Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

Hiber Radio: በደሴ በግብር ጫና ሳቢያ ሕዝባዊ ተቃውሚ ሊነሳ ነው፣ አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ በመምህር ግርማ ወንድሙ ላይ ዳግም ጥቃቱን ሰነዘረ፣ አዲሱ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ጥሪ አቀረበ፣መከላከያ፣አምንስቲ ዶ/ር አብይን መውቀሱ፣ የአየር መንገድ ሽያጭ ምስጢር፣ ኬኒያ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ማሰር፣ ከአሜሪካ የተባረረ ኤርትራዊ ስደተኛ ህይወቱን ማጥፋቱና ሌሎችም ዜናዎች

$
0
0
የህብር ሬዲዮ ሰኔ 3 ቀን 2010 ፕሮግራም መከላከያ ውስጥ በእርግጥ ለውጥ አለ? የጄኔራሎቹ ሹም የለውጡ ጅማሮ ወይስ ለውጡ ያበቃለት ነው ? የናድመስ ጉዳይ? ከሰራዊቱ የቀድሞ የጥናትና ምርምር ሀላፊ ኮ/ል ደረሰ ተክሌ ጋር ተወያይተናል (ክፍል አንድን ያድምጡት) የአገሪቱን ኢኮኖሚ ለማሻሻል የተወሰደ እርምጃ ከሆነ ለምን አትራፊ የሆነው ድርጅት ይሸጣል እርምጃው የቀረውን የሕዝብ ሀብት ማሸሽ ነው ከኢኮኖሚ ባለሙያና […]

አቶ ስዩም መስፍን “ባድመ” የኢትዮጲያ አካል መሆኗን የሚያሳይ ማስረጃ አለማቅረባቸውን የድንበር ኮሚሽኑ ሪፖርት አረጋገጠ!

$
0
0
ከስዩም ተሾመ የኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ኮሚሽን ሪፖርትና ሌሎች ጥናታዊ ፅሁፎች እንደሚጠቁሙት የባድመ አከባቢ ለረጅም አመታት ሰው-አልባ ነበር፡፡ በአከባቢው ሰዎች መስፈር የጀመሩት ከ1950ዎቹ ጀምሮ ነው፡፡ የባድመ ከተማ በራሷ የተቆረቆረችው በወቅቱ የትግራይ አውራጃ አስተዳዳሪ በነበሩት በራስ ስዩም መንገሻ ድጋፍ ነው፡፡ ከ1950ዎቹ ጀምሮ አከባቢው በኢትዮጲያ ስር ሲተዳደር እንደነበር ብዙ ማስረጃዎች አሉ፡፡ ይህንንም የኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ኮሚሽን በዝርዝር ገልጿል፡፡ ከ1950ዎቹ በፊት […]

አቶ ኤፍሬም ሌጄቦን አንድ በሏቸው! (ሐይሉ አባይ ተገኝ)

$
0
0
‘የምር ተኳሹን እኛ ስናውቀው ድንጉጡንባንዳ ማን ደባለቀው::’ ግን ይህ ለምን ትዝ አለኝ? እንጃ! አቶ ኤፍሬም ሌጄቦ ማናቸው? አቶ ኤፍሬም ማዴቦ ሌጄቦን በልጅነቴ አውቃቸዋለሁ:: የአቶ ሌጄቦ ማዴቦ ልጅም ናቸው:: በደርግ ዘመን ‘ማርክሳዊ ሌኒናዊ ሬቮሉሽናሪ ድርጅት- ማሌሬድ’ የሚባለው አቶ ተስፋዬ በተሰኙ የትግራይ ተወላጅ ተመስርቶ ከወታደራዊው ደርግ ጎን ተሰልፎ ይሰራ የነበረ ድርጅት አባልና በአቢዮት ጥበቃነትና ገራፊነት ከአጎታቸው ልጅ […]

የኢትዮጵያውያን ጓዳ! (ክፍል-3)  –ምሁራዊነት ከወዴት አለ?’

$
0
0
ፀጋዝአብ ለምለም ተስፋይ የኢኮኖሚክስ መምህርና ጸሓፊ (ሸክም የበዛበት ትውልድ፡ 2009 እና  የምሥራቃዊት ኮከብ፡ 2010 መጻሕፍት አዘጋጅ)    የሀገራችን ነባራዊ ኹለንተናዊ ኹኔታዎች በስሜት፣ በኹኔታዎች፣ በኹነቶችና እጅግ ጥቃቅንና አነስተኛ በኾኑ ጉዳዮች ላይ በማተኮር እየተንቀሳቀሰና እየተገዛ ብሎም በኹኔታዎች እየተመራ ባለበት ጊዜ – በሀሳብ፣ በዕሳቤ፣ በአስተምህሮ፣ በአቋም፣ በመርህ፣ በዲሲፕሊንና በአርቆ ማሰብ  – በድምሩ በኹኔታዎች ከመመራት ወደ ኹኔታዎችን ወደመምራት የሚያሸጋግር […]

“ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኤርትራዊ አንሆንም”–የባድመ ከተማ ነዋሪዎች

$
0
0
“ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኤርትራዊ አንሆንም” – የባድመ ከተማ ነዋሪዎች

የሰሞኑ ዜና ፡ (ከአምባሳደር እምሩ ዘለቀ)

$
0
0
ቁጥር ፪ ግንቦት ፪ሺ፲ ጠቅላይ ሚንብትሩ ከተሾመ እነሆ ሁለት ወር አለፈው፡ በዚህ ጊዜ ዉስጥ ጠ/ሚስትሩ ብዙ ተናግሯል ብዙ ቦታ ባገር ዉስጥ ውጪም እየተዘዋወረ ተናግሯል በተለይ የርትግራይን “የኢትዮጵያ ሕዝብ ፋና ሁኖ የበላይ ወርቃማ የተባረከ ልዮ መሪነት ስጦታ” እንዳለው መስክረዋል። ጎረቤት አገሮችንም ጂቡቲን ኬንያንና ሱዳንን ጎብኝተዋል፡ ጋዜጠኞችና አንድ አንድ ስማቸው የታወቀ እስረኞች ተፈተዋል፡ሳዊዲ አረብያ ተጉዞ አል ሙዲንና […]

በቅርቡ ማዕረጋቸው የተመለሰላቸው ብሪጋዲየር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ለመጀመሪያ ጊዜ ተናገሩ

$
0
0
VOA Amharic – ባሳለፍነው ሳምንት ወታደራዊና የደህነንት ሹም ሽር የተካሄደበት ሳምንት ነበር። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም የነበሩት ጀነራል ሳሞራ ዩኑስ ተሸኝተው በቦታው ላይ ጀነራል ሰዓረ መኮንን ተሾመዋል። የብሄራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር በነበሩት በአቶ ጌታቸው አሰፋ ምትክ ደግሞ ጄነራል አደም መሐመድ ተሾመዋል። ከዚህ ሹም ሽር በተጨማሪ ወታደራዊ ማዕረጋቸው ተገፍፎ ከሠራዊቱ ተባርረው […]

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የተሰኘ አዲስ ንቅናቄ ባህርዳር ላይ ተመስርቷል።የንቅናቄው እድሎች እና ፈተናዎች ምንድናቸው?

$
0
0
የንቅናቄው ምስረታ ላይ የተገኘው ሕዝብ    ጉዳያችን/ Gudayachn  ሰኔ 3/2010 ዓም (ጁን 10/2018 ዓም) የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ መስራች ጉባኤውን ለሁለት ቀናት ያህል ሰኔ 2 እና 3/2010 ዓም በባህር ዳር ከተማ  አካሂዷል።በጉባኤው ላይ ንግግር ያደረጉት ጀነራር ተፈራ ማሞን ጨምሮ በርካታ ወጣቶች የተገኙ ሲሆን የንቅናቄውን አመራሮችም ይፋ ሆነዋል።በእዚህም መሰረት አመራሮቹ የሚከተሉት መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል። እነርሱም : – 1-ዶር ደሳለኝ ጫኔ-ሊቀመንበር […]

“ያለውን የለገሰ ንፉግ አይባልም” (ዮፍታሔ)

$
0
0
ትሕነግ እብሪተኛ፣ ስግብግብ፣ ሕዝብን የምትጠላና ችግር ለመፍታት እውቀት የሌላት ድርጅት በመሆኗ እንጂ በአገሪቱ ውስጥ ያለው የኢኮኖሚ ችግር አስከፊነት ከፖለቲካው የማይተናነስ መሆኑን በመግለጽ መፍትሔውንም የጠቆሙ በርካቶች ናቸው። የቅርቡን እንኳን ብንመለከት ለአገሮች ዓመታዊ የኢኮኖሚ ሪፖርት ካርድ በመስጠት የሚታወቀው Fitch የተባለው ዓለም አቀፍ ድርጅት ባለፈው ዓመት June 8, 2017 ስለኢትዮጵያ ባወጣው ዘገባ በውጭ ንግድ፣ በውጭ ምንዛሪ እጥረት፣ በዕዳ ጫና፣ […]

በወልቂጤ ከተማ ዙሪያ ሁከትና ግጭት ተቀስቅሷል

$
0
0
ከስዩም ተሾመ በወልቂጤ ከተማና ዙሪያዋ በሚኖሩ የጉራጌና ቀቤና ተወላጆች መካከል ለተፈጠረው ግጭት መነሻ ምክንያቱ ከእግር ኳስ ጨዋታ ጋር የተያያዘ ነው። በመጀመሪያ ደረጃ የደቡብ ክልል ክለቦች ሻምፒዎና በአላባ ለማካሄድ ታቅዶ ነበር። ነገር ግን፣ በመጨረሻ ሰዓት የዝግጅቱ ቦታ ከአላባ ወደ ወልቂጤ ከተማ ይቀየራል። በዚህ ሻምፒዎና የወልቂጤ ከተማ እና የቀቤና ወረዳ ይሳተፋሉ። ከዚህ ቀደም አብዛኞቹ የቀቤና ወረዳ ተጨዋቾች […]

ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር ዓብይ አህመድ በቤኒሻንጉል ጉምዝ የዘር ጥቃት የደረሰበትን ህጻን አበጥር ወርቁን ጎበኙ

$
0
0
(ዘ-ሐበሻ) ጠ/ሚ/ር ዶ/ር አብይ በጳውሎስ ሆስፒታል ተገኝተው ene አበጥር ወርቁን መጎብኘታቸው አድናቆትን አጫረ:: ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በቤንሻንጉል በማንነቱ ሳቢያ ጥቃት የደረሰበትን ታዳጊ አበጥር ወርቁን እና ከሳዑዲ የመጣው ታዳጊ መሐመድ አብዱል አዚዝን በጳውሎስ ሆስፒታል በመሄድ ጠይቀዋል። ከሳውዲ ልጃቸውን በዶ/ር አብይ ቀጥተኛ ድጋፍ ልጃቸውን ይዘው የመጡት እናት ሐሊማ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ዋንጫ አበርክተዋል። ም/ል ጠ/ሚ/ር ደመቀ […]

ከአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጋር ኤርትራ የነበረው ወጣት 15 አመት ተፈረደበት

$
0
0
ተስፋዬ አያሌው (ሶራ) የአርበኞች ግንቦት 7 ወታደር ነው። ተስፋየ አባልነቱን አልካደም። ነገር ግን ዐቃቤ ሕግ የአርበኞች ግንቦት 7 አመራር አድርጎ ክስ አቅርቦታል። ፍሬው ተክሌ እንደዘገበው ተስፋዬ አያለው (ሶራ) ዛሬ ሰኔ 4/2010 ዓም የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ቀርቦ ነበር። ፍርድ ቤት የቀረበው የፍርድ ውሳኔውን ለመስማት ነበር። ፍርድ ቤቱ ውሳኔው በግለፅ ችሎት […]

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀናቸው

$
0
0
የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስዊድን ስቶኮልም ላይ ባካሄደው የዳይመንድ ሊግ ውድድር ኢትዮጵያውያን በድል አቀጠናቀቁ:: በሴቶች በተደረገው የ1500 ሜትር ውድድር ጉዳፍ ጸጋዬ 3 ደቂቃ ከ57 ሰከንድ ከ64 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት አንደኛ ወጥታለች:: በወንዶች በተደረገው የ5000 ሜትር ውድድር ሰለሞን ባረጋ 13 ደቂቃ ከ4 ሰከንድ ከ5 ማይክሮሰከንድ በመግባት አሸንፏል፡፡ በዚህ ውድድር ላይ አባዲ አዲስ 13 ደቂቃ ከ6 ሰከንድ […]

በመቀሌ ከተማ የፊታችን ቅዳሜ የተቃውሞ ሰልፍ ተጠራ

$
0
0
(ዘ-ሐበሻ) በሕወሓት አቅራቢነት የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ የአልጀርሱን ስምምነት ለመቀበል መወሰኑን ተከትሎ በትግራይ የተለያዩ ከተሞች የተለያዩ ሰላማዊ ሰልፎች ሲደረጉ ቆይተዋል:: የፊታችን ቅዳሜ በክልሉ ርዕሰ መዲና መቀሌ ከተማ ተቃውሞ ሰልፍ እንደሚደረግ ታውቋል:: በትናንትናው ዕለት በባድመ ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ ሲደረግ ውሏል:: ዛሬ ሰኔ 5, 2010 ዓም በዚሁ ባድመ አካባቢ በታሕታይ አድያቦ ወረዳ ዓዲ ፀፀር በተባለ ቦታ የሚኖር ህዝብ […]

“ፍቅር እና እዉነት ያሸንፋል! የክፉዎች ሴራ ይከሽፋል!” አቶ ታዬ ደንደኣ

$
0
0
ባለፈዉ ዓመት ኢሉ አባቦር ላይ በኦሮሞ እና በአማራ መሀከል ግጭት ተቀስቅሶ ነበር። ያ ግጭት ግብ ነበረዉ። ግቡ በሁለቱ ታላላቅ የኢትዮጵያ ብሔሮች መሀከል የነበረዉን ምናባዊ መጠራጠር ይበልጥ በማጠናከር በኢትዮጵያ ህዝብ ሰቆቃ እና ባርነት መበልፀግ ነዉ። ግን ህልም ሆኖ ቀርቷል። ግጭቱ ኦሮማራን ወልዶ የሴራኞችን ጉልበት እንዳልነበረ አድርጓል። ዛሬ የኢትዮጵያ ህዝብ ጥሩ ተስፋ ማየት እንደ ጀመረ ለማሳየት ምስክር […]

“ያለውን የለገሰ ንፉግ አይባልም” (ዮፍታሔ)

$
0
0
ትሕነግ እብሪተኛ፣ ስግብግብ፣ ሕዝብን የምትጠላና ችግር ለመፍታት እውቀት የሌላት ድርጅት በመሆኗ እንጂ በአገሪቱ ውስጥ ያለው የኢኮኖሚ ችግር አስከፊነት ከፖለቲካው የማይተናነስ መሆኑን በመግለጽ መፍትሔውንም የጠቆሙ በርካቶች ናቸው። የቅርቡን እንኳን ብንመለከት ለአገሮች ዓመታዊ የኢኮኖሚ ሪፖርት ካርድ በመስጠት የሚታወቀው Fitch የተባለው ዓለም አቀፍ ድርጅት ባለፈው ዓመት June 8, 2017 ስለኢትዮጵያ ባወጣው ዘገባ በውጭ ንግድ፣ በውጭ ምንዛሪ እጥረት፣ በዕዳ […]

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ከየትና እንዴት መጣ?

$
0
0
ሰሞኑን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰኘው አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ መመስረቱን ተከትሎ በአንዳንድ የአማራና ኦሮሞ ልሂቃን፣ እንዲሁም የአንድነት አቀንቃኝ በሆኑ ወገኖች መካከል አላስፈላጊ እሰጣ-ገባ እየተካሄደ ነው። ራሴን ማጋነን አይሁንብኝና፤ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የሚባል ፓርቲን ስለማቋቋም ሳይነሳ፣ ኦቦ ለማ መገርሳ ወደ ባህር ዳር መሄድ ሳያሰብ፣ የኦሮማራ ጥምረትና ትብብር ሳይጀመር፣… ከሁለት አመት በፊት ከታች በምስሉ ላይ በተገለፀው መልኩ […]

ቋንቋና ብሔራዊ ኵራት –ጌታቸው ኃይሌ

$
0
0
የጥንት አገሮችን እንመልከት። በጽሕፈት የሚገለጥ ቋንቋ አላቸው። ቅኝ ገዢዎች ሥር ቢወድቁም እንኳን፥ ቋንቋቸውን አለቀቁም። ኢትዮጵያም ክፍሏ ከጥንት አገሮች ጋር ስለሆነ፥ ከተፈጠረች ጊዜ ጀምሮ ቋንቋን በጽሕፈት ትገልጥ ነበረ። ብዙ ቋንቋዎች ባሉበት አገር አንድ ቋንቋ ብሔራዊ ቋንቋ የሚሆነው በቤተ መንግሥት የሚነገር ሲሆን ነው። በኢትዮጵያ ረጅም ታሪክ ውስጥ ግዕዝና አማርኛ ከቤተ መንግሥት ጀምሮ ለብሔራዊ ቋንቋነት የተለያየ መንገድ ይዘው […]

አሜሪካ ዜጓቿ ወደኢትዮጵያ ሶማሌ ክልልና ምስራቅ ሐረርጌ እንዳይጓዙ ማስጠንቀቂያ ሰጠች

$
0
0
(ዘ-ሐበሻ) የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ዜጎቹ ወደ ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል እንዳይጓዙ ጥሪ አቀረበ:: መስሪያ ቤቱ በድረገጹ ላይ ባሰፈረው መረጃ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ዜጎቹ እንዳይጓዙ ማስጠንቀቂያ የሰጠው ሕዝባዊ አለመረጋጋት ስላለ; የሽብርተኝነት ጥቃትና ፍንዳታ ሊደርስ ይችላል በሚል ስጋት ነው:: ሕዝባዊ አመጽ ከተነሳ በግንኙነት ችግር ሊፈጠር ይችላል ያለው መስሪያ ቤቱ በክልሉ ፈንጂ አለ; አሸባሪዎች በኢትዮጵያ ጠረፍ አካባቢ […]

የሲዳማ ሕዝብ አዲስ ዓመት በዓል እየተከበረ ነው |ሕዝቡ የክልል እንሁን ጥያቄን እያቀረበ ነው

$
0
0
(ዘ-ሐበሻ) ትናንት አዋሳ ከተማ ላይ የፍቼ ጨምበላላን በዓል ለማክበር በወጡና የሲዳማ ተወላጆችና አብረው በኖሩት የወላይታ ተወላጆች መካከል የተፈጸመው ግጭት ከጀርባው ሕወሓት/ደህዴን ስላለበት አብሮ የሚኖር ሕዝብ እንዳይጋጭ የአካባቢው ማህበረሰብ እየጠየቁበት ባለበት በዚህ ወቅት በዛሬው ዕለት የሲዳማ ህዝብ አዲስ ዓመት በዓል በሰላም እየተካሄደ መሆኑን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ይጠቁማል:: የህወሓት/ ደህዴን ካድሬዎች ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት በህዝቡ ውስጥ በመግባት […]
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live