Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የመከነው የተሐድሶ ተስፋ!

$
0
0

( ከኦህዴድ ሰማይ ስር ዶፍ ጥሎ እዛው ኦሄዴድ ምድር ላይ ያባራው የኢህአዴግ ጥልቅ ተሀድሶ)

ኢህአዴግ በዘጠኝ የገዛውን በዘጠኝ የመሸጥ ትርፍ አልባ ወከባ ብርቁ አይደለም በዘጠኝ የገዙትን በዘጠኝ መሸጥ ማለት በዋና ከመውጣጥ ስሌት ጋር ሲነጻጸር ፍጹም የሚለያይ የለየለት ትልቅ ኪሳራ ነው፤ ገንዘብ፣ … ጉልበት፣ጊዜ፣ እምነት፣ሞራል፣ተስፋ፣ጉጉት ወዘተርፈ- ብዙ ነገር ነው በዜሮ የሚባዛው እርግጥ መሪውን አለማመንን ቀለቡ ያደረገ እና፣ በተመሪው አለመታመንም ገንዘቡ የሆነ ህዝብ እና ፓርቲ ያሉበት ሀገር ውስጥ የምንኖር ቢሆንም የአሁኑ ግን ከመገረም በላይ የሆነ የተስፋ ማጣት መገረም ውስጥ እንድገባ ብቻ ሳይሆን በኢህአዴግም ተስፋ እንድቆርጥ አድርጎኛል::“ …በጥልቀት እንታደሳለን !” የሚለው የገዥው ፓርቲ ጮክ ያለ ፉከራ እና ፓርቲውን የመሰረቱት የአራቱም ተዋቃሪ ፓርቲ ፖለቲከኞች በየአቅጣጫው ለጥልቁ ተሀድሶ ጉባኤ ከመዘርጋታቸው ጋር ተያይዞ ተስፋ በራቃት ነፍሳቸው ላይ የተስፋ ጀምበር የፈነጠቀችባቸው ብዙ ናቸው:: እኔም ብሆን ኢህአዴግን ማመን ቀብሮ ብቻ ሳይሆን መቃብሩ ላይም ቆሞ ነው ከሚሉት ወገን ብሆንም በአሁኑ ሰአት ግን ሀገራችን ካለችበት አስቸጋሪ ሁኔታ አንጻር ቃሉን ሊያከብር ይችላል የምትል ጭላንጭል ተስፋ ሰንቄ ቀን ስቆጥር ከርሚያለሁ እጅግ የሚያሳዝነው ግን ኢህአዴግ ዛሬም እንደወትሮው ቃሉን ብቻ ሳይሆን ተስፋችንንም “ ” በልቶ ታድሰናል ከሚሉ የህወሀት እና የብአዴን ሚኒስትሮቹ ጋር እንደገና ተመልሷል::በርካታ ለውጥ፣ አዲስ ፊት፣ ትርጉማዊ እና ከልብ የሆነ የሚኒስትሮች ሹም ሽረት፣ ሌላ ተስፋ የሚያስታጥቀን ካቢኔ ይመጣልን ዘንድ በጉጉት ስንማትር ብንቆይም ለዚህ አልታደልንም:: የራቀ ተስፋችንን የሚያቀርብልን እና ባለመሆን ጭጋግ ተጋርዳ ከእውን እይታችን ልትሰወር የደበዘዘች የሳቅ ቀናችንን የሚያጠባልን አንዳች ተአምር ይፈጠራል በሚል ተስፋ ስናደርግ ብንሰነብትም ተስፋ ያደረግነው ተስፋ ሁሉ እንደ እንቧይ ካብ ተንዶ ከሌላ መብሰክሰክ ጋር ተጋብተናል ጥልቁ ተሀድሶ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ በኦፒዲኦ ቤት እየሆነ ያለውን ነገር ስመለከት እውነትም ይሄ ነገር ሊጠልቅ ነው የሚል ስሜት ተፈጥሮብኝ የነበረ ቢሆንም መቀሌ እና ባህርዳር ላይ ታጉረው ውሀ ሲወቅጡ የሰነበቱት ህወሀት እና ብአዴን ግን ለስንት በጎ መልክ የናፈቅነውን ተስፋ አይይዙት መንፈስ አድርገውት ጉም አስጨብጠውን አዲስ አበባ ተመልሰዋል::

 

ethiopia_cabinet-810x540
ኦህዴድ ተሀድሶውን በጀመረበት አፍታ የድርጅቱን ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀ መንበር በማስወገድ በተስፋ፣ በጉጉት እና ሌሎችስ ዘንድ ምን ይፈጠር ይሆን በሚል ናፍቆት አስጀምሮን ስድስት ሚኒስትሮቹን ሳይቀር በሌሎች እንዲተኩ በማድረግ ተሀድሶውን ሲያጠናቅቅ በሌሎቹ ቤት ግን ከህዝብ ጋር ሲደረግ የኖረው የድብብቆሽ እና የማስመሰሉ አኩኩሉ አሁንም ቀጥሎ የብአዴን እና የህወሀት በዘጠኝ ገዝቶ በዘጠኝ የመሸጥ ትርፍ አልባ አባዜ ከአዲስ ነገር እንዳፋታን ለስንት የተጠበቀው ተሀድሶ በተለባብሶ ተጠናቋል ይህ የአለባብሶ ማረስ የሰነፍ ፍልስፍናቸው በአረም መልሷቸው እንደገና ሱሪ ባንገትን ሲያስተርታቸው ለማየት ግን ቀጠሮውን ለጊዜ መተው ሳይኖርብን አይቀርም ኦህዴድ ካሉት ዘጠኝ ሚኒስትሮች ውስጥ ስድስቱ ተነስተው የቀሩትም ቢሆኑ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው ተዘዋውረው እንዲሰሩ ሲያደርግ፤ ሌሎች እህቶቹ ግን ሁሉንም ሊያስብል በሚችል መልኩ የቀድሞ ሚኒስትሮቻቸውን ሰብስበው ሴቶቹን ሌላ ሹሩባ አሰርተው፣ ወንዶቹንም ጺም ጸጉራቸውን አስተካክለው “ እና ላጭተው አይናቸውን በጨው በማጠብ ሌላ እኮ ነን!” ሊሉን ተመልሰው መጥተዋል:: በኦህዴድ ቤት የታየው ተሀድሶ የሚኒስትሮቹ ለውጥ ወይም የውጤታማ ፖለቲከኞቹ ወደ ክልል መሄድ ብቻ ሳይሆን በአካዳሚክ ዳራቸውም አንቱ የተሰኙ እና ከስማቸው ጫፍ ላይ ዶክተር እና ፕሮፌሰር የሚሉ ማእረጎችን ያስቀደሙ ምሁራንንም አሳይቶን የህወሀት አፈ ቀላጤ እንደሆነ የሚታማው ሪፖርተር ሳይቀር እንዳለው “በከፊልም ቢሆን ሹመት በብቃትን እንድናስተዛዝል ያደረገን ኦህዴድ ብቻ ሆኖ ተሀድሶው!” አልቋል22 ለስንት ነገር የጠበቅነው የኢህአዴግ ጥልቅ ተሀድሶ ግን በህወሀት እና በብአዴን ልፍስፍስ አካሄዶች ሳብያ የኦህዴድ ብርቱ ጥረት ላይም ጥቁር ጥላውን በማጥላት የነገረ ስራውን አጠቃላይ ሂደት ግማሽ ልጮ ግማሽ ቁንጮ አድርጎት ሌላ ስጋት ላይ ጥሎናል22 ለመታደስ ቃል ገብቶ ከነ ጭራሹ መከርከስ እያሳቀ የሚያስለቅስ አጉል ፌዝ ቢሆንም እነ እገሌ ኮከብ ሚኒስትሮች እንደነበሩ ቢረጋገጥም በሚኒስትርነት አላካተትናቸውም አይነት ቧልታይ ጫወታ ለመተወን መሞከር ግን ትርፉ ትዝብት ነው የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን የመሩት አቶ አብይ አህመድ፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትር የነበሩት ዶክተር ከሰተብርሀን አድማሱን ከነዚህ ውስጥ ስማቸው ተነስቷል ኮከቦችን ያጨለመው የኢህአዴግ ጥልቅ ተሀድሶ የሞሸርናትን ተስፋ አደብዝዞ ከሌላ ቀቢጸ ተስፋ ጋር አፋጦን አልፏል::


ለኢትዮጵያ ልጆች.

የሳሞራ ታማኝ የአድዋው ተወላጅ ሜ/ጄኔራል መሃመድ ኢሻ የአማራ ምድር ኮማንድ ፖስቶች አዛዥ ሆኖ ተሾመ

$
0
0

mohamed-isha
አለበል አማረ እንደዘገበው

ጄኔራሉ የአድዋ ተወላጅ ሲሆን የጄ/ል ሳሞራ የቅርብ ታማኝና እስከ 2008 አጋማሽ የአግአዚ ክ/ጦር ዋና አዛዥ የነበረ ነው። ጄኔራሉ ምንም ፊደል ያልቆጠረ፣ ከህወኃትና ከሳሞራ ሌላ እምነት የለለው ድፍን ነው። ጀኔራሉ በ23/02/09 ከሌላው ከሜቴክ በለስ ስኩአር ፋብሪካ ስ/አስኪያጅ ከሆነው ኮ/ል ገ/ሚካኤል ሃጎስ ጋር በመሆን በአዊ ዞን ጃዊ ወረዳ ህዝባዊ ስብሰባ ጠርተው ነበር፤ በስብሰባው የአዊ ዞን አስተዳዳሪወች፣የጃዊ ወረዳ ካቢኔዎች፣በጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት፣በብረታ ብረት ኮርፖሬሽን ሜቴክ አመራር ሰራተኞች እና ከግንባታ ድርጅቶችና የአካባቢው ነዋሪወች የተካተተበት አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በተመለከተ ማብራሪያና ማስፈራሪያ ለመስጠት ያለመ ነበር።

በስብሰባው በጀኔራሉ በአዠንዳነት ከተገለፁ ነጥቦች፤

1. በሁሉም የአማራ ምድር በዞን እና በወረዳ ደረጃ ኮማንድ ፖስት ማቋቋምና በነውጥ(በነሱ አማርኛ) ተሳታፊ የነበሩ ግለሰቦችን በሚደረገው ጥቆማና ማጣራት ለፍርድ ማቅረብ፤ጥፋተኛ ነን ብለው አምነው ተጸጽተናል ብለው ራሳቸውን አጋልጠው ለሚቀርቡት ደግሞ እንደ ጥፋታቸው መጠን ታርመውና ታድሰው መኖር እንዲችሉ ማድረግና ይህንንም ህዝቡ እንዲያውቀው ለማድረግ፤
2. ማንኛውም አካል ነውጠኞችን በማጋለጥ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪ ለህዝቡ ለማቅረብ፤

3. በህዝባዊ አመጹ ንብረታቸው የወደመባቸው ግለሰቦችን ካሳ ለመስጠትና ወደነበሩበት ለመመለስ ዞኑ እንቅስቃሴ መጀመር እንዳለበት ለመንገርና ይህም የህብረተሰቡን ተሳትፎ የሚሻ በመሆኑ ህዝቡን ለመቀስቀስና መዋጮም እንዲያዋጣ ለመንገር፤

4. በአዋጁ መሰረት እያንዳንዱ ከያዘው ሞባይል ጀምሮ በአዋጁ የተቀመጡትን እገዳዎች ማክበር እንዳለበትና እራሱንና አካባቢውን ከነውጠኞች እንዲጠብቅ ትዕዛዝ ማስተላለፍ ነበር፤
በዚህ መሃከል በነበሩ ዲስኩሮች ጄነራሉ ያለፋ ነግስታቶቻችን ለመተቸት ሲሞክር ተደምጧል። በተለይም ህዝቡን ቋቅ ያሰኘና እና ያስጠየፈ ነገር ቢኖር ጀኔራል ተብየው የሚያወሩትን የማያውቁና እና በርሳቸው አፍ እምዬ ምኒልክን ለመተቸት መሞከራቸው ነበር። የአሜሪካ የምርጫ ሂደትም በዚሁ ወደል ማህይም በጥቂት ቢልየነሮች የሚመራ መንግስት፣ለባለሃብት የቆመ መንግስት እያለ ለመተቸት ሲውተረተር ሲታይ ተሰብሳቢው በሳቅ እና በጩሀት አቁአረጠው ።

በመጨረሻም ተሰብሳቢው ለጀኔራል ተብየው በርካታ ጥያቄወች በማንሳት ጀኔራሉ መመለስ ተስኗቸው ሲቁለጨለጩ መዋላቸውና መጨረሻም ተሰብሳቢው ስብሰባውን በራሱ ኃይል በትኖት ወደ ቤቱ መሄድ ከስፍራው የደረሰን መረጃ አረጋግጧል።

በሚኒሶታ ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤተከርስቲያን ለሚያሰራው ባለ3 ወይም ባለ5 ጉልላት ቤተክርስቲያን የመሰረት ድንጋይ የፊታችን እሁድ ይቆማል

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በሚኒሶታ የሚገኘው የታላቁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሆነው ደብረሰላም መድሃኔዓለም የሚያሰራውን ባለ 5 ጉልላት ቤተክርስቲያን የመሰረት ድንጋይ የፊታችን እሁድ እንደሚያስቀምጥ የቦርዱ ሊቀመንበር አቶ መላኩ በቀለ ለዘ-ሐበሻ አስታወቁ::

እንደሊቀመንበሩ ገለጻ በሚኒሶታ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰራው ሕንጻ ቤተክርስቲያን ግንባታ በቅርቡ የሚጀመር ሲሆን የመሰረት ድንጋዩም የፊታችን እሁድ ኖቬምበር 6, 2016 በርካታ ም ዕመናን በሚገኙበት ይቀመጣል::

ይህን የመሰረት ድንጋይ የሚያስቀምጡት ብጹዕ አቡነ ዳንኤል እንደሚሆኑ ያስታወቁት አቶ መላኩ ይህ ስነ ሥርዓት የሚከናወነውም የጥቅምት መድኃኔዓለምን ጥቅምት 27 2009 (Nov 6, 2006) በደመቀ መልኩ ከተከበረ በኋላ በሰረገላ ከቤተክርስቲያኑ ወደ አዲሱ ቤተክርስቲያን ወደሚገነባበት ቤተክርስቲያን ሜዳ ላይ ክሚደረገው ጉዞ በኋላ ነው ብለዋል:: ሁሉም ሰው በዚህ ታሪካዊ ቀን ላይ እንዲገኝ ጥሪያቸውን ያቀረቡት አቶ መላኩ ይህ ባለ5 ጉልላት ቤተክስቲያን በሚኒሶታ መገንባት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ትልቅ ኩራት ነው ብለዋል::

ቦታውንና ሰዓቱን ለማወቅ የሚከተለውን በራሪ ወረቀት ይመልከቱ::
minnesota

“መንገጠልን የኦሮሞ ሕዝብ ሕልም አድርገው አሁንም የሚያስቡትን አልጋራም”ረዳት ፕሮፌሰር ሀሰን ሁሴን

“ለአማራ ህዝብ  የአማራ ተጋድሎ ጥሪ” !!!  የተጋድሎው መሪወችም በተግሉ ሜዳ የሚገኙ የአማራ ተጋድሎ የጎበዝ አለቆች ናቸው!!!

$
0
0

amhara

አማራነትን መስበክ ሀጢያት ወይም ወንጀል አይደለም፣ አማራነትን መስበክ በወያኔ የጎጥ ፓለቲካ ቋት ውስጥ ገብቶ ዘረኝነትን ማቀንቀንም አይደለም፣ ከሁሉም በላይ አማራነት ነፃነትና ኢትዮጵያዊነት የነፃነት እምነት ነው። ። አማራ ኩሩና አትንኩኝ ባይ ህዝብ ነው፣ አማራ አኩሪ በህልና ወግ ያለው፣ይሉኝታና ውለታን የሚያውቅ፣እንግዳ ተቀባይ ፣ሰው አክባሪ ፣ካልነኩት የማይነካ በሀገሩና በድንበሩ ቀልድና ይቅረታ የማያውቅ፣ በፍቅር እንጂ በጥላቻ ሽንፈትን የማይቀበል፣ የራሱን የማይሰጥ የሰው የማይመኝ፣ የማይነካ ለሀገሩና ለሀይማኖቱ ቀናኢ የሆነና ፈሪሃ እግዚአብሄር ያለው ህዝብ ነው። አማራ ማስመሰል የማያውቅ ፍቅርና ጠላቱን ፊትለፊት የመግለፅ ድፍረት ያለው ህዝብ ነው።

ለጠላቱ ኮሶ ለወዳጁ፣ቅን የሆነ ቅን ህዝብ ነው። አማራ የለም ሲባል የሚኖር አለቀ ሲሉት የሚበዛ፣ ጥላቻን በፍቅር የሚገዛ፣ ለወዳጆቹ ጋሻና መከታ፣ ለጠላቶቹ ፍም እሳት ረመጥ፣ የጋለ የብረት አሎሎ የሆነ ለጠላቱ የማይጨበጥ ህዝብ ነው። አማራ በአማራነቱ ይሰባሰብ፣ የአማራ ተጋድሎ ይደራጅ ፣ይታጠቅ ስንል በአማራነቱ ብቻ ተለይቶ “ኢትዮጵያ ወይም ሞት! “በሚል ጽኑ ታሪካዊ አ ቋሙ እንደ እብድ ውሻ ተደብድቦ ከሚደርስበት የጅምላ ጭፍጨፋና የዘር ፍጅት እራሱ መከላከል እንዲችል ለማስቻል እንጂ ፣የአማራን ኢትዮጵያዊነት ጥያቄ ላይ ጥሎ የወያኔን የጎሳ ፓለቲካ ለማቀንቀን አይደለም። አበው ” እሾህን በእሾህ ” እንደሚሉት ወያኔን በቆፈረው ጉርጓድ ውስጥ ለመቅበር በመረጠው የትግል ስልት በአማራ ተጋድሎ መጋፈጥ የግድ ይላል። ወያኔ ለዚህ እኩይ ተግባሩ” አማራ ቀንዳምና ጅራታም ተናካሽ አውሬ ነው፣ አማራ ከምድረገፅ መጥፋት ያለበት ታሪካዊ ጠላታችሁ ነው ” እያለ ቀስቅሶ በፀረ አማራ ትግሬውን ከጎኑ እንዲሰለፍ ያደረገው በኢትዮጵያዊነት ሰሜት ሳይሆን በትግሬነቱ በዘረኝነት መንፈስ በመቀስቀስ ነው። አማራ በአማራነቱ ብቻ በእሳት ተቃጥሏል።

በጥይት ተገድሏል፣ ከገደል ተጥሏል፣ የዘር ፍጅት ደርሶበታል፣ተፈናቅሏል ተሰዷል፣ታስሯል፣ ተዋልዶ ዘሩን እንዳይተካ መካን ተደርጓል፣ ተዋረዷል ተንቋል፣ ይሄ ሁሉ ሲሆን አይዞህ አለንልህ ብሎ ሊታደገው የሞከረ ማንም የለም። ሁሉም በየጎጡ ተደራጅቶ የጋራ ጠላቱን በጋራ ሲከላከል፣ አማራ ግን በኢትዮጵታዊነት ፀንቶ በጎሳ ከረጢት ውስጥ ሳይገባ እስካሁን የሚደርስበትን ግፍና ሰቆቃ ችሎ ቆይቷል ፣ አሁን ግን የግፉ ዋንጫ ሞልቶ ስለፈሰሰ አምርሮ እምቢ! ብሎ የአማራ ተጋድሎ ተነስቷል።አማራ በተለያዩ ክልሎች በግፍ የተጨፈጨፈው አማራ በመሆን ወንጀል ነው!ጎጃሜ፣ወሎዬ ፣ሸዌ ጎንደሬ እየተባለ ሳይሆን አማራ ተብሎ ብቻ ስለሆነ የተጀመረው ፀረ ወያኔ እራስንንና ሀገርን የመከላከል ትግል በድል ወደፊት መራመድ ካለበት በየትኛውም የሀገሪቱ ኢትዮጵያ ና በውጭ የሚኖር አማራ ለአማራ ተጋድሎ ጥሪ በአንድላይ መቆም አለበት፣ ሁለትና ሶስት አይነት አማራ የለም የትም ይኑርየትም አማራ ሁሉ አንድ ነው፣”አማራ “!!!

አንድነት ሀይል ነው፣ ማንም ወደደ ጠላ በአማራነቱ ይሰባሰባል፣የአማራ ተጋድሎ ይደራጃል፣ ይታጠቃል ፣ ሊየጠፉት የተነሱበትን ጠላቶቹን እንደ አማራ ተደራጅቶ ፊትለፊት ይጋፈጣቸዋል። ስለዚህ በዚህ ትግል ” በመረጠው ዳኛ የሚረታና በቆረጠው ዱላ የሚመታ” ማን ሊሆን እንደሚችል እየቆየን እናያለን። እስካሁን ባለው ሁኔታ በመላው ኢትዮጵያ አማራውን ጨርሶ ለማጥፋት እየተደረገ ያለው የዘር ፍጅት አማራ በመሆኑ ብቻ እንጂ ወሎዬ ፣ጎጃሜ፣ ጎንደሬ ሸዌ በመሆኑ አይደለም። ሰለዚህ የትም ይወለድ የትም ይኑር አማራ አማራ ስለሆነ ጎንደሬ ፣ጎጃሜ፣ ወሎዬ፣ሸዌ እየተባለ በጎጥና በመንደር የሚደረገው መሰባሰብ የተባበረውን የአማራ ህዝብ ትግል የሚያኮሰምን ከመሆኑም በላይ ለተናጠል ጥቃት የሚያጋልጥ ነው። የዚህ አይነቱ የአማራ ልጆች መከፋፈል ደግሞ የሚጠቅመው ወያኔን ብቻ ነው።

ይህ የገባንበት የአማራ ተጋድሎ የአልሞት ባይ ተጋዳይነት ትግል ወያኔን ለመከላከልና መልሶም ለማጥቃት የመረጥነው የአማራ ተጋድሎ ታክቲክና አስትራቴጂ ወደንና ፈልገን የገባንበት የትግል ስልት ” እሾክን ነእሾክ” በሚባለው አማራዊ ስልት ነው።ስለሆነም የተጀመረው ፀረ ወያኔ እራስንንና ሀገርን የመከላከል ትግል በድል ወደፊት መራመድ ካለበት በየትኛውም የአ ለም ክፋ ል የሚኖር አማራ በአንድላይ መቆም አለበት፣ወያኔ ያለርህራሄ እየገደለ እያሰረና እያሰቃየ ሥልጣኑን ለማቆየት በሚያደርገው ጥረት እስካሁን ከሆነው የወደፊቱ ሊከፋ እንደሚችል በጉልህ እየታየ ባለበት በዚህ ወቅት በተቃውሞው ጎራ ወቅቱን የሚመጥን -ራሱን በራሱ አደራጅቶ የአማራ ተጋድሎ ነጻነት ወይንም ሞት ብሎ በጀመረው ትግል መስዋእትነት እየከፈለ ባለበት፣ስለ ነገ መታሰብ ስለ ነገም ተጨንቆ መስራት መነታረኩን ትተን ፤አደጋን በቀነሰ ሁኔታ ወያኔን ማስወገድእያደረሰ ያለውን አደጋ በመከላከልና ትግሉን በማጠናከር ለድል የሚበቃበትን ስራ ለመስራት ሁለትና ሶስት አይነት አማራ የለም የትም ይኑር አማራ ሁሉ አንድ ነው፣ አንድነት ሀይል ነው፣ ወያኔ የሚንበረከከውና ቅስሙ የሚሰበረውም አንድ ሁነን በአማራ ተጋድሎ ሲያየን ነው፣ ሂዩመን ራይት አክቲቪስቶችና ሶሻል ሚዲያዎችም መፃፍና መናገር ካለባቸው አንድና አንድ ስለሆነው የአማራ ተጋድሎ ብቻ ነው። እንደዚያ ሲሆን የኛ ጡንቻ ሲፈረጥም የወያኔ ይላላል፣ የኛ ምሽግ ሲገነባ የወያኔ የውሸት ካብ ይፈርሳል፣ መተባበሩ ግድ ነው።

ይህ የአማራ ተጋድሎ ትግል የኢትዮጵያዊያን በሙሉ ትግል ነው። ይህ ትግል የዛሬ ነው።ይህ ትግል በሀገራዊ ራዕይና ተልዕኮ በመሳተፍ ከያንዳንዳችን የሚጠብቀው አስተዋፅዖ አለ። በርግጥ የሀገራችን የኢትዮጵያ ታጋዮች ያሉት በሀገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ ነው። ዛሬ ከፍተኛውን መስዋዕትነት በመክፈል፤ከስህተት ወደ ጥፋት ከተሸጋገረው የትግራይ ነጻ አውጭ ድርጅት /ከህወሃት ወያኔ ሰዎችና የኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር ሌት ተቀን በኑሯቸው እየተገደዱ፣ እየተሰቃዩ፣ በእስር ቤት እየተንገላቱ፣ እየተቀሙ፣ ግፍና የበደል በደል ለማስቆም የተጋድሎው መሪወችም በተግሉ ሜዳ የሚገኙ የአማራ ተጋድሎ የጎበዝ አለቆ ች ናቸው !!! በኢትዮጵያዊነት ትውፊት ለኢትዮጵያ ያሉት የአማራ ተጋድሎ ታጋይ ልጆች ናቸው የሕዝብ ጠላቶች መወገድ መሠረታዊ ስለሆነ፤ መተባበሩ ግድ ነው።የኢትዮጵያ ጉዳይ፤ ከንብረት፣ ከኑሮ የበለጠ ክብር የምንሠጠው ሰ ን ደ ቅ ነው :: “ለአማራ ተጋድሎ እንተባበር”ሁሉም ዘብ ይቁም በቦታው !!!
ኢትዮጵያ በቆራጥ ልጆቿ ታፍራና ተከብራ ትኖራለች!
ሰልፍ የጀግና ድል የእግዚአብሄር ነው።
ገብርኤል ብዙነህ

ኢትዮጲያዊነት ውስጤ ነው

$
0
0

screen-shot-2016-10-30-at-4-40-47-pm
አካዳር ኢብራሂም ነኝ ከብራሰልስ

ኦሮሞ ዴ/ ግንባር፣ አርበኞች ግንቦት 7 ፣ የአፋር ህዝብ ፓርቲና የሲዳማ ህዝብ ዴ/ ንቅናቄ የትግራይ ነጻ አውጪን መንግስት ለፋመለም ባለፈው እሁድ የጋራ ንቅናቄያቸውን ይፋ አድርገዋል።

ጥምረቱ ከጅምሩ ብዙ ምሁራን የለፉበት፣ አስፈላጊውን ግዜና ሁኔታን የጠበቀ ሰለነበረ የብዙዎችን ቀልብ የሳበ ደማቅ ሰነ ሰርዓት ነበር።
ካሁን በፊት በብዙዎች የተገልፀውና ግልጽ የሆነ ነገር ቢኖር ወያኔ እንደ አንድ ትልቅ ተራራ የተደገፈው የእኛ የተበታተነ ትግል መሆኑን ብዙዎቻችን ልብ ብለናል።
ወያኔም ቢሆን ከምንም በላይ የሰራበትና እየሰራበት ያለው ነገር ቢኖር የህዝብን አንድነት መበተን ነው።

ከጎንደር በኢትዮጲያዊነት የተሞላ የህዝብ ጎርፍ በኦሮሚያ የሚፈሰው ደም የእኛ ደም ነው ሲሉ እኛም እዚህ እኔ በምኖርበት ብራሰልስ በአንድነት ቆመን ኦሮሞ፣አማራ፣አፋር፣ ሶማሌ ወዘተ ተሰልፈን የህዝቦቻችን ድምጽ ማሰማት ጀምረን አሁንም ቀጥለናል።

ግን በፖለቲካ መሪዎች በኩል እንደዚህ አይነት ፀረ ወያኔ የሆነ ጥምረት እንዲመጣ በጉጉት ስንጠብቅ ነበር።
ይህ ማለት ግን አሁን ስራው አልቀዋል ማለት አይደለም።
ስራው ተጀምሯል እንጂ አልተነካምና። ግን ቢያንስ ተጀምሯልና ንቅናቄው እንዲመስረት የለፉትን ምሁራንን ሳላመሰግን ማለፍ አልፈልኩምና ምስጋናዬ ይድረሳቸው።

በንቅናቄው ምስረታ የንቅናቄው መሪዎች ያደረጉትን ንግግር ብዙ ግዜ በጣም ብዙ ግዜ ደጋግሜ አዳምጫለሁ ትክክለኛውን ቁጥር ባላውቅም በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጲያዊያን በቦታው ነበሩ።
በትክክል ግን እኔ በተከታተልኩበት የፈስቡክ የቀጥታ ስርትጭት ከ200ሺ በላይ የሚሆኑ ሰዎች የንቅናቄው ምስረታና የመሪዎች ንግግር ተከታተሏል።

የአፋር ህዝብ ፓርቲን የወከሉት ዶክተር ኮንቴ ሙሳ ገና ብዙ ሳይናገር የተሰብሳቢዎችን ቀልብ የሳበ ንግግር አድርገዋል።

ታሪክ እናውሳ ካልን ብዙ ብደሎች ደርሶብናል፤ ያም ሆኖ ግን የአፋር ህዝብ ኢትዮጲያዊነት ጥያቄ ውስጥ ገብቶበት አያውቅም ብሏል።
በትክክልም ዛሬ ላይ ሆነን የሌላ ክፍለ ዘመን ታሪክ እንደ ጥላቻ ከማውሳት ይልቅ ባለንበት ክፍለዘመን ጥሩ ነገር ሰርተን ለመጪው ትውልድ ብናወርስ የተሻለ ነው።
የአፋር ህዝብ ደግሞ በኢትዮጲያዊነት መቼም የማይደራደር፣ ግን ደግሞ እንደ ዶክተር ኮንቴ አይነት በሳል ልጆቹ ለመመራት ያልታደለ ጭቁን ህዝብ ነው።
አንድ የአፋር ወጣት በፈስቡክ የዶክተር ኮንቴን ንግግር ከሰማ በኃላ በአፋረኛ የጻፈው ጹሁፍ አይቸ ነበር።
ባለፉት ሃያ አምስት አመታት መጻፍና ማንበብ ያማይችሉ መሪዎች ተሹመውልን እንደዚህ እንደ ኮንቴ ሙሳ አይነት የ አፋር ምሁር በእንደዚህ አይነት ቦታ በሚገርም አቀራራብና ብቃት ንግግር ሲያደርግ ማየቴ ሁለት አይነት ሰሜት ፈጥሮብኛል ይላል።
1ኛ ዶር ኮንቴ ገና በአፋረኛ ናጋሴኒ ብሎ ንግግር ሲጀምር ለካ በተስፋም ቢሆን የተማሩ መሪዎች አለን የሚል ስሜት ተሰማኝ።
2ኛ ባለፉት ሃያ አምስት አመታት ( በእኔ ዕድሜ) ከመቀሌ የሚቀበሉትን ትዕዛዝ ብቻ የሚነግሩን መሃይም መሪዎች ሲንመራ የነብርነው ለካ እንደዚህ አይነት ብቃትና ወኔ ያላቸው መሪዎች እያለን ነው ብዬ የመቆጨት ስሜት ተስምቶኛል።
ህዋሃት መቼም ቢሆን እንዲዚህ አይነት ምሁርየ አፋር ህዝብ እንዲመራ አይፈቅድም
ሰለዚህ ጉዞው ለውጥ ፈለጋ ከሆነ ኮንቴን ተከተሉ ብሏል።

እኔም ጉዞው ለውጥ ፈለጋ ከሆነ የኢትዮጲያ አገራዊ ንቅናቄን እንከተል፣ እንቀስቅስ
እናበረታታና ከጎናቸው እንዲንሁን አደራ እያልኩኝ ልሰናብታችሁ።

በ40 ሚሊየን ብር ያለአግባብ ግዥ ሊጠየቁ የሚገባቸው ፕሮፌሰር ይፍሩ ብርሃነን ለሚንስትርነት ማዕረግ?

$
0
0

ከጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሠራተኞች አንዷ

ጥቅምት 22 ቀን 2009 ዓ.ም.፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ በድጋሚ ያቋቋሙትን ካቢኔ ከአንድ ዓመት ጊዜ ቆይታ በኋላ በማፍረስ እንደ አዲስ ያደራጁትን አዲስ ካቢኔ ጥቅምት 22 ቀን 2009 ዓ.ም. ለሕዝብ አሳውቀዋል፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ካዋቀሩት ካቢኔ ውስጥ አብዛኞቹ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመጡ መሆናቸው እስከ አሁን ካለው አወቃቀር ልዩ ያደርገዋል።

ከዚህ በፊት የነበረው ካቢኔ ለምን እና በምን ምክንያት እንዳፈረሱት በቂ ምክንያት ያላቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፓርቲያቸው “ጥልቅ ተሃድሶ” ብሎ ከጀመረው መንገድ አንዱ መሆኑን አንዳንዶች ይስማማሉ፤ ነገር ግን አዲስ የተቋቋው ካቢኔ ለወቅታዊ ችግሮች መፍትሔ እንደማይሆን ብዙዎች ይስማማሉ፤ የሕዝቡ መሰረታዊ ጥያቄዎችን ወደ ጎን ያለ እና የመፍትሔ አቅጣጫ ከመሆን በዘለለ መንግሥት እየሄደ ያለው የማደናገር አካሄድ መሆኑን ያሳያል። ለምሳሌ የቀድሞ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር የነበሩት ዶ/ር ከሰተ ብርሃንን የተኩት በሙያቸው የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ሐኪም የሆኑት ፕ/ር ይፍሩ ብርሃነ ከወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊነት፤ የዲላ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተርነት፤ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን፤ እና በቅርቡ ተሹመው ከነበሩበት የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አስተዳዳሪ ነበሩ።

ፕ/ር ይፍሩ ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሲመጡ፤ የሆስፒታሉን እጅግ የተንዛዛ አሠራርም ሆነ የኮሌጁን ወቅታዊ ቁመና ላይ ለውጥ ያመጣሉ ተብሎ ታስቦ ነበር። በነበራቸው የወራት የሆስፒታሉ ቆይታ ካስተካከሉት ይልቅ ያበላሹትና ያሰቃቀሉት፤ መልክ መልክ ያላስያዙት ሥራ እጅግ ገኖ ይታያል። ፕሮፌሰሩ ለሆስፒታሉም ሆነ ለኮሌጁ ላይ የለወጡት አሠራር ቢኖር ቀድሞ በሁለት ተቋም ተከፋፍለው ሥራቸውን ሲያካሂዱ የነበሩትን ሆስፒታሉንና ኮሌጁን በአንድ ዕዝ ሰንሰለት ማስገባታቸው እንደ በጎ ጅማሬ ታይቶ ነበር፤ በተጨማሪ ሆስፒታሉ ውስጥ የነበሩትን ቢሮዎች በማጥፋት “ሆስፒታሉን ለሆስፒታል አገልግሎት ብቻ” በሚል መርኅ ቢሮ ለቢሮ በመዞር በተለያዩ ፕሮጀክቶች እና ለቢሮ ሥራ ሲያገለግሉ የነበሩትን ክፍሎች ወደሕክምና መስጫነት ለመለወጥ ያደረጉት አካሄድ በበጎ የሚታይ ነው። ከዚህ በተጨማሪ በ“Office Reshuffling” ጊዜ ከሃያ ዓመታት በላይ ውሳኔ ሳይሰጥባቸው መወገድ የሚገባቸውን ንብረቶች በአጭር ጊዜ በማስወገድ ሆስፒታሉ የተሻለ ዕይታ እንዲኖረው የቻላቸውን ያህል ማድረጋቸው የሚያስመሰግናቸው በጎ ሥራዎች ናቸው።

ከዚህ በተቃራኒ ግን በርካታ የውስጥ ሠራተኞችን ከሚሠሩበት ቦታ በማመሰቃቀል፤ ቋሚ ሠራተኞች ሆነው ቦታ ስለታጣላቸው ብቻ ካለምንም አገልግሎት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በማባረር፤ ብቃት የሌላቸውን ሰዎች በዳይሬክተርነት ቦታ ላይ በመሾም፤ ከ40 ሚሊየን ብር በላይ የመንግሥት ገንዘብ በማውጣት የወንበርና የጠረጴዛ ግዢ በመፈጸም፤ ቀድሞ በኮሌጁ የዲን ቦታ ላይ የተቀመጡ እና በርካታ ዘርፈ ብዙ ሥራ ለኮሌጁ ሲሠሩ የነበሩትን በኮሌጁም ሆነ በሆስፒታሉ ማኅበረሰብ ከፍተኛ ግምት የሚሰጣቸው በወር 30 ቀናት በቀን ከ12 ሰዓት በላይ ሲያገለግሉ የነበሩትን ዲን ያለበቂ ምክንያት በማባረር፤ ለቦታው የማይመጥንን ሰው የእርሳቸውን ፍልስፍና ስለሚያቀነቅን ብቻ በመሾም፤ በመረጃ ሳይሆን በወሬ ላይ በመመስረት ውሳኔ በመስጠት እና በመሰል ነገሮች ሥማቸው ይነሳል።

1. ከ40 ሚሊየን ብር በላይ የተደረገ የወንበርና የጠረጴዛ ግዥ መፈጸም

ፕ/ር ይፍሩ ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሲመጡ ያደረጉት የመጀመሪያ ሥራ ቢኖር አሠራርን ከማዘመን ይልቅ፤ የሆስፒታሉም ሆነ በኮሌጅ ውስጥ የሚገኙትን ወንበርና ጠረጴዛ መቀየር ነበር። በቀን በርካታ ሰዎች ተገቢ የሕክምና አገልግሎት አግኝተው መዳን የሚችሉ ሰዎች ሕይወታቸውን እንደዋዛ በሚያጡበት ሆስፒታል ውስጥ ይህን ያህል ብር ከመንግሥት ካዝና በማውጣት ይህን ግዥ መፈጸም ብዙዎችን አግባብነቱ ላይ ጥያቄ ያጭራል። በርካታ የሕክምና ክፍሎች በቂ አልጋ ሳይኖራቸው በሽተኞች መሬት ላይ ተኝተው በሚታከሙበት ሆስፒታል ውስጥ በቀረጥ ከሕዝብ የተሰበሰበን ገንዘብ ለእንደዚህ አይነት አገልግሎት ማዋል ተገቢ ካለመሆኑ በተጨማሪ፤ በማአለብኝነት የተሠራ አሠራር መሆኑን ያመላክታል። ይህ ብር በርካታ የሕክምና መሳሪያዎችን በመግዛት፤ የነበረውን የሆስፒታል አገልግሎት አንድ እርምጃ ወደፊት የሚያራምድ መሆን ይችል ነበር።

ለተማሪዎች በቂ የሕክምና መጻሕፍት በሌለበት ቤተ-መጻሕፍት ውስጥ በሚኒስትር ደረጃ የእንግዶች መቀበያ የሚሆን 80 ሺህ ብር የሚያወጣ ሶፋና ወንበር ለተማሪዎች ኢንተርኔት መጠቀሚያ ማስቀመጥ እብደት ከመሆኑ በተጨማሪ፤ በየዘርፉ በተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ውስጥ ተጠያቂነት የሌለው አሠራር መስፈኑን የሚያሳይ ነው። ፕሮፌሰሩ በየቢሮዎች የሚገኙትን ከተገዙ ዓመት እንኳን ያልሞላቸውን ወንበር ጠረጴዛ እንዲቀየር ሲያደርጉ፤ ሠራተኞቹ ለምን? ብለው መጠየቅ ሌላ እርምጃ የሚያስወስድ ነበር። ፕሮፌሰሩ ከ10 ሚሊየን ብር በላይ አውጥተው ለላይብረሪ ወንበርና ጠረጴዛ ሲገዙ የተማሪዎችን የመጽሐፍ ፍላጎት ለማሟላት በነበራቸው የወራት ቆይታ አንድም ያደረጉት ነገር አለመኖሩ፤ ተማሪዎቹን አሮጌ መጻሕፍቶችን በአዲስ ወንበር ተቀምጠው እንዲያነቡ አስገድዷቸዋል። ይህ አይነት አሠራር ከተዛባ ዕይታ የሚነሳ፤ ቀድሞ ምን መደረግ እንዳለበት አለመገንዘብ እና የታይታ ሥራ ከመውደድ የሚመነጭ ነው።

ይህን ያህል ብር ለገጠሪቱ ድሃ አርሶአደሮች ማኅበረሰብ ክፍል ምን ያህል ጤና ጣቢያ፤ ምን ያህል አምቡላንስ እና ምን ያህል የሕክምና መገልገያ እቃዎችን እንደሚገዛ ሲታሰብ ድርጊቱ እጅግ ከማሳዘንም ባለፈ ያሳፍራል። መንግሥት እንዲ አይነት ኃላፊነት የማይሰማቸው የማያገናዝቡ ሰዎችን በመመዘን የሕዝብ ሀብት ያለአግባብ እንዳይወጣ የማድረግ ኃላፊነት ይኖርበታል። መንግሥት ከሕዝብ የሚሰበስበውን ግብር በአግባቡ ለታሰበለት አላማ በማዋል በተለያዩ ኃላፊዎች የሚደረግን የሀብት ብክነት ሊቆጣጠር ይገባል።

አሁን ቢሆን የዚህ የወንበርና የጠረጴዛ ግዥ አግባብነትና ላይ አሁን ያሉት ኃላፊዎችም ሆነ ፕሮፌሰሩ ሊጠየቁ ይገባል።

2. ሠራተኞችን ያለበቂ ምክንያት ከሥራ ገበታቸው ላይ ማባረር/ማንሳት

ፕሮፌሰሩ ሆስፒታሉንና ኮሌጁን አንድ በሚያደርጉበት ወቅት ያለ ግልጽነት እና ተጠያቂነት በሌለበት አሠራር በርካቶችን ከሥራ ገበታቸው ላይ ዝቅ ብለው እንዲሠሩ አድርገዋል። ሲብስም በጋርዮሽ የአስተዳደር እሳቤያቸው አንድ ላይ አብዮታዊ እርምጃ የተወሰደባቸው ሰዎች ብዙዎች ናቸው። ቀድሞ የኮሌጁ ዲን የነበሩትን ሰው፤ መቶ በመቶ የኮሌጁም ሆነ የሆስፒታሉ ማኅበረሰብ እኩል ድምጽ የሚሰጣቸው፤ እጅግ ሥራ ወዳድ እና የተማሪም ሆነ የሠራተኛውን ችግር ለመፍታት ደከመኝ ሰለቸኝ የማይሉ ሰውን በአንድ ደብዳቤ ከ10 ዓመት በላይ ካገለገሉበት ዩኒቨርሲቲ ከአመራርነት የማባረር ሥራ ሠርተዋል። ይህም ተግባራቸው እስከ አሁን ድረስ ማንንም ያላስደሰተ ተግባር ነበር። ፕሮፌሰሩ ሠራተኛ ማባረር ከማብዛታቸው የተነሳ ከዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር አድማሱ ከአሁን በኋላ ምንም አይነት ሠራተኛ እንዳያባርሩ ማሳሰቢያ ተሰቷቸው ነበር። ፕሮፌሰሩ ለጤና ጥበቃ ሚኒስትርነት እስከተሸሙበት ጥቅምት 22 ቀን ድረስ ሠራተኞችን ከፍና ዝቅ የማድረግ ሥራ ተጠናውቷቸው ነበር። በአሁኑ ሰዓት ያለአግባብ የተነሱ በርካታ ሠራተኞች ጉዳያቸውን ወደ ፍርድ ቤት በመውሰድ እየተሟገቱ ይገኛሉ።

ፕሮፌሰር ይፍሩ ብርሃነን

ፕሮፌሰር ይፍሩ ብርሃነን


በመሰረቱ አንድ ተቋም የተሰጠውን አላማ ከግብ ለማድረስ የባለሙያዎች አስቷጽኦ ከፍተኛ መሆኑ ይታወቃል፤ ነገር ግን ሠራተኛን በጥናት ላይ የተመሰረተ ምደባ በማድረግ አንድም የሠራተኛን መብት አክብሮ ተቋማዊ ግብንም ማሳካት ይቻል ነበር። የፕሮፌሰሩ አካሄድ ግን ከዚህ በጣም የራቀ እና አስተዳደራዊ ፍልስፍና ያልነካው መሆኑ እጅጉን ያስወቅሳቸዋል።

3. የተማሪዎችን የኮምፒዩተር መጠቀሚያ ክፍል የመዝጋት ሥራ

ኮሌጁ እንደ ኮሌጅ እንዲቀጥል የተማሪዎች ኤሌክትሮኒክ መጠቀሚያ ላይብረሪ ወሳኝነቱ አያጠያይቅም። በአሁኑ ሰዓት ብዙ ተማሪዎች ላፕቶፕ ተጠቃሚ የሆኑትን ያህል፤ ከገጠሪቱ ኢትዮጵያ የተገኙ የዝቅተኛ ቤተሰብ ልጆችም ቀላል ቁጥር አይዙም፤ ቀድሞ ተማሪዎች ሲጠቀሙበት የነበረው በርካታ ኮምፒዩተሮችን የያዘው ኮምፒዩተር ክፍል በአሁኑ ወቅት ከተዘጋ እና ከአገልግሎት ውጪ ከሆነ ሦስት ወራቶች አስቆጥረዋል። ይህም እሳቸው የሚመሩት ከፍተኛ ማኔጅመንት ለነገሮች ያለው ንዝህላልነትን የሚያመላክት ነው። ይባስ ብለው ፕሮፌሰሩ በአንድ ወቅት “ይህን ክፍል ከዚህ አንስተን ወደ ሌላ ቦታ እንወስደዋለን” በማለን በሚሊየን የሚቆጠር ሀብት የፈሰሰበትን ክፍል እንደ ተራ ነገር በመቁጠር ተናገረው ነበር።

4. የግል ጥቅማቸውን የሚያሳድዱ ሰዎች መከበብ

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ በሹመት ቀን “የትምህርት ዘርፍና በአመራር ዘርፍ በመሰማራት በጤና ልማትና ምርምር ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ፤ በቅርቡ በተመደቡበት የጥቁር አንበሳ ሆስፒታልና ጤና ሳይንስ ኃላፊነት ጉልህ ውጤት ማምጣት የጀመሩ” በማለት ስላልተመዘነው ሥራቸው መስክረውላቸዋል። መንግሥት እኚህን ሰው ወደ ሚኒስትርነት ማዕረግ ከማምጣቱ በፊት ያገለገሉበትን መስሪያ ቤት ሠራተኞች፤ የቀድሞ እና የአሁን አመራሮችና ተማሪዎች ጋር በመውረድ የዳሰሳ ጥናት በጥቂቱ ቢያካሄድ መልካም ነበር። በመሰረቱ ፕሮፌሰሩ የመሥራት ፍላጎት እና የመሥራት አቅም ቢኖራቸውም፤ የሚሄዱበት አካሄድ ግን ተቋምን ከማዘመን ይልቅ ቁልቁል እንደሚወስድ፤ ብዙ ነገሮችን እንደሚያመሰቃቅል የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተሞክሮን ባለማየት ለጤና ጥበቃ ሚኒስትር አድርጎ መሾም እጅግ ከመግረምም የተነሳ ያሳዝናል።

ፕሮፌሰሩ በዙሪያቸው የከበቧቸው ሰዎች መንግሥት ከተከለው ደመወዝ በላይ ከሦስትና ከአራት እጥፍ በላይ ለማካበት የተሰገሰጉ ናቸው፤ በወር እስከ 76ሺህ የኢትዮጵያ ብር ከተለያዩ ፕሮጀክቶች በመሰብሰብ የግል ጥቅማቸውን የሚያባርሩ ሰዎች ጥላ ከለላ አድርገው ሰውየውን ከበዋቸዋል። አሁንም ይህን አይነት አሠራር ጤና ጥበቃ ይዘው የሚሄዱ ከሆነ ተቋሙን ለከፋ ውድቀት የሚጋብዙት መሆኑን መንግሥት ሊረዳው ይገባል።

5. ያልተገባ ቦታ መገኝት

ፕሮፌሰሩ በሺህ የሚቀጠር ሠራተኛን በአግባቡ እንዲያስተዳድሩ ትልቅ ኃላፊነት ተሰቷቸው ከውጭ የመጡ እንግዶች እሳቸውን ለማነጋገር ቢሮ በሚጠብቋቸው ሰዓት እሳቸው በየሽንት ቤቱ እየዞሩ የተከፈተን ቧንቧ መዝጋት፤ ከውጭ የመጣን እቃ እንደ ግምዣ ቤት ኃላፊ ቆሞ ማስወረድ፤ በየቢሮ እየዞሩ ሠራተኞችን ክፍሉን እንዲለቁ ማድረግ፤ ቆሻሻ ማጸዳት፤ ቀለም ማስቀባት፤ ኮርኒስ ማሠራት፤ የሚወገዱ እቃዎች ማስቆጠር እና ለኤክሲኩቲቭ ዳይሬክተር የማይሠራውን ሥራ በመሥራት ዋና ጊዜያቸውን ያባክኑ ነበር።

በአንድ ወቅት ፕሮፌሰሩ የግል መኪናቸውን አቁመው ቢሮ ገብተው እስኪወጡ ድረስ የመኪናው ስፖኪዮ ከቦታው ላይ በማጣታቸው ደብዳቤ በመጻፍ የጥበቃ አባላቱን 1000 ብር ከማይደርሰው ደመወዛቸው ተቆርጦ የጠፋው ስፖኪዮ ከሰባት ሺህ ብር በላይ በማውጣት እንዲገዙ ማድረጋቸው ግርምት የፈጠረ ነገር ነበር። በቁጥር ለመቁጠር የሚያዳግት የሕክምና መሳሪያ ሲሰረቅ ቁጥጥር የማይደረግበት ሆስፒታል፤ የአንድን ኃላፊ የመኪና ስፖኪዮ ሲጠፋ አስተዳደራዊ እርምጃ ብሎ ይህን ማድረግ መቻል ብዙዎች እንዲገረሙ አድርጓል።

6. ሆስፒታሉ ግማሽ ክፍሉ እንዲፈርስ የማድረግ ውሳኔ

ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በርካታ የሕክምና አገልግሎቶችን እንዲሰጥ ታስቦ በወቅቱ በነበረው የኢትዮጵያ ሕዝቡ የአንድ ብር መዋጮ ከተሠራ 50 ዓመት አልፎታል፤ ይህ ሆስፒታል ያለውን ይዞታ ይዞ እንዲቆይ ማድረግ ይገባል፤ በፕሮፌሰሩ የወራት የሆስፒታሉ ቆይታ ግን የሆስፒታሉ የፊት ለፊት አካል እንዲፈርስ ውሳኔ ተሰጥቶበት ክፍሎች እንዲለቁ እያደረጉ ይገኛሉ። ይህም ትልቅ ሕንጻን በቦታው ላይ ለመሥራት በማሰብ ነበር፤ ነገር ግን ቅርስ ሊሆን የሚችልን ተቋም እያፈረሱ በመስታወት የተቀባ ሕንጻን መሥራት ዘመናዊነትን አያሳይም። አሁንም መንግሥትም ሆነ የኮሌጁ አስተዳደር የሆስፒታሉን አንድ ክንፍ ከማፍረስ እንዲታደጉት በፕሮፌሰሩ የተወሰነውን ውሳኔ ዳግም መጤን ይገባዋል።

ፕሮፌሰሩ የሚወስኑት ውሳኔ ቅጽታዊ ከመሆኑ በተጨማሪ የውሳኔው ትርፍና ኪሳራ በአግባቡ ሳያጤኑ ስለሚወስኑ ተቋሙን ያላስፈላጊ ዋጋ አስከፍሎታል፤ ሮም በአንድ ቀን አልተገነባችም የሚለው እሳቤ እሳቸው ጋር አይሠራም። ሮምን በአንድ ቀን ለመገንባት በቅጡ ያልተመከረበት ውሳኔን ሲወስኑ ይታያል። ይህን አይነት አካሄድ ደግሞ እያደር ከሚያመጣው ጥቅም ይልቅ ጉዳቱ እጅጉን ያመዝናል፤ ሠራተኞችን ለማንሳት ሲፈልጉ ቀጣይ ስለሚኖራቸው ቦታ ብዙም አያሳስባቸውም፤ ካነሷቸው በኋላ ቦታ ካለ ይሰጣሉ ያለበለዚያ ደግሞ ያባርራሉ። ሠራተኞች አስር ዓመት ተቀምጠው ከሚሠሩበት ቢሮ በአንዲት ቀን ተነስተው እንዲወጡ ይፈልጋሉ … ሌላም ሌላም …

በመጨረሻም

ፕሮፌሰር ይፍሩ በግላቸው በርካታ ጽሁፎችን ቢጽፉም፤ ግለሰባዊ ጥንካሬያቸውን ያሳያል እንጂ ጤና ጥበቃን የሚያክል መንግሥት ለአገሪቱ ከሚመድበው በጀት በላይ ከውጭ ተራድኦ ድርጅቶች የሚያገኝን እና ወደ ሥራ የሚቀይርን ተቋም የማስተዳደር አቅም አላቸው ማለት አይደልም። በአካዳሚክ እውቀት እና ተቋምንና ሕዝብን የማስተዳደር ክህሎት እጅግ የተራራቁ መሆናቸውን መንግሥት ሊረዳ ይገባል። አንድን ተቋም ለማስተዳደር በአካዳሚክ እውቀት መሰረታዊ ቢሆንም፤ የግለሰቡ አስተዳደራዊ ፍልስፍናው እና የሠራቸው ሥራዎች ሚዛን ላይ መቀመጥ ይኖርባቸዋል። አሁንም በዶ/ር ከሰተ ብርሃን ያዋቀሩትን የጤና ጥበቃን የበላይ አመራር እንዳልነበረ አድርገው አፈር እንደሚያበሉት፤ የሚሠራውን ከማይሠራው ጋር ደባልቀው እንደሚያባሩ ዝቅና ከፍ እንደሚያደርጉ እሙን ነው። ሲከተሏው የነበሩትን ሰዎች አስከትለው በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ እንደሚሰገስጉ እርግጥ ነው።

እኚህ ሰው ባልተመዘኑበት ሥራቸው ወደ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ሹመታቸው እንደተሳማ በሰዓታት ውስጥ በጥቂት የበላይ ወዳጆቻቸው እና በአጨብጫቢዎቻቸው አማካኝነት በኮሌጁ የስብሰባ አደራሽ “Congratulations!” በማለት ሽኝት ተደርጎላቸዋል። እሳቸው እጅጉን በብዙ ነገር ያመሰቃቀሉትን ተቋም “ከጎናችሁ ነኝ” በማለት ቃል ገብተዋል። አዲሱን ጤና ጥበቃን ለማመሰቃቀል ለውጥ የሚመስልን፤ ነገር ግን ለውጥ ያልሆነን ሥራ ለመሥራት የዶ/ር ከሰተን ወንበር ተረክበዋል። ውጤቱን ወደፊት የምናየው ይሆናል።

ቸር ሰንብቱ!
የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሠራተኛ


ስኬት የሚገኘው ራዕይ ፣ ዕሴትና ተግባር ሲዋሃዱ ብቻ ነው –ማርእሸት መሸሻ

$
0
0

ማስገንዘቢያ የዚህ ፅሑፍ ዋና ዓላማ በኢትዮጵያውያን ዘንድ በተለይም የሰባ ዓመታት የፖለቲካ ጉዞ የዘውዳዊውን፤ የወታደራዊውንናየዘረኛውን ወያኔ ሥርዓቶች ሲቃወሙ በባጁት ወገኖቼ መሃከል ውይይትን ለመቀስቀስ ነው። ይህን ጽሁፍ በእንግሊዝኛቋንቋ “a way forward to a post-woyane demoratic and Just Ethiopia” በሚል ርዕስ አዘጋጅቼ ለንባብ አብቅቼዋለሁ። የቀየርኩት ነገር ቢኖር ርዕሱን ብቻ ነው። የእንግሊዝኛውን ጽሁፍ ለማንበብ : http://www.ethiomedia.com/1016notes/a_way_forward.pdf ይጫኑ። ፅሑፉን በታችኛው የላቲኑ ፊደል ‘a’ የጀመርኩት ሆን ብዬና ለአንባቢዎቼ በዚያ ፅሑፌ ያስቀመጥኩት ትንተናከገባንበት ቅርቃር መውጫ መንገድ የእኔ ብቻ አይደለምና ሌሎች ሊቀርቡ ከሚችሉ አማራጮች እንደ ኣንድ ኣማራጭ እዩልኝ ለማለት ነው። የነቃሁ የበቃሁና የመጠቅሁ ነኝና “የእኔን መንገድ ካልተቀበላችሁ” ለማለት ሳይሆን እንዲያውም በተፃራሪው ያለኝ ዕውቀትና ልምድ በሳይንስና ቴክኖሎጂው መስክ ነውና የፖለቲካ ሳይንቲስት፤ የሥነ-አዕምሮ ጠቢብ ወይም የፍልስፍና አዋቂ አለመሆኔ በግምት ተይዞልኝ፤ እንደማንኛውም አገሩንና ወገኑን እንደሚወድ ዜጋ በጉዳዩ ያገባኛልና ባለኝ አቅም የድርሻዬን ላበረክት ለማለት ነው። የምፅፈው ባለፉት ሁለት አሥርተ ዓመታት በፀረ-ወያኔው ንቅናቄ ካዳበርኩት ልምድ ላይ በመመርኮዝ ነው። በዚህ ልምዴም ከተቃራኒው ወገን የኣሰራርና የኣላማ ጉድለትን አያለሁ። በዚያ ላይ ደግሞ ዴሞክራሲና ፍትህ የሰፈነባት አገርንበመመስረት ራዕይ ዙሪያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች – ሕፃናትና አረጋውያንን ጨምሮ – ከፍተኛ የሆነ መስዋዕት እየከፈሉ ነውና ስለታዘብኳቸው ጉድለቶች መናገር አለብኝ – እየተከፈለ ያለው መስዋዕትም መና ሆኖ እንዳይቀር መናገርአለብኝ! በተጨማሪም ይህ ለዘመናት በተቃዋሚነት ሥነልቦና ብቻ የተተበተበ የሚመስለው ትግላችን ተቀይሮ ውጤት-ተኮር በሆነ ሥነልቦና ተተክቶ ይጓዝ ዘንድ ለማሳሰብም መፃፍ አለብኝ።እንደገና መስቀለኛ መንገድ ላይ ደርሰናልመቼም ቢሆን የኋሊት ማሳያ መስተዋትን ብቻ ተጠቅሞ መንዳት ከግጭት ላይ ማድረሱ አይቀሬ ነገር ነው ይባላል። ያእንዳይሆን ሹፌሩ በሁሉም የማሽከርከር ወቅት ቀልቡን ሁሉ አሰባስቦ የሚጓዝበትን መንገድ ብቻ ሳይሆን አካባቢውን በሰፊ ዕይታና ቅኝት ውስጥ አስገብቶ ወጣ ገባውንና ጠመዝማዛውን ሁሉ እያማተረ ሲያሽከረክር ነው የወደ መድረሻውጉዞ ቀና የሚሆነው። ማንኛውም እይታና ራዕይ ምን ያህል የተወሳሰበ እንኳ ቢሆን – “ግብ” ብለን የተቀበልናቸው እምነቶቻችንላይ ያደርሰን ዘንድ በጥንቃቄ የተሰላ ውጤት-ተኮር ተግባር ማካሄድን ይጠይቃል።የወያኔን አገዛዝ ስቃወም ይኸው ሃያ ዓመታት ሆነኝ። የምወዳትን ሀገሬን ኢትዮጵያን ከለቀቅሁበት ጊዜ ጀምሮ የምወደውን አፈሯን ተመልሼ ሳልረግጥ አብዛኛውን የጉልምስና ሕይወት ያሳለፍኩት አውስትራሊያ ውስጥ ነው። በዚህም ምክንያት እንደ ቅንጅትና ህብረት ያሉ ፖለቲካዊ ቅርርቦችን ሳስተውልና ስከታተል ቆይቻለሁ። የትብብር ምሥረታዎቹም ሆነ የፍርሻዎቹ አካልየነበርኩበት ጊዜ ግን አልነበረም። ዛሬም የወያኔን በጭቆናና በአፈና ላይ የተመሰረተ አገዛዝ ሽረው ዴሞክራሲና ፍትህ የሰፈነባትን ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ እየታገሉ ያሉ ፖለቲካዊና ማኅበረሰባዊ/ሲቪክ ስብስቦች አባል በመሆን የበኩሌን ላበረክት የንቅናቄው አካል ነኝ። ” በወቅቱ ባለው አለመርካት ጥሩ ነው፤ በዚያም ምክንያት መብከንከን ካለ ደግሞ የተሻለ፤ ብሎም አለመረጋጋት ከተከሰተ ደስ የሚል፤ ከዚያ ሃሳቦች ይመንጩ፤ ከባድ ሃሳቦች – ከባድ ሥራዎችም ይፍለቁ፤ በዚህ ሁሉ ውስጥ ራሱን አሳንሶ የሚመለከት ራሱን ከፍ ያድርግ ” ሒዉበርት ሐምፍሬሕዝባችን በጨካኝ ዘረኛ አገዛዝ ሥር ከወደቀ ሩብ ምዕተ አመት ተገባደደ። ለማምጣት ያለምነውን ስኬት ሲታይ ግን የዛሬ ሃያ ዓመት ከነበርንበት ምንም ያህል ፈቀቅ እንኳ አላልንም። ለመሆኑ ግባችን (ያጭሩ ሆነ የረጅሙ) ያልነው ላይ የነጠረ ዕይታ አለን? ግባችን ብለን ወደአቀድናቸው ዐቢይ ጉዳዮች ሊያድርሱን በሚችሉ ተከታታይ ራዕዮቻችን፤ ልንከውን በምንፈልጋቸው ተግባሮችና ልናበረክት በምንችላቸው ድርሻዎች ላይ የጠራ ግንዛቤ አለን? በነዚህ ከልባችንና ከአዕምሮአችን መንጭተው ከወያኔበኋላ የምንመኛትን ኢትዮጵያ ዕውን ለማድረግ መከናወን ስላለባቸው ጉዳዮች የዳበረ ግልፅነት አለን? ራዕዮቻችንን የምናስተነትነው ፍፁም በሆነ ግልፅነት ላይ ተመስርተን ነው? ያንንስ ራዕይ በጸና ዕምነት ላይ አስደግፈን እናጸናዋለን? እያደረግንያለው ሁሉ በጠንካራ የተልዕኮና የስኬታማነት መንፈስ ላይ በፅኑ የተመሰረተ ነው? እነኝህ ሁሉ በጭንቅላቴ ውስጥ የሚመላለሱጥያቄወች ናቸው።ዛሬም ገና በተቃውሞው ምዕራፍ ውስጥ ነው ያለነው። ታዲያ ያለማቋረጥ እያዥጎደጎደን ያለነው መፈክርና እያከናወንን ያለው ከባድ ሥራ ሁሉ ህዝባችንን ወደተስፋይቱ ምድር ወደነፃነት እኩልነትና ፍትህ ሊያደርስ የሚያስችለውን ግልፅነትንና ጥራትን የተጎናፀፈ ነው? ከወያኔ ወዲያ ለምንፈጥራት ኢትዮጵያ ያሉን ራዕዮች ለመሆኑ ምንድን ናቸው? አልፈው አልፈው ብልጭ ድርግም ከሚሉ ቀውጢ ጊዜ ከሚወልዳቸውና በጥቂት ድርጅቶች መሃል ከመነጩ በትብብር የመስራትና የመግባባት መግለጫዎች ባሻገር እስካሁንም የጠራ የጉዞአችን አመላካች ካርታ ያለን አይደለንም። ይህ አጭር ፅሁፍ በርከት ያሉ ጥያቄዎችን በማንሣት ራዕያችን፣ እሴቶቻችንና ተግባራችን ምን ምን መሆን አለባቸው ከሚሉ ነጥቦች ላይ በመንተራስ አማራጭምላሾችን ለማበርከት ይሞክራል። ኣቢይ ኣላማው ግን የወደፊቷ ኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ዜጎች ሁሉ ያሉብንን ድርጅታዊና ግለሰባዊ ድክመቶች አንጥሮ ለማሳየትና እንድንወያይበት ለማበረታታት፤ እንዲሁም ሕብረተሰባችን ተሳስሮ የኖረበትን ማሕበረሰባዊ ድርና ማግ በማይሽር ሁኔታ ለመበጣጠስ ከዲያብሎስ ጋር እንኳን ሊዶልት የማይመለስን ወያኔን እኩይኣላማ ለማክሸፈና፤ ኣዲሲቷን ኢትዮጵያን ለመገንባት የተጠየቀውን መስዋዕትነት ሁሉ ያለስስት ከፍሎ ሊያስወግድ የተዘጋጀ በሃገርም ውስጥ ሆነ በውጭ ኗሪ ኢተዮጵያዊ ትግል የራዕይ፣ የዕሴትና የተግባር ጉድለቶች ያለምንም ፍርሃትና በግልጽነት መጠቆም ኣለባቸው ከሚል ዕምነት የመነጨ ነው።ራዕይ በረጅሙ ታይቶ ታልሞና ታቅዶ ስኬታማ ለሆነ የረጅም ጊዜ ለውጥ የተቀረፀ የተልዕኮ መርሐግብር ስልትና ግብን ስሜት በሚያቃጥል ጽኑዕ ኣላማ ወዳድነት ያካተተ ነው። በአሁኑ ጊዜ የተለያዩ የፖለቲካና ማህበረሰባዊ/ሲቪክ ድርጅት ወይም ስብስብነን የሚሉ በሙሉ ወያኔ የሚባል የጋራ ጠላት እንዳላቸው ከመግለፅ በተጨማሪ ፍትሓዊና ዴሞክራሲያዊ የሆነ ሥርዓትን መፍጠርንና መገንባትን የሚያስችል የሚል አንድ ወጥ የግብይት ቋንቋ አላቸው ለማለት እቸገራለሁ። ከላይ ከላይ ሲታይ ሁሉምመልካም ይመስላል እንጅ። ሁሉም ዲሞክራሲ ኣስተዳደርን ይፈልጋል። ዕኩልነትና ፍትህንም እንደዚሁ። ታዲያ በዚህ ራዕይ ዙሪያ በጋራ መሰለፍ እንዴት ኣልቻልንም? የፊደል ጋጋታ ድርጅት ስሞቻችንን ከማብዛት ይልቅ። ፍትሓዊና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትም በህግ የበላይነት ላይ የተመሰረተና ሁሉንም ዜጋ ነፃና እኩል በሆነ መንገድ የሚያስተናግድናለፀረ-ወያኔው ትግል የጋራ መግባቢያ ቢሆንም በራሱ ብሔራዊ/ሀገራዊ ራዕይ ሊሆንም፣ ሊያሳይም አልቻለም። ምክንያቱም ይህ ዓይነቱ ራዕይ ገና የጉዳይ ባለቤት ነንና ያገባናል በሚሉት ፖለቲካዊና ማህበረሰባዊ ድርጅቶች ገና አልተቀረፀምና ነው። ይህ ደግሞ ገና ተገንጥለው የራሳቸው ሥርዓተ-መንግሥት የመፍጠር ምኞታቸው ያልሰከነውን እንኳን ግምት ውስጥ ሳናስገባ የፀረ-ወያኔው ትግል አካል ነን ከሚሉትና በውጭ አገራት እየተደረጉ ካሉ የኦሮሞ የዑጋዴን የሲዳማ ወዘተ ማህበረሰብ አባላት በየጊዜው በሚያደርጓቸው ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ የሚንፀባረቅ ሀቅ ነው። የባንዴራ ትርጉም መጥፋቱ፤ ህጋዊ እውቅና የሌለውና ያገባኛል የሚል ሁሉ ያልተወያየበት፣ ውሳኔም ያልተደረሰበት ኣዕምሯዊ ሃገር ስም ወዘተ ……የመሳሰሉት ራዕየ ቢስነትን ወይም ብዥታን የሚያሳዩ ክስተቶች በሰፊው ሰፍነዋል።ችግራችን የወያኔ መወገድ ብቻ አይደለም። የወያኔን ኣምባ ገነናዊ ስርዓት ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ገጽ መክሰምና መጥፋትማ ልክ የፀሐይን ከበስተምሥራቅ የመውጣቷን ያህል (ያ ደግሞ በቅርቡ እንደሚሆን ተስፋዬ ነው!) እርግጠኛ ሆኖ መናገር ይቻላል። ራዕያችን፣ እሴቶቻችንና ተግባራችን ግን ከወያኔ ባሻገርና ወዲያውኑ የምንፈጥራትን ሀገር – ” ኢትዮጵያችንን ” – በግልፅ ተንትኖ ማስቀመጥ መቻል አለበት።እያንዳንዳችን ምንም የፖለቲካ ኣመለካከቶቻችን ተጻራሪ ቢሆኑ እንኳን እነዚያኑ እምነቶች በግልፅና በመልክ መልኩ አስቀምጠንና ከወዲሁ አርቀን ማቅረብ መቻል አለብን። የፖለቲካ ኣመለካከቶቻችን ድርጅታዊ ፍላጎቶቻችንና ኣላማወቻችንን በተደበቀ ካዝና ውስጥ ታሽገው ለአባላት ብቻ እየተመጠኑ የሚገለፁና ከህዝብ ዕይታ ተሰውረው በሚስጥር የሚያዙ መሆን የለባቸውም። ግልፅነትና ቅንነት ብቻ ነው መንገዳችን አባጣ ጎባጣ እንዳይሆን የሚያደርገው። ስለሆነም “ለመሆኑ ዕምነቶቻችን ምን ምን ናቸው?” የሚለው ጥያቄ መነሳት ያለበት ነው። ለምሳሌ ያህል – ኣለም ኣቀፍ ዳር ድንበሯ የታወቀ፣ የታፈረና የተከበረ፤ሁሉም ዜጋ የታወቀ ክልሏን እያንዳንዷን ካሬ ሴንቲ ሜትር በደሙ ጠብታ ሊከላከል ቁርጠኛ የሚሆንላትን ኢትዮጵያ መፍጠር እንችላለን? ወይንስ የግልም ሆነ የጋራ የረዥም ጊዜ ትግላችን ወራሪው ጣሊያን ያለመውንና ኣገር ኣጥፊው ወያኔ የተገበረውን የዘር ማንዘሬ አፅመ-ርስት የሚለውን የክልል ፍልስፍና ለማስረገጥ ብቻ ነው?የመንግሥት ግንዛቤያችንስ ምንድነው? አሀዳዊ የተማከለ መንግሥት? ወይስ ፌደራላዊ? አሀዳዊና የተማከለ ማለት ሥልጣኑን አማክሎ የያዘው ኅይል ለየክፍለ ሀገራቱ ተሿሚዎቹ በሚያወጣቸው ህጎችና በሚደነግጋቸው አዋጆች እየቆነጠረ ውስን ሥልጣንየሚቸርበት የሥነ-መንግሥት ዓይነት ነው። በንጉሳዊውና በደርግ ዘመን የነበሩት አስራ አራት ክ/ሀገራት የእንደራሴ ሥልጣን ሹም ሽር የአሀዳዊና የተማከለ መንግሥት ምሳሌ ነው። ሌላም ምሳሌ ካስፈለገ የታላቋ ብሪታኒያ የተባበሩ መንግስት United Kingdom ሥርዓተ መንግስትና ሥልጣንን በፈለገው መጠን ቀነጣጥቦ የሚቸራቸው ሰሜን አየርላንድ፤ ስኮትላንድና ዌልስ ተጠቃሽ ናቸው። በአንፃሩ ደግሞ ብዙ ጊዜ በኢትዮጵያውያን ፖለቲካ ኣቀንቃኞች በግርድፍ የሚገለጸው ፊዴራላዊ መንግሥት እንኳን ተግባራዊ በሆነባቸው እንደ ጀርመን፣ ቤልጂየም፣ ካናዳ፣ ኣውስትራሊያ ወዘተ ባሉ በቅልቅል ባህል፣ ፍልስፍናና ፖለቲካ በተመሰረቱ ሃገራት ምን ያህል ችግር ፈጣሪ እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል። እኛስ በእያንዳንዱ ክ/ሀገር እኩል ሥልጣን ያለበት ፌዴራሊያዊ የመንግሥት ሥርዓት (Symmetric Federal System) ነው የምንሻው? ወይንስ በሥልጣን ክፍፍሉ ጊዜ አንዳንድ ግንዛቤ ውስጥ መግባት ያለባቸው (የህዝብ ብዛት፤ የተፈጥሮ ሀብት ክምችት፤ ምርታማነት ሌላም ሌላም) ጉዳዮች ግምት ውስጥ አስገብቶ ሥልጣንን እንደየአበርክቶው የሚያደላድል (Asymmetric Federal System) ፌዴራሊዝምን? ሁለተኛው ጠቃሚ መነጋገሪያችን መሆን ያለበት ዕሴቶቻችን (የምናምናቸውና የምንታመንባቸው የህይወት መመሪያወቻችን) (Values) ጉዳይ ነው። እነዚህ ዕምነቶች የምንከተለውን የተግባር ክንዋኔና (Action) ውጤት ማስተንተኛ መሳሪያና የዕምነቶቻችን ዝንባሌዎቻችንና ባህሪዮቻችን ቅኝት ማስተካከያም ናቸው። ዕምነት የሞራል (ቅንነት፤ መከባበር፤ ፍትሃዊነት ወዘተ) የፍልስፍና ግንዛቤ (ኃይማኖት፤ ርዕዮተዓለም፤ ፖለቲካ) እንዲሁም ማህበረሰባዊ (የጋራ ብሩህ ተስፋ፤ የጋራ ዕድገት ምኞት፤ አብሮና ተባብሮ መኖር፤ የጋራ ክብርና ሞገስ፤ ከራስ-በላይ-ንፋስ-አለማለትን ወዘተ) የሚያካትት ሲሆን ቅዱስ ነው። “ነፃና ፍትሃዊ የሆነና ግልፅ ምርጫ፤ ኢትዮጵያዊነት፤ የዜጎች እኩልነት ወዘተ” የመሳሰሉት ዕሴቶች የጋራና የተቃውሞ ቋንቋችን ከሆኑ ውለው አድረዋል። ተግባራችንስ በነዚህ ቅዱስ ዕሴቶች የተደገፈ ነው ወይ?”ተስፋ ያለው ወገን ሕልሙ ዕውን ይሆንለት ዘንድ ይመኛል፤ ተስፋ ያጣው ግን ቅዠቱ ዕውን እንዲሆን ይጠብቃል” …. ምንጩ ያልታወቀፈታኝ በሆነ ወቅት የምንሰራው አምነንና የኛ ብለን አንግበን ያቆየናቸው ዕምነቶች ነፀብራቅ ነው። ስለሆነም ለወደቁ ጀግኖቻችንእናነባለን። አንዳርጋቸውን፤ እስክንድርን፤ አንዱዓለምን ስናስብ እናለቅሳለን። በኃዘን የተጎሳቀለች እናትን ስንመለከት ልባችን ይደማል። እምቢ ባይ አትሌት በዓለም ፊት የሕዝብን የተቃውሞ ምልክት ሲያሳይ “እሰይ! እንኳን የኛ ሆነ” ብለን ኩራት ይሰማናል። በኣንጻሩ ደግሞ በመሃላችን የቅቤ-ገበያ-ውሎ ዓይነት ቋንቋን ተጠቅመን ክቡሩን የሰው ልጅ ለማዋረድ፤ ዝቅ አድርገን ለመመልከትና (በነጠላም ሆነ በቡድን) ለማቅለል የምንሞክር ሞልተናል። ዮዲት ወ/ሩፋኤል የተባለችና የአሪዞና ነዋሪ የሆነች ሴት በፌስ ቡክ ላንጎደጎደችው ስድብ የሰተጣት ምላሽ በትግሬና አማራ/ኦሮሞ ዜጎቻችን መሀከል የዘር ፍጅት ጦርነትን ሊጭር የተቃረበ ይመስል ነበር። በርግጥ የዮዲት አባባል የትግራይን ህዝብ ሊወክል ይቅርና እዚህ ግባ የሚባል ግምት ሊሰጠውባልተገባ ነበር። ለኦሮሞና ለኣማራ ጥብቅና የቆሙትም ከትግሬ የተለየ ብልሃት ወይም ጀግንነት፣ ድድብና ወይም ዕውቀት እንደሌላቸው ማወቅ የተሳናቼው መስሎ ነበር። በእንዲህ ያለው ፈታኝ ወቅት በግለሰብ ድርጊት ወይም ርምጃ ተጎትተን ከወደቅንና በሁሉም ማህበራዊና ባህላዊ መስክ መከባበራችን በአንዴ ጥሎን ከነጎደ ታዲያ የቱ ጋ ነው ፍትህ እኩልነትና ዴሞክራሲ የሰፈነባት ኢትዮጵያን የመፈለግ አመክንዮአችን? ኣስተሳሰባችን ሁሉንም ፖለቲካዊና ማህበረሰባዊ ስብስቦችን አካታችና ቀና ኣመለካክትና ፉክክርን healthy competition የሚያበረታታ መሆን አለብን። ኢትዮጵያችን የበርካታዎች እናት፤ የብዙ ብሔር/ብሔረሰቦች አገር፤ የተለያዩ ፖለቲካዊ አመለካከቶች ክምችት ናትና ምንም ወይም ማንም ህብረ ብሄራዊም ሆነ ብሔር/ብሔረሰባዊ ድርጅት በኃይል ሊገዛት የሚገባት አይደለችም – በፍፁም! ሌላው መረዳት ያለብን የማንም ብሔር/ብሔረሰብ ከፖለቲካው ምህዳር መገለል ሰላምንና መረጋጋትን ሳይሆን ቅሬታንና መተረማመስን የሚያስከትል መሆኑን ነው። ስለዚህም ነው ሁሉም የፈረስ-ግብይት በግልፅና ባልተሸፋፈነ መንገድ ተካሂዶ የነገይቱ ኢትዮጵያ የምትገነባበት የመሰረት-ድንጋይ የሚተከልበት ሰነድ በሌጣ ወረቀት ላይ ሁሉም ያገባናል የሚል ወገን በተገኘበት መቀረፅ አለበት የምለው። ይህን ስል የቀደመ ማህበራዊና ባህላዊ የፖለቲካ ታሪካችን በፍፁም መረሳት የለበትም ማለቴ አይደላም። ያንን አለመርሳታችን ነው
እንዲያውም የግድ በአስቸኳይ ማደራጀት የሚያስፈገልንን የሐቅና ዕርቅ ሒደት ሥራችን የሚያቀልልን እላለሁ። ያ ኢትዮጵያና ህዝቧን ለመግዛት ተብሎ በወያኔ የተቀረፀና የተደነገገ ሕገመንግሥት ዕርባና ቢስና መና ነውና ወዳቂ ነው። ስለሆነም የነገዋን ኢትዮጵያ የምንገነባበትን፤ ፖለቲካዊና ማህበራዊ/ሲቪክ አደረጃጀትን የምንከባከብበትን፤ ግለሰባዊ ነፃነትን የማይገስሰውን፤ የሕግ የበላይነትን የሚያረጋገጠውን የመሰረት ሰነድ ለመቅረፅ የመንቀሳቀሻ ጊዜው አሁን መሆኑን ሁላችንም መገንዘብ አለብን። ያን ስናደርግ ነው ያለፈውን ምዕተ ዓመት በሙሉ ስንመለከት ከነበርነው የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ታሪክ ቅርቃር ልንወጣ የምንችለው። ይህ የመሰረት ሰነድ የእያንዳንዱን ዜጋ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ተሳትፎ ያለምንም ገደብ፤ አድልዎ፤ ማግለል፤ ወይም ማስፈራራት ማስገደድና ማጉላላት ማስከበር መቻል አለበት። ሁላችንም የሕይወትን ክብርነት መቀበልና በማንም ላይ ቢሆን የሚደርስን የአካልና የአዕምሮ ሥቃይን ማስቀረት እንዲሁም በጎሣ፤ በኃይማኖት፤ በፆታም ሆነ በዕድሜ ማግለልን ማስወገድ ዕምነታችን ሊሆን ይገባል። የምንፅፈውም ሰነዳችን ይህን ሁሉ በማያሻማ ቋንቋ መመዝገብ አለበት። ከሁሉም በላይ የሰዎችን የመንቀሳቀስናየመደራጀት መብትን፤ በንግግር፣ በፅሑፍና ኪነጥበብ በነፃነት መብት መግለጽ መቻልንና የነፃ አስተሳሰብ መጎልበትንና የእምነትነፃነትን ማክበር አለብን። ፖለቲካዊ ነፃነት፤ በሕግ ፊት በእኩልነት መታየት፤ የተከሳሽን የመከራከር መብትና ማንም ተከሳሽ በሕግ ፊት በማስረጃ እስኪረጋገጠበት ድረስ ጥፋተኛ ተደርጎ ያለመወስድ መብቱና ጥፋተኛ ሆኖ ካለተገኘም ካሣ የመጠየቅና የማግኘት መብት፤ የዜጎች ኑዛዜ የማድረግ መብት፤ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ፊርማ የማሰባሰብ መብት ወዘተ፤ በአጠቃላይ በዓለም ዐቀፉ ህብረተሰብ ዘንድ ተቀባይነትን አግኝተው የተደነገጉ መብቶች ሁሉ የሚከበሩበት እንዲሆን መትጋት አለብን።በተጨማሪም ራዕዬና ግቤ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን መገንባትና ማዳበር ነው ያለ ድርጅት ሁሉ ያንኑ ራዕይና ግብ ከአሁኑ በውስጠ-ድርጅት አሰራሩና አካሄዱ ሁሉ ሳይቀር መተግበር አለበት። በድርጅት ውስጥ የአመራር ክፍተት ሲፈጠር ዴሞክራሲያዊ ከሆነ ሁኔታ ውጭ የኣመራር ለውጥ የሚደረግ ከሆነ ይህን መሰል ድርጅት በምንም ዓይነት ሁኔታ ለማንም አድማጭ ስለዴሞክራሲ መስበክ የለበትም። የምንለውና የምንፈልገው ይሳካልን ዘንድ የምንሰብከውን መተግበር የግድ ይለናል።ፍትህን የምንሻ ሁሉ ፍትሓዊ መሆን ይኖርብናል። እኩልነትን የሚያነበንብ ሁሉ ሰብዓዊነታችን ብቻ ዕኩል እንደሚያደርገን መሆኑን መቀበልና ለዚያም መቆምና መሟገት አለበት። እኛ መሆን የምንፈልገውን ለመሆን መብት የምንጠይቅ ከሆነ የሌሎችንም ለመሆን የሚወዱትን የመሆን ነፃነት ማክበር ይጠበቅብናል። ተግባራችን ዕምነታችንና ራዕያችን ያንጸባርቃል?እኔ ማንም በፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ያለና ለነፃነት ተፋላሚ የሆነ ሁሉ የተሳተፈበት ድርጅት ግልፅና ተጠያቂ መሆኑን ማረጋገጥ እንዲኖርበትና እንዲሰማው እንዲሁም የድርጅቱ ባለቤት አመራር ብቻ ሳይሆን እያንዳንዱ አባል መሆኑን አበክሮ እንዲገነዘብ ብሎም የጎለበተ የድርጅት ውስጥ ዴሞክራሲ እንዲሰፍን፤ ግልፅ የሆነ ህግና ደንብ የተነደፈበትና በተለይም አመራር የተደነገጉ ህጎችን ቀስ በቀስ ሲሽር በተገኘበት ተጠያቂ የመሆን ፖለቲካዊ ባህል እንዲሰፍን ማንሳትና ማሳሰብ እወዳለሁ። መሪወቻችን ወንበር ላይ የሚኮፈሱ ሳይሆን ከአባላት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት proactive relationship ያላቸው፤ ኣባላትን እንደሃሳብ ማፍለቂያ think tank የሚጠቀሙ፤ የብዙሃን ኣባላትን ሃሳብና ውሳኔ የሚያከብሩና የሚያስተገብሩ መሆን ኣለባቸው። ጤናማ ኣዕምሮና ሰውነት ሊኖራቸውም ግድ ነው። ካልሆነ ከቦታ ቦታ የመዘዋወር፣ ብሩህ ሃሳብ የማፍለቅ፣ ረዥም ሰዓት የመስራት ችሎታቸው ውስን ይሆናል። የጤና ችግር ካለባቸው ልምድና ዕውቀታቸውን በማካፈል እንደኣቅማቸው ድርጅታቸውን መርዳት ይችላሉ። እስከ ዕለተሞት ስልጣን የሚባል ባህል ግን ማስቀረት መቻል ኣለብን። አባላት የድርጅታቸው የተልዕኮ ምሕንድስና ላይ መሳተፍ፤ ራዕያቸው ጥሩ ድምዳሜ ላይ ይደርስ ዘንድ መትጋት፤ አስተዳደራዊ ብቃቱን ማዘመንና ለመጪው ጊዜ ፈተና ማብቃት ይጠበቅባቸዋል። በድርጅት ውስጥ ግማሽ ሰው-ግማሽ አምላክ (ትናንሽ ታቦቶችን) መቅረፅን ማቆም አለብን። ተገቢውን መከባበር ሳይለየን ታማኝነታችን ለራዕዮቻችንና ለአመንባቸው አቋሞች መሆንነው ያለበት። ይህ ፅሁፍ በሁሉም የትግሉ ተሳታፊዎች (መቼም አንዱ ያለ ሌላው አይኖሩምና በአመራር ደረጃ ባሉትም ሆነ የታች አባላት) ዘንድ ውይይት ያስነሳል የሚል ተስፋና እምነት አለኝ። ይህንንም ስል በየድርጅቱ ውስጥ ያሉ የአመራር አባላትና ሊተኳቸው በሚመኙ አባላት ራዕይና አቋም ላይና የመመሪያ ሰነዶቻቸው ላይ በቂ ዕውቀት ይኖረን ዘንድ እወዳለሁ።ዜጎችም የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲወች የሚያቀርቡልንን የድጋፍ ጥያቄም ብዙ ጥያቄወችን መጠየቅ ኣለባቸው። ለመሆኑ ፖለቲካዊና ማህበረሰባዊ ድርጅትና ስብስቦች ስንት አባላት አሏቸው? ካሏቸውስ ምን ያህል? ለመሆኑ ፅ/ቤቶቻቸው የት ነውየሚገኙት? ስላላቸው ካፒታልና ስለምንጩም መጠየቅ መቻል አለብን። እያንዳንዱ ድርጅት የቆመለትን ዓላማ የጉዞ ስትራቴጂውን፤ ድህረ-ወያኔ ኣዲሲቷ ኢትዮጵያን ለማስተዳደር ያለውን ፖሊሲና ነገ ማንነቱን የምንሰፍርበትን የድርጊት መመሪያመግለጫውን ማየትና ማወቅ አለብን። የመመሪያው፤ የዕምነት፤ የራዕዩና ንድፈ ሃሣባዊ መሰረትና ምንጭ ከየት እንደሆነ ማወቅ አለብን። ራዕያችን ዕሴቶቻችንና ተግባራችን ይገጣጠሙ። ቆም ዕያልን ያሳለፍነውን ጊዜ እንፈትሽ። ውጤት ያላመጣልንን ስልት ችክ ብለን ኣንያዘው። ለመለወጥም ኣንፍራ። ኣስተሳሰባችን ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር እንዲጓዝ እናድርግ። በዚህ መንገድ በጊዜ የቤት ሥራችንን በአግባቡ ሳንሰራ ቀርተን ዘለዓለም ተቃዋሚዎች ሆነን እንዳንቀር። ንጉሳዊ ስርዓቱን የተቃወሙት ራዕያቸው ስኬታማኣልሆነም። ደርግንም የተቃወሙት እንደዚያው። ኣሁን ያለን ” ዕኩልነትና ፍትህ የሰፈነባት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ” ራዕያችንስ ተሳክቶ እናየው ይሆን?የዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ሕልማችን ይጠንክር!ነፃነት እኩልነትና ፍትህ ለኢትዮጵያ ህዝብ!ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!
ጥቅምት ፪፭ ቀን ፪፻፱ / 4 November 2016
mareshetmeshesha@gmail.com

መንግስት በባንዲራ ጉዳይ ውይይት የጀመረው መሃል ላይ ያለውን የሰይጣን ምልክት ሊያጠፋው አስቦ ነው?

$
0
0

የትግራዩ ነጻ አውጪ መንግስት አዲስ ካርታ በመሳብ የሕዝብን የትግል አቅጣጫ ለማስቀየስ ብዙ ሲሰራ ቆይቷል:: በውጥረት ላይ ያለው ይሄው መንግስት ሰሞኑን በባንዲራ ጉዳይ ላይ ውይይት ጀምሯል:: አንዳንድ ምንጮች ሕወሓት መራሹ መንግስት ባንዲራው ላይ ያለውን የሰይጣን ምልክት ለማጥፋትና ልሙጡን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ለማድረግ እየተሰራበት ነው ሲሉ መንግስት በበኩሉ በኢቢሲ በኩል በባንድራው ላይ ውይይት ሲያካሂድ ነበር:: በዚህ ስብሰባ ላይ አቶ ልደቱ አያሌው የተናገሩትን ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ ይዘናል::

መንግስት በባንዲራ ጉዳይ ውይይት የጀመረው መሃል ላይ ያለውን የሰይጣን ምልክት ሊያጠፋው አስቦ ነው?

ለትብብር እንቆቅልሽ መላ |ዶ/ር ዘላለም እሸቴ

$
0
0

tplf

በዚህ ፅሁፍ ስለ አማራጭ ሃይሎች ትብብር አስፈላጊነት የታወቀ ነገር ስለሆነ መናገር አልፈልግም። ማተኮር የምፈልገው እንዴት ትብብሩ እንደሚመጣ መላ ፍለጋ ላይ ነው። ይህም ሲባል ነገሮች ተድበስብሰው አንድ ላይ ተጨፍልቀው ማየት ሳይሆን፥ በየደረጀው ከመነሻው እስከ መድረሻው ጥርት ባለ መልኩ ለማስቀመጥ ነው። ከውጭ ለሚያይ የብሔር ተኮር ሃይሎችና የኢትዮጵያ አንድነት ሃይሎች ተባብለው በሁለት ትልቅ ጎራ ተከፋፍለው በጥርጣሬ መተያየታቸው የአደባባይ ሚስጢር ነው። ባብዛኛው ግን ልባቸው የሚፈልገው ለሁሉም አንድ ነው። ያም ሆኖ አንዳንድ ተስፋ ሰጭ ፍንጭ ከመታየቱ በቀር በሁለቱ ጎራ ዙሪያ ፈቀቅ ያለ ነገር እየተደረገ አይደለም። ስለዚህ አድበስብሰን ለመግባባት እስካሁን የሞከርነው ጠብ ስላላለ አዲስ መንገድ እንከተል። እስቲ ይህንን መንገድ በሶስት ደረጃ ከፍለን እንየው።
1ኛ/ ቅድመ መግባባት ለመሰባሰብ ነው
2ኛ/ መግባባት ለውይይት ነው
3ኛ/ ድህረ መግባባት ለአንድ ድምፅ ነው

1ኛ/ ቅድመ መግባባት ለመሰባሰብ
ስለ ውይይት ከማውራታችን በፊት ከየጎራችን ወጥተን በአንድ ቤት ውስጥ መሰባሰብ ይኖርብናል። ስለዚህ ቅድመ መግባባት ከተለያየ ጎራችን አውጥቶን ወደ አንድ መካከለኛ ቤት እንድንሰበሰብ አቅም ይሰጠናል። ይህም ማለት ቅድመ መግባባት ዓላማው ሁሉንም አግባብቶ አንድ ላይ እንድንቀመጥ እንድንችል መፈቃቀድ እንዲኖረን የሚያደርግ ነው። ለያይተውን በየጎራችን ተዘልለን እንድንቀመጥ ከሚያደርጉን ነገሮች ይልቅ የምንስማማባቸው ነገሮች ይበልጣሉ። አፋችን የተለያየ ነገር ቢያወራም ልባችን የሚፈልገው ነገር ግን ይመሳሰላል። ይህ ቅድመ መግባባት እንዲኖር ልብ ለልብ መናበብ እንደ መጀመሪያ ስሌት መምረጥን ይጠይቃል። ከምናወራው ወሬ ይልቅ፥ ስሩ ጋ ሄደን አንዳችን የሌላውን ልብ ማዳመጥ ይኖርብናል። ልብ ለልብ ስንናበብ፥ ይህ ቅድመ መግባባት እውን ይሆንልናል። ለአብዛኛው ህዝብ ልብ ለልብ በመናበብ ቅድመ መግባባት ይፈጥራል ብዬ የማስበውን ከዚህ በታች እዘረዝራለሁ።

ሀ/ መሬት ላይ ያለው ሕዝብ አንድ ነው
የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሔረሰብ ሳይለይ የተጨቆነና በድህነት ለዘመናት የኖረ ነው። በፍቅር ተጋብቶና ተዋልዶ ደጉንም ክፉውንም አብሮ የሚያሳልፍ ነው። በሕዝብ ደረጃ ጥልና መከፋፋት የለም። ለዳር ድንበሩ ብሔረሰብ ሳይለይ ደሙን አፍስሶ አጥንቱን ከስክሶ ኢትዮጵያን እዚህ አድርሷታል። ኢትዮጵያ የተያያዘችው ተፈጥሯዊ (organic) በሆነው የፍቅር ሰንሰለትና አብሮነት ነው። ዛሬም ደምህ ደሜ ነው እያለ ፍቅሩን እየገለጠ የሚገኝ ወንድማማች ነው። ይህ የቅድመ መግባባት መሰረትና መነሻ ነው። ልሂቃንን የሕዝቡ ነፀብራቅ እንዲሆኑ ግድ የሚል እውነት ይህ ነው።

ለ/ ልባችን ውስጥ ያለው ራዕይ አንድ ነው
አዲሲቷ ኢትዮጵያ ብለን ስናስብ የሚመጣልን ለሁሉ የምታጓጓውን ኢትዮጵያ ነው። ያም ኢትዮጵያ ዲሞክራሲ ሰፍኖባት፥ ሁሉም በእኩልነት፥ በነፃነት የሚኖርባት ሀገር የምትሆነው ናት። ሁላችንም ከሰፈነው መልካም አስተዳደር የተነሳ የሀገር ባለቤትነት ተሰምቶን ብሶታችንን ሳይሆን ኩራታችንን የምናውጅባት ሀገር የምትሆነው ናት። እኩልነትን መሰረት ባደረገው አንድነታችን ምክንያት ብልፅግና በፍትህ እንዲመጣልን ግድ የምትለን ሀገር የምትሆነው ናት። ይህ የቅድመ መግባባት ዓላማና ግብ ነው። በዚህ ራዕይ ቅድመ መግባባት ሁሉንም አግባብቶ ሁሉንም ያገባኛል ባይ መካከለኛ በሆነው የኢትዮጵያ ቤት አዳራሽ ውስጥ እንዲገኝ የግድ የለዋል።

ሐ/ ድል የሚገኝበት የህብረት አካሄድ አንድ ነው።
ተነጣጥለን እየተፎካከርን ብንገፋፋ ሁላችንም ባዶ እጅ መቅረታችን የታወቀ ነው። ድር ቢያብር አንበሳ ያስር እንዲሉ መደጋገፍና መተባበራችን ሃይላችን እንደሆነ ለሁሉም ግልፅ ነው። መከፋፈል ለመጥፋት ሲዳርገን፥ መያያዝ ደግሞ ለድል እንደሚያዘጋጀን እሙን ነው። ይህ ደግሞ የቅድመ መግባባት ስልት ነው። በዚህ ስልት አግባብቶ ሁሉንም ለድል እንዲሰለፉ ይችሉ ዘንድ አንድ ቦታ ለውይይት እንዲገናኙ አፅንዎት ይሰጣል።

በነዚህ ከዚህ በላይ በተዘረዘሩት የጋሪዮሽ ነጥቦች ላይ መተማመንና መስማማት ካለ ቅድመ መግባባት አለ ማለት ነው። ቅድመ መግባባት ካለ ደግሞ በየጎራችን ተወስነን በስማ በለው ከመጯጯህ ይልቅ፥ ከየጎራችን ወጥተን በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ ቁጭ ብለን ፊት ለፊት እየተያየን ለመወያየት ተዘጋጅተናል ማለት ነው። ስለዚህ ከቅድመ መግባባት በዋላ የሚመጣው ሁለተኛው ደረጃ ላይ የሚገኘው መግባባትን ደግሞ ቀጥለን እንይ።

2ኛ/ መግባባት ለውይይት
በዚህ ክፍል ውይይት ለማድረግ ዝግጁ ነን ማለት ነው። አብረን ለመኖር ተስማማን እንጂ እንዴት እንኑር የሚለውን ለመፍታት ውስብስብና አስቸጋሪ ነገር ነው። ለኢትዮጵያ ያለን የመፍትኤ አመለካከት ልዩ ልዩ ነው። ግን በዚህ ልዩነት ላይ ፈርጀ ብዙ የሆነውን መፍትኤ ለመፈለግና ለመግባባት የብሔር ተኮር ሃይሎችና የኢትዮጵያ አንድነት ሃይሎች የሚባለው ጎራ ውስጥ መሰወር ትርጉም የለውም (በቅድመ መግባባት ያንን ፈተነዋልና)። ምክንያቱም በአስተሳሰብ ላይ ውይይት ሲደርግ ከኢትዮጵያይ አንድነት ሃይል ጎራ ነኝ የሚለው ሁሉ አንድ ዓይነት አመለካከት አይኖረውም። ከብሔር ተኮር ሃይሎች ጎራ ነኝ የሚለውም እንደዚሁ የተለያየ ዓይነት አስተሳሰብ ነው ያለው። በዚህ ስፍራ የብሔር ተኮር ሃይሎችና የኢትዮጵያ አንድነት ሃይሎች የሚለው መለያ አርማ፥ እየሆነ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ከመግለፅ ይልቅ እውን ሊሆን የማይችለውን ቅራኔ በባዶ ሜዳ ያጋግላልና በቅድመ መግባባት መጀመሪያ ዕልባት ያግኝ የተባለው ለዚህ ነው። ይህ ሲባል በየብሔረሰቦች አይደራጁ ወይም በየብሔረሰብም አይወያዩ ማለት አይደለም። ግን የማታ ማታ የሚያያይዘን በጠረጵያ ዙሪያ ቁጭ ብለን እንድንወያይ የሚያደርገን በአንድ ቤት ውስጥ ለውይይት መቀመጥ ስንችል ነው። ቅድመ መግባባት ወደ አንድ ቤት ከሰበሰበን ዘንዳ ሰከን ብለን መወያየት እንችላለን ማለት ነው። በመፍትኤው ላይ ለመግባባት ቀጠሮ ሳንሰጠውና ለነገ ሳናሳድር ተወያይተን ዛሬ መንግስት በስራ ላይ ከሚተገብረው መፍትኤ ጋር በትይዩ አማራጭ የምንላቸውን አንድ፥ ሁለት፥ ሶስት ••• ብለን እንወስንና በነዚሁ ዙሪያ እንደ እምነታችን እንሰብሰብ።

3ኛ/ ድህረ መግባባት ለአንድ ድምፅ
በመግባባት በተለያዩ አማራጭ መፍትኤዎች ዙሪያ ከተሰባሰብን የሚቀጥለው ድህረ መግባባት ነው። በድህረ መግባባት አማራጭ ሃይሎች ሁሉ የመፍትኤ ሀሳብ ልዩነታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመቀናጀት አንድ የጋራ የሆነ ድምፅ ይኖራቸዋል። ያም ድምፅ ለምሳሌ ዲሞክራሲና የመብት መከበር ጉዳይ ሊሆን ይችላል። በቅድመ መግባባትና በመግባባት ያሉትን ሁለት የቤት ስራዎች ሳንሰራ አማራጭ ሃይሎች አንድ ሁኑ ብሎ መጮህ የትም አላደረሰንም። ግን ጥርት አድርገን በየደረጃው ያሉትን ጥያቄዎች እየመለስን ብንሄድ የትብብር ስኬት የእኛ ነው።

ማጠቃለያ
ኢትዮጵያ ለማንም የመለያያ መለያ አርማ አትሆንም። ምክንያቱም የሁሉም ናትና። ስለዚህ እርስ በርስ ከመካሰስ፥ ከሁሉ በፊት ደረጃ በደረጃ ቅድመ መግባባቱ ተደርጎ፥ በልባችን የተግባባንባቸው ነጥቦች አቀራርበውን ሲያበቁ ያኔ እናስተውልና ድልድይ ሰርተን በአንድ ላይ ቁጭ ብለን ለመነጋገር እንሰብሰብ። እየተፈራራን ሩቅና ሩቅ ሆነን ከምንፈራረድ፥ በቀና መንፈስ ተቀራርበን ፈቀቅ የሚል ነገር እንወያይና በተወሰኑ የተለያዩ አማራጭ የመፍትኤ አሳቦች ላይ መግባባት ላይ እንድረስ። በመጨረሻም በድህረ መግባባት ተቀናጅተን በአንድ ድምፅ እንቁም። በዚህ መንገድ ብንቆርጥና ብንሄድ ለዓመታት እውን ያልሆነው ትብብር በወራት ውስጥ ብቅ ብቅ ማለት ይችላል ብዬ ተስፋ አደርጋለው።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!
ኢሜል፦ ethioFamily@outlook.com

የቀድሞ ፍቅረኛው ላይ አሲድ የደፋው፤ የ18 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈረደበት

$
0
0

addis-admass
(አዲስ አድማስ ጋዜጣ) ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ በዳንግላ ከተማ የቀድሞ ፍቅረኛው ላይ የአሲድ ጥቃት የፈፀመው ሰለሞን በላይ፤ የ18 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈረደበት፡፡ የአማራ ክልል የዳንግላ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በትናንትናው ዕለት በዋለው ችሎት ተጎጂዋ መሰረት ንጉሴ በአካል ተገኝታ የጥቃቷን መጠን አስረድታለች፡፡ ምንም እንኳ ጥፋተኛው የፈፀመው ጥቃት በሞትና በእድሜ ልክ እስራት የሚያስቀጣ ቢሆንም ድርጊቱን መፈፀሙን በማመኑና ከዚህ ቀደም የወንጀል ሪከርድ የሌለበት በመሆኑ፣ ፍ/ቤቱ በ18 ዓመት ፅኑ እስራት እንደቀጣው የዳንግላ ከተማ ሴቶች፣ ህፃናትና ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ አዛሉ ናደው ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡

‹‹ጥፋተኛው ወንጀሉን ከፈፀመበት ዕለት አንስቶ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን እኛም በጉዳዩ ላይ ጥብቅ ክትትል ስናደርግ ነበር›› ያሉት ሀላፊዋ፤ ምንም እንኳ በሞትና በእድሜ ልክ እስራት የሚያስቀጣ ወንጀል ቢፈፅምም ፍ/ቤቱ አንዳንድ ነገሮችን ከግምት አስገብቶ የ18 ዓመት እስር መፍረዱ ሌሎችን የሚያስተምር ተገቢ ቅጣት ነው ብለዋል፡፡ ወጣቷ ተጎጂ አሁንም በከፍተኛ ስቃይ ላይ መሆኗን የገለፁት ሀላፊዋ፤ ወቅታዊው የፀጥታ ችግር ትኩረታቸውን ስቦት እንጂ ከዳንግላ ከተማ አስተዳደር፣ ከክልሉና ከባለሀብቶች ጋር በመተባበር ልጅቷ አስቸኳይ የውጭ ህክምና የምታገኝበትን መንገድ ለማፈላለግ እንተጋ ነበር ብለዋል፡፡

ወጣት መሰረት ንጉሴ አዲስ አበባ በሚገኙ በጎ ፈቃደኛ ግለሰቦች ድጋፍ ላለፉት አምስት ወራት የቀለብ፣ የህክምናና የቤት ኪራይ ወጪ ተሸፍኖላት፣ መጠነኛ ህክምና ብታደርግም ጤናዋ መሻሻል ባለመቻሉ ወደ ውጭ አገር ሄዳ ለመታከም እስከ 1 ሚ.ብር መጠየቋን ለአዲስ አድማስ ገልፃለች፡፡

ባለፈው ጥቅምት 3 ቀን 2009 ዓ.ም በአዜማን ሆቴል የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ተዘጋጅቶላት የነበረ ሲሆን በዚህ ዝግጅት ከ200 ሺህ ብር የበለጠ ባለመገኘቱ በአስቸኳይ ወደ ውጭ ሄዳ ለመታከም እንዳልቻለች ገልፃ፤ አሁንም የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲደርስላት ጥሪ አቅርባለች፡፡

ፍርድ ቤቱ በወንጀለኛው ላይ የሰጠውን ፍርድ በተመለከተ ለአዲስ አድማስ አስተያየቷን የሰጠችው ተጎጂዋ፤ ‹‹በእርግጥ ሞት ወይም የእድሜ ልክ እስራት ይፈረድበት ብለሽ ይግባኝ ጠይቂ ተብዬ ነበር፤ 18 ዓመት ከህሊና ፀፀት ጋር በቂ ነው ብዬ ትቼዋለሁ›› በዋና የምግብ አብሳይነት (Chef) እየሰራች ራሷንና ወላጅ የሌላቸውን ታናናሽ እህቶቿን ታሳድግ እንደነበር ያስታወሰችው መሰረት፤ አሁን በደረሰባት ጉዳት እህቶቿ ያለ ረዳት መቅረታቸውን ጠቅሳ፤ ይህም ሌላ ህመም እንደሆነባት ተናግራለች፡፡

ምንጭ አዲስ አድማስ ጋዜጣ

በጢስ አባይ መንደል አካባቢ የፌደራል ፓትሮል ወታደሮች ጭኖ ሲሄድ በጥይት ተመታ | 2 ሰዎች ሞቱ

$
0
0

Zehabesha-News.jpg

(ዘ-ሐበሻ) በአማራው ክልል የትግራዩ ነጻ አውጪ መንግስት እየወሰደ ያለው የበቀል እርምጃ ዛሬም እንደቀጠለ ነው:: በጎጃም እና በጎንደር ወጣቶችን እያፈሱ መውሰዱ በየቀኑ እንደቀጠለ ሲሆን በተለይ ምሽት እየጠበቁ ብዙ ወጣቶችን እንደሚያፍኑ ለዘ-ሐበሻ የሚደረሰው መረጃ ያመለክታል::
በተመሳሳዩም አማራውን ትጥቅ ለማስፈታት እየተንቀሳቀሰ ያለው የትግራይ ነጻ አውጪው መንግስት በየቦታው እየደረሰበት ያለው ጥቃት ራስ ምታት ሆኖበታል:: ዛሬ በጢስ አባይ ልዩ ስሙ መንደል በተባለ አካባቢ አማራውን ትጥቅ ለማስፈታት እየተንቀሳቀሰ የነበረና ፌደራሎችን ጭኖ እየተንቀሳቀሰ የነበረ ፓትሮል በአካባቢው የጎበዝ አለቆች በጥይት ተመቶ መገልበጡ ታውቋል:: በዚህም ጥቃት የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ሲሰማ የቆስሉ የትግራይ ነጻ አውጪ ወታደሮች ህክምና ላይ መሆናቸውን ምንጮች አስረድተዋል::

በጢስ አባይ አካባቢ ሌሊቱን ሙሉ የተኩስ ድምጽ ሲሰማ እንዳደረ አንዳንድ ነዋሪዎች ለዘ-ሐበሻ በላኩት መረጃ ተናግረዋል::

የአማራ የጎበዝ አለቆች እንዳስታወቁት የትግራይ ነጻ አውጪ ወታደሮች አማራው ጠመንጃውን ይዞ በሚንቀሳቀስበት ወቅት ለመቀማት በየቀበሌ ማህበሩ ያሰፈሰፉ ሲሆን ሕዝቡ በንቃት እንዲከታተላቸውና እርምጃም እንዲወስደባቸው ማሳሰቢያ ሰጥተዋል::

ህጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ አወጣ –“ለሕዝባችን ጠንቅ የሆነው የሕወሓት መንግስት ይወገድ”

$
0
0

holy sinod ethiopia

(ዘ-ሐበሻ) 44ኛ ጉባዔውን ከጥቅምት 23-26/2009 ዓ.ም በኦሃዮ ደብረ መድኃኒት መድሃኔዓለም ቤተክርስቲያን ያካሄደው ሕጋዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ አወጣ::

ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

የጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት በአማራነት መደራጀትን ይቃወማል? –ምላሹን ከፕሮፌሰር ዓለምአንተ ገ/ሥላሴ ያድምጡ

$
0
0

<…የጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት ወያኔ ጎንደርንም ሆነ ቀሪውን የአማራ ክፍል ለማዳከም የወጠነውን ጎሳ ሽንሸና ሆን ተብሎ ሕዝቡን ለማናከስ የተደረገ በመሆኑ ያን የሚያከሽፍ የአማራው፣የቅማንቱ፣የአገው፣የፈላሻው፣የኦሮሞው፣የአፋሩ በአጠቃላይ የሁሉም መብት ተከበረበት አደረጃጀት ነው. ..በጎንደርና በሌላውም አካባቢ ወያኔ ሆን ብሎ ክፍፍል ለመፍጠር አንዱን በአንዱ ያስነሳል በትግራይ ውስጥ ግን የሚኖሩ የተለያዩ ብሄሮች አሉ ለምን ለእነሱ ክልል አይሰጣቸውም? ከነመኖራቸውም ህልውናቸውን አይቀበልም ። ለምን ያን አደረጉ…> ፕ/ር አለምአንተ ገብረስላሴ የጎንደር ህብረት ለኢትዮጵያ አንድነት የቦርድ አባል ከሰጡን ቃለ መጠይቅ


ታማኝ በየነ በሚኒሶታ ተደርጎለት የነበረው አቀባበል |ቪዲዮ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በጽናት ኢትዮጵያ የውውይት መድረክ አማካኝነት ተደርጎ በነበረው ሕዝባዊ ውይይት ላይ የቀረቡትን ንግግሮች በተከታታይ ስናቀርብ ቆይተናል:: በርካታ የዘ-ሐበሻ ወዳጆች እንደኮራችሁብን ገልጻችሁልናል – እናመሰግናለን:: ለዛሬው በዚህ ስብሰባ ላይ ታማኝ በየነ ሲገባ የቀረበለትን ሞቅ ያለ አቀባበል ይዘንላችኋል::

ፕሬዝዳንቱም፣ ጠቅላይ ምኒስትሩም፣ ሕገ መንግሥቱን አያውቁትም |ይገረም አለሙ

$
0
0

ፕሬዝዳንት ሙላቱ በዘንድሮው ፓርላማ መክፈቻ ንግግራቸው አንዳንድ ማሻሻያዎች አንደሚደረጉ ገልጸዋል፡፡ የመንግሥቱን ሥልጣን በበላይነት የሚቆጣጠሩት ህውኃቶች የገጠማቸውን የህዝብ ተቃውሞ ለማስተንፈስ ያስችለናል ያሉትን ግን የማይፈጽሙትን የማሻሻያ ርምጃ ጽፈው ሲሰጡዋቸው ከማንበባቸው በፊት ቢያንስ ሁለት ነገሮችን ሊያገናዘቡ በተገባ ነበር፡፡ አንደኛው በአምናው የመክፈቻ ንግግራቸው ከተናገሩት ያልተፈጸሙት ይልቃሉና የማተገብሩትን ተናገር እያላችሁ ቃል አባይ ፕሬዝዳንት አታድርጉኝ ማለት፣ ሁለተኛው ደግሞ የተባሉት ማሻሻያዎች ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ የሚነገሩ ሳይሆን በርግጥ ታምኖባቸው ተፈጻሚ አንዲሆኑ ስምምነት ላይ የተደረሰባቸው ከሆነ አንዳንዶቹ ህገ መንግስታዊ ማሻሻያ የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ ህገ መንግሥቱ በሚፈቅደው መንገድ የህገ መንግስት ማሻሻያ አንዳረጋለን የሚል በንግግራቸው አንዲካተት ማድረግ ይገባቸው ነበር፡፡
mulatu

የርሳቸው ሲገርም ጠቅላይ ምኒስትሩ ማሻሻያዎችን ለማድረግ ሕገ መንግሥቱን ማሻሻል አስፈላጊ ቢሆን እንኳን..ማለታቸው መንግሥታቸው አሻሽላቸዋለሁ ብሎ በፕሬዝዳንቱ ያስነገራቸው ጉዳዮች አንዳንዶቹ የህገ መንግሥቱን መሻሻል የሚጠይቁ መሆናቸውን አለመገንዘባቸውን ያሳያል፡፡ ይህ ደግሞ ሕገ መንግሥቱን ካለማወቅ ወይንም ከቁብ ካለመቁጠር የሚመጣ ነው፡፡

የህዝቡን ቁጣ ያበርዳል የሥልጣን ፍርፋሪ ናፋቂዎችን በጉጉት ማኖር ያስችላል አውቆ ለሚታለለው ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም እጅ መንሻ ይሆነናል ወዘተ ተብሎ ከተነገረው የማሻሻያ ሀሳብ ውስጥ አንዱ የሆነው የምርጫ ሕግ እነርሱ በማን አለብኝነት ካልፈጸሙትና ተቃዋሚው ለእኛ እስከጠቀመ ድረስ ብሎ በዝምታ ካልተቀበለው በስተቀር የህገ መንግሥቱን መሻሻል የሚጠይቅ ነው፡፡ የምርጫ ሕጉን ማሻሻል የተፈለገው ፕሬዝዳንቱ እንደነገሩን የምርጫ ሥርዓቱን ወደ ተመጠጣኝ ውክልና ሥርዓት ለመቀየር ይሁን የቀድሞው ቃል አቀባይ አንደገለጹት ከተመጣጣኝና ከአብላጫ ሥርዓቶች የተዳቀለ ሥርዓት ለመፍጠር ህገ መንግሥቱ ሳይሻሻል የሚሆን አይደለም፡፡ እንዲህ አይነቱን ነገር እነርሱ ሆን ብለው ለማደናገሪያነት የሚያቀርቡት በመሆኑ አይደንቅም አዲስም አይደለም፡.ሌሎች ግን የምርጫ ሕጉን ለመለወጥ ህገ መንግሥቱን ማሻሻል አንደሚጠይቅ ባለማጤን አንደ መልካም ነገር ቆጥረው የተነገረውን አንደ ወረደ ተቀብለው ሲያስተጋቡትና ሲተቹት ማየትና መስማት ያስገርማል፡፡

ወያኔዎች እድሜ ማራዘሚያ መድሀኒት የሆነናል ብለው ካሰቡ ህገ መንግስት ምናቸውም አይደል ፡፡መጀመሪያም መጨረሻም ጉዳያቸው ስልጣን ነውና በነጋሪት ጋዜጣ ያወጁትን በጓዳ ሊሽሩት በአደባባይ የተናገሩትን እንዳልነበረ ሊያደርጉት ግድ አይሰጣቸውም፡፡ ህገ መንግሥቱ ሊሻሻሉ የሚገባቸው አንቀጾች አሉት ብሎ መናገር ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱን ማፍረስ አስብሎ ሲያስወነጅል በቅርቡም ከዳኝነት ስራ ሲያስባርር ኣይተናል፡፡ ህውኃቶች ግን ሊጥሱትም እስከ መኖሩ ሊረሱትም ሌላውን ሊያጠቁበትም እድሜ ለጠብ መንጃቸው መብት አላቸው፡፡ ይህ ደግሞ ከጫካ ጀምረው ደንባቸውን በመተላለፍ በአዋጅ ያጸደቁትን በጓዳ በማፍረስ ሌሎችን ጥፋት ብለው የወነጀሉበትን አነረሱ ይጠቅመናል ባሉ ግዜ በመፈጸም እያዳበሩት የመጡት አብሮ አደጋቸው ተግባር ነው፡፡

ለዚህ ማሳያ የሚሆኑኝ ሁለት አማስረጃዎችን ልጥቀስና ወደ ርእሰ ጉዳዬ እመለሳለሁ፡፡ ምን ያህል ሰው ልብ አንደሚለው አላውቅም እንጂ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የሚል አጠራር ከተጀመረ ሶስት አመት አልሞላውም፡፡ ታሪክ የማይረሳቸው በህገ መንግስቱ ጉባኤ ላይ ብቸኛ ኮከብ የነበሩት ሻለቃ አድምሴ ዘለቀ የጎሳና የቋንቋ አከላለሉን ተቃውመው በተለይ ደግሞ ምስራቁን አካባቢ ሲሆን የሶማሌ ክልል ባትሉት አምቢ ካላችሁ ደግሞ የሚሆነው አይታወቅምና የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ብትሉት በማለታቸው የወረደባቸውን ዘለፋና ስድብ አንረሳውም፡፡ ያኔ የነፍጠኛ አስተሳሰብ ያሉት ሰዎች ዛሬ እነርሱ ሲሉት የነፍጠኛ አስተሳሰብ አራማጅ ሆነው ነው ማለት ነው! ወያኔዎች ለሥልጣናችን ማቆያ ይጠቅመናል ካሉ አንዲህ ናቸው፡፡

ዋናው ጉዳይ ግን ይህ አይደለም የሻለቃ አድማሴ ተቃውሞ ኃላ ቀር የነፍጠኛ አስተሳሰብ ተብሎ በህገ መንግስቱ ላይ የሶማሌ ክልል ተብሎ ነውና የሰፈረው ህገ መንግስቱ ሳይሻሻል የተደረገው የስም ለውጥ የህገ መንግስት ጥሰት ነው፡፡ እነርሱ በማን አለብኝነት ጣሱት እኛ በምን አገባኝ ዝም አልን፡፡ ህገ መንግሥታችን እያሉ የሚመጻደቁብን ሰዎች ለህገ መንግስታቸው ያላቸው አክብሮትም ሆነ እውቀት እዚህ ድረስ ነው፡፡

በሁለተኛ ማሳያነት የማቀርበው በሕውኃት ክፍፍል ወቅት ቢኒያም ዮሃንስ የተባሉ ጸሀፊ ህውኃት -ምን ነበር ? ምንድን ነው ? ምን ሊሆን ይችላል? በሚል ርእስ ሪፖርተር መጽሄት ሚያዚያ 1993 እትም ላይ ካቀረቡት ጽሁፍ የተወሰደ ነው፡፡ አንዲህ ይላሉ፤ “ ማሌ ካለ ድል አለ የተባለለትን ማሌን ስሙን አትጥሩ፣ ማሌሊትን አታነሱ፣ማጭድና መዶሻ አታሳዩ፣ ባንዲራውን ደብቁ የሚል ሹክሹክታ የአባላቱን ጆሮ ሞላው፡፡ በፀሐይ የተፎከረለት ማሌ በጨለማ ለመናገር አሳፈረ፣ታጋዩ አመራሩ ምን እንደሚል ለመስማት ቢጠብቅም አመራሩ ግን ዝም ሆነ፡፡ ቢያንስ አቶ መለስ ማሌን አይጥሉትም፣አቶ አለም ሰገድም እንዲህ አያደርጉም ብሎ ጆሮውን አንቅቶ ቢጠብቅ ሁሉም ጭጭ አሉ፡፡ ያን ያህል የተዘመረለት ሌሎችን ‹ፕራግማቲስቶች› አስብሎ ከድርጅቱ ያስገለለ ርዕዮተ ዓለም በየኬላው እየተፈተሸ እንደሚቀር የኮንትሮባንድ እቃ የአንጦጦን ኬላ ሳያልፍ ቀረ፡” ይላሉ፡፡ አዎ በወያኔዎች ዘንድ ሁሉም ይደረጋል ለሀገርና ለሕዝብ ሳይሆን ለሥልጣን ሲባል፡፡

ስለ ሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት የሚገልጸው የህገ መንግሥቱ አንቀጽ 54 በንዑስ አንቀጽ 2 ላይ “የም/ቤቱ አባላት በአንድ ምርጫ ክልል ውስጥ ከሌሎች ተወዳዳሪዎች መካከል አብላጫ ድምጽ ያገኘ ተወዳዳሪ አሸናፊ በሚሆንበት የምርጫ ሥርዓት ይመረጣሉ፡፡ የተለየ ውክልና ያስፈልጋቸዋል ተብሎ የታመነባቸው አናሳ ብሔረሰቦች አና ሕዝቦች በምርጫ የህ/ተ ም/ቤት አባል ይሆናሉ ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል፡” ይላል፡፡ ዝርዝሩ በህግ ይወሰናል የተባሉ ጉዳዮች ብዙዎቹ ህጉ ያልወጣላቸው ሲሆን በዚህ አንቀጽ የተገለጸው ዝርዝር ህግ ወጣም አልወጣም አናሳ ብሄረሰቦችን አንጂ ውክልና ያላገኙ ፓርቲዎችን አይልምና ሕገ መንግሥቱን ሳያሻሽሉ ፓርቲዎችን በችሮታ ወደ ፓርላማ የማስገቢያ መንገድ ማበጀት አይቻልም፡፡

ስለሆነም የምርጫ ህጉን እናሻሽላለን የሚለው የፕሬዝዳንቱ ንግግር ኋላም ጠቅላይ ምኒስትሩ ህገ መንግሥቱን ማሻሻል አንኳን አስፈላጊ ከሆነ.. በማለት የገለጹት ይህን የህገ መንግስት አንቀጽ ያላገናዘበ ወይንም ሆን ብሎ የጣሰ ነው፡፡ ሌላው ሰውም ባለማወቅ፣ በየዋህነት ወይንም ሆነ ብሎ ለማስቀየሻነት እየተቀባበለ እንደ ድንቅ ተግባር ያስተጋባዋል፡፡ የተቀውሞው ጎራ በአብዛኛው የፊት የፊቱን እንጂ ግራና ቀኙን አለማስተዋል፤ የእለት የእለቱን አንጂ የትናንቱን አለማስታወስ ለወያኔዎች የማጭበርበር ጉዞ በእጅጉ ተመችቶአቸዋል፣ ጠቅሞአቸዋልም፡፡ መቼም ለበጎ ነገር ህገ መንግሥት ቢጣስ ምን አለበት የሚል ተከራካሪ ይኖራል ብዬ አልገምትም፡፡

ስለሆነም የተወራው የምርጫ ህግ ማሻሻያ የህገ መንግስቱን አንቀጽ መሻሻል የሚጠይቅ መሆኑ ታውቆ ለዚሁ ሲባል የህገ መንግሥት ማሻሻያ አንደሚደረግ አለመገለጹ ጉዳዩ የተነሳው ለማደንዘዣነት አንጂ ለተግባራዊነት አይደለምና በዚህ ለመታለልም ለመደለልም ራስን ማዘጋጀት አያስፈልግም ፡፡ በአንጻሩ ከላይ በማሳያነት አንደቀረበው የሶማሌ ክልልን ስም ያለ ህግ መንግስት ማሻሻያ እንደለወጡት ሁሉ ይህንስ ቢያደርጉት ብለን ብናስብ ህገ መንግሥቱን የጣሱት ለመልካም ተግባር ነውና ግዴለም ተብሎ ተቀባይነት ሊያገኝ የሚችል አይመስለኝም፡፡

ስለዚህ የምርጫ ህጉን በማሻሻል የተወሰኑ ተቀዋሚዎችን በፓርላማ አንዲታዩ ማድረግ የሚለው ትኩሳት ማብረጃ ከመሆን ባለፈ ቢያንስ በእነዚህ በተጠቀሱት ምክንያቶች ተግባራዊ ሊሆን አለመቻሉ ግልጽ ነው፡፡ የግድ የሀገ መንግስት መሻሻያ ይጠይቃልና፡፡ በማን አለብኝነት ወይንም ለተቀዋሚዎች የሚጠቅም ስለሆነ አይቃወሙትም በሚል ተግባራዊ ቢደረግ ደግሞ የህገ መንግስት መጣስ ወንጀሉን ተቀዋሚዎችንም በእኩል ተካፋይ ያደርጋል፡፡

ከአንጀት ካለቀሱ አንባ አይገድም አንዲሉ ወያኔዎች የምርጫ ሕጉን ሀገራዊ ጉዳት ተገንዝበው እሱን በማሻሻል ለውጥ ለማምጣት ከልብ ያሰቡበትና ያመኑበት ከሆነ እሱን የሚመለከተውን የሕገ መንግሥቱን አንቀጽ ማሻሻል ለእነርሱ በጣም ቀላል ነው፡፡ ምክንያቱም በህገ መንግሥቱ ድንጋጌ መሰረት ህገ መንሥቱን የማሻሻል ሰልጣን ያላቸው ፓርላማውም ሆነ የክልል ምክር ቤቶች በህውኃት ቁጥጥር ስር ናቸውና፡፡ ነገር ግን አንድም በመቃብራችን ላይ ካልሆነ በስተቀረ እያሉ ሲፎክሩለት የኖሩትን ህገ መንግሥት በሕዝባዊ አመጽ ተገዶ ማሻሻል ለእነርሱ ከሽንፈትም በላይ ሞት ሆኖ ስለሚታያቸው ሁለትም የህገ መንግሥቱን መሻሻል የሚፈልጉ ብዙ የህዝብ ጥያቄዎች በር ላይ አሉና አንዴ ከተጀመረ ከዚህም ከዛም እየተናደ ሥልጣናችንን የሚያሳጣን ደረጃ ያደርሰናል ብለው ስለሚሰጉ አይነኬ የሚሉትን ህገ መንግሥት ማሻሻል ውስጥ አይገቡም፡፡ ለዚህም ነው ጥያቄ በተነሳና ህዝባዊ ቁጣ በተቀሰቀሰ ቁጥር በህገ መንግስቱ አግባብ የሚለውን ቃል የሚያስቀድሙት፡፡ አቶ ይለማሪያምም የህገ መንግሥቱን መሻሻል የሚጠይቅ ማሻሻያ አንዳላቀረቡ ሁሉ ማሻሻል ቢያስፈልግ አንኳን በማለት የገለጹት፡፡ ስለሆነም የምርጫ ህግ ማሻሻያ ዲስኩሩ ከፕሮፓጋንዳ አልፎ ተግባራዊ ሊሆን የሚችል አይደለምና ከወያኔም ባህርይ ሥልጣንን የማጥበቅ አንጂ ከሕዝብ የመታረቅ ተግባር አይጠበቅምና፣ ለመሰረታዊ ለውጥ ሳይሆን ለእድሜ ማራዘሚያ ለተግባራዊነት ሳይሆን ለማደናገሪያና ለማስቀየሻ ከወያኔ ሰፈር በሚነገሩ ጉዳዮች አለመዘናጋት የነጻነቱን ቀን ለማቀረብ ይበጃል፡፡

በሰሜን ጎንደር የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስትን ለመፋለም አዛውንት እናቶች ሳይቀሩ ጫካ እየገቡ መሆኑ ተሰማ

$
0
0

በሰሜን ጎንደር የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስትን ለመፋለም አዛውንት እናቶች ሳይቀሩ ጫካ እየገቡ መሆኑ ተሰማ እና ሌሎችም ዜናዎች ከአማራ ድምጽ ራድዮ ያድምጡ::

ሕወሓት ቴዎድሮስ አድሃኖም የዓለም ጤና ድርጅት ዳሬክተርነት ካልተሳካለት በሚኒስተር ደኤታነት ይሾመዋል

$
0
0

Tewodros Adhanom
(ዘ-ሐበሻ) ኃይለማርያም ደሳለኝ ባለፈው ሳምንት በሕወሓት የተሾሙትን ካቢኔዎች ሲያስተዋውቅ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስተርነት የተነሳው ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ለዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ዳሬክተርነት ውድድር እየተሳተፈ ሲሆን በዚህ ካልተሳካለት በሚኒስተር ደኤታነት እንደሚሾም የዘ-ዘሐበሻ የውስጥ ምንጮች አስታወቁ::

ኃይለማርያም ደሳለኝ ባለፈው ሳምንት የሚኒስተሮችን ሹመት ሲያስታውቅ የቴውድሮስ አድሃኖምን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስተርነት ቦታ ሳያስቀምጠው የቀረው ለዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ዳይሬክተርነት ስለሚወዳደርና በዚያም እንደሚያሸንፍ ተስፋ አድርጎ ነበር:: እንደ ዘ-ሐበሻ ምንጮች ቴዎድሮስ ራሱ “እኔ የዓለም አቀፉን የጤና ድርጅት ዳሬክተርነት ቦታ ስለማሽንፍ አንሱኝ” እንዳለ የገለጹት ምንጮች ያ ካልተሳካ ግን በሚኒሰትር ደኤታነት ወይም በጠቅላይ ሚኒስተሩ አማካሪነት እንደሚቀመጥ ቃል እንደተገባለት ታውቋል::

መለስ በሕይወት በነበረበት ወቅት አስመራ የተማረው ቴውድሮስ አድሃኖምን ጠቅላይ ሚኒስተር አድርጎ እንዲተካው ሃሳብ እንደነበረው በተደጋጋሚ ሲዘገብ የቆየ ጉዳይ ነው::

ቴዎድሮስ አድሃኖም ዛሬ በዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት የ እጩዎች ጥያቄና መልስ ላይ የ እንግሊዘኛ ቋንቋ እጥረት ታይቶበት መዋረዱ በተለያዩ ሚዲያዎች ሲዘገብ ውሏል:: ቴዎድሮስ ይህን ቦታ እንደማያገኝም ከወዲሁ እየተገለጸ ሲሆን ይህን ካጣ በሚኒስተር ደኤታነት ተሾሞ ሌላኛውን የትግራይ ሰው ወርቅነህ ገበየሁን ከስር ሆኖ ያሽከረክረዋል:: በአሁኑ ወቅት የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ደኤታ በመሆን እየሰራ የሚገኘው ብርሃነ ገብረክርስቶስ ሲሆን የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ቃል አቀባዩም ሌላኛው የትግራይ ተወላጅ ተወልደ ሙሉጌታ ነው::

መንግስት ህዝብን በማይወክሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ ፕሮፓጋንዳ እየሰራ ነው

$
0
0

BBN News  | ኢህአዴግ በአምሳሉ ጠፍጥፎ በሰራቸው ተቃዋሚ ፓርቲዎች አማካይነት ፕሮፓጋንዳ ላይ ተጠምዷል፡፡ የኢህአዴግን እና የመንግስትን ማንኛውም ስራ በማድነቅ ላይ የተጠመዱት ተቀባይነት የሌላቸው ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ በተለይ አዲሱን ካቢኔ ማወደስ የዘወትር ስራቸው መሆኑን ታዛቢዎች ይናገራሉ፡፡ ጠንከር ያሉ እና በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸውን ተቃዋሚ ፓርቲዎች በማፍረስ የሚታወቀው ገዥው መንግስት፣ አሁን ካሉት ትክክለኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር የመስራት ፍላጎት እንደሌለው በተደጋጋሚ አስመስክሯል ይላሉ-ታዛቢዎቹ፡፡

Lidetu ayalew
ዓመቱን ሙሉ የት እንዳሉ ሳይታወቅ ሰንብተው ልክ መንግስት ለፕሮፓጋንዳው ሲፈልጋቸው ብቅ የሚሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ዓለማቸው እና ግባቸው ምን እንደሆነ ለማወቅ መቸገራቸውን የሚገልጹት ታዛቢዎች፣ የኢትዮጵያን ህዝብ ትግል ለመቅበር ከሚፈልገው ግዥው ፓርቲ ባልተናነሰ መልኩ I እነዚህም ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተጠያቂ ናቸውም ይላሉ ታዛቢዎቹ፡፡ ‹‹እነዚህ ፓርተዊች ለገዥው ፓርቲ የሚሰጡት የፕሮፓጋንዳ አግልግሎት በኢትዮጵያ ህዝብ ትግል ላይ የሚፈጥረው ተጽዕኖ ባይኖርም፣ በተቃዋሚነት ስም መነገዳቸው ግን ከተጠያቂነት አያድናቸውም፡፡›› ይላሉ አስተያየት ሰጪዎቹ፡፡


ፕሬዚዳንት ሙላቱ በፓርላማ መክፈቻ ስነ ስርዓት ወቅት ካሰሙት ንግግር አንደኛው ለተቃዋሚ ፓርቲዎች የፖለቲካ ምህዳሩን እናሰፋለን፤ የምርጫ ህጉንም እናሻሽላለን የሚለው ይጠቀሳል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝም ይህን ንግግር በተለያዩ መግለጫዎቻቸው የደገሙት ሲሆን፣ መንግስታቸው ግን የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት እየተመካከረ የሚገኘው ጥቅም አልባ ከሆኑ ተቃዋሚ ፓርቲዊች ጋር ብቻ መሆኑ በግልጽ እየታየ ነው፡፡ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ)፣ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ አነድነት መድረክ (መድረክ) እና ሰማያዊ ፓርቲ ከመንግስት ወገን ምንም ዓይነት የፖለቲካ ተሳትፎ ጥያቄ እንዳልቀረበላቸው የሚናገሩረት ታዛቢዎች፣ መንግስት በድጋሚ ራሱንም ህዝብንም ለማታለል በኢትዮጵያ ትግል ውስጥ ሚና ከሌላቸው ፓርቲዎች ጋር እየዳከረ ይገኛል ብለዋል-አስተያት ሰጪዎቹ፡፡


ሰሞነኛውን የካቢኔ ሹመት አስመልክቶ መንግስት ራሱን ለለውጥ ለማዘጋጀት አንድ እርምጃ መራመዱን እየገለጹ የሚገኙት ሚና አልባዎቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ከካቢኔው በተጨማሪም ብዙዎችን ለግድያ እና ለእስራት የዳረገውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሲያደንቁ አና ለሀገሪቱም መረጋጋት መፍጠሩን ሲመሰክሩ ማየት የተለመደ ሆኗል፡፡

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live