Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

በኢትዮጵያ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለተጨማሪ ወራት ሊራዘም እንደሚችል ተጠቆመ

$
0
0
ኢሳት (ጥር 12: 2009) በኢትዮጵያ ታውጆ የሚገኘው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተፈለገውን ሰላም ባለማምጣቱ፣ ለተጨማሪ ወራት ሊራዘም እንደሚችል አንድ በደህንነት ጉዳዮች ላይ ዘገባ የሚይቀርብ ጋዜጣ አስታወቀ። ከአንድ አመት በላይ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞን ተከትሎ በሃገሪቱ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ምንም አይነት ለውጥ እንዳላመጣ ጋዜጣው ዘግቧል። አፍሪካ ኮንፊደንሻል የተባለው ይኸው ጋዜጣ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ […]

በመንገዱ ፣,,, የማለዳ ወግ…ዱባይ ማራቶን፣ ባንዴራውና ቅስም ሰባረው ፖለቲካ ! –ነቢዩ ሲራክ

$
0
0
* ዱባይ ላይ ፈተና ውስጥ የወደቀችው ጀግና አትሌት ወርቅነሽ … በዱባይ 2017 ማራቶን አሸናፊዋ አትሌት ወርቅነሽ ደገፋ ሀገሯን ወክላ ሮጣ ተሯሩጣ አሸንፋ እንደገባች ቅስምን ሰባሪ ምርጫ ገጠማት ፣ ሁለት ባንዴራ ! ቅስም ሰባረውን ፖለቲካ ትርክት ለመታዘብና ለመቁሰል ጀግናዋ አትሌት ወርቅነሽ መመልከት በቂ ነው ! … አዎ ጀግናዋ አትሌት በድል አሸንፋ ገባች ፣ ደስታዋን እየዞረች ስትገልጽ […]

እንጀራዬን በአዲስ ትሪ (አሰገደች ቶሎሳ)

$
0
0
እንጀራዬን በአዲስ ትሪ (አሰገደች ቶሎሳ) መቼም ዘንድሮ ጆሮአችን የማይሰማው፣ዓይናችን የማያየው የለው የኸው ደግሞ የወያኔ ካሚኔ የጭንቁን አዋጅ አውጆ፣የኢንተርኔት መረበን ዘግቶ የሚታፈሰውን አፍሶ፣ የሚተሰረዎን አስሮ ና የሚገደለውን ገድሎ ከጨረሰ በኃላ በፖርላማዬ ተቀምጨ ለአገር የሚበጅ ብልሀት መከርኩ ይለናል። መምክራቸው ባልክፋ ነበር ማፅደቃቸው ግን አሁንም ፅኑ አቋማቸው አሳብቋል። እንድ ወዳጅ ድሮስ በገዥው የተተከለ አሁን ደግሞ ራሱ አፀደኩ ሲልህ […]

ካሰቡት ግብ ለመድረስ ፣ያመኑበትን ዓላማ አንግቦ በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ! –ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

$
0
0
ቅዳሜ  ጥር ፲፫ ቀን ፪ሺህ ፱ ዓ.ም.             ቅፅ፭፣ ቁጥር  ፲ የዛሬ አራት ዓመት ዐማራ ነኝ ብሎ ደፍሮ ለመናገር ብዙ ማሰብና ማውጠንጠን ይጠይቅ ነበር። ምክንያቱም ላለፉት 50 እና 60 ዓመታት በዐማራው ነገድ ላይ የተነዛው ፕሮፓጋንዳ በሁለት መሠረታዊ ምክንያቶች ዐማራ ነኝ እንዳይሉ ገደብ የጣሉ ነበሩ። የመጀመሪያው ምክንያት ዐማራው ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ የሚያምን በመሆኑ፣ ራሱን ወደ […]

ማህሙድ አህመድ አንድ ድምጻዊን ፍርድ ቤት ሊያቆም ነው

$
0
0
ማህሙድ አህመድ አንድ ድምጻዊን ፍርድ ቤት ሊያቆም ነው

የሳባ ንግሥት ትሩፋትና የዶክተር ጌታቸው ኃይሌ ስህተት |ከሙሉጌታ ውዱ

$
0
0
መግቢያ፤ mooloogeta@hotmail.com ዶክተር ዶናልድ ሊቫይን የሚባል በቺካጎ ዩኒቨርሲቲ አስተማሪ የሆነ አንድ “አይሁድ” አሜሪካዊ የዛሬ አሥራ ስድስት አመት አካባቢ እኔ ወደምኖርበት አካባቢ መጥቶ ደወለልኝና በቀጠሮ ተገናኝተን በአንድ የኢትዮጵያ ምግብ ቤት ውስጥ አብረን መመገብ ጀመርን። በጭውውታችን መካከል ስለ ኢትዮጵያውያን “ምሁራን” አነሳና አስተያየቱን ይሰጠኝ ጀመር። ከሁሉም የሚወደው (my favorite በሚል አገላለፅ) እንድርያስ እሸቴ የሚባለውን ሰው እንደሆነ ነገረኝ። አከታትሎም […]

አትነጋገሩ ብሎ መምከር ጥሩ ፖለቲካ አይደለም – ፍቃደ ሸዋቀና

$
0
0
የኢትዮጵያ ባለስልጣኖች ተቃዋሚዎችን ለድርድር መጥራታቸውን መቃወምም ሆነ እንዳይሳተፉ መምከር ጥሩ ፖለቲካ አይደለም። በመርህ ደረጃ አላማው ምንም ይሁን ምን ማንም ተቃዋሚውን ለውይይትም ይሁን ለድርድር ሲጠራ መቃወም ብልህ ፖለቲካ አይደለም። ፖለቲካ አኮ በትርጉም ደረጃ የመደራደር ጥበብ ( the art of compromise) ነው። ትልቁ ነገር በድርድሩ መድረክ ላይ የሚቀርበው ጉዳይ ነው። ማወቅና ማረጋገጥ ያለብን በድርድር ጊዜ ተደራዳሪ ወገን […]

የጋምቤላ ፍጅት ሲጋለጥ |የጋምቤላ ታጋች ህፃናት ለፖለቲካ ፎጆታ እየሆኑ ነው |ብርቱ ምስጢር

$
0
0
ሙሉነህ ዮሃንስ ህፃናቶቻቸውን እና እንስሶችን እንደፈለጉ የደቡብ ሱዳን የሙርሌ ጎሳ አባላት የሚነጥቁባቸው ዞን ውስጥ ከፍተኛ ሹመኛ የሆነ ሰው ነው ያደረሰን። ሚስጥሩ በደረስኩበት መረጃ መረጃ መሠረት ገና ከዚህ በላይ የወረዳው ሰው ሁሉ ሊወሰድ ይችላል ይላል፡፡ ምክንያቶቹን እንዲህ ዘርዝሮ ልኮታል፡- 1. ለም የእርሻ መሬት ከእኛ እስከ አጎራባች አለ ይህን በሚያርሱ የወያኔ ኢንቨስተሮች ለበርካታ አመታት ከህይወት እስከ ንብረት […]

ይሁኔ በላይ አዲስ ወቅታዊ ነጠላ ዜማ ዛሬ ለቀቀ –“በዘመን መባቻ”|ይዘነዋል

$
0
0
(ዘ-ሐበሻ) ባለፈው ዓመት ‘ሰከን በል’ የተሰኘውን ነጠላ ዜማውን እንደለቀቀ እጅግ ተወዳጅነትን ያተረፈለት ዝነኛ ይሁኔ በላይ አሁንም በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ተጨማር ነጠላ ዜማ ለቀቀ:: በራሱ ይሁኔ በላይ ግጥምና ዜማው የተደረሰው ይኸው “በዘመን መባቻ” ነጠላ ዜማ ወቅታዊውን የሃገራችን ሁኔታ ቃኝቶበታል:: ኢትዮጵያ ሃገራችን እኔ ብቻ አዋቂ የሚል እንደማትወድና እኔ ብቻ አዋቂ ነኝ ባይ ለሃገራችን ትልቁ የችግር ምንጭ […]

በዜጎች ላይ የሚፈጸመው ሕገወጥ ደባ –ዜጎች በፈረቃና በጨለማ እየኖሩ ኤሌክትሪክ ኃይል ለጎረቤት አገር መሸጥ ያሳፍራል።

$
0
0
በዜጎች ላይ የሚፈጸመው ሕገወጥ ደባ – ዜጎች በፈረቃና በጨለማ እየኖሩ ኤሌክትሪክ ኃይል ለጎረቤት አገር መሸጥ ያሳፍራል። Minilik Salsawi – mereja.com የወያኔው ኣገዛዝ ለጎረቤት ኬንያ በስድስት ወር ውስጥ የሸጠው ኤሌክትሪክ ኃይል ሰላሳ ኣምስት ሚሊዮን ብር ሲያተርፍ በሃገር ቤት መብራት ተቋርጦባቸው ስራ ካልሰሩ ፋብሪካዎች ለሃገሪቱ ያስገባሉ ከተባለው ውስጥ ስድሳ ሚሊዮን ብር ኪሳራ ደርሳል። ሃገሪቱን በኪሳራ ውስጥ እየዘፈቀ […]

“የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ መሪዎችና አባላት አሁን በኢትዮጵያ እየተደረገ ላለው ትግል መንገዱን ያሳዩ ናቸው፤ ቀድመው ገፈት የቀመሱትም እነሱ ናቸው”–ነጌሳ ኦዶ ዱቤ

$
0
0
(ዘ-ሐበሻ) በሃገር ቤት ውስጥ ትግል እያደረገ የሚገኘው የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ዓለም አቀፍ የድጋፍ ኮሚቴ ሊቀመንበርና የህግ ሰው ኦቦ ኔጌሳ ኦዶ ዱቤ በቪዲዮ ባስተላለፈው ወቅታዊ መልዕክት አሁን በኢትዮጵያ እየተደረገ ላለው ሕዝባዊ ትግል መንገዱን ያሳዩት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ መሪዎችና አባላቱ ናቸው አሉ:: በአሁኑ ወቅት በእስር ቤት እየማቀቁ የሚገኙ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ አመራሮችን በስም በመዘርዘር ለሕዝቡ የሰላማዊ ትግል […]

የጅቡቲ አፋሮች ትግል እንዴት ከሸፈ? ክፍል 3 |ከይገርማል

$
0
0
ጉዞ ወደጅቡቲ በረሀ   ወደጅቡቲ ይዞኝ ከሚሄደው ሰው ጋር ለመገናኘት ባቲ ከተማ ፍኖተ ሰላም ከሚባል ሆቴል በሀምሌ 1984 ዓ.ም የወሩ የመጀመሪያ ቀናት አካባቢ ቀጠሮ ተይዞልኛል። ከሆቴሉ ስደርስ ቀጠሮ የያዘችልኝ ልጅ ከአንድ መካከለኛ ቁመት ካለው ቀጠን ካለ ጠይም የአፋር ወጣት ጋር እያወራች ነበር። “ኦ! እንኳን ደህና መጣህ፡ ስንጠብቅህ ነበር” አለችኝ እንዳየችኝ። የሩጫ ያህል ተጣድፌ ከእቅፌ አስገባኋት። […]

“ኢትዮጵያውያን ስንሳሳት የኖርነው አባቶቻችን የነገሩንን ትተን የፖለቲከኞችን ይዘን ስነምንጓዝ ነው”–ተክሌ የሻው በዲሲ በተደረገው የአማራ ጉባዔ ላይ ያደረጉት ንግግር

$
0
0
“ኢትዮጵያውያን ስንሳሳት የኖርነው አባቶቻችን የነገሩንን ትተን ፖለቲከኞች የነገሩንን ይዘን ስነምንጓዝ ነው” – ተክሌ የሻው ዛሬ በዲሲ በተደረገው የአማራ ጉባዔ ላይ ያደረጉት ንግግር

“በኢትዮጵያ የብሄር ብሔረሰቦች ማንነት የተፈጠረው በአማራ ጥላቻ ላይ ነው”–አቻምየለህ ታምሩ በዲሲ አማራ ጉባዔ ላይ የተናገረው

$
0
0
“የትግራይ ብሔርተኝነት አቀንቃኝ ወያኔ ወይም መለስ ሳይሆን አሉላ አባ ነጋ ነበሩ” – አክቲቭስት አቻምየለህ ታምሩ በዲሲ አማራ ጉባዔ ላይ የተናገረው

የኢህአዴግ ተሃድሶና የምርጫ 2012 ሞት –ሽረት

$
0
0
ስዩም ተሾመ የኢህአዴግ ተሃድሶ መጀመሪያና መጨረሻ በሚለው ፅሁፍ ተሃድሶው ከየት ተነስቶ የት መድረስ እንዳለበት ለመጠቆም ሞክሬያለሁ፡፡ ይህ ፅሁፍ ደግሞ በተሃድሶው መነሻና መድረሻ መሃል ምን መደረግ አለበት በሚለው ዙሪያ ያጠነጥናል፡፡ አሁን ሀገሪቱ ያጋጠማትን የፀጥታና አለመረጋጋት ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ምን ዓይነት ለውጥና መሻሻል ያስፈልጋል? ተሃድሶው እንዴትና እስከ መቼ ተግባራዊ ሊደረግ ይገባል? የሚሉትንና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በዝርዝር ለማየት እንሞክራለን፡፡ […]

አፈትልኮ የወጣ ልዩ የወያኔ ደህንነት ሪፖርታዥ

$
0
0
ከሙሉነህ ዮሐንስ ወያኔ ከ3 ሳምንት በፊት ከሀገሪቱ በሙሉ ከሚገኙት ዞኖች/ክፍለ ከተሞች በተፅዕኖ ፈጣሪነታቸው ብቻ ሳይሆን በህወሃት ስለት የተገረዘ አእምሮ አላቸው ብሎ የሚመካባቸውን በየዞኑ ከ2-5 ካድሬወች በተለይም አማራና ኦሮሚያ ክልል(የህዝብ አመፅ ከሚበዛባቸው) አካባቢ በርካታ ታማኞችን በ4 ማዕከል(አ.አ፣ መቀሌ፣ ባህርዳርና አዳማ) እስከ 24/05/09 ዓ.ም የሚቆይ ብርቱ ስብሰባ ነው። አንድ ትልቅ ሆቴል ውስጥ በሚከተለው መልኩ ቆይታቸውን አውስተው በሞቅታ […]

የችግሮቻችን መፍትሄ የሚገኘው ሁሉንም ባለድርሻ ያሳተፈ ብሄራዊ መግባባትና እርቅን መሰረት ያደረገ ሀቀኛ ድርድር ሲካሄድ ነው።

$
0
0
ጥር 14፣ 2009 (ጃንዋሪ 22፣ 2016) ባለፈው ሳምንት የገዥው ህወሀት/ኢህአዴግ መሪና የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስቴር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ  ከተቃዋሚዎች ጋር ለመነጋገር እንደሚፈልጉ ከተናገሩ ወዲህ በሀገር ውስጥ በህጋዊነት ተመዝግበው የሚገኙ ፖለቲካ ድርጅቶች ተገናኝተው በድርድሩ አካሄድና አጀንዳ አቀራረጽ ላይ ውይይት እንዳካሄዱ በቀጣይም ተገናኝተው ለመነጋገር  እንደወሰኑ ተገልጿል። በሀገራችን ውስጥ እጅግ እየሰፋ፣ እየተካረረና እየተወሳሰበ በመሄድ ላይ ያለውን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊና […]

እጅግ ለተወደዳችሁ ኢትዮጵያዉያን: ጉዳዩ ስለ ሃብታሙ አያሌው ሕክምና

$
0
0
ለተወደዳችሁ ኢትዮጵያዉያን በወገኖቹ ላይ የሚደርሰውን ግፍና ኢፍትሃዊነት እያየ ዝም ማለት ሳላልቻለ ፣ መታሰር፣ መገደል፣ እንግልትና መከራ እንደሚያጋጥመው ቢያወቅም፣ ለአገርና ለሕዝብ መቆሙን መረጠ። በአደባባይ የአገዛዙን ግፍ ማጋለጥ ጀመረ። የአንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ እና የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቀ ሰብሳቢ ሆኖ በአገሪቷ በሙሉ ኢትዮጵያዉያንን ማደራጀት ጀመረ። ጠንካራና አልበገር መሪ መሆኑን ሲያውቁ ወደ ወህኒ ወሰዱት። ከፍተኛ ቶርቸር አደረጉበት። […]

Hiber Radio: በቋራ ለነጻነታቸው የሚታገሉትን ለማጥቃት የሔዱ የወያኔ ወታደሮች ያልጠበቁት ጉዳት ደረሰባቸው |በወሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በፌዴራል ፖሊሶች ጉዳት ደርሶባቸዋል

$
0
0
የህብር ሬዲዮ ጥር 14 ቀን 2009 ፕሮግራም – አክቲቪስት ነጌሳ ኦዶ ዱቤ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ዓለም አቀፍ የድጋፍ ቡድን ሊቀመንበር ሰሞኑን ገዢው ፓርቲ በኢትዮጵያ ከተቃዋሚዎች ጋር እያደረኩ ነው ስለሚለው ውይይትና ድርድር በተመለከተ ከህብር ተጠይቀው ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰደ( ክፍል አንድን ያድምጡት) – አክቲቪስት መስፍን አማን በኔዘርላንድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሊቀመንበርና ከቀድሞ የቅንጅት መሪዎች አንዱ ገዢው ፓርቲ እያደረኩ […]

የፍቅር ሰራዊት |ሳዲቅ አህመድ

$
0
0
አንድ ላይ ስንሆን እናሸንፋለን። ከተበታተንን እንሸነፋለን። ሐያ አምስት አመት በጫንቃችን ላይ የሻገተዉን ስርዓት በፍትህ ለመቀየር የሐማኖት፣የዘር፣የቋንቋን ልዩነት አስወግደን መነሳት አለብን። ትግላችን ወደ ድል ተቃርቦ፣ አምባገነናዊዉ ህወሃት መራሹ መንግስት ሲንገዳቀድ ለዉጡን የዘር ለማደረግ ጢቂቶች “ድክ…ድክ!” እያሉ ለህወሃት ምርኩዝ ሆኑት። ለተወሰኑ ወራትን እፎይታ ያገኘዉ ህወሃት ዘና ከማለቱ በፊት የዘርን ኬላ ሰብረን ከድል ደጃፎች ልንደርስ ይገባለ። ከወራት በፊት […]
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live