Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ሕወሓት መራሹ ኣገዛዝ አጣብቂኙ ስለበረታበት የኣስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ

$
0
0

stateofemeየመጨረሻው ሰዓት ነው። ወያኔ የኣስቸኳይ ጊዜ ኣዋጅ ኣውጇል። በኦሮሚያ ያለው የሕዝብ ተቃውሞ በመበርታቱ ኣላላውስ ያለው ኣጣብቂኝ ውስጥ የገባው ወያኔ ትላንትና ከሰዓት በኋላ ከሕወሓት ኣስቸኳይ ስብሰባ በኋላ ለሃይለማርያም በተሰጠው ትእዛዝ መሰረት የኣስቸኳይ ጊዜ ኣዋጅ እንዲነገር መደረጉ ወያኔ የደረሰበትን ውድቀት በገሃድ ያሳይል፤ ባለፉት ሃያ ኣምስት ኣመታት ውስጥ ኣስቸኳይ ጊዜ ኣዋጅ ሲታወጅ ይህ የመጀመሪያው ሲሆን ሃገሪቱ ከባድ ኣደጋ ውስጥ መሆኗንና ወያኔ መምራት ኣለመቻሉን የሚመሰክር ኣዋጅ መሆኑ ታውቋል።ሕዝባዊው ትግሉ ካለበት ደረጃ ከፍ ብሎና ጠንክሮ በመሄድ ላይ በመሆኑ ለነጻነት ፈላጊ ሕዝቦች ታላቅ የድል ብስራት ነው።

#MinilikSalsawi
ሕወሓት መራሹ ኣገዛዝ አጣብቂኙ ስለበረታበት የኣስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ


የትግራይ ነጻ አውጪው ኮማንደር ተገደለ |በምስራቅ ሸዋ 32 የአጋዚ ወታደሮች ተገደሉ

$
0
0

Zehabesha-News.jpg
(ዘ-ሐበሻ) ከመገደል ገድሎ ወደ መሞት የገባው የኦሮሞ ሕዝብ ትግል ዛሬም በተለያዩ ከተሞች ቀጥሎ ውሏል:: በተለያዩ ከተሞችም የትግራይ ነጻ አውጪ ወታደሮች ሕይወታቸውን እያጡ መሆኑ ተዘግቧል::

እንደ ዜና ምንጮች ገለጻ ከሆነ ዛሬ በየትግራይ ነጻ አውጪ ሰራዊት ሲገድልባት በከረመው አወዳይ ከተማ ዛሬ ዋናው ኮማንደር ተገድሏል:: እንደ መረጃዎች ከሆነ የኦሮሚያ ወታደሮች አጽብሃ አስገዶም የተባለውን ኮማንደር ዛሬ እርምጃ ወስደውበታል::

አጽብሃ አስገዶም በአወዳይና አካባቢው በርካታ ነዋሪዎችን በመግደልና በማስገደል አመራር ሲሰጥ የነበረ የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ኮማንደር ነበር::

በሌላ በኩል በምስራቅ ሸዋ ራሱን እየተከላከለ ያለው ሕዝብ በፈንታሌ ወረዳ ኤሚት አካባቢ 32 የትግራይ ነጻ አውጪ ወታደሮችን ገድሏል::

በአካባቢው የነበረው ሕዝብ ተሰብስቦ በወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ እየተወያየ ባለበት ወቅት የአጋዚ ወታደሮች ወደ ሕዝቡ መተኮስ በመጀመራቸው የተነሳ የታጠቁ የአካባቢው ነዋሪዎች ከጀርባ የአጋዚ ሰራዊትን በማጥቃት 32ቱን ገድለው ከ4 የማያንሱትን ማገታቸውና ማቁሰላቸው ተሰምቷል::

በፈንታሌ ወረዳ ከሕዝቡ በኩልም የተሰው እንዳለ ሲገለጽ በአካባቢው ያለው ውጥረት ከቁጥጥር በላይ እንደሆነና የትግራይ ነጻ አውጪ ወታደሮችም እየሸሹ መሆኑ ተሰምቷል::

የሃይለማርያም ደሳለኝ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምን ማለት ነው? ጋዜጠኛ አብዱረሂም አህመድ የህግ ተማሪውን አቶ አብዱረዛቅ እና አክቲቪስት የማነ ምትኩን ጋብዞ አወያይቷል

$
0
0

ቢቢኤን ሰበር ዜና: ሃይለማርያም ደሳለኝ ያወጁት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምን ማለት ነው? ጋዜጠኛ አብዱረሂም አህመድ የህግ ተማሪ የሆነውን አቶ አብዱረዛቅ እና አክቲቪስት የማነ ምትኩን ጋብዞ አወያይቷል
ሃይለማርያም ደሳለኝ ያወጁት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምን ማለት ነው? ጋዜጠኛ  አብዱረሂም አህመድ የህግ ተማሪ የሆነውን አቶ አብዱረዛቅ እና አክቲቪስት የማነ ምትኩን ጋብዞ አወያይቷል

ያረፈው ኃይሉ ነው እንጂ ኃይሉስ አብሮን አለ |ጌታቸው ኃይሌ

$
0
0

getachewየመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መሪ አቶ ኃይሉ ሻውል አመራሩን ለመሰሉ መሪ አስረክቦ በአማካሪነት እስኪነጋ ይቆያል ብለን ስንጓጓ፥ የፖለቲካው ሌሊት ሊነጋ ጥቂት ሰዓቶች ሲቀሩት አረፈ። አንድ ትልቅ ዛፍ ወደቀ። ሆኖም፥ ምንም ዓይነት ሞገድ የማያነቃንቀው የራእዩ ኃይል አብሮን ስላለ እንጽናናለን። ብናዝን፥ ነግቶ በብርሃን ሳይመላለስ ስለቀረ ለሱ ነው እንጂ፥ መሰሉንም በመከራ የተፈተነውን አቶ ማሙሸት አማረን ኮትኩቶ ተክቶልናል።

ኃይሉ ተራ ሰው አልነበረም። ብዙዎች በወያኔ ፊት ከእምነታቸው ወጥተው ሲፍረከረኩና የተሰጣቸውን አሜን ብለው እጅ ነሥተው እግር ስመው ሲሄዱ፥ ኃይሉ ሻውል “የጥንቷ አንድ ኢትዮጵያ በጥንቱ አንድነቷ ትኖራለች ብሎ ተሟገተ፤ በሕዝብ ዳኝነት በምርጫ 97 ረታ። ባለ ጠመንጃው ረታሁ አለ።

ኃይሉ ሰው በሚያስፈልግበት ጊዜ አምላክ ለሕዝብ ለሀገር ከሚልካቸው ጀግኖች አንዱ ነበር። በዓሥራ አምስተኛው ምእት ዓመት የአፄ ዘርአ ያዕቆብን አገዛዝ የተጋፈጡት አባ እስጢፋኖስ፥ “ኃይለኛና ጨካኝ ገዢ ሲነሣ፥ ግትር ተቃዋሚ ይነሣበታል” ያሉት በኛ ዘመን በኃይሉ ሻውልና በመንግሥቱ ኃይለ ማርያም፥ በኃይሉ ሻውልና በመለስ ዜናዊ ሲደርስ አየን። የደርግ መሪ መንግሥቱ ኃይለ ማርያም የሾማቸው ሁሉ ሲሰግዱለት፥ ኃይሉ “በተሰጠኝ ኃላፊነት አትግባ” ብሎ እንደገሠጸው አብረውት የነበሩ ይመሰክራሉ። መለስ ዜናዊ፥ ኢትዮጵያን በጎሳና በነገድ ከፋፍየና አጋጭቼ በዳኝነት እገዛታለሁ ብሎ ሲነሣ፥ ኃይሉ ሻውል፥ እኔ እያለሁ አታደርገውም ብሎ እስከ ዕለተ ሞቱ ተሟገተ። እነሆ ዛሬ የኃይሉ ኃይል ለሁለተኛ ጊዜ ሲረታ እናያለን። ሕዝቡ “አንድ ነን” ሲል በሀገሪቱ ዳር እስከ ዳር አስተጋባ።
መለስ ዜናዊና ደጋፊዎቹ በአማራው ላይ ሲዘምቱ፥ ዘመቻው በኢትዮጵያ አንድነት ላይ መሆኑ ለፕሮፌሰር ዓሥራት ወልደየስ ወዲያው ታየውና የመላው አማራ አንድነት ድርጅትን አቋቋመ። መለስም ዓሥራትም “አማራ” ይበሉ እንጂ በሁለቱም አእምሮ ውስጥ ያለው የኢትዮጵያ አንድነት ነበር። ወምበዴው አንድነትን ለመግደል፥ ሐኪሙ አንድነትን ለማዳን። ሁለቱም ደጋፊ አገኙ፤ መለስ ጥቅም ፈላጊዎችን እነ እንትናን ሲያገኝ፥ ዓሥራት የግል ጥቅሙን የሚሠዋ ኃይሉ ሻውልን አገኘ። የኢትዮጵያ አንድነት አሸነፈ።
hailu-shawel
የመላው አማራ አንድነት ድርጅት መሠረቱ የኢትዮጵያን አንድነት ለመጠበቅና የዜጎቿን ሁሉ እኩልነትና መብት በሕግ ፊት ለማስከበር መሆኑ በሕገ ድርጅቱ ውስጥ ግልጽ ቢሆንም፥ በስምና በመልክ ብቻ ለመፍረድ የሚቸኩሉ ድርጅቱን እውነትም አማርኛ ተናጋሪውን በሥልጣን ላይ ለማስቀመጥ የተቋቋመ ድርጅት አደረጉት። አቶ ኃይሉ ሻውል የአመራሩ ጥሪ ሲደርሰው የድርጅቱን እውነተኛ ገጽታ ግልጽ ለማድረግ ድርጅቱን የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ብሎ ጠራው። በዚህም ብዙዎችን ስቦና ድርጅቱ የቅንጅት መሠረትና ግድግዳ ሆኖ በምርጫ 97ድል ነሣ።

ያረፈው ኃይሉ ሻውል ነው እንጂ የጀግንነት ኃይሉስ ለትግል አርአያነት አብሮን አለ። ያረፈው ኃይሉ ባንዲራ ዝቅ ብሎ ይከበርለት፤ ሕያው የኃይሉ ራእይ፥ መጽሐፋችን “አገሪቱን ያላንዳች ቸር ሰው
አያስቀራትም” እንደሚለው፥ በአቶ ማሙሸት አማረ መሪነት ይቀጥል። ባለቤቱን፥ ልጆቹን፥ ዘመዶቹንና ወዳጆቹን እግዚአብሔር ያጽናቸው። ነፍሱን በቴዎድሮስ፥ በዮሐንስ፥ በምኒልክ፥ በኃይለ ሥላሴ ድንኳን ያኑርልን።

የአሰቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወይስ የወያኔ ወታደራዊ መንግስት ግልበጣ? ||ከያሬድ ጥበቡ

$
0
0

ባለፉት ወራት ወያኔ ሁኔታውን ለመቆጣጠር በወታደራዊ ግልበጣ ስም ከኋላ ሆኖ የሚዘውረው መንግስታዊ ግልበጣ ሊያካሂድ እንደሚችል ደጋግሜ ፍርሃቴን አካፍዬ ነበር ። የአሁኑ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስሙን ቀየረ እንጂ የተፈራው የወያኔ ወታደራዊ አገዛዝ መሆኑ የማይካድ ነው ። ወያኔ በዚህ እርምጃው ኢህአዴግንም ማፍረሱ መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል ።
yared
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከመታወጁም በፊት ቢሆን የአገሪቱ አብዛኛው ክፍል ፣ የኦሮሚያና አማራ ክልሎች በወታደራዊ አገዛዝ ስር ወድቀው ነበር ። ይህ አሁን የተጨመረው አዋጅ፣ በመሬት ላይ ተግባራዊ ሲደረግ የሰነበተውን የስለላና ወታደራዊ መዋቅሩን ጭቆና ህጋዊነት ከመስጠት በዘለለ የሚፈይደው ነገር የለም ። ወታደራዊ አገዛዙ ለህዝባዊ እምቢተኝነቱ መልስ እንደማይሆን በተለይ በኦሮሚያ ክልል የተዘረጋው ወታደራዊ አገዛዝ ከደረሰበት ውድቀትና ሽንፈት አገዛዙ መማር ነበረበት ። ያልተሞከረ አዲስ መላ መፈለግ ባለበት ሰአት፣ አገዛዙ ተሞክሮ የከሸፈውን ወታደራዊ አገዛዝ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጭምብል ማምጣቱ ራሱን ለማሞኘት ካልሆነ በቀር ለሁኔታው የሚመጥን ምላሽ ከቶ አይደለም ።

ይህ አዋጅ የሚያደርገው ነገር ቢኖር ውሳኔዎችን ከኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እጅ አውጥቶ፣ ወያኔ በግሉ የሚቆጣጠረው የደህንነቱና መከላከያው ተቋም ሥር በማስገባት፣ የወያኔ አምባገነንነትን ፍፁማዊ ማድረግ ነው ። ሌላ ትርጉም የለውም ። ሞት ለሁሉም አይነት ዘረኝነት!

ከወቅቱ ህዝባዊ እምቢተኝነት ጋር ተያያዥንት ያላቸው የህግ ጉዳይወች ዳሰሳ –ማህሙድ እሸቱ ትኩዬ

$
0
0

መግብያ

ሕወሓት መራሹ ኣገዛዝ አጣብቂኙ ስለበረታበት የኣስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀእንደሚታወቀው አብዘሀኛዎቹ የኢትዮጺያ ተቃዎሚወች በሀገሪቱ ውስጥ ለሚካሃደው ማንኛውም ድርጊት ሃላፊነት መውሰድ ያለበት ህውሃት ነው የሚል እምነት አላቸው። ሆኖም ይህ እቋም ከህግ አንጻር አግባብ ነውን? ይህ ጸሃፊ በመንግስት የሚጠላውን የከፋፍለህ ግዛ መርህ ተጠምዝዞ በከፋፍለህ አጥቃ መተግበር የለበትም ብሎ ይምናል።

እርግጥ ነው አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ የህውሃት ባለስልጣኖች ከእያንዳንዱ ውሳኔዎች ጀርባ መኖራቸው በስፋት ይጠቀሳል። ይህ ሁኔታ ሌሎች ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ፓርቲዎችንም ሆኑ ግለሰቦች ከተጠያቂነት አያድናቸውም። ከዚህ ጋር ተያይዞ የበላይ ትዛዝን እንደ ወንጀል ማቅለሊያነት የሚጠቅሰው የወንጀል ህግ አንቀጽ አግባብነት የሚኖረው በህግ ደንብ የአዛዥ እና ታዛዥነት ግንኙነት ባላቸው ሰውች መካከል ታዛዡ የታዘዘው ድርጊት ወንጀል መሆኑን በቅጡ መለየት የማይችል እና ትዛዙን ከመፈጸም ውጭ ሌላ አማራጭ ሳይኖረው ሲቀር ታዛዡ የበላይ ትዛዙን እንደ ወንጅል መቅለሊያነት ሊያነሳ እንደሚችል ደንግግዋል። ነግር ግን በህውሃት አመራሮች እና ሌላ ከታች ከተጠቀሱት ጉዳዩች ጋር ግንኙነት ያላቸው ፓርቲዎች እና አመራሮች ጋር ምንም አይነት ህጋዊ የሆነ የአዛዥ እና ታዛዥነት ግንኙነት በለመኖሩ (ለምሳሎ የጠ/ሚ እና ከህውሃት የተውጣጡ አማካሪዎቹ) እና ታዘው ነው ይህን ውስኔ የወሰኑት የሚባሉት የክልል ባለስልጣናት ትዛዙን አለመፈጸም የሚችሉበት አግባብ ሳላል ከዚህ የቅጣት ማቅለያ ተጠቃሚ መሆን አይችሉም። ስለሆነም ጸሀፊው ህውሃት ከሚለው ስያሜ ይልቅ ኢሃዴግ ወይም መንግስት የሚለውን ሰያሜ መርጧል።

በአሁኑ ግዜ ሀገራችን ኢትዬጺያ ከፍተኛ የሆነ አመጽ እና ህዝባዊ እምቢተኝነትን በማስተናገድ ላይ ትገኛለች። በኦሮምያ እና አማራ ክልል የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍልዎች ብዙ ሰላማዊ ሰልፍዎችን አካሂደዋል የተለያዩ አድማውችንም ( ከቤት አለመውጣት እና ገበያ ማቆም) በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።

ጠ/ሚ ሃይለማርያም አመጹን እና ህዝባዊ እምቢተኝነቱን ለማስቆም የመከላከያ ሰራዊቱን ማንኛውንም አስፈላጊ ሃይል እንዲጠቀም አዘዋል። በመሆኑም በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ሰወችን ተገድለዋል፤ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተደብድበዋል፤ ቆስለዋል፤ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የህብረተሰብ ክፍልዎችም ታስረዋል።

እነዚህ ድርጊቶች በብዙ የሰበአዊ መብት ተሟጋች ድርጅትዎች እና አክቲቪስቶች በጣም እየተራገቡ ተተችተዋል። እጅግ አሰቃቂ እና ኢ-ሰብአዊ ተብለውም ተፈርጀዋል።

መንግስት እንዚህን ድርጊቶች ለማስተባበል የተለያዩ የመከራከርያ ሃሳቦችን ያነሳል። በፊት እንደገለጽኩት መንግስት  ከዚህ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን የሚከተሉትን የመከራከርያ ነጥቦችን ሲያነሳ ይስትዋላል።

1. የተቃውሞ ሰልፍዎቹ የመንግስት አካላትን እውቅና እና ፍቃድ ስላላገኙ ህጋዊ አይደሉም።
2. መንግስት በሀገሪቱ ውስጥ ሰላም እና ደህንነትን የማስፈን ሀላፊነት ያለበት በመሆኑ እና የተቃውሞው ስልፎቹ ሰላማዊ ባለመሆናቸው አስፈላጊ እርምጃወችን ወስድዋል። እርምጃወቹም ህጋዊ እና መንግስት ከተጣለበት ሀላፊነት ጋር አብረው የሚሄዱ ናቸው።
3. የተቃውሞው እና የህዝባዊ እምቢተኝነቱ  ምክንያት ሀገሪትዋ እይስመዘገበች ያለችው ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ጋር ተያያዝነት ያላቸው የልማት እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በአግባቡ አለመለስ እንጂ ስርአት እና የፓሊሱ ችግሮች ውጤት አይደሉም።

ይህ ጽሁፍ እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ጉዳይዎች ላይ የህግ ትንተና ለመስጠት ታልሞ የተዘጋጀ ሲሆን የሚከተሉትን የህግ ጥያቄዎች ይመልሳል ተብሎ ይጠበቃል።

1. አሁን ከለው እና ስለ-ሰላማዊ ስልፍ የሚያትተው ህግ አንጻር የሰላማዊ ሰልፍ ህጋዊ ይሆን ዘንድ የመንግስት አካሎች እውቅና ያስፈልጋልን?
2. ጠ/ሩ የመከላከያ ሰራዊቱን ሁከቱን ለማስቆም ማንኛውንም ሀይል እንዲጠቀም ሲያዙ መከተል ያለባቸውን ህገ-መንግስታዊ ቅድመ ሁኔታ እና ሂደት (procedures) ተከትለዋልን?
3. ሲጀመር የመከላከያ ሰራዊቱ ሰላማዊ ሰልፉን የማስቆም ህገ-መንግስታዊ ስልጣን አለውን?
4. የመከላከያ ሰራዊቱ ይህንን ስልጣን ያገኘበት መንገድ በህገ-መንግስቱ ላይ ከተቀመጠው ቅድመ-ሁኔታ እና ሂደት ጋር ይጣጣማልን?
5. የተወሰዱት እርምጃዎች መንግስት በሀገሪቱ ውስጥ ሰላምንና ደህንነትን ከማስፈን ሃላፊነቱ አንጻር አግባብናቸውን? አግባብነታቸውን በተላይም መንግስት አላስፊላጊ ሃይል መጠቀሙን እና አለመጠቀሙን ማን ሊወስን ይገባል? ከዚህ እንጻር ኢትዬጺያ ያጸደቀቻቸው አለማቀፍ ስምምነቶች ምን ይላሉ?
6. እውን የተቃውሞው ምክንያት የመልካም አስተደር ችግር ወይስ የፓሊሲ እና የህግ የበላይነት አለመከበር ችግር?

ክፍል አንድ

<<ስለ ሰላማዊ ሰልፍ >>
1. አሁን ከለው እና ስለ-ሰላማዊ ስልፍ ከሚያትተው ህግ አንጻር የሰላማዊ ሰልፍ ህጋዊ ይሆን ዘንድ የመንግስት አካሎች እውቅና ፍቃድ ያስፈልጋልን?

እንደሚታወቀው ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት በተለያዩ አለማቀፍ የሰበአዊ መብት ሰነዶች እውቅና ካገኙ  መሠረታዊ ዲሞክራሲያዊ መብቶች መካከል በግንባር ቀደምነት ተጠቃሽ ነው። በሃገራችን ኢትዮጲያም ይህ መብት በህጎች ሁሉ የበላይ በሆነው ህገ-መንግስት ተረጋግጧል። የኢፌዴሪ ህገ-መንግስት አንቀጽ 30 ላይ “ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በመሆን መሰሪያ ሳይዝ በሰላም የመሠብሠብ ፥ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነጻነትና አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው” በማለት ይደነግጋል።  በተጨማሪም አንቀጹ ሰላማዊ ሰልፎች የህዝብ እንቅስቃሴ ላይ ችግር እንዳይፈጥሩ ለማድረግ፤ የዲሞክራሲያዊ መብቶችንና የህዝብን የሞራል ሁኔታን እንዳይጥሱ ለማስጠበቅ አግባብ ያላቸው ሰርአቶች (regulations) ሊደነገጉ ይችላሉ ይላል።

ከላይ የተጠቀሰው አንቀጽ የመብቱን ይዘትና መብቱ ሊገደብ የሚችልበትን ምክንይቶች ከመግለጽ ውጭ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የመንግስት አካሎችን ፍቃድ ወይም እውቅናን እንደ ቅድመ ሁኔታ አላስቀመጠም። በርግጥ ህገ-መንግስት ጥቅል መርሄችን መደንገግ እንጂ ዝርዝር ሁኔታዎችን  መግለጽ አይጠበቅበትም የሚል መከራከርያ ሊነሳ ይችላል። ሆኖም ጸሃፊው ህገ-መንግስቱን  ስለ ሰብአዊ መብቶች የሚደነግገውን ክፍል (Chapter three) በተመለከተ ይህ የመከራከርያ ሃሳብ ተቀባይነት የለውም ብሎ ይምናል። ምክንያቱም በህገ-መንግስቱ የተዘረዘሩት መብቶች በምን ቅድመ–ሁኔታወች፥ በምን ምክንያቶችና መመዘኛዎች ሊገደቡ እንደሚገባ ህገ-መንግስቱ በዝርዝር ካላስቀመጠ መንግስት የፈለገውን ህግ አውጥቶ ባሻው መልኩ መብቶቹን የሚገድበበት ሁኔታ ይፈጠራል። ይህ ከሆነ ደግሞ ዜጎች ህገ-መንግስታዊ መብቶቻቸውን መተግበር የማይችሉበትና መብቶቹም በወረቀት ከመጠቀስ ውጭ መሬት ላይ ዱብ የማይሉበት ሁኔታ ይፈጠራል። በዚህ ሁኔታ ለዜጎች የሰበአዊ መብቶች ጥበቃ ማድረግ (protection of human rights) የሚለውና ህገ-መንግስት ካስፈለገበት ዋና ምክንያይቶች አንዱ የሆነውን መርህ አላማን ማሣካት ፍጹም የማይሞከር ይሆናል። ስለሆነም መብቶች በምን ቅድመ–ሁኔታወች፥ በምን ምክንያቶች ( አንቀጽ 30 ምክንየቶቹን ዠርዝርዋል) እና መመዘኛወች ሊገደቡ እንደሚገባ ሣይገለጽ ዝርዝሩ በህግ ይገለጻል (claw back clause) የሚሉት የህገ-መንግስት አንቀጾች ከሰብአዊ መብቶች ጥበቃ አንጻር ችግር እንዳለበቸው ይህ ጸሃፊ ያምናል።

ስለ ሰላማዊ ሰልፍ በዝርዝር የሚደነግገውን ህግ በተመለከተ ጸሃፊው እስካሁን ካደረገው የህግ ጥናት አንጻር ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት ይለው ህግ በሽግግር መንግስቱ ጊዜ የወጣው የአዋጅ ቁጥር 3/ 1984 ( proclamation No.3 1991) ብቻ ነው። ይህን አዋጅ በግልጽም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የሚሽር ሌላ አዋጅ ሥለሌለና ከህገ-መንግስቱ ጋር የማይጣረስ በመሆኑ በህግ-መንግስቱ አንቀጽ 9(1) መሰረት አሁንም ተፈጻሚነት ይኖረዋል። አዋጁ በመግቢያው(preamble) ላይ አላማው የዲሞክራሲያዊ መብቶችን ካለምንም ገደብ ማክበርና በአግባቡ እንዲተገበሩ ሁኔታወችን ማመቻቸት መሆኑን ያትታል።

የሰላማዊ ሰልፍ የሚካሄድበትን ሂደት በተመለከተ አዋጁ እንደ ግዴታ ያስቀመጠው ቅድመ ሁኔታ ( procedural obligation)  ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ያሰበው አካል ሰላማዊ ሰልፉ በሚካሄድበት አካባቢ ለሚገኝው የአስተዳደር መስርያ ቤት ሰልፉ ከመካሄዱ ከ48 ሰአት በፊት በጹሁፍ የሰልፉን አላማ፥ ሰልፉ በየት አካባቢና መንገድ እንደሚካሄድ፥ ሰልፉን ማን እንዳደራጀው እና ከመንግስት ሰልፉን አስመልክቶ ምን እይነት ድጋፍ እንደሚፈልጉ ማሳውቅ ነው (Hence, what’s required is serving a written notice)።

አዋጁ አንቀጽ 6 ላይ  የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት የሰላማዊ ሰልፍ የማካሄድ ጥያቄው በጹሁፍ በደረሳቸው በ12 ሰአት ጊዜ ውስጥ መልስ የመስጠት ግዴታ እንዳለባቸው ከመደንገጉ በተጨማሪ ሰልፉን መከልከል እንደማይችሉ በግልጽ ያስቀምጣል። በተጨማሪ አንቀጹ ሰልፉ የሚካሄድበትን ቦታና ግዜ በተመለከተ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ከሰልፉ አስተባባሪዎች ጋር ሊደራደሩ እንደሚችሉ ያትታል። ድርድሩ በሁለቱ ወገኖች ስምምነት የሚወሰን በመሆኑ ከሰላማዊ ሰልፍ አድራጊዎቹ አንጻር ያለው ብቸኞ ግዴታ ሰልፍ ማድረግ እንደሚፈልጉ ማሳወቅ እንጂ ፍቃድ ማግኘት አይደለም ማለት ነው። ሰለሆነም ሰላማዊ ሰልፎቹ ከመንግስት አካላት እውቅና ወይም ፍቃድ ስላላገኙ ህጋወጥ ናቸው የሚለው ብዙ ግዜ በመንግስት በኩል የሚነሳው የመካራከርያ ሃሳብ ከህግ አንጻር ተቀባይነት የለውም።

አሁን በለው ሁኔታ መንግስት የፈለገውን ህግ አውጥቶ ያሻውን መብት መገደብ የሚችል በመሆኑ ይህ ጸሃፊ መንግስት ወደ ፊት ይህንን አዋጅ ሊሽረው እና ከመንግስት ፍቃድ ሳይገኝ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግን ህገወጥ ተግባር ሊደርገው ይችላል የሚል ስጋት አለው። ለዚህም ነው ስለ ሰበአዊ መብቶች የሚደነግጉት የህገ-መንግስቱ አንቀጾች ሰብአዊ መብቶች በምን ቅድመ–ሁኔታወች፥ በምን ምክንያቶችና መመዘኛወች ሊገደቡ እንደሚገባ በዝርዝር ሊጠቅሱ ይገባል የሚለውን ነጥብ ከላይ አንክሮት ለመስጠት የፈለገው።  በተጨማሪም የመንግስት ፍቃድ ሣይሰጥ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግን ህገወጥ ተግባር ሊያደርግ የሚችል አዋጅ ከወጣ አዋጁ ( ደንቡ እንደ ህገመንግስቱ አገላለጽ) ከህገ-መንግስቱ መንፈስ ጋር ከመቃረኑ በተጨማሪ ኢትዬጺያ ካጸደቀችው አለማቀፍ ስምምነቶች በተለይም ሰለ ሲቪል እና ፓለቲካል መብቾች የሚደነግገው አለማቀፍ ቃል ኪዳን ጋር ይጣረሳል። እንደዚያ ከሆነ በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 9(1) እና 13 (2) መሰረት አዋጁ ኢ-ህግ-መንግድታዊ ይሆናል ማለት ነው።

እዚህ ጋር በተግባር ሲካሄዱ የነበሩትን ሰልፎች ከላይ ከተጠቀሰው የህግ ማእቀፍ አንጻር ማየቱ ተገቢ ነው። አብዘሃኛዋቹ ሰላማዊ ሰልፎች ሰላማዊና ብዙውን ግዜ የመንግስይ ሀይሎች ሰልፎቹን በሀይል እናስቆማለን ሲሉ በወሰዱት እርምጃ ወደ ሁከትነት የተቀየሩ ቢሄንም አንዳንድ ቦታዎች ላይ በመሳርያ የታጀቡ ሰልፎች ሲካሄዱ ተስተውለዎል። ይህ ተግባር ከህገ-መንግስቱ ጋር የሚጣረስ ተግባር መሆኑን ይህ ጻሃፊ ይምናል። ሰላማዊ ሰልፎች ሁሌም ፍጹም ሰላማዊ ሊሆኑ የሚገባ ሲሆን የጸጥታ አካላት እና የሰላማዊ ሰልፎች አስተባበሪ ግለሰቦች ሰላምን ለማስፈንና የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ በጋራ ሊሰሩ ይገባል። በኢትዬጺያ ውስጥ ይህ ሲሆን የሚታየው መንግስት በጠራቸው ሰልፎች ብቻ መሆኑ እጅግ ያሳዝናል። ከዚህ ይልቅ የጽጥታ ሃይሎሽ የተቃውሞ ስልፎችን በሃይል ለማስቆም በሚሞክሩበት ሂደት ሰልፎቹ ወደ ሁከትነት የሚቀየሩበት ሁኔታ ዘውትር ይስተዋላል። ከውቅቱ ሁኔታ ጋር ተያይዞም ጠ/ር ሃይለማርያም አመጹን እና ህዝባዊ እምቢተኝነቱን ለማስቆም የመከላከያ ሰራዊቱን “ማንኛውንም አስፈላጊ ሃይል” እንዲጠቀም ማዘዛቸው ይታወሳል። ማንኛውም አስፈላጊ ሃይል ማለት ምን ማለት ነው? በህገ-መንግስቱ ከተደነገጉት የሰበአዊ መብቶች እንጻር እንዴት ይታያል? ጠ/ሩ ይህን ትዛዝ ሲያዙ መከተል ያለባቸውን ህገ-መንግስታዊ ቅድመሁኔታ እና ሂደት (procedures) ተከትለዋልን?

የነዚህንና ሎሎች ተያያዥ ጉዳዬችን ትንትናን ይዘን በክፍል ሁለት በቅርቡ እንገናኝ።

ይቀጥላል…..!!

ከወቅቱ ህዝባዊ እምቢተኝነት ጋር ተያያዥንት ያላቸው የህግ ጉዳይወች ዳሰሳ. –ማህሙድ እሸቱ ትኩዬ/

$
0
0

ክፍል ሁለት

ስለ ጠቅላይ ሚኒስተሩ ትዛዝ

hailemariam_desalgn-6-satenaw-newsበክፍል አንድ ላይ እንደተገለጸው ጠ/ሩ የህዝባዊ እምቢተኝነቱንና አመጹን ለማስቆም የመከላከያ ሰራዊቱ “ማንኛውንም ሃይል” እንዲጠቀም አዘዋል። ይህ ትእዛዝ የተለያዩ የህግ ጭብጦችን (issues) ያስነሳል።

የመጀመሪያው ጥያቄ የሚሆነው ትእዛዙ በኢፌደሪ ህገ-መንግስት ክፍል ሶስት (Chapter Three) ላይ ከሰፍሩት የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ አንጻር እንዴት ይታያል የሚለው ነው። ጠ/ሩ የመከላከያ ሰራዊቱን ማንኛውንም አስፈላጊ ሀይል ተጠቅሞ አመጹንና ህዝባዊ እምቢተኝነቱ (እንደ ጠ/ሩ አገላለጽ ሁከቱን) እንዲቆጣጠር ሲያዙ በህገመንግስቱ የተጠቀሱት የሰበአዊ መብቶች እንደሚጣሱና እንደሚገሰሱ እሙን ነው።

ምንም እንኳን ሰብአዊ መብቶች በመርህ ደረጃ የማይጣሱና የማይገሰሱ የሰው ልጅ ሰው በመሆኑ ብቻ የሚያገኛቸው መብቶች ቢሆኑም አግባብነት ባለው ስርአት መሰረት በተለይም በህግ አውጭው አካል (legislative organ) በከፊል ሊገደቡ እንደሚችሉ ግልጽ ነው (limitation)። እዚህ ላይ አግባብነት ያለው ስርአት መሰረት የሚለው ሰብአዊ መብቶቹን ሊገድብ የሚችል ህግ ብቻ ማውጣት እንዳልሆነ ልብ ይላል። ጸብሃፊው ከዚህ በፌት ባወጣው ጱሁፍ ላይ (የአማረኛ ትርጉሙን በቅርቡ) በሃገራችን ውስጥ ስላለው የዘፍቀደ የሰብአዊ መብቶች አገዳደብ እና ህጎች እንዴት የመንግስት የፓለቲካ መጠቀምያ መሳሪያወች እንደሆኑ በግልጽ በማሳየቱ ሰብአዊ መብቶች እንዴት መገደብ አለባቸው የሚለውን ጉዳይ በዝርዝር መተንተኑ አስፈላጊ ሆኖ አላገኘውም።

ከያዝነው ጭብጥ ጋር በቀጥታ ግንኙነት ያለው ጉዳይ  የአስፈጻሚው አካል (Executive Organ) ዜጎችን የሰብአዊ መብቶቻቸውን እንዳይተገብሩ በመከልከል መብቶቹን ሙሉ በሙሉ ስለሚገድብበትና ስለሚጥስበት ሂደት ነው(derogation and suspension)። ምህንይቱም “ማንኛውንም እርምጃ” የሚለው የጠ/ሩ ትእዛዝ ሁሉም የሰብአዊ መብቶች የሚጣሱበትን አግባብ የሚፈጥርና የመከላከያ ሰራዊቱ የመብቶች ሁሉ መሰረት የሆነውን በህይወት የመኖር መብት፥ በነጻነት የመንቀሳቀስ መብት፥ ሰላሚዊ ስልፍ የማድረግ መብትና ሌሎችን ስለጣሰ ነው።

በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 93 ላይ እንደተገለጸው የህገ-መንግስታዊ ስርአቱን አደጋ ላይ የሚጥል ሁኔታ ሲከሰትና በተለመደው የህግ የማስከበር ሥርአት ለመቋቋም የማይቻል ሲሆን የፍደራል መንግስቱ የሚኒስተሮች ምክርቤት የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ በመደንገግ ሰብአዊ መብቶችን መሉ በሙሉ በመገደብ በዜጎች እንዳይተገበሩ ሊያደርግ ይችላል (derogation and suspension)።

አንቀጹ የአስቸኳይ ግዜ እዋጅ ህጋዊነት ይኖረው ዘንድ ቅድመ ሁኔታወችን ይስቀመጠ ሲሆን አዋጁ በሚኒስተሮች ምክር ቤት በታወጀ በ48 ሰአት ውስጥ ለህዝብ ተወካዩች ምክርቤት መቅረብ እንዳለበትና የምክር ቤቱን ሁለት ሶስተኛ የድጋፍ ድንጽ ማግኘት እንዳለበት ( የህዝብ ተወካይወች ምክር ቤት ስራ ላይ ካልሆነ በ15 ቀን ውስጥ መቅረብ አለብት) ሊቆይ የሚችለውም ለ6 ወር ብቻ እንደሆነ ይጠቅሳል።  በተጨማሪም አንቀጹ ኢሰብአዊ አያያዝን(prohibition against inhuman treatment) የሚከለክለውን የህገመንግስት እንቀጽ 18 እና ሌሎች ( 25, 39(1)(2)) በማንኛውም መልኩ በአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ሊጣሱ እንደማይችሉ በግልጽ ያስቀምጣል። እዚህ ጋር በህይወት የመኖር መብት በግልጽ ባይጠቀስም የህግ-መንግስቱ ክፍል ሶስት ( Chapter 3) ላይ የተጠቀሱት የሰበአዊ መብቶች ኢትዮጲያ ከጽደቀቻቸው አለማቀፍ ስምምነቶች ጋር በተጣጣመ መልኩ መተርጎም አለባቸው በሚለው የህገ-መንግስት አንቀጽ 13(2) አማካኝነት በህይወት የመኖር መብት በአስቸካይ ግዜ አዋጅ ሊጣስ እንደማይችል ሊታወቅ ይገባል።

የጠቅላይ ሚኒስተሩን ትእዛዝ ከላይ ከተገለጸው የህግ-ማእቀፍ አንጻር መገምገሙ ተገቢ ነው። እንደሚታወቀው የጠቅላይ ሚኒስተሩ በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ብለው “ሁከቱን ለማስቆም የመከላከያ ሰራዊቱ ማንኛውንም ሃይል እንዲጠቀም አዝዣለሁ” ከማለት ውጭ ውሳኔው በሚኑስተሮች ምክርቤት የተወሰነ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ስለመሆኑ የተነገረ ነገር የለም። ውሳኔው በ48 ሰአት ግዜ ውስጥም ሆነ በ15 ቀን ውስጥ ለህዝብ ተወካዩች ምክርቤት ቀርቦ 2/3 ድምጽ አላገኘም። በተጨማሪም ውሳኔው ከላይ የተጠቀሱትን በአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ሊጣሱ የማይችሉ መብቶችን ከለላ ባልሰጠ መልኩ በማንኛውም ሃይል መጠቀም ሂደት ውስጥ እንዲጣሱ ተደርጎ የተወሰነ ውሳኔ ነው። ስለሆነም ውሳኔው የህግ መሰረት የለለው የሰበአዊ መብቶችን በማናለብኝና በዘፈቀደ የሚጥስ በህገ-መንግስቱ የተቀመጡትን ቅድመ ሁኔዎችና ሂደቶች (procedures) ያልተከተለ ኢ-ህግ መንግስታዊ ውሳኔ ነው ማለት ነው።

ሌላው እዚህ ጋር መነሳት ያለበት ጉዳይ የመከላከያ ሰራዊቱ አመጹንና ህዝባዊ እምቢተኝነቱን ማስቆም የሚችልበትን የህግ-አግባብ መመርመር ይሆናል። በዋናነት የመከላከያ ሰራዊቱ ስልጣን ድንበርን በመጠበቅ የሃገር ሉአላዊነትን ማስከበር መሆኑ እሙን ነው። ለዚህም ነው ኢፌድሪ ህገ–መንግስት ስለ መከላከያ ሰራዊ መርሆች በሚደነግገው አንቀጽ 87 ላይ የመከላከያ ሰርልዊቱ ስልጣን የሀገርን ሉአላዊነት ማስከበር መሆኑን በግል የጠቀስው።

ከዚህ ጋር ተያይዞ የሀገርን ሉአላዊነት ማስከበር በብዙ መልኩ መተርጎም የሚችል ሰፊ ሀስብ (vague) በመሆኑ የመከላከያ ሰራዊቱን አመጹንና ህዝባዊ እምቢተኝነቱን ለማስቆም የሚያግደው ነገር የለም የሚል መከራከርያ ሊነሳ ይችላል። ሆኖም ሁሉም አግባብነት ያላቸው የህገ መንግስት አንቀጾችን ስናይ በመርህ ደረጃ የመከላከያ ሰራዊቱ ስልጣን ድምበር ከመጠበቅ ጋር የተቆራኘ መሆኑን እንግነዘባለን።

እንደሚታወቀው ሃገራችን ኢትዮጺያ የፌደራል መንግስት አወቃቀርን የምትከተል ሀገር ናት። በዚህ የፌደራል ስርአት ውስጥ ክልሎች የራሳቸው በህገ-መንግስቱ የተረጋገጠ ስልጣን አላቸው። ስለ ክልሎች ስልጣን የሚያትተው የኢፌድሪ ህገ-መንግስት አንቀጽ 52(2) (ሰ) አማካኝነት ክልሎች የክልላቸውን ሰላምና ጸጥታ የማስጠበቅ ስልጣን እንዳላቸው በግልጽ ይጠቅሳል።

የፌደራሉን መንግስት ስልጣን የሚዘረዝረው አንቀጽ በበኩሉ በአንቀጽ 51(14) ላይ የፌደራል መንግስቱ “ከክልሎች አቅም በላይ የሆነ የጸትታ መደፍረስ ሲያጋጥም በክልሉ መንግስት ጥያቄ መሰረት የሀገሪቱን የመከላከያ ሃይል ያሰማራል” ይላል።  የህገመንግስቱ አንቀጽ 87 የመከላከያ ሰራዊቱ የሀገርን ሉአላዊነት ከመጠበቅ በተጨማሪ በአስቸኳይ ግዜ አዋጅ መሰረት የሚሰጡትን ተግባራት እንደሚፈጽም ያትታል። በተጨማሪም ህገ-መንግስቱ በአንቀጽ 62(9) ላይ የፌደሬሽን ምክርቤቱን ተግባር ሲዘረዝር ክልሎች ህገመንግስቱን በመጣሥ የህገመንግስታዊ ስርአቱን አደጋላይ የጣሉ እንደሆነ የፌደራል መንግስቱ ጣልቃ እንደሚገባ ይገልጻል።

ሌላው እነዚህን ህገ-መንግስታዊ መርሆችን ለመተግበር የወጣውና የፌደራል መንግስቱ በክልሎች የመከላከያ ሰራዊቱን በማሰማራት ጣልቃ የሚገባበትን ሥርአት የሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 359/1995( proclamation no. 359/2003) የፌደራል መንግስቱ በክሎች ላይ ጣልቃ የሚገበብትን ሶስት አግባቦች አስቀምጧል።  እነሱም፦
1. ክልሎች ከአቅም በላይ የጸጥታ ችግር ሲጋጥማቸውና የፌደራል መንግስቱን እርዳታ ሲጠይቁ።
2. ክልሎች ህገመንግስቱን በመጣስ የህገመንግስታዊ ስርአቱን አደጋላይ የጣሉ እንደሆነ።
3.  በክልሎች ውስጥ ከባድ የሰብአዊ ጥሰት ሲኖር ናቸው።
በክልሎች ጥያቄ ከሚካሄደው የፌደራል መንግስት ጣልቃ ገብነት ውጭ በሁለትና ሶስት ላይ በተጠቀሱት ሌሎቹ የፌደራል መንግስቱ መካላከያ ሰራዊቱን ወደ ክልሎች በሚያማራበት አግባቦች እንደ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ማውጅና ለፌደሬሽን ምክርቤቱ ሪፓርት የማቅረብ ያሉ ግዴታ  (procedural obligations) አለበት።

ከዚህ የህግ ማእቀፍ አንጻር ጠቅላይ ሚኒስተሩ የመከላከያ ሰራዊቱን በኦሮምያና አማራ ክልል የሚካሄደውን አመጽ እንዲያስቆም ያዘዙበት መንገድ አግባብነቱ እጅግ በጣም አጠያያቂ ነው። ይህ ጸሃፊ እስከሚያስታውሰው ደረስ የአማራም ሆነ የኦሮምያ ክልል የፌደራል መንግስቱ መከላከያ ሰራዊቱን እዞ ሀከቱን እንዲያስቄም አልጠየቁም። ጉዳዩም ክልሎች ህገ መንግስቱን በመጣስ ህገመንግስታዊ ስርአቱን አደጋ ላይ የከተቱበት ውይም ትልቅ የሰበአዊ ጥሰት የፈጸሙበት ሳይሆን ህዝብ ያመጸበትና አልገዛም ያለበት (እንደ መንግስት እገላለጽ ጥቂቶች ሁከት የፈጠሩበት) ሁኔታ ነው። ስለሆነም የፌደራል መንግስቱ የመከላከያ ሰራዊቱን በክልሎች እንዲያሰማራ ማሟላት ያለበትን ቅድመ-ሁኔታ አያሟላም። ያሟላል እንኳን ቢባል የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ስላልታወጀና ለፌደሬሽን ምክር ቤት መቅረብ ያለበት ተከታታይ ሪፓር ሳይቀርብ በአስፈጻሚው አካል ብቻ የተወሰነ ውሳኔ በመሆኑ የህግ መሰረት የለለው ኢ-ህግ መንግስታዊ ውሳኔ ነው ማለት ነው።

እንግዲህ በዚህ የዘፈቀደና ኢ-ህግ መንግስታዊ አመጽ የማስቆም ሂደት ውስጥ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ሰወችን ተገድለዋል፤ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተደብድበዋል፤ ቆስለዋል፤ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የህብረተሰብ ክፍልዎችም ታስረዋል። ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚነሳው ጥይቄ እነዚህ እርምጃዎች መንግስት በሀገሪቱ ውስጥ ሰላምንና ደህንነትን የምስፈን ሃላፊነቱ አንጻር አግባብናቸውን? አግባብነታቸውን በተላይም መንግስት አላስፊላጊ ሃይል መጠቀሙን እና አለመጠቀሙን ማን ሊወስን ይገባል? ከዚህ እንጻር ኢትዬጺያ ያጸደቀቻቸው አለማቀፍ ስምምነቶች ምን ይላሉ?

የነዚህንና ሌሎች ተያያዝ ጉዳዬች ትንተናን ይዘን በቅርቡ በክፍል ሶስት (3) እንገናኝ

ይቀጥላል……..!

አቶ ክቡር ገና “የኢትዮጵያ ፈተናዎች ምንጭና ከአጣብቂኙ መውጫ ቀጥተኛ መንገዶች”ን ይጠቁማሉ | VOA

$
0
0


አቶ ክቡር ገና “የኢትዮጵያ ፈተናዎች ምንጭና ከአጣብቂኙ መውጫ ቀጥተኛ መንገዶች”ን ይጠቁማሉ | VOA
አቶ ክቡር ገና “የኢትዮጵያ ፈተናዎች ምንጭና ከአጣብቂኙ መውጫ ቀጥተኛ መንገዶች”ን ይጠቁማሉ | VOA


“በሁሉም አካባቢ የሚገኙ የኢትዮጵያ ህዝቦች ለመጨረሻው የሞትና የሽረት ትግል ራሳቸውን ማዘጋጀት ይኖርባቸዋል”ጀዋር መሐመድ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በከፍተኛ ፍራቻ ውስጥ የሚገኘው የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት በስልጣን ማክተሚያው የመጨረሻ ሰዓት ላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማውጣቱን ተከትሎ አክቲቭስት ጀዋር መሐመድ በፌሰቡክ ገጹ በሰጠው ምላሽ “በሁሉም አካባቢ የሚገኙ የኢትዮጵያ ህዝቦች ለመጨረሻው የሞትና የሽረት ትግል ራሳቸውን ማዘጋጀት ይኖርባቸዋል” ሲል ጥሪ አቀረበ::
jawar
“ወያኔ ከኦሮሞ ከአማራና ከሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች የተነሳበትን ከፍተኛ ተቃውሞ ማስቆም ባለመቻሉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ደንግጎ ታጣቂዎቹን ለመጠነ ሰፊ ግድያና አፈና አሰማርቷል።” ያለው ጀዋር “ይህን የወያኔ ሴራ ለማክሸፍና ለመመከት ሁሉም ወገን በአንድ ልብ ሊነሳ ይገባል።” ብሏል::

“በሁሉም አካባቢ የሚገኙ የኢትዮጵያ ህዝቦች ለመጨረሻው የሞትና የሽረት ትግል ራሳቸውን ማዘጋጀት ይኖርባቸዋል።” የሚለው ጀዋር “በአገሪቱ አምባገነናዊ ሥርአት ለመጨረሻ ጊዜ ተወግዶ ሁሉም ዜጎች በእኩልነት የሚስተናገዱበት ፍትሃዊና ዲሞክራሲያዊ ስርአት ለመመስረት በጋራ የምንነሳበት ወቅት ላይ ደርሰናል። በመሆኑም ለመሞት እያጣጣረ ያለውን የወያኔ ሰው በላ ስርአት ተጨማሪ ጥፋት ከማድረሱ በፊት ተባብረን ወደግብአተ መሬቱ እናደርሰው ዘንድ ለሁሉም የኢትዮጵያ ህዝቦች ጥሪያችንን እናቀርባለን። ሞት ለወያኔ!!!!” ጥሪውን አቀርቧል::
screen-shot-2016-10-09-at-9-16-32-pm

በምዕራብ አሪሲ ሄራሮ ከተማ የትግራይ ነጻ አውጪ ወታደሮች 28 ሰላማዊ ሰዎችን ገደሉ

$
0
0

Zehabesha-News.jpg(ዘ-ሐበሻ) መሞታችን ካልቀረ እየገደልን እንሞታለን በሚል የተነሳው ሕዝብ አሁንም ለትግራይ ነጻ አውጪ መግግስት ራስ ምታት ሆኖበታል:: ላለፈው አንድ ሳምንት በከፍተኛ ትንቅንቅ ላይ የከረመው የአሪሲ ሕዝብ ከትናንት ጀምሮ ሙሉ በሙሉ በወታደራዊ ቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለጸ::

የአይን እማኞች ለዘ-ሐበሻ በላኩት አስተማማኝ መረጃ መሰረት በተለይ በምዕራብ አሪሲ ሄራሮ ከተማ የትግራይ ነጻ አውጪ ሠራዊት ዕድሜ ሳይመርጥ ከህጻናት እስከ አዛውንቶች ላይ ድረስ እየተኮሰ ነው:: ተሰብስቦ መሄድ ይቅርና ከቤት የሚወጡት ወገኖች ላይ ጭምር እየተኮሰ መሆኑን የሚገልጹት እነዚሁ እማኞች በትናንትናው ዕለት ብቻ 28 ሰዎችን ሕይወት መቅጠፉን አስታውቀዋል:: በርካታ የቆሰሉ ወጣቶች እንዳሉም መረጃው ጠቁሟል::

በም ዕራብ አሪሲ ያሉ ቄሮዎችም እንዲሁ በትግራይ ነጻ አውጪ ሠራዊት ላይ አጸፋውን እየመለሱ መሆኑን የሚገልጹት ምንጮች ሕዝቡ መሞታችን ካልቀረ እየገደልን እስከነጻነታችን ድረስ እንታገላለን የሚል ቃልኪዳን ይዟል ብለዋል::

ህዝባዊው ቁጣ ሲዳሰስ …. ( ክፍል አንድ)

$
0
0

አዜብ ጌታቸው

“ከዚህ ሁሉ በላይ ግን የሜሮንን ተግባር ክቡርና ድንቅ ያደረገው ….. ” ከሞት አንድ ነው በሚባለው በሠርጓ እለት የወገኖቿን መከራ፤ ሞትና፤ስቃይ ለመዘከር መወሰኗ ነው። ይህን ውሳኔዋን ምናልባት ለወዳጅ ዘመዶቿ ቀደም ብላ “ አማክራ ቢሆን እረ ተይ!” በዓለምሽ ቀን የምን ሃዘን ነው? ሊሏት ይችሉ እንደነበር እገምታለሁ። እሷም ይህንኑ ፈርታ ይመስለኛል ሃሳቧን ለእጮኛዋ ( አሁን ባለቤቷ) ብቻ ያማከረቺውµ: ባለቤቷም ሰብአዊ ስሜቷን አድንቆ ሃሳቧን መደገፉ የሚያስመሰግነው ነው። ትዳራቸውን ሰብአዊ ትዳር ፤ሰርጉን ብሔራዊ ሠርግ ያልኩትም ለዚህ ነው። እናም እህቴ ሜሮን ሆይ! ይህን በማድረግሽ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ሲያከብርሽ ይኖራል። ሰርግሽም በኢትዮጵያ የሰርግ ታሪክ ልዩ ምዕራፍ ይዞ ይዘከራል። ልጆችሽም በእናታቸው ገድል ይኮሩ ዘንድ ማድረግ ችለሻልና!

File Photo

File Photo

እንኳን ደስ አለሽ! ዘርሽም ይባረክ! ትዳርሽም የሰመረ ይሁን! እላለሁ። ለክርስትና እንመጣልን ገና ብለናል ! የምንመጣው ግን ሸገር እንጂ አሜሪካ አይደለም። የፕሮፌሰር መስፍን የመፍትሄ ሃሳብ ( የትግራይ ህዝብ ሆይ ለራስህ ስትል ጣፍጥ) ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርኩት የዛሬው ጽሁፌ ላለፉት ጥቂት ወራት የተከሰቱ ጉልህና አነጋጋሪ ነበሩ ያልኳቸውን ክስተቶች በወፈ በረር የሚቃኝ ነው። እናም እውቁ የሰባዊ መብት ተሟጋችና አንጋፋው ምሁር ፕ/ ር መስፍን ወልደማሪያም “ ”የወያኔ አገዛዝና የኢትዮጵያ ወደፊት በሚል ርዕስ ለንባብ ያቀረቡት በ 11 ገጾች የተካተተው ጽሁፍ ከጉልህ ክስተቶች አንዱ ነበርና በወፍ በረር ምልከታዬ ላካትተው ፈለኩ።የፕ/ ር መስፍን ወልደማሪያምን ጽሁፍ እንዳነበብኩ ወዲያው በአይምሮዬ ያቃጨለው ከ 25 ዓመታት በፊት በሳቸው አነሳሽነት ( ሌሎችም ምሁራን በሃሳብ የተጋሩት ይመስለኛል) ለኮ/ ል መንግስቱ ኃይለማሪያም ያቀረቡት የስልጣን ልቀቅ ደብዳቤ ነው። ታሪክ በሚያስገርም መልክ ራሱን ሲደግም ታየኝና እኝህ ሰው መንግስት ሲያቅተው የሚታያቸው ነገር አለና ወያኔ ለ 12 አምስት ጉዳይ ላይ እንደሚገኝ አንድ ማረጋገጫ ነው አልኩ። ደስም አለኝ። ከወገቤ ሸብረክ ብዬ መምህር ሆዬ! “እድሜ ይስጥልን እንኳን በህይወት ቆይተው ይህንንም መንግስት ይብቃህውረድ!” ለማለት በቁልን ብያለሁ። ወደ ፕ/ ር ጽሁፍ ይዘት ስመጣ፦ በፕ/ ር ጽሁፉ የተገለጹት አብዛኞቹ ሃሳቦች የሚያከራክሩ አይደሉም።ፕ/ ር በጽሁፋቸው 1 ኛ) ኢትዮጵያ እንደ ሃገር የምትገኝበትን አሳሳቢ ሁኔታ አመላክተዋል።2 ኛ) የትግራይ ህዝብ የአገዛዙ (የወያኔ) ጓዳ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ለምርጫ አስቸጋሪ የሆነ( ላም እሳትወለደች…) አይነት የታሪክ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ አብራርተዋል። የትግራይ ህዝብ ሁለት ምርጫዎች ከፊቱ ተደግነዋል 1 ኛው) ከወያኔ ጎን መቆም 2 ኛው) ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር መቆም እንደሆነ ጠቁመው፤ እንደ ምክርም ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እንዲቆም አሳስበዋል። የትግራይ ህዝብ ሆይ! ለራስ ብለህ ጣፍጥ አልያ …. አይነት ድምጸት ያለውን ማሳሳቢያና ምክርን አዋህደው አቅርበዋል።3 ኛ) አገዛዙ (ወያኔ) እያዋከበው ከሚገኘው ህዝባዊ አመጽ ሊወጣ ከማይችልበት ደረጃ መድረሱን አመላክተው ነገር ግን የአገዛዙ አካላት መልካም ፍቃድ ከታከለበት ( መልካም ፈቃድ ብሎ ነገር ባያውቁም አሁን ግን ከየትም ያምጡት ብለው) ስልጣን በሰላም ለቀው ለራሳቸውም ለትግራይ ህዝብም ለኢትዮጵያም የሚበጅ ነገር ማድረግ እንደሚችሉ የደቡብ አፍሪካውን ዴክለር ዋቢ አድርገው አስረድተዋል። አስከትለውም የአገዛዙ መልካም ፈቃድ ከተገኘ በቀጣይ ሊደረጉ ይገባል ያሏቸውን የመፍትሄ ሃሳብ ዝርዝሮች (ለውይይት) አቅርበዋል።በፕ/ ር ለቀረበው የመፍትሄ ሃሳብ ትልቁ እንቅፋትና ተግባራዊነቱን የህልም ያህል የማይጨበጥ የሚያስመስለው “ ” መልካም ፈቃድ ብሎ ነገር በማያውቁት ባለስልጣናት መልካም ፈቃድ ላይ የተመሰረተ መሆኑ ነው። ፕ/ ር ይህ “ ” መሆኑ የጠፋቸው አይመስለኝም። መልካም ፈቃዱን ከየትም ያምጡት ያሉትም ለዚህ ነውµ፤ ችግሩ መልካም ፈቃዱን ከየት ያመጡታል ?
ለረዥም ግዜ የፕ/ ር መስፍን ጽሁፍ ሳነብ ቆይቻለሁ! ፕ/ ር ሁሌም ቢሆን እገሌን ይከፋዋል እገሌን ያስደስተዋል በሚል ይሉኝታ የሚያምኑበትን ነገር ከመግለጽ ወደ ኋላ እንደማይሉ ሁሉ የማይምኑበትንም ነገር ኤክስ ለመስጠት አይፈሩም። በዚህ ጽሁፋቸው ላይ ግን ሊሆን እንደማይችል ነፍሳቸው እያወቀች ምናልባት… እንዲያው ምናልባት… በሚል ቀጭን ተስፋ ላይ የተንጠለጠለ የመፍትሄ ሃሳብ መሰንዘራቸውን አስተውያለሁ። ይህ ደግሞ ፕ/ ር በርግጥምበጣም…! በጣም..! መጨነቃቸውን እንድገነዘብ አድርጎኛል ። ፕ/ ር ከ ቪ.ኦ. “ኤ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስም ተስፋ” ቆርጫለሁ ማለታቸው ይህንኑ ጭንቀታቸውን የሚያሳይ ሆኖ ተስምቶኛል። ፕ/ ር በዚህ ጽሁፋቸው ዙሪያ በተደረገላቸው አንድ የፓልቶክ ቃለ- መጠይቅ ላይ፤ አዲስ መጪው ሂያጁን እየተበቀለ የሚቀጥልበትን መጥፎልምድ(አዙሪት) አንድ ቦታ እናቁመው! ቂምን አርግዘን ለበቀል ከመንደርደር ወጣ ብለን ስለዘላቂ ሰላም እናስብ የሚል ይዘት ያለው አባታዊ ምክርም ሲያስተላልፉ አድምጫለሁµµ ያም ሆነ ይህ አገዛዙ ምክራቸውን ተቀበለም አልተቀበለ! ፕ/ ር በተለይ የትግራይ ህዝብ በነገዋ ኢትዮጵያ ህልውና ላይ አዎንታዊ አልያም አሉታዊ ሚና የመጫወት ምርጫው ከፊቱ መደቀኑን አበክረው ያሳሰቡበት ክፍል ወቅታዊና ታሪካዊ ማሳሰቢያ ነው እላለሁ። ውድ ፕ/ ር እድሜ ሰጥቶዎት የኢትዮጵያን ትንሣኤ ለማየት ያብቃዎት እያልኩ ወደ ሌላው ምልከታዬ ልዝለል። አቶ ያሬድ ጥበቡ ሆይ ! ለአቶ አዲሱ ለገሰ የሽግግር መንግስት ወንበር ሳይሆን የመቃብር ቦታ አፈላልግለት ! ሌላው የሰሞኑ ጉልህ ክስተት በይሆንም በዛሬው ምልከታዬ በጥቂቱም ቢሆን ልነካካው የወደድኩት አቶ ያሬድ “ጥበቡ ዶ/ ” ር ብርሀኑ ነጋ ወደ ዋሽንግተን ይመለስ በሚል ርዕስ ለንባብ ያቀረበውን ጽሁፍ ነው። አቶ ያሬድ ዶ/ ር ብርሃኑ ወደ ዋሽንግተን እንዲመለሱ ሲል ያቀረበውን ሃሳብ በምክንያት ሲያስረዳµ ከ 40 ዓመት በላይ ወደ ኋላ ተጉዞ ብርሃነ መስቀል ረዳ በኤርትራ በርሃ እያለ ድንገት በተቀሰቀሰው የየካቲት 66 አብዮት ሊጫወት የሚችለውን የመሪነት ሚና ሳይጫወት መቅረቱን አስታውሶ ፤ ይህ የብርሃነ መስቀል መጥፎ አጋጣሚ ዛሬ በኤርትራ ምድር በሚገኙት ዶክተር ብርሃኑም ላይ እንዳይደገምና ዶክተሩ እየተቀጣጠለ ባለው ህዝባዊ አመጽ ሊጫወቱ የሚችሉትን ጉልህ ሚና ሳይጫወቱ እንዳይቀሩ ስጋት እንዳደረበት ያስረዳል። አቶ ያሬድ ምጸት በሚመስል መልክ ታሪክ እራሱን እንዳይደግም በሚል ያቀረባቸው ሁለት የታሪክ አጋጣሚዎች የሚመሳሰሉት ሁለቱም የትግል መሪዎች ህዝባዊ እንቅስቃሴ በተቀጣጠለበት ወቅት ኤርትራ ምድር መገኘታቸው ነው። ይህ በርግጥም ተመሳሳይ አጋጥሚ ነው።ነገር ግን የብርሃነ መስቀል እጣ ፈንታ የዶክተር ብርሃኑም ሊሆን ይችላል የሚለው ስጋቱ ግን በሁለቱ ክስተቶች መካከል ያለውን የ 40 ዓመታት ልዩነት ያገናዘበ አይመስለኝም። ብርሃነ መስቀል በበቅሎ ጀርባም ይሁን በእግር ተጉዞ አሲንባ ለመድረስ የፈጀበትን ግዜ ያህል ዛሬ ዶክተር ብርሃኑ የትግሉ ማዕከል ወደ ሚሆነው የትኛውም ስፍራ ለመድረስ ይፈጅባቸዋል ተብሎ አይታሰብምና ነው። ዋናው ቁምነገር ደግሞ ከትግሉ ወላፈን በምን ያህል ርቀት ላይ እንደሚገኙ ከማናችንም በላይ ዶ/ ሩ የሚያውቁት ይመስለኛልና ይሄ ብዙ የሚያሳስብ አይመስለኝም። ያም ሆነ ይህ አቶ ያሬድ ይበጃል ያለውን መምከሩ ክፋት የለውምµµ ዶክተሩ በህዝባዊ እንቅስቃሴው ውስጥ ሊጫወቱ የሚችሉትን ጉልህ ሚና ያስረዳበትን ክፍል መሉ ለሙሉ እጋራዋለሁ። ይህች አጭር ምልከታ እንድሰነዝር ምክንያት የሆነኝ የአቶ ያሬድ ሃሳብ ግን የስካሁኑ አይደለም። “ ወጣ ወጣና እንደሸንበቆ ….. እንደ …. “ ያሰኘኝ፦ የወቅቱን ህዝባዊ እንቅስቃሴ የሚመራ፤ ከሁሉም የፖለቲካና የብሄር ድርጅቶች የተውጣጣ አንድ ቡድን እንዲቋቋም ምክር የሰጠበት ክፍል ነው። አቶ ያሬድ ይህንኑ የአመራር ቡድን ሲያዋቅር፦ ከግንቦት ሰባት እነ ዶ/ ር በርሃኑ ፤ ከኦሮሞ አክቲቪስቶች እነ ጅዋርንና እነ በቀለ ገርባ …… አለ አለና በአሁኑ ወቅት የአማራውን ብሄር በመወከል የሚንቀሳቀሱት ወጣቶች ብዙም ስላልበሰሉ ( ልጆች ስለሆኑ) አዲሱ ለገሰን ማካተቱ ይጠቅማል ብሎ እርፍ።
ይህን ካነበብኩ በኋላ አቶ ያሬድ የቆመበትን ቦታ ማወቅ አቃተኝ። ስለ ብአዴን ያለው አመለካከት ከጓደኝነት ስሜት ያልዘለለ ሆነብኝ። ወጣቶቹን አልበሰሉም ለማለት የደፈረ ሰው እራሱ….? ስል ጠየቅኩ። ደግሞ ወዲያው፤ አባባሉ ምናልባት ወያኔን በመከፋፈልና በማስደንገጥ ረገድ ጥቂትም የስትራተጂ ጠቀሜታ ይኖራት ይሆን ብዬ “አሰብኩ ። በምንም ይሁን በምን ሊዋጥልኝ አልቻለም።ደግሞስ በምን መለኪያ ነው የቮሊቦል መምህሩ አዲሱ” ለገሰ አሁን ለአማራ መብት መከበር ከሚንቀሳቀሱት የተማሩ ወጣቶች የተሻለ የሚሆነው? ራሴን ጠየቅኩ በመጨረሻም ለአቶ ያሬድ አልኩ፦ አቶ ያሬድ ሆይ! አዲሱ ለገሰ በነገዋ ኢትዮጵያ ላይ ሚና እንዲኖረው ወንበር ከምታፈላልግለት ይልቅ ከወያኔ መቃብር ግርጌ የመቃብር ቦታ ብትይዝለት ይሻላል። በመቃብሩ ላይ ቆሞ አማራን ያልጠቀመው ሞቶም የማይጎዳው የቮሊቦል መምህሩ አዲሱ ለገሰ ይህ ነበር የሚል የግንባር ጽሁፍ እንዲያርፍ እኔም ምክሬን ላንተ እለግስሃለሁ። ( ይህን ስል ህዝባዊ ትግሉን በህቡ የሚያግዙ የብአዴን አባላት ሊኖሩ አይችሉም ከሚል እሳቤ እንዳልሆነ ይታወቅልኝ! አዲሱ ለገሰ ግን ከብአዴን ለህወሃት ይቀርባል) ለዛሬው በዚሁ ላብቃ በቅርቡ በዚህ ጽሁፍ ያልተካተቱ ሰሞነኛ ክስተቶችን በምዳሥበትና ከዚህ ወዴት? በሚለው ጥያቄ ላይ የታየኝ በምገልጽበት ( እንደ ሁለተኛ ክፍል) ሊወሰድ በሚችል ሌላ ጽሁፍ እስክንገናኝ ሰላም ሁኑልኝ! የኢትዮጵያ ትንሣኤ ቅርብ ነው።

አዜብ ጌታቸውazebgeta@gmail.com

በዝዋይ እስር ቤት በደረሰ ቃጠሎ 11 እስረኞች ሞቱ –በአዲስ አበባ ዊንጌት እና ኮልፌ ፍተሻው ተጠናክሯል

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በዝዋይ ባቱ እስርቤት ትናንት በደረሰ ቃጠሎ የ11 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰማ:: የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት በቂሊንጦ ሆን ብሎ እሳት በማስነሳት ከ49 በላይ እስረኞችን ከገደለ በኋላ በዝዋይ ባቱ እስር ቤት በተነሳ እሳት ቃጠሎ የ11 እስረኞች ሕይወት ማለፉ ታውቋል::

Zehabesha-News.jpg

እንደ አስተያየት ሰጪዎች ገለጻ በዝዋይ እስር ቤት የተነሳውም እሳት ሆን ተብሎ በትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት የተከናወነና ተፈላጊ እስረኞችን ለመግደል ሆን ተብሎ የተደረገ ሴራ ነው ሲሉ ይናገራሉ::

በዚሁ የ እሳት ቃጠሎ ከ300 በላይ የሚሆኑ እስረኞች ከ እሳቱ ማምለጣቸው ተዘግቧል::

በሌላ በኩል በአዲስ አበባ ዊንጌት አካባቢ ከፍተኛ ፍተሻ እንዳለ ታወቀ:: የአዲስ አበባ የዘ-ሐበሻ የዜና ምንጮች እንዳስታወቁት ፍተሻው መንግድ ላይ መኪኖችን እና እግረኞችን በማስቆም ምሽቱን ቀጥሏል::

በሌላ በኩል ኮልፌ ፈጥኖ ደራሽ በሕወሓት ወታደሮች መከበቧ ተዘገበ:: እንደ ዘ-ሐበሻ ምንጮች ገለጻ በኮልፌ ከባድ መሳሪያ የያዙ ወታደሮች አካባቢውን ከበው ሕዝቡን እያስጨነቁት ይገኛሉ::

50 የሚሆኑ ዐማሮች በአፋር ክልል ፖሊስ ተገደሉ፤

$
0
0

ሙሉቀን ተስፋው

በአፋኙ የወያኔ መንግሥት ትምህርታቸውን 10ኛ ክፍል በላይ እንዳይቀጥሉ የተፈረደባቸው የዐማራ ወጣቶች ዛሬ ደግሞ በአፋር ፖሊስ በጥይት ተጨፍጭፈው መገደላቸውን ከወልዲያ ሆስፒታል ያገኘነው መረጃ ያረጋግጣል።
ነገሩ የሆነው እንዲህ ነው፤ በአገራቸው ባይተዋር የሆኑት ከተለያዩ የወሎ አካባቢዎች የተሰባሰቡት ወጣቶች ለስደት ወደ ሰው አገር ተነሱ። 200 የሚሆኑ ወጣቶች በኮንቴነር እንደ እቃ ታሽገው በሚሌ በኩል አልፈው ወደ ጅቡቲ ብሎም ወደ አረብ አገር ለማቅናት ነበር እቅዳቸው። በልጅነት ከትምህርት ገበታቸው የተባረሩት እነዚህ ወጣቶች በአገር ላይ ተስፋ ቢያጡ ነበር እንዲህ ለስደት መውጣታቸው።
ነገር ግን ሕልማቸው አልተሳካም፤ የሌላ አገር ድንበርም አላቋረጡም። የአፋር ፖሊስ በዐማራ ፖሊስ የታጨቀውን ኮንቴነር በጥይት በዳደሰው። የመኪናውን ጎማም እንዲሁ። 200 ዐማራ ወጣቶችን የያዘው ኮንቴነር ተገለበጠ። ያልፍልኛል ብለው የወጡት ወጣቶች ፈቅ ሳይሉ ሕይወታቸውን አጡ። 50 የሚሆኑት ወዲያውኑ ሲሞቱ ከ100 በላይ ደግሞ በከፍተኛ አደጋ በወልዲያ ሆስፒታል ውስጥ ይገኛሉ።
በሆስፒታሉ ከፍተኛ የሆነ የደም እጥረት እንዳለም ሰምተናል፤ የወልዲያ ወጣቶች ደም በመለገስ ወንድሞቻችን ትታደጉልን ዘንድ ጥሪ እናቀርባለን//
ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እንመኛለን!!
Zehabesha-News.jpg

ይኽ ትግል ዳር ሳይደርስ ወደ ኋላ አይመለስም፦ (መስቀሉ አየለ ዘብሔረ ደሴ መድኀኔዓለም)

$
0
0

ብዙ ስዎች የተጀመረውን ህዝባዊ ተጋድሎ የምጥ መጨረሻ እንዲሆናላቸው አጥብቀው ይመኛሉ። ትግሉ በአግባቡ ተይዞ ለውጤት እንዲበቃ በጥፍራቸው ጭምሮ ቆመው መጸልዩን ተያይዘውታል። ስጋታቸው ግን ከምን እንደ መነጨ ግልጽ ነው። የዚህን መጻጉ ቡድን ባህሪ ከመረዳት ነው። ድንገት እንደ ምርጫ ዘጠና ሰባት የከሸፈ እንደሆነ የበቀል ሰይፉን አንችለውም ከሚል ስር የሰደደ ስጋት ነው። አንድ ነገር ግን እርግጠኛ መሆን ይቻላል። ዘንዶው አከርካሪውን ተሰብሮዋል። አይድንም።
ይኽ ክፉ ደዌ በምንም መልኩ እራሱን በራሱ ሊፈውስና ይኽንን ህዝባዊ አብዮት የሚቋቋምበት ምንም አይነት ቁምና ሊኖረው አይችልም ብለን ደረታችንን ነፍተን እንድንናገር የሚያስችለን ቀመር ደግሞ በጣም ግልጽና ቀጥተኛ ነው። ነጥቡም አንድ እና አንድ ነው። ሁኔታዎች መሪን ይፈጥራሉ እንጅ መሪዎች ሁኔታዎችን አይፈጥሩም ከሚል ቀመር ተነስተን ነው። ይኽ በምንም መልኩ የማይለወጥ የሶሻል ዳይናሚክስ ህግ ነው።

fist-hand-smashing-the-ground-vector-1329559

መሪዎች ሁኔታን ይፈጥራሉ ማለት ምን ማለት ይሆን፧

ያልታየ ያልተሰማን ነገር ካለመኖር ዎደ መኖር አምጥተው በህዝቡ ላይ ሊጭኑ እንዲሁም አዲስ ማንነት ሊፈሩጥሩ ይሞክራሉ ማለት ነው።ነገር ግን ያኔ የአንዲት አገር የመከራ ደዎል ጅማሮ ይሆናል ማለት ነው። መጨረሻውም እንዲህ እንዳሁኑ የሁለት ዘመን ትውልድ ሙሉ ጨልጦ የጋገረ ያልተቋጨ የአብዮት አዙሪት (ቪቺኦኡስ ችይችለ) ውስጥ መውደቅ ነው። በተማሪዎች ንቅናቄም የሆነው እንዲሁ ነበር።ይህ አገር ከምን ዓይነት ድርና ማግ እንደተሰራ ምንም የማያውቁ ገራገርና ልጅ እግር ተማሪዎች ከቀደመው ትውልድ ምንም አይነት የተጋድሎ ታሪክ እርሾ ሳይወስዱ በዘመኑ በነፈሰው የምስራቅ አይዲዎሎጅ (ማርኂስም) ተነድተው ሰከሩ። ከኦሪት ጋር በተቆራኘ በግዕዝ ቋንቋ በሚያስብ ህዝብ ላይ ኮሚኒዝምን እናውጅ ብለው ተነሱ። አለማመን ማለት ምን ማለት እንደሆነ መዝገበ ቃላቱ በማይታወቅበት አገር ውስጥ ዕእግዚአብሔር የለምዕ አሉት። ታሪኩን ከንግስተ ሳባ እየቆጠረ በማንነቱ ሲኮራና ለማንነቱ ሲዋደቅ በኖረ ህዝብ ላይ ዕታሪክ የሚባል ነገር የለም፤ እንደውም ማርክስ እንዳለው የሰው ልጅ ታሪክ ሁሉ የመደብ ትግል ታሪክ እንጅ አክሱም ታሪክ የዛግዌ ታሪክ ወዘተ ብሎ ነገር የለምዕ ብለውት አረፉት። ወድቃ በተነሳችው ባንዲራዬ፤ በኀይለ ሥላሴ አምላክ ብሎ ቃሉን ለሚሰጥ ህዝብ ዕንጉስ ብሎ ነገር የለም፣ ከእንግዲህስ አገሩ የወዛደር አርማውም ማጭድና መዶሻ ነውዕ ተባብለው ተከፋፈሉ። አዲሱ ማንነታችን ብለው የወሰዱት ፤ ቦልሸቪክ ፣ ሜንሸቪክ ትሮጽካያት ለሌላው ግን የሚገባ ነገር አልነበረም። ዕፋኖ ተሰማራ እንደ ቸኮቬራዕ የሚለው የወቅቱ መፈክር ለነፍጠኛው ባዕድ ቢሆን አይገርምም።

ይሄ ሁሉ በግዜው ጥቂት ኮሌጅ ቀመስ ተማሪዎች ካልሆነ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ በህዝቡ ዘንድ ያልነበረ፣ የማይታወቅ፣ የማይገባ ባዕድ አስተሳሰብ ነበረና አንድ ትውልድ አስጨርሶ እንደ ህወሃት፣ ኦነግ መሰል ተውሳክ ፈጥሮ አገሪቱም ሆነች ህዝባችን ዛሬ ለደረችበት ውርደት ትልቁን የመከራ በር ከፍቶ አለፈ። በመግቢያየ ላይ እንዳልኩት በሌለ ነባራዊ ሁኔታ ላይ የሚነሳ አብዮት ለምን ሳይጸነስ እንደሚጨነግፍና ይልቁንም ምን ያህል አደገኛም ጭምር እንደሆነ የተነሳበትን ሳያሳካ የትም ባክኖ የቀረው ያ ትውልድ እና አብዮቱ ትልቅ ምስክር ነው።

ሁኔታዎች መሪን ይፈጥራሉ ስንል ግን ምን ማለታችን ነው፧

በዚህ በጣም መሰረታዊ በሆነ ጭብጥ እንዲህ አይነት ድምዳሜ ላይ ለመድረስ ይኽን ሁለት ትውልድ ጨልጦ የጋገረ፣ የማናመልጠው እና ያፈጠጠው እውነት አገሪቱን ሁለት መቶ አምሳ ዓመታት ወደኋላ በመመለስ ወደ ዘመነ መሳፍንት አፋፍ ላይ እየገፋ ያለ አደገኛ ክስተት መሆኑን በ አይናችን በብሌኑ እያየነው ያለ እውነታ ነው።። ራስ ስሁለ ሚካኤል የተባለው የትግሬ ገዥ በ፩፯ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ በእንግድነት ጎንደር ቤተመንግስት ውስጥ ባደረበት ሌሊት ንጉሱን ከተኙበት አፍኖ በመግደሉ የተነሳ ኢትዮጵያ መቶ አመት ወደፈጀ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ መግባቷ ይታወቃል። ሁሌም ነገሮችን በተናቁ ሰዎች አድሮ መስራት የባህሪው የሆነው አምላከ ኢትዮጵያ የኮሶ ሻጯን ልጅ ቋረኛውን ካሳ እንደ ነቢይ በማስነሳት ታደጋት እንጅ። ከአህመድ ግራኝ ወረራና የኦሮሞዎች ወደ መሃል ኢትዮጵያ መስፋፋት የተነሳ ክፉኛ የተሰባበረው የአገሪቱ ቁመና ከደረሰበት ቁስል ገና ባልጠገገበት ሁኔታእንደ ገና መቶ አመት ወደፈጀ የእርስ በርስ ጦርነት በመግባቷ የተነሳ በህዝቡ ላይ የደረሰውን የመከራ ጥልቀት መስፈሪያ ቋት ማግኘት አይቻልም። እንግዲ እንዲህ አይነቱ ነባራዊ ሁኔታ የፈጠረው ክፉ ቀን ነበር የዚህን ህዝብ የመከራ ግማደ መስቀል የሚሸከም መንገድ መሪ ሲጣራ አጼ ቴዎድሮስን ያህል አጥቢያ ኮከብ ያገኘው።አዎ፤ ጀግና በክፉ ቀን ይወለዳል ማለት ይኸው ነው።

ዛሬ የተጀመረው ጸረ ወያኔ ትንቅንቅ ወደ ኋላ አይመለስም ስንል ምን ማለታችን ነው።

በበታችነትና በድህነት ሰቀቀን ውስጥ የሚሰቅዩና ታሪካቸውና ዘራቸው ሁሉ ከባንዳና ከከሃዲዎች የትግራይ ገዥ ጉጅሌዎች የወረሱት ጀሌዎች ደደቢት በሚባል ዋሻ ውስጥ ተፈልፍለው ለአቅመ ጥፋት በደረሱ ግዜ ብዙ አለም አቀፋዊ ሁኔታዎች አሲረው የዚህች ታሪካዊት አገርና የዚህ መከረኛ ህዝብ እጣ ፋንታ እጃቸው ላይ ገባላቸው። አገሪቱ በነርሱ ወርድና ቁመና አልተሰራችምና በልካቸው አሰፍተው ለመልበስና የበቀል ሰቀቀናቸውን ለመወጣት ያስችላቸው ዘንድ አገሪቱን ከፋፍለው መግዛት ጀመሩ። በተሰባበረ መስተዋት ውስጥ እንዴት የአገሪቱን ሙሉ ካርታ ማየት እንደሚቻል ጥራዝ ነጠቁ መለስ ዜናዊ በእፉኝት ምላሱ መስበክ ጀመረ። ሞትንለት የሚሉት ህገ መንግስት የአገሪቱ ብሔራዊ ቋንቋ አማርኛ ነው እያለ ነገር ግን በብዙ የአገሪቱ ክፍል በዚህ ቋንቋ መጠቀም ብሄራዊ ወንጀል ተደርጎ ተወሰደ። አንድነት ጠፍቶ ብሄርተኝነት በይፋ ተጸነሰ። ትውልዱ ከተከለለበት አጥር አሻግሮ እንዳይመለከት ተፈረደበት። ሙሶለኒ የጀመረውን አገር የማፍረስ ተልእኮ በሹምባሾቹ ልጆች ህልው መሆን ጀመረ። ይህ ድንቁርናን ከጥላቻ የቀላቀለ ፖሊሲ ሲነድፉት መድረሻ ግቡ ከፋፍለህ ግዛ መሆኑ ግልጥ ነበር። ያም ሆኖ ያኔ እንዳያዩት ድንቁርና ጥቁር ሰማይ ሆኖ የከለላቸው ነገር ግን ዛሬ አፍንጫቸው ስር መንቀልቀል የጀመረው እሳተ ጋሞራ አንድነት ጠፍቶ ብሄርኝነት ሲያንሰራራ አደጋው በማን እንደሚከፋ ነበር። በግድ የፈጠሩት የአማራና የኦሮሞ ብሄርተኝነት ዛሬ ሊደበቅ የማይችል ሱናሜ ሆኖ መጥቶዋል። ዘጠና አምስት በመቶ የሆኑትን የአገሪቱን ዜጎች ወደ ለየለት ባርነት አውርዶ እንደ ባዶ ፊኛ በተወጠረ የትግራይ ተጋሩ የበላይነት እንዲሁ እየገደሉ እና እንደፈለጉ እየዘረፉ መኖር እንደማይቻል ይኽ ዓመት ምስክር ሆኖ መጣ።
ከላይ በመግቢያየ ያነሳሁትና የከሸፈው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ መሪዎችን ደርግ የተባለ የአብዮት ጠባቂዎች ስብስብ እያወጣ ሲያርዳቸው በግል ያልተነካው የህብረተሰብ ክፍል ቀርቶ የገዛ ቤተሰቦቻቸው ትንፍሽ ለማለት የቸገራቸው ልጆቻቸው ይዘው የመጡት አይዲዎሎጅ ከህብረተሰቡ ውስጥ ያልበቀለ እንግዳ ነገር መሆኑም ጭምር ነው። ስለዚህ የነበረው ግብግብ በታጠቀው የወታደሩ ክፍል እና ፊደል በቆጠሩት ተማሪዎች እንጅ ሌላውን ባለማካተቱ የትም ሳይደርስ ክሬም የሆነውን የወጣት ክፍል ጨርሶ ከበላ ቦሃላ በክሽፈት ተጠናቛል።

ዛሬ ግን ሌላ ቀን ነው። ትግሉ ከውጭ መጥቶ የተጫነ አይደለም ስንል ዝም ብለን አይደለም። ለሁለት አስርተ ዓመታት ያህል በጥላቻ፣ በዘረኝነት እና በሰይፍ እንገዛለን ብለው ከጫኑት የአገዛዝ ቀንበር የተወለደ ብሶት መሆኑ ነው። የኛ ከሚሏቸው ሰሜነኞች ውጭ የዚህ ግፍ ሰለባ ያልሆነ የለም። ስደት ሁለተኛ ተፈጥሯችን ሆኖ የወጣበት በተጻራራሪው ደግሞ ትግሬ መሆን ፕሮፌሽን ሆኖ የያንበት እውነት ነው። ዛሬ ሰርቶ ተምሮ ሰው መሆን አይደለም ዋልድባ ገብቶ እራስን በረሃብ ለመቅጣት የነርሱ ፈቃደንነት የሚጠየቅበት አገር ባለቤቶች ሆንን። የግፉ ጥግ በዚህ መልኩ ሰፍቶ ልጆቿ ገና በጽንስ ላይ እያሉ ለሽያጭ በሚቀርቡባት አገር ውስጥ ሞልቶ የፈሰሰ ግፍ ቀን ቆጥሮ መጣ። ማእበል ሆኖ መጣ። እንደ ተማሪው ዘመን ንቅናቄ የጥቂት ተማሪዎች ጉዳይ መሆኑ ቀርቶ ከህጻን እስከ ሽማግሌ፤ ከከተማ እስከ ገጠር፣ ከአለማዊ እስከ ገዳማውያን ሁሉም ለግዳይ ወጥቶ ያረፈውን ይህን አስፈሪ ማእበል ወያኔ የሚባል የድኩማን ስብስብ ያቆመው ዘንድ እንዴት ይቻለዋል ፧።።እንዴትም። እምቢ ማንነቴ ብሎ ፈንድቶ የወጣውን የወልቃይት ንቅናቄ ከአርባ ዓመት የመከራ ጉዞ ለጸሃይ ብርሃን ካበቁትና ከአብራኩ ከተወለዱት አንዱ ደመቀ ዘውዴን ለወያኔ የስለት ቢላ አሳልፎ ላለመስጠት እየተከፈለ ያለው መስዋዕትነት እና በዚህ ደረጃ ለስርዓቱ ፈተና እስከመሆን የደረሰበት ዋናው ምክንያት የወልቃይት አጀንዳ ማለት ከውጭ የተጫነ ሳይሆን የወልቃይት የቁጭት ማህጸን የፈጠረውና መሪውም ከዚሁ ሁኔታ የተወለደ መሆኑ ነው።ቀይ ሽብርን ያየ በእሳት አይጫዎትም ብሎ መንገድ መሪ ሽማግሌና ጸልዮ ምህረት የሚያወርድ መንፈሳዊ አበው ቸግሮት ከጸጋ በታች ወርዶና ወና ቤት ተቀምጦ የተገኘው ህዝባችን በቀን ጎደሎ የትግራይ አካይስቶች እጅ በወደቀበት፣ ቤተመቅደሱ ተዋርዶበትና ዘመራ ዘውዱ ተሰርቆበት ተስፋ በቆረጠበት ሰዓት የተጫነውን መርገምት ይገፍ ዘንድ ገባሬ ሰናዩ ከጭንጫ ላይ ያስነሳለት አንዳርጋቸው ጽጌ፣ አርበኛው ብርሃኑ ነጋ፣ ዲባቶ ታደሰ ብሩ፣ አርበኛ ግርማቸው (ታጋይ ዜና ጉታ) ወዘተ የመሳሰሉትን የዚህ ዘመን ፈርጦች ሁሉ የተፈጠሩት ክእንዲህ አይነት ድቅድቅ ጨለማ ነው። በርግጥም በአስራዎቹ እድሜያቸው የያ ትውልድ አካል ሆነው በኢህአፓ ስር ትግሉን የተቀላቀሉትና የከሸፈውን አብዮት የመሩት አንዳርጋቸው ጽጌ እና ዲባቶ ብርሃኑ ነጋ በለጋ ማንነታቸው ኢትዮጵያን ለመቅረጽ ጀምረው የትም እንዳልደረሱ ሁሉ ዛሬ ግን ከአራት አስርተ አመታት ቦሃላ ያልተቁዋጨውን የአቢዮት ምዕራፍ ለመዝጋት በረሃ ወርደው ዘገር ሲነቀንቁ ግን ከያንነው ማንነታቸው በሁሉም ዘርፍ በሚባል መልኩ የተለዩና ከምንም በላይ ግን አሁን ካለው ተጨባጭ የአገሪቱ ሁኔታ የተወለደ አዲስ ማንነት ይዘው መሆኑ የሚገርም የታሪክ እንቆቅልሽ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ድሉንም አይቀሬ ያደገዋል።እንግዲህ ሁኔታ መሪን ይፈጥራል ስንል ይኼው ነው።

ሁኔታወች መሪን ሲፈጥሩ በሚቀጣጠል አብዮት ፊት ደግሞ ወያኔ የተባለ መጻጉ ቀርቶ ማንም ምድራዊ ሃይል ይቆም ዘንድ አይቻለውም። ፸ በመቶ የሚሆነው ህዝባችን በጣም ወጣት የሚባል በመሆኑ አገራችን ይህንን ጋንግሪን የሆነ የትግራይ ገዥ ጉጅሌ ጠራርጎ ሊሄድ የሚችል ምን ያህል የብሄርተኝነት አቅም እንደተገነባ ደምሮ ማስላት ለቻለ ማንም ሰው ይኽ አብዮት የበላውን በልቶ ዳር ከመድረስ የሚያቆመው ምንም አይነት ሃይል እንደሌለ ቅንጣት ታህል ጥርጣሬ ሊኖረው አይችልም። ስለሆነም ማንም የዢህችን አገር ትንሳኤ በአይነ ህሊናው ሲናፍቅ የኖረ ሰው በፍጻሜው ዋዜማ ላይ መቆሙን ልብ ይበል። ባይሆን ጥያቄው በምን ያህል ዋጋ ይሄዳሉ የሚለው ብቻ ማሰቡ ሳይሻል አይቀርም። መርገምቶቹ መቶ ሚሊዮን ሰው አርዶ ለመሄድ የሚያስችል በቂ ጭካኔ አለቸውና።

አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ:- የወያኔ ሰራዊት ቀኝ ሁዋላ ወደ ደደቢት

$
0
0

አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ:- የወያኔ ሰራዊት ቀኝ ሁዋላ ወደ ደደቢት ታሪኩ አባዳማ መስከረም 2009 ህወሀት ተልዕኮው በከፊል ሰምሯል ፤ ለብሔር ብሔረሰቦች መብት እስከ መገንጠል ቆሜያለሁ ብሎ ነበር ፣ ዲሞክረሲ ሳይሽራረፍ አረጋግጣለሁ ፣ ሰብአዊ መብት አሰፍናለሁ ብሎ ነበር ፣ ያለፍርድ አንድም ዜጋ ህይወቱን ቀርቶ መታሰር አይደርስበትም ብሎ ነበር ፣ … ከጎረቤት አገሮች ጋር በማይናወጥ ሰላም እንኖራለን ብሎም ነበር ከፖለቲካ ስርአት ምህዳር እና ሰማይ በታች ሁሉንም በጎ ነገሮች በኔ አገዛዝ ስር ትጎናፀፋላችሁ ሲል ቃል ገብቶ ነበር። ቃሉን በሰነድ ላይ አስፍሮ ህገ መንግስት አድርጎ – እሰከዚህ ድረስ ተጉዞ ነበር። … ራዕዩ ቃል ፣ ቃሉም ሰነድ ሆኖ ነበር በቃ ፣ ከዚያ ማለፍ አልቻለም። ሰነዱ ሳይነበብ ብል በላው ፣ ምስጥ መዘመዘው ፣ አረም … ዋጠው። ቃሉ ስጋ ወ ደም ሳይዋሀድ ጨነገፈ በመጨረሻም እነሆ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ። የተባባሰ ግድያ አዋጅ ፣ የላቀ ጅምላ መብት ጥሰት አዋጅ ፣ የጫካ አዋጅ ፣ የአራዊት አዋጅ ፣ የደደቢት አዋጅ አወጀ። ህወሀት ከሀያ አምስት አመታት የግፍ አገዛዝ በሁዋላ ቀኝ ሁዋላ ወደ ደደቢት አለ ፤ ጫካውን ናፈቀ። ተጠያቂነት እና ግልፅነት የማያውቀው የደደቢት ፖለቲካ ህይወት እጅጉን ናፈቀው። መጀመሪያ ያኔ ወደ ደደቢት ሲጓዝ የህዝብ ብሶት ሰንቆ ለጋ ወጣት ሳለ የተመኘውን ሊከውን ነበር – ይብዛም ይነስ ብሩህ አይምሮ ፣ ያልተልከሰከሰ መንፈስ እና ምኞት ነበረው። አሁን ወደ ደደቢት ለመጓዝ የተነሳው ደግሞ በህዝብ ልጆች ደም የጨቀየ እጆቹን ፣ በሙስና የበከተ ህሊናውን ፣ በውሸት እና ቅጥፈት የተባ ምላሱን አንዘላዝሎ ፣ ታሪክ ይቅር የማይለው ፣ ትውልድ አሳፋሪ ታሪኩን አንግቦ ነው። ህወሀት ቀኝ ሁዋላ ወደ ደደቢት አለ – አስቸኳይ ጊዜ አወጀ። ገድለው በህግ የማይጠየቁበት ፣ ዘርፈው የማይጠግቡበት ፣ ባሻቸው ውለው የሚያድሩበት ደደቢት ናፈቀው። ወንድም ወንድሙን ገድሎ የሚፎክርበት ፣ ሀውልት የሚገትርበት ፤ ድልድይ አፍርሶ ፣ ባንክ ዘርፎ ፣ ድሀ አስለቅሶ እለት ጉርሱን ሳይቀር ቀምቶ ወደሚያድርበት ደደቢት ቀኝ ሁዋላ ዙር አለ – አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ። ህወሀት እንደገና ኢትዮጵያ ለምኔ አለ ፣ ኢትዮጵያዊ ገድሎ ፣ ክብሯን አዋርዶ ፣ ባንዲራዋን እንደ ጨርቅ በሶ እየቋጠረ ወደማይጠየቅበት ደደቢት ፊቱን አዞረ። ትናንት በቃሉ መሰረት የሰጣቸውን ሰነድ የተማመኑ ፣ ተማምነውም መብታቸውን የጠየቁ አሸባሪ ተብለው አደባባይ በጥይት እሩምታ ታጨዱ ፣ በየወህኒው ታጎሩ ፣ ተሰደዱ። ያልተሸራረፈው ዲሞክረሲ ቀርቶ መሰረታዊ እና ተፈጥሯዊ መብታችን ይከበር ያሉ በወንጀል ተከሰው ወህኒ ተወረወሩ። በታጎሩበት ወህኒ እሳት ነደደባቸው። እሱም አልበቃ ብሎ ዛሬ ለሌላ ጅምላ ፍጅት አዋጅ ታወጀባቸው – አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ።

Demonstrators chant slogans while flashing the Oromo protest gesture during Irreecha, the thanksgiving festival of the Oromo people, in Bishoftu town, Oromia region, Ethiopia, October 2, 2016. REUTERS/Tiksa Negeri - RTSQF70

Demonstrators chant slogans while flashing the Oromo protest gesture during Irreecha, the thanksgiving festival of the Oromo people, in Bishoftu town, Oromia region, Ethiopia, October 2, 2016. REUTERS/Tiksa Negeri – RTSQF70

ህወሀት ትግራይን ነፃ ለማውጣት ተልሞ ድፍን ኢትዮጵያን ተቆጣጥሯል – ህዝቧን በከፋፍለህ ግዛ መርህ በጎጥ ሸንሽኖ አንድነቷን አናግቷል። አንድነቱ በተናጋ እና በተከፋፈለ ህዝብ ትከሻ ላይ ተደላድሎ እጅግ መጠነ ሰፊ የሆነ ሀብት መዝብሮ ቢጠሩት የማይሰማ ቱጃር ሆኗል። በጎጥ የከፋፈለውን ህዝብ በወረፋ አንዱን ዛሬ ሌላውን ነገ እየነጠለ ሲገድል ፣ ወህኒ ሲያግዝ ፣ ለስደት ሲዳርግ ፣ ንብረት ሲቀማ ሀያ አምስት አመታት አስቆጥሯል። ግን ዛሬ ህዝብ በቃ አለ – አለም ይህን ጅምላ ፍጅት መርምሮ ተጠያቂውን ለፍርድ ማቅረብ ግድ ይላል ሲል ሰምቶ ህወሀት ደነበረ ፣ ፊቱን ወደ ደደቢት አዞረ። አንዳችም ተጠያቂነት ወይንም ግልፅነት ወደሌለበት ወደ ደደቢት አለም ለመጓዝ ተጣደፈ። ኢትዮጵያን በታትኜ ፣ እንደ ሩዋንዳ የዘር ፍጅት አቀጣጥዬ ደደቢት ገባለሁ አለ። ይህም አይሆንም ሲል ህዝብ አንድነቱን አጥብቆ ከዳር እስከ ዳር ተሰለፈ – ህወሀት ግን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ – ደደቢትን ከነ አተላው እግታችሁዋለሁ አለ፤ ህዝብን ምን ያህል እንደ ናቀ ለማሳየት አዋጅ አወጀ። የአንዲት አገር ልጆችን በጎጥ ሸንሽኖ ፣ በክልል በረት አጉሮ እንኳ መግዛት ተሳነው። የትግራይን ሪፐብሊክ ለማወጅ የረቀቀው ሰነድ ከተቀበረት ዋሻ አቧራው ተራግፎ ወደ አደባባይ ብቅ እያለ ነው። ወያኔ/ ህወሀት‘ በብረት አስገብረን ፣ ደም አፍሰን ፣ እንደ ገል ቀጥቅጠን እንደ ብረት አቅልጠን መግዛት ካልቻልን እናንተን በታትነን እኛ ’ ሪፐብሊካችንን እናውጃለን በሚል እየተጋበዘ ቆይቷል። ህዝቡ አንተ እንደፍጥርጥርህ ለእኛ ግን አንድነታችን ፣ ሰብአዊ መብታችን ዋስትናችን ነው በሚል ፅኑ ተቃውሞ ማድረጉን ቀጠለ። ህወሀት ደደቢት ላይ ሲያደርግ እንደ ነበረው ጭፍን ጥላቻን በህዝብ ለመርጨት ሲል ሀውልት እስከ ማቆም ደረሰ። ህዝብ ግን ህወሀት ሰራሽ የሆነ አንዳችም ነገር እንደማይበጀው ይፋ አደረገ። Down down woyane እያለ መልካው እስኪናጋ ድረስ አስተጋባ። ህወሀት ግን ፊቱን ወደ ደደቢት አዞረ ፣ ተጠያቂነት ፣ ግልፅነት የሌለበትን ስርአት ናፈቀ – አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ። አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ይፋ ሆኗል – የደደቢት ስርዓት በመላው አገር በይፋ ይረጋገጣል ብለዋል። ከቶውንም ህግ ባልነበረበት አገር ፣ ስርአት ባልተጠበቀበት ምድር አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚያመጣው ምን አዲስ ነገር አለ? እስከ ዛሬ እንደ ጅረት ስላፈሰሱት ደም ፤ እስከ ዛሬ ከአፅመ ርስቱ ስላፈናቀሉት ዜጋ ፤ እስከ ዛሬ ህልውናውን ፣ ስብእናውን ክደው ስላዋረዱት ህዝብ ጉዳይ መልስ እየጠየቅን እንጂ መቸ ሌላ ዙር ፍጅት ጠየቅን። ሳይውል ሳያድር ለጥያቄአችን መልስ እንፈልጋለን። እስከ ደደቢት ድረስ እናንተን የምንሸኝበት አቅም ፣ ዝግጅትም ሆነ ፍላጎት የለንም ፤ አስቸኳይ ጊዜ አዋጃችሁን የምንሸከምበት ዕዳ ፣ በዚያም የምንገዛበት ትከሻ የለንም። ደደቢትን ወደ እኛ እንዳመጣችሁ ሁሉ መልሳችሁ እንድትረከቡ ህዝብ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይጮሀል። Down down woyane ይላል።


የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ወይስ በህዝብ ላይ የተከፈተ ጦርነት? በሳዲቅ አህመድ

$
0
0

አገሪቷ ዉስጥ የተቀጣጠለዉን የለዉጥ ፍፍላጎት ማዳፈን የተሳነዉ በህወሃት የሚመራዉ መንግስት ድንገተኛ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ማዉጣቱዜጎችን ለመግደልና ለማሰር የጀመረዉ ህጋዊ ሽፋን ነዉ በማለት የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እያስረዱ ነዉ። ለ25አመታት አገሪቱ በእጅ አዙርየአስችኳይ ግዜ አዋጅ ስር እንደነበረች የሚያስረዱት የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች አዋጁ የህዝብን እልቂትና ጉዳት የሚያባብስ በመሆኑ ህወሃት መራሹ መንግስት ለገባበት አጣብቂኝ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ነዉ የሚሆንበት በማለት አስተያየት የሚሰጡ ብዙ ናቸዉ።

14589942_909239355878894_2147367832247698469_o
የአስቸካይ ግዜ አዋጁን ለህዝብ ለማሳወቅ ወደ ቴለቭዥን መስመር ብቅ ያሉት የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለ ማሪያም ደሳለኝ በመደበኛ መንገድ አገሪቱ ዉስጥ የተነሳዉን ሁከት ለማስታገስ ስላልተቻለ የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን ማዉጣቱ አስፈላጊ እንደሆነ ተናግረዋል።የመንግስታቸውን ችግር በጉልህ ያላነሱት ሐይለማሪያም ደሳለኝ ለሁከቱ መንስኤ ያሏቸዉን በዉጭ ጠላቶቻችን የሚደገፉ ጸረሰላም ሐይሎች ከሁከቱ ጀርባ አሉ ሲሉ ወንጅለዋል። ሁከቱ አይሎ በብሔር ብሔረሰቦች መካከል፣በሐይማኖቶች መካከልና በአማኒያን መካከል ግጭትን አስነስቷል በማለት በመግለጫቸዉ ላይ አሳዉቀዋል።
ሐይለማሪያም ደሳለኝ ህዝቡ ከህወሃት መራሹ መንግስት ነጻ በሆነችዋ አገር የመኖር መብቱን ለማስከበር ለሚያደርገዉ ትግል በንግግራቸዉ ዉስጥ ዋጋ ሲሰጡት አልተስተዋሉም። በለመደዉ የኢህአዴጋዊ አገላለጽ “ህዝቡ አገሪቷ ዉስጥ የተነሳዉን ሁከት እንድናስቆም እርምጃ እንድንወስድ ጠይቆናል” በማለት የፈጠራ መልእክት ማስተላለፋቸዉ አስተችቷቸዋል።ህወሃት መራሹ መንግስት ያወጣዉን ህገ መንግስት በተገቢዉ መልኩ ባለመተግበሩ የህዝብ አብዮት መነሳቱን ለመናገር ያልደፈሩት ጠቅላይ ሚኒስቴር ህገ መንግስታዊ ስርዓቱ ሳይናጋ ይቀጥላል ብለዉ ሲናገሩ ተደምጠዋል።
የዉጭ ዜጎችን ከጥቃት ለመከላከል፣ የአገርና የዉጢ ኢንቨስተሮች ሀብት በመቃጠሉ፣የመንግስት ተቋማት ጸረ ሰላም ባሏቸዉ ሐይሎች እየጋዩ በመሆናቸዉ በአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ገደብ የሚጣልባቸዉ እንቅስቃሴዎች እንደሚኖሩአሳዉቀዋል። መሰል ችግሮች ሲከሰቱ የአገሪቱ ህግመንግስት ላይ በአንቀጽ 93 የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ እንዲታወጅ መደንገጉን የገለጹት ሐይለማሪያም ደሳለኝ፤ በህገ መንግስቱ ድንጋጌ መሰረት የሰብዓዊ መብት አይጣስም፤ በቬና ስምምነት መሰረት የሰፈሩት የዲፕሎማሲያዊ መብቶች ይከበራሉ፤ በማለት ቃል ገብተዋል። ሆኖም 25 አመት በሙሉ ዜጎችን በአንድ ለአምስት የስለላ መዋቅር ስር አርጎ፣እያሰረ፣እየገረፈ፣ሰዎች ካገር እንዲሰደዱ እያደረገ፣የጅምላ ግድያእየፈጸመ፣የአገር ንብረትን እየዘረፈ፣የመጽፍና የመናገር መብትን እየከለከለ አገሪቷን ሳይታወጅ በሚተገበር የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ መቀመቅ ዉስጥ የከተተዉ ህወሃት መራሹ መንግስት አሁን ንጹሗን ዜጎች ላይ አሳቃቂ ግድያን ለማድረግ፣ የሚጠረጥራቸዉን በሙሉ ለማፈንና ለማሰር ግልጽ ጦርነት አዉጇል የሚል ክስ ከተለያየ አቅጣጫ እየደረሰበት ነዉ።
ሐይለማሪያም ደሳለኝ የፖለቲካ ስርዓቱ እየታደሰ መሆኑን ገልጸዋል። የፖለቲካ ስርዓቱ እድሳትም በተሃድሶ እንደሚጠናከር አሳዉቀዋል። ሐያ አምስት አመት በሙሉ ኢትዮጵያን የመራዉ ህወሃታዊዉ ኢህአዴግ እድሳት እንጂ ለዉጥ የሚባል የወል ጥያቄ እንድማያሻዉ እገረመንገዳቸዉን የገለጹ አስመስሎባቸዋል። የመንግስት አሰራር መታደስ ማለት በዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ የሚታዩ ስተቶችን ማረም መሆኑን አመላክተዋል።ይህንን እርማት ተግባራዊ ለማድረግም ከሲቪክ፣ከሙያና ከኪነጥበብ ማህበራት ጋር ዉይይት እንደሚደረግ ገልጸዋል።መንግስታቸዉ ባለፈዉ ሳምንት በኢሪቻ በአል ወቅት በአንድቀን ብቻ 678 ሰዎችን ስለመግደሉ በመግለጫዉ ወቅት አልተናገሩም። ህዝቡ ላለፉት አምስት አመታት በየእምነት ተቋሙ፣በባእላት ቀን፣ባደባባይ፣በየትምርት ተቋሙ የሚያሰማዉን የለዉጥ እሮሮን ጠቅላይ ሚኒስተእሩ ጆሮ ዳባ ልበስ ያሉ አስመስሎባቸዋል።
የፖለቲካዉ ምህዳር ማስፋት አስፈላጊ መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለ ማርያም ደሳለኝ፤ የመድብለ ፓርቲ ዲሞክራሲ እንደሚያሻ ጠቆም አድርገዋል።እንደ አገላለጻቸዉ መድብለ ፓርቲ በተለያዩ ተለጣፊ የፖለቲካ ፓርቲዎች የታጀበዉ ኢህአዴግ ባለበት መልኩ ይቀጥላል የሚሉ ይመስላል።አገር ዉስጥ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር መወያየት እንደሚያሻ አሳዉቀዋል።”አገር ዉስጥ ካሉ የፖለቲካፓርቲዎች ጋር” ሲሉ ተቃዋሚና ደጋፊ የሚለዉን ነጥለዉ ባለማስቀመጣቸዉ መል እክታቸዉ አደናጋሪ ነበር። የፖለቲካ ምህዳር ማስፋት በሚለዉ ሐሳብ ላይ በዉጭ ያሉ ተቃዋሚ ድርጅቶችን፣ በሰላማዊና በትጥቅ ትግል የሚታገሉ ቡድኖችን በንግግራቸዉ ላይ ባለማካተታቸዉ ኢህአዴግ በህዝባዊ አብዮት እንጂ እራሱን ሊለዉጥ የማይችል ነዉ የሚለዉን ያንዳንድ የፖለቲካ ድርጅቶች አቋም የበለጠ አጠናክረዉታል።ኢህአዴግ በጥልቀት እንደሚታደስ ሐይለማሪያም ደሳለኝ ገልጸዋል።
ለመስተካከል ደግሞ ሰላምና መረጋጋት ያሻል ብለዋል። ሰላምና መረጋጋቱን ለማምጣት የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ አስፈላጊነትን እንደ ማመካኛ አቅርበዋል። ጠቅላይ ሚኒስቴሩ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅን አስፈጻሚዉ ልዩ ግበረሐይል (command pos) በርሳቸዉ እንደሚመራም ምጸት በሚመስል መልኩ አሳዉቀዋል።ህወሃት ሙሉ በሙሉ በሚቆጣጠረዉ መንግስት ዉስጥ ድምጻቸዉ የለሆሳስ እንደሆነ የሚታወቁት የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር፤ እርሳቸዉ የማይቆጣጠሩት የአጋዚ ጦር ህዝብን በህጋዊ መንገድ ለመጨፍጨፍ የሚያስችለውን አዋጅ ሲያወጣ፤ እርሳቸዉ የአዋጁ አስፈሳሚ መሆናቸዉን በቴሌቭዝን ላይ ወጥተዉ መናገራቸዉ፤ የህዝብን የማወቅና የማገናዘብ ችሎታ ያጣጣለ ነው። ሁናቴዉ እርሳቸዉ የስርዓቱ መገልገያ አሻንጉሊት መሆናቸዉን የበለጠ አመላካች ነዉ የሚል ሐሳብ ሲሰጥበት ተስተዉሏል።ጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለማሪያም ደሳለኝ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ወጣ ብለዉ ህዝቡን ቢሽነግሉም፤ ህዝቡ ነጻነትን እንጂ ሽንገላን እንደማይሻእየገለጸ ነዉ። በህጋዊ መንገድ ለመግደል አዋጅ ያወጀዉ ህወሃት ምንም ዘመናዊ የጦር መሳሪያን ቢታጠቅም፤ የነገይቱን ኢትዮጵያ ለመገንባት መስዋእትነት የሚከፍል በሚሊዮን የሚቆጠር ቆራጥ ህዝብ አለ የሚሉ ሐሳቦች ሲንሸራሽሸሩ እየታየ ነዉ።
አምባገነናዉያን ይሸነፋሉ እንንጂ ህዝብ አይሸነፍም የሚሉ የጋራ ድምጾችእየተሰሙ ነዉ። ሐያ አምስት አመት በሙሉ ህወሃት መራሹ መንግስት ሊጥለን ፣ሊደፈጥጠን ቢሞክርም እኛ አልወደቅንም። መንግስታትይወድቃሉ እንጂ ህዝብ አይወድቅም። በጫንቃችን ላይ የሻገተዉን ስርዓት ከጫንቃችን ላይ እናወርደዋለን የሚል ህዝባዊ የትግል መስተጻምር እየተስተዋለ ነዉ። ህወሃት መራሹ መንግስት አሁንም በአስራ አንደኛዉ ሰአት “በጠላቶቻችን የሚረዱ የጸረ ሰላም ሀይሎችን ለመታደግ” እያለ በማመካኘት ላይ ነዉ። የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ወይስ የጦርነት አዋጅ፧ በሒደት የሚታይ ይሆናል። ልብ ያለዉ ልብ ይበል።

ኢትዮጵያ ታማለች !!! –ከተማ ዋቅጅራ

$
0
0

ethiopia-3-satenaw-newsየታመመችው ኢትዮጵያ የምትባለዋ አገር ናት። አገር ከታመመ ደግሞ በውስጧ የሚኖሩ ልጆቿን ማቀፍ መንከባከብ አትችልም። ወገኔ ሆይ ኢትዮጵያ ታማለች የሰው ያለህ የወገን ያለህ ትላለች። ህመሟን የሚያስታምማት ደግፎ ቀና የሚያደርጋት ሰው ትፈልጋለች ህመሟን አስታሞ አክሞ የሚያድናት ህዝብ ትፈልጋለች። የት ናችሁ የኢትዮጵያ ወዳጆች ኸረ ወደት ናችሁ የሰው ያለህ እያለች ስትጣራ ተበታትነን ሁሉም በየፊናው በህመሟ የምንቀልድ በዛን። የወገን ያለህ ብላ ስትጣራ እኛም ሌላ ህመም ሆንባት ቀና አርጉኝ ስትል እንድትሞት እንጫናት ጀመር ተንከባከቡኝ ስትል እየገፋናት አታስፈልጊንም አልናት ለህመሜ የሚደርስ እና የደረሰልኝ ማን ነው ብላ ተኝታለች አስታሞኝ ለህመሜሜ ደርሶ የሚያድነኝ ማን ይሆን ብላ ትጣራለች። ወገኖቼ እውነት ኢትዮጵያ ታማላች።
አገር ስትታመም በውስጧ ያቀፈቻቸው ልጆቿ በታላቅ ስቃይ ይመታሉ ታላቅም መከራ ይደርስባቸዋል በውስጧ ያሉትን ሰብስባ መያዝ ስለማትችል ከጉያዋ ወጥተው ወደ በአድ አገር ይሰደዳሉ። ልጆቿን የመመለሱም ሆነ የመከልከሉ አቅም አይኖራትም ምክንያቱም ስለታመመች።
ከህመሟ ሊታደጋት ካጎነበሰችበት ቀና ሊያደርጋት ከተኛበት ሊያነሳት ብዙዎች ቢደክሙም ከህመሟ እንዳታገግም ካጎነበሰችበት ቀና እንዳትል ከተኛችበት እንዳትነቃ የሚተጉ የውስጥ እና የውጪ ጠላቶች እንዳሉ እሙን ነው።
አገር ስትታመም ጩኸት ይበረታል በውስጥም ጩኸት …ከአገርም ተሰዶም ጩኸት፣ በአገር ቤትም ለቅሶ… ተሰዶም ለቅሶ፣ በአገርም ሞት… ተሰዶም ሞት፣ በአገር ቤትም ውርደት… ተሰዶም ውርደት ይሆናል ምክንያቱም የሁላችንንም ጩኸት የምትሰማ የሁላችንንም እንባ የምታብስ የሁላችንንም ሞት የምትታደግ አገራችን ስለታመመች መከራችንን መሸፈን አትችልምና ነው።
በወለጋ፣ በጎንደር፣በሐረር፣በባህር ዳር፣ በአንቦ፣ በደብረማርቆስ፣ በሱልልታ፣ በወልቃይት፣ በአርሲ፣ በኮንሶ፣በባሌ፣ በአገው፣ በሰላሌ፣ ፣ በአንድ ላይ ሆነው ህዝባችን ተነስተው ድምጻቸውን ማስተጋባት ጀመሩ በደላቸውን መናገር ጀመሩ ህመማቸውን መግለጽ ጀመሩ ችግራቸውን ማስተጋባት ጀመሩ የተሰጣቸው ምላሽ ግን ጥይት፣ የተሰጣቸው መልስ ግን ድብደባ፣ የተሰጣቸው ምላሽ ግን እስራት ነው። ምክንያቱም አገር ስለታመመች።
ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምት፣ ሁመራ ለ25 አመት ከዛም በላይ በህዝባችን ላይ የዘር ማጥፋት እርምጃ ተወስዶብናል አሁን ግን ህዝባችን ላይ የሚወሰደው የዘር ማጥፋትም ሆነ ከመሬቱ የማፈላቀል ስራ እና ወንጀሎችን በዝምታ አናልፍም የተፈጸመብንን ግፍ እናጋልጣለን ብለው በተነሱበት ሰአት የተሰጣቸው መልስ ጥይት፣ ድብደባ፣ እስራት የማስፈራሪያ ዛቻ ነው። ምክንያቱም አገር ስለታመመች።
ይባስ ብሎ ጆሮን ጭው የሚያስብል ዜና ከወደ ደብረ ዘይት እና ከወደ ጋንቤላ ተሰምቷል። የደብረ ዘይቱ የኢሬቻን በአል በማክበር ላይ ባሉ ኢትዮጵያዊያን ለይ የተወሰደው ዘግናኝ ጭፍጨፋ ታሪክ የማይረሳው ነው። ከ670 ንጹሃን ዜጎቿን በወያኔ አጋዚ በመጨፍጨፋቸው ምክንያት በኢትዮጵያ ውስጥ ታላቅ ቁጣን በመቀስቀሱ ህዝቡ ወያኔን በመፋለም ላይ ይገኛል። ሌላው ደሞ ድንበር ጥሰው በመጡ የሱዳን ዜጎች አገር ሰላም ነው በሚኖሩ ዜጎች ላይ ከ280 በላይ ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ በጥይት ተደብድበው በአገራቸው ተገደሉ ህጻናት እና ሴቶች ታፍነው ተወሰዱ ሃብት ንብረታቸው ከውጪ በመጡ ታጣቂዎች ተዘረፉ ይሄ ሁሉ ዘግናኝ እና ውርደት የተሞላበት ድርጊት ሲደረግ ከመንግስት የሚሰጠው መልስ እጅግ ያሳፍራል ህዝቡን ለታላቅ በቀል ያነሳሳል በህዝባችን ሞት እና መከራ ላይ የሚያደርጉት ነገር በቁስል ላይ ጨው የመነስነስ ያህል ነው። ከአገር ቢሸሽም ሞትና ውርደት በአገር ቤትም ሞትና ውርደት መድረስ ከጀመረ ሰነባብቷል። ምክንያቱም አገረ ኢትዮጵያ ስለታመመች።
ኢትዮጵያን ህዝቦቿን ለማጥፋት ለሚሯሯጡ ቅጣቱን ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ለማዳን ለሚተጉ የአሸናፊነት ኃይሉን እንደሚጎናጸፉ እሙን ነው።
ሳጠቃልለው እግዚአብሔር በትላልቅ ጉባዬ እና በኃይላቸው በሚመኩ መሃል ተገልጦ አያውቅም በተናቁት እና እራሳቸውን ዝቅ ባደረጉት መሃል ነው ሃይሉን የሚገልጠው። ትልቁ ጎልያድ ለመጣል እረኛው እና ትንሹን ዳዊትን ነው የተመረጠው። እስራኤልን ከግብጽ ባርነት ነጻ ለማውጣት የመረጠው ባህር ላይ የተጣለው ኮልታፋው ሙሴን ነው። ሰማይና ምድርን በቃሉ የዘረጋው ክርስቶስ የተወለደው በቤተ መንግስት ሳይሆን በግርግም ነው። ቀድመውም መወለዱን ያዩት ነገስታቶች አልያም ባለስልጣኖች ሳይሆን የተናቁት እረኞች ናቸው። ዛሬም ኢትዮጵያ አገራችን ታማለች እንጂ አልሞተችም በአለም ደረጃ እና በግለሰቦች አመለካከት የተዋረደች እና የተናቀች ብትሆንም በእግዚአብሔር ዘንድ የተመረጠች እና የተወደደች አገር ናት። የወደዳት እና የመረጣት እግዚአብሔር ግዜው ሲደርስ ጠላቶቿን እንደ ዳዊት በጠጠር የምታሸንፍ አገር ናት። ስለ ኢትዮጵያ በእግዚአብሔር ዘንድ የተነገረው ትንቢቱ ሲፈጸም። የናቋት እና ያንቋሸሿት ሁሉ በእግዚአብሔር በትር ካልተመቱ እና ከቆዩ እያዩት ከአለም ሁሉ ከፍ ከፍ ስትል ይመለከታሉ። ያኔ ልጆቿን በእቅፏ ትሰበስባለች ያኔ የናቋትም ያንቋሸሿትም ከአሸናፊዎች ሁሉ በላይ ስትሆን ያፍራሉ። ይሄንን ሊቃወም አልያም ሊያሸንፍ የሚችል የትኛውም የምድር ሃይል የለም ምክንያቱም ከእግዚአብሔር ስለሆነ። ኢትዮጵያ ታማ እንጂ ሞታ አታውቅም። ከህመሟ ድና ልጆቿን የምትሰበስብበት ግዜ ቅርብ ነው።
እስከዛው ግን በህመሟ እና በልጆቿ ስቃይ የሚሳለቁ ይበዛሉ።
ከተማ ዋቅጅራ
11.10.2016
Email- waqjirak@yahoo.com

የወቅቱ ጥያቄ ራስን በወታደራዊ አቅም ማጎልበት ነው (ከአይናዲስ ተሰማ)

$
0
0

ethiopian-genocide-on-amharaአማሮች አማራ በመሆናቸው ብቻ በየአካባቢው እየተለቀሙ ሲሳደዱና ሲገደሉ አማራውን እወክለዋለሁ የሚለው ድርጅት ትንፍሽ አለማለቱን ሳስብ ዘወትር ይገርመኛል:: ለአማራው እልቂት መባባስ የብአዴን አመራሮች ምክንያት መሆናቸው ደግሞ ከግርምትም በላይ የሆነ ስሜት ይፈጥራል (አቶ ታምራት ላይኔ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ተገኝተው ያደረጉትን ንግግር ምሳሌ ማድረግ ይቻላል)::  ከሌሎች ጎሳወች ጋር ተዋልዶና ተመሳስሎ የሚኖረው አማራ በዘሩ ብቻ ሲባረርና ሲገደል የብአዴን አመራሮች የተባረሩት አማሮች ግብር ለመክፈል ያልፈለጉ አጭበርባሪወች እንደሆኑ ሲናገሩ ነበር (አቶ አዲሱ ለገሰ ከኦሮሚያ ክልል ሀብታቸውን ተነጥቀው ስለተባረሩት አማሮች የተናገሩትን በምሳሌነት ማንሳት ይቻላል):: ሕጻን ሽማግሌ ሳይል: በብዙ ሽህ የሚቆጠር አማራ: ለዘመናት ሲኖርበት ከነበረ አካባቢ አንዲት ነገር ሳያንጠለጥል እንዲባረር ሲደረግ: ለዚህ እወክለዋለሁ ለሚለው መከራ ተቀባይ ሕዝብ አቶ አዲሱ ሊሟገትለት ሲገባ “ወንጀል የፈጸመ ስለሆነ መባረሩ አግባብ ነው” የሚል እንድምታ ያለው ንግግር ማሰማቱ ከጉድም ጉድ ያሰኛል:: ወንጀል  የፈጸመ ሰው ሰብአዊ ክብሩ ሳይነካ በህግ አግባብ መጠየቅ እንደሚገባው በህገመንግስቱ ላይ በግልጽ ሰፍሯል:: እንደተባለው አማሮች ወንጀል ፈጽመው ተገኝተው እንኳ ቢሆን ህጉ ላይ በተቀመጠው መንገድ መጠየቅ እንጅ ለዚያ አይነት መከራ እንዲጋለጡ መፈቀድ አልነበረበትም:: በዚያ ላይ አማራው ራሱ ሲያፈናቅሉት ህመሙን በሆዱ ችሎ ሲፈናቀል: የግድያ ወንጀል ሲፈጽሙበትም ድምጹን አጥፍቶ ሞቱን ሲቀበል ማየት አላስችል ቢለኝ የዘመኑን ትውልድ ወቅሸ የሞቱት አርበኛ እናትና አባቶቻችንን ከሞት ልቀሰቅስ “ይድረስ ለነፍጠኞች” ስል የብሶት ግጥም ሞነጫጨርሁ::

 

ግጥሙ የግጥምን መሰረታዊ ባህሪያት የተከተለ ሊሆን እንደማይችል ይገባኛል:: እኔም ለዚያ አልተጨነቅሁም:: በመሰረቱ እኔ የስነጽሁፍም ሆነ የጋዜጠኝነት ትምህርት ወይም ሙያ ያለኝ ሰው አይደለሁም:: የእኔ ፍላጎት በምንም ይሁን በምን የውስጤን እሳት አውጥቶ መተንፈስ: ትውልዱን መጎንተል: መቀስቀስ ነበር:: የጫጫርሁትን ግጥም ለብዙወች ሜዲያወች የላክሁ ቢሆንም ማንም  ቀንጭቦና አስተካክሎ እንኳ መልእክቴን ሊያደርስልኝ የሚፈቅድ ባለመገኘቱ ሀሳቤ መና ቀረ:: ቆይቶ የመጣልኝ ሀሳብ በደብረማርቆስ: በጎንደር እና በወሎ ስም የተመሰረቱ የቡድን ፌስቡኮች (Group) አባል በመሆን ግጥሜን ፖስት ማድረግ ነበር:: ነገር ግን አንዳንድ ቡድኖች ፖስት ያደረግሁትን ግጥም ስላጠፉብኝ ተናድጀ ከሁሉም ቡድኖች ጋር የነበረኝን አባልነት ሰረዝሁ:: በእርግጥ ግጥሙ ቢሉት ቢሉት የማያልቅ: የግጥም አመሰራረት እና ውበት የሌለው በመሆኑ ሜዲያወች ባያወጡት እውነት አላቸው:: ከዚያ በኋላ ባሉት ጊዚያቶች ሌሎች ብዙ ግጥሞች እና አርቲክሎች ልኬ የነበረ ቢሆንም ለንባብ የበቁልኝ ግን በጣም ጥቂቱ ብቻ ናቸው:: አንዳንዶቹ ሜዲያወች ጭራሹኑ ተሳስተው አንድ ጊዜ እንኳ ሊቀበሉኝ አልፈቀዱም:: እንዳልሁት ባለሙያ አይደለሁም:: ነገር ግን ያነሳኋቸው ጭብጦች ጠብታ ቁም ነገር የሌላቸው ፍሬከርስኪ እንዳልነበሩ ይሰማኛል::

 

ጽሁፎቸ በሜዲያ ላይ ለንባብ ሊቀርቡ ያልቻሉት ከሁለት ነገሮች በአንዱ ወይም በሁለቱም ምክንንያት ሊሆን ይችላል ብየ አስባለሁ:: አንደኛው የስነጽሁፍ ለዛ እና ደረጃ ያልጠበቁ በመሆናቸው ሊሆን ይችላል:: ሌላው ደግሞ ድህረገጾች በሚፈልጓቸው መንገዶች ያልተቃኙ ወይም የማይፈልጓቸውን ነገሮች የነኩ በመሆናቸው ሊሆን ይችላል:: እንደ Zehabesha, EmF, Ethiopian review እና ቋጠሮ የመሳሰሉት ድረገጾች የሚያወጧቸውን ጽሁፎች ከራሴ ጽሁፎች ጋር ለማነጻጸር ብዙ ጊዜ ሞክሬአለሁ:: አንዳንድ ጊዜ እኔ ከጻፍሁት ያነሰ መልእክት ያላቸው: ሰዋሰዋዊ አጠቃቀማቸውም ሆነ ስነጽሁፋዊ ውበታቸው እዚህ ግባ የማይባሉ ጽሁፎች በነዚህ ድረገጾች ላይ ወጥተው ሳነብ ለምን የእኔስ? ብየ መጠየቄ አልቀረም:: የሆነው ሆኖ በራሴ ጥረት የደረስሁበት አንድ እውነት የሚመስል ነገር አግኝቻለሁ::

 

ሁሉም በነጻ ሜዲያ ስም የሚታወቁት የሬዲዮ: የቴሌቭዥን እና የህትመት ሜዲያወች ሊያወሩባቸው የሚፈልጓቸው እና እንዲነኩባቸው የማይፈልጓቸው ጉዳዮች እንዳሉ ለመረዳት ችያለሁ:: ተቃዋሚ መነካት የለበትም በሚል ምልከታ የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶችን በተናጠል ወይም በጅምላ ለመተቸት የሚነሳ ግለሰብ ወይም ድርጅት ላይ የህዝብን ትግል ለመግደል እንደተነሳ የወያኔ ተላላኪ አድርገው የሚወነጅሉና የጥቃት ኢላማ እንዲሆን የሚቀሰቅሱ ሀላፊነት የጎደላቸው ሜዲያወች መኖራቸው ሀቅ ነው:: አንዳንዶች የፈለገው የወረደ ጽሁፍ ቢቀርብም የቀረበው ጽሁፍ መንግስትን የሚቃወም እስከሆነ ድረስ ለመቀበል የማያመነቱ ናቸው:: ግንቦት 7ን የሚቃወም ጽሁፍ የሚወዱ ወይም የማይወዱ: ኢሕአፓ እንዲነቀፍ የሚፈልጉ ወይም የማይፈልጉ: ኦነግ በጥሩነቱ ብቻ እንዲነሳ የሚፈልጉ ወይም በመጥፎነቱ ብቻ እንዲነገርለት የሚፈልጉ –  –  – እንዳሉ ተረድቻለሁ:: ከሁለት ቀናት በፊት አቶ ይገርማል የሚባሉ ሰው ከመቶ አመት የቤት ስራወቻችን አንዱ የሆነው ኦነግ በሚል ያቀረቡት ጽሁፍ ቁምነገር ያለው መሆኑን ተረድቸ ወደ ፌስቡኬ ሸር ላደርግ ስል ከድረገጹ ላይ ላገኘው አልቻልሁም: ሰርዘውታል:: የመንግስት መገናኛ ብዙሀንን በአፋኝነት የሚከሱት ነጻ የሚባሉት ሜዲያወች የአቶ ይገርማልን ጽሁፍ ካወጡ በኋላ መልሰው መሰረዛቸው የተለያዩ ሀሳቦች እንዳይንሸራሸሩ እንቅፋት የሚፈጥሩ ማለትም ራሳቸውም አፋኝ መሆናቸውን ያሳያል::

 

ያም ሆነ ይህ ነፍጠኛ ማለት ከስድብ አልፎ የሚያሳፍር: የሚያስጠይቅ እና ለጥቃት የሚያጋልጥ መጠሪያ ተደርጎ ይታሰብበት በነበረበት ወቅት “ይድረስ ለነፍጠኞች” ብየ በፌስቡክ ላይ በማስነበቤ አሁን ላለው በነፍጠኛ አባት እናቶቻችን ታሪክ ለመኩራት እና ብሎም “አዎ ነፍጠኛ ነኝ” ብሎ ለመውጣቱ የራሴ የሆነ እገዛ አድርጌ ይሆን? ብየ አስብ እና ለህዝቤ ትንሽም ቢሆን በጎ ነገር አበርክቻለሁ በማለት ጮቤ እረግጣለሁ:: የአሁኑ የአማራ ወጣቶች በድፍረት አደባባይ ወጥተው መፋለም እንዲችሉ አንድ ምክንያት እንደሆንሁ: ብርታት እንደሰጠሁ አድርጌ አስብና በደስታ እሰክራለሁ:: የሞቱትን  እናትና አባቶቻችንን ቀስቅሸ “ይድረስ ለነፍጠኞች” የሚል ጥሪ በማድረጌ ሙት መንፈሶቻቸው ሰምተውኝ ህዝቡንና ሀገሩን ከጥቃት ለመከላከል ግንባሩን የማያጥፍ ወጣት ይኸው በአይኔ ለማየት በቃሁ::  ለዚህም ፈጣሪየን ከልብ እያመሰገንሁ የሞቱትን ወገኖቸን “ነፍስ ይማር! በሰላም እረፉ!” እላለሁ::

 

ኦነግ ለብዙ ኦነጎች የተከፈለ ቢሆንም ሁሉም ንዑስ ኦነጎች ዞረው ዞረው ያው የኦሮሞን ነጻነት ማለት መገንጠልን የሚደግፉ መሆናቸው የአደባባይ ሚስጥር ነው:: አንዳንዶቹ አሁንም በዚያው  በዱሮው የመገንጠል አቋማቸው ጸንተው የኦሮሚያ ሪፓብሊክን ለመመስረት የሚያልሙ ናቸው:: አንዳንዶቹ ደግሞ ኦሮሞው በኢኮኖሚው: በፖለቲካውም ሆነ በስልጣን እንደህዝቡ ብዛት ተመጣጣኝ ድርሻ እንዲሰጠው እና ራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር ለማስቻል የሚታገሉ እንደሆኑ ሲያስመስሉ ይቆዩና ተመልሰው ያንኑ የመገንጠል ጥያቄያቸውን ሲያራግቡ ይገኛሉ:: እነጃዋር የተናገሩት የሽግግር መንግስት እና የመከላከያ ሀይል ምስረታ አላማ የሚነሳው ከዚህ የመገንጠል ፍላጎት ነው:: ጃዋር እና አንድ ፕሮፌሰር BBN ከተባለ ሬዲዮ ጣቢያ ጋር ያደረጉትን ቃለመጠይቅ ተከታትያለሁ:: በዚህ ቃለመጠይቅ ላይ የተገነዘብሁት ነገር ቢኖር “ምንም ልታመጡ አትችሉም” የሚል ድብቅ መልእክት ያለው በሽፍንፍን የቀረበ ሊቀር የማይችል የኦሮሚያ ነጻ መንግሥት ምስረታ ፍላጎት መኖሩን ነው:: ማንም ደገፈውም አልደገፈውም ለውጡ አይቀርም ብሎናል ጃዋር:: የሽግግር መንግስት ስለሚል ነገር አልሰማሁም ብለውናል ፕሮፌሰሩ:: ሌላ አንድ ዶ/ ር ደግሞ እናውቅላችኋለን አትበሉን ብለውናል:: የሚያደርጉት ነገር ከሌሎች ወገኖች ጋር በሚናበብ መልኩ ሳይሆን እነርሱ በሚፈቅዱት መንገድ እንደሚሆን ነው እየነገሩን ያሉት:: በጋራ ግዴታ መታሰር እንደማይፈቅዱ ነው ሊያስገነዝቡን የፈለጉት::

 

የአማራ ልጆች ምን ዝግጅት እያደረጉ እንደሆነ አላውቅም:: አቅራሪ “እዚያ ማዶ ሆኖ ክፉ ሰው ተጣራ እዚህ ማዶ ሆኖ ክፉ ሰው ወይ አለው ጎበዝ ተጠንቀቁ ይህ ነገር ለኛ ነው” ያለው ካለ ነገር አይደለም:: ኦነጎች የኦሮሞ ካርታ አላቸው:: እኔም  የአማራን ካርታ አውጥቸ በልቤ ይዣለሁ:: ሞረሽ: ቤተአማራ: ዳግማዊ  መዐህድ: የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሀይልና ሌሎችም ሳያስቡበት አይቀርም ብየ አስባለሁ::

 

ለነገሩ ኦነግን ያተበተው ተቃዋሚ የአንድነት ሀይል የሚባለው ነው:: የኦሮሞ ህዝብ አሁንም ቢሆን ከአማራው ወንድሙ ጎን ተሰልፎ እንደዱሮው ሁሉ ኢትዮጵያን ለመከላከል ወደኋላ የሚል አይደለም:: ለኢትዮጵያ ሲሉ ያላቸውን ነገር ሁሉ አሳልፈው የሰጡ ወላጆቻቸውን አርማ አንስተው ለአንድነቷና ለሉአላዊነቷ የሚሰለፉ ኦሮሞወች ከኦነግ ጀሌወች በእጅጉ የበለጡ መሆኑ እየታወቀ የአንድነት ኃይል ነኝ የሚለው ወገን ህዝቡን ማእከል አድርጎ መስራት ሲገባው ኦነግን ወደመለማመጥ በመውረዱ የ50 አመት ጩጬው ኦነግ ሲገለማምጠን: በትእቢት ሲወራጭብን እያየን እየሰማን ነው:: ኦነግን በሰላ አንደበት እና በበሰለ ጽሁፍ የሚተቹትን አስተዋይ ሰዎች የሚያረክሱ የኦነግ ተከታዮች ሊመጣ የሚችለውን አስከፊ ውጤት አስቀድመው ማየት የተሳናቸው ናቸው:: ኦነግ አደብ ገዝቶ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ተሰልፎ ወያኔን ለማስወገድ እና ከወያኔ ውድቀት በኋላም የጋራ የሽግግር መንግስት እንዲመሰርት የሚመክሩትን ሁሉ እያበሻቀጡ እንደሆነ ከሚቀርቡ አስተያየቶች እየተረዳን ነው::

 

ስለመጭው የምንጨነቅ እኛ ብቻ ልንሆን እንደማይገባ ሁሉም እንዲገነዘበው ያስፈልጋል:: እስካሁን የጮህነው ጩኸት ከፍርሀት የመነጨ ሳይሆን ከማስተዋል የመነጨ እንደሆነ ማንም ሊረዳው ይገባል:: ስለዚህ ድንገት አስቸጋሪ ሁኔታ ቢከሰት መደነጋገር እንዳይፈጠር ሲባል አማራው ተጠንቅቆ መጠበቅና ራሱን መከላከል ይኖርበታል ብለን ስለምናምን የተጠናከረ ወታደራዊ ኃይል ማቋቋም እና የምንሞትለት ካርታ ማውጣት ግድ ይለናል:: ይህን ስል መአት ነገር እንደምባል አይጠፋኝም:: የአማራን እና የኦሮሞን አንድነት ለማደናቀፍ እንደተነሳሁ የሚያስቡ የዋሆች ሊኖሩ ይችላሉ:: የወያኔን ዕድሜ ለማስረዘም ቆርጨ የተነሳሁ አድርገው የሚወነጅሉኝ አይጠፉም:: ማንም ያለውን ይበል መሆን ያለበት ግን ይኸው ነው::  አማሮች ወገኖቸ ስጋቴ ይገባቸዋል:: እንደ እስስት የሚለዋወጡ ቡድኖችን አምኖ እጅና እግርን አጣጥፎ ተዘናግቶ መቀመጥ አግባብ አይሆንም:: ይነስም ይብዛም ኦነግ እና ወያኔ የረጅም ጊዜ ፖለቲካዊና ወታደራዊ እውቀትና አደረጃጀት አላቸው:: ሁለቱንም የሚያስተሳስራቸውና የሚያስማማቸው ደግሞ አማራ ጠላት ነው የሚለው አመለካከታቸው ነው:: እኛ ወታደራዊ ኃይል እናቋቁማለን ስንል ምንም ያላጠፉትን አማራ ያልሆኑ ወገኖቻችንን ለመደብደብ አይደለም:: እንዲህ አይነት ትምህርት ከወላጆቻችን አልተማርንም:: በንጹሀን ላይ ግፍ ለመፈጸም የሚያስችል በክፋት የተበከለ ህሊና ኖሮን አያውቅም: ወደፊትም ሊኖረን አይችልም:: ነገር ግን ጠላቶቻችን ናቸሁ የሚሉን: ሞትና ስደታችንን የሚመኙ ቡድኖች እንዳሉ እናውቃለን:: የኢትዮጵያ አንድነት በአንድ ወገን ፍላጎት ብቻ የሚመጣ አይደለም:: ሁሉም ቡድኖች ወደስምምነት መጥተው የጋራ ሀገራችንን ዴሞክራሲያዊት ለማድረግ ፍላጎቱ ካለ የመጀመሪያው ምርጫችን ይሆናል:: ካለበለዚያ ግን ራሳችንን ለመከላከል የሚያስችል አቅም ሊኖረን ግድ ነው::

 

ፈረንጆች might is right የሚሉት አባባል አላቸው:: በአለም ላይ ያለው እውነታም የሚያሳየው ይህንኑ ነው:: ጉልበት ያለው ሰው ማድረግ የሚፈልገውን የማድረግ ያልተጻፈ መብት አለው:: ለምሳሌ አሜሪካ ፓናማን ወርራ የፓናማን ፕሬዚደንት በምርኮ ወስዳ ስታስር ለምን ብሎ የጠየቃት አልነበረም:: የኢራቅን መንግስት የኒዩክሊየር ሀይል በማቋቋም ወንጅላ በአመራሯ ስር የተባበሩት መንግስታትን ጦር አሰልፋ ኢራቅን በሀይል ወርራ ፕሬዚደንት ሳዳም ሁሴንን ይዛ በሞት ስትቀጣ ልክ አይደለም ብሎ የሞገታት:  ከርምጃዋ እንድትቆጠብ ያደረገ አልነበረም:: ኢራቅ እየገነባች ነው ሲባል የነበረው የኒዩክሊየር ጣቢያ ሀሰት ሆኖ ሲገኝ ደፍሮ የወቀሳት እስካሁን በኢራቅ ውስጥ እየታየ ላለው ሁከትና ለሀገሪቱ ውድመት ምክንያት ነሽ ብሎ የጠየቃት የለም:: ብዙ ሽህ ኪሎሜትር ተጉዛ በቬትናም ሕዝብ ላይ ጦርነት ከፍታ ከአንድ ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ስትገድል ማንንም ሳትፈራ ነው:: የአሁኑን እስላማዊ አክራሪ ኃይል መሰረት የሆነውን ታሊባን የተባለውን የአሸባሪ ድርጅት በአፍጋኒስታን ስትመሰርት አይሆንም ብሎ ያስቆማት አልነበረም:: በሊቢያ: በሶሪያ: በየመን በሶማሊያ – – –  ላይ ቦንብ እያዘነበች ሕዝብ ስትጨፈጭፍና ንብረት ስታወድም ትክክል ነበረች:: ሌላው ቀርቶ የኛዋ ኢትዮጵያ እንኳ በአቅሟ አልሸባብ ዝቶብኛል ብላ ጦር ሰብቃ ሶማሊያ የገባችው ጉልበት አለኝ ከሚል እብሪት በመነሳት ነው:: ለዚያም ነው Might is right! የሚባለው:: ጉልበት ካለህ ትፈራለህ: ትከበራለህ:: ድሀ ብትሆንም ምንም ማለት አይደለም:: ያለው ካለው ፈቅዶም ይሁን ፈርቶ ያካፍልሀል:: ራስህ የፈለከውን ያህል ተምነህ ብትወስድም ጠያቂ የለህም:: አቅም የሌለህ ደካማ ከሆንህ ግን እጣ ፈንታህ የሚወሰነው በአንተ አይሆንም::ራስን በወታደራዊ አቅም ብቁ አድርጎ መገኘት ሁልጊዜም አስፈላጊ ነው:: ለሕዝባቸው ከሚያስቡት ነፍስ ያላቸው የብአዴን አባላት ጋር በተጠና መንገድ ግንኙነት መፍጠር ይጠቅማል:: ያ ካልሆነ ግን እንደባለፈው ጊዜ ሁሉ ትንሹም ትልቁም እየተነሳ የሚያሳድደንና የሚገድለን መሆናችን አይቀርም::

 

አማራ መሆን እንደወንጀል ተቆጥሮ በተለያዩ ክልሎች በግፍ የተገደሉት ወገኖቸ ከሞታቸው በላይ ነፍስ ከስጋቸው እስክትለይ ድረስ ያዩትን ስቃይ ማስታውስ አንጀትን እሳት ውስጥ እንደወደቀ ላስቲክ በሀዘን ጭምትርትር ያደርጋል:: እያዩ እየሰሙ በእሳት የተቃጠሉት ወገኖቸን ስቃይ ሳስብ የምሆነውን አጣለሁ:: ሳያውቅ በተዳፈነ እሳት ላይ ለአፍታ እግሩን ያሳረፈ ወይም የፈላ ውሀ ተደፍቶበት በዚያች ትንሿ የአፍታ ቃጠሎ የተንሰፈሰፈ ሰው ከነነፍሱ በእሳት እንዲቃጠል የተደረገ ሰብአዊ ፍጡር ነፍሱ እስክታልፍ ድረስ ሊሰማው የሚችለውን ስቃይ ሊያስብ ይከብደዋል:: እንደእኔ በድህነት በባዶ እግሩ እየሄደ ያደገ ሰው እንቅፋት ሲመታው የተሰማውን ጥዝጣዜ ሲያስታውስ ወገኖቻችን በገጀራ ተገዝግዘው ሲታረዱ ያሳለፉትን ስቃይ ለማሰላሰል አቅሙ አይኖረውም:: የራሳቸው ቤት እና ኑሮ የነበራቸው ቤት ያፈራውን ለተቸገረ ሲመጸውቱ የነበሩት ወገኖቸ የነበራቸውን ተነጥቀው ሲባረሩ የሚሰማቸውን ግራ መጋባትና ተስፋ ማጣት ማሰብ አንጀትን በሀዘን ያላውሳል:: ታያላችሁ አይደል አሁን እየሆነ ያለውን? እየተካሄደ ባለው የህዝብ አመጽ የትግራይ ሰዎች ተጎጅ ሊሆኑ ይችላሉ በሚል ጥርጣሬ እነርሱን ከአመጹ አካባቢ ለማሸሽ እስከ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ የደረሰ ጥንቃቄ ተደርጓል:: የእኛ ወገኖች በየጉራንጉሩ ሲታረዱና ሲሳደዱ ማን ደረሰላቸው? ከእንግዲህ በኋላ ይህ አይነት ሁኔታ እንዲፈጸም መፍቀድ የለብንም:: ራሳችንን መከላከል ከማንችልበት ደረጃ ላይ ከተገኘን በክልሉ የሚኖረውን ሕዝባችንን ሳይቀር አባረው ከኦሮሚያ እየተፈናቀሉ ያሉትን ትግሬወች ሊያሰፍሩበትም ይችላሉ:: ህልውናችንን እና መብታችንን ለማረጋገጥ ነው የመከላከያ ኃይል የሚያስፈልገን:: አሁን የምንገኘው በሽግግር ዋዜማ ላይ ነው:: እንዲህ አይነት ጊዜ ደግሞ ፈታኝ ነው:: የቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ ንጉሳዊ የአስተዳደር ስርአት ሲፈርስ በተለያዩ አካባቢወች የሚኖሩ አማሮች ላይ ጥቃት እንደተፈጸመ ከታሪክ እናስታውሳለን:: ሌላው ቀርቶ በወላይታ ሶዶ ይኖሩ የነበሩት አማሮች ላይ ምን እንደደረሰባቸው የሚያውቅ ያውቀዋል:: ደርግ ሲወድቅ የተፈጠረውንስ የማያውቅ ይኖር ይሆን?

ለእኛ ያለነው እኛው ነን!

 ዞኖች ተቀላቀሉ፤ ቀበሌዎች ተጨናነቁ  –ማስተዋል በለጠ (ከአዲስ አበባ)

$
0
0

 

“ሰላም ባይኖርም ሰላም ልበላችሁ” ይላል ያ ኪሩቤል በቀለ የተባለ ወዳጄ፤ እናም ‹ሰላም ለኩልክሙ› ብዬ ዘመነ ዲቁናየን በእግረ መንገድ ላስታውስ፡፡

ሰሞኑን ቀበሌዎች በሰው ብዛት እየተጥለቀለቁ እንደሆነ በቅርብ የማውቃቸው ነግረውኛል፡፡ ቀበሌዎቹ በሰው የሚጨናነቁባቸው ብቸኛ ምክንያትም ትግሬ ወያኔዎች መታወቂያቸው ላይ ያለውን ብሔር ከትግሬነት ወደ ኦሮሞነትና አማራነት ለመለወጥ ነው ተብሏል፡፡

 

Demonstrators chant slogans while flashing the Oromo protest gesture during Irreecha, the thanksgiving festival of the Oromo people, in Bishoftu town, Oromia region, Ethiopia, October 2, 2016. REUTERS/Tiksa Negeri

Demonstrators chant slogans while flashing the Oromo protest gesture during Irreecha, the thanksgiving festival of the Oromo people, in Bishoftu town, Oromia region, Ethiopia, October 2, 2016. REUTERS/Tiksa Negeri

አንድ ከቀበሌ መጣሁ ያለኝ የማይዋሸኝ ትልቅ ሰው – ትልቅ ፈጣሪ ብቻ መሆኑ በታሳቢነት ተይዞልኝ – እንደነገረኝ ከሆነ እጅግ በርካታ ትግሬዎች በሰሞኑ የኦሮሚያና የዐማራ ግርግር ከመደናገጣቸው የተነሣ መታወቂያቸውን ወደሌሎች ዘውጎች እየቀየሩ ነው፡፡ በዚህ የመታወቂያ ለውጥ ሰበብ የአዲስ አበባ ቀበሌና ወረዳ ጽ/ቤቶች ቅጥረ ግቢ ጠጠር ቢወረወር ማረፊያ የለውም ይባላል፡፡

“ፊቱን ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ…” ይባላል፡፡ ቀና ቀናውን ደጋግሞ ማሰብ ቀድሞ ነው፡፡ አንድ ነገር ከሆነ በኋላ መሯሯጥ ብዙም አይጠቅምም፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ መረን የለቀቀ ጠባይን በጊዜው ማረምና ማስተካከል ይገባ ነበር፡፡ በፊት “እዩኝ እዩኝ” ከማለትና ኋላ ላይ አሁን እየታዬ እንዳለው “ደብቁኝ ደብቁኝ” ከማለት አስቀድሞውኑ በትክክለኛ አቅጣጫ መጓዝ ይቻልና ይገባም ነበር፡፡ አሁን በጣም የመሸ ይመስለኛል፡፡ ለ25 ዓመታት እላዩ ላይ ሲጨማለቁበት የከረመ ሕዝብ አሁን ሲብስበትና ሞትና ስደቱ፣ ስቃይና እንግልቱ ሲበዛበት የመከራና የስቃይ ምንጮቹን ሀብትና ንብረት ማቃጠል ይቅርና እነሱ ራሳቸውንም በዘነዘና አናት አናታቸውን ቢጨፈልቃቸው አይፈረድበትም – የደረሰበት ግፍ ወደር የለውምና፡፡ ሕዝቡ ተናግሯል፤”በምታምኑት ይሁንባችሁ ማሩን፣ ድሃም ሆነን በቀያችን እንድንኖር ፍቀዱልን፣ ሀብትና ንብረታችንን ግዴለም ውሰዱት – በሕይወት የመኖር መብታችንን ግን እባካችሁ አክብሩልን” እያለ ግማሽ ምዕተ ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ ፈሪና ቦቅቧቋ ተብሎ እስኪሰደብና መሣቂያ መሣለቂያ እስኪሆን ድረስ ተንበርክኮ ወያኔ ትግሬዎችን ለምኗል፤ አስለምኗልም – ስለዚህም በዚህ በአሁን እርምጃው “አይዞህ፤ በርታና ግፋበት! ለነዚህ የሲዖል ትል ወያኔዎችና ደጋፊዎቻቸው ይህም ሲያንሳቸው ነው!” ብሎ ሊያደፋፍር የሚቃጣ ወገን አይኑር እንጂ “ለምን እንዲህ አደረግህ” ብሎ ማንም ሕዝቡን ሊወቅሰው አይገባም፤ እንኳንስ በጨዋ ደንብ እየመረጠ ለሚያወድመው የመዥገሮች ንብረት ከዚህ በላይ ቢሄድም የግፈኞቹ ጥጋብ ያስከተለው መርገምት ስለሆነ ማንም በሕዝ መፍረድ አይችልም – ጎርጉረህ ጎርጉረህ ለምታወጣው ግማት ተጠያቂው አንተ ራስህ እንጂ ሌላ ወገን አይሆንም – በምን ዕዳው? በጊዜው ሰሚ አጣን እንጂ እኛም ብዙ ጩኸናል፡፡ አንጎላቸውን ሞራ የሸፈነባቸው ጥጋበኛ ወንድሞቻችን ይሠሩትን አጥተው ሕዝብና ሀገር ላይ ያን ያህል የበደልና የግፍ ደለል ሲከምሩ መቆየታቸው ምን ሊያስከትል እንደሚችል ለነሱ ቢሰወር ለኛ ግልጽ ነበር – ማንኛውም ጨለማ ሌሊት ሳይነጋ እንደማይቀር የማወቅን ያህል ቁልጭ ብሎ የሚታይ ሃቅ ነበርና፡፡

አሁንም የግፍ ብድሩ መከፈል ተጀመረ እንጂ አላለቀምና እግዜሩ በቀላሉ ይማረን፡፡ ደግሞም አንድ አይደለም 30 ዐዋጅ ቢያውጁ ከላይ የታዘዘን መቅሰፍት ሊያስወግዱት አይችሉም – ብቸኛው የመዳኛ መንገድ የሕዝብን ጥያቄ በአግባቡ መመለስና እውነተኛ ድርድር ማድረግ ነው – ከወያኔ ጋር ድርድር ሊኖር እንደማይችል ግን ነጥብ ይያዝልኝ – እንዲህ የምለው በየዋህነትና ምናልባትም በተዘዋዋሪ አንዳች ዘዴ ካለ ብዬ ነው – ለምሣሌ ለነገብሩ አሥራትና ለነአረጋሽ አዳነ ጉዳዩ ተላልፎ የሚሰጥና በነሱ አማካይነት ምናምን ነገር…፡፡ ከዚያ ውጪ ያለው የኃይልም በሉት ጊዜ ለመግዛት የሚደረግ የማጭበርበር ሥልት ሁሉ ለበለጠ መላላጥና ለሕዝብና ሕዝብ መቃቃር በር ከመክፈት ባለፈ ፋይዳ የለውም – መጽሐፍ ምን አለ? “ኢይድኅን ንጉሥ በብዝኃ ሠራዊቱ” – ንጉሥ በሠራዊቱ ብዛት አይድንም – ሌላስ? “ቦዕ ጊዜ ለኩሉ” – ለሁሉም ጊዜ አለው፡፡ ለዚህ ለዚህማ ቁጥር ሥፍር የሌለው የደርግ ሠራዊትስ ያን ሁሉ ዘመናዊ መሣሪያ ይዞ መች እግር አውጭኝ ይፈረጥጥ ነበር? ቀን አያዘምብልብህ – ካዘነበለ አዘነበለ ነው፤ መመለሻም የለው፡፡ ለማንኛውም በወያኔ የደረሰው ጭቆና ዓለም የማታውቀው እጅግ ከባድ ነበር – የሚደርሰው የዕዳ ክፍያም እንዲሁ ዓለም የማታውቀው እጅግ አሰቃቂ ይሆናልና ይህን የድሃ ምክር የሚሰማ ይስማ!! ሳይቃጠል በቅጠል ከተቻለ ደግ ነው፡፡ አለዚያ በኔና በናንተ ይቅር እንጂ “እንዲህ ጨሶ ጨሶ የነደደ እንደሆን፤ ያመዱ ማፍሰሻ ሥርፋው ወዴት ይሆን” እያለ የጎንደርና የጎጃም ገበሬ እየፎከረ መሆኑን ሹክ ያለኝ ሰው አለና የወደፊት ጉዟችን እሾሃማ ነው፤ እንዲያውም የዚህ ፉከራ የኦሮምኛ ትርጉም በኦሮሞው ገበሬ መሀልም ተስፋፍቶ እንደቀጠለ ሰምቻለሁ፡፡

መታወቂያን በሚመለከት እኔ እንኳን በቅርብ ጊዜ የጻፍኩት አንድ አቤቱታ አለ፡፡ “በመታወቂያ ላይ ብሔራዊ ማንነት ይጻፋል እንጂ ጎሣና ነገድ አይጻፍም፤ እንዲያ ከተደረገ ለዘረኞች ጥቃት ግማሽ ሥራ እንደመሥራትና እነሱን እንደመርዳትም ነውና ዜጎችን በቀላሉ ለጥቃት መዳረግ ነው…” ብዬ አቤት ብያለሁ፡፡ ይሄውና ጊዜው ደረሰ፤ ዕብሪተኞቹ የዘሩትንም ማፈስ ጀመሩ፡፡ ግን ማን ተጎዳ? ማንስ ተጠቀመ? በመሠረቱ በዚህ ሂደት የሚጎዳ እንጂ የሚጠቀም የለም፡፡ በወረት ፍቅር የታወሩ፣ በዘረኝነት ዛር የሚያጎሩ፣ በጎጠኝነት የስሜት ስካር የደነዘዙ ቆሻሻ ሰዎች በተከሉብን የብሔር ፖለቲካ ምክንያት እየተላለቅን ነው፤ አሁን ከመሸ በኋላ መታወቂያ ቢቀየር አንደበት አይለወጥም፤ መታወቂያ ወረቀት ቢቀየር እውነት አትሰረዝምና ማንም ቢሆን ዘርቶ ካሳደገው ጌሾና አርሞ ኮትኩቶ ለመኸር ካበቃው እንክርዳድ የተዘለለ ጠላ መቃመሱ አይቀርም፡፡ ወዮ ለምሥኪን ዜጎች! ወዮ ምንም ጥቅም ሳይደርሳቸው መከራና ፍዳው በስማቸውና በዘውጋቸው ምክንያት ለሚደርስባቸው! ለኢትዮጵያ ወዮ በሉ ወገኖቼ፡፡

በልማድ ዞን ዘጠኝ  ይባል የነበረው የብዙዎቻችን ትልቁ እሥር ቤት ከትናንትናው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ በኋላ ወደ ስምንቱ ዞኖች ተቀላቀለ፡፡ በቃሊቲው ዘብጥያ ስምንት ዞኖች እንዳሉና እኛ ከጠባቦቹ እሥር ቤች ውጪ የምንኖረው ዜጎች በዘጠንኛው ዞን መመደባችን የሚታወስ ነው – እንደቀልድ ግን እውነት የሆነ እውነት፡፡ አሁን ግን ሁላችንም እኩል የምንሆንበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ ይህም ከአሁን በኋላ እስካሁን ጭል ጭል ትል የነበረችው በአንጻራዊ አነጋገር እንደመልካም አጋጣሚ የምትጠቀስ ትንሽዬ በነፃነት የመንቀሰቅ መብት በዚህ ዐዋጅ መሠረት ድራሽዋ ጠፍቷል፡፡ ከእስካሁኑ በከፋ ሁኔታ የምንገደልበት፣ የምንሰቃይበት፣ የምንታሰርበት፣ የምንበረበርበት፣ እንደዐይጥ በየተገኘንበት ሥፍራ የምንጨፈጨፍበት፣ ያለችን ሀብትና ንብረት በጠራራ ፀሐይ የምትዘረፍበት … አዲስ ዐዋጅ ታውጆ ለተግባራዊነቱ አጋዚዎች ነቅተው የሚጠባበቁበት ጊዜ ላይ እንገኛለን፡፡

ብቻ ለማንኛውም እግዚአብሔር ይሁነን፡፡ ኢትዮጵያዊቷ አርማጌዴዎን ሰተት ብላ እየመጣች ነው፡፡ ሀገርና ሕዝብን በገንዘብ የምትለውጡ ሁሉ ወዮላችሁ! ለእውነት ያልቆማችሁ ወገኖች ሁሉ የምትበጠሩበት፣ ያጠራቀማችሁትን ገንዘብ የማትበሉበት የመከራ ዘመን እየመጣ ነው፡፡ አስታውሱ – ይሁዳ በዘመኑ አንቱ የተባለ ትልቅ ክፍያ – 30 ዲናር – ከክርስቶስ ጠላቶች ከጻፎች ፈሪሣውያንና ሰዱቃውን ተቀብሎ ጌታውን በመሳም አሳልፎ ሸጠ፡፡ ኋላ ላይ ግን ተፀፀተና ከገንዘቡ አምስት ሣንቲም እንኳን ሳያጎድል ራሱን ሰቅሎ ገደለ፡፡ ያም ገንዘብ በአይሁዶች እጅ ገባና መሬት ተገዛበት – የደም መሬት ተባለ – አኬልዳማ! አለቀ፡፡ ተበልቶ ዕዳሪ፣ ተጠጥቶ ሽንት ለሚሆን ምድራዊ ሀብት ብለን ዘላለማዊት የሆነች ነባቢት ነፍስን፣ በአርአያ ሥላሤ የተገነባ ተክለ ሰውነትን አለጊዜው ብናጠፋ ወይም ለመጥፋቱ ምክንያት ብንሆን ጌታ በቀላሉ የሚለቀን ወይም ሂሳባችንን ሳናወራርድ እንዲሁ የሚምረን እንዳይመስለን፡፡ የጌታ መሐሪነት የማይቀጣጠቡት ሆኖ ነገር ግን የእጃችንን የማግኘቱን ጉዳይ ማናችንም ልንዘነጋ አይገባም፡፡ ጌታ ሌላ ምን ሥራ አለው? ሥራው ይሄው ነው – መፍረድ፡፡

ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውንን በመሸጥ በሀብት የከበራች አሁኑኑ ንስሃ ግቡና ወደሕዝብ ተመለሱ፡፡ ይህችን ጠባብ ዘመን የሚያልፍ እጅግ ጥቂት ሰው ነው – ያም የታደለና ከወንጀልና ከክፉ ሥራ ራሱን የገታ ነው፡፡ ወደ ሆድ ወርዶ የመሸገ ጭንቅላት በአስቸኳይ ወደቦታው ይመለስ – የሰማ ያሰማ፡፡ ይህን መልእክት በቻላችሁት መንገድ ሁሉ ለሁሉም አዳርሱልኝ፡፡ ይህ መልእክቴ ራዕይ ወይም ንግርትና ሟርት ወይም ትንቢት አይደለም – ማንም የዋህ ልቦና ያለው መሬት ላይ በጉልኅ ቀለማት ተጽፎ ሊያነበው የሚችል ግልጽ አውነት ነው፡፡ አጉሊ መነጽር ሳያስፈልገን በግልጽ በምናየው አደጋ መጠቃት የለብንምና ለሁላችንም አስተዋይ ልቦና ይስጠን፡፡

አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ:- የወያኔ ሰራዊት ቀኝ ሁዋላ ወደ ደደቢት –ታሪኩ አባዳማ

$
0
0

ታሪኩ አባዳማ መስከረም 2009

 

hailemariam_desalgn-6-satenaw-newsህወሀት ተልዕኮው በከፊል ሰምሯል ፤ ለብሔር ብሔረሰቦች መብት እስከ መገንጠል ቆሜያለሁ ብሎ ነበር ፣ ዲሞክረሲ ሳይሽራረፍ አረጋግጣለሁ ፣ ሰብአዊ መብት አሰፍናለሁ ብሎ ነበር ፣ ያለፍርድ አንድም ዜጋ ህይወቱን ቀርቶ መታሰር አይደርስበትም ብሎ ነበር ፣ ከጎረቤት አገሮች ጋር በማይናወጥ ሰላም እንኖራለን ብሎም ነበር… ከፖለቲካ ስርአት ምህዳር እና ሰማይ በታች ሁሉንም በጎ ነገሮች በኔ አገዛዝ ስር ትጎናፀፋላችሁ ሲል ቃል ገብቶ ነበር። ቃሉን በሰነድ ላይ አስፍሮ ህገ መንግስት አድርጎ – እሰከዚህ ድረስ ተጉዞ ነበር።

 

ራዕዩ ቃል ፣ ቃሉም ሰነድ ሆኖ ነበር… በቃ ፣ ከዚያ ማለፍ አልቻለም። ሰነዱ ሳይነበብ ብል በላው ፣ ምስጥ መዘመዘው ፣ አረም ዋጠው። ቃሉ ስጋ ወ ደም ሳይዋሀድ ጨነገፈ… በመጨረሻም እነሆ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ። የተባባሰ ግድያ አዋጅ ፣ የላቀ ጅምላ መብት ጥሰት አዋጅ ፣ የጫካ አዋጅ ፣ የአራዊት አዋጅ ፣ የደደቢት አዋጅ አወጀ። ህወሀት ከሀያ አምስት አመታት የግፍ አገዛዝ በሁዋላ ቀኝ ሁዋላ ወደ ደደቢት አለ ፤ ጫካውን ናፈቀ። ተጠያቂነት እና ግልፅነት የማያውቀው የደደቢት ፖለቲካ ህይወት እጅጉን ናፈቀው።

 

መጀመሪያ ያኔ ወደ ደደቢት ሲጓዝ የህዝብ ብሶት ሰንቆ ለጋ ወጣት ሳለ የተመኘውን ሊከውን ነበር – ይብዛም ይነስ ብሩህ አይምሮ ፣ ያልተልከሰከሰ መንፈስ እና ምኞት ነበረው። አሁን ወደ ደደቢት ለመጓዝ የተነሳው ደግሞ በህዝብ ልጆች ደም የጨቀየ እጆቹን ፣ በሙስና የበከተ ህሊናውን ፣ በውሸት እና ቅጥፈት የተባ ምላሱን አንዘላዝሎ ፣ ታሪክ ይቅር የማይለው ፣ ትውልድ አሳፋሪ ታሪኩን አንግቦ ነው። ህወሀት ቀኝ ሁዋላ ወደ ደደቢት አለ – አስቸኳይ ጊዜ አወጀ። ገድለው በህግ የማይጠየቁበት ፣ ዘርፈው የማይጠግቡበት ፣ ባሻቸው ውለው የሚያድሩበት ደደቢት ናፈቀው። ወንድም ወንድሙን ገድሎ የሚፎክርበት ፣ ሀውልት የሚገትርበት ፤ ድልድይ አፍርሶ ፣ ባንክ ዘርፎ ፣ ድሀ አስለቅሶ እለት ጉርሱን ሳይቀር ቀምቶ ወደሚያድርበት ደደቢት ቀኝ ሁዋላ ዙር አለ – አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ። ህወሀት እንደገና ኢትዮጵያ ለምኔ አለ ፣ ኢትዮጵያዊ ገድሎ ፣ ክብሯን አዋርዶ ፣ ባንዲራዋን እንደ ጨርቅ በሶ እየቋጠረ ወደማይጠየቅበት ደደቢት ፊቱን አዞረ።

 

ትናንት በቃሉ መሰረት የሰጣቸውን ሰነድ የተማመኑ ፣ ተማምነውም መብታቸውን የጠየቁ አሸባሪ ተብለው አደባባይ በጥይት እሩምታ ታጨዱ ፣ በየወህኒው ታጎሩ ፣ ተሰደዱ። ያልተሸራረፈው ዲሞክረሲ ቀርቶ መሰረታዊ እና ተፈጥሯዊ መብታችን ይከበር ያሉ በወንጀል ተከሰው ወህኒ ተወረወሩ። በታጎሩበት ወህኒ እሳት ነደደባቸው። እሱም አልበቃ ብሎ ዛሬ ለሌላ ጅምላ ፍጅት አዋጅ ታወጀባቸው – አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ።

 

ህወሀት ትግራይን ነፃ ለማውጣት ተልሞ ድፍን ኢትዮጵያን ተቆጣጥሯል – ህዝቧን በከፋፍለህ ግዛ መርህ በጎጥ ሸንሽኖ አንድነቷን አናግቷል። አንድነቱ በተናጋ እና በተከፋፈለ ህዝብ ትከሻ ላይ ተደላድሎ እጅግ መጠነ ሰፊ የሆነ ሀብት መዝብሮ ቢጠሩት የማይሰማ ቱጃር ሆኗል። በጎጥ የከፋፈለውን ህዝብ በወረፋ አንዱን ዛሬ ሌላውን ነገ እየነጠለ ሲገድል ፣ ወህኒ ሲያግዝ ፣ ለስደት ሲዳርግ ፣ ንብረት ሲቀማ ሀያ አምስት አመታት አስቆጥሯል።

 

ግን ዛሬ ህዝብ በቃ አለ – አለም ይህን ጅምላ ፍጅት መርምሮ ተጠያቂውን ለፍርድ ማቅረብ ግድ ይላል ሲል ሰምቶ ህወሀት ደነበረ ፣ ፊቱን ወደ ደደቢት አዞረ። አንዳችም ተጠያቂነት ወይንም ግልፅነት ወደሌለበት ወደ ደደቢት አለም ለመጓዝ ተጣደፈ። ኢትዮጵያን በታትኜ ፣ እንደ ሩዋንዳ የዘር ፍጅት አቀጣጥዬ ደደቢት ገባለሁ አለ። ይህም አይሆንም ሲል ህዝብ አንድነቱን አጥብቆ ከዳር እስከ ዳር ተሰለፈ – ህወሀት ግን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ – ደደቢትን ከነ አተላው እግታችሁዋለሁ አለ፤ ህዝብን ምን ያህል እንደ ናቀ ለማሳየት አዋጅ አወጀ። የአንዲት አገር ልጆችን በጎጥ ሸንሽኖ ፣ በክልል በረት አጉሮ እንኳ መግዛት ተሳነው።

 

የትግራይን ሪፐብሊክ ለማወጅ የረቀቀው ሰነድ ከተቀበረት ዋሻ አቧራው ተራግፎ ወደ አደባባይ ብቅ እያለ ነው። ወያኔ/ህወሀት ‘በብረት አስገብረን ፣ ደም አፍሰን ፣ እንደ ገል ቀጥቅጠን እንደ ብረት አቅልጠን መግዛት ካልቻልን እናንተን በታትነን እኛ ሪፐብሊካችንን እናውጃለን’ በሚል እየተጋበዘ ቆይቷል። ህዝቡ አንተ እንደፍጥርጥርህ ለእኛ ግን አንድነታችን ፣ ሰብአዊ መብታችን ዋስትናችን ነው በሚል ፅኑ ተቃውሞ ማድረጉን ቀጠለ። ህወሀት ደደቢት ላይ ሲያደርግ እንደ ነበረው ጭፍን ጥላቻን በህዝብ ለመርጨት ሲል ሀውልት እስከ ማቆም ደረሰ። ህዝብ ግን ህወሀት ሰራሽ የሆነ አንዳችም ነገር እንደማይበጀው ይፋ አደረገ። Down down woyane እያለ መልካው እስኪናጋ ድረስ አስተጋባ። ህወሀት ግን ፊቱን ወደ ደደቢት አዞረ ፣ ተጠያቂነት ፣ ግልፅነት የሌለበትን ስርአት ናፈቀ – አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ።

 

አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ይፋ ሆኗል – የደደቢት ስርዓት በመላው አገር በይፋ ይረጋገጣል ብለዋል። ከቶውንም ህግ ባልነበረበት አገር ፣ ስርአት ባልተጠበቀበት ምድር አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚያመጣው ምን አዲስ ነገር አለ? እስከ ዛሬ እንደ ጅረት ስላፈሰሱት ደም ፤ እስከ ዛሬ ከአፅመ ርስቱ ስላፈናቀሉት ዜጋ ፤ እስከ ዛሬ ህልውናውን ፣ ስብእናውን ክደው ስላዋረዱት ህዝብ ጉዳይ መልስ እየጠየቅን እንጂ መቸ ሌላ ዙር ፍጅት ጠየቅን።

 

ሳይውል ሳያድር ለጥያቄአችን መልስ እንፈልጋለን። እስከ ደደቢት ድረስ እናንተን የምንሸኝበት አቅም ፣ ዝግጅትም ሆነ ፍላጎት የለንም ፤ አስቸኳይ ጊዜ አዋጃችሁን የምንሸከምበት ዕዳ ፣ በዚያም የምንገዛበት ትከሻ የለንም። ደደቢትን ወደ እኛ እንዳመጣችሁ ሁሉ መልሳችሁ እንድትረከቡ ህዝብ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይጮሀል። Down down woyane ይላል።

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live