Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ እንኳንም ተወለድሽ

$
0
0

Ryot Alemu
ህክምና ሳይቀር ተከልክላ በግፍ በእስር ቤት እየማቀቀች ለምትገኘውና ለ3ኛ ጊዜ በወህኒ ልደቷን ለምታከብረው ጋዜጠኛ ር ዕዮት ዓለሙ መታሰቢያ በጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ የተጻፈ።
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ


ቴዲ አፍሮ ምላሽ ሰጠ፤ “ወደኋላ ተመልሰን በህይወት የሌሉ ሰዎችን መሸለም ወይም እዳ ማስከፈል አንችልም”

$
0
0

teddy afro
አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ከሰሞኑ በአወዛጋቢነት በቆዩት ጉዳዮች ዙሪያ ለአዲስ አድማስ ጋዜጣ ምላሽ ሰጥጧል። እንደወረደ እነሆ፤-

ፈጣሪ በየትውልዱ የራሱን ድምጽ ያወጣል
ፍቅር ያሸንፋል– የኔ ሳይሆን የትውልድ ድምጽ ነው
እዳ አለ የምንል ከሆነም፤ እዳ የሚከፈለውና የሚሸፈነው በፍቅር ብቻ ነው

“ከታሪክ ከወረስነው ቂም ይልቅ የምናወርሰው ፍቅር ይበልጣል”

የፍቅር ጉዞ ከሚለው ሃሳብ እንጀምር፡፡

መነሻው ምንድነው? “አቦጊዳ ብዬ፣ ፊደል “ሀ”ን ቆጥሬ፤

የፍቅርን ትርጉም ለልቤ አስተምሬ፣

ይዤሽ በአኮፋዳ እንደቆሎ ተማሪ፣

አቦጊዳ ልበል የፍቅር ጀማሪ…”

እንዲህ ነው የኔ የዘፈን ህይወት የሚጀምረው። አሁን የፍቅር ጉዞ ላይ ደርሷል፡፡ ሁላችንም፣ በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች ውስጥ እናልፋለን። ብዙ ቅሬታና ብዙ ደስታ፣ ብዙ ትክክል የሆኑ ነገሮችና ብዙ ትክክል ያልሆኑ ነገሮች አሉበት – ያለፍንበት ታሪክ፡፡ ትልቁ ነጥብ፣ ካለፍንበት ታሪክ ተነስተን ለሚቀጥለው ጊዜ ምን እናድርግ የሚለው ነው፡፡ ያዘንበትን ነገር በይቅርታ ሰርዘን፣ የወደድነውን ነገር ደግሞ አሳድገን ለመጓዝ፣ ትልቁ መድሃኒት ፍቅር ነው፡፡ ይቅር ተባብሎ የቀድሞ ስህተቶችን ለማስተካከልና በህብረት ተጠራርቶ የቀድሞ ትክክለኛ ነገሮችን ለማሳደግ፣ ፍቅር ያስፈልጋል፡፡ አቡጊዳ ብለን ነው ፍቅርን የምንጀምረው፡፡ “ዳህላክ” ላይም፣ ለልጆቻችን ቂምን አናውርስ ብለናል፡፡ “ካስተማርሽው ፍቅርን በጊዜ፣ አይሻለሁ ወይ ባሱ ጊዜ…” ኢትዮጵያና ኤርትራ ተራርቀው የተፈጠረው ግጭት የሩቅ ጊዜ ታሪክ አይደለም። የብዙዎችን ህይወት በቀጠፈው ግጭት፣ ብዙ የተበተነ ቤተሰብ፣ የደማ ስሜት አለ፡፡ ይሄ ቁስል ዘላለም እንደመረቀዘ መቀጠል አለበት? መዳን መፈወስ የለብንም? ይቅር መባባልን ነው በ“ያስተሰርያል” የዘፈንነው፡፡ ለምንወልዳቸው ልጆች፤ ለምንፈጥራቸው አዲስ ትውልዶች የምናወርሰው ቂምን ከሆነ፣ ያለፈው መቁሰል ሳይበቃ ለወደፊትም ሌላ አደጋ እንዲፈጠር እየተባበርን ነው ማለት ነው፡፡ የሚሻለው መፍትሔ፣ እኛ የወረስነው አለመግባባት ካለ፣ በቂም ሰበብ የተቋሰልነው ነገር ካለ፣ የአዲሱን ትውልድ ህይወት እንዳያውክ፣ እኛ ጋ መቆም አለበት ብዬ አምናለሁ፡፡

የዘመናችን ፈተናዎች ሳያንሱ፣ የቅርብ ጊዜ የቂም ታሪክንም እየተሸከመን፣ ከዚያም አልፎ የሩቅ ጊዜ የቅሬታ ታሪኩንም እየቆሰቆስን ቂምን የምናወርስ ከሆነ፣ ለማናችንም ሕይወት የማይጠቅም፣ የልጆቻችንንም ተስፋ የሚያጨልም አደጋ እየፈጠርን እናልፋለን፡፡ ቂምን መሻር፣ ቁስልን መፈወስ፤ ከዚያም አልፎ ለሁላችንም የሚበጅና የተስፋ ብርሃንን የሚያደምቅ ነገር መስራት የምንችለው በፍቅር ነው፡፡ ከ “አቡጊዳ” እስከ “ያስተሰርያል”፣ “ዳህላክ”፣ ቀላል ይሆናል”…እና ሌሎች ዘፈኖች ይህንን መልዕክት ያስተላልፋሉ፡፡ ግን ልዩ አዋቂ ስለሆንኩ ወይም ልዩ ሃይል ስላለኝ አይደለም፡፡ በፈጣሪ ሃይል ነው። ፈጣሪ በየትውልዱ የራሱን ድምጽ ያወጣል። የትውልዱን ድምጽ በኔ አድርጐ ማውጣቱን አምናለሁ፡፡ አሁን፣ ቅን እና ጥሩ ትውልድ አለ፡፡ የዚህ ቅን ትውልድ ድምጽ የፍቅር ድምጽ ነው። ግራ የሚያጋቡ፣ የሚያስጨንቁና የተተበተቡ ችግሮች ሁሉ በፍቅር ይፈታሉ፡፡ ከቂም፣ ከቁስል በፍቅር እንዳን፣ ፍቅር ያሸንፋል የሚለው መልዕክት የኔ ሳይሆን የትውልድ ድምጽ ነው፡፡ ይህ ቅን ትውልድ ተቀራርቦ፣ ተሰባስቦ አንድ ላይ የፍቅር ድምፁን የሚያስተጋባበት እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ ነው የፍቅር ጉዞ፡፡

በፖለቲካም ሆነ በሌላ ምክንያት፣ በተለያየ ችግርና አለመግባባት በአገራችን ለተከሰተው ቂምና ቁርሾም፣ እዚህ አገር ቤትም ሆነ በየአገሩ ተበታትነው የሚገኙ ወገኖቻችን፣ ቢያንስ ለልጆቻቸው ሲሉ ይቅር መባባልን እንዲቀበሉ ለመጋበዝ፤ የአዲሱ ትውልድ ስሜትም ይሄ እንደሆነ የሚገልፁ ዝግጅቶችን ለማቅረብ ነበር ያቀድነው፡፡ ዝግጅቱን በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች በስፋት ለማዳረስ ነው፤ በሄኒከን ከሚተዳደረው በደሌ ቢራ ጋር ተነጋግረን ውል የተፈራረምነው፡፡ በተፈራረምንበት እለት እንደተገለፀውም፤ የቋንቋና የብሔር ስብጥር ውስጥ ህብረትና አንድነታችንን የሚያጠናክር፣ ቂም እንዳንወርስና መልካም መንፈስን ለመጋራት አንድ ላይ የሚጮህ የፍቅር አላማ ያለው ዝግጅት ነው፡፡ ግን፣ የኢትዮጵያ ታሪክም ሆነ የኢትዮጵያውያን ሕይወት አንተ እንደምትለው፣ በፍቅርና ሰላም ብቻ የተሞላ ሳይሆን፣ በቂምና በግጭትም የተበረዘ ነው፡፡

አይደለም? ምን ጥርጥር አለው! ያሉና የነበሩ ነገሮች ናቸው፡፡ የህይወት እና የደስታ ውድነት ትርጉም የሚኖረው ከሞትና ከሀዘን ጋር ነው፡፡ የፍቅር ውበት የሚጐላው፣ ከጥላቻ ጋር ሲነፃፀር ነው። ነገር ግን ያሳዘኑን ነገሮች ላይ ብቻ ስናተኩር፣ አዲሱንና የወደፊቱን ትውልድ ያውካል፡፡ እዳ አለ የምንል ከሆነም፤ እዳ የሚከፈለውና የሚሸፈነው በፍቅር ብቻ ነው፡፡ ፍቅር መድሃኒት ነው፡፡ የነገር ሁሉ መጀመሪያና መጨረሻ ነው፡፡ ሁላችንም ህፃናትን ማቀፍና መሳም የምንወደው ለምንድነው? ገና ሲወለዱ፣ ገና ከመነሻው ሲፈጠሩ ፍፁም ፍቅር ስለሆኑ ነው፡፡ ያ የፍቅር ሃይል ነው የሚስበን፡፡ ህፃኑም እናቱ ጉያ ውስጥ የሚገባው በፍቅር ሃይል ነው፡፡ እንኳን ሰውን የመሰለ ክቡር ፍጥረት ይቅርና አውሬ የምንላቸው እንስሳት ውስጥም የምናየው የተፈጥሮ ሃይል ነው፤ ፍቅር፡፡ ነገር ግን በኑሮ ውስጥ በብዙ ውጣ ውረድ፣ ብዙ ቅሬታዎችና እንከኖች ስለሚያጋጥሙን ፍቅራችንን ሊበርዙብን ወይም ውስጣችንን መርዘው የውስጥ ህመም ሊሆኑብን ይችላሉ፡፡ ባዘንበትና በተቀየምንበት ነገር ላይ ቆመን ተውጠን ስንቀር በሽታ ይሆኑብናል፡፡ ለቅያሜ እልባት እየሰጠንና እየሰረዝን ካልሄድን፣ ይባስ ብለን ለልጅ ልጅ እያወረስን ከቀጠልን፣ በማህበረሰብ ደረጃ እንደዝገት ውስጣችንን እየበላ ይጨርሰናል ወይም እንደተዳፈነ እሳት በሆነ አቅጣጫ ተግለብልቦ ያቃጥለናል፡፡

እና ምን ይሻለናል ብለን ስናስብ፣ በቀድሞ ዘመን ወይም ባለፍንበት ጊዜ የተፈፀሙ መልካም ነገሮችን ወይም ስህተቶችን እንዳልነበሩ ማድረግ አንችልም። ወደኋላ ተመልሰን በህይወት የሌሉ ሰዎችን መሸለም ወይም እዳ ማስከፈል አንችልም፡፡ እነሱ በዘመናቸው አልፈዋል፡፡ ነገሩ ያለው የዛሬ ነዋሪዎች ላይ ነው፡፡ በቀድሞ ሰዎች ታሪክ የምንደሰትበትና የምናዝንበት፣ ትክክል የሆኑና የተሳሳቱ ስራዎች፣ የወደድነውና የተቀየምንበት ነገር ይኖራል፡፡ ቀጥለው የመጡ ትውልዶች የትኛውን ስሜት መያዝ፣ የትኛውን ስሜት ማውረስ አለባቸው? እኛስ የትኛውን ወርሰን የትኛውን ማሳደግ አለብን? ቅሬታና ቂምን ይዘው ያወርሱናል ወይስ ፍቅርንና መዋደድን? ቅያሜና ቂም ብንወርስ ምን ይበጀናል? ወደ ኋላ ተመልሰን እዳ ማስከፈል አንችል? ህይወት የሚቀጥለው፣ ካለው ነገር ላይ በመነሳት ነው፡፡ ስህተቶችን ትተን፣ ትክክል የሆኑትን ይዘን፣ ያን እያሳደግን ነው መቀጠል ያለብን፡፡ ታላላቆቻችን በተለያዩ አለመግባባቶች ውስጥ ያልፋሉ፡፡ አለመግባባትና ቅሬታ ባይፈጠር መልካም ነበር፡፡ ነገር ግን ቢያንስ ቢያንስ፣ የታላላቆችን አለመግባባት ወደ አዲሱ ትውልድ እንዳይሻገርና መጪውን ጉዞ እንዳያውክብን፣ ታላላቆቻችን ስለ አዲሱ ትውልድና ስለመጪው ትውልድ መጨነቅ ያስፈልጋቸዋል ብዬ አስባለሁ። ፍቅር ያሸንፋል የሚለው የታናናሾች የአዲሱ ትውልድ ድምጽም ጐልቶ መሰማት እንዳለበት አምናለሁ፡፡ የፍቅር ጉዞ የዚህ የአዲሱ ትውልድ መንፈስ ነው፡፡ የፍቅር ጉዞ ዝግጅት ከበደሌ ቢራ ጋር ተፈራርመህ በሳምንቱ ነው ውዝግብ የተፈጠረው። እንዴት ነበር የሰማኸው? ከጊዜ በኋላ ነው የሰማሁት፡፡
tedy afro new
አንደኛ በድሬዳዋ አንድ ተብሎ የሚጀመረው ጉዞ፣ ትልቅ የፍቅር መልዕክት የያዘ ስለሆነ፣ ያልተበታተነ ትኩረት ይፈለጋል፡፡ ከዚህ ውጭ ባለው ጊዜ ደግሞ፣ በሚቀጥለው መስከረም ወይም ብዙ ሳይቆይ አዲስ አልበም ለማድረስ የጀመርኩት ስራ አለ፡፡ ሁለቱም ቀናተኛ ስራዎች ናቸው፡፡ አእምሮህ ሌላ ነገር እንዲያስተናግድ አይፈቅዱልህም፡፡ በዚህ ምክንያት፣ ባልደረቦቼ በኢንተርኔት በተፈጠረው ውዝግብ ዙሪያ ሊያናግሩኝ ሲሞክሩ ስራ ላይ ሆኜ ብዙም ፈቃደኛ አልነበርኩም፡፡ ሲደጋገም ግን ሰማሁ፡፡ ማኔጀሬ (ዘካሪያስ) ተጨንቆ ነው የነገረኝ። ከሥራ አስኪያጅ አንፃር ሆነህ ስታየው መጨነቁ አይገርምም፡፡ ግን ተረጋግተን ነው የተነጋገርነው፡፡ አልተረበሻችሁም? ነገሩን አቅልለን አላየነውም፡፡ የፍቅር ጉዞ ትልቅ ዝግጅት ነው፡፡ ነገር ግን፣ በብዙ ወጣ ገባ መንገድ ከማለፍ እና ብዙ ውጣ ውረድ ከማየት የተነሳ፣ ችግሮችን ማስተናገድ ትለማመዳለህ፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ የፍቅር መልእክት፣ በቴዎድሮስ ካሳሁን የተፈጠረ ሃሳብ አይደለም፡፡ የነበረ ያለና የሚኖር የእግዚአብሔር ሃሳብ ነው፡፡ ያንተ ድርሻ ያ ሃሳብ ሲሰጥህ መቀበል ነው እንጂ፤ አንተ ከምትጨነቀው በላይ ከምንም አስበልጦ፣ ፈጣሪ ስለ አላማውና ስለሃሳቡ፣ ስለ እኛ እና ስለትውልዱ ስለሚጨነቅ፣ ብዙ አልተሸበርንም፡፡ ሁሉንም ነገር ለበጐ ያደርገዋል ብዬ አምናለሁ፡፡

“ጥቁር ሰው” በሚለው ዘፈንህ በአድዋ ጦርነት ዙሪያ ምኒልክንና ሌሎች የታሪክ ሰዎችን በማንሳት ዘፍነሃል፡፡ የምኒልክ ታሪክ ላይ ያለህን አስተሳሰብ በቅርቡ ቃለ ምልልስ አድርገህ በመጽሔት ታትሟል፡፡ ከዚህ ቃለ ምልልስ ጋር ተያይዞ ነው የምኒልክ ጦርነት ቅዱስ ነው የሚል አወዛጋቢው አባባል የተሰራጨው፡፡ በመጽሔት ታትሞ በወጣው ቃለምልልስ ላይ፣ እንደዚያ አይነት አባባል የለም፡፡ “አካሄዱን ያየ አመጣጡን ያውቃል” በሚል ርዕስ በእንቁ መጽሔት ታትሞ የወጣውን ቃለምልልስ ማየት ይቻላል፡፡ በምኒልክ መቶኛ የሙት ዓመት መነሻነት የተደረገ ቃለምልልስ ነው፡፡ በዚህ ቃለምልልስ ውስጥ ማንንም የሚያስቀይም አባባል የለበትም፡፡ ነገር ግን በኢንተርኔት ሲሰራጭ የኔ ያልሆነ አባባል ታክሎበት የተከፉ ሰዎች እንዳሉ ስሰማ፣ የተሳሳተውን መረጃ ለማስተካከል ምላሽ ሰጥተናል፡፡ እኔ ብቻ ሳልሆን፣ የመጽሔቱ አዘጋጅም አወዛጋቢው አባባል እኔ የተናገርኩት እንዳልሆነ፣ በመጽሔቱ ህትመት ውስጥም እንዳልነበረ አስረድቷል፡፡ ነገር ግን ውዝግቡ በዚህ አልተቋጨም፡፡ ለምን የፍቅር ጉዞን የሚያስተጓጉል ነገር ተፈጠረ አልልም፡፡ እዚህ ምድር ከተገለጡትም ሆነ ካልተገለጡት ሃይሎች ሁሉ የሚልቀው ፍቅር ነው፡፡ ክብደቱም የዚያኑ ያህል ነው፡፡

ስለዚህ የፍቅር ጉዞ ብለህ ስትነሳ፣ ያለ እክል እና ያለ ችግር ትደርሳለህ ማለት አይደለም፡፡ እንኳን ትልቁና ከባዱ ጉዞ ላይ ይቅርና፣ እንደ ቀላል የምናያቸው ጉዞዎች ላይም፣ ወደ ናዝሬት ወይም ወደ አዋሳ ለመሄድ ስትነሳ እንኳ፣ በመኪኖች መጨናነቅ ጉዞህ ሊጓተት ይችላል። ጐማ ቢተነፍስ ወይም ሞተር ቢግል፣ ጐማ ለመቀየርና የራዲያተር ውሃ ለመለወጥ መቆምህ አይቀርም፡፡ ከሁሉም የከበደው የፍቅር ጉዞ ላይማ፣ ለምን ፈተና ይፈጠራል ማለት አይቻልም። ከምንም በላይ ይቅር መባባልን የሚያበዛ የእርቅ መንፈስን ይዘህ ስትጓዝ፣ እንዲያውም ከተቻለ ታላላቆችህም እንዲግባቡልህና መግባባትን እንዲያወርሱ ስትጮህ፣ በዚህ ምክንያት ካንተ ጋር የማይግባባ ነገር ሲፈጠር፣ ነገሩን ንቀህ የምታልፈው አይሆንም፡፡ ምንም እንኳ፣ በተሳሳተ መረጃ ምክንያት የተፈጠረ ቅሬታ ቢሆንም፣ አንተም በተራህ የቅሬታ ባለቤት መሆን የለብህም፡፡ ፍቅር ሁሉንም ያቅፋል፡፡ በተሳሳተ መረጃ የተነሳ ያልወደደህንም ሰው ማቀፍ አለበት። የቃለምልልሱ ሁለተኛ ክፍል በሚቀጥለው ሳምንት ይጠብቁን፡፡

የኢቲቪ ሀሰተኛ ዶክመንታሪ ሲጋለጥ –በቢኤን ሬድዮ የተዘጋጀ ምላሽ

6 ቅን ጥያቄዎች ለአውራምባው ዳዊት ከበደ

$
0
0

ክዳጉ ኢትዮጵያ

ዳዊት ከበደ… የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲው የጋዜጠኝነት ምሩቁ ዳዊት… በ1997ዓ.ም ምርጫ መባቻ በነጻ ጋዜጠኝነቱ ምክንያት ከወቅቱ የቅንጅት አመራሮች ጋር ለሁለት አመት ጥቂት ፈሪ ጊዜ ከቃሊቲ በሮች ጀርባ ተከርችሞ የነበረው ዳዊት… ከቃሊቲ መልስ እጅግ በጠበበው የጋዜጠኝነት መከወኛ ክፍተት ከአጋሮቹ ጋር አውራምባ ታይምስ ጋዜጣን የመሠረተው ዳዊት… የአለም አቀፍ የጋዜጠኝነት ተሸላሚው ዳዊት… ከሁለት አመት ግድም በፊት “በገዢው ፓርቲና በአጫፋሪዎቹ ሚድያዎች የተከፈተብኝ ዘመቻ በደህንነቴ ላይ አደጋ ደቅኖብኛል በሚል በባሌ ሳይሆን በቦሌ ወደ ሰሜን አሜሪካ የተሰደደው ዳዊት… “ስደት ከምወደው የጋዜጠኝነት ሙያዬ አይነጥለኝም” በሚል አውራምባ ታይምስ ድረ-ገጽን የመሠረተው ዳዊት… በድረ-ገጹ ምስረታ ማግስት በሚያስተናግዳቸው ጽሑፎችና የምስል-ወ-ድምጽ መረጃዎች ከዲያስፖራ ሚዲያዎችና አለፍ ሲልም የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብቶ የቆየው ዳዊት… ወደ ኢት”ዮጵያ ተመለሰና ለመንግስታዊው ዘመን መጽሔት ስለ ዲስፖራ ተቃዋሚዎች የቁጥር አናሳነት፣ ስለ ብሔር ብሔረሰቦች በዓል ጥልቅ ትርጓሜ ወዘተ… ለማታዊ ማብራሪያ ሰጠ! ወይም የባለ ሽሙጡን የአቤ ቶኪቻውን አገላለጽ አዙሬ ለመጠቀም ይፈቀድልኝና “ከመውጣት” “መግባትን” መረጠ፡፡ ምክንያት- የጋዜጠኝነት ሙያን በስደት ሆኖ መከወን አዳጋች ነው በማለት፡፡
dawit kebede
የዳዊት ወደ ኢትዮጵያ መመለስ እዚህ አገር ቤት በምንገኘውም ሆነ በውጪ ሐገር ባሉ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን ዘንድ የተደበላለቀ ስሜትን ፈጥሯል፡፡ አበጀህ ያሉት እንዳሉ ሁሉ የዳዊት ሚና ለየለት ሲሉ የተደመጡም አሉ፡፡ መመለሱን በሐገሪቱ ለጋዜጠኞች ምቹ የስራ ከባቢ እንዳለ ማረጋገጫና የፕሬስ ተቆርቋሪ ተቋማትን አፍ ማስዘጊያ አድርገው የወሰዱት የመኖራቸውን ያህል የዲያስፖራው የፖለቲካ ንቃተ ሕሊና ደረጃ ለሠርጎ-ገብ ጋዜጠኝነት እንደማያመች በመረዳት የተደረገ የመልስ ጉዞ አድርገው የቆጠሩትም ጥቂት አይደሉም፡፡
በእኔ በኩል የዳዊትን ወደ “ቅድስቲቱ ሐገር” መመለስ ከማወደስም ሆነ ከማውገዝ በፊት ራሱ ዳዊት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ጥያቄዎች ቢመልስ ሸጋ ይሆን ነበር ባይ ነኝ፡፡ ጥያቄዎቼ በቅንነት እውነታውን ለማጥራት ከመፈለግ በመነጨ፤ ነገር ግን ያለምንም መሸፋፈን የቀረቡ ናቸው፡፡ ልቀጥል ዳዊት?

1. ከሁለት አመት ገደማ በፊት በስደት ወደ ሐገረ አሜሪካ ለማቅናትህ በምክንያትነት ያቀረብከው በወቅቱ “ገዢው ፓርቲ የሚቆጣጠራቸውና ለአገዛዙ ቅርበት ያላቸው ሚዲያዎች የከፈቱብኝ ዘመቻ በደህንነቴ ላይ ስጋት ደቅኖብኛል” የሚል እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ከስደትህ በኋላ በኢትዮጵያ የነጻ ሚድያ ከባቢ ምን አዲስ ነገር ተከሰተ?… የፍትሕ ጋዜጣ በስርአቱ ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነት ተዘጋች፣… በፍትሕ እግር የተተኩት ልዕልና ጋዜጣና አዲስ ታይምስ መጽሔትም የፍትህ ጋዜጣ ጽዋ እንዲደርሳቸው ተደረገ፣ የአንድነት ፓርቲ ልሳን የሆነችው ፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ “በማተሚያ ቤት እጦት” ከሕትመት ውጪ ሆነች (መንግስት የሚቆጣጠረው ማተሚያ ቤት በማያስፈልገው ድረ-ገጽ መታተሟ ቢቀጥልም)፣ ሐገር ቤት ትታተም በነበረችው አውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ያንተ ምክትል ሆኖ በአዘጋጅነት ሲያገለግል የነበረው የውብሸት ታዬ የይቅርታ ጥያቄ ውድቅ ተደረገ (በተቀራራቢ ጊዜ ተመሳሳይ የይቅርታ ጥያቄ ያቀረቡት ስዊድናዊያን ጋዜጠኞች ምንም እንኳ ከውብሸት ጋር ተመሳሳይ የደም ቀለም ቢኖራቸውም ጥያቄያቸው ተቀባይነት አግኝቶ ወደሐገራቸው ተሸኝተዋል)፣ ገዢው ፓርቲ የሚቆጣጠራቸውና ለአገዛዙ ቅርበት ያላቸው ሚዲያዎች (የአዲስ ዘመኑ አጀንዳ አምድ፣ የሚሚ ስብሐቱ የጋዜጠኞች ክብ ጠረጴዛ ወዘተ) አሁንም ከሥርዓቱ ተጽዕኖ በአንጻራዊነት ነጻ የሆኑ ሐሳቦችን ለማስተናገድ ድፍረት የሚያሳዩ ቁጥራቸው እንደዋሊያ የተመናመነ ጥቂት የህትመት ውጤቶችን በግንቦት ሰባትነትና በሻዕቢያ ተልዕኮ ፈጻሚነት በመወንጀል እርምጃ እንዲወሰድባቸው መወትወታቸውን ቀጥለዋል፡፡ ደጋግሜ ባስብም በስደት ወደአሜሪካ ከማቅናትህ በፊት ከነበረው የሚድያ ከባቢ የተለየ ለነጻ ጋዜጠኝነት ምቹ መደላድልን የሚፈጥር ሁኔታን መመልከት አልቻልኩም፡፡ ስለሆነም ለመመለስ ውሳኔ ያበቃህ ለእኔ ያልታየኝ አወንታዊ የሚዲያ ከባቢ ለውጥ ይኖር ይሆን? ወይስ አስቀድሞ ለስደት አብቅቶኛል ስትል ገልፀኸው የነበረውን ምክንያት ስህተትነት ገልፀህ ትስብ ይሆን?

2. በቅርቡ አንጋፋውን የህወሐት ሰው አቦይ ስብሀት ነጋን ጨምሮ በርካታ የስርዓቱ ቁንጮ ሰዎች በሰሜን አሜሪካ ተልዕኮው ብዙም ግልጽ ያልሆነ ቆይታ አድርገው ነበር፡፡ ለተልዕኳቸው በምክንያትነት ከቀረቡ መላ ምቶች “አንዱ አንድ እግራቸውን ሐገር ቤት ሌላኛውን በዲስፖራው መሐከል ያደረጉ” (አገላለፁ የCivilityው አባመላ ነው) የሚዲያ ሰዎችን ወደ ሐገር ቤት እንዲመለሱ ማማለያ ማቅረብ ነው የሚል ነበር፡፡ የስርዓቱ ቁንጮዎች ጉብኝት በመመለስ ውሳኔህ ላይ አንዳች ተጽዕኖ ይኖረው ይሆን? ከዚህ ቀደምም ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ አንድ አንጋፋ የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ጋዜጠኛን በብሮድካስት ፈቃድ አማልለው ከፕሮፌሽናል ጋዜጠኝነት ወደ ካድሬ ጋዜጠኝነት አስደናቂ መገለባበጥ እንድታሳይ አድርገው እንደነበረ በሰፊው ስለሚታመን የአንተ መመለስ ተመሳሳይ ውጤት እንደማይኖረው ማረጋገጫ ልትሰጠን ትችል ይሆን?

3. በሰሜን አሜሪካ ቆይታህ በድረ-ገጽህ በምታስተናግዳቸው ጽሑፎችና ሌሎች መረጃዎች ከዲያስፖራ የሚዲያ ተቋማትና አንዳንድ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ውዝግብ ውስጥ እንደነበርክ ይታወቃል፡፡ የመመለስ ውሳኔህ ይህ ውዝግብ በውስጥህ የፈጠረው አንዳች የመገፋት ስሜት ውጤት ይሆን? ከሆነስ ይህ የመገፋት ስሜት ወደሌላኛው ጽንፍ እንዳልወሰደህና በሐገር ቤት ልትሰራው በምታስበው የጋዜጠኝነት ሥራ ላይ ተጽዕኖ እንደማይኖረው ማረጋገጫ ልትሰጠኝ ትችላለህ?

4. ወደ ሐገር ቤት ለመመለስ ውሳኔህ እንደ መነሻ ያቀረብከው በስደት ዓለም ሆኖ በሐገር ቤት ላይ ያተኮረ ጋዜጠኝነት መከወን አዳጋች የመሆኑን እውነታ ነው፡፡ እኔ እስከሚገባኝ ድረስ ሐገራችንን በስደተኛ ጋዜጠኞች ብዛት ከዓለም በቀዳሚነት ያሰለፏት ጋዜጠኞች እንደ ጨው ዘር በመላው ዓለም ለመበተናቸው ሰበቡ ልክ ያጣው የአገዛዙ ውክቢያ እንጂ የስደት ዓለም ኢትዮጵያ ላይ ላተኮረ የጋዜጠኝነት ሥራ ምቹ ነው የሚል እምነት አይደለም፡፡ ምርጫው ያለው መንግስታዊ ውክቢያና ተግዳሮትን፤ አለፍ ሲልም የህትመት ፈቃድ መከልከልን ተቋቁሞ በመዝለቅ ወይም በስደት ሆኖ የቦታ ርቀትን በቴክኖሎጂ አቅም እያጠበቡ የሙያ ግዴታን ለመወጣት በመሞከር መካከል ይመስለኛል፡፡ ሌላው ምርጫ… ምርጫ ከተባለ… የጋዜጠኝነት መታወቂያ ይዞ በተግባር ግን የካድሬ ተግባር መከወን ነው፡፡ ምርጫህን ታሳውቀኝ ዳዊት?

5. አይበለውና፤ አገዛዙ በአንዳች ምክንያት የሕትመት ፈቃድ ቢከለክልህ አማራጭ ዕቅድ (plan B) ይኖርሃል? ወይስ ከዚህ ሥጋት ነፃ የሚደርግ አንዳች አይነት ማረጋገጫ ከመጋረጃው ጀርባ (Behind the scene) አግኝተሃል? መቼም እንዴት የህትመት ፈቃድ እከለከላለሁ ብለህ እንደማትጠይቀኝ ባለ ሙሉ ተስፋ ነኝ፡፡ ይህን መሳዩን ክልከላ በእስክንድር ነጋ፣ ሲሳይ አጌና ወዘተ ላይ በተደጋጋሚ አይተነዋልና፡፡

6. አውራምባ ታይምስ ድረ-ገጽ በተጀመረች በቀናት ውስጥ እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይታዩ በአገዛዙ የታገዱ ድረ-ገፆችን በመቀላቀሏ ይዘቷን ለማየት የምንፈልግ የዚህች የነፃነት ጠኔ ከዳቦ ጠኔ ባልተናነሰ ያጠቃን ምስኪን ዜጎች ፕሮክሲ ሰርቨሮችን በመጠቀም ከአገዛዙ ጋር ድብብቆሽ dawit kebedeለመጫወት ተገደን ቆይተናል፡፡ ነገር ግን የድረ-ገፁ ይዘት የአገዛዙን ፍላጎት በሚያንሟላ መልኩ መቃኘት ከጀመሩ በኋላ ያለአንዳች ከልካይ በሐገር ውስጥ መታየት ከመጀመሯም በላይ አይጋ ፎረምን የመሳሰሉ አፍቃሬ መንግስት ድረ-ገጾችም ወደ አውራምባ ታይምስ የሚመሩ አስፈንጣሪዎችን (Links) በገፆቻቸው ላይ አካተቱ፡፡ በድረ-ገጿ ላይ የተደረገው ክልከላ መነሳት በራሱ አንዳች ችግር ባይኖረውም፤ ይልቁንም ላይ ላዩን ሲታይ በጎ እርምጃ ቢመስልም ለዚህ በጎ እርምጃ ከጀርባ የተከፈላ ዋጋ ስለመኖሩ ጥያቄ ቢነሳ የሚገርም አይሆንም
ከላይ የዘረዘርኳቸው ነጥቦች እኔ እና በርካታ እኔን መሰል በኢትዮጵያ ጠንካራ የሚድያ ተቋማትን ለማየት የምንናፍቅ ዜጎች የአንተን ወደሐገር ቤት የመመለስ ውሳኔ ለማሞገስም ወይም ለመንቀፍ አቋም እንድንይዝ ከአንተ ዘንድ ምላሽ ልናገኝባቸው የሚገቡ የትኩረት ነጥቦች (concerns) ናቸው፡፡ ስለሆነም ፊት ለፊትና በተቻለ መጠን ከፍረጃ በፀዳ መልኩ ምላሽ እንደምትሰጠን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

የምንኖርበት ዘመን በመረጃ አብዮት በእጅጉ የተቃኘና የመረጃ ኃይልነት ከጥርጥር በፀዳ መልኩ የተረጋገጠበት ጊዜ ነው፡፡ እንደ አለመታደል ሆኖ ግን ነፃ የመረጃ ፍሰትን እንደ ዋነኛ የስልጣን ስጋት የሚያይ ሥርዓት በሐገራችን ሰፍኗል፡፡ የበለጠ እንደ አለመታደል ሥርዓቱ ነፃ የመረጃ ፍሰትን በሥጋት በማየት ሳይወሰን ይህን ፍሰት ለመገደብ አፋኝ ህጎች፣ የተደራጁ መዋቅሮች፣ ግዙፍ በጀትና ቀላል ቁጥር የሌለው የሰው ኃይል በመመደብ እንቅልፍ አጥቶ መሞከሩ ነው፡፡ ይህ ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታ ሰፍኖ ባለባት ሐገር ተግዳሮቶችን ተቋቁሞ የጋዜጠኝነት ሥራን ለመስራት የሚደረግ ማንኛውም ውሳኔ አድናቆት ሊቸረው የሚገባ ነው፡፡ ስለሆነም የውሳኔህ መነሻ ምንም ሆነ ምን… በሙያ ህይወትህ ላይ ውሳኔ የማድረግ መብትህን አከብራለሁ፡፡ መልካሙ ሁሉ እንዲገጥምህም ልባዊ ምኞቴ ነው!
አክባሪህ
ዳጉ ኢትዮጵያ
(ይህች ጽሑፍ የዳዊት ከበደ ወደሐገር ቤት መመለስ እንደዛሬው ታሪክ ሳይሆን ዜና በነበረበት ወቅት የጻፍኳት ነች፡፡ አሁን የዳዊትን የዘመን መጽሔት ቃለ መጠይቅ ሳነብ ከመጠነኛ ለውጥ ጋር ለንባብ በቅታለች)

እነአንዷለም አራጌ የቀጠሮ ቀናችሁ አልፏል፤ ለጥር 30 ተመለሱ ተባሉ

$
0
0

ፍርድ ቤቱ ለጥር 30 ቀጥሯቸዋል፤ ሬጅስትራር በበኩሉ ጥር 24 ቀን 2006ዓ.ም መቅረብ አለባቸው ይላል
Andualem aragie
የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ሪፖርተሪች ከአዲስ አበባ እንደዘገቡት በነአቶ አንዱአለም አሬጌ ስም ያለው የክስ መዝገብን በሚመለከት በፌዴራል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ከተከሳሽ ጠበቆችና ከቤተሰቦች ጋር ብንቀርብም ፍርድ ቤቱ ቀጠሮው ትላንት ስለ ማለፉ ተናግሯል፡፡ የተከሳሽ ጠበቆች በበኩላቸው አጀንዳቸው ላይ የያዙት ዛሬ ጥር 16 ቀን 2006 ዓ.ም መሆኑን ቢገልፁም በዳኛ አዳነ ንጉሴ፣ ዓሊ መሐመድ፣ አልመው ወሌ እና ሙስጠፋ አህመድ የተሰየመው ችሎት በበኩሉ የቀጠሮው ቀን ትላንት ማለፉን ተናግረዋል፡፡

ችሎቱ ቀጠሮው ዛሬ እንኳ ቢኆን መዝገቡ እጅግ ሰፊ በመሆኑ ውሳኔው እየተጻፈ በመሆኑ ምክንያት ለጥር 30 ቀን 2006 ዓ.ም እንዲቀርቡ አዟል፡፡

በሌላ በኩል የፍርድ ቤቱ ሬጂስትራር ቀጠሮው ዛሬ መሆኑን አምኖ ነገር ግን ለከሳሽ አቃቤ ህግ መጥርያ ያልተላከ በመሆኑ ለአቃቤ ህግ ድጋሚ ትዕዛዝ ለማፃፍ ጥር 21 ቀን 2006 ዓ.ም ችሎት እንድቀርቡ አዟል፡፡ ከሬጂስትራሩና ከፍርድቤቱ ቀጠሮ የትኛው ትክክል እንደሆነም ለማወቅ አልተቻለም፡፡
በሌላ በኩል አንድነት ፓርቲ ለክትትል ያመቸው ዘንድ የእስክንድር ነጋን የሰበር ሰሚ ይግባኝ ለማጣራት ሙከራ ቢያደርግም በእስክንድር ስም የቀረበ አንዳችም ይግባኝ እንደሌለ ሬጂስትራሩ አረጋግጧል፡፡ ባለቤቱን ጨምሮ ሎሎች አስተያየት ሰጪዎች ግን እስክንድር ያለ ጠበቃ ለመከራከር ይግባኝ ማለቱን አምነዋል፡፡

መንግስት ለአቶ አንዱአለም አያሌው ያቆማቸው ጠበቃና በሽብር ድርጊት ተጠርጥረዋል የተባሉትን ሰዎች ክስ የመሰረተው የመንግስት ዓቃቤ ህግ ከሀገር መሰደዳቸው ይታወሳል፡፡

የሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያውያን ጉዳይ፡ ሰሞነኛ ክራሞት

$
0
0

saudi ethiopian boy
ነብዩ ሲራክ ከሳዑዲ አረቢያ

ከመሰንበቻው …

በጅዳና በሪያድ መጠለያዎች …

* ባለፉት ቀናትም እንደ ክራሞቴ እኔን ጨምሮ የሳውዲ መንግስትና የእኛ መንግስት ተወካዮች “እጃችሁን ሰጥታችሁ ወደ ሃገር ለመግባት እጅ ስጡ ፣ ወደ ሃገር ግቡ! ” ስንል ወትውተን ወደ መጠለያ ያስገባናቸው በርካታዎች በጅዳ ሽሜሲ መጠለያ እና በሪያድ እስር ቤቶች ሮሯቸውን እየደወሉ ገልጸውልኛል። እኒሁ በመኖሪያ ፈቃድ ይኖሩ የነበሩ ነገር ግን የመኖሪያ ፈቃዳቸው የተበላሸባቸው ፣ ከአሰሪዎቻቸው ጋር የማይሰሩ እና በኮንትራት ሰራ መጥተው የሳውዲው የስደት ኑሮ ያላማራቸው “ወደ ሃገር እንግባ ብለን እጅ ሰጥተን ተሰቃየን “ብለውኛል ።እኒሁ ቁጥራው በውል ማረጋገጥ ያልቻልኩት ወገኖች ወደ ሃገር ለመግባት ቢፈልጉም በሳውዲም ሆነ በኢትዮጵያ መንግስት ተወካዮች በኩል መፍትሔ የሚሰጣቸው አጥተው ከወር በዘለቀ ጊዜ እንግልት እንደደረሰባቸው በምሬት ያስረዳሉ!

ለመናገር የሚከብደው አሰቃቂ ወንጀል ..

* ከትናነት በስቲያ ረቡዕ ማታ በስጨትጨት ያደረገኝን ወሬ ሹክ ያለኝ አንድ ከበድ ያለ መረጃ ሲደርሰው ብቻ “ሃሎ ” የሚለኝ ወዳጀ ነበር። አንድ የ7 አመት ታዳጊ በገዛ አባቱ የተፈጸመበት አሰቃቂ ወንጀል አሳፋሪ ነው ብቻ ተብሎ አይታለፍም ። ብቻ በዚህም ተብሎ በዚያ ጉዳዩን ወደ ፖሊስ ለማድረስ በተደረገው ርብርብ ወዳጆቸ ያደረጉት ትብበር ያኮራ ነበር ። ረቡዕ እኩለ ሌሊት መረጃው ደረሰኝ ። ሃሙስ በማለዳውም ጉዳዩን ቆንስል ሙንትሃ ሲነገራቸው የሆኑትንና የመስሪያ ቤታቸው ወንጀለኛውን ሱዳናዊ ባለጌ አባት ወደ ፍርድ ለማቅረብ ለፖሊስ ደብዳቤ በመጻፉ ረገድ ያልተለመደ ቀልጣፋ ትብብርንም ደንቆኝ አመስግኛለሁ! ከባለጉዳዩዋ ኢትዮጵያዊ ልበ ደንዳ እናት ጎን በመሆን ወዳጀ ” ሸሁና” ዘንድሮ በምትሰራውን መልካም ስራ የማውቃት አንዲት ወዳጀ የሰሩት አኩሪ ትብብርም አኩርቶኛል። ወገን ለወገን እንዲህ ሲደጋገፍ ፣ ሰብዕና ሲደፈር በህጻናት ላይ አስነዋሪ ወንጀል ሲፈጸም እንዲህ ተግቶ ለወገን አለኝታ የሚሆኑ ጥቂት ለሆዳቸው ብቻ ያላደሩ ለህሊናቸው የሚሰሩ በጣም ጥቂት ወገኖችን ማየት በእርግጥም ያስደስታል። ከቀትር በኋላ እናት ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሄዳ ክስ ስታቀርብ የገጠማት ቢያናድድም አይገርምም! የሆነው እየቆየሁ ሳስበው ግን ” ወዴት እየሄድን ነው! ” ስል ራሴን እንድጠይቅ አድርጎኝ ፣ አስደምሞኝ አመሸ .. !. ክሱን ተቀባይ ወታደር ” በልጀ ላይ በደል ፈጸመ !” ብላ ፍትህን ፈልጋ የሄደች እናት ባሏ ከሰራው ወንጀል ክብደት አንጻር የሚከተለውን ፍርድ ሃይለኛነት በመግለጽ ክስ አቅራቢዋን “በባልሽ ላይ ይህንን ከባድ ክስ ከመመስረትሽ በፊት አስቢበት !” ብሎ ህግ አስከባሪው እናት ከሁለት ቀን በኋላ አስባ ክሷን ለመመስረት እንድትመጣ መክሮ እንደመለሳት ሰማሁ ! ትናነት ሃሙስ …! ወቸ ጉድ … አልኩ የምለው ባጣ … ተናድጀ !

የውጭ ጉዳይ ሃላፊዎች ሽኝትና በጅዳ ቆንስል የጊዜያዊ ሰራተኞች ስንብት

* ከሁለት ወራት ወዲህ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተልከው በሪያድ እና በጅዳ መጠለያዎች ድጋፍ ሲያደርጉ የከረሙ ዲፕሎማቶች ወደ ሃገር ቤት መመለስ ጀምረዋል ። ችግሩ አለቀ እንዴ ? በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተልከው መጡ የተባሉትስ ሁሉ ቢቀር ለምን የነዋሪውን ሮሮ ሰብስበው ሳይሰሙት ሄዱ? በማለት ብዙዎች ጠይቀናል ። መልስ ግን የለም ! ስብሰባ ሲነሳ በወገን ችግር ሰብስቡን እያልን የምንለውን ጩኸት ባይሰሙትም የጉራጌ ልማት ማህበር አመታዊ ሪፖርት ሊያቀርብ በጠራው ስብሰባ አንድ በቅርቡ የሚሸኙ ልዑክ ከሪያድ መጥተው ከስብሰባው ተካፋይ እንደሚሆኑ በሹክሹክታ ተሰምቷል ። በጉራጌ ማህበሩ ስብሰባ የጨነቀውን ወገን ሮሮ ተሰምቶ ምክክር ቢደረግበትም አይከፋም ። ወዳጆቻችን የጉራጌ ተወላጆች “ነዋሪው ሰብስቡን !” ሲል አልሰማ ያሉትን ሃላፊዎችን በነዋሪውን ጉዳይ ዙሪያ ለማነጋገሩ ብርታቱን ይስጣቸው ብለን እንጸልይ !

የጅዳ ቆንስልም በተመላሽ ወገኖችን ሽኝት ለማሳለጥ በጊዜያዊነት ተቀጥረው የነበሩ በማስታወቂያ ተነግሮ የተቀጠሩ አልነበሩም ። በዋናነት በኢህአዴግ ድርጅት ፣ በማህበራታና ለመንግስት ቅርበት ባላቸው ግለሰቦች ጠቋሚነት ተቀጥረው በቆንስሉ ስር ይሰሩ የነበሩ ሰራተኞችን ቆንስሉ ማሰናበቱን እየሰማን እያየን ነው! ለመንግስት እና ለቆንስላው ከባባድ ሃ ፊዎች ካላቸው ቅርበት ብቻ ሳይሆን በኢህአዴግ ድርጅት አባልነት ፣ ደጋፊነት እና ተሰሚነት ባላቸው ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጠቋሚነት በጅዳ ቆንስል ተቀጥረው የነበሩት ወገኖች በስራቸው ያሳዩት ትምክህት ቢያናድድም አንዳንዶች በዚያ ክፉ ቀን ለወገን ያደረጉት ትብብር የሚመሰገን እንደ ነበር መናገር እወዳለሁ! ይህ የግል አስታያየቴ ነው!

ሹክሹክታው ሁሉ ከሹክሹክታ ያለፈ በጭብጥ መረጃ የተደገፈ ለመሆኑ አንድታምኑኝ አልማጸናችሁም ! መረጃ የማቀብላችሁ የመረጃ ክፍተቱን ለመዝጋትና ስለ እውነት ነውና እመኑኝ ! በቃ ! ሌላ የምለው የለም!

ሰላም

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ዛሬ የተቃውሞ ድምጻቸውን ሲያሰሙ ዋሉ (ቪድዮዎች ይዘናል)

$
0
0

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ዛሬ የተቃውሞ ድምጻቸውን ሲያሰሙ ዋሉ (ቪድዮዎች ይዘናል)
(ዘ-ሐበሻ) የእፎይታ ጊዜ ወስዶ የነበረው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች እንስቃሴ ዛሬ በኢትዮጵያና በአንዳንድ የዓለማችን ክፍሎች ቀጠለ። ‹‹730 ቀናት ለሃይማኖት ነጻነት›› በሚል ለዛሬ የተጠራው የአርብ (ጁምዓ) መርሀ ግብር በአዲስ አበባ የአንዋር መስጊድ ቁጥሩ በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ተገኝተው ድምጻቸውን ሲያሰሙ ውለዋል። ይህ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች “የ730 ቀናት የሃይማኖት ነፃነት” እንቅስቃሴ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በሚገኙባቸው የዓለም ክፍላት የሚቀጥሉ ሲሆን በሚኒሶታ ሴንትፖል ከ11:30 ጀምሮ እንደሚደረግ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

ድምፃችን ይሰማ ለዘ-ሐበሻ እንደላከው መረጃ ከሆነ ዛሬ በአንዋር መስጊድ የተደረገው እንቅስቃሴ ከመቼውም ጊዜ በላይ የሕዝብ ወኔ የታየበትና ጥያቄውም እንደሚቀጥል የሚያሳይ ነው።

ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እስር ቤት የሚገኙት ኮሚቴዎቻቸው እንዲፈቱ ቢጠይቁም፤ ከመንግስት በኩል የተሰጠ ምንም ምላሽ የለም። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በአደባባይ ድምጻቸውን እስከዛሬ ድረስ ቢያሰሙም መንግስታዊ ሚድያዎች “የሃይማኖት አክራሪነት ወንጀል ነው” የሚሉ ቪድዮችን ከማሳየት ውጭ አንዳችም ቀን ጥያቄያቸውን ዘግበው አለማወቃቸው ሙስሊሞቹን እያስቆጣ የሚገኝ ጉዳይ ነው ተብሏል።

በአንዋር መስጊድ የነበረውን በትንሹ በቪድዮ ለማየት፦

አያሌው ጎበዜ ቀለሉ “ለሱዳን መሬት እንዳይሰጥ አልፈርምም ስላለ ነው የተነሳው የሚባለው ውሸት ነው”

$
0
0

ከኢሳያስ ከበደ
ayalew gobeze
ከአማራ ክልል ፕሬዚዳንትነት በፈጣን ተነስተው የጡረታ ጊዜያቸውን በአምባሳደርነት እንዲያሳልፉ የተሾሙት አቶ አያሌው ጎበዜ በአንዳንድ የባህርዳር ከተማ ነዋሪዎች ትልቅ ክብር ይሰጣቸው እንደነበር ከሚሰሙ መረጃዎች ተገንዝበን ነበር። ክብር አሰጥጧቸዋል የተባለውም ጉዳይ “ለሱዳን ተቆርሶ የሚሰጠውን መሬት አልፈርምም ብለዋል፤ እርሳቸው አልፈርምም ያሉትን በወቅቱ ምክትላቸው የነበሩት አቶ ደመቀ መኮንን ፈርመዋል” በሚል ነበር። ዛሬ ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ጋር በሰጡት ቃለ ምልልስ ግን ያደንቋቸው፤ ያከብሯቸው የነበሩትን ሁሉ አንገት አስደፍተዋል። መቅለል ማለትም ይኸው ነው። አቶ አያሌው “በአመራር መተካካት በድንበር ምክንያት በከፍተኛ አመራሮች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት የተፈጸመ በማስመሰል የተነዛው ወሬ ጸረ ሰላም ሃይሎች የክልሉን ልማት ለማደናቀፍ የፈበረኩት ሴራ ነው” ሲሉ መናገራቸው አድርባይነታቸውን የሚያሳይ ነው ተብሏል። ይህም ደጋፊዎቻቸውን “ጸረ ሰላም ኃይሎች” የሚል ስያሜ እንዲሰጣቸው አድርጓል።

እርስዎ ሙሉውን ከዋልታ ጋር ያደረጉትን ቃለምልልስ ያንብቡትና ፍርድ ይስጡ – እኔ በበኩሌ አቶ አያሌው ቀለዋል ብያለሁ።

አምባሳደሩ በተለይ ከዋልታ ኢንፎርማሽን ማዕከል ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ መተካካቱ የተከናወነው የአገሪቱን ህዳሴ ዳር ለማድረስ የተነደፈውን የመተካካት መርህን ተከትሎ ለመልቀቅ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ነው።

የአማራ ክልል ከሱዳን ጋር ባለው ድንበር የተነሳ ከአንዳንድ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ምክንያት በአስቸኳይ ጉባኤ የተነሳሁ በማስመሰል የተነዛው ወሬ የክልሉን ልማትና ሰላም ለማደናቀፍ የታቀደ ነው ብለዋል።

አምባሳደር አያሌው አያይዘውም ጸረ ሰላም ሃይሎች በብአዴን ከፍተኛ አመራሮች መካከል ያለውን የጠበቀ ግንኙነትንና መተማመንን ለመሸርሸር፣ አመራሩን ለመነጣጠልና ሕዝብን ለማደናገር የፈጠሩት አጀንዳ መሆኑን ገልጸዋል።

በአማራ ክልል አመራሮች መካከል ድንበርን አስመልክቶ ውይይትና ክርክር የተደረገበት፣ ልዩነት የተፈጠረበት፣ አጀንዳ ሆኖ የቀረበበት ጊዜ አንዳልነበረም አምባሳደሩ ተናግዋል።

በሁለት አገራት መካከል የሚፈጠር የድንበር ጉዳይን የመወሰን ስልጣን ያለው የፌዴራል መንግስት እንጂ የክልል መንግስታት ስልጣን አለመሆኑን የገለጹት አምባሳደር አያሌው በፌዴራል መንግስት በኩልም ተላልፎ የተሰጠ መሬት የለም ብለዋል።

መንግስታችን መሬትን አሳልፎ የመስጠት ባህሪና ፍላጎት እንደሌለው የገለጹት አምባሳደሩ ተላልፎ የተሰጠ መሬት እንደሌለ ከሱዳን የሚዋስኑ የቋራ፤ የአርማጨሆና የመተማ አካባቢ ህዝቦች የሚያውቁት ጉዳይ ነው ብለዋል።

ባለፉት ጥቂት ዓመታት ብቻ በርካታ አዳዲስ አመራሮች በነባር አመራሮች መተካታቸውን የጠቆሙት አምባሳደር አያሌው የአማራ ክልልም በተቀመጠው የመተካካት መርህ መሰረት በወጣት አመራሮች እንዲጠናከር መደረጉን ገልጸዋል።

የክልሉ ምክር ቤት ጉባኤ ሰኔ መጨረሻ፣ በጥቅምት ወርና መንፈቀ ዓመት ላይ እንደሚደረግ ጠቁመው በጥቅምት ወር መካሄድ የነበረበት ጉባኤ የ2006 ዓ/ም እቅድ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ድረስ በማውረድ ከአርሶ አደሩ ጋር በመስኖ ልማት፣ በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃና በሚኖረን አደረጃጀት የጋራ ግንዛቤ ለመያዝ የተሰራው ስራ ሰፊ ጊዜ በመውሰዱ ጉባኤው ወደ ታህሳስ ወር መገፋቱን አምባሳደሩ ተናዋል። አምባሳደር አያሌው ጎበዜ በአማራ ክልል ለ21 ዓመታት በከፍተኛ አመራርነት ቆይታቸውም ደስተኛ እንደነበሩ ተናግረዋል።


የአርቲስት የሚኪያ በሀይሉ የቤተልሔም ት/ቤት የልጅነት አብሮ አደጐች የሀዘን መግለጫና የማጽናኛ መልዕክት

$
0
0

ሚኪያ በሀይሉን በሀዘን ላጣችሁ ሁሉ ፈጣሪ አምላክ መፅናናትን ይላክላችሁ!
Mikaya Behailu
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን! የእግዚያብሔር አብ ቸርነት፤ የድንግል ማሪያም አማላጅነት፤ የልጇ የእየሱስ ክርስቶስ ምህረት፤ የመንፈስ ቅዱስ ፀጋና በረከት፤ የጻድቃን ሰማዕታት ተራዳኢነት እህታችንን በሀዘን ከተነጠቅነው ቤተሰቦች፤ ዘመዶች፤ አብሮአደጐች፤ጐረቤቶች፤ ጓደኞችና የጥበቧ አፍቃሪዎች ጋር ሁሉ ይሁን አሜን! እሱ ሀያሉ አምላክ ልዑል እግዚያብሔር ብርታቱንና መፅናናቱን ለሁላችንም ይስጠን አሜን።

የኛ የሚኪያ አብሮ አደጐች ሀዘን ጥልቅና የመረረ ቢሆንም የውድ ቤተሰቦቿ፡ የቅርብ ዘመዶቿና የቦንቱ ናንሲ ሀዘን ግን ከእኛ በላይ የከበደ መሆኑን ከቅርብና ከሩቅ ሆነን በሚገባ ተረድተናል። በልጅነት ዕድሜ በቤተልሔም ት/ቤት ውስጥ አብረናት ያደግነው የእሷ ዘመን ተማሪዎች ከሀገር ውስጥም ሆነ ከባህር ማዶ ሁነን ውድ እህታችንን በሀዘን ስናስባት ሀዘናችሁ የእኛም ሀዘን መሆኑን በዚህ አጋጣሚ በመግለፅ ጭምር ነው። ሚኪያ
ከእኛና ከብዙዎቻችው ዘንድ በአካል የተለየች ነገር ግን በውስጣችን ህያው ሁና የምትኖር የዘመናችን ዕንቁ ወጣት ነች። እግዚያብሔር
መርጦ የሰጣትን የተፈጥሮ ችሎታ ያልቀበረች፤ ይልቁንም ለበጎ አላማ የተጠቀመችበትና ሀገርንና ህዝብንም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስጠራት የሞከረች የሀገርና የህዝብ ወኪልም ነበረች። ብዙ ታአምር መስራት በምትችልበት የለጋነት ዕድሜ በአምላኳ ፈቃድ በመጠራቷ ድንጋጤውና ሀዘኑ ቅስማችንን ቢሰብረውም ትታልን በሄደችው ቅርስና ጥበብ ግን ወደፊት ስንዘክራት እንኖራለን። አብረናት ባደግንባቸው በእነዛ የማይተኩ የልጅነት ዘመናት ውስጥ ያጠራቀምናቸው ትዝታዎች እንዲህ በቀላሉ የሚዘነጉና
ከአዕምሮአችን የሚጠፉ ባለመሆናቸው ምናልባት አንድ ቀን እሷንና ብዙዎቻችንን ያስተሳሰረውን የአብሮ አደጐች ትዝታ የምንተርክበት
አጋጣሚ ወደፊት ይመጣ ይሆናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። ፈጣሪ አምላክ ነፍሷን ከአብርሃም ከያዕቆብና ከይስሐቅ ጐን ያሳርፍልን። ምህረትን ሰጦ ነፍሷን ይማርልን። እናንተን ውድ ቤተሰቦቿንም ብርታቱን፤ መፅናናቱንና ጥንካሬውን በቶሎ ይላክላችሁ እንላለን።

ከቤተልሔም ት/ቤት የልጅነት ጓደኞቿ

Yebethlehembach1990@yahoo.com

ነፍስ ይማር

ከዚህ በታች ያለውን ግጥም ምትክ ለማናገኝላትና ገና በወጣትነት ዕድሜ ድንገት ለተለየችን ገጣሚና ታዋቂ ድምጻዊ ሚካያ በሀይሉ ሳበረክት ከህጻንነት ዕድሜ ጀምሮ በቤተልሔም ት/ቤት ውስጥ አብረናት ባደግነው የእሷ ዘመን ተማሪዎች ስምና ከእኛ ዕድሜ በላይ እንዲሁም በታች በዛው ት/ቤት ውስጥ በተማሩ ተማሪዎች፤ መምህራኖችና ሰራተኞች ስም ጭምር ነው። የሚኪያ ድንገተኛ ህልፈት በተለይ ከሀገረ ኢትዮጵያ ተለይተው በምዕራቡና በተለያዩ ዓለም ሀገራት ለረጅም ዘመን የሚኖሩትን የቅርብ ቤተሰቦች፤ ዘመዶች፤ አብሮ አደጐችና የጥበቧ አፍቃሪዎች ከማሰደንገጡም በላይ ለረጅም ዘመን በአካል ሳያገኟት በለጋነት ዕድሜ በመለየቷ የተሰማቸውን ከባድ የሀዘን ስሜት በአይነ-ህሊናዬ እንዳስተውለው አድርጐኛል። ህልፈቷን ድንገት በሰማሁበት ወቅትም የተሰማኝ ከፍተኛ የሀዘን ስሜት ከብዙዎቻችሁ ስሜት ጋር ይመሳሰል ይሆናል ብዬ ስለገመትኩ እንደ ፀበል ተረጭቶ የደረሰኝን በጣም ትንሽ የግጥም ስጦታ በመጠቀም የብዙዎቻችንን የሀዘን ስሜት (ከገለፀው በሚል) ከዚህ በታች እንደሚከተለው በግጥም ደረደርኩት ።

ከቅጥርዋ ግቢ ከሚሞቀው ጓዳ

ያቺ ቤተልሔም ኮከብ ወልዳ ወልዳ

እኔን ለምስክር እነሱን ለትንግርት ደባልቃ አሳድጋ የማልከፍለውን ሞት እንደ ብድር አርጋ

በል ክፈል አለቺኝ ሚካዬን በዕዳ።

ምነው እትዬ ቆንጂት ምነው ጋሽ አዲሱ?

በተቀደሰው ቀን መርዶን ማርዳታችሁ በዕለተ ሐሙሱ። ባሕር ማዶ ሆኜ ድምጿን ባየር ሞገድ ስጠብቅ በተስፋ

ቪኦኤ አረዳኝ ሳያስጠነቅቀኝ ገላልጦ በይፋ። መርዶ ሞገድ ሆኖ ባሕር ተሻገረ
ደረት መቶ መቅበር ሳልስት መቀመጥ 40 ማውጣት ቀረ።

ያ የጥበቦቸ ቤት የምርጦቸ መፍጠሪያ

ቴድሮስን የሰጠን ሚኪያን የሰጠን ለሀገር ማስጠሪያ

ምን ብሎ ይሆን ይሆን? ድንገት ሞት ሲነጥቀው ኮከቡን ከጉያ?

አባቷ ወለዱ እናቷ ወለዱ ላገር የምትበቃ ኩሩ ኢትዮጵያዊ

ቅኔውን የምትዘርፍ፤ ወርቁን የምትመዝን፤ሰሙን የምታቀልጥ አማላይ ድምፃዊ ግና ምን አተረፍን?
አስር ሀያ አመት አይኖችሽን ሳናይ አይናችንን ሳታይ ከአንጀት ተነፋፍቆ በሬዲዮ ሞገድ ለዛውም በግላጭ መርዶሽን ጠብቆ
በባይተዋር አገር በባዕዳን ምድር በእንባ ተንሰቅስቆ

ሀዘን ያደማውን የልጅሽን አንጀት እንደ ዝናር ታጥቆ ሰራቂ ድምፅሽን የጥንት ትዝታሽን ዘላለም ሰንቆ
ሚካዬን የሚያክል አብሮአደግ ያገር ልጅ በሀዘን ተነጥቆ እ…ህ….እየተባለ በቁጭት ህይወት ላይ ፀፀትን አጥልቆ ኪሳራ ነው እንጂ ትርፍማ መች ታውቆ!
እንግዲህ ቤተሎች እርማችሁን አውጡ ድፍን ኢትዮጵያዎች እርማችሁን አውጡ የድምጿ አፍቃሪዎች እርማችሁን አውጡ አምላክ የጠራትን ምትክ ላታመጡ። ከዚህ ክፉ ምድር የሱ-ዓለም ተሽሎ የፈጠራት አምላክ ልውሰድሽ ነኝ ብሎ በሰማዪ ገነት አኖራት ጨክኖ።
እንግዲህ ዘምሪ ከነኪሩቤል ጋር ከመላዕክቶች ጋር አውርጂ ምስጋና

ድሮም ስጦታሽ ነው ድምፅ ማንቆርቆሩ ማስረቅረቅ በዜማ። እኛ ግን……….
ነፍስ ይማር፤…. ነፍስ ይማር፤….. ነፍስ ይማር….. ብለናል

ለእናትና አባቷ ለምትክ ልጇ፤ ለስጋዋ ክፋይ መፅናናት ልከናል።

ደረጀ ሙሉጌታ ተፈሪ ከአትላንታ

Yebethlehembach1990@yahoo.com

በሚኒሶታ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ዛሬ ባደረጉት ተቃውሞ ሰልፍ ላይ የተደረገ ንግግር ሙሉ ቃል

$
0
0


(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የ እፎይታ ጊዜያቸውን ጨርሰው ወደ ተቃውሟቸው መመለሳቸውን ጠዋት ላይ በዘ-ሐበሻ ላይ መዘገባችን ይታወሳል። የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎቻችን ካልተፈቱ ተቃውሟችንን አናቆምም የሚሉት እነዚሁ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በ40 የኢትዮጵያ መስጊዶች፣ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ደጃፍ ያደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ እና ሴንት ፖል ሚኒሶታ በስቴት ካፒቶል ውስጥ የተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ለዚህ ተጠቃሽ ነው።

ዛሬ (ጃንዋሪ 24 ቀን 2014 ዓ.ም) ሪሳላ ኢንተርናሽናል ባዘጋጀውና በሚኒሶታ በተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የተደረገው ንግግር እንደሚከተለው አስተናግደነዋል።

እጅግ ሩህሩህና እጅግ አዛኝ በሆነው በፈጣሪአችን አሏህ ስም፡-
ውድ አባቶች፣ እናቶች፣ ወንድሞች እና እህቶች በቅድሚያ በዚህ ከፍተኛ ቅዝቃዜ የህንን ሰላማዊ ሰልፍ ተግባራዊ ለማድረግ እዚህ በተገኛችሁ በሪሳላ ኢንተርናሽናል ስም እጅግ በጣም አመስግናለሁኝ፤ አሏህ ደግሞ ምንዳችሁን ይክፈላችሁ፡፡
Ethiopian muslims in minnesota
ውድ ወገኖቼ፡-
በዚህ ስፍራ ላለፉት ሁለት አመታት በተከታታይ ለተመሳሳይ አላማ ተሰባስበን ድምጸችንን ስናሰማ ቆይተናል፡፡ ለዚህ ምክንያት የሆነው የሃገራችን ሙስሊም መብት መገፈፍና ጭቆናው ከእለት ወደ እለት አድማሱ እያሰፋ መምጣቱ ነው፡፡ የእምነታችን መብት ጥሰትና የወገኖቻችን እንግልት እሰካላቆመ ድረስ እኛም ከአሏህ ጋር ድምጻችን ማሰማተችንና በተለያየ መልኩ ትግሉን መደገፋችን የቀጥላል፤እዚህ ሆነን ልናደርጋቸው ከምንችላቸው ተግባራት ውስጥ አንዱና ትንሹ ነውና፡፡ አንዳንድ ወገኖች የኛን ጩሀት ጥያቄ ውስጥ ይከቱታል፣ ነግር ግን ልንገነዘብ የሚገባው አጃችን አጣጥፈን በመቀመጥ የሚመጣ ውጤትም የለም፡፡ የህብረት ድምጻችን ቢያንስ በጭቆናው የእሳት ወላፈን የሚለበለቡ ወገኖቻችን ከፍተኛ የሞራል ጥንካሬና የትግል መነቃቃትን ፈጥሯል፤ ይሀውም በተለያዩ መንገዶች ሲገለጹ በተግባር ተመልክተናል፡፡ ስለዚህ ወገኖቼ አሁንም ደግመን ደጋግመን ድምጻችን ይሰማ! የእምነት መብት ይከበር እንበል! እስራቱና እንግልቱ ይቁም! መንግስት ለህግ ተገዥ ይሁን! እንበል፡፡
የዛሬው የተቃውሞ ሰልፍ ትኩረት በውድ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ የተላለፈውን ፖለቲካዊ የምንግስት ውሳኔ በመቃወምና በተጓዳኝም ኮሚቴዎቻችን የእስር እንግልት ላይ ሆነው ስለትግሉ ቀጣይነት የሰጡት ታሪካዊ መግለጫ ከልብ በመደገፍ ምንጊዜም ከጎናቸው መሆናችንን ለመግለጽ ነው፡፡ ሪሳላ ኢንተርናሽናል ደግሞ ሶስቱን (ኢቅራዕ፣ ተውፊቅ እና ተውሂድ) ማህበረስብ ወክሎ የትግሉን የእለት ተእለት ሂደት በቅርብ የሚከታተል ሲሆን ከወራት በፊት በጀመረው የኦሮምኛ የሬድዮ ፕሮግራም ስርጭት ሂደቱንን በሳምንት ከ2-3 ቀናት ይዘግባል፤ ዝግጅቱን በድህረ ገጻችን (www.risalainternational.org) ወይንም በስልክ ቁጥር 712-432-7042 በስራም በእረፍት ላይ ሆናችሁ መከታተል ትችላላችሁ፡፡ በአሏህ ፈቃድ የአማርኛ ስርጭትም የሚጀመርበትን ሁኔታ በማመቻቸት ላይ ነን፣ ለሁሉም የናንተን እርዳታና የቅርብ እገዛ ለስኬቱ ወሳኝ ነው፡፡
በውጭ ሀገር ሆነን ለምናደርገው የመብት ማስከበር የትግል እንቅስቃሴ መተባበርንና በአንድነት መስራት ወሳኝ በመሆኑ የዛሬው የተቃውሞ ሰልፍ በተለያዩ የአለማት ክፍል የሚደረጉ ሲሆን እኛም የዚሁ ማህበረሰብ (ጀማ) አካል በመሆን ድምጻችን በማሰማት ላይ ነን፡፡ ሪሳላ ኢንተርናሽናል ከዚህ ስብሰባ በተጨማሪ ሌሎች 18 ያህል የተለያዩ የሙስሊም ኮሚኒቲዎችን በማስተባበር ባለ 6 ነጥብ የጋራ የአቋም መግለጫ የወጣን ሲሆን የህንኑ በተለያዩ ድህረ ገጾችና የሬድዮ ዝግጅቶች ላይ ተለቀዋል፡፡ የህም የትብብራችን መጀመሪያ ሲሆን ይበልጥ ተጠናክረን ሌሎች ወገኖችንም በመጨመር የአሏህ ፈቃድ ሆኖ የበለጠ ስራ እንሰራለን፡፡
በአሁኑ ወቅት የወያኔ/ኢህአዲግ ቡድን አንድን ጥፋት በሌላ ተጨማሪ ጥፋት የሙስሊሙን የትግል እንቅስቃሴ ለማጨነገፍ እየጣረ ነው፡፡ አካልዴማ የኢቲቪ ትረኢት ከሰሞኑ ሌላ አካልዴማ ወልዷል፡፡ ሙስሊሙን ማሰርና ማንገላታት በሌላ ተጨማሪ እስራቶችን እንግልቶች ቀጥሏል፡፡ይህ ሁሉ የጥፋት እርምጃ ሙስሊሙ ለጠየቃቸው ቀጥተኛና ቀላል የመብት ጥያቄዎች ፈጽሞውን ምላሽ ሊሆን አይችሉም፡፡ ትግሉም የተጠየቁት መሰረታዊ መብቶች እስኪመለሱ የሚቀጥል ይሆናል፡፡ የእምነት ነጻነታችንና የእምነት ተቋሞቻችን ነጻ እስካልሆኑ ድረስ ክንዳችንም ሆነ አእምሮአችን ሊያርፍ የሚችልበት አንዳችም ምክንያት የለም፡፡ መዳረሻችን ድላችን ነው፡፡ ድላችንም የእምነት ነጻነታችን ነው፡፡ ከዚህም በላይ አልጠየቅንም ከዚህ የተለየ ምላሽ ህዝባችንን ሊያረካው አይችልም፡፡
ውድ ወገኖቼ፡-
አሁንም ደግመን ደጋግመን በኢትዮጵያ ስልጣንን ለተቆጣጠረው ወገን ልናስገነዝብ የምንሻው የጭቆና እጁን ከእምነታችንና ከእምነት ተቋሞቻችን እንዲነሳልን ነው፡፡ የጭቆናው መጠን በዚህ መልኩ ከቀጠለና ማህበረሰባችን የመኖር ህልውና በመፈታተን መጨረሻው ለሁሉም ወገን አደጋ መሆኑን ማስገንዘብ እነወዳለን፡፡
የሀገራችን ዜጎች በሙሉ በተለይም የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖችን እሰካሁን በተያያዝነው ትግል የደረጋችሁልን የአጋርነት ሚና ከልብ የሚያስመሰግን ሲሆን፤ለወደፊቱ በምናደርገውም ተግል ከጎናችን ለመሆናችሁ አንጠራጠርም፡፡ የእመነት ነጻነት መከበር የሁሉም የሰው ልጆች ጥያቄ ነውና፡፡
በድጋሚ በዚህ ሰልፍ ላይ ለተገኛችሁ ሁሉ ልባዊ ምስጋናዬን እያቀረብኩ በቀጣይነት ለምደርገው የትግል እንቅስቃሴ ከጎናችን እነድትሆኑ አሁንም ጥሪአችንን እናቀርባለን በተለይም የወጣቶችንና የሴት እህቶቻችን ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ ሪሳላ ኢንተርናሽናል በጋራ እንድንሰራ ተደጋጋሚ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
• ተግላችን የእምነት ነጻነታችን እስኪከበር የቀጥላል!
• ዘወትር ከመፍትሄ አፈላላጊው ኮሚቴ ጎን እንቆማለን!
• በፍትህ ማላገጥ የቁም!
• የሙስሊም ተማሪዎች የእምነት ነጻነት የከበር!
• ፍትህ ለሁሉም!
• አንድነታችን ጥንካሬአችን ነው!
• እስላም ሰላም ነው!
• የድምጻችን ይሰማ ጥሪ ተግባራዊ እናደርጋለን!
• የኢቲቪ የውሸት ተካታታይ ድራማ አያወነብደንም!
• ድምጻችን ይሰማ!
• አሏሁ አክበር! አሏሁ አክበር! አሏሁ አክበር!

ማስገንዘቢያ ለዘ-ሐበሻ ወዳጆች

$
0
0

zehabesha

ባለፉት 3 ቀናት በአስተያየት መስጫ ሳጥኖች ላይ በሰርቨራችን ላይ ባጋጠሙን ቴክኒካል ችግሮች የተነሱ ሳናትማቸው ቀርተናል። ብዙዎቻችሁ አስተያየቶቻችሁን ለማተም ያልፈለግን እንደመሰላችሁ ከሰጣችሁን አስተያየት ለመረዳት ችለናል። ሆኖም ችግሩ ከአቅማችን በላይ ስለነበረ እንጂ በተፈጥሮ የተሰጣችሁን ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብቶቻችሁን እየተጋፋን እንዳልነበር ትረዱን ዘንድ በትህትና እንጠይቃለን።

ዕውነት ያሸንፋል!!

ሔኖክ ዓለማየሁ ደገፉ
የዘ-ሐበሻ ድረገጽ ዋና አዘጋጅ

ይድረስ ለጓድ መንግሥቱ ኃ/ማርያም

$
0
0

ከወልደ ቴዎፍሎስ (ኦታዋ፡ ካናዳ)
tewoflos2013@gmail.com
“የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል።”
ትንቢተ ኢዩኤል 2፡32፤ ሮሜ 10፡13.

የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት እና የደርግ ሊቀመንበር ጓድ መንግሥቱ ኃ/ማርያም፡ ባሉበት በሐራሬ ዝምቧብዌ ለጤናዎ እንደምን ከረሙ? መቼም “ጓድ” ብዬ ስጠራዎ ደስታ እንጂ ቅሬት እንደማይሰማዎ እርግጠኛ ነኝ፤ ይህን መጠሪያ ስለሚወዱት፡ የትግል አጋርዎችዎን ብቻ ሳይሆን ውድ ባለቤትዎንም “ጓድ” ብለው ለመጥራት ወደኋላ አላሉምና (ትግላችን፤ “ምስጋና” ገጽ ፭)።
mengistu hailemariam
“ትግላችን፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ የትግል ታሪክ” የተሰኘው መጽሐፍዎ ለህትመት ከበቃ ዓመት ከመንፈቅ ቢሆነውም፡ ሰሞኑን እጄ ገብቶ አነበብኩት። እኔ ያነበብኩት ለአምስተኛ ጊዜ በአዲስ አበባ በሐምሌ ወር 2004 ዓ.ም. የታተመውን ሲሆን፡ መጽሐፉ ብዙ ጥያቄዎችን ቢፈጥርብኝም ርዕሴ እንደሚያመለክተው በመረጥኩት ጉዳይ ላይ ብቻ ይህን አጭር ጦማር ልጽፍልዎ ወደድሁ።

የተወለድኩት እርስዎ እና መሰሎችዎ በኢትዮጵያ የፊውዳሉን ሥርዓት በገረሰሳችሁበት ዓመት ነው። ስለዚህ በዕድሜ አሳምረው አባቴ መሆን ይችላሉ። እንዲያውም ከመጽሐፍዎ ስለእርስዎ ዕድሜ እንደተረዳሁት ከወላጅ አባቴ በ5 ዓመት ይበልጣሉ። “ውሃ ሽቅብ አይፈስም” እንዲሉ ኢትዮጵያዊው ጨዋ ባህላችን እንዳስተማረን ልጆች በአባቶቻቸው ላይ ሂስ (ነቀፋ) መሰንዘር ባይችሉም፡ እንደ አንድ የ72 ዓመት (ካልተሳሳትኩ) ኢትዮጵያዊ አዛውንት እርስዎን በማክበር፡ ከይቅርታ ጋር መጠነኛ ምክር ልለግስዎ ወደድሁ። መቼም “በአብዮቱ ፍንዳታ ወቅት የተወለደ ልጅ እንዴት እኔን ይመክራል?”፤ “ወይኔ መንግሥቱ ተደፈርኩ!” በማለት ዘራፍ እንደማይሉ ተስፋ አደርጋለሁ። ይህን አነስተኛ ጦማር ለተለያዩ ድህረ ገጾች ለመላክ ስላሰብኩም፡ መጣጥፌን አንብበው በጽሑፍ መልስ ቢሰጡኝ ደስ ይለኛል።
ይህ ጦማር የመጽሐፍዎ አጠቃላይ ቅኝት (Book Review) ወይም ግምገማ ስላልሆነ፡ በመጽሐፉ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ላይ አስተያየት አልሰጥም። ነገር ግን ወደፊት በሚያዘጋጇቸው ተከታታይ ቅጾች ላይ ያካትቷቸው ዘንድ፡ የተወሰኑ ነጥቦችን ልጠቁም፤
- እስካሁን ድረስ የብዙ ኢትዮጵያውያን ጥያቄ የሆነው፡ 60ዎቹ የአፄ ኃይለሥላሴ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ዘግናኝ በሆነ መልኩ ያለፍርድ የተገደሉበትን ሁኔታ መጽሐፍዎ በዝርዝር አይዳስስም። አንባቢዎችዎን ተስፋ በሚያስቆርጥ መልኩ ከሌ/ጄነራል አማን ሚካኤል አንዶም አሟሟት ጋር በማያያዝ ይህን ዐቢይ ጉዳይ በአንድ ፓራግራፍ ብቻ ነው ያለፉት (ትግላችን፡ ገጽ 219)።

- ስለ ብ/ጄነራል ተፈሪ ባንቲ ግድያ በመጽሐፍዎ ምንም ነገር አልነገሩንም። ገጽ 253 ላይ ግን፡ ስለ እኚሁ ጄነራል ማንነት በቅጽ 2 እንደሚጽፉ ስላሳወቁን ይህን በተስፋ እንጠብቃለን።

- ስለ አፄ ኃይለሥላሴ እና ስለ ሌ/ኮሎኔል አጥናፉ አባተ አሟሟት (ግድያ) የተረኩት ትረካ፡ በወቅቱ በሕይወት የነበሩ እና እውነታውን የሚያውቁ ኢትዮጵያውያንን ቀርቶ ከአብዮቱ ፍንዳታ በኋላ የተወለድኩትን እና ስለወቅቱ ቀውጢ ሁኔታ ምንም የማላውቀውን እኔን እንኳ አላሳመነኝም። በመካከላችሁ በነበረው የሥልጣን ፉክክር ምክንያት ኮሎኔል አጥናፉን ከጄነራል ተፈሪ ባንቲ ጋር የእርስዎ ከሳሽ (ገጽ 246) እንዲሁም መስከረም 13/1969 ዓ.ም. የተሞከረብዎ ግድያ “ፈጣሪ፤ መሪ እና ተጠርጣሪ” (ገጽ 250) አድርገው ያስቡ ስለነበር፡ ኮሎኔል አጥናፉ በተወሰደባቸው አብዮታዊ እርምጃ የእርስዎ እጅ ወይም ግፊት የለበትም ብሎ ማሰብ ጥበብ የጎደለው የዋህነት ይመስለኛል። የአፄ ኃይለሥላሴ እና የጄነራል ተፈሪ ባንቲ ህልፈተ ሕይወት ጉዳይም እንዲሁ።

ሞት ይርሳኝ፡ የተነሳሁበትን ጉዳይ ረሳሁት እንዴ? አይ አልረሳሁትም፤ ጥቆማዬ አላልቅ ብሎኝ ነው እንጂ። ከላይ ያነሳኋቸውን ነጥቦች አብዛኞቹ የመጽሐፍዎ አንባቢዎች ይጋሩታል ብዬ አስባለሁ። አሁን ደግሞ የጦማሬ ርዕስ ወደሚያጠነጥንበት ጉዳይ ከመግባቴ በፊት በቅጽ 2 መጽሐፍዎ እንዲመልሱልኝ የምፈልጋቸውን የግሌን ጥያቄዎች ላቅርብ፤

- እርስዎ እና ባልደረቦችዎ የተከተላችሁት የኮሚኒስት ሥርዓት፡ በእግዚአብሔር ሕልውና በማያምኑ ሰዎች (atheists) የሚመራ ስለሆነ አንድ ሰፊ ሕዝብን ለማስተዳደር የሕዝቡን የእምነት ተቋማት በመቆጣጠር ላይ ያተኩራል። ይህ አባባል የራሽያ ኮሚኒስት ሥርዓት በራሽያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን፤ እርስዎ የመሩት ተመሳሳይ ሥርዓት ደግሞ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ ባደረሷቸው ተጽዕኖዎች ይረጋገጣል። ታዲያ በቅጽ 1 መጽሐፍዎ፡ ደርግ የኢትዮጵያ መኩሪያ ከሆነችው ከጥንታዊቷ እና የአገሪቱ ብሔራዊት ቤተክርስቲያን ተብላ ልትጠራ ከሚገባት (ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን) ጋር ስለነበረው ግንኙነት ምንም ነገር ያልነገሩን ለምንድን ነው?
- በወቅቱ የነበሩት የቤተክርስቲያኒቱ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስን በመጽሐፍዎ ያነሷቸው በአፄ ኃይለሥላሴ ጸሎተ ፍትሐት ጉዳይ ላይ ብቻ ነው (ገጽ 271)። እባክዎን የተከበሩ ኮሎኔል መንግሥቱ፡ በሞቴ ልበልዎና ፓትርያርክ ቴዎፍሎስን ማን እንደገደላቸው በክፍል 2 መጽሐፍዎ ይንገሩን።
- አያይዘው ደግሞ፡ ከፓትርያርክ ቴዎፍሎስ ግድያ በኋላ እርሳቸውን የተኳቸው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ-ሃይማኖት እንዴት እንደተሾሙ በዚሁ በቅጽ 2 ቢያብራሩልን ምስጋናዬ የላቀ ነው። መቼም ጓድ ሊቀመንበር፡ “እኔ ስለ ቤተክርስቲያኒቱ ፓትርያርኮች የማውቀው ነገር የለም” የሚሉ ከሆነ፡ አኔም ሆንኩ ሌሎች አንባቢዎች በጣም ነው የምንታዘብዎ።

ቅጽ አንድን ሳነብ፡ ከ50 እና ከ30 ዓመታት በፊት የተፈጸሙ ነገሮችን በዝርዝር የማስታወስ ችሎታዎን በጣም አድንቄያለሁ። እርስዎ የ20 ዓመት ወጣት መኰንን ሳሉ ስለገጠምዎት ጉዳዮችም ሆነ የፊውዳሉን ሥርዓት በገረሰሳችሁበት ጊዜ (ያኔ እርስዎ የ34 ዓመት ጎልማሳ ነበሩ) ስለተፈጠሩ ሁኔታዎች ያወጉን በሚገርም መልኩ ጠለቅ ካሉ መረጃዎች ጋር ነው። ጉዳዮቹ የተፈጸሙባቸውን ቦታዎች ከረጅም ዓመታት በኋላ እንኳን ቢሆን በፍጹም አልረሱም፤ በአካባቢዎ የነበሩትን ጓዶች ደግሞ፡ ከነማዕረጋቸው እና የአባት ስሞቻቸው ጭምር ላፍታ እንኳ አልዘነጓቸውም። ታዲያ በተፈጥሮ ስለተለገሱት ንቃተ ኅሊናም ሆነ የማስታወስ ከፍተኛ ችሎታ “የፍጥረታት ፈጣሪ ልዑል እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን” ብል በአባባሌ አይስማሙም?

መቼም የ72 ዓመት አረጋዊ ሆነው “የምን እግዚአብሔር አመጣህብኝ?” እንደማይሉኝ ተስፋ አደርጋለሁ፤ ተስፋ እና ምኞት አይከለከልም፡ አይደል? “ኢትዮጵያ ትቅደም” የምትለዋን መፈክር በጥቁር ሰሌዳ ላይ ለደርጉ አባላት ከጻፉበት ጊዜ ጀምሮ፡ እንደ ታላቁ ኢታዮጵያዊ ጀግና አፄ ቴዎድሮስ እስከመጨረሻዋ ጥይት ሳይዋጉ ወደ ሐራሬ እስከኮበለሉበት ግንቦት 1983 ዓ.ም. ድረስ የእግዚአብሔርን ስም በስህተት እንኳ ሲጠሩ አልሰማንም። እኔ እና የእኔ ትውልድ ያደግነው የሚያንባርቅ እና እሳት የሚተፋ የሚመስል ድምጽዎን በሬድዮ እየሰማን ሲሆን፡ ክርስትናን በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን የተቀበለች የታላቂቱ ኢትዮጵያ ርዕሰ-ብሔር እንደመሆንዎ የልዑል እግዚአብሔርን ስም በንግግርዎ መሀል ሲጠቅሱ ለመስማት አልታደልንም። የዚህ ምክንያቱ፡ ለቆሙለት የማርክሲስት ሌኒኒስት ርዕዮት (አመለካከት) ታማኝ ለመሆን ብለው ነው ወይስ ስለ ሀልዎተ እግዚአብሔር “እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች” (መዝሙረ ዳዊት 67፡31) ከተባለላት ከኢትዮጵያችን የተማሩት ምንም ነገር ስላልነበር?

ወላጅ አባትዎ አቶ ኃ/ማርያም (ይቅርታ ሌላ የማዕረግ ስም ካላቸው) ስለፈጣሪ ምንም ነገር ሳይነግርዎ ነው ያሳደጉዎት ብዬ ላስብ አልችልም። ለመሆኑ እርስዎ በልጅነትዎ ፊደል ሲቆጥሩም ሆነ ቄስ ትምህርት ቤት ገብተው ዳዊት ሲደግሙ (እንደደገሙ በመገመት ነው) የተማሩት የዳዊት መዝሙር ስለ እግዚአብሔር ምን እንደሚል አስበው ያውቃሉ? ወይስ ይኸው የዳዊት መዝሙር “ይብል አብድ በልቡ አልቦ እግዚአብሔር – ሰነፍ በልቡ ‘እግዚአብሔር የለም’ ይላል” ስለሚል (መዝ ፲፫፡ ፩) በልብዎ ‘እግዚአብሔር የለም’ እያሉ አድገው፡ ወታደራዊ ሳይንስ በሚማሩበት ጊዜ ይህን አመለካከትዎን አጸኑት? የደርግ ቁንጮ ለመሆን በቅተው “ጓድ ሊቀመንበር” ከተባሉ በኋላ ደግሞ በእግዚአብሔር መኖር እንደማያምኑ በተግባር አሳዩን። ይህንን የምለው፡ ሌላውን እንተወውና “እግዚአብሔር ያያል፤ ኃያሉ አምላክ ይፈርድብኛል” ብሎ የሚያስብ አንድ ግለሰብ፡ ቢያንስ ንፁህ ደም በግፍ ከማፍሰስ ይቆጠባል ብዬ ስለማምን ነው። ሌ/ኮሎኔል አጥናፉ አባተ እውነት በሆነው፡ ግን ለሞት ባበቃቸው ንግግራቸው እንዳሉት፡ እርስዎ እና መሰሎችዎ “ከአገራችን ባህል፤ [ሃ]ይማኖትና ታሪክ ጋር ፈፅሞ የማይገጥምና የማይስማማ የሶሻሊስት ሥርዓት እንከተላለን [ብላችሁ] አገሪቱን የጦርነት አውድማ [አደረጋችኋት]” (ትግላችን፡ ገጽ 254)። ተቆጡ እንዴ ጓድ ሊቀመንበር? ምን ይደረግ እንግዲህ፤ “እውነቱ ሲነገር ይጎዳል” ይባል የለ?

በቅጽ አንድ መጽሐፍዎ የኢትዮጵያን የቀድሞ አፄዎች ለአገሪቱ ካከናወኗቸው ዐበይት ተግባራት አንፃር ያወዳድሯቸው ነበር። አፄ ቴዎድሮስ የመሳፍንቱን “ከፋፍለህ ግዛ” ሥርዓት አስወግደው አንዲት ኢትዮጵያን ለመመሥረት ባደረጉት ጥረት ማንም እንደማይስተካከላቸው፤ የአፄ ዮሐንስን መንፈሳዊ መሪነት፤ አፄ ምኒልክ ትምህርትን እና አንዳንድ ሳይንሳዊ ውጤቶችን ወደ አገሪቱ በማስገባት የዘመናዊቷ ኢትዮጵያ መሐንዲስ ቢሆኑም የባሪያ ንግድን እና የገበሬውን ጭቆና ማስወገድ ስላለመቻላቸው፤ አፄ ኃይለሥላሴ ቀድመዋቸው ከነበሩት ነገሥታት በተለየ መልኩ የትምህርት እድል ስለገጠማቸው፡ ታላላቅ የፖለቲካ እመርታ የተሰኙ ሥራዎችን እንዳከናወኑ እና የእርሳቸው ዘመን ከደረሰበት የ እድገት ደረጃ አንፃር እርሳቸውን ከቀደምቶቻቸው አፄዎች ጋር ማወዳደር እንደማይቻል አስረድተውናል።

እስኪ እኔ ደግሞ በርእሴ ጉዳይ ላይ ብቻ እርስዎን ከመጨረሻው የዘውድ አገዛዝ መሪ (አፄ ኃይለሥላሴ) ጋር ለማወዳደር ልሞክር። አፄ ኃይለሥላሴ፡ እግዚአብሔርን የሚያውቁ እና የሚያምኑ መሪ እንደነበሩ ወደሌላ ዝርዝር ሳልገባ ከእርስዎ መጽሐፍ በመጥቀስ ብቻ ማረጋገጥ ይቻላል። ከዙፋናቸው ካወረዳችኋቸው በኋላ ወደ ማረፊያ ክፍል ተወስደው፡ እርስዎ “የጎደለ ነገር ካለ ለማሟላት ዝግጁ ነን” ሲሏቸው “ምንም አይደል፤ እግዚአብሔር እንደፈቀደ እንኖራለን” እንዳሉ ነግረውናል (ትግላችን፡ ገጽ 189)። ይህ ሁሉ ለደህንነታቸው እንደተረገ ሲነገሯቸውም፡ በእግዚአብሔር ላይ ያላቸውን እምነት ባንጸባረቀ መልኩ “ለደህንነታችንም የሚያውቀው ሁሉን የሚችለው አንድ አምላክ ብቻ ነው” በማለት መለሱ (ትግላችን፡ ገጽ 189)። በዚሁ ገጽ ላይ ከክብራቸው በተዋረዱባት በዚያች ቀን መጽሐፍ ቅዱስ ይዘው እንደነበርም ዘግበዋል። ከዚህ በመነሳት አፄ ኃይለሥላሴ እንደ ታላላቆቹ የአሜሪካ መሪዎች (አብርሐም ሊንከን እና ሩስቬልት) መጽሐፍ ቅዱስ የሚያነቡ፤ እንዲሁም እግዚአብሔር ለሰው ዘር ያስተላለፈውን መልዕክት ከያዘው ከታላቁ የሕይወት መጽሐፍ ጋር የሚተዋወቁ መሪ እንደነበሩ ለመረዳት ይቻላል።

እርስዎ ግን 17ቱን የመሪነት ዘመንዎ በጦርነት ተወጥረው ስላሳለፉ እና ደግሞም ጊዜ ቢኖርዎት እንኳ ለማንበብ የሚመርጡት የኮሚኒዝም ፍልስፍና መጻሕፍትን ስለሆነ ቅዱሱን መጽሐፍ ያነበቡ አይመስለኝም። በግንቦት ወር 1983 ዓ.ም. አስቀድመው በተዋዋሉበት መንገድ ወደ ዝምቧብዌ ካመለጡ በኋላ ላለፉት 22 ዓመታት በፍጥረታት ፈጣሪ በሕያው እግዚአብሔር ላይ ያለዎት እምነት ምን እንደሆነ አይታወቅም። “ትግላችን…” የተሰኘው መጽሐፍዎ ግን በባዕድ አገር ሁሉንም ነገር በሰከነ መንፈስ ማሰብ በሚችሉበት ሁኔታ እየኖሩ እንኳን፡ የእምነት ሰው ወደመሆን እንዳልተቀየሩ በመጠኑም ቢሆን ያመለክታል። መጽሐፉን ከጥግ እስከ ጥግ ያነበበ ማንኛውም አንባቢ፡ አብዮታዊው እና ተራማጁ ጓድ መንግሥቱ በስደት አገርም ቢሆን ምንም አይነት የዓላማ እና የአመለካከት ለውጥ እንዳላደረጉ ይገነዘባል።

መጽሐፍዎ “አብዮት፤ አድኃሪ፤ ጭሰኛ፤ ጉልተኛ፤ ከበርቴ፤ ምንደኛ፤ ገንጣይ፤ አስገንጣይ፤ ወያኔ፤ ባንዳ፤ ሠራዊት፤ ብርጌድ፤ ጦርነት፤ እዝ፤ ጠገግ፤ ሜካናይዝድ ጦር ወዘተ.” በሚሉ አብዮታዊ እና ወታደራዊ ቃላት የተመላ ሲሆን፡ “እምነት፤ ተስፋ፤ ፍቅር፤ ይቅርታ፤ ምሕረት፤ ቸርነት፤ በጎነት” የተሰኙት ውብ ቃላት መጽሐፍዎ ውስጥ በመብራት ቢፈለጉ እንኳ ለማግኘት ያዳግታል። አማኝ ወደ መሆን እንዳልተቀየሩ ከሚጠቁሙት አገላለጾች መካከል፡ ገጽ 55 ላይ ሙሶሎኒ ኢትዮጵያን “የምድር ገነት” እያለ ይጠራት እንደነበር ገልጸው፡ በዚህ አጠራር ላይ ያለዎትን አመለካከት “ገነት የሚባል ነገር ካለ…” በማለት አሳይተዋል። ምናልባት መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ ጊዜ ቢኖርዎት ኖሮ፡ ሙሶሎኒ ምድረ ኢትዮጵያን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የመጀመሪያው መጽሐፍ (ኦሪት ዘፍጥረት 2፡8) “የኤደን ገነት” ተብሎ ከተጠቀሰው ቦታ ጋር እንዳነጻጸራት መግለጽ ይችሉ ነበር። ደግሞም ይኸው መጽሐፍ “የሁለተኛውም ወንዝ ስም ግዮን ነው፤ እርሱም የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብባል” (ኦ. ዘፍ 2፡13) ስለሚል የሙሶሎኒ ስያሜ ትርጉም ሊገባዎ ይችል ነበር። በሙሶሎኒ ስያሜ ላይ ከሰጡት አስተያየት የተረዳሁት ነገር ቢኖር፡ ገነት፤ ሲኦል፤ የእግዚአብሔር መንግሥት (መንግሥተ ሰማያት) የሚባሉ ነገሮች እንዳሉ አለማመንዎን ነው።

በእግዚአብሔር ህልውና እና ለሰው ዘሮች ባለው ጥባቆቱ (መግቦቱ) እስካሁን ድረስ እንደማያምኑ የተረዳሁበት ሌላው የመጽሐፍዎ ክፍል ደግሞ፡ መስከረም 13/1969 ዓ.ም. ከተደረገብዎ የግድያ ሙከራ የተረፉበትን ምክንያት ሲያስረዱ፡ “ያንን ሁሉ ጥይት ሲያፈስብን እኛን ሊፈጀን ያልቻለው፡ አንደኛ የላንድሮቨሩ ተጠባባቂ ጎማ ከኋላ ከበሩ ጋር ተያይዞ የተቀመጠ በመሆኑ ስለተከላከለልን፤ ሁለተኛ አሉሚኒየም የሆነ ወፍራም የመኪናው ገላና እንዲሁም የመኪናው የኋላ መቀመጫ ጥቅልል ሽቦዎችና ስፖንጆቹ ጥይቶቹን ውጠው እየቀነሱና እያበ[ረ]ዱልን ነው” የሚለው ነው (ትግላችን፡ 7ጽ 248)። ይህ ሁሉ ዝባዝንኬ ውስጥ ከመግባት “እግዚአብሔር አትርፎን ነው” ቢሉ ምን ነበረበት? እዚህ ላይ መልስ ከሰጡኝ፡ እንዲመልሱልኝ የምፈልገውን አንድ የመጨረሻ ጥያቄ ልጠይቅዎ፤ እርስዎም ሆኑ ባልደረቦችዎ የደርግ አባላት በሀልዎተ እግዚአብሔር የማታምኑ የሶሻሊዝም ፖለቲካዊ ርዕዮት ተከታዮች ሆናችሁ ሳለ፡ ላለመከዳዳት በገባችሁት ቃለ መሐላ ውስጥ ለምንድን ነው “በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ” የሚል ዐረፍተ ነገር የጨመራችሁት? (ትግላችን፡ ገጽ 171)።

የተከበሩ ኮሎኔል መንግሥቱ፡ ይቅርታው እና ምሕረቱ የበዛ ቸሩ እግዚአብሔር ዕድሜ ለንስሐ ስለሰጠዎ፡ በብዙ ጥይቶች መካከል አልፈው፤ ምድራዊ ፍርድንም አምልጠው እስካሁን በሕይወት ይገኛሉ። በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት በዘር ማጥፋት ወንጀል ከስሶ ስለፈረደብዎ፡ በመሪነት ዘመንዎ የሠሩትን ሁሉ የኢትዮጵያን ሕዝብ እያማከሩ የሠሩ ይመስል ፍርዱን በሕዝቡ ላይ የተፈረደ ነው በሚል መንፈስ፡ “የኢትዮጵያ ሕዝብ ዘር አጥፊና የጦር ወንጀለኛ ተብሎ መፈረጁን በመስማቴ ለታሪክና ለሕዝቡ የተተወውን የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ የትግል ታሪክ እኔ እራሴ ለመጻፍ ተገደድኩ” ብለውናል (ትግላችን፡ ገጽ 5)። ፍርዱ አበሳጭቶዎት 500 ገጾችን የያዘ መጽሐፍ ስለጻፉ፡ እርስዎ ላይ ያደረሰውን አዎንታዊ ተጽዕኖ እረዳለሁ። ነገር ግን በሰከነ እና በተረጋጋ መንፈስ ማሰብ በሚችሉበት የኑሮ ሁኔታ እና የዕድሜ ክልል ውስጥ ሆነው ሳለ፡ በመሪነት ዘመንዎ በፍጹም ስህተት ሰርቻለሁ ብለው አያምኑም። በመጽሐፍዎ የመጸጸትም ሆነ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ የመጠይቅን ዝንባሌ አንድም ቦታ አላሳዩም። አቋምዎ አሁንም ‘አብዮት ልጇን ስለምትበላ የአብዮቱ ተጻራሪዎች እርምጃ ተወሰደባቸው (ተወገዱ)፤ እንዲሁም በወቅታዊው አጣብቂኝ እና አስገዳጅ ሁኔታዎች ለኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻነት እና ዕድገት ስንል አስፈላጊ ውሳኔዎችን ወሰንን’ የሚል ይመስላል።

ከሞት በኋላ ሕይወት (ያውም ዘለዓለማዊ) እንዳለ የሚያምኑ ከሆነ ግን፤ የኢትዮጵያ የቀድሞ መሪዎች ጽዋቸው ሞልቶ በሞት እንደተጠሩ፡ እርስዎም አንድ ቀን ይጠሩና ነፍስዎ ወደ ፈጣሪዋ ልዑል እግዚአብሔር ትመለሳለች (መጽሐፈ መክብብ 12፡7)። “የእግዚአብሔር እስትንፋስ” በመባል የሚታወቀው መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስረዳን “ሁላችን በክርስቶስ የፍርድ ዙፋን ፊት እንቆማለን” (2 ቆሮንቶስ 5፡10)። የነገሥታት ሁሉ ንጉሥ የሆነው ጌታም ለፍርድ ዳግም እንደሚመጣ እና ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው እንደሚከፍለው ነግሮናል (ራዕየ ዮሐንስ 22፡12)። በእግዚአብሔር የተወሰነልዎ የዕድሜ ገደብ አብቅቶ በአካለ ነፍስ በክርስቶስ ዙፋን ፊት ቆመው በሕይወት ዘመንዎ ስለሰሩት ነገር ሁሉ ከመጠየቅዎ በፊት፡ ቃሉ “ከወዴት እንደ ወደቅህ አስብ፤ ንስሐ ግባ፤ ያለበለዚያ ፈጥኜ እመጣብሀለሁ” (ራዕየ ዮሐንስ 2፡5) ይላልና ዛሬውኑ ከሕሊናዎ ጋር ተማክረው ወደ እግዚአብሔር ልብዎን ይመልሱ። “አባታችን ሆይ…” ብለን እንድንጠራው የፈቀደልን መሐሪው አምላክ፡ ልጆቹ በ11ኛው ሰዓት (የዕድሜያቸው መገባደጃ) ላይም ቢሆን በንስሐ ቢመለሱ በፍቅር ይቀበላቸዋልና “አቤቱ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ” ይበሉት (መዝሙረ ዳዊት 50፡1)።

በምሕረቱ ባለጸጋ የሆነው እውነተኛው አምላክ፡ የእርሱን ምሕረት እና ይቅርታን ለማግኘት ከፈለግን መጀመሪያ ከወገኖቻችን ጋር ይቅር መባባል እንዳለብን ነገሮናልና (የማቴዎስ ወንጌል 5፡24፤ የማርቆስ ወንጌል 11፡25-26) በሥልጣን ዘመንዎ ለወታደሮችዎ ባስተላለፏቸው ቀጫጭን ትዕዛዞች አማካኝነት ልጆቻቸውን ወይም ወላጆቻቸውን በሞት በመቅጠፍ ለዓመታት ደም ዕንባ ያስነቧቸውን ኢትዮጵያውያን ወገኖች በሙሉ በግልጽ ይቅርታ ይጠይቁ። አለበለዚያ እውነተኛው ዳኛ እግዚአብሔር፡ ለመጀመሪያው ነፍሰ ገዳይ ለቃየን እንደነገረው አሁንም “የወንድምህ የደሙ ድምፅ ከምድር ወደ እኔ ይጮኻል” ይላል (ኦ. ዘፍጥረት 4፡10)። ስለዚህ ከላይ የጠቀስኳቸውን የቃሉን መልእክታት በማስተዋል፡ የትዕቢት መንፈስ ቢጫንዎት እንኳ እንደምንም ይቃወሙት እና በትህትና ራስዎን ከኃያሉ አምላክ የጸጋ ዙፋን ሥር ይጣሉ። ምሕረቱን ይለምኑ፤ ቅዱስ የሆነውን ስሙንም ዘወትር ይጥሩት፡ መጽሐፍ እንደሚል “የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል[ና]።”

አብርሃ ደስታ አዲግራት ላይ በሕወሓት ካድሬዎች ተደበደበ

$
0
0

Abrha Desta
(ዘ-ሐበሻ) የአረና ለትግራይ ፓርቲ በትግራይ ክልል የተለያዩ ከተሞች ሕዝብን የማነቃቃስ ስብሰባዎችን በመጥራትና በማወያየት ላይ የሚገኝ ሲሆን በሚያደረጋቸው ሰላማዊ እንስቃሴዎች በሕወሓት ካድሬዎች ፈተና እየገጠመው ይገኛል። ዛሬ ከወደ አዲግራት የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው በፌስቡክ፣ በትዊትር እና በተለያዩ ድረገጾች ላይ “አብርሃ ደስታ ከመቀሌ” እያለ የሚዘግበው መምህር ድብደባ ተፈጽሞበታል።

አረና ፓርቲ ነገ እሁድ ጃንዋሪ 26 ቀን 2014 በአዲግራት ከተማ የጠራውን ሕዝባዊ ስብሰባ ለሕዝብ ለማስተዋወቅ በከተማዋ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት በሕወሓት ካድሬዎች በተደራጁ በተባሉ ወጣቶች “ሕዝብ መቀስቅሳችሁን አቁሙ” በሚል ጥቃት የተፈጸመባቸው አሰገደ ገብረ ሥላሴ፣ አምዶም ገብረስላሴና አብርሃ ደስታ ላይ ሲሆን በአብርሃ የደረሰው ድብደባ ከፍተኛ ጉዳት ባያደርስም አቶ አሰገደ እና አንዶም ወደ ሃኪም ቤት ተወስደው ህክምና እንደተደረገላቸው ለዘ-ሐበሻ የደረሱት መረጃዎች አመልክተዋል።

በተያያዘ ዜና በተጨማሪ የአዲግራቱን ስብሰባ ለማስተጓጎል ሕወሓት ወታደሮችን በማሰማራት የአረና ሰዎችን በማሳሰር ላይ እንደሚገኝ የደረሰን ዜና አመልክቶ ለማሰር የቀረበው ምክንያትም “ሕዝብ በስብሰባ እንዲሳተፍ ቀስቅሳችኋል” በሚል ነው።

ከዚህ ቀደም የአረና አባላት በተንቤይን ሕዝባዊ ስብሰባ ጠርተው የነበረ ስሂን እዚያም እስር እና እንግልት እንደደረሰባቸው ዘ-ሐበሻ በወቅቱ መዘገቧ አይዘነጋም።

(ከዚህ ቀደም የአረናን ሕዝባዊ ስብሰባ እንዳይሳተፉ የተከለከሉ የሽሬ ነዋሪዎች - ፎቶ ከአብርሃ ደስታ) - ፎቶ ፋይል

(ከዚህ ቀደም የአረናን ሕዝባዊ ስብሰባ እንዳይሳተፉ የተከለከሉ የሽሬ ነዋሪዎች – ፎቶ ከአብርሃ ደስታ) – ፎቶ ፋይል

የማለዳ ወግ …ወገንን በመርዳት ለኢትዮጵያ ያለን ፍቅር ይገለጻል !

$
0
0

Ethiopian Flag

እኔ የዶር ካትሪንን ፊስቱላ ከሃገረ ኢትዮጵያ ለማጥፋት እንቅስቃሴ እደግፋለሁ !
የዶክተር ካትሪን ሃምሊን እና የባለቤታቸው በዶ/ር ሬጅ ሃምሊን ግማሽ ክፍለ ዘመን የተጠጋው በጎ ምግባር የሚያሳዩ ድርሳናትን ስፈታትሽ አድሬ አረፋፈድኩበት ። “የፊስቱላ ተጠቂዎች የተስፋ ታሪክ ” በሚል በአንድ ወቅት በፊሱትላ በሽታና በዶክተር ካትሪን እና በቤተሰባቸው በስራ ባልደረቦቻቸው ተጋድሎ ዙሪያ የቀረበ በእጀ ነበረ ከሲድኒ አውስትራልያ መስፍን ማሞ ተሰማ ያቀረበልንን ድንቅ በበቂ መረጃ ደጋግሜ አነበብኩት። “ዶ/ር ካትሪን ሀምለን በአሁን ሰአት በአውስትርሊያ ግዛት በአንድ የባህር ዳርቻ በሚገኘው ምቾታማና የናጠጠ መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ቀሪውን የህይወት ዘመናቸውን እንኳ ለማሳለፍ አልፈለጉም።ዛሬም በዚህ እድሜያቸው ከሃገር ሃገር እየዞሩና እየተንከራተቱ ዕርዳታ በመጠየቅ የፊስቱላን በሽታ ከምድረ ኢትዮጵያ ለማስወገድ እንዲቻል የፋይናንስ፤ የማቴሪያልና የባለሙያ ኃይልን እያደራጁ ይገኛሉ።!” ይላል የመስፍን ነጋሽ መረጃ! እውነት ነው! ስለ ዶር ካትሪን ዘመን ተሻጋሪ ስራዎች ታዋቂዋን ቶክ ሾው አቅራቢ ኦፕራን ጨምሮ ከተለያዩ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ጋር ያደረጓቸውን ቃለ መጠይቆች ዙሪያ ዳሰሳ አደረግኩ ። ጥናታዊ ፍልሞችንም ተመለከትኩ ! የእኛዎቹ ምንዱባን ልብን ይነካሉ … የነጯ እምቤት ስራ ነፍስን በተስፋ ያድሳል! የእኛ ኑሮ ውሎ አዳር ያሳስባል እና አሰብኩት! እናም የእኒህ እመቤት ውለታ ቢከብደኝ የእኛ ነገር ቢያሳስበኝ እኔው ራሴ ለራሴን መላልሸ ኢትዮጵያዊነት ምን ማለት ነው ? ብየ ጠየቅኩት!
ሩቅ ተጉዠ ሃገር ቤት ያሉ የእኛ ሃኪሞችና በሰብአዊ እርዳታ መስሪያ ቤቶች በከባድ ሃላፊነት ተቀምጠው ለወገን በተለመነው እርዳታ የበለጸጉ የማውቃቸው የምናውቃቸውን ወገኖች በአይነ ህሊናየ አስታወስኩ ። በዙሪያየ ካለው የቅርብ ወራት ትዝታ አዝግሜም በሳውዲ የኮንትራት ስራ መጥተው የተለያዩ ጥቃቶች ደርሰውባቸው የጅዳና የሪያድ መጠለያዎች ተሞልተው የከረሙትን ተፈናቃይ ወገኖችና ከቅርብ ርቀት በባንዴራና በመፈክር አሸብርቀው ስብሰባ ድግስ ሲፈራረቅባቸው የከረሙትን አዳራሾች አስታወስኩ! ጉራጌ ፣ አማራ ፣ ትግሬ ፣ኦሮሞ ሁሉንም የሃገሬ ብሔር መወከል የሚችሉ ግፉአን የከፋ በደል ደርሶባቸው ቅስማቸው ተሰብሮ ውለው በሚያደረሩበት ግቢ ጉራጌ ፣ አማራ ፣ ትግሬ ፣ኦሮሞ እና በቀረው ብሔር ብሔረሰብ የቋቋሙት የልማት ማህበራትና ድርጅቶች ዲል ያለ ድግስ ደግሰው የተወለዱ፣ የተቋቋሙበትን፣ የአመት ሪፖርት ገንዘብ ማሰባሰቢያ ድግስ ዲል አድርገው ሲደግሱ የብሔር ብሔረሰብ ልጆችን እንባ መጥረጉ ቀርቶ ችግሩን አንስተው መወያየት የተሳናቸውን አጋጣሚ በንጽጽር አስታወስኩት ።

እንዲህ እንዲህ እያልኩ ብዙን አስታወስኩ ። ” አይ የእኛ ነገር !” አልኩ ከትንነት በስቲያ ወዳጃችን አርአያ ተስፋ ማርያም አንድ መጣጥፍ እንደገና ታውሶኝ … የአርአያ ተስፋ ማርያም ከዋሽንግተን ሆኖ እንደ ሸረሪት ድር በሚያገናኘን የኢንተርኔት መረብ አማካኝነት በፊስቡክ ገጹ የለቀቀው ገጠመኝ እንዲህ የሚል አለበት “በዲሲ 13ኛው መንገድ አመሻሽ ላይ በእግሬ ሳዘግም በስተግራ በኩል ካለ የተንጣለለ አዳራሽ አንድ ድምፅ ከጆሮዬ ጥልቅ አለ። በአማርኛ የሃይማኖት ስብከት ሲሆን ሰባኪው፥ « ኢየሱስ የተቸገሩ፣ የተራቡ፣ የታመሙ..እርዱ ይላል..» እያለ በአዳራሹ ለተሰበሰበው ህዝብ (ሃበሻ) ይሰብካል። በአዳራሹ ሁለተኛ መግቢያ በኩል ሁለት ሰዎች ጥግ – ጥግ ይዘው በዛ ቁር ኩርምት ብለዋል። … ተጠግቼ አናገርኳቸው። « ለምን እዚህ እንዲያስጠጓችሁ አትጠይቋቸውም?.» ስል ጠየኳቸው። ሙላቱ « ወንድሜ መኖራችንን ካወቁ ፖሊስ ጠርተው ያባርሩናል። ከሰው አይቆጥሩንም። እያንቋሸሹ፣ ሊደበድቡን ይቃጣቸዋል። ህይወት ፊቷን ስታዞርብህ ምንም ያልበደልከው ወገንህ ተደርቦ ለምን አሳርህን እንደሚያሳይህ ይገርመኛል!» አለኝ። ንግግሩ አንጀት ይበላል። … እምነት በተግባር ካልታጀበ ምን ዋጋ አለው?…ሰባኪው ስለየትኞቹ ችግረኞች ነው የሚናገረው?..አፍንጫው ስር የወደቁ ወገኖችን ካለመርዳቱ ባሻገር ጭራሽ ለአይን መጠየፍን ምን ይሉታል?..የሃይማኖቱ ተከታዮችስ ይህን እያዩ ማለፋቸው ምን ይባላል?.. ” ይለናል አርአያ በሃብታሟ ሃገር በአሜሪካ የብዙሃን መናህሪያ በዋሽንግተኗ በእኛ መንደር የሚታየውን ምስቅልቅል ህይዎት ሲያስቃኘን ። …ይህም ያማል !
ይህንና ያንን አውስቸ በራሳችን እየሆነ ባለው አፍሬ ተሸማቀቅኩ ፣ አዛውንቷ የሰው ሃገር ሰው ዶር ካትሪን ባከበሩት 90ኛ አመት የልደት መታሰቢያ ግን መልካም ስራቸውን አውስቸ ደምቅኩ ። ዶር ካትሪን ከልጅነት እስከ እውቀት ለእኛ በኖሩባቸውን ረጅም አመታት የደገፉዋቸውን ወደ 40 ሽህ የሚጠጉ ኢትዮጵያን የማህጸን (የፊስቱላ) ህሙማንን የሰመረ ህይዎት መልሸ መላልሸ አሰብኩት ። ማነጻጸር የማይመቸውን እያነጻጸርኩ ለምን እያልኩ ራሴን ወዘወዝኩት! “ኢትዮጵያን እንወዳለን! ” ለማለት ሰንደቅ ባንዴራ አረንጓዴ ቢጫ ቀለሙን በመላብስ ጌጣ ጌጦች የምንደምቀውን የእኛን ስራ አስታውሸ ውስጤን አንዳች ክፉ ሰሜት ሸነቁጠው … እናም ኢትዮጵያ ማለት ምን ማለት ነው ? ብየ ራሴ ላጠየቅኩት ራሴው በመመለስ ቢያንስ ለእኛ ሲሉ የሚሰሩትን በመደገፉ እንበርታ ለማለት ስንደረደር ኢትዮጵያ በሚለው መልስ ይሆናል ያልኩትን የሆዴን ለመናገር መሞነጫጨር ጀመርኩ …
ኢትዮጵያ ማለት ስም ነው ፣ የማይጨበጥ የማይቧጠጥ ! ምሳሌ ነው ፣ መለያ ነው ! ኢትዮጵያ ማለት ስም ነው መለያ ፣ በምድሯ የታጨቀው ወገን መታወቂያ ! ኢትዮጵያ ማለት ሰው ነው በቀየዋ የሚኖረው ፣ መሬቷን አርሶ ግሮ ጥሮ የሚኖረው ፣ ኢትዮጵያ ማለት ተምሮ ፣ አስተምሮ ፣ ተመራምሮ ተስፋን ሰንቆ የሚኖረው ! “ኢትዮጵያን እወዳለሁ!” የሚለው ወገኑን ለመታደግ አለፋ ስቅየት የሚከፍለው ! ለክብር ነጻነቷ ቀናኢው ኢትዮጵያ ማለት እሱ ነው በምድሯ የበቀለው ! “ኢትዮጵያን እወዳለሁ!” በሚል ደስኳሪው ፣ ሃገሩን አሳልፎ ሰጭው ፣ ወገኑን በመታደግ ፋንታ ዘራፊው፣ በራሱ ወገን የሚጨቆን የሚረገጠው ፣ የሚጨቁነው! ወገኑን መደገፍ ያቃተው … ኢትዮጵያዊ እሱ ነው ደጉም ክፉውም ሰው … !
ኢትዮጵያ ማለት ተራራ ምድር ሸንተረሩ ፣ ቆላው ፣ ደጋው ፣ ወይና ደጋው ፣ ለገዛው የሚገዛው መሬት ፣ አለያም በተቀደደለት የሚፈሰው ውሃ ማለት አይደለም ኢትዮጵያዊነት ! ኢትዮጵያዊነት ክብሩ ስሙ ነው የሰው ፣ የህዝብ የወገኑ … ! ኢትዮጵያን መውደድ ፣ ባንዴራን ማፍቀር ማለት ህዝብ ወገንን መውደድ፣ መደገፍ ፣ማበልጸግ ማለት ካልሆነ ፍቅር መውደዱ ከንቱ ነው … !
እናማ “ኢትዮጵያ ሃገራችን እንዎዳለን ? ” ካልን በተግባር እናሳየው ! ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ ወገንን በመርዳት ፍቅራችን በድጋፍ እንግለጸው ! የዶር ካትሪንን እና የቀሩትን ፈና ወጊ የሰው ሃገር ሰው ስራዎች ተመልከቱ ! ዛሬ ያነሳሳናቸውን እመቤት በጎ ምግባር ብንመረምረው ሰብዕና አስገድዷቸው ከሃገረ አውስትራልያ በለጋ የልጅነት እድሜ ጀምሮ ዛሬ እስከሚከበረው የ90ኛ እድሜያቸው ፊስቱላን ለማጥፋት ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም ! … ባላቻ ጋብቻና በአስገድዶ መድፈር እኛው ባጠፋነው ጥፋት ፣ በማህጸን በሽታ በለጋ እድሜ ለሚሰቃዩ እህቶች እና እናቶች ህይዎት ትንሳኤን እያበሰሩ ግማሽ ክፍለ ዘመን የተጓዙ ሃኪም ናቸው ! ዶር ካትሪን ፊስቱላን ከእኛ ሃገር ለማጥፋት የጀመሩት ጉዙ በእኛ ካልታገዘ የትም አይደርስም ” ባይባልም ቢያንስ የመልካሙ ዘመቻቸው አካል በመሆን ሰብዕናችን እናሳይ ዘንድ ግድ ይለናል!
“አብዛኛውን እድሜዬን ያሣለፍኩት ኢትዮጵያ ውስጥ ነው። ሌላ ሃገር ኖሬ አላውቃም። ከእንግዲህ ምን አልባት አንድ አመት ወይም አምስት አመት ልኖር እችል ይሆናል። እኔ ካለፍኩ በኋላ የጀመርነውን ሥራ ግቡን ሳይመታ እንዳታቆሙ አደራ!ፊስቱላን ከኢትዮጵያ ገጽ ማጥፋት አለብን።” በማለት የተናገሩት ዶር ካትሪን በኦክቶበር 2009 በአውስትራሊያ ርዕሠ ከተማ ካንቤራ ውስጥ የሳቸውን የኢትዮጵያ ቆይታ ተመርኩዞ በተሰራውን ዶክመተሪ ፊልም የምረቃ ዝግጅት የተናገሩት ቢሆንም ካትሪን በቀረቡባቸው መድረኮች ሁሉ ፊስቱላን በታዳጊ ሃገሮች ለማጥፋት ያላቸውን ቁርጠኝነት አመላክተዋል ።
አዎ እውነት ብለው ፣ ስለእውነት እየሰሩ ያሉት እናት የዶር ካትሪንን ፊስቱላ ከሃገረ ኢትዮጵያ ለማጥፋት እንቅስቃሴ እደግፋለሁ !
ዶር ካትሪን እርስዎስ ለኢትዮጵያ እንኳንም ተወለዱ!
ነቢዩ ሲራክ
እናታችን ዶር ካትሪን ሃምሊን ! እርስዎስ ለኢትዮጵያ እናቶች እንኳንም ተወለዱ !
አክባሪዎ
ነቢዩ ሲራክ

የኛ ነገር፡ የተሸነፈ ርእዮተአገርና ገፊ ፖለቲካ፤ (ተክለሚካሄል አበበ )

$
0
0

ስለመጪው ሶስተኛ ሪፐብሊክ፤ ካለፈው የቀጠለ፤ ሀ
Tekele ትንሽ ወደኁዋላ፤ እንደ መግቢያ
1. ግንቦት፤ 2003/2011፤ በቶሮንቶ ከተማ፤ ጃዋርና ኦባንግ፤ አሎ አይደሂስና (ሸጋ የአፋር ሰው ነው) አበበ በለው በእንግድነት የተገኙበትን ሕዝባዊ ስብሰባ ተንተርሼ፤ አንድ ወርቅ የሆነ ጽሁፍ ጽፌ ነበር፡፡ ጽሁፉን ያላነበባችሁ ብታነቡት፤ ያነበባችሁትም ብትደግሙት አይቆጫችሁም፡፡ ጽሁፉ ይቀጥላል ብዬ ጊዜ ጠፋና ቀጣዩን ክፍል ሳላቀርብ ቀጠልኩ፡፡ ስለኦባንግ ገጠመኝ ተርኬ፤ ስለጃዋር ጀምሬ ነበር ያቆምኩት፡፡ አሁን መቀጠሉ ወቅታዊ መስሎ ታየኝ፡፡ ከስብሰባው በፊት ይመስለኛል ስለወቅታዊና መሰረታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ ስናወራ፤ ተራው ህዝብ ለገዢ መደቦች ስራ ተጠያቂ ባሆንም፤ በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ውስጥ ግን፤ ተራው የአማራ ህዝብ፤ ገዢው መደብ የፈጠረውን ርእዮተአገር በገቢርም በነቢብም ተቀብሎ ኖሮበታል፤ በብዙ ስፍራዎችም ይሄንን ርእዮተ-አገር ተጠቅሞ ሌሎችን ጨቁኖበታልም፤ ብሎ ለማስረዳት ሞከረ፡፡ ምሳሌ ሰጠ፡፡ ነገሩ ከአመታት በፊት የሆነ፤ የተለመደ ሁሉም ወይም ብዙዎቹ ኦሮሞዎች እለት ተእለት የሚጋጥማቸው ቢሆንም፤ ነጥባችንን ለማስረዳት ይጠቅማልና እጠቅሰዋለሁ፡፡ እነሆ አጋጣሚው፡፡

ጃዋር መሀመድ
2. ጃዋር የገጠር ልጅ ነው፤ ከላይ በጠቀስኩት ጽሁፍ ላይ ራሱ እንዳለው፡፡ የዛሬ አስራምናምን አመት፤ ከቤተሰቦቹ ተለይቶ ከተማ ቤት ተከራቶ ትምህረቱን የሚከታተለው ታዳጊው ወጣት፤ ጃዋር ሲራጅ መሀመድ፤ አንድ ቀን አምሽቶ ዝናብ እየደበደበው ይመስለኛል ወደተከራው ቤት ይመጣል፡፡ አከራዩ ደግ አማራ ሴት፤ ለጃዋር ምግብ ሰጥታ፤ እሳት አንድዳ እያሞቀችዉ፤ ከላዩ ላይ ጋቢ ደርባ “ለምን እስኪመሽ ቆየህ አሁን ከመንገድ አንድ ጋላ ቢያገኝህና አንገትህን ቢልሀስ” አለችው፡፡ የዚህን ልጅ ስሜትና ምላሽ ለመረዳት ኦሮሞ መሆን አያስፈልግም፡፡ ራስን በሱ ቦታ ማስቀመጥና ነገሩን የራስን ጎራ ያለስስት በመተቸት ፈቃደኝነት ማሰላሰል እንጂ፡፡

3. ልክ ጅሁርና ጋይንት፤ ቢቸናና አንኮበር እንደምትኖር አንዲት አማራ ኢትዮጵያዊት፤ ይህቺ ሴት ክፋት እንደሌላትና የንግግሩዋን ፖለቲካዊ አንድምታ፤ በዚህ ልጅ ቀጣይ ማንነት ውስጥ የሚኖረውንም ፋይዳ እንደማታውቅ አሳምሮ መገመት ይቻላል፡፡ ይሄንን አጋጣሚ የነገረን ጃዋር ግን የሚለው፤ ይህቺ የዋህ ሴት የኢትዮጵያ ገዢ መደብ አካላት ያሰራጩትንና ለገዢ መሳሪያነት የተጠቀሙበትን የተወሰነ የህብረተሰብ ክፍልን ዝቅ የማድረግ አመለካከት፤ ሳታውቀው ከነፍሱዋ አዋህዳዋለች ነው፡፡ ስለዚህም፤ በቀጥታ ይሄንን የተወሰነ ብሄርን ዝቅ የማድረግ ባህል በመፍጠርና በመቅረጽ ባትጠየቅም፤ የዚህ ባህል በረከት ተቁዋዳሽ በመሆንና አውቃም ሳታውቅም ይሄንን ባህል እድሜ በመስጠት ተሳታፊ ነች ሲል ተከራከረ፡፡ በላይኛው ጽሁፍ ላይ ሰፈርኩትን የኦባንግን ገጠመኝ ጨምረን ካየነው፤ የጃዋር መከራከሪያ ስሜት ይሰጣል፡፡

ገረሱ ቱፋ፤

4. የላይኛው የጃዋር ገጠመኝ ቀሽም ሊመስል ይችላል፡፡ ከሰደበኝ መልሶ የነገረኝ እንዳልባል እንጂ፤ የገረሱ ቱፋ የከረሩ ምሳሌዎች ደግሞ አሉ፡፡ አንዱን ልጥቀስ፡፡ ኦሮሞው ወዳጄ ገረሱ ቱፋም፤ እንዲሁ ልጅ ሆኖ ሳለ፤ ጾም መሆኑን ረሳና፤ ወተት ጠጣ፡፡ እናቱ ወደንስሀ አባታቸው ላኩት፡፡ ቄሱ ቃል በቃል ምን ብለው እንደመለሱለትና ልቡን እንዳደሙት የነገረኝን በደንብ አላስታውሰውም፡፡ ብቻ፤ “ኤድያ ደግሞ፤ የጋላ ጹዋሚ ብሎ ነገር የለም” ብለው መለሱለት፡፡ “ለጋላ ንስሀ አባት ዲያቆን መች አነሰው” አይነት የሚለውን፤ የተለመደውን ክብረ-ነክ ተረት የሚያጠናክርና የሚያናንቅ መልስ ነው፡፡ በወቅቱ ገረሱ የሱ ጣፋት መስሎት ነበር፡፡ ነፍስ እያወቀ ሲመጣ ግን የሱ ጥፋት ሳይሆን ልክ እንደጃዋር ቀላቢ፤ አውቀውም ይሁን ሳያውቁ፤ በቄሱ ውስጥ የተተከለውን የሱን ብሄር ዝቅ የሚያደርግ ገዢው መደብ የፈጠረው ንቀትና ጥላቻ ተገለጸለት፡፡ ከአመታት በሁዋላ፤ እነሆ በገረሱ ነፍስ ውስጥ አብሮ የሚኖርና ዘወትር ቄሱ ስለወጡበት ህብረተሰብ ሲያስብና እኛ ጋር ክርክር በገጠመ ቁጥር ትዝ የሚለው መርዝ አጋጣሚ ሆነ፡፡ እንደውም ኢትዮጵያ ስትባል፤ የኚህን ቄስ ጋቢ የደረበች የአማሮች ፈጠራ መስላ ታየችው፡፡

jawar5. ይሄ ሁሉም ሆኖ፤ ጃዋር እንደውም ኢትዮጵያ ኦሮሞነትን የሚያንጸባርቅ ቀለም ከቀባናት፤ አንድ ነን ወይም ልንሆን እንችላለን የሚለውን ሀሳብ ይቀበል ነበር፡፡ የኛን ቄስ ንግግር ፖለቲካዊ አንድምታ ከተደራ በሁዋላ ለቀብር ካልሆነ ቤተክርስቲያን ደርሶ የማያውቀው ገረሱ ግን፤ የኢትዮጵያ አንድነት የሚባል ነገር አገባውም፡፡ አንድ አይደለንም ባይ ነው፡፡ ከሆንም፤ አንድነታችን የጎደፈ አንድነት ሆኖ ነው የሚታየው፡፡

6. ብዙ እላይ ከጠቀስኩዋቸው የከፉ ምሳሌዎችን ማንሳት ይሻላል፡፡ ግን እነዚህ የኦሮሞም ይሁን ሌሎች ብሄርተኞች የሚያነሱዋቸውን ፖለቲካዊና ማህበራዊ ክሶች በንደዚህ አይነት አጋጣሚዎችና ማስራጀዎች ለማስረዳት መሞከር፤ የክሱን ስፋትና ጥልቀት ማሳነስ ይመስለኛል፡፡ ማውራቱ ነገሩን ያቀለዋል፡፡ ያንን ስሜትና እውነታ መኖር ግን ከሕመም በላይ ነው፡፡ በዚህ አገባብ ውስጥ ነው ያለፉት ሶስት ወራት የነጃዋር ንትርክ የተጀመረው፡፡

7. እነዚህን ምሳሌዎች ያነሳሁዋቸው፤ አንደኛ፤ በዚህ ሰሞን ፖለቲካዊና ማህበራዊ ዝልዘላችንን ተቆጣጥረውት የቆዩትን ከአኖሎ ሀውልት እስከ በደሌ ኮንሰርት፤ ከምኒሊክ ቅድስና እስከ ጃዋር ትንተና ያሉትን ጉዳዮች ስንመለከት፤ በተወሰነ መልኩ የነዚህን ሰዎች ስሜት ለመረዳት የነዚህን ሰዎች አመለካከት የለወጡ ወይንም ያዳበሩ አጋጣሚዎችን መስማት ራሳችንንና የምንደግፈውን ርእዮተአገረ ለመደገፍ ከመሽቀዳደም ይልቅ የሰዎቹን ክስ በትእግስት ወደማድመጥ ሊወስደን ይችላል በሚል እምነት ነው፡፡ ሁለተኛ፤ የጃዋርና የገረሱ ፖለቲካዊ ማንነት የተወለደውና የተሞረደው ከንደዚህ አይነት ፖለቲካዊና ማሀበራዊ ክስተቶች ነውና እነጃዋር የሚሉትን መስማትም መገምገምም ያለብን በዚህ ማእቀፍ ውስጥ እንደሆነ ለማሳየትና፤ በዚያ አይነት ጉዞ ውስጥ ያደጉና የነቁ ወጣቶች ኢትዮጵዊነት ለምን እንደሚያስጸይፋቸው ሲናገሩ፤ በተስኪያን እንደገባች ውሻ ከማባረር፤ እንደግለሰብም ይሁን እንደተቁዋም፤ እነዚህን ልጆች ጸረ-ኢትዮጵያ አድርገን ከመፈረጃችን በፊት፤ ህመማቸውን ለማድመጥና ለማከም መጣር ይገባል፡፡ ኢህአዴግ ወደቆ እንድትኖር የምንፈልጋት ኢትዮጵያም፤ እነዚህን ህመሞች ለማስታመም የሚችል ህገመንግስታዊ፤ ስነልቡናዊና ፖለቲካዊ ዝግጅት ከሌላት፤ የተቃውሞ ፖለቲካችን በርግጥም የመፍትሄ ሳይሆን፤ የማውገዝ ብቻ ይሆናል፡፡ የዛሬው ጽሁፌ ስለዚህ ፖለቲካዊ ህክምናና ብናደርግ ስለሚበጁን ነገሮች መንገድ ለመጠቆም ነው፡፡ በዚህኛው ክፍል ጠቅላላ ነገሮች ይነሳሉ፡፡ በሚቀጥለው ክፍል ደግሞ መፍትሄዎች ይጠቆማሉ፡፡

መጀመሪያ አፍሪካዊ ወይስ ኢትዮጵያዊ?

8. ባለፈው ሰሞን፤ አልጀዚራ ላይ በቀጥታ ስርጭት ይመስለኛል፤ ጃዋር ፖለቲካዊ አጣብቂኝ ውስጥ የሚከተውን ጥያቄ ተጠየቀ፡፡ “መጀመሪያ ኦሮሞ ነህ፤ ኢትዮጵዊ?” የሚል፡፡ የሚቀጥለው ምሳሌ መቶ በመቶ ላይመሳሰል ይችላል፡፡ የተወሰነ መመሳሰል ግን አለው፡፡ አንድ ሰላሳ አመት ካናዳ ወይም አሜሪካ ውስጥ የኖረ ኢትዮጵያ፤ ወይንም እነዚህ አገር ውስጥ የተወለደ ናይጄሪዊ ይህንን ጥያቄ ቢጠየቅና፤ መጀመሪያ ናይጄሪያዊ ነኝ ብሎ ቢናገር፤ አሜሪካኖችን ወይንም ካናዳዎችን የሚያስቆጣ አይመስለኝም፡፡ ጃዋር ከኢትዮጵ በፊት መጀመሪያ ኦሮሞ ነኝ ብሎ ሲናገር ግን ብዙዎች አኮረፉ፡፡ ንትርክ ተጀመረ፡፡ የነቁና የበቁ የሚመስሉ የአንድነት አቀንቃኞች ራሱ ተቆጡ፡፡ አሁን በእመብርሀን ይሄ ምኑ ያበሳጫል? በዚህ መደንገጥም መቆጣትም የለብንም፡፡ ማድረግ ካለብን መጠየቅ ብቻ ነው፡፡ ችግሩ፤ እንድንሸመድድ እንጂ፤ እንድንጠይቅ በሚያበረታታ ባህል ውስጥ አላደግንምና፤ ከመጠየቅ ይልቅ፤ ልጁን ወደመዘልዘሉ ዘለልን፡፡

9. አንደኛ፤ ከአገሬ በፊት ብሄሬን ነኝ የሚለው መልስ እንደየአመለካከታችን ትክክል ሊሆን ይችላል፡፡ በርግጥም ሰው ከአገሩ በፊት ብሄሩን ነው፡፡ አንድ ኢትዮጵያዊ መጀመሪያ ኢትዮጵያዊ ነህ አፍሪካዊ ቢባልና መጀመሪያ ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ ቢመልስ፤ ምንም ብዙ ቁጣ የሚቀሰቅስ አይመስለኝም፡፡ ያ ባይሆንም እንኩዋን፤ እንዲህ አይነት ጥያቄዎች አንድ ወጥ የሆነ ሳንሳዊ መልስ ስለሌላቸው፤ ሰዎች አጣብቂኝ ውስጥ በሚያስገባ መልኩ ሲጠየቁ፤ ብዙ ሳያወጡ ሳያወርዱ እንዲህ አይነት መልስ ቢመልሱ፤ ሲሆን ሲሆን መልሳቸውን መቀበል፤ ያለበለዚያም የመልሳቸውን መሰረት ለመረዳት መሞከር እንጂ፤ ግፋ ካለም መልሳቸው ለምን ስህተት እንደሆነ ለመጠቆም መሞከር እንጂ፤ በመልሳቸው ማውገዝ አግባብ አይደለም፡፡ ለጃዋር የተሰጠው ተቃውሞ ደግሞ በብዛት የመጣው የአሜሪካና ካናዳ እንዲሁም የአውሮፓ ፓስፖርታቸውን ተሸክመው መጀመሪያ ኢትዮጵያዊ ነን ብለው ከሚናገሩ ሰዎች አንደበት መሆኑን ስናይ፤ አንዳንድ ግዜ ሚዛናችን ምን ህል የተዛባ ነው ያሰኛል፡፡

ጃዋር ሚናገረውን ያውቃል፤ ያለውንስ ለምን አለ?

10. በመሰረቱ፤ ይህ ልጅ መቼም ሰው ነውና አንዳንድ ግዜ አግባብ ያልሆነ ነገር ቢያመልጠውም፤ የሚሰራውንም የሚናገረውንም ያውቃል፡፡ ከላይ በጠቀስኩት ጽሁፍ ኦባንግ ሜቶ እንዳለው፤ “በኢትዮጵያዊነታችን ያጣነው ነገር ስላለ ብቻ ኢትዮጵያዊነታችን ይሰረዛል ማለት አይደለም”። ጃዋር፤ ልክ እንደ ኤርትራ እዚያ አካባቢ ኦሮሞ ወይንም ኦሮሚያ የሚባል መንግስት እስካልተመሰረተ ድረስ፤ ቢወድም ባይወድም፤ ጥንትም አሁንም ኢትዮጵያዊ እንደሆነ ያውቀዋል፡፡ ኤርትራ ተፈጥራም እንኩዋን፤ ኤርትራዊነትና ኢትዮጵያዊነት በሁለቱ አገሮች መካከል እንደሚሰመር ድንበር ይቀላል ማለት አይደለም፡፡ ጥምር ዜግነት የሚሉትን ጽንሰሀሳብም ማስታወስ አይጎዳም፡፡ ኢትዮጵያዊ መሆንም ሙሉ በሙሉ የስራችንና የምርጫችን ውጤት ሳይሆን፤ የትውልድና የሕግ ጉዳይ ነው፡፡ ጃዋር እስከቅርብ አመታት ድረስ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ይዞ እንደሚዞር እገምታለሁ፡፡ ልጁ እያለ ያለው ግን፤ ህግና አለማቀፍ ፖለቲካ አስገድዶኝ ኢትዮጵዊ ብሆንም፤ ፖለቲካዊ ነፍሴ ኢትዮጵያዊ አይደለም ነው፡፡

11. ነፍስ እንደዜግነት በህግ አትገደድም፡፡ ነፍስ ዜግነቱዋን ወይም ማንነትዋን ትመርጣለች እንጂ፡፡ ነፍሱ ማንነትዋን መረጠች፡፡ የኛ ስራ መሆን ያለበት፤ መናደድ ወይም ማበድ ሳይሆን፤ መጀመሪያ ማብረድ፤ ልክ አሁን እኔ እንደማደርገው፤ ከዚያ መጠየቅ ነው፡፡ ይሄ ልጅ ለምን እንደዚያ አለ፡፡ ኢትዮጵያዊ ነው ብለን፤ በየሬድዮና ቴሌቪዥናችን ስንሰቅለው፤ በየስብሰባና በየመድረካችን ስናቀርበው፤ ድንገት ተነስቶ እንዴት እንዲህ ጉድ አረገን፡፡ ብዙዎቻችን ግን አልጠየቅንም፡፡ ፈረድን እንጂ፡፡ አትፍረድ ይፈረድብሀል የሚል ብሂል ባነገበ ሀይማኖት ክርስትና የተነሳን ሁሉ ፈረድን፡፡

እንደሚመስለኝ፤ እኔ እንደማስበው፤

12. ጃዋር፤ ያንን የቴሌቪዥን ውይይት የሚከታተል ሁለት ትልልቅ ቡድን እንዳለ ያውቃል፡፡ አንደኛው በተለምዶ የአንድነት ሀይል የሚባለው፤ ሁለተኛው የነጻነት ወይንም የኦሮሞ ብሄርተኛ ሀይል፡፡ ሌሎች ሶስተኛም አራተኛም ቡድኖች ኖራሉ፡፡ ያለውን ፖለቲካዊ ራእይ በተደጋጋሚ የፈነጠቀው ጃዋር፤ ዞሮ ዞሮ የአንድነቱ ሀይል በጥርጣሬ እንደሚያየው ወይንም የብሄር ማንነቱን ጨፍልቆ እንጂ እሱ በሚፈልገው መልኩ እንደማይቀበለው በተለያየ አጋጣሚ አስተውሎዋል፡፡ ስለዚህ በሱ ቦታ ላለ፤ ከላይ በአንቀጽ 2፣ 3፣ እና አራት በጠቀስናቸው የእለት ተእለት ፖለቲካዊና ማህበራዊ ክስተቶች ውስጥ ላደገና ለሚኖር ኢትዮጵያዊ፤ እንደዚያ ባለ ፍጥነትን በሚጠይቅ አጣብቂኝ ውስጥ የሚሰጠው መልስ መጻኢ የፖለቲካ እድሉ ላይ እንደሚያጠላበት ያውቃል፡፡ ስለዚህ፤ መጀመሪ ኦሮሞ ነኝ አለ፡፡ በተወሰነ መልኩም ኢትዮጵያዊነት እንደተጫነበት ጠቀሰ፡፡

13. አስቀድመን ጃዋር ላይ የጫንበት ማንነት ወይንም ዜግነትና ለተጠየቀው ጥያቄ እኛ ያዘጋጀልነት መልስ ከሌለ በስተቀር፤ የሚሰማውን ማንነትና ውስጡ የሚቀበለውን ዜግነት የሚያውቀው እሱ እንጂ፤ እኛ አይደለንም፡፡ ስለዚህም በወቅቱ ብሄርን ማስቀደሙ ምክንያታዊ ውሳኔ ነው፡፡ ፖለቲካዊ ብልሀትም ነው፡፡ በርግጥም በሁዋላ የተከተለውን እሱንና አመለካከቱን የማሳደድ ዘመቻና ውግዘት ለተመለከተ፤ የጃዋር መልስ ትክክል ነበር ያሰኛል፡፡ ምክንያቱም እኝ የቀረጽንለት ኢትዮጵያ ለሱ ስሜት መፈናፈኛ የሌላት ሆና ተገኝታለችና፡፡ ጃዋር የቆየ የኢትዮጵያውን ልሂቃን፤ ”የኛ መንገድ ብቸኛውና አማራጭ የሌለው ምርጥ መንገድ ነው፤ ከኛ እውቅናና መንገድ ውጪ የሚጉዋዝ ውጉዝ ይደምሰስ”፤ የሚል ትውልድ ያጫረሰና፤ እነፍቅረስላሴ ወግደረስ ከ20 አመታት እስርም በሁዋላ ያልለወጡት፤ ችኮ ፖለቲካዊ ስነልቡና ሰለባ ነው የሆነው፡፡ እንደውም፤ ለጃዋር፤ እኛ ከቀረጽንለት ኢትዮጵያ ይልቅ፤ ኢህአዴግ የፈተለለት ኢትዮጵያ የተሻለች ብትመስለው አይገርመኝም፡፡

የብሄር ፖለቲካን፤ በከፊል መቀበል ነው፤

14. እነዚህ ወጣቶችም ሆኑ የፖለቲካ ንስሀ አባቶቻቸው፤ በዚህ በአልጀዚራ ላይ የሰማነውን አይነት፤ ኢትዮጵዊነትን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ፤ ለኛ ለመቀበል የሚያስቸግረን ንግግር ሲናገሩ፤ የቆሰለውና እንዲህ ወዳለው ስሜት ውስጥ የሰነቀራቸውን ፖለቲካዊ ሕመም በማከም ፈንታ፤ እንደጠላት የሚፈርጅ አካሄዳችንና ራሳችንን የኢትዮጵያ አንድነት ጋሻዣግሬዎች አድርጎ የመሾም ባህላችንን ነው፤ እነዚህን ሰዎች ወደጽንፈንነት የሚመራቸው፡፡ ያ ደግሞ ለኛም ለኢትዮጵያም አይበጅም፡፡ በዚህ ረገድ ይሄን ያህል አመት በኢህአዴግ መበለጣችን ሁሌም ይገርመኛል፡፡ ምክንያቱም፤ ኢህአዴግ ለነጃዋር፤ የአንድነቱ ሀይል ለመቀበል የሚያዳግተውን፤ ኦሮሚያ የሚባል ክልል/ካርታ፤ ሙሉ ነጻነት ባይኖረውም በራሱ ቁዋንቁዋ የሚተዳደር መንግስት ሰጥቶዋቸዋልና፡፡ ስለዚህ ከአንድነት ሀይሉ ውግዘት ጋር ሲወዳደር ብቻ ሳይሆን፤ ራሱን ችሎም፤ ኢህአዴግ ለብሄር ፖለቲከኞች የሰጠው ፖለቲካዊ ገጸ-በረከት፤ ልብ የሚማርክ ነው፡፡

15. የዚህ የብሄር ፖለቲካ ርእዮተአገር እንደአዲስ በመጣበት ሰዓት ለብዙዎቻችን አዲስና አስደንጋጭ ነበርና ባንቀበለው አይገርመኝም፡፡ እኔና ተስፋዬ ”ጋላው”፤ ስለሺና ወዲ ትግሬው በብሄር ሳይሆን በሰፈር፤ በቁዋንቁዋ ሳይሆን በክፍል፤ በሀይማኖት ሳይሆን፤ በእድሜ ተከፋፍለን ኩዋስ ስንጠልዝ፤ ሴት ስናባርር፤ ጠላ ስንገለብጥ፤ ድግስ ስናሳድድ ነበርና ድንገት የመጣው፤ በርግጥም የብሄር ፖለቲካ አስደንጋጭ ነበር፡፡ ከ22 አመታት ሽንፈት በሁዋላም ግን ራሳችንንና አስተሳሰባችንን አሸናፊ ሆኖ ከወጣው የብሄር ፖለቲካ ጋር ማጣጣም አለመቻላችን ግራ ነው የገባኝ፡፡ ለዚህም ነው፤ የብሄርተኞችን ቁስል በማከክና በማከም ረገድ ኢህአዴግ በልጦናል፡፡ እኛ እንደውም ቁስሉን የምናክም ሳሆን የምናመረቅዝ ሆነናል፡፡

16. ኢህአዴግ ለነሱ አስቦም ይሁን ለራሱ የፖለቲካ ጥቅም፤ የብሄርን ፖለቲካ በሚገባ ተጠቅሞበታል፡፡ 22 አመታት ያለብዙ ፈተና መርቶበታል፡፡ ስለዚህም እነሌንጮ ለታ እነሌንጮ ባቲ እንኩዋን፤ እንደገና ወደሁዋላ የኢህአዴግን አስተዳደር ተቀብለው ለመኖር እያኮቦኮቡ ነው፡፡ ምክንቱም ኢህአዴግ ጠላት ቢሆንም፤ በሌላ በኩል ከተሰለፈው ወደሁዋላ ሊጎትተን ይፈልጋል ብለው ከሚፈሩት የአንድነት ሀይል የተሻለ ጠላት እንደሆነ ያውቁታልና፡፡ ስለዚህ ይሄንን ጎሳን ወይንም ብሄርን መሰረት ያደረገ ፖለቲካዊ መሳሪያ ይዞ፤ ኢህአዴግ ሌላ 20 አመት ቢገዛም አይገርመኝም፡፡

17. እንደፖለቲካዊ ስበስብ፤ ሙሉ በሙሉ የኢህአዴግን የብሄር ፖለቲካ ባንቀበለውም እንኩዋን፤ ኢህአዴግ ክፉ መንግስት እንደሆነ ቢያውቁም፤ በተወሰነ መልኩ በፊት ያልነበረንን መብት አስከብሮልናል ብለው፤ የኢህአዴግን የብሄር ፖለቲካ ተቀብለው ኢህአዴግን በሀይለኛው የሚደግፉትን ቡድኖች የሚማርክ አማራጭ ማቅረብ አልቻልንም፡፡ እንደግንቦት ሰባት ያሉ በንጽጽር የተሸሉና የሰለጠኑ አባላት ያሉበት ድርጅት እንኩዋን፤ ብዙውን እንዲህ ያለውን ፖለቲካዊ ጉዳይ፤ ”ህዝቡ ይወስናል”፤ የሚል የስንፍናና የሽሽት አንቀጽ ሰንቅረው፤ በጎን ሸውደው አልፈውታል፡፡ በዚህ የፖለቲካ ድርጅቶቻችን፤ እንኩዋን የሚያሸንፍ፤ የሚያሰልፍም አማራጭ ርእዮተ-አገር ባልቀየሱበት ሁኔታ ነው፤ ይባስ ብለን፤ በተወሰነ መልኩም ከኛ ጋር ለመስራት የሚጥሩትን ጃዋሮች አመናጭቀን የምንገፋው፡፡ የዚህኛው ገፊ ፖለቲካ መጨረሻ፤ ልጆቹ ልክ እንደ ሌንጮ ለታ ወደጠላት ጎራ እንዲገቡ መገፋፋት ያለበለዚም ሌላ የፈተና ግንባር እንዲፈጥሩ ማበረታታት ነው የሚሆነው፡፡

18. ባንድ በኩል የሌንጮን ወደኢትዮጵያ የመመለስ ውሳኔ፤ ድፍረትና ብልሀት የተሞላበት ውሳኔ ነው ብዬ ባደንቅም፤ በሌላ በኩል ግን የሌንጮ ወደኢትዮጵያ የመመለስ ውሳኔ የአንድነቱን ሀይል ፖለቲካዊ ችኮነትና ውድቀትም ያሳያል፡፡ ሌንጮስ እድሜውም እየገፋ ነውና እንደጎልማሳነት ዘመኑ ብዙ ላያስቸግረን ይችላል፡፡ መጪውን ዘመን የሚዳኙትን፤ እነጃዋር መሀመድን፤ እነገረሱ ቱፋን ግን በትእግስት ልናስተናግዳቸው ሲገባ፤ ሌንጮን መማረክ የተሳነን፤ በኛ ብሶ፤ ደግሞ ይሄንንም ልጅ፤ ጃዋርን ገፋነው፡፡ ከገፋነው በሁዋላ፤ ምንስ ቢል፤ ምንስ ቢያደርግ፤ ምን ይደንቃል፡፡ ከሲያትል እስከ ለንደን፤ ከቶሮንቶ እስከ እስከ ሚኒያፖሊስ ቀድሞም የድርጅት ድክመት ይዞት እንጂ፤ በቁዋፍ የነበረውን የኦሮሞ ብሄርተኛ፤ ለዘብተኛ የነበረውን ሁሉ፤ ኦሮሞ ይቅደም እያለ ሰበሰበው፡፡ እርግጠኛ ነኝ፤ ጃዋር በህልሙም በእውኑም ያላሰበውን ፖለቲካዊ መድረክ ፈጠርንለት፡፡ ገፊ ፖለቲካችን እኛኑ ሳይፈጀን፤ ይሄንን ገፊ የፖለቲካ ቅኝታችንን መለወጥ አለብን፡፡

ሶስት ሀይሎች፤ አንድነት፤ ነጻነት እና ኢህአዴግ

19. እንደሚመስለኝ፤ ይህ ልጅ፤ በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ውስጥ በዋንኛነት፤ ሶስት አገራዊ ሀይሎች የኢትዮጵያን እጣ ፈንታ ለመለወጥ ትግል እንደገጠሙ ገምቶዋል፡፡ አንደኛው አህአዴግና አጋሮቹ፤ ሁለተኛው በተለምዶ የአንድነት ሀይል የሚባለው ቡድን፤ ሶስተኛው ደግሞ የነጻነት ሀይሎች ወይንም የዘውግ ብሄርተኞች የሚባሉት ናቸው፡፡ እንደሚመስለኝ የጃዋር ጠቅላላ ስሌት የሀይል ሚዛኑን ወደኦሮሞ ብሄርተኞች መድፋት ነው፡፡ ኢህአዴግ ኖሮም ይሁን ኢህአዴግ ወድቆ የምትቀጥለው ኢትዮጵያ እጣ ፈንታ አወሳሰን ላይ፤ ቀደም ሲል ኦሮሞ፤ በድምስሱ ደግሞ እስላም ኦሮሞው የአንበሳውን ድርሻ እንዲይዝ ፈልጋል፡፡ ለዚህ ደግሞ በተለምዶ የአንድነት ሀይል እየተባለ የሚጠራው ሀይል በተዘረረበት ወይንም እርስበርሱ በተከፋፈለበትና በአንድነት ለመስራት በየወንዙ እየተማማለ መሀላውን በየጋራው በሚያፈርስበት ሰዓት፤ ሲሆን ሲሆን ኦሮሞውን አንድ አድርጎ፤ አንድም ባይሆን አጠናክሮ መያዝ፤ በቀጣይዋ ኢትዮጵያ ውስጥ የይል ሚዛኑንን ወደነርሱ እንዲሆን ያሰፋዋል ብሎ ያምናል፡፡

20. ስለዚህ ጃዋር መጀመሪያ ኦሮሞ ነኝ ሲል፤ ይሄንን ኦሮሞን እንደአንድ ሀይል አጠናክሮ መጉዋዝ፤ መጪዋን ኢትዮጵያን ለመቅረጽ ያስችለናል ከሚል ስሌት ተነስቶ ይመስለኛል፡፡ ምክንቱም፤ ይሄ ልጅ ዞሮ ዞሮ፤ አማራ ወይንም አምሀራይዝድ ሌሎች የበዙበት የአንድነቱ ሀይል በቀላሉ እንደማይቀበለው ያውቀዋል፡፡ ትግሉን እንደከዳ፤ ከአማራ ጋር እንዳበረ እየተከሰሰም ቢሆን፤ ይህ ልጅ አምስት ስድስት አመት፤ ከአንድነት ሀይሉ ጋር አብሮ በልቶ ጠጥቶ፤ ተከራክሮና ተደራድሮ አየው፡፡ አንድነት ጭፍለቃ ነው የሆነበት፡፡ መፈናፈኛ አሳጣው፡፡ ስለዚህ፤ ጃዋር ተገኑን፤ ወይም ኮንስቲቲወንሲውን መምረጡ ነው መጀመሪያ ኦሮሞ ነኝ ያሰኘው፡፡ በሌላ አነጋገር፤ አማሮችና ትግሬዎች እየተፈራረቁ ይህቺን አገር መርተዋል፡፡ አሁን ደግሞ እኛ እንምራ ነው ነገሩ፡፡ በትግሬ ታኮ ወይንም በአማራ ጥላ ስር ሳይሆን፤ በራሳችን መታወቂያ፡፡ አገሪቱን መምራት ካልቻልንም፤ ቢያንስ የራሳችንን እጣ ፈንታ እንወስን ነው፡፡ የኛ ምላሽ ….

ይቀጥላል፤
ተክለሚካኤል አበበ፤ ጥር፤ 2006/2014፡፡ ተረንቶ፤ ካናዳ፤


ነፃነት ሰው የመሆን ቅኔ ነው!

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 23.01.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)
siraate
በነፃነት ያላደገ ማህበረሰብ ውስጡ ቀለም የለሽ ብዕር ነው ….

መነሻ ሲኖርህ ዛሬን ታውቃለህ። ዛሬን ካወቅህ ነገን ታያለህ። ነገን የማዬት ውስጥህ ሙሉዑ ሰው የመሆንህን ሚስጢር ይገልጽልኃል። በአንተ ውስጥ የሆነ፣ አንተን የሆነ፣ አንተን ያገኘ ረቂቅ ነባቢታዊ ህዋስ ማንነትህ መሆኑኑን ልብ ልትለው ይገባል። ማንነትህ „ማንነት“ ስላለው አንተን እንደራስህ የቀመረህ ቅኔው ነው። የቅኔው ወርቅ ሲገለጥ የነፃነት ትርጓሜ ይበራልኃል። የብርኃኑ ምንጩንና ማሰረቱን በፍላጎትህ መሃልና በአንተ ማሃል ያለውን፤ አንተ የማያታዬውን ግን የሚያበራራልህን ረቂቅ የደም ዋጋ አሳምሮ ያመሳጥርልኃል። ሚስጢሩ አንተን ለባዕድ ስሜት ወይንም ለተለጠፈ ልስን ቅርጽንት ሳይዳርግ ወይንም ከዲቃላነት አድኖ ወጥነትህን በችሎት ያጎናጽፍኃል። ታድለኃልና ለጥ ብለህ ሰግደህ ሁነው!

ወጥነት አንገትን ቀና አድርጎ ከእንሰሳ በላይ ብቻ ሳይሆን ቅኝ ካላሆነ ማንነት በላይ ሰለሆነ መንፈስህ ቅልውጥ ሳይማሳን የበታችነትን ገድሎ የእንደራሴ ውስጥነትን አብቅሎ አሳምሮ ይሸልምኃል። በሙሉ ሰው ሰውነት ቀጥ አድርጎ በማቆም እንደ ስው የማሰብ፤ የመኖር ሰማያዊ እኩል ጸጋህን ታፍስ ዘንድ በአክብሮትና በልግስና ይሰጥኃል። ግን ካልተላለፈክው ወይንም ካልረገጠከው ወይንም ካልጠቀጠከው ብቻ ….። ይህ ማለት አንደ እንሰሳ ከመሸጥና ከመለወጥ ድነህ፤ እንደ እቃ ለአግልግሎት ብቻ ከመመረጥና ከመታዬት ሳትደርስ የሰው ሰው መሆንህን፤ መተርጎም ትችል ዘንድ ይገልጥልኃል። ውስጥን የማንበብ መክሊትህ የሚመተረው ከዚህ ላይ ነው። በአፍንጫህ ዓይን ሳይሆን በህሊና ዓይንህ ማስተዋል ከተሰጠህ አስኳሉ አንተ ነህ።

ተርጓሚ ሲገኝ ነፃነት ቅኔ ነው። ነፃነት ረቂቅ ጥልቅ የተባረከ የመንፈስ ውስጥ ፍላጎት ነው። ዛሬ ነፃነት የሰለጠነ ህዝብ ብቸኛ የግናዛቤ መለኪያ ሆኗል። ነፃነት ሰፊ የሰብዕዊነት ማሳ ሀኖም ይታያል። ነፃነት የነበረ፤ የሚኖር የዕምነት መሰረታዊ ዶግማ ወይንም ልዕለ ቃል ነው። ነፃነት በጥሬው ብቻ ሊተረጎም የማይችል ውስጥን በራስነት የማነፅ ሥልጡን ክስተት ነው።
ነፃነት ዛሬ የዓለማችን ጉልተ – አጀንዳ ነው – አንጎልም። ነፃነት ዛሬ የዓለምን መንፈስ በአንድ ሃዲድ ያገናኘ ቅዱስ አምክንዮ ነው። ነፃነት ህይወት ላላቸው ብቻ ሳይሆን ለግዑዛን ሳይቀር ተቆርቋሪ ጠበቃ ነው። ይህችን ትንሽ ዘርዘር ባደርጋት መልካም ይመስለኛል፤ ከተጠቀለለች እንዳትጠጥር … በመጠኑ

ስለምን? ነፃነት ለግዑዛን አስትንፋስ ሆነ? ምክንያቱም ግዑዛኑም ቢሆኖ በሰው ልጅ ታሪካዊ ሂደቶች ብቁ ታዳሚ ከመሆናቸው በላይ ትናንትን ለዛሬ – ዛሬን – ለነገ፤ ነገን – ለነገ ተወዲያ ያቀባብላሉ፤ ያሰብላሉም። ባለውለታዎቻችን ናቸውና፤ አሁን የዋሻ ዘመናት ታሪክ በድንጋይ ላይ ተቀርጸው ይገኛሉ። ብዙም ይናገራሉ፤ መሬት በከርሷ እፍን ሽክፍ አድርጋ ያያዘቻቸው ቅሬተ – አካላት ትናትን አበክረው ያውጃሉ፤ ከመነሻም ይገነባሉ። ለዝንተ ዓለም ዝክረ ንዑዳን ናቸው። ለዛሬ ሥልጣኔም የምርምር ማዕከል እኮ የትናንት ትንግርት ክንውን ነው። ክንውኑ በምስል በቅርፃ ቅርጽ ወይ በፁሑፍ ሊሆን ይችላል። በባዕድ ተገዝቶ ውስጡ እርሾ አልባ ሆኖ ላልተሟጠጠ ማህበረሰብ ግዑዛኑ ያስቀሩት ታሪክ መስታውት ነው።
… አሁን በድንጋይ ግጭት የእሳት መገኘት በራሱ የሰው ልጅ ብርኃንን በእጁ የመፍጠር አቅሙን ጠቋሚ አድርጎታል። ሳይንሳዊ በሆነ መልኩም ለፊዚክስንና ለኬሚስትሪም መቅኖ ሆኖለታል። የሰው ልጅ ሥልጣኔ እንደ ገና መወለድን /ዬሪናይሰንስንም/ ዓላማ አሳክቷል። የሰው ልጅ የአንኗኗር ዘይቤ፤ አምልኮዊ ሆነ ዕምነታዊ ሂደት ሁሉ በስዕል ሆነ በመጸሐፍት ቅጅ ሳይሆኑ ከነተፍጥሯቸው ከሥረ መሰረታቸው ይገኛሉ። በጦርነት ሆነ በመስፋፋት ከወደሙት የተረፉት። ብቻ እነዚህ ሁሉ በነፃነት ማዕቀፍ ውስጥ ሲካተቱ የነፃነትን ሊቅነትን ቅኔነትን ያናግራሉ። ትውፊት የመሆን ዕድላቸውም የነፃነት ልዩ አቀም ያለው ሥጦታ ነው። አቅማቸው የመናገር ብቻ ሳይሆን የግኝትና የምርምር ማዕከላዊ ዝክረ ነገሮች ናቸው አዲስ የዕውቀት የሥራ መስክም ናቸው።።

የነፃነትን ድርሻ መጠነ ሰፊ ነው። አሁን ዩኒስኮ የተቋቋመበት መሰረታዊ ዓላማ የግዑዛንን መብት ለማስጠበቅ በጥብቅና ለመቆምም ጭምር ነው። እግዚአብሄር ይመስገን እሰከ 2012 ድረስ የእኛ ሰባት የነበረው በ2013 መጨረሻ ላይ ወደ ስምንት አድጓል። ይቀጥላልም። ያው ጠንክረን ከሰራን አደጉ ተመነደጉ የተባሉት ሀገሮች የሌላቸው እኛ ግን ያለን ብዙ የቅርስና የውርስን ጥበቃ በአለም ዓቀፍ ደረጃ የሚያስፈልጋቸው ሃብታት አሉንና … ይህ የማንነት ምንጭ አክባሪ ሲያጣ ግን እጅግ ያማል …. ውስጥንም ይመራል። ለማንኛውም ይህ በራሱ የሚያሳዬን የነፃነት ደንበርየለሽ፤ የአብሮነትን ስክነት – አመክንዮነት ዓለምን በሙሉ ባኃቲ መንፈስ ታዳሚ ማድረጉን ነው። የነፃነት ቤተኝነት ድንበር የለሽ መሆኑን ብቻ ሳይሆን የተረጋጉ ራሳቸውን ያወቁ፤ ዕውቅናቸውንም ያጸደቁ የነፃነት ውጤቶቸን ጥልቅነትን ያሳያል።

ከሁሉም ነገር በላይ ፍቅር በመተርጎም ሂደት ነፃነት ልዩ ልብ አለው። ነፃነት ሁሉንም በፍቅር አክብሮ የሚያወራርሰው የመንፈሳችን ልዑቅ ምኞት ነው። ምኞቱ እጅግ ተናፋቂ የሚየደርገው ከነፃነት መልስ የሰው ልጅ ደም መፋሰሱን፣ እረዳው … አቃጥለው … አንድድው የሚለውን ጠናና አመለካካትን ገርቶ ምህርትን አውጆ ከናፈቀው ሳላም ጋር የሚተቃቀፍ፤ ተግባራዊ ለማደረግም የሚተጋ ብቁ ሐዋርያ ስለሆነ ነው። ነገ መምጣት ወይንም መገኘት የሚችለው …. ዛሬን ሳናጠፋው ከቀረን፤ ዛሬን በላፒስ ካለሰረዝነው ብቻ ነው። ነፃነት ለትናንት ሰፊ አክብሮትና ምስጋና አለው፤ ለዛሬም ልዩ ዕውቅና ሰጥቶ ትርጉም አለው። ለነገም ዋቢነቱና ቋሚነቱ በሥነ – ጥብብ ነው። ስለዚህ የነፃነት ተፈጥሮ ቅድመ – ማዕክላዊና – ድህረ ሂደት በማስማማት እኩልነትን በገፍ ይሸልማል። መደማመጥን ይሞሽራል። መቻቻልን ያነግሳል። ይህ የነፃነት በኸረ አምክንዮ ህሊና ነው። ነፃነት የህብረት ጥረት ሰብል ነው።

የነፃነት መርህም፣ ህግግታም ጥብቅናም ሁሉንም ለመተግበር የመጀመሪያ ጥያቄ አለው። እሱ እራሱ ነፃ መውጣትን ይሻል። ማለት ተተርጓሚነት፤ ተጠባቂነት፤ ለጋስነት – በፈጻሚነት።

ሀ. ተተርጓሚነት ሲባል ነፃነት ያሰገኛቸው ፋይዳዎች መሪዎች እንዲሆኑ መፍቀድን፤
ለ. ተጠባቂነት ሲባልም ነፃነት ባስገኛቸው ውጤቶች ዙሪያ የማህበረሰቡ ወይንም የህብረ – ሃብት የሆኑ መስዋዕትነቶችና ውጤቶቻቸው ጣባቂ ባለቤቱ ተጠቃሚውና አስገኙ ህዝቡ እንዲሆን መሻትን።
ሐ. ለጋስነት በፈጻሚነት፤ ነፃነት ፈላጊው አካል ነጻነቱን ሲያገኝ ለጋስነቱን የማረጋገጥ ብቃትን። ለነፃነት ነፃነት መስጠት፤

እኔ ሥርጉተ … ከሩቆቹ ጋር ሳይሆን የጥቁር ህዝብ የነፃነት ታሪክ መሰረት ከሆነችው እናት ሀገረችን ኢትዮጵያ ላይ መነሳቱ እኛን አዙረን በማዬት ወደ ልቦናችን ቢመልሰን ሁለመናችን መነሳት ያለበት ከኢትዮጵያዊነት መሆን አለበት ብዬ አምናለሁ። የእኛ ማንነት እኛን ሳይቀይጥ የሰጠን በነፃነታችን በመኖራችን ብቻ ነው። ነፃነታችን ብቃትን በብልህነት ያስዋበ መሪ ነበረው። ተመሪውም ለነፃነቱ ቀናዕይና ዓለምን በተመክሮ ያሰተማረ፤ የእፍሪካን ነፃነት አስተምህሮ ዶክተሪን የቀረጸ ፤ አደራጅቶ፤ ረድቶ፤ በተግባር ያጡትን ነፃነት ያስመለሰ፤ የጥቁር ህዝቦች ቀንዲል ነውና። እኔ የማምነው ለማናቸውም ቀደምት ጉዳይ „በእጅ የያዙት ወርቅ“ ሆኖ እንጂ ከቅርባችን መነሳቱን ነው። ራስን የመተርጎም፤ የማድመጥና የመመርምር ብቁ ሥልጡን መንገድ ብዬ የማምነው እራስን ማዬትን ነው። እናት ኢትዮጵያ ለራሷ ብቻ ሳይሆን ለነፃነት ለራሱ ማገናዘቢያ ሆነ ማውጫ መሆን የምትችል ብቸኛ አፍሪካዊት ሀገር ናትና። ትውስት አይደለም የኢትዮጵያ ሥነ – ተፍጥሮ ያበቀለው። ስለሆነም መነሻዬ ከዚህ እንዲሆን እፈቅዳለሁ ትንሽ ዘርዘር አድርጌ ልሂድበት …..

ሀ. ተተርጓሚነት
በትርጉም ሊቃኑ የማይችሉ ፈላሲ ስሜቶችን ዘልዬ፤ መሬት ላይ ባሉት ባተኩር ይሻላል። ይህ በረቀቀ መልኩ ሊታይ የሚችል ነገር ነውና። በቀላሉ አገላለጽ ለንጽጽር በነፃነት ያደጉና በቅኝ ግዛት ኩርኩም አስተዳደግ ምክንያት በኮድኳዳ ወይንም በጎድጓዳ ዘመን እድገታቸውን ያሳለፉ ብናሰላው ፍቺውን ማግኘት በቀላሉ የሚቻል ይመስለኛል። ሩቅ አትሂዱ ይህን ዘመን በዚህ ልኬታ ፈትሹት ከጓዳችሁ ተነስታችሁ። … ስደት ላይ እኛ አዋቂዎች ኢትዮጵያውያን እና አንድ ኬኒያውያን ስደተኛ እኩል የመንፈስ አቅም ልኬታ አይኖረነም። እንዲያውም አይገናኝም። እኛ ብቁና ንቁ፤ ያልጎበጠ የፃነት ጸጋ የተገለጠልን የኖርነብትም ስለሆነ ቀና ያለ ሰብዕና፤ በራስ የመተማመን ሙሉዑነት አለን። የውስጣዊነት ርትህ ድባበቡ ለእኛ የሚሰጠን ወዛማ ነው። መንፈሳችን ተፈሪነት፤ የማይደፈር፤ መብቱንና ግዴታውን ጠንቅቆ የተገነዘበ የማያጎነብስ ወይንም ለማጣ ያልሆነ ተፈጥሮ ነው ያለን። የእነሱ ደግሞ አድርባይና የተሸበሸበ ከመሆን አልፎ ፍርኃት የከተመበት፤ ያልተቀዬጠ እንደ ራሳቸው የሆነ ነገር ውስጣቸው የራስነት ጥሪት የሌለው — ሰላላና ዝበት የዘፈነበት ዕይታና አቀረረብ ነው ያላቸው። ስለ ራሳቸውም ለመግለጽ ብናኝ ድፈረት እንኳን የላቸውም። ፍላጎታቸው የተቀረቀረ ነው ስልብ ነገር።

…. እራህብን የሚያውቀው የተራበው ብቻ ነው። ራህብን የማያውቀው ሰው ቢጠዬቅ „ራህብ ምንድን ነው ብሎ ይጠይቃችኋል።“ አያውቀውምና፤ በባዕድ ቅኝ ተገዝቶ የነበረ አንድ የአፍሪካ ሀገር ሰውና እኛ ስለ ቅኝ ግዛት አስከፊነት ብንጠዬቅ እሱ ይመልሰዋል። እኛ ግን ፈተናውን እንወድቃለን። ስለምን? አናውቀውም …. አልተገዛነም። የሚያሳዝነው ነገር በባዕድ ባለመገዛታችን ምክንያት የእኛነታችን መግለጫዎች ሁሉ ከእነሙሉ አካላቸው ሳይቀዬጡ እንደ ተፈጥሯቸው አሉን። ፈታተን ብናዬው ስሜታችንም፣ ፍላጎታችንም መነሻው ሆነ መደረሻው ከዛ ላይ ነው። እንጀራን ስታስቡት ሰፍ ብለን እንወደዋለን። ሆዳችን ሞልቶ እንኳን እንጀራ አለ ከተባለ ማዕደኛ እንሆናለን። ተገዘተን ቢሆንስ? ዕውነታውን ሳንርቅ አቅርበን እናወያዬው …. እባካችሁ ናፍቆቶቼ።

የዕምነት ተቋማትን ሥርዐትና ክንውን፤ ቋንቋውን ብትመለከቱት ቀበልኛው ብቻ ዬት እዬለሌ ነው፤ አለባበሱን ብታዩት ቀለማም፤ አመጋገቡን ብታዩት የማይጠገብ፤ የግብይት ሥርዓቱን ብትመለከቱት ወዝ ያለው፤ የማህበራዊ ኑሮ ትውፊቶቻችን ዘርዘር አድርገን ብንመለከታቸው ጠረናቸው የእኛ ብቻ የሆኑ በፍጹም ሁኔታ ያልተዳቀሉ። የአንኗኗር ሥርዓታችን የተደራጀና ያተወቀበት፣ የታቀደና የተዋበ ነው። የትም ቦታ በዬትም ሁኔታ ኢትዮጵውያን እንታወቃለን። ስለፊደል ገበታችን ሌላ ጊዜ ብመለስበትም እሱ በእራሱ ውበታችነን ያነጥረዋል። „የተወሶ ይሄዳል ተመልሶ“ አይደለም። በዛ ዘመን ፊደላችን የመቅረጽ ሥነ -ጥበብ በማስተዋል ስታሰሉት የአባቶቻችን የበራ፤ በቅኝ ያለተወረረ ሥልጡን አዕምሮን ብርኃንነት ይግልጥላችኋል። በነገራችን ላይ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ጋዜጣ ሥሙ „አዕምሮ“ ነበር። በ80ዎቹም መግቢያ ይህን ሥም ይዞ የተንቀሳቀሰ የግል መጽሔትና ጋዜጣ ነበር … ትውፊት መጠበቅ የትውልዱ ድርሻ ነውና!

ወደ ቀደመው … ከሁሉ በላይ የትም ቦታ በራስ የመተማመን መንፈሳችን ያልተቀማን በመሆናችን እርግጠኝነት በውስጣችን ስላላ ተሰደን እንኳን የበታችነት ስሜት ፈጽሞ የምይጨፍርብን አንቱዎች ነን። ስለምን? ማንነት ያለው ሙሉዑ ሰብእና ስላለን። ይህን ወርቅ ንጥር ተፈጥሯችን ውስጣችን ለማድረግ ከተሳነን፤ እኛና እኛ ሳንተዋወቅ ተዳብለን ነው የምኖረው ማለት ነው። በርጉማን ይህ የነፃነት ታላቁ ዕሴት ተዘሎ ነፃነቱን ለማስገኘት በተደረጉ ሂደቶች የተፈጠሩ ሳቢያዎች ላይ ብቻ ማተከሩ እራስን በራስ የማጥፋት ያህል ነው – ለእኔ።
የመኖራችን ምክንያታዊ ጭብጥ ኣናቱ ያለው እራሳችን የሰጠን የአባቶቻችን የተጋድሎ ጉልህ ዕንቁ ታሪክ ነበር። የመሪነት ብቃት፤ እንዲሁም የህዝቡ ለቅኝ- ግዛት ምኞት አልነበረከክም ብሎ የከፈለው የደምና የአጥንት ዋጋ ማመሳጠር ለምን እንደገደደን አይገባኝም። እኛ የሚገባን ቂመኞች የሚለጥፉልነን ቅርፊት ማተባችን አድርገን አንገት ደፊነትን በመቀበል አጽድቀን ከመንበራችን በፈቃዳችን መውረድ። ዙፋኑ …. ማማው የእኛ ሆኖ ትቢያ ያሰኘናል። ለምን እንደ ሆን አሁንም አይገባኝም? እነሱ ይባትሉ ትናንት ስላልተሳካላቸው ዛሬም ይማስኑ እኛ ግን መብለጣችን እንዲያስተምራቸው መንፈሳቸውን በድርጊት መቅጣት ይገባናል።

አውሮፓውያኑ አይተኙም፤ ለቀደምቷ የነፃነት ፋና ወጊ ሀገር ለኢትዮጵያ። … አሁንማ ቀንቷቸዋል አስፈጻሚ ባንዳ ሥልጣነ መንበሩን ላይ ሀገር ሻይጩ ወያኔ ስለያዘላቸው። …. ለዚህም ነው በመሰሪ የደህንነት ተቋመቸው ረዳትነት ለሥልጣን ያበቁት …. ትናንትን ለማጥፋት – ለማፍለስ፤ ዛሬን ለመፋቅ ነገን ከመምጣቱ ቀድሞ ለማድረቅ የተሴረው … ይህ እንዴት አይገባንም? እነሱ እኮ እንደ ጥንቸል ሁልጊዜ መሞከሪያ ጣቢያ እኛን ለማደረግ ነው ታጥቀው የተነሱት። የሚበልጥን መንፈስ ማን ይወድ – ማንስ ያደንቅው – ማንስ ዕውቅና ይሰጠው ይመስላችኋል – ወገኖቼ?! የውጭ ፖሊሲያቸው ሁሉ መክኖ እንኩትኩት ብሎ የቀረባት ብቸኛ ሀገር ኢትዮጵያ ስለሆነች አሁንም ህዝቧን በማከፋፈል በማጋጨት ለመበተን አይተኙም።

እኮ ስለምን መተላላፍ መጣ ሲባል … ? ነፃነትን መተርጎም ስለቃተን። ነፃነት ለራሱ ከሚፈልገው ነፃነት ላይ እንኳን ለመነሳት አቅማችን የሳሳ – ሰላላ በመሆኑ ምክንያት። አይደለም በቅኝ ግዛት ያለውን ባርነት ዘመን ከእንሳሳ አንሶ መኖር ቀርቶ ተሰደን እንኳን መኖሪያ ፈቃድ አጥተን ስንገላታ የሚደርሰው ሰቆቀቃ ሁሉ ብንፈትሸው ዋናውን አናቱን ነገር የነፃነትን ብሌን ማግኘት ይቻላል። አፈር ያለው ህዝብ ክብር ድንቅ እኮ ነው። በነገራችን ላይ ነፃነት ያላቸው ዜጎች ስደት አይጠይቁም። የሁለተኛ ደራጃ ዝቅተኛ ኑሮ አይናፍቃቸውምና። ለዚህ ነበር በአፄ ኃይለሥላሴ ጊዜ ከተማሩ፤ ውጭ ሀገር ዕውቀት ከቀሰሙ በኋላ ሙሑራን ወደ ሀገራቸው በደስታ የሚመለሱት። መሰደድ ውርዴት ነበር በዛ ዘመን። የዚህ ዋጋው የሚላካው በመንፈስ ስሌት ነው። ነፃነት ትክክለኛ መኖር ነው። መኖሩ ጣዕሙ በራሱ ይዘትና ቅርጽ የሚዋቀረው በነፃነት ብቻ ነው። የዛሬን የዘመነ ዬወያኔን ተውት … አድርጉት። በዬደቂቃው ወያኔ አሜኬላ ችግኝ ያፈላል፤ ተንከባክቦ ያጸድቃል ተዋጊ አድርጎ የፋልማል …. የተፋለሰ አረም …. ለማንኛውም ነፃነት አብዝቶ ሁሉም የተሰጠው ግን ተርጓሚ አጥብቆ የሚሻ ቅኔ ነው።

ለ. ተጠበቂነት
የነፃነት ግኝቱ ከሰማይ በታች በሰዎች መስዋዕትነት የቀለመ ነው። ይህ ቀለማም ጥሪት ቅርስና ውርስ ደግሞ የእኛ ሁለንትናዊ ሀብት እንጂ የአንድ ጎሳ ወይንም የአንድ ኢሊት አይደለም። ሃብትነቱ ውድ ህይወት ተከፍሎለት ስለሆነ የተከበረ ስጦታ ነው። የአደዋ – የማይጨው – የመቅደላ – የመተማ የዶጋሌ – የአንባለጌ ሚስጢር። ይህን ታላቅ ስጦታ ጠብቆ ለልጅ ልጅ ለማቆዬት ብቁና የሰለጠነ፤ የብሄራዊ ስሜት የሚያንገበግበው፤ ኃላፊነት የሚሰማው ዜጋ ብቻ ሳይሆን የመንግሥትም ግዴታ ነው። ምክንያቱም ሃብትነቱ የህዝብ ነውና። ይህንን ሃብትነት የመጠበቅ የማሰጠበቅ መብት ብቻ ሳይሆን ግዴታም ነበር …. ዛሬ በሃገራችን ሳንክ ቢገጥመውም የነፃነት ጥበቃ በኽረና በትረ አብይ ጉዳይ። ነገ ግን ኃላፊነት ያለው ሥርዓት ሲዘረጋ መዘከሩ አይቀሬ ነው ….. እርግጥ አሁንም ከእኛ አልፎ እነ ተፈሪውያን፤ የተከበሩ ቤተሰበ – ኔልሰን ማንዴላ …. መላ አፍሪካውያን የሚዘምሩለት የመንፈሳቸው ጣዕማዊ ዜማ ነው።

የፓን አፍሪካ ቀደምቶች፤ የአፍሪካ ድርጅት ያሁን ህብረት ይሁኑ የዛሬዎቹ አቀንቃኞች ሁሉ በክብር ያከበሩት በመንፈሳቸው አጉልተው የጻፉት ታላቅ መጽሐፋቸው ነው ኢትዮጵያዊነት። በመላ ዓለም ትውልድ ቢለዋዋጠም ዋጋው ሳይቀንስ እንዲዘልቅ የሚተጉ ቀለሞቻችን አሉ። ህያውም ናቸው። ተመስገን! ነፃነትን የተማሩበት ተቋማቸው – እነሱን እንደ ራሳቸው ወደ ራሳቸው የመለሳቸው፤ እነሱነታቸውን ከብክቦ የሰጣቸው ቅዱስ አንደበተ – ተግባር፤ ሁልአቀፍ ሚስጢር ነው ኢትዮጵያዊነት፤ ስለሆነም የጥቁር ህዝብ የነፃነት ታሪክ ጥበቃ ከእኛም አልፎ የተደራጀ ተግባር ከፈጸምን አፍሪካውያን ብቻ ሳይሆን የነፃነት ዓላማ አራማጆች ሰብዕዊ ድርጅቶች ሁሉ የሚጋሩት ይሆናል። ይህን መፋቅ ከቶውንም አይቻልም። ማሸለበም አይቻልም – ፈጽሞ።

አብሶ የነፃነት አቀንቃኝ ሁሉ ፍሰቱ የነፃነት ፍላጎትና ተፈጥሮ ተጋፍቶ ወይንም ገፍትሮ መሆን አይገባውም። ውስጥን አስቀድሞ መርምሮ መፈወስ ያስፈልጋል …. ወደ ኋላ ተኑሮ አይታወቅም – በፍጹም። ለዘመኑ የተመቹ ገጠመኞች ሁሉ ውስጥ ሊያበቅላቸው የሚገቡ ጭብጦች መሰረት ብቁ ድልዳል አላቸው። በስተቀር የነፃነትን ሥነ – ተፈጥሮ ጋር ተጣልተናል። ትናንት ያለተሳካላቸው ኃያላን በመቁንን በሚሰጡን ልጣፊ ሳንሸበብ ምኞታቸውን በማምከን እኔ የታሪኬ ባለቤት፤ ታሪኬም የእኔነት መግለጫ በማለት በሙሉ ልብነት ቅስማቸውን ሰብሮ ሴራቸውን አንኩቶ ማደረግ ይጠይቃል። ወደ ራስ መመለስ የወቅቱ ዓራት ኣይናማው መንገዳችን ሊሆንም ይገባል። ነገንም የማይሸጥ የማይለወጥ መሆን አለበት። ለጨረታና ለድርድር የማያቀርብ ትሩፋታችን መጠበቅ ግዴታችንም ነው። መጠሪያችን እራሱ እኮ አዲስ ነው ለዓለም ቅጂ አይደለማ። ለዚህ ነው ለመጥራት ሆነ ለመጻፍ የሚቸገሩት ነጮች። ያልተለመደ — የሚያሰከብር። ትርጉሙን እራሱ ይጠይቃሉ። አያውቁትማ! ማንነት መተርጎም ከተሰጠን … ጆሴፍ፤ ካሎሪን፤ ክርስቲና፤ ወልፍ፤ ስሚዝ፤ አንባልም እኛ … አበበ ፈለቀ ጃርሶ ኬሮድ አምርቲ ሃይሌ ዘለቀ …. ፋና ታዬ ሲራጅ ወዘተ

ሐ. ለጋስነት- በፈጻሚነት።

ነፃነት ከቤት ጀምሮ ተወዳጅ ጉዳይ ነው። ነፃነት ለዕድገት፤ ለሥልጣኔ ለፈጠራ ለሁሉም መንገድ ጠራጊ ነው። የነፃነት ፈላጊው ብዛት ህልቆ መሳፍርት ነው። ነፃነት የማደረግ የመንፈስ መብት ፈቃድ ሰጪ ድርጊት ገዢ ሳይኖርበት ማለት ነው። የመንፈስ ውጤት ተጠቃሚነትና ዲተናት ማለት ነው። ዲታነት በለጋሥነት ከሆነ ውስጥን ፏ አድርጎ ያበራል።
ነፃነት ፈፃሚነት ብቃትን ይጠይቃል። ብልህነትን ይፈልጋል። ማስተዋልን ይሻል። በስተቀር ምድረበዳ የበቀለ ለምልም ይሆንና ዕድሜ ሳይኖረው ጠውልጎ ይሞታል።

ነፃነት በፍላጎት መኖር ማለት ሲሆን፤ ፍላጎትን ፈልጎ ማወቅ የሚቻለው ግን ሥልጡን መንፈስና ተለዋዋጭ ያልሆነ ቋሚ እወቀት ሲኖር ብቻ ነው። አዋቂነት ከተፈጥሮ የተሰጠ ጸጋ ነው። የግድ ፊደል መቁጠር አያስፈልግም። የቀደመችው ኢትዮጵያ የነፃነትን ትርጉም ያወቀቸው እናት ሀገር ከመፈጠሯ በፊት ነበር የነፃነት ፊደልን ቆጥራ የተወለደቸው። ዘመናዊ ትምህርትም ሳይኖር። ይህ ጸጋዋ ነው። ልጇቿን ያሳደገቸውም በዚህ ወተት ነው። ከእቅፋ ወጥተው ሲሄዱ ብቻ ወተቱ ፈሶ መርዝ ይታከበታል። መርዝ አብቃዮች የተፈጠሩበት ዶክትሪን ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን ማጥፋት ነውና። ስለምን ኃያልነቷ ያስፈራቸዋል። ያርበደብዳቸዋል። በእፍሪካ ቀንድ አካባቢ የነበራትን የባላቤትነት መብት ተጋፍተዋት እንኳን ባድመ ላይ በዕውናቸው ታላቁ ሚስጢር ተርጎሞላቸዋል ማንነቷን። ሳውዲ አረብያ ላይ ሀገሬው ያልሞከረውን ነፃነት በድፈርት ወጥተው ውስጣቸውን የገለጹት የሚስጢር ልጆች ብቻ ናቸው። መዳፈር ሲመጣም እሳት ለብሰው እሳት ጎርሰው በዬትኛውም ዓለም የሚኖሩ ልጆቿ አሳይተዋል። ከውስጥ የሚንቀለቀል፤ ሊያዳፍኑት የማይችሉት የሚንቀለቀል ባለላንቃ የተፈሪነት በረከት ነው ኢትዮጵያዊነት። ስለሆነም ቀደምት ጠላቶቻችን በቀዳዳው ሁሉ ተግተው የጥፋት ተግባራቸውን መከወናቸው አይቀርም።

ስለዚህም ልጆቿ ልብ ሊሉት የሚገባው ፍሬ ዘር እራሳቸውን በለጋስነት ለነጻነታችው ትርጉም ከመስጠቱ ላይ ሊሆን ይገባል። የእኔ የነፃነት ዓርማ! የእኔ እናት! የእኔ መኩሪያ! እኔ እያለሁ ማንም አይነካሽም! እኔ ያንቺ አንቺም የእኔ፤ አንቺ የተገኘሽው በ እኔ ውስጥ እኔም የተገኘሁት በአንቺ ውስጥ። ከአንቺ የሚለዬኝ ማንም የለም። በማለት ሴራዎችን ሁሉ ብን ማደረግ ከቻሉ የነፃነት ወተት ፈውስና ድህነት ሆኖ ሙሉዑ ብቁ ባለቤት ያደርጋቸዋል። ከዚህ ከተላላፉፍን ግን የበታችነት ስሜት ይዳንስብናል። ማህከነ! ዛሬ የምንታገልለት ነፃነት ትርጉም የሚኖረው ትናንት ያገኘነውን ነፃነት በብቃት የመተርጎም አቅምና ችሎታ ከኖረን ብቻ ነው። ሥልጡንነት ማለትም ነፃነትን መተርጎም መቻል፤ በራስ ውስጥ ፈቅደን ተፋጻሚ ለማድረግ መቁረጥና መወሰን ነው ፋይዳው ሆነ እሴቱ።

ይቋጭ መሰል …

ትናንት — የሀገሪዊነትን ባላቤትነት የፈጠረ ማንነት፤ ባዕድነትን ገፍትሮ ድልን በደሙ ያቀለመ ማንነት፤ የመንፈስ ሆነ የአካል ወረራ በትውልዱ – በዘሩ – በሐረጉ – በማንነቱ ላይ ያልነበረ ኩሩ ዜጋ ዛሬ ላይ ሆኖ እንዴት ባዕዳዊ ወራራን ለማስተናገድ ይፈቅዳል? ከፈቀደ ግን – የተጣበቀ ገጠመኝ። የተቀረቀረ ዕሳቤ። አድነን በሉ!
ወዶቼ! ሳላውቀው መጪ አልኩኝ – ብዙ። ውስጤን ፈትሾ ልዩ ሐሤት በሚሰጠኝ እርእሰ ጉዳይ ላይ ስዘናከት እናንተንም በመንፈሴ ሰንቄ ነበር። ብርታቴና ጥጌ ናችሁና። ለነበረን የመደማመጥ ብቁ ቆይታ ፍቅሬን በልግስና ሰጥቻችሁ ልሰነበታችሁ። ደህና ሁኑልኝ – የእኔዎቹ!

ነፃነት ማለት ኢትዮጵያዊነት ማለት ነው።
የነፃነት ቀደምት መምህርት ታላቅ ሀገር ኢትዮጵያ!
የመስዋዕትነት ዕንቁዊ የትውልድ ሽልማት ነፃነት ነው።

እግዚአብሄር ለአፈራችን መሬት ያብቃን! አሜን!

ነፃነት ተግባራዊ በማደረግ እረግድ በአደጉ ሀገሮች አንፃራዊ በሆነ ወይንም ልቅ በሆነ ወይንም መጠራቅቅ ባላው ሁኔታ የተረጎሙት ሀገሮች አሉ። ይህ ወደ እኛ ስንመጣ እንደ ቀደምት መምህርነታችን ለነፃነት የቆመ አካል፤ ድርጅት ተቋም ነፃነት መስጠትን ወይንም ማግኘትን ራህብተኛ የመሆኑን ያህል በነፃነት ዙሪያ ያሉ ነፃነት የሚለግሳቸው አምክንዮችን በመተርጎም እረገድ ገና አልጀመርነውም። ፊደልም ያልቆጠርነበት ጉዳይ ይመስለኛል።

ዛሬ ማታ ነፃነታችን በእጃችን ቢገባ በአግባቡ አስተዳድረን የሚመቸንና የማይመቸንን ፍላጎቶች አስማምተን የነፃነትን ሥነ – ምግባር ካለ መጠራቅቅ እንፈጽማለን ወይ? ዝግጁ ነን ወይ? ስንዱ ነን ወይ? የዕውነት አይደለነም። ሃቁ ይህ ነው። ከእኛ ፍላጎት ትንሽ ፈቀቅ ያለ ነገር ቀርቶ ተመሳሳዩን ሃሳብ የሚደግፍ ግን የተሻለ ሃሳብን፤ የዳበረ ዕይታን፤ የተደራጀን ፈጠራን፤ የበለጠን አመለካከትን፤ የቀደመን መንፈስን ለማስናገድ እንኳን የፍርፋሪ ትዕግስት የለም። አልፍ ሲልም ጦርነት ይተወጅበታል። በዛው በእኔ ፍላጎት ዙሪያ እያለ ጦር ይመዘዝበታል። ስለዚህ አንዱ ለሌላው በ እጁ ያለውን ነፃነት ለመስጠት ገንፉግ ነው።
ይህ የሃሳብ ልዩነት መዋዋጥ መደማመጣ በጓዳ ይቀመጥና፤ በመስመራችን ላለውን እንኳን ከእኛ መንፈስ ወይንም ብቃት በታች መሆኑ ካልተረጋጋጠ ያዳልጠናል …. ስለዚህ በጠራ ቋምቋ ነፃነት በእጃችን ቢገባ ለሌላው ለመስጠት የወጣልን የንፉግነት ተዋናዮች ወይን አጋፋሪዎች ነን። ይህ ሲሰላ ሲመነዘር ስለ ነፃነት ብለን ከፈልን የምንለው መስዋዕትነት የውርንጫ ድካም ሆኖ ቁጭ ይላል። ተቆርቋሪነቱም ባዶ ቀረርቶ ብቻ ….
ንፉጎች። ዛሬ ነፃነት ከራበኝ ባገኘው እኔ እራሴ ሐዋርያ ሆኜ እራሴን ውስጤን መንፈሴ ለድምጽ ብልጫው ካላስገዛሁ ከንቱ ነው። ትግሉ በሉት፣ ልፋቱ በሉት፣ መስዋዕትነቱ በሉት፤ እኔ እጅግ ቁርጥምጥም የሚያደርገኝ ምን እንደሆን ታውቃላችሁ? ነፃነት ታጋይ ከመባላችን በፊት አመኑ በፈቀደው መጠን ስለ ነፃነት ተፈጥሮ ሆነ ሥነ – ምግባር የምናውቀው ምንም ነገር የሌላ መሆኑን ነው። ከዚህ ጋር ትናንት ነፃነታችን ያላስነጠቁትን ጀግኖችንም ከሳሾች መሆናችን።
ዚህ ባለፈ የመንፈሴ ሰሌዳ የማገድናቸው … ለበለኃሰብ አሳልፈን የሰጠናቸው ነፃነት፤ እኩልነት፤ የመጻፍ የመሰብሰብ የመደራጀት የመናገር ነፃነት እያዩሉ በዬዘመኑ በባሩድ የነደዱት፤ ዛሬም ሚሰውት፤ እስር ላይ የሚማቅቁት ወገኖቼን አብዛኞቹ ደግሞ መኖርን ያልጀመሩት ወጣቶች ናቸው እዬተጠፉ ያለቁት ወይንም በፋሽስት በቀል የሚሰለቁት። ይህን ሳስብ ውስጤ ይርመጠመጣል። ፈፃሚነታችን በ እጃችን ሲገባ ስለምነዘለው። ካለ ዘመኑ ካለ ብቃታችን የተፈጠሩ የበለለጡ ጀግኖች የሚከፍሉትን መስዋዕትንት ማድመጥ አለመቻለችን …. ሰቀቀን ነው። እሳት ነው ረመጥ። በተመሳሳይ ፍለጎትና ዓላማ ዙሪያ በተለያየ ሥም ስሜታችነን ከዘንነ የ እኔ ካልሆነ የ አስሱ ይገረብጠኛል … የምሽጉ ፍልሚያ ይህ ነው …. በቃ … ስለምን? ….

አንድ ለነፃነት የሚታገል ድርጅት፤ ግለሰብ፤ ቡድን ለሌላው ነፃነት ተቆርቋሪ መሆን አለበት። ለምሳሌ ሥነ – ጥበብን ልውሰድ። ሥነ ጥብብ ስለፈለግነው ብቻ ተስጥዖው ሊገኝ አይችልም። የሰማይ ሥጦታ ነው። ትግባባኢን ውዶቼ …. ለዚህ የሰማይ ሥጦታ እንኳን የምንፈጥረው ማጠበቂያ፤ የሚጣለው ተዕቅቦ በጣም ድልዝ የሆነ የነፃነት ፈላጊነታችን በእጅጉ የሚያሳርረው የተጋጠ ገጠመኝ ነው። ትናንት ልንሳሳት እንችላላን። ዛሬ ግን አለፍንበትን ገምግምን ሁሉንም በ አውንታዊና በቅንነት መተርጎም ይጋባል። ውስት ፈቅዶ ማረም ይገባል። ዕድሜም ቁጥር መማርም ቁትር መሆኑ እራሳችን አብሶም ህሊናችን እረፍት የማይሰጠን የትውለድ ዕዳ ተሸከምንን ሳናካፍል ማለፍ አለመፈጠር ይሻላል። የቀደምቱ ነብይ ጸሐፊ „የአልወለድም“ ሚስጢር ተዚህ ላይ ተገኘ። የነፃነት ታጋይ ነፃነትን ለመስጠት ስስታም ሳኢሆን ውስጡ በፈፃሚነት መዳሰስ አለበት … በስተቀር ውሃ ወቀጣ ነው …..

አንድ ሰው ሲጽፍ፤ ሲተውን፤ ሲዘፍን፤ ሲስል ሌላ ዓለም ውስጥ ሆኖ ነው። ለነገሩ በዚህ ልዩ ዓለም ለመኖር ላልታደሉት ምንም ሊመስል ይችላል ይሆናል። በሥነ ጥበብ ዓለም ሲኖር ጨለማ ውስጥ ሆናችሁ ብርኃን ይታያችኋል፡ ደማናማ ቀኖች የጸደይ አባባዎች ሆነው ፈክተው ይታያችኋል። ረግረግ ላይ ሆናችሁ መሰላሉን ያቀበላችኋል፤ እጅግ ጉድጓድ ወስጥ ሆናችሁ ካለ መሰናክል የምትወጡበት ደረጃ የሰራላችሁ። ወንዝ ሞልቶባችሁ መሻገሪያ ድልድይ ወይ ታንኳ ያቀርብላችኋል። በጣም ውስብስብ ያለ ፈተና እያሳሁ ወይ እንደ ጠፍር* መየመፍትሄ ጭላንጭል እነደሌለው እአያችሁት ግን ብቃትን – ጥንካሬን – ጽናትን – ተስፋን ያቀብላችኋል። ሥነ – ጥብብ አዲስ ፕላኔት ነው። በተለይ በተኛው በውስጡ ሆኖ ሲዋንበት። ታዳሚው ሲታከልበት ደግሞ ዳግሚያ ትንሳዓ ነው። መከራው፤ ፈተናው፤ ሳንኩ ሁሉ የጥቡ ዕድገት ወተቶች ናቸው። ስተወጡት ማደጋችሁን ታዩበታለችሁ። ይህንን የሰማይ መክሊት እንኳን እንገድባለን በማለት የነፃነትን ጅረት ለመገደብ ማሰብ ቀንና ሌሊትን የማቆምአህል ስለመሆኑ ማስተዋል የከሰለበት እርምጃ ኢሰዳል። ንጉሥ ዳዊት በመዝሙሩ „ህግ ተላላፊዎችን ጠላሁ ኢላል“ በዬትኛውም ዕምነት ወይንም ሃይማኖት ህግ ላይ ድርድር የለም ታዲያ የሰማይ ሥጦታን መዳፈር መተላላፍ አይሆንም …. የነፃነት ፈላጊነታችን ትርጉምስ የት ላይ ይረፍ?

መከወኛ?

አሁን ትግሉ ነፃነት ወይንስ ባርነት? ነፃነት ከሆነ አንተለላፈው። ነፃነት ተወዳጅ ሥነ ተፈትሮ አላው ግብታዊ ስሜቶቻችን ሁሉ መለስ ብለን ፈታታሸን …. ፍላጎታችን ነፃነት ስለመሆኑ ተግባር ላይ እንገኝ። ቅልሞሹ ገበጣ ጨዋታው እነድርቺ እንድርቺው ልልጆቻችን የልጅነት ህይወት እንዳይሾልክባቸው በዘመናቸው ይዝናኑበት በዚህ ውስጥም ኢለፉ። እኛ ግን እንደ ዕድሜያችን፤ እንደ ትምህርት ደረጃችን፤ እንደ ተመክሮችን ለመሆን ውስታችን እናሸንፈው፤ ግብታዊ ስሜቶቻኢነን እንግራቸው፤ ቅኑ እንሁን ….. አባቶቻችን አላፉበትን ቅኝ ተገዢነት ናፋቂ አንሁን። ኢልቅ ባለ አደራ ነንና ፍቅርን በፍቅር አባዝተን ከብረን እናስከብረው። ሁሉ ያላት ታላቅ ሀገር አለችናና እሷን ከፍ አድርገን ለማቆዬት ተግተን ለነፃነታችን እነሥራ።
እጅግ የማከብራችሁ የጹሑፌ ታዳሚዎች ስለፈቀዳችሁልኝ መልካም ጊዜ አትዮጵያዊ አክበሩት በ ያላችሁበት አንሆ ላኩኝ።

አምላካችን ቅዱስ እግዚአብሄር የሰጠንን መስተዋል እንተረጎምው ዘንድ ወደ ልቦናችን ኢመልሰን። አሜን

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
እሜቴ ነፃነት እንድምን ይዞሻል?
እንዴትስ ከርመሻል?
ከእመናው ሸክማ ሸክምሽ ዘንድሮስ ከብዶሻል
እልፈት የለው ኑሮሽ እንዲህ ይፈትልሻል።

http://ecadforum.com/Amharic/archives/10703/

https://www.zehabesha.com/amharic/archives/11816

Sport: የባርሴሎና ተጨዋቾች የእግር ኳስ ተንታኞች ሚዛን

$
0
0

በአዲስ አሰልጣኝ የ2013/14 የውድድር ዘመንን የጀመረው ባርሴሎና እንደቀድሞው አስፈሪ አለመሆኑ እየተነገረ ቢተችም ውጤት ከሚለውጡ ተጨዋቾች ጋር ውድድር ዘመኑን አጋምሷል፡፡ የተጨዋቾቹን ብቃት የታዘቡ የእግር ኳስ ተንታኞችም የባርሳን ከዋክብት
‹‹ልዩ ብቃት ያሳዩ››፣
‹‹ጥሩ አቋም ላይ የሚገኙ››፣
‹‹ሊሻሻሉ የሚገባቸው›› እና
‹‹የተቸገሩ›› በሚል እንደሚከተለው ለይተዋቸዋል፡፡


ልዩ ብቃት ያሳዩ

Barcelona v Real Madrid - La Liga
ቪክቶር ቫልዴዝ
ዘንድሮ በረኛው ጉዳት እስከሚገጥመው ድረስ በዓለም የጊዜው ምርጥ ግብ ጠባቂ ያስባለውን ብቃት አሳይቷል፡፡ አምና በረኛው ሲበዛ ብቃቱ ስለመውረዱ እና የሚሞክሩበትን ኳሶች ለማዳን ብዙም ጥረት እንደማያሳይ እየተነገረ ተተችቷል፡፡ እንዲያውም ቀደም ባሉት ዓመታት ለክለቡ የሰጠው ጥቅም ከግምት ገብቶለት እንጂ ቫልዴዝ ይፋ ወቀሳ ይገባው ነበር የሚሉት ጥቂት አይደሉም፡፡ ዘንድሮ ግን በባርሴሎና የግብ ቋሚዎች መካከል ቆሞ ሊያድናቸው የነበሩት ኳሶች በመጪው ክረምት በዓለም ዋንጫው የስፔን ቋሚ በረኛ እንደሚያስደርገው እስከ መነገር ደርሷል፡፡ ከአምናው አንጻር ዘንድሮ ያሳየው መሻሻል ብዙዎችን አስደንቋል፡፡
ዣቪ ሄርናንዴዝ
ባለፉት ሁለት ዓመታት የዣቪ ብቃት መጠነኛ መቀነስ ታይቶበታል፡፡ በተለይ ኳስ ሲነጠቅ ተመልሶ ቦታውን ለመያዝ እጅግ ሲቸገርም ተስተውሏል፡፡ ባርሴሎና በመልሶ ማጥቃት አደጋ ውስጥ ሲገባ የሚደርሱለት ፈጣን አማካዮች ያስፈልጉታል፡፡ ባርሴሎና በፔፕ ጋርዲዮላ ጊዜ ‹‹ከፈውስ አስቀድሞ መጠንቀቅ ይሻላል›› የሚል ፍልስፍና ነበረው፡፡ ቡድኑ የተወለደበትን ኳስ ለማስመለስ ከመሯሯጥ ይልቅ አስቀድሞ አለማስነጠቅ እንደሚሻል ያምናል፡፡ ሆኖም ይህንን ለማረጋገጥ ተከላካዮቹ ወደ ኋላ አፈግፍገው ሲጫወቱ በኋላ መስመር እና በአጥቂዎቹ መካከል ያለው ክፍተት ይሰፋል፡፡ ስለዚህ አማካዮቹ ክፍተቱን ለመሙላት ብዙ ይሮጣሉ፡፡
በእርግጥ ዣቪ የተዳከመ አይመስልም፡፡ ተጨዋቹ የሚነጠቃቸው እና ለተጋጣሚ ቡድን ተጨዋቾች የሚሰጣቸው ኳሶች ይኖራሉ፡፡ ሆኖም እንደ አማካይ ቦታ ተጨዋችነቱ የኳስ ንክኪው፣ የፓሲንግ ስኬቱ፣ ያለ ኳስ የሚያደርገው ሩጫ፣ ጉልበቱ፣ መረጋጋቱ እና የመሪነት አቅሙ አሁንም ድንቅ ነው፡፡ ዣቪ አሁንም መቼ ከመሀል ሜዳ ተነስቶ ወደ ፊት መሮጥ፣ ተጋጣሚውን ማስጨነቅ፣ የጨዋታውን ፍጥነት መጨመር እንዳለበት በሚገባ ይገነዘባል፡፡ ዘንድሮም ተጨዋቹ በልዩ ልእና የጥራት ደረጃውን በሚያሳይ መልኩ ቡድኑን መጥቀሙን ገፍቶበታል፡፡
Neymar-Barcelonaኔይማር
ከሀገር ወደ ሀገር ቀርቶ ከሀገር ሀገረ ተዛውሮ መጫወት በራሱ ፈተና ነው፡፡ በዚህ ላይ የኔይማር ዕድሜ እና የወጣበት ገንዘብ ብቻውን ከባድ ውጥረት ይፈጥራል፡፡ ሆኖም ወደ ባርሴሎና ከመጣበት ቀን ጀምሮ ዓለም አይኑን የጣለበት ብራዚላዊ በካታሎኒያው ክለብ ድንቅ ብቃቱን ማሳየት ጀምሯል፡፡ ተጨዋቾ ወደ ስፔን የመጣው ከብራዚል ጋር የኮንፌዴሬሽን ዋንጫን አንስቶ እና በራስ መተማመኑ ላቅ ያለ ደረጃ ላይ ደርሶ ቢሆንም ጅማሮው ቀላል አልሆነለትም፡፡ ሆኖም አሰልጣኙ ማርቲኖ የሰጡትን ምክር ተቀብሎ ሜዳ ላይ እየተገበረ አቅሙን ማሳየት ችሏል፡፡ በተለይ ኃላፊነት በጥሩ ሁኔታ እየከፈለ በትልቅ ደረጃ መጫወት እንደሚችል አስመስክሯል፡፡ ተጨዋቹ በመጀመሪያዎቹ ወራት ያሳየው ድንቅ ብቃት በቀሪዎቹ የውድድር ዘመኑ ወራት ብዙ እንዲጠበቅበት ያደርጉታል፡፡ ሆኖም ልጄ ይበልጥ ባይሻሻል እንኳን እስካሁን ያሳየውን ብቃት መድገም ብቻ ያስመሰግነዋል፡፡
ሰርጂዮ ቡስኬትስ
ይህ አማካይ በሚናው ላይ የሚያሳየው አስገራሚ ብቃት በቦታው የዓለም ምርጥ ያሰኘዋል፡፡ ኳስ ሲይዝ ፖሲንግ ችሎታው ያልተዛነፈ ነው፡፡ ኳስን በቁጥጥሩ ስር ለማቆየት ሲል አዟዟሩ እና አቅጣጫ የሚቀይርበት መንገድ የሚታመን አይደለም፡፡ ያለ ኳስም ቡስኬትስ ድንቅ ነው፡፡ በተለይ በአዲሱ አሰልጣኝ ስር ተጨዋቹ ይበልጥ መሻሻሉን እና የተከላካይ መስመሩን በመጠበቅም በኩል ሆነ መሀል ሜዳውን በበላይነት በመምራት የላቀ ብቃት ይስተዋልበት ጀምሯል፡፡ ሰርጂዮ አሁንም ሸርተቴ የመውረድ ድካም ቢታይበትም የእይታው እና የፓሲንግ ብቃቱ የተለየ ተጨዋች ሆኖ እንዲቀጥል አድርጎታል፡፡

ጥሩ ብቃት ላይ የሚገኙ

ጄራርድ ፒኬ
ተከላካዩ ዘንድሮ በገዛ ደጋፊዎቹ ሳይቀር ሲበዛ ተተችቷል፡፡ ሆኖም ተጨዋቹ ባርሳ በሊጉ አናት እንዲቀመጥ እና በቻምፒዮንስ ሊግም ምድቡን በመሪነት እንዲያጠናቅቅ ልዩ ብቃት አሳይቷል፡፡ በተለይ ከቡድኑ የፍፁም ቅጣት ምት ክልል በቴስታ እያገኘ ያራቃቸው የማዕዘን ምቶች እና ክሮሶች እጅግ ይበዛሉ፡፡ ሆኖም ማርቲኖ በግቡ ቋሚዎች ላይ የሚቆሙ ተጨዋቾችን በማዕዘን ምቶች ጊዜ አለመጠቀማቸው እና ዳኒ አልቬስ አብዝቶ ወደ ፊት መሄዱ በመከላከሉ ጨዋታ ላይ ለሚፈጥረው ችግር ፒኬ ተጠያቂ ይደረጋል፡፡ እንዲያውም ላለፉት ሁለት ዓመታት ያለ እረፍት የተጫወተ ተከላካይ ከጨዋታ መደራረብ ችግሩ ጎን ለጎን አሁን በሚያሳየው ብቃት መጫወቱ ሳያስመሰግነው አይቀርም፡፡ ፒኬ የሚሸፍነው ርቀት፣ አስደናቂ ረጃጅም ፓሶቹ፣ የማጥቃት ባህሪዩ እና የጎል ሪከርዱ በዓለም ላይ ከሌሎች የመሀል ተከላካዮች ሁሉ የላቀ ያደርገዋል፡፡ ከዚህ ውጪ የመከላከል ጨዋታ በቡድን የሚሰራ ነው፡፡ ጎሎች በቀላሉ ከተስተናገዱ ችግሩ ከግለሰብ ይልቅ የቡድን ነው፡፡ ለምሳሌ ቫልዴዝ ዘንድሮ ልዩ ብቃት አሳይቷል፡፡ የተከላካይ መስመሩ ቀሽም ቢሆን በረኛው ተመሳሳይ ውዳሴ ሊያገኝ አይችልም፡፡ ፒኬ ምፍትሃዊ ሚዛን ከታየ መጥፎ ብቃት ላይ አይደለም፡፡
ፍራንሴስክ ፋብሪጋዝ
ሴስክ ለባርሴሎና የሚሰጠውን ጥቅም በታክቲካዊ መለኪያ መመልከት እንችላለን፡፡ ስፔናዊው የማጥቃት ባህሪዩ የጎላ አማካይ ነው፡፡ ወደ ፍፁም ቅጣት ምት ክልል ሲቃረብ መቼ አደገኛ ኳሶችን ለጓደኞቹ መስጠት እንዳለበት ያውቃል፡፡ በአዕምሮው በኩል ፋብሪጋዝ አሰልጣኙ በሚሰጡት በየትኛውም ሚና ለመጫወት ዝግጁ ነው፡፡ በአካላዊ መመዘኛ ቀርፋፋ የሚባል ቢሆንም በመጨረሻ አቅሙ ሳይቆጥብ ለመሮጥ ግን ዝግጁ ነው፡፡ ሜሲ በጉዳት ከሜዳ ከራቀ ወዲህ ተጨዋቹ በሀሰተኛ ዘጠኝ ቁጥር ሚና እየተጫወተ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ ሚናው ፍጥነት የሚጠይቅ መሆኑ ለፋብሪጋዝ ፈታኝ ያደርገዋል፡፡
አለመታደል ሆኖ የባርሴሎና ተጋጣሚዎች ወደኋላ አፈግፍተው እና ተጠቅጥቀው የሚከላከሉ መሆናቸው ፋብሪጋዝ ተከላካይ ለንጣቂ ኳሶችን በተደጋጋሚ እንዳይሰጥ ይገድበዋል፡፡ አስፈላጊውን ክፍተት ሲያገኝም ቢሆን የክንፍ ተጨዋቾቹ ወይም አጥቂዎቹ ሰዓቱን የጠበቀ ሩጫ ካላደረጉ ዋጋ አይኖረውም፡፡ እንዲህም ሆኖ ፋብሪጋዝ ጎል በማስቆጠር ጥሩ ሲሆን ለጎል የተመቻቹ ኳሶችን በማቀበል በኩልም የላሊጋው የበላይ ነው፡፡
ካርሎስ ፑዮል
ፑዩል ዘንድሮ ብዙ ጨዋታ ላይ ያልተሳተፈ እንደመሆኑ በእርሱ ዙሪያ የሰላ ግምገማ ማድረግ ያስቸግራል፡፡ ጤንነቱ ሲሻሻል እና ወደ ሜዳ ሲገባ ግን ተከላካዩ ምርጥ ብቃቱን ለማሳየት ተቸግሮ አያውቅም፡፡ ነገር ግን ተደጋጋሚ የጉልበት ጉዳቱ አንጋፋውን አምበል ወደ ጫማ መስቀሉ እየገፋው ይገኛል፡፡ ባለፈው ክረምት እግርኳስን ለመሰናበት ከጫፍ ከደረሰ በኋላ ሀሳቡን አስለውጠው የአንድ ዓመት ኮንትራት ያቀረቡለት የክለቡ ፕሬዝዳንት ላንድሮ ሮሴል ናቸው፡፡ አሁን ግን በውድድር ዘመኑ ቀሪ ጊዜ ፑዩል በትልቅ ደረጃ ቡድኑን መጥቀም መቻሉ አጠራጣሪ ሆኗል፡፡ በዚህም የተከላካዮ እጥረት የሚገጥመው ባርሳ ምናልባት ለማርክ ባርትራ የተሻለ የመሰለፍ ዕድል ሊሰጥ ይገደዳል፡፡ እንደ አምናው የአደጋ ጊዜ መሸፈኛ በመሆን አድሪያኖም ሊጫወት ይችላል፡፡ ሆኖም ባርሴሎና በዋናነት አዲስ ተከላካይ ፍለጋ ወደ ገበያ እንደሚወጣ ይጠበቃል፡፡
አንድሬስ ኢኒዬሽታ
አማካዩ የጎል እድል በመፍጠር እና ጎሎች በማስቆጠር የተመሰገነ ይሁን እንጂ ዘንድሮ ወደ ኋላ እየተመለሰ ኳስ ለማስጣል ከባላጋራዎቹ ጋር የሚገጥመው ትግል ያስገርማል፡፡ በየጨዋታው በሙሉ ቁርጠኝነት ወደ ሜዳ የሚወጣው ስፔናዊ በተለመደ የጎል ምንጭነቱ ረገድ መቀዛቀዝ ታይቶበታል፡፡ በሌሎች መለኪያዎች ግን አሁንም ኢኒዬሽታ ምርጥ ነው፡፡ እንደ ጄራርድ ባለፉት ሁለት ዓመታት ብዙ ጨዋታዎች ያደረገው ኮከብ ምናልባት በእያንዳንዱ ግጥሚያ 90 ደቂቃ እንዳጨርስ እና ይበልጥ እንዳይደክም አሰልጣኙ ሊያግዙት ይገባል፡፡
ማርክ ባርትራ
በአሰልጣኙ ብዙም የመሰለፍ ዕድል የማይሰጠው ተጨዋች አጋጣሚው ሲፈጠርለት ምርጥ ብቃቱን ማሳየት ይኖርበታል፡፡ ይህ ልጅ አሁን ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻሉን እያሳየ መጥቷል፡፡ ከታዳጊ ማዕከሉ እንደ መምጣቱ ለዝውውር የተከፈለበት ገንዘብ ወይም ሌላ አይነት ወጪ ጫና አይሰማውም፡፡ ብዙ ከታዳጊ ማዕከል የሚመጡ ተጨዋቾች ችግር ውስጥ የሚገቡ ቢሆኑም ባርትራ በዋናው ቡድን በጊዜ ሂደት የሚሳካለት ይመስላል፡፡ ከዕድሜው አንጻር ወደ ሜዳ ሲገባ ያሳያቸው መሻሻሎች ጥሩ ተስፋ እንዲጣልበት ያደርገዋል፡፡
ዮርዲ አልባ
ፋልባኩ ለረጅም ሳምንታት በጉዳት ከሜዳ መራቁ ቢያሳዝንም በሌላ በኩል ሲሳይ ሳይሆንለት አልቀረም፡፡ ተከላካዩ በአጭር ጊዜ ውስጥ በብሔራዊ ቡድን እና በክለብ ብዙ ጨዋታ ካደረጉ ተጨዋቾች መካከል ይመደባል፡፡ በአውሮፓ ዋንጫ ፍጻሜ ጣልያን ላይ ጎል ያስቆጠረው ተጨዋች ራሱን እና ቡድኑን ከአደጋ ማዳን የሚችልበት የሩጫ ፍጥነት ባለቤት ነው፡፡ በቀጣዮቹ ወራት ባርሴሎና እንደ ቡድን ከበረታ አልባ ይበልጥ የመሻሻል ዕድል ይኖረዋል፡፡
አድሪያኖ
ይህ ተጨዋች ሁለገብ ባህሪይ መያዙ ለባርሴሎና ብዙ ጠቅሟል፡፡ ዘንድሮ ብዙ ጊዜውን በግራ ፉላብክ ቦታ ቢያሳልፍም በውድድር ዘመኑ መጀመሪያ ማላጋ ላይ የማሸነፊያውን ጎል እስከማግባት ደርሷል፡፡ አድሪያኖ በተደጋጋሚ ጉዳት ቢሰቃይም የክለቡ ሰዎች ተስፋ አልቆረጡበትም፡፡ በእያንዳንዱ ወደ ሜዳ በገባበት ጨዋታ በቁርጠንነት የሚሰጠውን ኃላፊነት ሲወጣ ተስተውሏል፡፡ አሁን የዋናው ቡድን ጠቃሚ አባል መሆኑንም አረጋግጧል፡፡
ዳኒ አልቬስ
ዘንድሮ በፉልባክ ሚና ባርሴሎናን በጥሩ ሁኔታ እየጠቀመ ያለ ሌላኛው ብራዚላዊ ነው፡፡ አልቬስ ሲጫወት ብቻ ሳይሆን ያልተሰለፈ ቀንም የሚናፈቅ አይነት ተጨዋች ነው፡፡ በቅርቡ ቡድኑ ከሄታፌ ጋር ሲጫወት ፉልባኩ ለግጥሚያው ዝግጁ ያልነበረ መሆኑ ቢታይም በቀጣዮቹ ጨዋታዎች ወደ ብቃቱ እንደሚመለስ ይጠበቃል፡፡
አልቬስ ባለፉት ዓመታት በክለቡ እና በብሔራዊ ቡድኑ የቀኝ ክንፍ ያለማቋረጥ እየተመላለሰ በመሮጥ ተጫውቷል፡፡ እንዲህም ሆኖ ብዙ ጉዳት አለማስተናገዱ ያስደንቃል፡፡ በቅርቡ በኢንተርናሽናል ጨዋታ ወቅት የገጠመው ጉዳት እግረ መንገዱን ተጨዋቹ እረፍት እንዲወስድ እና ለቀሪው የውድድር ዘመን በብቃት እንዲመለስ ሊያግዘው ይችላል፡፡
በታክቲክ በኩል የአልቬስ ወደ ፊት አብዝቶ መሮጥ የባርሴሎናን የተከላካይ መስር በተጋነነ መልኩ ወደ ጎን እንዲለጠጥ ሲያደርገው የመልሶ ማጥቃት አደጋዎችን ለመመከት ብዙ እንዲለፉ ያስገድዳቸዋል፡፡ ሆኖም ከትልልቅ ቡድኖች ጋር በሚደረጉት ጨዋታዎች ተከላካይ ክፍሉ ይበልጥ ወደ ኋላ አፈግፍጎ እንዲከላከል ይታዘዛል፡፡ በዚህ መሰል አጋጣሚዎች አልቬስ በሚገባ መከላከል እንደሚችል ታይቷል፡፡ ሆኖም በቀሪዎቹ የውድድር ዘመኑ ቀጣይ ወራት ብራዚላዊው ይበልጥ ተሻሽሎ ልዩ ብቃት ሊያሳይ ይችላል፡፡
barcelona
ሊሻሻሉ የሚገባቸው

ፔድሮ ሮድሪጌዝ
ወጣቱ አጥቂ በቅርቡ ለባርሴሎና ሀትትሪክ ቢሰራም ብቃቱ ይዋዥቃል፡፡ በዘንድሮ ብቃቱ ጥሩ ተጫወቱ የማያስብል አቋም ያሳዩ ከነበረ ሶስት ወይም አራት ተጨዋቾች በአንዱ ነው፡፡ በእርግጥ በሊጉ 10 ጎሎች ማስቆጠሩ (የሳምንቱ መጨረሻ ጨዋታን ሳይጨምር) እውነት ቢሆንም ራዮ ቫዬካኖ እና ሄታፌ ላይ ሁለት ጊዜ ሁት ትሪክ መስራቱ እንደጠቀመው መዘንጋት አይገባም፡፡ ስለዚህ ልጁ በተቀሩት ጨዋታዎች ሁሉ ያስመዘገበው አራት ጎሎች ብቻ ነው፡፡
በእርግጥ ፔድሮ በቡድኑ ከኔይማር እና ከተሸሻለው አሌክሲስ ሳንቼዝ ፉክክር አለበት፡፡ ሆኖም ብዙ መሻሻል እንደሚገባው መናገር ይቻላል፡፡ ምክንያቱም አሁን እያሳየ ከሚገኘው ብቃት የተሻለ የማሳየት አቅሙ አለው፡፡ ፔድሮ ሴፕቴምበር አጋማሽ አካባቢ ባርሴሎናን በሙሉ ኃይሉ እያጠቃ የኋላ ክፍሉ በሳሳው ቫዬካኖ ላይ ሶስት ጎሎች ካገባ በኋላ ቀጣይ ጎሉን በቤቲስ ላይ ለማስቆጠር እስከ ኖቬምበር ጊዜ ፈልጓል፡፡ ለጎል የተመቻቸ ኳስ በማቀበልም ቢሆን በጉዳት ብዙ ጨዋታዎች ያለፉት ማሊ ከፔድሮ መሻሉ ያስደንቃል፡፡
ሆኖም ፔድሮ ብዙ የመሻሻል አቅም አለው፡፡ አሁንም ቢሆን ያለኳስ የሚያደርገው እንቅስቃሴ እና የሩጫ ፍጥነቱ ድንቅ ነው፡፡ ፍጥነቱ ሲስክን ከመሳሰሉ ተጨዋቾች ተከላካይ ሰንጣቂ ኳሶችን ለመጠቀም የተሻለ ዕድል ይሰጡታል፡፡ ነገር ግን አፈግፍገው የሚከላከሉ ቡድኖች ሲገጥሙት ብዙ መቸገሩን በልምምድ መቀየር አለበት፡፡

ሊዮኔል ሜሲ

አርጀንቲናዊው ጉዳት ባይረብሸው ኖሮ በ11 የሊግ ጨዋታዎች ስምንት ጎሎች እና በሶስት የቻምፒዮንስ ሊግ ግጥሚያዎች ስድስት ጎሎች ማግባቱ ሊያስመሰግነው በቂ ነበር፡፡ ሆኖም ጉዳት የዓለማችንን ድንቅ ተጨዋች ሜዳ ላይ ሆኖም በከፍተኛ አቅሙ እንዳይጫወት አድርጎት ነበር፡፡ የኑካምፕ ታዳሚዎች ምርጡ ልጃቸውን ከቀጣዩ ኤልክላሲኮ እና ከቻምፒዮንስ ሊጉ የማንችስተር ሲቲ ፍጥጫ በፊት በጤንነት ሊያገኙት ይፈልጋሉ፡፡ የባርሴሎና ደጋፊዎች አምና በባየርን የደረሰባቸው ሰቀቀን እንዳይደገም ቢያንስ ሜሲ ያስፈልጋቸዋል፡፡ እርሱ ጤነኛ ከሆነ የብቃቱ መመለስ ብዙም አያጠራጥርም፡፡ የዚህ ኮከብ ስም ‹‹መሻሻል በሚገባቸው›› ተጨዋቾች ዝርዝር ውስጥ መገኘቱ እንግዳ ቢሆንም በክረምት በርካታ የወዳጅነት ጨዋታዎችን ማድረጉ እንዲሁም እንደጎዳው መናገር ይቻላል፡፡ ሆኖም ወደ ሜዳ ሲመለስ ይበልጥ ተሻሽሎ እንደሚቀርብ ይጠበቃል፡፡
ሀቪየሮ ማሼራኖ

ማሼራኖ ዘንድሮ እያሳየ ያለው ብቃት መጥፎ አይደለም፡፡ ሆኖም የአርጀንቲናዊውን ድንቅ ችሎታ ለሚያውቁ ሁሉ የዘንድሮ አቋሙ ይበልጥ መስተካከል ይኖርበታል፡፡ ባርሴሎና ሁነኛ የመሀል ተከላካይ ማስፈረም ነበረበት የሚለው ቅሬታ ትኩረት ሳይደረግበት ቀረ እንጂ ማሼራኖ ይሰራቸው የነበሩት ስህተቶች ከወቀሳ የሚያድኑት አልነበሩም፡፡ የስፔን ጋዜጦችም ማሼራኖ የፔኬ እና ፑዮልን ቦታ መረከብ እንዳለበት ከመናገር ይልቅ ከውጪ በዝውውር ሊመጣ ስለሚችለው ጥሩ ተከላካይ መናገር ቀጠሉ እንጂ አርጀንቲናዊው በሁለተኛው የውድድር ዘመኑ አጋማሽ ተሻሽሎ ቦታውን መሸፈን እንደሚጠበቅበት አልጠቆሙም፡፡ ዘንድሮ ባርሴሎና ከሜዳው ውጪ ተጉዞ በሚላን እና አምሰተርዳም ሲጫወት ማሼራኖ የፈጸማቸው ስህተቶች ወደ ጎልነት ተለውጠዋል፡፡ ተጨዋቹ ጥሩ እርምጃ ወስዶ ያስጣላቸው ኳሶች ብዙ ቢሆኑም በስንፍና ወይም በፍጥነት ማጣት ያበላሻቸው ኳሶች ሊሻሻል እንደሚገባው ያሳያሉ፡፡

አሌክስ ሶንግ
ካሜሮናዊውን ለመመዘን ተጨዋቹን ከኳስ ጋር እና ያለ ኳስ ብሎ መለያየት ያስፈልጋል፡፡ ዘንድሮ ሶንግ በባርሴሎና ይበልጥ ተደላድሏል፡፤ ወደ ፊት ተጠግቶ እንዲጫወት ከተደፈቀደለት በኋላ የኳስ አያያዙ እና ውሳኔው ጥሩ ሆኗል፡፡ በመከላከሉ ረገድ ግን አፍሪካዊው አሁንም እንከኖች አልጠፉበትም፡፡ ሶንግ ምርጥ ሽርተቴዎችን ቢወርድም ቀጣዩን እርምጃ ለመውሰድ የሚያሳየው መንቀራፈፍ ለተጋጣሚ ሌላ አደጋ የመፍጠር ዕድል ይሰጣል፡፡ ቡስኬትስ ጨዋታን በማንበብ በኩል የተሻለ በመሆኑ አንዳንድ ጊዜ ኳሷን እግሩ ላይ ሊያገኛት ሌላ ጊዜ ደግሞ ሸርተቴ ሳይወርድ እንዲቀማ ያስችለዋል፡፡ ሶንግ ይህ ብቃት የለውም፡፡ ቡድኑ በሊጉ አነስተኛ ግምት ከሚሰጣቸው ቡድኖች ጋር ሲጫወት የሶንግ ፓሲንግ ስኬት እጅግ ከፍ ይላል፡፡ ሆኖም በትልልቆቹ ጨዋታዎች ይህንን ማድረግ አይችልም፡፡ ቡስኬትስ በማንቸስተር ሲቲው ጨዋታ ጉዳት ቢገጥመው ሶንግ ምን ያህል ቦታውን እንደሚሸፍን መገመት ይከብዳል፡፡ የቀድሞው የአርሰናል አማካይ በጥቃቱ ረገድ ዘንድሮ ብዙ የተሻሻለ ቢሆንም በመካከሉ በኩል ብዙ መስራት ይኖርበታል፡፡

ክርስቲያን ሬዮ
የባርሴሎና የቡድን አባላትን በቅርበት የሚገመገትሙ ተንታኞች ቴዮ ባለፈው የውድድር ዘመን እና በተጠናቀቀው ግማሽ የውድድር ዘመን በውሰት ሊሰጥ ይገባ እንደነበር ይናገራሉ፡፡ ፈጣኑ ወጣት ብዙ የመሻሻል ዕድል ቢኖረውም በኑካምፕ የመጫወት ዕድል ማግኘት አይችልም፡፡ በቀጣዮቹ ሳምንታት ሜሲ ወደ ሜዳ ሲመለስ የቴዮ የመጫወት ዕድል ይበልጥ ያበቃለታል፡፡ ምናልባትም አሰልጣኙ ከኮፓ ዴል ሬይ እና አልፎ አልፎ በሊጉ ጨዋታዎች ይጠቀመብት እንደሆነ ለመመልከት ጊዜ መጠበቅ ያሻል፡፡ አሁን ባለበት ሁኔታ ግን ተጫዋቹ እምቅ ችሎታውን አውጥቶ ማሳየት የሚችልበት እድል የለም፡፡

አይዛክ ኩኤንካ
ኩኤንካ ዘንድሮ ለባርሴሎና የመጫወት ዕድል አላገኙም፡፡ ሆኖም ከጉዳቱ ሲመለስ ለቡድኑ መጫወት እና ዕድገቱን የመቀጠል አጋጣሚው ይፈጠርለታል፡፡ እንደበርካታ የክለቡ ደጋፊዎች እምነት ኩኤንካ በኑካምፕ ከኢብራሂም አፌ ላይ ወይም ጆናታን ዶስ ሳንቶ በተሻለ ስኬታማ ጉዞ ሊኖረው ይችላል፡፡ ሆኖም ተጨዋቹ ከጉዳቱ በሚገባ ማገገም እና ዕድገቱን መቀጠል ይኖርበታል፡፡

እንደወጡ ያልተመለሱ እንዳዲያቆኑ ያላቀሰሱ

$
0
0

ቤዝ አሲምባ ፀለምት – ዶሎኪያ ተርናሻ
መሰረት ያኖርነው – መነሻ መድረሻ
አንዷን ላውሬ ጥሎ – ሌላዋን ለውሻ
ሽንፈት አደረገው – ምሽጉን መሸሻ

Penግለሰቦች የየራሳቸውን ገጠመኞች (memoir) ይፅፋሉ። እንደ ስብስብ (as a group) የራሱን ገጠመኝ ( memoir) መፃፍ የማይችል ሕዝብ ብቻ ነው። ገጠመኙን መፃፍ ስላልቻለም ሕዝብ የራሴ የሚለው ታሪክ ኖሮት አያውቅም። በተለምዶ ታሪክ ብለን የምንጠራውም ትርክቱ የሕዝብ ታሪክ አይደለም። ለምን? ቢሉ ታሪክ ፀሃፊዎች ታሪኩን ሲፅፉ ትርክቱን ወይ በገናና ሰዎች የሾረ እንዝርት፤ አለያም በተወሰነ ድርጊት ዙርያ በግለሰቦች የተዘነገገ ዝንግግ ያደርጉታል። ፀሃፊዎቹ ዝንግጉን አጠንጥነው ልቃቂቱን ታሪክ ሲሉን እኛም ታሪክ አድርገን እንወስደዋለን።

ታሪኩ የሚከናወነው በሕዝብ ውስጥ ቢሆንም ትርክቱ ግን የሕዝብ ቢመስል እንጂ የግለሰቦች መድብላዊ ድርጊት ነው። ሕዝብ ዘወትር የታሪክ መድረክ ሆኖ ሳለ ትርክቱ ግን መድረኩን ሳይጨምር የተውኔቱና የተዋንያኑ ትግብርት እየሆነ ይተረካል። በታሪክ ዙሪያ ስለ ህዝብና ገጠመኙ ስናነሳ ወደ ህሊናችን ቀድሞ የሚመጣው የቬትናም ህዝብ ገጠመኝ ይሆናል። ለምን? ቢባል በመስዋዕትነቱም ሆነ በድል ግዝፈቱ በዓለም ወደር የማይገኝለት ትግል የተካሄደው በቬትናም ህዝብ ነበርና።

ለእናት ሀገር ጥርስ ይሰብሩላታል ይሉ ነበር ቬትናማዊያን። በትግላቸው ዘመን። ለየህዝቦቻቸው እንደ ቬትናም ታጋዮች ጥርስ የሰበሩ፤ አጥንት የከሰከሱ፤ ደም ያፈሰሱ፤ ስጋ የቆረሱ፤ ብሎም ህይዎት የገብሩ የህዝብ ቤዛዎች ብዙ ናቸው። ግን የብዞዎቹ ትግል እንደ እኛው ግባቸውን ያልመቱ አብዮቶች ማህበርተኛ ከመሆን አላለፈም።

ትንግርተኞቹ ቬታናማዊያን ቀደም የፈረንሳይን የቅኝ ቀንበር በኋላም የአሜሪካንን ኢምፔሪያል ክንድ ሲሰብሩ ዓለምን አስደምመው ነበር። ለዚህ ድል የበቁትም ራሳቸውን የጦር ማገዶ አድርገው እየተቆሰቆሱ ጦርነቱን ከሰሜን ቬትናም ወደ ደቡብ እንዲሸጋገር በማድረግ ነበር። ሰሚናዊያኑ አብዮተኞች ደቡባዊ ወንድሞቻቸውን ወደ ትግሉ ለማስገባት ሲሉ ነበር ጥርሶቻቸውን እንዲሰበሩ የተገደዱት። ደቡብ ቬትናም ውስጥ አሥር ዓመት ሲሞላቸው የታች ሁለት ጥርሶቻቸውን የማውለቅ ባህል ያላቸው/የነበራቸ ጎሳዎች ነበሩ። ሰሚናዊያኑ በነዚህ ደቡባዊ ወገኖቻቸው መሃል ገብተው አብዮታዊ የህቡዕ ሥራዎችን ለመስራት ህብረተሱቡን መምሰል ስለነበረባቸው ነበር ሁለት ጥርሶቻቸውን እያወለቁ የተቀላቀሏቸው።

በእኛውም ጭንግፍ አብዮት እንደ ቬትናሞች የአብዮት ማገዶ እየሆኑ ተቆስቁሰው ያለቁ አያሌ ነበሩ። ብዙ ወጣት ኢህአፓዎች የህዝባቸውን ነጻነት እየተመኙ እንደ ቬትናማዊያኑ ህዝቡን መስለው የህቡዕ ሥራዎችን ለመስራት ወደ ህዝቡ ጎርፈዋል። ሴቶቹ ረዥሙን ፀጉራቸውን ቆርጠው እንደ ጎጃሞች ጋርሶ፤ ወይም እንደ ጎንደሮች ጋሜና ሹርባ አለያም እንደ ትግሬዎች ቁንን እየተሰሩ፤ እንደ ህዝቡም በባዶ እግራቸው ተጉዘው፤ ጥሬ ቆርጥመው፤ ከጭቃ መደብ ላይ ተኝተው፤ ቅማል ቀምለው፤ እከኩን አክከው፤ ቅጭጭቱን ተቀጭጨው ወንዶቹም ሆኑ እሴቶቹ የህዝቡን ኑሮ እየኖሩ ነበር በትግሉ የተሰማሩት። ከነዚህ ውስጥ ማሬ አረጋ አንዷ ነበረች።

ማሬ የባህር ዳር ልጅ ነች። አባቷ አቶ አረጋ ወርቅነህ ባህርዳር ከተማ ውስጥ በወቅቱ አሉ ከሚባሉት ትልልቅ ሆቴሎች ያንደኛው ባለቤት ነበሩ። ማሬም ቅምጥል የሃብታም ልጅ ነበረች። ቦርቃቃ ኮረዳ። ዜንጦ የፒያሳ ልጅ። ግን አብዮቱ መጣና ጥሩዋን አደፈረሰው። የዘመኗ ወጣት በህዝብ ፍቅር ነዶ ባደባባይ እየተመመ

በዱር በገደሉ ፋኖ ተሰማራ
እንደ ሆቺሚኒህ እንደ ቼ ጉቬራ

ብሎ ሲዘምር እርሷንም ፋኖ ትሆን ዘንድ መዝሙሩ ልቧን አሸፈተውና አይገዛም ህዝቡ እስከ መጨረሻ፤ ለእስራኤል ቡችላ ላሜሪካ ውሻ ብላ ዘመረች። ልቧም ድል ሰንቆ ወደ በርሃው ነጎደ። አሲምባ ተራራን አሸጋግሮ የሚያየው ህሊናዋ ህይዎቷን የህዝብ ቤዛ ታደርገው ዘንድ ቃል አስገባት። በብስክሌት ተወዳዳሪነት የገነባችውን የግል ዝናም እንድትንቀው አደረጋት። እናም ሌት ሌት በጨለማ፤ ቀን ቀንም በከለላ በህዝብ መሃል ገብታ በማደራጀት ሥራ ባዘነች። ውሎ አደሮ ሥራዋ እንቅስቃሴዋን አጎላውና ማንነቷን አሳወቀው። እናም ከብስክሌት አልፋ እግሬም ኮረኮንቹን መንገድ ልመደው፤ ጎኔም ከመደቡ ምኝታ ጋር ተዋወቅ፤ ሆዴም ከእንግርግቡ ( አሹቅ ) ጋር ተዋዛ፤ እጆቼም ለመፍጨት መጁን ተዋወቁት. . . . ለማለት እድሉን ሳታገኝ ተጋለጠችና ወደ ሜዳ እንድትወጣ ተወሰነ። አንድ ምሽት ላይ ልትያዝ መሆኗ ተነግሯት ህቡዕ ገባች። በዚሁ የህቡዕ መጠለያ ጥቂት ቀናት እንደቆየች ወደ አሲምባ እንደምትወጣ ተነገራትና ጎዞዋን በጉጉት ትጠባበቅ ጀመር። ከዕለታት ባንደኛዋ ምሽት የባላገር ቀሚስና ነጠላ ከባራባሶ ጫማ ጋር የአለባበስ ልምምድ ታደርግ ዘንድ ተሰጣት። ልብሶቹ እንደ ደረሷትም ቀሚሱን አጥልቃ በመቀነቱ ሸበክ አደረገችና ባራባሶውን ተጫምታ ነጠላውን ና ተለበስ ብትለው አላውቅሽም አላትና በተለበስ አልለበስም መሃል ግብ ግቡ ቀጥሎ አመሸ።

ያን ዕለት ሌሊቱን እንቅልፍ በዓይኗ ሳይዞር አደረ። ሌሊቱን ሙሉ ቀዩን ሠራዊት አሲምባ ላይ ተቀላቅላ አቀበቱን ስተወጣና ቁልቁለቱን ስትንደረደር አደረች። እረፋዱ ላይ የሆነ ደረቅ ዳቦ በመዝጊያው ስር ተወረወረላት። በጋዜጣ ተጠቅልሎ ያገኘችውን ዳቦ ና ተነከስ ስትለው ግን አልደፈርሽ አላት። ግን ከደረቁ ዳቦ ጋር መለማመድ ነበረባትና ባፏ እየዞረም ቢሆን ጨረሰችው። በሂደት ግን ጉረሮዋና ዳቦው እየተዛመዱ መጡ። ማታ ማታ ጓዱ ሲመጣ ስለ ውጨኛው ዓለም ስትጠይቀው እርሱም ማወቅ የሚገባትን ሲነግራት ሰነበቱና

ፍትፍቱም ይቀራል በቀሪው ሊበላ
ቅንጨውም ይቀራል የኋላ የኋላ
ድሎትና ቅንጦት ደህና ሰንብች ብሎ
በቂጣ ይተካል አለያም በቆሎ

እንዲሉ ከችግሩ ጋር መተዋውቋ ቀጥሎ ሰነበተና የጉዞው ቀን ደረሰ።

አንድ ቀን አመሻሹ ላይ ሌሎች ጓዶች ተጨመሩና ሁለት ሁለት እየሆኑ ወደ ሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ ገሰገሱ። ከተማውን ለቅቀው ጥቂት እንደ ተጓዙ አንድ ቦታ ላይ ይጠብቃቸው የነበረው መስመረኛ ተቀበላቸውና የሌሊቱን ጉዞ በአዲስ ሞራልና ጉልበት ተያያዙት። ሌሊቱ ተዋግዶ ከዶሮ ጩኸት በፊት አንድ መንደር ውስጥ ገቡ። መንደሩ ውስጥ እንደገቡ መስመረኛው በሞተ ድምፅና ኮቴ እንዲራመዱ በሰጣቸው ትዕዛዝ መሰረት ተራምደው አንዲት ጎጆ ውስጥ ገቡ። እንደገቡም በያሉበት ተዘረሩ።

እረፋዱ ላይ የጎጆዋ መዝጊያ ሲከፈት ባሰማው ድምጽ ነበር ተቀሰቀሰው የነቁት። እንደ ነቁም የብረት ምጣድ የገብስ ቂጣ ተልባ ተቀብቶ ቀረበላቸው። ምግቡን ሲያዩ ሁሉም ፊታቸውን አኮሳተሩ። እጆቻቸውም ምግቡን ሲያዩ አነከሱ። ሁኔታቸውን የተመለከተው መስመረኛ ግን ይህ የተሻለው ማዕዳችን ነው፤ የከፋው ገና ወደ ፊት ይጠብቃችኋል አለና የድርሻውን ከቂጣው ቆርሶ መመገብ ጀመረ። አነጋገሩ ባንድ ወቅት እርሱም እንደ ነርሱ ከተሜ እንደ ነበር አስገንዝቧቸው እነርሱም እርሱን እንደሚሆኑ ታስባቸውና እጆቻቸውን ሰነዘሩ። አይበላ የለም ያ ቂጣ በውሃ እየታጠበ ወረደ።

ለምሳ የቀረበላቸው ደግሞ የባቄላ እንግርግብ ( አሹቅ) ነበር። አንዳንዶች በይሉኝታ ቁንጥር አድርገው አንድና ሁለት ጥሬ ወደ አፋቸው መወርወር ጀመሩ። ከፊሎቹ ግን አያሳየን ለማለት ይመስላል ሸፍንፍን ብለው መልሰው ጎናቸውን ከወለሉ ጋር አገናኙ። ከጥቂት ቆይታ በኋላ መስመረኛው ጓድ መጣና ማነቃቂያ የሚሆን ጥቂት ገጠመኞችን አካፈላቸው። በዚህ የገጠመኝ ጭውውት የተጀመረው መነጋገርም ወደ ዜና መቀያየር ተለወጠና እነርሱም ስለ ገጠሩ ትግል፤ ስለ ቀዩ ሰራዊት፤ እርሱም ስለ ከተማው ትግል ማወቅ የሚፈልጉትን እየተጠያየቁ ጊዜውን ገፉት። ለዐይን ያዝ ሲያደርግ ከጧት ቁርስ የተረፈው ቂጣና እንግርግብ ባቄላ ለእራት ቀረበ። ከራት በኋላም ጉዞ ተጀመረ። ካዲስ አበባ ወደ አስመራ የሚወስደውን አውራጎዳና ወደ ቀኝ እየተው ወደ ሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ የይልማና ዴንሳን ወረዳ ሰንጥቀው አዴት ከተማ ወደ ደቡብ ስትቀር ከባህር ዳር በወጡ በሶስተኛው ቀን ደብረታቦር አካባቢ ደረሱ።

ጧት ሲነቁ ካዲሱ ጣቢያ መስመረኛ ጋር ተገናኙ። ስላለፉት ጉዞዎች ከጠየቃቸው በኋላ ስለቀጣዩ ጉዞ የተፈጠረውን ችግር አካፈላቸው። እንዲህ ሲል፤ ወደ ፊት ሄደው ሊያርፉበት ይችሉ የነበረው ጣቢያ እንደተጋለጠና ሌላ መስመር እስኪ ዘረጋ እዚህ መጠለያ ሁላቸውንም ማቆየት አደጋ እንደሚኖረው ግልጽ አደረገላቸው። ለደህንነታቸው ሲልም ነጣጥሎ በጊዚያዊ መጠለያ በየግል አርሶ አደሮች ቤት ሊያቆያቸው ሁኔታው እንዳስገደደው አስገነዘባቸው። እነርሱ ግን በሰሙት ወሬ ደስተኛ አልነበሩም። ግን ምርጫ ስላልነበራቸው ሁሉም ወደ የምድባቸው ጉዞ ጀመሩ። ማሬ አረጋም ወደ አንድ ሃብታም ገበሬ ቤት ተወስደች። በቤት ሰራተኛ፤ በገረድ መልክ።

ከቤተሰቡ መሃል ጓዲት መሆኗን የሚያውቁ የቤት ዕመቤቷ ብቻ ነበሩ። ማሬም ይህኑ ምስጢር ተነግሯት የግርድና ኑሮዋን “ሀ” ብላ ጀመረች። በጧት ተነስቶ የጥጆቹን ሽንትና እበት መጥረግ፤ አመዱን ማፈስና ወለሉንም ማጽዳት፤ ለዕረኞቹም ሽሮ አፍልቶ፤ ለገበሬዎቹ ምሳ መቋጠር የዕለት ተዕለት ተግባሮቿ ሆኑ። ማታ ማታም አባውራው ወደ ምኝታ ከመሄዳቸው በፊት ውሃ ወዝቶ እግራቸውን ማጠብና እግራቸውንም መሳም የምሽቱ ሙያዋ ሆነ። ማሬና እመቤቲቱ የሚነጋገሩት ወይ ጧት ሰራተኞችን ከሸኙ በኋላ አለያም ማታ ሁሉም ወንዶች መተኛታቸውን አረጋግጠው ነበር። ያም ሆኖ ከስጋት ጋር እየታገሉ።

በሂደት ሴት ሠራተኞችን ቀረበቻቸውና ፊደል አስቆጠረቻቸው። በፆታቸው ስለሚደርስባቸው ጭቆናም ታስተምራቸው ጀመረች። ዕመቤቲቱም ተሳታፊ ስለሆኑ የካድሬነት ሥራዋ እየጎላ ሄደ። የግርድና ተግባሯም በሌሎቹ ገረዶች እገዛ እየቀለለ መጣ። ። የጎረምሳዎቹ ጉዳይ ግን ቤቱን እስከ ለቀቀችበት ጊዜ ድረስ ቀን በቀን የምትፋለመው ጦርነት ሆኖ ቀጠለ።

የግንኙነት መቋረጥ

የሁለተኛው ጣቢያ መስመረኛ ጓዶችን ለመቀበል አዴት አካባቢ ወደሚገኝው መጠለያ ጎራ ሲል ጣቢያው ተበልቶ ኖሮ ድንገት በጠላት እጅ ወደቀ። ይህም ችግር በራሱ ሌላ ችግር ፈጠረ። የጠፋውን ጓድ ተረገጥ ለማግኘት የሦስተኛው ጣቢያ መስመረኛም ከመዋቅር ውጭ ግንኙነት ለመቀጠል ሲጣድፍ በገበሬ ማህበር እጅ ወደቀ። እነዚህም ተደራራቢ ችግሮች ለማሬ የሰቆቃ ህይዎት እድሜ ለጋሽ ሆኑ።

በዚህ ሁሉ መሃል እመቤቲቱ የማሬን ችግር ለማቃለል የቦዘኑበት ጊዜ አልነበረም። አንዳንዴ ችግሩን ያቃለልኩ መስሏቸው ትንሿን ቡይት አሸክመው ውሃ እንድትቀዳ ወደ ወንዝ ይልኳት ነበር። ምናልባትም በዚሁ አጋጣሚ ጓዶቿን ታገኝ ይሆናል የሚል ተስፋ ሰንቀው ይሆናል ማሬን ወደ ወንዝ ይልኳት የነበረው። እርሷም ተስፋዋ ዕውን ይሆን ዘንድ ጊዜ ፈጅታ ነበር ወደ ቤት የምትመለሰው። ግን ተስፋቸው ከቀን ወደ ቀን እየመነመነ መጣ። እመቤቲቱ ግን ግርድናው እንዳይሰማት ብዙ ጣሩ። ግርድናዋን ግን ከትከሻዋ ሊያወርዱላት ባለመቻላቸው ሁሌም ይጨነቁ ነበር። ከሴት ሠራተኞቹ ጋር የተፈጠረው መልካም ግንኙነት ድሮ ትፈጨው የነበርውን እህል እንዳትፈጭ አድርጓታል። በምትኩ ትንሽ አተር ወይም ባቄላ ይሰጧትና መጁን በማንቀሳቀስ እየፈጨች ያስመስሏት ነበር። በዚህ መሃል ከዚህ መጣ የማይሉት ቁስል የማሬን ገላ አነፈረው። ይህም ድንገተኛ በሽታ ቀዩን ሠራዊት የመቀላቀል ምኞቷን ስላጨለመው ህሊናዋ ተረበሸ። እመቤቲቱም ሁኔታዋን አይተው ይበልጥ ተጨነቁ።

የሴት መላ የጉንዳን ጉልበት ይስጥህ እንዲሉ ይመስላል ከዕለታት ባንደኛዋ ቀን እመቤቲቱ ተነስተው ወደ አንድ ዘመዳቸው ቤት ይሄዱና ስለ ኢህአፓዎች ባካባቢው መኖር ዳር ዳር እያሉ ወሬ ጀመሩለት። ዘመዳቸውም የማሬን ነገር ያውቅ ኖሮ የመስመር ችግር እንደ ነበርና ችግሩም መቃለሉን ይነግራቸዋል። ከዚያም ጉዳዩን በግልጽ ተወያይተውበት ማሬ አረጋ ማታውኑ ወደ ሰውየው ቤት ሄዳ እንድታድር ይወስናሉ። ወደ ቤታቸው ተመልሰውም እቅዱን ለማሬ አጫወቷት። ሁሉም ነገር ተከናውኖ ቤተሰቡ ሲተኛ ጠብቀው ይዘዋት ወጡ። ከዘመዳቸው ጋርም አስተዋወቋት። ከዚያም ሁለቱ አርሶ አደሮች ከማሬ ገለል ብለው ስለ ጉዞዋ መነጋገር ጀመሩ።

ጎዞውን ሲያስቡት ገና ከጅምሩ የሰቀቀን ጎዞ ሆነባቸው። በእግሯ አይልኳት ነገር በባዶ እግር ቤት ለቤት እንጂ እርቀት ያለው መንገድ መሄድ አልተለማመደችም። በጫማ እንዳትጓዝ ቁስሏ ጫማውን አታስነኩኝ ባይ ነው። በፈረስ ላማጓጓዝም በቀን መጓዝ ሊኖርባት ሆነ። መንገዱ አውራ መንገድ ነውና የሚመጣውም ሆነ የሚሄደው መንገደኛ ስለሚተዋወቅ በመንገድ ላይ የሚያውቁት ሰው ቢገጥማቸው ይህች ልጅ ምንህ ነች? ብሎ ሊጠይቅ ይችላል። ፈረስ ይዞ በጨለማም አቀበት መውጣትና ቁልቁለት መውረድ ይከብዳል። መክበድ ብቻም አይደል አደጋም አለው። ፈረሱ ድንገት ኮሽታ ሲሰማ ሊደነበር ይችላል። ዞሮ ዞሮ መከራው ከማሬ ትከሻ ላይ አልወረደም አሉና በባዶ እግርና በጫማ በፈረቃ ሞክሪ ሊሏት ወሰኑ። እናም ነገሯት።

ለእናት ሀገር ጥርስ ይሰበርላታል እንዳሉት ቬትናማውያን ማሬም እግሮቿን ልትመላልጥ ወስና ይልቁን ጉዞው መቼ ነው? ስትል ጠየቀቻቸው። ሁሉም ነገር እንደተሳካ አሏት እመቤቲቱ ቀልጠፍ ብለው። ከዐይኖቻቸው ውኃ እየተቀዳ አትኩረው ሲያዩዋት አሳዘነቻቸውና በወገባቸው ተጠመጠመች እጃቸውን እያሻሸች ጓዲት ከቤቴ ስወጣ ለዚህ ሁሉ ተዘጋጅቼ ስለወጣሁ አትጨነቂ። ይልቁን ጫማ እግሬን የምጠመጥምበት ጨርቅ አፈላልጊ አለችና ዕምባቸውን አብሳ ሳመቻቸው።

እርሳቸው ግን አተኩረው እየተመለከቱ የምትላቸው ሁሉ ሆድ አልሆን ስላላቸው ሰቅ ሰቅ ብለው አለቀሱ። እቅፍ አድርገውም አወይ ወላድ መሆን፤ አወይ የናት አንጀት፤ እኔም እንደ እናትሽ ሬሳሽ ከቤቴ ሲወጣ ላለማየት ስል ጓዶችሽን የበላ ጅብ ይብላሽ ብየ ከቤቴ አስወጣሁሽ ብለው በዕምባ ይታጠቡ ጀመር። ምነው አፈር በበላሁ። ምነው ባላወቅሁሽ። በቁምሽ ቀበርኩሽ አሉና ማሬን ከደረታቸው ለትመው ተንሰቀሰቁ። ለማሬም ይህ ስንብት የጓዷም የናቷም ሆነባትና ዐይኖቿ ውኃ ሞሉ። በመጨረሻም ጉንጭ ለጉንጭ ተሳስመው ተለያዩ። እመቤቲቱም ዕምባ በሚያጎርፉ ዐይኖች እየተከተሉ ሽኛት። ማሬና መሪዋ ደብረታቦርን ወደ ደቡብ፤ እብናትንም ወደ ምዕርብ እየተው ወደ ሰሜን አቅጣጫ ወደ በለሳ ጉዞአቸውን ቀጠሉ። ሀሙሲትም ደረሱ። ሀሙሲት በሊቦ አውራጃ በዝዊ ወረዳ የምትገኝ የገጠር ከተማ ነች። ከሀሙሲት ወደ ሰሜን ምስራቅ ተከዜን ሲሻገሩ ወሎ ይሆናል። ሰቆጣ።

ሀሙሲትና ህክምና

አይደረስ የለም ሀሙሲት ተደረሰ። ወደ ህክምና ጣቢይውም ተወሰደችና ህክምናው ተጀመረ። በጣቢያው ያየቻቸው ጓዶች ግን ሀዘንና ብስጭት የተቀላቀለበት ስሜት አሳደሩባት። ስለ ሁኔታቸው አዘነች። ሁሉም ነገር ከጠበቀችው በታች በመሆኑም ግራ ተጋባች። የጠበቀችውን ቀይ ሠራዊት ስላልነበረ ያየችው ተስፋዋን አጨለመው። የወደፊቱም ጉዞዋ በምታየው ስእል አምሳያ ተሳለባት። በዚህ ሁኔታ ላይ እንዳለች አንድ ምሽት እራት ቀርቦ በገበታው ዙሪያ ተቀመጡ። ሁሉም እጁን ወደ ገበታው ሲሰድ እርሷም እጇን ስትልከው ያንደኛው ጓድ ፊት ሲለዋወጥ ዐይን ለዐይን ተጋጩ። እጇን ሰብሰብ አድርጋ ተነሳችና ወደ ጎጆዋ ሄዳ መጽፍ ጀመረች። አንድ ሁለቱ ተከትለዋት ሄዱና ሊይጽናኗት ሞክሩ። እርሷ ግን ጓዶች ሰው መሆኑን አትርሱ። አስቦት ሳይሆን ሳያስበው ነው ሰውነቱ የተፀየፈኝ አለቻቸው። ማታውኑ ወሬው ጣቢያውን አዳረሰውና ሁሉም ዓለሚቱን ከበቧት። የነፈረውን ሰውነቷንም አይተው አዘኑላት። ከዚያች ምሽት በኃላ ከዓለሚቱ ጋር ለመመገብ ጓዶች ይሽቀዳደሙ ጀመር።

ዓለሚቱም (ማሬ አረጋ) በሃሙሲት ቆይታዋ ብዙ ነገር አስተዋለች። ካስተዋለችው አንዱ ነገር በጣቢያው ከሚገኙት በሽተኞች የሚበዙት ሴቶች መሆናቸውን ነበር። እናም ለምን ይሆን? ስትል አስተውሎቷን በማስታወሻዋ አሰፈረችው። ከፊሉን በግጥም ከፊሉን ደግሞ በስድ ንባብ። አንድ ቀን ከራት በኃላ ለምን ይሆን ሴት ጓዲቶች በጣቢያው የምንበዛው? ስትል ጥያቄውን አነሳችላቸው። ከመሃከላቸው አንደኛው ጓድ ብዙዎቹ ከጾታ ጋር በተያያዘ ነው። ከኔ ይልቅ ግን ጓዲቶች ብታስረዷት ይመረጣል አለና ጥያቄውን መልሶ ወደ ሴቶቹ ወረወረው። አዎ አለች አንደኛዋ ጓዲት። አዎ በርግጥም እንደተባለው የጾታ ባህሪይ አለው በሽታችን። ጋአት እንለዋለ። ጋአት ከወር አበባ ጊዚያዊ መቋረጥ ጋር የተያያዘ በሽታ ነው። ብዙውን ጊዜ ጓዲቶች የወር አበባ ሳናይ ለሁለት ወርና ለሶስት ወር ከዚያም በላይ እንቆያለን። ጋአት ያመማቸው ጓዲቶች የበሉት ከሆዳቸው አይቆይም። ወዲያውኑ በገባበት ቡልቅ ብሎ ይወጣል። ሆዳቸው እርጉዝ እስኪመስል ይወጠራል። ውስጣቸውንም ጥሩ ስሜት አይሰማቸውም። ያስጨንቃቸዋል። በተለይ በሠራዊቱ ወስጥ የሚንቀሳቀሱ ጓዲቶች ከትጥቅ ጋር ብዙ መበገሰ (መጓዝ) ይከብዳቸዋል፤ አለችና ጥያቄሽን መለስኩልሽ? ስትል ዓለሚቱን ጠየቀቻት።

አዎ የኛ ትግል ገና ብዙ ዓመታትን የሚጠይቅ ሆኖ ነው የሚታየኝ። አፈጣጠራችን በራሱ ሙሉ ሰው አያደርገንም። ከአዳም ግራ ጎን ተፈልቀን እንደ ተፈጠርን ነው ቅዱስ መፅሃፍ የሚገልፀው ስትል የዕምነት ቀለም ቀባችው። ዓለሚቱ። ሌላዋ ጓዲትም ቀጠል አድርጋ ሴትነታችን በህብረተሰቡ ዐይን ግማሽ ሰው ሆነን እንድንታይ ሃይማኖቱ እየሰበከ እኩልነታችን አልተከበረም ስንል የምንታገለው አገዛዙን ብቻ አይመስለኝም። ሃይማኖቱንም ጭምር እንጂ። ጭቆናችን ድርብ ድርብርብ ነው ስንል ዕምነቱ በስብከት፤ ሥርዓቱ በትምክህት፤ ተፈጥሮም በዕናትነት (በወላድነት) ስለሚረገጡን ይምስለኛል። እኛ እንኳ ታግለን ነጻ ብንወጣ ሁሉም ሴቶች ነጻ ወጡ ለማለት አያስደፍርም። ሁሉም ሴቶች ነጻ እንዲወጡ በዓለም ዙሪያ የተቀነባበረ ትግል መካሄድና ከዕምነት እስከ ሥርዓት መለወጥ ይኖርበታል። ይህ ደግሞ ዕውን ሊሆን የሚችል ነገር አይደለም። አብዮት ዓለምን ባንዴ ማጥለቅለቅ አይቻለውምና።

ጭብጥና ቡርጋንዴ

በዚህ መልክ ዘወትር ከእራት በኋላ የተለያዩ ርዕሶች እየተነሱ ውይይት ሲካሄድባቸው ሰነበቱና በመጨረሻም ህክምናዋን ጨርሳ ወደ ተአሊም (ውታደራዊ ስልጠና) ተላከች። በስልጠና ላይ እያለች ቀደም ሲል ጀምሯት የነበረው የአእምሮ ህውከት እየከፋ መጣ። ስልጠናውን እንደጨረሰችም እርሷ ደሳለኝና ኮከቤ ከሌሎች አሥራ አንድ ጓዶች ጋር በወልቃይት ቀጠና ተመደቡ። ወደ ወልቃይት ሲጓዙ ተርናሻ ላይ ሠራዊቱ ተሰብስቦ ሲወያይ ደረሱ። የሠራዊቱን ተርናሻ ላይ መሰብሰብ ሲጠይቁ በማይፀምሪው ድርጊያ ( operation) የተሰውትን ሰማዕታት ለመዘከር እንደሆነ ተነገራቸው። ዓለሚቱ ይህን እንደ ሰማች ቅልቅል ስሜት ተሰማት። ባንድ በኩል ለሰማዕታታቱ የሚሰጠው ክብር አስቀናት። በሌላ በኩል ግን የጦሩ ሁኔታ አሳዘናት።

የከተማ ጓዶች አስፋልት ላይ ተጥለው የውሻ መራኮቻ ይሆናሉ በሠራዊቱ ግን ህይዎትና ሞት ተሳስመው ሲለያዩ ሥርዓቱ እንዲህ ይከበራል ስትል ለራሷ ነገረችው። ከተማ ሳለች ስለ ቀዩ ጦር ትሰማው የነበረውም ተስብስቦ ከምታየው ጎስቋላ ወታደር ጋር አልዛመድ አላትና አስቆዘማት። እናም ነገሩን ሁሉ ስታየው ዊሊያም ሸክስፒር እንዳለው ምንም ለማይፈይድ ነገር ብዙ መከናወት ( much ado about nothing) ሆነባትና ዘወትር ስሜቷ ሲነካ እንደ ምታደርገው ብዕሯን እንዲህ ስትል አስለቀሰችው፡

የሰማሁት ሌላ የማየው አስለቃሽ
ራሴው አድርጎት እኔውን ተወቃሽ
የእከኬን ጠባሳ የትናንቱን ቁስሌን
ይቅርታ ጠየቅሁት ማረኝ ብዬ አካሌን።

የዕኩለ-ቀን ላይ ጨለማ ( darkness at noon)

የፀለምቱ ቆይታዋ በዚህ ተገባድደና ወደ ወልቅይት አቀናች። ወልቃይት እንደ ገቡም ምድቧ ሀይል አምስት ውስጥ ሆነ። በሃይል አምስት ውስጥ ለዓመት ያክል እንደቆየች ለህክምና ወደ ደለሳ ቆቃ ጣቢያ ተላከች። በህክምና ጣቢያው ከነበሩት ከወደሬ፤ ከአበራ፤ ከፍሬወይን፤ ከደሳለኝ፤ ከከበደ፤ ከደምስና ከመሸሻ ጋር ህክምናዋን እየተከታተለች ለተወሰነ ጊዜ ቆየች።

ከነዚህ ህመምተኖች መሃከል መሸሻና አበራ መንቀሳቀስ አይችሉም ነበር። መሸሻ አንድ እግሩን በጦርነት አጥቷል። አበራም አንድ እግሩ ክፉኛ ቆስሎ ይጸዳዳ የነበረው ከተኛበት መሬት ስር ጉድጓድ ተቆፍሮ ከጉድጓዱ ውስጥ የሽንትና የዐይነ ምድር መቀበያ ዕቃ እየተቀመጠለት ነበር። ዓለሚቱም ወደዚህ ህክምና ጣቢያ ከመጣችበት ጊዜ ጀምሮ ጣቢያውን እስከ ለቀቀችበት ጊዜ ድረስ የአበራ የግል “ነርስ” ነበረች ማለት ይቻላል።

አበራ ቁስሉ ይንዠክው ስለነበር እንቅልፍ አይተኛም። ዓለሚቱና ከበደ ነበሩ እንቅልፍ የሚያስይዙት። ከበደ ድሮ ያያቸውን ሲኒማዎች ይተርክለታል። ዓለሚቱ ደግሞ በግጥም ህመሙ ተሽሎት ነገ መራመድ እንደሚችልና ብሎም ለውጊያ እንደሚሰለፍ ተስፋ ትሰጠው ነበር። አልፎ አልፎም ስለከተማው ትንቅንቅ ትርክቷን ስታካፍለው ለተወሰነች ሰዓትም ብትሆን ያሸልባል። ገጠመኟንም ከ “ሀ” እስከ “ፐ” ያጫወተቻቸው በዚህ ወቅት ነበር።

ዓለሚቱ ከእዕምሮ በሽታዋ በተጨማሪ ሌላም ህመም ነበረባት። ሌሊት ሌሊት ሳትነቃ ከምኝታዋ ተነስታ የመሄድ (sleep walk) በሽታ። ደለሳ ቆቃ ህክምና ጣቢያ በነበረችበት ወቅት አንድ ሌሊት ተነስታ ወደ አንድ መንደር ዘልቃ ገባችና አንድ ቤት ውስጥ ቡና እየተቆላ ደረሰች። ባለቤቶቹም እንዳዩአት ደንግጠው ከተቀመጡበት ተነስተው ውሾቹ እንዴት አሳለፉሽ? ሲሉ ጠየቋት። ራሴን ያወቅሁት ከቤት ከገባሁ በኃላ ስለሆነ ከዚያ በፊት ስለሆነው ሁሉ አላውቅም። ያነቃኝም የቡናው ሽታ ነው አለቻቸው።

አርሶ አደሮቹም በሁኔታዋ አዝነው አስቀመጧትና እህል ውኃ ቅመሽ አሏት። ዓለሚቱ ግን ከነቃች በኋላ ራሷን ሳተችና እህል ውኃ መቅመስ ቀርቶ መቆምና መራመድ አቃታት። አርሶ ስደሮቹም በሁኔታዋ ተደናግጠው ወደ ጣቢያው ተሸክመው ወሰዷት። ስለ ህመሟም የሰሙት ካዩት ጋር ተዳብሎ በጅጉ አሳዘናቸው። ሌላ ጊዜ ደግሞ ከጣቢያው ራቅ ብሎ ወደሚገኘው ወንዝ ወርዳ እግሯን ታጥባ ከወንዙ ዳር ተኝታ ተገኘች። ከነዚህ ሁለት አጋጣሚዎች በመለስ ምን ጊዜም ሌሊት ወጥታ ስትመለስ ዓለሚቱን ያጋጠማት ችግር አልነበረም።

በዚህ ሁኔታ ላይ እንዳሉ ነበር ወያኔ ወልቃይት ውስጥ መግባቷን የሰሙት። የወያኔ ወልቃይት መግባት የከባቢውን ፀጥታ ስላደፈረሰው ህክምና ጣቢይው እንዲዘጋና በሽተኞቹም አስተማማኝ ፀጥታ ወደ ሚገኝበት ቦታ እንዲሄዱ ተወሰነ። መንቀሳቀስ የሚችሉት ወደ ጸለምት ተላኩ። መንቀሳቀስ የማይችሉት መሸሻና አበራ ዋልድባ ገዳም ውስጥ ህቡዕ ገቡ። መንቀሳቀስ የቻሉት ጸለምት እንደገቡ ዓለሚቱ ከፀለምት ሀይሎች ጋር ላጭር ጌዜ ከተንቀሳቀሰች በኋላ በሬዲዮ ግንኙነት ክፍል ተመደበች። በዚሁ በሬዲዮ ግንኙነት ምድቧ እንዳለች ለህመሞቿ ትወስዳቸው የነበሩት መዳህኒቶች በሰውነቷ ውስጥ የርስ በርስ ግጭት መፍጠር ጀመሩ።

ዓለሚቱም ድሮ ይሰማት ከነበረው ህመም የተለየ ስሜት እየተሰማት መጣ። የሰውነት መዛልና ድካም አዘውትረው ይጎበኟት ጀመር። በዚህም ምክኒያት ወደ ጣራ የህክምና ጣቢያ ተወሰደች። ከዕለታት ባንደኛዋ ቀን ከጓዶች ጋር ምሳ በልታ ጥቂት እንደቆየች በቁሟ ወደቀች። አጠገቧ የነበሩት ጓዶች ደርሰው ሊያነሷት ሞክሩ። ዓለሚቱ ግን የወደቀችው እስከ ወዲያኛው ዳግም ላትነሳ ነበርና ወዲያው አንድ ጓድ ጥይት ተኮሰ። ባካባቢው የነበሩት ጓዶች ተሰባሰቡና ለዘመናት እየተዘመረ በወታደራዊ ሥነሥርዓት ሬሳዋ ወደ መቃብር ወረደ።
ማሬ አረጋ ይህችን ዓለምና ትግሉን እንዲህ ተሰናበተቻቸውና እርሷም እንደ ወጡ ያልተመለሱ ከሚባልላቸው ኢህአፓዎች አንዷ ሆነች። መሸሻ፤ አበራና የቀሩት ቁስለኞችም ትግሉ ገርገጭ ሲል እንዳዲያቆኑ ያላቀሰሱትን ጓዶቻቸውን ተቀላቅለው ተሰደዱ። ከንቱ ትግል። ከንቱ ደም። ከንቱ ህይዎት። የባከነ ትውልድ እንዲሉ።

የሰማዕታቱን ነፍስ ይማር።
ታህሳስ 2006
አብርሃም በየነ
abraham3106@comcast.net

የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ “የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት ጥሪ የሁሉም ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ጥሪ ነው”አለ

$
0
0

EYNM New Logo entc-logo-5“የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት ጥሪ የሁሉም ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ጥሪ ነው!” ሲል የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ ባወጣው መግለጫው አስታወቀ።
ንቅናቄው ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫ “የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት ጥሪ ወሳኝና ህዝባዊ ጥሪ እንደሆነ ታሪካዊ ምስክርናውን በመስጠት፤ በዚህ ዘረኛ የወያኔ/ኢህአዴግ መንግስት ከልክ ያለፈ ጭቆና ፣ ረገጣና ፣ እንግልት ደርሶብኛል የምትሉ ንፁሃን ኢትዮጵያውያን ዜጎችና ፣ በምንወዳት ሃገራችን ለህዝብ የሚበጅ ቀና ለውጥ ለዘለቄታው ይሰፍን ዘንድ የምትመኙ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ፤ እንዲሁም ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ፣ የሃይማኖት ተቋማትና ፣ የሲቪክ ማህበራት ታላቅ ሃገራዊ ሃላፊነትና የህዝብ አደራ በጫንቃችሁ እንደተሸከማችሁ በመገንዘብ ፤ የሚጠበቅባችሁን ህዝባዊ ተልኮ መፈፀም ታሪካዊ ግዴታችሁ መሆኑን በመረዳት ፤ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት ጎን እንድትቆሙ ሲል በጥብቅ እያሳሰበ ፤ ሃገራዊ ጥሪውን በአክብሮት ያቀርባል:: የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት ጥሪ የሁሉም ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ጥሪ ነው!” ብሏል።

ሙሉ መግለጫውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

Health: ‹‹ከድብርት ለመላቀቅ ወሲብ ማድረግ እንዳለብኝ ተነግሮኝ ባደርግም ከችግሩ አልተላቀቅኩም››

$
0
0

ሰላምና ጤና እየተመኘሁላችሁ እኔም እንደሌሎች ጠያቂዎች ችግሬን ላዋያችሁ፡፡ ዕድሜዬ 25 ነው ከጉርምስና ዕድሜዬ ጀምሮ ድብርት ያሰቃየኛል፡፡ በተለይ ሴት እንደመሆኔ መጠን ይህ ችግር ሊጎላብኝ አይገባም እያልኩ እጨነቃለሁ፡፡ ለመሆኑ ሴቶች ወይስ ወንዶች ናቸው ለድብርት የሚጠቁት? በጓደኞቼ ምክር መሰረት ከድብርት ለመላቀቅ ወሲብ ማድረግ እንዳለብኝ ሁሉ ተነግሮኝ ያን ሁሉ በጉርምስና ዕድሜዬ ጀመርኩ፡፡ ሆኖም ለውጥ የለውም፡፡ ዝም ብሎ ያለምንም ምክንያት ቢደብራችሁ ምን ታደርጋላችሁ? እስቲ አንድ በሉኝ ድብርት ሊገለኝ ነው፡፡
ዲ.አር

depression
ውድ አንባቢያችን: ሁሉም ሰው ለስነ ልቦናዊ ችግሮቹ መንስኤ ምክንያቶች ይኖሩናል፡፡ ከደብዳቤሽ ለመረዳት እንደቻልነው ስነ ልቦናዊ መንስኤሽ ምን እንደሆነ ግልፅ አይደለም፡፡ ሆኖም ለዚህ ሰፊ ችግር መንስኤ የምንላቸውን ስንዘረዝር ያንቺ የቱ እንደሆነ ለመገንዘብ ሞክሪ፡፡ ከዚህ በተረፈ መፍትሄዎችን እንደሚከተለው እንጠቁምሻለን፡፡

ድብርት የሚባለው ሁኔታ በማናችንም ላይ በተወሰነ መልኩ ሊከሰት የሚችል ሁኔታ ሲሆን መጠኑን ያለፈ ሲሆን ግን ከስነ አዕምሮ ውስጥ ይመደባል፡፡ ይህም ዲፕሬሽን በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ የደብርት ስሜት የተለያዩ ሀዘንን ወይም መከፋትን የሚያስከትሉ ሁኔታዎችን ተከትሎ ቢመጣም ከችግሩ ጋር ተመጣጣኝ ያልሆኑና ጊዜውም ከልኩ ያለፈ የድብርት ስሜትን ያስከትላል፡፡

Depression may be described as feeling sad, blue, unhappy, miserable, or down in the dumps. Most of us feel this way at one time or another for short periods.
Clinical depression is a mood disorder in which feelings of sadness, loss, anger, or frustration interfere with everyday life for a longer period of time.

For more information on the symptoms and treatment of depression, see:

- Adolescent depression
- Bipolar disorder
- Depression in the elderly
- Dysthymia
- Major depression – National Library of Medicine

በዓለማችን ውስጥ ድብርት በሁለተኛው ደረጃ በሰፊው የሚታይ የስነ አዕምሮ ችግር ሲሆን በአማካኝ ወደ ህክምና ማዕከል የተለያየ በሽታ ይዞናል ብለው ከሚሄዱት ሰዎች ውስጥ 10 በመቶ የሚሆኑት በድብርት ችግር ሳቢያ እንደሆነ የተለያዩ ጥናቶች ያመላክታል፡፡
አንድ ጊዜ ድብርት በሚከሰትበት ወቅት በአብዛኛው ከ6-9 ወር ሌላ ጊዜ ቢቆይ ከ15-20 በመቶ ባሉ ሰዎች ላይ ግን 2 ዓመትና ከዛ በላይ ሊቆይ ይችላል፤ በመቀጠልም በተለያየ ጊዜ በተደጋጋሚ ሊነሳ ይችላል፡፡

ድብርት በምን ይከሰታል?

በመሰረቱ የድብርት መንስኤ በውል ባይታወቅም ካለ ምንም ምክንያት ሊከሰት እንደሚችል ሁሉ የተለያዩ ሁኔታዎችን ተከትሎ ሊመጣም ይችላል፡፡
በጥቅሉ ስንመለከት የድብርት ስሜት ከወንዶች ይልቅ በሴቶች ላይ የመታየት እድሉ በሁለት እጥፍ ከፍ ሲል ይህ የሆነበት መሰረታዊ ምክንያት ባይታወቅም ከምክንያቶቹ ውስጥ ግን፤
- የሴቶች ባሪ ከወንዶች ይልቅ ሁኔታዎች በሚከሰቱበት ወቅት ወደ ውስጥ በመያዝ የበለጠ ስለሚጨነቁ፤
- በስነ ተፈጥሮ ላይ የሆርሞኖች መለዋወጥ ይበልጥ በሴቶች ላይ ስለሚታይና ይህም ለድብርት ሊያጋልጥ ስለሚችል፣ ለምሳሌ የወር አበባ ከመምጣቱ ጥቂት ቀናቶች በፊትና እንዲሁም ልጅ ከወለዱ በኋላ ለትንሽ ቀናት የድብርት ስሜት ሊከተል ይችላል፡፡
- የወሊድ መከላከያ እንክብል በሚወስዱ አንዳንድ ሴቶች ላይ ይህ ሁኔታ ሊከሰት ይችላል፡፡
- የታይሮይድ ዕጢ የሚያመነጩ ሆርሞኖች መዛባት በአብዛኛው ሴቶች ላይ የሚታይ ሲሆን ይህም የድብርት ስሜትን ሊያስከትል ይችላል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም በህይወት ውስጥ የተለያዩ መሰረታዊ የህይወት ለውጥና የመንፈስ መታወክን ሊያስከትሉ የሚችሉ ሁኔታዎች፣ ለምሳሌ የቅርብ ሰው ሲሞት ወይንም የሙት ዓመት ሲሆን፤ በማንኛውም ወቅት በተለይ ግን በበዓላት አካባ የብቸኝነት ስሜት ሲኖርና ከስራ መባረር፣ ከፍቅር/ከትዳር ጓደኛ ጋር መለያየት፣ ቤት መለወጥንና የተለያዩ ስር ነቀል ለውጦች ይህንን ስሜት ያስከትላሉ፡፡

Depression and heart disease

The link between heart disease and depression has long been thought of as cause-and-effect. Studies are now showing that depression itself may contribute to heart disease.

የተለያዩ በሽታዎች በሚከሰቱበት ወቅት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ድብርትን ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ ለመጥቀስ ያክል፤
- በቀጥታ፡- የታይሮይድ ዕጢ ችግር በሚኖርበት ወቅት የሆርሞኖች መለዋወጥ በቀጥታ ድብርትን ሊያስከትል ይችላል፡፡
- በተዘዋዋሪ፡- የአጥንት መገጣጠሚያ ችግር በሚኖርበት ወቅት ከፍተኛ የህመም ስሜት መኖሩና እንቅስቃሴም በመገደቡ የበሽተኛነት ስሜትና ድብርትን ሊያስከትል ይችላል፡፡
- በሁለቱም፡- አንጎል ላይ ጉዳቱን የሚያስከትሉ ሁኔታዎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የድብርት ስሜትን ያስከትላል፡፡
- የአንዳንድ መድሃኒቶች የጎንዮሽ ጉዳት የድብርት ስሜትን ማስከተል ሊሆን ይችላል፡፡ ይህም እንደ መድሃኒቱ አይነት ወይንም እንደ ብዛት ሊወሰን የሚችል ሁኔታ ነው፡፡
- በአመጋገብ ላይ የተወሰኑ ንጥረ ነገሮችን ካለመውሰድ፤ ለምሳሌ የቫይታሚን ቢ 5 እና ቫይታሚን ቢ 12 በሚያነሱን ጊዜ የድብርት ስሜት ሊከሰት ይችላል፡፡

በድብርት ጊዜ ሊታዩ የሚችሉ ስሜቶች

የድብርት ስሜት በአብዛኛው ጊዜ ቀስ በቀስ ቀናትንና ሳምንታት ጠብቆ የሚከሰት ሁኔታ ሲሆን በአብዛኛው ወደ ድብርት ስሜት ውስጥ የሚገባ ሰው ቀዝቀዝ ማለትና የማዘን ስሜት ወይንም በአንፃሩ የመበሳጫጨትና የመነጫነጭ ሁኔታ ሊታይበት ይችላል፡፡ ይህንንም ስንል፤
- Vegetative Depression:- ሰዎች ከነገሮች፣ ከእንቅስቃሴዎችና ከሌሎች ሰዎች ሲርቁ፣ በአጠቃላይ ከወትሮ ባህሪያቸው ውጪ ማውራት ሲቀንሱ፣ ምግብ መብላት ሲያቆሙ፣ እንቅልፍ መተኛት ሲያቅታቸው እንዲሁም ከፍተኛ የሀዘን ስሜት ሲሰማቸው የሚታይ ሁኔታ ሲሆን፤
- Agitated Depression:- ከላይ ከተጠቀሱት አንዳንድ ስሜቶች በተጨማሪ ካለማቋረጥ ሲያወሩ፣ ሲነጫነጩ፣ በአንድ ቦታ ረጋ ብለው መቀመጥ ሲያቅታቸውና ከሰው ጋር መግባባት ሲያቆሙ የሚታይ ሁኔታ ነው፡፡
በአብዛኛው በድብርት ውስጥ ያለ ሰው የደስታና የሀዘንን ሁኔታዎች በትክክል መስማትም ሆነ መግለፅ ያዳግተዋል፣ በዚህም ሳቢያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ስሜቶች ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡

በድብርት ውስጥ ያሉ ሰዎች በአብዛኛው የአነጋገራቸውና የአስተሳሰባቸውን የእንቅስቃሴያቸው ፍጥነት እጅግ ይቀንሳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በአብዛኛው ጊዜ ለነገሮች ውሳኔ መስጠት ከማቃትም በላይ ለብዙ ነገሮች ግድ ያለመስጠት ሁኔታና ብሎም ተስፋ የመቁረጥ ሁኔታ ያሳያል፡፡ ለሁኔታዎችም ራሳቸውን የመውቀስና እንዲሁም አልረባም ብሎ የማሰብ ሁኔታ ከጊዜ በኋላ ተስፋ መቁረጥንና ብሎም ራስን የማጥፋትን ሀሳብ ብሎም ሙከራን ያስከትላል፡፡

በአብዛኛው ድብርት ውስጥ ያሉ ሰዎች እንቅልፍ የመተኛት ችግር ሲኖርባቸው በተጨማሪም በተደጋጋሚ ከእንቅልፍ የመንቃት ሁኔታና ብሎም ወደ ማንጊያው አካባቢ ጨርሶ መንቃት ይከሰታል፡፡
የግብረ ስጋ ግንኙነት ፍላጎትም ሆነ ችሎታ መቀነስ በአብዛኛው የሚታይ ሁኔታ ነው፡፡

የምግብ ፍላጎት መቀነስና ብሎም የሰውነት ክብደት በእጅጉ መቀነስ እና በሴቶች ላይ የወር አበባ መቅረት ያስከትላል፡፡ ነገር ግን በአንድ አንድ ሰዎች ላይ ምግብን በኃይል መብላትና የሰውነት ክብደት ከቁጥጥር ውጭ መጨመርም የሚታይ ሁኔታ ነው፡፡
አንድ አንድ ሰዎች ከድብርት ስሜቱ የተነሳ የተለያየ በሽታ ይዞናል ብለው በማሰብ የህመም ስሜት፣ ሊሰማቸው ይችላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የማይድን በሽታ ይዞኛል ወይም የተለያዩ አስነዋሪ ናቸው ብለው የሚያምኗቸው ሁኔታዎች ይዞኛል በሚል እምነት ፍርሃትና ጭንቀት ሊይዛቸው ይችላል፡፡
ወደ 15 ከመቶ የሚሆኑ የድብርት ስሜት ያላቸው ሰዎች ይህንን ስሜት ተከትሎ ሌላ የስነ አዕምሮ ችግሮች ሊያጋጥማቸው ይችላል፡፡ ማለትም ነገሮችን ማየት ወይንም መስማት፣ ሌሎች ሰዎች ምን ያህል እንደማይረቡ የነገሯቸው መምሰል፣ ሰዎች ይቅር የማይባል ጥፋት ስላጠፉ ሲወቅሷቸው ወይንም ለግድያ ሲፈልጓቸው ማየት፣ ማሰብ፣ ወይንም መስማት ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡

በአጠቃላይ የድብርት ስሜት በሚኖርበት ጊዜ የስነ አእምሮ ሐኪም ጋር መሄድ ወይንም ሰዎችን እንዲሄዱ መምከር ተገቢ ሲሆን በተለያዩ ምክሮችና (psychotherapy) ሊሻሻል የሚችል ሁኔታ ነው፡፡ ሰዎች ራሳቸውን የማጥፋት ሀሳብም ሆነ ሙከራ በሚያደርጉበትም ወቅት በአፋጣኝ የስነ አዕሮ ሐኪም ጋር በመውሰድ እንደየአስፈላጊነቱ በሆስፒታል ተኝተው ወይንም በተመላላሽ ህክምና ነገር ግን በቅርብ ክትትል የህክምና መፍት እንዲያገኙ ማድረግ እጅግ ተገቢ ነው፡፡

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live