Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርና የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ ሰራዊት በጋራ ወታደራዊ ጥቃት መፈጸማቸውን አስታወቁ

$
0
0

Arbegnoch

(ዘ-ሐበሻ) የጋራ ትግል አስፈላጊ መሆኑን በፅኑ እንደሚያምኑ የሚገልጹት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር /ኢሕአግ/ እና የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ /ጋሕነን/ በሕዳር 13/2006 ዓ.ም በሁመራ ሉግዲ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1፡00 ለሶስት ሰዓት ያህል በወሰደው ውጊያ የወያኔው 24ኛ ክፍለ ጦር ድባቅ መመታቱን የአርበኞች ግንባር ቃል አቀባይ ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫ አስታወቀ። “ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በ24ኛው ክፍለ/ ጦር ላይ በተመሳሳይ ሥፍራ ከፍተኛ ድል መቀዳጀቱ ይታወሳል” ያለው ዘገባው ” በሕዳር 13/2006 ዓ.ም የኢሕአግና የጋህነን ሰራዊት በወሰዱት ድንገተኛ ወታደራዊ ጥቃት 66 /ስልሳ ስድስት/ ገድለው 113 /አንድ መቶ አስራ ሶስት/ በማቁሰል እንዲሁም ቁጥራቸው የበዛ የጦር መሳሪያዎችን ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ማርከዋል።” ብሏል።

“ሁለቱ ድርጅቶች በጋራ በተለያየ የትግል መስክ ሲተጋገዙና ሲተባበሩ ቆይተዋል” ያለው የአርበኞች ግንባር ቃል አቀባይ ይህ “የግንኙነታቸውን እድገትና ለውጥ የሚያሳይ ወታደራዊ ጥቃትም ፈፅመዋል። ይህ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚመኘውና የሚፈልገው የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ስምምነትና አንድነት መገለጫ ሊሆን የሚችል አኩሪ ጥቃት መሆኑ ይታመንበታል።” ሲል የትብብሩን አስፈላጊነት ገልጾታል።
Arebegnoch 1
“በጥቃቱ የተካፈሉ የሁለቱ ድርጅቶች ታጋዮች እንዳብራሩት ዛሬ በጋራ የጀመርነው ወታደራዊ ጥቃት በዚሁ የሚያበቃ ሳይሆን የጋራ ዓላማና ራዕይ እስካለን ድረስ ወደኋላ የማይቀለበስ ነው ሲሉ ተናግረዋል።” ያለው የግንባሩ ቃል አቀባይ “ከዚህም አክለው የዚህ ወታደራዊ ዘመቻ ዓላማ አገር እንደሌለው ሁሉ በሰው አገር ፍዳውን እያየና እየተሰቃየ እንዲሁም ለሞት እየተዳረገ የሚገኙውን በሳውዲ አርቢያ ለተፈፀመው በደል ለመበቀልና ሕዝባዊ ወገንተኝነታችንን ለማሳየት ታስቦ የተወሰደ ወገናዊ እርምጃ ነው በማለት አብራርተዋል። በውጊያው ከሞት ተርፎ ለከባድ ቁስልና የአካል ጉዳት የተዳረገው የወያኔው ቅጥረኛ የ24ኛ ክፈለ ጦር አባላትን ከሁመራ አንስቶ እስከ ትግራይ የሕክምና ማዕከሎች ማጋጋዝ ዋነኛ ተግባሩ ሆኗል።” ብሏል።

የአርበኞች ግንባር ቃል አቀባይ ለዘ-ሐበሻ የላከውን መግለጫ ሲያጠቃልልም “ይህንን የጀግና ጥቃትና ድል የተመለከቱ የአካባቢው ነዋሪዎች ሰራዊቱን እንኳን ደህና መጣችሁ ብሎ በመቀበልና ስንቅና ትጥቅ በማቅረብ አጋርነቱን ያስመሰከረ ሲሆን የተጀመረው ወታደራዊ ጥቃት በተለያዩ አካባቢዎች ላይ እንዲደገም ያላቸውን ልባዊ ምኞት ገልፀው በንፁሃን ላይ ያለ አግባብ ሲወሰድ የነበረው የቅጥረኞች እርምጃ አንጀቱ ላረረው ሕዝብ እምባ ያበሰ እንደሆነም ተናግረዋል። በመጨረሻም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር/ ኢሕአግ/ እና የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ /ጋህነን/ ወያኔ ለ22 ዓመት ያህል አገሪቷን ሲበዘብዝና ሕዝቡ የዲሞክራሲያዊ መብቱ ተጠቃሚ እንዳይሆን በሃይል የመግዛቱ ሂደት እንዲያከትም የተቻላቸውን ሁሉ ለማድረግ ቆርጠው መነሳታቸውን አስታውቀዋል።” ብሏል።

አርበኞች ግንባር እና የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ ሰነዘርን ባሉት ወታደራዊ ንቅናቄ ዙሪያ ከመንግስት አካባቢ የተገኘ ምላሽ የለም።

↧

↧

ከአቶ ኃይለማሪያም መጠበቃችን ስህተት ነበር –ግርማ ካሳ

$
0
0

(muziky68@yahoo.com)

ኖቬምበር 25 ቀን 2013

 
Hailemariam-PM1-300x282በሕገ መንግስቱ መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣  የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥና የሚኒስቴሮች ምክር ቤት ሰብሳቢ ናቸዉ። የጦር ኃይሎች ኤታ ማጆር ሹምን፣ ተቀዳሚ ጠቅላይ ሚኒስትርን፣ የሚኒስቴር ካቢኔዎችን፣ የፌደራል ፖሊስ አዛዦችን … የመሾምና የመሻር ሙሉ ስልጣን አላቸው። ፓርላማዉን በትነው አዲስ ምርጫ መጥራትም ይችላሉ። ፓርላማው በፈለገ ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስቴሩን አዉርዶ፣  ሌላ መሾም ይችላል። ጠቅላይ ሚኒስትሩም ተጠሪነታቸው ለፓርላማዉ ብቻ ነዉ።

የፓርላማ አባላት፣ በፓርቲያቸው ለእጩነት ቢቀርቡም፣ በሕዝብ የተመረጡ፣ ተጠሪነታቸው ለፓርቲዉ አመራር አባላት ሳይሆን፣ ለመረጣቸው ሕዝብ ብቻ ነዉ። በፓርላማዉ ካሉ 547 መቀመጫዎች ደግሞ፣ የሕውሃት አባል የሆኑት 38ቱ ብቻ ናቸው (6.9 በመቶ ብቻ)።

የአቶ መለስን ሕልፈት ተከትሎ፣ በሕጉ መሰረት፣ ፓርላማዉ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስቴር እስኪመርጥ፣ በወቅቱ ምክትል ጠ/ሚ ኃይለማሪያም ደሳለኝ፣ አክቲንግ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆነው ወዲያዉኑ መቀጠል ነበረባቸው። ነገር ግን የሕውሃት ሰዎች (አንዳንዶቹ የፓርላማ አባል እንኳን ያልሆኑ) «ኢሕአዴግ እንደ ፓርቲ ሳይወስን፣ አቶ ኃይለማሪያምን አክቲንግ ጠ/ሚ ማድረግ አይችልም» ብለው አቶ ኃይለማሪያም በምክትል ጠ/ሚኒስትርነት እንዲቀጥሉ አደረጉ። በሕገ መንግስቱ፣ ጠቅላይ ሚኒስቴርን የሚሾሙት፣ የፓርላማ አባላት እንጂ፣ የፓርቲዎች ፖሊት ቢሮ አለመሆኑ እየታወቀ፣ ሕውሃቶች በዚህ ሁኔታ፣ ለስድስት ወራት አቶ ኃይለማሪያም ጠ/ሚ እንዳይሆኑ፣  ማከላከላቸው የሚያሳየዉ፣  ሕገ መንግስቱን በአፍጢሙ እንደገለበጡት ነዉ።

ከስድስት ወራት በኋላ፣ ሕወሃት፣ አቶ ኃይለማሪያም ጠ/ሚ እንዲሆኑ እያቅማማ ለጊዜዉ ተስማማ። ነገር ግን በአቶ ኃይለማሪያም አንገት ላይ ማነቆ ታሰረላቸው። ሶስት ምክትል ጠ/ሚ እንዲሾሙ ተደረገ። አቶ ደመቀ መኮንን፣ አቶ ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል እና አቶ ሙክታር ከድር።

አቶ ደብረጺዮን እንደ ቴሌ ያሉትን መስሪያ ቤቶች ከመቆጣጠራቸዉ በተጨማሪ፣ የኢኮኖሚክና የፋይናንስ ዘርፉም በርሳቸው ስር እንዲሆን ተደረገ። በስልክ ፣ በኢንተርኔት የምንነጋገረዉን ሁሉ አቶ ደብረጽዮን ያዳምጣሉ፡፡ ባንኮችን፣ ቀረጥን የአገር ዉስጥና የዉጭ ንግድን የመዓድን እና የመብራት አገልግሎትን በሙሉ የሚቆጣጠሩትና የሚመሩት እኝሁ ሕወሃቱ አቶ ደብረ ጽዮን ናቸዉ።

ከትምህርት፣ ከጤና ፣ ከቱሪዝም ከመሳሰሉ ጋር የሚገናኙ  መስሪያ ቤቶች ብቻ፣  ለአቶ ሙክታርና ለአቶ ደመቀ ተሰጡ።  መከላከያ፣  ዉጭ ጉዳይና ደህንነት መስሪያ ቤቶች በአቶ ኃይለማሪያም ስር እንዲቆዩ ቢደረግም፣ ከታች ይቆጣጠሯቸው ዘንድ፣ አቶ ቴዎድሮስ አዳኖም የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሆነው ተሾሙ። ጀነራል ሳሞራ የነሱ የጦር ኃይሎች የኢታ ማጆር ሹም ፣ አቶ ጌታቸው ደግሞ የደህንነት ቢሮ ሃላፊ ሆነው እንዲቀጥሉ ተደረገ። ሁሉም ሕውሃቶች !!!!

«ዝም ብላችሁ ነዉ የምትደክሙት» ተብለን ነበር። እኛ ግን  « አይ ፣ አቶ ኃይለማሪያም  በሂደት ነገሮችን ያስተካክላሉ። ጊዜ ይሰጣቸው። ኢሕአዴግ ዉስጥ ጥሩ ልብ ያላቸው ብዙ አሉ»  እያልን ተከራከርን። በዚህ አቋማችንም በተቃዋሚ ወግን ባሉት ተተቸን። «ወያኔ ናቸው» እስከመባልም ደረስን። 94% በመቶ የሚሆኑት ሕውሃት ያልሆኑ የፓርላማ አባላትም፣ ሕገ መንግስታዊ መብታቸውን ተጠቅመው፣ ጡንቻቸውን በማሳየት በሕውሃቶች፣ ዉስጥ ዉስጡን የሚሰራዉን ጸረ-ዴሞክራሲያዊ፣ ጸረ-እኩልነትና ጸረ-ሕዝብ ተግባራትን ሊያስቆሙ የሚችሉበት ሁኔታ ሊኖር እንደሚችልም አሰብን።

ነገር ግን እንዳሰብነዉና እንደገመትነው አልሆነም። ኦሕድድ፣ የደቡብ ህዝቦች ፣ የነአዲሱ ለገሰ የአማራዉ ድርጅት አባላትና መሪዎች፣  በሚያስገርምና በሚያሳፍር ሁኔታ ለሕዝብ ጥቅም ከመቆም፣  ዉሻ ለባላቤቱን እንደሚታዘዘው፣ የጥቂት ሕወሃት ባለስልጣናት ታዛዦችና ባርያዎች መሆናቸውን ቀጠሉ።

በሳዉዲ ወገኖቻችን ላይ በተከሰተዉ ግፍ ዙሪያ «ተማጽኖ ለጠ/ሚ ኃይለማሪያም» በሚል ርእስ፣ ጠ/ሚኒስትሩ፣ ሕዝቡን እንደ አንድ ሕዝብ እንዲያስተባብሩና ከተቃዋሚዎች ጋር በመሆን፣ ገለልተኛ የስደተኞች ኮሚሽን እንዲያቋቅሙ ጠይቀን ነበር። ነገር ግን ፣ ዶር ቴዎድሮስ አዳኖምን፣ ቁልፍ ሚና ሲጫወቱ  በየሜዲያዉ ስንመለከት፣ አቶ ኃይለማሪያም ድራሻቸዉን አጠፉ። (በነገራችን ላይ ዶር ቴዎድሮስ የሕውሃት አመራር ሆነው በሕውሃት ድርጅታቸው የሚደረገዉን ግፍ እያዩ ዝም ማለታቸው፣ ወይንም የግፉ አካል መሆናቸው እንደተጠበቀና ወደፊት በስፋት የምንነጋገርበት ሆኖ፣ በስደተኖች ዙሪያ እየሰሩ ያሉት ግን ማለፊያ ነው)

«በዚህ ብሄራዊ ዉርደትና ቁስል ወቅት፣ ሕዝብ ከርሳቸው መስማት ሲፈልግ፣ አቶ ኃይለማሪያም መሰወራቸው ተገቢ አይደለም። ዛሬ ብቅ ብለው ይሆን?» ብዬ በስማቸው ጉግል ሳደርግና ድህረ ገጾችን ሳካልል ፣  ያላዳመጥኩት፣ ከአንድ ወር በፊት ገደማ፣ በጸረ-ሽብርተኝነት ሕግ ዙሪያ፣  በእንግሊዘኛ የሰጡትን ቃለ ምልልስ አገኘሁ። ሊንኩን ነካ አድርጌ ቪዴዎዉን ማየትና ማዳመጥ ጀመርኩ። ዘገነነኝ። ሰዉዬዉ «የአገር መሪ ነኝ ፤ መጽሃፍ ቅዱስ አነባለሁ፤ እጸልያለሁ ..» ይላሉ። ግን በዚህ ቃለ ምልልስ የሰማሁት የአንድ ዱርዬና ጀብደኛ ቃለ መልስን ነዉ። አዘንኩ። አፈርኩ። አቶ ኃይለማርያም ሕሊናቸውን፣ ወይንም «አነባለሁ» የሚሉትን መጽሃፍ ቅዱስ የሚያዳምጡ ሳይሆን፣ ሙሉ ለሙሉ የሕውሃትን ጥቅም የሚያስጠብቁ፣ ትግሪኛ የማይናገሩ «ሕውሃት» መሆናቸው ገባኝ።

«አንዳንዶች ሕውሃቶች አጥረዋቸው እያስገደዷቸው ነዉ» ሊሉ ይችላሉ። እኔ ግን አልስማም። የሚናገሩትን ተገደው ሳይሆን፣  የሚናገሩት፣ በስሜት፣  ጠረቤዛ እየደበደቡና አምነዉበት ሲናገሩ ነው የምንሰማቸው። ይቅርታ ይደረግለኝና፤  ለእኝህ ሰው የነበረኝ ከበሬታ ፍጹም ተሟጣል። እኝህ ሰው የመጡበትን ብሄረሰብ ያሰደቡ፣ የእግዚብሄርን ስም ያሰደቡ፣ ስለርሳቸው ጥሩ ሲናገሩና ሲጽፉ የነበሩትን  «ደጋፊዎቻቸውን» ያሳፋሩ የማይረቡ ሰው ናቸው። [1]

በቃለ ምልልሱ ፣ አቶ ኃይለማሪያም ስለ ቦምብ ያወራሉ። እስክንድር ነጋ፣ አንዱዋለም አራጌ፣ ርዮት አለሙ፣ በቀለ ገርባ እንዲሁም በፖለቲካ አቋማቸው ምክንያት ሽብርተኞች ተብለው የሚማቅቁ ወገኖቻችን፣ ጀግኖቻችን እንጂ ሽብርተኞች አይደሉም። በአንድ ሰዉ ላይ አንዲት ጠጠር አልወረወሩም። በቤታቸው የተገኘ ፈንጂ፣ የተገኘ የራዲዮ ኮሚኒኬሽን መሳሪያዎችና ሚስጥራዊ ሰነዶች የሉም። የቀረበባቸው የተጨበጠ ማስረጃ የለም። በዚህም ምክንያት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ፣ አቶ አማረ አሞኜም «ሽብርተኞች አይደሉም» ብለው ሊፈቷቸውም ነበር። ሕውሃቶች «መለስ አደገኛ ያላቸውን መፍታት የለብንም። እዚያዉ ቃሊቲ ይበስብሱ» በማለት አቶ አማረን፣ በሌላ ዳኛ ለዉጠው፣  ፍርደ ገምድል ዉሳኔ አስወሰኑ እንጂ። የእነ እስክንድር ወንጀል፣ ሕዝብና አገርን መዉደዳቸው፣ እዉነት፣ ፍትህና  እኩልነትን መስበካቸው ነዉ።

አቶ ኃይለማሪያም፣ የ«ሕወሃት» መሪ ሆነው እቅጩኝ ነግረዉናል። ደንፍተዉብናል። «የሕሊና እስረኞች አይፈቱም። የሕግ ስርዓት፣ መልካም አስተዳደር አይኖርም። የትግራይ ሕዝብን ሳይቀር እያሰቃዩ ካሉ፣ ከጥቂት የሕውሃት አመራሮች ፣ ከነስብሀት ነጋ ፍቃድ  ዉጭ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍቃድ የለዉም። እነርሱ የሚሉትን ተቀብሎ፣ ተሰለፍ ሲሉት በነቂስ እየተሰለፈ፣ ከቤትህ እንዳትወጣ ሲሉት ቤቱ እየተቀመጠ፣ ከወጣም ደግሞ እየተደበደበ፣ ተናገር የሚሉትን እየተናገረ ፣ ተናገር ያልተባለዉን ከተናገረ እየታሰረ፤ ምረጥ የተባለዉን እየመረጠ፣ ምረጥ ከተባለው ዉጭ ከመረጠ ደግሞ፣ ድምጹ እየተሻረ፣  የባርነት ኑሮ ይቀጥላል» ነዉ እያሉን ያሉት።

እንግዲህ አብዛኞቻችን በእርቅ በሰላም በንግግር እናምናለን። በገዢ ፓርቲ ዘንድ በማንኛዉም ጊዜ ለእርቅና ለሰላም ዝግጁነት ከታየ እሰየው ነዉ የምንለው። ነገር ግን ከአቶ ኃይለማያም ጸያፍ ንግግር እንደሰማነዉ፣ ሕወሃት ከሕዝብ ፍላጎት ተቃራኒ የሆነ መንገድ የመረጠ ይመስላል። በመሆኑም፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ የራሱን እድል በራሱ ለመወሰን መዘጋጀት ይጠበቅበታል። 90 ሚሊዮን የሚሆን ሕዝብ፣ እፍኝ በሚያህሉ ጥቂቶች፣  ታስሮና መብቱ ተረግጦ መቀጠል የለበትም። የአለም አቀፍ ሕግ በሚፈቅደዉ መሰረት፣ ሰላማዊ የእምቢተኝነት ዘመቻ በተቀናበረ መንገድ መደረግ አለበት።በዉጭ፣ በአገር የምንኖር ኢትዮጵያዊያን ሁሉ፣ በቤታችን ጸሎት ከማድረግ ጀምሮ፣  የድርሻችንን ለመወጣት መነሳት አለብን። ነጻነታችችን፣ መብታችንን፣ ክብራችንና ማስመለስ ይኖርብናል።

ስለሰላም፣ ስለእርቅ፣ ስለፍቅርና ስለ ብሄራዊ መግባባት ስናወራ፣ በዚያኛዉ ወገን እርቅን የሚፈልግ የሰለጠነ ቡድን አለ ብለን እንጂ፣ ፈርተን፣ ባርነትንና ዘረኝነት አሜን ብለን ተቀብለን አይደለም። የሰው ልጅ እግዚአብሄር ሲፈጥረው በነጻነት ነዉ። የሰው ልጅ ያለ ነጻነቱ ሰው አይደለም

↧

ኢትዮጵያዊ ዋጋው ስንት ነው? (ተመስገን ደሳለኝ)

$
0
0

ኢትዮጵያዊ ዋጋው ስንት ነው?
(ተመስገን ደሳለኝ)

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

የዚህ ፅሁፍ ማጠንጠኛ የፖለቲካ አመለካከትን መተቸት አይደለም፤ ከዋና ዋና ሀገራዊ አጀንዳዎች ወረድ ያሉ የጉልበታሙን ስርዓት የሥራ አፈፃፀሞችን ማብጠልጠልም አይደለም፤ የተቀናቃኝ ፓርቲዎችን ስንክሳር መንቀስም… አይደለም፡፡ ኢትዮጵያዊ (አል-ሀበሽ) መሆን ለፈተና፣ ለመከራ፣ ለሰቆቃ… መዳረጉ የወለደው ብሶት እንጂ፤ መመረር-ማምረር ነው፡፡ …ይህ የእኛ ዕጣ ፈንታ የሆነበትን ምስጢር መመርመር ነው፡  -

ሰሞኑን የሳውዲ አረቢያ መንግስት ታጣቂዎች እና በድጎማ የሚያድሩ የሀገሬው ተወላጆች በመሰረቱት የጥፋት  ግንባር ጉልበታቸውን ገብረው፣ በላብ በወዛቸው በሚያድሩ ስደተኛ ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመው አረመኔያዊ  ወንጀል፣ የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ልብ በከባድ ሀዘን የሰበረ፣ በቁጭት ያንገበገበ አሳዛኝ ፍፃሜ ሆኗል፡፡  ጭፍጨፋው ሃይማኖታዊው ጀሀድ ያወጀው አይደለም፤ ኢትዮጵያዊነት ባመጣው ዕዳ በድሃ ወንድም-እህቶቻችን ጀርባ ላይ ያረፈ ምህረት  የለሽ ብትር እንጂ፡፡..;;;ይህ ግን ለምን ሆነ? ጥያቄ ነው፡፡

ርግጥ ነው፣ እንዲህ አይነቱ የእልቂት ነጋሪት መጎሰም ከጀመረ ዓመታት ነጉደዋል፤ መነሻ ሀገሩ ግን ሳውዲ አረቢያ ወይም ሊቢያ አይደለም፤ እዚሁ ኢትዮጵያችን ምድር ላይ እንጂ…

ዘ-ፍጥረት…
የየካቲቱ አብዮት ድንብዥታ (ሀንግኦቭር) ዛሬም ድረስ ዘመን ተጋሪዎቼን እያሳደደና እያሰደደ ይገኛል፡፡ ያኔ ያ ትውልድ ‹ኑ እንነሳ፣ ከተማውን እንውረር፤ አሮጌውንም ቅፅር በጩኸት አፍርሰን፣ አዲሱን እንፍጠር!› የሚል መለከት መንፋቱ ሙሉ ለሙሉ ስህተት ባይሆንም ‹የተጠሩ ብዙዎች፣ የተመረጡ ጥቂቶች› እንዲል መፅሀፉ፣ እፍኝ ለማይሞሉ ‹ምርጥ ወታደራዊ መኮንኖች› የተናጠል አሸናፊነት፣ የወል ተጠያቂ መሆኑ አይቀሬ ነው፡፡ ስለምን ቢሉ? ስለተከሰተው ታሪክ ይሆናል መልሱ፡፡ በርግጥም ‹ፓርቲ› የሚባል የ‹ጦስ ዶሮ› ባነበረው ልዩነት በጥይት ደብድበው ሲያበቁ፣ አፈር ፈጭቶ፣ ውሃ ተራጭቶ ባደገበት መንደር እንደ መናኛ በየመንገዱ አስጥቶ ማዋል፣ ለግብዓተ መሬቱ የጥይት ዋጋ ማስከፈል፣ ወላጆችን እርም መከልከል… ከዚህ የከፋ ምን ሊያመጣ ኖሯል? …ከተኛበት አልጋ እያነቁ መስቀል፣ ከገሀነም በከፋው ቅጣት ‹ወፌ-ላላ› ገልብጦ ማሰቃየት፣ በአንድ ጉድጓድ ስልሳውን አነባብሮ መቅበር… ከዚህ ሌላ ምን ሊያስገኝ ኖሯል? …የሆነውም ይህ ነበር፡፡ እነሆም ያ ትውልድ የፀነሰው የተገነባውን መናድ፣ የተሰራውን ማፍረስ፣ በራስ ወገን ላይ መከራ ማዝነብን የሚመክረው የዘ-ፍጥረት መፅሀፍ ምዕራፍ እዚህ ጋ ነበረ የጀመረው፡፡
አዲስ ታሪክ አልተሰራም!

 

‹አዲስ ንጉስ እንጂ፣ ለውጥ መቼ መጣ!› እንዳለው ከያኒው፣ ታጋዮቹ በወታደሮቹ ቦታ ከተቀመጡ በኋላ የነበረው-እንደነበረው ነው የቀጠለው፤ ‹ባለሙያ› ገራፊዎች በአሸናፊዎቹ ከመተካታቸው በቀር፣ ማሰቃያ ጎሮኖቹ ዛሬም ወደ ሙዚየምነት አልተቀየሩም፣ መገረፊያው፣ መገልበጫው፣ መግደያው፣ መጋዣው… አሁንም የቀድሞውን ግልጋሎታቸውን እየሰጡ ነው፡፡ ማን ያውቃል? ነገም በዚሁ ይቀጥሉ ይሆናል፤ ለአጎራባች መንደሮች መቀጣጫ በሚል የጭካኔ ፈሊጥ፣ የአማፅያን ኮሽታ የተሰማበትን መንደር ሁሉ ዶግ አመድ ማድረግም፣ የጄነራሎቻችን የጦር ‹ጠበብ›ነት መገለጫ ሆኖ ቀጥሏል፤ በሀውዜን፣ አርባ ጉጉ፣ አርሲ፣ ሐረር፣ ጋምቤላ፣ አዋሳ፣ ኦጋዴን፣ ቀብሪ-ደሀር፣ ደገ-ሀቡር… የፈሰሰው የግፉአን ደም፣ የተከሰከሰው የንፁሀን አጥንት ታሪክ ነጋሪ ጥቁር ሀውልት መሆኑን ማን ይክዳል? ይህንን ሁሉ ምድራዊ ፍዳ፣ ዓለም እንደ ማንኛውም አሳዛኝ ዜና ሰማው እንጂ፣ ሰለባዎቹን ለመታደግ ያደረገው እዚህ ግባ የሚባል እንቅስቃሴ አልነበረም፤ በራስ መንግስት፣ በራስ ወገን መናቅ፣ ክብር መነፈግ፣ ለ‹ምርኮኛ ሕግ› ማደር… ክፋቱ እዚህ ላይ ነው፡፡ የዛሬዎቹ አረቦቹም በወገኖቻችን ላይ የጭካኔ እጃቸውን እንዲያነሱ የልብ ልብ የሰጣቸው፣ ይኸው የእኛው የእርስ በእርስ አለመደጋገፍና አለመከባበር ነው፡፡ ትላንትና በጉራ ፈርዳና ቤንች ማጂ ዞን ጎሳ መመዘኛ ሆኖ ‹ውጡ የክልሉ ተወላጅ አይደላችሁም› በሚል በገዛ ወገኖቻቸው እንደጠላት ሀገር ሰው በጦር መሳሪያ ተከበው፣ ንብረታቸውን ሜዳ በትነው ስለተባረሩ ኢትዮጵውያኖች፣ የሰሙ አረቦች ‹ሳወዲያ አረቢያን ልቀቁና ውጡ› ብለው ይህ አይነቱን መዓት ቢያወርዱ ምን ይደንቃል? የባዕድ ሀገር ሰው የትንኝ ነፍስ ያህል እንኳ ሳይጨነቅ እንደዘበት ህይወታችንን ቢነጥቀን በእርሱ ላይ መፍረድ እንዴት ይቻለናል? አሳልፈው የሰጡን እነማን ሊሆኑ ነው?

እመነኝ፣ በሳውዲ አረቢያ ጎዳናዎች የሰው ራስ ቅል እንደ በግ በመጥረቢያ ሲከሰከስ፣ እንደ ጦስ ዶሮ ተጋድሞ ሲታረድ፣ በቁሙ እሳት ሲለቀቅበት፣ ህፃናት የወታደር መለዮ በለበሱ አረመኔዎች ሲረገጡ… ልብህ እያለቀሰ፣ ፊትህ በእንባ እየታጠበ ያየኸው አይነት ጭካኔ ምንጩ ይህ ነው፤ ይህም ነው የኢትዮጵያን ሰው በአልባሌ ምክንያት መግደል፣ እያፏጩ ጉዞን የመቀጠል ያህል ያቀለለው፤ ለዚህም ነው በሙስሊሞች ቅድስቲቷ መዲና ላይ በድንጋጤ የጨው አምድ የሆነ አካለ-ቁመና፣ በሽብር ተውጣ አቅሏን የሳተች እህት፣ ስጋት ያናጠበው ወንድም ተመልክተህ በሀዘን የተቆራመድከው፤ ‹‹ወይኔ ወገኔ!›› ብለህ ደም እንባ የተራጨኸው፡፡ …እናስ! ለዚህ ሁሉ ጥፋት ተመጣጣኝ ዋጋ መክፈል ያለበት ማን ነው? ንጉሥ አብደላና ዕኩይ ተከታዮቹ ብቻ? ወይስ እንዲህ የፊጥኝ አስሮ ለአረብ ሀገራት መቀለጃ የዳረገህ መንግስትህም ጭምር?

 
ከችጋርና ጭቆና ያልተፋታ ሕዝብ ዳቦና ነፃነት ፍለጋ እግሩ ወዳደረሰው ሀገር ተሰዶ መኖሩ በእኛ የተጀመረ አይደለም፤ እንዲያውም ስደተኞችን ካስተናገዱ ከመጀመሪያዎቹ ጥቂት የዓለም ሀገራት መካከል በግንባር ቀደምነት የምትጠቀሰው የእኛዋ የአቢሲኒያ ምድር ኢትዮጵያ ነች፡፡ የሩቁን ትተን እስከ የኃ/ስላሴ ስርዓት ፍፃሜ ድረስ የነበረውን ተጨባጭ ሁነት ብንመለከት እንኳ፣ ‹አረብ ቤት› በሚል ተቀፅላ የሚታወቁት ብዙዎቹ ሱቆችና የንግድ መደብሮች፣ በስደት መጥተው እኩል እንደ ዜጋ ሀገራችን መኖር በቻሉ አረቦች የተያዙ ነበሩ፡፡ የዛሬን አያድርገውና ይህች ገናና ሀገር ለሌሎች ሀገራት ሕዝቦች የነፃነትና የክብር ተምሳሌትም ነበረች፡፡ በመፅሀፍ ቅዱስም ሆነ በቅዱስ ቁርአን ውስጥ በፈሪሐ እግዚአብሔርነቷ፣ በፍትሐዊነቷና በርትዓዊነቷ ስሟ ተደጋግሞ የተወሳና የተመሰከረላት፣ የታላቅ ሕዝብ ታላቅ ሀገር ነበረች፡፡ ዛሬ በተፈጥሮ ማዕድን በልፅጋ የሀበሻ ስደተኞች መናኸሪያ ለመሆን በበቃችው ሳውዲ አረቢያ የተወለዱት ነብዩ መሀመድ የዛሬ 1400 ዓመታት ገደማ በስደት መጠለያነት የመረጧት፣ ሀገሪቷም ተከታዮቻቸውን እጇን ዘርግታ በመቀበል ከራሷ ዜጋ እኩል ተንከባክባ ያኖረቻቸው ስልጡን ሀገር ነበረች፡፡ ማን ነበረ ‹ወርቅ ላበደረ…› ያለው? እነሆም ዘመኑ ተቀያየረና ‹‹የኋላኞቹ ፊተኞች፣ የፊተኞቹ ኋለኞች›› ይሆኑ ዘንድ ግድ በማለቱ ዛሬ አብዛኞቹ የአረብ ሀገራ ኢኮኖሚያዊ ልዕልና እየተጎነፀፉ ሲመጡ፣ እኛ የኋሊት ተንሸራተን ቁልቁል ለመውረድ በቃን፡፡

 
ምንም እንኳ እነዛ ሁሉ መልካም መገለጫዎቻችን ዛሬም ድረስ ባናጣቸውም፣ በብሔር ክፍፍልና በእርስ በእርስ ሹኩቻ የተነሳ ግን በደህነት ማጥ ውስጥ ተዘፍቀን፣ እኛም በተራችን መሰደድ ዕጣ ክፍላችን ሆኖ ቀረ፡፡ ዛሬ አብዛኛው ወጣት በሀገሩ የመኖር ተስፋው በመሟጠጡ፣ በስደት ወጀብ የሚንገላታ፣ ማረፊያ እንዳጣች ወፍ ሲናወዝ መሽቶ የሚነጋለት ብኩን ሆኗል፡፡ በሀገሩ እጅግ ከመመረሩም የተነሳ ራሱን ለሻርክ ጥርስ፣ ለእንግልት፣ ለግርፊያና ለበልዓ-ሰቦች አሳልፎ እስከ መስጠት በሚያደርሰው የስደት ጉዞ ለማለፍ የማያመነታ ትውልድ ለመሆን ተገዷል፡፡ ይህ ከድህነት ወለል ስር ያሳደረን የዘመን ግርሻ፣ ይህ ከመንግስት ጋር አይንና ናጫ ያደረገን አምባገነናዊ አገዛዝ፣ ለዚህ ሁሉ አሳረ-መከራ ዳርጎን፣ ከሀፍረት ጋር አንገታችንን እስደፋን… ውለታን ከማስረሳቱም በላይ ለከፋ በደል አጋልጦ ቁጭት አስታቀፈን፡፡

 
ሰሞኑን ‹‹የበላችበትን ወጪት…›› ከሰበረችው ሳውዲ አረቢያ የተሰማው አሰቃቂ ዜናም የእዚህ የኢትዮጵያን ስደተኞች ተከታታይ ፍዳ ጉትያ ነው፡፡ እርግጥ አብዛኛው የአረብ ሀገራት መሬቱ ሰለጠነ እንጂ ሕዝቡ ገና ጨለማ ዘመን ውስጥ ነው፤ ሌላ ሌላውን ወደጎን ብለን የሰሞኑን አውሬአዊ ባህሪያቸው እንኳን እንደ አይነተኛ ማሳያ ልንወስደው እንችላለን፤ ይህ ድርጊትም እንሰሳዊ ባህሪያቸው የስነ-ዝግመት ለውጥን ገና አለማገባደዱን ያመለከተ ነው፡፡ ከአንድ ክፍለ ዘመን በፊት ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ ምኒሊክ አድዋ ላይ፣ ያውም ሀገራቸውንና ዙፋናቸውን በጦር ኃይል ለመንጠቅ የጎመዠችው ሮም ያዘመተቻቸው ወታደሮች፣ እልፍ አእላፍ ሠራዊታቸውን ፈጅተው፣ የቅርብ ወዳጆቻቸው የሆኑ የጦር አበጋዞቻቸውን ገድለው የማታ ማታ የሽንፈትን ፅዋ አስጎንጭተው ከማረኳቸው በኋላ በርህራሄ ተንከባክበው እንደያዟቸው የዓለም ታሪክ ያውቀዋል፡፡

 
በሀገሩ ኑሮ አልቃና ብሎት፣ በሰው ምድር የሰው አደፋ አፅድቶ፣ ቆሻሻ ለቅሞ… ፋታ የማይሰጠውን የእህል ውሃ ጥያቄ ለመሙላት በማሰነ፣ ሆድቃን በሳንጃ መዘርገፍና የዱር አውሬ እንኳ የማይፈፅመው የጋርዮሽ ሴት ደፈራ መፈፀም… ምን አይነት ‹ኢብሊሳዊ› (ሠይጣናዊ) ተግባር ነው? የተቸነፈን መልሶ ማቸነፍ፣ የወደቀን መርገጥስ ‹ከመክፈር› (ፈጣሪን ከመካድ) በምን ይለያል?
አሁንም እደግመዋለሁ፡- ይህ ፖለቲካ አይደለም፤ እየፈሰሰ ስላለ የንፁሀን ደም፣ የወላድ መሀን ስለሆኑ እናቶች፣ ጧሪ ቀባሪ ስላጡ የተራቡ አባቶች፣ አሳዳጊ አልባ ስለሆኑ ህፃናት፣ ያለሚስት ስለቀሩ አባወራዎች፣ ባላቸውን ስለተነጠቁ የቤት እመቤቶች … የሰቆቃ እሪታ ነው፡፡ በወጡበት ሰው ሀገር ላይ ወድቀው ስለሚቀሩ ወገኖቻችን ዋጋ ስለመጠየቅ ነው፤ ለነጋዴው መንግስታችን ኢትዮጵያዊው ዜጋ ዋጋው ስንት እንደሆነ የመሞገት ጉዳይ ነው፡፡

 
ሀገር ማለት…

ሀገር ምን ማለት ነው? ‹ሀገር› የሚለውን ቃል የኢህአዴግ መራሹ-መንግስት መዝገበ ቃላት ምን ፍቺ ሰጥቶት ይሆን? ሉዓላዊነትስ በ‹አብዮታዊ ዲሞክራሲ› ቀዩ መፅሀፍ አንደምታው ምን ይሆን? …ቀለብ ሰፍረን የምናሳድረውን ሠራዊት ሞቋዶሾ ድረስ ልኮ፣ የባራክ ኦባማን ስጋት ማቃለል? በ‹ተባበሩት መንግስታት› ስም የሲ.አይ.ኤ ቅጥረኛ ሆኖ በሱዳናዊያን የውስጥ ችግር ላይ-ታች እንዲማስን ማድረግ? የሕዝብ ደህንነት መ/ቤትስ ኃላፊነቱ የእናንተንና የቅምጦቻችሁን ደህንነትና ምቾት መጠበቅ ነውን? የአምባሳደሮቻችን የሥራ ድርሻ ፓስፖርት ማደስና የመግቢያ ፍቃድ መስጠት ብቻ ነው? በስደተኛ ወገኖቻችን ላይ ‹ጊንጥ ሰላይ› መሆን? ቦንድ መሸጥ? ‹ኢህአዴግ ጌታ ነው› እያሉ መስበክ? …ወይስ የዜጎችንም ደህንነት መከታተልና መጠበቅንም ጭምር? …ይህ ነው የወቅቱ ዓብይ ጥያቄ፡፡
የዲፕሎማሲ ግንኙነትስ ምን ማለት ነው? አገዛዙ በአንድ ወቅት ተቀማጭነቱ ኳታር-ዶሀ የሆነው ‹አልጄዚራ› ቴሌቪዥን ‹ስሜን አጠፋ› በሚል የኳታርን ኢምባሲ እንደ ዘጋው አይነት ስራን ብቻ የሚመለከት ይሆን? ከዋነኞቹ ለጋሽ ሀገራት በግንባር ቀደምነት የምትመደበው ኖርዌይስ ኢምባሲዋ የተዘጋው ለማን ትርፍ ነበር? ለብሔራዊ ጥቅም መቆርቆርስ ‹ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት አልተከበረም› ብለው ዘገባ ባወጡ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ላይ ያንን ሁሉ አቧራ ማስነሳት ይሆን?

 
ሌላው ቢቀር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለምን እንደ ተመሰረተ ይዘነጋል? አባቶቻችን ኮሪያና ኮንጎ ድረስ የዘመቱት ለዓለም ዜጎች ሰላም መሆኑስ እንዴት ይረሳል? የድርጅቱ አባል ሀገራት የፈረሙት ስምምነትስ የሳውዲ አረቢያን ሽፍትነት እንኳ ለመከላከል አቅም አይኖረውም? በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት እልፍ አእላፍ ወታደሮቻችን ካለቁብን በኋላ ከባረንቱ የተመለስነው፣ ባድሜ ላይ የቆምነው፣ በዛላንበሳ የታገድነው… የማንን ሕግ አክብረን ነበር? ያውም ‹በስለላ ስራ ሊሰማሩ ይችላሉ› ተብለው የተጠረጠሩ ኤርትራውያን እንዲያ በክብርና በእንክብካቤ ወደ ትውልድ ሀገራቸው የተሸኙት፣ በጦር ሜዳ የተሸነፈው ሻዕቢያ ተፈርቶ ነበር እንዴ? …ይህ ነው እንቆቅልሹ፡፡

 
ዛሬስ መንግስታችን የስደተኛ ዜጎችን ደህንነት በምልዓት የማይከታተለውና የድረሱልኝ ጩኸታቸውን ሰምቶ ፈጥኖ እጁን የማይዘረጋላቸው ለምን ይሆን? ጉዳዩ ከአቅሙ በላይ ሆኖበት? ወይስ በለመደው የንቀት መነፅር አይቶ እንዳላየ በቸልተኛነት አልፎት ነውን? በርግጥ ይህንን የበደል ማማ ካለፈው ታሪኩ አንፃር ከገመገምነው ምክንያቱ ሀገራዊ ስሜቱ ደካማና ከሥልጣኑ ሌላ ምንም የሚያሳስበው ነገር ባለመኖሩ ብቻ እንደሆነ ይገባናል፡፡ ሌላው ቀርቶ ሠማያዊ ፓርቲ የአረቦቹን ወደር የለሽ ጭካኔ ለማውገዝ በሳውዲ አረቢያ ኢምባሲ በር አጠገብ የጠራውን የተቃውሞ ሰልፍ ያገደው ‹ይህ አይነቱ ሀገራዊ መቆርቆር ነገ ደግሞ መስቀል አደባባይን በሕዝብ ሱናሚ ለማጥለቅለቅ መነቃቃት የሚፈጥር ገፊ ምክንያት ሊሆን ይችላል› ብሎ በስጋት ስለተጠፈነገ ይመስለኛል፡፡

 
የሆነው ሆኖ የመንግስት ህልውናም ሆነ አቅም በእንዲህ አይነቱ ወቅት ነውና የሚፈተነው ኢህአዴግም በዚህ ተግባሩ ዜጎቹን የመታደግ ገት እንዳሌለው አስመስክሯል፡፡ መቼም በሲ.አይ.ኤ ተላላኪነቱ በ‹ዋይት ሀውስ› ማህደረ-መዝገብ ውስጥ ከጊዜ ጊዜ እየዳጎሰ የመጣው የ‹ውለታ›ው ዶሴ ለእንዲህ አይነቱ ፈታኝ ወቅት መሆን ይሳነዋል ማለት ይከብዳል፡፡ ሼክ መሀመድ አላሙዲንን ጨምሮ ጥቂት የማይባሉ የሳውዲ ነጋዴዎች፣ ሀገራችን ውስጥ በበርካታ የንግድ ዘርፎች ተሰማርተው አትርፈው ማደራቸው፣ በሰፋፊ እርሻዎች ዘርተው ማጨዳቸውስ እንደምን ተዘነጋ? ይህ ቢያንስ በነፍስ-ውጪ ነፍስ-ግቢ ለተያዙ ወገኖቻችን እንዴት የመደራደሪያ ጉልበት መፍጠር ሳይችል ቀረ? …በርግጥ መለስ ዜናዊ በ2004 ዓ.ም መጀመሪያ ላይ ከጎራ ፈርዳ ስላፈናቀላቸው አማርኛ ተናጋሪ ወገኖቻችን በተጠየቀበት ጊዜ ‹‹ደን ጨፍጫፊዎች ናቸው›› ሲል የስላቅ መልስ እንደሰጠው ሁሉ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኀኖምም የሳውዲውን እልቂት በተመለከተ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርቦ ‹‹የማባረር ሥራው በኢትዮጵያውያን ላይ ብቻ ያነጣጠረ እንዳልነበረ ተረድተናል›› በማለት መቀለዱ፣ ስርዓቱ ‹አስተዳድረዋለሁ› ከሚለው ሕዝብ ይልቅ ሥልጣኑንና ተያይዘው የሚመጡ ጥቅሞቹን በዜጎች ሕይወት ጭምር ተደራድሮ ከማስከበር እንደማይመለስ የሚያሳይ ይመስለኛል፡፡ እንደ መንግስት በሀገር ሀብት እንደአሻው እየተምነሸነሸ፣ ‹ግዴታዬ የባቡር መንገድና ኮንዶሚንየም ቤት መስራት ብቻ ነው› ማለቱ ይህንኑ ይመሰክራል፡፡ አሊያማ ፋሺስቱ ጣሊያን እንዲያ በርካታ ድልድዮች፣ መንገዶች፣ ቤቶች… ገንብቶ ሲያበቃ፣ ‹ሀገር› ማለት ሕዝብ የሰፈረበት ሉዓላዊ ግዛት ማለት ነው ተብሎ ያ ሁሉ መስዕዋትነት ተከፍሎ በኃይል እንዲባረር ባልተደረገ ነበር፡፡

 
‹ሕዝቤን ልቀቅ!›

 
በዘመነ-ኦሪት በግብፅ ዙፋን ላይ በተፈራረቁ ፈርኦኖች፣ ለባርነት የተዳረጉ ዕብራዊያንን ነፃ ያወጣ ዘንድ በፈጣሪ ተመርጦ የተላከው ሙሴ ‹‹እግዚአብሄር ‹ያመልከኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ!› ብሎሀል›› ማለቱ በቅዱሳት መፃህፍት መገለፁ እውነት ነው፡፡ በዚህ ዘመን ደግሞ ራሱን ‹ኢህአዴግ› ሲል በሚጠራው ‹አምሳለ-ፈርኦን› ለመከራና ለሀፍረት የተዳረጉ ሕዝቦች አርነት ይጎናፀፉ ዘንድ ‹የሙሴ ያለህ!› የሚለው ጩኸታቸው ከተራራ ተራራ እያስተጋባ መሆኑ ሌላ እውነታ ነው፡፡ በሳውዲ አረቢያ የግፍ ሰለባ የሆኑ ኢትዮጵውያን ደምም ዋይታ እየተበራከተ ነው፤ ስርዓቱ እንዲህ አይነቱ ሰቆቃን ለፖለቲካ ትርፍ እየተጠቀመበት መሆኑንም ሰሞኑን የመንግስት እና ደጋፊዎቹ ሚዲያዎች የሚያሰራጩትን ዘገባ መመልከት በቂ ነው፡፡ መቼም መሬት ልሰው፣ አፈር ቅመው ያፈሩትን ንብረት ተነጥቀው፣ ባዶአቸውን እየተመለሱ ያሉ ስደተኞችን ‹በሀገራችን መስራት ይሻለን ነበር› እንዲሉ ማስገደድ ለርካሽ ፖለቲካዊ ትርፍ ካልሆነ በቀር ሌላ ትርጉም የለውም፡፡ አስከፊው ድህነታችን ጉርሻ እስከ መግዛት፣ ከቆሻሻ ገንዳ ውስጥ ቅልጥም እስከ መምጠጥ፣ የወደቀ ምግብ ከውሻ ጋር ተጋፍቶ እስከ መመገብ… በደረሰበት በዚህ የችጋር ዘመናችን ላይ በምን አመክንዮ፣ ከየትኛው ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር ተመዝኖ ሊታመን ይችላል ተብሎ ነው ‹ሀገር ውስጥ ሰርቶ በሰላም መኖር ይቻላል› የሚለው ተራ ፕሮፓጋንዳ ነጋ-ጠባ የሚደሰኮረው? ምንድር ነውስ የሚሰራው? እዚህ እኛ ሀገር የማንን መፀዳጃ ቤት ንጽህና መጠበቅ ይሆን የአረቦቹን ያህል ዳጎስ ያለ ክፍያ ማስገኘት ቀርቶ፣ በቀን ሁለቴ ለመብላት የሚያግደረድረው? ቅጥ አንባሩን ያጣው የግብር ፖሊሲያችን፣ እንጀራ ቸርቻሪዎችን ሳይቀር አሳድዶ የእለት ጉርሻቸውን እየነጠቀና በተንሰራፈው ድህነት ላይ ተጨማሪ እልቂት አውጆ ድሆችን ለማጥፋት ሰይፉን በሚያወናጭፍበት በዚህ ወቅት፣ ወጣቱ እንዴት ብሎ ነው በሀገሩ ሰርቶ መኖር ይችላል የሚባለው? ገና ጀንበር ከማዘቅዘቋ ጎዳናውን የሚያጥለቀልቁት ህፃናት ሴተኛ አዳሪዎችንስ ምን እንበላቸው? የትኛው ተቀጣሪስ ነው በደሞዙ የወር ቀለቡን ሳይሳቀቅ መሸመት የቻለው? …ሁላችንም የመዳፋችንን ያህል አብጠርጥረን የምናውቀው በመሬት ያለው ተጨባጭ እውነታ ይህ ነው፡፡

 
እነሆም በመጨረሻ እንዲህ ማለት ወደድኩ፡- ስርዓቱ ሰባኪው እንዳለው ‹የከንቱ ከንቱ፣ ከንቱ› ቢሆንም፣ አቶ መለስ ዜናዊ በኤርትራ የመጀመሪያው የነፃነት ዓመታዊ ክብረ በዓል ላይ ተገኝቶ በአስመራ ሳባ ስታዲዮም ለተሰበሰበው ህዝብ በደርግ የደረሰባቸውን በደል በማስታወስ ‹‹በእናንተ ጀርባ ላይ ያለው ጠባሳ በእኛም ላይ አለ›› ሲል ሀዘኑንና መቆርቆሩን እንደገፀላቸው ሁሉ፣ በሳውዲ አረቢያ የግፍ ሰለባ የሆናችሁ ወንድም-እህቶቼ ሆይ! የእናንተ ሰቆቃና በደል፣ በእኛም ግንባር ላይ ተቸክችኮ ሀፍረታችችንና ውድቀታችንን የጋራ እንዳደረገው የታሪክ ፍርድን መጠበቁ አይቀሬ ነው፡፡ እመኑኝ ያች ዕለትም አብረን የምንነሳበት፣ ከፍ ብለን የምንበርበት ትሆናለች፡፡›

 
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

 
ኢት

 

 

↧

በእሁዱ ታላቁ ሩጫ ውድድር ላይ ታላላቅ አትሌቶች በፍርሃት ሳይገኙ መቅረታቸው ተዘገበ

$
0
0

ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ አረቢያ የደረሰባቸውን እና እየደረሰባቸው ያለውን ስቃይ በማስመልከት ባለፈው እሁድ በተደረገው የታላቁ ሩጫ ውድድር ላይ ተሳታፊዎች ለሃዘን መግለጫ እንዲሆን ጥቁር ሪቫን አስረው እንዲሮጡ ሰማያዊ ፓርቲ ጠይቆ የኃይሌ ገ/ስላሴ ንብረት የሆነው ታላቁ ሩጫ ይህን መከልከሉ ይታወሳል። ከውድድሩ በኋላ ከላስ ቬጋስ ከተማ የሚሰራጨው ሕብር ራድዮ እንደዘገበው በዘንድሮው ታላቁ ሩጫ ውድድር ላይ ታላላቅ አትሌቶች በአዲስ አበባ ላይ ይፈጸማል ተብሎ በተፈራ የሽብርተኝነት ጥቃት የተነሳ አለመገኘታቸውን ዘግቧል። ዝርዝሩን እንደወረደ ከራድዮው ያዳምጡት፦

↧

ከቁጫ ሕዝብ ጥያቄ ጋር በተያያዘ የቀድሞውን የዞን አስተዳዳሪ ጨምሮ 4 ግለሰቦች ታሰሩ

$
0
0

Fnoteየቁጫ ህዝብ ካለፈው አመት ጀምሮ እያነሳቸው ባሉት የማንነት ፣የመልካም አስተዳደርና የልማት ጥያቄዎች ከመንግስት ጋር ፍጥጫ ውስጥ መግባቱን ተከትሎ መንግስት የጀመረውን የእስር እርምጃ ገፍቶበታል፡፡

የአካባቢው ተወላጅ የሆኑት የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ምክትል የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሺ እንዳስታወቁት በትላንትናው ዕለት ኅዳር 16 ቀን 2006 ዓ.ም አቶ ቱማ አየለ የተባሉ ቀድሞው የጋሞ ጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እና በአሁኑ ወቅት የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሌክቼረር፣ አቶ ፍሬው ጳውሎስ የተባሉ ታዋቂ ባለሀብት እና አቶ እንድሪያስ ሄባና የተባሉ የቀድሞ የእርሻና እጽዋት ተመራማሪ በአሁን ወቅት ደግሞ ‹‹ሜርሲኮር-ኢትዮጵያ›› ተብሎ ለሚጠራው አለም አቀፍ የዕርዳታ ድርጅት የአርባ ምንጭና የአከባቢው ዳይሬክተር ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ጀምሮ በፖሊስ ታስረው ወዳልታወቀ ቦታ ተወስደዋል፡፡

በተያያዘ ዜና የትራፍክ ፖሊስ የሆኑት ዮሐንስ ፈረንጃ፤ ከባለፈው ዓርብ ዕለት ህዳር 13 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ትላንት ወደ አርባምንጭ ማረሚያ ቤት መወሰዳቸውም ታውቋል፡፡

ምንጭ፡ ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ

↧
↧

ጀኔራል ሓየሎምን እንደመጠቀሚያ –ከአሰገደ ገ/ሥላሴ

$
0
0

ስለ ጀኔራል ሓየሎም ማንነት በትጥቅ ትግል እና ደርግ ከተወገደ በኃላ ከሞተም በኃላ በተለያዩ አካላት ብዙ ተነግሮለታል፡፡ ጀነራል ሓየሎም በ ፀረ-ደርግ በተደረገዉ ትግል መጀመሪያ በትግራይ በኃላም ወደ ሰሜን ሸዋ ዘልቆ ከገባ በኃላ ስመ ጥሩና ገናና ነበር።

ሓየሎም በትጥቅ ትግል ጊዜ ወታደራዊ መሪ ብቻ ሳይሆን ፖለቲካ መሪም ነበር። በመሆኑም ህዝቡ ከህፃን እስከ አዛውንት ፆታና ሃይማኖት ሳይለይ ይወዱት ነበር፡፡ ሌላዉ ቀርቶ የደርግ ምርኮኞችና በደርግ ወታደራዊ መሪዎች የነበሩም ሓየሎምን በመልካም የሰብኣዊ አያያዙና ጀግንነቱ ያደንቁት ነበር። ሃየሎም የኛ ቢሆን ንሮም ይሉት ነበር ኮሎኔል መንግስቱ ሳይቀሩ ሳይወዱ በግድ ያደንቁት ነበር፡፡

hayelom areaya ደርግ ከተወገደ በኃላም ሓየሎምን በመጥፎ አይን የሚመለከተዉ ሰዉ አልነበረም ። በድንገት በባንዳዎች ከተገደለ በኃላም መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ አዝኖለታል። በወቅቱ የመንግስት የህዝብ ብዙሃን መገናኛዎች ተናግረውለታል። በተለይ ደግሞ የትግራይ ህዝብና ታጋዮቹ የሓየሎምን ሞት ምፅአተ ምጥ ሆነባቸዉ። ሓየሎም በተንቀሳቀሰበት ቦታ ክልልና ብሄር በማይለይ መሪር ሃዘኑን በእንባ ገለፀ።

ከሞተ በኃላም የሕ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ለተወሰነ ጊዜ በቴሌቪዢን መስኮት ፎቶግራፉን በማገላበጥ ብዙ ተናግረውለታል።

ስለ ሓየሎም ግን አንዳንድ መድረኮች ሲፈጠሩ ለጊዜው ፖለቲካ ፍጆታ ተብለዉ ፎቶ ግራፉን በቴሌቪዢን ስክሪን በማስቀመጥ የተበጣጠሰ ታሪክ ስለ ሓየሎም መናገር ካልሆነ በስተቀር ስለ ሓየሎም መሰረታዊ የሆነ ታሪክ ተፅፎ ለትውልድ እንዲያልፍ የሕ.ወ.ሃ.ት መሪዎችና ካድሬዎቻቸዉ እስከ አሁን ሳይቆርጡ ቆዩ። በመከላከያ ሚኒስቴርም የሚገኙ ጋዴዎቹም ሓየሎም በሚገባ የሚያውቁትም አንዳንድ የመታሰቢያ ወታደራዊ ት/ቤት ቢከፍቱለትም ፣አነስተኛ ሓወልት ቢሰሩለትም ስለ ሓየሎም ታሪክ ሊፅፉ አልደፈሩም ።አንዳንድ የሚፅፏቸዉ መፃህፍትም ቢኖሩም አሁን ላሉ የሕ.ወ.ሃ.ት መሪዎች የሚያሞካሹ ካልሆኑ በስተቀር ስለ ሓየሎምና የሌሎች በህይወት የሌሉ ወታደራዊ ና ፖለቲካዊ መሪዎች የጀግነነት ታሪክ የሕ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ሳያስፈቅዱና ሳያስባርኩ ሊፅፉ አይፈልጉም አንዳንድ የሕ.ወ.ሃ.ት መሪዎችም በተለያየ አጋጣሚዎች በመድረክ ላይ እየወጡ ሓየሎምን የሕ.ወ.ሃ.ት ፕሮግራም 85% አያውቀዉም ።በተጨማሪም ቀልቃላ ነበር ግን ደግሞ ተዋግቶ ደርግን አሸንፏል በማለት የሓየሎምን ህዝባዊ ፍቅርና ፖለቲከኛነት የሚያጎድፉ ወገኖች ነበሩ እነዚም ለራሳቸዉ ታሪክ የሌላቸዉ ናቸዉ።በተጨማሪም የኮነሬል ሃየሎም ለሃገሩ ሉኣላዊነትና ኣንድነት ጠንክሮ መታገሉ የማያስደስታቸው የነበሩ በመሆናቸው ለምን የሓየሎም መልካም ታሪክ ጎልቶ እንዲወጣ አልፈለጉም ? በኔ እምነት ከጅምሩ ወደ ትግል ሜዳ ሲወጣ የነበረዉን የሀገሩን ሉአላዊነትና አንድነት ፍላጎትና ፍቅር እጅጉን ቀና ስለነበረ የሕ.ወ.ሃ.ት መሪዎች በ1974 ዓ/ም ሻዕቢያን ለማዳን ሰራዊት መርተህ ወደ ኤርትራ በረሃዎችዝ መት ሲባል እምቢ ለማላምንበት ስትራቴጂና አላማ አልሄድም ብሎ የቀረ ነበር። ኃላም የሻዕቢያ መንግስት በህዝባችን ላይ ይፈጥረዉ የነበሩ ግፍ ተቃዋሚ ነበር። በየመንና በሻዕቢያ በሓኒሽ ምክንያት የነበረ ጠብም የኢትዮጵያ ጣልቃ ገብነት ይቃወም እንደነበረ ይታወቃል። የሆነ ሆኖ ሓየሎም በባንዳዎችና በከዳተኞች ተገደለና የሚያውቀዉ ሳይሰንደዉ አለፈ። የሓየሎም መልካም ዝና የማይፈልጉም በውስጣቸዉ ተደሰቱ። ሻዕቢያና መሰሎቹ በደስታ ፈነጩ።

አሁን የሓየሎም ወርቃማ ታሪክ በሰለሙን ገ/አረጋዊ ታጋይ ነበር ትውልድ ቀዬዉ በአጋሜ አውራጃ በጎሎ መኸዳ ወረዳ በብዘት ቀበሌ የሆነ በ8/03/2006 ዓ/ም የሓየሎምን ታሪክ የሚተነትን መፅሃፍ በመቀሌ ሚላኖ ሆቴል ተበሰረ ።

ፀሃፊ ሰለሞን ገ/አረጋዊ የሓየሎምን ታሪክ ሲፅፍ ከተወለደበት እስከ ታገለበት ጊዜ ኃላም የትጥቅ ትግል ታሪኩ መረጃ ለመሰብሰብ እጅጉን ብዙ ውጣ ውረድ አጋጥሞታል ። ከትግል በፊት የነበረ ታሪኩ ለመሰብሰበ ብዙ ችግር አልነበረም የትግል ታሪኩን ግን እራሱና የቅርብ ጓደኞቹ ጥቂት አካል ጉዳተኞች፡ ከጥቂት ወታደራዊ መሪዎች ፣ ከአርሶ ቸደሮች፣ ምልሻዎች፣ ምርኮኞች መረጃ ለማግኘት ችግር አልነበረዉም ትልቁ ችግር ግን ከሕ.ወ.ሃ.ት ፅ/ቤት ከሕ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ካድሬዎቻቸዉ መረጃ ለማግኘት ፈታኝ እንደነበር ይናገራል። ግን ደግሞ ብዙ ታሪካዊ ሃቆች በራሱ ጥረት አግኝቷል።

መፅሃፉ ተፅፎ ተጠናቀቀ

ፀሃፊዉ መፅሃፉ አጀጋጅቶ ከጨረሰ በኃላ የማተሚያ ገንዘብ የማግኘት ጉዳይ ፈተና ተጋረጠበት ፀሃፊዉ የሓየሎም ታሪክ ከፃፍኩ ይቅርና የሓየሎም መፅሃፍ ለማሳተም ብዙ ታሪካዊ ይዘት የሌላቸዉ እና የፓርቲ መፃሄቶች፣ ጋዜጦች፣ሲታተሙ እንኳን የኢፈርት ካምፓኒዎች የትግራይ እርዳታ ማህበር ፣ የትግራይ ልማት ማህበር፣ የደደቢት ብድርና ቁጠባ የመንግስት መ/ቤቶች ፣ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የትግራይ ቱሪዝም ቢሮ፣ የወረዳ የቀበሌ መስተዳደሮች የግል ካምፓኒዎች ብዙ ገንዘብ በመስጠት ታትሟል። በየመ/ቤቱ ካምፓኒዎች፣ ት/ቤቶቸ በህ.ወ.ሓ.ት ባለስልጣኖች ተፅእኖ እየተደረገ እንዲሸጡ ይደረጋል የመንግስት ሰራተኛ የሕ.ወ.ሃ.ት አባላት የኢፈርት ካምፓኒዎች ሰራተኞች የመከላከያ ሚኒስቴር ሰራዊት ከደሞዛቸዉ የሚቆረጥ መፅሃፎቹን እንዲገዙ ይገደዳሉ። ስለ ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ የሚተርክ ሰማኒያ ገፅ የያዘ ምፅሄት እንኳን በሚሊዮን የሚቆጠር መፅሄት ታትሞ በ100.00 ብር ተሽጣል በሁሉም ክልሎች የመንግስት መ/ቤቶች በአስር ሚሊዮን የሚቆጠር ብር ተሽጧል።ሌሎቹም እንደ ወይን ጋዜጣና መፅሄትም በመንግስት ተቃማት ስፖንሰርነት ይታተማሉ ወይን መፅሄትና ጋዜጣ ግን የ ሕ.ወ.ሃ.ት ልሳን ናቸዉ።

ለሓየሎም ታሪክ የያዘ የተፃፈ መፅሃፍ ግን ለማሳተም ለመቐለ ዩኒቨርሲቲ ለሁሉም የኢፈርት ካምፓኒዎች ፣ለደደቢት ብድርና ቁጠባ ፣ለትግራይ ቱሪዝም ቢሮ፣ ለባህል ትግራይ ፣ለትግራይ ኪነት ማህበር ፣ለትግራይ እርዳታ ድርጅት ለሌሎችም ፀሃፊዉ እርዳታ ጠይቋል። የተጠየቁት ግን 100% አሉታዊ መልስ ሰጡት። ሰውየዉ ማሳተሚያ አጥቶ በአሜሪካ ለሚገኙ የሓየሎም ቤተሰብ የሓየሎም ወዳጆች የድረሱልኝ ጥሪ አሰማ በጥሪዉ መሰረት ደግሞ የሚከተሉት ወገኖች የማሳተሚያ ገንዘብ ለገሱለት።

አቶ መኮነን ዘለለዉ ከዋሽንግተን 2. አቶ ኪሮስ አርአያ ገ/ሄር ከዋሽንግተን
3 . ወ/ሮ ዓወት መኮነን ዘለለዉ USA ዴንቨር ኮሎራዶ 4. አቶ ሙሉአለም ጎይቶኦም አውስትራሊያ

5. ወ/ሮ ፍረ ጎይቶኦም አውስትራሊያ 6. አቶ ሚኬኤለ ፍቕረ አርአያ ከዋሽንግተን

7. ሄኖክ ሙሉ አለም ገ/ህይወት ዋሽንግተን 8. አስገደ ገ/ስላሴ ከመቐለ

የምረቃ ዝግጅት

ፀሃፊዉ መፅሃፉን አሳትሞ ለምረቃ ሲዘጋጅ መፅሃፉን ሊመረቅ ለማሳወቅ ለኢተቪ፣ ለኢዜአ፣ ለድወት እና ኤፍ ኤም ድወት፣ ኤፍ ኤም መቐለ ኤፍ ኤም ፋና በሚድያ እንዲያስተላልፉለት ደብዳቤ ፅፎ አስገባ ሁሉም ሚድያዎች ሊያስታልፉለት አልቻሉም በምረቃዉ ቀን ብቻ ኢቲቪ እና ድወት ብቅ ብለዉ ነበር። ግን አልዘገቡም ምክንያቱም አሁን ባሉ የሕ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ቃለ-ቡራኬ ተሰጥቷቸዉ የታተሙና የትግላችንን ጉዞ አዛብቶ የግለዎችና የሕ.ወ.ሃ.ት ቁንጮዎች የሚያሞካሹ የታጋዮቹን ታሪክ የሚያጎድፉ የሃሰት ታሪክ የሚደረድሩ መፃህፍቶች የተፃፉ ህዝብና ህዝብን የሚያጋጭ ዘረኝነትን ጠባብነትን የሚቀሰቅሱ መፃህፍት ግን ሁሉም ሚድያዎች በማስተዋወቅ ይጠመዳሉ። የማተሚያ ገንዘብም በሽ ነዉ፡፡ የሚሆንላቸዉ ለመፅሃፍቶች ገበያም አስቀድመዉ ያዘጋጁላቸዋል የሰማአታት ሃወልት፣ አክሱም ሆቴል አ/አ፣ አክሱም ሆቴል መቐለ፣ ሸራተን አዳራሾች በተፅእኖ ፈጣሪዎችአ ኣዳራሾች በነፃ ይዘጋጅላቸዋል ።

ፀሃፊ ሰለሞን ገ/አረጋዊ ግን ስለ ሓየሎም የፃፈዉ ታሪክ አሁን ባሉ የሕ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ቃለ-ቡራኬ (ትእዛዝ ) ስላልተፃፈ ሁሉም ነገር ለማግኘት የታደለ አልነበረም ። ሰለሞን የሓየሎም መፅሃፍ ለማስመረቅ ብዙ አዳራሾች ጠይቆ አልተሳካለትም በመቐለ ዘመናዊ ሆቴል የሚላኖ ሆቴል ባለቤት አቶ ሙሉጌታ ግን ያዘመናዊ አዳራሻቸዉ ለሓየሎም ያልሆነ ለማን ይሆናል ብለዉ ያ በቀን በብዙ ሺ የሚከራይ አዳራሻቸዉ በነፃ ሰጡት ።

ለ መፅሃፍ ምርቃ ጥሪ

መጀመሪያ ለመፅሃፉ ምረቃ የሚያስተባብሩ (የሚያዘጋጁ) 3ት ሰዎች ማለት ዶ/ር ጌታቸዉ ተፈሪ አቶ አለማየሁ ገዛኸኝ ያሏቸዉ ኮሚቴ ተመሰረተ። የኮመቴዉ ዋና ስራ ለምረቃ ተሳታፊዎች መጥራት አዳራሽ ማዘጋጀት የምረቃዉ ስብሰባ መምራት መፅሃፉ በምሁራን እንዲገመገም ማድረግ ነበር። ስራቸዉን መበቀጠል መጀመሪያ ከ1300 በላይ የጥሪ ወረቀት አሳትሞ ማሰራጨት የጀኔራል ሓየሎም ፎቶ ያለበት በተጨማሪም ለምረቃ ተሳታፊ ገደብ ስላልነበረዉ ህዝብ በሚበዛበት አካባቢ በዩኒቨርሲቲዎች፣ ኮሌጆች ፣የመከላከያ ሚኒስቴር ካምፖች ፣ፖስተሮች ተለጠፉ ።

የጥሪ ወረቀቱ የፀሃፊዉ ስም ስላልነበረዉ የጀኔራል ሓየሎም መፅሃፍ ስለሚመረቅ ብቻ ነዉ የሚለዉ ሁሉም የትግራይ ክልል መሪዎች አና የህውሓት ማ/ኮሚቴ ከፍተኛ ካድሬዎች የጀኔራል ሓየሎም መፅሃፍ ሊመረቅ ነዉ ተሳተፉ የሚስጥር ድንገት ሆነባቸው እና ያነሱት ጥያቄ ቢኖር ፀሃፊዉ ማነዉ? መፅሃፉስ ምን ይዘት አለዉ? ለመሆኑ ጤናማ መፅሃፍ ነዉ ወይ? ምን ምን ይጠቅሳል ተቃዋሚዎችና ለፖለቲካ መቃወም ብለው የፃፉት እንዳይሆን ?የሚሉ ነበሩ።ሌላ ተራ ታዳሚዎችም መፅሃፉን ማነዉ የፃፈዉ ? የሕ.ወ.ሃ.ት መሪዎችስ ያውቁታል ወይ የፖለቲካ ይዘት እንዳይኖረዉ የሚሉ ነበሩ ሌላዉ ቀርቶ አንዳንድ የሓየሎም ቤተሰቦችም እየተፃፈ ያለዉ የሓየሎም መፅሃፍ የሕ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ያውቁታል ወይ የሚሉ ጥያቄዎች ያነሱ ነበሩ። በመጨረሻም መጥሪያ ወረቀቱ ለምሁራን ለወጣቶች በሙሉ ለመንግስት ሰራተኞች፣ ለነጋዴዎች፣ ለዩኒቨርሲቲዎች ፣ለመከላከያ ሰራዊት፣ ሰሜን እዝ ለኮሌጆች ተሰራጨ ለአቶ አባይ ወልዱ ለትግራይ ክልል አስተዳዳሪም በልዩ የተዘጋጀ የጥሪ ደብዳቤ ተሰጠ የመፅሃፉ ምረቃ ሪቫን እንዲከፍቱም ጭምር ነበር ። የተገለፀላቸው ኣባይ ወልዱ ግን ከመጦፍ ያህል ክብር ኣልሰጡትም ሌሎች ማ/ኮሚቴም ኣልመጡም፡፡

የመፅሃፉ ምረቃ በ8/03/2006 ዓ/ም ዕለተ እሁድ 8:00 ደረሰ የመፅሃፉ ምረቃ ተሳታፊዎች እንደተጠራዉ ብዛት አልመጡም አስቀድመዉ የመጡት ትላልቅ ምሁራኖች ጥቂት ወጣቶች ብቻ መጡ አንዳንድ የሕ.ወ.ሃ.ት ካድሬዎች ወደ አዳራሹ አካባቢ መጥተዉ ይመለሱ ነበር የሚመለሱበት ምክንያት መፅሃፉን የሚመርቁ መሪዎቻቸዉ ያሉ መስሏቸዉ መጥተዉ ግን ደግሞ መሪዎቻቸውን ስላጡ ተመልሰዉ የሄዱ መሆኑ ታውቋል። ከመከላከያ ሚኒስቴርም አልመጡም መፅሃፉን መርቀዉ ይከፍቱታል የተባሉት አቶ አባይ ወልዱም አልመጡም አንድ የሕ.ወ.ሃ.ት ባለስልጣንም አልመጣም ። ከብዙ ጥበቃ በኃላ በመጨረሻ የክልሉ ም/አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ንግስቲ ወ/ሩፋኤል መጡ። የተሰበሰበ ህዝብ ግን በጀኔራል ሓየሎም አርአያ የመፅሃፍ ምረቃ አንድ የሕ.ወ.ሃ.ት መሪና ካድሬ ይቀራል የሚል ግምት አልነበረዉም ተሰብሳቢዉ ጉዳዩን በመመልከት በመድረክ እየወጡ የተበጣጠሰ ንግግር የሓየሎምን ማንነት የሚደሰኩሩት የኖሩት ለጀኔራል ሓየሎም አርአያ አዝነዉ ሳይሆን ለፖለቲካ ፍጆታ እንደ መጠቀሚያ ነዉ እንዴ ብለዉ የንዴት ሁኔታ ይታይ ነበር። በተለይ ደግሞ በምርቃኑ ጊዜ የነበሩ ወጣት ምሁራን እጅጉን አዝነዋል። እንዱሁም የነበሩ የሓየሎም ቤተሰብም አዝነዋል።

በኔ እምነት የሕ.ወ.ሃ.ት መሪዎች በየመድረኩ እየወጡ ስለ በትግሉ ወቅት የወደቁ ጀግኖች ሲደሰኩሩ የውሸትና ከአንገት በላይ መሆኑን የማውቅ እንኳን ብሆን የጀኔራል ሓየሎም ታሪክ መፅሃፍ የሕ.ወ.ሃ.ት መሪዎችና ሎሌዎቻቸዉ ራሳቸውን በማግለላቸዉ ግን የጀግኖች ታሪክ ጎልቶ ሊወጣ የማይፈልጉና ቀናተቾኝ መሆናቸዉ በግልፅ የተጋለጡበት መድረክ ነበር። ይህ ደግሞ ለራሳቸዉ ተጋለጡ እንጂ የሓየሎም ታሪክ መፃፉ ትንሳኤ ሙታን ሆኗል። የሓየሎም ወዳጅ ተደስቷል ።

የምረቃ ስነ-ስርአት

መጀመሪያ መፅሃፉ በዶ/ር ጌታቸዉ ተፈሪ በአራት ደረጃ ከፋፍለዉ ከገመገሙ በኃላ ስለ መፅሃፉ ጠንካራና ደካማ ጎኑ ሳይንሳዊነቱ ከገመገሙ መፅሃፉ ሓየሎም ከተወለደበት እስከ ወደ ትግል የገባበትና የትጥቅ ትግሉ ጊዜ ታሪክ እስከ ሞተበት ጊዜ ብቻ ስለሚተርክ የሓየሎምን አሟሟት ስለማይገልፅ ዶ/ር ጌታቸዉ ግን ‹ ለወደፊት የሓየሎምን አሟሟት የተደበቀ ሚስጥር ለምን ግልፅ እንዳልሆነ ይህ ሚስጥር ለወደፊቱ ምሁራኑ ማጥናት አለባቸዉ ብለዉ ሃሳባቸዉን ትልቅ የቤት ስራ ለአዲሱ ትውልድ እና ለምሁራኖቹ አስተላለፉ። ከባድ ጥያቄ ነበር፡፡

የዶ/ር ጌታቸዉ ጥያቄ በአዳራሹ ውጥስ የነበረ ምሁር የሁሉም ጥያቄ ነበረ መሰለኝ ሁሉም ለማለት ይቻላል ትክክለኛ ጥያቄ ነዉ የሚል ንግግር ይሰማ ነበር። ከዶ/ር ጌታቸዉ ግምገማ በኃላ የጥቂት ተሳታፊዎች አስተያየት ከተሰማ መፅሃፉ በወ/ሮ ንግስቲ ወ/ሩፋኤል የትግራይ ክልል ም/ኣፈ ጉባኤ የመፅሃፉ ሪቫን ተከፈተ፤ ም/ኣፈጉባኤዋ ለሚላኖ ሆቴል ባለቤት አቶ ሙሉጌታ ላደረጉት አስተዋፅኦ የተዘጋጀ ምስክር ወረቀት ሽልማት ሰጡ።

የ ህ.ወ.ዋ.ሓት መሪዎች የሓየሎም ታሪክ በመፅሃፍ መልኩ መሰነዱ ለምን ደስ አላላቸዉም ? በኔ እምነት 1ኛ አሁን ያሉ ታጋይ ነበር መሪዎች በ17 አመት የትግል ወቅቱ ጀኔራል ሓየሎምና እንደሱ ያሉ ጀግኖች ሌት ተቀን ታሪክ ሲሰሩ እዚህ ግቡ የማይባሉ ስለነበሩ አመርቂ ታሪክ ስለሌላቸዉ ከቅናት የመነጨ ነዉ 2ኛ አንዳንድ መሪዎችም እንደ ሓየሎም ያለ ወርቃማ ታሪክ እንኳን ባይኖራቸዉ ትንሽ ታሪክ እንኳን ቢሰሩ በተለያዩ መንገድ ከሓየሎም ጋር በነበረዉ ቂም ምክንያት ጥሩ ግንኙነት ያልነበራቸዉ ናቸዉ።3ኛ ሌሎች የመከላከያ ሰራዊትና የህ.ወ.ሓ.ት ካድሬዎች ወደ መፅሃፉ ምረቃ ያልመጡበት ምክንያት ይዘውት የመጡት የካድሬነት ባሀል ካልተባልክ እንዳትፈፅም ወይ የታገልከውን ብቻ ፈፅም በሚሉት መርህ ባህልና አድር ባይነታቸዉ የመነጨ ነዉ። 4ኛ የመንግስት ሰራተኛና ነጋዴዎች ምሁራኖች ያልተሳተፉበት ምክንያት አሁንም የህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች ያልባረኩትና በሚዲያ ያልተነገረለት ስለነበር እንደተለመደዉ ፈርተውና ሰግተዉ ነዉ።ብዙሃን መገናኛም አስቀድመዉ ማስታወቂያ ያልሰሩበት የሚታዘዙት አሁን ባሉት የህ.ወ.ሓ.ት ማ/ኮሚቴ ስለሆኑ ያለ ትእዛዝ ስለማይሰሩ ነዉ። 5ኛ ከላይ እንደጠቀሰኩት ሓየሎም ከሞተበት ቀን ጀምሮ ለተለያዩ መድረኮች እንደ ፖለቲካ ፍጆታ መጠቀሚያነት ለማነሳሳት ሊጠቀሙበት ለጀኔራል ሓየሎም አርአያ ወዳዋቸዉ ሳይሆን ለጊዜዉ ለፖለቲካ ፍጆታ እንደመጠቀሚያ መሆኑን የህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች በዚህ የጀኔራል ሓየሎም ታሪክ የሚተነትነዉ መፅሃፍ ምረቃ ላይ ተጋልጠዋል። ይህ ደግሞ የ ህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች ነገሮች ለጊዜያዊ ጥቅም መናገር የተለመደ ባሀሪያቸዉ ነዉ።

ሌላዉ ቀርቶ እጅጉን የሚያስገርም የሚያሳዝን የህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች ተፅእኖ ምን ያህል አደገኛ እንደሆነ የሚያስረዳ የጀኔራል ሓየሎም ቤተሰብም በመቐለ ከተማ እያሉ ሳይሳተፉ የቀሩ ኣሉ ።ለዚሁ እንደ ምሳሌ የጀኔራል ሓየሎም አርአያ እህት ወ/ሮ አልማዝ አርአያ የፌዴራል ፓርላማ የህዝብ ተወካዮች የሆነች እንዳጋጣሚ ሁኖ የህ.ወ.ሓ.ት የሴቶች ሊግ ጉባኤ መቐለ መጥታ ሰንብታ መፅሃፉ እሁድ 8:00 ሰአት የሚመረቀዉ ተሳተፊ ተብላ ተነገሯት ኢትዮጵያ አየር መንገድ 300.00 ብር ስለሚቀጣኝ መሄድ አለብኝ ብላ እሁድ ከሰአት በፊት አ/አ በረረች። ወ/ሮ አልማዝ ደሃ ሁና 300.00 ብር ቅጣት በዝቶባት አይደለም ችግሩ የ ህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች በአባሎቻቸዉ ላይ ምን ያህል ነፃነታቸዉ እንደሚነጥቋቸዉ እና ሽብር እንደሚፈጥሩባቸውና አንዱ እንደማስረጃነት ማረጋገጫ ነዉ።ህ.ወ.ሓ.ት የመጣበትን ጉዞ ልጅ፣ አባት፣ እናት ባልና ሚስት ዘመድ አዝማድ እየለያየ እርስ በርሱ እንዳይጠጋጋ እያደረገ ነበር የመጣዉ። ወ/ሮ አልማዝ አርአያም የወንድማቸዉ ጀኔራል ሓየሎም ወርቃማ ታሪክ የያዘ መፅሃፍ ሲመረቅ ይቅርና በዛች የምረቃ ዕለት በ2:00 ሰአት ልዩነት አ/አ ሊሄዱ ይቅር ከ አ/አ መቐለ የትራንስፖርት ለሆቴል ከፍለዉም በምረቃዉ መገኘት ነበረባቸዉ ግን ለዚች ርካሽ አለምና ለእንጀራቸዉ ሲሉ የጀኔራል ሓየሎም መድረክ ረግጠዉ ሄዱ። መጥፎ ቀን ውለዋል የህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች ቢሆኑ ለጀኔራል ሓየሎም አልሆኑም። ም/ኣፈ ጉባኤዋ የመጣችበት ምክንያት በብዙ ካልኩሌሽን ታስቦበት አሁንም ትንሽ የፖለቲካ ፍጆታ ብናገኝባት ብለዉ ነዉ። ወ/ሮ ኣልማዝ ኣርኣያ መቀሌ ከመምጠጣታ በፊት መጥርያም ደርሳት ነበር ምን ይሁንና…..

በመጨረሻ በጀኔራለ ሓየሎም ታሪክ ለመፃፍ ብዙ ወጥመዶች በጣጥሶ ሃቀኛ ታሪክ ለህዝብ እንዲደርስ ያደረገ ፀሃፊ ሰለሞን ገ/አረጋዊ እጅጉን ምስጋና ይገባዋል። ሰለሞን አሁንም በትግርኛ የተፃፈዉ የጀኔራል ሓየሎም አርአያ ታሪክ ባማርኛ የተተረጎመዉ ቶሎ ብሎ ታተሞ ለመላዉ ኢትዮጵያዊ እንዲደርስ ማድረግ ሳትታክት ተሯሯጥ። ሃቀኛ ታሪክን ሊቀብሩ የሚፈልጉት አይሳካላቸውም ዘመኑ 21ኛ ክፍለ ዘመን ነውና። የጀኔራል ሓየሎም አርአያ ታሪክ መደበቅና ለሁሉም ፀረ-ፋሽስታዊ ደርግ ለተሰዉ አርበኞች ኢትዮጵያውያን ታሪክ መስረቅና እንደ መቅበር ይቆጠራል።

በመጨረሻ ኣንድ ኣንድ ወገኖች ፀረ ፋሽሽት ደርግ የተደረገው ጦርነት የእርሰ በርስ ጦርነት ብለው ይተረጉሙታል በኔ እምነት ግን የደርግን ፋሺዝም መዋጋት ከፋሽሽታዊ ጣልያንና ከሌሎች የባእድ ወራሪዎች ከተደረገው ጦርነት እኩል ኣድርጌ ነው የምመለከተው በማናቸውም ፓርቲ ተሰልፈው ከህውሓት ከኢህኣፓ፤ ከግግሓት ከጠራናፊት፤ ከኢዱዩ፤ ከኦብነግ፤ ከኦነግ፤ ከጋንቤላ፤ ከኣፋር፤ ከሱማሌ ፓርቲዎች ተሰልፈው ለደርግ እየተዋጉ የነበሩ ሃይሎች ኣርበኞች ኣድርጌ ነው የምመለከታቸው፡፡ እርሰ በርስ ጦርነት ተብሎ መገለፅ የለበትም ለደርግ ለመቃወም በርሃ ወጥተው በማይረባ ልዩነቶችና ኣለመቻቻል በተፈጠረው እርሰ በርሳቸው ጦርነት የተፋጁት ነው መውቀስ ያለባቸው፡፡ ይህ እርስ በርስ ጦርነት የምለው ያለሁ ከ 1983ዓ.ም የነበረ ነው፡፡ለሌላ ትርጉም እንዳይሰጠው፡፡

↧

Video: የአንዱአለም አራጌ ታሪክ በዳንኤል ተፈራ

$
0
0
↧

በእስራኤል የኢትዮጵያን እናድን ማኅበር የሳዑዲውን የወገን እልቂት ለማስቆም 8 ጥያቄዎችን አቀረበ

$
0
0


// ]]>
Save Ethiopian Unity Association in Israel (2)

(ዘ-ሐበሻ) በ እስራኤል ሐገር የሚገኘው የኢትዮጵያን እናድን ማኅበር በቴላቪቭ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በፃፈው ግልጽ ደብዳቤ በሳኡዲ አረቢያ የወገኖቻችንን እልቂት ለማስቆም 8 ጥያዊዎች በአስቸኳይ እንዲመለሱ ጥሪ አቀረበ። “የኢትዮጵያ መንግስት ፈጥኖ ለዜጐች ማድረግ የሚገባውን ህይወትን የማትረፍ ተግባር ባለማከናወኑ እስከዛሬ ከተገደሉና የአካል ጉዳት ከደረሰባቸው በተጨማሪ ቁጥራቸው ከ35000 /ሠላሳ አምስት ሺህ/ በላይ የሚሆን በሳኡዲ አረቢያ የሚገኙ ወገኖቻችን ህይወታቸው ለአደጋ ተጋልጦ ይገኛል።” ሲል ለኢምባሲው ደብዳቤ የጻፈው ማህበሩ ደብዳቤውን ቀጥሎም “ስለሆነም አንድን ሃገር እመራለሁ የሚል መንግስት ቀዳሚ ተግባሩ የሀገርንና የሚመራውን ህዝብ ሁልንተናዊ ደህንነት የመጠበቅና የማስጠበቅ ብሔራዊ ኃላፊነት ያለበት መሆኑ ይታወቃል። ከዚህ እውነታ በመነሳት ከዚህ በታች ያቀረብናቸውን ጥያቄዎች በአስቸኳይ ለኢትዮጵያ መንግስት በማሣወቅ ወገኖቻችን ከተደቀነባቸው የሞት አደጋ ይተርፉ ዘንድ ኤንባሲው የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ እንጠይቃለን።” ይላል።

ሙሉውን ግልጽ ደብዳቤ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

↧

“የህሊና እስረኛ መሪዎቻችን ላይ በሐሰት መፍረድ ህዝበ ሙስሊሙ ላይ መፍረድ ነው”–ድምጻችን ይሰማ

$
0
0

ከድምፃችን ይሰማ የተሰጠ መግለጫ

ማክሰኞ ሕዳር 17/2006

ከመንግስታዊው እስልምና መምጣት በኋላ የህዝበ ሙስሊሙን ድምጽ ለማሰማት የመንግስት ዋነኛ ቢሮዎች ድረስ የደረሱት መሪዎቻችን ዛሬ በግፍ እስር እየተጉላሉ ይገኛሉ፡፡ የህዝብን ድምጽ አሻፈረኝ ያለው መንግስት እያደረሰው ያለው ግፍ አሁንም በህዝበ ሙስሊሙ ላይ እንደቀጠለ ነው፡፡ አሁንም መድረሳዎች በመንግስታዊው እስልምና አጫፋሪዎችና የእነሱን ፍላጎት ለማስፈጸም በሚያጅቧቸው ጠመንጃዎች እየተነጠቁ፣ አላህ የሚመለክባቸው መስጂዶች እየተወረሱ ነው፡፡
muslim1

መስጂዶቻችንን ተራ በተራ እየቀሙና እያስቀሙ ያሉት አካላት አንዳችም ህጋዊ መሰረት ባይኖራቸውም ድርጊታቸውን ግን ቀጥለውበታል፡፡ ሜክሲኮ የሚገኘውና በተለምዶ ጀርመን ግቢ ተብሎ የሚጠራው መስጂድም በመንግስታዊው እስልምና አጋፋሪዎች ሊወሰድ መሆኑን መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡ በዚህ ሁሉ በደል መሀል ትእግስት አድርጎና ለመንግስት ነገሮችን በጥሞና የማሰቢያ የእፎይታ ጊዜ ሰጥቶ እየጠበቀ ያለው ህዝበ ሙስሊም የሚደረገውን በደል ሁሉ ያያል፤ ተከታታይ በደል ባላሸነፈው ወኔውም በአላህ ፈቃድ እስከመጨረሻው ይታገላል!

ኢትዮጵያዊው ህዝበ ሙስሊም እስካሁን መስዋእትነት ሲከፍልለት የቆየውን ሃይማኖታዊ ነጻነቱን ሳያገኝ ዳግም እንቅልፍ የሚወስደው አይደለም፡፡ ሲማረው ካደገው እስላማዊ ታሪኩ፣ በቅርብም ድምጹን ሊያሰሙ ዋጋ ከከፈሉለት መሪዎቹና ዳኢዎቹም ላመኑበት አላማ መስዋእትነት መክፈልን ወርሷል፡፡ ምንም እንኳን ዛሬ በዚያ በጎ አላማ ስር ያሰለፉን እነዚያ ብርቅዬ መሪዎቻችን በእስር ቢገኙም መንፈሳቸው ግን አልታሰረም፤ አካላቸው እንጂ ስብእናቸው አልተፈተነም፡፡ ይህንንም ነው በመንግስት ቀጥታ ትእዛዝ እንደልብ በሚጠመዘዘው ችሎት ስር ሆነው ህዳር 23 እየተቃረበ ሳለ ደጋግመን የምናስታውሰው፡፡ ቀኑ በቀረበ ቁጥር የከፈሉትን መስዋእትነት፣ ቃል የገቡለትን አላማ አስፈላጊነት ደጋግመን እያስታወስን ታሪክ መዝግቦ የሚያስቀምጠውን አካሄድ እንታዘባለን፡፡ እስካሁን ለመንግስት ነገሮችን በጥሞና ለማሰብ ከሰጠነው ጊዜ አንጻርም በቀጣይ የሚኖረንን የትግል ስልት ካሁኑ ወኔያችንን እያደስን ልንጠብቅ ይገባል፡፡

ኢትዮጵያዊው ሙስሊም መብቱን ያውቃል፤ ይፈልጋል፤ በሰላማዊ መንገድ ይታገልለታልም – እስከመጨረሻው!

ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

↧
↧

ፖሊስ ኢትዮ-አሜሪካዊው በሜሪላንድ ሚስቱን እና ልጁን ገድሎ ራሱን አጥፍቷል አለ

$
0
0

New Picture (13)
ባለፈው ሳምንት ኢትዮ-አሜሪካዊው ቢኒያም አሰፋ፣ ባለቤቱ እና ልጁ በቤት ውስጥ ሞተው መገኘታቸውን ዘ-ሐበሻ የሜሪላንድ የዜና ማሰራጫዎችን መዘገቧ ይታወሳል። በወቅቱ ለ3 ሰዎች ሞት ተጠያቂው ማን እንደሆነ ያልተገልጸ የነበረ ቢሆንም፤ የባልቲሞር ፖሊስ በዚህ የሶስት ሰዎች ህይወት መጥፋት ዙሪያ ደረስኩበት ባለው የምርመራ ውጤት ላይ በሰጠው መግለጫ “አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ሶስት የቤተሰብ አባላት የተገደሉት በአቶ ቢኒያም አሰፋ ነው” ብሏል። ፖሊስ ኢትዮአሜሪካዊው ቢኒያም ሚስቱን እና ልጁን ከገደለ በኋላ ራሱን አጥፍቷል ብሏል። ለበለጠ መረጃ የኤስቢሲ ባልቲሞር ቲቪ ዘገባ የሚከተለው ነው።
አቶ ቢኒያምን የምታውቁ በኮመንት ላይ አስተያየታችሁን ብትጽፉ ብዙ ወገኖች መረጃ ሊያገኙ ይችላሉ።

↧

በታላቁ ሩጫ ሕዝቡ በሳዑዲ ላይ ተቃውሞውን ሲያሰማ ነበር፤ ሕዝቡ “አዝኗል ሀገሬ”እያለ ዘፍኗል –ሪፖርተር

$
0
0

“ሥራ አጥነት የስደት አበሳ ማብቂያው ቅርብ ላለመሆኑ ማስረጃ” በሚል ርዕስ ሪፖርተር ጋዜጣ ባስነበበው ዜና ትንታኔ “ታላቁ ሩጫ እሑድ ኅዳር 15 ቀን 2006 ዓ.ም. በጃንሜዳ ሲካሄድ ተሳታፊው ሁለት ስሜቶችን እኩል ለማስተናገድ ሲታገል ተስተውሏል፡፡ አንዴ የሐዘን ደግሞ ወዲያው የደስታ ስሜቱን ሲያስተጋባ ታይቷል፡፡” ብሏል።
የሪፖርተር (የብርሃኑ ፈቃደ 0 ዘገባ እንደወረደ፦

የተቃውሞ ድምፁን በሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት ላይ ሲያሰማ ተደምጧል፡፡ የተቃውሞ ድምፁ የወቅቱን የኢትዮጵያን ስደተኞች እንግልት ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ በተቃወመበት አፍታ ደግሞ ዋልያዎቹን እያወደሰ ይደሰታል፡፡ መንግሥትንም በአሽሙር ይሸነቁጣል፡፡ የአርቲስት ስለሺ ደምሴ (ጋሽ አበራ ሞላ) አዲሱ ‹‹ኧረ ያምራል አገሬ›› ዘፈን፣ በሯጩ ሕዝብ ‹‹ኧረ አዝኗል አገሬ›› ተብሎ ተዘፍኗል፡፡

ከታላቁ ሩጫ ባሻገር የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሁኔታ በቢቢሲና በሌሎች የመገናኛ ብዙኃንም መነጋገሪያ ሆኖ ከርሟል፡፡ በሩጫው ዕለት ከሰዓት ቢቢሲ ‹‹ዎርልድ ሀቭ ዮር ሴይ›› በሚባለው ፕሮግራሙ ሁለት ኢትዮጵያውያንንና አንዲት ሳዑዲትን አሟግቷል፡፡ ኢትዮጵያውያኑ ስለስብዕናና ስለሰብዓዊነት አጥብቀው ሞግተዋል፡፡ ሙግታቸውም በርትዕ ነበርና መሬት ጠብ አላለም፡፡ ሳዑዲቷ በአገሯ ፖሊሶችና በመረን ነዋሪዎች ኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች ላይ የተፈጸመውን ግፍ ልታናንቀው ብትሞክርም አላዋጣትም፡፡ ይልቅም በአግባቡ ባልሠለጠኑ ፖሊሶች የተወሰደ ዕርምጃ ነው፣ በማለት ልትለሳለስ ስትሞክር ታየች፡፡ የሳዑዲ መንግሥት የወሰደው ዕርምጃ የአገሩን ኢኮኖሚ መሠረት በማድረግ እንደሆነ ቢነገርም፣ ዕርምጃው ግን አሳማኝ ምክንያት እንዳልሆነ ይህ ጽሑፍ ለማሳየት ይሞክራል፡፡ ከዚህ በፊት ስለወቅታዊው የተመድ ሪፖርት መመልከት ይበጃል፡፡

great runከሳዑዲው አደጋም ቀድሞ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ አምሳያ ከሆኑ ድሃ አገሮች የሚሰደዱ ዜጎች ላይ ሰው ማሰብ ከሚችለው በላይ የሆኑ ኢሰብዓዊ፣ የክፋት ተግባራት ሲፈጸሙ ዓለም በዝምታ ስትመለከት ቆይታለች፡፡ ስደተኞች የውስጥ አካላቸው እየተጎለጎለ ሲወጣ፣ በየበረሃው እንደውዳቂ ዕቃ የተጣሉ ኢትዮጵያውያን ጥቂት አይደሉም፡፡ በባህር ጉዞ ለአሳነባሪ የተወረወሩ፣ ሰጥመው የቀሩ፣ የየብስና የባህር ቀለብ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ቤቱ ይቁጠራቸው፡፡ የሳዑዲው ግን በጠራራ ፀሐይ፣ በአደባባይ የተፈጸመ አሰቃቂና አዋራጅ ተግባር መሆኑ አሳቀቀን እንጂ ከዚህም የከፉ የሰቀቀን ድርጊቶች በኑሮ ፈላጊና ነገን ናፋቂ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ ሲፈጸሙ ኖረዋል፡፡ ስደት ግን የሚቆምም ወይም የሚገታ አይመስልም፡፡

ከሰሞኑ ይፋ የተደረጉ የኢኮኖሚ ሪፖርቶች ስደትና ስደተኞችን ይብቃችሁ ለማለት የሚያስደፍሩ አይደሉም፡፡ ይልቁንም መጪውን ጊዜ ‹‹አስፈሪ›› እንደሚያደርጉት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ይፋ አድርጓል፡፡ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የንግድና የልማት ኮንፈረንስ ተቋም በኩል ይፋ የተደረገው፣ በልማት ኋላ የቀሩ አገሮች ሪፖርት፣ የኢትዮጵያን ጨምሮ የ49 አገሮችን አበሳ ይፋ አድርጓል፡፡ የሥራ ዕድል፣ የሕዝብ ቁጥር መጨመርና፣ የአመራረት ስልትና አቅም ያተኮረባቸው ነጥቦች ናቸው፡፡

ኢትዮጵያን ጨምሮ እነዚህ ኋላቀር አገሮች፣ በፍጥነት ለሚጨምረው የሕዝብ ቁጥራቸው ተመጣጣኝ የሥራ ዕድልና የገቢ ምንጭ እየፈጠሩ አለመሆናቸውን አስታውቋል፡፡ ምንም እንኳ ኢኮኖሚያቸው እያደገ ቢሆንም፣ የሚፈጥሩት ሥራና የገቢ ምንጭ ግን አስፈሪ ልዩነት እንደሚታይበት ይፋ ሆኗል፡፡

ባለፈው ሳምንት በ30 አገሮች አማካይነት ለመላው ዓለም ይፋ የተደረገው የተመድ ሪፖርት፣ ኋላቀር አገሮች በየዓመቱ ከ16 ሚሊዮን ላላነሱ ሕዝቦች የሥራ ዕድል መፍጠር ይጠበቅባቸዋል ብሏል፡፡ ይህን ሲያደርጉ በየዓመቱ ለሥራ ብቁ ሆነው ወደ ገበያው ለሚገቡ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ይችላሉ፡፡

የድሃ አገሮች የኢኮኖሚ ዕድገት በአብዛኛው ወደውጭ በሚላኩ ጥሬ ዕቃዎችና የማዕድናት ሽያጭ ላይ ተመርኩዘው የውጭ ምንዛሪ ገቢን ያገኛሉ፡፡ እንደ ተመድ ሪፖርት ደግሞ በዚህ ዘርፍ ላይ የተመረኮዘ ኢኮኖሚ የሚወዛወዝ ሸምበቆ ነው፡፡ ይኸውም የዓለም ገበያ ለእነዚህ ምርቶች በየጊዜው የሚሰጠው ዋጋ ስለሚዋዥቅና ድሆቹን አገሮች ተጋላጭ ስለሚደርግ ነው፡፡

ይህ ባለበት የድሃ አገሮች የሕዝብ ቁጥር ዕድገት በመጪዎቹ 25 ዓመታት በእጥፍ አድጎ 1.7 ቢሊዮን ይደርሳል፡፡ የድሃ አገሮች ከ60 በመቶ በላይ የሕዝብ ቁጥራቸው ከ15 እስከ 25 ዓመት ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፣ በዓለም ላይ ከሚኖሩ አራት ወጣቶች አንዱ በምስኪኖቹ አገሮች ውስጥ እንደሚኖር ይጠበቃል፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት 168 ሚሊዮን የነበረው የወጣቱ ሕዝብ ቁጥርም ከሩብ ክፍለ ዘመን በኋላ 300 ሚሊዮን ይደርሳል ተብሎ ይገመታል፡፡

እንዲህ የሚገሰግሰው የሕዝብ ቁጥርን የሚመጣጠን የሥራ ዕድልም ሆነ የኢኮኖሚ ዕድገት በድሆች አገሮች እየተመዘገበ አይደለም ያለው ተመድ፣ በዚህ አሥር ዓመት ውስጥ ብቻ 95 ሚሊዮን የሥራ መስኮችን ወደሥራው ዘርፍ ለሚገቡ የጉልበት ገበያው ተሳታፊዎች ተዘጋጅተው መጠበቅ አለባቸው፡፡

የተመድን የድሃ አገሮች ሪፖርት በአዲስ አበባ፣ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በመገኘት ይፋ ያደረጉት፣ የድሃ አገሮች ጉዳይ ዳይሬክተር ኢትዮጵያዊው ዶ/ር ተስፋቸው ታፈረ ናቸው፡፡ በፍጥነት እያደገ የሚገኘው የድሆች አገሮች ሕዝብ ቁጥር፣ ወደአስፈሪነት ደረጃ እየገሰገሰ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ኢትዮጵያን ጨምሮ በድሆች አገሮች የሚመዘገበው የኢኮኖሚ ዕድገት ለሥራ ብቁ በሆነው የዕድሜ ክልል ላይ የሚገኙ ወጣቶችን ለማስተናገድ እጅግ የሰለለ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ጉዳይ

በየዓመቱ በኢትዮጵያ ለሠራተኛነት አቅመ ዕድሜ ደርሰው ሥራ የሚፈልጉ ወጣቶች ቁጥር ከዘጠኝ ዓመት በፊት በነበረ አሃዝ መሠረት 1.4 ሚሊዮን በላይ ነው፡፡ ይህ እንግዲህ በአሁኑ ወቅት በየዓመቱ ሥራ እንደሚፈልግ የሚታወቀው ሕዝብ ቁጥር ነው፡፡ በመጪዎቹ 25 ዓመታት ውስጥ በእጥፍ ሲጨምር የሥራ ፈላጊው ቁጥር ከ2.7 ሚሊዮን በላይ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በኢትዮጵያ እየተመዘገበ የሚገኘው የኢኮኖሚ ዕድገት በተመድ አሃዝ መሠረት ሰባት ከመቶ ነው፡፡ በአንፃሩ እየተፈጠረ የሚገኘው የሥራ ዕድል በዓመት ሦስት ከመቶ ያልዘዘ በመሆኑ ኢኮኖሚው የቱንም ያህል ፈጣን ቢሆን፣ በቂ የሥራ ዕድል የሚፈጥር ሆኖ አልተገኘም፡፡ በመሆኑም መጪውን ጊዜ፣ በተመድ አገላለጽ አስፈሪ ያደርገዋል፡፡

መንግሥት በሚያካሂዳቸው ፕሮጀክቶችና ልዩ ልዩ ግንባታዎች አማካይነት በየዓመቱ ከፍተኛ የሥራ ዕድል መፈጠሩን አስታውቋል፡፡ በ2005 በጀት ዓመት ብቻ ከሁለት ሚሊዮን በላይ የሥራ ዕድል መፈጠሩን የከተማ ልማት፣ የቤቶችና የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወሳል፡፡ መንግሥት በሚያካሂዳቸው ግንባታዎች አማካይነት የሚፈጠሩት የሥራ መስኮች በተባበሩት መንግሥታት ዕይታ ለዘለቄታው አስተማማኝ አይደሉም፡፡ እምነትም አይጣልባቸውም፡፡ መጠነ ሰፊ ሊባሉ የሚችሉ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች በኢትዮጵያና በሌሎች ድሆች አገሮች እየተገነቡ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ፕሮጀክቶች ግን የቱንም ያህል የሥራ ዕድል ቢፈጥሩና በርካቶችን ቢደጉሙ፣ ለጊዜያዊ ካልሆነ በቀር በወቅታዊነታቸው ምክንያት ተመራጭ የሥራ መስኮች ሆነው እንዳይወሰዱ ተመድ አሳስቧል፡፡

በዚህ መንገድ የሚጓዙ አገሮች በተሳሳተ የፖሊሲ አቅጣጫ እየሾፈሩ መሆናቸውንም የተመድ ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ግን ከሚታሰበው በላይ የሥራ ዕድል መፍጠራቸውን፣ ይህም መንግሥት ባካሄደው የመሠረተ ልማት ግንባታ የተገኘ መሆኑን በመጥቀስ ሲገልጹ ይደመጣሉ፡፡ በአንፃሩ የሚገነቡት መሠረተ ልማቶች የግሉን ዘርፍ ለማበረታታትና ወደኢኮኖሚው ለመሳብ ድልድይ እንደሆኑ ተመድ ይተነትናል፡፡ የኢኮኖሚ ዕድገቱን የግሉ ኢኮኖሚ ክፍል መምራት እንዳለበትም በመፍትሔነት አመላክቷል፡፡ ከዚህ ባሻገርም ድሆች አገሮች በቴክኖሎጂ ምርጫቸው ላይ ጥንቃቄ እንደሚጎድላቸው ዶ/ር ተስፋቸው አብራርተዋል፡፡ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂን እናስፋፋለን በሚሉ አገሮች ውስጥ፣ ኮምፒውተር ለማስገባት ሲፈለግ የሚጠየቀው ከፍተኛ ታክስ ለዚህ ምስክር ነው ይላሉ፡፡

በአንድ ጎኑ የኢትዮጵያ መንግሥትም ይህነኑ እውነታ ይቀበለዋል፡፡ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በተመድ ይፋ የተደረገው ሪፖርት የያዛቸው አንኳር ሥጋቶችን እንደሚጋራ አስታውቋል፡፡ የሚኒስቴሩ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር አብርሃም ተከስተ እንዳረጋገጡት፣ መንግሥታቸው በተመድ ይፋ የተደረጉትን ትችቶችና ሥጋቶች ይቀበላል፡፡ የኢኮኖሚው ዕድገት ወዲያውኑ ሥራ አለመፍጠሩን አስታውቀዋል፡፡ ይህም ቢባል ግን የመንግሥት ኢንቨስትመንት መሠረታዊ አገልግሎቶችን ለማቅረብና ዕድገቱን ለማቀጣጠል ወሳኝ በመሆኑ የመንግሥት የፖሊሲ አጀንዳ ሆኖ እንደሚቀጥል ተናግዋል፡፡ በኢትዮጵያ ከ26 ከመቶ በላይ የሥራ አጥ ቁጥር መኖሩን መንግሥት ይፋ አድርጓል፡፡ ይህ ሥራ አጥነት በገጠሩ የሚኖረውን ወጣት የሚያካትት አይመስልም፡፡

ክሬዲት ስዊስ የተባለው የጥናት ተቋም በቅርቡ ይፋ ያደረገው ሪፖርት እንደሚያትተው ድሆች ድሆች ሆነው፣ ሀብታሞችም የበለጠ ሀብታም ሆነው እንደሚቀጥሉ የሚያመላክት ነው፡፡ ኢትዮጵያና በተርታዋ የሚሰለፉ ድሆች አገሮች በመጪዎቹ አምስት ዓመታት ውስጥ በቤተሰብ ደረጃ ይኖራቸዋል ተብሎ የሚጠበቀው ሀብት ከአምስት ሺሕ ዶላር በታች ነው፡፡ በአንፃሩ ሀብታሞቹና እንደቻይና ያሉት ተንደርዳሪ አገሮች፣ በአምስት ዓመት ውስጥ የሚኖራቸው ሀብት በቤተሰብ ደረጃ ተደምሮ፣ 334 ትሪሊዮን ዶላር ተገምቷል፡፡ በአሁኑ ወቅት የዓለማችን ሀብታሞች ያካበበቱት ሀብት ከ241 ትሪሊዮን ዶላር በላይ ነው፡፡ በዚያም ላይ የዓለም ሚሊየነሮች ቁጥርም 47 ሚሊዮን እንደሚሆን የመጪዎቹ አምስት ዓመታት ግምቶች ይናገራሉ፡፡

የሳዑዲዎች ምክንያት

እንዲህ ክፉኛ የተራራቀው የሀብታሞችና የድሆች አኗኗር፣ በገዛ አገራቸው ሠርቶ ለመኖር ያዳገታቸውንና ጥሩ እንጀራ ፍለጋ የሚባዝኑትን ሰዎች ብዛት በየጊዜው እንዲያሻቅብ ለማድረጉ ጠቋሚ ነው፡፡

ለተሰዳጅ ምስኪኖች ምቹ ከሆኑ ምክንያቶች ውስጥ በአገሬው ዘንድ የተጠሉ የሥራ መስኮች ላይ የውጭ ዜጎች እንዲንሰራፉባቸው መመቸታቸው ነው፡፡ ሳዑዲዎች የኢትዮጵያ መንግሥት ዜጎች ለሥራ ወደ ዓረብ አገር እንዳይሄዱ ለወራት የመከልከሉን ዜና ከማሰማቱ አስቀድመው፣ በየወሩ ከአሥር ሺሕ በላይ ኢትዮጵያውያንን ለቤት ውስጥ ሥራና ሠራተኛነት እንደሚፈልጉ አስታውቀው ነበር፡፡ ይህንን መግለጫ ሲሰጡም በሁለት ኢትዮጵያውያን የቤት ሠራተኞች አመካይነት ሕፃናት መገደላቸውን ሰበብ አድርገው ነበር፡፡ መንግሥት ኢትዮጵያውያን ያስፈልጉናል የሚለውን መግለጫ ለማውጣት ተገድዶ የነበረው፣ አብዛኛው የሳዑዲ ሕዝብና ሚዲያው፣ በሳዑዲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በጅምላ ወንጀለኛ ብሎ መፈረጁን በመቃወም ነበር፡፡

ሳዑዲዎች በዝቅተኛ የሥራ መደብ ላይ ለመሥራት ፍላጎት የሌላቸው በመሆኑ ሳቢያ እንደ ኢትዮጵያ ካሉ የድሃ አገር ዜጎች ላይ ጥገኛ ለመሆን መገደዳቸው ወድደውና ፈቅደው ያደረጉት ነበር፡፡ ሆኖም ኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች ላይ የሚደርሰው ሰቆቃ ቀድሞም የተንሰራፋ ነበር፡፡ የአሁኑን ሰቆቃ ያባባሰው ግን የሳዑዲ መንግሥት በራሱ ፖሊሶች በወሰደው ዕርምጃ ጭምር የተፈጸመ መሆኑ ነው፡፡ ለሰባት ወራት የጊዜ ገደብ በመስጠት ከአገር ውጡ ያላቸው ሰነድ አልባ ዜጎች፣ በቀነ ገደቡ አልወጡም በማለት በፖሊስ የተወሰደው ዕርምጃ ከጭካኔ በላይ አረመኔያዊነት ባህርይ እንዳለው በማኅበራዊ ድረ ገጾች በመጋለጡም ነበር፡፡

የሳዑዲ መንግሥት ዜጎችን ከአገር ሲያባርር ምክንያት ካደረጋቸው ነጥቦች ውስጥ ኢኮኖሚ አንዱ ነው፡፡ ይኸውም እየጨመረ ለሚገኘው የሳዑዲ ሕዝብ፣ የሥራ መስኮችን ለማፋፋት ያለመ ነው፡፡ በዝቅተኛ የሥራ መስኮች ላይ ለመሰማራት አገሬው ድፍረቱም ፍላጎቱም ባይኖረውም ቀስ በቀስ ይላመደዋል የሚል ምክንያት መሰጠቱን ሮይተርስ አስነብቧል፡፡ ይህ ግን አገሪቱ ላይ ወቅታዊ ሊባል የሚችል ጫና ማሳደሩን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ቢያንስ በመካከለኛ ትራንስፖርት ዘርፍ በሹፍርና የተሰማሩ በርካታና ኢትዮጵያውያንና ሌሎችም ዜጎች በመባረራቸው ዕቃዎችን ለማጓጓዝ የሚጠይቀው ወጪ በከፍተኛ መጠን ጨምሯል፡፡

የቢቢሲዋ ሳዑዲት ጨምሮ በርካቶቹ እንደሚስማሙበት፣ በዝቅተኛ ሥራዎች ላይ ተሰማርተው የነበሩ ሰዎች ከሳዑዲ መባረራቸው ገንዘብ ለማዳን እንደረዳቸውም ይናገራሉ፡፡ ይኸውም ስደተኞቹ የለፉበትን ገንዘብ ወደየአገሮቻቸው፣ ወደየዘመዶቻቸው ይልኩታል፡፡ ብዙ ገንዘብ ከሳዑዲ ይወጣል፡፡ አሁን ግን ያን ገንዘብ እዚያው ሳዑዲ ስለሚቀር፣ ሸማቾች ለፍጆታ እዚያው አገራቸው ውስጥ የሚያውሉት ተጨማሪ ገንዘብ ይኖራቸዋል፡፡ ይሄ ደግሞ ለኢኮኖሚው የሚፈለግ ምክንያት ነው የሚል መከራከሪያ ይቀርባል፡፡ ከተሰነዘሩት መላምቶች ይሄ ብቻ ሚዛን ሊደፋ ይችላል፡፡ ሆኖም ሳዑዲዎች ወደማጀቱና ወደሌላውም ዝቅተኛ ሥራ መግባት እስከቻሉ ድረስ ብቻ ነው፡፡ ይሄ ደግሞ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚለወጥ አይደለም፡፡

ስለዚህ የሳዑዲ መንግሥት ከየአገሩ የተጠራቀሙትን ምስኪን ስደተኞች ለማስወጣት ያስቀመጠው ኢኮኖሚያዊ ምክንያት ብዙም ሚዛን የሚደፋም ባይሆንም፣ ከአገሩ ማባረር የግዛት መብቱ በመሆኑ ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን እምቢ ማለት አይቻልም፡፡ በሰው አገር ውጣ ሲባል አልወጣም ማለትም የሚሆን አይደለም፡፡ ሰውን እንደእንስሳ በየጎዳናው ማሰቃየትና መግደል ግን አረመኔነት ነው፡፡ ኢትዮጵያውያኑን በቢቢሲ መስኮት ልትሞግት የከጀለችው ሳዑዲት ሰዎችን እንዴት ማባረር እንዳለባቸው ባልሠለጠኑ ሰዎች የተወሰደ ዕርምጃ ነው ለማለትና ለማስረዳት ሞክራለች፡፡ የቱንም ያህል ምክንያት ቢቀርብ ሲደረግ የታየው የሳዑዲ መንግሥትና ዜጎቹን ጭካኔ ያጋለጠ ተግባር ነው፡፡ ከኢኮኖሚያዊ ምክንያቱ ይልቅ ሌላ ሰበብ እንደሚመዘዝበት ያመላክታል፡፡

ከኢትዮጵያ ዜጎች ባሻገር በብዙ መቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከሳዑዲ ሲወጡ ምነው አልተገደሉ? ምነው ሰብዓዊ ክብራቸው አልተዋረደ? ለምን ኢትዮጵያውያን ብቻ? ለእነዚህ ጥያቄዎች የመላምት ሰበቦችን የሚያቀርቡ ጥቂት ኢትዮጵያውያን ተቺዎች፣ መንግሥት ወደሳዑዲና ወደሌሎችም አገሮች ኢትዮጵያውያን እንዳሄዱ በመከልከሉ የተወሰደ የከሰረ የበቀል ዕርምጃ ያደርጉታል፡፡

ስደት በዚህ አስከፊ ገጽታው ሊቀጥል እንደሚችል ሥጋት የገባው ተመድ፣ እያደገ የሚገኘውን የሕዝብ ቁጥርና የኢኮኖሚ ዕድገት ደረጃ ምክንያት ማድረጉ ወቅታዊ ያደርገዋል፡፡ ለኢትዮጵያውያን ስደተኞች ‹‹የሮጠ አይቅደምህ፣ የታገለ አይጣልህ›› የሚለው የአበው ምርቃት ከምንጊዜውም በላይ አሁን ሊያስፈልጋቸው እንደሚችል አንጋፎቹ ሲናገሩ ተደምጧል፡፡

ምንጭ፦ http://ethiopianreporter.com/index.php/business-and-economy/item/4146-%E1%88%A5%E1%88%AB-%E1%8A%A0%E1%8C%A5%E1%8A%90%E1%89%B5-%E1%8B%A8%E1%88%B5%E1%8B%B0%E1%89%B5-%E1%8A%A0%E1%89%A0%E1%88%B3-%E1%88%9B%E1%89%A5%E1%89%82%E1%8B%AB%E1%8B%8D-%E1%89%85%E1%88%AD%E1%89%A5-%E1%88%8B%E1%88%88%E1%88%98%E1%88%86%E1%8A%91-%E1%88%9B%E1%88%B5%E1%88%A8%E1%8C%83

↧

የሳዑዲ ጉዳይ የዛሬ አዳዲስ መረጃዎች –በነብዩ ሲራክ (ጋዜጠኛ)

$
0
0

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ከ40 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገራቸው ገብተዋል ይሉናል፤ የሳዑዲ ባለስልጣናት ደግሞ 28 ሺህ ኢትዮጵያውያንን ነው ወደ ሃገራቸው የላክነው ይላሉ። ዶ/ር ቴዎድሮስ 13 ሺህ ሰው ከየት ሸቅበው ነው?… ለማንኛውም ሳዑዲ አረቢያ የሚገኘው ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ የሚሰጠንን አዳዲስ መረጃዎች ይመልከቱ…

ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ በፌስቡክ ገጹ እነዚህን አዳዲስ ነገሮች አካፍሎናል፦

* ጅዳ …. ትናንት ከጅዳ ቆንስል አካባቢ ወደ ሽሜሲ ማቆያ እስር ቤት ከሌሊት እስከ ምሽት የሔዱት ወገኖች ቁጥር 1.500 እንደሆነ ታውቋል። መሔዳቸውን ተከትሎ በርካታ የተጨበጡና ያልተጨበጡ መረጃዎች እየተሰራጩ ነው ።
saudi arabia today
በሚቀርቡት ቅሬታዎችን ለማረጋገጥ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት እዚያው ሺሜሲ ካሉት ጥቂት እህቶች አነጋግሬ ነበር። የምግብና የውሃ አቅርቦት ችግር እንዳለና ፣ ምግብ እና ውሃ ሲታድ ጉልበት ያለው ብቻ ተጋፍቶ እንደሚበላ እና እንደሚጠጣ ገልጸውልኛል። የሻንጣ ኪሎውን ክፍያ ጉዳይም ነግረውኛል ። እዚህ ላይ እኔም ግራ የተጋባሁ ቢሆንም በቀጣይ ሰአታት ሁሉም ግልጽ ይሆናል። ምሬታቸውን ግን ለሚመለከታቸው አሳውቄያለሁ። ትልቁ ነገር በአሁኑ ሰአት ሰነዶች እየተሰሩላቸውና አሻራ በወረፋ እየሰጡ መሆኑን ከሃላፊዎች የሰማሁትን ከእህቶች ማረጋገጤ ነው! በአጠቃላይ ጅዳ ያለው ሁኔታ በተሻለ መንገድ መሔድ መጀመሩን ከሚደርሱኝ መረጃዎች ተነስቶ መናገር ይቻላል። ምክርና ዝክሩ ሰሚ ቢያገኝ በሽሜሲ ያለውን ሃይል አጠናክሮ በአጭር ጊዜ የበለጠ መስራት ይቻል ይመስለኛል !

* መካና መዲና … በትናንትናው እለት በመካ “ወደ ሃገራችን እንግባ! ” በሚል ተከስቶ የነበረው ድጥጫና አለመግባባት ዛሬ ገብ ብሎ ታይቷል ። በተመሳይ ሁኔታ በተከሰተው የትናንቱ ፍጥጫ ለየት ያለ እንደነበርና በሁከቱ ምክንያት ሰበብ አጠይባ ዩኒቨርሲቱ ተዘግቶ እንደ ነበር ተመልክቷል።

ሪያድ … ባሳለፍናቸው ስምንት ቀናት 28.000 ኢትዮጵያውን ወደ ሃገር ቤት መሸኘታቸውን የሳውዲ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ይህ በእንዲህ አንዳለ በርካታ ኢትዮጵያውያን በየመጠለያው የመጸዳጃ ፣ የምግብና የውሃ አቅርቦት ችግር እንዳለ ችግሩ በሰፊው እንዳለ ወደሚነገርበት አሚራ ኑራ መጠለያ ስልክ በመደወል ያነጋገርኳቸው ሳይቀር ገልጸውልኛል። በሪያድ ሃላፊዎችን ላማነጋገር ያደረግኩት ሙከራ አልተሳካም ።

* ደማም … ወደ ሳውዲ ሰራተኛ መላክ አቁሟል ቢባልም በኤጀንሲዎች መሰሪ የተቀነባበረ ሴራ ዜጎች ወደ ሳውዲ እየገቡ ነው ። 60 ያህል በአብዛኛው ኦሮምኛ እንጅ ሌላ ቋንቋ የማይናገሩ እህቶች በኩዌት በኩል ወደ ሳውዲ ደማም መግባታቸውንና መኖሪያና የስራ ፈቃድ ለመውሰድ ምርመራ ማከናዎናቸውን መረጃ ደርሶኛል። ወደፊት ዘርዘር አድርገን እናወራዋልን …

ቸር ያሰማን

ነቢዩ ሲራክ

↧

በኢትዮጵያ ሙዚቃ እንደነገሠ 50 ዓመት የደፈነው አሊቢራ

$
0
0

በሚኒሶታ የኦሮሞ ስፖርት ፌስቲቫልን አስታኮ ባለፈው ጁላይ ላይ 50ኛ ዓመት የሙዚቃ አገልግሎቱ ቢከበርም፤ አሁን ደግሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ የዚህ ብርቅዬ አርቲስት 50ኛ ዓመት በዓል እየተከበረ ነው።
ግንቦት 18 ቀን 1940 ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ የተወለደው የክብር ዶ/ር አሊ መሐመድ ብራ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን ድሬዳዋ ከተማ በቀድሞዎቹ መድረስ ጅዲዳ እና በልዑል ራስ መኮንን ት/ቤቶች፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ በአዲስ አበባ ካቴድራል ት/ቤት ተከታትሏል። በኋላም ካሊፎርንያ በሚገኘው ሳንታ ሞኒካ ኮሌጅ በሙዚቃ የትምህርት ዘርፍ ከፍተኛ ትምህርት ተከታትሏል። አሊ ብራ 8 ቋንቋዎችን አቀላጥፎ መጠቀም ይችላል።
ali b
የፈረንጆቹ አመት 1963 አሊ ብራ ሙዚቀኛ ሆኖ ዳግም የተወለደበት ዓመት እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ። ይህ ዓመት አሊ ብራ በድሬዳዋ ከተማ ከነበረው የአፈረን ቀሎ የሙዚቃና የባህል ቡድን ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ በመድረክ ላይ ሙዚቃ የተጫወተበት ነበር።
አሊ ለመጀመሪያ ጊዜ በመድረክ የተጫወተው “ብራዳ በርሄ – Birraadahaa Barihee” የተባለውን እጅግ ተወዳጅ ዘፈኑን ነበር። ቤተሰቦቹ ያወጡለትን ስም አሊ መሐመድ ሙሳን በመቀየር አሁን ሁለተኛ ስሙ የሆነውና (Second name) በጊዜው ቅፅል ስሙ የነበረውን “ብራ”ን ከህዝብ ያገኘው ከዚሁ ዘፈኑ መሆኑ አመቱ አርቲስቱ አሊ የተወለደበት አመት የመሆኑን ነገር ያጠናክራል፣ ከዚህ በኋላ አርቲስቱ የተጓዘባቸው ሃምሳ አመታት በሀገራችን ሙዚቃ ታሪክ የራሱን ጉልህ ምዕራፍ የፃፈባቸውና፣ በዚህም ሂደት በርካታ ውጣ ውረዶችንና ፈተናዎችን አልፎ ለታላቅ ስኬት የበቃባቸው አመታት ናቸው።
የክብር ዶ/ር አሊ ብራ በተፈጥሮው ተሰምቶ የማይጠገብ፣ ሁሌም የሚወደድ እጅግ ማራኪ ድምፅን የተለገሰና ከፍተኛ የዜማ ተሰጥዖን የታደለ ነው። በዚህ ችሎታውና በብርቱ ጥረቱ እስከ አሁን ከ260 በላይ ድንቅ ዘፈኖችን ዜማዎችን ለሕዝብ አቅርቧል። አሊ ያለውን ቋንቋ የመማር ከፍተኛ ክህሎት በመጠቀም በኦሮምኛና በ8 የተለያዩ ቋንቋዎች (ሶማልኛ፣ አማርኛ፣ አፋርኛ፣ ሀረሪኛ፣ አረብኛ፣ እንግሊዝኛ፣ ኪስዋሂሊ እና ስፓንሽ) ሥራዎችን አቅርቧል። በሥራዎቹም በርካታ የሕይወትን ገፅታዎችን ዳሷል።
አሊ ጊታር፣ ፒያኖ፣ ኡድ እና ሌሎች የሙዚቃ መሳሪያዎችን የሚጫወት ሲሆን፣ ለራሱና ሌሎች በርካታ ግጥምና ዜማዎችን ደርሷል። የራሱን ለየት ያሉ የዜማ ቅንብርና የአዘፋፈን ስልቶች የፈጠረ አርቲስትም ነው።
አሊ በሀገራችን ታሪክ ታላላቅ ከሚባሉ የሙዚቃ ቡድኖች ጋር ሰርቷል። ከአርባ በላይ ሀገራት (በሁሉም አህጉራት) እጅግ በርካታ በሆኑ መድረኮችም ላይ ተጫውቷል። የአሊ ስራዎች አፋን ኦሮሞንና ሌሎች የዘፈነባቸውን ቋንቋዎች ለሚሰሙ ብቻ ሳይሆን በሁሉም የሙዚቃ አፍቃሪ ዘንድ እጅግ የሚወደዱ ትውልድና ዘመን ተሻጋሪ ሥራዎች ናቸው።
ዶ/ር አሊ ብራ የዘመነኛ (contemporary) ኦሮምኛ ሙዚቃ አባት ሲሆን ለሀገራችን ሙዚቃ፣ ባህል እና ስነ ጥበብ ማንሰራራት፣ እድገትና መጠበቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል። ለመጀመሪያ ጊዜ የታተመው የኦሮምኛ አልበም የአሊ ብራ ነበር። የእርሱን ፈለግ ለተከተሉ በርካታ ድምፃዊያን አርአያና መምህር በመሆንም አገልግሏል። በርካታ ወጣት ድምጻውያን ስራ ሲጀምሩ፣ ዘፈኖቹን፣ ለልምምድ እንደ አፍ መፍቻ፣ ስራቸውን ለማድመቅ እንደ ማጣፈጫ ሲገለገሉባቸው ኖረዋል። አሊ ምርጥ አርቲስቶችን ያፈራ የአርቲስቶች አባት ነው።
ዶ/ር አሊ ብራ የኢትዮጵያን ልዩ ልዩ ብሔረሰቦች ሙዚቃዎች በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት በስፋት ያስተዋወቀና ለተለያዩ ሕዝቦችና ባህሎች መገናኛ ድልድይ የሆነ የባሕል አምባሳደርም ነው። በርካታ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ምሁራን ሙዚቃዎቹን አጥንተዋል፣ ስለ ሙዚቃዎቹም በርካታ ጽሁፎችን ጽፈዋል።
አሊ ብራ፣ በሙዚቃ ዓለም በቆየባቸው ዘመናት በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ ወደር የሌለው የሕዝብ ፍቅርና አክብሮትን ተቀዳጅቷል። በሚሊዮኖች ሕሊና እና ልብ ውስጥም ልዩ ቦታ አለው።

ለስኬቶቹና ለአስተዋጽዖዎቹ እውቅና ከሰጡ የተለያዩ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ተቋማትም ከሃምሳ በላይ ታላላቅ ሽልማቶችንም አግኝቷል። ከጅማ ዩኒቨርስቲ ያገኘው የክብር ዶክትሬት ዲግሪ በእነዚህ ሽልማቶች አንዱ ነው።
አሊ ትምህርትና ጥበብ የዕድገትና የስኬት መሰረቶች መሆናቸውንና፣ አለመማር ሕሊናን እንደሚያሳውር በጽኑ ያምናል። ለአሊ፣ ትምህርት በመደበኛ ትምህርት ቤት የሚገኝና አእምሮን ብቻ የሚያሳትፍ ሂደት ሳይሆን፣ የሰው ልጅ እድሜ ልኩን በእያንዳንዱ እንቅስቃሴው የሚያካሂደውና ሁለመናን (አካልን፣ አእምሮን፣ መንፈስንና፣ ልቡናን) የሚያሳትፍ ሰፊና ረጅም ሂደት ነው።
አሊ ብራ፣ እነዚህን እምነቶቹን በዘፈኖቹ ውስጥ በማስተላለፍ ብዙዎችን እንዲህ ላለ የትምህርት ጉዞ አነሳስቷል፣ ራሱም እምነቱን በተግባር በመኖር አርአያና ምሳሌ ሆኗል።
አሁንም የወርቅ ኢዩቤልዩ በዓሉ መሪ ቃል “Barnootaa ammas Barnootaal -መማር አሁንም መማር!” እንዲሆን የወሰነ ሲሆን፤ መሪ ቃሉን በመከተል በበዓሉ አከባበር ዝግጅቶች ላይ በሙሉ ስለ ትምህርት የተለያዩ መልዕክቶች ይተላለፋሉ።
ዶ/ር አሊ ብራ ለሀገራችን እድገትና አዲሲቱንና የበለፀገችውን ኢትዮጵያ ለመፍጠር በተለይ በትምህርት ዘርፍ የሚያደርገው አስተዋፅዖ ስለ ትምህርት በማስተማር ብቻ የተወሰነ አይደለም።
አሊ “Birra Children’s Education Fund” የተባለ ምግባረ ሰናይ ድርጅት ከባለቤቱ ጋር አቋቁሞ ለሕፃናት ትምህርት ድጋፍ በመስጠት ላይ ይገኛል። ድርጅቱ አሁን በድሬዳዋ አካባቢ ባሉ ትምህርት ቤቶች ላይ እየሰራ ሲሆን፤ በቀጣይነት በመላው የሀገራችን ክፍሎች የተጠናከረ ሥራ ለመስራት እቅድ አለው።
በቀጣዩ የህይወት ክፍለ ጊዜው፣ አሊ ብራ፤ በዋነኝነት በሚከተሉትን ተግባራት ለማከናወን አቅዷል።
- የጀመረውን የበጎ አድራጎት ስራ ማስፋፋትና ማጠናከር፣ ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም እንዲደርስ መስራት፣
- ፈለጉን የተከተሉ አርቲስቶችን በአማካሪነት በመደገፍና፣ እውቀትና ልምዱን በማካፈል ለኪነጥበቡ እድገት ሲያደርግ የቆየውን አስተዋጽዖ መቀጠል፣
የዚህን ታላቅ ኢትዮጵያዊ ሙዚቀኛ የሃምሳኛ ዓመት ክብረ በዓልን የሚያዘጋጀው የፕራክሲስ ኢንተርናሽናል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆነው ወጣት ዘላለም ቻላቸው በአሉን ለምን ማክበር እንዳስፈለገም ይገልፃል።
አንደኛው አሊ ብራ ለሀገራችንና ለሙዚቃው ዓለም ትልቅ ስጦታ ነው። የአርቲስቱ ሕይወት፣ ስራዎቹ እና ያስመዘገባቸው ውጤቶች የታሪካችንና የትውፊታችን ጉልህ አካላት ስለሆኑ፣ ሊዘከሩ፣ ክብር ሊሰጣቸውና ሊጠበቁ ይገባል። እርሱም ላደረገው ሁሉ ተገቢው ክብርና ምስጋና ሊሰጠው ይገባል። ይህ የወርቅ ኢዩ ቤልዩ በአል እነዚህን በይፋና በተደራጀ መልኩ እንደሚደረግ ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል።
ሁለተኛው፣ አሊ ብራ በሃምሳ ዓመታት ጉዞው ላስመዘገባቸው ስኬቶች ዋነኛው መሰረት ከአፍሪቃዎቹ፣ ከአድናቂዎቹና ከህዝብ የተደረገለት ድጋፍና እርዳታ መሆኑን በፅኑ ያምናል። ስለዚህም በአሉ አሊ ለተዋለለት ውለታ ለእነዚህ ሁሉ ምስጋናውን የሚያቀርብበትና የደስታው ማዕድ ከሌሎች ጋር የሚቋደስበት መድረክ ነው ይላል አዘጋጁ ዘላለም ቻላቸው።
ሶስተኛው ደግሞ፣ ታላላቆችን የማያከብር ማህበረሰብ ተተኪ ታላላቆችን አያፈራም ሲልም ተናግሯል። እንደ ዘላለም ገለፃ በዚህ በአል ለአሊ ቢራ የሚሰጠው ክብርና ምስጋና ፈለጉን ለተከተሉ አርቲስቶችና በተለያዩ ዘርፎች ተሰማርተው ለሚገኙ ሁሉ መነቃቃትን፣ መነሣሣትን እና ብሩህ ተስፋን ይፈጥራል፤ ነገ በየዘርፉ ብዙ አሊ ብራዎች እንዲኖሩ መንገድ ይጠርጋል። በሙያቸው ለሕዝብና ለሀገር ታላቅ ውለታ የዋሉ አንጋፋዎችን የማክበርና የማመስገን ባሕላችንን የምናዳብርበትም ይሆናል።
በአራተኛነት የገለፀው ደግሞ፣ በአሉ አሊ እምነቱን፣ ዕውቀቱን፣ እቅዱን፣ ተስፋውን፣ ራዕዩን በተለያዩ መድረኮች ለሌሎች በማካፈል እስከ ዛሬ ይዞት የመጣውን ችቦ ለሌሎች የሚያስተላልፍበት መድረክም ይሆናል ብሏል ዘላለም ቻላቸው። በመጨረሻም በአሉ፣ አርቲስቱ በቀጣይነት ሊሰራቸው ላሰባቸው ሥራዎች መሠረት የሚጥልበትም ይሆናል።
የአሊ ብራ የሃምሳኛ አመት የመድረክ ውሎው በአል በምን አይነት መልኩ ይከበራል የሚል ጥያቄም ተነስቶ ነበር። እንደ ወጣት ዘላለም ቻላቸው ገለፃ የበዓሉ አከባበር፣ የሚከተሉትን ዋና ዋና ዝግጅቶችና ተግባራት ያካተተ ይሆናል ብሏል።
ይህ ዝግጅት ሃምሳኛ አመት በአሉ በይፋ የሚጀመርበትና የሙያ አጋራቱ፣ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የተለያዩ ባለ ድርሻ አካላት፣ ቤተሰቦቹ፣ ወዳጆች እና ሚዲያ የሚገኙበት ዝግጅት ነው። ዝግጅት ስለ አሊ ብራ ሕይወትና ሥራዎቹ የሚቀርቡ ጥንታዊ ጽሁፎችን፣ ንግግሮችን እና የሙዚቃ ድግስን ያካትታል።
የአሊ ብራን ህይወትና ሥራዎች የሚያሳዩ ፎቶዎችና ቪዲዮዎች እንዲሁም የተሸለማቸውን ሽልማቶች የሚቀርቡባቸው ኤግዚቢሽኖች በአዲስ አበባና በአደማ ከተማዎች ይካሄዳሉ።
በአዲስ መልክ የተቀናበሩ 10 የተመረጡ የአሊ ዘፈኖችን የያዘ አልበም ለወርቅ ኢዩቤሊዩው ይለቀቃል ሲል ወጣት ዘላለም ቻላቸው ተናግሯል። ከዚህ ሌላም ኮንሰርቶች እንደሚቀርቡም ገልጿል። ኮንሰርቶቹም የሚካሄድባቸው ከተሞችም ይፋ ሆኗል።
1. አዲስ አበባ
2. ድሬዳዋ
3. ሌሎች የክልል ከተሞችና የኦሮሚያ ከተሞች
4. በውጭ ሀገራት (አውሮፓ፣ አፍሪካ፣ መካከለኛው ምስራቅና እስያ፣ አውስትራሊያ)
አሊ ቢራ በእስከዛሬ ህይወቱ ከ40 በላይ ሀገራት እየተዘዋወረ ሙዚቃዎቹን አቅርቧል። ስለዚህ አለማቀፋዊ ተቀባይነቱ ሰፊ እና ተወዳጅ በመሆኑ በየሐገሩ በጉጉት እንደሚጠበቅ ተናግሯል።

(ዘገባ ከሰንደቅ ጋዜጣ)

↧
↧

ማስታወሻ፡ እውን የባንዳውን ሚና የተጫወተው ኢሕአፓ ወይስ መኢሶን?

$
0
0

meison eprp
ከመኩሪያ ለዓለም

ይህ ጽሑፍ የኢትዮጵያ ህዝብ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕ አፓ) እና መላ ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ (መኢሶን)ን አስመልክቶ ሎሚ በሚባል በኢትዮጵያ ውስጥ በሚታተም መጽሔት ላይ የቀረቡ 4 መጣጥፎችን አንድ ላይ በማሰባሰብ የቀረበ ነው። የአቅርቦቱ ዓላማም በ1966 ዓ.ም በኢትዮጵያ የተካሄደውን ሕዝባዊ አብዮትንና በዚህ የአብዮት ሂደት ውስጥ የነበረውን የሁለቱን ድርጅቶች ሚና አስመልክቶ የሚያጠነጥን ስለሆነ፤ ጽሁፉ ዲያስፖራ ለሚኖረው ኢትዮጵያ አንባቢም በተለይም ለወጣቱ ክፍል፤ ከዚያ ያብዪት ጊዜ ጋር በተያያዘ በሁለቱ ድርጅቶች ላይ ስለሚቀርቡ አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ሁኔታ ቢያንስ ቀጣይ ጥያቄዎችን እያነሳ እንዲወያይ ይገፋፋዋል በማለት እሳቤ ነው፡-

ሙሉውን በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

↧

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ 3ኛ ዓመት ተማሪዎች ሲጮኹ ዋሉ፤ ዲኑ ተማሪዎቹን “በዩኒቨርሲቲው በቀን ሦስቴ እየበላችሁ ጠገባችሁ”አሉ

$
0
0

የዩኒቨርሲቲው ዲን ዶ/ር ባየልኝ ዳምጤ “በቀን ሦስቴ እየበላችሁ ጠገባችሁ” አሉ

(ዘ-ሐበሻ) በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ 3ኛ ዓመት ተማሪ የሆኑ ተማሪዎች ከውጤት አሰጣጥ ጋር ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጋር በፈጠሩት አለመግባባት ሲጮኹ መዋላቸውን የዘ-ሐበሻ የባህርዳር ዘጋቢዎች ከስፍራው ዘግበዋል። እንደ ዘጋቢዎቻችን ገለጻ የ3ኛ ዓመት ተማሪዎቹ ጩኸታቸውን ሲያሰሙ ከዋሉ በኋላ የዩኒቨሲቲው ዲን ዶ/ር ባየልኝ ዳምጤ ሰብስበው ያነጋግሯቸው ቢሆንም፤ ዶ/ሩ ችግሩን ከማብረድ ይልቅ እሳት ለኩሰውበት ሄደዋል ሲሉ ተማሪዎቹ ለዘ-ሐበሻ ዘጋቢ ነግረውታል።
bahrdar univesity
ዩኒቨርሲቲው አዲስ ባወጣው መመሪያ መሠረት በተማሪዎች ማርክ አሰጣጥ ላይ ከዚህ ቀደም 85 የነበረው ወደ 95 ያድጋል ባለው መሠረት ተማሪዎቹ ልክ እንደ 1ኛ እና 2ኛ ዓመት ተማሪዎች ማርክ ሊያዝልን ይገባል በሚል የዛሬው የባህርዳር ዩኒቨሲቱ ሁከት መፈጠሩን የገለጹት ዘጋቢዎቻችን፤ ይህን ተከትሎም በሃገሪቱ ያለውን ወቅታዊ ፖለቲካ የሚመለከቱ መፈክሮችን ተማሪዎቹ ሲያሰሙና ሲጮኹ ከዋሉ በኋላ ዶ/ር ባየልኝ ዳምጠው ጠርተው አንጋግረዋቸዋል። ተማሪው ዶ/ር ባየልኝ ወደ ጠሩት ስብሰባ ሲገባ የተለያዩ መፈክሮችን እያሰማ ሲጮህ ነበር ያሉት ዘጋቢዎቻችን ዲኑ ስብሰባውን ሲመሩ የነበረው እንደተማረ ሰው አልነበረም የሚሉ አስተያየቶች ከ3ኛ ዓመት ተማሪዎቹ ተሰምቷል።

ዶ/ር ባየልኝ ተማሪውን ሰብስበው “በቤታችሁ በነበራችሁበት ጊዜ በቀን 2 ጊዜ የምትበሉ ተማሪዎች እዚህ ዩኒቨሲቲ ውስጥ በቀን 3 ጊዜ እየበላችሁ ጠገባችሁ፤ ይሄ ጥጋብ ነው ስለማርክ አሰጣጥ ጥያቄ ያስነሳችሁ” የሚል አንባገነናዊ ንግግር በመናገራቸው ተማሪው ቁጣውን እንዳሰማ የገለጹት የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች “እኛ በችግረኛ ሃገር ላይ ሆነንና የትምህርት ጥራት በሌለበት መልኩ ያደጉ ሃገራት የትምህርት ፖሊሲ መሞከሪያ አንሆንም” በሚል የ3ኛ ዓመት ተማሪዎቹ ቁጣቸውን ገልጸዋል ብለዋል። ይህን ተከትሎም ጉዳዩ እኛንም ይመለከተናል በሚል የባርዳር ዩኒቨርሲቲ 1ኛ እና 2ኛ ዓመት ተማሪዎች የ3ኛ ዓመት ተማሪዎቹን ጥያቄ መቀላቀላቸው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ዘ-ሐበሻ ወደ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ዲን ቢሮ ደውላ የነበረ ቢሆንም ዶ/ር ባየልኝ ዳምጤን ማግኘት አልቻለችም። በዩኒቨርሲቲው ውስጥ አሁንም ውጥረቱ እንዳለ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ገልጸዋል።

↧

Sport: የዓለም ዋንጫ አዘጋጇ ብራዚል አሰቃቂ ገመና ሲገለጥ

$
0
0

ዳ ሲልቫ ካንታንሄዴ በአንደኛው እሁድ ከሰዓት ብስክሌቱ ላይ ሲወጣ አባቱ አይተውታል፡፡ እንደልማዱ መንደር ውስጥ እግርኳስ ሊጫወት እየሄደ መሆኑንም አውቀዋል፡፡ ነገር ግን ልጃቸው የተሳለ ቢላዋ ከጀርባው ሲደብቅ አላስተዋሉትም፡፡
አጭሩ እና ቀጭኑ የ19 ዓመት ወጣት ካንታንሄዴ ከታናሽ ወንድሙ ጆጅ ጋር በመሆን በሰሜን ምስራቅ በምትገኘው የብራዚል የገጠር ከተማ አልፈው ወደ ሴንትሮ ዶ ሜዮ ደረሱ፡፡ በቁርጥራጭ ቁሳቁስ የቆሸሸው የመጫወቻ ሜዳ መረብ ባይኖረውም የእንጨት ግቦች አሉት፡፡ የመሬቱ ሳሮች ተጋልጠው አሸዋው ይታያል፡፡ እዚህ የሚደረጉት ጨዋታዎች ይፋዊ አይደሉም፡፡ በተለምዶ ሁለቱ ቡድኖች ወደ ሜዳ ሲገቡ አንደኛው ቡድን ማሊያ ሲለብስ ተጋጣሚው ከወገብ በላይ ራቁቱን ይሆናል፡፡ ውጤት መመዝገቢያ ሰሌዳ ወይም ሌላ መረጃ መሳሪያ የለም፡፡ በሜዳው ዙሪያ የተንዠረገጉት ዛፎች ብቻ ጥላቸውን ይሰጣሉ፡፡
በጨዋታው የመጀመሪያ ግማሽ ካንታንሄዴ በተከላካይ ቦታ ተጫወተ፡፡ በኋላም በጉልበቱ እና ቁርጭምጭሚቱ አካባቢ ህመም ሲሰማው ለደቂቃዎች ጨዋታውን ትቶ ዳኛ ሆነ፡፡ በጁን መጨረሻ በዚያችው ዕለት በ1300 ማይል ርቀት ላይ በምትገኘው ሪዮ ዲ ጄይኔሮ የብራዚል ብሔራዊ ቡድን በኮንፌዴሬሽ ዋንጫ ስፔንን አሸንፏል፡፡ በዚያችው ዕለት በሴንትሮ ዶ ሜዮ የተፈጠረውን ዘግናኝ ታሪክ የዓለም ህዝብ የሰማው ግን ከሳምንት በኋላ ነው፡፡

Fifa-World-Cup-2014-Brazil
ከእረፍት መልስ ጨዋታው 15 ወይም 20 ደቂቃዎች እንደቀጠለ ካንታንሄዴ ለ30 ዓመቱ ጆሴሚር ሳንቶስ አብሬዩ ቢጫ ካርድ አሳይቶ ከጥቂት ቆይታ በኋላ ቀይ ካርድ መዘዘበት፡፡ ካንታንሄዴ እና አብሬዩ ጓደኛማቾች ነበሩ፡፡ ብዙ ጊዜም ለአንድ ቡድን ተጫውተዋል፡፡ ያን ቀን ጠላቶች ሆኑ፡፡ ድብድብ ተጀመረ፡፡ ካንታንሄዴ የደበቀውን ቢላዋ አውጥቶ አብሬዩን ሁለት ጊዜ ወጋው፡፡ አብሬዩ አቅራቢያው ወደሚገኝ ሆስፒታል ቢወሰድም አልተረፈም፡፡ ሞተ፡፡
ገዳዩ ካንታንሄዴ በስነ ስርዓት ፍርድ ቤት የመቅረብ እድል አላገኘም፡፡ የሟቹ አብሬዩ አራት ጓደኞች እጅ ገባ፡፡ አልኮል አብዝተው የወሰዱት እና ፀረ አደንዛዥ ዕፅ የተጠቀሙት ልጆች አልማሩትም፡፡ በመጠጥ ጠርሙስ ፊቱን ደጋግመው መቱት፡፡ ከእንጨት ጋር ካሰሩት በኋላ በሞተር ብስክሌት ገጩት፡፡ በመጨረሻም ጉሮሮውን በስለት ወጉት፡፡ በዚህ አልበቃቸውም፡፡ የእግሮቹን የታችኛው ክፍል ቆርጠው፣ እጆቹን ከሰውነቱ ጋር በቆዳው ብቻ እንዲንጠለጠል አድርገው እና ጭንቅላቱን ቆርጠውት በመጫወቻው ሜዳ ጠርዝ ጥለውታል፡፡
‹‹በመጀመሪያ ይህ በእርግጥ መደረጉን ማመን ተቸግሬያለሁ፡፡ የሰው ልጅ እንዲህ አይነት ክፋት ለመፈፀም አቅም ይኖረዋል ብዬ አላስብም›› ይላሉ የአካባቢው የፖሊስ አዛዥ እና የመርማሪው ቡድን መሪ ቫልተር ኮስታ ዶስ ሳንቶስ፡፡
ለአንድ ሳምንት ያህል ዜናው ታፍኖ ተያዘ፡፡ ሚዲያው ጆሮ ከደረሰ በኋላ ግን ለመራባት አፍታ አልፈጀበትም፡፡ ሁሉም የራሱን አስተያየት እና ስሜት ተናገረ፡፡ ብዙዎቹ ግን ውብ እግርኳስ ይታይባታል የተባለችው ሀገር ያለባትን ጉድ ሰምቶ የቀጣዩን የ2014 የዓለም ዋንጫ እና የ2016 ኦሎምፒክ እጣ ፈንታ ጠየቀ፡፡
እውነታው ከሚታሰበው በላይ የተወሳሰበ ነው፡፡ ክስተቱ በሁለት በዕድሜ የሚበላለጡ ወጣቶች መካከል የተፈጠረ ቁጣን መሰረት ያደረገ ግድያ ይሁን እንጂ አጋጣሚው በብራዚሎች ዘንድ እንደ ባህል የተለመደውን ስለት መሳሪያ የመያዝ እና የበቀል ችግር ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ነው፡፡ በዚህ የግድያ ታሪክ ውስጥ የተስፋ ቢስነት እንዲሁም የድህነት እና የሀብት አለመመጣጠን ተስተውሏል፡፡ እርስ በርስ የመተማመን እና በፍትህ ስርዓቱ ላይ እምነት የማጣትን ችግርም መመልከት ይቻላል፡፡
የሴንተሮ ዶ ሜዮ ነዋሪዎች አፍረዋል፡፡ የዓለም ህዝብ የአካባቢውን ነዋሪ ጭምትነት አያውቅም፡፡ አሁን ሁሉም ሰው በዚህች ምድር የሆነውን ሰምቷል፡፡ እዚያው ብራዚል ውስጥ ያሉ አቅራቢያ ከተሞች እና ክልሎች ሳይቀሩ ሴንትሮ ዶ ሜዮ የተረገመች ቦታ ስለመሆኗ ያምናሉ፡፡ የ13 ዓመቷ ለቫኔቴ ሳንቶስ በምትኖርበት አካባቢ ላሉት የትምህርት ቤት ጓደኞቿ ምን እንደተፈፀመ ስትነግራቸው አንዳንዶቹ ልጆች ያማትቡ ነበር፡፡ ‹‹ራሳቸውን ከእኛ መጠበቅ እንዳለባቸው ያምናሉ›› ትላለች ሳንቶስ፡፡

የሜዳ ላይ ረብሻ
ራይሙንዶ ሳ ከዛሬ 10 ዓመት በፊት በዳኝነት የመሩትን አንድ አማተር ጨዋታ ያስታውሳሉ፡፡ የፊሽካውን ድምፅ አሰምተው ለአንደኛው ቡድን የፍፁም ቅጣት ምት ሰጡ፡፡ ጉዳዩ ያስቆጣቸው እና ፍፁም ቅጣት ምቱ የተሰጠባቸው ተጨዋቾች ከበው ጮሁባቸው፡፡ እንዲሁም አስፈራሯቸው፡፡ ‹‹ከዚህ በህይወት አትወጣም›› አለው አንደኛው ተጫዋች፡፡ ሌላኛው ተከተለና ‹‹ፖሊስ ነው፡፡ ምናልባትም ሽጉጥ ታጥቆ ይሆናል›› አለ፡፡
በእርግጥም ይህንን ታሪክ ሳኦ ሉዊስ ውስጥ በሚገኝ ቢሯቸው ተቀምጠው የሚተርኩት ሳ አሁን የፖሊስ ኮሎኔል ናቸው፡፡ በሴንትሮ ዴ ማዮ አካባቢ በፕሮፌሽናል ጨዋታዎች ጊዜ የሚፈጠሩ ረብሻዎችን በስራቸው ካሉ ባልደረቦቻቸው ጋር የመቆጣጠር ኃላፊነት አለባቸው፡፡ ይሁን እንጂ አሁን በአካባቢያቸው የተፈጠረው ግድያ የሀገራቸው የእግርኳስ ውብ ገፅታ እንደማይበርዘው ያምናሉ፡፡
የጨዋታ ዳኛ ሽጉጥ እንዲይዝ መብት የለውም፡፡ ሆኖም ብዙ ጊዜ ይህ ያጋጥማል፡፡ በሳኦ ሉዊስ ፖሊስ በማይመጣባቸው ቦታዎች የሚደረጉ አማተር ጨዋታዎችን የሚዳኙ ሰዎች ራሳቸውን ለመጠበቅ ሰንጢ እንዲሁም አይን ላይ የሚረጭ የበርበሬ ስፕሬይ ይይዛሉ፡፡ ይህንን ሳ ራሳቸውም ያረጋግጣሉ፡፡ እዚህ ግባ የማይባል ገንዘብ የሚከፈላቸው እነዚህ ዳኞች ‹‹ለዚህችስ ብዬ ህይወቴን አላጣም›› እንደሚሉም ይገልፃሉ፡፡
የሶቪዮሎጂ ምሁራን የጥናት ውጤት እንደሚጠቁመው ከሆነ በብራዚል በደጋፊዎች ረብሻ ምክንያት የሚከሰተው ሞት በሌላ በየትም ሀገር በተመሳሳይ መልኩ ከሚፈጠረው በእጅጉ ይበልጣል፡፡ አሁን ደግሞ ይበልጥ ተባብሷል፡፡ ከ10 ዓመት በፊት በዓመት በአማካይ የ4.2 ሰዎችን ነፍስ ይቀጥፍ የነበረው ሰበብ አሁን ቁጥሩን በ2012 ወደ 23 አድርሶታል፡፡
የብራዚሉ ሳምንታዊ የእግርኳስ ጋዜጣ ላንሴ ከ1988 እስከ 2012 ድረስ የዘገበባቸው የእግርኳስ ተያያዥ ግድያዎች 155 ቢደርሱም ጥፋት አድርሰዋል ተብለው በህግ የተያዙት ሰዎች 27 ብቻ ናቸው፡፡ በእርግጥ ከእነዚህ ግድያዎች መካከል ብዙዎቹ ከድጋፍም ያለ የውንብድና ህይወት ውስጥ ገብተው ከክለቦች እና ከፖሊሶች ጋር ችግር ባለባቸው የረብሻ ቡድኖች መካከል የተፈጠሩ ናቸው፡፡
በሳልጋዶ ደ ኦሊቪዬራ ዩኒቨርሲቲ ሶሺዮሎጂስቱ ማውሪሲዮ ሙራድ በብራዚል የሚፈፀሙትን ግድያዎች ከስፖርቱ ጋር ማያያዝ ተገቢ እንዳልሆነ ይናገራሉ፡፡ ‹‹ከእግርኳስ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት የለውም፡፡ መጠት ቤትን ጨምሮ በሌላ በየትኛውም ቦታ ሊፈጠር የሚችል ነገር ነው፡፡ የእግር ኳስ ረብሻ ብለን መጥቀስ ያለብን ሁለት የተቃራኒ ቡድን ደጋፊዎች እርስ በርስ የሚገቡበትን ቀጥተኛ ግጭት ነው፡፡ ከእግርኳስ ረብሻ ይልቅ አሁን በብራዚል ያለው ‹‹ረብሻ›› ነው፡፡
ብራዚሊያን ሴንተር ፎር ላቲን አሜሪካን ስቲዲስ በተሰኘ የምርምር ማዕከል ባለፈው ጁላይ ይፋ የተደረገ ጥናት እንደመሰከረው ከሆነ ብራዚል በዓለም ሰባተኛዋ የረባሾች ሀገር ነች፡፡ ትልልቅ ግድያዎችን የፈፀሙ ሰዎች እና ሙስና ውስጥ የተፈቁ ባለስልጣናት ያለ ችግር ይንቀሳቀሱበታል፡፡ ግድያዎች በትልልቆቹ ከተሞች ሪዮ እና ሳኦ ፖሎ ቢቀንሱም በሰሜን ምስራቅ ብራዚል ተባብሷል፡፡ በዚህ ጥናት መሰረት የግድያዎቹ ዋነኛ ምክንያት የቡድን ወንጀለኝነት ወይም የአደንዛዥ መድሃኒት ሳይሆን በጓደኞች፣ በጎረቤቶች እንዲሁም በባል እና ሚስት መካከል የሚፈጠሩ ቀላል አለመግባባቶች ናቸው፡፡
ማራንሆ በተሰኘችው ቦታ ብቻ ከ2001 እስከ 2011 በ100 ሺ ነዋሪዎች መካከል የግድያው ቁጥር በዓመት ከነበረበት 9.4 ወደ 23.7 አድጓል፡፡ በእርግጥ ይህ አካባቢ በቂ የፖሊስ ቁጥር የማይመደብለት እንደሆነ መናገር ይቻላል፡፡ ለ6.7 ሚሊዮን ነዋሪ የተመደቡት ፖሊሶች 11 ሺ ብቻ ናቸው፡፡ በኒውዮርክ ከተማ 34,500 ፖሊሶች እንደሚገኙ አስተውሉ፡፡ የማራንሆ አካባ ፍትህ ቢሮ ኃላፊው ሴባስቲያዎ አልባኩሌኬ ኡቾ አካባቢው ስድስት ሺ ተጨማሪ ፖሊሶች እንደሚያስፈልገው ያምናሉ፡፡ አንቶኒዮ ሊማ ዲ ካርቫልሆ የተሰኙት የቦታው ፖሊስ ‹‹አለመታደል ሆኖ የሚጎድሉን ነገሮች ብዙ ናቸው፡፡ የፖሊስ መኪና፣ የሰው ኃይል፣ መሰረተ ልማት፣ ስልኮ፡፡ ሌላው ቀርቶ ራዲዮኖች እንኳን የሉንም›› ይላሉ፡፡

የስለት መሳሪያ እና ፍትህ
ሴንትሮ ዶ ሜዮ በመንግስት ብዙ ቃል ተገብቶላት ጥቂት የተፈፀመባት አካባቢ ነች፡፡ በቦታዋ ሞተር ብስክሌቶች ባልተጠረገው እና በድንጋያማው እና አቧራ ባለው መንገድ ላይ ሲበሩ ይውላሉ፡፡ የቀንድ ከብቶች በየሜዳው የሚጋጥ ሳር ፍለጋ ይፈስሳሉ፡፡ የአካባቢው ሙቀት ሲያይል ነዋሪዎቹ አነስተኛ ወንበሮች እየያዙ ዛፎች ስር ይቀመጣሉ፡፡ ሙቀቱን መቋቋሚያ የአየር ሁኔታ መቆጣጠሪያ ያልተገጠመባቸውን ቤቶቻቸውን በሮች እና መስኮቶች ይከፍታሉ፡፡ አይኖቻቸው እና ጆሮዎቻቸውም ከውጪ የሚመጡ እንግዶች ቢኖሩ ብለው እንደተከፈቱ ይጠበቃሉ፡፡
ጎብኚዎች ወደ አካባቢው ሲመጡ ፀሐይዋን ተጠልለው የሚቀመጡበት ወንበር ይሰጣቸዋል፡፡ አንዳንድ ጊዜም ምሽትን የሚያሳልፉበት በወንፊት ጨርቅ የተከለለ ማረፊያ ይቀርብላቸዋል፡፡ ህፃናት በፓፓያ ዛፍ ቅርንጫፍ የተሰራ ‹‹ዋሽንት›› ይጫወታሉ፡፡ ልጃገረዶችም በተለያዩ ጨዋታዎቻቸው ቦታውን ካርኒቫል ያስመስሎታል፡፡
‹‹ይህ የተረጋጋ ቦታ ነው›› ይላል የ30 ዓመቱ ጆዜ ኩንሀ ዛፍ ስር እንደተቀመጠ፡፡ ‹‹አልኮል ብዙ ጠጥተህ መንገድ ላይ ብትወድቅ ችግር አይደርስብህም፡፡ ቤቴ ብትመጣ እና ረሃብ ቢሰማህ ዶሮዎቻችንን አርደን እናበላሃለን›› በእርግጥ ይህቺ አካባቢ በቅርብ ዓመታት ያስተናገደችው ግድያ አንድ ብቻ ነው፡፡ በቦታዋ ፀጥታ ቢሰፍንም ጥበቃ የሚደረግላት በሰባት ፖሊሶች እና ሁለት የፖሊስ መኪኖች ብቻ ነው፡፡ አንዳንዶቹ የቦታዋ ነዋሪዎች የመንግስት ባለስልጣናት እያገዟቸው አለመሆኑን ያስባሉ፡፡
በቅርቡ የ31 ዓመቷ ኤድና ማሪያ ዶስ ሳንቶስ ከተቀመጠችበት ዛፍ ስር አንዲት አይጥ ስታልፍ ተመለከተች እና ወንዱ ልጇን አባርሮ እንዲይዛት ነገረችው፡፡ ልጇ የታዘዘውን ችላ ብሎ ቆሞ መቅረቱን የተመለከተችው ኤድና ‹‹አንተ ማለት ልክ እንደ ፖሊስ ነህ›› ብላ ልታበሳጨው ሞከረች፡፡
በሴንትሮ ጩቤ ታጥቆ መንቀሳቀስ የተለመደ ነው፡፡ ከወንዶቹ ካናቴራ ስር በቀላሉ ይታያል፡፡ የ67 ዓመቱ ጆአኪም አሩዳ አምስት ኢንች የሚረዝም ጩቤ በጅንስ ሱሪያቸው ሸጉጠው ይንቀሳቀሳሉ፡፡ ሰውዬው ስለራሳቸው እና ስለሌላ ሰው ሚስት ገጠመኛቸው ሲናገሩ በመዳፋቸው፣ በክንዳቸው እና አንገታቸው ላይ ያለውን ጠባሳ ‹‹የፍቅር ታሪክ ነው›› ብለው ይስቃሉ፡፡
‹‹ብርቱካን እና አናናስ ለመብላት ጩቤው ያገለግልሃል፡፡ ራስህም ትከላከልበታለህ›› ይላሉ አሩዳ፡፡ ‹‹ፖሊስ ማንንም ረድቶ አያውቅም›› የኤድና ባል የሆነው የ30 ዓመቱ ሜሮኤል ዶስ ሳንቶስ የመንደሩን ቆሻሻ እያነሳ የሚተዳደር ሰው ነው፡፡ ዶስ ሳንቶስ የፖሊስ ጣቢያውን የተጠራቀመ ቆሻሻ ሲያነሳ ብዙ ጊዜ ማጠራቀሚያው ውስጥ ጩቤዎች እንደሚያገኝ ይመሰክራል፡፡ በሳኦ ሴባስቲያኦ ሆስፒታል የሚሰሩት ዶክተሮች እና ነርሶችም በየወሩ አንድ ወይም ሁለት በጩቤ የተወጋ ሰው እንደሚያጋጥማቸው ይናገራሉ፡፡
አልኮል፣ ማሪዋና እና ኮኬይን በአካባቢው በብዛት ጥቅም ላይ እንደሚውል ባለስልጣናት ይናገራሉ፡፡ ነርሷ አልሜርንዳ አልቬሽ ሶውሳ ባለማወቅ አደንዛዥ ዕፆችን እየተጠቀሙ ችግር ውስጥ ገብተው የሚመጡ እንዲሁም አዕምሯቸው የተቃወሰባቸው እና እይታቸው የተበላሸባቸው ወጣቶች እንደሚያጋጥሟት ትመሰክራለች፡፡ ‹‹ሰዎች ሁል ጊዜም ከቤታቸው የሚወጡት ከሰው ጋር ግጭት ውስጥ ላለመግባት እየፈሩ ነው›› ትላለች የ27 ዓመቷ ሶውሳ፡፡
ለበርካታ አስርት ዓመታት በብራዚል የጆዜ ሳርኔይ ቤተሰቦች በፖለቲካው ትልቅ ድርሻ ነበራቸው፡፡ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ልጅ ሮሴይና ሳርኔይ የማራንሆ ገዢ ነበረች፡፡ በእነዚያ ዓመታት ገዢዎቹ ብዙ መሬት የያዙ እንዲሁም ሚዲያውን የተቆጣጠሩ ነበሩ፡፡ የሳርኔይ ቤተሰብ ህዝቡን ‹‹ጥገኛ፣ ዝቅተኛነት የሚሰማው እና የተተወ›› መሆኑን እንዲቀበል አድርጎት እንዳለፈ የብራውን ዩኒቨርሲቲ ምሁሩ ጀምስ ግሪን ይናገራል፡፡

የጆዜ ልጅ
የካንታንሄዴ እና አብርዲን ህይወት የቀጠፈው አጋጣሚ ከመከሰቱ በፊት የሁለቱ ልጆች መንደር ሰዎች አንዳቸው ለሌላቸው እንደ ባይተዋር መተያየት ጀምረው ነበር፡፡ እንዲያውም ካንታንሄዴ ወደዚያች መንደር ሄዶ ኳስ ሊጫወት መሆኑን ያወቁት አክስቱ እንዳይሄድ ጠይቀውት ነበር፡፡ ከሞቱ ሁለት ቀናት በፊትም ሴትየዋ ወደዚያ መሄድ ይቅርብህ ብለው ሲመክሩት ‹‹አትጨነቂ! ልጆቹ ጓደኞቼ ናቸው›› ብሏቸዋል፡፡
ካንታንሄዴ ያደገው ከአባቱ፣ ወንድሙ እና እህቱ ጋር መካከለኛ ደረጃ ባላት የሳንቶ አንቶኒዮ አካባቢ መኖሪያ ቤታቸው ነው፡፡ በሳምንቱ ቀናት ልጁ በማለዳ ዶሮ ሲጮህ ተነስቶ ከብቶችን ወደ ግጦሽ ሲያሰማራ እግረ መንገዱንም ለአጥር የሚሆን እንጨት ለማግኘት ዛፎች ይቆርጣል፡፡ ማታ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ይከታተላል፡፡ ወደፊት አካውንታንት ለመሆንም ይመኛል፡፡ ‹‹አዎ ትልቁ ህልሙ ይህ ነበር›› ትላለች የ27 ዓመቷ ታላቅ እህቱ ለሴሊያ ስራይቫ፡፡
የሳምንቱ መጨረሻ ቀናት የእግርኳስ ናቸው፡፡ ካንታንሄዴ በራዮ ከሚገኙት ፕሮፌሽናል ክለቦች አንደኛው የሆነውን ፍሉሚኔንሴ ይደግፋል፡፡ በግል ደግሞ ለኔይማር አድናቆት ነበረው፡፡ የባርሴሎናው ኮከብ ብሔራዊ ቡድኑ ስድስተኛውን የዓለም ዋንጫ እንዲያነሳ እንዲያግዝ ይመኝ ነበር፡፡
በጁን ወር የመጨረሻዋ ቀን ካታንሄዴ ምሳውን ከበላ በኋላ ወደ ጨዋታው ከመሄዱ በፊት ጥቂት እንቅልፍ ተኛ፡፡ ሲነሳም ካናቴራውን እና ሰማያዊ ጂንስ ቁምጣውን ለበሰ፡፡ ከጉልበቱ በታች የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቼልሲ አርማ ያለበትን የግጭት መከላከያ አደረገ፡፡ አባቱ የመጨረሻ ልጃቸው ሲወጣ ከጀርባው መጠነኛ ቦርሳ መሸከሙን ብቻ እንዳዩ ይገልፃሉ፡፡ ‹‹ቤት ውስጥ ወዲያ ወዲህ ሲል የነበረው ጩቤ ታጥቆ ነው ብዬ ማመን ያስቸግረኛል›› ይላሉ ጆዜ ሬይመንዶ ሮድሪጌዝ ካንታንሄዴ፡፡ ‹‹ምናልባት ታጥቆ ይሆናል፡፡ ነገር ግን አላየሁትም›› ሌሎች ግን አይታውታል፡፡ የ14 ዓመቱ የጎረቤታቸው ልጅ ፊሊፔ ፍራንካ ቀደም ብሎ አንድ ቀን ካንታንሄደ ጩቤ ይዞ ቤታቸው ፊት ለፊት ተቀምጦ እንዳገኘው ተናግሯል፡፡ ሌላው ጓደኛው የ14 ዓመቱ ጉስታቮ ሄንሪኬም በሌላ ጊዜ ካንታንሄዴ ኳስ ለመጫወት ሲል እንዲመቸው ብሎ የጩቤውን ቦታ ከጎኑ ለማድረግ ሲያስተካክል አስተውሎታል፡፡
የልጁ ህይወት ምናልባትም ብዙዎች ከገመቱት በላይ የተወሳሰበ ነበር፡፡ ባለፈው ፌብሩዋሪ በአካባቢው የተከበረው የካርኒቫል በዓል ላይ ካንታንሄዴ በሌላ ሰው በጩቤ ክንዱ እና ከጆሮው አካባቢ መወጋቱን አባቱ ያስታውሳሉ፡፡ በዚህም በሆስፒታል አንድ ሌላት አሳልፎ ቁስሎ ተሰፍቶለታል፡፡
‹‹የወጋው ሰው ካንታንሄዴ ሌላ ከሚፈልገው ሰው ጋር ተመሳስሎበት ነበር›› የሚለው የ20 ዓመቱ ሊዮኒልዶ ሲማ ነው፡፡ በካርኒቫሉ ጊዜ ከካንታንሄዴ ጎን ቆሞ የነበረው ሊማ አጋጣሚው የተፈጠረው በስህተት እንደነበር ይናገራል፡፡ ሌላኛው የካንታንሄዴ ጓደኛ የ18 ዓመቱ ሀድሰን ሮኒ ኦሊቪዬራ ሊማ ግጭቱ የተፈጠረው በእንስት ምክንያት ሳይሆን እንደማይቀር ይጠረጥራል፡፡ ሆኖም ‹‹ካንታንሄዴ ከዚያ ግጭት በኋላ ፈርቶ ነበር›› ይላል፡፡
ካንታንሄዴ ከእናቱ ሞት በኋላ ተስፋ ቢስነት ይሰማው እንደነበር እህቱ ትናገራለች፡፡ እናቱ ወሊዳ ማርኬዝ ዳ ሲልቫ በ46 ዓመታቸው ከሁለት ዓመታት በፊት ሲሞቱ የህልፈት ህይወታቸው ሰበብ አንድ የከባድ መኪና በዋና ጎዳና ከሚያሽከረክሩት ብስክሌት ጋር መትታቸው ነበር፡፡ ለካንታንሄዴ ‹‹የእናቱ ሞት እጅግ አስደንጋጭ ሆኖበት ነበር›› የምትለው ሳራቪያ ነች፡፡ ከባድ መኪና ሹፌሩ አደንዛዥ ዕፅ ሳይወስድ እንዳልቀረ የካንታንሄዴ ጓደኛ ሊማ ይጠረጥራል፡፡ ‹‹ይህንን መበቀል እንዳለበት ያስብ ነበር››

የማሪያ ልጅ
እንደ ጆሴሚር አብሬዩ እናት ምስክርነት ከሆነ ልጃቸው ከቤቱ የወጣው ጨዋታ ለማየት ብቻ ነበር፡፡ ሆኖም በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ሊያማ ብቻ የተገኘበት ጨዋታ ላይ እንዲሳተፍ ተጋበዘ፡፡ አብሬዩ የ30ኛ ዓመት ልደቱን ያከበረው ከሁለት ቀናት አስቀድሞ ነበር፡፡ በልደቱ ዝግጅት ከፀለየ በኋላ ከሚስቱ ጋር ኬክ እና ለስላሳ መጠት ተቃመሰ፡፡ አብሬዩ የልጅ አባት የሆነው ገና በታዳጊነቱ ነበር፡፡ ስለዚህም ትምህርቱን አቋርጦ ለስራ ተነሳ፡፡ በትዳር የተጣመራት እንስት መምህር መሆኗ ጠቅሞት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ወደ መጨረሱ ተቃርቦ ነበር፡፡ ከማሪያ አምስት ልጆች ሶስተኛው አብሬዩ ዘመዶቹን እጅግ የሚወድ እና ሌላ ልጅ ለመውለድ የሚጓጓ ነበር፡፡ ‹‹ስፖርት ይወዳል፡፡ ሌላ አመል የለበትም›› ይላሉ እናቱ፡፡
ሜዳ ላይ አብሬዩ ተፋላሚ እና ሀይል ቀላቅሎ የሚጫወት አማካይ ነው፡፡ ሆኖም ልጅ የሚጥል በሽታ አለበት፡፡ እናቱ ማሪያ ልጃቸው ይህ በሽታ ያገኘው በ13 ዓመቱ ከዛፍ ስለወደቀ መሆኑ ተነግሯቸው አምነዋል፡፡ ጨዋታ ላይ አንዳንድ ጊዜ ሜዳ ላይ ይጥለዋል፡፡ ሆኖም መድሃኒቱን ተከታትሎ እንደሚውጥ እና ችግሩ መለስ እንዳለበት እናቱ ያስረዳሉ፡፡
አብረውት ከሚጫወቱት አንዱ የሆነው ሊዮኒልዶ ሊማ ስለ አብሬዩ ሲናገር ‹‹ሁልጊዜም ሊጣላን ይፈልግ ነበር›› ይላል፡፡ የሊዮኒልዶ ወንድም የሆነው ሊኦናርያ ሊማ ፌሩይራም በበኩሉ አብሬዩ ባህሪይ የማይገመት እና ሜዳ ላይ ከሌሎች ጋር መስማማት የማይችል እንደነበር ይመሰክራል፡፡ ሆኖም ሁሉም ልጆች ተመሳሳይ አለመግባባቶች ሲፈጠሩ ቁጣቸውን ለማብረድ ዘወር ይላሉ፡፡ ‹‹አሁን የተፈጠረውን አልጠበቅንም፡፡ ሁለቱም ጓደኞቻችን ነበሩ›› ይላል ፌሬይራ፡፡
አብሬዩ እና ካንታንሄደ ከግጭታቸው አንድ ሳምንት በፊት እንኳን አብረው ለአንድ ቡድን ተጫውተው ካሸነፉ በኋላ በጋራ ጨፍረዋል፡፡ ቢራ እየተጎነጩም ድላቸውን አክብረዋል፡፡ ባለፈው ፌብሩዋሪ ካንታንሄደ በጩቤ መወጋቱን ሲሰማ አብሬዩ ሆስፒታል ድረስ ሄዶ ጠይቆታል፡፡ ‹‹የልብ ጓደኛሞች አልነበሩም፡፡ ሆኖም በእግርኳስ ምክንያት ይተዋወቁ ነበር›› ትላለች የአብሬዩ ሚስት ጆሴሚር፡፡

ነፍስ የቀማው ጠብ
የጨዋታው ሁለተኛ አጋማሽ ተጀምሮ 15 ወይም 20 ደቂቃ እንደሆነው በጉዳት ምክንያት ወደ ዳኛነት የተለወጠው ካንታንሄዴ በአብሬዩ ላይ ቢጫ ካርድ መዘዘ፡፡ ካንታሄዴ ካርድ ያወጣው ለወንድሙ ጆርጅ አድልቶ እንደሆነ ያመነው አብሬዩ በቁጣ ብዙ ተከራከረ፡፡ ከዚያ በኋላ ተከታታይ ጥፋቶች አጠፋ፡፡ የፊሽካ ድምፅ ከሰማ በኋላ ኳሷን በሀይል መታት፡፡ ሳይቆይ ደግሞ ሆን ብሎ ኳስ በእጁ ነካ፡፡ ቀጥሎም እግሩን ከፍ አድርጎ አደገኛ አጨዋወት ሊጫወት ሞከረ፡፡ አብሬዩ ቀይ ካርድ ማየት የፈለገ ይመስል ነበር፡፡ ካንታንሄዴ ቀይ ካርድ ካሳየው በኋላ ግን ሜዳውን ሊለቅ አልፈቀደም፡፡ ካንታንሄዴም አብሮት ሊወጣ እንደሚገባ ተሟገተ፡፡ ግርግሩ ሲበረታ አንድ በዕድሜ ሄድ ያሉ ሰው ጣልቃ ገቡ፡፡ ነገሩ የበረደ መሰለ፡፡
ካንታንሄዴ እና አብሬዩ ወደቤታቸው እንደሚሄዱ ተገምቶ የነበረ ቢሆንም ቃላት መወራወር ጀመሩ፡፡ ካንታንሄዴ አብሬዩን ‹‹ጅል›› ብሎ ሰደበው፡፡ አብሬዩ በፈንታው በህይወት የሌሉትን የካንታንሄዴ አናት ‹‹ሴተኛ አዳሪ›› ብሎ መሳደቡን ሊማ ሆድሰን ይናገራል፡፡ ከዚህ በኋላ ተያያዙ አብሬዩ በቦክስ እና ‹‹በጠረባ›› ደጋግሞ መታው፡፡ የወደቀው ካንታንሄዴ ከመሬት ሲነሳ በእጁ ጩቤ ይዞ ነበር፡፡ አብሬዩን ጎኑ ላይ እና ደረቱ ላይ ሁለት ጊዜ ወጋው፡፡ አብሬዩን ወደ ሆስፒታል ሲወስድ ካንታንሄዴ እንዳያመልጥ ታሰረ፡፡
ስልኮች ወደ ፖሊስ ጣበያ ቢደወሉም መልስ አልነበረም፡፡ ሉዊስ ሞራይስ ደ ሶዛ ሜዳው ጠርዝ ላይ ቆሞ በዋጋ ርካሽ የሚባለውን መጠጥ እየወሰደ ነው፡፡ ከደቂቃዎች በፊት እየተጫወተ እያለ ሰክረሃል ተብሎ ከሜዳ እንዲወጣ ከተደረገ ጀምሮ እየጠጣ ነው፡፡ ሞራይስ የአብሬዮ አብሮ አደግ ነው፡፡ የመጠጡ ኃይል እና ከአብሬዩ ጋር የነበረው ቅርበት ተደማምሮ ወደ ታሰረው ካንታንሄዴ አመራ፡፡ ሌሎችም ወሬውን የሰሙ የሰፈሩ ልጆች ግማሹ ባዶ እግሩን ሌላውም በሞተር ብስክሌት መጡ፡፡
ካንታንሄዴ እንደታሰረ የፖሊሶችን መድረስ ቢጠባበቅም አልመጡለትም፡፡ ሞራይስ ጠየቀው፡፡ ‹‹ጆሴ ሚርን ለምን ወጋኸው?›› ‹‹የእናቴን ሞት ለመበቀል!›› ሞራይስ በድጋሚ ጠየቀ፡፡ ‹‹የገደላት ማን ነው?›› ካንታንሄዴ ‹‹የከባድ መኪና ሾፌር›› ሲል መለሰ፡፡ ከዚህ በኋላ እንደታሰረ አሰቃቂው ድብደባ እና ግድያ ተፈፀመ፡፡

↧

የሳዑዲ ጉዳይ –ከረመጥ ወደ ረመጥ (ከፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም)

$
0
0

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም ከነጻነት ለሀገሬ

ባለፉት አስርት ዓመታት በመቶሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች በአገራቸው ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አህጉር በተለየ መልኩ ተንሰራፍቶ እየተፈጸመ ካለው ጭካኔና ርህራሄ የጎደለው አምባገነናዊ ስርዓት ለማምለጥ ሲሉ እግራቸው ወዳመራቸው አገር በመሰደድ ላይ ይገኛሉ፡፡ የኢትዮጵያ “ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር” እንደዘገበው ከሆነ እ.ኤ.አ በ2012 በግምት 200,000 ኢትዮጵያውያት ሴቶች በውጭ አገር በአብዛኛውም በመካከለኛው ምስራቅ አገሮች የውጭ የስራ ዕድል ለመፈለግ ተገደዋል፡፡ ከእነዚህ ኢትዮጵያውያት ሰራተኞች አብዛኞቹ በኢትዮጵያ ተንሰራፍቶ ከሚገኘው አምባገነናዊ የእሳት ነበልባል አመለጥኩ የሚል እምነት ነበራቸው፣ ሆኖም ግን ወደ ሳውዲ አረቢያው የእሳት እረመጥ ተወርውረው እራሳቸውን አገኙት፡፡    

በኢትዮጵያውያን ስደተኛ ሰራተኞችና በሌሎች በሳውዲ አረቢያ ጥገኝነት በጠየቁ ዜጎች ላይ ገደብ የለሽ አደን እየተካሄደ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ በዚህ ወር በየዕለቱ በሚባል መልኩ የሳውዲ አረቢያ ፖሊሶች፣ የደህንነት ኃላፊዎች፣ ወሮበሎች እና ህገወጦች ኢትዮጵያውያንን/ትን ሁሉ በየመንገዱ እያደኑ ይደበድባሉ፣ ያሰቃያሉ፣ አንዳንድ ጊዜም ይገድላሉ፡፡ የሳውዲ አረቢያ ፖሊሶች ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎችን ሲደበድቡ የሚያሳየውን የዩቱቤ የቪዲዮ ምስል መመልከት ለህሊና የሚሰቀጥጥ ነገር ነው፡፡ የሳውዲ አረቢያ ወሮበሎችና ህገወጦች ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎችን በየመንገዶች ሲያሳድዱ፣ ሲያጠቁና ሲገድሉ የሚያሳየው የቪዲዮ ምስል ለኩነቶቹ እውንነት ምንም ዓይነት ማብራሪያ አላስፈለገውም፡፡ በአሁኑ ጊዜ የሳውዲ አረቢያ ወሮበሎችና ጋጠወጦች በኢዮጵያውያን/ት ዜጎች ላይ እየፈጸሙት ያለው በቪዲዮ ማስረጃነት ተደግፎ የቀረበው የሰብአዊነት መብት ረገጣ ወንጀል በጣም የሚዘገንንና በሰለጠነ የሰው ልጅ ህሊና ሊታሰብ የማይችል ነገር ነው፡፡ 

ze ethiopiaኢትዮጵያና ሳውዲ አረቢያ፡ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች፣ 

ኢትዮጵያና ሳውዲ አረቢያ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው፡፡ የሳውዲ አረቢያና የኢትዮጵያ ገዥዎች ከአንድ ጥለት የተቆረጡ ናቸው፡፡ የሳውዲ አረቢያ መንግስት በሰብአዊ መብት አያያዝ መዝገቡ በመጥፎ ተምሳሌነቱ ይታወቃል:: በተመሳሳይ መልኩ የኢትዮጵያ መንግስት በሰብአዊ መብት አያያዝ እንደ ሳውዲ አረቢያ ሁሉ ያስጠይፋል፡፡ የሳውዲ አረቢያው ገዥ ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎችን በጣም ሰብአዊነት በጎደለው መንገድ ከግዛቱ በኃይል እንዲጋዙ/እንዲባረሩ የሚያደርግ መርህን ተከትሏል፡፡ በኢትዮጵያ ያለው ገዥ መደብም በተመሳሳይ መልኩ በሀገሩ ግዛት ውስጥ ኢትዮጵያውያንን/ትን ከሚኖሩበት ቀያቸው በግዳጅ ወደሌላ አካባቢ በማጋዝ አስደንጋጭ የሆነ የሀገር ውስጥ የማጋዝ (ሰፈራ) መርህን ተከትሏል፡፡ የሳውዲ ገዥ አናሳ የእምነት ተከታዮችን አሰቃይቷል፣ የኢትዮጵያ ገዥ መደብም እንደዚሁ አድርጓል፡፡ በሳውዲ ያለው ገዥ መደብ ዜጎችን በስፋት በዘፈቀደ በቁጥጥር ስር ያውላል፣ በእስር ቤት ያጉራል፣ ያሰቃያል፣ እንዲሁም በህግ ከለላ ጥላ ስር በሚገኙት ዜጎች ላይ ህገወጥ የእስር ቤት አያያዝን ያራምዳል፡፡ የኢትዮጵያ ገዥ መደብም በተመሳሳይ መልኩ የሳውዲ ገዥ የሚፈጽማቸውን የአፈና ድርጊቶች ሙሉ በሙሉ ይፈጽማል፡፡ የሳውዲ ገዥ የባሪያ ንግድን እ.ኤ.አ በ1962 በአዋጅ ካስቆመ በኋላ “ከፋላ” “kafala” (ተያዥ ያላቸው ስደተኛ ሰራተኞች፣ ሆኖም ግን በባሪያ ንግድ የአሰራር ሁኔታ የሚሰሩ) የሚል ቅጥያ በመስጠት ብዝበዛውን ቀጥሎበታል፡፡ እ.ኤ.አ በ2009 የባህሬን የሰራተኛ ሚኒስትር ማጅድ አል አላዊ ሲናገር ከፋላ የሚለውን የማደናገሪያ ቅጥያ ከባሪያ ንግድ ጋር አመሳስሎታል፡፡ እ.ኤ.አ የ2013 ዓለም አቀፍ የባርነት አመላካች አሀዝ/Index እንዳመለከተው 651,000 የሚሆኑ በባርነት ተይዘው ህይወትን በመግፋት ላይ የሚገኙ የኢትዮጵያ ዜጎች ሲኖሩ ከእነዚህም የዓለምን ሶስት አራተኛ ከሚይዙት ከመጀመሪያዎቹ አስር አገሮች ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን በግልጽ አስቀምጧል፡፡ 

ሂዩማን ራይትስ ዎች/Human Rights Watch እ.ኤ.አ በ2013 ባቀረበው ዓለም አቀፋዊ ዘገባው የኢትዮጵያንና የሳውዲ አረቢያን የሰብአዊ መብት አያያዝ ሬከርድ በሚመሳሰል መልኩ እንደሚከተለው አቅርቦታል፤

በ2012… የኢትዮጵያ ባለስልጣኖች ሀሳብን በነጻ የመግለጽ፣ የመደራጀትና የመሰብሰብ መሰረታዊ መብቶችን መገደብን በስፋት ቀጥለውበታል፡፡ ሂዩማን ራይትስ ዎች ዘገባውን በመቀጠል በአዲስ አበባ ማዕከላዊ እየተባለ በሚጠራው የፌዴራል ፖሊስ የምርመራ ማዕከል ፣ እንዲሁም በሶማሊ፣ በኦሮሚያ እና በጋምቤላ ክልሎች እስር ቤቶችና በወታደራዊ ማዕከሎች የሚፈጸሙትን የማሰቃየት ድርጊቶች ዝርዝር ዘገባ አቅርቧል፡፡

የሙስሊሙን ህብረተሰብ አመጽ ተከትሎ በኦሮሚያና የአገሪቱ መናገሻ በሆነችው በአዲስ አበባ ከተማ አመጹን ለመግታት በሚል ሰበብ የደህንነት ኃይሎች ሰላማዊ ሰዎችን ከህግ አግባብ ውጭ በቁጥጥር ስር በማዋል፣ እስራትና ድብደባዎችን ፈጽመዋል፡፡ የፌዴራል ፖሊስ ድብደባን ጨምሮ በአገሪቱ ከፍተኛ የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ላይ መንግስት ጣልቃ መግባቱን እንዲያቆም የሚጠይቀውን የሙስሊሙን ህብረተሰብ ሰላማዊ ተቃውሞ ለመግታት ሲል መንግስት ከልክ ያለፈ ኃይልን ተጠቅሟል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት መሰረታዊ አገልግሎቶችን ለህብረተሰቡ ለማድረስ በሚል ሰበብ የመንደር ማሰባሰብ ተግባሩን እውን ለማድረግ በአምስት የአገሪቱ ክልሎች 1.5 ሚሊዮን የገጠር ሰፋሪዎችን የማሰባሰብ ስራ ቀጥሏል፡፡ በጋምቤላ ክልል ብዙ ሰፋሪዎች ከሚኖሩበት ቀዬ በኃይል ተፈናቅለው ብዙ መከራ ደርሶባቸዋል… በመንግስት ጥረት የሚከናወን የሸንኮራ አገዳ ልማትን ለማፋጠን ሲባል በኢትዮጵያ የታችኛው ኦሞ ሸለቆ የሚኖሩትን ኗሪ የፓስቶራል ህዝቦች መንግስት በኃይል አፈናቅሏል:: በደቡብ ኦሞ ዞን ወደ 200 ሺ የሚሆኑ የአካባቢው ኗሪ ህዝቦች መሬታቸውን ለሸንኮራ አገዳ ልማት ይፈለጋል በሚል ሰበብ መንግስት መሬታቸውን በመንጠቅ ወደ ሌላ ቦታ እንዲሰደዱ አድርጓል፡፡   

ሳውዲ አረቢያን በሚመለከት ሂዩማን ራይትስ ዎች የሚከተለውን ዘገባ አቅርቧል፣

እ.ኤ.አ በ2012 ከህግ አግባብ ውጭ የሚከናወኑትን እስራቶችና ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን የማዋከቡ ሁኔታ እየጨመረ በመምጣቱ ዜጎች ሰላማዊ ሰልፍ በማድረጋቸው ምክንያት የሳውዲ አረቢያ መንግስት የኃይል እርምጃን ተጠቅሟል… እንዳለፉት ዓመታት ሁሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ፍትሀዊ ያልሆነ ፍርድን ተቀብለዋል፣ ወይም ደግሞ ከህግ አግባብ ውጭ ለእስራት ተዳርገዋል… እስረኞች ህጻናትን ጨምሮ ስልታዊ የህግ የበላይነት ጥሰት እና ፍትሃዊ ህግ የማግኘት መብት የመነፈግ፣ ከህግ አግባብ ውጭ እስራትና ማሰቃየት እንዲሁም ህገወጥ የእስር ቤት አያያዝ ደባ ይፈጸምባቸዋል… ባለስልጣኖች የ9 ሚሊዮን የውጭ ሰራተኞችንና የ9 ሚሊዮን የሳውዲ ሴቶችና ልጃገረዶች መብት ማስከበር አልቻሉም ወይም ጭቆናውን ቀጥለውበታል…

ወደ 1.5 ሚሊዮን የሚሆኑ የአገር ውስጥ ስደተኛ ሰራተኞች ከ2005 የሰራተኞች ህግ ውጭ ተደርገዋል… ባለፉት ዓመታት የኤሲያ ኤምባሲዎች ዘገባ እንደሚያመለክተው ከሀገር ውስጥ ሰራተኞች ቅሬታ እንደሚያሳየው በቀን ከ15 እስከ 20 ሰዓታት፣ በሳምንት ደግሞ 7 ቀናት እንዲሰሩ ከመገደዳቸውም በላይ ደመወዛቸውን ያለመክፈል ሁኔታም ተንጸባርቋል፡፡ የሀገር ውስጥ ሰራተኞች በአብዛኛውም ሴቶች በተደጋጋሚ ጊዜ ተገደው እንዲወልዱ ይደረጋል፣ ምግብ የማግኘት መብታቸውን ያጣሉ፣ እንዲሁም የጾታ ትንኮሳ፣ የአካልና የስነልቦና ጫናዎች ይደረጉባቸዋል፡፡ 

ሳውዲ አረቢያ ከእስልምና አስተህምሮ ውጭ የሌሎችን እምነቶች አስተምህሮዎችን ለመቀበል ትዕግስቱ የላትም፡፡ ባለፈው መጋቢት ወር ልዩ ልብስ ለባሹ ሸክ በአረቢያ ፔንሱላ የሚገኙ ማናቸውም ቤተክርስቲያኖች በሙሉ እንዲወድሙ ጥሪ አስተላልፎ ነበር… 

“የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር” ቴዎድሮስ አድሃኖም ምን እንዳሉና ያሉትንም እንዳላወቁ፣ 

tewedros adhanom with returneesበኢትዮጵያ ያለው ገዥው አካል በሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን/ት ላይ በአሁኑ ጊዜ እየደረሰ ያለውን አስፈሪ ሁኔታ በማስመልከት የሚሰጠው ምላሽ ጭንቅላትን ይበጠብጣል፡፡ የወባ ትንኝ ተመራማሪውና ከመቅጽበት ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት የተቀየሩት ቴዎድሮስ አድሃኖም እንዲሁም እ.ኤ.አ ከ2015 ሀገራዊ ምርጫ በኋላ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ ይረከባሉ ተብለው የሚጠበቁት ባለስልጣን ስለሳውዲ አረቢያው የኢትዮጵያውያን/ት ሁኔታ አስመልክቶ በኖቬምበር አጋማሽ በአዲስ አበባ ላይ በተካሄደው በ3ኛው ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ዕቅድ ምጣኔ ጉባኤ ላይ ሲናገሩ ግራ ተጋብተዋል፣ እዚህና እዚያ የሚዋዥቅ ንግግርም አሰምተዋል፡፡ ቅንነት የጎደለው እርግጠኝነትና በባዶ ተስፋ የተሞሉ ቃልኪዳኖችን አነብንበዋል፡፡ ወገኖቻችን ወደ ትውልድ አገራቸው እንዲመጡ በደስታ ለመቀበልና ዓለም ቀፋዊ ተብብርን ማጠናከር አስፈላጊ እንደሆነ በየኋህነት/ሞኝነት አገላለጽ አስቀምጠውታል፡፡ 

እንደምታውቁት፣ ከሳውዲ አረቢያ እንደምታውቁት ኢትዮጵያውያንን ብቻ ቢያግዙም/ቢያባርሩም ቅሉ ሌሎችን ዜጎችም እንዳባረሩ እንረዳለን… ባለፉት አስርት ቀናት እንዳየሁትም፣ ምክንያቱም በቤተሰብ ምጣኔ ዕቅድ እንደምንለው ለልጃገረዶችና ለሴቶች ክብካቤ እናደርጋለን፣ ከጣቢያዎች እርዳታ በመፈለግ ከሚጮሁ ሴቶች በቀጥታ ጥሪዎች ደርሰውኛል… በመቶዎቸ የሚቆጠሩትን በእርግጠኝነት ተቀብለናል፣ በሺዎችና በአስር ሺዎች የሚቆጠሩትን እንቀበላለን ብለን እንጠብቃለን፣ በእርግጠኝነት ለመናገር የምፈልገው ዜጎቻችንን ወደ አገራቸው እንዲመጡ ለመቀበል ሙሉ በሙሉ ዝግጁ ነን፡፡

በጣም አዝኛለሁ፣ ስሜቴም ተጎድቷል፡፡ ለዚህም ነው ይህ ሁኔታ ከተጀመረ ወዲህ ባለው የጊዜ መደበላለቅ ምክንያት ወደዚህ ላለመምጣት ዶ/ር ተከስተን ጠይቄ የነበረው፡፡ ሆኖም ግን በዓለምአቀፋዊነት ትብብር መሰረት ህገወጦችን ማባረር/ከአገር ማስወጣት የምንችል ቢሆንም ይህንን ጉዳይ በሰከነና በሰለጠነ መልክ እናደርገዋለን፣ ምክንያቱም ይህ ድርጊት የጦርነት ሁኔታ አይደለምና፡፡ እንደዚህ ያለው ሁኔታ ተቀባይነት ሊኖረው የሚችለው አገሮች በጦርነት  ላይ ሲሆኑ ብቻ ነው፣ ህዝብም በፈጠነ መልኩ ነገሩን ሊረዳው ይችላል፣ ነገር ግን በሰላማዊ ሁኔታ ሊሆን አይችልም፡፡ 

…በመሆኑም በዚህ መልክ በመጀመሬ አዝናለሁ፣ ይህ ሁኔታ እስከ አሁን ድረስ እየቆጠቆጠኝ የቆየ ጉዳይ ስለሆነ ነው፡፡

በእርግጥ በኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ የአጭርና የረዥም ጊዜ መፍትሄ በማስቀመጥ ችግሮቹን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመፍታት ጥረት ስናደርግ ቆይተናል፣ ምክንያቱም ችግሮቹ ስር የሰደዱና ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መወገድ ያለባቸው በመሆናቸው ነው፡፡ እንደምታውቁት ኢትዮጵያ እያደገችና ባለሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ እድገት ምጣኔ እያስመዘገበች ነው፣ በዚህም አካሄድ ከጨለማው ዋሻ የውስጥ ጉዞ በኋላ ከጫፍ ላይ ብርሀን ይታየኛል፣ እና ይህንን ያለጥርጥር ተግባራዊ እናደርገዋለን፣ በዚህም ጥረታችን ድህነትን ተረት እናደርጋለን፡፡ በትክክለኛው መንገድ ላይ ነን፣ ሆኖም ግን ዓለም አቀፋዊ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ እምነቴ የጸና ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ይሳካል ብለን አንጠብቅም፡፡ 

ነገሩን ለማታውቁት አንድ ነገር ላካፍላችሁ እፈልጋለሁ፡፡ ነብዩ መሀመድ ታላቁን የእስልምና እምነት አስተምህሮቱን ሀ ብሎ ሲጀምር በደረሰበት መሳደድ ምክንያት ደቀመዝሙሮቹን/ተከታዮቹን ወደ ኢትዮጵያ ነበር የላከው… ስለዚህ አዝናለሁ፣ ንግግሬንም እዚህ ላይ አቆማለሁ…ሆኖም ግን የሚሰማኝን ስሜት ሁሉ በዝርዝር በመግለጼ፣ ያለፉት 10 ቀናት በህይወቴ ካየኋቸው ነገሮች ሁሉ እንዴት መራር እንደነበሩና ይከሰታሉ ብለን የማንጠብቃቸው አስገራሚ ነገሮች እየሆኑ በማየቴ እዚህ በመካከላችሁ በመገኘት ለእናንተ ሀሳቤን በማካፈሌ ደስታ ይሰማኛል…:: 

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች ላይ በሳውዲ አረቢያ መንግስት አየተፈጸመ ያለውን አስደንጋጭ የሰብአዊ መብት ረገጣ ወንጀል በማስመልከት የኢትዮጵያ “ቁንጮ የዲፕሎማት ሰው” እንደዚህ ያለ ተያያዥነት የሌለው፣ የተበታተነ፣ ዝብርቅርቅ ያለ እና እጅ እግር የሌለው ትንታኔ እና ገለጻ ሲያቀርቡ ስሰማ እጅጉን ነው ያዘንኩት፡፡ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ከወባ ትንኝ ተመራማሪነትና ከመቅጽበት ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት በተቀየሩ ግለሰብ የአፍ ካራቴ ዥዋዥዌ ልምምድ መቀለጃ ሆነ! ማንም ሊያደርገው እንደሚችለው የአድሃኖምን ቅጥ አምባሩ የጠፋ ንግግር መሰረት በማድረግ የሚከተሉትን ጭብጦች መመርመር ተገቢ ይሆናል፡፡

1. አድሃኖም እንዲህ አሉ “…በቃላት ሊገለጽ በማይችል መልኩ በኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች ላይ የሳውዲ አረቢያ መንግስት ያደረሰውን ሰቆቃ ሲያስታውሱ “እስከ አሁን ድረስ ነገሩ እየቆጠቆጣቸው“ እና አሁንም ድረስ “እንዳዘኑ“ እና የሳውዲ አረቢያ መንግስት በኢትዮጵያውያት ሴቶች ላይ በሚፈጽመው ደባ ምክንያት ሰብአዊ መብታቸው እየተረገጠ ያሉ ሴቶች እገዛ ለማግኘት በሚያሰሙት ጩኸት “ስሜታቸው እንደተጎዳ“ ተናግረዋል፡፡ ይኸ “ታላቁ የዘመኑ ውሸት!“ ሊባል ይችላል፡፡

ምናልባትም አድሃኖም በእንግሊዝኛ ቃላት መካከል ያለውን ጥቃቅን ልዩነት ማስተዋል ባለመቻላቸው በተለይም ቀጥተኛ ያልሆነውን የአነጋገር ዘየ/colloquialism ተከትለው ይሆናል በማለት አስተያየት መስጠት ይቻል ይሆናል፡፡ ሆኖም ግን እንደ ቁንጮ የዲፕሎማት ሰውነታቸው ለአላዋቂነት የቃላት አጠቃቀሞቻቸው ይቅርታ ሊደረግላቸው አይገባም (በእርግጥ የቃላት እና የሀረጎች አመራረጣቸው አመለካከታቸውንና ስሜታቸውን የሚገልጹ ቢሆንም)፡፡ በኢትዮጵያውያን/ት ላይ በሳውዲ አረቢያ መንግስት እየተደረገ ያለው ግፍ “እስከ አሁን ድረስ ነገሩ እየቆጠቆጣቸው“ እንደሆነ የሚገልጸው አባባል ተጎጂ ኢትዮጵያውያን/ት በሳውዲ አረቢያ ያሉበት ሁኔታ የንዴት ምንጭ እንደሆናቸውና ጥቂት እንዳሳሰባቸውም ጠቋሚ ነው፡፡ ይህ ትልቅ ጉዳይ አይደለም እንደማለት አነጋገር ነው ፡፡ በዓለም ላይ የየትኛውም አገር የዲፕሎማሲ ቁንጮ የሆነ ሰው በዜጎቹ ላይ ኢሰብአዊና ኃላፊነት የጎደለው አያያዝ መደረጉን አስመልከቶ “እስከ አሁን ድረስ ነገሩ እየቆጠቆጠው” መሆኑን ለሌላ አገር ሰው ሲናገር አልተሰማም፣ አልታየምም፡፡ 

አድሃኖም በውል ያላጤኑት ቢሆንም ቃላት በዓለም አቀፍ የዲፖሎማሲው ቋንቋ ትልቅ ትርጉም አላቸው፣ ቃላት የዲፕሎማቶች ዓላማ ማስፈጸሚያ መሰረታዊ ሀብቶች ናቸው፡፡ የዲፕሎማቲክ ሰዎች እነርሱ በመረጧቸው ቃላትና የቃላት አጠቃቀም ዓለም እንዲቆምና እንዲሄድ የማድረግ ወይም አንዳንድ ጊዜም ሆን ብለው ለትርጉም ልቅ የሆኑ ወይም ደግሞ ውሱን የሆኑ ቃላትን በመጠቀም ዓላማቸውን ለማሳካት የሚሄዱበት ዘዴ ነው፡፡ የዲፕሎማቶች ቃላት ግልጽና ድብቅ ትርጉም ባላቸው መልዕክቶች የተሽሞነሞኑ እና ድብቅ ዓላማን ለማሳካት የተዘየዱ ማስፈጸሚያ መሳሪያዎች ናቸው፡፡ በሰዋስዋዊው የቃላት አመሰራረትና በሚሰጡት ትርጉም ጥንቁቅነት በዲፕሎማሲው ቋንቋ ቃላት ሰላምን ያሰፍናሉ፣ ጦርነትን ያውጃሉ፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ የዲፕሎማቶች ቃላት የዲፕሎማቶችን ግላዊ የሀዘን ስሜትና የስሜታቸውን መጎዳት ብቻ የሚገልጹ ሳይሆን ከዚህ በተጨማሪ የዲፕሎማቶቹን የሞራል ስብእና፣ የስቅይቱን ጥልቀትና የሀገራቸውን ህዝቦች ስሜት ሊያንጸባርቅ ይገባል፡፡ 

አድሃኖም በሳውዲ አረቢያ ያሉ ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች ሁኔታ “እስከ አሁን ድረስ ነገሩ እየቆጠቆጣቸው“ እንደሆነ ሲገልጹ ለሳውዲ አረቢያ መንግስት አደገኛ የሆነ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ሊገነዘቡ ይገባል፡፡ እንዲህም ብለው እየነገሯቸው ነው፣ አዲሱ የይስሙላው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ የዓለም አቀፉን የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ለማውገዝ በአፍሪካ ህብረት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተገኝተው የተናገሩትን በመዋስ “የዘር አደን“ በኢትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ሰራተኛ ዜጎች ላይ በሳውዲ አረቢያ ፖሊሶችና ጋጠወጦች በየመንገዱ እየተደረገ ያለውን ሁከትና ትርምስ አሳሳቢ ያደርገዋል፡፡ ተገቢ የዲፕሎማሲ ንግግር ከተደረገ ይህንን አደገኛ ሁኔታ  እንዲቀንስ ያደርገዋል፡፡ 

በአሁኑ ወቅት በሳውዲ አረቢያ እየተካሄደ ያለው ኢትዮጵያውያንን/ትን የማዋረድና ኢሰብአዊ የሆነ ድርጊት የመፈጸም ሁኔታ ትልቅና በጣም ትልቅ የሆነ አገራዊ ጉዳይ ነው፡፡ በግሌ ለምሳሌ በዋና የስራ ሰዓት ጊዜ የሚይዝ የትራፊክ መኪና መጨናነቅ የንዴት ደረጃየን ከፍ ያደርገዋል፣ የተሰጣቸውን የቤት ስራ ሳይሰሩ በሚመጡ ተማሪዎቼ ላይ የሚኖረኝ ንዴት ከልኩ ያለፈ ነው:: ሳውዲዎች በኢትዮጵያውያን/ት ላይ እየፈጸሙት ያለው ግፍ ግን እንድናደድ ብቻ አላደረገኝም፣ ደሜ እንዲፈላ ጭምር አደረገኝ እንጅ፡፡ የሳውዲ አረቢያ ፖሊሶች በኢትዮጵየውያን/ት ላይ ሲፈጽሙት የነበረውን አረመኒያዊና ኢሰብአዊ የሆነ ድርጊት ስመለከት እሳት ነበልባል ሆኛለሁ፡፡ የሳውዲ አረቢያ ወሮበሎችና ጋጠወጦች በኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች ላይ ሲፈጽሙት የነበረውን አረመኒያዊና ጭካኔ የተሞላበት የሰብአዊ መብት ረገጣ ስመለከት በንዴት ድብን ብዬ አራሴን አስከ መሳት ደርሼ ነበር፡፡ በኢትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ሰራተኞች ላይ በሳውዲ አረቢያ ወሮብሎችና ጋጠወጦች እየተደረገ ያለውን ኢሰብአዊና ከህግ አግባብ ውጭ እየተደረገ ያለውን ጀብደኝነት የሳውዲ ገዥው አካል እያየ ጆሮዳባ ማለቱ የበለጠ እንድበሳጭና እራሴን እንድስት አድርጎኛል፡፡ የሳውዲ መንግስት ዓለም አቀፍ ሕግን በጠበቀ መልኩ በኢትዮጵያውያን ስደተኛ ሰራተኛ ዜጎች መብት አያያዝ ላይ ምንም ነገር ባለማድረጉ በጣም ተበሳጭቻለሁ፣ አማርሪያለሁም፡፡ ኢትዮጵያውያን/ት በሳውዲ አረቢያ እየተፈጸመባቸው ያለው ግፍና መከራ አድሃኖምን ብዙም ያሳሰባቸውና ያስጨነቃቸው አይመስልም፡፡ 

በዓለም አቀፋዊ የዲፕሎማሲ ቋንቋ መርህ መሰረት ጠንካራና ፊትለፊት በመግጠም የሚደረግ እና አስታራቂና ዲፕሎማሲያዊ በሆነ ለስለስ ባለ ቋንቋ ለመጠቀም የራሱ ጊዜ አለው፡፡ በእውነቱ ይህ ታላቅ ሀገራዊ ውድቀት ነው፣ አድሃኖም በሁለቱ መካከል ያለውን ልዩነት በውል የተገነዘቡት አይመስለኝም፡፡

1463694_604158499630460_178987358_n2. ሳውዲ አረቢያዎች በኢትዮጵያውያን/ት ላይ እንዲህ በፈጣን መልኩ እየፈጸሙ ያሉት ከአገር የማባረርና የማስወጣት ሁኔታ “አንድ አገር በጦርነት በወደቀችበት ጊዜ የተደረገ ቢሆን ኖር ተቀባይነት ሊኖረው ህዝብም ሊረዳው ይችል ነበር” ብለዋል አድሃኖም፡፡ ከዚህ አንጻር አድሃኖም ያልተገነዘቧቸው በርካታ ዓለም አቀፍ ስምምነቶች፣ በጣም መሰረታዊ የሆኑ መርሆዎችና ህጎች መኖራቸውን ያሳያል፡፡ ከጦርነት ጋር በተያያዘ መልኩ ዜጎችን ከሀገር የማባረሩ ሁኔታን አስመልክቶ ያሉትን ህጎችና ልምዶች አንዳንድ ጊዜም የዘር ማጽዳት ድርጊቶች እንደሚፈጸሙ አድሃኖም የተገነዘቡ አለመሆኑን ይህ ሁኔታ በግልጽ ያመላክታል፡፡ እ.ኤ.አ 1990ዎቹ የመጀመሪያዎቹ ዓመታት ገደማ በሄርዞጎቪና እና ቦሲኒያ መካከል በተደረገው ጦርነት በርካታ የቦሲኒያ እስልምና እምነት ተከታዮች፣ ክሮሽያዎች፣ ሰርቦችና ቦሲኒያዎች ከትውልድ ቦታቸው የተቀነባበረ የማባረር/የማስወጣት ስልት በመጠቀም ተግባራዊ ተደርጎባቸዋል፡፡ ያ የጦር ወንጀለኝነት ነው፡፡ ይኸ እንዲሁ “ህዝብ በቀላሉ ሊረዳው የሚችል” ጉዳይ አይደለም አድሃኖም አንዳሉት፡፡ በጦርነት ጊዜ በኃይልና በማስገድደ ከአገር የማስወጣት አስፈላጊነት ለህዝቡ ደህንነት ሲባል በሚጠበቁ ሰዎች ወይም በጦር መሪዎች ላይ የሚፈጸም መሆኑን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በ1949 የጸደቀው ስምምነት (IV) በጦርነት ጊዜ የሲቪል ሰዎችን ለመከላከል የተዘጋጀው ሰነድ በግልጽ ያሳያል፡፡ የስደተኞችን ጉዳይ አስመልክቶ በ1951 ስምምነት መሰረት በ1967 የስደተኞችን ሁኔታ አስመልክቶ የተዘጋጀው ፕሮቶከል እንዲሁም በአንቀጽ 3 በ1984 ማሰቃየትን በተመለከተ የተዘጋጀውን ስምምነት መሰረት በማድረግ ኢትዮጵያውያን/ት ስደተኞች ከማንኛውም ህገወጥ ማባረር/ማስወጣት ድርጊት መጠበቅ እንዳለባቸው በግልጽ ያሳያሉ፡፡ በጣም መሰረታዊ በሚባሉ የዓለም አቀፍ ህጎች፣ ደንቦችና መርሆዎች አንጻር አድሃኖም ያላቸው ግንዛቤ ሲመዘን በጣም አናሳ ሆኖ መገኘቱን ስናጤን እንደ ሀገር አሳሳቢ ሀገራዊ ኪሳራ መሆኑን ያሳያል፡፡ 

3. በአሁኑ ጊዜ በሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን/ት ላይ ለሚፈጸመው ሰቆቃና አንገብጋቢ ችግር መፍትሄው ዜጎቹ ከዚያ ሀገር የሚወጡበትን ስራ ማፋጠን እንደሆነ አድሃኖም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን/ት ስደተኞች ላይ የሚፈጸመውን የኃይል እርምጃ፣ አስገድዶ መድፈር፣ ግድያና ማሰቃየት ማስቆም ጊዜ የማይሰጠው አጣዳፊ፣ ወሳኝ፣ አንገብጋቢ እና ክብደት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ በእርግጥ አድሃኖም ይህንን ጉዳይ በሚመለከት እንደሚከተለው አስረግጠው ተናግረዋል፡፡ “በእርግጥ ችግሩን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመፍታት የረዥምና የአጭር ጊዜ መፍትሄዎችን በመንደፍ ጥረት ስናደርግ ቆይተናል፣ ምክንያቱም እነዚህ ችግሮች ለብዙ ጊዜ የቆዩና ስር የሰደዱ በመሆናቸው ነው“ በማለት አስተያየታቸውን ቋጭተዋል፡፡ እርግጥ ነው የረዥምና የአጭር ጊዜ መፍትሄዎች ሊቆዩ ወይም ጊዜ ሊወስዱ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን በሳውዲ አረቢያ ፖሊሶች፣ ወሮበሎች እና ህገወጦች በየዕለቱ እየተፈጸሙ ያሉ የውርደት ሰራዎች፣ ህገወጥ አያያዞች፣ ፍትህአልባነት እና ወንጀሎች በእንዲህ ያለ ሁኔታ ሊቆዩ በፍፁም አይችሉም፡፡ በአሁኑ ጊዜ በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን/ት ላይ እየተፈጸመ ያለው መጠነሰፊ ኪሳራ ነው፡፡ ስቅይቱን በፍጥነት ለማስቆም አድሃኖም ምንም ዓይነት ሀሳብ የሌላቸው እና መፍትሄዎችን ያላመላከቱ በመሆኑ ይህ አንገብጋቢ አገራዊ ኪሳራ ነው፡፡ 

አድሃኖም እንዲህ ይላሉ፣ በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ትዮጵያውያን/ት ስደተኞች ላይ “እንዲህ ያለ ድርጊት ይፈጸማል ብለን በምንም ታምር አልጠበቅንም“፣ እንዲህም ይላሉ ለእራሳቸው፣ “ሁሉም ነገር የሚያስደንቅ ነው“፣ በመቀጠልም እንዲህ ይላሉ፣ “የረዥምና የአጭር ጊዜ መፍትሄዎችን ለማምጣት ለብዙ ጊዜ ጥረት አድርገናል“፡፡ ይህ የተምታታ እና የተዘበራረቀ አባባል እርስ በእራሱ የሚጣረስ ብቻ አይደለም፣  ሊታመን በማይችል መልኩ አሳሳች መግለጫ እና የአድሃኖምን የዋህነትና የዲፕሎማሲ  እውቀት እጥረትና ችሎታ ማጣት የሚያሳይ መገለጫ እንጅ፣ በሳውዲ አረቢያ የኢትዮያውያንን/ትን ሁኔታ በሚመለከት “ሁሉም ነገር የሚያስደንቅ ነው“ የሚለው የአድሃኖም አባባል ተቀባይነት የሌለው ነገር ነው፡፡ ምክንያቱም እ.ኤ.አ በኤፕሪል 2013 አድሃኖምና የእርሳቸው ገዥው አካል  የሳውዲ አረቢያ ገዥ በሀገሩ ውስጥ በህገወጥ መንገድ ገብተው ምንም ዓይነት ህጋዊ ሰነድ ሳይኖራቸው በሀገሩ የግዛት ክልል ውስጥ የሚገኙ የውጭ አገር ሰራተኞችን ህጋዊ ለማድረግ ወይም ደግሞ ወደየመጡባቸው አገሮች እንዲመለሱ እና ህገወጥ ማባረር፣ እስራትና ስቅይትን ለማስቀረት በማለት ያስተላለፈውን ትዕዛዝ በሚገባ ያውቃሉ፡፡ የአድሃኖም ገዥው አካልም በተመሳሳይ መልኩ በሳውዲ አረቢያ ውስጥ ምንም ዓይነት ህጋዊነት  ሳይኖራቸው የሚሰሩና የሚኖሩ በርካታ ህገወጥ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን/ት እንዳሉ ከማመናቸውም በላይ አሳምረው ያውቃሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የሳውዲ ገዥ እ.ኤ.አ በጁላይ 2013 በሀገሩ ውስጥ የሚገኙትን ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ሳይኖራቸውና ምንም ሰነድ የሌላቸውን የውጭ አገር ዜጎች በማስመልከት ህጋዊ እንዲሆኑ ወይም ሀገር ለቀው እንዲወጡ አጽንኦ በመስጠት እ.ኤ.አ እስከ ኖቬምበር 2013 ድረስ ቀነ ገደብ መስጠቱን አድሃኖምና ገዥው አካላቸው በሚገባ ያውቁታል፡፡ ግና የአድሃኖም ገዥ አካል ከመስማት ባለፈ የአዋጁን እንደምታና ወደፊት በስደተኛ ዜጎቹ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን በአዎንታዊም ሆነ በአሉታዊ ጉኑ ሊያየው ስላልፈለገ የወደፊቱን ማቀድም አልቻለም፣ በቀጣይነት በገፍ ወደ ሳውዲ አረቢያ በሚጓዙ ዜጎች ላይ እንዲሁም በሳውዲ አረቢያ ፖሊስና ወሮበሎች በቀጣይነት ስለሚደረገው ጥቃት የሚሉት ነገር አልነበራቸውም፡፡ በአጭሩ ምንም ነገር ሳያደርጉ እጃቸውን አጣጥፈው በመቀመጥ ሲመለከቱ በከንቱ ሳይጠቀሙበት ጊዚያቸውን አባክነዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ እ.ኤ.አ በኖቬምበር 2013 በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ዜጎች ላይ ማህበራዊ ቀውስ ይደርሳል የሚለውን ሁኔታ እንዴት አድሃኖም በእርግጠኝነት መተንበይ አልቻሉም ይቻላል? 

Police-Addisአድሃኖም ፈጣን የፖሊሲ እርምጃ ለመውሰድ ብቃት የሌላቸው ሰው መሆናቸውን የድርጊቶች ኩነት በተጨባጭ ያሳያል፡፡ እንደ “ቁንጮ የዲፕሎማሲ ሰው” ብዙ መማር ይጠበቅባቸዋል፣ እንዲሁም ወደፊት ሊከሰቱ በሚችሉ ነገሮች ላይ ትኩረት በመስጠት የነገሮችን የአመጣጥ ሁኔታና ችግሮችን አስቀድሞ በማየት ተጨባጭ መፍትሄ ለማምጣትና ወደተግባር ለመፈጸም የሚያስችል ብቃትን ሊጎናጸፉ ይገባል፡፡ ፈላስፋው ጎቴ የሚከተለውን ሲል እውነትም ትክክል ነበር፣ “ምንም  ድንቁርናን በተግባር ከማየት የበለጠ አስደንጋጭ ነገር የለም ብሏል:” 

አድሃኖም ያልተናገሩት ወይም ያላደረጉት፤ 

በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለውን የኃይል እርምጃ ለማስቆም የኢትዮጵያ ገዥው አካል ስላደረገው ሁኔታ አድሃኖም አንድም ያሉት ነገር የለም፣ ሆኖም ግን አገዛዙ ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ ዘለቄታዊ መፍትሄ ለመስጠት የረዥም እና የአጭር ጊዜ መፍትሄዎችን ለማምጣት ብዙ ርቀት የተጓዘ መሆኑን ከመግለጽ ውጭ ተጨባጭነት ያለው እርምጃ አልታየም፡፡ በተጨባጭ እየሆነ ያለው ግን አድሃኖም እና ገዥው አካላቸው አትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ዜጎቻቸው በሳውዲ አረቢያ መንገዶች እንደ አውሬ እየታደኑ ኢሰብአዊ ድርጊት ሲፈጸምባቸው ከዳር ቆመው ጣቶቻቸውን በመቀሰር፣ ጭንቅላቶቻቸውን በመነቅነቅ ከመታዘብ ውጭ ሌላ መገለጫ የለውም፡፡ አድሃኖም በዜጎቻችን ላይ እየተፈጸመ ያለውን የኃይል እርምጃ ለማስቆም ምንም  ጥረት አለማድረጋቸው ብቻ ሳይሆን ትንሿን ነገር ለዓም አቀፉ ማህብረሰብ በማሳወቅ በሳወዲ አረቢያ መንግስት ላይ ጫና እንዲደረግ እንኳን ሙከራ አላደረጉም፡፡ አድሃኖም ካልተናገሯቸው ወይም ካልፈጸሟቸው ጉዳዮች ውስጥ ከብዙ በጥቂቱ እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡ 

በጠንካራ ቃላት የተዘጋጀ የውግዘት መግለጫ፤ አድሃኖም እንዲህ ብለዋል፣ “ገዥው አካል የሳውዲ አረቢያ መንግስት በግዛት ክልሉ ውስጥ ባሉ ስደተኛ ሰራተኛ ዜጎቻችን ላይ ያደረሰውን ጭካኔ የተሞላበት የኃይል እርምጃ እናወግዛለን፣ ይህ በምንም ዓይነት መልኩ ተቀባይነት የለውም፣ የሳውዲ መንግስት ለጉዳዩ አጽንኦ በመስጠት ምርመራ እንዲደረግ ጥሪ እናደርጋለን፣ ዜጎቻችን ባሉበት በክብርና በመልካም ሁኔታ እንዲያዙ ሆኖ ዜጎቻችንን ወደ ሀገራቸው የምንወስድ መሆኑን እናሳውቃለን“ የሚል ነበር፡፡ “ተቀባይነት የለውም“ የሚለው ቋንቋ በሳውዲ አረቢያ ገዥ አካል፣ በፖሊስ ኃይሉ እና በወሮበሎች እየተፈጸመ ያለውን ዘገናኝ ጭካኔ፣ ለመናገር የሚዘገንን አረመኔነት፣ አስደንጋጭ ስቅይትና ወንጀለኝነት ለመግለጽ የሚጠቀሙበት የውግዘት ቃል ነው፡፡ እንደ አድሃኖም ግንዛቤ “ምርመራ“ ማለት የሳውዲ ገዥ ክፍል ከዚህ ከተፈጸመው ዘግናኝ ወንጀል አንጻር ጠንካራ እርምጃ ተወስዶ ማየት ነው፡፡ 

አድሃኖም “ተቀባይነት የለውም“ የሚለውን ቋንቋ በውል የተገነዘቡት አይመስልም፡፡ ይህ አባባል በዲፕሎማሲያዊ ቋንቋ የዲፕሎማሲ ሰዎች ምንም ነገር ሳይሉ አንድ ነገር እንዳሉ በማስመሰል የሚጠቀሙበት ባዶና መሰረት የለሽ ቃል ነው፡፡ ሁሉንም ነገር የሚል ትርጉም የያዘ ቃልም ነው…”ምንም ዓይነት ጠንቅ የለዉም አይኖረዉም ማለትም  ነው”:: እንደዚህ ነው እንግዲህ የዲፕሎማሲያዊ ቋንቋ  ባህሪያት፡፡ አንድ መስመር ዓረፍተ ነገር ሁለት የማይገናኙ ዓላማዎችን ሊያስተላልፍ የሚችል መልዕክት ሊኖረው ይችላል፡፡ በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ አትዮጵያውያን/ት ላይ እየተፈጸመ ያለው ድርጊት “ተቀባይነት የለውም” የሚል መልዕክት ለሳውዲ አረቢያ አምባሳደር በማስተላለፍ አድሃኖም በጉዳዩ ላይ የይስሙላ ስራን በመስራት ጉዳዩ አስኪረጋጋ ድረስ መጠቀሚያ ያደርጉታል፣ ከዚያ በኋላ ግን ሁሉቱም ወገኖች ወደነበሩበት ግንኙነት ተመልሰው የመሞዳሞ ስራቸውን ይቀጥላሉ፡፡ ቃሉን በትክክል ለመግለጽ “ተቀባይነት የለውም” የሚለው ቃል ብልህነት የጎዳላቸው ፉከራና ባዶ ኳኳታ በሚያሰሙ ምንም ነገር እና አንድም ነገር የማያደርጉ ሰዎች መገለጫ ነው፡፡ 

የጥገኛውን ሀገር አምባሳደር በመክሰስ የብጥብጡን ሁኔታ እንዲረዳና በፖሊስና በህገወጦች የሚፈጸመውን ህገወጥ ድርጊት በአስቸኳይ እንዲያስቆም ማድረግ፡ አድሃኖም የሳውዲ አረቢያ አምባሳደርን በመክሰስ እንዲህ ብለዋቸዋል፣ “የሳውዲ አረቢያ መንግስት ህገወጥ ስደተኞችን ለማስወጣት የተከተለውን መርህና የሳውዲ አረቢያ ባለስልጣኖች በህገወጥ ስደተኞች ላይ የወሰዷቸውን እርምጃዎች በተመለከተ ኢትዮጵያ ታላቅ አክብሮት አላት፡፡ እንዲሁም በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ዜጎቻችን ላይ የተወሰደውን ህገወጥ አያያዝና ግድያ ታወግዛለች“ ይላል፡፡ ግን ሰው  ምን ዓይነት አሽከርነትና ጫማ ላሽነት ውሰጥ ይዘፈቃል?! ለዜጎቹ የሚቆረቆር በምድር ላይ የሚኖር ማንም አገር ቢሆን የራሱን ዜጎች የስቃይ ሰለባ ላደረገ ሌላ አገር በምንም ዓይነት መልኩ ቢሆን “ክብር አለው” የሚል ቃል አይተነፍስም፡፡ አድሃኖም በጉዳዩ ላይ ጥልቅ ግንዛቤ ያላቸው አይመስልም፣ ምክንቱም ጉዳዩ ስለሳውዲ አረቢያ የግዛት ሉዓላዊነት ወይም ስለስደተኞች ፖሊሲ ጉዳይ አይደለም፣ ጉዳዩ የሳውዲ አረቢያ ገዥ አካል በኢትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ሰራተኛ ዜጎች ላይ እየፈጸመ ስላለው የሰብአዊ መብት ረገጣ ተገቢውን እርምጃ የመውሰድና ያለመውሰድ ጉዳይ ነው፡፡ 

ከዚህም በላይ አደሃኖምም ሆነ ወይም ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው ከሳውዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር የሚኖርን ተቃውሞ በይፋ ለህዝብ አላሳወቁም፡፡ “የተቃውሞ ደብዳቤ” ወይም “የዲፕሎማቲክ ማስታወሻ” የአንድ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለሌላው ጥፋት ለፈጸመው መንግስት ይቅርታ የማይደረግለትን የማይናወጥ አቋም በመግለጽ በይፋ ያሳውቃል፡፡ የተቃውሞ ደብዳቤው በምንም ዓይነት መልኩ ቢሆን “ተቀባይነት የለውም” የሚል ቃል አይጠቀምም፡፡ በጥቂቱም ቢሆን ስለ “”አሳሳቢ ጉዳዮች” እና ነገሮች መሻሻል ካላሳዩ ወደፊት “ጉዳት ሊያመጡ” የሚችሉ ጉዳዮችን በመጥቀስ ሊያሳውቅ ይችላል፡፡ አድሃኖም እንዳደረጉት እንቁጠረውና የተቃውሞ ደብዳቤ ለሳውዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የጻፉ መሆኑን ለህዝብ ይፋ ሊያደርጉ ይገባል፡፡ 

በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች ላይ የተፈጸመውን የሰብአዊ መብት ረገጣ በሚመለከት የአፍሪካ ህብረት የውግዘት መግለጫ እንዲያወጣ ማድረግ፤ እ.ኤ.አ በ2015 አስከሚደረገው አገር አቀፍ ምርጫ ድረስ የአድሃኖምን ወንበር እያሟሟቁ የሚገኙት የይስሙላው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያ ደሳለኝ የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት የዝውውር ሊቀመንበር ናቸው፡፡ ኃይለማርያም ደሳለኝ የተባበሩት መንግስታት የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በአፍሪካ መሪዎች ላይ የዘር አደን ይፈጽማል በማለት የዘር አደናውን ለማስቆም የአፍሪካ መሪዎችን በማሰባሰብና በማስተባበር ቆላ ደጋ በማለት ጥረት ሲያደርጉ የቆዩ እና እንዲያውም የህብረቱ አባል አገራት የሮማ ስምምነተን በመጣስ ከአይሲሲ አባልነት እንዲወጡ በመሃንዲስነት ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸወ የሚታወስ ነው፡፡ ነገር ግን በመቶዎችና በሺዎች የሚቆጠሩ የአገራቸው ዜጎች በሳውዲ አረቢያ መንገዶች በፖሊሶች፣ በወሮበሎችና በህገወጦች “የዘር አደና” ጥቃት ሲፈጸምባቸው ትንፍሽ አላሉም፣ የጎመንዘር ቅንጣት የምታክል ድርጊት አልፈጸሙም፡፡ (በነገራችን ላይ ይህ ሁሉ ስቃይ በኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች ላይ ሲፈጸም የይስሙላው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በአገር ውስጥ ነበሩን? ኢትዮጵያውያን በሳውዲ አረቢያ “የዘር አደን” እየተፈጸመባቸው መሆኑን አስመልክቶ ቃል ትንፍሽ ሲሉ የሰማ ይኖራልን?) 

አስቸኳይ ምርመር እንዲካሄድ ለተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን (UNHCR) ኮሚሽነር ማሳወቅ፣ ዩኤንኤችሲአር/UNHCR በተባበሩት መንግስታት በተሰጠው ኃላፊነት መሰረት “ዓለም አቀፍ የስደተኞችን ጥበቃ ማድረግና በስደተኞች ችግር ላይ ውሳኔ የመስጠት እንዲሁም ስደተኞችን የመምራትና የማስተባበር ስራ” ያከናውናል፡፡ ስደተኞች አግባብ ባልሆነ መልክ ሲያዙና የሰብአዊ መብት ጥሰት ካለ የመመርመር ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡ አድሃኖም UNHCR ጉዳዩን እንዲመረምረው መጠየቃቸውን የገለጹበት ሁኔታ የለም፡፡ ምናልባትም ጥያቄ አቅርበው ከሆነ መጠየቃቸውን የሚገልጽ መረጃ አልቀረበም፡፡ 

እንዲህም ሆኖ UNHCR ስደተኛ ሰራተኞችን ግጭት ከተከሰተበት ቦታ ወደ ሌላ ለማዘዋወር የሎጅሰቲክስ እርዳታ ብቃት አለው፡፡ ለምሳሌ ያህል እ.ኤ.አ በ2011 በሊቢያ ጸረ መንግስት አመጽ በተቀሰቀሰ ጊዜ UNHCR በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኛ ሰራተኞችን ከሊቢያ ወደ ጎረቤት አገሮች በማመላለስ የተቀላጠፈ ስራ ሰርቷል፡፡ 

ጉዳዩ በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን ኮሚሽነር/UNHCR እና በተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ጽ/ቤት/OHCHR ቀርቦ እንዲጣራ ቅሬታን ማስመዝገብ፤ ከOHCHR ዋና ዋና ተግባራት መካከል “የከፋ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ማጣራት” እና “የሰብአዊ መብት ጥበቃ ስራዎችን ማከናወን” ናቸው፡፡ የማጣራት ስራውን እንዲሰራ የሳውዲ ገዥ አካልን ከመጠየቅ ይልቅ አድሃኖም እንዲያጣሩትና ጣልቃ እንዲገቡ UNHCR እና OHCHRን መጠየቅ ነበረባቸው፡፡ 

የኢትዮጵያ ዜጎች ከሳውዲ አረቢያ ኤምባሲ ፊት ለፊት ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ እንዲያደርጉ መፍቀድ፤ ኢትዮጵያውያን/ት በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ላይ በተፈጸሙባቸው እና እየተፈጸሙባቸው ባሉት የሰብአዊ መብት ረገጣዎች ምክንያት ተዋርደዋል፣ ሀፍረትም ደርሶባቸዋል፡፡ አድሃኖም በኢትዮጵያ ጥገኝነት እንዲጠይቁ ነብዩ መሀመድ ተከታዮቹን ወደ ኢትዮጵያ ልኮ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ በአንድ ወቅት ጥገኘነት የሚጠየቅባት ምቾትና እርዳታ የሚደረግባት ቅዱስ ቦታ ነበረች፡፡ ኒልሰን ማንዴላና ሌሎች የአፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ ፓርቲ አመራሮች እ.ኤ.አ በ1962 ስልጠና ለመውሰድ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ነበር፡፡ በአጼ ኃይለ ስላሴ ልዩ ትዕዛዝ መሰረት ኒልሰን ማንዴላ የኢትዮጵያ ፓስፖርት እንዲሰጣቸው ተደርጎ ያለምንም ችግር ዓለምን ሲዞሩ ነበር፡፡ በአንድ ወቅት ኢትዮጵያውያን/ት በዓለም ላይ የሚከበሩና የሚሞገሱ ነበሩ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ደካሞችና በባርነት የሚገዙ ሆነዋል፡፡ ያሰቡትን በመናገራቸው ይደበደባሉ፣ ይታሰራሉ፡፡ አዲስ አበባ በሚገኘው የሳውዲ አረቢያ አምባሳደር ፊት ለፊት በመገኘት ተቃውሟቸውን በሰላማዊ መንገድ ለማሰማት ሲሞክሩ የሳውዲ አረቢያ ፖሊስ በሀገሩ ኢትዮጵያውያንን/ትን ባስተናገደበት መጥፎ አያያዝ ሞዴልነት በተመሳሳይ መልኩም በአዲስ አበባ እንዲደረግ ሆኗል፡፡ ተዋርደዋል፣ ርህራሄ በጎደለው መልኩ ተደብድበዋል፣ በቁጥጥር ስርም ውለዋል፡፡ የገዥው አካል አፈቀላጤ የሆነው ሽመልስ ከማል ገዥው አካል በሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፈኞች ላይ እርምጃ መውሰድ ይገባዋል ብሏል፣ ምክንያቱም ይላል፣ “አብዛኞቹ ሰላማዊ ሰልፍ አድራጊዎች በኢትዮጵያና በሳውዲ አረቢያ መካከል ጸንቶ የቆየውን ጠንካራ ግንኙነት የሚያበላሽና ጸረ አረብ የሆኑ መልዕክቶችን የያዙ በመሀናቸው ነው::”

ማንም ቢሆን ከሚቀርበው ጓደኛው ጋር የመስታወት ላይ ጠብ ያደርጋል የሚል ግምት የለኝም፡፡ አድሃኖምና ገዥው አካል እንዲያስታውሱት የምፈልገው ነገር…”ለመበሳጨት ዘገምተኛ የሆነውን እሱን ተጠንቀቁ፣ ለመምጣት ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ፣ ከመጣ ደግሞ ኃይለኛው እርሱ እንደሆነ እና ለብዙ ጊዜ የሚቆይ ነው፡፡ የተዋረደ ትዕግስተኝነት ወደ ቁጣ ይቀየራል::” 

የአጣዳፊ ሁኔታውን ለመስራት ልዩ ግብረ ኃይል አያስፈልግምን? ኢትዮጵያ በሳውዲ አረቢያው እንደደረሰባት ዓይነት ኪሳራ በሚደርስባት ጊዜ ለዜጎቹ የሚያስብ ገዥ አካል ተገቢውን ምላሽ ለመስጠትና ለማስተባበር የአስቸኳይ ጊዜ ማስፈጸሚያ ግብረ ኃይል ያቋቁማል፡፡ የሲቪል ማህበረሰብ ቡድኖች ተመላሽ ስደተኛ ወገናቸውን ለማገዝ  እንቅስቃሴ ያደርጋሉ፡፡ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች እገዛ እንዲያደርጉ ይጠየቃሉ፡፡ አነዚህ አልተደረጉም:: በሳውዲ አረቢያ ያለው የኢትዮጵያውያን/ት ሁኔታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ያልፋል፣ ስለዚህም ብዙ ሚሊዮን ሄክታር መሬት ለሳውዲ አረቢያ ኢንቨስተሮች በመስጠት የተለመደው ቢዝነስ በተለመደው ሁኔታ ይቀጥላል የሚል ስሌት በአድሃኖምና በገዥው አካል አቅዋም የተያዘ መሆኑም ይገልጣል፡፡ 

አድሃኖም ወደፊት አንደሚሉ ፤

አድሃኖምና ገዥው አካል ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ለሚመለሱትና ለሚቋቋሙበት የተመደበውን 50 ሚሊዮን ብር ተመድቧል ብለዋል:: ይህ ከባልዲ ውኃ አንዷ ጠብታ ናት፡፡ ይህም ገንዘብ ወደ 2 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ይሆናል፡፡ በዚህች በጣም ትንሽ በሆነች 2 ሚሊዮን ዶላር 200 ሺ ወይም ከዚያ በላይ የሚሆኑ ከስደት ተመላሾችን ለማስፈር፣ ለማዘዋወርና ለማጓጓዝ የሚያስችል አይደለም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ገዥው አካል ይህን ያህል ገንዘብ ለእነዚህ ተግባራት ተብሎ የተያዘ ለመሆኑ ማረጋገጫ የለም፡፡ እ.ኤ.አ ጁላይ 2013 የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ባለሙያዎች ተልዕኮ መግለጫ መሰረት ኢትዮጵያ ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ ለምታስገባቸው ሸቀጦችና አገልግሎቶች ለሶስት ወራት ብቻ ሊያቆይ የሚያስችል የውጭ ምንዛሬ ክምችት እንዳላት ይፋ አድርጓል፡፡ 

አድሃኖምና ገዥው አካል ብዙም ሳይቆዩ ተመላሽ ዜጎቸን ለማጓጓዝና ለማቋቋም የልመና ኮሮጃቸዉን አንጠልጥለው ወደ ዓለም አቀፉ የመንገድ ልመና መውጣቸው የማይቀር ጉዳይ ነው፡፡ በእርግጥ የሚገኘውን እርዳታ ለመቀራመት የሚችሉ የራሳቸውን አትራፊ ያልሆኑ ድርጅቶችን አስቀድመው ያቋቁማሉ፡፡ አድሃኖም ይለምናሉ፣ እንዲህ በማለት፣ “ከሳውዲ አረቢያ ለሚመለሱ ስደተኛ ዜጎች ገንዘብ በጣም ብዙ ገንዘብ እንፈልጋለን፡፡“ ጋሻጃግሪዎቻቸው በህዳሴው ግድብ ወይም በሌላ መልክ እንደሚጠሩት እንዳደረጉት ሁሉ በዓለም ዙሪያ በመሰማራት ኑስ ሳንቲም ሳይቀር ልመናቸውን ያጧጡፋሉ፡፡ ለገዥው አካል መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጀቶች ይህ ሁኔታ ንፋስ አመጣሽ ዘረፋ ነው፡፡ በልመናው በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር እንደሚገኝ በመገመት እነዚህ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እጃቸውን በማሻሸት እና ለሀጫቸዉን በማንጠባጠብ ሰፍ ብለው ይጠባበቃሉ፡፡ ግን በልመና ብዙ ዕርዳታ ላያገኙ ይችላሉ፡፡ ለዚህም ነው በሳውዲ አረቢያ መንገዶች ላይ እጃቸውን በመዘርጋት ምጽዋት፣ ቢለምኑ አልደነቅም ያልኩት፡፡ 

ለኢትዮያችን አለቅሳለሁ፣ ለውዲቷ አገሬ! ግን “ከዋሻው መጨረሻ ብርሃን አለ“ 

አድሃኖም እንዲህ አሉ፣ “ከዋሻው መጨረሻ ብርሃን አለ፣ እና ይህን እውን እንደምናደርገው እናውቃለን፣ እና ድህነትን ተረት እንደምናደርገው ጥርጥር የለንም”፡፡ እኔ ደግሞ እላለሁ በኢትዮጵያ ምድር ውስጥ ከዘውዳዊነትና ከአምባገነንነት ዋሻ መጨረሻ ብርሃን አለ፡፡ ከአድማስ ባሻገር አዲስ ቀን አለ፡፡ መደጋገፍ አለብን፣ እጅ ለእጅ ተያይዘን ሁለት አስርት ዓመታት እና ከዚያ በላይ ከዘለቀው የጭቆና እና የመሰረታዊ የሰብአዊ መብቶች እጦት ዋሻ ውስጥ ተጉዘን በድል አድራጊነት መውጣት አለብን፡፡

በሳውዲ አረቢያ ያሉ ኢትዮጵያውያን/ት ያሉበትን አስከፊ ሁኔታ አስመልክቶ የተዘጋጁትን የእኔን ትንታኔዎች ያነበበ ሁሉ እኔ በጣም ህግ አጥባቂና ሲበዛ ትንታኔ ሰጭ እንደሆንኩ ሊናገር ይችላል፡፡ እንዲያውም ታላቁን የሰው ልጅ ሰቆቃ “ለመፈላሰፊያ ትምህርታዊ ክህሎት” አውሎታል ብለው ሊከሱኝ ይችላሉ፡፡ ይህን ሊሉ ይችላሉ ምክንያቱም ለዚህች ተወዳጅ አገሬ ምን ያህል እንዳለቀስኩና ምን ያህል ተስፋ እንደቆረጥኩ ስለማያውቁ ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ1948 በዚሁ ዓመት አፓርታይድ በአፍሪካ ህግ ሆነ፣ አላን ፓቶን እንዲህ ሲል ጻፈ…”ውዷ ሀገሬ አልቅሽ“… እና በደቡብ አፍሪካ ዕጣ ፈንታ ላይ ያለውን የታሟጠጠ ተስፋ ገለጸ፡፡ የእኔም በኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ ላይ ያለኝ ተስፋ ፓቶን ካለው ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ፓቶን ሲጽፍ፣

ለተገነጣጠለው ጎሳ፣ ለወደቀው ባህልና ህግ አልቅስ! አዎ! ለሞተው ሰውዬ ድምጽህን ከፍ በማድረግ አልቅስ፣ ፍቅሩን ላጣችው ሴትና ለልጆቹ አልቅስ፡፡ ለውድ ሀገርህ አልቅስ፣ እነዚህ ነገሮች በእራሳቸው የመጨረሻ አይደሉም፡፡ ፀሐይ በመሬት ላይ ብርሀኗን ትፈነጥቃለች፣ በተወዳጁ መሬት ሰው ባልተደሰተበት ላይ፡፡ የልቡን ፍርሃት ብቻ ያውቃል፡፡ 

አኔም በኢትዮጵያ “ለተበጣጠሰው ጎሳ” አለቅሳለሁ፡፡ ከሰውነት በታች ሆነው በሳውዲ አረቢያ ለሚሰቃዩት ወንድሞቸና እህቶቸ በዝምታ አለቅሳለሁ፡፡ በመካከለኛው ምስራቅ ለሚደፈሩት፣ ለሚደበደቡት እና በመስኮት ለሚወረወሩት፣ ከጣራ እና ከዛፍ ላይ ተሰቅለው ለሚሞቱትና በፈላ ውኃ ሰውነታቸውን ለሚጠበሱት እህቶቸ አለቅሳለሁ፡፡ በሳውዲ ሌባ ጭንቅላቱን ለሚበረቅሰው ወጣት አለቅሳለሁ፡፡ ነጻነት በማጣታቸው እና በሀገራቸው መብት እንደሌላቸው በመቆጠራቸው ምክንያት ሀገር ጥለው ለመሰደድ ለሚገደዱት ወጣት ወንዶች እና ሴቶች አለቅሳለሁ፡፡ ህይወታቸውን ለማሻሻል በማሰብ የየመንንና የሳውዲ አረቢያን በረሀዎች ሲያቋርጡ በሞት ለተለዩ ኢትዮጵያውያን አለቅሳለሁ፡፡ በየዕለቱ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሲኦሉ ሳውዲ አረቢያ ለሚበሩ ወጣት ኢትዮጵያውያት ቆነጃጅት አለቅሳለሁ፡፡

የ2005 ሀገራዊ ምርጫን ተከትሎ በኢትዮጵያ በየጎዳናው በግፍ ለተገደሉት ወጣት ወንዶችና ሴቶች፣ እንዲሁም አባቶች እና እናቶች አለቅሳለሁ፡፡ ለእህቴ ለርዕዮት ዓለሙ እና ለወንድሞች ለእስክንድር ነጋ፣ አንዷለም አራጌ፣ ውብሸት ታዬ፣ በቀለ ገርባ፣ አቡበከር አህመድ፣ እና በብዙ ሺዎች ለሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞች አለቅሳለሁ፡፡ መሪ በመምሰል በባዶ ልብስ ለተጀቦኑትና በሙሰኛ ሌቦች መዳፍ ስር ለወደቁት ኢትዮጵያውያን/ት አለቅሳለሁ፡፡

አዎ አለቅሳለሁ እናም አለቅሳለሁ፣ “ልቅሶዎቸ ያልተሳኩ ቢሆንም“ ለውዲቷ አገራችን አለቅሳለሁ፣ ግን እኮ ጩኸታችን ይሰማል፣ ደቡብ አፍሪካ ከአፓርታይድ የአምባገነንነት ዋሻ ወጥቷል፣ ኒልሰን ማንዴላም ቃል ገብተዋል…”በፍጹም በፍጹም እና በፍጹም ይህች የተዋበች መሬት ተመልሳ የአንዱ በአንዱ ላይ መጨቆኛ አትሆንም፣ ክብር የታጣባት የተዋረደች ዓለም አትሆንም“::

ኢትዮጵያውያን/ት እንደገና ክብራቸውን ይቀዳጃሉ፣ እና በአገር ውሰጥም ሆነ በውጭ የተከበሩ ይሆናሉ፡፡ “የዓለም ተዋራጂ” ሆነው አይቀጥሉም፡፡ እና በጥልቅ ከልብ አምናለሁ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች፣ እንደገና አናለቅስም፣ ሀሴትንም እናደርጋለን፡፡

↧
↧

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ያልተናገሩት ወይም ያላደረጓቸው 8 ነገሮች

$
0
0

ከኢሳያስ ከበደ
tewedros adhanom with returnees
ዶ/ር ቴዎድሮስ በፌስቡክ በያዙት የቁጥር ጨዋታና በሳዑዲ መንግስት ገንዘብ ከተመለሱት ኢትዮጵያውያን ጋር በተነሱት ፎቶ ግራፎች የተነሳ አንዳንዶች ጥሩ ሥራ እየሰሩ ነው በማለት ሲያሞካሿቸው ይደመጣሉ። በተለይ በሳዑዲው ጉዳይ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ትንፍሽ እንዳይሉ በተደረገበት ሁኔታ፤ ዶ/ር ቴዲ በቀጣዩ ምርጫ ለጠ/ሚ/ርነት የሚያደርጉትን የሕልም ሩጫ ለማሳካት፤ ወደ ሃገራቸው የሚመለሱትን ዜጎች በሳዑዲ መንግስት ገንዘብ መሆኑን አንድም ሳይነገሩን፤ የሳዑዲውን የወገን ስቃይ ቁጥር በፌስቡክ እየተጫወቱበት ለራሳቸው ፖለቲካዊ ጥቅም እያዋሉት ነው። ዶ/ር ቴዲን በቁጥር ጨዋታ ተሸውዳችሁ Good Job ለምትሉ ሰውዬው ያልተናገሩት ወይም ያላደረጓቸውን 8 ነገሮችን ጥሩ ሕሊና ያለው አንብቦ ያገናዝብ፦

1. በጠንካራ ቃላት የተዘጋጀ የውግዘት መግለጫ፤
2. የጥገኛውን ሀገር አምባሳደር በመክሰስ የብጥብጡን ሁኔታ እንዲረዳና በፖሊስና በህገወጦች የሚፈጸመውን ህገወጥ ድርጊት በአስቸኳይ እንዲያስቆም ማድረግ፡
3. ከዚህም በላይ አደሃኖምም ሆነ ወይም ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው ከሳውዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር የሚኖርን ተቃውሞ በይፋ ለህዝብ አላሳወቁም፡፡
4. በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች ላይ የተፈጸመውን የሰብአዊ መብት ረገጣ በሚመለከት የአፍሪካ ህብረት የውግዘት መግለጫ እንዲያወጣ ማድረግ፤
5. (በነገራችን ላይ ይህ ሁሉ ስቃይ በኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች ላይ ሲፈጸም የይስሙላው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በአገር ውስጥ ነበሩን? ኢትዮጵያውያን በሳውዲ አረቢያ “የዘር አደን” እየተፈጸመባቸው መሆኑን አስመልክቶ ቃል ትንፍሽ ሲሉ የሰማ ይኖራልን?)
6. አስቸኳይ ምርመር እንዲካሄድ ለተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን (UNHCR) ኮሚሽነር ማሳወቅ፣
7. ጉዳዩ በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን ኮሚሽነር/UNHCR እና በተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ጽ/ቤት/OHCHR ቀርቦ እንዲጣራ ቅሬታን ማስመዝገብ፤
8. የኢትዮጵያ ዜጎች ከሳውዲ አረቢያ ኤምባሲ ፊት ለፊት ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ እንዲያደርጉ መፍቀድ፤

ቴዎድሮስ የሠሯቸው 3 ነገሮች
1ኛ. ለፌስቡክ የሚሆን ፎቶ ከተመላሾች ጋር መነሳት
2ኛ. የተመላሾችን ቁጥር በ13 ሺህ በመሸቀብና በመጨመር የፌስቡክ ገጻቸውን ማሳመር
3ኛ. የሳዑዲውን የወገን ስቃይ ለፖለቲካ ጥቅም ማዋል

(ከፕ/ር አለማየሁ ገ/ማርያም – ጽሑፍ ውስጥ ተመርጦ የወጣ)
ሙሉው ጽሁፍ እዚህ አለ፦

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/10028

↧

ከሳዑዲ የተመለሱ 7000 በላይ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በየመን ችግር ላይ ናቸው

$
0
0

yemen 3
ግሩም ተ/ሃይማኖት (ጋዜጠኛ) ከየመን

በባህር ተሻግረው በየመን በኩል ያንን እልህ አስጨራሽ በረሃና ፈተና አልፈው ወደ ሳዑዲ አረቢያ የገቡ ኢትዮጵያዊያን ከአበሀ፣ ከሚስ ምሽት፣ ናጂራንና አሲር… ከመሳሰሉት የመን ድንበር አቅራቢያ ያሉ የሳዑዲ ከተማዎች ላይ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ወደ የመን እየገቡ ነው፡፡ ጅዳ ሄደው ወደ ሀገራቸው ለመግባት የማይችሉ በመሆኑ የመን መግባት አማራጭ ሆኖባቸዋል፡፡ ምክንያቱም ወደ ጅዳ ለመሄድ በየቦታው ሊፍጸምባቸው ወይም ሊገጥማቸው የሚችለውን ችግር በማሰብ ነው፡፡

yemen 1

እነዚህ ኢትዮጵያዊያ ወደ የመን የገቡት በሁለት መንገድ ሲሆን አንደኛው ከላይ እንዳልኩት ያላቸው አማራጭ በመሆኑ ባሳቸው ፍላጎት ሲሆን ሁልተኛው እና ወደ 3000 የሚጠጉትን ግን የሳዒዲያ መንግስት የመናዊያኑን እንደ ቆሻሻ በጭነት መኪና አምጥቶ ድንበር ላይ ሲገለብጣቸው አብሮ የጫናቸው ናቸው፡፡

እነዚህ የሳዑዲ መንግስት አምጥቶ የገለበጣቸው ራሱ በሁለት መንገድ ይከፈላሉ፡፡ ድንበር ድረስ እንሂድ ብለው ለምነው የተጫኑ መኖራቸውን ካናገርኳቸው ልጆች ተረድቻለሁ፡፡ ሁለተኞቹ የሳዑዲ ፖሊሶች አፍነው ጭነዋቸው የሚያመጧቸው ናቸው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ከጅዳ ታፍነው የተጫኑ ሁለት ልጆች በስልክ አግኝቻለሁ፡፡ እርጉዞች የተደበደቡ የተደፈሩ ሁሉ ህዝቡ፣ መንግስት እንዳዳያቸው ተብሎ ወደ የመን እንደተጣሉ ነው ያናገርኩት ልጅ የገለጸልኝ፡፡
yemen

ሀረድ የሚገኘው IOM (International organization of migrant) ካምፕ እየተቀበላቸው ሲሆን በአሁኑጊዜ በፊት MSF( medical san frontan) ያዘጋጀውን ካምፕ IOM እየተጠቀመበት ስለሆነ እሱንም ከፍተውታል፡፡ ቢሆንም ይህ ቦታ ከሳዑዲ እና የመን ድንበር ከ 100 ኪ.ሜ በላይ ርቀት ስላለው ይህን ሁሉ መንገድ በእግር መጓዝ ግድ ብሏቸዋል፡፡ ያም ቢሆን መንገዱ በሰላም እንዳያልቅ መካከል ላይ አፋኞች ከሳዑዲ ገንዘብ ይዘው ነው የሚመጡት በማለት የተለያየ ጉዳት እያደረሱባቸው ነው፡፡ ዘርፈው፣ ደብድበው፣ ደፍረው ለፖሊስ ስለሚያስረክባቸው እንዲሁም መንገድ ላይ በቁጥጥር ስር ስለሚያውላቸው በአሁኑ ሰዓት ሰነዓ ኢሚግሬሽን (ጀዋዛት) እስር ቤት ከ3200 በላይ እንደሚገኙ አይቻለሁ፡፡
1394347_506079912824109_833975638_n

ባለፈው እርብ በወርሃዊ ፕሮግራማችን መሰረት እስረኞች ለመጠየቅ ስንሄድ 2700 አካባቢ ኢትዮጵዊያን ስደተኞች እስር ቤቱን አጣበውት ነበር፡፡ አሁን ግን ከ3200 በላይ በመሆናቸው እስር ቤቱ ሞልቶ ጊቢው ውስጥ እና ከጊቢው ውጭ ሁሉ ፈሰው ይገኛሉ፡፡ እነዚህን ወገኖች በርሃብ እንዳይሞቱ ሁላችንም ማድረግ ያለብንን ማድረግ አለብን፡፡ በዚህ አጋጣሚ ሳዑዲ ላለው ስደተኛ በኢሳት ቴሌቪዥን አሰባሳቢነት የተጀመረው ነገር ከሳዑዲ ሸሽተው የመን ለሚገቡትም በርሃብ ሊያልቁ ነው እና ትኩረት እንዲደረግበት ጥያቄዬን አቀርባለሁ፡፡ በይበልጥ ሰሞኑን ወደ ቦታው በድጋሚ ሄጄ ማየት ስለምፈልግ ያለውን ሁኔታ አሳውቃለሁ፡፡ = በግሩም ተ/ሀይማኖት

↧

በሳዑዲ አረቢያ ወገኖቻችን ላይ የሚደርሰው በደል ስቃይ ዛሬም ቀጥሏል (አዳዲስ መረጃዎች ከጅዳ)

$
0
0

በኢትዮጵያን ሃገሬ ጅዳ በዋዲ

* በሪያድ መለዝ አካባቢ የሚገኝ፡ አሚራ ኑራ ዩንቨርስቲ ግቢ ሜዳ ላይ ያለዳስ ብርድ እና ጸሃይ የሚፈራረቅባቸው ከ 7 ሺሕ የሚበልጡ ወገኖቻችን በምግብ ውሃ እና የመጸዳጃ ቦታ እጦት እየተሰቃዩ ነው። የተጠቀሰው መጠለያ ውስጥ ያሉት ወገኖቻችን አብዛኛዎቹ ሴቶች ህጻናት እና አረጋውያን እንደሆኑ መረጃዎች ያመለክታሉ።
saudi arabia today
* በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች በወገኖቻችን ስም በእጅ አዙር ገንዘብ ማሰባሰብ መጀመራቸው እየተነገረ ነው ። በተለይ በሪያድ አለም አቀፍ የኢትዮጵያ የኮሚኒቲ ት/ቤት አንዳንድ መምህራኖችን ለዚህ ድብቅ አጀንዳዎቻው ማስፈጸሚያ በማድረግ ላይ መሆናቸው እየተሰማ ነው ። ለዚህም ሰሞኑን ት/ቤቱ ለወገኖቻችን መርጃ የሚውል ገንዘብ ከወላጆች እና ከተማሪዎች ለመሰብሰብ እቅድ መያዙን ከት/ቤቱ የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ ።

* በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች እንደተቋቋመ የሚነገርለት ይህ የእርዳታ አሰባሳቢ ኮሚቴ ቀደም ሲል በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ ውስጥ ለሚገኙ 12 ነስፈስ ጡሮችን ጨምሮ ከ 200 የሚበልጡ ወገኖቻችን ከስቃይ እና መከራ ለመታደግ በሚል « የአይሮፕላን ትኬት መግዣ በሚል ሽፋን ቀደም ብሎ 1 መቶሺህ ሪያል አሊያም ግማሽ፡ሚልዮን ብር መሰብሰቡን የሚናገሩ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ግር ግር ለሌባ ያመቻል እንዲሉ የመንፉሃውን የሁከት ተከትሎ ዲፕሎማቱ እህቶቻችንን ወደ አልታወቀ ግዜያዊ መጠለያ በመበተን የተጠቀሰውን ገንዘብ ለምን እንዳዋሉት እንደማይታወቅ ምንጮች ከሪያድ ገልጸዋል። ።

* ሪያድ ውስጥ ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በአሰሪዎቻቸው (በከፊሎቻቸው) የመኖሪያ ፈቃዱ በመስረዙ ለህገወጥነት የመዳረጋቸው ጉዳይ እያነጋገረ ነው ።

* ከሪያዱ የመንፉሃው ከሁከት በኋላ ጸጥ ረጭ እንዳለች የሚነገርላት የሃበሾቹ መንደር ዛሬ በአያሌ ወገኖቻችን ላይ ፊቷን ያዞረች ትመስላለች ! የተለያዩ ንግድ ስራዎች ላይ ተሰማርተው የኖሩ የነበሩ ወገኖቻችን በአጋጣሚ በተፈጥረው ሁከት በሚልዮን የሚቆጠር ገንዘባቸውን ማጣታቸውን አሊያም ባለ እዳ መሆናቸው እይተነገረ ነው ። በዝች የሃበሾች መንደር ከሚገኙ ጥቂት ሱቆች ውስጥ የፈጅር ሱቅ ባለቤት አቶ መሃመድ ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ትላንት ቤታቸው ውስጥ እራሳቸውን ሰቅለው ተገኝተዋል። በተያያዘ ዜና የአምባሳል ንግድ ቤት ባለቤት እሳካሁን ያለበት ቦታ እንደማይታወቅ መረጃዎች ይገልጻሉ ።

* አንዳንድ ቪዛ ነጋዴዎች « የኤጀንሲ ባለበቤቶች » ኢትዮጵያውያኑን ከሃገር በማስመጣቱ ረገድ በአቋራጭ ወደ ሳውዲ አረቢያ ኢትዮጵያውያኑንን እያስገቡ መሆኑ እየተነገረ ነው ።

↧
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live




Latest Images