Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የኢትዮጵያ መንግስትን አሳሪነት አትሌት ፈይሳ አሳዳጅነቱን ደሞ አትሌት ዮናስ ያጋለጡበት መድረክ ይደገማል

$
0
0

ዘአብርሃም ከጀርመን

አትሌት ፈይሳ ሌሊሴ እንዴት አድርጎ የወያኔን መንግስት አሳሪነት እንዳሳየ እየተደመምን እስቲ ደሞ አትሌት ዮናስ ክንዴ የተባለ ሌላ ጀግና እንዴት አድርጎ በሪዮ ኦሎምፒክ የወያኔን መንግስት አሳዳጅነት እንዳጋለጠ እንመልከት።
ጉዳዩ እንዲህ ነው። አለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ በአለም ላይ ተሰደው የሚገኙ ሀገር አልባ ስደተኞችን ለማስታወሰ እና እነሱንም ወክሎ ከሌሎች ሀገራት እኩል የሚወዳደሩ 43 ሰዎችን በመጋቢት ወር መረጠ። ከነዚህም ውስጥ ስደተኛ በጣም የሚሰደድባቸው ሀገራት በሚል መስፈርት ከተለዩት ውስጥ ከሶርያ ጀርመን ና ቤልጅየም የገቡ 2፣ ከዴሞክራቲክ ኮንጎ ወደብራዚል የተሰደዱ 2፣ ከደቡብ ሱዳን ኬንያ ካኩማ የስደተኞች ካምፕ የተጠለሉ 5 አትሌቶችና ከኢትዮጵያ ወደ አውሮፓዊቷ ሉግዘምብርግ የተሰደደው ዮናስ ክንዴ በድምሩ 10 አትሌቶች ሪዮ ዴጄነሮ ብራዚል ለኦሎምፒክ ውድድር አመሩ። ከመክፈቻው ዕለት አንስቶ ይዘውት የነበረው የተሰደዱበትን ሃገር ባንዲራ ሳይሆን አምስቱ ቀለበቶች ያሉበትን ነጩን የኦሎምፒክ አርማ ባንዲራ ነው።የሚወክሉት ሃገር ኣልባ የሆነውን ስደተኞችን ነው። Refugee Olympic Team/ROT/ በሚል መጠሪያ።

Yonas Kinde
ቀውሱ በጣም ከፍተኛ ከሆነባቸው ከሶርያ አትሌቶች ፣ ከደቡብ ሱዳን ከ ደሞክራቲክ ኮንጎ እኩል የዚህ ትውልደ ኢትዮጵያዊ በሰደተኛች ቡድን መታቀፍ ሲዘገብ ከረመ። በአንጻሩ ከትዮጵያ የተሰደዱ ወገኖች ያሳደዳቸው ምክንያት ከእነዚህ ሶርያዎች ወይም ደቡብ ሱዳኖች እኩል እንደሆነ ታየ። የወያኔው መንግስት እንደ ኮንጎዎቹ ዘረኛና እኩይ መሆኑ ተመሰከረ።

በዉሃ ዋና ትግሬ በመሆኑ ብቻ ተመርጦ ዉሃ ውስጥ ያዋረደን የሮቤል ጉዳይ በአለም ሚዲያ ሲዘገብ ከሰደተኞቹ ውስጥ ሁለቱ ሶርያውያን ራኒ ኣኒስ እና ያሱራ ማርዲኒ በሴቶች ውሃ ዋና ተወዳዳሪ ነበሩ።በአስራ ሰባት አመቷ ከሶሪያ ተሰዳ ከእህቷ ጋር በባህር ሊሰምጡ የነበሩ 20 ሌሎችን በዋና ጠበቧ ታድጋ ጀርመን በርሊን የደረሰችው ይችው የሰደተኞች ተወካይ አትሌት ተንደላቆ ተዳልቶለት በ አባቱ ዳኝነት ከተመረጠው የሕወሃቱ ቦርጫም ዋናተኛ ሮቤል የበለጠ ተዘግቦላታል።ስደተኞች ተዘግቦላቸዋል። ከኮንጎ ዲሞክራቲክ ረፐብሊክ ወደ ብራዚል የተሰደዱት ሁለቱ በጁዶ ስፖርት ሲሳተፉ ፣አምስት የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በሩጫ ሲወዳደሩ ሁሉ የኢትዮጵያ ስም በስደተኛ አበርካችነቷ እየተጠራ ነበረ። እነ ፈይሳ ሌሊሴ በሪዮው ኦሎምፒክ የኢትዮጵያ አትሌቶች ተብለው ሰማቸው ሲተዋወቅ ዮናስ ክንዴ ከኢትዮጵያ ግን በሃገር አልባ ስደተኞች ማልያ በማራቶን ተሰለፈ። ሁለት ኢትዮጵያውያን አንዱ በመንግስት ተወክሎ አንዱ በመንግስት ተፈናቅሎ። ዞሮዞሮ ኢትዮጵያን ወክሎ ሁለተኛ የወጣው አትሌት እሱም ሰደተኛነቱን አስመሰከረ የታሰሩ የተገደሉ የኦሮሞያ የጎንደር ወገኖቹን ደም ሲቃ እያየ ወደ ወያኔው የአትሌቶቹ ካምፕ መሄድ አልወደደም። በይፋ የለም ህዝብ በሙሉ በትኩረት እያየው ኢትዮጵያውያን ታስረዋል አለ። የኢትዮጵያ መንግስት አሳዳጅነት እና አሳሪነት ወትሮዉኑም ሲታወጅ የቆየ ነው አሁን ሰበብ ተገኘ።
ኤስቢ ኔሽን የተባለው የዜና አውታር

<< Bringing athletes from war-torn countries to Rio>> በጦርነት ከፈረሱ
ሃገሮች የመጡ አትሌቶች በሚል ርዕስ ስር ነሃሴ መጀመሪያ ሳምንት ላይ ያወጣውን ሃተታ በማየት ብቻ እንደምንረዳው ከሶርያ ፣ከደቡብ ሱዳን፣ ኮንጎ እኩል ኢትዮጵያም በጦርነት ስር እንዳለች ለ አለም አስነብቧል።
የተባበሩትን መንግስታት የስደተኞች መስሪያ ቤትን ጠቅሶ ኤስቢ እንዲህ ሲል << The civil war in Syria has been driving an outright refugee crisis in Europe. The United Nations Refugee Agency says there are 4.8 million Syrian refugees, plus an estimated 8.7 million people displaced inside Syria this year. Its count of refugees and asylum-seekers from South Sudan is 850,000. In the Democratic Republic of the Congo, it is more than 384,000 refugees and more than a million internally displaced persons. There are more than 700,000 Ethiopian refugees. This is just a sampling.>> ሰባት መቶ ሺ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች አሉ የሚለው ይሄ የመጨረሻው አረፍተ ነገር የወያኔን መንግስት አጋኖ አጋለጠው እንዳንል እነ ቢቢሲ ሲኢኤን ኤን ኣልጀዚራ ወዘተ የተባሉት ዝነኛ ሚድያዎች ሳይቀሩ ኢትዮጵያን ከጎንደር ኦሮሚያ አመጽ እስከ ሪዮ ኦሎምፒክ የ አትሌቶች አመራረጥ አድልዎ እያብጠለጠሉ የመንግስትን ሙስና ሲዘግቡ ነበሩ።
በተለይ የሶርያ ቀውስ ጉዳይ አለም ኣቀፍ አጀንዳ ከመሆኑ ጋር እና ሁለት ሴት አትለቶቹ በዉሃ ዋና ሪዮ ኦሎምፒክ ላይ ከተሳተፉ ቀን ጀምሮ የእያንዳንዱ ስደተኛ አትሌት የስደት መንስኤ በስፋት ተራግቧል። በሁሉም ዜናዎች የኛው አትሌት ዮናስ ክንዴ በፖለቲካ ምክንያት ከሃገር መባረሩን እና ለአትሌቶች ምቹ መንግስት እንደሌለ የገለጸው ለመላው አለም ህዝብ አይን እና ጆሮ ደርሷል።
በሉግዘምብርግ በታክሲ ሹፌርነት ኑሮውን የሚገፋው የ36አመቱ ዮናስ 2ሰዓት ከ17 ደቂቃ ምርጥ የማራቶን ሰዐቱን በፍራንክፈርት በግል ያስመዘገበ ሲሆን በሪዮው ኦሎምፒክ ዘጠናኛ ወጥቶ ስደተኞች ከማንም እንደማያንሱ አትሌቶችን ወክሎ የተናገረው ይጠቀስለታል።
ታዋቂው ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ አስሩ አትለቶች ከ ስልሳ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ በ አለም ላይ የተበተኑ ስደተኞችን ይወክላሉ ሲል ከአስሩ ስድስቱ ወንዶች አራቱ ሴቶች ሲሆኑ ሁሉም በሃገራቸው ባለ ግጭት የተነሳ የተሰደዱ ናቸው በማለት የአሜሪካው ኒውዮርከር ድረገጽ ደሞ አትቷል። ኢትዮጵያዊው ዮናስ ክንዴ ከ ኢትዮጵያ የተሰደደው በ2013 ሲሆን በዛ ወቅት አስከፊ ግጭት ነበረ ካለ በአሁን ሰኣት ደሞ ያለውን ጄኖሳይድ ምን ብሎ ህወሃትን እንደሚያብጠለጥለው መረዳት አይከብድም ።
Lalisa

The ten team members—six men and four women—were announced in June. All have fled conflicts in their home countries. There are two swimmers from Syria, two judokas from the Democratic Republic of Congo, a marathoner from Ethiopia, and five middle-distance runners from South Sudan.

ህወሃት ወያኔ በሁሉም ቦታ ተዋረደ አይቀናውም። በኢትዮጵያ ውስጥ ባለው አብዮትም በውጪ ሀገራትም። በሃገር ውስጥ ህዝቡ
በአንድነት ተነስቷል። ከእንግዲህ ዘረኛ መንግስት ይብቃን ፋሺስት ወያኔ ይወገድ ብሏል ከጫፍ እስከ ጫፍ።በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ለህወሃት ያደሩ ካድሬዎቹ አምባሳደሮቹ ሳይቀር የወያኔን ኤምባሲ ከድተው ለቀዋል። ህወሃት በየፊናው እየተፍረከረከ ስለመሆኑ ከነሱም ምስክር ሞልቷል። በውጭው ሃገራትም የህወሃት መንግስትን የሚያወግዙ ሰልፎች በኢትዮጵያውያን እየተስተጋባ ነው።
ሌላው የአለም ህብረተሰብም ገመናውን ከተረዱት ቆዩ። ከነዚህም የተባበሩት መንግስታት ሰሞኑን በ አማራ ክልልና እና ኦሮሚያ ክልል በግፍ ለተጨፈጨፉት ኢትዮጵያውያን አጣሪ ኮሚቴ ይመደብ ማለቱ ፥ ግድያውንም እነ ቢቢሲ እና ሌሎች ተደማጭ ሚዲያዎች እያሳበቁት መሆኑ የሚጠቀስ ሲሆን የ አለም አይንና ጆሮ በሙሉ ወደ ብራዚሉ ኦሎምፒክ ትኩረት ባደረገበት ወቅት ላይም የዚህን አምባገነን መንግስት አሳሪነት በማራቶን ሁለተኛ የወጣው አትሌት ለሊሳ ፈይሳ እጁን በማሳየት ተናግሯል። እየደጋገመ የዘገበውም ይሄንን ነው።

የአለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በዚህ አመት ጀመረው ይሄ የ አለም ስደተኞችን ራሳቸውን ወክሎ ማወዳደር የሚበረታታ ተግባር መሆኑን በመቶዎች የሚቆጠሩ አለም አቀፍ ሚዲያዎች አድንቀውታል። በዛው ልክ የተጠቀሱት ሃገራት ሶርያ፣ደቡብ ሱዳን፣ዲ አርሲ፣ ኢትዮጵያ ያለባቸው የመንግስታት ችግር ሙስና በመላው አለም ታውቋል።

በዘንድሮው ኦሎምፒክ ከምንግዜውም በተለየ ህወሃት አንገቱን የደፋበት ሆኖ በማለፉ ደስ ይለናል።
እስከመጨረሽው ህወሃትን በአለም አቀፉ መድረክ እናጋልጣለን::


“ሥራዬን ባጣም ግድ የለኝም…በወር 15 ሺህ ዶላር የሚከፍልበት ሥራ አግኝቻለሁ”ዮዲት ወልደርፋኤል – Video

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ትናንት በፌስቡክከምትሰራበት አሪዞና ኤርፖርት ቭድዮ በመልቀቅ በተለይም ኦሮሞውን እና አማራውን ህዝብ ጸያፍ ቃላት በመናገር እንዲሁም በሁለቱ ብሔሮች ላይ ዛቻ ሰንዝራለች ተብላ በሰፊው መነጋገሪያ የሆነችው ወጣት ዮዲት ሁለተኛውን ቭድዮ ለቀቀች:: በቭዲዮዋ ከሥራዋ ብትባረርም ግድ እንደሌላትና ካሁን በኋላም እዚህ ሃገር ሥራ ላልሰራ እችላለሁ ስትል ገልጻለች:: በሌላ በኩልም 15 ሺህ ዶላር በወር የሚያስገኝ ሥራ ማግኘቷንም ጠቅሳለች:: ሁለተኛው ቭዲዮዋ ላይ የተዘበራረቁ ሃሳቦችን በብዛት ትናገራለች ሲሉም ቭድዮውን የተመለከቱ ተችተዋል::

“ሥራዬን ባጣም ግድ የለኝም… በወር 15 ሺህ ዶላር የሚከፍልበት ሥራ አግኝቻለሁ” ዮዲት ወልደርፋኤል – Video

ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው! (ከይገርማል)

$
0
0

Tomar

አንዳንድ ሰዎች “ለምን ትግሬወችን ከወያኔ ጋር አዳብላችሁ ትወነጅላላችሁ?” ብለው ሲቆጡ አንዳንዴም ሲሳደቡ እያየን: እየሰማን: የጻፉትንም እያነበብን ነው:: እነዚህ ሰዎች ከሁለት የተለያዩ አቅጣጫወች የተነሱ ሊሆኑ ይችላሉ::

 

የመጀመሪያወቹ የመንግስትን አስነዋሪ: ከፋፋይ: ጨቋኝና ዘረኛ ስርአት በማውገዝ ለውጥ መምጣት አለበት ብለው የሚከራከሩና የሚታገሉ አስር የማይሞሉ ትግሬወችን ስም በመጥቀስ ትግሬን ከወያኔ ጋር ደርቦ መወንጀሉ የእኒህን የጸረ ወያኔ ትግል አራማጅ የሆኑ ትግሬወች ትግል ብላሽ የሚያስቀር ብቻ ሳይሆን በተስፋ መቁረጥ ወደወያኔ እንዲጠቃለሉ የሚገፋ ስለሚሆን የተቃውሞውን ጎራ ይጎዳል የሚሉ የዋሆች ናቸው::

 

እኒህ በመጀመሪያው ምድብ የተካተቱት ሰዎች ያልተገነዘቡት ነገር ያለ ይመስላል:: ከልብ አምነው አምባገነኖችን የሚታገሉ ሰዎች ከየትኛውም ጎራ በሚወረወር አፍራሽ እንቅስቃሴ ተበራገው መጠለያ ፍለጋ ወደዚህ ወይም ወደዚያ ሰፈር የሚያጋድሉ አይደሉም:: የሎጅክ ሰዎች ስለሆኑ ማንንም ለማስደሰትም ሆነ ለማስቀየም ብለው የሚያደርጉት ነገር አይኖርም:: የሚያደርጉት ትክክል ነው ብለው የሚያምኑበትን ብቻ ነው:: ያመኑበትን ነገር ለማድረግ የሚያስፈራቸው ነገር የለም:: የተፈጠሩት የተዛባን አመለካከት ወይም ድርጊት ለማስተካከል ስለሆነ ይህን ያመኑበትን ጉዳይ ለማስፈጸም ማንኛውንም መስዋእትነት ለመክፈል ጀርባቸውን የማያሳዩ ናቸው:: የነርሱ የሞራል እርካታ የዴሞክራሲና የፍትህ መስፈን ጉዳይ ነው:: በነዚህ ሰዎች ዘንድ ቀረቤታ: ዝምድና ወይም ጠላትነት ቦታ የለውም:: እነርሱ የሚፈልጉት ዴሞክርሲ: ፍትህና እኩልነት ሰፍኖ ማንም ይሁን ማን በሰራው ስራ በህግ እንዲመዘን ነው::

 

ሌላው  መታወቅ ያለበት ዕውነታ የትግራይ ሕዝብ ፍላጎት አስር በማይሞሉ ውክልና በሌላቸው የወያኔ ተቃዋሚወች የሚለካ አለመሆኑ ነው:: እኒህ ወያኔን እየተቃወሙ ያሉት ሰዎች ዘረኝነት ያልተጠናወታቸው: ሕገወጥ ተግባር በማንም ይፈጸም በማን ህገወጥ እስከሆነ ድረስ እንቃወማለን በማለት ለትግል የተሰለፉ ከብዙሀኑ ለየት ያለ ባህሪ ያላቸው ግለሰቦች(Exceptions) ናቸው:: ከብዙሀኑ አስተሳሰብ ያፈነገጠ አመለካከት ያላቸው ግለሰቦች በየትኛውም ቡድን ነበሩ: አሁንም  አሉ: ወደፊትም ይኖራሉ:: እኒህ በጣት የሚቆጠሩት የራሳቸው ለየት ያለ ስብዕና ያላቸው ግለሰቦች አማኙን ብዙሀን የሚወክሉ ናቸው ብሎ መውሰድ ትክክል አይሆንም::

 

በአሁኑ ጊዜ እየተካሄደ ባለው የሕዝብ የነጻነት ጥያቄ ላይ ችግር እየፈጠሩ ካሉት የለየላቸው ግለሰቦች ወይም ቡድኖች በተጨማሪ የእኛም ድርሻ ቀላል የሚባል አይደለም::

 

ከሊቅ እስከደቂቅ: ከአለቃ እስከምንዝር ያሉት ትግሬወች በማያሻማ መልኩ ትግሬና ወያኔ አንድ ነው ብለው በተደጋጋሚ ነግረውናል:: ከዚህ በላይ ምን ይበሉን? ሲነግሩን እየሰማን መቀበል ካቃተን ችግሩ የማንም ሳይሆን የራሳችን ነው:: እነሱ የሚነግሩንን ሰምተን እንዳልሰማን በተግባር እያደረጉት ያለውን አይተን እንዳላየን ስለሆንን አይደል ጅሎች: ደደብ አህያወች እያሉን ያሉት!

 

እስቲ እንዲያው በሞቴ የትኛው የትግራይ አካባቢ ነው ሰብሰብ ብሎ ወያኔን ሲቃወም የተሰማው? ደርግን ለመቃወም ያልፈራው የትግራይ ህዝብ የራሱን ልጆች ለመገሰጽ የሚፈራ ይመስላችኋል? እሽ! አዎ ፈርቶ ነውም እንበል! ከሀገር ውጪ የሚኖረው የትግራይ ህዝብስ እየተሰባሰቡ ለወያኔ ድጋፍ ከመስጠትና ወያኔን እየተቃወሙ ነው የሚሏቸውን ሁሉ ከማዋከብና ከማዋረድ ወጥተው “ሕዝብን በዘር: በቋንቋና በሀይማኖት መከፋፈሉ ይቁም! የሀገር ጥቅም ይከበር! መንግስታዊ ሙስና ይወገድ!  በትግራይ ሕዝብ ስም አይነገድ!- – -” ብለው የኢትዮጵያን ባንዲራ ለብሰው: መፈክር አንግበው አደባባይ ወጥተው የተቃውሞ ድምጽ ሲያሰሙ ታይተዋል?

 

“ወያኔን እየተቃወሙ ያሉት ጥቂት ትግሬወች እንዳይቀየሙ ስናወግዝ ወያኔን ከትግራይ ሕዝብ ለይተን መሆን ይኖርበታል” ብለው ሊመክሩን የሚነሱት ወይም “ክፉ የሚያደርጉባችሁን በበጎ መልሱላቸው” የሚሉት የግብረገብ ምሁራን የተጣለብንን የጭቆና ቀንበር የሚያጠብቁብን የወዳጅ ጠላት ከመሆን አይዘሉም::

 

ሁለተኛው ቡድን ትግሬወች አድልኦና መገለል ሳይደርስባቸው ከሁሉም ኢትዮጵያዊ ጋር ተመሳስለው እየኖሩ በየአካባቢው የሚደረገውን ፀረ-ወያኔ እንቅስቃሴ እንዲሰልሉ ለማስቻል በሕዝብ አንድነት ስም የሚሰብኩ ልበ-ስውር ሰዎች የተሰባሰቡበት ነው:: ደርግ ከትግራይ ተመቶ የወጣው በወያኔ ሀይል ብቻ አልነበረም:: በወቅቱ የኢትዮጵያ ፕሬዚደንት የነበሩት ኮሎኔል መንግሥቱ ኃ/ማሪያም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪወችን ሰብስበው ሲያነጋግሩ እንዳሉት የትግራይ ሕዝብ ከገበሬ እስከምሁር ወንድ ሴት ሳይሉ ተሰባስበው በሽሬ የነበረውን የመንግስት ሰራዊት እንደጠላት ጦር እንደጨፈጨፉት ነው:: ይህ ብቻም አይደለም: በመላ ኢትዮጵያ በተለይ ደግሞ ወታደራዊ ካምፖች ባሉባቸው አካባቢወች ሁሉ እብድ መስለው: ዘበኛና ገረድ ሆነው: በሽርሙጥና ስራ ተሰማርተው – – -ነው ለወያኔ ሲሰልሉ የነበረው:: ዛሬም በዚያው ተግባራቸው ተሰልፈው ያለስጋት መረጃ እያቀበሉ እነሱ በደስታ እኛ በመከራ: እነሱ በአሰሪነት እኛ በተቀጣሪነት: እነሱ በሀብታምነት እኛ በድህነት: እነሱ በገዥነት እኛ በተገዥነት: እነሱ በመሪነት እኛ በጀሌነት- – – እንድንኖር ለማድረግ ነው ሲያዩት ልክ የሚመስል ሀሳብ እያራገቡ የምናካሂደውን የሞት ሽረት ትግል ለማደናቀፍ በስልት እየተንቀሳቀሱ ያሉት::

 

የኢትዮጵያውያን ሰቆቃ የሚያበቃው በመልመጥመጥ አይደለም:: የህዝብ ትግል ዳር የሚደርሰው በፍርሀት እየራዱ: እንደቄጠማ እያረገዱ የማባበያ ቃላት በመደርደር አይደለም:: እነሱ እንደሚሉን እውነትም ደደብ አህያ ካልሆንን በስተቀር “በደም የተገኘን ስልጣን በካርድ አሳልፈን አንሰጥም! ትግሬና ወያኔ አንድ ነው! ወያኔ ከሌለ ትግሬ የለም ማለት ነው! –” እያሉ እየነገሩን ባለበት ሁኔታ “ወያኔና ትግሬ አንድ ነው የሚለው የወያኔ ወሬ ሀሰት ነው!” ብሎ ያወገዘ አንድም  የትግራይ አካባቢ ሳይኖር ካለማወላወል የሚናገሩትን ትተን ያላሉትን ብለን ለመከራከር ባልደፈርን ነበር!

 

እነ አቦይ ስብሀት ነጋ: እነ ብቸኛው ጀኔራል ሳሞራ የኑስ: ሰምና ወርቅ በሌለው አገላለጽ የወያኔን እና የትግራይን ሕዝብ አይነጣጠሌነት ቁልጭ: ቅቡጭ አድርገው ነግረውናል:: ድርጅቱም ቢሆን የትግራይ ሕዝብ እንጅ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻ አውጭ እንዳልሆነ ከሚጠራበት ስም ጀምሮ እስከሚፈጽማቸው ተግባራት ድረስ ያሉት ጭብጦች አስረጅ ናቸው::

 

ሁሌም ሳስበው ከሚረብሹኝ ነገሮች አንዱ የወልቃይት ጉዳይ ነው:: የወልቃይት ሕዝብ “ኧረ እኛ አማሮች ነን” እያሉ ሲጮሁ “እናንተ ባታውቁት ነው እንጅ ትግሬወች ናችሁ” በሚል መንፈስ በግዳጅ ወደትግራይ መካለላቸውን በመቃወማቸው የደረሰባቸውን ግፍ ሁላችንም እናውቃለን:: ይህን በ21ኛው ክ/ዘመን እየተደረገ ያለውን የወያኔ የቅኝ ገዥነት ተግባር ያወገዘ የትኛው የትግራይ አካባቢ ነው? ወልቃይት አማራ ነው የሚሉትን ወልቃይቴወች ለመቃወም “ለሀገር ሰላም ለህዝብ ፍቅር” ሊለምኑ የሚገባቸው አዛውንትና አሮጊቶች ሳይቀሩ ጠበንጃ ይዘው መውጣታቸውን የማያውቅ ማን አለ? በተቃዋሚወች ጎራ የተሰለፉት ግለሰቦች ሳይቀሩ ታሪክን መሰረት ያላደረገ የተዛነፈ ፍርድ የሚሰጡትስ ለምን ይመስላችኋል? እያሉን ያሉት እኮ ወያኔ በሀይል ስልጣን ላይ ከወጣ ጀምሮ የወልቃይትን ህዝብ እያፈናቀለ የራሴ የሚለውን ወርቅ የትግራይ ሕዝብ እንዲሰፍር አድርጎ ዲሞግራፊውን ካዛባ በኋላ “ሕዝቡ ዴሞክራሲያዊ መብቱ ተከብሮለት በድምጽ ብልጫ ወደሚፈልገው ክልል እንዲካለል ይደረግ” ነው::  እስቲ ሁላችሁም ይህን አካሄድ ልብ በሉት!

 

ክልሎች አብረው መኖር እስካልፈለጉ ድረስ ተገንጥለው የራሳቸው ሀገር ሊመሰርቱ ይችላሉ የሚል የመገንጠል መብት በሕገመንግስት ተቀምጦ እያለ ይቅርና ባይኖር እንኳ ካላንዳች ታሪካዊ መሰረትና ካለሕዝብ ፈቃድ አንድን አካባቢ ከአንዱ ክልል ወደ ሌላ ክልል  በጉልበት ማካለል ፍትሀዊ ሊሆን አይችልም::

 

በወያኔ መሰሪ አካሄድ ሀገራችን ችግር ላይ ናት:: በሕዝቡ መሀል ከአንድነት ስሜት ይልቅ የፍርሀትና የጥርጣሬ ስሜት አይሏል:: የስራ እጦቱ: ድህነቱ: የኑሮ ውድነቱ: የመልካም አስተዳደር ችግሩ: ሙስናው: የዘር ክፍፍሉ: – – – እየከፋ በመሄድ ላይ ነው:: ወያኔ ችግሩን ሁሉ እየፈታ ያለው በኃይል ነው:: ይህ ኃይል የትግራይ ሕዝብ ነው:: ምኑም ያልገባቸው ወይም ለሆዳቸው ያደሩት የሌላ ብሄር አባላትም ቀላል የማይባል ድጋፍ እያበረከቱ ነው:: የትግራይ ሕዝብ እንደህዝብ ወያኔ እንደ ድርጅት በየአገኙት አጋጣሚ ሁሉ አንድ ነን እያሉን ነው: እኛ ደግሞ “ሀሰት አንድ አይደላችሁም!!” ብለን ክርክር ገጥመናል::

 

በደባርቅ ለሶስት ቀን የሚቆይ ከቤት ያለመውጣት አድማ መጀመሩን ተከትሎ ግጭት ተቀሰቀሰ |በትንሹ 10 ሰዎች ተጎድተዋል

$
0
0

ኢሳት (ነሃሴ 17 ፥ 2008) የደባርቅ ከተማ ነዋሪዎች ለሶስት ቀን የሚቆይ ከቤት ያለመውጣት አድማ ማክሰኞች መጀመራቸውን ተከትሎ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ነዋሪዎች የወሰዱትን ዕርምጃ ለማስቆም ያደረጉት ጥረት ግጭትን ቀሰቀሰ።
ESAT
የስራ ማቆም አድማ ያካተተውን ተቃውሞ የተቀላቀሉ የደባርቅ ከተማ ሆስፒታል የህክምና ስራተኞች በቅጥር ግቢው ውስጥ በጸጥታ ሃይሎች ድብደባ እንደተፈጸመባቸው እማኞች ከዜና ክፍላችን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ አስረድተዋል።
በጎንደር ባህር ዳር ከተማ የተፈጸመ ግድያን ለማውገዝና በየከተሞቹ እየተካሄዱ ያሉ ተቃውሞዎችን በመደገፍ የከተማዋ ነዋሪ ማክሰኞ ለሶስት ቀን የሚቆይ ከቤት ያለመውጣትና የስራ ማቆም አድማ መጀመራቸው ታውቋል።
ይሁንና በከተማዋ የሚገኙ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ነዋሪው አድማውን እንዲያቆምና ድርጅቶችን እንዲከፍት ሃይል ቢጠቀሙም ድርጊቱ ወደ ግጭት መለወጡን ነዋሪዎች ለኢሳት አስታውቀዋል።
የጸጥታ ሃይሎች ከነዋሪዎቹ ጋር ያደረጉት ግጭት ለበርካታ ሰዓታት በተኩስ ልውውጥ ውስጥ ቆይቶ የነበረ ሲሆን፣ በትንሹ አስር ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ እማኞች ለኢሳት አስረድተዋል።
በተኩስ ድርጊቱ ጽኑ ጉዳት የደረሰባቸው ነዋሪዎች ወደ ጎንደር ከተማ መወሰዳቸውን የተናገሩት እማኞች ከጸጥታ ሃይሎች መካከልም የተጎዱ መኖራቸውን አከለው ገልጸዋል።
በከተማዋ ለሰባት ሰዓታት ያህል የቆየ የተኩስ ልውውጥ እንደነበር የተናገሩት የደባርቅ ከተማ ነዋሪዎች የሆስፒታል ሰራተኞችና ሃኪሞች በስራ ማቆም አድማ ለመሳተፍ የወሰዱት እርምጃ በስራ ገበታቸው ላይ ድብደባ እንዲፈጸምባቸው ማድረጉን አክለው አስታውቀዋል።
በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የተወሰደው የሃይል እርምጃ በነዋሪው ዘንድ ቁጣን የቀሰቀሰ ሲሆን፣ የከተማዋ ነዋሪዎች ለቀጣዩ ሶስት ቀናቶች ከቤት ያለመውጣት አድማ ውስጥ ለመሰንበት መወሰናቸውን ለመረዳት ተችሏል።
በከተማዋ ውጥረት መንገሱን ለኢሳት በሰጡት ቃለምልልስ የገነጹት የደባርቅ ከተማ ነዋሪዎች ህዝቡ በተለያዩ የሃገሪቱ ቦታዎች ለሚካሄድ ተቃውሞዎች አጋርነቱን ለመግለጽ ውሳኔ መድረሱን አክለው አስረድተዋል።

ለኢትዮጵያ ድምፃውያን በሙሉ! አፋጣኝ መልዕክት

$
0
0

ከጌታቸው በቀለ

በአዲስ አበባ የኢትዮ-ፍራንስ አልያንስ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ዙርያ በተለይ ባህላዊው ላይ ያተኮሩ ጥናታዊ ፅሁፎች እና ታዋቂ ድምፃውያንን እየጋበዘ ሽልማት ይሰጥ እንደነበር አስታውሳለሁ።በአንድ ወቅት ለምሳሌ ጋሽ መሐሙድ አህመድ የአንድ ዓመት እንግዳ ነበር።ከጥቂት አመታት በፊትም አሁን ዓመተ ምሕረቱን ባላስታውሰውም፣ በእዚሁ ዝግጅት ላይ አንዲት ፈረንሳዊት የኢትዮጵያ አዝማሪን በተመለከተ አንድ ፅሁፍ ማቅረቧን አስታውሳለሁ።በእዚህ ፅሁፍ ላይ ከጥንት ጀምሮ አዝማሪ በሕበረተሰቡ መልካም ግንኙነት ላይ ያለውን ሚና በዝርዝር ካቀረበች በኃላ አዝማሪን ስትገልፀው እንዲህ አለች።
´´ አዝማሪ በኢትዮጵያ በፖለቲካም ሆነ በተለያዩ ምክንያቶች የልዩነት ስፋቶች ሲመጡ ይህንን የልዩነት ክፍተት የሚሞሉት አዝማሪዎች ነበሩ´´ብላለች። አባባሉን በደንብ አስፍተን ብናየው ከብዙ አቅጣጫ በደንብ መፈተሽ ይቻላል።
getachew
ይህች ማስታወሻ ግን የኢትዮጵያ ድምፃውያን
– የኢትዮጵያን ሕዝብ አንድነት፣
– የቀደመ እና አሁን መጉላት ያለባቸው የሕዝብ ፍቅር፣
– ኢትዮጵያዊነት፣
– በጎጥ መከፋፈል ያለውን አደጋ ወዘተ ላይ ያተኮሩ አዲሱን ትውልድ ሊያስተምሩ የሚችሉ የኪነት ስራዎች መስራት እንደሚጠበቅባቸው አበክሮ ለማሳሰብ ነው።ወጣቱ ትውልድ ሊሰማቸው እና ጎጠኝነትን እንዲጠላ ሕብረት፣ፍቅር እና በነፃነት መኖር የነገ የኢትዮጵያን ሕይወት ብሩህ የሚያደርግ መሆኑን ሁሉ ማሳየት አሁንም ከከያንያኑ ይጠበቃል።በአገር ቤት ያሉ ከያንያን በተለይ አንጋፋዎቹም እንደገና ማይክ የምታነሱበት እና ስለ ኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነት የምታስተምሩበት ጊዜ ነው።ባለፈ ዘመን ጥሩነት እያሰቡ ከንፈር መምጠጥ አንዳች አይፈይድም።

ይህ ትውልድ በማህበራዊ ድረገፆች አንዴ ኦሮሞነትን ብቻ ሌላ ጊዜ አማራነት ብቻ፣በተደራጀ መንግስታዊ መልክ ደግሞ ትግራይነትን ብቻ በጆሮው ላይ እየጮሁበት ኢትዮጵያዊነት ሳይጎላ እየቀረ የታሪክም ሆነ የትውልድ ተጠያቂ እንዳትሆኑ አስቡበት።እኔ እንደማስበው ከላይ በተጠቀሱት ሃሳቦች ዙርያ አዳዲስ ነጠላ ስራዎችን ለማውጣት ስሜቱ፣ቁጭቱ እና ከጉዳዩ አጣዳፊነት አንፃር ሲታይ በቀናት ውስጥ ሰርታችሁ ማድረስ ያለባችሁ ይመሰልኛል።

በመጨረሻም አንዲት የቴዎድሮስ ካሳሁንን (ቴዲ አፍሮ) የዜማ ስንኝ ብቻ በመምዘዝ ምን ያህል በሕዝብ ዘንድ ኃይለኛ እና አዎንታዊ ስሜት እንደፈጠረ በናሙናነት ላንሳ።

´´ ተስማምቶ የሚኖረው እስላም ክርስቲያኑ፣
ተዘነጋሽ እንዴ ኢትዮጵያ መሆኑ ´´

ይህ ስንኝ ቴዲ አፍሮ ከዘፈነው በኃላ አዲሱ ትውልድ ላይ እስልምና እና ክርስትና ኢትዮጵያ ውስጥ ያላቸው ግንኙነት ከሌላው ዓለም የተለየ መሆኑን በማስተማር ደረጃ የእራሱን በጎ አሻራ ጥሎ አልፏል።ይህ ማለት ቀድሞ አይታወቅም ለማለት ሳይሆን የኪነት ሰዎች በጎ ግንኙነታችንንም አጉልተው እና አስፍተው ሲያሳዩ ሕዝብ በበጎ ግንኙነቱ ይበረታታል።በሌላ በኩል ሕዝቡን ሊለያዩ የሚፈልጉ በጎጥ ሲከፋፍሉት እና ከያንያን ይህንኑ ወቅሰው ስራቸውን ሲያቀርቡ አጥፊም እጁን ይሰበስባል። ስለሆነም የኪነት ሰዎች ከእናንተ ብዙ ይጠበቃል።ኢትዮጵያ መከራ ላይ ሆና አንዳች ሳትሰሩ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከእዚህ ፈተና የወጣ ጊዜ የድል አጥብያ አርበኛ ብትሆኑ ሕዝብ አይቀበላችሁም።

www.gudayachn.com

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክን የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ዋና ጸሐፊ፤ ሃገር ቤት ያለው ሲኖዶስ መንግስት እየፈጸመ ያለውን ኢሰብአዊ ድርጊት እንዲያወግዝ ጥሪ አቀረቡ

$
0
0

london
«አቤቱ የሚገፉኝን ግፋቸው፤ የሚወጉኝንም ተዋጋቸው፤»

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ዋና ጸሐፊ:

ቤተ ክርስቲያናችን የሀገር እና የሕዝብ ባለአደራነት ሃይማኖታዊና ታሪካዊ ግዴታዋን የመወጣት አቅሟ የደከመ፣ ሀኬተኛና ምንደኛ እረኛ ሁናለች። በኦሮሚያና በአማራ የሚደረገው የሕዝብ ጭፍጨፋ አላወገዘችም። ከሦስት ሚሊዮን በላይ የአማራ ከርስቲያኑ ሕዝብ ሲጠፋ ጥያቄ አላቀረበችም። በጋንቤላ የሰው ልጆች ከእንስሳት ባነሰ እየተሰቃዩ በግፍ ሲገደሉ ሐዘንዋን አልገለጸችም። የንጹሐን ደም በግፍ እንደ ጅረት እየፈሰሰ እንደ አቤልና እንደ ናቡቴ ደም የሚያሰማውን ጩኸት ማዳመጥ አልቻለችም። በጠቅላላው በሕዝብና በሀገር ላይ የሚደርሰውን መከፋፈልና መድልኦ የከፋ መከራ ሁሉ በማጋለጥ «አቤቱ የሚገፉኝ ግፋቸው፤ የሚወጉኝንም ተዋጋቸው» የሚል አቤቱታ አላቀረበችም። ሕዝብ በጎሳው ተከፋፍሎ በቂም በቀል ዱላ ለመጨፋጨፍ የተዘረጋው መረብ አንዥባል። ይህ አሁኑኑ በእንጭጩ ካልተቋጨ በቀላሉ የሚገታ አይደለም። በአሮሚያና በአማራ ጎንደር/ጎጃም ክክልል የሲቭል አስተዳደር በወታደራዊ አስገዳጅነት ተተክቶ በተጠመንጃ አፈሙዝ ተከቦና ታፍኖ የቤት እስረኛ ሁኖ ይገኛል። የኢትዮጵያ አርቶዶክስት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አሁንም ጊዜው ሳይመሽ በሀገሪቱ ውስጥ የሚደረገው ጭፍጨፋ ተወግዞ ሰላማዊ ሽግግርና ሁሉን አቀፍ ማዕከሉን የጠበቀና የሰከነ ለውጥ እንዲከናወን ቤተ ክርስቲያን በቁርጠኝነት ከሕዝብ ጎን ቁማ ተቀዳሚ ድርሻዋን መወጣት አለባት በማለት ለቅዱስ ሲኖዶስና ለጠቅላላው በሀገር ውስጥና በሀገር ውጪ ለሚገኙ አህጉረ ስብከትና አጥቢያ አቢያተ ክርስቲያናት በሙሉ በኃይልና በጉልበት ተመክቶ የሰው ልጆችን ሕይዎት ከማጥፋት የፀዳ ሰላማዊ የአንድነት ለውጥ ለማድረግ ሁላችንም በአንድነት እንነሳ”

በማለት ድብዳቤ ጻፉ፤

የደብዳቤውን ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ያንብቡ | PDF

ዮዲት ወልደሩፋኤል (ሄለን ሃይሉ) ለለቀቀችው ዘረኛ ቪዲዮ በኢትዮጵያዊቷ ወጣት የተሰጠ የ12 ደቂቃ የቪዲዮ ምላሽ

$
0
0


ዮዲት ወልደሩፋኤል (ሄለን ሃይሉ) ለለቀቀችው ዘረኛ ቪዲዮ በኢትዮጵያዊቷ ወጣት የተሰጠ የ12 ደቂቃ የቪዲዮ ምላሽ
ዮዲት ወልደሩፋኤል (ሄለን ሃይሉ) ለለቀቀችው ዘረኛ ቪዲዮ በኢትዮጵያዊቷ ወጣት የተሰጠ የ12 ደቂቃ የቪዲዮ ምላሽ

ሀምሌ 06 ቀን 2008 ዓ/ም በአጋዚ የተመታው ወጣት ዛሬ አረፈ |ጎንደር የቤት ውስጥ አድማ ለ2ኛ ጊዜ ተጀምሯል

$
0
0
በወጣት አዳነ ቀብር ላይ የተገኘው የጎንደር ሕዝብ

በወጣት አዳነ ቀብር ላይ የተገኘው የጎንደር ሕዝብ

በወጣት አዳነ ቀብር ላይ የተገኘው የጎንደር ሕዝብ

በወጣት አዳነ ቀብር ላይ የተገኘው የጎንደር ሕዝብ


ወጣት አዳነ

ወጣት አዳነ


ከሙሉቀን ተስፋው
አቶ አዳነ አየነው (የ30 ዓመት ዐማራ) ሀምሌ 6 ቀን በአጋዚ ጦር በጥይት ተመቶ ካንድ ወር በኋላ ሕይወቱ ማለፋን ከወደ ጎንደር የተገኘው መረጃ ያመለክታል። የሰማእቱ ወንድማችን የቀብር ሥነ ሥርዓት በቅዱስ ገብርኤል ቤተ ከርስቲያን ይካሄዳል።

ይህ በዚህ እንዳለ ጎንደር ከተማ በዳግም የቤት ውስጥ አድማ ተመታለች። የጎንደር መንገዶች ሰውም ተሽከርካሪም የለባቸውም። የቤት ውስጥ አድማው ከ5 እስከ 15 ቀን ሊረዝም እንደሚችል ተሰምቷል።


ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ማን ነው? |ሊያደምጡት የሚገባ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በኢትኦጵ ጋዜጣና መጽሔት እንዲሁም በምርጫ 97 ሰሞን ባቋቋማት አባይ ጋዜጣ አዘጋጅነት የምታውቁትና በአሁኑ ወቅት በኢሳት ቲቭና ራድዮ በሚያቀርባቸው ቃለምልልሶች እና ትንታኔዎች የምትወዱትና የምታከብሩት ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና በአውስትራሊያ ለኢሳት ገቢ ማሰባሰብ ላይ ይገኛል:: እዚያው አውስትራሊያ የሚገኘው ጋዜጠኛ ካሳሁን ሰቦቃ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌናን ይበልጥ እንድናውቀውና ስለማንነቱም እንድንገንዘብ የሚያስችል ቃለምልልስ አድርጎለታል – ያድምጡለት::

በኦክላንድ ኒውዚላንድ የምንገኝ ኢትዮጵያዊያን በወቅታዊ የኢትዮጵያ ህዝብ የትግል እንቅስቃሴ አስመልክቶ የወጣ የአቋም መግለጫ

$
0
0

እንደሚታወቀው ላለፉት 25 አመታት መላውን የኢትዮጵያን ህዝብ አፍኖ እየገዛ የሚገኘውና በወንበዴው ህወሀት የበላይነት የሚመራው የወያኔ ቡድን የአገራችንን አንጡራ ሀብት እየዘረፈና ውድ የኢትዮጵያ ፈርጥ የሆኑ ልጆቿን በማሰር በመግደልና በአጠቃላይ የግፍ ቀንበር በመጫን እያደረገ ያለውን ጭፍጨፋ በቁጭት እየተከታተልነው እንገኛለን፡፡
aukland

የኢትዮጵያን ህዝብ በዘርና በቋንቋ በመከፋፈል ህዝብን እርስ በርስ ለማጫረስ ወያኔ እያደረገ ያለውን እኩይ ተግባር የኦሮሞና የአማራ ልጆች እጅ ለእጅ ተያይዘው አስከፊውን ስርአት ከስሩ ገርስሶ ለመጣል በከፍተኛ ደረጃ እየተዋደቁ ይገኛሉ፡፡
በተለይም ከ 8 ወራት በላይ እየዘለቀ ያለው የኦሮሞ ወገኖቻችን እያደረጉ ያለውን መብት የማስከበር ትግል፣ በመቀጠልም በአማራው ወገናችን የተቀጣጠለውን ህዝባዊ እምቢተኝነትና በቀሪዎች የአገራችን ግዛቶች እየተዛመተ ያለውን የአልገዛም ባይነት እንቅስቃሴ ለማፈን በንጹሃን ወገኖቻችን ላይ የወያኔ ወንበዴ አጋዚ ወታደሮች እያደረሱ ያለውን ኢ-ሰብአዊ ጭፍጨፋ እናወግዛለን፡፡

በአገራችን አራቱም ማእዘናት የኢትዮጵያ ህዝብ ለመሰረታዊ የመብት መከበር ጥያቄ ባነሳው የህዝብዊ እምቢተኝነት እንቅስቃሴ በወንበዴው ስርአት እየደረሰበት ያለውን ማንኛውም የኢ-ሰብአዊ ድርጊት ሊያስቆመው አይችልም፡፡ እየተደበደበ፣ እየታሰረ፣
እየተሰደደ፣ እየሞተና ቢዘረዘሩ ቦታ የማይበቃቸው ግፎች እየተፈጸመበት እንኳን ግንባሩን ሳያጥፍ እያደረገ ያለው ተጋድሎ እኛን ያኮራን ሲሆን ይህንኑ ቀጣይ ለማድረግ አስፈላጊውን እገዛ ለማድረግ በቁርጠኝነት እንንቀሣቀሣለን፡፡
በአገራችን ያልተሸራረፈ የዴሞክራሲያዊ ስርአት እንዲገነባ በህዝቦች መካከል ለዘመናት የቆየውን አንድነት ማጠናከርና የሀገራችን ዳር ድንበር ተከብሮ ህዝባችን በአለም አደባባይ ኮርቶ የሚንቀሳቀስበት፣ ከስደትና ረሃብ የሚላቀቅበት እንዲሆን ለማስቻል በወያኔ ህወሀት የሚመራው አምባገነናዊ ስርአትን ለማስወገድ በሚደረገው ህዝባዊ እንቅስቃሴ አጋር በመሆን የተከበረች ኢትዮጵያ እስክትገነባ ድረስ ትግላችን ይቀጥላል፡፡

የወያኔ ቡድን ስርአት እንዳይወድቅ የአጋዚ ቅልብ ወታደሮችና የስርአቱ ደጋፊ በመሆን ትርፍራፊ ለማግኘት የተለጠፉ ሆዳም የስርአቱ አገልጋዮች ከሚያደርጉት እኩይ ተግባራቸው እንዲታቀቡና በመደረግ ላይ ያለውን የህዝባዊ እምቢተኝነት እንቅስቃሴ በመደገፍ ከህዝቡ ጎን እንዲቆሙ አበክረን እናሳስባለን፡፡ የመከላከያም ሆነ የፖሊስ ሰራዊት ዋና ተግባራችሁ የሆነውን አገር ዳር ድንበር የማስከበርና የህዝብን ሰላም ማረጋገጥ መሆኑን ተገንዝባችሁ ከህዝብ ጎን በመቆም አጋርነታችሁን የምታሳዩበት ወቅት አሁን ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በአካባቢያችን ለወያኔ ስርአት የስለላ ተግባር እየፈጸሙ የሚገኙ ወገኖች ከእኩይ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ እያስጠነቀቅን ከዚህ ተግባራቸው የማይታቀቡ ከሆነ ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ እንደምናጋልጥና ጉዳዩንም ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት እንደምናሳወቅ በዚህ አጋጣሚ እንገልጻለን፡፡

በተለይ በህዝባችን መካከል ለዘመናት የቆየውን የአንድነት ትስስር በመናድ በከፋፍለህ አገዛዝ በስልጣን ላይ መቆየት እንደማይቻል እስከዛሬ የዘለቀው የህዝባችን የጋራ ትግል እንቅስቃሴ አይነተኛ ማሳያ መሆኑን የወያኔ መንግስትና ለሰርአቱ በማደግደግ ላይ ያሉ ወገኖች ሊረዱት ይገባል እንላለን፡፡

ስለሆነም በአሁን ወቅት እየተቀጣጠለ ያለውን የነጻነት ጥያቄ መልስ የሚያገኘውና በህዝቦች መካከል ለዘመናት የኖረው አንድነት በአስተማማኝነት ተጠብቆ በሰላም መኖር የሚቻለው ለነዚህ አቢይ የህዝብ መለያ የሆኑትን ሰላምና አንድነት ጠላት የሆነው የወያኔ አምባገነናዊው ስርአት ሲወገድ ብቻ ነው፡፡

በመጨረሻም የሁላችን ጠላት የሆነውን የወያኔ ስርአት ለማስወገድ እና ሁላችንም ተጠቃሚ የምንሆንባትና ነጻነት የሰፈነባትን አገራችን ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በአንድነት ተነስተን እየተቀጣጠለ ያለውን የህዝባዊ እምቢተኝነት ትግል በማንኛውም መልኩ በመደገፍ መሆኑን ሙሉ በሙሉ በማመን ወያኔን በማስወገድ የድል ችቦ እስክናበራ ድረስ ድጋፋችንን በቆራጥነት የምንቀጥል መሆናችንን እንገልጻለን፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

በኦክላንድ ኒውዚላንድ የምንኖር የኢትዮጵያ ማህበረሰብ

ልትጠፋ ያለች ከተማ  በሃዘን ግዜ ዳንኪራ ታበዛለች። –ከተማ  ዋቅጅራ

$
0
0

tiyሰዶም እና  ጎሞራ ሊጠፉ የቻሉበት ምክንያት ነውራቸው ሳያሳፍራቸው ዳንኪራ በማብዛታቸው ነው። በደላቸውን እንደ መላካም ነገር በመናገር፣ ሃጥያታቸውን እንደ ጽድቅ በማውራታቸው፣ ነውራቸውን በአደባባይ ያለ ህፍረት በመግለጻቸው ነበረ የጥፋት እሳት ወርዶ ያጠፋቸው። ዛሬም ገዳይ እንደ ጀግና፣ በዳይና ጨቋኝ እንደ መልካም አስተዳዳሪ፣ በመቁጠር መልሰው መላልሰው ነውራቸውን ይነግሩናል። እኛም ስንመልስ ተዉ…. ዛሬ እዩኝ እዩኝ ነገ ደብቁኝ ይመጣል፣ ግዜ ያነሳውን ግዜ ይጥለዋል፣ መግቢያ  እስቀሚጠፋባችሁ ድረስ የጭንቅ ቀን ይመጣባችኋል፣ እያለን ሰሚ ከተገኘ ከቅድመ አደጋ በፊት  ማሳሰቢያዎችን ከመናገር ውጪ ሌላ የምናደርገው ነገር የለንም።

 

ኢትዮጵያ ድፍን 25 አመት ህዝቦቿን በማጠላለፍ እርስ በራሱ እንዲጠላላና በጠላትነት እንዲተያይ  ያለ መታከት በመስራት እርጉም ሐዋርያ በመሆን በመርዝ የተለወሰ  በብሔር እና ብሔረሰቦች ስም ስብከትን በመስበክ TPLF የበላይ ሆኖ ሁል ግዜም በንግስናው ለማስቀጠል ህዝብንና አገርን በማጥፋት ተልኮአቸውን ሲከውኑ ከርመዋል። የባህር በርን አሳልፈው የሰጡ፣ ከጎንደር እስከ ጋንቤላ የሚያካልለውን ለም መሬት ለሱዳን ለመስጠት ደፋ ቀና የሚሉ፣ በድርጊታቸው ሳያፍሩ መልካም እንደሰሩ በአደባባይ ነውራቸውን ሊነግሩን የሚዳዱ ጉዶች ናቸው።

 

በኢትዮጵያ ውስጥ ህዝቡ ወያኔ አይወክለንም ብሎ በግልጽ በማመጽ ተቃውሞውን የጀመረው በ1997 አመተ ምህረት ነው። ከዛ ግዜ ጀምሮ ውስጥ ውስጡን ሲንከባለል የመጣው ተቃውሞ ዛሬ ሙሉ ኦሮሚያን  እና  ሙሉ አማራን በማካለል እንቢ ለወያኔ ብለው ተቃውሞአቸውን በማቀጣጠል ላይ ይገኛሉ። በኦሮሚያ ከ9 ወር በላይ ያለማቋረጥ ወያኔ በቃኝ ብለው ሲቃወሙ የሚሰጣቸው መልስ ግን ሞትና እስራት በመሆኑ የኦሮሞ  እናቶች ልባቸው በሃዘን ቆስሏል። ህዝባችን ሃዘን ላይ በሆነበት ሰአት የትግራይ እናቶች በወርቅ ቀለም በተጻፈ ትግራዋያን የሚል ሪባን በደረታቸው ላይ በማንጠልጠል በአሜሪካ አገር በኢትዮጵያ  ህዝብ ሃብት ይጨፍሩ ነበረ። ወዮ ለናንተ ወዮ በደሃው ሃዘን ለምትደሰቱ ለናንተ ወዮታ አለባችሁ።

 

በአማራ  ክልል የተነሳው የህዝብ ንቅናቄ የወያኔ ጀሌዎችን እና የTPLF ስር መሰረቱን ያናጋው እንቅስቃሴ ነበረ። ሰላሚዊ ሰልፍ የወጡትን ገሎ መሄድ የለመደው ደም አፍሳሹ  ወያኔ ወደ አማራው ክልልም በመግባት አፍኜ እና ገድዬ እሄዳለው ብሎ የመጣውን የTPLF ሰራዊት በጀግናው ኮሬኔል ደመቀ ዘውዴ መሪነት ለዘላለም እንዲያሸልቡ በማድረግ ለአማራው ህዝብ የትግል አርማ  ሆኖ የተነሳ የዘመኑ ቴዎድሮስ ነው። ጀግናው የጎንደርም ህዝብ ጀግናውን በመከተል በውስጣቸው የነበረውን ጀግንነት እና ለጨቋኝ አልገዛም ባይነት ወኔ ተላብሰው የTPLFን ሰራዊት አብረከረኩት። በውስጣቸው የታመቀው ጭቆና ፈነዳ የነጻነት ሻማም በኮሬኔል ደመቀ አማካኝነት በጎንደር ተለኮሰ። ጎንደር የተለኮሰው የነጻነት ሻማ ጎጃምን፣ ወሎን፣ ሸዋን በማዳረስ ሙሉ አማራን በአንድነት አስተሳስሮ አስነሳ። የአማራው እንቅስቃሴ በመሳሪያ  የታጀበ ስለነበረ  የTPLF ጦር ተብረከረከ ሞት ሞት ሸተተው ድንጋጤም ዋጠው። የወያኔ ንግስና  የታወጀው በወልቃይት በኩል ነበረ ዛሬም የወያኔ ሞት የሚበሰረውም በወልቃይት በኩል ነው። እመኑኝ ይሄ ያልተበረዘ  እውነት ነው። ጀግና  ማለት ሰይጣናዊ ተልኮውን ለማሳካት ህጻንን፣ ሴትን፣ ወጣቱን፣ አዛውንቱን፣ የንጹሃንን ደም እያፈሰሰ  እናቶችን የሚያስለቅስ ሳይሆን …. ጀግና  ማለት እውነትን አንግቦ አንባ  ገነኖችን የሚጥል ሃቀኛ ታጋይ ነው።  ይሄ ጀግንነት ደግሞ  በመላው ኢትዮጵያ  ልቦናውስጥ ያለ  ሃቅ ነው። ሃሰትን ይዞ በጉልበቱ እና በጦሩ ከተመካው ጎልያድ ይልቅ እውነትን ይዞ በእግዚአብሔር የተመካው ትንሹ ዳዊት በጠጠር እና በወንጭፍ አሸናፊ እንደሆነ አስቡ። እውነት ምን ግዜም አሸናፊ ነው። በሰራዊት እና  በፈረሰኞቹ ከሚመኩት ጥጋበኞች ይልቅ እውነትን ይዘው የሚወጡት ሰፊው የኢትዮጵያ  ህዝብ ድል በእጁ ነው።

 

የጥፋት ምልክቶች እየታዩ  ነው።

የኢትዮጵያ  እናቶች እና  ህዝብ ሃዘን ላይ ናቸው። የስራ ማቆም አድማ፣ የሃዘን ቀን አዋጅ፣ የነጻነት ተጋድሎ ቀን፣ ህዝባችን እየወደቀ  እየተነሳ ባለበት ወቅት የትግራይ ህዝብ ግን ከበሮ እየደለቁ በአደባባይ ህዝባቸውን ሰብስበው አሸንዳ እያሉ ይጨፍሩብናል። ልትጠፋ  ያለች ከተማ  እና  ህዝብ በሃዘን ወቅት ጭፈራ  ያበዛሉ ይባላል። እነሱ ይጨፍሩብናል ምክንያቱም ሞት እነሱ ጋር አልገባማ ሃዘን እነሱ መንደር የለማ ጭቆና በነሱ መንደር አይታወቅማ። ዋ ለናንተ ልቦናችሁን ላደነደናችሁ፣ ዋ ለዛች ትግራይ ከተማ፣ ዋ ለናንተ  በራችሁን ዘግታችሁ በሰው ሃዘን በደስታ ለምትጨፍሩት፣ ደስታቹሁ በሃዘን ሳቃችሁ በለቅሶ እልልታችሁ በዋይታ እንደሚቀየር  አታውቁምን? አንድ ጽሁፍ አንብቤ  ነበረ  (ለትግራይ ህዝብ ጸልዩ) የሚል አዎ በእውነት ለሚመጣባችሁ እና  ለማይቀረው መዓት ትልቅ ጸሎት ያስፈልጋችኋል።  ጸሎቱ ምህረትን ሊያመጣ የሚችለው ግን ለሚመለስ ልብ ባቻ ነው እንጂ ጥፋቱ በራፉ ላይ ደርሶባቸው ዛሬም ያልሆኑትን ትግራዋያን ጀግና እያሉ ጥፋታቸውን ለሚያፋጥኑት አይደለም።

 

ሳጠቃልለው እውነት እውነት እላችኋለው ሰዶምና ጎመራ በነውራቸው እየጨፈሩ እንደጠፉት ሁሉ ዛሬም በኢትዮጵያ  ህዝብ በአዘናቸው ሰዓት ደስታቸው በማድረግ የሚጨፍሩት ከተማና  ህዝብ ይጠፋሉ። ይሄ  የሚሆነው ስለተናገርንም አልያም ዝም ስላልንም አይደለም መሆን ያለበት እውነት ስለሆነ እንጂ። ህዝብ ከተነሳ  ሰደድ እሳት ነውና ከፊቱ ያለውን በሙሉ ጠራርጎ ያጠፋል። አበቃው።

 

 

ከተማ ዋቅጅራ

26.08.2016

Emial- waqjirak@yahoo.com

ቋሪት በሕዝብ ቁጥጥር ስር ዋለች  በወልቃይት የአማርኛ ሙዚቃ አትሰሙም በሚል ግጭት ተፈጠረ * በበርከታ የጎጃም ከተሞች የዐማራ ተጋድሎ ተፋፍሟል (የዛሬው የትግል ውሎ ዝርዝር ዘገባ)

$
0
0

በበርከታ የጎጃም ከተሞች የዐማራ ተጋድሎ ተፋፍሟል፤ ራሳቸውንም ከወያኔ አገዛዝ ነጻ አድርገዋል

• 40 የዐማራና ኦሮሞ የጸረ ሙስና ኮሚሽን አቃቢ ሕግ ባለሙያዎች ከሥራ ተባረሩ
 በቡሬ ከተማ ከሠላሳ ሺህ በላይ ዐማራ ለተጋድሎ ወጥቷል፤ የኦሮሚያ ኢንተ. ባንክን ሕዝቡ ጥበቃ አድርጎለታል
 በጅጋ የተጋድሎ ሰልፉ ሦስተኛ ቀኑን ይዟል
 ቋሪት ወረዳ ሙሉ በሙሉ በሕዝብ ቁጥጥር ሥር ሆኗል
 ማንኩሳ፣ ፍኖተ ሰላምና ጉንደወይን ሌሎች የዐማራ ተጋድሎ የተካሄደባቸው ከተሞች ናቸው
 በጎንደር ብዙ የዐማራ ልዩ ኃይል ፖሊስ አባሎች ከሥራ ታግደዋል
 በደብረ ታቦር የሥራ ማቆም አድማ ሊጀመር ነው
 በወልቃይት የአማርኛ ሙዚቃ አትሰሙም በሚል ግጭት ተፈጠረ

ከሙሉቀን ተስፋው

ቡሬ፤ በሬ ዛሬ የዐማራ ተጋድሎ ከተካሔደባቸው ከተሞች ዋነኛዋ ናት፡፡ ከጠዋቱ ሦስት ሰአት አካባቢ የጀመረው የዐማራ ተጋድሎ እስከ ምሽት 12 ሰአት ድረስ ቆይቷል፡፡ የተጋድሎ ሰልፉ ማዶ በሚባለው የከተማው ክፍል የተጀመረ ሲሆን ከሰላሳ ሺህ በላይ የሚሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች ተጋድሏቸው ሲያሰሙ ውለዋል፡፡ ወልቃይት ዐማራ ነው፤ ኮ/ል ደመቀ እና የወልቃይት ጠገዴ የዐማራ ማንነት ጥያቄ አቅራቢ ኮሜቴዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይፈቱ፤ መሬታችን ይመለስ፤ 25 ዓመት ታስረናል አሁን ግን በቃን፤ ዐማራነት ወንጅል አይደለም፣ ወያኔ ሌባ ነው፤ ብአዴን እኛን አይወክልም… የሚሉ መፈክሮች ገልተው ሲሰሙ ውለዋል፡፡ የወያኔ ደጋፊ የሆኑ ድርጅቶችና ግለሰቦች ንብረት ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ ትንሳኤ ሆቴል (ባለቤቱ ዐማራ ሲያስገድል የኖረ ሕወሓት ነው)፣ ቀበሌ 01 ጽ/ቤት፣ አብቁተ፣ የዓባይና የንግድ ባንኮች መጠነኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክን ሊያወድሙ የሚፈልጉ ተላላኪዎችን ወጣቱ ዐማራ አክሽፎታል፡፡ ኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ የሚደርሰው ግፍ መቆም አለበት ሲሉም የዐማራ ሕዝብ አጋርነቱን አሳይቷል፡፡

በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ አደጋ መኖሩን በተመለከተ ላቀረብነው ጥያቄ የዐይን ምስክር ሲናገሩ ‹‹እኔ በዐይኔ አንድ ለእረፍት የመጣ የዩንቨርሲቲ ተማሪ አጋዚ ሲገድለው አይቻለሁ፤ ሦስት ዐማሮችም በጥይት ተመተው ሆስፒታል ገብተዋል፤ በሕይወት ስለመኖር አለመኖራቸው ያወቁት ነገር የለም›› ብለዋል አንድ እማኝ በስልክ እንዳረጋገጡልን፡፡ የአጋዚ ወታደሮች ያቆሰሏቸው ሰዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ በቡሬ ከተማ መግቢያና መውጫ በሮች ሙሉ በሙሉ በወጣቱ ተዘግተዋል፡፡
bure1
ጅጋ፤ የጅጋ ዐማሮች ዛሬ ለሦስተኛ ቀን የዐማራ ተጋድሎ አድርገዋል፡፡ የጅጋ ከተማ ሕዝብ ከነሃሴ 18 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ በየቀኑ ወደ አደባባይ እየወጣ ተጋድሎውን እያደረገ ነው፡፡ በጅጋ እስካሁን አንዲት እህታችን ተሰውታለች፡፡ ከተማዋንና አጠቃላይ ወረዳውን ዐማሮች ራሳቸው የተቆጣጠሩ ሲሆን ዛሬ ላይ የሃይማኖት አባቶች ወጣቱን ለመሰብሰብ ሞክረው ነበር፡፡ የዐማራው ወጣትም ከእንግዲህ በኋላ የዐማራ የመኖር መብት ሳይረጋገጥ ተጋድሎው እንደማይቆም እንቅጩን በአንድ ድምጽ ተናግረው ስብሰባው ያለስምምነት መበተኑን ከቦታው በስልክ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ በጅጋ ለተከታታይ ሦስት ቀናት ምንም ዓይነት የንግድ እንቅስቃሴም የለም፡፡ ሁሉም ዐማራ የተጋድሎ ጥያቄውን እያስተጋባ ነው፡፡ በስልክ ያነጋገርናቸው ወጣቶች ‹‹ከእንግዲህ በኋላ ዐማራነት ወንጅል ሆኖ የምንኖርበት ምንም ምክንያት የለም፤ የአባቶቻችን የአርበኝነት ታሪክ በዚህ ትውልድ ይደገማል›› ሲሉ በጎበዝ አለቃዎች ጭምር መመራት መጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡
ቋሪት፤ በቋት ወረዳ ገነት አቦ ከተማ ትናንት ነሃሴ 19 ቀን 2008 ዓ.ም. የተጀመረው የዐማራ ተጋድሎ አድማሱን አስፍቶ የወረዳዋ ከተማ ገበዘ ማርያምም በሕዝብ ቁጥጥር ሥር ሆናለች፡፡ ገነት አቦ ከተማ ትናንት ከቀኑ ከ9፡00 እስከ 12፡00 የነበረውን የዐማራ ተጋድሎ ለማደናቀፍ ከወረዳው የወያኔ ተላላኪዎች የተውጣጡ የፖሊስና የሚንሻ አባላት ወደ ገነት አቦ ተላኩ፡፡ የገነት አቦ ዐማሮችም በአንድ ድምጽ ‹‹በመጣችሁበት መኪና አሁኑ ተመለሱ፤ አይ ካላችሁ ሕይወታችሁን ጠልታችኋል ማለት ነው›› አላቸው፡፡ ከመኪና ሳይወርዱ ተመለሱ፡፡ የከተማዋ ነዋሪዎች ለዛሬ ጠዋት ቀጠሩ፡፡ በቃላቸው መሠረት ከጠዋቱ 12፡00 ጀምሮ የተጋድሎ ሰልፉ ተካሄደ፡፡ የገበዘ ማርያም ከተማ ዐማሮችም ተጨመሩ፡፡ የከተማ ፖሊሶች ዝም አሉ፡፡ ከዞን የመጣ ሁለት መኪና የፌደራል ፖሊስም የቋሪትን ዐማራ መጋፈጥ አልቻለም፡፡ የፌደራል ፖሊሶች ልብሳቸውን ቀይረው ተደብቀው ዋሉ፡፡ ነፍጠኛው ዐማራ ጥይቱን ሲቆላው ዋለ፡፡ ለዚህማ ቋሪትን ማን ብሎት፡፡ በቋሪት ነገም የዐማራ ተጋድሎ ይቀጥላል፡፡
ማንኩሳ፤ በማንኩሳ የተጀመረው የዐማራ ተጋድሎ ለሁለተኛ ቀን መቀጠሉን ሰምተናል፡፡ በማንኩሳ ትናንት የተካሔደው የዐማራ ተጋድሎ መጠነኛ ቢሆንም ዛሬ ግን ወደ አደባባይ ያልወጣ የከተመዋ ነዋሪ አልነበረም ነው የተባለው፡፡ በማንኩሳ ዝርዝር ጉዳዮችን በስልክ መቆራረጥ ምክንያት ማግኘት አልቻልንም፡፡
Bure
ፍኖተ ሰላም፤ በፍኖተ ሰላም ከተማ የዐማራ ተጋድሎ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል፡፡ ትናንት የአንድ ዐማራ ወጣት ነፍስ ያጠፈው ቅጥረኛ ምንሻ ቤት መቃጠሉንም ሰምተናል፡፡ የፌደራልና የአጋዚ ጦር በፍኖተ ሰላም ከተማ ከመጠን በላይ መግባቱን ሰምተናል፡፡ ዛሬ ይህ ሪፖርት እስከተሠራበት ሰዐት ድረስ መንገዶች ሁሉ ዝግ መሆናቸውን ሰምተናል፡፡

ጉንደወይን፤ በእነሴዎች አገር ጉንደወይን ትናንት ነሃሴ 19 ቀን 2008 ዓ.ም. ታላቅ የዐማራ ተጋድሎ ሰልፍ ተካሒዷል፡፡ የጎንቻ ሲሦ እነሴ ወረዳ ዐማሮች ትናንት ባካሔዱት ተጋድሎ የትግራይ የበላይነት ይብቃ፣ የማንነት ጥያቄያችን መልስ ይሰጥ፣ ዐማራነት ወንጀል አይደለም፣ የወንድሞቻችን ደም መፍሰስ መቆም አለበት… የሚሉ መፈክሮች መሰማታቸውን ዛሬ ከጉንደ ወይን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ በተያያዘም ነሃሴ 18 ቀን 2008 ዓ.ም. በብቸና አንድ የአገዛዙ መሣሪያ የሆነ ሰው ተገድሎ መገኘቱንም ሰምተናል፡፡

ደብረ ታቦር፤ በደብረ ታቦር ከተማ ከነሃሴ 22 ቀን ጀምሮ ለሦስት ቀን የሚቆይ የቤት ውስጥ አድማ እንደሚደረግ መርሃ ግብሩ ያሳያል፡፡ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች እንዳትወጡ የሚሉ ማስታዎቂያዎች ተለጥፈዋል፡፡ ይህን ተላልፎ በሚገኝ ሰው ላይም የዐማራውን ተጋድሎ እንደመተላለፍ ስለሚቆጠር ከህዝብ ጋር እንደተጣላ ይቆጠራል ተብሏል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ቅጥረኛ ካቢኒዎች ነጋዴዎችን ሱቆቻቸውን እንዳይዘጉ ያስጠነቀቀ ሲሆን የቤት ውስጥ ተጋድሎው አስተባባሪዎች ማንኛውንም ተቋም የሚከፍት ሰው ከወያኔዎቸ ጋር እንዳበረ ስለሚቆጠር የሚያስከፍለው ዋጋ የከፋ ነው ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ጎንደር፤ ጎንደር የቤት ውስጥ አድማው ለሦስተኛ ቀን ቀጥሏል፡፡ የቤት ውስጥ አድማው እስከ እሁድ ይደርሳል ተብሏል፡፡ ኮሎኔል ደመቀን የመውሰድ እቅዱ መክሸፉን የሰማን ሲሆን ትናንት ምዕራብ አርማጭሆ አብደራፊ አካባቢ አንድ ዐማራ የተሰዋ ሲሆን ሁለት የወያኔ ቅጥረኛ ፖሊሶች ዛሬ መገደላቸውን ሰምተናል፡፡

የጎንደር ከተማ ልዩ ኃይል ፖሊስ ምክትል አዛዥ መልካሙ የሽዋስ ጋርም ብዛት ያላቸው የፖሊስ አባላት በወያኔ ትእዛዝ መቀነሳቸውን ሰምተናል፡፡ የተቀነሱት የዐማራ ልዩ ኃይል ፖሊስ አባላት በሕዝብ ላይ ባለመተኮሳቸው ነው የተባለ ሲሆን ሁሉም የዐማራ ፖሊሶች በዐማራው ሕዝብ ላይ እንደማይተኩሱ ቃል ገብተዋል ሲሉ ምንጮቻችን ነግረውናል፡፡

gonder

አዲረመጥ፤ በወልቃይት ከተማ አዲረመጥ ትናንት ነሃሴ 19 ቀን 2008 ዓ.ም. የወልቃይት ዐማሮች የፋሲል ደመወዝን ‹‹ዐማራ ነኝ›› አዲስ ሙዚቃ ከፍተው ሲያዳምጡ የትግራይ ልዩ ኃይል ፖሊስ ‹‹አማርኛ ሙዚቃ ማዳመጥ አትችሉም›› በማለቱ በተፈጠረ ግጭት ከስድስት በላይ የሚሆኑ ፖሊሶች በከፍተኛ ሁኔታ ቆስለው አምልጠዋል፡፡ አንድ የወልቃይት ዐማራ በጥይት የተመታ ሲሆን ለሕይወቱ አስጊ እንዳልሆነ ከቦታው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አዲስ አበባ፤ 40 የዐማራና ኦሮሞ ተወላጅ የጸረ ሙስና ኮሚሽን አቃቢ ሕግ ባለሙያዎች ከሥራ ተባረሩ፡፡ ከአዲስ አበባ የጸረ ሙስና ኮሚሽን ዋና መሥሪያ ቤት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው በሙስና ወንጀል የተዘፈቁ የትግራይ ተወላጆችን መዝገብ ክስ የያዙ 40 የዐማራና ኦሮሞ የአቃቢ ሕግ ባለሙያዎች ከሥራ ተባረዋል፡፡ የተባረሩት የአቃቢ ሕግ ባለሙያዎች በሥራቸው የተመሰከረላቸውና አንቱ የተባሉ የሕግ ባለሙያዎች ናቸው ተብሏል፡፡ ሆኖም የያዙት የሙስና ክስ መዝገብ የትግራይ ተወላጅ ሙሰኞችን በመሆኑ ሕወሓትን በከፍተኛ ሁኔታ ያዳክማል በሚል የዐማራና የኦሮሞ የሕግ ባለሙያዎቹ ከሥራ ገበታቸው ለመጨረሻ ጊዜ ተባረዋል፡፡ ወያኔ ከዚህ በፊትም እንደ ዳኛ ግዛቸው ምትኩ ያሉ ጠንካራ የዐማራ የሕግ ባለሙያዎችን የማባረር ልምድ መኖሩን ያስታውሷል፡፡

የዐማራ ሕዝብ ተጋድሎ ያሸንፋል::
ይህ ሁሉ የመጨረሻው መጀመሪያ ነው!!

ውሾቹን «ተው» በሏቸው –ዲ/ን ዳንኤል ክብረት – (ማሳሰቢያ አንብበው ካልጨረሱት አያንብቡት)

$
0
0

በኦሮምኛ አንድ ድንቅ ተረት አለ፡፡ በአንድ የኦሮሞ መንደር ውስጥ ሮቤል መገራ የሚባሉ ጥበበኛ ሽማግሌ ነበሩ፡፡ አንድ ቀን የሁለት ጎረቤታሞች ንብረት የሆኑ ሁለት ውሾች ሲጣሉ ያያሉ፡፡

እኒህ ጥበበኛ ሽማግሌም «እነዚህን ውሾች እንገላግላቸው፤ ያለበለዚያ ችግራቸው ለሁላችንም ይተርፋል፣ በዓለም ላይ ችግር የሚነሣው ከአጥንት በላይ ማሰብ በማይችሉ ውሾች የተነሣ ነው» ይላሉ፡፡ በአካባቢው የነበሩ ሽማግሌዎች እና መንገደኞችም በሽማግሌው አባባል ተገርመው «ሁለት ውሾች ተጣልተው ምን ሊያመጡ ነው» እያሉ ሳቁባቸው፡፡

በዚህ መካከል ከሁለቱ ጎረቤታሞች መካከል አንድ ልጅ ወጣና የውሾቹን ጠብ ተመለከተ፡፡ የእርሱ ውሻ የተበደለ ስለመሰለው ፍልጥ አምጥቶ ያኛውን ውሻ ደበደበው፡፡ ወዲያውም ከሌላኛው ቤት ሌላ ልጅ ወጣና ያኛውን ውሻ መደብደብ ጀመረ፡፡

daniel

ነገሩ ወደ ሁለቱ ልጆች ተዛመተና በውሾቹ ምትክ ልጆቹ ይደባደቡ ጀመር፡፡ ሽማግሌውም «እባካችሁ እነዚህን ልጆች አስታርቁ» አሉ በሥፍራው የነበሩትም «ተዋቸው ይዋጣላቸው» ብለው እንደ ቀልድ አለፉት፡፡

ልጆቹ እየተደባደቡ እያሉ የአንዱ እናት ብቅ አለች፡፡ ወዲያውም ያኛውን ልጅ በፍልጥ ታንቆራጥጠው ጀመር፡፡ የልጇን ጩኸት የሰማቺው ሌላዋ እናትም መጣች፡፡ የልጆቹ ጠብ ቀረና ድበድቡ በሁለቱ እናቶች መካከል ሆነ፡፡

ሮቤል መገራም «እባካችሁ ይህ ጠብ ተዛምቶ ሁላችንንም ከማካተቱ በፊት ገላግለን እናስማማቸው» አሉ፡፡ ተመልካቾቹ ግን የሁለቱን ጠብ እንደ ነጻ ትግል እያዩ ይዝናኑ ነበር፡፡ አንዳንድ ሽማግሌዎችም «ሁለት
ሴቶች ተጣልተው የት ይደርሳሉ» እያሉ ንቀው ተውት፡፡

በግርግሩ የከበቡትን ሰዎች እየጣሰ አንድ ሰው ወደ መካከል ገባ ያንደኛዋ ባል ነበር፡፡ እንዴት ሚስቴን ትመቻታለሽ ብሎ ያቺኛይቱን ሴት መደብደብ ያዘ፡፡ ይኼኔ ነገሩን የሰማው ሌላኛው ባልም ሲሮጥ መጥቶ ድብድቡን ተቀላቀለ፡፡

ሮቤል መገራ አሁንም «እባካችሁ ገላግሏቸው፤ ይህ ጠብ ለሀገር ይተርፋል» ሲሉ ተናገሩ፡፡ ሰሚ ግን አላገኙም፡፡ ሁሉም የራሱን ልጅ፣ ሚስት እና ቤት ብቻ ይጠበቅ ነበር፡፡

ወንዶቹም ልጆቻቸው እና ሚስቶቻቸው እንዳይገቡ ይቆጡ ነበር። የሁለቱ ባሎች ጠብ ተባባሰ፡፡ ሕዝቡም ከብቦ ያይ ጀመር፡፡ በዚህ መካከል የሰውዬው ወገኖች ነን ያሉ ያንደኛዋን ባል መደብደብ ያዙ፡፡

ተመልካች ሆነው ከቆሙት መካከል የዛኛው ወገን ነን የሚሉ ደግሞ ያኛውን ይዘው ይደበድቡ ጀመር፡፡ እንዳጋጣሚ የሁለቱ ሰዎች ጎሳች የተለያዩ ስለነበሩ ጠቡ ወደ ጎሳ አደገ፡፡ ዱላ እና እጅ ብቻም ሳይሆን የጦር መሣርያም ተጨመረበት፡፡

ቤት ንብረት መዝረፍ፣ ማቃጠል እና መግደል እየተባባሰ መጣ መንደሩም የጦርነት አውድማ ሆነ፡፡ ከሁለቱም ወገን ስምንት ስምንት ሰዎች ሞቱ፡፡ በስንት መከራ ጠቡ ቆመ፡፡

ሮቤል መገራም አዘኑ፡፡ «ውሾቹ ሲጣሉ ብናስቆማቸው ኖሮ ጎሳዎቹ አይጣሉም ነበር» አሉ፡፡ ሽማግሌዎቹ ጉማ ተቀመጡ፡፡
በባህሉ መሠረት ለእያንዳንዱ ለሞተው ነፍስ ከሌላው ወገን ሰው
ይገደላል ወይንም መቶ መቶ ከብት ይሰጣል፡፡

ይህ ከሆነ ደግሞ ከሁለቱም ወገን ስምንት ስምንት መቶ ከብት ያስፈልጋል ማለት ነው፡፡ በሞቱት ምትክ ከሌላው ወገን ሰው ይገደልም ከተባለ በተጨማሪ አስራ ስድስት ሰዎች ሊገደሉ ነው፡፡ የሟቾቹም ቁጥር ወደ ሠላሳ ሁለት ከፍ ሊል ነው፡፡ ይህ ነገር ሽማግሌዎቹን አስጨነቀ፡፡

ይኼኔ ሮቤል መገራ ተነሡ፡፡ «ቅድሞ እኔን ሰምታችሁኝ ቢሆን ኖሮ
መልካም ነበር፡፡ እያንዳንዳችን ስለ ራሳችን እንጂ ስለ ሌሎች ግድ ስለሌለን ዕዳው በመጨረሻ እኛው ላይ መጣ፡፡ ውሾቹን ተው
ማለት አቅቶን እዚህ ደረጃ ደረስን፡፡

ምን ጊዜም ጦርነቶች የሚነሡት ውሾቹን ተው የሚል እየጠፋ ነው፡፡ ጎረቤት እና ጎረቤት፣ ጎሳ እና ጎሳ፣ ንጉሥ እና ንጉሥ፣ ሀገር እና ሀገር፣ እስላም እና ክርስቲያን፣ መንደር እና መንደር፣ የሚጣላው ውሾቹን ተው
የሚል እየጠፋ ነው፡፡ የጦርነት መነሻ ውሾች ናቸው፡፡

ውሾቹ በአጥንት የጀመሩት ጠብ ሕይወት አስከፈለን፡፡ እነዚህ ውሾችኮ
ከአጥንት በላይ አርቀው ማሰብ የማይችሉ ውሾች ናቸው፡፡ ዓላማቸው አጥንት መጋጥ ብቻ ነው፡፡ አገር ቢጠፋ፣ ሕይወት ቢጠፋ፣ ንብረት ቢጠፋ እነርሱ ምን ጨነቃቸው፡፡

እንዴት ከአጥንት በላይ ማሰብ የማይችሉ ውሾች ይህንን ሁሉ ዋጋ ያስከፍሉናል? «እነዚያን ውሾች ለያዩዋቸው ስላችሁ ሁላችሁም የእናንተ ውሾች አለመሆናቸውን ብቻ ነበር የምታዩት፡፡ ሌሎች ተበጥብጠው እኛ እንዴት ሰላም እንሆናለን? ሌሎች እየተዋጉ እንዴት እኛ በደኅና እናድራለን? ሌሎች ተርበው እንዴት እኛ እንጠግባለን? የማይሆን ነገር ነው፡፡

በሉ አሁንም ሌላ ሕይወት ማጣት የለብንም፣ ከብቶቻችንንም ማጣት የለብንም፤ ከሁለቱም ወገን የየአንገ ታችሁን የብር ማተብ አምጡ፤ ያንንም ሰብስባችሁ ወንዝ ውስጥ ጣሉ፣ ሁሉም ጦሱን ይውሰድ፤ እናንተ ግን ይቅር ተባባሉ» ብለው አስታረቋቸው ይባላል፡፡

ውሾቹን «ተው» ካላልናቸው የመጨረሻውን ውጤት ማንም ሊገምተው አይችልም፡፡ ሂትለር እና ሞሶሎኒ የሚባሉ ውሾች ሲነሡ ማንም «ተው» ማለት አቅቶት ዓለምን በእሳት ለበለቧት፡፡ በወቅቱ አይሁድ እየተሰቃዩ መሆኑን የተለያዩ ምንጮች እየተናገሩ ምዕራባውያን ግን ዓይናችንን ግንባር ያድርገው ብለው በበርሊን ኦሎምፒክ ሂትለርን ሲያመሰግኑ ሰነበቱ፡፡

እንዲህ በመጨረሻ ጦሱ ለእነርሱም ሊተርፍ፡፡ ቀዳማዊ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ በዓለም ማኅበር ተገኝተው ውሾቹን «ተው» በሏቸው ሲሉ ተናግረው ነበር፡፡

ብዙዎች ራሳቸው እንደ ውሻ በመጮኽ የንጉሠ ነገሥቱን ንግግር ለመበጥበጥ ሞከሩ እንጂ አልሰ ሟቸውም ነበር፡፡ በመጨረሻ ግን የውሾቹ ጠብ ወደ ዓለም ጦርነት ተቀየረ፡፡

ዛሬ ዓለም በኢራን የኑክሌር መሣርያ እንዲጨነቅ ያደረገቺው ራሷ አሜሪካ ናት፡፡ ኢራኖች ኒኩልየር የሚባል መኖሩን ባላወቁበት ዘመን የግድ ኒኩልየር ካልኖራችሁ ብላ በራቸውን አንኳኩታ ስትሄድ ዓለም በዝምታ ነበር ያያት፡፡ ያኔ ውሾቹን «ተው» የሚላቸው ቢኖር እንዲህ እሥራኤል እና አሜሪካ በጭንቀት ውለው አያድሩም ነበር፡፡

አሜሪካ ሶቪየት ኅብረትን ከአፍጋኒስታን ለማስወጣት ቢን ላድንን
ስታሠማራ ተይ የሚላት ባለመኖሩ ራስዋ ያመጣችው መከራ ለእርሷም ለዓለምም ተረፈ፡፡ ያሳደግኩት ውሻ ነከሰኝ፣ የቀለብኩት ፈረስ ጣለኝ እንደሚባለው ሆነ፡፡

ሩዋንዳ ላይ ሬዲዮ ከፍተው ጎሳ ከጎሳ የሚያጣላ ፕሮግራም የሚያራምዱትን፣ ግደሉ ጨፍጭፉ እያሉ የሚያቅራሩትን ውሾች በወቅቱ ፈረንሳዮች በዝምታ ነበር ያዩዋቸው፡፡ የሩዋንዳ ጭፍጨፋ
ሲጀመር የተባበሩት መንግሥታት ድርጀትን ጨምሮ ብዙዎች አይተው እንዳላዩ፣ ሰምተው እንዳልሰሙ ሆኑ፡፡ ውሾቹን ተው የሚል ጠፍቶ ውሾቹ ያመጡት ጣጣ ምሥራቅ እና መካከለኛው አፍሪካን የሚያቃጥል እሳት ወለደ፡፡

ለዚህ ነው ከአጥንት በላይ ማሰብ የማይችሉትን ውሾች በጊዜ «ተው» ማለት የሚያስፈልገው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ እዚህ ቦታ እንዲህ ያለ ቤተ እምነት ተቃጠለ ሲባል በዝምታ እየታየ ነው፡፡ ይህ እኩይ ተግባር ማንኛውንም የእምነት ማኅበረሰብ የሚወክል ነው ተብሎ ፈጽሞ አይታመንም፡፡ ነገር ግን ሙስሊሞችም ሆኑ ክርስቲያኖች ይህንን እሳት
የሚለኩሱትን ውሾች «ተው» ልንላቸው ይገባል፡፡

ያለበለዚያ ፍጻሜው ለሁላችንም ይደርስና ከባድ ዋጋ ይጠይቀን ይሆናል፡፡ እነዚህ ውሾች ከዕለት አጥንት አርቀው ማሰብ አይችሉም፡፡
ለጊዜው ከሌላው ጋር ተሻምተው አንድ አጥንት ማግኘታቸውን ብቻ
ነው የሚያውቁት፡፡

እዚህ ዓይን ማጥፋት፣ እዚያ አሲድ መድፋት፣ እዚያ ሕፃን መድፈር፣ እዚህ ግብረ ሰዶም፣ እዚያ አካል ማጉደል፣ እዚህ በፈላ ውኃ መንከር ሚዲያዎቹ ይጮኻሉ፣ በሹክሹክታ ይነገራል፣ አንድ ሰሞን ጉድ ይባላል፡፡ ውሾቹን ተው የሚላቸው ግን እየጠፋ ነው፡፡

እነዚህን ሕፃናትን የሚደፍሩትን፣ የእኅቶቻችንን አካል የሚያጎድሉትን፣ በአውሬነት መንፈስ አረመኔ ተግባር የሚፈጽሙትን ውሾች ተው የሚል አልተገ ኘም፡፡ ምናልባት ሁላችንም የምንነቃው የሁላችን በር ሲንኳኳ፣ የሁላችንም ልጆች ሲነኩ፣ የሁላችንም አካል ሲጎድል፣ የሁላችንም አኅቶች ሲደፈሩ ነው ማለት ነው፡፡

ኧረ ውሾቹን ተው እንበላቸው፡፡ ገንዘብ ከማግኘት ባለፈ ማሰብ የማይችሉ፣ የሀገር ክብር፣ የዜጎች መብት፣ የሰው ልጅ ሰብአዊነት የማይገዳቸው ላኪዎች አቀባዮች እና ተቀባዮች ከየገጠሩ ምንም የማያውቁ ኢትዮጵያውያንን እየመለመሉ፣ ሕጋዊ በሚመስል ሕገ ወጥነት ወደ ዓረቡ ዓለም ሲያሻግሩ ዝም እየተባሉ ነው፡፡ ውሾቹ
አጥንታቸውን ብቻ እንደሚያዩት እነርሱም ገንዘባቸውን ብቻ ነው
የሚያዩት፡፡

የሚላከው ሰው የት ይውደቅ የት፣ ምን ይግጠመው ምን፣ እንዴት ይሁን እንዴትም አያገባቸውም፡፡ ወገን ግን እየተሰቃየ ነው፡፡ የሰው ኃይል ወደ ዓረብ ሀገር መላክ በኛ አልተጀመረም፡፡

ሕንዶች፣ ፊሊፒኖች፣ ፓኪስታኖች፣ ባንግላዴሾች፣ ሱዳኖች፣ ግብጾች
ይጎርፋሉ፡፡ የኛ ሰውን ያህል ግን መከራ የበዛበት የለም፡፡ ለምን?
ውሾቹን ተው የሚል በመጥፋቱ፡፡ የናንተ ጦስ ለሀገር እና ለወገን
ይተርፋል ብሎ የሚቆጣ በመጥፋቱ፣ መሥመር የሚያስይዘ በመጥፋቱ፡፡

ዛሬ ዛሬ አንዳንድ ሀገሮች አበሻ አታምጡበን፣ ቪዛ አንሰጥም፣ አንቀበልም እስከማለት የደረሱት ኃላፊነት የማይሰማቸው እንደ ውሾች አጥንታቸውን ብቻ የሚያስቡ ሰዎች በሚፈጽሙት ሕገ ወጥነት ምክንያት ነው፡፡

አንዱ እምነት በሌላው ላይ፣ አንዱ ብሔር በሌላው ላይ፣ አንዱ ፓርቲ በሌላው ላይ ቂም እንዲቋጥር፣ እንዲያዝን፣ የጥላቻ ስሜት
እንዲያዳብር፣ የሚያደርጉ ትምህርቶች፣ ጽሑፎች፣ ንግግሮች፣
ዘፈኖች፣ አሠራ ሮች፣ በዝምታ እየታዩ ነው፡፡ እነዚህን ከጊዜያዊ
ሥልጣን፣ ሹመት፣ ገንዘብ፣ ግብዣ፣ ጭብጨባ ባለፈ ማሰብ
የማይችሉ ውሾችን ተው ማለት ይገባል፡፡

አንዳንዶቻችን የኛ በመሆናቸው፣ ሌሎቻችን የተነኩት ከኛ ውጭ ያሉት በመሆናቸው ዝም እያልናቸው ነው፡፡ ነገር ግን ሁላችንም ቤታችን የተሠራው በመስተዋት መሆኑን አንዘንጋ፡፡ ውሾቹን ተው ካላልናቸው እነርሱ እንደ ዋዛ መወራወር የጀመሩት ድንጋይ በመጨረሻ የሁላችንንም ቤት ሊፈረካክሰው ይችላል፡፡

እናም ውሾቹን «ተው» በሏቸው
ቸር ያሰማን!

ከዚህ ወዴት? –ከያሬድ ጥበቡ

$
0
0

Yared

ኢትዮጵያችን ያለችበት ሁኔታ ለብዙዎች የጭንቀት ምክንያት ሆኗል ። ማለቂያችን ምን ይሆን በሚል ። ለእኔ ዛሬ ካለኝ የተጨባጭ ሁኔታ ግንዛቤ በመነሳት ስድስት የተለያዩ ውጤቶች ሊያጋጥሙን ይችሉ ይሆናል ብዬ አስባለሁ ።

1) ሥርአቱ ቀውሱን አሸንፎ ይደላደላል
2) ቀውሱ አሸናፊም ተሸናፊም ሳይኖረው ለረጅም ጊዜ በመቀጠል፣ ሃገሪቱ ረጅም ውጥረት ውስጥ ልትገባ ትችላለች
3) የህዝባዊ እምቢተኝነቱ አሸንፎ ከሁሉም የተውጣጣ ብሄራዊ የሽግግርና እርቅ መንግስት ይመሰረታል
4) ኢህአዴግ ውስጥ ያሉት ሃይሎች በህዝባዊ ድጋፋቸው እየተማመኑ ሄደው፣ የወያኔን የበላይነት እምቢተኛ በመሆን ኢህአዴግ ራሱን አርሞና፣ ነፃ የምርጫ ቦርድና ፍትሃዊና ርቱአዊ ምርጫ የሚቀበል ፓርቲ እንዲሆን በማስገደድ፣ ወደ ዴሞክራሲያዊ ተስፋ የምንሸጋገርበት እድል ሊፈጠር ይችላል።
5) ህወሐት ኢህአዴግ ላይ ያለውን የበላይነት ማስጠበቅ ሲያቅተው፣ የመከላከያ ጄኔራሎችን ከፊት አስቀምጦ የመንግስት ግልበጣ ሊያካሂድ ይችላል
6) አሜሪካ የፀጥታ ሁኔታው ስጋት ላይ ጥሎኛል ብላ ካመነችና፣ ጦሩን ሊያስተባብር የሚችል ወታደራዊ/ደህንነት መሪ ካገኘች ወይም ካላት መፈንቅለ መንግስት ልታካሂድ ትችላለች ።
ዛሬ ለኔ የሚታዩኝ አደጋዎችና እድሎች እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ናቸው ። ኢትዮጵያችን ያለችበት ሁኔታ በብዙ አደጋና ያንኑ በሚመጥን ተስፋ ውስጥ በመሆኑ፣ እነዚህ ሁኔታዎች በአፋጣኝ ተለዋዋጭነት ሊያሳዩ ይችላሉ ። ዛሬ ይሆናል ብለን የተነበይነው በብርሃን ፍጥነት ሊኮሰምንና ሊጠፋ ይችላል ። ዛሬ የህዝብ ወዳጅ ነው ብለን ተስፋ የጣልንበት በብርሃን ፍጥነት ተቀይሮ ሊያድር ይችላል ።

በቁጥር አንድ ያስቀመጥኩት ሥርአቱ አሸናፊ ሆኖ በቶሎ የመደላደሉ እድል እጅግ በጣም ደካማው አማራጭ ይመስለኛል ። በኦሮሞ ክልል የአስር ወራት ህዝባዊ እምቢተኝነት የተገነዘብነው ነገር ቢኖር፣ መንግስት የህዝቡን ተቃውሞ በጥገናም ሆነ በአመፅ መደምሰስ እንዳልቻለ ነው ። ኦሮሚያን በወታደራዊ ቀጣና ከፋፍሎ የሽብር አገዛዝ የጫነበት ቢሆንም፣ ይበልጥ ከህዝቡ እየተነጠለ እንጂ እየተደላደለ መሄድ አልቻለም ። ይባስ ብሎም በአማራ ክልል ወደተነሳ ህዝባዊ እምቢተኝነት ረመጥ ውስጥ ጨምሮታል ። በተለይ በጎንደርና ጎጃም የተነሱት እንቅስቃሴዎች ስርአቱ ጥገና ሊሰጥ ወይም ሊያደርግ በማይችልበት የወልቃይት ጠገዴ ማንነት ጥያቄ ጋር ስለተቆላለፈ፣ ለሥርአቱ ፋታ ባለመስጠት እየጠነከረ የሚሄድ ተቃውሞ የመሆን እድሉ እጅግ ከፍተኛ ነው ። ይህ የአማራ ክልል ህዝባዊ እምቢተኝነት ዛሬ ያፈነውን የድርጅትና አመራር ችግሮች ተወጥቶ ባልገመትነው ፍጥነት የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ሆኖ ሊወጣ የሚችልበት እድሉ ሰፊ ነው ። ስለሆነም፣ ሥርአቱ በኦሮሚያና አማራ ክልሎች የተነሳበትን ተቃውሞዎች አሸንፎ በቶሎ ይደላደላል ለማለት አስቸጋሪ ብቻ ሳይሆን አይችልም ። በቶሎ ለመደላደል ከፍተኛ አመፅ መጠቀም ስለሚገደድ፣ ዛሬ ያለውን የሰራዊት ተዋፅኦ በሆነ ተአምር ካልቀየረ በቀር፣ አብዛኛው ዝቅተኛ መኮንንና ወታደር አማራና ኦሮሞ የሆነ ሰራዊት በራሱ ህዝብ ላይ ከፍተኛ አመፅ እያካሄደ ይቀጥላል ብሎ ለማመን አስቸጋሪ ነው፣ እንዲያውም አይቻልም ።

ሁለተኛው አማራጭ ቀውሱ ለረጅም ወራት የመቀጠሉ ጉዳይ የመሆን እድሉ ከፍተኛ ሲሆን፣ ሃገራችንን የበለጠ የሚያዳክማትና፣ ላልተጠበቁ ዘርፈ ብዙ ችግሮችና ቀውሶች ውስጥ ሊያስገባን የሚችል ይመስለኛል ። ወያኔ የበላይነቱን ለመጨበጥ በሚያደርገው ትግል፣ ሁለተኛ ደረጃና ኮሌጅ የጨረሱ የትግራይ ልጆችን ለመከላከያ ሀይሉ በእጩ መኮንንነት በመመልመል፣ መጠነ ሰፊ የወታደር ምልመላ በደቡብና ሱማሌ ክልሎች በማካሄድ፣ በኦሮሞ ፍርሃትና አማራ ጥላቻ ላይ የተማከለ አዲስ ሰራዊት ወደመገንባት ሊሸጋገር ይችላል ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሱማሌ ክልል ያገኘውን ከበሬታና ማንቆለጳጰስ ማየት ነው ። ይህንንም ስራ በፍፁም ህቡእነት ትግራይ ውስጥ ሊያከናውን ይችላል፣ ምናልባትም ይህ ስራ ተጀምሮ ሊሆን ይችላል ። ይህን አዲስ ሰራዊት መገንባቱን ሲተማመን፣ በመከላከያ ሀይሉ ውስጥ ያሉትን ኦሮሞዎችና አማሮች ሊያባርር ይችላል ። በምርጫ 97 ማግስት የወሰዳቸውን ተመሳሳይ እርምጃዎች ማጤን ተገቢ ነው ። ከዚህ ይሰውረን በሉ ። ወይም እዚህ ውስጥ ላለመነከር ማድረግ የምንችለውን ሁሉ ዛሬውኑ እናድርግ ። አንዱ መደረግ የሚገባው ጉዳይ የመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ ያሉት መኮንኖች ይህን ነቅተው እንዲጠብቁና እንዲያከሽፉ ዓይናቸውን መግለጥ ነው ።

በሶስተኛ አማራጭነት ያቀረብኩት ህዝባዊ እምቢተኝነቱ በብሄራዊ የሽግግር መንግስት ብሎም ወደ ዴሞክራሲያዊ ተስፋ የመግባታችን እድል እጅግ ተመራጩ አማራጭ ቢሆንም፣ ዛሬ ላይ ሆነን የህዝባዊ እምቢተኝነቱን የአመራርና ድርጅት አቅም ስናይ፣ ይህ የመሆን እድሉ የቀጨጨ መስሎ ይሰማኛል ። ግን ማን ያውቃል፣ እምቢተኞቹም ድክመቱ ታይቷቸው ይህን ችግር ለመቅረፍ እየሰሩ እንደሆን? ማን ያውቃል የመስቀል ወፍና የአደይ አበባ ቀጠሮ እንዳላቸው መስከረም ሲጠባ? የጎንደሩና ጎጃም እምቢተኝነት ከብአዴን፣ መላ አማራ ህዝብ ደርጅት፣ ቤተ አማራና ምናልባትም ግንቦት ሰባት ጋር ተቆላልፎና፣ ዛሬ የሚታይበትን የአመራርና ድርጅት ድክመት በአፋጣኝ መፍታት ቢችል? ይህም እውን ቢሆንና፣ ማእከላዊ መንግስቱ ወደ ድርድር ጠረጴዛ እንዲመጣ በማስገደድ፣ የብሄራዊ እርቅ መንግስት ብሎም ወደ ዴሞክራሲያዊ ተስፋ የምንሸጋገርበትን እድል ቢከፍትልንስ? ከላይ እንዳልኩት የመሆን እድሉ ጠባብ ነው እንጂ ሊመረጥ የሚገባው ይመስለኛል ።

በቁጥር አራት ያስቀመጥኩት ኢህአዴግ ውስጥ የሚደረግ የውስጠ ዴሞክራሲያዊና እርማት ንቅናቄ ድርጅቱን ከተነከረበት የማፊያና እብሪት መንገድ አውጥቶት ፣ ወደ ዴሞክራሲ የመሸጋገር እድል ጠባብ ሲሆን፣ ተመራጭ የመሆን እድሉ ግን ከፍተኛ ነው ። ሃገራችን የማትወጣባቸው ቀውሶች ውስጥ ከምትዘፈቅ፣ ገዢው ፓርቲ ራሱን አርሞ፣ የውስጥ ዴሞክራሲያዊ ህይወቱን አስፍቶ፣ የወያኔን የበላይነትና አፋኝ አሰራሮችን አስወግዶ፣ ነፃ የምርጫ ኮሚሽን ብሎም ፍትሃዊና ርቱአዊ ምርጫ እንዲደረግ ማድረግ ይችል ይሆናል ። ይህ አማራጭ የመሆን እድሉ ዛሬ ላይ ሆነን ስናየው ደካማ ቢመስልም፣ በዞንና ወረዳ ደረጃ ያሉት አመራሮችና ካድሬዎች ብአዴን ላይ በሚያደርጉት ጫናና፣ ህዘቡ ከውጪ የሚያደርገው እምቢተኝነት ተዳብለው ብአዴን ከወያኔ ቁጥጥር ነፃ ሊወጣ ከመቻል አልፎ፣ ኦህዴድና ደህዴድ አርአያነቱን ሊከተሉና፣ ወያኔ ከቁመቱ ጋር የሚመጣጠን ተሳትፎ ያለው የእህት ድርጅት እንዲሆን ሊያሰገድዱት ይችሉ ይሆናል ።

በቁጥር አራት የተቀመጠው አማራጭ መውደቅ፣ በቀጥታ ወደ አምስተኛው አማራጭ ይወስደን ይመስለኛል ። ወያኔ ከእህት ድርጅቶቹ የሚቀርብበትን የውስጣዊ ተሃድሶ አልቀበልም ከማለት አልፎ፣ ብቻውን በመቆም፣ መከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ በሚገኙ ጄኔራሎቹ አማካይነት መፈንቅለ መንግስት ሊያካሂድ ይችላል ። ይህ የመሆን እድሉ ከፍተኛ ይመስለኛል ። ለሃገራችን ግን ከፍተኛ አደጋ የሚደቅንና ባለፉት 25 አመታት ሲያላዝኑ የኖሩት “በታትነናት ነው የምንሄደው” የሚለውን ሟርት ተግባራዊ ለማድረግ የሚጥሩበት፣ ሆኖም አማራውና ኦሮሞው በመፍጠር ላይ ባለው አዲስ የትግል ህብረት የሚከሽፍበት ሁኔታ ሊከሰት ይችላል ።

በመጨረሻ ያየሁት አማራጭ አሜሪካ ራሷ በአመታት ስልጠናና ቀረቤታ በያዘቻቸው የጦር መኮንኖች አማካይነት መፈንቅለ መንግስት ልታካሂድ የምትችልበት ሁኔታ ያለ ይመስለኛል ። አሜሪካ በአፍሪካ ቀንድ ካሉ ሃገሮች ሁሉ ተባርራ ለእግሯ እንኳ ማረፊያ ያገኘችው ኢትዮጵያ ላይ ብቻ ነው ። ኢትዮጵያን መልቀቅ አትፈልግም ። ስለሆነም፣ ኢህአዴግ ከውስጡ የመቅለጥ አደጋ እንዳለው ከተሰማት፣ የምትተማመንበት ተቃዋሚ ስለሌለ ራሷ ወደ መንግስት ግልበጣ ልትሰማራ የምትችል ይመስለኛል ። ለዚህ የሚሆኑ ተባባሪዎች ታጣለች ማለት ሞኝነት ይመስለኛል ። አፍሪካ ቀንድ ውስጥ ኢትየጵያ ብቸኛዋ የመረጋጋት ገነት ከመሆኗ ባሻገር የቻይና መንደርደሪያ ሆና እንዳትቀጥል የአሜሪካ ፍላጎት ይመስለኛል ። ስለሆነም፣ አሜሪካ የራሷን ጄኔራሎች ይዛ መፈንቅለ መንግስት ልታካሂድ ትችላለች ። ይህ አማራጭ የመሆን እድሉ ከፍተኛ ባይሆንም፣ ስልጣን ላይ የሚወጡት ጄኔራሎች ግን የኢትዮጵያ ብሄርተኝነትንና ዴሞክራሲያዊ ተስፋን አዳብለው ከመጡ፣ በቁጥር 1, ፣ 2ና 5 ከቀረቡት አማራጮች የተሻለው ሊሆን ይችላል ። ምን ይመስላችኋል?

ቸር ይግጠመን

በፍራንክፈርት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሕወሓትን መንግስት በተቃውሞ ሰልፍ አስጠነቀቁ |ቪዲዮ ይዘናል |“የአማራና የኦሮሞ ህዝብ በተባበረ ክንድ ያሸንፋል”

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በጀርመን ፍራንክፈርት በዛሬው ዕለት ኢትዮጵያውያን የተሳካ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸው ተሰማ:: ከስፍራው የነበሩ የዘ-ሐበሻ ወኪሎች እንዳስታወቁት በፍራንክፈርት በዛሬው ሰልፍ ላይ የሕወሓት መንግስት ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶታል:: ሰላማዊ ሰልፈኞች ከዚህ ቀደም በሌሎች ከተሞች እንደተደረገው የኦሮሞ ሕዝብን እና የአማራ ሕዝብን የሕይወት መንግስት መጨፍጨፉን አውግዘዋል:: በአስቸኳይ ግድያውን እንዲያቆም እና ስልጣኑን እንዲለቅም ሕዝብ በተቃውሞ ሰልፍ አስጠንቅቋል:: ሰልፈኛው “የአማራና የኦሮሞ ህዝብ በተባበረ ክንድ ያሸንፋል”; “ገዳይ የሕወሓት ባለስልጣናት ለፍርድ ይቅረቡ” “በቀለ ገርባ መሪያችን ነው” “የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱና” ሌሎችም መፈክሮች ተሰምተዋል::
ቪዲዮ አለን:


ኢትዮጵያውያን ለዮዲት ወልደርፋኤል (ሄለን ሃይሉ) መልስ መስጠታቸውን ቀጥለዋል |ሊደመጥ የሚገባው ምላሽ ቪድዮ

$
0
0

ኢትዮጵያውያን ለዮዲት ወልደርፋኤል (ሄለን ሃይሉ) መልስ መስጠታቸውን ቀጥለዋል | ሊደመጥ የሚገባው ምላሽ ቪድዮ

ኢትዮጵያውያን በአትላንታ CNN ስቱዲዮ አጠገብ የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ |ዝርዝር ከቪዲዮ ጋር አለው

$
0
0


ዳዊት ከበደ ወየሳ ከአትላንታ | ለዘ-ሐበሻ

በአትላንታ የተግባር ኮሚቴ እና የኦሮሚያ ኮሚዩኒቲ በህብረት የጠሩት ሰላማዊ ሰልፍ በድምቀት ተጠናቋል። CNN ዋና ማዕከል ፊት ለፊት በተደረገው በዚህ ሰልፍ ላይ እስከ አንድ ሺህ የሚገመት የአትላንታ ነዋሪ ተገኝቶ ነበር። ሰልፈኞች በተደጋጋሚ ከሚያሰሟቸው መፈክሮች መካከል… (ብዙዎቹ በእንግሊዘኛ የተባሉ ሲሆን፤ እኛ ወደአማርኛ ስንመልሰው እንዲህ የሚል ነው።)

“አሜሪካ… ለገዳይ መንግስት የምታደርጊውን እርዳታ አቁሚ!
“ህወሃት ገዳይ ነው!
“ወያኔ አሸባሪ ነው!
“በኦሮሚያ የሚደረግ ግድያ ይቁም!
“ነጻነት ለኢትዮጵያ ህዝብ!
“ነጻነት ለአንዷለም አራጌ!

“ነጻነት አንዳርጋቸው ጽጌ!” የሚሉና ሌሎች መፈክሮችም በኦሮሚፋ ሲባሉ ነው። በተለይም አንድ ኦሮምኛ መዝሙር በህብረት ሲባል ነበር። የመዝሙሩ ሃሳብ… “እናንተ የተሰዋቹህ ወገኖቻችን ክብር ለናንተ ይሁን! በቁም ከመዋረድ የናንተ ሞት ይመረጣል!” የሚል ሃሳብ ያለውን መዝሙር በህብረት ሲዘምሩ ተሰምቷል።

ይህ ሁሉ ሲደረግ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ከ CNN መጥቶ ሰልፈኞችን ያነጋገረ የለም። ይህ ደግሞ በተደጋጋሚ ስለተደረገ የተለመደ ጉዳይ ሆኗል። ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ እንዳልነው፤ አጋጣሚውን በመጠቀም ህዝቡ መሰባሰቡና በሰላማዊ መንገድ ሃሳቡን መግለጹ መልካም ነው። ሆኖም የሰልፉ አዘጋጆች ቀደም ብለው የ CNN ሰዎችን ማነጋገር እና ማሳወቅ ይኖርባቸዋል። ለምሳሌ በቅርቡ የ CNN አለም-ዓቀፍ ዴስክ አዘጋጅ፤ Robyn Curnow ስለአትሌት ፈይሳ ሌሊሳ በማንሳት፤ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ጉዳይ በዚያው ዘግባለች።
በዚህ የ CNN ዘገባ፤ አሜሪካኖቹ የገባቸውን ያህል በጥቂቱ ጥቂት ብለዋል። ይህን በማድረጓ፤ አዘጋጅዋ ልትመሰገን ይገባል። ከምስጋናው ቀጥሎም፤ “ነገር ግን CNN የማያውቀ ው ሌላም ጉዳይ አለ። ስለዚህ በዚህ ቀን እና ሰአት CNN ማዕከል ስለምንገኝ፤ የሚመለከተው የ CNN ዘጋቢ በስፍራው ተገኝቶ የህዝቡን ድምጽ ሰምቶ ያሰማልን።” የሚል ትንሽ የሚመስል ሃሳብ በማቅረብ፤ ትልቅ ስራ መስራት ይቻል ነበር።፡
ኢትዮጵያውያን በአትላንታ CNN ስቱዲዮ አጠገብ የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ | ዝርዝር ከቪዲዮ ጋር አለው
ይህም ሆኖ ግን… በአትላንታ በተደጋጋሚ የተደረጉ ሰልፎች በ CNN ቢተላለፉም ባይተላለፉም፤ ሁሌም ለህዝቡ ትልቅ መልእክት ጥለው ያልፋሉ። የኦሮሚያ እና የአማራ፤ ብሎም የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲህ በአንድነት መታየቱ በራሱ አበረታች ጅምር ነው። ከምንም በላይ ግን… የህዝቡን ድምጽ በማሰማት ሰልፉ ዋናውን አላማ የመታ ይመስላል። ሁሉም እያደረጉ ያሉት የታፈነው የኢትዮጵያ ህዝብ ጩኸት እንዲሰማ ለማድረግ ነው። ይህ አላማ ግቡን መትቷል።

በአገር ቤት ሰሚ ያጡ ድምጾችን፤ ሰባዊነት በሚከበርበት የውጭ አገር ሆኖ የህዝቡን ድምጽ ማሰማት ትልቅ ቁምነገር ነው። በኢትዮጵያ የታፈነው ወገን፤ ድምጹን የሚያሰማለት ህዝብ መኖሩን ማየቱ በራሱ ትልቅ ተስፋ ይሰጠዋል። በመሆኑም በውጭ አገር የሚደረጉት ሰልፎች፤ በአካባቢው ሚዲያ ስፋን ቢሰጣቸውም ሆነ ቢነፈጋቸውን መደረጋቸው ግን መቀጠል ይኖርበታል። ምክንያቱም ለአገር ቤቱ ትግል ኃይል የሚሰጡ ናቸውና!

ድል ለተበደለው የኢትዮጵያ ህዝብ ይሁን!

ለሁሉም ጊዜ አለው |ማስተዋል በለጠ

$
0
0

በመላዋ ሀገራችን ለነፃነታችን እየተዋደቁ የሚገኙ ዜጎች ውድ ሕይወታቸውን እየሰው የነፃነት ቀንዲሉን በማብራት ላይ ናቸው፡፡ ታሪክ ሲዘክረው የሚኖር ታላቅ መስዋዕትነት እየከፈሉ በመሆናቸው በአልሞ ተኳሽ የወያኔ አጋዚ ጦር አንገታቸው እየተቀላና ጭንቅላታቸው እየተገመሰ ሕይወታቸውን የሚያጡ ውድ ወገኖቻችንን ነፍሳቸውን ፈጣሪ ይማርልን፡፡

opp
በዚያን ሰሞን ካነበብኳቸው መጣጥፎች አንዱ በ16 የትግራይ ተወላጆች የተጻፈው በወያኔ ላይ የተወሰደ አቋም ነው፡፡ ኪዳነ ምሕረት ትባርካቸው፡፡ ፕሮፌሰር መስፍን አንድ ወቅት ጥሩ ኢትዮጵያውያን ተጋሩን(ትግሬዎችን) መቁጠር ጀምረው የቀኝ እጅ ጣቶቻቸውን ተጠቅመው (ይመስለኛል) አንድ ሁለት ሦስት ያህል እንደተጓዙ አምስትን እንኳን መዝለል አቃታቸውና “አሥር ቢሞሉልኝ ደስ ባለኝ” ብለው ተስፋ በመቁረጥ መቁጠሩን እንደተውት አርድተውናል፡፡ አሁን 16 መድረሳቸው ተስፋን የሚያጭር ነው፡፡ እየበዙ እንደሚሄዱ ደግሞ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ዕድሉን ስላላገኙት እንጂ በቁም ነገር ከተጫወትን ኢትዮጵያውያን ተጋሩ ቁጥራቸው ከዚህ እንደሚበልጥ መገመት አይከብድም፡፡ አገዛዙ ከትግሬ አይውጣ እንጂ ወያኔ ሥልጣን ቢለቅ የሚወዱ ትግሬዎች ደግሞ ጥቂት እንደማይሆኑ መገመት ይቻላል፤ ይህን ወያኔ የተከለብንን የዘር መዘዝ ለማጥፋት ማርከሻውን በቶሎ ካላፈላለግንና በ“ሜሪቶክራሲ”(በችሎታና ዕውቀት) መተካት ካልቻልን ገና ወደፊትም ብዙ እንዳክራለን፡፡

በመሠረቱ ከኢትዮጵያዊነት በወረደ ከዚህኛው ወይም ከዚያኛው ጎሣ እየተባባሉ ማናቸውንም ዓይነት ተቃውሞን መግለጹ ዘመናዊነትን ሊገልጽና የሥልጡን ፖለቲካ መታወቂያ ሊሆን እንደማይገባው አምናለሁ፤ በሃይማኖትና በአካባቢ ልጅነት መደራጀትም እንደዚሁ ተገቢ አለመሆኑ ይገባኛል፡፡ ቢሆንም ቅሉ … ከዐማራ ተወላጆች፣ ከኦሮሞ ተወላጆች፣ ከትግራይ ተወላጆች … የምንለው ነገር ለጊዜው ጠቃሚ ሆኖ ከተገኘ ማለትም እየወረደብን ያለውን የመከራ ዶፍ ከመመከት አኳያ አንዳች ፋይዳ ካለው ቢያንስ በመርኅ ደረጃ ብደግፈው ብዙም አይከፋኝም፡፡ እናም አብላጫውን ደሜን ያገኘሁት ከሦስቱም ‹በጥባጭ‹ ዘውጎች መሆኑን ከሕይወት ተሞክሮ የተረዳሁት ማስተዋል በለጠ በዚህ መጣጥፍ ውስጥ ያለውን አስተያየት በቀናነት የምሰነዝረው አድማጭ አገኛለሁ ከሚል ትልቅ ተስፋ ነው፡፡

ታሪኬን ብዙዎች ይጋሩት ይናል ብዬ ስለማምን ስለራሴ ትንሽ ብናገር ደስ ይለኛል፡፡ መነሻየ ግምት እንጂ ጥናት አይደለም፡፡ የብዙ ጥናቶች መሠረት ለእውነት የቀረቡ ግምቶች መሆናቸውንም አንዘንጋ፡፡ እናም የእኔ ዘውጋዊ ቀመር እንደሚመስለኝ 30% ዐማራ፣ 30% ኦሮሞ፣ 30% ትግሬ እና 10% ከሌሎች ነው፤ እንዲህ የሆንኩ ያህል ይሰማኛል፡፡ እንደዚህ ስል ደግሞ የሚያምነኝ እንደማላገኝ ብቻ ሣይሆን ጥቂት የማይባሉ ሰዎች እንደሚያላግጡብኝም ይገባኛል፡፡ የእኔ እውነት መነሻ ግን ይሄውላችሁ፡፡

መልኬን አሁን ላሳያችሁ ባለመቻሌ አዝናለሁ፡፡ ትግሬ ጋ ስሆን ፊቴን ያዩና “ደምህ ወደደቡብና ወደ ኦሮሞ ይሄዳል” ይሉኛል፡፡ ኦሮሞ ጋ ስሆን “መልክህ የዐማራና የትግሬ ይመስላል” ይሉኛል፡፡ ዐማሮች ጋ ስሆን “አባትህ ከደቡብ የተቀጠሩ ወታደር ሳይኑ አይቀሩም” እያሉ ይቀልዱብኛል፡፡ እኔ ራሴን በመስተዋት ስመለከት አንዱንም የማልመስል ከሁሉም ግን ጥቂት ጥቂት እንደወሰድኩ ያህል ይሰማኛል፡፡ ትልቁ ማስረጃየ ግን ሦስቱም ዘውጎች ከየተነሱበት መጥተው የሚያልቁበት ቦታ ላይ መወለዴ ነው፡፡ አዎ፣ የአማራ፣ የትግሬና የኦሮሞ ጠቅላይ ግዛቶች የሚጫፈሩበት(overlap የሚያደርጉበት) ሥፍራ ላይ ነው የትውልድ መንደሬ፡፡ ለዚህም ነው ቁርጥ ባለ ሁኔታ ይህን ወይ ያን ልመስል ያልቻልኩት፡፡

ስለዚህ አንዱ በዐማራነቴ አህያ ቢለኝ ወይም ዛሬ ጧት በፕሮፌሰር አልማርያም መጣጥፍ ላይ እንዳነበብኩት “የአእምሮ ዘገምተኛ” ቢለኝ ወይም በኦሮሞነቴ “ሽብርተኛ”ና “ወንጀለኛ” ብባል ወይም በትግሬነቴ ዘረኛና ጎጠኛ ብባል ብዙም የሚሰማኝ አልሆንም፡፡ ሁሉን መሆን አንዳንዴ ዕዳ አንዳንዴ ደግሞ በረከትም ነው፡፡ የሆንኩትን እንድሆን የመምረጥ ዕድል ያልተሰጠኝ መሆኔ ግን በከንቱዎች ከንቱ አባባል እንዳልቆጣ ትልቅ የትግስት ጋሻ አስጨብጦኛል፡፡ ለመሆንና ላለመሆን ምርጫ ባልተሰጠኝ ሁኔታ በሆንኩት ነገር መበሳጨትም ሆነ ከሰው ጋር ትርፍ ንግግር ውስጥ መግባት ትልቅ ሞኝነት ነው፡፡
ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሣ ሰሞኑን በጻፈው መጽሐፍ የትውልድ አካባቢየና ተፈጥሮ ቀድመው ያቆራኙትን ዐማራነቴንና ኦሮሞነቴን በተመለከተ ብዙ ነገር አትቷል፡፡ የፕሮፌሰሩ ልፋትና ድካም ይገባኛል፤ በሕዝቡና በሀገሩ ሰላምንና ፍቅርን፣ ወንድማማችነትንና እትማማችነትን ለማስፈን በመፈለጉ ብዙ ርቀቶችን ተጉዞ በእምቅድመ ዘመነ ታሪክ በአዳምና ሔዋን አንድ የሆንነውን ግን የዘነጋነውን እኛን አንድ አድርጓል፡፡
በመሠረቱ ታዲያ ጥቁሮች ኢትዮጵያውያንን ብቻ ሣይሆን የሰውን ዘር በሞላ በሥነ ፍጥረት አንድ ያደረገ ፈጣሪ ከአዳምና ከሔዋን አንስቶ አሁን የምንገኝበትን የሰባት ቢሊዮን የሕዝብ ቁጥር ለበረከትም ይሁን ለእርግማን እንደሰጠን ለምናምን ሰዎች የሰውን ልጅ አንድነትና የዘር ሐረግ ወጥነት ለመረዳት አንዳችም ምርምር ባላስፈለገን ነበር፡፡ ይሄ አንድ የመሆን ወይም ያለመሆን ችግር አይደለምና ዋናው እየበጠበጠን የሚገኝ ችግራችን፡፡

(እንደኔ አስተሳሰብ) የሰው ልጅ ዋና ችግር የዘር ሐረጉ መለያየት አይደለም፡፡ ትልቁ ችግር የተፈጥሮ ሀብትን በአግባቡ ከመከፋፈል አንጻር የሚታየው ኢ-ፍትሃዊነት ነው፡፡ ምክንያቶቹ የፈለገውን ያህል በቅርጽ ቢለያዩም ዋናው ችግራችን የሀብት ክፍፍል ላይ የሚፈጠር የ“ያንተ በዛ፣ የኔ አነሰ” ዓይነት መፎካከርና ያን ተከትሎ የሚፈጠር ቀውስ ነው፡፡ አንዱ በጉልበቱ ወይም በብልጠቱ ቢሊዮን ሲወስድ ሌላው መቶም አያገኝም፡፡ አንዱ ያለ የሌለ ዘዴና ብልኃቱን ተጠቅሞ ወደሀብትና ሥልጣን ማማ በአቋራጭ በመውጣት እንደካሙዙ ባንዳ ዕድሜ ልኩን ሲጎለት ይህን ቅጥፈት የታዘበ ሌላው ባለወር ተራ ደግሞ ወደዚያ ሥፍራ ለመጓዝ የንጹሓንን ደም እየገበረ ሌት ከቀን በእውኑም በህልሙም ይባዝናል፡፡ እንጂ የመለስ ዜናዊ የ17 ዓመታት ጉዞና የቢሊዮን ዶላሮች ክምችት ለእንደርታው ገበሬ ለአቶ ሐጎስ ፀጋዝኣብ የፈየደለት አንድም ነገር እንደሌለ ቢያንስ ኅሊናችን ይረዳዋል – ይህን የምለው ታዲያ አጠቃላዩን እውነታ ለመግለጽ እንጂ የመለስ ሸፋፋና ወልጋዳ አስተሳሰብና አመራር ጥቂት የማይባሉ ተጋሩ ወንድምና እህቶቼን አልጠቀመም እያልኩ አይደለም፡፡ የተጠቀመ ተጠቅሟል፤ የተጎዳም እንዲሁ፡፡

ሁላችን እናውቀዋለን፤ የሰው ልጅ ዘር አንድ ነው፡፡ ነጭና ጥቁር የመጣው ከጊዜ በኋላ እንደሆነ መጻሕፍት ይናገራሉ፡፡ የመልክና የቁመት ልዩነት እንደሆነ በማኅበረሰብ ደረጃ ይቅርና በኔ ቤትም ጎልቶ የሚታይ ግን ተዓምራዊ ያልሆነ ተራ ክስተት ነው፡፡ በኔ ቤት ለምሣሌ እኔ ወደጥቁርነት የማደላ ፉንጋ የቀይ ዳማ ስሆን አንዱ ልጄ ቆንጆ ቀይ፣ አንዱ ደግሞ ከኔ የባሰ አሻሮ ናቸው፤ ሌሎቹም እንዲሁ የተለያዬ መልክ፣ ቁመትና ጠባይ አላቸው – “ቤቴ መንገድ ዳር አለመሆኑን”ና ታማኝ የትዳር አጋር ያለኝ መሆኔን አስቡልኝ ታዲያ! (በነገራችን ላይ አንዳንድ ሸረኛ አንባቢ ምን ሊለኝ እንደሚችል እያሰብኩ ነው ከመንገድ እየወጣሁ ደረጃውን ባልጠበቀ የመነቸከ ቀልድ ላስፈግጋችሁ የምሞክረው)፡፡ እነዚህን ልዩነቶች እኔና እናታቸው አልሰጠናቸውም – ባልሰጠናቸው ልዩነት ደግሞ አይጣሉም፡፡ ስለዚህ ልዩነትን ለጠብ ማዋል የከይሲዎች ተግባር እንጂ የደግ ሰው ጠባይ አይደለምና መጠንቀቁ ጠቃሚ ነው፡፡

ይህን የልዩነት ሰበዝ በኦሮሞነትና በዐማራነት ካየነው እርግጥ ነው “ይህ ሰው ኦሮሞ ነው”፣ “ይህ ሰው ጉራጌ ነው” የምንልባቸው ልማዳዊ የሰውነት ቅርፆች ሊኖሩ እንደሚችሉ በበኩሌ እረዳለሁ፡፡ ለዚህም ነው ከፍ ሲል የኔ የሰውነት ቅርጽና የመልክ ይዘት የዚህ ወይ የዚያ ሣይሆን ድብልቅ ነው ለማለት የደፈርኩት – ለፖለቲካ ፍጆታ አይደለም፡፡ To my belief, there are some typically subtle features of ethnics if they are not mixed up and diluted through intermarriage. And, in most cases, the Ethiopian societies are said to be interwoven to the extent of not being able to be clearly and unmistakably identified as this or that ethnic group, excepting some incidents especially in remotest rural areas where there is less chance of intermingling through intermarriage.

እውነት እንነጋገር ካልን ታዲያ ከሥነ ልሣናዊ ተቀራራቢነትም ይሁን ከአካላዊ ቅርጽ አኳያ አንድ ትግሬና አንድ ዐማራ የሚለዩበትን ገጽታ(feature) ለመለየት በበኩሌ እቸገራለሁ – ተፈጥሯዊ ዝምድናቸው በጣም ያቀራርባቸዋል፡፡ ይህንን ስል ፕሮፌሰር ፍቅሬ ያለውን የኦሮሞና የአማራ ጎሣዎች የመባቀያ ተመሳሳይነት ጨብጬ ይህን እኔ የምለውንም በተጨማሪነት ለማስገንዘብ ፈልጌ እንደሆነ መግለጽ እፈልጋለሁ፡፡ ዐማራና ኦሮሞ አንድ መሆናቸው የሚያስደስተኝን ያህል ትግሬና ዐማራም አንድ ብቻ ሣይሆኑ እንደኔ እንዲያውም ሁለቱ ጎሣዎች ወያኔን ተመስሎ ከፋፋይ ሰይጣን በመካከላቸው ገብቶባቸው እንጂ በልይት ዘውግነት መለያየት ራሱ ይበዛባቸዋል ባይ ነኝ – በአንድ ዘውግ ሥር መመደብ ነበረባቸው እያልኩ ነው በግልጽ ዐማርኛ፡፡ የአሁኑን ባላውቅም በኔ የወጣትነት ዘመን አንድን ትግሬ ከአንድ ዐማራ ለመለየት ምናልባት በትግሬው ግምባር ላይ ይቺ 11 ቁጥር የምንላት ታርጋ ኖራ በሷ ካልለየነው በስተቀር በምንም መንገድ አይለዩም ነበር – በነገራችን ላይ የሌላቸውም አሉ (ባይገርማችሁ ባለ 11 ቁጥር ዐማራ አለ፤ 11 ቁጥር የሌለው ትግሬም አለ)፡፡ ወያኔ እንደጣዖት የሚያመልክባትን የብሶተኞች የምትመስል 11 ቁጥርን በድንበር አካባቢ ያለን ሰዎችም አለችን፡፡ ለዐይን ህመም ተብሎ ብዙዎቻችን እንቀነደብ እንደነበር የኔም ግምባር ኅያው ምሥክር ነው፡፡ በኔ አካባቢ የባህሎች መዋሃድ ስላለ የብዙ ማኅበረሰቦች አሻራ በሁሉም ሰው ላይ ይታያል፡፡

በተረፈ ግን ዱሮ ትግሬን ከዐማራ ለመለየት የሚቻልበት ዘዴ አልነበረም፡፡ መልክና ቁመናቸው፣ ሥነ ልቦናዊ ቀመራቸው፣ ሥነ ልሣናዊ ዳራቸው፣ ሃይማኖታዊ ሥርዓታቸው፣ አመጋገባቸውና አለባበሳቸው፣ እንግዳ አቀባበላቸው፣ ሰውን አክባሪነታቸው፣ ባህላቸውና ኢኮኖሚያዊ ትስስራቸው ሲታይ አንዳቸውን ከሌላኛቸው መለየት የማይቻልበት ሁኔታና ወቅት ነበር – የዛሬውን ዘመነ ጥልሚያኮስ አያድርገውና፡፡ ለምሣሌ ሁለት ኦሮሞዎች እዚህ አጠገቤ እያወሩ ነው ልበል፡፡ በዚህኛው ሌላኛው አጠገቤ ደግሞ ሁለት ትግሬዎች እያወሩ ነው ልበል፡፡ አንድ ኦሮምኛም ትግርኛም የማይችል በዐማራነት የሚታወቅ ሰው ቢያዳምጥና ከየትኛዎቹ ምን እንደተረዳ/እንደሰማ ይህ ቢጠየቅ በርግጠኝነት ከትግርኛ ተናጋሪዎቹ በአነስተኛ ግምት ወደ 25 በመቶ የሚጠጋውን ሊረዳ ሲችል ከኦሮምኛ ተናጋሪዎች ግን 5 በመቶውን እንኳን ስለመረዳቱ እጠራጠራለሁ፡፡ ታዲያ ይህን የትግሬ-ወያኔዎችን በዐማሮች ላይ መጨከን ምን አመጣው? ይህ ይመስኛለል ትልቁ የዘመናችን ዕንቆቅልሽ፡፡ ፍቺ ያጣንለት ሚሌኒየማዊ ጥያቄ ነው፡፡ ምን ዓይነት ሰይጣን በወንድማማቾች መካከል ገባ? በውነቱ በተለይ በተጋሩ ወንድሞቼ አካባቢ ይህን የምለውን እውነት የሚያስታውስ ጠፍቶ ነው ወይንስ ማስታወስ አስፈላጊ ሣይሆን ቀርቶ ይሆን? ለምን? ማንን ለመጥቀም? እነዚህን ወንድማማች ማኅበረሰቦች በማፋጀት የሚገኘው ጥቅም ምንድን ነው? ጥላቻን ዘርቶ ዐመፃን ማጨድ ማንን ነው የሚጠቅመው? ተጋድመው የተፉት ምራቅ ተመልሶ ወደራስ እንደሚመጣስ መገንዘብ እንዴት ያቅታል? አሁን በዐማሮች ላይ እየተደረገ ያለው ሊታመን የማይችል ሲዖላዊ ተዓምር ወደሰማዩ ጌታ መጮኹና መልስ ማግኘቱ ይቀራል? ያኔ ምን ይውጠናል?

የሰዎች ትክክለኛ የኅሊና ፍርድ ተዛብቶ ወደ ከፋና ከረፋ ዝቅተኛ የአስተሳሰብና የአመለካከት ደረጃ ለምን እንደሚወርድና አንዱ በአንዱ ለምን እንደሚጨክን ብዙ ጊዜ ይጠየቃል፡፡ መልሱ ደግሞ ቀላል ነው – እሱም ጥቅም ነው፡፡ ጥቅም አይደለም ጎሣና ነገድን ወንድምና እህትን ያገዳድላል፡፡ አባትና ልጅን ያባላል፡፡ ቤተ ዘመድን ያጨራርሳል፡፡ ጥቅምና ሥልጣን በጣም አደገኛ መርዝ ናቸው፡፡ “የአቦይ ስብሃት ሀብት ከሚነካ የትግራይ ሕዝብ ጥንቅር ይበል፤ የአባይ ፀሐዬ ሥልጣን ከሚሸረሸር የትግራይና ዐማራ ሕዝብ ሚና ለይቶ ይጨራረስ፡፡ መንግሥቱ ኃ/ማርያም ሥልጣኑን ከሚያጣ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ባፍ ጢሟ ትደፋ፡፡…” ይህ ነው የግለሰቦች የሥልጣንና የሀብት አምልኮ፡፡ እንጂ ሕዝብና ሕዝብ በየትም ሀገር ለጠብና ለፍጅት ተፈላልጎ አያውቅም፡፡ የዕልቂት ከበሮ የሚጎስሙ ወገኖች በሀብትና በሥልጣን ሱስ ናላቸው የዞረ ጥቂት ግለሰቦችና በሥራቸው የሚኮለኩሏቸው አጥፊ ጀሌዎች ናቸው፡፡ ይህ ዓይነቱ የትያትር መድረክ ደግሞ መጋረጃው ሲዘጋ አብሮ የሚዘጋና በሌላ የተሻለ ወይም እንደኛ እንደስካሁኑ ከሆነ የጥንቱን በሚያስመሰግን መጥፎ ታሪክ የሚተካ ነው – እስካሁን እንዲህ ነበር ወደፊትም እንዲሁ ነው፤ ክፉም ሆነ ደግ መንግሥት ወይም ሥርዓት ባለበት ለዘላለም አይኖርም፡፡ ሕዝብ ግን ዘላለማዊ ነው፡፡ እናም ውድ ኢትዮጵያውን አይዞን ይህ ወያኔዊ የጥፋት ዘመን አልፎ የፍቅርና የመተሳሰብ ዘመን በቅርብ ይመጣል፡፡ ጸሎታችን መሆን ያለበት መስዋዕትነቱ እንዲቀንስልን “ጌታ ሆይ ዕርዳን” ነው – እኛም ከክፋትና ከአጥፊነት ርቀን ታዲያ፡፡ ደግሞም በመካከላችን ጥላቻን አናባብስ፡፡ የሚተርፈን ትዝብቱ ነው፡፡ ኢትዮጵያ እንደሆነች ጠፍታ የማትጠፋ የፈጣሪ ቃል ኪዳን የሚጠብቃት ሀገር ናት – በወረት የዘረኝነትም እንበለው የትምክህተኝነት ንፋስ አንወሰድ፡፡ ከሁሉም ከሁሉም ምንም ዓይነት ጥጋብ አይፈታተነን፡፡ ብናገኝ አንኩራ፣ ብናጣም አንፍራ፡፡ “ሁሉም በርሱ ሆነ – ያለርሱ በሰማይም በምድርም ምንም አልሆነም፡፡” ስለዚህ ለምኑ እንጨነቃለን? የተወሰደ እንደሚመጣ፣ የመጣም እንደሚወሰድ አናውቅምን? ማን ነው እንደኮራ እንደደራ የኖረ? ማን ነው እንዳነሰ እንደኮሰመነ ኖሮ ከምድር የተሰናበተ? ጠቢቡ አስቀድሞ “ለሁሉም ጊዜ አለው” ብሏል፡፡

ከአዳም ጀምሮ እስካሁን ድረስ ይህ የጥቅምና የሆድ ጉዳይ የዓለም ሕዝቦችን እያፋጀ ነው፡፡ አዳምና ሔዋን ከገነት የተባረሩት፣ አቤል በወንድሙ በቃየል የተገደለው፣ ያቆብ ጭብጥ በማትሞላ ምሥር ብኩርናውን የለወጠው፣ ይሁዳ ጌታውን በሠላሣ ዲናር የሸጠው፣… በዘመናችንም ሲአይኤና ሞሳድ በዲሞክራሲ ጭምብላቸው ዓለምን እንዲህ የሚያሽቃንጡባትና እንደፈለጉ የሚፈነጥዙባት በጥቅምና ለጥቅም ሲባል ነው(ህእ! ሳውዲ ዐረቢያ ውስጥ የዴሞክራሲ ጭላንጭል የለም … በአውራ መንገዶችና በሠፈር ውስጥ ብቻዋን መሄድ የማይፈቀድላት ሴት መኪና እንኳን አትነዳም፤ ስለዴሞክራሲ ጭንቅ ጥብብ የምትለውና በዴሞክራሲ በሚመጣባት ሀገር ላይ ከማዕቀብ እስከ ጦር ማዝመት የምትደርሰው አሜሪካ የዚህች ሀገር የበላይ ጠባቂና ዘበኛ ናት – ለጥቅም ሲባል… ዕንቆቅልሽ፡፡)

… እንጂ ዐማራ ከማንም የበለጠ “አህያና ደደብ” ወይም “የአእምሮ ዘገምተኛ” ሆኖ አይደለም – ሰፊው ኦሮሞ ከትግሬ በልጦ ጠባብ ሆኖ አይደለም፡፡ ትግሬ ከማንም በልጦ ጀግናና አልሞ ተኳሽ ሆኖ አይደለም፡፡ ማዕከላዊው የግጭት መንስኤ ጥቅም ነው፡፡ በጥቅም የታወሩ ወንድሞቻችን አቅል አጡና ከምድረ ገጽ ሊያጠፉን ቆርጠው ተነሱ፡፡ ባጭሩ ይህን ሁሉ ዕልቂትና ፍጅት እያስከተለ ያለው ከፀሐይ በታች ያለ የሸርና የተንኮል ጉንጉን የተላበሰ የወያኔዎች የሀብትና የሥልጣን ጉጉትና የዓለም አቀፉ የኢትዮጵያ ጠላቶች ሤራ ድምር ውጤት ነው፡፡ ከወያኔዎች ጋር ተሰልፎ ጃዝ ሲሉት እየገደለና እየዘረፈ የሚተመው የጥፋት ሠራዊት ደግሞ ከዕውቀትም ከባህልም ከሃይማኖትም የወጣ ወፍ ዘራሽ ጀሌ ነው – አብዛኛው ከእረኝነት በቀጥታ የመጣና ማኅበራዊ እንስሳነቱ የተጓደለበት ከመሆኑም ባሻገር ዐማራን እንዲጠላና ከጥላቻውም ብዛት የተነሣ በጭካኔ እንዲፈጀው ሥነ ልቦናዊ ጫና የተደረገበት አሳዛኝ ፍጡር ነው፡፡ ሳይፈልግ በተደረገበት ተፅዕኖ ምክንያት ስለሆነ ይህን ሁሉ ግፍ የሚፈጽመው ሙሉ በሙሉ በርሱ ለመፍረድም ይከብዳል፤ በዚያ ላይ የውጭ ጠላቶቻችን ለውስጥ ምንደኞች ያሸከሙት ታሪካዊ የጥፋት ተልእኮም ቀላል አይደለም – የየትኛውንም ሀገር ባለሥልጣናት ብሔራዊ ስሜት በማጥፋት የነርሱ አሽከሮች የሆኑ መሪዎችን በማፍራት የሚታወቁት የዐውሬው ልጆች ምዕራባውያንና አውሮፓውያን ካልጠፉ ወይም ሰይጣናዊ ተፈጥሯቸውን ካልቀየሩ (ይህ የማይሆን አማራጭ ነው) አለዚያም እኛ ይህን መርዝነታቸውን ነቅተንባቸው በኅብረት ካልታገልናቸውና ድል ካልነሳናቸው ደግሞ ዕረፍት እንደሌለን መረዳት ተገቢ ነው፡፡ የዘመቻቸው ጅማሮ ጥንታዊ ነው፤ ድላቸው ግን ጊዜያዊ ነው፡፡

ጥቂት ታገሱኝ – አንዲት ነገር ብቻ ትቀረኛለች፡፡ የትግራይ የወቅቱ መሣፍንትና መኳንንት ትግራይን ይዘን እንሄዳለን ቢሉ ጥርሳችንን ተነቅሰን እንስቅባቸዋለን፡፡ በርግጥም ጤነኛ ነኝ የሚል የዚህች ዓለም ዜጋ ይስቅባቸዋል፡፡ “እውነት እውነት እላችኋለሁ” ብሎ ይጀምር ነበር ክርስቶስ የመረረ እውነት ሲናገር፡፡ እኔም ልዋሰውና – እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ ትግራይን መገንጠል ቢያስፈልግ ኖሮ ይቻል የነበረው የዛሬ 25 ዓመት ገደማ በ1983ዓ.ም ወርኃ ግንቦት ላይ ነበር፡፡ አሁን እጅግ መሽቷል፤ “ቢያዩኝ እስቅ፣ ባያዩኝ እሰርቅ“ የሚለው ብሂል የማይሠራበት የመጨረሻው ሰዓት ላይ ስላሉ ያን ቅዠታቸውን ዘመን ሽሮታል፡፡ “ዕድላችንን እንሞክር” የሚባልበት ጠባብ የተስፋ ጭላንጭል እንኳን የለም፡፡ አንድ የትግርኛ ብሂል ላስታውስ – ወዳማርኛ ልመልሰው ፡- “የሚበቃትን ያህል ጥሬ ከፈጨች በኋላ የማርያም በዓል ነው ትላለች” ይላል፡፡ ግሩም ብኂል ነው፡፡ በልጆች ጨዋታ ጊዜ “ጨዋታው ፈረሰ፣ ዳቦው ተቆረሰ” ሊባል ይችል የነበረው ዛሬ ሣይሆን ከዛሬ 25 ዓመታት ገደማ በፊት ነው፡፡

ወልቃይትንና አካባቢዋን ከጎንደር፣ ራያዎችን ከወሎ፣ የአባይ ግድብን ከቤንሻጉል፣ እንትናን ከአፋር … ከዘረፉና ወደ “ታላቋ የትግራይ ሪፐብሊክ” ካካለሉ በኋላ፣ ሰፊ የዐማራ ግዛትን ለሱዳን ከሸጡ በኋላ፣ የኢትዮጵያን ሀብትና ንብረት ለ40 እና 25 ዓመታት በተከታታይ ካለተቆጣጣሪ እንደልብ ከመዘበሩና ወደሚፈለጉት ቦታ ካዘዋወሩ በኋላ፣ በሚሊዮን የሚገመት ሕዝብ በልዩ ልዩ ዘዴ ከምድረ ገፅ ካጠፉና እንዲሰደድም እንዲፈናቀልም እንዲራብና እንዲታረዝም ካደረጉ በኋላ፣ የኢትዮጵያን አስተዳደር በአንድ ጎሣ ቁጥጥር ሥር አውለው የሀገሪቷን አንጡራ ሀብት እንዳሻቸው ከቦጠቦጡና መዋቅሮቿን ሁሉ ካፈራረሱ በኋላ፣ የሚንቀሳቀስንም ሀብትና ንብረት ወደ አሳቻ ቦታ ካሻገሩ በኋላ… ለዚህ ሁሉ ዘመን በአንዲት ሉዓላዊት ሀገርና በአንድ ሕዝብ ላይ እንደልብ ከፈነጩ በኋላ አሁን ሲመሽ “የያዝኩትን ይዤ የራሴን ግዛት እመሠርታለሁ” የሚለው ብልጣብልጥነት ከማሣቅም ያልፋል – ወያኔ ከኢትዮጵያ የአንበሣና ዝኆኑን ድርሻ ዝቆ ወደራሱ ጎተራ ካስገባ በኋላ ለመሆኑ ለሌላው ሕዝብ ምን የቀረለት ነገር አለና ብቻውን መንግሥት መሥርቶ ከነሱ ጋር በአቻ ጉርብትና የሚኖረው? የመረጃ ቋቱ ሳይቀር ተጉዞ መቀሌ ገባ ከተባለ በኋላ ሌሎቹን እንደፍጥርጥራችሁ ብሎ “ትግራይ ሪፐብሊክ” የምትመሠረተው በየትኛው ሥሌት ነው? የዋህነት ወይንስ ድምበርን የማያውቅ ብልጠት? ሀገርን ማስተዳደርና ሀገርን መመሥረት የልጆች የቃቃ ጨዋታ አይደለም፡፡ አንድን ሀገር አፍርሶም ሌላ ሀገር መገንባት የሚታሰብ አይሆንም፡፡ ቂልነት ነው፡፡ ወይም የለዬለት ዕብደት፡፡

የወያኔዎች አጀማመር ሁሉ እንዳይሆን ነው፤ ሲጀምር ትልቅ ሀገርን እየገዙ የ”ገዛ ሀገር”ን መሬት ለባዕድ መሸጥና በነሱው አጠራር ካንዱ ‹ክልል‹ ወደሌላው ‹ክልል‹ ቁርጥራጭ መሬት እየቀደዱ መስፋት ጥንቱንም አላስፈላጊ ነበር – ሌላ ታሳቢ ተንኮል እስከሌላቸው ድረስ፡፡ ኢትዮጵያ የኢትዮጵያውያን የጋራ ሀገር እስከሆነች ድረስ በግዛት መካለልና ያንንም ተከትሎ በመጣ ዕልቂት የሰውና የንብረት ውድመት መከሰት አልነበረበትም፡፡ ማንም ዜጋ የትም ሄዶ መሥራትና ሀብት ንብረት ማፍራት ስለሚችል አዲስ አከላለል ወይም ኬሌላ ግዛት የመሬት ዝርፊያ ባላስፈለገም ነበር፡፡

ወያኔ ግን የነገን ሣይሆን የዛሬን ብቻ ስለሚያስብ የሆነው ሁሉ ሳንወድ በግዳችን ሆነ፡፡ ግዴለም – “በዚሁ ይለፍ፡፡” ዋናው ነገር ግና ከዚህ ሁሉ የሰው ዕልቂትና የንብረት ውድመት በኋላ የ“ታላቋን ትግራይ ሪፐብሊክ” ለመመሥረት ማሰብ ከፍ ሲል ለመግለጽ እንደተሞከረው ዕብደት እንጂ ሌላ ሊሆን አለመቻሉን መረዳት ተገቢ ነው፡፡ ወያኔዎች እንደዚህ ያለ ጅል አስተሳሰብ ውስጥ የሚገኙ ከሆነ ከፍ ሲል በዐማርኛ የጠቀስነውን የትግርኛ ብሂል ደግመን በማስታወስ ”ዝአኽለን ጥሂነን በዓል ማርያም ትብላ” ብለን እንተርትባቸዋለን፤ ወቅቱ የሀዘን ቢሆንም በለበጣ የአግራሞት ሣቅ እንፈግባቸዋለን፡፡ ይህን ቅዠት ማንም ወያኔም ይሁን የትግራይ ክፍለ ሀገር ሰው ሊያስበው አይገባም፤ አይችልምም፡፡ ሁለት ተቃራኒ ነገሮች ኅብረት የላቸውም፡፡ ብርሃንና ጨለማ በአንድ ጊዜ አይገኙም፡፡ ኢትዮጵያዊነትና ትግራዊነትም እንዲሁ፡፡ ጤናማ ተጋሩ ከዚህ ወያኔያዊ ቅዠት ባፋጣኝ ውጡና የሚሻለውን ለማድረግ ተመካከሩ፡፡ ይህ “ወርቃማ” ዕድል የዛሬ 25 ዓመት አለፈ፡፡ የፈሰሰን ውኃ ማፈስ ደግሞ አይቻልም፡፡

ይልቁንስ ለትግራይና ለተጋሩ የሚያዋጣው ብቸኛ መንገድ የሆነች መፈንቅለ መንግሥት ማድረግና ያችን ተከትሎ ጤናማ ትግሬዎች የያዙት “የክልሉ መንግሥት” ከሌሎች ጤናማ ወገኖች ጋር አዲስ ድርድር ማድረግ ነው፡፡ ለዚህም የጤናማ ትግሬዎች ሚና በጣም ወሳኝ ነው – በተለይ ወጣቱ፡፡ ይህ ሣይሆን ቀርቶ ወያኔ የትግራይን መፃዒ ዕድል እንደእስከዛሬው ሁሉ እንዲወስን ከተደረገ በርግጥም የትንቢቱ ፍጻሜ ይሆንና ሊያስወግዱት በሚቻል ችግር ሀገራችን የማትወጣው አደጋ ውስጥ ትገባለች፡፡ ይህን እውነት አሁን ሳይመሽ በጊዜ እንዲህ ባልተለመደ ድፍረት የምናገረው ሌላውን ተውትና ከነባራዊው ዓለም ተጨባጭ ወይም ገሃድ እውነት በመነሳት የተበደለ ሲነሳ የሚያቆመው ነገር እንደሌለ በመረዳት ነው፡፡

እዚህች ላይ አንዲት ጠቃሚ ነጥብ ላንሳ፡፡ … ደጋግ ሰዎች ለፈጣሪ ከጮኹና የፈጣሪን ልብ ካራሩ ትንቢት ሊለወጥ ወይም የሚከሰት ውድመት ሊቀንስ እንደሚችል መገንዘብ ተገቢ ነውና ለፈጣሪ የቀረባችሁ ዜጎች የእንቅልፍ ሰዓታችሁን በመቀነስ ሌት ተቀን ወደፈጣሪ ጩኹ፤ እየመጣ ያለው የመከራ ዶፍ ሰው ቀርቶ ምድር አትችለውም – በዓለም ታሪክ ወደር የሌለው የወያኔዎች ዐረመኔነት የሚያስከትለው ጦስ እንዲህ በቀላሉ የሚገመት ነው ብሎ የሚያስብ ሰው ካለ ስለወንጀል ዕዳ አከፋፈል ምንም የማያውቅ የዋህ ሰው መሆን አለበት፡፡ ይህን የማይም ማስጠንቀቂያ እየተናገርኩ ያለሁት በዱባ ጥጋብ ለታበዩትና በዕብሪት ጉሽ ጠላ ለሰከሩት ወያኔዎችና መሰሎቻቸው አይደለም፤ ተፈጥሮን ተመክሮ አይመልሰውምና እነሱ መቼም ሊለወጡ አይችሉም – እንዲለወጡ የሚጠብቅም ሰው ካለ የአእምሮ ህክምና የሚያስፈልገው የለዬለት ሞኝ ነው፤ እነሱና ጋዳፊ ሊለወጡ እንደማይችሉ በበኩሌ በደንብ አውቃለሁ – ጋዳፊ ስምንት ቀን ተሸሽጎበት ከነበረው የቆሻሻ ቱቦ ወጥቶ “ምን ሆናችሁ? ሊቢያ ውስጥ ምን ተፈጠረ?” እያለ መሪው እርሱ የሆነ ያህል ቆጥሮ በባትሪ እየፈለጉት የነበሩትን ተቃዋሚዎች ለማዘዝ ቃጥቶት ነበር አሉ – ግን ወዲያው ያዙትና በመቀመጫው በኩል ሣንጃቸውን ወድውደው አንጀቱን በጣጥሰው ገደሉት – የአምባገነኖች መጨረሻ እንዲህ ነው፡፡ እኚህን መሰል ደናቁርት ከአህያ የማይሻል የማየት ችሎታ ነው ያላቸው፤ የጅልነታቸው መጠን የጨካኝነታቸውን ያህል ነው፡፡ …

እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ሀገራችንን ከተጋረጠባት የጥፋት ዳመና ያውጣልን፤ ፍቅርና አንድነትን ይስጠን፡፡ ለሳዖል የሰጠውን ማስተዋል ለሕወሓትም ሰጥቶ ሕዝብንና አገርን እያረዱበት የሚገኙትን ጎራዴ/ሠይፍ ወደ አፎቱ እንዲያስገቡና ዕርቅና ሰላም በሀገራችን እንዲሰፍን እግዜር ይርዳን፤ ምርጫ አጥተን የምንገባበት መብታችንን የማስከበር ትግል ሁሉ ብዙ የሕይወትና የንብረት መስዋዕትነትን ይጠይቃልና የእስካሁኑ መከራችን በቃችሁ ብሎ ባፋጣኝ ምሕረቱን ይላክልን፤ አሜን፡፡
mz23602@gmail.com

ምዕራብ በለሳ ወረዳ በሕዝብ ቁጥጥር ስር ዋለ • በጃቢ ጠናን ከ10 በላይ ቀበሌዎች የዐማራ ተጋድሎ ተቀጣጥሏል (የአማራ ተጋድሎ የዛሬው ውሎ ዜና ትንታኔ)

$
0
0

Update ዐማራ ዛሬ (ነሃሴ 21 ቀን 2008 ዓ.ም)

የቋሪት ዐማሮች አስደናቂ ገድል ፈጸሙ፣ የዐማራ ሕዝብ ከጫፍ እስከ ጫፍ ተጋድሎውን ተቀላቅሏል 
• ምዕራብ በለሳ ወረዳ በሕዝብ ቁጥጥር ሥር ውሏል፤ ገበሬው ወደ ወልቃይት ለመዝመት የጎበዝ አለቆችን እየጠየቀ ነው
• በጃቢ ጠናን ከ10 በላይ ቀበሌዎች የዐማራ ተጋድሎ ተቀጣጥሏል
• በባሕር ዳርና በደብረታቦር ከነሃሴ 22 እስከ 24 የቤት ውስጥ አድማ ይደረጋል፤ በደብረ ታቦር መንግሥት ፈርሷል እየተባለ ነው

 

ከሙሉቀን ተስፋው

ደንበጫ/ የጨረቃ፤ በደንበጫ ወረዳ በደንበጫ፣ በየጨረቃና በሌሎች ከተሞችም የዐማራ ተጋድሎ ዛሬ ቀጥሎ ውሏል፡፡ ‹‹ወልቃይት የዐማራ ነው፤ የወያኔ ኑሮ ይለያል ዘንድሮ፣ ኮሎኔል ደመቀና የወልቃይት ጠገዴ የዐማራ ማንነት አቅራቢ ኮሚቴዎች በአስቸኳይ ይፈቱ፣ ዐማራነት ወንጀል አይደለም…›› የሚሉ መፈክሮች ሲሰሙ ውለዋል፡፡ የዐማራ ተጋድለ ጠዋት 2፡30 የተጀመረ ሲሆን ይህ ዝግጅት እስከተጠናቀቀበት ጊዜ ድረስ ተጋድሎው መቀጠሉን ሰምተናል፡፡ የደንበጫና የጨረቃ ከተማ የዐማራ ተጋድሎ ሰላማዊ በሆነ መልኩ ተጀምሮ መጠናቀቁንም ሰምተናል፡፡ ከቦታው መረጃውን ያቀበሉን ሰዎች እንደሚሉት ምንም ዓይነት ንብረት እንዳይወድም የጎበዝ አለቆች ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል ብለዋል፡፡ የወረዳዋ ካቢኔዎች ከተማዎቹን ለቀው የጠፉ ሲሆን እስከ ምሽት ድረስም የወያኔ ባንዲራ ያለባቸው ቢሮዎች ባባቶቻችን ደም የተመሠረተችው ሰንደቅ ዓላማ ተተክታለች፡፡ በደበንበጫ ከተማ ከ30 ሺህ በላይ ዐማሮች የተጋድሎ ሰልፉን ተቀላቅለውታል፡፡
እንደመረጃ አቀባዮቻችን ከሆነ በደንበጫ ማንኛውም የወያኔ ኃይል ምንም ዓይነት ጣልቃ እንዲገባ አልተፈቀደለትም፤ ፖሊስና ምኒሻም ከሕዝብ ጋር ቆሟል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ አንድ የወያኔ ባንዳ የነበረ ከደንበጫ ከተማ ወጣ ብሎ ያለ የኪዳነ ምሕረት አካባቢ ቀበሌ ሊቀ መንበር ቤት ብቻ ተሰብሯል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ከሰአት በኋላ መጠነኛ ተኩስ ቢኖርም በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም፡፡ ሆኖም ምሽቱን ወጣቶችን የሚያስሩ ነገ እንደምናስፈታቸው እርግጠኞች ነን ብለውናል፡፡
የአማኑኤል ከተማም የዐማራ ተጋድሎ እንዳለ የሰማን ቢሆንም በቂ መረጃ ማሰባሰብ አልቻልንም፡፡
ጃቢ ጠናን/ ብር ሸለቆ፤ በጃቢጠናን ወረዳ ያሉ አብዛኛዎቹ የገጠር ቀበሌዎች ለዐማራ ተጋድሎ ሰልፍ ወጥተዋል፡፡ ዛሬ በብር ሸለቆ ከተማ የተጀመረው የዐማራ ተጋድሎ እርግብ፤ ወይንማ ወርቅማ፣ አዲስ ዓለም እና ሌሎች ከዐሥር የሚልቁ የገጠር ቀበሌዎች ላይ ተጋድሎው ተፋፍሞ ውሏል፡፡ ጃቢ ጠናን ወረዳ አብዛኛው በዐማራ ሕዝብ በራሱ ቁጥጥር ሥር መዋሉን ነው ለማወቅ የቻልነው፡፡ በሁሉም የዐማራ አካባቢዎች እንዳለው ሁሉ በጃቢ ጠናን የገጠር ቀበሌዎችም የዐማራ ሕዝብ ጥያቄዎች ሲስተጋቡ ውለዋል፡፡ የብርሸለቆ ከተማ የወታደራዊ ማሰልጠኛ ጣቢያው አካባቢ ቢሆንም የጎጃምን ገበሬ የደፈረ ሠራዊት ግን እንዳልነበረ ለማወቅ ችለናል፡፡ ከብር ሸለቆ ከተማ በስልክ ያናገርናቸው ሰዎች እንደሚገልጹት አንዳንድ ተላላኪ ባንዳዎች ሰልፍ ያስተባብራሉ የሚባሉ ሰዎችን መዝግበው ለወታደሮች መስጠታቸውን ገልጸው የእኛን ጎበዝ አለቆች እንወስዳለን ብሎ የሚመጣ ማንኛውም ኃይል ከእኛ ነጥቆ ከወሰዳቸውማ ምንኑን የበላይ ዘለቀ ልጆች ሆንን ሲሉ በስሜት ተናግረዋል፡፡
ቡሬ፣ በቡሬ ከተማ ትናንት የተጀመረው የዐማራ ተጋድሎ ዛሬም ቀጥሎ መዋሉን ሰምተናል፡፡ እስከ እኩለ ቀን ድረስ ወጣቶች የዐማራን ሕዝብ ጥያቄዎች ሲያሰሙ ውለዋል፡፡ እኩለ ቀን አካባቢ የተወሰነ የጥይት ድምጽ ቢኖርም በሕይወት ላይ የደረሰ ጥፋት እንደሌለ ሰምተናል፡፡
ቋሪት፤ የቋሪት ዐማሮች አስደናቂ ገደል ፈጸሙ፡፡ በቋሪት ወረዳ የገበዘ ማርያም እና የገነት አቦ ከተማ ነዋዎች ዛሬም የዐማራ ተጋድሎን ለሦስተኛ ቀን ቀጥለው የዋሉ ሲሆን ማንኛውም የወረዳዋ እንቅስቃሴ በሕዝቡ ቁጥጥር ሥር እንደዋለ ነው፡፡ የቋሪት ዐማሮች ሌላው የፈጸሙት ገደል የወያኔ ተላላኪ ቅጥረኛ ካቢኔዎችንና የወረዳውን አስተዳዳሪ በመያዝ የወያኔን ባንዲራ ካቢኔዎቹ በየመሥሪያ ቤታቸው አውርደው የአባቶቻችን ሰንደቅ ዓላማ እንዲሰቅሉ ተገደዋል፡፡ የንግድ ባንክ ሥራ አስኪያጅም ተገዶ የወያኔን ባንዲራ በማውረድ ሰንደቅ ዓላማችን ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ሰቅሏል፡፡
ገዥው መንግሥት ያሰማራቸውን የጸጥታ አካላት በሙሉ ከከተማዋ አባረው አስወጥተዋል፡፡ ከፖሊስ ጣቢያው ፊት ለፊት ባለው አደባባይ ላይ ጉድጓድ ተቆፍሮ የሰንደቅ ዓላማ መስቀያ እንጨት ተተከለ፡፡ ከዚያም በታላቅ ደስታና እልልታ የአባቶቻችን ደም ያለባት ሰንደቃችን ተውለበለበች፡፡ ማንም ጀግና የሆነ ከቋሪት ምድር ያችን ሰንደቅ የሚያወርድ የለም ተብሏል፡፡
በቋሪት ዛሬ በዋለው ሰልፍ ወጣቶች የዐማራን የተጋድሎ ጥያቄዎች ሲያስተጋቡ ጎልማሳዎች ደግሞ ከፍተኛ ትጥቅ እና ጥይት በመያዝ በፉከራና በሽለላ የአርበኝነት ዘመንን ሲያወድሱ ውለዋል፡፡ ፖሊሶችም ተገደው ጥይይት እንዲተኩሱ ይደረግ ነበር፡፡ ሆኖም አሁን ላይ ምንም ዓይነት የመንግሥት ተወካይ በወረዳው እንደሌለ ነው የተነገረው፡፡
አዴት፤ የይልማና ዴንሳዋ መናገሻ አዴት ከተማ ውጥረት ላይ መሆኗን ሰምተናል፡፡ የዐማራ ተጋድሎ ይቀሰቀሳል በሚል ስጋት ገበሬዎች ወደ አዴት ከተማ እንዳይገቡ መከልከላቸውን ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ የጎንች ቆለላ ወረዳም እንዳዴት ሁሉ ገበሬዎች ወደ ከተማ እንዳይቡ መደረገቸው ታውቋል፡፡
ባሕር ዳር/ደብረ ታበር፤ ባሕር ዳር እና ደብረ ታቦር ከተሞች ከነገ ነሃሴ 22 እስከ 25 ቀን 2008 ዓ.ም. የቤት ውስጥ አድማ ይደረጋል፡፡ በባሕር ዳር ለአገዛዙ የሚያግዙ የባጃጅ ተሸከርካሪዎች ታርጋ ቁጥር ተለይቷል፡፡ ስለሆንም ከነገ ጀምሮ ማናቸውም ሥራ እና እንቅስቃሴ ዝግ የሚሆን ሲሆን ይህን ህግ ተላልፎ የሚገኝ ሰው የዐማራ ሕዝብ ጠላት እንደሆነ ይቆጠራል ተብሏል፡፡

ዛሬ የቋሪት ህዝብ ፀረ አማራዉን የወያኔን ስርዓት በማፍረስ የራሱን የጎበዝ አለቆች መረጠ | ፎቶ ከቤተአማራ

ዛሬ የቋሪት ህዝብ ፀረ አማራዉን የወያኔን ስርዓት በማፍረስ የራሱን የጎበዝ አለቆች መረጠ | ፎቶ ከቤተአማራ

በሌላ በኩል በደብረ ታቦር ከተማ ከነገ ጀምሮ ለ3 ቀን የሚቆይ የቤት ውስጥ አድማ የሚኖር ሲሆን አድማውን የሚተላለፉ ግለሰቦችንና ቡድኖች የሚቀጣ የጎበዝ አለቃ ቡድን ተቋቁሟል፡፡ በደብረ ታቦርና በፋርጣ አካባቢዎች ‹‹መንግሥት ፈርሷል›› በመባሉ የአካባቢ የመንግሥት ባለሥልጣናትም ሕግ ማስጠበቅ ባለመቻላቸው የጎበዝ አለቆች ሕግ እያስከበሩ እንደሆነ ገልጸውልናል፡፡ ዛሬ ማምሻውን የስርዓቱ ቅጥረኛ ባለሥልጣናት ነገ አገልግሎት መስጫ ተቋማት እንዳይዘጉ የሚሉ ማስታዎቂያዊችን ሲለጥፉ ውለዋል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ የጎንደር ከተማ የቤት ውስጥ አድማ ዛሬም ተጠናክሮ መቀጠሉን ሰምተናል፡፡
አርባያ፤ ሰሜን ጎንደር ዞን የምዕራብ በለሳ ወረዳ ያገኘነው መረጃ አጃኢብ አስብሎናል፡፡ በምዕራብ አርባያ ወረዳ መንግሥት ፈርሷል፡፡ የአርባያ ከተማና የምዕራብ በለሳ ዐማሮች ዛሬ ተጋድሏቸውን የተቀላቀሉ ሲሆን ‹‹በወታደር አንገዛም፣ ሥርዓቱ አያስፈልገንም፣ የአንድ ብሔር የበላይነት ከዚህ በኋላ አይኖርም፤ ወልቃይት የዐማራ ነው ..›› የመሳሰሉ ጥያቄዎች ሲስተጋቡ ውለዋል፡፡
በከተማዋ በመለስ ስም የተሰየመው ትምህርት ቤት ስሙ ተቀይሮ በአጼ ቴዎድሮስ ስም ተሰይሟል፡፡ የምዕራብ አርባያ ወረዳ የዐማራን ተጋድሎ ለመደፍጠጥ የ2.4 ሚሊዮን ብር በጀት በመመደብ 144 ቡችሌ የሚባሉ የአገዛዙ ባሪያ ወታደሮችን አሰልጥኖ ነበር፡፡ ሆኖም እነዚህን ቡችሌዎች ከከተማዋ ጠራርጎ አስወጥቶ አካባቢው ሙሉ በሙሉ በሕዝብ ቁጥጥር ስር ሆኗል፡፡
ዛሬ ምሽቱን ከቦታው የገኘናቸው ሰዎች እንደሚሉት ‹‹በእኛ አገር መንግስት ፈርሷል፤ ራሳችን በራሳችን ነው የምናስተዳድረው›› ብለውናል፡፡ ገበሬው ግብር ለማንም ከዚህ በኋላ ላለመክፈል ያቀደ ሲሆን እርሻችን ጨርሰን ወደ ወልቃይት እንድንዘምት የጎበዝ አለቆች ምሩን እያሉ እንደሆነ ነው የሰማነው፡፡
የመከላከያ ሠራዊት አልመጣም ወይ ብለን ላቀረብንላቸው ጥያቄ ‹‹መከላከያ እንዲመጣ በናፍቆት እየጠበቅን ነው፤ የመሳሪያ ችግራችን በምርኮ እናማላ ነበር›› ሲሉ በወኔ ተናግረዋል፡፡ በአርበኝነት ዘመን አባት አርበኞቻችን መሳሪያ የሚያገኙት ከባንዳዎችና ከጠላት ላይ በመማረክ መሆኑን ጭምር ነው ያስረዱን፡፡ ትናንት ምሽት አንድ ቅጥረኛ ቡችሌ ከመገደሉ ውጭ ምንም ዓይነት በሰውም ሆነ በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም ብለዋል፡፡ ሕብረተሰቡም ለሕዝብ ንብረቶች ጥበቃ እንደሚያደርግ ጭምር ገልጸዋል፡፡
የዐማራ ተጋድሎ ያሸንፋል//
ይህ ሁሉ የመጨረሻው መጀመሪያ ነው!

ቢቢኤን ሰበር ዜና: በምዕራብ ሐረርጌ ሁለት መስጊዶች ላይ የቦምብ ጥቃት ደረሰ |ብዙ ሰዎች ቆስለዋል

$
0
0

(ቢቢኤን ሰበር ዜና) ምእራብ ሀረርጌ ማሳላ ወረዳ ልዩ ስሙ ዋልተሲስ በሚገኘው መስጂድ የመንግስት ወታደሮች (አጋዚዎች) ከባድ የቦንብ ጥቃት አድርሰዋል፤ መስጂዱንም አውድመውታል። ቁጥሩ ያልታወቀ ሰው ለሞትና ለአካል ጉዳት ተዳርጓል ትንታኔውን ይከታተሉ::

ቢቢኤን ሰበር ዜና: በምዕራብ ሐረርጌ ሁለት መስጊዶች ላይ የቦምብ ጥቃት ደረሰ | ብዙ ሰዎች ቆስለዋል

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live