Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

በብዙ የጎጃምና የጎንደር አካባቢዎች መንግሥት ፈርሷል –ባሕር ዳር፣ መራዊና ዳንግላ ከተሞች በጪስ ታፍነው ተኩስ ሲናጡ ውለዋል (ዜና ትንታኔ)

0
0

በብዙ የጎጃምና የጎንደር አካባቢዎች መንግሥት ፈርሷል፤ የጎበዝ አለቆች ክፍተቱን እየሞሉ ነው
• ባሕር ዳር፣ መራዊና ዳንግላ ከተሞች በጪስ ታፍነው ተኩስ ሲናጡ ውለዋል
• ‹‹በአዴት ከተወለዱ በጤና እያለ አንድስ እንኳ እቤት የዋለ የለም›› የአዴት ሪፖርታዥ
• ከወረታ ከተማ አቅራቢያ ጉማራ ላይ በገበሬውና በትግረው መከላከያ መካከል ከባድ ጦርነት ሲደርግ አድሯል
• ቋሪት፣ አገው ምድር፣ ጋይንት፣ በለሳ፣ አብዛኛው የደበርቅና የጃናሞራ አካባቢዎች ከመንግሥት ቁጥጥር ውጭ ናቸው
• በአንዳቤትና በፋርጣ የጎበዝ አለቆች አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል

ከሙሉቀን ተስፋው

ባሕር ዳር፤ በባሕር ዳር ከተማ በሕዝብ የተጠረውን የቤት ውስጥ አድማ ለማደናቀፍ በሞከሩ የወያኔ አባላትና ቅጥረኛ ባንዳዎች ንብረት ላይ ዐማራው እርምጃ እየወሰደ ነው፡፡ የዐማራው ሕዝብ ቆራጥነቱን በተግባር ያሳየበት ከዛሬ የበለጠ ቀን አልነበረም፡፡ ጠዋት አካባቢ አድማውን ችላ በማለት ሥራ የጀመረ አንድ የከተማ አውቶቡስ ሾፌር መኪናውን ሰባብረው ልጁን እንዲማር መጠነኛ አካላዊ ጉዳት ደርሶበት አሰናበቱት፡፡ ሥራ የጀመረው የንግድ ባንክም ሕንጻ መስኮቶች ተሰባብረዋል፡፡ በሕዝብ አስቀድመው የተለዩ የሕወሓት አባላት እና የዐማራ ቅጥረኛ ባንዳ ሰዎች ስም ዝርዝር አስቀድሞ የተሰራ ሲሆን ተራ በተራ ሲቃጠል ውሏል፡፡ ባሕር ዳር አሁን ከዝናቡ ጋር በጭስ ታፍናለች፡፡ ከቦታው አስተያየቱን እንዲሰጠን የጠየቅነው የከተማዋ ነዋሪ ‹‹የጥይት ሩምታው ይሰማሃል? የቤት ጣራ ላይ ሆኜ ነው የማወራህ አንድ ሁለት… ወደ ዘጠኝ ቤት ሲቃጠል ይታየኛል እኛ ሰፈር እንኳ፡፡ የአምቡላንስና የጥይት ድምጽ እየረበሸኝ ነው›› ሲል የነበረበትን ሁኔታ ገልጦልናል፡፡ ቀበሌ 08 የሚባለው ሰፈር በርካታ ቤቶች የተቃጠሉበት ነው ተብሏል፡፡

agew gojam3
በባሕር ዳር በዛሬው የዐማራ ተጋድሎ ቀበሌ 06 ሦስት ዐማሮች ተሰውተዋል፡፡ ቀበሌ 14 ኤፍራታ እሚባለው አካባቢ ደግሞ ለታጋይ ዐማሮች ውሃና ምግብ ለማቅረብ ሲሄዱ የነበሩ እናት ወድቀው መሰዋታቸውን ሰምተናል፡፡ በርካታ ተሸከርካሪዎች የተቃጠሉ ሲሆን ዐማራው በየሰፈሩ የጎበዝ አለቃዎችን እየመረጠ በመታገል ላይ መሆኑን ሰምተናል፡፡ ያልተዘጋ መንገድ የለም፡፡ የዐማራ ፖሊስ ሕዝብን በመጠበቅ ያደረገው ተጋድሎ የሚደነቅ መሆኑን ሰምተናል፡፡ በባሕር ዳር ዛሬ የተደረገው ተጋድሎ እጅግ የሚያኮራና ከተማዋን ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ሕዝቡ የተቆጣጠረበት ሁኔታ እንዳለ ሰምተናል፡፡ የባሕር ዳር ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች በግቢ የዐማራን ተጋድሎ ሲያንጸባርቁ ውለዋል፡፡

ከባሕር ዳር ከተማ 17 ኪሎ ሜትር አካባቢ ያለችው የመሸንቲ ከተማና የይባብ ኢየሱስ ቀበሌም የዐማራ ተጋድሎ ከዋለባቸው ቦታዎች ውስጥ ናቸው፡፡ መሸንቲ ያለው የሕወሓት አባል የድንጋይ ጠጠር ማምረቻ ፕላንትም ተቃጥሏል ተብለናል፡፡
bahardar
መራዊ፤ በመራዊ ከተማ የዐማራ ሕዝብ ለተጋድሎ የወጣው በጠዋት ነበር፡፡ የሜጫዋ መራዊ ከተማ እንደ ባሕር ዳር ሁሉ በጢስ ታፍና ውላለች፡፡ ለተጋድሎ የወጣው የዐማራ ሕዝብ ከጉያው ተሸጉጠው ሲያንገላቱት የነበሩትን የሕወሓት አባላትና ቅጥረኛ ባንዳዎች ሀብትና ንብረት ተለቅሞ ተቃጥሏል፡፡ የገብረ ሥላሴ ኃይለማርያም ክሊኒክና ፋርማሲ፣ የገ/ድህን ክሊኒክ፣ ፒታ ዳቦ ቤት፣ ኃይሌ ፎቅ፣ የኢትዮጵያ እህል ንግድ ድርጅት፣ ብአዴን ጽ/ቤትና በርካታ የሰላዮች መኖሪያ ቤትና ንብረት ወድሟል፡፡ የዐማራ ሕዝብ ከተማዋን ይህ ሪፖርት እስከተሠራበት ጊዜ ድረስ ተቆጣጥሯት ይገኝ እንደነበር ለማወቅ ችለናል፡፡

አዴት፤ የይልማና ዴንሳዋ አዴት ከተማ በዐማራ ተጋድሎ ስትናጥ ውላለች፡፡ ከአዴት ከተማ የሚገኘው ሪፖርተራችን የላከልን መረጃ እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡ የአዴት ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ ወያኔን ሲቃወም ዋለ፡፡ በአዴት ከተወለዱ በጤና እያለ አንድስ እንኳ እቤት የዋለ የለም፡፡ ከወጣት እስከ ሽማግሌ፣ ሴትና ወንድ፣ እስላምና ክርስቲያን ሁሉ በቁጣ ገንፍሎ ወጥቷል፡፡ ሰልፉን የሰሙ የይልማና ዴንሳ አርሶ አደሮችም ከወንዳጣ ድረስ እየመጡ በወኔ ተጋድሎውን ተቀላቅለው ውለዋል፡፡

‹‹ወያኔ ሕወሓት ሌባ ነው፤ ቅጥረኛው ብአዴን አይወክለንም፤ ድንበራችን ተከዜ ነው፤ ወልቃይት ዐማራ ነው፤ በዐማራ ላይ የሚደርሰው ጭቆና ይቁም፤ የሃይማኖት ጣልቃ ገብነት ይቁም፤ …›› እና ሌሎችም መፈክሮች ሲሰሙ ውለዋል፡፡ የዐማራው ሕዝብ ወደ ባሕር ዳር በኩል 2 ኪሎ ሜትር መንገድ በመጓዝ አቦላ ተራራ አካባቢ ያለውን መንገድ መዝጋት ቅድሚያ የሠጠው መርሃ ግብር ነበር፤ ይህም የወያኔን አልሞ ተኳሾች እንዳይመጡ መንገዱን ማበላሸት ሲሆን ይህን የሰሙት የባሕር ዳር አናብስት ወጣቶች ሰባታሚት አካባቢ መንገዱን ጠርቅመው በመዝጋት የአዴት ዐማሮችን ተባብረዋል፡፡ ሰልፈኞች ፖሊስ ጣቢያ የታሰሩ ወጣቶችን ሰብረው በመግባት አስፈትተዋል፤ የአስተዳደር ቢሮው ተሰባብሯል፡፡ የገንዘብና ኢኮኖሚ ጽ/ቤት ኮምፕዩተሮች በእሳት ጋይተዋል፡፡ አካለ መንግሥቱ የሚባለው የወያኔ ቅጠረኛ ዐማሮችን ሲሰልልና ሲያሰቃይ የሰነበተ ሲሆን የሕንጻ መሣሪያ መደብሩ ወድሞበታል፡፡
bahardar3
ክሊኒክና ፋርማሲ በመክፈት የአዴት ዐማራን ጊዜው ባለፈበት መድኃኒት ሲበዘብዙና ሲሰልሉ የነበሩት የገ/እግዚአብሔር ቤተሰቦች ከሳምንታት ቀደም ብለው ከአዴት ቢወጡም ንብረታቸውና መኖሪያ ቤታቸው በእሳት ከመጋየት አልዳነም፡፡ የገ/እግዚአብሔር ልጅ የሆነው አቶ አማኑኤል ዐማሮችን በሽጉጥ ሲያስፈራራ የሰነበተ ሲሆን ዛሬ ተፈልጎ የገባበት ሳይታወቅ ቀርቷል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ የወያኔ ቀኝ እጅ የሆኑት የሃይማኖት አባቶች ሰልፉን ለመገላገል ቢገቡም እናንተን አንሰማም ብሎ አሳፍሮ መልሷቸዋል፡፡ ይልማና ዴንሳ በህዝብ ቁጥጥር ስር ውላለች፡፡ ለዘጋቢያችን ምስጋና ይድረሰው፡፡

ዳንግላ፤ የአገው ምድሯ ዳንግላ ከተማ የዐማራን ተጋድሎ የተቀላቀለችው ትናንት ነበር፡፡ ትናንት ነሃሴ 22 ቀን 2008 ዓ.ም. ከጠዋቱ 1፡00 ጀምሮ የዳንግላ አገው ዐማራ ሕዝብ ለተጋድሎ ወጣ፡፡ የዐማራውን ጥያቄዎች አንግቦ ወደ ወኅኒ ቤቱ አቅጣጫ ሲሄድ መዘጋጃ ቤት አካባቢ ሲደርስ የወያኔ አባል የሆነው የመዘጋጃ ቤት ሠራተኛ አቶ ሀብተወልድ ወደ ሕዝብ በመተኮስ ሁለት ሰዎችን አቆሰለ፡፡ ሕዝብ ተቆጣና የአቶ ሀብተወልድን ቤት ሙሉ በሙሉ አቃጠለው፡፡
ወደ መሃል ከተማ ሲመጣ አንድ ቅጥረኛ የሆነ ያረጋል የሚባል ፖሊስ የዳሸን ቢራ ማስታወቂያን ከሚቀዱት የአገው ዐማራ ወጣቶች ላይ ጥይት አርከፈከፈ፡፡ ፖሊሱ የቤቱን አጥር ጉድብ ይዞ ሁለት ሰዎችን ገደለ፡፡ ከሕዝብ ጋር በሚያደርገው ትንቅንቅ ጥይት ጨረሰ፡፡ ሕዝቡ ሊይዘው ሲል ጎረቤቱ አንድ ካዝና ጥይት ሲሰጠው አናብስቶቹ አዩት፡፡ ባንዳው ጎረቤቱ ተጨፍጭፎ ተገደለ፡፡ ፖሊሱ ቢያመልጥም ቤቱ ከመቃጠል አላመለጠም፡፡ ይህ ሙሰኛ ፖሊስ መኖሪያ ቤት ውስጥ 50 ኩንታል ስኳርና 20 ጀሪካ ዘይት ተደብቆ ተገኘ፡፡ ሁሉም ንብረት አብሮ እንዲወድም ተደረገ፡፡ መኪናም ነበረችው፤ ወደመች፡፡

ዳንግላዎች ወደ ቤታቸው ገቡ፡፡ ነሃሴ 23 ቀን ጠባ፡፡ ዳግም ለተጋድሎ ተሰለፉ፡፡ ከዚያም ዳንግላ ከተማ ከክረምት ጉም እኩል የእሳት ጭስ አፈናት፡፡ የህወሓት አባላትና የቅጥረኛ ባለሥልጣናት ቤት ሙሉ በሙሉ ወደመ፡፡ ከተማዋም በሕዝብ ቁጥጥር ሥር ሆነች፡፡ የከንቲቫው (አቶ ሙላት እሸቴ) በሙስና የተከማቹ ሦስት ቤቶች፣ የጥቃቅን ኃላፊው አቶ ያለው ዘለቀ፣ የብአዴን ኃላፊው አቶ ዳዊት ብርሃኑ፣ የማዘጋጃ ኃላፊው አቶ መንግሥቴ ቢተው፣ የትራፊክ ፖሊሱ አቶ አይተነው፣ የደኅንነቱ አቶ ይመኑ፣ እና ሌሎችም ዛሬ ወደ አመድነት ከተለወጡ በቶች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
የአጋዚና የፌደራል ፖሊስ አባላት ከተማዋን ቢወሯትም ሕዝብን ግን እስካሁን ማሸነፍ አልተቻለም፡፡


መስፍን በቀለ “ወታደሩ ጓዴ አንተ ያገሬ ሰው ወንድምክን አትግደል ብረትክን መልሰው”ሲል የለቀቀው ወቅታዊው ዘፈን ሙሉ ግጥም

0
0

መስፍን በቀለ “ወታደሩ ጓዴ አንተ ያገሬ ሰው ወንድምክን አትግደል ብረትክን መልሰው” ሲል የለቀቀው ወቅታዊው ዘፈን ሙሉ ግጥም
አርቲስት መስፍን በቀለ “ወታደሩ ጏዴ አንተ ያገሬ ሰው ወንድምክን አትግደል ብረትክን መልሰው” ሲል የዘፈነውና ባለፈው ቅዳሜ የተለቀወው ወቅታዊ ዘፈንን በርካታ አንባቢዎች ሙሉ የዘፈኑን ግጥም እንድንለቅላችሁ በጠየቃችሁን መሠረት እነሆ ግጥሙን ከአርቲስቱ አግኝተናል:: ይህን ተወዳጅ ዘፈን ግጥምና ዜማውን የሰራው ራሱ ድምጻዊው መስፍን በቀለ ነው::

የነጻነት ድምፅ ሲሰማ
ሰማዩ ጉሙ ከጠራ
የቃልኪዳን ምድር ነች
ኢትዮጲያችንን አደራ
ላንሳው ላንሳው ሀገሬ ስምሽን ላንሳው
ላንሳው ላንሳው ደግሜ በክብር ላንሳው
ላንሳው ላንሳው ኢትዮጲያ ስምሽን ላንሳው
ላንሳው ላንሳው እናቴ ክብርሽን ላንሳው
አረንጏዴ ቢጫቀይ አርማሽ
ነጻነት ነው ለሚሰማሽ
እናያለን ሳይመሽ ሳይነጋ
ይመታል ያቀን ተክፍሎል ዋጋ
ኢትዮጲያ……..
አዲስ ትውልድ በቅሎል እንደሳት ነበልባል
መብቱን የሚጠይቅ ኬት ነህ ሳይባባል
ለነፃነት ድምፁን ከፍ አርጎ እያሰማ
ደሙ ከፈሰሰ መሬቱ አኬል ዳማ
ወታደሩ ጏዴ አንተ ያገሬ ሰው
ወንድምክን አትግደል ብረትክን መልሰው
ለሀገሩ የሚተርፍ ስንት ጥበብ ያለው
ነፃነቱን ወስደህ አስረህ አታጉላላው
ይህ ነገር አይበጅ እንዳይብስ ሲያድር
በሀገራችን ጉዳይ ሁሉም ዪነጋገር……

500 ሳጥን ዳሸን ቢራ የጫነ ከባድ መኪና በሕዝብ ተቃውሞ ወደመ |በባህርዳር የዛሬ ተቃውሞ 4 ሰዎች ሞተዋል

0
0

500 ሳጥን ዳሸን ቢራ የጫነ ከባድ መኪና በሕዝብ ተቃውሞ ወደመ | በባህርዳር የዛሬ ተቃውሞ 4 ሰዎች ሞተዋል
ለኢሳት አሁን የደረሰ ዜና:

-ወደ አዲአርቃይ ሲጓዝ የነበረና 550 ሳጥን ዳሽን ቢራ የጫነ ከባድ መኪና አምባ ጊዮርጊስ ላይ በህዝብ ተቃውሞ ወደመ። የቢራ ሳጥኖቹ መንገድ ለመዝጋት መዋላቸውን በቪዲዮ ተደግፎ ለኢሳት የደረሰው መረጃ ያመለክታል።
-ባህር ዳር በተቃውሞ እየተናወጠች ባለችበት በዛሬው ዕለት አንዳንድ የክልሉ መንግስት ሃላፊዎች ከተማዋን ለቀው መውጣታቸው ተገለጸ። ኢሳት ማረጋገጪያ ባያገኝም አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የወከሏቸው አቶ ያየህ አዲስ ቤተሰቦቻቸው ይዘው በአውሮፕላን ከባህር ዳር መውጣታቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው አንድ ነዋሪ ገልጸዋል። በዛሬው የባህር ዳር ተቃውሞ 4ሰዎች እንደተገደሉ ይነገራል።

የግዢ እና ሽያጭ ማቆም አድማ ጥሪ ከጷግሜ 1- መስከረም 2፣ 2009 |ከጀዋር መሐመድ

0
0

Jawar Mohamed
ቀደም ብለን እንዳስታወቅነው ለቀጣዩ ዘመቻ የተመረጠው ሳምንት በሃገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ የሚደረግበት ነው። ስለሆነም ዘመቻው የስርዓቱን ኢኮኖሚ ከማድቀቅም አልፎ የኦሮሞ ህዝብ የሃገሪቱ ኢኮኖሚ ግንድ መሆኑን የሚያሳይበት ይሆናል። በተጨማሪም በኦሮሚያ ከተሞች ውስጥ ለጨቋኙ ስርዓት ያደሩ ነጋዴዎችንም ለመለየት ይጠቅማል ዘመቻው። በዚሁ መሰረት ከጳጉሜ አንድ እስከ መስከረም ሁለት 2009 ዓ.ም የሚቆይ በስርዓቱ ኢኮኖሚ ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ ይደረጋል። ዓላማውም የስርዓቱን ኢኮኖሚ በመምታት የጭቆና አቅሙን ማንኮታኮት ይሆናል። ወቅቱ የዘመን መለወጫና የኣረፋ በዓላት ወቅት ነው። ባሮጌው ዓመት የኦሮሞ ህዝብ ለነጻነቱ ባደረገው ከፍተኛ ተጋድሎ ብዙ ልጆቹን ሰውቶ ሺዎችን ላይ ደግሞ የኣካል ጉዳት ደርሷል። በኣስር ሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ በስርዓቱ አስቃቂ እስር ቤቶች አሁንም እየተሰቃዩ ይገኛሉ። ስለሆነም በዓሉ እነዚህን ጀግኖቻችንን እያሰብንና እነርሱ የተሰውለትን ዓላማ ለማሳካት በሚያስችል መልኩ ትግላችንን እየቀጠልን ነጻነታችንን የምናፋጥንበት እንጂ በጭፈራና በከበርቻቻ የምናሳልፈው አይሆንም። በዚሁ መሰረት የሚወሰዱት እርምጃዎች፥

1) አርሶ አደሮቻችን እህል፣ የእርድ ከብት፣ ዶሮ፣ እንቁላል፣ ቂቤ፣ ቅመማ ቅመሞች፣ አትክልቶች፣ ፍራፍሬዎች የመሳሰሉትን በሳምቱ ለገብያ ባለማቅረብ (ጨው፣ ስኳር ፣ዘይትና ሌሎች መሰረታዊ የቤት ውስጥ ፍጆታዎችን በሳምንቱ መጀመሪያ ቀድሞ ባሉት ቀናት በመግዛት)፤

2) ነጋዴዎቻችንም ከላይ የተጠቀሱትን የበዓል ፍጆታዎች ፊንፊኔን ጨምሮ ወደ ሌሎቹ ትልልቅ ከተሞች ከማቅረብ በመቆጠብ፤
3) ይሄን ዘመቻ ለማክሸፍ የሚንቀሳቀሱ ለስርዓቱ ያደሩ ነጋዴዎችንም መንገድ በመዝጋት ጨምሮ በተቻለው መንግድ ሁሉ በማደናቀፍ፤

4) በከተሞችም ሆነ በገጠር የሚኖረው ህዝባችን በነዚህ ቀናት ምንም ነገር ከመሸመት መቆጠም። ምግብ ቤቶች፣ መዝናኛ ቤቶች፣ ሻይ ቤቶች፣ መጠጥ ቤቶች ወዘተ….ሁሉ ገብቶ ምንም ዓይነት ወጪ አለማውጣት። በቤት ውስጥ ከዘመድ ወዳጅ ጋር ተስብስቦ ሰማዕቶቻችንን ማሰብ። እነሱ የተሰውለትንም ትግል እንዴት በፊጥነት ወደፊት ማስቀጥል እንደሚቻል መወያየት። እንደየእምነታችን ወደ እምነት ቤቶች ሄደን ጸሎት ማድረግ። እዛም በጉዳዩ ላይ በጋራ ሆነን መወያየት።

ከላይ በመግቢያው ላይ እንደተጠቀሰው፣ ሳምንቱ ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ የሚደረግበት ወቅት ስለሆነ፣ እነዚህን እርምጃዎች በመውሰድ ስርዓቱ ላይ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጉዳት በማድረስ የጭቆና ጉልበቱን ማሽመድመድ ይቻላል። ከዚህም በተጨማሪ የኦሮሞን ህዝብ የኢኮኖሚ ዋልታነት ከማሳየትም አልፎ ለስርዓቱ ያደሩና የህዝብ ወገንተኘት ያላቸውን ነጋዴዎች ለመለየት ጥሩ አጋጣሚ ይፈጥራል።

ስለሆነም በህዝባችን ላይ እየተካሄደ ያለውን የግፍ የጅምላ ግድያ እና እስራት የምትቃወሙ ሁሉ በዚህ ሰላማዊ ግን ውጤታማ የትግል ስልት እንድትሳተፉ በአክብሮት እንጠይቃለን::

የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች የዓመቱን ምርጥ ሰው ይምረጡ!!

0
0

zehabesha person of the year

ዘ-ሐበሻ አንባቢዎቿን በማሳተፍ በየዓመቱ የዓመቱን ምርጥ ሰው ስትሰይም ቆይታለች:: እስካሁን ዘ-ሐበሻ አንባቢዎቿን አሳትፋ በየዓመቱ ምርጡ ሰውን መምረጥ ከጀመረች ወዲህ ይህን ክብር ከተጎናጸፉት መካከል ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ መምህር የኔሰው ገብሬ፣ አንዱዓለም አራጌ፣ አብርሃ ደስታና ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተጠቃሽ ናቸው:: ዘንድሮም እያጠናቀቅነው ባለው በዚህ ዓመት በሃገሪቱ ታላቅ ሥራ አክናውነዋል፣ አረአያም ይሆናሉ ያላችኋቸውን ሰዎች እስከ ጷጉሜ 5 ድረስ በስልክ/ቫይበር/ዋትሳፕ 612-226-8326 ቴክስት በማድረግ፣ በኢሜይል info@zehabesha.com ወይም በፌስቡክ facebook.com/zehabesha ለምን ያን/ያቺን ሰው እንደመረጡ በአጭሩ በመለጽ ይምረጡ::

 

ዲያቆን ዳንኤል ክብረት መንግስትን ክፉኛ ነቀፈ |ሰሞኑን ለተነሱት ሕዝባዊ አመጾች የመንግስት ምላሽ ምን መሆን እንደነበረበት ነጥቦችን ያስቀምጣል

0
0


ዲያቆን ዳንኤል ክብረት መንግስትን ክፉኛ ነቀፈ | ሰሞኑን ለተነሱት ሕዝባዊ አመጾች የመንግስት ምላሽ ምን መሆን እንደነበረበት ነጥቦችን ያስቀምጣል

በደቡብ አፍሪካ የጠፉት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የድረሱልን ጥሪ አቀረቡ “ሰው ቤት እየተኛን ነው…የተቻላችሁን እርዱን”

0
0


በደቡብ አፍሪካ የጠፉት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የድረሱልን ጥሪ አቀረቡ “ሰው ቤት እየተኛን ነው… የተቻላችሁን እርዱን”

አዲስ አበባዎች ይነቅላሉ –ዳዊት ዳባ

0
0
comment symbol icon

comment symbol icon

የሌሊሳ ተግባር  ጀግንነት ነው። ድረጊቱ ትግሉ ላይ ያስገኘው ጠቀሜታ እስካሁን ከተባለለትም የላቀ  ነው። ደስታዬንና ምስጋናዬን ለመገለፅ ቃላት የለኝም ።  የኢሳት የእስፖርት ጋዜጠኛ  ወንድማገኘው እንዲሁ ምስጋና ይገባሀል። ከአምት በፊት ያን ዝግጅትህን ሳዳምጥ እጅግ አድርጌ መውደድ ብቻ ሳይሆን  አንድ ቀን የወንድም ሌሊሳ አይነት  ጀግንነት እንደሚሆን ቀድሜ  አይቼበታለው። ሰውዝ አፍሪካ ላይ የአለም ዋንጫ ሲደረግ  መልካም አጋጣሚ ነበር። “እነሱም እኛም እስፖርቱን ለፖለቲካ {ለኛ ለትግል} ላንጠቀምበት  ተስማማን “ የሚለውን ስሰማ አንጀቴ ነበር የተቃጠለው። በዚህ አይነት አስከፊ ጭቆናና ዘግናኝ አድሎ ውስጥ እየኖረ “ወገኛ ህዝብ” ብዬ ሁሉ በሆዴ ተሳድባያለው። እስፖርትና ትግል  ስል መጎልጎል የጀመርኩት ያኔውኑ ነበር። በዚህ ጊዜ ነበር የጥቁር አሜሪካኖቹን ታሪክና ሌሎች ከእስፖርት ጋር የተገናኙ የትግል ታሪኮችን ያወኩት። ልፅፍበት እያሰብኩ ሳለው ዝግጅትህን አዳመጥኩ ድንቅ ሆኖ ስላገኘሁት በጭራሽ ልንበዛበዝበት አልፈለኩም። ሌሊሳ ያን ዝግጅት መስማት አለመስማቱን የማውቀው ነገር የለም። ጠቃሚ ሀሳብ እንዲሰማና ጉልበት እንዲኖረው ተደርጎ ሲለቀቅ ግን ጊዜ ይወስድ እንደው እንጂ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ብዙ እርቀት እንደሚጓዝ  አውቃለው። ኢትዬጵያዊያን  በዚህ አይነት ታላቅ መድረክ ላይ ባይሆንም ያደርጉት ጀማምረዋል። አሁንም  ፈተናን በማውጣት የአገዛዙን የማስተዳደር አቅም ማዳከምና የማሳጣት ትግል ተደርጓል። እዚህ ትግል ላይ ከፍ ብሎ የሞራል ጥያቄ ተነስቷል። በፈለገ አይነት የከፋ ጭቆናና እየተጨፈጨፈ ቢሆንም ዜጋው ሲታገል ሊተላለፍ ስለማይገባው መስመር ሁሉ ተስብከናል። የሰው ልጅ ለነፃነቱና እራሱን ከጥቃት ለመከላከል የሚያደርገው የትኛው ተግባሩ ነው ትክክል የማይሆነው? የሚለው ጥያቄ በአይምሮዬ እንደተመላለሰ እንደከነከነኝ  አለ።

አንድ ባለንጀራዬ ትግሉ አንቀሳቃሾች ውስጥ ቅርብ ነው ብሎ ባሰበው  ወንድም በኩል ይህን የውጪ ሜዲያዎች ዝምታ አስገድደን ልንሰብረው እንችላለን ሲል አዲስ ሀሳብ ለማስረፅ መክሮ ነበር። እኔ አለው አንድ አስር ሀያ ቆራጥ ታጋዬች ካሉ እናፈላልግና በቀጣይ ሰልፍ ስንወጣ ጋዝ ወይ ምላጭ ነገር ይዘን እንውጣ። በተገቢው  ካልተስተናገድንና እውነታችን እስካልተነገረ ሌላ መጉዳት አይሆንልንም እራሳችንን ግን እንጎዳለን ብለን አዋራ እናስነሳ ሲል። አክቲቪስቱ አፍጥጦ እንደ እብድ ሲያየው ቆይቶ ምን ይበል  ጥሩ ሀሳብ አለ እየተገረመ። ግን ተግባራዊ አልሆነም። እስከዛሬም ማሰብና መፈተግበር እንጂ የማይሰበር ነገር ግን የለም። ጀግናው ሌሊሳ  ሰባበረው።

አዲስ አበባ ላይ በቅርብ ታላቅ ህዘባዊ እንቢተኛነት ይካሄዳል። የጎንደርና የጎጃም ህዘብ ላይ ጦርነት አውጀው ፍጅት እየፈፀሙ ነው። ይህንን ዝም ብለን ልናየው የሚገባ አይደለም። ህዝባዊ አመፁ እንደሰደድ እሳት አገሩን  እያዳረሰና እየተጠጋ ቢሆንም ለጊዜው ለብቻቸው ተጠቂ የሆኑት በአገር አቀፍ ደረጃ ህዘባዊ እንቢተኛነቱን ማምጣት ስላልቻልን ነው። ከሳምንት በፊት አዲስ አባባ የነበረው ጥሪ ትክክለኛ እርምጃ ነበር። ይህ ሙከራ አገዛዙን ብዙ ሚሊዬን ብር እንዳስወጣው ሰማው። ታዲያ በየሳምንቱ እሁድ እሁድ አደባባይ እየወጣን ህዘባዊ እንቢተኛነት የምናደርግብት ቀን አድርገን ብንይዘው  ስንት ሳምንታት ይህን ያህል ብር እያወጣ ሊዘልቅ ነው?።  በነገራችን ላይ ያልተካሄደው አገሩን ወታደር በወታደር ስላደረጉ በጭራሽ አይደለም። እሱን ሌላ ቦታ ሰባብረውት እየወጡ እንዳለው በገፍ ወጥቶ መና ማስቀረት ይቻላል። እንዲሁም እንደ አዲስ አበባዊነቴ ስለዚህ ህዘብ እንቢተኛነቱን በተመለከተ የሚሰጡ ፖለቲካዊ ትንታኔዎች የበዙት የሚገዙኝ ሆነው አላገኘሗቸውም። ትግሉ ከኦሮሚያ ሊሻገር አልቻለም፤ እራሱኑ ህዝባዊ እንቢተኛነቱን በተመለከተም ሲሰጡ የነበሩ ትንታኔዎች ሁሉ ትክክለኛ እልዳልነበሩ እያየን ነው። ባለፈው ጥሪ ተቃውሞው ያለተደረገበትን ምክንያት  ብዙዎች በስሱ ስለሄዱበትና ስለማይፈይድ እዚህ አላነሳውም። ትምህርት ሊወሰድበት ግን ይገባል። ያም ሆኖ ጥሪው ጊዜን ቦታና ሁኔታዎችን በአግባቡ የሰላ  ነበር። መልክቶቹ ይዘታቸውና አቀራረባቸው ድንቅ ነበር። ላሁኑ ተደረገ አልተደረገ አይደለም ዋናው ነገር፡፤ መነጋገርያ መሆኑ በራሱ በቅርብ በቀጣይ ለታቀደው እጅጉኑ አጋዥ ነው።

ሰዎቻችን ዛሬም ግድያ መፍትሄ ነው ላይ ናቸው። ምንም አይነት የአንባገነን የሀይል ከህዘብ ሀይል አይበልጥም የሚባለው ዝም ብሎ መስሏቸዋል። ተመልከቱ ሌሊሳ ብቻውን ባፍጢም ነው አፈር ውስጥ የደፋቀው። ገና ገና ነው። ህዝብ  መምዘዝ የሚችለውን ልምጭ በጣም በጥቂቱ ነው የተጠቀመው። የአዲስ አበባ ህዘብ ወደ ስድስት ሚሊዬን የሚጠጋ ነው። እራሱ  አይደለም መኪና ቢያሰለፍ ፍፃሜ ይሆናል። ታክሲዎች ስራ ሲያቆሙ መኪናዎቻቸውን እቤት የማቆም ግዴታ የለባቸውም። እንደጎንደርና ጎጃም ህዘብ እቤቱ ቢቀመጥ  አለተፈለጋችሁምና ጎሽ  ውረዱን በአለም ዘንድ ይናኛል። ህዘብ ባንድ ጊዜ አንድን ነገር ማድረግ አይችልም ከሆነ ዛሬም ክርክሩ የኦሮሞን የጎጃምና የጎንደርን ህዝብ አይቶ መማር ለሚፈልግ ከበቂ በላይ ነው። ስድስት ሚሊዮን ህዘብ ስልክ አንስቶ ቢደውል ወታደሩን ሁሉ ይደርሳል። የዛኑ ቀን መሳርያ ያዞራል። ቀን ወስኖ ተቃዋሚዎች ቢሮ በመሄድ አባል ለመሆን ቢሰለፍ እረሱን የቻለ ታላቅ ሰልፍ ይሆናል። ላስር ደቂቃ በያለበት ቢቆም ቢጨፍር ቢስቅ ችግር ነው። ገንዘቡን መከልከልና ገንዘቡን በጁ ማድረግ ይችላል። እናንተም ልጆቻችሁም ንብረታችሁም የበዛው እዛው ነው ያለው። እራሱን ለመከላከል እነዚህን ገነሮች መያዣ ሊያደርጋቸው ይችላል። ከወሰነ ወሮ ሊቀማቸው የሚቺሉ ብዙ ወሳኝ የቀበሌ ቢሮዎች አጠገቡ አሉ፡፤ አንድ አይነት መልእክት የያዘ ወረቀት ቢለጥፍ አጥርና ስልክእንጨቱ ሁሉ በመልክት ያሸበረቅል። እየተመናመነ ባለ ሀይል ማፅዳቱ ብቻ ወራቶች ይፈልጋል። በዛ ላይ የሚለቅመው መሳርያ የያዘውን ካድሬ ነው።

አንድ ቀን ጠዋት ላይ ስትነሱ መንገዶች በሙሉ በከተሜው ህዘብ ተሞልቶ ሊገኝ ይችላል፤ አዲስ አባባ ለሚገኙ ቻይናዊያን በሙሉ ለቃችሁ ውጡ ብሉ ድብዳቤ ቢልክላቸውስ፣… ተዘርዝሮ አያልቅም።

አዲስ አበባ ላይ ለውጥን ፈላጊውም ሊያንቀሳቅስ የሚችለውም ህዘብ ቁጥር የበዛ ነው። የስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን በሚሊዬን አደባባዩችን ተቆጣጥረውት የነበረው ትናንትና ነው። ህዝቡ መታገል ሳይደክመው መሪነቱን በአደራ የተረከቡ መምራት ደክሟቸው ነው ትግሉ የቀዘቀዘው። ሶስት ቀላል የመብት ጥያቄዎቻቸው ውስጥ አንዳቸውም አልተመለሱም።  ሳይገባቸው ለመከራ የተዳረጉ ንፁሀን ዜጎች ሂወት ጉዳይ ለሁላችንም የእግር እሳት ነው። ይህ የህብረተሰብ ክፍል የተደረጃና፤ ዘመኑ ባፈራቸው መገናኛዎች የተጣመረ ነው።  ስራውን ያውቀዋል። የአዲስ አበባ ካድሬዎች ከሌሎች ክልሎች ላይ ካየነው ወግንታዊነት በላይ ከህዘብቸው ጎን ለመቆም ብዙ ተጨማሪ ምክንያቶችም አሏቸው። ትናንትና በመድረክ፤ በሰማያዊ፤ በአንድነት፤ በመኢአድ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ የወጣው ህዘብ ሁሉ ዛሬ በተራው ትግሉን አንቀሳቃሽ ነው።  የማቀናጀት ድክምት ካልሆነ የሚጠብቃቸውን እያወቁ አዲስ አበባ ላይ በቆራጥነት የተሰለፉ የኦሮሞ ወጣቶች ብዙውን መሬት ላይ የሚያስፈልገውን ስራ ይሸፍኑታል። የጎንደር ህብረት የዚህን ያህል ካንቀሳቀሰ በውጪ ያሉ የካሳንቺስ፤ የጎላ፤ የሽሮ ሜዳ… ማህበሮች ምስር ወጥ በሄንከን እየበሉ መበተን ብቻ ሳይሆን እራሳቸወን ወደ ለውጥ አንቀሳቃሽንት ይቀይራሉ። እንደሚታወቀው አገዛዙ ሁሌም ቆረጣ ነው። በከተማዋ ያሉ ማህበራት በተመለከተ መሪዎቻቸው ላይ ነው የሰራው። የሚያሞዳምደውም ። ሊገባቸው ያልቻለው አስተማሪውም፤ ታክሲ ነጂውም፤ ጋዜጠኛውም፤ ጥቃቅኑም… ያው ተራ ህዘብ ነው። ተራ የከተማዋ በለቤት ነው። የነዚህ ማህበራት መሪዎች ወና ስራ የህዘብን ትግል ለማውገዝ መሆኑን አባላቱም ህዝብም የለመደው ነው። በዋናነት አየሩ በለውጥ ሽታ ከታወደ በሗላ ምርጥ ጓደኛሞች በሙሉ አንዳንድ ሴል ናችሁ። በመቶ ሺ ሰሎች አዲስ አባባ ውስጥ አሉ ማለት ነው። ለአዲስ አበባዊያን ከድጋሚ ጥሪ በፊት በንቃት ሁኔታዎችን መከታተል፤ መወያየት እራስን ማዘጋጀት ሲታትሩ መጠበቅ ነው።  ይተገበራል!!!።

ብሔራዊ ጭቆና ይብቃ።

ዳዊት ዳባ።

Monday, August 29, 2016

 

 

 

 


ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይለማሪያም ደሳለኝ |ከፓስተር ያሬድ ጥላሁን

0
0

pastor yared
ይህን ደብዳቤ የምጽፍሎት ሰው ያሬድ ጥላሁን እባላለሁ። የወንጌል አገልጋይ ነኝ። ከጌታ ምሕረትን ተቀብዬ ላለፉት 27 ዓመታት ዘር፣ ጎሣ፣ ቀለም፣ ጾታ፣ እምነትና የፖለቲካ አመለካከት ሳልለይ ለትንሽ ለትልቁ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ስሰብክ የኖርኩ ነኝ። ዛሬ ይህንን ደብዳቤ የምጽፍሎት በልብ ጭንቀትና በብዙ ዕንባ ነው። ከሰሞኑ በእርሶ አንደበት የተነገረውንና የኢትዮጵያ የመከላከያ ኃይል በዜጎች ላይ የኃይል እርምጃ እንዲወስድ የሚፈቅደውን ንግግር አድምጫለሁ። ከተቀመጡበት ወንበር ግዝፈትና በዙሪያዎ ከከበቦት ውጥረት አንጻር የገቡበትን አስጨናቂ ሁኔታ ለመረዳት እሞክራለሁ። የሚወስኑትም ውሳኔ በግል የእርሶ ብቻ እንዳልሆነና አንዳንድ ጉዳዮች ከዐቅሞት በላይ ሊሆኑ እንደሚችሉ እገምታለሁ።

ሆኖም በአንደበትዎ የተነገረውና በታሪክ መዝገብ ተቀርጾ የሚኖረው ይህ ውሳኔዎ በእግዚአብሔር፣ በሰውና በኅሊናዎ ዘንድ ከፍተኛ ተጠያቂነት እንደሚያመጣብዎ ሳስብ ከልብ አዝናለሁ። እርሶ በእግዚአብሔር ምህረት የተፈጠሩ፣ በምሕረቱ ያደጉና አሁን ለደረሱበት ከፍተኛ የኃላፊነት ሥፍራ የበቁ መሆንዎን በሚገባ ያውቃሉ። ይህን ለእርስዎ የተሰጥዎትን የመኖር መብት ለሌሎች ይነፍጋሉ ብዬ አላስብም። ሆኖም አሁን በእርሶ መሪነት በገዛ አንደበትዎ የተሰጠው ይህ ውሳኔ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ምትክ የማይኖራቸው ኢትዮጵያውያን ሕይወት ላይ ሞት የሚያጠላ ነው።

ሕዝብ ጥያቄ አለኝ ብሎ አደባባይ ሲወጣ፣ አጥጋቢ ምላሽ አላገኘሁም፣ እንዳልናገር ታፍኛለሁ ብሎ እምቢተኝነት ሲያሳይ የተለያዩ ፖለቲካዊ መፍትሄዎችን በማፈላለግ ሕዝብን ማረጋጋት የመንግሥት ባሕሪ ነው። ይህ ዛሬ ድምጹን ለማሰማት በየሥፍራው እንደ አሸን የፈላው ሕዝብ ላለፉት 25 ዓመታት ለኢሕአዴግ አመራር ጸጥ ለጥ ብሎ የተገዛ፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ባረፉ ጊዜ ዕንባውን የረጨ፣ ደረቱን የደቃ ሕዝብ ነው። የፍትሕ ዕጦትና የመድልዎ ብሶት አንገሽግሾት የሚሰማኝ መንግሥት አለ በሚል አደባባይ ቢወጣ እንደ እባብ ተቀጥቅጧል፣ ተዋክቧል፣ ታስሯል፣ ተሰዷል፣ ተገድሏል። ለዚህ እውነታ ማስረጃ ማቅረብ የሚገባኝ አይመስለኝም፤ እርሶም አጥርተው እንደሚያውቁት አልጠራጠርም።

“በቁስል ላይ ዕፀጽ” እንዲሉ አሁን በኢሕአዴግ ጉባዔ የተወሰነውና በእርስዎ ትዕዛዝ የተንቀሳቀሰው ኃይል ጉዳዩን ወደ ከፋ ደረጃ እንደሚያሸጋግረውና በብሔሮች መካከል የማይሽር ጠባሳ እንደሚያሳድር እርሶዎንም በእግዚአብሔርና በሰው፣ በታሪክና በሕሊናዎ ተወቃሽ እንደሚያደርግዎ በብዙ ትህትና መግለጽ እወዳለሁ።

አሁንም ጊዜው ሳይመሽ ፖለቲካዊ መፍትሔዎች ላይ እንዲተኮር፣ የኃይል እርምጃው እንዲቆም፣ ተዓማኒ እርምጃዎች እንዲወሰዱና ሌሎችንም ያሳተፈ አገራዊ መግባባት ላይ እንዲደረስ አቅምዎ እሰከሚፈቅድ የበኩሎትን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ፤ ይህንንም ማድረግ ካልቻሉ ከሚፈሰው የንጹሐን ደም እጅዎን እንዲያነጹ ሰውን በመልኩና በምሳሌው በፈጠረ በሕያው እግዚአብሔር ስም እማጸኖታለሁ።
የጌታ ጸጋ ከእርስዎ ጋር ይሁን! እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!

ከኢህአደግ ደጋፊዎች ለኢህአደግ ላዕላይ ምክር ቤት የቀረበ ባለ 9 ነጥብ አቤቱታ |ተሰርቆ የወጣ

0
0

eprdf
ከኢህአደግ ደጋፊዎች ለኢህአደግ ላዕላይ ምክር ቤት 9 ነጥብ ያለው አቤቱታ በደብዳቤ አቅርበዋል:: ይህ ምስጢራዊ አቤቱታን የውስጥ አርበኞች ለዘ-ሐበሻ እንዲደርስ አድርገዋል:: ለግንዛቤ ይረዳችሁ ዘንድ ያንብቡት::

ሐሙስ ነሐሴ 26 ቀን 2008 ዓ.ም

ከኢህአደግ ደጋፊዎች ለኢህአደግ ላዕላይ ምክር ቤት የቀረበ አቤቱታ
1. አማራ ክልል ላይ መንግስትን የሚቃወመው ሕዝብ ብዛቱ ምን ያክላል ለሚለው የሚሰጠው የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩን ትዕዛዝ ይዞታ የየሚተረጉም ይሆናል፡፡ በእኔ አመለካከት ከ90% በላይ ሕዝብ ይቃወማል፡፡
በዚህ ሕዝብ ላይ የመንግስት ጸጥታ ኃይሎች ማንኛውንም እርምጃ እንዲወስድ ማዘዝ ጂኖሳይድ አይሆንም ወይ የሚለው ጥያቄዬ እንዲመለስልኝ እፈልጋለሁ፡፡
2. እንደምናየው የመንግስት ጸጥታ ኃይሎች ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እንዳዘዙት እርምጃ አልወሰዱም፡፡ ማስረጃው እስካሁንም ድረስ ተቃውሞው እንደቀጠለ ሆኖ የፀጥታ ኃይሉ ከዚህ በፊት ከሚወስደው የተለየ እርምጃ እንደወሰደ አለመሰማቱ ነው፡፡ ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩን መመሪያ ለመቀበል ገሸሽ ማለት ሥጋት የለውም ወይ?
3. ጠቅላይሚንስትሩ አጠቃላይ ሕዝብ ተገልብጦ የሚያሰማውን ተቃውሞ ለወጣቶች ብቻ መስጠቱ ተገቢ ነው ወይ? ማስረጃ የጎንደር፣ የባህር ዳር እና የማርቆስ ሕዝብ ቤቱን የዘጋው ወጣት ልጆቻቸው አስገድዶአቸው አይደለም፡፡
4. መንግስት ከአጠቃላይ የአገሪቱ ሕዝብ ጋር የሚያጣላውን ድርጊቶች ለምን ይፈጽማል?
ማስረጃ፦ የመጀመሪያው የአዲስ አበባ ቤቶች ፈረሳ
ሀ.. ሕገ ወጥና ሕጋዊ መካከል ሰነድ አልባ ቤቶች የሚለውን የፈጠረው መንግስት ነው፡፡ ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዕረፍት በፊት ሕገወጥ ይዞታወችን በሙሉ በትንሽ የሊዝ ዋጋ ሕጋዊ እንደሚያደርግ ለሕዝቡ ገልጾ ነበር እንዲያውም የወቅቱ ጥያቄ በሊዝ ሕጋዊ መደረጉን አንቀበልም የሚል ነበረ፡፡ ያንጊዜ ከነበረው ከክቡር አቶ መኩሪያ መሥሪያ ቤት የተሠራጨ የሊዙን ከአፈጻጸም የሚያትት ሃያ ገጽ ያለው ብሮሸር ተበትኖ ነበር፡፡ አሁንም በሕዝቡ እጅ ይገኛል፡፡
ለ. መንግስት በእነዚህ በፈረሱ መንደሮች ከፍተኛ ኢንቨስት አከናውኗል፡፡
መብራት፣ ውኃ፣ ፖሊስ ጣቢያዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ መዝናኛዎችን፣ መንገዶችንና ሌሎችን የሚያካትት ነው፡፡
ሐ. ዘጎች ቤታቸው ሕጋዊ ይደረግላችኋል በሚል ለኮንደሚኒዬም ቤት እንዳይመዘገቡና እንዳይቆጥቡ በመንግስት መመሪያ ተከልክለዋል፡፡
መ.በአዲስ አበባ ከተማ ሃያ ሺ ቤት ሲፈርስ በመንግስት ስሌት አንድ ቤት
አምስት አባላት ስለሚኖሩት 100.000 ሕዝብ ተፈናቅሏል
ውጤት፦ ሃያ ሺ ቤት መፍረሱ በአገራችን ማህበራዊ ኑሮ ስሌት የአንዱ ጥቃት በትንሹ በሁለት መቶ ሰዎች ላይ ቀጥተኛ ቁስል ያደርሳል፡፡ የወንዱ ዘመዶች፣ የሚስቱ ዘመዶች እና ጓደኞቻቸውን ያካትታል፡፡ ሃያ ሺ ሰው በሁለት መቶ ሲባዛ አራት ሚሊዬን ሕዝብ በአንድ ላይ ያቆስላል፡፡ አራት ሚሊዬን ሰው በቀን አንዳንድ ሰው ከመንግስት ቢያስኮበልል በየቀኑ አራት
ሚሊዬን እየካደ አገር ሁሉ ይገለበጣል፡፡
5. በወልቃይት ጉዳይ መላው የአማራ ክልል እየታመሰ መንንግስት የወልቃይትን ጥያቄ ትግራይ ክልል እንዲፈታ መወሰኑ ትክክል ነው ወይ?
6. በወልቃይት ምክንያት በአማራ ክልል ያለውን ተቃውሞ በጠመንጃ አፈ ሙዝ ለማንበርከክ ጦርነት በማወጅ የወልቃይትን ጉዳይ ለትግራይ ክልል መስጠት ጠቅላይ ሚኒስትሩና ፓርቲያቸው ለሕወሀት የሚሠሩ አያስመስላቸውም ወይ?
7. ጠቅላይ ሚኒስትሩ የወጣቶችን ጥያቄ የፖለቲካ ጥያቄ መሆኑን በመካድ የሥራ ማጣት ወይም ኢኮኖሚያዊ ጥያቄ አድርጎ መቅረባቸው ትክክል ነው ወይ? እስካሁን ድረስ ሥራ አጥተናል በሚል አንድም የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደው አያውቁም፡፡
8. የወልቃይት ጥያቄ የአገር ባለቤትነት ጥያቄ እንደመሆኑ መጠን በአማራ ሕዝብና በትግራይ ሕዝብ መካከል ለዘላለም የማይታረቅ ግጭት ምክንያት ሆኖ እንደሚዘልቅ መንግስት መመልከት አለመቻሉ የመንግስትን ጠባብነት አያሳይም ወይ?

9. በመንግስት ሚዲያዎች ላይ ይህ ነው የማይባል የመንግስት በጎ ሥራ እየተሰበከ በማህበራዊ ሚዲያዎች ተቃዋሚዎች የሚሰብኩት ሕዝቡን እንዳሳሳተ ማማረር የፕሮፓጋንዳ ሽንፈትን አያሳይም ወይ?

በእነዚህ ጥያቄዎች በመጀመሪያ ደረጃ ለራስ ህሊና ታማኝ በመሆን በሁለተኛ ደረጃ ለአገር ሰላም ሲባል በሦስተኛ ደረጃ በህሊናችን አለቃ በእግዚአብሔር ፍርሃት ተገቢ ምላሽ እንድትሰጡን በትህትና እንጠይቃለን፡፡ መኖር የምንችለው አገር ስትኖር በመሆኑ አሁንም መንግስ ውሳኔዎቹን በድጋሚ እንዲያያቸው በትልቅ ትህትና እናመለክታለን፡፡

የደብረታቦር ማረሚያ ቤት በእሳት እየጋየ ነው |ከተማዋ የጥይት ድምጽ ይሰማል

0
0

debretabor
(ዘ-ሐበሻ) ሕዝባዊው አመጽ እየተደረገባቸው ካሉት የአማራ ከተሞች መካከል አንዷ በሆነችው ደብረታቦር ከተማ የሚገኘው ማረሚያ ቤት በ እሳት እየነደደ መሆኑ ተሰማ::

እንደ ምንጮች ዘገባ ከሆነ ከሰሞኑ በከተማዋ አግባብ ያለው ጥያቄ በመጠየቃቸው የታሰሩ ወገኖች በሚገኙበት የተነሳው እሳት መነሻው ምን እንደሆነ አይታወቅም::

እሳቱ እየነደደ ቢሆንም የአጋዚ ጦር እስር ቤቱን ከቦ እስረኞች እንዳይወጡ እየተከላከለ ሲሆን ምንም ዓይነት የነብስ አድን ሥራ እየተሰራ እንዳለሆነ እነዚሁ የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታውቀዋል::

በደብረታቦር ከተማ ከፍተኛ የጥይት ድምጽ የሚሰማ ሲሆን የትግራይ ነጻ አውጪ ወታደሮች ወደ ሕዝብ እየተኮሱ መሆኑ ተሰምቷል:: የሕወሓት መንግስት ወታደሮች በወሰዱት እርምጃ በርካታ ሰዎች መሞታቸውና መቁሰላቸው እየተሰማ ነው::

በሰሜን ጎንደር አምባጊዮርጊስ የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ሰራዊት ህጻናትን ጨምሮ 15 ሰዎችን ገደለ |ሕዝቡ ጫካ እየገባ ነው

0
0

amhara2

amhara1
(ዘ-ሐበሻ) የሕወሓት ምክትል ሊቀመንበርና የሃገሪቱ ም/ል ጠቅላይ ሚኒስተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል አይደለም 30 ሚሊዮን ሕዝብ ይቅርና የአፍሪካን ሕዝብ የመደምሰስ አቅም ያለው የመከላከያ ሰራዊት አለን ብለው በፎከሩ ማግስት በአማራው ላይ የትግራዩ መንግስት እየፈጸመ ያለው የዘር ማጥፋት ግድያ ተባብሶ መቀጠሉ ተሰማ::

በሰሜን ጎንደር አምባጊዮርጊስ ከተማ የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ሰራዊት ህጻናትን እና ሴቶችን ጨምሮ ከ15 በላይ አማሮችን በትናትናው እና በዛሬው ዕለት መግደሉን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል::

እንደ አካባቢ ነዋሪዎቹ ገለጻ አምባ ጊዮርጊስ ከተማ በአሁኑ ወቅት በወታደሮችና በጦር መሳሪያዎች ተከባ የምትገኝ ሲሆን በርካታ ወጣቶች ጫካ ገብተዋል::

ጫካ የገቡት ወጣቶች በትግራዩ ነጻ አውጪ ሰራዊት ላይ እርምጃ ለመውሰድ ቁርጠኝነት ያላቸው ሲሆን በተቻለ መጠን የሚያስታጥቀን ኃይል እንፈልጋለን የሚሉ ጥያቄዎችንም እያሰሙ ነው::

30 ሚሊዮኑን የአማራ ሕዝብ አይደለም ድፍን የአፍሪካን ሕዝብ ለመደምሰስ አቅም አለን እየተባለ በትግራይ መሪዎች በአደባባይ መነገሩ በሃገሪቱ የብሄር ግጭት እንዳያስከትል ፍራቻን አሳድሯል:: በተለይም አቶ ደብረጽዮን እውክለዋለው የሚሉት ሕዝብ ይህን የሳቸውን አባባል ከማስተጋባት ይልቅ ማውገዝ እንዳለበትም የፖለቲካ ተንታኞች ይመክራሉ::

የደብረታቦር እስር ቤት ሲቃጠል የሚያሳይ ቪዲዮ

ኢትዮጵያ፡ #ከተቃውሞ እና #ከተጋድሎ በኋላ!? [የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ]

0
0

Obangአሰላሙ አሌይኩም፣ እንደምን አላችሁ፣ አካም ጂርቱ፣ እንደምን አረፈዳችሁ (good afternoon everyone)፡፡ የኢትዮጵውያን ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ኅብረት በዚህ ስብሰባ ላይ እንድናገር ስለ ጋበዘኝ ልባዊ ምስጋናዬን ላቀርብ እወዳለሁ፡፡[1]

ከእናንተ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ ጋር በመሆን ስለምትወዷት አገራችን የወደፊት ሁኔታ ለመወያየት መብቃት ታላቅ ዕድል ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት አገራችን በከባድ ቀውስ ውስጥ እንደምትገኝ ሁላችንም የምናውቀው ሃቅ ነው፤ ይህም ቀውስ በአንድ ጊዜ የተከሰተ ሳይሆን ለዓመታት ሲጠራቀምና ሲከማች የቆየ ነው፡፡ የአገራችን የወደፊት ሁኔታ ሁላችንንም የሚያሳስበን በመሆኑ እናንተም ይህንኑ ሃሳብ እንዳቀርብ በጠየቃችሁኝ መሠረት እኛ ኢትዮጵያውያን በኅብረት በመሥራት ለአገራችን የተሻለ የወደፊት ተስፋ ማምጣት እንዴት እንደምንችል ሃሳቤን ከዚህ እንደሚከተለው አቀርባለሁ፡፡

በቅድሚያ ጥያቄዎችን እንዳቀርብ ይፈቀድልኝ፤ ባለፉት ዓመታት ካገኘነው ውጤት በተሻለ ለወደፊቷ ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ የምናበረክተው አስተዋጽዖ ምንድነው? ባለፉት ዓመታት በተደጋጋሚ ስናካሂደው የነበረው ትግል ነጻነትና እኩልነት የሰፈነባትን ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን እንድንመሠርት ያላስቻለን ለምንድነው? ካለፉት የትግል ልምዶቻችን እንደገና እንድንቃኘው የሚያስፈልጉን የትኞቹን ነው? በለመድነውና በባህል በተቆራኘን ራሳችን ለሽንፈት በሚዳርግ መንገድ አሁንም መቀጠል ይገባናል? ወይስ የእኛ የረጅም ጊዜ ዕቅድ ውስጥ የተካተተ ባይሆንም ከሌሎች ቡድኖች በሚደርሱብን ምክንያት አጸፋ መመለሳችንን እንቀጥል? መፍትሄ ፍለጋ አውቀንም ይሁን ሳናውቅ ከመንገድ ወጥተናል? ከወጣንስ እንዴት መመለስ እንችላለን? ካልወጣን ያለምነውን ከግብ ማድረስ ለምን ተሳነን? ለችግራችን መፍትሄ እንዳናገኝ የሳትነው የት ላይ ነው?

በቅድሚያ ማወቅ የሚገባን ከዱሮ ዓመሎችንና ልምምዶችን መላቀቅ ቀላል እንደሆነ አቃልለን መመልከት የለብንም፡፡ ስለሆነም ኢትዮጵያ የእኛ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ዜጎች መብቶችና እሴቶች ክብርና እውቅና የምትሰጥ አገር እንድትሆን ካስፈለገ በመጀመሪያ ወደ ራሳችን መመልከት ይገባናል፡፡ አሁንም እየተከተልን ካለውና ካለፈው ታሪካችን ውስጥ መልካምና መጥፎ የምንላቸው የትኞቹ ናቸው? መልካም የምንላቸውን ለወደፊቱ እየጠበቅን በክፉ የተጠናወቱንን መጥፎ ባህሎችና አስተሳሰቦች እንዴት ነው የምናስወግደው? እነዚህ እያንዳንዳችን ራሳችንን ልንጠይቅ የሚገቡ ጥያቄዎች ናቸው፡፡

ዛሬና በቀጣይ ባሉት ሳምንታት፣ ወራትና ዓመታት የምናደርጋቸው ውሳኔዎች የአገራችንን የወደፊት ዕጣ ይወስናሉ፡፡ ነገር ግን አንዳንዶቻችን የምንታገለው ከመደናገጥ፣ ተስፋ ከመቁረጥ ወይም በሁኔታዎች ግፊት በመነሳሳት ነው፡፡ የዚያኑ ያህል ደግሞ በዚህ ባለንበት አገር ያለው የኑሮ ሁኔታ ወጥሮ ሲይዘን ከትግል ሃሳባችን እንደናቀፋለን፤ ሆኖም እናንተ ስለ ወደፊቱ የአገራችንና የልጆቻን ሁኔታ ያሳሰባችሁ በመሆናችሁ እዚህ ተገኝታችኋል፤ ግድ ባላችሁማ ኖሮ እዚህ ባልተገኛችሁ ነበር፡፡

ስለዚህ የወቅቱ አንገብጋቢና ቀዳሚ ጉዳይ የሚያለያዩን ነገሮች እንዳሉ ሆነው ሁላችንንም ለሚመለከተው ችግራችን መፍትሄ ለማምጣትና ነጻ፣ እኩልነት የሰፈነባት፣ ዴሞክራሲዊት ኢትዮጵያን ለመመሥረት የምንችለው እንዴት ነው? የሚለው ነው፡፡ ይህንን ማድረግ ስንችል ብቻ ነው ለሁላችንም የሚበጅ የወደፊት ማኅበራዊ መዋቅር መገንባት የምንችለው፡፡ ሆኖም አንዳንዶች ይህ አስተሳሰብ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ የተከፋፈሉ አገራት የወደፊቱን በማለም ተግባራዊ ማድረግ ይቻል ይሆን እያሉ በአግራሞት ይጠይቃሉ?

በአንድ አነስተኛ ምሳሌ ልጀምር – ከራሳችን ማለትም ከእኔ እና እናንተ ልጀምር! በኢትዮጵያ ውስጥ ሁላችንም በበርካታ መንገዶች ልዩ መሆናችን ይጎላል፡፡ ነገር ግን ዛሬ እዚህ ስብሰባ ላይ ከእናንተ ኢትዮጵውያን ሙስሊም ወገኖቼ ጋር ለመነጋገር ስመጣ በውስጤ ታላቅ ቅርበት፣ ወዳጅነትና አብሮነት እየተሰማኝ መሆኑን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ፡፡ ግን ቆም ብለን ካሰብነው ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? እንደኔ ዓይነት የቆዳው ቀለም የጠቆረ፣ በእምነቱ ክርስቲያን የሆነ፣ በሞቃታማዋ ጋምቤላ በወንዞች መካከል የተወለደ፣ ከትንሽ መንደር የመጣ፣ አኙዋክ ከተባለ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ብዛት 0.01 በመቶ የሆነ፣ የተረሳ፣ ከእናንተ የቆዳ ቀለማችሁ ፈገግ ካለ፣ ከደጋና በረሃማው የኢትዮጵያ ክልል – ከኦሮሚያ፣ ከአፋር፣ ከሶማሊና ከሌሎች ሥፍራዎች ከመጣችሁ ሙስሊም ወገኖቼ ጋር እንዴት ለመገናኘት ቻልኩ?

የሁላችንም ባህል እና አኗኗር የተለያየ ቢሆንም ዛሬ ግን በዚህ ቦታ ለእያንዳንዳችን የሚጠቅምና ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚበጅ አንድ ዓላማ ተሰባስበናል፡፡ ማናችንም ብንሆን ግን ይህንን መሰሉ ትግል ስንጀምር በዚህ መልኩ አልነበረም፤ በጊዜ ብዛት ግን ሁላችንም እየተማርን አሁን ካለንበት ደረጃ ላይ ደርሰናል፤ ልክ ነኝ አይደል?

የኔን ብነግራችሁ፤ የኔ ህይወት ፍጹም የተቀየረው ታህሳስ 3፤ 1996ዓም (December 13, 2003) በአኙዋክ ሕዝብ ላይ በደረሰው ጭፍጨፋ ምክንያት ነበር፡፡ ለሶስት ቀናት በተካሄደው ግድያ 424 የአኙዋክ መሪዎች በግፍ ተገደሉ፡፡ ግድያውን የፈጸሙት ህወሃት/ኢህአዴግ ያሰማራቸው ወታደሮች ከታጠቁ የደጋው ክፍል ሚሊሻዎች ጋር በመተባበር ነበር፡፡ የጭፍጨፋው ዋና ተልዕኮም የራሱን ዕድል በራሱ ለመወሰን ለፈለገው “የአኙዋክ ሕዝብ ትምህርት ለመስጠት” እንደሆነ በወቅቱ ተነግሯል፡፡

ሕገመንግሥት በተባለው ሰነድ ላይ ይህ መብት በግልጽ የሰፈረ ቢሆንም አኙዋክና ሌሎች የላይኛው ናይል ሸለቆ ወገኖች መሬት ከነዋሪዎቹ ጋር ምክክር ሳይደረግ ለምን ሃብታቸውና መሬታቸው ይወሰዳል ብሎ መጠየቅ ዋጋ ያስከፍላል፡፡ በዚያን ወቅት ዋንኛው ምክንያት ነዳጅ ነበር፤ ሲቀጥል ደግሞ ለም ምድር፣ የውሃ ሃብትና ማዕድናትን መዝረፍ ሆነ፡፡ ይህ መሰሉ ድርጊት በመፈጸሙ ለልማት መንገድ ለመጥረግ በሚል 16ሺህ አኙዋኮች የመኖር ኅልውናቸው ስለተጠረገ በጎረቤት ኬኒያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ዑጋንዳ ተሰድደዋል፡፡

ከ1996ዓም በፊትም በአገራችን ላይ ኢፍትሃዊነትና የሰብዓዊ መብቶች ረገጣ ይካሄድ ነበር፤ ሆኖም እውነቱን ለመናገር በዚህ ዓይነቱ ትግል ሳይሆን ጋምቤላን ለማልማት በሚል ደፋ ቀና ስል ነበር፡፡ ነገር ግን የአኙዋክ ሕዝብ በአስከፊው የህይወት መስመር ውስጥ በገባበት ጊዜ በጣም ጥቂት የሆኑ ለመርዳት እጃቸውን የዘረጉ መሆናቸውን በወቅቱ መመልከት የሚያም ክስተት ነበር፡፡ ይህ የሆነው ከምክንያቶቹ እንደ ዓቢይ ምሳሌነት ሊጠቀስ የሚገባው እኛ ከሌሎቹ ኢትዮጵውያን የተለየን በመሆናችን ነበር፡፡ እውነቱን ለመናገር እኛ ከጋምቤላ የመጣን ወይም የደቡብ ኦሞ ሸለቆ ተወላጆች የሆኑ “እንደ እውነተኛ ኢትዮጵያዊ” የምንታይ ባለመሆናችን ነው፡፡

ትግሉ በብዙ መልኩ እየተካሄደ ከቆየ በኋላ አካሄዳችንን መመርመር አለብን በሚል አንድ ጥያቄ ለራሴ ማቅረብ ጀመርኩ፡- ይኸውም “የአኙዋክ ሕዝብ ለራሱ ብቻ ፍትህና ነጻነትን መጎናጸፍ ይችላል? የሚል ነበር፡፡ በሌላ አነጋገር እንደ ኦሮሞ ባሉ በሌሎች ላይ የሚደርሰውን በምንመለከትበት ጊዜ የሚሰማን ነው፡፡

በ1997ዓም በተደረገው ምርጫ እና ከዚያ ጋር ተያይዞ በተካሄደው ማጭበርበር 197 ዜጎች በአዲስ አበባ ሲገደሉ ክስተቱ ሁላችንንም ሊያስተባብረን የሚችል ዕድል ነበር፤ ሆኖም ሳንጠቀምበት ቀረን፡፡ በዚያን ወቅት ግን እኔ ጭንቅላት ውስጥ ይደውል የነበረው በዘር ላይ፤ ያውም ደግሞ በአናሳ የዘር ድርጅት፤ የተመረኮዘ ድርጅት አቋቁሞ ፍትህን ማምጣት የሚቻለው እንዴት ነው? የሚለው ጥያቄ ነበር፡፡ በወቅቱ የቅንጅት ፓርቲ የተነሳበት ዓላማ በብዙዎች ዘንድ ታላቅ ተስፋ ተሰጥቶት የነበረ ቢሆንም ሁኔታው ከከሸፈ ከሁለት ዓመታት በኋላ የህወሃት/ኢህዴግ ሠራዊት ከጋምቤላ ወደ ሶማሌ ክልል ሲንቀሳቀስ ድምጻቸውን ያሰሙ አልነበሩም፡፡ የህወሃት ገፈት ቀማሽ የሆንነው እኛ አኙዋኮች ግን ሠራዊቱ ለምን ክልላችን ጥሎ እንደሄደ መገመት አላቃተንም ነበር፡፡ በዚህም በአንዳንድ ዓለምአቀፍ መያዶች ዘንድ “ያልተነገረው ዳርፉር” ተብሎ የሚጠቀሰውን የኦጋዴንን ዕልቂት አስከተለ፡፡

በወቅቱ በአኙዋክ የፍትሕ ምክርቤት የነበርን ከኦጋዴን ወገኖቻችን ጋር ብዙም ግንኙነት ባይኖረንም ስለ ሶማሊ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ዕልቂት፣ የሰብዓዊ መብቶች ረገጣ፣ የመንደሮች መፍረስ፣ የመሰረታዊ ልማቶች መፍረስ እና ስደት ድምጻችንን ማሰማት እንዳለብን ግድ አለን፡፡ በዚህም ምክንያት ያኔ ነበር ከእነርሱ ጋር ግንኙነት የጀመርነው፡፡ አንድ እንድንሆን የሚያመጣን ነገር ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነው ለነጻነት፣ ለፍትሕና ለአገራችን ሕዝብ ብልጽግና ለመሥራት እንደሚችሉ ተስፋ የሚሰጠን ነው፡፡ ይህ ሆኖ ሳለ እኛ ኢትዮጵያውያን ትርጉም ሊሰጥና ገቢራዊ ለውጥ ሊመጣ በሚችል መልኩ መተባበር ያልቻልነው ለምን ይሆን?

እኔ እንደማምነው ከሆነ የዚህ መልስ እኛ ኢትዮጵያውያን ተቀብለን በተግባር ላይ ያዋልናቸው ነገርግን ተዓማኒነት የሌላቸው፣ የማይጠቅሙ፣ የማይሰሩና እውነተኛ ያልሆኑ አመለካከቶቻችን ናቸው፡፡ እነዚህ አስተሳሰቦች በዚህ ዘመን የማይሰሩ ብቻ ሳይሆኑ ለጋራ ስኬታችን እንቅፋት በመሆን ክሽፈትን ያስከተሉብን ናቸው ብዬ አምናለሁ፡፡ እነዚህ እንደገና መመርመር፣ መታየትና መጠናት የሚያስፈልጋቸው ሲሆኑ ስህተት የሆኑትንና የማይጠቅሙትን ሁሉ ልናሸንፋቸው ወይም ልናስወግዳቸው የሚገቡ ናቸው፡፡

ለጋራ ስኬታችን ዕንቅፋት የሆኑብን ምክንያቶች

ለጋራ ጥቅማችንና ስኬታችን ዕንቅፋት የሆኑብን ምክንያቶች የመጡት ከየት ነው? ብለን መጠየቅ መጀመሪያው ሲሆን እንዴት ከእነዚህ ዕንቅፋቶች አልፈን በከፍታዎች ላይ በመብረር የችግራችን ዋንኛ ምክንያቶች እንዳይሆኑ ማድረግ እንችላለን የሚለው በተጓዳኝ ሊጠየቅ ይገባዋል፡፡ በቅድሚያ ሊጠቀስ የሚገባው ዕንቅፋት ክሽፈት የተሞላበት አካሄዳችን ነው፡፡ በዘር፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ አመለካከት ላይ የተመረኮዘ የተናጠል ወቅታዊ ትግል የመጀመሪያ ዕንቅፋት ነው ብዬ መጥቀስ እፈልጋለሁ፡፡

  1. የተናጠል ወቅታዊ ትግሎች፡- ይህ ማለት በአንድ ወቅት የሚነሳና የሚከስም በዘር፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካዊ አመለካከት ወይም ከአንድ ቡድን የተገነጠለ አንጃ ሃሳብ ላይ ትኩረት ያደረገ በነጠላ ሃሳብ ላይ የተመሠረተ ትግል ነው፡፡

በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያውያን ትልቁ ችግር፤ ነጻነት፣ ፍትህና ለህዝባችን ሙሉ ዴሞክራሲ እንዳያገኝ ዕንቅፋት ሆኖ ከፊታችን የተጋረጠው ነገር ሁሉን አሳታፊ ዘላቂ ትግል ከማድረግ ይልቅ የተናጠል ወቅታዊ ትግል ማድረግ ነው፡፡ ይህ በነጠላ እየተነሳን የምናደርገው ትግል በጣም የምንወደውና የተዋሃደን የትግል ስትራቴጂ ቢሆንም በታሪካችን በተደጋጋሚ የተረዳነው ግን ይህ አቀራረብና አካሄድ ፈጽሞ እንደማይሰራ ነው፡፡

የተናጠል ወቅታዊ ትግል በምናካሂድበት ጊዜ ዋንኛ ዓላማችን “የወቅቱን ፍላጎታችን” ማሳካት ነው፡፡ ይህንን እንድናደርግ የሚነሳሳን ደግሞ በወቅቱ የተከሰተ ግድያ፣ የሰብዓዊ መብቶች ረገጣ፣ ኢፍትሃዊነት፣ መሬት ነጠቃ፣ ወይም ተመሳሳይ በህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ወይም በፊት በነበሩት አገዛዞች ባደረሱት ጭቆና የሚጭረው ቅሬታ፣ ብስጭትና ንዴት ነው፡፡ ለእነዚህ ዓይነቶች ኢፍትሃዊ ተግባራት ምላሽ ስንሰጥ ሥራችንን የምናከናውነው ሌሎችን ሳንጋብዝ ወይም ሌሎች ከእኛ ጋር ሳይተባበሩ በተናጠል ነው፡፡ በመሆኑም የራሳችንን ሰልፎች፣ የራሳችንን የተቃውሞ ጥሪዎች፣ የራሳችንን ውይይቶች፣ የራሳችንን አቤቱታዎች (ፔቲሽን)፣ … በማቅረብ የራሳችንን ውሳኔዎች አሳልፈን ባላጋራችንን ለመታገል እንነሳና በራሳችን ችግር ላይ ራሳችን ጠላት ሆነን ክሽፈታችንን እንጋብዛለን፡፡

ከዚህ በፊት የተካሄዱና በዚህ ምድብ ውስጥ የሚገቡ፤ ህወሃት/ኢህአዴግ ከአነሳሱ ጀምሮ እየነጠለ ጥቃት ሲያደረገባቸው በመቆየቱ የተነሳ የራሳቸውን የተናጠል ትግል ያደረጉ እጅግ በርካታዎችን መጥቀስ ይችላል፡፡ እነዚህ በተናጠል ከተካሄዱ ወቅታዊ ትግሎች መካከል የኦሮሞ፣ የአማራ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ፣ የሲዳማ፣ የአኙዋክ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ የአፋር፣ የሶማሊ፣ የሙስሊም፣ የክርስቲያን፣ አሁን ደግሞ የኦሮሞ ተቃውሞ፣ የአማራ ተጋድሎ፣ እያለ መዘርዝሩ ይቀጥላል፡፡ እኛ ስንጠቃ ሌሎች ከእኛ ጋር አለማበራቸውንና ድጋፍ አለማሳየታቸውን ስንመለከት እንናደዳለን፣ ተስፋ እንቆርጣለን፡፡ በመሆኑም እኛም ሆንን ሌሎች ለብቻችን ተጉዘን ስኬትን ማግኘት እጅግ አስቸጋሪ ወይም የማይቻል መሆኑ እንረዳለን፡፡ በሌላ በኩል ይህ ስሜት ሌሎች ከእኛ ጋር ለመተባበር አለመፈለጋቸው ንዴት፣ መራርነትና ጥርጣሬ ውስጥ ይከትተንና ሌሎች ስለ እኛ ግድ የላቸውም ወደሚል ድምዳሜ ላይ እንድንደርስ በማድረግ የበለጠ መራርነት፣ ቂም፣ ቅሬታ፣ ቅያሜ፣ ጥርጣሬ፣ ራስን ማግለል፣ ባይተዋርነት፣ ከዚያም አልፎ “አይፈልጉንም፤ አንፈልጋቸውም” ወደሚል ጥልቅና መራር ስሜት ውስጥ ያስገባናል፡፡

  1. ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ሊጠቅም የማይችል የትግል ስልት በተደጋጋሚ የምንከተለው ለምንድን ይሆን?

ሀ. ታሪካዊ ምክንያት፡- የተለያዩ እርስበርሳቸው የተቆራኙና ሥር የሰደዱ ሁሉን አቀፍ ከሆኑ መብቶች ጋር የሚጋጩ አመለካከቶች፡፡ እነዚህም፤

  • ጎጠኝነት – አንድን ጎሣ ወይም ጎጥ ከፍ በማድረግ “አንዱ ጎሣ/ጎጥ ሁሉንም ነገር ለራሱ ማድረግ አለበት” ወይም “የመብላት ተራው የእኛ ነው” በሚል ከፋፋይነት ላይ የተመሠረተ ነው። ይህ ላለፉት አርባ ዓመታት ስናየው የኖርነው ሃቅ ሲሆን ለራሴ ጎጥ፣ መንደር፣ እና/ወይም ቤተሰብ እኔ ካልቆምኩለት ማን ይቆምለታል? የሚል አስተሳሰብና ራስንና “የራሴ” ብለን የምንጠራቸውን ለማዳን የተመሠረተ አሠራር በዚህ ውስጥ ይካተታል፡፡
    • አጸፋ/ብድር መመለስ፡- አንዱ ጎጥ ወይም ጎሣ በሌላው ላይ ብድሩን መመለስ፤ የራሴ ለሚባሉ ወገኖች፣ ለቅርብ ወዳጆች፣ ለታማኞች፣ በማድላት ጥቅማጥቅሞችን በወገንተኝነት በመነሳሳት መፈጸም የጎጠኝነት አመለካከት ነው፡፡
  • ዘውዳዊ – በዘውዳዊ አገዛዝ ሥር የነበረው የኢትዮጵያ ታሪክ በዘር፣ በቤተሰብ ትስስር፣ በደም፣ “በእገሌ ልጅነት”፣ ወይም ለመሣፍንትና ለመኳንንት ታማኝ በመሆን የተመሠረተ ነበር፡፡ ይህ ስሜት አሁን ከሞላ ጎደል መልኩን እየቀያየረ ሲንጸባረቅ ይስተዋላል፡፡
  • ፊውዳላዊነት – አንድን ቡድን ወይም ጎሣ ወይም ወገን ከሌላው የተለየ፣ የተሻለ፣ የተመረጠ፣ የበቃ፣ ወይም “ስዩመ” ስለሆነ የመግዛት/የመምራት መብት አለው፤ “ወርቃማ ዘር” ስለሆነ ትርፉንም ለራሱ የማድረግ ሥልጣን ተሰጥቶታል፤ ሌሎች ዕድለቢሶች በሥሩ የመሆን ግዴታ አለባቸው የሚል ነው። ይህ ዓይነት አስተሳሰብ የለም ብሎ የሚከራከር ሊኖር ቢችልም እውነታው ግን የፖለቲካ ሥልጣን ወይም ከሕዝብ የሚነጭ ሥልጣን ምንነትን ባልተለማመደችው አገራችን አሁንም እየታየ ያለ አስተሳሰብ ነው፡፡
  • ማርክሲስት-ሌኒንስት ኮሙኒዝም – የሚቃወሙትን ሁሉ የመርገጥ ባህርይ ያለው ሲሆን ከፊውዳላዊነት በተለየ መልኩ ማርክሲስታዊ አስተሳሰብ “ሰፊውን ሕዝብ” እየጠቀምኩ ነው ቢልም በተግባር ግን “በጭቁኑ ሕዝብ” ስም የራሱን ሥልጣን ማመቻቸት ነው፡፡ ይህ በተለምዶ “የግራው አመለካከት” እየተባለ የሚጠራው በ1960ዎቹ የአገራችንን ወጣቶች የተጣባ ርዕዮት ነው፡፡ በዚህ አመለካከት ውስጥ ለአንዱ መኖር የሌላው መጥፋት የግድ ነው የሚል ጽንፈኛ አመለካከት እንደ ሃይማኖት የሚወሰድ ነው፡፡ ደርግ “በጠላቶቻችን መቃብር ላይ …” ይል እንደነበረው አሁንም ይህ አባባል በግልጽ ሲነገር ባይሰማም በድርጊት “ለእኔ መኖር ያንተ መጥፋት የግድ ነው” የሚለው የከረረ የግራ አስተሳሰብ በሁሉም መስክ ሲንጸባረቅ ይታል፡፡
  • ሥልጣን የማግኛው መንገድ ይኼው ነው – ከሌሎች በመንጠቅ ሥልጣንን የራስ የማድረግ አካሄድ ነው፡፡ በታሪክ እንደታየው ሥልጣን ለማግኘት በተናጠል በሚደረግ ትግል አንዱን የዘር/የጎሣ ቡድን በሌሎች ላይ እንዲነግሥ በማድረግ ሌሎችን የበዪ ተመልካች ማድረግ ነው፡፡ የህወሃት/ኢህአዴግ የሥልጣን አወጣጥ ይህንን ስልት ከሌሎቹ ስልቶች ጋር ያጣመረ ሲሆን በወቅቱ የሚካሄዱት የተናጠል ትግሎችም ወደዚሁ የሚመሩ ናቸው፡፡
  • ከእናንተ ይልቅ እኛ ጭቆናን ታግለን ለድል የበቃን ስለሆነ ሥልጣን የመያዝና በሥልጣን የመቆየት እንዲሁም ምርኮን በመበዝበዝ ተጠቃሚ የመሆን ተራው የእኛ ነው፤ ይገባናል የሚል አመለካከትና አሠራር፡፡ ህወሃት የዚህ ሁነኛ ተጠቃሽ ነው፡፡ ደርግን ለመጣል ምንም እንኳን ሌሎችም አብረዋቸው የተዋጉ ቢሆንም በራሳቸው ብቃትና በብረት ሥልጣን ላይ እንደመጡ አሁንም በብረት ኃይል ሥልጣን ላይ የመቀጠል ጥማት በግልጽ ይታባቸዋል፡፡ ሥልጣን ከፈለግህ እንደ እኛ ተዋግተህ የራስህ ማድረግ ነው የሚል አስተሳሰብ በዚህ ውስጥ የሚካተት ነው፡፡

ለ. አለመተማመን፡ የራስን ዓላማ በሚፈልጉት መንገድ እያስፋፉ ሌሎችን ግን በጥርጣሬ መመልከት፤

  • በዘር ላይ በመመርኮዝ ሥልጣንን የመያዝ አባዜ፣ ክህደት፣ ክፍፍል፣ ጥቃት፣ ጉዳት፣ ቁስል፣ ክሽፈት፣ የቆዩ ቅሬታዎች ኢትዮጵያውያንን ሲከፋፍላቸው የኖረ ከመሆን አልፎ ተገቢው ቅጣት ካልተበየነ ወይም ሃብትና የዕድሉ ተጠቃሚነት ወደ እኛ ካልዞረ እነዚህ ቁርሾዎች ዕልባት ሊያገኙ አይችሉም የሚል አስተሳሰብ፤
  • አንድን መሪ፣ ወይም አንድን ጎሣ፣ ዘር ወይም ቡድን ለመጥቀም የሚደረገው አሠራር አብሮ የመሥራትንና የመተባበርን ጥረቶች ሲያመክን መቆየቱ፤ ከህወሃት/ኢህአዴግ አሠራር ያልተለየ አዲስ መሪ የሚያመጣ ነገር ግን ለውጥ አልባ አካሄድ፤
  • በኢትዮጵያውያን ዘንድ ያለው የድብቅነት፣ ምሥጢራዊነት፣ ተንኮለኝነት፣ መጠላለፍ፣ የሚናገሩትና የሚያደርጉት የመለያየት፣ የአስመሳይነት፣ የማታለልና የግብዝነት ባህርያት ግልጽነትን፣ መተማመንና ተጠያቂነት ያሳጣን በመሆኑ፤
  • በአንዳንዶች ዘንድ በግል ወይም በቡድን በሚደረጉ ትግሎች ሥልጣን የመያዝ ድብቅ ምኞቶች መኖራቸው፤ ይህም ማለት “ምንም ችግር የለም አብረን እንሥራ” በሚል አብሮ ቆይቶ በኋላ ሥልጣን ላይ የመቆናጠጥ ድብቅ ዓላማ የማስፈጸም ሁኔታ፤
  • ሌሎችን የማሳተፍ እና ወደ እነርሱ የመድረስ ፍላጎት አለመኖር፤ የመከፋፈል፣ የመለያየት፣ የማግለል፣ የመገለል እና ከሌሎች ጋር ለመነጋገር አለመፈለግ፤
  • በተቀናጀ ዓላማ፣ መርህ፣ አመራርና አጀንዳ ለመመራት አለመፈለግ፤
  • ከማንም ጋር ቢሆን አብሮ ለመሥራት ያለመፈለግና ይህንንም በጠነከረ ሁኔታ መቃወም፤ ምክንያቱም አብሮ በመሆን ሰበብ ሌላውን ለሥልጣን የማብቃት ፍርሃቻ ውስጥ መግባት፤ ወይም እኔ በታገልኩት አንተ ሥልጣን ልትይዝ የሚል አስተሳሰብ፤
  • ተመቻችቶ ከተቀመጡበት የራስ ቡድን በመውጣት ከሌሎች ጋር መሥራት ከራስ ቡድን የመገለልና የመባረር አደጋ ውስጥ የሚያስገባ በመሆኑ፤
  • ሌሎች የሚፈልጉን ለራሳቸው ዓላማ ማሳኪያ “ሊጠቀሙብን ነው” የሚል አስተሳሰብ በመያዝ በቀጣይ በእነርሱ መዳፍ ሥር በመውደቅ ለችግር እንዳረጋለን የሚል ፍርሃቻ ከዝርዝሮቹ ውስጥ በዋንኝነት የሚጠቀሱት ናቸው፡፡

ሐ. በቅድሚያ ሰብዓዊ ፍጡር ተብሎ ከመጠራት ይልቅ “የዘር/የጎሣ” መለያን እንደማንነት መታወቂያ አድርጎ ላለመተው ማንገራገር፤ የዚህ ምክንያቶች፡-

  • ከተለያዩ በርካታ ቡድኖች ድጋፍ ከማሰባሰብ ይልቅ የራሴ ከምንለው ጎሣ ወይም ቡድን የምንፈልገውን ድጋፍ ለማግኘት ቀላል በመሆኑና በተለይም ለዚህ ቡድን ልዩ መብትና ሥልጣን ለማስገኘት የምንታገል መሆናችንን በመግለጽ ተስፋ የሰጠን ከሆነ፤
  • ከቡድኑ ወይም ከጎሣው ስብስብ ውጪ የሚሆኑትን ወይም የተለየ ሃሳብ የሚይዙትን እንደ ከሃዲ በመቁጠር ማግለልና ማዋረድ ስለሚቀል፤
  • ከታሪክ አኳያ በዘር ላይ የተመሠረተ ነፍጥ የማንሳት (የአርነት ንቅናቄ) ትግልን ለመቀላቀል/ለማድረግ ቀላል በመሆኑ፤
  • ከኅብረብሔራዊ ይልቅ በጎሣ ወይም በዘር ላይ በተመረኮዘ አጀንዳ ሥር ሰዎችን ማሰባሰብ የሚቀል በመሆኑ፤
  • ኅብረብሔራዊ ከሆነው ይልቅ የራሴ በሚሉት ቡድን ተቀባይነት ለማግኘት የማይከብድ በመሆኑ፤ ቡድኑን በሚፈልጉት አቅጣጫ ለመንዳት ስለሚቀልና የመርህ ጥያቄ ስለማያስነሳ፤
  • የቀድሞ ያልተፈወሱ ቁስሎች መገለልን በመፍጠራቸው የባይተዋርነት ወይም የብቸኝነትን ሠንሠለት ለመስበር አስቸጋሪ ማድረጋቸው ከብዙ በጥቂቱ የሚጠቀሱ ምክንያቶች ናቸው፡፡

መ. በቅሬታ ወይም በክስተቶች የሚመራ ትግል ጥልቅ መሠረት ከሌለው አይዘልቅም፤

  • በአንድ ወቅት የሚፈጸም ኢፍትሓዊነት፣ ግድያ ወይም አሠቃቂ ተግባር የአጸፋ ምላሽ እንድንሰጥ የሚያስተባብረን ቢሆንም ውሱን የተናጠል ወቅታዊ ትግል ከማካሄድ ሌላ ለዘላቂ ትግል ፋይዳ የሌለው መሆኑ፤ ይህ ዓይነቱ ቅሬታ ላይ ያተኮረ ትግል በአንድ ጎሣ፣ ዘር፣ ሃይማኖት፣ ክልል፣ የፖለቲካ አመለካከት ያላቸው የተሰባሰቡበት በመሆኑ ለዚህ ቡድን ጥቅም ብቻ የሚሆን ምላሽ ከመስጠት ያለፈ ተግባር ለመፈጸም አለመቻሉ፤
  • በስሜት የሚነዳ መሆኑ፤ ይህም ደግሞ በአንድ ወቅት የሚነሳሳውን ስሜት ለረጅም ጊዜ ብርታት ኖሮት ለማስቀጠል የሚቻል ባለመሆኑ፤
  • እነዚህ በስሜት የሚነሳሱ ትግሎች ሌሎችን ወይም አብዛኛዎችን የሚያነሳሱ ባለመሆናቸው ወይም ሌሎችን በማዕቀፉ የሚይዝ ባለመሆኑ “የኔ ትግል አይደለም” ወይም “ለኔ ምን ይረባኛል?” ወይም “ለኔ ምን ፋይዳ አለው?” የሚሉ አስተሳሰቦችንና አመለካከቶችን በሌሎች ላይ የሚያመጣ በመሆኑ፤ ይህም ደግሞ እነዚህ ትግሉን ያልደገፉ ጥቃት በሚደርስባቸው ጊዜ በተራው “እኛ ስንሰቃይ ስላልረዳችሁን እኛ ስለእናንተ አያገባንም የሚል” አጸፋዊ ምላሽ የሚያስከትል በመሆኑ በዚህ ሥር ከሚጠቀሱት በርካታ ምክንያቶች የተወሰኑት ናቸው፡፡

እነዚህን መሰናክሎች ማሸነፍ የምንችለው እንዴት ነው?

ከላይ ከተጠቀሱት መሰናክሎች አኳያ እነዚህ እንቅፋት የሆኑብንን የታሪክ፣ ያለፉ ቅሬታዎችን፣ የግልና የጎሣ ግጭቶችና ምኞቶች አሸንፈን ይህንን የሽንፈት ዑደት ሰብረን የምንወጣው እንዴት ነው? የሚለው መጠየቅ ያለበት ጥያቄ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ በአገራችን ከምንጊዜውም በላይ የከፋ አደጋ ተጋርጦብናል፤ ታዲያ ምን ማድረግ ነው የሚሻለን?

  1. የተለያዩ ሰዎችን የተካተቱበት ሁሉን አሳታፊ ዘላቂ ትግል መፍጠር፤

ሀ. ሁሉን አሳታፊ ዘላቂ ትግል እንደ ባህል በህዝብ ውስጥ እንዲሰርጽ ማደፋፈር፤

  • ትግሉ የሰው ልጆችን ሕይወት፣ መብቶች እና የሁሉንም ኢትዮጵያውያን ማንነት በሚያከብር መልኩ በመርህ ላይ መመሥረት፤
  • ትግል ማለት መቃወም ብቻ አይደለም፤ ትክክለኛው ትግል ሁሉንም ኢትዮጵውያንንም የሚጠቅም መሆን መቻል አለበት – ይህ ደግሞ ተሳስተዋል የምንላቸውንም የሚጨምር ነው፤
  • እንደ አገር ችግራችን የተጀመረው ህወሃት/ኢህአዴግ በ1983 ወደ ሥልጣን ሲመጣ አይደለም፤ ወደኋላ መለስ ብለን የቀደመውን ሥርዓታችንን፣ አንዳችን በሌላችን ላይ ያለንን አመለካከታችንን፣ ወዘተ ማጥናት ያስፈልገናል፤ ይህንን በማድረግ ሌሎችን በዘር፣ በጎሣ፣ በአመለካከት፣ በሃይማኖት፣ በቆዳ ቀለም፣ በፊት መልክ፣ በቋንቋ፣ በባህል፣ ወዘተ ሳንከፋፍል ለሁሉም የሚበጅ የፍትሕ ሥርዓት፣ እኩል መብቶችና የኢኮኖሚ ጥቅማጥቅሞች፣ ነጻነትና አክብሮት ለመሥጠት የሚያስችል ሥርዓት ለመመሥረት ያስችለናል፤
  • ለሥልጣን እና የራሳችንን ልዩ መብት ለማስከበር የምናደርገው የተናጠል ወቅታዊ ትግል ጊዜውን ጠብቆ የሚከሽፍ ነው፡፡ ከላይ ለማስረዳት እንደሞከርኩት እኔ ራሴ የነበርኩበት የአኙዋክ ትግል የተናጠል ወቅታዊ የነበረ በመሆኑ ከእኛ አካባቢ ያሉት ሌሎች ነጻነታቸውን ሳይጎናጸፉ በአኙዋክ ትግል መቼም ቢሆን ነጻነትን መጎናጸፍ እንደማይቻል ግልጽ ነበር፡፡ አሁንም ያለው ሁኔታ ይኸው ነው – በተናጠል የሚደረግ ወቅታዊ ትግል የታሰበበት ለመድረስ ራሱ ችግር ውስጥ የሚከት በመሆኑ፡፡
  • የምንፈልገውን ለውጥ ሆነን መገኘት ይገባናል፡፡ ይህ ከአሁኑ የሚጀምር እንጂ ሥልጣን ላይ ተኹኖ የሚታሰብ አይደለም፡፡ ስለሆነም ለምንሻው ለውጥ ከአሁኑ ኃላፊነት ልንወስድ ይገባናል፡፡
  • ከሌሎች አገራት መማር ያስፈልገናል፤ ከሶማሊያ፣ ከሊቢያ፣ ከሶሪያ፣ ወዘተ፤ የሚገባንን ትምህርት ልናገኝና ለአገራችን በተግባር ልናውለው ያስፈልጋል፤ የእነዚህ አገራት ዜጎች ተሰባስበው ለሕዝባቸው የሚጠቅምና ሁሉንም የሚሳትፍ የላቀ አጀንዳ ይዘው በመነሳት ተግባራዊ ማድረግ ተስኗቸው የራሳቸውን ከፋፋይ ሃሳቦችና ዓላማዎች ለመተግበር በመወጠን ለአገራቸው መፍረስ ከሆኑ ምክንያቶች አንዱ ሆነው ይጠቀሳሉ፤
  • “ሌሎችም” ይገባቸዋል የሚል አስተሳሰብ በግልጽ ልናስቀምጥ ይገባናል፤ ባለፉት ጊዜያት ባብዛኛው ያለው አመለካከት የአንድን ቡድን ዓላማ ወደፊት በማድረግ አገሬን እወዳለሁ በሚል ማስመሰያ የሌሎችን መብቶች በመርገጥ የራስን ቡድን ብቻ ማበልጸግና ከፍ ማድረግ በተደጋጋሚ የከሰረና የማይሰራ መሆኑን መገንዘብ በውል ያስፈልጋል፡፡

ለ. እነዚህን የላቁ መርኾዎች የሚያስተዋውቁ ፖለቲካዊ ያልሆኑ ተቋማት ሊፈጠሩ ይገባል፤

  • ፈጣሪ ለእኛም ሆነ በቅርብና በሩቅ ለሚገኙት ወገኖቻችን የሰብዓዊነትን ክብር ሰጥቶናል፤ ይህንን ተጠቅመን በተሻለ አመለካከት ለሕዝባችን የሚረባውን ልናደርግለት ያስፈልጋል፤
  • በፖለቲካ ፓርቲዎች፣ በዘር፣ በአርነት ንቅናቄዎች፣ በሃይማኖት ድርጅቶች፣ በክልል፣ እና በሌሎች ቡድኖች የተደራጁ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚሠራ ዓላማ፣ ግብና መርኽ ሊኖራቸው ይገባል፤
  • እነዚህን መርኾዎች በሲቪክ ድርጅቶች አማካኝነት እንዴት መጠናከር እንዳለባቸው፤ ወደፊት ሊመጣ ስላለው ችግር ካሁኑ እንዴት እነዚህን መርኾዎች ማቀናበር እንደሚገባ እንዲሁም ይህንን በማድረግ በኢትዮጵያ ላይ ሊመጣ ካለው መከራ እንዴት መጠበቅ እንደሚቻል ሊመክሩበት ይገባል፤
  • እነዚህን ሁሉ በቅንብር በማካሄድ የአገራችንን የወደፊት ዕጣ እንዴት በሰላማዊ ሽግግር ለማምጣት እንደሚቻል እነዚህ ቡድኖች ሊመክሩበት የሚገባ ነው፤
  • ሁሉንም የምታስተናግድና ለሁሉም የምትሆን ኢትዮጵያ እንዴት መመሥረት እንደሚቻል በማጥናት በአገራችን ላይ ውድመትና ጥፋት እንዳይመጣ እንዴት መከላከል እንደሚቻል አስቀድሞ ሊሰራበት የሚገባ ተግባር ነው፤ ይህንንም ለመተግበር ሁሉን ዓቀፍ የሆነ ጠንካራ ተቋም – የኢትዮጵያ ጉዳዮች ተቋም (ኢጉተ) – የሚባል ካሁኑ ልንመሠርት እንችላለን (ወደፊት እንዳስፈላጊነቱ የሚቀየር ስም ነው፤ እኔ የራሴን ስም ነው የሰጠሁት)
  • ተቋም ማቋቋም እና በዚያ መስክ የተቀናጀ ሥራ መሥራት ከሚለው አኳያ የጋራ ንቅናቄያችን በቅርቡ የኢትዮጵያ የዕርቅና ርትዓዊ ፍትሕ ምክርቤት የሚባል ተቋም መሥርቷል፡፡

ሐ. በሽግግር ወቅት ተቋማት ሊኖራቸው ስለሚገባ ባህርያት፤

  • ለነጻነት፣ ለፍትሕ፣ ለደኅንነት፣ ለመብቶች መከበር እና ሁሉም ኢትዮጵያዊ – ትግሬዎችንም ጨምሮ – በሁሉም ክልል በሰላም በሚኖርበት ሁኔታ ላይ መሥራት፤
  • የአገር ውስጥ ልዕልና እንዲከበርና ይህም በመርህ ላይ የተመሠረተ እንዲሆን በማድረግ መበታተንና መከፋፈል እንዳይኖር ማድረግ፤
  • ለሁሉም ሰው ደኅንነት መሥጠት – የሁሉም ሰው ህይወት እንዲከበርና በማንም ሰው ላይ አንዳች አደጋ ወይም ጉዳት እንዲደርስ አለመፍቀድ፤ ይህ ደግሞ በተለይ በዘር ላይ የተመረኮዘ አደጋና ደም መፋሰስ እንዳይኖር ማድረግን ይጠቀልላል፤
  • በሽግግሩ ወቅት ለኢፍትሃዊነት ማብቂያ ማድረግ፤ የሕግ የበላይነትን ማክበር፤ ይህንንም በማድረግ ትርጉም ያለው ተሃድሶ እንዲመጣ ማድረግና ይህም ደግሞ አድልዖ በሌለበት መልኩ ርትዓዊ ፍትህ በዕርቅ እንዲመጣ መሥራት፤
  • ጠንካራ እና ገለልተኛ ድርጅቶች የሚኖሩ ከሆነ አገሪቱን ከመፈራረስ የሚታደጉ በመሆናቸው ብሶት ያለባቸው ወገኖች በግጭት፣ በዓመጽ ወይም በሌላ አገር ጠለላ በማግኘት መፍትሄ ከሚሹ ይልቅ በሰላማዊ መንገድ መፍትሔ የሚገኝበትን መንገድ መፈለግ፤ ማመቻቸት፤
  • በአገሪቷ ውስጥ በተንሰራፋው ሥር የሰደደ ጥላቻ ምክንያት ፍትሕ እንዳይጓደል ተቋማት መብቶች እንዲከበሩ እና የሕዝቡ ልዕልና እንዲከበር የማድረግ ሚና እንዲጫወቱ፤

በቅርባችን ያለችውን ሊቢያ ብንመለከት በተቃዋሚነት የተነሱት ኃይላት ለሕዝባቸው የሚጠቅም በመርህ ላይ የተመሠረተ ራዕይ ሊኖራቸው ባለመቻሉ፤ ለሁሉም የሚቆም ተቋም ባለመመሥረቱ አገራቸው ከሸፈች፡፡ በሶሪያም ዜጎች በትናንሽ ቡድኖች በመከፋፈላቸውና የጋራ ዓላማና ራዕይ ሳይኖራቸው በመቅረቱ በሚያሳዝን ሁኔታ አገራቸው ክፍቷን እየቀረች ነው፡፡

የኢትዮጵያ የዕርቅና ርትዓዊ ፍትህ ምክርቤትን ማቋቋም ለምን አስፈለገ?

በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲኖርና የወደፊቱ የአገራችን ሁኔታ ተስፋ ያለው እንዲሆን አንዱና ብቸኛ አማራጭ ዕርቅና ርትዓዊ ፍትሕ ማስፈን ስንችል ነው፡፡ ይህ ማለት ያለፉትን፣ አሁን ያሉትን እና ወደፊት ሊነሱ የሚችሉትን የበርካታ ዓመታት ጥርቅም ብሶቶች የምናመክንበትና ትርጉም ያለው ተሃድሶ ማድረግንም የሚጨምር ነው፡፡ ላለፉት መቶዎች ዓመታት እርስበርስ በተፈጠሩት ቁርቋሶዎች፣ ስህተቶች፣ በደሎች፣ … የተከሰተው የኅሊና ወቀሳ፣ ሃዘን፣ ቁስል፣ ህመም፣ መራርነት፣ … ይህንን ተከትሎ በማያቋርጥ አዙሪት ውስጥ እንድንገባ ያደረገንን ያለፈውን ህመማችን ሁሉ ወደ ዕርቅና ፈውስ መምጣት አለበት፡፡ እጅግ አሰቃቂ ነገሮች የደረሱብን ነን፤ በዚህም ምክንያት በአንድ ወቅት አሳዳጅ የነበረው ጊዜ ጠብቆ ተሳዳጅ ይሆናል፤ ይህ የማያቋርጥ የበዳይና የተበዳይ ዑደት አልለቅ ብሎን ዘመናትን አስቆጥረናል፡፡

ከዚህ ግን መውጣት የምንችልበት አማራጭ መንገድ አለ፡፡ በአገራችን የሕግ የበላይነትን ተለማምደን የምናውቅበት ዘመን ባለመኖሩ ብሶቶቻችን መፍትሔ ሳያገኙ እዚህ ደርሰናል፡፡ ባለፉት ዘመናት የተከሰቱትን እያንዳንዱን ስህተቶች ወደኋላ ሄዶ ለማስተካከል አይቻልም፤ ነገር ግን ለወደፊቱ ህይወታችን አዲስ ራዕይ ከፈጠርን ይህን ያለፈውን ታሪካችንን በአንድ ምዕራፍ ዘግተን የወደፊቱን በአንድነት መጓዝ እንችላለን፡፡ ይህንን እናደርጋለን የምንል ከሆነ ያለፈው ታሪካችን አስተማሪያችን ሊሆነን ይገባል እንጂ የወደፊቱን የሚወስንልን አድርገን በመውሰድ በመንገዳችን ላይ ዕንቅፋት አድርገን ፍትሕ፣ የሕግ የበላይነትና የበለጸገች ኢትዮጵያን እንዳናይ ሊጋርደን አይገባም፡፡ እንግዲህ እነዚህ መሠረታዊ እሳቤዎች ከላይ በተጠቀሰው በምክርቤቱ ተልዕኮ ውስጥ የተካተቱ ናቸው፡፡

የተናጠል ትግል የሚያደርጉ ግፍን በሚታገሉ ጊዜ የራሳቸውን የአርነት ንቅናቄ መፍጠር አማራጭ ያለው መፍትሄ አድርገው ይወስዳሉ፡፡ በ1960ዎቹ የተጀመረው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ የሁሉንም ኢትዮጵያውያን ጥያቄ መልስ ማስገኘት ቀዳሚ ዓላማው አድርጎ መቀጠል ነበረበት፡፡ ይህ ግን ሳይሆን ቀረ፡፡ ከዚያ ኪሣራ በኋላ ያየነው ነገር ቢኖር በየቦታው የራስን ወገን ነጻ ለማውጣትና ከኢትዮጵያ ለመገንጠል በየክልሉ የተነሱ የአርነት ንቅናቄዎችን ነው፡፡ ሁሉም ለነጻነት እታገላለሁ በማለት የራሱን የአርነት ንቅናቄ ዓላማ ማስተጋባት ጀመረየኦሮሞ ነጻነት ግምባር (ኦነግ)፤ የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጪ ግምባር (ኦብነግ)፤ የቤንሻንጉል ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ቤሕነግ)፤ የጋምቤላ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ጋሕነግ)፤ የሲዳማ ብሔራዊ ነጻ አውጪ ግምባር (ሲብነግ)፤ የአፋር አብዮታዊ ዴሞክራሲዊ አንድነት ግምባር (አርዱፍ) ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

መብቶችን መጣስ የሚያስከትለውን ውጤት ለመረዳት ከዚህ በላይ የተጠቀሱትንና ሌሎች ድርጅቶች ባህርይ ማጥናት ምላሽ የሚሰጥ ነው፡፡ ይህ ግን በራሱ ለችግሮች ዘላቂ ምላሽ የሚሰጥ ሳይሆን ይበልጡኑ ችግሮችን እያሰፋ የሚሄድና ስህተትን እየደገምን እንድንሄድ የሚያደርገን አካሄድ ነው፡፡ በሥልጣን ላይ የሚቀመጠው ማንም ይሁን ሥርዓቱን የሚገዳደር ጠንካራ ተቋም መመሥረት ነው እንጂ የሚያሻው ሌላ አካሄድ የሚፈይደው አንዳች ነገር የለም፡፡ አለመታደል ሆኖ ይህ አመለካከት አሁንም ህወሃትን እንታገላለን በሚሉ አንዳንዶች ዘንድ ያልተለወጠ አመለካከት ነው፡፡

ከሁለት ዓመት በፊት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ህወሃት/ኢህአዴግን በሃይማኖታቸው ውስጥ ጣልቃ መግባቱን ተቃውመው በሰላማዊ መንገድ መታገል ጀመሩ፡፡ እናንተ እዚህ ስብሰባ ላይ ያላችሁ እንደምታውቁት እናንተም ሆነ አገር ቤት ያሉት የታገሉት ለአንድ ቀን፣ ለአንድ ሳምንት፣ ለአንድ ወር ወይም ለአንድ ዓመት ሳይሆን አገዛዙ አመራሮቻችሁን ሰንጥቆ በመግባት ዓላማውን ለማሳካት እስከቻለበት ጊዜ ድረስ ለሁለት ዓመታት ነው የታገላችሁት፡፡ ብዙዎች እስርቤት ገቡ ከእነርሱም መካከል እስካሁን ያልተፈቱ አሉ፡፡ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ትግል ስኬት ሊያገን ያልቻለው ሌሎች በደል በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ የደረሰባቸው ኢትዮጵያውያን – ኦሮሞዎች፣ አማራዎች፣ ሶማሊዎች፣ ወዘተ ትግሉን ሊቀላቀሉ ባለመቻላቸው ነው፡፡ ነገርግን በእናንተው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ውስጥ ከሁሉም ኢትዮጵያ ዘር፣ ጾታ፣ ዕድሜ ክልል፣ የቆዳ ቀለም፣ ክልል፣ ቋንቋ፣ በአንድ ጥላ ሥር የተሰባሰቡ ነበሩ፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ይኸው ዓይነት ስብጥር በኢትዮጵያውያን ኦርቶዶክስም ይሁን ፕሮቴስታንቶች መካከል አለ፡፡ ውጤቱ ግን እንደምናየው ሆነ!

አሁን አንድ ዓመት ሊሞላው የተቃረበው የኦሮሞ ትግል እየተካሄደ ነው፤ የአማራው ተጋድሎም እንዲሁ እየተቀጣጠለ ነው፡፡ ኢትዮጵያውን ሙስሊሞችም ሆኑ ኦሮሞዎች፣ አማራዎች፣ … የሚጠይቁት አንድ ትልቅ ጥያቄ ለውድቀት ሳንዳረግ ተባብረን መቆም የምንችለው እንዴት ነው? የሚለው ነው፡፡ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ እንዳየነው የዚህች አገር ችግር በተናጠል ትግል የሚፈታ አይደለም፡፡ ሁላችንም አብረን ነጻ ካልወጣን ማንም ብቻውን ነጻ መሆን አይችልም!

ትልቁ ጥያቄ – አሁን የምንታገለውን ሥርዓት ማፍረስ የምንፈልገው ይህንኑ በሚመስል ሌላ ሥርዓት ለመለወጥ ነው? በተናጠል ወቅታዊ ትግል የምናደርግ ከሆነ ውጤቱ ከዚህ የተለየ ሊሆን አይችልም፡፡ የአገራችንም ሁኔታ ባክኖ ይቀራል፡፡ መባከን ማለት አንድ ታላቅ ዋጋ ያለው ነገር እንደሚገባው ባለመጠቀማችን ምክንያት ዋጋው ከንቱ ሲሆንና ጥቅሙ ባክኖ ሲገኝ ነው፡፡ ይህ የእኛ ሁኔታ ሲሆን በተደጋጋሚ ታይቷል፡፡ ዓቅማችንና ዕድሎቻችንን በተደጋጋሚ ስናባክን ኖረናል፡፡

በኢትዮጵያ ያለን የተፈጥሮ፣ የውሃ፣ የማዕድናት፣ ወዘተ ሃብት ብቻ ሳይሆን የሰውም ሃብት ነው ያለን፡፡ በጋምቤላ ስላለው የሺያ ዛፍ ሳስብ ብዙ ነገር ወደ አእምሮዬ ይመጣል፡፡ ይህ ዛፍ እጅግ በርካታ ለሆኑ ጥቅሞች በዓለም ዙሪያ መዋል ሲችል አለአግባብ እየተጨፈጨፈ ይገኛል፡፡ ይህንን ደግሞ ለመተካት በርካታ ዓስርተ ዓመታትን ይወሰዳል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ እስቲ ስለ ወጣቶቻችን እናስብ፡፡ ስንቶቹ በድህነት፣ በዓመጽ፣ በመብት ገፈፋ፣ በህክምና ዕጦት፣ … ገና በጨቅላ ዕድሜቸው እየተቀጡ ይሆን?! ስንቶቹስ የህይወታቸውን መስመር ለማስተካከል ብለው እንደወጡ ቀርተዋል? ስንቶቹስ የአልጋ ቁራኛ ሆነዋል? እጅግ በጣም ብዙ! ስለዚህ ፈጣሪ የሰጠንን መርኾዎችን በመከተል ይህንን መከራ ማስቆም፤ አሁን ያለን ዕድል እንዳያመልጠን፤ እንዳይባክንብን አጥብቀን ልንሰራ ይገባናል፡፡

በታሪክ እንደምንመለከተው ኢትዮጵያውያን እርስበርሳቸው አንዱ የሌላው መጥፊያ ምክንያት ሲሆኑ አይታይም፡፡ እናንተ ሙስሊም ሆናችሁ እዚህ እኔ አንድ ክርስቲያን ለእናንተ እንድናገር ማድረጋችሁ ሁላችንም ለአገራችን የምንመኘውና እርስበርሳችን የምንካፈለው እሴቶች በመኖራቸው ነው፡፡ በእናንተ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች እምነት ውስጥ ህወሃት/ኢህአዴግ ጣልቃ በመግባት ሰላማችሁን በነሳችሁ ጊዜ የጋራ ንቅናቄያችን በጉዳዩ ላይ በተደጋጋሚ የተናገረው ብዙ የምንገናኝባቸውና የተሳሰርንባቸው ምክንያቶች ስላሉ ነበር፡፡ ይህ አንድ መሠረታዊ ተግባር በመሆኑ ነው እናንተ ሙስሊሞችም በሰሜኑ የአገራችን ክፍሎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ገዳማት በወደሙበት ጊዜ ድርጊቱን ያወገዛችሁት በነጻ ማኅበረሰብ ውስጥ የሚኖር ሰው የሚያደርገውን ትክክለኛ ተግባር በመከተል ነው፡፡

አቅጣጫችንን ለመቀየር ከየትና እንዴት እንጀምር?

  1. በምንስማማባቸው ጉዳዮች ላይ የጋራ ራዕይ መቅረጽ፤ ስኬትን የምንሻ ከሆነ ለማግኘት የምንፈልገው ዋናው ነገር ምን እንደሆነ በቅድሚያ ልናውቅ ይገባናል፡፡ ይህንን ካስቀመጥን በኋላ አንድ የጋራ ራዕይ መቅረጽ ወደሚያስችለን ደረጃ ላይ እንደርሳለን፡፡ ይህ ራዕይ ሁላችንንም የራሴ ብለን በምንወስዳቸው እሴቶች ዙሪያ እና የሁሉንም ጥቅም ሊያስከብር በሚችል መሠረት ላይ ሊገነባ ይገባዋል፡፡ ወደ ሌሎች የተለያዩ አጀንዳዎች ከመገባቱ በፊት ይህ ራዕይ በቅድሚያ ተቀምጦ የሁሉንም አዎንታ ማግኘት አለበት፡፡
  • የጋራ ራዕይ፡ ማንኛውንም ችግር፣ ለዘመናት የተጠራቀመ ቅሬታ፣ አለመግባባት፣ … ለመፍታት ከመጀመራችን በፊት የጋራ ራዕይ በቅድሚያ ያስፈልገናል፡፡ የጋራ ራዕይ በስምምነት ከነደፍን በዚያ ላይ ተመርኩዘን ሁሉንም ችግሮች ወደ ስምምነት በሚያመጣ መልኩ መፍትሔ ልንሰጣቸው እንችላለን፡፡
  • ራዕያችን በስሜት ሳይሆን በመርህ ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት፤ ለምሳሌ አንዱ መርህ “ከጎሣ በፊት ሰብዓዊነት ይቅደም” የሚለው ሊሆን ይችላል፤ ወይም “ሁላችንም ነጻ ካልወጣን ማንም ብቻውን ነጻ ሊሆን አይችልም” በሚል መርህ ለሌሎች ነጻነት ግድ ማለት፡፡
  • ይህንን የጋራ ራዕይ ለመንደፍ በሁሉም ባለጉዳዮች ዘንድ ውይይት እንዲኖር ማድረግ፤ ሁሉንም የሚያካትት ራዕይ ለመቅረጽ እንዲቻል፣ ሁሉንም የሚጠቅም የፍትሕ ሥርዓት ለመዘርጋትና ነጻነት ለማምጣት የአገራችን ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ሁሉ ተገናኝተው መወያየት፣ መነጋገር ይገባቸዋል፡፡
  1. በኢትዮጵያ ደም መፋሰስ እንዳከሰትና አገሪቷ እንዳትከፋፈል በኅብረት መሥራት፤
  • በህወሃት/ኢህአዴግ ውስጥ ያሉትንም ጨምሮ የማንም ኢትዮጵያዊ ህይወት አደጋ ላይ እንዳይወድቅ ከለላ ማድረግ፤ ቃል መግባት፡፡
  • የጋራ ራዕይ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ጠቅሞ በሰው ህይወት፣ በንብረት ወይም በማንኛውም መዋዕለንዋይ ላይ ጥቃት እንዳይኖር በማድረግ ኢትዮጵያ ቀጣይ ሊቢያ ወይም ሶሪያ እንዳትሆን መታደግ፡፡
  1. የሽግግር መንግሥት ማቋቋም፤
  • ፓርቲዎች፣ የተለያዩ መሪዎች፣ ባለጉዳዮች፣ ለመርህ የሚገዙና የጋራ ራዕዩን የሚያከብሩ ኃላፊዎች የተካተቱበት የሽግግር መንግሥት ማቋቋም፤
  • ርትዓዊ ፍትሕና እውነተኛ ተሃድሶ በትብብር ማከናወን፤
  • ያለፉ ዘመናት ብሶቶችን፣ ምሬቶችን፣ የራስን ዕድል የመወሰን መብት፣ የመሬት ባለቤትነት፣ የሃብት አጠቃቀም፣ እና ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ሌሎች ክልሎችን፣ አካባቢዎችን በተመለከተ ተራ በተራ ውሳኔ ላይ መድረስ፤
  • ለሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የፖለቲካ ምህዳሩን ክፍት ማድረግ፤
  • የዕርቅ ሒደትን ማስጀመር፣ ማዳበርና ተግባራዊ ማድረግ፤

ይህንን ዓይነት የጋራ ራዕይ መንደፍ ከቻልንና ሁሉንም ሊያስተባብር ወደሚችል ተቀባይነት ያለው መርህ ላይ እኛ ኢትዮጵያውያን መድረስ ከቻልን የሌሎችን ክብር፣ ማንነትና እሴት የምታከብር የሁላችንም የምትሆን አዲስ ኢትዮጵያን መመሥረት እንችላለን፡፡ የጋራ ንቅናቄያችን ከዚህ በፊት ሲያደርግ እንደኖረው አሁንም ለዚህ መሳካት የሚጠበቅበትን ሁሉ ለማድረግ እና ከሁሉም ወገኖች ጋር ለመሥራት፤ ሁሉንም ወገኖች ወደ ውይይት ለማምጣት ያለውን ፍላጎትና ፈቃደኛነት በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡ ሁላችንም ለእያንዳንዳችን፤ እያንዳንዳችንም ለሁላችን መቆም አለብን፡፡

ስለዚህ “የወንድሜ ጠባቂ ማነው?” የሚለውን ዘመናት ያስቆጠረው ጥያቄ ሲጠየቅ እያንዳንዳችን ኢትዮጵያውያን በዘር፣ በጎሣ፣ በቆዳ ቀለም፣ በሃይማኖት፣ በቋንቋ፣ በፖለቲካ አመለካከት፣ በመልከዓምድር፣ በእውቀት፣ ወይም በማንኛውም መስፈርት ሳንከፋፈል “የወንድሜ ጠባቂ እኔ ነኝ፤ እኔን ያገባኛል” ማለት መቻል አለብን፡፡

ይህን ለማድረግና እያንዳንዳችን በትክክለኛው የአንድነት፣ የፍትህና የነጻነት መንገድ ለመጓዝ እንድንችል ፈጣሪ ይርዳን!

አክባሪያችሁና ወንድማችሁ

ኦባንግ ሜቶ

 

የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር

[1] አቶ ኦባንግ ይህንን ጽሁፍ በንግግር ያቀረቡት ሐምሌ 9፤2008 (July 16, 2016) የኢትዮጵውያን ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ኅብረት በተጠራው ስብሰባ ላይ ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ በአገራችን ፖለቲካ ከተከሰተው ለውጥ አኳያ በጽሁፉ ላይ መጠነኛ ለውጦች ተደርገዋል፡፡

የደቡብ ጎንደር ዞን ፖሊስና ጸጥታ 92 የሥርዓቱ አገልጋዮችን ለይቶ ይፋ አደረገ

0
0

ከሙሉቀን ተስፋው
በደብረታቦርና አካባቢው የወያኔ አባልና ቅጥረኛ የሆኑ የዐማራውን ሕዝብ የሚያስፈጁ 92 ሰዎች የደበብ ጎንደር ዞን ፓሊስና ጸጥታ መዋቅር ከሕዝብ ጋር በመተባበር ለይቷል። ሕዝቡም ወረቀት አባዝቶ እያሰራጨ ነው። ሥም ዝርዝራቸው ቀጥሎ ቀርቧል።
ይህ በዚህ እንዳለ የማረሚያ ቤቱ በአራቱም አቅጣጫ እየተቃጠለ ሲሆን የከባድ መሣርያ በቃጠሎው ውስጥ ባሉ ታሳሪዎች ላይ እየዘነበ ነው።
የደብረታቦር ዩንቨርሲቲ የክረምት ተማሪዎች ወገኖቻችን እያለቁ አንማርም ብለው ዛሬ ጠዋት ግቢውን ለቀው ወጥተዋል።

 

14202584_1176086612463543_1909228206327054391_n

 

 

 

 


ህዝባዊዉን ተጋድሎ እንዴት እና መቼ መቀላቀል እችላለሁ? በተጋድሎዉ ሂደትስ ዉስጥ ምን ማበርከት እችላለሁ? –ሸንቁጥ አየለ

0
0

 

UNIty - satenaw 9ይሄ ጥያቄ የብዙ ሰዉ ጥያቄ ነዉ:: ህዝባዊዉን ተጋድሎ እንዴት እና መቼ መቀላቀል እችላለሁ? በተጋድሎዉ ሂደትስ ዉስጥ ምን ማበርከት እችላለሁ? የሚለዉ ጥያቄ የብዙ ኢትዮጵያዉያን ጥያቄ እየሆነ ነዉ::

ተጋድሎዉን ስለመቀላቀል ከማሰብ በፊት መጀመሪያ ተጋድሎዉ ለምን አስፈለገ የሚለዉን ጥያቄ መመለስ ይገባል::

እያንዳንዱ ህዝብ የተጋድሎ ዘመን አለዉ::ለኢትዮጵያዉያን ይህ የተጋድሎ ዘመን ነዉ::ተጋድሎዉ ከመንፈስ ልዕልና በላይ የህዝብን ህልዉና የማስጠበቅ ተልዕኮ አንግቧል::ተጋድሎዉ ህዝብን ነጻነቱን ከቀሙት: ዘረኛ ህሊና ቀፍዶ ከያዛቸዉ እና በባርነት አስተሳሰብ ከተቃኙ ዘረኞች እና እብሪተኞች ነጻ የማዉጣት ረዥም ጉዞን ሰንቋል:: ተጋድሎዉ የዲሞክራሲ: የሰባዊነት: የእኩልነት ብሎም የሁል አቀፍ ብልጽግና መሰረቱን የተነጠቀ ህዝብን ነጻ ስለማዉጣት ነዉ:: ተጋድሎዉ የአንድ ሰሞን እሩጫ አይደልም:: ህዝባዉያን አይደክሙም::ህዝብም እንደ ዉቃያኖስ ጥልቅና ሰፊ ነዉ::ተጋድሎዉ ትናንት አልተጀመረውም::ከሳምንት በፊት ወይም ካመት በፊት አልተጀመረም:: ተቃዉሞዉ ወያኔ መንበሩን ጨብጦ ዘረኝነትን: ኢፍትሃዉነትን: ኢ-ዲሞክራሲያዊነትን: ወገንተኝነትን ማስፈን ሲጀምር የተጀመረ ነዉ::ምናልባትም በብዙ መቶ ሽህ ሰዎች የተሰዉለት ተጋድሎ ነዉ:: ሌሎች በብዙ አስር ሽህዎች አሁንም በሰር ቤት የሚማቅቁለት ነዉ::ሌሎች ሽህ ዎች ደግሞ እየተሳደዱ መስዋ ዕተነት እየከፈሉት ያለ ታላቅ ሰበአዊ ተል ዕኮን ያነገበ ነዉ:: ተጋድሎዉ ዛሬ ኢትዮጵያዉያን አለም ከደረሰበት የሰበአዊነት: የዲሞክራሲ እና የሁል አቀፍ ብልጽግና ይቋደሱ ዘንድ ለማስቻል የማይታጠፍ የህዝብ ምኞትን የሰነቀ ይሄንንም እዉን ለማድረግ ያልተቆጠበ ህዝባዊ መስዋዕትነትን የተንተራሰ ነዉ::

እና አንተ የዚህ የተጋድሎ አካል ለመሆን ምን ቅድመ ሁኔታ ያስፈልግሃል? ድርጅት? ጓደኛ? ዘመድ? ገንዘብ? የተለዬ እዉቀት? የተለዬ ትምህረት? የተለዬ ወኔ?

ድርጅት ግድ አይደለም:: ምክንያቱም ያዉ እንደምታስተዉለዉ በኦሮሚያ የተጀመረዉ ተቃዉሞ ህዝቡ እራሱ ነዉ ያለ ድርጅት የመራዉ:: ህዉሀትንም አፍንጫዉን ይዞ የህዝብን ጥያቄ ተቀበልኩ እሲኪል ያስለፈለፈዉ:: ወያኔን ምጥ እና ጭንቅ ያስያዘዉ የአማራ ተጋድሎም ያለ ድርጅት እና ያለ መሪ በህዝብ ቀጥተኛ አመራር ነዉ እየቀጠለ ያለዉ:: ምናልባት ስለ ተጋድሎ ለመነጋገር የቅርብ የምትላቸዉን ሰዎች ስትጠይቅ አርፈህ ተቀመጥ ሊሉህ ይችላሉ:: ወገኖችህ እና ዘመዶችህ ገና ነገሩ አልገባቸዉ ሆኖ ያንተዉ ተቃዋሚ ሊሆኑም ይችላሉ::አንተንም እንደሞኝ ሊያዩህ ይችላሉ::ወይም ፈርተዉ ሊያስፈሩህ ይችላሉ::

እና ምን ያስፈልግሃል? እንዴትስ ተጋድሎዉን መቀላቀል ትችላለህ? እዉቀትና ገንዘብ የተጋድሎ ትራስም መሰረትም ሊሆኑ አይችሉም::የያዛቸዉ ሰዉ ሊጠቀምባቸዉ ፈቃደኛ እስካልሆነ ድረስ እንዴዉም የሰበብ እና የፍርሃት ምንጭ ናቸዉ:: ለህዝባዊ ተጋድሎ የተለዬ ወኔ እና ጀብደኝነት አያስፈልግም::ህዝባዊ መሆን በራሱ በቂ ነዉ::

እና ምንድን ነዉ ሚስጥሩ?

ተጋድሎዉ መንፈሳዊነት እና ልባዊነት ነዉ::ተጋድሎዉ ገንዘብ ያለዉ ሰዉ ገንዘቡን ለመስጠት እና ወገኑን ነጻ ለማዉጣት ሲወስን ነዉ::ተጋድሎ በሀሳብ ነዉ:: ተጋድሎዉ እዉቀት ያለዉ ሰዉ እዉቀቱን ስለወገኑ ነጻነት ወደ ስራ ላይ ሲተረጉመዉ ነዉ:: ተጋድሎዉ በአካልም ነዉ::ተጋድሎዉ ከሁሉም በፊት ያገባኛል ከሚለዉ አስተሳሰብ ጋር መጋባት ነዉ::

ተጋድሎዉ በጣም ቀላል ከሆነ ግን እጅግ ምጡቅ ከሆነ መሰረት ላይ ይጀምራል::ከመንፈሳዊነት:: አይሁዳዉያን በዘር ፍጅት ዘመናቸዉ አንድ ድንቅ እና ዉብ የተጋድሎ መርህ ነበራቸዉ::መንፈሳዊ ተጋድሎ::በጸሎት መጋደል ይቻላል::ስለህዝብህ ወደ አምላክህ ጠዋት ማታ በመጸለይ መጋደል ይቻላል;;ሚኒስቴሩ አጠገብ ሆነህ ስለሚያስተላልፈዉ የተሳሳተ ዉሳኔ በልብህ በመራገም እና በዉስጥህ እንቢተኝነትን በመኮትኮት ብሎም በማበልጸግ መጋደል ይቻላል::ቤተክርስቲያን ዉስጥ ስለ ህዝብህ ድምጽህን ከፍ አድርገህ ከወንድሞችህ ጋር በመጸለይ መጋደል ይቻላል::

አይሁዳዉያን ልጃገረዶች የናዚ ባለስልጣናት አለፈቃዳቸዉ ሊደፍሯቸዉ ሲሞክሩ የወንዶቹን ብልት መተዉ እራሳቸዉን የሚያጠፉ እንደነበሩ ታሪክ ይዘግባል:: ተጋድሎው ወሰን እና ልክ የለዉም::ህንዳዉያን የእንግሊዝን ቅኝ አገዛዝ በመቃወም ልዩ ልዩ የተጋድሎ ስልቶችን ሲከተሉ ነበር:; አንዱ እና የሚያስቅ ግን የሚያስገርም ተጋድሏቸዉ ታዲያ እንግሊዝ ባለስልጣናት ቢሮ ከገቡ ብኋላ እንግሊዛዉያን ባለስልጣናት ላይ ፈሳቸዉን ፈስተዉባቸዉ ይወጡ ነበር:: የእንግሊዝ ባለስልጣናት ናላቸዉ እስኪዞር: ወኔያቸዉ እስኪብረከረክ እና የሚያደርጉትን እሲያጡ ድረስ ይቅበጠበጡ ነበር::በህንዳዉያን የፈስ ተጋድሎ:: በ2002 የተመረጡት የህንድ ጠቅላይ ሚኒስቴር ይሄን እዉነታ እና የህንዶችን የነጻነት ተጋድሎ በዋዛ እያሳሳቁ ብዙ ተናግረዉበታል::

መስሪያ ቤት ዉስጥ የሚሰሩ አሻጥሮችን እና ኢፍትሃዊነቶችን ተደብቀህ በማጋለጥ መጋደል ይቻላል::ማህበራዊ ሚዲያዉ ላይ የተደበቁ ወንጀሎችን እና ግፎችን በብዕር ስም በማጋለጥ ተጋድሎዉን መቀላቀል ይቻላል:: ለአንድ ወገንህ ጥቂት የተጋድሎ ምክር በመለገስ እና መንፈሱን ከፍ በማድረግ መጋደል ይቻላል:: ከምትበላዉ ምግብ ላይ ቀንሰህ እና ገንዘብ አጠራቅመህ ለአንድ እስር ቤት ለተወረወረ የተጋድሎ ጀግና የተቃዋሚ መሪ/አባል/ ወይም ጋዜጠኛ አንድ ነገር ይዘህ በመሄድ ተጋድሎዉን በዉስጥህ ማቀጣጠል ትችላለህ::የመጀመሪያዉ ትግል ከራስህ ጋር ነዉ:: እራስህን ስታሸንፍ ታጋይ ሆነህ ትወጣለህ::

የት ነዉ የምትኖረዉ? ስራህ ምንድን ነዉ? ምሁር ነህ ወይስ ጨዋ? ፖለቲከኛ ነህ ወይስ መንፈሳዊ ? ሴት ነህ ወይስ ወንድ? ወጣት ነህ ወይስ ሽማግሌ ? ቆንጆ ነሽ ወይስ ፉንጋ? አርቲስት ነህ ወይስ አርሶ አደር? ጋዜጠኛ ነህ ወይስ ፖሊስ? የትም መሆን ይቻላል::ምንም መሆን ይቻላል::ስለ ነጻነት:ፍትህ: እኩልነት እና ዲሞክራሲ ለመዘመር እና ለመጋደል ግን ሰዉ መሆን በቂ ነዉ::

ወያኔዎች ለምሳሌ ዉጭ ያለዉ ኢትዮጵያን ከተቃዉሞ እና ከተጋድሎ ጉራዉ እንዳይገቡባቸዉ ብዙ ጥረት ያደርጋሉ:: ምንም እንኳን አሜሪካ እና አዉሮፓ ተቀምጦ ስንቱ ስለተቃዉሞ እና ተቃዋሚ ሲነሳበት እንደሚንቀጠቀጥ በደንብ ቢያዉቁም ዉጭ ሀገር ተቀምጦ ጸረ ወያኔ ተጋድሎዉን መቀላቀል እንደ ፈሪነት እንዲቆጠር በደላሎቻቸዉ እና የተጋድሎ ሚስጢር ባልገባቸዉ የዋሆች ያስወራሉ:: ሆዱን ተሞላ እና መኪና ከቀየረ ብሎም ዲግሪ ካንጠለጠለ ወገናዊነት እና ህዝባዊነትን የሚረሳዉ ዲያስፖራ እንደሚበዛ ወያኔዎች ያዉቃሉ:: ይሄን የብዙ ዲያስፖራዎች ፈሪ ልብ ወያኔዎች በደንብ ያዉቃሉ:: ሆኖም ለማደናገሪያነት ለትግሉ የሚያስፈልገዉን ቦታ እና ሁኔታ እነሱ ሊመርጡልህ ሲፈልጉ ዉጭ ቁጭ ብሎ መታገል ፈሪነት ነዉ እያሉ የመንፈስ ነጻነት የተጎናጸፉትን ኢትዮጵያዉያን ሊያጣጥሉ እየሞከሩ ፈሪዎቹን ዲያስፖራዎች ግን በፍርሃታቸዉ ተጀቡነዉ እንዲቀጥሉ ያበረታቷቸዋል::

ዛሬ በጎጃም እና በገንደር ኢትዮጵያዉያን የመኖር: የነጻነት እና የዲሞክራሲ መብታቸዉን ስለጠየቁ ያለ ርህራሄ በጥይት እየተደበደቡ ነዉ::እና አንተ አሁን ምን ማድረግ ትችላለህ? ተጋድሎዉን ለመቀላቀል ዛሬ ቁርስህን ሳትበላ ስለወገኖችህ በማዘን መጀመር ትችላለህ::ምሳህን በመተዉ ወገኖችንህን ማሰብ ትችላለህ::የሀዘን ልብስ በመልበስ የሞተ ወገን እና ዘመድ እንዳለ በማስነገር የአካባቢህ ሰዎች ለቅሶ እንዲደርሱህ ማድረግ ትችላለህ:: ወገኖቻቸዉ ለተገደሉባቸዉ ሰዎች ገንዘብ:ልብስ እና ልዩ ልዩ ቁሳቁስ አሰባስበህ ይዘህ መሄድ ትችላለህ:: ጮክ ብለህ ተራራ ላይ ወጥተህ ማልቀስ እና መጮህ ትችላለህ::ወይም ቤተክርስቲያን ከምታምናቸዉ ሰዎች ጋር ባዶ እሬሳ ሳጥን ተሸክማችሁ በመሄድ እዬዬ እያላችሁ ማልቀስ ትችላላችሁ::

ተጋድሎዉ ዘርፉ ብዙ ነዉ::ለተጋድሎ የተነሳዉን ወገን በቀጥታ መርዳት ትችላለህ::በገባህ እና በምትችለዉ መጠን ሁሉ እጅህን መዘርጋት ትችላለህ::አስተባባሪ የለም::መሪ የለም::ማህበረሰቡን ያለመሪ እና ያለ አስተባባሪ ያስቀረዉ ወያኔ ኢትዮጵያዉያንን ለዘላለም በጎሳ ፖለቲካ ባርነት ሲገዛ ለመኖር በማቀድ ነዉ::እናም እራስህ አስተባባሪ መሆን መቻል አለብህ::ብዙ ሰዉ ማስከተል የለብህም::ከምታምናቸዉ መጀመር ትችላለህ::ያም ባይሆንልህ ብቻህን መጀመር ትችላለህ::እንቢተኝነት እዉስጥህ መፈጠሩ ነዉ የተጋድሎ መጀመሪያ::

ስለ ህዝብህ በደል : መገደል : መገፋት : መሰደድ : የዘር መድሎ እና ኢፍትሃዊ አያያዝ ሁሉ መንፈስህ እንቢ ማለት አለበት::ሁሉም ነገር ቢያቅትህ መንግስት የሚባለዉን እና በጎሳ ፖለቲካ ላይ ተመስርቶ ኢትዮጵያዉያንን የነጣጠላቸዉን ሀይል ከጎሳ አባላትህ እና ከዘመዶችህ ጋር ሆነህ ማማት እና ማንቋሸሽ መጀመር አለብህ:: ይሄም የተጋድሎዉ መንገድ መጀመሪያ ነዉ::

ስለህዝብህ ስትል አንድ የተጋድሎ መሳሪያ እና ስልት እጅህ ላይ እንዳለ እንዳትረሳ::ለምሳሌ አንተ የአንድ ብሄር አባል ብትሆን እና ጎረቤትህ ደግሞ የሌላ ብሄር አባል ቢሆን አንተ ለጎረቤትህ ፍቅር በመለገስ እና ኢትዮጵያዉያኖች አንድ እንደሆኑ በማስተማር ኢትዮጵያዉያን ሁሉ በጸረ ወያኔነት በአንድ እንዲቆሙ መጋደል ትችላለህ::በዚህም የወያኔን የከፋፍለህ ግዛዉ ደባ ማፍረስ ትችላለህ::የኢትዮጵያዉያን የወደፊት ተስፋ በዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ዉስጥ በነጻነት እና በእኩልነት መሰረት ላይ ሊቆም የሚችለዉ ይሄን ዘረኛ እና ከፋፋይ ሀይል ሁሉም ኢትዮጵያዊ በጋራ ሲቃወመዉ ብሎም ሲያወርደዉ እንደሆነ በማስረዳት በፍቅር ኢትዮጵያዉያን ወደ አንድ መንፈስ እንዲመጡ መታገል ትችላለህ::እስላም የለም::ክርስቲያን የለም::ይሄ ብሄር ወይም ያ ብሄር የለም::ኢትዮጵያዉያን ሁሉ በአንድ መስመር ሆነዉ ለተጋድሎ ወያኔን መግጠም አለባቸዉ::ወያኔ ሲወድቅ ብቻ ኢትዮጵያ ወደ ዲሞክራሲያዊነት እና ነጻ ማህበረሰብነት ትሸጋገራለች:: ይሄን ስታስብ ታላቅ የነጻነት መንፈስ ዉስጥህ ተጸንሶ ሲላወስ ይሰማሃል::

አላስተዋልከዉ እንደሆነ እንጅ በ1997 ዓም ወጥተህ ረዥሙን እና አታካቹን ሰልፍ ተቋቁመህ ቅንጅትን መርጠህ ወያኔን ዉድቅ ያደረግህ እለት ተጋድሎ ዉስጥ ነበርህ::አላስተዋልከዉ እንደሆነ እንጅ ያ የተሰረቀ ድምጽ እና የተጭበረበረ የምርጫ ዉጤት በተነሳ ቁጥር ልዩ ልዩ ሀሳብን የሚያጭርብህ ተቃዉሞ ዉስጥ ስለሆንህ ነዉ:: እያንዳንዱ ድርጊትህ የባህሪህ: የስሜትህ እና የእዉቀትህ መገለጫ ነዉ::የመምረጥ ነጻነት እና መብት ብታገኝ ወያኔን በካርድ ዉድቅ ለማድረግ መዘጋጀትህ በራሱ የነጻነት ተጋድሎ መንፈሱ እዉስጥህ በጉልህ እንዳለ ይነግርሃል::

ተጋድሎዉ ወደ ከፍታ በሚዘልቅበትም ጊዜ እንደ አንበሳዉ ህዝባችን ከኦሮሚያ እስከ አማራ እንደ ተቀጣጠለዉ ህዝባዊ መናወጥ ሊሆንም ይችላል::ግፋም ሲል እንደ ጎጃም እና ጎንደር አማሮች የወያኔን ተመራጮች አዉርዶ የራሳቸዉን የአስተዳደር ስርዓት በመምረጥ የጎበዝ አለቃቸዉን መሾም ድረስ ይሻገራል:: :ተጋድሎዉ እንዲህ እያለ ወደ ብዙ ከፍታ እና አንገት ላንገት ትግል ይዘልቃል::ስለ ትልልቅ ተጋድሎ ከማሰብህ በፊት ግን እጅህ ላይ ያለዉን መሳሪያ ተጠቀምበት::

ለምሳሌ ዛሬ እንዲህ ብለህ ጸሎት በማድረግ ጀምር:-

እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርካት

ክፉዎችን እና ደም አፍሳሾች ወያኔዎችን እግዚአብሄር ስራቸዉን ይነቀለው

ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያዉያን የከፍታ የፍቅር ዘመን ይምጣላቸዉ

ህዝቤ ሆይ የመንፈስ ነጻነትህን የመንፈስ ነጻነታቸዉን ለሸጡ ዘረኞች አሳልፈህ እንዳትሰጥ እግዚአብሄር ካንተ ጋር ይቁም
እኔም ካንተ ጋር ነኝና

እግዚአብሄር ሆይ ኢትዮጵያን ከዘረኝነት አስተሳሰብ ፈዉሳት::በህዝቧም መሃከል ፍቅርን አምጣ !

ሆኖም ሁል ጊዜ ማወቅ ያለብህ ያንተን የተጋድሎ እና የብዙዎችን የተጋድሎ መንፈስ ለመግደል ወያኔ ተጋድሎዉን በሰላማዊ ተቃዋሚ ፓርቲነት መመዝገብ ብቻ አድርጋ ትቀሰቅሳለች:: በሰላማዊ ፓርቲነት የተመዘገቡትን ሀያላን የሰላማዊ ታጋይ ፓርቲዎችን ግን መሪዎቻቸዉ እና አባላቶቻቸዉን ታሳድዳለች: ታስራለች ብሎም ትገላቸዋለች::

ከዚያም ሲዘል ደግሞ የህዝብ ልጆችን ህዝባዊነት ለመግደል እና ህዝባዊዉን ተጋድሎ ለማኮስመን የወያኔ ተላላኪዎች አዉሮፓ ቁጭ ብላችሁ: አሜሪካ ተጎልታችሁ: ካናዳ መሽጋችሁ : አፍሪካ አገር ጥግ ይዛችሁ እያሉ ኢትዮጵያዉያን ዲያስፖራዎች በተጋድሎዉ ላይ እንዳይሳተፉ ይቀሰቅሳሉ::መንፈሰ ደካሞችን ያሸማቅቃሉ:: መታለል የሚፈልጉትን ያታልላሉ:: ከዚያም ሲዘል አንድ ሰዉ የህዝብን ጥያቄ እና ተጋድሎ ደግፎ አንድ ቃል ሲተነፍስ አንተ ደግሞ የማን ፓርቲ አባል ነህ? እያሉ የወያኔ ተላላኪ እና አድር ባዮቾ ሰዉን ያሸማቅቃሉ::

“ስለህዝባችን : ስለወገናችን እንዴት እንደምንጋደል የምንወስነዉ እያንዳንዳችን በተናጠል እና በጋራ ነዉ:: እና ዝም ብለህ ተጋደል::በቻልከዉ ሁሉ ተጋደል::ትግሉ ዘርፈ ብዙ ነዉ::ረዥምም ነዉ::ገና ወንድ ይፈተንበታል::ገና የኢትዮጵያዊነት መንፈስ ይነጥርበታል::ገና የእግዚአብሄር ተልዕኮ ይስተዋልበታል::ይሄ የኢትዮጵያ ጉዳይ ብቻ የሚወሰንበት ሂደት አይሆንም::ብዙ ተሳሳቢ ጉዳዮች አብረዉ አሉበት:: የህዝባችን መራራ ትግል ዘርፉ ብዙ ነዉ::የትም ብትሆን ተጋደል::ህዝባዊነትህን እንዳትተዉ::ዛሬ ብራስልስ ወይም ኒዮርክ ልትሆን ትችላለህ:: ወይም በሚያምር ቤትህ ዉስጥ ቦሌ ልትሆን ትችላለህ::አለዚያም ጎንደር ከተማ:: ምናልባትም ባሌ ጥግ:: ወይም ሶማሌ ጫፍ ላይ:: ነገ ግን ጫካ ልትሆን ትችላለህ::ተነገወዲያ ደግሞ ህዝብህ ጉያ::ይሄ ሁሉ የሚሆነዉ ግን የህዝባዊነት መንፈስህን ከህዝብህ ጋር ካስተሳሰርህ ብቻ ነዉ:: ህዝብህ ጀግና ይፈልጋል::ህዝብህ ተቆርቋሪ ይፈልጋል::” ይሄን ጥቅስ ለማንኛዉም ልቡ ስለ ተጋድሎ የሚዋዥቅ ሰዉ ስታገኝ ልትነግረዉ የሚገባ ቁርጥ መልዕክት ነዉ::

እያንዳንዱ ህዝብ የተጋድሎ ዘመን አለዉ::ለኢትዮጵያዉያን ይህ የተጋድሎ ዘመን ነዉ::ተጋድሎዉ ከመንፈስ ልዕልና በላይ የህዝብን ህልዉና የማስጠበቅ ተልዕኮ አንግቧል::ተጋድሎዉ ህዝብን ነጻነቱን ከቀሙት: ዘረኛ ህሊና ቀፍዶ ከያዛቸዉ እና በባርነት አስተሳሰብ ከተቃኙ ዘረኞች እና እብሪተኞች ነጻ የማዉጣት ረዥም ጉዞን ሰንቋል:: ተጋድሎዉ የዲሞክራሲ: የሰባዊነት: የእኩልነት ብሎ የሁል አቀፍ ብልጽግና መሰረቱን የተነጠቀ ህዝብን ነጻ ስለማዉጣት ነዉ:: ተጋድሎዉ የአንድ ሰሞን እሩጫ አይደልም:: ህዝባዉያን አይደክሙም::ህዝብም እንደ ዉቃያኖስ ጥልቅና ሰፊ ነዉ::ተጋድሎዉ በተወሰኑ ግለሰቦች መሪነት ግብ አይደርስም:: ላንተ የተጋድሎ መጀመሪያ ቀንህ ግን ዛሬ ነዉ::ህዝብም ተጋድሎዉ እስከ ነጻነት ነዉ::ሀያ አምስት አመታት የታጋደለ ህዝብ ነጻነቱን ሳያስመልስ እና ነጻነቱን ሳይጨብጥ እረፍት የለዉም:: የኢትዮጵያዉያን ተጋድሎ እስከ ነጻነት የሚዘልቅ ነዉ:: ያንተ ቀንህ ዛሬ ነዉ::ስለህዝብህ መቆርቆር የምትጀምርበት አሁን ነዉ:: የመዳን ቀን አሁን ነዉ::የማሸነፍ ቀን አሁን ነዉ እንዳለ መጽሀፍ::ስለ ህዝብህ እዉነት የምትቆምበት ሰዓቱ አሁን ነዉ:: እናሳ ? ህዝባዊ ነህ? ወይስ ግላዊ?

https://www.facebook.com/S.Ayele.Eth/posts/11166156883874

የጠ/ሚ ኃ/ማርያም የጭፍጨፋ አዋጅ ተቀበሉ የሚል ስብሰባ በደቡብ ወሎ ተጠራ

0
0

amhara2
ከሙሉቀን ተስፋው

ዛሬ ነሃሴ 27 ቀን 2008 ዓ.ም. በደቡብ ወሎ ባሉ ወረዳዎች ጠ/ሚው ‹‹በእኔ በኩል ማንኛውንም ኃይል ያለምንም ምሕረት ውሰዱ ብያለው›› ያለውን የዘር ማጥፋት መግለጫ ትክክለኛነት ዐማራው እንዲደገፍ በሚል በደቡብ ወሎ ዞን ባሉ ወረዳዎች ስብሰባ ተጠርቷል፡፡

ከመካነ ሰላም ወረዳ ተሳታፊ እና አወያይ ካቢኔዎች የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው ሰሞኑን ደሴ ከተማ ላይ በአቶ አህመድ አብተው ኦሬንቴሽን ከየወረዳው ለተውጣጣነው የወረዳ አመረሮች ሰልጠና ሰጥቷል፡፡ መረጃውን የላከለን ግለሰብ እንደሚለው ‹‹ይህንኑ የተወያዬንበትን ወቅታዊ የአማራ ክልል ጉዳይና በኢሕአዴግ ምክር ቤት የተወሰነውን ብሎም የተሠጠውን የዘር ማጥፋት መግለጫ በአባላት ድጋፍ እንዲያገኝ አሳምኑ ሰለተባለ እረፍት የወጡ የመንግሥት ሠራተኛ አባላት ሣይቀሩ እረፍታቸውን አቋርጠው ወደ ሥብሠባው እንዲገቡ ጥሪ ተላልፏል›› ሲል ተናግሯል፡፡ ስብሰባው ዛሬ በጠዋት ተጀመረ ሲሆን የነበረውን ግብረ መልስ እንደደረስን የምናቀርብ ይሆናል፡፡

ከሰሜን ጎንደር የአማራ ሕዝብ ትግል አስተባባሪዎች ለምሊሻ ታጣቂዎችና ለመላው የአማራ ሕዝብና ሰላም ወዳድ ኢትዮጵያዊ ወገናችን ሁሉ የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ

0
0

ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ሰሞኑን በተደጋጋሚ እንደዛተው የአማራን ክልል የጦርነት ቀጠና አደርጋለሁ ብሎ ተግባራዊ አድርጓል። ንጹሃን የአማራ ተወላጆችን ህጻናትን ጨምሮ ያለርህራሄ ባሰማራው አጋዚ ታጣቂዎች እያስገደለ ይገኛል።የሕዝባዊ ወያኔ መሪዎች የአጋዚ ጦር ብቻ ሳይሆን በሀሰት የገበሬ ታጣቂዎችን ጭምር > በሚል ወገን ወገኑ ላይ እንዲተኩስ አበል እየከፈሉ መሳሪያ እያስታጠቁ ጭምር አሰማርተዋል። ይሄ ብዙ ርቀት አይወስዳቸውም።ሐቁን የአማራ ምሊሻ ይረዳል።ያውቃል።ሕወሓት በአማራ ሕዝብ ላይ ወልቃይት የአማራ ነው በማለቱ ለሰላማዊ ተቃውሞ የሰጠው የጥይት ምላሽ ሰጥቷል።
north Gonder

ብዙዎቹ የምሊሻ ታጣቂዎች በአገር ሽማግሌ ሐቁ ተነግሯቸው የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይን ጸረ አማራ የግፍ ግድያ ተቃውመው ሸሽተው ተመልሰዋል።አንዳንድ ይህን ዓላማ ያልተረዱትን የአካባቢ የአገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች፣መላው ሕዝባችን የወያኔ ሐርነት ትግራይ የራሳችንን ንጹሃን የገበሬ ምሊሻ ጭምር ለከፈተው ጸረ አማራ ጦርነት እንዳይጠቀም ማሳወቅ ማስጠንቀቅ አለብን።በደባርቅ የተስተዋለው የወያኔ ግልጽ ሴራ ማሳያ ነው:

ይሄ በአማራ ንጹሃን ላይ የተከፈተ ጦርነት መነሻው የወልቃይትን የአማራ ማንነት ክዶ ሕወሓት ወልቃይት የትግራይ ብሎ አስተዳደር ከልሎ ላለፉት ሃአ አምስት ኣመታት ስፍር ቁጥር የሌለው ዘር ፍጅት አድርጓል። ይሄ የወያኔ የጉልበት እርምጃና ሕገ ወጥ ውሳኔ የመተው ወልቃይት ጉዳይ በሕግ እልባት እንዲያገኝና እንዲስተካከል ህዝቡ ወኪል ኮምቴ መርጦ በሰላማዊ መንገድ ያቀረበውን ጥያቄ ወደ ሀይል ግጭት ሆን ብሎ ወያኔ ስለቀየረ ነው። ይሄ ጦርነት ስለ አባይ መገደብ አይደለም። የህዝቡ በዙሃኑ ምሊሻ ወገናችን ዛሬ በአማራ ክልል የተሰማራው አጋዚ አልበቃ ያለው ወያኔ ጥቂቶችን በሀሰት በመደለል የተከፈተው ጦርነት አማራን ለማጥፋት፣ወልቃይትን በጉልበት ወስዶ ለማስቀረትና የአማራን ሕዝብ ረግጦ ለመግዛት ነው።

ልጆችህ ተምረው የበይ ተመልካች እና ስራ አጥ ያደረገ፣ወገኖችህን ራሱ ባመጣው የዘር ፖለቲካ አማራ ስለሆኑ ብቻ ከተለያዩ ክልሎች ያሳደደ ነው።ለመሆኑ ወያኔ ያልሰራው ግፍ የቱ ነው? ይህን ላንተ መዘርዘር ለቀባሪው ማርዳት ነው።

ከወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አስተባባሪዎች መካከል ኮ/ል ደመቀ ዘውዱን ጨምሮ ታጋዮች የነበሩ ደርግን ለመጣል የተዋደቁ እንጂ ወያኔ እንደሚለው የሻዕቢያም ሆነ የግብጽ ተላላኪዎች አይደሉም።አይሆኑምም።

ለዚህ የወያኔ ቅጥፈት ቦታ ሳትሰጥ ዛሬ በአማራ ሕዝብ ላይ ወያኔ ለከፈተው ግልጽ የዘር ማጥፋት ጦርነትን አውግዘህ በወገኖችህ ላይ አትተኩስ።መሳሪያህን ሕዝብ ግደል ብለው ባሰማሩህ ላይ አዙር። ከአጋዚ ጋር እንዳታብር:፡ ሲጠይቁህ የአማራን ሕዝብ እንደ ጠላት ወታደር ሊጨፈጭፉ ከመጡት ጋር አላብርም በል።

ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በዚህ አጋጣሚ የሕወሓት ዘረኛ አገዛዝ ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ተራ በተራ ያልረገጠው፣ያልገደለውና ያላስለቀሰው ብዙሃን ሕዘብ የለም።ላለፉት ዘጠኝ ወራት በኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ እየተፈጸመ አለው ዘር ማጥፋት፣ ከሸኮ መዠንገር ጭፍጨፋ እስከ ኦጋዴን የዘር እልቂት፣ ከጋምቤላ የአኙዋ ንጹሃን የሁለት ዙር የዘር ፍጅት እስከ ሲዳማ ሕዝብ ላይ ተፈጸመ ግድያ እአሉ ብዙ መዘርዘር ይቻላል:፡ ዛሬም ወህኒ ቤቶች በሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵአውያን አበሳቸውን ያያሉ። ከትላንት እስከ ዛሬ እየተፈጸመ ያለው የአማራ ግድያ የተግባር ምስክር ነው። ዛሬ በአማራ ሕዝብ ላይ በይፋ ያወጀውን የዘር ማጥፋት እርምጃ አጠናቆ ነገ ወደ ሌላው ወገናችን መዞሩ አይቀርም። ባለፈው በጎንደር ተቃውሞ ወቅት በኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ግፍ ስንቃወም ፍጹም ወገናዊ በሆነ ተቆርቋሪነት ነው።ዛሬ በአማራ ሕዝብ ላይ ወያኔ ዘምቶበታል። በየትኛውም አካባቢ ያለ ወገናችን ይህን የወያኔ ፋሺስት ስርዓት እርምጃ በአገኘው አጋጣሚ ሁሉ እንዲያወግዝ እንጠይቃለን።

በየአካባቢው የሚገኘው ሰላም እና ለውጥ ናፋቂ ሕዝብ ለመብቱ የሚነሳበት ወሳኝ ወቅት ነው። የሕዝብ ጠላት የሆነውን ወያኔን ማዳከም የሚቻለው በጋራ በተመሳሳይ ወቅት ፋታ የሚነሳ የጋራ ትግል በማድረግ ጭምር ነው።የሕዝቡ መሪዎች በአማራና በኦሮሚያ ክልል እንደተደረገው ይህ ወሳኝ ወቅት ሳያልፍ ተረባርበን ይህን ፋሺስታዊ የወያኔ ስርዓት ለመገርሰስ በበኩላችን የተጠናከረ ትግላችን ይቀጥል።

ሞት ለፋሺስቶች

የአማራ ሕዘብ ከተከፈተበት የዘር ማጥፋት ጦርነት ተባብሮ ያሸንፋል!

የሕግ ባለሙያዎች ታሪክና ግዜ የጣሉባችሁን ኃላፊነት እንደምትወጡ ይጠበቃል! [በላይነህ አባተ]

0
0

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

justice
ታሪክና ግዜ በትውልድ ኃላፊነትን ይጥላል፡፡ ይህ ትውልድ በሮማውያን ዘመን ኃላፊነቱን በሚገባ እንደተወጣው ትውልድ ታሪክና ግዜ ኃላፊነት ጥለውበታል፡፡የሮማውያንን ተደጋጋሚ ጪፍጨፋ አያት ቅደመ-አያቶቻችን በሚያስደንቅ ጀብዱ መክተውታል፡፡ ከሮማውያን ቅኝ ገዥዎች ጪፍጨፋ በከፋ ሁኔታ በእጅ አዙር ቅኝ ገዥ አገልጋዮች ህጻናት ጭንቅላታቸውን በላውንቸር እንደሚበረቀሱ፣ እግራቸውን በባሩድ እንደሚቆረጡና ሆዳቸውን እንደሚዘረገፉ አምባ ጊዮርጊስ በዚች ቅጽበት አስገንዝቦናል፡፡ እነዚህን የእጅ አዙር ቅኝ ገዥ አገልጋይ ጨፍጫፊ ባንዳዎችም ሕዝብ ግብግብ ገጥሟቸው ይገኛል፡፡ ይህ የጪፍጨፋ ግዜ ከገዳዮች የወገነውን እርጉሞችና ድምጣችንን አጥፍተን እንጀራችንን የምናሳድደውን አድርባዮች በትዝብት ቴሌስኮፕ ይመለከተናል፡፡

በመላ አገሪቱ በአረመኔዎች እሚፈጸመው የሕዝብ ጪፍጨፋ በደመነፍስ የሚንቀሳቀሱ አውሬዎች እንኳ በሰው እማይፈጽሙት ጪፍጨፋ ነው፡፡ ይህንን ጪፍጨፋ የሚፈጽሙትን አረመኔዎች ከፍርድ ለማቅረብ እናንተ የሕግ ባለሙያዎች የመሪነቱን ሥፍራ እንድትይዙ ግዜና ታሪክ አደራ ጥለውባችኋል፡፡ ሕግ የተሰራው ህሊናውና እምነቱ ያላሰረውን መረን ለማሰር ይመስለኛል፡፡ ህሊናውና እምነቱ ያላሰረው መረኑ ኃይለ-ሰይጣን ደሳለኝ ዛሩን አውርሶ ከወንበር ጎልትቶት እንዳለፈው ሰይጣን በሕዝባችን የጪፍጨፋ አዋጅ አውጇል፡፡ ኃይለ-ሰይጣ ደሳለኝንና የጪፍጨፋ አዋጁን እንዲያውጅ ያዘዙትን አረመኔዎች ከፍርድ እንድታቀርቡ ታሪክ፣ ግዜና ሕዝብ በእናንተ በሕግ ባለሙያዎች ኃላፊነት ጥለዋል፡፡ ይህንን የሕዝብ፣ የታሪክና የግዜ ኃላፊነት ያልተወጣ ዜጋና የሕግ ባለሙያ በሞቱት አጽም፣ ከሞት በተረፉት ዜጎች፣ በመጪው ትውልድ፣ በታሪክና በእግዚአብሔር ሲጠየቅና ሲወቀስ ይኖራል፡፡

የሕግ ባለሙያዎች ሆይ! ጠበቃ፣ ዳኛ፣ አቃቤ ሕግ፣ ሚኒስቴር፣ ፕሮፌሰር፣ ወዘተርፈ ሆናችሁ የምታግበሰብሱት ገንዘብ፣ የምትነዱት መኪና፣ የምትኖሩበት ቪላ በማታውቁት ሰዓት ሞት ሲጠልፋችሁ ተከትሏችሁ አይሄድም፡፡ ታሪክ፣ ትውልድና እግዚአብሔር ግን እየተከተሉ እስከ ዓለም ፍፃሜ ሲወቅሷችሁ ይኖራሉ፡፡ ባልጠበቃችሁት መንገድ አፈር ለሚሆነው ገላችሁ ሳስታችሁ የሕዝብን ጪፍጨፋና የፍትህን መታረድ አግዛችሁ ወይም ችላ ብላችሁ እንደ በፊቱ ባንዳዎችና አድርባዮች የራሳችሁንና የልጅ-ልጆቻችሁን ቅልብ በታሪክና በትውልድ ወቀሳ ሲሸማቀቅ ከመኖር አድኑ፡፡ በህሊናውና በእምነቱ እሚገዛውን ሕዝባችንን የሚጨፈጭፉትን አረመኔዎች ለሕግ አቅርቡ፡፡ ህሊናና ሕግ ቀርቶ ደመነፍስም በማያስራቸው ጭራቆች እንደ ዓባይ እሚፈሰው የንጹሐን ደም የችሎት ያለህ፣ የፍትህ ያለህ፣ የጠበቃ ያለህ፣ የዳኛ ያለህ ሲል ይጮሃል፡፡

የሕግ ባለሙያዎች ሆይ! የንጹሐን ደም ጩኸት፣ ታሪክና ግዜ የጣሉባችሁን ሐላፊነት እንደምትወጡ ይጠበቃል፡፡ አመሰግናለሁ፡፡

 

ነሐሴ ሁለት ሺ ስምንት ዓ.ም.

የኦሮሞው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ለምን ገብ አለ? |ጥበቡ ታዬ

0
0

oromo 1
አንድ የሕዝብ እንቅስቃሴ ለመነሳት ምክንያት አለው፣ለመቆምም እንዲሁ።ብሶትና ምሬት የሕዝብን እምቢባይነት ይቀሰቅሳል።እንቅስቃሴው ከተሳካ በድል ይጠናቀቃል፤ አለዚያም በመንግሥት ሃይል የጥቃት እርምጃ ለጊዜው ሊገታ ይችላል። በዚህ መልክ የሚረጋገጥ የበላይነት ቂምን ስለሚወልድ ቅራኔውና ትግሉ እስከነአካቴው አይጠፋም።ጊዜ ጠብቆ ያገረሻል።ሌላው ምክንያት ደግሞ በመንግሥትና በተነሳው ሕዝብ መካከል ውይይት ተካሂዶ ሕዝቡ የሚፈልገውን እንደሚያገኝ የተስፋ ቃል ተሰጥቶትና ያንን ተቀብሎ ከተነሳበት እንዲያፈገፍግ የሚያደርግ ስራም ከተሰራ የሕዝብን ትግል ሊገታው ይችላል።
በኢትዮጵያ ውስጥ ላለፉት ወራቶች በተለያዩ ቦታዎች የተካሄደው ሕዝባዊ ትግል ገዥውን የወያኔ ቡድን እንዳርበተበተው የሚካድ አይደለም።ለዘጠኝ ወራት በኦሮሞው ኢትዮጵያዊ የተካሄደው ትግል ብዙ መስዋዕት ተከፍሎበታል።ሆኖም ግን ብዙ ሕይወት ከማስከፈሉ ውጭ የተገኘ ውጤት የለም።በቅርቡም በአማራው ማህበረሰብ በጎንደርና በጎጃም ውስጥ ብዙ ሕይወት የተከፈለበት ሕዝባዊ እንቅስቃሴ በባዶ እጅ ከመሰለፍ አንስቶ ነፍጥን ባካተተ መልኩ የመቋቋም ትግል በመካሄድ ላይ በመሆኑ ገዢውን ቡድን እስከዛሬ አይቶት ከማያውቀውና ካልጠበቀው የሕዝብ አመጽ ውስጥ ነክሮታል።ሕዝቡ መሞት ብቻ ሳይሆን መግደልም እንደሚያውቅ አሳይቶታል።በዚህም ምክንያት በስልጣን ላይ ያለው ቡድን ከውጭ አገር ወራሪ ጋር ከሚደረግ ጦርነት ባላነሰ ደረጃ በከባድ መሳሪያ የታጀበ የአገሪቱን የመከላከያ ሃይል ወደ ጎንደርና ጎጃም አዝምቷል፤ይህም ብቻ ሳይሆን የሱዳንን ወራሪ ጦር በእርዳታ እንዳሰለፈና በድንበር ከተማዎች ዙሪያ በመተማና በወልቃይት በአየር ሃይል ጭምር የጥቃት እርምጃ በመወሰድ ላይ እንዳለ በሰፊው ይነገራል።ጎን ለጎንም የተነሱበትን ሁለት ማህበረሰቦች ለማለያየት አንዱን በመቅረብ ሌላውን በማራቅ የስልት ጉዞ በማድረግ ላይ ይገኛል።

በዚህ የአገርን ክብር፣ ነጻነትና አንድነት በሚፈታተን ወረራ የወያኔ መሪዎች አጥፍቶ ለመጥፋት እንደቆረጡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተብየው አንደበት የተነገረው የጸረ ሕዝብና የእብሪት መግለጫ ያመለክታል።
በዚህ የሞት የሽረት ሕዝባዊ ትግል ሁሉም የአገሪቱ ዜጋ እጅ ለእጅ ተያይዞ የጀመረውን የነጻነትና የእኩልነት ትግል ከዳሩ ማድረስ ይገባዋል። በአማራው ኢትዮጵያዊ ዜጋ የሚካሄደውን የሕዝብ ትግል ለማኮላሸት ሃይማኖት አባቶች ታቦት ተሸክመው እንዲማጸኑ፣ የተደረገው ሙከራ ተቀባይነት ስላጣ ከሽፏል። ወጣቶችን በመግደል፣በማቁሰል፣ በጥርጣሬ ብቻ እያፈሱ በማሰር ፋታ ለመግዛት የታሰበው ስልትም አልሰራም።አሁን የተደረሰበት ውሳኔ የክተት አዋጅ በማወጅ በሃይል መደፍጠጥና የሕዝቡን ትግል እስከነአካቴው ማኮላሸት ነው።

በኦሮሞውም ህብረተሰብ በኩል የሚደረገውን ሕዝባዊ ትግል ለማኮላሸት ተመሳሳይ እርምጃዎች ተካሂደዋል።በመግደልና በማሰር የተደረገው ሙከራ አልተሳካም።ሁለተኛው ስልት በአዳማ ከተማ አዛውንቶችንና የአገር ሽማግሌዎችን በመሰብሰብ የአስታራቂ ሚና እንዲጫወቱ ማድረግ ነው።በሌላም ዙሪያ የተለያዩትን የኦሮሞ ድርጅቶች ሰብስቦ በማነጋገር ወደ አንድ የጋራ ጥቅም ወደ ሚያመራ ስምምነት ላይ የመድረሱ ሂደት መጀመር ነው።ይህ ስልት አሁን በአገር ውስጥና በውጭ አገር በመካሄድ ላይ ነው።የውጭ አገር መንግሥታትም በስልጣን ላይ ያለው አገልጋያቸው እንዳይወገድ ስለሚሹ የጥገና ለውጥ ተደርጎ እንዲቀጥል ምርጫቸው ነው።ያንን ደግሞ ለማሳካት በኦሮሞው ስም ከሚንቀሳቀሱትና የነሱም አጋር ከሆኑት ተቃዋሚ ነን ከሚሉት ቡድኖች ጋር ወያኔን ማስማማት ነው። እነዚህ ስምምነቶች ከዳር ከደረሱ፣ የአማራውን ማህበረሰብ ያገለሉና ለጥቃት አጋልጠው የሚሰጡ እንደሚሆኑ ግልጽ ነው። አሁን በመሬት ላይ ያለው ሃቅ የተጀመረውና ብልጭ ብሎ የታየው የኦሮሞና የአማራው ሕዝብ የመደጋገፍ የትግል አንድነት ሻማ እየከሰመ መሄዱ ከዚሁ አዝማሚያ የተነሳ መሆኑን ነው።በኦሮሚያ አካባቢ ላለፉት ዘጠኝ ወራት ሲካሄድ የነበረው የሕዝብ ትግል ጋብ ማለቱ የሚያመላክተው ነገር ቢኖር ይህንኑ ነው።አሁን ስርዓቱ በሚንገዳገድበት ወቅት የተቀጣጠለውን ትግል እንዳይበርድ በማድረግና መንግሥትን በየቦታው ወከባ ውስጥ በማስገባት ፈንታ በአማራው ላይ የጦር ሃይሉ ሲረባረብበት በዝምታ ማየት ወይም ከትግሉ ሜዳ ማፈግፈግ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ እንደማለት ይሆናል ሲተረጎምም የትግሬ መንግሥትና አማራው ሲዋጋ የሁለቱም ሃይል ሲዳከም በጎን የኦሮሞን ዘላቂ ፍላጎትን ማስከበር ይቻላል ከሚል ስሌት በመነሳት የተደረገ ውሳኔ ሊሆን ይችላል።

እውነት የኦሮሞ ድርጅቶች ጥቅማችንን በአማራው ኪሳራ ላይ እናስከብራለን ብለው የሚያስቡ ከሆነ ትልቅ ስህተት ንደፈጸሙ ሊያውቁት ይገባል።አማራው እስከመጨረሻው ድረስ ለህልውናውና ለኢትዮጵያ አንድነት ይቆማል፣ ይፋለማልም። ወያኔ ደግሞ አማራውን ካዳከመ በዃላ ኦሮሞውን ነጥሎ በተራው ይቀጠቅጠዋል እንጂ በእኩል ደረጃ የስልጣኑ ባለቤት አያደርገውም።በፊትም የታየው ይኸው ነው።ብልህ አንድ ጊዜ ብቻ ሊሞኝ ይችላል፤ደጋግሞ መሞኘት ከጅልነት በላይ ቂልነት ነው። አሁን ያለው አማራጭ አንድና አንድ ብቻ ነው።በኢትዮጵያዊነት እጅ ለእጅ ተያይዞ ከውጭ ሃይሎች ዘረፋና የነሱም ጉዳይ ፈጻሚ ከሆነው ዘረኛና ጨካኝ የወያኔ አገዛዝ ነጻ ለመውጣት ትግሉን በየቦታው እየተመካከሩ ማፋፋም። በድሉም የአንድ ነጻ አገር ባለቤት ሆኖ በእኩልነትና በነጻነት መኖር ። ሌላው ምርጫ ሳይሆን ፍርጃ ደግሞ የራሱን ቋንቋ በሚናገሩ አገር በቀል ሆዳሞች፣ ለውጭ አገር የእጅ አዙር አገዛዝ መሳሪያ በሆኑ አምባገነኖች መዳፍ ስር ወድቆ እያለቀሱ መኖር ይሆናል።
የማን ቤት ፈርሶ የማን ሊበጅ፣ እንረስ ካላችሁ ተስማምተን እንረስ፣ ያውሬ መፈንጫ ይሆናል እንጅ። የሁላችንም ቤት አንድ ላይ አይፍረስ።

የሚሉት አባባል በተግባር እንዳይገለጽ ብልህነትና ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። አንዱ በሌላው ኪሳራ ላይ የሚኖርበት ወቅት አክትሟል።በአንድነት ተከባብሮና ተስማምቶ መኖር እንጂ ተለያይቶ በሰላም መኖር አይቻልም።

የኢትዮጵያን አንድነት የምትሹ ሁሉ የተቀጣጠለው ሕዝባዊ ትግል እንዳይሰናከል ተባበሩ፣ለትግሉም አስተዋጽኦ አድርጉ።ትግሉ ኢትዮጵያዊነትንና ኢትዮጵያን የማዳን ትግል ነው።በዚህ የትግል ዓላማ የሚስማማ የሁሉም ማህበረሰብ አባል ሊሳተፍበት ይገባል።

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live