Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ፈይሣ ሌሊሣ በድርጊቱና በአስተሳሰቡ ሁሉንም ኢትዮጵያውያን እንደራሳችን ወገን እንድቆጥር አድርጎናል!

$
0
0

ከአንድ ወር በፊት በሪዮ ኦሎምፒክ ሁለት እጆቹን በማንሳት በኢትዮጵያ የሚፈጸመውን ግፍ የተቃወመው ፈይሣ ሌሊሣ “ሁላችንንም እንደ ኢትዮጵውያን እንድንተያይ አድርጎናል” በማለት አቶ ኦባንግ ሜቶ ገለጹ፡፡

የፈይሣን የጀግንነት ተግባር በተመለከተ አቶ ኦባንግ በሚመሩት ድርጅት ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ስም ባሰራጩት መግለጫ ላይ ነበር ይህንን ሃሳብ የገለጹት፡፡ “ኦገስት 21፤ 2016ዓም ኢትዮጵያውያን አዲስ የመንፈስ መነቃቃት ሆነላቸው” በማለት የፈይሣን አኩሪ ተግባር የገለጸው መግለጫ ይህ የኦሮሞ ወጣት ለወገኖቹ ብቻ ሳይሆን ለሁላችንም ድምጻችንን በዓለም ላይ እንዲሰማ አድርጎልናል ብሏል፡፡ ድርጊቱም የዓለምአቀፉን ሚዲያ ትኩረት በመሳብ በህወሃት የግፍ አገዛዝ ላይ ብርቱ ጡጫውን አሳርፏል፡፡
obangfeisa2

“በርግጥ ፈይሳ የኦሮሞ ሕዝብ ኩራት ነው” ያሉት አቶ ኦባንግ፤ “ነገርግን ፈይሣን በዋሽንግተን ዲሲ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጥ በሰማሁት ጊዜ እንዲሁም በግሌ ካገኘሁት በኋላ ከብሔር ማንነቱ በላይ እጅግ ታላቅና አስደናቂ ሰው መሆኑን ለመረዳት እያለሁ” በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

“የኢትዮጵያ መንግሥት የራሱን ሕዝብ እየገደለ፣ እያሰረና እየጨቆነ ይገኛል፤ በኦሮሚያ፣ በአማራ እና በጋምቤላ ያለው ሁኔታ በጣም አሳሳቢ ነው፤ … እኔ ኦሮሞ ነኝ፤ ያደኩትም በኦሮሚያ ነው፤ የሕዝቤን ስቃይ በደንብ አውቃለሁ፤ መብታቸውን በሰላማዊ መንገድ በጠየቁ ሰልፈኞች ላይ መንግሥት ተኩስ ከፍቶ እስካሁን ከ1000 በላይ ሰዎች ሞተዋል፤ ሌሎች ደግሞ ከአገር ለቅቀው እንዲወጡ በመደረጋቸው በሊቢያ በረሃ ታርደዋል፤ ሌሎች በጣም ብዙዎች ደግሞ በሜዲተራንያን ባሕር የባህር አውሬ ሲሳይ ሆነዋል” በማለት ፈይሣ ለጋርዲያን ጋዜጣ የተናገረውን በመግለጫው ላይ ተጠቅሷል፡፡

ይህንን የፈይሣን ንግግር አቶ ኦባንግ ከራሳቸው የሕይወት ተሞክሮ ጋር አዛምደውታል፡፡ “ፈይሣ የተናገረው የራሴን ሕይወት የሚያሳይ ነው፤ ከተወለድኩበት የአኙዋክ ጎሣ በዲሴምበር 2003 ዓም 424 ወገኖቼ ከሦስት ባነሱ ቀናት ውስጥ መሬታቸውን እና የመሬት ሃብታቸውን ለመቀማት በተመኘው የህወሃት ቡድን ተጨፍጭፈዋል፤ ከዚህ አሰቃቂ ድርጊት በኋላ በሌሎች ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰውን ስመለከት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ነጻ መውጣት እውን ካልሆነ አንድ ጎሣ ወይም ብሔር ብቻውን ነጻ መውጣት እንደማይችል፤ ይህም ደግሞ ለዘላቂ ነጻነትና ፍትሕ ወሳኝ መሆኑን ተገነዘብኩ፤ ይህም ግንዛቤዬ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) መቋቋም በር ከፋች ሆነ፤ አኙዋኮች በመጨፍጨፍ በቀጣይ ተመሳሳይ አመለካከትን ህወሃት/ኢህአዴግ እንደሚያራምድና በሌሎች የኢትዮጵያ ወገኖች ላይ ተመሳሳይ እርምጃ እንደሚወስድ ግንዛቤ ወሰድኩ፤ ለዚህ ነው የሁሉም ነጻ መውጣት ወሳኝ መሆኑን የተረዳሁት፤ ፈይሣም እንዲሁ ህወሃት/ኢህአዴግ በፈጠረው የጎሣና የዘር ወጥመድ ውስጥ መግባት ለኢትዮጵያውያን አደገኛ ነገር መሆኑን በውል የተረዳ ነው” በማለት አቶ ኦባንግ በመግለጫው ላይ ተናግረዋል፡፡

ለማስረጃም ይህንን ጠቅሰዋል፤ ከላይ ፈይሣ መግለጫ በሰጠበት ጋዜጣ ላይ የሚከተለውን ብሎ ነበር፤ “አሁን ያለው ሁኔታ (ብሔርን እየለዩ የማጥቃት እርምጃ) በዚሁ ከቀጠለ የኢትዮጵያ ሁኔታ አደገኛ እንደሚሆን አልጠራጠርም፤ ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ጣልቃ በመግባት በዚያች አገር ላይ ለውጥ እንዲመጣ መርዳት አለበት፤ እኔ በግሌ ሁኔታው በዘር ላይ ወደማነጣጠር እንዳይሄድ እፈራለሁ፤ ሁኔታው ወደከፋ ደረጃ ሳይደርስ ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ጣልቃ መግባቱ የግድ ነው” ብሏል፡፡

“በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ የጠፋው ነገር ሰብዓዊነት ነው፤ በፊታችን የተጋረጠው ጦርነት እንደ እውነት የተዘራውን ውሸት መፋለም ነው” ያሉት አቶ ኦባንግ ላለፉት 25 ዓመታት ህወሃት በኢትዮጵያ ውስጥ የነዛው ጥላቻ፣ ዘረኝነት፣ መከፋፈል፣ … በብዙዎቻችን ዘንድ ሥር ሰድዶ ከሰብዓዊነት በፊት ጎሣን፣ ዘርን፣ ብሔርን፣ … በሚያስቀድም አዙሪት ውስጥ እንድንወድቅ አድርጎናል ብለዋል፡፡ ይህንን እንደምናሸንፈው የተናገሩት ኦባንግ እንደ ጋምቤላ፣ እንደ ኦሮሞ፣ እንደ አማራ፣ እንደ ሶማሊ፣ … ሆነን ሳይሆን እንደ አንድ ባለዓላማ ኢትዮጵያዊ ሆነን ህወሃት የደገሰልንን ጥፋት አልፈን መሻገር እንችላለን ብለዋል፡፡

እንዲህ እንድንሰባሰብ የፈይሣ ድል ያደፋፍረናል ያለው መግለጫ ፈይሳ ሁለተኛ ሆኖ በማሸነፍ የድል መስመሩን ሲያልፍና እጁን አጣምሮ ድምጻችንን ከፍ አደርጎ ሲያሰማልን በኢትዮጵያ ላይ የሰፈረው ጭለማ ተገፈፈ፤ የብርሃን ጭላንጭል ታየን፤ ድምጻችን ጎልቶ በዓለም ተሰማልን፤ የፈይሣ የጀግንነት ተግባር አዲስ ተስፋ በልባችን ውስጥ ፈነጠቀ፤ የውድድር መስመሩን አልፎ ድል ሲጎናጸፍ ለአንድ ወገን ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ኢትዮጵያዊ በህወሃት/ኢህአዴግ የተመሠረተውን የዘረኝነት መሠረት አናወጠው በማለት መግለጫው ፈይሣ ለኢትዮጵውያን ያስገኘውን ድል ይጠቅሳል፡፡

ከዚህ ባለፈ መልኩ በብዙዎቻችን ላይ የተደፋውን እና አሜን ብለን የተቀበልነውን የህወሃት/ኢህዴግን የዘረኝነት ማታለያ ፈይሣ እምቢ በማለት ነጻ ሰው መሆኑን ማሳየቱ ብዙዎቻችንን ከታሰርንበት የዘር ፖለቲካ ወጥተን ለኅብረት እንድንቆም ያደፋፈረን ነው ብዬ እንዳምን ተስፋ ሰጥቶኛል በማለት አቶ ኦባንግ የግል ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡ በዚህ ብቻ አላቆሙም “ከዘርና ብሔር ልዩነታችን ባሻገር ፈይሳ ለእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ጀግና ነው፤ ባለፈው ዋሽንግተን ዲሲ ላይ ባገኘሁት ጊዜ አገር ወዳድ፣ ትሁት፣ ተወዳጅ፤ የዓላማ ሰውና ደፋር መሆኑን ለማወቅ ችያለሁ” ብለዋል፡፡

በዚሁ መግለጫ ላይ አቶ ኦባንግ ፈይሳን ሊገጥሙት ከሚችሉት አስቸጋሪ ሁኔታዎች ዋንኛውን ጠቅሰዋል፤ “ፈይሣን ህወሃት/ኢህአዴግ ባስቀመጠለት የዘር ሳጥን ውስጥ እንዲገባና ለብዙዎቻችን የትግል ተስፋ እንዳይሆን ይበልጡኑም በኦሮሞነቱ እንዲወሰን ሊያደርጉት ይሞክሩ ይሆናል፤ ሆኖም ማወቅ የሚገባን ነገር ማነው ማንነታችንን የሚወስንልን? ይኼ ነህ ብሎ የሚነግረን ወይም በዚህ የዘር ሣጥን ውስጥ ግባ ብሎ የሚደርገን ማነው? ህወሃት ያመጣው የዘር ፖለቲካ በርካታ ኢትዮጵውያንን በዚህ ዓይነት የዘር ሣጥን ውስጥ እንዲገቡ አድርጓቸው ከሰብዓዊነት ወደ ዘር ዝቅ ብለዋል፤ ይህንን በማድረግ ህወሃት ተሳክቶለታል ሊባል ይችላል፤ ኢህአዴግን በአንድ ዓመት የሚበልጠው ፈይሣ ለ25 ዓመታት የተዘራውን የዘር ፖለቲካ አልፎ በመውጣት ቢሳካለት አገሩ ነጻ ሆና ወደ አገሩ ተመልሶ በሩጫ ለመወዳደር እንደሚፈልግ መስማት የህወሃት የዘር ፖለቲካ ያላሰከራቸው በርካታ ፈይሣዎች እንዳሉ ያሳየ ጉልህና ተስፋ የሚሰጥ ተግባር ነው፡፡”

የፈይሣን አኩሪ ተግባር የተከተሉ በርካታዎች እየመጡ መሆናቸውን የጠቀሰው መግለጫ ከፈይሣ ሌሊሣ የድል ተግባር በኋላ ኤቢሣ እጅጉ በኪዩቤክ ካናዳ ማራቶን፤ በሪዮ ፓራኦሎምፒክ በ1500 ሜትር የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊ ታምሩ ደምሴ፤ እንዲሁም በማርሻል አርትስ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሌላ ኢትዮጵያዊ ካሣ ይመር፤ በድፍረት እጃቸውን አጣምረው በማንሳት ለአገራቸውና ለወገናቸው ድምጽ ሆነዋል ብሏል፡፡

በማጠቃለያም “በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ እንደነዚህ ዓይነት ልጆች ያስፈልጓታል፤ የሞራል ልዕልናቸው የላቀ፤ ሰውን ሁሉ በሰብዓዊ ፍጡርነት የሚያዩና የሚያከብሩ አዲስ ለምንመሠርታት ኢትዮጵያ ያስፈልጉናል፤ ከጎሣ ይልቅ ለሰብዓዊነት ቅድሚያ የሚሠጡ፤ የሌላው ህመምና ሥቃይ የራሳቸው አድርገው የሚወስዱ፤ የወገናቸውን መከራ በሚችሉት ሁሉ ለዓለም ለማሰማት በሕይወታቸው የሚደፍሩ ያስፈልጉናል” በማለት በአኢጋን መግለጫ ላይ የተናገሩት አቶ ኦባንግ ፈጣሪ እነ ፈይሣ፣ ኤቢሳ፣ ካሣ፣ እና ታምሩ ሕዝባቸውን የሚያገናኙ ድልድዮች ሆነው እንዲሰሩ እንዲረዳቸው ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

ይህ መግለጫ የተዘጋጀው በአኢጋን የሚዲያ ክፍል ሲሆን በኢሜይል አድራሻችን media@solidaritymovement.org ወይም አቶ ኦባንግ ሜቶን Obang@solidaritymovement.org ኢሜይል ሊያገኙ ይችላሉ፡፡


ዓመተ ፍዳ ዘነገደ አማራ!

$
0
0

ቤተክርስቲያን “ዓመተ ፍዳ” የሚለውን ቃል ዓለም ከተፈጠረ አንሥቶ ከክርስቶስ መወለድ በፊት ያለውን የሰው ልጆች በነፍስና በሥጋችን በአጋንንት አስከፊ የፍዳ፣ የመከራ፣ የሰቆቃ፣ ግዞት የነበርንበትን ዘመን ለማመልከት የምትጠቅሰው ቃል ነው፡፡

በቅርቡ “የጥፋት ዘመን” በሚል ርእስ በዋናነት በጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው የተዘጋጀ በ25 ዓመታቱ የወያኔ አገዛዝ ዘመን በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በአማራው ሕዝብ ላይ አጋንንት በተዋሐዷቸው በወያኔ ኦነግና ሌሎች የጥፋት ኃይሎች የተፈጸመውን የዘር ማጥፋትና ማፅዳት እልቂት የሚያትት ጥናታዊ መጽሐፍ ታትሞ ለአንባቢያን መቅረቡ ይታወቃል፡፡

አስቀድሜ ከጅማሬው አንሥቶ ይህ መጽሐፍ ታትሞ ለአንባቢያን እስኪደርስ ባለው ሒደት የተሳተፉ ወገኖችን በሙሉ በግሌ እጅግ አድርጌ ላመሰግን እወዳለሁ፡፡ ተባረኩ!

ከዓመታት በፊት ቀደም ሲል በዚህ ጉዳይ ላይ የጻፍኩትን “የዘር ማጥፋት ወንጀሎች በአማራ ሕዝብ ላይ በታሪክ ሒደት ውስጥ ከጥንት እስከ ዛሬ!” የሚለውን ረዘም ያለ ጽሑፍ በማካተት እንዲህ ዓይነት መጽሐፍ ለማዘጋጀት አስቤ ለዚህ እነ ጋዜጠኛ ሙሉቀን ላዘጋጁት መጽሐፍ መዘጋጀት እስፖንሰር (ደጋፊ) የሆነው ሞረሽ ወገኔ እንደተመሠረተ ሰሞን ለአንደኛቸው የድጋፍ (የስፖንሰር) ጥያቄ አቅርቤ ነበር፡፡ ሰውየው እንደሚያቀርበው ከነገረኝ በኋላ ምን ውሳኔ ላይ እንደተደረሰ ሳይነግረኝ በመቅረቱና በእኔም ላይ ታች አምና ኦነግ ያሳሳታቸው የጅማ ዩኒቨርስቲ (መካነ ትምህርት) ተማሪዎች ተገንብቶ ሊመረቅ በነበረው በአኖሌ ሐውልትና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ መጽሔት ላይ የጻፍኩትን ጽሑፍ ምክንያት በማድረግ ቁጥሩ ያልተወቀ ሰው የሞተበትን ዐመፅ አስነሥተው በእኔና በመጽሔቱ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ሲጠይቁ (በጥቂት ቀናት ውስጥም ዐመፁ ወደ ሌሎች ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሲቀጣጠል የኦሕዴድ ሰዎች “አሃ! ሕዝባችን በዚህ ደረጃ መነሣሣት የሚችል ከሆነማ!” በማለት አጋጣሚውን ለመጠቀም በማሰብ እጃቸውን አስገቡበትና የተማሪዎቹን ጥያቄ የአዲስ አበባን ዐቢይ የማስፋፊያ አቅድ ወደ መቃወም እንዲዞር አደረጉት)

እናም በዚህ መልኩ በእኔና በመጽሔቱ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ሲጠይቁና በግልም የተለያየ ዛቻና ማስፈራሪያ ሲደርስብኝ ጊዜ ወያኔና ሌሎች የጥፋት ኃይሎች ኦሮሚያ ሲሉ በሚጠሩት የሀገራችን ክፍል በነጻነት ተዘዋውሬ በአማራ ኅብረተሰብ ላይ የተፈጸመውን አረመኔያዊ ኢሰብአዊ ዘር የማጥፋትና የማጽዳት ግፍ የማጥናት የማጣራትና የመዘገብ ዕድሌ እንደተበላሸብኝ ሲገባኝ ለሞረሽ ወገኔም ሆነ ለሌላ አካል ጥያቄውን ደግሜ ሳላቀርብ ቀረሁ፡፡

ይሁንና ይህ መሠራት መከወን የነበረበት ሥራ በእኔ ባይሠራም በእነ ሙሉቀን ተስፋው ተሠርቷልና ዋናው ጉዳይም መሠራቱ ነውና ምንም ዓይነት ቅሬታ አላደረብኝም፡፡ ከዚህ በፊት በዚህና ተያያዥ ጉዳይ ላይ በጻፍኳቸው ጽሑፎች ላይ ያነሣኋቸው ሐሰቦች እዚህ መጽሐፍ ላይ በመንጸባረቃቸውም አልተከፋሁም ጉዳዩ የሀገርና የወገን ነውና፡፡

ethiopian-genocide-on-amhara
እነ ጋዜጠኛ ሙሉቀን ሁኔታው የፈቀደላቸውንና መድረስ የቻሉትን ያህል በመድረስ ነፍሳቸውን ለአደጋ በማጋለጥ ጭምር በአማራ ሕዝብ ላይ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋትና ማጽዳት በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸም የመጨረሻ ወንጀል ለመዘገብ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል፡፡ ያልደረሷቸው አካባቢዎችና የፍጅት ኩነቶች ቢኖሩም መጽሐፉ ግን በሀገራችን በ21ኛው መቶ ክ/ዘ በፍጹም በፍጹም ይፈጸማል አይደለም ይታሰባል እንኳን የማይባል አረመኔያዊ ድርጊት ምናልባት አጋንንት ይሆናሉ እንጅ ሰው መሆናቸው በእጅጉ በሚያጠራጥሩ አራዊት የተፈጸመውንና አሁንም እየተፈጸመ ያለውን የግፍ ደረጃና ክብደት ለመረዳት ከበቂ በላይ መረጃና ግንዛቤ ሰጪ ነው፡፡

እነኝህን እጅግ ኢሰብአዊ የአውሬዎችን ድርጊቶች ድርጊቶቹ ለተፈጸመባቸው አካባቢዎች ሰዎች ካልሆነ በስተቀር ለብዙዎቻችን ጭምጭምታውን ካልሰማን ወገኖች መሀል ግን በሌላው የዓለም ክፍል በፍጹም ተሞክረው የማያውቁ ዘግናኝና አረመኔያዊ ግፎች በአማራ ብሔረሰብ ተወላጆች ላይ በብዛት መፈጸማቸውን የሚያውቅ እንደሌለ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል፡፡

የዚህ ምክንያቶቹ ደግሞ አንደኛ፦ ጥቃቱ የተፈጸመባቸው ወገኖቻችን የተፈጸመባቸውንና እየተፈጸመባቸው ያለውን ግፍ ማውራታቸው ወይም መናገራቸው ለተጨማሪ ጥቃት የሚያጋልጣቸው መሆኑ ሲሆን፡፡ ሌላው ደግሞ “አማራ እንደ ሕዝብ የአጋንንቱ ኢላማ ሆኖ እየተጠቃ መሆኑ በይፋ ቢታወቅ ይህ ግፍ የዘነበበት ሕዝብ ተገዶ በሚወስደው የመከላከል እርምጃ እንዳለ ብሔረሰቡን ብሎም ሀገሪቱን ችግር ላይ መጣል ይሆናልና በእኛው ቢቀር ዋጥ አድርገነው ብንጠፋ ይሻላል!” ከሚል ከፍተኛ ኃላፊነት የተሞላበት አስተሳሰብ ነገር ግን የተሳሳተ አቋም የተነሣ ነው፡፡

ብዙዎቻችን በተለይም መረጃው የሌለን ወገኖች ለመረጃው ሩቅ ከመሆናችን የተነሣ ከፊሉ የተፈጸመው የግፍ ዓይነት ለማመን እጅግ የምንቸገርበት ነገር ቢሆንም ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉ በተለይም የአማራ ተወላጅ የሆነ ሁሉ ይሄንን መጽሐፍ ማንበብና ያለንበትን ሁኔታ መረዳት ይኖርበታል፡፡

ለሰብአዊ መብቶች መከበርና መጠበቅ የጸና አቋም ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሁሉ በተለይም የጥቃቱ ኢላማና ሰለባ የሆነው ዘር አባል የአማራ ተወላጅ የሆነ ሁሉ ይሄንን መጽሐፍ አንብቦ ያ ግፍ የተፈጸመባቸው ወገኖች ሰቆቃና ሕመም አጥንቱ ድረስ ዘልቆ ካልተሰማው፣ ካልተንገበገበ፣ ቁጭት ካላቃጠለው፣ ይሄንን አረመኔያዊ ግፍ የፈጸሙና እየፈጸሙ ያሉ አራዊትን የመታገልና የመደምሰስ የትግል ስሜት ከውስጡ ካልተቀጣጠለበት ካልነደደበት እሱ በድን፣ እሬሳ፣ ጤና በእጅጉ የተጓደለው ወይም የተሟላ የስሜት ሕዋሳት የሌለው መሆኑን እርግጠኛ ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም በዚህ የራሱ ጉዳይ በሆነ ነገር ያልተነሣሣ ያልተቀሰቀሰ ያልተቃጠለ በሌላ በምንም ሊቀሰቀስ አይችልምና፡፡

አርጀንቲኒያዊው ቸ ጉቬራ በዘርና በቀለም ለማይመስሉት ግፉአን ጥቁር አፍሪካውያን ሲል ለነጻነታቸው ለህልውናቸው አንዲት ነፍሱን መሥዋዕት እስከማድረግ ድረስ ቆርጦ መሰለፉን እያወቅን፣ የእኛም አባቶች በኮሪያ በሊቢያ በኮንጎ ወዘተርፈ ለሌሎች ሕልውና ነጻነትና ደኅንነት አንዲት መተኪያ የሌላት ነፍሳቸውን መሥዋዕት ለማድረግ ቆርጠው በመሰለፍ ዋጋ መክፈላቸውን እያወቅን፤ እኛ ይሄ ግፍ እየተፈጸመብን ለራሳችን ህልውና ነጻነትና ደኅንነት ዋጋ ለመክፈል ካመነታን ወደኋላ ካልን ይሄ በድን ሬሳ ካላስባለ ሌላ ምን ሊያስብል ይችላል? ለሆድህ ስትል ሆድህ አምላክህ ሆኖብህ የምትሸሽ ካለህ መብላት የምትችለው ስትኖር ነውና እንዳትኖርም ደግሞ አማራ በመሆንህ ምክንያት ብቻ እየታደንክ እንድትጠፋ ተፈርዶብሀልና ሆዳም ሆይ! እባክህን ሆድህን ምክንያት አታድርግ፡፡

ጥቂት የማንባል የአማራ ተወላጆች አጋንንቶቹ የጥፋት ኃይሎች በአማራ ተወላጆች ላይ የፈጸሙትንና እየፈጸሙት ያሉትን አረመኔያዊ ጥፋት አለመስማታችን አማራ በመሆን ብቻ እየተፈጸመ ካለው መጠነ ሰፊ አረመኔያዊ ጥቃት ሰለባነት ወይም ተጠቂ ከመሆን ያድነን ይታደገን ይመስል ጉዳዩ ሲወራ ላለመስማት እንሸሻለን እንጅ የራሳችኑ ጉዳይ እንደመሆኑ በንቃት ትኩረት ሰጥተን የት ቦታ ምን እየተደረገ እንዳለ በመከታተል ለመፍትሔው አንታትርም፡፡ ብዙዎቹም ይሄንን አደጋ ለመቀልበስ ከመታገል ይልቅ አማራነታቸውን መካድ መፍትሔ አድርገውታል፡፡ ይሁንና እነኝህ አማራነታቸውን የካዱ ወገኖች በአንድም በሌላም መንገድ አማራ ወይም የአማራ ደም ያለባቸው መሆኑ እየታወቀባቸው ለጥቃት ሲዳረጉ ዓየን እንጅ አማራነታቸውን መካዳቸው ከጥቃት ሲታደጋቸው ዓላየንም፡፡ ምንም ይምጣ ምን ማንነትን መካድ እራሱ እጅግ ወራዳና ነውረኛ የለፈስፋሶች ተግባር ነው፡፡

በመሆኑን መፍትሔው ወገብን አስሮ በቁርጠኝነት በጋለ ወኔና ጀግንነት አራዊቶቹን ታግሎ መጣልና መቅጣት ነው እንጅ ክህደት አይደለምና ለዚሁ ቆራጥ እርምጃ የበርካቶችን ነፍስ የሚያስበላ ሌላ ተጨማሪ ጊዜ ሳናባክን አጋንንቶቹን በተለያየ የትግል ስልት ለመታገል በፍጥነት ቆርጠን እንነሣ!!!

ከዚህ ቀደም አነኚህ ሁሉ በ21ኛው መቶ ክ/ዘ ፈጽሞ የማይጠበቁ አረመኔያዊ ግፎች ሲፈጸሙ ፈተናው በሚጠይቀው ጥንካሬና ቁርጠኝነት በመነሣሣት ተገቢውን የተጠናከረ ተቃውሞ አለማሰማታችን የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በግድ እንዲያውቀው ዐውቆም እንዲያወግዘውና እርምጃ እንዲወስድበት አለማድረጋችን ይህ አረመኔያዊ ግፍ እስከአሁንም እንዲቀጥል ምቹ ዕድል ሰጥቷል፡፡

ወገን ሆይ! ስለ ዲሞክራሲ (መስፍነ ሕዝብ) ሥርዓት መመሥረት መታገሉን ምንንትስ እርሱት፡፡ በአሁኑ ሰዓት ይሄ ዓይነት ትግል ለአማራ ሕዝብ ሲበዛ ቅንጦት ነውና፡፡ መጀመሪያ በገዛ ሀገርህ አማራ በመሆንህ ብቻ እንደ አውሬ በየትም ቦታ እየታደንክ ከመታረድ ከመቃጠል ከመሳደድ ወጥተህ እንደሰው የመኖር መብትህን አረጋግጥ!!

በዚህ መጽሐፍ የተዘረዘሩ ግፎችን ስንመለከት ወያኔ ኦነግና ሌሎች የጥፋት ኃይሎች እንደ አኖሌ ያሉ የፈጠራ ስም የማጥፋት ክሶችን እውነት እያስመሰሉ ለምን እየፈጠሩ እንደሚያናፍሱና እንደሚያራግቡ በሚገባ ግልጽ ይሆንለታል፣ የጥፋት ኃይሎቹ እጅግ አስገራሚ በሆነ ሁኔታ በምን ያህል ደረጃ ደንቆሮዎች, የማሰብ ችሎታቸው እጅግ የተገደበና ኃላፊነት የሚባል ነገር ቅንጣት ታክል እንኳ የማይሰማቸው መሆናቸውን ይረዳል፡፡ ምክንያቱም ይሄንን አረመኔያዊ ግፍ በዚህን ያህል ስፋትና ጥልቀት በደል በሌለባቸው ወገኖች ላይ አማራ መሆናቸውን ብቻ ወንጀል አድርገው ጥቃቱን ሲፈጽሙ ወደፊት እነሱን ምንም ዓይነት ዋጋ ሳያስከፍላቸው የአንድ ሰሞን ተራ ወሬ ሆኖ የሚቀር ተራ ነገር እንደሆነ አድርገው ያስባሉና ነው፡፡

ይሄንን ባለፉት 25 ዓመታት በአማራ ሕዝብ ላይ የተፈጸመውን በመጽሐፉም ውስጥ የተገለጸውን በታሪክ ጨካኝና አረመኔያዊ ግፍ በሕዝባችን ላይ ፈጽመዋል የተባሉት ፋሺስት ጣሊያን፣ ግራኝ አሕመድና ዮዲት ጉዲት እንኳን ፈጽሞ ያልሞከሩትን ሰው የአንድ ዘር አባል (አማራ) በመሆኑ ብቻ ሰብአዊና የዜግነት ክብሩን እጅግ ከተዳፈረው፣ ሥነልቡናን እጅግ ከሚያውከው፣ ጭንቅላትን እጅግ ከሚያደማው በርካታ የበደል ዓይነቶች አንሥቶ ፈጽሞ ለማመን በማይቻል ደረጃ እንደበግ ታርዶ ኩላሊቱና ጉበቱ በሚጥሚጣ እየተጠቀሰ እስከመበላት ድረስ በሰው ልጆች ታሪክ ታይተውና ተሰምተው የማያውቁ የግፍ ዓይነቶች መፈጸሙን ስመለከት እጅግ ግርም የሚሉኝ ሰባት ነገሮች አሉ፡፡

1ኛ. ይህ አማራን ከሀገር መንጥሮ የማጥፋት እርምጃ ወያኔ ክልል ብሎ በሚጠራቸው የሀገሪቱ የግዛት አሥተዳደሮች ሁሉ በሱ ትዕዛዝ ይህ ሁሉ ግፍ በአማራ ማኅበረሰብ ላይ ሲፈጸም በወያኔና ግብረ አበሮቹ ቀስቃሽነት አነሣሽነት ገፋፊነት አቀነባባሪነት አደራጅነት ካልሆነ በስተቀር በእየአካባቢው ሕዝብ የራስ ተነሣሽነት የተፈጸመ አለመሆኑ፡፡

2ኛ. በእነዚያ ወያኔ ክልል በማለት በሚጠራቸው የሀገራችን ክፍሎች ያለቀው የአማራ ማኅበረሰብ ሊያርዱት፣ ገደል ሊወረውሩት፣ ሊረሽኑት፣ ሊያቃጥሉት እየወሰዱት ወይም እያጎሩት እንደሆነ እያወቀ ሦስትና አራት ቦታዎች ላይ ከተደረገው በስተቀር በአልሞት ባይ ተጋዳይነት መንፈስ ወይም “ሞቴ ካልቀረ ጠላቴን ይዠው ልሙት!” በሚል መንፈስ አንገቱን እያነቁም ይዘውት አብረው ገደል እየተወረወሩም መሞት ሲገባቸው ለመሥዋዕት እንደሚነዳ በግ ዝም ብለው መታረዳቸው፣ ገደል መወርወራቸው፣ መረሸናቸው፣ መቃጠላቸው፡፡

3ኛ. ይሄ ሁሉ ሕዝብ “አማራ ነህ!” ከሚለው ምክንያት በተጨማሪ በክርስቲያንነቱ ከነ አብያተክርስቲያናቱ እየተቃጠለ፣ እየታረደ፣ እየተሠየፈ ሲፈጅ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን እንደተጠቂነቷና ጉዳዩ በቀጥታ እንደሚመለከተው አካል ለአንድም ጊዜ እንኳ ጠንካራ የአቋምና የኃዘን መግለጫ አሰምታ አለማወቋ ጉዳዩንም አለመከታተሏ፡፡

እርግጥ ነው በዚህ 25 ዓመታት የቤተክርስቲያኗን የሥልጣን ቦታዎች በየእርከኑ የወያኔ የውሸት ካህናት ተቆጣጥረው እንደያዙት ግልጽ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ይህን ዓይነት እርምጃ ቤተክርስቲያን ትወስዳለች ብሎ ማሰብ ፈጽሞ የማይታሰብ የማይጠበቅም ነው፡፡ ይሁን እንጅ የወሳኝነት የሥልጣን ቦታ አይሁን እንጅ የአገልግሎት የሥልጣን ቦታ ላይ ከጵጵስና እስከ ዲቁና ያሉ በርካታ የአማራ ተወላጆች አሉ አይደለም ወይ? (ጉዳዩ በቀጥታ የአማራ ተወላጆችን ይመለከታል ለማለት ነው እንጅ ይሄንን አረመኔያዊ ግፍ ማውገዝስ የሁሉም ሰው ግዴታ ነበር፡፡)

እናም እነኝህ ሰዎች እንደእረኝነታቸው በግልም ይሁን በቡድን ምን ያደረጉት ነገር ነበር? “ስለበጎችህ ቤዛ እራሴን አሳልፌ እሰጣለሁ!” ብለው በክርስቶስ ፊት ቃል ገብተው የእረኝነትን ሥልጣን ከተቀበሉ በተለይም “መነኮስኩ ነገንዠ ሞትኩ!” ካሉ በኋላ ምን የሚያስፈራቸውና ወደኋላ የሚስባቸው ነገር ኖሮ ነው ለክርስቶስ የገቡትን ቃልና ክርስቶስ የጣለባቸውን አደራ እየበሉ ጭጭ ያሉት?

“ምእመናን በአብያተክርስቲያናት ውስጥ እየታጎሩ ተቃጠሉ፣ ተመንጥረው በመጨፍጨፋቸው ይኖሩበት የነበረው ሀገር ወና ሆነ አብያተክርስቲያናቱንም አሕዛቡ አረማዊያኑ ከመዘበሯቸው በኋላ ጫት ማመንዠኪያቸው አደረጓቸው!” የሚለው ለሚሰማው ሁሉ ጆሮዎቹን ጭው የሚያደርግ የቤተክርስቲያን ታላቅ መርዶ ያልገደደው፣ ያልተሰማው፣ ኃላፊነቱንና ግዴታውንም ለመወጣት ያልቻለ እረኛ “እረኛ ነኝ!” ብሎ አፉን ሞልቶ ያወራል??? አደራቹህን! ሥራቹህ ቁልጭ አድርጎ እንደሚመሰክርባቹህ እናንተ ምንደኞች እንጅ እረኞች አይደላቹህምና ተሳስታቹህም እንኳ ቢሆን “የመንጋው እረኞች፣ የቤተክርስቲያን ጠባቂ ነን!” እንዳትሉ! የምታመልኩትም የምታገለግሉትም ሆዳቹህን እንጅ እግዚአብሔርን አይደለምና ይሄን ትሉ ዘንድ በፍጹም በፍጹም የተገባቹህ አይደላቹህም!

4ኛ. ምንም እንኳን ብአዴን ትግሬ ተሰግስጎ የሞላበት የወያኔ አሻንጉሊት ድርጅት ቢሆንም ያሉትንም ያህል ቢሆን የአማራ ተወላጅ የሆኑ ወይም ነን የሚሉም በሽዎች የሚቆጠሩ አሉና እነኝህ ሁሉ እያሉና ድርጅቱ “ለአማራ ሕዝብ መብት ነፃነት ህልውናና ጥቅም የቆምኩ ነኝ!” ብሎ እየለፈፈ እያለ በተባባሪነትና በቀጥታ ተሳታፊነት በአማራ ሕዝብ ላይ ሲፈጸም በቆየውና እየተፈጸመም ባለው የዘር ማጥፋትና ማጽዳት በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸም ከፍተኛ ወንጀል ውስጥ መገኘታቸው፡፡

መቸስ ትንግርት ነው! ሰው ራሱን ይበላል? እጅግ የሚያስገርመው ነገር ደግሞ ብአዴን ይሄንን እያደረገ ያለው ወያኔ ሌት ተቀን ለሚደክምለት ለትግሬ ሕዝብ ጥቅም መሆኑ ነው፡፡ “የብአዴን አማሮች የገዛ ሕዝባቸውን ለትግሬ ጥቅም ሲሉ ይፈጃሉ ያስፈጃሉ!” ሲባል እንዴት ሊሆን እንደቻለ በጣም ግራ አይገባቹህም? እጅግ አይደንቃቹህም? አሁን እነዚህ ብአዴን ውስጥ ያሉ አማሮች ሰው ነን ብለው ሳያፍሩ ከሰው ፊት ይቀርባሉ? እንደሚቀርቡማ ዕለት ዕለት ዕያየናቸውም አይደል! ግን ምን ጉድ ፍጥረቶች ቢሆኑ ነው? እውነት ግን እንደኛ ሰዎች ናቸው? ምንድን ነው እንደዚህ ተናጋሪ ዕቃ ወይም ተናጋሪ እንስሳ ሊያደርጋቸው የቻለው? ዕቃ ወይም እንስሳ ብቻ ነው ለምን? እንዴት? ሳይል እንዲያደርግ ያስደረጉትን ነገር ዝም ብሎ የሚያደርገው፡፡

ከዚህ ቀደም የብአዴኑ አቶ ታምራት ለዓይኔ ምን ብሎ ቀስቅሶ የአማራን ሕዝብ እንዳስፈጀው እናውቃለን፡፡ በዚህ መጽሐፍ ላይ ደግሞ ሌላኛው የብአዴን ባለሥልጣን የዛሬው ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን 1983/84ዓ.ም. ላይ መንታ ውኃ አካባቢ ሰዎችን አደራጅቶ በአብዛኞቹ የመተከል ሰፋፊ ጫካዎች ውስጥ ከ50 እስከ መቶ እርምጃ ልከ እምብርት (ራዲየስ) ርቀት ውስጥ ሲያንስ በአንድ ሲበዛ በበርካታ የአማራ ተወላጆች አስከሬን እንዲሞሉ ያደረገ፣ 1986ዓ.ም. ፓዊ በገበያ ቀን ሀገር ሰላም ብሎ በደራ ገበያ ሲገበያይ የነበረን በሽዎች የሚቆጠርን የአማራ ሕዝብ በድንገት ዙሪያውን አስከብቦ በመትረጊስ እርምት አድርጎ በማስፈጀት ገበያ የነበረውን ሜዳ ወደ የሰው ቄራነት በመቀየር በአስከሬን ቁልልና በሕዝብ ደም ኩሬ ማጥለቅለቁ በድፍን የመተከል የቻዌ ነዋሪ ይታወቃል፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን አማራ ነው ይባላል፡፡ ከሆነ እሱና ያንን እልቂት የፈጸሙት ጓዶቹ እንዴት በገዛ ወገናቸው ላይ ምንም በደል ሳይኖርበት የእነሱን አማራነት የት ጥለውት ነው አማራነቱን ወንጀል አድርገው እንዲህ ሊፈጁት የቻሉት? ዘር ደም ከሆነ ብአዴኖች የአማራነት ደማቸውን እንዴት አድርገው ቀድተው ደፍተው ቀይረውት ነው አማራነትን ወንጀል አድርገው እንዲህ ሕዝብ ለመፍጀት የበቁት? በገዛ ወገናቸው ላይ እንዲህ ዓይነት ክሕደት ፈጽመው የፈጁ ሰዎች በደም ለማይዘመዳቸው ለማይመስላቸው ለራሱ ለወያኔ (ለትግሬ) እንዴት ነው ታማኝ ሊሆኑ የቻሉት??? ይሄ የሆነው በአንዳች መተት ወይም አጋንንታዊ ኃይል ካልሆነ በስተቀር አንድን ሰው ለራሱ ለሥጋው ለወገኑ ያለውንና ሊኖረውም የሚገባውን አግባብነት ያለው ተቆርቋሪነትን አጥፍቶ፣ ሚዛናዊ አመለካከቱን አዛብቶ እንደ ዕቃ ወይም ሮቦት (ምስለ ፍጡር) እንደፈለጉ እያሽከረከሩ “ለምን? እንዴት?” ሳይል እንዲህ ዓይነት አረመኔያዊ ድርጊት በገዛ ወገኑ ላይ በግፍ እንዲፈጽም ማድረግ እንዴት ነው የቻሉት???

ብዙዎቻቹህ “ኧረ ባክህ! የምን መተት ነው ደግሞ? ሰዎቹ ከልክ በላይ ራሳቸውን ስለሚወዱ ለግል ጥቅማቸው ብቻ ስለሚያስቡ ነው!” ትሉኝ ይሆናል፡፡ ለእኔ ግን ይሄ አሳማኝ ምክንያት አይደለም፡፡ ምክንያቱም ሀገርና ወገን በሌሉበት ሁኔታ እኮ “እኔ” ማለትና የግል ጥቅም የሚባል ነገር እኮ ሊኖር አይችልም! በእርግጥ ይሄው በሰዎቹ ላይ እያየን እንዳለነው ለጊዜው ሊመስል ይችላል፡፡ ስር መሠረትና ዘለቄታዊነት ግን አይኖረውም፡፡

“የሰው ልጅ ማኅበራዊ ፍጡር ነው!” ይባላል፡፡ ትክክልም ነው፡፡ የሰው ልጅ “እኛ” ማለት ካልቻለ “እኔ” ብሎ መኖር ፈጽሞ አይችልም! እኛ ሲል ደግሞ እኛ ሊል የሚገባው ሀገርንና ሕዝብን በፍትሐዊነት ተጠቃሚ ማድረግን መሠረት በማድረግ ካልሆነ በስተቀርና “እኛ” የሚለው ሰው የሱን ቢጤዎች አራዊት ሰብስቦ እነሱን እያሰበ ከሆነ ገና “እኛ” ማለት አልጀመረም፡፡ “እኛ” የሚሉ መሰላቸው እንጅ “እኔ” ነው እያሉ ያሉት፡፡

የሰው ልጅ “እኛ” ማለት ካልቻለ በስተቀር ለአንዲት ነፍሱ ሳይሳሳ የሚሠዋላት የጋራ ሀገር ሊኖረው አይችልም! የሰው ልጅ ራሱን ሲወድ ጥሩ ነው፡፡ ያኔ ነውና “እኛ” ማለት የሚችለው፡፡ “እኛ” ማለት ሳይችል ያለሥጋትና አደጋ የሚወደውን እራሱን ተጠቃሚ ማድረግ እንደማይችል ጠንቅቆ ያውቃልና ነው ማኅበራዊ ሰላሙ “እኔ” በሚሉ ከመታወኩ ነጻ ሆኖ ባያውቅም “እኛ” በማለት የጋራ ሀገር መሥርቶ አብሮ ለመኖር የቻለው፡፡

በመሆኑም ይህ የብአዴን ሰዎች ችግር የራስ ወዳድነት ችግር አይደለም፡፡ ምንድነው ታዲያ? ካላቹህኝ፦ ሌላ ምንም ሳይሆን በሆዳምነታቸው ላይ እጅግ ከባድ የሆነ የአእምሮ፣ የአስተሳሰብ፣ የሥነ ልቡና መታወክና መዛባት ችግር (Mental & Psychological disorder) ያለባቸው ስለሆኑ ነው፡፡ ለዚህም ነው ባደረጉትና በሚያደርጉት ኢሰብአዊ ግፍ ሁሉ እንደ ሰው ቅንጣት ታክል እንኳ የማይሰማቸው፣ የማያሳስባቸው፣ የማይገዳቸው፣ ኃላፊነት የማይሰማቸው ሊሆኑ የቻሉት፡፡ ራሳቸው፣ የሚያገለግሉት ወያኔ፣ የኢትዮጵያም ሕዝብ ተጠቃሚ የማይሆኑበትን ተግባር ታጥቀው እየፈጸሙ ያሉት፡፡

5ኛ. ይህ ሁሉ አረመኔያዊ የዘር ማጥፋትና ማጽዳት በዚህ ክ/ዘ ይፈጸማል አይደለም ይታሰባል እንኳ የማይባል እጅግ አደገኛው በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸም ወንጀል እራሱን “የኢትዮጵያ መንግሥት ነኝ!” ባለ ኃይል አደራጅና አቀነባባሪነት ያለማሰለስ በስፋት ላለፉት 25 ዓመታት ያህል ሲፈጸም ምሁራኑ በተለይም የአማራ ምሁራን በግልም ይሁን በመደራጀት ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ማጋለጥንና ጉዳዩ የሚገባውን ትኩረት እንዲያገኝ ማድረግን ጨምሮ ሊያደርጉት የሚገባቸውን ሁሉ አለማድረጋቸው፡፡

እርግጥ ነው የቀድሞው ኢሰመጉ የአሁኑ ሰመጉና ሌሎች ተመሳሳይ ድርጅቶች ላስተማራቸው ሕዝብና ሀገር የሚጠበቅባቸውን ለማበርከት የሚጥሩ ምሁራን ፍሬዎች መሆናቸውን እረዳለሁ፡፡ ይሁንና ግን እነኝህ ድርጅቶች ያለብንን ፈተና በሚመጥን ጥንካሬ ትጋትና ቁርጠኝነት ነው ወይ እየሠሩ እየታገሉ ያሉት? እንዳልሆነ ሁላችንም እናውቃለን፡፡

አሁንም እርግጥ ነው መጽሐፍ በመጻፍ፣ ይህን የዘር ፍጅት የPHD (የሊቀ ጥብና) ትምህርታቸው የመመረቂያ ጽሑፍ ርእሰ ጉዳይ በማድረግና በሌሎችም መድረኮች ሦስት አራት የሚሆኑ ምሁራን ይሄንን የወያኔን አረመኔያዊ ተግባር ያጋለጡ አሉ፡፡ ሊመሰገኑም ይገባል፡፡

ነገር ግን ይሄ ሕዝብ ያስተማረውና ኃለፊነቱም ያለባቸው እነዚህ ብቻ ናቸው ወይ? የተቀረውስ? በእውነት በእውነት ምሁሩ ክፍል በዚህ ጊዜ የማይሰጥና አንገብጋቢ ጉዳይ ላይ የሚጠበቅበትን ርብርብ አለማድረጉና ዝም ጭጭ በማለቱ የወገኑ ደም ዕዳ አለበት! ለምንስ ጭጭ አላቹህ? እንዴት ነው ታዲያ እናንተ ያዳፈናቹህትን ያልተናገራቹህትን ባዕዳኑ እንዲጮሁት እንዲያስተጋቡት ልንጠብቅ የምንችለው? ከቶ እንዴትስ አስቻላቹህ? እንቅልፉስ እንዴት ተተኛላቹህ? እህልስ እንዴት ተበላላቹህ? ይሄ ድሀ ሕዝብ በድህነት አቅሙ ሳይማር እናንተን አስተምሮ ለዚህ ካበቃበት ዐበይት ምክንያቶች አንዱ ለእንደዚህ ዓይነቱ ክፉ ቀን እንድትደርሱለት ነበር እንጅ ወደ አደጉ ሀገራት ጣጥላቹህት እየሔዳቹህ እራሳቹህን በምቾት እያኖራቹህ እንድትረሱት ወይም ከንፈር እንድትመጡለት ነው ወይ???

6ኛ. የተባበሩት መንግሥታት፣ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችና ኃያላን መንግሥታት ይህ በዚህ ዘመን ይሆናል ተብሎ በፍጹም የማይታሰብ አረመኔያዊ የዘር ማጥፋትና ማጽዳት በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸም የመጨረሻ ወንጀል መንግሥት ነኝ በሚል አካልና አጋሮቹ በተለያዩ ቦታዎች ትናንትና እስከሸኘነው 2008ዓ.ም. ድረስ በአማራ ሕዝብ ላይ በስፋት ሲፈጸም እንደቆየና እየተፈጸመም እንዳለ እያወቁ መረጃዎች በሚገባ እያሏቸው ለእንዲት ጊዜም እንኳ ቢሆን መግለጫ አውጥተው አለማውገዛቸው፡፡

መረጃው ስለሌላቸው ስላልሰሙ እንዳይመስሏቹህ እንዳላዩና እንዳልሰሙ ሆነው ዝም ጭጭ ያሉት፡፡ እነኝህ ዓለም አቀፍ አካላት በወያኔና በሌሎቹ የጥፋት ኃይሎች በአማራ ዘር ላይ ለተፈጸመችው ለእያንዳንዷ የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ወንጀል መረጃው በሚገባ እንዳላቸው መቶ በመቶ እርግጠኛ ነኝ፡፡ እነሱ እንኳንና በብዙኃን መገናኛዎች ሳይቀር በተደጋጋሚ የተዘገበባቸውን የአደባባይ ምሥጢሮች ይቅርና ወያኔ ተቃዋሚዎችን ለመወንጀል እያጠመደ ያፈነዳቸውንና ንጹሐንን የፈጀባቸውን የፈንጅ ጥቃቶች ሳይቀር ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ እኛ ዜጎች በሀገራችንና በራሳችን ላይ መፈጸሙን ፈጽሞ የማናውቀውን ስንት የተሠወረ ጉድ ሁሉ በሚገባ ያውቃሉ፡፡

እነሱ ሰሜን ኮሪያ፣ ኤርትራ፣ ሶሪያ፣ ቻይና፣ ኢራን ምንትስ እያሉ “በዓለማችን ላይ የሰብአዊ መብቶች እጅግ የሚጣስባቸው ሀገራት!” እያሉ ያብጠለጥላሉ እንጅ የሁሉም ግፍ ቢደመር ወያኔ የፈጸመውን ቅንጣት እንደማያክል በሚገባ ያውቃሉ፡፡ እነኝህ ከላይ የተጠቀሱት ሀገራት ፈጸሙ የተባሉት ወንጀል የሰብአዊ መብት ጥሰት ነው፡፡ ወያኔ ግን የፈጸመውና እየፈጸመው ያለው በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸመውን የመጨረሻ ወንጀል የዘር ማጥፋትና ማፅዳት ወንጀልን ነው፡፡ በመሆኑም በዚህች ዓለም ላይ ፍትሕና ርትዕ ቢኖር ኖሮ በዚህች ዓለም የወያኔን ያክል የሚወገዝና እርምጃ የሚወሰድበት አገዛዝ ከቶውንም ባልነበረ፡፡

“እና ታዲያ እነዚህ ምዕራባውያን መንግሥታት በተለይም የተባበሩት መንግሥታትና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ለሰብአዊ መብቶች መጠበቅ ቆመናል! እያሉ በዚህ ዘመን ፈጽሞ የማይጠበቀውን የወያኔን አረመኔያዊ ወንጀል ካወቁ ለምንድነው የማያወግዙትና እርምጃስ የማይወስዱበት?” ካላቹህኝ ኃያላኑ ሀገራት እስከዛሬ በወያኔና አጋሮቹ በይፋ የሚደረገውን የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ወንጀል አለማውገዛቸውንና ለማውገዝም አለመፈለጋቸውን በምናይበት ጊዜና ወያኔም በአቶ አቦይ ስብሐት በኩል ያለአንዳች የተጠያቂነት ስሜትና ፍርሐት በአደባባይ “የአማራንና የኦርቶዶክስን አከርካሪ እንዳያንሰራራ አድርገን ሠብረናል!” ብሎ መናገሩን ስንመለከት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየታተሙ በሚወጡ መጻሕፍት ላይ “ኃያላኑ ሀገራትና ወያኔ በአውሬው 666 የዲያብሎስ መንፈስ እየታዘዙና እየተመሩ ይሄንን ወንጀል በሀገራችንና በሃይማኖታችን ለመፈጸም በርትተው እየሠሩ ነው!” በማለት የሚያቀርቡትን ክስ እንድናምን ያስገድደናል፡፡

ይህ የመጻሕፍቱ ክስ እውነት ሆነም አልሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት የጀርባ አጥንት የሆነው የአማራ ሕዝብ ጉልበቱን እግዚአብሔርን አድርጎ ውጊያውን መዋጋት ግዱ መሆኑን ጠንቅቆ ሊያውቅ ይገባል፡፡ እዚህ ላይ ምንም ዓይነት መዘናጋት እንዳይኖር እጅግ ጥንቃቄ እንዲደረግ አጥብቄ ማሳሰብ እወዳለሁ፡፡ እርግጥ ነው በእርኩሰት ተዳድፈን ለይስሙላ በዘልማድ ካልሆነ በስተቀር እንደቀድሞው ከልብ በንጽሕናና ቅድስና በሚደረግ አገልግሎትና አምልኮ ከእግዚአብሔር በመራቃችን እግዚአብሔር ለዚህ ውርደት ስብራትና ጥፋት አጋልጦናል፡፡ እነኛ አብያተክርስቲያናት በአረማውያኑ ሲቃጠሉ ሲፈርሱና አሕዛብ አረማውያኑ የጫት ማመንዠኪያ ስፍራቸው ሲያደርጓቸው የተደፈረው ክብር የእሱም መሆኑን እግዚአብሔር አጥቶት አይደለም እንደማያይና እንደማይሰማ በዝምታ እየተመለከተ ያለው፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔርን አሕዛብ አረማውያኑን በደል እንደፈጸሙ እንዲቀስፍ እንዲበቀላቸው ወይም ደግሞ ምንም እንዳልተፈጠረ ዝም ብሎ እንዲመለከት የሚያደርገው የእኛው ሥራ ነው፡፡

የካህኑን የዔሊንና የልጆቹን የአፍኒንና የፊንሐስን ሥራ አስታውሱ፡፡ 1ኛ ሳሙ. ከም. 2-4 የእነሱ መበደል ታቦተ ጽዮን በአሕዛብ እጅ እንድትማረክ፤ ወስደውም እንደምናምንቴ በጣኦት ቤታቸው ከጣኦታቸው ስር እንዲወረውሯት፣ እስራኤላውያንም በጦርነቱ እንዲሸነፉና እንዲዋረዱ እንዲደቆሱም እንደዳረጋቸው አስታውሱ፡፡

እኛም በራሳችን ላይ እየደጋገምነው ያለነው ይሄንን ታሪክ ነው፡፡ እግዚአብሔር የሚፈልገው ንጹሕ እኛነታችን ነው እንጅ ከረከሱ እጆች የሚበረከት ገንዘባችንን አይደለም፡፡ እራሳችንን ሳንቀድስ እያሳመፅንና እያረከስን ሕንፃ ቤተክርስቲያኑን በግንብ አይደለም በዕንቁ እንኳ ብንሠራለት ለእሱ ምኑም አይደለም! አይደሰትበትምም፡፡ እንዲያውም አጥፊ ያዝበታል፡፡ ነገር ግን እንዳስቻለን መጠን እራሳችንን ቀድሰን ሕንፃ ቤተክርስቲያኑን ወይም የእግዚአብሔርን ቤት በጭራሮ እንኳን ብንሠራው ለእሱ በዕንቁ ከተሠራም በላይ ነው፡፡ ይሄንን ልብ ልንል ይገባል፡፡

ካልሆነ ግን እሱ ምንጊዜም ቢሆን የዐመፃን ዋጋ ከመክፈል ወደ ኋላ አይልም፡፡ ቃሉም እንደሚል “እሽ ብትሉ ለኔም ብትታዘዙ የምድርን በረከት ትበላላቹህ እንቢ ብትሉ ግን ብታምፁም ሰይፍ ይበላቹሀል” ትን.ኢሳ. 1፤19-20 እንዳለው ይህ ሁሉ ጉድ የመጣብንና የተሰበርነው እንቢ በማለታችን በማመፃችን መሆኑን መገንዘብ ይገባናል፡፡

መቀጣታችን ሌላም ዐቢይ ምክንያት አለው ቃሉ እንዲህ ይላል “ልጀ ሆይ የጌታን ቅጣት አታቃልል በሚገሥጽህም ጊዜ አትድከም ጌታ የሚወደውን ይቀጣዋልና የሚቀበለውንም ልጅ ሁሉ ይገርፈዋል፡፡ ብሎ የሚነጋገረውን ምክር ረስታቹሀል፡፡ ለመቀጣት ታገሡ እግዚአብሔር እንደ ልጆች ያደርጋቹሀልና፡፡ አባቱ የማይቀጣው ልጅ ማን ነው? ነገር ግን ሁሉ የቅጣት ተካፋይ ሆኗልና ያለ ቅጣት ብትኖሩ ዲቃሎች እንጅ ልጆች አይደላቹህም፡፡ ከዚህም በላይ የቀጡን የሥጋ አባቶች ነበሩን እናፍራቸውም ነበር እንዴትስ ይልቅ ለመናፍስት አባት አብልጠን ልንገዛና በሕይዎት ልንኖር በተገባን? እነሱ መልካም ሆኖ እንደታያቸው ለጥቂት ቀን ይቀጡን ነበርና እርሱ ግን ከቅድስናው እንድንካፈል ለጥቅማችን ይቀጣናል፡፡ ቅጣት ሁሉ ለጊዜው የሚያሳዝን እንጅ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም ዳሩ ግን በኋላ ለለመዱት የሰላምን ፍሬ እርሱም ጽድቅን ያፈራላቸዋል” ይላል ቃሉ ዕብ. 12:5-11፡፡

“የእስራኤል ልጆች ሆይ! እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላቹህምን? ይላል እግዚአብሔር” ትን. አሞ. 9፤7 በመሆኑም እኛ ኢትዮጵያዊያን ልጆች እንጅ ዲቃሎች አይደለንምና ምንም ቢበድሉ የቱንም ያህል ቢረክሱ ቢያምፁበትም ምንም እንደማይላቸው እንደ ሌሎች ሀገራትና ሕዝቦች ዝም አይለንም፡፡ እሽ እስክንልና እስክንመለስ ድረስ ይቀጣናል እንጅ፡፡ ስለሆነም ትቶ ላይተወን ነገር እሱን “እሽ!” ካለማለት በስተቀር ሌላ ምንም መፍትሔ የለንምና እሽ እንበል! ንስሐ እንግባ! ወደ እግዚአብሔር እንመለስ! ከዚያ እንደ እናት አባቶቻችን ለእግዚአብሔር ታምነን ስሙን ጋሻና ጦራችን አድርገን ያለብንን ውጊያ እንዋጋ በእኛና በጠላቶቻችን መሀከል ያለው የኃይል አሰላለፍ ልዩነት የሰማይና የምድር ያህል ርቀት ቢኖረውም እንኳ ያለጥርጥር እናሸንፋለን!!!

7ኛ. የወያኔ የኦነግና የሌሎች የጥፋት ኃይሎች ድንቁርና፡፡ እነኝህን ሰዎች ሳስብ ዓለም እንደዛሬው አንድ መንደር ሆና በአንደኛው የዓለም ጫፍ የተደረገው በሌላኛው የዓለም ጫፍ ላለው ምን እየተደረገ እንዳለ በዓይን ቅጽበት በሚታወቅበት ዘመን ሳይሆን ጥንት ሥልጣኔ ባልነበረበትና አንዱ ስለሌላው መረጃ በማያገኝበት ዘመን ላይ ይሄንን ሥልጣን የያዙ ሆነው ቢሆን ኖሮ ምን ሊያደርጉን ይችሉ እንደነበር ሳስብ በጣም ያስፈራኛል፡፡ እርግጥ ነው ወያኔ “መረጃ በዓይን ቅጽበት ከአንዱ የዓለም ጫፍ ወደሌላው በሚደርስበት ዘመን ላይ ነው ያለሁትና” ብሎ ምንም ነገር ከማድረግ አልተቆጠበም፡፡ ይሁንና ግን ይሄንን ሁሉ ጉድ ስናይ “በዚህ ዘመን ይሄንን ያደረገ በዚያ ዘመን ቢሆን ኖሮስ ምን ሊያደርግ ይችል ነበር?” ያሰኛል፡፡ አንድ ሰው ወይም ቡድን ኃላፊነት ተጠያቂነት ሰብአዊነት የማይሰማው፣ ነገን የማያስብ ሆኖ ካገኛቹህት ምንም ስለሆነ እንዳይመስላቹህ! ደንቆሮ ስለሆነ ብቻና ብቻ ነው፡፡ የድንቁርናቸው ድድርናና ጥልቀት እንደየሚሠሩት አውሬአዊ ተግባሮቻቸው ይወሰናል፡፡

ወያኔ ኦነግና ሌሎች የጥፋት ኃይሎች ይሄንን የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ወንጀል በአማራ ሕዝብ ላይ ሲፈጽሙ በየቦታው የሚሰጡት ምክንያት የተለያየ ነው፡፡

ወያኔ ኦሮሚያ ብሎ በከለለው አካባቢ የሚጠቀሰው ምክንያት፦ “እናንተ የምኒልክ ዘሮች ናቹህ! ምኒልክ አሩሲ ሔጦሳ ላይ የወገኖቻችንን እጅና ጡት ቆርጧል!” የሚል ምንም ዓይነት መረጃ የሌለው ፋሽስት ጣሊያን “ልመሠርተው ያሰብኩትን ቅኝ አገዛዝ ያከሽፍብኛል!” ብሎ የፈራውን አማራን ለማስጠቃትና የሕዝቡን አንድነት ፈረካክሶ ለማዳከም ሆን ብሎ ፈጥኖ ያወራውን በጊዜውም ተሳክቶለት በአማራ ላይ ብዙ ግፍ እንዲፈጸምበት ለማድረግ አስችሎት የነበረውን የፈጠራ ወሬ ይዘው “እንበቀላቹሀለን!” በማለት እንደሆነ ይነገራል፡፡ ይሁንና አሁን አሁን እንኳ ይህ ወሬ ነጭ ውሸትና ፈጠራ መሆኑንና ወያኔና ኦነግ ለተመሳሳይ ዓላማ ከፋሺስት ጣሊያን ተውሰው ያመጡት የፈጠራ ወሬ መሆኑን እኛ ብቻ ሳንሆን የኦሮሞ ምሁራንም ሳይቀሩ ያረጋገጡት ሀቅ በመሆኑ ይሄንን ፈጠራ ምክንያት ማድረግ አይቻልም፡፡

ሌላኛው ወያኔ ኦሮሚያ ሲል በከለለው የሀገራችን አካባቢ የሚጠቀሰው ምክንያት ደሞ “አኛ የሀገሩ ሰዎች ደሀ ሆነን እያለ እናንተ ያለሀገራቹህ መጥታቹህ በእኛ ላይ ሀብታም ሆናቹህብን!” የሚል ነው፡፡ የገጠሩ ሰው ብዙ የሚያውቀው ነገር የለምና ወያኔና ኦነግ እውነት አስመስለው ለጥቃት ሲያነሳሡት የሚነግሩትን ነገር እንዳለች ይተፋታል፡፡ ሀቁ ግን ማን የመሬቱ ባለቤት፣ ማን ደግሞ በወረራና በመስፋፋት ይሄንን መሬት ከመቸ ጀምሮ ማንን አፈናቅሎ አሰድዶና አጥፍቶ ይሄንን መሬት እንደያዘ በግልጽ ይታወቃልና ወደ ሐተታ መግባት አያስፈልገኝም፡፡ ነገር ግን ወያኔ በገዛ ሕገመንግሥቱ ላይ “ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በሀገሪቱ በየትኛውም አካባቢ በነጻ የመዘዋወር፣ ኑሮን የመመሥረት፣ ሀብት የማፍራት መብቱ የተጠበቀ ነው!” እያለ በጎን ደግሞ ለየ ክልል ለሚለው አሥተዳደር የዚህን ተቃራኒ መልዕክት እየረጨ አማራን መጨፍጨፍ ማስጨፍጨፍ ማፈናቀሉ ደንቆሮነቱን፣ ኃላፊነት የማይሰማው የወሮበላ ቡድንነቱን፣ አርቆ ማሰብ አለመቻሉን እንጅ ሌላ የሚያረጋግጠው ነገር የለም፡፡

ወያኔ “የደቡብ ክልል” ሲል በሚጠራው የሀገሪቱ ክፍል የሚጠቀሱት ምክንያቶች ደግሞ፦ ደን ያቃጥላሉ!፣ ሕገወጥ ሰፋሪ ናቸው!፣ ከተወላጁ ጋር ተስማምተው መኖር አይችሉም! ፣ ሀገራቹህ አይደለም ከሀገራችን ውጡልን! የሚሉ ናቸው፡፡

እያንዳቸውን ዕንይ፦ ደን ያቃጥላሉ! ያ አካባቢ ከብት አርቢ ማኅበረሰብ ያለበት አካባቢ ነው፡፡ ደርግ በሰፈራ “ውጡልን!” የተባሉትን ወገኖች እዚያ ከማስፈሩም በፊት ከብት አርቢዎቹ ለከብቶቻቸው መሬቱ በየዓመቱ አዳዲስ ሳር እንዲያበቅልላቸው የግጦሽ መሬቱን የማቃጠል ልማድ እንዳላቸው እየታወቀ ራሳቸው በሚለኩሱት እሳት ሁሌም ጠተያቂ የሚያደርጉት አማራውን ነው፡፡ መረጃ ተገኝቶ ደን ሲያቃጥል የተያዘ ሰው ኖሮ ያ ሰው በሕጋዊ መንገድ ቢቀጣ ምንም ባልነበረ ተገቢም ነው፡፡ የሚሆነው ይህ አይደለም፡፡ ቀድሞውንም ቢሆን ምክንያቱ የሚጠቀሰው ሆን ብሎ ለማጥቂያ ሰበብ ለመፍጠር ነው እንጅ በትክክል ስለተፈጸመ አይደለምና፡፡

ሕገወጥ ሰፋሪ ናቹህ! ወደሚሉት ምክንያት ስንሔድ እንዲህ እያሉ የሚያፈናቅሏቸው በሙሉ በደርግ መንግሥት የሰፈራ መርሐ ግብር የሠፈሩ ከዚያም በኋላ የገቡትም የእርሻ መሬት ተሰጥቷቸው ሕጋዊ የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ተሰጥቷቸው ግብር ሲከፍሉ የኖሩ ስለሆኑ ይሄኛው ምክንያትም አይሠራም፡፡

ከተወለለጁ ጋር ተስማምተው መኖር አይችሉም፦ በዚህ የሚወነጀል ካለ ያልተስማማው በምን ጉዳይ ነው? እንደ ዜጋ መብትና ግዴታውን በመተላለፉ ነው ወይ እንዲህ ሊባል የቻለው? ከሆነም ወንጀል የሠራ ሰው በሚጠየቅበት ሕግ ተጠይቆ በአግባቡ ማስቀጣት ነው እንጅ ሕጋዊው አሠራር ዛሬ ዜጎች ባሕር ተሻግረው በባዕዳን ሀገራት በነጻነት ሠርተው መኖር ኑሮን መመሥረት በተቻለበት ዘመን በገዛ ሀገራቸው ወንጀላቸው ምን እንደሆነ ሳይጠቀስ “ከተወላጁ ጋር ተስማምታቹህ መኖር አትችሉምና!” ብሎ ዜጎችን በጅምላ ማፈናቀል፣ መዝረፍ፣ መፍጀት፣ ማቃጠል የትኛው የወንጀል ሕግ የደነገገው ድንጋጌ ነው?

እጅግ እጅግ የሚያሳዝነው የሚያስደነግጠውና የሚያስገርመው ደግሞ “ከተወላጁ ጋር ተስማምታቹህ መኖር አትችሉም!” የሚለው ክስ ትርጉም አባዎራዎች ዋልጌና ውርጋጦች እቤታቹህ እደገቡ ባለቤቶቻቹህንና ልጆቻቹህን ሲደፍሩባቹህ፣ ከብቶቻችሁን ከበረትና ከመስክ እንደፈለጉ ነድተው ሲወስዱባቹህ፣ ከሱቆቻቹህ ያለክፍያ ዕቃ ያሻቸውን ያህል እያነሱ ሲወስዱባቹህ፣ በፀብ የሚተናኮላቹህ ጥጋበኛ ሲኖር ወዘተረፈ. ወዘተረፈ. ሲሆን ምንም እንዳልሆናቹህ ምናቹህም እንዳልተነካ በዝምታና በጸጋ ተቀበሉ! ማለት መሆኑን በደሉ ለተፈጸመባቸው ዜጎች ይህ ቃል የሚጠቀስላቸው እነኝህ በደሎች ተፈጽመውባቸው ፍትሕ ይሰጣቸው፣ የሚደርስባቸው ገደብ የለሽ ግፍ ይቆምላቸው ዘንድ ወደ ሕግ አካላት አቤት! ባሉ ጊዜ ሕግ ያስከብራሉ ከተባሉ ወንጀሉን ከሚፈጽሙት የባሱ እንስሳ ሕግ ያስከብራሉ ተብለው በኃላፊነት ከተቀመጡ ከሕግ አካላት ዘወትር የሚጠቀስላቸው ጉዳይ በመሆኑ ነው፡፡ መቸስ በጣም የሚገርምና እጅግም የሚያሳፍር ነገር ነው፡፡

ሀገራቹህ አይደለም ከሀገራችን ውጡልን! ወደሚለው ስንሔድ፦ ይሄንን ችግር የበለጠ ከባድና የተወሳሰበ የሚያደርገው ምን እንደሆነ ታውቃላቹህ? ጥቃት ፈጻሚዎቹ የበሰለ ንቃተ ኅሊና ደረጃ ላይ ያሉ አለመሆናቸው ነው፡፡ ጥቃት ፈጻሚዎቹ ሀገር ማለት ምን ማለት እንደሆነ፣ ይህች ሀገር እንደሌሎቹ ሀገራትና ሕዝቦች በቅኝ ተይዛ ሕዝቧ እንዴት በባርነት ተቀጥቅጦ እንዳልጠፋ፣ የሀገሪቱ የገጸ ምድርና የከርሰ ምድር ሀብቷ እንዴት ሳይቦጠቦጥ ሳይዘረፍ ሳይወሰድ እንደቀረ፣ ማን ምን ዓይነት መራራ መሥዋዕትነት ለሽዎች ዓመታት ሲከፍል ስለኖረ የሀገሪቱ መሬት እንደተፈጠረ ድንግል መሬት ሊሆን የቻለው፣ የተለያዩ ጎሳዎችም እንዳሉ ሳይበረዙ ሳይከለሱ እንደተፈጠሩ ለሥነ ሰብእ (ለአንትሮፖሎጂ) ጥናቶች ምቹ መሆናቸው እስኪመሠከርላቸው ድረስ የተጠበቁ ሆነው ሊገኙ እንዴትና በምን ምክንያት እንደቻሉ ቢያውቁ ኖሮ አማራን “ሀገራቹህ አይደለም! ሀገራችንን ለቃቹህ ውጡልን!” ሊሉ አይደለም ለውለታው ምንም ቢያደርጉ ቢከፍሉት የማይጨርሱት እጅግ የበዛ ዕዳ እንዳለባቸው ተረድተው አክብረውት አድንቀውት አመስግነውት ወደውት ባልጠገቡት ባልረኩ ውለታው ባስጨነቃቸው ነበር፡፡

ግን ምን ያደርጋል ድንቁርናና አለማሰብ አለማስተዋል የሚባል አውሬ በወገኖቻችን ላይ ሠልጥኖ በባለውለታው በአማራ ሕዝብ ላይ በማነሣሣት እንዲህ ዓይነት ግፍ እያስፈጸመበት ይገኛል፡፡ ምን ማድረግ ይቻላል? ዕውቀት እንደ ክትባት በመርፌ አይሰጥ!

ለማንኛውም ወያኔ ደቡብ ሲል በከለለው የሀገራችን ክፍል ለሚፈጸመው የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ወንጀል የሚጠቀሱ ምክንያቶች እነኝህን ይመስላሉ፡፡

ወያኔ ቤንሻንጉል ጉምዝ ሲል ወደሚጠራው የሀገራችን ክፍል ለጭፍጨፋው ወደሚጠቀሰው ምክንያት ስናልፍ ደግሞ የሚከተለውን እናገኛለን፦ “የክልላቹህ መንግሥት በማዳበሪያ ዕዳ ስለሚፈልጋቹህ ለቃቹህ ሒዱ!” የሚል ነው፡፡ የሚሉት እኮ ቢያጡ ነው! ለሚያይ ለሚሰማ “አማራ ስለሆኑና አማራ እንዲጠፋ ስለምንፈልግ ነው የምንጨፈጭፋቸው!” ላለማለት እኮ ነው እንጅ ሰዎቹ እዚያ ቦታ ላይ ያሠፈራቸው ደርግ በመላ ሀገሪቱ ይዞት በነበረው ሰፊ መርሐ ግብር ሳቢያ ነው፡፡

ስንት ችግርና ፈተናን አሳልፈው የሰፈሩባቸውን ቦታዎች ሁሉ ከአራዊቱ ከእባቡ ከጊንጡ ጋር ታግለው መሬቱን ሲያለሙትና ከዓመታት በኋላ የድካማቸውን ፍሬ መቅመስ ማጣጣም ሲጀምሩ “ብርቱና አርአያ አርሶ አደር!” እየተባሉ በየ የወያኔ ክልሉ የሚሸለሙት እነሱው ሲሆኑ ሰይጣን ያደረበት ሁሉ በቅናት ተቃጠለ “እኔ መጥፋቱን እፈልጋለሁ እሱ ጭራሽ ይፋፋልኛል? በል በልልኝ!” እያለ ይፈጀው ያዘ፡፡ እንጅ እውነቱማ እዚያ ቦታ ላይ የሠፈሩት በደርግ ዘመን ሆኖ ወያኔ ገብቶ “የአማራ ክልል” ብሎ ከሠየመው አሥተዳደር ዕዳ ሊኖርባቸው የሚችልበት አንዳችም መንገድ ሊኖር እንደማይችል ሁሉም ሊረዳው የሚችለው ነገር ነው፡፡

ወልቃይት ላይ ለሚፈጸመው የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ወንጀል የሚጠቀሰው ምክንያት ደግሞ፦ “ትግሬ ነን! ካላቹህ ተቀመጡ፡፡ አይደለንም! የምትሉ ከሆነ ግን መሬቱ የእኛ ነውና ለቃቹህ ውጡ!” የሚል ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ በተለያዩ ጽሑፎቸ ላይ በሚገባ የተነተንኩት ጉዳይ በመሆኑ ጽሑፌ በጣም ስለረዘመ በጣም ይቅርታ አድርጉልኝና ይሄን በዚህ ልለፈው፡፡ በአፋርና በሌሎች የወያኔ ክልሎች በአማራ ማኅበረሰብ ላይ ለሚፈጸመው የዘር መጥፋትና ማፅዳት ወንጀል የሚሰጠው ምክንያትም ከላይ ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይ በመሆኑ እነሱንም አልፋቸዋለሁ፡፡

ጽሑፌን ላጠቃልለውና እንዳያቹህት ጅቡ ወያኔ ሳያመኻኝ ላለመብላት ዘጠና ዘጠኙን ይቀባጥራል፡፡ አንዴ ታስታውሳላቹህ አቶ ዓለምነው የተባሉ የብአዴን ባለሥልጣን የአማራን ሕዝብ እንዲህ ፈጅቶ ለመጨረስ ላበቃቸው ጉዳይ ምክንያት ለማበጀት ሲከጅሉ ምን ነበር ያሉት? “አማራ የትምክሕት ለኻጩን ካልጣለ ካላራገፈ በስተቀር ከሌሎች ሕዝቦች ጋር መኖር አይችልም!” ሲሉ ነበር በአራት ነጥብ የደመደሙት፡፡ “እንዲህ እያደረግን በስውርና በግልፅ በምንፈጽምብህ ጥቃት አጥፍተን ፈጅተን እንጨርስኻለን እንጅ!” ማለታቸው ነው፡፡

አቶ ዓለምነው ማየት የተሳናቸው ልበ ዕውር ደንቆሮ ሆነው ነው እንጅ ሥነሥርዓት አክብሮት ጨዋነት የሚባል ነገርን ከቶውንም የማያውቁትን በባሕርያቸው እንደ ፋብሪካ ዕቃ አንድ ዓይነት የሆኑትን ስድ፣ ዋልጌ፣ ባለጌ፣ ጭንጋፍ፣ ውርጋጥ፣ ቆሻሻ፣ ምናምንቴ፣ ጥጋበኛ የዕድሜ መግፋት እንኳ ከእነኝህ የሥነምግባር ጉድለቶቻቸው የማያርማቸውን የወያኔን መንጋ ከጎናቸው አስቀምጠው አክብሮቱና ሰላምታው ከሰው አልፎ ለእንስሳት የሚተርፈው ሥነሥርዓት ባሕሉ የሆነውን ታጋሽ አስተዋይ በሳል የአማራን ሕዝብ እንዲያ ብለው ለመዝለፍ ድፍረት ባላገኙም ነበር፡፡ ሲጀመር አእምሮውና ሥነልቡናው ከላይ አስቀድሜ በጽኩላቹህ ሁኔት እንዲያ ሆኖ የተዛባና የታወከ በሽተኛ ይሄንን እንዴት ሊረዳ ይችላል?

የዚህ ሁሉ ሐተታ ቁልፍ መልእክት ፈጥነን እንንቃ! ይህ አሁን ሕዝባችን እያደረገ ያለው ዐመፅና ተቃውሞ ወያኔ አጋሮቹ ለ25 ዓመታት በመላ ሀገሪቱ በአማራ ሕዝብ ላይ በሥውርና በግልፅ ሲፈጽምብንና ሲያስፈጽምብን የኖረውን የዘር ማጥፋትና ማጽዳት አደገኛና ከባድ ወንጀል በዋናነት ታሳቢ ባደረገና አደጋውንም ለመቀልበስ በቆረጠ ዝግጅት መነቃቃት ወኔ ቁርጠኝነትና እልህ መሆን ይኖርበታል!! የሚለው ነው፡፡

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኩዳን

amsalugkidan@gmail.com

አቡነ አብርሃም: ሕዝቡና ሠራዊቱ እንዲተዛዘኑ መከሩ፤ መንግሥትንና ሚዲያውን አሳሰቡ፤“በመሣርያ ሰላም አይገኝም፤ አይተነዋል፤ እያየነውም ነው፤ ሊኾንም አይችልም!”

$
0
0

ሐራ ዘተዋሕዶ
የመሣርያ ምላጭ ከመሳብ ይልቅ፣ የፍቅር መሳቢያን ተጠቀሙ፤ የፍቅር ማሰርያን ተጠቀሙ
ጉልበታችን ሊያስመካን አይገባም፡፡ ሊያስመካን የሚችል ቢኖር መስቀሉ ብቻ ሊኾን ግድ ነው
ሰላም፣ የሰዎችን ድምፅ ሰምቶ፣ መልስ በመስጠትና ችግርን በማስወገድ ነው የሚመሠረተው
በኃይል ሰላምን አምጥተው በሰላም የኖሩ፣ በየትም ዓለም የሉም፤ የቀን ቆጠራ ካልኾነ በቀር!
* * *
ምንጊዜም ችግር የመሪው መንግሥት እንጂ የተመሪው ሕዝብ አይደለም፤ በቤተ ክህነትም!
መንግሥት፣ እንደ ወላጅም እንደ መሪም፣ ችግሮችን በመፍታት መፍትሔ መስጠት አለበት
በግድያ እና ሕዝቡን በማላቀስ፣ ነገ ሌላ የታሪክ ጠባሳ በስሙ እንዳያኖር ሊጠነቀቅ ይገባዋል!
የጩኸቱን ድምፅ ሰምቶ ለጩኸቱ ካልመለሰ፣ ሕዝቡ ጩኸቴን አላቆምም ቢል የተለመደ ነው
* * *
ሚዲያዎች፣ ያሻችኹን እየቀጠላችኹ ከሕዝቡ አጋጫችኹን፤ ምን አባት አለን? አሰኛችኹ
የቤተ ክርስቲያን፣ ድምፅዋ ይሰማ! ለማንም አትወግንም፣ የምንናገረውን በትክክል አድርሱ!
ቤተ ክርስቲያንን የሚናፍቃት የውሸት ዕርቅና የምፀት ሰላም ሳይኾን የመስቀሉ ሰላም ነው
እርስበሳችን በፈጠርነው መከራና ችግር መሣቂያና መሣለቂያ ከመኾን እግዚአብሔር አድነን!!
* * *በቤተ ክርስቲያን ቀኖና መሠረት፣ በትሩፋቱና በትምህርቱ ልቆ በአንብሮተ እድ የሚሾም ኤጲስ ቆጶስ፣ በቅዱስ ሲኖዶስ በተመደበበት ሀገረ ስብከት ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል፣ በበላይነት ለሚመራቸው ካህናትና ምእመናን ያለበትየኖላዊነትና የመግቦት ሓላፊነቱ ቀዳሚው ነው፡፡ ምእመናኑ፣ በተደራጀና በተሟላ ኹኔታ የትምህርተ ወንጌል አገልግሎት እንዲያገኙና ስለ ሃይማኖታቸው በሚገባ እንዲያውቁ፣ በመንፈሳዊ ሕይወት እንዲጸኑና በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን እንዲመሩ በትኩረት መሥራትና መከታተል ይኖርበታል፡፡ ከዚኽም ጋር ኤጲስ ቆጶሱ፡- የሀገር ፍቅር እና አንድነት በሰላም ተጠብቆ እንዲኖር በማድረግ፣ የቤተ ክርስቲያንን ጥንታዊና ታሪካዊ አገራዊ ሚና አጠናክሮ የማስቀጠል የመንፈሳዊ አባትነት ድርሻም አለበት፡፡
ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ የየጊዜውን ሥልጣኔ ተከትሎ እንዲሔድና ስለ ሀገር ፍቅር፣ ስለ ነፃነት ጥቅም፣ ስለ ዳር ድንበር መከበር፣ ስለ ብሔራዊ ምንነት ከምትሰጠው የተቀደሰ ትምህርት ሌላ፣ ለወገንና ለሀገር ትምክህት የሚኾኑ ጀግኖች ከታሪክ እንዲወለዱ ወቅቱ የሚፈቅደውን ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ትምህርት በማዘጋጀት ስታስተምር የኖረች የኢትዮጵያ ባለውለታ ቤተ ክርስቲያን ነች፡፡ የአኹኑ ትውልድም የአባቶቹን ታሪክ ተከትሎ ሀገሩን፣ ነፃነቱን፣ ክብሩንና ሃይማኖቱን ጠብቆ እንዲኖር ቤተ ክርስቲያን ከማስተማር የተገታችበት ጊዜ የለም፡፡
ከትላንት በስቲያ፣ መስከረም ፲፮ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም.፣ በባሕር ዳር መስቀል ዐደባባይ በተከበረው፣ የመስቀል ደመራ በዓል፣ የምዕራብ ጎጃም፣ አዊ፣ መተከል እና ባሕር ዳር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ ያስተላለፉት መልእክትም በዚኹ ዐይን የሚታይ ነው፡፡ ባሳለፍነው ፳፻፰ ዓ.ም. መገባደጃ በተቀሰቀሰው ሕዝባዊ ተቃውሞ፣ በርካታ ግድያዎች፣ የአካል መጉደልና የንብረት ውድመት በተፈጸመበት የሠቆቃ ድባብ ውስጥ፣ በተከናወነው በዚኹ ክብረ በዓል፣ ብፁዕነታቸው ባስተላለፉት መልእክት፣ በርካታ ኦርቶዶክሳውያንና ዜጎች ደስታቸውን እየገለጹ ነው፡፡
ብፁዕነታቸውን፣ ከሰማዕተ ጽድቅ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሊቀ ጳጳስ እና ከብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ጋር እያመሳሰሉ ያወደሱ ወገኖች፤ ኢሰብአዊነትንና ኢፍትሐዊነትን ያለአድልዎ በመቃወም፤ ያዘኑትን በማጽናናትና የተጨነቁትን በማረጋጋት፣ በተቃራኒዎች መካከል በአስታራቂነት የመቆም የቤተ ክርስቲያን ሞራላዊ ልዕልና እና የገለልተኛነት ሚና አኳያ፣ ሌሎችም አባቶች ሓላፊነታቸውን እንዲወጡ አርኣያነት ያለው ወቅታዊ መልእክት እንደኾነ በአጽንዖት ጠቅሰዋል፡፡

meskel-demera-celebration-in-bahirdar09
“ቤተ ክርስቲያን ከሕዝብዋ ጋር በመወገን፣ መንግሥት የሕዝብ እምባ ጠባቂ ግዴታ እንዳለበት የሚመክርና የሚያስጠነቅቅ ፈር ቀዳጅ አስተምህሮ በማድረጋቸው ሊመሰገኑ ይገባል፤” ብለዋል፣ አንድ ታዋቂ ፖሊቲከኛ በፌስቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት አስተያየት፡፡ “ነዋ ብእሴ መስቀል – እነኾ የመስቀሉ ሰው” ሲሉ ብፁዕነታቸውን ያመሰገኑት ዲያቆን ኢንጅነር ዓባይነህ ካሴ በበኩላቸው፣ “ፍርሃት በራቀለት የጥብዓት አንደበት የተጌጠ ግሩም ቃል ከሊቀ ጳጳሱ ሰማን፡፡ ወሰኑን ሳያፋልስ፣ በዓለማዊ ፖለቲካ ውስጥ ዠቅ ሳይል፣ መንግሥት እና ሃይማኖት የተለያየ ነው የሚለውን ብሂል ሳይጋፋ ሓላፊነትን መወጣት፣ የመንፈሳዊ መሪ ድርሻ እንደኾነ የብፁዕነታቸው ቃል ያረጋግጣል፤ ዝም በማይባልበት ዝምታ ተገቢ አለመኾኑንም ያመለክታል፤” ብለዋል፡፡
“በሃይማኖት መሪነት ለብዙ ዓይነት አካላት ብዙ ዓይነት መልእክት ማስተላለፍ ይገባል፤” የሚሉት ዲያቆን ዓባይነህ፣ የብፁዕነታቸው ትምህርት በአድራሻው፣ ከሚዲያውና ከሕዝቡ ጋር በተለይም “ለባለጡንቻው” መንግሥት የተላለፈ መልእክት እንደኾነ በጭብጥ በመለየት አብራርተዋል፡፡ ለክብረ በዓሉ ምክንያት የኾነውን የመስቀሉን መገኘት ታሪክ፣ ከወቅቱ ኹኔታ ጋር በማገናዘብ ያስተማሩት ብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ መንግሥት የሕዝቡን ብሶትና ጩኸት በቶሎ ሰምቶ ችግሮቹን በመፍታትና ጥያቄዎቹን በመመለስ የማስተዳደር፣ የመሪነትም የአባትነትም ድርሻ እንዳለበት አስታውቀዋል፡፡ ሰላምን የማስፈን ግዴታ ቢኖርበትም፣ በቀጠለው የሕዝቡ ጩኸት ሳቢያ በሚወስደው የጭካኔ ርምጃ፣ “ነገ ሌላ የታሪክ ጠባሳ በስሙ እንዳያኖር ሊጠነቀቅ ይገባዋል፤” ሲሉ አሳስበዋል፡፡
ዘላቂ ሰላም፡- በመግባባት፣ የሕዝብን ድምፅ በወቅቱ ሰምቶ ተገቢ ምላሽ በመስጠትና ችግርን በማስወገድ እንጂ፣ በመሣርያ ኃይል የሚመሠረት እንዳልኾነ፣ ይልቁንም የሀገርን አንድነትና ህልውና ለአደጋ በመዳረግ፣ ለታሪካዊ ጠላቶቻችን መሣቂያና መሣለቂያ እንደሚያደርገን አመልክተዋል – “ሰላምን በኃይል አምጥተው በሰላም የኖሩ በየትኛውም ዓለም የሉም፤ የቀን ቆጠራ ካልኾነ በስተቀር፤” ሲሉ አስጠንቅቀዋል – ብፁዕነታቸው፡፡ ከዚኽም አኳያ ፣ ዳር ድንበርንና የሀገርን ሰላምን ለሚጠብቅበት የመከላከል ትድግናው ቤተ ክርስቲያን ሌት ተቀን የምትጸልይለት ወታደሩና ሠራዊቱ፣ መሣርያውን ይያዝ እንጂ ምላጩን ከመሳብ ይልቅ የፍቅር መሳቢያን፣ የፍቅር ማሰርያን እንዲጠቀም፤ ሕዝቡም በአላስፈላጊ ጉልበትና ስሜታዊነት ከመተላለቅ፣ መስቀሉን መሣርያው አድርጎ ወደ እግዚአብሔር እንዲጮኽ በመንፈሳዊ መሪነታቸውና አባትነታቸው መክረዋል፡፡
ስለዚኽ ኹላችንም በያለንበት እንደ ወገንነት እንተዛዘን፡፡ እንደ ወገንነት እንተባበር፡፡ ስንቱ ወገን ነው በበረሓ ያለቀው፤ ስንቱ ወገን ነው እንጀራ ፍለጋ በየሀገሩ የተሰደደው፤ ስንቱ ወገን ነው ባሕር የሰጠመው፤ ስንቱ ወገን ነው ዘንዶ የዋጠው፤ እዚኽኮ ሰላማችን ቢበዛ፣ መደማመጥ ቢኖር፣ መቀባበል ቢኖር፣ መፍትሔ በየሰዓቱ ቢሰጥ ኖሮ ኹሉም ሰላም ይኾን ነበር፡፡ ሰላም ካለ ደግሞ ኹሉም ነገር አለ፡፡
እንደ ቅዱስ መጽሐፍ ቃል፣ ቤተ ክርስቲያን፣ የእምነት ነፃነትዋና ተቋማዊ ሉዓላዊነትዋ እስካልተጣሰ ድረስ፣ “ነፍስ ኹሉ፣ ለበላይ ባለሥልጣኖች እንድትገዛ” ብታስተምርም፣ ለማንም እንደማትወግን፣ ብፁዕነታቸው፣ በተለይ ለሚዲያ ሰዎች ተናግረዋል፡፡ የመንግሥት እና የሃይማኖት መለያየት፣ በኤፌዲሪ ሕገ መንግሥት ብቻ ሳይኾን፣ በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ ስምንት የተደነገገ የገለልተኛነት መርሖዋ ነው፡፡ በመኾኑም፣ ሚዲያዎች፣ የቤተ ክርስቲያን መሪዎችንና አባቶችን ቃል እንዳሻቸው እየቀጣጠሉ፣ ከሕዝቡ ጋር ከማጋጨትና ሕዝቡን ተስፋ ከማስቆረጥ እንዲታቀቡ፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ምክርና ማሳሰቢያ ሰጥተዋል፡፡
በዚኹ ክብረ በዓል፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ ከወትሮው በተለየ፣ ተባርኮ የተለኮሰው ደመራ ተቃጥሎ እስኪያልቅ በዚያው በዐደባባዩ ከሚዘምሩት የሰንበት ት/ቤቶችና ማኅበረ ምእመናን ጋር በመቆየትና ሕዝቡን ወደየመጣበት አስቀድመው በመሸኘት ነበር፣ ወደ መንበረ ጵጵስናቸው ያመሩት፡፡ የበዓል አዘጋጅ ኮሚቴው፡- ከሀገረ ስብከቱ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት፣ ከአካባቢ የጽዋ ማኅበራት፣ ከማኅበረ ቅዱሳን የባሕር ዳር ማዕከል አባላት የተውጣጣ ሲኾን፣ ከብፁዕነታቸው ትምህርት አስቀድሞ ጸሎተ ምሕላ ደርሷል፤ በሊቃውንቱ፣ በሰንበት ት/ቤቶቹ ወጣቶችና በማኅበረ ቅዱሳን የተሰማው ያሬዳዊ ወረብም፣ ያለከበሮ በጽፋት ብቻ የቀረበ ነበር፡፡ ከበሮ የተመታውም ደመራው ከተለኮሰ በኋላ ተቃጥሎ እስኪያልቅ ብቻ ነበር፡፡
ምእመናኑና ካህናቱ፣ “ዘንድሮም መስቀል አለ እንዴ” እስኪሉ ድረስ ስጋት የነበረባቸው ቢኾንም፣ የኖላዊነትና የአባታዊነት ሓላፊነታቸውን በአግባቡ በተወጡት ብፁዕ አቡነ አብርሃም አጽናኝነት መንፈሳዊ ደስታውን ገልጧል፤ በእልልታና በጭብጨባም እግዚአብሔርን አመስግኗል፤ የቤተ ክርስቲያናችንን ቀጣይ አገራዊ ሚናን በተመለከተም ተስፋው ለምልሟል፡፡ በደመራው ምሽት፣ የብፁዕነታቸውን ከፊል ትምህርት የያዘ ቪድዮ፣ በማኅበራዊ ብዙኃን መገናኛ በስፋት ተሰራጭቷል፡፡ “በዝንቱ ትእምርተ መስቀል ትመውዕ ፀረከ” በሚል ርእስ፣ ለ25 ደቂቃ የዘለቀውና በጽሑፍ የተገለበጠው፣ የብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ የባሕር ዳር መስቀል ዐደባባይ ትምህርት ሙሉ ይዘት ደግሞ እንደሚከተለው ተጠናቅሮ ቀርቧል፡፡
በዝንቱ ትእምርተ መስቀል ትመውዕ ፀረከ
በዚኽ የመስቀል ምልክት ጠላትኽን ድል ታደርጋለኽ!
/በብፁዕ አቡነ አብርሃም/
ኹላችኁም ወደዚኽ ወደ መስቀል ተመልከቱ(መስቀላቸውን ከፍ አድርገው እያሳዩ) ፡፡ መስቀል፣ ነፍስንና ሥጋን፣ ሕዝብንና አሕዛብን፣ ሰውንና መላእክትን ያገናኛል፡፡ መስቀል በአጠቃላይ፣ ሰውንና እግዚአብሔርን ያገናኛል፡፡ የክብር ባለቤት፣ የኹላችን ንጉሥ፣ የኹላችን ገዥ፣ በመስቀሉ ደሙን አፍስሶ፣ በደሙ ዋጅቶና ቀድሶ፣ አክብሮ፣ ልጆቹ አድርጎ፣ ነፃነትን ከማጎናጸፉ በፊት፣ እንደሚታወቀው ኹሉ፣ መስቀል የወንጀለኞች መቅጫ፣ የኃጢአተኞች መግደያ ኹኖ ኖሯል፡፡ በዚኽም የመጀመሪያዎቹ ፋርሳውያን እንደኾኑ ቤተ ክርስቲያናችን ትተርካለች፡፡ የምድር አምላክ የሚሉት ነበርና የምድር አምላካቸው እንዳይረክስ ወንጀለኞችን በመስቀል ላይ ይቀጡ ነበር፡፡ በታሪክም ብንሔድ ወንጀለኞች ሲገኙ የሚቀጡት በመስቀል ነበር፡፡ የክብር ባለቤት ግን የተዋረደውንና የተናቀውን ከፍ ማድረግ፣ ማንም ማን የለውም የተባለውን ያለው ማድረግ፣ የባከነውን የተቅበዘበዘውን፣ የጠፋውን፣ የተቸገረውን መርዳት፤ እርሱ የባሕርይው ነውና፣ የተዋረደውን መስቀል ለክብር ይኾን ዘንድ እነኾ በመስቀል ተሰቅሎ ደሙን አፍስሶ ስላዳነን፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን፡- መስቀል ነፃነታችን፣ መስቀል የነፃነታችን ዓርማ ብላ ታከብራለች፡፡
ዛሬ፣ ይህን በዓል ስታከብር፣ በዝንቱ ትእምርተ መስቀል ትመውዕ ፀረከ የተባለው ቆስጠንጢኖስ ነው፡፡ ምንጊዜም በዓሉን ስናከብር ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ እና እናቱ እሌኒ ይጠቀሳሉ፡፡ የእሌኒን ታሪክ እንዳልተርክ ረዥም ሰዓት ይወስዳል፡፡ ባለፈው ዓመትም በሰፊው ተነጋግረንበታል፡፡ እሌኒ፣ የተቀበረውን መስቀል ፈልጋ በማግኘት፣ በደመራው፣ ቅድም መንፈሳውያን ወጣቶችም ሲዘምሩልን እንደነበረው፤ ‹‹ሰገደ ጢስ››(ጢሱ ወደ ላይ ወጥቶ ወደ ታች ወርዶ መስቀሉን ስላመለከተ) መስቀሉ የተቀበረበትን ያወጣችበትን ዕለት፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ታከብረዋለች፡፡የመስቀሉ ነገር ሲነሣ ልጅዋ ቆስጠንጢኖስም አብሮ ይነሣል፤ በሥርዓት ያሳደገችው በመኾኑ፡፡ ቆስጠንጢኖስ በእናቱ አይሁዳዊ፣ በአባቱ አሕዛባዊ፣ እናቱ አምልኮተ እግዚአብሔር ያላት፣ እግዚአብሔርን የምትፈራ፣ በኋላም ክርስቲያን የነበረች ናት፡፡ አባቱ ደግሞ በጣዖት አምልኮ የሰከረ፣ ለማንም ለምንም ስሜት የሌለው፣ ደም አፍሳሽ ነፍሰ ገዳይ እንደነበረ የታወቀ፣ የተረጋገጠ ነው፡፡
እግዚአብሔር በኪነ ጥበቡ፣ እሌኒ ወደዚያ ሔዳ፣ የቆስጠንጢኖስን አባት ቁንስጣን አግብታ፣ ቆስጠንጢኖስን ወልዳ፣ በሥርዓት ስላሳደገችው፣ እነኾ በዚያ ዘመን አብያተ ክርስቲያናት ኹሉ ተዘግተው፣ አብያተ ጣዖታት ተከፍተው፣ ክርስቲያኖች ድምፃቸውን ከፍ አድርገው፣ ጩኸታቸውን ወደ እግዚአብሔር የሚያስተጋቡበት ዘመን ነበረና፣ ቆስጠንጢኖስን አሥነስቶ፣ ጠላቶቹን ኹሉ በመስቀሉ ኃይል ድል አድርጎ፣ የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናትን ከፍቶ፣ የተከፈቱ አብያተ ጣዖታትን ከፍቶ፣ ለክርስቲያኖች ነፃነት የሰጠበት በዓል ስለኾነ፣ ይህን በዓል በዐደባባይ እንድናከብረው ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ከወሰነችበት ጊዜ ጀምሮ፣ በመከራም ይኹን በደስታ፣ ወደ ዐደባባይ ወጥታ፣ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ዘርግታ፣ ድምፅዋን ከፍ አድርጋ፣ በመስቀሉ ሰላምን ስጠን፤ በመስቀሉ ክብርን አጎናጽፈን፤ በመስቀሉ ጠላትን ድል አድርግልን፤ የሰው ልጅ ጠላት ሰው ሳይኾን ሰይጣን ነውና፣ እርስ በርስ እንድንጣላ፣ አንዱ የአንዱን ደም እንዲያፈስ፣ አንዱ አንዱን እንዲያሳድደው፣ አንዱ አንዱን እንዲያስጨንቀው፣ አንዱ አንዱን እንዲያስቸግረው የሚያደርግ ሰይጣን እንጂ ሰው ሲፈጠር በርኅራኄ፣ በቅድስና፣ በክብር ነውና፣ እነኾ ሰይጣንን ቅጣልን፤ አሳፍርልን፤ አንድነታችንን ሰላምን ስጠን፤ እያለች በዓሉን ታከብረዋለች፡፡
ዛሬም ይህን በዓል ለማክበር ዐደባባይ የተገኛችኹ በሙሉ፣ እንኳን ደስ አላችኹ፡፡ እግዚአብሔር ይባርካችኹ፡፡ በዝንቱ ትእምርተ መስቀል ትመውዕ ፀረከ፤ የክርስቲያኖች ድል ማደረጊያችን፣ የክርስቲያኖች አለኝታችን፣ የክርስቲያኖች ጋሻችን፤ ለዚኽም ነው፣መስቀል ኃይልነ – መስቀል ኃይላችን ነው፤ መስቀል ጽንዕነ – መስቀል መጽኛችን ነው፤ መስቀል ቤዛነ – መስቀል ቤዛችን ነው፤ መስቀል መድኃኒትነ፤ መስቀል መድኃኒታችን ነው፤ ብለን የምንሰመሰክረው፡፡በመስቀሉ እናማትባለን፤ በመስቀሉ ርኵሳን መናፍስትን እንገሥጻለን፤ በመስቀሉ ሰላምን እንዋጃለን፤ በመስቀሉ የራቁትን እናቀርባለን፤ በመስቀሉ የታመሙትን እንፈውሳለን፤ በመስቀሉ የተቸገሩትን እንረዳለን፤ በመስቀሉ የተጨነቁትን እንባርካለን፤ እናረጋጋለን፤ እያለች ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ መስቀል በእጆችዋ፤ መስቀል በልጆችዋ አንገት ላይ ጎልቶ ደምቆ የሚታይ እንደ መኾኑ፣ በዓለ መስቀሉን ስናከብር፣ ዛሬም ያጣነውን ሰላም እንዲሰጠን፤ የጥያቄዎቻችንን መልስ እንዲሰጠን፣ መግባባት የሚፈጠርበት፣ እንደ ኢትዮጵያዊ ስሜትና እንደ ኢትዮጵያዊ ባሕርይ፡- አንተ ትብስ፣ አንቺ ትብሽ ተባብለን የምንኖርበትን፣ አንዱ አንዱን የማያሳድድበትን፣ የማያስጨንቅበትን፣ ንጹሕ ደም የማይፈስበትን፣ ሰዎች ያለአግባብ የማይታሰሩበትን፣ በነፃነት በሀገራቸው በፍቅርና በሰላም ሠርተው፣ ጥረው ግረው እግዚአብሔርን እያመለኩ፣ የሚኖሩበትን በዓለ መስቀሉን ስናከብር፣ ይህን እንዲያደርግልን ነው፣ ጸሎቱም ልመናውም፡፡ እግዚአብሔር ጸሎታችንን ይስማ፡፡(ሕዝቡ፣ አሜን እለ ይከተላል)
ምንጊዜም መስቀልን መሣርያ እናድርግ፡፡ በዝንቱ ትእምርተ መስቀል ትመውዕ ፀረከ፤ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች መሣርያ ስለያዙ፣ በመሣርያ ድል የሚያደርጉ ይመስላቸዋል፡፡ ብዙ ጊዜ በመሣርያ ድል አድርጎ ማንም ማን አልኖረም፡፡ የዕለቱን በዓል ስናስታውስ፣ ቆስጠንጢኖስ እና መክስምያኖስ፣ ትልቅ ምስክሮች ናቸው፡፡ መክስምያኖስ እጅግ ጦረኛ የኾነ፣ ክርስቲያኖችን ያስጨነቀ፣ አብያተ ጣዖታትን የከፈተ፣ ብዙና ብዙ መከራ ያደረሰ ነበር፡፡ ለዚኽ ነበር ክርስቲያኖች ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ወደ እግዚአብሔር እየጮኹ፣ በክርስትና ሕይወቱ የታወቀውን፣ በምግባር ያደገውን፣ በትሩፋት የበለጸገውን፣ በርኅራኄ የተሞላውን ቆስጠንጢኖስን፣ እባክኽ ርዳን፤ ክርስቲያኖች በዋልንበት ማደር አልቻልንም፤ ባደርንበት መዋል አልቻልንም፤ ብለው ለመኑት፡፡ እርሱም ነገሩን መረመረ፤ ችግሩን ተረዳ፣ ግፉንም አየ፡፡ ‹‹የተቃጠሉትን አልባሳት፣ ቅዱሳት መጻሕፍት፣ የተሠባበሩትን መስቀሎች፣ ጽዋዎች በአጠቃላይ የቤተ ክርስቲያን ንዋያተ ቅድሳትን አሳዩት፤›› ይላል የቤተ ክርስቲያናችን ታሪክ፡፡
ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ያን ከተመለከተ በኋላ፣ መሣርያ አለኝ፤ ኃይል አለኝ፤ ወታደር አለኝ፤ ጉልበት አለኝ ብሎ በጉልበቱ ተመክቶ፣ በመሣርያው ራሱን ከፍ ከፍ አድርጎ ወደ ጦር ሜዳ አልሔደም፡፡ የመጀመሪያ መሣርያው ያደረገው መስቀሉን ነው፡፡ በጸሎት እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ ከዚያም በጸፍጸፈ ሰማይ፣ በዝንቱ ትእምርተ መስቀል ትመውዕ ፀረከ፤ በዚኽ የመስቀል ምልክት ጠላትኽን ድል ታደርጋለኽ፤ ተብሎ ተጽፎ አነበበ፡፡ ቋንቋውንም የሚተረጉሙ ተረጎሙለት፤ ከዚኽ በኋላ ውጊያውን ገጠመ፤ እርሱም ቻለ፤ ትእምርተ መስቀሉን ትምክሕት፣ መሪ አድርጓልና፡፡ ጠላትን ድል አድርጎ ለክርስቲያኖች የእምነት ነፃነትን አጎናጸፈ፡፡ አኹንም ለሀገራችን ነፃነትን ያጎናጽፍልን፡፡ መተሳሰብን ይስጥልን፡፡ መተዛዘንን ይስጥልን፡፡ አንተ ትብስ፣ አንቺ ትብሽ መባባልን ይስጥልን፡፡ ጠላታችንን ያርቅልን፡፡(ሕዝቡ፣ አሜን እያለ ይከተላል)
በመስቀሉ ጥላቻንም አስወግዷል፡፡ በኤፌ. ምዕ. 2 ቁ. 16 ላይ ስናነብ፣ ‹‹ጥላቻን ያስወገደ፤ ኹለቱን አንድ ያደረገ በመስቀሉ ነው፤ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ››፤ ሰላምን ያጡ ኹሉ በመስቀሉ ነው ሰላምን ያገኙት፡፡ በመሣርያ ሰላም አይገኝም፤ አይተነዋል፡፡ እያየነውም ነው፡፡ ሊኾንም አይችልም፡፡ ሰላም በፍቅር የሚመሠረት ነው፤ ሰላም በመስቀሉ ነው የሚመሠረተው፡፡ ሰላም በሃይማኖት ነው የሚመሠረተው፡፡ ሰላም በመግባባት ነው የሚመሠረተው፡፡ ሰላም የሰዎችን ድምፅ በመስማትና መልስ በመስጠት ነው የሚመሠረተው፡፡ ሰላም ችግርን በማስወገድ ነው የሚመሠረተው፡፡ በኃይል ሰላምን አምጥተው በሰላም የኖሩ በየትኛውም ዓለም የሉም፤ የቀን ቆጠራ ካልኾነ በስተቀር፡፡
ስለዚኽ ማንኛውም ባንኖ፣ ከችግሩ ነቅቶ፣ ሰላምን አስፍኖ፣ ኹሉም የሰላምን አየር እንዲተነፍስ፣ በመግባባት እና ሰላም፣ ችግርን ፈትቶ፣ እነኾ አገራችንን የነፃነት አገር፣ ለማንም ያልተገዛች፣ ለማንም ያልተንበረከከች፣ ለማንም እጅዋን ያልሰጠች፣ በሃይማኖትም በጀግንነትም የጀግኖች አገር፡፡ ያች የጀግና አገር፣ ዛሬ እርስ በእርሳችን በመጠላላት፣ ባለመደማመጥ፣ ለችግር መፍትሔ ባለመስጠት፣ እንዲኹ ዝም ብሎ በስጋት ላይ የተመሠረተ አኗኗር፤ ነጋዴው ነግዶ የማይበላበት፣ ገበሬው ሠርቶ አምርቶ የማያፍስበት፣ የማይቆፍርበት፣ ራሱን የማይረዳበት፣ ተማሪው ተምሮ ተምሮ በትምህርቱ ነገ ለሀገር ደራሽ የማይኾንበት አኗኗር፣ አኗኗር ሊኾን ስለማይችል፣ እነኾ ማንም የሚመለከተው ኹሉ ችግሩን ለመፍታት እንደየሃይማኖቱ(ከአቅራቢያው መስጊድ አዛን ይሰማ ነበር)፣ ክርስቲያኑም ወደ መስቀሉ በመመልከት፣ በመስቀሉ ጥላ ሥር ሰላም መኖሩንና ንጹሕ አየር ያለ መኾኑን በማመን፣ የተጣሉ በመስቀሉ የሚገናኙ መኾኑን በማመን፤ ቅድም እንዳልነው አሕዛብና ሕዝብኮ ተገናኝተው አያውቁም፤ ሕዝብ የሚባለው በእግዚአብሔር የሚያምን ነው፤ አሕዛብ ደግሞ እግዚአብሔርን የማያምን፣ በዘፈቀደ የሚመላለስ ነው፡፡ ሕዝብ እና አሕዛብ የተገናኙ በመስቀሉ ነው፡፡ ነፍስና ሥጋ እንኳ የተዋሐዱት፣ የተገናኙትና የእግዚአብሔርን ክብር ለመውረስ የበቁት በመስቀሉ ነው፡፡
ዛሬም በዓለ መስቀሉን ስናከብር፣ መስቀሉን እንመልከት፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ተናግሮታል – ‹‹ከጌታዬ ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ››፤ ጉልበታችን ሊያስመካን አይገባም፡፡ ሊያስመካን የሚችል ቢኖር መስቀሉ ብቻ ሊኾን ግድ ነው፡፡ መስቀሉን የመረጠ ሰው ደግሞ ሰላም አለው፡፡ መስቀሉ ስንል፣ መስቀል የሰላም ዓርማ ስለኾነ ነው፡፡ ከመስቀል ጋር ጥላቻ አይስማማም፡፡ ከመስቀል ጋር እሰጥ አገባ አይስማማም፡፡ ከመስቀል ጋር አንዱ አሳዳጅ ሌላው ተሳዳጅ፤ አንዱ ገዳይ ሌላው ተገዳይ እንዲኾን አይስማማም፡፡ መስቀሉ ኹሉንም እኩል ይዋጃል፤ በመስቀሉ ድነናልና፡፡ በዚኽ መስቀል ላይ ነው፣ መድኃኒታችን ተሰቅሎ የነፃነትን ዐዋጅ ሲያውጅ፣ ይህ መስቀል የክርስቶስ ዙፋን ነው፤ ይህ መስቀል የነፃነት ዐዋጅ ማወጃ ነው፡፡ ለዚኽ ነው፤ አማናዊትዋ፣ ጥንታዊትዋ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ መስቀሉን የምታከብረው፡፡ እግዚአብሔር ያከበረው ስለኾነ ነው፡፡
ቅድም የዕለቱ ወንጌል(ዮሐ. ምዕ.19 ቁ.25) ሲነበብ ሰምታችኋል፤ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ፣ አላዋቂዎች ሲዘባበቱበት፣ ሲቀልዱበት፣ ሲተፉበት፣ ራስኽን አድን እያሉ የምፀት ቃል ሲናገሩበት፣ ከመስቀሉ ላይ እንዳለ ለቅዱስ ዮሐንስ፣ ‹‹እነኋት እናትኽ››፤ ለቅድስተ ቅዱሳን ለድንግል ማርያም ደግሞ፣ ‹‹እነኾ ልጅሽ›› በሚል ቃል ኪዳኑ የጸናበት፤ እኛ ልጆቹ፣ የቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ልጆች፣ ቅድስተ ቅዱሳን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የእኛ እናት ትኾን ዘንድ በመስቀሉ ቃል ኪዳን የገባበትም ስለኾነ፣ የተዋሕዶ እናት ቤተ ክርስቲያናችን መስቀሉን በዚኽ ዓይነት ታከብረዋለች፡፡
ስለዚኽ ባለንበት ሰዓት ብዙ አይተናል፡፡ የዘመኑን የማኅበራዊ መገናኛ መሥመሮችን ብዙ ተመልክተናል፡፡ እጅግ የሚያሳዝንም፣ የሚዘገንንም ድርጊት ሲፈጸም፣ ሲደረግ፤ ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያዊ፣ ወገን በወገኑ ላይ ያደርጋል ተብሎ በማይታሰብ መልኩ እያየን ነው፡፡ ይህ ይበቃል ልንል ይገባል፡፡ በቃ! ወደ ሰላማችን እንመለስ፤ ችግሮች ይፈቱ፤ መግባባት ይስፈን፤ ኹሉም ሥራውን እየሠራ ለጥያቄው በሰላም መልስ እያገኘ መኖር አለበት፤ ወደሚለው ኹሉም ማዝመም አለበት፡፡ እንደ ፖሊቲካ አይደለም የምናገረው፤ እንደ ሃይማኖት ግን መናገር ያለብኝ ነገር አለ ብዬ አምናለኹ፣ መንግሥትንም በተመለከተ፡፡ በፖሊቲካ ከመነዘረው የእርሱ ጉዳይ ነው የሚኾነው፤ የእኔ አይደለም፤ እንደ ሃይማኖት ግን በነፃነት፣ በድፍረት ነው የምናገረው፡፡
ትላንትና መንግሥት፣ የሞቱትን ዐፅም በማውጣት፣ በመሰብሰብ፡- ‹‹አረመኔው እና ጨካኙ፣ ይኸው ልጆቻችኹን ገደለላችኹ›› ብሎ፣ ማላቀሱ የትላንትና ትዝታ ነው፡፡ ይህ ታሪክ ደግሞ ዛሬም በውስጣችን ተፈጽሞ፣ ነገ ሌላ የታሪክ ጠባሳ በስሙ እንዳይኖር ሊጠነቀቅ ይገባዋል፡፡ ነገሮችን ኹሉ በመወያየትና ችግሮችን በመፍታት፣ ሰላምን ለማስፈን መንግሥትም ግዴታ አለበት – ከላይ እስከ ታች፡፡ ያ እስከ ኾነ ድረስ ሰላምን የተጠማ ሕዝብ ነው፡፡
ማንኛውም እንደሚናገረው፣ በርግጠኝነት፣ ምንጊዜም ችግር የመሪው እንጂ የተመሪው ሕዝብ አይደለም፡፡ በቤተ ክህነትም፣ ኹልጊዜም ችግር የመሪው እንጂ የሕዝብ አይደለም፡፡ የምለውን ካላደረግኽልኝ፣ ጩኸቴን ካልሰማኸኝ…(የምእመናን እልልታና ጭብጨባ ይሰማል፤ ብፁነታቸውም …ግዴለም፣ ግዴለም አጨብጭቡልኝ እያልኩ አይደለም፤ ዝም ብላችኹ ስሙ፤ በማለት ይቀጥላሉ) የጩኸቱን ድምፅ ሰምቶ ለጩኸቱ ካልመለሰ፣ ማስተባበያ ካልሰጠ፣ አዎንታዊነቱን፣ እውነቱን እውነት፣ ሐሰቱን ሐሰት ብሎ ካላረጋገጠ፣ መልስ እስካልሰጠኸኝ ድረስ ጩኸቴን አላቆምም ማለት የተለመደ ነው፡፡
አንድ ሕፃን ልጅ ወደ ወላጆቹ ያለቅሳል፤ እናት ይኑረውም አይኑረውም ጡትዋን ስትሰጠው ጸጥ ይላል፡፡ ማግኘት አለማግኘት፣ ያ ሌላ ጉዳይ ነው፡፡ እንደ እርሷ አመጋገብ ነው፡፡ ለምግብም የደረሰ እንደ ኾነ እርጥብም ይኹን ብስል እንደ አኗኗሯ፣ የተወሰነ ነገር ስትሰጠው ያን ይዞ ዝም ነው፡፡ አለበለዚያ ሕፃኑ ማልቀሱን አይተውም፡፡ መንግሥት፣ እንደ ወላጅም እንደ መሪም እንደ ሀገር ጠባቂም ኹለንተናዊ ሓላፊነት እጁ ላይ የተጣለበት እንደ መኾኑ፣ ችግሮችን በመፍታት መፍትሔ መስጠት አለበት፡፡
በአንፃሩ፣ የሚዲያ ሰዎችም እዚኽ አያችኋለኹ፡፡ ወደፊት በዚኽ ዓይነት እንድትቀርጹ የምንፈቅድ አይመስለኝም፤ ከይቅርታ ጋር፡፡ ዛሬ፣ እዚኽ ነፃ ስለኾነ መልካም ነው፡፡ ለምን ቢባል፣ አንዳንድ ጊዜ እኛን ትጠይቃላችኹ፤ ታናግሩናላችኹ፤ እኛ ከሕዝቡ ጋር የምንጋጭበትን የፈለጋችኹትን ቃል ቀጥላችኹ ታስተላልፋችኹ፤ ሕዝቡ ያን ይሰማና፣ ምን አባት አለን? ይላል (ጭብጨባ ይሰማል)፡፡ የምንናገረውን በትክክል አድርሱ፡፡
ቤተ ክርስቲያን፣ ለማንም ለማን አትወግንም፡፡ ጥላቻን አትሰብክም፤ መገዛትን ታምናለች፤ ተገዙም ትላለች፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል ነውና አትገዙ አትልም፡፡ ቤተ ክርስቲያን፣ አልገዛም የምትልበት ጊዜ ቢኖር፣ በሃይማኖትዋ ሲመጣ፤ ሃይማኖትን ካድ፤ ማዕተብን በጥስ፤ ቤተ ክርስቲያን የሚዘጋ ካለ፣ አዎ፣ አልገዛም ብላ አንገትዋን ትሰጣለች፡፡ ግደል ግን አትልም፡፡ ሞትን ተማርን እንጂ መግደልን አልተማርንም፡፡ መሰደድን ተማርን እንጂ ማሳደድን አልተማርንም፡፡ ክርስቲያን ይህ ነው – ይሰደዳል እንጂ አያሳድድም፡፡ ይሞታል እንጂ አይገድልም፡፡ ይወቀሳል፤ ይሰደባል እንጂ አይወቅስም፣ አይሰድብም፡፡ እውነትን ግን በዐደባባይ ይናገራል፡፡
ለዚኽ ነው ዛሬ፣ ከትንሽ እስከ አዛውንቱ በአማናዊት ቤተ ክርስቲያን ተሰብስቦ፣ ለሀገር ሰላም የቆመው፤ ለሀገር አንድነት የሚጸልየው፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የሀገርን ሰላም ትፈልጋለች፤ ባለታሪክ ስለኾነች፡፡ ከጥንትምኮ ለዚኽች ሀገር ነፃነት ማን ነው አንድዋና ተጠቃሹዋ ባለታሪክ? ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ ታቦትዋን መስቀልዋን አዝማች፣ መሪ አድርጋ፡፡ እስከዛሬ ድረስኮ ቋንቋችን፣ ባህላችን፣ ሥርዓታችን ተደበላልቆ የባዕዳን አገር ትኾን ነበርኮ፣ እንደሌላው፡፡
ይህች አማናዊት ቤተ ክርስቲያን ግን ኹልጊዜ በመስቀል እየባረከች፣ በመስቀል እያቀረበች፣ በመስቀል እየሳበች፣ በመስቀል እያስታረቀች፣ የተለያየውን በመስቀል እያገናኘች፣ በመስቀል ነፃነት ያላትን አገር ለትውልድ አውርሳለች፡፡ ዛሬም ምኞትዋም ዓላማዋም ይኸው ነው፤ ሌላ ዓላማ የላትም፡፡ ሌላ የሚናፍቃት ነገር የለም፡፡ ቤተ ክርስቲያን የሚናፍቃት ሰላም ነው – የመስቀሉ ሰላም፡፡ የምፀት ሰላም አይደለም፡፡ የመስቀሉ ሰላም፣ ‹ለማግባቢያ› የሚነገር ሰላም አይደለም፡፡ ለማጥመጃ የሚነገር ሰላም አይደለም፡፡ የውሸት ዕርቅም አይደለም፡፡ በመስቀሉ የተፈጸመው አማናዊ ሰላም፣ ዛሬም፣ ነገም ከነገ ወዲያም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይናፍቃታል፡፡ ሥራዋም፣ ልመናዋም፣ ጸሎትዋም ይኸው ነው፡፡ (ጭብጨባ)
ለዚኽም ነው፣ ሌትም ቀንም፣ አይደለም ስለ ሰው ልጆች ስለ ሀገር ጠባቂዎች፣ ስለ ወታደሩ፣ በሀገሩ በድንበሩ፣ ‹‹ዕቀብ ሕዝባሃ ወሠራዊታሃ ለሀገሪትነ ኢትዮጵያ፤ ዳር ድንበሯን፣ ሕዝብን የሚጠብቀውን ሠራዊት በአጠቃላይ ከላይ እስከ ታች ከጠላት ከወራሪ ጠብቅ፤ ታደግ›› እያለች በመስቀሉ የምትጸልይ ይህች ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ ስለዚኽ የቤተ ክርስቲያን ድምፅዋ ሊሰማ ይገባል፡፡
ዐዋጅዋ፣ ማንኛውም ነገር፣ የታሰሩት እንዲፈቱ፣ ያዘኑት እንዲጽናኑ ነው፡፡ በማወቅም ባለማወቅም፣ የሚገርመው ነገር፣ እያንዳንዱ የየግሉን ጥላቻ ምክንያት አድርጎ፣ የመስቀሉን ቃል ኪዳን ረስቶና ዘንግቶ፣ አጋጣሚውን ተጠቅሞ ጠላትን ለመበቀል፣ ባልሠራው፣ ባልዋለበት፣ ሰውዬው ያለ፣ ሌላ አገር ነው፣ እንዳለ እየተደረገ ታስሯል፡፡ ይኼ በደል ነው፡፡ አንድ ሰው ባልሠራው ከታሰረ፣ ባላደረገው ከተወነጀለ እግዚአብሔርስ እንዴት ዝም ይላል? ሰላምን ያሳጣል፡፡ስለዚኽ ማንኛችንም ለሰላም፣ ለሀገር ፍቅር፣ ለሀገር ነፃነት፣ ለሀገር ዕድገት፣ ለኹለንተና፣ ከልመና ለምንላቀቅበት ነገር ኹሉ፣ በአንድ ድምፅ ቤትን ዘግቶ ጠላት ሳይሰማ፣ በእልክ፣ በአላስፈላጊ ነገር፣ እኔ እበልጥ፣ እኔ እበልጥ፣ እስኪ የታባትኽንስ ምን ታመጣለኽ ብሎ፣ ዘመን የፈጠረውን መሣርያ አንግቦ ከመሮጥና፤ ሌላውም የመጣው ይምጣ ልሙት ብሎ ከመጋፈጥ ይልቅ፣ ወደ መስቀሉ ተመልክተን፣ ወደ እግዚአብሔር ነግረን፣ እውነተኛ ፍርድ ሰጪው እግዚአብሔር፣ ፍርዱን ሰጥቶ፣ ሰላሙን አብዝቶ፣ በቃችኹ ብሎ ኹላችንም በሰላም እንድንኖር የቅድስት ቤተ ክርስቲያን መልእክት ነውና፣ ኹላችን ይህን ገንዘብ ልናደርግ ይገባል፡፡(ጭብጨባ እና እልልታ)
ለክርስቲያኑ፣ ለሠራዊቱ – ወታደራዊው ትእዛዝ፣ ከዚያው ካላችኹበት ኹኖ፣ ለክርስቲያኖች፣ እንደ መንፈሳዊ መሪነቴ የማዝዘው፣ ለሠራዊቱ፣ ለወታደሩ፣ ለኹሉም፤ መሣርያው ይያዝ እንጂ ምላጩን ከመሳብ ይልቅ የፍቅር መሳቢያን ተጠቀሙ፡፡ የፍቅር ማሰርያን ተጠቀሙ፡፡(እልልታ እና ጭብጨባ) አዎ፣ ሌላውም ደግሞ እስኪ ምን ታደርገኛለኽ ብለን፣ እሳት ይዞ እሳት በሚተፋ ፊት፣ በአላስፈላጊ ጉልበትና ስሜታዊነት አትተላለቁ፡፡ ወደ እግዚእብሔር ቀርበን እንጩኽ፤ እግዚአብሔር መልስ ይሰጣል፣ ከዚያ በላይ ከኾነ፡፡(እልልታ እና ጭብጨባ)
ስለዚኽ ኹላችንም በያለንበት እንደ ወገንነት እንተዛዘን፡፡ እንደ ወገንነት እንተባበር፡፡ ስንቱ ወገን ነው በበረሓ ያለቀው፤ ስንቱ ወገን ነው እንጀራ ፍለጋ በየሀገሩ የተሰደደው፤ ስንቱ ወገን ነው ባሕር የሰጠመው፤ ስንቱ ወገን ነው ዘንዶ የዋጠው፤ እዚኽኮ ሰላማችን ቢበዛ፣ መደማመጥ ቢኖር፣ መቀባበል ቢኖር፣ መፍትሔ በየሰዓቱ ቢሰጥ ኖሮ ኹሉም ሰላም ይኾን ነበር፡፡ ሰላም ካለ ደግሞ ኹሉም ነገር አለ፡፡
ስለዚኽ ዛሬ ስጋት ነው፤ መስቀል እናክብር አናክብር፤ እንዲኽ ቢኾንስ እንዲኽ ቢደረግስ፣ ብዙ ተብሏል፡፡ ይህ የምታዩት ሕዝብ፣‹ሃይማኖቴ ነው፤ የመጣው ይምጣ› ብሎ ለሃይማኖቱ ቆርጦ የመጣ እንጂ፣ አኹን እገሌ ይጠብቀኛል እገሌ ያስጠብቀኛል ብሎ አይደለም፡፡
ሃይማኖት ከኹሉም በላይ ስለኾነ፣ ተደብቆ መዋልን ትታችኹ፣ በዚኽ ሃይማኖት፣ በዚኽ መስቀል ዐደባባይ፣ የእናት ቤተ ክርስቲያንን ጥሪ ሰምታችኹና ተቀብላችኹ፣ መስቀሉን መሪና ሠሪ፣ በመስቀሉ ሰይጣንን ድል አድርጋችኹ፣ በአንድነት በፍቅር መስቀሉን እንድናከብር፣ ጥሪውን ሰምታችኹ በዚኽ የተገኛችኹ ኹሉ፣ እግዚአብሔር በኃይለ መስቀሉ ይባርካችኹ፤ እግዚአብሔር ይጠብቃችኹ፤ ኹሉንም እግዚአብሔር ይጠብቅልን፡፡
ዛሬ ለጠላት መሣቂያና መሣለቂያ የኾነችውን አገራችንን፤ በሩቅ ኹነው እየተመለከቱ፡- አለቀላቸው፣ አበቃላቸው ለሚሉት ባዕዳን፤ ትላንት፡- በሰማይ በራሪ፣ በምድር ተሽከርካሪና ተወንጫፊ ኾነው መጥተው በኀፍረት ለተመለሱ፣ የሀገራችንን ጀግንነትና ወኔ ለቀመሱ፣ ካህናቱ በመስቀላቸው በታቦታቸው፣ ጀግናው በጀግንነቱ ተከላክሎ ማንነታቸውን አሳፍሮ ለሰደዳቸው፤ ዛሬ እርስ በርሳችን በፈጠርነው መከራና ችግር መሣቂያና መሣለቂያ ከመኾን እግዚአብሔር አድነን፤ ምኞታቸውን ኹሉ አርቅልን፤ ተማምነን ተደማምጠን፣ መንግሥትም የሕዝቡን ጩኸትና ብሶት ሰምቶ፣ ችግሩን ፈትቶ፣ በሰላማዊ መንገድ እንኖር ዘንድ የእግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃዱ ይኹንልን፡፡
እንደ ዛሬው ኹሉ ለሚመጣው ዓመትም ያድርሰን፡፡ አሜን፡፡ ጸሎት፡፡

“የመለስ ልቃቂት” ሆድ እቃ ሲገለጥ”  –ሚካኤል ደርቤ (ቦስተን ማሳቹሴት)

$
0
0

 

መንደርደሪያ    

ye-meles-lekakit-standing-bookደረቅ ፖለቲካዊ መረጃዎች የተዘጋጀበት መጽሀፍ እንዲነበብ ከተፈለገ በአቀራረቡና በአፃፃፍ ስልቱ የሚያጓጓ ሊሆን ይገባል። በተለይም ስለ ዘረኛ ኋላቀርና ቆሞ ቀር የሆነውን የወያኔ ፖለቲካ መጽሐፍ ጽፎ አንባቢ መሳብ በጣም አስቸጋሪ ነው። ሩቅ ሳንሄድ  የእንግሊዝ የወያኔ መፈንጫ የሆነው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ውስጥ ተከማችቶ የአይጥ መናኸሪያ የሆነውና በአስወጋጅ ኮሚቴ የተቃጠለው የውሸት አለቃ የሆነው በረከት ስምኦን የበሬ ወለደ ፕሮፖጋንዳ መጽሃፍ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው። የውሸት አለቃው መጽሃፉን በውድ ዋጋ ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ ቢያሳትምም፣ በሸራተን ሆቴል ውስኪና ሻምፓኝ አስከፍቶ ቢያስመርቅም፣ በታዋቂ ሆድ- አደር አርቲስቶችን ምዕራፍ እያስነቀሰ ቢያስነብብም፤ በማዕዛ ብሩ ሸገር ሬዲዮ በግድ እንዲተረክ ሙከራ ቢያደርግም መነበብ አልቻለም ከዚህ በተጨማሪ አንባቢዎች መጽሃፉን የፃፈው ሰው የደበቀው ነገር ሊኖር ይችላል፤ አሊያም ሃሰትን በእውነት ተለውሶ የተከተበ መሆን ጥርጣሬ ካሳደረ የመነበብ እድሉ ዝቅተኛ ነው። እርግጥ “ማን ያውራ የነበረ፣ ማን ያርዳ የቀበረ” የሚባል የተለመደ ሀገራዊ ብሂል ቢኖርም የወያኔን የሴራ ፖለቲካ ለማንበብ ከዚያም በላይ ትዕግስት ይጠይቃል። ወያኔ በጠላትነት መጥቶ እንደ ንብ መንጋ ኢትዮጵያን አፓርታይድ በሚመስል አሰራር ተቆጣጥሮ ያደረሰው የግፍ ግፍ የሂሳብ ስሌት ሳይሰሩ የሚያቀርቡ ሰዎች ለማውራትም ሆነ ለማርዳት የመታመን እድላቸው ጠባብ አይደለም። የሚቀርቡት መጽሀፎች በመረጃ የተጠናከሩ፤ ግራ ቀኝ  አመለካከቶችን ማገናዘብ ከቻሉ፤ በሀቅ ላይ የተመሰረቱ ትናንትናዎች ይዘው የሚነሱ ከሆነ መነበብ የሚችሉበት እድል ሰፊ ይሆናል።

ስለሆነም በአንድ በኩል ተጨባጭ መረጃዎችንና እውነታዎችን ሳይዛቡ የሚቀርቡበት፤ በሌላ በኩል ከሙያም ከፖለቲካ ልምድም በመንሳት የግል ምልከታን ሳያቅማሙና ሳይተሻሹ ለማቅረብ ከፍተኛ ድፍረት ይጠይቃል። ለምሳሌ ወያኔ ከልቡ ማውጣት ያልቻለው ገብሩ አስራት ጠቃሚ መረጃዎችን የያዘ ዳጎስ ያለ መጽሃፍ ቢያበረክትም በርካታ ሚስጥሮችን ሊሸሽግ በመሞከሩ “ከነገረን የደበቀን ይበልጣል” መባሉ መነሻው ይሄ ነው። በተለይም ኤፈርትን የመሳሰሉ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ አጥንት የጋጡ የዝርፊያ ማዕከላት “በኢትዮጵያ ያሳደሩት ኢኮኖሚያዊ ተጽእኖ እዚህ ግባ አይባልም” ማለት እንኳን የገፈቱ ቀማሽ ለሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ለገብሩ የመንፈስ ልጆችም አያሳምንም። ከገብሩ አስራት ጋር “መድረክ” የሚል ድርጅት የመሰረቱን ፕሮፌሰር መረራንም ሆነ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በገብሩ አገላለጥ ከማዘን አልፈው መናደዳቸው አይቀርም።

 

“የመለስ ልቃቂት” የተባለው የኤርሚያስ ለገሰ መጽሀፍ በቅድሚያ ለመመርመር የሞከርኩት ከዚህ አንጻር ነበር። ይህንን ጽሁፍ ለመሞነጫጨር ያነሳሳኝ የመጀመሪያ ምክንያት ይሄ ነው። ያለማጋነን ከገመትኩት በላይ በበርካታ መረጃና ማስረጃዎች የታጨቀው ይህ መጽሀፍ የህዉሃት በዝርፊያ የተመሰረቱና የፋፉ ኢኮኖሚያዊ ሃይሎች ላይ መብረቃዊ ምት ያሳረፈ ነው። ፀሃፊው ኤፈርት-መር ካፒታሊዝም እያለ በተደጋጋሚ ቢገልጠውም ለእኔ ግን በዝርፊያ የገነባው ካፒታሊዝም (Crony Capitalisim) ሆኖ አግንቼዋለሁ። በሌላ በኩል ፀሃፊው የዝርፊያ ማዕከሉን በግማሽ መንገድ እንዳለ አስልቶ “ልቃቂት” ደረጃ ደርሷል ቢልም በዚህ መልኩ ለጥቂት ጊዜያቶች ከቀጠለ የአገሪቱ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ህይወት በአያሌው የሚናጋ ይሆናል። ጊዜ ከተሰጠው የኢትዮጵያ ህዝብ ስርአቱን ለመገርሰስ ከፍተኛ መስዋዕትነት የሚያስከፍል ይሆናል። ከልቃቂት ያለፈው የዝርፊያው ካፒታሊዝም (ክሮኒክ ካፒታሊዝም) በጠምንጃና በሰደፍ የፖለቲካ ስልጣንን ማቆየትንና በህዝብ ላይ ሸክሙ የሚከብድበት ሁኔታ ይፈጠራል። ከመጽሀፉ መገንዘብ የቻልኩት ነገር ቢኖር የወያኔ አገዛዝ በዝርፊያ ቁምጣን የያዘው ቢሆንም በቃን የሚል አይደለም። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢትዮጵያ ህዝብ ባደረሰባቸው አደገኛ ምት እንደተጎዱ መውሰድ ቢቻልም የቆሰለ አውሬ ሆነው የሚቀትሉበት ሁኔታ እድሉ ዝግ አይደለም። አደብ እንዲገዙ ካልተደረገ አልጠግብ ባይነታቸው በበለጠ ቁጭትና በቀል ተጠናክሮ የሚቀጥልበት ሁኔታ ይፈጠራል።

የአገሪቱን ሀብት የተቆጣጠሩት የህዉሃት የብርቅ ልጆች በአንድ በኩል በሃብት ጋራ ላይ ሰማየ ሰማያት እየረገጡ የሚሄዱበት፤ በሌላ በኩል ኢትዮጵያ የሃዘን ቤትነቷ የሚቀጥል ይሆናል። ይህ እንደ አሳ ከጭንቅላቱ የገማ ስርአት ያለምንም ከልካይ የአገሪቷን አንጡራ ሃብት የሚቆጣጠርበት ሁኔታ ይፈጠራል። ፀሃፊው በመጽሐፉ እንደገለጸው ሁኔታዎች በፍጥነት ካልተቀየሩ ነገ ከነገወዲያ “የኢትዮጵያ አየር መንገድ”፣ “የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ”፣ “የኢትዮጵያ ቴሌኮሚዩኒኬሽን” የሚባሉ ተቋማት በባለቤትነትና በስም ተቀይረው የምናይበት ጊዜ ሩቅ አይደለም። ዛሬ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከሰጠው ብድር 40% ያህሉን ወያኔ ኤፈርትን ለመሰሉ ዘራፊ ኩባንያዎች እንዲሰጥ ካስገደደ፤ ከአመታት በኋላ እንደ አንፀባራቂው የመቶ ፐርሰንት ምርጫ ውጤት የብድር መጠኑም ተመሳሳይ ይሆናል።

ለምሳሌ ያህል “የመለስ ልቃቂት” ገጽ 139 ላይ “ልማት ባንክ የማነው? የትግራይ አይደለምን?” በሚል ርዕስ ስር እንዳመለከተው “በዘመነ መለስ ዜናዊ” የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከሰጠው 8.5 ቢሊዮን ብር ብድር ውስጥ 5ቢሊዮን ያህል (59%) የወሰዱት የትግራይ ክልላዊ መንግስትና የዘረፋ ካፒታሊዝም እየገነባ ያለው ኤፈርት ነው። ልማት ባንኩ ዳይመንድ ጁባይል ኢዩቤልዩውን ባከበረ አመት ብቻ  ለማበደር በእቅድ ከያዘው 2.78 ቢሊዮን ብር ውስጥ 1.7 ቢሊዮን ብር (63%) የዘራፊው ቡድን ንብረት ለሆነው መሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ማስፋፊያ ፕሮጀክት አስቀድሞ የተያዘና የተፈቀደ ነው። ከሁሉም የሚያሳዝነው አበዳሪም ተበዳሪም የሆነው ኤፈርት በራሱ የሰጣቸው ብቻ ሳይሆን እንደ ጆፌ አሞራ ከየቦታው የለቃቀማቸውን የኤፈርት ብድሮች የተበላሹና የማይሰበሰቡ በማለት ከአካውንቱ እንዲወጣ አድርጓል። “የመለስ ልቃቂት” የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ምዕራፎች አየር መንገዱ፣ ጉምሩክ ባለስልጣን፣ ቴሌ ኮሙዩኒኬሽን፣ መንገዶች ባለስልጣን፣ ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ፣ ንግድ ባንክ፣ የፍትህ ሚኒስቴር፣ ደህንነት ቢሮ፣ መከላከያ፣ ኢምግሬሽን ቢሮ፣ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤትና ኤምባሲዎች፣ የሚዲያ ትርቋማት (ኢቲቪ፣ ፋና፣ ዋልታ)…. ወዘተ በምግባር የማናቸው የሚለውን ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ ነው።

 

“የመለስ ልቃቂት ጭብጦች”

                                                                                                                                                                                 

እስከገባኝ ድረስ “የመለስ ልቃቂት” መፅሃፍ ውስጣዊ ይዘት ስመረምር ለጊዜው ሦስት ያህል ቁልፍ ጉዳዮችን ተመልክቻለሁ። እነዚህ ቁምነገሮች በተጠናጥል የቆሙ ሳይሆን አንደኛው ለቀጣዩ መሰረት ሆኖ የሚያገለግል ነው። ለዚህም ሃፍረተቢስነታቸውም ያስመሰከሩ በቂ ምክንያቶች ቀርበዋል። ወያኔዎች ከራስ በላይ ንፋስ እንደሚባለው ብሂል “ወደ ውስጥ ተመልካች” (Inward Looking) በመሆናቸው ስለደህንነት መዋቅራቸው፣ ስለ ኢኮኖሚ ሞኖፖሊያቸውና የፖለቲካ የበላይነት ለማረጋገጥ የሚሰሩት የተቀናጀ ስራ ጠቅላላውን የፖለቲካ ሃይል አሰላለፍና ጉዞ እንድንመለከት ያስችለናል። ለማንኛውም “የመለስ ልቃቂት” ዋና ዋና ጭብጦች የሚከተሉት ይመስሉኛል።

ጭብጥ አንድ፦ የመጽሃፉ መንደርደሪያና ፍሬ ሃሳብ በምዕራፍ አምስት “የማስታወሻ አስኳል” በሚል ርዕስ እናገኘዋለን። የማስታወሻው አስኳል ባለቤት ሟቹ መለስ ዜናዊ ሲሆን ኤርሚያስ “ስድስቱ የመለስ አስተምህሮዎች” በማለት ከፋፍሎ ለብቻ አቅርቦታል። እነዚህ አስተምህሮዎች መለስ ዜናዊ ድንክዬ ልጆቹንና የቤት ውስጥ ባለሟሎቹን ለማደቆን ያዘጋጀው ሰነድ ላይ እንደሚገኝ ያስገነዝባል። “የመለስ ልቃቂት” ገጽ 165- 166 ስድስቱ አስተምህሮቶችን ጭማቂ እንደሚከተለው ይገልጻል፦

 

አስተምህሮ አንድ፦“ትእምት የህዉሀት ንብረት ያልሆነ በትጥቅ ትግሉ ወቅት በተሠባሠበ ገንዘብና ንብረት በህግ የተቋቋመ                         ግብረ-ሠናይ ድርጅት ነው”

አስተምህሮ ሁለት፦“ትእምት የተቋቋመበት ተልዕኮ በመንግስትም ሆነ በባለሀብቶች ሊሸፈን የማይችል ቀዳዳ ለመድፈን

                         ነው።”

አስተምህሮ ሶስት፦  “ትእምት አመራር ስርአት በግልፅነት መርህ ላይ የተመሠረተ ነው።”

አስተምህሮ አራት፦ “ትእምት ከመንግስት ያገኘው ወይም የወሰደው ቅንጣት ሳንቲም የለም። ወደፊትም አይኖርም።”

አስተምህሮ አምስት፦ “ትእምት ኢኮኖሚውን ሊቆጣጠር፣ ባለሀብቶችን ሊያፍን ነው የተቋቋመው በማለት የሚናፈሠው

                         አሉባልታ መሠረ-ቢስ ነው”

አስተምህሮ ስድስት፦ “ትእምት በክልሎች መካከል የተመጣጠነ እድገት መኖር አለበት ብለን ያስቀመጥነውን መርህ

                           አይጻረረም”

 

ኤርሚያስ በመጽሀፉ አስኳል ላይ የመለስን አስተምህሮ ለምን በስድስት ገድቦ ለማቅረብ እንደፈለገ ግልፅ አይደለም። የማስታወሻውን አስኳል ነጥብ በነጥብ ለተመለከተ ሰው ተጨማሪ የመለስ የቅጥፈት አስተምህሮቶችን መመልከት ይቻላል። ለምሳሌ ያህል “በመለስ ልቃቂት” ገጽ 182 ላይ እንደተገለጸው መለስ ዜናዊ “ኩባንያዎቹ የወያኔን ፖለቲካዊ ስራዎች ለማከናወን ገንዘብ አይሰጡም” የሚል የጠራራ ፀሃይ ውሸት ጽፏል። ድንክዬዎቹና ባለሟሎቹ “የደንቆሮዎች ውይይት” በመሰለ የሃሳብ ውዥንብር ውስጥ ካልዳከሩ በስተቀር ህዉሃትና በተለያየ ጊዜ ጠፍጥፎ የፈጠራቸው ድርጅቶች በዘረፋ የተደራጁት ኩባንያዎች ቀጥተኛ ተጠቃሚዎች ናቸው። ከዚህ አንፃር የዝርፊያ ኩባንያዎቹ ያደረጉትና እያደረጉት ያለው አስተዋጽኦ በለሆሳስ የሚታለፍ አይደለም። ፓርቲዎቹ ለሚሰሩት ስራ፣ ለአባሎቻቸው የሚከፍሉት መደለያ ገንዘብ ህዝቡን ለማፈን ለሚዘረጉት መዋቅር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የገንዘብ ምንጫቸው እነዚህ ኩባንያዎች ናቸው።

 

ያም ሆነ ይህ “የመለስ ልቃቂት” ከመጀመሪያው ምዕራፍ እስከ መጨረሻው  ገጽ ድረስ የሟቹ መለስ ዜናዊ ኑዛዜ ቃላት (“አስተምህሮ”) በቅጥፈት የተሞሉና ውሸት መሆናቸውን በመረጃ አስደግፎ ያቀርባል። በዝርዝር እንዳየሁት ከሆነ ይህ “አሳ ጎርጓሪ” የሆነ መጽሃፍ ከኢኮኖሚ ሂሳብ ባሻገር የወቅቱን የህዉሃት የፖለቲካ የበላይነት የተረጋገጠበት ነው።

ጭብጥ ሁለት፦ “የመለስ ልቃቂት” የወያኔ ሦስቱ የዘረፋ የኢኮኖሚ ሃይሎች የሆኑትን ኤፈርት፣ ትልማ(ትግራይ ልማት ማህበር) እና ማረት (ማህበረ ረድኤት ትግራይ) አስቀድሞ በታቀደና የአፓርታይድ መርሆ በሆነ መንገድ የኢትዮጵያን አንጡራ ሃብት የማግበስበስ ስራ በቅንጅትና በመደጋገፍ እንደሚፈጽሙት ያስረዳናል። በጠምንጃ የተደገፈው የወያኔ ስልጣነ መንግስት ለሦስቱ የፖለቲካል- ኢኮኖሚ ሃይሎች የተለያየ ተልዕኮ በመስጠት የኢትዮጵያንም ሆነ ከውጭ የሚመጡ እርዳታዎችን በመቀራመት ወደ ትግራይ እንዴት እያሻገረ መሆኑን መረዳት ይቻላል። የኤፈርት፣ ትልማና ማረት ጓዳ ጎድጓዳ ሲመረመር በአገሪቷ ላይ ያደረሱትና እያደረሱ ያሉት የጥፋት መጠን ምን ያህል ከፍተኛ እንደሆነ በቀላሉ መገመት ይቻላል። ርግጥም በኢትዮጵያ የሰፈነውን ኢ-ፍትሃዊነትና የተዛባ ተጠቃሚነት ለመዳሰስ የሦስቱን የፖለቲካል- ኢኮኖሚ ሃይሎች አመሰራረት፣ አደረጃጀት፣ ራዕይ፣ ተልዕኮና ተጨባጭ ተግባራት አብጠርጥሮ ማወቅ የወያኔ መሪዎች የኢኮኖሚ ራዕይ “የትግራዋይ” መሆኑን ይደርስበታል። ያለምንም ማጋነን “የመለስ ልቃቂት” ኢትዮጵያን አፓርታይድ በሚመስል መልኩ የያዙት የወያኔ መሪዎች ለሩብ ክፍለዘመን ቆዳቸውን እየቀያየሩ የሚያሳዩትን ድራማ በመረጃ አስደግፎ ያቀረበ በሳል መጽሃፍ ነው።

በተለያዩ መጽሃፍትና መጣጥፎች እንደተገለጠው የወያኔ የኢኮኖሚ አውታር ስለሆነው “ኤፈርት” ብዙ ተብሏል። ኤርሚያስ በዚህ መጽሃፍ ላይ በርካታ መረጃዎችን በመጨመር ያጠናከረው ሲሆን በአገሪቷ ህግ መሰረት የተቋቋመ መሆኑና አለመሆኑን ጥያቄ አስነስቶበታል። የፖለቲካ ፓርቲዎችና አመራሮቻቸው ላይ መነጋገር መጀመር እንዳለባቸው አስገንዝቧል። እኔም የጸሃፊውን ሃሳብ እጋራለው። ከወያኔ በኋላ የሚገነባው አዲስ ስርአት በእነዚህ የዝርፊያ ተቋማት ላይ አስቀድሞ አቋም መውሰድ እንደሚገባው አምናለሁ። የተዘረፈው የኢትዮጵያ ህዝብ ሀብት ለባለቤቱ የሚመለስበት ሁኔታ መፈጠር ይኖርበታል። በስሙ የሚነግድበት የትግራይ ህዝብም ኤፈርት፣ ትልማም ሆነ ማረት ህገ-ወጥና ኢፍትሃዊ በሆነ መንገድ የተቋቋሙና የኢትዮጵያን ህዝብ አጥንት በመጋጥ የፋፉ መሆኑን ተገንዝቦ ድርጅቶቹ ላይ ለሚወሰዱት እርምጃዎች ትብብር ማድረግ ይጠበቅበታል።

ጭብጥ ሦስት፦ “የመለስ ልቃቂት” የወያኔ ሦስቱ የዝርፊያ ድርጅቶች የትግራይ የህዝብን በልዩ ሁኔታ ተጠቃሚ አድርገዋል የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሱን በተለያዩ ቦታዎች አሳይቷል፡፤ ይህንን ድምዳሜ በመጽሃፉ ሆድ እቃ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በጀርባ ሽፋኑም ላይ አጽንኦት ሰጥቶ አስፍሯል። ከብዙ በጥቂቱ እንዲህ ይላል፣

“ትግራይ አልተጠቀመችም የሚለው የፖለቲካ መንገድ በየትኛውም መከራከሪያ እያረጀና እያፈጀ ሄዷል። ተጠቃሚነት መለካት ያለበት በየደረጃው ነው። …. ሁሉም የትግራይ ተወላጅ ሚሊኒየር ሊሆን አይችልም። ሁሉም የትግራይ ተወላጅ የመንግስት ተቀጣሪ ሊሆን አይችልም። ሁሉም የትግራይ ተወላጅ ዩንቨርስቲና ኮሌጅ ሊገባ አይችልም።…. ትግራይ ተጠቅማለች ሲባል ሁሉም የትግራይ ወጣትና ሴት የፋብሪካ ሰራተኛ ኩባንያዎች በሆኑት አዲግራት መድሃኒት ፋብሪካ፣ አልመዳ ጨርቃጨቅ፣ በትራንስ፣ በህይወት ሜካናይዜሽን፣ መሶቦ ሲምንቶ፣ ኢዛና…. ወዘተ የመሳሰሉት ዘመናዊ ፋብሪካዎች ተቀጥረው የሚሰሩት የትግራይ ተወላጆች ናቸው” ይላል።

“የመለስ ልቃቂት” የወያኔ መሰረት የትግራይ ስለሆነች የትግራይ ህዝብ በየደረጃው እንዲጠቀም አድርጓል ትለናለች። ወያኔ ከምንም በላይ የሚፈራውና የመኖር ህልውናውን የሚያናጋው የትግራይ ህዝብ ስለሆነ ህዝቡ ቢፈልግም/ባይፈልግም የኢኮኖሚ ተጠቃሚነቱን ማረጋገጡ የማይቀር እንደሆነ ያስገነዝበናል። ትግሬዎች ለወያኔ አገዛዝ ባላቸው ቅርበትና ርቀት ልክ ተጠቃሚነታቸው እንደሚረጋገጥላቸው ኤርሚያስ እማኞችን እያቀረበ ያሳየናል።  በዚህ ማስረጃ ውስጥ ገዥዎቻችን ምን አይነት ሰዎችና ምን አይነት ባህሪ እንዳላቸው እንመለከታለን። ወያኔዎች ከኢትዮጵያ ጥቁር አፈር ስለመፈጠራቸው ሳንወድ በግድ ጥያቄ እንድናነሳ ያደርገናል።

በአጠቃላይ መልኩ ብዙ እንደተላለፉት የሚያስታውቀው “የመለስ ልቃቂት” መጽሃፍ ወያኔ የፖለቲካ ሞኖፖሊውን እያስፋፋ የሄደውን ያህል የኢኮኖሚ ሞኖፖሊውን በአስተማማኝ መሰረት ላይ እየገነቡ ነው። ለፖለቲካው ፍፁም የበላይነትና መደላድል ወሳኝ የሚሆነው ኢኮኖሚውን መቆጣጠር እንደሆነ የሚገለጥበት አባባል ትክክል መሆኑን ያረጋገጠበት ነው። አዋጁን በጆሮ ካልተባለ በስተቀር ወያኔ የገነባው የዝርፊያ ካፒታሊዝም በራሱ መናገር ጀምሯል። የንቅዘቱ ደረጃ ከወያኔ የፕሮፖጋንዳ ማሽን ከሚነዛበት ቅጥፈት በላይ ተሻግሯል። ሦስቱ የወያኔ የዝርፊያ ማዕከላት ሁሉንም እየጠቀለሉ ነባር ሀገራዊ ከበርቴዎችን ከጨዋታ ውጭ እየወጡና ከትግራይ ውጭ አዳዲሶች እንዳይወለዱ እየተደረገ ነው። ከዚህ ሁኔታ ተነስተን አገራችን ኢትዮጵያ ያለችበት የወቅቱ ሁኔታና የወደፊት እጣ ፋንታ እጅግ አሳሳቢ ሆኗል። በአድሎና መገለል ምክንያት ጨጓራው የተላጠውና ቆሽቱ ድብን ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ በአንድ ባልታወቀ ጊዜ ፈንድቶ የወጣ እለት ውጤቱ ምን እንደሚሆን ለመገመት ነብይ መሆን አይጠይቅም።  “የመለስ ልቃቂት” የታመቀውን የህዝብ ብሶት በንዴት ገንፍሎ ሊያወጣው እንደሚችል ሙሉ እምነት አለኝ። ከዚህ አንጻር ኤርሚያስ መጽሓፉን መታሰቢያ ያደረገለት አንጋፋው ሙሉጌታ ሉሌ በጦቢያ መጽሔት ላይ “ስም ያልወጣለት ወንጀል” በሚል ርዕስ ያቀረበው መጣጥፍ ይታወሰኛል። አንጋፋው ብዕረኛ እንደገለጠው ከሆነ አንድ በአገዛዝ ውስጥ ያለ ህዝብ ደም የሚያስተፋ ንዴትና ቁጣ ካልተሰማው መሰረታዊ ለውጥ አይመጣም ይለናል።

“መናደድ ትልቅ ነገር ነው። መናደድ ብንችል ደግሞ አንዱ የዚች አገር ማዳኛ የትግል መቅድም ይሆናል። ግን ለመናደድ ለመብሸቅና ከተቻለም እህህህ ብሎ ደም መትፋት መቻል አለብን!! በማለት ብዕረኛው ይገልፃል።

“የመለስ ልቃቂት” መናደድ የማይፈልገውን ከውስጡ ፈንቅሎ በተዋረደ ስሜት የሚናደድበት ሁኔታ ይፈጥራል። ወጣቱ አዲስ የቁጭት ስሜት ፈጥሮ ወደ ተግባር የሚገባበት “የማታገያ ሰነድ” እንዳገኘ እቆጥራለሁ።

መልካም ንባብ!!

የማለዳ ወግ…በጅዳ 3 ሽህ ታዳጊዎችን ለመታደግ መምህራን ሲተጉ … ! -ነቢዩ ሲራክ

$
0
0

* በጅዳ የኢትዮ አለም አቀፍ ት/ቤት ዘንድሮም በአደጋ ላይ
* በትውልድ ላይ መቀለድ ይቁም … !
* መምህራንና ሰራተኞችን ተቆጥተዋል

እለተ ሃሙስ መስከረም 19 ቀን 2009 ዓም ምሽት ላይ በጅዳ አለም አቀፍ ት/ቤት ዙሪያ አንድ ሰበር መረጃ አቅርቤ ነበር ። ሰበሩ መረጃ ለአመታት ከግል ጥቅማ ጥቅም ባለፈ ከሶስት ሽህ በላይ (3000) ታዳጊ ኢትዮጵያውያንን ተማሪዎች ጉዳይ “ያገባናል ” ብለው የማያውቁት መምህራን ዘንድሮ ” ያገባናል ” ብለው ከጅዳ ኮሚኒቲ አመራሮችን ጋር ስብሰባ ላይ መፋጠጣቸውን ይመለከት ነበር ። ዛሬ የምናዎጋው በስብሰባው ዙሪያ ቢሆንም እንደ መግቢያ ትናንት መምህራኑ ሲዎሱ አሞን የባጀው ግዴለሽነትና ዝምታቸውን እናዎሳለን ፤ ዛሬም ሌላ ቅን ነውና መምህራኑ ለታዳጊዎች መብት መከበር ያሳዩትን ትጋት በጨረፍታ እንቃኛለን ! የፈቀደ ይከተለኝ …

nebiyu-1-satenaw-news

አሞን የባጀው የመምህራኑ ግዴለሽነትና ዝምታ …
===========================
አዲስ አመት በመጣና በሄደ ቁጥር ሁሌም ለጅዳና አካባቢው ቀዳሚው ህመም “የትምህርት ማዕከሉ አደጋ ላይ ወደቀ !” የሚለው መረጃ ነው ፤ በእርግጥም የትምህርት ማዕከሉ ማደግ ባለበት ፍጥነት ቀርቶ ለመቀጠል አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱ የመኮላሸት አደጋው መረጃ አሳሳቢ ነው ። ይህ ላለፉት በርካታ አመታት ወላጅ ነዋሪውን ሲያመን ቢከራርምም የውስጥ ብክለቱን አሳምረው ከሚያውቁት ከመምህራን የሚሰማው ሮሮ በተናጠል ከንፈር ከመምጠጥ የዘለለ እንዳልነበር በቅርብ የምናውቅ የምንመሰክረው እውነታ ነው ። ተማሩ ተመራመሩ የተባሉት መምህራን የውስጥ ችግሩን እያወቁና ትውልድ የሚቀረጽበት ማዕከል ወዳልተፈለገ አደጋ እየተጓዘ ዝምታን መርጠው ከርመዋል ። ባንድ ወቅት ” ት/ቤቱ አስተዳደርና ኮሚኒቲው በመኖሪያ ፍቃዳችን ዝውውር ዙሪያ መጉላላት አደረሰብን !“ ብለው የማስተማር ማቆም አድማ አድርገው መብታቸውን ያስከበሩ መምህራን የታዳጊዎችን የትምህርት ማዕከልን የውስጥ ገመና ከማናችንም በላይ እያወቁትና ችግሩን ለመፍታት ቀዳሚ መሆን ሲገባቸው ፈቃደኛ ሳይሆኑ ከርመው አሳዝነው ያውቃሉ ። ከእጅ ወደ አፍ በሆነ ኑሮ ልጅ ወልደን በአሳር በመከራ የምናሳድግ ስደተኞች ልጆች ትምህርት አሰጣጥና ግዙፉ የመቀጠል ያለመቀጠል አደጋን ችግር ቀድመው ቢረዱና መድሃኒቱን ቢያውቁትም ሊያክሙት ተስኗቸው ባጅቷል … እኒሁ ተስፋ የጣልንባቸው መምህራን እንኳንስ በታዳጊዎች መማሪያ ማዕከል የመጣውን ችግር ሊቀርፉ የውስጥ ህብረት አጥተው ግዙፉን ችግር በግድ የለሽነትና በትዝምታ ማለፍ መምረጣቸው መላ ነዋሪው አስከፍቶና አሳዝኖን መክረሙም ሌላው የማይደበቅ ነጭ እውነታ ነው …

አደጋው ገዝፎ መምህራን ሲቆጡ …
==============================
ዘንድሮ ግን ነገሮች ተለዋውጠዋል ፤ በጅዳ አለም አቀፍ ት/ቤት መምህራንና ሰራተኞች በህብረት ተቆጥተው ታይቷል ፤ ምክንያታቸው ደግሞ ከሶስት ሽህ (300) በላይ ታዳጊ ተማሪዎች ትምህርት የሚገበዩበት ማዕከል እያደር የመዝቀጡ እውነታ ገንፍሎ መውጣቱ ነበር ። መምህራንና ሰራተኞች ከላይ እስከታች ፤ ከኮሚኒቲው እስከ ት/ቤቱ አስተዳደር በኢህአዴግ አደረጃጀት በተዋቀረው አመራር የውስጥ ህብረት አጥተውና ተፈራርተው ቢባጁም ዘንድሮ እንደባጁት ፈርተው መቀጠልን አልፈቀዱም ። ለአመታት አርቆ የያዛቸውን ፍርሃት ሰብረው ከመውጣት ባለፈ ተቀናጅተው ወደ ትምህርት ቤቱ ባለቤቶች ቀርበው ” ግፍ በዝቷልና ሊቆም ይገባል ” ብለው ድምጻቸውን ማስማት ጀምረዋል ። በትምህርት ማዕከሉ የሚሰራው ሸፍጥና ግፍ ” መቆም አለበት” በማለት ተቃውሞ ጥያቄያቸውን አቅርበዋል ! ከሶስት ሳምንት በፊት የተቆጡት መምህራንና የት/ቤቱን ባለቤት ከሆነው የኮሚኒቲውን አመራሮች ጋር ለመምከር ደጋግመው ቢጠይቁም አመራሩ እድል አለመስጠቱ ይጠቀሳል ። ዳሩ ግን ኮሚኒቲው አሻፈረኝ ሲል የወላጅና መምህራን ህብረትን በማማከር ወደ ቆንስላው ኃላፊዎች ቀርበው ብሶታቸውን ቢያሰሙም “ ህብረታችሁን አጽንታችሁ ከተጓዛችሁ ወላጁን በማቀፍ ለውጥ እንደምታመጡ ለታዳጊዎች ማዕከል ማንሰራራትና ትንሳኤ ተስፋ ያለው በእናንተ በመምህራን ላይ ነው ” ከሚል ዲፕሎማሲዊ የኃላፊዎች ምላሽ ባለፈ ላቀረቡት ስሞታ የረባ መፍትሔ እንዳልተሰጣቸው ከአስተባባሪዎች መካከል አንድ መምህር አጫውተውኛል … በያዝነው ሳምንት ግን ሳይታሰብ የኮሚኒቲው አመራር ከመምህራኑ ጋር ለመገናኘት ፕሮግራም መያዛቸው በተነገራቸው መሰረት ሐሙስ መስከረም 19 ቀን 2009 ዓም ምሽት ተቃውሞ ጥያቄያቸውን ከትምህርት ቤቱ ባለቤት ለት/ቤቱ አስተዳደር ፤ ለት/ቤቱ ባለቤት ለጅዳ ኮሚኒቲ አመራር አባላት እና ለመንግስት ዲፕሎማቶች አቅርበዋል !

በጦፈው ስብሰባ ምን ተባለ … ?
===========================
በእርግጥም ሐሙስ ምሽት የጅዳ ኮሚኒቲ አዳራሽ መምህራንና ሰራተኛች በነቂስ ተገኝተዋል ፤ በት/ቤቱ በኩል ስብሰባው ይጀምራል ተብሎ የተነገረው ሰዓት የተወሰነ ክፍተት ቢፈጥርም ስብሰባው ዘግይቶ ጀመረ … አጀንዳ ያልያዙት የኮሚኒቲው አመራሮች ያለ አጀንዳ ስብሰባውን መምራት ሲጀምሩ እርምት ተደረገ … እናም በቀጥታ ወደ ውይይቱ ተገባ ፤ መምህራን ጥያቄያችውን አዘነቡት … እንዲያ እያለ ቀጠለ ! …በእርግጥ መረጃውን ሳዳምጠው ማመን አልቻልኩም ፤ ብዙዎች እንደኔ መገረማቸውንም ሰምቻለሁ … በጦፈው ስብሰባ የተሰማው የመምህራንና ሰራተኛ ጥያቄ ፡ ቁጣ ፡ ሮሮና ተማጽኖ በወገናዊ ስሜት የተነገረ ፤ ከዚህ ቀደም ታይቶም ሆነ ተሰምቶ የማይታወቅ ነበር ማለት ይቻላል !
…በዚሁ ስሜት ቀስቃሽ በሆነ ስብሰባ በመምህራን የት/ቤቱ ፈቃድ አለመታደስ ፣ ካለው የተማሪ ብዛት አንጻር ተጨማሪ ት/ቤት ለመከራየት እቅድ ቢኖርም ፣ ት/ቤቱን መከራየት አለመቻሉን እንኳ የሰሙት በቅርቡ መሆኑን ተናግረዋል ። ዘንድሮም ወላጅ በፈረቃ ሊያስተምር ሲወሰን ፣ በጉዳዩ ባለድርሻ መምህራን እንዲመክሩና እንዲወያዩ አለመደረጉንም አንስተዋል ። ከሽዎች የሚቆጠሩ ታዳጊዎች ትምህርት የሚቀስሙበት ማዕከል አደጋ ላይ መሆን ያስቆጣቸው መምህራን በድፍረት ” ድብቅብቁ ይቁም! ” በማለት ሞጋች ጥያቄዎችን ለኮሚኒቲው ምክር ቤት አመራሮ ች ፤ ለት/ቤቱ አስተዳደር እና ለዲፕሎማቶች ያቀረቡ ሲሆን የቀረቡት ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው :-

በመምህራንና ሰራተኞች የቀረቡት ጥያቄዎች…
==========================
* የትምህርት ቤቱ ህጋዊነት ተረጋግጦ ተማሪዎች ወላጅ ብሎም ሰራተኛው ከስጋት ነፃ ይሁን
* በሳውዲ ት/ሚኒስትር ፈቃድ ይታደስ ፣ ትምህርት ቤቱ በአስቸኳይ በቦርድ ይተዳደር
*የት/ቤቱ የተወላከፈው አስተዳደር በአግባቡ ተዋቅሮ ተጠያቂነት እና ህግና ስርአትን የተከተለ አሰራር ይኑረው
*የት/ቤቱ አስተዳደር ከዝምድና ከጎሰኝነት እና ከመሳሰሉት ነፃ ይሁን
* ማህበረሰቡ የራሱ የሆነ ት/ቤት እንዲገነባ ሁነኛ ስራ ይሰራ
* አዲስ አመት ምዝገባ ላይ የሚስተዋለው በዘመድ አዝማድና በመሳሰሉት መሆኑ ኢ-ፍትሀዊነት ነው ይቁም
* መሰረታዊ የአሰራር እና የአስተዳደር ለውጥ ይኑር
* በትምህርት ደረጃቸው ማስተርስ ያላቸው ሰራተኞች ማግኘት ያለባቸውን ቦታ ይሰጣቸው
* የኮሚኒቲው ምክር ቤት በብቃት ሀላፊነቱን ይወጣ
* ት/ቤቱ ባለቤት አልባ እና ተቆርቋሪ አጥቷል
* በማዕከሉ አላፈናፍን ያለው ” ኪራይ ሰብሳቢነት” ተነቅፏል
* “የኪራይ ሰብሳቢነት” ምንጩ ቢታወቅም ኪራይ ሰብሳቢዎች ተሸፋፍነዋል ተለይተው ይታወቁ የሚሉት ከብዙው በጥቂቱ ይጠቀሳሉ

ለመምህራኑ ጥያቄ የተሰጠው ምላሽ …
=====================
ከዚህ በላይ በመምህራኑ የቀረቡትን ጥያቄዎችና ያነሷቸውን አንኳር መሰረታዊ ጥያቄዎችም የጅዳ ኮሚኒቲ አመራሮችንጨምሮ የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር ምላሽ ሰጥተውባቸዋል። በምላሹም የኮሚኒቲው አመረሮች ” ኃላፊነታችንን ለመወጣት ወደ ኋላ አላልንም ፣ ነገር ግን መንገድ ከያዝን በኋላ ይበላሽብናል ። በተበላሸ መሰረት ላይ ስለገባን ስራው አስቸጋሪ ሁኖብናል ” ብለዋል ። … ለትምህርት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ለማፈላለግ በሚደረገው ሂደት እግር በእግር እየተከታተሉ የሚያበላሹት ” ኪራይ ሰብሳቢዎች ” እንደሚያስቸግሯቸው በሚያሳብቅ ሁኔታ በሂደቱ ተማረው ምላሽ ሰጥተዋል። በሳውዲ ትምህርት ሚኒስቴር በኩል “ ቦርድ አቋቁሙ ” ተብሎ የተጓተተበትን ሂደትና ምክንያት አጥጋቢ ምላሽ ባይሰጥም ቦርድ ለማቋቋም በቅርቡ የተጠቆሙ የቦርድ አባላት ስላሉ ኮሚኒቲው ተመራጮችን እንደሚያጸድቅ ቃል ገብተዋል ።

ባልተለመደ መልኩ የህዝብ ወገናዊነትን ያሳዩትና ፍርሃትን አስወግደው ኮሚኒቲውን የሞገቱት መምህራን በስብሰባው ላይ ብሶት ስጋታቸውን ለማቅረብ ተደራጅተው በነቂስ መገኘታቸው ይጠቀሳል ። ” የትምህርት ማዕከሉ እያደረ መዝቀጥ የለብትም ፣ አሉ ያላችኋቸውን ኪራይ ሰብሳቢዎችን አጋልጡ!” ተብለው ለተጠየቁት የኮሚኒቲ አመራሮችን በምላሻቸው “ኪራይ ሰብሳቢ” ያሏቸውን ለማጋለጥ አልደፈሩም። የኮሚኒቲው አመራሮች ት/ቤቱን ለማሰራት እየተደረገ ስላለው ጥረት ሲዘረዝሩ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ወደ ሳውዲ በመጡ ቁጥር የነዋሪውን ብሶት ማሳዎቃቸውን አስረድተዋል ፤ ወደ ኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስቸኳይ የትብብር ደብዳቤ መላካቸውን ገልጸዋል ፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት አልፎ « ትምህርት ቤት ይሰራልን!» የሚል ደብዳቤ ተልኮ ከጠቅላይ ሚኒስተሩ እጅ መግባቱንም ለተሰብሳቢው አሳውቀዋል ። በዚህ ላይ አስተያየት የሰጡት የጅዳ ቆንስል ኃላፊ አምባሳደር ውብሸት “ ከመንግስት የተጠየቀው ድጋፍ በአሁኑ ሰአት ባለው የፓለቲካ አለመረጋጋት ትኩረት ላይሰጠው ይችላል ” የሚል ግምት እንዳላቸው ጠቁመዋል ። ከአንባሳደሩ ጋር ተቀራራቢ አስተያየት የሰጡት መምህራኑና ሰራተኞች በበኩላቸው ” ነዋሪው የሚያስተባብረው ቢያገኝና ኮሚዩኒቲው ከጉቦኝነት ነፃ ከሆነ ማንንም ሳይፈልግ ማህበረሰቡ የራሱን ህንፃ ይሰራል!”ሲሉ ተናግረዋል ። በዚህም በዚያም ተብሎ የጅዳ ኮሚኒቲ አመራሮች የመምህራኑን ጥያቄ ለመመለስ በሞከሩበት ምሽት በሁለት ወር ውስጥ አዲስ ነገር እንደሚታይ ቃል በመግባት ” ጥረታችን እንዲሳካ ታገሱንም እርዱንም ” በማለት መምህራንና ሰራተኞቹን ተማጽነዋል!

የዳይሬክተር አብዱ አባ ፎጌ ዲስኩር …
======================
የኮሚኒቲው አመራሮች በፈታኝ ጥያቄዎች ሲፋጠጡ የኮሚኒቲውን አመራር ትንፋሽ ለመስጠት የት/ቤቱ ዳይሬክተር አብዱ አባ ፎጌም የተለመደ ረዠምና አደንዛዥ የማይጨበጥ ትንተናቸውን ማቅረባቸው ይጠቀሳል። ለትምህርት ቤቱ አለመቀየር ብዙው ነዋሪ ጣቱን የሚቀስርባቸው የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር አብዱ አባፎጊ የተናገሩትን ሁሉ ዙሪያ ጥምጥም ትተን ወደ ፍሬ ነገሩ ስናመራ የፈቃዱን ጉዳይ እና ተዛማጅ ጉዳዮችን በሚመለከት በሰጡት ምላሽ ” ለማስተካከል የበኩላችንን ጥረናል ፣ ወደ ሳውዲ ት/ሚኒስተር ከአመት በላይ ተመላልሰናል። ብዙ በጀት ለዚሁ ጉዳይ ወጪ አድርገናል ። በእርግጥ የተጨበጠ ነገር በማጣቴ ሰራተኛውን ሰብስቤ ማወያየት አልቻልኩም ” በማለት የተለመደ እርባና ቢስ ዲስኩር ማሰማታቸው ይጠቀሳል ።

አስተያየት ፤ የምክር ቤቱ አባል …
===================
ከኮሚኒቲና ለት/ቤቱ ቅርብ የሆኑ የኮሚኒቲ ምክር ቤት አባልን የትምህርት ማዕከሉን ለማዳን መፍትሔው ምንድነው ? ብዬ ጠይቄያቸው ዋናው እየታየ ሰው ሊናገረው የማይደፍረው የኮሚኒቲው እና ት/ቤቱ በፖለቲካ ድርጅቶት አባላት ተጽዕኖ ስር መውደቃቸው እንደሆነ አጫውተውኛል ፣ ከኮሚኒቲው ስራ አስፈጻሚዎች መካከል ( 7 ለ 3 )አብዛኛው የኢህአዴግ አባላት በመሆናቸው በውሳኔ ድምጽ አሰጣጡ ተጽዕኖ መፍጠሩን ያስረዳሉ ። ከዚህም አልፎ የኢህአዴግ አባላት የበላይ መሆን ”በት/ቤቱ ውስጥ ያለውን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ፤ ስብሰባ ሲጠራ ፤ መዋጮ ሲጠየቅና ለመሳሰሉት ድርጅታዊ ጥቅማ ጥቅሞችን ለማስፈጸም ተብሎ የትምህርት ማዕከሉ እየተጎዳ ነው ።” ካሉ በኋላ ከዚህም አልፎ በትምህርት ቤቱ ዙሪያ ገብ ላለው መሰረታዊ ችግር ተጠያቂ የሆነውን የት/ቤቱን አስተዳደር ለመቀየር የሚደረገውን እንቅስቃሴ እስካሁን የሚያሰናክለውና የማይደፈርበት ምክንያት ዳይሬክተሩና የአስተዳደር ኃላፊው የድርጅት አባላት መሆናቸው እንደሆነ ዘርዝረው አውግተውኛል ። ይህም ዛሬ ኮሚኒቲው አስቸግሮኛል ያለው ኪራይ ሰብሳቢነት ተዛማጅ ችግሮች ተጠናክሮ መቀጠል ምክንያት መሆኑን “ ስሜን አትጥቀስ ” ያሉኝ የምክር ቤት አባሉ አስረድተውኛል ! ቀጠሉና “ አንተ ስታስበው የትምህርት ቤቱ ቁንጮ አስተዳደር በኦሆድድ ፤ በህዎሃት እና በብአዴን ወፍራም ተጽዕኖ ሹሞች ተይዞ ለውጥ ለማምጣት እንዴት ይቻላል?ከዚህ ቀደም ይህን ማሰብ የዋህነት ነው፤ ለውጥ ማምጣት የሚቻለው በድርጅት ሸፋን ለውጥ እንዳይመጣ እክል የሆኑትን በማንሳት ብቻ ነው ፤ እመነኝ እስካልሆነ ድረስ ለውጥ ላለመምጣቱ ምክንያት ይህ ብቻ ነው ፤ በዚህ ምክንያት ወላጆች ሁሌም ስለጆቻችን ት/ቤት ስናስብ በስጋት ኖረናል ፤ ከሰሞኑ የነዋሪው ብሶትና የታዳጊዎች ማዕከል ጉዳይ አሳስቧቸው መምህራን እውነቱን መጋፈጥ ጀምረዋል ፡ ትልቅ ለውጥ ነው ! ድሮም ያጠፋን የእነሱ ዝምታ ነበር ። ዘንድሮ ደፍረው ለእውነትና ለህዝቡና ለታዳጊዎች መቆማቸው ትልቅ ተስፋ ነው ። እነሱ ከበረቱ ነዋሪው ይደግፋቸዋል ፤ ነዋሪው ከደገፈ ደግሞ ለውጥ አይቀሬ ነው !” ሲሉ ጥልቅና ዘርዘር ያለ አስተያየታቸውን አካፍለውኛል …
አስተያየት ፤ ዲፐሎማቱ …
========================
ሌላው በትምህርት ቤቱ ዙሪያ አስተያየታቸውን እንዲሰጡኝ የጠየቅኳቸው ስማቸው ለደህንነታቸው ሲባል እንዳይጠቀስ የፈለጉ ሳውዲ የሚገኙ ዲፕሎማት ” ነቢዩ የምሰጥህን አስተያየት እንደ ዲፕሎማት ሳይሆን እንደ ዜጋ ተቀበለኝ ፤ ነዋሪው ከዚህ ቀደምም ሸህ ሁሴን አልሙዲ ይሰራሉ ብሎ በሌለ ተስፋ ፕሮጀክት ይሰራ ተብሎ ኮሚኒቲው ለሙስና ተጋልጧል ፤ አሁን ደግሞ መንግስት ት/ቤት ይስራልን የሚል ጥያቄ መቅረቡን እየሰማን ነው ፡ ይህ ትክክለኛ አካሄድ አይደለም ፤ መንግስት ትምህርት ቤት ለመስራት በጀት ይመድባል ብሎ ጊዜ ማባከን ተገቢ አይደለም !አሁን እንቅስቃሴ የጀመሩት መምህራን ከጠነከሩ ፣ ወላጅና ነዋሪው ትምህርት ቤት እንዲሰራ የሚያደራጀው ካገኘና ወላጅ ከመምህራን ጎን ከቆመ በአጭር ጊዜ ስኬት ይኖራል ! ” በማለት ሲናገሩ እስካሁን ምንም ማደረግ ያልቻለው የቆንስል መስሪያ ቤት ወደ ፊትም ምንም ማድረግ እንደማይችል ጠቁመውኛል ።

አስተያየት ፤ መምህሩ …
======================
ከስብሰባው በኋላ አስተያየታቸውን እንዲሰጡኝ የጠየቅኳቸው አንድ የስብሰባው ንቁ ተሳታፊ መምህር ” የሚሰራው ስራ አሰላችቶንና አንገሽግሾን ላቀረብነው ተደጋጋሚ መሰረታዊ ጥያቄ የተሰጠው መልስ ቀድመን የገመትነው ነው፤ አያጠግብም ! ዘንድሮ አምና አይደለም ፡ ወላጅ ከጎ ናችን ከቆመ ታዳጊ ልጆቻችን ትምህርት ቅበላ በመምህራን ጉድለት በሚከሰተውን የትምህርት ጥራት ለማካካስ ከመትጋት ባሻገር ኪራይ ሰብሳቢነትን ለማስዎገድና የበከተው አስተዳደር ብቃት ባለው አስተዳደር እንዲተካ ጥረት ከማድረግ አንመለስም ። ፍርሃቱ በቅቶናል ፤ ወላጁም ስለ ልጆቹ ከጎ ናችን ሊቆም ይገባል ” ሲሉ በስሜት አስተያየታቸውን ሲያቀብሉኝ “ጀሮ ያለው ይስማ ! ” በማለት ጭምር ነበር !

አዎ ! በጅዳ ሶስት ሽህ (3000)ታዳጊዎችን ለመታደግ መምህራን ሲተጉ ማየት ያስደስታል ፤ በትውልድ ላይ መቀለድ ይቁም !እኔም እንደሚያገባው ዜጋ ” ጀሮ ያለው ይስማ” እላለሁ !

ቸር ያሰማን !

ነቢዩ ሲራክ
መስከረም 21 ቀን 2009

– See more at: http://www.satenaw.com/amharic/archives/22232#sthash.EPBrJBJT.dpuf

ዘላቂ ጉዳት የማያስከትል ለውጥ!  –አስራት አብርሃም

$
0
0
asrat abereha

አስራት አብርሃም


በአሁኑ ሰዓት የስርዓት ለውጥ እንዲመጣ የማይፈልግ ያለ አይመስለኝም፤ ሁላችንም ለውጥ እንዲመጣ እንፈልጋለን። መሰረታዊው ጥያቄ ግን ዘላቂ ጉዳት የማያስከትል፤ ሁሉንም አሸናፊ፤ ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ የስርዓት ለውጥ እንዴት ማምጣት ይቻላል? የሚለው ነው። ከደርግ ወደ አሁኑ ስርዓት ለመሻገር እንደ ሀገር ብዙ አላስፋለጊ ዋጋ ከፍለናል፤ የብዙ ኢትዮጵያውያን ቤት ፈርሷል፤ በመቶ ሺዎች ህይወታቸውን አጥቷል፤ አካለ ጎደሎ ሆኗል፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ የባህር በራችን አሳልፈን እንድንሰጥ ተደርገናል፤ ይሄኛው ከደረሱብን ጉዳቶች ሁሉ የከፋ፣ ለቀጣይ ትውልዶች ሳይቀር ዋጋ የሚያስከፈል ነው። አሁን ማሰብ ያለብን እንደነዚህ ዓይነቶቹ ተጨማሪ ጉዳቶች ሳናስተናግድ እንዴት ነው ከዚህ መንግስት መላቀቅና የተሻለ ስርዓት ማምጣት የምንችለው የሚለው ጉዳይ ነው። ለዚህ የተሻለ መፍትሄ ለማግኘት በጉዳዩ ላይ በስፋትና በጥልቀት መወያየት፣ መግባባት መቻል አለብን፤ ፍላጎቶቻችን ማቀራረብና ማስማማት መቻል አለብን።

ስርዓቱን የሚቃወም ሁሉ ለውጥ ለውጥ ፈላጊ መሆኑ እውነት ቢሆንም ሁሉም ግን ኃላፊነት በተሞላበት ሁኔታ እየታገለ ነው ማለት አይቻልም። አንዳንድ የምናያቸው ምልክቶችም የሚያሳዩት ይህኑኑ ነው። ስለመጭው ጊዜ፣ ስለሀገር አንድነት፣ ሁሉም ዜጋ በእኩልነት ስለሚኖርባት ኢትዮጵያ እያሰበ የሚታገለው ኢትዮጵያዊ ድምፁ እየሰለለ ነው፣ እዚህም እዚያም በጎጥ በተደራጁ ቡድኖች እየተዋጠ ነው ያለው። አንዳንዶች ደግሞ አንድም በተስፋ መቁረጥ አንድም ደግሞ በራራቸው መንደር በሚኖረው ጊዚያዊ ሞቅታ ልባቸው እየተሰለበ ከነበሩበት የዜግነት ከፍታ ወርደው ወደ ጎጣቸው ገብቷል፤ እርግጥ ነው በዚህ መንገድ መታገል ቀላልና ጥረት የማይጠይቅ ነው። በጎጥ ተደራጅቶ እንደፈለጉ ማውራት፣ በቀላሉ ህዝብን ማነሳሳትና ማሰለፍ ይቻላል። ዘላቂ ውጤት፣ ሰላምና አብሮነት ማምጣት ባይቻልም፤ ለራስህ ጠባብ ቡድን ጊዜያዊ ድልና ጥቅም ማግኘት እንደሚቻል በህወሀትም እያዩት ስለሆነ ሊያጓጓቸው ይችላል።

በመሆኑም እኔ በዚህ ፅሁፍ በወደፊቷ ኢትዮጵያ የሁሉም የዜግነት መብት በእኩልነት የሚረጋገጥበት፤ ተከባብሮ በፍቅርና በአንድነት መኖር ስለሚቻልበት ነው ሀሳብ መስጠት የምፈልገው። ከአሁን በፊት እንደገለፅኩት ሁላችንም በኢትዮጵያ የተገኘነው መርጠነው አይደለም፤ ተፈጥሮ ነች አንድ ላይ እንድንሆን ያደረገችኝ። መለያየት ብንችል እንኳ ሀሳባዊ ልዩነት እንጂ ከቦታው ነቅለን መሄድ የምችል አይደለንም። ስለዚህ አንድ ላይ መኖር እጣ ክፍላችን ከሆነ እንዴት ነው አብረን ሳንጎዳዳ፤ ተጠቃቅመን፤ ተደጋግፈን መኖር የምንችለው የሚለው ጉዳይ ላይ መነጋገር አለብን።

በአሁኑ ወቅት በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ ሰዎች የተለያዩ ሀሳቦች እየሰጡ ነው ያሉት፤ እኔም የበኩሌን ሳቀርብ ሀሳቡን ለማዳበር ይረዳ ይሆናል በሚል እምነት ነው። ከሌሎች፤ ከሚመስሉኝ ሰዎች ጋር ሆኜ በጋራ ለመስጠት ብችል ደስ ይለኝ ነበር፤ ነገር ግን በፓርቲ ማዕቀፍ ውስጥ እንዳይሆን የነበርኩበት ፓርቲ (አንድነት) ተወስዷል። ከዓረና ከወጣሁም ቆይቻለሁ (ይሄ የምለው አንዳንድ ሰዎች አሁንም ዓረና የምመስላቸው ስላለሁ ነው) በእርግጥ ዓረና ሲታሰብ ጀምሮ የነበርኩበት፤ የፖለቲካ ጥርሴ የነቀልኩበት፤ በሁኔታዎች የማይለዋወጡ ጓደኞች ያፈራሁበት ቢሆንም በአንዳንድ አካሄዶች ላይ በነበረኝ ልዩነት ምክንያት ከፓርቲው እንደተለየሁ የሚታወቅ ነው። ከተለመደው የሀገራችን የመለያየት ባህል በተለየ ሁኔታ በሰላምና በክብር ነው የተለየሁት። ስለዚህ ከቀድሞ የአንደነት አመራሮች ጋር በግል ከማደርጋቸው ውይይቶች ውጪ በአሁኑ ሰዓት የየትኛውም ፓርቲ አባል አይደለሁም።

ወደ ዋናው ዳጉይ ስገባ፣ በመጀመሪያ ምን እናድርግ በሚለው ጉዳይ ላይ እየቀረቡ ባሉት አማራጮች ላይ የራሴን ምልከታ ላስቀምጥና ወደ መፍትሄ ሀሳብ እሻገራለሁ። በአንዳንድ ታዋቂ ሰዎችና የፖለቲካ ቡድኖች በቀዳሚነት እየቀረበ ያለው አማራጭ የሽግግር መንግስት ይመስረት የሚል ነው። የሽግግር መንግስት ጥያቄ አቶ ግርማ ሰይፉ እንዳሉት ያለህዝብ ውክልና በአቋራጭ ስልጣን የሚገኝበት መንገድ እንጂ በአሁኑ ሰዓት አዋጭ የመፍትሄ ሀሳብ አይደለም፤ ኢህአዴግም በዚህ መንገድ ወደ ድርድር ማምጣት የሚቻል አይመስለኝም፤ ይህን የሚያደርግበት አስገዳጅ ሁኔታ ውስጥ ገብቷል ብዬም አላስብም። ስለዚህ የሽግግር መንግስት የሚለው አማራጭ አሁን ባለው ሁኔታ እውን የሚሆን ነገር አይደለም፤ ከዚህም ባሻገር ደግሞ ሁሉንም ነገሮች ከዜሮ እንዲጀመር የሚያደርግ በመሆኑ ጠቃሚነቱም ያን ያህል ነው።

ሁለተኛው አማራጭ የባለአደራ መንግስት ነው። ይህ በህዝብ የተመረጠ መንግስት እስኪቋቋም ድረስ ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከሲቪል ተቋማት፣ ከታዋቂ ግለሰቦች፣ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጣ የባለአደራ መንግስት ተቋቁሞ ሀገሪቱን በጊዚያዊነት እንዲመራ ማድረግ ነው። እንዲህ ዓይነቱ መንግስት ሰላምና ስርዓት ለማስፈን ሰራዊቱንና የፀጥታ አካላትን እንዴት አድርጎ ሊያዛቸው እንደሚችል ግልፅ አይደለም፤ ምን ዓይነት የህግ መሰረት እንደሚኖረውም ለመገመት የሚያስቸግር ነው። ከሽግግር መንግስትም ብዙ የሚለይ አይመስልም፤ የሚለየው ነገር ቢኖር የሽግግር መንግስት በፖለቲካ ኃይሎች የሚቋቋም መሆኑ ላይ ነው።

በሶስተኛው ረድፍ የሚቀመጡት ደግሞ ከኢህአዴግ ጋራ ጥምር መንግስት መመስረት የሚፈልጉ ናቸው። ከሁሉም በላይ ይሄ አማራጭ የከፋ ይመስለኛል። አንዳንድ የስልጣን ጥማት ያላቸው የፖለቲካ መሪዎች በአቋራጭ ስልጣን እንዲያገኙ ይረዳ እንደሆነ እንጂ ወደ ለውጥ ጎደና የሚወስድ አይደለም። በአንፃሩ ገዢው ፓርቲ ራሱን ዳግም ለማጠናከር እድል የሚሰጥ ነው የሚሆነው። ከኢህአዴግ ባህርይና አሁን በሀገራችን ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ካየነው የጥምር መንግስት ጥያቄ የፖለቲካ ሽርሙጥና ነው። በእርግጥ ጥምር መንግስት መመስረት ተገቢ የሚሆንበት ሁኔታ አለ፤ ህዝባዊ ምርጫ ተካሄዶ አንዱ ፓርቲ አሸናፊ ሳይሆን ሲቀር ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ፓርቲዎች ባገኙት የህዝብ ድምፅ መሰረት ድርድር አድርገው በስምምነት የጥምር መንግስት ሊያቋቁሙ ይችላሉ። ከዚህ ውጪ የሆነ ጥምር መንግስትም እንበለው ሽግግር መንግስት ዘላቂ መፍትሄ የማያመጣ ያለህዝብ ውክልና በአቋራጭ ስልጣን ፍለጋ ነው የሚሆነው።

ስለዚህ ለእኔ የተሻለ አማራጭ የሚመስለኝ ፓርላማውን በትኖ አዲስ ምርጫ እንዲካሄድ ማድረግ ነው። ኢህአዴግ ከልብ ለበጎ ነገር የሚነሳ ከሆነ፣ በዚች ሀገር ሰላማዊ የሆነ የስልጣን ሽግግር እንዲኖር ከቆረጠ ማድረግ ያለበት በሀገሪቱ ጉዳይ ላይ ያገባናል የሚሉ፣ በሀገር ውስጥም በውጭም ያሉ፤ በሰላማዊ መንገድም በጥትቅም እየተንቀሳቀሱ የሚገኙትን ቡድኖች ሁሉ ጠርቶ ወደ ሀገር ቤት እንዲገቡና በሰላም እንዲንቀሳቀሱ ማድረግ ነው፤ ቀጥሎ ምርጫ ቦርድን ሙሉ ለሙሉ አፍርሶ ከሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ተነጋግሮ በስምምነትና በመተማመን አዲስ ምርጫ ቦርድ በማቋቋም፤ ነፃና ገለልተኛ ምርጫ እንዲካሄድ አድርጎ በህዝብ ለተመረጠው አካል ስልጣኑን በሰላማዊ መንገድ ማስረከብ ነው።

እዚህ ላይ መታየት ያለበት ዋናው ነገር ሁሉንም ነገር እንደአዲስ ከመጀመር ይልቅ አሁን ያሉትን የመንግስት ተቋማት ገለልተኛ ሆነው የሚሰሩበትና የሚጠናከሩበት መንገድ ነው። ለምሳሌ ጦር ሰራዊቱ ከላይ ያሉትን የጦር አዛዦች ጡረታ እንዲወጡ በማድረግ የብሄር ተዋፅኦ የጠበቀ አመራር እንዲኖረው በማድረግ ማስተካከል የሚቻል ነው። የደህንነት መስራቤቱንም እንደዚሁ፤ ሌላውም በተመሳሳይ መንገድ ማስተካካል ይቻላል። ከላይ ለመግለፅ እንደሞከርኩት ሙሉ ለሙሉ መፍረስና መቀየር ያለበት ምርጫ ቦርድ ነው፤ ከሁሉም ገለልተኛ የሆነ በሁሉም ዘንድ ተአማኒነትና ከበሬታ ያለው፤ በሰው ኃይል፤ በአደረጃጀት ጠንካራ የሆነ ምርጫ ቦርድ ማቋቋም ያስፈልጋል።

ሌላው መስማማት የሚያስፈልገው ነገር ቢኖር የህገ መንግስት ማሻሽያ ጉዳይ ነው፤ ህገ መንግስቱ ለሚደረገው የስርዓት ለውጥና እንዲኖር ለሚፈለገው ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በሚያመች መልኩ መሻሻል መቻል አለበት። በሀገሪቱ ውስጥ የሚኖረው አስተዳደርም ለልማትና አስተዳደር በሚያመች መልኩ፤ የብሄረሰቦች ራሳቸውን በራሳችው የማስተዳደር መብት ሳይገፋ፤ ቋንቋቸውን ለመጠቀም፣ ባህላቸውን ለመጠበቅና ለማሳደግ እንቅፋት በማይሆን መልኩ መስተካከል አለበት። ይህ ማለት ግን አንድ ቋንቋ የሚናገር ሁሉ በአንድ ክልል መጠቃለል አለበት ማለት ላይሆን ይችላል። ይህም የሚሆነው በህዝብ ፍላጎትና ፍቃደኝነት ተመስርቶ ነው። በተመሳሳይ ሁኔታ በተለያዩ አከባቢዎች ያሉት የአከላለል ጥያቄዎች በኗሪው ህዝበ ውሳኔ እንዲፈቱ በማድረግ ዘላቂ መፍትሄ እንደሚደረግባቸው መስማማት ያስፈልጋል። እዚህ ስምምነት ላይ ለመድረስ ግን መደረግ ያለባቸው ቅድመ ሁነቶች ይኖራሉ፤ ከላይ ለመግለፅ እንደፈለኩት ኢህአዴግ ስልጣኑን በህዝብ ለተመረጠ አካል ለማስረከብ ቁርጠኛ መሆኑን ማረጋገጥ መቻል አለበት። በምትኩ ለኢህአዴግ ባለስልጣናት የሚሰጥ ልዩ ልዩ ዋስትና ሊኖር ይችላል።

በነገራችን ላይ “የኢህአዴግ ባለስልጣናት ስልጣን ይልቀቁልን እንጂ በወንጀል ያለመጠየቅ ዋስትና መስጠት ይቻላል” የሚሉ አሉ። በዚህ ጉዳይ ላይ እኔ የተለየ አቋም ነው ያለኝ። “አተርፍ ባይ አጉዳይ” እንደሚባለው ወንጀልና ወንጀለኞችን ማበረታታት እንዳይሆን መጠንቀቅ ያስፈልጋል። በግልፅ የሚታወቅ በተለይ ከሰብአዊ መብት አያያዝ ጋር የተገናኘ ወንጀል ያለባቸው ባለስልጣናት ያለመክስስ መብት ሊሰጣቸው አይገባም። በአንፃሩ ምንም ወንጀል የሌለባቸው የስርዓቱ ባለስልጣናት በሰላም የመኖር መብት ሊከበርላቸው፤ ከዚያም ባሻገር በቀሪ ህይወታቸው ሊያኖራቸው የሚችል ነገር ሊሰጣቸው ይችላል።

ዋስትና ስለመስጠት ጉዳይ መነጋገር ካለብን በእርግጥም ዋስትና የሚያስፈልገው የትግራይ ህዝብ ነው። በተለይ ከክልሉ ውጩ የሚኖረው ትግርኛ ተናጋሪ ዜጋ ከለውጥ በኋላ አሁን ካለው ስርዓት ጋር በተያያዘ ምንም ነገር እንደማይደርስበት ማረጋገጥ ያስፈልጋል። እንደማነኛውም ዜጋ በፈልገው ቦታ ተንቀሳቅሶ የመስራት፤ የመኖርና ሀብት የማፍራት መብቱ ሊጠበቅለት ይገባል። ይህ ስጋት ተገቢ ይሁንም አይሁንም ሊታይና ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ ነው። በእርግጥም ይሄ ሀሳባዊ ስጋት አይደለም፤ በአሁኑ ሰዓት በኢህአደግ በኩልም በአንዳንድ ፅንፈኛ ኃይሎችም ተደቅኖበት ያለ ስጋት ነው። ስጋት ካለ ደግሞ አንድም የለውጡ ሂደት የሚያዘገየው ነው የሚሆነው፤ ሌላው ደግሞ የሆነ ህዝብ መስዋዕት በማድረግ የሚመጣ ለውጥ ከሞራልም ከህግም አንፃር ተቀባይነት የለውም፤ ይሄ የህወሀት መንገድ ነው። ባለፉት ዓመታት በተለያዩ ክልሎች የሚኖሩ አማርኛ ተናጋሪዎች ላይ ሲደርስ የነበረው መፈናቀል፤ ጭቆናና ስቃይ ዳግም በየትኛውም ህዝብ ላይ እንዲደርስ መመኘት የለብንም። ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለማምጣት የሚታገል ማነኛውም ኃይል አንድን ህዝብ በሌላ ህዝብ ላይ እንዲነሳ የሚያደርግ ተደጋጋሚ ስህተት አይሰራም፤ የጥላቻ፣ የፍረጃና የፍርሀት ፖለቲካም አያራምድም።

በተወሰነ መልኩ በጎንደርና በመተማ አከባቢዎች እንደተየው ዓይነት በስርዓቱ ምክንያት የትግራይ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት መፈጠር ያልነበረበት ነው። እንዲህ ማድረጉ ለትግሉም የሚጨምረው ነገር የለም፤ በእርግጥ “ከስርዓቱ ጋር ግንኙበት ያላቸው ብቻ ናቸው ጥቃት የደረሰባቸው” የሚል ነገር ተደጋግሞ ሲነግር ሰምቻለሁ፤ በእነዚህ አከባቢዎች ከሚኖረው የትግራይ ተወላጆች ብዛት አንፃር ጉዳት የደረሰባቸው ጥቂት መሆናቸው ሲታይ የተባለው እውነትነት ሊኖረው እንደሚችል መገመት ይቻላል። ነገር ግን አንድ ግልፅ መሆን ያለበት ነገር አለ፤ አንድ ሰው ከስርዓቱ ጋር ያለው ትስስር በማስረጃ ማረጋገጥ የሚችል የተደራጀ አሰራር በሌለበት ህዝባዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ንፁሃን ሰዎች አይጎዱም ማለት አይደለም። በራሴ አቅም በተለያየ መንገድ ለማጣራት ሞክሬ የተረዳሁትም ይሄኑኑ ነው። በአጋጣሚው ንፁሃን ዜጎች ላይም ጉዳት ደርሷል። በመሰረቱ ህዝቡ በየአከባቢው እንደመሰለው እርምጃ ይውሰድ ብሎ መቀስቀስ በደርግ ጊዜ እንደነበረው ዓይነት ሁኔታ መፍጠር ነው የሚሆነው፤ በየቀበሌው ለሚገኘው አብዮት ጥበቃ ሳይቀር እንደመሰለው እርምጃ እንዲወስድ በመፈቀዱ ጉዳዩ ሀገር ከመከላከል ወደ ግል ቂም በቀል ወርዶ የብዙ ንፁሃን ህይወት ጠፍቷል። በተመሳሳይ ሁኔታ ስርዓትና ቁጥጥር የሌለው እርምጃ እንዲኖር መፍቀድ በህዝብ ላይ ጉዳት ማድረስና ስርዓት አልበኝነት እንዲነግስ ማድረግ ነው የሚሆነው። የዘር ፍጅትም የሚከተለው እንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ሲፈጠር ነው።

ስርዓቱ የሚያደርገው ነገር ሁሉ ማውገዝ አለብን፤ መታገልም ያስፈልጋል። በኦሮሚያና በአማራ ክልል የተፈፀመው የህይወት መጥፋት እጅግ የሚያንገበግብ ነው፤ የወገን ህይወት ነው የጠፋው፤ የወገን ደም ነው የፈሰሰው፤ ይሄ መታገል ያስፈልጋል። ኃላፊነት መውሰድ ያለባቸው አካላትም ተለይተው በህግ መጠየቅ አለባቸው። ህወሀትን ይደግፋሉ በሚል መነሻ ጥረው ግረው በሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ላይ ጥቃት ማድረስ ግን ፈፅሞ ተቀባይነት ያለው ጉዳይ አይደለም። ህወሀት ባጠፋ ቁጥር የራስ ወገን በሆነ የትግራይ ህዝብ ላይ ጥቃት ማድረስ መቼም ቢሆን ተገቢነት ሊኖረው አይችልም። እንኳን ዛሬ ዓለም በሰለጠነበት፤ የሰብአዊ መብት ጉዳይ ዋነኛ አጀንዳ በሆነበት ዘመን ቀርቶ በድሮ ጊዜም ቢሆን እንዲህ ዓይነቱ ነገር ተቀባይነት አልነበረም። ለዚህ አንድ የሚገርም በአፄ ምኒልክ ዘመን የሆነ ጉዳይ ብጠቅስ ደስ ይለኛል፤ የእንደርታ ገዥ የነበሩት ደጃች አብርሃ በማመፃቸው ምክንያት በሸዋና በሌሎች አከባቢዎች በሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ላይ ጥቃት ደርሶ ነበር ይባላል፤ በዚህ ምክንያት አፄ ምኒልክ አዋጅ አውጥተው ነበር፤ እንዲህ የሚል፦

…አንድ ሰው ደጃች አብርሃ ቢከዳ እዚህ የተቀመጡትውን እኔን የሚወደኝን የትግሬ ሰወ ሁሉ ታስቀይማለህ አሉ። አባያ ወንድሙ ይታሰርበታል እንጂ ይታረዳልን። አሁንም ዳግመኛ በአደባባይ ያለውን የትግሬ ሰው የሚያስቀይም ነገር የተናረ ትቀጣለህ። አደባባይ ያለውን የትግሬ ሰው የሚያስቀይም የተናገረውን ተያይዘህ አምጣልኝ ዳኝነት ይታይልሃል።

                    (የአጤ ምኒልክ የሀገር ውስጥ ደብዳቤዎች፣ ገፅ 589)

የድሮ መሪዎቻችን ቢያንስ ፈሪሃ እግዚአብሄር የነበራቸው በመሆኑ ከአሁኖቹ በእጅጉ ይሻላሉ። የራሳቸው የሆነ ጥሩ ነገርም እንደነበራቸው የምንረዳው እንዲዚህ ዓይነቱ ነገር ስናገኝ ነው። በሌላ በእኩል ደግሞ አሁን ያለንበት ሁኔታ፣ የሞራል ድቀት ከመቼም ጊዜ የከፋ መሆኑ እንረዳለን። ህዝባዊ እንቅስቃሴዎች ተጠናክረው መጠቀል አለባቸው፤ ግን ደግሞ በስርዓቱ ላይ ያነጣጠሩ እንጂ ፍፁም ህዝብ በህዝብ ላይ እንዲነሳ የሚያደርጉ መሆን የለባቸውም፤ እንደዚህ ዓይነት አሰራር በግልፅ ነው መወገዝ ያለበት። በራስ ወገን ላይ በፖለቲካ ምክንያት ጥቃት ማድረስ ዘላቂ ሰላምና አብሮነትም የሚፈጥር አይሆንም። በአንድ ወገን የሚኖርን ተቃውሞና ውግዘት በመፍራት ዝም መባል የለበትም፤ እንደህ ዓይነቱ አካሄድ አደርባይነትና እወደድ ባይነት ነው (opportunism and populism) ነው።

እስካሁን እንደታዘብኩት በዚህ ጉዳይ ላይ አፅንኦት ሰጥተው ሲናገሩ የሰማቸው ፕሮፌስር መስፍን ወልደማርያም እና ፕፎሰፌር ብርሃኑ ነጋ ይመስሉኛል። ፕሮፈሴር መስፍን ለአዲስ አድማስ በሰጡት ቃለ መጠይቅ “ወያኔን ትግሬ እያደረጉ፣ ትግሬን ሁሉ ወያኔ እያደረጉ የሚኬድበት ሁኔታ መታረም አለበት፤ አደገኛ መርዝ ነው፡፡ሀገሪቱን አደጋ ላይ የሚጥል ነው፡፡” ማለት እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ በትግራይ ህዝብ እየተደገሰ ያለው አደጋ እንደሚያሳስባቸው ተናገሯል። ፕሮፈሴር ብርሃኑ ነጋም በዴምህት ሁለተኛ ጉባኤ ላይ “ከትግራይ አብራክ የወጡና ይህን ስርዓት የሚቃወሙትን በቆራጥ ወኔ ነው የምናደንቀው” በሚል ርዕስ ባቀረቡት ንግግር የጥላቻ ፖለቲካ ስለሚያራምዱ ወገኖች እንዲህ ብሏል፦

…ለጊዜያዊ የፖለቲካ ጉልበትነት እንጠቀምበታለን ብለው የሚያስቡ አክራሪና አጥፊ ኃይሎች ትግሉን ወደ ጥላቻ ትግል ለማስቀየስ የሚሞክሩ ሊኖሩ እንደሚችሉ እናውቃለን። እንደነዚህ አይነት ጥቂት ኃይሎች በህዝቡ ትግል ውስጥ ተመሽገው የሚወስዷቸው እርምጃዎችንና የሚያካሂዷቸውን የጥላቻ መርዛማ ፕሮፓጋንዳ ህወኃት/ኢህአዴግን ስለተቃወሙ ብቻ ዝም ብለን “የህዝቡ ትግል አካላት ናቸው” ብለን የምናልፋቸው ሊሆኑ በፍጹም አይገባም። እንዲህ አይነት እኩይ ኃይሎችን ማውገዝ ብቻ ሳይሆን አስቀያሚ ገጽታቸውን በሚያሳዩበት ጊዜ ሁሉ እነሱን ማጋለጥና ከህዝቡ ፍትሀዊ ትግል ማግለል ለእውነትና ለፍትህ፤ ኢትዮጵያችንን ከተጋረጠባት አደጋ ለመታደግ፤ ብሎም ለእውነተኛ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እንታገላለን የምንል ኃይሎች ሁሉ ያለማሰለስ ልንሰራው የሚገባን ስራችን ነው።

ይህ የሁሉም ኃላፊነት የሚሰማው ዜጋ አቋም ነው ሊሆን የሚገባው፤ እንደ ዜጋ ከፍ ሲል ደግሞ እንደሰው ለሰብአዊነት፣ ለእውነትና ለትክክለኛነት መቆም ያስፈልጋል። በመሰረቱም አንድን ህዝብ በጠቅላላ ማስፈራራት ውጤት የሚያመጣ ነገር አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ ህዝቡ የስርዓት ለውጥ ቢመጣ ስለሚኖረው የተሻለ ነገር በማስረዳት ነው ማሰለፍ የሚቻለው። ከለውጥ በኋላ ከህወሀት ጋር በተያያዘ ምንም የሚደርስበት ጉዳት ሊኖር እንደማይችል፤ እንደማነኛውም ዜጋ አሁን ካለው በተሻለ ሁኔታ በነፃነት ሰርቶ የመኖር መብቱ እንደሚከበርለት ማሳየት ያስፈልጋል። በተለይ ደግሞ በትግራይ ህዝብ ላይ ያነጣጠረ የዘረኝነት ቅስቀሳ የሚያካሄዱ ግለሰቦችና ቡድኖች በማሻማ ሁኔታ ማውገዝና ራስን ከእነዚህ አካላት መለየት ያስፈልጋል። ከእስትራቴጂ አንፃርም የተደባለቀ ትግል ለውጤት የሚበቃ አይደለም፤ ለውጤት ቢበቃም እንኳ ዘላቂ ሰላም ሊያመጣ አይችልም፤ ሀገር ከመበታተን፤ ህዝብ ለህዝብ ከመተላለቅ የሚያድን አይደለም። አዋጪው መንገድ ኢትዮጵያ የሁላችን እንድትሆን፤ የጋራ ራዕይና ህልም መፍጠር እንጂ የተወሰነ ህዝብ በመነጠል እንዲመጣ የምንፈልገው የተሻለ ለውጥ ሊመጣ አይችልም። ጠቡ ህዝብ ለህዝብ ስለሚሆን አሸናፊ ወገን አይኖርም፤ ተያይዞ መውደቅ ነው የሚሆነው፤ የፖለቲካ ኃይላት ናቸው ሊሸናነፉ የሚችሉት፤ ህዝብ እንደህዝብ ሊሸነፍ አይችልም።

የመጣህበትን ህዝብ ከቻልክም ደግሞ በማነኛውም ህዝብ ላይ በደልና ጭቆና ሲደርስ መጮህና መታገል ተገቢ ነው። ከዚህ ባለፈ ሁኔታ የራስህን ህዝብ የተጎዳ፣ ከሌላው በተለየ ሁኔታ አደጋ ያንዣበበት በማስመሰል ፖለቲካ መስራትና የኑሮ መሰረት እንዲሆን ማድረግ ከሞራልም ከሰብአዊነትም አንፃር ተገቢ ያልሆነ አካሄድ ነው። በተለይ ለለውጥ ከሚታል ሰው የሚጠበቅ አይደለም። አብሮ ለዘላለም የሚኖር፤ ተለያየቶ ላይለያይ ህዝብ መሀል ዘላቂ ጠብና ቂም መፍጠር ተገቢ አይደለም። ስልጣን መፈለግ ኃጢአት ባይሆንም በዚህ መንገድ የሚገኝ ስልጣን ግን ቢቀር ነው የሚሻለው። ከሁሉም በላይ ደግሞ ከቋንቋ በስተቀር በዘርም፣ በኃይማኖትም፣ በባህልም፣ በመልክም አንድ ዓይነት በሆነው የትግራይና የጎንደር ህዝብ ማሀል የጥላቻ ግንብ እንዲገነባ ማድረግ ይቅር የማይባል ስህተት ነው። ለወደፊት በሚኖሩት ትውልዶች ፊትም የሚያሳፍር ኋላቀር ተግባር ነው የሚሆነው። በአጠቃላይ የትግራይና የአማራ ህዝብ ተመሳሳይ ዕጣ ክፍል ያለው፤ ተደጋግፎና ተገባብቶ ከመኖር ውጪ ሌላ አማራጭ ተፈጥሮም ታሪክም ያልሰጠው ህዝብ ነው። በመሰረቱ በሁለቱም ወገን ባሉት የስልጣን ኃይሎች እንጂ በሁለቱም ህዝብ መሀል ጥላቻ አለ ብዬ አላምንም።

የምናደርገው ትግሉ ሁሉም የሚያሳትፍ፤ ለሁሉም ተስፋ የሚሰጥ፤ በማንም ህዝብ ላይ ስጋት የማይፈጥር እንዲሆን መጣር ያስፈልጋል። እንኳን በአንድ ሀገር የሚኖር፤ በደም፣ በአጥንት፣ በታሪክ፣ በዜግነት የተሳሰረ ህዝብ ይቅርና ከአውሮፓ ድረስ መጥተው ለብዙ መቶ ዓመታት ህዝቡን በቀኝ ግዛት ይዘው ሲገዙትና ሲጨቀኑት የነበሩትን የደቡብ አፍሪካ ነጮችም የሚያቃፍ ትግል እነማንዴላ አድርጓል። ታሪክ ሰርተው፤ ለሁሉም ዜጋ በእኩልነት የሚያገለግል ስርዓት መስርተው አልፏል፤ እኛ ኢትዮጵያውያንም እንዲህ ያለ የተገባ ትግል እንዳናከሄድ የሚያግደን ነገር ምንድነው?!

 

ቢቢኤን ሰበር ዜና: በታሳሪዎች ላይ የሚፈጸመው ግፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል |ከድር ታደለ በሸዋሮቢት በደረሰበት ድብደባ ሆስፒታል አደረ

$
0
0


ቢቢኤን ሰበር ዜና: በታሳሪዎች ላይ የሚፈጸመው ግፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል | ከድር ታደለ በሸዋሮቢት በደረሰበት ድብደባ ሆስፒታል አደረ
ቢቢኤን ሰበር ዜና: በታሳሪዎች ላይ የሚፈጸመው ግፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል |  ከድር ታደለ በሸዋሮቢት በደረሰበት ድብደባ ሆስፒታል አደረ

በአዲስ አበባ “አቧሬ” አካባቢ ሁለት ሺህ ሕጋዊ ቤቶች ይፈርሳሉ –ዋዜማ ራዲዮ

$
0
0

abware-area-satenaw-newsበየካ ክፍለ ከተማ ሚስስ ሳንፎርድ ትምህርት ቤት አካባቢ የሚገኙ ሁለት ሺሕ የሚጠጉ ቤቶች በቅርብ ወራት ዉስጥ የመፍረስ አደጋ ተጋርጦባቸዋል፡፡ ከነዚህ ዉስጥ ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት ሰፋፊ የግለሰብ ይዞታዎች ሲሆኑ ቀሪዎቹ የቀበሌ ቤቶች ናቸው፡፡ እንዲፈርሱ የዉሳኔ ሐሳብ የተሰጠባቸው የአቧሬ ሰፈሮች ሕገወጥ በመሆናቸው ሳይሆን ቦታው ለመልሶ ማልማት ፕሮጀክቶች በእጅጉ በመፈለጉ ነው፡፡

በየካ ክፍለ ከተማ የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ጽሕፈት ቤት ሰራተኞች ባሳለፍነው ሳምንት በጽሑፍ የተላለፈላቸው መመሪያ እንደሚያስረዳው አቧሬና አካባቢውን በአስቸኳይ ለማልማት አቅጣጫ በመያዙ በወረዳ 6 (በቀድሞ አጠራር ቀበሌ 09) ዙርያ የሚገኙ የግል ይዞታዎችና የቀበሌ ቤቶች ቁጥርና ስፋት በዝርዝር አጥንተው በአጭር ጊዜ ዉስጥ እንዲያቀርቡ በማዕከል ኃላፊዎች ታዘዋል፡፡

በአንጻሩ የቤቶቹን መፍረስ ዉሳኔ በጥርጣሬ የሚመለከቱ በክፍለከተማ በተለያየ ኃላፊነት ደረጃ እየሰሩ የሚገኙ የዋዜማ ምንጮች በቅርብ ወራት ዉስጥ ምንም አይነት የቤት ማፍረስ ሥራ እንደማይከናወን ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡ ይህም የሚሆነው ቤቶችን ለልማት ሲባል የማፍረስ ተግባር ለተቃውሞ እንቅስቃሴ በር ሊከፍት ይችላል የሚል ስጋት በካቢኔው ዘንድ በመኖሩ ነው፡፡

አገሪቱ ወደለየለት ብጥብጥ እንድታመራ የሚሹ አክራሪ ኃይሎች በዋና ከተማዋ አመጽ ለመቀስቀስ አጀንዳ አጥተዋል፤ እኛ ቤቶችን ለልማት ስናፈርስ እነርሱ እንደ ጥሩ አጋጣሚ ሊጠቀሙበት ይችላሉ የሚል ስጋት በከንቲባው ዋና የሕዝብ ግንኙነት አማካሪ አቶ ተወልደ ገብረጻዲቅ ሲንጸባረቅ በተደጋጋሚ ሰምቻለሁ ይላል በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የይዞታ ጽሕፈት ቤት ዉስጥ በኦፊሰርነት የሚያገለግል ወጣት የድርጅት አባል፡፡

ቤት የማፍረስ ተግባር ዘንድሮ የማይታሰብ ነው የሚሉት ወገኖች እንደ ተጨማሪ ማስረጃ የሚያቀርቡት በ2008 መጨረሻ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቀርሳ፣ ኮንቶማና ማንጎ ሰፈሮች ዉስጥ ሕገወጥ ሰፋሪዎችን ለማንሳት በተደረገው ሙከራ የወረዳ አንድ ሥራ አስፈጻሚን ጨምሮ የነዋሪዎች ሕይወት መጥፋቱን ተከትሎ ዉጥረት መንገሱን በማስታወስ ነው፡፡ በወቅቱ በነዋሪውና በፀጥታ ኃይሎች መሐል የተነሳውን ግጭት ተከትሎ ከንቲባው አቶ ድሪባ ኩማ ሕገወጦችን የማፍረስ ጉዳይ ለድርድር አይቀርብም የሚል መግለጫ ቢሰጡም በዚያው ሰሞን እንዲፈርሱ ቀነ ቀጠሮ ተይዞላቸው የነበሩ ሰፈሮች ለጊዜው እንዲታለፉ ለክፍለ ከተማ የመሬት ልማትና ማደስ ኃላፊዎች የቃል ትዕዛዝ ተሰጥቶ ነበር፡፡

እንደ ምሳሌም የቀርሳና ኮንቱማ ሰፈሮችን የሚያዋስነውና በርካታ ሕገወጥ ሰፋሪዎች ይገኙበታል የሚባለውን የአቃቂ ቃሊቲ መንደር ለማፍረስ ግብረኃይል ተደራጅቶ፣ ቀን ተቆርጦ፣ ልዩ የፖሊስ ኃይል ተመድቦ፣ ዶዘሮች ወደ አካባቢው እንዲቀርቡ ከተደረገ በኋላ ባልታወቀ ምክንያት የማፍረስ ሂደቱ ድንገት እንዲታጠፍ ሆኗል ይላሉ የወረዳው ባልደረቦች፡፡

የዋዜማ ዘጋቢ ያናገራቸውና ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው አንድ የአራዳ ክፍለ ከተማ ሰራተኛ ዉሳኔው የታጠፈው ዜጎችን በክረምት ማፈናቀል አግባብ እንዳልሆነ በካቢኔው አቅጣጫ በመያዙ ነው ሲሉ ሌሎች በመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ጽሕፈት ቤት የሚሰሩ ኦፊሰሮች ደግሞ በተቃራኒው እንዲያውም ሕገወጥ ቤቶች እንዲፈርሱ የሚመረጠው በክረምት ወቅት ነው፡፡ ይህም በበጋ ቤቶችን ማፍረስ ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታ ሊያርቃቸው ስለሚችል ነው ሲሉ ተጻራሪ ሐሳቦችን ያቀርባሉ፡፡

በኦሮሚያ መንግሥትን ለሰፊ ሕዝባዊ ተቃውሞ የዳረገው የተቀናጀ ማስተር ፕላን ለጊዜው እንዲታጠፈ ከተደረገ በኋላ አዲስ አበባ የተናጥል የከተማ መሪ ፕላን ለማዘጋጀት ተገዳለች፡፡ ኾኖም ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ እስከዛሬም በይፋ አላጸደቀችውም፡፡ የሕዝብ ዉይይት ተደርጎ በአስቸኳይ ይፀድቃል የተባለው መሪ ፕላን ከዛሬ ነገ እየተባለ ለወራት ሲንከባለል ቆይቷል፡፡ ያም ኾኖም አስሩም ክፍለ ከተሞች በአሁኑ ሰዓት የመሬት ጉዳዮችን እየፈጸሙ ያሉት ያልጸደቀውን የከተማዋን መሪ ፕላን መሠረት በማድረግ ነው፡፡ ባይፀድቅም እየሰራንበት ነው፤ በሱ መስራት ከጀመርን ዓመት አልፎናል ይላል ለዋዜማ ሐሳቡን የገለጸ አንድ የአራዳ ክፍለ ከተማ የመሬት ባለሞያ፡፡

በአዲሱ መሪ ፕላን የከተማዋ 30 በመቶ ለአረንጓዴ ልማት የሚፈለግ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ለአረንጓዴ ቦታ የተከለሉ ሥፋራዎች ዉስጥ እየኖሩ ያሉ ዜጎች በሂደት እንዲነሱ እንደሚደረግ የከተማዋ ኃላፊዎች ተናግረዋል፡፡ ኾኖም ቁጥራቸው በርካታ ከመሆኑ ጋር ምትክ ቦታ ለመስጠት አስተዳደሩ ፈተና እንደሚገጥመው ከወዲሁ ተሰግቷል፡፡

ባለፉት ዓመታት የከተማዋን አብዛኛዎቹን የቆረቆዙ መንደሮች በመልሶ ማልማት ለማልማት በተደረጉ እንቅስቃሴዎች በሰንጋ ተራና አካባቢው 14 ሄክታር መሬት ለፋይናንስ ተቋማትና ለ40/60 የቤት ልማት ፕሮጀክት የተላለፈ ሲሆን በልደታ ቤተክርስቲያን አካባቢ 16 ሄክታር መሬት ደግሞ ለ20/80 ቤቶች ልማት ማከናወኛ የተሰጠ ነው፡፡ በተለይ በልደታ ክፍለ ከተማ የልደታና አካባቢው መልሶ ማልማት ፕሮጀክት በመስተዳደሩም ሆነ በፌዴራል ደረጃ በስኬታማነቱ በተደጋጋሚ የሚወደስ ፕሮጀክት ነው፡፡ የግልና የመንግሥት ባንኮች ሕንጻዎችን፣ ፀሜክስ ኢንተርናሽናል እያስገነባው እንዳለው አይነት ባለ ኮከብ ሆቴል ፕሮጀክቶችን፣ ፍሊንስቶን ያስገነባውን ዘመናዊ የገበያ ማዕከል (ሞል) ተግባራዊ ማድረግ የተቻለው በዚህ እንደ ሞዴል በሚወሰድ የመልሶ ማልመት ሥራ እንደሆነ በኃላፊዎች በተደጋጋሚ ይገለጻል፡፡

ይህ የልደታ መልሶ ማልማት ፕሮጀክት የኮንዶሚንየም ነዋሪዎች ከመሀል ከተማ ርቀው እንዳይሰፍሩ፣ በመካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ዜጎች መሐል መራራቅ እንዳይኖር ያደረገ ልማት እንደሆነ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊሲ አማካሪ አቶ አባይ ፀሐዬ በተደጋጋሚ ሲያሞካሹት ይሰማል፡፡ ኾኖም ተመሳሳይ የመልሶ ማልማት ስኬት ሊደገም አልቻለም፡፡ ብዙዎቹ በመልሶ ማልማት ቤቶቻቸው የፈረሱባቸው ዜጎች ከነባር ይዞታቸው ተፈናቅለው በከተማዋ ጫፍ በሚገኙና መሠረተ ልማት ባልዳሰሳቸው ሥፍራዎች እንዲሰፍሩ ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በቅርቡ የመፍረስ አደጋ የተጋረጠበት አቧሬ ሰፈር ከአንድ ሺ ካሬም የሚልቁ ሰፋፊ ይዞታዎች የሚገኙበት ሲሆን የመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን ዋና መቀመጫም የሚገኘው በዚህ ወረዳ ነው፡፡ በመልሶ ማልማት ምክንያት የሚነሱ ዜጎች ይዞታቸው ምንም ያህል ሰፋፊ ቢሆን እንኳ በመኖርያ ቤት እስከተመዘገበ ድረስ በምትክነት የሚሰጣቸው የካሬ ስፋት ከ500 ሜትር ስኩዌር ካሬ በላይ እንዳይሆን መመሪያው ያዛል፡፡ ኾኖም ተነሺዎቹ ይዞታቸውን በግላቸው የማልማት ፍላጎት ካላቸውና የፋይናንስ አቅም በራሳቸው መፍጠር ከቻሉ መሪ ፕላኑ በሚያዘው መሠረት በአካባቢው ዘጠኝ ፎቅና ከዚያ በላይ የመገንባት መብት ይሰጣቸዋል፡፡ ይህ ግን ለብዙ የከተማዋ ጎስቋላ ነዋሪዎች የሚታሰብ ጉዳይ አይሆንም፡፡

ባለፉት ጥቂት አመታት ዉስጥ በልማት ስም ከፈረሱ የአዲስ አበባ ከተሞች መሐል አሜሪካን ግቢ ተጠቃሽ ነው፡፡ በአካባቢው ለ30 አመታት ነዋሪ የነበሩ ዜጎች የይዞታ ባለቤትነትን ከማረጋገጥና ከካሳ ክፍያ ጋር በተያያዘ የተፈጠረው ዉዝግብ ዛሬም ሙሉ በሙሉ ምላሽ አላገኘም፡፡ ኾኖም ከአካባቢው የተነሱ ሱቆች ራሳቸውን በቡድን እያደራጁ ቁራሽ መሬቶች እየተሰጣቸው ቆይቷል፡፡

ከነዚህ አካባቢዎች በተጨማሪ አዲስ ከተማ፣ ጎጃም በረንዳ፣ ቁጭራ ሰፈር፣ ጣሊያን ሰፈርና ገዳም ሰፈር በመልሶ ማልማት የሚፈርሱና እየፈረሱ ያሉ አካባቢዎች ናቸው፡፡

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዉስጥ የሚካተተው የመስቀል አደባባይ ኢሲኤ ጀርባ 4 ሄክታር መሬት፣ አራዳ ክፍለ ከተማ ዉስጥ የሚካተተው የ አራት ኪሎ ባሻ ወልዴ ችሎት አካባቢ 24 ሄክታር መሬት በመልሶ ማልማት ተነስቷል፡፡ የባሻ ወልዴ ችሎት አካባቢ በሊዝና በምሪት ለባለሀብቶችና ለድርጅቶች የተላለፈ ሲሆን ቦታ ከወሰዱ ድርጅቶች መሐል የብአዴን ጽሕፈት ቤት ግንባታ፣ ሁለት የግል ሆስፒታሎች ግንባታ፣ የዳሽን ባንክ ቅርንጫፍ ቢሮ ግንባታ፣ የሂልኮ ኮምፒውተር ኮሌጅ ግንባታ በአመዛኙ ተጠናቋል፡፡

የባሻ ወልዴ ችሎት አካባቢ እየተከናወኑ ካሉ ፕሮጀክቶች ትልቁ በአምባሳደር ልብስ ስፌት ባለቤት በአቶ ሰኢድ መሐመድ ብርሃን እየለማ ያለው ቦታ ሲሆን ከአርበኞች ግንብ ሕንጻ ጎን ከፓርላመው ባሻገር የሚገኝ 3ሺ ካሬ ቦታ ነው፡፡ አገልግሎቱም ባለ 4 ፎቅ ሰፊ የገበያ ማዕከል ግንባታ ነው፡፡ ይህ ግንባታ ረዥም ዓመታትን የወሰደ ቢሆንም እስካሁንም አልተገባደደም፡፡ የባሻ ወልዴ ችሎት መልሶ ማልማት ቦታዎች በተፈለገው ፍጥነት አለመሄዳቸው ብቻም ሳይሆን ብዙዎቹ ቦታዎች ከፈረሱ አመታት ቢያስቆጥሩም አሁንም አለመልማታቸው የነዋሪዎች መነጋገሪያ ሆነዋል፡፡ በመሪ ፕላኑ መሰረት አካባቢው ለቤተመንግሥትና ፓርላማ ቅርብ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከ4 ፎቅ በላይ መገንባትን አይፈቅድም፡፡

ተመሳሳይ ሰፊ የመልሶ ማልማት ሥራ ካከናወኑ ክፍለ ከተሞች መሐል የቂርቂስ ክፍለ ከተማ ተጠቃሽ ሲሆን ለአፍሪካ ሕብረት አዲሱ ሕንጻ ግንባታና ለኢሲኤ (የቀድሞው አፍሪካ አንድነት ድርጅት የመጀመርያ መሰብሰቢያ አዳራሽ) ማስፋፊያና ፓርክ ሲባል ኢስጢፋኖስ ጀርባ የነበሩ በርካታ ነዋሪዎችን ከቀያቸው ለማፈናቀል ተገዷል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ካዛንቺስና አካባቢዋ በርካታ ባለ ኮከብ ሆቴሎች ግንባታ መከናወን የቻለውም ቦታው ለመልሶ ማልማት በመዋሉ ነው፡፡

አሁን ተመሳሳይ ሰፋፊ የሆቴል ፕሮጀክቶች ይካሄዱበታል ተብሎ የሚገመተውና የካዛንቺስ 2 መልሶ ማልማት ዘመቻ በሚል የሚታወቀውን የልማት ፕሮጀክት ተግባራዊ ለማድረግ ራዲሰን ብሎ ማዶ፣ ኢንተርኮንቲነንሰታል ሆቴል ፊትለፊት፣ ኦራኤል ቤተክርስቲያን ተሻግሮ የሚገኙ ሰፈሮች ሙሉ በሙሉ እንዲነሱ ተደርጓል፡፡ ይሁን እንጂ ቦታዎቹ ከጸዱ ዘለግ ያለ ጊዜ ቢያስቆጥሩም የፈረሱት ቦታዎች እስከአሁንም ለአልሚዎች አልተላለፉም፡፡

በከተማዋ ነዋሪዎች እንደ ተደጋጋሚ ቅሬታ የሚነሳውም ይኸው ጉዳይ ነው፡፡ ድሀን በልማት ስም አፈናቅሎ መተው፣ ወቅቱን ያገናዘበ ተገቢ ካሳን አለመስጠት፣ የማኅበራዊ ምስቅልቅል የሚፈጥሩ አሰፋፈሮችን መከተል የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ለረዥም አመታት ያማረረ ጉዳይ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የፈረሱ ቦታዎች ለአመታት ያለምንም አገልግሎት ተጥረው እንዲቀመጡ መሆናቸው ግርትን የሚፈጥር ጉዳይ ነው፡፡ ይህም አንድም በመስተዳደሩ ድክመት ቦታዎቹን ለአልሚዎች በጊዜ ያለማስተላለፍ ችግር ጋር የሚያያዝ ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ደግሞ አልሚዎች ቦታዎቹን አጥረው ይዞታቸውን ካስከበሩ በኋላ ለዓመታት ግንባታ ለማከናወን ሳይፈቅዱ መቆየታቸው ነው፡፡

ይዞታዎች ለአልሚዎች ሲተላለፉ የግንባታ መጀመርያ ጊዜና ማጠናቀቂያ ጊዜ በዉል ተለይተው፣ የሊዝ ዉል ፈርመው የሚገቡበት አሰራር ቢኖርም ይህ ሁኔታ ለሁሉም ዜጎች በእኩል የሚሰራ አልሆነም፡፡

በዚህ ረገድ በከተማዋ የአስተዳደር እርከን በሁሉም ደረጃ ከኤህአዴግ አባላት ሳይቀር ሰፊ ትችትና ትዝብትን የሚያስተናግዱት በሳኡዲያዊው ባለሀብት ሼክ መሀመድ አላሙዲ የተያዙ ሰፋፊ የከተማዋ ይዞታዎች ናቸው፡፡ በተለይም ከካዛንቺስ ኢንተርኮንቲነንታል ሆቴል ጎን ተቆፍሮ የሚገኘው ቦታ መለስተኛ ኩሬ ፈጥሮ ለአካባቢው የጤና ጠንቅ እስከመሆን የደረሰ ሲሆን በኢንተርኮንቴኔንታል ሆቴል የሚያርፉ እንግዶች መስኮቶቻቸውን ለመክፈት እስከመቸገር መድረሳቸው ይነገራል፡፡ የሸራተን ማስፋፊያ በሚል ለጎልፍ ክለብና ልዩ ልዩ መዝናኛዎች የታጠረውና በተለምዶ ፖሊስ ጋራዥ የሚባለው ሰፊ ቦታ ማጅራት መቺዎችና ኪስ አውላቂቆች መሸሸጊያ እየሆነ እንደመጣ ነዋሪዎች ብቻም ሳይሆን የከተማዋ ፖሊስ ጽሕፈት ቤትም የሚያነሳው ጉዳይ ሆኗል፡፡ የፒያሳው ግዙፍ የመንታ ሕንጻዎች ፕሮጀክት በዲዛይን ለውጥና በሌሎች ጥቃቅን ሰበቦች የተነሳ ይህ ነው የሚባል ግንባታ ሳይካሄድበት ለ18 ዓመታት ታጥሮ መቀመጡም የከተማዋ ነዋሪ በአስተዳደሩ ላይ እምነት እንዲያጣ ካደረጉት አበይት ምክንያቶች አንዱ ነው፡፡


በዱርቤቴ ከተማ ላይ ወጣቱን እያሳፈኑት ያሉት የህወሓት ተላላኪዎች ስም ዝርዝር ይፋ ሆነ

$
0
0

Zehabesha-News.jpg
በዱርቤቴ ከተማ ላይ ወጣቱን በትግራይ ነጻ አውጪ ሰራዊትና ደህንነቶች እያሳፈኑ ያሉት የአካባቢው ነዋሪዎች ስም ዝርዝር ይፋ ወጣ:: በአካባቢው ያሉ የጎበዝ አለቆች ለዘ-ሐበሻ በላኩት ስም ዝርዝር መሰረት ሕዝቡ ማንነታቸውን እንዲያውቅ አሳስበዋል::

ዝርዝራቸው እነሆ

1.. አቶ ይርጋ ሚኒሻ ሀላፊ.
2..አቶ በቀለ ሀይሉ
3..አቶ ተሰማ ስቪልሰረቪስ ሀላፊ
4..አቶ ጎሹ ም.ጎጃም ም.ሀላፊ
5..አቶ ፋቃዴ ዋና አስተዳዳሪ
6.አቶ ሀይሌ መብራቴ
7..አቶ ስላም ሰዉ
8..አቶ ፋቃዴ ሙሌ መዘጋጃ ሀላፊ
9.. ኢንስፔክተር መለሰ በሬ
10..ኢኒስፔክተር ዳዉድ አራጋዉ

የአማራ ተጋድሎና መንስዔው |አቻምየለህ ታምሩ

$
0
0

EthioTube ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ የቀረበ

ዛሬ አማራው በያለበት በነቂስ ወጥቶ በየጎበዝ አለቃው በመደራጀት እያደረገው ያለው ተጋድሎ ባለፉት የወያኔ ሀያ አምስት የአገዛዝ አመታት ውስጥ ተቋማዊ ቅርጽ ተሰጥቶት፤ በአማራ ላይ የተፈጸመው እንግልት፣ እስራት፣ መድሎ፣ ግድያ፣ ግፍ፣ በደል፣ የዘር ማጥፋት፣ ሰቆቃና መከራ የወለደው፤ በማንኛውም መመዘኛ እጅግ ህዝባዊ የሆነ አብዮት ነው።
ፋሽስት ጥሊያን ጀምሮ የተወውን ኢትዮጵያን በብሔር፣ በጎሳና በመንደር የመከፋፈል [የማስተዳደር አላልሁም] አባዜ የተከተሉት በኢትዮጵያ መንግስትነት የተሰየሙት የትግራይ ነጻ አውጪዎች ባቀናበሩት በአዲሱ የኢትዮጵያ የመቶ አመት ታሪክ፤ ረጅሙ የኢትዮጵያ ታሪክ «በአማራ ብሔር» የበላይነት ተፈርጆ በአማራ ላይ ያልተፈጠረ የሐጢዓት ክስና ያልተደረተ የፈጠራ ድርሰት የለም።
ወያኔዎች በረሀ የገቡት በአማራ መቃብር ላይ የታላቋ ትግራይን ሪፑብሊክ የመመስረት አላማ ይዘው ቢሆንም፤ ኋላ ላይ በተፈጠረው አለማቀፋዊ ለውጥና በደርግ አረመኔነት የተነሳ ሻዕብያን ተከትለው አዲስ አበባ እንደሚገቡ ሲያውቁት፤ አማራን ለማጥፋት ከ1967— 1981 ዓ.ም. የታገሉበትን ፍኖተ መርህ በግንቦት ወር 1981 ዓ.ም. ቀይረው «ኢህአዴግ» የሚባለውን የማታለያ ጭንብል ሲመሰርቱ ጫካ ሲገቡ፤ ያነገቡትን አማራን የማጥፋት አላማቸውን በመንግስትነት ከተሰየሙ በኋላ ለማስፈጸም፤ አማራን የማጥፋት አላማቸውን ወደ ርዕዮተ አለም ደረጃ ከፍ አድርገውታል። ይህንን ርዕዮተ አለም እነሱ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ይሉታል።
achamyeleh
አብዮታዊ ዲሞክራሲ የሚባለውን የወያኔ ርዕዮተ አለም ከፍቶ ለተመለከተ የርዕዮተ አለሙ ዋና ማዕከሉ ወይንም coreሩ የአማራ ጥላቻ ነው። ባለፉት ሀያ አምስት የፋሽስት ወያኔ የአገዛዝ አመታት ውስጥ በአማራ ላይ የተፈጸመው ግፍና በደል ባጋጣሚ የተከሰተ፤ የአማራ የአይን ቀለም ስላላማረ የተፈጸመ አይደለም። ባለፉት ሀያ አምስት የፋሽስት ወያኔ የአገዛዝ አመታት በአማራ ላይ የተፈጸመው ግፍና በደል ታሪካዊ መነሻ ያለው፤ ተቋማዊ ቅርጽ የተሰጠውና በርዕዮት አለም የታገዘ ግፍና በደል ነው። ታሪካዊ መነሻውን ለጊዜው ልተወውና የፋሽስት ወያኔ የአማራ ማጥፊያ የፖለቲካ ርዕዮተ አለም መሰረት የሆነውን አብዮታዊ ዲሞክራሲን ዘርዘር አድርጌ ልገልጸው እፈልጋለሁ።

አብዮታዊ ዲሞክራሲ የሚባለው የወያኔ ርዕዮተ አለም የሌሊኒን ፍልስፍና ሲሆን በባህሪው ያዳላል። አብዮታዊ ዲሞክራሲ ዲሞክራሲያዊ አይደለም። አብዮታዊ ዲሞክራሲ የሚነሳው ዲሞክራሲ የሚገባቸውና የማይገባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች አሉ ብሎ በማሰብ ነው። ዲሞክራሲ የሚገባቸውና የማይገባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች አሉ የሚለው የፋኖዎቹ ብሒል የአብዮታዊ ዲሞክራሲ መነሻና ማጠንጠኛ ሀሳብ ነው።
በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ዲሞክራሲ አይገባቸውም የሚባሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ወይ «በዘር» አልያም «በመደብ» ይለያሉ።
የወያኔ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ደርግ በሚያዚያ ወር 1968 ዓ.ም. ይፋ ካደረገው የኢትዮጵያ አብዮት ፕሮግራም ወይንም National Democratic Revolution (NDR) program ጋር አንድ አይነት ነው። የሁለቱ አገዛዞች ርዕዮተ አለም ማህደር የካርል ማርክስ Dictatorship of the Proletariat ወይንም የወዝ አደሩ አምባገነንነት የሚለው አስተምህሮ ነው። የሁለቱ አገዛዞች አብዮታዊ ዲሞክራሲ ልዩነት በደርጉ የኢትዮጵያ አብዮት ፕሮግራም ዲሞክራሲ አይገባውም የተባለው የህብረተሰብ ክፍል በመደብ ሲለይ [ ደርግ «ፊውዳል፣ ባላባት፣ በዝባዥ፣ አብዮት ቀልባሽ» የሚላቸውን ማለቴ ነው] የወያኔው አብዮታዊ ዲሞክራሲ ደግሞ ዲሞክራሲ አይገባውም የተባለው የህብረተሰብ ክፍል በኮድ ስም ትምክህተኛ፣ የድሮ ስርዓት ናፋቂ፣ ወዘተ ተብሎ የተለየ ሲሆን ወያኔ ግን እነዚህን የኮድ ስሞች የሚጠቀመው ዲሞክራሲ አይገባውም የሚለውን ክፍል በቀጥታ አማራ ላለማለት ነው።
ባጭሩ ወያኔ ዲሞክራሲ አይገባውም ብሎ የመደበው የህብረተሰብ ክፍል የተለየው በዘር ሲሆን ያ ዘር ደግሞ ወያኔ ከምስረታው ጀምሮ ሊያጠፋው የተነሳው የአማራ ዘር ነው። በዚህም የተነሳ ደርግ ከ1967—1983 ዓ.ም. «ፊውዳል፣ ባላባት፣ በዝባዥ፣ አብዮት ቀልባሽ» በሚላቸው ላይ ቀይ ሽብር አውጆ ካካሄደው ጅምላ ግድያ የከፋ አረመኔያዊ ጭፍጨፋ ወያኔ ባለፉት ሀያ አምስት አመታት በአማራ ላይ ፈጽሟል። በዘመነ አብዮታዊ ዲሞክራሲ አማራው ዲሞክራሲ አያስፈልገውም በመባሉ በአገሩ አገርህ ሂድ ተብሎ ከተራራ ላይ ተወርውሯል፤ ቤት ተዘግቶበት በእሳት እንዲቃጠል ተደርጓል፤ ከነሰፍሱ በማይሞላ ገደል ውስጥ ተጨምሯል፤ አማራ ዘሩን እንዳይተካ የአማራ ሴቶች የሚያመክን መርፌ ተወግተዋል፤ የህግ ጥበቃ፣ ስራ የማግኘትና የትምህርት እድል ተነፍጓል፤ የንብረት መብት፣ ያለመፈናቀልና የመኖር መብቱ በግላጭ ተገፏል።
አማራው በፋሽስት ወያኔ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ዲሞክራሲ አያስፈልገውም በመባሉ ግብር ከፍሎ በሚያስተዳድረው በራሱ መገናኛ ብዙሀን ሳይቀር ሀያ አምስት አመት ሙሉ በህዝብ ተመረጥን በሚሉ፤ ኃላፊነት ሊሰማቸው በሚገባ የፖለቲካ መሪዎች፤ ነፍጠኛ፣ ትምክህተኛና በዝባዥ በሚሉ የኮድ ስሞች እንደ አደገኛ ርዕዮተ አለም ሁሉም እንዲፋለሙት ተዘምቶበታል። ይህ ዘመቻ ዛሬም አልቆመም። ከሁለት ሳምንት በፊት የትግራዩ ገዢ በትግርኛ ባደረገው ንግግር «ጎንደር ላይ የተፈጸመውና በትግሬዎች ላይ የተካሄደው ተግባር ምንጩ ትምክህተኝነት ነው። ይህንን ትምክህት ከስሩ ለመንቀል ያቺን ተንለሲስ እያመረተች የምትልክ ጉድጓድ መድፈን አለብን።» ሲል በይፋ በአማራ ላይ ቀይ ሽብር አውጇል። ዛሬ ዛሬ ድምጸ ወያኔና የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በተለይም የትግርኛው አገልግሎት እንደ ሩዋንዳው ሬዲዮ ሚሌ ኮሊንስ ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ ዝቅተኛውን የጋዜጠኝነት መስፈርትን በማያሟላ መልኩ አፍራሽ በሆነ ፕሮፓጋንዳ ተጠምዶ በአማራ ላይ የዘር ማጥፋትና እልቂት እንዲካሄድ ቤንዚን እያርከፈከፈ ይገኛል።
በፋሽስት ወያኔ አብዮታዊ ዲሞክራሲ አማራው ዲሞክራሲ አያስፈልገውም ተብሎ ስለተደመደመ፣ ለንብረቱም ሆነ ለህይወቱ ጥበቃ አያስፈልገውም ስለተባለ ወያኔ ባመነው እንኳ 2.40 ሚሊዮን አማራ ከምድረ ገጽ እንዲጠፋ ተደርጓል። በፋሽስት ወያኔ አብዮታዊ ዲሞክራሲ አማራው ዲሞክራሲ አያስፈልገውም በመባሉ በርዕዮተ አለም የታገዘ፣ ስልታዊ [ systematic] የሆነ፤ በተለያዩ ነገሮች ወደፊት እንዳይሄድ እልቆ መሳፍርት በደልና ግፍ ተፈጽሞበታል። አቃለልኸው ካላላችሁኝ ዛሬ በፋሽስት ወያኔዋ ኢትዮጵያ ውስጥ በህይወት ያለው አማራ የሚኖረው ወያኔ ባበጀለት የቁም መቃብር ውስጥ ነው።
መለስ ዜናዊ የአማራ ማጥፊያ የፖለቲካ ርዕዮተ አለም መሰረት የሆነውን አብዮታዊ ዲሞክራሲን ሲተቹበት፤ ለሁሉም እኩል የንብረት መብት የሚሰጠውን፤ በየትም ቦታ የመወከልና የመወከል መብትን የሚያጎናጽፈውን፤ የመምረጥና የመመረጥ፣ ድምጽን የማሰማት፣ ባጠቃላይ ሁሉንም መብቶች ለሁሉም በእኩል መጠን የሚሰጠውን ሊብራሊዝምን ስድብ አድርግት አስተሳሰቡን የሚከተሉትንና የሚጠላቸውን ሰዎች «ኒዮ ሊብራል ኃይሎች» እያለ ያንጓጥጣቸው ነበር።
ባጭሩ ከ1967 ዓ.ም. እስከ ዛሬ ድረስ ያለው የወያኔ ፖለቲካና የመለስ ዜናዊ የርዕዮተ አለም ፍልስፍና መነሻ በአማራ ላይ የሚፈጸም የዘር ማጥፋት ወይንም በእግሊዝኛው አጠራር Genocide (of the Amharas) ነው ማለት ይቻላል። ይህንን ስል ብዙ ሰው ለመቀበል ሲቸገር እመለከታለሁ። እስቲ የዘር ማጥፋት ወይንም Genocideን አለማቀፋዊና አህጉራዊ ፍቺውን ትተን በተሻሻለው የኢትዮጵያ የወልጀል ህግ ውስጥ በምን አኳኋን እንደተቀመጠ እንመልከት።
የኢትዮጵያ የወንጀል ህግ አንቀጽ 269 ስለ ዘር ማጥፋት ወንጀሎች ምንነት የተብራሩ ዝርዝሮችን አካቷል። አንቀጹን እንደሚከተለው አቀርበዋለሁ:-
አንቀጽ 269፡ የዘር ማጥፋት፤
ማንም ሰው በሰላምም ሆነ በጦርነት ጊዜ በብሔር፣ በብሔረሰብ፣ በጎሳ፣ በዘር፣ በዜግነት፣ በቀለም፣ በኃይማኖት ወይንም በፖለቲካ አንድ የሆነን ቡድን በመላ ወይንም በከፊል ለማጥፋት ማሰብ፣ የጥፋቱን ድርጊት ማደራጀት፣ ትዕዛዝ መስጠት ወይንም ድርጊቱን የመፈጸመ እንደሆነ፤ወይንም
ሀ) በማንኛውም ሁኔታ የማህበረሰቡን አባሎች የገደለ፣ አካላዊ ወይንም የአካል ጉዳት ያደረሰ ወይንም ያጠፋ እንደሆነ፤ ወይንም
ለ) የማህበረሰቡ አባላት በዘር እንዳይራቡ ወይንም በሕይወት እንዳይኖሩ ለማድረግ ማንኛውንም ዘዴ በስራ ላይ ያዋለ እንደሆነ፤
ሐ) የማህበረሰቡን አባላት ወይንም ህጻናት በግዴታ ከስፍራ ወደ ስፍራ ያዛወረ ወይንም የበተነ ወይንም ሊሞቱ ወይንም ሊጠፉ በሚችሉበት የኑሮ ሁኔታ እንዲኖሩ ያደረገ እደሆነ የዘር ማጥፋት ፈጸመ ይባላል።
ከዚህ በተጨማሪ የተሻሻለው የወያኔ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ አንቀጽ 269 የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሟል ለማለት ሶስት ነገሮች መሟላት እንዳለባቸው በማያሻማ ሁኔታ በግልጽ አስቀምጦታል። እነርሱም:-
1) መግደል፣ በሰውነት ላይ ጉዳት ማድረስ ወይም ደግሞ ከፍተኛ የሆነ አካላዊ ጉዳት ማድረስ ወይም ደግሞ በቡድን አባላት ላይ የስነ ልቦና ጉዳት ማድረስ፣ በማንኛውም መንገድ ወይም ደግሞ ምንም ይሁን ምን ሰውሮ ማጥፋት፣
2) በአባላት ወይም ደግሞ በልጆቻቸው ላይ ዘለቄታዊ በሆነ መልኩ መኖር እንዳይችሉ ተከታታነት ያለው ቅስቀሳ ማድረግ እና ይህንን መከላከል ያለመቻል፣ ወይም ደግሞ፣
3) በግዴታ ማፈናቀል ወይም ደግሞ ሰዎችን ወይም ልጆቻቸውን ከቦታዎቻቸው ለሞት በሚያበቃ መልኩ ተገቢ ያልሆኑ ተግባራትን መፈጸም ወይም መሰወር፣ ወይም ደግሞ ሆን ተብሎ በጅምላ ወይም በከፊል ብሄርን፣ ብሄረሰብን፣ ጎሳን፣ ዘርን፣ ዜግነትን፣ ቀለምን፣ ኃማኖትን ወይም ደግሞ የፖለቲካ ቡድንን ማጥፋት።
ወያኔ በኢትዮጵያ የወንጀል ህግ የተቀመጠውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ዝርዝሮችም ሆነ የሚፈጸምን አንድ ወንጀል «የዘር ማጥፋት ወንጀል» ለማለት መሟላት አለባቸውን የሚላቸውን ሶስት ነገሮች ሁሉ ከምስረታው ከ1967 ዓ.ም. እስከ ዛሬ ድረስ ፈጽሟቸዋል፤ እየፈጸማቸውም ይገኛል።
ወያኔ በታህሳስ 1968 ዓ.ም. ባወጣው የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ድርጅት ማኒፌስቶው የትግራይ ህዝብ ትግል ጸረ አማራ ብሔር እንደሆነ በግሏጭ አስፍሯል፤ በተግባርም ባለፉት ሀያ አምስት አመታት ተርጉሞታል። ፋሽስት ወያኔዎች በዘፈኖቻቸው «ገረብ ገረብ ትግራይ፣ መቓብር ኣምሐራይ፤» ብለው ዘፈውነዋል። በአማርኛ «ገረብ ገረብ ትግራይ፣ መቓብር ኣምሐራይ፤» ማለት የትግራይ ተራሮች የአማራ መቃብር ይሆናሉ ማለት ነው። ወያኔዎች አማራ እንዳይራባ የሚያመክን መርፌ ወግተውታል፤ የድሮ ስርዓት ናፋቂ፣ ባሪያ ፈንጋይ፣ አድሀሪ በማለት የመንፈስ ጉዳት አድርሰውበታል፤ የጥፋተኛነት ስሜት እንዲሰማውና ቅስሙ እንዲሰበር ያላባራ የስነ ልቦና ጦርነት አካሂደውበታል። በአገሩ ተረጋግቶ እንዳይኖር በአገሩ አገርህ ሂድ ብለው አሳደውታል፤ በግፍ ረሽነውታል፤ የወንድ አማሮችን የዘር ፍሬ አኮላሽተዋል፤ ከ2.4 ሚሊዮን በላይ አማራ በአስራ አምስት አመት ውስጥ አጥፍተዋል፤ በአንጡራ ሀብቱ የፈጠረው ሀብቱ ተነቅሎ ወደ ትግራይ በመወሰዱና ሊሞት ወይንም ሊጠፉ የሚችልበት የኑሮ ሁኔታ ውስጥ እንዲኖር በመገደዱ ወያኔ «አማራ ክልል» ብሎ የፈጠረው «ቀጠና» በአለም ላይ የመጨረሻ ድሀ «ክልል» እንዲሆን አድርገውታል።
አንዳንድ ሰዎች የወያኔው የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ 2.40 ሚሊዮን አማራ ጠፋ ያለውን ማስረጃ አንቀበልም ይሉና በአማራ ላይ ተፈጸመ የምንለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ላለመቀበል ሊሟገቱ ይሞክራሉ። አላስተዋሉትም እንጂ የአማራ ቁጥር በ2.40 ሚሊዮን ጎድሏል የሚለውን «ኦፊሲያላዊ» መረጃ በራሱ «የሞተ ሰው ቁጥር» አይደለም ብለን እንኳ ብንወስድ የአማራ ቁጥር በ2.40 ሚሊዮን ያህል እንዲቀንስ መደረጉ በአማራው ላይ የተፈጸመ የዘር ማጥፋት ወንጀል እንደሆነ ማየት ይችሉ ነበር። የአማራ ቁጥር በ2.40 ሚሊዮን ጎደለ ማለት ለአስር አመት [ድጋሚ የቤትና የህዝብ ቆጠራ እስኪካሄድ ድረስ፤ ያውም ድጋሜ ቆጠራ ሲካሄድ ጠፋ የተባለው 2.40 ሚሊዮን የሚካተት ከሆነ ነው] ያህል 2.40 ሚሊዮን የሚሆን አማራ ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ የመሰረተ ልማቶች ዝርጋታ፤ለገጠርና ከተማ ልማት እንዲሁም ለዴሞክራሲና ሰላም ግንባታ የሚውል አመታዊ ባጀት ለአስር አመታት ያህል አልተመደበለትም ማለት ነው። ይህ ማለት 2.40 ሚሊዮን አማራ ለአስር አመት መሰረታዊ የሆኑ ፍላጎቶች ሳይሟሉለት እንዲኖር ተደርጓል ማለት ነው።
መሰረታዊ ፍላጎቶቹ ያልተሟሉለት ህዝብ ደግሞ በድህነት፣ በርሀብና በችጋር ተጎሳቁሎ ይጠፋል። ስልታዊ በሆነ መልኩ 2.40 ሚሊዮን አማራ መሰረታዊ ፍላጎቶቹ ሳይሟሉለት ቀርተው በድህነት፣ በርሀብና በችጋር ተጎሳቁሎ ሊሞት ወይንም ሊጠፉ የሚችልበትን የኑሮ ሁኔታ እንዲኖር ማድረግ ደግሞ ከፍ ብሎ በቀረበው የኢትዮጵያ የወንጀል ህግ አንቀጽ 289 መሰረት የዘር ማጥፋት ነው። ስለዚህ 2.40 ሚሊዮን አማራ ጠፋ የሚለውን ኦፊሴላዊ ማስረጃ መቀበል የሚቸግራቸው ሰዎች በቆጠራ ወቅት 2.40 ሚሊዮን አማራ እንዲጎድል መሆኑና ላለፉት አስር አመታት 2.40 ሚሊዮን አማራ ስልታዊ በመሆነ መልኩ የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ የመሰረተ ልማቶች ዝርጋታ፤የገጠርና ከተማ ልማት እንዲሁም የዴሞክራሲና ሰላም ግንባታ ተጠቃሚ እንዳይሆን መደረጉ በአማራ ላይ የዘር ማጥፋት እና የሰብአዊ መብት ረገጣ ወንጀሎች መፈጸማቸው ማረጋገጫ ነው።
ከዚህ በተጨማሪ የዘር ማጥፋት የዘር ማጽዳት ወንጀልን ይጀምራል። ላለፉት ሀያ አምስት አመታት ወያኔ «ከአማራ የጸዳ አካባቢ መፍጠር» የሚለውን ፕሮጀክቱን ለማስፈጸም ሲል አማራ በመሆናቸው ብቻ ከአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች እንዲፈናቀሉና ሜዳ ላይ እንዲወድቁ አድርጓል። ይህ የግፍ ተግባር ዛሬም ቀጥሎ ንብረታቸው የተዘረፈ፤ ደማቸው የፈሰሰ የአማራ አርሶአደሮችን ቁጥር በሚሊዮኖች የሚቆጠር አድርጎታል። ባጠቃላይ ላለፉት ሀያ አምስት አመታት በአማራ ላይ የተፈጸመው ግድና፣ ሰቆቃ፣ መከራ፣ የዘር ማጥፋትና ተያያዥ በደሎች ምድሪቷ ከምትሸከመው በላይ ሆኗል።
የፋሽስት ወያኔ አብዮታዊ ዲሞክራሲ የወለደውን የአማራ ግፍና በደል ወጣቱ ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው በቅርቡ «የጥፋት ዘመን» በሚል ርዕስ ባሳተመው መጽሀፍ አቅርቦታል። ባለፉት ሀያ አምስት ዓመታት በአማራ ላይ የተፈጸመውን ግፍና በደል ዝርዝርና ስፋት ማወቅ የምትሹ ብትኖሩ የሙሉቀን ተስፋውን መጽሀፍ ገዝታችሁ አንብቡ።
ባጠቃላይ ዛሬ አማራው እያካሄደው ያለው ተጋድሎ የፈነዳው የወልቃይት የአማራ ማንነት ኮምቴ ላይ የተቃጣውን የወያኔ እብሪት ለመከላከል የተጀመረ ቢሆንም ቅሉ፤ የተጋድሎው መግፍኤ ግን ሀያ አምስት አመታት ሙሉ ሳያባራ በአማራ ላይ ሲፈጸም የኖረውና ዛሬም እየተፈጸመ ያለው የፋሽስት ወያኔ ግፍና በደል ድምር ውጤት ነው። ይህ የህልውና ተጋድሎ ግብ «አብዮታዊ ዲሞክራሲ የሚቀየረው በመቃብሬ ላይ ነው» በማለት የአማራ የዘር ማጥፋት ፖለቲካው የሆነውን ግፈኛ አገዛዝ ማስወገድ ነው። ይህ ተጋድሎ የህልውና ተጋድሎ እንደመሆኑ መጠን ወደፊት የሚገሰግስና የአማራን ህልውና የሚያረጋግጥ እንጅ ሊቀለበስ የሚችል ትግል አይደለም።
ዛሬ ፋሽስት ወያኔ በአማራና ኦሮሞ ላይ ጦርነት አውጆ ህዝብ ለመጨፍጨፍ ጦርነት ያሰማራቸው የትግራይ ወታደሮች የሚፈጽሙትን ግድያና ግፍ በማህበራዊ ሜዲያ ያያቸው ይመስለኛል። ፋሽስው ወያኔ ጎንደርና ጎጃም፤ ሀረርና ወለጋ ያሰማራቸውን ነፍሰ በላ የትግራይ ወታደሮች ሳስብ ከፊቴ ድቅን የሚሉት የአይሲስ ነፍሰ በላ ወታደሮች ናቸው። የአረመኔው አይሲስ ወታደሮች በክርስቲያኖች፤ በኢራቅና በሶርያ ንጹሀን ሰዎች ላይ የሚፈጽሙትን አረመኔያዊ ጭካኔ ወያኔ ያሰማራቸው የትግራይ ወታደሮች በአማራና በኦሮሞ ላይ ፈጽመውታል። የአይሲስ ወታደሮች የሰውን ልጅ በቁሙ አይኑ እያየ በእሳት አቃጥለውታል። ወያኔ ያሰማራቸው የትግራይ ወታደሮችም በግፍ የታሰሩ አማራና ኦሮሞዎችን በቂልንጦ፣ በጎንደርና በደብረ ታቦር እስር ቤቶች በእሳት ጠብሰዋቸዋል፤ ነፍሳቸውን ሊያተርፉ እሳቱን የሸሹትን ደግሞ በጥይት ቆልተዋቸዋል። እውነቱን ለመናገር የጨካኑ አይሲስ ወታደሮች በሰው ልጅ ላይ ፈጽመውን ጭካኔ ሁሉ ፋሽስት ወያኔ ያሰማራቸው የትግራይ ወታደሮች በኢትዮጵያውያን ላይ ፈጽሞታል።
በርዕዮተ አለም የታገዘው የትግራይ ነፍሰ በላ አውሬ ወታደሮች ባህሪ ነው እንግዲህ አማራው እያደረገው ያለውን ትግል ተጋድሎ ያደረገው። ሊገድለን ከተሰማራ ጨካኝ አውሬ ራሳችንን ለመከላከል የምናደርገው ተጋድሎ ተገቢ ብቻ ሳይሆን ህጋዊም ነው። ዛሬ አማራ እያደረገው ያለው ተጋድሎም ከፍ ብዬ ካቀረብሁላችሁ የትግራይ የሰው አውሬ ወታደሮች ራሱን ለመከላከል፣ ፖለቲካው የአማራ ዘር ማጥፋት ከሆነው ፋሽስታዊ አገዛዝ ለመገላገልና የፍትህ አየር እየተነፈሰ ለመኖር የሚያሂደውና በማንኛውም መመዘኛ ህዝባዊ የሆነ ትግል ነው።
የአማራ የህልውና ችግር ችግሩን የፈጠረው ፋሽስታዊ አእምሮ ሳይወገድ ሊፈታ አይችልም ነው። ፋሽስት ወያኔ አንድ ሺህ አንድ ጊዜ ጥልቅ ተሀድሶ ቢያካሂድ የአማራ ግፍና መከራ አብዮታዊ ዲሞክራሲ የሚሉት የአማራ ማጥፊያው የወያኔ paradigm እንካልተቀየረ ድረስ ችግራችን ሊቃለል አይችልም። በወያኔ መቃብር ካልሆነ የparadigm ለውጥ ብሎ ነገር ሊኖር እንደማይችል ደግሞ ሎሌው ኃይለ ማርያም «ሳይበረዝ ሳይከለስ የመለስን ራእይ ለመጪው ሀምሳ አመታት እናስቀጥላለን» ሲል ጌቶቹ የላኩትን ሲያላዝን ነበር ። በአማራ ህልውና ላይ የተጋረጠው ችግር የሚቃለለው በወያኔ መቃብር ላይ ብቻ ስለሆነ ዛሬ የአማራ ወጣቶች በአንድነት ተነስተው የወያኔን መቃብር አዝልቀው እየቆፈሩ ነው። ዛሬ አዲሱ የአማራ ትውልድ ወያኔ ካበጀለት የቁም መቃብሩ የወያኔን መግነዝ ቀዳዶና በጣጥሶ፤ የተጫነበትን የመቃብር ድንጋይና አፈር ፈነቃቅሎ በመውጣት የአማራ ታሪካዊ ጠላት የሆነውን ፋሽት ወያኔን በተጋድሎው አስወግዶ የአያቶቹን ታሪክ ሊያድስ ቀፎው እንደተነካበት የንብ ሠራዊት ተቆጥቶ ለተጋድሎ ተነስቷል።
ቀፎው እንደተነካበት የንብ ሠራዊት ተቆጥቶ ለተጋድሎ የተነሳው አዲሱ የአማራ ትውልድ ባተሌ አርሷደሩን ከፋሽስት ወያኔ ገባርነትና ስደት፣ የሠራተኛውን ክፍል ከድህነት ለማውጣትና ከምንዳ ለማላቀቅ፣ ጠቅላላውን ባተሌ ሕዝብ ከፈጽሞ መጥፋትና እጅግ አሳፋሪ ከሆነ የዘላለም ርሀብና ችጋር መንጥቆ በማውጣት፣ ራሱንና ወገኑን ለመለወጥ በጀመረው ተጋድሎ መሪር መስዋዕትነትን እየከፈለ ተስፋው የጨለመበት አሳዛኝ ሕዝብ እንደገና ለማንሳት በጀመረው ተጋድሎ ግፈኛውን አገዛዝ አነቃንቆታል። ይህ ተጋድሎ በዘመናቸው ሰርተውት እንዲያልፍ ታሪክ የቤት ስራችን በጣለባቸው ወጣቶች ብርታትና ጥንካሬ እስከ ድል ድረስ ይቀጥላል!
#የአማራ_ተጋድሎ ይቀጥላል!
አመሰግናለሁ!
አክባሪያችሁ
አቻምየለህ ታምሩ ነኝ!

ዜና በጣም ይረብሻል—ኦሮምያ በእሬቻ ባዕል በደም ታጠበች

$
0
0

የኢሬቻ በዓል በማክበር ላይ በነበሩ የኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ጭፍጨፋ ለማውገዝ የግድ ኦሮሞ መሆን አይጠበቅም፡፡ ያሳዝናል፤ ያናድዳል፡፡ ለነጻነት በሚደረግ ትግል የንጹሐን ዜጎች ሞት የሚጠበቅ ቢሆንም ባዶ ቄጠማን በእጃቸው ይዘው ከአምላካቸው ለአገራቸው ሰላም ሲለምኑ በነበሩ ሰዎች ላይ ይህን ዓይነት መቅሰፍት ሲወርድ በምን ቃል መግለጽ ይቻላል?
በዚህች አገር ላይ በዓልን በፌሽታና በደስታ እንዲያከብሩ የተፈቀደላቸው ከተከዜ ማዶ ያሉ ሰዎች ብቻ መሆናቸውን በግልጽ እያየን ነው፡፡
ለሞቱ ቤተሰቦች መጽናናትን እመኛለሁ፤ በአካባቢው ያላችሁ የአማራ ተወላጆች ከተጎዱ የኦሮሞ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ጎን በመቆም አጋርነታችን የምናሳይበት ከዚህ ጊዜ በላይ የለም፡፡
ትግላችን መራር ቢሆንም ማሸነፋችን ግን ጥርጥር የለውም!!

 

ይህ ለሰላማዊ ህዝብ ይገባዋልን??

j0-copy-2-copy

j1-copy-2-copy

j2-copy-2-copy

j3-copy-2-copy

j4-copy-2-copy

j5-copy-2-copy

j6-copy-copy

j7-copy-copy

j8-copy-copy

j11-copy-copy-copy

j11-copy-2-copy

j12-copy-copy-copy

 

j13-copy-copy

 

j14-copy

j15-copy

አንዳንዴ ሸረሪትም በራሷ ድር ትያዛለች (ከይገርማል)

$
0
0

TPLFበ1999 ዓ.ም ይመስለኛል አንድ የደቡብ አፍሪካ ምሁር የወያኔ-መሩ ኢሕአዴግና የሀገር ቤት ሰላማዊ ተቃዋሚወች ከመጠፋፋት ፖለቲካ ወጥተው ታሪካዊት ሀገራቸውን ወደ ዴሞክራሲ: ሰላምና ብልጽግና እንዲያሸጋግሩ ሲያሳስቡ እንዲህ ብለው ነበር::

“ኔልሰን ማንዴላ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚደንት ሆነው በተመረጡ ጊዜ በሀገሪቱ በሚኖሩት ነጮች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ በርካታ ሰዎች ጎትጉተው ነበር:: ማንዴላ ግን ‘የበደለን ስርአቱ እንጅ ሰዎች አይደሉም:: ያ አስከፊ ስርአት ተመልሶ እንዳይመጣ ሁላችንም ተረባርበን አርቀን ልንቀብረው ይገባል:: ደቡብ አፍሪካ ሰፊ ሀገር ናት: ለሁላችንም ትበቃናለች::’ በማለት ሀገራቸውን ከጥፋት በመታደግ በመላው አለም ለዘላለም የሚታወስ ታሪክ አስመዘገቡ::

ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀርቶ ለመላው አለም ምሳሌ የምትሆን ጥንታዊና ታሪካዊ ሀገር ናት:: የአፍሪካ ሀገሮች እንደሀገር በማይታወቁበት ጊዜ ኢትዮጵያ በንግድ: በስልጣኔና በወታደራዊ ሀይሏ ታዋቂ ነበረች:: አሁን የሚታየው ሁኔታ መታረም አለበት:: መንግስትና ተቃዋሚወች በሀገራችሁ ጉዳይ ላይ ቁጭ ብላችሁ መነጋገር ይኖርባችኋል:: ሶማሌወች ‘ከቆመ ወጣት የተቀመጠ ሽማግሌ አሻግሮ(አርቆ) ማየት ይችላል’ ይላሉ:: አፍሪካውያን ከናንተ የረጅም ጊዜ ልምድና ተሞክሮ የምንማረው ብዙ ነገር አለ::”

 

ወያኔወች በጣሊያን ፉርኖና ካልቾ አድገው መንገድ በመምራትና በስለላ ሀገራቸውን የበደሉ የባንዳ ልጆች መሆናቸውን ዶ/ሩ አላወቁም:: የጣሊያንን ባህርይ ተላብሰው በዚያው በጣሊያን ስታይል ኢትዮጵያን በዘርና በቋንቋ ከፋፍለው እየገዙን ያሉ ጸረ-ሕዝብና ጸረ ሀገር መሆናቸውን አልተረዱም:: ስለሀገርና ስለአንድነት የሚያወራ ትምክህተኛ የሚባልበት ጊዜ ላይ እንደምንገኝ:  ከአንድነት ይልቅ ልዩነት: ከሀገር በፊት ጎሳ ይቅደም የሚል መፈክር የሚያስተጋባ በስምም ሆነ በተግባር ኢትዮጵያን የማይወክል ቡድን ጥንታዊቷንና ታሪካዊቷን ሀገር በጉልበት እየገዛ እንደሆነ አልተገነዘቡም::

 

የወያኔን ድብቅ ፍላጎት ለማሳካት በሚመች መልኩ ሀገራችን ኢትዮጵያ በክልሎች ተከፋፍላ በዜጎቿ መሀል የመጠፋፋት ፖለቲካ ሲቀነቀን ኖሯል:: በመንግሥት ደረጃ በሚካሄደው የጥላቻና የዘረኝነት ሰበካ ምክንያት ከትግራይ ክልል በስተቀር ደረጃው ይለያይ እንጅ ሁሉም ክልሎች ተጠቂ ሆነዋል:: ከጥቂት ጊዚያት ወዲህ ግን ነገሮች ተገለባብጠው እንዲጠፋፉ ይቀሰቀሱ የነበሩት ጎሳወችና ሀይማኖቶች ግምባር ፈጥረው የጥፋት አራማጁን ኃይል ለጠፋው ጥፋት አንደኛ ደረጃ ተጠያቂ ያደረጉበት ሁኔታ እየታየ ነው:: አንዳንዴ ሌላውን ለማጥመድ በምትተበትበው ድር ራሷ ድር-አድሪ ሸረሪቷም ልትያዝ ትችላለች:: በወያኔወች ላይ የደረሰው ሁኔታ ይኸው ነው:: የዘር ፖለቲካ ይቅር የሚሉትን ሰዎች እያዋረዱ በሰላምና በፍቅር በአንዲት ኢትዮጵያ ውስጥ ይኖር የነበረውን አንድ ሕዝብ በቋንቋና በዘር ከፋፍለው ሲያናቁሩ የኖሩት ወያኔወች ችግሩ አቅጣጫውን ቀይሮ ወደራሳቸውና ወርቅ ወደሚሉት ሕዝባቸው ፊቱን በማዞሩ በድንጋጤ መደናበር ይዘዋል:: አንድ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ማህበረሰብ ለመፍጠር እየደከሙ እንደሆነ የሚደሰኩሩት ውሸት የማይሰለቻቸው እኒህ ወመኔወች እነርሱ ይጠሩበት የነበረውን ስም ለተቃዋሚወቻቸው አሻግረው በሀገራችን ዘር-ተኮር እልቂት ለመፍጠር እና የልማትና የአንድነት እቅዳቸውን ለማበላሸት “ጸረ-ሰላም ኃይሎች” የሚሏቸው ተቃዋሚወች እንቅልፍ አጥተው ለጥፋት እንደተሰለፉባቸው አድርገው ያለሀፍረት መተርተር ይዘዋል::

 

እውነታው ግን እኒህ የወያኔ እብዶች ከስህተታቸው ተምረው ሕዝብን ከሕዝብ የሚያቀራርብ ስራ እየሰሩ አለመሆኑ ነው:: ለችግሮች ትክክለኛ መፍትሄ ክመፈለግ ይልቅ ችግሩን ለማባባስ  በእሳት ላይ ቤንዚን ማርከፍከፍ መርጠው የትግራይ ሰዎችን በሙሉ  አስታጥቀው ለጦርነት አዘጋጅተዋል:: ትግሬ የተባለን ሁሉ መሳሪያ ማስታጠቅና በወታደር ማስጠበቅ በምንም መለኪያ መፍትሄ ሊሆን አይችልም:: ለተቃውሞ የሚወጡትን ሰዎች በማሰርና በመግደል በግፍ ላይ ግፍ ይከምሩ ካልሆነ በስተቀር መፍትሄ ማምጣት አይቻልም:: እየተፈጠረ ያለውን ሕዝባዊ እንቅስቃሴ የጥፋት ሀይሎች ሴራ አድርጎ ማውራትና ችግሩን ወደሌላ መግፋት ወይም በሀይል ለመፍታት መሞከር ዘላቂ ሰላም አያመጣም::

 

የትግራይ ሕዝብ በወያኔ ጊዜ የተፈጠረ አይደለም:: ወያኔ ከመፈጠሩ በፊት ከሌሎች ጎሳወች ጋር ችግሩንም ደስታውንም ተካፍሎ አብሮ የኖረ ሕዝብ ነው:: በተፈጥሮ አደጋም ይሁን በጦርነት ቢፈናቀል አቅም እንደፈቀደ የወገኖቹ ድጋፍ ተችሮት በየትኛውም ክልል ያለመሸማቀቅ ኖሯል:: በአሁኑ ጊዜ ግን ሁኔታው ተለውጦ በቀሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥርስ ውስጥ የገባበት ሁኔታ ይታያል:: ይኸ ሀቅ ነው:: ቢያለባብሱት መፍትሄ አይሆንም:: የትግራይ ሕዝብ በሌሎች ክልሎች ተገልሎም: ተፈርቶም: ተጠልቶም: ኮሽ ባለ ቁጥር በፍርሀት እየባነነ የሚኖር ለጥቃት የተጋለጠ ሕዝብ ሆኗል:: ለምን? ለሚለው ጥያቄ የተለያዩ መልሶች ሊኖሩ ይችላሉ:: ብዙወች የሚስማሙበት ግን ትግሬ የተባለ ሁሉ ሕወሀት ጥቅሜን የሚያስጠብቅልኝ ድርጅቴ ነው ብሎ ደግፎት ስለቆመ ነው የሚለው መልስ ነው:: ከኗሪው ጋር ተሰባጥረው  በየክልሎች የሚኖሩት ትግሬወች ሴት-ወንድ: ትንሽ-ትልቅ ሳይል መሳሪያ ታጥቀው ለወያኔ መረጃ የሚያቀብሉ ሰላዮች እንደሆኑ ነው የሚታወቀው:: ከሀገር ውጪ የሚኖሩት በበኩላቸው የወያኔ ክንፍ በመሆን ሁለንተናዊ ድጋፍ ሲያደርጉ እንጅ ሲቃወሙ አይታዩም:: በትግራይ የሚኖረው ሕዝብም ቢሆን የወያኔን ዕቅድ ለማስፈጸም ከመሰለፍ ውጪ በአጎራባች ክልሎች የሚኖረው ሕዝብ እየተፈናቀለ በምትኩ የትግራይ ተወላጆች በቦታው እንዲሰፍሩ ሲደረግ: ሰላማዊ ዜጎች ሲገደሉና በሕዝብና በሀገር ላይ በደል ሲፈጸም ድጋፍ እንጅ ተቃውሞ ሲያሰማ አልተደመጠም:: እንደ ፖለቲከኛ አንድን ሕዝብ በጅምላ በአንድ መልክ መፈረጅ ተገቢ ላይሆን ይችላል:: እውነታው ግን ይኸው ነው:: በተቃውሞው ጎራ ተሰልፈናል የሚሉ አንዳንድ ሰዎች ራሳቸው ወሳኝ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ወደኋላ ሲንሸራተቱ ማየት እንግዳ ነገር አይደለም:: ከሕዝብ ርቆ ወደወያኔ በመጠጋት የጥፋት ሀይልና ምሽግ ሆኖ እያገለገለ በመሆኑ ነው የትግራይ ሕዝብ ከቀሪው ኢትዮጵያዊ የመገለል እጣ እየደረሰበት ያለው:: “የትግራይ ሕዝብ ከማንም ባላነሰ በወያኔ የተበደለ ሕዝብ ነው:: ተቃውሞውን እንዳያሰማ ከፍተኛ አፈና አለበት ገሌ መሌ” የሚለው ፍሬ ከርስኪ ወሬ አይሰራም:: ከሶማሌ እስከ ጋምቤላ ከጎንደር እስከ ሞያሌ ያለው ሕዝብ እየታገለ ያለው ከአፈና ነጻ ስለሆነ ወይም የተለዩ ምቹ የመታገያ መንገዶች ስላሉት አይደለም:: ከስራ መባረሩን: ዱላውን: እስሩን: ግድያውን ችሎ ነው እየጮኸ የተቃውሞ ድምጹን እያሰማ ያለው::

 

ከክልሉ ወጥቶ በሌሎች አካባቢወች ለሚኖረው ለተራው የትግራይ ሕዝብ የበፊቱ ኑሮ ይሻለዋል ወይስ የወያኔው ጊዜ? መሳሪያ ታጥቆ  ወይም በወታደር ጥበቃ እየተደረገለት የሚኖር ሰው በነጻነት የሚኖር ሰው ነው ለማለት ይቻላል? እንዲህ ተሁኖ ኑሮስ ኑሮ ነው? በዚህ ሁኔታስ እስከመቸ መቀጠል ይቻላል? እኒህ ጥያቄወች በትግራይ ልጆች ምላሽ ሊሰጥባቸው የሚገቡ ጥያቄወች ናቸው:: የኢትዮጵያ ሕዝብ በዝባዥና ጨቋኝን እንጅ ሰላማዊ ወገኑን የሚጠላ ሕዝብ አይደለም:: የትግራይ ሕዝብ ሰልፉን አስተካክሎ ወያኔን ለመታገል መንቀሳቀስና መስዋእትነት መክፈል ሲጀምር ያን ጊዜ የጦርመሳሪያና ጠባቂ ታጣቂ ኃይል ሳያስፈልገው እንደማንኛውም ሰው በፈቀደው የሀገሪቱ ክልል ተዘዋውሮ ሰርቶ መኖር ይችላል::

 

የብሄር-ብሄረሰቦች መብት ተከብሮ ሁሉም ክልሎች በቋንቋቸው እየሰሩ ራሳቸውን በራሳቸው እያስተዳደሩ ነው ተብሎ የሚቀለድባት ኢትዮጵያ በወያኔወች መዳፍ ውስጥ ውላ እንደቆሎ እየታሸች ነው:: የወያኔወች ግፍ አንድ ሁለት ተብሎ ተቆጥሮ የሚያልቅ አይደለም:: ሌላው ቀርቶ ከትግራይ በስተቀር ሌሎች ክልሎች በራሳቸው ሰዎች እንዲተዳደሩ አልተፈቀደም:: ብሔር-ብሔረሰቦች ራሳቸውን በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ መብቱ ቢሰጥ ኖሮ እነ በረከት ስምዖን: ህላዊ ዮሴፍ: ገነት ገ/እግዚአብሔር— የአማራ ክልል መስተዳድር ውስጥ ምን ይሰሩ ነበር? ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በሀገሪቱ ውስጥ ተዘዋውሮ የመኖርም ሆነ ሀብት የማፍራት መብቱ የተጠበቀ ነው በሚለው አረዳድ ከክልላቸው ወጥተው በሌሎች ክልሎች የሚኖሩትን ሰዎች በሀገር ልጅነታቸውና በሕገ-መንግሥቱ አግባብ ልክ ነው ብለን እንቀበል:: በስልጣን ላይ ተቀምጠው “ያዘው! ጣለው! ግረፈው!” እያሉ የሚቀልዱብንን በምን ስሌት ይሁን ብለን እንቀበላቸው? ትግራይ ውስጥ ከቀበሌ እስከክልል ድረስ ባሉት የፖለቲካ ስልጣኖች በአመራር ሰጭነት የተቀመጠ  የአማራ: የኦሮሞ: የደቡብ:— ሰው አለ? ሌሎች ክልሎች ለምን ከክልላቸው ውጪ ባሉ ሰዎች እንዲተዳደሩ ይደረጋል? እነ አቶ በረከት: ወ/ሮ ገነት አማራ ክልል ምን ያደርጋሉ? ወርቅነህ ገበየሁ: አባዱላና ኩማ ደመቅሳ ኦሮሚያ ክልል ምን ይሰራሉ? ለመሆኑ በረከት ስምዖን ኢትዮጵያዊ ነው? ኢትዮጵያ እንደአሜሪካ በሀገሪቱ ውስጥ በመወለድ ዜግነት ትሰጣለች ወይስ ፎርማሊቲውን አሟልቶ ዜግነት እንዲሰጠው ማመልከቻ  አቅርቦ ጥያቄው ተቀባይነት አግኝቶ ዜግነት ተሰጥቶት ነው? “አንችው ታመጭው አንችው ታሮጭው” እንደሚባለው የማንፈልገውን ዘረኝነት ከጫናችሁብን በኋላ ይሁን በቃ ራሳችንን በራሳችን እናስተዳድራለን ብለን ስንል ፊልትሮው እንደተበላሸ መኪና ትንተፋተፋላችሁ::

 

ብአዴን ሲመሰረት የቀበሌወች: የመንግሥት መ/ቤቶችና ድርጅቶች ወኪሎች የተገኙበት ስብሰባ በየቀበሌው ተደርጎ ነበር:: በአንደኛው ቀበሌ ከተሰብሳቢወቹ መሀል ብዙ ትግሬወችን የተመለከቱ አንድ አማራ “የተሰበሰብነው የአማራ ድርጅት ለመመስረት ወኪል ለመምረጥ ነው ብላችሁናል:: ታዲያ ከእኛ መሀል ያሉት ትግሬወች ምን ያደርጋሉ?” ብለው ጠይቀው ነበር:: ከሕዝቡ መሀል ተመሳስለው ተቀምጠው የነበሩ አንድ የብአዴን አመራር አባል እመር ብለው ተነስተው “የሰውን ደም እየመረመርን ፖዘቲቭ ከሆነ አማራ ኔጌቲቭ ከሆነ ሌላ የሚል ቀልድ ለመጫወት አይደለም እዚህ የተሰበሰብነው” የሚል አስገራሚ መልስ ነበር የሰጡት::

 

ወ/ሮ ገነት ገ/ እግዚአብሔር የሚባሉ የአማራ ክልል ከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ ከወያኔ ጋር በመተባበር ወጣቶችን እያስገደለች ነው ተብላ ስሟ ከብዙወች መሀል በመጠቀሱ የአማራው ክልል ቃል አቀባይ አቶ ንጉሱ አዝነው ለወ/ሮይቱ የሚከላከልና የሚያሞገስ ጽሁፍ በፌስቡክ ላይ ማስነበባቸውን ሰማን:: አቶ ንጉሱ ጥላሁን ለወ/ሮዋ ብቻ  ጠበቃ ሆነው የቆሙት በቀሪወቹ ላይ የተሰነዘረው ክስ ትክክል ነው ብለው ተቀብለውት ነው ወይስ ምን? ወ/ሮይቱ ተወልዳ ያደገችው ባ/ዳር ነው ይሉናል አቶ ንጉሱ:: ዶሮና ቆቅ ዝርያቸው አንድ ነው:: ነገር ግን በቤት ውስጥ የተፈለፈለች ቆቅ ዶሮ ልትሆን አትችልም:: የዘር ፖለቲካ ቀርቶ እንደሆነ ይነገረን:: የዘር ፖለቲካ ካልቀረ ግን ለማም ጠፋም ሁሉም በየራሱ ሰው ይተዳደር እንላለን:: የሆነው ሆኖ በአማራ ክልል አማራ ያልሆኑ ሰዎች በፖለቲካ አመራር ሰጭነት እንዲቀመጡ የተደረገው እነርሱን የሚተካ አማራ ማግኘት ስላልተቻለ ነው? በሌሎች ክልሎች ያለው ሁኔታስ ተመሳሳይ ነው ማለት ነው: ወይስ ምን?

 

አሁን ካለው የሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ተነስተን ስንገመግም የወያኔ የዘር ፖለቲካና የተዛባ አመራር መቋጫው እየቀረበ ይመስላል:: ብዙ ያስሄደናል ተብሎ የተጠረገው የከፋፍለህ ግዛው ጎዳና ሱር ኮንስትራክሽን እንደሰራው መንገድ እየፈራረሰ ነው:: ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት ይጠቀሙበት የነበረው መላ ከሽፏል:: በብሔር-ብሔረሰቦች መሀል የዘሩት ቂምና ጥላቻ የፈለጉትን ያህል ምርት ሳያስገኝ ደርቋል:: በፍርሀት የተሸበበው ሕዝብ ልጓሙን አውልቆ ጥሎታል:: እስከ የልጅ ልጅ ድረስ በዙፋን ቁጭ ብለን እንድንገዛ ያስችለናል ብለው የቋጠሩት ሸር ተፈቷል:: ለጻድቃን የወረወሩት ጦር ወደሀጥአን ዞሯል:: ወያኔወች ግን አሁንም ቢሆን ከስህተታቸው ሊማሩ ባለመፍቀዳቸው ከራሳቸው አልፈው በደጋፊወቻቸው ላይ አደጋ ደቅነዋል:: በእርግጠኝነት ለመናገር ወያኔ መቸም እንዳያቀጠቅጥ ሆኖ ይቆረጣል:: የወያኔን ውድቀት ተከትሎ ዜጎች በነጻነት የሚኖሩባት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እውን ትሆናለች::

ትንሳኤ ለኢትዮጵያ!

 

በኢረቻ በዓል ላይ ከ175 በላይ ዜጎች በግፍ ተገደሉ

$
0
0


በኢረቻ በዓል ላይ ከ175 በላይ ዜጎች በግፍ ተገደሉ
በኢረቻ በዓል ላይ ከ175 በላይ ዜጎች በግፍ ተገደሉ

በአምቦ ከፍተኛ የህዝብ ተቃውሞ ተቀስቅሷል

$
0
0
Oromo

ፋይል- ኦሮሞ ተቃውሞ ሰልፍ

ከተማዋ በተኩስ እሩምታ ውስጥ መሆኗን የከተማዋ ነዋሪዎች ይናገራሉ:: ተጨማሪ ሃይል ወደ አምቦ እንቅስቃሴ እያደረገ በመሆኑ
ሆሎታ
አዲስ አለም
ኦሎንኮሚ
ጊንጪ ያላችሁ መንገድ በመዝጋት በጉዞ ያለውን ሃይል ባለበት አስቁሙት የሚል መልዕክት በማስተላለፍ ላይ ናቸው:: በተያያዘ ዜና በአወዳይም የዛሬው የቢሾፍቱ ጭፍጨፋ ያስቆጣቸው የከተማዋ ነዋሪዎች አደባባይ መውጣታቸው እየተነገረ ነው

እኛ እያለቀስን..እነሱ በደስታ

$
0
0

14572192_675203989308611_2001452800520476251_nእኛ እያለቀስን
እነሱ በደስታ
እንዴት እንቻለው
ሰው በሰው ሲመታ
ጥይት መጫወቻ
ሆነ እና በአገሩ
ወገን ተገደለ
በአገር በመንደሩ
እረ እናተ ሰወች
በቃ አትግደሉብን
መሬት ፈልጋችሁ
ሰው አትጨርሱብን
ማነው ሽማግሌ
መካሪ በአገሩ
ሰው እዬሞተነው
መንግስትን እሰሩ
መግስት ገዳይ ሆኖ
እኛ እዬሞትንለት
ሊተናኮል መጣ
ኢሬቻን ይዞበት
ይህ ኩሩ ጀግናዬን
አስለቅሶት ዋለ
ገሎበት ልጇቹን
ጥሎበት በረረ
በዚህ አያበቃም
ትግላችን በወኔ
ድባቅ ሳንከተው
ይህንን ወመኔ
ከእነ ምናምቴው
ይሞታል ወያኔ
ይህ አንድነት አለን
እኛ ታላቅ ህዝቦች
ይሰማናል ሁሌም
የወገናችን ሞት።


በዛሬው የኢሬቻ በዓል በተፈጠረው ግጭት በመቶዎች የሚቆጠር ህይወት መጥፋቱን ኦፌኮ አስታወቀ

$
0
0

Sunday, October 2, 2016/ VOA Amharic

1451በዛሬው ዕለት በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ ኃይቅ ለመከበር በዝግጅት ላይ የነበረውና ከኦሮሞ ክብረ በዓሎች አንዱ የሆነው ኢሬቻ በዓል መንግሥትን በተቃወሙ ወጣቶችና በመንግሥት ታጣቂዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ተቋርጦ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወት ማለፉን የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አስታወቀ። የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፤ ፓርቲያቸው ባጠናቀረው መረጃ ሰዎች በተኩስ፣ በአስለቃሽ ጭስ እና በመረጋገጥ ሕይወታቸው እንዳለፈ ነው። 
በርካታ የቆሰሉ ሰዎች አሁንም በሆስፒታል እንደሚገኙ አክለው የተናገሩት ዶ/ር መረራ የሟቾች ቁጥር አሁንም ሊጨምር እንደሚችል ተናግረዋል።
በሌላ በኩል የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው በቦታው የነበሩ የዐይን እማኞች ግጭቱ የተጀመረው በበዓሉ መክፈቻ ላይ ንግግር ሊያደርጉ የነበሩ ሰዎች ላያ እና ሊሰቀል በነበረው ባንዲራ ላይ ተቃውሞ በመነሳቱ ነው።
ከግጭቱም በኋላ በርካቶች በተኩስ፣ በአስለቃሽ ጭስ፣ በመረጋገጥ እና ገደል ውስጥ ገብተው ሕይወታቸው እንዳለፈ ተናግረዋ። የተጎዱ ሰዎችን በተመለከተ እስካሁን ይህ ነው የተባለ ትክክለኛ ቁጥር ማግኘት ባይቻልም የዐይን እማኞች ተጎጂዎች 25 በሚሆኑ መኪኖች ሲወሰዱ ተመልክተናል ብለዋል።
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በሰጠው መግለጫ፤ “የኢሬቻ በዓልን ባህላዊ አከባበር ጠብቆ ለማክበር የኦሮሞ ህዝብ አባገዳዎችና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ያደረጉት ሰፊ ቅድመ ዝግጅት በሁከት ፈጣሪ ኃይሎች ተስተጓጉሏል፡፡ ሁከት ፈጣሪዎቹ ባስነሱት ሁከት በተፈጠረ ግርግር በመረጋገጥ የሰው ህይወት ጠፍቷል፡፡” ብሏል። ዝርዝሩን ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ይጠብቁ። (ፎቶ፡ አንዷለም ሲሳይ)

 

በቢሾፍቱ በሕዝባችን ላይ በሂሊፕተር አስለቃሽ ጭስ እየተበተነበት ጥይት ሲዘንብበት የሚያሳይ ቪዲዮ

$
0
0


በቢሾፍቱ በሕዝባችን ላይ በሂሊፕተር አስለቃሽ ጭስ እየተበተነበት ጥይት ሲዘንብበት የሚያሳይ ቪዲዮ
በቢሾፍቱ በሕዝባችን ላይ በሂሊፕተር አስለቃሽ ጭስ እየተበተነበት ጥይት ሲዘንብበት የሚያሳይ ቪዲዮ

የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት በቢሾፍቱ የገደላቸው ወገኖች ቁጥር 500 በላይ ደረሰ

$
0
0

irrecha

አንድ የወያነ ትግሬ የአጋዚ ወታደር ፊቱን በመሸፈን ቦ ኦሮሚያ ክል ቢሸፍቱ (ደብረዘይት) ላይ ህዝቡን እንዲህ ነው የፈጀው።

አንድ የወያነ ትግሬ የአጋዚ ወታደር ፊቱን በመሸፈን ቦ ኦሮሚያ ክል ቢሸፍቱ (ደብረዘይት) ላይ ህዝቡን እንዲህ ነው የፈጀው።

(ዘ-ሐበሻ) በዛሬው እለት ቢሾፍቱ እየተከበረ ባለው የእሬቻ በዓል ላይ የሞቱት ቁጥር ከ500 በላይ እንደሆነ ተዘገበ:: ቁጥሩ በየሰዓቱ እንደሚጨምር የተገለጸ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖችም መቁሰላቸውን ከስፍራው ያነጋገርናቸው እማኞች ገልጸዋል።

በዚህ የ እሬቻ በዓል ላይ በአብዛኛው ሕይወታቸው የጠፋው ወገኖች ኦሮሞዎች እና አማሮች መሆናቸው ተገልጿል:: የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት በሰላም የ እሬቻን በዓል እያከበረ ባለው ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ሲጨምር ሂሊኮፕተርና መትረየስ ተጠቅሟል:: አፍቃሪ ሕወሓት የሆኑ የመንግስት ድረገጾች ሂሊኮፕተሮች ወረቀት እየበተኑ ነበር ይበሉ እንጂ ሂሊኮፕተሮቹ አስለቃሽ ጭስ እየበተኑ በመትረየስ የትግራይ ነጻ አውጪ ወታደሮች ሕዝቡን ፈጅተውታል::

ከእሬቻው ጭፍጨፋ በኋላ የአምቦ ሕዝብ ተነሳ |የተቆጣው ሕዝብ በርካታ የመንግስት መኪኖችን አቃጠለ

$
0
0

ambo
(ዘ-ሐበሻ) የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ኦሮሞዎችን እና አማሮችን በ እሬቻ በዓል ቢሾፍቱ ላይ ዛሬ ከጨፈጨፈና ከ500 በላይ የሰው ሕይወት ካጠፋ በኋላ በአምቦ ሕዝብ በቁጣ ተነሳ:::

በአምቦ በተነሳው ሕዝባዊ አመጽ ሕዝቡ ቁጣውን በመንግስት ንብረቶች ላይ እርምጃ በመውሰድ እየገለጸ ነው:: እንደዘ-ሐበሻ ዜና ምንጮች ገለጻ ከሆነ በአምቦ በርካታ የመንግስት መኪኖች እና አንዳንድ መስሪያ ቤቶች በ እሳት ወድመዋል:: ይህን ተቃውሞ ሊያረግቡ በመጡ የሕወሓት ወታደሮች ላይም እርምጃ መውሰድ የጀመረ ሲሆን ወታደሮች እየሸሹ መሄዳቸው ተሰምቷል::

በአምቦ መንገዶች መዘጋጋታውም ተሰምቷል::

የአምቦ ሕዝብ እጅጉን ከመቆጣቱም ባሻገር በሌሎች የኢትዮጵያ ክልል ከተሞችም እንዲሁ ይህው ሕዝባዊ ተቃውሞ እንደሚቀጥል ይጠበቃል::

ቢቢኤን ልዩ ፕሮግራም በቢሾፍቱው ጭፍጨፋ ዙሪያ: ዶ/ር መሐመድ ጣሂርና ገረሱ ቱፋ ይናገራሉ |ቪዲዮ

$
0
0


ቢቢኤን ልዩ ፕሮግራም በቢሾፍቱው ጭፍጨፋ ዙሪያ: ዶ/ር መሐመድ ጣሂርና ገረሱ ቱፋ ይናገራሉ | የሚታይ
ቢቢኤን ልዩ ፕሮግራም በቢሾፍቱው ጭፍጨፋ ዙሪያ: ዶ/ር መሐመድ ጣሂርና ገረሱ ቱፋ ይናገራሉ | ቪዲዮ

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live