Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ቢቢኤን ሰበር ዜና: በምዕራብ ሐረርጌ ሁለት መስጊዶች ላይ የቦምብ ጥቃት ደረሰ |ብዙ ሰዎች ቆስለዋል

$
0
0

(ቢቢኤን ሰበር ዜና) ምእራብ ሀረርጌ ማሳላ ወረዳ ልዩ ስሙ ዋልተሲስ በሚገኘው መስጂድ የመንግስት ወታደሮች (አጋዚዎች) ከባድ የቦንብ ጥቃት አድርሰዋል፤ መስጂዱንም አውድመውታል። ቁጥሩ ያልታወቀ ሰው ለሞትና ለአካል ጉዳት ተዳርጓል ትንታኔውን ይከታተሉ::

ቢቢኤን ሰበር ዜና: በምዕራብ ሐረርጌ ሁለት መስጊዶች ላይ የቦምብ ጥቃት ደረሰ | ብዙ ሰዎች ቆስለዋል


ለሁሉም ጊዜ አለው –ማስተዋል በለጠ

$
0
0

 Justice

በመላዋ ሀገራችን ለነፃነታችን እየተዋደቁ የሚገኙ ዜጎች ውድ ሕይወታቸውን እየሰው የነፃነት ቀንዲሉን በማብራት ላይ ናቸው፡፡ ታሪክ ሲዘክረው የሚኖር ታላቅ መስዋዕትነት እየከፈሉ በመሆናቸው በአልሞ ተኳሽ የወያኔ አጋዚ ጦር አንገታቸው እየተቀላና ጭንቅላታቸው እየተገመሰ ሕይወታቸውን የሚያጡ ውድ ወገኖቻችንን ነፍሳቸውን ፈጣሪ ይማርልን፡፡

በዚያን ሰሞን ካነበብኳቸው መጣጥፎች አንዱ በ16 የትግራይ ተወላጆች የተጻፈው በወያኔ ላይ የተወሰደ አቋም ነው፡፡ ኪዳነ ምሕረት ትባርካቸው፡፡ ፕሮፌሰር መስፍን አንድ ወቅት ጥሩ ኢትዮጵያውያን ተጋሩን(ትግሬዎችን) መቁጠር ጀምረው የቀኝ እጅ ጣቶቻቸውን ተጠቅመው (ይመስለኛል) አንድ ሁለት ሦስት ያህል እንደተጓዙ አምስትን እንኳን መዝለል አቃታቸውና “አሥር ቢሞሉልኝ ደስ ባለኝ” ብለው ተስፋ በመቁረጥ መቁጠሩን እንደተውት አርድተውናል፡፡ አሁን 16 መድረሳቸው ተስፋን የሚያጭር ነው፡፡ እየበዙ እንደሚሄዱ ደግሞ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ዕድሉን ስላላገኙት እንጂ በቁም ነገር ከተጫወትን ኢትዮጵያውያን ተጋሩ ቁጥራቸው ከዚህ እንደሚበልጥ መገመት አይከብድም፡፡ አገዛዙ ከትግሬ አይውጣ እንጂ ወያኔ ሥልጣን ቢለቅ የሚወዱ ትግሬዎች ደግሞ ጥቂት እንደማይሆኑ መገመት ይቻላል፤ ይህን ወያኔ የተከለብንን የዘር መዘዝ ለማጥፋት ማርከሻውን በቶሎ ካላፈላለግንና በ“ሜሪቶክራሲ”(በችሎታና ዕውቀት) መተካት ካልቻልን ገና ወደፊትም ብዙ እንዳክራለን፡፡

በመሠረቱ ከኢትዮጵያዊነት በወረደ ከዚህኛው ወይም ከዚያኛው ጎሣ እየተባባሉ ማናቸውንም ዓይነት ተቃውሞን መግለጹ ዘመናዊነትን ሊገልጽና የሥልጡን ፖለቲካ መታወቂያ ሊሆን እንደማይገባው አምናለሁ፤ በሃይማኖትና በአካባቢ ልጅነት መደራጀትም እንደዚሁ ተገቢ አለመሆኑ ይገባኛል፡፡ ቢሆንም ቅሉ … ከዐማራ ተወላጆች፣ ከኦሮሞ ተወላጆች፣ ከትግራይ ተወላጆች … የምንለው ነገር ለጊዜው ጠቃሚ ሆኖ ከተገኘ ማለትም እየወረደብን ያለውን የመከራ ዶፍ ከመመከት አኳያ አንዳች ፋይዳ ካለው ቢያንስ በመርኅ ደረጃ ብደግፈው ብዙም አይከፋኝም፡፡ እናም አብላጫውን ደሜን ያገኘሁት ከሦስቱም ‹በጥባጭ‹ ዘውጎች መሆኑን ከሕይወት ተሞክሮ የተረዳሁት ማስተዋል በለጠ በዚህ መጣጥፍ ውስጥ ያለውን አስተያየት በቀናነት የምሰነዝረው አድማጭ አገኛለሁ ከሚል ትልቅ ተስፋ ነው፡፡

ታሪኬን ብዙዎች ይጋሩት ይናል ብዬ ስለማምን ስለራሴ ትንሽ ብናገር ደስ ይለኛል፡፡ መነሻየ ግምት እንጂ ጥናት አይደለም፡፡ የብዙ ጥናቶች መሠረት ለእውነት የቀረቡ ግምቶች መሆናቸውንም አንዘንጋ፡፡ እናም የእኔ ዘውጋዊ ቀመር እንደሚመስለኝ 30% ዐማራ፣ 30% ኦሮሞ፣ 30% ትግሬ እና 10% ከሌሎች ነው፤ እንዲህ የሆንኩ ያህል ይሰማኛል፡፡ እንደዚህ ስል ደግሞ የሚያምነኝ እንደማላገኝ ብቻ ሣይሆን ጥቂት የማይባሉ ሰዎች እንደሚያላግጡብኝም ይገባኛል፡፡ የእኔ እውነት መነሻ ግን ይሄውላችሁ፡፡

መልኬን አሁን ላሳያችሁ ባለመቻሌ አዝናለሁ፡፡ ትግሬ ጋ ስሆን ፊቴን ያዩና “ደምህ ወደደቡብና ወደ ኦሮሞ ይሄዳል” ይሉኛል፡፡ ኦሮሞ ጋ ስሆን “መልክህ የዐማራና የትግሬ ይመስላል” ይሉኛል፡፡ ዐማሮች ጋ ስሆን “አባትህ ከደቡብ የተቀጠሩ ወታደር ሳይኑ አይቀሩም” እያሉ ይቀልዱብኛል፡፡ እኔ ራሴን በመስተዋት ስመለከት አንዱንም የማልመስል ከሁሉም ግን ጥቂት ጥቂት እንደወሰድኩ ያህል ይሰማኛል፡፡ ትልቁ ማስረጃየ ግን ሦስቱም ዘውጎች ከየተነሱበት መጥተው የሚያልቁበት ቦታ ላይ መወለዴ ነው፡፡ አዎ፣ የአማራ፣ የትግሬና የኦሮሞ ጠቅላይ ግዛቶች የሚጫፈሩበት(overlap የሚያደርጉበት) ሥፍራ ላይ ነው የትውልድ መንደሬ፡፡ ለዚህም ነው ቁርጥ ባለ ሁኔታ ይህን ወይ ያን ልመስል ያልቻልኩት፡፡

ስለዚህ አንዱ በዐማራነቴ አህያ ቢለኝ ወይም ዛሬ ጧት በፕሮፌሰር አልማርያም መጣጥፍ ላይ እንዳነበብኩት “የአእምሮ ዘገምተኛ” ቢለኝ ወይም በኦሮሞነቴ “ሽብርተኛ”ና “ወንጀለኛ” ብባል ወይም በትግሬነቴ ዘረኛና ጎጠኛ ብባል ብዙም የሚሰማኝ አልሆንም፡፡ ሁሉን መሆን አንዳንዴ ዕዳ አንዳንዴ ደግሞ በረከትም ነው፡፡ የሆንኩትን እንድሆን የመምረጥ ዕድል ያልተሰጠኝ መሆኔ ግን በከንቱዎች ከንቱ አባባል እንዳልቆጣ ትልቅ የትግስት ጋሻ አስጨብጦኛል፡፡ ለመሆንና ላለመሆን ምርጫ ባልተሰጠኝ ሁኔታ በሆንኩት ነገር መበሳጨትም ሆነ ከሰው ጋር ትርፍ ንግግር ውስጥ መግባት ትልቅ ሞኝነት ነው፡፡

ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሣ ሰሞኑን በጻፈው መጽሐፍ የትውልድ አካባቢየና ተፈጥሮ ቀድመው ያቆራኙትን ዐማራነቴንና ኦሮሞነቴን በተመለከተ ብዙ ነገር አትቷል፡፡ የፕሮፌሰሩ ልፋትና ድካም ይገባኛል፤ በሕዝቡና በሀገሩ ሰላምንና ፍቅርን፣ ወንድማማችነትንና እትማማችነትን ለማስፈን በመፈለጉ ብዙ ርቀቶችን ተጉዞ በእምቅድመ ዘመነ ታሪክ በአዳምና ሔዋን አንድ የሆንነውን ግን የዘነጋነውን እኛን አንድ አድርጓል፡፡

በመሠረቱ ታዲያ ጥቁሮች ኢትዮጵያውያንን ብቻ ሣይሆን የሰውን ዘር በሞላ በሥነ ፍጥረት አንድ ያደረገ ፈጣሪ ከአዳምና ከሔዋን አንስቶ አሁን የምንገኝበትን የሰባት ቢሊዮን የሕዝብ ቁጥር ለበረከትም ይሁን ለእርግማን እንደሰጠን ለምናምን ሰዎች የሰውን ልጅ አንድነትና የዘር ሐረግ ወጥነት ለመረዳት አንዳችም ምርምር ባላስፈለገን ነበር፡፡ ይሄ አንድ የመሆን ወይም ያለመሆን ችግር አይደለምና ዋናው እየበጠበጠን የሚገኝ ችግራችን፡፡

(እንደኔ አስተሳሰብ) የሰው ልጅ ዋና ችግር የዘር ሐረጉ መለያየት አይደለም፡፡ ትልቁ ችግር የተፈጥሮ ሀብትን በአግባቡ ከመከፋፈል አንጻር የሚታየው ኢ-ፍትሃዊነት ነው፡፡ ምክንያቶቹ የፈለገውን ያህል በቅርጽ ቢለያዩም ዋናው ችግራችን የሀብት ክፍፍል ላይ የሚፈጠር የ“ያንተ በዛ፣ የኔ አነሰ” ዓይነት መፎካከርና ያን ተከትሎ የሚፈጠር ቀውስ ነው፡፡ አንዱ በጉልበቱ ወይም በብልጠቱ ቢሊዮን ሲወስድ ሌላው መቶም አያገኝም፡፡ አንዱ ያለ የሌለ ዘዴና ብልኃቱን ተጠቅሞ ወደሀብትና ሥልጣን ማማ በአቋራጭ በመውጣት እንደካሙዙ ባንዳ ዕድሜ ልኩን ሲጎለት ይህን ቅጥፈት የታዘበ ሌላው ባለወር ተራ ደግሞ ወደዚያ ሥፍራ ለመጓዝ የንጹሓንን ደም እየገበረ ሌት ከቀን በእውኑም በህልሙም ይባዝናል፡፡ እንጂ የመለስ ዜናዊ የ17 ዓመታት ጉዞና የቢሊዮን ዶላሮች ክምችት ለእንደርታው ገበሬ ለአቶ ሐጎስ ፀጋዝኣብ የፈየደለት አንድም ነገር እንደሌለ ቢያንስ ኅሊናችን ይረዳዋል – ይህን የምለው ታዲያ አጠቃላዩን እውነታ ለመግለጽ እንጂ የመለስ ሸፋፋና ወልጋዳ አስተሳሰብና አመራር ጥቂት የማይባሉ ተጋሩ ወንድምና እህቶቼን አልጠቀመም እያልኩ አይደለም፡፡ የተጠቀመ ተጠቅሟል፤ የተጎዳም እንዲሁ፡፡

ሁላችን እናውቀዋለን፤ የሰው ልጅ ዘር አንድ ነው፡፡ ነጭና ጥቁር የመጣው ከጊዜ በኋላ እንደሆነ መጻሕፍት ይናገራሉ፡፡ የመልክና የቁመት ልዩነት እንደሆነ በማኅበረሰብ ደረጃ ይቅርና በኔ ቤትም ጎልቶ የሚታይ ግን ተዓምራዊ ያልሆነ ተራ ክስተት ነው፡፡ በኔ ቤት ለምሣሌ እኔ ወደጥቁርነት የማደላ ፉንጋ የቀይ ዳማ ስሆን አንዱ ልጄ ቆንጆ ቀይ፣ አንዱ ደግሞ ከኔ የባሰ አሻሮ ናቸው፤ ሌሎቹም እንዲሁ የተለያዬ መልክ፣ ቁመትና ጠባይ አላቸው – “ቤቴ መንገድ ዳር አለመሆኑን”ና ታማኝ የትዳር አጋር ያለኝ መሆኔን አስቡልኝ ታዲያ! (በነገራችን ላይ አንዳንድ ሸረኛ አንባቢ ምን ሊለኝ እንደሚችል እያሰብኩ ነው ከመንገድ እየወጣሁ ደረጃውን ባልጠበቀ የመነቸከ ቀልድ ላስፈግጋችሁ የምሞክረው)፡፡ እነዚህን ልዩነቶች እኔና እናታቸው አልሰጠናቸውም – ባልሰጠናቸው ልዩነት ደግሞ አይጣሉም፡፡ ስለዚህ ልዩነትን ለጠብ ማዋል የከይሲዎች ተግባር እንጂ የደግ ሰው ጠባይ አይደለምና መጠንቀቁ ጠቃሚ ነው፡፡

ይህን የልዩነት ሰበዝ በኦሮሞነትና በዐማራነት ካየነው እርግጥ ነው “ይህ ሰው ኦሮሞ ነው”፣ “ይህ ሰው ጉራጌ ነው” የምንልባቸው ልማዳዊ የሰውነት ቅርፆች ሊኖሩ እንደሚችሉ በበኩሌ እረዳለሁ፡፡ ለዚህም ነው ከፍ ሲል የኔ የሰውነት ቅርጽና የመልክ ይዘት የዚህ ወይ የዚያ ሣይሆን ድብልቅ ነው ለማለት የደፈርኩት – ለፖለቲካ ፍጆታ አይደለም፡፡ To my belief, there are some typically subtle features of ethnics if they are not mixed up and diluted through intermarriage. And, in most cases, the Ethiopian societies are said to be interwoven to the extent of not being able to be clearly and unmistakably identified as this or that ethnic group, excepting some incidents especially in remotest rural areas where there is less chance of intermingling through intermarriage.

እውነት እንነጋገር ካልን ታዲያ ከሥነ ልሣናዊ ተቀራራቢነትም ይሁን ከአካላዊ ቅርጽ አኳያ አንድ ትግሬና አንድ ዐማራ የሚለዩበትን ገጽታ(feature) ለመለየት በበኩሌ እቸገራለሁ – ተፈጥሯዊ ዝምድናቸው በጣም ያቀራርባቸዋል፡፡ ይህንን ስል ፕሮፌሰር ፍቅሬ ያለውን የኦሮሞና የአማራ ጎሣዎች የመባቀያ ተመሳሳይነት ጨብጬ ይህን እኔ የምለውንም በተጨማሪነት ለማስገንዘብ ፈልጌ እንደሆነ መግለጽ እፈልጋለሁ፡፡ ዐማራና ኦሮሞ አንድ መሆናቸው የሚያስደስተኝን ያህል ትግሬና ዐማራም አንድ ብቻ ሣይሆኑ እንደኔ እንዲያውም ሁለቱ ጎሣዎች ወያኔን ተመስሎ ከፋፋይ ሰይጣን በመካከላቸው ገብቶባቸው እንጂ በልይት ዘውግነት መለያየት ራሱ ይበዛባቸዋል ባይ ነኝ – በአንድ ዘውግ ሥር መመደብ ነበረባቸው እያልኩ ነው በግልጽ ዐማርኛ፡፡ የአሁኑን ባላውቅም በኔ የወጣትነት ዘመን አንድን ትግሬ ከአንድ ዐማራ ለመለየት ምናልባት በትግሬው ግምባር ላይ ይቺ 11 ቁጥር የምንላት ታርጋ ኖራ በሷ ካልለየነው በስተቀር በምንም መንገድ አይለዩም ነበር – በነገራችን ላይ የሌላቸውም አሉ (ባይገርማችሁ ባለ 11 ቁጥር ዐማራ አለ፤ 11 ቁጥር የሌለው ትግሬም አለ)፡፡ ወያኔ እንደጣዖት የሚያመልክባትን የብሶተኞች የምትመስል 11 ቁጥርን በድንበር አካባቢ ያለን ሰዎችም አለችን፡፡ ለዐይን ህመም ተብሎ ብዙዎቻችን እንቀነደብ እንደነበር የኔም ግምባር ኅያው ምሥክር ነው፡፡ በኔ አካባቢ የባህሎች መዋሃድ ስላለ የብዙ ማኅበረሰቦች አሻራ በሁሉም ሰው ላይ ይታያል፡፡

በተረፈ ግን ዱሮ ትግሬን ከዐማራ ለመለየት የሚቻልበት ዘዴ አልነበረም፡፡ መልክና ቁመናቸው፣ ሥነ ልቦናዊ ቀመራቸው፣ ሥነ ልሣናዊ ዳራቸው፣ ሃይማኖታዊ ሥርዓታቸው፣ አመጋገባቸውና አለባበሳቸው፣ እንግዳ አቀባበላቸው፣ ሰውን አክባሪነታቸው፣ ባህላቸውና ኢኮኖሚያዊ ትስስራቸው ሲታይ አንዳቸውን ከሌላኛቸው መለየት የማይቻልበት ሁኔታና ወቅት ነበር – የዛሬውን ዘመነ ጥልሚያኮስ አያድርገውና፡፡ ለምሣሌ ሁለት ኦሮሞዎች እዚህ አጠገቤ እያወሩ ነው ልበል፡፡ በዚህኛው ሌላኛው አጠገቤ ደግሞ ሁለት ትግሬዎች እያወሩ ነው ልበል፡፡ አንድ ኦሮምኛም ትግርኛም የማይችል በዐማራነት የሚታወቅ ሰው ቢያዳምጥና ከየትኛዎቹ ምን እንደተረዳ/እንደሰማ ይህ ቢጠየቅ በርግጠኝነት ከትግርኛ ተናጋሪዎቹ በአነስተኛ ግምት ወደ 25 በመቶ የሚጠጋውን ሊረዳ ሲችል ከኦሮምኛ ተናጋሪዎች ግን 5 በመቶውን እንኳን ስለመረዳቱ እጠራጠራለሁ፡፡ ታዲያ ይህን የትግሬ-ወያኔዎችን በዐማሮች ላይ መጨከን ምን አመጣው? ይህ ይመስኛለል ትልቁ የዘመናችን ዕንቆቅልሽ፡፡ ፍቺ ያጣንለት ሚሌኒየማዊ ጥያቄ ነው፡፡ ምን ዓይነት ሰይጣን በወንድማማቾች መካከል ገባ? በውነቱ በተለይ በተጋሩ ወንድሞቼ አካባቢ ይህን የምለውን እውነት የሚያስታውስ ጠፍቶ ነው ወይንስ ማስታወስ አስፈላጊ ሣይሆን ቀርቶ ይሆን? ለምን? ማንን ለመጥቀም? እነዚህን ወንድማማች ማኅበረሰቦች በማፋጀት የሚገኘው ጥቅም ምንድን ነው? ጥላቻን ዘርቶ ዐመፃን ማጨድ ማንን ነው የሚጠቅመው? ተጋድመው የተፉት ምራቅ ተመልሶ ወደራስ እንደሚመጣስ መገንዘብ እንዴት ያቅታል? አሁን በዐማሮች ላይ እየተደረገ ያለው ሊታመን የማይችል ሲዖላዊ ተዓምር ወደሰማዩ ጌታ መጮኹና መልስ ማግኘቱ ይቀራል? ያኔ ምን ይውጠናል?

የሰዎች ትክክለኛ የኅሊና ፍርድ ተዛብቶ ወደ ከፋና ከረፋ ዝቅተኛ የአስተሳሰብና የአመለካከት ደረጃ ለምን እንደሚወርድና አንዱ በአንዱ ለምን እንደሚጨክን ብዙ ጊዜ ይጠየቃል፡፡ መልሱ ደግሞ ቀላል ነው – እሱም ጥቅም ነው፡፡ ጥቅም አይደለም ጎሣና ነገድን ወንድምና እህትን ያገዳድላል፡፡ አባትና ልጅን ያባላል፡፡ ቤተ ዘመድን ያጨራርሳል፡፡ ጥቅምና ሥልጣን በጣም አደገኛ መርዝ ናቸው፡፡ “የአቦይ ስብሃት ሀብት ከሚነካ የትግራይ ሕዝብ ጥንቅር ይበል፤ የአባይ ፀሐዬ ሥልጣን ከሚሸረሸር የትግራይና ዐማራ ሕዝብ ሚና ለይቶ ይጨራረስ፡፡ መንግሥቱ ኃ/ማርያም ሥልጣኑን ከሚያጣ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ባፍ ጢሟ ትደፋ፡፡…” ይህ ነው የግለሰቦች የሥልጣንና የሀብት አምልኮ፡፡ እንጂ ሕዝብና ሕዝብ በየትም ሀገር ለጠብና ለፍጅት ተፈላልጎ አያውቅም፡፡ የዕልቂት ከበሮ የሚጎስሙ ወገኖች በሀብትና በሥልጣን ሱስ ናላቸው የዞረ ጥቂት ግለሰቦችና በሥራቸው የሚኮለኩሏቸው አጥፊ ጀሌዎች ናቸው፡፡ ይህ ዓይነቱ የትያትር መድረክ ደግሞ መጋረጃው ሲዘጋ አብሮ የሚዘጋና በሌላ የተሻለ ወይም እንደኛ እንደስካሁኑ ከሆነ የጥንቱን በሚያስመሰግን መጥፎ ታሪክ የሚተካ ነው – እስካሁን እንዲህ ነበር ወደፊትም እንዲሁ ነው፤ ክፉም ሆነ ደግ መንግሥት ወይም ሥርዓት ባለበት ለዘላለም አይኖርም፡፡ ሕዝብ ግን ዘላለማዊ ነው፡፡ እናም ውድ ኢትዮጵያውን አይዞን ይህ ወያኔዊ የጥፋት ዘመን አልፎ የፍቅርና የመተሳሰብ ዘመን በቅርብ ይመጣል፡፡ ጸሎታችን መሆን ያለበት መስዋዕትነቱ እንዲቀንስልን “ጌታ ሆይ ዕርዳን” ነው – እኛም ከክፋትና ከአጥፊነት ርቀን ታዲያ፡፡ ደግሞም በመካከላችን ጥላቻን አናባብስ፡፡ የሚተርፈን ትዝብቱ ነው፡፡ ኢትዮጵያ እንደሆነች ጠፍታ የማትጠፋ የፈጣሪ ቃል ኪዳን የሚጠብቃት ሀገር ናት – በወረት የዘረኝነትም እንበለው የትምክህተኝነት ንፋስ አንወሰድ፡፡ ከሁሉም ከሁሉም ምንም ዓይነት ጥጋብ አይፈታተነን፡፡ ብናገኝ አንኩራ፣ ብናጣም አንፍራ፡፡ “ሁሉም በርሱ ሆነ – ያለርሱ በሰማይም በምድርም ምንም አልሆነም፡፡” ስለዚህ ለምኑ እንጨነቃለን? የተወሰደ እንደሚመጣ፣ የመጣም እንደሚወሰድ አናውቅምን? ማን ነው እንደኮራ እንደደራ የኖረ? ማን ነው እንዳነሰ እንደኮሰመነ ኖሮ ከምድር የተሰናበተ? ጠቢቡ አስቀድሞ “ለሁሉም ጊዜ አለው” ብሏል፡፡

ከአዳም ጀምሮ እስካሁን ድረስ ይህ የጥቅምና የሆድ ጉዳይ የዓለም ሕዝቦችን እያፋጀ ነው፡፡ አዳምና ሔዋን ከገነት የተባረሩት፣ አቤል በወንድሙ በቃየል የተገደለው፣ ያቆብ ጭብጥ በማትሞላ ምሥር ብኩርናውን የለወጠው፣ ይሁዳ ጌታውን በሠላሣ ዲናር የሸጠው፣… በዘመናችንም ሲአይኤና ሞሳድ በዲሞክራሲ ጭምብላቸው ዓለምን እንዲህ የሚያሽቃንጡባትና እንደፈለጉ የሚፈነጥዙባት በጥቅምና ለጥቅም ሲባል ነው(ህእ! ሳውዲ ዐረቢያ ውስጥ የዴሞክራሲ ጭላንጭል የለም … በአውራ መንገዶችና በሠፈር ውስጥ ብቻዋን መሄድ የማይፈቀድላት ሴት መኪና እንኳን አትነዳም፤ ስለዴሞክራሲ ጭንቅ ጥብብ የምትለውና በዴሞክራሲ በሚመጣባት ሀገር ላይ ከማዕቀብ እስከ ጦር ማዝመት የምትደርሰው አሜሪካ የዚህች ሀገር የበላይ ጠባቂና ዘበኛ ናት – ለጥቅም ሲባል… ዕንቆቅልሽ፡፡)

… እንጂ ዐማራ ከማንም የበለጠ “አህያና ደደብ” ወይም “የአእምሮ ዘገምተኛ” ሆኖ አይደለም – ሰፊው ኦሮሞ ከትግሬ በልጦ ጠባብ ሆኖ አይደለም፡፡ ትግሬ ከማንም በልጦ ጀግናና አልሞ ተኳሽ ሆኖ አይደለም፡፡ ማዕከላዊው የግጭት መንስኤ ጥቅም ነው፡፡ በጥቅም የታወሩ ወንድሞቻችን አቅል አጡና ከምድረ ገጽ ሊያጠፉን ቆርጠው ተነሱ፡፡ ባጭሩ ይህን ሁሉ ዕልቂትና ፍጅት እያስከተለ ያለው ከፀሐይ በታች ያለ የሸርና የተንኮል ጉንጉን የተላበሰ የወያኔዎች የሀብትና የሥልጣን ጉጉትና የዓለም አቀፉ የኢትዮጵያ ጠላቶች ሤራ ድምር ውጤት ነው፡፡ ከወያኔዎች ጋር ተሰልፎ ጃዝ ሲሉት እየገደለና እየዘረፈ የሚተመው የጥፋት ሠራዊት ደግሞ ከዕውቀትም ከባህልም ከሃይማኖትም የወጣ ወፍ ዘራሽ ጀሌ ነው – አብዛኛው ከእረኝነት በቀጥታ የመጣና ማኅበራዊ እንስሳነቱ የተጓደለበት ከመሆኑም ባሻገር ዐማራን እንዲጠላና ከጥላቻውም ብዛት የተነሣ በጭካኔ እንዲፈጀው ሥነ ልቦናዊ ጫና የተደረገበት አሳዛኝ ፍጡር ነው፡፡ ሳይፈልግ በተደረገበት ተፅዕኖ ምክንያት ስለሆነ ይህን ሁሉ ግፍ የሚፈጽመው ሙሉ በሙሉ በርሱ ለመፍረድም ይከብዳል፤ በዚያ ላይ የውጭ ጠላቶቻችን ለውስጥ ምንደኞች ያሸከሙት ታሪካዊ የጥፋት ተልእኮም ቀላል አይደለም – የየትኛውንም ሀገር ባለሥልጣናት ብሔራዊ ስሜት በማጥፋት የነርሱ አሽከሮች የሆኑ መሪዎችን በማፍራት የሚታወቁት የዐውሬው ልጆች ምዕራባውያንና አውሮፓውያን ካልጠፉ ወይም ሰይጣናዊ ተፈጥሯቸውን ካልቀየሩ (ይህ የማይሆን አማራጭ ነው) አለዚያም እኛ ይህን መርዝነታቸውን ነቅተንባቸው በኅብረት ካልታገልናቸውና ድል ካልነሳናቸው ደግሞ ዕረፍት እንደሌለን መረዳት ተገቢ ነው፡፡ የዘመቻቸው ጅማሮ ጥንታዊ ነው፤ ድላቸው ግን ጊዜያዊ ነው፡፡

ጥቂት ታገሱኝ – አንዲት ነገር ብቻ ትቀረኛለች፡፡ የትግራይ የወቅቱ መሣፍንትና መኳንንት ትግራይን ይዘን እንሄዳለን ቢሉ ጥርሳችንን ተነቅሰን እንስቅባቸዋለን፡፡ በርግጥም ጤነኛ ነኝ የሚል የዚህች ዓለም ዜጋ ይስቅባቸዋል፡፡ “እውነት እውነት እላችኋለሁ” ብሎ ይጀምር ነበር ክርስቶስ የመረረ እውነት ሲናገር፡፡ እኔም ልዋሰውና – እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ ትግራይን መገንጠል ቢያስፈልግ ኖሮ ይቻል የነበረው የዛሬ 25 ዓመት ገደማ በ1983ዓ.ም ወርኃ ግንቦት ላይ ነበር፡፡ አሁን እጅግ መሽቷል፤ “ቢያዩኝ እስቅ፣ ባያዩኝ እሰርቅ“ የሚለው ብሂል የማይሠራበት የመጨረሻው ሰዓት ላይ ስላሉ ያን ቅዠታቸውን ዘመን ሽሮታል፡፡ “ዕድላችንን እንሞክር” የሚባልበት ጠባብ የተስፋ ጭላንጭል እንኳን የለም፡፡ አንድ የትግርኛ ብሂል ላስታውስ – ወዳማርኛ ልመልሰው ፡- “የሚበቃትን ያህል ጥሬ ከፈጨች በኋላ የማርያም በዓል ነው ትላለች” ይላል፡፡ ግሩም ብኂል ነው፡፡ በልጆች ጨዋታ ጊዜ “ጨዋታው ፈረሰ፣ ዳቦው ተቆረሰ” ሊባል ይችል የነበረው ዛሬ ሣይሆን ከዛሬ 25 ዓመታት ገደማ በፊት ነው፡፡

ወልቃይትንና አካባቢዋን ከጎንደር፣ ራያዎችን ከወሎ፣ የአባይ ግድብን ከቤንሻጉል፣ እንትናን ከአፋር … ከዘረፉና ወደ “ታላቋ የትግራይ ሪፐብሊክ” ካካለሉ በኋላ፣ ሰፊ የዐማራ ግዛትን ለሱዳን ከሸጡ በኋላ፣ የኢትዮጵያን ሀብትና ንብረት ለ40 እና 25 ዓመታት በተከታታይ ካለተቆጣጣሪ እንደልብ ከመዘበሩና ወደሚፈለጉት ቦታ ካዘዋወሩ በኋላ፣ በሚሊዮን የሚገመት ሕዝብ በልዩ ልዩ ዘዴ ከምድረ ገፅ ካጠፉና እንዲሰደድም እንዲፈናቀልም እንዲራብና እንዲታረዝም ካደረጉ በኋላ፣ የኢትዮጵያን አስተዳደር በአንድ ጎሣ ቁጥጥር ሥር አውለው የሀገሪቷን አንጡራ ሀብት እንዳሻቸው ከቦጠቦጡና መዋቅሮቿን ሁሉ ካፈራረሱ በኋላ፣ የሚንቀሳቀስንም ሀብትና ንብረት ወደ አሳቻ ቦታ ካሻገሩ በኋላ… ለዚህ ሁሉ ዘመን በአንዲት ሉዓላዊት ሀገርና በአንድ ሕዝብ ላይ እንደልብ ከፈነጩ በኋላ አሁን ሲመሽ “የያዝኩትን ይዤ የራሴን ግዛት እመሠርታለሁ” የሚለው ብልጣብልጥነት ከማሣቅም ያልፋል – ወያኔ ከኢትዮጵያ የአንበሣና ዝኆኑን ድርሻ ዝቆ ወደራሱ ጎተራ ካስገባ በኋላ ለመሆኑ ለሌላው ሕዝብ ምን የቀረለት ነገር አለና ብቻውን መንግሥት መሥርቶ ከነሱ ጋር በአቻ ጉርብትና የሚኖረው? የመረጃ ቋቱ ሳይቀር ተጉዞ መቀሌ ገባ ከተባለ በኋላ ሌሎቹን እንደፍጥርጥራችሁ ብሎ “ትግራይ ሪፐብሊክ” የምትመሠረተው በየትኛው ሥሌት ነው? የዋህነት ወይንስ ድምበርን የማያውቅ ብልጠት? ሀገርን ማስተዳደርና ሀገርን መመሥረት የልጆች የቃቃ ጨዋታ አይደለም፡፡ አንድን ሀገር አፍርሶም ሌላ ሀገር መገንባት የሚታሰብ አይሆንም፡፡ ቂልነት ነው፡፡ ወይም የለዬለት ዕብደት፡፡

የወያኔዎች አጀማመር ሁሉ እንዳይሆን ነው፤ ሲጀምር ትልቅ ሀገርን እየገዙ የ”ገዛ ሀገር”ን መሬት ለባዕድ መሸጥና በነሱው አጠራር ካንዱ ‹ክልል‹ ወደሌላው ‹ክልል‹ ቁርጥራጭ መሬት እየቀደዱ መስፋት ጥንቱንም አላስፈላጊ ነበር – ሌላ ታሳቢ ተንኮል እስከሌላቸው ድረስ፡፡ ኢትዮጵያ የኢትዮጵያውያን የጋራ ሀገር እስከሆነች ድረስ በግዛት መካለልና ያንንም ተከትሎ በመጣ ዕልቂት የሰውና የንብረት ውድመት መከሰት አልነበረበትም፡፡ ማንም ዜጋ የትም ሄዶ መሥራትና ሀብት ንብረት ማፍራት ስለሚችል አዲስ አከላለል ወይም ኬሌላ ግዛት የመሬት ዝርፊያ ባላስፈለገም ነበር፡፡

ወያኔ ግን የነገን ሣይሆን የዛሬን ብቻ ስለሚያስብ የሆነው ሁሉ ሳንወድ በግዳችን ሆነ፡፡ ግዴለም – “በዚሁ ይለፍ፡፡” ዋናው ነገር ግና ከዚህ ሁሉ የሰው ዕልቂትና የንብረት ውድመት በኋላ የ“ታላቋን ትግራይ ሪፐብሊክ” ለመመሥረት ማሰብ ከፍ ሲል ለመግለጽ እንደተሞከረው ዕብደት እንጂ ሌላ ሊሆን አለመቻሉን መረዳት ተገቢ ነው፡፡ ወያኔዎች እንደዚህ ያለ ጅል አስተሳሰብ ውስጥ የሚገኙ ከሆነ ከፍ ሲል በዐማርኛ የጠቀስነውን የትግርኛ ብሂል ደግመን በማስታወስ ”ዝአኽለን ጥሂነን በዓል ማርያም ትብላ” ብለን እንተርትባቸዋለን፤ ወቅቱ የሀዘን ቢሆንም በለበጣ የአግራሞት ሣቅ እንፈግባቸዋለን፡፡ ይህን ቅዠት ማንም ወያኔም ይሁን የትግራይ ክፍለ ሀገር ሰው ሊያስበው አይገባም፤ አይችልምም፡፡ ሁለት ተቃራኒ ነገሮች ኅብረት የላቸውም፡፡ ብርሃንና ጨለማ በአንድ ጊዜ አይገኙም፡፡ ኢትዮጵያዊነትና ትግራዊነትም እንዲሁ፡፡ ጤናማ ተጋሩ ከዚህ ወያኔያዊ ቅዠት ባፋጣኝ ውጡና የሚሻለውን ለማድረግ ተመካከሩ፡፡ ይህ “ወርቃማ” ዕድል የዛሬ 25 ዓመት አለፈ፡፡ የፈሰሰን ውኃ ማፈስ ደግሞ አይቻልም፡፡

ይልቁንስ ለትግራይና ለተጋሩ የሚያዋጣው ብቸኛ መንገድ የሆነች መፈንቅለ መንግሥት ማድረግና ያችን ተከትሎ ጤናማ ትግሬዎች የያዙት “የክልሉ መንግሥት” ከሌሎች ጤናማ ወገኖች ጋር አዲስ ድርድር ማድረግ ነው፡፡ ለዚህም የጤናማ ትግሬዎች ሚና በጣም ወሳኝ ነው – በተለይ ወጣቱ፡፡ ይህ ሣይሆን ቀርቶ ወያኔ የትግራይን መፃዒ ዕድል እንደእስከዛሬው ሁሉ እንዲወስን ከተደረገ በርግጥም የትንቢቱ ፍጻሜ ይሆንና  ሊያስወግዱት በሚቻል ችግር ሀገራችን የማትወጣው አደጋ ውስጥ ትገባለች፡፡ ይህን እውነት አሁን ሳይመሽ በጊዜ እንዲህ ባልተለመደ ድፍረት የምናገረው ሌላውን ተውትና ከነባራዊው ዓለም ተጨባጭ ወይም ገሃድ እውነት በመነሳት የተበደለ ሲነሳ የሚያቆመው ነገር እንደሌለ በመረዳት ነው፡፡

እዚህች ላይ አንዲት ጠቃሚ ነጥብ ላንሳ፡፡ … ደጋግ ሰዎች ለፈጣሪ ከጮኹና የፈጣሪን ልብ ካራሩ ትንቢት ሊለወጥ ወይም የሚከሰት ውድመት ሊቀንስ እንደሚችል መገንዘብ ተገቢ ነውና ለፈጣሪ የቀረባችሁ ዜጎች የእንቅልፍ ሰዓታችሁን በመቀነስ ሌት ተቀን ወደፈጣሪ ጩኹ፤ እየመጣ ያለው የመከራ ዶፍ ሰው ቀርቶ ምድር አትችለውም – በዓለም ታሪክ ወደር የሌለው የወያኔዎች ዐረመኔነት የሚያስከትለው ጦስ እንዲህ በቀላሉ የሚገመት ነው ብሎ የሚያስብ ሰው ካለ ስለወንጀል ዕዳ አከፋፈል ምንም የማያውቅ የዋህ ሰው መሆን አለበት፡፡ ይህን የማይም ማስጠንቀቂያ እየተናገርኩ ያለሁት በዱባ ጥጋብ ለታበዩትና በዕብሪት ጉሽ ጠላ ለሰከሩት ወያኔዎችና መሰሎቻቸው አይደለም፤ ተፈጥሮን ተመክሮ አይመልሰውምና እነሱ መቼም ሊለወጡ አይችሉም – እንዲለወጡ የሚጠብቅም ሰው ካለ የአእምሮ ህክምና የሚያስፈልገው የለዬለት ሞኝ ነው፤  እነሱና ጋዳፊ ሊለወጡ እንደማይችሉ በበኩሌ በደንብ አውቃለሁ – ጋዳፊ ስምንት ቀን ተሸሽጎበት ከነበረው የቆሻሻ ቱቦ ወጥቶ “ምን ሆናችሁ? ሊቢያ ውስጥ ምን ተፈጠረ?” እያለ መሪው እርሱ የሆነ ያህል ቆጥሮ በባትሪ እየፈለጉት የነበሩትን ተቃዋሚዎች ለማዘዝ ቃጥቶት ነበር አሉ – ግን ወዲያው ያዙትና በመቀመጫው በኩል ሣንጃቸውን ወድውደው አንጀቱን በጣጥሰው ገደሉት – የአምባገነኖች መጨረሻ እንዲህ ነው፡፡ እኚህን መሰል ደናቁርት ከአህያ የማይሻል የማየት ችሎታ ነው ያላቸው፤ የጅልነታቸው መጠን የጨካኝነታቸውን ያህል ነው፡፡ …

እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ሀገራችንን ከተጋረጠባት የጥፋት ዳመና ያውጣልን፤ ፍቅርና አንድነትን ይስጠን፡፡ ለሳዖል የሰጠውን ማስተዋል ለሕወሓትም ሰጥቶ ሕዝብንና አገርን እያረዱበት የሚገኙትን ጎራዴ/ሠይፍ ወደ አፎቱ እንዲያስገቡና ዕርቅና ሰላም በሀገራችን እንዲሰፍን እግዜር ይርዳን፤ ምርጫ አጥተን የምንገባበት መብታችንን የማስከበር ትግል ሁሉ ብዙ የሕይወትና የንብረት መስዋዕትነትን ይጠይቃልና የእስካሁኑ መከራችን በቃችሁ ብሎ ባፋጣኝ ምሕረቱን ይላክልን፤ አሜን፡፡

mz23602@gmail.com

መስፍን በቀለ “ወታደሩ ጓዴ መተኮስህን አቁም”የሚል አዲስ ወቅታዊ ነጠላ ዜማ ለቀቀ (ይዘነዋል)

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ተወዳጁ ድምጻዊ መስፍን በቀለ በወቅታዊው የሃገራችን ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ አዲስ ነጠላ ዜማ መልቀቁ ታወቀ:: ዛሬ በተለቀቀው ነጠላ ዜማው መስፍን “ወታደሩ ጓዴ መተኮስህን አቁም” የሚል ዜማ በማውጣት ከሕዝብ ትግል ጎን መቆሙን አሳይቷል:: መስፍን በዚህ ዘፈኑ ወቅታዊ ጉዳዮችን ዳሷል:: ያድምጡት; ሼር ያድርጉት:: ሕዝባዊ ክብር ለዚህ አርቲስት ይስጡት::

መስፍን በቀለ “ወታደሩ ጓዴ መተኮስህን አቁም” የሚል አዲስ ወቅታዊ ነጠላ ዜማ ለቀቀ (ይዘነዋል)

ማዲንጎ አፈወርቅ በኢሳት ራድዮ ቀርቦ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ ጠየቀበት ቃለምልልስ ተለቀቀ |ይዘነዋል

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ባለፉት 2 ሳምንታት በኢትዮጵያ በነበረው ወቅታዊ ሁኔታ የተነሳ በኢሳት ራድዮ እንደሚለቀቅ ቃል ተገብቶ ሳይለቀቅ የቆየው ማዲንጎ አፈወርቅ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ የጠየቀበት ቃለምልልስ ዛሬ ማምሻውን ለአየር በቅቷል:: ማዲንጎ ይቅርታ ያለበትን ምክንያትና ሌሎችንም ጉዳዮች ጋዜጠኛ ተቦርነ ቦየነ ጠይቆታል – ማዲንጎም መልሷል:: ያዳምጡት::
ቃለምልልሱን ለማግኘት ወደ 41ኛው ደቂቃ ጋር አሳልፈው ያድምጡት

መስፍን በቀለ “ወታደሩ ጓዴ ወንድምህን አትግደል ብረቱን መልሰው”የሚል አዲስ ወቅታዊ ነጠላ ዜማ ለቀቀ (ይዘነዋል)

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ተወዳጁ ድምጻዊ መስፍን በቀለ በወቅታዊው የሃገራችን ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ አዲስ ነጠላ ዜማ መልቀቁ ታወቀ:: ዛሬ በተለቀቀው ነጠላ ዜማው መስፍን “ወታደሩ ጓዴ መተኮስህን አቁም” የሚል ዜማ በማውጣት ከሕዝብ ትግል ጎን መቆሙን አሳይቷል:: መስፍን በዚህ ዘፈኑ ወቅታዊ ጉዳዮችን ዳሷል:: ያድምጡት; ሼር ያድርጉት:: ሕዝባዊ ክብር ለዚህ አርቲስት ይስጡት::

ዮዲት ወልደርፋኤል (ሄለን ኃይሉ) –“የኩናማ ተወላጅ ነኝ…ይቅርታ እጠይቃለሁ”አለች

$
0
0


ዮዲት ወልደርፋኤል (ሄለን ኃይሉ) – “የኩናማ ተወላጅ ነኝ… ይቅርታ እጠይቃለሁ” አለች
ዮዲት ወልደርፋኤል (ሄለን ኃይሉ) – “የኩናማ ተወላጅ ነኝ… ይቅርታ እጠይቃለሁ” አለች

ዛሬ ኦሮምያ እየተባለ የሚጠራው ምድር የማን ነው? የማይረባ ጥያቄ!!!! ሌሎችም የሰሞኑ ክስተቶች! –ሰርጸ ደስታ

$
0
0

በቅጽበት የተናደው የ25 ዓመት የዘረኝነት ግንብ
ሰሞኑን ፕሮፌሰር መስፍን ወልቃይት የማን ነው? የሚለውን ጥያቄ የማይረባ ጥያቄ ያሉበት መልዕክታቸው እጅግ አስደስቶኛል፡፡

OromiaMap12_71.jpgበ60ዎቹ ከተነሱት የጠባብ ብሔረተኝነት አራማጅ ቦድኖች አንዱ ወያኔ ዛሬ የዛን ጠባብነት ተግባር ላይ አዋለው እንጂ በ60ዎቹ የተነሱ ቡድኖች በአብዛኛው የዚሁ ልክፍት የተጠናወታቸው የሕዝብና የአገር ጉዳይ የማይገባቸው ዘረኞች ናቸው፡፡ ይሄን እውነታ ለወያኔ ብቻ ብንሰጠው ከዚያ የወረደ ጠባብነት የተፈወስን እንዳይመስለን፡፡ እውነታው ከወያኔም በከፋ ዘረኛ አስተሳሰብ ያላቸው የ60ዎቹ ቡድኖች አሉ፡፡ ይሄው የዘረኝነት መርዝ ዛሬ ሁሉንም በክሎት ስለሚሰራው እንኳን እንዳያስተውል አእምሮው መክኗል፡፡ ወያኔ የኢትዮጵያ ሕዝብ በዘረኝነት ልክፍት እንዲበከል 25 ዓመት በገዛ አገራችን ሀብት ብዙ ሠርቷል፡፡ እግዚአብሔር ግን ይህ እንዳይሆን ሕዝቡን (ከተማረውና ብልጣብልጥ ከሆነው በቀር) ከዚህ መርዝ ጠብቆታል፡፡ በደንብ አስተውሉ ዛሬ ዘረኝነት ያለው በማን ዘንድ ነው? በዲያስፖራ ወይስ በአገር ቤት? በተማረው ወይስ በተራው ሕዝብ? በትክክልም ወያኔ ዘረኛ ነው፡፡ ግን በየ አገሩ የምትኖር ራስህን በኦሮሞነት፣ አማራነት፣ ትግሬነት ወዘተ ኪስ ከተህ ሌላው አልታይ ብሎህ እጅግ የከፋ የዘረኝነት አዘቅት ውስጥ እንደገባህ ሳይታወቅ በምን ሞራል ዘረኛን የማወገዝ አቅም ይኖርሀል፡፡ የወያኔን የዘረኝነት ፕሮገራም በዋነኝነት የሚያሰፈጽምለት ማን ነው? ተማርኩ አወቅሁ የሚለው የመከነው ትውልድ አይደለም?  ተራው (መሠረታዊው በቦታው የሚኖረው) ሕዝብ ጋር እኮ ይሄ የለም፡፡ ሲሆን እኮ መማር ሌሎች አገሮችን ማየት የበለጠ ብዝሐነትን ለማስተናገድ እድል ይሰጥ ነበር፡፡ መሠረቱም መሠረታዊ ወገንተኝነት እንጂ ዘረኝነት ባልሆነ፡፡ ሰው በአእምሮው እየበሰለ ሲሄድ ጥበብን ይለብሳል፡፡ ጥበብ ደግሞ ሁሉን እንድንረዳ ታደርጋለች፡፡ የምናደርገውና የምንወስነው ነገር ሁሉ ከአመክንዮ (ሎጂክ) እንጂ ከጠባብ ስሜተኝነት አይሆንም፡፡

ዛሬ እኮ ሰማያዊ መንግስትን እናስተምራለን በስላሴ አምሳል የተፈጠረው ሁሉ ይገደናል የሚሉት የሐይማኖት አባቶች ሳይቀሩ እኮ በአደገኛ የዘረኝነት ልክፍት ውስጥ ናቸው፡፡ ዛሬ እኮ የተማረው በአብዛኛው በዘረኝነት ልክፍት ታውሯል፡፡ አሁን አኮ ለዘመናት የታፈነውን የኢትዮጵያዊነት መንፈስ እንዲፈነዳ ያደረገው እኮ የጎንደር ተራ(ተራ ግን አይደለም) ሕዝብ ነው! ተማርኩ፣ አወቅሁ የሚለውማ የወያኔ ዋነኛ የዘረኝነት መንፈስ አሰራጭ ሆኖ 25 ዓመት ሲያገለግል ነበር፡፡ ዛሬ ደርሶ አንድነትን ለመስበክ ፊት አውራሪ መሆኑ ደግሞ የሚያሳየው ተለዋዋጭነቱን ግልብነቱን፣ መካንነቱን  እንጂ መሠረታዊ ማንነቱን አይደለም፡፡

እንደ እግዚአብሔር ቸርነት እንጂ እንደዘረኛው የ60ዎቹ ትውልድማ ዛሬ ኢትዮጵያ የለችም፡፡ 25 ዓመት ሙሉ ወያኔ በስልጣን ላይ ሌሎች ደግሞ በያሉበት ሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲበታተን ብዙ ተሠራ፡፡ በተለይ ደግሞ አማራና ኦሮሞ በሚል የአገሪቱን ብዙውን ሕዝብ ለማቃረን ከፍተኛ በጀት ተመድቦለት ተዘመተ፡፡ እግዚአብሔር ግን ከላይ ሆኖ ሁሉን እስከጊዜው ይታዘብ ነበር፡፡ በመጨረሻም ዘረኞቹ ራሳቸው ባሰቡት አካሄድ የተሄደባቸው የአገርንና ሕዝብን የማፍረስ ሥራ ውጤቱ በተቃራኒው እየሆነ እራሳቸው እስከሚታዘቡት ድረስ ይሄው የ25 ዓመት ግንብ ተንዶ ዛሬ ላይ ይፋዊ አንድነት መሰበክ ጀመረ፡፡ የዛሬ 10 ወር ገደማ የአዲስ አበባውን ማስተር ፕላን ተከትሎ የኦሮሞ ወጣቶች በተናጥል (በኦሮሞነት ብቻ በሚመስል መንፈስ) ማስተር ፕላኑን ሲቃወሙ አሁን ወልቃይት የማን ነው? የሚለውን የማይረባ ጥያቄ ያሉት ፕሮፌሰሩ የዛሬ 10 ወሩን የኦሮሞ ወጣቶች ተቃውሞ  አልገባኝም በማለት መልዕክት ማስተላለፋቸውን እናስታውሳለን፡፡ በትክክልም ውጤቱ እንጂ የተቃውሞው መንፈስ የማይረባ ነበር፡፡ ውጤቱ ግን የዛሬን አንድነት የጸነሰ ነበር፡፡ ማንም ሰው በዚህ ፍጥነት 25 ዓመት ታቅዶና ያለ የሌለ ሀብት ፈሶበት የተገነባ ዘረኝነት እንዲህ ፍርስርሱ ይወጣል ብሎ አልገመትም፡፡ የወያኔውን አፈቀላጤም በብስጭት የተናገሩት ይሄንኑ ነበር፡፡ 25 ዓመት ሙሉ እሳትና ጭድ እንዲሆን ያደረግናቸው ሕዝቦች እንዴት አንድ ሆኑ? አሉን፡፡ ከዛሬ 10 ወሩ የኦሮሞ ወጣቶች ተቃውሞ በኋላም ብዙ ጭራሽ በተለይም የኦሮሞና የሌላው ሕዝብ የሚቃረንበት ድምጾች በስፋት ተሰሙ፡፡ ኦሮምያ የኦሮሞ የሚል አዲስ መፋተጊያ ተፈጠረ፡፡ ሂደቱ ሁሉ ካልደፈረሰ አይጠራም የሚባለው ነበር፡፡ ወያኔ አጋጣሚውን በደንብ ተጠቀመበት፡፡ ውጤቱ ግን የተንኮልን ጉድጓድ አርቀህ አትቆፍር ለተኮለኛ የተነገረው ምክር ነበር፡፡ ብዙ ተማርን ብለው ራሳቸውን የቆለሉ ዘረኞችም በይፋ ከማውገዝ ይልቅ ሌላ ትንታኔ እየሰጡ በመከነው አእምሮአቸው አመክኒዮ ቢስ (ሎጂክ የሌለው) ፍልስፍና ሲፈላሰፉብን ቆዩ፡፡ ሁሉም ነገር ለበጎ ነው የሚል አባባል ከብዙዎች ዘንድ አሰማለሁ እኔ አባባሉን ባልጠቀምበትም፡፡ አሁን የመጣንበት ሂደትን ግን ሳስብ ግርም ይለኛል፡፡ እግዚአብሔር ጥፋትን ወደ በጎነት መቀየር እንጅ ጥፋትን መከልከል አያስፈልገውም፡፡ ለዛም ነው መሰለኝ ከእግዚአብሔር ሲመጣ ሁሉም ነገር ለበጎ ነው የሚባለው፡፡ የዛሬ 10 ወሩ የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ተከትሎ የተነሳው የኦሮሞ ወጣቶች ተቃውሞ የቱንም ያህል ዘረኝነት መንፈስ ቢመስልም ወጤቱ ማንም ሊያስበው ከሚችለው በላይ በጎ የሆነ ስኬት ሆነ፡፡ አሁን ላይ ቆሜ ሳስብ በእርግጥም በዛ ወቅት በኦሮሞ ወጣቶች የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ባይገታ ማንም ይመለከተኛል ብሎ በኢትዮጵያዊነት ሊያስቆመው የሚችል አልነበረም፡፡ የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ከማይደግፉት ሰዎች አንዱም ብሆን ማስተር ፕላኑን ያስቆመውን የተቃውሞ መንፍስ ግን የማይረባ ነበር (አነጋገሬን አንሻፎ መጠቀም አይቻልም)፡፡ በወቅቱም የተሰማኝን ስሜት እንዲሁ ነው የገለጽኩት፡፡ ዛሬ በድፍረት ወልቃይት የማን ነው የሚለውን የማይረባ ያሉት ፕሮፌሰር መስፍን በዛን ወቅት የኦሮምያ ተቃውሞ አልገባኝም በማለት በመለሳለስ የተቹት ወቅቱ የማይረባ ለማለት ምቹ አልነበረም፡፡ ያ አነሳሱ የማይረባ የነበረው እንቀስቃሴ የሚረባ ጽንስን ጸንሶ ዛሬ ላይ አገርንና ሕዝብን የሚታደግ ክስተት ሆኖ ተወልዶ እናየዋለን፡

ማንም ይሄንን አልገመተም!! ዛሬ ላይ ለብዙዎች ኦሮምያ የማን ነው? የሚለው የማይረባ ጥያቄ ሆኖ ትክክለኛው ጥያቄ የገባቸው ይመስለል፡፡ 25 ዓመት በማይረቡ ጥያቄዎች ስንደናበር ለጠላቶቻችን ተመቻችነትን ኖረን ነበር፡፡ አልገባንማ፡፡ የኢትዮጵያን ሕዝብ አንድ አድርጎ ያሰረው ሞገሱና ኃይሉም ኢትዮጵያዊነት እንጂ ኦሮሞነት፣ አማራነት፣ ትግሬነት ….ወዘተ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያዊነት ነው ጉልበቱም ውበቱም፡፡ ወያኔ ኢትዮጵያዊነት አደገኛ ጠላቱ እንደሆነ ከመጀመሪያውም ሲለሚያውቅ ነበር ሕዝብን ከታላቅነቱ አውርዶ በየጎጡ የኮሰሰ ያደረገው፡፡ ልብ በሉ እኔ ኦሮሞነት አማራነት ምናምን የሚገባኝ ሰው አደለሁም፡፡ ከዛ ይልቅ ከዚህም የበዛ የህዝብ ማንነት፣ ባሕል፣ አኗኗ እሴት ይማርከኛል፡፡ አማርኛ ተናጋሪ ሁሉ አንድ ነው የሚል እምነት የለኝም፡፡ ሲጀምር ከቤሰብ ጀምሮ የተለያየን ነን፡፡ ግን በተቻለ መጠን ብዛታችንን እንጂ ትንንሽነችንን አልወደውም፡፡ እኔ ከኢትዮጵያም ያለ ግዙፍነት እመኛለሁ፡፡ እንደ 60ዎች ያለ የመከነ ዘረኛ አእምሮ ባይገጥመን አይደለም ኤርትራ ሌላውም የአካባቢው ሕዝቦች በአንድ አገርነት (ሕብረ-ብሔርነት) ሊኖሩ የሚችሉበት እድሉ ነበር፡፡ ቢያንስ ዛሬ የአውሮፓ አገራት ያደረጉትን አይነት ውሕደት ከመሠሎቻቸን በተለይም ሱዳን፣ ኢትዮጵያ(ኤርትራን ጨምሮ)፣ ጂቡቲ ሶማሊያን ያካተት የአገራት ውሕደት መፍጠር የሚያስችል የሕዝቦች የአኗኗርና ባህል  መሠረት ነበር፡፡ እንዲህ በማሰብ ለአፍሪካም ጭምር አርዐያ መሆን ሲገባን ራሳችንን በመከኑ አእምሮዎች ባርነት ሥር ጣልን፡፡ የማይረቡ ጥያቄዎች እየጠየቅን እስከአሁንም የማንረባ ሆንን፡፡

የሪዮው ጀግና ፈይሳ ሌሊሳና የአዲስ አበባው ሰላማዊ ሠልፍ መቀረት 

የወያኔ ቡድን ሳምንት እሁድ በአዲስ አበባ ተጠርቶ የነበረውን ሠላማዊ ሰልፍ ሕዝቡን በማስፈራራት ሰልፉን ማስቀረቱን እንደ ትልቅ ድል አስቦት መደንፋቱን ሳያቆም ነበር ባላሰበውና ባልገመተው ቦታ በሪዮዎ የኦሎንፒክ ጎዳናዎች አንበሳውን ፈየሳን ሲያይ በድንጋጤ ከተራራነት ወደ ሸለቆነት የተቀየረው፡፡ የአዲስ አበባ ሕዝብ ሰልፍ ቢወጣ ማን ያየው ነበር?  ያው ደም የጠማቸው አጋዚዎች ሰለባ ይሆን ነበር እንጂ፡፡ የወያኔን ቡድን ግፍ ለዓለም ለማሳየት አንዱ ፈይሳን እግዚአብሔር ወገኖቹን አሳሰበው፡፡ እንዲህ ያለውን ድፍረትና ለወገን ራስን መሠዋዕት ማድረግ የሚያስችል አቅም ሥንቶቻችን እንዳለን አላውቅም፡፡ እኔ አለኝ ብዬ አላምንም፡፡ ዓለምንም ያስደመመ ጀግንንነትና ቁርጠኝነት ነው፡፡ ዛሬ ላይ አገር ቤት ራሳቸውን መሥዋዕት እያደረጉ ያሉትን ወገኖቹን ለማብና ስለነሱም ወሳኝ መስዋዕትነትን ለመክፈል ፈይሳ በጣም አስቦበት የወሰነው እንጂ በስሜት እነዳልነበርም አስተውለናል፡፡ ይሄ ከባድ ነው!! ወያኔን አከርካሪውን የሰበረ ነበር፡፡ ወደፊት ተስፋ የምናደርጋት ኢትዮጵያ ለዚህ ልጇ ምን መታሰቢያ እንደምታኖርለት አላውቅም፡፡ ለነገሩ ማን ያስታውሳል? ኢጣሊያን በረሃዎች አለምን ጉድ የሚያሰኝ ጀግንነት የፈጸሙና የጀነራልነት ማዕረግን የተቀዳጁ እንደነ አብዲስ አጋ ያሉ ጀግኖች ከጀነራልነት ወደ መቶ እልቅና የሚወርዱባት አገር ምን ውለታ አሳቢ አለባት? አጎብዳጆችና ባንዳዎች እንጂ ጀግኖች አልታሰብባት ያለች ምድር!!

የገዱ አንዳርጋቸው የሰሞኑ ጋዜታዊ መግለጫና የመንግስት ሚዲያ

በአማራ ክልል በሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ ከበሬታ እንዳላቸው የሚነገርላቸው የክልሉ ፕሬዘዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ይሄ ሁሉ ወጥንቅጥ በሚመሩት ክልል ሲካሄድ ዝም የማለታቸው ነገር ብዙ ብዙ ሲያስብል ቆይቶ ሰሞኑን በቴሌቪዥን ብቅ ብለው 15 ደቂቃ ገደማ ጋዜታዊ መግለጫ መስጠታቸው አንዱ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር፡፡ አቶ ገዱ ሲናገሩ በቀጥታ የሚሰማውና በተለያዩ ሚዲያዎች ጋዜጣዊ መግለጫቸው እየተጠቀሰ የሚነገረው አንዳንዴ ከነጭረሱ የሚቃረን ሆኖ ታዘብኩት፡፡ አሸባሪው ኢቢሲ አቶ ገዱ የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን አሉ ብሎ ሲጠቅስ ቀዳሚው ነበር፡፡ ይሄንኑ የአሸባሪውን የኢቢሲን ነገር ጠቅሶ የጀርመኑ ሬዲዮም ዘገበው፡፡ በኃላም በተለያዩ ድረ-ገጾች ተመሳሳይ ይዘት ያላቸውን አስተያየቶች ሰማን፡፡ አቶ ገዱ የማያዳግም የሚል ቃል ከአንደበታቸው ሲወጣ ፈጽሞ አይሰማም፡፡ አስፈላጊውን የማስተካከያ እርምጃ እንስዳለን ነው ያሉት፡፡ አቶ ገዱ በንግግራቸው ሁሉ ኃላፊነት በተሰማውና በጥንቃቄ ሕዝብን  የማያስቆጡ ቃላቶችን እየመረጡ እንደነበር በደንብ ማስተዋል ይቻላል፡፡ አቶ ገዱ ስለ ኮሌኔል ደመቀ ሲናገሩ መጀመሪያ የኮሌኔሉን ሙሉ ሥም ጠቅሰው ከዛ ግለሰቡ የሚልን ቃል ተጠቅመዋል፡፡ አሸባሪው ኢቢሲ ገዱ የጠቀሱትን የኮሌኔሉን ሥም ቆርጦ ግለሰቡ ከሚለው ንግግራቸው አንስቶ ሊያሰማን ሞክሯል፡፡ ያም ቢሆን ገዱ አረጋግጠው የተናገሩት የኮሌኔሉ ጉዳይ የሕዝብ ጥያቄ እንዳለበት ነው፡፡ ሕዝቡንም ማክበር እንደሚገባም በመጠቆም፡፡ ገዱ በእርግጥም እንደ ኃይለማሪያምና ሙክታር በወያኔ ትዕዛዝ በሕዝብ ላይ የሚደነፉ አይደሉም፡፡ በእርግጥም እንደ ክልል አስተዳዳሪነታቸው አሁን እየሆነ ያለው ጉዳይ ያሳስባቸዋል፡፡ የገዱ ሙሉ ንግግር እንሆ

http://www.ena.gov.et/index.php/video/video/item/6654-2016-08-25-20-36-40

የወያኔን ደጋፊዎች ለእብደት የዳረጋቸው ክፉ ዘረኝነት 

አሁን ላይ እግዚአብሔር ይመስገን ነገሩ እየጠራ መጥቷል፡፡ በአለማወቅም የተሸወዱት በጸጸትና በቁጭት አውቀው ያደረጉት ደግሞ ሳይወዱ በግድ የማይወዱትን አንድነት እየሰበኩ ነው፡፡ በዛው ልክ የዘረኝነት ልክፍቱ የባረቀባቸውም ብዙዎች ናቸው፡፡ አሁን አሁን የሕወሐት ደጋፊ የነበሩ ግለሰቦች ወደ እብደቱም እየቃጣቸው ይመስላል፡፡ ሰሞኑን አንደ አንድ የሕወሐት አምላኪዎች በየማሕበራዊ ገጹ በእብደት ሲሳደቡና ሲጮሁ ተመልከትኩ፡፡ የሕወሐት ዋና የሆነቸው ሚሚ ስበሐቱን ከዚህ በፊት ሰምቼ ሰው ምን ቢያደርጉት እንደዚህ ይሆናል ብዬ ነበር፡፡ ችግሩ ለካ የእብደት ነበር፡፡ ለእንደ ሚሚ ያሉት በእርግጥም የወያኔ መውደቅ ማሳበድ አይደለም ራሳቸውን ሊያስጠፋቸው እንደሚችል እገምታለሁ፡፡ ሰሞኑን አንድ የወያኔ እንዲህ ለአደጋ መጋለጥ ያሳበዳት እብድ በየፌስቡኩ እብደቷን አሳውቃለች፡፡ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ እብደቷ ሳያንስ በዚሁ እብደቷ ሳቢያ ከአፏ በወጣው ንግግሯ ከሥራዋም ተሰናብታለች የሚል ዜናን ሰማን፡፡ ሚስኪን፡፡ ይች አሁን የዘረኝነት ልክፍት ያሳበዳት እንጂ ከወያኔው ቡድን ተጠቃሚም አትመስለኝም፡፡ ባይሆን እንደነ ሚሚ ያሉት ማበድ አይደለም ራሳቸውን ቢሰቅሉ አይገረምም፡፡ በዘረኛው ቡድን ከለላ ሥር ያለቸው ሚሚ እንኳን ከሥራ ልትታገድ ጭራሽ የሰላምና የሕዝቦች መፈቃቀር መገለጫ መድረክ በሆነው  የሪዮ ኦሎምፒክ የኢትየጵያው የኦሎሚፒክ ልዑክ አባል ሆና እንደተሳተፈች ሰማን፡፡ ለነገሩ ሮቤልን አባቱ ለዋና ከሄዱ እሷ በጅምናስቲክ ልትወዳደር ይሆናል፡፡ አሁን ደግሞ አንደ ወዳጄ አንድ ሌላ እብድ ሼር አደረገኝ፡፡  አንድ ነገር አሁንም አስጠነቅቃለሁ፡፡ ወያኔና የትግራይ ሕዝብ የተለያየ ነው፡፡ ወያኔ ከትግራይ የወጣ የወረበሎች ቡድንም ቢሆን የትግራይን ሕዝብ አይወክልም፡፡ ደጋፊዎቹና ወያኔ የሚያደርገውን መረኔነት አይቶ የትግሬ ማለት እንዲህ ነው የሚያስብል ድምዳሜ ስህተት ነው፡፡ በአጋጣሚ ለማሕበራዊ መገናኛ እዱሉ ዛሬ በብዛት ያለው ለወያኔና ደጋፊዎቹ ስለሆነ የሰፊውን የትግሬ ወካይ አስመስሎት እንዳይታይ፡፡ ለምን እንደሆነ ባይገባኝም እስካሁን የታዩት ሚሚ ስበሐቱን ጨምሮ ሶስቱም ሴቶች ናቸው፡፡

ለወያኔው በድን እየቀረበ ያለው የተሳሳተ ጥሪ

እኔ በሕይወቴ ኢትዮጵያ እንደ ወያኔ ያለ አደገኛ ቡድን ገጥሟታል የሚል እምነት የለኝም፡፡ ብዙዎች ለወያኔ የብሔራዊ እርቅ ጥሪ እያቀረቡለት እሰማልሁ፡፡ በትክክል ከተረዳንው የወያነው ቡድን ይሄን ለማድረግ የማያስችሉት ችግሮች ስላሉበት እንጂ አሁን ላይ እንዲሀ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቶ ሌሎች ብለውት ሳይሆን ራሱ የሚያደርገው ጥሪ ነበር፡፡ ብሔራዊ እርቅ በሉት፣ ሌላ ስልጣኑን የሚሻማበት ሂደት የወያኔን ቡድን አባላት ለ25 ዓመት ሲሰሩት የነበረውን ወንጀል ስለሚያጋልጥባቸው አልፎም ለፍርድ ሊያቀርባቸው ስለሚችል አሁን የዚህ ቡድን አባላት ጭንቀት እሱ ነው፡፡ ማንም ትክክለኛ የሆነ ተፎካካሪ ወደ ስልጣን መጋራት መጥቶ ሊያልፈው የማይችል በአገርና ሕዝብ ላይ የፈጸሙትን ወንጀል አይቶ ሊያልፋቸው አይችልም፡፡ ለመሆኑ ኢትዮጵያ ዛሬ በወንጀለኞች ቡድን ሥር እንዳለች በደንብ አስተውለንዋል? እና ይሄንን ቡድን ሥልጣን አጋራኝ ማለት ራስህን አጋልጥ ወይም አባል አድርገኝ እንደማለት ነው፡፡ ዶ/ር አረጋዊ በርሄ በትክክል የገለጹት መሠለኝ፡፡ አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ የዚህ ቡድን አባላትና ደጋፊዎች የአገርቱን ሐብት ሁሉ ለራሳቸው አድርገው እየኖሩ ነው፡፡ ሌላ ኃይል ቢመጣ ምን ብሎ ሊያልፋቸው ይችላል፡፡ ብሔራዊ ዕርቅ ምናምን የሚባለው ቀደም ብሎ ቢሆን ዕድሉ ነበር፡፡ አሁን ላይ አስቸጋሪ ነው፡፡ እርቅ ብሎ የሄ ቡድን ከተቀበለ አሁን የገባበትን አጣብቂች ለማብረድና እርቅ ብለው የቀረቡትን ለመመረብ እንደሚሆን መገመት ብልህነት ነው፡፡ ልብ በሉ በመንግስት መዋቅር ከሚታወቁትም የቡድኑ ባለስልጣናት ወጭ በወሳኝ አገሪቱንና ሕዝቦቿን ለዛሬው አረንቋ የከተቷት አደገኛ የሥውር አባላት አሉት፡፡ ለምሳሌ ስበሐት ነጋ የተባሉት ግለሰብ እስከዛሬ በሚታወቅ የመንግስት መዋቅር ውስጥ የገቡበት ዋቅት ትዝ አይለኝም፡፡ ሆኖም የአገሪቱ አራጊ ፈጣሪ መሆናቸው ግልጽ ነው፡፡ ልብ በሉ በምን መስፈረት ነው እንዲህ ያለው የወሳኝነት መብት ለስብሐት ነጋ የተሰጠው? ተብሎ ቢጠየቅ የወንጀለኛ ቡድን መሪነት አወቃቀር ባለው ሥልጣን ነው፡፡ ስለዚህ ወያኔን አሁን ላይ ብሔራዊ ዕርቅ ምናምን ብሎ መዘናጋት አደገኛ ውጤት ይኖረዋል፡፡ ጠልቼው እንዳይመስላችሁ፡፡ በግሌም ይቻል እንደሁ በሚል ጉዳዩን ሊያነሱ ከሚችሉ ጋር ለመወያየት የሞከርኩት ነበር ግን የማይታሰብ ነው፡፡ የፓርላማ አባል የነበሩት ግርማ ሰይፉ ተናግረውታል ምንም ዕድል የለም፡፡ ሽግግርም በሉት በሔራዊ ዕርቅ ሊኖር የሚችለው ከወያኔ በኋላ ነው፡፡

 

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!

 

አሜን!

 

ሰርጸ ደስታ

 

 

እንጅባራ፣ ሃሙሲት፣ ወረታ፣ አመድ በር፣ ጋይንት፣ ቲሊሊ፣ ኮሶበርና ሌሎች የአማራ ከተሞች ሕዝባዊው ተቃውሞ ተቀጣጠለ |መንገዶች ተዘጋግተዋል

$
0
0

Screen Shot 2016-08-28 at 7.23.22 AM
(ዘ-ሐበሻ) በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች ሕዝባዊው ተቃውሞ እየበረከተ የመንግስት መዋቅሮችም እየፈራረሱ መሆናቸው ተሰማ:: ከጎንደር ተነስቶ የነበረው ተቃውሞ በአሁኑ ወቅት በጎጃም ታላላቅ ከተሞች ውስጥ የሕወሓት መንግስት ስልጣኑን እንዲለቅ የሚጠይቁ ሰላማዊ ሰልፎች ተካሂደዋል::

በዛሬው ዕለት በእንጅባራ፣ በሃሙሲት፣ በወረታ፣ በአመድ በር፣ በጋይንት፣ በቲሊሊና ኮሶበር ከተሞች ከፍተኛ ሕዝባዊ ተቃውሞ መደረጉ ታውቋል:: በነዚህ ከተሞች በተደረጉ ተቃውሞች ቁጥሩ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ሕዝብ ወጥቷል::

በአዊ ዞን የእንጅባራ፣ ቲሊሊ እና ኮሶበር ህዝብ በነቂስ ወጥቶ የትግራይ ነጻ አውጪውን መንግስት ተቃውሞ ከአዲስአበባ ባህርዳር የሚወስደው መንገድ ተዘግቷል። ይህ የሆነበት ምክንያት የአጋዚ ጦር መሳሪያዎችን ወደ ከተማው እንዳያስገባ ለመከላከል ታስቦ እንደሆነ ለዘ-ሐበሻ የደረሱ መረጃዎች አስረድተዋል::

ከቤተ አማራ የተገኘው መረጃ እንደሚያስረዳው ከፋፋዩ የወያኔ ስርዓት የአገውን እና የአማራውን ሕዝብ ለመከፋፈል በእንጅባራ ከተማ አንድ የወያኔ ሰላይ « እንዴት እናንተ አገው ሆናችሁ 25 ዓመት የሞላው የአማራ የድንበር ጥያቄ ታነሳላችሁ?» በማለቱ የተቆጡ የአገው ወጣቶች እኛ ሁሌም አንድ ነን በማለት የዚህ የስርዓቱ ተላላኪ ሆቴል አውድመውበታል::
Gojam2
በጋይንት ነፋስ መውጫ ሕዝብ መንገድ ዘጋግቶ ከደብረታቦር ወደ ጋይንት የሚያሳልፈውን መንገድ የዘጋጋው ሲሆን ከሕወሓት ነጻ አውጪ መንግስት ወታደሮች ጋር ግብግብ መግጠሙ ተሰምቷል:: በጋይንት ነፋስ መውጫ መንገዶች በ እንጨት; በድንጋይና በጎማዎች ተዘጋግተዋል:: በጋይንት 2 ሲቭል የለበሱ የመንግስት ኃይሎች 4 ሰላማዊ ሰልፈኞችን ካቆሰሉ በኋላ አንድ ሰው ገድለዋል:: እነዚህ ኃይሎች ወደ ሄዱበት ፖሊስ ጠባያ ሕዝቡ ሄዶ ከቦታል::

ጋይንት ነፋስ መውጫ የተሰዋው ወጣት ስሙ አዳነ መኮነን ካሴ ሲሆን የተወለደው ጉና ነው። እድሜ 25 ። አባቱ የጉና ጋይንት ህዝብ ወያኔን በ1983 በተፋለመበት ሰዓት መስዋዕት የሆኑ መሆናቸውን ቤተአማራ ዘገቧል::

በመላው የአማራ ከተሞች እየተደረጉ ባሉ ተቃውሞች የትግራይ ነጻ አውጪ ግምባር ባንዲራዎች ተነስተው ትክክለኛው ልሙጡ አረንጓዴ; ቢጫ ቀይ ባንዲራ ተተክተዋል::


የአዘዞ ነዋሪዎች በስራ ማቆም አድማ ለተጎዱ ወገኖቻችን ትናንት ምሳ ሲያበሉ የሚያሳይ ቪዲዮ

$
0
0

ቀጣዩን ቪድዮ የለቀቀው አክቲቭስት ኄኖክ የሺጥላ ነው:: ሕዝቡ በጎንደር አዘዞ የሥራ ማቆም አድማ ማድረጉ ይታወሳል:: በዚህ የሥራ ማቆም አድማ የተጎዱ ወገኖችን ምሳ የማብላት ተግባር በአካባቢው ነዋሪዎች ተደርጓል:: ሰው ያለውን እያካፈለ ትግሉ ይቀጥላል:: ሪፖርተር ጋዜጣ ዛሬ እንደዘገበው በጎንደር እየተደረጉ ያሉ የሥራ ማቆም አድማዎች ኢኮኖሚውን እየጎዳው ነው:: ሕዝብ እምቢ ካለ ሥር ዓቱን መጣል ይችላል – ይመልከቱት ይህን ታሪካዊ ቪድዮ::

የአዘዞ ነዋሪዎች በስራ ማቆም አድማ ለተጎዱ ወገኖቻችን ትናንት ምሳ ሲያበሉ የሚያሳይ ቪዲዮ

በኢትዮጵያ ውስጥ በተከሠተው ጉዳይ ላይ የሕዝባዊ ማስታወቂያ ጥሪ

$
0
0

ከአቤቱታ አቀነባባሪ ኮሚቴ
Ethiopiaከኢትዮጵያ ውጭ የሚኖሩ የሰብእና [humanities]ና፣ የማኅበራዊ[social sciences]፣ እንዲሁም የሳይንስ [sciences] ጥናቶች ሊቃውንትና ምሁራን የሆኑት ኢትዮጵያውያን ባገራችን ውስጥ የተፈጠሩት አንገብጋቢ የፖለቲካ፣ የሰብኣዊ መብት፣ የምጣኔ-ሀብትና የማኅበራዊ ኑሮ ከፍተኛ ቀውሶች እንዲፈቱና ዘላቂ መፍትሔ እንዲሰጣቸው ለማድረግ፣ ለተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሓፊ አቤቱታ ለማቅረብ፣ ከላይ የተጠቀሰው ኮሚቴ ፊርማ በማሰባሰብ ላይ ይገኛል። ኮሚቴው በውጭ የምትኖሩት ኢትዮጵያውያን ሊቃውንትና ምሁራን የሆናችሁ በሙሉ ከዚህ በታች በሚገኘው ድረ-ገጽ ገብታችሁ ፊርማችሁን በማስፈር ላገራችሁና ለወገኖቻችሁ ስትሉ ድጋፋችሁን በማበርከት በአቤቱታው እንድትተባበሩን በአክብሮት ይጠይቃል። የአቤቱታው ቅጂ፣ እንዳስፈላጊነቱ ተስተካክሎ፣ ለአሜሪቃ ፕሬዚደንት [USA President]፣ ለአውሮጳ አንድነት ሸንጐና[European Union Parliament] ለአውሮጳ አንድነት የሰብኣዊ መብቶች ጉዳይ ወኪል [European Union Commission for Human Rights] ይላካል። የድረ-ገጹ አድራሻ እንደሚከተለው ነው።
http://www.petitionbuzz.com/petitions/appeal-to-the-un-secretary-general

 

 

//

የህወሃትን ሥልጣን ትሽራለህ፤ የነፃነትንም ቀንዲል ታበራለህ |እነዚህን 7 ነገሮች አድርግ

$
0
0

ከነጻነት ታጋዮች የቀረበ ጥሪ

ወያኔ ተብሎ የሚታወቀው ቡድን የሰው ልጅ ጠላት መሆንን መርጧል። ኢትዮጵያም ጠላቷ መሆኑን አውቃለች። ከዚህ ጠላት እጅ ሠላም አይጠበቅም ። ከዚህ ጠላት ደጅ ነፃነት የለም ። ከዚህ ጠላት ቤት ክብር አይገኝም ። ይህ ጠላት እንደሌሎች ጠላቶች አይደለም።ይህ ጠላታ የተለየ ጠላት ነው ። ይህን ጠላት ወዳጅ ማድረግ አይቻልም። ይቻላል የሚል ከተገኘም አሁን ግዜው አልፏል ። ሁሉም በግዜው ሲሆን መልካም ነው ።

የህዝብ ጠላት መሆንን የመረጠውን ህወሃት/ወያኔን ራሱ ከቆፈረው ጉድጓድ ውስጥ ከተህ ትቀበረው ዘንድ ተጠርተሃል።እስከ አሁን በአገሪቷ እዚያም እዚህም የሚደረጉ አመፆች የብዙ ወጣቶችን ህይወት አስቀጥፈዋል። የትግሉ አቅጣጫ መስተካከል ይኖርበታል ። የሰውን ልጅ ደም በማፈሰስ የሚደሰቱት አጋዚዎች ተነጣጥሎ በሚደረግ አመፅ ምክንያት የግፍ ዱላቸውን አጠንክረዋል። ይህን የጭካኔ ጉልበታቸውን ለማንበርከክ በአገሪቷ ውስጥ የሚካሄዱት አመፆች በተመሳሳይ ሠዓት ሠዓት መሆን ይኖርባቸዋል።
Gojam2

ካሁን በኋላ እንዲሁ መሞት ይቁም ። ዛሬ አንድነታችን ከመቸውም ግዜ በላይ ተጠናክሯል ። ከጋምቤላ እስከ ኦጋዴን፤ ከአማራ እስከ ኦሮሞ፤ ከስሜን እስከ ደቡብ የወያኔን የግፍ ፅዋ ያልተጎነጨ አይገኝም ።የግፉን ፅዋ አልተጎነጨሁም የሚል ካለ እርሱ የግፉ አካል የሆነ ብቻ ነው ። ይሄውልህ አንተ አንባቢ ጀግንነት የአያቶችህ ወይም የአባቶችህ ነው። አንተ ጀግና ነህ ። ጀግና ጥበበኛ እና ብልህ ነው ።ጀግና ፈሪ ሳይሆን ለእምነቱ የጨዋ ድፍረት ያለው ነው። እስከ አሁን ጅግኖቹ ወያኔን በተገኘው ቦታና ሁኔታ እየታገሉት ነው። ይሄ ትግል ደግሞ በትንሽ በትንሹ ቢደራጅ ውጤቱ ያማረ ፤የትግሉም ግዜ ያጠረ እንዲሆን ያደርገዋል። በትንሽ በትንሹ አስተዋይ የሆነ የጎበዝ አለቃ እየመረጥን መደራጀት ይኖርብናል ።የአንተ ጀግንነት ላይ ትህትናህ ታክሎበት ለመረጠከው የጎበዝ አለቃ ጥሩ መሪ ትሆነዋለህ ። አንተ የጎበዝ አለቃ ከሆንክ ጥሩ ተመሪ አለህና ውጤታማ መሪ ትሆናለህ።

እንግዲህ ካሁን በኋላ አጋዚ እየገደለን አንቀጥልም። የሚገድለንን የበለጠ እንዳይገድል ማስቆም ግድ ነው።ገዳዮችን ለማስቆም የሚከተሉትን እናደርጋለን፤
1.በትንሽ በትንሹ በሚስጥር እንደራጃለን፤እንታጠቃለን፤መግቢያና መውጪያ እናዘጋጃለን፤የእርስ በእርስ መገናኛ ቋንቋዎችን እንፈጥራለን ።

2.በተገኘው አጋጣሚ ታጥቀውም ሆነ ሳይታጠቁ መድረሻ ያሳጡንን እናጠቃለን፤የያዙትን ማንኛውንም ዓይነት መሣሪያ በቁጥጥር ሥር አውለን ለሚቀጥለው ትግል እንጠቀምበታለን።
3.ርህራሄ የማያውቁትን አጋዚዎችንና መሰሎቻቸውን ፊት ለፊት አንገጥማቸውም፤በድንገት በደፈጣ ምሳቸውን እንሰጣቸዋለን፤ከዚያም አስቀድመን ወዳዘጋጀነው ሥፍራ እንሰወራለን።
4.በሁሉም ሥፍራ አቀናጅተን መንገዶችን በሌሊት እንዘጋለን።ወያኔ ሁሉንም መንገዶች ለመቆጣጠር አቅም የለውም። መንገዶችን በሙሉ ለመዝጋት እንሠራለን።ይህንንም በመላ አገሪቷ እናደርጋለን።
5.በሠፈር በመንደር ውስጥ ለወያኔ የሚሰልሉ።መረጃ የሚያቀብሉ ምናምንቴዎችን ለይተን እናወጣለን እንደ አስፈላጊነቱ እርምጃ እንወስዳለን።

6.የወያኔ የጉልበቱ ምንጭ ገንዘቡ ነው ። ከእኛ የዘረፈው ገንዘብ ። በእርሱ ሥም የተያዘ ወይም ከእርሱ ጋር በሽርክና የተያያዙ የንግድ ድርጅቶች በሙሉ በጥቃት ራዳራችን ውስጥ ይገባሉ።
7.ዘይትና ቤንዚን ሲቀላቀሉ ብርቱ የሆነ የጦር መሣሪያ ይፈጥራሉ።ለወያኔ አጋዚ ወታደሮች ትጥቅና ሥንቅ የሚያመላልሱ ተሽከርካሪዎች በጀግኖቹ መንደር እንዳይመላለሱ ይደረጋል።የሚያልፉበት መንገድ ይዘጋል ።ሲቆሙም ለነፃነታችን ሲባል እርምጃ ይወሰድባቸዋል፡፡

ስማ አንተ አንባቢ ታላቋ አሜሪካን በቬትናም ገበሬዎች ተለብልባ ተሸንፋለች ። የምታስፈራው ሩሲያ በአፍጋኒስታን ታጋዮች ዋጋዋን ተቀብላለች ።ህወሃት/ወያኔ በውኑ ከአሜሪካን ይበልጣልን ? እኛስ ከቬትናም ገበሬ እናንሳለን ?አንተ አንባቢ የብዙ ጀግኖች መፍለቂያ አገር ውስጥ ነው ያለኸው ። አንተም ጀግና ነህ ። የጀግና አገር ልጅ ።

እንግዲህ የነፃነቱን ቹቦ አንስተህ ለኩሰው ። የነፃነቱን ወጋገን ከጎንደር እስከ ወለጋ ያበራ ዘንድ ከፍ አድርገው ። ወያኔ የጥቂት ራዕይ አልባ እና ከመብልና ከመጠጥ የዘለለ ህልም የሌላቸው የደካሞች ስብስብ ነው ። ይህን ደካማ ቡድን ከጫንቃችን አውርደን ለመጣል የሚያስችለን ኃይል ወደ እኛ እየገሰገሰ ነው። ጠላት አይኑ እያየ ፤ጆሮውም እየሰማ በትንሽ በትንሹ እንደራጃለን፤እንታጠቃለን፤እናጠቃለን ፤እናሸንፋለን ።
ወያኔ ይውደም !
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !

የአትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ታላቅ ተግባር በአትሌት ኢብሳ እጅጉም ተደገመ |ታሪክ ተሠራ

$
0
0

ibsa

(ዘ-ሐበሻ) አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ በሪዮ ኦሎምፒክ እጆቹን ወደላይ አጣምሮ የታሰርናል ምልክትን አሳይቶ ገዳዩን የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት በተቃወመ በሳምንቱ ሌላው ጀግና አትሌት ኢብሳ እጅጉም ታሪክ በመስራት ዛሬ በካናዳ የታረናል ምልክት በማሳየት ተቃውሞን ገለጸ::

አትሌት ኢብሳ እጅጉ በካናዳዋ ኪውቤክ ከተማ በተደረገው የማራቶን ውድድርን 2:30:40 በመግባት ያሸነፈ ሲሆን የውድድሩን ሪቫን በጥሶ ሊገባ ሲል እጆቹን ወዳላይ በማንሳትና በማጣመር በሕወሓት መንግስት ኢትዮጵያ ውስጥ እየተደረገ ያለውን የሰብ አዊ መብት ጥሰትና ግድያን አውግዟል::

የአትሌት ኢብሳን ዜና በርካታ የውጭ ሚድያዎች ከአትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ጋር በማያያዝ በሳምንቱ ታሪክን ደገመ እያሉ እየዘገቡት ይገኛሉ::

ለስለስ ያለች መሳሳም ቁጣን አብርዳ ሰላምን ታሰፍናለች

$
0
0

ከ…. ዓለማየሁ

በሥራ ላይ እድገት አግኝተሽ ወደ ቤት ለመሄድ ቸኩለሻል:: ከመኪናሽ እንዴት እንደወረድሽ ራሱ ትዝ አይልሽም:: ለባለቤትሽ ይህን ታላቅ የምስራች ለመናገርና ደስታሽን አብራችሁ በመፈንደቅ ለማሳለፍ አቅደሻል:: “ፐ አሁን ባለቤቴ ሲሰማ እንዴት ይደሰት ይሆን? መቼም እቅፍ አድርጎ አንገቱ ስር ጠምጥሞ አስገብቶኝ ይስመኛል:: የእኔ ባለቤት እኮ አንበሳ ነሽ ይለኛል” እያልሽ በአይነ ሕሊናሽ እያሰብሽ ነበር መኪናሽን በፍጥነት እየነዳሽ ቤት የገባሽው:: የባለቤትሽን ስም እየተጣራሽ በየክፍሉ ስትፈልጊው ባለቤትሽ የለም:: “ውዴ.. የእኔ ፍቅር… የት ነህ?” እየደጋገምሽ እየተጣራሽ ነው:: ግን ባለቤትሽ በቤት ውስጥ የለም:: በሁኔታው በጣም ተደናግጠሽ ወደ ቤትሽ ጀርባ ስትሄጂ ባለቤትሽ ብቻውን ባልተመለደ መልኩ ተቀምጧል::


እሱን ከቁብ ሳትቆጥሪ ደስታሽን መናገር ቀጠልሽ: “”የሥራ እድገት አገኘሁ እኮ”” ብለሽ ስትነግሪው ባለቤትሽ እንዳሰብሽው ከእቅፍሽ አስገብቶ ሳይስምሽ: ወይም ደስታሽ ደስታዬ ነው ሳይልሽ ጥሎሽ ቢሄድ ምን ትያለሽ?… በትዳርሽ ውስጥ አንድ ትልቅ ችግር አለ ማለት ነው:: ይህን እንዳወቅሽ ከባለቤትሽ ጋር ንትርክ ትጀምሪያለሽ ወይስ ምን ታደርጊያለሽ?  አብረን እንቆይ::

kiss
በሺዎች የሚቆጠሩ ትዳሮች ውስጥ ባልና ሚስት በቤት ውስጥ የጎሪጥ የመተያየታቸው ነገር ይታያል:: የአብዛኞቹ ትዳር ውስጥ ፍቅር በፍቅረኛነት ዘመን ያለቀ ይመስል አንድ ቤት ውስጥ አንድ ሶፋ ላይ ተቀምጠው ጀርባና ፊት መሰጣጠት የተለመደ ሆኗል:: ሁለታችሁም ከሥራ ገብታችሁ አንቺ ወደ ጓደኞችሽ ደውለሽ ስልክ የምታወሪ ከሆነ እሱም ጋዜጣ ይዞ ተቀምጦ የሚያነብ ከሆነ ፍቅራችሁ ውስጥ መሰለቻቸት የገባ አይመስላችሁም?

 

አብሮ ተቻችሎ መኖር እጅግ ከባድ ነገር ቢሆንም ይህንን የሚወጡ ባለትዳሮች ከጀግናም በላይ ጀግና አድርገው ሳይኮሎጂስቶች የሚጠሯቸው ለምን ይመስላችኍል?? የሀገሬ ሰው ”ባል እና ሚስት ከአንድ ባልዲ ይቀዳሉ”” ብሎ የተረተውም ከላይ ያልኩትን ሀሳብ ያወፍርልኛል:: ባልና ሚስት ከአንድ ባልዲ ይቀዳሉ ሲባል ሁለቱን አንድ አይነት ሀሳብ ያስባሉ ማለት ብቻ ሳይሆን: በአይን ተነጋግረው ይግባባሉ: በአይን ብቻ ፍቅር ይሰራሉ: የሚፋቀሩ ከሆነ ቢጣሉ እንኳን የትም ዞረው ይገናኛሉ የሚሉትንም ያጠቃልላል:: የትዳር አጋሩን ሀሳብና ፍላጎት የማይረዳ ካለ እርሱ ከትዳር አጋሩ ጋር በአንድ ባልዲ ውስጥ እንዳለ ውሀ አይደለም ማለት ነው::

በትዳር ውስጥ ለሚፈጠሩ ችግሮች ወይም ሰላማዊ ትዳር ላለመምራት እክል ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮች የታወቁ ቢሆኑም ብዙ ጊዜ ልብ ብለን እነዛን ነገሮች ለማስተካከል ስለማንሄድ ችግሩ አፍጦ መጥቶ ጋብቻን እንደ ከርቸሌ (እስር ቤት) የምንቆጥር ብዙ ነን:: ከጭንቀት እና ፍርሀት: ረዥም ሰአት ከመስራት: ከድካም: የሰው ወሬ ከመስማት: ያለሆነ ነገር በአእምሮ ፈጥሮ ከማሰብ የተነሳ የትዳር አጋርን ጣል ጣል የማድረግ ነገር ይመጣል:: “”ረዥም ሰአት የሚሠራ: ፍርሀት እና ጭንቀት ያለበት እንዲሁም የሚደክመው ሰው ችግሩን ቀስ ብሎ ከማስረዳት ይልቅ ቁጣ ቁጣ ይለዋል::”” የሚሉት የስነ-ልቦና ባለሙያዎች “”ንግግሩ ሁሉ የፍቅርና ትህትህናን የተሞላ ሳይሆን የንቀትና በጣም የጮኸ ስለሚሆን የትዳር አጋርን ሊበጠብጥና ወደ አልተፈለገ ንትርክ ሊመራ ይችላል::”” ይላሉ:: እነዚህ የስነ ልቦና ባለሙያዎች ለዚህ እንደመፍትሄ ሀሳብ የሚያቀርቡት ባልና ሚስት ረዥም ሰአት የሚፈጅ ሥራ መስራት እንደሌለባቸው ነው:: ሁለት ሙሉ ሰአት ሥራ የሚሠራ አንድ ወገን ለ16 ሰአታት ከሚስቱ ተለይቶ በሥራ ላይ ተወጥሮ ውሎ በ17ኛው ሰአት እቤቱ ሲገባ አልጋው ነው የሚናፍቀው ወይስ ከሚስቱ ጋር ቁጭ ብሎ የፍቅር ጨዋታ መጫወት?

አብዛኞቻችን በትዳር ውስጥ ችግሮች እንዴት እንደሚፈጠሩ በልምድም ልናውቀው ስለምንችል ወደ መፍትሄዎቹ ብናመራ የተሻለ ይሆናል::
ታደምጣታለህ ወይ?

የትዳር አጋርህ ላንተ ልክ እንደ ሴት አያትህ ናት ይላሉ የስነልቦና ባለሙያዎች:: አያቶች ለልጅ ልጆቻቸው እድሜያቸው በገፋ ቁጥር ብዙ ማውራትን እና ብዙ መምከርን ያበዛሉ:: ስላሳለፉት ነገርም በብዛት ያወራሉ:: አያቶች ዝም ብሎ ጆሮ ሰጥቶ የሚያዳምጣቸውን እንደሚወዱት ሁሉ የትዳር አጋርህም እንደዚያው ናት:: ምንም ዝምተኛ ሚስት አገባው ብትልም ሚስት ከባሉዋ የምትደብቀው የላትምና ያሳለፈችውን ውሎ ስትነገርህ ማዳመጥ አለብህ:: ወሬው የሚያስጠላ ቢሆን እንኳ በአጽንኦት እየተከታተልክ መሆንን ለማረጋገጥ ”እህ”” “”አሀ”” “”ከዛስ?” እያልክ በማዳመጥ ልታበረታታት ይገባል:: ከትንሽ ጀምሮ ሚስትህን የምታደምጣት ከሆነ ጸብ ቢፈጠር እንኳ የመደማመጡ ባህልን ስላዳበርክ በአጭሩ እሳትን ማብረድ ትችላለህ::

እርሷ ስትናደድ ምን ታደርጋለህ?

እርሷ ተናዳ በነገር ልትቆሰቁስህ ትችላለች:: ጮክ ብላ እየተናገረች ታቆስልሀለች:: በዚህ ወቅት አንተም እንደ እርሷ እሳት ትሆናለህ? መልስህ አዎ ከሆነ ተሳስተሀል:: አንዲት ሴት ልጅ ጮክ ብላ በንዴት ከተናገረች “”የጎደለኝ አለና ስማኝ”” እያለችህ መሆኑን ማስተዋል አለብህ:: የጎደለባትን ነገር ለማስተካከል መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ አብረሀት ብትጮህ እና ብትለፋልፍ: ቃላት ብትወራወር ትርፉ ራስን ማዋረድ ነው:: ቃላት በተወራወርክ ቁጥር የሚያደማ ቃል ትነጋገሩና ቁርሾ ማሳደር ይሆናል:: ነገርን ከመፍታት ይልቅም የባስ ትልቅ ጦርነት በቤትህ አወጅክ ማለት ነው:: ለዚህ ነው በተለመዶ “”ትዳሩን መምራት ያልቻለ ሰው ለሀላፊነት አይበቃም”” የሚባለው:: ስለዚህ ለማዳመጥ የፈጠንክ ለመልስ የዘገየህ ሁንላት::

ይባስ ብለህ እንደውም እርሷ በምትበሳጭበትና ጮክ ብላ በምትናገርበት ወቅት ንዴት ውስጥ ብትሆንም ዓይን ዓይኑዋን እና ከንፈር ከንፈሯን ብቻ ተመልከት ይላሉ የስነ-ልቦና ሊቆች:: እርሷ በንዴት ውስጥ ሆና አንተ ዓይን ዓይኑዋን የምትመለከታት ከሆነ ንዴቷ እየበረደ ከመሄዱም በላይ ያሳለፋችሁትን መልካም ጊዜ በዛች ቅጽበት ውስጥ አስታውሳ እርሷም ታጋሽ ባል አለኝ ብላ እንድትኮራብህ ታደርጋታለህ:: ትንሽ በረድ ካለች በሗላ ደግሞ ከንፈሯ አተኩእርህ በመመልከት ከአንገት በላይ ከእርሷ ጋር አንድ ለመሆን ፍላጎትህን አሳያት:: ለስለስ ያለ የከንፈር ለከንፈር መሳሳም ቁጣን አብርዶ እቤትህ ውስጥ ሰላምን እንደሚፈጥርልህ ሁልጊዜም አስተውል::

ስልክ ባታነሳስ?
አንተ ሥራ ቦታ ነህ እንበል:: እርሷ እቤት ውስጥ ነች ወይም ከቤት ውጭ ወጥታለች:: ባለቤትህ ናፍቃህ ወደ እርሷ ቴሌፎን ስትደውል የስልክ ጥሪ ባትመልስ ምን ታደርጋለህ? እንደ የስነልቦና ሊቆች አጠቋቆም ከ100 አስር የሚያህሉት እንኳ ሚስታቸው ቴሌፎን አለማንሳቷን በጥሩ ጎኑ አይመለከቱትም:: አብዛኛው ወንድ የሚያስብው “”ስልኩን ከሌላ ወንድ ጋር እያወራችበት ነው: ወይኔ በእኔ ላይ ደርባ ይዛብኛለች”” ብሎ ነው ወዲያው የሚያስበው:: ምናልባት በኔት ወርክ ምክንያት እየጠራ እርሷ ጋር ላይሰማ ይችላል: የቴሌፎን ባትሪ አልቆባት ይሆናል: ምን አልባት ስልክ ማውራት የማትችልበት ቦታ ይሆናል: ወይም ሥራ ቦታ ውጥረት ውስጥ ትሆናለች ብሎ የሚያስብ ከስንት አንድ ነው:: አንተም ለአጋርህ ስትደውል ስልክ የማትመልስ ከሆነ ወዲያውኑ በመጥፎ ጎኑ የምትመለከተው ከሆነ አመለካከትህ መልካም ስላለሆነ ለመቀየር ሞክር::
እድሜ ለቴክኖሎጂ “”የድምጽ መልእክት ማስተላለፊያ”” (Voice massage) ተፈጥሮልናልና ይህን ተጠቀምበት:: ስልኩ ጠርቶ የማይነሳ ከሆነ “”የእኔ ፍቅር… (እንደዚህ ያሉትን ቃላት በጸብም ሆነ በፍቅር ጊዜ አትርሳ) የእኔ ፍቅር ናፍቀሺኝ ደውዬልሽ ነበር:: ሆኖም ስልክ ማናገር በማትችይበት ሁኔታ ውስጥ እንዳለሽ እገምታለው:: ስለዚህ በሗላ እንደዋወላለን:: እወድሻለው”” የሚል አይነት ትህትናንና ፍቅርን የተላበስ መልእክት አስቀምጥላት:: እንደዚህ ያሉት መልእክቶች ሚስትህ አንተ እንደምትጠረጥረው ከሌላ ወንድ ጋር እንኳ ሄዳ ቢሆን ትህትህናን እና አስተዋይነትህን አይታ ራሷን ትሰበስባለች:: “”ባለቤቴ ራሱን ስለሚያምን እኮ ነው እኔን የሚያምነኝ”” ብላ እንድታስብ ታደርጋታለህ:: አለበለዚያ ግን ለምን ስልክ አታነሺም እያልክ የምትጮህ ከሆነ: የስልክ ጥሪ አለመመለሱዋንም በመጥፎ መንገድ የምታየው ከሆነ “”ራሱን የማያምን ሰው ሰውን አያምንም”” የሚለውን ብሒል እውን እንዲሆን ታደርጋለህ::

የፍቅረኛነት ዘመንን የሚያስታውስ ትዝታን ትፈጥራለህ ወይ?

በፍቅረኛንት ዘመንህ ታሳያት የነበረህን የሰጪነት (የለጋስነት) ባህርይ ትዳር ውስጥ የሚከለከል እንዳይመስልህ:: ትዳር እስር ቤት አይደለም:: እንደውም በፍቅረኛንት ዘመን ከነበርክበት ጊዜ በበለጠ አሁን ከአጋርህ ጋር በነጻነት የምትገናኙበት ጊዜ ነውና ይበልጥ ለጋስነትህን ማሳደግ ይኖርብሀል:: ምንም እንኳ በፍልስፍና ዓለም ውስጥ ያሉ ሰዎች “”ሴቶች ፍላጎታቸውን አይደለም ወንድ ራሳቸውም አያውቁትም”” ቢሉም እንደፍላጎቷ ሁንላት:: በመንገድ ላይ ስትሄዱ የልብስ መሸጫ ሱቅ አጠገብ ስታልፉ “”ይህ ልብስ ያምራል”” ብትልህ እንድትገዛላት ፍላጎቷን እያሳየችህ ነው:: ገንዘብ ባይኖርህ እንኳ አብረሀት ልብሱን አድንቅ እንጂ “”አንቺ ደግሞ ሁሉም ያምርሻል”” ብለህ ፍላጎቷን ኩም አታድርገው:: ዛሬ ባትገዛላት ሌላ ጊዜ እንደምትገዛላት በፍቅር ቃላት ንገራት:: ይሄኔ ልብሱን የለበሰችው ያህል ከአፍህ የወጣው የትህትና ቃል ሰውነቷን ይሞላዋል::

ልክ እንደዚሁ ሁሉ በትዳር ውስጥ አብረህ በምትኖርበት ወቅት በተቻለህ መጠን የተዋወቃችሁበትን ቀን ሁልጊዜ አንተ አስተዋሽ ሆነህ አነሰም በዛም ስጦታ ስጣት:: ሴቶች እንደዚህ የሚያደርግን ወንድ እንደ ንጉሥ የመመልከት ባህርይ ስላላቸው በተቻለህ መጠን እርሷን ድንገት የሚያስደስቱ (surprise) ነገሮችን ለማድረግ ሞክር:: በተለይ አመታዊ የትውውቅ በዓላችሁን ስታከብሩ ድሮ በፍቅረኛነት ዘመን ትዝናኑበት የነበረው ሆቴል ይዘሀት ሄደህ ራት ጋብዛት:: እዛም እደሩ:: ይህን ካደረግክ ቤቷ እንዲናፍቃት ከማደረግህ በላይ የፍቅረኛነት ጣፋጭ ጊዜያችሁን በትዝታ መነጽር ዞር ብላ እንድታስታውስ ታደርጋታለህ:: ይህ ሲባል ግን ራት ይዘሀት የምትወጣው የግድ በዓላትን መጠበቅ የለብህም:: አብሮ ለሚኖር ሰው ሁልጊዜ በዓል ነው::

የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር የውጭ ግንኙነቶች ኃላፊ “ትናንሽ ሰንደቅ ዓላማዎችን በየቦታው መትከል አንሻም” አሉ

$
0
0

አቶ አብዲራህማን ማኅዲ፤ የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) የውጭ ግንኙነቶች ኃላፊና የሕዝባዊ አንድነት ለነፃነትና ዲሞክራሲ የዓለም አቀፍ ግንኙነቶች ኃላፊ፤ ስለ ድርጅቶቹ ሚና፣ ዓላማና ግቦች ይናገራሉ።
“ትናንሽ ሰንደቅ ዓላማዎችን በየቦታው መትከል አንሻም” – አብዲራህማን ማኅዲ
Screen Shot 2016-08-28 at 9.52.32 PM

ህወሓት ምንም አዲስ መልዕክት የሌለው መግለጫ ዛሬ ሰጠ –ጉዳያችን

$
0
0

ለመግለጫው አጭር መልስ የሚሆነው ´´ከዝንብ ማር አይጠበቅም´´ የሚል ነው EPRDF press release is the same as ´´square one´´ expression of its failed policy for the last 25 years

የአማርኛ ፅሁፍ ከስር ይመልከቱ።
woyaneEPRDF press release of August 28,2016 is the same as ´´square one´´ expression of its failed policy for the last 25 years. It is  full of empty words. There is no single word of ´´excuse´´ for over 1000 Ethiopians killed in last seven months by the regime. The press release is expected to invite more people to protest  TPLF. Because it did´t even reason out the real situation of the country plus the possible solutions suppose to be proposed by this particular press release. In addition to that the press release, at the last statement conclusion, warns peaceful protestors and appreciate the regime´s security personnels. Such a kind of approaches of TPLF is very common for Ethiopians in the last 25 years. In short it is possible to say that this is another confirmation as dictators will make fast their last days by following poor minded advisers. The same is happening in TPLF. For your easy information about the press release, please read the below Amharic version of Gudayachn´s view and full press release of TPLF video at the end of article.
የኢትዮጵያ ሕዝብ እያገባደድነው ባለው የ2008 ዓም ለነፃነት የሚያደርገውን ትግል በአዲስ መልክ ያቀጣጠለበት ዓመት ነው።በእዚህ ዓመት ብቻ እስካሁን ትክክለኛ ቁጥሩ ባይታወቅም በኦሮምያ እና አማራ ክልሎች ብቻ በሰላማዊ ሰልፍ መብታቸውን በመጠየቃቸው ብቻ ከ1000 በላይ ኢትዮጵያውያን በጥይት አረር ተገድለዋል። በአስር ሺዎች ወደ እስር ቤት ተግዘዋል።ሌሎች አስር ሺዎች ካሉበት ቀዬ ወደ ሌላ ቦታ ተሰደዋል።
ሕዝባዊ አመፁ እያየለ መጥቶ ይህ ፅሁፍ በምፃፍበት በእዚህ ቅፅበት በጎንደር እና ጎጃም ሕዝብ የህወሓት መዋቅር የሆኑ የአስተዳደር እርከኖችን አፍርሶ እራሱን በእራሱ ጊዝያዊ የአስተዳደር መዋቅር እየዘረጋ እና መሪውን እየመረጠ መሆኑ እየተዘገበ ነው።በእዚህ ሁኔታ እያለ ነው እንግዲህ የኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ከስብሰባ በኃላ ደረሰበት የተባለውን ውሳኔ ዛሬ ነሐሴ 22፣2008 ዓም በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የተነበበው።
መግለጫው በእራሱ የኢህአዴግ ነው ወይ? የሚለው መሰረታዊ ጥያቄ ነው።ምክንያቱም የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ብአዴን እና ኦህዴድ ቀድሞም በህወሓት መዋቅር የመታዘዛቸው ጉዳይ እንዳለ ሆኖ በእዚህ ዓመት ይብሱን በሕዝባዊ አመፁ ሳብያ ሕልውናቸው ማክተሙን በግልፅ የታየበት ነው።ስለሆነም የኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ሲባል ህወሓት እና ህወሓት ብቻውን ያሰበውን መግለጫ በሚል ስም እንዳወጣው መረዳት ተገቢ ነው።
በተሰጠው መግለጫ ላይ በመጀመርያ ክፍል ላይ ´´ውዳሴ ህወሓት´´ የተሞሉ ቃላት ብቻ ሲገኙበት።በሚልዮን የሚበሉት እና የሚጠጡት ባጡባት አገር ውስጥ ይልቁንም ረሃብ እንደ አዲስ አበባ ያሉ ታላላቅ ከተሞች ውስጥ ተማሪዎች የምግብ ድጋፍ ካልተደረገላቸው ትምህርታቸውን መቀጠል እንደማይችሉ እነዩኒሴፍ የመሳሰሉ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች በገለፁበት ሁኔታ ሁሉ የኢህአዴግ መግለጫ ኢትዮጵያ እንዳደገች ለመስበክ መሞከሩ አሁንም በአስራአንደኛው ሰዓት ላይ ቆመውም ህወሓቶች ለለውጥ ሳይሆን ለበለጠ ግድያ መነሳታቸውን አመላካች ነው።
የመግለጫው ዋና እና ቁልፍ ምክንያት የኢትዮጵያን ሕዝብ አዘናግቶ የበለጠ ጦር ሕዝባዊ አመፁ ወደተነሳባቸው ቦታዎች አዝምቶ ለመጨፍለቅ እና የምዕራባውያንን ውትወታ በሆነች ለውጥ በምትመስል መግለጫ ይሄው እየሰራን ነው ለማለት የታሰበ ነው።ለእዚህም ነው የህወሓት የማኅበራዊ ሚድያ አፈቀላጤዎች  መግለጫውን በተመለከተ በእንግሊዝኛ ለመፃፍ የሚደክሙት።ሌላው አስቂኝ የመግለጫው ሂደት አሁን ኢህአዴግ የሚያደርገው ለውጥ ከአስራ አምስት ዓመት በፊት የተጀመረው አካል ነው ሲል መደመጡ ነው።ይህ ´´ ሃያ አምስት ዓመት በጥይት ስገድሉን ኖረው አሁን ደግሞ በሳቅ ገደሉን ´´የምትለዋን አባባል ያስታውሳል። ስህተት ተሰርቷል ለውጥ ያስፈልጋል ብሎ በድፍረት የለውጥ አስፈላጊነትን አፍን ሞልቶ ለመናገርም ያፈረ ስርዓት ዛሬ በህዝባዊ አመፅ ለለውጥ ተገደድኩ ይሉኛል በሚል ጭንቀት ለውጡን ከአስራ አምስት ዓመት በፊት ባቀጣጠልነው መሰረት ነው ብሎ መግለጫ ማውጣት ለምንም አይነት እርምጃ አለመዘጋጀታቹን የበለጠ ግልፅ ያደርገዋል።
ህወሓት በእዚህ መግለጫ ላይ ለችግሩ መነሻ ብሎ ያቀረባቸው ነጥቦች በእራሳቸው ደካማ እና መሰረታዊ የህወሓት የፖሊሲ ውድቀት እና ስልጣንን በብቸኝነት የመቀራመት አባዜ ያገለለ ነው።በዛሬው መግለጫ ህወሓት የአገራችን ችግር ብሎ ያቀረባቸው ችግሮች ያሉ ችግሮች ቢሆኑም ዋናው እና መሰረታዊው ችግር ከላይ እንደተጠቀሰው የህወሓት የፖሊሲ ውድቀት፣ጎጠኛ እና አድሏዊ ስርዓት መስፈን እና ስልጣንን በብቸኝነት የመቀራመት አባዜ የሚሉት ዋነኛ ናቸው።ለእነኝህ መፍትሄዎቹ ደግሞ በዋናነት ህወሓት ስልጣኑን በፍጥነት እንዲለቅ ማድረግ እና ሕዝባዊ እና የሽግግር መንግስት መመስረት ነው።ከእዚህ ያነሰ መፍትሄ ቁስል የበለጠ እንዲመረቅዝ እና ኢትዮጵያን ወደ ባሰ ማጥ ውስጥ የመክተት ግልፅ ፍላጎትን ብቻ ያመለክታል።ህወሓት በዛሬው መግለጫው ግን ችግሮች ብሎ ጉዳዩን በጥገናዊ ለውጥ ለማለፍ የሞከረበት መንገድ ችግሮቹን  የህዝብ መብዛት፣የሕዝብ ፍላጎት መጨመር፣ስልጣንን የሀብት ማከማቻ የማድረግ ሂደት በኢህአዴግ ውስጥ በመስረፁ ወዘተ ናቸው በሚሉ ቃላት ለማድበስበስ ሞክሯል።
ባጠቃላይ መግለጫውን በሶስት ክፍሎች ልንከፍለው እንችላለን።የመጀመርያው ክፍል ህወሓት እራሱን ያሞገሰበት እና ኢትዮጵያውያን ´´ምግብ በልታችሁ ያደራችሁት እኔ ስልጣን ከያዝኩ በኃላ ነው´´ ቀረሽ ሐተታ ሲሆን ሁለተኛው ችግሩን ከህወሓት የስልጣን ጥማት እና አገሪቱን በተሳሳተ የጎጥ ፖለቲካ  መከፋፈል የመጣ መሆኑን ሸሽጎ የችግሩን መነሻ በገሃድ ካሉ ግን ብቸኛ ችግሮች ካልሆኑት የስልጣን መባለግ፣የህዝብ ብዛት መብዛት እና የህዝብ አዳዲስ ፍላጎቶች በሚሉ ቃላት ሊያድበሰብስ የሞከረበት ነው።በመግለጫው የመጨረሻ ክፍል ላይ ደግሞ ሕዝባዊ አመፁን የጥፋት ኃይሎች መሆኑን ሊሰብክ ይሞክርና ከጎኑ ቆመው ሕዝብ የገደሉትን ሲያሞግስ እና አይዟችሁ በርቱ ሲል ታገኙታላችሁ። መግለጫው ባጭሩ ይሄው ነው።ለመግለጫው አጭር መልስ የሚሆነው ´´ከዝንብ ማር አይጠበቅም´´ የሚል ነው።ህወሓት ማር ሊያመነጭ አይችልም።ማር የንብ ሥራ እንጂ የዝንብ ሊሆን እንደማይችል ሁሉ።

ሙሉ መግለጫውን ለመመልከት  ይህንን ይጫኑ።

ጉዳያችን GUDAYACHN 

 www.gudayachn.com


እጅግ በጣም አስቸኳይ መልእክት –ብሥራት ደረሰ

$
0
0

 

Tomarበአሁኒቷ ቅጽበት በዐማራው አካባቢ ሕዝቡ ከወያኔ ታጣቂዎች ጋር በባዶ እጁ እየተፋለመ ይገኛል፡፡ ይህ ለዓመታት ታፍኖ የነበረ የነፃነት ጥያቄ ወቅቱን ጠብቆ አሁን በቅርብ ከሞላ ጎደል በሁሉም የጎጃምና የጎንደር አካባቢዎች ፈንድቷል፡፡ ይህ የሚያሳየው ጭቆናና ምሬት በኃይል ታፍኖ ሊቀር የማይችል መሆኑን ነው፡፡

ይሁንና ነፃነት የጠማው የኢትዮጵያ ሕዝብ በጎሣና በሃይማኖት ተወስኖ የአንዱ ንቅናቄ ለሌላኛው ባይተዋር ሊሆን እንደማይገባ ሁላችንም ማሰብ ይኖርብናል፡፡ እርግጥ ነው እስካሁን ስህተቶች አልነበሩም አንልም፡፡ ንስሃ ልንገባባቸውና ይቅርታ ልንባባልባቸው የሚገቡ ስህተቶችን ሁላችንም ስንሠራ ለመቆየታችን ትልቁ ማስረጃ የወያኔ ሥልጣን ላይ ለ25 ዓመታት ተገሽሮ ሁላችንንም ሲቀጠቅጥ መቆየቱ ነው፡፡ ብንተባበር ኖሮ 25 ዓመታትን ቀርቶ 25 ቀናትንም አራት ኪሎ ምንሊክ ቤተ መንግሥት ውስጥ ወያኔ አይቆይም ነበር – ታሪካዊ ፀፀት፡፡

ስህተት አንድ – ሙስሊሙ ማኅበረሰብ የመብት ጥያቄ አንስቶ ብቻውን ሲታገል ሌላው በአብዛኛው በታዛቢ ወንበር ላይ ተቀምጦ ነበር፡፡ ያ ትልቅ ስህተት ነበር፡፡ እርግጥ ነው የሙስሊሙን ጥያቄ ከሃይማኖት አውጥቶ ወደ አጠቃላይና ሁሉንም ሊያቅፍ ወደሚችል የመታገያ መስመር ማስገባት ይቻል እንደነበር ብንጠቁም አግባብ ነው፡፡ ጥያቄዎችን ከማጥበብ ይልቅ ማስፋትና ሁሉንም አሳታፊ እንዲሆኑ ማድረግ ይገባል፤ ይቻላልም፡፡ ጠባብ ጥያቄዎችን መጠየቅ ለወያኔዎች የተናጠል ብትር ይዳርጋል፤ ማንም ደግሞ በተናጠል ጥያቄዎች ድልን ሊቀዳጅ አይችልም፡፡ በትልቅ ጥያቄ ፍቺ ውስጥ ብዙ ትንንሽ ጥያቄዎች ሊፈቱ እንደሚችሉ ባለመረዳት ወይም ለመረዳት ባለመፈለግ ብዙ ዘመን ተሞኝተናል – በዚህም ሰበብ ለወያኔ ምቹ ፈረስና መጋጃ ሆነን ለብዙ ዘመን ባጅተናል፡፡ ይህን ሞኝነታችንን ተረድተን ባፋጣኝ ካልተስተካከልን የሰሞኑ እንቅስቃሴም ከጊዜያዊ ጫጫታነት አያልፍም፡፡

ስህተት ሁለት – ኦሮሞ ኢትዮጵያውያን በተለይ ከዚህ ዓመት(2008) መባቻ ጀምሮ በየአካባቢያቸው ሰላማዊ ተቃውሞ ሲያደርጉና በወያኔ ቅልብ የአጋዚ ጦር እንደዐይጥ ሲጨፈጨፉ ሌላው ዳር ቆሞ ይታዘብ ነበር – የወንድሞቹ ቁስል አልተሰማውም ማለት ግን አይደለም፡፡ ለወያኔ የከፋፍለህ ግዛ ሥልት ተንበርክከን ራሳችንን በየግል ቋጠሮ በማስቀመጣችን ግን አልተባበርንም፤ በዚያም ምክንያት ወያኔ ተመቸውና በተናጠል መደቆሱን ቀጠለ፡፡ አሁንም እርግጥ ነው – የኦሮሞዎችን ጥያቄ ከኦሮሞ ግዛት መጥበብና መስፋት ጋር ብቻ ከማያያዝ ይልቅ እሱን በእርሾነት ይዞ ለትልቁ ሀገራዊ ነፃነት ሁሉም በአንድነት እንዲነሣ ቢደረግ ኖሮ ይሄኔ ይሄ በየአካባቢው የሚደረግ የቁጥ ቁጥ ትግል ባላስፈለገ ነበር፡፡ ይህችን ሒሣባዊ ቀመር እንዴት ማወቅ እንዳልቻልን ሳስበው ይገርመኛል፡፡ ጥቂት ወያኔዎች በአእምሮ ማለትም በተንኮል በተካነ አእምሮ በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ ይህን ያህል እንዴት ሊበልጡ እንደቻሉ ሳስበውም እንደዚሁ ይደንቀኛል፡፡ በምን አፈዘዙን?

ስህተት ሦስት – ሰሞኑን የዐማራው ሕዝብ ፀረ ወያኔ እንቅስቀሴውን ጀምሯል፡፡ የዘገዬ ቢሆንም ጅምሩ መልካም ነው፡፡ ሆኖም በተለይ በመነሻው አካባቢ ጥያቄው ልክ እንደላይኞቹ ሁሉ ጠበበና ወይም የሚጠበቀውን ያህል ሌሎችን አሳታፊ ሆኖ የተገኘ አልሆነምና ከክልሉ ውጪ ያሉትን ለመሳብ አቅም ያነሰው መሰለ፡፡ ጎንደር ላይ “የኦሮሞ ወንድሞቻችን ደም የኛም ደም ነው” በሚል ሕዝቡ በራሱ ተነሳሽነት የኦሮሞ ወንድምና እህቶቹን ሰማዕትነት ማስታወሱ አዲስ ምዕራፍ ከፍቶ ሁለቱን የወያኔ መጫወቻ ታላላቅ ብሔሮች (በእስካሁኑ ሁኔታ ማለቴ ነው) ቢያቀራርብም አሁንም ብዙ የሚቀረው ነገር እንዳለ መገንዘብ ይገባል፡፡ ወያኔዎችና ተባባሪዎቻቸው ለዘመናት የሠሩት ዕኩይ ተግባር በአንድና በሁለት የተቃውሞ ሰልፎች የሚናድ እንዳልሆነ መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡ ሁለትም ይሁኑ ከዚያ በላይ ትልልቅ ግንዶችን የሚያሸንፍ ቅርንጫፍ – ቅርንጫፉ ምንም ያህል ቀጭንና ላንቁሶም ይሁን – የግንዶቹን ሥሮች እንደምሥጥ እምሽክ አድርጎ በመብላት ግንዶቹን ከናካቴው ሊያጠፋቸው እንደሚችል እስካሁን ማንም አልተረዳም፡፡ ታላላቆችን ለማጥፋት ደግሞ አካላዊ ግዝፈት የግድ አይደለም – ብልጠትና መሠሪነት ብቻቸውን ብዙ ሚና ይጫወታሉ – በዚያ ላይ መካሪና ሁለገብ ረድኤት የሚሰጥ አጋዥ ኃይል ካለ አናሳዎች የጥፋት መንገዳቸው ቀኝ በቀኝ ነው የሚሆንላቸው፡፡ በዓለም 14.2 ሚሊዮን አካባቢ የሕዝብ ቁጥር ያላት እስራኤል የዓለምን ፖለቲካና ኢኮኖሚ በተቆጣጠሩ ምርጥ የኅቡኣን ድርጅቶች አባላት ልጆቿ አማካይነት የሰባት ቢሊዮኑን የዓለም ሕዝብ የዕለት ተለት ሕይወትና እስትንፋስ እንደምትቆጣጠርና እንደምትወስንም ለሚረዳ ዜጋ ከስድስት ሚሊዮን የፈለቁ ጥቂት አሰለጦች ከውጪ ረዳቶቻቸው ጋር ተዓምር አይሠሩም ብሎ መገመት ሞኝነት ነው፡፡ ብዛት ብቻውን አይጠቅምም – በራሱ ዋጋቢስ ነው፤ እንዲያውም ብዛት ያጃጅላል ይመስለኛል፡፡ የሌለህን እንዳለህ፣ ያልሆንከውን እንደሆንክ በሥነ ልቦና ጥጋብ እያሰከረ ተጠቂ ያደርግሃል – ብዛት፡፡ ስታንስ ግን ጠርጣራና ፈሪ ያደርግህና ከቢጤዎችህ ጋር እያቆራኘ – እንደሙጫ እያጣበቀ – ብዙ ትንግርት እንድትሠራ ያደርግሃል – ጥቂትነት፡፡ ዕድሜ ደጉ… ማንበብም ደጉ… ከብዙው ጥቂቱን አየን፡፡

ከቅርብ ቀናት ወዲህ የዐማራው ጥያቄ ለአጠቃላዩ ሀገራዊ ነፃነት የጥሪ ደወል ማሰማት ቢጀምርም ከፍ ሲል እንደተገለጸው በመነሻው አካባቢ በወልቃይት ዙሪያ ያጠነጥን ስለነበር ያ ጥያቄ ለጋሙጎፋውና ለአፋሩ ሩቅ መስሎ ሊታይ ቢችል አያስወቅስም ባይ ነኝ፤ ጥያቄው ሁሉን ቆንጣጭ ነበር ለማለት አያስደፍርም፡፡ አሁን መስተካከሉና ብሔራዊ አጀንዳ መያዙ ግን ደግ ነው፡፡ መስተካከሉን አምነን ታዲያ እንቀላቀለው፡፡ ምክንያቱም የዋናው ድል መቋጫ በዋናነት አዲስ አበባን ጨምሮ የሁሉም ሕዝብ ንቁ ተሣትፎ ነውና፡፡

ስህተት አራት – የዐማራው ጥያቄ ከጎጥና ከሸጥ አልፎ ሀገራዊ ቅርጽ ከያዘም በኋላ የመላዋ ኢትዮጵያ ሕዝብ ለጋራ ሀገራዊና ብሔራዊ ነፃነቱ በአንድነት “ሆ!” ብሎ እንዳይነሣ ያደረገው ነገር አለ፡፡ ይህን ነገር ሁነኛ የፖለቲካ ቡድች በአፋጣኝ አጥንተው መፍትሔ ካልተፈለገለት ይሄ አንዴ ወለጋ ሌላ ጊዜ ጎንደር የሚደረግ ሕዝባዊ የእምቢተኝነት ዐመፅና የነፃነት ትግል የትም አይደርስም፡፡ አዎ፣ የትም! ለሕወሓት ግን ሠርግና ምላሽ ነው፡፡ ለዚህ ጎጠኛ የአናሳዎች ቡድን መሠሪ ተንኮል መሸነፍ ይብቃን፡፡

ነፃነት ቆራጥነትንና እልህን ትፈልጋለች፡፡ ነፃነት ሸረኝነትና ተንኮልን ያዘለ ፉክክርን አትሻም – የነፃነት ፍልሚያ ውጤታማ እንዲሆን በቀናነትና በእኔ እብስ አንተ ትብስ የጋራ መግባባትና መተሳሰብ መቃኘት አለበት፡፡ ሁሉም እንደየአቅሙ በስሜትና በከፍተኛ ወኔ ከተሳተፈ የነፃነት ቀን ቅርብ ናት፡፡ ነገር ግን “ቆይ እነእንትና ይለይላቸው፣ እነሱ ሲያዳክሟቸው እኛ እንቀጥልና የመጨረሻ ግብኣተ መሬታቸውን እናሳያቸዋለን…” በሚል የማይረባ ሥልት በተናጠል መጓዝ ካለ መቼም ቢሆን ነፃነት አትገኝም፡፡ ነፃነት በእልህ አስጨራሽ የጋራ ትግል እንጂ በብልጣብልጥነትና ከጋራ ትግል በመሸሽ ልትገኝ አትችልም፡፡ በአንዱ ሞት ሌላው ነፃ እንዲወጣ ተደብቆ ወይ አሸምቆ ቢጠባበቅ ደግሞ ከኅሊናም ከሃይማኖትም አንጻር ወንጀልና ኃጢኣትም ነው፡፡ ሁሉም የድርሻውን ይወጣ፡፡ “ማን ይጠይቀኛል? ማንስ ያየኛል?” የሚሉት ጥያቄዎችም የጅል ፈሊጦች ናቸው፤ በመጀመሪያ ዋናው ጠያቂ ኅሊናችንና የሚሰውት ወገኖቻችን ነፍሳት ናቸው፡፡ ከዚህ ነጥብ አኳያ ሁሉም ዐይን ነውና እንዳንታለል፡፡

ስህተትን ለማስወገድ እንዲህ ቢደረግ ጥሩ ይመስለኛል፡-

ኦሮሞው፣ ዐማራውና ሌላው ጎሣ ሁሉ በተጀመረው መንገድ ለአንድ ዓላማ ይተባበር፡፡ የተናጠል ትግል የትም እንደማያደርስም ከልምድ ይረዳ፡፡ ጠላት አንድ ነው፡፡ የጥቃቱ ሰለባዎችም አንድ ናቸው ወይም ቢያንስ አንድ መሆናቸውን ሊረዱ ይገባቸዋል፡፡ ራሳቸውን እየለያዩ በተለያዬ ጊዜ ከሚጠቁ በአንድነት ተባብረው ከዘላለም ባርነት በአንዲት ጀምበር የዘላለም ነፃነታቸውን መጎናጸፍ ይችላሉ፡፡ እንደእስከዛሬው በመለያየትና የመቃብር ጉድጓድ እየቆፈሩ በዐፅምና ባለፉ ሰዎች የታሪክ ጠባሳ የሚጃጃሉ ከሆነ ግን ልክ  እንደስካሁኑ ለጠላታቸው ምቹ እንደሆኑ አንዱ ምዕተ ዓመት አልፎ ሌላው ይተካል፡፡ በሰው ሠራሽና በጠላት-ጠመድ የልዩነት ቦምቦች ፍንዳታ ጊዜያቸውን በከንቱ ማባከን የለባቸውም፡፡ ከዚህ ሞኝነታቸው ተምረው ብልኅነትን ገንዘባቸው ያድርጉ፡፡

ለምሣሌ የቋንቋና የሰንደቅ ዓላማ ልዩነቶች ወደ ውስጥ ገብተው ካጤኗቸው መሠረታዊ ችግሮች አይደሉም፡፡ ያገሬ ባላገርና ሕጻናት ልጆቹ በሕወሓት አልሞ ተኳሾች ጭንቅላታቸው እየተበተነ በቀያቸው ሥጋቸውን አሞራና ውሻ እየጎተተው ሳለ፣ ሕወሓት ኑሯችንን አመሰቃቅሎና ሰብኣዊ ተፈጥሯችንንም  ከእንስሳነትም በታች አውርዶ በነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ የሰቀቀን ኑሮ እየገፋን ሳለ፣ እትብቴ በተቀበረባት የገዛ ምድሬ እኔን ለመንግሥት ሥራ መቅጠሩ እንደቅንጦትና ብርቅ ይቆጠርና እንደህንድ የካስት ሲስተም ሊጨብጡኝ እንኳን እየተፀየፉኝ በምገኝበት ሁኔታ … ፖለቲከኞች ሚዛን በማይደፉ የአዛኝ ቅቤ አንጓች ዓይነት ጉንጭ አልፋ ክርክሮች ቢጠመዱ ሕዝብና ታሪክ ይቅር የማይሉት ሌላ ስህተት ነው – “ቀድሞ የመቀመጫየን” ብላለች ዝንጀሮ፡፡ ከሌላው እንቶፈንቶ ይልቅ የተበላሸን በማቃናት፣ የተሳሳተን በማረም፣ የተዛነፈን በማስተካከል … ወደ ደገኛው መንገድ እንግባና እንደቀድሟችን በቶሎ አንድ ብንሆን ሁላችን እንጠቀማለን፤ ሌላው ቀስ ብሎ ይደረስበታል፡፡

ሞኝነትንና ብልጣብልጥነትን አርቆ መቅበር ይገባል፡፡ ይህን በሕዝብ ደምና አጥንት ላይ የቆመ ከፋፋይ የወያኔ ብልሹ ሥርዓት ከሥሩ መንግሎ ከነሰንኮፉ ለመጣል ሁሉም “ሆ!” ብሎ በአንድ ወቅት መነሣት አማራጭ የሌለው የጊዜው አንብጋቢ ጉዳይ ነው – ከዳር እዳር ተነጋግሮና በጥሞና ተመካክሮ በአንድ ወቅት መነሣት!! ጎጃም የሚፈሰው ደም የአርሲው ነው፤ ወለጋ የሚፈሰው ደም የጎንደሬው ነው፡፡ የወያኔን ሤራ በጣጥሰው ካልጣሉና ሰሞኑን በተጀመረው የአንድነት መንፈስ ካልታገሉ ማንም ነፃ ሣይወጣ የወያኔ አሽከርና ደንገጡር ሆኖ የመከራ ኑሮን መግፋት ነው – እስከወዲያኛው፡፡ መጥፎ ህልም ስታልም መፍትሔው ከእንቅልፍህ መንቃት ነው – ከወያኔ ሰቆቃ ለመዳንም መፍትሔው በከፋፋይ ሤራው ላይ የማያዳግም እርምጃ ወስዶ ኅብረትን ማጽናት ነው፡፡

ያለፈ አልፏል፡፡ “ላለፈ ክረምት ቤት አይሠራም”፡፡ በእጃችን ያለችዋ ጊዜ ናት ወርቃማ ጊዜያችን፡፡ ወንድሞቻችን በጎጃምና በጎንደር እየተዋደቁ በወሎና በሸዋ እንዲሁም በአዋሣና በጋሙጎፋ የሚገኝ ሕዝብ ተኝቶ እንቅልፉን የሚደቃ ከሆነ የምትጠበቀዋ ነፃነት ቅዠት ናት – አትገኝም፡፡ ጎንደርና ባህር ዳር እየታመሱ አዲስ አበባና ናዝሬት በአሥረሽ ምቺው “ዓለማቸውን የሚቀጩ” ከሆነ የነበረችን አነስተኛ በሕይወት የመቆየት ነፃነት ራሷ ወደለዬለት ባርነት ትለወጥና ትልቁ እሥር ቤታችን – ዞን ዘጠኝ – ወደማዕከላዊ የወያኔ የ”ወንጀል ምርመራ” ዘብጥያነት ይለወጣል፡፡ ለዚህም ነው “የነብርን ጅራት አይዙም…” የሚባለው፡፡ ወያኔና የቆሰለ ነብር አንድ ናቸው፡፡ የወያኔን ተፈጥሯዊ የበቀለኛነት ስሜት አዲስ አበቤዎች በተለይ ጠንቅቀን እናውቀዋለን፡፡ ከ97 ምርጫ በኋላ ምን እንደደረሰብን እንኳንስ እኛ ሌላው ዓለምም ያውቃል፡፡ ወያኔ በየጊዜው በደም ካልዋኘ ያስተበተበው ድግምት አይሠራለትም – ትልቁ የሰይጣን ምስ ወይም ግብር ደግሞ ደም ነው፡፡ ለዚህም ነው በበቀል የሰከሩት ወያኔዎች በተለይ ዐማራውንም ሆነ ሌላውን – ዓላማቸውን የማይደግፍና የሚቃወማቸውን ትግሬም ሳይቀር – አዛዣቸው ዲያብሎስ በሉ ባላቸው ቁጥር ባልተወለደ አንጀታቸው ጭንቅል ጭንቅሉን እያሉ ለአባታቸው የሚገብሩት፡፡ እነሱ ካልጠፉ ሞታችንና አሟሟታችን እየከፋ እንጂ እየቀነሰ አይሄድም፡፡ በሰይጣን የቆረበ ሰው የተጎጂዎች አበቅቴ እስኪብት ድረስ ዘመኑ ከሚፈቅድለት የወንጀል ድርጊት ውጪ ሌላ ደግ ነገር ይሠራል ተብሎ አይጠበቅም – የባሕርዩ መገለጫ ክፋት ብቻ ነውና፡፡

ምርጫው የኛ ነው እንግዲህ፡፡ በሕዝብ መተባበር ወያኔዎች ሰሞኑን ደንግጠዋል፡፡ የድንጋጤያቸው ደረጃም ሱሪያቸው ከፊትም ከኋላም እስኪረጥብ ድረስ መሆኑን ምሥጢሩን የሚያዉቁ እየተናገሩ ነው፡፡ ይህን በጥርጣሬ ደረጃ ያለ የወያኔ መረጣጠብ ማፋጠንና የዚህን ሰው-በላ የአፓርታይድ ሥርዓት ዕድሜ በደቂቃዎች እንዲገመት ማድረግ ይቻላል፡፡ እንደዚያ የሚሆነው ግን የተጨቋኞች ዓላማና ፍላጎት አንድ ሆኖ ሁሉም በያለበት ወያኔን ሲያርበደብድ እንጂ አንዱ ከነሱ ጋር ማኪያቶ እየጠጣና ውስኪ እየጨለጠ፣ ሌላው ደግሞ በአልሞ ተኳሾች ልዩ ጥይት ጭንቅቱ እየፈረሰ አይደለም፡፡ አሁንም እርግጥ ነው – ኢትዮጵያ ኢያሪኮ እንዳልሆነች ልብ ይሏል፡፡ የኢትዮጵያ ነፃነት ካለደም እንደማትገኝ የጎንደርና የጎጃም ዐማሮች እያስመሰከሩ ነው፤ ከወያኔ ተፈጥሮ የምንረዳውም የኢትዮጵያ ሕዝብ ሙሉ በሙሉ ያልቃታል እንጂ ወያኔዎች ፈረንጆቹ ዴሞክራሲ በሚሉት ቀልድ ወይም በሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ቤተ መንግሥት እንደማይለቁ ግልጽ ነው፡፡ ስለሆነም የነሱን ፈለግ በመከተል ሁሉም በተቻለው መፋለም ይገባዋል እንጂ በጩኸት ብቻ ወያኔ አራት ኪሎን ይለቃል ማለት ዘበት ነው፡፡ የዓለም ገዢ ኃይልም ከነርሱ ጋር ስለሆነ ሰሞነኛው ጩኸታችን ቀርቶ የገፍ ዕልቂታችን እንኳን ተገቢውን ዓለም አቀፍ ትኩረት አላገኘም – ማን እንደሰው ቆጥሮን! ይሄኔ የሮበርት ሙጋቤ የክብር ዘብ የአንድ ነጭ ዚምባብዌያዊ የሣሎን ውሻን በባረቀ ጥይት አቁስሎ ቢሆን ኖሮ የነቢቢሲና ሲኤንኤን እንዲሁም የነስካይኒውስና አልጀዚራ ቲቪዎች የአንድ ሣምንት የመክፈቻ ዜና በሆነ ነበር፤ ዘርንና ምጣኔ ሀብትን መሠረት ባደረገ መልክ ዓለም ይህን ያህል አሽቃባጭ ናትና ወደ አምላካችን ብቻ እንጩህ ይልቁንስ፡፡ ከሰው ምንም አንጠብቅ፡፡ ከራሳችን ውስጥ ብዙ ሥጋዊና መንፈሣዊ ኃይል አለ፡፡ ያን እናውጣውና እንጠቀምበት፡፡ ሕዝባችንንም እናንቃው፡፡ የምንችል እናስተምረው፡፡ ከተኛበትም እንቀስቅሰውና የጥንት የጧት አያት ቅድመ አያቶቹ የሠሩትን የመሰለ ታሪክ እንዲሠራ ለዳግም ልደት እናብቃው፡፡…

ልብ ያለው ልብ ይበል፡፡

ሕዝቡ ማናቸውንም ዓይነት ፖለቲከኛ በልጦ ሄዷል – ወያኔንም ተቃዋሚንም፡፡ ወያኔ ተጎልቶ ያለው ከ41 ዓመታት በፊት በነበረበት ደደቢት ላይ ነው – ሰውነታቸው በዐማራና በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ጥላቻ እንደተሞላና ገድሎ በማይረካ የበቀል ስሜት እንደተምቦገቦገ፡፡ ተቃዋሚዎች ያሉት የዛሬ 160 ዓመታት ገደማ ኢትዮጵያ የነበረችበት የዘመነ መሣፍንት ወቅት ላይ ነው – በማይጨበጥ ህልማዊ ሥልጣን እርስ በርስ ሲራኮቱ፡፡ ከሞላ ጎደል ሁሉም አእምሮውን የነሣው ነገር አለ፤ ሆድ ይሁን የዝናና የታዋቂነት ልክፍት በውል ለይቼ አላውቅም፡፡ ግን ግን አሁን እኔ እምለው ሁሉም ምናልባትም አብዛኛው ራሱን መፈተሸና ከሕዝብ የነፃነት ፍላጎትና የአርነት ትግል ጎን መሰለፍ የሚችልበትን ብልሃት ባፋጣኝ መቀየስ ይገባዋል ነው – በሕዝብ መበለጡን አውቆ ራሱን “ሳያስፎግር” በቶሎ ይስተካከል – በተቃዋሚነት እያምቧተሩና በሕዝብ ስም እየቀለዱ(እየነገዱም) መኖር ከእንግዲህ የሚታሰብ አይመስለኝም፡፡ አንዳንዱ ተቃዋሚ ይህን ዓይነት ሕዝብ የሚቀድምበትን የአጣብቂኝ ወቅት የጠበቀ አይመስልም – ለዚህም ነው ተደናግጦና ፈዝዞ ጥግ ጥጉን ይዞ እንደማንኛውም ተራ ዜጋ የነገሮችን አነሳስና ጡዘት እየታዘበ የሚገኘው፡፡ በየተወሰነ ወቅት ይሰጥ የነበረው መግለጫና ፉከራ(ፉገራም ቢባል ያስኬዳል) እንግዲህ ለላንቲካው ነበር ማለት ነው፡፡ አዎ፣ ትዝብትንና ምን ይሉኝን ዕንወቅ፡፡ እንደካሮት ወደታች ሣይሆን እንደሸምበቆ ወደላይ እንደግ፡፡ የአእምሮ መካንነትን እንዋጋና ጤናማ ሰው እንሁን፡፡ ያኔ ሀገራችን ትነሣለች፡፡

… ብዙ ማሰብ፣ ብዙ መሥራት፣ መጥፎ ነገሮችን መርሳት፣ ደጋግ ነገሮች ማስታወስ፣ ፍቅርንና አንድነትን መዘከር፣ ቂምንና በቀልን እርግፍ አድርጎ መተው፣ ወንድማማችነትን መስበክ፣ ጎሠኝነትን መጠየፍ፣ ሰውኛነትን ማጉላት፣ ከሕዝብ መማር፣ በሌሎች ወንጀል ንጹሕን ሰው ከመጠየቅና በሌሎች ደግ ሥራና ምሥጉን ትውፊት ምንም ያልሠሩ ሰነፎችን ማወደስን መተው፣ … በቃ … ባጭሩ ጤናማ ኅሊና ያለው ሰው መሆን …. የሁሉንም ችግር እንደራስ ችግር መቁጠር፣ የሁሉንም የነፃነት ትግል እንደራስ ትግል አምኖ በጋራ መታገል፣ ያንደኛው መክሸፍ የሌላኛውም መክሸፍ መሆኑን ከልብ መገንዘብና የጋራ ኃላፊነትን መውሰድ … ከሌሎች ብዙ አለመጠበቅ፣ የራስንም ድርሻ መወጣት … በገንዘብም በጉልበትም በዕውቀትም በጊዜም … አቅም በቻለ ሁሉ ለዚህች የጋራ ሀገራችን መስዋዕትነትን መክፈል፣ ካለመስዋዕትነት ነፃነት እንደማይገኝ መረዳት…ነፃነት እንደቡና ቁርስ ከሙዳይ ተቆንጥራ የምትሰጥ የዳቦ ፍርፋሪ ወይም ጭብጥ ቆሎ ሣትሆን የደምና የአጥንት ግብር የምትጠይቅ መሆኗን አምኖ ለሚፈለገው ግዳጅ ሁሉ ራስን ማዘጋጀት …ገና ለገና ሥልጣን አገኝ ይሆናል በሚል ከመጠን በላይና ለትዝብት በሚዳርግ ሁኔታ በሥልጣን ሱስ/አራራ አለመስገብገብ … ከሁሉም በላይ በሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት ማመን … ፡፡ ወቅቱ የክተት ነው፡፡ ዐጤ ምንሊክ ወደ ዐድዋ ሲዘምቱ በዘርና በጎሣ የተከፋፈለ የውጊያ ጥሪ አላደረጉም – ይህን ዓይነት ሸንካላ ወያኔያዊ አካሄድ አያውቁትምም ነበር፡፡ ባጠፋሁ ይቅርታ … በስሜት ስትናገሪ የምታስቀይሚው ሰው ይኖራል መቼም፡፡ … ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር፡፡ ለአሁኑ በቃኝ፡፡

ወይ አብረን እንሳቅ ካልሆነም አብረን እናልቅስ! (ከይገርማል)

$
0
0

unity

በየአካባቢው እየተደረጉ ያሉት ጸረ-ወያኔ እንቅስቃሴወች ክልላዊ ባህሪ መያዝ ያሳሰባቸው ግለሰቦች የሰሞኑ የአማራ እንቅስቃሴ የኢትዮጵያውያን እንጅ የአማሮች መባል የለበትም ብለው ሲከራከሩ እየተደመጡ ነው:: ከኢትዮጵያዊነት ደረጃው ዝቅ ብሎ የማያውቀው አማራ ዛሬ ላይ በአካባቢው የታጠረ የሚመስል ትግል እያደረገ መሆኑ ግልጽ ነው:: “ወልቃይት የአማራ ነው! በአማራ ላይ ያነጣጠረ የዘር ምንጠራ ይቁም! የወያኔ የበላይነት ይብቃ!—” እያለ ድምጹን ከፍ አድርጎ መፈክር እያሰማ ነው:: ይህን እንዲል ያስገደደው በራሱ ላይ ያነጣጠረ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ስለተከፈተበት እንደሆነ በበኩሌ እረዳለሁ:: በህልውናው ላይ የተጀመረውን የጥፋት ዘመቻ ለመመከት ደፋ ቀና እያለ ያለው አማራ የሌሎች ወገኖቹ ህይወት አሳስቦት በኦሮሚያና በሌሎች ክልሎች የሚፈጸመውን የወያኔ የዕብሪት ጭፍጨፋ እያወገዘ ኢትዮጵያዊነቱን ማስመስከሩም አልቀረም::

 

የአማራውን ትግል ፍጹም ኢትዮጵያዊ መልክ ለመስጠት የሚደረገው ሙከራ ከጥቅሙ ጉዳቱ ሊያመዝን እንደሚችል መገንዘብ ተገቢ ነው:: የአማራው ትግል በሀገራችን እንደቅንጦት የሚታዩት የዴሞክራሲያዊ መብቶች ይከበሩ በማለት የሚደረግ ትግል ሳይሆን ከወያኔ የዘር ማጥፋት ዕቅድ ለማምለጥ የሚደረግ የሞት ሽረት ትግል ነው:: አማሮች በሰላም ከሚኖሩበት አካባቢ እየተለቀሙ ሲታረዱ አንድም ክልል ሀዘናቸውን የተጋራ: የተቃውሞ ድምጹን ያሰማ አልነበረም:: ወደፊት ጊዜ ፍንትው አድርጎ የሚያወጣው ሀቅ የሚጠበቅ ሆኖ አሁን ባለን ግርድፍ መረጃ መሰረት በግላጭ ከተገደሉት በተጨማሪ ሦስት ሚሊዮን ያህል አማራ ያርግ ወይ ይስረግ ሳይታወቅ ዳብዛው ጠፍቶ ቀርቷል:: ይህንን አማራ-ተኮር እልቂት ሲያቀነባብሩ ከነበሩት ወያኔወች ጎን በመሰለፍ የአማራ ወኪል ነኝ የሚለውን ብአዴንን ጨምሮ ሁሉም ክልሎች በአማሮች ላይ የተለያየ የግፍ አይነት ፈጽመዋል:: ዛሬ ላይ እኒህ የጥፋት ሰለባ የሆኑት መከረኞች እየደረሰባቸው ያለው የዘር ማጽዳት ዘመቻ እንዲገታ ተቃውሟቸውን በማሰማት ላይ ናቸው:: ከእኛ የሚጠበቀው የእነዚህ ወገኖቻችንን ስሜት ተጋርተን ጩኸታቸውን አብረን እየጮህን በደላቸው እንዲሰማ የድርሻችንን ማበርከት እንጅ በጥቃት ስሜት እየተንተከተከ ያለውን የሕዝብ እንቅስቃሴ የሚያጠፋ ቀዝቃዛ ውሀ መቸለስ አይደለም::

 

ኢትዮጵያን ከወያኔ የጭቆና አገዛዝ ነጻ ለማድረግ የሚደረገው ግብግብ በአማሮች ላይ ብቻ የተጣለ ሸክም እንዲሆን የማይፈቅዱ አማሮች መኖራቸውን አምነን መቀበል ከስህተት ያድነናል:: ስለዚህ መተያየት እንዳይፈጠርና ወደኋላ ማለትን እንዳያስከትል በሚተላለፉት መልእክቶች ላይ ጥንቃቄ ሊደረግ ተገቢ ነው:: የሚሻለው: እንቅስቃሴ በማይታይባቸው አካባቢወች የጸረ-ወያኔው የአመጽ እንቅስቃሴ እንዲጀመር አመቻችቶ ሀገራዊ ገጽታ እንዲላበስ የተቀናጀ ትግል ለማድረግ መጣር ነው::

 

እንደሚገመተው ከሆነ ዛሬ ላይ የሕዝባቸው ሰቆቃ ያንገፈገፋቸው  በብአዴን ውስጥ ያሉ የአማራ ልጆች ከወገናቸው ጋር መስዋእትነትን ለመቀበል ወስነው በጽናት እንደቆሙ ነው:: እኒያ የወያኔን የጥፋት አላማ በአማራ ላይ ሲፈጽሙና ሲያስፈጽሙ የነበሩት የቀድሞ የብአዴን አመራሮች ከታች እየተሳቡ በወጡ እውነተኛ የአማራ ልጆች የተተኩ መሆኑን የሚያሳይ የተግባር እንቅስቃሴ እንዳለ ለመገንዘብ አያዳግትም::

 

በአማራ ላይ የሚፈጸመው ሰቆቃ ያብቃ ብላችሁ የሕዝባችሁን የትግል እንቅስቃሴ ደግፋችሁ እየታገላችሁ ያላችሁ እናንተ የአማራ ልጆች ብርቱ ጥንቃቄ ልታደርጉ ይገባል:: ወያኔወች በክፋትና በተንኮል የተራቀቁ ናቸው:: ሌት ከቀን የሚያስቡት ጠላት ነው ብለው የፈረጁትን አማራ ከማጥፋት ጎን ለጎን የሕዝቡን አንድነት ሸርሽረው የተቃውሞውን እንቅስቃሴ ማርገብና ለማይጠረቃ የንዋይ ፍላጎታቸው ለብዝበዛ የተመቸ ሜዳ መፍጠር ነው:: የሚደክሙት ለዳር ድንበር መከበርና ለሀገር ብልጽግና: ለህዝብ ሰላም: ፍቅርና አንድነት አይደለም:: እነርሱን የሚያሳስባቸው  ከፈረሹበት የእርዝቅ መንበር ላይ የሚቀመጥ የልጅ ልጅ ተክተው ትግራይ-መር ኢትዮጵያን ለማስቀጠል ምን እናድርግ የሚለው ጥያቄ ብቻ ነው::

 

ይህን እነርሱ በጎ የሚሉትን አላማቸውን ለማደናቀፍ የሚነሳን ማንኛውም አካል ከማጥፋት ወደኋላ አይሉም:: ቂመኞች በመሆናቸው ይቅርታን አያውቁም:: ሽንፈትን አምኖ እንደ እንግዳ ዶሮ አንገትን ቀብሮ ከነርሱ ስር ማደር ከመጠቃት አያድንም:: በህይወት ላሉ አማራወች ይቅርና ለሞቱ አባቶቻችን ያልተኙ መርዘኞች መሆናቸውን ለአፍታም ቢሆን መዘንጋት አያስፈልግም:: የሚሻለው “ከውርደት ሕይወት-የኩራት ሞት!” ይመረጣል ብሎ ከህዝብ ጎን ተሰልፎ እስከመጨረሻው ድረስ እየተፋለሙ ጥሎ መውደቅ ነው:: ነካክቶ ማፈግፈግ የረባ ነገር ሳይሰሩ ቀስ በቀስ ከምድረገጽ መጥፋትን ያስከትላል:: የሚያሸንፉን አንድ ሆነው በአንድ ልብ ስለተሰለፉ እንጅ በምናቸውም ከእኛ ስለሚበልጡ አይደለም:: ልብ አድርጉ! ይህንን የተነቃቃ የህዝብ ትግል እንዲበርድ አድርጎ ማፈግፈጉ ጉዳቱ ቀላል አይሆንም:: በቅንጅት አመራሮች የተሳሳተ አካሄድ የሕዝባችን የትግል መንፈስ የተቀዛቀዘበት ሁኔታ ተከስቶ እንደነበር ማንም አይስተውም:: አሁን ገንፍሎ እየወጣ ያለውን የሕዝብ አመጽ በአግባቡ ካልተጠቀምንበት ጭራሹኑ የተሰበረ መንፈስ ፈጥሮ ዳግም ይህን እድል የማናገኝበት ሁኔታ ሊያስከትል ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነው::

 

ትግሉን ለማቀላጠፍ ዝግጁ ሆኖ መጠበቅ ኋላ ላይ ከመደናበር ያድናል:: ለዚያም ነው እስከቀበሌ ድረስ ወርዶ ሕዝብን የማንቃት: የማደራጀትና የማስታጠቅ ስራ ለይደር የሚተው የማይሆነው::  ስለሀገር አንድነትና ስለሕዝብ ነጻነት የሚጨነቁ ግለሰቦችና ፓርቲወች ድጋፋቸውን እንዲያበረክቱ ለማስቻል በራችሁን ብትከፍቱ የተሻለ ነገር አቅዶ ለመተግበር ይጠቅማል:: እናንተ ለማስተባበር ከቆረጣችሁ ጥሎ ለመውደቅ ፈክሮ የሚነሳው አማራ ድፍን ኢትዮጵያን እንደጉድ ማጥለቅለቁ የማይቀር ነው:: ይህን ለማድረግ ስትነሱ በቅድሚያ ከመሀላችሁ ተሰግስገው ለወያኔ አይንና ጆሮ ሆነው እየሰሩ ያሉትን ባንዳወች በማጽዳት መሆን አለበት::

 

አማራ ሲፈጥረው በሞራል የተገነባ ሕዝብ ነው:: ከሌላ አካባቢ መጥተው ተመሳስለው ለሚኖሩ ሰዎች ያለው ፍቅርና ክብር የተለየ ነው:: በሆነ ምክንያት ከሌላ አካባቢ ከመጡት ሰዎች ጋር የተጋጨ ያገር ሰው ቢኖር ይወቀሳል:: “የሰው አገር ሰው እንዴት ለማስቀየም ደፈርህ? ከወዳጅ ከዘመድ ርቆ እኛን አምኖ እኛኑ ዘመድ አድርጎ ተጠግቶ የሚኖርን ሰው ማስቀየም ደግ ነው?” ተብሎ ውግዘት ይደርስበታል:: በዚህም የተነሳ በአማራ ክልል የሚኖሩ የሌሎች ክልሎች ኗሪወችም ሆኑ የውጭ ሀገር ሰዎች ከአካባቢው ተወላጅ በተሻለ ሁኔታ ያለሀሳብ ተከብረው በሰላም ይኖራሉ:: ይሁንና “ያልበደለ ሰው ለምን ይቀጣል!” የሚሉ ተቆጭ ሽማግሌወች በሌሉባቸው አካባቢ የሚኖሩ ዘረኞች ከሌላ አካባቢ የመጡ ናቸው በሚሏቸው ምንም ጥፋት በሌላቸው ሰላማዊ አማራወች ላይ አማራ በመሆናቸው ብቻ ሀብታቸውን ይዘርፏቸዋል: ያፈናቅሏቸዋል: አስረው ያሰቃይዋቸዋል: ይገድሏቸዋል:: ይህን ከሞራልና ከሐይማኖታዊ ባህሪይ ያፈነገጠ ወንጀል ሲሰሩ ጠያቂ ሕግ: ወቃሽ ህሊናም ሆነ የሚፈሩት አምላክ የላቸውም:: እንዲህ ያለውን የሕዝብ ሰቆቃ ማስቆም የሚቻለው አንገትን ደፍቶ በመኖር ሳይሆን ግንባር ለግንባር ገጥሞ በመፋለም ነው::

 

አማራው ከአማራ ክልል ውጭ ሲኖር በየትኛውም ደረጃ በፖለቲካ አመራርነት መሰየም ቀርቶ የግልም ሆነ የሲቭል ስራውን በሰላም ሰርቶ መኖር አልፈቀድለት ብሎ ፍዳ ሲያይ ኖሯል:: በሌላ በኩል በአማራ ክልል የሚኖሩ የሌላ ክልል ተወላጆች በክልሉ የፖለቲካ ሀላፊነት ሳይቀር ከታች እስከላይ ድረስ ተሰግስገው ያለሀሳብ እየፈረዱ እያስፈረዱ ተቀምጠዋል:: በግል ስራ የሚተዳደሩትም ቢሆኑ ከኗሪው በላይ ሆነው ስለያንዳንዱ ግለሰብ መረጃ በማቀበል ሲያሳፍኑና ሲያስገድሉ እስካሁን ድረስ ዘልቀዋል:: በዚህ የተዛባ ተግባራቸው ለማፈር ያልታደሉት እኒህ ሰዎች ይባስ ብለው በአንድ ድምጽ “አህያ: ደደብ: የማይመጥኑ—” ናቸው ብለው የአማሮችን ተግባርና ባህሪ የማይገልጽ የስድብ ስም ሰጥተው አማሮችን በማንቋሸሽ እየጠሯቸው ነው:: ከአሁን በኋላ አማራው ግፍ ተሸክሞ አህያ የሚባልበት የትግሬ ወያኔወች የሀገር ሀብት እየዘረፉ ብልጥ የሚባሉበት ጊዜ ያበቃል:: ቢችሉ ከብልጥነት ወጥተው ብልህ ለመሆን ቢሞክሩ በዋናነት ለራሳቸው ይጠቅማቸዋል::

 

አማራ ማንንም በክፉ የሚያይ ሕዝብ አይደለም:: ሌላውም እንደራሱ የሚያስብ መስሎት ለረጅም ጊዜ ለመከራ ተጋልጦ ቆይቷል:: “ሞኝ የዕለቱን ብልህ ያመቱን” እንዲሉ አማሮች የዘላለም ህይወት ለመታደል ለህሊና የማይቆረቁር በፈጣሪ ዘንድ የተወደደ ተግባር በመፈጸም ታጋሽነታቸውን ሲያሳዩ የትግሬ ወያኔወች ግን የአፍታ ህይወት አጓጉቷቸው: ትዕቢት ልቦናቸውን ሰውሮት ከህዝብ ቀምተው ህዝብን እያዋረዱ ጥለውት የሚሄዱት ሀብት ያከማቻሉ:: ከእንግዲህ በኋላ ግን ሁኔታወች መስተካከል ይኖርባቸዋል:: ከቀን ቀን ይማራል የማይባልን አጥፊ ሰው አዝሎ እሹሩሩ ማለት ጉዳት እንጅ ጥቅም የለውም:: አማሮች አሁንም ቢሆን ባለጌወችን ፈርተው ሳይሆን አምላክን ስለሚያስቡ መሰረታዊ ባህሪያቸውን ቀይረው ማንንም ለማጥፋት ወይም ለመበቀል የሚነሱ አይሆንም:: ነገር ግን ከእንግዲህ በኋላ የትግሬ ወያኔወች ከመሀላቸው ዘና ብለው ተቀምጠው መረጃ እያቀበሉ ትግሉን እንዲያከሽፉ: ጭቆናን እንዲያስቀጥሉ  ሊፈቀድላቸው አይገባም:: ” የሰው ሞኝ የለውም ብልሀቱ ይለያያል እንጅ!” አይደል የሚባለው? እኛም እንዳቅማችን ብልሀት አናጣም:: ሰላማዊ ኗሪ መስለውም ሆነ በግላጭ የጦር መሳሪያ ታጥቀው የወያኔ የመረጃና የአፋኝ ኃይል ሆነው የሚሰሩ በክልሉ የሚኖሩ ግለሰቦችና ቡድኖች ባስቸኳይ ክልሉን ለቀው እንዲወጡ ይደረግ:: ይህን የሕዝቡን ትግል ለማኮላሸት የተሰገሰገን የጥፋት ኃይል በጉያ ታቅፎ ይዞ ታግለን እናሸንፋለን ማለት ከየዋህነት የዘለለ ሞኝነት ነው:: ይህ የዘረኝነት ጉዳይ አይደለም: መተኪያ የሌለው የትግል ስትራቴጅ እንጅ::

 

አማሮች አሁንም ኢትዮጵያን ይወዳሉ:: አሁንም የህዝብን በሰላም አብሮ መኖር ይፈልጋሉ:: አይደለም በአንድ ሀገርና በአንድ ሰንደቅ አላማ ስር ክፉና ደጉን ተጋርተው አብረውት ለኖሩ ሕዝቦች ይቅርና ከሌላ ሀገር ለመጣ ሰላማዊ ሰውም ቢሆን ፍቅርና ክብር የሚሰጥ ትሁትና ፈሪሀ-እግዚአብሔር ያደረበት ሕዝብ ነው: አማራ:: ሰላም የሚነሱት ወያኔወች በያዙት መንገድ እስከቀጠሉ ድረስ ግን “ለሰላም ስትሉ ሁሉንም ነገር ተውት” ማለት “በወያኔ የሚደርስባችሁን ግፍ ችላችሁ አንገታችሁን ደፍታችሁ ተቀመጡ” ማለት ነው:: ከእንግዲህ በኋላ በሀገር ልጅነት ስም ነጻነታቸውን ተገፈው በባርነት ለመኖር አይፈቅዱም:: በዚህ ምክንያት የሚደፈርስ ሰላም ካለ መደፍረሱ የግድ ይሆናል:: ሰላም በአንድ ወገን ፍላጎት ብቻ የሚመጣ አይደለም::

 

ካድሬወቹን በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን እያቀረበ “ጥያቄ ካለ በሰላማዊ መንገድ መጠየቅ ሲቻል ለአመጽ መነሳሳት አግባብ አይደለም” የሚል የማጭበርበሪያ አስተያየት የሚያሰጠው ወያኔ ከስህተቱ ቢማር ይበጀዋል:: ለሕዝብ ጥያቄ ጆሮ ሰጥቶ የሕዝቡን ፍላጎት ተከትሎ የሚሰራ ቢሆን ኖሮ አሁን እየታየ ያለው አመጽና ውድመት ባልተከሰተም ነበር:: በየአካባቢው የሚደረጉት እንቅስቃሴወች በሙሉ የሕዝብን ጥያቄ አዳምጦ ትክክለኛ ምላሽ ለመስጠት ፍላጎት ባለመኖሩ የተፈጠሩ መሆኑን ማንም አይስተውም:: ሰላማዊ በሆነ መንገድ የሕዝብን ጥያቄ ያቀረቡ የሕዝብ ወኪሎች በእብሪት ስለታፈኑ ነው ተቃውሞው የተቀሰቀሰው::

 

የትግራይ ሕዝብ “ጥሩውን ጥሩ: መጥፎውን መጥፎ” ማለት ማወቅ አለበት:: ከዚያም አልፎ ጥሩውን በመደገፍ መጥፎውን ደግሞ በማውገዝ ከሌሎች ሕዝቦች ጎን ተሰልፎ አጋርነቱን መግለጽና መስዋእትነት መክፈል ይኖርበታል:: ያ ሲሆን ነው መተሳሰብ አለ ማለት የሚቻለው::

 

ኢትዮጵያውያን ክፉውንና ደጉን ተጋርተን አብረን ኖረናል:: ዛሬም ያንኑ ልማዳችንን ሳንቀይር እንደወቅታዊ ሁኔታው ወይ አብረን እንስቃለን ወይም አብረን እናለቅሳለን:: አንዳችን እየሳቅን ሌላችን የምናለቅስበት አግባብ ግን ሊኖር አይችልም::

ትንሳኤ ለኢትዮጵያ!

Hiber Radio: ግርማ ብሩ ለሕወሓት ደጋፊዎች በውጭ ያሉ ተቃዋሚዎችን ክሰሱ ያሉበት ምስጢራዊ ድምጽ ወጣ |ሳዲቅ አህመድ በምስራቅ ሐረርጌ 2 መስጊዶች ላይ ስለደረሰው የቦምብ ፍንዳታ ተናገረ

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


የህብር ሬዲዮ ነሐሴ 22 ቀን 2008 ፕሮግራም

ጋዜጠኛ ሳዲቅ አሕመድ በምዕራብ ሐረርጌ በሁለት መስጊዶች ላይ ፍንዳታ ተፈጽሞ ንጹሃን ሰለባ ስለሆኑበት ሂደት ከህብር ሬዲዮ ተጠይቆ ከሰጠው ምላሽ የተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)

ዓለም አቀፍ መገናኛ ብሁሃን ስለ ጀግናው አትሌት ፈይሳ ለሊሳ ያቀረቡት ዘገባ ሲቃኝ (ልዩ ጥንቅር)

በቬጋስ በተደረገ ተቃውሞ ላይ የሀይማኖት አባቶችን ቸምሮ የተለያዩ ቡድኖች ያስተላለፉት መልዕክት

ዜናዎቻችን

አምባሳደር ግርማ ብሩ ከአገዛዙ ደጋፊዎች ጋር በምስጢር ባደረጉት ውይይት በውጭ ያሉ ተቃዋሚዎችን ክሰሱ ሲሉ ተደመጡ

የምስጢር ስብሰባው ድምጽ ማስረጃ ደርሶናል

የአማራ ሕዝብ ተጋድሎና ተቃውሞ ተጠናክሮ ቀጥሏል

አትሌት ኢብሳ እጅጉ የታላቁን አትሌት ፈይሳ ለሊሳን የሪዮ ተቃውሞ በካናዳ ማራቶን አሸንፎ ደገመው

የሕዳሴውን ግድብ ለመጎብኘት የሔዱ ባለስልጣናት ተቃውሞ ላይ ባሉ የጎጃም አማሮች ተገደው ጉብኝታቸውን ሰርዘው መመለሳቸውን ገለጹ

የአማራ እና የኦሮሞ ህዝቦች ጸረ ሕወሓት/ኢህአዲግ ጥምረት ለአገዛዙ ታላቅ ፈተና መሆኑን ታዋቂው አፍሪካን ኮንፊደንሻል መፅሔት አጋለጠ

* 6 ሜሊዮን የአገዛዙ ካድሬዎች ድርጅቱን ገዝግዘው እየጣሉት ነው ተባለ

የብአዴን እና የኦህዴድ ባለስልጣናት ህዝባቸውን ለችግር አጋልጠዋል ተባሉ

ኢትዮጵያ፣ግብፅ እና ሱዳን በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ሊፈራረሙ መሆኑን የካርቱም ባለስልጣን ተናገሩ

በሳውዲ አረቢያ ህንጻ ተደርምሶ ኢትዮጵያዊ እና ግብጻዊያኖች ህይወታቸው አለፈ

ግብጽ ዜጎቾን ለመታደግ ልኡካን ወደ ስፍራው ልካለች

*የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ግን ዝምታን የመረጡ ይመስላሉ

*በኩዊት አንዲት ኢትዮጵያዊት ከባህር ውስጥ ሰጥማ ህይወቷ አለፈ

የአሜሪካው እጩ ፕሬዝዳንታዊ ተወዳዳሪ ዶናልድ ትራምፕ በምርቻው ካሸነፉ የመኖሪያ ፈቃዳቸው የተቃጠለባቸውና ቪዛቸው ያለቀባቸውን ጭምር ከአገር አባርራለሁ ሲሉ ዛቱ

የሞህ ፋራህን ወንድም እንግሊዝ ከአገሬ አባርራለሁ አለች

በምርጫ 97 እንዳደረገው ሕወሃት በአዲስ አበባ የትግራይ ተወላጆችን ብቻ ለይቶ ስብሰባ ጠራ

ሌሎችም

ጎጃም ተቃውሞው ቀጥሏል –ቻግኒ ሕዝቡ መንገድ ዘግቶ አጋዚን አላሳልፍ ብሏል |የጎጃምና ጎንደር ሕዝብ በየቦታው የጎበዝ አለቆችን እየመረጠ ነው

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) የጎጃም ቻግኒ ሕዝብ የአማራው ሕዝብ እያደረገው ያለውን ከፍተኛ ሕዝባዊ ተጋድሎ ተቀላቀለ:: ከቻግኒ በተጨማሪ ሕዝባዊ እምቢተኝነቱ በመሸንቲ፣ በመራዊ፣ ዳንግላና ሌሎችም ከተሞች እየተቀጣጠለ መሆኑ ለዘ-ሐበሻ የሚደርሱ መረጃዎች አመልክተዋል::

agew gojam

ይህ ዜና እየተጠናከረ ባለበት ወቅት በርካታ ከተማዋ በፌደራል ፖሊሶች ብትወረርም; የአጋዚና የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ ቻግኒ ከተማ እየገቡ ቢሆንም ሕዝቡ በድንጋይ እና በ እንጨት መንገዶችን በመዘጋጋት እንደተፋጠጣቸው ለመረዳት ተችሏል:: የቻግኒ ሕዝብ በትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ መንግስት አንመራም; የታሰሩት ይፈቱ; ወልቃይት የአማራ ነውና ሌሎችም ጥያቄዎችን እያሰማ ነው::

በሌላ በኩልም በተመሳሳይ በመሸንቲ; በመራዊና ዳንግላ ከተሞችም እንዲሁ ሕዝባዊ እምቢተኝነቱ ከከፍተኛ ተቃውሞ ጋር ቀጥሏል:: በየከተማው ያለው ሕዝብ በሕወሓት መንግስት አንመራም እያለ ነው::

agew gojam2

በጎጃም ያሉ የክክሉ ፖሊስ አባላት ወደ ሕዝባችን አንተኩስም በሚል አኩሪ ተግባር እንደፈጸሙ የሚገልጹት የዘ-ሐበሻ ምንጮች የትግራይ ነጻ አውጪው መንግስት የአጋዚና የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ከሌሎች ክልሎች በማምጣት በጎጃምና በጎንደር ለማስፈር እየሞከረ ነው:: ሆኖም ሕዝቡ መንገዶችን እየዘጋጋ ላለማሳለፍ እየሞከረ ነው ተብሏል:: በጎጃም በርካታ የክክሉ ፖሊሶች ራሳቸውን እየሰወሩ ሲሆን ባለፉት 3 ቀናት ብቻ ከ30 በላይ የፌደራል ፖሊስ አባላት ትጥቃቸውን ለነዋሪዎች እየሰጡ መጥፋታቸውም በኢሳት ቲቭ ተዘግቧል::

ይህ በ እንዲህ እንዳለ ሕዝቡ በየቦታው የሚመሩትን የጎበዝ አለቆች እየመረጠ ነው:: አዴት ከተማ የጎበዝ አለቆችን መርጣ በነርሱ በኩል እየተመራች ሲሆን በቋሪትም በተመሳሳይ የጎበዝ አለቆች መመረጣቸው ይታወሳል:: በደቡ ጎንደር አርብ ገበያም ሕዝብ ነገ ተሰብስቦ የጎበዝ አለቆችን እንደሚመርጥ የሚደርሱን መረጃዎች አመልክተዋል::

agew gojam3

 

ባህርዳር ከተማ በተቃውሞ እየተናጠች ነው –ተኩስ ይሰማል –ሕዝብ የአባይ ድልድልይን ተቆጣጥሮ ወታደሮችን አላሳልፍ ብሏል (+Video)

$
0
0

bahardar

(ዘ-ሐበሻ) ዛሬ የባህርዳር ሕዝብ ሆ ብሎ በመውጣት በከተማዋ ከፍተኛ ተቃውሞውን እያሰማ ነው:: የትግራይ ነጻ አውጪ ወታደሮች ወደ ሕዝብ መተኮስ የጀመሩ ሲሆን እስካሁን በርካታ ሰዎች መቁሰላቸው ተሰምቷል:: ዘ-ሐበሻ የሞቱ ሰዎች እንዳሉ ለማረጋገጥ ያደረገችው ሙከራ ባይሳካም ሕዝቡ ግን እየተተኮሰበትም ቢሆን ተቃውሞውን መንገዶች በመዝጋት እና ጎማዎችን በከተማው በማቃጠል እየተቃወመ ነው::

bahardar2

የባህርዳር በተለይም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወጣት እየተሳተፈበት ባለው ተቃውሞ የሥርዓቱ ደጋፊ የሆኑ የንግድ ድርጅቶች ንብረቶቻቸው እየወደመ መሆኑም ተሰምቷል:: በተለይም ባለፈው ሳምንት የባህርዳር ሕዝብ የቤት መቀመጥ አድማ ባደረገበት ወቅት ጥቂት የመንግስት ደጋፊ የሆኑ የንግድ ድርጅቶች ሌሎች ነጋዴዎችን ለማስመታት ከሕዝቡ በመነጠል ንግዳቸውን መክፈታቸውን ተከትሎ የብዙ የባህርዳር ነዋሪዎች የንግድ ፈቃድ መሰረዙን ተከትሎ በዛሬው ተቃውሞ በነዚህ የመንግስት ደጋፊ ድርጅቶች ላይ ውድመት እንዲደርስበት ምክንያት ሆኗል::


bahardar3

የሕወሓት መንግስት ወታደሮች ሕዝቡ ላይ ከመተኮሳቸውም በላይ ወጣቶችን ማፈስ መጀመራቸው ሲሰማ በሌላ በኩል በባህርዳር የአባይ ድልድይ በሕዝብ ተዘግቶ ወታደሮችን አላሳልፍም ማለቱ ታውቋል:: ነዋሪው ጎማዎችን በማቃጠልና በድንጋይና በ እንጨት ድልድዩን በመዝጋት የሕወሓት ወታደሮች እንዳይገቡም እንዳይወጡም እየተፋለማቸው ነው::

ሌሎች መረጃዎችን አጠናክረን ይዘን እንመለሳለን::

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live