Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የትግሬዎች መንግሥት አወዳደቁና ክፋቱ! -አንዱዓለም ተፈራ

$
0
0

እስከመቼ cropped-eskemeche-question32

ሐሙስ ነሐሴ ፲ ፪ ቀን ፳ ፻ ፰ ዓመተ ምህረት ( 08/18/2016 )

ባሁን ሰዓት፤ በገዥነት ሕልሙ እየተንሳፈፈ ካለው የትግሬዎች ቡድን በስተቀር፤ ኢትዮጵያን አደጋ ላይ የጣላት ይሄው ቡድን፤ የውድቀት አፋፉ ላይ መሆኑ ለሁላችን ግልጽ ነው። አሁን ካለንበት ሰዓት እስከመጨረሻው ውድቀቱ ያለው ጊዜ ግን፤ በጣም የከፋና የተመሰቃቀለ ነው። ይህ የሚሆነው፤ ከፊል በዚህ ወራሪ ቡድን ተግባር ሲሆን፤ ከፊሉ ደግሞ በኛው በታጋዩ ክፍል ያለነው ለዚህ ውድቀት በማድረግና ባለማድረግ ላይ ባለው ሂደታችን ነው። በተጨማሪ ደግሞ፤ የሃያ አምስት ዓመት የዚህ ቡድን ፀረ-ኢትዮጵያ አገዛዝ፤ ሀገራችንን ለከፋ ወደፊት አዘጋጅቷታል። ሀቁን ተቀብለን ከአሁኑ መደረግ ያለበትን ካላደረግን፤ በኋላ ይሄን ብናደርግ ኖሮ ብለን የመቆጫ ሰዓት አናገኝም፤ ያኔ ሁኔታውን አንገዛውምና!

ይህ ወራሪ ቡድን፤ የመጨረሻ እስትንፋሱን የሚያወጣው በቃሬዛ ነው። ሕዝቡ አቸናፊ ሆኖ እንደሚወጣ ምንም ዓይነት ብዥታ ባይኖረንም፤ የሚከተለው ምን ይሆን? የሚለው ስጋት ሀቅ ነው። ያንን ሳጋት የበለጠ ለማክፋት ይህ የትግሬዎች ቡድን ሲጥር፤ ታጋዩ ክፍል የሚሠጠው መልስ ወሳኝ ነው። ህዝቡ ማቸነፍ የሚችለው፤ ከዚህ ቡድን በልጦ ሲገኝ ነው። ጎልብቶ ሲገኝ ነው። ጎብዞ ሲገኝ ነው። ይህ ቡድን ምን እያቀደ ነው? ብሎ ቀድሞ ሲዘጋጅ ነው። ምን ሊያደርግ ይችላል? የሚለውን ወስዶ አደናቃፊ ዝግጅቶችን ሲያሰላ ነው። አስኪ ይህ ቡድን ሊያደርጋቸው የሚችሉትን እንመልከት፤

  • እንዳየነውና እንደሰማነው፤ አልቃይዳ ወይንም አልሸባብ ወይንም አይሲስ ብሎ ታጋዩን ያልሆነ ቀለም በመቀባት፤ የውጪ ሀገሮችን ድጋፍ ለማግኘት ይጥራል። አይሆንም ማለት ሞኝነት ነው። ዛሬም ድረስ በሺር አል አሳድ ሶሪያን የሚገዛው፤ አሜሪካና አውሮፓ በከፍተኛ ድጋፍ ተቃዋሚዎቹን ቢረዱም፤ በሶቪየቶችና ቻይናዎች ድጋፍ ነው። እኒህም ሆኑ ሌሎች ሀገራት፤ ስሌታቸውን የሚያተኩሩት፤ ለኔ ሀገር ሁኔታው ምን ያስገኝልኛል? ብለው ነው።
  • ከዚህ አያይዞ፤ የውጭ ቅጥረኞች በማለት ታጋዮችን በሀገር ቤት ለማስጠላት ይሞከራል። እያደረገውም ነው። ይህ፤ ጊዜ ለመገብያ የሚጠቀምበት ዘዴ ነው። ወረሩኝ ብሎም ጦርነት በጎረቤት ሀገሮች ሊከፍት ይችላል። ይህ ሁሉ፤ የሕዝቡንና የታጋዩን እንቅስቃሴ ለማለዘብ ነው። ጊዜው አልፏል።
  • ዋናው የዚህ የትግሬዎች ቡድን አስከፊ ተግባር፥ ጉልበቱን መጠቀም ነው። ይህ እብሪተኛ ቡድን መቼም ቢሆን የሚተማመነው፤ “ጉልበቴ ከሁሉም ይበልጣል!” ብሎ ነው። አሁንም ሁሉን ነገር “በጉልበቴ እወጣዋለሁ!” ብሎ፤ አረመኔያዊ ተግባሩን ቀጥሎበታል። ነገሮችን አጢኖ መመልከት ድክመት ይመስለዋል። በሰላም ባዶ እጁን አቤቱታ ሊያሰማ የወጣውን ሕዝብ፤ እስካፍንጫው የታጠቀ አጋዚ አሰልፎ በቀጥታ በሰልፉ ላይ በመተኮስ አሁን በመቶዎች የሚቆጠሩትን እየገደለ ነው። ነገ ደግሞ በሺዎች የሚቆጠሩትን ይረሽናል። እስኪሞት ድረስ ሌላ ዕውቀት የለውም። ካልገደለ ውሎ የሚያድር አይመስለውም። ሕዝብ ቆርጦ ከተነሳ፤ መመለም የሌለው መሆኑን ሊረዳው አይችልም። የዚህ ቡድን መነጽር፤ የተቃወመኝን ገድዬ፤ ጉዳዩን አጠፋለሁ ነው።
  • ታጋዩን ከሕዝቡ ለመነጠል ይጥራል። ደደብ ሆኖ ነው እንጂ፤ ታጋዩ እኮ ሕዝቡ ነው! ሊገባው አይችልም። ታጋዩን ሊከፋፋል ይሞክራል። ታጋዩን እኮ፤ ከዚህ ቡድን ሕልውናና ጥፋት የበለጠ የሚያንገበግበው የለም። ለነገሩ ይህ አዲስ አይደለም። እስከዛሬ ያቆየው፤ የሕዝቡ በአንድ አለመነሳት ነበር። በዘር፣ በሃይማኖትና በጥቅም መከፋፈሉን ተክኖበታል። አሁን ግን ሕዝቡ ይህን ሁሉ ጥሶ እንዲወጣ የዚህ ቡድን ለከት የለሽ በደል አስገድዶታል።
  • “አሸባሪዎች ናቸው!” ብሎ ማላዘን የዕለት ተግባሩ ነው። ነገ ደግሞ የየሰዓት ጸሎቱ ይሆናል። ለዚህም የሃይማኖት አባቶችን አሰልፎ ያስወግዛል፣ ይማጠናል፣ ያባብላል። የቤተክህነትና የመስጊድ መሪዎችን አቅርቦ ሊናዝዝ ይቻላል። አብሮም ሆዳም የመንግሥት ሠራተኞችንና የጦር መሪዎችን አሰልፎ ሊያስወግዝ ይቻላል።
  • መላ የፌዴራልና የክልል አስተዳደራዊ መዋቅሮችን የስለላ ድርጅት ያደርጋቸዋል። እያንዳንዱን ትግሬና የስመ ኢሕአዴግ አባል ተራ ሰላይ ያደርጋል። ከታጋዩ ከድተው ወደኔ ገቡ ብሎ የውሸት ታጋዮችን በቴሌቪዥን ሊያቀርብ ይችላል። ተዘረፈ ብሎ የመንግሥትን ካዝና ወደ መቀሌ ሊያሻግረው ይችላል። ይህ ቡድን ሌብነት ኒሻኑ ነው።
  • ለመታያ የተቀነባበረ የሱ ደጋፊ ሰላማዊ ሰልፎችና ትዕይንቶች ሊያዥጎደጉድ ይችላል። በማስፈራራት፣ በመደለልና በማስገደድ ሰልፍ እንዲወጡ ሊያደርግ ይችላል። ይህን ማንም አይስተውም። ሆኖም ግን የራሱን የመንፈስ ጭንቀት እንኳን አይበርድለትም። አምባገነን መንግሥታት ሙያቸው ነው። ትናንት መንግሥቱ ኃይለማርያም አድርጎታል።
  • ሲያስበረግገው የሚያድረው የሕዝቡ ቁጣ፤ በፓልቶክ፣ በፌስቡክ፣ በሬዲዮና በድረገጾች ላይ ዘመቻውን እንዲያበዛ ያደርገዋል። መስሎት ነው። ኢንተርኔቱን ይዝጋው፤ ሕዝቡ በኢንተርኔት ሳይሆን በሚኖርበት ሀቅ ተገፋፍቶ ነው የተነሳው። ፓልቶክ ደግሞ ሕዝቡን ወደ አንድ አመጣና በትክክለኛው ጠላቱ ላይ እንዲያተኩር ረዳው እንጂ፤ ችግሩ ያስተዳደር በደል ነው። የዜና ልውውጡን ሊያግት ቢሞከርም፤ በየቦታው ያለው የሱ ግፍ ያነሳሳው ነው።
  • በማታለልና በማውገርገር የተካነው ይህ የትግሬዎች ቡድን፤ እደራደራለሁ፣ ለውጥ አደርጋለሁ፣ ሽምግልና እገባለሁ ሊል ይቻላል። ይህን እያለ ግን፤ በጎን በከፋ ሁኔታ ያው መግደሉን ይቀጥልበታል። ይህን የሚለው ጊዜ ለመግዣ ብቻ ነው። ተገዶም ቢሆን ለድርድር ቢቀርብ፤ ሥልጣኑን ማጋራት ወይንም የሰረቀውን ሀብት መመለሾ አይፈልግም። ሥልጣኑን የሚያስረክበው ወድሞ ነው።

ይህ ሁሉ ተግባሩ፣ አንድ ቀና አንድ ሌሊት ሊገዛለት ቢችልም፤ በአንጻሩ ግን፤ ትግሉን በትግሬዎችና በኢትዮጵያዊያን መካከል በማድረግ፤ የትግራይን ሕዝብ ለነገ ዕልቂት ያዘጋጀዋል። ይህ እየመጣ ያለ ሀቅ ነው። በርግጥ አሁን ሊለወጥ የሚችልበት ሰዓት ነው። ይህን ደግሞ እንደሚከተለው አቀርበዋለሁ።

ምንም አንኳ ይህን ፈጻሚው የትግሬዎች ቡድን ቢሆንም፤ በዚያው አኳያ፤ የታጋዩ ክፍል ጥረት፤ ሊያስተካክለው ወይንም ሊያባብሰው ይችላል። በአሁኑ ወቅት ታጋዩ ያለበት ሁኔታ አመቺ አይደለም። በርግጥ ሕዝቡ ራሱ እየመራ ያለበት ይህ እንቅስቃሴ፤ ወደፊት እንዲሄድና ለስኬት እንዲበቃ፤ መልክ መያዝ አለበት። ማዕከል ሊኖረ ይገባል። ይህ ማለት፤ አሁን ካሉት ድርጅቶች አንዱ ወይንም ሌላው ይምራው ማለት አይደለም። አሁንም መሪው በቦታው ሕይወቱን እየከፈለ ያለው ሕዝቡ ራሱ ነው። ታዲያ በውጪም ሆነ በሀገር ውስጥ ያለን የታጋዩ ክፍል ነን የምንል ሰዎች፤ እገዛችን መሆን ያለበት፤ ይህን ሕዝባዊ አካል መርዳትና ማጠናከር ነው። ለዚህ አመራር ተገዥ መሆን ነው። በየቦታው በመደረግ ላይ ያለው ሰላማዊ ሰልፍ፤ እንዲያው ከየሰማዩ ዱብ ዱብ ያለ አይደለም። ሕዝባዊ ቅንጅት አለው። ወጣቶቹ ከፍተኛውን መስዋዕትነት እየከፈሉ ያዋቀሩት የደማቸው ሐረግ ነው። ይህን ማጎልበት አለብን። የኔን ድርጅት ወይንም የኔን ድርጅት እያልን፤ ድርጅቶቻችን በሕዝቡ ላይ ለመጫን ያጎበጎብነው፤ ልጓማችንን መያዝ አለብን።

ጎንደር የተሰለፉት ወጣቶች፤ የእስልምና ተከታይ ወኪሎችና የኦሮሞ ወጣቶች ጉዳይ ጉዳያችን ነው! አሉ። የኦሮሞ ወጣቶች ተከትለው፤ ጠላታችን አማራ አይደለም ጠላታችን ወያኔ ነው! አሉ። የትግሬዎችን ቡድን አከርካሪ ሰበሩት። ይህ በተግባር መያያዝ አለበት። ጊዜውና ምቾቱ ያለን እኛ በውጭ የምንገኝ ይሄን አንድነትን የመፈለግ ጥረት ማጎልበት እንችላለን። አለዚያ፤ እንደ ግብፁ ሙባረክ ሳይሆን እንደ ሶሪያው አሳድ የተጓተተና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ብዙ ታጋዮች የሚያልቁበት ሀቅ መልበሳችን ነው። ግንቦት ሰባት የራሱን ንጉስ ለማንገስ ሲሯሯጥ፣ ኢሕአፓ የራሱን ለማንገስ ሲጣደፍ፣ ሰላማዊ የራሱን፣ መድረክ የራሱን ሲያዘጋጅ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል፤ አንድነት አጥቶ፤ ይጓተታል። ሶሪያ ውስጥ የየውጪ ሀገሮች፤ ማለትም የቱርክ፣ የሊባነን፣ የኩዌት፣ የአሜሪካ ደጋፊ ታጋዮች ተለያይተው በየበኩላቸው ባንድ በኩል፤ ሶቪየት ኢራንና ቻይና ደግሞ የአሳድን ማዕከላዊ መንግሥት ደግፈው፤ የሶርያ ሕዝብ እያለቀ እንዳለበት ሀቅ፤ ተያይዘን እንዳንሰምጥ እሰጋለሁ።

አንድነት አለመሰለፋችን ትግሉን ጎድቶታል። አንድ ጠላት አለን ብቻ ሳይሆን፤ ሁሉም ድርጅቶች ሕዝቡ የበላይና ወሳኝ ነው ብለዋል። ታዲያ ይሄን ከተቀበሉ፤ ለምን የየራሳቸውን ጥንካሬ አጉነው፤ ሌሎችን እንደሌሉ በመቁጠር ይሯሯጣሉ? ለምን ሀገርን በማስቀደም የትግሉ አካል ለመሆን ፈቃደኛ አይሆኑም? ይህ ተጠያቂነታቸውን ያጎላዋል። ይህ ትግሉን በመጎተት ያስጠይቃቸዋል። የትግሬዎች ቡድን የሚያደገውን ጥፋትና የሚያደርሰውን በደል መዘርዘሩ በቂ አይደለም። ባሁኑ ሰዓት ደግሞ፤ ሕዝቡ ደሙን እያፈሰሰ ባለበት ወቅት፤ ስለ በደሉ መዘርዘር ትርጉም አጥቷል። አሁን ትግሉ ወደፊት መሄዱንና የድል ጎዳና መቀየሱን ነው ማብሰር ያለብን። አሁን፤ የሕዝቡን ድል መዘርዘር ላይ መሆን አለብን። ይህ ግን በምኞት አይመጣም። ተጨባጭ ሥራዎችን መሥራት አለብን። ይህ ደግሞ የሚጀምረው፤ ትግሉን በአንድነት ለማድረግ ወደ አንድ በመሰባሰብ ነው። ምንም እንኳ ይህ የአንድነት ጥሪ ለፍቶ ለፍቶ የሟሸሸ ቢሆንም፤ አሁን ክፍተት ተፈጥሮ ማዕከሉ ባዶ ሲሆን፤ እንደ ትግሬዎች ቡድን ዘሎ ለሚገባ የታጠቀ ቡድን በሩን በርግደን እንዳንተው እፈራለሁ። ሕዝባዊ ድል የሚገኘው፤ ሕዝቡ ሲመራና ሲታገል ብቻ ነው። ድርጅቶች የሚታገሉት ለድርጅታቸው ነው። የሕዝብ ድርጅት ደግሞ የለንም።

ከታላቅ አክብሮታ ጋር

አክባሪያችሁ አንዱዓለም ተፈራ

↧

↧

በባሕርዳሩ ሰላማዊ ሰልፍ በትግሬ-ወያኔ ግፍ የተጨፈጨፉትን እንድናውቃቸውና እንድንዘክራቸው! –ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት       

$
0
0

ሐሙስ ነሐሴ ፲፪ ቀን ፪ሺህ፰  ዓ.ም.              ቅፅ ፬ ፣ ቁጥር ፳፭

Moresh-901.jpg

ዘረኛው የትግሬ ወያኔ የወልቃይት ጠገዴን የማንነት ጥያቄ ደግፈው በወጡ የባሕርዳሩ ሰላማዊ ሰልፍ በግፍ የገደላቸው ወገኖቻችን ዝርዝር በከፊል።

«የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ፣ የእኛም የዐማራነት ጥያቄ ነው፣» ብለው እሑድ ነሐሴ 1 ቀን 2008 ዓም ላይ በባሕርዳር ከተማ፣ በሰላማዊ መንገድ ድምፃቸውን ለማሰማት በወጡ ዐማሮች ላይ፣ የትግሬ ወያኔ ዘረኛ ቡድን በርካታ፣ ሩቅ አሳቢ፣ ለሥራ የጓጉ፣ ላገርና ለወገን ታላቅ ተስፋ ሰንቅው የነበሩ የአያሌ ወጣቶችን ሕይዎት በግፍ ነጥቋል። በባሕርዳሩ ሰላማዊ ሰልፍ ወያኔ ከገደላቸው በርካታ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች መካከል ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት በውስጥ የመረጃ ምንጮቻችን የከፊሎቹን አገኝቷል።

ከሰንጠረዡ ለመረዳት እንደሚቻለው፣ በግፍ ከተገደሉትና ዝርዝራቸውን ማወቅ ከተቻለው አርባ ዘጠኝ(49) ሰዎች ውስጥ፣ ዕድሜአቸው ሰላሳና ከዚያም በላይ የሆኑት ስምንት ( 8) ብቻ ነው። አርባ አንዱ (41) በወያኔ የግፍ አገዛዝ የተወለዱና ወያኔ ሲገባ ከአምስት ዓመት ዕድሜ የማይበልጡ መሆኑ በግልጽ ይታያል።  በመሆኑም  ያለፈውን ሥርዓት የማያውቁ፣ ያልኖሩበት፣ በትህምርትም ያልተማሩት በመሆኑ የሚናፍቁት አንዳች ነገር ይኖራ ተብሎ አይታሰብም።  ወጣቶቹ ሰዎች ናቸው እና እንደማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር መልካም ነገርን፣ እንደሰው ዕኩል መታየትን፣ ጥሩና መልክ ነገሮችን የመመኘት፣ ራሳቸውን ከሌሎች አቻዎቻቸው ጋር አመዛዝኖ ለእኛ ለምን ሰብአዊ መብቶቻችን፣ ተዘዋውሮ የመሥራትና ያመኑበትን በግልጽ የመናገር፣ የመደራጀት፣ ወዘት መብትና ነፃነት እንነጠቃለን፣ ከዚህ ሁሉ በላይ ማንነታቸውን ለምን ይካዳል ብለው መጠየቃቸው ሰው ሆኖ በመፈጠራቸው ብቻ የተሰጣቸው መብት እንጂ፣ ያለፈ ሥርዓት የመናፈቅ ወይም ትምክህተኛ የመሆን ውጤት አይደለም።

በሌላም በኩል እነዚህ በወያኔ ዘመን ተወልደው፣ በርሱ የትምህርት ሥርዓት ያለፉ ወጣቶች ያነሱት የማንነት ጥያቄ ሥርዓቱ ገነባሁት ያለው «የነገዶች ዕኩልነትና ሰላም» አስገኘሁት እያለ የሚለፍፈው «ልማት» ውሸት መሆኑን ገላጭ ነው። የዘረኝነት ሥርዓቱ፣ ዐማራውን በጠላትነት ፈርጆ ያወጀበት የዘር ጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል፣ እየከፋ መምጣቱን፣ የዐማራው ወጣት ትውልድ ማንነታችን እናስከብር ብሎ በቁርጠኝነት መነሳቱን የሚያመለክት ነው። ባጭሩ ወያኔ  የወልቃይት ጠገዴን የማንነት ዕውነተኛ ጥያቄ «ያለፈው ሥርዓት ናፋቂዎች፣ ትምክህተኞች፣ ነፍጠኞች» እያለ ያልሆነ ስም የሚለጥፍባቸው ንፁሐን ዜጎች የራሱ ከፋፋይ፣ አጥፊና ዘረኛ ሥርዓት ውጤቶች፣ የዘረኛና ብልሹ አስተዳደሩ ውጤት መሆኑን፤ ይህንም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ያልተቀበለው እንደሆነ የሚያሳይ አጉሊ መነፀር ነው።

በወያኔ አጋዚ ጦርና ከሕዝቡ መሀል ለዘመናት በኖሩና የባሕርዳር ሕዝብ እንደወገን በሚያያቸው፣ እነርሱ ግን እንደጠላት ቆጥረው  ለገዳዩ ቡድን መረጃ በማቀበል በተሰማሩት የትግሬ ነገድ አባሎች የተጨፈጨፉት ሰላማዊ ዜጎች፣ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ስማቸውን ለማግኘት የቻላቸው የሚከተሉት ናቸው። ለወራት ያህል በዘለቀው ሕዝባዊ እንቢተኝነት ሕይዎታቸውን ያጡ ወገኖቻችን ስምና ማንነት እየተከታተልን የማሳወቅ ተግባራችንን በንቃት ለመወጣት የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን። 

ተራ

ቁጥር

የተገዳይ ሙሉ ስምዕድሜመኖሪያ አድራሻ
1ዕድሜዓለም ዘውዱ27ባሕር ዳር
2ገረመው አበባው25ባሕር ዳር
3ተፈሪ ባዩ16ባሕር ዳር
4ሰሎሞን አስቻለ25ባሕር ዳር
5ሙሉቀን ተፈራ27ባሕር ዳር
6አደራጀው ኃይሉ19ባሕር ዳር
7አስማማው በየነ22ባሕር ዳር
8ታዘበው ጫኔ21ባሕር ዳር
9አሥራት ካሣሁን24ባሕር ዳር
10የሽዋስ ወርቁ20ባሕር ዳር
11ብርሃን አቡሃይ29ባሕር ዳር
12ሽመልስ ታዬ22ባሕር ዳር
13አዛናው ማሙ20ባሕር ዳር
14ሢሣይ አማረ24ባሕር ዳር
15ሞላልኝ አታላይ21ባሕር ዳር
16መሣፍንት አማራ22እስቴ
17እንግዳው ዘሩ20ባሕር ዳር
18ዝናው ተሰማ19ባሕር ዳር
19ዋለልኝ ታደሰ24ባሕር ዳር
20ይታያል ካሤ25ባሕር ዳር
21እሸቴ ብርቁ37ባሕር ዳር
22ሞገስ40ባሕር ዳር
23አደራጀው ደሣለኝ30ባሕር ዳር
24አበበ ገረመው27ጢስ ዐባይ
25ማኅሌት23ባሕር ዳር
26ተስፋዬ ብርሃኑ58ባሕር ዳር
27ፈንታሁን30ባሕር ዳር
28ሰጠኝ ካሤ28ባሕር ዳር
29ባበይ ግርማ26ባሕር ዳር
30አለበል ዓይናለም28ደብረማርቆስ
31አብዮት ዘሪሁን20ባሕር ዳር
32አበጀ ተዘራ28ወረታ
33ደመቀ ዘለቀ22ወረታ
34አለበል ሃይማኖት24ወረታ
35ሰሎሞን ጥበቡ30ቻግኒ
36ፍሥሃ ጥላሁን25አዲስ አበባ

…

↧

የዶ/ር መረራና በዕውቀቱ መንገድ! –በዮሴፍ ሙሉጌታ  ባባ (ዶ/ር)

$
0
0

kankokunmalimaali@gmail.com

ክፍል 13

merera

የሱጌቦ፣ የጫላ፣ የሐጎስ፣ የአበበ፣ የኦባንግ…ወዘተ የማንነት ጥያቄ አንፃራዊ ምላሽ ካገኜ ከ25 ዓመት ቦኃላ፣ ዛሬም የ“አበበ በሶ በላ”ና “ጫላ ጩቤ ጨበጠ” ፖሊማኖታዊ አስተሳሰብ ጨርሶ መርገብ እንዳልቻለ ከዝህ በፊት በግልጽና በድፍረት ሞግቼ ነበር። በአንድነት ኋይሎችና (ultra-right) በብሔርተኞች (ultra-left) መካከል ያለው ይህ ፖሊቲካዊ ጽንፍ፣ ከ1966 ዓ፣ም ጀምሮ ቁም ስቅላችን እያሳየን የሚገኝ ሲሆን፣ በአሁኑ ጊዜ አሳሳብ ደረጃ ላይ ደርሷል። ሁኔታው እንደዝህ የሚቀጥል ከሆኔ፣ በአፊሪካ ቀንድ ማኅበራዊና ሃይማኖታዊ ቀውስ ያስከትላል የሚል ስጋት አለኝ። የምዕራቡን ‹‹ዓለም›› ፖሊቲካዊ ፍልስፍና በሚገባ የተረዳ ሰው፣ ይህ እውኔታ ፈጽሞ ይጠፈዋል የሚል ግምት የለኝም። የሆነ ሆኖ፣ በኢትዮጵያ ፖሊቲካዊ ፍልስፍና ታሪክ ውስጥ፣ እነዝህን ጽንፈኛ አመለካከቶች ለማስታረቅ የደፈሩ ጥቂት ምሁራንና ጸሐፍዎች አልጠፉም።

(ሀ) ‹ያ ትውልድ›:- የሔኖክ የማነ ‹‹የዶ/ር መረራ የገመድ ላይ ጉዞ›› ‹ፖሊቲካዊ ትንተና› እንዳለ ሆኖ፣ በኢትዮጵያ ፖሊቲካዊ ፍልስፍና ታሪክ ውስጥ፣  ሁለት ጽንፈኛ አመለካከቶችን ለ‹‹ማስታረቅ›› ከፊተኛ ጥረት ካደረጉ ጥቅት ምሁራን መካከል፣ ዶ/ር መረራ ጉዲናን ለአብነት መጥቀስ ይቻላል። ከዝህ በፊት ለንባብ የበቁ የምርምር ሥራዎቹ፣ በአንድነት ኋይሎችና በብሔርተኞች መካከል ያለው እልህ አስጨራሽ ፍልሚያ ማብቃት እንዳለበት በግልጽ ያሳያሉ። (Merera Gudina, Ethiopia: Competing Ethnic Nationalisms and the Quest For Democracy, 1960-2000, 2002, Passim; Ethiopia: From Autocracy to Revolutionary Democracy, 1960s-2000, 2011, Passim፣ መረራ ጉዲና፣ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምስቅልቅ ጉዞና የሕይወቴ ትዝታዎች፣ 2006፣ Passim የኢትዮጵያ የታሪክ ፈተናዎች እና የሚጋጩ ሕልሞች፣ 2008፣ Passim) በተለይ፣ የኦሮሞና የአማራ ልሂቃን ፖሊቲካ፣ ብዙም ያለተንቀሳቀሰና ‹‹በዋናነት በሁለት ጫፎች ላይ ቆሞ ገመድ ከመጓተት ወደ መሃል መጥቶ የጋራ ዴሞክራትክ አጀንዳ መቅረጽ›› እንዳላስቻላቸው ዶ/ር መረራ ያሰምርበታል። (መረራ ጉዲና፣ 2008፣ ገጽ 11) የሁለቱን ልሂቃን ፖለቲካዊ ውይይት አንዱ ሌላውን የማይሰማ ‹‹የዶንቆሮዎች ውይይት (dialogue of the deafs)›› ሲል አካሄዳቸውን አጣጥሏል። (ገጽ 11፣12) ለወደፊቱ በአፊሪካ ቀንድ ለሚነሳው‹‹ግጭት/ጦርነት›› ተጠያቅዎቹ የትግራይ፣ የአማራና የኦሮሞ ልሂቃን መሆናቸውን በሚያሳይ መልኩ የሚከተለውን ሐሳብ በድፍረት ሰንዝሯል፡-

‹‹ለታሪክም፣ ለሕዝብም አስረድቼ ማብቃት የሚፈልገው  መሠረታዊ ነጥብ፣ አብዛኛው የትግራይ ልሂቃን ‹ስልጣን ወይም ሞት› ብለው ሥልጣን ላይ የሙጥኝ እስካሉ ድረስ፤ አብዛኛው የአማራ ልሂቃን በአፄዎች ዘመን የነበረውን የበላይነት መልሼ አገኛለሁ ብሎ የሚያስበውን የሕልም ፖሊቲካ እስካልተወ ድረስ፣ ብዙሃኑ  የኦሮሞ ልሂቃን ኦሮሚያን ለብቻ የማውጣቱን ሕልም እስካልተወ ድረስ ሀገራችን ከአደጋ ቀጠናና ቀውስ የምትወጣ አይመስለኝም። በሌላ ቋንቋ ለነዝህ መሠረታዊ በሽታዎቻችን መድኃኒት እስካላገኘን ድረስ ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምም ሆነ ዴሞክራሲያዊ አስተዳደርን ፈጽሞ የምታገኝ አይመስለኝም።›› (ገጽ. 12)

ዶ/ መረራ ታሪክና ሕዝብን ለምስክርነት መጥራቱ፣ በኢትዮጵያ ፖሊቲካ ጉዳይ ተስፋ መቁረጡን ያሳያል። ‹‹ያ ትውልድ›› ካለፈው ጥፋቱ ተምሮ፣ ልዩነቱን አቻችሎና አንድነቱን ጠብቆ ኢትዮጵያን ከመበታተን ይታደጋት ይሆን? ጊዜ የሚነግረን ይሆናል!

(ለ) ‹‹የእኔ ትውልድ››፡- በአሁኑ ጊዜ ‹‹የኢትዮጵያ ታሪክን›› በተመለከተ የጋራ ግንዛቤ ያላቸውን ወጣቶች ፈልጎ ማግኘት ብርቅ እየሆነ መቷል። በተለይ፣ የአንድነት ኋይሎችና ብሔርተኞች ‹‹የሀገራችንን ታሪክ›› የሚረዱበትና የሚተነትኑበት መንገድ፣ ብሔራዊ መግባባት ላይ እንዳንደርስ ትልቅ እንቅፋት ሆኗል። ከዝህ ‹ጽንፋዊ የታሪክ ትንተና› ለመራቅ ብቸኛው መንገድ ደግሞ፣ ‹ሌላው ወገን› የሚለውን ልብ ብሎ ማዳመጥ ነው። የበለጠ ግልጽ ለማድረግ፣ የማንነት ጥያቄን ከጠባብነት፣ የሀገር አንድነት ጉዳይን ከትምክህተኝነት ጋር ብቻ አቆራኝቶ ‹መገንዘብ›፣ ወደ ፖሊቲካዊ ጽንፍ ሊያመራ ይችላል። ስለዝህ፣ በሁለቱ ጽንፈኛ አስተሳሰቦች ውስጥ ያለውን እውኔታ በትክክል ለመረዳት፣ ከዝህ ቀደም በሁለቱ ወገኖች በኩል የተደረሱትን ጥልቅ የምርምር ሥራዎች በሰከነ መንፈስ መመርመር ያስፈልጋል።

የዘመኑ (contemporary) ወጣት ጸሐፍ በእውቀቱ ሥዩም የጽፈኝነት ፈተናን ማለፍ የቻለው ይህንን በማድረጉ ይመስለኛል። በቅርቡ ለንባብ የበቃ ‹‹ከአሜን ባሻገር›› የተሰኘ ሥራው፣ ጸሐፍው ስበዛ የመጽሐፍ ትል መሆኑን ይመሰክራል። ይህ ማለት ግን ጸሐፍው የሰነዘራቸው ሐሳቦች ሁሉ ተቀባይነት አላቸው ለማለት ፈልጌ አይደለም። (እኔ ራሴ በሁለት ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ ‹ጥንቃቄ› እንድያደርግ አጭር-መልዕክት (e-mail) ሰድጄለት ነበር—‹ጆሮ› ካለው ይስማ!) ይልቅ፣ እዝ ላይ ለማለት የተፈለገው የኢትዮጵያ ሕዝቦች ታሪክ በጥልቀትና በ‹ትክክል› መረዳት የሚንችለው በአንድ ወገን ብቻ የሚደረሰውን የምርምር ሥራዎች ዋብ በማድረግ ሳይሆን፣ በሌላ ወገን በኩል ያለውን ታሪካዊ-ጥያቄ በሚገባ መገንዘብ ስንችል ብቻ ነው። ሰውሻውያን እንደሚዘባርቁ ሳይሆን፣ በእውቀቱ ከ‹ቀበሌ አስተሳሰብ› ተላቆ ያንን ማድረግ የቻለ ‹ደፋር› ወጣት ነው!

ከ ‹‹ያ ትውልድ›› ዶ/ር መረራን፣ ከ ‹‹እኔ ትውልድ›› በዕውቀቱን ማንሳቴ ያለ ምክንያት አይደለም። የኢትዮጵያ ፖሊቲካዊ ፍልስፍና ታሪክን በሚገባ ለመረዳት፣ ከምርምር ዓለምም ሆነ ከሥነ-ጹሑፍ ዓለም ለብዝኃ-ዕይታ (multi-perspective) ዝንባሌ ያላቸው ብዙ መረራዎችና በእውቀቱዎች በጣም እንደሚያስፈልጉን ለማሳየት ብቻ ነው። እርግጥ ነው ለብዝኃ-ዕይታ ትኩረት የሚሰጡ ብዙ ተመራማርዎችና ጸሐፍዎች ዛሬም አሉን። ለእነኝህ ግለሰቦች ትልቅ ክብር አለኝ። ይሁን እንጅ፣ የፖሊቲካና የሃይማኖት ጽንፈኝነት ጡዘት ላይ በደረሰበት በአሁኑ ጊዜ፣ እንደዝህ ዓይነት አስተሳሰብ ያላቸው ምሁራንና ወጣቶች በብዛት ያስፈልጉናል።

በመጨረሻ፣ ለ ‹‹ያ እና አሁኑ ትውልድ›› ማስተላለፍ የሚፈልገው አንድ ‹‹መልዕክት›› አለኝ፡-

የኢትዮጵያ ፖሊቲካዊ ፍልስፍና ታሪክ በጣም ውስብስብ ነው። አንድ ወጥ አመለካከትን ሳይሆን ብዝኃ-ዕይታን (multi-perspective) ይፈልጋል። በግልብ አስተሳሰብ የችግሩ መንሥኤ ላይ መድረስ አይቻልም። የችግሩ ምንጭ በሚገባ አውቆ፣ ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት፣ አንዱ ሌላውን ማዳመጥ ያስፈልጋል። መከባበር፣ መደማመጥና መነጋገር የ‹‹ስልጣኔ›› ምልክት ይመስለኛል። ከዕድሜ ልክ እንቅልፋችን ነቅተን፣ የኢትዮጵያ ፖሊቲካዊና ማኅበራዊ ችግሮችን በራሳችን እንፍታው። የሦስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት አያስፈልገንም። የምዕራቡን ‹‹ዓለም›› የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት በጣጥሰን፣ ብሔራዊ እርቅ አንፍጠር። ዳግም የቆንጨራ ‹ጨወታ› ወስጥ መግባት ትልቅ ዋጋ ያስከፍለናል። ‹የታሪክ ሒሳብ ማወራረድ› የሚለው ፈልስፍና የትም አያደረሰንም። እንደ አውሬ መበላላቱን ትተን፣ ፍቅርና መቻቻልን እንላበስ። የአስተሳሰብ ሽርሙጥናን አጥብቀን እንታገል!  የአስተሳሰብ ለውጥ ከተግባር እንደምቀድም ለማወቅ ደግሞ፣ የሚከተለውን  ግጥም ልብ ማለት በቂ ነው፡-

ማጭድ ይሆነን ዘንድ―ምኒሽር ቀለጠ

ዳሩ ብረት እንጂ―ልብ አልተለወጠ

ለሳር ያልነዉ ስለት―እልፍ አንገት ቆረጠ

(ግጥም፡ በዕውቀቱ ሥዩም)

የመንግስት ባለሥልጣናትና የሃይማኖት መሪዎች ሆይ! ዝለዝህ ጉዳይ በደንብ አስቡበት! ስለ ‹ዶላርዝም›ና ስልጣን ብቻ ሳይሆን፣ ስለብሔራዊ እርቅም አስቡ! በሕዝቦች መካከል ጥላቻና ዘረኝነት እየዘራችሁ፣ ሰዎች ስለ ቆንጨራና ማጭድ አብዝቶ እንድያስቡ አታድርጉ። ሰውን እንኳ ባትፈሩ ለፈጣሪ ስትሉ የድሆችን አሰቃቅ ሁኔታ ተመልከቱ! ለህሊናችው ሲትሉ እውነትን ውደዱ፤ ‹‹ከባላጌ ክቡር የድሃ ስልጡን ይሻላልና›› ለመልካም ስማችው ተጠንቀቁ። ስለ ልጆቻቹ አስቡ። ለምሳሌ፤- ልጆቻቹ ‹‹የሌባ ልጅ›› ተብለው እንዳይጠሩ ከፈለጋችው ፣ ከድሆች ኪስ በወጣ ገንዘብ መኪናና ቤት አትግዙ። ወይም ‹‹የሰሙኒ-ልጅ›› ተብለው እንዳይጠሩ ከፈለጋችው፣ ለትዳራችው ታማኝ ሁኑ! ‹‹ከመጠምጠም መማር ይቅደም›› እንደሚባለው፣ ዕድሜ ልካችውን ገንዘብና ሴቶችን ከሚታሳድዱ፣ ጥበብን አብዝታችው ውደዱ። ብሔርን ወይም ኅይሞኖት እየለያችው ሰውን አትበድሉ፤ ድሆችን አትበዝብዙ፤ እንባቸው እንደ ጎርፍ ጠራርጎ እንዳይወስዳችውም ተጠንቀቁ!

   ነገር ግን፣ ሕዝባቸውን በቅንነት እያገለገሉ ያሉ ጥቂት የመንግስት ባለሥልጣናትንና የሃይማኖት መሪዎችን እንወዳቹዋለን፤ እናከብራቹዋለን፤ ዋቃዮ/እግዝአብሔር/አላህ ረዥም ዕድሜና ጤና ይስጣቸው!

በክፍል 14 ‹‹ዴሞክራሲ ‹ማሽላ› ይሁን ‹ገብስ› ገና አልታወቀም›› የሚለውን እንመለከታለን!

ቸር እንሰንብት!!          

↧

እንዲህ ተፅፎ ነበር !! –መስፍን ማሞ ተሰማ

$
0
0

መንደርደሪያ፤

Gonder6ኢትዮጵያዊው የሥነፅሁፍና የምርምር ሊቅ፤ ዲፕሎማትና መምህር፤ እንዲሁም በቀዳማዊ ሃይለ ሥላሴ መንግሥት የልዩ ልዩ መሥሪያ ቤቶች ከፍተኛ ሃላፊ፤ ጋዜጠኛ፤ ደራሲ ገጣሚና ተርጓሚ ክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤል በ1930ዎቹ ዓ/ም በፃፉት “ታሪክና ምሳሌ” 1ኛ መፅሐፍ ላይ (እሳቸው በ30 ዓመት የሥነ ፅሁፍ ዘመናቸው 26 መፃህፍትን አቅርበዋል) ከሚገኙት የተለያዩ ትውልድን ቀራጭና ታሪክን አስራጭ ሥራዎች ውስጥ በመንቀስ ሀገራችን አትዮጵያና እኛም ዜጎቿ ዛሬ በምንገኝበት የሕወሃት/ኢህአዴግ አፓርታይዳዊ አገዛዝ፤ ወደር አልባ ሰቆቃ፤ ግፍና ምዝበራ . . . አንፃር በእኛ በኩል (ከህወሃት/ኢህአዴግ ያልተዋለድነው) ለዜግነት/ኢትዮጵያዊነት ካለን ቁርኝትና ሃላፊነት፤ ለሀገር ነፃነትና ክብር ካለን መስዋዕትነት፤ ለባንዲራ ማተብ ካለን ፍቀርና ቀናዒነት አንፃር በዘመን ሂደት የደረስንበትን ለመመርመርና ከተቻለም ተማምሮ የጎበጠውን ለማቃናት ማስታወሻ አልያም የቀደመው ትውልድ መሥዋዕትነት መማፀኛ/ወይም መዘከሪያ ይሆን ዘንድ ታስቦ የቀረበ መሆኑ ይታወቅ ዘንዳ እንወዳለን። ይህ አቅርቦት በ’ታሪክና ምሳሌ’ 1ኛ መፅሐፍ ሙሉ ይዘት ላይ የቀረበ ቅኝት ወይም ዳሰሳም አይደለም፤ ይልቁንም በግፈኞች እየተገፋ እየተጋዘና እየተገደለም ለሚታገለው ይህ ትንታግ ኢትዮጵያዊ ወጣት ትውልድ ለሚገኝበት ዘመንና ወቅት ለትግሉ ፅናትና ለድሉ ብቃት በማስተማሪያነት ወይም በአስታዋሽነት በቀጥታ የተፃፉ የሚመስሉትን ጥቂት የመፅሐፉን ገፆች በንዑስ ማብራሪያ አጅቦ ያወረደ እንጂ። እነሆ ከበደ ሚካኤል እንዲህ ፅፈዋል፤ =የሚቀጥለውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ====

↧

ጀግናው የጎንደር፤ የጎጃም፤ የሸዋና የወሎ አማራ ህዝብ ሆይ

$
0
0

ዶ/ር ደጀኔ አለማየሁ ላቀው

ዘርህን፤ ሃገርህንና ማንነትህን ከጥፋት ለመጠበቅ ላለፉት ሳምንታት ያሳየሃቸዉን የጀግንነት የብልህነትና የሃገር ወዳድነት እርምጃ በጽሞና መላው አለም አይቷል። ኢትዮጵያም የተደፋ አንገቷን ቀና አድርጋ አይታለች፤ ተደስታለች፤ በርግጥም ልጆቸ አሉ ብላለች። በቅርቡም እነሳለሁ፤ እንደገናም አብባለሁ ብላለች።

Al 898

እርምጃህም የትግራይ ወያኔ የአማራዉን ህዝብ፤ ታሪክ፤ ባህልና ያስተሳሰብ ሃያልነት እንደማያዉቀውና አማራው ታጋሽ ህዝብ እንደሆነ፤ ግን ምንጊዜም የኢትዮጵያ መካች፣ ደጀንና አለኝታ ህዝብ መሆኑን ነው ። ትግስት ፍርሃት ሳይሆን ብልህነት፤አስተዋይነት ነው፤ የበሰለ የባህል ነጸብራቅ ዉጤት ነው ። የአማራዉ ህዝብ ላለፉት 25 አመታት የትግራይ ወያኔ የወሰነበትን የጥፋት አዋጅና ተግባር ለመቋቋም ያሳየዉም ይህንን ታልቅ ባህሉን ነው ። ይህ እርምጃችሁ የምእራባዉያን ሃገሮች የኢትዮጵያን ህዝብ ከራሱ ዉስጥ በበቀሉ ግን እነሱን በማገልገል፤ የኢትዮጵያን ህዝብ በመበቀልና በባንዳነት ባህላቸው የዉጭ ሃይሎችን ለማስደስትና ፈጥኖ ደራሽ ከምንም የማይቆጠር ሰራዊት ከድሃው ኢትዮጵያ ህዝብ በማቅረብ በተለያዩ የአፍሪካ በረሃወች እንዲሞቱና አሞራ እንዲበላቸው በማድረግ፤ በምትኩ በብዙ ሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር ሃብት በማግኘት የራሳቸዉን የተንደላቀቀ ህይዎት ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚኖረው የትግራይ ወያኔ እስትንፋሱ የሚዘጋበት ና ከተቀደሰችና በታሪኳ ኩርህ የሆነች ሃገር ይህ እርኩስ ቡድን የሚጠፋበት ፈር ቀዳጅ እርምጃ ነው ።

የኢትዮጵያን ባንዲራ በመያዝ የትግራይ ወያኔ በየበረንዳው ያንጠለጠለዉን የለማኝ ድሪቶ ጨርቅ በመጣል ፤ ኢትዮጵዉያንን ሁሉ አንድ ነን ፤ ባንዴራችንም ይችዉ የጥንቷ፤ ወራሪወችን የምታንቀጠቀጠው፤ ተፈጥሮ እንኳን የሚያዉቃት በሰማይ ላይ የምትታየው አረንጓዴ፤ ቢጫና ቀይ አርማችን፤ ሃይላችን ነች፤ እኛ የኢትዮጵያ ልጆች ነን፤ ወልቃይት ጠገዴ የአማራው ታሪካዊ ቦታው ነው፤ ተከዜ ወንዝ፤ የጎንደርና የትግራይ መካለያ ተፈጥሮአዊ ደንበር ነው፤ ኦሮሞ ወንድማችን ነው፤ የትግራይ ወያኔ ኦሮሞዉን መግደል ያቁም፤ ጋምቤላዉ ወንድማችን ነው፤ ጋምበላዉን መግደል ያቁም ብላችሁ:ጀግናው አጼ ተዎድሮስ በትግራዩ ወሮ በላ ስሁል የሚባል አወናባጅ ምክንያት የፈረሰችዉን ኢትዮፕያን እንደገና እንደገነባት ሁሉ እናንተም በሌባው የትግራይ ወያኔ የፈራረሰችዉን ውድ ሃገራችን ኢትዮጵያ ከሞት አደጋ የሚያድናትን የጀግነት ጥሪና ተጋድሎ ፈጸማችሁ። ይህ ጀግነታችሁ እነሆ ወደተለያዩ የኦሮሞ ክልሎች፤ ባጠቃላይ በመላዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ በመባዛት ጀግናዉን የአማራ፤ የኦሮሞ እና የደቡብ እትዮጵያን ህዝብ አነሳስቷል። የትግራይ ወያኔ ያጭበራባሪ ቡድን የዘራጋዉን የዝርፊያ መዋቅር በጣጥሳችኋል፤ ለኢትዮጵያና ለአለም ህዝብ አሳይታችኋል።

ከዚህ በኋል የትግራይ ወያኔ ማድረግ ያለበት የሚከተሉት ብቻ ናቸው

(1) ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ወልቃይት ጠገዴ ጠለምትን ወደጎንደር የወሎንም መሬት ወደወሎ የጎጃም መሬቶችን ወደጎጃም መመለስ ያንንም ዉሳኔ ለኢትዮጵያ ህዝብ ማሳወቅ፤ የአማራዉን ህዝብ ይቅርታ መጠየቅ፤ ወንጀላቸዉንም አምነው፤ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚሰጠዉን ፍትሃዊ እርምጃ ለመቀበል መዘጋጀት

(2) ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ስልጣን መልቀቅና አስቸካይ የሆነ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም ሁኔታወችን ማመቻቸት፡ በዚህም ተግባር ዉስጥ የትግራይ ወያኔ ምንም አይነት አስተዋጾ እንዳያደርግ ማድረግ

(3) የኢትዮጵያ ሰራዊት ሃገሪቱን ከዉጭ አጥቂ ሃይል ለመከላከልና የኢትዮጵያን ህዝብ ለመጠበቅ እንጂ ድሃ ልጆቿን ለማፈን፤ ለመረሸን፤ ለመግደል አይደለም። ይህንንም በማወቅ መላው የኢትዮጵያ ሰራዊት አባል የሆነ ሁሉ፡ የጠበንጃዉ አፈሙዝ ወደ ወገኑ ድሃ ህዝብ ሳይሆን ሃገርን ወደሸጠዉና የንግድ ስራ በተሰማራው የትግራይ ወያኔ አባል፤ አመራርና የጦር ክፍል ሃላፊ ወደሆነው ነው። ይህ እርምጃችሁ የኢትዮጵያን ህዝብ የነጻነት ትግል ያፋጥነዋል፤ የህዝብ አጋርነታችሁንና ከታሪክ ተጠያቂነት ያድናችኋል። የሙሶሎኒ ተወካዮችን ካገለገሉት ባንዳ ባለስልጣኖች ይልቅ እነሱን ለመግደል የሞከሩት ቆራጥ የኢትዮጵያ ልጆች በኢትዮጵያ ታሪክ ዉስጥ ትልቅ ስፍራ ይዘው ይገኛሉ፤ እናተም ከነዚያ ጀግኖች አንዶቹ ለመሆንና በኢትዮጵያ ዘላለማዊ አንጸባራቂ ታሪክ መዝገብ ዉስጥ እንድትሆኑ የሚያስችህላችሁን ተግባር ፈጽሙ።

የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ከዉስጡ እንደመዥገር በቅለው ሃገርን ለማጥፋትና ህዝቧን በዉስጥ ባርነት በማፈን እጅግ ከፍተኛ በደልና የግፍ ወንጀል የሚፈጽሙትን የትግራይ ወሮበላ ቡድን ቀርቶ ዘመናዊ የሆነ የጦር መሳሪያ ዪዞ ፤ መርዝና ጋስ የተጠቀመን የዉጭ ወራሪን አንበርክኳል፤ ለዚያም ነው የኢትዮጵያ ህዝብ ነጻና ኩሮ ህዝብ ሆነ የሚኖረው፡ ባርነት፤ ባንዳነት፤ ሃገርን ማፍረስ ሁልጊዜም የትግራይ ወያኔና መሰሎቹ ስራ ብቻ ነው፤ በዚህም ምክንያት ከኢትዮጵያ መሬት ላንዴና ለሁሌም ዪወገዳሉ። የዘረጉት የስርቆት ስርአትም ይበጣጠሳል፤ እንደ ጤዛም ዪጠፋሉ። ስልታችሁን ጥበባዊ በሆነ መንገድ በመቀያየር ትግላችሁን ማጠናከር፤ ወያኔን በያለበት መምታት፤ እንቅስቃሴውን መግታትና፤ አንድም ነገር እንዳያደርግ ማድረግ፤ ኑሮን ዱርቤቴ ብሎ የወጣን ህዝብ ማንም ሃይል ሊያስቆመው አይችልምና ። ነጸነት በነጻ የሚገኝ አለመሆኑን ከሁሉም በላይ የኢትዮጵያ ህዛብ ያወቀዋል፡ ያንን ነው ሁልጊዜ ማሰብና በተግባርም መፈጸም ።ይህ ሃገር በቀል የመሬት አረም ፤ የእንስሣ መዥገር፤ የሰው ትኋን ባጭር ጊዜ ዉስጥ ከኢትዮጵያ ተነቅሎ እንደሚጠፋ እርግጠኛ ነኝ።

ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ህዝብ ለዘላለም ይኑር!!

↧
↧

በባህርዳር በኮሌራ ሴንተር ያሉና የሕወሓት መንግስት መድሃኒት በአግባቡ እንዳያገኙ እየተበቀላቸው የሚገኙ ዜጎች ፎቶዎች እጃችን ደርሰዋል

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በባህርዳር ሕዝባዊው ተቃውሞ ከበረታ በኋላ መንግስት ይህን ሕዝባዊ ቁጣ ለማብረድና አቅጣጫም ለማስቀየር ባዮሎጂካል ጦርነት ጀምሯል; ህዝቡንም በኮሌራ እንዲጠቃ አልያም መድሃኒት ሳያገኝ እንዲያልቅ እያደረገ ነው የሚል ክስ በአማራ አክትቭስቶች ዘንድ ሲቀርብበት ሰንብቷል::

በባህርዳር በተለይ አንድ ሰፈር ብቻ ላይ በተፈጠረ ኮሌራ በርካታ ሰዎች ዓዲስ ዓለም ሆስፒታል መግባታቸውን ያጋለጠችው በቅድሚያ ዘ-ሐበሻ ነበረች:: ዛሬ ባህርዳር ያሉ የዜና ምንጮቻችን እንዳደረሱን መረጃ ከ500 በላይ ሰዎች በአዲስ ዓለም ሆስፒታል እና በጊዜያዊነት የተለሉበትና በድንኳን ብቻ በተሰራ የኮሌራ ሴንተር ሰፍረዋል: እነዚህ ህሙማንን በኮሌራ ሴንተር ያሉበትን ሁኔታ የሚያሳዩ ፎቶዎች ደርሰውናል:: የአማራ አክቲቭስቶች እንደሚከሱት “ላለፉት 25 ዓመታት አማራውን ለማጥፋት ብዙ የሰራው የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ሆን ብሎ አማራውን ለማጥፋት መድሃኒት እንዳያገኙ በማስተጓጎልና ሆን ብሎ ውሃም እንዲበከል በማድረግ እየተበቀለው” ነው::

በሌላ በኩል “የባህርዳር በተለይም የአዲስ ዓለም ሆስፒታል ሰራተኞችን እነዚህን የባህርዳር ነዋሪዎችን ለመታደግ እየጣሩ ቢሆንም ከፌደራል መንግስቱ እጅ ያለው ለኮሌራ የሚሆነው መድሃኒት ሆን ተብሎ ሕዝብ ጋር እንዳይደርስ እንዲስተጓጎል እየተደረገ ነው” የሚሉት የዜና ምንጫችን ሕዝብ ይህን ሴራ ይወቀው ብለውናል::

bahardar 4 bahardar bahdar 3 bahrdar 2

↧

የአሜሪካ መንግስት በአዲስ አበባና በሌሎች ክልሎች ይደረጋል በተባሉት ሰልፎች ዙሪያ ለዜጎቹ የጉዞ ማስጠንቀቂያ ሰጠ

$
0
0
file photo

file photo

(ዘ-ሐበሻ) በአዲስ አበባ የፊታችን እሁድ ይደረጋል በተባለው ሰላማዊ ሰልፍ እንዲሁም በሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎች በዚህ ሳምንት መጨረሻ ላይ በሚኖሩ ሰላማዊ ሰልፎች ዙሪያ የዜጎቹ ደህነት ያሳሰበው የአሜሪካ መንግስት የጉዞ ማስጠንቀቂያ አወጣ::

“ተቃውሞዎች ሊቀጥሉ ይችላሉ:: አዲስ አበባን ጨምሮ በተለየያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ይህ ሰላማዊ ሰልፍ ሊሰራጭ ይችላል::” ያለው የስቴት ዲፓርትመንቱ መግለጫ በሃገሪቱ የኢንተርኔት መቋረጥ ሊከሰትም ስለሚችሉ ይህም ዜጎቻችን ከኢምባሲው ጋር ለመገናኘት ችግር ሊፈጥርባቸው ስለሚችል ካሁኑ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ሲል መግለጫው ያስጠነቅቃል::

በአዲስ አበባ የፊታችን እሁድ ይደረጋል ለተባለው ሰላማዊ ሰልፍ ሕዝብ ከየቦታው እየተነጋገረበት ሲሆን ከተማዋም በክፍተኛ ወታደራዊ ጥበቃ ላይ ናት:: በወልቂጤና ቡታጅራም እንዲሁ ከፍተኛ የሆነ ጥበቃ አለ::

↧

“አዋጅ ተነገረ! ዉሻና ዝንጀሮ ተባበረ!” (ዉሻና ዝንጀሮ ያደረጉት ክርክርና በመጨረሻ ያደረጉ ቃልኪዳን) [ከተፈራ ድንበሩ]

$
0
0

unity-300x2191.jpg

ከተፈራ ድንበሩ

ውሻ፡  አንተ ዝንጀሮ ከዚህ አካባቢ ብትሔድ ይሻልሃል፤ ሂድ! ሂድ! ሂድ! ነው የምልህ! ቶሎ ከዚህ አካባቢ ባትጠፋ ቦጫጭቄ ቦጫጭቄ ነው አፈር የማደርግህ!

ዝንጀሮ፡ እስቲ ሞክር! ዋጋህን ታገኛለህ! እኔ ብቻዬን ያለሁ መሰለህ? የኔ ሠራዊት አንድ ጊዜ ቢዘምትብህ አንተን ብቻ ሳይሆን ዘመድ አዝማድህን ሁሉ ፈጅተን ነው ለአውሬ እራት የምናደርገው!

ዉሻ፡ ይኸውልሃ! ፉከራህ ሁሉ ወደፍርሃት ተለውጦ ሠራዊት ከምትላቸው ጀሌዎችህ ጋር ዛፍና ገዳላገደልን የሙጥኝ ያልከው ታዲያ ለምንድነው? እስኪ ውጡ እና ኑ! እኛና እናንተ ይለይልናል! እኛ ሁለት ሆነን እናንተ ሃያ ሆናችሁ አገር እስኪሸበር በሲቃ እያስጮህናችሁ እያሳደድን እስከገደል አፋፍ ድረስ  አደረስናችሁ፤ በራሳችሁ የምትተማመኑ ከሆነ ውጡ እስኪ! ቦቅቧቆች! ቅዘናሞች! ቂጣችሁ እስኪላጥ በየገደሉ ያንፏቀቅናችሁ እኛ ጌቶቻችሁ ነን፤ እመኑ።

ዝንጀሮ፤ አዎን የፈራነው እኮ እናንተ ውሾች እያነፈነፋችሁ ሰዎችን በኛ ላይ ስለምትጠሩብን ነው፤ እንዲህ እንድትጮኹብን ያደረጉትና እናንተን ለዚህ ዕድል ያበቋችሁ ሰዎች ናቸው እንዲህ እንድትፎክሩብን ያደረጓችሁ፤ እናንተ የምትቦርቁበት ሜዳ፤ ውሀ እየተንጣለለበት የተለያዩ እህሎች፣ አታክልቶች፣ ፍራፍሬዎች የሚመረትባቸውና ስፍር ቁጥር የሌለው የቀንድ ከብት እና ሌሎች እንሰሳት የሚረቡበትን ሜዳ ትተን በተራራማና ገደላገደል ላይ የምንኖረው ቀደም ሲል ሰዎች አሳደውን እና መድረሻ አሳጥተውን ነው እናንተን ለዚህ ያበቋችሁ። ያን ሁሉ አገር ምድር ትተንላችሁ በየቋጥኞችና ገደላገደል አፋፍ ላይ መኖራችን አንሶባችሁ ለምን አሁንም ደግሞ ታሳድዱናላችሁ?

ዉሻ ፤ የሌባ አይነደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ ይላል ሰው! ደግሞ ለምን ታሳድዱናላችሁ ትላለህ እንዴ? በየማሳው ላይ የምትሸመጥጡትን ሰብል ዘርታችሁታል? ከናንተ ተርፎና ታጭዶ የተከመረን ክምር በየአውድማው እየዘረጠጣችሁ  የምትበሉት ባለርስት ሆናችሁ ነው ወይንስ የሌብነት ሙያችሁን ለመሸፋፈን ነው?

ዝንጀሮ፡ ዘረፋ የምንገባው ቢቸግረን ነው፤ ያን ሁሉ ሜዳ እና ለም አገር ሁሉ ትተንላችሁ በየጫካው ስንኖር ፍራፍሬ እንኳ እየለቀምን እንዳንኖር ጌቶቻችሁ እንደዋርካ፣ ዝግባ፣ እንኮይ ዶቅማ፣ ያሉትን ዛፎች ሁሉ እየቆረጡ ቀጋ፣ እንጆሪ፣ አጋምና ኮሽም ሳይቀር ቁጥቋጦውን ሁሉ እየመነጠሩ ደኑን ስላጠፉት የምንበላው የምንቀምሰው አጥተን በችጋር ስናልቅ ታዲያ  ዝም ብለን ነው የምንሞተው?

ውሻ፡ እናንተ እርስበርሳችሁ እንኳ የማትስማሙ ጠባይም የሌላችሁ አስቀያሚዎች፤ እንደኛ ጠባይ ቢኖራችህ ኖሮ በየገዳላገደሉ እየተንፉዋቀቃችሁ አትኖሩም ነበር፤ እኛ ግን ታማኞች ስለሆን ኮርተን ተንቀባረን እንኖራለን።

ዝንጀሮ፡ አዎን አስቀያሚዎች ነን፤ በአስቀያሚነታችን አናፍርበትም፤ እናንተ ለጌቶቻችሁ ባሪያ በመሆን ከነሱ የተራረፈውን ፍርፋሪ እና ልፋጭ ሥጋ ተኝታችሁ እየዋጣችሁ፤ ሰው የቀዳውን ውሀ እንዲሁም የወተት ጭላጭ እና አሬራ እየጠጣችሁ ወዛሞች ትሆናላችሁ እንጂ እንዴት እንደኛ አስቀያሚ መሆን ትችላላችሁ? ያውም ቢሆን አንድ ቀን የማታስፈልጉ መሆናችሁን ሲረዳ ጌታችሁ የት እንድሚጥላችሁ እንኳ አታውቁትም። እስከዚያው ይህን የምትጨፍሩበትን የተለያዩ ሰብሎችና የሚመረትባቸውን፣ የተለያዩ እንስሳት የሚረቡበትን አገር ሁሉ ከሌሎች ጠላቶቻችን ጠብቀን ስናቆይ ዱር እየዋልን ዱር እያደርን ሐሩሩ፣ ውርጩ፣ ረሀብ፣ ጥሙ ተፈራርቆብን ነው መልካችን አስቀያሚ መሆን የቻለው፣ ቆዳችንም የገረጣው፤  በዚህ ደግሞ እንኮራለን እንጂ አናፍርበትም። መልካችን ኑሮአችንን ይመስላል፤ የድካማችንን ውጤት ባንጠቀምበትም እንደናንተ ያሉ ውሾች እና ጌቶቻችሁ እየተጠቀማችሁበት ትገኛላችሁ፤ ታዲያ ባለውለታዎች በመሆናችን መጥፎ ስምና ስድብ ይገባናል?

ዉሻ፤ አገሩን ሁሉ የጠበቁት ሰዎች ናቸው እንጂ እኛ ነን ትላላህ እንዴ? በሌላ በኩል ደግሞ ተሰደን ኖርን ትላለህ፤ አታፍርም ስትዋሽ?  ደግሞ የኛም አገር ባለቤት መሆን ያምራችኋል እንዴ? ጌቶቻችን አደላድለው ማድሪያችንን ስለሰጡን ከነሱ ጋር ሆነን  ያላችሁበትንም አስለቅቀናችሁ መድረሻ ልናሳጣችሁ እንችላለን፡፡ ደግሞ ከፍተኛ የማሽተት ችሎታ ስላለን መረጃ በወቅቱ በማቀበልና የስዎችን ደህንነት በመጠበቅ በታማኝነት ስለምናገለግል ሰው ላደረገው የአገር ጥበቃ ሁሉ የኛም ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለበት።

ዝንጀሮ፡ ይህን እንድትናገር የሚያደርግህ ሆዳችሁን እየሞላችሁ ለሰው ታማኝ ሆናችሁ መኖራችሁ አርቃችሁ እንዳታስቡ ስላደረጋችሁ ነው፤ ብታስትውሉ ኖሮ በየጊዜው አገር ምድሩን በሙሉ ሊወስዱት ከመጡ ወራሪዎች ተከላክለንና ተቆጣጠረን ባናቆየው ኖሮ አሁን ሰዎችና እናንተ የምትፈነጩበት ባላገር ሁሉ የሌሎች ፍጥረታት ግዛት ሆኖ ይቀር ነበር። እናንተም የቀብሮንና የተኩላን ያህል እንኳ ችሎታ ስለሌላችሁ ተበታትናችሁ ዘራችሁ ሁሉ ይጠፋ ነበር፤ ዉሾች የተባላችሁ ፍጡራን የምታደርጉትን አታውቁትም፤ የጌቶቻችሁን ጥፋቶች ማስፈጸም ሥራ ነው ትላለህ እንዴ? ማስተዋል ቢኖራችሁ ኖሮ ውለታችንን ታደንቁት ነበር። ስውም ለራሱ ጥቅም ሲል እየተጠቀመባችሁ ስለሆነ ያላችሁበት ሕይወት ጊዜያዊና አስተማማኝ አለመሆኑን መረዳት አልቻላችሁም፤ ብታስተውል ኖሮ ለታሠሩት ዉሾች ወገኖችህ ሁሉ ትቆረቆር ነበር፣ የልጆችህና ቤተስብህም እጣፋንታ ይኸው ስለሆነ አርቀህ ብታስብ ጥሩ ነው።

ውሻ፡- የምናደርገውንማ እናውቃለን፤ ይኸው ከናንተ በተሻለ ተንቀባረን መኖራችን አይታይህም እንዴ? ይልቅ ማንነትህን አውቀህ ወደጎሬህ ብትሄድ  ይሻልሃል፡፡

ዝንጀሮ፡ አንተ ችሎ፣ ዘወትር እያሳደድከኝ መኖርህ ምን ያስደስትሃል? የምትጠብቀውን ይህን ሀብት ሁሉ ታየዋለህ እንጂ አታዝበትም፤ አትጠቀምበትም፤ ሰብሉንም እንደሆነ በፈቃድህ አትበላውም፤ ጌታሀ አንተን በየዱሩ ሲያንገላታህና ከኛ ጋር ሲያጣላህ ኖሮ በመጨረሻ ሁሉንም ምርት ከጎተራው አከማችቶ ሲሻው ይበላዋል፤ ሲሻው ሸጦና ለውጦ ይንደላቀቅበታል፤ ላንተ እንደሆነ ከፍርፋሪ በስተቀር የሚደርስህ ምንም ነገር የለም፤ ያችም ብትሆን ነፍስህን ለማቆየትና በቀጣዩ ደግሞ የጌታህን ከብቶችም ሆነ ሌሎች ፍጥረቶችን በንብረትነት ለመጠበቅ እንድትችል ወስፋትህን ለመሙላት ብቻ እንደሆነ አይታወቅህም?

ውሻ፡ እናንተ ዝንጀሮዎች ወይ አትቆፍሩ፣ ወይ አትዘሩ ወይ አታርሙ፣ ሰው ያበቀለውን እና ያመረተውን በአሳቻ ሰዓት እየሸመጠጣችሁ ከመብላት በስተቀር ምን ደግ ነገር ትሠራላችሁ? እያጠፋችሁ ከመኖር በስተቀር ምን ሥራ አላችሁ? እኛስ ጌቶቻችንን እያገለገልን እንኖራለን።

ዝንጀሮ፡ ተሳሳትክ፤ እኛኮ በአንድ በኩል ከእናንትና ከስዎች ጋር፣ በሌላ በኩል ከተፈጥሮ ጋር እየታገልን እራሳችንን ችለን ነው የምንኖረው፤ በጥርሳችሁና በአፋችሁ ጩኸት የምትኖሩ ስለሆነ የራሳችሁን ዕድል እንኳ የማታውቁ የስዎች ተቀጥላዎች ናችሁ፡፡ ጌቶቻችሁ ሲፈልጉ በሰንሰለት እያሠሯችሁ ወይም ኅሊናችሁ ተገድቦና ድምጻችሁ እንኳ እንዳይሰማ በሕይወት እያላችሁ በሳጥን ውስጥ ተቆልፎባችሁ ያለነፃነት ትኖራላችሁ፤ እኛ ዝንጀሮ የተባልነው ፍጡራን ግን ከአንድ ጫካ ወደሌላ ጫካ እየዞርን ተፈጥሮ የሰጠንን ፍራፍሪዎች እየተመገብን በነፃ እንኖራለን፤ ሰው ጫካውን እየመነጠረ ተፈጥሮ የሰጠንን እንዳንጠቀም ሲያደርገን ደግሞ ከአንድ ማሳ ወደሌላ ማሳ እየዞርን በሜዳ ላይ ያልተሰበሰበውን ሰብል ወይም ደግሞ ታጭዶ የተከመረውን ነዶ እየዘረጠጥን እንበላለን። ሰው እኛን የናቀው ሕንፃ ስለገነባ፣ ሀብት ስለሰበሰባና የጦር መሣሪያ ስለአከማቸ በዚያ ተመክቶ ይንቀናል እንጂ በተፈጥሮ እኩል ነን። እናንተ ነፃነታችሁን አሳልፋችሁ ህሊናችሁን ሸጣችሁ ለሆዳችሁ የተገዛችሁ ምቀኞች ባትኖሩ ኖሮ እኛ ሙሉ ነፃነት ኖሮን እንደናንተ ያሉትን እንሰሳት የተባላችሁ ጭቁን ፍጥረታት ጭምር ነፃ እናወጣ ነበር፤ አሁንስ ቢሆን በኑሯችን ብንጎሳቆልም እንደኛ ነፃነት ያለው የት ይገኛል? አንድ ቀን በጭቁን ፍጥረታት የተባበረ ትግል የሰው ኃይል ሲዳከም መድረሻ የምታጡት እናንተ ውሾች ናችሁ፡፡ ሰው የሠራውን ሕንፃ እያያችሁ በዘበኝነት ትጠብቃላችሁ እንጂ የናንተ ስላይደለ የምትተኙት ከስብሳብ፣ የምትበሉት ከወጭት አያልፍም፤ ይልቁንስ ብንስማማ አይሻልም? እናንተ እከብቶቻችሁ ጋ ሂዱ፤ ሰብል ሰብሉን ለኛ ብትተዉልን ምን አለ? ሰው ፍየል፤ በግ፤ ወይም ሌላ ሌላ እንሰሳዎችን ቢያርድ ምርጥ ምርጥ የሆነውን እንዲሁም ልብና ኩላሊት እንኳ ባይሰጧችሁም ሽንፍላና እንጀት እየበላችሁ ትኖራላችሁ። እናንተ ልክስክሶች ስለሆናችሁና የምትበሉትን እንኳ  ስለማትመርጡ ተጸይፈዋችሁ ነው እንጂ ሰዎች እናንተንም ከመብላት አይመሱም ነበር።

ዉሻ፦ ሽንፍላም ሆነ ልፋጭ ትበላላችሁ የምትሉን እንደናንተ ሣርና  የእንጨት ፍሬ ከመባላት ሳይሻል እንደማይቀር አጥተኸው አይመስለኝም፤ ዝናም ሲጠፋ ሣሩም ቅጠሉም ፍራፍሬውም ስለማይኖር በችጋር የምታልቁት እናንተ ናችሁ እንጂ እኛ አይደለንም። እኛ በታማኝነታችን ጦማችንን አለማደራችን አልታየህም፤  እናንተ ግን ዕድሜ ልካችሁን ስትሠጉ ነው የምትኖሩት፤  ታማኝ በመሆናችን ሳያበሉን የማያሳድሩን ሰዎች  የሚሰጡንን ክብር አታውቀውም፤ እናንተ ድሮስ ማዕርግ የት ታውቃላችሁ?

ዝንጀሮ፦ አዎን የጌቶቻችሁ ዘበኞች ስለሆናችሁ ሆዳችሁ እንዴት ሊጎድልባችሁ ይገባል? ሆዳችሁ ከጎደለባችሁማ  እንኳን ሮጣችሁ ልትናከሱ ቀርቶ ላንቃችሁ እንኳ መጮህ አይችልም፤ ይህን አገግሎት ካቆማችሁ ሰው እንደቆሻሻ እንደሚጥላችሁ አታውቁም? ሌላው ልታውቁት የሚገባው ደግሞ  እኛ ተፈጥሮ የሰጠችንን ምንም ሳንለውጥ የምንመገብ ስለሆነ ስካር ወይም የእእምሮ መቃወስ የሚባል ነገር አናውቅም፤ ሰው ግን ብዙ የተለያዩ ምግቦችን ያለቅጥ እያግበሰበሰ፤ እየቀመመ ከተፈጥሮ ሕግ ውጭ እንደሱ ነፍስ ያላቸውን ፍጥረታት ሁሉ በግፍ እየገደለ ስለሚበላና ስለሚጠጣ አእምሮው ከመደንዘዙም በላይ  ገሚሱ የማይድን በሽታ ይዞት ዕለተ ሞቱን እየተጠባበቀ በሥጋት የሚኖር ሲሆን፤ እናንተ ውሾችም ከሱ የተረፈውን ስለምትመገቡ የሰው በሽታ ይተላለፍባችኋል፤ አለቅጥ ለረዥም ጊዜ መተኛታችሁ በሽታ መሆኑ አይታውቃችሁም? እስቲ ምን የመኖር ዋስትና አላችሁ?  ዕድሜያችሁስ ምን ያህል አጭር መሆኑን ተገንዝበኸዋል? እንደኛ በአካልም በአእምሮም ጤነኛ ሆናችሁ በነፃነት እንድትኖሩ የምንላችሁን ብትሰሙና ብትተባበሩ ይጠቅማችኃል፤ ለምሳሌ እንደኛው ያሉ ፍጥረታት የሚመስሉ የጋራ ጠላት ሆነው የሚያጠቁንን ጅቦች ለመከላከል ብንተባበር ከመጠቀም በስተቀር ምን ትጎዳላችሁ?

ውሻ፡ ጅብ በእርግጥ የሁላችንም ጭቁን ፍጥረታት ጠላት ነው፤ ሆኖም ጅቦችን መቋቋም የምንችለው እኛ ውሾች የተባልን ፍጥረቶች እንጂ እናንተ ምንም ማድረግ የማትችሉ ፍጥረቶች ናችሁ፤ እናንተ ጅቦችን ተዋጉ የምትሉት ለብልጠታችሁ ነው፤ እኛ ከጅብ ጋር ጦርነት ስንከፍት እናንት ሰብሉን ለመሸምጠጥ ዕድል እንዲኖራችሁ  ስለሆነ ከናንት ጋር መተባበር አንችልም፤ አትቀልድ።

ዝንጀሮ፡ የተሳሳትከው አንተ ነህ፤ ጅብም ሆነ ሰው የናንተም የኛም ጠላቶች ናቸው፤ ሁለቱም ጠላቶቻችን ባይሆኑ ኖሮ በምድር ላይ የሚገኘው ተፈጥሮ በሙሉ ዱሩና ደኑ በሰዎች መመንጠሩ ሲቀርለት እየተስፋፋና እያፈራ ምድር በተፈጥሮዋ ተሞልታ የሁላችንም መመኪያ ትሆን ነበር፤ ደግሞ በየጫካው እየዞርን የፈለግነውን ተፈጥሮ የለገሰንን ሁሉ እንደልባችን እየተመገብን እንኖር ነበር። እኛ ዝንጀሮ የተባልን ፍጡራን ምንም እንኳ ዱር የምንኖር ቢሆንም፤ እንደናንተ በሰንሰለት ታሥሮና ለሰው በሪያ ሆኖ ከመኖር የተሻለ ሕይወት አለን፤ በዱር በገደሉ በየቁጥቁዋጦውና አረሁ ብንዘዋወርም ደኑ በኛ ቁጥጥር ሥር ስለሆነ ዋና ጠላታችን ከሆነው ሰው ነፃ ወጥተን እንደልባችን እየተዘዋወርን እንኖራለን፤ ሰው ደግሞ እኛን ለማጥቃት ቢዘምትም የምንበቀለው በድንገት በደፈጣ በምናደርገው ወረራ ነው፤ ዓመት ሙሉ የደከመበትን በአንድ ቀን ሌሊት የማውደም ልዩ ችሎታ አለን። ይህ በደፈጣ የምናደርገው ትግል የባላገር ባለቤት አድርጎናል፤ እናንተ ከጌቶቻችሁ ተለይታችሁ መኖር አትችሉም፤ አይፍፈቀድላችሁም፤ ወደዱር እንኳ ስትሄዱ ለሰው አሽከር ሆናችሁ ነው እንጂ ራሳችሁን ችላችሁ መሄድ አትችሉም፤ ምክንያቱም እናንተ የምትኖሩት ጌቶቻችሁን ለማገልግል ብቻ ስለሆነ ለሆዳችሁ የተገዛችሁ እንሰሳት ናችሁ። ሁሉንም ለራሱ ሊሰበስብ በሚያደርገው ጥረት ሰው እኛን ለመቋቋም የሚሞክረው በመሣሪያ ኃይል ብቻ ነው፤ ሆኖም፣ በጠመንጃ ሊገድለን ሲሞክር ባለን ከፍተኛ ወታደራዊ ቅልጥፍና ስለምንገለባበጥ ጥይት ሊመታን አይችልም፤ በየቦታው ከትሞ በየጊዜው አዳዲስ የመሣሪያ ክምችት እየጨመረ ያለው አቅም ስለሌለው ነው። ተባብረን ባላገሩን በሙሉ ብንቆጣጠርበት ሰው የሚያግበሰብሰውን ሀብት ሁሉ ያጣዋል፤ መሣሪያ የሚያገኝበት ምንጭ ይደርቃል፤ በመሣሪያ መጠቀም ካልቻለ ደግሞ በቀላሉ በእጃችን ሥር ወደቀ ማለት ነው።

አንድ ቀን ዝንጀሮ የተባለ ሠራዊት ሁላ ግምባር ከገጠመ እናንተ ውሾች ከጌቶቻችሁ ጋር መግቢያ አይኖራችሁም፤ እናንተ የምታመልኩት ሰው ሲጨፍርበትና ሲዘባነንበት የነበረውን ቤት ጥሎ ሲፈረጥጥ ከኛ እጅ አያመልጥም። እሱም የሠራዊታችን ተገዥ ይኖናል፤ ዛሬ ሰው የሚሰድበንና የሚንቀን ሁላችን በአንድነት ሆነን ፍርድ ስንሰጠው ነፃነት፤ እኩልነት፣ ፍትህ፣ ማለት ምን እንደሆነ ሰናሳየው፤ ዝንጀሮ መባላችን ቀርቶ እኛም የሰውን ክብር እናገኛለን፤ ይልቅስ የነፃነት ቀናችን እንዲፋጠን እኛ የምንላችሁን ብትሰሙን እና ብንደማመጥ ጥሩ ነው።

ውሻ፡ ከናንተ ጋር ሆነን ጅብን ልንዋጋ? ሞኛችሁን ፈልጉ! እናንተ ዝንጀሮዎች፤ ሰው ባያስጠጋንና በጫካ ብንኖር ኖሮ ዘራችን በጅብ ያልቅ ነበር፤ በየዛፉ ስለምትንጠላጠሉ ነው እንጂ እናንተ ነበራችህ የመጀመሪያዎቹ የጅብ ቀለቦች፤ ለመሆኑ ጅብ ምን ይበቃዋል? እነዚህን የዱር እንሰሳትም ሆነ የቤት እንሰሳትን ለመጨረስ አይመለስም።  ስለዚህ አሁንም ይህች ሐሳብህ እኛ ዱር ገብተን በጅብ ስናልቅላችሁ እናንተ ያለተቀናቃኝ እንደልባችሁ የሰውን ሰብል ለመሸምጠጥ አይደል? ሰብል ደግሞ ተሽምጥጦ ካለቀ ሰው ለኛ የሚሰጠን ስለሚያጣ በረሀብ ማለቅ አንፈልግም፤  ስለዚህ ይህ ሐሳብህ ሌላ የብልጠት ዘዴ ስለሆነ እናንተን ማመን አይቻልም፤ እናንተ ለመሆኑ ምናችሁ ይታመናል? የወለዳችሁት ልጅና አባቱ እንኳ አይተመማኑም፤ እናት ዝንጀሮ ወንድ ልጇን የገዛ አባቱ እንዳይገድልባት ደብቃ ነው የምታሳድገው፤ ልጁም የአባቱን ኮቴ ሲለካ ሲለካ እያደገ አንድ ቀን ኮቴው ከአባቱ ኮቴ ጋር እኩል መሆኑን ሲያውቅ የጅር የበላይ ለመሆን አባቱን ከመዋጋት አይመለስም፤ እኛ ግን ውሾች የተባለን ፍጡራን ምንም እንኳን እናንተ ነፃነት የምትሉት ነገር ባይኖረንም ልጆቻንንና ወገኖቻችንን በጣም እናከብራለን፤ የተሰጠንን አክብረን እንበላለን እንጂ እንደናንተ ሠርቀን ወይም ዘርፈን አንበላም።

ዝንጀሮ፤ እንደናንተ ዝንጀሮ የሚባል ፍጥረት ጭላዳ፣ ጎመር፣ ወዘተ ተባብሎ በአፍና በዘር ተለያይቶ ሳይለያይ ከጦጣና ጉሬዛ ጭምር በሠራዊት በሠራዊት ተከፋፍሎ እየተመራ ነው የሚተዳደረው፤ እንደጉሬዛ ያለው  በመንፈሳዊነት ይታወቃል፤ እንደአውራ ዶሮ ሊነጋ ሲል ደጋግሞ በመጮህ ፈጣሪውን ከማመስገኑም በላይ የቀኑን ምሥራች ለኛ ያበሥረናል፤ እያንዳንዱም ሠራዊት ወይም ጅር ደግሞ የየራሱን ባላገር ይቆጣጠራል፤ ታዲያ አንድ የዝንጀሮ መሪ በራሱ ሠራዊት ውስጥ ተቀባይነት ኖሮት መሪ መሆን የሚችለው ከማንኛውም ሌላ ዝንጀሮ ጋር ተፋልሞ ኃይለኛነቱንና ጀግንነቱን በተግባር አሳይቶ ነው እንጂ እንደናንተ ለማንም ጅራቱን እየቆላ አይደለም፤ ይህን ብታስተውል ኖሮ ጥያቄውን አትጠይቀኝም ነበር።

ዉሻ፤ በናንተ መካከል ዘወትር የሚታየውን ጠብ እና ጀብደኝነት ጀግንነት ትለዋለህ? እርስበርሳችሁ ባትጣሉ ኖሮ ለመሆኑ ምን አገር ይበቃችሁ ነበር? እኛስ ብንጣላ እንኳ ሰው በመካከላችን ገብቶ ጠበኛውን አሥሮ ስለሚያገላግለን አንጨነቅም፤ የምንጨነቀው ነገር ቢኖር አልፎ አልፎ በጭለማ ወጣ ወጣ ስንል ጅብ እንዳያጠቃን ብቻ ነው።

ዝንጀሮ፡ ሰውስ ከጅብ በምን ይለያል? ጅብ ጅብ የተባለበት ምክንያት እኮ ከመጠን ያለፈ ስለሚበላ ነው፤  እናንተ የምታመልኩት ሰው ግን መቼ በልቶ ይበቃዋል? ዘርፎ ዘርፎ እኛ ልንጠቀምበት እንችል የነበረውን ሁሉ የተፈጥሮ ሀብት ሰብስቦና አግብስብሶ በግል ሊጠቀምበት ከሚያስፈልገው በላይ እጅግ ያከማች የል? መች ይጠግባል?  እንዲየውም ከሰው ጅብ ሳይሽል ይቀራል? ምክንያቱም ጅብ እኮ ከወገኑ ጋር ተካፍሎ ይበላል። እንደሰው ያለ ክፉ እንኳን ያለ አይመስለኝም፤ ጌታህ ብቻ ስለሆነ የማይገባውን ክብር ልትሰጠው አይገባም።

ውሻ፡ ታዲያ እናንተ ከሰው ይበልጥ ደግ ነን ነው የምትለው? ምንም ቢሆን ሰው ይሻለናል፤ የናንተና የኛ አኗኗር ለየብቻ ነው፤ ባላገሩን ለብቻው ከተማውን ለብቻው ተቆጣጥሮ የሚያስተዳድረው ሰው በሌለበት እንዴት እኛና እናንተ ተስማምተን መኖር እንቻላለን?

ዝንጀሮ፡ ቀስ እያልኽ አትጠጋኝ፤ እዚያው ባለህበት ቆይ፤ እናንተ ውሾች እኮ ከኛ ጋር በአንድ ቦታ ኑሩ አላልናችሁም፤ እናንተ የምትመገቡት ሌላ እኛ የምንመገበው ሌላ፤ እንደየልማዳችን ለየራሳችን መኖር የሚከለክለን ምንም ነገር የለም፤ እኛ የእናንተን ሳንፈልግ፤ በየቀያችን፣ እናንተም በየቀያችሁ እየኖርን፣ እናንተም የኛን ሳትፈልጉ በጋራ ጠላቶቻችን ላይ የጋራ አቅዋም ብንወስድ ማን ይጎዳል?  በነዚህ ጠላቶቻችን ላይ ብንተባበር ጥንትም የራሳችን የነበረው ደኑ ተራራው፤ ሽንተረሩ ወንዛወንዙና የዱር ሀብቱ ሁሉ የናንተና የኛ የተናቅን እንሰሳት የተባልን ፍጡራን ስለሚሆን እናንተ የሚስማማችሁን እኛም የሚስማማንን እየተመገብን እናንተ እኛ ጋ ሳትደርሱ፤  እኛም የናንተን ሁሉ ሳንነካ የናንተም ሆነ የኛ ትውልድ ጦርነት አለብኝ በማለት ሳይጨነቅ በሰላም ተከባብረን መኖር እንችላለን።

ውሻ፤– አሁን ገና እውነት የምትናገር መሰለኝ። ስው እኮ እኛ ተዋግተን አንዳንዶቻችን ክፉኛ ቆስለንና ሞተን ከብቱንና ንብረቱን ብንጠብቅለትም ሰው የፈለገውን ይወረውርልናል እንጂ የደከምንበትን ከማየት በስተቀር አንጠቀምበትም፤ ጌታችን ሰው ከፈለገ  ይሸጠናል፤ ይለውጠናል፤ በማናውቅበት አገር ከዘመዶቻችን ተለይተን ስዎችን ለመጥቀም ሰላማዊ ፍጥረታትን በማጥቃት ጠላት ከማብዛት በስተቀር ምንም መብት የሚባል ነገር አናውቅም። ረሀብና በሽታ እንኳን ሲያጠቃን የመዳን ተስፋ ስለሌለን ሞታችንን ብቻ ነው የምንጠቀው፤ እንደዚህ ባለው ኑሮ ከመካከላችን አንዱ ሲጎድል ወይ ሞቶ ወይ ተሽጦ መሆኑን ተረድተን ለዛሬ ከማሰብ በስተቀር የወደፊቱን ስለማናውቀው የያንዳንዳችን ቀን እስኪደርስ መስለን እንኖራለን ። ሌላው ነገር ደግሞ የእናንተ ኑሮ በየቁጥቋጦውና ገደላ ገደሉ የሆነው የተፈጥሮ ሀብታችሁ ስለተወሰደባችሁና  ስለተሳደዳችሁ ምርጫ አጥታችሁ መሆኑን ተረድቻለሁ። ለካ ሁለታችንም ጭቁኖች ነን! ያውም የጋራ ጨቋኛችን በሆነው ሰው። የድሮውን የጥላቻ ታሪክ ትተን አሁን ያለንበትን ጭቆና በጋራ ለማስወገድ መተባበራችን የሚከፋ አይመስለኝም፡፡ ታዲያ እናንተ የኛን ሳተፈልጉ ወደኛ ሳትደርሱና እኛም ለራሳችን በሚስማማን ሁኔታ መኖር የምንችል ከሆነ ሊያስማማን ይችላል፤ ግን ሰው እኮ በጣም አዋቂና ከአቅማችን በላይ የሆነ መሣሪያ ስላለው እሱን ክደን እንዴት ሊሆንልን ይችላል?

ዝንጀሮ፦ አይ ችሎ ማደር እውነቱን መናገርህም ያሰመሰግንሃል፤ የዋህ መሆንህንም እረዳለው፤  ሆኖም እናንተ ውሾች የተባላችሁ ፍጡራን ሰው ካላሳደራችሁ ሕይወት እንደሌላችሁ ማመን የለባችሁም፤ ዋናው ነገር ይኸ ነው።  በራሳችሁ ጥረት ለኑሮአችሁ የሚያስፈልጋችሁን ማግኘት እንደምትችሉ አንተ ራስህ አሁን ተናግረከዋል፤ እናንተ የቤት እንሰሳት የተባላችሁትና እኛ የዱር አራዊት የተባልነው ዝንጀሮዎች የአንደኛችን  ወገን የሌላውን ወገን እንደጠላት አለማየታችን የመጀመሪያው ትልቅ እርምጃ ነው። ሰው በኛና በእናንተ ልዩነት ተጠቅሞ እናንተን በኛ ላይ እያዘመተ ነው ተንደላቆ የሚኖረው፤ ወደፊትም ዘራችን ከዘራችሁ ጋር ደም ተቃብቶ በጠላትነት ሲዋጋ ሰው ግን ተደላድሎ ለመኖር ነው የሚያቅደው። ወደፊት ከማሰብ ይልቅ ወደኃላ እያሰብን እና እየተጋጨን መኖር የለብንም፤ ድሮ ማ በማን ላይ የበለጠ ጉዳት አድርሷል የሚለውን ለማጣራት ብንሞክር አጣርተን ለማረጋገጥ ያስቸግረናል። እንደዚያ ብናስብ ቂምበቀል እየተወረሰ በናንተም በኛም ወገኖች መካከል ሳያቋርጥ እያጣላን ከሚኖር በስተቀር የሞቱትን አያስነሣም፤ ለወደፊቱም ሁላችንንም አይጠቅመንም፡፡  ዛሬ ያለንበትን ጭቆና በጋራ እናስወግድ ማለትህ ትልቅ እርምጃ ነው፡፡ ይህ የአስተሳሰብ ለውጥ ነው የድል በር የሚከፍትልን፡፡ አቋማችን አንድ ከሆነ እና እርስበርሳችን ላለመጣላት ከተስማማን የሰው መሣሪያ የትም አያደርሰውም፤ በመጀመሪያ ሰው የሚኖረው በኛ ልዩነትና ጠብ ላይ መሆኑን እንተማመን፤ ዘለዓለም እንሰሶች ተብለን አንኖርም፤ የእስከዛሬው ይበቃናል፤ በተባበረ ትግላችን ከሰዎች እኩል መሆናችን አይቀርም፤ ሆኖም በጋራ ለመታገል ቃለመሐላ መፈጸም አለብን። ከዚህ በኃላ ያለው ቀላል ነው።፡

ውሻ፦ እኛ እኮ እናንተን የምናሳድደው ጌቶቻችንን ፈርተን እነሱን ለማገልገል እንጂ እናንተ ዝንጀሮ የተባላችሁ ፍጡራን ምንም ልታደርጉን አትችሉም፤ ከናንተ ጋር መሠረታዊ ጠብ ሊኖረንም አይችልም፤ እኛ ከጌቶቻችን ነፃ መሆን ከቻልን በባላገር ውስጥ መኖር እናውቅበታለን፤ ከዘመዶቻችን መካከል ተኩላ የሚባል ዘር ከናንተ ጋር በጉርብትና እንደሚኖር ታውቃለህ። እናንተን ማሳደድ ስንተው ታዲያ ስው ወደባላገር እንዳይመጣ በመሣሪያው ተጠቅሞ ጉዳት እንዳያደርስብን ምን ማድረግ ይቻላል?

ዝንጀሮ፡ ቀበሮ “ሰውን ማመን ቀበሮ ነው” ያለችው ከናንተ ያነስ አቅም ያላትና የናንተው ወገን አይደለችም እንዴ ቤቷን ጫካ አድርጋ እንደኛ የምትኖረው? አትስጉ። በመጀመሪያ የውሻ ወገን ሁሉ ወራዳ ልክስክስ ተብሎ በመቃብርና ሕይወት መካከል እንዲኖር ሰው ለራሱ ጥቅም ያደረገው ተንኮል መሆኑን መረዳቱ ነው። ይህን ውሻ ለተባለ ፍጡር ሁሉ ማስረዳትና ማሳመን የናንተ ተግባር ይሆናል። ውሻ የተባለ ሁሉ ከትንሽ እስከትልቅ ሴትና ወንድ ሳይባል በሰንሰለት የታሠረውም ያልታሠረውም እንዲያምን ማድረግ አስፈላጊውን ጊዜ ወስዶ መሠራት ያለበት ትልቅ ሥራ ነው። ታዲያ ቀጥሎ በጋራ ተስማምተን አብረን እርምጃ ከመውሰዳችን በፊት ሴቶች ውሾችም ሆኑ ቡችሎች ተሳስተው አንዳች የጥላቻ ምልክት በጌቶቻቸው ላይ እንዳያሳዩ ጥንቃቄ መደረግ አለበት።

ውሻ፤– እኛ ወደን አይደለም ታማኝ ሆነን የምንኖረው፤ ምርጫ አጥተን ነው እንጂ፤ አብዛኛዎቻችን ጌቶቻችን ወደውጭ ለአገልግሎት ሊያሰማሩን ካልሆነ በስተቀር ወይ በር ተዘግቶብን ወይ ደግም በሰንሰለት ታሠረን ነው የምንኖረው፤ ታዲያ እንዴት የጋራ እርምጃ መውሰድ እንችላለን?

ዝንጀሮ፦ ዘዴማ ያስፈልጋል፡፡ ለምሳሌ በመጀመሪያው እርምጃ እኛ ስንመጣ እንድታጠቁን ይልካችኃል፤ በዚህን ጊዜ ጩኹና ስንሸሽ ተከሉን፤ ሰው እስከማይደርስበት ዱር ድረስ ያባረራችሁን መስላችሁ በመጨረሻ እንደደመሰስናችሁ ለመምሰል ሁላችሁም ድምፃችሁን አጥፉ፤ ይህን ጊዜ ሰው ያመፃችሁበት ሳይሆን ሞታችሁ ያለቃችህ ስለሚመስለው ሌሎች ውሾች ወገኖቻችሁን ማዝመቱ አይቀርም፤ በሁለተኛው ጊዜ ሲያሰማራችሁ ጩኸቱን እየቀጠለ ዉሻ የተባለ ሠራዊት ወደፊት ወደኛ በመገስገስ የበፊተኛውን እርምጃ እየደጋገመ ከወገኑ ጋር ይደባለቃል። እኛም ለሰው ጥይት ብቻ እንደማንሸነፍ ከዚህ በፊት እንደነገርኩህ በተለመደው የደፈጣ ውጊያ ስልታችን የተለያዩ የጥቃት እርምጃዎችን ስለምንወስድበት ሰው የሚመካበት ሰው-ሠራሽ ነገር ሁሉ እንደማያድነው ያየዋል።  በምናደርገው የመረጃ ልውውጥ እና ስልታዊ አመጽ በየአቅጣጫው እንቅስቃሴያችን ሲበረታበት ትዋጉለት የነበራችሁ እናንተ ጭቁን ፍጡራን ሁሉ ትታችሁት ከገኛ ጋር ስትሆኑ መሣሪያውን መጠቀም እንኳ አቅቶት ብቻውን ይቀራል። እኛና እናንተ ጭቁኖች ሁሉ አንድነት ስንፈጥር ክዚህ ቀደም የምታደርጉት የሕይወት መስዋዕትነት ይቀራል። እነዚህ እርምጃዎች ተደጋግመው ሲፈጸሙ ሰው  ብቻውን ስለሚቀርና አብዛኛዎቻችሁን ወደኛ ለማዝመት ሲል ስለሚፈታችሁ ነፃ እየወጣችሁ ባላገር ትገባላችሁ፤ እኛም ከናንተ ጋር በመተባበር ታሥረው የቀሩትን ባለን ጥበብ ዘምተን እንፈታቸውና የሰውን ገዥነት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እናስቀራለን፤ ከዚህ በኃላ ገዥና ተገዥ ሳይኖረን ሁላችንም ተከባብረን በሰላም እንኖራለን፤ ገባህ?

ውሻ፦ እውነት ነው፤ እኛ ከተባበርን ሌሎች ጠላቶቻችንን መቋቋም እንችላለን፤ ሰው የሚገለገልባቸውን በጎች፣ ፍየሎች፣ ወዘተ በማደን መኖር እናውቅበታለን።

ዝንጀሮ፦ ልብ በል፤ የናንተም ሆኑ የኛ ወገኖች በሙሉ እንዲቀባሉን እኛ ተንቀን የነበርንና በዚህ የነፃነት ጎዳና የተሠማራን ሁሉ የሌሎች የተናቁትን ፍጡራን መብትና ክብር በመጠበቅ ጥሩ ምሳሌዎች መሆን ይኖርብናል፤ አቅም አለን ብለን ደካማና አናሳ የሆኑትን የሆኑትን ፍጥረታት በፍጹም መጉዳት የለብንም፤ አንዱ ኃይላችን በሁሉም ወገኖች መታመናችን ነው፤ በተጨባጭ ጥሩ ምሳሌ እያሳየን ስንቀሳቀስ በየቦታው ውዳቂ መስለው የሚታዩት ፍጡራን ሁሉ  የቆምንላቸው መሆኑን ሲረዱ በምናደርገው የጋራ እርምጃ ሁሉ በፍላጎታቸው  ከጎናችን ይቆማሉ። ሁሉም ፍጡር አካባቢውን በነፃ ያስተዳደራል፤ የተናቁ ፍጡራን ሁሉ እንዳቅማቸው ለትግላችን ጠቃሚ አስተዋፅዖ ማድረግ ስለሚችሉ ሌሎች ፍጡራንን ሁሉ እንዳይጠላ ትንሹም ትልቁም ሴቱም ወንዱም የኛና የናንተ ወገን ሁሉ እንዲማር የማድረግ ኃላፊነት አለብን፤ አርስ በርስ በጠላትነት መተያየት ጨርሶ ቆሞ የሚቀጥሉት ትውልዶቻችን እኩልነትንና ፍቅርን ብቻ ማዳበር ይኖርባቸዋል።

ውሻ፦ የጋራ ጠላታችን የሆነውን የሰውንም መብት ማክበር አለብን ማለት ነው?

ዝንጀሮ፦ አዎን፤ የመጨረሻው ግባችን ሰውንም ነፃ ማውጣት ነው፤ እዚያ ደረጃ ላይ ለመድረስ ግን በሁላችንም በኩል የአስተሳሰብ ለውጡ የሠረጸ መሆን አለበት፤ በመጀመሪያ አሁን በላያችን ያለውን የገዥነት ኃይሉን በሙሉ አስወግደን ሰውን ከተራ ፍጡራን እኩል ማድረግ ብቻ ሳይሆን፤ እሱም ለዘመናት በራሱ ተመክቶ ሲፈጽም የነበረውን የገዥነት አቅሙ እና የበላይነት ሕልሙ ሁሉ ጠፍቶ ካለእኩልነት  ሌላ የጋራ ጥቅም እንደሌለ የሚያምንበት ሁኔታ መፈጠር ይኖርበታል። ከላይ እንደገለጽኩልህ ሰው ራሱ አልፈጸመውም እንጂ የባህል ለውጥ የሚለውን በናንተና በእኛ የተናቅን ፍጡራን ብቻ ሳይሆን ሒደቱን ጠብቆ ሰውም ራሱ የባህል ለውጡን በተግባር እንዲፈጽም ይደረጋል።

ውሻ፦ አሁን በሁሉም ነገር የተግባባን መሰለኝ፤ ስለዚህ የጋራ ቃልኪዳናችንን በቃለመሐላ ማረጋገጥ እንችላለን።

ቃልኪዳን

  1. እኛ የተናቅን ፍጡራን ውሻ፣ ዝንጀሮ፣ ወዘተ እየተባልን በሰው እጅ ተጨቁነን መኖራችን የመነጨው ባለመተባበራችን መሆኑን ተማምነን ከዛሬ ጀምሮ አንደኛው ወገን ሌላውን በጠላትነት እንዳያይ፣ የአንደኛችን ወገን መጠቃት የሌላው ወገን መጠቃት እንደሆነ ተማምነን ኃይላችንን ሁሉ በጋራ ጠላታችን በሆነው ሰው ላይ አዙረን ባላገሩ በሙሉ በኛ በጭቁን ፍጥረታት ቁጥጥር ሥር እስከሚውል ድረስ ማንኛውንም መስዋዕትነት በመክፈል በተፈጥሮ ላገኘነው የጋራ ነፃነታችን ለመታገል ተስማምተናል።
  2. ዋናው የጋራ ጠላታችን ሰው መሆኑን ተረድተን ማንኛውም ሰውን የሚመለከት ምሥጢር ከመኻከላችን ሳይወጣ እንዲጠበቅ ማድረግ እንዳለብን ተስማምተናል። ለጋራ መብታችንና ኅልውናችን ስንል ማናቸውንም ጠላትን የሚመለከት መረጃ በወቅቱ ለመለዋወጥ ተስማምተናል።
  3. ዋናው ጠላታችን ማናቸውንም ጥቃት በአንደኛችን ወገን ላይ ቢፈጽም ሁላችንም ባለን አቅም ሁሉ በጋራ ለመከላከልና ብሎም በማጥቃት ይህን የጋራ ጠላታቻንን ለማንበርከክ ቆርጠን ተስማምተናል።
  4. በመካከላችን መከፋፈል እንዳይፈጠር፣ ሁላችንም ነቅተን ሕፃን፣ ሴት፣ ሽማግሌ አሮጊት ጎልማሳ ሳይቀር በዚሁ ጉዳይ እንዲያምኑ በየበኩላችን የዕለት-ተዕለት ከፍተኛ ዘመቻ ለማድረግ ተስማምተናል።
  5. በያለበት ያለው ጭቁን ፍጡር ሁሉ ለአንድ የጋራ ዓላማ መቆም የሚችለው ከልብ ሲከበርና ስለመከበሩም በተግባር ሲያይ ስለሆነ፣ በችግርና በውርደት መኖራችን እንዲቀርልን እንደምንፈልግ ሁሉ ፣ እንደኛ የተጨቆኑ ፍጡራንን በሙሉ መብታቸውን አውቀንላቸውና አክብረናቸው በጋራ ነፃነቱ መንገድ እንዲያምኑና ከጭቆናው ለመላቀቅ በውዴታቸው ከጎናችን እንዲሰለፉ የየበኩላችንን ጥረት ሁሉ ለማድረግ ተስማምተናል።
  6. ከዛሬ ጀምሮ ለዘመናት በመካከላቻን የነበረው ቂም ሁሉ እንዲቆም፤ አንዱ ወገን የሌላውን ዘር በመጥላት በጥላቻ ስም መጠራራታችን እንዲቀር፤ በየትኛውም ቀበሌና መንደር አንዱ የሌላውን ስም እንዳያጠፋ፤ ሁላችንም በየበኩላችን ለጋራ መብታችንና ክብራችን በመቆም ይህንንም  አውቀን ልጆቻችንና በተሰቦቻችንን ለማስተማር ተስማምተናል።
  7. ከላይ ከተጠቀሱት ውስጥ እንደሁኔታው በሚያስፈልግበት ሁሉ በየኩላችን ዳይረክተሮችን፣ መምሪያዎችንና ቡድኖችን አቋቁመን እንዳስፈላጊነቱ ግንኙነቶችን በማድረግ ለመተባበር ተስማምተናል።
  8. አንዱ ወገን በሌላው ወገን ጣልቃ ሳይገባ፤ እያንዳንዳችን ወገኖች በውስጣችን ያለውን ጉዳይ በየራሳችን የውስጥ አመራር ለማስተዳደርና በውስጣችን አጥፊም ቢኖር በየራሳችን የውስጥ ሕግና ደንብ መሠረት እርምጃ ለመወሰድ እንደምንችል ተስማምተናል።
  9. እንደወንዝ ያሉትን የተፈጥሮ ሀብቶችና ከአንድ ዳር ወሌላ ዳር የሚወስዱ መንገዶችን በጋራና በእኩልነት የመጠቀም መብት እንዳለን ተስማምተናል።
  10. እኛ ዝንጀሮና ዉሻ የተባልን ጭቁን ፍጥረቶች ሰው እንደኛው ፍጡር መሆኑን አውቆ እስከዛሬ የፈጸመብንን በደል ተረድቶና ባደረገው ጥፋት ተጸጽቶ የሚያምንበት ደረጃ መድረሱን በጋራ ስናረጋግጥ በኛም ሆነ በማናቸውም ጭቁን ፍጥረታት ላይ ምንም ዓይነት ጥቃት ወይም የበቀል እርምጃ እንደማይወስድ ሲረጋገጥና ለፍትሕ ተገዥ ሲሆን፤ የሰው ዘር ሁሉ ከኛ ከጭቁን ፍጥረታት እኩል በነፃነት መኖር እንደሚችል እናምናለን።

“ሰውን ማመን ቀብሮ ነው”

↧

የትግሬዎች መንግሥት አወዳደቁና ክፋቱ!

$
0
0

አንዱዓለም ተፈራ – የእስከመቼ አዘጋጅ

ሐሙስ ነሐሴ ፲ ፪ ቀን ፳ ፻ ፰ ዓመተ ምህረት ( 08/18/2016 )

ባሁን ሰዓት፤ በገዥነት ሕልሙ እየተንሳፈፈ ካለው የትግሬዎች ቡድን በስተቀር፤ ኢትዮጵያን አደጋ ላይ የጣላት ይሄው ቡድን፤ የውድቀት አፋፉ ላይ መሆኑ ለሁላችን ግልጽ ነው። አሁን ካለንበት ሰዓት እስከመጨረሻው ውድቀቱ ያለው ጊዜ ግን፤ በጣም የከፋና የተመሰቃቀለ ነው። ይህ የሚሆነው፤ ከፊል በዚህ ወራሪ ቡድን ተግባር ሲሆን፤ ከፊሉ ደግሞ በኛው በታጋዩ ክፍል ያለነው ለዚህ ውድቀት በማድረግና ባለማድረግ ላይ ባለው ሂደታችን ነው። በተጨማሪ ደግሞ፤ የሃያ አምስት ዓመት የዚህ ቡድን ፀረ-ኢትዮጵያ አገዛዝ፤ ሀገራችንን ለከፋ ወደፊት አዘጋጅቷታል። ሀቁን ተቀብለን ከአሁኑ መደረግ ያለበትን ካላደረግን፤ በኋላ ይሄን ብናደርግ ኖሮ ብለን የመቆጫ ሰዓት አናገኝም፤ ያኔ ሁኔታውን አንገዛውምና!

TPLF

ይህ ወራሪ ቡድን፤ የመጨረሻ እስትንፋሱን የሚያወጣው በቃሬዛ ነው። ሕዝቡ አቸናፊ ሆኖ እንደሚወጣ ምንም ዓይነት ብዥታ ባይኖረንም፤ የሚከተለው ምን ይሆን? የሚለው ስጋት ሀቅ ነው። ያንን ሳጋት የበለጠ ለማክፋት ይህ የትግሬዎች ቡድን ሲጥር፤ ታጋዩ ክፍል የሚሠጠው መልስ ወሳኝ ነው። ህዝቡ ማቸነፍ የሚችለው፤ ከዚህ ቡድን በልጦ ሲገኝ ነው። ጎልብቶ ሲገኝ ነው። ጎብዞ ሲገኝ ነው። ይህ ቡድን ምን እያቀደ ነው? ብሎ ቀድሞ ሲዘጋጅ ነው። ምን ሊያደርግ ይችላል? የሚለውን ወስዶ አደናቃፊ ዝግጅቶችን ሲያሰላ ነው። አስኪ ይህ ቡድን ሊያደርጋቸው የሚችሉትን እንመልከት፤

  • እንዳየነውና እንደሰማነው፤ አልቃይዳ ወይንም አልሸባብ ወይንም አይሲስ ብሎ ታጋዩን ያልሆነ ቀለም በመቀባት፤ የውጪ ሀገሮችን ድጋፍ ለማግኘት ይጥራል። አይሆንም ማለት ሞኝነት ነው። ዛሬም ድረስ በሺር አል አሳድ ሶሪያን የሚገዛው፤ አሜሪካና አውሮፓ በከፍተኛ ድጋፍ ተቃዋሚዎቹን ቢረዱም፤ በሶቪየቶችና ቻይናዎች ድጋፍ ነው። እኒህም ሆኑ ሌሎች ሀገራት፤ ስሌታቸውን የሚያተኩሩት፤ ለኔ ሀገር ሁኔታው ምን ያስገኝልኛል? ብለው ነው።
  • ከዚህ አያይዞ፤ የውጭ ቅጥረኞች በማለት ታጋዮችን በሀገር ቤት ለማስጠላት ይሞከራል። እያደረገውም ነው። ይህ፤ ጊዜ ለመገብያ የሚጠቀምበት ዘዴ ነው። ወረሩኝ ብሎም ጦርነት በጎረቤት ሀገሮች ሊከፍት ይችላል። ይህ ሁሉ፤ የሕዝቡንና የታጋዩን እንቅስቃሴ ለማለዘብ ነው። ጊዜው አልፏል።
  • ዋናው የዚህ የትግሬዎች ቡድን አስከፊ ተግባር፥ ጉልበቱን መጠቀም ነው። ይህ እብሪተኛ ቡድን መቼም ቢሆን የሚተማመነው፤ “ጉልበቴ ከሁሉም ይበልጣል!” ብሎ ነው። አሁንም ሁሉን ነገር “በጉልበቴ እወጣዋለሁ!” ብሎ፤ አረመኔያዊ ተግባሩን ቀጥሎበታል። ነገሮችን አጢኖ መመልከት ድክመት ይመስለዋል። በሰላም ባዶ እጁን አቤቱታ ሊያሰማ የወጣውን ሕዝብ፤ እስካፍንጫው የታጠቀ አጋዚ አሰልፎ በቀጥታ በሰልፉ ላይ በመተኮስ አሁን በመቶዎች የሚቆጠሩትን እየገደለ ነው። ነገ ደግሞ በሺዎች የሚቆጠሩትን ይረሽናል። እስኪሞት ድረስ ሌላ ዕውቀት የለውም። ካልገደለ ውሎ የሚያድር አይመስለውም። ሕዝብ ቆርጦ ከተነሳ፤ መመለም የሌለው መሆኑን ሊረዳው አይችልም። የዚህ ቡድን መነጽር፤ የተቃወመኝን ገድዬ፤ ጉዳዩን አጠፋለሁ ነው።
  • ታጋዩን ከሕዝቡ ለመነጠል ይጥራል። ደደብ ሆኖ ነው እንጂ፤ ታጋዩ እኮ ሕዝቡ ነው! ሊገባው አይችልም። ታጋዩን ሊከፋፋል ይሞክራል። ታጋዩን እኮ፤ ከዚህ ቡድን ሕልውናና ጥፋት የበለጠ የሚያንገበግበው የለም። ለነገሩ ይህ አዲስ አይደለም። እስከዛሬ ያቆየው፤ የሕዝቡ በአንድ አለመነሳት ነበር። በዘር፣ በሃይማኖትና በጥቅም መከፋፈሉን ተክኖበታል። አሁን ግን ሕዝቡ ይህን ሁሉ ጥሶ እንዲወጣ የዚህ ቡድን ለከት የለሽ በደል አስገድዶታል።
  • “አሸባሪዎች ናቸው!” ብሎ ማላዘን የዕለት ተግባሩ ነው። ነገ ደግሞ የየሰዓት ጸሎቱ ይሆናል። ለዚህም የሃይማኖት አባቶችን አሰልፎ ያስወግዛል፣ ይማጠናል፣ ያባብላል። የቤተክህነትና የመስጊድ መሪዎችን አቅርቦ ሊናዝዝ ይቻላል። አብሮም ሆዳም የመንግሥት ሠራተኞችንና የጦር መሪዎችን አሰልፎ ሊያስወግዝ ይቻላል።
  • መላ የፌዴራልና የክልል አስተዳደራዊ መዋቅሮችን የስለላ ድርጅት ያደርጋቸዋል። እያንዳንዱን ትግሬና የስመ ኢሕአዴግ አባል ተራ ሰላይ ያደርጋል። ከታጋዩ ከድተው ወደኔ ገቡ ብሎ የውሸት ታጋዮችን በቴሌቪዥን ሊያቀርብ ይችላል። ተዘረፈ ብሎ የመንግሥትን ካዝና ወደ መቀሌ ሊያሻግረው ይችላል። ይህ ቡድን ሌብነት ኒሻኑ ነው።
  • ለመታያ የተቀነባበረ የሱ ደጋፊ ሰላማዊ ሰልፎችና ትዕይንቶች ሊያዥጎደጉድ ይችላል። በማስፈራራት፣ በመደለልና በማስገደድ ሰልፍ እንዲወጡ ሊያደርግ ይችላል። ይህን ማንም አይስተውም። ሆኖም ግን የራሱን የመንፈስ ጭንቀት እንኳን አይበርድለትም። አምባገነን መንግሥታት ሙያቸው ነው። ትናንት መንግሥቱ ኃይለማርያም አድርጎታል።
  • ሲያስበረግገው የሚያድረው የሕዝቡ ቁጣ፤ በፓልቶክ፣ በፌስቡክ፣ በሬዲዮና በድረገጾች ላይ ዘመቻውን እንዲያበዛ ያደርገዋል። መስሎት ነው። ኢንተርኔቱን ይዝጋው፤ ሕዝቡ በኢንተርኔት ሳይሆን በሚኖርበት ሀቅ ተገፋፍቶ ነው የተነሳው። ፓልቶክ ደግሞ ሕዝቡን ወደ አንድ አመጣና በትክክለኛው ጠላቱ ላይ እንዲያተኩር ረዳው እንጂ፤ ችግሩ ያስተዳደር በደል ነው። የዜና ልውውጡን ሊያግት ቢሞከርም፤ በየቦታው ያለው የሱ ግፍ ያነሳሳው ነው።
  • በማታለልና በማውገርገር የተካነው ይህ የትግሬዎች ቡድን፤ እደራደራለሁ፣ ለውጥ አደርጋለሁ፣ ሽምግልና እገባለሁ ሊል ይቻላል። ይህን እያለ ግን፤ በጎን በከፋ ሁኔታ ያው መግደሉን ይቀጥልበታል። ይህን የሚለው ጊዜ ለመግዣ ብቻ ነው። ተገዶም ቢሆን ለድርድር ቢቀርብ፤ ሥልጣኑን ማጋራት ወይንም የሰረቀውን ሀብት መመለሾ አይፈልግም። ሥልጣኑን የሚያስረክበው ወድሞ ነው።

ይህ ሁሉ ተግባሩ፣ አንድ ቀና አንድ ሌሊት ሊገዛለት ቢችልም፤ በአንጻሩ ግን፤ ትግሉን በትግሬዎችና በኢትዮጵያዊያን መካከል በማድረግ፤ የትግራይን ሕዝብ ለነገ ዕልቂት ያዘጋጀዋል። ይህ እየመጣ ያለ ሀቅ ነው። በርግጥ አሁን ሊለወጥ የሚችልበት ሰዓት ነው። ይህን ደግሞ እንደሚከተለው አቀርበዋለሁ።

ምንም አንኳ ይህን ፈጻሚው የትግሬዎች ቡድን ቢሆንም፤ በዚያው አኳያ፤ የታጋዩ ክፍል ጥረት፤ ሊያስተካክለው ወይንም ሊያባብሰው ይችላል። በአሁኑ ወቅት ታጋዩ ያለበት ሁኔታ አመቺ አይደለም። በርግጥ ሕዝቡ ራሱ እየመራ ያለበት ይህ እንቅስቃሴ፤ ወደፊት እንዲሄድና ለስኬት እንዲበቃ፤ መልክ መያዝ አለበት። ማዕከል ሊኖረ ይገባል። ይህ ማለት፤ አሁን ካሉት ድርጅቶች አንዱ ወይንም ሌላው ይምራው ማለት አይደለም። አሁንም መሪው በቦታው ሕይወቱን እየከፈለ ያለው ሕዝቡ ራሱ ነው። ታዲያ በውጪም ሆነ በሀገር ውስጥ ያለን የታጋዩ ክፍል ነን የምንል ሰዎች፤ እገዛችን መሆን ያለበት፤ ይህን ሕዝባዊ አካል መርዳትና ማጠናከር ነው። ለዚህ አመራር ተገዥ መሆን ነው። በየቦታው በመደረግ ላይ ያለው ሰላማዊ ሰልፍ፤ እንዲያው ከየሰማዩ ዱብ ዱብ ያለ አይደለም። ሕዝባዊ ቅንጅት አለው። ወጣቶቹ ከፍተኛውን መስዋዕትነት እየከፈሉ ያዋቀሩት የደማቸው ሐረግ ነው። ይህን ማጎልበት አለብን። የኔን ድርጅት ወይንም የኔን ድርጅት እያልን፤ ድርጅቶቻችን በሕዝቡ ላይ ለመጫን ያጎበጎብነው፤ ልጓማችንን መያዝ አለብን።

ጎንደር የተሰለፉት ወጣቶች፤ የእስልምና ተከታይ ወኪሎችና የኦሮሞ ወጣቶች ጉዳይ ጉዳያችን ነው! አሉ። የኦሮሞ ወጣቶች ተከትለው፤ ጠላታችን አማራ አይደለም ጠላታችን ወያኔ ነው! አሉ። የትግሬዎችን ቡድን አከርካሪ ሰበሩት። ይህ በተግባር መያያዝ አለበት። ጊዜውና ምቾቱ ያለን እኛ በውጭ የምንገኝ ይሄን አንድነትን የመፈለግ ጥረት ማጎልበት እንችላለን። አለዚያ፤ እንደ ግብፁ ሙባረክ ሳይሆን እንደ ሶሪያው አሳድ የተጓተተና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ብዙ ታጋዮች የሚያልቁበት ሀቅ መልበሳችን ነው። ግንቦት ሰባት የራሱን ንጉስ ለማንገስ ሲሯሯጥ፣ ኢሕአፓ የራሱን ለማንገስ ሲጣደፍ፣ ሰላማዊ የራሱን፣ መድረክ የራሱን ሲያዘጋጅ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል፤ አንድነት አጥቶ፤ ይጓተታል። ሶሪያ ውስጥ የየውጪ ሀገሮች፤ ማለትም የቱርክ፣ የሊባነን፣ የኩዌት፣ የአሜሪካ ደጋፊ ታጋዮች ተለያይተው በየበኩላቸው ባንድ በኩል፤ ሶቪየት ኢራንና ቻይና ደግሞ የአሳድን ማዕከላዊ መንግሥት ደግፈው፤ የሶርያ ሕዝብ እያለቀ እንዳለበት ሀቅ፤ ተያይዘን እንዳንሰምጥ እሰጋለሁ።

አንድነት አለመሰለፋችን ትግሉን ጎድቶታል። አንድ ጠላት አለን ብቻ ሳይሆን፤ ሁሉም ድርጅቶች ሕዝቡ የበላይና ወሳኝ ነው ብለዋል። ታዲያ ይሄን ከተቀበሉ፤ ለምን የየራሳቸውን ጥንካሬ አጉነው፤ ሌሎችን እንደሌሉ በመቁጠር ይሯሯጣሉ? ለምን ሀገርን በማስቀደም የትግሉ አካል ለመሆን ፈቃደኛ አይሆኑም? ይህ ተጠያቂነታቸውን ያጎላዋል። ይህ ትግሉን በመጎተት ያስጠይቃቸዋል። የትግሬዎች ቡድን የሚያደገውን ጥፋትና የሚያደርሰውን በደል መዘርዘሩ በቂ አይደለም። ባሁኑ ሰዓት ደግሞ፤ ሕዝቡ ደሙን እያፈሰሰ ባለበት ወቅት፤ ስለ በደሉ መዘርዘር ትርጉም አጥቷል። አሁን ትግሉ ወደፊት መሄዱንና የድል ጎዳና መቀየሱን ነው ማብሰር ያለብን። አሁን፤ የሕዝቡን ድል መዘርዘር ላይ መሆን አለብን። ይህ ግን በምኞት አይመጣም። ተጨባጭ ሥራዎችን መሥራት አለብን። ይህ ደግሞ የሚጀምረው፤ ትግሉን በአንድነት ለማድረግ ወደ አንድ በመሰባሰብ ነው። ምንም እንኳ ይህ የአንድነት ጥሪ ለፍቶ ለፍቶ የሟሸሸ ቢሆንም፤ አሁን ክፍተት ተፈጥሮ ማዕከሉ ባዶ ሲሆን፤ እንደ ትግሬዎች ቡድን ዘሎ ለሚገባ የታጠቀ ቡድን በሩን በርግደን እንዳንተው እፈራለሁ። ሕዝባዊ ድል የሚገኘው፤ ሕዝቡ ሲመራና ሲታገል ብቻ ነው። ድርጅቶች የሚታገሉት ለድርጅታቸው ነው። የሕዝብ ድርጅት ደግሞ የለንም።

ከታላቅ አክብሮታ ጋር

አክባሪያችሁ አንዱዓለም ተፈራ

↧
↧

ከአዲስ አበባ ሕዝባዊ እምቢተኝነት አስተባባሪ ኮሚቴ የተላለፈ አስቸኳይ መግለጫ | Video

↧

አንድ አልማዝ፤ አንድ ወርቅ ፣ አንድ ነሐስ

$
0
0

Screen Shot 2016-08-19 at 8.00.45 PM
(ዘ-ሐበሻ) በሪዮ ኦሎምፒክ በ10 ሺህ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት የነበረችው አትሌት አልማዝ አያና በአምስት ሺህ ሜትር ለሃገሯ የነሐስ ሜዳሊያ አገኘች::

ኢትዮጵያ ማሞ ወልዴ፣ ምሩጽ ይፍጠር፣ ጥሩነሽ ዲባባ እና ቀነኒሳ በቀለ በአንድ ኦሎምፒክ ሁለት ወርቅ በማምጣት ታሪክ ያላቸው ሲሆን አልማዝ ዛሬ ወርቅ ብታገኝ ኖሮ ከላይ ከተጠቀሱት አትሌቶች ጎን ስሟ ይቀመጥ ነበር:: ሆኖም ግን  በዘንድሮው ኦሎምፒክም ለኢትዮጵያ ሁለት ሜዳሊያ በማምጣት አልማዝ ብቸኛዋ አትሌት ሆናለች:: ከዚህም በተጨማሪ አልማዝ አዳዲስ ታሪኮችን አስመዝግባለች:: አልማዝ ዛሬ ያገኘችው ሁለተኛ ሜዳሊያ በኦሎምፒክ የመጀመሪያ ተሳትፎ ሁለት ሜዳሊያ ያስገኘች ብቸኛዋ  አትሌት አስብሏታል:: በኦሎምፒክም የዓለም ክብረ ወሰን ያሸሻለች ባለታሪክ ናት::

አልማዝ በ5 ሺህ ሜትሩ ውድድር የመጨረሻው 2 ዙር እስኪቀር ድረስ ብቻዋን በመውጣት ስትመራ የነበረች ቢሆንም በውድድሩ የተካፈለኡት 3ቱ ኬንያውያን በአስናቂ የቡድን ሥራ አልማዝን አድክመው አንደኛና ሁለተኛ ወጥተዋል::

በዚህ ውድድር 5ኛ የወጣችው ኢትዮጵያዊት ሰንበሬ ተፈሪና 14ኛ የወጣችው አባብል የሻነ ከአልማዝ ጋር በ5 ሺህ ሜትር ውድድር ቢሮጡም እንደታሰበው ተከታትለው ለመግባት ይቅርና በቡድን ሥራ አልማዝን ሲያግዟት አለመታየቱ በስፖርቱ ተመልካች ዘንድ እንደ አሳዛኝ ሁነት ተቆጥሯል::

Screen Shot 2016-08-19 at 8.15.33 PM

የአልማዝ አያና ቀድሞ መውጣትና ውድድሩን ማፍጠኗ ለኬንያዊቷ አትሌጥ ቪቪያን ችሪዮት ትልቅ ድል ነበር:: አንደኛ ከመውጣቷም በላይ
በ14:26.17 በመግባት የኦሎምክን ሪከርድ ሰብራለች:: ቪቪያን ችሪዮት አልማዝ 10 ሺህ ሜትሩን ሩጫ የዓለምን ሪከርድ ሰብራ ስታሸንፍ 2ኛ መውጣቷ አይዘነጋም::

ለማንኛውም አንድ አልማዝ 1 ወርቅ እና 1 ነሐስ ለምንወዳት ሃገራችን አምጥታለችና ክብር ይገባታል:: በአትሌቲክሳችን ውስጥ ግን የቡድን ሥራው ጉዳይ ሊታሰብበት ይገባል:: ከራስ ጥቅም ይልቅ የሃገር ክብር ይቅደም::

↧

በሰሜን ጎንደር ጃናሞራ የሚገኘው አኪራ የመንገድ ስራ ድርጅት ካምፕ በአካባቢው ህዝብ ነደደ

$
0
0

በሰሜን ጎንደር ጃናሞራ የሚገኘው አኪራ የመንገድ ስራ ድርጅት ካምፕ በአካባቢው ህዝብ ነደደ
በሰሜን ጎንደር ጃናሞራ የሚገኘው አኪራ የመንገድ ስራ ድርጅት ካምፕ በአካባቢው ህዝብ ነደደ

↧

ድር ቢያብር አንበሳ ያስር! –በተክሉ አባተ (ዶ/ር)

$
0
0

unityታሪካዊ የለውጥ ጎዳና ለኢትዮጵያ በሚል ርዕስ በአገራችን እየተደረገ ያለው የሕዝብ ተቃውሞ አስፈላጊና አበረታች እንደሆነ ሞግቻለሁ። የትግሉም ዓላማ እውነተኛና ዘላቂ ዴሞክራሲና ነጻነት ማስፈን እንደሆነም ከሕዝቡ መፈክሮች በመነሳት አትቻለሁ። በተጨማሪም መንግስትና ደጋፊዎቹ፣ ትግሉን በማካሄድ ላይ ያለው ሰፊው ሕዝብ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሃይማኖት ተቋማትና የመገናኛ ብዙኅን ይህን መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት ልዩና ላቅ ያለ አስተዋጽዖ ማድረግ እንዳለባቸው ጠቁሜያለሁ። ሕዝቡ የትግሉ ባለቤትና ኦዲተር ሆኖ ሥራ አሥፈጻሚ አካል ወይም ልዩ ብሄራዊ ኮሚቴ መምረጥ እንዳለበትም ለማሳየት ሞክሬ ነበር። በመጨረሻም ኮሚቴው ለምንና እንዴት መመረጥ እንዳለበት ለመነሻ ያህል ጥቂት ነጥቦችን አንስቻለሁ። በዚህ ጽሑፍ ደግሞ ይህ ለውጥ አስተባባሪ ኮሚቴ እንዴት እንደሚመረጥና የትግል መርሆቹና ስልቶቹ ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ዘርዘር አድርጌ አቀርባለሁ።

እስካሁን ድረስ እንደታዘብነው ከሆነ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፍጹም ውህደት እንዲፈጥሩ መጠበቅ የሚከብድ ይመስላል። ያለው ብቸኛ አማራጭ እያንዳንዱ ፓርቲ የራሱን ምንነትና ማንነት እንደያዘ የጋራ ፕሮጀክቶችን መንደፍ ነው።: ይህም ማለት ፓርቲዎች ስማቸውንና የራሳቸውን ፕሮግራም እንደያዙ በጋራ ሊሠሯቸው የሚገቡ ጉዳዮችን አብሮ መለየትና መሥራት ነው።: ሁሉም የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ ባይቻል አብዛኛው ተገናኝቶ  መወያየትና ሁሉንም የሚወክል አስተባባሪ ግብረ ኃይል ማቋቋም ወሳኝ ነው። ግብረ ኃይሉ ለውጥ እስኪመጣ ትግሉን በበላይነት ይመራል። አመቺና ውጤታማ የትግል ስልቶችን ለይቶ ለሁሉም ፓርቲና ለሕዝቡ በተለያዩ መንገዶች ይፋ ያደርጋል። የሚመረጡት የትግል ስልቶች በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች በአንድ ጊዜ ሥራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋል። ተፈጻሚነታቸውን ይከታተላል። የቋንቋና የባህል ልዩነት ስላለ እያንዳንዱ ፓርቲ የራሱ አባላትና ደጋፊዎች የሚበዙበትን አካባቢ በዋናነት ሊያስተባብር ይችላል።

የሚመረጡት የትግል ስልቶች (ለምሳሌ የተቃውሞ ሰልፍ፣ ማእቀብ ማድረግ፣ ማግለል፣ ወዘተ) በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች አንድ ላይ መደረግ አለባቸው። ይህ ከሆነ የተቃዋሚው ጎራ ይበልጥ እየተባበረ እንደሄደ ሕዝብና መንግስት ያውቃሉ። አስገዳጅና አማራጭ ኃይል እንዳለም አመላካች ይሆናል። በሁሉም ቦታ አንድ ላይ የሚደረጉ ትግሎች የፖሊስንና የካድሬውን ስምሪት ያሳሳዋል። ይህም ሊከሰት የሚችለውን የተለመደ ግድያና ዱላ እንዲሁም አፈና በእጅጉ ይቀንሰዋል። መንግስት የፍርሃት መጠኑን እንዲጨምርና ሕዝብን እንዲያዳምጥ ያስገድደው ይሆናል።

ወሳኝ ተግባራት

ለሕዝብ ቆሜአለሁ የሚል ትክክለኛ ፓርቲ በሚከተሉት መሠረታዊ በሆኑ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ አቋም ይኖረዋል ተብሎ ስለሚታሰብ አስተባባሪ ግብረ ኃይሉ በቀጣይነት የሚደረጉ ሰላማዊ ትግሎች እነዚህንና ሌሎችንም ጥያቄዎች ያማከሉ እንዲሆኑ ማድረግ ይችላል። በሌላ አባባል የትግሉ ዓላማ የኢትዮጵያዊያንን መብትና ነጻነት ማምጣትና ሁሉንም በአንድነት አቅፋ የምትሄድ ፍጹም ዴሞክራሲያዊት አገር መገንባት ነው። ይህን ዓላማ ለማሳካት ቀጥለው የተዘረዘሩትንና ሌሎችንም ጥያቄዎች ማንሳትና ለነሱም አጥጋቢ መልስ ማግኘት ወሳኝነት አለው።

  • ሕገ መንግስቱን የሚጻረሩ ሕጎች መመሪያዎችና ደንቦች ይሻሩ
  • ነጻና ገለልተኛ የፍትህ ሥርዓት ይቋቋም
  • ምርጫ ቦርድ ከመንግስት ተጽእኖ ይላቀቅ
  • ሃሳብን በነጻነት መግለጽ ይፈቀድ
  • መንግስታዊ አሸባሪነት ይቁም
  • ፓርቲዎች በነጻ የመሰብሰብና ሰልፍ የመውጣት መብታቸው ይጠበቅ
  • የፖለቲካ  እስረኞች ያለቅድመ ሁኔታ ይፈቱ
  • መንግስት በሃይማኖት ተቋማት የሚያደርገውን ጫና ያቁም
  • በሙስና የተጨማለቁ ባለሥልጣናት ለፍርድ ይቅረቡ
  • የመከላከያ ፖሊስና ደኅንነት መስሪያ ቤቶች ብሄራዊ ተዋጽኦ ይኑራቸው ለሕዝብም ይቁሙ
  • ሁሉን አቀፍ ብሄራዊ መግባባትና እርቅ  ይደረግ
  • የሽግግር መንግስት ተመስርቶ ትክክለኛና ነጻ ምርጫ ይካሄድ ወዘተረፈ

የትግል ስልቶች

ለመነሻ ያህል ወይም ለምሳሌ ይሆን ዘንድ አስተባባሪ ግብረ ኃይሉ ቀጥለው የተዘረዘሩትን የትግል ስልቶች ደረጃ በደረጃ ሥራ ላይ ሊያውል ይችላል።

  • ጥርት ያለ የትግል ቅደም ተከተልና ስልት በጋራ መንደፍና ፕሮግራሙንም በተለያዩ  ቋንቋዎች አዘጋጅቶ ለሕዝብና ለፓርቲ አባላት ማሳወቅ የትግሉን መጀመር ለማብሰርና ቆራጥነት ያለው አስተባባሪ ግብረ ኃይል እንተመሰረተ ለማሳየት ሕዝብን ሳይጨምር የሁሉም ፖለቲካ ፓርቲዎች ሼል አመራሮች ሼል አስፈጻሚዎችና ሌሎች የፓርቲዎች የቢሮ ሠራተኞች ያሉበት ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ ማካሄድ፣ በሰልፉ ላይ እያንዳንዱ ፓርቲ አርማውንና በጋራ የሚዘጋጁትን መፈክሮች መያዝ
  • መንግስት በሰልፉ ወቅት የሚጠየቁትን ጥያቄዎች በተመለከተ መልስ የሚሰጥበት የተወሰነ ጊዜ ገደብ ማስቀመጥ
  • ሰልፉን በቪዲዮ ቀርጾ በማኅበራዊ ሚዲያዎች መልቀቅ በጽሑፍም ማዘጋጀትና መበተን
  • መንግስት በተሰጠው ጊዜ ውስጥ አጥጋቢ መልስ ካልሰጠ በዋና ዋና ከተሞች (ለምሳሌ በአዲስ አበባ፣ በናዝሬት፣ በአዋሳ፣ በጅማ፣ በዲላ፣ በነቀምት፣ በደሴ፣ በባህር ዳር፣ በጎንደር፣ በመቀሌ፣: በደብረ ማርቆስ፣ በአሰላ፣ በሐረር፣ በድሬዳዋ፣ በሰመራ፣ በጋምቤላ፣ በአሶሳ፣ ወዘተ) ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ በአንድ ቀን ውስጥ ማካሄድና የሰልፉን የአቋም መግለጫ ለመንግስት በጽሑፍ መስጠት፣ አጥጋቢ መልስ መንግስት በተወሰ ጊዜ ውስጥ እንዲሰጥ ማሳሰብ
  • መንግስት በተሰጠው ጊዜ ውስጥ አጥጋቢ መልስ ካልሰጠ በግብረ ኃይሉ አማካኝነት በጥንቃቄ በሚመረጡ ጥቂት ከገዥው ፓርቲ ጋር ግንኙነት ባላቸው ወሳኝ ተቋማት ላይ ብሄራዊ ማእቀብ መጣል፣ ማእቀቡ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ ቀድሞ መወሰንና መንግስት በዚያ ጊዜ ውስጥ መልስ እንዲሰጥ ማስገደድ
  • መንግስት በተሰጠው ጊዜ ውስጥ አጥጋቢ መልስ ካልሰጠ ህዝቡ በአስተባባሪ ግብረ ኃይሉ በዝርዝር የሚቀርቡትን ሁሉንም ንብረትነታቸው የገዥው ፓርቲ የሆኑ ድርጅቶች (ባንኮችን ጨምሮ)  ላይ ማእቀብ መጣል
  • አሁንም መንግስት ለህዝብ ጥያቄ መልስ የማይሰጥ ከሆነ በመላ ኢትዮጵያ በአንድ ቀን ያመረረ ሰልፍ ማድረግ፣ መንግስት ጥያቄዎችን እንዲመልስ ዳግም ማሳሰብ
  • አጥጋቢ ምላሽ ከመንግስት እስኪገኝ ድረስ እንደአስፈላጊነቱ ስልትን እየቀያየሩ (ለምሳሌ ካድሬዎችንና ባለሥልጣናትን ከማህበራዊ ሕይወት ማግለል፣ መንግስት በሚጠራቸው ስብሰባዎች አለመገኘት ወይም ተገኝቶ ጆሮንና አፍን መዝጋት፣ ተቀማጭ ገንዘብን ከባንክ ማውጣት፣ በጭቆና ምክንያት ለታሰሩት ለተደበደቡት ለተሰደዱት ለጠፉት በህብረት ሻማ ማብራትና ሥራቸውን ለሕዝብ ማቅረብና ለውይይት ማብቃት፣ የተቀናጀ ሼል ማቆም አድማ ማድረግ፣ ትግሉን በሁሉም የአገሪቱ ክፍል መቀጠል…
  • የስለላ ሼል በመንግስት ባለሥልጣናትና በካድሬዎች ላይ ማካሄድና መጥፎ ሥራቸውን በተለያዩ  መንገዶች ለሕዝብ ይፋ ማድረግ
  • እውነታ ላይ የተመሰረተ የፕሮፓጋንዳ ሼል መሥራት፣ የተለያዩ መገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም ሕዝብን በመረጃ ማንቃት
  • በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የትግሉ አካል ስለሆኑ በንቃት ማሳተፍ
  • ለመንግስት የሚላኩ ውሳኔዎችን የአቋም መግለጫዎችን እንዲሁም ሼል ላይ ያሉ የትግል ስልቶችን ለዲፕሎማቶች ማሳወቅ
  • ይህ ሁሉ ሲደረግ የመንግስት ባለሥልጣናትና ደጋፊዎች ሕዝቡን መቀላቀል ቢፈልጉ ይቅርታ እየጠየቁ እንዲቀላቀሉ ማድረግ

ማጠቃለያ

ይህ ሁሉ ሲደረግ መንግስት ዝም ብሎ አይቀመጥም።: ከአስተባባሪ ግብረ ኃይሉ እየቀደመ የማስታገሻና የማርከሻ እርምጃዎችን ሊወስድ እንደሚችል ግልጽ ነው። በተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል ልዩነት እንዲኖር ያደርጋል።: የትግሉን አስተባባሪዎች ሊያስር ሊያንገላታ ሊገድልም ይችላል። ሕዝቡንም ሊያስፈራራና ሊደበድብ ሊያስርም ይችላል። ይህ ሁሉ ሊመጣ እንዳለው ቀደም ብሎ መገመትና መስዋእት ለመክፈል መዘጋጀት ያስፈልጋል። ለውጥ ባጭር ጊዜም ሊመጣ ስለማይችል የተለያዩ  ስልቶችን በቀጣይነት መጠቀም ወሳኝ ነው። ሕዝብን የማንቃትና የማረጋጋት ሥራ ግን የሁል ጊዜ ተግባር ሊሆን ይገባል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች ፍጹም ውህደት እንዲመጣ ከሚጥሩ ይልቅ ከላይ በተጠቀሰው መንገድ ቢጓዙ ውጤታማ ይሆናሉ። እንደ ድር ቀጥነው የሚታዩት የፖለቲካ ፓርቲዎች በወሳኝ የለውጥ ሥራዎች ላይ የሚተባበሩ ከሆነ እንደ አንበሳ አይሎ የሚታየውን መንግስትንና ታጣቂ አካሉን ሁሉ ሊያሸንፉ ይችላሉ። ድር ቢያብር አንበሳ ያስር ይባል የለ!

ማሳሰቢያ:- ይህ ጽሑፍ የዛሬ ሁለት ዓመት ሰላማዊ ሕዝባዊ ትግል! በሚል ርዕስ ከጻፍኩት የተወሰደ ነው። ጥቂት ማሻሻያ ግን አድርጌለታለሁ!

ገንቢ አስተያየት ካለዎት በteklu.abate@mail.com ይላኩልኝ!

↧
↧

አብዱ ኪያር በመቀሌ ኮንሰርቱን ሊያቀርብ ነው

$
0
0

Screen Shot 2016-08-20 at 1.12.02 AM
(ዘ-ሐበሻ) ድምጻዊው አብዱ ኪያር በመቀሌ ኮንሰርቱን ሊያቀርብ እንደሆነ በትግራይ ክልል ለሚተላለፍ አንድ ራድዮ ጣቢያ በሰጠው ቃለምልልስ አስታወቀ:: ድምጻዊው በትግርኛ ለሚተላለፈው ራድዮ በአማርኛ ቋንቋ በሰጠው ቃለምልልስ እንዳስታወቀው በዚህ ወር ለአሸንዳ በዓል እንደሚዘፍን በፖስተር የተለቀቀው ውሸት ነው ብሏል:: ከ እኔ እውቅና ውጭ በአሸንዳ በዓል ላይ እንደምዘፍን ተደርጎ በመቀሌ እየተቀሰቀሰ ያለው ውሸት ነው ሲል ያስተባበለው አብዱ እኔ በመቀሌ ኮንሰርት የማቀርበው ኦክቶበር ላይ ነው ብሏል:: በትግራይ ከሚተላለፍ የትግርኛ ኤፍ ኤም ራድዮ ላይ በአማርኛ ቋንቋ ያደረገው ቃለምልልስ ይኸው//:-

አብዱ ኪያር በመቀሌ ኮንሰርቱን ሊያቀርብ ነው

↧

(ሰበር ዜና) –በጎንደር ለምን ነጭ በነጭ ለበሳችሁ በሚል የትግራይ ነጻ አውጪ አልሞ ተኳሽ በወሰደው እርምጃ 4 ሰዎች በጥይት ተገደሉ | Video

$
0
0
በዛሬው እለት በጎንደር የአምባገነኑን መለስ ዜናዊን ሙት ዓመት አናከብርም ብለው ነጭ ልብስ በመልበሳቸው በአልሞ ተኳሾች ከተገደሉት 4 ሰወች አንደኛው::

በዛሬው እለት በጎንደር የአምባገነኑን መለስ ዜናዊን ሙት ዓመት አናከብርም ብለው ነጭ ልብስ በመልበሳቸው በአልሞ ተኳሾች ከተገደሉት 4 ሰወች አንደኛው::

(ዘ-ሐበሻ) በዛሬው እለት ጎንደር ከተማ የአቶ መለስ ዜናዊን ሙት ዓመት አናከብርም በሚል ለተቃውሞ ነጭ በነጭ ከለበሱት መካከል በአጋዚ ሰራዊት 4 ሰዎች በጥይት ተደብድበው ተገደሉ:: የአጋዚ ጥይት ሰለባ ከሆኑት መካከል አንዱ ወጣት ፎቶ በማሳት የሚተደደር ወጣት ግዛቸው የሚባል እንደሆነና ለምን ነጭ ልብስ ለበስክ በማለት ቀበሌ 03 አስተዳደር አካባቢ ከጓደኞቹ ነጥለው በአሰቃቂ ሁኔታ በጥይት ደብድበው ከገደሉት በኋላ አስከሬኑን ወደ ጎንደር ሆስፒታል ወስደው ጥለውት ተገኝቷል ሲሉ ዘ-ሐበሻ ያነጋገረቻቸው የአይን እማኞች ገልጸዋል::

የጎንደር ወጣትም አስከሬኑን ከሆስፒታል በማስወጣት ወደ ከተማው ይዘውት በመዞር ላይ እንዳሉ ወታደሮች በአስለቃሽ ጢስ የወጣውን ወጣት በጢስ በመበትን አስከሬኑን ቀምተው በመንግስት መኪና በመጫን ወስደውታል፡፡ ይህ የተደረገው ዛሬ ነሀሴ 14 ቀን 2008 ዓ.ም ከስዓት በሀዋላ ነው::

ዘ-ሐበሻ ከስፍራው ያነጋገረቻቸው አንድ ሰው እንደገለጹልን “አሁን ጎንደር ከተማ ውስጥ የሚንቀሳቀስ ሰው የለም ወታደር ብቻ፡፡ ይህን መረጃ የምሰጣችሁ እኔም የድርሻየን እንደ ኢትዮጵያዊነት የተሰማኝ ትልቅ ሃዘን ሆዴ ውስጥ ነው የሚሰማኝ ፡፡” ብለውናል::

↧

የዲሞክራሲ ቀለሞች –ከሽግግር እስከ ችግግር! |ዳዊት ከበደ ወየሳ (አትላንታ –አሜሪካ)

$
0
0
(ኢትዮጵያ ውስጥ በሚታተመው “አዲስ ገጽ” መጽሄት ላይ ወጥቶ የነበረ ጽሁፍ ነው)
 
በሽግግሩ መንግስት ወቅት የጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ፤ ከፓርላማው ወረድ ብሎ፤ ከቤተ መንግስቱ በአጓዳኝ፤ ወይም ወደ ግቢ ገብርኤል መሄጃ ላይ ይገኝ ነበር። ያን ሰሞን ከበአላት ወይም ቅዳሜና እሁድ በቀር የአዘቦት ቀናት በሰልፍ ይሞላሉ። ጋዜጦችና ጋዜጠኞች የየእለቱ ዘገባቸው ስለተደረጉት ዲሞክራሲያዊ ሰለሰልፎች ብቻ ሆነ። በኋላ ላይ የሰልፈኞቹ ነገር ቀስ በቀስ እየቀነሰ መጣና ነገሩ ቀዘቀዘ። ያን ሰሞን በሆነ ባልሆነ ሰላማዊ ሰልፍ የሚያደርጉም አልታጡም። 
 
አንድ ቀን ፓርላማው ጋር ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የተሰበሰቡ ሴቶችን የሚበትን የወያኔ ዋርድያ አጋጠመን። ሴቶቹን “ሂዱ” ሲሏቸው፤ “ዲሞክራሲያዊ መብታችን ነው። ደርግ ያፈነን አነሰና እናንተም…” እያሉ አንጃ ግራንጃ ሲፈጥሩ፤ የወያኔዎቹ አለቃ ድምጹን ከፍ አድርጎ… “ካላስ ተበተኑ!” ብሎ ንግግር ጀመረ። 
 
 “ቧ አልግሱ! ዲሞክራሲ ተወዲኡ!” ወይም በአማርኛ ትርጓሜው “በቃ ዞር በሉ! ዲሞክራሲ አልቋል” አላቸው። ይሄንን በወቅቱ በስፍራው ሆነን የታዘብን ጥቂት ሰዎች፤ በነገሩ ስቀን አለፍን። እየቆየን ስንመጣ ግን… ‘እውነትም ንፉግ መንግስት ነው ያለን፤ ለካ ዲሞክራሲም እንደ ስኳር ሬሽን ያልቃል!’ ብለን መገረማችን አልቀረም። 
 
በአጠቃላይ “የሴቶች መብት ይከበር” ከሚለው ጥያቄ ጀምሮ “የኢትዮጵያ ዳር ድንበር ቀይ ባህር ነው” እስከሚሉት መፈክሮች ድረስ ያስተናግድ የነበረው የአራት ኪሎ መንገድ ቀስ በቀስ ጭር እያለ መጣ። የሁለት አመቱ የሽግግር መንግስት ሲያበቃ የኛም ሰላማዊ ሰልፎች አበቁና ከሽግግር ወደ ችግግር በሰላም ተሻገርን። በችግግሩ ዘመን ቀስ በቀስ ወደ ሰላማዊ ኑሮ ተመለስን። ከሰላማዊ ኑሮ ወደ ሰላማዊ ትግል ስንሸጋገር ግን… መንግስት እና የመብት ጥያቄ ምን እና ምን እንደሆኑ ገና በጠዋቱ ተረዳነ – እነዚያ ፈቃድ እና ፈቃጅ ሳያስፈልጋቸው የተደረጉ ሰላማዊ ሰልፎችም፤ የሽግግሩ መንግስት ለሁለት አመታት እራሱን እንዲያረጋጋና ግዜ እንዲገዛ ረዱት እንጂ፤ ለህዝቡ አንዳች ነገር ጠብ አላለትም።
 
Gonder6
የዲሞክራሲ ቀለሞች – ከሽግግር እስከ ችግግር!
 
ዳዊት ከበደ ወየሳ (አትላንታ – አሜሪካ)
ኢህአዴግ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ… የ”አትነሳም ወይ?!” መዝሙሮች ተደምጠዋል፤ በርካታ የተቃውሞ ሰልፎች እና የስራ ማቆም አድማዎች ተደርገዋል። የተቃውሞ ሰልፉ ከመብዛቱ የተነሳ ሁሉንም መዘርዘር ያታክታል። ለምሳሌ “የአጼ ምኒልክ ሃውልት ይፍረስ” የሚሉ ሰዎች ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ። ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ብቻ ሳይሆን የሃውልቱን ዙሪያ በጥቁር ጨርቅ ሸፈኑት። ይህ ዜና ተብሎ በሬድዮ እና በቴሌቪዥን ቀረበልን።
ከዚህ በኋላ የኢህአዴግ ሹማምንት የህዝቡን የጩኸት ትርታ ለማዳመጥ ጸጥ ሲሉ፤ እኛ ደ’ሞ ‘ሃውልቱን በመድፍ እናፍርሰው ወይስ በቦንብ እንናደው ወይስ ዲሞክራሲያዊ መብቱን ጠብቀን በገመድ ጎትተን እንጣለው?’ እያሉ ብበምት የሚንሾካሾኩብን መሰለን። እንደእውነቱ ከሆነ ግን… ኦህዴድ እና ህወሃት በሃውልቱ መፍረስ ቢስማሙም፤ ኢህዴን (የአሁኑ ብአዴን) ሃሳቡን በመቃወም የራሱን ስብሰባ አደረገ። በዚህ ታሪካዊ ስብሰባ ላይ፤ “እኛ የታገልነው የምኒልክን ሃውልት ለማፍረስ ነው ወይ?” የሚል በሲቃ የታጀበ ንግግር ተደመጠ።
በዚህ ሁሉ ውዝግብ መሀል ግን… እኛ ጋዜጣችንን ለማሳተም የብርሃን እና ሰላም ማተሚያ ቤትን ደጀ ሰላም ስንጠና፤ በድንገት ታይቶ የማይታወቅ የኦሮሞ ፈረሰኞች ከኮተቤ፣ ከሱሉልታ እና ከሰላሌ ተሰባስበው… የአጼ ምኒልክ እና የእቴጌ ጣይቱን ፎቶ ከፊት ለፊት ይዘው፤ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማን እያውለበለቡ አራት ኪሎን አቋርጠው፣ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት በኩል አድርገው፤ ራስ መኮንን ድልድይን ተሻግረው፤ ወደ ምኒልክ ሃውልት  ተጓዙ። ብዙዎቻችን የዚህን ጉድ መጨረሻ ለማየት ፈረሰኞቹን ተከተልናቸው። ፈረሰኞቹ አራዳን አልፈው ከአጼ ምኒልክ ሃውልት ዘንድ ሲደርሱ ሃውልቱን ክብ እየዞሩ ቀረርቶ እና ጌራርሳ እያሰሙ፤ ከጥቂት ቀናት በፊት ሃውልቱ የተሸፈነበትን ጥቁር ጨርቅ ቀደው እና ቀዳደው ጣሉት። (ይህን ለምስክርነት የምንናገረው በወቅቱ  ኢዜአ ያልዘገበው… ህዝቡ በአይኑ የታዘበው፣ የሴቶች እልልታ የወንዶች ፉጨት ያጀበው ታሪካዊ ትእይንት ስለነበር ነው)
ከዚያ በኋላ እንኳንስ ሃውልቱ ሊፈርስ ቀርቶ፤ ጭራሽ ወርቃማ እና ብርማ ቀለም እንዲቀባ አደረጉ – ህዝቡና የልጅ እያሱ ልጅ። 
አጼ ምኒልክ በያዙት ጦርም ላይ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ተደርጎበት፤ ቢያንስ ለብዙ ወራት ቆየ። በጨዋታችን መጀመሪያ ላይ ይህን ጉዳይ የምናነሳሳው… የህዝብን ሃያልነት ማሳያ ምስክር እንዲሆነን ጭምር ነው። ሆኖም የዲሞክራሲ ቀለም ደምቆ እንዲዋብ ህዝቡ መብቱን አውቆ ማስከበር መቻል አለበት። አስቡት። በሽግግር መንግስቱ ዘመን የአጼ ምኒልክ ሃውልት ፈርሶ ቢሆን ኖሮ፤ እንደሌኒን ሃውልት የት እንደደረሰ ላይታወቅ ይችል ነበር። ክብር ሃውልቱን ለታደጉ ጀግኖች ሁሉ ይሁን።
እንዲህ የአገር ቅርስን በሰላማዊ ሰልፍ የማስተረፍ ስራ የመሰራቱን ያህል፤ ፈገግ የሚሰኙ አይነት ሰልፎችም ተካሂደው ነበር። ከእነዚህ አንዱ ጭር ሲል የማይወደው ኢህአዴግ ያዘጋጀው የህጻናት ሰላማዊ ሰልፍ ነው። ሰልፉ በሴቶች ቢሮ በኩል አድርጎ ለአደባባይ የበቃው፤ የእናት ጡት ወተትን አስፈላጊነት ግንዛቤ ለመፍጠር በሚል ነበር። እናም አንድ ቀን የአካባቢው ትምህርት ቤቶች ተዘግተው… የህጻናት ሰልፍ አራት ኪሎን እንዲያጨናንቅ ተደረገ። የህጻናቱም ጥያቄ አንድ እና አንድ ብቻ ሆነ። አንዷ “የእናት ጡት ለህጻናት!” ስትል ሁሉም በአንድ ድምጽ “የእናት ጡት ለህጻናት” እያሉ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ግቢ ደረሱ።
ከያዙት መፈክር ጎን፤ የተዘቀዘቁ ትላልቅ የጡጦ ስዕሎች አሉ። ሁሉም ደግመው ደጋግመው “የእናት ጡት ወተት ለህጻናት፡፡” የሚለውን መፈክር እንደውዳሴ ማርያም ይደጋግሙታል። እንዲህ እንዲህ እያሉ በጠቅላዩ ሚንስትር ደጃፍ ትንሽ ቆዩ። በኋላ ላይ የቴሌቪዥን ጋዜጠኞች በስፍራው መኖራቸውን ካረጋገጡ በኋላ የጠቅላይ ሚንስትሩ ተወካይ ሽክ ብለው መጡ። እንዲህም አሉ።
 “እርግጥ ነው። ህጻናት የእናት ጡት ወተት ያስፈልጋቸዋል።” ካሉ በኋላ የጠቅላይ ሚንስትሩ ተወካይ…የእናት ጡት ወተት ለህጻናት አስፈላጊ መሆኑን አስረዱ። “አሁንም የእናት ጡት ለህጻናት አስፈላጊ መሆኑን ስለተረዳን፤ የሽግግር መንግስቱ አስፈላጊውን ሁሉ ያደርግላችኋል።” ሲላቸው ከህጻናቱ ጋር የመጡት እናቶች አጨበጨቡ፤ ህጻናቶቹም ተንጫጩ። የሽግግር መንግስቱን አመስግነው ከመበተናቸው በፊት፤ ጋዜጠኞች ለአንዳንድ ህጻናት ጥያቄ አቀረብን። 
“ጥያቄያቹህ የእናት ጡት ወተት ማግኘት ነው። አሁን እንደሰማነው ‘የሽግግር መንግስቱ አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋል’ ተብሏል። እንዴት ታዩታላቹህ?” አልናቸው።
አንደኛው ህጻን ተገርሞ እኛንም ጓደኞቹንም እያየ፤ “የሽግግር መንግስቱ ጡት አለው እንዴ?” ሲል፤ እኛም ሆንን ጓደኞቹ ዛሬም ድረስ ያልመለስነውን ጥያቄ አቀረበልን።
እንዲህ አስቀው የሚያስቁንን ሰላማዊ ሰልፎች ወደ ጎን ትተን… ወደኋላ ተመልሰን ስንመለከት ግን… ከምንወቃቀስበት ጉዳይ ይልቅ የምንሞጋገስባቸው ጉዳዮች ብዙ አሉን። ከምንም በላይ “ጨርቅ” ተብላ የተንቋሸሸች ሰንደቅ አላማችን፤ ከወደቀችበት ተነስታ ከፍ ብላ መውለብለቧ ይሰመርበት።
በሽግግሩ ዘመን… የወቅቱ የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሃፊ ቡትሮስ ቡጥሮስ ጋሊ አዲስ አበባ መጥተው ነበር። የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችም “ኢትዮጵያ ህጋዊ የባህር በር ያስፈልጋታል” የሚል መሰረታዊ ጥያቄ ያነገበ ደብዳቤ አዘጋጅተው ሰላማዊ ሰልፋቸውን ስድስት ኪሎ ላይ ጀመሩ።
ሰልፉ ተጀምሮ ገና ከግቢው እንደወጡ አንድ ተማሪ ተገደለ (ተስፋሁን ይመስለኛል የተማሪው ስም)። ይህን ተከትሎ ብዙዎች ተደበደቡ፤ አካላቸውም ጎደለ። ምሽቱን በተላለፈው ዜና፤ የተገደለው የዩኒቨርስቲ ተማሪ የቀድሞ ደርግ ኢሰፓ የነበረ መሆኑን ሳያፍሩ ተናገሩ። ከዚያ ሁሉ ሺህ ህዝብ መሃል… “ኢሰፓ የሆነውን ነጥሎ የሚገድል ጥይት አለ እንዴ?” ብለን ተገርመን ሳናበቃ፤ “እንዲያውም ሟቹ ትምክህተኛ አማራ ነበር” አሉን። ቀጥሎም የወቅቱ ፕሬዘዳንት መለስ ዜናዊ በቲቪ ቀርበው እንዲህ አሉ።
“እኛ ሰልፈኞቹን በአስለቃሽ ጢስ ብንበትናቸው ደስ ይለን ነበር። ሆኖም ከደርግ መንግስት የተረከብነው አስለቃሽ ጢስ ሳይሆን፤ ታንክ እና ሚሳየል ነው።” ብለው የመጀመሪያ ቀልዳቸውን ከምር ነገሩን። እንደሳቸው አባባል፤ “እንደውም እኛ ሰልፉን በጥይት ስለበተንን ልንመሰገን ይገባል። ደርግ ቢሆን በታንክ ይረመርማቸው ነበር” የሚል አንደምታ ያለው ንግግር ነበር – ያሰሙን።
በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የሚከፈተው የጠመንጃ ላንቃ ግን፤ በተስፋሁን ላይ ተጀመረ እንጂ አላበቃም። በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ፤ ምንም ያላደረጉ ሰላማዊ ዜጎች በጠራራ ጸሃይ ጥይት እየተርከፈከፈ ተገድለዋል – “ክብር ለነሱ ይሁን” ሌላ ጉዳይ እናውጋ።
ከሽግግሩ ዘመን በኋላ “አባይ ተገንብቶ ለልማት ይዋል።” ስንል፤ በረከት ስምኦን ራሱ ቃል በቃል እንዲህ ብሎን ነበር። “በአባይ ወንዝ ላይ ግድብ ስሩ የሚሉ ቅዠታሞች አሉ። አባይ ቢገነባ ኢትዮጵያ በውሃ ተጥለቅልቃ እናልቃለን እንጂ፤ ምንም አናተርፍም።” ብሎ መግለጫ ጭምር ሰጥቶ ነበር። በኋላ ላይ የአባይ ግድብ ግንባታ ሲታወጅ፤ በረከት ስምኦን ዋና ተዋናይ ሆኖ፤ ጉዳዩን ለፖለቲካ ጥቅም ሲመነዝረው እያየን… “ወይ ግዜ” ያልንበት ወቅት እሩቅ አይደለም። በዚያም ተባለ በዚህ ግን ለሰንደቅ አላማችን ከፍ ማለትም ሆነ፤ ለአባይ መገደብ ትልቁ ምክንያት ሳያሰልስ ይታገል የነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ እንጂ፤ አብዮታዊ ዲሞክራሲ አለመሆኑን እነሱም ያውቁታል፤ እኛም እንመሰክራለን። በመሆኑም በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ህዝባዊ መብቱን ተጠቅሞ  የዲሞክራሲው ቀለም እንዲደምቅ፤ የህዝብ ፍላጎት እንዲጠበቅ ያደረገው የኢትዮጵያ ህዝብ… ከምንም በላይ ሊመሰገን ይገባዋል።
ከሽግግር መንግስት እስከ ችግግር ዘመናችን ድረስ ብዙ አሳልፈናል። አሁንም በትዝታ ወደ ሽግግሩ መንግስት ዘመን እንውሰዳቹህ። ከሃያ አመታት በፊት ነው። ብዙዎቹ ሰልፈኞች መፈክር እያሰሙ ወደ ጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ ያመራሉ። በወቅቱ ጠቅላይ ሚንስትር የነበሩት አቶ ታምራት ላይኔ ናቸው። ሰልፈኞቹ በመፈክራቸው መጀመሪያ  እና በደብዳቤያቸው መጨረሻ ላይ “የሽግግር መንግስቱን ቻርተር እንደግፋለን” የሚል ሙሻሙሾ የሚያወርዱ ከሆነ፤ የሰልፈኞቹ ተወካዮች ወደ ውስጥ እንዲገቡ ያደርጉና ያናግሯቸዋል።’
ሰልፉን እራሱ ኢህአዴግ ያቀናበረው ከሆነ ደግሞ ሃያ እና ሰላሳ ሰው ያለበትም ቢሆን፤ በሬድዮ፣ በቲቪ፣ በጋዜጣም ጭምር ስለሰላማዊ ሰልፉ ብዙ ይባልለታል። ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ከሚሆኑት መካከል፤ “ፓትርያርኩ ስልጣናቸውን እንዲለቁ ሰላማዊ ሰልፈኞች ጠየቁ” የሚለው ዜና አንደኛው ነበር።
በምሽቱ ዜና ላይ… “ፓትርያርኩን በመቃወም ከወጡት ሰልፈኞች መካከል አንዳንዶቹ እንዲህ በማለት አስተያየት ሰጥተዋል።” ይባልና… በቃለ መጠይቁ ላይ የሚቀርቡት ሰዎች፤ “ፓትርያርኩ በደርግ ዘመን ያገለገሉ ስለሆኑ አንቀበላቸውም” ይላል አንደኛው። ሌላኛው አስተያየት ሰጪ… “የደርግ ኢሰፓ አባል ናቸው” ብሎ ይከሳቸዋል። ቀጥሎ ያለው ደግሞ “ከስልጣናቸው ወርደው ለፍርድ ይቅረቡ” በማለት ይደነፋል። አቡነ መንቆርዮስም ይህን ድራማ አዘል የተቃውሞ ሰልፍ ማታ ላይ በቲቪ ሲመለከቱ ልባቸው ተሰብሮና መንፈሳቸው ተሸብሮ፤ በንጋታው ኢትዮጵያን ለቀው ወደ ጎረቤት አገር እንዲሰደዱ የተደረጉበትን፤ በ’ሳቸውም መንበር አባ ጳውሎስ እንዲተኩ የተደረገበትን ድራማ እንደትላንት የምናስታውስ ብዙዎች ነን።
በሌላ በኩል ደግሞ… የኢትዮያን ህዝብ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚደረጉ ሰላማዊ ሰልፎች…  በማንም በምንም አይነት ተቀባይነት አይኖቻውም ነበር። ከኤርትራ የተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ፤ ከስራ የተባረሩ ሰራተኞች፤ ጡረታቸውን የተነጠቁ አባቶች፤ በብሄራቸው የተገፉ ዜጎች፤ ኢትዮጵያዊነትነት ከፍ አድርገው የዘመሩ የሌላ ብሔር አባሎች… የ’ነዚህ ሰዎች ጩኸት የውሃ ሽታ ሆኖ ቀርቷል። “መብታችን ይከበር” የሚሉ ድምጾች በአራት ኪሎ ጎዳና ላይ ብዙ ተደምጠዋል። አንዳንዶቹ ምላሽ ሲያገኙ፤ የተቀሩት ደግሞ ጩኸት ብቻ ሆነው ቀርተዋል። በኋላ በኋላ ላይ… የማይቀረው ህዝባዊ መዝሙር እና መፈክር የአራት ኪሎን ግቢ ሲያነቃንቀው “ጠቅላይ ሚንስትሩ ስራ ላይ ናቸው… አትጩኹ” በሚል የታጠቁ የወያኔ ሰዎች ወደላይ እየተኮሱ ጩኸቱን ይብሱን አባብሰው ሰልፍ መበተን ጀመሩ። 
በጋዜጠኝነታችን የህዝቡን ድምጽ ለማሰማት፤ በስፍራው ተገኝተን ክፉና ደግ መታዘባችን አልቀረም።  ሰላማዊ ሰልፈኞች ሰፈር አቋርጠው ሲመጡ በእጃቸው መፈክር ተሸክመው፤ አንዳንዶችም ዘንባባና የዛፍ ቅጠል ይዘው ‘ሆ’ እያሉ ጠቅላይ ሚንስትሩ ሰፈር ይደርሳሉ። እዚያ ሲደርሱ መጮህ ስለማይቻል ተወካዮቻቸው ወደ ውስጥ እስከሚገቡ ወይም ደብዳቤውን እስከሚያስረክቡ ድረስ፤ አገር ሙሉ ሰልፈኛ ጥላ ፍለጋ በየአጥሩ ጥግ ለሰአታት ያህል ይቀመጣል። በዚህ አይነት መሰላቸት ሰአታት ያልፉና ሰልፈኞች ወደየጉዳያቸው ይበተናሉ። ከየመንደሩ ይዘዋቸው የመጡት ቁሳቁሶች፤ የካርቶን ላይ ጽሁፎች፣ የወረቀት ስእሎች፣ የጨርቅ ላይ መፈክሮች እዚያው ይጣሉና አካባቢው እብድ የጨፈረበት ገበያ ይመስላል። ሰልፈኞቹ ከተበተኑ በኋላ ወረቀትና ጨርቁን የሚሰበስቡ ሰዎች ይመጡና ያን ሁሉ ግሳንግስ ሰብስበው ያቃጥሉታል። ልክ እንደተቃጠሉት የመፈክር ካርቶኖች… በሽግግር መንግስቱ እና ከዚያ በኋላ የተነሱ በርካታ ህዝባዊ ጥያቄዎች፤ ምላሽ ሳያገኙ ዶግ አመድ ሆነዋል። ብዙዎቹ የ”መብታችን ይከበር” ጥያቄዎች ግን ከወረቀት ባለፈ፤ በህዝብ ልብ ላይ  የታተሙ በመሆናቸው በውድ ሳይሆን በግድ ተከብረዋል። 
እነዚህ ተሸራርፈውም ቢሆን… ለአጭር ግዜም ቢሆን… ብልጭ ድርግም እያሉም ቢሆን… ህዝቡ እንዲከበሩለት ያደረጋቸው መሰረታዊ የመብት ጥያቄዎች… ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት፤ የመሰብሰብ እና የመደራጀት፣ በነጻ ዳኝነት ፍርድ ማግኘት፣ የሰብአዊ መብት ጥበቃ እና የህዝባዊ ስልጣን መረጋገጥ ናቸው። “እነዚህ የመብት ጥያቄዎች በተገቢው መልክ ተግባራዊ ሆነዋል” ብሎ ክርክር የሚገጥም ካለ ውሸታም እንጂ ሌላ ስም አይሰጠውም። ነገር ግን እነዚህ የዲሞክራሲ ደማቅ ቀለም የሆኑ የመብት ጥያቄዎች፤ መንግስት በቸርነቱ ሳይሆን፤ ህዝብ በእምቢ ባይነቱ ያገኛቸው የትግል ስጦታዎች ሆነዋል፤ ይህ እውነት ነው። ‘እነዚህ መብቶች በመንግስት በኩል ከመከበር ይልቅ ተሸርሽረው ተሸርሽረው እያለቁ ናቸው።’ ብንል ይህም ሌላ እውነት ነው።
እውነትን መደርደር የሚያስጣላ እና የሚያከራክር ነገር አይደለም። ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት መንግስት የሚያሳስበው ባይሆን ኖሮ፤ ሌላ ተዛማጅ እና ግራ ተራማጅ ህጎች ማውጣት ባላስፈለገው ነበር። ህገ መንግስቱ ሲረቅና ሲጻፍ ሁሉንም ወገን የሚያረካ ሆኖ አልተዘጋጀም። ቢያንስ ቢያንስ ግን… የሰው ልጅ ሰብአዊ መብቶች እንደሚከበሩ ይደነግጋል። ይህ ደግሞ በቀዳማዊ ኃይለስላሴም ሆነ በደርግ ህገ መንግስት ላይ በግልጽ የተካተተ ነው። ነገር ግን እነዚህ መሰረታዊ መብቶች በጽሁፍ እንጂ በተግባር ባልተረጋገጡባት አገር… በአሳዛኝ መልኩ ትውልድ አልፎ ትውልድ በመተካት ላይ ይገኛል። እንደእውነቱ ከሆነ… ሰብአዊ መብት፣ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት፣ የፍትህ፣ የመሰብሰብ እና የመደራጀት መብት ሙሉ ለሙሉ ያልተረጋገጠባት  አገር፤ “ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ” የሚለውን ስም ለመሸከም አቅም አይኖራትም። ይህን እያልን… መብታችን እየተበዘበዘ፤ የዲሞክራሲ ቀለም እየደበዘዘ ሊሄድ ይችል ይሆናል። ይህ ግን ለዘላለሙ አይቀጥልም። የሰው ልጅ… እስከልጅ ልጁ እየተረገጠ ሊገዛ አይችልምና… ጨለማ በጠዋት ጮራ እንደሚገፈፍ ሁሉ… የደበዘዘው የዲሞክራሲ ቀለም የሚደምቅበት ምዕራፍ ቀስ በቀስ መምጣቱ የተፈጥሮ ግዴታ ነው።
ከማጠቃለላችን በፊት የዚህን ጽሁፍ ዋና መልእክት እዚህ ላይ ለማስፈር ወደድን። ኢህአዴግ አዲስ አበባ እንደገባ ጥቂት ግዜ ቆይቶ የሽግግር መንግስት አቋቋመ። እኛም (አብዱራህማን አህመዲን እና ሙሼ ሰሙ) ጋር በመሆን “የኢትዮጵያ ወጣቶች ህብረት” የሚባል ሊግ አቋቋምን። አላማችን ወጣቱን በኢትዮጵያዊነት ዙሪያ ማሰባሰብ ነበር። እንደታሰበውም በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ወጣቶች ህብረቱን ተቀላቀሉ። እንቅስቃሴው አዲስ አበባን አዳረሰ። ስብሰባ የምንጠራባቸው አዳራሾች እስከአፍንጫቸው ድረስ እየሞሉ ህዝቡ በውጭ ሆኖ ስብሰባውን ይከታተል ጀመር። ይህ ሁሉ ሲሆን ግን ከመንግስት የምዝገባም ሆነ የስብሰባ ፈቃድ ተሰጥቶን አያውቅም። (በ’ርግጥ  ኢህአዴግ፤ በኋላ ላይ ሊጉን በጉልበት አፈረሰው) ወጣትነት ደፋር ያደርጋል። የመሰብሰብ እና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብታችንን መንግስት እንዲሰጠን ስላልፈለግን እኛም በህዝብ ጉልበት መብታችንን አስከበርን። ከምንም በላይ ግን፤ “መንግስት መብት ይሰጥሃል እንጂ፤ መብትህን አያስጠብቅልህም።” የሚለው መመሪያችን ተስማምቶናል። እውነት ነው። መንግስት መብትህን በህግ እና በህገ መንግስት ላይ ጽፎ ይሰጥሃል እንጂ፤ መብትን የማስጠበቅ ሃላፊነት የሚጣለው በ’ያንዳንዱ ግለሰብ እና ማህበረሰብ ላይ ይሆናል። 
መሰረታዊ መብቶቻችን በህጉ እና በህገ መንግስቱ ላይ እንዲሰፍሩ ትውልድን የተሻገረ ትግል ተካሂዷል። እነዚህን መብቶች በውድም ሆነ በግድ ተግባራዊ ስናደርግ፤ አምባገነናዊ አስተዳደር እየወደቀ፤ የዲሞክራሲ ቀለም እየደመቀ ይሄዳል። ከሽግግሩ መንግስት እስከ ችግግሩ ዘመን ድረስ የሄድንበት መንገድ… የግል እና የወል መብትን የማስጠበቅ ታሪክን የያዘ ባለብዙ ምእራፍ ታሪክ ነው። በሁሉም ምእራፎች መብታችንን ለመጨፍለቅ ጥረት ሲደረግ እንጂ ስንወድቅ አልታየንም። አሁንም ከመጨረሻው ምእራፍ በፊት የመጨረሻውን ጩኸት እየጮሁ፤ “በህግ አምላክ!” የሚሉ ደፋሮች አልታጡም። የ’ነሱ ጩኸት ከዳር እስከዳር እንዲደመጥ፤ የለኮሱት ሻማ ብርሃን እንዲሰጥ… የዲሞክራሲ ቀለሞች በብዕሮቻቸው ጫፍ እንዲደምቅ ለሚያደርጉት ትግል ህዝቡ ሊያግዛቸው ይገባል።  
በአጠቃላይ ከሽግግር መንግስት እስከ ችግግር ዘመናችን ድረስ ብዙ ግዜ ወድቀን፤ ብዙ ግዜ ተነስተናል። በዚህ የቀራንዮ መንገድ ላይ ብዙዎች ወድቀው ቀሩ፣ ሌሎች መንገዳቸውን ቀየሩ። አንዳንዶች ሞቱ፤ ሌሎች ታሰሩ፤ ቀንበሩ የከበደን አገር ለቀን ተሰደድን። እንዲህም ሆኖ ከያለንበት የምንጮኸው ወድቀን እንዳልቀረን ለማብሰር ጭምር ነው። የዲሞክራሲ ቀለሞች እስከሚደምቁ ድረስ ድምጻችንን እናሰማለን። እንደዘፈን አዝማች፤ “መንግስት መብት ይሰጥሃል እንጂ፤ መብትህን አያስጠብቅልህም።” እንላለን። ጎበዝ! እንግዲህ ለራስህ እወቅበት።
 
(ይህ ጽሁፍ ከወራት በፊት፤ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚታተመው አዲስ ገጽ ጋዜጣ ላይ ወጥቷል። ጽሁፉ በተዘጋጀበት ወቅት፤ በኦሮሚያ ተጀምሮ በአማራ ክልል እየተቀጣጠለ ያለው፤ ህዝባዊ አመጽ አሁን ያለበትን አይነት መልክ ገና አልያዘም። ይህ ጽሁፍ ሰሞኑን የተዘጋጀ ቢሆን ኖሮ፤ የ’ነዚህን ህዝባዊ አመጾች ቀለም ያካትት ነበር። አሁንም ቢሆን “መንግስት መብት ይሰጥሃል እንጂ፤ መብትህን አያስጠብቅልህም። መብቱን የሚያስከብረው እያንዳንዱ ዜጋ በግል፤ ህብረተሰቡን በወል ሆኖ ነው።” የሚለው ቀለም ደምቆ ወጣ እንጂ አልደበዘዘም። ስለሆነም ከትላንት እስከዛሬ በሰላማዊ መንገድ ድምጻቸውን ሲያሰሙ ለነበሩ፤ በዚህ ሂደትም መስዋዕት ለሆኑ ውድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ… ይህ ጽሁፍ ለነሱ መታሰቢያ ይሁንልን። ክብር ለ’ነሱ ይሁን!)
↧

ህወሃት በሕዝብ ላይ የደገሰው በዶ/ር ደብረጽዮን አንደበት |ከክንፉ አሰፋ

$
0
0

debrestion

        ባለፈው ሳምንት ጌታቸው ረዳ ከአልጃዚራ ቴሌቭዥን ጋዜጠኛ ጋር ተጋፍጦ ነበር። አንድ ጥያቄ ቀረበለት።”በራሳችሁ የምትተማማኑ ከሆነ ለምን የተባበሩት መንግስታት ታዛቢዎች እንዳይገቡ ከለከላችሁ?”

        ምኒስቴር ጌታቸውም። “የተባበሩት መንግስታት አያስፈልገንም። እኛው ራሳችን ከህዝቡ ጋር እንነጋገራለን።” ሲል ነበር የድፍረት መልስ የሰጠው። 

        ይህ የትእቢት መልስ ለጋዜጠናዋ እንግዳ ኢሆንም፣  ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን ግልጽ ነበር። እነሆ ከህዝብ ጋር ንግግር  መጀመራቸውን እያሳዩን ነው።  እንደ ፋሺሽት ጣልያን በከባድ መሳርያ ሕዝብን ለመደብደብ ቆርጠው መነሳታቸውን ተመልከቱ።  

        በምክትል ጠቅላይ ምንስቴርነት ማእረግ ሃገሪቱን የጠቆጣጠሩት ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረ ማርያም በዛሬው እለት በፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ አንድ የጦር አዋጅ አስነብበውናል። በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ተታወጀ ጦርነት። የጦርነት መግለጫው እንዲህ ይነበባል፤

“ጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን የሀገራችንን ሰላም ለማረጋገጥ ከመቸውም ጊዜ በላይ በነቃ እና በተጠናከረ ሁኔታ በመንቀሳቀስ፤ በቅርቡ በሃገራችን የተከሰቱ አመፆችን ስልታዊ በሆነ መልኩ ሥርዓት በማስያዝ ላይ ይገኛል።በየክልሉ የሚነሡ ረብሻዎችን ሰበብ በማድረግ በአንድ ብሔር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በመካሄድ ላይ ይገኛል። በተለይም ብጥብጡ ከበረታባቸው አካባቢዎች የጎንደር ነውጥ በጉልህ የሚጠቀስ ሲሆን ሠራዊታችን ከነውጠኞች ጋር ያደረገውን ፍልሚያ በጀግንነት እየተወጣ ይገኛል። ከዚህ ጋር በተያያዘ አመፅ ፈጣሪ የሆኑ አካባቢዎችን በመለየት የጦር መሣርያ የማስፈታቱ ሂደት የመንግሥት የቅርብ የቤት ሥራ ይሆናል። እንደዚህ ዓይነት ሥርዓት አልበኝነትን የማክሸፉ ሂደት በተጠናከረ ሁኔታ የሚቀጥል ነው የሚሆነው። ድል ለመከላከያ ሠራዊታችን!”

የዚህ “አዋጅ” ትርጉም ግልጽ ነው። የሕዝበን ጥያቄ በማሳርያ ለመስበር ከመቸውም ጊዜ በላይ መነሳታቸውን ነው ደብረጽዮን ያሳወቁን። በአጭሩ ለአራትና አምስት ሰዎች ደህንነት ሲባል በመላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ጦርነት ለመግጠም የተሰጠ መግለጫ ነው። 

        ከዚህ ቀደም ውስጥ ለውስጥ ይናገሩት የነበረውን ምስጢራቸውን አሁን በይፋ በአደባባይ መናገር መፈለጋቸው አንድ ከበድ ያለ ችግር ውስጥ እንዳሉ ያሳየናል።  እንዲህ አይነት ድፍረት የተሞላበት ንግግር በአደባባይ ወጥተው የመናገራቸው ምክንያትም ምስጢር አይደለም። የህወሃት የውስጥ ምስጢሮች ሁሉ በራሳቸው ሰዎች እየሾለኩ ወደ መገናኛ ብዙሃን መድረሳቸው ይመስላል ለእንዲህ አይነት ንቀት እና ድፍረት ያበቃቸው። 

        የፌስቡኩ ሚንስቴር ቴድሮስ አድሃኖምም ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ የጦር አዋጅ አሰምቶን ነበር፤

“..ይህንን ምክንያት በማድረግ የሚነሡ ረብሻዎችን መንግሥት ለመታገስ የሚቸገር በመሆኑ ሕግ የማስከበር ኃላፊነቶቹን በመወጣት ላይ ይገኛል። ነፍጠኛ አመለካከት ባላቸው ኃይሎች የሚነሣ አመጽ ምንጊዜም ቢሆን መድረሻው ከሁለትና ሦስት ቀን ያልበለጠ ግርግርና ረብሻ ነው።  … በመሆኑም መንግሥታችን ነፍጠኝነትን ለአንዴና ለመጨረሻ ከሀገሪቱ ለማጥፋት በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።

ልብ በሉ ሕዝባዊ አመጹ እየተካሄደ ያለው በመላው ኢትዮጵያ ነው።  እነዚህ  የህወሃት ምኒስትሮች እየነገሩን ያለው ደግሞ ይህንን ህዝብ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ግዜ እንደመስሰዋለን  ነው።

እነዚህን ጠባቦች እንደ መንግስት ለሚመለከቱት ሁሉ ጄኔራል ፃድቃን ገብረተንሳይ መልስ የሰጠ ይመስለኛል። በቅርቡ በኢንተርነት በለቀቀው ጽሁፍ ጄኔራል ፃድቃን እንዲህ ብሎናል።

… በርከት ባሉ የትግራይ ተወላጆች የሚነሳ አንድ ጥያቄ አለ። ይኸውም አሁን ባለው መንግስት ላይ ያለንን “የበላይነት” ካጣን ጠቅላላ መብቶቻችን አንድናጣ መልሰን እንድንጨቆን አድልዎ እንዲፈፀምብን ቢደረግስ ምን ዋስትና አለን? የሚል ነው። ዋስትናችን በትግላችን ያገኘነው አሁንም ከሌሎች ህዝቦች ጋር ሆነን እየታገልን የምንጠብቀው ሕገ-መንግስታችን ያለምንም ማቅማማት ተግባራዊ ማድረግ ነው።…

ሕገ-መንግስታችን የሚሉት ስልጣን ለማለት ነው። የስልጣን ወይም ሞት ምስጢሩም ይህ ነው።

በሕዝብ ላይ ጦርነቱን ጀምረውታል። ውጤቱን ደግሞ በቅርብ የምናየው ይሆናል። ከህዝባቸው ጋር ውግያ ገጥመው የዘለቁ አንባገነኖች ከተፈጠሩ እነዚህ የመጀመርያዎቹ ይሆናሉ።

↧
↧

ቢቢኤን ሰበር ዜና –ጎንደር ዳግም ተቃውሞ ተቀሰቀሰ |ግድያውም ቀጥሏል

$
0
0

በዛሬው እለት በጎንደር የአምባገነኑን መለስ ዜናዊን ሙት ዓመት አናከብርም ብለው ነጭ ልብስ በመልበሳቸው በአልሞ ተኳሾች ከተገደሉት 4 ሰወች አንደኛው::

በዛሬው እለት በጎንደር የአምባገነኑን መለስ ዜናዊን ሙት ዓመት አናከብርም ብለው ነጭ ልብስ በመልበሳቸው በአልሞ ተኳሾች ከተገደሉት 4 ሰወች አንደኛው::

↧

አዲስ አበባ : የአዲስ አበባ ልጅ ነኝ

$
0
0

14102347_10206973158153743_6094082353928561593_nአዱ ገነት የምድር እምብርት ፥ የፍቅር አድባር ፥ የመተሳሰብ እና ያንድነታችን መቀነት። የህብረታችን ዜማ ፥ የውህደታችን ቅኔ ፥ ጅረት ከሚፈስበት ሰፈር ነው የተፈጠርኩት እኔ ! አዲስ አባባ ፥ እስላሙ እና ክርስቲያኑ ድርጅት ሳይሆን ህይወት ፥ ጥርነፋ ሳይሆን ኑሮ ባስተሳሰረው ፥ ታሪክ ባመሳሰለው የማንነት ፍሰት ውስጥ ባንድነት ዧ ብሎ የሚፈስ የብርሃን ጎርፍ የሚመስል ህዝብ ያለበት ከተማ! አዲስ አበባ ። አዲስ አባባ ወንድሞቼ ፥ እህቴ ፥ እናት እና አባቴ የሚኖሩበት ፥ እንዲህ ትግል ሲኖር ደግሞ ታግለው የሚሞቱባት ከተማ ነች ! የልጅነት አሻራዬን ፥ የእግሮቼን ዱካ እየለካች ያሳደገችኝ መንደሬ ያለችው እዛው አዲስ አበባ ነው ። ለፋሲካ እና ለኢድ የሁለት እምነት ድስት የተጣደባት መንደር አዲስ አበባ ነች ። የወያኔን ገበና ፍንትው አድርጋ ማንነቱን ገሃድ ያወጣች ከተማ አዲስ አበባ ነች ። አዲስ አበባ የታጋዮች ከተማ!
አዲስ አባባ የኔ ሰፈር! በተዘጉ ቤቶች ውስጥ መፅሃፍ ስናጥብ ያደርንብሽ ከተማ። ወያኔ ላይ ስናሴር የዋልንብሽ ሰፈር ። የማንተቴን ትዝታ አቅፈሽ የያዝሽ ፥ እኔን የሰራሽ ፥ የኄኖክ ደጀ ሰላም ፥ አዱ ገነት ! ከጎንሽ ቆመን እጃችንን ባናወጣም ፥ ላንቺ የሚሆን አንድ ዘለላ አንጓ ቅኔ ግን አናጣም!
አዲስ ነውና ስምሽ
አዲስ ሁኝ እባክሽ!

↧

የዲሞክራሲ ቀለሞች –ከሽግግር እስከ ችግግር! –ዳዊት ከበደ ወየሳ (አትላንታ –አሜሪካ)

$
0
0
(ኢትዮጵያ ውስጥ በሚታተመው “አዲስ ገጽ” መጽሄት ላይ ወጥቶ የነበረ ጽሁፍ ነው)
 
በሽግግሩ መንግስት ወቅት የጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ፤ ከፓርላማው ወረድ ብሎ፤ ከቤተ መንግስቱ በአጓዳኝ፤ ወይም ወደ ግቢ ገብርኤል መሄጃ ላይ ይገኝ ነበር። ያን ሰሞን ከበአላት ወይም ቅዳሜና እሁድ በቀር የአዘቦት ቀናት በሰልፍ ይሞላሉ። ጋዜጦችና ጋዜጠኞች የየእለቱ ዘገባቸው ስለተደረጉት ዲሞክራሲያዊ ሰለሰልፎች ብቻ ሆነ። በኋላ ላይ የሰልፈኞቹ ነገር ቀስ በቀስ እየቀነሰ መጣና ነገሩ ቀዘቀዘ። ያን ሰሞን በሆነ ባልሆነ ሰላማዊ ሰልፍ የሚያደርጉም አልታጡም።
አንድ ቀን ፓርላማው ጋር ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የተሰበሰቡ ሴቶችን የሚበትን የወያኔ ዋርድያ አጋጠመን። ሴቶቹን “ሂዱ” ሲሏቸው፤ “ዲሞክራሲያዊ መብታችን ነው። ደርግ ያፈነን አነሰና እናንተም…” እያሉ አንጃ ግራንጃ ሲፈጥሩ፤ የወያኔዎቹ አለቃ ድምጹን ከፍ አድርጎ… “ካላስ ተበተኑ!” ብሎ ንግግር ጀመረ።
 “ቧ አልግሱ! ዲሞክራሲ ተወዲኡ!” ወይም በአማርኛ ትርጓሜው “በቃ ዞር በሉ! ዲሞክራሲ አልቋል” አላቸው። ይሄንን በወቅቱ በስፍራው ሆነን የታዘብን ጥቂት ሰዎች፤ በነገሩ ስቀን አለፍን። እየቆየን ስንመጣ ግን… ‘እውነትም ንፉግ መንግስት ነው ያለን፤ ለካ ዲሞክራሲም እንደ ስኳር ሬሽን ያልቃል!’ ብለን መገረማችን አልቀረም።
 
በአጠቃላይ “የሴቶች መብት ይከበር” ከሚለው ጥያቄ ጀምሮ “የኢትዮጵያ ዳር ድንበር ቀይ ባህር ነው” እስከሚሉት መፈክሮች ድረስ ያስተናግድ የነበረው የአራት ኪሎ መንገድ ቀስ በቀስ ጭር እያለ መጣ። የሁለት አመቱ የሽግግር መንግስት ሲያበቃ የኛም ሰላማዊ ሰልፎች አበቁና ከሽግግር ወደ ችግግር በሰላም ተሻገርን። በችግግሩ ዘመን ቀስ በቀስ ወደ ሰላማዊ ኑሮ ተመለስን። ከሰላማዊ ኑሮ ወደ ሰላማዊ ትግል ስንሸጋገር ግን…  መንግስት እና የመብት ጥያቄ ምን እና ምን እንደሆኑ ገና በጠዋቱ ተረዳነ – እነዚያ ፈቃድ እና ፈቃጅ ሳያስፈልጋቸው የተደረጉ ሰላማዊ ሰልፎችም፤ የሽግግሩ መንግስት ለሁለት አመታት እራሱን እንዲያረጋጋና ግዜ እንዲገዛ ረዱት እንጂ፤ ለህዝቡ አንዳች ነገር ጠብ አላለትም።
 ———————–//—————————-
የዲሞክራሲ ቀለሞች – ከሽግግር እስከ ችግግር!
ዳዊት ከበደ ወየሳ (አትላንታ – አሜሪካ)
ethiopia
ኢህአዴግ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ… የ”አትነሳም ወይ?!” መዝሙሮች ተደምጠዋል፤ በርካታ የተቃውሞ ሰልፎች እና የስራ ማቆም አድማዎች ተደርገዋል። የተቃውሞ ሰልፉ ከመብዛቱ የተነሳ ሁሉንም መዘርዘር ያታክታል። ለምሳሌ “የአጼ ምኒልክ ሃውልት ይፍረስ” የሚሉ ሰዎች ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ። ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ብቻ ሳይሆን የሃውልቱን ዙሪያ በጥቁር ጨርቅ ሸፈኑት። ይህ ዜና ተብሎ በሬድዮ እና በቴሌቪዥን ቀረበልን።
ከዚህ በኋላ የኢህአዴግ ሹማምንት የህዝቡን የጩኸት ትርታ ለማዳመጥ ጸጥ ሲሉ፤ እኛ ደ’ሞ ‘ሃውልቱን በመድፍ እናፍርሰው ወይስ በቦንብ እንናደው ወይስ ዲሞክራሲያዊ መብቱን ጠብቀን በገመድ ጎትተን እንጣለው?’ እያሉ ብበምት የሚንሾካሾኩብን መሰለን። እንደእውነቱ ከሆነ ግን… ኦህዴድ እና ህወሃት በሃውልቱ መፍረስ ቢስማሙም፤ ኢህዴን (የአሁኑ ብአዴን) ሃሳቡን በመቃወም የራሱን ስብሰባ አደረገ። በዚህ ታሪካዊ ስብሰባ ላይ፤ “እኛ የታገልነው የምኒልክን ሃውልት ለማፍረስ ነው ወይ?” የሚል በሲቃ የታጀበ ንግግር ተደመጠ።
በዚህ ሁሉ ውዝግብ መሀል ግን… እኛ ጋዜጣችንን ለማሳተም የብርሃን እና ሰላም ማተሚያ ቤትን ደጀ ሰላም ስንጠና፤ በድንገት ታይቶ የማይታወቅ የኦሮሞ ፈረሰኞች ከኮተቤ፣ ከሱሉልታ እና ከሰላሌ ተሰባስበው… የአጼ ምኒልክ እና የእቴጌ ጣይቱን ፎቶ ከፊት ለፊት ይዘው፤ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማን እያውለበለቡ አራት ኪሎን አቋርጠው፣ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት በኩል አድርገው፤ ራስ መኮንን ድልድይን ተሻግረው፤ ወደ ምኒልክ ሃውልት  ተጓዙ። ብዙዎቻችን የዚህን ጉድ መጨረሻ ለማየት ፈረሰኞቹን ተከተልናቸው። ፈረሰኞቹ አራዳን አልፈው ከአጼ ምኒልክ ሃውልት ዘንድ ሲደርሱ ሃውልቱን ክብ እየዞሩ ቀረርቶ እና ጌራርሳ እያሰሙ፤ ከጥቂት ቀናት በፊት ሃውልቱ የተሸፈነበትን ጥቁር ጨርቅ ቀደው እና ቀዳደው ጣሉት። (ይህን ለምስክርነት የምንናገረው በወቅቱ  ኢዜአ ያልዘገበው… ህዝቡ በአይኑ የታዘበው፣ የሴቶች እልልታ የወንዶች ፉጨት ያጀበው ታሪካዊ ትእይንት ስለነበር ነው)
ከዚያ በኋላ እንኳንስ ሃውልቱ ሊፈርስ ቀርቶ፤ ጭራሽ ወርቃማ እና ብርማ ቀለም እንዲቀባ አደረጉ – ህዝቡና የልጅ እያሱ ልጅ።
አጼ ምኒልክ በያዙት ጦርም ላይ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ተደርጎበት፤ ቢያንስ ለብዙ ወራት ቆየ። በጨዋታችን መጀመሪያ ላይ ይህን ጉዳይ የምናነሳሳው… የህዝብን ሃያልነት ማሳያ ምስክር እንዲሆነን ጭምር ነው። ሆኖም የዲሞክራሲ ቀለም ደምቆ እንዲዋብ ህዝቡ መብቱን አውቆ ማስከበር መቻል አለበት። አስቡት። በሽግግር መንግስቱ ዘመን የአጼ ምኒልክ ሃውልት ፈርሶ ቢሆን ኖሮ፤ እንደሌኒን ሃውልት የት እንደደረሰ ላይታወቅ ይችል ነበር። ክብር ሃውልቱን ለታደጉ ጀግኖች ሁሉ ይሁን።
እንዲህ የአገር ቅርስን በሰላማዊ ሰልፍ የማስተረፍ ስራ የመሰራቱን ያህል፤ ፈገግ የሚሰኙ አይነት ሰልፎችም ተካሂደው ነበር። ከእነዚህ አንዱ ጭር ሲል የማይወደው ኢህአዴግ ያዘጋጀው የህጻናት ሰላማዊ ሰልፍ ነው። ሰልፉ በሴቶች ቢሮ በኩል አድርጎ ለአደባባይ የበቃው፤ የእናት ጡት ወተትን አስፈላጊነት ግንዛቤ ለመፍጠር በሚል ነበር። እናም አንድ ቀን የአካባቢው ትምህርት ቤቶች ተዘግተው… የህጻናት ሰልፍ አራት ኪሎን እንዲያጨናንቅ ተደረገ። የህጻናቱም ጥያቄ አንድ እና አንድ ብቻ ሆነ። አንዷ “የእናት ጡት ለህጻናት!” ስትል ሁሉም በአንድ ድምጽ “የእናት ጡት ለህጻናት” እያሉ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ግቢ ደረሱ።
ከያዙት መፈክር ጎን፤ የተዘቀዘቁ ትላልቅ የጡጦ ስዕሎች አሉ። ሁሉም ደግመው ደጋግመው “የእናት ጡት ወተት ለህጻናት፡፡” የሚለውን መፈክር እንደውዳሴ ማርያም ይደጋግሙታል። እንዲህ እንዲህ እያሉ በጠቅላዩ ሚንስትር ደጃፍ ትንሽ ቆዩ። በኋላ ላይ የቴሌቪዥን ጋዜጠኞች በስፍራው መኖራቸውን ካረጋገጡ በኋላ የጠቅላይ ሚንስትሩ ተወካይ ሽክ ብለው መጡ። እንዲህም አሉ።
 “እርግጥ ነው። ህጻናት የእናት ጡት ወተት ያስፈልጋቸዋል።” ካሉ በኋላ የጠቅላይ ሚንስትሩ ተወካይ…የእናት ጡት ወተት ለህጻናት አስፈላጊ መሆኑን አስረዱ። “አሁንም የእናት ጡት ለህጻናት አስፈላጊ መሆኑን ስለተረዳን፤ የሽግግር መንግስቱ አስፈላጊውን ሁሉ ያደርግላችኋል።” ሲላቸው ከህጻናቱ ጋር የመጡት እናቶች አጨበጨቡ፤ ህጻናቶቹም ተንጫጩ። የሽግግር መንግስቱን አመስግነው ከመበተናቸው በፊት፤ ጋዜጠኞች ለአንዳንድ ህጻናት ጥያቄ አቀረብን።
“ጥያቄያቹህ የእናት ጡት ወተት ማግኘት ነው። አሁን እንደሰማነው ‘የሽግግር መንግስቱ አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋል’ ተብሏል። እንዴት ታዩታላቹህ?” አልናቸው።
አንደኛው ህጻን ተገርሞ እኛንም ጓደኞቹንም እያየ፤ “የሽግግር መንግስቱ ጡት አለው እንዴ?” ሲል፤ እኛም ሆንን ጓደኞቹ ዛሬም ድረስ ያልመለስነውን ጥያቄ አቀረበልን።
እንዲህ አስቀው የሚያስቁንን ሰላማዊ ሰልፎች ወደ ጎን ትተን… ወደኋላ ተመልሰን ስንመለከት ግን… ከምንወቃቀስበት ጉዳይ ይልቅ የምንሞጋገስባቸው ጉዳዮች ብዙ አሉን። ከምንም በላይ “ጨርቅ” ተብላ የተንቋሸሸች ሰንደቅ አላማችን፤ ከወደቀችበት ተነስታ ከፍ ብላ መውለብለቧ ይሰመርበት።
በሽግግሩ ዘመን… የወቅቱ የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሃፊ ቡትሮስ ቡጥሮስ ጋሊ አዲስ አበባ መጥተው ነበር። የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችም “ኢትዮጵያ ህጋዊ የባህር በር ያስፈልጋታል” የሚል መሰረታዊ ጥያቄ ያነገበ ደብዳቤ አዘጋጅተው ሰላማዊ ሰልፋቸውን ስድስት ኪሎ ላይ ጀመሩ።
ሰልፉ ተጀምሮ ገና ከግቢው እንደወጡ አንድ ተማሪ ተገደለ (ተስፋሁን ይመስለኛል የተማሪው ስም)። ይህን ተከትሎ ብዙዎች ተደበደቡ፤ አካላቸውም ጎደለ። ምሽቱን በተላለፈው ዜና፤ የተገደለው የዩኒቨርስቲ ተማሪ የቀድሞ ደርግ ኢሰፓ የነበረ መሆኑን ሳያፍሩ ተናገሩ። ከዚያ ሁሉ ሺህ ህዝብ መሃል… “ኢሰፓ የሆነውን ነጥሎ የሚገድል ጥይት አለ እንዴ?” ብለን ተገርመን ሳናበቃ፤ “እንዲያውም ሟቹ ትምክህተኛ አማራ ነበር” አሉን። ቀጥሎም የወቅቱ ፕሬዘዳንት መለስ ዜናዊ በቲቪ ቀርበው እንዲህ አሉ።
“እኛ ሰልፈኞቹን በአስለቃሽ ጢስ ብንበትናቸው ደስ ይለን ነበር። ሆኖም ከደርግ መንግስት የተረከብነው አስለቃሽ ጢስ ሳይሆን፤ ታንክ እና ሚሳየል ነው።” ብለው የመጀመሪያ ቀልዳቸውን ከምር ነገሩን። እንደሳቸው አባባል፤ “እንደውም እኛ ሰልፉን በጥይት ስለበተንን ልንመሰገን ይገባል። ደርግ ቢሆን በታንክ ይረመርማቸው ነበር” የሚል አንደምታ ያለው ንግግር ነበር – ያሰሙን።
በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የሚከፈተው የጠመንጃ ላንቃ ግን፤ በተስፋሁን ላይ ተጀመረ እንጂ አላበቃም። በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ፤ ምንም ያላደረጉ ሰላማዊ ዜጎች በጠራራ ጸሃይ ጥይት እየተርከፈከፈ ተገድለዋል – “ክብር ለነሱ ይሁን” ሌላ ጉዳይ እናውጋ።
ከሽግግሩ ዘመን በኋላ “አባይ ተገንብቶ ለልማት ይዋል።” ስንል፤ በረከት ስምኦን ራሱ ቃል በቃል እንዲህ ብሎን ነበር። “በአባይ ወንዝ ላይ ግድብ ስሩ የሚሉ ቅዠታሞች አሉ። አባይ ቢገነባ ኢትዮጵያ በውሃ ተጥለቅልቃ እናልቃለን እንጂ፤ ምንም አናተርፍም።” ብሎ መግለጫ ጭምር ሰጥቶ ነበር። በኋላ ላይ የአባይ ግድብ ግንባታ ሲታወጅ፤ በረከት ስምኦን ዋና ተዋናይ ሆኖ፤ ጉዳዩን ለፖለቲካ ጥቅም ሲመነዝረው እያየን… “ወይ ግዜ” ያልንበት ወቅት እሩቅ አይደለም። በዚያም ተባለ በዚህ ግን ለሰንደቅ አላማችን ከፍ ማለትም ሆነ፤ ለአባይ መገደብ ትልቁ ምክንያት ሳያሰልስ ይታገል የነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ እንጂ፤ አብዮታዊ ዲሞክራሲ አለመሆኑን እነሱም ያውቁታል፤ እኛም እንመሰክራለን። በመሆኑም በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ህዝባዊ መብቱን ተጠቅሞ  የዲሞክራሲው ቀለም እንዲደምቅ፤ የህዝብ ፍላጎት እንዲጠበቅ ያደረገው የኢትዮጵያ ህዝብ… ከምንም በላይ ሊመሰገን ይገባዋል።
ከሽግግር መንግስት እስከ ችግግር ዘመናችን ድረስ ብዙ አሳልፈናል። አሁንም በትዝታ ወደ ሽግግሩ መንግስት ዘመን እንውሰዳቹህ። ከሃያ አመታት በፊት ነው። ብዙዎቹ ሰልፈኞች መፈክር እያሰሙ ወደ ጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ ያመራሉ። በወቅቱ ጠቅላይ ሚንስትር የነበሩት አቶ ታምራት ላይኔ ናቸው። ሰልፈኞቹ በመፈክራቸው መጀመሪያ  እና በደብዳቤያቸው መጨረሻ ላይ “የሽግግር መንግስቱን ቻርተር እንደግፋለን” የሚል ሙሻሙሾ የሚያወርዱ ከሆነ፤ የሰልፈኞቹ ተወካዮች ወደ ውስጥ እንዲገቡ ያደርጉና ያናግሯቸዋል።

Latest Images