Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

በመንግስት ላይ እየተቆጣ ያለው ሕዝብ በቡሌሆራ (ሐገረ ማርያም) ፍርድ ቤት በእሳት አነደደ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ትናንት በ እሬቻ በዓል ላይ በትግራይ ነጻ አውጪ ጦር ከ500 በላይ ሰዎች ከተገደሉ በኋላ በኢትዮጵያ የተለያዩ ከተሞች እየተደረገ ያለው ተቃውሞ ወደ መንግስትን ንብረት ወደ ማውደም ተሸጋግሯል::

በቀደሞዋ ሐገረ ማርያም በአሁኑ ቡሌ ሆራ ወረዳ የሚገኝ የመንግስት ፍርድ ቤት ሙሉ በመሉ በ እሳት መውደሙ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ያሳያል::

ሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ ያልተገባ ፍርድ ሲሰጥበት የነበረው ይኸው የወረዳ ፍርድ ቤት ከነሙሉ የክስ ፋይሎች መውደሙ ሲታወቅ ምን ያህል ሕዝብ እንደተጎዳ ለማወቅ አልተቻለም::

በቡሌ ሆራ ሕዝባዊው አመጽ ቀጥሎ የመንግስት መኪናዎች እየተቃጠሉ ሲሆን በባለስልጣናት ንብረቶች ላይም ጥቃት እየተሰነዘረ ነው::

መንግስት የሞቱት 52 ብቻ ናቸው እያለ እያወራ ሲሆን እንደብሉምበርግ ያሉ ሚድያዎች ሟቾችን ከመቶ በላይ ያደርሱታል:: ሆኖም ግን የሟቾች ቁጥር ከ500 በላይ እንደሆነ ከተለያዩ ቦታዎች የተሰበሰቡ መረጃዎች ይጠቁማሉ::: ይህም ሕዝብን አስቆጥጦታል::
14441071_10102576237296603_3643303376849212074_n

በሙገር የዳንጎቴ ሲሚንቶ የጫነ ትራክ በ እሳት ወደመ –ቡራዩ ከፍተኛ የጥይት ድምጽ ይሰማል

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ትናንት ከ500 በላይ ሰዎች በቢሾፍቱ እሬቻ በዓል ላይ ከተገደሉ በሏ እንደገና እየተቀጣጠለ ያለው ሕዝባዊ አመጽ የተለያዩ ከተሞችን እያዳረሰ ይገኛል:: በኦሮሚያ ልዩ ዞን ስር ያለችው ቡራዩ ከተማ ኬታ በተባለው አካባቢ ከፍተኛ የሆነ የተክስ ድምጽ እንደሚሰማ ከፍስራው የደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ::
14492624_10102576260749603_340539769715569458_n
በሌላ በኩል በሙገር የዳንጎቴን ሲሚንቶ ጭኖ ሲሄድ የነበረ ትራክም ለተቃውሞ በወጡ ሰዎች መውደሙ ተሰምቷል:: በተለያዩ ቦታዎች ከመንግስት ጋር የሚሰሩ ባለሃብቶች እና ባለስልጣናት ንብረቶች እየወደሙ ይገኛሉ::

ሌሎች ዜናዎቻችንን ለበለጠ መረጃ ይመልከቱ::

በመንግስት ላይ እየተቆጣ ያለው ሕዝብ በቡሌሆራ (ሐገረ ማርያም) ፍርድ ቤት በእሳት አነደደ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ትናንት በ እሬቻ በዓል ላይ በትግራይ ነጻ አውጪ ጦር ከ500 በላይ ሰዎች ከተገደሉ በኋላ በኢትዮጵያ የተለያዩ ከተሞች እየተደረገ ያለው ተቃውሞ ወደ መንግስትን ንብረት ወደ ማውደም ተሸጋግሯል::
14441071_10102576237296603_3643303376849212074_n

በቀደሞዋ ሐገረ ማርያም በአሁኑ ቡሌ ሆራ ወረዳ የሚገኝ የመንግስት ፍርድ ቤት ሙሉ በመሉ በ እሳት መውደሙ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ያሳያል::

ሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ ያልተገባ ፍርድ ሲሰጥበት የነበረው ይኸው የወረዳ ፍርድ ቤት ከነሙሉ የክስ ፋይሎች መውደሙ ሲታወቅ ምን ያህል ሕዝብ እንደተጎዳ ለማወቅ አልተቻለም::

በቡሌ ሆራ ሕዝባዊው አመጽ ቀጥሎ የመንግስት መኪናዎች እየተቃጠሉ ሲሆን በባለስልጣናት ንብረቶች ላይም ጥቃት እየተሰነዘረ ነው::

መንግስት የሞቱት 52 ብቻ ናቸው እያለ እያወራ ሲሆን እንደብሉምበርግ ያሉ ሚድያዎች ሟቾችን ከመቶ በላይ ያደርሱታል:: ሆኖም ግን የሟቾች ቁጥር ከ500 በላይ እንደሆነ ከተለያዩ ቦታዎች የተሰበሰቡ መረጃዎች ይጠቁማሉ::: ይህም ሕዝብን አስቆጥጦታል::

ለዘብተኞችን ማጥቃት፤ አክራሪዎችን ማብዛት –አንዱዓለም ተፈራ  –የእስከመቼ አዘጋጅ

$
0
0
ሰኞ፤ መስከረም ፳ ፫ ቀን ፳ ፱ ዓመተ ምህረት
cdo-debretsionየሃሳብ ልዩነት፤ ያለ ነገር ብቻ ሳይሆን፤ አስፈላጊም ነው። የተለያዩ ሃሳቦች መከሰት፤ አማራጮችን በመድረክ ላይ በማቅረብ፤ ልዩነቶችን እንድንመረምርና፤ በብዙኀኑ ዓይን የተሻለ የተባለውን እንድንመርጥ ዕድል ይፈጥርልናል። በነዚህ የተለያዩ ሃሳቦች ተነስቶ ርስ በርስ መወነጃጀሉ፤ አንድም እኔ ያልኩት ብቻ ይሁን ባይነት ብሎም ራስን የማግዘፍ ጥንውት ነው። ሌላም ትግሉ መልክ ይዞ ወደፊት እንዳይሄድ እንቅፋት ለመሆን የተጠነሰሰ ሴራ ነው።
አክራሪዎች መኖራቸውንና የትግላችን አንዱ ገፅታ መሆኑን መቀበል አለብን። ይህ በቀኝ ይሁን በግራ፣ በፊት ይሁን በኋላ፣ ፈለግነውም ጠላነውም፤ ያለ ሀቅ ነው። ይህ የትግል አቅጣጫችን ሊቀይር ቀርቶ፤ ትኩረታችን ሊስብ አይገባውም። የሀገራችን የፖለቲካ እውነታ፤ ያደግንበትም ሆነ አሁን ያለው ተጨባጭ ሀቅ፤ መፈናፈኛ በማሣጣቱ፤ አክራሪዎች መፈጠራቸው፤ ሁኔታው የወለደው ክስተት ነው። እናም አክራሪ የምንላቸውን ለማጥቃት ወይንም ለማጥፋት ዓይኖቻችንን ከዋናው ግባችን መንቀል፤ ለራሳችን ጥቃት በሩን ለጠላት በርግደን መክፈታችን ነው። ትኩረታችን መሆን ያለበት ሰፊው ሕዝብ የሥልጣኑ ባለቤት የሚሆንበትን በመፈለግና ያን በመቀበል ላይ ነው። ብዙኀኑ የተቀበሉት ለስኬት እንዲበቃ፤ ጥረታችንን በሙሉ በዚያ ላይ ማረባረብ አለብን። በግራና በቀኝ ተፋሰሶች እያበጀን፤ ጉልበታችንን እኛው ራሳችን አናዳክም።
“አስቀድሞ መግደል አሾክሿኪውን ነው!” ብለው ቀደምቶቻችን ሲያስተምሩን፤ አሾክሿኪው የጠላት አንድ አካል መሆኑን፤ እነሱም ሆኑ ራሱ አሾክሿኪው ስለሚያምኑበትና ስለሚቀበሉት ነው። በተጨማሪም፤ እጅ ከፍንጅ መረጃው ስለተያዘ ነው። እኛ የያዝነው ግን፤ “እኔ የምለውን ያልተቀበለ፤ ‘ወያኔ’ ነው!” የሚል ጠባብ፣ ራስ ተኮር፣ እኔ ብቻ ነኝ አዋቂ ባይነትና ከሀገር በላይ ግለሰብን ወይንም የራስ ድርጅትን የሚያስቀምጥ አባዜ ነው።
ባሁኗ ሰዓት፤ በፖለቲካ ትግሉ መስክ፤ ባንድ በኩል የሀገር አንድነትን ፈላጊዎች፤ “ሀገር አቀፍ ትግል እንጂ ሌላ ምን ሲባል!” የሚል ምሽግ ሠርተናል። በሌላ በኩል ደግሞ በሀገር ውስጥ ባለው የፖለቲካ እውነታ በመመርኮዝ፤ “የለም፤ የአማራ ወጣቶችና የኦሮሞ ወጣቶች የትግሉን የበላይነት ጨብጠውታል። እናም ያን ሀቅ ተቀብለን፤ እኒህ ክፍሎች የሚቀራረቡበትንና የሚተባበሩበትን በመፈለግ፤ የወደፊቷን ኢትዮጵያ እንመሠርታታለን!” ባዮች አንድ ምሽግ ሠርተናል። ለኒህ ሁለቱ የትግል መስመሮች ጠላታችንም ግባችንም አንድ ነው። መንገዳችን ግን የተለያየ ነው። በርግጥ የትኛው የተሻለ ይሆናል የሚለውን፤ ሁለቱ ክፍሎች ቀርበን ለመነጋገር፤ አሁን ትልቅ ችግር ላይ ነን። የዜሮ ድምር ፖለቲከኞች፤ “ሌላው መታሰብ እንኳን የሌለበት ነው!” የሚል አቋም ያራምዳሉ። እንዲያውም ሁለቱም ክፍሎች በየጎራችን ጎድበን፤ አንዳችን ሌላችንን፤ ከወራሪው ፀረ-ኢትዮጵያ የትግሬዎች ቡድን የበለጠ ጠላት አድርገን በመፈረጅ፤ ለመጠፋፋት ተነስተናል።
እንግዲህ ሀቁ እንዲህ ነው። አስታራቂ ሽማግሌ ከየትም አይመጣም። እውነት የሕዝቡን ድል ፈላጊዎች ከሆን፤ ከባህላዊ ዘፈናችን አንድ ስንኝ ልዋስና፤ አስታራቂም የለን፤ እኛው እንታረቅ። የርስ በርሳችን መወነጃጀልና ጉልበታችን ለዚሁ ማጥፋት ማንን እንደሚረዳ፤ እኔ ለናንተ አልነግርም። አስቸጋሪ የሆነው ደግሞ፤ ይህ የታጋዮች በሁለት ጎራ መመሸግ፤ እየተከሰተ ያለው በቀጥታ ሳይሆን፤ በተዘዋዋሪና ትግሉን በቀጥታ በሚጎዳ መልክ ነው። መድረካችን በሳል የትግል ነጥቦችን በርጋታ የምንነጋገርበት ሕዝባዊ ስብስብ ሳይሆን፤ ፓልቶክና ፌስቡክ፣ ቲውተርና የየግል የሬዲዮ ስርጭት መሰምሮች ሆኗል።በመጀመሪያ ደረጃ፤ የፖለቲካ ልዩነት መግለጫና መነታረኪያ ባህላችን፤ ስድብ ማሽጎድጎድ ሆኗል። ብዙ በመሳደብ፤ የአቸናፊነት ሽልማት ለመቀበል መስገብገብ ይታያል። “ወያኔ!” ብሎ አንዱ ሌላውን አስቀድሞ ስለወነጀለ፤ ወንጃዩ የሕዝብ ወገን፤ ታርጋው የተለጠፈበት ደግሞ የጠላት ወገን የሆነ ይመስለዋል። አጉል ቅዠት ነው። ስድብ ስለ ቆሸሸውን የሰዳቢ አፍ ይናገራል እንጂ፤ የተሰዳቢውን ማንነት አይገልጽም። ይህ መጥፎ ባህል ነው። ይቅርብን።
አንዱ የመነጋገርያ ነጥብ የአማራውን መደራጀት የሚመለከት ነው። አማራው መደራጀት አለበት ብለው ያመኑና በዚሁ እምነታቸው የገፉ አሉ። ባለፉት ሃይ አምስት ዓመታትና አሁንም በአማራው ላይ እየደረሰበት ያለውን የዘር ማጽዳት ወንጀል በመንተራስና፤ የትግሬዎችን ቡድን የፖለቲካ ፍልስፍናና የአስተዳደር መመሪያ መረጃ በመያዝ፤ አማራው በሕልውና እንዲኖር፤ ተደራጅቶ መታገል አለበት! የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል። በሌላ በኩል ደግሞ አማራው መደራጀት የለበትም በማለት፤ “ትግሉ መካሄድ ያለበት በኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው!” የሚለውን ሃሳብ ሙጥኝ ብለው የተጣበቁ አሉ። በጄ! ይህን በተለያየ መልኩ ማየት ይቻላል። ነገር ግን፤ አንዱ ወገን የሌላውን ወገን ከመስማት ይልቅ፤ በራስ ጭንቅላት የፈጠሩትን ደጋፊ ወይንም ነቃፊ ነጥብ በማብጠልጠል፤ ከራስ ጋር ሙግት የተያዘበት ሀቅ ነግሷል። የሌላውን ነጥብ ማዳመጡ ቦታ አልተሠጠውም። አማራው ያለበት የዘር ማጽዳት አውነታ ለመቀየር፤ ማንኛውንም በማድረግ ሕልውናውን መጠበቅ እንዳለበት መረዳት ያስፈልጋል። ይህን እረዳለሁ ብሎ የተነሳን ደግሞ፤ ማንም ቢሆን ማን ሊያቆመው፣ ሊከለክለው ወይንም ሊቃወመው አይገባም። መቃወም ማለት በአማራው ላይ መዝመት ማለት ነው። ለዚህ ክፍል፤ ኢትዮጵያን ከማስብ በፊት፤ አማራው መዳን አለበት። ይህ አከራካሪ የመሆኑን አጥር ዘሏል። ስለዚህ፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ መሄዱ አስፈላጊ አይደለም። ይልቁንስ ለመረዳት መጣሩ ተገቢ ነው። ኢትዮጵያ እንዴት ትድናለች የሚለው ጥያቄ ያንገበገባቸው ሰዎች፤ ታጋዮችንና በሀገሪቱ ያለውን ሀቅ፤ የምርምራቸው መነሻ ማድረግ ይገባቸዋል።
ሁለተኛው መነጋገሪያ ነጥብ፤ ኢሳትን የተመለከተ ነው። ኢሳት የራሱ ግብ ያለው የግል ተቋም ነው። ባለቤት አለው። ኢሳት የኢትዮጵያ ሕዝብ ንብረት አይደለም። ውሎ አድሮ ለንግድ የተዘጋጀ ተቋም ነው። ስለዚህ ባለቤቱ የሚያዝበት እንጂ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያዝበት ተቋም አይደለም። ይህን ማለት፤ ኢሳት መጥፎ ነው ማለት አይደለም። ነገር ግን፤ ማንም ተነስቶ ይሄን ካላደረገ ወይንም ያንን ከላደረገ የሚልበት አለመሆኑን ለማስጨበጥ ነው። ማንም ግለሰብ ይህን የግል ተቋም፤ በግሉ ሊረዳ ይችላል። ማንም ግለስብ ደግሞ፤ በግሉ ይሄን የግል ተቋም ላይረዳ ይችላል። ነገር ግን ማንም ግለሰብ፤ ከባለቤቱ በስተቀር፤ ሊያዝበት አይችልም። ይህ መታወቅ አለበት። እናም ይሄን ይዘን፤ የግሉን ተቋም ለምን ይሄን አላደረገም ብሎ መወንጀል፤ ተገቢ አይደለም። ይህ በታጋዮች መካከል ለመጣላት ምክንያት ሊሆን አይገባውም። የኢትዮጵያዊያን ንብረት ቢሆን ኖሮ፤ ለምን እንዲህ ወይንም ለምን እንዲያ አላደረገም ብለን መናገር መብታችን ይሆን ነበር። አሁን ግን መብታችን አይደለም። ከወደድን እንደግፈው፤ ካልወደድንም ደግሞ እንተወው። በቃ።
ሶስተኛው መነጋገሪያ ነጥብ ደግሞ ትግሬዎችን የተመለከተ ነው። ባሁኑ ሰዓት፤ በሀገራችን ላለው የግፍና የስቃይ ውርጅብኝ፤ ተጠያቂው ወራሪው የትግሬዎች ቡድን ነው። ይህ ወራሪ ቡድን፤ በምንም መንገድ ይሁን በምንም፤ ትግሬዎችን ወክያለሁ ብሎ፤ በኢትዮጵያዊያን ላይ ግራና ቀኝ ጥፋት፤ በተለይም ደግሞ በአማራው ላይ የዘር ማጽዳት ወንጀል እየፈጸመ ነው። ይህን የሚፈጽመው፤ በአብዛኛው ትግሬዎችን በመሣሪያነት ይዞ ነው። በርግጥ ከሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች የሆኑ አንዳንድ ሆድ አደሮች፤ በግለሰብ ደረጃ፤ በባንዳነት እየረዱት ናቸው። እኒህ ሆድ አደሮች ይሄንን በሚያደርጉበት ሰዓት፤ ሕልውናቸውን ሸጠው፤ የዚሁ የወራሪው የትግሬዎች ቡድን አካልና አምሳል ሆነው ነው። እናም እነሱ ትግሬዎችም ባይሆኑ፤ የዚህ የወራሪው የትግሬዎች ቡድን አካል ናቸው። ስለዚህ ይህን ቡድን በምንም መልኩ ብናየው የትግሬዎች ቡድን ነው። አማራውን ለማጥፋት የተነሳው ይህ የወራሪው የትግሬዎች ስብስብ ነው። ኦሮሞዎችን እየገደለ ያለው ይህ የወራሪው የትግሬዎች ቡድን ነው። አኝዋኮቹን የጨፈጨፈው ይህ የወራሪው የትግሬዎች ቡድን ነው። ኦጋዴኖቹን የበደለው ይህ የወራሪው የትግሬዎች ቡድን ነው። እና ገና ለገና ትግሬዎች ይበደሉ ይሆናል በማለት፤ በውጪ ሀገር ያሉ “ታጋይ ነን!” ባይ ትግሬዎች፤ ጥብቅና ከትግሬው ቡድን ጋር አብረው ተሰልፈዋል። አልሸሹም ዞር አሉ ነው። ጠላት የማብዛትና የማሳነስ ስልት አይደለም። አሁንም፤ ዛሬ የዘር ማጽዳት ወንጀል እየተፈጸመበት ላለው አማራና ዛሬ ለሚያልቀው የኦሮሞ ወጣት ከመቆም ይልቅ፤ ገና ለገና በትግሬዎች ንብረት ላይ ጉዳት ይደርስ ይሆናል ብሎ የሚጮኽ፤ በምንም መለኪያ ቢታይ፤ የወራሪው የትግሬዎች አጥፊ ቡድን አካል እንጂ፤ የሕዝብ ወገን አይደለም። ጠላቱንና የትግል መስመሩን ለይቶ ያልተነሳ ታጋይ፤ የያዘውን ትግል አያውቀውም፤ ድሉም ምን እንደሆነ ስለማያወቅ፤ ለድል አይበቃም።
የያዝነው የምኞትና የፍላጎት ትግል አይደለም። በቦታው ያለውን ሀቅ ተቀብሎ፤ ያን ለማስተካከል የሚደረግ ትግል ነው። ወራሪው የትግሬዎች ፀረ-ኢትዮጵያዊያን ቡድን የሚታረቅ፤ የሚሻሻል፤ የሚታረም አይደለም። መሠረታዊ እምነቱ ኢትዮጵያዊነት አይደለምና! ከዚህ ቡድን ጋር እርቅ ለማድረግ የሚፈልጉና “ብዙ ሰው እንዳያልቅ!” እያሉ የሚያላዝኑ ሰዎች፤ ጎራቸው ከዚሁ ወራሪ ቡድን ጋር ይቀራረባል። ይህ ወራሪ ቡድን፤ ከትግራይ ውጪ ለሚያልቀው ወገን ደንታ የለውም። እየገፋበትም ነው። ይህን ቡድን በምንም መልኩ ለማዳን መሞከር፤ የዚሁ ቡድን ደጋፊነት ነው። አጥሩ ግልጽ ነው። ይልቅስ በታጋዩ ወገን ያለውን እናስተካክል። ለወራሪው ቡድን አሳቢዎች ብዙ አሉ። እኛ ለሱ መጨነቁን እንተወው። በአንድነት መታገሉን እስከወደድን ድረስ፤ ወደ አንድነት የሚወስደውን መንገድ እንከተል። በታጋዩ ጎራ ያለን ሁሉ፤ ወደ አንድ ለመምጣት ያለው በር አንድ ነው። ተቀራርቦ መነጋገር። እንዴት ወይንም መቼ ወይንም የት የሚለው፤ በሁለተኛ ደረጃ የሚከተል ነው። መጀመሪያ የአንድነቱን አስፈላጊነት መቀበል ነው። ይሄን ደግሞ ያልለፈለፈለት የለም። ታዲያ ቀጥሎ መገናኘት ነው። ለዚህ ጠሪው ብዙ አድማጩ ዜሮ ለሆነበት ትንግርት፤ እግሬን አስቀድሜ አነሳለሁ። እናም ውይይቱ ትናንት መሆን ቢኖርበትም፤ ትግሉ እየተካሄደም፤ ዛሬ ይቀጥል።  

ከእሬቻ እልቂት በኋላ በመላ ሀገሪቱ ከባድ ተቃውሞ ተቀስቅሷል

$
0
0

ዘግናኙን የእሬቻ እልቂት ተከትሎ በመላው ኢትዮጵያ ከባድ የተቃውሞ ንቅናቄ መጀመሩን ከስፍራው የሚደርሱ መረጃዎች እየገለጹ ነው። የሆራው ጭካኔ የተሞላበት የትግራይ ነጻ አውጪ ቡድን ግድያ ከኢትዮጵያ አልፎ አለምን በሙሉ አስቆጥቷል

meki

በቡራዩ የከባድ መሳሪያ ቶክስ ሰኞ ምሽት ላይ የጀመረ ሲሆን በሙገር የዳንጎቴ ንብረት የሆነ ከባድ መኪና በሕዝባዊ ንቅናቄው ኣራማጆች ጋይቷል። በቡሌ ሆራ ፍርድ ቤቶች መንደዳቸውን እና፤ በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች በቢሾፍቱ የተገደሉ ንጹሃንን ለመቅበር በተደረገ ስነስርዓት ላይ ከባባድ ተቃውሞዎች የተሰሙ ሲሆን በምዕራብ ሀረርጌ ፪ የሰላም ባስ አውቶብሶች ከጥቅም ውጭ ሆነዋል ሲል ምኒሊክ ሳልሳዊ የተሰኘው ብሎገር ገልጽዋል።
14492624_10102576260749603_340539769715569458_n
በሌላ ዜና መቂ፣ ዝዋይ እና ሻሸመኔ ከባድ ተቃውሞ መቀስቀሱ ተሰምቷል። ከትላንት ምሽት አንስቶ መንገዶች በተደጋጋሚ እየተዘጉ- ተሽከርካሪዎች እየተቃጠሉ ሲሆን ህዝብ ወደ ጎዳና ወጥቶ ቁጣውን በምሬት እየገለፀ ነው።
በጂማ፣በአምቦ፣ በጊንጪ፣ በሸኖ፣ በመቂ፣ በባሌ ሮቤ፣ በደንቢ ዶሎ፣ በቄለም ወለጋ፣ በም ዕራብ ሸዋና በሌሎችም ከተሞች ተቃውሞው ተቀጣጥሏል::
cars

በተለያዩ ከተሞች በተነሱት በነዚሁ ሕዝባዊ አመጾች የመንግስት መኪኖች ሲነዱ ታይተዋል::

በጂማ፣ በአምቦ፣ በጊንጪ፣ በሸኖ፣ በመቂ፣ በባሌ ሮቤ፣ በደንቢ ዶሎ፣ በም ዕራብ ሸዋ ሕዝብ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞውን እያሰማ ሲሆን በመንግስት ንብረቶች ላይ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይም ይገኛል።

በሃረር ተመሳሳይ አመጽ ተነስቷል – የሕወሃት ንብረት የሆነው ሰላም ባስ ተቃጥሏል።

source:-ethioforum.org

ለዘብተኞችን ማጥቃት፤ አክራሪዎችን ማብዛት -አንዱዓለም ተፈራ

$
0
0

የሃሳብ ልዩነት፤ ያለ ነገር ብቻ ሳይሆን፤ አስፈላጊም ነው። የተለያዩ ሃሳቦች መከሰት፤ አማራጮችን በመድረክ ላይ በማቅረብ፤ ልዩነቶችን እንድንመረምርና፤ በብዙኀኑ ዓይን የተሻለ የተባለውን እንድንመርጥ ዕድል ይፈጥርልናል። በነዚህ የተለያዩ ሃሳቦች ተነስቶ ርስ በርስ መወነጃጀሉ፤ አንድም እኔ ያልኩት ብቻ ይሁን ባይነት ብሎም ራስን የማግዘፍ ጥንውት ነው። ሌላም ትግሉ መልክ ይዞ ወደፊት እንዳይሄድ እንቅፋት ለመሆን የተጠነሰሰ ሴራ ነው።
አክራሪዎች መኖራቸውንና የትግላችን አንዱ ገፅታ መሆኑን መቀበል አለብን። ይህ በቀኝ ይሁን በግራ፣ በፊት ይሁን በኋላ፣ ፈለግነውም ጠላነውም፤ ያለ ሀቅ ነው። ይህ የትግል አቅጣጫችን ሊቀይር ቀርቶ፤ ትኩረታችን ሊስብ አይገባውም። የሀገራችን የፖለቲካ እውነታ፤ ያደግንበትም ሆነ አሁን ያለው ተጨባጭ ሀቅ፤ መፈናፈኛ በማሣጣቱ፤ አክራሪዎች መፈጠራቸው፤ ሁኔታው የወለደው ክስተት ነው። እናም አክራሪ የምንላቸውን ለማጥቃት ወይንም ለማጥፋት ዓይኖቻችንን ከዋናው ግባችን መንቀል፤ ለራሳችን ጥቃት በሩን ለጠላት በርግደን መክፈታችን ነው። ትኩረታችን መሆን ያለበት ሰፊው ሕዝብ የሥልጣኑ ባለቤት የሚሆንበትን በመፈለግና ያን በመቀበል ላይ ነው። ብዙኀኑ የተቀበሉት ለስኬት እንዲበቃ፤ ጥረታችንን በሙሉ በዚያ ላይ ማረባረብ አለብን። በግራና በቀኝ ተፋሰሶች እያበጀን፤ ጉልበታችንን እኛው ራሳችን አናዳክም።
“አስቀድሞ መግደል አሾክሿኪውን ነው!” ብለው ቀደምቶቻችን ሲያስተምሩን፤ አሾክሿኪው የጠላት አንድ አካል መሆኑን፤ እነሱም ሆኑ ራሱ አሾክሿኪው ስለሚያምኑበትና ስለሚቀበሉት ነው። በተጨማሪም፤ እጅ ከፍንጅ መረጃው ስለተያዘ ነው። እኛ የያዝነው ግን፤ “እኔ የምለውን ያልተቀበለ፤ ‘ወያኔ’ ነው!” የሚል ጠባብ፣ ራስ ተኮር፣ እኔ ብቻ ነኝ አዋቂ ባይነትና ከሀገር በላይ ግለሰብን ወይንም የራስ ድርጅትን የሚያስቀምጥ አባዜ ነው።
ባሁኗ ሰዓት፤ በፖለቲካ ትግሉ መስክ፤ ባንድ በኩል የሀገር አንድነትን ፈላጊዎች፤ “ሀገር አቀፍ ትግል እንጂ ሌላ ምን ሲባል!” የሚል ምሽግ ሠርተናል። በሌላ በኩል ደግሞ በሀገር ውስጥ ባለው የፖለቲካ እውነታ በመመርኮዝ፤ “የለም፤ የአማራ ወጣቶችና የኦሮሞ ወጣቶች የትግሉን የበላይነት ጨብጠውታል። እናም ያን ሀቅ ተቀብለን፤ እኒህ ክፍሎች የሚቀራረቡበትንና የሚተባበሩበትን በመፈለግ፤ የወደፊቷን ኢትዮጵያ እንመሠርታታለን!” ባዮች አንድ ምሽግ ሠርተናል። ለኒህ ሁለቱ የትግል መስመሮች ጠላታችንም ግባችንም አንድ ነው። መንገዳችን ግን የተለያየ ነው። በርግጥ የትኛው የተሻለ ይሆናል የሚለውን፤ ሁለቱ ክፍሎች ቀርበን ለመነጋገር፤ አሁን ትልቅ ችግር ላይ ነን። የዜሮ ድምር ፖለቲከኞች፤ “ሌላው መታሰብ እንኳን የሌለበት ነው!” የሚል አቋም ያራምዳሉ። እንዲያውም ሁለቱም ክፍሎች በየጎራችን ጎድበን፤ አንዳችን ሌላችንን፤ ከወራሪው ፀረ-ኢትዮጵያ የትግሬዎች ቡድን የበለጠ ጠላት አድርገን በመፈረጅ፤ ለመጠፋፋት ተነስተናል።
እንግዲህ ሀቁ እንዲህ ነው። አስታራቂ ሽማግሌ ከየትም አይመጣም። እውነት የሕዝቡን ድል ፈላጊዎች ከሆን፤ ከባህላዊ ዘፈናችን አንድ ስንኝ ልዋስና፤ አስታራቂም የለን፤ እኛው እንታረቅ። የርስ በርሳችን መወነጃጀልና ጉልበታችን ለዚሁ ማጥፋት ማንን እንደሚረዳ፤ እኔ ለናንተ አልነግርም። አስቸጋሪ የሆነው ደግሞ፤ ይህ የታጋዮች በሁለት ጎራ መመሸግ፤ እየተከሰተ ያለው በቀጥታ ሳይሆን፤ በተዘዋዋሪና ትግሉን በቀጥታ በሚጎዳ መልክ ነው። መድረካችን በሳል የትግል ነጥቦችን በርጋታ የምንነጋገርበት ሕዝባዊ ስብስብ ሳይሆን፤ ፓልቶክና ፌስቡክ፣ ቲውተርና የየግል የሬዲዮ ስርጭት መሰምሮች ሆኗል።በመጀመሪያ ደረጃ፤ የፖለቲካ ልዩነት መግለጫና መነታረኪያ ባህላችን፤ ስድብ ማሽጎድጎድ ሆኗል። ብዙ በመሳደብ፤ የአቸናፊነት ሽልማት ለመቀበል መስገብገብ ይታያል። “ወያኔ!” ብሎ አንዱ ሌላውን አስቀድሞ ስለወነጀለ፤ ወንጃዩ የሕዝብ ወገን፤ ታርጋው የተለጠፈበት ደግሞ የጠላት ወገን የሆነ ይመስለዋል። አጉል ቅዠት ነው። ስድብ ስለ ቆሸሸውን የሰዳቢ አፍ ይናገራል እንጂ፤ የተሰዳቢውን ማንነት አይገልጽም። ይህ መጥፎ ባህል ነው። ይቅርብን።
አንዱ የመነጋገርያ ነጥብ የአማራውን መደራጀት የሚመለከት ነው። አማራው መደራጀት አለበት ብለው ያመኑና በዚሁ እምነታቸው የገፉ አሉ። ባለፉት ሃይ አምስት ዓመታትና አሁንም በአማራው ላይ እየደረሰበት ያለውን የዘር ማጽዳት ወንጀል በመንተራስና፤ የትግሬዎችን ቡድን የፖለቲካ ፍልስፍናና የአስተዳደር መመሪያ መረጃ በመያዝ፤ አማራው በሕልውና እንዲኖር፤ ተደራጅቶ መታገል አለበት! የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል። በሌላ በኩል ደግሞ አማራው መደራጀት የለበትም በማለት፤ “ትግሉ መካሄድ ያለበት በኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው!” የሚለውን ሃሳብ ሙጥኝ ብለው የተጣበቁ አሉ። በጄ! ይህን በተለያየ መልኩ ማየት ይቻላል። ነገር ግን፤ አንዱ ወገን የሌላውን ወገን ከመስማት ይልቅ፤ በራስ ጭንቅላት የፈጠሩትን ደጋፊ ወይንም ነቃፊ ነጥብ በማብጠልጠል፤ ከራስ ጋር ሙግት የተያዘበት ሀቅ ነግሷል። የሌላውን ነጥብ ማዳመጡ ቦታ አልተሠጠውም። አማራው ያለበት የዘር ማጽዳት አውነታ ለመቀየር፤ ማንኛውንም በማድረግ ሕልውናውን መጠበቅ እንዳለበት መረዳት ያስፈልጋል። ይህን እረዳለሁ ብሎ የተነሳን ደግሞ፤ ማንም ቢሆን ማን ሊያቆመው፣ ሊከለክለው ወይንም ሊቃወመው አይገባም። መቃወም ማለት በአማራው ላይ መዝመት ማለት ነው። ለዚህ ክፍል፤ ኢትዮጵያን ከማስብ በፊት፤ አማራው መዳን አለበት። ይህ አከራካሪ የመሆኑን አጥር ዘሏል። ስለዚህ፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ መሄዱ አስፈላጊ አይደለም። ይልቁንስ ለመረዳት መጣሩ ተገቢ ነው። ኢትዮጵያ እንዴት ትድናለች የሚለው ጥያቄ ያንገበገባቸው ሰዎች፤ ታጋዮችንና በሀገሪቱ ያለውን ሀቅ፤ የምርምራቸው መነሻ ማድረግ ይገባቸዋል።
ሁለተኛው መነጋገሪያ ነጥብ፤ ኢሳትን የተመለከተ ነው። ኢሳት የራሱ ግብ ያለው የግል ተቋም ነው። ባለቤት አለው። ኢሳት የኢትዮጵያ ሕዝብ ንብረት አይደለም። ውሎ አድሮ ለንግድ የተዘጋጀ ተቋም ነው። ስለዚህ ባለቤቱ የሚያዝበት እንጂ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያዝበት ተቋም አይደለም። ይህን ማለት፤ ኢሳት መጥፎ ነው ማለት አይደለም። ነገር ግን፤ ማንም ተነስቶ ይሄን ካላደረገ ወይንም ያንን ከላደረገ የሚልበት አለመሆኑን ለማስጨበጥ ነው። ማንም ግለሰብ ይህን የግል ተቋም፤ በግሉ ሊረዳ ይችላል። ማንም ግለስብ ደግሞ፤ በግሉ ይሄን የግል ተቋም ላይረዳ ይችላል። ነገር ግን ማንም ግለሰብ፤ ከባለቤቱ በስተቀር፤ ሊያዝበት አይችልም። ይህ መታወቅ አለበት። እናም ይሄን ይዘን፤ የግሉን ተቋም ለምን ይሄን አላደረገም ብሎ መወንጀል፤ ተገቢ አይደለም። ይህ በታጋዮች መካከል ለመጣላት ምክንያት ሊሆን አይገባውም። የኢትዮጵያዊያን ንብረት ቢሆን ኖሮ፤ ለምን እንዲህ ወይንም ለምን እንዲያ አላደረገም ብለን መናገር መብታችን ይሆን ነበር። አሁን ግን መብታችን አይደለም። ከወደድን እንደግፈው፤ ካልወደድንም ደግሞ እንተወው። በቃ።
ሶስተኛው መነጋገሪያ ነጥብ ደግሞ ትግሬዎችን የተመለከተ ነው። ባሁኑ ሰዓት፤ በሀገራችን ላለው የግፍና የስቃይ ውርጅብኝ፤ ተጠያቂው ወራሪው የትግሬዎች ቡድን ነው። ይህ ወራሪ ቡድን፤ በምንም መንገድ ይሁን በምንም፤ ትግሬዎችን ወክያለሁ ብሎ፤ በኢትዮጵያዊያን ላይ ግራና ቀኝ ጥፋት፤ በተለይም ደግሞ በአማራው ላይ የዘር ማጽዳት ወንጀል እየፈጸመ ነው። ይህን የሚፈጽመው፤ በአብዛኛው ትግሬዎችን በመሣሪያነት ይዞ ነው። በርግጥ ከሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች የሆኑ አንዳንድ ሆድ አደሮች፤ በግለሰብ ደረጃ፤ በባንዳነት እየረዱት ናቸው። እኒህ ሆድ አደሮች ይሄንን በሚያደርጉበት ሰዓት፤ ሕልውናቸውን ሸጠው፤ የዚሁ የወራሪው የትግሬዎች ቡድን አካልና አምሳል ሆነው ነው። እናም እነሱ ትግሬዎችም ባይሆኑ፤ የዚህ የወራሪው የትግሬዎች ቡድን አካል ናቸው። ስለዚህ ይህን ቡድን በምንም መልኩ ብናየው የትግሬዎች ቡድን ነው። አማራውን ለማጥፋት የተነሳው ይህ የወራሪው የትግሬዎች ስብስብ ነው። ኦሮሞዎችን እየገደለ ያለው ይህ የወራሪው የትግሬዎች ቡድን ነው። አኝዋኮቹን የጨፈጨፈው ይህ የወራሪው የትግሬዎች ቡድን ነው። ኦጋዴኖቹን የበደለው ይህ የወራሪው የትግሬዎች ቡድን ነው። እና ገና ለገና ትግሬዎች ይበደሉ ይሆናል በማለት፤ በውጪ ሀገር ያሉ “ታጋይ ነን!” ባይ ትግሬዎች፤ ጥብቅና ከትግሬው ቡድን ጋር አብረው ተሰልፈዋል። አልሸሹም ዞር አሉ ነው። ጠላት የማብዛትና የማሳነስ ስልት አይደለም። አሁንም፤ ዛሬ የዘር ማጽዳት ወንጀል እየተፈጸመበት ላለው አማራና ዛሬ ለሚያልቀው የኦሮሞ ወጣት ከመቆም ይልቅ፤ ገና ለገና በትግሬዎች ንብረት ላይ ጉዳት ይደርስ ይሆናል ብሎ የሚጮኽ፤ በምንም መለኪያ ቢታይ፤ የወራሪው የትግሬዎች አጥፊ ቡድን አካል እንጂ፤ የሕዝብ ወገን አይደለም። ጠላቱንና የትግል መስመሩን ለይቶ ያልተነሳ ታጋይ፤ የያዘውን ትግል አያውቀውም፤ ድሉም ምን እንደሆነ ስለማያወቅ፤ ለድል አይበቃም።
የያዝነው የምኞትና የፍላጎት ትግል አይደለም። በቦታው ያለውን ሀቅ ተቀብሎ፤ ያን ለማስተካከል የሚደረግ ትግል ነው። ወራሪው የትግሬዎች ፀረ-ኢትዮጵያዊያን ቡድን የሚታረቅ፤ የሚሻሻል፤ የሚታረም አይደለም። መሠረታዊ እምነቱ ኢትዮጵያዊነት አይደለምና! ከዚህ ቡድን ጋር እርቅ ለማድረግ የሚፈልጉና “ብዙ ሰው እንዳያልቅ!” እያሉ የሚያላዝኑ ሰዎች፤ ጎራቸው ከዚሁ ወራሪ ቡድን ጋር ይቀራረባል። ይህ ወራሪ ቡድን፤ ከትግራይ ውጪ ለሚያልቀው ወገን ደንታ የለውም። እየገፋበትም ነው። ይህን ቡድን በምንም መልኩ ለማዳን መሞከር፤ የዚሁ ቡድን ደጋፊነት ነው። አጥሩ ግልጽ ነው። ይልቅስ በታጋዩ ወገን ያለውን እናስተካክል። ለወራሪው ቡድን አሳቢዎች ብዙ አሉ። እኛ ለሱ መጨነቁን እንተወው። በአንድነት መታገሉን እስከወደድን ድረስ፤ ወደ አንድነት የሚወስደውን መንገድ እንከተል። በታጋዩ ጎራ ያለን ሁሉ፤ ወደ አንድ ለመምጣት ያለው በር አንድ ነው። ተቀራርቦ መነጋገር። እንዴት ወይንም መቼ ወይንም የት የሚለው፤ በሁለተኛ ደረጃ የሚከተል ነው። መጀመሪያ የአንድነቱን አስፈላጊነት መቀበል ነው። ይሄን ደግሞ ያልለፈለፈለት የለም። ታዲያ ቀጥሎ መገናኘት ነው። ለዚህ ጠሪው ብዙ አድማጩ ዜሮ ለሆነበት ትንግርት፤ እግሬን አስቀድሜ አነሳለሁ። እናም ውይይቱ ትናንት መሆን ቢኖርበትም፤ ትግሉ እየተካሄደም፤ ዛሬ ይቀጥል።

የሰው ሕይወትን እና፤ ንብረትን በጭካኔ ማቃጠል የወያኔ ግባ ከመሬት መጨረሻ ደወል!! –ጎንደር ህብረት ለኢትዮጵያ አንድነት (ጎሕ) – ልዩ መግለጫ

$
0
0

እስካሁን በታሪክ ያየናቸው አምባ ገነን መንግሥታት ገዥዎች፤ በጊዜ እና በአገር አበቃቀላቸው፤ የተለያዩ ይሁን እንጅ፤ በአፋኝነታችው፤ ለሕዝብና ለአገር ያላቸው ንቀት፤ ለሥልጣናቸውና ለግል ሐብታቸው ያላቸው ስግብግብ አቋቋም አንድ ነው። በሕዝብ ተገፍትረው ከሥልጣናቸው እስከሚወርዱ ድረስ በሚያገኙት አጋጣሚ ሁሉ ያላቸውን ሐይል በመጠቀም የሚቃወሟቸውን ሁሉ መጨፍጨፋቸው አይቀርም ።

File Photo

File Photo

በተመሳሳይ መልኩ፤ በአገራችን በኢትዮጵያ የተፈጠረው የትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር ኃይል፤ በአለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ትውልድና ታሪክ ያስተሳሰረውን ሕዝባችን በዘርና በቋንቋ ከፋፍሎ ሙሉ ለሙሉ በመዳፉ ሥር ለማድረግ እና የሥልጣን ጊዜውን ለማራዘም፤ በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠሩ ብርቀየ እና ተተኪ የሌላቸው ዜጎቻችንን ጨፍጭፏል፤ የአገሪቱን መዋዕለ ንዋይ ዘርፈዋል፤ ለውጭ ዘራፊ አሳልፈው በመስጠትም አዘርፈዋል። በጨለማ እስር ቤት ታጉረዉ በግርፋት ደማቸዉ የሚፈሰዉና በዘራቸዉ ተሰድበዉ ህሊናቸዉ የቆሰሉ በሚሊዮን የሚቀጠሩ ናቸዉ። እጅግ የሚያሳዝነዉ ደግሞ ህዝብ በቃችሁ ብሎ “እምብኝ አንገዛም” ሲል፤ በተሌብዥን መስኮት ብቅ ብለዉ የአገር መሪ መስለዉ “ስተት ልናርም ነዉ” እያሉ አሁንም ለማሞኘት መንግስት ነን ብለዉ መቅረባቸዉ፤ “የሌባ አይነ ደረቅ፤ መልሶ ልብ ያደርቅ” እንዲሉ፤ እንደ ሰው ማሰባችውን ያጠራጥራል።

የኢትዮጵያን ሕዝብ ምንም እንደማያስብ፤ እነሱ ደግሞ ከማንም በላይ ብልጥ እንደሆኑ አድርገው ነው የሚቆጥሩት። የሰሞኑ የካርታ እርማት እና የትቢታቸው ምልክት አንዱ፤የራስ ደጀንን ተራራ እና እስከ ወለጋ የአማራን መሬት ካራታ ቀርጸዉ፤ ሱዳንን እንደማያካልል ወደ ትግራይ አስምረዉ፤ ለአስር ዓመታት በካርታ መጽሐፋቸው አሳትመው ሲያስተምሩ መቆየታቸው የአደባባይ ሚስጥር ሁኖ ሳለ፤ ስህተት ነበር በሚል ቀልድ፤ በቀላሉ ሸውደውን ለማለፍ ሞክረዋል። ከተከዜ ምላሽ ወረራቸዉ ግን ጀሮ ዳባ ልበስ ብለዋል። “አለባብሶ ቢያርሱት፤ በአረም ይመለሱ” ነዉና የአማራ መሬት ጉዳይ በማጭበርበር የሚቀር አይደለም፤ ዘመቻ ተከዜ ይቀጥላ። የሕዝብ ጥያቄ መልስ የሚገኘዉ ደግሞ፤ ዘረኛዉ ወያኔ ቡድን ከስልጣን ሲወርድ ብቻ ነዉ።

አሁን ጥፋታችን ነዉ ብለዉ የሃሰት ካርታዉን መቅደዳቸዉ መልካም ቢሆንም፤ የወልቃይት ጠገዴን/ጠለምት ቃፍቲያ፤ ሁመራን መሬት ስርቆት ተሳስተናል ብለዉ፤ ካርታ ያለመሰረዛቸዉ ምክንያት፤ የጎንደር፤ ብሎም የመላ ኢትዮጵያን ህዝብ እጅግ ያስቆጣ መሆኑን አዉቀዉ ምላሽ አለመስጠታቸዉ ደግሞ፤ መላ የማይገኝለት እንቆቅልሽ ሳይሆን፤ እጅግ አላዋቂነት፤ የአጥፍቶ ጠፊነት ድርቅና ነዉ።
ሌላዉ አስደንጋጩ እና ወያኔን ሰዉ ነዉ ብለዉ ለሚያምኑ ግብዞች እርማቸዉን እንዲያወጡ ምስክር የሆነዉ፤ በጠራራ ጸሃይ የሰረቁትን መሬት አስተካከልን ባሉ ማግስት፤ ከዘረፋ የተረፈዉን የአማራን አገር አቃጥለዉ ምድረበዳ ለማድረግ፤ በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆችን መልምለው፤ እያንዳንዳቸውን ዘጠኝ መታወቂያ ካርድ አሳቅፈዉ በመላ ኢትዮጵያ ለጥፋት ማሰማራታቸዉ ነዉ። ለዚህም ጎንደር ቅዳሜ ገቢያን፤ የባታ ወህኒ ቤትን፤ የደብረታቦር እና የቅሊንጦ እስርቤትን አቃጥለዉ፤ እንደገና ደግሞ፤ ሰሞኑን፤ ጎንደር የቀሩ ንግድ ቤቶችን በእሳት ለማዉደም፤ ቤንዚን ይዘዉ ሲጣደፉ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል።

በአጠቃላይ፤ የወያኔ አዉሬነት፤ በየትኛዉም ዘመን ካሳለፍናቸው መንግሥታት ጋር የሚነጻጸር አይደለም። ቅኝ ገዥዎች በተለያዩ አገሮች የፈጸሙትን የጭካኔ አይነት በከፋ መልኩ በሥራ ላይ እያዋሉት ይገኛሉ። ሮዴዣንና ደቡብ አፍሪቃን በቅኝ የገዙ ነጮች በጥቁር አፍሪቃዊያን ላይ ካአደረሱት በደለ ጋር ሲነፃጸር፤ ወያኔ አሁን በህዝባችን ላይ እያደረሰ ያለው እጅግ የከፋ ነዉ። አነጣጥሮ የተነሳውም፤ ከራሱ ብሔረሰብ ውጭ ያለውን፤ ሁሉ፤ እርስ በርስ በማባላት ነው። ይህ አንድን ዘር በሌላው ለማጥፋት የሚደረግ አረመኒያዊ እርምጃ ደግሞ፤ ሂትለር በጅዊሾች ላይ ከወሰደው አሰቃቂ የዘር ማጥፋት እርምጃ ተለይቶ አይታይም።

በብዙሃን መገናኛ ስህተታችን እናርማለን እያሉ፤ በሌላ በኩል ግን፤ የፖለቲካና የህሌና እሰረኞችን፤ በጥይት ደብድበው እሬሳቸውን በእሳት አቃጥለዋል። በዚህ ምክንያት ልባቸን በኃዘን የተሰበረው ልባቸን ሳይፅናና፤ በአገራቸን ብቻ ሳይሆን፤ የዓለም ቱርሪስቶችን ጭምር በውበቱ የሚያስደንቀውን፤ የእሪቻ ባህል በሚያከብሩ የኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ ሌላ በእምነትም ሆነ በሰባአዊነት ሊታመን የማይችል እና የሚዘገንን ጭካኔ የተሞላበት ታሪክ የማይረሳው አረመኔያዊ፤ የጭፍጨፋ እርምጃ በመፈፀም እጅግ ብዛት ያላቸውን የወገኖቻችን ህይወት ቀጥፈውዋል።

ከዚህ በላይ ከተዘረዘሩት የበለጠ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ የወያኔን አዉሬነት ያወቀዉ ቢሆንም፤ ከወያኔ ግፍ ባልተናነሰ መልኩ፤ የኢትዮጵያውያንን ልብ እያደማችሁ ያላችሁ፤ አማራን እንወክላለን የምትሉ የብአዴን /ወያኔ ጉልት አመራሮች፤ አሁንም፤ የመጨረሻዋ የፍፃሜ ደወል፤ ሳታቃጭል፤ የጥፋት ደሞዝ እና ስልጣን ይቅር ብላችሁ በአስቸኳይ ከህዝብ ጎን ትቆሙ ዘንድ ጎንደር ሕብረት ያሳስባል።
ዛሬም እንደ ትናንቱ! ደግመን ልናስጠነቅቅ እንወዳለን። የአማራዉ መለዮ ለባሾች፤ በአዋቂ የዕድሜ ክልል ያላችሁ ወገኖች፤ አገራችሁን እና ሕዝባችሁን፤ ከወያኔ ግፍ እና በደል ለማላቀቅ የምትሹ አርሶ አደሮች! በአጠቃላይ ማንነታችሁ፤ በወያኔ ማናለብኝነት፤ የተረገጠ እና የተናቀ ዜጎቻችን በሙሉ! በአሁኑ ሰዓት በወያኔ ማስፈራራት ትጥቃቸዉን ብትፈቱ! ወያኔ እንደ ዶሮ በያላችሁበት አንድ በአንድ እያረደ እንደሚጨርሳችሁ ከወዲሁ ተረዱ።

በመጨረሻም የጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት ፤ በዉጭ አገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ወዳጆቻችን በሙሉ በአክብሮት የምናስተላልፈው መልክት አለን። የመልክታችንም መነሻ፤ ወያኔ በህዝባችን እና በወገኖቻችን ላይ እያደረስ ያለው አስከፊ በደል እና ግፍ እጅግ ውስብስብ እየሆነ በመምጣቱ የመፍትሔው አካል ለመሆን ቆርጠን በመነሳታችን ነው። ስለዚህም፤ የሕዝብን እና የአገርን ጥቅም ቀዳሚ አድርገን በህብረት ከሰራን ጠንካራ የህዝባዊ ትግል አጋር እንሆናለን የሚል ፅኑ እምነት አለን።

ስለሆነም የፖለቲካ ድርጅቶች፤ ብዙሃን ማህበራት፤ የሃይማኖት ተቋማት፤ታዋቂ የመብት ተከራካሪ ግለሰቦች፤ የብዙሃን መገናኛ ተቋማት እና ለህዝባችሁ ድምጽ ሆናችሁ ሌተ ከቀን የምትሰሩትን ሁሉ ተመሳሳይ አቋም ይኖራችኋል ብለን እናስባለን።

ምክንያቱም፤ አገርም፤ ሕዝብም ሳይኖረን፤ የአላማ ራዕይ ሊኖረን ስለማይችል፤ ለመብቱ እና ለነፃነቱ፤ ሕይወት እየከፈለ ያለውን ሕዝብ ለመደገፍ እና የትግል ውጤቱን ለማረጋገጥ ያግዝ ዘንድ፤ የለጋሽ አገሮችን፤ የጨለማ ድጋፍ ቀልብ ለመግፈፍ፤ የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል የምትሉ ሁሉ፤ የጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት የጋራ አገራዊ መፍትሔ ለማፈላለግ፤ የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በአንድ ጥላ ሥር ተሰባስቦ በሕብረት እንዲቆም ይሻል።

በመሆኑም፤ ለዚህ አገራዊ እና ሕዝባዊ ሃላፊነት፤ ጥሪ በጎ አመለካከት ያላችሁ፤ በዚህ ጉዳይ ላይ እየሰራችሁ ያላችሁ ወገኖቻችን ሁሉ፤ አብረን እንድንመክር እና ለምክክሩ የሚያስፈልጉትን ማንኛውንም አይነት አስተዋፆኦዎች የድርሻችን ለማድረግ ዝግጁ መሆናችንን ልንገልጽ እንወዳለን።

ጎንደር ህብረት ለኢትዮጵያ አንድነት (ጎሕ)
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
Email: gonderhibret72@gmail.com | www.gonderhibret.org
September 30, 2016

ባልሽን አያርገኝ –መታሰቢያነቱ እሬቻ በዓል ላይ ለተገደለችው ወጣት

$
0
0

balshin
ከአያሌው መንበር

በእርግጥ ሁሉ አልቃሽ ነው ሀገር አዘንተኛ
ትውልድም ከንቱ ነው እንደወጣ ቀሪ የሌለው እረኛ
ግና ግና ግና እኔ እርሱን አያርገኝ የትዳር አጋርሽን
በህልሙም በውኑም የሚዳብስሽን
ውጥንሽ ሳይሰምር ህልሙም በአጭር ቀርቶ
እንዴት ይገፋዋል የቃል ኪዳን ሰነድ አብሮነቱን ትቶ???
በክንዱ ሊያንተርስ፣
በሎጋ ጣቶቹ ገላሽን ሊዳብስ
ከንፈርሽን ሳም አርጎ ፍቅሩን ለማጣጣም
አይኑን እያሻሸ ከእንቅልፉ ሲነቃ አንቺ ግን የለሽም
በውድቅት ሌሊት ገላሽን ሲዳብስ፤ ህልሙን ሊያጫውትሽ
ዳቢሎሱን መንግስት ባንቺ ቦታ አገኘው ከእቅፉ ሲነጥቅሽ

(መታሰቢያነቱ እሬቻ በዓል ላይ ለተገደለችው ወጣት

በምስራቅ ወለጋ የተደረገው ሕዝባዊ ተቃውሞው ቪዲዮ ይዘናል

$
0
0

በምስራቅ ወለጋ የተደረገው ሕዝባዊ ተቃውሞው ቪዲዮ ተለቋል
በምስራቅ ወለጋ የተደረገው ሕዝባዊ ተቃውሞው ቪዲዮ ይዘናል

ሙሽሪት በሠርጓ ላይ የይሁኔ በላይን “ሰከን በል”አስከፍታ የታስረናል ምልክትን በማሳየት ሕዝቤን አትግደሉት ስትል ተቃወመች

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ሙሽሪት ሠርጌ ላይ የሚዘፈነው የይሁኔ በላይ “ሰከን በል” የሚለው ዘፈን ነው በማለት ሙዚቃውን ካስከፈተች በኋላ በመንግስት ላይ ያላትን ተቃውሞውም እጆቿን ወደላይ በማጣመር ሕዝቤን አትግደል ስትል ተቃውማለች:: ይመልከቱት:: ቭዲዮውን የላከልልን Clear Photo & Video Production : 202-445-7769 እናመሰግናለን::ሜሮን መልካም የትዳር ዘመን ይሁንልሽ!!

ሕወሓት የማይወድቅባቸው የትግል ሥልቶች –ነፃነት ዘለቀ

$
0
0

tplf-ethiopian-leadersባሳለፍነው እሁድ በደብረ ዘይት የእሬቻ በዓል አከባበር ላይ በአጋዚ የወያኔ ቅልብ ጦር ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖቻችንን ነፍስ እግዚአብሔር ይማርልን፤ ከዚህች ዘግናኝ ቀን በፊትም ሆነ በኋላ በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች በዚሁ የወያኔ ጦር ያለቁና ወደፊትም የሚያልቁ ወንድም እህቶቻችንንና ልጆቻችንን መንግሥተ ሰማይን ያውርስልን፡፡ ፈጣሪ የነሱን መስዋዕትነት እንደአቤል ንጹሕ ደም ቆጥሮልን የነፃነታችንን ቀን ያፋጥንልን፡፡ የቤተሰባቸውንም ሆነ የሁላችንን የተሰበረ ልብ ይጠግን፡፡ አሁንስ እጅግ በጣም እየተጎዳን ነው፡፡

ወያኔ በምን እንደማይወድቅ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለይ ቁልጭ ብሎ እየታየ ነው፡፡

  1. በምንም ዓይነት መንገድ ወያኔ በጩኸት አይወድቅም፡፡ እርግጥ ነው ሰሚ ከተገኘ ጩኸት ብሶትንና ግፍን ለመግለጽ ይጠቅማል፡፡ በኛ የእስካሁኑ ሁኔታ ግን ሰሚ የለንምና ጩኸታችን አልጠቀመንም፡፡ ኢትዮጵያን ለማጥፋት የተሰማራው ኃይል ብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ ይዘት ያለው በመሆኑ “ዐውቆ የተደበቀ ቢጠሩት አይሰማም” እንዲሉ ሆኖ ለማንም ብንጮኽ ሰሚ አናገኝምና ትርፉ ድካምና ጩኸትን በከንቱ ማባከን ነው፡፡ የኛ ደም ውኃ ይመስል በየቀኑ እንደጎርፍ እየፈሰሰ በዋና ዋና የሚዲያ አካላት በስፋትና በጥልቀት የማይዘገብበት ምክንያት ሌላ ሣይሆን ጥፋትና ውድመታችን የታዘዘው ዓለምን ከተቆጣጠረው ዋናው የአጋንንት ኃይል በመሆኑ ነው፡፡ እንጂ አንድ የስዊድን ወይም የእንግሊዝ ዜጋ የወያኔ ወንድሞች ማለትም አይሲሶች ቢገድሉት ኖሮ የሣምንታት የዜና መክፈቻቸው በሆነ ነበር፡፡ እነዚህ ጉደኞች ከአምስት መቶ ሕዝብ በላይ በጠራራ ፀሐይ የታጨደበትን አሳዛኝ ዕልቂት በመኪና ተገጭቶ የሞተ አንድ የአውሮፓ ውሻ ያህል እንኳን አልቆጠሩትም፡፡ ለይስሙላ ግን “In God we trust.” እያሉ በፈጣሪ ኅልውና ሲያላግጡ አያፍሩም፤ የሥራቸውን ይስጣቸው እንጂ ምን ይባላል፡፡ ለነገሩ ከሞላ ጎደል ሁሉም የዘሩትን እያጨዱ ነው፤ ወደፊትም ይህ የፈጣሪ ፍርድ በነሱም ላይ አይቀርም፡፡ ማንም የሥራውን ያገኛል፡፡
  2. በምንም መንገድ በሰላማዊ ሰልፍ ወያኔ አይወድቅም፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ ጊዜ ማባከኛ ነው፡፡ 25 ዓመት ተሰልፈን ያመጣነው ለውጥ የለም፡፡ “ደግሞ ጀመራቸው!” ከማስባልና ለዘመናት የተተከለን ጠባይ ከማሳየት ውጪ ምንም አልፈየደም፡፡ ሰልፍ የሚሠራበት ሀገር አለ፤ ለኛ ግን አይሠራም፡፡
  3. በምንም መንገድ ሕወሓት በድርድር አይወድቅም፡፡ ወያኔ ዘንድ ሰጥቶ መቀበል ብሎ ነገር የለም፡፡ የወያኔ ጠባይ ጨርሶ ማጣት ወይም ጠቅልሎ መውሰድ እንጂ የቁጥ ቁጥ ነገር አይዋጥላቸውም፡፡ አንድም የሕዝብ ጥያቄ በአወንታ መልሰው የማያውቁት ጥያቄን በአግባብ መመለስን እንደመሸነፍ ስለሚቆጥሩት ነው፡፡ ለምሣሌ ሁለትና ሁለት ሲደመር ስንት እንደሚሆን ወያኔዎችን ብትጠይቋቸው ሦስት ወይም አምስት ይሉ ይሆናል እንጂ እቅጩን “አራት ነው” አይሉም፡፡ ምክንያቱም በትክክል መመለስ ጠያቂን እንደሚያስደስት ስለሚያምኑና ያንንም ለነሱ እንደሽንፈት ስለሚቆጥሩት ነገረ ሥራቸው ሁሉ ጠማማ ነው፡፡ ይህ ጠባያቸው የሚያሳየን አእምሯቸው ያልሠለጠነና በዕድገቱ ከእንስሳትም በታች መሆኑን ነው፡፡ ስለሆነም ከወያኔ ጋር ተደራድሬ ሀገሬን ነፃ አወጣለሁ የሚል አካል ቢኖር ራሱም ያበደ ነው፡፡ ወይም ወያኔ ጊዜ ገዝቶ ከጭንቀቱ እስኪገላገልና አንዳች ዘዴ ፈልጎ እስኪያጠፋው በመሣሪያነት ሊያገለግል የወደደ ጊዜያዊ የሥልጣን ፍርፋሪ የሚፈልግ መሆን አለበት፡፡ እርግጥ ነው ወያኔ በጣም ሲጨነቅ ከነልደቱ አያሌውና ከነፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ዓይነቶቹ የሥልጣን ጥመኞች ጋር ሊደራደር ይችል ይሆናል፡፡ እነዚህ ወገኖች በሥልጣን አራራ ሰለባነት የሚታሙና በኅብረተሰቡ ዘንድ በብርቱ የሚወቀሱም በመሆናቸው ለወያኔ የተወሰነ እፎይታ ለመስጠት በመናጆነት ሊያገለግሉ ቢሞክሩ አይገርምም – ጊዜና ዕድል ከገጠማቸው ሊያውም፡፡
  4. በምንም መንገድ ወያኔ በምርጫ አይወድቅም፡፡ ይህ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ምርጫን በማንአለብኝነትና በጀብደኝነት በማጭበርበርና ኮረጆን በመገልበጥ የሚታወቁ ወያኔዎችን በምርጫ አሸንፌ ሥልጣን እረከባለሁ ማለት ከጅብ መንጋጋ ሥጋ ለመቀማት እንደመሞከር ያለ ቂልነት ነው፡፡ ይህ በፍጹም አይታሰብም፡፡
  5. በምንም መንገድ ሕወሓት በምዕራባውያን ተፅዕኖ አይወድቅም፡፡ ሞልቃቃ ልጃቸው ስለሆነ ሰሞኑን በደብረ ዘይትና በሌሎችም አካባቢዎች እየታዘብነው እንደምንገኘው በጠራራ ፀሐይ ሚሊዮኖችን እንደዐይጥ ቢጨፈጭፍና የዘር ማጥፋት ወንጀል ቢፈጽምም በሞራል ከማበረታታትና የገንዘብ ድጋፍ ከመለገስ ባለፈ ፊቱን የሚያዞርበት አንድም ምዕራባዊ ሀገር አይኖርም፡፡ ምክንያቱም ከፍ ሲል ለመጥቀስ እንደተሞከረው የኢትዮጵያ ጥፋትና ውድመት የተቀነባበረው በነዚህ ልዝብ ሰይጣናት የምዕራቡ ዓለም የደኅንነት ተቋማትና በዐረቦችም ጭምር የወልና የተናጠል ድጋፍ ነውና፡፡
  6. በምንም መንገድ እዚያና እዚህ በሚደረግ ያልተቀናጀ ሕዝባዊ እምቢተኝነት ወያኔ አይወድቅም፡፡ በዘርና በጎሣ እንዲሁም በሃይማኖት በተከፋፈለ ሕዝባዊ ዐመፅ ወይም የእምቢተኝነት ንቅናቄ ወያኔ ይወድቃል ብሎ ማሰብ የወያኔን ተፈጥሯዊ ጠባይ ካለመረዳት የሚመነጭ ሞኝነት ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ ነገር ለወያኔ ሥራ ያበዛበት እንደሆነ እንጂ፣ የመቆያ ሥልቶችን እንዲያሰላስል ዕድል ይሰጠው እንደሆነ እንጂ፣ ከችግሩ መውጫ ቀዳዳ እስኪያገኝ ድረስ ለተወሰነ ጊዜ ትንሽ እንዲጨነቅ ያስገድደው እንደሆነ እንጂ ከአራት ኪሎ ቤተ መንግሥት አያስወጣውም፡፡ እንዲህ ዓይነቱ የተነጣጠለ ትግል ለአደጋና ዕልቂት የሚጋብዝ እንጂ ውጤት የለውም፡፡ በዘመናት የመከራ ኑሯችን የተፈተነ ሃቅ ነው፡፡
  7. በምንም መንገድ በጋዜጣዊ መግለጫና በፉከራ አይወድቅም፡፡ ወያኔዎች ምሥጥ ናቸው፡፡ ዕድሜ ለላኪዎቻቸው የትም ሆነህ ብትቃወማቸው ክንዳቸው ረጂም ነው፤ ባለህበት ይመጡልሃል፡፡ አንተን የመሰለ ሰው አስርገው ይልኩብሃል፡፡ እናም እንኳንስ በጋዜጣዊ መግለጫና በፖለቲካዊ ጫጫታ ይቅርና በተደራጀ ጦርም እነሱን በቀላሉ ማንበርከክ አስቸጋሪ ነው፤ ጨርሶ አይቻልም እያልኩ ግን አይደለም፡፡ ገንዘባቸው፣ ስለላቸው፣ በአባቶቻቸው የሚደረግላቸው የመረጃና የበጀት ድጋፍ፤ በጥቅም፣ በዘርና በቋንቋ ሰውን መከፋፈላቸው፣ እኛን የሚመስለው የሰውነትና የቋንቋ እንዲሁም ሌላው ቅርጻቸው የኛን ትግል እጅግ ከባድና ውስብስብ ያደርገዋል፡፡ በዚያ ላይ ብዙ ተቃዋሚዎቻቸው ወያኔዎችን ይንቃሉ፡፡ እንደውነቱ ከሆነ በዋናነት ወያኔን የጠቀመው የነሱ ሸረኝነትና የኛ እነሱን መናቅ ነው፡፡ እነሱ እያደቡ ዕቅዳችንን ሁሉ ሲያከሽፉ እኛ ደግሞ ስንፎክርና በመግለጫ “ድባቅ ስንመታቸው” ይሄውና ሩብ ምዕተ ዓመት ዘለቅን – ሁነኛ የማስወገጃ ሥልቱን በቶሎ ካልነቃንበት ደግሞ ምዕተ ዓመቱን ይደፍናሉ፡፡ አሁን አሁን ግን ሕዝቡ ቀደመና መቆሚያ መቀመጫ እያሳጣቸው ይገኛል፡፡ የነሱ ተንኮል ማርከሻ ይህ ዓይነቱ መነሻው እንጂ መድረሻው በውል የማይታወቅ ሕዝባዊ ቁጣ ነው፡፡ ብልህ ሰው ታዲያ ያስፈልገናል፡፡ ይህን ሕዝባዊ እምቢተኝነት ወያኔዎች ብቻ ሣይሆኑ አለቆቻቸውም ይፈሩታል፡፡ ለምን ቢባል የሕዝብ ዐመፅ የት ጀምሮ የት እንደሚያልቅ አይታወቅም፡፡ የወያኔ ጌቶች ወያኔንና መሰል አሸባሪ ድርጅቶችን ጠፍጥፈው ሲሰሩ በርቀት መቆጣጠሪያ ሳይቀር እየተከታተሉ የሚያሸክሟቸውን ተልእኮ ተፈጻሚነት ያረጋግጣሉ፡፡ ሕዝባዊ እምቢተኝነት ግን ከነሱ ዓላማና ፍላጎት ሊወጣ የሚችልበት አጋጣሚ ብዙ ስለሆነ ይፈሩታል፤ ፊት ለፊት ሊጋፈጡትም ብዙውን ጊዜ አይደፍሩም፡፡ ስለዚህ ይህን የትግል ዓይነት ገፋ አድርጎ መቀጠል ተገቢ ነው፡፡
  8. በምንም መንገድ በስደተኞች ብዛትና ሀገርን ለወያኔ ለቅቆ በመሄድ ወያኔ አይወድቅም፡፡ ይህ ዓይነቱ ነገር ሳይዋጉ እጅን እንደመስጠት ነውና በሀገር ውስጥ ሆኖ መታገል አማራጭ የለውም፡፡
  9. በምንም መንገድ በማዕቀብና ዕቃና አገልግሎት ከሕወሓት ባለመግዛት ወያኔ አይወድቅም፡፡ ምክንያቱም በቂ የሀብት ክምችት አላቸው፤ ሁሉ በጃቸው ሁሉ በደጃቸው – ምን ሲጎድልባቸው፡፡ ሕወሓት ሀገሪቱን ላለፉት 25 ዓመታትና ከዚያም በላይ ለሚቆጠር ጊዜ በብቸኝነት ሲበዘብዝ በመክረሙ የገንዘብም ሆነ የማቴሪያል ችግር ሳይኖርበት ብዙ ዓመታትን መዋጋት የሚያስችለውን አቅም አጎልብቷል፡፡ ስለዚህ ከነሱ ዕቃ ባለመግዛት የምንጎዳቸው ነገር የለም፡፡ ዳሸን ቢራቸውን ባትጠጣ፣ ጨዋቸውን ባትገዛ አይጎዱም፡፡…
  10. በምንም መንገድ ወያኔ ሥልጣንን በፈቃዱ አይለቅም፡፡ ብሔራዊ ስሜት ቀርቶ የሰውነት ደረጃም የሌላቸው የለየላቸው ዕብዶችና ሰካራሞች በመሆናቸው የሀገሪቱና የሕዝቧ ችግር ገብቷቸው ሥልጣናቸውን ለሽግግርም ይሁን ለቋሚ የሕዝብ ተመራጭ መንግሥት ሊያስረክቡ አይችሉም፡፡ ትግራይንና የትግራይን ሕዝብ በሆነ ኮሮጆ ውስጥ ይዘህ “ይህን ኮሮጆ እሳት ውስጥ ከምጨምረውና ሥልጣናችሁን ከምትለቁ የትኛውን ትመርጣላችሁ?” ብለህ ብትጠይቃቸው ወያኔዎች ሥልጣናቸውን እንደሚመርጡ ግልጽ ነው፡፡ ትግራይንና ተጋሩን ይቅርና በሚስትና በልጆቻቸው ሳይቀር ቁማር የሚጫወቱ የብዔል ዘቡል ደቀ መዛሙርት ናቸው፡፡ የሚገርም ተፈጥሮ እኮ ነው ያላቸው!

ስለዚህ መፍትሔው ምንድን ነው ቢባል መልሱ በበኩሌ እንዲህ ይመስለኛል፡፡

ሁሉም ከተሞችና የገጠር ቀበሌዎች በአንድ ወቅት ተባብረው በመነሣት በየአካባቢያቸው የሚመጣውን የወያኔ ጦር ቢቻል መማረክና ማስተማር፣ ያ ባይቻል አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ በቁጥጥር ሥር ማዋልና ለፍርድ ማቅረብ፡፡ ዕቃና ንብረት እየዘረፉ የሚያሸሹባቸውን መንገዶች ሁሉ መዝጋት፤ የጎበዝ አለቃ እየመረጡ ትግሉን በአንድ ጊዜና በሁሉም ሥፍራ ማጧጧፍ፡፡ የወያኔ ወታደራዊ ክንድ ከተመታ፣ በተለይም አጋዚ የሚባለው የሰይጣን መንጋ ከተበተነ ሕወሓት ምንም አቅም አይኖረውምና በፍጥነት ይፍረከረካል፡፡ ያኔ ከያካባቢው የሕዝብ ተወካዮች ተመርጠው ትልቅ ሀገራዊ ስብሰባ በማካሄድ ከታዋቂ ጤናማ ፖለቲከኞችና ታዋቂ ግለሰቦች እንዲሁም የሕዝብ እምነት ከሚጣልባቸው ተቃዋሚዎች የሚውጣጡ ዜጎች ያሉበት የአደራ መንግሥት ማቋቋም፡፡ ያ የዐደራ መንግሥት ለሁለት ዓመታት ያህል ሀገሪቱን ካረጋጋ በኋላ በእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት አዲስና ለሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል የሚያለግል መንግሥት መመሥረት፡፡ ስንታገል ደግሞ በአንድነት እንጂ ዘርና ጎሣ፣ ሃይማኖትና ክልል ለይተን መሆን የለበትም፡፡ እንደዚያ ካደረግን የወያኔን ፈለግ እንደመከተል ያለ ከንቱነት ነው፡፡ አሮጌው ወይን በአዲስ አቅማዳ ከተገለበጠ ጥፋትን በጥፋት መተካት ነውና ካለፈ ጠመዝማዛ ሕይወታችን መማር አለብን፡፡ ስለዚህ ትግሬን ከዐማራ፣ ኦሮሞን ከሶማሌ፣ ከምባታን ከአፋር … አንዱ ከሌላው ሳይለያይ የአንዲት ሉዓላዊት ሀገር ሕዝብ ባንድ ልብና ባንድ መንፈስ መታገል ይኖርበታል፡፡ ወያኔዎች በተለይ ትግሬን ከሌላው ለመለየትና በሌሎች ጉዳት እንዲደርስበት በማድረግ ከነሱ ጋር ለመለጠፍ የሚያካሂዱትን የቀቢፀ ተስፋ ሸርና ተንኮል ነቅተን መጠበቅ አለብን፡፡ የወያኔን ሤራ በንቃት መከታተልና ሆን ብለው እሳት የሚለኩሱትን የሰውና የንብረት ቃጠሎ ጨዋታ ሁሉ ሳይቀር እየተከታተልን ማጋለጥ አለብን፤ ለመሠሪ ተልእኮ የሚጭሯቸውን ግጭቶች እየተከታተልን እውነቱን በወቅቱና አደጋ ሳያስከትሉ ይፋ ማድረግ አለብን፡፡ ሟች ይዞ ይሞታልና እነሱ ሥልጣናቸውንና ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ የማያደርጉት ነገር አይኖርም፡፡ እኛን ለመለያየትም የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡ መለያየትን ደግሞ እስኪያንገሸግሸን አየነው፤ ክፉኛ ጎዳን እንጂ አልጠቀመንም፡፡ መኖር ከፈልግን እንግዲህ ማድረግ ያለብን እንደዚህ ነው፡፡ ሁሌ መሞኘት የለብንም፡፡ በመሠረቱ ብልጥ ከአንዴ በላይ መብለጥ አልነበረበትም፡፡ እኛ ግን የሆንነውን ሳናውቀው ዕድሜ ልካችንን በነዚህ ሰይጣኖች ስንታለልና ስንበለጥ ኖርን፡፡

እንጂ እንዳሁኑ አካሄዳችን ከሆነ ሶማሊያና ሦርያ በስንት ጣማቸው የሚያስብል አስቀያሚ ሁኔታ እንደሚፈጠር በጣም ግልጽ ነው፤ የሚደርስልን ደግሞ እንደሌለ መረዳት ይገባል፡፡ ወያኔዎች አያያዛቸው “የምፅዓት ቀን ለምን ዘገዬ?” እያሉ ለአባታቸው ለዲያቢሎስ ከፍተኛ ተማፅኖ በማቅረብ ላይ የሚገኙ ይመስሉኛል፡፡ ዱሮውን የታወከን ሀገር በብልሃትና በዘዴ እንደማረጋጋት ቦሃ ላይ ቆረቆር እንዲሉ በሰላም በዓልን በሚያከብር በሚሊኖች የሚቆጠር ሕዝብ ላይ ከመሬትና ከሰማይ ጥይት ማዝነብ በየትኛውም ሥሌት ትርጉም የለውም፡፡ እነዚህ ድፍን ቅሎች የጥጋብ ሞራ ሁለመናቸውን ስለጋረደው የሚያደርጉት ነገር ምን ሊያስከትል እንደሚችል ማሰብ አልቻሉም፤ ተፈጥሯቸው ሁሌም በተቃርኖ የተሞላ ነው – “እንብላ” ሲሏቸው “እንተኛ” ዓይነት፡፡ ገና ለገና የላኳቸው የጥፋት ኃይሎች በሁሉም ረገድ አይዟችሁ ስላሏቸው ብቻ ምድራችን ዐይታውም ሆነ ሰምታው የማታውቀውን የክፋት ሥራ በኢትዮጵያውያን ላይ ይፈጽማሉ፡፡ በመጨረሻው የሚያስደስተው ነገር ግና – በማንም ላይ ሊደርስ በሚችል ስቃይ መደሰት ተገቢ ባይሆንም – የሠሯትን ሁሉ አንድ ባንድና በዕጥፍ ድርብ የሚያወራርዱ መሆናቸው ነው፤ ያም ቀን ደርሷል፡፡

እንደማሣረጊያ – ያገሬ ባላገር ምን አለ?

የማን ቤት ፈርሶ የማን ሊበጅ፤

ያወሬ መፈንጫ ይሆናል እንጂ፡፡

እባክሽ እናቴ ውለጅ መንታ መንታ፤

ቀኝ እጄ ሲመክት ግራ’ጄ ተመታ፡፡

እዚያ ማዶ ሆኖ አንድ ሰው ተጣራ፤

እዚህ ማዶ ሆኖ አንድ ሰው ወይ አለው፤

ጎበዝ ተጠራጠር ይህ ነገር ለኛ ነው፡፡

በዓለም ገና የአላሙዲን ስሚንቶ ፋብሪካ መኪናዎች ወደሙ –ቦሌ ሩዋንዳ አካባቢ መንገዶች ተዘጋግተዋል

$
0
0

Zehabesha-News.jpg(ዘ-ሐበሻ) ከሆለታ ወደ አዶስ አበባ እንዲሁም ወደ አምቦ የሚወስደው መንገድ በተቃውሞ የተነሳ መዘጋጋቱ ተሰማ:: በዓለም ገና የተነሳው ሕዝባዊ አመጽ ተቀጣጥሎ የአላሙዲን ንብረት የሆኑት የደርባን ሲሚንቶ ፋብሪካ መኪናዎች መውደማቸውን ከስፍራው ለዘ-ሐበሻ የደረሱ መረጃዎች አመልክተዋል::

እንደመረጃው ከሆነ በዓለም ገና የተቀጣጠለው ሕዝባዊ አመጽ ከቁጥጥር ውጭ ሆኗል:: በዓለም ገና ከሚገኘው የመንገዶች ባለስልጣን መስሪያ ቤት የትግራይ ነጻ አውጪ ወታደሮች ቤዝ አድርገው በሕዝብ ላይ እየተኮሱ ቢሆንም ሕዝቡ ግን እርምጃውን በመውሰድ ላይ ይገኛል::

ይህ በ እንዲህ እንዳለ በአዲስ አበባ ቦሌ መንገድ ከሩዋንዳ ጀምሮ መዘጋጋቱና ማንም ሰው ወደ አየር መንገድ መሄድ እንዳይችል መደረጉ ተሰምቷል::

ሕዝባዊው አመጽ ለ4 ኪሎው ቤተመንግስት 25 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ደረሰ –የአቃቂ ቃሊቲ ሕዝብ ተነሳ –መርካቶ ሱቆች እየተዘጉ ነው

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በዛሬው እለት በሃገሪቱ እየተደረገ ያለው ሕዝባዊ ቁጣ ወደ አራት ኪሎ ቤተመንግስት እየተጠጋ ነው:: በአቃቂ ቃሊቲ እጅግ በረካታ ቁጥር ያለው ሕዝብ አደባባይ በመውጣት እምቢተኝነቱን እያሳየ ሲሆን መንገዶች ሁሉ እየተዘጋጉ ይገኛሉ::

ከ4 ኪሎው ቤተመንግስት 25 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው አቃቂ ቃሊቲ አካባቢ ሕዝብ አንገዛም ከማለቱ በተጨማሪ ሙሉ በሙሉ ንግድ እና ትምህርት ቤቶች መዘጋጋታቸው ተሰምምቷል:: የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት በሕዝብ ላይ እርምጃ ቢወስድም ሕዝቡ ግን በጥንካሬ ተቃውሞውን በመግለጽ ላይ ይገኛል::

ይህ ሕዝባዊው አመጽ ወደ ሃና ማሪያም እና መርካቶ አካባቢም የተዳረሰ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በመርካቶ ሱቆች በመዘጋጋት ላይ ይገኛሉ:: በኢትዮጵያ በተለይም በኦሮሚያ ከተሞች ውስጥ ያለው ሕዝባዊ አመጽ ከትግራይ ነጻ አውጪው መንግስት ቁጥጥር ውጭ እየሆነ መሆኑን የሚገልጹት የዜና ምንጮች በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ቦታውን ለቆ ካልወጣ መፍትሄ እንደማይገኝ ይናገራሉ::
Zehabesha-News.jpg

አዲስ አበባ በፍርሃት ተሰንጋለች -ዋዜማ ራዲዮ-

$
0
0

12ስዓት የተጠናቀረ/የተከለስ

ከሜክሲኮ ጀሞ የታክሲ እጥረት ይታያል፡፡

የቤት መኪኖች በታክሲ የተቸገሩ እግረኞችን እየተባበሩ ነው፡፡

ረዣዥም የታክሲ ሰልፎች በመሐል ከተማ ቢኖሩም በቂ ታክሲዎች ግን የሉም፡፡

በአስኮ መስመር ከፍተኛ የፀጥታ ኃይል ፈሷል፡፡

በአስኮ መስመር ካታ በሚባል ሰፈር፣ ኦሮሚያን ከአዲስ አበባ የሚለያት ሳንሱሲ ሰፈር ከዚያም አልፎ በተለምዶ ሸክላ የሚባል አካባቢ፣ ከሸክላ ሰፈር አልፎ ከርታ የሚባል ሰፈር እንዲሁም ቡራዩ ከዋና መንገዶች ገባ ብሎ መጠነኛ የወጣቶች ስብስብና የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ታይተው ነበር፡፡ ኾኖም ማምሻውን ጋብ ብለዋል፡፡

በታጠቅ መስመር ጉጂና አሸዋ ሜዳ ነዋሪዎች የቃጠሎ ጭስ እንደተመለከቱ ለዋዜማ በስልክ ተናግረዋል፡፡ እየነደደ ያለው ምን እንደሆነ ግን ማወቅ አልቻሉም፡፡ ጉጂ ከዚህ ቀደም በተቀናጀው ማስተር ፕላን ምክንያት በተነሳው የኦሮሚያ አመጽ ምክንያት ተደጋጋሚ ግጭቶች ይቀሰቀሱበት የነበረ ሰፈር ነው፡፡ እነዚህ ሰፈሮች አብዛኛዎቹ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ከመሐል ከተማ ረዥም ርቀት ተጉዘው የሚኖሩባቸው ሲሆን ከፊሎቹም በጨረቃ ቤትነት የተያዙ ናቸው፡፡

ከጦርኃይሎች ጀምሮ በቤቴል ዓለም ባንክ ድረስ ምንም አይነት የተቃውሞ ምልክቶች አይታዩም፡፡ የጸጥታ ኃይሎችም በአካባቢው የሉም፡፡ ኾኖም ሱፐርማርኬቶችም ሆኑ መለስተኛ ሱቆች ተዘግተዋል፡፡ አልፎ አልፎ ከሚታዩ መዝናኛ ቤቶች በስተቀር የንግድ እንቅስቃሴ የለም፡፡ በመዝናኛ ቤቶች የሚታየው የሰው ቁጥር እንደወትሮው አይደለም፡፡

መጠነኛ ረብሻ በታየባቸው የአየርጤና፣ አለምገናና ፉሪ ሰፈሮች ማምሻውን ወጣቶች ሊታፈሱ ይችላሉ የሚል ወሬ በመነዛቱ ወላጆች ልጆቻቸውን ዘመድ ቤት ለማሳደር እየሞከሩ እንደሆነ በስልክ መረጃ ካቀበሉን ቤተሰቦች መስማት ችለናል፡፡

ፉሪ አደባባይ ላይ በዛ ያሉ ፖሊሶች ቆመው ቢታዩም በዋና መንገድ ላይ እየተካሄደ ያለ ምንም አይነት ተቃውሞ የለም፡፡

ከፉሪ ጀሞ ሁለት አልፎ መስታወት ፋብሪካውን አካባቢ በግምት 500 ሜትር ርቀት ላይ ወደ የስ ዉሃ ፋብሪካ በሚወስደው ጎዳና ከመንታ መንገዱ አንደኛው በድንጋይ ተዘግቷል፡፡

ከአስኮ እስከ ሳንሱሲ ታክሲ ቢኖርም ከዚያ በኋላ ወደ ቡራዩ ትራንስፖርት የለም፡፡ ከፍተኛ የወታደር ቁጥር የሚታየው በዚህ መስመር ሲሆን መትረየስ ደግነው የሚሄዱና በፌዴራሎች የተሞሉ ፒክአፕ ተሸከርካሪዎች በብዛት ይታያሉ፡፡ ወታደሮቹ የቤት መኪኖችን በግዳጅ እያስቆሙ ታክሲ ያጡ እግረኞችን እንዲሸኙ ያስገድዳሉ፡፡

11: 30 ስዓት የተጠናቀረ

የኮንትራት ታክሲ ዋጋ ንሯል፡፡
ሕዝቡ ወደቤቱ በጊዜ ለመግባት ጥድፊያ ላይ ነው፡፡
መሐል ከተማው የትራፊክ እንቅስቃሴው ተዳክሟል፡፡ ከከተማ ወጣ ያሉ ሰፈሮች የሚወስዱ መንገዶች መጨናነቅ ይታያል፡፡
መርካቶ ነጋዴዎች ሱቃቸውን ዘግተው መሄድ የጀመሩት ከ11 ሰዓት ጀምሮ ነው፡፡
እስከነገ ድረስ ነገሮች መልክ ካልያዙ ኢንተርኔት በዋና ከተማው ሊቋረጥ ይችላል እየተባለ ነው፡፡
በአዲስ አበባ መውጫዎች የጸጥታ ችግር መከሰቱ ከተሰማ ወዲህ በአዲስ አበባ ሰዎች ወደቤታቸው በጊዜ ለመግባት ሽርጉድ ላይ ናቸው፡፡ አየር ጤና፣ ፉሪ፣ አለምገና፣ ቡራዩ መለስተኛ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ታይተዋል፡፡ በተለይ ፉሪ ሁሉም የግል ባንኮች ከምሳ ሰዓት ጀምሮ ተዘግተዋል፡፡
በአንዳንድ መስሪያ ቤቶች ሰራተኞች በጊዜ ካልወጣን በሚል ከአለቆቻቸው ጋር አተካራ ዉስጥ መግባታቸው ተሰምቷል፡፡ አንዳንድ ሰዎች የታክሲ ሰልፍ ሲረዝምባቸው ኮንትራት ታክሲ ለ3 እና 4 ሆነው ሲኮናተሩ ተስተውሏል፡፡ ብዙ ሰዎች በስልክ የሚነጋገሩት በአዲስ አበባ የጸጥታ ችግር በየሰፈሩ መኖር አለመኖሩን ነው፡፡
አለምገና በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ወላጆች በፍጥነት ልጆቻቸውን መጥተው እንዲረከቧቸው ከትምህርት ቤቶች ስልክ ተደውሎላቸው ስለነበር ወላጆች በከፍተኛ ጭንቀት የትምሀርት ቤት በሮች ላይ ተኮልኩለው ታይተዋል፡፡ ፉሪ የኦሮሚያ ፖሊስ ዩኒፎርም የለበሱ የጸጥታ ኃይሎች ግራና ቀኝ ቆመው ይታያሉ፡፡ ባጃጅ የሚሰሩ አንዳንድ ወጣቶች ለምን እኛ እያመጽን እናንተ ትሰራላችሁ በሚል ሲያስቆሟቸው በአቅራቢያው የሚገኙ የኦሮሚያ የጸጥታ ኃይሎች ለማስቆም እንኳ ሙከራ ሲያደርጉ አይታዩም፡፡
ሜክሲኮና መርካቶ ረብሻ ተነስቷል የሚል ወሬ መናፈስ የጀመረ ቢሆንም አካባቢዎቹ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ ናቸው፡፡
ሦስት የጸጥታ ኃይል የጫኑ ካሚዮኖች ከማዘጋጃ ቤት እየወጡ በቸርችል ጎዳና ወደ ሚክሲኮ መንገድ ሲሆዱ ታይተዋል፡፡
አዳዲስ መረጃዎችን በቀጣይ ሰዓታት ይዘን እንቀርበለን

addis_abeba01_sam_effron

በዓለም ገና የጋየው የሕወሃት ንብረት የሆነው ከባድ መኪና ፎቶ ደርሶናል –በሰበታ እና በአስጎሪ የሕወሓት ፋብሪካዎች እየተቃጠሉ ነው

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ንብረትነቱ የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት የሆነውና በመስፍን ኢንጂነሪንግ የተገጣጠመው ከባድ መኪና ዛሬ በዓለም ገና ጋይቷል:: ሙሉ በሙሉ በ እሳት የጋየው ከባድ መኪና ፎቶ ከታች ቀርቧል:: በነገራችን ላይ የሕወሓት መኪኖችን ማቃጠል ዛሬ የተጅመረው አየር ጤና የነበረ ሲሆን አሁን ወደ ዓለም ገና ተሻግሯል::
በሰበታ እና በስግሪ እንዲሁም በሌሎች ከተሞች የህወሓት ፋብሪካዎች በተቆጣው ሕዝብ እየተቃጠሉ መሆኑ ተሰምቷል::

ይህ በ እንዲህ እንዳለ ስድስት ኪሎ ግብጽ ኢምባሲ ጎን በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ጊቢ ትርምስ መኖሩ ተሰማ:: በኦሮሞ እና የትግራይ ተወላጅ ወታደሮች መካከል አለመግባባት በመፈጠሩ በፌደራሉ ጊቢ ውስጥ ውጥረቱ አይሏል::
14572383_1090746660993562_1796869226746295138_n

ከመላዉ የኦሮሞ ህዝብ ጋር በተጋድሎ እና በፍቅር አብረን እንቆማለን

$
0
0

(ከኢትዮጵያዉያን ተጋድሎ የተሰጠ መግለጫ)
—————————————
በአለም ታሪክ እንደዚህ አይነት ወንጀል ከቶም ታይቶ አይታወቅም:: የሬቻ በዓል ለማክበር የተሰበሰበን ንጹህ እና ሰላማዊ ዜጋ በእግረኛ ሰራዊቱ እና በአ…የር ሀይሉ ተጠቅሞ የጨፈጨፈ ዘረኛ : ወንጀለኛ : አንባገነን እና በጥላቻ የተሞላ አናሳ ቡድን ከቶም በዬትኛዉም የአለማችን ክፍል ተከስቶ አያዉቅም:: ከወያኔ በቀር የዚህን አይነት ወደር የሌልዉ የዘር ፍጅት ወንጀል የሰራ ሀይል ከቶም እስካሁን በታሪክ ተዘግቦ አይገኝም::

ወያኔ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ኦሮሞዎችን ገድሎ ሌሎች በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩትን ደግሞ ማቁሰሉ እጅጉን የሚያበሳጭ እና የሚያስቆጣ ነዉ:: ስንቱ ኢትዮጵያዊ ዜጋችን ገደል እንደገባ: ስንቱ ወገናችን ባህር እንደሰጠመ እና ስንቱ የኦሮሞ ህዝብ ልጅ በትርምሱ እንደተጎዳ ገና አልታወቀም:: ወያኔም ይሄ እንዳይታወቅ ከፍተኛ አፈና እንደሚያደርግ ይታወቃል:: ይሄን ድርጊት መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ በጋራ ተነስቶ ማዉገዝ አለበት:: በጋራ ከኦሮሞ ወንድሞቻችን ጋር በመሆንም ለተጋድሎ መነሻዉ ወቅት አሁን ነዉ::

አንዱ አካባቢ እና አንዱ ማህበረሰብ ሲገደል ሌላዉ የሀገሪቱ ክፍል እና የማህበረሰብ ክፍል በዝምታ ዉስጥ ሆኖ ማስተዋያዉ ጊዜ ማክተም አለበት::ዛሬ እና አሁን ከመላዉ የኦሮሞ ህዝብ ጋር በተጋድሎ እና በፍቅር ለመቆም መነሳት አለብን:: መላዉ የአማራ ህዝብ ከኦሮሞ ወገኖቹ ጋር በተጋድሎ ለመቆም መነሻዉ ሰዓት አሁን ነዉ:: መላዉ የደቡብ ህዝብ: መላዉ የሶማሌ ህዝብ: መላዉ የአፋር ህዝብ እና በአጠቃላይም መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ተጋድሎዉን ከኦሮሞ ወገኖቹ ጋር በመሰለፍ ማጧጧፊያ ጊዜዉ አሁን ነዉ::

የዉስጥ ቅኝ ገዥ ሀይል ከሆነዉ የወያኔ ሀይል ኢትዮጵያን ነጻ ሳናወጣ እና ዲሞክራሲያዊት ሀገር ሳንመሰርት መቼም አናርፍም::

ሞት ለወያኔ !

የኢትዮጵያዉያን ተጋድሎ እስከ ነጻነት ይቀጥላል::
አንዲት ሀገር : አንዲት ኢትዮጵያ !
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቅ !

revolution-fists

የአፍሪካ ህብረት ወደ አሜሪካ ለሚጓዙ አፍሪካውያን ዜጎች እና ባለስልጣናቶች በአሜሪካ ጉዳይ ላይ ማስጠንቀቂያ ሰጠ። (የአመቱ ቀልድ)

$
0
0

(ዘ-ሃበሻ)የአፍሪካ ህብረት ወደ አሜሪካ ለሚጓዙ አፍሪካውያን ዜጎች እና ባለስልጣናቶች በአሜሪካ ጉዳይ ላይ ማስጠንቀቂያ ሰጠ።
ተቀማጭነቱን በአዲስ አበባ ያደረገው የአፍሪካ ህብረት ድርጅት በሰሜን አሜሪካ በፖሊሶች እና በጥቁር አሜሪካውያን ላይ በሚፈጸመው ግድያን አስመልክቶ በሰፊው በሃገሪቱ ላይ እየተዛመተ ነውእና በየትኛውም አቅጣጫ ስትጓዙ ጥንቃቄ ይገባችኋል ሲል ሃተታውን ጀምሮአል ።
ct8fm-vxyaamosm-jpg-large

ቁጥራቸው በዛ ያሉ የጦር መሳሪያ ያልያዙ ጥቁር አሜሪካኖችን ግድያ በየእለቱ እየተሰፋፋ ከመምጣቱም በላይ ለህዝቡ ሃይል እና ቦታ ሊሰጠው እንደሚገባ ፣እረፍትም ኣሜሪካ ፖሊስ ሊሰጣቸው እንደሚገባ በማተት በቻርሎቴ (ሰሜናዊ ካሎራይና) ውስካንስን (ሚልዋኪ) ዳላስ ቴክሳስ እና ታላላቅ ከተሞች እና ስቴቶች እየተፈጸመ ያለው ግድያ ውጤቱ እየተዛመተ ስለሆነ ተጓዦች ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸውል ሲሉ አትተዋል
የአፍሪካ ህብርት በጣም የተወሰነ የአደጋ ጊዜ የሚሆን አገልግሎት በአሜሪካ የሚሰጠው አገልግሎት በጣም ጥቂት በመሆኑ ተጓዦች ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል መጭውም የአሜሪካ ፕረዚዳንታዊ ምርጫ የሚካሄድበት ወቅት በመሆኑ አሜሪካ ከፍተኛ ዝግጅት እና ትኩረት እያደረገች ስለሚሆን አሁንም የአድን ወራት ያህል የቀረው የፕረዚዳንታዊው ምርጫ እስኪጠናቀቅ የአፍሪካ አምባሳደሮች ጉዞአቸው ጥንቃቄ የተሞላበት ይሁን ሲሉ አትተዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ይህ ተቀማጭነቱን በአዲስ አበባ ያደረገው የአፍሪካ ህብረት በሃገሪቱ ኢትዮጵያ ላይ ወያኔ መንግስት የሚፈጸመውን አሰቃቂ ግፋዊ ጥቃት ግን ከምንም ሳይቆጥረው ከ6 ወር አንድ ጊዜ በሚደረግ በጥቁር እና ነጭ የግድያ ሁኔታ ላይ ትኩረቱን ስቦታል ።
በቢሾፍቱ በአንድ ቀን ውስጥ ከ750 በላይ ንጹሃን ዜጎች በጥይት ፣ገደል በመግባት እና ብቢሾፍቱ ወንዝ በመስጠም የሚታወቅ ሲሆን በመላው አለም መገናኛ ብዙሃን ትኩረትም እንደሳበ ግልጽ ነው ።
ሆኖም ለአፍሪካውያኖች ቆሜአለሁ የሚለው የአፍሪካ ህብረት በአፍሪካ ህዝብም ሆነ በኢትዮጵያን ዜጎች ላይ የማላገጥ ስራ እንደሰራ ያሳያል ።
Zehabesha-News.jpg

በእሬቻ በአል በተወሰደው ግፋዊ እርምጃ ላይ የተለያዩ ከተሞች እና ከፊል አዲስ አበባን ጨምሮ የተቃውሞ አሰሙ በወያኔ ንብረቶች ላይ እርምጃ ወሰዱ።

$
0
0

(ዘ-ሃበሻ)በእሬቻ በአል ላይ በጨካኙ የወያኔ ሰራዊት የተፈጸመው ህዝባዊ ተቃውሞ በጃሞ የተነሳው ተቃውሞ በተለያዩ የኦሮሚያ እና የአዲስ አበባ ክልሎች እየተዛመቱ መምጣቱ ተገልጦአል ። በአዲስ አበባም የተለያዩ የንግድ ሱቆች ተዘግተዋል ። በሌሎችም ቦታዎች የኦሮሞ ተወላጆችም ሆኑ ሌሎችም ዜጎች በህብረት የኦሮሞ ህዝብ ነጻ መሆን አለበት ግድያ ይቁም ፣ወያኔ ከስልጣን ይውረድ በማለት ከፍተኛ ድምጽ በማሰማላት ላይ ይገኛል ።
በአለም ገና ሞጆ ፣ቡራዩ እና ሌሎችም ቦታዎች ከፍተኛ ንቅናቄ ከመታየቱም በላይ በአሸዋ ሜዳም ከፍተኛ ሃይል ያለው ህዝብ ወደ ከተማ በመግባት የተለያዩ ድምጾችን አሰምቶአል ፣መንገዶችም ተዘግተዋል ። የትራንስፖርት አገልግሎቶች የቆሙ ሲሆን የአጋዚ ጦርም በተለያዩ ቦታዎች ተሰግስገው የገቡ ሲሆን በአንዳንድ ቦታውችም በንጹሃን ዜጎች ላይ ከፍተኛ እርምጃ እየወሰዱ ይገኛሉ ።
ትምህርትቤቶችም በጊዜ የተዘጉ ሲሆን በሰሜን ሸዋ በሰላሌ አካባቢ ህዝቡ በአደባባይ ከገበሬው ጋር በመተባበር ወደ አደባባይ ወጥተዋል ። በሌሎች ገጠር ከተሞች ከፍተኛ እንቅስቃሴ ቀጥሎአል ተቃውሞው በሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች እንደሚዛመት ምንጮቻችን ገልጸዋል ።

ከአዲስ አበባ ከተማ መውጫ ላይ የምትገኘው ዳላቲ ከተማ መንገዶች ተዘግተዋል እንዲሁም የወያኔ ንብረቶች ወደመዋል።

የህዝብ እውነት ፣ አጋርነትና የወደድኩት የሙሽሪት ትጋት!

$
0
0

የማለዳ ወግ…
የህዝብ እውነት ፣ አጋርነትና የወደድኩት የሙሽሪት ትጋት !

* የህዝቡ ስሜት በየፈርጁ ይገለጻል ፣ ዛሬም ጀግና ሙሽራ አየን !
* ከሪዮ እሰከ ዲሲ፣ ከአማራ እሰከ እስከ ኦሮሚያ የህዝብ ሀቅ !
* እጁን ቆልፎ ” አቅመ ቢሶች ነን ፣ ታስረናል !” ሲል ” አሸሻሪ ነህ ” አትበሉት
* ስማን ” ሰከን በል” ዘማች ፣ አዝማች ወታደሩ ፣ ሰከን ! ! !

በደል ፣ ጭቆናና አድልኦና ግፍ በከፋ ቁጥር ሀገሬው የጭቆና ቀንበር መሸከሙን አሻፈረኝ ይላል … የሰላም በሮች ሲዘጉ ፣ ለእንቢተኝነት በሮችን ይከፍታሉ ! ሀገሬው እየተቀጠቀጠ እየተገዛም እንቢተኝነቱን በተለያዬ ፈርጄ ብዙ መንገዶች ጉዳት ስሜቱን ሳይፈራ ደፍሮ ይገልጻል ። ብዙዎቻችን ህመሙ እያመመን ሳንገልጸው ፣ አለያም ሆድ አደር ሆነን ስንንከላዎስ የወገናቸውን ትክክለኛ ብሶት ፣ የህዝብ እውነት ፣ የአጋርነት ድምጽ በተለያዩ አጋጣሚዎች የገለጹ በእርግጥም የታደሉ ናቸው ! በቅርብ ወራትበፊት በሪዮ አትሌት ፈይሳ ሌሌሳ ባሳለፍነው ሳምንት ደግሞ በዲሲ በአንዲት መልከ መልካም ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊት ሠርግ ላይ ያየነው ነፍሳችን በሃሴት ነጥቆናል ፣ እናም ከሪዮ እስከ እሰከ ዲሲ፣ ከአማራ እሰከ እስከ ኦሮሚያ የተመለከትነው የህዝብ አጋርነት የህዝብ እውነት እውነታችን ነውና የሀገረ አሜሪካ የዲሲዋን ሙሽራ በዛሬው የማለዳ ወግ ክብር ሰጥተን እናወሳታለን !
ሙሽሪት በሠርጓ ላይ የይሁኔ በላይን “ሰከን በል” አስከፍታ የታስረናል ምልክትን በማሳየት ሕዝቤን አትግደሉት ስትል ተቃወመች
” ሰከን በል ” የሚለውን የአርቲስት ይሁኔ በላይን ወኔ ቀስቃሽ ወቅታዊ ዘፈን በሠርጓ ቀን እንዲዘፈን የመረጠችው ሀገር ወዳድ አስገራሚና አስደናቂ ሙሽራ ቪዲዮ የደረሰኝ ከትንናት በስቲያ ነው ፣ መረጃውን ያደረሱኝ ደግሞ እዚህ ሳውዲ የሚገኙ ቤተሰቦቿ ናቸው ። ስመለከተው በስሜት የሸነቆጠኝን የሙሽሪት ልዩ የሀገር ፍቅር መግለጫ የሆነውን የሙሽሪት የሠርግ ቀኗ ምርጫ ” ሰከን በል ” ጣዕመ ዜማ ልዩ መልዕክት የሰማሁት በመሪሩ ሀዘን ሳምንት መካከል ቢሆንም ዜማው ከፈንጠዝያና ዳንኪራ የወጣ መልዕክት አለውና ከሙሽሪት ወኔ ጋር ” ሰከን በል ” ሰከን በል እያልን ስለሚያገባን እናዎጋለን … !

የሙሽሪት ሜሮንን ቪዲዮ እንዳሰራጨው ጠየቄ በሙሽሪት ቤተሰቦች በኩል ሙሉ ፈቃድ ሰጥተውኝም ነበር ። ቢሸፍቱ አልቅሳ ቀኑ ጥቁር የሀዘን ቀን ስለነበር ከማሰራጨት ወኔውን አጣሁት … መረጃው ሲደርሰኝ ሠርጉ በሃገረ አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ እንደተከወነ የገለጸችልኝ እህቷን የሙሽሪትን ሙሉ ስሟን ማን ይባላል ስል ጠየቅኳት ፣ መለሰችልኝ ” በስሟ ትገረማለህ ሜሮን መሀመድ ያሲን ትባላለች ፣ ለእኔ የእናቴ ልጅ ናት በአባቷ አፋር ናት ፣ እሷ ግን ክርስቲያን ናት ፣ መቼም ኢትዮጵያ ውስጥ የቀራት ገድማት ቤተክርስቲያን የለም ፣ እንደሚመስለኝ ብቸኛዋ የአፋር ክርስቲያን እሷ ናት ! ” አለችኝ ! ተደመምኩ ፣ አፋሮች ሲነሱ አባት አሊ ሚራህ ትዝ ይሉኛል ፣ ” የኢትዮጵያን ባንዴራ እንኳን እኛ ግመሎቻችን ያውቋታል !” ሲሉም በቦታው ነበርኩ ! አሳይታ … የአፋሯ ሙሽራ ስለ ኢትዮጵያ የሆነችውን ብትሆን እሷ የጀግኖች ዘር መሆኗ ነው አክኩና አሁንም በሰማሁት ታሪክ ተደመምኩ !

ብቸኛዋ የአፋር ክርስትያን ልትሆን የምትችለው ሙሽሪት ሜሮን ዛሬ የወገኗ ነገር አንገብግቧት ” ሰከን በል ” እያለች በሠርጓ አዳራሽ በስሜት ስትውረገረግ ፣ እጆችዋን ወደ ላይ ከፍ አድርጋ ከነሚዜዎቿ በማንሳትና በማቆላለፍ ከህዝቡ ጋር መሆኗን በልዩው የሠርጓ ቀን በወኔ ተሞልታ ስታሳይ አለቀስኩ … በሚታየው ጥልቅ ስሜቷ ውስጤን ነካችውና ሆዴ እንደ መባባት አለ …

” ሰከን በል ” የሀገር ወዳዱ የታዋቂው ዘፋኝ የይሁኔ በላይ የአዲስ አመት ልዩ ማስታወሻ ቢሆንም ሰከን ባላለው ወታደር ህዝብ እየተጨፈጨፈ ላዘነ ለተቆጨና እንደኔ ቆሽቱ ላረረው ጥሩ ሰሜት መግለጫ ሆኖም ሰንብቷል … ዛሬ በሙሽሪት እጅ በአዳራሹ ገብቷል … ሙሽሪትን ደጋግማ ” ሰከን በል ” ስትል ስማኋት ፣ ከአርቲስት ይሁኔ ድምጽ እኩል ስታዜመው ” ሰከን በል ” ስትል ሰማኋት ፣ ሰከን ማለት ደግሞ ግድ ይላል ! ወታደሩ ሰከን በል ፣ ገዳይ አስገዳይ ጨምላቃው ፖለቲከኛም ሰከን በል ፣ የሚሞተው ወንድምህ ነው ፣ የሚሞተው እህት ናት ፣ እናም ሰከን ማለት ይበጅሃል ፣ ሰከን በል ! ስትል እስክታውን በቁጭት ስታስነካው የፈንጠዝያና ዳንኪራ ስሜት ላለመሆኑ ያሳብቅባታል !

የሰከነ ነገር ጠፍቶ …እዚህም እዚያም ግፍ በዝቶ የማንፈልገውን እንድንደግፍ ፣ እንድንመርጥ እየተገፋን ነው …የምንወዳት ሀገራችን ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ መጓዝን በውል ለታዘበ ይህ እውነት የማያንገበግበው ወገኔ የለም ፣ እናም ሙሽሩት ሜሮን አንዷ ናት ፣ የሙሽሪት ሜሮን ሰከን በል ምርጫ ከእነ ሙሉ እንቅስቃሴዋ እየተመለከትኩ በሙሉ ሀገራዊ ወኔ በሀዘን ውስጥ ሆኖም በቁጭት እልህ ጥልቅ ስሜት ተዘፍቆምና በሀዘን ስሜት ውስጥ ገብቶ በእልህ ይነሸጣል …

ይሁኔና ሙሽሪት ” ሰከን በል ” እያሉ ባንድ መድረክ የተጫወቱትን ያህል ሰርጾ ሊገባ የቻለው እንቅስቃሴ መሰረቱ በውስጡ ያለው እውነት ለመሆኑ አልጠራጠርም ። በሙሽሪት የደስታ ቀን በሀገር ስሜት ዋጅታ በነፍሷ አልፎ በፊቷና በመላ አካሏ የሚታየው ቁጭት ብሎም የወገናዊነት ፣ የህዝባዊነት ስሜት እውነት ቁልጭ ብሎ በሙሽሩት ላይም ይታያል ! ያ ብዙዎች ዘንድ በጥቂቶች ላይ ያደረው የወገናዊነት ” ያገባኛል “ስሜት እውነት በእርግጥም በሙሽሪት ይገለጻል ! በሀገረ አሜሪከ በዲሲ ከተማ በታላቁ የሙሽሪት የደስታ ቀን የሠርጓ እለት አብሮበትና ከህዘብ አጋር መሆን ስለእውነት እንዲህ ወኔን ቀስቃሽ ሆኖ ጀግንነት በየፈርጁ እንድናይ ምክንያት የሆነችውን ሜሮን ጀግና የእኛ ሙሽራ ብያታለሁ :)

ሙሽሪት ሜሮን ” በሰከን በል ” ልዩ ሀገራዊ ጣዕመ ዜማ ያንጸባረ ቀችው ሀገሬ ተጎዳች በሚል ቁጭትን ” መለያየት አይጠቅምም በማለት ነበር …
” ድር እንኳን ቀጭኑ ድር እንኳን ለስላሳው
ሲያምር ሲተባበር ይበልጣል ካንበሳው ” ይል ዘንድ ይሁኔ በሜሮን ሰርግ አብሮነትና የሀገር ፍቅርን በልዩ መሳጭ ስሜት ተሰብኳል !
” ወታደሩ ሰከን በል
አፈሙዙን ሰከን ዐርገዉ
ቃታዉን እንዳተትስበዉ
ቧዶ እጁን ነው እሚጮኸው
ሠላማዊ ወንድምህ ነዉ ” ተበሎም ወታደሩ “ተረጋጋ ፣ ሰከን በል ” ትበሎ ወታደሩ ምክር ሲለገሰው ” ሰከን ማለት ነው ጀግንነት ” ተብሎ በሰርጉ አዳራሽ በህበረት ተስተጋብቷል ፣ ያውም በልዩው የግሏ የደስታ ቀን … ! ጀግናዋ የኢትዮጵያ ሙሽራ !

ህዝቤን ተውት እንዲል ደጉ አባት … ባለቅኔው አንጎራጓሪ ” ሰከን በል ” ሲል በሰራው ነጠላ ዜማ አዛዥ ፣ ገዳይ ፣ አስገዳይ አዛዦችም እንዲህም ተብለዋል በይሁኔ ማራኪ ጣዕመ ዜማ
” ሰከን በሉ ህዝቤን ተዉት
ድምጹን ስሙት ፣አትግደሉት
መንግስት በአገሩ በህዝብ ላይ አይተኩስ
ዘር አጥያት ይሁን ንጉስ ከማሪዮሰ ” የተባለው በሙሽሪት ሠርግ ላይ ደምቆ ሲሰማ ማስተዋል ፣ በተበደለ ህዝቧ የተጎዳ የሙሽሪትን ስሜት ማየት ያልቻላችሁ ካላችሁ ስሜታችሁን ፈልጉት … እኔ ይህን የሙሽሪትን ሠርግ “ሰከን በል !” ምርጫና ፣ የመልከ መልካሟን እህት ውስጥና ውጫዊ ስሜት ተረድቸው ረክቸበታለሁ !

ሰሚ ቢገኝ ሀገሬው በደስታ በሀዘን ፣ በየተናጠል በህብረት ስሜት ፍላጎቱን ፣ የዲሞክራሲ ጥማት ነጻነቱን እየጠየቀ ነው ፣ ሆዳም ካልሆነው ተትረፍርፎ ከሞላው እስካጣ የነጣው እጁን ወደ ላይ በማንሳት ” አቅመ ቢሶች ነን ፣ ታስረናል !” ብሎ የተቃውሞ ድምጹን ሲያሰማ ” አሸሻሪ ነህ ” አትበሉት ! የውስጥ እውነቱ ፣ የተቃውሞ ህብረቱ መገለጫ ምልክት አድርጎታልና እየመረራችሁም ቢሆን ተቀበሉት !

ሙሉ የሙሽሪት ሜሮንን ቪዲዮ እንዳሰራጨው ጠየቄ በሙሽሪት ቤተሰቦች በኩል ሙሉ ፈቃድ ሰጥተውኝም ነበር ። ቢሸፍቱ አልቅሳ ቀኑ ጥቁር የሀዘን ቀን ስለነበር ከማሰራጨት ወኔውን አጣሁት … መረጃው ሲደርሰኝ ሠርጉ በሃገረ አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ እንደረከወነ የገለጸችልኝ እህት የሙሽሪትን ስሟን ማን ይባላል ስል ጠየቅኳት ፣ መለሰችልኝ ” በስሟ ትገረማለህ ሜሮን መሀመድ ያሲን ትባላለች ፣ ለእኔ የእናቴ ልጅ ናት በአባቷ አፋር ናት ፣ እሷ ግን ክርስቲያን ናት ፣ መቼም ኢትዮጵያ ውስጥ የቀራት ገድማት ቤተክርስቲያን የለም ፣ እንደሚመስለኝ ብቸኛዋ የአፋር ክርስቲያን እሷ ናት ! ” አለችኝ ! ተደመምኩ ፣ አፋሮች ሲነሱ አባት አሊ ሚራህ ትዝ ይሉኛል ፣ ” የኢትዮጵያን ባንዴራ እንኳን እኛ ግመሎቻችን ያውቋታል !” ሲሉም በቦታው ነበርኩ ! አሳይታ …

ብቸኛዋ የአፋር ክርስትያን ልትሆን የምትችለው ሙሽሪት ሜሮን ዛሬ የወገኗ ነገር አንገብግቧት ” ሰከን በል ” እያለች እጆችዋን ወደ ላይ በማቆላለፍ ከህዝቡ ጋር መሆኗን በልዩው የሠርጓ ቀን በወኔ ተሞልታ አሳይታናለች ፣ እናመሰግናለን !

እናንተም! ሙሽሪትን ስሟት ! ” ሰከን በል ” ትላለች ፣ ሰከን ማለት ደግሞ ግድ ይላል ! ወታደሩ ሰከን በል ፣ ገዳይ አስገዳይ ጨምላቃው ፖለቲከኛም ሰከን በል ፣ የሚሞተው ወንድምህ ነው ፣ የምትሞተቅ እህት ናት ፣ እናም ሰከን ማለት ይበጅሃል ፣ ሰከን በል !

ለጀግናዋ ሙሽራ መልካም ጋብቻ ተመኘሁ !

ሰናይ ቀን !

ነቢዩ ሲራክ
መስከረም 24 ቀን 2009 ዓም

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live