Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ስሜቱ ይቁምና እስቲ አማራጮችን በእርጋታ እንመልከት –ግርማ ካሳ

$
0
0

«አበው ሲተርቱ ላም ባልዋለበት ኩመት ለቀማ ይላሉ። ሰላም ጠላቱ ከሆነ የአገዛዝ ቡድን ጋራ በሰላማዊ ትግል ገጠሞ ሰለማዊ ድል አስመዘግባለሁ ብሎ ማሰብ ከሰላማዊ ጭንቅላት የሚፈልቅ ሰላማዊ አስተሳሰብ ነዉ ብዬ አላምንም። …ትግል ሱስ አይደለም። እንደ አቦል ቡና ሱስ አይደለም። አሁን የምናየዉ የሰላማዊ ታጋዮች፣ የትግል ሱስ ያለባቸው አይነት ነዉ እንጂ ከዉጤት አኳያ የፖለቲካ ምህዳሩ በጠበበት አገር ዉስጥ ምንም አይነት ለዉጥ ሊያመጡ የሚችሉበት ሁኔታ አይታየኝም። እስካሁን የአገዛዙን እድሜ በማራዘም ረገድ አስተዋጾ እያደረጉ ነዉ ። ምናልባትም የታሪክ ተወቃሽነት ሊያደርጋቸዉም ይችላል። ከልምዳቸውም ተነስተዉ ዉጤት ይመጣክል ብለው ይጠብቃሉ ?»
freedome
አንድ አድምጫ ለወጣት የአንድነት ፓርቲ አመራር አባላት፣ ም/ፕሬዘዳንቱ አቶ በላይ በፈቃዱና የሕዝብ ግንኙነት ክፍላ ሃላፊዉ አቶ ሃብታሙ አያሌዉ፣ በኢሳት ያቀረቡት አስተያየት በዛሽ ጥያቄ ነበር።

አሁን በስልጣን ላይ ያለዉ መንግስት፣ የሰብአዊ መብትን የሚረገጥ፣ ፍርድን የሚያዛባ ፍጹም አምባገነን እንደሆነ ሁላችንም የምናወቀው ነዉ። ታዲያ ምንድን ነዉ መፍትሄዉ ?

አራት አማራጮ ነው ያሉት።

1) በግብጽ እና በቱኒዚያ እንደታየው፣ ሕዝብን አደራጅቱ ፣ ሰላማዊ በሆነ መንገድ የእምቢተኝነት ዘመቻ በማካሄድ መንግስት ለሕዝብ ጥያቄ እንዲገዛ ማስገደድ፣
2) በደቡብ አፍሪካ የነጮች ፓርቲ የነበረዉ፣ ብሄራዊው ፓርቲ፣ ፒተር ቦታን አስወገዶ በምትካቸዉ ፍሬደሪክ ደክለርክን በማስመረጥ፣ ከጨቋኙ ፓርቲ ዉስጥ ለዉጦች እንዲመጣ እንደተደረገዉ፣ በኢሕአዴግ ዉስጥ ያሉ ፣ ጥሩ ልብ ያላቸዉ መልካም ሰዎች አይለው እንዲወጡና የሚፈለገዉ ለዉጥ በኢሕአዴግ በራሱ እንዲመጣ ማድረግ፣
3) ሕወሃት/ኢሕአዴግ ደርግን እንዳደረገው መሳሪያ አንስቶ በኃይል የመንግስት ለዉጥ ማምጣት፣
4) አርፎ፣ ባርነትን ተቀበሎ፣ አንገት ደፍቶ፣ እንደ እንስሳ መኖር፣

አብዛኞቹ ኢትዮጵያዊያን አራተኛዉን አማራጭ የመረጡ መሰለኝ። በተለያዩ ምክንያቶች። አንደኛው ፍርሃት ነዉ። ገዢው ፓርቲ ከስራቸው እንዳያባርራቸው፣ ከቤታቸው እንዳያፈናቅላቸው፣ ማዳበሪያ እንዳይከለከላቸው፣ እንዳያስራቸው ……ሁለተኛው ምክንያት ተስፋ መቆረጥ ነዉ። በኢሕአፓ ጊዜ፣ በቅርቡ ደግሞ በቅንጅት የነበረዉን በማስታወስ «አይ ዝም ብለን ነዉ የምንደክመው ለዉጥ እንደው አይመጣም። ተቃዋሚዎቹ ደካማ ናቸው» የሚል አስተሳሰብን በመያዝ፣ አገዛዙን አጉዝፎ የራስን ኃይል ግን አሳንሶ ማየት። ሶስተኛው ምክንያት፣ ዳያስፖራዉ ወይንም ደግሞ «እንዋጋለን» የሚሉ ሽምቅ ተዋጊዎች፣ «ነጻ ያወጡኛል» ብሎ በመጠበቅ ቁጭ ማለትን መምረጥ ነዉ።

እንግዲህ እዚህ ላይ ኢትዮጵያዉያን ማሰብ ያለብን ይመስለኛል። ይሄ አማራጭ ስብእናችንን እና ክብራችንን የሚያወርድ አማራጭ ነዉ። በአጭሩ «ባርነት» ነዉ። ከዚህ አማራጭ ፈቀቅ ብለን መሄድ ያለብን ይመስለኛል። ዘጠና ሚሊዮኖች ሆነን ጥቂቶች በአንገታችን ላይ ቀንበር አስረው፣ ተናገሩ የሚሉንን ብቻ እየተናገርን፣ ቁጭ በሉ ሲሉን እየተቀመጥን እንደ እንሥሳ መኖር የለብንም።

ሌላው አማራጭ ሶስተኛው አማራጭ ነዉ። ነፍጥ የሚያስነሳ ሰላማዊ ያልሆነዉ አማራጭ። ይመስለኛል ከላይ የጠቀሷቸው ኢትዮጵያዊ የሰላማዊ ትግል አማራጮችን አጣጥለው ሲናገሩ፣ ይሄንኑ የጠመንጃ ትግል አስበው ሳይሆን እንዳልቀረ ነዉ። ዜጎች ግፍን ለመቃወም መሸፈት እና ነፍጥ ማንሳት ሙሉ መብታቸው እንደሆነ አያከራክርም። የትጥቅ ትግል አንስተናል የሚሉትን «ለምን አነሳችሁ» የማለት የሞራል ብቃትም የለኝም። ነገር ግን በትጥቅ ትግል አኳያ አንዳንድ መሰረታዊ ሃቆችን ለማንሳት እወዳለሁ፡

የትጥቅ ትግል ሲደረግ ወታደሮች ያሰፈልጋሉ። ወታደሮች ደግሞ ዉሃ አይደለም የሚተኩስት። መሳሪያ፣ ጥይት ያስፈልጋል። ወደ ጦርነት ሲኬድ መቁሰል መጎዳት አለ። በመሆኑም መድሃኒቶች፣ የሕክምና ባለሞያዎች መኖር አለባቸዉ። በትጥቅ ትግሉ የተሰማሩ መልበስ፣ መብላት አላባቸው። ወታደሮችን ከአንድ ቦታ ወደ አንድ ቦታ ለማሰማራት ከባባድ የጭነት መኪናዎች፣ ናፋጣና ነዳጅ የግድ ነዉ። እዚህ ላይ አላበቃም። ወታደሮች የሚሰለጥኑበት ቦታ ያስፈልጋል።

ያኔ ሕወሃት እና ሻእቢያ፣ ድፍን ሱዳን ከጎናቸው ነበር። አሜሪካ፣ አረቦች የሚፈልጉትን ያስታጥቋቸዉ ነበር። አሁን ሽምቅ ተዋጊዎችን ሊረዱ የሚችሉት፣ በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ እንደ ጠላት የሚታዩ ሻእቢያ እና ግብጽ ብቻ ናቸው። የግብጽ እና የሻእቢያ አጋር መሆን ደግሞ በቀጥታ ከሕዝብ ጋር የሚያላትም ነዉ። በመሆኑም አስተማማኝ ፣ ደጀን የሚሆን ፣ የሚረዳ አለ ማለት አይቻልም። ይህ የዉጭ ረዳት ኃይል በሌለበት ሁኔታ ፣ የትጥቅ ትግልን እንደ አማራጭ መዉሰድ አያስኬድም።

እርግጥ ነዉ፣ ከላይ እንደጠቀስኩት፣ ኮንቬሽናል በሆነ መንገድ የትጥቅ ትግል ማድረጉ ባያስኬድም፣ ግፍ ሲበዛበት፣ ሕዝቡ ግን በየቀበሌዉና በየወረዳው ጠመንጃ ሊያነሳ ይችላል። ጠመንጃም ከሌለው ቆመጥ። ይህ አይነቱ አመጽ ደግሞ አንዴ ከተለኮሰ፣ ማቆም የማይችልበት ሁኔታም ሊፈጠር ይችላል። ሶሪያን ተመለከቱ። ለስንት አመት ሊባኖስ የሆነቸዉን አስታወሱ። ሶማሊያን አስቡ። ይሄ ከእያንዳንዳችን ቁጥጥር ዉጭ የሆነ፣ እንደ አማራጭ ሊወሰድ የማይችል፣ ገዢዉ ፓርቲ ከወዲሁ ሊስይቆመው የሚችል ጉዳይ ነዉ። ይሄ እንዳይሆን ጸሎቴና ሞኞቴ ነዉ።

እንግዲህ የተሻሉት የምላቸው አማራጭች፣ አማራጭ አንድ እና ሁለት ናቸው። ሕዝቡ ወደ ጠመንጃ ሳይዞር፣ ሰላማዊ በሆነ መንገድ እምቢተኝነቱን እንዲገልጽ ማደራጀቱ ፣ ለዉጥ ከገዢዉ ፓርቲ ዉስጥም እንዲታይ መገፋፈቱ ብቸኞቹ ጠቃሚ አማራጮች ናቸው። እነዚህ አማራጮች እንደ ተጠበቀዉ ዉጤት ላያመጡ ይችላሉ። ጊዜ ለኢፈጁ ይችላሉ። ሶስተኛዉ የጦርነት አማራጭ፣ አማራጭ እንደማይሆን እየታወቀ፣ የሰላም አማራጮቹ አይሰሩም ብሎ መቀመጡ፣ አራተኛዉን የባርነት አማራጭ መምረጥ ነዉ። ከላይ የጠቀስኳቸው ኢትዮጵያዊ ወንድሜም በአገር ቤት የሚደረገዉን ሰላማዊ ትግል በሚያጣጥሉበት ጊዜ፣ አላወቁትም እንጂ፣ «ከቻላችሁ እንደ እኔ ተሰደዱ ፤ አለበለዚያ አርፋችሁ፣ ባርያ ሆናችሁ ተገዙ» እያሉን ነዉ።

አንደኛዉና ሁለተኛዉ አማራጮች ፣ በተለይም በአንደኛው (ሕዝብን አደራጅቶ አገዛዙን ማስጨነቅ) እንዴት ሊሰራ እንደሚችል የሚያመላክቱ አንዳንድ ሃሳቦችን በሚቀጥለው ጊዜ ይዤ እቀርባለሁ።

(በነገራችን ላይ አይሰራም ፣ አያዋጣም የምለው የትጥቅ ትግል አማራጭ ያዋጣል የሚሉ ካሉ፣ ለመማር ዝግጁ ነኝ፡፤ ታዲያ ወሬና ፉከራ ሳይሆን አሳማኝ ነጥቦች ያስቀምጡልኝ። ስለጠመንጃ ማዉራት ቀላል ነዉ። ባሩዱን ማሽተት ግን ሌላ ነገር ነዉ)


የባንዳ ደም

$
0
0

……………..
እዚያ ቀዬ
እዚያ መንደር
እነዚያ እልፍኝ
እዚያ ሰፈር
ያሉ ሰወች
ምን ነክቷቸው ሰው መሆንን የሚንቁ
ከራሳቸው የሚጣሉ
ከራሳቸው የሚርቁ
ምን ተውሳክ ነው የምን ደዌ
የምን ዛር ነው የምን ጋኔን
መለያቸው ሀገር መካድ
ጥረታቸው ታሪክ መናድ
ስብከታቸው ማንነትን ማደባየት
ስኬታቸው ሀገር ወዳድ ማሰቃየት
እዚያ ቤት ምንድነው ያለው
መስተፃልእ ከህዝብ ልብ
ለባርነት የሚያሰልፍ
ፍቅር ክብር የሚያጸይፍ
ለውርደት ሞት የሚያሰይፍ
ድንበር እንደጉድ የሚያስንቅ
ቅጥፈት እንደ እናት የሚያስወድድ
ምን ቅጠል ነው ምን ስራስር
ምኑን ዕፅ ነው የሚውጡ
በጠላ ድፍድፍ የሚጋቱ
ለሀገርና ወገን ሳይሆን
ለ’አለቃ የሚሞቱ
ለሀቅ እና ለእምነት ሳይሆን
ለክህደት የሚሟገቱ
የምን ደም ነው በስራቸው
በአካላቸው የሚዛወር
ምን መርዝ ነው በአንጎላቸው
በአእምሮአቸው የሚንፏለል
ከህብረት ይልቅ መነጠል
ከማዳን ይልቅ ማቃጠል
ከእምነት ይልቅ ክህደትን
ወገን ከድቶ ባንዳነትን
የሚያስወድድ
የሚያስመልክ
እጸ ቅጥፈት
እጸ ክፋት
እጸ ሴራ
እጸ ጥፋት
ምን መድሀኒት ነው የሚውጡ?
ምን ሀሺሽ ነው የሚያጤሱ?
ከአናት ወጥቶ የሚያቀውስ
መልካም ሲያይ የሚያንዘፈዝፍ
የህዝብ ውለታ
የሀገር መዝገብ የሚያጎድፍ
ለአድር ባይነት አደቁኖ
በሃሰት ለመፍረድ የሚያቀስስ
መሰረት ለመናድ ተክህኖ
ትውልድ ለማበስበስ የሚያጰጵስ
ከእባብ ምላስ ወተት አይፈልቅ
የባንዳ ደም በውሀ አይለቅ
ተኩላም እርግብ አትወልድ
የሌሊት ወፍ መዓልት አትለምድ
አመላቸው ካልሞቱ በቀር
በአርባም በሀምሳ አመት የማይለቅ
በእርጅና በሽበታቸው
በህይወት ሳሉ የማይደርቅ
አገር አፍርስ በሽታቸው
ተዋህዶ ከመቅኔያቸው
እነሱን አጥምቆ ላይተው
ለሃገር ተረፈ መርዛቸው፡፡

19/04/006
ተጻፈ በእስክንድር ልሳነወርቅ

Pen

አብርሃ ደስታ የአረና አባላትን እንዲደበድቡ በሕወሓት የተቀጠሩት አብዛኞቹ ኤርትራውያን እንደሆኑ መረጃ ደረሰኝ አለ

$
0
0

አብርሃ ደስታ

አብርሃ ደስታ

(ዘ-ሐበሻ) በሕወሓት በደረሰበት ጫና፣ እንግልት፣ እስር እና ድብደባ እንዲሁም የአካባቢው ፖሊስ ለስብሰባው ጥበቃ አልሰጥም በማለቱ ለመሰረዝ የበቃው የአዲግራቱ የአረና ስብሰባን ተከትሎ በቅስቀሳ ላይ የነበሩትን አባላት በሕወሓት ዘንድ በተከፈላቸው ኤርትራውያን እንደተደበደቡ መረጃ ደርሶኛል ሲል አብርሃ ደስታ ከመቀሌ ገለጸ።

“ስሙ እንዲታወቅ ያልፈለገ የዓዲግራት ከተማ ፖሊስ እንደነገረኝ ህወሓቶች የዓረና አመራር አባላትን ለመደብደብ ከተከፈላቸው ወጣቶች አብዛኞቹ ኤርትራውያን ነበሩ።” ያለው አብረሃ ደስታ “ኤርትራውያን ስደተኞቹ በከተማው አስተዳደር የተቀጠሩ ናቸው።” ብሏል።

“ከዓዲግራት ሰዎች ኤርትራውያን ስደተኞች ለገዢዎቹ የተሻሉ ታማኞች ናቸው።” ያለው አብረሃ ህወሓት በተቃዋሚዎች ላይ የሐይል እርምጃ ለመውሰድ የኤርትራ ዜጎችን የመጠቀም ዕቅድ እንዳለው ገልጿል።

“አንድ የከተማው ፖሊስ አዛዥ “ስርዓት አስከብርልን!” የሚል አቤቱታ ስናቀርብለት “ወደኛ ምን ልታደርጉ መጣቹ?” የሚል መልስ ሰጥቶናል።” የሚለው አብርሃ “አሁን የደረሰኝ መረጃ እንደሚያሳየው ግን የፖሊስ አዛዡ ኤርትራዊ ነው።” ካለ በኋላ “ቆይ ግን ይቺ “ትግራይ” የምትባል ክልል የኤርትራውያን ነች ወይ የኢትዮጵያውያን ተጋሩ? እስከመቼ ነው በኤርትራውያን የምንገዛ? እኛ ራሳችን በራሳችን ማስተዳደር አንችልም ማለት ነው? እስቲ በየወረዳው(እስከ ፌደራል መንግስት) ያሉ አስተዳዳሪዎች ከየት እንደመጡ ጠይቋቸው? ከኢትዮጵያ አይደሉም። ከኤርትራ የመጡ ናቸው። በኤርትራውያን ከምንገዛ በራሳችን (ኢትዮጵያውያን) ሰዎች ብንተዳደር ይሻላል።” ሲል ይጠይቃል።

በጎንደር ሰማያዊ ፓርቲ ለድንበር መከበር፤ የቅማንት ማህበረሰብ የማንነት መብቱ እንዲከበር በተመሳሳይ ቀን ሰልፍ ሊወጡ ነው

$
0
0

“በጥይት ትመታላችሁ፣ መትረየስ ጠምደን እንፈጃችኋለን እያሉ እያስፈራሩን ነው”

- የቅማንት ማህበረሰብ የማንነት መብት ጥያቄ ሰልፍ አስተባባሪዎች

በዘሪሁን ሙሉጌታ (የሰንደቅ ጋዜጣ ሪፖርተር)

በመጪው እሁድ ጥር 25 ቀን 2006 ዓ.ም በጎንደር ከተማ ሰማያዊ ፓርቲ በኢትዮ-ሱዳን ድንበር መካከለል ጉዳይ ለሕዝብ ግልፅ አለመሆኑን በመቃወም ሰልፍ የጠራ ሲሆን፤ በተመሳሳይ ቀን በጎንደር ዙሪያ የሚኖሩ የቅማንት ብሔረሰብ አባላት ማንነታችን አልተከበረም በሚል ሕገ-መንግስታዊ ጥያቄአቸውን ለማቅረብ የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄ አቅርበዋል።

የጎንደር ከተማ (ፎቶ ፋይል)

የጎንደር ከተማ (ፎቶ ፋይል)

ለጎንደር ከተማ አስተዳደር ሁለቱም ወገኖች የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄ ቢያቀርቡም፤ ለሁለቱም ወገኖች ለሰላማዊ ሰልፉ መካሄድ ማረጋገጫ አለማግኘታቸውን እየተናገሩ ነው። ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፉን ለማስተባበር ወደስፍራው የላከውን የፓርቲውን አመራር ጨምሮ ሌሎች የፓርቲው አስተባባሪዎች ታስረው መፈታታቸውን ገልጿል። ሆኖም ሰልፉን ለማካሄድና የማሳወቂያ ደብዳቤ ለከተማው አስተዳደር ቢያቀርቡም አስተዳደሩ ደብዳቤውን ባለመቀበሉ ጠረጴዛ ላይ ትተው መውጣታቸውን የፓርቲው ሕዝብ ግንኙነት አስታውቋል። እስካሁን የከተማው አስተዳደር ምንም አይነት ምላሽ ያልሰጠ በመሆኑ ሰላማዊ ሰልፉ እንደተፈቀደ በመቁጠር ሰልፉን ለማካሄድ በዛሬው ዕለት 12 የአመራር አባላት ያሉት ቡድን ወደ ጎንደር እንደሚሄድ አስታውቋል።

በሌላ በኩል በበርካታ ጊዜያት የቅማንት ብሔረሰብ የቋንቋ፣ የባህልና የማንነት መብቱ አልተጠበቀም የሚሉ ወገኖች በተመሳሳይ ቀን (ጥር 25 ቀን 2006 ዓ.ም) ጥያቄአቸውን በሰላማዊ ሰልፍ ለመጠየቅ ሰልፍ መጥራታቸውን የቅማንት ብሔረሰብ የማንነት የራስ አስተዳደር ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴ ሊቀመንበር አቶ አበራ አለማየሁ ለሰንደቅ ጋዜጣ አስታውቀዋል።

የኮሚቴው ሊቀመንበር የጎንደር ከተማ በጉዳዩ ላይ ለማነጋገር ጥረት ማድረጋቸውን ገልፀዋል። አስተዳደሩም የእነሱ ጥያቄ ሕገ-መንግስታዊ እንጂ የፖለቲካ አይደለም። ነገር ግን እናንተ ጥያቄ ካቀረባችሁ በኋላ ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ ጠይቋል በማለት አጀንዳችሁ ተመሳሳይ ነው የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸው አጀንዳችን የተለያየ መሆኑን ብንገልጽም፤ “በጥይት ትመታላችሁ፣ መትረየስ ጠምደን እንፈጃችኋለን” እያሉ እያስፈራሩን ነው ብለዋል።

ከዚህ ቀደም ጥር 4 ቀን 2006 ዓ.ም በጅልጋ ወረዳ አይከል ከተማ ላይ ከ70 ሺህ በላይ ሕዝብ የተገኘበት ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸውን ያስታወሱት አቶ አበራ፤ በዚያን ጊዜም “በመትረየስ እንፈጃችኋለን” ቢሉንም ሕዝቡ ነቅሎ መውጣቱን ተናግረዋል። አሁንም በጎንደር ከተማ ከሰማያዊ ፓርቲ ቀድመው ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ቢዘጋጁም በየቀበሌው ሕዝቡን በስብሰባ በመጥራት ወደ ሰልፉ እንዳይወጡ ቅስቀሳ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። በመሆኑም ያለውን ጫና ተቀቁመው ሰልፉን ለማካሄድ ወደኋላ እንደማይመለሱ ተናግረዋል።
እንደ አቶ አበራ ገለፃ፤ እነሱ የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄ ተቀባይነት ያላገኘው በተመሳሳይ ቀን ሰማያዊ ፓርቲ በሌላ አጀንዳ ሰልፍ በመጥራቱ እኛም ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር አብረን እንደምንሰራ ተደርጎ ታይቶብናል ብለዋል። ይሁን እንጂ የእኛ ጥያቄ ሕገ-መንግስታዊ እንጂ የፖለቲካ ወይም የድንበር አይደለም ብለዋል።

የቅማንት ብሔረሰብ በአማራ ክልል በጎንደር የተለያዩ ወረዳዎች የሚኖር ሕዝብ መሆኑን የጠቀሱት አቶ አበራ፤ የሕዝብ ብዛቱም አንድ ሚሊዮን እንደሚሆን፣ የቋንቋው ተናጋሪዎችም ከ20 ሺህ በላይ እንደሚሆኑ ገልፀው፤ ሕዝቡ እራሱን በቻለ ዞን ለመተዳደር ተደጋጋሚ ጥያቄዎችን ሲያቀርብ ቆይቷል ብለዋል። በያዝነው ዓመት መስከረም ወር ጥያቄውን ለፌዴሬሽን ም/ቤት አቅርቦ ውሳኔ አለማግኘቱንም ተናግረዋል። የጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ጌትነት አማረን በስልክ አግኝተን በዚሁ ጉዳይ ላይ የአስተዳደራቸውን አቋም እንዲያብራሩልን ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት አልተሳካም።

“በዝዋይ የታሰሩት ባለቤቴ እዛው እስር ቤት መሞታቸውን ሕዝብ ይወቅልኝ”–ወ/ሮ ፈሪሃ አብድርሃማን

$
0
0

በዳዊት ሰለሞን

rest and peace
(ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ እንደዘገበው) አቶ አህመድ ነጃሽ ሐሰን በ2002 ዓ.ም በተደረገ አገር አቀፍ ምርጫ በድሬዳዋ ክልል የኦሮሞ ኮንግረስ/ መድረክን በመወከል ተወዳድረው ነበር፡፡የፖለቲካ ተሳትፏቸውን እንዲያቋርጡ በተለያዩ መንገዶች ሲነገራቸው ቢቆዩም በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞ ማሰማትና መደራጀት ህገ መንግስታዊ መብት መሆኑን በመጥቀስ ሲከራከሩ መቆየታቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ ፈሪሃ አብድርሃማን የሱፍ ለፍኖተ ነጻነት አስታውሰዋል፡፡

በ2003 የመንግስት የጸጥታ ሰዎች አቶ አህመድን በኦነግ አባልነት ተጠርጥረሃል በማለት ያስሯቸዋል፡፡የ57 አመቱ አህመድ ከታሰሩ በኋላ ለአራት ወራት ያህል በህይወት ይኖሩ ወይም ይሙቱ ለቤተሰብ ሳይታወቅ ከቆዩ በኋላ ፍርድ ቤት ቀርበው በኦነግ አባልነት ተከሰው ይፈረድባቸዋል፡፡ፍርዳቸውን ተከትሎም ለምርመራ ከቆዩበት ማዕከላዊ ወደ ዝዋይ ወህኒ ቤት እንዲዘዋወሩ ይደረጋሉ፡፡

ከአቶ አህመድ ነጃሽ ያገኟትን አንድ ልጅ ለብቻቸው የማሰደግ ዱብ ዕዳ የወደቀባቸው ወይዘሮ ፈሪሃ ገቢያቸው በመቋረጡ ስራ ፍለጋ ወደ አረብ አገር ያቀናሉ፡፡በአረብ አገር ያለሙትን ማግኘት ባለመቻላቸው ወደ አገር ቤት ይመለሳሉ፡፡ካልተሳካው ስራ ፍለጋ መልስ ወይዘሮዋ ባለቤታቸውን ለመጠየቅ ወደ ዝዋይ ሲያመሩ የማረሚያ ቤቱ ሃላፊዎች ባለቤታቸው ወደ ቃሊቲ መዘዋወራቸውን ይነግሯቸዋል፡፡

ከዝዋይ በቀጥታ ወደ ቃሊቲ በማምራትም ይጠይቃሉ፣ቃሊቲዎች እንዲህ አይነት እስረኛ ወደ እነርሱ አለመምጣቱን በመጥቀስ ያሰናብቷቸዋል፡፡ከብዙ የዝዋይና ቃሊቲ ምልልስ በኋላ አቶ አህመድ በጠና ታመው ምኒሊክ ሆስፒታል እንደገቡ ይነገራቸዋል፡፡ምኒልክ ሆስፒታል ለጥየቃ ባመሩበት ወቅት መጥፎውን ዜና ይሰማሉ፡፡አቶ አህመዲን ይህችን አለም ከተሰናበቱ ረዘም ያሉ ወራቶች ተቆጥረዋል የሚል፡፡

አስከሬን የለ፣ የት እንደተቀበሩና የሞታቸው መንስኤ ምን እንደነበር የሚያስረዳ የለ፣ ሁሉ ነገር ድፍንፍን ያለባቸው ወይዘሮዋ ለፍኖተ ነጻነት በሰጡት ቃል‹‹የመንግስት ሰዎች ምንም አይነት ቀና ምላሽ እንደማይሰጡኝ አውቃለሁ ነገር ግን በታሰሩበት ወቅት ፍጹም ጤነኛ የነበሩት ባለቤቴ መሞታቸውን ህዝቡ ይወቅልኝ ብለዋል፡ ፡የኦሮሞ ኮንግረስ በኋላም የኦፌኮ ፕሬዘዳንት የሆኑት ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና የአቶ አህመድን ሞት ከባለቤታቸው እንደሰሙ በመጥቀስ ነገር ግን ምንም ማድረግ አለመቻሉን አውስተዋል፡፡

Health: “ከእርሱ ጋር አብረን መሆኑ ያማል፤ ጨርሶ ከእርሱ መራቁም ከብዶኛል፤ ምን ይሻለኛል?”

$
0
0

በቅድሚያ ለጥያቄዬ መልስ ለመስጠት በመቻላችሁ ምስጋናዬን ላቀርብ እወዳለሁ፡፡ እንዴት ናችሁ? ጤና ይስልኝ፡፡ ስሜ ሃና ይባላል፡፡ ዕድሜዬ 28 ነው፡፡ በአንድ ዩኒቨርሲቲ ተምሬ በሶሲዮሎጂ ተመርቄ በሙያዬ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ውስጥ ተቀጥሬ በመስራት ላይ እገኛለሁ፡፡ የምኖረው ከቤተሰቦቼ ጋር ነው፡፡ ከልጅነት ጀምሮ የማውቀው አንድ ጓደኛ አለኝ፡፡ ምንም እንኳን ሁለታችንም ከልጅነት ጀምሮ በፍቅር መፈላለጉ ውስጣችን እንዳለ ብናውቅም አንዳችንም አፍ አውጥተን ስሜታችንን ለመግለፅ ባለመቻላችን ምክንያት እንዲሁ በጓደኝነት ብቻ ረዘም ላለ ጊዜ ቆይተናል፡፡ ቅርብ ጊዜ ግን በጋራ አብረን የምናሳልፋቸው ጊዜያት በመጨመራቸው ሁለታችንም ለዓመታት አፍነን ያቆየነውን ስሜት አፍረጥርጠን ለመነጋገር ችለናል፡፡ እርሱ ከጥቂት ዓመታት በፊት ቀለበት ያሰረላት ልጅ አለች፡፡ እርሷ ደግሞ የምትኖረው እንግሊዝ ሀገር ነው፡፡ ከዛሬ ነገ ትመጣና ተጋብተን እኔም ወደዛው አመራለሁ የሚል ሀሳብ አለው፡፡ እርሱ እንደዚህ ይበል እንጂ ተጋብተው ለመሄድ ግን እስከዛሬ ድረስ ለእኔም ግልፅ ባልሆነ ምክንያት አልቻሉም፡፡
ታዲያ መገናኘቱ እና አብሮ ማምሸቱ እየጨመረ ሲመጣ ስሜታችንን መቆጣጠሩ ለሁለታችንም አስቸጋሪ ሆነና አብረን ማደር ጭምር ጀመርን፡፡ በዚህ መልኩ ለጥቂት ጊዜያት እንደቆየን እያደረግን ያለነው ነገር ትክክል እንዳልሆነ ተነጋግረን ተለያየን፡፡ ምንም እንኳን እንለያይ፤ ከዚህ በኋላ አንገናኝ የሚል ውሳኔ ከእርሱ ሲመጣ እኔም አጨብጭቤ ብቀበለውም ስሜቴ ግን በጣም ነበር የተጎዳው፡፡ ለበርካታ ቀናት ደብሮኝ፣ ሰው ማግኘት አስጠልቶኝ መኝታ ቤቴን ዘግቼ አለቀስኩ፡፡ እንደምንም መጎዳቴን አባብዬ አሁን ቆረጠልኝ ስል በድጋሚ መደወል እና እንገናኝ ማለት እርሱ አመጣ፡፡ አይሆንም ማለት ደግሞ እኔ አልቻልኩም፡፡
‹‹በዚህ ሁኔታ እስከመቼ እንቀጥላለን? ግልፅ አድርግላትና ተለያይታችሁ አብረን እንሁን ለቤተሰብም እናሳውቅ›› ብለው እርሱ እምቢ አለ፡፡ ሌላው ቀርቶ በግልፅ ለመወያየት እንኳን ፈቃደኛ አይደለም፡፡ ይህ ጠባዩ ግራ ቢያጋባኝም፣ ቢያናድደኝም ከልቤ ስለምወደው ግን ሁለተኛ አይንህን ማየት አልፈልግም ማለት አልቻልኩም፡፡ ነገ አብረን እንሁን አንሁን ግልፅ መሆን ባልቻለበት ሁኔታ ውስጥ አብረን መሆኑ ያማል፤ ጨርሶ ከእርሱ መራቁም እንዲሁ ከብዶኛል፡፡ ከዚህ ግራ አጋቢና አስጨናቂ ግንኙነት እወጣ ዘንድ ምን ትመክሩኛላችሁ፡፡
ሐና ነኝ ምስጋና ጋር

Boring marriage
የኢሳያስ ከበደ ምላሽ፦ ውድ ሐና፣ ጤና ይስጥልን! እንዲህ አይነቱን በጣም የግል የሆነውን ጥያቄ ለመጠየቅ ድፍረት ስላገኘሽ ላመሰግንሽ እወዳለሁ፡፡ በደብዳቤሽ ውስጥ የተጠቀሰውን መረጃ መሰረት በማድረግ ለጉዳይሽ መፍትሄ ሊሆኑ የሚችሉ ሐሳቦችን ለማቅረብ እሞክራለሁ፡፡
የፍቅር አካሄድ ውጣ ውረድ የተሞላበት መንገድ ነው አንዳንድ ጊዜ ፍቅር ሰው በሚፈልገው መንገድ ላይሄድ ይችላል፡፡ ስለዚህ የተፈለገው ባይገኝ ከተገኘው ጋር ወዳጅነትን መመስረት ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡፡ የማግባት ፍላጎት ካለሽ (ከደብዳቤሽ መንፈስ ለማግባት ፍላጎት ያለሽ ይመስላል) ምቹ ሁኔታ አለሽ፡፡ ዕድሜሽ ለጋብቻ ደርሷል፤ ስራና የገቢ ምንጭ አለሽ፣ ወንድን የመውደድ ችሎታና ልምድ አለሽ፡፡

ስለ አንቺ የተቃራኒ ፆታ የፍቅር ጉዞ ምን እንደሚመስል ከደብዳቤሽ ዝርዝር መግለጫ ባይኖርም የወደድሽውን ወንድ ‹‹እወድሃለሁ›› ብሎ በልብሽ ውስጥ ያለውን ሐሳብሽን መግለፅ እንደሚከብድሽ መገመት ይቻላል፡፡ አሁን የፍቅር ጓደኛሽ ከሆነው ወንድ ጋር ከልጅነት እስከ ወጣትነት ዕድሜሽ ድረስ ብታፈቅሪውም እንደምትወጂው መናገር አልቻልሽም ነበር፡፡ ከዚህም የተነሳ የአንቺ ሊሆን የሚችለው ሰው በሌላ ሴት ተይዟል፡፡ ልብሽ እየፈቀደ፣ አንደበትሽ ግን አልከፈት በማለቱ ዕድሉ ሊያመልጥሽ ሆነ፡፡ ይህ ስለአንቺ ሁኔታ የሚናገረው መልዕክት አለው፡፡ የተሰማሽን ስሜት፣ ያሰብሽውን ሀሳብ ለመናገር የሚያስቸግርሽ ይመስላል፡፡ አዕምሮሽን የሞላውን ሀሳብ ይዘሽ የማያዳግም ውሳኔ ለመወሰን ትቸገሪያለሽ፡፡

የሚጠቅምሽን ነገር ለማግኘት በተገቢው ጊዜ መወሰን አለመቻል ብቻም ሳይሆን የሚጎዳሽንም ነገር ለመተው ቆራጥ ውሳኔ ለማድረግ እየተቸገርሽ ነው፡፡ የአንቺ ጓደኛ ከአንቺ ጋር በፍቅር ለመቀጠል ፍላጎት እንደሌለው በግልፅ ነግሮሻል፡፡ አንቺ ግን በጣም ስለወደድሽው የእርሱን ፍላጎት እያረካሽ ከእርሱ ጋር አለሽ፡፡ እርሱ ሌላይቱን ለሚስትነት እየጠበቃት ከአንቺ ጋር ጊዜያዊ ስሜቱን እያረካ ይገኛል፡፡

በእኔ መረዳት አማራጭ ሊሆኑ ይችላሉ ብዬ የማስባቸው ሐሳቦችን ልጥቀስ፡፡ የመጀመሪያው አማራጭ ሀሳብ ይህ ጓደኛሽ የወደፊት ባልሽ ሆኖ በዘላቂነት ከአንቺ ጋር ባይኖርም የፍቅር ግንኙነቱን ከእርሱ ጋር መቀጠል ነው፡፡ በዚህ አማራጭ መፍትሄ መሰረት ወዳጅሽ በእንግሊዝ ሀገር ያለችውን እጮኛውን እስኪያገባት ድረስ ለጊዜው ከእርሱ ጋር መቆየት ትችያለሽ፡፡ በዚህ አይነት ከእርሱ ጋር መቆየት ትችያለሽ፡፡ በዚህ አይነት ሁኔታ ለተወሰነ ጊዜ ከምትወጂው ሰው ጋር በፍቅር መኖ ትችያለሽ፡፡ ድብርት አይሰማሽም፡፡ ሆኖም ይህ ፍቅርና ወዳጅነት ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ይቆያል፡፡ እርሱ ወደ ዘላቂ ግንኙነቱ ሲሄድ አንቺ ብቻሽን ትቀሪያለሽ፡፡ ያን ጊዜ የስሜት መጎዳት ያጋጥምሻል፤ አሁን ከእርሱ በራቅሽ ቁጥር የሚሰማሽ ድብርቱና ሀዘኑ ያን ጊዜ እጥፍ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ የመፍትሄ መንገድ ነገ ሊመጣ የሚችለውን ጉዳት ሳያስቡ በጭፍን የዛሬውን ስሜት ብቻ ተከትሎ መሄድ ነው፡፡
ሁለተኛው አማራጭ ሐሳብ ደግሞ ወዳጅሽን ከእጮኛው መለየት ነው፡፡ ከዚህ በፊትም አንዳንድ ሙከራዎችን አድርገሻል፡፡ ከእርሷ ጋር ያለውን ግንኙነት ማቋረጥ የሚችልበትን መንገዶች መፈለግና ይህ ከተሳካ ከእርሱ ጋር መጋባት ነው፡፡ አሁን ያለው ሁኔታ ግን ይህን ለማድረግ የተመቻቸ አይመስልም፡፡ በወዳጅሽና በአንቺ መካከል ያለው የፍቅር ስበት ኃይል በእርሱና በእጮኛው መካከል ካለው የስበት ኃይል የበለጠ አይመስልም፡፡ የወዳጅሽ ልብ ከአንቺ ጋር ሳይሆን ከእጮኛው ጋር ነው፡፡ በእርግጥ እርሷን ስለወደዳት ወይስ እንግሊዝ ሀገር ለመሄድ ከእርሷ ጋር እንደተጣበቀ አይታወቅም፡፡ ከሁለቱ አንዱ ወይም ሁለቱም ሊሆን ይችላል፡፡ እንግዲህ ከልጅነት ጀምሮ የሚያውቅሽና የሚወድሽ (አንቺ እንዳልሽው ከሆነ) ቢሆንም ልቡ ለአንቺ አልተሸነፈም፡፡ ከእርሱ ጋር አብረሽ አድረሽም ልቡ አልተማረከም፡፡ ከዚህ በላይ እርሱን መማረክ የሚያስችል ጥበብ ካለሽ መሞከር ነው፡፡ ሌላው ደግሞ እርሱ ከልጅቷ ጋር ያለው ወዳጅነት ቀለበት ማሰር ደርሷል፡፡ ይህ ማለት ምናልባት ቤተሰብም አውቋል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ አንቺን ቢወድሽም እንኳ ከቤተሰብ ጋር ያለው ግንኙነቱ እንዳይበላሽ ፈርቶ አቋሙን ላይቀይርም ይችላል፡፡ ይህ ቢሳካስ ለአንቺ ምን ያህል የአዕምሮ እርካታ ይሰጥሻል? አንቺ ራስሽን በልጅቷ ስፍራ ብታስቀምጪ፣ የአንቺን እጮኛ ሌላ ሴት ብትቀማሽ ምን ይሰማሻል? ይህ ተቀምቶ የመጣ ባልስ፣ ነገ በሌላ ሴት ተታሎ ከእርሷ ጋር የማይሄድበት ምን ዋስትና ይኖራል?

ሶስተኛው አማራጭ ሐሳብ ከወዳጅሽ ጋር ያለውን የፍቅር ግንኙነት ማቋረጥ ነው፡፡ ይህ ሰው ለጊዜው የፍቅር ፍላጎትሽን ቢያሟላም በዘላቂነት ከአንቺ ጋር አይቆይም፡፡ ከእርሱ መለየት የስሜት ጉዳት ሊያስከትልብሽ ይችላል፡፡ አሁንም ቢሆን ከእርሱ ለመለየት ወስነሽ ለተወሰነ ጊዜ ስትቆዪ የሚሰማሽ ድብርት፣ ሐዘንና ተስፋ መቁረጥ አለ፡፡ ከእርሱ መለየት የሚያስከትለውን የስሜት ጉዳት ፈርተሽ ከእርሱ ጋር መቆየትሽ መፍትሄ አይሆንም፡፡ አንድ ቀን እርሱ ከእጮኛው ጋር ተጋብቶ በዘላቂነት ከአንቺ ሲለይ የስሜት ስብራትሽ ከፍተኛ ይሆናል፡፡ ከእርሱ ጋር በፍቅር ጓደኝነት መቆየትሽ የአንቺን የስሜት ጉዳት ተጋላጭነትን እየጨመረ ይሄዳል፡፡ ስለዚህ አንቺ ሌላ አማራጭ እያለሽ ከእርሱ ጋር በከንቱ ጊዜሽን ማጥፋት የዋህነት ይመስላል፡፡ የአንድ ወገን ፍቅር ዘላቂ የፍቅር ወዳጅነትን አይመሰርትም፡፡ አንቺ በጣም ትወጅዋለሽ፤ አንቺ ለልብ ወዳጅነት ትፈልጊዋለሽ፤ እርሱ ግን አንቺን ለዘላቂ ወዳጅነት ሳይሆን ለጊዜው ከአንቺ ጋር ስሜቱን ለማርካት ነው የሚፈልግሽ፤ የሚደውልልሽም፡፡ ወዳጅነቱን ቢፈልግማ ኖሮ ከዚያች ጋር ያለውን ግንኙነቱን ትቶ ከአንቺ ጋር ይጋባ ነበር፡፡ አሁን ግን እርሱ በዚህ ጉዳይ ላይ ከአንቺ ጋር መነጋገርም አይፈልግም፡፡ ስለዚህ አንቺ ስራ ያለሽ፣ ዕድሜሽ ደህና ሁኔታ ላይ ሆኖ፣ የሚደግፉሽ ቤተሰብ እያለሽ አንቺ ለጊዜው ብቻ ከሚፈልግሽ ሰው ጋር ለምን እንደምትንከራተች ራስሽን መጠየቅ ይገባሻል፡፡ ይህ አማራጭ የመፍትሄ ሀሳብ ለጊዜው የስሜት ጉዳት ቢኖውም፣ በዘላቂነት ግን ህይወትሽን ሊጎዳ ከሚችል ግንኙነት አርነት ያወጣሻል፡፡ በዚህ ውሳኔ ሌላ ከአንቺ ጋር ዘላቂ ግንኙነት ሊመሰርት የሚችል ወዳጅ መፈለግ ትችያለሽ፡፡

‹‹ነገ አብረን እንሁን አንሁን ግልፅ መሆን ባልቻለበት ሁኔታ ውስጥ አብረን መሆኑ ያማል፤ ጨርሶ ከእርሱ መራቁም እንዲሁ ከብዶኛል›› ከሚለው ሁኔታ ለመውጣት ቁልፉ ያለው በእጅሽ ነው፡፡ ከሁለቱ የትኛው የስሜት ህመም ይበልጣል?›› እንግዲህ ‹‹ከዚህ ግራ አጋቢና አስጨናቂ ግንኙነት›› ለመውጣት ከላይ ከተሰጡ አማራጭ የመፍትሄ ሐሳቦች አንዱን መምረጥ ይረዳል የሚል ተስፋ አለኝ፡፡

የሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽንና የአፍሪካ አምባገነን መሪዎች –ዘንድሮስ ተሸላሚ ያገኝ ይሆን ወይ?

$
0
0

Pupet hailemariam
በአፍሪካ መዲናዋ አዲስ አበባ ከጥቂት ወራት በፊት የሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን ኮንፈረንስ አዘጋጅቶ የነበረ ሲሆን ኮንፈረንሱ አፍሪካ ውስጥ ስላለው የመልካም አስተዳደርና ዲሞክራሲ በተመለከተ እንዲሁም አህጉሪቷ ወደፊት ስለሚኖሩዋት እድሎችና ስላጋጠሙዋት ችግሮች ከተለያዩ ሃገራት ከመጡ ፖለቲከኞ፤ ታዋቂ ግለሰቦችንና ጋዜጠኖችን ጨምሮ የተካሄደ ነበር።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ/ Read Full Story in PDF

በጎንደር የሰላማዊ ሰልፍ ቅስቀሳ ላይ የነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች እና ደጋፊዎች ታሰሩ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) የፊታችን እሁድ በጎንደር ከተማ የሚደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ በማስመልከት ሕዝቡ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ወጥቶ ለሱዳን በሚሰጠው መሪት ዙሪያ ድርጊቱን እንዲቃወም በቅስቀሳ ላይ የነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች እና ደጋፊዎች በጎንደር ከተማ መታሰራቸው ተሰማ።

ዘ-ሐበሻ ከሰማያዊ ፓርቲ አካባቢ የደረሳት መረጃ እንደሚያመለክተው ዛሬ የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች እና ደጋፊዎች በጎንደር ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ ይገኛሉ።

ፖሊስ የሰልፉን ቀስቃሶች ካሜራ እና ላፕቶፖችን ጨምሮ ሌሎች ቁሳቁሶችን መውሰዱን የጠቆመው ከሰማያዊ ፓርቲ የተገኘው መረጃ ፖሊስ ዛሬ በቅስቀሳ ላይ የነበሩትን “እሁድ የሚደረገው ሰልፍ ሕጋዊ ፈቃድ ስለሌለው መቀስቀስ አትችሉም” ያላቸው ሲሆን አስተባባሪዎችም “በሕገመንግስቱ መሠረት ሰልፍ ለማድረግ ማስፈቀድ የለብንም። ቀድመን ማሳወቅ እንጂ። ይህን ደግሞ አድርገናል” ቢሉም ፖሊስ ማስተዋወቅ አትችሉም በሚለው አቋሙ ጸንቶ መደብደብ መጀምሩም ተሰምቷል።

የሰማያዊ ፓርቲ የጎንደር ሰልፍ አስተባባሪዎች እና ደጋፊዎች ከድብደባው በኋላ ወደ ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደው መታሰራቸውንና ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ አለመፈታታቸውም ታውቋል።
blue party gonder flyer


እስር ላይ የሚገኙት የሙስሊሞች ጉዳይ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀጠሮው ተራዘመ

$
0
0

muslim dim
(ዘ-ሐበሻ) በእስር ላይ የሚጎኙት የሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ዛሬ ጥር 22 ቅነ 2014 ዓ.ም ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ የተገረ ቢሆንም ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ላልታወቀ ጊዜ ቀጥሮው መራዘሙ ታወቀ።

ታህሳስ 3 ቀን 2014 ዓ.ም ፍርድ ቤት ቀርበው የጥፋተኝነት ብይን የተላለፈባቸው እነዚሁ የሙሊሙች ጉዳይ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ለዛሬ ተቀጥረው የነበረው የመከላከያ ምስክር እንዲያቀርቡ የነበረ ሲሆን በውል ባልታወቀ ምክንያት ፍርድ ቤቱ ቀጠሮውን ማራዘሙን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመልክቷል።

አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ቀጠሮው የአፍሪካ መሪዎች ስብሰባን ኢትዮጵያ ውስጥ ስብሰባ ላይ በመሆናቸው ለጸጥታ በሚል ይሆናል የሚል ግምት ቢሰጡም ድምጻችን ይሰማ የተባለው እንስቃሴ ትናንት ባወጣው መግለጫ በዛሬው ፍርድ ቤት ላይ ለቤተሰቦቻቸውና ለጋዜጠኞች ቦታ ለመልቀቅ ሲባል ፍርድ ቤት ተከታዮቹ እንዳይገኙ ጠርቶ ነበር። ለነዚህ የሙስሊሞች ጉዳይ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ የተሰጠው ተለዋጭ ቀጠሮ መቼ እንደሆነ ለማወቅ የተደረገው ለጊዜው ጥረት ባይሳካም ለጠበቆቻቸው ግን ሳይነገራቸው እንደማይቀር ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ጠቁሟል።

“ታሪክ ለባለ ታሪኩ” –ከገብረመድህን አረአያ

$
0
0

(ገብረመድህን አረአያ ከፐርዝ አውስትራሊያ)

(ገብረመድህን አረአያ ከፐርዝ አውስትራሊያ)

ኢትዮጵያ ሃገራችን ትልቁ እድሏ ከጥንት ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ብዙ የታሪክ ሊቃውንትና ጸሓፍት ያፈራች ሃገር መሆኗ ነው። በጥንቱ ዘመን በኢትዮጵያ መቀመጫቸውን አክሱም ያደረጉት ነገሥታት ታሪካቸውን እና ጥበባቸውን በሳብኛና በግእዝ እያጻፉ አዘጋጀተዋል። በመቀጠልም መቀመጫቸውን ወደ ዛጔ፣ ላስታ ላሊበላ፣ ወሎ ሲተላለፍ በዚያ የነገሡ ነገሥታትም ታሪካቸውን እና ጥበባቸውን በግእዝና በአማርኛ እያዘጋጁ አልፈዋል። የነገሥታቱ መቀመጫ ከወሎ ወደ ሸዋ፤ ከዛም ወደ ጎንደር ሲሸጋገር፣ የነበረው ታሪክ፣ ጥበብና የነገሥታቱ ዝርዝር ሁኔታ ተዘጋጅተው ተመዝግበዋል።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ/ Read full story in PDF

“ወርቃማዎቹ ብዕረኞች”

$
0
0

Eskinder-Nega
ናትናኤል ካብቲመር (ኦስሎ)

(ናትናኤል ካፕትይመር)

(ናትናኤል ካፕትይመር)

“እናንት ከእስር ቤት ፍርግርግ ጀርባ ያላችሁ የእውነት ሐዋርያዎች የቆማችሁለትን ፣ የተሰቃያችሁለትን እውነት የኢትዮጲያ ህዝብ ብቻ ሳይሆን አለም ያውቀዋል አካላች ሁ እስር ቤት ሆኖ በህመም በግርፋት ቢሰቃይም ስብዕናችሁ ግን ውብ ሆኖ ይኖራል”
አምባገነኑ የወያኔ መንግስት እንደተራ ወንጀለኞች በየእስር ቤቱ የሚያንገላታቸው ንፁሀን እስረኞች በአለማቀፍ ደረጃ ክብርን የተጎናፀፉ መሆናቸውን ስንናገር እኛ የምንደግፈውን ሀሳብ ስለደገፉ ወይም አምባገነናዊውን ስርዓት ስለሚቃወሙ ብቻ አይደለም ስለእውነት ስለቆሙ ነው። የወያኔም መንግስት የሚጠላቸው ሊያጠፋቸውም ሌት ተቀን የሚታትረው የሱን በውሸት የተመሰረት ስርዓት የሚያጋልጥ የጠራ እውነት በመፃፋቸው በመናገራቸው ነው። አዎ ለወያኔ ስርዓት አሸባሪ ናቸው ምክንያቱም የውሸት ክምር አንዲት እውነት ትንደዋለችና።
በተለያዩ ግዜያት የተለያዩ አለማቀፍ ተቋማት ለነኚህ ለእውነትና ለነፃነት የቆሙ ጀግኖች የተለያዩ ሸልማቶችን በክብር ሰጥተዋቸዋል። ነገር ግን የወያኔ ጥቅመኞች እነኚህን ክቡር ሽልማቶች ለማቃለል ሲጥሩ ይስተዋላል። እኔም የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን የ2014 “ወርቃማ የነፃነት ብዕር (Golden Pen of Freedom Award)” ተሸላሚነት አስታክኬ ስለሸልማቶቹ ክቡርነት ፣ ስለሸላሚ ድርጅቶች ታላቅነትና ለዚህ ክብር ስለበቁ የነፃነትና የእውነት ፈርጦቻችን አንዳንድ ነገር ለማለት ብዕሬን አነሳሁ።

ወርቃማ የነፃነት ብዕር (Golden Pen of Freedom Award)

ይህ ሽልማት በ አለማቀፍ ጋዜጦችና የዜና አዘጋጆች ማህበር (World Association of Newspapers and News Publishers WAN-IFRA) በሚባል አለማቀፍ ማህበር አመታዊ የፕሬስ ነፃነት ወርቃማ የነፃነት ብዕር ሽልማት በሚል ስያሜ እ ኤ አ ከ1961 ጀምሮ በአለማቀፍ ደረጃ በየአመቱ የተከበረውን የጋዜጠኝነት ሞያ ለነፃነትና ለእውነት ያዋሉ በብዕራቸው ጨቋኝ መንግስታትን የታገሉ ግለሰቦችን ሲሸልም ቆይቷል። ማህበሩ ዋና መቀመጫውን በፈረንሳይ ፓሪስና በጀርመን ዳርምስታት እንዲሁም አጋር ቢሮዎችን በሲንጋፖርና ህንድ ያደረግ አለማቀፍ የጋዜጦችና ዜና አዘጋጆች ማህበር ነው። ማህበሩም በአለማችን 120 ሀገራት የሚገኙ 18 ሺህ አለማቀፍ ዜና አታሚዎችን ፣ 15ሺህ ድረገፆችንና 3ሺህ ድርጅቶችን ይወክላል። ይህም ታሪካዊ ሽልማት በየአመቱ በአለማቀፍ የጋዜጦች ኮንግረስና አለማቀፍ አርታኢዎች ፎረም (World Newspaper Congress and World Editors Forum) አመታዊ በዓል መክፈቻ ስነስርዓት ላይ ለተሸላሚው ይበረከታል።

በእስከዛሬውም ከተለያዩ የአለማችን ሀገራት ለነፃነትና ለእውነት የቆሙ ጋዜጠኞችና የጋዜጣ አዘጋጆች ለዚህ ክብር በቅተዋል። ለአብነት ለመጥቀስም ያህል በ2013 የማይናማር ዜጋ የሆኑት ዶክተር ታን ኦንግ ፣ በ2012 ደግሞ የሜክሲኮን የፖለቲካ ሙስናና ስውር የሀሺሽ ንግድ የማጋለጥ ታላቅ የጋዜጠኝነት ሞያዋን ለተወጣችው ሜክሲኮአዊቷ አናቤል ኸርናንዴዝ ፣ በ2011 ደግሞ በሀገር ክህደት ወንጀል ተከሶ በእስር ላይ የሚገኘው ኤርትራዊው ጋዜጠኛ ዳዊት ይሳቅ ይገኙበታል። ጋዜጠኛ ዳዊት የስውዲን ዜግነት ያለው ኤርትራዊ ሲሆን በኤርትራ ታዋቂ የነበረችው የ “ሰቲት” ጋዜጣ አዘጋጅ ነበር።
በ2014 ደግሞ ማህበሩ በጃንዋሪ 27 2014 እንዳሳወቀው ኢትዮጲያዊው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ለዚህ የተከበረ ሽልማት በቅቷል። በቅርቡ ኢትዮጲያን ጎብኝተው የእውነተኛ ጋዜጠኞችን እስርና እንግልት እንዲሁም የፕሬስ ነፃነት መታፈን ያስተዋሉት የማህበሩ ፕሬዝዳንት ቶማስ ብሩንጎርድ የጋዜጠኛ እስክንድርን የጋዜጠኝነት ሞያና ስነ ምግባር እንዲሁም ለእውነት ሲል የከፈለውን መስዋትነት አድንቀው የኢትዮጲያ መንግስት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን እንዲሁም ሰለሞን ከበደን ፣ ውብሸት ታየን ፣ ርዕዮት አለሙን ፣ ዩሱፍ ጌታቸውንና መሰል ንፁሃን እስረኞችን በአስቸኳይ እንዲፈታ በአፅን ኦት ጠይቀዋል።

ጋዜጠኛ እስክንድር አቻ በማይገኝለት የጋዜጠኛ ስነ ምግባሩ በ2012 የባርባራ ጎልድ ስሚዝ የመፃፈ ነፃነት The PEN/Barbara Goldsmith Freedom to Write Award ተሸላሚም ነበር። ይህም ሽልማት ከተጀመረበት ከ1987 ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ በአለማቀፍ ዙሪያ ለ 42 ጋዜጠኞች ተበርክቷል። ከነዚህም 42 ተሸላሚዎች ሰላሳ ሁለቱ ሽልማቱን ባሸነፉ ግዜ በእስር ላይ ነበሩ። በዚህ የሽልማት ዘርፍ ከጋዜጠኛ እስክንድር ሌላ በ1989 ማርታ ኩምሳ የተባለች ኢትዮጲያዊት ጋዜጠኛ ተሸላሚ እንደነበረች የተሸላሚዎች ዝርዝር ያሳያል።
ሌላኛዋ በጋዜጠኝነት ሞያዋ ለአለማቀፍ የክብር ሽልማት የበቃችው ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ ናት። የኮሎምቢያ ኤል ኤስፔክታዶር ጋዜጣ አዘጋጅ የነበረውና የኮሎምቢያን ሀሺሽ ነጋዴዎችን በማጋለጡና በመቃወሙ ሳቢያ የተገደለው ጋዜጠኛ ጉዊሌርሞ ካኖ ስም የተሰየመው የዩኒስኮ ጉዊሌርሞ ካኖ አለማቀፍ የፕሬስ ነፃነት ሽልማት (UNESCO/Guillermo Cano World Press Freedom Prize) የ2013 ተሸላሚ ሆናለች።

ከዚህ በተጨማሪም ጋዜጠኛ ርዕዮት በአለማቀፍ የሴቶች ሚዲያ ፋውንዴሸን (International Women’s Media Foundation IWMF) የ 2012 Courage in Journalism Award ተሸላሚም ነበረች። ይህ ድርጅት መቀመጫውን ዋሽንግተን ዲሲ አድርጎ በ አለማቀፍ ደረጃ በተለያዩ የሚዲያ ተቋማት የሴቶችን ተሳትፎ የሚያበረታታ ድርጅት ነው። በዚህ የሽልማት ዘርፍ የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ባለቤት የሆነችው ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል የ2007 ተሸላሚ እንደነበረች የተሸላሚዎች ዝርዝር ያሳያል።
እነኚህ ጋዜጠኞች ከላይ ከጠቀስኳቸው በተጨማሪ ለበርካታ ክብርና ሽልማቶች መብቃታቸውን በዚህ ፅሁፍ ግን ዋና ዋናዎችን ብቻ ማንሳቴን አንባቢ ልብ እንዲልልኝ እማፀናለሁ። ለዛሬ በዚህ ላብቃ። በሌላ ግዜ ደግሞ ሌሎች ለነፃነትና ለእውነት የቆሙ በሃገራችን ብቻ ሳይሆን በአለማቀፍ ደረጃ እውቅናና ክብርን ያገኙ ጀግኖቻችንን ለማቅረብ እሞክራለሁ።

“እውነት ነፃ ነች ፣ ውብ ነች ከጎኗም የቆመ ዘላለም እንደተከበረ እንዳማረ ይኖራል”

ለእውነትና ለነፃነት የቆሙ ንፁሃን ጋዜጠኞች ከእስር ተፈተው ከስደት ተመልሰው በሃገራቸው ስለሃገራቸው በነፃነት እንዲፅፉ የበኩላችንን እንታገላለን !!

Health: ፍቅረኛ ልታጡ የቻላችሁባቸው 8 ምክንያቶች

$
0
0

በሊሊ ሞገስ

አንዳንድ ሰዎች መርጠው ብቸኛ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ አንዳንድ ሰዎች ቅርብ ጊዜ ከጥሩ የፍቅር ግንኙነት ውስጥ በመውጣታቸው ምክንያት እና የሚመስላቸውን ሰው እስከሚያገኙ ድረስ ብቸኛ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ የዚህ ፅሑፍ አላማ ብቸኛ ሆኑ ወንዶችን እና ሴቶችን በሙሉ አንድ ሳጥን ውስጥ ጨምሮ ብቸኛ ልትኑ የቻላችሁት በዚህ በዚህ ምክንያት ነው ማለት አይደለም፡፡ ይልቁንም ዕድሜያችሁ ከ30 በላይ የሆነ እንደሆነ እና እንዴት እስከ ዛሬ ድረስ ብቸኛ ልሆን ቻልኩ? የሚለው ጥያቄ እንቆቅልሽ ከሆነባቸው ለጥያቄያችሁ መልስ ሊሆኑ የሚችሉ ውስጣችሁ የሚገኙ ያልተለመዱ ምላሾችን እነሆ ብለናል፡፡

ከተቃራኒ ፆታ ፍቅር ግንኙነት ጋር በተያያዘ የትኛውም ሰው ቢሆን እንደው አንድም ጊዜ እንኳ ተጎድቼ አላውቅም ለማለት ይቸገራል፡፡ የሆነ ጊዜ ላይ ሰዎች መራራት ሊሳናቸው፣ ራስ ወዳድ ሊሆኑ እና ልትጎዱ ትችላላች፡፡ በዚህ ወቅት ታዲያ ‹‹የእኔ ጥፋት ነው›› የሚል ድምዳሜ ላይ መድረስ ትክክል አይደለም፡፡ የሆነ ሆኖ ግን እውነታው ምንድን ነው? አብዛኞቻችን ከምናስበው በላይ የፍቅር ህይወታችን ላይ የቁጥጥር ኃይል አለን፡፡ ምንም እንኳ ብዙ ጊዜ ብንዘነጋውም ሁላችንም አውቀንም ይሁን ሳናውቅ የምንኖርበትን ዓለም እንፈጥራለን፡፡ ራሳችንን ሁል ጊዜ በተጎጂ መነፅር ለመመልከት አልያም ዕቅድ ያለው እና የገዛ ህይወቱን እጣ ፈንታ መቆጣጠር የሚችል ሰው በሚል መነፅር ራሳችንን ለመመልከት መምረጥ እንችላለን፡፡ መቆጣጠር የማንችለው ነገር ላይ ሳይሆን መቆጣጠር የምንችለው ነገር ላይ ትኩረተ ብናደርግ የተሻለ ተጠቃሚ እንሆናለን፡፡ ሰዎች ስለ እኛ የሚሰማቸውን ስሜት መወሰን የምንችልበት አቅም አለን፡፡ ይህ አቅም ታዲያ አሉታዊ ስሜቶችንም ይጨምራል፡፡ ስለዚህ ብቸኛ የሆነና የፍቅር አጋር በመፈለግ ላይ የሚገኝ ሰው ለራሱ ሊያቀርበው የሚገባው ጥያቄ ‹‹ብቸኛ ልሆን የቻልኩበት ትክክለኛ ምክንያት ምንድን ነው?›› የሚል ነው፡፡

images
1. ማስተባበያዎች (Defenses)

ብዙ ሰዎች ከሌሎች ሰዎች ጋር ባላቸው ግንኙነት ተጎድተው ያውቃሉ፡፡ በዚህ ምክንያት መሽቶ በነጋ ቁጥር ውስጣችን ቅያ፣ ቁጣ እና ጥርጣሬ ያድጋል፡፡ ስለዚህ ሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት ውስጥ ማስተባበያዎችን አለልክ እንጠቀማለን፡፡ ይህ ሂደት የሚጀምረው በልጅነታችን ሊሆን ይችላል፡፡ በተለያየ አጋጣሚ ሰዎች ስሜታችንን በመጉዳታቸው የተነሳ ራሳችንን ከጉዳት ለመከላከል ያስችላል ብለን ያሰብነውን በተለይ በተለይ ነፍስ ከአወቅን በኋላ ህይወታችንን አሉታዊ በሆነ መንገድ ሊጫን የሚችል ዓለምን የምንመለከትበት፣ ክፉ እና ደግ ነው የምንለውን ነገር የምንለይበት ማጣሪያ እናዘጋጃለን፡፡ እነዚህ ማጣሪያዎች ከልክ በላይ ራሳችንን ከጉዳት ለመከላከል ብቻ የምንተጋ፣ የትኛውንም ግንኙነት ለማስወገድ የምንጥር፣ ለማፍቀር ሳይሆን ለአለመጎዳት የምንሰራ ሰዎች ሊያደርጉን ይችላሉ፡፡ ይህ ጠባይ በአዋቂነት ዘመናችን ራሳችንን ለፍቅር አጋር አሳልፈን ከመስጠት እንድንቆጠብ እና በቀላሉ በሰዎች ተስፋ የምንቆርጥ አይነት እንድንሆን ያደርጋል፡፡

ለምሳሌ፤ ፍቅር ተነፍጋችሁ ከሆነ ያደጋችሁት አዋቂ ስትሆኑ ሰዎች ፍቅራቸውን ሊገልፁላችሁ ሲሞክሩ ትጠራጠራላችሁ፡፡ እንደውም በምትኩ የልጅነት ህይወታችሁን መልሶ የሚደግም አይነት፤ ፍቅር የሌለበት፤ በቅናት፣ ጥርጣሬ እና ጥል የተሞላ ግንኙነት ልትመሰርቱ ሁሉ ትችላላችሁ፡፡ እንደ ወላጃችሁ ወይም አሳዳጊያችሁ ፍቅር መስጠት የማይችል ሰው ልታፈቅሩ ትችላላችሁ፡፡ ይሁን እንጂ ብቸኛ ልንሆን የቻልነው በዚህ በዚያ ምክንያት ነው እያልን ውጫዊ ነገሮችን ብቻ በመውቀስ ውስጣችን የሚገኙ እውነተኛ ምክንያቶችን ሳንመለከት እንቀራለን፡፡

sex2. ጤናማ ያልሆነ መሳሳብ

ቀደም ሲል ያነሳነው አይነት ማስተባበያ ውስጣችን ከኖረ አጋር ስንመርጥ የምንፈልገው አይነት ሰው ላንመርጥ እንችላለን፡፡ ይልቁንም እምብዛም ፍቅር የማይሰጠን እና በስሜት ሩቅ የሆነ ሰው ላይ እናተኩራለን፡፡ የሚቀርበንን ሳይሆን የሚርቀንን፤ የሚያከብረንን ሳይሆን የሚያጣጥለንን ሰው እናሳድዳለን፡፡ ይህ ሂደት በአመዛኙ ለእኛ የሚታይ ባለመሆኑ አልሰራ ላለው ግንኙነት ተወቃሽ የምናደርገው አጋራችንን ብቻ ይሆናል፡፡ እነዚህን መሰል ግንኙነቶች እየመሰረትን የምንገኘው በገዛ እጃችን መሆኑን መመልከት ስለሚከብደን በተደጋጋሚ በሚያጋጥመን መገፋት እንጎዳለን፡፡

ለምንድን ነው እንዲህ የምናደርገው?

ምክንያቶቹ ብዙ ጊዜ የተወሳሰቡ ሲሆኑ መሰረት የሚያደርጉት ውስጣችን በጥልቀት የተቀበረ ጥልቅ ወዳጅነትን የመፍራት አባዜ ላይ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ለእነሱ ያን ያህል ጎልቶ የማይታይ ነገር ግን በራሳቸው ዙሪያ ቀደም ሲል ያስቡ የነበሩትን ቁልፍ አስተሳሰቦች የሚያጠናክር ግንኙነት የመሳብ ተነሳሽነት ውስጣቸው አለ፡፡ በዚህ ምክንያት የልጅነታቸውን አሉታዊ ገፅታዎች መልሰው በአዋቂነታቸውም ዘመን ይደግሙታል፡፡

3. መቀራረብን መፍራት

ብዙዎቻችን አፍቃሪ አጋር እንደምንፈልግ እንናገራለን፡፡ ይሁን እንጂ እውነተኛ ፍቅር ወደ ህይወታችን ሲመጣ ያ ከልጅነት ጀምሮ ውስጣችን ያደገውን የፍቅር ቅዠት አልመስል ስለሚለው ልባችንን አንከፍትም፡፡
ቅርርብን መፍራት ከሚገለፅባቸው መንገዶች አንዱ አንድ ሰው ‹‹ከልክ በላይ ነው የሚወደኝ፤ ከእሱ/እሷ ጋር መሆን ይከብደኛል›› የሚል ማስተባበያ ነው፡፡ ይህ ምክንያት ከአንድ ሰው ጋር የፍቅር ግንኙነት ለመመስረት በፍፁም ሊከለክል አይችልም፡፡ የሚወደንን ሰው በማብጠልጠል እና በመግፋት አጣን የምንለውን ፍቅር እውነትም እንዳጣን ለማረጋገጥ እንሞክራለን፡፡ እውነቱን ለመናገር ብዙ ሰዎች የሚመርጡት በተወሰነ መልኩ መቀራረብን ብቻ ነው፡፡ ምንም እንኳ የፍቅር አጋር እንደምንፈልግ ብንገልፅም ውስጣችንን ግን በዚህ መልኩ ልንዘጋው እንችላለን፡፡ ነገሩን በጥልቀት ስትመለከቱት እንፈልጋለን እንላለን እንጂ አንፈልግ ሁሉ ይሆናል፡፡

4. ሲበዛ መራጭ መሆን

ማስተባበያዎች ብዙ ጊዜ አለልክ መራጭ ያደርጉናል፡፡ ይህ በተለይ እውነት የሚሆነው በአንድ አጋጣሚ በጣም በምናወድሰው ሰው የተጎዳን እንደሆነ ነው፡፡ ብዙ ሴቶች ‹‹ጥሩ ወንድ እኮ የለም፤ ያሉት ጥቂቶችም ተይዘዋል›› ሲሉ ይደመጣል፡፡ ወንዶች በሌላ በኩል ‹‹ሴቶችን ማመን አይቻልም፤ ተጠቅመውብህ ዞር ይላሉ›› ይላሉ፡፡ እውነታን ያላገናዘበ ነገር ከሰዎች እንጠብቅና ገና ከመገናኘታችን ‹‹አይ ይሄ/ይቺ እንኳን ሊሆን/ልትሆን አትችልም›› የሚል ድምዳሜ ላይ እንደርሳለን፡፡ በአብጠልጣይ አይን ዓለምን የምንመለከት ከሆነ ወደ ፊት አብረውን ቢሆኑ አስደሳች ህይወት ለመምራት ሊረዱን ሁሉ የሚችሉ ብዙ ሰዎችን እናጣለን፡፡ ወደ ፊት ያ ሰው ምን ያህል ሊያስደስተን እንደሚችል ሳናውቅ ተስፋ እንቆርጣለን፡፡

5. ዝቅተኛ በራስ መተማመን

አንዳንድ ሰዎች የፍቅር አጋር እንደሚፈልጉ ከልባቸው ያምናሉ፡፡ ይሁን እንጂ ከዚህ በበለጠ መልኩ የሚፈልጉት አይነት ሰው እነሱን እንደማይፈልጋቸው ያምናሉ፡፡ ሁላችንም ውስጣችን በጣም ወፍራም፣ መልከ ጥፉ፣ ልዩ እንደሆንን የሚነግረን ድምፅ ይኖር ይሆናል፡፡ በዚህ ምክንያት ሰዎችን የሚያርቅ ነገር እናደርጋለን፡፡ አንዳንድ ሰዎች ዝቅተኛ በራስ መተማመን ውስጣቸው ሲነግስ ሌላው ቀርቶ ከቤት መውጣት ሁሉ ያስጠላቸዋል፡፡ አይን ለአይን መተያየት ይከብዳቸዋል፡፡ በአንድ አጋጣሚ ሊወዱት ከሚችሉት ሰው ጋር ቢተዋወቁ እንኳ ‹‹ልትፈልገኝ ትችላላች/ሊፈልገኝ ይችላል›› ብለው ስለሚያስቡ ፍላጎታቸውን አይገልፁም ይልቁንም ሽሽት ውስጥ ይገባሉ፡፡

6. ፉክክርን መፍራት

ዝቅተኛ በራስ መተማመን ፉክክር እንድንፈራ ያደርጋል፡፡ በተለይ ከተቃራኒ ፆታ ግንኙነት ጋር በተያያዘ ራሳችንን ከሌሎች ጋር አወዳድሮ ዝቅ ዝቅ ማድረግ በጣም ቀላል ነው፡፡ እኛ ፍላጎት ያሳደርንበት ሰው ላይ ሌላ ሰው ፍላጎት እንዳሳደረ ስናውቅ እግሬ አውጪኝ ብለን እንሸሻለን፡፡ በተለይ ዕድሜያችን እየገፋ ሲሄድና ሰዎች ‹‹ቆመህ መቅረትህ/መቅረትሽ ነው›› ነው ትችት መሰንዘር ሲጀምሩ የመፎካከር መንፈስ ከውስጣችን ሙልጭ ብሎ ሊጠፋ ይችላል፡፡ መፎካከርን የምንፈራ ከሆነ ወጣ ብለን የሚመስለንን ሰው ለማግኘት ሙከራ አናደርግም፡፡ አንዳንዴ መሸነፍን ብቻ ሳይሆን ማሸነፍን ሁሉ እንፈራለን፡፡ እኛ አሸንፈን ልባችን የፈቀደውን ሰው ብናገኝ ሌላኛው ሰው ሊጎዳ ይችላል የሚል ፍርሃት ውስጥ እንገባለን፡፡ ቀላል እውነታ ግን ምንድነው? ፍቅርን አጋርን ማግኘት ፉክክር የሚጠይቅ ሂደት ነው፡፡

7. መገለል እና ልማድ

በተለይ ዕድሜ እየገፋ ሲመጣ ሰዎች የለመዱት ነገር ውስጥ ከልክ በላይ የመወሸቅ ፀባያቸው እየጨመረ ይሄዳል፡፡ ዘመናዊ ሴቶች በብዙ መልኩ ስኬታማ ናቸው፡፡ ይህ ጥሩ ነገር ነው፡፡ ይሁን እንጂ ዘመናዊ ወንዶች እና ሴቶች በሀብትም ይሁን በሌላ መልኩ ሊደላደሉ አንዳንዴ ከምቾት መጋረጃቸው ውስጥ ወጥተው ሰዎችን ለመተዋወቅም ሆነ ለመቀራረብ ይቸገራሉ፡፡ አደጋን ለመግፋት እና ራሳቸውን አሳልፈው ለመስጠት ሊቸገሩ ይችላሉ፡፡ ከረጅም የስራ ቀን በኋላ ብዙዎቻችን ወደ ቤታችን አምርተን ቢጃማ ለብሰን እረፍት ማድረግ እንጂ ወጣ ብሎ ሊያስፈራ የሚችለውን ሰዎችን የመተዋወቅ እና መቀራረብ ሂደት አንመርጥም፡፡

ቤት እንድንሄድ የሚያበረታታን አንድም ውስጣችን የሚገኘው ያ ድምፅ ሊሆን ይችላል፡፡ ‹‹ግድ የለም ብቻችሁን ብትኑ ይሻላል››፣ ‹‹ምን ጎደለባችሁ››፣ ‹‹እንደውም ልብስ ቀያይራችሁ ያንን የቴሌቪዥን መርሀግብር ተከታተሉ›› ወዘተ… ሊለን ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ ይኸው ድምፅ ኋላ መልሶ ‹‹ምን ነካችሁ! ዕድሜያችሁ እኮ ሄደ››፣ ‹‹ቆማችሁ መቅረታችሁ ነው››፣ ‹‹ብቻችሁን መሞታችሁ ነው›› ብሎ ሊረብሸን ይችላል፡፡
ስለዚህ እንደዚህ አይነት ልማድ ውስጥ ሰምጠን እንዳንቀር ወጣ ብሎ ሰዎች መተዋወቅ፣ የፍቅር አጋር እየፈለግን እንደሆነ ለጓደኞቻችን መናገር ወዘተ አስፈላጊ ነው፡፡

8. ህግ ማውጣት እና ማጥበቅ

ጊዜያቶች ሲሄዱ የተቃራኒ ፆታ ግንኙነትን የሚመለከቱ ህጎች ለራሳችን እናዘጋጃለን፡፡ በዚህ መሰረት በጎ ነው ብለን የምናስበውን ወረቀት ላይ እናሰፍራለን፡፡ ይሁን እንጂ ወረቀት ላይ ያማረ ነገር ተግባራዊ ሲሆን ላያምር ይችላል፡፡ ያለፈ ግንኙነታችንን መሰረት ያደረገ ህግ አውጥተን ለመኖር ስንሞክር አሳዛኝ አጋጣሚዎች ሊደጋገሙብን ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ አንዳንድ ሰዎች ያማረ የሚሉት የፍቅር ህይወታቸው ሲፈርስ ‹‹ከዚህ በኋላ ከምወደው ሰው ጋር አብሬ መሆን የለብኝም›› የሚል ድምዳሜ ላይ ይደርሳሉ፡፡ በዚህ መሰረት ያን ያል ከማይወዱት ሰው ጋር ፍቅር ለመመስረት የሚያደርጉት ጥረት መጨረሻው ደስታ አልባ እየሆነ ይቸገራሉ፡፡

የፍቅር አጋር በምንፈልግበት ወቅት ልናደርግ የሚገባው ትልቁ ነገር ምን ጊዜም ልባችንን ክፍት ማድረግ ነው፡፡ እውነት ነው አንዳንዴ በዚህ ምክንያት ልንጎዳ እንችላለን፡፡ ነገር ግን ላለመጎዳት በማሰብ ብቻ ልባችን ዝግ ሲሆን ደግሞ በአንፃሩ ወደፊት አብሮን ሊሆን የሚችልን ሰውል ናጣም እንችላለን፡፡
የፍቅር አጋርን የማገኘት ሂደት አልጋ በአልጋ የሆነ ጉዞ አይደለም፡፡ የሆነ ሆኖ ግን ሁልጊዜም በእኛ በኩል ያለውን ኃላፊነት መወጣት አስፈላጊ ነው፡፡ ወደ ኋላ የሚጎትቱንን ውስጣችን የሚገኙ ልማዶች መዋጋት ያስፈልጋል፡፡ ራሳችንን እንዴትም ቢሆን ፍፁም ከአደጋ መከላከል አንችልም፡፡ ሁላችንም ደካማ ጎን ያለን ሲሆን እነዚህ ጎኖች ደግሞ በተለይ ሌላ ሰው እየቀረብን ስንሄድ መጉላታቸው አይቀርም፡፡ ስለዚህ ጥልቅ የፍቅር ግንኙነት መመስረት ትልቅ ጥረት የሚጤቅ ሲሆን ስኬቱም አስደሳች እና ‹‹እንኳንም ደከምኩ›› የሚያሰኝ በመሆኑ ውስጣችን የሚገኙ ጎታች አስተሳሰቦችን፣ ፍርሃቶችን፣ ልማዶችን መታገል እና መጣል አስፈላጊ የቤት ስራ ነው፡፡
Zehabesha.com

[የሚኒሶታው መድሃኔዓለም ቤ/ክ ጉዳይ] መድኃኔዓለም በእርቅና በሰላም ጎዳና ይምራችሁ

$
0
0

የተከበራችሁ የሚኒሶታ ደብረሰላም መድኅኒዓለም ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ምእመናን፤ አባቶች ካህናት፤ ወንድሞች ዲያቆናት ከሁሉ አስቀድሜ የከበረ የኢግዚአብሔር ሰላምታየ ከካናዳ ይድረሳችሁ። ሚኒሶታን በተለያየ ጊዜ ጎብኝቻታለሁ። . በመጣሁበት ጊዜ ሁሉ መድኅኒዓለም ቤተከርስቲአናንን ሳልሳለምና ፀሎት ሳላደርግ የተመልሱሁበትን ጊዜ አላስታውስም። የምእመናኑ ፍቅር፤ አንድነትና የምነት ጽናት ሁልጊዜ በአረያነት ስጠቅሰው ኖሬአለሁ።
debereselam Minnesota
በቅርቡ በኢትዮጵያዊያን ድረገጾች ላይ የሚወጡትን ዜናዎች ሳይ ግን አዘንሁ። ለማመንም ተቸገርሁ። ሰላማችሁ ተቃውሶ ፍቅራችሁ ደፍርሱዋል። ሠይጣን በናንትና በእምነታችሁ መካከል ገብቶ እያተራመሳችሁ ነው። በከባድ ፈተና ላይ እንዳላችሁ ይሰማኛል። በእምነት ፀንታችሁ ከገባችሁበት የችግር አረንቋ እንድትወጡ እፀልያለሁ። ችግርና ፈተና በመንፈሳዊ ሕይወት ውስጥ ያለና የሚኖር ስለሆነ ጽናቱን ይስጣችሁ።።

በርቀት እንዳነበብሁትና እንደተረዳሁት የችግሩ መንስዔ ቀላል ይመስለኛል። ችግሩ በቅርቡ ጠቅላላው ጉባኤ ቤተክርስቲአንዋ በገለልተኝነትዋ ትቀጥል ብሎ ባሳለፈው ውሳኔ ላይ ያጠነጠነ ይመስለኛል። ይህን ሕዝበ ውሳኔ የተወሰኑ የቦርድ አባላት ምላተ ጉባዔ የጎደለው ውሳኔ ስለሆነ አንቀበለውም ወይም በይደር ይቆይ የሚሉ በመኖራችው የተነሳ እንደሆነ ገምቻለሁ። እንደኔ አስተያየት ይህ የአሰራር ድክመት (procedural inconsistency ) በጠረጴዛ ዙሪያ በውይይት የሚፈታ ጉዳይ ነው።

ውሳኔውን የተቃወመው የቦርድ ቡድን ሊቀመንሩን አውርደን ሌላ ተክተናል ብሎ ባወጣው መግለጫ ቤተክርስቲአንዋ በገለልትኝነቱዋ ትቀጥላለች ብሎ አውጁአል። ስለዚህ ጠቡ የት ላይ እንደሆነ ግራ ያጋባል። በአመራሩ (በሊቀመንበሩና በምክትል ሊቀመንበሩ) ላይ የተደረገ ዘመቻ ቢሆን እንኩዋን ለዚህ ሁሉ ብጥብጥ የሚዳርግ መሆን የለበትም ።

በአንጻሩ የፖለቲካ አጀንዳ ይዘው የሚበጠብጡ ካሉ ለችግሩ መፈጠርና ለሚያስከትለው መዘዝ ደንታ ላይኖራቸው ይችላል። ምክንያቱም የነዚህ ቡድን ዓላማ እምነታችንን፤ ባህላችንን፤ ቅርሳችንንና ታሪካችንን ማስከበር ሳይሆን የሃገርና የህብረተሰብ እሴቶችን ደፍጥጦ የፖለቲካ አሸናፊነትን ማግኘት ነው። ይህ ደግሞ ጊዚያዊ ግኝት እንጅ ዘላቂነት ያለው ማሸነፍ አይሆንም። የሊቀመንበሩን የአቶ ጥበቡን ስነልቡናና ባህሪ ሳጠያይቅ የተረዳሁት ግለሰቡ ልዩ ዓጀንዳ የሚኖራቸው ሰው ሆነው አይታዩም። ይህን አባባሌን በማስርጃ ላመሳክረው፥

ከጥቂት ዓመታት በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ በሕዝብ ተመርጠው ቤተክርስቲአኑዋን አገልግለዋል። ባገለገሉበት ጊዜ አብዛኛው ምእመን በምስክርነት የሚገልጸው-በሃቅ ሰርተው ለተተኪው ቦርድ እንዳስረከቡ ታውቁአል/ ሰምቻለሁ፤

ለሁለተኛ ጊዜ ሲመረጡ ዕድሜየ ገፍትዋል፣ የጤና ችግር አለብኝ ብለው ቢያንገራግሩም ህብረተሰቡ ያገልግሉን ብሎ በድጋሚ ስለመረጣቸው ሃላፊነቱን የተቀበሉ ናቸው። ለዚህም ይመስለኛል የቦርዱ አባላት በሊቀመንበርነት የመረጡአቸው። ደመወዝ ተከፍሉአቸው፤ጥቅማ ጥቅም አግኝተው አይሰሩም። ሰውናቸውና አይሳሳቱም ማለት ግን አይቻልም። የሚሳሳቱ ስለሚሰሩ ነው። ልዩ ዓጀንዳ ያላቸው አለመሆኑ ግን በግልጽ መታወቅ አለበት።

አገር ቤት በነበሩበት ጊዜ የነበራቸውን ስብእና ስንመለከት የግለሰቡን ሃቀኝነትና ባመኑበት የመቆም ባሕሪአቸውን ለመረዳት እንችላለን። በደርግ ዘመነ መንግስት በተለያዩ የመንግስት መስሪያቤቶች በመምርያ ኃላፊነት ሰርተዋል። በዚያን ዘመን በኢሰፓ መመሪያ መሰረት ማንኛውም የመምሪያ ኃላፊ የኢሰፓ አባል ሆኖ የካድሬነት ደብተር መያዝ የውዴታ ግዴታ ነበር። እኒህ ግለሰብ ግን እኔ ሙያዊ ስራ የምሰራ እንጅ የፖለቲካ ስራ የምሰራ ሰው አይደለሁም በማለት በአቍማቸው እንደፀኑ እስከደርግ ፍጻሜ ድረስ ያገለገሉ ሰራተኛ ናቸው። ይህን ስነምግባራቸውን በቅርብ ከሚአውቋቸው ሰዎች ለማጣራትና ለማወቅ ችያለሁ። ስለሆነም ግለሰቡ ድብቅ ዓጀንዳ ይኖራቸዋል ብሎ መጠርጠር የሚቻል አይሆንም። ችግሩ የሚመስለኝ በሃገራችን ባህል እውነትን ፊትለፊት ያለዲፕሎማሲ መናገር ብዙ ጠላትን እንጅ ወዳጅን አያስገኝም። በዚህም የካህናትንና ያንዳንድ ቦርድ አባላትን ቅሬታ የፈጠረባቸው መስሎ ይታየኛል።

የሰበካ ጉባኤ ቦርድ በጠቅላላው ጉባኤ ተመርጦ ስራውን ከጀመረ አንድ ዓመት ከሶስት ወር ሆኖታል። ያገልግሎት ዘመኑን ሊጨርስ ስምንት ወራት ይቀረዋል። ሁላችሁም ምርጫውን ተቀብላችሁ በእግዚአብሔር ስም ቃል ገብታችሁ የቤተክርስቲያኒቱን መተዳደሪያ ደንብ አስከብራችሁ ለመስራት እንደሆነ የምታጡት አይመስለኝም። የምትሰሩትም የእግዚአብሔርን ቤት ለመጠበቅና ምእመናን በሙሉ ልብ፤ ቅንነትና ታማኝነት ለማገልገል ነው። ማናችሁም (ከካህናቱ በስትቀር) ተከፍሎት የሚአገለግል የለም። የምትሰሩት የመንፈሳዊና የግብረሰናይ ስራ ብቻ መሆን አለበት። ባለፉት 13 ወራት በብዙ ጉዳዮች ላይ በህብረት ወስናችሁአል። በምትሰሩበት ጌዜ ስህተቶች ይኖራሉ። ሆን ብሎ ግን ስህተት የሰራ አለ ብሎ ማመን ግን ይቸግራል። ሁላችሁም የእግዚአብሔርን ቤት ሰሪዎች ናችሁና። የማይሳሳት የማይሰራ ብቻ ነው። ከስህተታችሁ ተምራችሁ ይቅር ለእግዚአብሔር ወርዳችሁ ሠላምን ልትፈጥሩ ይገባል። እስኪ ከኔልሰን ማንዴላ ይቅር ባይነትና ሰላም ፈጥሪነት ትምህርት ቅሰሙ። በፖለቲካው ዓለም ይቅርታን መፍጠር ከተቻለ በእግዚአብሔር ቤትማ የበለጠ መቻል አለበት እላለሁ። ሁላችሁም ደረጃው ይለያይ እንጅ የተማራችሁ ናችሁ። አገራችሁ ከናንተ ብዙ ትጠብቃለች። ይህን መለስተኛ ችግር መፍታት ይሳናችሁአል የሚል እምነት የለኝም።

ከዚህ የተለየ ዓላማና ዓጀንዳ ያለው ካለ የሕዝብን አደራ የብላ ስለሆነ ውጉዝ ከማሪወስ ሊባል ይገባዋል። አቶ በቀለ ገብረሚካኤል ከተባሉ ፀሃፊ መረዳት እንደቻልሁት ካህናቱ በሳቱ ላይ ውሃ በማርከፍከፍ ፋንታ በችግሩ ላይ ጭድ የጨመሩ መስሎ ይታያል። ይህን አርገው ከሆነ በእግዚአብሄር ቤት የሚጠይቁበት ይሆናል። አሳዛኝና አሳፋሪም ነው። የመጀመሪዎቹ (front line fire brigades) ችግር ፈቺ፤ አስታራቂ፤ አንተም ተው አንቺም ተይ ማለት የሚገባቸው ካህናት ናቸው። ፍቅርን፤ ሰላምንና ይቅርባይነትን ማስተማር ዋናው ተግባራቸው ነው። በመሃልቤት ቤተክርሲያንዋ ብትፈርስና ብትበጣበጥ በመንፈሳዊ ሕይወትና በዓለማዊ ፍላጎታቸው አይሞቱ ሞት፤ አይቀጡ ቅጣት፤ አይከስሩ ኪሳራ የሚደርስባቸው እነርሱ ናቸውና።

በከተማችሁ የሚታተመዉ ዘ-ሐበሻ የተባለው ድረገጽ እንዳለው ችግሩ በውይይትና በመደማመጥ ሊታረቅና ሊሰክን የሚችል ነው ያለውን ሃሳብና ምክር እጋራለሁ። ለእምነቴ ካለኝ ፍቅርና ጽናት የተነሳ የሚከተሉትን የመፍትሄ ሃሳቦች ወርውሬ ጽሁፌን ልቋጭ።

የመፍትሄ ሃሳቦች፥
1. ከሁለቱም የተውጣጣ የመፍሔ አፈላላጊ ኮሚቴ (conflict resolution committee) ባስቸኩይ አቐቁሞ ችግሩ በሰላም የሚፈታበትን መንገድ መሻት። በዚህ ቡድን የሚካተቱ ሰዎች በዕድሜአቸው ጠናያሉ፤ ነገሮችን በኣራቱም ማእዘናት መመልከት የሚችሉ፤ ያስተሳሰብ አድማሳቸው ሰፋያለ፤ የህበረሰባችሁ አመኔታና ተቀባይነት የተቸራቸው ሊሆኑ ይገባል፤

2. በቦርዱ አባላት መካከል ያለው አለመግባባት በአፈጻጸም ምክንያት የደረሰ ሲሆን ሁለቱም የከረረ አቁኣም ይዘው የተጋጩ ናቸው። ጉዳቱ ለቤተክርስቲአንዋ፤ ለምእመኑና ለቆምነልት ሃይማኖት ነው። ከላይ እንደጠቀስሁት ቦርዱ የቀረው የስራ ዘመን ስምንት ወራት ብቻ ስለሆነ የቦርዱን አጠቃላይ ኅላፊነት ዝቅ አድርጎ የቤተከርስቲያኑአን የዕለት ተዕለት ተግባር ብቻ እየሰራ የአገልግሎት ዘመኑን እንዲጨርስ ማድረግ። ባስቸኩይ አስመራጭ ኮሚቴ አቋቁሞ አዲስ ቦርድ የማስመረጡን ሂደት (nomination process) መጀመር። ይህ በዚህ እንዳለ ከካህናቱና ከምእመኑ የተውጣጣ ሽማግሌ መርጦ ሁለቱን ተቃራኒ ቡድኖች አቀራረቦ በይቅር ለእግዚአብሄር አስታርቆ ስራቸውን እንዲቀጥሉ ማድረግ፤

3. ከላይ የተጠቀሱት የማይሰሩ ሆኖ ቢገኝ ቦርዱን በሙሉ አውርዶ (ሊቀመንበሩን ጨምሮ) እንባ ጠባቂ ኮሚቴ ( care taker body) በማቋቋም ቀሪውን ስምንት ወር መወጣት። ይህ ኮሚቴ ስምንት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አዲስ ምርጫ አካሂዶ አዲስ ቦርድ አስመርጦ ኅላፊነቱን ለተመራጩ ቦርድ እንዲአስረክብ ማድረግ፤

4. ምናልባት ይህን ለማድረግ ገለልተኛ የሆነ አካል መኖር አስፈላጊ ሊሆን ይችል ይሆናል። ሁለቱም ቡድኖች ጠበቃ ገዝተው ጉዳዩን በፍርድ ቤት ለመቋጨት ይሞክሩ ይሆናል ብዬ እገምታለሁ። በሰሜን አሜሪካ (ካናዳን ጨምሮ) ፍርድ ቤቶች የግብረሰናይ ድርጅቶችን የሚዳኙበት ሁኔት ከንግድ/ግል ድርጅቶች የተለየ ነው። ስለሆንም ጉዳዩን በእርቀ ሰላም እንዲጨረስ በአጽኖት ይመክራሉ ብዬ አስባለሁ። ስለዚህ በሁለቱ ቡድኖች የተቀጠሩት ጠበቆች ገለልተኛ ሆነው ይህን ችግር እንዲፈቱ ያጭር ጊዜ ያማካሪነት (short term consultancy ) ስራ መሰጠት። መተዳደሪያ ደንባችሁ ብዙ ድክመቶች ያሉት መስሎ ይታየኛል። እነኚሁ ጠበቆች አጥነተው የተሰተካከል መተዳደሪያ ደንብ እንዲቀርጹላችሁ ቢደረግ ይበጃል።

በመጨረሻም ምን አልባ ትመግባባት አቅትዋችሁ እርስ በርስ ብትፈርሱ እግዚአብሄርን ከማሳዘናችሁም ባሻገር በእናት ቤተክርስቲአናችን ላይ ጥቁር ጠባሳ ጥላችሁ የምታልፉ መሆኑን አትዘንጉ። የሌሎች ሃይማኖቶች መሳቂያና መሳለቅያ መሆናችሁን ሰከን ባለ ልቡና አስቡት። ለዚህ ሁሉ ካህናት ከመላው ምእመን ጎን መቆም ይጠበቅባቸዋል። አንደኛውን ደግፎ ሌላውን የሚያወግዙ ከሆነ ሌላ ተልዕኮ እንዳላቸው የሚጋለጡበት ይሆናል። የካህናቱን ደመወዝና መኖሪያ የሚከፍለው ምእመኑ እንጅ ቦርዱ እንዳልሆነ ሊገነዘቡ ይገባል። ለሁላችሁም ልቦና ሰጥዋችሁ ቤተከርስቲያኑኣንና ምእመናን ለመታደግ እንድትችሉ እግዚአብሔርና መድኅኒዓለም በእርቅና በሰላም ጎዳና ይምርዋአችሁ።

አቢቹ ነጋ
ታህሳስ 23, 2006

“የህዝብን የነጻነት ፍላጎት አፍኖ እስከ መጨረሻው መቆየት አይቻልም”–ሸንጎ

$
0
0

ከሸንጎ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

ጥር 22፣ 2006

shengo ለ22 አመታት የዘለቀው የህወሀት ኢህአዴግ የግፍ አገዛዝ ዛሬም እንደትላንቱ እድሜውን ለማራዘም ያፈና ተጋባሩን ቀጥሎበታል።

ባለፉት ሳምንታት እና ጥቂት ወራት ብቻ አሳፋሪ በሆነ መልኩ በአረና ፓርቲ አባላት ላይ ድብደባ እና አሰጸያፊ ተግባር ተፈጽሟል። ለምሳሌም ባለፈው ሳምንት ማለትም በጥር 16 ቀን 2006 ዓ/ም በኣቶ ኣስገደ ገ/ስላሴ፣ ኣቶ ኣብርሃ ደስታ፣ አቶ አንዶም ፤ መምህር ፍፁም ግሩም፣ ገዛኢ ንጉሰ እና ሌሎችም የአረና አባላት ላይ በዓዲግራት ከተማ ድብደባ እና አስጸያፊ የሆነ ተራ የዱርየ ምግባርን የሚያንጸባርቅ ክብረነክ ተግባር ተፈጽሞባቸዋል፡፡

ይህ የሆነው የአረና አባላት የገዥው ቡድን የማስፈራራት ዘመቻ ሳይበግራቸው ስርአቱ በመፈጽም ላይ ያለውን ግፍ እና በደል ለትግራይ ህዝብ ለማሰማት የሚያደርጉትን ተጋድሎ ለማጨናገፍ ነው። እጅግ አሳፋሪ የሆነው ጉዳይ ደግሞ፣ ገዥው ቡድን ለዚህ እኩይ ተግባሩ ህጻናትን በማሰማራት የአረናን አባላት በመከታተል እንዲሰድቡ፣ እንዲደበድቡና ተመሳሳይ አሳፋሪ ተግባር እንዲፈጽሙ ማድረጉ ነው።

ኢትዮጵያዊ ባህላችን ህጻናት ታላቆቻቸውን እንደ ወላጆቻቸው አክብረው እንዲያዩ ያስተምራል። ገዥው ቡድን ህጻናትን በዚህ አይነቱ እጅግ ዝቅ ያለ አሳፋሪ ምግባር ውስጥ እንዲሳተፉ ማድረጉ፣ ለአካባቢውም ሆነ ባጠቃላይ ለኢትዮጵያ ህዝብ ባህል ምን ያህል ግድ የሌለው እንደሆነ ያሳያል። በተጨማሪም ገዥው ቡድን ከርሱ የተለየ ሀሳብ ያላቸውን ለማኮላሽት ምን ያህል እንደሚጓዝና በአሁኑ ሳአትም ምን ያህል የሚይዘውና የሚጨብጠው እየጠፋበት እንደሆነ ያመለክታል።

ገዥው ቡድን የትግራይን ህዝብ በቋሚ እስረኛነት አፍኖ ለመያዝ በሚያደርገው መፍጨርጨር ቀደም ባሉ ወራቶችም በመቀለ፣ በክልተ አውላእሎ ፣በሽረ፣ በማይጨው፣ በተምቤን ዓብይ ዓዲ እና ሌሎችም ከተሞች ህዝባዊ ፖለቲካዊ ስብሰባዎች እንዳይካሄዱ እጅግ ስፊ አደናቃፊ ተጋባሮችን ሲያካሂድ እንደነበር ይታወሳል፡፤

ገዥው ቡድን ተቃዋሚውን የማዋከቡን ሩጫ በመላ ሀገሪቱ በስፋት እያካሄደ ሲሆን በቅርቡም በደቡብ የሀገራችን ክፍል አቶ አለማየሁ ለፌቦ የተባሉ የሲዳማ ጭሬ የአንድነት ፓርቲ አባል የፓርቲያቸውን ጠቅላላ ጉባኤ ተሳትፈው ሲመለሱ ያለምንም ወንጀል ለእስር እንደዳረጋቸው ይታወሳል።

የሰማያዊ ፓርቲ አባላትም መሰረታዊ መብታቸውን በመጠቀም ሀሳባቸውን በሰላማዊ መንገድ በሰልፍ ለመግለጽ በሚያደርጉት ሙከራ ተመሳሳይ እንግልት እየገጠማቸው ነው።

የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሽንጎ (ሽንጎ) በአረና፣ በአንድነት፣ በሰማያው ፓርቲ እንዲሁም በሌሎች ላይ በገዥው ቡድን የሚካሄደውን አፈናና የመብት ረገጣ በጥብቅ ያወግዛል። ህጻናትን ለፖለቲካ መሳሪያ መጠቀሚያ ማድረግ እጅግ ህገወጥ እንደሆነ እየገለጥን ይህ አሳፋሪ ተግባር ባስቸኳይ እንዲቆም ሽንጎ ያሳስባል።

ሁሉም ኢትዮጽያውያን መሰረታዊ መብታችንን፣ ሀገራዊ ጥቅማችንን እና አንድነታችንን ለማስከበር ፍርሀትን አስወግደን የጋራ ትግላችንን አጠናክረን እንድንቀጥል ሽንጎው አሁንም ያሳሰባል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ

የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት የፍርድ ቤት ቀጠሮ ለፊታችን ሰኞ መዘዋወሩን ለጠበቆቻቸው በስልክ ተነገራቸው

$
0
0

ከአቡዳውድ ኡስማን

ለጥር 22 ተቀጥረው የመከላከያ ምስክራቸውን ለፍርድ ቤቱ እንዲያቀርቡ የታዘዙት ኮሚቴዎቻች፣ኡስታዞቻችን እና ወንድሞቻችን በቀነ ቀጠሯቸው መሰረት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀነ ቀጠሯቸው መራዘሙን እንደተገለፀላቸው በሰበር ዜና በማህበራዊ ድህረ ገፅ በሆኑት በፌስቡክ እና በቲውተር አድራሻችን ዘግበን ነበር።
muslim dim
ፍርድ ቤቱ ቀነ ቀጠሮውን ማራዘሙን በስልክ ለጠበቆቹ ማሳወቁን ፣ተለዋጭ ቀነ ቀጠሮም በውል እንደማይታወቅ እና ጠበቆቻቸውም የፊታችን ሰኞ ሊሆን እንደሚችል መግለፃቸውን አስረግጠን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ፍርድ ቤቱ ህጋዊ የፍርድ ቤት አካሄዱን ሙሉ በሙሉ በመጣስ በተደጋጋሚ ለጠበቆቹ ስልክ በመደወል የፍርድ ቤቱ ቀነ ቀጠሮዎች መራዘማቸውን ሲገልፅ የቆየ ሲሆን የጥር 22 ቀነ ቀጠሮውም በተመሳሳይ ሁኔታ በስልክ በመደወል ትክክለኛውን ቀነ ቀጠሮ እንደሚያስታወቀ በዘገብነው መሰረት ፍርድ ቤቱ ለኮሚቴዎቻችን ጠበቆች በመደወል ተለዋጭ ቀነ ቀጠሮውን ለፊታችን ሰኞ ጥር 26 መስጠቱን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

ኮሚቴዎቻችን ኡስታዞቻችን እና ወንድሞቻችን ወደ ፍርድ ቤት ለመጓዝ ቢዘጋጁም ቀነ ቀጠሮው መራዘሙን ከቤተሰቦቻቸው እንደ አዲስ መስማታቸውን ምንጮች ዘግበዋል፡፡

የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ቀነ ቀጠሯቸው መቀየሩን ያላሳወቃቸው ሲሆን ቤተሰቦቻቸው ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በመሄድ ቀነ ቀጠሮ በውል ላልታወቀ ጊዜ እንደተዘዋወረ እንዳሳወቁዋቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡

ቤተሰቦቻቸውም የፍርድ ቤት ሂደቱን ለመከታተል በጠዋቱ ወደ ፍርድ ቤቱ አምርተው የነበረ ቢሆንም ቀነ ቀጠሮ መራዘሙን ከጠበቆቹ ተደውሎ እንደተነገራቸው ነው የገለፁት፡፡

ፍርድ ቤቱም ለጠበቆቻቸው ስልክ በመደወል ቀነ ቀጠሮ ለፊታችን ሰኞ ጥር 26 መዛወሩን ካስታወቀ ቡሃላ ጠበቆቻቸው ለፊታችን ሰኞ መራዘሙን ለታሳሪዎቹ ማሳወቃቸውን ምንጮች ዘግበዋል፡፡


የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት መተማ አካባቢ ጥቃት ፈጸምኩ አለ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር የአገራችን ኢትዮጵያን ዳር ድንባር ለሱዳን ለማስረከብ ሽር ጉድ እያለ የሚገኘውን የወያኔን አገዛዝ ጸረ-አገርና ጸረ-ህዝብ እንቅስቃሴ በመቃወም በመተማ አካባቢ ልዩ ስሙ ዘባጭ ባህር በተባለ ቦታ ከወያኔው 24ኛ ክፍለ- ጦር ጋር በጥር 21- 2006 ዓ.ም ከቀኑ 6 ሠዓት ላይ ባደረገው ውጊያ 14(አስራ አራት) ገድሎ 12(አስራ ሁለት) ማቁሰሉን አርበኛ ኑርጀባ ለዘ-ሐበሻ በላከው መረጃ አስታውቋል።

(የአርበኞች ግንባር ሠራዊት - ፎቶ ከፋይል)

(የአርበኞች ግንባር ሠራዊት – ፎቶ ከፋይል)

“በመተማና አካባቢው በተደጋጋሚ በአርበኛው ጥቃት እየተፈፀመበት የሚገኘው የወያኔው ቅጥረኛ ሠራዊት ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው እየፈረጠጠ መሆኑ ሲታወቅ በደረሰበትም ጉዳት ማካካሻ ይሆነው ዘንድ ሰላማዊውን ነዋሪ በእናንተ ምሽግነት ነው እየተመታን ያለነው በሚል እንግልት እያደረሱበት መሆኑ ታውቋል።” የሚለው የአርበኛ ኑርጀባ ዘገባ “በተያያዘ ዜናም በጭልጋ ወረዳ ጫቁ የተባለ አካባቢ ነዋሪዎች ከብት፣በግና ፍየል በአካባቢው የወያኔ ታጣቂዎች እየታረደ እየተበላባቸው መሆኑ ታውቋል” ብሏል።

አርበኛ ኑርጀባ ዘገባውን ቀጥሎ “በዚሁ አካባቢና አጎራባች ወረዳዎች የወያኔው ተላላኪዎች ተደጋጋሚ ንብረትን የመዝረፍ ሂደት የተቆጣው ነዋሪ ለምንድን ነው ንብረታችንን የምትዘረፉት ምን አደረግናችሁ ብለው ሲጠይቁ እናንተ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ደጋፊዎች ፣መንገድ መሪዎች እንዲሁም ስንቅ አቀባዮች ናችሁ የሚል ምክንያት ሰጥጧቸዋል። ሕዝቡም እኛ የአርበኛው አባልም ደጋፊም አይደለንም ከፈለጋችሁ እነሱን ተከታትላችሁ መዋጋት ትችላላችሁ እኛን ምን አድርጉ ነው የምትሉ? ሲሉ ምሬታቸውን ቢገልፁም እንግልቱ እንዳላበራ” ከአርበኛ ኑርጀባ መረጃ መረዳት ተችሏል።

ዘገባው ቀጥሎም “የወያኔው ተላላኪዎች በሕዝቡ ላይ እያደረሱ ያለው እንግልት ያስቆጣቸው ብዛት ያላቸው የአካባቢው አርሶ አደሮች የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኛች ግንባር ሠራዊትን እየተቀላቀሉ መሆኑን አስታውቋል።” ብሏል።

“በሌላ ዜና የአማራ ክልል ፀጥታ ዘርፍ ሃላፊ የሆነው ሙሉጌታ ወርቁ የተባለው ግለሰብ በክልላችን ቢሮዎች በሙሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰዎች ተሰግስገዋል በሚል ምክንያት ሰሞኑን በየወረዳው ፅ/ቤት የማፅዳት ዘመቻ በሚል ከፍተኛ ስብሰባ እያደረገ ነው” ሲል አርበኞች ግንባር አስታወቀ። ግንባሩ ለዘ-ሐበሻ በላከው ዜና ” የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ተደጋጋሚ ጥቃት እያሰጋው የመጣው ሆድ አደሩ የአማራው ክልል ባልስልጣናት ሕዝቡን በተለያየ ምክንያት ማሰቃየቱ ሳያንሰው የራሱ ታማኝ የሆኑ ቅጥረኞቹ ላይ እምነት በማጣት የሚያደርገውም የጠፋበት መሆኑ ግልፅ እየሆነ መምጣቱን አመላካች እንደሆነ የዚሁ ችግር ሰለባ ልንሆን እንችላለን ያሉ ወገኖች ጠቁመዋል። በይበልጥ አማራዉን በማይወክሉት የወያኔ አገልጋዮች እየተሰቃየው ያለው ሕዝቡ ሲሆን ፣ እነሱም ሕዝቡ ከጎናችው አለመኖሩን በመረዳታቸው የተፈጠረው ክፍተት በፈጠረባቸው ጭንቀት የመንግስት ሠራተኛውንም ሆነ ነጋዴውን ማመሱን እንደቀጠሉበት ለማወቅ ተችሏል።” በማለት ዘግቧል:፡

የአርበኞች ግንባር ሰራዊት በመተማ አካባቢ አደረስኩት ስላለው ጥቃት ከመንግስት በኩል የተሰጠ ማስተባበያም ሆነ መረጃ የለም።

በጎንደር ክ/ሃገር ሳንጃ ወረዳ የልዩ ሃይል አዛዥ ሻለቃ ቀለሙ ክብረት መገደላቸው ተሰማ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በጎንደር ክ/ሃገር ሳንጃ ወረዳና አካባቢው ሕዝብን ሲያሰቃይ ነበሩ የተባለት የልዩ ሃይል አዛዥ ሻለቃ ቀለሙ ክብረት መገደሉ ተሰማ። የአርበኞች ግንባር ለግድያው ሃላፊነቱን ወስዶ “ግለሰቡ የተገደለው በጥር 21-2006 ዓ.ም ከቀኑ 12 ሰዓት ላይ በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰርጎ ገቦች ማሰሮ ደንብ የተባለ ቦታ በጥይት ተደብድቦ ቆስሎ ወዲያውኑ ወደ ጎንደር ቸቸላ ሆስፒታል ቢወሰድም በማግስቱ ማለትም በጥር 22-2006 ዓ,ም ህይወቱ አልፏል።” ብሏል።

(የአርበኞች ግንባር ወታደር - ፎቶ ፋይል)

(የአርበኞች ግንባር ወታደር – ፎቶ ፋይል)

እንደ አርበኞች ግንባር ገለጻ ከሆነ “ይህ ግለሰብ በወረዳው የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን የአርበኞች ደጋፊ ናችሁ በሚል ሲያሰቃይ የነበረ ሲሆን፣ ብዙ ንፁሃን ግለሰቦችን በድርጅቱ ደጋፊነት ስም እየፈረጀ እንደገደለ፣ እንዳሰረና እንዲሰደዱ ሲያደርግ የነበረ መሆኑ ይታወቃል ። ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ግለሰቡ ከድርጊቱ ታቅቦ ሰላማዊ ኑሮውን እንዲኖር ካልሆነ ግን አስፈላጊው እርምጃ እንደሚወሰድበት የፅሁፍ መልዕክት የደረሰው ቢሆንም ሊታረም ባለመቻሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰርጎ ገቦች እርምጃ እንዲወስዱበት ተደርጓል።” ብሏል።

(የአርበኞች ግንባር ሠራዊት በምረቃ ላይ - ፎቶ ከፋይል)

(የአርበኞች ግንባር ሠራዊት በምረቃ ላይ – ፎቶ ከፋይል)


“በጎንደር አካባቢ ምንም አይነት ወታደራዊ እርምጃ በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት ሲወሰድ የአካባቢውን ሕዝብ ማንገላታቱ የተለመደ ቢሆንም ሻለቃ ቀለሙ ክብረት ከሞተበት ከትናንት ጀምሮ ግን በህዝቡ ከፍተኛ ስቃይ እያደረሰበትና ገዳዮቹን ታውቃላችሁ እናንተ ናችሁ እየደበቃችሁና ቀለብ እየሰፈራችሁ የምታስጨርሱን በሚል ብዙ ሰዎች እንደታሰሩ ታውቋል።” የሚለው የአርበኞች ግንባር ዜና “የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ወታደራዊ መምሪያ በበኩሉ ወደፊትም ቢሆን ወያኔና ተላላኪዎቹን ከዚህም በከፋ ሁኔታ አይቀጡ ቅጣት እንደሚቀጣ አስታውቆ ሕዝቡም ከመሬቱና ከንብረቱ እየተፈናቀለ መኖሩ ያበቃ ዘንድ ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት ጎን በመሰለፍ ይህን አፋኝ ስርዓት ለመገርሰስ የበኩሉን አስተዋፅዖ ማበርከት እንዳለበት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን” ብሏል።

በዚህ ዜና ዙሪያ የመንግስትን ምላሽ ለማካተት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ይድረስ ለዶክተር ታደሰ ብሩ –ባሉበት!

$
0
0

ነፃነት ዘለቀ (ከአዲስ አበባ)
tadesse

ከምቸገርባቸው ነገሮች አንዱ ለምጽፋቸው መጣጥፎች ርዕስ ማውጣት ነው፡፡ አንዳንዴ ርዕሴና በጽሑፌ ውስጥ የማነሳው ጉዳይ አልገናኝ ይሉብኛል – ልክ እንደአሁኑ፡፡ ዛሬና አሁን ለዶክተር ታደሰ ብሩ የምለው አንድም ነገር የለኝም፡፡ ነገር ግን እሱ አሁን በትምህርት ብልጭታ የኢሳት ቆንጅዬ ፕሮግራሙ ላይ ባነሳው የእስታስቲክስ ጉዳይ እኔም አንድ ቀን እተነፍስበታለሁ ብዬ እዝት ስለነበር ያን ስላስታወሰኝ ርዕሴን ለሱ መታሰቢያ አደረግኋት፡፡ ደርባባው ታዱ የሥራ-ፈት ኤፍኤሞቻችንን ቋንቋ ልጠቀምና “እወድሃለሁ፤አከብርሃለሁ” – ባለህበት ይመችህ፡፡(ኤፍ ኤሞችን የማልወዳቸው አዘናጊ ስለሆኑ ነው፤ በተለይ ወጣቱን በእግር ኳስ ጨዋታ ሱስ እያሰከሩ፣ በአይሬ የጫት ዙርባ እያመረቀኑ፣ በፆታዊ ወሬ ምድረ ሴሰኛን እያነሆለሉ፣ በትርኪ ምርኪ ወሬ ማኅበረሰቡን እያጃጃሉ ወያኔያዊ ተልእኮኣቸውን በመወጣት ላይ ስለሚገኙ ነው፡፡ በተለይ ያቺ ሙግድ አፍማ … ቆይ ብቻ፣ ይንጋማ! ልክ ልኳን ያልነገርኳት እንደሁ ቁጭ ብዬ ተኝቻለሁ፡፡)
በዚያ ላይ የወያኔ የስለላ መረብ ጋማ ኢንተርናሽናል ከተባለ የእንግሊዝ የስለላ ቴክኖሎጂ አፍላቂ ባለዬ ድርጅት በገዛው አንድ የቴክኖሎጂ ውጤት የታዴ ኮምፒውተር በስለላ ቫይረስ መጠቃቱን በዚያው ኢሳት የዜና ዕወጃ ስለሰማሁ በእግረ መንገድ እግዜር ያጽናህ ለማለትም ነው፡፡ እነዚህ ወያኔዎች ግን በርግጥም ይሠሩትን አጥተዋል ማለት ነው – ሶልዲ አሰከራቸውና እሚሆኑትን አሳጣቸው፡፡ እንዴት ነው ነገሩ? እኛ እዚህ ኑሮ እንትኗን አፈንድዳብን እምንቀምሰውንና እምንልሰውን አጥተናል፤ እነሱ ከድሃው ሕዝብ በሚዘርፉት ገንዘብ ወንበራቸውን ለማስጠበቅ በውድ ዋጋ የስለላ ሶፍትዌሮችን ይገዛሉ – ዓለመኞች ናቸው፤ ግፈኞችም ጭምር! ይህን ዕኩይ ተግባራቸውን ያጋለጠው ፕራይቬሲ ምንትስ የተባለው ድርጅት እንደታዘበው እነዚህ ሰዎች ከድሃ ሕዝብ ጉሮሮ እየነጠቁ ይህን ውድ ዕቃ መግዛታቸው በርግጥም የገቡበት ክፉ አጣብቂኝ ቢኖር ነው ብሎ መጠርጠር ይቻላል፡፡ አባታቸው ሰይጣን ይሁናቸው ከማለት ውጪ ምን ይባላል?
(በነገራችን ላይ ለዕድገታችን ቀን ከሌሊት የሚለፉልን የአፍሪካ መሪዎች በዚህ ሣምንት አዲስ አበባ ላይ ለስብሰባ ተቀምጠዋል፡፡ መንገድ እየተዘጋጋ መንቀሳቀስ አቅቶናል፡፡ እነሱ ባይኖሩ ኖሮ – ባይሰበሰቡልንም ኖሮ ምን ይውጠን ነበር? ስብሰባውን እየተው ሸቀጥ የሚያጋብሱም ገጥመውኛል፤ ለሴትና ለሸቀጥ እንዲሁም በመብል በመጠጥ ከርሳቸውን እየሞሉ በጭቁኖች ገንዘብ እንደልባቸው ለመዝናናት የሚመጡት ይበልጣሉ – ሌላ ምን ቁም ነገር ሊሠሩ ዱሮውንስ፡፡ ፍሬፈርስኪ ለሆነ ስብሰባ ከአፍሪካ ድሆች በግድ የሚዘረፈው ገንዘብ አለመላው ሲከሰከስ ለሚታዘብ ጤናማ ወገን ያሳዝናል፡፡ አንድ የሰማሁት አስገራሚ ነገር አለ፤ እነዚህ የአፍሪካ አለኝታዎች ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ የአፍሪካ ኅብረት የተባለው ሥራ-ፈት ድርጅት ከግለሰቦችና ከድርጅቶች ለእንግዶቹ ማጓጓዣ መኪና ይከራያል፡፡ ያስገረመኝ ነገር ታዲያ ወያኔ የሠረገበት ይህ ድርጅት መኪና የሚከራየው ከወያኔዎች እንጂ ከሌላ አለመሆኑ ነው፡፡ ሾፌር የሚቀጠረውም ከወያኔው ዘውግ ብቻ እንደሆነ ውስጥ ዐዋቂ ሰሞኑን አረዳኝ፤ ለዚህች ለሣምንት ሥራም አድልዖ ይፈጸምባታል፡፡ ገቢው ከፍተኛ ስለሆነ ለማንም ከወያኔዎች ውጪ ለሆነ ግለሰብና ድርጅት አይሰጥም፡፡ እነሱው በነሰው ያለውን ሁሉ ይቀራመቱታል፡፡ አሁንስ የበይ ተመልካችነታችን ጠርዝ ለቀቀ፡፡ አይ፣ በጣም ተናደድኩ፡፡
እንደአንዳንዶች ሃሜት በርግጥም ይሉኝታ ከሰሜን ተጠራርጎ ወጥቷል ማለት ነው? ሰሜን ተወልጃለሁ፤ ሰሜን አድጌያለሁ፤ ሰሜን ኖሬያለሁ፤ ያኔ እንዲህ ያለ ይሉኝታቢስነት አላየሁም፡፡ አሁን ምን እንደመጣብን አላውቅም፤ ይህ ዘረኝነት ከምን እንደመነጨ መመርመር አለበት፡፡ ዐይን ያወጣ ዘረኝነት ነው እየታዬ ያለው፡፡ መሌ ገሞራው ስለህዳሴው ግድብ አንድ ወቅት እንዲህ አለ፡- “መሃንዲሶቹም እኛው፤ የገንዘብ ምንጮቹም እኛው፤ ምናምንቴዎቹም እኛው …”፡፡ እኔ ደግሞ እላለሁ፡- ከሳሾቹ እነሱ፣ ዳኞቹ እነሱ፣ ፍርድ አስፈጻሚዎቹ እነሱ፤ ሻጮቹ እነሱ፣ ገዢዎቹ እነሱ፤ ባለሥልጣኖቹ እነሱ፣ በፍጥነትና በጥራት ተስተናጋጆቹ እነሱ፤ ጨረታ አውጪዎቹ እነሱ፣ ጨረታ ተወዳዳሪዎቹ እነሱ፣ ጨረታ አሸናፊዎቹ እነሱ፤ ኮንታራት ሰጪዎቹ እነሱ፣ ኮንትራት ተቀባዮቹ እነሱ፣ ኮንትራት አዳሾቹ እነሱ፤ ሕንጻ ተቋራጮቹ እነሱ፣ ሕንፃና የገበያ ማዕከላት ባለቤቶቹ እነሱ፣ ፋብሪካና ኢንዱስትሪ ገምቢዎቹ እነሱ፣ አየር ኃይሎቹ እነሱ፣ አየር ወለዶቹ እነሱ፣ አየር አብራሪዎቹ እነሱ፤ ሹዋሚዎች እነሱ፣ ተሸዋሚዎች እነሱ፣ ሰላዮቹ እነሱ፣ ተሰላዮቹ እኛ፤ ባለገንዘቦቹ እነሱ፣ ከግብርና ከቀረጥ ነፃ ሆነው የሚነግዱ እነሱ፣ ግምባርና ኪስ ቦታዎችን እያደኑ የሚይዙና የሚሸጡ የሚለውጡ እነሱ፣ ከሕግ በላይ ሆነው ማንም ላይ እሚያሽቃንጡ እነሱ፣ ገና ጡት ሳይጥሉ ቱጃር ሆነው በመቶ ሺዎች የሚገመት ብር በአንድ አዳር በየዳንኪራ ቤቱ ሲከሰክሱና በገንዘባችን ሲሸራሞጡ የሚያድሩ እነሱ፣ ጠግበው የሚዘፍኑና እንደኬንያ ማታቱ አደንቋሪ ሙዚቃ ሌሊት ከየቤታቸውና ከየመኪኖቻቸው ሙዚቃ እስከጣራ እየከፈቱ እንቅልፍ የሚነሱን እነሱ፣ … በችጋርና በችግር የምናንቋርር እኛ፣ የነሱን ዕዳ የምንከፍል እኛ፣ የምንታሠር የምንሰደድ እኛ፣ ከትምህርትና ከዕውቀት ዓለም ወጥተን ወደምድራዊ ሲዖል የተጣልን እኛ፣ የምናቀምሳቸውን ምናምኒት አጥተን ልጆቻችንን በርሀብ አለንጋ የምናስገርፍ እኛ፣ የትውልድ መርገምት የተሸከምን እኛ፣ … አፄ ቴዎድሮስ ያናደዱትን ካህናት ሰብስቦ “አንድሽ አንባቢ አንድሽ ተርጓሚ ሆነሽ መንግሥቴን ታውኪያለሽ…” ያለው ለካንስ ወዶ አልነበረም፡፡ ወያኔም የተለያዬ ካባ እየለበሰች አባት ዳኛ ልጅ ቀማኛም እየሆነች በኢትዮጵያ ላይ ታሪካዊ ሚናዋን መጫወቷን ቀጥላለች፡፡ ማን ተይ ብሏት? ማንንስ ፈርታ? (አንዱ አንዱን “ሚስትህ ወንድ ወለደች?” ብሎ ቢጠይቀው “ማንን ወንድ ብላ!” አለው አሉ፡፡) ወያኔ እያጠራቀመችው ያለችው ታሪካዊ ዕድፍ የሚያመጣባትን ዕዳ ግን ከፍላ የምትጨርሰው አይመስለኝም፡፡ የፈጣሪ የጽዳት ቀን ሲመጣ ምን ይውጣት ይሆን? ክበበው ገዳ፡- “ወዮልሽ አንቺ ኮሜዲ ሆይ…” ያለው በተወራራሽ ለወያኔም ይሠራል፡፡
(Literally, almost all privileges and benefits that Ethiopia has in her meager store, within or without her ever-shrinking border, willy-nilly belongs to TPLFites; Oh, shame on them! What a curse has descended upon these crooked creatures, and by extension, upon us, the oppressed majority? I wish I had a chance to examine the essence of the gray mud they are supposed to carry in their skull; I hope its content must be the same as that of the hyenas’ and pigs’ brain. They have fallen in love with MONEY and have gone crazy with this blind love. There is no JOKE; they do everything and anything to get MONEY. They have already evicted most of OTHERS from any ETHIOPIAN income generating means. They have convinced themselves that they are the sole owners or possessors of this ill-fated nation. Wonderful! They have controlled virtually everything. There is a rumor that some of them have gone as far as owning their own minting machine which is why the circulation of Birr has become uncontrollably rampant especially in the hands of TPLFites; am not lying; what I am talking is the stark truth. Most of them are joining the camp of billionaires, while on the other hand, we the majority of OTHERS are obliged to join the camp of absolute poverty where there is nearly nothing for survival. The gap between the rich (in this specific case the TPLFites) and the poor is beyond explanation; there is no word (of any language on earth) to explain the discrepancy between THEM and US. Life in Ethiopia is skyrocketing in an alarming manner. The life style of THEIRS and OURS, i.e., the difference between THEM and US, is terribly shocking. Since the time this dichotomy, the ‘THEM’ and ‘US’ duality, has come onto the surface of this country, the ‘THEM’ group has boldly been committing all sorts of crimes and mischievous acts under the sun to impoverish the ‘US’ bloc.)
ታደሰ ብሩ በግሩም ሁኔታ እያቀረበው የነበረው አንዱ ሀገራዊ ችግር በእስታትስቲክስ ረገድ ሀገራችን ቀደም ካለ ጊዜ ጀምሮ የምታሳየውን “ዕድገት” ነው፡፡ እናንተዬ በርሀብና በጦርነት እንዲሁም አረመኔና አውሬ መንግሥታትን በማፍራትና በመሸከም ብቻ ሳይሆን በውሸትም አንደኛ ሳንሆን እንቀራለን? ምን ዓይነት ጉድ ነው? ይሄ ቤተ መንግሥት አንድ መቶና ሁለት መቶ ሰባቶችን ካልተጠበለ ከገባበት አባዜ በቀላሉ የሚፈወስ አይመስለኝም፡፡ አንድ የበቃ ባህታዊ ተፈልጎ ድርሣነ ሚካኤልን ይድገምበትማ እባካችሁ፡፡ አድምጥ ልንገርህ፡-

ደግሞ ለውሸት አለው ድካ፤
አምሳ ሰው ገዳይ ባንድ አማሪካ፡፡

ይህ ሥነ ቃል የቋንቋ መምህራን ስለ ግነት ሲያስተምሩ በረጂም ዘመን ትውፊት ከደለበው ቃላዊ ሥነ ጽሑፋችን የሚመዙት አንዱ የንግግር ማጉሊያ ፈርጥ ወይም የጨዋታ ማድመቂያ ሰበዝ ነው፡፡ እውነት ነው – ውሸት ድካ ወይም ድንበር የለውም፡፡ ድንበሩ የተናጋሪው ኅሊና ብቻ ነው፡፡ ኅሊናውን መጠቀም የማይፈልግ ወገን፣ ኀሊናውን ለገንዘብ ወይም ለጥቅምና ለተለዬ ዓላማ የሸጠ ሰው እውነትን ሽምጥጥ አድርጎ ሲክድ ቅር አይለውም – የበሽታ ከሆነ እንዲያውም አንዳንዴ ምናልባትም ሁልጊዜ፣ መዋሸቱን ላያውቀው ይችላል – መረገም ነው፡፡ መዋሸትም ይባል ማጋነን በግለሰብ ደረጃ የጥፋት አድማሱና ክብደቱ ቀለል ስለሚል ምንም አይደለም ሊባል ይችላል፤ በሀገር ደረጃ ሲሆን ግን የሀገርን ኅልውና እስከመፈታተን የሚደርስ አደጋና ችግር ሊፈጥር ይችላል፤ በኛ ሀገር በተለይ በመንግሥት ደረጃ መረጃን ማንሻፈፍና በቤተ ሙከራ የተፈበረኩ ቁጥሮችን በሚዲያ መዝራት እንደሱስ ሳይጣባን አልቀረም፡፡ “እውነትን ተናግሮ እመሸበት ማደር” የ‹ፋራው ዘመን› ብሂልና የ‹ፋራዎች› ተረት ሆኗል፡፡
ውሸት ዓይነቱ ሊለያይ ቢችልም ሁሉም ውሸት እውነትን ለማፈን እስከዋለ ድረስ ማንም ይዋሸው ማን ያው ውሸት ነው፤ ጉዳቱም ከፍተኛ ነው፡፡ በግለሰብ ደረጃ እኔም አንተም እንዋሻለን – ቀላልም ከባድም ውሸት፡፡ “እኔ አልዋሽም” ብሎ የሚመፃደቅ ሰው ካለ እርሱ የመጨረሻው ውሸታም ነው – ግን ስንዋሽ መልክ ውሸታችን መልክ ያለው እንዲሆን መጣር የሚኖርብን ይመስለኛል – እንደወያኔና ሚዲያው የለዬለት ቀዳዳና ቱሪናፋ መሆን አይኖርብንም፡፡ በልማድ ለደግ ነገር – ለምሳሌ የተጣሉ ሰዎችን ለማስታረቅ – መዋሸት መልካም እንደሆነ ሲያንስ ለክፋት እንደማይሰጥ ሰዎች ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡
እዚህ ላይ በኩሸት፣ በውሸትና በእውነት መካከል ያለውን ልዩነት ልብ ማለት ሳያስፈልግ አይቀርም፡፡ ኩሸት ትንሽ እውነት ይዞ ምናልባትም ከባዶም ተነስቶ አንድን ሰው ማጋነን ወይም ማሽበልበል ነው – ለምሳሌ ባልዋለበት ጦር ሜዳ እንዳሸነፈ፣ ባልታጠቀው መሣሪያ ልክ እንደሶምሶን(ሳምሶን) መቶዎችን እንዳረገፈ፣ ወዘተ. በመኳሸት ፈሪን እንደጀግና፣ ንፉግን እንደቸር፣ ጨካኝን እንደሩህሩህ የሚያደርጉበት ሥነ ምግባራዊ ብልሽት ኩሸት እንደሚባል መምህራን ይናገራሉ፡፡ በመሠረቱ ውሸትም ኩሸትም በብዙ ነገር ይመሳሰላሉ፡፡ ጊዜ ለመቆጠብ ወደ ሀገራችን ይሉኝታቢስ እስታትስቲክስ እንለፍ፡፡

በመንጌ ጊዜ ነው፡፡ መንጌ ገሞራው በኢትዮጵያ ያለው እራሽ መሬት (arable land) ምን ያህል እንደሆነ ተጠንቶ ይቅረብልኝ ይልና ለግብርና ሚኒስቴር ትዕዛዝ ያስተላልፋል፡፡ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱም በተዋረድ ይህን ትዕዛዝ ለአሥራ አራቱም ጠቅላይ ግዛቶች ይልክና በቶሎ ተጠንቶ እንዲቀርብለት ያዛል፡፡ ከየክፍለ ሀገሩ “መረጃው” ቀረበ፡፡ ማዕከላዊ ፕላን ይባል በነበረው የስብሰባ ቦታ የሚኒስትሮች ጉባኤ ይዘጋጃል – ጥቁሩ ነብር አራስ ሲሆን እፊቱ የሚገኝን አሽትሬይና እስክርቢቶ በደመ ነፍስ እያነሣ ወዳናደደው ባለሥልጣን ይወረውር በነበረበት ዘመን መሆኑ ነው፡፡ የግብርና ሚኒስትሩ ተራው ይደርስና ሪፖርቱን በንባብ ማሰማት ይጀምራል፡፡ … ሰውዬው በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን ለእርሻ ተስማሚ የሆነ የመሬት የቆዳ ስፋት ሲናገር ከሞላ ጎደል ሁሉም ተሰብሳቢ በሣቅ ይፈነዳል፡፡ ለካንስ በቀረበው እስታትስቲካዊ መረጃ መሠረት ከየጠቅላይ ግዛቱ የመጣውና አንድ ላይ የተደማመረው ሊታረስ የሚችለው የመሬት ስፋት ከጠቅላላው የሀገሪቱ የቆዳ ስፋት በልጦ ኖሯል! የኛ አስታስትስቲክስ እንግዲህ እንዲህ ነው፡፡ “የኛ ስታይል እንዲህ ነው!” የሚል የቀልድ ዘፈን አለ፡፡ ያስ ዱሮ ነው፡፡ አሁን ብሶ ቀጠለም አይደል? ይሄ ቆርጠህ ቀጥል የምንለው የውሸት ሀድራ ከመንግሥታችን እንዲወገድ በርትተን እንጸልይ ግዴላችሁም፡፡ ግን ግን እኮ ያልዘሩት አይበቅልምና እኛም እንደነሱው ቆርጠህ ቀጥል እንሆን እንዴ?
በቁሙ የሞተ የእስታቲስቲክስ መሥሪያ ቤት ያላት ኢትዮጵያ ብቻ ለመሆኗ ሌላ ባያውቅ እኞች እናውቃለን፡፡
በግንቦት 97 ምርጫ የኢትዮጵያ ሕዝብ በብዛት ወጥቶ መሪዎቹን የመረጠበት ወቅት ነበር – የምርጫውን ውጤት ያልተቀበለው ወያኔ ሥልጣኑን በኃይል እንደያዘ ቀጠለ እንጂ፡፡ ያኔ በወያኔ መንግሥት የቀረበው የመራጭ ብዛት 26 ሺህ አካባቢ ነው፡፡ ውሸት ነበር፡፡ ውሸት መሆኑን የምንረዳው የቀጣዩን የ2002ዓ.ም ምርጫ ተመዝጋቢ ቁጥር ስናይ ነው፡፡ በ2002 መረጃን መፈብረክ ተፈጥሮው የሆነው ወያኔ ለምርጫ የተመዘገበውን የሕዝብ ቁጥር 32 ሺህ አደረሰውና አሣቀን – እኔ ጥርሴን ተወቅሬ ነበር በሣቅ የፈነዳሁት፡፡ ይታያችሁ – ሕዝብ በነቂስ በወጣበት ምርጫ የተመዝጋቢው ቁጥር አነሰ፡፡ ሕዝብ ተስፋ ቆርጦ እቤቱ በተሰበሰበበትና ከወያኔው ጋር በጥቅምና በዓላማ የተቆራኙ አንዳንድ ዜጎች ውር ውር ባሉበት የምዝገባ ወቅት ቁጥሩ ተነረተና 32 ሺህ ደረሰ፡፡ ምን ትሉታላችሁ? የእስታትስቲካዊ መረጃው ሲነፋ(ሲያብጥ) ወያኔን የሚጠቅም ከሆነ ነፊዎቹ አንድም የይሉኝታ አጥር ሳይገድባቸው ሰማይ ያደርሱታል፤ ትዝብት ግዛዕምዛ አያውቁም፡፡ ዋናው ዓላማቸው የላይኞቹን ማስደሰት ብቻ ነው፡፡ የእስታትስቲክሱ መረጃ መጫጫት መንግሥታቸውን የሚያስደስት ከሆነ ደግሞ ለምሳሌ “ከመቀሌ አዲስ አበባ ያለው ርቀት መቶ ሜትር ነው” ብለው በዓይነቱ ልዩ የሆነ መረጃ እስከመስጠት በሚደርስ ድፍረት አዲስ እስታትስቲክስ ከመፍጠር አይመለሱም – “ዋሽ ቢሉኝ እዋሻለሁ፤ ንፋስ በወጥመድ እይዛለሁ” ያለው ባላገር እንዴት ብልህ ነበር፡፡ አንዱ ወያኔን በውሸት ፈጠራ የሚስተካከል ልጅ ደግሞ አባቱን “አባዬ፣ እስኪ ውሸት አስተምረኝ” ብሎ ይጠይቀዋል አሉ፡፡ አባትም በእሺታ ይቀበለውና ማስተማሩን ሊጀምር “ልጄ፣ እዚያ ሰማይ ላይ በነጫጭ በሬዎች ሰዎች እህል ሲያበራዩ ይታዩሃል?” ይለዋል ወደሰማዩ አንጋጥጦና ሌባ ጣቱን ወደተባሉት ሰማይ ላይ እህል ወደሚወቁት ሰዎች ቀስሮ፡፡ ልጅም ቀበል ያደርግና “ውይ ውይ አባዬ …” ብሎ ይጮሃል – ዐይኖቹን በእጆቹ ከድኖ፡፡ አባት ይደነግጥና “ምን ሆንክ ልጄ ምን ነካህ” ይለዋል፡፡ የውሸት ሥልጠና ኮርስ ከመመዝገቡ ትምህርቱን የጀመረው ታዳጊ ወያኔ “ውይ አባዬ፣ የጭዱ ብናኝ ዐይኔ ውስጥ ገባ!” ይላል፡፡ አባትም “አሃ፣ አንተንማ ውሸት ማስተማር አልችልም፤ ከኔስ በልጠህ የለም እንዴ” ይለውና ኮርሱን ‹ድሮፕ› አድርጎ የኤግዘምሽን ቅጽ እንዲሞላ ይመክረዋል – እንዲህ እየተቀላለዱ ነው የወያኔን ዘመን ሸውዶ ማለፍ ወንድምዬ ፡፡ እባክህን በነካ እጄ አንድ የወያኔን ባሕርይ የሚያሳይ ሌላ ረቀቅ ቀልድ ልንገርህና ትንሽ ዘና በል፡፡ …
አንድ ጉልበተኛ ጨቡዴና አንድ የኔ ቢጤ ኮሣሣና ፈሪ የሆኑ ሁለት ጓደኛሞች ወደ አንድ ቦታ በመጓዝ ላይ እንዳሉ መንገዳቸው ላይ አንድ ጥቁር ነገር ቁጭ ብሎ ከሩቅ ያያሉ፡፡ ይሄኔ ጨቡዴው “አየኸው ያንን በግ?” ይለዋል – ለአቅመ ደካማ ጓደኛው፡፡ ፈሪ ጓደኛም “የቱን በግ?” ብሎ ይጠይቀዋል፡፡ “እዛ ጋ ቁጭ ያለው ጥቁር በግ” ይለዋል እሱ ከሩቅ አይቶ ከነምንነቱ የለዬውን ጥቁር በግ ጓደኛው ከነአካቴው ምንም ነገር አለማየቱን ተገንዝቦ በመደነቅ፡፡ “እንዴ፣ አሞራውን ነው እምትለኝ?” ይለዋል፡፡ “የምን አሞራ አመጣኽብኝ! በግ ነው እንጂ” በማለት ጡንቻውን ጭምር እያሳዬ በኃይል ሊያሳምነው ይሞክራል፡፡ በዚህ መሀል ወዳጨቃጫቂው ነገር እየቀረቡ ሲሄዱ ያ በጉልበተኛው ጓደኛ ጥቁር በግ የተባለው ነገር ይበራል፡፡ ይሄኔ ደካማ ጓደኛ “ይሄው፣ በግ አይደለም – አሞራ ነው አላልኩህም? በረረልህ፡፡ ” ቢለው “በረረም አልበረረም በግ ነው ብዬሃለሁ በግ ነው!” ይልና ዐይኖቹን እያጉረጠረጠ ያስፈራራዋል፡፡ ደካማ ጓደኛ ምን ምርጫ አለው? “እሺ ይሁንልህ በግ ነው” አለውና ከጡጫው ተረፈ፡፡ እኛስ ምን ምርጫ አለን? ምርጫችን “ወያኔ ፍጹም ዴሞክራሲያዊ ነው፤ ዘላለማዊ ክብር ለሕዝብ ለተሳዋው ጠቅላይ ሚኒስትራችን፤ የኢሕአዴግ ዕድሜ ዘላለማዊ ይሁንልን፤ ወያኔ ከጠፋ ኢትዮጵያ ትበታተናለች፤ ወያኔ ከወረደ ልማታችን ይደናቀፋል፤ ወያኔ ከጠፋ ዘረኝነት ተመልሶ ኢትዮጵያን ድምጥማጧን ያጠፋዋል፤ ከኢሕአዴግ ጋር መጪው ዘመን ጨለማ ማለትም ብሩህ ነው፤ ቀኝ መንገደኛው መኢሶንና ማለቴ ሽብርተኛው ግንቦት ሰባትና ሰማያዊ ፓርቲ ለተፋጠነው ልማታችን ፀርና አሸባሪዎች ናቸው …” እያሉ መፈክር ማሰማት ነው፡፡
እነመንግሥቱ እነመለስ እነሂትለር እነሙሶሎኒ እነኢዲያሚን እነሳዳም እነአላሳድ እነሁሉም እነዚህን በእናታቸው ማኅጸን ቢጨነግፉ የሚሻላቸው ሰብኣዊ ፍጡራንን የመሰሉ ሰዎች ሁሉ ባሕርያዊ ተፈጥሯቸው አንድ ነው፤ አንድኛቸው የሌላኛቸው ቅጂ ናቸው፡፡ አባ ጉልቤዎች በመሆናቸው የሚያስቡት በአንጎል ሳይን በጡንቻ ነው – ሁሉም አምባገነኖች ከፍ ሲል በተቀመጠው ምሳሌ እንዳየነው ጨቡዴ ናቸው፡፡
ወደእስታትስቲክሳችን እንመለስ፡፡ በ1997 ሚያዝያ 29 ቀን ለወያኔ ድጋፍ የወጣው ሰው ብዛት በወያኔ ሚዲያ ሲገለጽ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ነበር፡፡ በማግሥቱ ሚያዝያ 30 ለቅንጅት የወጣው ሠልፈኛ ግን በአሥር ሺዎች የሚገመት ነበር – አሁንም በወያኔ ሚዲያ፡፡ ይህን ምን እንለዋለን ? የሰዎች ተፈጥሮ አስቸጋሪ ነው፡፡ በተለይ የወያኔ በቁጥርና በመረጃ የመጫወት ልምድ እጅግ የሚያሣፍር የሚያስቅም ነው፡፡
የአዲስ አበባ ሕዝብ ቁጥር ማነስ ለወያኔ የሚጠቅም ሆኖ ከተገኘ 500 ሊሆን ይችላል፡፡ የገጠሩ ሕዝብ ብዛት ለወያኔ የሚጠቅም ሆኖ ከተገኘ ከሀገሪቱ ሕዝብ ቁጥር በእጅጉ በልጦ እስታትስቲካዊ መረጃው ሊለጠጥ ይችላል፡፡ ወያኔ አዲስ አበቤዎችን ስለማይወዳቸው ቁጥራቸውን ሁልጊዜ እንደቀነሰው ይኖራል፡፡ አሁን ድረስ የአዲስ አበባ ሕዝብ ቁጥር ከሁለት ሚሊዮን እምብዝም አይበልጥም – በወያኔ ግምት ወይም ቆጠራ፤ ወያኔ ሲዋሽ ትንሽም አፈር አይልም – ይገርመኛል፡፡ ሁለት ሚሊዮን ማለት እኮ የመርካቶ ሕዝብ ብቻውን ሊሆን ይችላል፡፡ አዲስ አበባ በኔ አነስተኛ ግምት ከስምንት ሚሊዮን ያነሰ ሕዝብ አይኖርባትም ባይ ነኝ፤ እምዬ አዲስ አበባ በጣም ብዙ ሕዝብ ይኖርባታል፡፡ ነገር ግን የአዲስ አበባን ሕዝብ ምርጫ ዋጋ ለማሳጣትና ከሀገሪቱ አጠቃላይ የሕዝብ ቁጥር አንጻር አቅልሎ ለማሳየት ሲፈልጉ ለከት የሌለው እስታትስቲካዊ ውሸት ይዋሻሉ፡፡ እስታትስቲክስ ማለት ባጭሩ የመንግሥት የውሸት ፋብሪካ ማለት ነው ቢባል ትክክል ነው፤ ሠራተኞቹ ደሞዝ የሚከፈላቸው መንግሥትን የሚያስደስት ውሸት ለመጠፍጠፍ ነው፤ የሕዝብ አንጡራ ሀብት በብዙ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በከንቱ እየባከነ እንደሆነ መገመት አይከብድም፡፡ የአፍሪካ መንግሥታት በተለይም የኛዎቹ ካልዋሹ ሥልጣናቸው የሚረጋላቸው አይመስላቸውም፡፡ የወያኔን ሚዲያ ስትከፍቱ ውሸቱ በቲቪው መስኮት አልፎ ወደዬስሜት ሕዋሳታችሁ ይገባና ያጥወለውላኋል፤ ሊያስታውካችሁም ይደርሳል፡፡ ሌላው ቀርቶ ሰዓትም ይዋሻሉ፡፡ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ሆኖ እያለ እነሱ ሁለት ከአምስት ሊሉ ይችላሉ፡፡ ኢትሬድ ማለት እውነት እሚያቅረው ነጋ ጠባ እንደጣቃ የሚቀደድና የውሸት ቱሪናፋ የሚያሰራጭ የወያኔ ብስናት ነው፡፡ የወያኔ መሥሪያ ቤት ሁሉ በውሸት መረጃ የተጥለቀለቀ የተሳሳተና የተጋነነ እስታትስቲክሳዊ አሃዝ በመስጠት ታችኛው ላይኛውን ለማስደሰት አደግድጎ ያለበት ሁኔታ ነው የሚታየው – በነሱው አገላለጽ፡፡ ሰዎች በውሸት መረጃ እንዴት እንደሚደሰቱ አይገባኝም – “አለባብሰው ቢያርስ ባረም ይመለሱ” እየተባለ በሚተረትበት ሀገር ውስጥ ይህን ያህል በውሸት መለከፍ የሚያሳዝንም የሚቆጭም ሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታ ነው፡፡ እውነቱን ልቦናቸው እያወቀው በመዋሸት የመደሰት ተፈጥሮ እንደምን እንደተጠናወታቸው ሲያስቡት ይጨንቃል – የመፍትሔው መራቅ ደግሞ ይበልጥ ያበሳጫል፡፡ ከዚህ ከውሸት ዓለም የምንወጣበት ጊዜ ናፈቀኝ፡፡ እዚህም ውሸት፣ እዚያም ውሸት፡፡ ትልቁም ውሸት ትንሹም ውሸት፡፡ የግሉም ውሸት የመንግሥቱም ውሸት፡፡ በተናጠል ውሸት – በቡድንም ውሸት፡፡ በንግዱ ውሸት በፖለቲካውም ውሸት፡፡ በሃይማኖቱም ውሸት በኢኮኖሚውም ውሸት፡፡ ውሸት – ግነት – ውሸት፤ ዕብለት – ቅጥፈት – ጉራ – ዕብሪት ፤ አቤት ያንት ያለህ!!

ዬማረተ ማጭድ ሸክም፤ በሀቅ ጭብጥ ይረታል።

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ (ሲዊዘርላንድ ዙሪክ)

ንጋት ላይ እንደ ሀገሬ ገበሬ ካሊሜን ተከናንቤ ጉብ አልኩ። ያው ብራና እና ኮቢን በማገናኘት ሰንበት ላይ ከእናንተ ከውዴቼ ጋር ለመታደም ፈለግሁ። ከተሳካና ሃሳቤ ተሳክቶ ጡሑፌ መልክ ከኖራት መንገዱ ጨርቅ ያደርግላታል። ይገርማችኋል … በነፃነት አንደበት እርምቷን፣ ወቀሳዋን፣ ነቀሳውን ለመቀበል ተሰናድታለች። ሸብ አድርጋ መልካሙን መቀነት ተድባ ሽብሽቦዋ ላይ፤ ከራሷ ተረከዝ ላይ ደግሞ ቀልቤዋን ውሽክ አድርጋ፤ ለስታዋን ከአናቷ በፈገግታ አውጣ እንሆ ገሰገሰች ናፍቆቶቿን ፍለጋ …. የሀገሯ ጠረን ሽው አላትና … አሁንማ በተያዘ በተረዘዘው ጠብታ ጠሪ ሆነች …

እንዴት ናችሁ ውዶቼ? … ያላመረኝ ነገር ሲከነክነኝ ሰነበተ። የትውልዱ መንፈስ ጤናማ ሆኖ ብክል የሚያደርጉ ጠንጋራ አመለካከቶች በወጉና በጊዜው ካለተቀጡ፤ ነገ መርቅዘው ካለአቅማና ካለወርዳቸው ታሪክን በመጋፋት እንዳይንጠራሩ በማሰብ በተገቢው ተዳስስው መልክ መያዝ ያለባቸው ጉዳዮች በጥልቅ ዕይታዎች ካለፈው ግርምታ ጹሑፌ ጋር ታዳሚ ቢሆኑም፤ በተናጠል አውጥቶ ብልታቸውን እንደ አግባብነታቸው ማዬት ግን ግድ ሆነ። ሲበተን – ሲረጭ እዬቆ ሲሄድ መርዝ እንደ ማገናዛቢያ ተቆጥሮ እሳት እንዳይጭር ሚዛን ላላቸው የነገ ሀገር ተረካቢዎች ማነፃጸሪያ ሥራዎችን መሥራት ያስፈልጋል።
obang
በቅድሚያ ግና አንድ የጸሁፌ ታዳሚ ለሰጡኝ ገንቢ አስተያዬት ቅድሚያ መስጠትን ወደድኩ። ባለፉት ጹሑፌ „ሞገደኛው ተክሌ“ እይልኩ ነበር የፃፍኩት። ታዳሚዬ እንዲገነዘቡልኝ የምሻው ይህን ስም እኔ ሳልሆን እራሱ የተጠቀመበት ስለመሆኑ መግለጽ እፈልጋለሁ „ጥምረት“ እንደ ተመሰረተ …..
ሞገደኛው ተክሌ በነሃሴ 29.2011 ላይ “ታየኝ እኮ፡ ሀረርና ወለጋ ገጥሞ፡ የ“ኦሮሚያ”ን ሪፐብሊክ ሲመሰርት ችግሩ ግን፡ ግንቦት ሰባትና እኛ ጋር ነው።“ https://ecadforum.com/Amharic/archives/621/ የዛሬን ያላዬ …. ወቼ ጉድ …
እራሱ የሰጠው ሥም ነው። ደግሞ „ሥምን መላእክ ያወጣዋል“ እንዲሉ እኔም የተመቸኝ ስለመሆኑ ያን ጊዜ ከጻፉኩት አስተያዬት ዝቅ ብሎ ማንበብ ይቻላል – ከትሁት ምስጋና ጋር። አሁንም በዚህው እቀጥላለሁ። ያቀበለው መላዕክ እንዳለ ስለማምን …. ልኩና ግጥሙም ሥም ነው።
ሀ. ቁምነገር ….
ድርጀት ማለት አንድ ወይንም ከዛ በላይ ያሉ ሰዎች የሚያስማማቸውን ጉዳይ በተሰበሰበ – ፍላጎታቸውን ማዕክል ባደረገ ሁኔታ የሚመሰረቱት የሰዎች ማህበር ነው። ድርጅት ሴቶች በጾታቸው፤ የኃይማኖት ሰዎች በዕምነታቸው፤ ፖለቲከኞች በዓላማቸው፤ ወጣቶች በዕድሚያቸው፤ ሙያተኞች በሙያቸው፤ ሃብታሞች በኢኮኖሚ አቅማቸው፤ የማህበራዊ ኑሮ አድናቂዎች በስሜታቸው፤ የጥበብ ሰዎች በጸጋቸው ዙሪያ ኃይላቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ጊዚያቸውን ፈቅደው በመስጠት ባጸደቁት ወይንምም በደነገጉት ህግጋት ሥር ለመተዳደር የሚፈጥሩት የአቅምና የመንፈስ ጥምር ማዕዶት ነው።
ለእኔ መቼ ተጀመረ ለሚለው ጌታችን መዳህኒታችን እዬሱስ ክርስቶስ ለአዳም ከአካሉ ሄዋንን የፈጠረለት ዕለት ድርጀት ተፈጠረ ብዬ አምናለሁ። ከዚህ ስነሳ ጋብቻ የመጀመሪያው የድርጅት ጽንሰ ሃሳብ ተግባራዊ የሆነበት ማህበራዊ ተቋም ነው። ጋብቻ የሁለት ሰዎች ብቻ ሳይሆን የማህበረሰቡ ሁለንትና ውህዳዊ ቅንበር ነውና። ከዚህ ቀጥሎ ሁለተኛው የድርጅት እድገት ምልክት የኖህ መርከብን የድህነት ስበስብ ተቋም ነውም ባይ ነኝ።
obang5

አንድ ዓላማና ግብ ያለው ድርጅት ሲሆን በዚህ መልክ ከሰው ልጅ እድገት ጋር ድርጀት ከፍ እያለ ሄዶ ዛሬ ካለበት ደረጃ ደርሷል። ሀገር ድርጅት ነው። አኽጉርም ድርጀት ነው፤ ዓለምም ድርጅት ነው። ሀገር ማለት ለእኔ መሬቱ ብቻ ሳይሆን ህዝቡም ነው። ሀገር ማለት በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ዕውቅና ባላው ደንበር የተከለለት መሬት ማለት ሲሆን፤ ህዝብ ማለት ደግሞ በዛ ዕውቅና ባገኘ ክልል ውስጥ ኑሮውን ያደረገ የሰዎች ማህበር ማለት ነው። የሁለቱ ጥምረት ነው የአንድ ሀገርን ምስል ሊሰጠን የሚችለው። አኽጉርም ሆነ ዓለምም ለእኔ የሚሰጠኝ ትርጉም በዚህ መልክ ነው።
በድርጅት ዙሪያ ቅንጅት ሲዊዘርላንድ ሚያዚያ 29.2006 ሲመሰረት ጄኔባ ዩንቨርስቲ አዳራሽ ትቢያዋ ሥርጉተ ሥላሴ አፍ ካለው መቃብር ብቅ ብላ ትንሽዬ ገለጣ ቢጤ አድርጋ ነበር። ያን ጊዜ … ማለት በዕለቱ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ስለ ድርጅታቸው ቅንጅት፤ ዶር አሰፋ ነጋሽ የወያኔ የጤና ፖሊስና ጦሱን በሚመለከት ሰፊ የሆነ ትንተና በመረጃ የተደገፈ ገለጣ አድርገው ነበር።
ከዛ በኋላ ደግሞ ዘርዝር አድርጌ የድርጅት ጽንሰ ሃሳብ፤ ምን ማለት ነው? ድርጀት ምንድን ነው? ድርጀት ለማን? ድርጅት ለምን ያስፈልጋል፤ በጸረ ወያኔ ትግልስ የድርጅት ሚና ምንድን ነው? አፈጻጻም ሂደቱስ በሚል በጸጋዬ ድህረ ገፄ በድምጽ በስፋት ሰርቼው ነበር። ጊዜ ከኖረዎት ጎራ ይበሉና ከክፍል 1 እስከ 6 በዚህ ሊንክ http://www.tsegaye.ethio.info/maedot.html1 ማዳመጥ ስለሚቻል በዝርዝሩ መሄድ አያስፈልግኝም።

ድርጅት ለነፃነት ትግል ገዢ መሬት ነው። እንኳንስ ነፃነትን ለተቀማ ሀገርና ህዝብ ቀርቶ ነፃነት ባለበት ሀገርም የተሰበሰበ የተማከለ፣ የተደራጀ፣ መልክ ዬያዘ ጉዳይ ዓላማና ተግባሩን በሥልጡን – በቅልጡፍ – በታቀደ አኳኋን ለመከወን ከእለት ኑሮ ጀመሮ መንፈስን – አካልን – ፍላጎትን – ራዕይን – ተስፋን – ማደራጀት ለድል ያበቃል። ምርተ – ዝቀሽ – ሰብላማ፤

እንደ እኛ ለአለችች መተንፈሻ ቧንቧዋ በጉልበተኛው ወያኔ ለታፈነ እናት ሀገር ደግሞ ብቸኛው መድህን ነው። አቅምን የመጠነ፤ ኃይልን ያሰባሰበ፤ የሀገርን ልዑላዊነት ያከበረ፤ ከህዝቡ ብሶትና ችግር የተነሳ፤ ወቅቱንና ፍላጎቱን የተረዳ መሪ ድርጅት በጣም ያስፈልገናል። በዚህ ስሌት መደራጅት መብትና ፈቃድ ሆኖ ኢትዮጵያ ላይ ግን፤ ርግጫውና ፍጥጫው፤ ግፊያውና መከራው፤ ባይታዋርነቱና ቅጣቱ የጠነባት ቢሆንም ነፃነትን ፍለጋ የተደራጁ ኃይሎች አሉን። መከራውን ከረመጡ ላይ ሆነው በጸጋ የሚቀበሉ። ውጪ ሀገርም የሀገራችን ጉዳይ ያገባናል፤ ይመለከተናል የሚሉ ወገኖችም በነፃነት ተደረጀተው ትግሉን ተያይዘውታል። አንድ ድርጅት ሲደራጅ በፈለገው ምርጫ ስለሚሆን አደረጃጃቱ የሲቢክስ ወይንም የፖለቲካ ፓርቲ ንቅናቄ ወይንም ግንባር ሊሆኑ ይችላል። ስያሜውም ከፍላጎቱና ከይዘቱ ይመነጫል።
obang7
ለ. የሲቢክስ ድርጅቶች መብራት ናቸው ለፖለቲካ ፍላጎቶች ተፈጻሚነት ….
የሲቢክስ ድርጅቶች ገፍተው ከታገሉ የመፍትሄ ቁልፍ ናቸው። ጸጥ ያለውን አብዛኛውን ኃይል የማሰባሰብ አቅማቸው ሙሉዑ ስለሚሆን። የአብዛኛውንም ፈቃድ ስለማይነፈጉ በርካታዎች ሊታደሙባቸው ይችላሉ።። አቻችለው መስመር የማስያዝ ሂደታቸው በአንጻራዊነት የተመቸ ነው። እርግጥ ወገንተኛ ናቸው። ወገንተኝነታቸው ግን በመጫን ሳይሆን አለስልሶ በማቀራረብ። ነፃነት ለአባልተኞቻቸው የመስጠት አቅማቸውም ያልተገደበ ነው። የበታችና የበላይ ግንኙነቱም ቤተሰባዊ ነው። ቢሮክራሲያዊ ነገር ግጥማቸው አይደለም።
በዚህ መሰል ግንዛቤ የሚጓዙ፤ ወይንም ይህ ስሜት የሚማርካቸው የሰዎች ስበስብ ብቻ ሳይሆን ሀገሮችም አሉ ይህን መሰል አቋም የሚያራምዱ። እኔ እንደማስበው ሲዊዝ እንዲህ ያለ ማዕካላዊ ፍላጎትን የማስተናገድ አቅም እንዳላቸው አያለሁ በሀገር ደረጃ።
ምን ለማለት ነው እነዚህ ከፖለቲካ ሥልጣን ዕይታ ባሻገር የተላያዩ የማህበረሰቡን ሙያዊ፤ መክሊታዊ፤ ዕምነታዊ ፍላጎቶችን አስቀድመው የሚነሱ እንቅስቅሴዎች ቅናዊ ዕይታ ከተሰጣቸው፤ ሙሉ ድጋፍና አክብሮት ከተለገሳቸው፤ አዎንታዊ ስሜትን ካልተነፈጉ፤ ለማድምጥ ጆሮ ከተሰጣቸው ለነፃነት ትግሉ ማገር ናቸው። ከስሚንቶ ባላይ የእንቁላል ውሃ ናቸው። ታውቃላችሁ አይደለም የቀደሙ አግናባት በእንቁላል ውሃ እንደሚገነቡ?! በጎንደር ደብረብርሃን ሥላሴ ዙሪያ ያሉት አግናባት የእንቁላል ግንብ ነው የሚባሉት። ውበታቸውም ጥንካሬያቸውም ተፈጥሯዊ ወይንም ኦርጋኒክ ነውና። የሲብኪስ ማህበራት ወይንም ድርጅቶች የሲናሪዎ ችግር ስለሌለባቸው ለአባላቶቻቸው ሆነ ለደጋፊያቸው እንዲሁም ለአድናቂዎቻው ቅርብ ናቸው። ፕሮቶኮሉ የተሰረዘ ነው። ይህ ደግሞ ኃይለኛ ሞገድ ፈጥሮ ድርጅታቸው መንገድ ጠራጊና ተደማጭ ያደርግላቸዋል። ፍላጎት ለውጤቱ እራሱን ይገብራል ደስ ብሎት ….
ሐ.አብነት!
„የድምጻችን ይሰማ“ የእስልምና ዕምነታዊ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ወደር የለሽ፤ ዓላማውን ጠንቅቆ የተረዳ፤ በአንዲት ቅንጣት መልእክት እልፎችን የማስተዳደር ብቃትና ክህሎትን የተቀዳጀ፤ ማንም ሀገር – ማንም ህዝብ ፈጽሞ ያላገኘው፤ ያላለፈበትም ሥልጡን ብልህ እንቅስቃሴ ነበር። አመራሩ በመሪው ሙሉ ድምጽና ፍላጎት ይለፍ የተሰጠው እጹብ ድንቅ እንቅስቃሴ ነበር። ከሰማይ የተፈቀደልት። ጥበቃም የተደረገለት። እጅግ ረቂቅ ፍጹም ድርጊትን የታጠቀ፤ መደማመጠን ያነገሰ፤ ልዑቅ እንቅስቃሴ ነበር። ፍቅሩ፣ መምህርነቱ፣ ተስፋነቱ፣ ብርሃናማነቱ መሆኑ ብቻ ሳይሆን የማይጠፋ … ዘላለማዊ ጧፍ …. ነው። ኢትዮጵዊነትን በአግባቡ በተግባር የተረጎመ። የእንቅስቃሴው ጸሐዮች በሀር ውስጥም ሆነ በውጭ ደግሞ ሴቶች …. ነበሩ። እንዴት እንደምወዳቸው …. አትጠይቁኝ። ትንግርት!
„የድምፃችን ይሰማ“ እንቅስቃሴ አሁን እንኳን ይህ ሁሉ ፈተና በሀገር ውስጡም በውጭም በቀንዳሙ ወያኔም በስፋት እዬተፈተነ ነጥሮ በመውጣት ድንግልናውን በጥር 24.2014 እኤአ በድጋሚ አስመስክሯል። የሰሞናቱ ድንቅ ተግባር የተስፋ ሰብላማ ማህደር አድርጎታል። ታምርና ገድል ነው ለዘመኑ። ለሰላማዊ ትግል የማይደክም ድንቅ ተቋም።
ቀደም ባለው ጊዜ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማህበር፤ የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበር ሆነ አንጋፋው የመምህራን ማህበር በሀገራችን ወሳኝ ድህነታዊ ጉዞ የበቃ ተግባር ፈጽመው ነበር። የዛሬን አያድርገውና በወያኔ ለጠፍ ተሸበበ። የሚተጉ ወገኖች መኖራቸው ሳይዘለል ….
ከዚህ አንጻር ነው ሰፊ ጊዜ ሰጥተን ሞቅ ያለውን ተስፋችን በማረተ ማጭድ ሸክም የሚጭኑ አገላለጾች አግባብነታቸውን እንደ አለ በግልቡ ሳይሆን፤ ፊት ለፊታችን ቁጭ አድርገን፤ በአግባቡ ፈትሸን በደሙ ውስጥ ያለውን መርዝ ማስወጣት አስፈለጊ የሆነው። በዓይን ቀልድ የለምና! በትርጓሜ አቃንቶ መስመሩን መሳተከከል የእያንዳንዳችን መሰረታዊ ተግባር ሊሆን ይጋባል። ቀላል የትም አይደርስ ብሎ ማለፍ ኃላፊነት የጎደለው ጉዞ ነው ለእኔ – ለሥርጉተ።
„ እኛ ስንወለድ ዕምነት አልነበረንም፤ እኛ ስንወለድ ሃይማኖት አልነበረንም … እኛ ስንወለድ ጎሳ እልነበረንም “ ይህን መድህን ቃል፤ ይህን የህይወት ቃል፤ ይህን አጽናኝ ቃል፤ ይህን ቅዱስ መንፈስ የረበበት ቃል ባለፈው ሳምንት „የእኛ ነገር የተሸነፈ ርዕዮትና ሀገር ..“ በሚል ማገደኛው ተክሌ በጻፈው ጹሑፉ ላይ አንዲት ነጠላ ስሜትን ብቻ ለማጣቀሻ ወስዶ ….. “በኢትዮጵያዊነታችን ያጣነው ነገር ስላለ ብቻ ኢትዮጵያዊነታችን ይሰረዛል ማለት አይደለም”። ከባዕድ ስሜት ጋርም አዳብሎ ያስነበበን። ለዛውም ከጃዋርያን ጋር …. ማህጸንን ደም ያስለቅሳል ….
እኔ ዶር. ኦባንግ ኢትዮጵያ ነው የምለው። ዛሬ አይደለም እንዲህ ብዬ የምጠራው ከአምስት ዓመት በፊት እሱ በሚያደርጋቸው ንግግሮች ሥር የምጽፍቸው አስተያቶች ላይ ነበር። እርሰዎም አልለውም። ለምን አርቀዋለሁ? ለመንፈሴ ጥግ ነው። ከስሜቴ ውስጥ እኮ ነው ያለው። አምላኬን ፈጣሪዬን ቅዱስ እግዚአብሄርን አንተ ነው የምለው። አንተ ቅዱስ ገብርኤል እባክህን እርዳኝም እለዋለሁ። እናቴ ቅድስት ድንግል ማርያምንም ከሴቶች የተለዬች ሆና አንቺ እላታለሁኝ። ዶር ኦባንግንም አንተ ስለው በውስጤ አስቀምጬ ነው።

ዶር ኦባንግ ኢትዮጵያ ለእኔ ጠያቂ ነው። የነፃነት ትግሉ ቤተሰቦች ስንጠፋበት የት ጠፋችሁ? ምን ልርዳችሁ? ብሎ የሚጠይቅ መንፈሳችን ነው። በ2012 የካቲት ላይ „ጠፋሽ“ ሲለኝ ጉልበተኞች ጠቀጠቁኝ መሸሸግ አለብኝ ስለው „ እኔ እታዘዝሻለሁ አለኝ። እባክሽን አብረሽን ሥሪ“ ነበር ያለኝ። እንደ እኔ በጣም በብዙ ሰው በውስጥ የተቀመጠ ሰው ቢኖር ዶር. ኦባንግ ነው። ግን ተመስጥሮ ነው።
መንፈሳችን የገዛው ጥሩ አያያዙ ነው። ጹሑፎቹ ሁሉ መጨረሻ ላይ የእግዚአብሄር ቃል አለበት። ፈጣሪውን ቅርቡ አድርጎ እያማከረ፣ ፈቃድም እዬጠዬቀ ነው ለነፃነታችን ታግሎ እያታገለን ያለው። ሰላም ፍቅር ምህረትን እያወጀ ህሊናው የታወረው ወያኔ በአሸባሪነት ወንጅሎ የፈረደበት ብርቅዬ የሰው ሰዋችን ነው። እንሱን እንኳን ተዉ እያለ ይመከራል፤ የአዲሲቱ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ፕሬዚዳንት ሁላችንንም በፍቅር ለመቀበል ለማስተናገድ የተዘጋጀ ነው።

በማናቸውም ጊዜ ሌት ይሁን ቀን እንደ እኔ ካለች ትቢያ እሰከ ሊቃናት ድረስ ደውለው ያገኙታል። ይህ ስደት ላይ ለምንኖር ለእኛ ለግፉዕና፤ በተለይም ለሴት የነፃነት ትግሉ ቤተኛ እጅግ አስፈላጊና መዳህኒት መንገድ ነው። እኔ በራሴ ስላማወቀው። ይህ የብዕረ -ሞገደኛው መንገድ ኢትዮጵያ በድላሻለች፣ ዝመችባት፣ ጦርነት እወጂባት፣ ምንሽ ናት፣ ግፊያት በአማራ ቆዳ በተዋህዶ መንፈስ የተጠቀለለች በሚል ቄንጠኛ ስሜትን በሚያቀጣጥል …. አቁስሎ ቁስልን እዬቀረፈፉ እንዲደማ፤ መግል እንዲቋጥር የሚያደርግ ነው። ለምን የጃውርን መንፈስ ከኦባንግ ጋር ማገናኘት እንደፈለገ ባይገባኝም ተወን ማለት አለብን። ይህ ወደ ዶር ኦባንግንም ኮተት ማለቱን እኔ የማዬው በዋዛ አይደለም። እም! …. የተላዬዬ ሃሳብ ሰንቃ ስታባትለን የከረመችው ብዕሩ … ስንት ቦታ በወጀብ ስታስመታ ባጅታ አሁን ደግሞ መርዝ መጋዝን …. ልትከዝንን። እእ! አይቻልም። እንብኝ! አ ሻም! አታምሪም እንበላት …. እናትን መጋፋት እንዴት? አኮ!
ዶር ኦባንግ ኢትዮጵያ …ጥቅምት 12.2013 ሲዊዘርላንድ ዙሪክ መጥቶ ነበር። የጋባዙት የአዲሱ ትውልድ ቅዱስ መንፈስ ያላቸው የወጣቶች የሰብዕዊ መብት ድርጅት ነበር … በምን ቋንቋ በምን ቃላት በምን ዜማ የስበሰባው ታዳሚዎችን ስሜት ልግለጽላችሁ ……..
እሱን ስናይ፣ እሱን ስናገኝ፣ እሱን ስናደምጥ፣ ድህነትን ሲያውጅ ቂም በቀልን ሲያወግዝ “ወገኖቼ ከወያኔም እኮ ጥሩዎች አሉ አስኪ ምርመሩት” ሲለን … አዬ አንተ ትሩ ሰው። የተዘጋጀለትን የክብር ቦታውን ትቶ መጥቶ ነበር ከ እኛ ጋር የተቀመጠው። ከአጠገቡ ለመቀመጥ ሽሚያ ነበር …
እስራኤል ላይም በነበረው ቆይታው … ወጣት የትግራይ ልጆች ስሰባውን ጠቅጥቀው ሲወጡ “የእኛ ትግል እናንተንም ነፃ ለማውጣት ነው” ነበር ያላቸው።
እጅግ የማከብራችሁ የሀገሬ ልጆች … ካለ እንደዚህ ዓይነት ፈውሶች እንደ በደላችን እንጨራረሳለን። ወያኔ አቁስሎናልና ወያኔ ሲለቅ፤ በቀል ተጠምቆ መጨፋጨፍ አይቀሬ ነው። ግን እንደ ዶር ኦባንግ ያለ …. እንደ ጋዜጠኛ አብርኃም ደስታ ዓይነት ወጣቶችን ንጹህ መንፈስ ጥሶ የሚሄድ ሞራልም ተፈጥሮም የኢትዮጵያዊነት ጨዋነት የለም። …. ይህ ሚስጢር ነው ለተፈቀደላቸው ብቻ የሚገልጽ። እስራኤል ላይ ፈልቶ የነበረውን ስሜት አብርዶ፤ አስታግሶ ወጣቶቹ አብዛኞቹ ተምልሰው ከወገናቸው ጋር ታዳሙ በኢትዮጵያዊነት፤ በዛ ድንቅ የወል ማራኪ መንፈስ „….. አቶ መለስ የሚነዳው ባቡር የጥላቻ ባቡር ነው…..አሁን ባቡሩ እየቆመ ነው” በ25.06.2013 እስራኤል ከተደረገው ንግግር የተወሰደ።
ሲከፋን ብቸኝነት ሲያለፋን፤ ዙሪያ ገባው ሲጨልምብን የወገን ነገር ሲቆጠቁጠን፤ እረፍት ሲነሳን መተንፈሻ ቧንቧ እሱ ነው።
እኔ የሳውዲ ችግር ሲመጣ ወዲያውኑ ነበር የደወልኩለት። አሞት ነበር፤ ግን ሥራ እንደ ተጀመረ ሲነግረኝ ተገስ አለልኝ። ሰው እኮ ነን፤ ማሽን አይደለንም። የፈለገ ጠንካራ ብንሆንም አንድ አጽናኝ ያስፈልገናል። “አንድ ዓይን ቢኖራት እሱንም በዘነዘና” እንዳይሆን ሃብቶቻችን በጥንቃቄ ልንይዝ ይገባል። እንዲህ ዓይነት መንፈስ ያለው ሰው በ100 ዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ነው የሚፈጠረው። ለነገሩ እኛ ማድነቅም ማመስገንም ሆነ በቅን ዓይን ማዬትም አይሆንልንም። … ተበድለናል ይመስለኛል። ይህም ሆኖ ደግሞ ተስፋችን ላይ ዲዲቲ መነስነስ አይፈቀደም። ….. http://freedom4ethiopian.wordpress.com/2013/06/page/8/

ዶር ኦባንግ …. ስለ ሴቶችም ቀና አመለካከት ነው አለው …. ያለንን ተዝቆ የማያልቅ አቅምና ዕምቅ ጥሪት አሳምሮ ያውቃል …. የማረተ ማጭድ ሊያሸክመን የፈለገውን ጠቀራ ማሸቀንጠሪያችን ሌላው ድንቅ ገለጻ ….
“(መጋቢት 7 ቀን 2004 ዓ.ም. March 16, 2012)፦ የአገራችን ግማሽ ህዝብ የሚሆኑትን ሴት እህቶቻችን ያልተሳተፉበት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ ምስረታ ስኬቱ ያማረ እንደማይሆን፣ ቢሆንም ራሱን ለጥፋት እንደሚያጋልጥ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ተናገሩ።“አገራችን ሁሉም ዓይነት ሴቶች ያስፈልጓታል። አምላክ ለዚህ የተቀደሰ ተግባር የጠራው የተማሩትንና የተሻሉትን ብቻ አይደለም። ሁሉንም እንጂ! ስለዚህም በኦሞ ሸለቆ ከንፈሮቿ ላይ ሸክላ ከምታንጠለጥለው ውብ ጀምሮ በአዲስ አበባ ከንፈሮቿን ቀይ ቀለም እስከተቀባችው ቆንጆ፤ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ባዶ እግሯን ከተዋበችው ጀምሮ በዋንዳቢቲ እስካጌጠችው የኦሮሞ ኮረዳ፤ በኦጋዴን በሒጃብ ካሸበረቀችው ኢትዮጵያዊት ጀምሮ ባማረ ጥለት እስከተዋበችው የአማራ ቆንጆ፤ ግማሽ አካሏ እርቃን ከሆነው የአፋር ድንቅ ጀምሮ በሹርባዋ እስከተዋበችው የትግራይ ሴት … ሁሉም ዓይነት ሴቶች ኢትዮጵያችን ያስፈልጓታል።” ሲሉ አቶ ኦባንግ ተናግረዋል።

http://ethiopiazare.com/the-news/2236-obang-speech-to-ewccc-conf

መ..ዶር. ኦባንግ ኢትዮጵያ ለወገኖቹ ትልቅ ጆሮ አለው በፍቅር የማዳመጫ፤ ኖሮይ ላይስ? …. ኦባንግ ሜቶ በተጋባዥነት የተገኙበት ይህ ውይይት ሲጀመር የማህበሩ ሊቀመንበር ወ/ሮ ዙፋን አማረ “ውድ ወንድማችን፣ ውድ የኢትዮጵያ ልጅ፣ኢትዮጵያዊያን ርዳታ በጠየቁበት ሁሉ ጊዜ፣ ገንዘብ፣ የቦታ ርዝማኔ ሳያግድህ ፈጥነህ ትደርሳለህና ሁላችንም ላንተ ታላቅ አክብሮት አለን” አሉ። ኦባንግ መድረኩን ተረክበው “የማደርገው ሁሉ ለህሊናዬና ነው። ማድረግ የሚገባኝን አደርጋለሁ። ግዳጄም ነው። ምስጋና አያስፈልግም ዛሬ ንግግር ሳይሆን ምክር እሰነዝራለሁ” የሚል ምላሽ ሰጡና ስለ መደራጀት፣አበክረው፤ተናገሩ።

“አማራጭ ቢኖረን ስደትን አንመርጥም ነበር። በአገራችን ግፍ ባይፈጸምብን ኖሮ አገራችን እንኖር ነበር”

https://www.facebook.com/ethionewss/posts/373710216047710

በ2009 እ.ኤ.አ አንድ ዓለምአቀፍ የ የኢትዮጵያውያን የጋራ አሜሪካን ሀገር ስበስባ ነበር። ከርንት አፊረስ ላይ በቀጥታ ይተላለፍም ነበር። ቀኑን አላስተወስውም ከዛ ላይ የሴቶች ተወካይ ዶር አበባ ተገኝተው ነበር። የሚናገሩት ከዶር ኦባንግ ቀጥለው ነበር። እንዲህም አሉ። ” እኔ በኦባንግ ንግግር በጥልቀት ተመስጬ ስለነበር ልናገር ያስብኩትን ሁሉ እረስቼዋለሁ። በጣም ነበር ስሜቴን የገዛው። ከዚህ በላይ መናገር አልችልም፡” ሴቶች ይህን ወንድም በምን መልኩ አዬት? እናት ባላት ጥልቅ ጸጋ ተረጎሙት።
ለማሰረጊያ በ2013 የተገኘው ድንቅ ፍሬ ….
በሀገረ አሜሪካ ታላቅ የምክክር ሸንጎ ከሹሞች ጋር “ኢትዮጵያና ድሕረ መለስ” ስለወገኖቹ ስለ ነፃነት ጥማታችን ዶር ኦባንግ ምን ተናገረ …“ህወሓት እስካሁን በነጻ አውጪ ስም አገር እየመራ እንደሆነ፤ መለስ ለህዝባቸው “ሬት” ለምዕራባውያንና “ማር” (የቤት ቀጋ፤ የውጭ አልጋ) ዓይነት መሪ እንደነበሩና የኢትዮጵያ ሕዝብ ላለፉት 22ዓመታት በመከራ ውስጥ ያለና የዛሬ 8ዓመት በዚሁ ቦታ ላይ ያማሞቶ ኢትዮጵያ በአቋራጭ መንገድ (ክሮስሮድ) ላይ እንደምትገኝ” መናገሩ አቶ ኦባንግ ካስታወሱ በኋላ “መቼ ነው መንገዱን የምናቋርጠው? ከስምንት ዓመት በኋላ አሁም አንሻገርም ወይ፤ አናቋርጠውም ወይ” በማለት ተሰብሳቢውን ያስደመመ ለሰብሳቢዎቹ ግልጽ ጥያቄ ጠይቀዋል፡፡
አቶ ኦባንግ ሲቀጥሉም “ኢትዮጵያውያን የምንጠይቀው በጣም ቀላል ጥያቄ ነው፤ አሜሪካኖች የሚመኩበትን ሰብዓዊ መብት እኛ ተነፍገናል፤ ..” አሜሪካኖች ነጻ እንድታወጡን አንጠይቃችሁም። የኢትዮጵያ ህዝብ እንዴት ነጻ እንደሚወጣ ያውቃል። እናንተ ግን በነጻነት መንገዳችን ላይ ዕንቅፋት አትሁኑብን፤ (የነጻነት መንገዱን አትዝጉብን)። ከመንገዱ ላይ ገለል በሉ … እስካሁን ያልተሞከረ መንገድ አለ … እሱም እርቅ ነው … ከመንግሥትም ሆነ ከተቃዋሚው በኩል ዓመኔታ የሚጣልባቸው አሉ … ” አቶ ኦባንግ ሜቶ፡፡ http://www.goolgule.com/ethiopia-after-meles/

የእኔ ጌጦች ይህን አልማዝ ያመረተ ህሊና ኢትዮጵያዊነትን የሰበከ አንደበት ታሪክና ትውልድን፤ ዕመነትንና መከባበርን፤ ፍቅርና ናፍቆትን፤ ፍልቅ ስሜትና ተስፋን ለነገ ያጫ፤ ለዛም ቀን ተሌት በተጠራበት ቦታ ሁሉ አቤት ወዴት ብሎ የሚታዘዝን መንፈስ ነው ከጃዋርውያን ጋር አዳቅሎ አቶ ሞገደኛው ያቀረበው። ስለሆነም እዬተስተዋለ በጥንቃቄ ይምርምር እንላላን እኔና ብዕሬ። በሉ እንግዲህ … የነጠረውን ፍርድና ዳኝነት ከጨዋውና ሚዛን ከሆነው ወገኖቼ ንዑድ መንፈስ ውስጥ አስቀምጬ እኔ በለመደ እጄ በሌላ ጉዳይ ዙሪያ ከች እስክል ድረስ ሞቅ ደመቅ ባለ ፍቅር፤ በዘንካታው ኢትዮጵያዊ ትህትና እሰናበታለሁ። ደህና ሁኑሉኝ …. የኔዎቹ መንፈሶቼ።
• ማሳሰቢያ ዛሬ ማገናዘቢያ ሊንኮች በርከት ብለዋል። የግድ ነበር። ነገን ሲታሰብ ከተቻለ በተሟላ መረጃ መሆኑ እጅግ ጠቃሚና አስፈላጊም ነው። ሰው ቋሚ አይደለም …. ጊዜም፤ ከተረት ተረትም መዳንም ይቻላል።
• የሀገረ እስራኤል ወገኖቻችን ፎቶ ከከረነት አፊረስ ድህረ ገጽ፤ የዶር ኦባንግ ከጎልጉል፤ የሲወዝ ፎቶ ከእኛው ቤት፤
“ከጎሳ ይልቅ ለሰብዕዊነት ቅድሚያ እንስጥ!” የአዲሲቱ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ መሪ ቃል ።
እግዚአብሄር አምላክ ኢትዮጵያዊነትን ከሚዋጋ ጠላታዊ ስሜት ያድነን! አሜን!
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

ዛሬም በሰልፍ ቅስቀሳ ላይ የነበሩ 8 የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ታሰሩ፤ ሰልፉ ነገ በጎንደር ይደረጋል

$
0
0

ከዳዊት ሰለሞን

ትናንት ታስረው አመሻሹ ላይ ተፈትተው የነበሩት የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ ማለዳ ለነገው ሰላማዊ ሰልፍ ህዝብን ለመቀስቀስ አደባባይ እንደወጡ በፖሊስ በድጋሚ መያዛቸው ተዘገበ። ሰላማዊ ሰልፉ የኢትዮ –ሱዳን የድንበር ስምምነትን መንግስት ግልጽ እንዲያደርግና በድንበር ማካለሉ ወቅትም ህዝቡ ቀጥተኛ ተሳትፎ እንዲኖረው መጠየቅን የሚያካትት ስለመሆኑ በአዘጋጆቹ መነገሩ አይዘነጋም፡፡

በማለዳው ቅስቀሳ ተይዘው አዘዞ ፖሊስ ጣብያ የታሰሩት
1-ጌታነህ ባልቻ -የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ
2-ብርሀኑ ተክለ ያሬድ-የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ
3-የሽዋስ አሰፋ የብሄራዊ ም/ቤት ሰብሳቢ
4- ዮናታን ተስፋየ -የወጣቶች ጉዳይ ሀላፊ
5- ሀብታሙ ደመቀ የብሄራዊ ም/ቤት አባል
6- ወይንሸት ሞላ የም/ቤት አባል
7- አቤል ኤፍሬም-የህዝብ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ አባል
8 – እየሩስ ተስፋው -የሴቶች ጉዳይ ም/ሀላፊ ሲሆኑ ሹፌሩ ና እረዳቱ ከታሳሪዎቹ መካከል ይገኙበታል፡፡
blue party gonder flyer

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live