Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የትራፊክ መጨናነቀ አቢሲንያ ባንክን ለመዝረፍ የሞከሩ ተጠርጣሪዎች እንዲያዙ ረዳ

$
0
0
(ሪፖርተር) ቦሌ መድኃኔዓለም አካባቢ የሚገኘው የኢቢሲንያ ባንክ ቅርንጫፍ በስለት በማስፈራራት ዘረፋ ለመፈጸም የሞከሩ ተጠርጣሪዎች ተያዙ፡፡ ሪፖርተር በቅርንጫፍ ባንኩ ተገኝቶ ከዓይን እማኞችና ከመርማሪ ፖሊሶች ለመረዳት እንደቻለው፣ ማክሰኞ ሰኔ 5 ቀን 2010 ዓ.ም. ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ገደማ ወደ ባንኩ የገቡ ዘራፊዎች በስለት በማስፈራራት በባለ 50 ኪሎ ግራም ሁለት የማዳበሪያ ከረጢቶች አንደኛው ውስጥ ከ2.7 ሚሊዮን ብር በላይ በማጨቅ […]

በትግራይ ክልል(ሽሬ?) ለሁለት አመት ስቃይ የተፈጸመበት አበበ ድሪርሳ አብረውት የታሰሩት ጓደኞቹ የት እንደደረሱ እንደማያውቅ ገለጸ

$
0
0
  የማህሌት ፋንታሁን ዘገባ እንደሚከተለው ይቀርባል አበበ ድሪርሳ ይባላል። የአምቦ ልጅ ሲሆን በ2008 በባህርዳር ዩንቨርስቲ 2ኛ ዓመት ኢንጂነሪንግ ተማሪ ነበር። በ2008 በባህርዳር ከተማ በነበረው ተቃውሞ ጋር በተያያዘ ታስሮ ትግራይ ክልል (ሽሬ?) የሚገኝ የወታደር ካምፕ ለሁለት አመት ከቆየ በኋላ ከሳምንት በፊት ነው ከሌሎች ሰላሳ የሚሆኑ አብረውት በካምፑ ታስረው ከነበሩ ተማሪዎች ጋር በሲኖትራክ በለሊት አምጥተው ባህርዳር የተጣሉት። […]

በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ፈተና አንፈተንም ያሉ ተማሪዎች በልዩ ኃይል ተደበደቡ

$
0
0
(ዘ-ሐበሻ) በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ከሦስተኛ ዓመት ወደ አራተኛ ዓመት የሚዘዋወሩ ተማሪዎች ሆልስቲክ የሚባል ፈተና እንዲወስዱ በዩኒቨርሲቲው የቀረበላቸውን ጥያቄ ባለመቀበክላቸው በተነሳ ተቃውሞ ልዩ ኃይል በመግባት ድብደባ መፈጸሙን ከስፍራው ያገኝነው መረጃ አስታውቋል:: የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የምህንድስና ተማሪዎች ፈተናውን አንወስድም ያሉት “እንደዚህ ዓይነት ፈተና በሌሎች የሃገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች አይሰጥም; ለምን እኛ ብቻ ተመርጠን ፈተና ተቀመጡ እንባላለን:: በየጊዜው የምንወስደው ፈተና ለመመዘኛ በቂ […]

“ለመታወቅ ተብሎ እና ገንዘብ ለማግበስበስ ብዬ በየወሩ ነጠላ ዜማን ሆነ ሙሉ አልበም አለቅም”–ብዙአየሁ ደምሴ

$
0
0
ዘለአለም ገብሬ በሰሜን አሜሪካ ካናዳ ኑሮውን ያደረገው ድምፃዊ ብዙአየሁ ደምሴ ፣ኑሮውን በውጭ ሀገር መኖር ከጀመረ ጊዜ ጀምሮ ከሙዚቃ ህይወቱ ጋር ሙጥኝ ብሎ እንደሚኖር መረጃዎቻችን የሚጠቁሙ ሲሆን በተለይም በአሁን ሰአት አብዛኞቹ ወጣት አዝማሪዎች በውጭ ሀር ባህል ቁራኛ ሆነው በዘመናዊ ባርነት መገዛታቸው የሙዚቃውን የረጅም ጊዜ ህይወት እና የጥበባዊ ስርአቱን እየገደሉት የመጡ መሆናቸው የሚገለፅ ሲሆን ፣ ብዙአየሁ ግን […]

በወልቂጤ ከተማና ዙሪያዋ የተከሰተው ግጭትና ሁከት ዛሬም ተባብሶ መቀጠሉ ታወቀ

$
0
0
ስዩም ተሾመ በእግር ኳስ ውድድር የጀመረው ግጭት ትላንት ማለዳ ላይ በጉራጌው የቀቤና መኖርያዎችን ማፍረስና የወረዳውን አስተዳደር; ቢሮዎች ማቃጠል የጀመረው አመፅ ለሊቱን ሙሉ በሁለቱም ብሄሮች ቀጥሎ በርካታ ቤቶች ሲቃጠሉ ማደራቸውንና ሁለት ሰዎች መሞታቸው ተረጋግጧል። ስማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ የአካባቢው ነዋሪ እንደገለጹት ” ትላንት ማለዳ የጀመረው ችግር ከጉራጌው ከተወሰደው እርምጃ ቀጥሎ ወልቂጤን ዙርያ ከቦ የሚገኘው የቀቤና ማህበረሰብ “ጉራጌ […]

ሕወሓት ዶ/ር ዓብይ አህመድን በይፋ ተቃወመ

$
0
0
ሕወሓት ዛሬ ያወጣው መግለጫ እንደወረደ ይኸው:- የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ መግለጫ I. መግብያ፡- የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ከሰኔ 3-5 ያካሄደዉን ኣስቸኳይ ሰብሰባ ኣጠናቋል። ህወሓት/ኢህወዴግ በ17 ዓመቱ የትጥቅ ትዓልም ሆነ ሩብ ክፍለ ዘመን ባለቆጠረው የልማት፣ የሰላምና የዴሞክራሲ ትግል ምዕራፎች ሁሉ ከሌሎች እህት ድርጅቶች ጋር በመሆን ባደረግነው ትግል በርካታ ድሎችን እየተጎናፀፈን እዚህ ላይ መድረስ ችለናል። የ43 ዓመታት የድልና የፅናት […]

ከሰሞኑ ግጭትና አለመረጋጋት በስተጀርባ የህወሓት እጅ አለበት!

$
0
0
ከስዩም ተሾመ አንዳንድ ግዜ በጣም ግራ የሚያጋቡ ፖለቲካዊ ክስተቶች ይከሰታሉ። ፍፁም ያልተጠበቁ በመሆናቸው የተከሰቱበትን ምክንያትና የሚያስከትሉትን አሉታዊና አዎንታዊ ተፅዕኖ በቀላሉ መገመት አስቸጋሪ ይሆናል። እንዲህ ያሉ ፖለቲካዊ ክስተቶችን መንስዔና ውጤት ለመረዳት ዝርዝር መረጃዎችን ከማሰባሰብና በተጨማሪ ከመሰረታዊ የፖለቲካ መርህ አንፃር መመልከት ያስፈልጋል። ለምሳሌ ባለፉት ጥቂት ቀናት በደቡብ ክልል ዲላ፣ ሐዋሳ፥ ወልቂጤ፥… ወዘተ በመሳሰሉ ከተሞች ያልተጠበቀ ግጭትና አለመረጋጋት […]

መግለጫዉ ወዴት? ህወሀት የት ነበር? |ከታዬ ደንድአ

$
0
0
የህወሀት ማዕከላዊ ኮሚቴ በቅርቡ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የሰጠዉን ዉሳኔ በመቃወም መግለጫ ሰቷል። በጣም ደግ! መቃወም መብት ስለሆነ ይችላሉ። እኛም ዕድሉን እንጠቀምበታለን። ደግሞም ታሪክ ሰርቷል። ለ 27 ዓመታት ያልተሞከረዉን ለመጀመሪያ ጊዜ አደረጉት። አንድ አባል ድርጅት የኢህአዴግን የEC ዉሳኔ ሲቃወም ይህ የመጀመሪያዉ ነዉ።ግን ዉሳኔዉ ሲሰጥ በቦታዉ የነበሩ መሰለኝ። ህወሀት ወደ አጋር ፓርቲነት መቀየሩን ከመግለጫዉ አላነበብኩም። ተሳስቼ […]

ወዴት ገልበጥበጥ ??? |ከአስገደ ገብረስላሴ ፣ መቀለ

$
0
0
ከኢህአደግ ስራ አስፈጻሚ ከሚቴ ስለ የአልጀርስ ሰምምነት እና የወሰን ኮሚሽን ውሳኔ የህወሓት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በኢህአደጉ ስብሰባ ውሳኔው ተቀብሎ ሲያበቃ እንደገና ውሳኔው ሳይውል ሳያድር በመገልበጥ የህዝብ ተቃውሞ ለስልጠኑ አስጊ ሆኖበት ስላአገኜው ውሳኔው በመሰረተ ሀሳቡ የኢህአደግ መርህ የተከተለ ሆኖ ነገር ግን ወደህዝብ ወርደን አሳማኝ ስራ ባለመስራታችን ትክክል ያልሆነ ውሳኔ ወስነናል ብለውናል ። ዋዋ እነዚህ ሰዎች አስተሳሰባቸው […]

“አገር አጥፋ”አረም – (በዳንኤል ክብረት)

$
0
0
ብሽሽቅ ሃይማኖትም፣ ፖለቲካም፣ ወግም ሥርዓትም አይደለም፡፡ ብሽሽቅ ከከሠረ ኅሊና የሚበቅል ‹አገር አጥፋ› አረም ነው፡፡ ‹አገር አጥፋ› አረም የከብቶች ፀር የዕጽዋት ቀበኛ የሆነ ገበሬ አስቸግር አረም ነው፡፡ ‹አገር አጥፋ› አረም መስከረም መጥባቱን የሚያበሥረንን አደይ አበባ ሳይቀር ከሀገር የሚያጠፋ አረም ነው፡፡ አረሙን ከብቶቹ ስለሚያውቁት በአካባቢው ድርሽ አይሉም፡፡ ለስሙ የሚያፈካውን አበባ ንቦች ከቀሰሙት ማር ሳይሆን የሚገድል መርዝ ነው፡፡ […]

የነ ነውር ጌጡ መግለጫ! –አቻምየለህ ታምሩ

$
0
0
ሕወሓት የሚባለው የቅሚያና ግድያ ድርጅት ያወጣውን መግለጫ አነበብሁት። መግለጫው አንዳች ኢትዮጵያን የሚነካ ነገር የለውም። ሕወሓት እንደ ድርጅት ከምስረታው ጀምሮ ከበርካታ ግራ አጋቢ ነገሮች ጋር የተወሳሰበ ነውረኛ ድርጅት ነው። ነው ጌጡ የሆነው ይህ ድርጅት ያለ አንዳች ተቃውሞ አዲስ አበባ ላይ አብሮ የወሰነውን «የኢሕአዴግ» ውሳኔ መቀሌ ላይ ባደረገው ጉባኤው ተቃውሞታል። ከሽፍትነት ወደ «መንግሥትነት» የተለወጠው ይህ የማፍያ ቡድን […]

የኢትዮጵያ ሕዝብ በመጪው ዕሁድ የህወሓትን መግለጫ ተቃውሞ በመላው የኢትዮጵያ ከተሞች ሰልፍ በመውጣት ህወሓትን ማስጠንቀቅ አለበት። መቶ ሚልዮን ሕዝብ ዲሞክራሲ ወይንም ሞት! ብሎ ለመፋለም መነሳት አለበት።(የጉዳያችን መልዕክት)

$
0
0
ጉዳያችን/ Gudayachn ሰኔ 7/2010 ዓም (ጁን 14/2018) የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰኔ 9/2010 ዓም ቅዳሜ የመቀሌ ሰልፍ በተደረገ ማግስት ሰኔ 10/2010 ዓም ዕሁድ በአዲስ አበባ፣ሐዋሳ፣አዳማ፣ባህርዳር፣ጎንደር፣ደሴ፣ሐረር፣ነቀምት፣ወዘተ ዲሞክራሲ ወይንም ሞት! የሚል አስገራሚ ሰልፍ በማድረግ ለሕወሐትም ሆነ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ከዶ/ር ዓብይ የለውጥ ሂደት ጋር አብሮ መቆሙን ማሳየት አለበት። ህወሓት ወጣቱ የዓለም ዋንጫ በሚመለከጥበት ሰሞን ተቃውሞው ይቀንሳል የሚል የተሳሳተ እሳቤ […]

“በእስር ላይ ብሆንም ግንቦት 7 አንድም ጥይት በኢትዮጵያ ምድር እንዳላጮኸ ነው የማውቀው።”አንዳርጋቸው ጽጌ ለቢቢሲ

$
0
0
ማክሰኞ ግንቦት 21 2010 ዓ.ም ከእስር የተፈቱት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ነፃ ከወጡ በኋላ በቤተሰቦቻቸው መኖሪያ ከተደረገላቸው ሞቅ ያለ አቀባበል ባሻገር ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተገናኝተው ከአንድ ሰዓት ተኩል በላይ መወያየታቸውን ለቢቢሲ ሃርድ ቶክ ተናግረዋል። አቶ አንዳርጋቸው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ስላደረጉት ውይይት ለየትኛውም የሀገር ውስጥና የውጭ መገናኛ ብዙሃን ሳይናገሩ ቆይተው ለቢቢሲ አንዳንድ […]

በአዲግራት የተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ |አክቲቭስቶች ለሕወሓት መግለጫ ምላሽ ሰጡ

$
0
0
(ዘ-ሐበሻ) በሕወሓት አቅራቢነት በኢህ አዴግ ሥራ አስፈጻሚ የተሰጠውን ” የአልጀርስ ስምምነትና የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ኮሚሽን ውሳኔ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተቀብለናል” ውሳኔ በመቃወም በዛሬው ዕለት በአዲግራት ከተማ ተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ:: ትናንት ህወሓት ባወጣው መግለጫው “ኢትዮ-ኤርትራ ዘላቂ ሰላም ጉዳይም ሆነ ከመንግስት የልማት ድርጅቶች ጋር በተያየዘ የተወሰኑ ውሳኔዎች ወደ ኢህአዴግ ምክርቤት ሳይቀርቡ፣ አጋር ድርጅቶች ሳይሳተፉበት እና የሚመልከታቸው አካላት በዝርዝር […]

የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ የፌስቡክ ገጽ ዳይሬክተር ከሥራው ተባረረ

$
0
0
  (ዘ-ሐበሻ) የጠቅላይ ሚኒስተሩን ፌስቡክ ገጽ የሚመራው አቶ አስራት አሳለ ከሥራው መባረሩን ይፋ አደረገ:: የቀድሞው የመንግስት ኮሙኒኬሽን መስሪያ ቤት ሰራተኛ የነበረው አስራት ከሥራ የተባረረው ስለወላይታ ህዝብ ተቆርቁre ከጻፍኩ በኋላ ነው ብሏል:: ሃይለማርያም ደሳለኝ ስልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ የሃይለማርያምንም ፌስቡክ ገጽ በዳይሬክተርነት የሚመራው አስራት ከሥራ ከተሰናበተ በኋላ በፌስቡክ ገጹ “በሃዋሳ ከተማ በዋላይታ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን […]

ይድረስ ለክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸዉ እና ለ አቶ ደመቀ መኮነን

$
0
0
የመንግስት ድርጅቶችን ፕራይቬታይዜሽን ይመለከታል፡፡ ——————– ከሚኪ አማራ ህወሃት ትናንት በመግለጫዉ እንዳመላከተዉ የፕራይቬታይዜሽን ጉዳይ ሙሉ ለሙሉ እንደሚደግፈዉ እና እንደሚስማማዉ ገልጧል፡፡ እንዲሁም ጉዳዩን እራሱ ህወሀት ያመጣዉ መሆኑን ተናግሯል፡፡ እንደሚታወቀዉ የአማራ ክልል በኤሊክትሪክ ስርጭት የሃገሪቱ ጭራ መሆኑን እናንተም ገምግማችዋል፡፡ ክልሉ ካሉት የወረዳ ከተሞች ዉስጥ 46 በመቶ ብቻ የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንደሚያገኙ ይታወቃል፡፡ በክልሉ ስድስት ወረዳወች ጭራሽ ኤሌክትሪክ የሚባል የላቸዉም፡፡ […]

ከመቀሌው ዱለታ በስተጀርባ ያሉ እውነታዎች –ክንፉ አሰፋ |በጽሁፍና በቪዲዮ የቀረበ

$
0
0
የህወሃት መግለጫ በመስመሮች መካከል ሲነበብ በተቀማ ጩኸት ሊመሰል ይችላል። ከመቀሌው ዱለታ በስተጀርባ የነበሩ እውነታዎችን ለመዳሰስ የፖለቲካ ሊቅ መሆንን አይጠይቅም። ህወሃቶች አብረው ወስነው ያስተላለፉትን ጉዳይ እንደመጋዣ አኝከው ሲያበቁ፤ ከብዙ ገጽ የክስ ቻርጅ ጋር ብቅ ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩን ለማስጠቆር የሄዱበት ርቀት ግልጽ እና መሳጭ ነው። ሰማይ ወጥተው ቁልቁል ቢወርዱም ግን ከቶውንም የህዝብ ቀልብ ሊስቡ አይችሉም። እኛ ከሌለን […]

በእስር ቤት የሚገኙ የፖለቲካ እስረኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ እጠይቃለው::(ዶክተር ፍቅሩ ማሩ)

$
0
0
ሰኔ 7 ቀን 2010 ዓም ለሚመለከተው ሁሉ! በፖለቲካና በ”ሽብርተኝነት” ተከሰው ጉዳያቸው በሂደት ላይ ያሉትም ሆነ፣ ተፈርዶባቸው በእስር ላይ የሚገኙትን እስረኞች መንግስት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እፈታለሁ ካለ 3 ወራት አልፈወል። እስካሁን የተወስኑ እስረኞች ተፈትተዋል። ነገር ግን ጉዳያቸው ከተፈቱት ጋር በአንድ ፈርጅ የሚጠቃለሉ አሁንም በእየስር ቤቱ ይማቅቃሉ። የኢትዮጵያ መንግስት፣ በተለይም አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እየወሰዱ […]

ኦቦ ለማ መገርሳ ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉት የአማራ ተወላጆች ወደ መኖሪያቸው ይመለሳሉ አሉ

$
0
0
(ዘ-ሐበሻ) የረመዳንን ጾም ፍቺ በማስመልከት ከኦሮሚያ ተፈናቅለው ራያ ቆቦ ለሚገኙ የአማራ ተወላጆች በህዝበ ሙስሊሙ ኮሚቴ አስተባባሪ ኡስታዝ አቡበክር አህመድ አማካኝነት የተሰበሰበ 100,000 ገንዘብ በዛሬው ሲደርስ በሌላ በኩል ደግሞ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ኦቦ ለማ መገርሳ ከኦሮሚያ ክልል ለተፈናቀሉት የአማራ ተወላጆች መፈናቀል ምክንያት የሆኑ አመራሮችን ማሰናበታቸውን አስታውቀዋል:: ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ክልል ተወላጂዎችን በአጭር ጊዜ ወደ ቦታቸው […]

በሕወሓት የተገደለው ሳሙኤል አወቀ እየታሰበ ነው

$
0
0
(ዘ-ሐበሻ) የሰማያዊ ፓርቲ የምስራቅ ጎጃም ዞን ፀኃፊና በ2007 ዓ.ም ምርጫ የፓርቲው ዕጩ ተወዳዳሪ ነበረ – ወጣት ሳሙኤል አወቀ፡፡ ወጣት ሳሙኤል አወቀ ሰኔ 8/2007 ዓ.ም ምሽት ላይ ወደ ቤቱ እየገባ በነበረበት ወቅት በሁለት ሕወሓት ባሰማራቸው ግለሰቦች ከፍተኛ ድብዳባ ከተፈፀመበት በኋላ ሆስፒታል ውስጥ ነፍሱ አልፋለች፡፡ ወጣት ሳሙኤል ከቀድሞው አንድነት ጀምሮ ሲታገል የቆየ ሲሆን የሰማያዊ ፓርቲ መስራች አባል […]
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live