Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ኢትዮጲያ፤ የሚያድንሽ የልጆችሽ አንድነትና ትብብር ብቻ ነው።

$
0
0

ከሙሉቀን ገበየው
46517119-10-4-15-a-760x434

በሓሳብ ምናብ ከሩቅ ከሚፍላቀለቁ ከዋክብት መሃል በፍጥነት ተጉዘን ወደኛይቱ ሶላር ሲስትም እንክነፍና ወደ ውቧ ሰማያዊ ፈርጥ ፕላኔታችን መሬት እንዝለቅና የሰው ልጆች እናት ወድሆነችው የድንቅንሽ (ሉሲ) ምድር እንውርድ። በውብ ግርማ ሞገስ በተለባሱ የሰሜን ተራሮች ተከባ፣ በደንከል ትኩስ አስተ- ጎምራ ተሸልማ፣ በኦጋዴን በርሃ ዘና ብላ፣ በአባይ ሽለቆ ፈታ ብላ ወዳለቸው ምድር ኢትዮጲያ። ከ 3000 አመታት በላይ በባእዳን ያለተገዛች፣ ነጻ የሆነ ህዝብ የኖረባት አገር፣ ኮሎኒያንዝምን ድል ያደረገ ታላቅ ህዝብ የኖርባት ምድር። ጥንታዊ ግብጻውያን በታሪክ ድርሳናት የዘገብዋት፤ የጥንት ግሪኮች፣ ሮምውያን፣ የፋርስ ታሪክ አዋቂውች የጻፉላት ሃገርና ህዝብ። የመጀመሪያዊቹ ክርስቲያን ፣እስላምና አይሁዳያን የኖሩባት የታላልቅ ነግስታት ምድር። የአክሱም፣ላሊበላ፣ የሃ፣ ጎንደር ፍሲለድስ፣ የሓረር ግንብና ሌሎችንም የታሪክ አሽራና የታላቅ ስልጣኔ ምስክር ምድርና ህዝብ። በታላላቆቹ ቅዱሳን መጻሃፍት ( መጽሃፍ ቅዱስና ቅዱስ ቁራን) የተወሳች ሀገርና ህዝብ። በባርነት ብዝበዛና በቀኝ አገዛዝ ስር ለማቀቁ ህዝቦች የነጻነት ተስፋና ቀንዲል የነበርች አገርና ህዝብ። ስንቱ የአልም ህዝብr በታሪኳ፣በስልጣኔዋ፣ በባህሏ፣ በደግነቷና በህዝብዋ ሃገር ፍቅርና አርበኝነት የሚቅኑባት አገርና ህዝብ። ይህቺ ወብ አገርና ድንቅ ህዝብr በሚያሳዝን ሁኔታ ባለፉት ቅርብ አመታት ግን የስልጣኔና የታሪክን ቁልቁልት እየውርዱ ይግኛሉ። እንሆ አለምr ሁሉ በሚያሳፈር ሁኔታ በረሃብና እርዛት፣ በድርቅና ቸነፈር፣ በርስ በርስ ጦርነትና አምባገነንት እንዲሁም የአልም ከፋት ሁሉ የነገሰባት አገር አድርጎ ያያታል። አሁንም ድርስ ከውጭ ወረራ ነጻ ምድር ብትሆንም ከራሷ በፈለቁ ጥቂት ልጆቿዋ r ታርኳን፤ ስላጣኔውዋን፣ ሀይማኖትዋን፤ ባህልዋን ታላቅነትዋን ክደው እላይዋ ላይ ተፈናጠዋል። እነዚ ልጆቿ ስግብግብ ፣ ለራስ ብቻ አሳቢ፣ በወንድምና እህቶቻቸው ላይ ክፉና ጠላት ሆነውባቸዋል። ምድሪቷም የለቅሶ፣ የዋይታና የሞት ምድርም እይሆነች ነው። ወጣቶች የሚገደሉባት፤ እናቶች አምርረው የሚያለቅሱባት ምድር ሆናለች። ልጆቿ ታሪካቸውንና አሁን ያሉበትን ሁኔታ ላለማየትና ላለመስማት አይንና ጆሮቻቸውን አወቀው ዘግተወታል። በ ራስ በመውደድና በጠባብ ሃስብ ተይዘዋል። እርስ በራስም ሊጠፋፉም ተዘጋጅተዋል። በመካከላቸው ያለውን ፍቅር አርቀዋል። በብልጣብልጥ ራስ መወደድ አባዜቸውና በታሪካዊ ጠላቶቻቸው ሴራ ታውርዋል። ይህቺ ታላቅ አገር መስቀልኛ መንግድ ላይ ናት። ኢትዮጲውያን የራሳቸውን የወደፊት እጣ ፈንታ የሚወሱንበት ታርካዊ ወቅት ላይ ናቸው። አንድነትና ተባብሮ መስራት ብቻ ነው አገራቸውንም እራሳቸውንም የሚያድንና ወደ ታላቅነት የሚወስዳቸው መንገድ። የተደገሰላቸው እጣ ፈንታ ትልቅ ነው። ይህን ከሳቱት ግን የሚጠብቃቸው የነበራቸውንና ያላቸውን ሁሉ ማጣት ነው። መንግስት አልባ፣ቤት አልባ፣ምድር አልባና ስደትኞች መሆናቸውነው። ኢትዮጲያውያን ወገኖች፣ ጎሳዎችና፣ ቤሄርሰቦች ሆይ፤ አይኖቻችሁና ጆርውቻችሁን ክፈቱ። እንደ ቅን ሰውና መልካም ኢትዮጲያዊ አስቡ።ጠባብ ቤሄርተኝነትና ትምክህተኝነት ፈጽሞ
አይጠቅምም። ከአፋፈ ላይ ቁልቁል ለመውርድ እየተዘጋጃችሁ ነው ። አገራችሁናና እራስችሁን የሚያድነው ህብረትና ተባብሮ መስራት ብቻ ነው።

↧

↧

የትግራይ ነጻ አውጪ ወታደሮች በፍኖተሰላም ከተማ በአማራ ሴቶች ላይ አሰቃቂ ድርጊት ፈጸሙ |ስርዓቱን በቃኝ ያለ ሚኒሻ ተገደለ

$
0
0

የአማራ ድምጽ ራድዮ ዜናዎችን ይዘናል ያድምጡት::

የትግራይ ነጻ አውጪ ወታደሮች በፍኖተሰላም ከተማ በአማራ ሴቶች ላይ አሰቃቂ ድርጊት ፈጸሙ | ስርዓቱን በቃኝ ያለ ሚኒሻ ተገደለ

↧

መልእክት፤ ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ መስራቾች (ይገረም አለሙ)

$
0
0

የተቀዋሚዎች ብዛት የርስ በርስ ሽኩቻና የጎንዮሽ ትግል ለወያኔ እድሜ መርዘም ዋናው ምክንያት መሆኑ አሌ የማይባል ነው፡፡ የድርጅቶቹ ዓላማ ሳይሆን የመሪዎቹ ፍላጎት አይታረቄነት ተባብሮ ለመስራት የማያስችል ሆኖ ውሾቹም ይጮኻሉ ግመሉም ይሄዳል እየተባለ ሀያ አምስት አመት ዘልቀናል፡፡
በተግባር እንዳየነው ለፓርቲዎቹ መብዛትም ሆነ ለመተባበር አለመቻል ዋናው ችግር የአደረጃጀትና የትግል ስልት ወይም የዓላማና ግብ ልዩነት ሳይሆን የትግል ጽናትና ቆርጠኝነት አለመኖርና ከሚነገረው በስተጀርባ የተደበቀ የመሪዎች ፍላጎት መኖር ነው፡፡

ethiopian-national-movement-meeting
ሀገራዊ ንቅናቄን የመሰረቱት አራት ድርጅቶች ዘግይተውም ቢሆን ከዚህ በኋላ የወያኔ አገዛዝ እንዲቀጥል መፍቀድ የለብንም በማለታቸው ለመተባበር አደረጃጀታቸውም ሆነ የትግል ስልት ምርጫቸው መለያየት እንቅፋት አልሆነባቸውም፡፡ ከአንጀት ካለቀሱ እንባ አይገድም እንደሚባለው ከምር ለነጻነት ለመታገል ከተሰለፉና ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ በእነርሱ መስዋዕትነት እውን አንድትሆን ከወሰኑ ለመተባበር የሚገድ አንዳችም ምክንያት አይኖርም፡፡
ስለሆነም ከደረሰባችሁም ሆነ ካደረሳችሁት ተምራችሁ በተለይ ህዝቡ ከእናንተ ቀድሞ ሞትን ተጋፍጦ ነጻነቴን በማለት የከፈለው መስዋዕትነት አነሳስቶአችሁ ልዩነቶቻችሁን በማስወገድም ሆነ በማቻቻል እዚህ ደረጃ በመድረሳችሁ እንደ አንድ ነጻነት ናፋቂ ዜጋ ምስጋናየ ይድረሳችሁ እላለሁ፡፡
የፊርማ ሥነ-ሥርዓቱን ለመከታተል በአዳራሽ የተገኘው ነጻነት የናፈቀው ዴሞክራሲ በሀገሩ አብቦ ማየት የሚሻው(ለሱም ባይደርስ ለልጆቹ )ኢትዮጵያዊ የየድርጅቶቹ መሪዎች ለመናገር ከመቀመጫችሁ ስትነሱና ወደ ወንበራችሁ ስትመለሱ እንዲሁም ስምምነቱን ስትፈርሙ ቆሞ አጨብጭቦላችኋል ፣ያጨበጨበው ለእናንተ ሳይሆን ላነገባችሁት ክቡር ዓላማ ነው፤ ለደረሳችሁበት የመተባበር ስምምነት ነው፤ ቃላችሁን ተግባራዊ አድርጋችሁ ትግላችሁን አስተባብራችሁ ከወያኔ አገዛዝ ኢትዮጵያን ታላቅቋት ዘንድ መልእክት ነው፡፡ እናም ጭብጨባው የአድናቆት መግለጫ ከመሆኑ በላይ አደራ ነው፤ ትልቅ ሸክም ፡፡
በመሆኑም አዛውንት ወጣት፣ ወንድ ሴት ሳይል አዳራሽ የሞላው ታዳሚ በየደቂቃው ከመቀመጫው እየተነሳ ያጨበጨበበት ትእይንት እንዴትነትና ምንነት ሁሌም የሚታወሳችሁ፣ በእያንዳንዱ ርምጃችሁ የገባነውን ቃል ምን ያህል እየተወጣን ነው እያላችሁ ራሳችሁን እንድትጠይቁ የሚያነሳሳችሁ፣ ሸብረክ ስትሉ ወኔ የሚለግሳችሁ፣ ደከም ባላችሁ ግዜም እንቅልፍ የሚነሳችሁ ትልቅ አደራና መልእክት ነው፡፡
ጥያቄው ከወያኔ አገዛዝ የመላቀቅ የነጻነት ጥያቄ ነውና ፣ነጻነት ደግሞ አለ ትግል አይሆንምና፣ ትግልም ያለ ድርጅት ለውጤት አይበቃምና ይህ ነጻነት ናፋቂ ወገን ተደራጀን ላሉት፣ ተባበርን ላሉት ሁሉ ብዙ ግዜ አጨብጭቧል፤ ገንዘቡን ለግሷል፤በሚችለው ሁሉ ረድቷል፡፡ ነገር ግን ብዙዎቹ ቃል አባይና አደራ በል ሆነው አሳዝነውታል አሳፍረውታል፡፡
ነገር ግን በሀገር ገዳይ ተስፋ አይቆረጥምና ይሄው ዛሬም ተባበርን ስላላችሁት በአዳራሽ ተገኝቶ ደስታውንም አደራውንም በጭብጨባ ገለጸ፡፡ ጅምራችሁ መልካም ነው፣ ታሪክ ለክብር አጭቷችኋል፣ ህዝቡም አደራውን ጥሎባችኋል፣ ቃላችሁን የምትተገብሩ የተሰጣችሁን አደራ የምትወጡ ህዙቡን ለነጻነት ሀገሪቱንም ለዴሞክራሲዊ ሥርዓት የምታበቁ ያድርጋችሁ፡፡
ከዳር ሆናችሁ ለምትመለከቱ፣
ድርጅቶቹን የማቀራረብና እዚህ ደረጃ ለማድረስ ብዙ የጣሩትና በከፊልም ቢሆን የተሳካላቸው (ብዙ ድርጅቶች ባለመካተታችሁ) ተመስጋኝ ዜጎች ሲናገሩ እንደሰማነው ለአብሮ መስራት የቀረበው መስፈርት የኢትዮጵያን ሉአላዊ ሀገርነት፣ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን እውን ማድረግና ሥልጣን የሚያዘው በሕዝብ ፈቃድ ብቻ መሆኑን መቀበል ነው፡፡ ይህን መስፈርት ኢትዮጵያዊ አይደለንም ወይንም ኢትዮጵያዊ ለመሆን አንደራደራለን ከሚሉትና መገንጠልን ዓላማ አድርገው ከሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ውጪ ማንም አይመቸኝም ልቀበለው ይቸግረኛል ሊለው አይችልም፡፡ ካለም ራሱን ትልቅ ጥያቄ ውስጥ ይጥላል፡፡
ታዲያ ምን ሆናችሁ ምን አስቸግሮአችሁ ምንስ ልታልፉት የማትችሉት ደንቃራ ገጥሞአችሁ ነው አራት ድርጅቶች ለወራት ሲወያዩና ሲደራደና ከስምምነት ሲደርሱ የዳር ተመልካች መሆን የመረጣችሁት፡፡ የሀያ አመት ልምዳችን እንደሚነግረን ችግሩ የግለሰቦች ነውና የየድርጅቶቹ አባላትና ደጋፊዎች መሪዎቻችሁ ለምን ከሌሎች ጋር እንደማይተባበሩ ጠይቁ፣ ውስጠ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ትግል አድርጉ፣ እናም የመሪዎቻችሁን ጠባብ ፍላጎት አሸንፉና ድርጅቶቻችሁን ከዳር ተመልካችነት ወደ ትብብሩ አካልነት አሸጋግሩ፡፡ ለዚህም ነገ ሳይሆን ዛሬ ስራ ጀምሩ፡
ተቃውሞ ለምታሰሙ፤
በሀገር ጉዳይ ጋባዥና ተጋባዥ ሊኖር አይገባምና ድርድሩ/ ውይይቱ ሲከናወን አድፍጦ ቆይቶ አይሆንም ያሉት ሲሳካ አልተወከልንም አልተጋበዝንም የሚል ተቃውሞ ማሰማቱ ተገቢ አይደለምና አባላትና ደጋፊዎች ጣታችሁን መቀሰር ያለባችሁ ትብብር ወደ ፈጠሩት ድርጅቶችና ወደ አመቻቹት ሰዎች ሳይሆን ወደ መሪዎቻችሁ ነው፡፡ ለምን የሀገራዊ ንቃናቄው አካል አልሆናችሁም ብላችሁ ጠይቁ፣የትብብሩ አካል መሆን አለባችሁ ብላችሁ ሞግቱ፣አባል ለመሆን የማያበቃ ችግር በየድርጅቶቻችሁ ካለ ቤታችሁን አጽዱ፣ አመራራችሁን አስተካክሉ፡፡ አባልነት ተከታይነት ሳይሆን ባለቤትነት ነው፡፡ደጋፊዎችም የሚነገራችሁን ብቻ እየተቀበላችሁ የምታስተጋቡ ሳይሆን ለምን እንዴት ወዘተ እያላችሁ የምትጠይቁ መሆን አለባችሁ፡፡እናም ጥያቄአችሁን ወደ ቤታችሁ መልሱና ምከሩ መፍትሄ ፈልጉና እምቢተኛውንም አስገድዱና ድርጅቶቻችሁ የሀገራዊ ንቅናቄው አካል እንዲሆኑ አብቁ፡፡
ትብብር የሚመሰረተው ትግሉን ወደ ድል ለማምራት እንጂ በድርጅቶች ልዩነት ለመጠመድ ባለመሆኑ በአንድ ብሄር ስም አራት አምስት ሆናችሁ የተደራጃችሁና ስምምነት አጥታችሁ ርስ በርስ የምትናቆሩ ሁላችሁም ሆናችሁ ከመካከል አንዱ የንቅናቄው አባል ቢሆን ጤና አይሰጥም፡፡
መጀመሪያ ነገር የተደራጃችሁት በርግጥ እንወክለዋለን ለምትሉት የህብረተሰብ ክፍል ነጻነት ከሆነ እንዲህ በዝቶ መደራጀቱ አስፈላጊ አልነበረም፤ከሆነም በልዩነታችሁ በዝታችሁ በሚየስማማችሁ አንድ መሆን የሚገድ አልነበረም፤ ስለሆነም በቅድሚያ በየቤታችሁ በሽታችሁን እወቁ በቂ ህክምና አድርጉ ከዛ ጋርዮሽ ፈጥራችሁ ካልሆነም ከመካከላችሁ ከበሸታው የተፈወሰ አንዱ አባል ሊሆን ይችላል፡፡ ይህን ሳታደርጉ ሌላውን መውቀስ ግን እንደምን ይቻላል፡፡ ነገም ሌላ ቀን ነው፡፡

↧

(Video)በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የታክሲ ሹፌሮች የወያኔን መንግስት ተቃወሙ::

↧

(Video)በጄኔቫ ሲውዘርላንድ ኢትዮጵያን ታላቅ ተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ::

↧
↧

የዞምቢዎች አገዛዝ ሊታደስ አይችልም! (አቻምየለህ ታምሩ)

$
0
0

የወያኔ አገዛዝ የትግራይ ዞምቢዎች ጥርቅም ነው። ዞምቢ ማለት ህሊናው የበሰበሰ፤ስብዕናው የቆሸሽ፤ በአስተሳሰብ የነቀዘ፤ ጭንቅላቱ የተመረዘ፤ አእምሮው የደነዘዘ፤መንፈሱ የታመመ፤ በመከነ ርዕዮተ አለም እውር ድንብሩን የሚጓዝ ነፍስ የሌለው፤ በሞተ ልብ የሚገለጥ የሚንቀሳቀስ አካል ነው።
ወያኔ «በጥልት እየታደስሁ ነው» የሚለን በጥልቀት መበስበሱን ሲነግረን ነው። ይህ በጥልቅ የበሰበሰው የትግራይ ሽፍቶች ስብስብ በነቀዘ አስተሳሰብ፣ በተመረዘ ጭንቅላት፣ በደነዘዘ አእምሮ፣ በሙት መንፈስና በመከነ ርዕዮተ አለም እውር ድንብሩን የሚጓዝ የዞምቢዎች አገዛዝ ነው።
ወያኔዎች ሰው ለማጥቃት የተደራጁ የትግራይ ዞምቢዎች ናቸው። ዞምቢ አይታደስም። ዞምቢ እንኳን በምድራዊ ኃይልና በሰብዓዊ አስተሳሰብ ሊታደስ የፈጠራቸው እግዚያብሔር ራሱ እነዚህን ሰው ለማጥቃት የሰለጠሱ የትግራይ ዞምቢዎች ሲያይ እነሱን በመፍጠሩ የሚጸጸት ይመስለኛል።
እነዚህ ሰው ለማጥቃት የሰለጠኑ የትግራይ ዞምቢዎች የበሰብሰ አካላቸውን፣ የደነዘዘ ጭንቅላታቸውን፣ የታመመ መንፈሳቸውን እየጎተቱ ቢሰነብቱ ህያዋንን ወደ ሞት ቀይረው ሁሉን አበስብሰው ሞትን በማንገስ የሰው ስጋ እየበሉ፣ የሰው ደም እየጠጡ፣ የሰው አጥንት እየቆረጠሙ የጭቃኔ ጥማታቸው ለማስታገስ የሚያስችላቸው ተጨማሪ ጊዜ ያገኙ እንደሆነ እንጂ መሻሻል ወይንም ለውጥ ሊያመጡ አይችሉም።

pm-hmd
በጥልቅ የበሰበሰው የዞምቢዎቹ የወያኔዎች አገዛዝ ተጨባጭ የለውጥ መስፋፋት ይቅርና በውስጥ ለይስሙላ እንኳ ሊታይ የሚችል የለውጥ መንፈስ የሚባል ነገር የለውም። ዛሬ የወላይታው ምስለኔ የበላውንና የጠገበውን ዞምቢ በራበውና ሁሉ ብርቁ በሆነ ሎሌ ወያኔ እንዲተካ ስላዘዘው ለውጥ መጣ ሊባል አይችልም።
ዞምቢ ሄደ ዞምቢ መጣ! በዛሬ የወያኔ ድራማ በጥልቅ የበሰበሱት አሮጌ የወያኔ ዞምቢዎች ዘወር ብለው ህያዋንን የበለጠ የሚያበሰብሱ፤ በቁም የሚገድሉ፤ ስጋ የሚያረክሱ፤ ነፍስ የሚያሳድፉ፤ ፈጣሪ፣ ህሊና እና እውነት የሚባሉ የሰው ልጅ የቆመባቸውን መሰረቶች የማያውቁ፤ የህግ መጣስ፣ የእምነት መጉደል የማያስጨንቃቸው አዳዲስ ዞምቢዎች ተተኩ። የድራማው ደራሲና ዋና አዘጋጅ የጭካንው አገዛዝ ባለቤት ፋሽስት ወያኔ ነው። በድራማው የተለወጥው ጉልቻው እንጂ ማገዶውና የሚጠበሰው ያው ነው።
ትግራይ ዞምቢዎችን የጭካኔ አገዛዝ ለማቆም የበሰበሱ ዞምቢዎች ወደ ዞምቢነት ለመለወጥ በፈቀዱ ሎሌዎች ቢለወጡ ካናቱ የበሰበሰው የዞምቢዎች ስርዓት ሊታደስ አይችልም። ተለወጡ የተባሉት የዛሬዎቹ ሎሌዎች የለውጥ ዘዋሪዎች ሳይሆኑ ወደ ዞምቢነት ለመለወጥ የፈቀዱ፣ የበሰበሰውን የትግራይ አገዛዝ በራሳቸውን ላይ እንዲፈርስ ወደው የገቡ ምርኮኞችና በሌላው መከራና ስቃይ ለመፈንደቅ የተዘጋጁ ሳዲስቶች ናቸው።
ዛሬ ላይ የኢትዮጵያ ችግር የበሰበሰው ዞምቢ ወያኔ ነው። ይህ የኢትዮጵያ ችግር ሳዲስቶችን ከያሉበት እየጠራ አንድ ቀን ባደረ ቁጥር ህያው በሙሉ ተወግዶ የኢትዮጵያም ችግር exponentially እያደገ ያድራል! የኢትዮጵያ ችግር የሚቃለለው የማይታደሰው፤ ሰው ለማጥቃት የሰለጠኑ የትግራይ ዞምቢዎች የገነቡት ፋሽታዊ አገዛዝ ሲወገድ ብቻ ነው።

↧

ሰበር ዜና- የአማራ ወጣቶች በባሕር ዳር እርምጃ ወሰዱ፤

$
0
0

ሙሉቀን ተስፋው

የህዝብን ጥያቄ ወደ ጎን በማሸሽ መልስ የማይሰጠው ወያኔና ብአዴን ትምህርት የሚወስዱበት እርምጃ በባህር ዳር ወጣቶች ተወሰደባቸው። ከቀናቶች በፊት የተለያዩ የማህበር ክፍሎችና ነጋዴዎች ከእስር እንዲለቀቁ የጠየቁት ወጣቶች ለ5 ቀን የሰጡት ማስጠንቀቂያ ምላሽ ባለማግኘቱ እርምጃ መወሰዳቸውን አስታወቁ። እርምጃውም ቀበሌ 03 በሚገኘው የባለስልጣኖች መኖሪያ ኪቢአድ ግቢ እና የባህር ዳር መዘጋጃ ቤት( ከተማ አተዳደር)በተመሳሳይ ሰአት ከምሽቱ 2 ሰዓት የቦንብ ፍንዳታ ተፈጽሟል። ይሄንን ተከትሎ አካባቢው ላይ ከፍተኛ የሆነ ውጥረት ከመንገሱም በላይ አምቡላንሶች ሲሯሯጡ ይታያል።
አሁንም ወጣቶቹ ይናገራሉ የታሰሩ ወንድሞቻችንና ነጋዴዎች እስካልተፈቱ ድረስ ይሄ ጥቃት በሰፊው እና በተጠናከረ ሁኔታ እንደሚካሄድ አስጠንቅቀዋል። ከዚህ በዃላ ሊደረግ የሚገባውን እርምጃና ማስጠንቀቂያ ከቀናቶች በዃላ ያስታውቃሉ።

bahir_dar_city_03

↧

የ”ጥልቅ ተሃድሶ”ድራማ ተጀምሯል!

$
0
0

eprdf
ከክንፉ አሰፋ

በቤተ ሙስና፣ የ”ጥልቅ ተሃድሶ”ው ድራማ ተጀምሯል!  የእርስ በርስ እና ራስን በራስ መተካካት ቧልት እና ፌዝ። 

ከመጋረጃው ጀርባ ስብሃት ነጋ፣ አቦይ ጸሃይ፣ ጌታቸው አሰፋ፣ ደብረጽዮን እና በረከት ስምኦን የሚቆምሩትን ካርታ ሃይለማርያም ደሳለኝ እንደቬጋስ አጫዋች ፊት እያመጣ ይዘረጋዋል። በዲዮጋን ያደረጉት አብዮታዊ እና ልማታዊ “ምሁራን” ፍለጋ ውጤት ነበረው። “የዶክተር ያለህ”  ፍለጋ  ጥቂት ታማኝ አገልጋዮችና ፣ በርካታ ሮቦቶችን አስገኝቷል። “በዲሞክራሲ” በተመረጠው  “የህዝብ ምክር ቤት” የሚኒስትሮቹ ስም ይፋ በሆነ ግዜ፤ ለይስሙላ እንኳን ተቃውሞ፣ አልያም ድምጸ-ተአቅቦ ቢያደርግበት ድራማውን ያሳምረው  ነበር። በሙሉ ድምጽ ጸደቀ ተባለ።  የነዚህ ሮቦቶች ምርጫ የፍልፍሉን ቀልድ ያስታውሳል።

የድሃው ልጅ ለሃብታሙ ልጅ፣ “ምን ያንጠባርርሃል? አንተም የምትበላው አንድ እንጀራ፣ እኔም የምበላው አንድ እንጀራ…” ይለዋል።

የሃብታሙ ልጅ መለሰለት፣  “እንጀራውን ተወውና ስለ ወጡ እንነጋገር?”

ነገሩ ወዲህ ነው። ተጫዋቾች እና አጫዋቾች።  መቼም ሹመኛው ሚኒስቴር ነኝ ብሎ ደፍሮ ቢያወራም፣  ሚኒስቴር ነኝ ብሎ ግን ደፍሮ ውሳኔ አይሰጥም። ውስጡን ያውቀዋል። ሰለዚህ ስለ ተጫዋቾቹ ሳይሆን ሰለ አጫዋቾች እንነጋገር። ሰለ ሚንስትሮቹ  ሳይሆን ስለ ምክትሎቹ እናውራ።  በቀላል አማርኛ “ዶክተሩ” ከላይ ይቀመጣል። ከስር ያለው ካድሬ እንደ እንዝርት ያዞረዋል። ላለፉት 25 አመታት ከዚህ የተለየ ነገር አልነበረም። ወደፊትም ከዚህ የተለየ አይሆንም። ጨዋታው እንደነበረ ይቀጥላል።  የሳሞራ የኑስ የግል ንብረት የሆነው የመከላከያ ሚኒስቴርን ሲራጅ ፈጌሳ ይመራዋል ብሎ የሚያምን ካለ ልጅ ወይንም ጅል መሆን አለበት።  ለውጥ የሚመጣው ጌታቸው አሰፋ የደህነንቱን ስፍራ ለተቀናቃኝ አስረክቦ ቢሄድ ነበር። ወርቅነህ ገበየሁ ወ/ኪዳን የተሰጠውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ነገር ወደ ኋላ ልመለስበት። ድራማውን ስንቃኘው አሁንም በጥልቅ ተሃድሶ ስም ቀልድ ነው የተያዘው።  ይህቺ ሃገር ገና ከአሁኑ የባሰ አንባገነን፣ ሙስና፣ ስቃይ እና አፈና ይጠብቃታል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁንስ እያሳዘኑን መጡ። በእርግጠኝነት ለመናገር ማን እንደተሾመ እንኳን ለፓርላማው ከማንበባቸው በፊት አያውቁትም። በሙስና እና በወንጀል እጃቸው የተጨማለቁ ሰዎችን ጭምር ሹመት አደባባይ ወጥተው ሲናገሩ በኩራት ሳይሆን በፍራት ነበር መሆን የነበረበት። እሳቸው ግን  ትልቅ እና ግዙፍ ለውጥ ነው ብለው ተናገሩ።  በዚህ “ጥልቅ ተሃድሶ” ሕዝባዊ አመጹ  ይቆማል ብለውም ያምናሉ።  በጥይት እና በጭስ ከ700 ሕዝብ በላይ ሲያልቅ የቶክስ ድምጽ አልነበረም ብሎ በአለም አቀፍ ሜዲያ ለሚናገር ምስኪን ጠቅላይ ሚኒስትር ማዘን እንጂ ማውገዝ አይገባም።

የሚኒስትሮቹን ምክር ቤት የእግር ኳስ ቲም አስመሰሉትኮ። የመብት ጥያቄ በመጣ ቁጥር የሚፐወዝ ቲም። ጥያቄው የስርዓት ለውጥ እንጂ የሰዎች መገለባበጥ አይደለም። ካቢኔውን ሺህ ግዜ ቢፐውዙት፤ ለሃገሪቱ ችግር መፍትሄ አይሆንም።   የእግር ኳስ ቲምም ቢሆን እኮ ሲገነባ የእያንዳንዱ ተጫዋች ብቃት እና ስነ ምግባር በባለ ሞያዎች ተገምግሞ ነው። እጃቸው በደም እና በሙስና የጠጨማለቁ ሰዎችን እያመጡ፤  የሕጻን አይነት ድብብቆሽ መጫወት ግዜ ለመግዛት ይረዳቸው ይሆን እንጂ ሕዝባዊ ቁጣውን ሊያቆመው አይችልም።  በዚያ ሰሞን በቴሌቭዥን ቀርበው መንግስታችን ጥልቅ በሆነ ሙስና ተዘፍቋል ያሉን እነሱው ናቸው። ሙስኞቹ አሁንም አሉ።  በጥልቅ ሙስና የተዘፈቁ ሰዎች የችግር እንጂ የመፍትሄ አካል እንደማይሆኑ እያወቁ በህዝብ ላይ ማፌዙ ለምን አስፈለገ? የሚደረገው ድራማ ለመግለጽ የአናንያ ሶሪን ቃል ልዋስ፣  “በዚህ ሁኔታ የሚመጣው በጥልቅ መታደስ ሳይሆን በጥልቅ መበስበስ ነው።”

“ጥልቅ ተሃድሶ” ሲሉን ቢያንስ አዲስ ምርጫ ያደርጋሉ ብለን ጠብቀን ነበር። እውነት ይቀየራሉ ብለን አምነን ተሳስተናል።እነሱ ግን ሕዝብን ሳይሆን ራሳቸውን ነው እይታለሉ ያሉት።

ከተሾሙት ሚንስትሮች ውስጥ ሁለት ፕሮፌሰሮች፣ ሁለት ኢንጅነሮች እና አስራ አራት ዶክተሮች ይገኙበታል። ያልተገነዘቡት ከለውጥ ይልቅ የዶክተር መደርደር ሾተልን ወደ ሰገባ ቁጣን ወደ ትእግስት እንደማይመልሰው ነው። የዶክትሬቱ ዲግሪም እኮ ከየት እንደመጣ ለሕዝብ የተደበቀ ነገር አይደለም።  ግን የዶክተር ያለህ እየተባለ ከየስፍራው ሲለቀም ጀነራል ባጫ ደበሌ ለምን ተረሳ? ምሁር የሚያሰኘው የዲግሪ ወረቀቱን ከሁሉም በፊት እሱ ገዝቷል። ጀነራል የሚለውን የፉገራ ማእረግም ከፕሮፋይሉ ላይ አንስቶት ነበር።  አባ ዱላ ገመዳስ ቢሆን ለአዲሱ ከቢኔ ምን ያንሰዋል? ሳይማር  ዶ/ር አባ ዱላ እየተባለ አይደል የሚጠራው?  ፕ/ር ቆስጠንጢኖስም  ከሴንቸሪ ዩኒቨርሲቲ  ዲግሪ ገዝቷል። እሱስ ቢሾም ምን ይለዋል?

ከሆነ አይቀር ለምን ሁሉንም ሚኒስተሮች በባለ ዶክተር ማዕረጎች አልተኩትም ነበር?  ለወረቀቱም ቢሆን ችግር የለም። የሲቪል ሰርቪስ ወፍጮ ዶክተሩን እና ፕሮፌሰሩን በገፍ እያመረተ ነው። ዘንድሮ ከአንዳንድ የርቀት ትምህርት  ቤቶች በሳምንት ግዜ ፕሮፌሰር መሆን ይቻላል።

በሸገር የሚነገር አንድ ቀልድ አለ። ወያኔ ስልጣን ሲይዝ መጀመርያ የወረረው ወታደራዊ ካምፖችን ነበር። መኮንኖችን ለመያዝ።  ወያኔ ሲወድቅ ደግሞ ተቃዋሚው  ሃይል  መጀመርያ የሚወርረው ሲቪል ሰርቪስ “ኮሌጅ”ን ነው።  እንደ ድንጋይ የሚያስቡትን እያመረተ ሕዝብን የሚፈጅ ተቋም!

መቼም ተቀለደ።  ተቀልዶ ግን አይቀርም።  መዳኛ ያልተገኘለት የህወሃት የፖለቲካ መፍትሄው የህዝብ ድምጽ ነው። የህዝብ ድምጽ ደግሞ በሶስት ቃላት ተገልጿል። ለውጥ!

“መተካካት” እያሉ ጆሮ ሲያደነቁሩ የነበረው ይኽንን ነበር እንዴ? ወርቅነህ ገበየሁ ወ/ኪዳን ከትራንስፖርት ሚኒስትር አንስቶ በወርቅነህ ገበየሁ ነገዮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መተካት?   እርግጥ ነው ፈረንጆቹ በጥቂቱም ቢሆን ተሸውደዋል። አሶሴትድ ፕሬስ ዜናውን ሲዘግብ፣ “The new ministers of foreign affairs — Workneh Gebeyehu, a former transport minister is Oromo, replacing the Tigrayans who previously held the posts.” ኦሮሞው ወርቅነህ ገበየሁ ትግሬ ይዞት የነበረውን የውጭ ጉዳይ ሚንስተር ተክቶታል ብሎናል።

ምነው እነ ደብረጽዮን በወርቅነህ ኦሮሞነት አመረሩ?  እኔ ያልገባኝ ወርቅነህ የኦሮሞ የገዳ ሥርዓት በሚፈቅደው ”ጉዲፈቻ” እና ”ሞጋሳ” ባህል መሰረት ወደ ኦሮሞነት ቀይረውታል እንዴ? ይህ ነገር ግልጽ ይሁን። ካልሆነ የሱን ማንነት የሚገልጸውን ዶክመንት እንልቀዋለን። ጥያቄው ሹመቱ ላይ አይደለም። ሲፈልጉ  ጠ/ሚኒስቴርም ያድርጉት። ግን በኦሮሞ ካርድ አስይዘው ማጫወታቸው ነው የሚደብረው።  የሕወሃት አባል ሆኖ ጨዋታውን በዚያው ካርድ ቢያደርገው ችግር የለውም። ውሸት ሲደጋገም እውነት ይሆናል  ይሚለውን የሂትለሩን ጎብልስ ብሂል የሙጥኝ ያሉም ይመስላል።

የዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት መወገድ ያልተጠበቀ አልነበረም። ከፍተኛ የህወሃት አመራሮች የድል አጥቢያውን ታጋይ፣  ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖምን እንደማይወደዱት በስፋት ይነገር ነበር። ዶ/ሩ ፌስ ቡክ በብዛት ይጠቀማል። ስራውን ብርሃነ ገብረክርስቶስ ስለሚያከናውንለት ለፌስ ቡክ በቂ ግዜ ነበረው።  እታች ወርዶ ከተራው ዜጋ ጋር  በማህበራዊ ሜድያ መነጋገሩ ግን በህወሃት ዘንድ “ፖፑሊስት” የሚል ስያሜ አሰጥቶታል – ልክ እንደ አርከበ እቁባይ። በዘር መስፈርት ብቻ ከመንገድ ተወስዶ  የተቀመጠ ምኒስቴር ነበር። “ይሰረዝ !” ብለው ከፈረዱበት ቆይቷል። ከዚያ በፊት ግን ሁነኛ ሰው መፈለግ ነበረባቸው።  እነሆ አሮምኛ ተናጋሪ ትግሬ ተገኘ። የማኬያቬሊ ሊቅ!

በአሮጌ ጠርሙስ አዲስ ወይን ቢያቀርቡ አንድ ነገር ነው። በአዲስ ጠርሙስ አሮጌ ወይን ቢጨምሩ ደግሞ ሌላ የተለየ ነገር ሊመስል ይችላል። የነሱ ሙከራ ሁለቱም አይደለም።  በአሮጌ ጠርሙስ አሮጌ ወይን ይዘው የተሃድሶ ዘፈን ይዘፍናሉ። በአስተሳሰብም በመልክም አንድ የሆኑ የድሮ አሻንጉሊቶችን  እንደ እላቂ እቃ እያሽከረከሩ ያመጧዋቸውና ተሃደሶ ይሉናል።  ችግሮችን መፍታት ሲሳናቸው ስህተትን እንደመፍትሄ ይወስዱታል።  ሁለት ስህተት ደግሞ አንድ እውነት አይሆንም።  አሸዋወዱንም አላወቁበትም። ዳሩ ሕዝብ ቀድሟቸው ሄዶ እንዴትስ ያታልሉታል?

አካሄዳቸው የሚነግረን ነገር አለ። እነዚህ ሰዎች አሁንም ለለውጥ ዝግጁ አይደሉም።    ሕወሃት ፈጽሞ አይታደስም!

ህወሃት በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ ግድያ፣ ሙስና እና አፈና ከሃገሪቱ አይጠፋም። “አደገኛ ፎርስ ናቸው … ይጥፉ ወይንስ እንጥፋ!” ያለው ማን ነበር?

ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት ችግር የምትወጣው ይህ ፋሽታዊ አገዛዝ ሲጠፋ ብቻ ነው!

↧

በዲሲና አካባቢዋ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወያኔ ወደ አሜሪካ የሚልከውን እንጀራ አልገዛም በማለታቸው በካርቶን የታሸጉ እንጀራዎች ቆሻሻ ማጠራቀሚያ እየተጣሉ ነው

↧
↧

አባ ሰረቀ ከቤተክህነት ፤ እነ ወዲ አድሃኖምም ከቤተመንግሥት ለጊዜውም ቢሆን ገለል ተደርገዋል |ዘመድኩን በቀለ

$
0
0

eprdf

✔ አባ ሰረቀ ከቤተክህነት ፤ እነ ወዲ አድሃኖምም ከቤተመንግሥት ለጊዜውም ቢሆን ገለል ተደርገዋል ። ጌታቸው ረዳን የበላ ጅብም አልጮህ ብሏል ።

✔ አሁንም ” ምስኪኑ ዐማራ ” ከአሽከርነት የዘለለ አቅም እንደሌለውም ቢሆን ከሚታወቀው የህወሓት ” የቁጩ ” የሥልጣን ማዕድ በርግጫ ተገፍትሮ እንዲባረር ተደርጓል ።

በቅድሚያ ዜና ቤተክህነት ። ቀጥሎም ዜና ቤተመንግሥት ።

ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዓመታዊውን የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ መጠናቀቋ ይታወሳል ። የስብሰባውን መጠናቀቅ ተከትሎ ሲኖዶሱ ከወትሮው ባልተለመደ መልኩ አስደማሚ መግለጫም ማውጣቱ ይታወሳል ። ከመግለጫዎቹም መሃል መንግስት ከተቋዋሚ ፓርቲዎች ጋር በሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በአስቸኳይ ውይይት ይጀምር ማለታቸውና ” በመላው ዓለም የሚገኙ የስብከተ ወንጌል ሃላፊዎች ስለ ኢትዮጵያዊነት በአዲስ መልኩ ለምእመናን እንዲሰብኩ ይደረግ የምትል ጭንቅ ያላት ዓረፍተ ነገር የያዘች ሀረግ መገኘቷ አግራሞትን ፈጥሯል ። ” የሲኖዶሱ አባላት ተቃዋሚዎች እግር እስኪያወጡ ጠብቄ እቆርጣቸዋለሁ እያለ ህወሓት ሲፎክር እዚያው 4 ኪሎ ቤተመንግሥቱ አጠገብ ቁጭ ብለው ተቃዋሚዎቹ እግር አይደለም ገና ስም ሲያወጡ አየተቀጩ ሲገደሉ ፣ ሲታሰሩ ፣ ሲሰደዱ ዐላየንም አልሰማንም ሲሉ ከርመው አሁን ተቃዋሚዎች ከምድረ ኢትዮጵያ ድራሻቸው ከጠፋ በኋላ በ11 ኛው ሰዓት ቅዱስ ሲኖዶሱ ህወሓት በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ቢሮ ከሌላቸው ተቃዋሚዎች ጋር ተወያዩ ማለታቸው አስገራሚም አስቂኝም ሆኗል ። በሌላም በኩል ይሰበክ የተባለው ኢትዮጵያዊነትም ቢሆን እስከዛሬ እንዲቀበርና እንዳይነገር የመከላከያ አጥር ሲበጅለት የከረመ ጉዳይ ሲሆን በመግለጫው ውስጥ የተሰነቀረችዋ ” ከአንዳንድ ቦታዎች የተፈናቀሉ ወገኖች ስላሉ ” የቀድሞው የመረዳዳትና የመከባበር መንፈስ የነበረበት ኢትዮጵያዊነት በደንብ ይሰበክ ሲሉ የስጋታቸው ምንጭ ከወዴት እንደሆነ ጠቁመዋል ። ወይ መፈናቀል አለ ዐማራ ።

aba

በሌላ ዜናም ” አባ ሰላማ ” የተባለውን የክህደት ማስተላለፊያ ብሎግ በዋናነት ከቂርቆሱ መምህር ሰሎሞን ጋር በማዘጋጀት ቅድስት ቤተክርስቲያንን ሲያደሙ የነበሩት መናፍቁ ” አባ ” ሰረቀብርሃን ወልደ ሳሙኤል ከተመደቡበት የቅዱስ ፓትርያርኩ ልዩ ፀሐፊነት ወንበር መወገዳቸው ታውቋል ። ቀደም ካሉት ጊዜያት ጀምሮ አባ ሰረቀ የአስተዳደር ብቻ ሳይሆን ” እመቤታችን ጥንተ አብሶ አለባት ” የሚል መጽሐፍ እስከማሳተም የደረሰ የሃይማኖት ችግርም ያለባቸው ሰው በመሆናቸው በየትኛውም የቤተክርስቲያኒቱ የአመራር ቦታ መቀመጥ የለባቸውም በሚል በብዙ ብንሞግትም ሰሚ አለማግኘታችን ይታወቃል ። የዘር ፖለቲካው ጉዳይ ልክ እንደ ቤተመንግስቱ ሁሉ ቤተክህነቱንም ከእግር ጥፍሩ እሰከ ራስ ፀጉሩ ድረስ የተቆጣጠረው በመሆኑ ሰሚ ጠፍቶ ከላይ እስከታች እስከ አሁን ድረስ ዘረኞች መቅደሱንም ቢሮውንም ተቆጣጥረው ቤተክርስቲያኒቱን የፊጥኝ አስረው በቁሟ አጥንቷ እስኪቀር እየጋጧት መሆኑ ይታወቃል ።

አባ ሰረቀ አሁን ከቦታቸው ለመወገዳቸው የተሰጠው ምክንያት የአቅም ማነስ፣ አለመታዘዝና ችኩልነታቸው እንደሆነ የተነገረ ሲሆን ፤ ምንፍቅናቸውና ሌብነታቸው ግን ሳይጠቀስ ታልፈዋል ። እንግዲህ ልብ በሉ አባ ሰረቀ በዚህ ሁኔታም ቢሆን ለጊዜው ከዚህ የኃላፊነት ስፍራ መነሳታቸውን የሰማን ቢሆንም ፤ ይህን ዜና በሰማን ማግስት ግን ሰሞኑን ይህንኑ የአቅም ማነስ፣ አለመታዘዝና ችኩልነታቸውን እንደተሸከሙና እሽኮኮ እንዳሉ ከጥቂት ቀን በኋላ በሌላ ከፍተኛ የቤተክርስቲያኒቱ የስልጣን እርከን ላይ መሾማቸውን እንሰማለን ። ቱ ምን አለ በሉኝ ደግሞ ይሄ ባይደረግ ታዘቡኝ ።

በሌላም በኩል ደግሞ ከገደል አፋፍ የቆመው የጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ መንግስትም በዛሬው ዕለት ወጥ የማያጣፍጠውን ጉልቻ መቀያየሩን በይፋ አውጇል ። 6 አቶዎችን አንድ ወይዘሮና 12 ደክተሮችን 2ፕሮፌሰሮችና 1 ኢንጅነር “አዲሱ የህወሓት ጉልቻዎች” በመሆን እንዲያገለግሉ በዛሬው ዕለት ተመርጠዋል ። ህወሓቶች ከዚህ ቀደም የፓርቲውን ትእዛዛት እስከፈፀመ ድረስ ተሿሚው ለምን ዘበኛ አይሆንም ችግር የለውም በማለት ብዙ ሺህ ሱፍ የለበሱ መሃይሞችን በመሾም ዜጎች በጠራራ ፀሐይ እንዲጨፈጨፉ ማድረጋቸው ይታወሳል ። እናም አሁን ከዚህ ቀደም የተማረ ሰው አለርጂካቸው የሆኑት ህወሓቶች የአራዳ ልጆች “የተማረ ይግደለኝ ” ሲሉ በመስማታቸው እነሆ ይኸው አሁን ዛሬ የእስከአሁኖቹን ዘበኞች ከመጠሪያ ስማቸው በፊት ፕሮፌሰር ፣ ደክተሮችና ኢንጅነሮች የሚል የቅጥያ ማእረግ የተሰጣቸውን ” የተማሩ አዳዲስ ገዳይ” ግለሰቦችን ወደ ስልጣን በማምጣት ስልጣኑን በሙሉ በዶክተሮችና ኢንጅነሮች አጥለቅልቃ ጉድ አስብላናለች ። አዲሶቹ ምሑራን ተሿሚዎች ” በየተማረ ይግደለኝ ” መርህ አሟሟታችንን ለማሳመር ይጥራሉ ተብሎም ይጠበቃል ። ባልተማሩ መሃይሞች እጅ ከመሞት እስቲ በተማሩ ፕሮፌሰሮች እጅ መሞት ምንሸምን እንደሚል በጥቂት ቀናት ውስጥ የምናየው እንደሚሆን እንጠብቃለን ። እንደሚገመተው እነዚህ ምሑራን የቀደሙ መሃይማን ” የጀመሩትን የሚጨርሱ ” ይሆናሉ ተብሎም ይጠብቃል ። የተማረ ይግድለን ይሏችኋል ይኸው ነው ። ታድለን ።

በዚህ አዲስ ካቢኔ ውስጥ አንድ ዓመት ሙሉ የዘለቀ ተቃውሞ በማድረግ በሺህ የሚቆጠሩ ንፁሐን የኦሮሞ ተወላጆች በግፍ የተጨፈጨፉባቸው የኦሮሞ ልጆችን አፋቸውን ለማስያዝ በሚመስል መልኩ በዛ ያለውን የስልጣን እርከን ኦሮሞ የሆኑም ሆነ የኦሮምኛ ስም ለያዙ ፎርጅድ ኦሮሞ ለሆኑ ግለሰቦች እንዲሰጥ ተደርጓል ። የፈረደበት ዐማራ አሁንም በደሙ በመሠረታት ሀገር ከስልጣኑ ማዕድ ተገፍቶና ተገፍትሮ የበይ ተመልካች እንዲሆን ተፈርዶበታል ። ለዓመታት የዘለቀውና በሺህዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን የኦሮምኛ ተናጋሪዎችን ሲያስፈጅ ደማቸውንም በከንቱ ሲያሰፈስስ የከረመውን ውጤት አላባ የነበረውን የኦሮሞውን የለውጥ እንቅስቃሴ ፤ በጥቂት ወራት ትግል የህወሓትን ጥርስ የነቀነቁት ዐማራዎች ገዢውን ፓርቲ አስደንግጠውና ” ሱሪያቸውንም አስረጥበው ” ለይስሙላም ቢሆን አሁን ይኸው ኦሮሞዎቹን ወንድሞቻቸውን ምንም እንኳን በሙሉ ኃይል የማያዙበት ሹመት ፤ ወደ አርቴፍሻሉና ” የዛፍ ላይ እንቅልፍ ” ወደ ሆነው የህወሓት የኃይል ሚዛን ማስጠበቂያ ወደሆነው የስልጣን ዙፋን አስጠግተዋቸዋል ። ከ21ዱ አዳዲስ ጉልቻዎች ውስጥ 3 ጉልቻዎች ብቻ የዐማራው ብሔር ወኪል ተደርገው የተሾሙ ቢሆንም ፤ እነዚህ ዐማራ ናቸው ተብለው ከተሾሙት ውስጥም የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ተብለው የተሾሙት ” ፕሮፌሰር ይፍሩ ብርሃነ ” የተባሉት ግለሰብ ከወዲሁ ዐማራ አይደሉም ” ብርሃነ ” ብሎ ዐማራ የለም ትግሬ እንጂ የሚል ተቃውሞ እየቀረበባቸው ነው ። ህወሓት በህይወት እስካለች ድረስና በመርፌም ሆነ በኪኒን የዐማራውን ብሔር ከኢትዮጵያ ምድር እስክታመናምን ድረስ በዋዛ የጤና ጥበቃ ሚኒስትርነቱን ስፍራ እንደማትለቅና ለሌላ ብሔር አሳልፋ እንደማትሰጥም እየተነገረ ነው ። ሌላው የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሃላፊ ሚንስትር ሆነው የተሾሙት አቶ ከበደ ጫኔም ቢሆኑ ለዐመል ታህልም ቢሆን ይህችንም ስልጣን ያገኙት ” በግፍ ” ከዐማራ ክልል የተፈናቀሉ የተባሉ የትግራይ ተወላጆችን መቀሌ ድረስ በመሄድ በዐማራ ስም ድንጋይ ተሸክመው ይቅርታ በመጠየቃቸው ለውለታቸው የተሰጣቸው ስፍራ እንጂ በችሎታም ሆነ ብሔረሰቡን ወክለው እንዳልሆነ እየተነገረ ነው ። ለዚህ ነው አብዛኛው የመንግስቱ ደጋፊዎች ” ዐመት ሙሉ እየሞተ የሚጮኸው የኦሮሞው ጥያቄ ህጋዊና ትክክልም ነበር ” ። ሲገሉኝ ዝም ብዬ እንደ ኦሮሚያ ልጆች አልሞትም ፤ ስትገድሉኝም እገድላለሁ ፣ ስትተኩሱም እተኩሳለሁ ብሎ የትግሉን አቅጣጫ በፍጥነት ዙሩ ከርሮ ህወሓት የመቃብር አፋፍ ላይ ቆሞ ግብአተ መሬቱን እንዲጠባበቅ ያደረገው አማራው ግን ህገወጥ ድርጊት ነው የፈጸመው ። ለምን ዝም ብሎ እንደኦሮሞ ልጆች አልሞተም ተብሎ ተከሳሽ መሆኑ ይታወቃል ። ከዚህም የተነሳ የዐማራ ልጆች ትምህርት ሚኒስቴር እንዳይማሩ ፣ ሌሎቹም ባለስልጣን እንዳይሆኑ ተፈርዶበታል ።

አሁንም ቢሆን ህወሓት ቁልፍ የሆኑ ቦታዎችን ጠርቅማ እንደያዘች ነው ። የውጭ ጉዳዩን ዘርፍ እና የደም ስር የሆነውን የገንዘቡንና የፈረንካውን ደግሞም የቀርሺና የጨላውን ስፍራም አልለቀቀችም ። ከወራት በፊት የአያታቸውን ስም” ነገዎ” አድርጋ ለኦሮሞ ህዝብ ልትሾምበት የነበረውን አቶ ወርቅነህ ገበየሁን አሁን የጭንቁ ጊዜ ሲመጣ ያለምንም እፍረት ” ነገዎ ” የነበረውን የአያቱን ስም ወደ ቀድሞው ገብረኪዳንነት መልሳ በመቀየር ብሔሩን ” ትግሬ ― ኦሮሞ ” በማድረግ ኦሮሞ የውጭ ጉዳይ ሚንስትርነትን ስልጣን አገኘ ለማስባልና ” የኦሮሞዎቹን ” አፍ ለማስዘጋት ቀሽም ድራማ በመሥራት በአዲስ ምእራፍ ብቅ ብላለች ። ሌላው የትምህርት ሚኒስቴር አሁንም ትውልድ እየገደለ እንዲቀጥል የተፈረደበት ይመስላል ። የጠቅላይ ሚኒስትርነትና የፕሬዝዳንትነቱ ቦታ ብቻ ሲቀራቸው በዘመነ ኢህአዴግ እንደ ” ማያ ” ራሳቸውን በመቀያየር በብዙ የኢህአዲግ “የሺ ― ሞት ” እርካብ ላይ በማንጠላጠል እንደ ፔንዱለም ስታወዛውዛቸው የከረመችውን ዶ/ር ሺፈራውን አሁን ደግሞ ቀድሞም የሞተውን የትምህርት ዘርፍ በደንብ እንዲገድለው በማሰብ የትምህርት ሚኒስቴርን አሁንም በአፈር መልሰውበት መቃብሩን በደንብ እንዲሠሩ አዲስ ስልጣን ሰጥታ ሹማቸዋለች ። ለየት የሚለው ነገር የባህል ሚኒስቴር ስፍራውን ከሙስሊሞችና ከፕሮቴስታንቶች በቀር እንዲመሩት የማትፈቅደዋ ህወሓት አሁን ለእምነታቸው ኦርቶዶክሳዊ መሆን ማረጋገጫ ባይገኝለትም ብቻ ስማቸው ኦርቶዶክስ የሚሸት ሴት ሚኒስትር ተሹመዋል ብዬ ፈገግ ከማለቴ ፤ ተሿሚዋ አዲሷ ሚንስትር ዶ/ር ሂሩት ወ/ ማርያም በአዲስ አበባ የኒቨርሲቲ በሥነ ልሣን ትምህርት ክፍል ውስጥ መምህር የነበረች እና በዩኒቨርሲቲው የፀረ ሙስና ኮምሽን መኮንን በነበረች ጊዜም ስልጣኗን ተጠቅማ ዶር ግርማ አውግቸውን ያሳሳረችው ሴት እንደነበረች ፣ በዚህ ትጋቷም ምክትል ፕሬዘዳንት ሆና ተሹማ እንደነበር ፡፡ ምክትል ፕሬዘዳንት በነበረች ጊዜም ብዙ ክፉ ሥራዎችን አንደሠራች ፣ በዚህ የተናደዱ ሠዎች የዶሯን ኢሜል ሃክ አድርገው ከትዳሯ ውጭ ከሦስት የዩኒቨርሲቲ ምህራን ጋር የነበራትን የወሲብ ግኑኝነት ይፋ አውጥተውባት ልታብድ ትንሽ ቀርቷት እንደነበር፡፡ በዚያን ወቅት ከተማሪ ጀምሮ የወሲብ ቅሌቷን አንብቦ ሁሉም ይስቅባት እንደነበር ፤ በዚያም ኢሜል የተነሳ ሁለቱ አፍቃሪዎቿ ከትዳራቸው እንደተፋቱ ፣ አሁን የደረሰችበት ባይታወቅ እርሷም ወደ ፍቺ ሄዳ እንደበርና በየኒቨርሲቲው ውስጥ ብዙ መምህራንን ለኢህአዴግ አባልነት ትመለምል የነበረች ሴት መሆኗን የሚያሳዩ መረጃዎች መውጣት ጀምረዋል ። እናም ለትዳሯ ያልታመነች ሴት እንዴት ለኢትዮጵያ ሀገሯ የሚታመን ሥራን ትሠራለች ተብሎ ህወሓት እንደመረጣት ከህወሓት በቀር የሚያውቅ ማንም የለም ።

የሆነው ሆኖ የዱሮውም ሆነ አዲሱ ካቢኔ ያው ዞሮ ዞሮ ከኋላው እጅ ጠምዛዡ ህወሓት ናት የሚሉ ተከራካሪዎች እንዳሉት ሁሉ ፤ አይ ምን ሲደረግ በአሁኑ ካቢኔ ላይ እንኳን የምንታማበት አንዳችም ምክንያት የለም ። ከቢኔው ኦሮሞ 9 ፣ አማራ 3 ፣ ደቡብ 5 ፣ ትግራይ 2 ፣ አፋር 1፣ ሶማሌ 1 ነው አድርጎ ነው መርጦ የሾመው ። እናም አሁን የምንወቀስበት አንዳችም አይነት ምንም ምክንያት የለም ይላሉ ። እንዲያውም ይላሉ ህወሓቶች በፊት ከነበሩት 4 የዐማራ ባለስልጣናት ላይ አሁን አንድ ኦሮሞም 9 ተጨምሯል ይሉና በዚህም መሰረት አጠቃላይ የሚኒስትሮች ስብጥር ሲታይ ኦሮሞ 9 ፣ አማራ 7+1 ፣ ደቡብ 6+1 ፣ ትግራይ 4 ፣ አፋር 1እና ሱማሌ 1 ቦታ አግኝተው መንግሥት ከሚፈልገው 30 የሚንስትርነት ስፍራዎች ውስጥ ሕወሓት ያገኘው 4 ቦታዎችን ብቻ ነው ። እናም ህወሓት እጅግ ተፈላጊ የሆነውን የጠቅላይ ሚኒስትርነትን ስፍራ ለደቡቡ ሰው ለፕሮቴስታንቱ ኃይለማርያም ደሳለኝ ፣ የምክትል ጠቅላይ ሚንስትርነቱን ስፍራም ለሙስሊሙ ለዐማራው ተወላጅ ደመቀ መኮንን ፣ መከላከያ ሚንስትርንም የስልጤው ተወላጅ ሲራጅ ፈርጌሳ እንዲመሩት አድርገን ባዶ እጃችንን ቀርተናል። እናም ከእንግዲህ ወዲህ የህወሓት የበላይነት አለን? አገሪትዋን የሚመራትስ ህወሓት ነውን? ስለ እውነት እንነጋገር ከተባለ እውነት እነዚህ 4ቱ የህወሓት ተወካዮች የተቀሩትን 26 ሚኒስትሮች ላይ በምን አቅማቸው ጫና ያሳርፋሉ ? በማለት በሳቅ የሚያፈርስ ኮሜዲያቸውን ሊለቁብን ሲሞክሩ ይታያሉ ። እውነታው ግን የሌላ ብሄር ባለስልጣናት ገሚሶቹ የብሔሩ ስም የተሰጣቸው የትግራይ ሰዎች ሲሆኑ እንደ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አይነቶቹ ባለስልጣናት ደግሞ ለላንቲካ የተቀመጡና አዛዦቹ በአማካሪና በምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ማእረግ በዙሪያው ሰንገው የያዙት እነ ደብረጽዮን መሆናቸው ይታወቃል ። እንዲያው ማን ይሙት በ ” ዶር ጀነራል ሰሞራ የኑስ የሚመራውን መከላከያና 60ዎቹን የመከላከያ የትግራይ ጀነራሎች ስልጤው ሲራጅ ፈርጌሳ ነው የሚያዛቸው ሲባል እንዴት አድርገን ነው ለማመን የምንገደደው ። ” ቀልዱን ተይ ” አለ አዝማሪ ።

በሌላ በኩል አሁንም ቤተክህነቱም ሆነ ቤተመንግስቱ በአንድ ብሔር የበላይነት እየተመራ መሆኑ ግልጽ መሆን አለበት ። ከሚንስትርነት እስከ ተላላኪነት ድረስ ማለት ነው ። በቤተክህነቱ አንድ አባ ሰረቀን ብቻ በማስወገድ ለማስተንፈስ መሞከሩ ጊዜው ያለፈበት ቲያትር ነው ። አሁን የተሾሞት ወደ ስልጣን ሲመጡ የተነገረን የቀድሞዎቹ የአቅም ማነስና የአፈጻጸም ችግር ስላለባቸው ነው ተብሎ በግልፅ መነገሩ ይታወቃል ። ሆኖም ግን እነዚህ በደካማነታቸው ተከሰስው ከስልጣን የተባረሩት በሙሉ በሌላ ሹመት በጓሮ በኩል ሙሉ ስልጣን ይዘው ቤተመንግስት ነው የገቡት ። ኤርትራዊውና ነገር ግን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሆን የገለግሉ የነበሩት የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ቴዎድርሶ አድሃኖም ምንም እንኳን በትግራይ ተወላጁ የኦሮሞ ቅብ በሆኑት አቶ ወርቅነህ ገበየሁ ቢቀየሩም ፤ እኚህ “ትንሿ ኢትዮጵያ” በደካማ አመራራቸው ምክንያት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ያስወገደቻቸው ግለሰብ ፍጥጥ ብለው ዐይናቸውን በጨው በመታጠብ ለዓለም ጤና ድርጅት ጄኔራል ዳይሬክተርነት እየተወዳደሩ መገኘታቸውን ባሰብኩ ጊዜ ስለእሳቸው እኔ ተሸማቅቄ ማለቄ ያሳዝነኛል ። በሳቅ !!

ቤተክርስቲያንም አባ ሰረቀን እንዲህ አሸማቅቃ በደብዳቤ ከማይመጥናቸው ስፍራ ማንሳቷን ብትነግረንም በቅርብ ቀን ልክ እንደ ህወሓት ሁሉ የአባ ማትያስ አገዛዝም እኚህኑ ሰው በሌላ ከፍ ያለ ሹመት መልሶ በሚገርም ደብዳቤ ሥልጣን እንደሚሰጧቸው ይጠበቃል ። እስከዚያው በየአድባራቱ የተሾሙት ሌቦች ለጊዜው ከስልጣናቸው ገሸሽ የሚያደርግ ደብዳቤ እስኪደርሳቸው ድረስ ዘረፋውን አጧጡፈው እንደሚቀጥሉ ይጠበቃል ።

ሻሎም ! ሰላም !

ዘመድኩን በቀለ ነኝ
ጥቅምት 22 /2009 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ

↧

የትግራዩ ነጻ አውጪ መንግስት በጎንደርና ጎጃም አማራ ላይ የተጠናከረ ጥቃት ከፍቷል

$
0
0
File Photo

File Photo

አለበል አማረ እንደዘገበው

የህወኃት አገዛዝ ራሱን በኮማንድ ፖስት ካደራጀበት ጊዜ ጀምሮ በአንዳንድ የአማራ ከተሞች፤ ህዝቡ ለወሳኙ ተጋድሎ ለሚያደርገው ሁለገብ ዝግጅት የተፈጠረውን ክፍተት ተጠቅሞ ባለፉት የተጋድሎ እንቅስቃሴወች እንቅስቃሴውን በማስተባበርና በመምራት ወሳኝ ያላቸውን ወጣቶች፤ በክልላችን በሚኖሩ የትግራይ ተወላጆችና በተወሰኑ የኛወቹ አጋሰሶች ጥናት አካሂዷል።
ይህንን ጥናት ታሳቢ በማድረግም በያዝነው ሳንት ጀምሮ የተጠናከረ ግን ያልተሳካ ጅምላ አፈሳ በማድረግ ላይ ነው።
ጀግኖቹ የጎንደርና የጎጃም አማራ ወጣቶች በያሉበት በቻሉት ሁሉ እየተፋለሙ ነው፤ በአንዳንድ አካባቢወችም ድንቅና ግሩም የሆኑ አኩሪ ታሪኮች እየተሰሩ ነው።
በዚህ በያዝነው ሳምንት በአንዳንድ አካባቢወች የተወሰነ ወጣት በህወኃት የአፈና ኃይሎች ተይዘው በኮማንድ ፖስቱ እስር ላይ የሚገኝ ቢሆንም ( ኮማንድ ፖስቱ የራሱ እስር ቤቶች መመስረቱ ታውቁአል) አብዛኛው ወጣት ግን ጫካ መግባቱ ተረጋግጧል።
እየተፈፀመ ያለውን ጥቃት ለማክሸፍና ወደ ተሟላ አጥቂነት ለመሸጋገር የአማራ የጎበዝ አለቆች እያካሄዱት ያለውን ተጋድሎ እንዲሁም በውጭ ያሉ የተጋድሎ አክቲቪስቶች የተቀናጀ የተጋድሏቸው እንቅስቃሴወችን በማድነቅና የሚካሄዱት የተጋድሎ ስራወች እንደተጠበቁ ሁነው፤
ከማያቸውና ከምታዘባቸው ይበልጥ ልንረባረብባቸው፤ ትኩረት ልንሰጥባቸው የሚገቡን ጉዳይዮችን ለማጋራት ፤
√ የአማራ ወጣት ገዳይ ጠላቶቹን በዱር በገደሉ በከተማ በገጠሩ አምርሮ እየተጋደለ ይገኛል፤ ወጣቱ የሚታገለው ከተደራጀ፣ የፋይናንስና የማተሪያል አቅም ካለው ጨቁአኝ ኃይል ጋር በመሆኑ ተመጣጣኝ ነገር ኣንኩኣን ማቅረብ ባይቻልም አቅም የፈቀደውን ያክል ድጋፍ ማግኘት ይገበዋል፤ ስለሆነ በአማራ ተጋድሎ ስም ግልፅና አስቸኩኣይ የሃብት (ገንዘብ) ማሰባሰብ ስራ በዘመቻ መከናወን አለበት። ይህንንም በተለይ በውጭ በስራው እየተሳተፉ ያሉ ወጣቶች ተቀዳሚ ተግባራቸው ማድረግ አለባቸው።
√የተጋድሎው አዝማሚያ ሁለገብ ስራው እንደተጠበቀ ሁኖ፤ በበረሃ የመደራጀትና የመዘጋጀት ስራ ትኩረት የሚያስፈልገው ይመስላል። ይህን ስራ በተወሰኑ አካባቢወች ብቻ አለመወሰን፣ የሰው ኃይል ችግር እስከለለ ድረስ የበዙ መሬቶችን መጠቀም ለተጋድሎው ስራ ጊዜ ያሳጥራል ኪሳራ ይቀንሳል በአንጻሩ የጠላትን ኃይልና ሃሳብ ይበታትናል።

√የአማራ ህዝብ በቀንደኛ ጠላቱ ህወኃት ላይ ራሱን የመካለከል ተጋድሎ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ አሁን እስካለንበት ጊዜ ድረስ የትግራይ ተወላጆች በቀጥታ በመሳተፍም ሆነ የመረጃ ምንጭ በመሆን ከባድ ጉዳት እያደረሱብን ነው፤ ስለሆነም እነዚህን የጠላት አቅሞች መስበርና የጥንካሬ ምንጭ እንዳይሆኑ የማድረግ ስራ በቁርጠኝነት መስራት ቀጣይ መሆን አለበት፤ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የራሳችን አጋሰሶችንም ለይተን የማውገዝና በማይታረሙት ላይም አስተማሪ ኣርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል።
√ለአማራው ተጋድሎ እንቅፋት ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ የኃይማኖቶቻችን ሃላፊወችና መሪወች ናቸው። የአማራ ህዝብ ለየኃይማኖቱ በጥብቅ አማኝ መሆኑን የተረዳው ህወኃት ይህንን ክፍተት በሚገባ በመጠቀም ከባድ ጉዳት እንዲደርስብን እያደረገ ነው። ጥቂት የሃይማኖት አባቶች እውነተና አባትነታቸውን እያስመሰከሩ ያሉ ቢሆንም አብዛናው የኃይማኖቶቻችን መሪወች የፖለቲካ ሹመኞች መሆናቸው ከተረጋገጠ ቆይቷል፤ በተግባርም የህወኃትን ስርዓት ዕድሜ ለማርዘም ተግተው የሚሰሩ ቅጥረኞች ናቸው። የአማራ ወጣት እምነቱን እና መሪወቹን ለይቶ መመልከት አለበት እላለው። እምነቱን ማመን ይኖርበታል ለህወኃት ዕድሜ ምርዘም የሚሰሩ መሪወቹ ግን ህዝቡ የከዱ ስለሆኑ ማመን የለበትም።
ውድማው ይለቅለቅ ይሰጣበት ነዶ፣
የኛ ተራ ቀርቷል ያ ሂዶ ያ ሂዶ፡፡

↧

የለንደኑ ጉባዔ አስተባባሪዎች ተናገሩ |“ተጨበጨበ ማለት ተስማማ ማለት አይደለም…ሃገር ገንጣይ ኦሮሞ ሳይሆን ወያኔ ነው…ጉባዔው ላይ የተነገረው ማህበሩንም ጉባዔተኛውንም አይወክልም”|ሊደመጥ የሚገባው

$
0
0

hiber
“…የለንደኑ ጉባዔ ዓላማ ያ በግለሰቦች የተባለው አይደለም። እሱ የነሱ ሀሳብ ነው ። የኦሮሞ ክልል የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች በአንድነት የሚኖሩበት ነው።ኢትዮጵያ የሚለው ትክክለኛ ቦታ ኦሮሚያ ነው ከ11 ሚሊዮን በላይ ልዩ ልዩ ብሄሮች ይኖሩበታል። ጉባዔው ላይ የተነገረው ማህበሩንም ጉባዔተኛውንም አይወክልም። ሕዝቡ ማን አቅም እንዳለው መሬት ላይ አለውን እውነታ ያውቃል …”
– አቶ ጌታቸው ወየሳ የኦሮሞ ዓለም አቀፍ የሕግ ባለሙያዎች ማህበር ሊቀመንበር ለህብር ከሰጡት ቃለ መጠይቅ (ቀሪውን ያዳምጡት)

“…ኦሮሞ አይደለም አገር በመገንጠል የሚታወቀው። ወያኔ ነው አገር ገንጣይ ጎሰኛ ስለ ጉባዔው ግለሰቦች ያራመዱት አቋምን ሆን ብሎ ለራሱ እንደሚያመቸው ተጠቅሞ አራግቦታል በሁለት ቀኑ ጉባዔ የተነገሩ ጠቃሚዎቹ ንግግሮች አልተጠቀሱም…ተቃዋሚዎችም ሆኑ ግለሰቦች ሀላፊነት የማይሰማው ንግግራቸውን በተመለከተ ግን …” አቶ ሁንዴ ዱጋሳ የኦሮሞ ዓለም አቀፍ የህግ ባለሙያዎች ማህበር ጸሐፊ(ቀሪውን አዳምጡት)

↧

9 ለኩላሊት ጤና ወሳኝ የሆኑ ምግብና መጠጦች

$
0
0

Garlic Cloves
በሊሊ ሞገስ – zehabesha.com

ወሳኝ ከሚባሉ የሰውነት አካላት አንዱ የሆነው ኩላሊት ስራው ሲስተጓጎል ለከፍተኛ ህመም እና ስቃይ እንዲሁም ከፍተኛ የህክምና ወጪ ይዳርጋል፡፡ ‹‹በኩላሊት ህመም ጋር የሚኖሩም ሆኑ ጤነኛ ሰዎች ከምግብ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ጤናማ ቢያደርጉ  ከብዙ የኩላሊት ችግር ይድናሉ›› ሲሉ የሚመክሩት ባለሞያዎች ለኩላሊት ጠንቅ የሆኑ ምግብና መጠጦችን እንዲሁም የኩላሊት ህመም ያለባቸው ሰዎችም ሊመገቧቸው እና ሊርቋቸው የሚገቡ ምግቦችን ይፋ አድርገዋል፡፡

ኩላሊት ጤናን ጉዳት ላይ የሚጥሉ በርካታ ከዘር የሚወረሱም እና ከአኗኗር ስልት ጋር ተያይዘው የሚመጡ ምክንያቶች አሉ፡፡ ከኑሮ ዘዬ ምክንያቶች የሚመደቡት አመጋገብ፣ አልኮል መጠጦች እና ሲጋራ ላይ ጥንቃቄን በማድረግ እስከ 60 በመቶ የሚደርሰውን የኩላሊት ጉዳት ማስቀረት እንደሚቻል በአሜሪካ ጆርናል ኦፍ ኪድኒ ዲዝዝ ላይ ባለፈው ዓመት ታትሞ የወጣ ጥናት ይገልጣል፡፡ በጆንሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ በዶ/ር አሌክስ ቻንግ መሪነት በተሰራው ጥናት የተጠበሰ እና ጥሬ ሥጋን፣ ጣፋጭነት የበዛባቸውን ምግቦች፣ ቅባት የበዛባቸውንና የአስር (ፋይበር) ይዘታቸው አነስተኛ የሆኑ ምግቦች እንዲሁም አትክልትና ፍራፍሬ የራቀው አመጋገብ የሚከተሉ ሰዎች ከሌሎች በብዙ እጥፍ ለኩላሊት ችግር የተጋለጡ መሆናቸው ተመልክቷል፡፡ ከእነዚህ የአመጋገብ ልምዶች ጋር ከልክ ያለፈ ክብደት ካለ፣ አልኮል መጠጥ የሚያዘወትሩ ከሀነ እና ሲጋራንም ወዲህ በል የሚሉ ከሆነ ኩላሊትዎን በገዛ እጅዎ እያጠፋ ነው ሲሉ የጥናቱ ባለሞያዎች አመልክተዋል፡፡ በዚህ መነሻነትም በዚህ የጥናት ቡድን የተለያዩ ጥንቃቄ የሚደረግባቸውን የምግብ አይነቶች ጥቆማ ሰጥተዋል፡፡ ጥቆማው በዚህ ጥናት ብቻ ሳይሆን በሌሎች ተመሳሳይ ጥናቶች ውስጥም ተካትቷል፡፡

ሥጋ

ሥጋ ከኩላሊት ፀሮች አንዱ ተብሎ ይነሳል፡፡ መቼም ይህን አንቀፅ ማንበብ ገና ሳይጀምሩ ስጋ ላይ ስዘምት ቅር ሳይልዎት አይቀርም፡፡ ኢትዮጵያውያን ለጥብሱም ለጥሬውም ስጋ ያላቸውን ፍቅር ያየ ስጋ ይቅርብዎት ብሎ መምከሩ ሳያስቸግር አይቀርም፡፡ ነገር ግን ለዘላቂ ጤና ሲባል በሙሉ መተውም ባይሆን መጠኑን በእጅጉ መቀነስ አስፈላጊ መሆኑን የስነ ምግብ ባለሞያዎችም ሆኑ የኩላሊት ስፔሻሊስቶች ይመክራሉ፡፡ በማዮ ክሊኒክ ባለሞያዎች የተሰራ ጥናት እንዲሁም በአውሮፓ ጆርናል ኦፍ ኒውትሪሽን ለይ የታተመ ምልከታ በሥጋ የበለፀጉ ምግቦችን የሚደጋግሙ ሰዎች የኩላሊት ጠጠር መፈጠርን ያበረታታሉ፡፡ በኩላሊት የማጣራት ስራ ላይም ከፍተኛ ጫናን እንደሚፈጥሩ አመልክተዋል፡፡ በመሆኑም አብዛኛው ሰው ሆኖለት በየቀኑ ሥጋ የሚመገብበት ሁኔታ ባይኖርም በተገኘም ጊዜ ተመራጭ የምግብ አይነት ማድረጉ ለኩላሊት ጤና ሲባል ብቻ ሳይሆን ለአጠቃላይ የልብና የደም ቧንቧዎች ሰላም ሲባልም ተመካሪ አይደለምና ይህን ማስተዋል አስፈላጊ ይሆናል፡፡

ጨው

የኩላሊትን ጤና ክፉና ከሚጎዱ ነገሮች አንዱ ከልክ ያለፈ ጨው ነው፡፡ ሰውነታችን በተፈጥሮ በየቀኑ ከ1.5 ግራም ያልበለጠ ጨው ያስፈልገዋል፡፡ ከዚህ በብዙ መጠን በበለጠ መውሰድ የአብዛኞቻችን ልምድ መሆኑ ኩላሊትን ከባድ ጉዳት ላይ እንደሚጥል በተለያዩ ጥናቶች ተመልክቷል፡፡ ብዙ መጠን ያለው ጨው በምንወስድበት ጫና ለመበረዝ ሲል ብዙ ውሃን ያጠራቅማል፡፡ ይህ በኩላሊት አቅም እና ስራ ላይ ጫናን ይፈጥራል፡፡ በአጠቃላይ ብዙ ጨው የደም ግፊትን በመጨመር፣ የልብ ህመምን በማባባስ እና የኩላሊትን ዋነኛ የስራ ህዋሳት በማጥቃት ለከፋ አደጋ ያጋልጣል፡፡ የተጠባበሱ ምግቦች በተለይ ፈጣን ምግቦች ከፍተኛ የጨው መጠን ስላላቸው ከእነዚህ መሰል ምግቦች መራቅ፣ በሚቻል መጠን ጨውን መጥነው ምግብ በቤትዎ አብስለው መመገብ፣ ቀድሞ በምግቡ ውስጥ ከተጨመረው ውጪ የመጨመር ፍላጎት እንዳይኖር ጠረጴዛ ላይ የተፈጨ ጨው አለማስቀመጥ ከጨው ጣጣ ሊርቁ የሚችሉባቸው አማራጮች ናቸው፡፡

ለስላሳ መጠጦች

ዛሬ ላይ ለስላሳ መጠጦች ከፈጣን ምግቦች ጋር ላይለያዩ የሚሉ ያህል ከምግቦቹ ጋር የግድ በሚመስል በብዛት እየተጠጡ ይገኛሉ፡፡ የኩላሊትን ጤና ከሚያውኩ መጠጠች ዝርዝር እንደሆኑ በባለሞያዎች ቢነገርም በተለይ ወጣቶች ከፍተኛ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማያቋርጡ የሚዲያ እና የቤልቦርድ ማስታወቂያዎች እየተወተወቱ ይገኛሉ፡፡ ለዚህም ሲባል እነዚህን የንግድ ድርጅቶች ስለጤና ጉዳይም እንዲጨነቁ መጠነኛ ማሳሰቢያ መስጠቱ አስፈላጊ ሳይሆን አይቀርም፡፡

በካርበን ጋዝ የተቀመሙትን የለስላሳ መጠጦችና የኃይል መጠጦችን የሚያዘወትሩ ሰዎች ለህይወት ዘመን ዘላቂ ከሆነ የኩላሊት ህመም ጋር የመታገል ዕድላቸው ሰፊ መሆኑን ጥናቶች አመልክተዋል፡፡ ከለስላሳ መጠጦች ይልቅ ሁልጊዜም ንፁህ ውሃ ወይም ሎሚ የገባበት ውሃን መጠቀም ለኩላሊት የማሰብ ጥሩ እርምጃ ነውና ይህን ቢመለከቱት ሲሉ የጥናቶቹ ፀሐፊዎች ያሳስባሉ፡፡

አልኮል መጠጦችን ባይወዳጁ

መቼም ምክር ለሰጪው ቀላል ነው ሳትሉ አትቀሩም፡፡ አዎን አልኮል የደረሰበት አትድረሱ የሚል የባለሞያ ምክርን በተደጋጋሚ የሚነገራቸው ሰዎች በርካታ ናቸው፡፡ አዎን አልኮል ለኩላሊት ተመካሪ መጠጥ አይደለም፡፡ ተደጋጋሚ የአልኮል መጠጥ የኩላሊትን የሆርሞን ቁጥጥር ስርዓት በማዛባት የአሲድና ቤዝ ምጣኔን ያበላሻል፡፡ የኩላሊታቸው  ጉዳት ስጋት ውስጥ ያለ ህሙማን ብዙ ጊዜ ከሚሰጣቸው ምክሮች መካከል ዋነናው አልኮልን እንዲ ቀንሱ፣ ቢችሉ ደግሞ እርግፍ አድርገው እንዲተዉ መሆኑ መነሻው ይህ የአልኮል መጠጦች መጥፎ ተፅዕኖ ነው፡፡

ጎመን

ለኩላሊት መልካም ከሚባሉት የምግብ አይነቶች ጎራ ስንል ከምናገኛቸው አንዱ ጎመን ነው፡፡ ጎመን በውስጡ በርካታ ለኩላሊት ጠቃሚ ማዕድናትና ቫይታሚኖች ይዟል፡፡ ከእነዚህ መካከል ቫይታሚን ኬ እና ሲ፣ ቫይታሚን ቢ6 እና ፎሊክ አሲድ እንዲሁም ፋይቶኬሚካልስ የተበሉት ውህዶች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ የፖታሲየም ማዕድን ይዘቱ አነስተኛ መሆኑም በኩላሊት ላይ ጫና እንዳያሳድር ይረዳዋል፡፡ በተለይ ፋይቶኬሚካልስ ፍሪ ራዲካልስ የሚባሉትን መርዛማ የኩላሊት የማጣራት ሂደት ውጤቶች ከሰውነት የማስወገድ ብቃት ስላላቸው በእጅጉ ተፈላጊ ናቸው፡፡ በውጪው ዓለም ጎመንን በተለያየ መልክ ከክሬም ጋር በከፊል ወይም በሙሉ አብስለው ይጠቀሙበታል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥም በተለያየ መልክ ጎመንን በርካሽ ዋጋ ገዝቶ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮቹ እስኪሟጠጡ ሳያበስሉ በመጠቀም ኩላሊትን መጠበቅ ይቻላል፡፡ በኩላሊት ጉዳት የዲያሊሲስ ህክምና እያገኙ ላሉ ሰዎችም ጎመን ጥሩ የምግብ ምርጫ ነው ይላሉ ባለሞያዎቹ፡፡

ሽንኩርት

ሽንኩርትም መልካም አስተዋጽኦ አለው፡፡ ነጭ ሽንኩርት የሰውነት መቆጣትን በማከም እና ኮሌስትሮልን ከሰውነት ውስጥ በመቀነስ ሰፊ ጠቀሜታ አል፡፡ የፀረ ደም መርጋት ባህሪውና ኩላሊት በማጣራት ስራው ወቅት የሚቀሩ መርዛማ ኬሚካሎችን በማስወጣትም ጥሩ አስተዋፅኦ አለው፡፡ ስለሆነም የተለያዩ ምግቦችን ሲያበስሉ ነጭ ሽንኩርቱ ብዙ ሳይበስል በመጠቀም ከበረከቱ መካፈል ይችላሉ፡፡ነጭ ሽንኩርት ብቻ ሳይሆን ቀይ ሽንኩርትም ለኩላሊት ጥሩ ነው፡፡ ሽንኩርት በተፈጥሮ ፍላቭኖይድስ የሚባሉ የተፈጥሮ ኬሚካሎች በብዛት አለው፡፡ እነዚህ ኬሚካሎች በኩላሊት እና ደም ቧንቧዎች ውስጥ ቅባት ነክ የምግብ ቅራትና ውህዶች እንዳይጠራቀሙ የማገዝ ሚና አላቸው፡፡ ሽንኩርት ዝቅተኛ የፖታሲየም ይዘት ያለው መሆኑም ለኩላሊት ሳይከብድ ጥሩ ጠቀሜታ ሊሰጥ የሚችል በጥሬውም ሆነ እሳት ነክቶት ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል የምግብ ቅመም ነው፡፡

አፕል

ኩላሊትና አፕል ወዳጆች ናቸው፡፡ አንድ አፕል በቀን መውሰድ ሐኪምን ያርቃል የሚሉት አባባል እውነትም በሳይንስ ስለመረጋገጡ የተለያዩ አስረጂዎችን ማምጣትይቻላል፡፡ ከፍተኛ የአስር (ፋይበር) እና የሰውነት ህዋሳትን በተለያዩ ምክንያቶች መቆጣት እና መቁሰል የሚፈውሱ ውህዶች በውስጡ በመያዙ ለኩላሊት በጤንነት መዝለቅ ጥሩ አስተዋፅኦን ያደርጋል፡፡ አፕል ኮሌስትሮልን በመቀነስ፣ የሆድ ድርቀትን በማስወገድም ተወዳጅ ነው፡፡ ቢፈልጉ በጭማቂ መልክ ካለዚያም ጥሬውን ያዘወትሩት ሁነኛ የኩላሊት ወዳጅ ነው ሲሉ የስነ ምግብ ባለሞያዎች ይመክራሉ፡፡

አሳ

ለሰውነት ቀልጣፋ ተግባር ፕሮቲን አስፈላጊ መሆኑ አያጠያይቅም፡፡ ስጋ በቀዳሚነት በሰዎች የሚነሳ የፕሮቲን ምንጭ ቢሆንም አዘውትሮ ለፕሮቲን ፍላጎት ስጋን መጠቀም ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናልና ከፕሮቲን ይዘቱ በተጨማሪ በርካታ ጠቀሜታዎችን የሚሰጠውን አሳን መመገብ ተመካሪ ነው፡፡ በሳምንት ቢያንስ ሁለት ጊዜ አሳን መመገብ ፕሮቲን ብቻ ሳይሆን ኦሜጋ 3 ፋቲ አሲድ ለሰውነት በመስጠት ከተለያዩ ጎጂ ኬሚካሎች ኩላሊትን የመጠበቅ በረከትንም ያስገኛል፡፡

የወይራ ዘይት

የወይራ ዘይት ለሰውነት የሚሰጠው ጠቀሜታን የሰው ልጆች ተረድተው መጠቀም የጀመሩት ከብዙ ሺ ዓመታት በፊት ቢሆንም አሁንም ድረስ በስፋት በመጠቀም የስካንዴኔሺያን አገራትን የሚያህል የለም፡፡ ከሌሎች የዘይት ምንጮች ይልቅ የወይራ ዘይትን በሚጠቀሙት በእነዚህ አገራት ተደጋግመው የተሰሩ ጥናቶች የሚያሳዩት የካንሰርና ልብ ህመም በእነዚህ አገራት ሰዎች ዘንድ የሚከሰቱበት አጋጣሚ ከሌላው የዓለም ክፍል በጣም አናሳ መሆኑን ነው፡፡  ለዚህ ልዩ የወይራ ዘይት ብቃት በቀዳሚነት የሚነሱት ደግሞ በውስጡ ያሉት ፀረ መርዛማ ኬሚካል የሆኑት አንቲኦክሲዳንትስ ናቸው፡፡ የወይራ ዘይትን በማብሰያነት እንዲሁም ለሰላጣ መቀመሚያነት በመጠቀም ኩላሊትዎን ጨምሮ ለተለያዩ አካላትዎ ጤና አስተዋፅኦ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡

 

 

 

 

↧
↧

በዐማራ ፖለቲካ ዙርያ የሚታየኝ እውነት እና ስጋት (የጉዳያችን አጭር ማስታወሻ)

$
0
0

amhara
ጉዳያችን /Gudayachn
ጥቅምት 23/2009 ዓም
====================
አንድን ነገር ፈርተነው ዝም ካልን አላዋቂ እንዲመራን መንገድ መክፈት ነው።ይህንን ጉዳይ የማነሳው አዲስ የውይይት ርዕስ ለመክፈት አይደለም።በፌስ ቡክ ላይ አንድ ግለሰብ ስለፃፈ/ስለፃፈች ወይንም ሶስት እና አራት ሰዎች ሃሳባቸውን ስላሰፈሩ ሃሳቡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ወይንም እንወክለዋለን ያሉት ሕዝብ ሃሳብ ነው ለማለትም አይደለም። ሃሳቦች ግን ከመጀመርያው ካልተነሱ ጊዜ በወሰዱ ቁጥር እየጠጠሩ እና ንግግሮች ሁሉ ሕግ ሆነው ሳይታወቅ ይቀራሉ።

ፖለቲካ መነሻ እና ግብ ከሌለው መውጫው ጭንቅ ነው። ፖለቲካ አስፍቶ የማየት አዕምሮ ላይ ካላረፈ አንድ ሰው ላይ ወጥታ አጠገቧ ያለውን አንድ ቅንጣት ፀጉር ትልቅ ዛፍ አድርጋ አይታ ደን ውስጥ ነኝ ብላ እንደምታስብ ቅማልም በጠበበ መረጃ ላይ መመስረትን ያመጣል። ፖለቲካ ልምድ እና ሙያም ይፈልጋል።ፖለቲካ በፍፁም ፍቅር እና የሰውን ልጅ ሁሉ የመውደድ ፀጋ ሳይታደሉ የሚገቡበት አይደለም።የሰውን ልጅ ሁሉ ሳይወዱ የሚገቡበት ፖለቲካ በአለማችን ላይ እንደተመለከትነው መጨረሻ ላይ የእራስን ጎሳ ወደማምለክ ይቀየርና ግቡ ´´ፋሽዝም እና ናዚዝም´´ ይሆናል። ስለዚህ ጥንቃቄ ይፈልጋል።

እውነታው
=======
የዐማራ ማኅበረሰብ ለሕወሐት ´እንደጠላት ተቆጥሮ በግልፅ እና በስውር ላለፉት 25 ዓመታት በተለየ መልኩ ተጠቅቷል።በሕወሓት ማኔፌሥቶ ውስጥ እንደተገለፀው በገዢ መደብነት ተጠቅሶ ቁጥር አንድ ጠላት ተብሏል።ላለፉት 25 ዓመታትም በሺህ የሚቆጠሩ በዐማራነታቸው ብቻ እና ብቻ ተጠቅሶ ተገድለዋል፣ከቤታቸው ተባረዋል፣በርካታ ስውር ጥቃቶች ተፈፅመዋል።እነኝህን ትውልድ፣ታሪክ እና እግዚአብሔር በጊዜው የሚፈርዱት ይሆናል።ይህ ማለት በሌላው ብሔር ላይ አልደረሰም ማለት አይደለም።በተለይ በዐማራው ላይ የተደረገው ግን ማኅበረሰቡን የስልጣን ስጋት ነው በሚል ብቻ ሳይሆን ከሰይጣናዊ ፍፁም ጥላቻ የተፈፀመ መሆኑ ነው።በሌላው ላይ የተፈፀመው አንድ፣የተፈጥሮ ሃብቱን ለመቆጣጠር አልያም ለመብቱ በተነሳበት ወቅት ስልጣንን ለመጠበቅ በሚል ሕወሓት የወሰዳቸው እርምጃዎች ናቸው። በዐማራው ላይ የተወሰደው ግን ከእዚህ በተለየ ስልታዊነት ላይ የተመሰረተ ከፖለቲካ፣ማኅበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ዘርፎች ሁሉ የማስወገድ እና በመጨረሻም ወደ ማጥፋት የዞረ ተግባር ነው። ይህ በርካታ ማስረጃዎች ያሉት ያለፉት 25 ዓመታት እውነታ ነው።

ስጋት
====
ከላይ የተጠቀሰው እውነታ በርካቶች ስለ ማኅበረሰቡ መብት፣ነፃነት (በኢትዮጵያ ውስጥ ያለ ነፃነት) እና እኩልነት ድምፃቸውን እያሰሙ ነው።ይህ ክስተቱ ያመጣው ሂደት ነው።ይህ ማለት ግን ብሶት በእራሱ ፖለቲካ አይሆንም።ብሶት ቁጭት እና የንዴት ማብረጃ ብሎ ያገኘውን ዕቃ ሁሉ የመወርወር ክፉ አባዜ ያስከትላል። ስለሆነም በዐማራ ማኅበረሰብ ዙርያ የሚነሱ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች መልሶ እራሱን ዐማራውን የሚያስከፋ እንዳይሆን ጥንቃቄ ይፈልጋል።የዐማራ ማኅበረሰብን ስነ ልቦና፣ብሔራዊ እና ዓለም አቀፋዊ የሞራል ልዕልናን ከግንዛቤ ያላስገባ ፖለቲካ መጨረሻ ላይ ፈረንጆቹ እንደሚሉት ወደ እራስ መተኮስ (fire back) ያስከትላል።ይህንን ለማለት ያስገደደኝ በማኅበራዊ ሚድያ ላይ አንድ ሰሞን በርካታ ተከታይ ስላገኙ ብቻ እራሳቸው የፖለቲካ ፕሮግራም አውጪ ቀጥለው ወክለነዋል ስለሚሉት ሕዝብ የወደፊት እጣ ለመወሰን የሚዳዱ ደፋሮች ስመለከት ነው።

ስለ ዐማራ ማኅበረሰብ እውነቱን የሚናገሩ በደሉ ስልታዊ መሆኑን በማስረጃ የሚያቀርቡ እና ይህ ለነገዋ ኢትዮጵያ አደጋ መሆኑን የሚያሳስቡ ሁሉ ክብር ይገባቸዋል።ይህንን በደልም አንስተው ቆርጠው ለመታገል የወሰኑም እውነተኞች እና ስለ ፍቅር የሚያደርጉት እንደሆነ የታመነ ነው።ከእዚህ አልፈው ይህንን ስሜት እየኮረኮሩ ስለ ዐማራ ነፃ መንግስት ለመስበክ የሚፈልጉ ግን ´´ሰከን በሉ´´ ማለት ተገቢ ነው። ፖለቲካ የዕቃ ዕቃ ጫወታ አይደለም።ፖለቲካ ሰፊ ልቦና እና አሁንም ልድገመው በደልን ውጦ ሌላውን በፍፁም ፍቅር መውደድ ይፈልጋል።

የዐማራ ማኅበረሰብ የእረጅም ጊዜ የፖለቲካ ተሞክሮ አለው።ኢትዮጵያን ብሎ የሚኖረው ስለተመቸው እና ስላልተመቸው አይደለም።የዛሬ የሁላችንም ኢትዮጵያውያን መደህየት የነገ እንዳልሆነ ያምናል። ያጣነው መልካም መንግስት ነው።ይህንን ደግሞ በበደላችንን እያሰማን ወደ እኩል ኢትዮጵያ የሚወስደንን መንገድ እንከታለለን እንጂ በማኅበራዊ ሚድያ የሚመራን ሕዝብ አይደለንም።በእርግጠኝነት የእዚህ አይነቱ የዐማራ መንግስት የምትል አጀንዳ ማራገብ አንድ ወያኔ በውጭ ባለው ማኅበረሰብ ዘንድ ሌላ አጀንዳ ለመፍጠር ያሰባት ነች። አልያም አዲስ ነገር የፈጠሩ መስሏቸው ወይንም ጊዚያዊ የፖለቲካ አጀንዳ በማንሳት ጥሩ ስልት የፈጠሩ የመሰላቸው የሚያነሱት ነው።

ባጠቃላይ ግን ያኛውም ተባለ ይሄኛው ቁም ነገሩ የዐማራ ማኅበረሰብን ብሔራዊ እና ዓለም አቀፋዊ የሞራል ልዕልና ከኢትዮጵያዊነት ጋር ያለውን ቁርኝት የዐማራ መንግስት በሚል የፌስ ቡክ አጀንዳ አትጉዱት።በእርግጥ ይህ ሃሳብ በእራሱ ለመውቀስ ገና ነው ሊባል ይችላል።የእኛ ችግር ይህ ነው።ነገሮችን ከወዲሁ በእንጭጩ ሃሳቡ ካልተቀጨ ነገ የሚናገር የለም።እያየን ማለፍ መቼም ባህላችን ሆኗል።ስለዚህ ነው በደሉን አብረን እንጩህ፣ለነገዋ ኢትዮጵያ አብረን እንስራ ነገር ግን አጀንዳውን ወደተለየ መንገድ የሚወስዱትን ´´ሰከን በሉ´´ እንበል የምንለው።

ጉዳያችን GUDAYACHN

www.gudayachn.com

↧

እውነተኛ “አማራጭ ኃይል”

$
0
0

(ዮፍታሔ)

ከሚነገረውና ከሚጻፈው በላይ የማይነገረውና የማይጻፈው እየበለጠ ነው።

በተቃዋሚዎች መካከል በውጭም ሆነ በአገር ቤት፣ በኢትዮጵያም ሆነ በኤርትራ የሚካሄደው ሽኩቻና መገፋፋት በአረጋውያኑ እና በወጣቱ መካከል የሚካሄድ እየመሰለ ነው።

አረጋውያኑ ዘንድ ስም፣ ልምድና የውጭ ግንኙነት አለ። ወጣቶቹ ዘንድ አፍላ ኃይል፣ ቴክኖሎጂና የውስጥ ግንኙነት አለ።

በአገር ቤት ድንገት መሬት አንቀጥቅጥ እንቅስቃሴ ሲፈጠር አረጋውያኑ የሚያውቁት ነገር አልነበረም። ወጣቶቹ ግን እጅና ጓንት ሆነው ትግሉን እያርገበገቡት ነበር።

የአገር ቤቱ ተጋድሎ የደከሙበትን ሁሉ ውኃ የሚያስበላ ስለመሰላቸው አረጋውያኑ ደነገጡ። አንዳንዶች አረጋውያን ከድንጋጤያቸው ብዛት “አለንበት” ቢሉም ወጣቶቹ ደግሞ “ይህ የእኛና የሕዝቡ ሥራ እንጂ የላችሁበትም” ብለው ኩም አደረጓቸው።
አረጋውያኑ ሳይውሉ ሳያድሩ ለወጣቶች (እና ከጀርባቸው ላሉ የጎበዝ አለቆችና ቄሮዎች) ሌላ መልስ ነበራቸው። በአደራዳሪዎች (የውጭ ኃይሎች) ርዳታ ቶሎ ብሎ ወደ”ባለአደራ መንግሥት” ምሥረታ፣ ጎላ ብሎ ለመታየት ወደመተባበርና ወደ”ሽግግር መንግሥት ቻርተር” ማጽደቅ መሄድ። እንግዲህ ይህ የሚሆነው አንዳንዶቹ ምርጫ፣ ሌሎቹ ደግሞ “ሁለገብ ትግል” የሚሉትን ትተው መሆኑ ነው። ምን ያድርጉ! እጃቸው ላይ ያለውን ነው የተጠቀሙት።

የዚህን ጊዜ አንዳንድ ወጣቶች ለአረጋውያኑ “ቻርተሩ ውስጥ አስገቡን” አሏቸው። “ካልሆነ አገር እንበትናለን” ያሉም ነበሩ።
አረጋውያኑ ‘እነዚህ ልጆች ያደረጉትን ረሱት እንዴ?’ በሚል ዓይነት “ሃሳባችሁ ለአሁኑ አልተሳካም። ለወደፊቱ ተደራጅታችሁ ተመለሱ” ብለው እነሱም በተራቸው ኩም አደረጓቸው።

ከነዚህ ከሁለቱ የሕወሐት ልብ ለአረጋውያኑ ሊያደላ ይችላል። የመንግሥታቱም ልብ ከዚህ አይርቅም። ብዙ ትውውቅ አላቸው። አረጋውያኑ አስጊ ካለመሆናቸውም በላይ በባለአደራ መንግሥቱ በኩል የ “ምሕረት” እጃቸውን ዘርግተዋል። ይህ ለአረጋውያኑ ዕቅድ ስምረት ትልቅ ርዳታ ሊኖረው ይችላል። ሆኖም ሕወሐት የተሰጣትን “የወንድ በር” ትጠቀምበታለች ወይስ እስከወዲያኛው አትጠቀምበትም? የሚለው ጥያቄ ገና በይፋ መልስ አላገኘም።

ከሕዝቡና ከሚሊሽያው ሌላ የብአዴንና የኦሕዴድ ታችኛው አመራርና አባል ልቡ ከወጣቶቹ ጋር ነው። ሕወሐት ተገፍታ ከወደቀች ወጣቶቹ የበላይነት እንደሚኖራቸው መገመት ይቻላል።
አሁን ጥያቄው፡
1. የወጣቶቹ መልስ ምን ይሆናል? እነርሱስ እጃቸው ላይ ያለውን አውቀውታል? አውቀውስ ይጠቀሙበታል ወይስ አይጠቀሙበትም?
2. አረጋውያኑስ የጎደላቸውን ሞልተው፣ ያሰቡትን አደራዳሪ አግኝተው የተረጋጋ “ባለአደራ መንግሥት” ማቋቋሙ ይሳካላቸዋል ወይስ አይሳካላቸውም?
የሚለው ሆኗል።
ለወጣቶቹ “የሽግግር ቻርተር” ማጽደቅ ጉዳት ባይኖረውም ጥቅሙ ውስን ነው። ለወጣቶቹ ዋና ጉልበታቸው ተጋዳዩ ሕዝብ፣ የጎበዝ አለቆቹ፣ ቄሮዎቹና ደጋፊው ካድሬ ናቸው። ካወቁበት ሁሉ በደጃቸው ነው። ፍጥነት ቀኝ እጃቸው ነው።
ሆኖም ያስተዋሉ እንዲህ ይላሉ። ቢሳካ እንኳ የሁለቱም የተናጠል መንገድ አለው ሳንካ። አባጣ ይበዛዋል ጎርባጣ፤ አስተማማኝነቱና ዘላቂነቱ አይሆንም ብርቱ።
ስለዚህ አረጋውያኑ ከወጣቶቹ እንዲተማመኑ፣ አሁን ያላቸውን እንደያዙ ቢተባበሩ።
በአረጋውያኑ ወጣቶቹ ለአደራዳሪዎቹ፤ በወጣቶቹ አረጋውያኑ ለሰፊ ሕዝባዊ ድጋፍ ቅቡል ይሆናሉ። እውነተኛ “አማራጭ ኃይል”!
ያኔ አይደለም ሰላማዊ ሽግግር፣ የማይገሰስ የወገን ክብር፣ ሉዓላዊነቱ የታፈረ ድንበርና ዜጎች በፍቅርና በእኩልነት የሚኖሩባት አስተማማኝ አገር እውን ማድረግ ይቻላል።

↧

ከእጅ አይሻል ዶማ!

$
0
0

ዶማ አባጣ ጎባጣ የሆነውን መሬት ለመደልደልና ለማስተካከል፣ መንገድና የእርሻ መስኖ ለመቅደድ፣ለተለያዩ ግንባታ ስራዎች ለማመቻቸት የሚረዳ፣ ስር የሰደደን አረም ከሥሩ ነቅሎ ለመጣል፣በእጅ ሊያሶግዱት የማይችሉትን እሾህ አሜኬላ ጎልጉለው ሊያሶግዱበት የሚችሉበት አጋዥ መሳሪያ ነው።ታዲያ ዶማ ብዙ አዳጋች ስራ ለመስራት የሚጠበቅበት ሲሆን ፣ያንን ለማሟላት ደግሞ የተዘጋጀ፣ስለት ያለው፣ችግሩን ከመሰረቱ ተነቅሎ እንዲጠፋና ዳግመኛ እንዳይከሰት ለማድረግ ብቃት ያለው መሆን ይገባዋል።ብቃት በሌለው ዶማ የሚፈለገውን አከናውናለሁ ቢሉ በባዶ እጅ ከሚሰሩት የተሻለ ውጤት ስለማይመጣ ልፋት ብቻ ይሆናል፤ዶማውም ከእጅ የተሻለ ስራ አይሰራም።

26-2699-rxrud00z
እንደዚያ ያለው ዋጋቢስ ዶማ ከሸክም በስተቀር የሚሰጠው ጥቅም የለም።ከእጅ የማይሻል ዶማ ነው። በዚህም አኳያ የሚታይ ብዙ ስራዎችና ተግባሮችን ለማከናወን የሚረዱ መሳሪያዎችና ዘዴዎች አሉ።የእነሱም ለተገቢው ስራ ብቃት አለመኖር እንደ ዶማው ውጤተቢስ ሆነው ይቀራሉ። በዶማው ቦታ የቤተሰብን፣የህብረተሰብን፣የአገርን፣ችግርና እንቅፋት፣እንዲሁም ቅራኔ ለማሶገድ የምንገለገልባቸው ዘዴና መሳሪያዎች አሉ።ሽማግሌና ድርጅት ዋናዎቹ ናቸው። እርቅ ለማውረድ የተሰየመ ሽማግሌ ችሎታና ብቃት ከሌለው ልዩነቱን ይበልጥ ያከረውና ፣በተለኮሰው ጠብ ላይ ቤንዚን አርከፍክፎ ከባሰ ቀውስና አለመግባባት ውስጥ ይከታል።በተመሳሳይም በአገር ደረጃ በህብረተሰቡ መካከል ለሚነሳ የፖለቲካም ሆነ ማህበራዊ ችግርና ጥያቄ መልስና መፍትሄ ለማምጣት ታስቦ የሚቋቋም ድርጅት፣አሰራሩና አደረጃጀቱ ከችግር ፈጣሪው አካል የማይለይ ከሆነ ያለውን ችግር በተመሳሳይ መልክ የሚያስቀጥል፣ አስቸጋሪውን አካል ተክቶ በተራው የሚያስቸግር ይሆናል።የዚህ አይነቱ አደረጃጀትና አሰራር ከላይ እንደታየው ጥቅመ ቢስ ዶማ የሚመሳሰል ነው።ለማህበረሰቡ፣ለአገር ጥያቄና ችግር መፍትሔ የማያመጣ ከንቱና የጥፋት ዓላማ ተከታይ ይሆናል። በአገራችን በኢትዮጵያ ያለው ችግር መንስኤው በጎሳ የተደራጁ ዘረኞች ያሰፈኑት ስርዓት ነው።ስርዓቱን ለማስፈን ከዚያና ከዚህ ተጠራርተው በመሰባሰብ ጦር ገጥመው የነበረውን የወታደር አምባገነን በሃይል አሸንፈው በፈረንጆች እርዳታና አቀነባባሪነት ስልጣኑን የጨበጡ ቡድኖች ናቸው።በሕዝቡ ፍላጎትና ምርጫ የተመረጡ ባለመሆናቸው የሕዝቡን ፍላጎት ለመመለስ አልቻሉም።ይበልጥ አገሪቱንና ሕዝቡን እስረኛና የግል ንብረት አድርገው የፈለጉትን እየፈጸሙ ለሃያ አምስት ዓመት የኖሩ ወንጀለኞች ናቸው።የነሱ ውጤት አሁን አገሪቱን ከመበታተንና ሕዝቡን እርስ በርስ ከመተላለቅ አደጋ ጠርዝ ላይ አድርሷል። በስልጣን ላይ ያለውን ቡድን በመቃወም በተመሳሳይ መልክ ና ለተመሳሳይ ዓላማ የቆመ የተሻለና ለአገሪቱና ለሕዝቡ የተለዬ ፍቅርና አክብሮት አለው ማለት አይደለም።የእሱም ዓላማና ፍላጎቱ ተመሳሳይ የዘር ፖለቲካ ማራመድ ነው።የዘር ፖለቲካ ደግሞ ውጤቱ ያው ተመልሶ ሕዝቡን ማተራመስና አገሪቱን መገነጣጠል ይሆናል። ሰሞኑን በአሜሪካ ዋና ከተማ በዋሽንግተን ሜሪላንድ በተባለው ቦታ አገር ወዳድና፣መሰረታዊ የዴሞክራሲ ለውጥ የሚሹ ኢትዮጵያንን በማግለል በተወሰኑ የጎሳ ድርጅቶች መካከል የተደረገው ስምምነት ወያኔ ከሃያአምስት ዓመት በፊት ካካሄደው አይለይም። የኦሮሞ፣የአፋር፣የሲዳማ በማለት የተደራጁት የጎሳ ድርጅቶች ድንኳን ውስጥ ግንቦት ሰባት የሚባለው ድርጅት መሰግሰጉና እንደመሪ መቀመጡ ሂደቱንና ውጤቱን የተለዬ አያደርገውም።እንደውም የጎሰኞች መሳሪያና በአዲስ አቀራረብ አገሪቱንና ሕዝቡን ለባሰ አደጋ የሚዳርግ ነው። በአገሪቱ ውስጥና ውጭ ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ስርዓት መስፈን የሚንቀሳቀሱና የሚታገሉ ድርጅቶች ባልተሳተፉበትና በተለይም በአገራችን በኢትዮጵያ የልዩነትና የግጭት ምክንያት የሆነውን የዘር አጀንዳ ይዞ መነሳት ወያኔና አበሮቹ ቡድን ከሚከተለው የተለዬ አያደርገውም። ስለሆነም ከእጅ እንደማይሻለው እንደ እርባና ቢሱ ዶማ ከወያኔ የማይሻል ስብስብ ነው።የጎሰኞቹ ዓላማ እንደሚታወቀው የወያኔ ሕገመንግሥት ያጸደቀውን በተግባር ለመተርጎም ነው።ተቃውሟቸውም ለምን በተግባር አልተተረጎመም ነው።የግንቦት ሰባት ዓላማ ግን በግልጽ ባይታወቅም በተግባር ግን አቋሜ ከምሰበስባቸው አይለይም ያለ ይመስላል።ከብሔር አቀፍ ድርጅቶች ይልቅ የጎሳ ድርጅቶችን መምረጥ
2 ሌላ ምን ትርጉም አለው?የጎሳ ፖለቲካ አገር ሲንድ እየታዬ ለተመሳሳይ ጉዞ አብሮ መሰለፍ ከቶ ለምን ጥቅም ይሆን? የማያጠግብ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል እንዲሉ ይህ የተጀመረው አካሄድ ካለው ችግር የሚያወጣን አይሆንም።እውነት ለዴሞክራቲክ ስርዓት ለውጥና ለኢትዮጵያ አንድነት የተነሱ ቢሆን ኖሮ በተለያዬ ባንዲራ ስርና በተለያዬ የጎሳ ድርጅት ስም በጠረጴዛ ላይ ተደርድረው ከመፈራረም ይልቅ ሌሎችንም ባካተተ መልኩ በአንድ ሰንደቅ ዓላማ ስር በኢትዮጵያዊነት የኩራት መንፈስ የጋራ መግለጫ ባወጡና ባወጁ ነበር።ያንን ለማስተካከልና ሕዝቡ የሚሻውን ነገር ለማድረግ አሁንም ጊዜው አልመሸም። በጣም የሚያስገርመው ደግሞ ስብስቡን አቀነባበርን የሚሉት ጥላ ካቢኔ(shadow cabinet)አባላት ቀደም ሲል ለአሜሪካ መንግሥት ባቀረቡት የእወቁልን የሽግግር ሰነድ አንቀጽ 39 የተባለውን አፍራሽ አንቀጽ ያካተተ የወያኔ ሕገመንግሥት ሳይለወጥ እንደሚያገለግል የሚገልጽ ነበር።አሁን በስብስቡ እንደተነገረው ከሆነ ግን አዲስ ሕገመንግሥት እንደሚረቅ ተደርጎ ነው። ግን በአገር አፍራሹ አንቀጽ 39 ላይ ያላቸውን አቋም ይፋ አላደረጉም።ለአገር አንድነት የሚያስቡ ቢሆን ኖሮ ይህንን አደገኛ አንቀጽ በይፋ አውግዘው መግለጫ ባወጡ ነበር። ወጣም ወረደ በጎሳ የሚነደፍ ሕገመንግሥት የጎሰኞችን ጥቅምና ፍላጎት የሚያስከብር ይሆናል እንጂ ለተባበረች፣ አንድነቷ ለተጠበቀ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ሊሆን እንደማይችል ካየነው መማር እንችላለን። አሁን ደግሞ በፌስቡክና በሌሎቹም የዜና አውታሮች የሚሰራጨው በሚመጣው ሳምንት በኖቬምበር 10 2016 በቤልጅዬም ዋና ከተማ ብራሰልስ ውስጥ በሚገኘው የአውሮፓ ፓርላማ (በአና ጎሜዝ አዘጋጅነት ሊሆን ይችላል) በብራዚል ኦሎምፒክስ የማራቶኑ ውድድር የብር መዳሊያ ባለቤት የሆነው ፈይሳ ለሊሳ፣ የኦሮሞ ፍዴራል ፓርቲ ሊቀመንበር መረራ ጉዴናና የግንቦት ሰባቱ ብርሃኑ ነጋ እንደተጋበዙ የሚገልጽ ነው።ተጋባዦቹ የፖለቲካ ድርጅቶች እስከ አሁን ድረስ በተደጋጋሚ በየቦታው ተመርጠው በመጋበዛቸው ከመፈንደቅ ውጭ ኢትዮጵያን የምንወክለው እኛ ብቻ አይደለንም፣ሌሎችም ስላሉ ይጋበዙ ብለው አያውቁም።እንዲህ አይነቱ የአውሮፓውያኑና የአሜሪካኖች የመከፋፈል ስልት ከዚህ በፊትም በተደጋጋሚ ታይቷል።አሁን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዳር እስከዳር ተነስቶ በሚፋለምበትና ብዙ የሕይወት ዋጋ በሚከፍልበት ወቅት ነጥሎ ማቅረብና ማራቅ ለምን አስፈለገ ብሎ መጠየቅ ብልህነት ነው።ይህ የሚያሳየው አሁንም አውሮፓውያን ከፋፍለው አገራችንን በመዳፋቸው ስር ለማድረግ እንደማይቦዝኑ ነው። ይበልጥ ትኩረት የሰጡት ለኦሮሞው ጥያቄ ነው። ሌላው ቀርቶ በስደተኛ ጥያቄ ላይ እንኳን ፈጣን የመኖሪያ ፈቃድና እርዳታ የሚሰጡት በኢትዮጵያዊነቱ ለሚቀርበው ሳይሆን በኦሮሞነትና በኤርትራዊነት ለሚቀርበው ስደተኛ ነው።እዚህ ላይ ወገኖቻችን ለምን አገኙ የሚል አሳብ እንደሌለል ግልጽ ማድረግ እፈልጋለሁ።ማንኛውም ሰው በአገሩ መቀመጥ ሳይችል ቀርቶ ቢሰደድ ክብሩና መብቱ መጠበቅ አለበት ባይ ነኝ።የምቃወመው እየነጠሉ ማስተናገዱን ብቻ ነው።ለምን እንደሚያደርጉትም እናውቀዋለን። ከሁሉም በላይ ኢትዮጵያ በነጮች የቅኝ አገዛዝ ስርዓት ላይ ያደረሰችው ጥቃት ላለሙት ዘረፋ አመቺ ባለመሆኑ የታሪክ ቂም በመቋጠራቸው በመከፋፈል በቀል ለመወጣት የሚሸርቡት ተንኮል ነው።በአሁኑም ጊዜ በወያኔ ፈቃድ በብዛት የንግድና የምርት እንቅስቃሴ የሚካሄደው በኦሮሞው አካባቢ በመሆኑ ሲሆን የተፈጥሮ ሃብትና ማእድንም በሰፊው ይገኝበታል ከሚለው የዝርፊያ ስትራቴጂ አንጻር በመነሳት ነው።ለዚህም ወጣቱ በአገሩ ላይ እየኖረ ስለአገሩ እንዳይታገል ሃይሉን ለማመንመን ከማሰብ የሩቅ ጊዜ ስሌትም እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል። አዛኝ ቅቤ አንጓች እንዲሉ! ይህ ምኞታቸው ግን በተባበረ ኢትዮጵያዊ አገር ወዳድ አንድነት ይከሽፋል፣ምኞታቸውም ላም አለኝ በሰማይ ሆኖ ይቀራል። አገር ወዳዱ፣የአንድነትና የዴሞክራሲ ሃይሉ ከጎሰኞች ጠብ የሚልለት መልካም ውጤት እንደማይኖር ተረድቶ በውስጡ ያለውን ጥቃቅን ልዩነት አሶግዶ አገሩንና ሕዝቡን ከተመሳሳይ አደጋ ለማዳን አንድ ሆኖ መሰባሰብ አለበት።ተለያይቶ እየተነታረኩ መኖር ወይም እኔ ካልመራሁት እያሉ መፎካከር የፉክክር ቤት ሳይዘጋ ያድራል ሆኖ ለተደራጀ ዘራፊ ዕድል መስጠት ነው።ወይም በሰሞኑ የብልጣ ብልጦች ድራማ ተጃጅሎ መቀመጥ በአንገት ላይ ማነቆ ማጥለቅ ነው።የአንድነት ሃይሉ “አገርህን አድን” በሚለው የጋራ መርሆ በአዲስ መልክ ተደራጅቶ በአንድ የጋራ አመራር ስር መታገል ይኖርበታል።በተለመደው አካሄድ መቀጠል ድካም ብቻ ነው፤ከእጅ አይሻል ዶማ!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
አገሬ አዲስ

↧

ፓርላማው ይበተን! ሃገራዊ ምርጫ አሁኑኑ ይካሄድ! (አበጋዝ ወንድሙ)

$
0
0

በህይወቴ በኢትዮጵያ ሶስት መንግስት የማየት ዕድል አጋጥሞኛል። ሶስቱም መንግስታት አገዛዛቸውን የሚፈታተን ተቃውሞ ከህዝብ ጠንከር ብሎ ሲመጣባቸው የተጠቀሙት የፕሮፓጋንዳ ስልት ተመሳሳይነት በጣም አስገራሚ ነው። አጼ ሃይለስላሴ ስልጣናቸው ከላይ ከፈጣሪ የመጣ ነው ብለው ያምኑ የነበረ፣ መንግስቱ ሃይለማርያም የኮምኒስት ፓርቲ መሪ ነኝ ይል የነበርና፣ ያሁኖቹ ኢህአዴጎች ደግሞ የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ደቀ መዘሙራን ነን ባዮች፣ የህዝብ ተቃውሞን አስመልክቶ የሚከተሉት የማጥላላት ፕሮፓጋንዳቸው መመሳሰል፣ ምናልባት ቤተ መንግስቱን ባለ ተራ ሆነው ለሚይዙት ቀድሞ የተዘጋጀ የሚሞሉት ሰነድ ይኖራል የሚያስብል ነው። ሶስቱም ስርዓቶች የህዝብ ትግል ጠንከር ብሎ ሲመጣ ወደ ራስ በመመልከት፣ የችግሩን ምንጭ ፈልጎ ለህዝቡ አጥጋቢ መልስ በመስጠት ችግሩን ለመቅረፍ ከመሞከር ይልቅ፣ ህዝቡ የራሱን ፍላጎትና መብት የማያውቅ፣ በውጭ ሃይሎችና ለውጭ ሃይሎች ያደረና ፣የነሱን ሃገር አፍራሽ ተልዕኮም ተግባራዊ ለማድረግ የሚንቀሳቀስ ሃይል አድርገው ጧት ማታ የፕሮፓጋንዳ ተጠቂ ያደርጉታል። በአጼው ጊዜ፣ የሶሻሊስት አገሮችና አረቦች ፣ በደርግ ዘመን የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝምና የአረብ አድህሮት ሃይሎች፣ በህወሃት/ኢህአዴግ ዘመን ግብጽና ኤርትራ ለዚህ ፕሮፓጋንዳ ፍጆታ የዋሉ ሃይሎች ናቸው። ህዝብ ትዕግስቱን ጨርሶና ጭቆና አስመርሮት ሲነሳ፣ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ፣የገዢዎች አሰልቺ የማጥላላት ዘመቻዎችም ሆነ እስርና ግድያ ሳይበግረው፣ በበለጠ እልህ ትግሉን ጠበቅ እንደሚይደርግና በሰተመጨረሻም፣ ገዢዎቹን መንግሎ እንደሚጥል በሁለቱ መንግስታት ያየነው ጉዳይ ነው። የህወሃት ቁንጮዎች ከታሪክ የመማር እምቢተኝነት ካሳዩ፣ ይዋል ይደር እንጂ እጣ ፈንታቸው ከቀደሟቸው መንግስታት የተለየ አይሆንም። ኢትዮጵያን ባለፉት ጥቂት አመታትና በተለይም ባለፉት አስራ ሁለት ወራት በማናወጥ ላይ ያሉት የህዝብ እንቅስቃሴዎች ስፋት ባለው የሀገሪቷ ክፍሎች መሆናቸው ብቻ ሳይሆን፣ ከበተናጠል መጠቃት ትምህርት የወሰደው ህዝብ ትግሉን የማቀናበር ፍንጭ ማሳየቱ፣ ስልጣን ላይ ላለው የህወሃት ቁንጮ ቡድን፣ ለስርዓቱ ማብቃት ማንቂያ ደወል በመሆኑ ትግሉን ለማጨናገፍና ለመምታት ሙከራው ሁሉ ቢከሽፍበት፣ በስተመጨረሻ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ካወጀ ሁለት ሳምንት አልፎታል። በዚህ የጥፋት አዋጅ አማካይነትም፣ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን በእስር በማጎርና ፣በርካቶችን በመግደል፣ ለእስር ያልተዳረጉትን ደግሞ ነገ እገደል ወይ እታሰር በሚል ስጋት ጨምድዶ በመያዝ መላ ሃገሪቱን ወደ አስከፊ እስር ቤት ለውጠዋታል።ይሄ ስብዓዊ መብትን አስመልክቶ ሲሆን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ የሚያስከትለው በአስር ቢሊዮን ብሮች የሚቆጠር ኪሳራ ደግሞ ለረጅም ጊዜ አገራችንን ከፍተኛ ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑ ግልጽ ነው። በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈልግከውን ፓርቲ/ሰው የመምረጥ ሙሉ መብት አጎናጽፈንሃል ብለው ሲምሉ ሲገዘቱ የከረሙት የህወሃት/ኢህአዴግ ቁንጮዎች ስልጣን ላይ ከወጡ ጀምሮ በተካሄዱ፣ የከተማ፣ የክልሎችም ሆነ ሃገራዊ ምርጫዎችን ግን ከድጡ ወደማጡ በሆነ አካሄድ ምርጫዎችን ሁሉ ሲያጭበረብሩ ከርመው፣ ይባስ ብለው ባለፈው 2007 ምርጫ ጭርሱኑ መቶ በመቶ አሸንፈን መንግስት መስርተናል በሚል መሪር ፌዝ የሀገራችንን ህዝብ ከማሳዘናቸውም በላይ ፣ ኢትዮጵያን በምርጫ ስም ከሚቀልዱ የአለም አምባገነኖች ተርታ የአንደኛነቱን ስፍራ እንድትይዝ አድርገዋታል። ግንቦት 2007 ተካሄደ የተባለው ምርጫ በምንም መመዘኛ ተአማኒነት ሊኖረው እንዳልቻለ መቶ በመቶ አሸንፈናል ባሉ ማግስት የኢትዮጵያ ህዝብ ባካሄደው ትግል ስለታየና፣ በአለምም ፊት እንዳዋረዳቸው በመገንዘብ የህወሓት/ኢህአዴግ ቁንጮዎች አዲስ ትርክት ፈጥረው ተራ አጭበርባሪነት ሲያካሂዱ ከርመዋል። በጠቅላይ ምኒስትሩ ሀይለማርያም ደሳለኝ፣ በውጭ ጉዳይ ምኒስትሩ ቴዎድሮስ አድሃኖም፣በአማካሪው በረከት ስምኦንና በሌሎች ቦዘኔ ምሁራን አማካይነት “መቶ በመቶ አሸነፍን እኮ ስንል ሁሉንም ድምጽ አግኝተናል በሚል መልኩ ሳይሆን፣ የምርጫ ህጉ በሚያዘው መሰረት አብላጫውን ድምጽ በማግኘታችን ነው የፓርላማውን ሁሉንም ወንበር ያሸነፍነው” “ተቃዋሚ ፓርቲዎች ብዙ በመሆናቸውና ተቀናጅተው መወዳደር ባለ መፈለግ በተናጠል ባደረጉት ፉክክር እንደ ቅርጫ የህዝቡን ድምጽ በመከፋፈላቸው ለኛ ባብላጫ ድምጽ መቶ በመቶ እንድናሸንፍ በር የከፈቱልን…” ወዘተ የሚሉ ተራ ቅጥፈቶች፣ ለሃገር ቤትና ለውጭ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ሲያስተጋቡ ሰምተናል። እውነቱ ግን የግንቦቱ ምርጫ ከተጠናቀቀ በኋላ፣ በገለልተኛ ምርጫ ቦርድ ስም እንደ አንድ የኢህአዴግ መስሪያ ቤት የሚንቀሳቀሰው ይሄ ተቋም ሰኔ 2007 ባወጣው ሪፖርት መሰረት፣ ኢህአዴግና አጋር ፓርቲዎቹ 95.05% የህዝብ ድምጽ በማግኘት የክልሎችንም ሆነ የፌዴራል ፓርላማ መቀመጫዎችን መቶ በመቶ እንዳሸነፉ መለፈፉ ነው።

eprdf
የህዝቡ ትግል ጠንከር ሲል ሰሞኑን ለማደናገር በማሰብ ዘፈናቸውን ለውጠው ችግሩ የምርጫ ህጉ ላይ ያለ ለማስመሰል፣ ለመጭው ምርጫ አብላጫ ድምጽ ያገኘ ያሸንፋል የሚለውን ህግ አሻሽለን ተመጣጣኝ ውክልና በሚል እንደርገዋለን የሚል መጀመሪያ በበረከት ስምኦን እንደ አንድ አማራጭ፣ በኋላ ደግሞ ፕሬዘዳንቱ ለፓርላማው ባደረገው አመታዊ ንግግር ተግባራዊ ሊደረግ እንደሚችል ይፋ አድርገዋል። ህዝብ ግን ምርጫውን አስመልክቶ ያለው መሰረታዊ ችግር፣ ህጉ ሳይሆን የህወሓት/ኢህአዴግ ቁንጮዎች የአምባገነንነት አባዜና ይሀንን ፍላጎታቸውን ተግባራዊ ለማድረግ ያቋቋሟቸው ፣እንደ ምርጫ ቦርድ ያሉ ተቋማት መሆናቸውን ጠንቅቆ ያውቃል። ለዚህም ነው ገለልተኛ ምርጫ ቦርድ ይቋቋም ፓርላማው ይበተን፣ አዲስ አገራዊ ምርጫ ይካሄድ ወቅታዊው ጥያቄ የሚሆነው። “ሕዝብ አለቃችን ነው” የሚል መፈክር በየቦታው በመለጠፍ፣ ዳግማዊ ጥልቅ ተሃድሶ አካሂደን ከመበስበስ ጸድተን፣ የህዝብ አገላጋይነታችንን አንደገና አናስመሰክራለን በማለት ደጋግሞ በመለፈፍ ህዝብን ማታለል ጊዜው ያለፈበት መሆኑን በመገንዘብ፣ የህዝብ ትግል ወቅታዊ ያደረገውን “ፓርላማው ይበተን ” (ሃቀኛ የህዝብ ተወካዮች አይደሉምና !) ” ሃገራዊ ምርጫ አሁኑኑ ይካሄድ” (ያምናውን ምርጫ መቶ በመቶ አሽንፈናል የሚለው መቶ በመቶ ቅጥፈት ነውና!) በጸጋ ተቀብሎ ተግባራዊ ከማድረግ ውጭ አገራችን ከገባችበት አጣብቂኝ መውጫ ሌላ መንገድ የለም:: ፓርላማው ይበተን ! ሃገራዊ ምርጫ አሁኑኑ ይካሄድ! የሚለው የህዝብ ጥያቄ በማያሻማ መንገድ መቅረቡን የተረዱት የህወሃት/ኢህአዴግ ቁንጮዎች የቀድሞ ቃል አቀባያቸው ጌታቸው ረዳን ጋዜጣዊ መግለጫ እንዲሰጥ በመላክ ለዚህ የህዝብ ጥያቄ ጊዜያዊ እምቢተኝነታቸውን አሳውቀዋል። የቪኦኤ ጋዜጠኛ ማርት ቫን ደር ዎልፍ ጥቅምት 18፣ 2009 ባጠናቀረው ሪፖርት እንደዘገበው ጌታቸው እንዲህ ብሏል “እኛ ለመከተል የምንሞክረው የምርጫ ህጉ ያስቀመጠውን የጊዜ ገደብ ነው” “ይሄ መንግስት ድንገት ህጉን ለውጦ፣ በተለወጠው ህግም ምክንያት ምርጫ (አዲስ) የመጥራት ቅንጣትም ፍላጎት የለውም። እኛ እዚህ ያለነው ለዘለቄታው ነው።” ጌታቸውም ሆነ አለቆቹ የህወሓት/ኢህአዴግ ቁንጮዎች ያልተገነዘቡት ወይንም መገንዘብ ያልፈለጉት ጉዳይ፣ የህዝቡ ምሬት አሁን በደረሰበት ደረጃ ፣ አዲስ ሃገራዊ ምርጫ ማካሄድ ህዝቡ ሊቀበለው የሚችለው ትንሹ አስታጋሽ እርምጃ እንደሆነ ነው። ይሄም የህዝብ ጥያቄ የህወሓት/ኢህአዴግ ቁንጮዎች በሚመፃደቁበት ህገ መንግስት ህጋዊ ድጋፍ እንዳለው አንቀጽ 54 ቁጥር 7 በደነገገው መሰረት “ማንኛውም የምክር ቤቱ አባል የመረጠው ሕዝብ አመኔታ ባጣበት ጊዜ በሕግ መሰረት ከምክር ቤት አባልነት ይወገዳል” በማለት ግልጽ ያደርገዋል። ህዝብ ደግሞ በማያሻማ መንገድ የምክር ቤቱ አባላት ላይም ሆነ በመንግስት ላይ ምንም አይነት አመኔታ እንደሌለው ባለፉት አስራ አንድ ወራት ባካሄደው ትግሉ አረጋግጧል፣ ህዝባዊ ጥያቄውም አጥጋቢ መልስ እስኪያገኝ ድረስ ትግሉን ከመቀጠል ውጭ አማራጭ የለውም የበሰበሰ አይፀዳም! ፓርላማው ይበተን! ገለልተኛ ምርጫ ቦርድ ይቋቋም! ሃገራዊ ምርጫ አሁኑኑ ይካሄድ! * ይሀን አጭር ጽሁፍ እያጠናቀርኩ እያለሁ የህዝብን ተቃውሞ ያስታግስልኛል ብሎ በማሰብ ጠቅላይ ምኒስትሩ አምና የሾማቸውን ሹመኛ ምኒስትሮች በውዞና አንዳንዶችንም ሸኝቶ አዲስ ካቢኔ ሰይሟል። ህወሃት እንደ ርስተ ጉልት ይዞት የነበረውን የውጭ ጉዳይ ምኒስቴር ለሌላ ማስተላለፉና በባለጌ አፉ ብዙ ሰው ያስቆጣ የነበረውን ጌታቸው ረዳን ማንሳቱ ጥሩ ቢሆንም ፣ሹም ሽሩ ፈጦ ላለው የህዝብ ጥያቄ በጭራሽ መልስ ሊሆን አይችልም። ከዚህ ይልቅ ያለአንዳች ተጨባጭ ማስረጃም ሆነ መረጃ ለእስር የዳረጋቸውን ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ቢፈታ እንደበለጠ በጎ እርምጃ መውሰድ ይቻል ነበር። በመሰረቱ ግን አሁን ሀገራችንን ከገባችበት አጣብቂኝ ማውጣት የሚቻለውና ህዝብ መንግስት ላይ ያለውን የተሟጠጠ ተስፋ በመጠኑም ቢሆን ሊያድስ የሚችለው፣ ገለልተኛ የምርጫ ቦርድ አቋቁሞ አሁኑኑ ሃገራዊ ምርጫ በማካሄድ አመኔታ እሚያሳድርባቸውን ሰዎች መምረጥ ሲችል ብቻ ነው።

↧
↧

ሠአት እላፊ ከየት ወዴት?|በእውቀቱ ሥዩም

$
0
0

Beweketu Seyoun joke about African leaders summit [Very Funny]

ሠአት እላፊ ከየት ወዴት?
ካልፎሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ
(በእውቀቱ ሥዩም፤ የመ.ሳ.ቁ =የመልክት ሣጥን ቁጥር፤ 26119 ኮድ 1000)

የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ በውቀቱ ሥዩም ወደ ፌስቡክ ተመልሷል፡፡ በነገራችን ላይ“ የቁርጥ ቀን ልጅ” ማለት ቁርጥ በሚበላበት ቀን የተወለደ ልጅ ማለት ነው፡፡ ሌላ ትርጉም የለውም፡፡

ሰሞኑን በምትገምቱት ነገር ምክንያት ስለፖለቲካ ላልጽፍ ወስኛለሁ፡፡ ቀን እስኪያልፍ ስለ ወሲብ እየተማማርን እንቆይ፡፡
ለወንዶች፤
ከሴት ጋር ወሲብ ሲያደርጉ በፍጥነት ይጨርሳሉ ?ገንዘብዎትን ማለቴ ነው፡፡ መፍትሄው ቀላል ነው፡፡ በደመወዝ ማግስት በችቺኒያ በኩል አይንዱ፡፡
ግን የምር፤ ከፍቅረኛዎት ጋር ወሲብ ሲያደርጉ ለረጅም ጊዜ መቆየት ይፈልጋሉ? መፍትሄው ቀላል ነው፡፡ ሲወስቡ፤ ሌላ ነገር ያስቡ፡፡ ለምሳሌ ስለ ጸረ-ሽብር ሕጉ ያስቡ፡፡ ስለ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ያስቡ፡፡ ይህንን ካደረጉ በፍጥነት የሚረጩት እንባዎትን ብቻ ነው፡፡ ለፍተሻ ምኝታቤትዎ የሚገባው ፖሊስ “ለዛሬው ይበቃል “ብሎ ማጅራትዎትን ጨምድዶ እስኪያላቅቅዎ ድረስ ከፍቅረኛዎት ገላ ላይ አይወርዱም፡፡

መንግሥትን “ እኛ ወደ ቤተመንግሥትህ ድርሽ እንደማንል ሁሉ አንተም ወደ ቤታችንና ወደ መስርያ ቤታችን ድርሽ አትበል! በቃ leave us alone ” ስንለው” ዲሞክራሲ ባንድ ጀንበር አልተገነባም “ ብሎ ይገግምብናል ፡፡ እንደ እግዜር አቆጣጠር አንድ ሺህ ዘመን አንድ ቀን ነው፡፡ እንደ መንግስት አቆጣጠር ሃያ አምስት አመት አንድ ጀንበር ነው፡፡ ሳይታገል የሚያታግለን ፓርቲ በበኩሉ ተነሡ ሲለን ስንነሣለት፤ ተደብደቡ ሲል የቆመጥ በረከት ስንቀበልለት ኖረን “ድሉ የታለ?” ስንለው“ ትንሽ አሥር ዓመት ታገሡ፤ ትግሉ ረጅምና መራራ ነው “ይለናል፡፡ መልካም ነገሮች ለመምጣት ረጅም ጊዜ የሚፈጂባቸውን ያክል ፤ክፉ ነገሮች ከቀጠሮው ሰአት ቀድመው የሚጠብቁን ለምን ይሆን?

ስኬት ድልና ጤና
ዳምጠው እንደሚባለው መኪና
ፈጥነው መቸም አይደርሱ
እድሜና ትግስት ሳያስጨርሱ
ችግር ደዌና አፈና ፤ የክፉ ሰውም ኢላማ
ፍጥነታቸው የብርሀን፤ ባሕርያቸው የጨለማ ፡፡

” አንገብጋቢ ችግር -አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት- አስቸኳይ ጊዜ አዋጂ- ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ደባሪ ነገሮች በሙሉ “ፈጣን”ናቸው፡፡ በፍጥነት መጥተው ደሞ በፍጥነት አይመርሹም ፡፡ ድንኳን ተሸክመው መጥተው ከተማቸውን በላያችን ላይ ሠርተውብን ይቀራሉ፡፡

በነገራችን ላይ ፤ የሽግግር መንግሥቱ ላልተወሰነ ጊዜ ተሸጋገረ የሚባለው ነገር እውነት ነው?በጣም የሚገርመው ነገር፤ በውጭ አገር የሚኖሩ ጮሌዎች የሽግግር መንግሥት ቻርተር ሲያረቁ ይውላሉ፡፡ አገር ቤት የሚኖረው ጮሌ ደግሞ ወደ ፈረንጅ አገር የሚሸጋገርበትን መንገድ ሲያረቅ ይውላል፡፡ እንዴው ምን ይሻላል?

ባለፈው ቅዳሜ በእኩለቀን ላይ አንዱ እዚህ እኛ ሠፈር ፤ ቤቱ ውስጥ ሆኖ፤
“አትነሣም ወይ ?!
አትነሣም ወይ
አትነሣም ወይ ?”
እያለ ቀወጠው፡፡ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ አካባቢውን የፖሊስ ብረት ለበስ መኪና ወረረው፡፡ አንድ አየር ወለድ ፖሊስ ባጃጅ ከምታክል አገር- በቀል ሄሊኮፍተር በገመድ ሲወርድ ታየ፡፡ የፖሊስ አዛዡ ተገን ይዞ፤ ባሊ በሚያክል የድምጽ ማጉያ “ ባለመፈክሮች ተከባችኋል፡፡ እጃችሁን ወደ ላይ ሰቅላችሁ ውጡ” በማለት አስጠነቀቀ፡፡

ከጥቂት ጊዜ በኋላ ጎረቤታችን አቶ ካሣ-ኖቫ ሙታንታ ብቻ እንደታጠቀ ፎጣ ካገለደመች ጨብራራ ሴት ጋር እጁን ዘርግቶ ወጣ፡፡

“ማን አባህን ነው አትነሣም እያልክ የምትቀሰቅሰው ?አለ የፖሊሱ አዛዥ ገና እንዳየው፤
“ብልቴን ነው ጌታየ!ትንሽ ቅሜ ስለነበር አልነሣም ብሎ ገገመብኝ ፡፡

ውድ አንባቢ እስካሁን የጻፍኩት መግቢያ ነው፡፡ አሁን ዋናው መጣጥፍ ይቀጥላል፡፡ ሠአት እላፊ ከየት ወዴት?
በቅርቡ እንደሚታወጅ የተነገረው ሰአት እላፊ ያዲሳባን የ”ምሽት ክለብ“ ወደ ቀትር ክለብነት ከመቀየር ያለፈ ጥቅም ሊኖረው ስለማይችል እንዲቀር ጥሪየን አስተላልፋለሁ፡፡ ትዝ ይለኛል ፤ ልጅ እያለሁ ሰአት እላፊ ተቆጣጣሪዎች ሮንድ ይባሉ ነበር፡፡ በጊዜው አንድ ልጅ ተወልዶ የማይረባ ሆኖ ከተገኘ“አንተ በተጸነስክበት ቀን ምናለ አባትህ ሮንድ ቢያድር ኖሮ”ይባል ነበር፡፡ ብዙ አባዎራዎች ለእናታገራቸው ሰላምና ደህንነት ሲሉ ከሚስታቸው እቅፍ ተለይተው እንቅልፋቸውንና ምቾታቸውን ሲሰው ያድራሉ ብለን እናደንቃቸው ነበር፡፡ ዘግይቶም ቢሆን እንደተሸወድን ገብቶናል፡፡ አንዳንዱ አባዎራ ሮንድ አድራለሁ በሚል ሰበብ ቅምጡን አላስቀምጥ ሲል ያድር ነበር፡፡ በሮንድ ሰበብ ከቤት ለቤት እየተዘዋወረ ግብረስጋ ሲያደርግ የሚያደር ሮንድ በህዝብ ዘንድ በጅ-ሮንድ የሚል ማእረግ ይቀዳጃል፡፡

የሆነ ጊዜ ላይ በመንቆረር ከተማ፤ አንድ ሰውየ ሮንድ ለማደር ከዘራውንና ሦስት ጎራሽ ባትሪውን ታጥቆ ወጣ፡፡ ሚስትዮዋም ይህን ታሪካዊ አጋጣሚ በመጠቀም፤ ከጎረቤት የሚኖረውን ውሽማዋን ሰበር ግብዣ አደረገችለት፡፡ በሽቶ ሳሙና ተጣጥባ ሦስት ማእዘኗን ተለጫጭታ ጠበቀችው፡፡ ውሽምየውም መጥቶ፤ በዱባ ወጥ ራቱን በልቶ፤ ዙርያ ገባውን እየተመለከተ ቀጥሎ የሚያደርገውን በማሰብ ተጠመደ፡፡ መጀመርያ፤ጭድ ፍራሹ ላይ የእንግላል አደርጋለሁ ፤ቀጥየ አጎዛ የለበሰውን ሳንዱቅ አስደግፌ ጫንቃ- ሰበር አስከትላለሁ ፤ቀጥየ ብሎ ሳይቀጥል የኮቴ ድምጽ ከደጃፉ ግድም ተሰማ፡፡ ባልየው ብርዱ ጸንቶበት መመለሱ ነው፡፡

ሚስትዮዋ በጣም ከመደንገጧ የተነሣ ውሽምየውን እንደፋሲካ ዶሮ ቅርጫት ደፍታበት ቁጭ አለችበት፡፡ከዚያም ከፊቷ ያለውን እሳት መሞቅ ጀመረች፡፡ ባልየው ገብቶ ፤ በሚስቱና በምድጃው ፊትለፊት ተጎልቶ፤ በእግሮቿ ማህል አሻግሮ እየተመለከተ ስሜት በተጫነው ወፍራም ድምጽ “ ዛሬ ይሄንን መላጣ ስመልጠው ነው የማድር” በማለት አጉተመተመ፡፡ ቅርጫቱ ውስጥ ያደፈጠው ውሽምየ፤ ባጋጣሚ መላጣ ስለነበር፤ ዛቻው የተሰነዘረው ለርሱ መስሎት ቅርጫቱን ከነሴትዮዋ ገልብጦ ተፈተለከ፡፡ እና አሁን ይሄ ምን ለማስተላለፍ ነው?ሠኣት እላፊ ፤ዜጎች እላፊ ብልት እንዲለምዱ ከማድረግ ያለፈ አስተዋጽኦ አይኖረውም ለማለት ነው፡፡
በመጨረሻ ብዙ አንባቢዎቼ ፤ ከኮማንድ ፖስቱ በኋላ ፤ ምኡዝ ምን ሁኔታ ላይ እንዳለ እንድገልጽላችሁ ጠይቃችሁኝ ነበር፡፡

በቀደም ለታ ምኡዝና ሚስቱ ሄለን፤ በረከቦት ጎዳና ወክ ሲያደርጉ መታጠፍያው ላይ የሆነ ፖሊስ ቆሟል፡፡ ምኡዝ ፖሊሱን ሲያይ መንገድ ቀይሮ ለመሄድ ቃጣ፡፡ ፖሊሱ ትንሽ ጥርጣሬ ስለገባው ምኡዝን አስቁሞ መፈተሽ ጀመረ ፡፡ ሄለን “ ባለቤቴ ከማንም የፖለቲካ ድርጅት ጋር ግኑኝነት የለውም፡፡ ሺህ ጊዜ ብትፈትሹት ምንም ነገር አታገኙም“ አለች በግብዳ ልበሙሉነት፡፡ ፖሊሱ ከምኡዝ ኪስ ውስጥ ሁለት ፓኮ ኮንደም እየጎለጎለ ሲያወጣ ስታይ ግን አይኗን ማመን አልቻለችም፡፡ “ አንት ሸሌ!አሁንም በኔ ላይ “እያለች የምኡዝን ፊት በጥፍሯ ግልገል ዝንጀሮ የላጠው ቀይሥር አስመሰለችው፡፡ ፖሊሱ እየሳቀ ትንሽ ከገላገለ በኋላ መንገዱን ሊቀጥል ሲል ምኡዝ እየሮጠ ደረሰበት፡፡
ፖሊሱ “ ምን ፈለግህ?” ሲለው ምኡዝ አንጀት በሚበላ ድምጽ ” በዚህ አይነት ሁኔታ ወደ ቤቴ እንድመለስ ከምትፈርድብኝ፤ አንድ ሳምንት በማሠር ለምን አትተባበረኝም ?ብሎ እጁን አመሳቅሎ የተቃውሞ ምልክት አሳየ፡፡

↧

የጢስ አባይ ሕዝብ ከትግራይ ነጻ አውጪው መንግስት ጋር እየተፋለመ ነው

↧

የቅማንትን ሕዝብ ከቀሪው የአማራ ህዝብ ጋር ለማጋጨት የትግራይ ነጻ አውጪው መንግስት አዲስ ስልት ቀይሶ እየተንቀሳቀሰ ነው ተባለ

$
0
0

የአማራ ድምጽ ራድዮ እንደዘገበው የቅማንትን ሕዝብ ከቀሪው የአማራ ህዝብ ጋር ለማጋጨት የትግራይ ነጻ አውጪው መንግስት አዲስ ስልት ቀይሶ እየተንቀሳቀሰ ነው ተባለ:: የዚህን ዜና ዝርዝር እና የተጨማሪ የራድዮውን የዛሬ ዜናዎች ያድምጡ::

↧
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live