Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ድምጻዊት ብሩክታዊት ጌታሁን (ቤቲ ጂ) የሙዚቃ ሕይወቷና ሥራዎቿ

$
0
0


ድምጻዊት ብሩክታዊት ጌታሁን (ቤቲ ጂ) የሙዚቃ ሕይወቷና ሥራዎቿ
ድምጻዊት ብሩክታዊት ጌታሁን (ቤቲ ጂ) የሙዚቃ ሕይወቷና ሥራዎቿ


“ከዚህ በኋላ የትግራይ ሕዝብ ታፍኗል የሚባል ነገር አይሰራም፤ እንደአማራውና ኦሮሞው ሕዝብ አፈናውን ሰብሮ መውጣት አለበት”–ሊደመጥ የሚገባው የአቶ ገብረመድህን አረአያ ቃለምልልስ

$
0
0

“ከዚህ በኋላ የትግራይ ሕዝብ ታፍኗል የሚባል ነገር አይሰራም! እንደአማራው እና ኦሮሞው ሕዝብ አፈናውን ሰብሮ መውጣት አለበት” – ሊደመጥ የሚገባው አዲስ የአቶ ገብረመድህን አረአያ ቃለምልልስ
“ከዚህ በኋላ የትግራይ ሕዝብ ታፍኗል የሚባል ነገር አይሰራም! እንደአማራው እና ኦሮሞው ሕዝብ አፈናውን ሰብሮ መውጣት አለበት” – ሊደመጥ የሚገባው አዲስ የአቶ ገብረመድህን አረአያ ቃለምልልስ

“ከዚህ በኋላ የትግራይ ሕዝብ ታፍኗል የሚባል ነገር አይሰራም፤ እንደአማራውና ኦሮሞው አፈናውን ሰብሮ መውጣት አለበት”–አቶ ገብረመድህን አረአያ (የሚደመጥ)

$
0
0

“ከዚህ በኋላ የትግራይ ሕዝብ ታፍኗል የሚባል ነገር አይሰራም! እንደአማራው እና ኦሮሞው ሕዝብ አፈናውን ሰብሮ መውጣት አለበት” – ሊደመጥ የሚገባው አዲስ የአቶ ገብረመድህን አረአያ ቃለምልልስ

አርተስት መላኩ ቢረዳ በወልቂጤ ከተማ ለመስቀል ሊያቀርብ የነበረውን ኮነሰርት ሰርዞ የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፏል!

$
0
0
መላኩ ቢረዳ

መላኩ ቢረዳ

ስላም ውድ ወገኖቼ በመላው አለም ያላችሁ ኢትዮጵያዊያን እንደ ክፉ ልማድ ሰላም ቢሆንም ባይሆን ስንገናኝ ሰላም ነው የሚሉት ሶስቱ ፊደላት ልማዳችን ሆነዋል።

    መልእክቴ ይህ ነው በበቅርቡ ሙሉ ገቢው ለሶስት የበጎ አድራጎት ድርጅቶች የሚውል ሙሉ አልበም ስርቼ መጨረሴ ይታወቃል ። ሆኖም ከፈጣሪ ቀጥሎ አስታዋሽ ባልበረኝ ሰአት ከጎዳና አንስተህ አልብሰህ አጉርሰህ አስተምረህ ላሳደከኝ ውድ የኢትዮጵያ ህዝብ ደስታህ ደሰታዬ ሀዘንህ ሀዘኔ ካልሆነ ምኑ ያንተ ልጅ ሆንኩት ። በተጨማሪም ከመስከረም 5/1/2009 ጀምሮ ለመስቀል በአል በወልቂጤ ከተማ ላይ በሚደረጉ የሙዚቃ ባዛርና ኮንሰርቶች በምንም መልኩ በሙዚቃ ዝግጅቱ ላይ ስለማልሳተፍ እባካችሁ ፕሮሞተሮች ያለፍላጎቴ ፎቶዬን በፖስተር በማሳተም ሰውን አታደናግሩ።ይህ የፖለቲካ ጉዳይ አይደለም ይህ የእምቢተኝነት ጉዳይ አይደለም ።ይህ የህሊና ጉዳይ ነው  ።

ገንዘብ እድሜም እውቀትም ችሎታም ሁሉም አላፊ ነው ። ግን የአለም ፍፃሜ እስኪደርስ ሀገርና ህዝብ ዘላለማዊ ነው። ይህ ቁጥር ሶስት አልበሜ ሀገራችን ሰላም ፣ ህዝባች ሰላም እሲኮሆን ሳይሸጥ መቆየቱ ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች ከገባሁት ቃሌ ይልቅ ህዝቤና ሀገሬ ሰለላቀብኝ ነውና እንዴትስ ወገኔን ህይወቱን ማንነቱን ሰላሙን እያጣ ሀገሬ አዝና ወገኔ እንካ በአዲሱ አልበሜ ጨፍር ተዝናና እንዴት ልለው እችላለሁ። ሰላም ሰላም ሰላም ለኢትዮጵያንና ለኢትዮጵያዊያን።

መላኩ ቢረዳ ።

ጅግ አጣዳፊ ጥሪ በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ላላችሁ ኢትዮጵያውያን በሙሉ (እባካችሁ አሁኑኑ ሼር አድርጉት)

$
0
0

አሁኑኑ ወደ Walter E. Washington Convention Center (Address: 801 Mt Vernon Pl NW, Washington, DC 20001, United States) እንድትንቀሳቀሱ
ዛሬ ቅዳሜ September 17th, 2016 ከ 5PM ጀምሮ ባራክ ኦባማ ንግግር በሚያደርግበት እና ሂላሪ ክሊንተን ለጥቁር ህዝቦች ጥሩ ሥራ የሰሩ ሰዎች የሚሸለሙትን የ Phoenix Award በምትሸለምበት የ Congressional Black Caucus Foundation (CBCF) አመታዊ ስብሰባ ሁላችን ኢትዮጵያውያን ሂላሪ ክሊንተን እና ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በ ኢትዮጵያ የሚያራምዱትን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ እና የ ወያኔ አጋዚ ጦር በአማራ ሕዝብ ላይ የሚያደርጉትን የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ፣በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የሚደረገውን ጭፍጨፋ እንዲሁም ኮንሶ ሕዝብ ላይ የሚደረገውን ግድያ በመቃወም ስብሰባው በሚደረግበት

the Walter E. Washington Convention Center (Address: 801 Mt Vernon Pl NW, Washington, DC 20001, United States) ፊት ለፊት ከ 5pm ጀምሮ ተቃውሞ እንድናሰማ ሰልፍ ተጠርቱዋል። Stop the

#AmharaGenocide
#amhararesistance #

ጅግ አጣዳፊ ጥሪ በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ላላችሁ ኢትዮጵያውያን በሙሉ (እባካችሁ አሁኑኑ ሼር አድርጉት)

ልማት የሕዝብ ነው –መንግስት ጥገኛ ነው |ከስዩም ተሾመ

$
0
0

eprdf
አብዛኞቹ የኢህአዴግ ባለስልጣናት በሀገሪቱ ታይቶ የማይታወቅ ልማትና እድገት እያስመዘገቡ እንደሆነ ይናገራሉ። ነገር ግን፣ እነሱ እንደሚሉት በሀገሪቱ ታይቶ የማይታወቅ ልማትና እድገት እያስመዘገቡ አይደለም። ይሄን ያልኩበት ምክንያት “ኢህአዴግ ልማት አምጥቷል/አላመጣም” ወደሚለው ጉንጭ-አልፋ ክርክር ለመግባት ፈልጌ አይደለም። የኢህአዴግ መንግስት ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ ሁሉም መንግስታት በራሳቸው የልማትና እድገት ምንጭ ሊሆኑ አይችሉም። ምክንያቱም መንግስት በሀገር ልማትና እድገት ውስጥ ከደጋፊነት የዘለለ ሚና ሊኖረው አይችልምና።

ስዩም ተሾመ

ስዩም ተሾመ

ፅንሰ-ሃሳቡን በተጨባጭ እውነታዎች ላይ ተመስርተን እንመለከታለን። በእርግጥ ኢህአዴግ ራሱን የልማትና እድገት ዋና ተዋናይ አድርጎ እንደሚመለከት ግልፅ ነው። ለዚህ ደግሞ ለከፍተኛ ትምህርት ማህብረሰብ ሥልጠና የተዘጋጀውን ሰነድ ውስጥ“የሃያ አምስት አመታት ጉዞ የስኬት ምንጮች” በሚል የተጠቀሰው እንደ ማሳያ ሊጠቀስ ይችላል፡-

“የዴሞክራሲያዊ ልማታዊ መንግስት አስተሳሰብ በትክክለኛ ፖሊሲ፣ እስትራቴጂ፣ ፈፃሚና አመራር የፖሊሲ ነፃነት በማስከበር ያሳካው ድል መሆኑ፣ … ህዝባችንን ከድህነት የሚያላቅቅልን ርዕዮት በቂ ሳይንሳዊ ትንተና በማድረግ ከሌሎች ልማታዊ መንግስታት ተሞክሮ በመማርና ከልምዳችን ችግሮቻችንን በማረም ያሳካነው ውጤት መሆኑ፣ መንግስታዊ ስልጣን ለህዝብ ጥቅም እንዲውል ለማድረግ የሚያስችል የፖለቲካ ስርዓት በመፍጠር የተገኘ ውጤት መሆኑ” የከፍተኛ ትምህርት ማህብረሰብ ሥልጠና ለ2009 ትምህርት ዘመን ዝግጅት ምዕራፍ ማጠናቀቂያ፣ ትምህርት ሚኒስቴር፥ መስከረም 2009፥ ሰነድ-አንድ፥ Slide-14.

እንደ ኢህአዴግ አገላለፅ፣ ላለፉት 25 ዓመታት የተመዘገቡት አንኳር አገራዊ ለውጦች የመንግስታዊ ስርዓቱና የመንግስት ተግባራት፤ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች፣ አቅጣጫዎች እና አስተዳደር ውጤቶች ናቸው። ነገር ግን፣ መንግስታዊ ስርዓትና ተግባራት ለሀገር ልማትና እድገት ምቹ ሁኔታ ከመፍጠር ባሻገር የስኬት ምንጭ ሊሆኑ አይችሉም። በዚህ ጉዳይ ጥናት ያደረጉ ምሁራን ችግሩ በብዙ ታዳጊ ሀገሮች ላይ እንደሚስተዋል ይገልፃሉ።

“Many developing nations discovered the hard way the obvious truth that no government can develop a nation. Nations are developed by their people. …. People develop themselves. It is the role of government to foster and support that process of self-development. …Society is the whole of which economy is only a part. Economy is the whole of which money is a part. Society creates jobs, not economy or money.” Employment, Individuality and Development, MSS Research, Feb 14, 2010.

ከላይ እንደተጠቀሰው፣ መንግስት ሀገርን አያሳድግም። ከዚያ ይልቅ፣ ሀገር የሚያሳድገው ህዝብ ነው። እዚህ ጋር የመንግስት ድርሻ፣ ለኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ሕዝቡ ራሱን በራሱ ለማሳደግ የሚያደርገውን ጥረት መደገፍ ነው። ነገር ግን፣ በትኛውም የፖለቲካ ሥርዓት የመንግስት ተግባርና ኃላፊነት ለሕዝቡ እንቅስቃሴ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ድጋፍ ከማድረግ የዘለለ ሊሆን አይችልም። መንግስት በኢኮኖሚው ዋና ተዋናይ ከሆነና ልክ እንደ ኢህአዴግ ራሱን የስኬት ምንጭ አድርጎ የሚቆጥር ከሆነ ፍፁም ስህተት ነው። ምክንያቱም መንግስት ያለ ኢኮኖሚና ገንዘብ የሥራ እድል መፍጠር ሆነ መሰረተ-ልማት መገንባት አይችልም። እንዴትና ለምን የሚለውን ከገንዘብ በመጀመር እንመልከት።

የአንድ ሀገር ኢኮኖሚ እና የገንዘብ እንቅስቃሴ የሚወስነው በሕብረተሰቡ (Society) እንጂ በመንግስት ውሳኔና ፖሊሲ አይደለም። “Carl Menger” በ1892 (እ.አ.አ) “On the Origins of Money” በሚለው መፅሃፉ እንዲህ ይላል፡- “In its origin money is a social, not a state institution”። በዚህ መሰረት፣ ገንዘብ በሕብረተሰቡ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ አማካኝነት እንጂ በመንግስት ፍቃድ የተፈጠረ አይደለም። ይህንንም ፀኃፊው “Money has not been generated by law” በማለት ይገልፀዋል።

ከገንዘብ (money) በተጨማሪ መንግስት የሕብረተሰቡን የኢኮኖሚ አንቅስቃሴ በበላይነት መቆጣጠር አይችልም። የአንድ ሀገር ኢኮኖሚን ለማንቀሳቀስ የቋሚ ሃብቶች (fixed capitals) እና ጥሬ-ሃብቶች (resources) ያስፈልጋሉ። የሥነ-ምጣኔ ፈር-ቀዳጅ የሆነው አዳም ስሚዝ መሰረት አራት አይነት ቋሚ ህብቶች ያሉ ሲሆን፣ እነሱም፡- መሬት (land)፣ መስሪያ ቦታ (buildings)፣ የመስሪያ ማሽን (machinery) እና የሰው ሀብት (human abilities) ናቸው። ከእነዚህ በተጨማሪ፣ ለኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴው ሌሎች የተለያዩ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ግብዓቶች ጥቅም ላይ ይውላሉ። ነገር ግን፣ ሁሉም ሀብቶችና ግብዓቶች ያለ የሰው ልጅ ዕውቀትና ክህሎት ፋይዳ-ቢስ ናቸው።

Ludwig von Mises” የተባለው የሥነ-ምጣኔ (Economics) ምሁር ዘርፉን “Economics is not about goods and services; it is about human choice and action” በማለት ይገልፀዋል። በዚህ መሰረት ኢኮኖሚያ በሰዎች ምርጫና እንቅስቃሴ እንጂ በሸቀጣ-ሸቀጦች እና አገልግሎቶች አቅርቦት ላይ የተመሰረተ እንዳልሆነ እንረዳለን። በአጠቃላይመ የአንድ ሀገር ለኢኮኖሚያዊ አንቅስቃሴው መሰረት የሆኑት ቋሚና ጥሬ ሀብቶች በራሳቸው የሰው-ልጅ እሳቤና ግንዛቤ ውጤት ስለመሆናቸው እንደሚከተለው ተገልጿል፡-

“The very notion of capital is a human conception. In this sense, anything becomes a resource by the action of the human mind. Resources are perceived and developed. Materials exist in nature, but anything becomes a resource only when its potential value is recognized by the human mind. Human mental activity creates resources by discovering new productive relationships between existing elements.” Human Capital and Sustainability, Sustainability Journal, Volume 3 Issue 1.

በኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ብቻ ሳይሆን በመሰረተ-ልማት ግንባታ ረገድም ጭምር መንግስት ራሱን ችሎ ምንም ነገር የመስራት እቅም የለውም። ምክንያቱም በመሰረታዊ የሥነ-ምጣኔ መርህ መሰረት ገንዘብ የሕብረተሰቡ ኢኮኖሚያዊ አንቅስቃሴ ውጤት እንጂ በመንግስት ፍቃድ የሚመነጭ ነገር አይደለም። ሕብረተሰቡ የጋራ ጥቅሙን ለማረጋገጥ በግብር መልክ (tax) ለመንግስት ገቢ ከሚያደርገው ውጪ መንግስት በራሱ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ አድርጎ ገቢ ማመንጨት አይችልም። ስለዚህ፣ መንግስት በገቢ ረገድም በሕብረተሰቡ ፍቃድና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ጥገኛ ነው። በመሆኑም፣ ከሕዝብ ፍቃድና ድጋፍ ውጪ መንግስት በራሱ የልማትና እድገት ምንጭ ለመሆን የሚያስችል አቅም የለውም።

ኢህአዴግ ባለፉት 25 ዓመታት ለተመዘገቡት አንኳር ሀገራዊ ለውጦች መንግስታዊ ስርዓቱና የመንግስት ተግባራት፤ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች፣ አቅጣጫዎች እና የአስተዳደር ተግባራት እንደ ዋና የስኬት ምንጮች ጠቅሷል። ከላይ በዝርዝር ለመግለፅ እንደተሞከረው የሀገር ልማትና እድገት ሊመጣ የሚችለው በሕብረተሰቡ ነፃ እንቅስቃሴና ምርጫ እንጂ በመንግስት አማካኝነት እንዳልሆነ አይተናል። ስለዚህ፣ ኢህአዴግ ራስን እንደ የስኬት ምንጭ አድርጎ ማየቱ ከተሳሳተ እሳቤ የመነጨ ነው። ይሁን እንጂ፣ ይህ እሳቤ በኢህአዴግ ላይ ብቻ ሳይሆን በብዙ የበለፀጉ ሀገሮች ዘንድም የሚስተዋል ችግር ነው። ከዚህ አንፃር፣ የዓለም አቀፉ የምግብና ሰላም ከሚሽን (International Commission on Peace and Food (ICPF)) ችግሩን እንዲህ እንደሚከተለው ይገልፀዋል፡-

“for millennia we have tended to overlook or, at best, grossly underestimate the greatest of all resources and the true source of all the discoveries, inventions, creativity and productive power found in nature, the ultimate resource, the human being”

በአጠቃላይ ከላይ የተነሳውን ሃሳብ፤ “Man himself is the beginning and the end of every economy” በሚለው አባባል ማጠቃለል ይቻላል። አዎ… የእያንዳንዱ ኢኮኖሚ መነሻና መድረሻ ሰው ነው። የኢትዮጲያ ልማትና እድገት መነሻና መድረሻ የሀገሪቱ ሕዝብ ነው። እንደ መንግስት ከሕዝቡ በሰበሰበው ግብር ማህበራዊ ግንኙነቱንና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴውን የሚያቀላጥፉ መሰረተ-ልማቶችን መገንባት አለበት። ስለዚህ፣ እንደ ማንኛውም መንግስት ኢህአዴግ “ለሀገሪቱ ልማትና እድገት ምቹ ሁኔታ በመፍጠር የደጋፊነት ሚናዬን በአግባቡ ተወጥቼያለሁ” ማለት ወግ ነው። ነገር ግን፣ የለውጥ መሰረት የሆነውን ሕዝብ ወደ ጎን ትቶ ራሱን በስኬት ምንጭነት የሚጠቅሰው ኢህአዴግ ምን ይሉታል? በእርግጥ ልማትና እድገት በሕዝብ ጥረት የሚመጣ ለውጥና መሻሻል ነው፡፡ እንደ ኢህአዴግ ያለ መንግስት ግን በራሱ ለውጥ ማምጣት የማይችል ጥገኛ አካል ነው፡፡

የኛ ነገር፤ ትግሬን መነጠል፤ ሐሳዊ-ኢትዮጵያዊነት ነው |ከተክለሚካኤል አበበ

$
0
0

tekelemicael-abebe

ሰሞኑን በሰጠሁት በትግሬነት ላይ የሚሰነዘረው ውግዘት ትክክል አይደለም የሚል አስተያየት ላይ፤ የተለያዩ ሀሳቦች ተሰንዝረዋል፡፡ የሚነሳው የተዛባ አመለካከት ከገመትኩት በላይ አሳሳቢና፤ የመልስ ዘረኝነት ወይም ጥላቻ፤ ፈረንጆች reverse racism የሚሉት ነገር የተጸናወተው ይመስላል፡፡ የብዙዎቹ ትችት አሁን ያለው የኢትዮጵያ መንግስት የትግሬዎች መንግስት ስለሆነ፤ መንግስት ለሚፈጽመው ጥፋት ትግሬዎች ሁሉ ተጠያቂ ናቸው የሚል ድምጸት አለው፡፡ ብዙዎቹ ተቺዎች፤ ትግሬዎች ሕወሀት ካልሆኑ ያረጋግጡልን የሚል ፈተና ያቀርባሉ፡፡ ነጻ መሆናቸውን ካላረጋገጡ በስተቀር፤ ትግሬዎች ሁሉ ወንጀለኞች ናቸው አይነት ነገር፡፡ ይሄ፤ አለም የተቀበለውን፤ እኛም በአገራችን እንዲሰፍን የምንመኘውን የነጻነት መርህ የሚጻረር፤ ከምንም በላይ ደግሞ ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነ አቋም ነው፡፡

ትናንትናና ዛሬ ሕወሀት/ኢህአዴግ፤ ነጋሪት ጎስሞ፤ አዋጅ ነግሮ፤ የኢትዮጵያን ችግር ሁሉ የፈጠረ አማራ ነው ሲል፤ ያንን ስንቃወም የኖርን ሁላ፤ አሁን ደግሞ መልሰን የኢትዮጵያ ችግር ሁሉ ፈጣሪ ትግሬ ነው ስንስል፤ ለሕወሀት/ኢህአዴግ የአመታት ዘመቻ እጅ ብቻ ሳይሆን፤ እግርም እየሰጠን ይመስላል፡፡ እነሆ ከ25 አመታት በኋላ፤ አያቶቻቸውና አባቶቻቸው፤ ኢትዮጵያን ከውስጥም ከውጭም ጠላት ለመከላከል፤ በኢትዮያዊነት ኩራት የሞቱ ጎንደሮች፤ ጎዣሞች፤ ሸዋዎች፤ ዛሬ የአማራ ምንትሴ፤ የአማራ ቅብርጥሴ ብለው ሲደራጁ ማየት እንዴት ያስፈራል፡፡ ያ ብቻም አይደለም፤ ትናንት ሕወሀቶች አማራን ጠላት ባደረገ ርእዮተ-አገር አሳብረው አራት ኪሎ ገብተዋልና፤ እኛም እነዚህን ዘረኞች የምናሸንፈው፤ ትግሬዎችን ሁሉ ጭራቅ አድርገን በመሳል ነው የሚው ቅኝት ነው ሌላው ትልቅ ስህተት፡፡ በዚህ አቋሜ፤ ከወዳጆቼ ጋር መጋጨቴ አልቀረም፡፡ ግን፤ ሀሳብን በነጻነት ከመግለጽ አንጻር፤ ወዳጄቼ ከኢህአዴግ እንደማያንሱ ስለማውቅ፤  የመሰለኝን ልጻፍ፡፡

አሁን ያለው መንግስት የትግሬዎች መንግስት ነው የሚለውን ዜማ ይዘው የሚከራከሩት ሰዎች የሚነሱት፤ አንደኛ የትግራይ ህዝብ ከስርአቱ ተጠቃሚ ስለሆነ ስርአቱን ይደግፋል ከሚል ግምት ነው፡፡ ይሄንን ለማስረዳት፤ አንዳንዶቹ ቦሌና 22 ላይ የተደረደሩትን ፎቆች ይቆጥራሉ፤ ይሄ የጀነራል ሰዓረ ነው፡፡ ይሄ ደግሞ የጀኔራል ገብረዮሀንስ፡፡ ይሄ ደግሞ የአርከበ እቁባይ፡፡ ይቀጥላል፡፡ የግለሰቦች ሀብት በምን ስሌት የህዝብ እንደሚሆን አይረዳንም፡፡ በርግጥ፤ ባለፉት 25 አመታት በንጽጽር፤ ከሌሎች ክልሎች በተሻለ በትግራይ የተነገቡትን የኢኮኖሚና ማህበራዊ ተቋማት፤ እንዲሁም የትግሬዎችን በማእከላዊ መንግስት ውስጥ ያላቸውን የተዛባ ድርሻም ጠቅሰው የሚከራከሩ አሉ፡፡ ሁለተኛው የሚነሱት፤ ይሄንን በሌሎች ኢትዮጵያዊያን ላይ የሚደርሰውን ግፍ፤ ትግሬ ጠንቅቆ ያውቃል ከሚል ግምት ነው፡፡ የትግራይ ህዝብ በሙሉ፤ ወይም ባብዛኛው፤ የህወሀትን መንግስት አውቆ፤ ተጠቃሚ ከሆነም፤ ተጠቃሚነቱ በሌሎች ኪሳራ የመጣ እንደሆነ ተረድቶ፤ ሕወሀትን ይደግፋል የሚል እምነት የለኝም፡፡ ያንን ሀሳብ የሚያራምዱ ሰዎች፤ ግምት እንጂ፤ አሳማኝ ማስረጃ አያቀርቡም፡፡

ቁሳዊ ሀብትና ንብረት፤ የባህል የበላይነትም እንደማስረጃ ከተቆጠረ፤ በተለይ ከኢህአዴግ በፊት በነበሩት ዘመናት፤ በኢትዮጵያ ውስጥ የአማራውን ያህል ሀብት ያከማቸ ብሄር የለምና ይሄኛው ክስ ከአማሮች ባይመጣ ይመረጣል፡፡ በርግጥ አማራው ባለፉት 25 አመታት ክፉኛ ተመቷል፡፡ አንዳንዶች፤ በተለይም የትግሬ ልሂቃን፤ እነስዬ አብርሀ፤ ሕወሀት በአማራው ላይ የፈጠነውን ደባ ለማሳነስ፤ በኢህአዴግ አገዛዝ ዘመን፤ ኦሮምኛ የእስርቤት ቋንቋ እስኪመስል ድረስ፤ ኦሮሞው ተጠቃ ይላሉ እንጂ፤ ባሳለፍነው 25 አመታት እንደአማራው የተጠቃ ብሄር የለም፡፡ ግን ደግሞ፤ ባብዛኛው በቀደሙት አመታት፤ በፊታውራሪነት ኢትዮጵያን የቃኘው ብሄር አማራው ስለሆነ፤ አማራው በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የቁሳዊና መንፈሳዊ ሀብት የበላይነት፤ እንዲህ በ25 አመታት አይደለም በ250 አመታትም የሚናድ አይደለም፡፡ እንደውም ሳስበው ሳስበው፤ የህወሀት ትልቁ የ25 አመታት ፈታና፤ እነሱ ራሳቸው የጠሉትን አማራ እየሆኑ መምጣታቸው ይመስለኛል፡፡ ሕወሀት፤ ጭራቅ አድርጎ የሳለውን አማራና የአማርኛ ባህል ማሸነፍ አቅቶት፤ እንደውም እለት እለት እንደጠላት በሚቆጥረው ባህል እየተሸነፈ መምጣቱ መሰለኝ ብጥብጥ ያደረገው፡፡ ይሄንን ወደፊት አስረዳለሁ፡፡ ለዛሬ ግን በትግራይ ህዝብ ላይ ስለሚቀርበው ጎዶሎና የነቂስ ክስ ስህተት ማስረዳት ልቀጥል፡፡

ብዙ ሰዎች የላይኛውን ትግሬ ነገሰብን፤ በዚህም የንግስና ሂደት፤ የትግራይ ህዝብ እንደደጋፊም፤ እንደአጃቢም፤ እንደባለቤትም ሆኖ፤ ከሕወሀት ጎን ቆሟል የሚል ሀሳብ ለማስረዳት በዋንኛነት እንደማስረጃ የሚጠቀሙት፤ ሁለት ነገሮችን ነው፡፡ አንደኛው፤ የህወሀት መሪዎች፤ እነሳሞራ የኑስ እነአባይ ጸሀዬ እነስብሀት ነጋ እነስዩም መስፍን፤ ብድግ ብለው የትግራይ ህዝብና ሕወሀት አንድ ነው፤ ማንም አይለያያቸውም ሲሉ፤ የትግራይ ህዝብ አላስተባበለም፡፡ ስለዚህ ዝምታ የመቀበል ያህል ይቆጠራል ነገር ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ፤ የሌሎች አካባቢዎች ህዝቦች ለመንግስት ያላቸውን ተቃውሞ በተለያየ መንገድ ሲያሰሙ፤ የትግራይ ህዝብ ግን ተቃውሞ አድርጎ አያውቅም የሚል ነው፡፡ ሁለቱም መከራከሪያዎች፤ አንዳንዶቻችን በጥላቻ አጥቅሰን ካልዋጥናቸው በቀር፤ ወይንም ገሚሶቻችን አገርቤት በሚፈጸመው ግድያ ደማችን ተንተክትኮ፤ አዝነን፤ በንዴት መንፈስ ካልተቀበልናቸው በስተቀር፤ ውሀ አይቋጥሩም፡፡

የትግራይ ህዝብ፤ በርግጥም ሕወሀትን ወይንም አሁን ያለውን መንግስት ደግፎ ከሆነ፤ ፈረንጆች የምክንያታዊ ሰው መስፈሪያ (the reasonable person standard) በሚሉት ሚዛን ሲለካ፤ የትግራይ ህዝብ ደግ ነው ያደረገው፡፡ የትግራይ ህዝብ ህወሀትን ለመደገፍ የሚያበቃ፤ ማንም ምክንያታዊ ሰው የሚቀበለው፤ በቂ ምክንያት አለው፡፡ ቢያንስ ከማህጸናቸው የወጡ ልጆች፤ አንድን፤ ሀያል የተባለን ሰራዊትና ስርአት አሸንፈው፤ በማእከላዊ መንግስት ውስጥ ጉልህ ሚና ሲጫወቱ ማየት ማንንም ያኮራል፡፡ ስለዚህ የትግራይ ህዝብ በልጆቹ ቢኮራ፤ ህወሀትን ቢደግፍ ብዙም አያሰደንቅም፡፡ አያስቆጣምም፡፡ ትናንት ጦርነት ይካሄድበት የነበረ ምድረ፤ በተወሰነ መልኩ፤ ከጦርነት ተላቆ፤ ከብቶች በሰላም የሚግጡበት፤ ሰዎችም በሰላም ወደስራ የሚሰማሩበት፤ ልጆች የሚማሩበት፤ የስራ እድሎችና የንግድ እንቀስቃሴዎች የሚሟሟቁበት ሁኔታ ሲፈጠር፤ ቀድሞ ከነበረው ጦርነት ጋር በማስተያየትም ይሁን በራሱ፤ ያንን ሰላማዊ ህይወት የሰጠን ህወሀት ነው ብለው ቢያምኑና ቢደግፉት ሊያስከስሳቸው አይገባም፡፡

ሕዝብ ባይወቀስም፤ የትግራይ ህዝብ ግን መወቀስ ካለበት ሊያስወቅሰው የሚገባው፤ ሕወሀት በሌሎች ኢትዮጵያዊያን ወገኖቹ ላይ የሚሰራውን ሸፍጥና ተንኮል ያወቀና የተባበረ እንደሁ ነው፡፡ ከላይ እንዳልኩት፤ የትግራይ ህዝብለ ራሱም የጭቆና ሰለባ በመሆኑ እንጂ፤ በሌሎች ወገኖቹ ላይ የሚደርሰውን ግፍ አውቆ ሕወሀትን አይደግፍም፡፡ በዚህ የትግራይ ህዝብ በሙሉ ሕወሀትን አውቆና ነቅቶ ይደግፋል በሚለው የአስተሳሰብ መንገድ ከተጓዝን፤ እድለኞች ሆነን፤ እንደብርሀኑ ነጋ ሸዋ፤ እንደኤፍሬም ማዴቦ ሌላ ቦታ፤ እንደኔ ቦረና ካልተወለድን በስተቀር፤ ሁላችንም ከዚህ ክስ አንተርፈም፡፡ ሁላችንም፤ ትግራይ ተወልደን አድገን ቢሆን፤ እስከተወሰነ ደረጃ ሕወሀትን ከመደገፍ ወደኋላ አንልም፡፡ ነአምን ዘለቀ፤ አልማዝ መኮ፤ ኡስታዝ አቡበከር፤ አበበ ገላው፤ ሲሳይ አጌና፤ ተክሌ የሻው፤ ብርሀኑ ነጋ፤ ሌንጮ ለታ፤ ጃዋር መሀመድ፤ ታማኝ በየነ፤ ወይም እኔም ራሴ ትግራይ ብንወለድ ሕወሀትን የመደገፍ እድላችን በጣም ሰፊ ነው፡፡ እኔ እንኳን ዘወትርም የተቃራኒን ጎራ ክርክር ማየት ደስ ስለሚለኝ፤ ቀንደኛ የህወሀት ደጋፊ ላልሆን እችላለሁ፡፡ የሆነ ሆኖ ግን፤ ዛሬ መፈክር ይዘው ትግሬ ይውደም የሚሉ ሁሉ፤ ትግራይ ተወልደው ቢያድጉ አክራሪ ትግሬዎች ነበር የሚሆኑት፡፡

ብዙ ታዋቂ አክራሪ ኢትዮጵያዊያን አሉ፡፡ ብዙ አክራሪ ኦሮሞዎችም አሉ፡፡ ብዙ አክራሪ አማሮችም እተፈጠሩ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ትግራይ ተወልደው ቢያድጉ፤ አክራሪ  ትግሬዎች ነበር የሚሆኑት፡፡ የትግራይ ህዝብ ሁሉ ወያኔን ይደግፋል የሚለው መከራከሪያ ካሳመነን፤ እንግዲያውስ ማናችንም ትግራይ ብንወለድ እንደትግራይ ህዝብ ነው የምናደርገው፤ ወያኔንን እንደግፋለን፡፡ ስለዚህ፤ እስክናጣራ፤ ትግሬ ሁሉ ወያኔ ነው የምንል ሰዎች፤ ስለትግሬዎች ስንናገር፤ ስለራሳችንም እየተናገርን ነው፡፡ እስኪጣራ፤ አማራ ሁሉ፤ ትምክህተኛ ነው፡፡ እስኪጣራ፤ ኦሮሞ ሁሉ ጠባብ ነው፡፡ እስኪጣራ፤ እስላም ሁሉ ሽበርትኛ ነው አይነት ነገር፡፡ ያ ትክክል አይደለም፡፡ ገደል የሚከት አስተሳሰብ ነው፡፡

የትግራይ ህዝብ ግን አውቆና ነቅቶ ሕወሀትን ይደግፋል የሚል እምነት የለኝም፡፡ ወይንም ሕወሀት በሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች (ወይ ጉድ፤ ሕዝቦች ማለት ለመድኩ እኔ ራሴ)፤ በተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚፈጸመውን ግፍና ጭቆና አውቆ፤ ወይም የተወሰነ አብላጫ ተጠቃሚነት ካገኘም፤ ያ ተጠቃሚነት የመጣው በሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጭቆናና በደል እንደሆነ ቢረዳ፤ አቅምና እውቀት አንሶት ካልሆን በስተቀር፤ የትግራይ ሕዝብ ከህወሀት ጎን ይሰለፋል ብዬ አልገምትም፡፡ ከደገፈም ሌላ ምርጫ ስላልተሰጠው ይመስለኛል፡፡ ልብ በሉ፤ የትግራይ ህዝብ ላይ የተለቀቀው የ43 ምናምን አመታት ፕሮፓጋንዳ አለ፡፡ ጥርነፋውስ፡፡ የትግራይ ህዝብ ከተቀረው ኢትዮጵያ ህዝብ በፊት ነው አስቀድሞ የተጠረነፈው፡፡ ሌላ እንዳይሰማ፤ ሌላ እንዳያውቅ ተደርጎ የታፈነና የተቀፈደደ ህዝብ ነው፡፡

ገብሩ አስራት እንደጻፈው፤ ብዙዎች ሕወሀትን ጠንቅቀው በሚያውቁ ሰዎች እንደተነገው፤  ሕወሀቶች በትግላቸውም ይሁን በአገዛዛቸው ዘመን፤ እንዴት አድርገው ከነሱ አመለካከት የተለየ አመለካከት ያላቸውን ትግሬዎች ሁሉ አጥፍተው እዚህ እንደደረሱ ገልጧል፡፡ በነገብሩ ላይ የደረሰው፤ የሕወሀትን አንድ ወጥ አመለካከት ለመቅረጽ የሚሄድበትን ርቀት የሚያሳይ ነው፡፡ ከነሱ የተለየውን ከማሰር፤ ከማሰቃየት፤ ከማደህየት፤ ከማግለል፤ ካስፈለገም ከመግደል ጭምር አይመለሱም፡፡ ሕወሀት የተቀረውን ኢትዮጵያ የሚያስተዳድርበትን መንግድ በደንብ ከተመለከትንም፤ ያ በሌሎች ክልሎች ያየነው፤ ሕወሀት እንዴት አድርጎ ትግራይን አፍኖ እንደሚስተዳድር ይነግረናል፡፡ ስለዚህ ይሄንን የታፈነ ህዝብ፤ በማያውቀውና በሌለበት፤ እንዴት ከተቀረው ህዝብ አይቆምም፤ ወይም ዝም ያለው ደግፎ ነው ብሎ መውቀስ ተገቢ አይደለም፡፡

እንደህዝብ፤ ጭቁን የትግራይ ህዝብ ከተቀረው ምስኪን የኢትዮጵያ ህዝብ የሚለየው ነገር ያለ አይመስለኝም፡፡ አንዲት የትግራይ እናት፤ ልክ አንድ የኦሮሞ እናት፤ ወይም አንድ የአማራ እናት ወይም አንድ የጉራጌ እናት ያላት ደግነት አላት፡፡ የትግራም አባት እንደዚያው፡፡ ይሄንን መርሳትና፤ የተወሰኑ ትግሬዎች፤ ከተወሰኑ አማራዎችና ኦሮሞዎች ጋር ተባብረው ለሚሰሩት ወንጅል፤ የትግራይን ህዝብ ብቻ ወይንም ትግሬን በነቂስ መወንጀል ጤናማ ክስ አይደለም፡፡ ይሄ ኢትዮጵያዊ አስተሳሰብም አይደለም፡፡ የአማራ ህዝብ በስሙ ግፍ ከተሰራ፤ ግፍ ሰሪዎቹ እንጂ አማራው እንደማይጠየቀው ሁሉ፤ የትግራይ ህዝብም እንደዚያ በስሙ ለሚሰራ ግፍ ተጠያቂ ሊሆን አይችልም፡፡ መቼም ዛሬ አማራውንም፤ ኮንሶውንም፤ ኦሮሞውንም የሚገድሉት ጥይቶች ትግርኛ ይናራሉ ካላልን በስተቀር፤ አማራና ኦሮሞ፤ ወይም ጋምቤላና ሶማሌ ሰው ላለመግደሉ ማስረጃ የለንም፡፡ ስለዚህ፤ ይሄ ትግሬ ላይ ያነጣጠር ክስ በደንብ ይፈተሸ፡፡ በብሄር መጠየቅ ከመጣ፤ በአማራው ላይ የሚቀርበው ክስ ይገዝፋልና፡፡

ትግሬን ብቻ ነጥሎ የሚከስ አካሄድ፤ ጸረ-ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ በዘመናት ሂደት የተገመደ ኢትዮዊነታችን የምንለውን ነገር ባዶ ያስቀረዋል፡፡ አለበለዚያ የምንለው ኢትዮጵያዊነት ጎዶሎና ሰንካላ ነው፡፡ በውስጡ ዘረኝነት የተበረዘበት ወይንም ሀሳዊ ኢትዮጵያዊነትን ነው የምናራምደው ማለት ነው፡፡ ሰው በተገደለ ቁጥር ብድግ ብለን አንዱን ብሄር ተጠቂ አንዱን ብሄር ተጠያቂ የምናደርግበት ማንነት መሆን የለበትም፤ ኢትዮጵያዊነት፡፡ ኢትዮጵያዊነት፤ ከዚያ ይሰፋል፡፡ ኢትዮጵያዊነት ከዚያ ይጠልቃል፡፡ ኢትዮጵያዊነት ትንሽ ትግሬነት፤ ትንሽ አማራነት፤ ትንሽ ኦሮሞነት፤ ትንሽ ትንሽ ከየብሄሩ የተወጣጣ፤ ክፋትም ልማትም ያለበት ስሪት ነው፡፡ ባለፈው እንደጻፍኩት፤ ስልጣኔን ተጋርተን፤ ሰይጣንነትን ግን ላንድ ብሄር ብቻ የምንጭን ከሆነ፤ ያ ጸረ-ኢትዮጵያዊነት ነው፡፡

ኢትዮጵያዊነት ገና ያላለቀ ሂደት ነው፡፡ ሲጀመር ሲቋረጥ፤ ሲጀመር፤ ሲቋረጥ፤ አንዱ ሲጀምር ሌላው ሲያፈርስ፤ አሁን ደግሞ ኢህአዴግ የጀመረው ኢትዮጵያዊነት እነሆ እዚህ አደረሰን፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ፤ የአርከበ እቁባይ ሚና ይበዛ እንደሆን እነጂ፤ የሙክታር ከድርም አስተዋጽኦ አለበት፡፡ የጌታቸው አሰፋ ወንጀል ይገዝፍ እንደሆን እንጂ፤ የኩማ ደመቅሳ አድርባይነትም አለበት፡፡ እነአባይ ጸሀዬን ወንጅሎ፤ እነአባዱላ ገመዳን፤ እነገዱ አንዳርጋቸውን መተው ስህተት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ችግሮች፤ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ናቸው፡፡ ይሄ የጳውሎስ ነው፤ ይሄ የአጵሎስ አልልም፡፡ ስለዚህ የትግራይ ህዝብን ወይም ትግሬዎችን የጥቃት ዒላማ ያደረገ ፕሮፓጋንዳ መቆም አለበት፡፡

ይልቅስ፤ እንደሀሳብ፤ ትግሬዎችን ወይም የትግራይ ህዝብን፤ የጥቃት ዒላማ ሳይሆን፤ የንቃት ማእከል ያደረገ ፕሮፓጋንዳ ያስፈልጋል፡፡ አሁን አሁን ሳስበው፤ ኢሳት ከኦሮምኛ ይልቅ፤ ትግርኛ ፕሮግራም ቢጀምር የተሻለ ነበር፡፡ መጀመርም አለበት፡፡ ሕወሀት የጋተውን ለማስተፋት፤ ሕወሀት የሞላውን ለማጉደል፤ ሕወሀት ያሳሳተውን ለማስተካከል፤ ሕወሀት የጋረደውን ለመቅደድ ያለመ ፕሮፔጋንዳ ያስፈልጋል፡፡ ትግሬዎችን የሚያገልና የሚስደነግጥ ሳይሆን፤ ትግሬዎችን የሚያቅፍና የችግሩም የመፍትሄውም አካል ያደረገ ፕሮፔጋንዳ ነው የሚያስፈልገን፡፡ ጎበዝ፤ በሱ ላይ እንስራ፡፡ አሁን እየተከሄደበት ያለው የፕሮፓጋንዳ ስልት ግን፤ ከኢትዮጵያ ይልቅ፤ ለኢህአዴግ ያደላ ስልት ነው፡፡ ምክንያም፤ አንድም ጭፍንና የመንጋ ባህርይን የሚያበረታታ ነው፤ አንድም ትግሬዎችን ሁሉ በፍራቻ ከኢህአዴግ ጉያ የሚያስገባ ነው፡፡ ይሄ ደግሞ፤ ትናንት በብሄራችን ተጠቃን ብለው እሪ ሲሉ በነበሩ አማሮች ሲቀጣጠል፤ አያምርም፡፡ ይሄ መታረም አለበት፡፡ ያበለዚያ፤ በ2009 እኔም ትግሬ ነኝ ብዬ አውጃለሁ፡፡ ለነገሩ፤ ኢትዮጵያዊ ብሄር የለውም፡፡ ብሄሬ በኢትዮጵያዊነት እሳት ቀልጧልና፡፡

ተክለሚካኤል አበበ፤ ቶሮንቶ፤ ካናዳ፤ መስከረም፤ 2009

ተራራም ይሰረቃል?  የራስ ዳሽኑ ፖለቲካ |ከክንፉ አሰፋ

$
0
0

ras-dashen

        ራስ ዳሸን  ተራራ ከትግራይ “ክልል” ካርታ የመውጣቱ አሲዮ ቤሌማ  በብሄራዊ  ቴሌቪዥን ሲነገር፤  “ደፍረውናል! ንቀውናል! ብታምኑም ባታምኑም በቁም ሞተናል!” የሚለው የኮሎኔል መንግስቱ ንግግር በጆሮዬ ላይ አቃጨለ። ድፍረቱ እና ንቀቱ እንዳለ ሆኖ፣ በቁም የሞቱት ግን እኛ ሳንሆን እነሱ መሆናቸውን የሚያበስር የዜና እወጃ ነበር።

        ነገሩ እንጂ ሁሉም የተለመደ ነገር ነው። ውሃ ይጠፋል፣ መብራት ይጠፋል፣ ስልክ ይጠፋል፣ ገንዘብ ይጠፋል፣ ኮንዶሚንየም ህንጻም ይጠፋል። ይህ በህወሃት ፖለቲካ ጥርሳቸውን ላልነቀሉትም አዲስ ነገር አይደለም።  ዘረፋም ለነሱ አዲስ አይደለም። መንግስት ሆነው ከተቀመጡ በኋላ እንኳን 10 ቶን ቡና ሰርቀዋል፣ የመብራት ጀነሬተሮች  ሰርቀዋል፣ ከብሄራዊ ባንክ ወርቅ ሰርቀዋል… የህዝብን ድምጽም በተደጋጋሚ ሰርቀዋል። ተራራ ተሰርቆ ሲመለስ ግን የመጀመርያው ነው። 

        ከኢትዮጵያ አንደኛ፣ ከአፍሪካ ደግሞ በከፍታ 4ኛው ተራራ ነው ራስ ዳሸን። ከሰሜን ጎንደር ከየዳ ወረዳ ተሰርቆ ለ25 አመታትሙሉ ትግራይ ክልል ገብቶ ነበር። ወንጀሉ ወደ ትግራይ “ክልል” መግባቱ ብቻ አይደለም። አንድ ትውልድ  እና በስነ-ምድር ሳይንስ በውሸት ታሪክ እንዲታነጽ መደረጉ እንጂ!

        በነገራችን ላይ በመላው ሃገሪቱ መስከረም 2 ላይ  መጀመር የነበረበት ትምህርት እስካሁን አልተጀመረም። ምክንያቱም ግልጽ ነው። ተማሪዎች እየተካሀደ ያለውን  አመጽ መጨረሻው ደረጃ ያደርሱታል በሚል ስጋት ነው። በሁለተኛው አለም ጦርነት ግዜ እንኳን ትምህርት አልተቋረጠም ነበር።  ሂትለር ትምህርት እንዳይቋረጥ አዝዞ ነበር። ጦርነት እየተካሄደም፣  ትውልድ እንዳይጠፋ ውስጥ ለውስጥ ትምህርት ይሰጥ ነበር።   የኛዎቹ  ጉዶች ግን ለአራት ወይንም አምስት ሰዎች ስልጣን ጥማት ሲባል “ትምህርት ገደል ይግባ” ያሉ ይመስላል።

        ለመሆኑ ማን ነው ወንጀለኛው? መምህሩ፣ ህዝቡ ወይንስ ስርዓቱ?  በመማርያ ካሪኩለም ውስጥ ራስ ዳሽንን ትግራይ ካርታ ውስጥ አስገብተው፣ መጽሃፍም አሳትመው ሲያበቁ ፣ የንግድ ድርጅቶቻቸውን ዳሽን ባንክ፣ ዳሽን ቢራ… እያሉ የሰየሙት የ”አማራው” ተወካዮች ከዶሮ ያልታሻለ ጭንቅላት ይዘው፣ ስብእናቸውን እና ማንነታቸውን ጥለው ፓርላማ የተባለው ጉረኖ ውስጥ ተሰግስገዋል።

አንድ ትውልድን በዘረኝነት መርዝ ብቻ ሳይሆን በዚህ አይነት ውሸት ክመረዙ በኋላ ይቅርታ መጠየቁ ምን ይበጃል? በፈተና ግዜ ራስ ዳሽን ተራራ የሚገኘው በሰመን ጎንደር  ነው ብለው የወደቁትስ የአእምሮ ካሳ ሊከፈላቸው ነው?  የህወሃት ሰዎች አፍ እንጂ ጆሮ ስለሌላቸው ጥያቄዎችወች እንጂ አንድም መልስ አናገኝም።

ለመጀመርያ ግዜ ከህወሃት አንደበት ይቅርታ የሚል ነገር ሰማን ልበል? አንድ የፖለቲካ ተንታኝ በአንድ ወቅት ሲናገር የበታችነት ስለሚሰማቸው ይቅርታን ከሌላው ይሿታል እንጂ ፈጽሞ አይሏትም እንዳለ ትዝ ይለኛል። ይህ አንደኛው መጨረሻውን ጠቋሚ መሆኑ ነው።  በመጨረሻም እንዲህ ይሆናል። የፖለቲካ እስረኞች ይፈታሉ። ይቅርታ ማለት ይጀምራሉ። አጠር ያለች ረጅም የአብዮት ትንታኔ!

ይህ ይቅርታ ከመባሉ ሳምንታት በፊት፣ ሰላሳ ሚሊዮን አማራን ማጥፋት የሚችል ሃይል እንዳላቸው ደብረጽዮን በፌስ ቡክ ገጻቸው ጽፈውልናል። “አባ በጠጡ አቃቢቱን…”  እንዲሉ ይህንን የደብረጽዮን ጽሁፍ ሃይለማርያም ተቀብለው ሲያበቁ በመገናኛ ብዙሃን ቀርበው አንቦርቅቀውታል። “አብዮታዊ ሰራዊቱ ሕዝቡን እንዲገድል ትእዛዝ ሰጥቻለሁ!” ያሉ መሰለኝ። ለማመን እስኪከብድ ሂትለራዊ ቀረርቶ እና ፉከራም ሳይቀር አሰምተውናል።   እነ አቦይ ስብሃት ታዲያ ጥጋቸውን ይዘው፣ በጨበጡት ብርጭቆ ሰንጥቀው እየመነጠሩዋቸው “ደፋር!” ሳይሏቸው አልቀረም።   “ስልብ፣  በጌታው ብልት ይፎክራል!”  ይላሉ አበው።

        ሕዝብን ለመጨረስ ትዕዛዝ  አስተላልፈናል ያሉበት አንደበታቸው ገና ሳይዘጋ ከጎንደር የሰረቅነውን ተራራ መልሰናል። ይህንን ተራራ ትግራይ ላይ አኑረነው ስለነበር ይቅርታ! ብለው መናገራቸው  ጨዋታ የመቀየር ስልት መሆኑ ነው።   ሕዝብ ቀድሟቸው ባይሄድ ኖሮ ሊሸውዱት ይሞክሩ ነበር። የተለመደ ነጠላ ዜማ፣ በተመሳሳይ ግጥም –  በተመሳሳይ ዜማ ይዘው መከሰታቸው ግንከእንሰሳ እንኳን ያልተሻሉ መሆናቸውን  የሚያሳይ ነው።   ህዝቡን የሚያዩበት መነጽር አሁንም አልቀየሩትም።

        ራስ ዳሽንን ከይቅርታ ጋር ለባለበቱ መልሰናል ብለዋል። ከዚህ ቀደምም የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ ተገቢ ነው ብለውናል። የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ ተገቢ መሆኑን የባነኑት የአማራ ሕዝብ ሲነሳ መሆኑ ግን የፖለቲካ ጨዋታውን ቀልድ አስመስሎታል። በዚህ አላበቁም ለፈሰሰው የወገናችን ደም ካሳ እንደሚከፍሉም ተናግረዋል።  የሰው ልጅን ህይወት እንደ እቃ ቆጥረው ሲያበቁ  በገዛ ራሱ  ገንዘብ ሊክሱት ቃል መግባታቸው የባሰ ያሳምማል።   የህይወት ካሳ አለ እንዴ?  ለመሆኑ የአንድ ሰው ነብስ ስንት ያወጣል?

        የራስ ዳሽን መመለስ ኢትዮጵያ አሁን የገባችበትን ችግር አይፈታውም። የሕወሃትን ማንነትን ግን የበለጠ ይፋ አድርጎታል።


አንጋፋው ጋዜጠኛ አበራ ወጊ አረፈ |በስደት የሚገኙ የኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞች መግለጫ አወጡ |ይዘነዋል

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በሃገር ቤት ማዕበል ጋዜጣን ጨምሮ በተለያዩ የፕሬስ ውጤቶች ውስጥ ሲሰራ የነበረውና በትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ለአንድ ዓመት ከ4 ወር ታስሮ የነበረውና በስደት በካሊፎርኒያ ይኖር የነበረው ጋዜጠኛ አበራ ወጊ በመኪና አደጋ ሕይወቱ ማለፉ ተሰማ:: ይህን ተከትሎ በስደት የሚገኙ የኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞች መግለጫ አውጥተዋል – እንደሚከተለው ተስተናግዷል::

abera-wegi በጋዜጠኛ አበራ ወጊ ህልፈት አዝነናል – መልካም ስሙ ግን ከመቃብር በላይ ይኖራል!

Hiber Radio: በመተማ ሰፍረው የነበሩ 35 ወታደሮች የሕዝቡን ትግል ተቀላቀሉ፣ አርብ በተደረገ ውጊያ በወገራና በመተማ ዮሐንስ 11 የሕወሓት ወታደሮች ተገደሉ፣የተማረኩ ትግሉን ተቀላቅለዋል ፣ ጀግናው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ በአገሪቱ ውስጥ ፍትህ ካልስፈነ አገሪቱ ወደ ከፋ ሁኔታ እንደምትሄድ አስጠነቀቀ

$
0
0

የህብር ሬዲዮ መስከረም 8 ቀን 2009 ፕሮግራም

የአምቦ ዩኒቨርስቲ መምህር ስዩም ተሾመ ከህብር ሬዲዮ በወቅታዊው የመምህራን ውይይት እና የዝምታ ተቃውሞ ላይ ተጠይቆ ከሰጠው ምላሽ የተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)

habtamu-150x150.jpg
የዘ-ሐበሻ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ሔኖክ ዓለማየሁ በሚኒሶታ ለጀግናው አትሌት ፈይሳ የተደረገውን ታላቅ አቀባበል በተመለከተ ከሰጠን ማብራሪያ (ቀሪውን ያዳምጡት)

አክቲቪስት እና የኦሚኔ ዋና ዳይሬክተር ጃዋር መሐመድ ኢትዮ ቲዩብ የማህበራዊ ሚዲያው አክቲቪዝም በኢትዮጵያ በሚለው ውይይት ላይ ተገኝቶ ከሰጠው ማብራሪያ የተወሰደ(ቀሪውን ያዳምጡት)

አቶ ጁነዲን ሳዶ የሕወሃት ቡድን በአማራና በኦሮሞ ባለስልጣናት ላይ ያደርገውን ተጽዕኖ፣ከምርቻ 97 በሁዋላ የተከተለውን ዘረና እርምጃና የሌላውን ብሔር ነጋዴ ከገበያ ያወጣበትንና በስርዓቱ ደጋፊ የትግራይ ተወላጅ ነጋዴዎች የተካበትን ሂደትና ለምን ሐይለማሪያምን እንደሾሙና ሌላውንም ያብራሩበትን ጽሑፍ ዳሰነዋል (ልዩ ጥንቅር)

አንጋፋው ጋዜጠኛ አበራ ወጊ ሲታወስ (ቃለ መጠይቅ)

ለአትሌት ፈይሳ ለሊሳ አቀባበል በተደረገው ዝግጅት ላይ አቶ መላኩ በቀለ የሚኒሶታ የኢትዮጵአ ኮሚቲ ተወካይ አኢና አቶ መሐመድ አባስ የኦጋዴን ኮሚኒቲ ተወካይ ያደረጉትን ንግግር (አዳምጡት)

የመብት ተሞጋቹ ኦክላንድ ኢንስቲቲዩት በኢትዩጵያ ውስጥ ለውጥ ካስፈለገ ብቸኛው ወቅት አሁን ብቻ ነው ሲል ጥሪ አቀረበ

ዜናዎቻችን

በመተማ ሰፍረው የነበሩ 35 ወታደሮች የሕዝቡን ትግል ተቀላቀሉ፣ አርብ በተደረገ ውጊያ በወገራና በመተማ ዮሐንስ 11 የሕወሓት ወታደሮች ተገደሉ፣የተማረኩ ትግሉን ተቀላቅለዋል ፣ ጀግናው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ በአገሪቱ ውስጥ ፍትህ ካልስፈነ አገሪቱ ወደ ከፋ ሁኔታ እንደምትሄድ አስጠነቀቀ

ሕወሓት ዩኒቨርስቲዎች ሲከፈቱ በአማራና በኦሮሞ ተማሪዎች መካከል የጎሳ ግጭት እንዲቀሰቅሱ ላዘጋጃቸው ሽሬ ላይ ስልጠና እየሰጠ መሆኑ ተገለጸ

የአሜሪካው ፕ/ታዊ እጩ ትራምፕ የተፎካ ካሪያቸው ሔለሪ ጠባቂዎች ትጥቅ እንዲፈቱሀሳብ ማቅረባቸው ተቃውሞ አስነሳ

“አንድ የአሜሪካ መከላከያ ሀይል የበላይ ጠባቂ ለመሆን የሚጥር ስው እንዲህ ማለቱ ያሳፍራል”ተቀናቃኞቻቸው

እስራኤል በቤተእስራኤሎች ላይ የሚደርስው ዘርኝንትን አስቆማለሁ አለች፣ለዘመቻውም ከፍተኛ። ገንዘብ መድባለች

ትውልደ ኢትዩጵያኖች አሜሪካ በበሕወሓት/ኢህ አዲግ አገዛዝ ላይ ጫና እንድታርግ በፊርማ ማስባስብ ዘመቻ እንዲግፉ ተጠየቀ

አንጋፋው ጋዜጠኛ አበራ ወጊ በሳንዲያጎ በድገተና የመኪና አደጋ ሕይወቱ አለፈ

ሌሎችም

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

VIDEO: ኢትዮጵያን በዋሽንግተን ዲሲ ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፍ እያድረጉ ነው

አቶ ጌታቸው ረዳ የሸገር ካፌ ቆይታ ….

$
0
0

ግርማ ሠ ይፉ ማሩ

የኮሚኒኬሸን ሚኒሰትሩ አቶ ጌታቸው ረዳ በሸገር ካፌ ላይ ቀርበው ከእሸቴ አሰፋ ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ ሰጥተዋል– ጥያቄዎቹ የህዝብ መልሶቹ ግን የተለመዱ የኢህአዴግ ናቸው– ያሰገረሙኝን ብቻ ላካፍላችሁ– አቶ ጌታቸው ያለምንም ይሉኝታ ዳግም ተሃድሶ የታችኛውን ክፍል እንደሚጠራርግ ነግረውናል– ምክንያቱም መመረያ በሚል ሰበብ ህዝብ አያጉላሉ ያሉት እነርሱ በመሆናቸው የሚል አስቂኝ ሰበብ ሰጥተዋል– እግረ መንገዳቸውም ሚኒስትሮች እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከህግ በላይ እንዲሆኑም ፍላጎት አሳይተዋል– ሚኒስትሩ/ ጠቅላይ ሚኒስተሩ ሲያዙ መመሪያ አይፈቅድም ይላሉ– እኔ እስከ ዛሬ ባለኝ ልምድ የመመሪያው ባለቤቶች እነዚያው ሚኒስትሮች መስለውኝ– መቼም እዚህ ሀገር ጉድ ሳይሰማ መሰከረም ስለማይጠባ በየመስሪያ ቤቱ ያሉ ኤክስፐርቶች መመሪያ የማውጣት ስልጣን ተሰጥቶ ከሆነ ልክ አይደሉም ሰልጣናቸውን ያለ አግባብ ሚኒሰትሮች እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለማሳቀቅ ሊጠቀሙበት ባልተገባ ነበር– ይህ ካልሆነ ግን እርሰ በእርሱ የሚጋጭ መመሪያ ያወጣ ሚኒስትር ያወጣውን መመሪያ ኤክስፐርት ቢያስታውሰው ክፋቱ አልታየኝም እና አቶ ጌታቸው በድጋሚ ቢያብራሩልን– በነገራቸን ላይ መመሪያ ደንብ የሚያከብሩና የሚያስከብሩ ሚኒስትሮች እና ጠቅላይ ሚኒስትር ነው የሚያስፈልገን– መቼም አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝን ያዘዙት እንቢ ያለ ኤክስፐርት ማን እንደሆነ ማወቅ ጥሩ ነበር– ይህ ኤክስፐርት አቶ መለስንም እንዲህ ይል ነበር? የሚል ጥያቄም ያጭራል– አቶ መለስ እንዲህ ብለዋል እየተባለ ባልወጣ መመሪያ እንተዳደር እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም– ይህ ጉዳይ እኮ የቅርብ ጊዜ ነው– ሌላው አቶ ጌታቸው ረዳ ካለፈው ስህተታቸው መማር ያልቻሉት በሚዲያ በሚተላለፍ ውይይት ቃላት
girma seifu

መረጣ አለመቻላቸው ወይም ፍላጎት ያለማሳየታቸው ነው– ጭራቅ እና አጋንንት መውደዳቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ማለቴ ነው– ለምሳሌ “ ህዝብ አሁን ካሉት 28 ካቢኔ ሚኒስትሮች ስንቱ ቢታሰር፣ ስንቱ ”ቢሰቀል እንደሚረካ አይገባኝም ብለዋል– እኛ ይስቀሉ አላልንም– ነገር ግን እሰከሚገባኝ ድረስ ያለ አግባብ ከተሰቀሉበት ስልጣን ይውረዱ– ወርደው ባለጉዳይ ሆነው ይህችን ሀገር ይመልከቷት ነው የተባለው– እኔ እስከሚገባኝ ኢህአዴግ እስከ አሁን በፍፁም እንዲገባው የማይፈልገው ተጠያቂነት በውክልና አይተላለፍም ውክልና ለበታች ሰራተኛ ሲሰጥ ስራውን/ ሃላፊነቱን ብቻ ነው– የተወከለው ሰራተኛ ካጠፋ የሚጠየቀው የወከለው ሃላፊ ነው– ይህ ሀሁ እንዲት ለሃያ አምስት ዓመት መረዳት ያቅታል– መቼም የጫካውን ዘመን እንርሳው ብዬ ነው–
እሸቴ አሰፋ በግልፅ ያቀረበላቸው አንዱ ጥያቄ የአንድ ብሔር የበላይነት/ የህወሃት የበላይነት አለ የሚል ቅሬታ አለ የሚል ነው– ይህ ጉዳይ በግምገማቸው ላይ ተነስቶ በስፋት ውይይት መደረጉ አቶ ጌታቸው ነግረውናል– የተነሳው የአንድ ብሔር /የትግራይ/ የበላይነት አለ የሚለው አንድ በጎ ነገር ሲሆን የተደረሰበት ነገርም ጥሩ ነው– አንዱን ኪራይ ስብሳቢ በሌላ ብሔር ኪራይ ስብሳቢ መተካት አይደለም– ህዝቡ እያለ ያለው ህውሃት ወርዶ በብአዴን ወይም በኦህዴድ ይተካ አይደለም– ሁላችሁም ውረዱ ነው– አሁን ያለው የህወሃት የበላይነት እንዲነግስ ያደረጉ አሁን ጥያቄያቸው በተራችን እኛ እንሁን ከመሆን ሊዘል አይችልም– የእኛ ጥያቄ ግን የዚህ ዓይነት ስርዓት አያስፈልገንም የሚል ነው– ከአንድ ብሔር የበላይነት ጋር ተያይዞ የተነሳው አንድ ቁልፍ ነገር የቁልፍ ቦታዎች ነገር ነው– ቁልፍ የሚባሉት ቦታዎች ለምን ቁልፍ ሆኑ? ሲባል ኪራይ ማደያ ሰለሆኑ ነው:: ምርጥ መልስ ነው– ያሳዝናል– አንድ የመንግሰት ተቋም ሃላፊ መሆን የራስን ግሳንግስ መሰብሰቢያ ስርዓት ከመገንባት የከፋ ውርደት ከየት ይመጣል– በኢትዮጵያ የሲቪል ሰርቪስ ታሪክ ሚኒስትር መሆን የራስን ቡድን መጥቀሚያ እንዲህ ዓይን ባወጣ መልኩ የሆነበት ጊዜ አሁን ብቻ ነው– ለምሳሌ የውጭ ጉዳይ ስራተኞች ምደባ ከብቃት ይልቅ በድርጅት ሰለሚሆን ኢህአዴግ አራት ድርጅቶች እንዲሁም በጨረፍታ ለአጋር ድርጅቶች ይታደላል– ከውጭ ጉዳያ ጋር ተያይዞ በቅርቡ የሰማሁት አንድ ነገር አለ– ህወሃት የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትሩን ቦታ ቢይዝም ዋና ዋና የሚባሉትን ቦታዎች ለብአዴን/ ብራሰልስ፣ እንግሊዝ፣ እስራኤል፣ወዘተ/ ለቋል የሚል ቅሬታ አለ– በአሜሪካ ግርማ ብሩም ቢሆን ከኦህዴድ ይልቅ የሸዋ ሴረኝነቱ ይበልጣል ይሉታል- ህወሃቶች– ይህ እንግዲህ ህወሃቶች አሁን በያዙት የውጭ ጉዳይ ኪራይ ስብሳቢነት አልረኩም ማለት ነው– ይህን ለማስተካከልም ሙከራዎች አሉ ይባላል– መቼም ለምን ከፊት አልሆንም ካልሆነ በሰተቀር በሁሉም ቦታ እንዳሉ በግሌአውቃለሁ– “ አቶ ጌታቸው ረዳ አንድ አሰቂኝ ምላሽ ሰጥተዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የከበቧቸው አማካሪዎች ወሳኝ” አይደሉም የሚል– እንደ ምሳሌም ያቀረቡት እራሳቸውን አማካሪ በነበሩበት ወቅት ወሳኝ አልነበርኩም በማለት ነው– እኛ የምናውቀው የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ቦታዎች በሶሰት ሊከፈሉ እንደሚችሉ ነው–አንደኛው የእውነት የማማከር ስራ የሚሰሩ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ ቤት የተቀጠሩ ባለሞያዎች ናቸው–ሁለተኛው ደግሞ በሸተኞች እና ጡረታ እስኪወጡ ሊጠቀሙ የሚፈልጉ ሰዎች የሚገኙበት ነው– ይህ ምድብ እንደ ማግለያም ማገገሚያም ያገለግላል– የኤምባሲ ክፍት ቦታም እስኪገኝ መጠባበቂያም ሆኖ ያገለግላል– ሶሰተኛው ደግሞ ወሳኝ የሚባሉት የሚገኙበት ነው– በቁጥርም ውስን ናቸው– ጠቅላይ ሚኒስትሩን በፓርቲ ማዕቀፍ መስመር በማስያዝ ውሳኔ የሚሰጡ ናቸው– ይህ ሶሰተኛው ቡድን አማካሪ በአቶ መለስ ዜናዊ ጊዜ አልነበሩም- ሊኖሩም አይችሉም– ሰውዬ በራሳቸው ወሳኝ ነበሩ– የተቀሩት ሁሉቱ ዓይነት አማካሪዎች ግን ድሮም የነበሩ ናቸው– ይህን ህዝቡ በደንብ ያውቀዋል ማን በየትኛው ምድብ እንዳለም ይታወቃል– ሰለዚህ የአቶ ጌታቸውን መልስ አልተቀበልነውም–
ቸር ይግጠመን!!!

Video: ኢትዮጵያን የተቃውሞ ሰልፍ በዋሽንግተን ዲሲ

በእስራሄል የተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ..

የትግራይ የበላይነት ጉዳይ

$
0
0

በታምሩ ሁሊሶ
ገና ድሮ

10365740_10205799880460884_1385927631577657048_nኢህአዴግ አዲስ አበባን በ1983 ከረገጠ ማግስት አንስቶ የትግራይ ህዝብ ከመንግስት የተለየ ጥቅም የሚየገኝ ተደርጎ መወራቱ የአደባባይ ሚሰጥር ነው፡፡ ጥቂት ለማይባለው ህብረተሰብ ላለፉት 25 ዓመታት የተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ ንብረት ወደትግራይ ነው የሚጋዘው፡፡ አንድ ወቅት አፈር ሁሉ ከጎጃምና ከጎንደር ተጭኖ ተወሰደ የሚሉ ”አሉባልታዎች” ሁሉ ይናፈሱ ነበር፡፡ ይህ የአንድ ብሄር የበላነይነት ጉዳይ እስከ 1998 መጀመሪያ በነበሩት የግል ጋዜጦች የእለት ከእለት አጀንዳ(ብዙ ጊዜም በተጋነነ መልኩ) ነበረ፡፡የግሉ ሚዲያ ትግራዮች ስማቸውን ሁሉ ቀይረው ነው ሌላው ህዝብ ላይ የሰፈሩት ለማለት፤ ትዝ ይልኛል የዶር ነጋሶ ስማቸው ነጋሲ ብሎ ሲጽፍ፡፡ በመንግስትና የኢህአዴግ አጋር ሚዲያዎች ይህ ጉዳይ ነውር (ወራዳ አጀንዳ) ተደርጎ ተንቆ የቆየ ቢሆንም፤ የምርጫ 97 ክርክርን ሳይጨምር፤ በህዝቡ ውስጥ የአንድ ብሄር የበላይነት ጉዳይ እየተላወስ ያለ ነገር መሆኑን በመንግስት ሚዲያዎች የተገለጸበት ሁለት አጋጣሚዎችን በግርድፉ አስታውሳለሁ፡፡

ወቅቱ 1985 መጨረሻ ላይ ነበር፡፡ የዚያን ጊዜው መንግስት ጊዜያዊ ነበር፡፡ኢህኣዴግም በወቅቱ ጊዜያዊ እንጂ አሁን የምናየውን ቋሚ ባህሪውን አላመጣም ነበር፡፡ የሚዲያው ነጻነት ለግሉ ብቻ ሳይሆን ለመንግስቱም የኢትዮጵያ ሬዲዮ የተረፈ ይመስል ነበር፡፡በሳምንት የተወስኑ ቀናት የአድማጮች ድብዳቤ አይነት ነገር ፕሮግራም ነበረ፡፡ አድማጮች የተሰማቸውን ጽፈው ይልካሉ፤ካለምንም ገደብ አሳባቸው ይነበባል፡፡ አንድ ምሽት አንድ ከአድማጭ የተላከ አንድ ግጥም ይነበባል፡፡ የግጥሙ ይዘት ምን እንደነበረ አላስታውስም፡፡ በሌላ ጊዜ ሌላ አድማጭ ያንን ግጥም መሰረት አድርጎ ቁጣ የተሞላ ደብዳቤ ለጣቢያው ይልካል፡፡ የዚህ ግለሰብ ደም ፍላት ምክንያት ደግሞ፤ ቀደም ባለው ቀን የተነበበው ግጥም የያንዳንዱ ስንኝ የመጀመሪያ ፊደላት ቁልቁል ሲነበብ ”ትግራይ እስክትለማ ሌላው አገር ይድማ ” የሚል መልዕክት መያዙ ነበረ፡፡
ግንቦት 20፤1990-በወቅቱ ኤርትራ ባድመን በወረራ ከያዘች ሁለት ወር እንኳን አልሞላም ነበረ፡፡ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትርም የወረራውን ጦስ ጥንቡሳስ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የሆነ ቡድን ወይም ግለሰብ ይዞ ወደገደል እንደሚወርድ አስቀድመው የገባቸው ይመስላሉ፡፡ ባልተለመደ መልኩ ለህዝብ ተደራሽ መሆንን ፈለጉ፡፡ በመሆኑም የ1990 ግንቦት 20 የሬድዮ ፋና እንግዳ ሆነው ለመቅረብና ከአድማጮች የሚመጣ ማንኛውንም ጥያቄ ለመቀበል ዝግጁነታቸውን ይገልጻሉ፡፡ በዕለቱ በርካታ ጥያቄዎችን ተቀበሉ፤ያላቸው የሃብት መጠን ስንት እነደሆነም ተጠይቀው፤ ከሚለብሱት ልብስና ከሚያነቡት መጽሃፍ በስተቀር ሌላ ጥሪት እንዳልቋጠሩ ገለጹ፡፡ አንድ አድማጭም ”እርስዎ ግን እውነት ለትግራይ አያዳሉም ?” የሚል ጥያቄ አነሳባቸው፡፡ ጠቅላዩም ” እኔ ለትግራይ አላዳላም፤እንደኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትርነቴ ሁሉንም እኩል ነው የማየው ” አሉና ”እርግጥ ነው” ሲሉ ጨመሩ ” እርግጥ ነው፤ ከጦርነቱ ማብቂያ፤ 1983 በኋላ በነበሩት 3 እና 4 ዓመታት በጦርነት ለተጎዱ ክልሎች ልዩ ድጋፍ ይደረግ ነበረ፤ትግራይም ዋነኛዋ ድጋፍ የሚሰጣት ክልል ነበረች ፡፡ ከዛ ውጭ ሌላ አድልኦ የለም ”በማለት ጥያቄውን ዘጉት፡፡ ቃል በቃል አደለም ይህንም የማስታውሰው፡፡ በኋላ የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት አልቆ በ1993 የወያኔ እንፍሽፍሽ ወቅት፤ ሟቹ እነስዬን አነፍሰው አንፍሰው ከጣሉባቸው ጉዳዮች አንዱ ግን ይሄው ነበር፡፡ በወቅቱ አቶ መለስ እነስዬን የናንተ ዘር ማንዘሮች ከድንጋይ ውስጥ በአንድ ምሽት ድንገት ሚሊዬነር ሆነው ሲበቅሉ፤የትግራይ ህዝብ ግን ባልበላበትና ባልዋለበት ጠላት ያፈራል ብለዋቸዋል (በወቅቱ ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ይወጡ የነበሩ ረጃጅም ጽሁፎችን ልብ ይሏል)፡፡
ከዚያ በኋላ ይህን ጉዳይ በገደምዳሜም ቢሆን በአደባባይ ያነሱትና ሰዎች እኩልነት እንደማየሰማችው የገለጹት በምርጫ 97 የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ነበሩ፡፡ ነገርግን የኢህአዴግ ሰዎች ይህን ጉዳይ ያነሱ ተቃዋሚዎችን ዘረኛና የኢንተራምዌ ዛር የሰፋረባቸው አራዊቶች አስመስለው በመሳል የትግራይ ህዝብን ለማስደንገጥ ተጠቅመውባታል፡፡
ዘንድሮ
አሁን ብዙው ህዝብ ደምድሞ የጨረሰ መስሏል፡፡ ”ነፍስ ያለው ቢዝነስ” ከትግራይ ልጆች ቡራኬ ውጭ አይታሰብም ብሎ ተስማምቷል፡፡ ”ጉዳይ ለመግደል” ትግርኛ ተናጋሪን ይዞ መሄድ አማራጭ የሌለው ነገር መሆኑን ተግባብቷል፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ ያሉ ህንፃዎችን ቆጥሮ በብሄር አከፋፍሏል፡፡ በቅርቡ በፍቄ ” ትግራይ ለምን አታምጽም ” የሚል ጽሁፉ ላይ እንደጠቀሰው አባባል እስከመቀየር ድረስ ሄዶ ”ቤት የእግዚያብሄር ኮንዶሚኒየም የገብረ እግዚያብሄር ” ማለት ጀምሯል፡፡ ሰዉ በሁሉም ዘርፍ የትግራይ የበላይነት እንዳለ ሲያወራህ ግራና ቀኙን እንኳን እየተመለከተ አይደለም፤ቅቡልነት እንዳገኘ የሥርሃቱ አካሄድ በግልጽ ነው፡፡ ከሁለት ዓመታት በፊት ላፍቶ አካባቢ የሚገኝ ኮንዶ ውስጥ ነበር የምንረው፡፡ አንድ ጠዋት አንድ ብሶተኛ ድሃ ጎልማሳ ቄራ ድረስ እንድሸኘው ጠየቀኝና መኪና ውስጥ ገባ፡፡ ብዙም ሳንሄድ በለስ በጋሪ ሞልቶ የቆመ ልጅ አየን፡፡ አብሮኝ ያለው ጎልማሳ ድሃ ማንነቴ ምንም ሳያስጨንቀው ”ተመልከት ” አለኝ ወደ በለሱ እየጠቆመ፡፡ ”ተመልከት ከተማውን እኮ በቁልቋል ሞሉት ፤ይሄ ሁላ ምንድነው ካልክ ፤ቅመሱት፤ እኛም እዚህ የደረስነው ይሄን በልተን ነው መልዕክቱ!!፡፡ የሚገርምህ አሁን የአዲስ አባ ህዝብ እራሱ እየለመደው ነው፤ በችግር ብዛት!!፡፡ምሳውን ሁለት ቁልቋል በልቶ የሚውል ጓደኛ ሁሉ አለኝ!!፡፡እነሱስ በለኛ?!!፤እነሱ በምርኩዝ ዝላይ ከቁልቋል ጥሬ ስጋ ላይ ጉብ ብለውልሃል ወገኔ!!፡፡ ግፋቸው እኮ.. ሶስት ኪሎ ጥሬ ለሁለት በልተው አንድ ኪሎ አነስ አድርገህ ጥበስ ብለው ያዙብሃል እላይህ ላይ” አለኝ ሆድ እየባሰው፡፡የሚያወራው ነገር በጥቂት ናሙና ግዙፍ የሆነ ድምዳሜ ላይ የሚያደርስ ነገር መሆኑን ባውቅም አልተቃወምኩትም፡፡ ምንም አላልኩትም፤ሁሉም ትግሬዎች እኮ እንደሱ አይደሉም በኑሮዋቸውም ባስተሳሰባቸውም ብዬ ለመናገርና አመለካከቱን ለማስተካከል ድፍረት አላገኘሁም፡፡ ምክንያቱም ከንቱ ድካም ነው፤ከሞላጎደል ተቀባይነትን ያገኘ አመለካከትን ለመቀየር በኔ አቅም መሞከር ፡፡ ከመኪና ከወረደ በኋላ ግን ይሄ መንገድ ወዴት ይወስደን ይሆን እልኩ ማሰቤ አልቀረም፡፡
የጉዳዩ ባለቤቶችስ-የትግራይ ልሂቃን
ለመሆኑ የጉዳዩ ባለቤቶች የሆኑት በመሃል አገር አካባቢ ያሉ የትግራይ ልሂቃን ይህን የሌላው ህብረተሰብ አመለካከት እንዴት ነበር የሚወስዱት ብሎ መጠየቅ አግባብ ነው፡፡ ብዙዎቹ ”እና ምን ይጠበስ ? ” ዓይነት አተያይ እንደነበራቸው መረዳት ቀላል ነው፡፡ ለዚህ ሥርሃት ከማንም በላይ እኛ ብዙ ከፍለናል ድርሻችንም የከፈልነውን ያህል ሊሆን ይገባል መሳይ ክርክሮችን ከአንዳንዶች ብዙ ጊዜ እናደምጣለን፡፡ እነሱ ይገባናል ብለው ከሚያስቡት የስልጣን ድርሻ በተጨማሪ ደግሞ ሌለው ህብረተሰብም ”ያሸከማቸው” ስንልቦናዊ የበላይነት (Perceived Power) ነበረ ፤አለ፡፡ ይህኛውንስ ስልጣን እንዴት ይመለከቱት ነበር ብለን ጉዳዩን ያጤንን እንደሆነ የሚመለከቱት በደስታ እነደሆነ ለመረዳት የሚያስችሉ ነገሮች አናጣም፡፡ብዙው የትግራይ ኢሊት ስለሱ የተቀረው ህዝብ የሳለው ስዕል ጮቤ የሚያስረግጠው ይመስለኛል፡፡የዚህ ዓይነቱ ስልጣን ወይም የበላይነት በብላሽ የሚገኝና ከ”ብዙ ከፍያለሁ፤ ብዙ ይገባኛል” የሚል እብሪት ጋር ሲጨመር ከፍ ያለ ቁሳዊ ጥቅም የሚያሳፍስ የንጉስ ዙፋን እንደሆነ ያውቀዋል ፡፡ይህኛው ስልጣን መገለጫው ብዙ ነው፡፡ አንድ ሰው በዚህ ለመጠቀም የግድ የመንግስት ባለስልጣን መሆን የለበትም ፡፡ ይህንኑ ተጠቅሞ በከንትሮባንድ ንግድ ዲታ የሆነ፤ትላልቅ ጫረታ ያሸነፈ፤ድንገት በአንድ ሌሊት ሚሊዮነር የሆነ፤የመንግስት ቀረጥ ያጭበረበረው ብዙ ነው፡፡ ጉዳይ ሊያስጨርሱ ገብተው በአማርኛ ሲጠየቁ በትግርኛ የሚጮሁ ብዙዎች ነበሩ፡፡በርግጥም እንደነዚህ ዓይነቶቹ ግለሰቦች ድርጊታቸው በህዝቦች አብሮ መኖር ላይ የሚኖረውን ጥላ ሊያገናዝቡ የማይችሉ ጅቦች ሲሆኑ፤ሁሉም የትግራይ ተወላጅ ሁሉንም የሌላ ብሄር ተወላጅ የሚበልጥ ተደርጎ መታሰቡ ለራሳቸው ጊዜያዊ ጥቅም አስፈላጊ ሆኖ እስካገኙት ድረስ ”አዎ ልክ ነው የበላይ ነው” ብለው ከመናገር የመይመለሱ፤ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል አይነቶች ናቸው፡፡
የዛሬዋ ኢትዮጵያ ተቃውሞና የትግራይ ኢሊቶች መልስ
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የምናየቸው ነገሮች ያስጠላሉ፡፡ የተጠራቀመ ብሶትና ምሬት ኢትዮጵያን የመሰለችን ታላቅ አገር የርዋንዳ ታናሽ እህት ሊያደርጋት እየቀረበ ይመስላል፡፡ የ1994ቱ የርዋንዳን ቋቁቻ የኢትዮጵያ አንገት አካባቢ እየታየ ነው፡፡ ገዳይ፤ዘራፊውና ሌባው ሁሉ አንድ ብሄር (ትግራይ) ነው የሚል ያልተገራ ፕሮፓጋንዳ የማህበራዊ ሚዲያው ማድመቂያ ሆኗል፡፡ ተው ይህ ነገር ጥሩ አደለም ያለ ግለሰብ ፤ተቃዋሚ እንኳን መሆኑ ቢታወቅ በቁርጥ ቀን እንደተልባ የተንሸራተተ ከዳተኛ የሚል ካባ ይለብሳል፡፡ብዙው ድፍረት አጥቷል፤ያልመሰለውን ነገር ለመቃወም፡፡እናም ብዙዎች ባለጌዎች ካለምንም ሃግ ባይ የእልቂት ፍልውሃ እያንተከተኩ ነው፡፡ በማዕበራዊ ሚዲያው ላይ ያሉት የትግራይ ልሂቃንም ለችግሩ እኛ ምን አዋጣን ሳይሆን ሌሎችን ዘረኞች እያሉ መከሰስ ሆኗል ስራቸው፡፡ ችግሩም ለጊዜው እንዴት በቁጥጥር ስር ይውላል ነው እንጂ በዘላቂነት መፍትሄው ምን መሆን አለበት የሚለውን አሁንም የሌሎች ራስ ምታት ብቻ አድርገው ይወስዱታል፡፡ አንዳንዶቹ እንዲያውም ክስተቱ የትግራይ ብሄረተኛነትን የበለጠ የሚያጠናክር ሌላ ተጨማሪ በረከት ሁሉ አድርገው እየወሰዱት ነው፡፡ አሳሳቢው ነገር አሁንም ሌላውን ብሄርና ህብረተሰብ የምሳደበው የትግራይ ህዝብን ወክዬ ነው ብሎ የሚናገር ያልተገረዘ ሸለፈታም ኤሊት መታየቱ ነው፡፡ እኛና ኢትዮጵያ ወይ ደግሞ እናንተና ሶሪያ የሚል ካርታ በመሳብ በአገራችሁ ቁማር አትጫወቱ እያለ የሚያስፈራራውና እሱ ብቻ ልቆምር የሚለውን፤ ራሱን የትግራይ ህዝብ ተወካይ ያደረገ ድውይ እየበረከተ መሄዱ ነው፡፡
በዚህ መሃል የአቶ ስዩምን ቃለምልልስ ከፋና ጋር አደመጥኩት፡፡ ቀደም ብዬም የዶር ድበረጽዮንን ቪዲዮ ከሆርንአፌይርስ ጋር ተመልክቼው ነበር፡፡ ዛሬ ጠዋትም አቶ ጌታቸው ከሸገር ጋር ያደረገውን ውይይት ተከታተለኩ፡፡ ሶስቱም ”የትግራይ የበላይነት” የሚባለውን ጉዳይ አንስተውት ነበር፡፡አቶ ስዩም ሆሎካስትን ሁሉ አንስተው፤ ይሄ ጉዳይ ለረጅም ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ሲነገርና ሲሰራበት የነበረ፤ እነሱ (ወያኔዎች) ግን እንደቀልድ እየተሳሳቁ ሲያልፉት የነበረ ”አደገኛ ሁኔታ” መሆኑን ገለጹ፡፡ ደብረጽዮንም የትግራይ የበላይነት የሚባል ነገር እነደሌለ ገልጸው ” አሁን እኮ ፌደራል መንግስቱ ላይ እኩል ነው ስልጣኑን ያያዝነው ” በማለት ” ያው ከወታደሩ ታሪካዊ አመጣጥ አንጻር ትንሽ ሚሊታሪው አካባቢ ነው እንግዲህ የሚቆጠሩ ጀነራሎች አሉን ከተባለም ” ይዘት ያለው ነገር በሳቂታ ጩጬ ፊታቸው ፈገግ እያሉ ተናገሩ፡፡አቶ ጌታቸውም መከላከያው አካባቢ የበላይ የሚባል ብሄር እንደሌለ ቢኖር እንኳን ሃገሩን በሞቱ ሊጠብቅ የቆረጠ ጄንራል ነው አይነት ዲስኩር አሰሙ፡፡ አቶ ስዩምና ደብረፅዮን ግን የትግራይ የበላይነት እውነታ ሳይሆን፤ ሌላው ህዝብ ነገሮችን የሚመለክትበት ወይም የሚረዳበት መንገድ (Perception) ነው ደጋግመው ብለዋል፡፡ ብርሃንን ደጋግመን ጨለማ ነው ብንል ጨለማ መስሎ ይታያል የሚል ምሳሌ ሁሉ ነበር፡፡ መቼም Perception ወደ ”ቆሌዬ ነገረኝ” የሚጠጋ ስሜት ሳይሆን፤ ሰው አካባቢውን የሚገነዘብበት እጅግ ከፍ ያለ እይታውና መረዳቱ ነው፡፡ አቶ ስዩም እንዳሉትም በርካታ የሚባለው የትግራይ ኤሊት ሌሎች ስለሱ የነበራቸውን አማለካከት ሲመለከተው የቆየው እንደቀልድ አደለም፡፡ ከላይ እናዳነሳሁት እየቦረቀ ነው፡፡
ከሌላው ህብረተሰብ ”የተሸከሙት” የበላይነት ሳያንስ ይባስ ብሎ እራሳቸው ዶር ደብረጽዮን እንደተገለጹት የትግራይ ኤሊቶች ወታደራዊው ተቋማትን በግላጭ ተቆጣጥረዋል፡፡ መከላከያው ከዓመት ዓመት የሚመደብለት በጀት አድጓል፤ይህ ነው የሚባል ቁጥጥርና ኦዲት የሚያውቀው ተቋምም አደለም፡፡ደብረጽዮን ምን አላት እሷ ይበሉ እንጂ፤ሜቴክን የሚያክል ግዙፍ ግን ዝርክርክ ተቋም ከስሩ የያዘ መከላከያ ላይ የአንድ ብሄር ተጽህኖ መታየቱ በሌላው ዘንድ ምን አላት የሚባል ነገር አደለም፡፡
የሶስቱም ሰዎች ምላሽ የሌላው ህብረተሰብ አመለካከት የተሳሳተ ነው የሚል ድፍረት አዝሏል፡፡ይህ ደሞ ወደክህደት የቀረበ ነውና ብዙው ህዝብ ” አዪ ስንተዋወቅ፤ አንተላለቅ ” እያለ በማፌዝ ላይ ነው፡፡
እኔ አሁንም የትግራይ ህዝብና ህወሃት አንድ ናቸው ብዬ ራሴን ወደሳሞራ የኑስነት አልቀይርም፡፡ የትግራይ ህዝብ ሁሉ እየመጣ በጆሮዬ ” እኔና ወያኔ አንድ ነን ብሎ ” ቢነግረኝ እንኳን ይህን አልቀበልም፡፡ ስለኢትዮጵያ ተስፋ ካልቆረጥኩም ኢትዮጵያን ከትግራይ ውጭም ላስባት አልፈልግም፡፡
በዛኛው ጥግ ቆሞ በእያንዳንዱ የጥይት ራት መቃብር ላይ የትግራይን ህዝብ ስም እየጻፈ ደመኝነት የሚቆልለውም ፤ህዝባቸውን የጥይት መከላከያ ለማድረግ ከማይመለሱት ጥቅመኛ የትግራይ ኤሊቶች ያልተለየ ሸለፋታም ፖለቲከኛ ነው ፡፡ ነገር ግን እንደ ዶር ደብረጽዮን በሥርሃቱ ታሪካዊ አመጣጥ ምክንያት ወታደራዊውና [የደህንነት መስሪያ ቤቱ] በትግራይ ተወላጆች የበላይነት ይታይበታል ከተባለ፤ጥገኝነቱም ፤በሌብነት መበልፀጉም፤ካለእውቀትና ብቃት ስልጣን ላይ መሳፈሩንም የትግራይ ልጆች ይመሩታል ወይም ባርከውታል ብሎ ሌላው ሰው ማሰቡስ ነውሩ ምንድነው?


የማለደ ወግ …ክበረ ነክ ፣ ጸያፍ ስድብ በመንግሥት ቴሌቪዥን !

$
0
0

* ቴሌቪዥኑ ከዘባተሎ ፖለቲካ መረጃ ቅበላ ወደ ብሽሽቅ መድረክነት
በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩው የኢትዮጵያ ሶማሌ ዲያስፖራዎች የወያኔ / ኢህአዴግን መንግሥት ደግፈው ፣ ግንቦት 7 እነ ኦነግን ተቃውመው ሰልፍ መውጣታቸውን ሰምተናል ። በዚሁ ሰልፍ ይዘውት የወጡት መፈክርን የያዘውን ክበረ ነክና ጸያፍ ስድብ ከትናንት ምሽት ጀምሮ በማህበራዊ ድረ ገጾችና በፊስ ቡክ ሲሰራጭ ተመልክተናል ። ምራቃቸውን የዋጡ አባቶች ፣ ወንድሞች ሂጃብ ያደረጉ የኢትዮ ሴቶች የተካተቱበት የድጋፍና ተቃውሞ ሰልፍ ይዘውት የወጡት” ኦነግ ተ… ዳ !” የሚለውን መፈክር ይገኝበታል ፣ ደጋግሜ አይቸው ማመን እቅቶኝም ነበር ። ወደ ኋላ ግን እርጠኝነቱን ስረዳ እዝነ ልቦና ያለው ያደርገዋል በማልለው ስድብ አዘል መፈክር ለእነሱ እኔ እስከ መሸማቀቅ ደርሻለሁ ፣ ያሳፍራል ፣ ያሳዝናል :(

14359236_10210894916794890_2196115700497151474_n
ዛሬ እኩለ ቀን ደግሞ ክበረ ነክ ፣ ጸያፍ ስድቡ በመንግሥት ቴሌቪዥን ላይ ቀርቦ ስመለከተው ደግሞ ይበልጥ ተሸማቀቅኩ ፣ አዘንኩ :( የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ተገቢ የልሆነ መረጃ ለመሰራጨቱ አዲስ ባይሆንም ” ኦነግ ተ… ዳ !” ብሎ የተጻፈን ነውረኛ መልዕክት በህዝቡ በሚደጎም ጣቢያ ማሳዬት ትልቁ የመንግሥት ተቋም ምን ያህል በዘቀጠ አስተደደር እንደሚመራ በገሃድ ያሳይ ይመስለኛል ።
በመንግሥት ቴሌቪዥን ይህን መሰል ጸያፍና ተገቢ ያልሆነ ተራና የወረደ የወሮበላ ስድብ ማስተናገዱ ያስቆጫል ። ይህም የመንግሥት ቴሌቪዥኑ ወደ ከተራ የተዛባ ዘባተሎ ፖለቲካ መረጃ ቅበላ ወደ ብሽሽቅ መድረክነት እየቀየረው መሆኑ በእርግጥም እንደ ዜጋ ያስቆጫል … በዚህች ሀገር የሰው ሰብአዊ መብት በጠመንጃ ሲጣስ ብቻ ሳይሆን ክብረ ነክ ጸያፍ የሚባል ነውር በአደባባይ ሲናኝ ” ተው ” ባይ ሽማግሌ ጠፍቶ እንዲህ መባዘናችን ልብ ይሰብራለረ ያማል :(
እስኪ ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ
መስከረም 9 ቀን 2009 ዓም

አትሌት ፈይሣ ሌሊሣ በሪዮ ኦሎምፒክ ያገኘውን የብር ሜዳልያ ለቤተ መዘክር አበረከተ።

$
0
0

4d280e0c49e5d492bcaa2bce88ad20bf

(ዘ-ሃበሻ) አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ በሪዮ ኦሎምፒክ ያገኘውን የብር ሜዳሊያ ወደፊት በቤተ-መዘክር እንዲቀመጥ ለኮሚኒቲ አበረከተ በእርዳታ ካገኘውም ገንዘብም ብዙ ሺውን ያስፈለጋቸዋል ብሎ ላመነባቸው ወገኖች ሰጥቱአል ::

ማኅበራዊ ሚዲያው እና የመንግሥት ስጋት

$
0
0

በተስፋዬ ዓለማየሁ
የማኅበራዊ ሚዲያውን አጠቃቀም በተመለከተ ተከታታይ ዘመቻዎች እና ማጥላላቶች በተለያዩ ግዜያት በሕትመት ሚዲያው ሳነብ፣ በብሮድከስት ሚዲያውም ሳደምጥ ቆያቻለሁ፡፡ እነዚህን የአጠቃቀም ጉድለቶች ላይ ያተኮሩ ዘመቻዎች ታዲያ እንደ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ስመለከታተቸው ነው የሰነበትኩት፡፡ ምክንያቱም መሰል ፈራጅ ዘጋቢ ፊልሞች በሕትመት ሚዲው ላይ ይሠሩ እና ጠንከር ያለው እርምጃ ይከተል ስለነበር ነው፡፡ በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ በመጀመሪ የኮረኮረኝ ጽሑፍ “ከማኅበራዊ ሚዲያው በስተጀርባ” በሚል ርዕስ በሪፖርተር ገዜጣ ላይ ከወጣ በጣም ቆየት ብሏል፡፡ የጽሑፉ ዋና ዓላማ የነበረው ከማኅበራዊ ሚዲያ ጠቀሜታ ‹በስተጀርባ ያለውን አደጋ ነው ማመመልከት› ነበር፡፡ የጽሑፉ አዘጋጅም በሚገባ አስረጅ ምሳሌዎችን አስቀምጠው ጠቀሜታውንም ለመዳሰስ ሞክረው ጽሑፋቸውን ቢያበቁም፣ ከዚያ በኋላ በተከታታይ እንዲሁ በተለያዩ ግዜያት ቅኝታቸው ማኅበራዊ ሚዲያው ከጥቅሙ ባሻገር ጉዳቶቹ ላይ ያተኮሩ ጽሑፎችን አንብቤያለሁ፡፡ እርግጥ ነው በተነሱት ሐሳቦች ዙሪያ የማኅበራዊ ሚዲያው፣ በዋነኛነትም ፌስቡክ ከጥቅሙ በዘለለ ባሉት አሉታዊ ተፅዕኖዎች ላይ መሠረታዊ ልዩነት ከጸሐፊዎቹ ጋር የለኝም፡፡ “የጥላቻ ንግግሮችን ማስተላለፊያ ነው”፣ “አሉባልታ ማሰራጫ ነው”፣ “የሠራ ግዜን ይሻማል”፣ “በቅርባችን ካሉ ወዳጅ ጓደኞቻቸችን ጋር ይለያየናል”፡፡ ሌሎችም የፌስቡክ እንከኖችን እያስታወስን መዘርዘር አንችላለለን፡፡

social-media
ማኅበራዊ ሚዲያው ግን በርካታ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ልንዘነጋው አይገባም፡፡ የማኅበራዊ ሚዲውን ችግሮች ማሳየቱ ለተጠቃሚው አጠቃቀሙን እንዲፈትሽ ስለሚያደርጉ መልካም ሊባል ቢሆንም፡፡ ችግሮቹን ማጉላቱ ላይ ግን አልስማማም፡፡ ከሚጠቀሱት ችግሮች ውስጥ ለራሳችን በጣም ተስማሚ የሆኑ ችግሮች አይጠፉምና በአግራሞት ወይም በድንጋጤ “ይህማ የእኔም ችግር ነው” የምንለው እና ለችግሩም ተጋላጭ እንደሆንን፣ በደንብ እንዲሰማን የሚያደርጉን ማሳያዎች ስለሚዘረዘሩ ሊያሸማቅቁን ይችላለሉ፡፡ ይህንን ስሜት ከመፍጠር ተሻግረው ግን በሕትመት ሆነ በብሮድካስት ሚዲያ የሚተላለፉት መልዕክቶች ውጤታቸው (ኢፌክታቸው) ምን ያህል እንደሆነ ትዝብቱን ለየግላች ልተወውና፣ ማኅበራዊ ሚዲያው ንበማስተዋል መጠቀም የሚለው ምክር ላይም እንስማማና፣ ፌስቡክ በአሁኑ ሰዐት ሁነኛ አማራጭ ሚዲያ እንደሆነ ለማሳየት የሚከተለውን እጽፋለሁ፡፡
መነሻ፤ በአገራችን የሕትመት እና የብሮድካስት ሚዲያ ሁኔታ ወፍ በረር ቅኝት
በአገራችን ውስጥ ያለት የብሮድካስት እና ሕትመት ሚዲያዎች ከሚጠበቅባቸው አንፃር ብዙ ይቀራቸዋል፡፡ በአግባበቡ እያገለገሉን አይደለም፡፡ ለዚህም በርካታ ምክንያቶችን ልንደረድር እንችላለለን፤ የጋዜጠኞች ብቃት ማነስ፣ የጋዜጠኞች የሥነ ምግባር ጉድለት፣ የጋዜጠኞች እና የሚዲያ ባለቤቶች የፖለቲካ ፍላጎት እና አመለካከከት፣ የገበያው ትርፋማነት እያልን በርካታ ምክንያቶችን ብንደረድርም “የእናቴ መቀነት…” ከመሆን አይዘልም፡፡ ምክንያቱም በእነዚህ ሰበቦች ወይም ችግሮች ውስጥ እንኳን የጋዜጠኝነት መርሖዎችን ለማክበር ከመሞከር ይልቅ ሲጥሷቸው በግልጽ ይስተዋላሉ እና ነው፡፡ በተለይም ደግሞ ጠንከር ባሉ ሁሉን ዐቀፍ ተሳትፎ እና ውይይት በሚፈልጉ አገራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ሁሉንም በዕኩል ደረጃ አያሳትፉም አያገልግሉም፡፡ አብዛኛዎቹ የአገራች ሚዲያዎች በጣም የተካኑባቸው እና የሚሽቀዳደሙባቸው ዘገባዎች በጣም ለስለስ ያሉ ማኅበራዊ፣ የመዝናኛ እና የስፖርት፣ የኪነ ጥበብ፣ የፊልም እና የፋሽን ጉዳዮች ናቸው፡፡
ጋዜጠኞች ማንም ደሞዝ ቢከፍላቸው፣ አገልጋይነታቸው ለዜጎች፣ ጥብቅናቸውም ለእውነት መሆን ሲገባው፣ በእኛ አገር ዐውድ ግን አብዛኞቹ ጋዜጠኞቻችን ሥራቸው ኅልውናቸው ስለሆነ የዜጎች አገልጋይነታቸው እና የእውነት ፍለጋቸውን ዘንግተውታል፡፡ በአንድ ወቅት በከፍተኛ ደረጃ ሠራተኛ ይለቅበት (turn out) የነበረው የሚዲያ ተቋም ከቅርብ ግዜ ወዲህ ግን በጣም ሳቢ የሆነ የደሞዝ ማሻሻያ እና ጥቅማ ጥቅሞችን በማድረግ ሠራተኞቹን ከማቆየቱም በላይ ሌሎችንም ለመሳብ ጥረት እያደረገ ነው፡፡ የበጀት ምንጩ ምንም እንኳን ከማስታወቂ የሚገኘው ገቢ ቢሆንም ከዜጎች ግብር የሚሰበሰበው ገንዘብም ቀላል አይደለም፡፡ የጋዜጠኞቻችን ትኩረት ግን የቀጣሪያቸው ትኩረት እና ፍላጎት መሳብ ብቻ ነው፡፡ ሙሉ በሙሉ ልማት እና ዕድገት ብቻ፡፡ በልማቱ ምክንያት እና ለልማት ሲባል ዜጎች ከአንድ አካባቢ ሲፈናቀሉ ወይም በልማታዊ ቋንቋ ለልማት ሲነሱ፣ የት ይድረሱ? ተመጣጣኝ የካሣ ክፍያ ያግኙ አገኙ? ቀጣይ ኑሮአቸውስ እንዴት ነው የሚሆነው? የሚለው ጉዳይ ከሚሰጠው ትኩረት ይልቅ ሰዎቹ ተነስተው ስለሚተከለው ግንባታ የሚወራው ይበዛል፡፡
የዚህ ዓይነቱ ጋዜጠኝነት ትኩረቱ ሰው ሕያው ፍጡር ሳይሆን ሕይወት አልባ ግዑዙ ነገር ነው፡፡ ቶማስ ሙር የተባለ እንግሊዛዊ ባለ ቅኔ በኢንድስትሪ አብዮት ወቅት ለሱፍ ልብስ የሚሆን የበጎች ፀጉር በብዛት ለማምረት ሲባል ጭሰኞች ከቦታቸው እየተፈናቀሉ በጎች ሲረቡ ሲመለከት “በጎች ሰዎችን በሏቸው” እንዳለው የልማታችንን ትክክለኛ ገጽታ ለመተቸት አልቻልንም፡፡ እንዳንተችም ተደርገናል፡፡ ሚዲያዎቻችንም ነፃ መድረክ በመሆን እንድንወቃቀስ እና እንድንተራረም ክፍት ስላልሆኑ ሌላ መንገድ፤ ሌላ መድረክ አስፈልጎናል፡፡ በዋነኛነት ማኅበራዊ ሚዲያ ግንኙነታችንን የምናጠናክርበት የቴክኖሎጂው ውጤት ቢሆንም ቅሉ ማኅበራዊ ግንኙነትን ከማገዝ ቢሆንም ባሻገር ግን ከቅርብ ግዜ ወዲህ ግን “ችግር በቅቤ ያስበላል” እንደሚባለው፣ የሁነኛ ሚዲያ እና የግልጽ እና የነጻ መድረክ መጥፋት የማኅበራዊ ሚዲያውን እንደ ሁነኛ ሚዲያ ለመረጃ ማግኛ ምንነችነት እና የመወያያ መድረክነት እንድንጠቀመው ተግደናል፡፡
ከምርጫ 97 በኋላ የጋዜጦች መዘጋት እና የጋዜጠኞችም መሰደድ በመረጃ ፍሰት እና የሕዝብ ውይይት ላይ ትልቅ ክፍተት ፈጥሯል፡፡ እንደ እኔ ዕይታ ታዲያ ፌስቡክም ይህን የሚዲያ ክፍተት ሊሞላ በሚፈለግበት ወቅት የተገኘ የቴክኖሎጂው ትሩፋት ነው፡፡ ምክንያቱም የወቅቱ የጋዜጣ አንባቢ እና የሕዝብ ውይይት ተሳታፊ፣ ታዳሚ፣ የለመደውን የሕትመት ሚዲያ ሲያጣ ወደ አዲሱ ሚዲያ ፈልሷል፡፡ በዚህም ምክንያት ማኅበራዊ ሚዲያው ጠንክራ የውይይት መድረክ የሆነው፡፡ ማኅበራዊ ሚዲያው በባሕርይው የሁሉም ነው፡፡ ሁሉንም አካታች ነው፡፡ ሁሉንም አካታች ሲባል አዲሱ ሚዲያ፣ ማኅበራዊ ሚዲያውን ጨምሮ ኢንተርኔት ማግኘት ለሚችል እና መሠረታዊ የኮምፒውተር ዕውቀት ላለው፣ እንዲሁም ሐሳቡን እና አመለካከከቱን ለሌሎች ማካፈል ለሚፈልግ በሙሉ ክፍት ነው፡፡ ሚዲያው በባሕርይው ለግለሰቦች አንፃራዊ ነጻነትን ስለሚሰጥም ተመራጭ ገበታ (ፕላት ፎርም) ሆኗል፡፡ በተጨማሪም የሞባይል ስልክ ቴክኖለጂ ዕድገት ዜጎችን ማኅበራዊ ሚዲያ መጠቀም እንዲችሉ የሚታይ አስተዋፅዖ አድርጓል፡፡
የመረጃ ምንጭ እና ነጻ መድረክ፤ የማኅበራዊ ሚዲያ
ማኅበራዊ ሚዲያው መንግሥት በተለያየ መልኩ ቁጥጥር ቢያደረግበትም፣ በተለይም ዋነኛ ተጠቃሚዎቹን ከግለሰብ ጀምሮ እስከ ጅምላ ማስፈራራት እና እስራት ድረስ ቢሔድም፣ በሚገባ ለተመለከተው፣ ማኅበራዊ ሚዲያው ከመወያያ መድረክነቱ ባሻገር ተመራጭ እና ዋነኛ አማራጭ ሚዲያ እየሆነ ነው፡፡ በዋነኛው የመንግሥት ሚዲያ የሚቀርቡ ትርክቶችን ሚዛን መጠበቂያ እና የተገለሉ እና የታፈኑ ድምፆች የሚደመጡበት መድረክም ሆኗል፡፡ ከዓመታት በፊት አሁን ከሕትመት ውጭ የሆነቸው “አዲስ ጉዳይ” መጽሔት በአንድ እትሟ ማኅበራዊ ሚዲያው አማራጭ የመረጃ ምንጭ እና የሐሰብ መድረክ እንደሆነ የሚያትት ጽሑፍ አስነባባን ነበር፡፡ የመንግሥት ዋነኛ ትኩረት ማኅበራዊ ሚዲያው የሆነበት ምክንያት በፈቃድ አሰጣጥም ይሁን በስርጭት ወቅት እንደ ዋነኛው ሚዲያ በቀጥታ እና በቀላለሉ መቆጣጠር ስለማይቻለው ነው፡፡
ማኅበራዊ ሚዲያው ከማጠልሸት፣ ከማንቋሸሽ እና ከማንኳሰስ ይልቅ በማኅበራዊ ሚዲያው የሚወጡ መረጃዎች በአግባቡ እያጣራ እና እያጠራ ሚዛን የሚያስጠብቅ ሁነኛ እና ታማኝ ሚዲያ ያስፈልግ ነበር፡፡ ሚዲያው ሥራውን በአግባቡ አለመሥራቱ ማኅበራዊ ሚዲያውን ከአማራጭ ሚዲያነት ይልቅ ወደ ዋነኛ የመረጃ ምንጭነት እንዲቀየር አድርጎታል፡፡ ስለሆነም በማኅበራዊ ሚዲያ የሚለቀቁ መረጃዎችን በዋነኛው ሚዲያ ከማጣራት ይልቅ፣ በተቃራኒው በፖለቲካ እና ጠንካር ባሉ ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ በዋነኛው ሚዲያ በኦፊሴል ለሚነገረው ማጣሪያ እና የጉዳዩን አንድምታ የመወያያ መድረክ እየሆነው ነው፡፡
የመንግስት ስጋት…
“የአረብ ፀደይ” ተብሎ የተሰየመው በአረብ አገራት የተደረገው ፖለቲካዊ እቅስቃሴ እና የመንግሥታት ለውጥ የማኅበራዊ ሚዲያው ሚናው ከፍ ያለ ስለነበር በአረብ አገራት የደረሰው እንዳይደርስበት አስቀድሞ ለመከላከል ከሚወስዳቸው እርምጃዎች አንዱ ማኅበራዊ ሚዲያውን ማውገዝ እና ማስወገዝ ሆኗል፡፡ እርግጥ ነው እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር 2001 በፍሊፒንስ ማኒላ በአጭር የስልክ መልዕክት ከተጠራው እና የፕሬዘዳንት ጆሰፍ እስትራዳን መንግሽት ከለውጠው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ጀምሮ በርካታ የመንሥግት እና የስርዓት ለውጦች በተለያዩ አገራት ቴክኖሎጂውን በመታገዝ በማኅበራዊ ሚዲያው የማስተባበር ሥራ ተሠርቶበታል፡፡ ከዚህም በመነሳት ሲንካ ሳሲ የተባለች የዘርፉ ተመራማሪ ከሚደረጉት የፖለቲካ እና የባሕል ለውጦች ጀርባ ያለው ኃይል አዲሱ ሚዲያ እንደ ሆነ ጽፋለች፡፡ ይህም የመንግሥት ስጋት ይመስለኛል፤ አፍጥጦ የመጣ… ይህ ሚዲያ ውጤቱ አዝጋሚ ቢሆንም በስተመጨረሻ ግን ወደ ዲሞክራሲያዊ ማኅበረሰብ ማምራቱ አይቀሬ እንደሆነ ዊሊያም የተባለ የዘርፉ ምሁር ያብራራል፡፡ ይህም እንዴት ሊሆን እንደሚችል የሀርቫርድ ዩኒቨርስቲው ዮቺያ ቤንክለር ሲግልጸው “የማኅበራዊ ሚዲያው ከታች ወደ ላይ አጀንዳ በመቅረፅ፣ መረጃ ለሁሉም ተደራሽ በማድረግ እና ከመንግሥት ጣልቃ ገብነት በመላቀቅ ለማኅበረሰቡ ነጻ መድረክ በመሆኑ ነው” ይላል፡፡ ባሮውል የተባለ ምሁር ይህን ሲያጠናክረው ኮምፒውተሮቻችን ከመንግሥታት አገዛዝ ነጻ አውጥተውናል ይላል፡፡
ሌላኛው የመንግሥት ስጋት ደግሞ ብቻውን የመናገሩን እና ብቻውን የመሰማቱን ነገር እንደቀረበት እርግጥ ከመሆኑ የመነጨ ይመስለኛል፡፡ የመንግሥት ጩኸት ደግሞ የመረጃ ምንጫችሁ እኔ ነኝ፤ እኔን ብቻ ስሙኝ፤ እኔን ብቻ እመኑኝ፤ እኔን ተከተሉኝ ነው፡፡ ለዚህም ማሳያ በኢብኮ የሚተላለለፉ ዜናዎች በሙሉ ምንጫቸው በተለያየ ደረጃ የሚገኙ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤቶች ናቸው፡፡ እነዚሁ በተለያየ መዋቅር የሚገኙ የመንግሥት ጉዳዮች ኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤቶች ዋነኛ ሥራቸው ለመንግሥት የሕዝብ ግንኙነት ሥራ ቢሆንም ከቅርብ ግዜ ወዲህ ግን ለሚወጡ ዜናዎች ብቸኛ ምንጮች ሆነዋል፡፡ በእነዚሁ ቢሮዎችም ተሠርተው የሚላኩ ዜናዎችም በሚዲያው ሪፖርተ ማጣራት ሳይደረግበት እንደ ወረደ ይቀርባል፡፡ ከመንግሥት የሕዝብ ግንኙነት ቢሮ የሚወጡ ዜናዎችን ደግሞ የምናያቸው ናቸው፤ ሁልግዜ ለውጥ እና ዘወትር ሕዳሴ፡፡ ያለመደመጥ እና ያለ መታመን ስጋት
ማኅበራዊ ሚዲያው የተመራጭ የሆነበት ምክንያት የምንፈልገውን አስተሳብ እና አመለካከት በየዓይነቱ ማግኘት መቻላችን ብቻ አይደለም፡፡ የማኅበራዊ ሚዲያ ገበታው (ፕላት ፎርሙ) ሁሉንም ዓይነት የሚዲያ ውጤቶች ሬዲዮኑንም፣ ቴሌቭዥኑንም ፣ጋዜጣውንም እንደልብ በአንድ መስኮት ማግኘነት አስችሎናል፡፡ በሬዲዮቻችን እና በቴሌቭዥናችን መከታተል ያልቻለናቸውን የተቃውሞ ድምፆች፣ በኢንተርኔት የሬድዮ እና የቴሌቭዥን ስርጭቶችን በቀላሉ ማግኘነት የሚያስችለን የመረጃ ገበታ በመሆኑም ነው፡፡
በማኅበራዊ ሚዲያ ብዛት ያላቸው የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ስለሚነሱ፣ ሰዎችም የሚፈልጉትን ጉዳይ እንዲለዩ እና ከመሰሎቻቸው ጋርም እንዲጋሩ፤ በተጨማሪም ማንን ጓደኛ ማድረግ እና ማንን መከታተል እንዳለባቸው እንዲመርጡ ዕድሉን ሰጥቷቸዋል፡፡ በዚህም ምክንያት የማኅበራዊ የሚዲያው ተጠቃሚዎች ሰፊ አማራጭ አላቸው፡፡ ከደጋፊ እስከ ነቃፊ፤ ከተቆርቋሪ እስከ ነቋሪ ድረስ ከሁሉም ወገን በማኅበራዊ ሚዲያው ላይ እንደልብ ይገኛሉ፡፡ የተቃውሞው ጎራ በማኅበራዊ ሚዲያው ብቸኛው መድረኩ ስለሆነ ጎልቶ ይደመጣል እንጂ፣ የመንግሥት ደጋፊዎችም በተሻለ ቁሳቁስ እና ማበረታቻ በማኅበራዊ ሚዲያው ላይ እንቅስቃሴያቸው በጣም የጎላ ነው፡፡ በአንድ ወቅት ከመንግሥት ወገን ከሆነ ወዳጄ ጋር ስናወጋ ይህንኑ አዲስ ሚዲያ የሚቆጣጠር (የኦንላይን ሞኒተሪንግ) ክፍል በኢቲቪ ውስጥ እንዳለ እና ይኸው ክፍል በሚያቀርበው ግምገማ መሠረት በማኅበራዊ ሚዲያም ይሁን በሌሎች ዌብሳይቶች ለተነሱ ጉዳዮች እንደ አስፈላጊነቱ በዋነኛው የቴሌቭዥን ጣቢያ ምላሽ እንደሚሠሩ እና ይህንንም ለሚያደርጉበት የተሻለ አቅም ያለው ኮምፒዩተር እና የተሸለ የኢተርኔት መሥመር ያለ አንዳች ክልከላ እንዳላቸው አጫውቶኛል፡፡ ማኅበራዊ ሚዲያው ላይ ያለው ዘመቻ የቃላት ብቻ አይደለም፡፡ ከቃላት ጦርነቱ በዘለለ የተመረጡ ዌብሳይቶችን መዝጋት፣ ሰላይ ሶፍተዌሮችን በመጠቀም በተጠቃሚዎች ላይ ስለላ ማካሔድን ይጨምራል፡፡ ታዲያ በዚህ ሁሉ ቁጥጥር እና ተፅዕኖ ውስጥ ባለው ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ማነንታቸው ባልታወቁ ሰዎች የሚለቀቁ መረጃዎች አጥፊ ናቸው፤ ከምን የመጣ ስጋት ነው? ካለማዳመጥ ስጋት ነው ወይስ ከለውጥ እንቅስቃሴው? ሌለው ደግሞ የዚህ አስረጅ በመሆን የቀረቡት ምሁራን እና ባለሙያዎች የማኅበራዊ ሚዲያ ትንታኔ ትኩረት ግንጥል የሆነውስ ለምንድነው?

የወጣት ንግሥት ይርጋ ወደ ስቃይ እስር ቤት መግባት ሚልዮን ኢትዮጵያውያን ሴቶችን ውደ ትግሉ ሜዳ ይጠራል !

$
0
0

በሙሉቀን ተስፋው

ወጣት ሴቶች ለነፃነት ትግሉ የሚነሱበት አዲስ ምዕራፍ ተከፈተ።
የአንዳርጋቸው ፅጌ መታሰር ሚልዮኖችን ወደ ትግሉ ሜዳ እንዳስገባ ሁሉ የንግሥት ወደ መሰቃያ ቦታ መውሰድ ሚልዮን ኢትዮጵያውያንን ወደ ትግል ሜዳ ያስገባል።
ወጣት ንግስት ይርጋ በጎንደር በተደረገው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ስሜቷ ተነክቶ በሰልፉ መካከል ከእንባ፣እልህ እና ሲቃ ጋር ነበር በሰልፉ የተሳተፈችው።ከኢህአዴግ ሰራዊት ጋር አብሮ ተሰልፎ ደርግን የታገለው በኃላም በሱዳን የተባበሩት መንግሥታት ሰላም አስከባሪ ሰራዊት ውስጥ በብቃቱ ተፈልጎ አገሩን የወከለው በመቀጠልም የታገልኩት ትግራይ ሁን ተብዬ እንድገደድ አይደለም ስነ ልቦናዬም፣ባሕሌ እና የአኗኗር ዘይቤዬ የእኔም ሆነ የሕዝቤ የአማራ ነው።የግድ ትግሬ ሁን አትበሉኝ! ብሎ በሕጋዊ መስመር ተከትሎ ከአስተባባሪ ኮሚቴዎች ጋር በመሆን መብቱ የጠየቀውን ኮ/ል ደመቀ ዘወዱ ፎቶ ግራፍ በትሸርት አድርጋ ከስር ´´አማራ አሸባሪ አይደለም´´በሚል ፅሁፍ ሰልፉን የተቀላቀለችም ወጣት ታጋይ ንግስት ይርጋ በወያኔ ወታደሮች መታፈኗ እና ወደ አዲስ አበባ መወሰዷን ´´የጥፋት ዘመን´´ መጽሐፍ ፀሐፊ ሙሉቀን ተስፋው በገፁ ላይ ባሰፈረው ዜና ገልጧል።

nigist-1

የሕወሓት እስር ቤቶች በሴቶች ላይ የሚፈፅሙት ግፍ በሰው ህሊና ከሚታሰበው በላይ ነው።ከእዚህ በፊት በቂልንጦ እስር ቤት ሴት እስረኞች ላይ ምን እንደደረሰ የዞን 9 ታሳሪ ወጣትን ታሪክ ማስታወስ በቂ ነው።በሌሊት እራቁቷን እንድትመጣ እየተደረገ በርካታ በደሎች በማንነት ላይ ያተኮረ ስድብን ሁሉ ጨምሮ ተፈፅሟል።በንግሥት ይርጋ ላይ ደግሞ ምን አይነት ፋሽሽታዊ ሥራ እንደሚሰራ መገመት ይቻላል። ይህ ሁኔታ በእራሱ የኢትዮጵያ ወጣት ሴቶችን በአዲስ መልክ የሚጣራ አዲስ እና ልዩ ለነፃነት የሚደረግ የትግል ጥሪ ነው።በሴትነት እና በማንነት ላይ የተነሱ ፋሽሽቶችን ዝም ብሎ መመልከት አይቻልም።ከአገር ቤት እስከ ውጭ ያሉ ሴቶች የነፃነት ትግሉን በአዲስ መንገድ የሚቀላቀሉበት አዲስ ምዕራፍ ተከፈተ። ሕወሓት በማሰር እና በማፈን ትግል የምታዳክም ይመስላታል።የአንዳርጋቸው ፅጌ መታሰር ምልዮኖችን ወደ ትግሉ ሜዳ እንዳስገባ ሁሉ የንግሥት ወደ ስቃይ እስር ቤት መግባት ሚልዮን ኢትዮጵያውያን ሴቶችን ውደ ትግሉ ሜዳ ያስገባል።

ከእዚህ በታች የወጣት ንግስት መታፈን አስመልክቶ ሙሉቀን ተስፋው የለቀቀውን ዜና አንብቡት።

ወጣቷ የነጻነት ታጋይ ንግሥት ይርጋ በወያኔ መታፈኗ ተሰማ፥
ወጣት ንግስት ይርጋ፥ አርብ መስከረም 6 ቀን 2009 ዓ.ም ከጎንደር ከተማ ተነስታ፥ በታች አርማጭሆ ሳንጃ ከተማ ወደ ሚገኘው ቤቷ ስታመራ መንገድ ላይ ታፍና ወደ አዲስ አበባ ማዕከላዊ የማሰቃያ ቤት መወሰዷ ታውቋል።
ወጣት ንግስት ይርጋ ተፈራ፥ ሰሞኑን ጎንደር በተቀሰቀሰው ሕዝባዊ ንቅናቄ ላይ ባደረገችው የማስተባበር ተሳትፎ በከተማው ታዋቂነትን ያተረፈች፥ ገና በሃያዎይቹ መጀመሪያ የእድሜ ክልል የምትገኝ፥ ምንም ወንጀል የሌለባት ወጣትና ፍትህ ፈላጊ ታዳጊ ዜጋ መሆኗ ነግሯል።

ወጣት ንግስት ወደ ትግሉ የገባችውና በሕዝብ ዓይን ጎልታ መታየት የጀመረችው፥ የወልቃይት ማንነት ኮሚቴዎችን በሕገ ወጥ መንገድ ዓፍነው ለመውሰድ በመጡ የወያኔ ታጣቂዎችና በኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ የመከላከል እርምጃ ምክንያት ጎንደር ላይ በተቀጣጠለው ሕዝባዊ ተቃውሞ፥ ሰልፍ በመምራትና በማስተባበር ባደረገችው ከፍተኛ እንቅስቃሴ ነበር።

ይህች ወጣት ንግስት የአማራ ተጋድሎ በመባል የሚታወቀውን ሕዝባዊ ንቅናቄ የተቀላቀለችው ቂሊንጦና ቃሊቲ እስር ቤት ጓደኛ ለመጠየቅ ሂዳ ባየችው የወጣት ኢትዮጵያውያን እስረኞች ብዛትና የአማራ እስረኞች ስቃይ፥ በተለይም ከገጠሪቱ ጎንደር ባልሰሩት ወንጄል ታፍነው ተወስደው መዳረሻቸው ሳይታወቅ ለእረጅም ጊዜ ያለጠያቂ ሲሰቃዩ ላየቻቸው ወገኖቿ ጩኸትና የመከራ ድምጾች ምላሽ ለመስጠት እንደሆነ ያጫወተቻቸው የትግል አጋሮቿ ይናገራሉ።

“ከስዩም መስፍን ጋር አልስማማም” –ዶ/ር ፍቅሩ ገብረኪዳን

$
0
0


“ከስዩም መስፍን ጋር አልስማማም” – ዶ/ር ፍቅሩ ገብረኪዳን

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live