ይሆናል እንጂ የህወሓት ካድሬዎችና መሪዎቻቸው የሚሰሩትን አስቂኝና አሳዛኝ
ድራማ ይስቷል ብለን አናምንም። ማን በሙሱና ተነክሮ ጨለማ ለብሶ የሀገርና የህዝብ ሀብት እየዘረፈና ወደ ዉጭ እያሸለከ እንዳለ ማን ደግሞ
ለሀገሩና ለወገኑ በፅናት እየታገለ እንዳለ በውል ይገነዘባል። ትላንት ማን ከጎኑ እንደቆመ ማን ደግሞ ለሻዕቢያ ወረራ ለጅብ አሳልፎ እንደሰጠው
ስለሚያስታውስ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ልቡ ከማን ጋር እንዳለ ጠንቅቀን እናውቃለን። በአጠቃላይ የትግራይ ህዝብ ክብሩንና ማንነቱን በሻዕቢያ
በመደፈሩ፣ ለም መሬቱንና አንጡራ ሀብቱን ለባዕድ አሳልፎ በመሰጠቱ፣ ራሱ የሰራውን ቤት፣ በደሙና በአጥንቱ ራሱ የገነባትን ሀገር ፈርሶ
የባሕር በር የሌላት ጎራዳና ሽባ ሀገር ይዞ በመቅረቱ ደስተኛ ነው ብለን በፍፁም አናምንም።
ስለሆነም ዛሬም ለገዢው ፓርቲ ህወሓት/ኢሕአዴግ መሪዎችና ካድሬዎቻቸው ደግመን ደጋግመን ልናስገነዝባቸው የምንፈልገው ጉዳይ አንድና
አንድ ብቻ ነው። በሀገራችን ፍትሕ የጠማው፣ በረሃብ አለንጋ የሚገረፍና በልቡ የሸፈተ ህዝብ እስካለ ድረስ እናንተ የምትፈፅሙትን ጊዜው
ያለፈበትና አረሜናዊ የቀቢፀ ተስፋ እርምጃ ትግሉን የበለጠ እንዲግልና እንዲጎለብት ያደርገዋል እንጂ በፍፁም አይገታውም። እኛም የበለጠ
እንድንጠነክርና ቀና ብለን በፅናት ከህዝባችን ጎን እንድንቆም ያደርገናል እንጂ አንገታችንን እንደማንደፋ ደግመን ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን።
ኢትዮጵያ ሀገራችን ለዘላለም ትኑር

ቃላትን ማባከን! (ከበልጅግ ዓሊ)

$
0
0

በጀርመን ውስጥ እንደ አውሮፓውያን አቆጠጠር 1971 ጀምሮ የዓመቱ ምርጥ ቃል ይመረጣል። ይህ በየዓመቱ የሚደረገው ምርጫ አዲስ የተፈጠሩ አባባሎች ወይም ቃላቶች አሮጌም ቢሆኑ በአለፈው ዓመት ውስጥ የአጠቃቀማቸው ሁኔታ ታይቶ የሚካሄድ ብሂል ነው። ለአሸናፊነት የሚበቃው ቃል በሕብረተሰቡ ውስጥ ተቀባይነት ያገኘው ይሆናል። ምርጫው በኮሚቴ ዳኝነት ተሳታፊዎቹን ቃላቶች አወዳድሮ ከፍተኛ ድምጽ ያገኘውን አሸናፊ ያደርጋል።
በዚህ ውድድር ማንም ሰው ሊያሸንፍ ይገባዋል የሚለውን ቃል መጠቆም ይችላል። በዚህ ዓመት የተመረጠው ቃል አሸናፊ የሆነው ከተጠቆሙት ከ2400 ቃላቶች ውስጥ ከፍተኛውን ድምጽ አግኝቶ ነው። ከተጠቆሙት 2400 ቃላቶች ውስጥ 10 ቃላት በዳኞች ይመርጡና ለሕዝብ ለድምጽ ይቀርባሉ ። ከዛም ሕዝብ ድምጽ ይሰጥበትና አሸናፊው ይወሰናል። ጀርመኖች በተለይ ከሥነ ጽሁፍ ጋር ግንኙነት
ያላቸው ቃላትን ያከብራሉ። በዓመቱ ውስጥ የዓመቱ ቃል ብቻ አይደለም የሚመረጠው። ሌሎችም ለምሳሌ የወጣቶች የዓመቱ ቃል፣ የሽማግሌዎች የዓመቱ ቃል ወዘተ . . .የሚባሉ የተለያዩ ምርጫዎች አሉ.።
በ2013 የጀርመን የዓመቱ ቃል ሆኖ ያሸነፈው “GROKO“( grossen Koalition) ሆኗል። ይህ ቃል ከሁለት ቃላት የተፈጠረ ነው። grossen – ትልቅ . . . . Koalition – ጥምረት ማለት ነው። አንድ ላይ ሲሆን ትልቁ ጥምረት ማለት ነው። ቃሉ የተመረጠው ጀርመኖች በዚህ ዓመት ምርጫ አካሂደው በዚህ ምርጫ ሁለቱ ትልልቅ ፓርቲዎች ማለትም ሶሻል ዲሞክራቱም (SPD) ሆነ ወግ አጥባቂው (CDU) ሃገሪቱን ብቻቸውን ለመምራት የሚያስችል ድምጽ ባለማግኘታቸው ጥምረት መፍጠር ስለነበረባቸው ነው። ጥምረቱን ለመፍጠር ብዙ ወራት የወሰደ ድርድር አድርገዋል። በዚህ ድርድር ወቅት ጋዜጠኞች አጭር ቃል ፈጥረው ነበር ይህን ቃል “GROKO“ የሚል ስያሜ ሰጥተው ነበር። ይህ ቃል ነው የዚህ ዓመት አሸናፊ የሆነው።
በእኛም ሃገር ይህንን መጀመር ያስፈልግ ይሆናል። በተለይ በዚህ ዓመት በወያኔ በታሰሩት የሃይማኖት መሪዎች ምክንያት የተፈጠሩ ቃላቶች አሉ።“ አል ሃብሽነ“Al Habash” ወይም ዋሃቢነት “Wahhabism” “ድምጻችን ይሰማ“ ለውድድር ሊቀርቡ ይችላሉ። ከሳውዲ ስለተመለሱት ስደተኞቻችንም በተመለከተ “የመጀመሪያው ሒጂራ“ የሚል ቃል ነበር። ቴዎድሮስ አፍሮ አለ የተባለው “ቅዱስ ጦርነትም“ ለውድድር መቅረብ ይችላል። ከዛው ተያይዞ “ጡት ቋራጭ“ የሚለውም የነ ጃዋር ክስ ሊወዳደር ይችላል። ለነ ጃዋር የወጣውም “ሜንጨኞች“ የሚለው መጠሪያ ድጋፍ ሊያገኝ ይችላል። በሃገሪቱ የታወቁ ድረ ገጸች ይህንን ቢያዘጋጁና ድምጽ ቢያሰጡበት ጥሩ ይሆን ነበር።
ከዚሁ ከጀርመን ሳንወጣ ለውድድር አይቅረቡ እንጂ በኢትዮጵያውያን አዳዲስ የአማርኛ ቃላትም ተፈጥረዋል። እነዚህ ቃላት ቢወዳደሩ ሊያሸንፉ ይችላሉ። ከሁሉም ያስደነቀኝና ሊያሸንፍ ይችላል ብዬ የማምነው ቲታኒክ (Titanic) የሚለው መጠሪያ ነው። ይህ መጠሪያ የተሰጣቸው በሰሃራ በረሃ አድርገው፣ ሜዲትራንያን አቋርጠው፤ ላፓዱሳ ላይ ባሕር ላይ ሳይሰምጡ አውሮፓ የደረሱ ዜጎቻችንን ነው። ይህ ስም አትላንቲክ ውስጥ የሰመጠችውን ታላቋን መርከብ ቲታኒክ (Titanic) በማስታወስ ነው። አንድ ሰው በሳሃራ አቋርጦ አውሮፓ የደረሰ ከሆነ እሱ “ቲታኒክ” ነው ይባላል። በዚሁም ብዙ ዜጎቻችን ከአደጋ ተርፈው አውሮፓ ገብተዋል። “ቲታኒኮች” ብዙ የሚተረክ ታሪክ አላቸው። በዚህ ዓመት የጀርመንን የአማርኛ ቋንቋ በአንድ ቃል ከፍ አድርገውታል።
በጀርመን አዲስ ቃላቶች እየተፈጠሩ ቢሆንም በሌሎች አገሮች ደግሞ ያሉትን ቃላት መጠቀም እንዳይቻል አዲስ ሕግ ለማውጣት ሙከራ እየተደረገ ነው። እስራኤል ውስጥ “ናዚ” የሚለውን ቃል አላግባብ መጠቀም እንዲከለከል በእስራኤል ፓርላማ(knesset)እቅንስቃሴ ተጀምሮ የመጀመሪውን ክፍል አልፏል። እስራኤሎች በተለምዶ ፖሊስም ይሁን ወታደር ወይም ባለስልጣን ሥልጣኑን በመጠቀም ከተጋፋቸው ይህ ሰው “ናዚ” ነው ይላሉ።

http://www.haaretz.com/news/national/1.569281

ይህ ሕግ ከጸደቀ ብዙ ሕይወት ያለቀበትን የናዚ ድርጊት በተራ ቃል አለቦታው ወይም አላግባብ መጠቀም ይከለከላል ማለት ነው። ቃላትን በሕግ መከልከል ጥቅሙ የጎላ ላይሆን ይችላል። ከመናገር ነጻነት ጋርም የሚያያዝ ይሆናል። እያንዳንዳችን ከምንጠቀምበት ቃል ጋር የተያያዙ አስከፊ ነገሮችን ማሰብና የቃሉን ጥቅም ማልከስከስና የተፈጸመውን ግፍ እንደማቅለል እንዳይቆጠር መጣር ይኖርብናል። “ናዚ” የሚለው ቃል ከዘር ማጥፋት ጋር የተያያዘ ነውና። በትራፊክ ጥፋት የቀጣንን ፖሊስ ሁሉ “ናዚ” ነው ማለት የናዚን ትርጉም ዝቅ ያደርገዋል። ተራ ጠብቅ ብሎ ሥነ ሥርዓት ያስጠበቀውንም “ናዚ“ ማለት ቃሉን ትርጉም ያሳጣዋል ነው የእስራኤሎቹ እምነት።
ወደ ሃገራቸን ስንመጣ ደግሞ ብዙ ቃላትን አለ ቦታቸውና አላግባብ መጠቀም እየለመደብን መጥቷል። በመንግሥት ሥልጣን ላይ የተቀመጠው ወያኔ ቃላትን አላግባብ በመጠቀም የተጨበጨበለት ነው ብንል ስህተት አይሆንም። የምዕራብያውያንን ድጋፍ በመሻትም ሆነ የፖለቲካ ጥቅምን በሚመለከት ከብዕር በስተቀር ምንም የሌለውን ጋዜጠኛ “ ሽብርተኛ“ ወይም “ፀረ ሰላም“ ብሎ ወያኔ ሲፈርጅ የትርጉም ስህተት መስሎ የሚታየን አንጠፋም። በአሁኑ ወቅት በመንግሥት የሕዝብ መገናኛ መንገዶችና(እንደ ኢቲቪ ዓይነታቸው) ደጋፊዎቻቸው “አክራሪ“ የሚባሉት በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉት የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች የወጣላቸው ከእነርሱ ጋር ግንኙነት እንደሌላው የሚታወቅ ነው። ሰላማዊ ሰዎችን “ሽብርተኛ“ ወይም “አክራሪዎች“ ብሎ መጥራት እውነተኞቹ አሸባሪዎች በሕዝብ ላይ የሚያደርሱትንና ወይም ያደረሱትን ጉዳት ማሳነስ ይሆናል።
በተቃዋሚ በኩልም ቃላቶች ይባክናሉ። የዓባይን መገደብ የደገፈን ወይም አባቱን ለመጠየቅ ወደ ሃገሩ ጎራ ያለውን ሁሉ “ወያኔ“ ማለት የወያኔነትን ትርጉም ዝቅ ማድረግ ይመስለኛል። ናዚነት ለእስራኤሎች ትርጉም እንደሚሰጥ ወያኔነት ለእኛም የሚሰጠን ዘግናኝ ትርጉም አለው። ስለዚህ ያለፈ ያገደመውን ስላልደገፈን ብቻ ተነስተን “ወያኔ“ ማለት የወያኔን ግፍ በጣም ማቅለል ይሆናል። ለነገሩ የአርሶ አደሮች ንቅናቄ የነበረውንና የተከበረውን “ወያኔ“ የሚለውን ስም ያልከሰከሰው ራሱ ወያኔ ነው። የሕዝብን ንቅናቄ የነበረው መጠሪያ ለአንድ ዘረኛ ድርጅት መጠሪያ ሲያደርግ ነው ነገሩ የተበላሸው። ዛሬ በወያኔ መጥፎ ተግባር ምክንያት “ወያኔ“ የሚለው ቃል የትግል መጠሪያ ሳይሆን ዘረኛ፣ ጠባብ ፣ ከፋፋይ ፣ ግፈኛ የሚል ትርጉም ይዟል።
በሌላ በኩል ደግሞ በድርጅት ውስጥ ዴሞክራሲ የጠየቀውን ሁሉም አንጃ ማለት ስህተት ነው። በተለይ እንደ ሃገራችን አቆጣጠር 1969-70 ዓ.ም በኢሕአፓ ውስጥ በነብርሃነ መስቀልና ጌታቸው ማሩ ደጋፊ አንጀኞች የተፈጸመውን ግፍ ማቅለል ይመስለኛል። ይህ በአሁኑ ወቅት የምንሰማው የአንጃነት አፈራረጅ በእነ ብርሃነ መስቀልና ጌታቸው ማሩ ደጋፊዎች የደረሰውን ጥፋት የሚያልከሰክስና በዚያም ወቅት ሕይወታቸውን ያጡትን ዜጎች ደመ ከልብ የሚያደርግ ሆኖ ነው የታየኝ። ፓሊስ ሲቀጣን ናዚ ማለት የቃሉን ክብደት ካቀለለው በድርጅት ውስጥ በተነሳ የሃሳብ ልዩነት የተለየንን ወይም የተቃወመንን ሁሉ አንጃ ስንልም የአንጀኞችን በደል ተራ እናደርገዋለን።
ቃላትን ትርጉም እንዲኖራቸው ስናደርግ ከግል ጥቅም አንጻር ወይም ከወቅታዊ የፖለቲካ እሰጥ አገባ ብቻ ሳይሆን እንደ ጀርመኖች ከሀገርና ከሕዝብ ጥቅምና ጉዳት አኳያ እየመዘንን ቢሆን ነው ከበሬታ የሚኖረን። በዚህ ውድድር ጀርመን ውስጥ በስልጣን ያለውን መንግሥት የሚያጋልጡ ቃላት የማሸነፍ እድላቸው ትልቅ ነው። ጋዜጠኛውን “ሽብርተኛ“፣ የዓባይ ግድብን የደገፈውን “ወያኔ“፣ ከእኛ ጋር የሃሳብ ልዩነት ያለውን “አንጃ“ ብሎ ከመሬት ተነስቶ ደፍሮ መናገር ወይም መጻፍ የራስን ማንነት የሚያጋልጥ ነው። ይህ ደግሞ ወዳጅንም ሳይሆን ጠላትን እያበዛ የሚሄድ አሰራር ነው የሚሆነው። በሕዝብ ታማኝነትንም ያሳጣል። ሲበዛ ደግሞ ቀበሮ መጣብኝ ብሎ ሲያታልል እንደቆየው እረኛ፣ የእውነቱ ቀበሮ ሲመጣ ጩኸቱ እንደ ማታለል ነው የሚቆጠረው።
ቃላትን በሕግ መከልከል ልዩነት ያመጣል ብዬ አላምንም። በሕግ መገደብን ከተቃወምን ደግሞ ራሳችንን በተፈጥሮ ሕግ ማስተዳደር ይኖርብናል። ስንት ዜጎች ያለቁበትን ጉዳይና ስያሜ ወደ ጊዜያዊ የፖለቲካ ጥቅም መተርጎም ኢሰብአዊነት ነው የሚሆነው። በተለይ የምንወነጅለው ግለሰብ ነጻ ከሆነ በግለሰቡ ላይ የሰራነው ወንጀል ትልቅ ነው።እንደ ወያኔ ራስ ከሳሽ፣ ራስ ፈራጅ እስከ አልሆንን ድረስ በነጻ መድረክ መረጃ አቅርቡ ብንባል ማጣፊያው ሊያጥረን ይችላል። ማንም የሚጠይቀን የለም ብሎ ያልሆነውን መለደፍ ደግሞ የዝቅተኝነታችን ምልክት ነው የሚሆነው። መድረክ አገኘሁ ብለን ደግሞ የጠላነውን ሁሉ “አንጃ“ ብሎ መጻፍ ወይም በሰፈር ጠብ “ወያኔ“ ብሎ መሳደብ ትዝብት ላይ ይጥላል።
በሁሉ የሚገርመው እኛ በውጭ ሃገር ተቀምጠን፣ ወያኔ የማይደርስብን መሆኑን አረጋግጠን፣ አገር ውስጥ የሚችሉትን የሚያደርጉትን “ቡከን“ ብለን ብንሳደብ ማን ነው የሚሰማን? ይህንን ዓይነት ሁኔታ ቃላትን ከማባከን በላይ ፋይዳ ሊኖረው አይችልም። “ቡከን“ ብለን ስንተች ሌሎች የፈሩትን እኛ ሰርተን ካላሳየን ባዶነታችን ነው ጎልቶ የሚታየው። ስድባችንም የአህያ ፈስ ነው የሚሆነው። አይሸትም አይገማም። ማንም ለአህያ ፈስ አፍንጫውን የሚይዝም አይኖርም።
በደርግ አስራ ሰባት የግፍ አገዛዝ ውስጥ የተፈጠሩ የማውገዣ ቃላት ብዛታቸውን ማስታወስ ያዳግታል። ግን ሁሉም መፍትሄ አላመጡም። ዛሬም ወያኔ የማያወጣው ስም የለም ግን ቃላት ማባከን እንጂ የሚያመጣው ትርፍ የለም። ከስድቡ ባሻገር አልፈን “ወያኔም“ ሆነ “አንጃ“ “ቡከን“ ሆነ “ሽብርተኛ“ ብለን የምንፈርጃቸው ሰዎች እውን እንደምንላቸው ናቸው ወይ? ካልሆኑ ደግሞ ችግራቸውን አጥንተን ችግሩን ለመፍታት ስንጥር ነው መፍትሄ የምናገኘው። “ጸረ ሰላም“ “ሽብርተኛ“ ብሎ ተቃዋሚዎችን መፈረጅ ችግሩን አይፈታም፣ የውስጥ ዴሞክራሲን የጠየቀውን ሁሉ አንጃ ብሎ መለደፍ ድርጅትን ዴሞክራሲዊ አያደርግም። ሙከራችን ቃላትን ማባከን እንዳይሆን ከመፈረጃችን በፊት ማሰብ መቅደም አለበት።
ሰለ ሃገራችን ሰላም የሚያስቡ ሁሉ በሰላም ይክረሙ!
በልጅግ ዓሊ
23.01.14 ፍራንክፈርት
Beljig.ali@gmail.com

አንድነት ህወሓት/ኢህአዴግ የትግራይ ህዝብ አማራጭ ሀሳብ እንዳያገኝ እያካሄደ ያለውን አፈና አጥብቆ እንደሚቃወም ገለጸ

$
0
0

የመቀሌ ከተማ (ፎቶ ፋይል)

የመቀሌ ከተማ (ፎቶ ፋይል)


(ዘ-ሐበሻ) አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫው “ህወሓት/ኢህአዴግ የትግራይ ህዝብ አማራጭ ሀሳብ እንዳያገኝ እያካሄደ ያለውን አፈና አጥብቀን እንቃወማለን” ሲል አወገዘ።

የትግራይ ህዝብ እንደ ሌላው ኢትዮጵያዊ ሁሉ የዴሞክራሲ ዕጦት ሰለባ እንደሆነ ፓርቲያችን ያምናል ያለው አንድነት ስርዓቱ በየትኛውም የኢትዮጵያ ክልል እንደሚያደርገው በትግራይም ሰብዓዊ መብት ይረግጣል፣ ፍትህ ይደፈጥጣል፣ በካድሬዎች ይደበደባል፣ ይንገላታል፣ እንዲሰደድ ይደረጋል፡፡ ስርዓቱና በስርዓቱ ውስጥ የደላቸው ሹማምንት በስሙ ከመነገድ በዘለለ ዋጋ የተከፈለበትን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ዘርግቶ ተጠቃሚ ማድረግ አልቻለም ሲል በመግለጫው ላይ አስቀምጧል።

“ህወሓት/ኢህአደግ ክልሉን እንደዋና ካምፕ በማየት በአፈና ውስጥ እንዲኖር አድርጎታል፡፡ የትግራይ ህዝብ የነፃ ፕሬስ ውጤቶችን እንዳያገኝ፤ አማራጭ የፖለቲካ ፓርቲዎችን እንዳያዳምጥ የተፈረደበት ሕዝብ ነው ማለት ማጋነን አይደለም፡፡ ይሄ እውነትም ሕወሓት/ኢህአዴግ በተለያየ ጊዜ በህዝቡ ላይ በፈፀማቸው ኢ-ዴሞክራሲያዊና ኢ-ፍትሃዊ ድርጊቶች የታየ ነው፡፡” የሚለው የአንድነት መግለጫ ” ለዚህ ማሳያ የሚሆነው አምባገነኑ ህወሓት/ኢህአዴግ አረና ባለፈው ሳምንት በትግራይ ክልል አዲግራት ከተማ ሊያደርግ የነበረው ሕዝባዊ ስብሰባ ልክ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ታፍኖበታል፣ አባላቱ ተደብድበዋል እንዲሁም ታስረዋል፡፡ ይሄ የሆነበት ምክንያት የትግራይ ህዝብ አማራጭ እንዳያገኝና በጉልበት የህወሓት አንጡራ ሀብት ብቻ ሁኖ እንዲያገለግል ከመፈለግ ነው፡፡ ከዚህ በፊትም ፓርቲያችን በመቀሌ ከተማ ሊያደርግ የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ በከፍተኛ አፈናና እስር እንዲያስተጓጉል መደረጉ የቅርብ ግዜ ትዝታ ነው፡፡ አንድነት ፓርቲ የትግራይ ህዝብ አማራጭ ሓሳብ የማዳመጥ፣ የሚጠቅመውን የመምረጥና የመቃወም ሕገ-መንግስታዊ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን በፅኑ ያምናል፡፡” ብሏል።

አማራጭ ሓሳብ በሚያቀርቡ ፓርቲዎች ላይ ህወሓት/ኢህአዴግ እየወሰደ ያለውን ኢ-ዴሞክራሲያዊ ርምጃና አፈና በጥብቅ እንደሚያወግዝ ያስታወቀው አንድነት “አንድነት የአረና ፓርቲ የሚያደርገውን ዴሞክራሲያዊ እንቅስቃሴ ተከትሎ ህወሓት/ኢህአደግ ለማደናቀፍ የሚያደርገውን ህገወጥ ዘመቻ እንዲያቆም እየጠየቀ አሁንም ተቃዋሚዎችን ‹‹ከጠላቶቻችን ጋር የሚተባበሩ›› በማለት የትግራይን ህዝብ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ለመነጠል የሚካሄደውን ዘረኝነት የተሞላበት ከፋፋይ ርምጃ ለአገራችን እጅግ አደገኛ እንደሆነ አምኖ እንደ ሌላው ህዝብ ሁሉ ለነፃነቱ መከበር የሚያደርገውን ትግል አጠናክሮ እንዲቀጥልና ሰላማዊ ትግሉን በመደገፍ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እውን እንዲሆን የከበረ ጥሪ እናቀርባለን፡፡” ሲል መግለጫውን ቋጭቷል።

“በልቡ የሸፈተ ህዝብ የካድሬዎች ጋጋታና ሽብር አይገታውም”–በዲያስፖራ የአረና ደጋፊዎች መግለጫ

$
0
0

(መግለጫውን በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ)

(ዘ-ሐበሻ) ሰሞኑን በትግራይ የህወሓት መሪዎችና ካድሬዎቻቸው ከየመንደሩ የተውጣጡ ነብሰ ገዳይ፣ ስብሰባ በታኝና አፋኝ የዱዬ ቡድኖችን በተለያየ መልኩ በማደራጀት በአረና ትግራይ አባላትና አመራር ላይ የከፈቱትን አዲስ የመንጥርና የድብደባ ዘመቻን አስመልክቶ በዲያስፖራ የአረና ትግራይ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫ ድርጊቱን አወገዘ።

“ትግራይ እንደነ አሉላ አባ ነጋና ዮሐንስ የመሳሰሉ የብዙ ጀግኖች ዓፅም የተቀበረባትና አኩሪ ታሪክ ያላት ምድር ብትሆንም ዛሬ ህዝብዋ በአንድ ቤተሰባዊ ቡድን ለሚመራ ፓለቲካዊ ድርጅት በሞኖፓልና በንብረትነት ለማገልገል የተፈጠረ ህዝብ አድርገው በመቁጠር እንደ ህፃን ልጅ አፍህን ያዝ እየተባለ በካድሬ ዱላ እየተኰረኰመ ሲኖር ማየች እጅግ የሚያሳዝን የታሪክ ጠባሳ ነው።” የሚለው ይኸው መግለጫ “ስለሆነም ህወሓት በህዝቡም ሆነ የተለየ አመለካከት ይዘው በሚንቀሳቀሱ ወገኖቻችን ላይ የሚያካሂደው የስነ ልቦናና የአክል ጥቃት የዲሞክራሲ መርህ የሚፃረር ኢ ሰብኣዊ ተግባር ብቻ ሳይሆን የዜጎች ሕገ መንግስታዊ መብት የሚጥስ ሕገ ወጥ ተግባር ስለሆነ ድርጊቱን እናወግዛን።” ብሏል።

“ህወሓት/ኢሕአዴግ በትረ ስልጣኑን ከተጎናፀፈና ካደላደለ ወዲህ ከሱ የተለየ አመለካከትና ሃሳብ ያላቸው ወገኖች ሁሉ የተለያዩ ቀለማ ቀለሞችን በመቅባት፣ የፈጠራ ስም በመለጠፍና ሰበብ አስባብ በመፈለግ በቀጥታም ሆነ በረቀቀ መንገድ የመመንጠር፣ የማፅዳት፣ የመሰወር፣ የማሰር፣ የመግደልና እርስ በርስ የማናቆር ስራ ዋነኛ የስርዓቱን ባህርይ መገለጫ ሆኖ መቆየቱ እሙን ነው።” ያለው የአረና ደጋፊዎች መግለጫ “የእርምጃው ዋናው ምክንያትም እውነት ተቃዋሚዎቹ የሀገርና የህዝብ ጠላቶች ስለሆኑ አይደለም። ነገር ግን ጥያቄያቸው “ስለ ሀገራችንና ህዝባችን ጉዳይ እኛም ያገባናል!! አባቶቻችን ደም ከፍለው ያቆዩልንን ሀገር የመጠበቅ የኛም ግዴታ ነው!! ዘላቂ ልማትና ዕድገት የሚመጣው እውነተኛ ዲሞክራሲ፣ የሕግ ልዕልና፣ ፍትሕ፣ ነፃነት፣ ሰላምና አንድነት ሲረጋገጥ እንጂ በጡንቻ አይደለም!! ሕገ መንግስቱ የሰጠንን የመናገር፣ የመፃፍ፣ የመደራጀት፣ የመንቀሳቀስ፣ የእምነት፣ የመምረጥና የመመረጥ ነፃነታችንን ይከበር!!” ብለው ሰላማዊና ሕጋዊ መንገድን ተከትለው በቆራጥነት ስለተንቀሳቀሱና ስለጠየቁ ብቻ መሆኑን ማንም ቅን ህሊና ያለው ኢትዮጵያዊ ሊገነዘበው የሚችል ጉዳይ ነው።” ብሏል።

በዲያስፖራ የአረና ትግራይ ድጋፍ አስተባባሪ ያወጣው መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይቀጥላል፦

ሰሞኑን የመድረክ አባል ከሆኑት የፓለቲካ ድርጅቶች አንዱ “በአረና ትግራይ ለሉዓላዊነትና ለዲሞክራሲ” አባላትና ከፍተኛ አመራር ላይ እየደረሰ ያለው ግፍና አፈና ማየቱ በቂ ይመስለናል። የአረና ትግራይ ፈጣን ዕድገትና በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት እያገኘ መሄድ ያስደነጋጣቸው የህወሓት ካድሬዎችና መሪዎቻቸው እንቅስቃሴውን ለመግታት የማይፈንቅሉት ድንጋይና የማይሸርቡት ተንኰል እንደሌለ በተደጋጋሚ አይተናል። ዛሬም እንደለመዱት አዲስ የማጥቃት ስልት በመቀየስ ነብሰ ገዳይ፣ በታኝና አፋኝ የዱሩየዎች ቡድን በተለያየ መልኩ በሕቡእና በግልፅ በማደረጃት በአረና አባላትና መሪዎች ላይ አዲስ የመንጥር ዘመቻና ጥቃት ጀምሯል።

የማጥቃት ዘመቻው ቀደም ብሎ በሽሬ እንዳስላሴ የተጀመረ ሲሆን ሰሞኑን ደግሞ በባሰ መልኩ በአዲ ግራት ከተማና በሌሎች አካባቢዎችም በስፋት ቀጥሏል። በዚሁ ተከታታይ ዘመቻቸው ያነጣጠሩት አረና ትግራይ የጠራውን ስብሰባ እየተከታተሉ መበተን፣ ህዝቡን ወደ ስብሰባው እንዳይሄድ በተለያዩ ዘዴዎች ማስፈራራትና ማሰናከል፣ በታኝ የዱሩየዎች በዱን በማደራጀት ለመበጥበጥና ለማወክ ያለ የሌለ ሀይላቸውን በማንቀሳቀስ ስብሰባዎችን እንዲቋረጡ አድርጓል።

(ከዚህ ቀደም የአረናን ሕዝባዊ ስብሰባ እንዳይሳተፉ የተከለከሉ የሽሬ ነዋሪዎች - ፎቶ ከአብርሃ ደስታ) - ፎቶ ፋይል

(ከዚህ ቀደም የአረናን ሕዝባዊ ስብሰባ እንዳይሳተፉ የተከለከሉ የሽሬ ነዋሪዎች – ፎቶ ከአብርሃ ደስታ) – ፎቶ ፋይል


ጉዳዩን በቅርብ ተከታትለን እንዳረጋገጥነው የሚያሳዝነውና የሚያስገርመው ስብሰባውን መበተኑና መቋረጡ ብቻ ሳይሆን ህዝቡን ለመቀስቀስ በአካባቢው የተሰማሩ በሶስት ከፍተኛ የአረና ትግራይ መሪዎች በአፋኝና በታኝ ቡድን እንዲደበደቡ ማደረጋቸውና ማሰራቸው ነው። የዚሁ ጥቃት ሰለባ ከሆኑት ሰዎች ውስጥ አቶ አስገደ ገብረስላሴ የቀድሞ የህወሓት መስራችና አስልጣኝ የነበሩ፣ አቶ አብርሃ ደስታ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የፓለቲካ ሳይንስ መምህርና ተመራማሪ፣ አቶ ዓንዶም ገብረስላሴ የዓረና ማእከላይ ኮሚቴ አባልና የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ይገኙባቸዋል።

በአንጋፋ ወንድሞቻችን ላይ የደረሰባቸው ኢ ሰብኣዊ ጥቃት እጅጉን ያስቆጣንና ያስገረመን ቢሆንም በኛ እምነት ይህ ሁሉ ግፍና መሰሪ ተግባር በድምር ሲታይ የሚከተሉትን ሓቆችንና ክስቶችን የሚያመላክቱ የስርዓቱን ባህርይ ገላጭ ናቸው ብለን እናምናለን።

1. ህወሓት ታሪክ፣ ባህልና ሕግ የማይገዛው፣ መሰረታዊ እውነታዎችንና ዲሞክራሲያዊ መርሆዎችን የሚፃረርና የህዝቡን ሉዓላዊ ህልውና የሚያፈርስ የጥፋት መንገድ እየተከተለ በመሄድ ላይ እንደሆነ የሚያሳይ የቀቢፀ ተስፋ እርምጃ መሆኑን ራሱ በራሱ ጋሃድ እየሆነ መምጣቱ የሚያመላክት ነው።

2. ይህ ዓይነቱ ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት የሚያሳየን ህወሓት ራሱን ከመንግስትነት ወደ ተራ ዘራፊነትና ማፊያነት በመቀየር የዜጎችን ድህንነት ለመጠበቅ የማይችል ሕገ አልባና የሻገተ ስርዓት መሆኑን ራሱን በራሱ እያስመሰከረ ያለ ድርጅት መሆኑን እንገነዘባለን። አንድ መንግስት በራሱ ህዝብና በገዛ ወገኑ ላይ ነብሰ ገዳይና አፋኝ ቡድንን በማደራጀት ዜጎቹን በአደባባይ ማስደብደብ ማለት የባዕድ ወራሪ እንኳን ያላደረገው ከዚህ የባሰ ጭካኔ፣ ውድቀትና ዝቅጠት አለ ብለን አናምንም።

3. የህወሓት ፀረ ህዝብ ተግባር ለይስሙላ ስለዲሞክራሲና ስለየብዙሃን ፓርቲ ስርዓት ይናገር እንጂ በተግባር በህዝብ ፊት ቀርቦ ለመከራከርና ለመዳኘት አቅምና ሞራል የሌለው፣ በህዝቡ ዘንድ ምን ያህል የተተፋና ጊዜ የጣለው ድርጅት መሆኑን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው። ህወሓት የትግራይ ህዝብን ነፃነትና ደህንነት ጠባቂ ለመሆን ቀርቶ የነገ የሀገር ተረካቢና ተስፋ የሆነውን ወጣት በነፃነት አየር ተኰትኵቶና የወገንና የሀገሩን ፍቅር ተላብሶ እንዳያድግ ወኔን የሚያኰላሽ ትውልድ ገዳይ ድርጅት መሆኑን ከተግባሩ በላይ ሌላ ምስክር የሚያሻ አይደለም።

4. ህወሓት የትግራይ መንግስት ነኝ ይበል እንጂ ራሱ የፃፈውን ሕገ መንግስት እንኳ ጠንቅቆ የማያውቅ፣ በተግባር የሕገ መንግስቱን መሰረታዊ መርሆዎችን የሚፃረር ስራ የሚሰራ አፍራሽ ድርጅት መሆኑን ራሱን በራሱ እያስመሰከረ ይገኛል። የትግራይ ህዝብ እየተዳደረ ያለው ራሱ ባፀደቀው ሕገ መንግስት መሰረት ሳይሆን ገና በበረሃ የነበረው የደደቢት የካድሬ ሕግ መሆኑን ካለው ተጨባጭ ሁኔታና ከተግባራቸው መረዳት ይቻላል።
5. ህወሓት የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ነኝ በማለት የትግራይ ህዝብ ነብዪ መስሎ ለመቅረብ ይሞክር እንጂ በተግባር ግን የታገለለትን አላማ የሚፃረር ስራ የሚሰራና የህዝቡን ተስፋ እያጨለመ የሚገኝ ድርጅት መሆኑን ራሱ በራሱ እያስመሰከረ ይገኛል።

6. የጥቃቱ መንሲኤ ካድሬዎቹ እንደሚሉት የአረና ትግራይ አባላትና ደጋፊዎቻቸው የህዝብ ጠላት ስለሆኑ፣ ሕግ ስለጣሱ፣ የትምክሕተኞች አመለካከት ስለሚያራምዱ ወይም የደርግ ስርዓትን ዳግም ለመመለስ የሚታገሉ ስለሆኑ አይደለም። አረና ትግራይ ሕገ መንግስቱ የሚጠይቃቸው መመዘኛዎችን አሟልቶ በሕጋዊ መንገድ ተመዝግቦ በሰላማዊ መንገድ የሚታገል ድርጅት መሆኑን ይታወቃል። ይሁን እንጂ “አያ ጅቦ ሳታማኸኝ ብላኝ” እንደሚባለው ሁሉ ከጥቃቱ በስተጀርባ ያለው ሚስጢር ግን ባንድ በኩል ገዢው ፓርቲ በሀገር ደረጃ በተለይም በትግራይ ምድር እነሱ የማይቆጣጠሩት ትርጉም ያለው ነፃ የፓለቲካ ድርጅት እንዲፈጠር ፍፁም አይፈልጉም። በሌላ በኩል ደግሞ በትግራይ ህዝብ ላይ ያላቸው ንቀትና ዝቅተኛ ግምት የሚያሳይ ነው። ሕብረተሰቡ በፓለቲካ ድርጅትና በህዝብ መካከል ያለው ግንኙነትና ነፃነት፣ የዲሞክረሲ “ሀ ሁ”፣ ሕገ መንግስታዊ መብቱንና ታሪኩን በትንሹ ያውቃል ብለው ቢገምቱት ኖሮ እንዲህ ዓይነቱ ዓይን ያወጣ አረሜናዊ ተግባር አይፈፁምም ነበር።

የተከበራችሁ በሀገር ውስጥና በውጭ የምትኖሩ ውድ ኢትዮጵያውያን!!

Arena-Tigray-logoእኛ በዲያስፓራ የምንኖረው የአረና ትግራይ የድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴና መላ የትግራይ ተወላጆች በሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ በየማዕዝናቱ በተለይም በበንሻንጉል፣ በጋምቤላ፣ በደቡብና በሌሎች ቦታዎች በወገኖቻችን ላይ የሚፈፀሙ አፈናዎችና እንግልት በቅርብ ስንከታተልና በተለያየ መልኩ ድምፃችንን ስናሰማ ቆይተናል። በቅርቡ በሳውዲ ዓረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ላይ የደረሰው ልብ ሰባሪ የሆነ አሳዛኝና አሳፋሪ ዜና ስንሰማም በቁጣ ስሜት በመነሳሳት በያለንበት ከሌሎች ወገኖቻችን ጎን በአደባባይ ቆመን ጭኾናል። አውግዘናልም። ዛሬም በተመሳሳይ መልኩ እንደተለመደው በትግራይ በወገኖቻችን ላይ እየተካሄደ ያለው ጥቃትም ከዚሁ ተለይቶ የማይታይ ስለሆነ አሁንም የተሰማንን ቁጣና ብሶት ይህንን የጋራ መግለጫ በይፋ እንድናወጣ ተገደናል። ያልታደለች ሀገር ሁሉጊዜ መርዶ ነውና!

ትግራይ እንደነ አሉላ አባ ነጋና ዮሐንስ የመሳሰሉ የብዙ ጀግኖች ዓፅም የተቀበረባትና አኩሪ ታሪክ ያላት ምድር ብትሆንም ዛሬ ህዝብዋ በአንድ ቤተሰባዊ ቡድን ለሚመራ ፓለቲካዊ ድርጅት በሞኖፓልና በንብረትነት ለማገልገል የተፈጠረ ህዝብ አድርገው በመቁጠር እንደ ህፃን ልጅ አፍህን ያዝ እየተባለ በካድሬ ዱላ እየተኰረኰመ ሲኖር ማየች እጅግ የሚያሳዝን የታሪክ ጠባሳ ነው። ስለሆነም ህወሓት በህዝቡም ሆነ የተለየ አመለካከት ይዘው በሚንቀሳቀሱ ወገኖቻችን ላይ የሚያካሂደው የስነ ልቦናና የአክል ጥቃት የዲሞክራሲ መርህ የሚፃረር ኢ ሰብኣዊ ተግባር ብቻ ሳይሆን የዜጎች ሕገ መንግስታዊ መብት የሚጥስ ሕገ ወጥ ተግባር ስለሆነ ድርጊቱን እናወግዛን። እንዲሁም በግፍ የታሰሩ ወገኖቻችን ከእስር እንዲፈቱና በነሱ ላይ ድብደባ ያደረሱ የማፊያና የነብሰ ገዳይ ቡድን አባላትም በአስቸኳ ለፍርድ እንዲቀርቡ አበክረን እንጠይቃለን።

በስልጣን ላይ ያለው ገዢው ፓርቲ ዜጎቻችንን ለያይተህ ግዛ በሚል ፈሊጥ በየተራ እንደ ፈለገ እያጠቃን እንዲኖር ምቹ ሁኔታ የፈጠርንለት እኛው ራሳችን በተለያየ ጎራ የየራሳችን ጎጆ አበጅተን በረባም ባልረባም በመነጣጠላችን መሆኑን እሙን ነው። ህዝብ ከተባበረ ምን ዓይነት ለውጥ ሊያመጣ እንደሚችል በሌሎች አጋጣሚዎች አይተናል። ስለዚህ በሀገር ቤትም በውጭም የምንኖር ኢትዮጵያውያን ሁሉ ለሀገርና ለወገን ሲባል መለስተኛ ልዩነታችንን ወደ ጎን ትተን በዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ያለው አስነዋሪ ጥቃት በጋራ ልንቆምላቸው ይገባል። በመሆኑም ዛሬ በትግራይ ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው በደል ነገ በሌሎች ክልሎችም የሚደርስ ጉዳይ ስለሚሆን ድርጊቱን በጋራ እንድናወግዘው ወገናዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

ጀግናው ኩሩና ታጋሽ የትግራይ ህዝብም በአካል ይቆጣጠሩት ይሆናል እንጂ የህወሓት ካድሬዎችና መሪዎቻቸው የሚሰሩትን አስቂኝና አሳዛኝ ድራማ ይስቷል ብለን አናምንም። ማን በሙሱና ተነክሮ ጨለማ ለብሶ የሀገርና የህዝብ ሀብት እየዘረፈና ወደ ዉጭ እያሸለከ እንዳለ ማን ደግሞ ለሀገሩና ለወገኑ በፅናት እየታገለ እንዳለ በውል ይገነዘባል። ትላንት ማን ከጎኑ እንደቆመ ማን ደግሞ ለሻዕቢያ ወረራ ለጅብ አሳልፎ እንደሰጠው ስለሚያስታውስ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ልቡ ከማን ጋር እንዳለ ጠንቅቀን እናውቃለን። በአጠቃላይ የትግራይ ህዝብ ክብሩንና ማንነቱን በሻዕቢያ በመደፈሩ፣ ለም መሬቱንና አንጡራ ሀብቱን ለባዕድ አሳልፎ በመሰጠቱ፣ ራሱ የሰራውን ቤት፣ በደሙና በአጥንቱ ራሱ የገነባትን ሀገር ፈርሶ የባሕር በር የሌላት ጎራዳና ሽባ ሀገር ይዞ በመቅረቱ ደስተኛ ነው ብለን በፍፁም አናምንም።
ስለሆነም ዛሬም ለገዢው ፓርቲ ህወሓት/ኢሕአዴግ መሪዎችና ካድሬዎቻቸው ደግመን ደጋግመን ልናስገነዝባቸው የምንፈልገው ጉዳይ አንድና አንድ ብቻ ነው። በሀገራችን ፍትሕ የጠማው፣ በረሃብ አለንጋ የሚገረፍና በልቡ የሸፈተ ህዝብ እስካለ ድረስ እናንተ የምትፈፅሙትን ጊዜው ያለፈበትና አረሜናዊ የቀቢፀ ተስፋ እርምጃ ትግሉን የበለጠ እንዲግልና እንዲጎለብት ያደርገዋል እንጂ በፍፁም አይገታውም። እኛም የበለጠ እንድንጠነክርና ቀና ብለን በፅናት ከህዝባችን ጎን እንድንቆም ያደርገናል እንጂ አንገታችንን እንደማንደፋ ደግመን ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን።

ኢትዮጵያ ሀገራችን ለዘላለም ትኑር

[የሳዑዲ ጉዳይ] ዛሬም ያልታወቀውን እያየን ትተን ፣ የታወቀውን አስከሬን ሸኘን…ነብዩ ሲራክ

$
0
0

ነብዩ ሲራክ ከሳዑዲ አረቢያ

“ከሞቱ አሟሟቱ “

እኔና ወዳጆቸ ከወር ላላነሰ ጊዜ እንከታተለው የነበረ የአንዲት እህት አስከሬንን ዛሬ ተሸኘ …ምሽት ላይ የከሬኑን መሸኘት አረጋግጨ እና በስራ የደከመ አዕምሮየን ላሳርፍ ስውተረተር አንድ መልዕክት ቢጤ በኤሌክትሮኒክስ መልዕክት መላኪያ የአስከሬኑን መሸኘት መረጃ አስተላለፍኩ … ጉዳዩ እንድከታተል አደራ ጨምረው ለተመጸኑኝን ቤተሰቦች የላኩት መልዕክት የጉዳዩን ማለቅ የሚየሳወቅ ወደ ሃገረ አሜሪካ የላኩት መልዕክት ምላሽ ከምስጋና ጋር ሳይዘገይ ደረሰኝ ። ከደረሰኝ የምስጋና ምላሽ ውስጥ ስለ ማላውቃት ሟች ማንነት የሚገለልጽ መረጃ ሰፍሮበታል። የሚያሳዝን …
ዛሬ የተሸኘው አስከሬን የሁለት ወንድና ሴት ለአቅመ አዳምና ሔዋን የደረሱ ልጆች እናት መሆኑን እንግዳ የሆነኝ መረጃ አሳዝኖ ቅስሜን ቢሰብረው ከሰሞኑ ያየኋቸውን ማንነታቸው የማይታወቁት ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ሩቅ ወስዶ መለሰኝ ። እናም ዛሬ መናገር ያልፈለግኩት እናገረው ዘንድ ..ተገደድኩ ! መረጃየን ወደ ኋላ አሁን ወደ ደረሰኝ መልዕክት ላቅና …

(ፎቶ ፋይል)

(ፎቶ ፋይል)


ከሟች ቤተሰቦች የደረሰኝ መልክት አንድ ክፍል” ሟች ልጆችዋ እናታችን የታለች?” እያሉ ዘመድ አዝማዱን ሌት ተቀን አፋጠው የእናታቸውን መዋደቂያ ይጠይቁ እንደ ነበር እና የሟች ልጆች ጥያቄ መላ ቤተሰቡን ለወራት በጭንቀት የምይዙ የሚጨብጡት አጥተው እንደ ነበር በመጠቆም ምንም እንኳን ሃዘኑ የከበደ ቢሆንም የልጆችና የሚወዷት የናፈቋት ቤተሰቦችዋ ጥያቄ ዛሬ አስከሬኑ ሲሸኝ መልስ ማግኘቱን መልዕክቱ ይገልጻል።
በአስከፊው ሞት “አተርፍ ባይ አጉዳይ ” እህታቸውን የተነጠቁት ወላጆች ፣ልጆችና ቤተሰብ የእናት እህታቸውን ሞት መርዶ መራራ የሟችን መዳረሻ ሳያውቁ ለወራት መባዘናቸው እንደ ትልቅ ነገር መቆጠሩ እውነት ነው ። ለቀሪው ቤተሰብና ለዘመዱ” እንኳ አረብ ሃገር ሄዳ ቀረች !” ቢባል ተቀባይነት ሊኖረው ይችላል ። ነፍስ ላወቁ ልጆችን ግን በዚህ ዘመን “እናታችሁ ሞታለች! ” ብሎ ማርዳት ብቻ በቂ አይደለም ። ይህን ለመረዳት ነገሮችን አዟዙሮ ማየት ፣ ጭንቀት ፣ ሰቀቀን ጸጸቱን ባለ ጉዳዩን እንደራስ አድርጎ ማየት ብቻ በቂ ነው ። ውስብስቡን የአረብ ሃገር ስደት በቦታው ሆኖ ለተመለከተ “ማንቴስ ” ተብላ በወላጆቻቸው የሚታወቁ ዜጎች ኑሮን ለማሸነፍ ፣ ኑሮን ለመቀየር ፣ ለማደግ ሌላ ስም ተቀብተው ከልታማውን ህይወት ተቀላቅለዋልና መዳረሻቸውን ማወቅ ከሁሉም የከባደ ነው ። አሁን አሁን በተለይ ዜጎች ከዚህ አለም በሞት መለየታቸው ሲታወቅ የሟችን ስም አረጋግጦ ፣ የአስከሬኑን ማንነት ከብዙው ባለቤት ካልቀረበለት ኢትዮጵያዊ መካከል ለይቶ ማወቅ በራሱ እድለኛ መሆን ያስፈልጋል።

እነሆ ነገ በአስከፊው ሞት የተበጠቁት ቤተሰቦች የእናት እህታቸውን ክቡር አስከሬን ይረከባሉ። በከራረመ ሃዘን ተኮራምተው ፣ ውዳቸውን በክብር ሊሸኙት መቻላቸው ከፍ ያለ ደስታና ወሰን የሌለው እርካታ እንዳለው ከምስጋና ጋር የደረሰኝ መልዕክት ይገልጻል። የእኒህ ወገኖች የእኒያ ታዳጊዎች ጥያቄ ዛሬ መልስ አግኝቷል! ይህ እንዲሳካ እኔ መልዕከት በማስተላለፍ ብሳተፍም የትልቁን ምስጋና ባለቤቶች ሌሎች ናቸው! ትልቁን ስራ ለከወናችሁ በቤተሰቡ ስም የእኔም ምስጋና ይድረሳችሁ! የሟችን ነብስ አብዝቶ ይማር !
ይብላኝላቸው ማንነታቸው ሳይታወቅ ለሚሸኙት ሙታን የዚህች እህት ጉዳይ በሰመረ መንገድ ተከውኗል። ይህችን ማስታወሸሰ እንድጽፍ ስሜቴን ወደ ሸነቆጥ ክፍል ላምራ … መሰንበቻውን የዚህችን እህት ሽኝት ጉዳይ በቅርብ ስከታተል የታዘብኩት እውነት በተለያዩ ሆስፒታሎች ቁጥራቸው አነስተኛ የማይባል ማንነታቸው የማይታወቅ ዜጎች አስከሬን ለበርካታ ሳምንታት በማቀዝቀዣ ውስጥ እንደሚገኝ መረጃ መሰባሰቤ ነበር ። የእኒህ ዜጎች ማንነት አለመታወቅና ጠያቂ ማጣት በእርግጥም እንደ ሰው ያሳስባል ፣ ያማል! ዘመዳቸው የተገኘ አይሆኑ ሁነው የወገናቸውን መዳረሻ ያገኛሉ ፣ የፈለጉ ወደ ሃገራቸው ይሰዳሉ ፣ ያልቻሉት እርማቸውን አውጥተው እዚሁ እንዲቀበር ይፈቅዳሉ ። ባለቤት ያልተገኘላቸው ሟቹች ያለ ቤተሰብ፣ ወገን እና ዘመድ አዝማድ አልተፈጠሩም እና ማንነታቸው ሳይታወቅ ወደ አፈር የሚሸኙበት የመጨረሻ ግብአት የእኔ ጉዳይ ብለው ሲያስቡት ያሳዝናል ።
እኒህ ምንዱባን ወደ ማይቀረው አለም መሄዳቸው ያለና የማንመክተው የተፈጥሮ ህግ መሆኑ እንዳለ ሆኖ አበው ” ከሞቱ አሟሟቱ !” እንዲሉ ማንነታቸው እና አሟሟታቸው አቅም በፈቀደ መጠን በተለያየ መንገድ እየተጣራ በወጉ አፈር እንዲቀምሱ ማድረግ ቢቻል መልካም ነው ቢያንስ ለቀሪ ቤተሰብ ለማርዳት ማንነታቸው ያልታወቀ አስከሬኖችን በማጣራቱ ረገድ የመንግስት ተወካዮቻችን አንድ ሊሉት ይገባል ። ” ነግ በኔ ” ነውና በዚህ ጉዳይ ሌላው ቢቀር ለህሊናችን ስንል የሁላችንም ትብብር ታክሎበት አንድ መላ ሊበጅለት ይገባል !
አዎ ዛሬም ያልታወቀውን እያየን ትተን ፣ የታወቀውን አስከሬን ሸኘን …

የሟችን ነፍስ ይማር ፣ የቤተሰብን ሃዘን እሱ ያቅልል!
ነቢዩ ሲራክ

[በሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ] ያየሁትን ልመስክር

$
0
0

debereselam Minnesota
በቀለ ገብርኤል (ሲሳይ) – ከሚኒሶታ

ዛሬ (እሁድ) ከእንቅልፌ እንደተነሳሁ መጀመሪያ የደረኩት ነገር ቢኖሮ የመሶኮቱን መጋረጃ ከፈት Aድርጌ ውጪውን ማይት ነበር። በረዶው እንደጉድ ተከምሮዋል። የታየኝ ገና መኪና አሙቄ፣ በረዶ ጠርጌ፣ መጥረግማ ቢሆን በማን እድል ፈቅፍቄ ጉዞዬን ወደ ቤተ ክርስቲያን ማቅናት ነበር። መንገዱም ከሞላ ጎደል ቢጠረግም ፍጥነትን በተመለከተ እንኳን ለመብረር በተፈቀደው ፍጥነትም ለመሄድ የደፈረ የለም። ሁሌ መኪና የሚያሽከረክሩ ጸባያቸው እንደዚህ ቢያምር እንዴት ጥሩ ነበር። ሁሉም በጥናቃቄ መሪውን እንደ ህጻን ልጅ ታቅፎ የሚነዳው ነው የሚመስለው። በእርግጥ አናዳንዶቹ በራሳቸውም ይሁን ከቁጥጥር በላይ በሆነ ምክንያት እዚያም እዚህም በረዶው ውስጥ ውትፍ ብለው የሚታዩ አሉ።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

በሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ በቦርዱ የተነበበው ጽሑፍ

$
0
0

የሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ጉዳይ ቁጭብሎ በመነጋገር በሰላም መፍታት እየተቻለ፤ ወደ አላስፈላጊ ሁኔታዎች እየተደረሱ ነው። ዘ-ሐበሻ የሁሉንም ወገን ድምጽ ለማሰማት አሁንም ጠንክራ በመሥራት ላይ ትገኛለች። ከዚህ ቀደም ባለፈው እሁድ የተፈጠረውን በማስመልከት አቶ በቀለ ገብር ኤል (ሲሳይ) የተባሉ የቤ/ክስቲያኑ አባል “ያየሁትን ልመስክር” በሚል የጻፉትን ጽሁፍ አስተናግደን ነበር። አሁን ደግሞ ቦርዱ ባለፈው እሁድ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ያነበበውን ደብዳቤ ደርሶናል – አስተናግደነዋል። የተፈጠረው ነገር ሁሉ በመነጋገር ሰላም እንዲፈጠር በዚህ አጋጣሚ ጥሪ እናቀርባለን።
debereselam Minnesota

የደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሠላሟ ከዕለት ወደ ዕለት አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል። ችግሩም በተለይ በDecember 15, 2013 ከተጠራው የአባላት ጠቅላላ ጉባዔ ወዲህ ጥሩ መልክ እየያዘ እንዳልመጣ ሁላችንም በየሳምንቱ እሁድ እያየን ያለነው ክስተት ነው።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ


ላፈቀራት ልጅ ሲል 5 ዓመት በአሜሪካ የታሰረው ድምጻዊ –አበበ ተካ

$
0
0

abebe teka
ከኢየሩሳሌም አረአያ

አሜሪካ መኖር ከጀመረ 16 አመት አለፈው። ለፍቅር ሲል ከፍተኛ መስዋእትነት የከፈለ ታዋቂ አርቲስት ነው። እጅግ ለሚያፈቅራት ልጅ አቀንቅኖላታል። ይህ ድምፃዊ፥ አበበ ተካ ነው። “ሰው ጥሩ..” የሚለው የግጥም ድርሰት በህልሙ ነበር የታየው። ፍቅረኛው እታገኝ ሙላው ትባላለች። አቤ በህልሙ “ፍቅረኛውን ጥቅጥቅ ባለ ጫካ ውስጥ እየሮጠ ሲከተላት..ሲሮጥ…ሳይደርስበት ይቀራል። ከዛም ደክሞት ለምለም ሳር በሆነ ሜዳ ቁጭ ብሎ…”ሰው ጥሩ..” እያለ ያዜማል፤”. ህልሙን ለገጣሚ ሙልጌታ ተስፋዬ (ነፍሰ ሄር) ይነግረዋል። ዘፈኑም ተሰራ። “ምንድነው ቀለበት፣.. እንዳንቺ አላየሁም በዝች ምድር ላይ፣.. አገሯ ወዲያ ማዶ፣..በይ ካልረሳሽኝ-ንገሪኝ..” ዜማዎች ለፍቅረኛው እታገኝ የተደረሱ ናቸው።

አበበ ተካ በ1989ዓ.ም “ምርጥ የአመቱ ድምፃዊ” ተብሎ የገንዘብና ወርቅ ሽልማት አግኝቷል። ብዙ ጊዜ መድረክ ላይ ሲዘፍን እንባው ይፈስ ነበር። ምክንያቱ ደግሞ በመለየት ስቃይ ውስጥ አሻግሮ የእርሱ አይነት እጣ (የመለያየት) የደረሰባቸውን እያሰበ ጭምር ነበር።…አበበ በ1990ዓ.ም ለንደን ይጓዛል። በዛው የጣሊያን ፓስፖርት አሰርቶ ፍቅረኛውን ለማግኘት ወደ አሜሪካ ይበራል። እንዳቀደው ግን አልሆነም። ፓስፖርቱ ተመሳስሎ የተዘጋጀ ስለነበረ በአሜሪካ ፖሊስ ተይዞ እስር ቤት ተላከ። 5 አመት ተፈረደበት። ጎንደር ይኖሩ የነበሩት አባቱ አቶ ተካ የልጃቸውን መታሰር እንደሰሙ (በደም ግፊት) ደንግጠው ሕይወታቸው አለፈ። እስር ቤት እንዳለ መርዶ መጣበት።.. አቤ በእስር ቤት በነበረው መልካም ባህርይ 1አመት ከ8 ወር ከታሰረ በኋላ እንዲለቀቅ ተደረገ። በብዙ ፈተና ያለፈበትን ፍቅረኛውን የማግኘት ህልም እውን ሆነ። አበበ አሁን ድረስ ፈጣሪን ያመሰግናል።

ከፍቅረኛው እታገኝ ሙላው ጋር ጎጆ ቀልሰው ሶስት ልጆች አፍርተዋል። ልጆቹ ትእግስት አበበ፣ ብርሃን አበበ፣ አዲስኪዳን አበበ ይባላሉ። አበበ እጅግ ሲበዛ ትሁትና ሰው አክባሪ ሲሆን በዲሲ የሚኖሩ ሃበሾች ትልቅ ከበሬታ ይሰጡታል። ስለእርሱ ሲናገሩ፥ « አበበ የትዳርና ፍቅር ተምሳሌት ነው። ጨዋና ቤተሰቡን አክባሪ ሰው ነው። ብዙ ቦታ ልታይ- ልታይ አይልም። ከስራው መልስ ከቤተሰቡ ጋር ነው የሚያሳልፈው። ስለ ሃገሩ ኢትዮጲያ በየመድረኩ ያዜማል።» በማለት ምስክርነት ይሰጣሉ። በየሳምንቱ ቅዳሜ በ”ዱከም” መዝናኛ የሚዘፍነው አበበ ሲናገር፥ « የሰው ልጅ በተለይ በስደት አገር ያለው ሃበሻ ወገኔ..ከሚወደው አገሩ፣ከቤተሰቡ፣ ከፍቅረኛው…እንዲገናኝ ሁሌም ፈጣሪን እለምናለሁ። የተለያየ ሰው ናፍቆቱን ሳይወጣ ክፉ አይንካው!!

ተነጣጥሎ መኖር ከባድ ስቃይ ነው። የናፍቆትና ብቸኝነት ስቃይን የደረሰበት ያውቀዋል። » ይላል። ከኳስ የቡና ክለብ አድናቂና ደጋፊ የሆነው ድምፃዊ አበበ ሁለተኛ አልበም ሊያወጣ ነው። በአንድ ሰው አገናኝነት ገጣሚና ደራሲ ፋሲል ተካልኝ የላካቸውን ጨምሮ የግጥምና ዜማ ስራዎች ቅድመ ዝግጅት እየተደረገባቸው ነው። በእውነተኛ ታሪክ ዙሪያ የተመሰረቱ እንዲሁም አገርና ህዝብን የተመለከቱ ዜማዎች ይገኙበታል።..የሰው ልጅ ህልሙ ሲሰምር እንዴት ያስደስታል!!

ጊዜ መስታወቱ!! ተስፋዬ ገብረአብ ማነው? ቁጥር – 2

$
0
0

ጌዜ መስታወቱ!! ተስፋዬ ገብረአብ ማነው?  ቁጥር – 2

(ተስፋዬ ገብረአብ)

(ተስፋዬ ገብረአብ)


ከዓለማየሁ መሰለ

ውድ አንባብያን፣ ይህ ጽሁፍ ከዚህ ቀደም ከዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻ ጋር ተስፋዬ ገብረአብን አስመልክቶ አወጥተን ከነበረው ሪፖርት ጽሁፍ ተከታይ ነው። በዚህ መሰረት ከተስፋዬ ገብረአብ ጋር አብረን ስንኖር እጄ ላይ ከወደቁትን መረጃዎች መሃከል የመጀመሪያው ጽሁፍ ተከታይ ይሆናል ብዬ የመረጥኳቸውን ቃል በገባሁት መሰረት ከነማብራሪያቸው አቀርባለሁ።
ለዛሬ የማቀርበው መረጃ ተስፋዬ ገብረአብ እንደ ሸፋን ከሚጠቀምበት የደራሲነት እና የጋዜጠኘነት ስራ ባሻገር ለማመን በሚያዳግት ይሰራ የነበረውን የወንጀል ድርጊት ፍንትው አድርጎ ያሳያል።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ/ Read full story in PDF

[የሚኒሶታው መድሃኔዓለም ቤ/ክ ጉዳይ] “ነዋያተ ቅድሳት ለእግዚአብሔር ክብር እንጂ ለአመጽና ለረብሻ ሊውሉ አይገባም”

$
0
0

debereselam Minnesota
ለቤተክርስቲያን ሰላም እና አንድነት ከቆሙ ምእመናን የተሰጠ መግለጫ

ሰንበት ት/ቤት መንፈሳዊ ሕይወት በወጣትነት ጊዜ የሚገበይበት፣ በምግባር የሚታነጹበት፣በኃይማኖት የሚጎለምሱበት የቤተክርስቲያን፣የአገርና የህዝብ ተስፋ የሚሆኑ ዜጎች የሚፈጠሩበት መንፈሳዊ የአገልግሎት ክፍል ነው። ይሁን እንጂ ይህ የቤተክርስቲያን፣የአገርና የህዝብ ተስፋ የሆነ የልጆችና የወጣቶች መንፈሳዊ ተቋም በሚኔሶታ ‘‘ ቤዛ ኵሉ ’’ ሰ/ት/ቤት ሲረክስ መታየቱ እጅጉን ያሳዝናል።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ኬንያታ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)

$
0
0

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
የዘገዬ ፍትህ እንደተነፈገ መቆጠር የለበትምን?
icc_logo1381718589
በአህጽሮ ቃሉ አይሲሲ/ICC እየተባለ የሚጠራው ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት/International Criminal Court የኡሁሩ ሙጋይ ኬንያታን ጉዳይ አስመልክቶ እያደረገ ያለው ተደጋጋሚ የፍትህ ሂደቱን የማዘግየት ስራ፣ በቀጠሮ የማሳለፍ እና “የውሸት መረጃዎች” እንዲሁም “የሀሰት ምስክሮች” በማቅረብ እንደገና የመታየት ዕድል ለመፍጠር እየተነገረ እና በተግባር እየተፈጸመ ያለው አጠቃላይ ወደኋላ የመንሸራተት ሁኔታ አንቅልፍ ባያሳጣኝም ከፉኛ አሳስቦኛል፡፡ ይኸ ነገር ሙሉ በሙሉ ትክክል አይደለም ለማለት ባይዳዳኝም የጥርጣሬ ጠረኑ ግን እየሸተተኝ ነው፡፡ ኬንያታ ከተከሰሰበት የሰብአዊ መብት ጥሰት ነጻ በመሆን ከዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት/አይይሲ መዳፍ እንዲወጣ መድረኩ እየተመቻቸ ነውን?
ዓለም አቀፉ የወንወጀለኞች ፍርድ ቤት/ICC ቀደም ሲል በሰብአዊ መብት ጥሰት ክስ መስርቶባቸው የነበሩትን ኡሁሩ ኬንያታ እ.ኤ.አ ከጃንዋሪ 2012 ጀምሮ የኬንያ ርዕሰ ብሄር ሆነው ስልጣን ከተቆናጠጡ በኋላ የክስ ሂደቱን የማቆየት፣ የማዘግየት እና የማቋረጥ አድሏዊ ጥረቶችን በማድረግ አዝማሚያ ላይ ይገኛል፡፡ በተባበሩት መንግስታት የኬንያ አምባሳደር ሆነው በመስራት ላይ የሚገኙት ማቻሪያ ካማው እ.ኤ.አ ሜይ 2013 በተጻፈ “የሚስጥር ደብዳቤ” ለተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የኡሁሩ ኬንያታ ጉዳይ ከዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት እጅ ወጥቶ በኬንያ ፍርድ ቤት እንዲታይ ትዕዛዝ እንዲሰጥ የሚጠይቅ ባለ 13 ገጽ የተማጽኖ አቤቱታ አቀረቡ፡፡ በዚያ ወር የኢትዮጵያ የይስሙላው ጠቅላይ ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት ተዘዋዋሪ ሊቀመንበር ኃይለማርያም ደሳለኝ ንዴት እና ስሜታዊነት በተቀላቀለበት አኳኋን ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በጥቁር አፍሪካውያን መሪዎች ላይ የሚያካሂደው “የዘር ማደን” ዘመቻ መቆም አለበት የሚል ክስ በጩሀት አሰሙ፡፡ እ.ኤ.አ ጁን 2013 ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የኡሁሩ ኬንያታን የክስ ሂደት ጉዳይ በማስመልከት የኬንያታ ወንጀል መከላከል ቡድን አባላት በቂ ማስረጃዎችን ማሰባሰብ እና ማቅረብ እንዲችሉ በማለት የክስ ሂደቱ እስከ ኖቬምበር 12/2013 ድረስ እንዲዘገይ ብይን ሰጠ፡፡ እ.ኤ.አ መስከረም 2013 ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የኬንያታ እና የሩቶን ሁለቱንም ክሶች ውድቅ እንዲያደርጋቸው አቶ ኃይማርያም ደሳለኝ በይፋ ጠየቁ፡፡ በሌላ በኩልም አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በተባበሩት መንግስታት 68ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በመገኘት ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት “በኬንያ መሪዎች ላይ ክስ በመመስረት መሪዎቹ ህገመንግስታዊ ኃላፊነቶቻቸውን በአግባቡ መወጣት እንዳይችሉ ያላቸውን አቅም” ያዳከመ መሆኑን በመግለጽ ጉባኤው ክሶቹ እንዲሰረዙ ውሳኔ ቢያሳልፍ “በኬንያ ለሰላም ግንባታው እና ለብሄራዊ ዕርቅ ሂደቱ ወሳኝ ድጋፍ እንደሚያደርግ“ ለጉባኤው ጩኸታቸውን አሰምተዋል፡፡
እ.ኤ.አ ኦክቶበር 2013 የአፍሪካ ህብረት/AU በህብረቱ ጽ/ቤት ልዩ ጉባኤ በማድረግ የኬንያታ እና የሩቶ የክስ ሂደት ጉዳይ ከዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ተነስቶ በኬንያ ፍርድ ቤቶች መታየት እንዲችል ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት/ICC ጥያቄ አቀረበ፡፡ ይህ ካልሆነ ግን እንደ አማራጭ የአፍሪካ የህብረቱ አገሮች በ በደቦ “ከሮም ስምምነት” እራሳቸውን እንዲያገሉ ለማድረግ ዛቻ አሰሙ፡፡ በዚህም መሰረት አፍሪካውያንን እያሳደደ ከሚያድነው “ዘር አዳኝ” ፍርድ ቤት ለማዳን እና ደህንነታቸው እንዲጠበቅ ለማድረግ የሚል ሀሳብን መሰረት በማድረግ በአዲስ አበባ ከተማ ስብሰባቸውን አደረጉ፡፡ መሪዎቹ ከዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በተጻራሪ በመቆም ባዶ፣ የተጋነነ እና እራሳቸውን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ጩኸትና አምቢልታ አሰሙ፡፡ ሆኖም ግን ከሮማ ስምምነት እራስን ማግለል የሚለው “የብዙህን ስምምነት መጣስ” ጩኸትና ሴራ ሳይሳካ ከሸፈ፡፡ ከሮማ ስምምነት በደቦ እንወጣለን የሚለው ስሜታዊነት እና እብደት የተሞላበት ማስፈራሪያ ባዶ ጩኸት ከመሆን ባለፈ የፈየደው ነገር የለም፡፡ በቀጣይነትም የአፍሪካ ህብረት የኬንያታ የፍትህ ሂደት ጉዳይ ለአንድ ዓመት እንዲዘገይ ለተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ጥያቄ አቀረበ፡፡ ሆኖም ግን እ.ኤ.አ በኖቬምበር 2013 አጋማሽ የፍትህ ሂደቱ ለአንድ ዓመት እንዲዘገይ የቀረበውን ጥያቄ የጸጥታው ምክር ቤት ውድቅ በማድረግ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ ይህንንም በማስመልከት በተባበሩት መንግስታት የኬንያ አምባሳደር የሆኑት ካማዉ እንዲህ በማለት ደነፉ፣ “የፍርድ ሂደቱን ለማዘግየት የቀረበው ጥያቄ ተቀባይነትን አላገኘም፣ ምክንያት እና ህግ በመስኮት ተወርውረዋል፣ ፍርኃት እና አለመተማመን እንዲነግሱ ተፈቅዶላቸዋል፡፡“ በሌላ በኩል የሚያስገርመው ነገር ግን ዩናይትድ ስቴትስ ያልተጠበቀ ጥሩ ነገርን አደረገች፡፡ በተባበሩት መንግስታት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር የሆኑት ሳማንታ ፓወር እንዲህ በማለት የመንግስታቸውን አቋም ግልጽ አድርገዋል፣ “በ2008 ድህረ ምርጫ በኬንያ ለተፈጸመው የኃይል እርምጃ ሰለባ ለሆኑት ቤተሰቦች የፍርድ ሂደት ለመጀመር ማስረጃዎችን የመገምገም እና የማሰባሰብ ስራ ከአምስት ዓመታት በላይ ጊዜ ፈጅቷል፡፡ በዚያ ብጥብጥ በተወሰደው የኃይል እርምጃ ሰለባ ለሆኑ ወገኖች ፍትህ መስጠት ለሀገሪቱ ዘለቄታዊ ሰላም እና ደህንነት ወሳኝ ጉዳይ እንደሆነ እናምናለን፡፡ በሰዎች ላይ በሚፈጸሙ ሰብአዊነትን በሚጥሱ ወንጀሎች ላይ ተጠያቂነት እንዲኖር እና ወንጀል ፈጻሚዎችም ለህግ እንደቀርቡ የማድረግ ግዴታ አለብን፡፡“ በማለት ግልጽ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ባለፈው ሳምንት የኡሁሩ ኬንያታን የፍትህ ሂደት አስመልክቶ “አንድ ምስክር የምስክርነት ቃል ላለመስጠት እራሱን ካገለለ እና ሌላኛውም የሀሰት ማስረጃ አቅርቧል“ ከተባለ በኋላ እ.ኤ.አ ፌብሯሪ 5/2014 ለመታየት ተይዞ የነበረው ቀጠሮ የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አቃቢ ሕግ በኬንያታ ላይ የቀረቡትን ማስረጃዎች እንደገና ለመገምገም እንዲቻል ሌላ ሶስት ተጨማሪ ወራት እንደጠየቁ እና የፍትህ ሂደቱ እንደተላለፈ ግልጽ ተደርጓል፡፡
የውሸት ማስረጃ እና የሀሰት ምስክሮች ሲባል ለምን?
ባለፈው ወር በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አቃቤ ሕግ ቢሮ ውስጥ “የውሸት ማስረጃ“ እና “የሀሰት ምስክሮች“ የሚሉ ስሜትን ዕረፍት የሚነሱ ንግግሮች ተደምጠዋል፡፡ እ.ኤ.አ ዴሴምበር 19/2013 የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ዋና አቃቤ ሕግ ወይዘሮ ፋቱዋ ባንሱዳ እንዲህ በማለት ተናግረዋል፣ “ዴሴምበር 4/2013 በዚህ ጉዳይ ላይ ሁለተኛ ቁልፍ ምስክር ተብሎ የቀረበው በወሳኙ ድርጊት ላይ ለፍትህ ሂደቱ የውሸት መረጃ መስጠቱን አምኗል፡፡ ይህ ምስክር በአሁኑ ጊዜ ከፍትህ ሂደቱ የምስክርነት ዝርዝር ውስጥ እራሱን አግልሏል… አሁን በእጆቼ ያሉትን ማስረጃዎች በጥንቃቄ መርምሬ እና እንዲሁም የእነዚህ እራሳቸውን ከምስክርነት ያገለሉት ሁለት ምስክሮች በፍትህ ሂደቱ ላይ የሚያስከትለውን አሉታዊ እንደምታ ከግንዛቤ በማስገባት የሚስተር ኬንያታን የክስ ሁኔታ ስገመግመው ከፍተኛ የሆነ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መረጃ ሆኖ ስላላገኘሁት በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚካሄድን የፍትህ ሂደት አያሟላም ወደሚል መደምደሚያ ላይ ደርሻለሁ… በዚህም መሰረት እስካሁን ድረስ ያደረግኋቸውን ጥረቶች ምሉዕ ለማድረግ ተጨማሪ መረጃዎችን እና እነዚህ መረጃዎች በፍትህ ስርዓት ሂደቱ ዘንድ መኖር ያለበትን የቢሮዬን ዝቅተኛውን የመረጃ ድንበር በትክክል ማሟላት አለማሟላታቸውን ለማረጋገጥ ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገኛል…“ በማለት ሀሳባቸውን አጠቃለዋል፡፡
እ.ኤ.አ ማርች 2013 የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አቃቤ ሕግ በቀድሞው የኬንያ ሲቪል ሰርቪስ ኃላፊ በነበሩት እና አብረው ይከላከሉ በነበሩት ፍራንሲስ ሙታውራ ላይ ተመስርቶ የነበረውን የወንጀል ክስ ጉዳይ ውድቅ ባደረጉበት ጊዜ ወይዘሮ ቤንሱዳ የእኒሀ ሰው ጉዳይ ውድቅ መደረጉ እኔ በያዝኩት በአዲሱ የኬንያ ዕጩ ተመራጭ ፕሬዚዳንት የፍትህ ሂደት ጉዳይ ላይ ምንም ዓይነት ተጽዕኖ አይኖረውም በማለት ተናግረው ነበር፡፡ “የሁኔታዎች አመክንዮ እንደሚያሳየን አንድ የክስ ጉዳይ ውድቅ ተደርጎ ተከሳሹ ሲሰናበት ይህ ነጻ የተለቀቀው ሰው በሌላው በክስ ሂደት ላይ ላለው የወንጀል ተጠርጣሪ ተመሳሳይ ክስ በቀጥታ በሚታይ መልኩ ቀጥተኛ ያልሆነ ተባባሪ ሆኖ ተጽዕኖ ላያሳይ ይችላል፡፡ ብዙ ሰዎች በአንድ ዓይነት የክስ ጉዳይ ላይ ክስ ተመስርቶባቸው ሁሉም በአንድ ዓይነት ያለምንም ተለዋዋጭነት በእያንዳንዱ ተከሳሽ ላይ አንድ ዓይነት ብይን ሊሰጥ ይገባል ለማለት አይቻልም… ኬንያታ ግን ለእያንዳንዱ በወንጀል ተጠያቂ ግለሰብ የገንዘብ እና የሎጅስቲክስ ቀጥተኛ ድጋፍ ሲያደርጉ እንደነበር በተጠርጣሪነት ክስ ተመስርቶባቸው እያሉ ሙታውራ በበኩሉ ከሙንጊኪ/Mungiki (የወንጀል ባለሙያዎች ድርጅት) ድጋፍ ያገኝ ነበር የሚል የተጠርጣሪነት ክስ ተመስርቶበት እያለ እንዲሁም ይህ ተጠርጣሪ ለፒኤንዩ ጥምረት/PNU Coalition አባላት ድጋፍ ለማድረግ ሲባል በናኩሩ እና ናይቫሻ/Nakuru and Naivasha አባላት ላይ ወንጀል እንዲፈጽም ተቋማዊ ድጋፍ ሲደረግለት እንደነበር የተጠርጣሪነት ክሱ ያመላክታል፡፡“
ኬንያታን እና ሩቶን ከዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት መዳፍ ለማውጣት በመቅረብ ላይ ያሉ የክርክር ጭብጦች
ኬንያታን እና ሩቶን ከዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት መዳፍ ለመልቀቅ ወይም ደግሞ ተጠርጣሪዎቹ የስልጣን ዘመናቸውን እስኪያጠናቅቁ “በማዘግየት“፣ አንድ ዓመት “የማዘግየት” ዕድል በመስጠት፣ የክስ ሂደቱን ላልተወሰነ ጊዜ በማስተላለፍ፣ የዓለም አቀፉን የወንጀለኞች የክስ ሂደት በማቋረጥ እና ጉዳዩ በኬንያ ፍርድ ቤቶች መታየት እንዲችል በማድረግ በርካታ የህግ፣ የፖለቲካ እና የፖሊሲ የመከራከሪያ ጭብጦች አስከዛሬ ቀርበዋል፡፡ ኬንያታን ከዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ነጻ ለማውጣት የሚያቀርቡ ዋና ዋናዎቹ የመከራከሪያ ጭብጦች እንደሚከተለው ናቸው፣ 1ኛ) የኬንያታ እና የሩቶ የክስ ጉዳይ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት መታየቱ የኬንያን ሉዓላዊነት ይዳፈራል፣ 2ኛ) እ.ኤ.አ ማርች 2013 በኬንያ በተደረገው አገር አቀፋዊ ምርጫ ኬንያታ እና ሩቶ ያለመከሰስ መብት ተጎናጽፈዋል ምክንያቱም መመረጣቸው “ነጻ“ መሆናቸው ተረጋግጧል፣ 3ኛ) በኬንያታ እና በሩቶ ላይ የቀረበው ክስ ማስረጃ “ውሸት እና በፈጠራ ላይ የተመሰረተ ነው“፣ 4ኛ) የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አቃቤ ሕግ ፍትሀዊ አይደሉም፣ እናም አላግባብ ስልጣናቸውን በመጠቀም የክስ ሂደቱን በማጣመም የህግ የበላይነት እንዳይሰፍን በኬንያታ እና በሩቶ ላይ ተግባራዊ ያደርጉታል፣ 5ኛ) ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት እና ዋና አቃቤ ሕጉ ያልተገደበ እና ለማንም ተጠሪነት የሌለው ስልጣን ተሰጥቷቸዋል፣ 6ኛ) ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በኬንያታ እና ሩቶ ላይ ብይን በመስጠት ለተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት የተሰጠውን ስልጣን በመጋፋት የስልጣን መብቱን ይነጥቃል፣ 7ኛ) የተባበሩት መንግስታት ቻርተርን እና በኬንያታ እና ሩቶ ላይ የተፈጸመውን የፍትህ ሂደት ህገወጥ እና ድርጅቱ ከተሰጠው የስልጣን ኃላፊነት (ከተሰጠው የህግ ስልጣን በላይ) ስለሆነ የሮማ ስምምነትን ይጥሳል፣ 8ኛ) ኬንያ ፈቃደኝነቱ እና ችሎታውም ስላላት ወንጀለኞችን በሮማ ስምምነት መሰረት በእራሱ አገር ለመዳኘት ዝግጁ ናት፣ 9ኛ) ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በኬንያታ እና በሩቶ ላይ የመሰረተው ክስ መሰረተቢስ ነው፡፡
አቧራው መርጋት ከጀመረ በኋላ የአፍሪካ አምባገነን መሪዎች በእርግጠኝነት የሚፈልጉት የእያንዳንዳቸው ጉዳይ ከተለመደው ፍትሀዊ የህግ ስርዓት ውጭ በተለዬ መልኩ ለእነሱ በሚስማሙ ህጎች መዳኘት እንደሚኖርባቸው ነው፡፡ አምባገነኖቹ የአፍሪካ መሪዎች እራሳቸው በእጃቸው መርጠው በሚያስቀምጧቸው አቃቢያነ ሕጎች እና ዳኞች ብቻ የፍትህ ሂደት ጉዳያቸው እንዲታይ እና የህግ ውሳኔም በእነርሱው በኩል ብቻ እንዲያገኙ የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት እንዲፈቅድላቸው ይፈልጋሉ፡፡
የወደፊቱ አደገኛ ሁኔታ፡ “በሰው ልጅ ላይ ወንጀል ለሚፈጽሙ የአፍሪካ መሪዎች የሚስማማ ኢፍትሀዊ ህግ”
በአሁኑ ጊዜ የሚታዩት የፍትህ ሂደቱን የማዘግየት፣ ቀጠሮዎችን የማስተላለፍ እና የማቆየት ሁኔታ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት እና በኬንያታ፣ እንዲሁም በአፍሪካ ህብረት እና በተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት መካከል ኬንያታን ከዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት መዳፍ ለማስለቀቅ የሚደረግ የፖለቲካ “ስምምነት” ምልክቶች እና አዝማሚያዎች ያሉ አይመስልምን? ማስረጃ ተብለው ቀደም ሲል ተይዘው የነበሩት ምስክሮች የሚያምኑበትን እንደገና ሲክዱ እና የሀሰት ምስክርነት ሲሰጡ ሲታይ የፍርድ ሂደቱን ፊኛ መሆን (የሀብረተሰቡን ሀሳብ ለመገምገም እና ወደፊት ሊነሳ የሚችል ተቃውሞ ካለ ለማጤን) እና የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ አመለካከት በማየት ማስረጃ አልተገኘም በሚል ሰበብ በኬንያታ ላይ የቀረበውን ክስ ውድቅ በማድረግ ኬንያታን ከዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ለመልቀቅ የሚደረግ የፖለቲካ ትወና አንድ አካል አይመስልምን? ጉዳዩ ሲታይ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት፣ በአፍሪካ ህበረት፣ በኬንያታ እና በተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት መካከል የህግ የቴክኒክ ጉድለት ስበብ ያለበት በማስመሰል ኬንያታን ለመልቀቅ እየተደረገ ያለ ተውኔትነት መሰል ነገር (ሻጥር አላልኩም) ያለበት አይመስልምን? ስህተት ባለበት ሁኔታ አትገንዘቡኝ፡፡ ወደፊት የሚመጣውን አዳጋች ሁኔታ አስቀድሜ በማየት ነው ጥያቄዎችን እየጠየቅሁ ያለሁት፡፡ ይኸው ነው!
እ.ኤ.አ በ2014 ኡሁሩ ሙጋይ ኬንያታ “በመረጃ እጥረት ምክንያት“ ከዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት መዳፍ በመውጣት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲህ ሊሉ ይችሉ ይሆን? “ነግሪያችሁ አልነበረም፣ ይኸውላችሁ እኔ ነጻ ሰው ነኝ፣ የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በእኔ ላይ የመሰረታቸው ክሶች የዘር አደና እና በህግ ጥላ ስር ሰው ገዳይ ሆኖ ከመቅረብ የዘለለ አልነበረም፡፡ የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የአፍሪካን ጥቁር መሪዎች አያሳደደ ነው… አንዱ በመጨረሻ የማነሳው ነገር ደግሞ የሱዳኑ ኦማር አልባሽር በሀሰት የተከሰሰ መሆኑን ነው፡፡ በእርሱ ላይ በሀሰት የመሰረታችሁትን ክስም አንሱለት…”
ከፈለጋችሁ ተጠራጣሪ ብላችሁ ልትፈርጁኝ ትችላላችሁ፡፡ ይኸ የሙያ ጉዳይ ነው፡፡ የመከላከል የህግ ባለሙያዎች በጣም ሲበዛ ተጠራጣሪዎች እና ገና በሩቁ ማነፍነፍ የሚችሉ የማሽተት የስሜት ህዋሳቶች ያሏቸው ናቸው፣ (በጣም ትንሽ የሻጥር ጠረን ቢሆንሞ በሚገባ ማሽተት እችላለሁ)፡፡ ስለህግ ባለሙያዎች በምናገርበት ጊዜ የመከላከል የህግ ባለሙያዎች በተደጋጋሚ የሚጠቀሙባቸው ዘዴዎች “ጉዳዩን መካድ፣ ማዘግየት እና መከላከል“ የሚሉት ናቸው፡፡ ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት “ማቆየት፣ ማዘግየት እና ክሱን መሰረዝ“ የሚሉ አዲስ ዘዴዎችን በመፍጠር ስሜት አልባ በመሆን አወዛጋቢ ከሆነው የፍርድ ሂደት ኬንያታን ነጻ ለማውጣት የሚሞክር ከሆነ በኬንያታ የፍትህ ሂደት ላይ መገረም የምጀምር ይሆናል፡፡ ሰለዚህ በጣም አስባለሁ፡፡ ጮክ ብዬም እናገራለሁ፡፡ እኔ የቆዬ፣ የዘገዬ እና የተሰረዘን ፍትህ እንደተካደና አንደተነፈገ ፍትህ እቆጥረዋለሁ፡፡
በኬንያታ ላያ ያለ ማስረጃ
አንድ ጉርሻ ብቻውን አንደማያጠግብ ሁሉ አንድ ወይም ሁለት ምስክሮች ብቻም በወጀንጀል ጉዳዩ ላይ የሚፈጥሩት ጫና አይኖርም:: በሮማ ስምምነት አንቀጽ 25 (3) (a) መሰረት በሰው ዘር ላይ የተፈጸመ ወንጀል በማለት ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በኬንያታ ላይ 5 ዋና ዋና ክሶችን በመዘርዘር ክስ መስርቷል፡፡ እነርሱም፣ ግድያ፣ (አንቀጽ 7 (1) (a)፣ ማጋዝ ወይም ከህግ አግባብ ውጭ ከቦታ ማፈናቀል፣ (አንቀጽ 7 (1) (d)፣ አስገድዶ መድፈር፣ (አንቀጽ 7 (1) (g)፣ ማሰቃየት፣ (አንቀጽ 7 (1) (h)፣ እና ሌሎች ኢሰብአዊ ድርጊቶች፣ (አንቀጽ፣ 7 (1) (k) ናቸው፡፡ ክሱ ለህሊና አስደንጋጭ እና በሚሰቀጥጥ ሁኔታ ጥልቅነት ባለው መልኩ በ155 ገጾች በመቶዎች የሚቆጠሩ ምስክሮችን መሰረት አድርጎ የተዘጋጀ ሰነድ ነው፡፡ የቅድመ ፍትህ ምርመራ ቻምበሩ በኬንያታ ላይ ስለሚመሰረተው ክስ እንዲህ ሲል ማረጋገጫ በመስጠት ጽፏል፣ “አቃቤ ሕጉ በሰው ልጅ ወንጀል መፈጸም ላይ ከተያያዙ ነገሮች ጋር በማየት ክስ ለመመስረት የሚያስችል መሆኑን ያሟላል በማለት መረጃ ሰጥተዋል፡፡ “በኬንያታ ላይ የቀረቡት ብዙዎቹ ማስረጃዎች ነጻ እና በእውነታ ላይ የተመሰረቱ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የቅድመ ምርመራ ቻምበር “እ.ኤ.አ ጃኗሪ 3/2008 በናይሮቢ ክለብ… ሚስተር ኬንያታ ከሙንጊኪ አባላት ጋር (አንዳንድ ጊዜም የኬንያ የማፊያ የወንጀል ድረጅት እየተባሉ ከሚጠሩት ጋር) ተገናኝተዋል፡፡ እናም ክስ የተመሰረተበትን ወንጀል እንዲፈጽሙ ቀጥታ ተዕዛዝ ሰጥተዋል በማለት ወስኗል፡፡“ ኬንያታ እና ሌሎች በጋራ በመሆን “የቀድሞው ፕሬዚዳንት የኪባኪ ፓርቲ የሆነው የብሄራዊ አንድነት ፓርቲ/National Unity Party(PNU) አባላት በማንኛውም መንገድ ቢሆን ስልጣናቸውን እንደያዙ እንዲቆዩ፣ እንዲሁም በሰዎች ላይ ወንጀሎች ቢፈጸሙም ፖሊስ በቦታው ደርሶ መቆጣጠር እንዳይችል እና እንዳይገኝ በማድረግ የድርጅታዊ ፖሊሲ በማውጣት ለመተግበር ስምምነት አድርገው የትወና ድርጊታቸውን ፈጽመዋል፡፡“ በማለት ሁኔታውን ሊያሳዩ የሚችሉ በቂ ማስረጃዎች እንደሆኑ ግልጽ አድርገዋል፡፡ ኬንያታ እና ግብረ አበሮቻቸው… “በብርቱካናማው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/Orange Democratic Movement (ODM) ደጋፊዎች አባላት ላይ የጋራ ዕቅድ በማውጣት መጠነ ሰፊ እና ስልታዊ ጥቃቶች፣ 1ኛ) የብቀላ ጥቃቶችን እንደፈጸሙባቸው፣ 2ኛ) የብቀላ ጥቃቱን ለመከላከል ወይም ደግሞ ለማስቆም እንዳይቻል ሆን ተብሎ ታስቦበት የፖሊስ እርምጃ እንዲታቀብ በማድረግ የሚሉት በቂ ማስረጃዎች መሆናቸውን ያመላክታሉ፡፡
ኬንያታ “በፒኤንዩ/PNU እና በሙንጊኪ/Mungiki ወንጀለኛ ድርጅት መካከል የአስታራቂነት ሚና የሚጫወቱ መስለው በመቅረብ እ.ኤ.አ ከኖቬምበር 2007 ጀምሮ ተከታታይ ስበስባዎችን በማካሄድ” እንዲሁም ደግሞ “የፒኤንዩ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ፖለቲከኞች፣ የንግዱ ማህበረሰብ እና የሙንጊኪ የአመራር አባላት በዴሴምበር 2007 በሚደረገው ሀገር አቀፍ ምርጫ የሙንጊኪ አባላት ለመንግስት ድጋፍ እንዲያደርጉ“ ያደረጉትን በበቂ ሁኔታ ሊያሳይ የሚችል መረጃ መሆኑን ያመላክታል፡፡ ከድህረ ምርጫው ማግስት ኬንያታ እና ሌሎች በአንድነት ሆነው “በስምጥ ሸለቆ አካባቢ በብርቱካናማው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ አባላት ላይ የበቀል እርምጃ እንዲወስዱ የሙንጋኪ አባላትን ተከታታይ ስብሰባ እየጠሩ ሲያስተባብሩ እንደነበር፣ እንዲሁም ፕሬዚዳንቱ ቃለመሃላ ከፈጸሙ በኋላ የብሄራዊ አንድነት ፓርቲ/PNU ይዞታዎች እንዲጠናከሩ“ በማለት የሙንጊኪ/Mungiki አባላት ጥቃት እንዲፈጽሙ ሲያስተባብሩ እንደነበር በቂ መረጃዎች እንዳሉ ያመላክታሉ፡፡ በኬንያታ እና በሌሎች “የኬንያ ፖሊሶች የተቀሰቀሰውን ብጥብጥ እንዳይከላከሉ እና እንዳያቆሙት እንዲሁም ጥቃቱን በሚፈጽሙ በጥባጮች ላይ እርምጃ እንዳይወስዱ በማሰብ የጋራ ዕቅድ ነድፈው የራሳቸውን ድርሻ ሲያበረክቱ እንደነበር“ የሚያመላክቱ ከበቂ በላይ የሆኑ መረጃዎች አሉ፡፡
ሁለቱ የሀሰት ማስረጃ ምስክሮች የአቃቤ ሕጉን ጉዳይ ፍጹም የሚያሳንሱ በመምሰል የዓለም አቃፉን የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አቋም በመረጃዎቹ ላይ የእምነት መሸርሸር በማሳየት ውኃ የሚቋጥሩ መስለው ያለመታየት አዝማሚያን አንጸባርቋል፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ሁለቱ ምስክሮች ለምን የሀሰት ምስክርነት እንደሰጡ፣ እንዲሁም የክስ ሂደቱ ከመጀመሩ በፊት የአቃቤ ሕጉ ቢሮ አስተማማኝ እና ጠንካራ መረጃዎችን ለምን እንዳላሰባሰበ ግልጽ አይደለም፡፡ ሆኖም ግን በኬንያታ ላይ ምስክርነት ለመስጠት የሚቀርቡት ማስፈራሪያ የደረሰባቸው እና እንዳይመሰክሩም ጉቦ የተሰጣቸው ናቸው፡፡ እ.ኤ.አ ፌብሯሪ 13/2013 አቃቤ ሕግ ወይዘሮ ቤንሱዳ ኬንያታ በተያዘው ጉዳያቸው ላይ ምስክርነት እንዳይሰጥባቸው በማሰብ ጉቦ በመስጠት ምስክሩ አስረጅ ሆኖ እንዳይቀርብ እና ከምስክርነት እንዲያፈገፍግ አድርገዋል በማለት ተናግረዋል፡፡ ወይዘሮ ቤንሱዳ እንዲህ በማለትም ሀሳባዋቸውን አጠናክረዋል፣ “እ.ኤ.አ ሜይ 2012 አራተኛ ምስክር ሆኖ የቀረበው ሰው በተደረገለት ቃለመጠይቅ መሰረት የኬንያታ ኡሁሩ ተወካይ የሆኑ ሰዎች በኬንያታ ላይ ምስክርነት እንዳይሰጥ የገንዘብ ጉቦ እንደሰጡት እና እንደተቀበለ ግልጽ አድርጓል… ይህ ምስክር የጉቦ አሰጣጡን ዕቅድ ሊያስረዱ የሚችሉ የኢሜል አድራሻውን እና የባንክ ምዝገባ መረጃዎችን አቅርቧል፡፡ በእንደዚህ ያለ ተደራራቢ መግለጫዎች አቃቤ ህጉ እንደዚህ ያለውን ለምስክርነት መጥራት ጥሩ አይደለም የሚል ሀሳብ አላቸው፡፡ የኬንያታ የመከላከያ ቡድን በበኩሉ “በእራሳቸው ፈቃድ ያመኑትን ወንጀለኞች ምሰከሮች” የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አሳልፎ ለኬንያ እንዲሰጥ እና የኬንያ ፍርድ ቤት ሙሉ ፍርዳቸውን እንዲሰጣቸው ጠይቋል፡፡ አቃቤ ህግ ቤንሱዳ ፍርድ ቤቱ ለምስክሮቹ የህግ ከለላ እንዲሰጥ እንዲሁም የድምጽ እና የምስል ማዘበራረቅም እንዳይኖር፣ መረጃ በመፈለጉ ረገድ የውሸት ስም የመስጠት እና ካሜራም ያለመጠቀም እንዲቻል ጠይቀዋል፡፡“ በኬንያ መንግስት ከፍተኛ የሆነ የበቀል እርምጅ ያጋጠማቸው ምስክሮች በብርሀን ፍጥነት ተግልብጠው ህይወታቸውን ለማዳን ሲሉ የሀሰት ምስክርነት መስጠታቸውን ቢናገሩ ማንንም ሊያስገርም የሚችል ጉዳይ ሊሆን ይችላልን?
ሁሉም “የሀሰት ምስክሮች“ “የውሸት ምስክሮች“ ቅንነት የጎደላቸው ንግግሮች ናቸው የሚል እምነት አለኝ፡፡ በኬንያታ ላይ ለቀረበው ክስ በጥቂት ምስክሮች ብቻ ላይ ተመስርቶ የሚከናወን ጉዳይ አይደለም፡፡ ሆነኖም ግን በመቶዎች የሚቆጠሩ ማስረጃ የሚሰጡ ምስክሮችን ማግኘት ይቻላል፡፡ ኬንያታን ወደ ፍትህ ሂደቱ ለማቅረብ እና ፍርድ ቤቱም የኬንያታን ጥፋት ከምንም ጥርጣሬ በላይ ሊያስረዱ የሚችሉ “ከበቂ በላይ መረጃዎች” እንዳሉ መታወቅ አለበት፡፡ የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አቃቤ ሕግ በያዟቸው በአንድ ወይም ደግሞ በሁለት ምስክሮች ላይ ብቻ መሰረት በማድረግ እና የያዙትን የህግ ጉዳይ እውነትነት እና የምስክሮች ቃላቸውን የማጠፍ ክህደት በመመልከት የፍትህ ሂደቱን የተሟላ ሊያደርገው አይችልም፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ተራራ የሚያህል የተከመረ መረጃ አለ፡፡
የዓለም አቀፉን የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ምስክርነት የመከላከል ፕሮግራም ጊዜው አሁን አይደለምን?
ምስክሮችን ማስፈራራት፣ የገንዘብ ጉቦ መክፈል፣ ቃለመኃላ ፈጽመው በትክክል መስክረው የነበሩትን ቃላቸውን እንዲያጥፉ በማድረግ የተለየ ታሪክ እንዲያቀርቡ በተለይም በከፍተኛ ወንጀል በሚጠረጠሩ ሰዎች ላይ ምንም አዲስ ነገር አይደለም፡፡ ከፍትህ ሂደቱ በፊትም ሆነ በኋላ ቃልን በማጠፍ የሀሰት ምስክርነት መስጠት የተለመደ ጉዳይ ነው፡፡ ከአቃቤ ሕጎች ጋር እንዳይተባበሩ እና የምስክርነት ቃላቸውን እንዳይሰጡ የማስፈራራት ድርጊት የተፈጸመባቸው ሰዎች ወይም ደግሞ ሆን ተብሎ የፍርድ ሂደቱ በሚሰማበት ዕለት በቦታው ተገኝተው የምስክርነት ቃላቸውን እንዳይሰጡ ማድረግ የተለመደ ተግባር ነው፡፡ ለምሳሌ በማፊያ አለቆች እና በሌሎች ወንጀለኞች የፍትህ ሂደት ወቅት ምስክሮች (አስረጅዎች) ቃላቸውን አጥፈው ወይም ክደው መመስከር ወይም ደግሞ ከምስክርነት እራሳቸውን ያገላሉ ምክንያቱም በእራሳቸው እና በቤተሰቦቻቸው አባላት ላይ በሚደረግባቸው የማስፈራራት ድርጊት የተነሳ ነው፡፡ ዳኞች የጥፋተኝነት ውሳኔ እንዳይሰጡ በወንጀለኛ አለቆች ጉቦ ይሰጣቸዋል፡፡ በፍትሀዊ የዳኝነት ጊዜም አቃቢ ሕጎች ምስክሮች ሚስጥራዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ላይ ለመመስከር “ተባባሪ” እንዳይሆኑ ያነሱ ክሶች እና ቀላል ውሳኔዎች እንዲሰጡ እና ሌሎች ጥቅሞች በመስጠት የምስክርነት ቃል እንዳይሰጡ ማስፈራሪያ ይደረግባቸዋል፡፡ የኬንያታ ምስክሮች ቃላቸውን የማጠፍ ወይም የመካድ ሁኔታ መታየቱ ያልተቋጩ እና እንቆቅልሽ የሆኑ ጥያቄዎችን እንድናነሳ ያስገድዱናል፡፡ ምስክሮቹ የምስክርነት ቃላቸውን የሰጡት በትክክል ክደው ሳይሆን ለሕይዎታቸው ፈርተው ነው፡፡ ለምስክርነት በፍትህ ሂደቱ ላይ ቢገኙ እና ምስክርነት ቢሰጡ የሚደርስባቸውን በቀል በመፍራት ነው፡፡ እነዚህ ምስክሮች ክደው የምስክርነት ቃላቸውን መስጠታቸው እንደ መልካም ነገር መታየት የለበትም ነገር ግን መታየት ያለበት የፍርድ ሂደቱ እና የተከሳሾቹ የማስፈራራት ውጤት ተደርጎ ሊወሰድ ይገባል፡፡
በኬንያታ የፍትህ ሂደት ላይ ክደው ቃል በሰጡ ምስክሮች ችግር ጉዳይ ላይ በቂ የሆነ መፍትሄ አለ የሚል እምነት አለኝ፡፡ ይኸውም ምስክሮች ያዩትን የሰሙትን ሳይፈሩ የእምነት ቃላቸውን ያለምንም ፍርሀት መስጠት እንዲችሉ “ዓለም አቀፋዊ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የምስክርነት ከለላ ፕሮግራም” መፍጠር እንዳለበት ማወቅ አለበት፡፡ በዩናይት ስቴትስ የፌዴራል የምስክሮች ከለላ ፕሮግራም ከፍርድ ሂደቱ በፊት፣ በፍርድ ሂደቱ ወቅት እና ከፍርድ ሂደቱ በኋላ ለምስክሮቹ በቂ ከለላ ይሰጣል፡፡ በዚህ ፕሮግራም ምስክሮች እና ቤተሰቦቻቸው አዲስ ማንነት እና መረጃዎች እንዲሁም የቦታ ለውጥ ሁሉ እንዲያደርጉ ይመቻችላቸዋል፡፡ ይህ ፕሮግራም እ.ኤ.አ በ1971 በስራ ላይ መዋል ከጀመረ ወዲህ ወደ 10,000 የሚሆኑ ምስክሮች እና ቤተሰቦቻቸው በምስክርነት ከለላ ፕሮግረሙ አገልግሎት አግኝተዋል፡፡ በሚያስገርም ሁኔታ “95 በመቶው የሚሆኑት የምስክርነት ከለላ ተጠቃሚዎች ወንጀለኞች ናቸው፡፡”
ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በሰው ልጅ ላይ ሰብአዊነት የጎደለው ወንጀል በሚፈጽሙ ተጠርጣሪዎች ላይ፣ የዘር ማጥፋት ወንጀል በሚፈጽሙት ላይ እና ሌሎችንም አስቀያሚ ወንጀሎችን በሚፈጽሙ ተጠርጣሪዎች ላይ ምስክርነት ለመስጠት በሚመጡ ምስክሮች ደህንነት ሲባል “የእራሱን የምስክርነት ከለላ ፕሮግራም” መጀመር ይኖርበታል የሚል እምነት አለኝ፡፡ በብዙዎቹ የሙንጊኪ (“የኬንያ ማፊያ” ወሮበላ ወንጀለኞች) ሀሳብ ሳይሆን ትክክለኛ ማስፈራሪያ እና የህግ የቅጣት ሰለባ እንደሚሆኑ ከኬንያ መንግስት ብቻ የተሰጠ ዛቻ ብቻ አይደለም፡፡ ነገር ግን ከመንግስት ጋር መልካም ግንኙነትን ለመፍጠር ሲባል ከተበሳጨው ከእራሳቸው ድርጅት ጋር ጭምርም እንጅ፡፡ የሙንጊኪ ምስክሮች እውነተኛውን የምስክርነት ቃላቸውን እንዲሰጡ ሁኔታዎች ሊመቻቹላቸው ይገባል፡፡ ከኬንያታ ጋር ባለው የፍትህ ሂደት ጉዳይ ላይ እውነታውን ብቻ እንዲመሰክሩ እና የምስክርነት ከለላ ፕሮግራም ከኬንያ ውጭ እንዲሰጣቸው ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ ከዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የምስክሮች ከለላ ፕሮግራም ውጭ ተባባሪ የሆኑ ምስክሮችን በማግኘት በእውነታ ላይ የተመሰረተ የምስክርነት መረጃ ለማግኘት አይቻልም፡፡ ምናልባት በጣም ጥቂት ምስከሮች እውነታው እንዲታወቅ እስከ የህይወት መስዋዕትነት ድረስ ለመክፈል ዝግጁ ሊኖሩ ይችላላ፣ አጅግ በጣም ብዙ ምስከሮች ግን ለህይዎታቸው ፈርተው ድርሽ አይሉም፡፡ ከምስክርነት ከለላ ፕሮግራም ወጭ በአሁኑ ጊዜ በአፍሪካ በስልጣን ላይ ያሉ በሰው ልጅ ላይ ወንጀል የሚፈጽሙ አምባገነኖች በአገራቸው ውስጥ ማንም ቢሆን በእነርሱ ላይ ደፍሮ የምስክርነት ቃል እንደማይሰጥ አስቀድመው በማወቅ የልብ ልብ ተሰምቷቸው በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የአሰራር ሁኔታ ላይ እየቀለዱ ይኖራሉ የሚል እምነት አለኝ፡፡ የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ከኬንያታ ጉዳይ ጋር በተያያዘ መልኩ ጥሩ ትምህርት መቅሰም ይኖርበታል፡፡
የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ኬንያታን ከመዳፉ ስር እንዲወጣ ሊያደርግ ይችላልን?
የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በፖለቲካ ወይም በሌሎች ምክንያቶች ኬንያታን ይለቅቃል የሚል መረጃ ወይም አሳማኝ የሆነ መሰረታዊ ዓላማ የሌለኝ መሆኑን ፍጹም በሆነ መልኩ ግልጽ ማድረግ እፈልጋለሁ፡፡ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ተቋሙ ላይ ጥንካሬ ያለው እምነት አንዳለኝ እራሴን በፈቃደኝነት “የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ምስክር” አድርጌ እቆጥራለሁ፡፡ ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ኬንያታን ከመዳፉ በማውጣት ሊለቅ ይችላል በሚለው የእኔ የእራሴ ንቁ ዕይታ እና የህግ ምናባዊ ጥርጣሬ ላይ ተመስርቶ የሚሰጥን ማንኛውንም ትችት ለመቀበል ዝግጁ ነኝ፡፡ ሁኔታው “የሀሳብ ቤተሙከራ” ነው፣ ግምታዊ የሆኑ እውነትነት ያላቸውን ሃሳቦች እና ምናባዊ ሁኔታዎችን በማየት ሊከሰቱ የሚችሉ ነግሮችን መተንበይ እና በትክክል ሊከሰቱ የሚችሉ የችግሮቹን ውጤቶች ማሰብ መቻል የተሻለ ነገር ነው፡፡ ይኸ ትችት የማይታሰበውን የማሰብ፣ የማይታለመውን የማለም የእራሴ “የሀሳብ ቤተሙከራ” ነው፡፡ ይሄዉም “የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በማስረጃ እጥረት ምክንያት የኡሁሩ ሙጋይ ኬንያታን የክስ ጉዳይ ዉደቅ አርጎታል” የሚለዉን አስከፊ ዜና መስማት ስለምፈራም ነው፡፡
በተባበሩት መንግስታት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ከሆኑት ከሳማንታ ፓወር ምልከታዎች ጋር ሙሉ በሙሉ እስማማለሁ፡፡ “በ2008 ድህረ ምርጫ በኬንያ ለተፈጸመው የኃይል እርምጃ ሰለባ ለሆኑት ቤተሰቦች የፍርድ ሂደት ለመጀመር ማስረጃዎችን የመገምገም እና የማሰባሰብ ስራ ከአምስት ዓመታት በላይ ጊዜ ፈጅቷል፡፡ በዚያ ብጥብጥ በተወሰደው የኃይል እርምጃ ሰለባ ለሆኑ ወገኖች ፍትህ መስጠት ለሀገሪቱ ዘለቄታዊ ሰላም እና ደህንነት ወሳኝ ጉዳይ እንደሆነ እናምናለን፡፡ በሰዎች ላይ በሚፈጸሙ ሰብአዊነትን በሚጥሱ ወንጀሎች ላይ ተጠያቂነት እንዲኖር እና ወንጀል ፈጻሚዎችም ለህግ እንደቀርቡ የማድረግ ግዴታ አለብን፡፡“ በሌላ አባባል “ማቆየት፣ ማዘግየት እና ክሱን መሰረዝ፣ ፍትህ እንደተካደ ይቆጠራል!
ውድቀት ለአምባገነኖች፣ ፍትህ ለብዙሀኑ!
ጥር 20 ቀን 2006 ዓ.ም

ኳሱ በማን እጅ ነው ? (ከይድነቃቸው ከበደ)

$
0
0
(ይድነቃቸው)

(ይድነቃቸው)

ከአምስት ወር በፊት የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የአዲስ ዓመት የሥራ ዘመን መጀመር አስመልክቶ በጋራ ባአካሂዱት ጉባዔ አዲሱ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመም ፕሬዚዳንታዊ የመክፈቻ ንግግር ማድረገቸው የሚታወቅ ነው፡፡ የፕሬዚዳንቱ የንግግር ይዘት መንግሥት በ2006 ዓ.ም. ትኩረት ሊያደርግባቸው የሚገቡ ዋና ዋና ተግባሮች ላይ ብቻ ያተኮረ ነበር፡፡ይሁን እንጂ የፕሬዚዳንቱ ንግግር በሕግ መንግስቱ በተሰጣቸው ሥልጣንና ተግብር መሠረት የተደረገ ንግግር ስለመሆኑ የሚያመላክት አንዳችም ነገር አላየሁበትም፤በመሆኑም የፕሬዚዳንቱ ንግግር በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢነገር የተሸለ ይሆን ነበር ግን በሁለቱም ቢነገር ውጤቱ ዉሃ ቢወቅጡት እንቦጭ ነው፡፡
በዚህም መሠረት ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ባቀረቡት የመክፈቻ ንግግር ላይ ሊካተቱ የሚገባቸው ነገር ግን ያልተካተቱ፣ እንዲሁም መካተት አልነበረባቸውም ያሏቸውን በመለየት አቶ ግርማ ሰይፉ ጥያቄና አስታየት አቀርበዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በምክር ቤቱ በመገኘት በአቶ ግርማ ነጥቦች ዙሪያ ምልሽ መስጠታቸው የሚታወቅ ነው፡፡ይሁን እንጂ ምላሻቸው ሙሉ በሙሉ በሚያስብል ደረጃ ስኬታማ አልነበረም ለዚህም ዋንኛው ምክንያት የመንግስት የአስተዳደር ብሉሹነት ነው ፡፡
የፕሬዚዳንቱ የመክፈቻ ንግግር ከተደረገ እና የመንግስት አቋም በጠቅላይ ሚኒስተር አቶ ኃይለማርያም ከተገለፀ ስድት ወር ሊሞላው የተወሰኑ ቀናት ይቀረዋል፡፡በሚቀሩት የተወሰነ ቀናት ውስጥ የግማሽ ዓመት ወይም የስድስት ወር የመንግስት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ምን ያኸል ውጤታማ ነበር የሚለውን በመንግስት እይታ ወደፊት የሚገለፅ ቢሆንም ወደ ጉሮሮ ጠብ ያላለ እድገት እና የዜጎች ሰብአዊና ዲሞክራሳዊ መብቶች የታፈነበት ወራት መሆኑ ግልፅ ነው፡፡
ይህ በእንዲ እንዳለ ለዘህ ፁሁፍ መነሻ የሆነው ዋና አሳብ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከአምስት ወር በፊት በፓርላማ ያደረጉት ንግግር ነው፡፡ ንግግራቸውም ስለተቃውሞ ሠልፍ እና ስለህዝባዊ አብዮት የሰጡት ማብራሪያ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ጠ/ሚ ኃይለማርያም ስለ አብዮት ያላቸው ፍራቻ ከምን እንደመነጨ መገመት ቀላል ቢሆንም ስለ ህዝባዊ ስብሰባና የተቃውሞ ሠልፍ የያዙት ሃሳብ ግን የመንግስታቸው እየታ ጤናማ አለመሆኑ በሚገባ የሚሳይ ነው፡፡
በወቅቱ አቶ ኃይለማርያም እንዲህ ነው ያሉት ‹‹ ሌት ተቀን የጐዳና ላይ ነውጥ አምጥቼ ገዥውን ፓርቲ እቀይራለሁ ብሎ አቅዶ መንቀሳቀስ ወንጀል ነው፤ የጐዳና ላይ ነውጥ በዚች አገር ላይ እንሞክራለን የምትሉትን አቋሙ፡፡ ይህንን ለሕዝቡም ጭምር ነው የምናገርው በቂ መረጃ ስላለን ነው በተግባር ላይ ስላልዋለ ምንም ማድረግ ስለማንችል እንጠብቃለን፡፡ በተግባር ላይ የማዋል ሙከራ ካለ ትክክል ስላልሆነ እርምጃ እንወስዳለን ‹ኳሱ› በእናተ እጅ ነው ››፡፡ በማላት በሰማያዊና በአንድነት ፓርቲ እየተደረጉ ያሉ ሕዝባዊ ስብሰባና የተቃውሞ ሠልፎች መንግስታቸው በምን መልኩ እንቅስቃሴውን እየተከታተለ እንደሆነ እና ሊወሰድ የታሰበውን እርምጃ የሚያመላክት ነው፡፡
የአቶ ኃይለማርያም ማስጠንቀቂ በቀጥታ የተላለፈው አንደኛ ለህዝብ ሲሆን ሌላው ደግሞ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች ነው፡፡ በእርግጥ ይህ ንግግር ከተደረገ ወራቶች የተቆጠሩ ቢሆንም መንግስት ከማስጠንቀቅ ባለፈ የተፈራውን ህዝባዊ አብዮት እና የተቃውሞ እንቅስቃሴ ሊጋታ የሚያስችል አንድም የመንግስት መልካም አስተዳደር በአገራችን ላይ አልታየም፡፡ ለዚህም እንደማሳያ ብዙ ምክንያቶች መጥቀስ ቢቻልም በእያንዳንዱ ሰው ንሮ ላይ የሚታይ ችግር መልሶ መድግም ለቀባሪው እንደማርዳት ነው፡፡ በተጨማሪ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ሰላማዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ሊያቀዘቅዝ ሳይሆን የበለጠ ሊያነሳሳ የሚያስችል የመንግስት የአስተዳደር ሽባነት ጎልቶ የታየበት ወራት ነው፡፡ በመሆኑም ለእዝብ እና ለተቃዋሚ ፓርቲዎች የተላለፈው የመንግስት ማስጠንቀቂያ ተግባራዊነቱ እስከምን ድረስ ነው ? ::
በመንግስት የተፈራው እና ማስጠንቀቂያ የተሰጠበት አንደኛው ነገር ሕዝባዊ አብዮት ነው፡፡ ሕዝባዊ አብዮት በይተኛውም የዓለማችን ክፍል በህግ ተፈቅዶ ወይም ቅድመ እውቅና ተሰጥቶት የሚከናወን ተግባር አይደለም ፡፡ዜጎች በመንግስታቸው የሚታየው የአስተዳደር ብሎሹነት መሸከም ሲከብዳቸው እና ሸክማቸውን ያበዛባቸውን ደካማ መንግስት ለመለወጥ ወይም ለማውረድ ሲፈለጉ ምርጫና መሰል ነገሮችን ሣይጠብቁ በአደባባይ በመውጣታ ስልጣን የህዝብ መሆኑን በማሳየት ብልሹ የመንግስት ባለስልጣናትን እና ስልጣንን አሽቀንጥሮ የሚጣልበት አይነተኛ መንገድ ነው፡፡በመሆኑም ኢትዮጵያን ጨምሮ እንደዚህ አይነቱ አብዮት በተለያዩ አገራት ተግባራዊ ተደርጓል ፤ይሁን እንጂ እስከዛሬ ድረስ የተደረጉ አብዮቶች ሙሉ በሙል ውጤታማ ናቸው ብሎ መደምደም ባይቻለም አብዛኞቹ አብዮቶች ስኬታማ ነበሩ፡፡ስኬታማ ያልሆኑ አብዮቶች ደግሞ ውጤታቸው የተበላሻ ያደረገው ዜጎች ያነሷቸው መሠረታዊ ጥያቄዎች ሣይሆን አብዮቱን ከፊት ሆኖው ሲመሩት የነበሩ መሪዎች አብዮቱን የመምራት እና የማስተባበር እንዲሁም የተገኘውን ውጤት የማስጠበቅ ድከመት ነው፡፡
በመሆኑም በጨቋኝ ሥርዓት መንግስት አስተዳደር ውስጥ ስለአብዮት ተግባራዊነት ይቅርና ስለ አብዮት ማሰብ እዳው ብዙ ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ እነኚ አምባገነን መሪዎች ስልጣናቸው ሕዝብን ለማገልገል ሣይሆን እራሳቸው የሚገለገሉበት ዓይነተኛ መንግድ ነው፤ በመሆኑም ይህን ስልጣናቸው ማጣት ለእነሱ ከባድ ኪሳራ ነው፡፡ ስለዚህ የፈጀውን ይፍጅ በማለት ለተነሱ እና ለሚነሱ አብዮቶች ለማኮላሸት ዘብ ነው የሚቆሙት፡፡ ይሁን እንጂ ህዝባዊ አብዮት በይትኛውም መለኪያ ስዕተትም አጥያትም አይደለም ይህዝብ ጥያቄ እንዴት ስዕተት ሊሆን ይችላል ? በመሆኑም ሕዝባዊ አብዮት በአገራችን ላለመከሰቱ ኳሱ በማን እጅ ነው ? ፡፡ እንዲሁም መንግስት እየታየበት ያለው የአስተዳደር ብሉሽነት ለማረም እና ህዝብን ለማገልገል ካልተቻለው አለመቻሉንም ተገንዝቦ ለሚችሉት እድሉን ካልሰጠ እና ይባስ ብሎ ወደለየለት የአምባገነን ስርአት የሚያመራ ከሆነ ሕዝባዊ አብዮት ምን ይጠብቃል !፡፡
ሌላው እና ዋንኛው ጉዳይ በአገራችን ኢትዮጵያ እታየ ያለው የመንግስት የአስተዳደር ብሉሽነት ለማጋለጥ እና አማራጭ መፍትሔ ለመስጠትና ለማስተዳደር በሰላማዊ መንገድ በአገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች መኖራቸው የሚታወቅ ነው፡፡ ይሁን እንጂ እነኚኽ ፓርቲዎች በተለይ ሰማያዊና አንድነት የሚያደርጓቸው ማናቸውም ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ በመንግስት በኩል የሚሰጠው ምላሽ ድብደባና እስራት ነው፡፡
እርግጥ ነው በሠላማዊ ትግል ሂደት ውስጥ ውጣ ውረዶ የበዛ ነው፡፡ በዓለማችን ላይ የተካሄዱት ሠላማዊ ትግሎች ውጤት ያስመዘገብት መተኪያ የሌለውን የሰው ልጅ ሕይወትን እስከመንጠቅ በመድረሰ ነው፡፡ሠላማዊ ትግል ማለት ታጋዩ የሚታገልለትን ውጤት ሳይመለከት በትግሉ ሂደት የሚሰዋበት ፅኑ እምነት ነው እስከመባል ይደርሳል፡፡
ይህን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል በመረዳት ሰማያዊ እና አንድነት ፓርቲ የሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች በህዝቡ ውስጥ ጥሩ መነቃቃትን የፈጠረ ነው፡፡በተለይ ሰማያዊ ፓርቲ በወጣት አመራሮቹ እና አባላቶቹ በመታገዝ የሚያደርጋቸው ሰላማዊ ተቃውሞ ድርጊቶች እጅግ በጣም የሚበረታታ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ የዜጎች ሰብአዊና ዲሞክራሳዊ መብቶች ባለተከበረበት፣መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ እየገባ አንድን ሃይማኖት ከሌላው ሃይማኖት እያጋጨ፣ዜጎች የሚናገሩትን ቋንቋ መሠረት በማድረግ ብቻ ከመሬታቸው የሚፈናቀሉበት፣የኑሩ ውድነት እና እጅግ በጣም ቅጥ ያጣው ሙሰኝነት በተስፋፋበት፣የአገር ሀብት ፍታሃዊ ክፍፍል ባልታየበት እነዚህ እና መሰል ችግሮች ሙሉ በሙሉ ባይሆን እንኳን በከፊል መፍትሔ ባልተገኘባቸው ጉዳዮች ተከታታይ እና ጠንካራ የተቃውሞ እንቅስቃሴ አለመደረጉ የፓርቲዎቹ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ጥያቄን የሚያጭር ነው፡፡
እርግጥ ነው ተቃዋሚ ፓርቲዎች በመንግስት እየደረሰባቸው ያለው ተፅኑ ቀላል የሚባል አይደለም በተለይ ሰማያዊ ፓርቲ እየደረሰበት ያለው ጫና ስራዎችን የሚሰራበት ቢሮ እስከማስከልከል የደረሰ ነው፡፡ ነገር ግን ከላይ የተገለፁት እና መስል የመንግስት አስተዳደር ችግሮች እልባት እንዲያገኙ ይህ ባይቻል እንኳን መጠነኛ ማሻሻያ እንዲታይ ምርጫን 2007 እየተጠበቀ ከሆነ ሠላማዊ ወይም አመፅ አልባ ትግል ህዝብን ከምን ሊታደግ ነው ? :: በመሆኑም የመንግስት የአስተዳደር ሃላፊነት ለማግኘት ምርጫን መጠበቅ ግድ ቢልም በመንግስት ላይ እየታየ ያለው የአስተዳደር ችግሮች እንዲታረም እና ማሻሻይ እንዲደረግባቸው ምርጫን መጠበቅ ተገቢ ሆኖ አይታይም፡፡ ስለዚህም በሠላማዊ መንግድ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች የተለያዩ አመፅ አልባ ትግሎችን በመንደፍ እና በማስተባበር ውጤት ሊያመጣ የሚያስችል እንቅስቃሴዎቻቸውን በይበልጥ አጠናክረው መቀጠል አለባቸው፡፡ እንዲህ አይነቱ እንቅስቃሴ ለገዢው ስርዓት የአስተዳደር ብሉሹነት ዕድል እና ትምህርት ካልሰጠው አሁንስ ኳሱ በማን እጅ ነው ? ::

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live