Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ኢህአዴግ – ከለውጥ እና ከሞት አንዱን ምረጥ

$
0
0

ስዩም ተሾመ | ከኢትዮጵያ

ስዩም ተሾመ

ስዩም ተሾመ

ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማህብረሰብ ሊሰጥ የታቀደው ስልጠና ዛሬ ላይ ተጀምሯል። ለስልጠናዉ ከተዘጋጁ ሰነዶች ውስጥ የመጀመሪያው “የሩብ ምዕተ ዓመታት የልማት፣ ሰላምና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ጉዞ…” የሚል ርዕስ ተሰጥቶታል። በመረሃ-ግብሩ መሰረት ጠዋት ላይ በአሰልጣኞቹ ገለፃ ሲሰጥ እንደተለመደው በአሰልጣኝነት የተመደቡት የመንግስት ኃላፊዎች ለታዳሚው የሚመጥን ስልጣና ለመስጠት የአቅምና ክህሎት ችግር እንዳለባቸው በግልፅ ያስታውቃል። ይህ ግን ላለፉት አስር አመታት የታዘብኩት ነገር ስለሆነ ብዙም አላሳሰበኝም። ከዚያ ይልቅ ትኩረቴን ሰነዱ ላይ አድርጌ ነበር።

ለውይይቱ የቀረበው ፅሁፍ ላለፉት 25 ዓመታት የተመዘገቡ አንኳር አገራዊ ለውጦችን በመዘርዘር ይጀምራል። የሚቀጥለው ንዑስ-ክፍል ደግሞ በሀገሪቱ እየታዩ ያሉ ፈተናዎችንና መፍትሄዎቻቸውን ይዘረዝራል። እዚህ ጋር ስደርስ ግራ ገባኝ። ማንበቤን አቁሜ በዙሪያዬ የተቀመጡትን መምህራን ስመለከት ሁሉም ገለፃውን በቸልተኝነት እየተከታተሉ ነው። ከምሳ በኋላ ግን በእኔ ውስጥ የነበረው ግራ-መጋባት በሁሉም ፊት ላይ በግልፅ መታየት ጀመረ።

ከሰዓት በኋላ በነበረን ውይይት ሲነሱ የነበሩት ጥያቄዎች በሙሉ በስልጠናው ስለተነሱ ሃሳቦች ላይ ሳይሆን በስልጠናው አግባብነት ላይ ብቻ ያተኮሩ ነበሩ። ሊደረግ የታሰበው የውይይት ፕሮግራም ስለ ውይይቱ በመወያየት ላይ ብቻ ታጥሮ ቀረ፡፡ ለዚህ ደግሞ “እየታዩ ያሉ ፈተናዎችንና መፍትሄዎቻቸው” በሚለው ስር ከተዘረዘሩት ሃሳቦች የሚከተለው በዋናነት የሚጠቀስ ነው፡-

“ባለፉት ሃያ አምስት አመታት የነበሩ የመልካም አስተዳደር፣ የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር፣ የትምክህትና ጠባብነት አደጋዎች እንዲሁም ሃይማኖትን ሽፋን የሚያደርገው አክራሪነት ፈተናዎች አሁንም ቅርፃቸውን ቀይረው ወይም በሌላ ተተክተው ስላሉ ፈተናዎቹን ለማለፍ የተከተልናቸውን ስልቶች ይበልጥ አጠናክረን ያገራችንን ሰላም፣ ልማትና ዴሞክራሲ ለማደናቀፍ ወደ የማይቻልበት ደረጃ ማድረስ አስፈላጊ በመሆኑ…”
የከፍተኛ ትምህርት ማህብረሰብ ሥልጠና ለ2009 ትምህርት ዘመን ዝግጅት ምዕራፍ ማጠናቀቂያ፣ ትምህርት ሚኒስቴር፥ መስከረም 2009፥ ገፅ-7

በመጀመሪያ ደረጃ የተጠቀሱት ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው በጣም ከመደጋገማቸው የተነሳ ትርጉም-አልባ ወደ መሆን ተቃራበዋል። ከዚህ በተጨማሪ፣ የተጠቀሱት ችግሮች በዋናነት ከመንግስት ኃላፊዎች ጋር የተያያዙ እንደመሆናቸው ከመምህራን ሥራና ኃላፊነት ጋር ብዙም የተያያዙ አይደሉም። በአብዛኛው ከመምህራኑ ሲነሳ የነበረው ጥያቄ ግን፤ “‘መልካም አስተዳደር፣ የኪራይ ሰብሳቢነት፣ የትምክህት፣ ጠባብነትና አክራሪነት’ የሚባሉት ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ከአመት-እስከ-አመት አይቀየሩም እንዴ?” የሚለው ነበር።

File Photo

File Photo

የዛሬው ስልጠና እንደተጠናቀቀ በቀጥታ ወደ ቤት በመሄድ በ2006 ዓ.ም ላይ ተሰጥቶ ለነበረው ተመሳሳይ ስልጠና የተዘጋጀውን ሰነድ ማገላበጥ ጀመርኩ። በሐምሌ ወር 2006 ዓ.ም “የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ስርዓት ግንባታ ትግላችንና ፈተናዎቹ” በሚል ርዕስ በተዘጋጀው ሰነድ ውስጥ የሚከተለው ሃሳብ አገኘሁ፡-

“በቅድሚያ በማንም ሊላከክ የማይችል የመልካም አስተዳደር ችግር፣ ቀጥሎም ትምክህትና ጠባብነት እንዲሁም የሃይማኖት አክራሪነት እና የእነዚህ ሁሉ መንስዔ የሆነው ያለአግባብ የመጠቀም ዝንባሌ (ኪራይ ሰብሳቢነት) በመፍታት የተያያዝነውን የልማት፣ ሰላምና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ጉዞ አጠናክረን ልንቀጥልበት እንደሚገባ…”
የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ስርዓት ግንባታ ትግላችንና ፈተናዎቹ፥ ሐምሌ 2006 ዓ.ም፥ ገፅ-34

በ2006 ዓ.ም የተዘጋጀው የሥልጠና ሰነድ በሐምሌ ወር ይሁን እንጂ ስልጠናው ግን የተሰጠው እንደ ዘንድሮው በመስከረም ወር 2006  ዓ.ም ላይ ነበር። ከዘንድሮው አንፃር ሲታይ በወቅቱ ሰፋ ያለ ግዜ ተሰጥቶት እንደተዘጋጀና ብዙ ጉዳዮችን የሚዳስስ እንደነበረ መገንዘብ ይቻላል። ሆኖም ግን፣ በ2006ቱ እና በ2009ኙ ሰነዶች ውስጥ በሀገሪቱ እየታዩ ስላሉት ችግሮች በመንስዔነት ሆነ በመፍትሄነት የተጠቀሱት ነገሮች አንድና ተመሳሳይ ናቸው፡-መልካም አስተዳደር፣ የኪራይ ሰብሳቢነት፣ የትምክህት፣ ጠባብነትና አክራሪነት፡፡

ከላይ እንደተጠቀሰው የኢህአዴግ መንግስት አመት በወጣና በገባ ቁጥር ተመሣሣይ ችግሮችና መፍትሄዎች ላይ የሙጥኝ ማለቱ ባለበት እየረገጠ ከመሆኑ በላይ ሌላ ነገር አያሳይም። አዎ… አሁን በሀገሪቱ እየታዩ ያሉ ፈተናዎች የኢህአዴግ መንግስት ከሕዝብ ጥያቄና የለውጥ ፍላጎት ጋር አብሮ መሄድ ባለመቻሉ የተከሰቱ ሲሆን መፍትሄዎቻቸውም ከሕዝቡ ጥያቄና ፍላጎት ጋር አብሮ መሄድ ብቻ ስለመሆኑ ጥርጥር የለውም።

ለምሳሌ በ2006 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር ተያይዞ የነበረው የተቃውሞ እንቅስቃሴ እንደ አምቦ ባሉ አከባቢዎች ላይ ብቻ የተወሰነ ነበር። በ2008 ዓ.ም የታየው የሕዝብ አመፅና ተቃውሞ ግን በመላው ኦሮሚያ የተስፋፋ ከመሆኑም በላይ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን በመቋረጥ እንኳን ሊገታ አልቻለም። ከዚህ ይልቅ፣ የተቃውሞ እንቅስቃሴው ወደ አማራ ክልል በመስፋፋቱ ለሀገሪቱ ሰላምና መረጋጋት ላይ ከፍተኛ ስጋት እየሆነ መጥቷል። ከኦሮሚያና አማራ ክልሎች በተጨማሪ በደቡብ ብሔር፥ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ጭምር እየተስፋፋ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው።

በእርግጥ እንደ ኢህአዴግ አገላለፅ፣ ከሁለት አመት በፊት ሆነ ከሁለት አስርት አመታት በፊት ለሀገሪቱ ልማት፣ ሰላምና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ፈተና የሆኑት ችግሮች አንድና ተመሳሳይ ናቸው፡፡  ነገር ግን፣ ባለፉት ሁለት አመታት ውስጥ ብቻ እንኳን በሀገሪቱ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ላይ የታየው ለውጥ የሩብ ምዕተ አመታት ያህል ልዩነት አለው። ሕዝቡ የሚያነሳቸው ጥያቄዎችና እያሳየ ያለው የለውጥ ፍላጎት ከእለት-ወደ-እለት እየተቀያየሩና እየጨመሩ መጥተዋል። በዚህ ፈጣን የለውጥ ሂደት ውስጥ ባለበት የቆመ ብቸኛ አካል ቢኖር ኢህአዴግ ነው።

ከወራት በፊት ባወጣሁት ፅሁፍ የኢህአዴግ መንግስት ባለበት የቆመና ከሕዝቡ የለወጥ ፍላጎት ጋር አብሮ መሄድ የተሳነው እንደሆነ ለመግለፅ ሞክሬ ነበር። ነገር ግን፣ በወቅቱ ይህን ያልኩት ‘ኢህአዴግ ከሕዝቡ ጋር በሚፈለገው ፍጥነት የመጓዝ ችግር አለበት’ ከሚል እሳቤ እንጂ ‘እንዲህ እንደ አሁኑ ባለበት ተቸንክሮ፥ ተቀርቅሮ ይቀራል’ የሚል ግምት ግን አልነበረኝም። አሁን ላይ ግን ይበልጥ እያሳሰበኝ ያለው ነገር፣ ኢህአዴግ ከሕዝቡ ጥያቄና ፍላጎት ጋር አብሮ መሄድ አለመቻሉ ብቻ ሳይሆን በዚህ ምክንያት የሀገሪቱ ዜጎች ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ እየወደቀ መምጣቱ ነው።

3ኛው ማዕበል በሚለው ፅሁፍ የአሁኗ ኢትዮጲያ ሁኔታ ከ30 አመት በፊት በደቡብ ኮሪያ ከነበረው ፖለቲካዊ ኢኮኖሚ ሁኔታ አንፃር ዝርዝር ትንታኔ ለመስጠት ሞክሬያለሁ። በአጭሩ ለማጠቃለል ያህል፣ ከ1984 – 1994 ዓ.ም ባሉት የመጀመሪያ አስር አመታት የመንግስት ዋና ትኩረት የሚሆነው አዲስ የተገነባውን ስርዓት ህልውና ማረጋገጥ (Survival) ላይ ነበር። በመቀጠል ከ1995 – 2005 ዓ.ም ባሉት አስር አመታት ደግሞ በሀገሪቱ ኢኮኖሚና የመሰረተ-ልማት ግንባታ ረገድ እምርታ የሚታይበት የእድገት (Growth) ዘመን ነው። ከ2005 – 2015 ዓ.ም ባሉት አስር አመታት ደግሞ የልማት (Development) ዘመን ሲሆን አራተኛውና የመጨረሻው ዘመን ደግሞ በሁሉም አቀፍ የዳበረ የፖሊቲካዊ-ኢኮኖሚ ሥርዓት በመገንባት ብልፅግናን (Evolution) መቀዳጀት ነው።

ባለፉት ሃያ አምስት አመታት የኢህአዴግ መንግስት አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ላይ የተጠቀሱትን ከሞላ-ጎደል አሳክቷል ማለት ይቻላል። ነገር ግን፣ በሦስተኛ ደረጃ ላይ ከተጠቀሰው ልማት (Development) አንፃር ግን አስፈላጊውን ለውጥና መሻሻል ከማምጣት አንጻር የመጀመሪያውን እርምጃ እንኳን ለመራመድ ተስኖታል።

በ3ኛው ማዕበል የሚነሳው ዋና የሕዝብ ጥያቄና ፍላጎት ከዜጎች ነፃነት እና የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ጋር የተያያዘ ነው። በ2ኛ ደረጃ ላይ የተመዘገበው ፈጣን የኢኮኖሚ እድገትና የመሰረተ-ልማት መስፋፋት የአብዛኛውን የህብረተሰብ ክፍል ንቃተ-ህሊና ያጎለብቷል። በዚህም፣ ስለ ዜጎች መብትና ነፃነት፣ እኩልነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት፣ እንዲሁም የሕግ-የበላይነትና ሌሎች ዴሞክራሲያዊ እሴቶች የጋራ ግንዛቤ ተፈጥሯል። ከዚህ አንፃር፣ የመንግስት ሥራና አሰራር ከሕዝቡ ጥያቄና የለውጥ ፍላጎት ጋር አብሮ መጓዝ መቻል አለበት። እ.አ.አ በ1987 ዓ.ም የደቡብ ኮሪያ መንግስት በዚህ ወሳኝ የለውጥ ደረጃ ላይ ደርሶ የነበረ ሲሆን በትክክለኛው ግዜ ተገቢውን ምላሽ መስጠት በመቻሉ ሀገሪቱን ዛሬ ላይ ከደረሰችበት የብልፅግና ደረጃ እንድትደርስ አስችሏታል።

በተመሣሣይ፣ ዛሬ ላይ ኢትዮጲያ በተመሳሳይ ወሳኝ የለውጥ ደረጃ ላይ ትገኛለች። በአሁን ላይ የኢትዮጲያ የሕዝብ ጥያቄ ነፃነት፣ እኩልነትና ፍትህ ናቸው። በሕዝቡ ዘንድ ያለው የለውጥና መሻሻል ፍላጎት የዜጎች መብት፣ ነፃነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የሚረጋገጥበት ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በመግንባት ላይ ያነጣጠረ ነው። እዚህ ጋር የኢህአዴግ መንግስት ሁለት አማራጮች አሉት።

የመጀመሪያው አማራጭ ከሕዝቡ ጥያቄና የለውጥ ፍላጎት ጋር አብሮ በመጓዝ የሀገሪቱን የልማት፣ ሰላምና ዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ወደ ወሳኝ ምዕራፍ ማሸጋገር። ሁለተኛው አማራጭ ደግሞ በሕዝቡ ዘንድ እየተነሳ ያለውን ጥያቄና የለውጥ ፍላጎት በማፈን የተሻለ ሕይወት የመኖር ተስፋን ማጨለም ነው። በሁለተኛው መንገድ የብዙ ንፁሃን ዜጎችን ሕይወትን በመስዕዋትነት የሚጠይቅ ከመሆኑ በስተቀር እንደ ማንኛውም አምባገነናዊ ሥርዓት መጨረሻው ውድቀት ነው።

አሁን በሀገራችን እያታዩ ያሉት ችግሮች መሰረታዊ መንስዔያቸው የኢህአዴግ መንግስት በሕዝቡ ዘንድ ካለው የለውጥና መሻሻል ፍላጎት ጋር አብሮ መሄድ ባለመቻሉ ምክንያት የተከሰቱ ናቸው። ችግሩ አንድ እንደመሆኑ መጠን መፍትሄውም አንድና አንድ ነው። የኢህአዴግ መንግስት ከሕዝቡ ጥያቄና የለውጥ ፍላጎት ጋር አብሮ መለወጥ ወይም እንደ ማንኛውም አምባገነናዊ ሥርዓት ውድቀትን መጎንጨት ይሆናል። በአጠቃላይ፣ የኢህአዴግ መንግስት በተለይ በዚህ አመት የሚወስደው እርምጃ ወይ ለለውጥ ወይም ደግሞ ለሞት ይዳርገዋል፡፡

↧

↧

ሰበር ዜና: ሕወሓት መራሹ መንግስት ዘንድሮ በአ.አ. መስቀል አደባባይና በጎንደር መስቀል እንዳይከበር ሊያደርግ ነው |መስቀልን በየቤተክርስቲያናችሁ አክብሩ የሚል ትዕዛዝ ወርዷል

$
0
0

mesekel

(ዘ-ሐበሻ) በሕዝባዊ ንቅናቄና አልገዛም ባይነት ጭንቅ ውስጥ የወደቀው የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት በዚህ አጣብቂኝ ሰዓት ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው ከተመለሱ ተቃውሞው ይጧጧፋል በሚል ስጋት ትምህርት እንዳጀመር አስተማሪዎችን በስልጠና ወጥሮ የያዘ ሲሆን በቀጣይ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ እና በጎንደር በመስቀል በዓል የተነሳ ብዙ ሕዝብ ከተሰባሰበ ወደ ተቃውሞ ሊቀየር ይችላል በሚል ስጋት መስቀል በየቤተክርስቲያኑ እንዲከበር ትዕዛዝ መውረዱን አንድ ታማኝ የኢሕአዴግ የውስጥ ምንጭ ለዘ-ሐበሻ ገለጹ::

እንደምንጩ ገለጻ በፌደራል ጉዳዮች ሚ/ር አማካኝነት ለቤተክህነት ይህ መመሪያ የወረደ ሲሆን ቤተክህነት እስካሁን ምላሽ እንዳልሰጠች ገልጸዋል::

ምንጩ ለዘ-ሐበሻ እንዳሉት መንግስት የመስቀል በዓልን በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ እና በጎንደር ብዙ ሺህ ሕዝብ በተሰበሰበት እንዳይከበር ማዘዙን ሚዲያዎች ተቀባብለው ከዘገቡትና ሕዝቡም ይህን ካወቀ ምናልባት አቋሙን ሊቀይር ስለሚችል ይህን ዜና ሕዝብ እንዲቀባበለውና ላልሰማ እንዲያሰማ ጥሪያቸውን አቅርበዋል::

ከአባይ ጸሐዬ በኩል በፌደራል ጉዳዮች አማካኝነት የወረደው ይኸው ት ዕዛዝ እንደሚያመለክተው ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት የዘንድሮውን የመስቀል በዓል ጸረሰላም ኃይሎች ሊያውኩት ስለሚችሉ በየቤተክርስቲያናችሁ አክብሩ የሚል ነው ያሉት እኚሁ ታማኝ ምንጭ ስርዓቱ በአሁኑ ወቅት በገባበት ፍርሃት የተነሳ ከዚህም ሌላ ውሳኔ ሊያሳልፍ ይችላል ብለዋል::

የመስቀል በዓል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ እንዲሁም በጎንደር በብዛት ከሚከበርባቸው ቦታዎች መካከል የሚጠቀስ ሲሆን በተለይ በነዚህ ቦታዎች ብዙ ሺህ ሕዝብ መገኘታቸው ለመንግስት እንቅልፍ የነሳው ጉዳይ ነው::

↧

አማራውን ትጥቅ ለማስፈታት ወደ ወገራ ወረዳ የሄደው የትግራይ ነጻ አውጪ ጦር አፍረትን ተከናነበ

$
0
0

Zehabesha-News.jpg

(ዘ-ሐበሻ) የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት አስተዳደሮች አባይ ጸሓዬ; ደብረጽዮን ገብረሚካኤል እና አባይ ወልዱ በተደጋጋሚ በየሚዲያው ወጥተው አማራውን ትጥቅ እናስፈታለን በሚል የፎከሩትን ፉከራ ለማሳካት በጎንደር እንቅስቃሴ ቢጀምሩም ዛሬም ለሁለተኛ ጊዜ ውርደትን እንደተከናነቡ ከስፍራው የመጡ መረጃዎች ጠቆሙ::
በጎንደር ወረዳደርጋጅ ቀበሌ ታግራ ጎጥ ገበሬዎችን ትጥቅ ለማስፈታት የሄደው ከ25 የማያንስ የትግራይ ነጻ አውጪ ሠራዊት ሙሉ በሙሉ ተደምሥሷል:: የአማራ ገበሬዎች መሣሪያችንን አናስረክብም በሚል ከትግራይ ነጻ አውጪ ሰራዊት ጋር እልህ አስጨራሽ ተኩስ መክፈታቸውንም የክስፍራው የደረሱን መረጃዎች አመልክተዋል::

እንደሌሎች የመረጃ ምንጮች ገለጻ የትግራይ ነጻ አውጪ ሰራዊት በአማራው ክልል ውርደትን ሲከናነብ ይህ የመጀመሪያው አይደለም:: ከጥቂት ቀናት በፊት በሰሜን ጎንደር ወገራ ወረዳ ታግራ መድሃኔዓለም ቀበሌ ገበሬውን ትጥቅ አስፈታለው ብሎ የተንቀሳቀሰው ቁጥሩ በይፋ ያልታወቀው የሕወሓት ሰራዊት በገበሬዎች ተደምስሷል::

በአማራው ክልል ያሉ ገበሬዎች አሁንም ትጥቃችንን አንፈታም በሚል ከትግራይ ነጻ አውጪ ሰራዊት ጋር በተለያዩ ቦታዎች እየተዋደቁ ቢሆን በኢንተርኔትና በስልክ እጦት የተነሳ መረጃዎች ሕዝብ ጋር በቶሎ ሳይደርሱ ቀርተዋል::

↧

ነውረኞቹ አባይ ጸሀዬና ስዩም መስፍን (ከአቻሜለህ ታምሩ)

$
0
0

አባይ ጸሀዬንና ስዩም መስፍንን እናውቃቸዋለን። የህዝብ «ጠላቶች» እያሉ ከሚፈርጇቸው «ከፍተኛ አመራሮች» የከፉ እንጂ የተለየ ጠባይ በሕይወታቸው ሙሉ ታይቶባቸው አያውቅም። «ሙሰኞች» እያሉ ከሚፈርጇቸው «የመንግስት ሌቦች» ግንባር ቀደሞቹ አባይ ጸሀየና ስዩም መስፍን ናቸው። ከነሱ ውጭ ያሉት የወያኔ «ከፍተኛ» አመራሮች ከታሰሩ አባይና ስዩም ካገር በፊት መታሰር አለባቸው፤ ሌሎች ከተገደሉ አባይና ስዩም ካገር በፊት መሰቀል አለባቸው። አባይ ጸሀዬንና ስዩም መስፍንን እንዲህ የሚያናግራቸው፤ ንጹህም ያደረጋቸው ያሰለፏቸው ወታደሮችና በእጃቸው ያለው የጦር መሳሪያ ብቻ ነው። ከዚህ ውጭ በህግ ፊት አባይ ጸሀዬና ስዩም መስፍን የህዝብ «ጠላቶች» እና ሙሰኞች እያሉ ከሚፈርጇቸው ሰዎች የባሰ የከፉ ናቸው።

hqdefault
አባይና ስዩም «አንዳንድ» የሚሏቸውን የወያኔ አመራሮች ሙሰኞችና እና የሕዝብ ጠላቶች ይሏቸዋሉ። እግርጥ ነው እዚያ ቤት የህዝብ ጠላትና ሙሰኛ ያልሆነ አይገባም። እንደሚታወቀው አባይና ስዩም የወያኔ ፊታውራሪዎች ናቸው። እንደፊታውራሪነታቸው ዛሬ የህዝብ «ጠላቶች» እና ሙሰኞች ናቸው እያሉ የሚከሷቸውን «ከፍተኛ አመራሮች» የመለመሉና ለከፍተኛ ስልጣን ያበቁ እነሱ ራሳቸው ናቸው። የህዝብ «ጠላቶችን» እና ሙሰኞች የሚባሉትም ሰዎች የህዝብ «ጠላቶችን» እና ሙሰኞች የሆኑት አባይና ስዩም ለዘረፋ በፈጠሩት የግፍ መዋቅር ተደግፈው ነው።
አባይና ስዩም የህዝብ ጠላቶችና ሙሰኞች ካልሆኑ እንደምን አምነው የህዝብ «ጠላቶችን» እና ሙሰኞችን ከፍተኛ አመራሮች አደረጓቸው? የትግራይን የበላይነት ለማስጠበቅ ሲሉ ነፍሰ በላ የትግራይ ወታደሮችን ልከው ጎንደርና ጎጃም፣ ወለጋና ሐረር ህጻናትን ያስጨፈጨፉ አባይና ስዩም አይደሉምን? መንጋ አጋዚ ጎንደርና ጎጃም፣ ወለጋና ሐረር ልከው ሰላማዊ ወጣቶችን በኃይል ያሳፈሱና ያስተለተሉ አባይና ስዩም አይደሉምን?
ነገሩ ግን ወዲህ ነው። አባይ፣ ስዩምና በረከት የሰው አውሬዎች ሆነው ሌሎችን የህዝብ «ጠላቶችን» እና ሙሰኞች እያሉ የሚፈርጁት እነሱ ጲላጦሶች ሆነው ራሳቸውን ንጹህ በማድረግ ከጀርባ ሆነው የሚዘውሩት አልበቃ ብሏቸው የህዝብ «ጠላቶች» እና ሙሰኞች የሚሏቸውን ምስለኔዎች ገፍትረው በማስወጣት የተገፊዎቹን ወንበር እነሱ ጭንብላቸው በማውለቅ ለመጠቅለልና ወደፊት ለመምጣት ነው። እነሱ እስካሉ ድረስ ግን ካለፈው የሚከፋ እንጂ የተሻለ እድል እንደማይኖር ከነሱ ውጭ ያለነው እኛ ግፉዓን አውጥተን አውርደን እንደጨረስንና ተጋድሎ ላይ እንዳለን ፈጽሞ ማሰብ አይፈልጉም።
የሰው ደም የሚጠጡት፣ የሰው ስጋ የሚበሉት፣ የሰው አጥንት የሚቆረጥሙት፣ የዝርፊያና የግፍ ስልጣን የተቆጣጠሩት እነ አባይ ጸሀዬና ስዩም መስፍን ርስ በርሳቸው በተለዋወጡ ቁጥር የሚሰጡትን የፕሮፓጋንዳ ተስፋና በደርግና በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ላይ የሚያወርዱትን ነቀፌታና ጥላቻ እንደ እድገትና ልማት እንድንቆጥርላቸው ዛሬም እንደ ትናንቱ ይሰብኩናል። እኛን እየገደሉና እየዘረፉ እነሱ ስለበለጸጉ ለኛ መልካም እድል ያመጡልን አድርንገን እንድናስብ ዛሬም ያለሀፍረት ይነግሩናል። «የድሮ ስርዓት» እያሉ ከሚያከፏቸው እጅግ የከፋውን ነውረኛውን የትግራይ የአፓርታይድ አገዛዝ « አንዳንድ እንከኖች» የሚሏቸውን «ጉድለቶች» እንደ መልካም አስተዳደር ጉድለት እንድንቆጥርላቸው ዛሬም ያግባቡናል። የአገዛዛቸውን መሰረት ለማጠንከር የሰሩትን ሁሉ ለአገር ውለታ እንደሰሩና እድገትና ልማት እንዳመጡ ዛሬም ሳያፍሩ በኩራት ይነግሩናል። የዘረጉት የግፍ ስርዓት የአረመኔ ትግሬዎች የወሮበላ አገዛዝ መሆኑን ረስተውት «እኛ ብቻ ነን ዲሞክራሲ ማምጣት የምንችለው» እያሉ ራሳቸውን ያሞግሳሉ። ነውር የማያውቁ የሰው አውሬዎች! ድሮ «ጅብ በማያውቁት አገር ሄዶ ቆርበት አንጥፉልኝ አለ ነበር» በቤተ ወያኔ ግን «ጅብ በሚታወቅበት አገር ቆርበት አንጥፉልኝ» ሆኖል።
ስዩም መስፍን የአለም ውሸታም ነው። ባድመ ለኢትዮጵያ ተወሰነ ብሎ ለአገር የሚዋሹ ቅሌታም ነው።
አባይ በ1977 ዓ.ም. ማሌሊት ሲመሰረት የነግደይ ዘርዓጺዮን የኃሳብ ደጋፊ ነበር። እነግደይ ሲወገዱ ግን ሀሳቡን ቀይሮ የመለስ ጀሌ ሆነ። በወያኔ ታሪክ በጠቅላላ ጉባኤ ተመርጦ የስልጣን ጊዜውን ሳይጨርስ ያለጠቅላላ ጉባኤ የህወሀት ሊቀመንበርነቱን በመለስ የተቀማ ብቸኛ ታጋይ አባይ ጸሀዬ ነው።
በ1993 ዓ.ም. ወያኔ ለሁለት ሲሰነጠቅ የመለስን አንጃ በብርቱው የተገዳደረውን ስብስብ ይመራ የነበረው ግለሰብ ታጋይ ተወልደ ወልደማሪያም ይባላል። ታጋይ ተወልደን ወያኔዎች ግደይ ዘርዓጺዎን ከድርጅቱ ከተወገደ በኋላ የድርጅቱ «ጭንላት» ይሉታል። ይህ የድርጁቱ «ጭንቅላት» አልባንያን የአለም ስልጣኔ ሞዴል አድርጎ የሚቆጥር ጉድ ነው። የነተወልደ አንጃ ከብዙ በጥቂቱ አባይ ፀሀየና ሀሰን ሽፋ የሚባሉ ፋኖዎችን አቅፎ የያዘ ነበር።
ታዲያ የነተወልደ አንጃ ማህበርተኛ የነበሩት አባይና ሀሰን ከአንጃቸው ጋር የነበራቸው ቆይታ ዘላቂነት አልነበረውም። አባይ የነገሮችን ተለዋዋጭ አዝማሚያ ቃኝቶ ህሊናውንም ቢሆን በመሸጥ አሰላነፉን የሚያሳምር ሰው እንደሆነ በቤተ ወያኔ በስፋት የሚታወቅበት ባህሪው ነው። ለዚያም ይመስላል በ93ቱ ክፍፍል ወቅት የነተወልደን አንጃ አባላት እያናጠሉ እነመለስ ሎቢይ በሚያደርጉበት ወቅት፡ አንዱ ታጋይ «እኔ አባይን ላሳምን እንተ ደግሞ ሀሰን ሽፋን አሳምን» ባለው ጊዜ፡ መለስ የአባይን ባህሪ ጠንቅቆ ያውቅ ኖሮ «አባይን ግደፎ» ብሎ ለአንጃው ጓድ መለሰለት። ነገሩ አባይን «ተውት የትም አይደርስም አወቀዋለሁ» እንደ ማለት ነው። መለስ አባይ ሳይለመን ንፋሱን አይቶ በራሱ ጊዜ ወደ መለስ ጎራ እንደሚመለስ እርግጠና ነበር። ኋላ ላይ የሆነውን ያ ነው።
እንደተባለው ሆነ፤ ብዙም ሳይቆይ አባይ አይኑን አጥቦ የነ ተወልደን ስብስብ ከድቶ በመሄድ የመለስን አንጃ ተቀላቀለ። ወዶገብነቱ ሳያንሰው ግለሂስ አውርዶ የመለስን ቡራኬ አገኘ። ሀሰን ሽፋም አባይን ተከትሎ እነተወልደን በመተው ወደነመለስ ቡድን ተቀላቀለ። ሀሰን ሽፋ ግን እንደአባይ ወዶ ገብ ሳይሆን በነመለስ ቡድን ሎቢና ጠመንጃ ተገድሎ ምርኮኛ በመሆን ወደእናት ድርጅቱ ተመለሰ። ሀሰን ሽፋ ዛሬም ምርኮኛ ነው።
ተወልደ ወልደማርያም በወቅቱ የአባይና የሀሰን ሽፋን ወደመለስ ቡድን መኮብለል አስመልክቶ ለነሰነዘረለት ጥያቄ ሲመልስ «አባይ እንኳ ልማዱ ነው፤ ሀሰን ሽፋ ግን ለምን እንደከዳን አላውቅም» ብሎ መልሷል።
አባይ ጸሀዬ የስኳር ኮርፖሬሽን ሀላፊ ሆኖ «ሜቴክ» ከሚባለው የትግራይ ጀኔራሎች ኩባንያ ጋር ተመሳጥሮ 77 ቢሊዮን ብር የሚሆን የአገር ሀብት ለብክነትና ለዝርፊያ እንደዳረገ የስኳር ኮርፖሬሽን ሀላፊዎች ለፖርላማ አቅርበዋል። ስዩም መስፍንና ቤተሰቦቹ በዘረፋ ከኢትዮጵያ በላይ ሀብታሞች ሆነዋል። የስዩም መስፍን ልጅ በአፍሪካ ቀንድ አሉ ከሚባሉ የትግራይ ቱጃሮችና ዶላር ቢሊዮነሮች መካከልአንዱ ነው።
እነዚህ ሰዎች ናቸው እንግዲህ ሰሞኑን በወያኔ የፕሮፓጋንዳ ማሰራጫ ቀርበው ትኩስ በማይፈራው ምላሳቸው ቆርጠው እየቀጠሉ የወያኔን ድርጅት ከጅማሮው ጀምሮ ለኢትዮጵያ አንድነት ያለውን ቀናኢነትና ጠበቃነት የሚደሰኩሩት። እኛ ግን እናውቃለን። በመንግስትነት የተሰየመው ወያኔ የቅሚያ፣ የዘረፋና የግድያ ድርጅት እንደሆነ እናውቃለን። «ህገ መንግስት» እያሉ የሚደሰኩሩት ዝባዝንኪም ክፉና ትዕቢተኛ ፍላጎታቸውን በኢትዮጵያ ውስጥ ያለ ገደብ ለማስፈጸምና ለወንጀል ያቋቋሙት የሌብነትና የቅሚያ ደንብ እንደሆነ እናውቃለን። እውነታው ይሄ ነው። አበቃ!

↧

ከወልቃይት ዐማራ የማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የታሰረው ዐማራ በቂሊንጦ ተገደለ

$
0
0

ሙሉቀን ተስፋው
ወያኔ የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ አቅራቢ ኮሚቴዎችንና መላውን የዐማራ ሕዝብ በመግደል፣ በማሰርና በማሰደድ ጥያቄውን ለማፈን እየሞከረ ባለበት በአሁኑ ሰአት ከማንነት ጥያቄው ጋር በተያያዘ በቂሊንጦ ታስረው የነበሩ አቶ ይላቅ አቸነፍን ገድሎ ዛሬ አስከሬኑን አስረክቧል፡፡ አቶ ይላቅ አቸነፍ በላይ አርማጭሆ የትክል ድንጋይ ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ የወልቃይት ጠገዴ የዐማራ ማንነት ጥያቄን ይደግፋሉ ተብለው ከታሠሩ ሰዎች መካከል በዋነኛነት የሚጠቀሱ ነበሩ፡፡
የቂሊንጦን ማረሚያ ቤት በጥይት ገድሎና በእሳት ጠብሶ ካሰነበተ በኋላ ዛሬ አስከሬናቸውን አስረክቧል፡፡ የአቶ ይላቅ አቸነፍ ቀበር ሥነ ሥርዓት ከጎንደርና ከአርማጭሆ በተሰበሰቡ ዐማሮች በአሁኑ ሰአት (መስከረም 5 ቀን 2009 ዓ.ም.) እየተከናወነ ይገኛል፡፡
ወያኔ የኮሚቴ አባላቱን እያሳደደና እያገደለ የማንነት ጥያቄውን ማፈን እንደ ስትራቴጂ አሁንም ድረስ እየተከተለው ያለ ቢሆንም የዐማራ ሕዝብ ትግል ግን ያሸነፋል፡፡ ያለጥርጥር ትግላችን በተሰው ጀግኖቻችን ደም ወደ ፊት ይገሰግሳል፡፡

↧
↧

ከወልቃይት ዐማራ የማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የታሰረው ዐማራ በቂሊንጦ ተገደለ

$
0
0

ሙሉቀን ተስፋው
14344869_1197334543622376_2190956561404245985_n
ወያኔ የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ አቅራቢ ኮሚቴዎችንና መላውን የዐማራ ሕዝብ በመግደል፣ በማሰርና በማሰደድ ጥያቄውን ለማፈን እየሞከረ ባለበት በአሁኑ ሰአት ከማንነት ጥያቄው ጋር በተያያዘ በቂሊንጦ ታስረው የነበሩ አቶ ይላቅ አቸነፍን ገድሎ ዛሬ አስከሬኑን አስረክቧል፡፡ አቶ ይላቅ አቸነፍ በላይ አርማጭሆ የትክል ድንጋይ ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ የወልቃይት ጠገዴ የዐማራ ማንነት ጥያቄን ይደግፋሉ ተብለው ከታሠሩ ሰዎች መካከል በዋነኛነት የሚጠቀሱ ነበሩ፡፡
የቂሊንጦን ማረሚያ ቤት በጥይት ገድሎና በእሳት ጠብሶ ካሰነበተ በኋላ ዛሬ አስከሬናቸውን አስረክቧል፡፡ የአቶ ይላቅ አቸነፍ ቀበር ሥነ ሥርዓት ከጎንደርና ከአርማጭሆ በተሰበሰቡ ዐማሮች በአሁኑ ሰአት (መስከረም 5 ቀን 2009 ዓ.ም.) እየተከናወነ ይገኛል፡፡
ወያኔ የኮሚቴ አባላቱን እያሳደደና እያገደለ የማንነት ጥያቄውን ማፈን እንደ ስትራቴጂ አሁንም ድረስ እየተከተለው ያለ ቢሆንም የዐማራ ሕዝብ ትግል ግን ያሸነፋል፡፡ ያለጥርጥር ትግላችን በተሰው ጀግኖቻችን ደም ወደ ፊት ይገሰግሳል፡፡

↧

የመምህራን ዝምታ አስፈሪ ጩኸት ነው (በስዩም ተሾመ)

$
0
0

ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማህብረሰብ እየተሰጠ ያለው ስልጠና በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የወሊሶ ካምፓስ እንደቀጠለ ነው። ዛሬ ጠዋት ሊካሄድ የታቀደው የውይይት ፕሮግራም ነበር። ነገር ግን፣ መምህራኑ ሃሳብና አስተያየት እንዲሰጡ ሲጠይቁ ምላሻቸው ዝምታ ነበር። በአሰልጣኝነት የተመደቡት የመንግስት ኃላፊዎች “ኧረ እባካችሁ ተናገሩ?” እያለ ቢለምኑም ለመናገር ፍቃደኛ የሆነ መምህር አልነበረም። አንዱ አሰልጣኝ በሁኔታው ግራ በመጋባት “ባለፈው አመት ከእናንተ ጋር ተመሳሳይ ውይይት አድርጌያለሁ። ከመምህራን ጋራ የተደረጉ ውይይቶችን ስመራ ይሄ ሦስተኛዬ ነው። እንዲህ ያለ ነገር ግን አጋጥሞኝ አያውቅም” አለ። ነገር ግን፣ ለሁለት ሰዓታት ያህል የመምህራኑ ምላሽ ዝምም…ማለት ነበር። በመጨረሻም የሻይ-ሰዓት ሲደርስ ሁሉም በአንድ ድምፅ “የሻይ ዕረፍት!” ብለው ከስብሰባው ወጡ።
13769561_1005472749522045_1303864547072374891_n
ዶ/ር መረራ ጉዳና “ኢህአዴግ ማውራት እንጂ ማዳመጥ አይችልም” አሉ ይባላል። በእርግጥ መቼና የት እንዳሉት’ አላውቅም፡፡ የሃሳቡን ትክክለኝነት ማረጋገጥ ግን በጣም ቀላል ነው። ለዚህ ደግሞ ዛሬ የታዘብኩትን ነገር መጥቀስ በቂ ነው። መምህራኑ ለሁለት ሰዓታት ያህል በዝምታ ተቀምጠው እንደ ተማሪ የዕረፍት ሰዓታቸውን ሲናፍቁ ማየት በራሱ ይገርማል። እንደ አጠቃላይ ሲታይ ግን፣ መምህራን በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ሃሳብና አስተያየት እንዲሰጡ እየተለመኑ ዝም ማለታቸው ሰሚ ጠፍቶ እንጂ በራሱ ጩኸት ነው። 
በእርግጥ ማዳመጥ አለመቻል አንድ ችግር ነው። ማዳመጥ ለማይችል አካል መናገር ግን ከመጀመሪያው የባሰ ድንቁርና ነው። ኢህአዴግ ብዙ ግዜ ተነግሮት አንድም ግዜ በትክክል ማዳመጥ የተሳነው ድርጅት ነው። ስለዚህ፣ መምህራኑ ‘ማዳመጥ ለተሳነው ድርጅት መናገር ፋይዳ-ቢስ ነው’ በማለት ነው ዝምታን የመረጡት። በቦታው የነበሩ የመንግስት ኃላፊዎችም የሚሰጡት አስተያየት ይህን የሚያጠናክር ነው። ለምሳሌ በአሰልጣኝነት የተመደበው የመንግስት ኃላፊ “ከመምህራን ጋራ ተመሳሳይ ውይይቶችን ስመራ ይሄ ሦስተኛዬ ነው” ሲል፣ እኔ ደግሞ “ሁለቴ ነግረንህ ካልሰማህ ለምን ለሦስተኛ ግዜ እንነግርሃለን?” እያልኩ በውስጤ ስጮህ ነበር። 
በመምህርነት መስራት የጀመርኩት ከ1998 ዓ.ም ነው። ታዲያ በዚያኑ ዓመት ከ1997ቱ ምርጫ ጋር ተያይዞ በተፈጠረው ችግር ዙሪያ ለመወያየት በአከባቢው የሚገኙ መምህራንና የኦህዴድ/ኢህአዴግ ባለስልጣናት ስብሰባ ተቀምጠው ነበር። በወቅቱ ብዙም ልምድ ስላልነበረኝ እንደ አሁኑ ሃሳብና አስተያየት አልሰጥም ነበር። የረጅም አመት ልምድና ተሞክሮ የነበራቸው አንጋፋ መምህራን ግን “ኢህአዴግ ማውራት እንጂ መስራት የማይችል ድርጅት ነው” እያሉ ሲተቹት አስታውሳለሁ። 
ከ1998 – 2007 ዓ.ም ባሉት አስር አመታት በአመት ወይም በሁለት አመት የፓርቲ ይሁን የመንግስት የተምታታበት ስብሰባ መደረጉ አይቀርም። በእነዚህ ስብሰባዎች መምህራንም በሀገራቸው ጉዳይ ላይ ጠቃሚ የሚሏቸውን ሃሳቦችና አስተያየቶች ከመስጠት አይቆጠቡም። ምክንያቱም፣ የአንድ ሀገር ልማት፣ ሰላምና ዴሞክራሲ የመጨረሻ ግቡ የዜጎችን ነፃነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነው። የዜጎችን መብትና ነፃነት የሚጋፉ ሥራዎችና አሰራሮች እንዲሻሻሉ በመጠቆም ረገድ ደግሞ ምሁራን የማይተካ ድርሻ አላቸው። በዚህ ረገድ በ2007 የትምህርት ዘመን መጀመሪያ ላይ በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተሰጠው ተመሳሳይ ስልጠና በአብነት የሚጠቀስ ነው። 
መስከረም 2007 ዓ.ም ላይ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መምህራንና ሰራተኞች ጋር በተደረገው ውይይት ላይ የኢህአዴግ መንግስት ያሉበት ችግሮች እና የመፍትሄ እርምጃዎች በግልፅ የተጠቆሙበት መድረክ ነበር። በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ወደ አንድ ሺህ የሚጠጉ መምህራን በውይይቱ ተሳታፊ ነበሩ። በተለይ እኔ የነበርኩበት የውይይት ቡድን በአረዓያነት ሊጠቀስ የሚችል ነበር። የሕግ፣ የፖለቲካ ሳይንስ፣ የማህብረሰብ ሳይንስ፣ የፍልስፍና፣ የቋንቋ፣ የሕክምና፣ የሥራ አመራር፣…ወዘተ መምህራን ለአስር ቀናት ሲያደርጉ የነበረው ውይይትና ክርክር እጅግ በጣም ማራኪና አስተማሪ ነበረ። 
ኢህአዴግ፡ ከለውጥ እና ከሞት አንዱን ምረጥ በሚለው ፅሁፍ ውስጥ እንደተጠቀሰው በ2007ቱ ስልጠና ኢህአዴግ ለልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ስርዓት ግንባታ መሰረታዊ ችግሮች ይላቸው የነበሩት፡- “የመልካም አስተዳደር ችግር፣ ኪራይ ሰብሳቢነት፣ ትምክህት፣ ጠባብነትና አክራሪነት” ነበሩ። ታዲያ በውይይት መድረኩ ላይ፤ ኢህአዴግ በሚያስተዳድረው ሀገር ላይ “የመልካም አስተዳደር ችግር መኖሩ”፣ የፓርቲው አመራሮችና አባላቱ በሙስና ተዘፍቀው “የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከት ችግር አለ” ማለቱ፤ የአንድ ብሔር ወይም ሕዝብ መብትና ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ የሚጠይቁትን – “በጠባብነት”፣ ስለ ብሔራዊ አንድነት የሚያነሱትን – “በትምክህተኝነት”፣ ‘መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ-አይግባ’ ያሉትን – “በአክራሪነት” በመፈረጅ ኢህአዴግ ራሱ በራሱ የፈጠራቸው ችግሮች እንደሆኑ አስረግጠን ነገርነው።     
የአምቦ ዩኒቨርሲቲ መምህራን በኢህአዴግ ከተጠቀሱት ችግሮች ይልቅ ሕዝቡ በተጨባጭ እያነሳቸው ያሉትን ችግሮች በመዘርዘር በአስቸኳይ የመፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠየቁ። ከእነዚህ ውስጥ የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል፤ በወቅቱ በአምቦ ከተማ ለብዙ ሰዎች ሕይወትና ንብረት መጥፋት ምክንያት የሆነው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን የክልሉን ሕዝብና መንግስት አሳታፊ በሆነ መልኩ እስካልተዘጋጀ ድረስ ተግባራዊ እንዳይደረግ፣ በኦሮሚያ እና በአዲስ አበባ መካከል ከአገልግሎት አቅርቦትና የሃብት አጠቃቀም ጋር ተያይዞ በኢፊዴሪ ሕገ-መንግስት አንቀፅ 49(5) መሰረት ዝርዝር የሕግ ማዕቀፍ እንዲዘጋጅ፣ በመሰረተ-ልማት ግንባታ ሰበብ የአርሶ-አደሮች ከመሬት ይዞታቸው ማፈናቀል እንዲቆም፣ መንግስት ራሱ ለሕገ-መንግስታዊ ሥርዓቱ ተገዢ በመሆን ለህግ የበላይነት ተገዢ እንዲሆን፣ የሕገ መንግስቱን መርሆች የሚፃረሩና የዜጎችን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የሚገድቡ የህግ አንቀፆች፣ መመሪያዎች እና አሰራሮች መስተካከል እንዳለባቸው፣ የመንግስት ሥራና የአሰራር ሂደት ግልፅነትና ተጠያቂነት እንዲኖረው … ወዘተ ናቸው። 
ነገር ግን ኢህአዴግ ከመምህራኑ የቀረቡትን የመፍትሄ ሃሳቦች አንዱንም አንኳን ተግባራዊ አላደረገም። ኢህአዴግ በመምህራኑ ከተሰጡት የመፍትሄ ሃሳቦች በተቃራኒ አቅጣጫ መሄዱን ቀጠለበት። የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ መሻሻል አለበት ሲባል የኮምፒውተር ወንጀል አዋጅን አፀደቀ። ሀገራዊ ምርጫን ከ99.6% ወደ 100% አሳደገ። ዴሞክራሲን ስንጠይቅ አምባገነንነትን አሰፈነብን። ነፃነትን ለጠየቀ ሕዝብ ፍርሃትን ለቀቀበት። በመጨረሻም መብቱንና ነፃነቱን ለማስከበር ባዶ እጁን አደባባይ የወጣን ሕዝብ እንደ ጠላት በጥይት ይገድለው፣ ያለ ርህራሄ ይደበድበው፣ ያለ ፍርድ ያስረው ጀመር። 
በዚህ ምክንያት በሀገሪቱ ግጭትና አለመረጋጋት ነገሰ። አንደተለመደው ኢህአዴግ በሀገሪቱ በተከሰተው ግጭትና አለመረጋጋት ዙሪያ ከመምህራን ጋር ለመወያየት እንኳን አይደለም “ስልጠና” ልስጥ ብሎ መጣ። በ2009 ዓ.ም ለልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ስርዓት ግንባታ ችግሮች ናቸው በማለት ምን ይዞ መጣ? በ2007 ዓ.ም ኢህአዴግ ራሱ በራሱ የፈጠራቸውን፡-“የመልካም አስተዳደር፣ ኪራይ ሰብሳቢነት፣ ትምክህት፣ ጠባብነትና አክራሪነት” የፈጣሪ ያለህ!!! ታዲያ ከዚህ ጋር ማን ይነጋገራል??? 
አዎ…ኢህአዴግ ይናገራል እንጂ አያዳምጥም። የመምህራን ዝምታ ግን ጩኸት ነው። ከውጪ ሳይሆን ከውስጥ የሚሰማ ድምፅ ነው፣ ከሌላ ሳይሆን ከራስ ጋር የሚያወሩት። በጆሮ የሚሰሙት ሳይሆን በህሊና የሚያስቡት፣ መልስ ሳይሆን ጥያቄ ነው። ዝምታ “ለምን ዝም አሉኝ?” ብሎ መጠየቅ ነው። ይህን ጥያቄ ስታብሰለስል ጩኸቱ ይሰማሃል፣ የመምህራኑ ጭንቀት ይገባሃል። ባለፉት አመታት የሰራኸው ስህተት በግልፅ ይታይሃል። አዎ…በደንብ ላስተዋለው የመምህራኑ ዝምታ አስፈሪ ጩኸት ነው!! 
With Regards,
Seyoum T.
Ambo University, Woliso Campus
Dept. of Management
Tel: +251911320447
Email: seyee123@gmail.com
Blog: http://ethiothinkthank.com or http://hornaffairs.com/am/author/seyoumteshome/

↧

Video: ኢትዮጵያን ዛሬም ያለቅሳሉ

↧

የኮንሶዎች ጥያቄ፤ ግጭትና ጥፋት

$
0
0

ሰሞኑን ደግሞ ፀጥታ አስከባሪዎች ጥያቄ ያቀረበዉን ሕዝብ አስተባብረዋል ባሏቸዉ ሰዎች ላይ እርምጃ በመዉሰዳቸዉ ግጭት ተከስቷል።በግጭቱ በርካታ ሰዎች መገደላቸዉን፤ ቤትና ንብረት መጥፋቱን የአይን ምስክሮችና ፖለቲከኞች አስታዉቀዋል
konso

ደቡብ ኢትዮጵያ የኮንሶ ወረዳ ነዋሪዎች ያነሱት የማንነትና የአስተዳደር ጥያቄ ሰሞኑን ደም አፋሳሽ ዉዝግብና ግጭት አስከትሏል።የአካባቢዉ ነዋሪዎች እንደሚሉት የኮንሶ ሕዝብ ከዚሕ ቀደም አካባቢዉ የነበረዉ የልዩ ወረዳ የአስተዳደር ሥልጣን እንዲመለስለት በተለያየ ደረጃ ለሚገኙ የክልልንና የፌደራል መንግስት መስሪያ ቤቶች አቤቱታ አቅርቦ ነበር።አቤቱታዉ ግን ሰሚ አላገኘም።ሰሞኑን ደግሞ ፀጥታ አስከባሪዎች ጥያቄ ያቀረበዉን ሕዝብ አስተባብረዋል ባሏቸዉ ሰዎች ላይ እርምጃ በመዉሰዳቸዉ ግጭት ተከስቷል።በግጭቱ በርካታ ሰዎች መገደላቸዉን፤ ቤትና ንብረት መጥፋቱን የአይን ምስክሮችና ፖለቲከኞች አስታዉቀዋል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር የኦሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባር ሊቀመንርን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

——————————————–
እዚያዉ ኮንሶ የሚገኙ ነዋሪዎችም ሰሞኑን የተነሳዉ ግጭት ከባድ ጉዳት መድረሱን ይናገራሉ።ለአጭር ጊዜ ልምምድ አብሮን የሚገኘዉ ተስፋአለም ወልደየስ ያነጋገራቸዉ የአይን ምስክሮች እንደሚሉት የመንግሥት ፀጥታ አስከባሪዎች በርካታ ሰዎችን ገድለዋል።ቤትና ንብረት አቃጥለዋልም።የኮንሶ ሕዝብ ጥያቄ ለመንግሥት አካል እንዲያቀርብ የተሰየመዉ ኮሚቴ አባልንም አነጋረናል። የደቡብ መስተዳድር ባለሥልጣናትም ግጭትና ጥፋት መድረሱን አምነዋል።

በኮንሶ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት እና በግጭቱ የደረሰውን ጉዳት የተመለከቱት አቶ ዕድሉ አይለቴ ጳጉሜ 5 የተቀሰቀሰው ግጭት እስካሁንም ቀጥሏል ይላሉ፡፡ በግጭቱ ምክንያት የጠፋውን ህይወት እና ሁኔታውን በዝርዝር ያስረዳሉ፡፡

የደቡብ ክልል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሒክማ ከይረዲን ግጭቱ እንደነበር ቢያምኑም የጉዳቱ መጠን በዓይን እማኞች ከተገለጸው ያነሰ እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡

በኮንሶ ከዞን ይገባኛል ጥያቄ ጋር በተያያዘ ባለፈው ዓመትም ተመሳሳይ ደም አፋሳሽ ግጭት ተከስቶ ነበር፡፡ የሰሞኑ ግጭት መንስኤ ግን በአካባቢው ባለስልጣናት ለረጅም ጊዜ ሲቀናበር የቆየ እና በአጎራባች ወረዳዎች ተሳትፎ የታገዘ እንደነበር የዞን ጥያቄው አስተባባሪ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ገመቹ ገንፌ ይናገራሉ፡፡

አቶ ገመቹ በኮንሶዎች ላይ ያነጣጠረ ነው ባሉት ጥቃት “የመከላከያ ሰራዊት እና የጸጥታ ኃይሎች ተሳትፈዋል” ይላሉ። የክልሉ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ግን ክሱን ያጣጥሉታል፡፡ እንደውም ለግጭቱ መነሻነት ኮሚቴውን ተጠያቂ ያደርጋሉ፡፡

ኮንሶ አሁንም በውጥረት ላይ ትገኛለች፡፡ ነዋሪዋቿ 23 አባላት ባሉት ኮሚቴ አማካኝነት ለፌደሬሽን ምክር ቤት ያቀረቡት ጥያቄም በእንጥልጥል ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ ወር መጨረሻ ላይ ስብሰባውን ያካሄዳል ተብሎ የሚጠበቀው የፌደሬሽን ምክር ቤት ጉዳዩን ተመልክቶ መፍትሄ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ተስፋዓለም ወልደየስ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

source:-dw.com/

↧
↧

በምዕራብ በለሳና በወገራ አካባቢ በተነሳው ግጭት የሞቱ የወያኔ ወታደሮች 30 ደርሰዋል

$
0
0
File Photo

File Photo

ከሙሉቀን ተስፋው

የወገራንና የበለሳን ዐማራ ትጥቅ ለማስፈታት በሁለት ዙር የተንቀሳቀሰው የወያኔ ጦር ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ወድሟል። የሞቱ የጠላት ወታደሮች 30 ሲደርስ 15 የተማረኩት በሕይወት በሕዝብ ቁጥጥር ስር ናቸው። ከገበሬዎች በኩል 3 ቆስለዋል። 41 ክላሽና መትረጊስ ተማርኳል።

አመሻሹን ብዛት ያለው የወያኔ ጦር ወደ ቦታው የተንቀሳቀሰ ሲሆን ገበሬዎች ሸሽተን ኃይላችን በማደራጀት ላይ ነን ብለዋል።

ይህን ጉዳይ እየተከታተልን እናሳውቃለን::

↧

ድምጻዊ ኤሊያስ ተባባል አዲስ የትግል ነጠላ ዜማ ለቀቀ –“ወልቃይትን እንቁልጭልጭ….አማራው አያይም ሲገደል ኦሮሞ”

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ከነመሰንቆው የምታውቁት አንጋፋው ድምጻዊ ኤሊያስ ተባባል በወቅታዊው የአማራ እና የኦሮሞ ሕዝብ ትግል ዙሪያ የሚያጠነጥን አዲስ የትግል ነጠላ ዜማ ለቀቀ:: የጎንደር አማራ ሕዝብ ወልቃይትን አላስነካም በሚል ስለመታገሉና በኦሮሞ እና አማራ ህዝቦች መካከል ስላለው የደም አንድነት የሚያጠነጥነው ይኸው ነጠላ ዜማ
“ወልቃይትን እንቁልጭልጭ
ጠገዴን እንቁልጭልጭ
አርማጭሆን እንቁልጭልጭ
አላስነካም ብሏል ጀግናው እኔ ተቀምጬ” የሚል ስንኝም አለው:: ያድምጡትና አስተያየትዎን ያስፍሩ::

አንጋፋው ድምጻዊ ኤሊያስ ተባባል አዲስ የትግል ነጠላ ዜማ ለቀቀ – “ወልቃይትን እንቁልጭልጭ….አማራው አያይም ሲገደል ኦሮሞ” ይላል

↧

አትሌት ሙሉጌታ ዘውዴ በከፍተኛ ችግርና በህመም ላይ እንደሚገኝ ገለጸ

$
0
0

መስከረም ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም

14291888_1736777826574391_2927463673673526476_nኢሳት ዜና :- ከሁለት ዓመታት በፊት በኖርዌይ በተደረገ ተደጋጋሚ የማራቶን ሩጫ ኢትዮጵያን ወክሎ በመወዳደር አንደኛ የወጣውና የአሸናፊነት ገመዱን ሲበጥስ ሁለት እጆቹን ወደ ላይ በማጣመር የተቃውሞ ምልክት ያሳየው አትሌት ሙሉጌታ ዘውዴ በክፍተኛ ችግርና በህመም ላይ እንደሚገኝ ገለጸ።
በኖርዌይ በስደት የሚገኘው አትሌት ሙሉጌታ ለሁለት ጊዜ በተደረገ የማራቶን ውድድር ነበር ሁለት ጊዜ የኢሳትን ቲሸርት ለብሶ በመሮጥ ያሸነፈው።
ውድድሩንም ከማሸነፉ ባሻገር በማጠናቀቂያው መስመር ላይ እጆቹን ወደ ላይ በማጣመርና የኢትዮጵያን መንግስት በመቃወም በነጻነት ትግሉ ላይ ችቦ የለኮሰ ፈር ቀዳጅ አትሌት
ነው-ሙሉጌታ። አትሌት ሙሉጌታ ከኢሳት ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ በአትሌቲክሱ ዘርፍ እሱ የለኮሰው ችቦ እነ ፈይሳ ሌሊሳ ተረክበው በሪዮ ኦሎምፒክ ከፍ አድርጎ ሲያበሩት መመልከቱ ልዩ ደስታን እንደሰጠው ተናግሯል። ይሁንና ይህ የትግል ቀንዲል የሆነው አትሌት ዛሬ በከፋ ችግር ውስጥ ይገኛል።
አትሌቱ እንደገለጸው ከሰራው ልምምድ ጋር በተያያዘ ለልብ ህመም መጋለጡ በሀኪም ቢነገረውም በቂ ህክምና ሊያገኝ አልቻለም።
እንዲሁም ደጋፍና በቂ ህክምና ሊያገኝ ባለመቻሉ ሳቢያ የመጣውን ለመቀበል በመፍቀድ ወደ ሀገሩ እንዲልኩት የኖርዌይን መንግስት እስከመጠየቅ መድረሱን የገለጸው አትሌት ሙሉጌታ፤ሆኖም የኢትዮጵያ መንግስት “አትሌቱ አሸባሪ ስለሆነ አልቀበልም” የሚል ምላሽ መስጠቱን ጠቅሷል።
14329894_1736777769907730_1874380211098015751_nይህ ሁሉ ቢሆንም የኖርዌይ መንግስት የመኖሪያ ፈቃድ ሊሰጠው አልቻለም።
ጠበቃ በማቆም ያደረገው ክርክርም ውጤት ሊያሥገኝለት እንዳልቻለ ያመለከተው ሙሉጌታ፤ ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ በሚችሉት ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርጉለት ተማጽኗል።

↧

አባይ ፀሐዬ –አሰቃቂው የሩዋንዳ ዘር ፍጅት ናፋ

$
0
0

ታሪኩ አባዳማ መስከረም 2009

እውቁ እና ዝነኛው የጭፍጨፋ መሀንዲስ አባይ ፀሐዬ በንፁሀን ዜጎች ላይ ህወሀት እያካሄደ ያለውን ፍጅት እጥፍ አሳድጎ አንደሚቀጥል በማረጋገጥ ለሌላ ዙር ጅምላ ጭፍጨፋ እንድንዘጋጅ በማያሻማ ቋንቋ ነግሮናል። አባይ ፀሐዬ በአዲሱ አመት መግቢያ ላይ በሰጠው ቃለ ምልልስ እንዳመለከተው ህወሀትን ለማስወገድ የሚካሄደው ህዝባዊ ተቃውሞ ከቀጠለ አገሪቱን እስከ ወዲያኛው መበታተን የሚያደርስ ጭፍጨፋ ይመጣል። በዚህም ሩዋንዳ ላይ ሁቱ ጎሳ በቱትሲ ወገኑ ላይ ያደረሰውን ዘር ላይ የተመረኮዘ ዘግናኝ ጅምላ ጭፍጨፋ በማጣቀስ ኢትዮጵያ ተመሳሳይ እጣ እንደሚጠብቃት ምኞቱን እና እቅዱን በይፋ ግልፅ አድርጓል። አባይ ፀሐዬ እስከ ዛሬ የጠጣው የንፁሀን ደም አላረካ ብሎት ስለ ቀጣዩ ጅምላ ጭፍጨፋ የተነበየውን ቃለ መጠይቅ ከዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ማዳመጥ ይቻላል http://www.ethiomedia.com/1016notes/7451.html ይህ የእልቂት ጥሪ ጭብጥ የሆነ በማይፋቅ እና በማይክዱት ሰነድ ላይ የተመዘገበ ከፍተኛ የወንጀል ስራ ዝግጅት ማስረጃ ነው። ትናንት ልክ እናስገባቹሀለን ብሎ የዛተው ቀንደኛ የህወሀት ፖለቲካ መሀንዲስ ቃል ነው። ህወሀት ምን እየደገሰልን እንደሆነ መሪው በማያሻማ ቋንቋ የመሰከረበት ሰነድ ነው። አባይ ፀሐዬ በዚህ ግልፅ በሆነ ጥሪው የዘር ጭፍጨፋ ሩዋንዳ እንደደረሰው ሁሉ ኢትዮጵያም ይደገማል ብሎናል። የህወሀት ጭፍጨፋ ድርጅቱ ከተመሰረተበት እና በተለይም የመንግስት ስልጣን ከተቆጣጠረበት ጊዜ አንስቶ አላባራም። በተለይም ካለፈው አንድ አመት ወዲህ የጭፍጨፋው አድማስ ሰፍቶ ዜጎች በዘር ግንዳቸው ብቻ እየተመረጡ በመጨፍጨፍ ላይ መሆናቸወን አለም የሚመሰክረው ነው። እናም ሰውየው በንፁሀን ዜጎች ደም የሰከረ እንደመሆኑ ዛሬ ለምን ይህን ተናገረ ብሎ የሚደነቅ የለም። ይልቁንም የተደገሰልንን ሌላ ጅምላ ጭፍጨፋ ዘርዘር ባለ መልኩ እሱ ራሱ ከሰጠው የሩዋንዳ ጀኖሳይድ እልቂት አንፃር ብንመረምረው የተሻለ ስዕል ይሰጠናል በሚል እምነት አጠር ያለ ቅኝት ለማድረግ ወደድኩ።

abay Tsehaye
ለመሆኑ ሩዋንዳ የደረሰው ጭፍጨፋ በምን ፣ እንዴት እና በማን እንደ ነበር እነ አባይ ፀሐዬ ይስቱታል? በሩዋንዳ የደረሰው ፍጅት እንዲህ ነበር – አንድ በስልጣን ላይ የቆየ ጎሳ/ ዘር (ብሄረሰብ) (ሁቱ) በበታችነት በሚያየው በሌላው ዝርያ የሩዋንዳ ጎሳ/ ዘር (ብሔረሰብ) (ቱትሲ) ላይ የተካሄደ ዘር ላይ የተመረኮዘ ጭፍጨፋ ተካሄደ። ጭፍጨፋውን ያቀደው ፣ የመራው እና የፈፀመው በዘር ማንነት ላይ ተደራጅቶ እና ታጥቆ አገሪቱን ይቆጣጠር የነበረው ከሁቱ ጎሳ የመጣው የሩዋንዳ ጎሳ ፖለቲከኛ ፣ ወታደር ፣ ጋዜጠኛ ፣ ሚሊሺያ እና ሌላውም ተራ የሁቱ ዘር ዜጋ ነው። በሁቱ ዘር የበላይነት ስልጣን ለብቻው ሲቆጣጠር የቆየው ሀይል ከስልጣን ተገልሎ የነበረውን እና ፍትሀዊ የስልጣን ክፍፍል የጠየቀውን የቱትሲ ዘር ጨፈጨፈው ፤ የታጠቀው የሁቱ ዘር ያልታጠቀውን የቱትሲ ዘር ፈጀው ፤ ያገሪቱን የሩዋንዳን ጥሬ ሀብት በብቸኝነት ይቆጣጠር የነበረው የሁቱ ዘር ከፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል የተገለለውን የቱትሲ ዘር በጥይት ፣ ገጀራ ፣ አካፋ እና መጥረቢያ ሳይቀር እጁ ላይ ባገኘው መሳሪያ ተጠቀቅሞ ረፈረፈው። በጊዜው ጉልበተኛ የነበረው ሁቱ ርህራሄ የጎደለው ጭፍጨፋ አካሄደ። ዘግናኙን እና አለምን ያሸማቀቀው ጭፍጨፋ የተካሄደው ቀድሞውኑ በዘር ተደራጅተው ፣ ነቅተው እና ታጥቀው በተደራጁ የሁቱ ጎሳ ሩዋንዳውያን ነበር። የተቆጣጠሩትን የመንግስት ስልጣን ከለላ በማድረግ ያገሪቱን ሀብት በብቸኝነት ከመዝረፍ በላይ በወቅቱ የነበረውን ወታደራዊ ተቋም ሙሉ ለሙሉ ሲቆጣጠር የቆየው ካንድ ዘር ከሁቱ የመጣው ወገን ነበር። ከዚህ አልፎ ተርፎ በአገሪቱ የሚሰራጩትን የራዲዮ ፣ የቴሌቪዥን እና ጋዜጣ ባጠቃላይ የነበረውን የመገናኛ አውታር ይቆጣጠር የነበረው ይኸው የሁቱ ዘር ነው። ሁሉም ነገር በዘር ግንድ በተደራጁት ከሁቱ ብሔረሰብ በመጡ ሩዋንዳውያን ቁጥጥር ስር ውሏል። በሚለየን የሚጠጉ ቱትሲዎች በጠራራ ፀሀይ ሲጨፈጨፉ እነኝህ ከፍ ሲል የተጠቀሱት በሁቱ ዘር ቁጥጥር ስር የነበሩት የመንግስት ልዩ ልዩ ዘርፎች ሙሉ ለሙሉ ጭፍጨፋውን በማቀላጠፍ ተሳትፈዋል። እንግዲህ ይህን ዘር ላይ የተመረኮዘ ፍጅት እንደ ምሳሌ ጠቅሶ ኢትዮጵያ ላይ ይደገማል የሚል ሰው ያውም ዛሬ ቁልፍ ስልጣን ላይ የተቀመጠ ብሎም በዘር ማንነት ተደራጅቶ የታጠቀ ሀይል መሪ ምን ሊነግረን እንደፈለገ ለመገንዘብ የፖለቲካ ሳይንስ ተመራማሪ መሆን አይጠይቅም። ስል ሩዋንዳ ጭፍጨፋ ስናስብ እጅግ ዘግናኝ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ሁቱዎች በቱትሲዎች ላይ ሲዘምቱ የሚገድሉትን ሰው ይመርጡ የነበረው በቂም ፣ በቁጭት ፣ በፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ሳይሆን ሌላ ዘር በመሆኑ ብቻ መሆኑ ነው። በዚህም የተነሳ ቡና አጣጭ ጎረቤታቸውን ፣ የስራ ባልደረባቸውን ፣ በመልኩ እና ቁመናው ቱትሲ ሆኖ ያገኙትን ሁሉ ሰለባ አድርገዋል። አንድ የቱትሲ ብሔረሰብ አባል ሁቱዎች በበላይነት ይቆጣጠሩት በነበረው የሩዋንዳ ፖለቲካ ህይወት ውስጥ ተሳትፎ ይኑረው አይኑረው ፣ የተቀዋሚ ድርጅት ደጋፊ ይሁን አይሁን ፣ የሁቱ አባል የሆነ ጓደኛ ወይንም የንግድ ሽርክ ይኑረው አይኑረው ቱትሲ በመሆኑ ብቻ የጭፍጨፋው ሰለባ ከመሆን ማምለጥ አይችልም –
የሌላ ብሔረሰብ አባል በመሆኑ ብቻ እንደ ወንጀል ተቆጥሮ ግድያ ይፈፀምበታል
እንግዲህ አባይ ፀሐዬ በቃለ መጠይቁ እንዳሰመረበት የደገሰልን ፍጅት ይህን እንደሚመስል በማያሻማ ቋንቋ ነግሮናል። ህወሀት እስከ አፍንጫው የታጠቀ የዘር ድርጅት እንደ መሆኑ እንደ አባይ ፀሐዬ አባባል ከሆነ እንደ ሩዋንዳ አይነት ጭፍጨፋ ከተደረገ በአብላጫው ሰለባ የሚሆነው ማን ሊሆን ነው ብሎ ለማወቅ ሩቅ መሄድ አያሻም። ባዶ እጁን ለመብቱ መረጋገጥ ጥያቄ ያነሳ ሁሉ በነ አባይ ፀሀዬ የፍጅት ራዳር ውስጥ ተነጣጥሮበታል። ህወሀት በዘር ተዋቅሯል ፣ ተደራጅቷል ፣ እስከ አፍንጫው ታጥቋል። ብሎም ህወሀት የመንግስት ስልጣኑን ተቆጣጥሯል ፣ ህወሀት ወታደራዊ ተቋማትን ተቆጣጥሯል ፣ ህወሀት ቁልፍ የሚባሉ የኢኮኖሚ ምንጮችን ተቆጣጥሯል ፣ ህወሀት ሁሉንም የመገናኛ አውታሮች ተቆጣጥሯል። ሌላ ቀርቶ ከህወሀት ተዋጊ ሰራዊት ተቀንሶ ወደ ሲቪል ህይወት የተቀላቀለው ተዋጊ ሙሉ ትጥቁን እንደያዘ ከአዲስ አበባ እስከ ሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች ባለ መሬት እና ባለ ሀብት ሆኖ በተጠንቀቅ ተሰልፏል። ስለ ሩዋንዳ የዘር ጭፍጨፋ የሚነግረን እና ኢትዮጵያ ላይ ይደገማል የሚለን አባይ ፀሐዬ የህወሀት መሪ ነው። የህወሀትን ራዕይ በገለፀልን ቃለ መጠይቁ ግልፅ እንዳደረገው ሁሉ ሩዋንዳ ይደገማል ብሎናል። ማን በማን ላይ ፍጅት እየደገሰ መሆኑን ግልፅ ያደረገ ቃለ መጠይቅ ነው። ህወሀት የትግራይን ህዝብ ከለላ አድርጎ እንደ ሁቱ ሁሉ በዘር መደራጀቱ ለማንም ሚስጥር አይደለም። እናም በዘር ታጥቋል ፣ በዘር ምርኩዝ የአገሪቱን ሀብት አግበስብሶ እጁ አስገብቷል ፣ በዘር ቅኝት የሚመራ መገናኛ አውታር በእጁ ነው። በተቃራኒው ዛሬ ባዶ እጁን አደባባይ ተሰልፎ በሰላማዊ መንገድ ስለ መብቱ የሚሟገተው ዜጋ እጁ ላይ ትጥቅ የለም ፣ የሚቆጣጠረው አንዳችም ቅርስ የለም ፣ መሬቱን ተዘርፏል ፣ መብቱ ተረግጧል ፣ የፍትህ ያለ ይላል ፣ ሀሳቡን በነፃ ሊገልፅ የሚችልበት አንዳችም አውታር ወይንም አሰራር የለም። የህግ የበላይነት እንጂ ያንድ ዘር የበላይነት አይበጀንም ብሎ መነሳት የሩዋንዳን አይነት ጭፍጨፋ የሚጋብዝበት ምክንያት ምን እንደሆነ ለመረዳት በጣም ያዳግታል። እንደ አባይ ፀሐዬ ምኞት የሩዋንዳ አይነት ጭፍጨፋ ኢትዮጵያ ውስጥ ቢፈፀም ያንን ጭፍጨፋ ማን በማን ላይ ሊያካሂድ በዝግጅት ላይ እንዳለ በቀላሉ ማመልከት ይቻላል። ታጥቀናል እንፈጃቹሀለን – ልክ እናስገባቹሀለን እየተባልን ነው። ጉዳዩ ኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆኑ ሰላም ወዳድ የሆነው የአለም ህዝብ ይህን እብደት ባስቸኳይ ማስቆም አለባቸው። ዘር ላይ የተመረኮዘው የሩዋንዳ ጭፍጨፋ ከቶውንም የሚጠየፉት ፣ የሚያርቁት እና በምንም ምክንያት በየትኛውም የአለም ክፍል እንዳይደገም ማናቸውንም ጥረት ማድረግ የሁሉም ሰው ዘር ሀላፊነት ነው – ከአባይ ፀሐዬ በስተቀር። በተለይ መልዕክቱ በቀጥታ የሚመለከተው የኢትዮጵያ ህዝብ በውስጥም ሆነ ውጪ ይህን እርኩስ የእልቂት ድግስ ለማምከን በሁሉም ዘርፍ መታገል አለብን። ናዚ ጀርመን ስለ ዘር ጥራት እና ሰለ አርያን ዝርያ ሀያልነት ሲሰብክ የጀርመንን ህዝብ ሸንግሎት ይሆናል። በዚህ የተነሳም ናዚ ፓርቲ ከጀርመን ህዝብ ቀላል የማይባል ፖለቲካዊ ድጋፍ አግኝቷል። ይሁንና የአለም ህዝብ ጀርመናውያን መጥፎ ዘሮች ናቸው ከሚል ድምዳሜ ላይ አልደረሰም። በመሰረቱ መጥፎ የፖለቲካ ድርጅት ፣ መጥፎ የፖለቲካ አመለካከት ፣ መጥፎ አስተዳደር እንጂ መጥፎ ህዝብ ወይንም መጥፎ (ጥሩ) የሚባል የዘር ክፍፍል የለም። ህወሀት በወገናችን በትግራይ ህዝብ ስም መደራጀቱ እና ፀረ አገር ድርጊት እየፈፀመ መሆኑ ግልፅ ቢሆንም የትግራይን ህዝብ ኢትዮጵያዊ ታሪክ የሚያጠቁር አይሆንም። የተጋፈጥነው ከመጥፎ ትግራዋይ ሳይሆን ከመጥፎ ህወሀት ጋር ነው ፤ ከመጥፎ ፣ ከሌባ እና ከዘራፊ ድርጅት ጋር ነው። ትግሉ መጥፎ አስተዳደር ፣ መጥፎ የፖለቲካ ድርጅት ፣ መጥፎ የዘር አደረጃጀት ከሚከተለው ህወሀት ጋር ነው።‘ ’ ህወሀት ሌባ እያለ ለመብቱ የሚዋደቀው ኢትዮጵያዊ ጣቱን በቀጥታ የቀሰረው እና በሀላፊነት የሚጠይቀው ህወሀትን እና ህወሀትን ብቻ ነው። ይህ ለማንኛውም ትግራዋይ ግልፅ ሊሆን ይገባዋል። ጨዋነትህን የሚያረክስ ፣ ሰላማዊነትህን የሚያደፈርስ ፣ አገር ወዳድነትህን የሚያጣይቅ ባጠቃላይ ኢትዮጵያዊ ተፈጥሮህን የሚፃረር ድርጊት በስምህ እንዳይፈፀም በግንባር ቀደምነትነት ተሰልፈህ የህግ የበላይነት እውን እንዲሆን መታገል ይኖርብሀል። በትግሉ ውስጥ በምታደርገው ተሳትፎ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደቀድሞው ሁሉ ችግርህን ፣ ደስታህን እና ድልህን ለጋራ ቤታችን ፅናት ሲል አብሮህ መቆሙን በተደጋጋሚ አረጋግጧል። የትግራይ ህዝብ ሆይ! ታሪክ ይቅር የማይለውን የሩዋንዳ አይነት የዘር ጭፍጨፋ የሚመኙልንን እብድ ውሾች ከመካከልህ ጠራርገህ አውጣ።

↧
↧

ካሚል ሸምሱ እውነት ነጻ ያወጣችው ጀግና (በሱፈቃድ ደረጀ)

$
0
0

በሱፈቃድ ደረጀ
(besufekadreje@gmail.com)
እውነትን መናገር ለራስ ነው
የሚያምኑበትን ሳይናገሩ ከመኖር ይሰውረን!!!
ከአንድ አመት በፊት ልክ በዛሬዋ እለት ስለ ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ የማውቀውን ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ እስከ ቂሊንጦ በሚል ርእስ አንዲት ጽሁፍ ጀባ ብዬ ነበር፤ ዛሬ ደግሞ እነ ካሚል ሸምሱ ከቂሊንጦ ቃሊቲ ከዛም ወደ ቤተሰብ ተቀላቅለዋል፤ ደስ የሚያሰኝ ዜና ነው፤
በርካታ ጓደኞቼን ስለ ካሚል ሳጫውታቸው በቅድሚያ ግራና ቀኛቸውን ይመለታሉ፣ ይቀጥሉና አንገታቸውን እስቲሰበር ድረስ ወደ ኋላቸው ገልመጥ ይላሉ፣ ይቀጥሉና የአግአዚ ስናይፐር እንዳይመታቸው ይመስል ወይንም ነፍሴን አደራ በሰማይ በሚመስል መልኩ ሽቅብ ያንጋጥጣሉ፣ በመጨረሻም ራሴውኑ በጥርጣሬ አይን ይመለከቱና ስለ ካሚል ሸምሱ ያላቸውን አስተያየት በሹክሹክታ ይነግሩኛል፤
ብሽቅ ብዬ ትቻቸው ልሄድ ስልም ምክንያታቸውን ይገልጹልኛል፣ ‹ምን ነካህ አብረውን የተማሩት እነ እከሌ እከሊት እኮ የማእከላዊ ባልደረባ ሆነዋል፣ እነ እንትና እኮ የደህንነቱን መስሪያ ቤት ከሚያሾሩት ውስጥ ይመደባሉ፣ በዛ ላይ ደግሞ ባለትዳርና የልጆች አባት ነኝ› ሲሉ ይደመጣሉ፤ እንዲህ አካባቢያቸውን በአይነ ቁራኛነት ሲከታተሉ ሳይ አዝኜላቸዋለው፤ በአንጻሩ ደግሞ ለመብቱ መከበር ሲል ዋጋ የከፈለውንና ድል ያደረገውን ካሚል ሸምሱን ሳስብ ሀገራችን ሰው እንዳላጣች ማረጋገጫ ይሆነኝና እጽናናለው፤
ወዳጄ ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ የነጻነት ምልክት ሆነሀልና እንኳን ደስ አለህ! ከምትወዳቸው ቤተሰቦችህ ለመቀላቀል እንኳን አበቃህ፤ ከባለቤትህ ጋር ምን ያህል እንደምትዋደዱ አውቃለው፤ ካምፓስ እያለን ባለቤትህ ውጭ አገር ሆና ስትደውልልህ ‹ተራርቀን እስከመቼ ?› ተባብላቹሁ የተላቀሳችሁበትን ጊዜ አስታውሳለው፤ ባለቤትህም እንኳን ከልደታ-ቂሊንጦ-ቃሊቲ ከመመላለስ አረፈች፤ አላህ እንኳን አንድ አደረጋችሁ!!!
በነገራችን ላይ ከሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች መካከል በቀዳማይ ሚኒስትራችን አይተ መለስ ዜናዊ ጥርስ የገባ ሰው ቢኖር ካሚል ሸምሱ ነበር፤ ይህንንም በአፍ ወለምታ የምናገረው ሳይሆን በማስረጃ ነው፤ ካሚል ሸምሱ በተለያየ ጊዜ ለሙስሊሙ ህብረተሰብ መፍትሄ ለማፈላለግ ባደረገው ጥረት በርካታ ስብሰባዎችን መርቷል፤ ታዋቂው ደራሲ አሌክስ አብርሀም ካሚል በሻሸመኔ ከተማ ተገኝቶ ህገ መንግስቱን የተመረኮዘ ማብራሪያ ሲተረጉም የሚያሳይ ምስል በመጽሀፈ ገፁ ለጥፎ ተመልክተናል፤
ካሚል ሸምሱ በተደጋጋሚ የሚናገረው አንድ ኃይለ ቃልም ነበር፣ ‹ መንግሰት እኛን ወንጀለኛ ብሎ ለማሰር ማስረጀ ሳይሆን መረጃ የለውም› የምትል ነበር፤ የሰዎችን ሀhሳብ የራሳቸው እንደሆነ አድርገው ማቅረብ የሚቀናቸው አይተ መለስ ዜናዊ ፓርላማ ላይ እንደ ጎበዝ ተማሪ ከፊት ወንበር ላይ ተሰይመው፤ ‹ ኮሚቴዎቹን ለማሰር ማስረጃ መረጃም አለን› ሲሉ ተናገሩ፤ የካሚል ሸምሱ አነጋገር እንቅልፍ ነስቷቸው እንደነበር ራሳቸውን በራሳቸው አጋለጡ፤
ጥርስ ውስጥ የገባው ካሚል ሸምሱ ፌዴራል ፓሊስ፣ የደህንነት መስሪያ ቤቱ፣ ኢቲቪ፣ ማእከላዊ፣ ቂሊኒጦና ቃሊቲን የመሳሰሉ የመንግሰት ተቋማት ተባብረው አብጠርጥሮ የሚያውቀውን ሰብአዊ መብት አንድ ሁለት … እያሉ አራቆቱት፤ አሸባሪ ነህ ሲሉም ሮቦት ዳኞች ፈረዱበት፤ ከወህኒም ጨመሩት፤ ጊዜ ለኩሉ እንዲል ጠቢቡ ከፍርግርጉ ጀርባ የነበረውን ካሚል ሸምሱ እውነት ነጻ አወጣችው፤ ምናልባትም አንዳንድ የዋሆች ይህንን የህወኃት ድርጊት ‹ምህረት› ብለው ይጠሩት ይሆናል፤
አትሳሳቱ ! ኮሚቴዎቻችን የታሰሩት፣ የተሰቃዩትና የተፈረደበቸወ ጥፋተኞች ሆነው እንዳልሆነ ራሱ ወያኔ አሳምሮ ያውቀዋል፤ እነ ካሚል ሸምሱን ነጻ ያወጣቸውም እውነትን ይዘው እስከ መጨረሻው በመጓዛቸው ነው፤ መሀሪ የሚባል የወያኔ አባል ሊኖር ይችላል፤ ወያኔ ግን መሀሪ አይደለም፤

↧

ካልፎሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ (በ.ሥ)

$
0
0

አሪፍ የፍቅር ግጥም ጽፌ ለመለጠፍ አስቤ ነበር፡፡ ግን ብለው ብሠራው “ እኔ እምልሽ ውዴ” ከሚለው ቃል ውጭ ጠብ ሊልኝ አልቻለም፡፡
እኔ እምልሽ ውዴ!
ብለው ሳይጀምሩ- ስለፍቅር መጻፍ አይቻልም እንዴ?
አንዳንድ ባለንጀሮቼ በውስጥ መሥመር ይሄን ድብርታም ዘመን እንዴት እያሳለፍከው ነው ምናምን እያሉ ይጠይቁኛል፡፡ ለጊዜው ቲቪ በማየትና አካላዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ለማሣለፍ እየሞከርኩ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ፤ የመንግሥትን ቲቪ ዜና ስከታተል ፤ የጋዜጠኛውን ዐማርኛ ወደ ራሴ ዐማርኛ በመመለስ ወደ እውነታው ለመድረስ ጥረት አድርጋለሁ፡፡ ለምሳሌ፤
ጸጥታ አስከባሪ= ጸጥ የሚያሰኝ፤ ንግግርን አዋርዶ ጸጥታን የሚያከብር ታጣቂ
ማረምያ ቤት= እሥረኛ እንደ አረም የሚታረምበት ቤት፡፡
አርብቶ አደር= ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ልጅ የሚያስወልድ ገበሬ
አንዳንድ ያዲሳባ ነዋሪዎች= አንዳንድ ያዲሳባ አስ-ነዋሪዎች
ችግሩን ለመፍታት በሂደት እየተንቀሳቀስን ነው=ችግሩ ካቅማችን በላይ ነው፡፡
ገለጹ=ተቀደዱ
ወዘተረፈ፡፡

ዲሼ ላይ ርግብ ጎጆ ሠርታበት ስለተበላሸ ዐልፎ ዐልፎ ጎረቤት እየሄድኩ የቃና ቲቪ እሾፋለሁ ፡፡ ፊልሙን ከማይበት ይልቅ ባልና ሚስቱ በፊልሙ ምክንያት በተጣሉ ቁጥር በመገላገል የማሳልፈው ጊዜ ይበልጣል፡፡ በቀደም ለት ሶፋው ላይ ተደርድረን ፊልም እያየን ሚስትዮዋ “ወይኔ ኦ-ማር! ዛሬ ደሞ እንዴት አባቱ እንደሚያምር!”ስትል፤ ባል ድል በተመታ ድምጽ ”አሁን ይሄ መጥረቢያ ፊት ምኑ ያምራል!”ብሎ ቀወጠው፡፡ ሚስት ምናለች” ኦማርን የሚመስል መጥረቢያ ቢኖር ኖሮ ዛፎች በቆረጣ ሳይሆን በፍቅር ይወድቁ ነበር :: “ ኧረ ሴቱ እንዴት እንዴት ይፈላሰፋል ጎበዝ!ለዚህ አባዋራ ኢትዮጵያ ሶርያ ትሆናለች የሚለው ሥጋት የኦማርን ፊት ያክል አያስጨንቀውም፡፡
አካላዊ እንቅስቃሴ አደርጋለሁ ያልኩት እንኳ ስቀደድ ነው፡፡ በርግጥ አሜሪካ እያለሁ ረጅም እድሜ ለመኖር ስል ባመት ሁለቴ ሮጫለሁ፡፡ የመጀመርያው፤ ፋሲል ደሞዝ በጥቁር ማጅራት መችዎች በተደበደበ ማግስት አምሽቼ ወደ ቤቴ ስመጣ፤ መታጠፊያው ላይ ግብዳ ጥቁር አይቸ የሮጥኩት ሩጫ ሲሆን ፤ ሁለተኛውን ረስቸዋለሁ፡፡ (በማግስቱ ሳጣራ፤ መታጠፊያው ላይ ቆሞ ያስቦካኝ ነገር ወይም ኒገር የማልኮም ኤክስ ሀውልት ኑሯል)፡፡
ያሜሪካ ውስጥ ሩጫ ቢያምርህ የሩጫ መንገድ አለልህ ፡፡ ሳይክል ቢያምርህ የሳይክል መንጃ መንገድ አለልህ፡፡ ቀዘፋ ቢያምርህ ሀይቁ በየደጅህ አለልህ፡፡ አየ!ሰው ካሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ይሰደዳል?
አዲሳባ ውስጥ ሳይክል አይመርህ እንጂ ካማረህ አውሮፕላን ተሣፍረህ ወደ ባህርዳር መሄድ አለብህ፡፡ ስማ! እዚህ ሃያሁለት ማዞርያ ረፋድ ላይ ለመሮጥ ብትፈልግ በየትበኩል ልትሮጥ ትችላለህ፡፡ ትንሽ ሮጥ ሮጥ እንዳልክ መንገድህ ላይ በቆሎ የሚጠብሱ አሮጊት ይገጥሙሀል፡፡ ከነምድጃቸው ዘለሃቸው ታልፋለህ፡፡ ትንሽ ሮጠህ የለማኝ ምርኩዝ ትዘላለህ፡፡ ትንሽ እንደሮጥህ በኮንትሮባንድ የገባ የጫማ ክምር ትዘላለህ፡፡ እንዲህ እየኖርን በመሰናክል ሩጫ ወርቅ አለመብላታችን ይገርመኛል፡፡
በእኛ ሠፈር በእኩልነት ተፈጥረው በኩሊነት እንዲኖሩ የተፈረደባቸው ብዙ ብሄረሰቦችን እናገኛለን ፡፡ እኛ ሠፈር ሰማይ ጠቀስ ፎቅ ለመሥራት የታደለ ጎጄ አይገኝም ፡፡ ግን ብዙ ጎጄዎች ሰማይ ጠቀስ የመጽሐፍ ክምር ተሸክመው ሲያዞሩ ታያለህ፡ያዳም ረታን “ ግራውንድ ፕላስ ዋን” ልቦለድ ተሸክሞ አዲሳባን በግር ማካለል ምን ያህል ከባድ እንደሆነ አስበው፡፡ እንኮኮ የማለት እድሉ ባይኖረኝም ፤ ራሱ አዳም ረታ የመጽሐፉን ያክል የሚመዝን አይመስለኝም፡፡ ለነገሩ ፤ይሄን ሁሉ የሚያናግረኝ ኮምብሌክስ ሳይሆን አይቀርም፡፡ አንባቢ ሆይ !የኔ አምስት መጽሐፎች ተደማምረው፤ ያዳም አንድ ምራፍ በመጠን ሲበልጣቸው ዝም ብየ የማይ ይመስልሃልን??
እኛ ሠፈር ያሉ ብዙዎቹ ፎቆችና ቢዝነሶች የሙስና ውጤት ናቸው ይባላል፡፡ እንዲያውም የኛ ሠፈር መንግስታዊ ሀብታሞች ቅሌት አንድ ሳላስቀር ብዘከዝክ ደስ ይለኝ ነበር፡፡፡ ይሁን እንጂ የሀብታሞቹን ጉድ በዘከዘክሁ ማግሥት “በሃያ ሁለት ማዞርያ ኮንደሚኒየም ሁለተኛ ብሎክ ላይ በትናንትናው ምሽት ምነቱ ባልታወቀ ምክንያት በተነሣው እሣት ቃጠሎ፤ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ፡፡ በጭስ ታፍነውና ተረጋግጠው ለህልፈት ከተዳረጉ ሰዎች መካከል፤ በእውነቱ ሥዩም የተባለ ተከራይ ይገኝበታል፡፡ በዚህ አጋጣሚ መንግሥት ለደረሰው የንብረት ውድመት የተሰማውን ልባዊ ሀዘን ይገልጻል“ የሚል ዜና ለመስማት እንደማትፈልጉ ስለገባኝ ትቸዋለሁ፡ አያድርገውና እኔ ቤት ውስጥ እሣት ቢነሣ፤ የሣት አደጋ መቆጣጠርያ ግብረኃይል ደውየ የምጠራ አይመስለኝም፡፡ ከነበልባሉ አምልጨ ብሮጥ እንኳን የሣት አደጋ መኪናው እስከፒያሳ አባሮ የሚገጨኝ ይመስለኛል፡፡
እኛ ሠፈር ከመንግሥት ጋር ሳይሞዳሞድ ሚሊኒየር የሆነ ሰው ቢኖር ሙሳ ብቻ ነው፡፡ ሙሳ ከሊስትሮነት ተነስቶ እንዴት የአምስት ኮከብ ሆቴል ባለቤት እንደሆነ መተረክ ላንባቢ መነቃቃት የሚፈጥር ይመስለኛል ፡፡ ሙሳ ጫማ እየቀባ አስር አመት ሠርቷል፡፡ አንድ ቀን የናይጄሪያ አምባሳደር፤ ለሙሳ በርሚል እግሩን አሳልፎ ሰጥቶ ጫማ እያስቀባ በመንገድ የሚያልፉ ቆነጃጅቶችን ፈዞ ሲያይ ቆይቶ በዶላር የተሞላ ሳምሶናዊቱን ረሥቶ ሄደ፡፡ ሙሳ ሳምሶናይቱንና ይዞ ካካባቢው ሽል አለ ይባላል፡፡ከሁለት አመት በኋላ ይሄው መለስተኛ ሆቴል ከፍቷል፡፡ ሙሳ ሆቴሉን“ የመለስ ራእይ ሆቴል ”ብሎት ነበር፡፡ ባለፈው አመጹ ሲበረታ የሆቴሉ ስም“ የዮሐንስ ራእይ ”ተብሎ እንዲቀየርለት ማመልከቻ አስገብቷል ይባላል፡፡
በነገራችን ላይ እኛ ሠፈር ፊታውራሪ አመዴ ለማ ያለሙት ጫካ አለ፡፡ መንግሥት ጫካው ላይ አንድ ሁለት የጽድ ችግኞች ጣል ጣል ካረገበት በኋላ የመለስ ፓርክ ብሎ ሰይሞታል ፡፡ በፓርኩ ውስጥ የቆመውን የመለስ ሀውልት ባየሁ ቁጥር ሳቄ ይመጣል፡፡ መለስን በሁለት ባህርዛፎች መሀል ቆሞ ስታየው የሆነ የደበረው ደን ጠባቂ ነው የሚመስለው፡፡
ከፓርኩ ፈንጠር ብሎ ባለው አውራጎዳና ዳር ፤ቆሻሻ ከረጢት ካብ ተዘርግቶ በሃያሁለት ማዞርያና በካዛንቺስ መካከል የበርሊን ግንብ ሠርቷል፡፡ የመጀመርያ ቀን ግማቱን ስላልቻልኩት አፍንጫየን እና አፌን አፍኘ ወደቤቴ ሸሸሁ፡፡ ምስጋና ላዲሳበባ ከንቲባ ይሁንና ፤የሰው ልጅ አፍና አፍንጫ ለሃያ ደቂቃ አፍኖ በህይወት መቆየት የሚችል ፍጡር መሆኑን ተረዳሁ፡፡ ከሦስት ቀን በኋላ በቦታው የተለመደው የጥንብ ሽታ ሳይሸተኝ ቀረ ፡፡ አሃ !ከሰንዳፋዎች ጋር ተደራድረው ቆሻሻው አስወግደውታል ማለት ነው ብየ ዞር የጥንቡን ካብ በነበረበት ቦታ አየሁት፡፡ ለካስ የተወገደው ቆሻሻው ሳይሆን የማሽተት ችሎታየ ኑሯል፡፡
ባለፈው እነ ጃዋር መሀመድ የሚላስና የሚቀመስ ወደ አዲሳባ እንዳይገባ የገበያ ማእቀብ ጥሪ ማስተላለፋቸው ይታወሳል ፡፡ አዲስአበቤስ ምኑ ሞኝ ነው ፤አስቀድሞ አስርኩንታል አስፈጭቶ ፤ ፍሪጁንም በመብልና በመጠጥ ሞልቶ ፤ ሲጠብቅ ስለነበር ያብዮቱን ሂደት በፌስቡክ መከታተሉን ቀጠለ፡፡ የእቀባው ጫና የተጫወተብን እኔንና ብጤዎቼን ነው፡፡ በቀደም ለት የሆነ ምግብ ቤት ገባሁና ምሳ አዘዝኩ፡፡ እንጀራው ከመሳሳቱ የተነሣ ” ተች እስክሪን” ነው፡፡ በልቸ ጨረስኩ አስተናጋጁ መቶ ኣምሳ ብር እንከፍል ፈረደብኝ፡፡
“ምነው ምን ጉድ መጣ! ትናንትኮ ከማርቆስ ተሳፍሬ ስመጣ ፍቼ ላይ ምን የመሰለ ምስር ወጥ በሃያ አምስት ብር በልቻለሁ”አልሁ በምሬት፡፡
አስተናጋጁ ቱግ ብሎ ምን መለሰኝ መሰላችሁ ፤
“እና ሁኔታው እስኪረጋጋ ድረስ ለምን ፍቼ እየሄድክ አትበላም?
“

↧

የትግራይና የህወሀት የበላይነት ጥያቄ –ዕውነቱ ውሸቱና ማስፈራሪያው

$
0
0

ከፈቃደ ሸዋቀና

“ኮሎኔል መንግስቱ ሀይለማሪያም እንድ ጊዜ ኢህድሪ የሚባለውን መንግስታቸውን ካቋቋሙ በኋላ ዕውን አሁን ደርግ አለ?” ብለው አገሩን በሳቅ ሊፈጁት ነበር። ይዘቱ ያው የሆነ ነገር በቅርጹ ስለተለየ በውጤቱ የተለየ ይሆናል ብለን እንድናመን ፈልገው ነበር መሰለኝ። አሁን ደግሞ የህወሀት መሪዎች ተራ በተራ “ ካላንዳች ተከራካሪ በሞኖፖል በያዙት ቴሌቪዝን ላይ እየወጡ ዕውን አሁን የትግራይና የህወሀት የበላይነት ”ኢትዮጵያ ውስጥ አለ ? የሚል ተጨፈኑልኝ ላሞኛችሁ ዘፈን መሰል ነገር በኦርኬስትራ መልክ እየተቀባበሉ እየደለቁት ነው። ( ከብዙ ጥቂቱን እዚህ ይመልከቱ) ። ተከራክረው እንደማይረቱ ሰለሚያውቁ ራሳቸው ጎን ለጎን ተኮልኩለው እየተቀባበሉ ይነጋገራሉ እንጂ ሞጋች አያስቀርቡም። ጥያቄ አቅራቢውም መልስ ሰጭውም እነሱ ናቸው። ዲሞክራሲ ማለት ያንድ አቅጣጫ መንገድ ነው ወያኔዎች ቤት። እነሱ ከተናገሩት ዕውነት ነው። አለቀ። ክርክርና ትችት እንደጦር ሲፈሩ ይገርሙኛል። ተቺ ጠቃሚ አስተካካይ ሳይሆን አሸባሪ ነው። ተቃዋሚ ጠላት ነው ብለው ያምናሉ። ይህ ባህሪያቸው እነሱንም ሃገራችንንም አብሮ እያጠፋና ሊያጠፋ የተቃረበ መሆኑ ፈጽሞ የገባቸው አልመሰለኝም። የመንግስት ባለስልጣን አይዋሽም አይባልም። ውሸቱ ግን ወይ ለከት ወይ የማስመሰል ቅንብር (nuance) እንዲኖረው ይጠበቃል። ውሸት ብዙ አይነት ነው። አንዳንድ ውሸት ያስቃል። ዕውነት ከመሰለ የሚጠቅምውሸትም አይጠፋም። አንዳንዱ ውሸት ያሳዝን ይሆናል። ውሸት እየዋሹ ሰው የሚያዝናኑ ሰዎችም አውቃለሁ። እንዳንዱ ውሸት ግን የአድማጩን የመገንዘብ ችሎታ (intelligence) የሚሳደብ ይሆንና ያናድዳል። ሰሞኑን የሰማሁት የአቶ ስዩም መስፍንና የሌሎች ህወሀት ባለስልጣኖች አይነቱ ከኋለኛው አይነት የሚመደብ ነው። አቶ ስዩም መስፍን ከዚህ ቀደም በማግስቱ የተጋለጠ አገር ጉድ ያለው ውሸትሲዋሹ ያየሁዋቸው ሰው ሰለሆኑ ውሸት ካፋቸው እንዴት ወጣ ብዬ የምሞግታቸው ስው አይደሉም።በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት የግልግል (arbitration) ውሳኔ ማግስት ባድሜም ሁሉም ነገር ለኛ ተወሰነልን ደስ ይበላችሁ ያሉንንና በማግስቱ ጭልጥ ያለ ውሸት ሆኖ መገኘቱን ያልሰማ ኢትዮጵያዊ አይኖርም።
tplf-ethiopian-leaders
እንደዚያየቀናት አድሜ የሌለው ውሸት በሚሊዩኖች ፊት ለምን እንደዋሹ እስከዛሬ ይገርመኛል። ያሁኑን የትግራይናየህወሀት የበላይነት በኢትዮጵያ ምድር የለም የሚለውን ሌላ ቆሞ የሚሄድ ውሸት ምን እንደምንለው አላውቅም። ሳይኮሎጂስቶች አንዳንድ ሰዎችን እንዲህ ጸባየ ውሸታም (habitual liar) የሚያደርግ የሚገፋና የሚወተውት በሽታ (Compulsive Obsessive Disorder) የሚባል ህመም አለ የሚሉትን ነገር እንጠርጥር ይሆን? “ ለነገሩ አሁን የምንሰማው እውን የትግራይና የህወሀት የበላይነት አለ?” ዘመቻ የተቀነባበረ(orchestrated) ይመስላል። ባለስልጣናቱ ተራ በተራ እየደጋገሙት ነው። አቶ አባይ ጸሐዬ፣ አቶ ደብረ ጽዮን ፣ አቶ በረከት ስምኦንና ሌሎችም ይህንኑ አይኔን ግምባር ያርገው ከማለት ያልተናነሰ ነገር ሲናገሩ ሰምተናል።ሁሉም ሹማምንት ባንድ ሀገር ውስጥ ያንድ ብሔረሰብ የበላይነት አለ ሲባል ምን ማለት ነው የሚለውን ጽንሰ ሀሳብ ለመተርጎም ምንም ሙከራ አላደረጉም። እራሴው ልጽደቅባቸውና ከተለያዩ ምንጮችያገኘሁትን ትርጉም አሳጥሬ ለሁሉም በሚገባና በሚያስማማ መልክ ተርጉሜ ልጀምር። ያንድ ብሄረሰብወይም ቡድን የበላይነት ማለት በ ቡድኑ ወይም በብሔረሰቡ ስም የተሰበሰበው ስብስብ በግልጽና ግልጽባልሆነ መንገድ የሌላ ሕዝብ ስብስብን ወይም ስብሰቦችን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ህልውና በበላይነት የሚቆጣጠርበትና ሌሎቹን በመጫን ራሱንና የራሱን ስብስብ ወይም ወገን ለመጥቀምና በበላይነት ለማስቀመጥ የሚሰራበት ስርዓት ነው። (Polical dominaon is an explicit or tacit measures takenwhich put a group or groups of people under the polical, and somemes, economic control ofanother group or groups በማለት Emeena Ezeani የሚባል “In Biafra Africa Died” ና ሌሎችንምመጽሀፍ የጻፈ አፍሪካዊ ምሁር ከሰጠው አጭር ትርጉም ጋር ይቀራረባል) ። የህወሀት መሪዎችን ዕምነትና ክህደት የምንመረምረው ከዚህ ቀላልና ብዙ ሰው ከማያጣላ ትርጉም ተነስተን ቢሆን ይሻላል ብዬ ነው ስለትርጉሙ የተጨነኩት። አቶ ስዩም መስፍን ትግሬ ያልሆኑ ኢትዮጵያውያን 25 ዓመት ሙሉ ደጋግመው በመዋሸት የትግራይና “ ” የህወሀት የበላይነት እውነት ያለ እንዲመስል አድርገዋል ፣ ፕርሴፕሺን ፈጥረዋል ይላሉ። በሳቸው ቤት ያለው ዕውነታ ሳይሆን ፐርሴፕሺን ( ዕውነት የሚመስል ቅዠት) “ ነው። ትግራይ እስክትለማ ኢትዮጵያ” ትድማ ብለው ተርተዋል ፣ የትግራይ መሬት በልማት ሊሰምጥ ነው ብለው ተሳልቀዋል ፣ ትግራይ ፋብሪካ በፋብሪካ ሆነች ፣ መንገድ በመንገድ ሆነች ብለው ዋሽተዋል እያሉ ይከሳሉ። ይህን ሲሉ የኢትዮጵያውያንን የመገንዘብ ችሎታ የሰደቡም አልመስላቸውም። አቶ ስዩም ሲሆን የኢትዮጵያ ህዝብ የዘረጉለትን ሥርዓት አፓርታይድ ብሎ ስላልጠራው ባያመሰግኑት እንኳን የፈጠራ ወሬ የሚያወራ ውሸታም ብለው ሊሰድቡት አይገባም ነበር። እስኪ ዝርዝር ውስጥ ሳንገባ አገር ስለሚያውቃቸው ነገሮች ከብዙ በጥቂቱ እንነጋገርና ይህን ውሽልሽል ውሸት እንየው። በደርግ ጊዜ የነበሩትን የመንግስት እርሻ ተቋማት ንብረት መሳሪያዎች ትራክተሮች መኪኖች ጄኔሬተሮች ( ለምሳሌ ያህል ጣና በለስ የነበረውን) ከዚያ በተጨማሪ ያውራ ጎዳና መስሪያ ዶዘር ኤክስካቬተርና ያ ሁሉ ማሽኒነሪ በጠራራ ጸሀይ ከየቦታው እየተጋዘ ይሄድ የነበረው ወደቱርክ ነበር እንዴ አቶስዩም? ያንን ባይኑ በብረቱ የሚያይ ሰው ምን እንዲል ትጠብቁ ነበር? የትግራይ መሬት ሊሰምጥ ነው ማለት ብዙ ንብረት ወደዚያ መጋዙን ለመናገር የቀረበ ዘይቤያዊ እነጋገር እንጂ መቼም ተፈጥሮ መሬቱ ይሰምጣል ማለቱ ነው ብለው ሕዝቡን የሚከራከሩት አይመስለኝም። እስቲ ሌላው ሁሉ ይቅርና አቶ ስዩምን እንድ ቀላል ጥያቄ እንጠይቅ። ለመሆኑ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ሁሉ ጉልሕና ዋና የሆነውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት በርስትነት ለብዙ አመታት ይዘው ቁጭ እንዲሉና ዛሬም ከትግሬ እጅ ያልወጣው እንዲሁም አቶ መለስ እስኪሞት ድረስ 21 አመት ሙሉ በያዘው ስልጣን ላይ የተቀመጠው በብሔረሰብና ድርጅታዊ የበላይነታችሁ ነው ወይስ በብሔረሰብ ቁጥራችሁ ተመዝኖ ባገኛችሁት ድምጽ? ነው ወይስ የናንተን ያህል ችሎታ ያለው ሰው ካገር ስለጠፋ? መልሱ ቀላል ነው። ሕወሀትና እናንተ የትግራዩ ልሒቃን ጠያቂና ተቆጣጣሪ የሌለበት የበላይነት ስላላችሁ ነው። የሌሎቹ ብሄረሰብ ድርጅት አባሎችና ድርጅቶች የናንተ የበታች ፓርትነሮች ስለሆኑ አንዳንዶቹም የናንተ ፍጡራን በመሆናቸው ስለሚፈሯችሁ መሆኑን ድፍን አገር ያውቀዋል። እነሱም ይናገራሉ። ከስር ቤታችሁ አውጥታችሁ የፓርቲ መሪ ያደረጋችኋቸው እነ አባዱላና እነኩማ የበላይ ወይም እኩል እንሁን ብለው ይፎካከሩናል ብለው በሳቅ እንዳይገሉን ብቻ። ይህን ገብስ ገብሱን ቀለል ስለሚል እነሳሁ እንጂ በብሔረሰብ ስብጥር ከሐይለስላሴና ከደርግ መንግስት ቀርቶ ከሚኒሊክ መንግስት ጋር ስለማይወዳደረው የሀገሪቱ ሰራዊት አመራር አላነሳሁም። ከ 95 በመቶ በላይ የሚሆነውን ቁልፍ የመከላከያ ሰራዊት ጄኔራሎችና የሰራዊት አዛዦች የትግራይ ብሔረሰብ ተወላጆች የያዙበትን ሁኔታ ምን ብለን እንጥራው? በሌላ ሀገር እንዲህ አይነቱን ስርዓት አፓርታይድ ነው እኮ የሚሉት። ዶክተር ደብረ ጽዮን መካድ ስለከበደውና ብልጥ የሆነ መልስ የሰጠ መስሎት የመከላከያ ተቋሙ ምን ይሰራል ብላችሁ ጠይቁ እንጂ ብሔረሰቡን አትዩ። መታየት ያለበት የሰራዊቱ አመራር ብሔረሰብ ሳይሆን ሚሺኑ ነው። ስራው ደግሞ ያገር ሰላም መጠበቅ ነው የሚል ደረቅ ሳቅ የሚያስቅ ድሪቶ ነገር ነገረን። የሰራዊቱ ተቋማዊ ስራ የሰራዊቱ መሪዎች ትግሬዎች ብቻ ይሁኑ ብሎ ያስገደደ አስመስሎት አረፈ። የድፍረቱ ብዛት ደግሞ ያስተሳሰብ ቀረጻ ስላልሰራን ነው ህዝቡ እንዲህ የሚያስበው ይላል። የህዝቡን ጭንቅላት ማጠብ ነበረብን ማለቱ ነው። የአቶ በረከት ስምዖን ቅብዥር (bizzare) አስተያየት ደግሞ እንዲህ ይነበባል።“በኢትዮጵያ ውስጥ ፌዴራል የሚባል ህዝብ የለም፤ ክልላዊ ህዝብ ነው ያለው።አማራ በራሱክልል ነው ያለው። ኦሮሞ በራሱ ክልል ነው ያለው። ትግራይም በራሱ ክልል ውስጥ ነው ያለው።ትግራይ ልማቱም ውድቀቱም በራሱ ልጆች እጅ ነው ያለው። አማራ ልማቱም ውድቀቱምበራሱ ልጆች እጅ ነው ያለው። ኦሮምያ ልማቱም ውድቀቱም በራሱ ልጆች እጅ ነው ያለው።እያንዳንዱ ክልል ከለማ የራሱ ልጆቹ እየመሩት ነው የሚለማው። እያንዳንዱ ክልል ካለማ ልጆቹ ፌል (fail) ስላደረጉ ነው የማይለማው። ስለዚህ ሌላ ክልልን ሰበብ ማድረግ አይቻልም።አዲስቱን ኢትዮጵያ ባህሪዋ ይህን ነው። ሌላ ክልልን ሰበብ ማድረግ አይቻልም። ሌላ ክልልንሰበብ ማደረግ የሚመጣው መቼ ነው? እያንዳንዱን ክልል ራሱን የማልማት ተልእኮ ሳይፈፅምይቀርና ህዝቡን ሊጠይቀው ይጀምራል። የክልል የወረዳ አመራር ‘ለምን አላለማህኝም’ ብሎሲጠይቀው ‘እኔ እኮ ሞክሬ ነበር ግን እከሌ አደናቀፈኝ’ የሚል አመራር ………ሲኖር ” በአቶ በረከት ሎጂክ ኦሮሚያ ወይም አማራ ክልል ውስጥ የሚኖር ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ እኖራለሁ ማለት አይችልም። ክልላዊ ነዋ። ክልላዊ ሰው እንጂ ኢትዮጵያዊ ሰው የለም። ክልሎቹን ራሳቸውን ነፃ ሀገር አስመሰላቸው። በሱ ቤት የፌዴራል መንግስቱ ውሳኔዎች ክልሉን አይነኩትም። ሕይወቱ ውስጥ አይገቡም። ጉዳያቸውን በጋራ የሚወስን ፓርላማም የላቸውም። ያለው ክልላዊ ሕዝብ ነው። የፌዴራል ህዝብ የለም። ክልሉ ውስጥ የፌደራል መንግስት አይገባም። የጋምቤላን መሬት ነዋሪ እያፈናቀለ ለህንድና ላረብ የሚቸበችበው የፌዴራል መንግስት አይደለም። ባሁኑ ሰዓት በኦሮሚያና ባማራ ግዛቶች ውስጥ ተሰማርቶ ህዝቡን እየፈጀ ያለው ሰራዊት ሁሉ የፌዴራል መንግስቱ አይደለም። በጣም የሚገርም ነው። ሰው ያውም ትልቅ ባለስልጣን ጭልጥ ያለ ውሸት ሲዋሽና ሲቀዣብር ትንሽ እኳን ትዝብት አይፈራም? ዛሬ የኢትዮጵያ ዘመናዊ ኢኮኖሚ ሁለት ሶስተኛው ኤፈርት የሚባል ባሰራሩ ከህጋዊነት ይልቅ ወደማፊያ ኦፐሬሺንነት የሚቀርብ የውሸት ኢንዳውመንት የሚቆጣጠረው መሆኑ የታወቀ ነው። ይህ ኩባንያ የፖለቲካ ፓርቲዎች በኢንቨስትሜንት ውስጥ እንዳይገቡ የሚከለክለው ህግ ተጥሶ በህወሀት ባለቤትነት እየሰራ ያለ ኩባንያ መሆኑ ሚስጥር አይደለም። ይህን ማድረግ ካለበላይነት ይቻላል? ይህ የበላይነት ማረጋገጫ ካልሆነስ የበታችነት ትርጉሙ ምንድን ነው? የኛን ኢንቨስትመንት ያህል በኢትዮጵያ የሚወዳደር የለም ብለው በአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ የነገሩን እኮ አቶ ስብሐት ናቸው። ዋሸተዋል? ኢንዳውመንት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ቢያውቁስ ባያውቁስ ምናባታቸው ያደርጉናል ብላችሁ ያቋቋማችሁት የፓርቲ ኩባንያ ያስተዳደር ቦርዱ ቤተመንግስት ውስጥ እየተሰበሰበ ይሰራ እንደነበር እኮ በኋላ ከመሀላችሁ የወጡት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባሎች መጽሀፋቸው ላይ ጽፈው ነገሩን። ስልጣን የወጣችሁ ሰሞን ቅድሚያ በጦርነት ለተጎዱ አካባቢዎች የሚል ውሳኔ አሳልፋችሁ ሌላው የኢትዮጵያ ክፍል በዚያ ክፉ ጦርነት ያልተጎዳ ይመስል ለትግራይ ለይታችሁ ትደጉሙ አልነበረም እንዴ! የትግራይ ህዝብ እንደህዝብ ከዚህ ምን ያህሉ እንደተጠቀመ የሚያውቀው እግዜር ነው። ይህ ግን ባደባባይ ካለፍረት ያወጃችሁት አዋጅ ነው። እኔ እንኳን ባቅሜ ባጋጣሚ የማውቀው እኤአ በ 1993 ዐመተ ምህረት ላይ ትምህርት ሚኒስቴር ውስጥ ባጋጣሚ ባገኘሁት መረጃ አንድ ትግራይ ውስጥ ላለ የመምህራን ማሰልጠኛ ተማሪ የቦርዲንግ ወጭ 180 ብር ሲከፈል በሌላው የሀገራችን ክፍል በሙሉ ላሉት 30 ብር መሆኑን ማወቅ ችዬ ነበር። ይህን ምን አይነት እኩልነት እንበለው? ለመሆኑ አሁን ትግራይ ውስጥ የተሰሩትን አልሜዳ ጨርቃጨርቅ መስፍን ኢንጂነሪንግ መሶቦ ሲሚንቶ የኬሚካልና የማዕደን ፋብሪካዎችና ያገልግሎት ተቋሞች በብዙ ሰው መቅጠርም ይሁን በዘመናዊነት የሚወዳደራቸው ፋብሪካ የትኛው ሌላ ክልል ውስጥ ነው ያለው? ከህዝብ ባንክ ለኤፈርት ኢንቨስትመንት የተበደራችሁትን ብድር ከሰረ ብላችሁ ስትሰርዙና የኢትዮጵያ ሕዝብ ባዶ ከረጢት ይዞ እንዲቆም ማድረግ የቻላችሁት የናንተ የበላይነት ስላልነበር ነው? ይህን ለሌላ ለማንፈቅዳችኋል? የኦሮሚያን ቡና የውጭ ንግድ የሚነግደው የናንተ ኩባንያ አይደለም እንዴ? እስኪ ሀገሪቱን የሚቀልበው ዋናው የሀብት ምንጭ ኦሮሚያና ትግራይ ውስጥ ባለፈው 25 ዓመት የተገነባው ዘመናዊ ፋብሪካ ልዩነት ይወዳደር። መስፍን እንጂኔሪንግስ የገጣጠማችኋቸውን ካሚዎኖች ለመሸጥ ገበያ የምትፈጥሩት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ ገብታችሁ ለገዥ ብድር በማመቻቸት ( በማዘዝ ማለት ይቀላል) መሆኑን ያላየንና ያልሰማን መሰላችሁ? በመንግስት በኩል ኮንትራት ሰጭ በኤፈርት በኩል ኮንትራት ተቀባይ ሁናችሁ ኮንትራት በመዋዋል የምትሰበስቡት ገንዘብስ ካለማናለብኝ የበላይነት የሚቻል ነው? በህዝብ መዋጮ ለሚሰራው ያባይ ግድብ ሲሚንቶና ሌላ ዕቃ ካላጨረታ የሚያቀርቡት የናንተ ኩባንዮች አይደሉም? አንድ ነገር ያንድ ብሔር ልሒቃንና ድርጅት ዝርፊያ ነው የሚባለው ምን ሲሆን ነው አቶ ስዩም? ሜቴክ የሚባለው የናንተ ሰዎች በበላይነት የሚመሩት ጉደኛ ድርጅት ጋ ከገባሁ ስላማልወጣ ባላነሳው ይሻላል። ጋምቤላ ክልል ውስጥ በሚካሄደው የመሬት ዝርፊያ ውስጥ ሰባ በመቶ የሚሆኑት ተካፋዮች የትግራይ ተወላጆች ናቸው ማለት የምን ምልክት ነው? ለልሂቃኖቻችሁ ቅርበት (access) የበላይነታችሁን መከታ በማድረግ አመቻችታችኋል ማለት ነው። ሌላ ምን ትርጉም አለው። ርግጥ ነው ይህ ማለት መላው የትግራይ ህዝብ የዚህ ተግባራችሁ ተጠቃሚ ነው ማለት አይደለም። መምህራችሁ ቭላዲሚር ሌኒን ራሱ እንደሚለው እኮ አንድ ሌሎችን የሚጨቁን ብሔር የራሱንም ብሔር አባላት አይምርም። አሁን ተጠቂ እያስመሰላችሁ የትግራይን ህዝብ በመናጆነት ባታሰልፉት ይበልጥ ትጠቅሙታላችሁ። የትግራይ ህዝብም ረጋ ብሎ ሲያስብና ሲገባው ዝም ብሎ የሚከተላችሁ አይመስለኝም። የምናወራው በስልጣን ላይ ያላችሁትና ተባባሪያችሁ ልሒቅ ሆናችሁ ሀገራችን ላይ ስላሰፈናችሁት የበላይነት ነው ፣ ስለህወሀት ስለሚባል የትግሬዎች ድርጅት ሰራሽ የበላይነት። ይህን ዶሮ ጭራ የምታወጣውን ነገር በጥልቅ የተቀበረ ሚስጥር ማስመሰል ለናንተም ለማንም አይበጅም። በመጀመሪያዎቹ ጥቂት አመታት የህወሀትም የበላይነት ሆነ የሀገሪቱ ጦር ባብዛኛው በትግሬ አዛዦች መመራቱ ብዙ ነውርነት አልነበረውም። በትግሉ ውስጥ የህወሀት ሚናና ተሳትፎ ትልቁ በመሆኑ ይህ አላስገረመንም። አሁን ግን ሩብ ምዕተ ዓመት አለፈው። ይሉኝታ ይዟችሁ ታሻሽሱታላችሁ ብለን ስንጠብቅ አባሳችሁት። ከሚገባ በላይ ትዕግስት ጠየቃችሁኝ ነው የሚለው አሁን ህዝቡ። ይህን በጩኸት የሚወጣ ድምጽ ሰው እንዴት መስማት ያቅተዋል? አደገኛው የውሸት መደምደሚያ ውሸቱ ምንም ሶፍስቲኬሽን የሌለበት ሌጣ ውሸት ስለሆነ ከላይ ያነሳሁዋቸው አይነት ጥቂት ዉሸቶችና ጥቂት አገር የሚያውቃቸው ምሳሌዎች ብቻ ጠጥቶ ርቃኑን ማስኬድ ይቻላል። እኔን ያሳሰበኝና ከማሳሰብም አልፎ ያስፈራኝ ባለስልጣናቱ ከዚህ ውሸት ላይ ተንደርድረው የሚሰጡት ትንታኔና ሀላፊነት የጎደለው መደምደሚያቸው ነው። ለዚህ ጽሁፍ ዋነኛ መነሻ የሆነኝም ከዚህ ያገጠጠ ውሸት በኋላ እነ አቶ “ ” ስዩም መስፍን የሚሰጡት ትንታኔና ሊከተል ይችላል የሚሉት የሰይጣን ጆሮ አይስማው የሚያሰኝና በነሱ ቤት ሕዝብ ማስፈራሪያ ይሆናል ብለው የሚጠቅሱት ዘግናኝ የታሪክ ምስስል (analogy) ነው። አቶ አባይ ጸሐዬ ይህንኑ ውሸት ከተናገረ በኋላ የጠቀሰልን ምሳሌ የሩዋንዳ እልቂት ጉዳይ ነው። እንደሩዋንዳ ልንሆን እንችላለን እያለ ነው የሚያስፈራራን። አቶ ስዩም መስፍን ደግሞ ስለ አይሁዶች ሆሎከስትና የናዚዎች ጭካኔ በሰፊው ነገረን። የመንግስት ቃል አቀባዩ ቢሮ ደግሞ ድረ ገጽ ላይ የሶሪያን የፈራረሱ ከተሞች ፎቶግራፍ እየለጠፈ ያስፈራራናል። ትግሬ ያልሆነውን የኢትዮጵያ ማህበረሰብ በጅምላ የትግሬ የበላይነት አለ ይላል ብለው ከከሰሱ በኋላ ሩዋንዳ የሆነውንና የጀርመን ናዚዎች ያደረሱትን ጥፋት ሊያደርሱ የተዘጋጁ ኢትዮጵያውያን አሉ ነው የሚሉን ባጭሩ። ለዚህ ሰለባ የሚሆነው ደግሞ እነሱ እንደሚሉት የትግራይ ህዝብ ነው። የፈረደበትን የትግራይ ህዝብም አደጋ መጥቶብሀልና ሌሎች ወገኖችህን ፍራ ከሁዋላችን ሆነህ ለመዋጋትም ወይም ሌሎች ወገኖችህን ለመፍጀት ተዘጋጅ ነው የሚሉት። ሊከሱ የፈለጉት ደግሞ አሁን ራሳቸው እየቀጠቀጡት ያለውን የኦሮሞና ያማራ ህዝብ መሆኑ ነገሩን አሳዛኝ ስላቅ ያደርገዋል። ለመሆኑ ዛሬ በኢትዮጵያ ናዚ ናዚ የሚሸተው ማነው? እነዚህ ሰዎች ለነዚህ ዋና ጥያቄዎች ምን መልስ ይሰጡ ይሆን። ለመሆኑ ዛሬ በኢትዮጵያ የናዚዎቹን የሚመስል ቁመና ላይ ያለው ማነው? ማለትም በኢትዮጵያ ዛሬ እንደ ናዚዎቹ ባለጠማንጃው ባለስልጣኑና ወታደር የሚያዘው ማነው? እየገደላችሁት ያለው ኦሮሞና አማራ ናዚዎቹን ይመስላል ወይስ ስለባዎቹንአይሁዶች? በየክፍለ ሀገሩ የሠራችኋቸው ኦሮሞና አማራ ያጎራችሁባቸው አውችዊትዝን (Auschwitz) የመሳሰሉ የሰው ማሰቃያ ኮንሴንትሬሽን ካምፖች ከማን ሥራ ጋር ይመሳሰላሉ? አማሮችና ኦሮሞ እስረኞቻችሁ የታጎሩባቸውን የብር ሸለቆና የሁርሶ ካምፖችን የመሳሰሉትን ማለቴ ነው። የናዚዎቹ ወይስ ያለቁት አይሁዶች መታጎሪያ ነው የሚመስሉት? ተብለው ቢጠየቁ አቶ ስዩም መስፍን ምን እንደሚሉአላውቅም። ልጇን ገድሎ እናትዮዋን ልጅሽ ሬሳ ላይ ተቀመጭ ብሎ የሚቀጠቅጠው ነው ናዚ የሚመስለው ወይስ የልጇን ሬሳ ታቅፋ ሰውነቴ እስኪሰባበር ደበደቡኝ የምትለው እናት? መሀል አራዳ አዲስ አበባ ያለው ማዕከላዊ የተባለውን የሰው መጥበሻ የሰቆቃ ማዕከል የትኛው ብሔረሰብ ሰዎች ናቸው የሚያስተዳድሩት? እዚያ ተቁዋም ውስጥ ዋናው የሹሞቹ ቋናቋ ትግሪኛ መሆኑን አገር እንደሚያውቅ እነ አቶ ስዩም መስፍን የሚያውቁም አይመስሉም። ከዚያ የወጡ ሰዎችን አቶ ስዩም ቢጠይቁ ማን ናዚ እንደሚመስልና በቀላሉም መሆን እንደሚችል በቅጡ ይረዱት ነበር። እነ አቶ ስዩም መስፍንና እነደብረጽዮን ለምን እንድ ጊዜ ቃሊቲ ወይም ቂሊንጦ ብቅ አይሉም። የወህኒ ቤቱ ሀላፊዎች ከየትኛው ብሔረሰብ ናቸው? ታሳሪዎቹስ? ይትኛው ብሔረሰብና የፖለቲካ ድርጅት ሰዎች ናቸው ወደ ናዚዎቹ የተግባር ስምሪት የሚቀርቡት? ለመሆኑ ከዚህ የተለየ ያንድ ጎሳ ድርጅት የበላይነትንስ የሚያሳይ ምን ልታመጡ ነው ተብለው ቢጠየቁ ምን ሊሉን ነው? የትግራይ ህዝብ ላይ የተነጣተረ ጥላቻ ኢትዮጵያ ውስጥ አለ ብሎ ለመደምደም የሚያስችል ያለቀለት መረጃ አላየንም። ዉሱንም ቢሆን አለ ከተባለ ግን ህወሀት ሁሉንም ቦታ ለመቆጣጠር ሲል በፈጠረው ስራ የተፈጠረ ሊሆንእንደሚችል መገመት ይቻላል። የፖሊስ ጣቢያው አዛዦች ትግሬዎች፣ የወህኒ ቤቱ አዛዞች ትግሬዎች፣ የግርፊያውመስሪያ ቤት አዛዦች ትግሬዎች ሆነው መታየታቸው የሚፈጥረው መጥፎ ስዕል (Image) አለ። ይህ ኢሜጅ በራሱ ቁጣ (resentment) ቢፈጥር የሚያስገርም አይመስለኝም። እኔ ከሀገር ከወጣሁ ስለቆየሁ ባይኔ ያላየሁት ነገር ግንበተደጋጋሚ ከብዙ ሰዎች የምሰማው ብዙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ ከመጠኑ በላይ (Disproporonate) የሆነየትግራይ ተወላጆች ቁጥር አለ ሲባል እሰማለሁ። ከተለያዩና ከብዙ ሰዎች ስለምሰማው ውሸት ነው ለማለት አልችልም። አየር መንገድ፣ ኢሚግሬሺን መስሪያ ቤት፣ ጉምሩክ ወዘተ ያላቸው ከሌላው የላቀ ቁጥር ሌሎችብሔረሰቦች ላይ ጥሩ ስሜት እንደማይፈጥር ለማወቅ ብዙ መማር አያስፈልግም። ችግሩን ማስወገድ የፈለገ ሰውይህንን ማስተካከል ነው። ሕዝቡ እኮ ዛሬ ባመጸባቸው ቦታዎች ሁለተኛ ዜግነት መረረኝ እያለ ነው። ይህን በተግባርእንጂ በውሸት መቀየር አይቻልም። የትግራይ ህዝብ በጅምላ የዚህ መድሎ ተጠቃሚ እንዳልሆነ ከሌሎቹ ብሔረሰቦችግን ለመንግስት የተሻለ ቀረቤታ (access) አለው ብለው የሚያምኑ ኢትዮጵያውያን አሉ። የወያኔዎቹ ሹሞችየሚክዱት የበላይነት ትርጉምም ይህ ነው። ድህነት በበዛበት ሀገር ውስጥ ባለው የስራ እድል ሽሚያ ያንድ ብሔረሰብአባላት እድሉን በማግኘት በልጠው ከታዩ ሌላው ከንፈሩን ይነክሳል። ይህ ይህን ያህል ለሁላችንም ሊገባን ይገባል። ሰብዓዊ ስሜት ነው። የህወሀት ሰዎች የአማራ ለማኝ ባማርኛ በመለመኑ ምክንያት የትግሬውን ለማኝ ይጨቁነዋልእያሉ አልነበር ስታሊኒዝምና ማርክሲዝም ሲያስተምሩ የነበሩት። ነገሩ እኮ ለማያውቅሽ ታጠኝ ነው። የዚያ ሁሉ የህወሀት ጸረ አማራ ዘፈንና ስነጽሁፍ መሰርቱስ ይህ አይደል። ግዙፉ ዕውነት ይህ ነው።በቅርቡ ከትግራይ ማህበረሰቦች ጋር ተደረጉ የተባሉትን ግጭቶች እያጋነኑ ለመጠቀም መሞከር ለዘለቄታው ሀገርየሚጎዳ ነገር ነው። በተለይ በህዝብ መገናኛ ይህን ወሬ የሚነዙት ባለስልጣኖች ሀላፊነት የጎደለው ስራ እየሰሩ መሆኑንሊያውቁት ይገባል። መኖር የሌለበት ግጭት ለመፍጠር የሚደረግ የከይሲ ሙከራ ነው። ቢያንስ ከአማራ ክልልባለስልጣኖች የምንሰማው ህዝቡ ቁጣውን የገለጠው ከመንግስት ጋር ሆነው አጠቁኝ ባላቸው በርካታ አማሮችና ጥቂትትግሬዎች ላይ እንጂ ትግሬዎችን በዘር እየለየ አይደለም። የኢትዮጵያ ሕዝብ በዘር ተጣልቶ ለመጋደል የሚያስችልየተፈጥሮም የታሪክም መሰረት የለውም። ኢትዮጵያ ውስጥ የሩዋንዳም ሆነ የሌላ ሀገር አይነት የዘር ግጭትየሚመጣው ባለስልጣኖች የራሳቸውን ስልጣን ለመጠበቅና የዘረፉትን ሀብት ለመንከባከብ ሲሉ ሊፈጥሩ በሚችሉት እኩይ ተግባር ምክንያት ብቻ ነው።ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ የህወሀትና የትግራይ ልሂቃን የበላይነት ያንፈራጠጠበት ሁኔታ አለ። ኢትዮጵያ በታሪኳ እንደዛሬ የተደራጀ ለአፓርታይድ የቀረበ (Instituionalized and systematic) ብሔረሰብ ጭቆና አይታ አታውቅም።ይህ የትም ቦታ ቢሄዱ አግጦ የሚታይ ሊደብቁት የማይቻል እውነት ነው። ይህን በትልልቅ ስልጣን ላይ የተቀመጡትሰዎች እነ አቶ ሐይለማሪያም ደሳለኝ መሆናቸው አይቀይረውም። በከፍተኛ ስልጣን ላይ ካሉት ሰዎች በቁጥርየሚበልጡት ትግሬ ያልሆኑ ሰዎች ናቸው የሚለው አባባል ዕውነታውን አይቀይረውም። የሀገሪቱ የምር የሀይል ማዕከልየት እንዳለ ትንንሽ ልጆች ሳይቀሩ ያውቁታል። ሰራዊቱን ኢኮኖሚውንና ደህንነቱን ማን እንደሚቆጣጠረውና በሌላው ብሔረሰብ ተወላጅ ጉያ ቁጭ ብለው ሐይለማሪያምን የመሳሰሉትን ሹማምንት የሚቆጣጠሩት እነማን እንደሆኑ አገር ያውቃል። ችግርና ጥፋት የሚያስወግደው ይህንን ነገር እያፍረጠረጡ በመወያየትና በማረም እንጂ በመሸምጠጥ አይደለም።

↧

ለመራራዉ ትግል በስነ ልቦና መዘጋጀት ብሎም ለማያዳግም እርምጃ ተቋማዊ እና ህዝባዊ ዝግጅት ማድረግ ይገባል

$
0
0

ከሸንቁጥ አየለ

አሁን ትግሉ ህዉሃት በአንድ ወገን የተሰለፈበት እና የኢትዮጵያ ህዝብ በአንድ ወገን ጎራ ለይቶ የቆመበት ሆኗል:: ለጊዜዉ ህዉሃት በመላ ሀገሪቱ ህዝባችንን የመግደል እና የማሰቃዬት ስራዋን በታጠቀችዉ መስራያ ተማምና እያከናወነች ነዉ::

gonder-satenaw-news-56

ጎንደርን እያቃጠለች ነዉ::መላዉ አማራን እያሰረችዉ እና በገፍም እያሰቃዬችዉ ነዉ::መላዉ ኦሮሚያን እያሰረች በገፍ እያሰቃዬቸዉ ነዉ::በደቡብ ኢትዮጵያ በሚገኙ ልዩ ልዩ ማህበረሰቦች ላይ ማለትም በኮንሶዎች: በጋምቤላዎች: በሲዳማዎች እና በልዩ ልዩ ማህበረሰቦች ላይ የማሰቃዬት ስራዋን ቀጥላለች::የማያፍሩት ህሊና ቢሶቹ ወያኔዎች አሁንም አማሮችን ከኮንሶ እና ከልዩ ልዩ የደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ማሰደዳቸዉን ቀጥለዋል::

የአፋር ህዝብ ላይ የሚያደርሱት በደል መቆሚያ ስላጣ የአፋር ህዝብ ከወያኔ ጋር አንገት ላንገት ተጋድሎዉን ተያይዞታል :: የሶማሌ ክልል አሁን በከፍተኛ ሁኔታ እየተደበደበ ነዉ::መላዉ ኢትዮጵያን ወያኔ ጤና አሳጥቶታል:: ህዝባችንን መገል: ማሰር: ማፈናቀል እና ማሰቃዬት ለ25 አመታት የተካነዉ ስራዉ ነዉና አሁን ይሄንኑ ስራዉን አጠናክሮ ቀጥሎበታል::የኢትዮጵያም ህዝብ በክብር ለነጻነቱ እየሞተ ነዉ::
በመላዉ ኢትዮጵያ እንዲሁም በመላዉ አለም ያለህ ኢትዮጵያዊ ሁሉ እንዲሁም በልዩ ልዩ ድርጅቶች ስር የተሰባሰባችሁ የተቃዋሚ ሀይሎች አንድ ነገር ግልጽ ሊሆንላችሁ ይገባል::ትግሉ የአንድ ሰሞን እሩጫ አይደለም:: ለመራራዉ ትግል በስነ ልቦና መዘጋጀት ብሎም ለማያዳግም እርምጃ ተቋማዊ እና ህዝባዊ ዝግጅት ማድረግ ይገባል::

የኢትዮጵያ ህዝብ በክብር ለነጻነቱ እየሞተ ነዉ:: የኢትዮጵያዉያን ተጋድሎ እስከ ነጻነት ይቀጥላል !

↧
↧

የኢትዮጵያ “የፌደራል ሥርዓት” ችግሮችና አማራጭ መፍትሄዎች |ገለታው ዘለቀ

$
0
0

እንደ መግቢያ

ከዚህ በፊት “ኢትዮጵያ የፌደራል ሥርዓትን የምትከተል አገር አይደለችም” ብዬ ፅፌ ነበር። ዛሬም ትንሽ አዳብሬ በዚሁ ላይ ትንታኔ መስጠት አምሮኛል። ይህ ጽሁፍ ደግሞ እንዲነሳልኝ የፈለኩበት ምክንያት በቅርቡ የህወሃት አንጋፋ ታጋዮች የሆኑት አቶ ስዩም መስፍንና አቶ አባይ ፀሃየ በቅርቡ በኢትዮጵያ “ወቅታዊ” ጉዳይ ላይ የተሰኘ መግለጫ ሰጥተው ነበር። የነዚህን ከፍተኛ ባለስልጣናት ንግግር ያዳመጠ ሁሉ የየራሱን ምልከታ ያስቀምጣል። እጅግ ብዙ ሰው ግን አዲስ ነገር የማይገኝበት ወቅታዊ የማይባል ያደርገዋል። አገሪቱን ህዝባዊ ተቃውሞ በሚንጥበት በዚህ ሰአት ቢያንስ ስለብሄራዊ መግባባት ስለ ብሄራዊ እርቅ ስለ ይቅርታ ማውራት ተገቢ ነበር። የፓለቲካ መሪ ምንም እንኳን የያዘው አቅጣጫ ለራሱ አዋጭ ቢመስለውም ነገር ግን ህዝብ ካልተቀበለው ራሱን ይመረምራል። ይህ ግን በኛ ሃገር ፓለቲካ አለመታየቱ ያሳዝናል። ስልጣን ለሚወዱ ባለስልጣናትም የስልጣን እድሜ የሚጨምረው ይቅርታና መታረም መለወጥ ነበር።

federalism

በዚህ “ወቅታዊ” በተሰኘው የነዚህ የህወሃት መሪዎች መግለጫ ውስጥ አንድ ነገር ስላስደመመኝ በዚያ ላይ በተለይ ለነዚህ ለሁለቱ መሪዎችና ለተከታዮቻቸው ማስተላለፍ እፈልጋለሁ። በዚህ ገለፃ ወቅት አቶ ስዩም ስለ ፌደራል ስርአት ተናግረዋል። የኢትዮጵያ የፌደራል ስርአት “አለም የሚቀናበት” ነው ይሉናል። እንዴውም የኢትዮጵያ የፌደራል ስርአት የሌሎች ፌደራል አገሮችን የፌደራል ስርአት የገለበጠ ነው ይላሉ። ይህንን ሲያስረዱ የሌሎች ሃገራት የፌደራል ስርአት ፌደራሉ የተወሰኑ ስልጣኖችን ይሰጥና ከዚያ ቀሪው በሙሉ የኔ ነው ይላል ይሉናል። ይሰስታል አይነት ነው። ስልጣን የሚሸነሽነው ከላይ ያለው የፌደራል ስርአት ነው ይላሉ። በአንፃሩ የኢትዮጵያ የፌደራል ስርአት ደግሞ የተገነባው ብሄሮች ትንሽ ትንሽ ቆንጥረው ስልጣን ወርውረውለት የተቋቋመ የፌደራል ሥርዓት ሲሆን ብዙውን ስልጣን ግን ብሄሮች ለራሳቸው እየተደሰቱበት እንደሆነ ያስረዱናል። ይህንን ሳዳምጥ አቶ ስዩም በከፍተኛ ሁኔታ የፌደራልን ጽንሰ ሃሳብ አለመረዳታቸውን አሳየኝ። ተከታዮቻቸው ሁሉ እንዲሁ ከተረዱት በውነት ከስረዋል። እኚህ ሰው እንደኔው ተራ ሰው ቢሆኑ አልሟገትም ነበር። ነገር ግን እኚህ ሰውና ፓርቲያቸው ያመኑበትን ተግባራዊ የሚያደርጉና ያደረጉ በመሆናቸው የኝህ ሰው ግንዛቤ አገርን ስላወከ ነው ለሙግት ያስነሳኝ።

እንግዲህ በመሰረቱ የፌደራል ስርአት ብዙ አይነት ነው። እንደ ስምምነቱ ነው። በከፍተኛ ሁኔታ ስልጣን ለክልል የሰጡ ሃገራት በኮንፌደሬሽን ስርአት ይተዳደራሉ። ከዚያ በመለስ ደግሞ በተለያየ ግዝፈት በፓለቲካ ዩኒቶች መሃል ስልጣን እየተካፈሉ የሚኖሩ ደግሞ አሉ። ዋናው አቶ ስዩም የሳቱት ነገር በሌሎች ሃገሮች የፌደራል ስርአት ውስጥ ፌደራሉ ነው ስልጣን የሚሸነሽነው የሚለው ነው። ፌደራል ጥቂት ስልጣን ይሰጥና ሌላውን ለራሱ ይወስዳል ይላሉ። ይሄ ስህተት ነው። በሰኪዩላር የፌደራል ስርአት ውስጥ ስልጣን የሚያካፍለው ህገ

መንግስት ነው። በህገ መንግስት የስልጣን ክፍፍል ተቀመጠ ማለት የፌደራል መንግስት ስልጣን አዳይ ሆነ ማለት አይደለም። ሁሉቱም መንግስታት በተቀመጠላቸው ህግ መሰረት ይሰራሉ። ይህ ህገ መንግስት ደግሞ የሁሉ ነው። በአሜሪካ የፌደራል ስርአት ውስጥ ፌደራል መንግስት የስቴቶችን ስልጣን ሲፈልገው እየጨመረ ሲፈልገው እየቀነሰ አያድልም። ህገ መንግስቱን የማሻሻል ስልጣንም ቢሆን ለፌደራል መንግስት ብቻ የተሰጠ ስልጣን አይደለም። አቶ ስዩም ይህንን ማወቅ አለባቸው። የአቶ ስዩም የፌደራል ሥርዓት አረዳድና ትንታኔ እንዲሁም የኢትዮጵያን የፌደራል ስርአት በተመለከተ የሰጡት ግምት የተሳሳተ በመሆኑ እነሆ ዛሬ እሳቸው አለም ይቀናበታል ያሉት የብሄር ፌደራሊዝም ምን ምን ውጥንቅጥ እንዳለው፣ እንዴት እንዴት አድርጎ እየጎዳን እንደሆነ በዚህ ጽሁፍ ሥር እተነትናለሁ። ከሁሉ በፊት ግን የፌደራል ስርአት የፍልስፍና መሰረቱ ምን እንደሆነ በመወያየት ወደ ዋናው አሳብ ብንወርድ ሳይምረጥ አይቀርም።

የፌደራል ስርዓት የፍልስፍና መሰረቶች

የኢትዮጵያን የፌደራል ስርአት ለመተቸት ከመነሳታችን በፊት በፌደራል ስርአት ፅንሰ ሃሳብ ዙሪያ መወያየቱ ለግምገማችን መሰረት ይሆናል። እንደሚታወቀው የፌደራል የመንግስት መዋቅር የተፈጠረው በተባበረችው ኣሜሪካ የፖለቲካ መሪዎች ነው። እነዚያ የቀደሙት የተባበረችው ኣሜሪካ መሪዎች ኣንድ ወቅት የፈጠሩት ይህ የፌደራል ስርዓት የመነሻ ኣሳቡ ህዝብን በኣንድ ትልቅ ኣዳራሽ ውስጥ ኣስገብቶ ዙሪያውን ኮልኩሎ ከማስተናገድ ይልቅ ክፍል ክፍል ፈጥረንለት በነዚያ ክፍሎች ደግሞ የመንግስትን ስልጣን የሚጋሩ የስቴት መንግስታት ቢመሰረቱ ኣገልግሎት ይሳለጣል ከሁሉም በላይ ደግሞ ለህዝቡ የህግ ሪሶርሶች ይጨምራሉ ከዚህም በላይ ጠቅላላ የሆነውን የመንግስት ስልጣን በየስቴቱ ብናካፍል የሚሰጠው ስልጣንና ህገ መንግስት ጠቅላላ ነገር ሲሆን አተገባበሩ ግን ጥበብ (art) ይጠይቃል። ይህ ጥበብ ደግሞ ከመንግስታት መንግስታት በየተወሰነ ደረጃ ሊለያይ ይችላል። ስቴቶች የፌደራሉን ስርዓት ህገ መንግስቱን ሳይጥሱ በኣሰራር ጥበብ ለመለያየትና ለመወዳደር እድል ስለሚሰጥ የስቴቶች ጥበብ መለያየት ለህዝቡ የህግ ሪሶርስ እንዲጨምር ምርጫዎች እንዲበዙ ስለሚያደርግ ለመልካም ኣስተዳደርና ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እንዲሁም ለኢኮኖሚ እድገት ትልቅ ጠቀሜታ ያመጣል ከሚል ነው። በፌደራል ስርዓት ጊዜ ዜጎች የፖለቲካ ተሳትፎ ምህዳራቸው ይሰፋል። በክልልና በፌደራል ደረጃ ይመርጣሉ። ሁለት መንግስታት ይኖራሉ። ለዜጎች የሚያስቡ ተመራጮች ይበዛሉና ስለዜጎች ምክር ይበዛል። የፌደራል ስርዓት ማለት መንግስት የሚባለውን ጽንሰ ሃሳብ መዘርዘር ማለት ነው። መንግስት ተዘርዝሮ ሲሰራበት ኣገር የበለጠ ያተርፋል የሚል እምነት ኣለው። ስቴቶች እንደየአቅማቸው መክሊትን እየወሰዱ ይሰሩበታል። እነዚህ ስቴቶች መንግስት ይባሉ እንጂ ዜጎች ኣይኖራቸውም። ዜግነት በስቴት የሚወሰን ባለመሆኑ ስቴቶች የሚሰሩት ዞሮ ዞሮ ለዜጎች ሁሉ በመሆኑ ትልቁ ግብ ኣገርን በሁለንተናዊ መልኩ ማሳደግ ነው።

የፌደራል ስርዓት ከመነሻውም ዴሞክራቲክና ብዝሃዊነት ካለው ሰፊ ልብ የመነጨ ነው። ስልጣንን ማካፈል ለኣምባገነን መሪዎች በጣም ከባዱ ነገር ነው። ከብዙ ኣመታት በፊት የኣሜሪካ መሪዎች ይህንን ስርዓት ሲያመጡ ለዴሞክራሲ ስልጣንን ለማካፈል የቆረጡ ጀግኖች እንደነበሩ ያሳያል። በኣጠቃላይ የፌደራሊዝም ስርዓት ያመጣው ለውጥ ለብዙ ዘመናት ስልጣን በኣንድ ኣካባቢ ተጠቅልሎ የቆየውን ከማእከል በማውጣት ለስቴቶች ማካፈል ሲሆን በዚህ የኣስተኣደር ጥበብ አገርን በፍጥነት ለማሳደግ ይረዳል የሚል ነው። በሌላ በኩል በፌደራል ስርአት ስር ለከረመ አገር ወደ አምባገነን ስርአት የመመለስ እድልን ያጠባል። ስልጣን ስላልተማከለ ስቴቶችም ስለበዙ በቀላሉ ሃይልን ለመጠቅለል ስለሚያስቸግር አስቸጋሪ መሪዎች ቢመጡም አምባገነን ስርአት እንዳያብብ ያደርጋል። ሌላው የፌደራልን ሥርዓት ተመራጭ የሚያደርገው ነገር ደግሞ ማንነትን ለመንከባከብ ይረዳል ከሚል ነው። ማንነት ሲባል በተለይ የብሄር ማንነትን ለማለት ነው። ብሄሮች በቋንቋቸው እንዲዳኙ እንዲተዳደሩ ለማድረግ ከአሃዳዊ ስርአት ፌደራላዊ ስርአት ይመረጣል ይባላል።

የኢትዮጵያ የፌደራል ስርዓት ምን ይመስላል? ስንት ችግሮች አሉበት?

የፌደራል ስርዓት በተባበረችው አሜሪካ መሪዎች ከተፈጠረ በሁዋላ ሌሎች ኣገሮችም ይህንን ስርዓት ተማርከውበት እየተጠቀሙበት ነው። በርግጥ በዓለም ላይ ያለ የፌደራል ስርአት ሁሉ ኣንድ ኣይነት ኣይደለም። የኣሰራር ኣንዳንድ ልዩነቶች ኣሉ። ለምሳሌ የህንድን የፈደራል ስርዓት ስናይ ስቴቶች ህገ-መንግስት የላቸውም። ከካሽሜር ግዛት ውጭ ሌሎቹ ስቴቶች የሚጠቀሙት የሃገሪቱን ኣንድ ህገ መንግስት ብቻ ነው። የካናዳ የኣውስትሬሊያና የጀርመን የመሳሰሉት ኣገሮች የፌደራል ስርዓቶች በየተወሰነ ደረጃው የተለያዩ ናቸው። ይሁን እንጂ በመሰረታዊ መርሃቸው ማለትም ስልጣንን በማካፈል በኩል ሁሉም ሃገራት እምነቱ ኣላቸው። ወደ ኢትዮጵያ ስንመጣ የተለየ ነገር እናያለን። ኢትዮጵያ ስያሜዋ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ነው። ከዚህ ስያሜ የምንረዳው የፌደራል ስርዓትን ተቀብያለሁ በትምህርቱ ተማርኪያለሁ የምትል ኣገር እንደሆነች ነው። ታዲያ የፌደራል ስርዓትን ልትቀበል የዘረጋችበት እጅ ደግሞ በቡድን በቡድን ነው። በህገ መንግስቷ መግቢያ ላይም እኛ ብሄር ብሄረሰቦች…… በሚል ነው ኣዲሱን ስርዓት ኣሃዱ ብላ የጀመረችው። ይህ መሰረታዊ እምነቷን ከፌደራል ስርዓት ጋር እንዴት ለማስኬድ እንደሞከረችና ያመጣባትን ችግር ኣንድ ሁለት እያልን እንመለከታለን።

በዚህ ጽሁፍ ውስጥ የምናየው ዋና ጉዳይ ሳይንሳዊ የሆነው የፌደራል ስርዓት

ከብሄር ፖለቲካ ጋር ሲገናኝ ምን ኣይነት መስተጋብር አንዳለውና ኣጠቃላይ ፌደራሊዝሙን በብሄር ላይ ማቆሙ ምን ያህል የፌደራልን ጽንሰ ሃሳብ እንዳፋለሰ በአጠቃላይም በሃገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ያመጣውን ችግር እንዳስሳለን። የውይይታችን ማጠንጠኛዎች ሰባት ነጥቦች ሲሆኑ እነሱም፦

  1. የመንግስት ኣወቃቀር
  2. የሃይል መካፈል ጉዳይ
  3. የማንነት ጉዳይ
  4. የዴሞክራሲ ጉዳይ
  5. የኢኮኖሚ ጉዳይ
  6. ለኣስተዳደር ኣመቺነት
  7. አብዮታዊ ዴሞክራሲና ፌደራሊዝም ናቸው

በነዚህ ከፍ ሲል በዘረዘርናቸው ስድስት ማእዘኖች አንፃር የኢትዮጵያን የፌደራል ስርአት መተቸት አሁን እንጀምር።

1. የመንግስት ኣወቃቀር

በመግቢያ ላይ ጠቆም እንደተደረገው በፌደራል ስርዓት ጊዜ መንግስት ሲዋቀር ሶስቱ የመንግስት አካላት ማለትም ህግ ኣውጭው፣ ህግ ኣስፈጻሚውና ህግ ተርጓሚው ተለይተው በሚገባ መዋቀር ኣለባቸው። ይህ የፌደራል ስርዓት ዋና ጉዳይ ነው። የመለያየታቸው ዋና ምስጢር በተለያየ ኣጋጣሚ ስልጣን የሚይዙ ባለስልጣናት እነዚህን ኣካላት መሳሪያ ኣድርገው ድሆች እንዳይበዘበዙ ነው። እነዚህ ሶስት ኣካላት ቼክና ባላንስ እያደረጉ እየተጠባበቁ ሲኖሩ ሚዛናዊ የሆነ ተጠያቂነት ያለበት ስርዓት ይፈጠራል። እነዚህ ሶስት ኣካላት ጎን ለጎን

እየተያዩ ቼክና ባላንስ እያደረጉ የሚጠብቁት ኣንድ ነገር ቢኖር የህዝብን ስልጣን ነው። እውተኛው የስልጣን ባለቤት ህዝብ በመሆኑ እነዚህ ሲስተሞች በህይወት ዘመናቸው ይህን የህዝብ ስልጣን ይጠብቃሉ። ያገለግላሉ።

አነዚህ ሶስቱ የመንግስት መዋቅሮች ሳይለያዩ ከተፈጠሩ ተጠያቂነት ስለሚጠፋ ስልጣን ከህዝብ እጅ ይወጣና የጥቂቶች ፍላጎት መፈጸም ይጀምራል። ፍርድ ቤት ህግ ኣውጭው ኣስፈጻሚው ሁሉ የጥቂቶችን ፍላጎት እያስፈጸመ የሚኖርበት ሁኔታ ይፈጠራል።

እንግዲህ ኢትዮጵያ የፌደራል ስርዓት ኣራምዳለሁ ባይ ናት ብለናል። በርግጥ የብሄር ፌደራሊዝም የሚባለውን ፖለቲከኞች ኣይጠቀሙበትም። የፌደራል ኣገር ነን ብቻ ነው የሚሉት። ትንሽ ኣፈር ይሉበት ይመስላል። ተቃዋሚው ግን ፍርጥ አድርገው የብሄር ፈደራሊዝም ነው ያለው ይላሉ። መንግስት የፖለቲካ መሰረቴና የስልጣን ምንጮቼ ዘውጎች ይሆኑና ነገር ግን የፌደራል ስርዓት መርሆዎችን ኣከብራለሁ የሚል ነገር ያንጸባርቃል።

የብሄር ፖለቲካና ፌደራሊዝም ኣብሮ ሲመጣ ምን ሊከሰት እንደሚችል ቆየት ብለን እናነሳለን ለኣሁኑ ግን በኢትዮጵያ የብሄር ፌደራል ስርዓት ውስጥ ኣንዱ የሚታየው ነገር እነዚህ ሶስቱ ማለትም ህግ ኣውጭው ኣስፈጻሚውና ተርጓሚው ሲዋቀሩ የተፈጠረ ስህተት ኣለ። ይህ ስህተት ደግሞ በከፍተኛ ሁኔታ የነዚህን ሶስት ኣካላት ተለያይቶ የመፈጠር መርህ እንዲፈርስ ኣድርጓል።

በኢትዮጵያ ህገ መንግስት ኣንቀጽ 62 ንኡስ አንቀፅ 1 መሰረት የሃገሪቱን ከፍተኛ የፍትህ ስልጣን የያዘው የፌደሬሽን ምክር ቤት ነው። ይህ ምክር ቤት የዳኝነት ስራን ነጥቆ የወሰደ ሆኖ ነው የተዋቀረው። በዚህ ኣንቀጽ ላይ እንደተደነገገው የሃገሪቱን ህገ መንግስት የሚተረጉመው ይህ ምክር ቤት ነው። በሌሎች የፌደራል ኣገራት የሃገሮችን ህገ መንግስት የሚተረጉመው ኣካል ኣንድም የህገ መንግስት ዳኛ ተቋቁሞ ወይም ደግሞ የሃገሪቱ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ነው። የህገ መንግስት ፍርዱም ስራ በተፈጥሮው የህግ ስራ በመሆኑ ሃገሮች በባለሙያ ያሳዩታል። ባለሙያው ሲተረጉም ጣልቃ ሳይገቡ እየተዳኙ ይኖራሉ። ኣንድ የፖለቲካ ስልጣን ያለው መንግስት ፓርላማውን ኣቋቁሞ ህጎችን ያወጣል። እነዚህን ህጎች ያወጣሁት እኔ ነኝ ስሜታቸውን፣ ቋንቋቸውን የምረዳው እኔ ነኝና እኔው እተረጉማለሁ እኔው እፈጽማለሁ ኣይልም። ጠቅላላ ህጎችን ያወጣና ለባለሙያዎች ሲሰጥ እነዚያ ባለሙያዎች ይተረጉማሉ። በኢትዮጵያ ሁኔታ ግን የተለየ የሆነው እንደሚታወቀው የፌደሬሽን ምክር ቤት የሚዋቀረው በፖለቲካ ሰዎች በመሆኑ ይህ ኣካል የህግ ትርጉም ስራ ሲሰጠው የሚፈጠረው ችግር የመንግስት የስልጣን ክፍፍል ብቻ ሳይሆን ኣሰራርም ላይ ትልቅ ችግር ያመጣል። የህግ ባለሙያ የሆኑት ዶክተር ጸጋየ ረጋሳ ሲናገሩ ኣንዱ የዚህ ኣወቃቀር ትልቅ ችግር ኣፈጻጸሙ ላይ ነው ይላሉ። እንደሚታወቀው ፍርድ ቤት የወሰነውን ውሳኔ ለማስፈጸም ፖሊሲ ሊታዘዝ ይችላል። የፌደሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ ሲያሳልፍ ውሳኔውን ተግባራዊ ለማድረግ የሚሄድበት መንገድ ህጋዊነት ኣጠያያቂ ነው። ከሁሉ በላይ ግን ይህ ምክር ቤት ዳኝነት እንዴት ይሰጣል? ይህ ጉዳይ ከህገ መንግስቱ ጋር ይሄዳል ኣይሄድም ካለ ቡሃላ እንዴት ነው የአፈፃፀም ሂደቱ? የሚለው ጉልህ ጉዳይ ነው። ለምሳሌ ኣንድ ጠቅላይ ሚንስትር የሆነ ግድፈት ቢያመጣ ፓርቲዎች ቢጋጩ ጉዳዩ ከህገ መንግስት ጋር ይሄዳል ኣይሄድም ለማለት ይህ ምክር ቤት እንዴት ገለልተኝነት ይሰማዋል? ካድሬዎች የተሰበሰቡበት ቤት እንዴት ብይን ይሰጣል? መንግስት ራሱ ህገ መንግስቱን የሚፃረር ከባድ ነገር ቢያደርግ ዳኛው ራሱ ኢህአዴግ ሆኖ ይመጣል ማለት ነው። ይህን ጉዳይ ስናጤን በኣሁኑ የመንግስት ኣወቃቀር ኢትዮጵያ የፍትህ ስራዋን ዋና ጉዳይ የፖለቲካ ውክልና ያላቸው ኣካላት ነጥቀዋት ይታያል። ይህ የሚያሳየው ደግሞ የሃይል ክፍፍል( Separation of power) እንደጠፋ ነው። ህግ ተርጓሚው የፓለቲካ ሰው በመሆኑ ነው ይህ ችግር እንዲከሰት ያደረገው። ለምሳሌ እንዲሆነን አንዳንድ ተግባራዊ ምሳሌዎችን እናንሳ። ወልቃይቶች ማንነታችን ተጎዳ በግድ ትግራይን ምሰሉ ተባልን ብለው ይከሳሉ። እነዚህ ወገኖች ይህን ክስ ይዘው ወደ ፍርድ ቤት አይሄዱም። ምክንያቱም የማንነቶችን ጉዳይ የሚያየው አካል የፌደሬሽን ምክር ቤት በመሆኑ ነው። ወልቃይቶች መንግስትን ከሰው እዚያው መንግስት ጋር ይሄዳሉ። ክልሎች ቢጋጩም ፈራጁ ያው የፌደሬሽን ምክር ቤት ነው። በህግ ተርጓሚው ውስጥ ኢህአዴግ የፓለቲካ ፓርቲ አባሎቹን ዳኛ ስላደረገ ነው የሃይል መለያየት ጉዳይ በኢትዮጵያ የመንግስት ሥርዓት የፈረሰው።

በፌደራል ስርዓት ውስጥ የነዚህ ሶስት ስልጣናት መለያየት ዋና ጉዳይ ሲሆን ኢትዮጵያ ባዋቀረችው ሲስተም ግን ይህ ፎርሙላ ሲሰበር እናያለን። ከዚህ የተነሳም የኢትዮጵያ የፌደራል ስርዓት የፌደራል ስርዓትን ዋና መርሆን ለመከተል ያልቻለ ሆኖ እናያለን።

2. የሃይል መካፈል ጉዳይ

የፌደራል ስርዓት ሲጀምር የሚያምነው ነገር ሃይልን ለስቴት መንግስታት በማካፈል ኣገልግሎትን ማሳለጥ ነው። በብዙ የፌደራል ኣገራት በፌደራልና በስቴቶች መካከል የሃይል መከፋፈል ኣለ። በኣንዳንድ ጉዳዮች ላይ ኣብረው ይሰራሉ በኣንዳንድ ጉዳዮች ላይ ለየብቻ ይሰራሉ። በኢትዮጵያ ሁኔታ ስናይ በርግጥ ክልሎች ሁሉ የየራሳቸው ህገ መንግስት ኣላቸው። የየራሳቸው ምክር ቤት ኣላቸው። ነገር ግን ሃይል ሲበዛ ፌደራል ኣካባቢ የተሰበሰበ ሲሆን ክልሎች ክንፍ ሳይኖራቸው ይበራሉ የተባሉ አካላት ናቸው። ሃይል በጣም ለመማከሉ የተጻፈ መረጃ ብዙ የለም። ነገር ግን የህዝቡ ግንዛቤ የሚያሳየው ግን ይህንን ሃቅ ነው። ኢትዮጵያ የብሄር ፌደራሊዝም ነው የማራምደው ብትልም የፌደራል ስርዓት ዞሮ ዞሮ የሚጠይቃት ሃይልን ለክልሎች ማካፈል ነው። ብሄሮች ራሳቸውን እንዲያስተዳድሩ ሃይል መስጠት ነው። ነገር ግን ይህ ኣልሆነም። ሃይል ተማክሏል። ለዚህም ነው ዛሬ የኦሮሞና የኣማራ ህዝብ የኮንሶና የኦጋዴን ወዘተ ህዝቦች በሃይል ያመጹት። ትልቁ ጥያቄያቸው ህወሃት የበላይ ሆኖ በየክልሉ ኣገልጋዮቹን እየሾመ እየጨቆነን ነው የሚል ነው። ይህ የህዝቡ ግንዛቤ የሚያሳየው ሃይል እንዳልተካፈለ ነው። እውነቱን እንነጋገር ከተባለ ህወሃት ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ከሚጨቁነው በላይ የራሱን ኣጋር ድርጅቶች ኣጥብቆ ጨቁኖ የያዘ ድርጅት ነው። መጠቀሚያዎቹ ስለሆኑ እጅግ ኣጥብቆ የያዛቸው ናቸውና ነጻነት የላቸውም። እነዚህ ሰዎች ኣንድ ቀን ያበጠው ይፈንዳ ህወሃትን ኣባጠጥን አናታችን ላይ ወጣ ብሄሮቻችንንም ኣገራችንንም ጎዳን ብለው የፍርሃትን ቀንበር ሰብረው ካልተነሱ ህወሃት እንዲሁ ጋልቧቸው መጓዙ ጥሞታል። በኣጠቃላይ እንደ ፌደራል ስርዓት ስናይ ኣንድ የፌደራል ስርዓት በተለይም የብሄር ፖለቲካ የምታራምድ ኣገር፣ የብሄሮችን መብት እስከ መገንጠል የተቀበለች ኣገር ስለ ራስ ማስተዳደር የምትዘምር ኣገር የሃይል መካፈል ጉዳይ ዋና ጉዳይ ነው። ብሄሮች የተፈጥሮ ሃብታችሁ ሁሉ በዋናንት የናንተ ነው ተብለው ነገር ግን በቴክኒክ ስልጣናቸው ከተቀማ የሃይል መካፈል ጉዳይ ዳዋ በልቶታል። ከዚህ ኣንጻር ስናይ ኢትዮጵያ የሃይል ክፍፍልን እየተደሰተችበት ያለች ኣገር ባለመሆኗ የፌደራል ስርዓትን እከተላለሁ ብትልም ከቶ ማን ሊሰማ።

3. ማንነት

ከሰኪዩላር ፌደራሊዝም ዶክትሪን ጽንሰ ሃስብ የምንማረው ነገር ማንነትን መንከባከብ ሲባል የቡድን ወይም የብሄርን ማንነት ብቻ ማለት ኣይደለም። ብዙህ የሆኑ ሃገራት የፌደራል ስርዓትን የሚመርጡት ክልላዊ ማንነትንና ብሄራዊ ኣንድነትን ወይም ብሄራዊ ማንነትን ኣቻችሎ ጠብቆ ለመኖር ስለሚያስችል ነው። በሳይንሳዊ የፌደራል ስርዓት ውስጥ ሁሉም ማንነቶች እንክብካቤ ይሻሉ። ማንነትን ማሽቀዳደምና ከኣንዱ ማንነት ኣንዱ ይበልጣል ማለት የፌደራል ዶክትሪን ኣይመስልም። ማንነቶች እርስ በርስ ሳይጋጩና ኣንዱ ኣንዱን ሳይገዳደረው ማኖር የፌደራል ዶክትሪን ይመስላል። በመሆኑም ክልላዊ ማንነት ብሄራዊ ማንነትን ወይም ብሄራዊ ማንነት ክልላዊ ማንነትን ለማፍረስ ሳይጣጣሩ የሚኖሩበትን የመንግስት ስርዓት መቅረጽ ነው የፌደራል ስርዓትን መከተል ማለት። ወደ ኢትዮጵያ ስንመጣ ህገ መንግስቱ ወይም መንግስታዊ ስርዓቱ ሲዋቀር ኣንዱ ማንነት ኣንዱን በፈለገው ጊዜ ኣፍርሶት እንዲሄድ በር ከፍቶ ነው የተዋቀረው። የክልል መንግስት ከፈለገ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ፌደራሉን ሽርፍ ኣርጎ ገምሶት ሊሄድ ይችላል። ኣንቀጽ ሰላሳ ዘጠኝ የሚያሳየው ሃቅ ይህንን ነው። የኢትዮጵያ የፌደራል ስርዓት ሲዋቀር ክልላዊ ማንነት ብሄራዊ ማንነትን እንዲያፈርስ ተደርጎ የተዋቀረ በመሆኑ ከፌደራል ጽንሰ ሃሳብ በተቃራኒ የሚሄድ ነው። አቶ ስዩም ገልብጠነዋል የሚሉት ይህንን ከሆነ ተሳስተዋል። የሚገርመው ይህ አንቀፅ ሲፀድቅ ያልታየው ሌላው ጉዳይ ለምሳሌ ሌሎች ብሄሮች ሁሉ አብረው መኖርን ፈልገው ነገር ግን ኦሮምያ መገንጠል ቢፈልግ አገር መፍረሱን አለማስተዋሉ ነው። ኦሮሚያ ካለው የጂኦግራፊ አቀማመጥ አንፃር ቢገነጠል ደቡብና ሰሜን አብረው መኖር ቢፈልጉም እንኳን መኖር እንዳይችሉ አድርጎ ይሄዳል ማለት ነው። ይህ የሚያሳየው ይህ አንቀጽ አንዱ ሌላውን እያፈረሰ እንዲሄድ የሚያደርግ የኢትዮጵያንና የአለምን ሁኔታ ያላገናዘበ ነው። ለምሳሌ የተባበረችው ኣሜሪካ ብዙ ስቴቶች ኣሏት። ነገር ግን እነዚህ ስቴቶች በፈለጉት ጊዜ የፌደራል መንግስቱን የሚያፈርሱበት ስርዓት የለም። በኣንጻሩ የፌደራል መንግስትም ስቴቶችን ኣያፈርስም። ሁለቱም መንግስታት ስልጣን እየተጋሩ አየተጠባበቁ የሚኖሩበት ስርዓት ነው የተዋቀረው። የፌደራል ስርዓት የሚባለው ይሄ ነው። የኢትዮጵያ የፌደራል ስርዓት ከፍ ሲል እንደገለጽኩት የክልል መንግስት የመብቶችን ጥግ ይዞ እስከ መገንጠል ሲሄድ ብሄራዊ ማንነት ምንም ጠባቂ በህገ መንግስቱ ኣልተበጀለትም። እንዴውም ይሄ የመገንጠል መብት ዋስታና ነው ይጠብቀናል እያሉ ይቀልዳሉ። ይህ ኣይነት ስርዓት በኣለም ኣልታየም። ለምን የኢትዮጵያ የፌደራል ስርዓት ኣንዱ ማንነት ኣንዱን እንዲያፈርስ ሆኖ ተዋቀረ ካልን ኣንዱ ችግር ለብሄር ማንነት የተሰጠው የተሳሳተ ትርጉም ነው። የብሄር ማንነትን የሰው ልጆች የመጨረሻ የማይነካ ጠገግ ኣድርጎ ማሰብ ያመጣው ችግር ነው። ነገር ግን ኣንድ ቡድን ኣንድ ቋንቋ እየተናገረም በጭቆና ስር ሊሆን ይችላል። በቤተዘመድና በጂዖግራፊ ክፍፍሎች ግፎች ሊደርስበት ሊቀበል ይችላል። ኣንድ ብሄር ብቻውን ሜዳ ላይ ሲያገኘው ማይክሮ ልዩነቶች እየጎሉ ወደ ማክሮ ያድጉና እስከ መገንጠል ይደርሳሉ። ሁለቱ ኮርያውያን በኣሳብ ስለተለያዩ ብቻ ተለያይተው ኣሉ። ሶማሊያ ኣንድ ብሄር የምትባል ሆና ሶማሌ ላንድ ተገንጥላ ትኖራለች። ሆሞ ጂኒየስ የሆኑ ኣገራት በግፍ ኣገዛዝ በኣድልዎ የሚኖሩ ኣሉ። በመሆኑም ይህን ጠገግ ዞሮ መግቢያ የመጨረሻ ዋስትና ኣድርጎ ማሰቡ ማህበራዊ ሳይንስ ይጎድለዋል። ለነገሩም ከብሄር በታችም ሌሎች ልዩነቶች ኣሉ። እነዚህ ልዩነቶችም ጠገግ ናቸው ነገር ግን የሰው ልጅ የማምለጫ ዓለት ተደርገው ኣይወሰዱም። ጠንካራ ጠገግ የሚባለው ቤተሰብ ሲሆን ይህም ቢሆን ስፋት ስለሌለው የሰው ልጆችን ሰፊ ፍላጎት ኣያረካምና የግድ ሰፊ ጠገግ የሰው ልጅ ይሻል። ይህ ጠገግ ደግሞ በመርህ ላይ የተመረኮዘ ሆኖ የተለያዩ ቤተሰቦችን ቋንቋና እምነቶችን ሁሉ ይዞ መኖር ይችላል። ዋናው ጉዳይ የስብስቡን መውጫና መግቢያ ህግጋት መርህ ሳይንሳዊ እንዲሆን ማድረግ የህጉን ጨዋታ ከደምና ከዘር በላይ ማዋል ነው። በመሆኑም ብሄርን ያን ያህል መብት ኣጎናጽፎ ብሄራዊ ኣንድነትን የኮንትራት ቤት ኣድርጎ መነሳቱ በዚያ ጠገግ ስር ያሉትን ዜጎች ሁሉ ግራ ያጋባ የፌደራል ጠገግ ያደርገዋል። ኣገራቸው ዘላለማዊ ኣትመስላቸውም። አገር የሰው ልጆች ትልቁ ጠገግ ነውና ክብርና ትኩረት ይሻል። ዜጎች ሃገራቸው በየትኛውም ጊዜ የምትፈርስ ኣድረገው እንዲያስቡ የሚያደርግ ሥርአት መፈጠሩ ትልቅ ኪሳራ ነው። በመሆኑም ኣንድ የፌደራል ስርዓት ሲዋቀር እነዚህን ሁለት ማንነቶች እርስ በርስ እንዲጠባበቁ ተደርጎ መሆን ኣለበት። ሁለቱንም ጠገጎች መንከባከብ ያሻል።

ከዚሁ ከማንነት ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ የፌደራል ስርዓት ችግር ሁለቱን ማንነቶች እርስ በርስ እንዲፈራከሱ ኣድርጎ መዋቀሩ ሲሆን ሌላም ችግር ኣለበት። ለመሆኑ ብሄራዊ ማንነትን ችላ ብሎም ቢሆን የብሄሮችን ማንነትስ መጠበቅ ተችሏል ወይ? የሚል ጥያቄ እናንሳ። ባለፉት ሃያ ኣምስት ኣመታት ውስጥ የብሄሮች ማንነት የተጠበቀበት መንገድና ዘዴ ትክክል ኣልነበረም። በመሰረቱ ኣንድን ቡድን ማንነቱን እንጠብቅ ስንል በቋንቋው እንዲጠቀም በባህሉ እንዲጠቀምና እንዲኮራ ማድረግ ማለት ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ የሆነው ምንድን ነው? ካልን የብሄሮችን ማንነት ለመጠበቅ ሲባል ብሄሮችን ከኣለፈ መጥፎ ታሪክ ጋር ማጋጨት ኣንዱ ዘዴ ነበር። በተለይ የኦሮሞና የደቡቡን ማህበረሰብ በኣጼ ምኒልክ ላይ ቂም እንዲይዙ የታሪክ ግድፈቶችን ወደ ኣንድ ብሄር እንዲያላክኩ የማድረግ ዝንባሌ በሃይል ነበር። መንግስት ይህን ጉልበት ለብሄርተኝነት ስሜት ማሳደጊያ ሲጠቀም የሃገሪቱ ማህበራዊ ሃብት ጠፋ። መተማመን እየተነነ መጣ። የጎኖሽ ግንኙነትን ኣሻከረ። ይህ ኣይነቱ የብሄርተኝነት እድገት ሰዎች በባህላቸው እንዲደሰቱ የሚያደርግ ሳይሆን ከሌላው ጋር በባለፈ ታሪክ እንዲናቆሩ የሚያደርግ ጸረ ፌደራል ስርዓት ነው። ይህ የእድገት ዘዴ ሄዶ ሄዶ ያንኑ ብሄራዊ ኣንድነትን እየጎዳ የሚሄድ ነው። በርግጥ በኣሁኑ ጊዜ ከሃያ ኣምስት ኣመት በሁዋላ በተለይ ኣማራና ኦሮሞ ይህን ነገር እየሰበሩት ይገኛሉ። መንግስት በርግጥ ይህን ሲያደርግ የነበረው ለኣንድ ጠባብ ቡዳን ጥቅም ሲል ነው። ይህ ኣካሄዱ ጸረ ፌደራል ዶክትሪን ነው በርግጥ። የፌደራል ስርዓት ፍላጎት ብሄሮች ማንነታቸውን በኣንድ በኩል እየገነቡ በሌላ በኩል ደግሞ ብሄራዊ ማንነታቸውን እንዲያሳድጉ እጅ ለእጅ እንዲያያዙ ነበር።

4. የዴሞክራሲ ጉዳይ

የፌደራል ስርዓት የተፈጠረበትና የሚመረጥበት ኣንዱ ጉዳይ ሲስተሙ ዴሞክራሲን እንደ ልብ ያንሸራሽራል ከሚል ነው። የህግ ሪሶርስ ስለሚጨምር፣ ምርጫ ስለሚጨምር ዜጎች ታለንታቸውን እውቀታቸውን የሚያሳድጉበት ኢንቨስት የሚያደርጉበት መም ብዙ ይሆናል። ሰባዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸው የሚጠበቁበት ሲስተም ነው። ዶክትሪኑ ለቡድንም ለግለሰብም መብቶች የሚጨነቅ ይመስላል። ወደ ኢትዮጵያ ስንመጣ ግዙፍ ችግሮችን በዚህ ኣቅጣጫ እናያለን። ከመንግስት ኣምባገነናዊ ተፈጥሮ ባሻገር ሲስተሙ በራሱ የፈጠረው ግዙፍ የዴሞክራሲ ድርቅ (deficit ) እንዳለ እንመልከት።

የፌደራል ሲስተሙ ሲዋቀር እንደ ልዩነት የመጨረሻ ቅንጣት የታየው ብሄራዊ ልዩነት በመሆኑና ይህ ጠገግ እየተቆጠረ በነዚህ ጠገጎች ላይ የተመሰረተ የብሄር ፖለቲካ ስለተዋቀረ ዜገነት በመሃል ተረስቷል። ገና ሲጀምር ኢትዮጵያ የብሄር ብሄረሰቦች ኣገር ናት…. ብሎ የሚጀምር ህገ መንግስታዊ ስርዓት ያለ ሲሆን ዜጎች በነዚያ ቡድን ውስጥ ታጭቀው የሚታዩ ሲሆን ዜግነት በክልል ወይም በቡድን ስልቻ ውስጥ እንዲታፈን ተደርጓል። ዜጎች በኢትዮጵያ ኣገራቸው ውስጥ ከወዲያ ወዲህ ሲንቀሳቀሱ የዴሞክራሲ ድርቅ ይመታቸዋል። ለምሳሌ ያህል በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኣማሮች ኦሮሚያ ይኖራሉ። እጅግ ብዙ ኦሮሞዎች በደቡብ በሰሜን ይኖራሉ፣ ወላይታዎች፣ ጉራጌዎች፣ ዶርዜዎች ወዘተ ተንቀሳቅሰዋል። እነዚህ ዜጎች ያለ ስልቻቸው ሲገኙ ዴሞክራሲያዊ መብታቸው ይሸራረፋል። ምክንያቱም ስርዓቱ የሚቆጥረው በነሲብ ወይም በጅምላ ስለሆነ ዜግነት ስለተዘለለ ነው። ቀላል ምሳሌ እናንሳ ብንል የሃረሪን ጉዳይ ማንሳት ይቻላል። ይህቺ ክልል ስትመሰረት ኣስራ ዘጠኝ ወረዳዎች ከኦሮምያ የተጨመረ ሲሆን ሃረሪዎች ስምንት በመቶ ገደማ ብቻ ናቸው። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኦሮሞዎችና ኣማራዎች ናቸው። በፌደራል ስርዓቱ እምነት ይህ ክልል በዋናነት የሃረሪ ነው። ይህ “በዋናነት የሃረሪ ተወላጆች ነው” ማለት ምን ማለት እንደሆነ ኣልተበየነም። ዋናው ጉዳይ ግን ዋና ያልሆኑ ዜጎች ግን ፖለቲካዊ መብታቸው ይሸራረፋል። በዚያ ክልል ኣማራ የሃረሪ ሊቀመንበር መሆን ኣይችልም። የፈለገውን ያህል ህዝብ ቢመርጠውም ችሎታ ቢኖረውም ኣይችልም። ኦሮሞ ወይም ትግሬ የፈለገውን ያህል አቅም ቢኖረውም ሊመረጥ አይችልም። ያም ብቻ ሳይሆን የዚያ ክልል ዋና ባለቤት ባለመሆኑ ከፍተኛ የዜግነት መብቱን የጣሰ የፌደራል ስርዓት ነው የተመሰረተው። ይህ ኣይነት የፌደራል ስርዓት ኣገሪቱን የተለያዩ ኣገራት ህብረት ያስመስላታል እንጂ በፌደራል ስርዓት የምትተዳደር ኣያስመስላትም። ቤንሻንጉል ጉሙዝ ብንሄድም ተመሳሳይ ችግር ኣለ። ኣማራና ኦሮሞ ብዙ ያሉ ሲሆን በዚያ ያሉ እነዚህ ብሄሮች የዜግነት መብታቸው ይገፈፋል። በኣጠቃላይ ከክልሉ ውጭ የሚኖረውን የኢትዮጵያን ህዝብ ስናይ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ሲሆን በድምሩ ምናልባትም በቁጥሩ ከኦሮሞና ከኣማራ ቀጥሎ በሶስተኛ ደረጃ ይሰለፍ ይሆናል። እንግዲህ ይህ ሁሉ ሚሊዩን ህዝብን ነው በዚህ የፌደራል ስርዓት ውስጥ የክልል ዋና ባለቤት ያልሆነውና የዴሞክራሲና የዜግነት መብቱ የተገሰሰው። ይህንን ስናይ ከፍተኛ የዴሞክራሲ ደፈዚት ያለበትን የፌደራል ስርዓት ኢትዮጵያ እየተከተለች እንደሆነ መረዳት ይቻላል። ሌላው ለዴሞክራሲ ድርቅ የተጋለጠው ማህበረሰብ ደግሞ ቅይጡ ዜጋ ነው። ከሁለትና በላይ ብሄሮች የተወለደው ህዝብ ብዙ ሲሆን ይህ ህዝብ በዚህ መንግስት የፌደራል ስርዓት ጊዜ ቀርቦለት የነበረው ምርጫ ሳይንሳዊ ኣልነበረም። መንግስት ይህን ሁሉ ዜጋ ወይ ከናትህ ወይ ካባትህ ኣንዱን ምረጥ ተብሎ ነበር። ይሄ ሥነህይወታዊም ሆነ ማህበራዊ ሳይንስ የጎደለው ተራ የሰፈር ኣሳብ ነው። ይህ ችግር የመጣው ከፍ ሲል እንዳልነው የሰው ልጆችን ጠገግ ስናይ ኣገርን ሳይሆን የብሄርን ጠገግ አልፋና ኦሜጋ ኣድርገን ከማሰባችን ጋር ተሳስቶ የመጣ ችግር ነው። በሌላ በኩል ከተሞች ኣካባቢ ኣድገው ስለብሄር ደንታ የሌላቸው ቤተሰብ የማይጠይቁና የማይፈልጉ ብዙ ዜጎችም ይህ ስርዓት ኣስጨንቋቸዋል። ለነሱ ኢትዮጵያዊነት ብሄር ቢሆን ይመርጣሉ። እንዲህ ኣይነት ዜጎችን ያስጨነቀ የፌደራል ስርዓት ነው። በኣጠቃላይ ግን ለዴሞክራሲ እድገት ከፍተኛ መሰናክል ያለበት ስርዓት በመሆኑ የፌደራልን ትምህርት ይቃወማል። ስርአቱ ከላይ ሆኖ ማየት ያልቻለ ስለሆነ ከላይ ያለውን ትልቅ ጠገግ ከቁም ነገር አይቆጥረውም።

5. የኢኮኖሚ ጉዳይ

የፌደራል ስርዓት ኣንዱ ዋና ኣጀንዳው ልማት ነው። ለኢኮኖሚ እድገት ትልቅ በር መክፈት የመሮጫ መም ማብዛትና ዜጎች ውጤታማ ትርፋማ እንዲሆኑ ማድረግ ነው። የኢትዮጵያን የፌደራል ስርዓት ለኢኮኖሚ እድገት ይመቻል ወይ? ስንል ሌላው በጣም ኣሳሳቢ ነገር ይታየናል። ከመነሻው የተፈጥሮ ሃብት ክፍፍል ላይ ግልጽነት የለውም። ክልሎች የራሳቸውን ሃብት ይጠቀማሉ ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ኣልተበየነም። ከሁሉ በላይ ግን ኣንዱ ማንነት ሌላው እንዲያፈርሰው ሆኖ የተዋቀረ ኣገር እንደምን ሆኖ ነው ብሄራዊ ቅርስ የሚይዘው? ለብሄራዊ ቅርስ ብሄራዊ ኣንድነት ወሳኝ ነው። በቅርቡ የተከሰተን ምሳሌ ላንሳ። የመንግስት ሰዎች ተማሪዎችን ሰብስበው ለኣባይ ግድብ ብር ኣዋጡ ያላሉ። ከተማሪዎች የተጠየቀው ጥያቄ ግን ኣስደንጋጭ ነበር። ተማሪዎች ምንድን ነው ያሉት ገንዘባችንን ኣዋጥተት ኣዋጥተን ከገነባን በሁዋላ ይህ ኣሁን ግድቡ ያለበት ብሄረሰብ እኔ በቃኝ ብሎ ኣንቀጽ ሰላሳ ዘጠኝን ጠቅሶ ቢገነጠልስ? የሚል ጥያቄ ቀርቧል። ይሄ የሚያሳየው ዜጎች ለብሄራዊ ቅርስ ሃይላቸውንና ገንዘባቸውን ኢንቨስት እንዳያደርጉ የሚከላከል እንቅፋት መኖሩን ነው። በርግጥም መንግስትም ትንሽ ጅልነት ያለው ይመስላል። በኣንድ በኩል መገንጠል መብት ነው ብሎ ኢትዮጵያን የኮንትራት ኣገር ኣድርጎ ካዋቀረ በኋላ በሌላ በኩል ደግሞ ኑ ብሄራዊ ልማት እንስራ ብሎ እንዴት ይቀሰቅሳል። ከተለያየን ለማን ሸጠን እንካፈለዋለን። ውጥንቅጡ የወጣ ስርዓት ነው በውነት።

በሌላ በኩል ደግሞ መሬት የመንግስት ሲሆንና የዜጎች የመንቀሳቀስ መብት በክልል ሲገደብ ኢኮኖሚው እንዳያድግ ማድረጉ ኣያጠያይቅም። ከዚህ ችግር በተጨማሪ የፖለቲካው ጨዋታ በብሄር ላይ በመቆሙ ለሙስና በጣም ተጋልጠናል። የኣንድ ቡድን ሃብት ያለልክ ሲያድግ ሌላው እየቆረቆዘ እንዲሄድ ኣድርጓል። እነ ኤፈርት የሀገሪቱን ኣንጡራ ሃብት የያዙ ድርጅቶች ሲሆኑ በዋናነት ሃብትነታቸው የትግራይ ነው ይባላል። ይህ ኣይነቱ የኢኮኖሚ እድገት ለዜጎች ምቾት ኣይሰጥም ብቻ ሳይሆን ለግጭትም መንስዔ ይሆናል።

በሌላ በኩል ኣንድ የኢኮኖሚ ምሁር የኢትዮጵያን ብሄራዊ ሃብት በተመለከት ጥሩ ግምገማ ኣድርገው ነበር። እኚህ ምሁር ያሉት ምንድን ነው ኣገሪቱ በኣጠቃላይ ሁለት ጊዜ የብሄራዊ ሃብት ዝውውር ኣድርጋለች ይላሉ። የመጀመሪያው የሃብት ዝውውር በደርግ ጊዜ የተካሄደው መሆኑ ነው። እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ ከዘውድ ኣገዛዝ ስትላቀቅ ደርግ ያደረገው የመጀመሪያ ነገር የመሬት ኣዋጅ ነበር። በባላባቶች ተይዞ የነበረውን መሬት በኣንድ ለሊት ኣዋጅ ነጥቆ ለድሆች በገመድ ኣካፍሏል። ቀጥሎም የከተማ ትርፍ ቤትና ቦታን በሚመለከት በኣንድ ለሊት ኣዋጅ አውጆ ሁለት ቤት ያለውን ኣንዱን በመንጠቅ ያንን የተነጠቀውን ቤት ለቀበሌ እየሰጠ ድሆችን እያዳበለ ሸንሽኖ ኣድሏል። ይህን የሃብት ዝውውር ስናይ ውሳኔው ፖለቲካዊ ብቻ በመሆኑ የሃገሪቱን የረጅም ጊዜ የኢኮኖሚ እድገት ሳያገናዝብ የተወሰነ ነበር። ሃገሪቱ ሃብትን ስታዛውር ጥበብን ኣላሳየችም ለማለት ነው። የሆነ ሆኖ ግን መሬት የሌላቸው መሬት በማግኘታቸው የቀበሌ ቤት በመብዛቱ የተደሰቱ ፍትህ ወረደ ያሉ ብዙ ናቸው። ይሁን እንጂ ኣንዳንድ ምሁራን እንደሚሉት ሃብት ተበጣጠሰ ሃገሪቱ ለእድገት የሚያንደረድራትን ሁሉ በጣጠሰች ይላሉ። ስለሆነም ሁላችን ተያይዘን ተመሳሳይ ድሃ ሆነን ቁጭ ከማለት ውጭ የመጣ ነገር የለም እንዴውም ድህነት ወደ ገበሬው የገባው በዚህ ዘመን ነው ይላሉ። ያም ኣለ ይህ በወቅቱ ኢትዮጵያ የተከተለችው የሃብት ክፍፍል የሶሻሊዝም ርእዩትን መሰረት ያደረገ በመሆኑ ሁኔታው በደርግ በኩል በጣም ስሜታዊና የማይቀለበስ ኣይነት ነበር። ደርግ በዚህ ጉዳይ ላይ የባለሙያ ምክርም ሊሰማ ኣይፈልግም ነበር። ይህ የብሄራዊ ሃብት ዝውውር ከተጠናቀቀ በሁዋላ የሃገሪቱ ኣጠቃላይ እድገት በጣም ኣዝግሟል። ጎረቤት ኣገራት የተሻለ ሲራመዱ እኛ ዘገየን።

ደርግ በኢህኣዴግ ሲተካ ደግሞ ሌላው የሃገር ሃብት ዝውውር ተደረገ ይላሉ ምሁራን። ይህ ዝውውር እንደ ደርግ በህግና በግልጽ ሳይሆን በጣም ሲስተማቲክ በሆነ መንገድ የሃገር ሃብት ወደ ኣንድ ጠባብ ቡድን ተዛውሯል። ፖለቲካው ብሄርተኛ ሲሆን ስልጣኑን የያዘው ህወሃት የራሴ ወደሚለው ቡዽን ብዙ ሃብት ኣዛውሯል። ሲጀምር ሃገሪቱ ሃብታም ታፈራ የነበረው ብዙ ድሆችን እየጨመረች ነው። ብዙ ድሆችን እያፈራች ኣንድ ሃብታም ታወጣለች። ይህ ሃብታም ደግሞ በኣብዛኛው ከኣንድ ብሄር እንዲሆን በመደረጉ የተዛወረው ሃብት ለቅራኔ ምክንያት ሆኗል። ይህ ችግር የፖለቲካው ተፈጥሮ ስሜት ያመጣው በመሆኑ ከፌደራሉ ቅርጽ ጋር ይያያዛል። ዛሬ የኦሮምያና የኣማራ ኣንዱ ጥያቄ በኢኮኖሚ እኛ ተጎዳን ሃብት ወደ ኣንድ ጠባብ ቡድን ተዛውሯል ነው። ለምን ድሃ ሆንን ሳይሆን ያልንን ሃብት ወደ ኣንድ ቡድን ለምን ኣዞራችሁት ነው። የፍትህ ጥያቄ ነው። በሌላ በኩል መሬት የመንግስት በመሆኑና ባለመሸጥ ባለመለወጡ ግብርናው እንዳያድግ ኣድርጎታል። በዚህ የግብርና ፖሊሲ ኢትዮጵያ የቱንም ያህል ግብአት ብትጠቀም ኣታድግም። በአጠቃላይ ግን የብሄር ፌደራሊዝሙ ብሄራዊ ሃብት እንዳንይዝ የሃብት ክምችት ለጥርጣሬና ለግጭት መንስዔ እንዲሆን ሙስና እንዲጨምር ኣድርጎብናል።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያን ፊስከል ፌደራሊዝም ስናይ የምንማረው ጉዳይ አለ። ሁሉም ክልሎች የራሳቸውን ባጀት ለመሸፈን ያላቸው አቅም ወደ 27 እና 28 ምን አልባት ቢበዛ 30 በመቶ ብቻ ነው። የሚያገኙት ገቢ ይህን ያህል ብቻ ነው የሚደግፋቸው። ሁሉም ክልሎች በአማካይ እስከ 70 በመቶ የሚሆነውን ባጀታቸውን የሚደጎሙት ከፌደራል መንግስት ነው። የፌደራል መንግስት እርዳታና ብድርንም ጨምሮ ነው ይህን ድጎማ የሚያደርገው። ይህ የሚያሳየው ሃገሪቱ ከኢኮኖሚ አንፃር ማእከላዊነት እንዳላት ነው። የፌደራል መንግስትም ከኢኮኖሚ አንፃር እጅግ ጠንካራ ነው። ብሄሮች ልባቸው እዚያ ፌደራል ላይ የተሰቀለውም ሰርተንም በርዳታም ያገኘነውን ፍትሃዊ በሆነ መንገድ እንድንካፈል የፌደራሉ ስልጣን ፍትሃዊ በሆነ መንገድ መከፋፈል አለበት ነው።

6. ለኣስተዳደር ኣመቺነት

የሚገርመው ነገር እስካሁን ባየንበት ኣንግል በሙሉ ከፌደራል ጽንሰ ሃሳብ ጋር የሚጣረስ ስርዓት ነው ኢትዮጵያ የምትከተለው። ይህንን ሁሉ ካየን በሁዋላ ለመሆኑ እንዴው ለኣስተዳደርስ ይመቻል ወይ ብለን ብንጠይቅም ትላልቅ ችግሮች ተጋርጠውበታል። ሃረሪን የምታክል ኣራት መቶ ኪሎሜትር ስኮየር የማትሞላ ክልል ኣድርጎ በሌላ በኩል ደግሞ ኦሮምያን የሚያህል ግዙፍ ኣገር ኣንድ ክልል ኣድርጎታል። የክልሎችን ዲሞግራፊና ደንሲቲ ስናይ በጣም ለኣስተዳደር የማይመች ክፍፍል እንደሆነ እናያለን።

7 አብዮታዊ ዴሞክራሲና የፌደራል ሥርዓት

አብዮታዊ ዴሞክራሲ የሚባለው ነገር በኢትዮጵያ ውስጥ ከህገ መንግስቱም በላይ ቦታ የተሰጠው ይመስላል። በርእዮቱ ግልጽነት ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች እንዳሉ ሆነው ምሁራን እንደሚሉት አብዮታዊ ዴሞክራሲ ቀድሞ የተፈጠረው በሌኒን ሲሆን ዓላማው ወደ ሶሻሊዝም ስርአት መሸጋገሪያ ይሆናል ተብሎ ነበር ይባላል። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ደግሞ ወደ ሊብራል ዴሞክራሲ እጓዝበታለሁ ትላለች እያሉ የሚተቹ አሉ። ርእዮቱ ራሱ የተሳሳተ ባቡር ነው ነው ነገሩ። ትልቁ ጉዳይ ግን ይህ አብዮታዊ ዴሞክራሲ የሚባል ትምህርትና ልማታዊ መንግስት የሚባል ዶክትሪን የሚፈልገው አንድ ነገር ቢኖር ጠንካራ ማእከላዊነት ያለው ሥርዓት ነው። ህወሃት/ኢህአዴግ ሁሉ በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ትምህርት ካልተጠመቀ ሞቼ እገኛለሁ የሚያሰኘው ትምህርቱ ዩኒፎርሚቲን ወጥነትን ስለሚጠይቅ ነው። ኢትዮጵያ ይህንን ርእዮት ከህገ መንግስት አብልጣ ይዛ በሌላ በኩል የፌደራል ስርአትን መተግበር አትችልም። ፌደራሊዝም በተፈጥሮው ሊብራል ነው። ለቀቅ ብሎ ስቴቶች በራሳቸው እውቀትና ችሎታ እንዲንቀሳቀሱ እድል የሚሰጥ ሲሆን አብዮታዊ ዴሞክራሲ ጠንካራ አሃዳዊ መንግስትን ይሻል። በአሁኑ ሰአት በገዢው ፓርቲ አካባቢ የዚህ ችግር ነፀብራቅ ብዙ ያልታየው በእውኑ የፌደራል ስርአት ስለሌለ ነው እንጂ እውነተኛ

የፌደራል ስርአት ቢኖር አብዮታዊ ዴሞክራሲ ችግር ፈጠረ ተብሎ ቶሎ ይጣል ነበር። ልማታዊ መንግስትነትም እንደዚሁ ነው። ከፍተኛ የሆነ ብሄራዊ ስሜትና አሃዳዊ አስተዳደር ይጠይቃል። እንግዲህ ሃገራችን እየሆነ ያለው ምንድን ነው? አገሩን ሁሉ በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ለማጥመቅ እየተሞከረ በሌላ በኩል የፌደራል ስርአትን ለመጎተት ይሞከራል። አብዮታዊ ዴሞክራሲ እንኳን አቶ ስዩም የሚሉትን አይነት ፌደራሊዝም ይቅርና መድብለ ፓርቲን የሚሸከም ትከሻ የለውም። በጣም ወጥነትን ይሻል። በአጠቃላይ ያለው የፓለቲካ ውቅር ማለትም የብሄር ፓለቲካ፣ አብዮታዊ ዴሞክራሲ፣ልማታዊ መንግስት፣ የብሄር ፌደራሊዝም አብረው የማይሄዱ አንዱ ለአንዱ ጠንካራ ደጋፊ ያልሆኑ ናቸው። እነዚህ የማይደጋገፉ ነገሮች ሁሉ የሚተራመሱበት ስርአት ነው ያለን።

በአጠቃላይ ከመንግስት አምባገነናዊ ባህርይ በተጨማሪ ከፍተኛ የአወቃቀርና የርእዮት ችግሮች አሉብን።

ምን ዓይነት የመንግስት ስርዓት ያሻናል?

እንግዲህ ኣሁን ያለው የኢትዮጵያ የመንግስት ስርዓት ግዙፍ ችግሮችን የያዘ በመሆኑ ባስቸኳይ መለወጥ ይኖርበታል። ታዲያ ሲለወጥ ምን ኣይነት የመንግስት ስርዓት ያሻናል የሚለው ጥያቄ በጥብቅ መታየትና መጠናት ኣለበት። ከዚህ በፊት ደጋግሜ በጻፍኳቸው ጽሁፎች እንደጠቋቆምኩት ኢትዮጵያ አዲስ የመንግስት ስርዓት ያሻታል። ይህ ስርዓት ምን መምሰል ኣለበት ካልን ሰኪዩላር የፌደራል ስርዓት ሆኖ ነገር ግን የኣገር ኣስተዳደር ስናዋቅር ከተለመዱት ሶስቱ የመንግስት ኣካላት ማለትም ህግ ኣውጭው ህግ ኣስፈጻሚውና ህግ ተርጓሚው በተጨማሪ ኣንድ የአርበኞች ቤት ቢኖረንና አራት ሲስተሞች ቢኖሩን ጥሩ ነው። ይህ የኣርበኞች ቤት የባህል መሪዎችን የሚይዝ ከየባህላዊ ቡድኑ የተውጣጡ ኣባላትን የሚይዝ ሆኖ የባህልና የሰላም ጉዳዮችን እየሰራ ተከብሮ ይኖራል። በዚህም የቡድኖች የባህላዊ ማንነት ይጠበቃል የእኩልነት ስሜት ይመጣል። የብሄር ኢንተርፕሩነርስ የተባሉት ቦታ ያገኛሉ። ሁለተኛው ክፍል ደግሞ ሶስቱን የመንግስት መዋቅሮች የሚይዘው መንግስት በህዝብ ምርጫ ስልጣን እየያዘ የሚኖር ይሆናል። እነዚህ ሶስቱ የመንግስት ስልጣኖች ቼክና ባላንስ እያደረጉ ይኖራሉ። የሃገሪቱ የስልጣን መወጣጫ ደግሞ የፖሊሲና የኣመለካከት ልቀት ብቻ እንዲሆን ማድረግ ያሰፈልጋል። ኢትዮጵያን ከብሄር ፖለቲካ በማላቀቅ ጨዋታው በብሄራዊ ኣጀንዳ ዙሪያ እንዲሆን መደረጉ የፌደራል ስርዓቱን ሰኪዩላር ወይም ሳይንሳዊ ያደርገዋል። ኢትዮጵያ ኣዲሱን የፌደራል ስርዓት ስታዋቅር በስቴቶችና በፌደራል መንግስት መሃል የስልጣን መካፈል የሚኖር ሲሆን ኣንዱ መንግስት ሌላውን እንዲጠብቅ ተደርጎ መዋቀር ይኖርበታል። በሌላ በኩል ደግሞ በኣሁኑ ሰዓት ያለውን የፍትህ ስርዓትና የፖለቲካ ሹመትን መጣበቅ ማላቀቅ ያስፈልጋል። የፌደሬሽን ምክር ቤት የሚሰራውን የህገ መንግስት ትርጉም ጉዳይ ኣፍርሶ ራሱን የቻለ የህገ መንግስት ትርጉም ፍርድ ቤት ማቋቋም ኣንዱ የኣዲሱ የፌደራል ስርዓት ስራ መሆን ያይኖርበታል።

ሌላው ትልቁ የኣዲሱ የፌደራል ስርዓት ዋና መሰረት ሊሆን የሚገባው የኢትዮጵያውያን አዲስ ኪዳን ነው። ይህ ማለት ካለፍንበት የፖለቲካ ስርዓትና ኣሁን ካለንበት የብሄር ፌደራሊዝም ኣንጻር ብዙ ብዥታዎች ተፈጥረዋል። የተፈጥሮ ሃብትን በሚመለከት፣ ባህላዊ ማንነትን በሚመለከት፣ የጋራ ሃብትን በሚመለከት ብዥታዎች ተፈጥረዋል። ይህንን ጉዳይ ለማጥራትና ኣገራችንን በማይነቃነቅ መሰረት ላይ ጥለን ወደ ልማት ለመግባት ኢትዮጵያውያን ኣንድ ከፍ ያለ ኪዳን መግባት ይኖርብናል። ይህ ኪዳን ህገ መንግስት ሳይሆን ከዚያ በላይ የሚውል ለትውልድ የምናሳልፈው ቃል ኪዳን ነው። በይዘቱ የምናነሳው ጉዳይ ያሉንን የተፈጥሮ ሃብትና እሴቶች ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት መስዋዕት የምናደርግበት ከፍተኛ ኪዳን ነው። ይህ ኪዳን የፖለቲካ መሰረታችን የፌደራል ስርዓት መሰረታችን ይሆናል። በጠራ ማህበረ ፖለቲካ መሰረት ላይ ቆመን እንድንቀጥል ይረዳናል። በሌላ በኩል ኣዲሱ የፌደራል ስርዓት ሲዋቀር ስቴቶች የብሄር ስም ይዘው ሳይሆን ሌሎች ስያሜዎች እየተሰጧቸው እንዲዋቀሩ መደረግ ኣለበት። ከዚህ በተጨማሪ የፌደራል

ስርዓቱ ህገ መንግስታዊ ዳኛ ብቻ ሳይሆን ኦዲተርም ቢኖረው ጥሩ ነው። ይህ ኦዲተር ስቴቶችን የሚያነቃቃ ስራ እየቆጠረ የሚከታተል ቢሆን ጥሩ ነው። ይህ የፌደራልን ስርዓት ኣይጥስም። ይህ ኦዲተር ስቴቶችን ብቻ ሳይሆን የፌደራል ተቋማትንም የሚያነቃቃ ስራ የሚቆጥር ቢሆን መነቃቃትን ያመጣል።

አዲሱ የፌደራል ስርዓት ሲዋቀር የቋንቋ ኣጠቃቀምን በተመለከት ኣዲስ የቋንቋ ኣጠቃቀም መቀየስ ይኖርበታል። ኢትዮጵያ እንደ ሃገር ያላትን የጎኖሽና ቀጥታ ግንኙነት ለማሳለጥ የህብረት ቋንቋ ይሻታል። በዚህ መሰረት ኣንድ የህብረት ቋንቋ ይኖረናል። ከዚህ በሁዋላ ስቴቶች እንደ ሁኔታው እስከ ሁለት የሚደርስ ኦፊሺያል ቋንቋ እንዲኖራቸው ሊደረግ ይቻላል። ይህ ማለት የህብረቱ ቋንቋ እና ኣንድ በዚያ ስቴት ስር ያሉ ብዙ ሰዎች የሚናገሩት ቋንቋ ማለት ነው። ከዚህ በሁዋላ በመላው ሃገሪቱ በማዘጋጃ ቤት ደረጃ የህብረት ቋንቋና የኣካባቢ ቋንቋ ኦፊሺያል እንዲሆኑ ማድረግ ይቻላል። ይህ ኣሰራር በኢኮኖሚ ላይ የሚያመጣው ተጽእኖ ጉልህ ኣይሆንም። የግድ የብሄሮች መብት መጠበቅ ኣለበት። ስለዚህ ኢትዮጵያ በኣዲሱ ኣስተዳደር የቋንቋ ኣጠቃቀሟን እንዲህ ብታደርግ ሁሉም የሃገሪቱ ቋንቋዎች በታችኛው የስልጣን ርከን ላይ ስለሚሰሩ የቋንቋ አጠቃቀም ፍትህ ይወርዳል። ዜጎች በቋንቋቸው ኣገልግሎት ሲያገኙ ልማት ይፈጥናል። የሃገር ፍቅር ስሜት ይጨምራል። በመሆኑም ኣዲሱ ስርዓት በዚህ መንገድ ቢዋቀር የተሻለ ነው። ስርዓቱ ማንነትን ሊንከባከብ የሚችለው በዚህ መንገድ ቢሆን የተሻለ ይሆናል። የስቴቶችን ኣመሰራረት በተመለከተ የህዝብ ኣሰፋፈርን ለኣስተዳደር ኣመቺነትን እያዩ መመስረት ይገባል። ከዚህ በተጨማሪ ህገ መንግስቱ ስቴቶችና ፌደራል መንግስት የሚካፈላቸውን ስልጣኖች ለይቶ ማስቀመጥ ኣለበት። ሁሉቱ መንግስታት ኣብረው የሚሰሯቸውንም እንዲሁ በግልጽ ማስቀመጥ ይኖርበታል። ግልጽና ሃቀኛ የስልጣን ክፍፍል ያለበት ስርዓት መፍጠር ጥሩ ነው። በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ፓለቲካዋን ከብሄር ፓለቲካ ማላቀቅና ባህልን በሌላ ጠገግ መጠበቅ ይኖርባታል። እንዲህ ስታደርግ የተሻለ ሥርአት ትመሰርታለች።

አስተያየት ወይም በጽሁፉ ዙሪያ ጥያቄ ካለ በሚከተለው አድራሻ ያገኙኛል

geletawzeleke@gmail.com

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!

↧

በሳውዲ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ኢህአዴግ ተወግዶ በአስቸኳይ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም ጠየቁ።

$
0
0

ኢንጂነር መሃመድ አባስ ከሪያድ | ሳውዲ አረቢያ

ሴፕቴምበር 15 2016 ምሸት ሪያድ ከተማ ውስጥ የዱአ እና ሰደቃ ፕሮግራም በማድረግ ለሃገራቸው ሰላም ጸሎታቸውን ያደረሱት ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ ሙስሊሞች አንድነት ድረጀት አስተባባሪነት ኢትዮጵያ ስላለችበት ወቅታዊ ሁኔታ እና በድርጀቱ ቀጣይ የትገል መረሃግበር ዙሪያ ባደረጉት ሰፊት ውይይት የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስረአት ኢትዮጵያ እና ህዝቧ አሁን ከገቡበት ቀውስ ለማዳን የሽግግር መንግስት ማቋቋም እንዳልበት ባወጡት የአቋም መግለጫቸው አሳስበዋል ። የኢትዮጵያ ሙስሊም የአወሊያ ን የትምህረት መዕከሉን እና የሙስሊሞች ጉዳይ ከፍተኛ ጉባኤ ካጣበት እና ሀባሽን አልጋትም ብሎ ላለፉት 4 አመታት እልህ አስጨራሽ ትግል ካደረገ በሃላ በከፊልም ቢሆን ከጎኑ ያጣቸው ወኪሎቹ ከእስር ነጻ ወጥተው ለማየት በመብቃታቸው ፈጣሪያቸውን በማመስገን አሁንም የቀሩት ከእስር እንዲወጡ ነጻነታቸውን እንዲያፋጥነው ምኞታቸውን ገልጸዋል ።
muslim

የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስረአት በወሰደው እርምጃ ግራ የተጋባው ሙስሊሙ ማህበረሰብ ስረአቱ የሰማኝ እንድሆን ብሎ የካቲት 26 2004 ወኪሎቹ ከፌደራል ጉዳዩች ሚንስትር ጋር ውይይት ካደረጉ በሃላ እስላምዊ መንግስት ልታቋቁሙ ነው በሚል በአሸባሪነት በመፈረጅ ሃምሌ 6 2004 ለሊት የአጋዚን ጦር አወሊያን ሰብሮ በመግባት ብዙዎችን ደበደበ አቆሰለ ገደለ የተረፉትን እስርቤት በማጋዝ አንከራተተ አሰቃየ ብለዋል። ሃምሌ 12 2004 ጀምሮ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን ደጋፊዎች እና ተባባሪዎች ናቸው ያላቸውን ንጽሀን ከያሉበት አስሶ በመያዝ በማዕከላዊ የስቃይ እስርቤት በማጎር ብርቅ የሃገር አሌታዎችን የስቃይ ሰለባ አደረጋቸው ፡፤ ይህ ባለበት ሁኔታ ላለፉት 4 አመታት ህዝበ ሙስሊሙ በሰላማዊ መንገድ ሲያቀርቡ የነበረውን የመብት ጥያቄ ጆሮ ዳባ ልበስ ያለው የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስረአት ግፍ ሲፈጽምባቸው የነበሩትን የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት በነጻ በማሰናበት ከመሸበት በሃላ ህዝበ ሙስሊሙን ለመጨበጥ እያደረገ ያለው ጥረት ተያይዞ ለመውደቅ ካልሆነ በቀር ትርጉም እንደሌለው ሙስሊም ኢትዮጵያውያኑ ባወጡት የአቋም መግለጫቸው ገልጸዋል፡፡ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ የዘራውን እያጨደ መሆኑን የሚጠቅሰዋ መግለጫ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በስረአቱ የተነጠቁትን ህገመንግስታዊ መብቶቻቸውን ለማስከበር ጠላትህን ውሃ ሲወስደው እትፍ ብለህ ጨምረበት በማለት ስረአቱ ያበቃለት መሆኑን አመልክቷል፡፤ የኦሮሚያን ህዝብ አመጽ ተከትሎ በአማራ የተቀጣጠለው ህዝባዊ እቢተኝነት ሰረአቱን በአጭር ግዜ ውስጥ ምን ያህል እንዳሽመደመደው ያወሳው መግለጫ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች አንድነታቸውን ጠብቀው ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ላይ ተመሳሳይ የትግል ስልቶችን ተከትለው ቢሆን ኖሮ ለ አይቀሬው ድል ይበቁ እንደ ነበር በመግለጽ የጎንደር ህዝብ አንድነቱን ጠብቆ በስረአቱ ላይ እያሳደረ ያለው ተጽእኖ ለህዝበ ሙስሊሙ ትምህረት ሊሆን እንደሚገባ ጠቅሷል::

በተደጋጋሚ ህዝበ ሙስሊሙ ላቀረበው ህገመንግስታዊ የመብት ጥያቄ መልስ ከመስጠት ይልቅ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ለሚመከረው ምክር እና ለሚጠየቀው ጥያቄ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ያዋጣኛል ባለበት መስመር ህዝብ እየደፈጠጠ እዚህ ደርሷል የሚለው መግለጫ። ትላንት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስረአት በሙስሊሙ ህዝብ ላይ የጀመረውን የግፍ ዱላ በደሃው አርብቶ አደር እና አርሷ አደሩ ላይ በማሳረፍ በኦሮሚያ ያቀጣጠለውን እሳት በአማራው ህዝብ ላይም በመለኮስ የሰፊው ህዝብ ጠላት መሆኑን በገሃድ አረጋግጦል ብሎል። የኦሮሚያ እቢትኝነት ወደ ሰሜኑ ተሸጋግሮ ስትንት የተለፋበት እና ለብዙዎች ስለባ መረብ የሆነው የአንድ ለአምስት የአደረጃጀት መረብ ተበጣጥሶ ምንም መቋጠር አቅቶታል የሚያወሳው መግለጫ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ሲመካበት የነበረው የፌደራል እና የአጋዚን ጦር ሃይል በህዝብ ላይ የከፍተው ጥቃት እንደማያዋጠው ተገንዝቦ የጥፋት እጁን በመስብሰብ ህዝቤን ማለት ጀመሯል ብሏል፡፤ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች አንድነት መግለጫ በማጠቃለያው ዛሬ ለኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት የምናስተላልፈው መልዕክት እስረኞቼን ፍታ ጥያቄን መልስ ሳይሆን ታስረሃል እና ከዚህ በኃላ የመጨረሻ ስህተት እንዳትሰራ የሽግግር መንግስት ተቋቁሞ ሃገር እንድትደን በአስቸኳይ ተገቢውን እርምጃ እንድትወስድ በአጽኖት እናሳስባለን ብሏል።

↧

“ደም የሚያፈስ መንግስት ሃገር ሊያለማ አይችልም…”ሲሉ ዲያቆን ሃይለጊዮርጊስ ተፈራ አስተማሩ |ቪዲዮውን ይዘነዋል

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ዲያቆን ሃይለጊዮርጊስ ተፈራ “የደሙ ድምጽ ይጮሃል” በሚል ርዕስ ባስተላለፉት አዲስ ስብከት ነብሰገዳዮች ሃገር ሊያለሙ አይችሉም ሲሉ በግልጽ አስተማሩ:: በወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ አስታከው የእግዚአብሔርን ቃል የሰበክኩት ዲያቆን ሃይለጊዮርጊስ የ26 ደቂቃውን ስብከታቸውን ይዘነዋል:: ያድምጡና ሼር ያድርጉት::

“ደም የሚያፈስ መንግስት ሃገር ሊያለማ አይችልም…” ሲሉ ዲያቆን ሃይለጊዮርጊስ ተፈራ አስተማሩ | ቪዲዮውን ይዘነዋል

↧
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live




Latest Images