Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

በሪዮ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የብር ሜዳልያ በገንዘቤ ዲባባ አማካኝነት በ1500 ሜትር አገኘች

$
0
0

genzebe

(ዘ-ሐበሻ) በሪዮ ኦሎምፒክ በ1500 ሜትር የሴቶች ውድድር ኢትዮጵያዊቷ ብርቅዬ አትሌት ገንዘቤ ዲባባ ሁለተኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ የመጀምሪያውን የብር ሜዳሊያ አስገኘች::

ገንዘቤ ውድድሩን ወደ መጨረሻው አካባቢ ለመምራት ችላ የነበረች ቢሆንም በኬንያዋ አትሌት ፌዝ ኪፕዮጎን ተቀድማ ሁለተኛ ወጥታለች:: ኬንያዊቷ አትሌት ውድድሩን በ4:08.92 ስታሸንፍ ገንዘቤ 4:10.27 ለመግባት ችላለች:: አሜሪካዊቷ ጄኔፈር ሲምፕሰን በ4:10.53 በመግባት የነሐስ ሜዳሊያ አሸንፋለች::

ለሆላንድ የምትሮጠው ትውልደ ኢትዮያዊቷ ሲፋን ሃሰን ውድድሩን በአምስተኛነት ስታጠናቅቅ ኢትይዮጵያዊቷ ዳዊት ስዩም 8ኛ ወጥታለች::

↧

↧

‘’ የኢትዮጵያዊኖች ተጋድሎ! ወይስ የማን ተጋድሎ ነው…..?” –ፊልጶስ

$
0
0

Woyane

ወያኔ  ኢትዮጵያን  እያፈራረሰና  ህዝቡን ‘ርስ በርስ እያባላ  ያለው  ብቻውን  አይደለም። የሀገሪቱ ጠላቶች፣  ሆድ-አደሮች፣  መሀል-ሰፋሪዎች፣  ግብዞችና  የመሳሰሉ  ሁሉ  አጋጣሚውን  ይጠቀማሉ። ሲጠቀሙም  ኖረዋል። ወያኔና  ግብረ – አበሮቻቸው  እኮ ኢትዮጵያን  የማፈርስረሱን  መረሀ-ግብር  የተቀበሉት  ከምዕራቡና  ከዐረቡ ዓለም ነው።   መርሳት  የሌለብን  ወያኔ  ከዚህ  ደርጃ  እንዲደርስ  የኛ  አስተዋ’ጾ መሆኑን  መቀበል አለብን።  ማርቲን  ሎተር  ይመስለኛል፤ ” ካልተጎነበስክላቸው  እነሱ  ከአንተ  ጀርባ  ላይ  አይወጡም !”ያለው።  ቁምነገሩ  ካለፈው  መማር  መቻላችን  ላይ ነው።

በርግጥ  አሁን  ብዙሀኑ  የወያኔን  “አሪወሳዊነት”  ከማንኛውም  ግዜ  በበለጠ  የተረዳበትና  የ40 ዓመት የከፈፍለህ  የቤት  ስራ ”ፉርሽ” የሆነበት ነው።   ይሁን  እንጂ  ብዙ  ድህረ-ገጾች፣  ዜና – ዘጋቢዎች፣ ዘፋኞች፣  ሰላምዊ  ሰልፎኞች፣  የፓለቲካ  ተንታኞች፣  መግለጫዎችና   የመሳሰሉት  በሚያሳዝንና በሚያሳፈር  ሁኔታ  ከወያኔ  የጎሳ  ወጥመድ   ያለመላቀቃችን ፤ ” አንድ ‘ርምጃ  ወደፊት፣  አንድ ‘ርምጃ ደግሞ  ወደ  ኋላ“  መሆኑ  በግዜ  ሊታሰብበትና   ሊታረም   የሚገባ   ጉዳይ ነው። እናም  የምንናገረውንና  የምንጽፈውን  በጥንቃቄ   መመርመርና፤ ወያኔ  የማይቆፍረው  ጉድጎዳ፣  የማያፈሰው  ደም  እንደሌለ  ከምንግዜውም  የበለጠ   አሁን  መረዳት  ያስፈልጋል።

  • ”የአማራ ተጋድሎ!….. የኦሮሞ ተጋድሎ!….. የመሳሰሉ ዜናዎችና  መፈክሮች   የሚያመለክቱት አሁንም   ደም  እንደጎርፍ  እየፈሰሰና  ምድራዊን  ስቃይ  እየተቀብለን፣  ወያኔ  ካሰመረልን የጎሰኝነት  ስሜት  ያለመውጣታችን  የሚያመለከት ነው።  ለምንድን  ነው ”የኢትዮጵያኖች ተጋድሎ ! “ የማንለው?? ?….. እድግመዋለሁ፤ ”የኢትዮጵያዊኖች ተጋድሎ!” ። አማሮች እንዲህ…አድረጉ…  ኦሮሞዎች  እንዲህ ሆኑ………አደረጉ… ..ወዘተ…..እያልን ፤ በአንድ  አካባቢ  አንድ  ወጥ  ህዝብ   እንዳለ   አድርገን   ማቅረባችንና   መዘገባችን  ይቁም። በተለይም ኢሳት  (ቲቪና  ሬዲዮዎ )  የኢትዮጵያ ህዝብን ዓይና ጆሮ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በዚህ ጉዳይ ግን ቢያስብበት መልካም ነው እላለሁ።

በዚች ሰዓት ጋምቤላዎች  የከፍሉት  መሰዋ’ትነና  እየከፈሉት  ያለው  ተጋድሎ፣  የኦጋዴኖችና  አንዲሁም  በተለያየ  ግዜ  በተለያዩ  የሀገሪቱ  ግዛቶች   ከወያኔ ጋር  የሚተናናቁት ሁሉ የኢትዮጵያኖች ያውም  የዚህ ኢትዮጵያዊ ትውልድ  ተጋድሎ  እንጅ  የማን   ሊባል  ይችላል?  ካላያማ  ከወያኔ  በምን  ተለየን?  የተጀመረውን  የጸረ-ወያኔ  የጎሳ ከፋፍለህ  ግዛው  እንዴት ነው  የምናከሽፈው? “የዚያ  ጎሳ  ተጋድሎ!….. የዚህ  ጎሳ  ተጋድሎ!…..” እያልን  እንዴት  አድርገን  ነው  ትግሉን  ለህዝባዊ ፣ ለሁሉሙ  ኢትዮጵያዊ  ድል  የምናበቃው?

 

 

 

  • ሌላው የስሞኑን  ህዝባዊ  አመጽ  ያቀጣጠለው  የወልቃይት  ጉዳይ  ነው። የወልቃይት ጥያቄ የሁሉም  ኢትዮጵያዊ  ጥያቄና  ትግል  ነው። ኢትዮጵያዊ  ዜጋ  ነኝ  የሚል ሁሉ ይመለከተዋል። ይሁን  እንጂ   ”ወልቃይት አማራ !…” የሚለው  አባባል፣ መፈክርና  ቀረርቶ  የወያኔ  የጎሳ ሾል መስራቱን  ነው  የሚያመለክተው።  “ወልቃይት …..  የጎንደር  አንዱ  ግማድ  ነው፤ ለዚህም የህይወት  መሰዋትነት  ብቻ  አይደልም፤  የዘር  ማጥፋት  ወንጀል  እየተፈጸመበት  ያለ  ህዝብ ነው። ያ  ማለት  ደግሞ  ‘’ወልቃይት – ጎንደር፤  ጎንደር – ኢትዮጵያ  ነው።”’  ይህም  ማለት “ኢትዮጵያ  ከሌለች   – ወልቃይት –ጎንደር  የለም“።  ሁሉም  ኢትዮጵያዊ  የሚስማመው ”  በኢትዮጵያዊያን   ተጋድሎ !….” ነው።   ትግሉ  የሁሉም  ኢትዮጵያዊ  መሆኑ  በዚህ ሰዓት መዘንጋት  የሌለበት  ጉዳይ ነው።  ለመሆኑ  የሌላው  ኢትዮጵያዊ  ተጋድሎና  መሰዋትነት  የት ሊጣል  ነው?  የአብሮነት  ትግል  ባላማካሄዳችን  አይደልም  ወይ፤  ወያኔና  ሆድ-አደሮቹ ሀገራችን  የግላቸው  እቃ  አድርገው   ህዝብን  እንደቅጠል  የሚያረግፉት።

 

  • ወያኔ ለኢትዮጵያ  ጎሳዎች  ብሎ   የጫነብን  ሰንደቅ –ዓላማ፤  በየተኛውም  ኢትዮጵያዊ ተቀባይነት  አለመኖሩ  ብቻ  አይደለም ፤ ነባሩ ሰንደቅ – ዓላማ   የኢትዮጵያ ህዝብ የአንድነትና   የተጋድሎ  መግለጫ   መሆኑን  እያስመሰከረ  ነው።  ስለዚህም  በህዝባዊ  አመጽ   ወቅት  የቡድን  ወይም  የድርጅት  ሰንደቅ  ዓላማ  ይዘን  መውጣታችን  ይከፋፍለናል  እንጅ  አንድ  አያደርገንም።  በርግጥ  በአንዳንድ  የደቡብ  ክፍል  የወያኔ ካድሪዎች  የአንዳንድ ድርጅቶችን “ሰንደቅ  ዓላማ”   ይዘው  በመውጣት  ህዝብን  ለመምታትና  ለመከፋፈል  እየተጠቅሙብት  ቢሆንም፤  እኛ  ግን  አንድነታችን  በተግባር  እናስመስክር። እየተከፈለ  ያለው  የህይወት  መሰዋትነት  ነው።

 

  • ሰሞኑን  ከተቀሰቀሰው  ህዝባዊ  አመጽ ጋር  አንዳንድ  ዘፋኞች  ከትግሉ  ጋር  በተያያዘ   ነጠላ ”የቅሰቀሳና  የውዳሴ”  ዜማ ለቀዋል፡:  በተለይም  ሾለ  “ወልቃይት-ጎንደር፣ …….ሾለ ኦሮሚያ፣….  ወዘተ።  ይሁን  እንጂ  በ’ኔ  እይታ   ዜማዎቹ  በደንብ  የታሰበባቸው  አይደሉም። ”ኢትዮጵያዊ”  አንድምታ  የላቸውም።  ተጋድሎውና  ህዝባዊ  አመጹ  የመላው  ኢትዮጵያዊ በመሆኑ  ዜማዎቹም  የሁሉንም  ኢትዮጵያዊያን   አንድነትና  ጅግንነትን  የሚያወድሱና የሚቀሰቅሱ   መሆን  ሲገባቸው  በአካባቢያቸው  ተወስነዋል።   የወያኔች  በጎሳ  ላይ  በተመሰረተ የጥላቻና  የግብዝነት  ከበሮ -ድለቃ ፤ የምን ያህል  የወርዱና  የዘቀጡ ኅሊና   ያልፈጠረባቸው  መሆናቸውን  የሚያመለክት  ሆኖ   ሳለ፤  የ’ነሱን  ፈለግ  መከተሉ   “በአንድ  አፍ  ሁለት  ምላስ  …” ይሆንብናል።   ”ወልቃይት  ብረሳሽ ፣  ቀኜን  ይርሳኝ!..!”  ከማለት  ”ኢትዮጵያ ….ብረሳሽ ፣ ቀኜን  ይርሳኝ!”  ብሎ  ቢያንጎራጉር፤  ለአንድነታችንና   ለትግላችን   የሚኖረው  ፋይዳ  ከፍተኛ   ነው።  ለወያኔም  የራስ  ምታት  ነው።  ኢትዮጵያ  እንዳትኖርና  እንድትፈራርስ   እኮ ነው  ወልቃይትና  ሌሎችም  አካባቢዎች  ለወያኔ  የተከለሉትና  ለሱዳን  እጅ  መንሻ የሚቀርቡት።  እናም  በተቻለ  መጠን   የትግል  ዜማችን  የሁላችንም  ሀገር  ልናደርጋት  መሰዋ’ት   ለምንከፍልላት  ኢትዮጵያችንና  ህዝባችን  ይሁን።

 

 

 

 

 

ያለፉትም  ሆነ  አሁን  ያሉት ”ጅግኖቻችን”  የከፈሉት  መሰዋትነትና  እየከፈሉ  ያሉት  ለኢትዮጵጵያና  ለኢትዮጵያዊያን  ነው።  ታዲያ   እነዚህን  የክብር  የኢትዮጵያዊያን  ጀግኖች  ወደ  መንደርተኛነት  ማውረድ  ምን  ይሉታል?።  ቢቻል  በዚህ ሰዓት   ዘፋኞች  በህብረት  ለሁሉም  ኢትዮጵያዊ  የሚሆን  በተለያዩ   የሀገሪቱ   ቋንቋዎች  ዜማ  ቢለቁ   ለትግሉም  ሆነ  ለአንድነታችን  የበኩላቸውን  አስተዋ’ጾ  ያደርጋሉ። በዚህ ጉዳይ ላይ በተለይም  ባህር-ማዶ የምትገኙት እንደ አለምፀሀይ  ወዳጆና  ታማኝ  በየነ ያላችሁ፤ የጥበብ ሰዎችን እንደተለመደው  ብታሰተባብሩ ”ለቀባሬው ማርዳት” ባይሆንብኝም  መለዕክቴ  ይድረሳችሁ።

 

—//—-

 

ፊልጶስ / ነሀሴ 2008 / E-mail: philiposmw@gmail.com

 

↧

በቺካጎ ከተማ ከፍተኛ ድምቀት ያለው ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ |ቪድዮም ይዘናል

$
0
0


ዘላለም ገብሬ | ለዘ-ሐበሻ ከቺካጎ

(ዘ-ሐበሻ) በቺካጎ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሃገራችን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን አስከፊ ግድያ በመቃወም የንጹሃን ዜጎችን ግድያ በስፋት እየፈጸመ የሚገኘው የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስትን ከሚያደርገው የከፋፍለህ ግዛው አስተዳደር እንዲታቀብ እና አንድ የሆነው ህዝብ በአንድነቱ እንዲቆይ ለማድረግ; ይህ ገዳይ መንግስትን ከስልጣነ መንበሩ ሊወርድ ይገባዋል በማለት በከተማው የሚኖረው ሕዝብ ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣት ለቺካጎ ከንቲባ ረሃም ኢማኑኤል ጽህፈት ቤት ጥሪውን አቀረበ::

በሃገራችን እየተፈጸመ ያለው የዘር ማጥፋት ወንጀል እና የመሬትን ነጠቃ መከላከል የህላችንም ግዴታ ነው; በኦሮሞ ወጣቶች ፣ በአማራ ብሄርሰብ እና እንዲሁም በተለይም በወልቃይት ጠገዴ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፋዊ አገዛዝ እንዲቆም ሲሉም ጠይቀዋል።
በቺካጎ ከተማ ከፍተኛ ድምቀት ያለው ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ | ቪድዮም ይዘናል

የአሜሪካው ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍም ሆነ፣ በአጠቃላይ በሃገራቸው የፖለቲካዊ ጥቅምን በማስመልከት ባልተድረገ ጉዳይ ላይ ኢትዮጵያ አድጋለች ፣ችዲሞክራሲያዊ ምርጫ አድርጋለች የሚለውን አቋማቸውን ስቴት ዲፓርትመንቱ በአጽኖት እንዲመለከትው ጠይቀው ይህንን ውሽት ከፕሬዚዳንቱ መስማትም ለአፍሪካ ህዝብ ያለውን ንቀት እያሳየ ነው ሲሉ ሰልፈኞቹ ተናግረዋል።

በዛሬው ሰላማዊ ሰልፍ የተለያዩ መፈክሮች የተሰሙ ሲሆን ፣ ሰብአዊ መብት በኢትዮጵያ ይከበር ፣ የኦሮሞ ተማሪዎች ከእስር ይለቀቁ፣ ጋዜጠኞች ወንጀለኞች አይደሉም፣ የወልቃይት ማንነት ይከበር፣ በቀለ ገርባ ይፈታ፣ እስክንድር ነጋ ይፈታ እና ሌሎችም መፈክሮች የተሰሙ ሲሆን የወያኔ መንግስት ከስልጣኑ እንዲለቅ እና በሃገራችን ሰላማዊ የሆነ መንግስት እንዲፈጠር እንሻለን ሲሉ ተደምጠዋል።

ሰልፈኞቹ በተጨማሪም በዘረኝነት የተጠመደው የወያኔ ህወሃት መንግስት በየስቴቱ የሚያስቀምጣቸውን የስለላ አጋፋሪዎችን ለኤፍ ቢ አይ ጥቆማ እንዲደረግ እና ማንኛቸውንም ስራዎቻቸውን በቪዲዮ ፎቶ በማያያዝ መረጃ ማቅረብ ጥቆማውን ሊያጠናክር ስለሚችል በማንኛውም መልኩ በኢትዮጵያዊነትችን መስራት አለብን ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። የኦሮሞ ኮሙኒቲም በኢትዮጵያዊነታችን ጸንተን ሃገራችንን አስከብረን ነጻ መንግስት እንዲፈጠር መጣር አለብን አሁንም አንድነታችን ይቀጥላል ሲሉ ገልጸዋል።

↧

እናት ሆይ! ጀርባሽን እሚዘነችሩትን እስከ መቼ እሹሩሩ ትያለሽ? –በላይነህ አባተ

$
0
0

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

Cry-ethiopia1.jpgእናት ሆይ! የደራሲና የዘፋኝ መዋኛ ባህሩ፣ የድርሰትና የዘፈን መቅጃ ምንጩም ማህበረሰብና የማህበረሰቡ ባህል መሆኑን ልብሽ ይነግርሻል፡፡ ከማህበረሰቡ የባህል ባህር የወጣ ድርሰትና ዘፈን ከባህር እንደ ወጣ አሳ እድሜው አጭር መሆኑን ዛሬ ተነበው ነገ የማይደገሙት ድርሰቶች፣ ዛሬ ተደምጠው ነገ የማይደመጡት ዘፈኖች ያረጋግጡልሻል፡፡ የማህበረሰቡን ደስታ፣ ችግር፣ መከራና ሐዘን ያልዳሰሰ ድርሰትና ዘፈን ከባህር ውጪ እንደቆየ አሳ የሞተ መሆኑንም አእምሮሽ ያስረዳሻል፡፡ የማህበረሰቡ ችግር፣ መከራና እልቂት መንስኤ የሆኑትን ከንቱዎች እሚያወድስ ድርሰትና ዘፈን እንዲያውም እንደ ጠነባ አሳ ወዲያው እንደሚወረወር ህሊናሽ ያሳውቅሻል፡፡

እናት ሆይ! ጣሊያን ገረድ ሊያደርግሽ ሲደነፋ ቀረርቶና ፉከራዎች በዋሽንት፣ በክራር፣ በመሰንቆ፣ በበገና፣ በጸናጽል፣ በከበሮና በሌሎችም ባህላዊ መሳሪያዎች ታጅበው እንደታደጉሽ ታስታውሻለሽ፡፡ በእነዚህ ባህላዊ መሳሪያዎች የታጀቡ ቀረርቶዎችና ፉከራዎች ስንት ድንበር ጠባቂ ጀግኖች እንዳፈሩልሽ ትዝ ይልሻል፡፡ እነዚህ የጀግና መኮትኮቻ ቀረርቶዎችና ፉከራዎች በምድርሽ እንዳይሸለሉ ከሃያ አምስት አመታት በፊት በድንበር ሻጮች እንደተከለከሉም ትገነዘቢያለሽ፡፡ ድንበር ሻጮችን በመከተልም ብዙዎቹ የኪነ-ጥበብ ልጆችሽ ከቀራርቶና ከፉከራ እንደራቁ ታውቂያለሽ፡፡ አንዳንዶች ራሳቸውን የጠሉ ዘፋኞችም ቀረርቶና ፉከራን እንደ ስልጣኔ-አልባ ሕዝብ ኪነ-ጥበቦች በመቁጠር ከራሳቸው የባህል ባህር ወጥተው ከማያውቁት የባህል ባህር ገብተው እንደ ጀማሪ ዋናተኛ ሲንጨቧረቁና የባህል ተገዥ ባሪያዎች ሲሆኑም ትታዘቢያለሽ፡፡

ያለሽበት የእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ ዘመን ከቱርኩ፣ ከደርቡሹና ከጣሊያኑ የወረራ ዘመን የከፋ መሆኑን የተቆረጠው አንገትሽ፣ የተሸጠው ፍሪንባሽ፣ የተሰነጣጠቀው ሆድ እቃሽና የወደቀው ክብርሽ እንደሚያስረዳ ታውቂያለሽ፡፡ የዛሬው መከራሽ ካለፉት መክፋቱን በባሩድ የተረሸኑት፣ ከገደል የተወረወሩት፣ በወህኒ የተሰቃዩት፣ በርሃብ የተጨረገዱት፣ በስደት ባህር የገቡት፣ በሊቢያ የተቀሉት፣ ባረብ ታንቀው የሞቱት፣ ባፍሪካ በእሳት የጋዩትና በእስር የተንገላቱት ልጆችሽ ምስክሮች እንደሆኑ ትረጃለሽ፡፡ ታዲያ ለዚህ ከድሮው የከፋ ህመምሽ ስንት ምሁራን መድኃኒት ፍለጋ ኳተኑልሽ? ስንት አቀንቃኞች ሰቆቃሽን አቀነቀኑልሽ? በሌጣ እግርሽ ተጉዘሽ ኩበት ለቅመሽና በኩበት ጪስ ታጥነሽ እንጎቻ አነጉተሽ ያስተማርሻቸው ምሁራን ሲመረቁ የገቡትን መሐላ ዘንችረው ለምን እጀ አመድ አፋሽ አደረጉሽ? በቅኔሽና በዜማሽ እንጀራ እሚጎርሱት ካህናትና ዘፋኞችሽ ይሉኝታን ጎርድመው ለምን ፊታቸውን አዞሩብሽ?

የቆሎ ተማሪሽ ቁራሽ ሲለምንና እንደ ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ በኮር አባልነት የበረዶ ስኳር(ዓይስ ክሬም) መላስ ሳይጀምር  “ያሁኑ ይባስ!” ይል እንደነበር ታስታውሻለሽ፡፡ ያሁኑ ብሶ አንዳንድ ምሁራንና ዘፋኞችሽ ካንቺ ከእናታቸው ፊታቸውን ከማዞርም አልፈው የጣሊያንን ያልተሳካ ምኞት ከሚፈጥሙት ጡት ነካሽ ልጆችሽ ጋር ቦጫጭቀውና በከረጢት ቋጥረው መቃብር ሊወስዱሽ ተሰልፈው ትመለከቻለሽ፡፡ እንዲያውም ይንጠስልሽ ብለው ልቅሶሽን ሰርግ ለማስመሰል ስለ ልማት ሲወሸክቱና ስለ ህዳሴ ሲዘፉኑ ትሰሚያለሽ፡፡ አንገትሽን ገዝግዘው የቀነጠሱትን፣ ጀርባሽን ተልትለው የሸጡትን፣ ሆድ እቃሽን ወጋግተው ወንፊት ያደረጉትና የልጆችሽን ደም እንደ ዓባይ ፏፏቴ ያፈሰሱትን “አምሳለ ሙሴ” ብለው እየደረሱና እየዘፈኑ ካንቺ አልፈው ከታሪክ፣ ከፍትህና ከእግዚአብሔር ሲጣሉም ታዳምጫለሽ፡፡ ታዲያ ካንቺ፣ ከታሪክ፣ ከፍትህና ከእግዚአብሔር ለተጣሉት ምሁሮችሽና ዘፋኞችስ ምን ምክር አለሽ? ጣልያን ገረድ ሊያደርግ ሲወርሽ መንገድ እያሳዩ ፋኖዎችሽን ካስፈጁትና ለፋኖዎችሽ ገዳዮች እንቁላል አቅራቢ ከነበሩት እርጉም ልጆችሽ ምን ተማርሽ?

እናት ሆይ! እናት ሆደ ሰፊን እያወጋሽ እስከ መቼ ባንዳን ትታገሻለሽ? እናት አትጨክንምን እየተረትሽ ጡት ነካሽ ልጆችሽን እስከ መቼ ጡት አጉርሰሽ ታድሪያለሽ፡፡ የወለደ አይጥልምን እየተረትሽ ጀርባሽን እሚዘነችሩትን እስከ መቼ እሹሩሩ ትያለሽ?

 

ነሐሴ ሁለት ሺ ስምንት ዓ.ም.

 

↧

በደቡብ ኮሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሃገር ቤት ሕዝብ እያደረገ ያለውን ትግል በመደገፍ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ

$
0
0

south Korea south koria
(ዘ-ሐበሻ) በደቡብ ኮሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሃገር ቤት እየተደረገ ያለውን ሕዝባዊ ትግል በመደገፍና በሰላም ጥያቄውን ላቀረበው ህዝብ ምላሹን ጥይት ያደረገውን የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት በመቃወም በኢትዮጵያ ኢምባሲ ፊትለፊት ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸውን የዘ-ሐበሻ ተባባሪ ዘጋቢ ተገኝ ይመር ከደቡብ ኮሪያ ዘግቧል::

ኢትዮጵያውያኑ የኢትዮጵያ ባንዲራንና የኦሮሞን ሕዝብ የትግል ባንዲራ በመያዝ ባደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የተለያዩ መፈክሮች የተሰሙ ሲሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ ድሉን ተጎናጽፎ በሃገራችን ዘረኛው ስርዓት እስኪወገድ ድረስ ከሕዝቡ ጎን ነን ሲሉ ቃል ገብተዋል:: በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ላይም የታሰሩ እንዲፈቱ; የወልቃይትና የሌሎች ሕዝቦች ጥያቄዎች እንዲመለሱ በኢትዮጵያ ኢምባሲ ፊትለፊት ጮኸታቸውን አሰምተዋል::

↧
↧

በባሌ የአጋዚ ሰራዊት በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ሲተኩስ እና ሲገድል የሚያሳይ ቪዲዮ ተለቀቀ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) የትግራይ ነጻ አውጪ ሰራዊት በንጹሓን ሕዝብ ላይ እያደረሰ ያለው ለከት የሌለው ርምጃ አሁንም እንደቀጠለ ነው:: በባሌ ሮቤ በሰላም ተቃውሟቸውን ለማሰማት የወጡ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ልክ እንደ ባዕድ ተቆጥረው በትግራይ ነፃ አውጪ ሰራዊት ሲተኮስባቸውና ሲገደሉም የሚያሳይ ቪዲዮ ተለቋል:: በቪዲዮው ላይ በዚህ ሰራዊት ከተገደሉት መካከል አንዱ አብደላ ከድር እንደሚሰኝም ታውቋል:: የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! ይህን ቪዲዮ ላልደረሰው አድርስ::

Screen Shot 2016-08-17 at 1.05.23 PM

↧

የትግራይ ነፃ አውጪ ሰራዊት በወሎ ባቲ ከተማ ሕዝቡን ገበያ ላይ ሰብስቦ ሲያስፈራራ ዋለ

$
0
0
በባቲ ገበያ ላይ የተሰበሰበውን ሕዝብ ለማስፈራራት የወጣው የትግራይ ነፃ አውጪ ሰራዊት

በባቲ ገበያ ላይ የተሰበሰበውን ሕዝብ ለማስፈራራት የወጣው የትግራይ ነፃ አውጪ ሰራዊት

(ዘ-ሐበሻ) የትግራይ ነጻ አውጪ ሰራዊት በወሎ ባቲ ለገበያ የወጣው ሕዝብን ሲያሸብር ዋለ:: ሕዝቡ ገበያ ሊገበያይ በወጣበት ሰዓት በርካታ የትግራይ ነጻ አውጪ ወታደሮችን እና ፌደራል ፖሊሶችን ገበያው መካከል በማስፈር “ሰልፍ ትወጡና ዋ!” የሚል ማስፈራሪያ እንደሰጡ የዘ-ሐበሻ የዜና ምንጮች ከፎቶ ግራፍ ጋር አስደግፈው በላኩት መረጃ አስታውቀዋል::

እንደምንጮቹ ገለጸ ባቲ ገበያ ላይ ከተሰባሰበው ሕዝብ ቁጥር የወታደሩና የፌደራሉ ቁጥር የሚበዛ ሲሆን “ስለጎንደር መንገድ ላይ የሚያወራ; ስለ ኦሮሞ ጉዳይ የሚወያይና የአሜሪካ ድምጽ ራድዮና የጀርመን ድምጽ ራድዮን ጨምሮ የአሸባሪ ሚድያዎችን የሚከታተል እርምጃ ይወሰድበታል” ሲሉ ሕዝቡን ለማስፈራራት ሞክረዋል::

ስለጎንደርና ኦሮሚያ ጉዳይ የሚያነሱ ጸረሰላም ኃይሎች በመሆናቸው እነርሱን አትስሙ በማለት የትግራይ ነጻ አውጪ ሰራዊት ሕዝቡን ሊያስፈራራው ቢሞክርም በገበያው ላይ የነበረው ሕዝብ ግን ጩኸቱን እንዳሰማባቸውና ማስፈራሪያቸውን እንደማይቀበል ነግሯቸዋል::

↧

አፈትልከው የወጡ የሕወሓት ሚስጥሮችና የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታዎች

$
0
0

TPLF Ethiopian Leaders

መግቢያ
ኢትዮጵያ በባንዳ መንግስት መመራት የጀመረችው መቼ ነው?

በቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት እናት ሀገር ኢትዮጵያ ከ1927ዓ.ም እስከ 1932ዓ.ም ለአምስት አመት በወራሪው የፋሺስት ጣልያን መንግስት ባልተሳካ ሁኔታ የተመራችበት ወቅት ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ግን መሪ ሳይኖረው ዘር፤ጎሳ፤ ብሄር፤ ቋንቋና ሀይማኖት ሳይለይ እጁ ላይ በሚገኘው መሳሪያ ሁሉ ድንጋይን ጨምሮ በመዋጋት የዘመናዊ ጦር መሳሪያ ባለቤት፤ባለግዙፍ ኢኮኖሚ ፤ለሁለተኛው የአለም ጦርነት በአንደኛው ጎራ ከጀርመን ጋር መሪ የነበረችው ጣሊያንን በማንበረከክ የሚታወቅ የእግዚአብሄር ባላደራ ህዝብ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ባለፈችባቸው ዘመናት በጣም በጣም አያሌ ጠላቶች የነበሯት ሀገር ብትሆንም የእግዚአብሔር ሀይል የተሰጣቸው መሪዎቿ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሀገራቸውን ብቻ በማስቀደም እስከ 1983ዓ.ም አቆይተውናል፡፡አሁን ግን ሌላ መዓት ወረደባት፤ በሀገራችን ሌላ ታሪክ ተፈጠረ፤ኢትዮጵያን አምላኳ የረሳት መሰለች ፤ ኢትዮጵያ ሰው እንደሌላት ሆነች፤ሌቦች አደንዝዘው ዘረፏት፤ይህች ውብ ሀገር የብዙ አስደናቂ የተፈጥሮ ሀብት ባለቤት ፤ የአለም አቀፍ ምሁራን አንኳ ስለኢትየጵያ ቢጽፉ ቃላት ይቸግራቸዋል፤ ኢትዮጵያዊ መሆን እድለኝነት ነው፤ግን ይህ እድለኝነት ዛሬ አይዋጥልንም ወያኔ የረሀብ ሀገር አደረጋት፡፡

ኢትዮጵያ ጡቷን አጥብታ ያሳደገቻቸው ልጆቿ ባንዳ ሆኑባት፤ የልጅ ኪሳራ ማለት እንዲህ ነው፤ኢትዮጵያ በድጋሚ ለ25 አመት በባንዳ መሪ ተገዛች፤ህዝቦቿ በታሪክ አይተውት የማያውቁትን ውሸት፤የሞራል ውድቀት፤በሽታ ፤ረሃብ፤ግድያ፤ወኔ አልባ መሆን፤በጭንቀትና በብስጭት በሽተኛ የሚሆን ህዝብ፤ በበሽታው ምክንያት ካቃሰተ ወደ ከርቸሌ የሚወረወር ህዝብ ባለቤት ሆናለች፡፡

የባንዳው የሕወሓት ገዥ ዋና ዋና ጭብጦች

በመጀመሪያ ባንዳው ገዥ ሲጸነስ በደደቢት በረሃ የገበሬዎች አመጽ ሲሆን ምንም አይነት ፊደል ያልቆጠሩ ከሰፈርና ጎጠኝነት አስተሳሰብ ውጭ ሌላ የማሰብ እድሉ በሌላቸው ገበሬዎችና ቀጥሎም ተማርን በሚሉ የአሁኑ ወያኔዎች የተጀመረ ሲሆን፤ የሚኖሩበትን ቀበሌ ነዋሪ ብሎም በለስ ከቀናቸው ደግሞ አንድ አይነት ቋንቋ ተናጋሪ የሆነውን ህዝብ ብቻ ነጻ ለማውጣት የታሰበ አመጽ ነበር፡፡ በጊዜው በመንግስቱ ሀይለ ማሪያም አገዛዝ ወቅት በመላ ሀገሪቱ በነበረው አመጽ መሪ ተዋናይ የነበረው የአማራው ኢሃፓ በተማረ የሰው ሀይል የተደራጀና ሀገሩን ከነበረው አገዛዝ በተሻለ ህዝቡ ሰላማዊ በሆነ መንገድ አንዲኖር ለማድረግ ከወያኔ በአመታት ቀድሞ የተወለደው ኢሃፓ፤አንድ ሰላማዊ ኢትየጵያን በህዝቧ ፍላጎት ለመምራት ደፋ ቀና በሚልበት ወቅት ነበር ከወያኔ አባላት ጋር ለመወየያት የተወሰነው፤በዚሀም መሰረት ለህዝቡና ለሀገሩ ቆርጦ የተነሳው ኢሃፓ ምንም ሳይፈራ ሳይጠራጠር ከወያኔ ጋር ውይይት አደረጉ፤በሁለቱ አካላት መካካል ውይይቱ ተደረገ ግን ባለመስማማት ተለያዩ ፤ ከዚያም ባልታወቀ ሁኔታ ኢሃፓ ፈራረሰ ፡፡ሌላው ታሪክ ደግሞ ኢትዮጵያን አንድ አድርገን በሰላም እንኑር ሲል የነበረው የሰሜን ትግራዩ ተቃዋሚ ቡድን ስለኢትዮጵያ አንድነት ሲሰብክ የአሁኑ ባንዳና ጎጠኛው የትግራይ አማጺዎች እነመለስ ዜናዊ መስማማት ተሳናቸው፤የምን ኢትዮጵያ ነው አሉ፤አኛ ትግራይን አንጅ ኢትዮጰያን አናውቅም አሉ፤በወቅቱ የመንግስቱ ሀ/ማሪያም መንግስት በመላው ሀገሪቱ በነበረው አመጽ ተዳክሞ ነበር ፤በዚያው በትግራይ ሁለቱም ወገኖች በአሁኑ ወያኔ እምቢተኝነት ቀኑ ጨለመ፤ሁሉም በስብሰባ ተዳክመው ስለነበር ወደ መኝታቸው አመሩ፤ ሲነጋ አዲስ ነገር ተከሰተ ፤የትግራዩን ተቃዋሚ የራሳቸውን ወገኖች፤ የነጻነት አቀጣጣዮች በጥይት ተረሽነው ተገኙ፤ ነገሩን ሸፋፈኑት፤ለራሳቸው ዘር ያላዘኑ ሰዎች ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዴት ያዝናሉ፤በደም የተጨማለቀ እጅ ባለቤት ናቸው፡፡ ከዚያም በሂደት አጋጣሚውን ተጠቅመው ኢትዮጵያን ወረሩ፡፡ የኦሮሞና የመላው ኢትዮጵያ ህዝብ አማፂዎችን መግደል ማስፈራራት ጀመሩ፡፡ ውሸት ፤ማስመሰል ፤ሰውን መግደል የወያኔ ህግና ደንብ ነው፡፡ ከዚያም ተቀናቃኝ ስላልነበራቸው ሌላ ሀሳብ መጣላቸው ፤ወያኔ ያላሰበውን ሲሳይ በማየቱ ስልቱን በመቀየስ የኢትዮጵያ ህዝብን በማታለል በድብቅ (በህቡዕ) መራመድ ጀመረ፡፡ ህዝቡ እርስ በርሱ ሲበላላ ሲተራራድ ድምጻቸውን አጥፍተው የእነርሱን አላማ የሚያሳካ የሕወሓት ህቡዕ ቡድን መሰረቱ፡፡

በመጀመሪያ በእግዚአብሔር ትእዛዝ በኢትዮጵያ ልጆች ደም እየተጠቀሰ የተጻፈውን የሀገሪቱን ህገ መንግስት ባንዳዎች በመሰሪና ውሸታም ፤ነፍሰ ገዳይ እጃቸው አረሙት፡፡ ያኔ ነበር ኢትዮጵያ ህዝቦቿ አንዳይፋቀሩ ፤አንዳይጠራጠሩ የሚያደርግ፤ ለታላቋ ትግራይ መወለድ መንገድ የሚጠርገውን አንቀጽ 39 የወለዱት፡፡ ወያኔ ለአማራ ያላቸው ጥላቻ የሚደንቅ ነገር ነው፤ የሰሩትን አና የመሰሩትን ስለሚያውቁ አማራን ይፈሩታል፤ አምርረው ይጠሉታል፤ በአንድ ወቅት የቀድሞው ጠ/ር መለስ ዜናዊ ጥንተ ጠላታችን ድህነት ነው በሚለው አንደበቱ ጥንተ ጠላታችን አማራ ነው፤ አማራ መጥፋት ያለበት ዘር ነው ብሎ ለትግራይ አመራሮች በትግርኛ ቋንቋ ተናግሮ ነበር፡፡ ንጹህ የኢትዮጵያ ልጅ የሆኑትን ህዝቦች በዘር እየከፋፈሉ አንተ ኦሮሞ ነህ፤አንተ አማራ ነህ፤ አንተ ሶማሌ፤ጉራጌ፤ወላይታ ወዘተ እያሉ የሚያፋጁት ሕወሓቶች ቀጥሎም ሌላ ሴራ ጀመሩ፤ በሰለጠነ ዘመን ደካማ ቃላትን እየፈጠሩ አንተ እኮ ጺላ ተብለሃል፤ ጋላ ተብለሃል፡ ወላሞ ተብለሃል፤ቅማላም ተብለሀል፡ ጨቋኝ ተብለሀል፤ትምህክተኛ፤ ጠባብ እያሉ ህዝቡን የማዘናጋት፤ግራ የመጋባት ስሜት ውስጥ ከተውት ቆይተዋል፡፡ ሌላም በሚመቻቸው መልኩ ለዘጠኝ ከፈሉና ዘጠኝ ዘር ነው ያለህ አሉት፤ህዝቡም በደካማ ጎኑ ገቡበትና አመናቸው፡፡ በዘር ማባላት እንኳ ባይሳካላቸው በሀይማኖት ስልታቸውን ቀይሰው ይመጡብሃል፡፡ይህ ሀይማኖት የኦሮሞ ነው ነው ይህ ሀይማኖት የአማራ ነው ይህ ሀይማኖት የደቡብ ነው ብለው ዘሩን ከሀይማኖት ያደበላልቃሉ፡፡ ከዚያም ህገ መንግስቱ መንግስትና ሀይማኖት የተለያዩ ናቸው በማለት ውሸት አቀነባብረው ሀዝቡ ነው ጥፋተኛ ለማለት በኢቲቪ ይዘው ይቀርባሉ፡፡ በተለይም በሙስሊሞች ላይ የሚያደርጉት ጫና አሰቃቂ ነበር ስለ እኩልነት ያነሳ ሙስሊም ሁሉ አሸባሪ ነህ እየተባለ ከርቸሌ ይወረወራል፡፡ ይህ ሌላ የወያኔ ሴራ ስለሆነ ከመሬት ተነስተው የአልሻባብ ምልምል ነው ብለው ህዝቡን እንዲነግሩት ለእነንትና በኢቲቪ ውሸት አንዲቀነባበር ትእዛዝ ያስተላልፋሉ፡፡ ይህ አማራጭ የማይሳካ ከሆነ ደግሞ በህቡዕ ቡድኑ ትእዛዝ ታማኝ ፌዴራል ፖሊስ ፤ሲቀጥል አጋዚ ጦርን በህዝቡ ላይ በመልቀቅ በስናይፐርና በመትረየስ ጠላታቸው የኢትዮጵያ ህዝብን ጭንቅላቱን እያሉ ሀገሪቱን የጦርነት አውድማ በማድረግ ማሰብ እንድታቆም ያደርጉሀል፡፡ የአምቦ፤ የወለጋ፤የጎንደር፤የባህርዳር ወጣቶች ጭንቅላታቸውን በስናይፐር አቃጠሏቸው፡፡ አዲስ አበባ የተነሱ ሰላማዊ ሰልፎች በሙሉ በሀይል እርምጃ ተቋርጠዋል፡፡

በግፍ የተጨፈጨፉ አትዮጵያውያን ምስል በትንሹ

ይህ ሁሉ ነገር መነሻው እነሱ በፈጠሩት የህገ መንግስቱ አንቀጽ 39 ምክንያት ነው፡፡ ይህ አንቀጽ የተጻፈው በዘረኛውና ለክልሉ ህዝብ የቆመው የሕወሓት ህቡዕ ቡድን ትእዛዝ አማካኝነት ነው፡፡ ይህ አንቀጽ ሲጻፍ የሚከተሉት ሚናዎች ነበሩት፤ የመጀመሪያው አላማ የኢትየጵያን ህዝብ ከፋፍሎ ለመግዛት፤ህዝቦችን በዘር በመከፋፈል የፈጠራና ቀደምት ታሪኮችን በማንሳት በማጣላት፤ህዝቡ አንቀጽ 39 ነጻ ያወጣኛል ብሎ እንዲያስብ በማድረግ የጎጠኝነት አስተሳሰብ እንዲኖረው ማድረግ ነው፡፡ ሁለተኛውና ዋነኛው የአንቀጽ 39 አላማ የሀገሪቱን ሀብት፤ንብረት ፤ሰፊና ለም መሬት ጠራርጎ በመውሰድ ታላቋን ትግራይ በመመስረት ሂደት ላይ በመሆናቸው ነው፡፡ በስተመጨረሻም የኢትዮጵያ ህዝብ ሲጠላቸውና በቂ ሀብትና ንብረት ከወሰዱ በኋላ ቀድመው ባዘጋጁት ሴራ መሰረት አንቀጽ 39 ፍሬ ታፈራለች፡፡ ይህም እስካሁን ሲጭበረበር እንደነበረው ምርጫ የተጭበረበረ ሪፈረንደም በማድረግ ታላቋን ትግራይ ይመሰርታሉ፡፡ ግን የኢትዮጵያ ህዝብ አይለቃቸውም የትግራይ ምስኪን ህዝብ እንኳ ይነሳባቸዋል ፤ውለታ ቢስ ብሎ ምራቁን ይተፋባቸዋል፡፡

የሕወሓት መንግስት የህቡእ ቡድን ታላቋ ትግራይ የራሷን ሉዋላዊ ሀገር ይዛ እንድትቀጥል በማሰብ በ1983 ተመሰረተ፡፡ህቡእ ቡድኑ የራሱን የግንኙነት ጊዜ በመወሰን የጥፋት ስራውን ይገመግማል፡፡ ዋናው አጀንዳ የድንበር ወይም ይዞታ ማስፋፋት ጉዳይ ነው፡፡ ክልል ሶስት ወይም አነሱ ትምህክተኛ ብለው በሚጠሩት፤ በሚጠሉት ክልል የተያዘውን ሰፊና ለም የመሬት ይዞታ መንጠቅ ነው፡፡ በመጀመሪያ በህገ መንግስቱ እነሱ በሌባ እጃቸው ባሰፈሩት የብሄር ብሄረሰብ እኩልነት እያሉ፤ የትግራይ አጎራባች ለም አካባቢዎችን የቀበሌ አመራሮችን የሚያሰልጥን ፤ቋንቋናባህል የሚያስተምር ኮሚቴ ማወቀር ነው፡፡ ይህ የህቡእ ቡድኑ ያሰማራው ኮሚቴ ትእዛዙን ከቡድኑ በጸጋ ተቀብሎ ተግባራዊ ያደርጋል፡፡ ከዚያም ውሸት መፍጠር አንዱና ዋነኛው ዘዴያቸው በመሆኑ ለተነጣቂው ህዝብ አማራ ሲበድልህ ነው የኖረ እያሉ የህዝቡ ንጹህ አእምሮ ላይ ጥላሽት በመቀባት ብሎም በማስገደድ ሴራቸውን እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ በዚህም መሰረት የሕወሓት ህቡእ ቡድን ተሳክቶለታል፡፡ በመጀመሪያ ቡድኑ ራሱን በድብቅ ከመሰረተ በኃላ ለም መሬት የሆነውን ራያን ለራሳቸው አደረጉ፤ቀጥሎም በአለም አቀፍ ደረጃ ያሳወቃቸውን ሰሊጥ ኤክስፖርት የሚያደርጉበትን መተማን ጠቅልለው ወሰዱ፤ ከዚያም የሰሜን ወሎ የቆቦን ግማሽ ክፍል ወሰዱ፤ ሌላውን ክፍል ህዝቡ አመጸባቸው፡፡ ይህን የሚያደርጉት የአጎራባች አካባቢዎችን ተወካዮች በመምረጥና ራሳቸው የማህበረሰቡ አካል በመሆን የትግርኛ ቋንቋ በማስተማር ፤የህብረተሰቡን ተወካዮች መቀሌ ከተማ በመውሰድ አይተውት የማያውቁትን መስተንግዶ በማሳየትና በቅንጦት በማሳበድ ህዝቡን እንዲያሳምኑላቸው ያደርጋሉ፡፡ይህ የህቡእ ቡድኑ ትእዛዝ ነው፤የሰቆጣ መሬት አፈሩ የተጎሳቆለ በመሆኑ ለጊዜው ኢላማቸው አይደለም፡፡ አሁን ደግሞ

አይናቸውን በጨው አጥበው፤በፍጹም ንቀት የኢትየጵያን ሀዝብ የሚያበሳጭ ስራ ሰሩ፤ የጀግናውን የጎንደር ህዝብ ፤ለኢትዮጵያ ታላቅነት ባለውለታ ህዝብ፤ከኢትዮጵያ አንድነት ውጭ ሌላ ህልም የሌለውን የጎንደር ህዝብ፤የአማራ ህዝብ ቅስም የሚሰብር ፤ያኔ ስልጣኔ ባልነበረበት ዘመን እንኳ ከጎጠኝነት በጸዳ ስለሀገር ሲጨነቅ የነበረው የአማራ ህዝብ አሁን ሀገሪቱ ሲኦል ሆና ከዳችው፤እሱም አንደ ኦሮሞ አና እንደ አፋር መኖሪውን እየተነጠቀ ሀገሬ ናት ብሎ ሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች ሆዱን ለመሙላት ሲባክን በሄደበት ይገደላል፡፡ እናም የክልል ሶስት ንብረት የሆነውን ወልቃይት የሰሜን ጎንደር ሰፊ ለም መሬት ለራሳቸው አደረጉ፡፡ የአመጹ መሪ ተዋናይ ኮለኔል ደመቀ ዘውዴ በአንደበቱ እንዲህ ሲል ተናገረ ‘ ትገሬ ነኝ ብለህ ወላቃይት ለትግራይ እንደሆነች ማረጋገጫ ስጥና ሁለት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር( 2,500,000 ብር) እንስጥህ አሉኝ ፤እምቢ ሀገር በብር አይሸጥም አልኳቸው ፤ አንለቅህም ብለውኛል ፤ ህዝቤ ሆይ እኔን እንደሚገሉኝ አውቃለሁ አንተ ግን ትግልህን ቀጥልና ሀገርህን አስመልስ ፤እንደኔ ለለሀገርህ ከታገልክ እኔም እተርፋለሁ ፤አደራ ብሞትም ትግልህ እንዳይቆም ብሎ ተናገረ’ ህዝቡም ሸለመው ዳግማዊ አጼ ቴወድሮስ ብለንሃል አለው፡፡ ጎንደር፤አምቦ፤ባህር ዳር፤ሀረር ፤ደሴ፤አዲስ አበባ፤ወለጋ፤ጂማ የግብጹን ታህሪር አደባባይ ለመድገም ተዘጋጅተዋል፡፡ጎንደርና ጎጃም እንደወንድሞቹ የወለጋ፤የአምቦ፤ የሻምቡ ፤የሐረር፤የኮንሶ፤የአዲስ አበባ፤ወዘተ ህዝቦች ወጥቶ ሲያለቅስ የሕወሓት ወታደሮች ጥይት አርከፈከፉበት፤የአጋዚ ወታደሮች ምስኪኑን ህዝብ ጭንቅላቱን በስናይፐርና በመትረየስ አፈራረሱት፡፡ይህም የህቡእ ኮሚቴው ሴራ ነው፡፡ቅድመ ጠላታቸው አድርገው የሚያስቡት የክልል ሶስት ህዝብ ከሌሎች የኢትዮጵያዊነት መንፈስ አቀንቃኝ ህዝቦች ጋር አጣሉት አዋረዱት፡፡እነ አቦይ ስብሀት፤ደብረ ጽዮን ፤ ሳሞራ የኑስ እና ሌሎች የሕወሓት አመራሮች ቡድኑን በግንባር ቀደምትነት ይመሩታል፡፡ ኢትዮጵያም የምትመራው እነዚህ ሰይጣን ሰዎች በሚያስተላልፉት መልእክት ነው፤የኦህዴድ፤የብእዴን፤የደህዴን ቡችሎች እንደ መሳሪያ ወይም የሴረኞች መልእክት ማስተላለፊያ ማይክራፎኖች ናቸው፡፡ከዚህ የበለጠ ሚና ባይኖራቸውም ለህዝቡ አይን ማረፊያ መሰረተ ልማቶችና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞችን ስለሚሰሩ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡ ነገር ግን ንጹህ ሰዎች አይደሉም ፤ካሳ ተክለ ብርሃን አማራ አይደለም፤አባዱላ ኦሮም አይደለም፤ ኩማ ደመቅሳ ኦሮሞ አይደለም፤በረከት ስምኦን ኤርትራዊ ነው ፤ ነገር ግን በብእዴን ና ኦህዴድ ስም ተገደው ይኖራሉ፡፡

የኢትዮጵያ የመንግስት መዋቅር ከ95 በመቶ በላይ የተያዘው በሕወሓት አመራሮች ነው፤ቀሪው 5 በመቶ በሌሎች ቢሆንም ምክትላቸውና ደህንነቶች የራሳቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ለአብነት ብንመለከት የሕወሓት ህቡእ ቡድን አጀንዳዎች የሚከተሉት ናቸው፡- ቁልፉ የመከላከያ ሚኒስተር በሕወሓት አመራሮች እጅ ነው፤ከ95 በመቶ በላይ የወታደር አመራሮች በየቀጠናው የሕወሓት ሰዎች ናቸው፤ ውትድርና የተከበረ ሙያ ነው ለሌላው ግን ፈተና ነው፡፡የመረጃና ደህንነት መረብ ኤጀንሲ ውስጥ ከባለሙያ ጀምሮ የሕወሓት ሰዎች ናቸው፡፡ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ፤የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ፤አራት ኪሎ ከወታደር ጀምሮ የአንድ ቋንቋ የበላይነት ይታይበታል፡፡ በአዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ ቁልፍ የመንግስት መዋቅሮች የተያዙት በሕወሓት ሰዎች ነው፤ታጋይ ነኝ ያለ ሁሉ ባይማርም ዲግሪ ተሰጥቶት መሪ ይሆናል፤ አሁን ደግሞ ታጋይ ሲያልቅባቸው ለሰዎቻቸው ታጋይ የሚል ታፔላ እየተለጠፈ ወደ አዲስ አበባ እየተላኩ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ ታላላቅ ሆቴሎች፤ታላላቅ ህንጻዎች፤የንግድ ቦታዎች፤ አስመጭና ላኪዎች፤ታላላቅ የግል ኮሌጆች፤የግል ት/ቤቶች፤ኢንቨስትመንቶች፤ የኮንስትራክሽን ተቋራጮች ፤ታላላቅ የቢዝነስ ቦታዎች ለሕወሓት ሰዎች ነው፡፡ ለኢንቨስትመንት ተብሎ የሚሰጠው ቦታ ለማንም የኢትዮጵያ ህዝብ አይሰጥም፤ማንም ጠይቆ የኢንቨስትመንት ቦታ አያገኝም፤መሰናክሎች ይበዙበታል፤የትግራይ ተወላጅ ሆኖ በሕወሓት ዘሩ የተጠና ከሆን ጉዳይ ለማስፈጸም በሚሄድበት ቢሮ ሁሉ የይለፍ ደብዳቤ ተዘጋጅቶ ይጠብቀዋል፤ይህ የኢሉሚንስቶች አሰራር በሕወሓት መንግስት ተግባራዊ መደረግ ከጀመረ ቆይቷል፤ አብዛኛው የሕወሓት ዘር ያለው ሰው በአዲስ አበባ ውስጥ በግልም በመንግስትም የተሰጠው ከበቂ በላይ መኖሪያ ቤት አለው፡፡ከ100 ሚሊዮን በላይ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ግን አንኳን ቤት ሊኖረው ነገ ስለሚበላው ምግብ ሲጨነቅ ያድራል፡፡ ቢርበውም ጤና የሰጠኽኝ አምላኬ እያለ እያመሰገነ ይተኛል፡፡

አነጋጋሪው ጉዳይ ደግሞ ለሱዳን የተሸጠው መሬት አቀማመጥ ከትግራይ ተነስቶ ወደ ጎንደር 60 ኪሎ ሜትር ገባ ብሎ እስከ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ታላቁን የህዳሴ ግድብ ያለበት ስፍራ የሚነካ ቦታ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ በታላቅ ሞራልና ቁጭት የሚሰራው ግድብ ቢሆንም በአስደናቂ ሁኔታ የሕወሓት ህቡእ ቡድን እጁን ማስገባቱ ነው፡፡ የአሁኑ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን በወቅቱ የክልል ሶስት ምክትል ፕሬዝዳንት የነበረ ሲሆን የወቅቱ የክልል ሶስት ፕሬዝዳንት አቶ አያሌው ጎበዜ ከላይ የተጠቀሰው የመሬት ይዞታ ለሱዳን ይሸጥ የሚል ጥያቄ ሲቀርብላቸው አሻፈረኝ በማለታቸው በሌላ ምክንያት ወደ አሜሪካ እንዲሄዱ የሕወሓት ህቡእ ቡድን አዘዘ፡፡ ከዚያም ይህ የአሁኑ ምክትል ጠ/ሚንስተር ደመቀ መኮንን ቢሮ በመግባት የክልሉን መሬት የሽያጭ ውል እንዲፈርም ተደረገ፡፡ በጣም ለማመን የሚከብደው ግን ይህ የጎንደር ፤የቤንሻንጉል ጉሙዝ መሬት እስከ ግድቡ ድረስ ያለው በውሉ መሰረት ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ በኋላ ለሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ለትግራይ ክልል የሚመለስ እንደሆነ በተረዳ ጊዜ አቶ ደመቀ መኮንን ቅሬታ ቢያቀርብም በሳሞራ የኑስ ወታደሮች ታፍኖ የተለያዩ ማስፈራሪያዎች ሞትን ጨምሮ ተሰጠው፡፡ እሱ ግን በወቅቱ ከተሰጠው አማራጮች ለሱ የሚሻለውን አሁን ያለበትን ቦታ መረጠ፡፡

ይሁንም እንጅ ይህች ቅድስት ሀገር ሁሉም ሀይማኖቶች ተዋደው ተከባብረው የኖሩባት አምላክ ቃልኪዳኑን የሰጣት ሀገር ወደ ነበረችበት ታላቅነት ትመለሳለች፡፡

የትግራይ ህዝብ ሲበዛ ደግ ህዝብ ነው፤ለትግራይ ምስኪን ህዝብ ትልቅ ክብር አለኝ፤የተከበረና አምላክን የሚወድ በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ አክሱም ጽዮንን ጠብቆ የኖረ፤ታላቁን የሙስሊም መስጂድ የጠበቀ፤ታታሪና ለፍቶ አዳሪ የእግዚአብሔር አምላኪ ህዝብ ነው፡፡ ነገር ግን ከእሱ አብራክ የወጡ ምንም ሳይኖረው ፤ሳይማር ያስተማራቸው ልጆቹ ሀገር ሻጭ እንደሆኑ አያውቅም በድብቅ ለእርሱ እንደሚሰሩለት እንኳን አያውቅም፡፡የትግራይ ህዝብ ኢትዮጵያዊ መሆን ይፈልጋል፡፡ነገር ግን ባለስልጣናትና የተማረው የትግራይ ህዝብ ይህን ስሜት አይወደውም፡፡ስለዚህ የመሰናዶ ትምህርት አጠናቀው ወደ ተለያዩ ክልሎች የሚሄዱ ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ የሕወሓት ህቡእ ቡድን ሚስጥር በጥቂቱ ይነገራቸዋል፡፡ከዚያም ራሳቸው ተመራምረው አላማውን ማወቅ ይችላሉ፡፡ተራውና ኗሪው የትግራይ ህዝብ በነዚህ ትንሽ ሰዎች በመላው ኢትዮጵያ እንዲጠሉ፤እንዲዋረዱ ፤አንገታቸውን ዝቅ አድርገው እንዲሄዱ፤ በቋንቋቸው እንዲያፍሩ፤ስማቸውን ከክርስትና ስማቸው ውጭ እንዲያወጡ እያደረጋቸው ነው፡፡የሕወሓት ህቡእ ቡድን በዚህ ሴራው አላቆመም ሁሉንም የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተለያዬ ታሪክ በመፍጠር ማፋጀት፤መግደል፤ማዋረድ ቀጥሎበታል፤የራሱን ወገን ጨምሮ፡፡

ከምንም በላይ የኦሮም ብሄር እየደረሰበት ያለው ግፍና መከራ ከልክ ያለፈ ነው፤ በየጊዜው የሕወሓት አመራር ከህቡእ ቡድን ጋር በመነጋገር በሚፈጥረው የጥፋት ስልት የኦሮሞ ህዝብ ለታላቅ ሰቆቃ ተዳርጓል፡፡አንደኛው በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጉዳይ ባነሱት ጥያቄ ብቻ ከ400 በላይ ንጹህ ኢትዮጵያዊ የክልል አራት ልጆች ተገድለዋል፤ ብዙዎች ቆስለው አካል ጉዳተኛ ሆነዋል፤ ሌሎቹ አሸባሪና የኦነግ ተላላኪ ተብለው ከርቸሌ ገብተዋል፤ቀሪዎቹ ታፍነው የት እንደገቡ አይታወቅም ፡፡

የሕወሓት ህቡእ ቡድን ማስተር ፕላኑ ለምን አስፈለገው?

የማስተር ፕላኑ ዋና አላማ የአዲስ አበባ ከተማን ለማሳደግ ብቻ ሳይሆን የሕወሓት ወገን ኢንቨስተሮችን ለመጥቀም የታቀደ ነበር፡፡አዲስ አበባ ውስጥ ለኢንቨስትመንት ምቹ አለመሆንና በቂ ቦታ አለመኖሩ በሕወሓት ህቡእ ቡድን ተለይተው የተመዘገቡ ኢንቨስተሮች ቁጥር በመጨመሩ የታለመ እንጅ የኦሮሞን ህዝብ ለመጥቀም አልነበረም፡፡ጀግናው የኦሮሞ ህዝብ ግን ደሙን አፍስሶ ቅስማቸውን ሰበራቸው፤ እንደሚታወቀው የኦሮም ህዝብ ታጋሽ፤አዋቂ፤ለፍቶ አዳሪ፤ለታሪኩ የሚጨነቅ ህዝብ ነው፡፡ ኦሮሞን ከሌሎች ክልሎች በማጋጨት በሕወሓት ህቡእ ቡድን በተመለመሉ በመቶ ሺዎች በሚቆጠሩ የደህንነት አባላት አማካኝነት በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች በሚስጥር በመዘዋወር የህዝቡን ልብ፤የህዝቡን ታሪክ በመለወጥ፤ያልሆነ ታሪክ በመፍጠርና በማሳመን እንደቀላል የታሪክ አጋጣሚ የሚታለፉ ጉዳዮችን እንደ ትልቅ የፖለቲካ ትርፍ ይጠቀማሉ፡፡ይህንን ደግሞ የክልል አራት ህዝቦች በግልጽ አውቀውታል፡፡

በቅርቡ ወንድምሀ የእናትህን ጡት ቆርጧል ለምን ዝም ትላለህ ብሎ ከስር ከስር መርዛቸውን ረጩባቸው ስለዚህ አኖሌ ላይ ሀውልት በማቆም ሁልጊዜ በማሳየት የዘላለም ጠላትህ ናቸው አሉት፤ የራሳቸውን ጥላቻ ለሁሉም ማካፈላቸው ነው፡፡በአንድ ብሄርና በአንድ ሀይማኖት ተመርተሃል እያሉ 25 አመት ሙሉ ጆሯችንን አደነቆሩት ፤ በዚህ ዘመን ሌሎች ሌላ ፕላኔት ለመኖር እተዘጋጁ ባሉበት ጊዜ፤የኢትዮጵያን ህዝብ የአማራ እምነት ያንተ አይደለም ይሉታል ፤ነገሩ እንዲህ ነው አንድ ሀገር ሀገር ሆና እንድትቀጥል የሆነ ትውልድ ጥረት አድርጓል፤ዛሬ ደግሞ የሁሉም ሚና ነው፡፡

ቤንሻንጉል ጉመዝ ክልልን በታላቋ ትግራይ ግዛት ስር ለማድረግ በቡድኑ የደህንነት አባላት አማካኝነት ለየዋሁ የጉሙዝ ማህበረሰብ ታሪክ በመፍጠር በሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ህዝቦች ተፈናቀሉ፤ ተገደሉ፤ተራቡ፡፡ በደቡብ ክልል ጉራፈርዳ ወረዳ የክልል ሶስት ሰዎች እንዲገደሉ ፤እንዲፈናቀሉ ተደርጓል፡፡

ለኢትዮጵያውያን ግልጽ ያልሆነው ጭቆና ደግሞ ታዳጊ ክልሎች እየተባለ አፋር፤ሶማሌ፤ ጋምቤላ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፤ የኦሞ ማህበረሰብ፤የኮንሶ ማህበረሰብ፤የአዊ ማህበረሰብ፤ የቦረና ማህበረሰብ ወዘተ ታዳጊ ወይም የአእምሮ ዝግመት ያለበት ህዝብ ነው ብለው በመናቅ ከውጭ በሚመጣ እርዳታ(ፍርፋሪ) ብቻ ሆዳቸውን እንኳ በማይሞላ ስንዴ ብቻ ደልለው ለዘላለም ተመጽዋች ሲያደርጓቸው የኢትዮጵያ ህዝብ ዝም አለ፡፡ እነዚህ ክልሎች ያላቸውን አስገራሚ የተፈጥሮ ሀብት እየሄዱ ይዘርፋሉ፤ለውጭ ሀገር ዜጋ ያዘርፋሉ፤ ኢትዮጵያዊ ውስጥ ነዳጅ እንዳይወጣ የበኩላቸወን ጥረት አደረጉ፡፡ይህም የሕወሓት አመራሮች ሚስጥራዊ ሴራ ነው፡፡

ህቡእ ኮሚቴው የራሱን ሰዎች ቻይና፤ጀርመን፤አሜሪካ እና ሌሎች ሀገሮች እየላከ የሀገርን ሚስጥር ለመዝረፍ የሚያስችል ትምህርት ያስተምራል፤ሌላውን የኢትዮጵያ ልጅ አቡጊዳ ተማር ይላል፤የእርሱ አባላት የመጠቀ የቴክኖሎጅ እና ምጡቅ የሆነ ትምህርት አስተምሮ እንዲሰልሉለት ያሰማራል፡፡

እርሱ ባጸደቀው ህገ-መንግስት የብሔርብሔረሰብ መብት፤የቋንቋ እኩልነት እያለ የአካባቢውን ቋንቋ ተናጋሪ የሆነ ማህበረሰብ ወደፈለገው ክልል መሄድ ይችላል በማለት የክልል ሶስት አካባቢዎችን ትግረኛ ቋንቋ በማስተማርና የተለያዩ ሴራዎችን በመጠቀም ግዛቱን እያስፋፋ ነው፡፡ ቀድሞ የተሰረቀው የራያና የመተማ ህዝብ ከፊል ዜጋ ሆኖ ለም አፈሩን ብቻ እየተጠቀሙበት ባይተዋር ሆኖ ይኖራል፤ ሰሜኑ የትግራይ ክፍል ለነዚህ አካባቢዎች ዝቀተኛ ግምትና ከፍተኛ ንቀት አሏቸው፤ያገሏቸዋል፡፡

ክልልን በቋንቋ ማስፋፋት ቢሆንማ ብዙ የኦሮምኛ ተናጋሪዎች በኦሮሞ አጎራባች አካባቢዎች ይገኛሉ፤ኦሮሞ ይህን እድል ተጠቅሞ ክልሉን ለማስፋት ሴራ አልጠነሰሰም፤ በክልል ሶስት መሬት ልዩ የኦሮምያ ዞን ተብሎ በደቡብ ወሎ የሚገኙ ሰፋፊ ቦታዎች ቋንቋውንና ባህሉን ስለሚያዉቁ ተብሎ ወደ ክልል ሶስት ለማጠቃለል አይፈልግም፡፡

ስለዚህ ይህ ህገ መንግስት የሚሰራው ለሕወሓት ብቻ ነው፡፡ ግን እስከ መቼ ካልን ጊዜው አሁን ነው፤አሁን፤ዛሬ፤በቃ!!!

በኢትዮጵያ የጦር መሳሪያ ትጥቅ ህግ በተመለከተ ለሁሉም የማህበረሰብ ክፍል መሳሪያ መስጠት አግባብ ባይኖረውም ሕወሓት ኢትዮጵያን እንደተቆጣጠረ ለድርጅቱ ደህንነት በማሰብ የመጀመሪያው ተግባር የኦሮሞ፤የአማራ፤የአዲስ አበባ፤አፋር፤ደቡብ፤ ጉሙዝ ወዘተ ህዝቦችን ማሳሪያ መንጠቅ ታላቅ ተግባር ነበር፡፡ የአማራና ኦሮሞ ህዝቦች ያለ ምንም ቅደመ ሁኔታ እየተገረፉ መሳሪያ አንዲመልሱ ተደርጓል፡፡በአሁኑ ሰዓት ደግሞ ከትግራይ ህዝብ ከመቶ እጥፍ በላይ የሚሆን መሳሪያ በሕወሓት ህቡእ ቡድን አማካኝነት ተጓጉዞ ወደ ክልል አንድ ገብቷል፤በየቀኑ ሳይፈተሹ የሚገቡ የተከለከሉ የጦር መሳሪያዎች ጭምር ይጋዛሉ፤ይህን ሚስጥር ያወጣ አንድ የፓርላማ አባል አሁን በእስር ላይ ይገኛል፡፡

ይህ ታላቅ የህዝብ ጥሪ ነው፡፡

በሊቪያ ፤በግብጽ ፤በቱኒዝያ፤በሶሪያ፤በየመን የተቀሰቀሰው አመጽ መንግስት ቀይሯል፤አሁን ደግሞ በኢትዮጵያ ተደገመ፡፡ መንግስት ስልጣን የሚይዘው ህዝቡን በሰላም፤በምቾት፤በእውነት እንዲመራ ነው፤በረሃብ ፤በመግደል፤በማሰቃየት፤ሀገር በመሸጥ፤የሌለውን ክልል መሬት በመንጠቅ ለሌላው በመስጠት መሆን የሌበትም፤ ወንድም ከወንድም ማጋጨት መሆን የለበትም፡፡ ስለዚህ የኢትዮጵያ ህዝብ ከዳር እስከዳር የተነሳው የበቃኝና የመሰላቸት ጩኸት መቀጠል ይኖርበታል፤በሐረር፤በድሬዳዋ ፤በአዲስ አበባ ፤በወለጋ፤በባህርዳር፤በጎንደር፤በደብረታቦር፤በደብረማርቆስ የተነሳው አመጽ በሁሉም አካባቢዎች ይጠናከራል፡፡

እግዚአብሔር አንድ ጊዜ ለዚህች ሀገር ቃልኪዳን ሰጥቷል፤በአንድ ወቅት ኢትዮጵያ ሀያል ሀገር እንደምትሆን ቅዱሳዊ ትንቢት አለ፤ኢትዮጵያ በአንድ ወቅት ከአሜሪካ በላይ ሀያል ሀገር ትሆናለች፡፡

ስለዚህ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ተነስ ምን ትጠብቃለህ ይህን ባንዳ መንግስት በቃህ በለው!!!

***********************
ኢትዮጵያ ከሕወሓት ቅኝ አገዛዝ ትላቀቃለች ወደ ቀድሞ ታላቅነቷ ትመለሳለች!!

“ለሱዳን ተሸጠ የተባለው መሬት፤ወልቃይት፤ራያ፤አላማጣ፤መተማና ቆቦ የኢትዮጵያ ናቸው፤እነዚህ ቦታዎች ሳይመለሱ ኢትዮጵያ ዝም አትልም፤ ማሪያምን!!!” Love Ethiopia

*************************
ይህን መረጃ ኮፒ በማድረግ ለሌሎች ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውን ይድረስ፡፡

ምንጭ፡- የወጣ ሚስጥር፤ከተለያዩ ድህረ ገጾች፤መጽሃፍትና ከወቅታዊ ጉዳዮች የተቀነጫጨበ (05/12/2008ዓ.ም ተጻፈ)

ነሀሴ 5/2008 ዓ.ም ሰላም፤ነጻነት፤አንድነትና ብልጽግና ለኢትዮጵያ!! ABTAGAAF!

ነሀሴ 5/2008 ዓ.ም ሰላም፤ነጻነት፤አንድነትና ብልጽግና ለኢትዮጵያ!! ABTAGAAF!

↧

የትግሬ-ወያኔ የዐማራ እና የኦሮሞ ነገዶችን ሕዝብ ጨርሶ ለማጥፋት ያቀደው ሚስጢራዊ አዲስሤራ –ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

$
0
0

            ማክሰኞ ነሐሴ ፲ ቀን ፪ሺህ፰  ዓ.ም.             ቅፅ ፬ ፣ ቁጥር ፳፪

Moresh-901.jpgላለፉት 25 ዓመታት የትግሬ-ወያኔ በሕዝብ ላይ የፈጸመው ግፍና በደል ከመጠን በላይ በመሆኑ፣ ሕዝቡን ለእምቢተኝነት አነሳስቷል። ይህ ግፍና በደል መጠን የለሽ በመሆኑ፣ በአገሪቱ ልዩ ልዩ ክፍሎች፣ በተለይም በጎንደር፣ በጎጃም፣ በሸዋ፣ በወሎ፣ በሐረርጌ፣ በአርሲና በወለጋ ክፍለ-ሀገሮች የሚኖረው ሕዝብ፣ የትግሬ-ወያኔ «ለብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ዕኩልነት» ሲል «አመጣሁት» ያለውን «ሕገ-መንግሥት» የማይቀበለው መሆኑንና፣ የዚሁ  «ሕገ-መንግሥት» ተብየ መገለጫ የሆነውን ሠንደቅ ከተሰቀለበት በማውረድ፣ ከጥንት ጀምሮ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት መገለጫ፣ የነፃነት ቀንዲል የሆነችው ሠንደቅ ከፍ-ብላ እንድትውለበልብ እያደረገ መሆኑ በግልጽ ተስተውሏል። ይህም የትግሬ-ወያኔ አመጣሁት ያለው ዕኩልነትና የነገዶች አንድነት ውሸት መሆኑን፣ ባንፃሩ ግን የትግሬ-ወያኔ የውስጥ ቅኝ ገዥ ኃይል እንደሆነ፣ በተከታታይ በተደረጉት የሕዝባዊ እንቢተኝነት ሰላማዊ ሰልፎች በግልጽ ታይቷል።

ይህ የሕዝብ አመጽ ያርበደበደው የትግሬ-ወያኔ ቡድን፣ የሚይዝ የሚጨብጠውን በማጣቱ፣ የእርሱ ምርኮኛ የሆነውንና በጥቅማጥቅም የገዛውን የትግራይ ትውልድ በነቂስ አስታጥቆ፣ በዐማራና በኦሮሞ ነገዶች ሕዝብ ላይ ለመዝመት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስተማማኝ ከሆኑ የውስጥ ምንጮቻችን ያገኘናቸው መረጃዎች ያሳያሉ። የትግሬ-ወያኔ ከሚያደርገው ሠፊ የጥፋት ዝግጅቶች ውስጥ፣ የትግራይን ትውልድ «በትግልህ ያገኘኸውን ልዩ መብትና ነፃነት፣ ትምክተኞች፣ ነፍጠኞች፣ የድሮው ሥርዓት አራማጆችና ዐማሮች ሊነጥቁህ ነውና ዐማራን ለማጥፋት ዝመት፣ ተንቀሳቀስ» በማለት፣ በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በጠለምት፣ በአርማጭሆ ነዋሪዎች ላይ ክተት አውጇል። በአጠቃላይም በጎንደር፣ በጎጃም፣ በሸዋና በወሎ የዐማራ ነገድ ሕዝብ ላይ መጠነ ሠፊ የዘር ማጥፋት ወንጀል ለመፈጸም ዝግጅቱን አጠናቋል። በመሆኑም ሰሞኑን በጎጃምና በጎንደር የተለያዩ ከተሞችና ገጠሮች ቅጥር የነፍሰ ገዳይ ቡድኖችን በማሰማራት ሌሊት ሌሊት ወጣቱን እየፈነ ወደ ማሰቃያ እስር ቤቶቹ እያስገባ መሆኑ ታውቋል።

ይህ ድርጊቱ ፍላጎቱን ሙሉ በሙሉ ሊሳካለት እንደማይችል በመረዳት፣ በመላ ኢትዮጵያ የሚያካሂደው ሌላም ሠፊ የጥፋት ዕቅድ አቅዶ ለተግባራዊነቱ በጥድፊያ እየሠራ መሆኑ እየተሰማ ነው። ይህም መጠነ ሠፊ የሆነ ጥፋት ያነጣጠረው በዐማራና በኦሮሞ ነገዶች ሕዝብ ላይ እንደሆነ ታውቋል። የትግሬ-ወያኔ በእነዚህ ነገዶች ሕዝብ ላይ የጥፋት ተልዕኮውን ለመወጣት ያቀደው ዕቅድ፣ «በዐረብ ኢሚሪቶችና በሻዕቢያ የሚታገዙ አሸባሪዎች፣ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመናድ እየተንቀሳቀሱ ነው» የሚለውን ሀሳብ የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ፣ በተለይም ሽብርተኝነት ለመዋጋት በሚል ሸሪክ የሆነውን የምዕራቡን ዓለምና የአሜሪካንን ልብ ለማማለል እንደሆነ ይገመታል። በዚህ ረገድ በቅርብ ቀናት ውስጥ የትግሬ-ወያኔ በሐረር፣ በድሬደዋ፣ በጎንደር፣ በባሕር ዳርና መሰል ከተሞች፣ የሕዝብ ክምችት በሚበዛባቸው ቦታዎች፣ በመንግሥታዊ ተቋሞች፣ በመገናኛ አውታሮች ወዘተርፈ ፈንጅ በማፈንዳት እኩይ ዓላማውን በተግባር እንደሚያውል ውስጥ አዋቂዎች አስጠንቅቀዋል። ፈንጂዎችን ራሱ አፈንድቶ፣ «የዐማራ እና የኦሮሞ ጽንፈኞች እንዲህ አደረጉ» በማለት ለደጋፊዎቹ  የተቀነባበረ የሤራ መረጃ በማቅረብ፣ «ሕገ-መንግሥት» ተብየውን አግዶ፣ የአስቸኳይ ጊዜ ወታደራዊ አገዛዝ በማወጅ፣ በሁሉም ቦታዎች ለወያኔ ጄኔራሎች የመግደልና የማሰር ሥልጣን በመስጠት በዐማራውና በኦሮሞው ነገዶች ሕዝብ ላይ መጠነ ሠፊና አሰቃቂ ዕልቂት ለመፈጸም ቁርጠኛ አቋም መያዙ ታውቋል።

በሰኔ 1980 ዓ.ም. «ነፃ ላወጣህ መጣሁ» ባለውና በራሱ ነገድ በሆነው የሀውዜን ከተማ ነዋሪ ሕዝብ ላይ ያን የመሰለ የተቀነባበረ ሤራ ሠርቶ ሕዝብ ያስጨረሰ ድርጅት፣ «ጠላቶቼ ናቸው» ባላቸው የዐማራና የኦሮሞ ነገድ ሕዝብ ላይ ይህን ዓይነቱን ድርጊት አያቅድም፣ አይፈጽምም፣ አያደርጉትም፣ አይሆንም የሚያሰኝ አመክንዮ አይኖርም። ኢትዮጵያዊ የሆኑትንና «ለትግሬ-ወያኔ ዓላማ አንገዝም፣ አባልም አንሆንም» ያሉትን የትግራይ ልጆች፣ «አባሎቼ ናቸው» የሚል የተቀነባበረ የሐሰት መረጃ፣ ለደርግ የመረጃ አካላት እያቀበለ ወገኖቹን ያስጨፈጨፈ ድርጅት ይህን አያስብም አይባልም። በሂደት እንዳስተዋልነው፣ ወያኔ «አደርገዋለሁ፣ አጠፋዋለሁ» ብሎ ያቀደውንና ያለው በተግባር ከመፈጸም ወደ ኋላ ያለበት አንድም አጋጣሚ አላየንም። ይህንም እኩይ ድርጊት አያደርገውም ለማለት የሚያስችል ምክንያት ለማቅረብ አስቸጋሪ ነው።

የትግሬ-ወያኔ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን፣ ዐማራንና ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖትን አጠፋለሁ ብሎ አቅዶ መነሳቱ ይታወቃል። በዕቅዱ መሠረትም 5 ሚሊዮን ዐማራ አጠፋ። የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አመራርን ከሦሥት ከፈለ፥ የአገር ቤትና ስደተኛ ሲኖዶሶች እንዲሁም ገለልተኛ በሚል። የሃይማኖቱ ነባር ተቋሞችን፣ ለምሣሌ ያህል፥ የዋልድባን፣ የዝቋላ አቦን እና የማኅበረሥላሴን ገዳማትን አቃጠለ፤ ቅጥረ ግቢያቸውን መነጠረ። የሃይማኖት አባቶችን አሰደደ። ቱባ ባለሥልጣኖቹ ዐባይ ፀሐየ፤ ስብሃት ነጋ፣ መለስ ዜናዊ፣ ሣሞራ የኑስ ሌሎችም በአደባባይ፣ «ዐማራና ኦርቶዶክሱን አከርካሪውን ሰብረነዋል፣» «ገድለን ቀብረነዋል» ማለታቸውን አንዘነጋም። እናም ባለፉት 25 ዓመታት ገድለው ካልጨረሱት ውስጥ የቀረውን የዐማራና የኦሮሞን ነገዶች ሕዝብ «አስቸኳይ ወታደራዊ» አገዛዝ በማወጅ ሊጨርሱት ቁርጥ ሀሳብ ማድረጋቸውን የዐማራውና የኦሮሞው ነገድ አባሎች ለአፍታም መጠራጠር አይኖርባቸውም። ስለሆነም፣ የትግሬ-ወያኔ ዝግጅቱን አጠናቅቆ ወደ ጥፋት ተልዕኮው ሳይገባ፣ ዐማሮችና ኦሮሞዎች ዕቅዱን ለማክሸፍ መተባበር ይጠበቅባቸዋል።

ከሁሉም በላይ «ሺህ ጋን ቢታለብ ወይ በገሌ» እንዳለችው ድመት፣ ዐማራው በብሔርተኞቹ ድርጅቶች በቀና ስለማይታይ፣ ልጆቹ በመካከላቸው አለን የሚሏቸውን ጥቃቅን ልዩነቶች በማርገብ፣ በአንድነት በመቆም ለወገናችን መከታ መሆን ይጠበቅብናል። የዐማራው ምሁራንና ፖለቲካኞች በአንድነት መቆም፣ የአንድነት ኃይሉን ለተፈላጊው አጠቃላይ የኢትዮጵያውያን አንድነት ጽኑ መሠረት ስለሚሆን፣ የዐማራው ምሁራን በቅድሚያ የነገዳቸውን አንድነት ዕውን በማድረግ፣ በሌሎች አቻ ቡድኖችና ድርጅቶች ላይ መልካም ተጽዕኖ ማሳደር ይጠበቅባቸዋል። ይህን ለማድረግ ስበቦችን መደርደር አስፈላጊ አይደለም። በወገናችን አንገት ላይ ሳንጃ ተጥሏል፤ በግንባርና ደረቱ ላይ አፈሙዝ ተደግኗል። ስለዚህ ይህ ጊዜ አይሰጥምና በዐማራ ስም የተደራጃችሁ ድርጅቶች ከያላችሁበት «አለን» ብላችሁ በጋራ የምትሠሩበት መንገድ ካሁኑ ካልጀመራችሁ፣ ይህንም ለወገናችሁ በግልጽ ካላሳያችሁ፣ የጥፋቱ አካል እንጂ፣ የመፍትሔው አካል ናችሁ ብሎ ማኅበረሰቡም ሆነ ታሪክ  ሊያወሳችሁ እንደማይችል በእርግጠኝነት መናገር ድፍረት አይሆንም። ስለሆነም ሁላችንም ለዐማራው ኅብረትና አንድነት ኅሊናችን ከፍተን በቅንነት እንነሳ! በዚህ የመከራ ጊዜ የዐማራው ልሂቅ በአንድነት ቆሞ፣ ለወገኖቹ ቤዛ ካልሆነ ምንጊዜም ዐማራው አንድ ይሆናል ለማለት ያስቸግራል። እንኳን የአንድ ታላቅና ታሪካዊ ነገድ ልጆች ቀርቶ፣ በክረምት እባብና ጓጉንቼር በአንድ ጉድጓድ ይኖራሉ። ይህ ክፉ የወያኔ ዘመን ዐማራውን ቀርቶ፣ ዐማራና ኦሮሞውን በአንድ ካላሰላለፈ የኢትዮጵያ አንድነት ርቆ የተሰቀለ ባዶ ተስፋ ከመሆን አያልፍም።

 

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!

ዐማራነት ነፃነት፣ ዕኩልነት አንድነት ነው!

ኢትዮጵያ በቆራጥና ጀግና ልጆቿ ታፍራና ተከብራ ለዘለዓለም ትኖራለች!

 

↧
↧

የፍራንክፈርት ከተማ ባሕርዳርንና ጎንደርን መስላ ዋለች! –ከ ኆኅተብርሃን ጌጡ

$
0
0

-ለ 25 ዓመታት የተገነባዉ የዘረኝነት ግንብ በመፈራረስ ዋዜማ ላይ


ቀኑ ዓርብ ነሐሴ 12 ቀን 2016 ነበር።  የትዕይንተ ሕዝቡ መገናኛ ማዕከል ቦታ ዋናዉ ባቡር ጣቢያ አካባቢ ነዉ። በተጠቀሰዉ የሰልፉ መጀመሪያ ሰዓት ኢትዮጵያዉያን አካባቢዉን አጥለቀለቁት። ፍራንክፈርት ከተማ በአረንጟዴ፣ ቢጫና ቀይ ኅብረ-ቀለም ባለዉ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ደምቃና ተዉባ ትታያለች። ከሁሉም የጀርመን ከተሞች በመምጣት ፍራንክፈርትን ከኢትዮጵያ  ከተሞች አንደኛዋ አስመስሏት ዉሏል። መነኮሳትና ቀሳዉስቱም ልብሰተክህኗቸዉን ደርበዉ ሰልፉን አድምቀዉታል። የሴቶች እህቶቻችንም ቁጥር ከሁልጊዜዉ በተለየ ቁጥሩ አይሎ የታየበት ብቻ ሳይሆን፣ ቁጭትና ሀገራዊ ስሜታቸዉም ከፊታቸዉ ላይ ይነበብበት የነበረ ሰልፍ ነዉ። የሰልፉ መጀመሪያ ፍራንክፈርት ዋናዉ ባቡር ጣቢያ ሆኖ፣ መዳረሻዉ ሄሰን ቲሌቪዥን ጣቢያ  ( Hessischer Rundfunk) እንዲሆን ነዉ የተዘጋጀዉ። ይህም የሆነበት ምክንያት የትዕይንተ ሕዝቡ (የሰላማዊ ሰልፉ) መደረግ ዓላማዎች ለጀርመን ሕዝብ በመገናኛ ብዙኃን እንዲተላለፍ ለማድረግ የታሰበበት እንደሆነ የሰልፉ አስተባባሪዎች በአፅንኦት ይናገራሉ። ካለፈ ተመክሮ በመነሳት ሚዲያዎች ወደ እኛ የማይመጡ ከሆነ፣ እኛ ወደ ሚዲያዎቹ በመሄድ የሰልፉ ዓላማ ወደምንኖርበት ሀገር ሕዝብ ጆሮ መድረስ ስላለበት ሂደን በራቸዉን መክፈት አለብን በሚል ዘዴ የታሰበ እንደነበር አዘጋጆቹ ጨምረዉ ይናገራሉ። የዚህ ፅሁፍ አቅራቢም የዓይን ምስክርነት ይሰጥበታል። ይህ ብቻም አይደለም። የሰላማዊ ሰልፉ መነሻና መድረሻ የቦታ ርቀት ወደ  6 ኪሎ ሜትር የሚጠጋ ሲሆን በዚህ ረዥም የእግር ጉዞ ግራና ቀኝ ሰልፈኛዉን እየተመለከተ ለሚገኘዉ የከተማዋ ኗሪ በጀርመንኛና በእንግሊዘኛ ቑንቑዎች የተዘጋጁትን  የሰልፉን ዓላማዎች የሚገልፁትን መፈክሮች በበቂም ለማደል እንደታቀደ ጊዜዉ አጭር ቢሆንም የታሰበበት ሰልፍ እንደነበርና እንደተሳካም አዘጋጆቹ አበክረዉ ይናገራሉ። ይህም በመሆኑ በጀርመንኛ ቑንቑ ተፅፎ በተበተነዉ ፅሁፍ ማለትም … Wie lange werden Diktatoren, die die eigene Bevolkerung umbringen noch von Deutschland und der EU unterstutzt ???? …. የገዛ ሕዝባቸዉን ለሚገሉና ለሚጨፈጭፉ አምባገነኖች ማለትም እንደ ኢትዮጵያ ላሉ መንግሥታት የጀርመን መንግሥትና የኤዉሮፓ ህብረት እስከ መቼ ነዉ እርዳታቸዉንና ድጋፋቸዉን የሚቀጥሉት? የተሰኙ መልዕክቶች ተላልፈዋል። ይህ ዓይነቱ መልዕክትም ታክስ ከፋዩ ሕዝብ የሀገሩን መንግሥት ለምን ብሎ እንዲጠይቅ የሚያስችለዉ አቀራረብ የሰላማዊ ሰልፉ አቅም መሆኑን በተግባር ለማሳየት ተሞክሯል። በዕለቱም ምሽት በጀርመን አገር ሁለተኛዉና ትልቁ የቴሌቪዥን ጣቢያ ማለትም ZDF (Zweites Deutsches Fernsehen)  እና ሰልፉ የተካሄደበት የሄሰን ክፍለ ሀገር ዋንኛ የቴሌቪዥን ጣቢያ በሆነዉ ሄሲሼር ሩንድፉንክ (Hessischer Rundfunk)  ኢትዮጵያዉያን  ለምን ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ እንዳስፈለጋቸዉ ተገቢ በሆነ መንገድ በዜና መልክ የሚዲያ ሽፋን አግኝቶ፣ ለጀርመን ሕዝብ መቅረብ ችሏል። ዓላማዉም ይህ ነበር እንጅ ለመዋጋት አልነበረም።

ታዲያ የሰላማዊዉን ሰልፍ ዜና ላዳመጠና የሰልፉን የትዕይንተ ሕዝብ ትርጉም ምንነት ከመነሻና እስከ መዳረሻ ለተከታተለ፣ ኢትዮጵያዊ ብዙ ነገሮች በአእምሮው ብልጭ ይሉበታል። በመጀመሪያ ደረጃ ያን ያህል ረዥም መንገድ ሰልፈኛዉ ሲጟዝ ፖሊስ ግራና ቀኝ ቆሞ የመኪና መንገዶች ሰልፈኛዉ እስኪያልፍ እየተዘጉ ነዉ። ዲሞክራሲ ባደገበት አገር ሕዝባዊ ሰልፍ ከብር አለዉ። አሽባሪዎች ተብለን አልተፈረጅንም። በሻዕቢያ ተላላኪነትም አልተጠረጠርንም። የአጋዚ ጦር በቦታዉ ስላልነበር መሞት ቀርቶ መገፍተር የደረሰበት ሰልፈኛም አልነበረም። አደለም መገፍተር በግልምጫ የታየም አልነበረም። እነሱ በቦታዉ ኖረዉ ቢሆን ኖሮ፣ ፍራንክፈርት በሚገኘዉ የሕወሓት/ኢሕአዴግ ቆንስል አጠገብ ሰልፈኛዉ ሲያልፍ  አንድ ቆራጥ ወጣት ኢትዮጵያዊ የእነሱን ኦፊሴላዊ ሰንደቅ ዓላማ አውርዶ፣ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ከቆንስላዉ ቢሮ  ጎን የመስቀል እርምጃ ሲወስድና ሲያዉለበልብ፣ ያለምንም ጥርጥር ቢያንስ መጠነኛ የሰዉ ሕይወት ማለፉ አይቀሬ ነበር። እና ማደግና የዲሞክራሲ ማበብ ለሰልፍም ሆነ ለሕዝባዊ ጥያቄዎች መልሱ ጥይት አይደለም። የእኛ መሪዎች የዲሞክራሲን ቃል ባፋቸዉ ደጋግመዉ ይጠሩታል እንጅ ከተግባሩ ጋር ግን አይተዋወቁም። ማወቅም አይፈልጉም።

ለሃያ አምስት ዓመታት የተገነባዉ የዘረኝነት ግንብ በመፍረስ ዋዜማ ላይ እንደሚገኝ ኢትዮጵያ ዉስጥም ሆነ በዉጭ አገር ከሚኖረዉ ሕዝባችን አንደበት የሚነገረዉ የሰሞኑ የሰላማዊ ሰልፎች መልዕክት አንድ እራሱን የቻለ የምሥራች ዜና ነዉ። በዕለቱ በፍራንክፈርቱ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ይስተጋቡ ከነበሩት መፈክሮች መካከልም …አማራም፣ ኦሮሞም አንድ ነዉ፣ የጋራ ሀገሩም ኢትዮጵያ ነች፣ ያለፈዉ አኩሪም ሆነ አሳፋሪ ታሪካችን የጋራችን እንጅ፣ የአንድ ወገን ዕዳ አይደለም፣ በየቦታዉ የሚነሱ የማንነት ጥያቄዎች በሕዝብ ይሁንታ ይፈታሉ እንጅ፣ በጫካዉ የወያኔ ሕግ አይዳኙም፣ የፖለቲካ ደመኛችን ወያኔ እንጅ፣ የትግራይ ሕዝብ ምንጊዜም ወገናችን ነዉ ወዘተ…. የተሰኙ መፈክሮች በአማርኛና በኦሮሞኛ ቑንቑዎች ሲስተጋቡ ዉለዋል። ያለምንም ጥርጥር ኢትዮጵያዊነት አሽንፎ እየወጣ ነዉ። ትናንት ለጎሪጥ በመተያየት ሁሉም በየፊናዉ ያደርገዉ የነበረዉ ሰልፍ ቀርቶ፣ ሁላችንም በኢትዮጵያዊነታችን ትዕይንተ ሕዝብ ስናደርግ ከዚህ የበለጠ ገዥዉን መደብ የሚያሸማቅቅ የፖለቲካ ድል ምን አለ?  የሃያ አምስት ዓመቱ የፖለቲካ መዘዉር ኢትዮጵያዊነት እንዲኮስስ ተደርጎ፣ በምትኩ፤ ኦሮሞነት፣ አማራነት፣ ሱማሌነት፣ ትግሬነት፣ ስልጤነት….ወዘተ እንዲነግሱ በማድረግ ኢትዮጵያዊነታችን ሆን ተብሎ  እንዲደበዝዝ  ስዉር የፖለቲካ ደባ ተሰርቷል።  ይህን ዘገባ እያዘጋጀሁ እያለሁ ጎረምሳዉ የመንግሥት የኮሜኒኬሽን ሚኒስትር አቶ ጌታቸዉ ረዳ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጥ ማለትም በእሱ አነጋገር በጣም ተናዶ፣ (… እሳትና ጭድ የሆኑ አስተሳሰቦች  ሁላችንም አንድ ነን በተለይም አማራም፣ ኦሮሞም አንድ ነዉ)  የሚለዉ የወቅቱ የኢትዮጵያዊነትን አሸንፎ የመዉጣት ድል የሚያንፀባርቀዉ መልዕክት … እንዴት አንድ ሊሆኑ ይችላሉ? በማለት በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ብስጭቱ ከፊቱ ላይ ይነበብ ነበር። ጋዜጠኞቹ ሰዉየዉን እንዴት ይመለከቱት እንደነበር ለተከታተለ ሰዉ ይህ ሰዉ በዕዉኑ ጤነኛ ነዉን? ይሉ እንደነበር ያለማጋነን ከፊታቸዉ ማንበብ ይቻላል። ጋዜጠኞቹም አሳዘኑኝ። የሚያምኑበትን ሳይሆን በእንጀራ ምክንያት መንግሥት እንዲባል የሚፈልገዉን  ማዘጋጀት ስላለባቸዉ  መግለጫዉን እየተከታተሉ ለጎሪጥ በመተያየት ይጎሻሸሙ ነበር። እንዳይሳሳቁ ካሜራዉ ያጋልጣቸዋል። የሆድ ሕመም ሆኖባቸዉ፣ የማይቻል የለም ቻሉት። እነሱም አንድ ቀን ነፃ ይወጣሉ። ሁሉም ጋዜጠኞች እስክንድር ነጋንና ተመስገን ደሳለኝን መሆን አይችሉም። እንደ ሻማ ቀልጦ ለሌሎች መብራት የመሆን መስዋዕትነት ግለሰብም ሆነ ትውልድ ቁጥሩ ገፍ አይደለም። ይህ ጥቂቶች የሚታደሉት በደም የሚፃፍ የታሪክ አሻራ ነዉ። መፅሃፉ …የተጠሩ ብዙዎች የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸዉ… እንደሚለዉ መሆኑ ነዉ። መስዋዕትነቱም እንደዚያዉ ነዉ። ሁሉም አይታደለዉም። አይደፍረዉምም።

የሰሞኑ በየሀገሩ የሚደረጉት ሰላማዊ ሰልፎች የሀገር ቤቱ እንቅስቃሴ ነፀብራቆች መሆናቸዉ ለሁላችንም ግልፅ ነዉ። በዉጭ የሚኖረዉ ኢትዮጵያዊም የተፈጠረባት ምድር ሀገሩ ፣ የተወለደበት ቤተሰብ፣ ያደገበት ቀዪ ሁሉም አካባቢ በጥይት እየነደደ መሆኑን ጧት ማታ ያስተዉላል። በዓይን በብሌኑ እያየ ለማመን እስከሚያቅተዉ ይከታተላል። እንደ ሰዉ ለሚያስብ አርፎ መቀመጥን አይመርጥም። የወገን ደም እየፈሰሰ በር ዘግቶ መቀመጥ፣ አባባሉ እራሴንም ይጨምራል የኅሊና ቁስል እየሆነ ከመኝታ ያባንናል። በመብት ማስከበርና በነፃነት ጥያቄ ድርድር ባለመኖሩ የሕዝቡ ጥያቄ መብታችን ይከበር ነዉ። ባለብዙ ብሄረሰቧ ሀገር ባንድ ጥቂት አናሳ ቡድን ተቀፍድዳ  እየተገዛች ስለሆነ፣ ይህ ይብቃና የሁላችንም ሀገር መሆኗ በተግባር ይረጋገጥ ነዉ ጥያቄዉ። ገዥዉ መደብ ግን …የብሔረሰቦቿን መብት አስከብሮ ሀገራዊ አንድነትን የሚያጠናክር መንግሥት ከእኛ የተሻለ ሰለሌለና ስለማይመጣም ዝምብላችሁ ሰጥለጥ ብላችሁ ተገዙ…. ነዉ የሚለዉና የግል ጡሩምባዎቹ በሆኑት ኢቲቪና የኢትዮጵያ ራዲዎች ጧት ማታ የሚለፍፈዉ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ደግሞ በኢቲቪ የምትቀርብልን ኢትዮጵያና  እኛ በዓይናችን ብሌን የምንመለከታት መሬት ላይ ያለችው ኢትዮጵያ እናንተ እንደምትነግሩንና እናንተ እንደምታቀርቧት ሆና ስለማናገኛት የጥቂቶች የምድር ገነት ለብዙኃኑ የምድር ሲኦል የሚያደርግ የዘር ፖለቲካ መርሆን አቁሙና ለእኛ ለሁላችን ሀገር የሆነች ኢትዮጵያ ትኑረን ነዉ። ይህ ዕዉን ሊሆን ከቻለ ደግሞ የጥቂቶች ሀገር መዝረፍና በሃያ አራት ሰዓት ሚሊዪነር መሆን የሚችሉበት ዘመን ለያከትም ነዉ። አናሳዉ ቡድን በትረ ሥልጣኑን ለብዙሃኑ ሊያስረክብ ነዉ። አሳዳጁ ተሰዳጅ ሊሆን ነዉ። አሳሪዉ ታሳሪ ሊሆን ሊገደድ ነዉ። አንደኛዉ የበኩር፣ ሌላኛዉ እንደ እንጀራ ልጅ መብት የመታየት መኖር ሊያከትም  ነዉ።  በገዛ ሀገሩ የመንገድ ዳር ለማኝ ሆኖ፣ የሌሎችን ፎቅ የሚቆጥርበትና ወደ ሰማይ አንጋጦ የሚመለከትበት ጊዜ ማክተሚያ ሊደርስ ነዉ። ይህ ግን በሰላም የማይታሰብ ነዉ። ግድያዉ መፍትሄም ባይሆን ለቀጣይነቱ በየቦታዉ ርችቶች እየታዩ ነዉ። አንድ ገበሬ ሽንኩርት ጭኖ ወደ ገበያ ሲገሰግስ አህያዉ ከተማዉ አካባቢ ስትደርስ ለገመችበት። ጭራሽ መንቀሳቀስ አቆመች። ይኽዉ ገበሬ የግድ ካልተራመድሽ ብሎ አህያዋን ባልተወለደ አንጀቱ በዱላ ይቀጠቅጣት ጀመር። ይህን የተመለከተ የአካባቢዉ አልፎ ሂያጅ መንገደኛ …ጌታው እንዲያዉ ለመሆኑ ሕሊና የለህም ተዉ አትቀጥቅጣት፣ ነፍሷ መዉጣት እኮ ነዉ የቀራት ሲለዉ፣  አይ ጌታየ! ኀሊናስ የለኝም ጨርሻለሁ፣  ወደ ገበያ የምወስደዉ ሽንኩርት ብቻ ነዉ የቀረኝ። እሱንም ይኽዉ መንገድ ላይ እያስቀረችዉ ነዉ..? እንዳለዉ ባለጊዜዎች የሚታያቸዉ ሟቹ ሳይሆን የደራዉ የሀገር ዘረፋ ገበያቸዉ ነዉ።

እስኪ ማን ይሙት የአንድ ሀገር ሕዝብ ከዳር እዳር ተንቃስቅሶ ለመብቱና ለነፃነቱ መከበር ከእንግዲህስ ይብቃ ብሎ የመንግሥት ለውጥ እንዲደረግ በሰላማዊ እምቢተኝነት ጥያቄ ሲያቀርብ፣ …ባለቤት የሌላቸዉ አመፆችና እንቃስቃሴዎች በየቦታዉ እየተደረጉ… ብሎ ማፌዝና ስለሆነም መንግሥት ሰላም የማስከበር ሕገመንግሥታዊ ኀላፊነት ስላለበት… በሚል መመሪያ የጅምላ ግድያ በሰላማዊ ሰልፈኛው ላይ ማድረግ ተገቢ ነበርን? ያዉም የሕዝብ ብሶት ወለደኝ ከሚለዉ ኢሕአዴግ። ደግሞስ በአንድ ሀገር እንቅስቃሴ ከሕዝብ በላይ ምንስ አለና ነዉ ባለቤታቸዉ የማይታወቁት እንቅስቃሴዎች በማለት ሕዝባቢዉን አመፅ ለማጣጣልና ቦታ ላለመስጠት መንግሥታዊ ሽወዳ የሚደረገዉና የሚቀለደዉ። በሽወዳ 25 ዓመታት አልፈዋል። ብሔረሶቦችን እርስ በርስ በማጋጨት የሥልጣን ዕድሜን ማራዘም ተችሏል። ግን አሁን ጊዜዉ አከተመ። ማጣፊያዉ አጠረ።  እንዲህ  ዓይነቱ የፖለቲካ ጨዋታ የተበላ ቁማር ሆኗል። ሕዝቡ ኦሮሞም አማራም አንድ ነዉ ብሎ ዘመረ። በቅርብ ጊዜ የምናየዉ ዕዉነታ ቢኖር ኦሮሞዉና አማራዉ ብቻ ሳይሆን አንድነታቸዉን የሚገልጹት፣ በሀገሪቱ የሦሥተኛነትን  ቁጥር ይዞ የሚገኘዉና አኩሪ ታሪክ ያለዉ የትግራይ ሕዝብም  በከንቱ የፈሰሰዉ የኦሮሞ፣ የአማራ ወንድሞቻችን ደም የእኛም ደም ነዉ ብሎ እንደሚነሳና በእሱ ስም የሚነግዱትን የፖለቲካ ነጋዴዎች አቁሙ! ከኢትዮጵያ ሕዝብ የሚነጣጥለንን ስዉር የፖለቲካ ጨዋታ ምዕራፍ ዘግታችሁ ብሔራዊ የአንድነት አጀንዳ ክፈቱ! አለበለዚያ …ዉጉዝ ከመ አርዮስ… ከእናንተ ጋር አይደለንም እንደሚላቸዉ ጥርጣሬ ሊገባን አይገባም። ይህ ዕዉን የሚሆንበትን ጊዜ ለማቃረብ ደግሞ ሁላችንም የየአቅማችንን የቤት ሥራ እንሥራ። ከፋፋይ የዘር ፖለቲካን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከፍነንና ገንዘን እንዳይነሳ አድርገን እንቅበረዉ። ማቅ እናልብሰዉ። ይጥቆር። ያንጊዜ ኢትዮጵያዊነት አብቦ ይፈካል። ኢትዮጵያዊነት ይነግሳል። የገዥዎቻችንም ዓላማ ይከሽፋል። ከሥር መሠረቱም ይናጋል። በየቦታዉ በተደረጉ ሰላማዊ ሰልፎች መምሕር በቀለ ገርባም ሆነ ኮሎኔል ደመቀ ዘዉዱ ብርቅዬ የነፃነት አርበኞቻችን እንጅ፣ አሽባሪዎች አይደሉም በማለት ድምፁን ከፍ አድርጎ ያስተጋባዉም መልዕክቱ ጥልቅ የሚሆነዉ ለዚህ ነዉ። እነ እስክንድር ነጋ፣ አንዱዓለም አራጌ፣ እነ ተመስገን ደሳለኝ የሰላማዊ ትግል ቀንዲሎች እንጅ የጥፋት ዘመን  መልዕክተኞች አለመሆናቸዉን ሕዝቡ በአንደበቱ ምስክርነቱን የሚቸራቸዉም ለዚህ ነዉ። አብርሃ ደስታ ከእስር ቢፈታም በትግራይ ተወላጅነቱ ሳይወገንለት የሥርዓቱ ሰለባ ሆኖ መሰቃየቱን አብዛኛዉ ኢትዮጵያዊ የማይዘነጋዉ የቅርብ ጊዜም ትዝታ ነዉ።

በሁሉም ሕዝባዊ የፖለቲካ ጥያቄዎች መንግሥት ገታራ አቑም ባይወስድ ኖሮ፣ ሀገራዊ መፍትሔዉ  በሀገሪቱ የብሔራዊ ዕርቅ መዉረድ ነበር።  ለእራሳቸዉም የመንግሥት ባለሥልጣናትም ሆነ ለሀገሪቱ መድኀንና አንድና አንድ የፖለቲካ ፈዉሱ አሁንም ብሔራዊ ዕርቅ ከሁሉም አማራጮች የቀዳሚነቱን ሥፍራ ከመዉሰድ እንደ ብቸኛ መፍትሄም ባይወሰድ (ስለዘገየ) የአማራጭነቱ ሚና ጉልህ ሥፍራ ይኖረዋል።  ግን የቤተ መንግሥቱ  ወንበር አንድ ጊዜ ከተቀመጡበት ላለመልቀቅ አዚም ያለዉ ይመስለኛል። ኀሊና ይጋርዳል። ዓይን ያዉራል። ለሕዝብ የተገባዉ ቃል ሁሉ ይረሳል። የማሰቢያ ጭንቅላትም ይደፈናል። ለዚህም ነዉ አንድ የወሎ ገበሬ በኢሕአዴግ የሥልጣን መጨበጥ ዋዜማ ሰሞን ነፃ ባወጡት የሰሜን ወሎ አካባቢ በተደረገ ስብሰባ፣…ነፃ አዉጭዎች ነን ካላችሁማ ምን ይደረግ፣ እስኪ ደግሞ እናንተን እንያችሁ… ግን እናንተም አሁን ማር ሆናችሁ ቀርባችሁን በሁዋላ እንደ ደርግ እሬት እንዳትሆኑብን… በማለት ነበር ነቢዩ ገበሬ አስቀድሞ የነገራቸዉ። ወጣም ወረደ፣አልታደልንም። ደም ካልተገበረ በሰላማዊ መንገድ መሠረታዊ  ለዉጥን ማምጣት አልተቻለም። ይህ ዕድል በ 1997 በቅንጅት ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ወቅት አመለጠ። አሁን የፖለቲካ ድርጅቶች ሳይሆኑ ሕዝብ በቃኝ ብሎ ተነሳ። ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ማሳወቅ እንጅ፣ ሕገመንግሥታዊ ፈቃድ መጠየቅ አያስፈልገንም አለ። በሕገመንግሥቱ ላይ የሰፈረዉ ሰንደቅ ዓላማም ሕዝቡ የሚቀበለዉ አይደለም ብሎ ከዳር እስከዳር የቀድሞዉን ባንዲራ ይዞ ወጣ። ባጭሩ በተዘዋዋሪ መንገድ ሕዝቡ ሕገመንግሥቱን እንደማያምንበትና እንደማይቀበለዉም መልዕክቱን አስተላለፈ። ይህ ብቻም ሳይሆን የሀገሪቱ የችግሮቹ ሁሉ ምንጭ ሕገመንግሥቱ ስለሆነ፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሕገመንግሥቱን የሀገሪቱ መመሪያ ገዥ ሕግ አድርጎ እንደማይቀበለዉ አሳወቀ። ይሁን እንጅ አሁንም ቢሆን ይኽዉ እኛ በሕገመንግሥታችን የብሔር ብሔረሰቦችን መብት ለማክበር በባንዲራዉ መካከል በተለያዩ ሕብረ ቀላማት አስዉበን የብሔር ብሄረሰቦችን እኩልነት መብት በሚያስከብር መልኩ ያወጣነዉን ሕገመንግሥት በመጣስ ጠባቦችና ትምክህተኞች (ኦሮሞዎችና አማራዎች ለማለት) ጨቁነዉ ሊገዙህ ተነስተዉብሃል የሚል የማደናገሪና ከፋፋይ ቅስቀሳ ከማድረግ ወደሁዋላ እንደማይል ሳይታለም የተፈታ ነዉ። እንዲያዉ ለነገሩ …ዶሮን ሲያታልሏት… ካልሆነ፣ በዓመት አንድ ጊዜ የሰንደቅ ዓላማና የብሔረሰቦች ቀን በዓል እያከበሩ ማስጨፈር  የብሔረሰቦች እኩልነት ተከብሯል ለማለት ያስደፍራል? በዚህ መታለልም ለመገዛት አምችቷል ቢባል ማጋነን አይሆንም።

ምናልባት አንዳንድ የዋሆች የወልቃይት የአማራን የማንነት ጥያቄ ለሰሞኑ እንቃስቃሴ እንደ ምክንያት ሊቆጥሩት ይችላሉ። የወልቃይት ኗሪዎች ቀያቸዉን ከተነጠቁበት ጊዜ ጀምሮ በየማሳቸዉ እያንጎራጉሩ፣

እናንተም እረሱ እኛም እናርሳለን፣

መኽር (ሰብል) ሰብሳቢዉን አብረን እናያለን።

እያሉ የዉስጥ አንጀታቸዉ አርሮ ዓመታትን አሳልፈዋል። ግን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊያጤነዉ የሚገባዉ፣ወያኔዎች ከኢትዮጵያዊነት ሌላ  የተለየ አመለካከት ከሌላቸዉ መጀመሪያዉኑ ገና ጫካ እያሉ፣ ለምን ከዉጭ አገር ጋር ወልቃይትን ወደ ትግራይ በማጠቃለል ለምሳሌ (ከሱዳን) ወሰን አስፈለጋቸዉ? መንግሥት ከሆኑ በሁዋላስ ለምን በትግራይና በጎንደር መካከል ወሰኑ ወደ ቀድሞዉ (ተከዜ) እንዲመለስ አላደረጉም? ጎንደርም፣ ትግራይም የኢትዮጵያ ግዛቶች ናቸዉ የሚል ዕምነት ቢኖራቸዉ ኖሮ፣ ይህ ጥያቄ ይህን ያህል ደም አፋሳሽ መሆን አልነበረበትም። አሁንም የተደበቀ ዓላማ እንዳላቸዉ ለአንዳፍታም መጠራጠር የማያስፈልገዉ እዉነታ ነዉ። ወጣ ወረደም ሰበቡ የወልቃይት የአማራ የማንነት ጥያቄ ሆኖ ብቅ ይበል እንጅ፣ መሬት ላይ የሚነበበዉ ዕዉነታ በሥልጣን ላይ ያለዉ መንግሥት ከደርግም እየባሰ ስለመጣ፣ ብሶት የወለደዉ ሆኖ የመጣ መንግሥት መሆኑንም ስለዘነጋ፣ የሃያ አምስት ዕድሜዉም ዲሞክራሲያዊ መንግሥት ሊያደርገዉ ስላልቻለ፣ የተሰጠዉ የሙከራ ጊዜም ስላለፈ፣ የብሔራዊ ዕርቅ በሩንም ክርችም አድርጎ ስለዘጋ፣ ባጭሩ መንግሥታዊ አስተዳደሩን ስላላወቀበትም ወደ መጣበት ባይመለስም ከሥልጣን ይዉረድ  ነዉ ጥያቄዉ። በጣም የሚያስገርመዉ እኮ ሰሞኑን በየቦታዉ በሚካሄዱት የገዥዉ መደብ የአዉራ ካድሬዎችም ሆኑ የሌሎች ዉሎ ገብ ካድሬዎች  የስብሰባ መድረኮች ላይ የሚንፀባረቁት ዲስኩሮች በእኛ ጊዜ ከሞተዉ በደርግ ጊዜ የተገደለዉ ይበልጣል እየተባለ፣ የሰዉ ልጅ ሞት (ግድያ) ቁጥር/አኀዝ መብዛትና ማነስ እንዴ ዲሞክራት መንግሥትነት የመለኪያ መመዘኛ ሆኖ እየቀረበ ነዉ። አኀዝን የምንጠቀምበት ብዙዉን ጊዜ ለኢኮኖሚ ዕድገት ማነፃጸሪያነት ነበር እንጅ ለሞት የሰዉ ቁጥር ብዛት ማወዳደሪያነት እስታትስቲክስ አልነበረም። እና ይህ የጤነኝነት አካሄድ ነዉ ትላላችሁ ወገኖቼ? ገሰሰዉ እንግዳ የሚባል ፀሐፊ ይመስለኛል …ታሪክ አጉዳፊዉ የአልባንያ ደብተራ… በሚል ርዕስ ለንባብ ባበቃዉ መፅሃፍ …ደርግም፤ ወያኔም ሁለቱም ገዳይ መንግሥታት ናቸዉ። አገዳደላቸዉ ግን የተለያየ ነዉ። ደርግ ጅል መንግሥት ስለነበረ በስም ጠቅሶ እነገሌን፡ እነገሌን ገድያለሁ ብሎ ማታ በሬድዮና በተሌቪዥን መግለጫ ይሰጣል። ወያኔዎች ደግሞ እራሳቸዉ ይገሉና …እንዲያዉ ለመሆኑ ማን ይሆን የገደለዉ ብለዉ ከሟች ቤተሰቦች ዘንድ መጥተዉ፣ ዓይናቸዉን በጨዉ አጥበዉ  ለቅሶ ይደርሳሉ በማለት የዉስጥ ማንነታቸዉንም ስለሚያዉቅ ትክክለኛ ባሕርያቸዉን በሚገባ ገልጾታል። አለመታደልም ሆኖ በገደሉት ሰዉ ቁጥር ብዛትና ማነስ ካለፈዉ የተሻሉ ዲሞክራሲያዊ መንግሥትነታቸዉን እየለኩበት ነዉ።

ሀገር ዉስጥም ሆነ በዉጭ አገር የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችም ሆኑ ሰላማዊ ሰልፎች ዓላማቸዉ አንድና አንድ ይመስለኛል። የሕዝቦቿ እኩልነት የተረጋገጠባት፣ ሁሉም ዜጎቿ የእኛ ሀገር ናት የሚሏት ኢትዮጵያ ትገንባ ነዉ ማሳረጊያዉ። የመንግሥት ለዉጥ በተደረገ ቁጥር፣ ሥልጣን ላይ ላለዉ መንግሥት ብቻ የሚጠቅም ብቻ ሕገመንግሥት በየጊዜዉ የሚወጣባት አገር ሳትሆን፣ ሀገር የምትመራበት፣ ሕዝብ የሚተዳደርበት፣ መንግሥትም ለሀገርና ለሕዝብ ተጠያቂ የሚሆንበት እንጅ ከሀገርና ከሕዝብ በላይ ሆኖ፣ ሕዝብ ለሚያሸብር ሕገመንግሥት በተግባር ላይ የማይዉልባት ሀገር እንድትኖረን፣  ባጭሩ የአንድ አገር ሕዝብ በአፈሙዝ የሚገዛበት አገር ከመሆን ዘመን ነፃ ሆነን የመኖር መንግሥታዊ ባሕል እንገንባ ነዉ እንቃስቃሴዉ።  በትረ ሥልጣን የጨበጠዉ ወገን ደግሞ በግሉ ሚዲያዎች ከእኔ የተሻለ መንግሥት ሊመጣም ስለማይችል የእኔን የፖለቲካ ቀመር ተቀብላችሁ፣  በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ተጠምቃችሁና ቆርባችሁ  ከኖራችሁና  ከተገዛችሁ ኢትዮጵያ እንደ  ሀገር የመቀጠል ዕድሏ ሰፊ ነዉ። አለበለዚያ የሀገሪቱ ማጣፊያ ያጥራል፣ እኛም ከሌለን ሀገሪቱ ትበታተናለች እየተባልን ነዉ፣ እየተስፈራራን ያለነዉ። ሕዝቡ ግን በደማችን ነፃነታችን ይከበራል እንጅ፣  ከእናንተ በደጅ ጥናት የሚገኝ የዜግነት የመብት ከበሬታ  እንደማይገኝ እናዉቃለን እያለ ነዉ ድምፁን ከፍ አድርጎ እያስተጋባ የሚገኘዉ። ይህ የተራራቀ ፅንፈኛ አመለካከት እንዴት ይታረቅ? ነዉ ጥያቄዉ። የፍራንከፈርቱ ሰላማዊ ሰልፍ ዓላማም ከሕዝቡ ጥያቄዎች ጎን በመሰለፍ ለሚኖርበት ሀገር የተለያዩ ተቑማት መልዕክቱን ማስተላለፍ ነዉ። ይህንንም በተሳካ ሁኔታ አካሂዷል። ባጭር ጊዜ ዉስጥ በተደረገ መሰናዶ ፍራንክፈርት አካባቢ ለመጀመሪያ ጊዜ ቁጥሩ በርከት ያለና ትርጉም ያለዉ ትዕይንተ ሕዝብ በማድረግ  ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን መቆሙን በተግባር አሳይቷል። ለሚኖርበት ሀገር መንግሥትና ሕዝብም ዓላማዉን በትክክል አሳዉቑል። ወሳኙ የሀገር ቤቱ ትግል መሆኑ ቢታወቅም፣ በየሀገሩ የሚደረጉ ሰላማዊ ሰልፎችም የራሳቸዉ የሆነ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸዉ ሊዘነጋ አይገባዉም።

↧

የሕወሓት መንግስት በአዳማ፣ በድሬዳዋ፣ በጎንደር፣ በባህርዳርናና ሻሸማኔ የሽብር ጥቃት አድርሶ በአልሸባብ ላይ ሊያሳብብ አቅዷል ተባለ

$
0
0
File Photo (Adama City)

File Photo (Adama City)

ኢሳት (ነሃሴ 11 ፥ 2008) ህወሃት የሚመራው መንግስት የዓለም ዓቀፉን ማህበረሰብ ትኩረት ለመሳብ በማሰብ በኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ ትላልቅ ከተሞች የሽብር አደጋ በማድረስ በአልሸባብ ላይ ለማላከክ ማቀዱን ተገለጸ።

የሽብር ጥቃት እንዲደርስባቸው በህወሃት አመራር የተመረጡ ከተሞች አዳማ፣ ድሬዳዋ፣ ጎንደር፣ ባህርዳርና፣ ሻሸማኔ መሆናቸው ተነግሯል። በተጨማሪም ህወሃት በተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ጥቃት ለመፈጸም ማቀዱን ለኢሳት ከደረሰውና ለህዝብ ይፋ ከሆነው መረጃ ለማወቅ ተችሏል።
ህወሃት/ኢህአዴግ ሶማሊኛ ተናጋሪ የሆኑትን የሶማሌ ክልል ተውላጆችን ወደተጠቀሱት ከተሞች በማምጣት በህዝቡ ላይ ጥቃት ለመፈፀም እንዳቀደ የተናገሩት የኢሳት ምንጮች፣ ይህ የሽብር ጥቃት በጸረሽብር ጦርነት ላይ የኢትዮጵያ መንግስት የወሰደው አቋም አለም አቀፍ ድጋፍ ያስገኝልኛል ብሎ እንደሚያስብ ለማወቅ ተችሏል። በከተሞች ላይ የህወሃት አመራር ሊወስደው ያሰበው ጥቃት በአገር ውስጥ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ በጸረሽብር ህግ መሰረት ለማስቆም ይረዳል ብለው እንደሚያስብ ተነግሯል።
“በህዝብ ላይ ጥቃት ከመፈጸም ለምን ሌላ አማራጭ አንፈልግም?” ብለው የጠየቁ የአማራና ኦሮሞ ብሄር ተወላጅ የሆኑ የፌዴራል ፖሊስ አባላት፣ በህወሃት ሃይሎች ታፍነው ወዴት እንደተወሰዱ ለማወቅ አለመቻሉ ተነግሯል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ)፣ አልሸባብ የቀጣናው የፀጥታ ሥጋት መሆኑ እንደጨመረና የሽብር ጥቃት ሊፈጽም እንደሚችል ማሳሰቡን ሪፖርተር ረቡዕ ባወጣው ዘገባ ገልጿል።
የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና ከፍተኛ የፀጥታ ሥጋት እየሆነ መጥቷል ያለው የኢጋድ ሪፖርት፣ ‹‹አልሸባብ የሶማሊያ የፀጥታ ሥጋት ብቻ አይደለም፡፡ በመሆኑም አካባቢያዊ የተቀናጀ ምላሽ ይጠይቃል›› ማለቱን ሪፖርተር በዘገባው አስፍርሯል።
አሁን ኢጋድ ያወጣውን ሪፖርት በማስመልከት ማብራሪያ እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የፖለቲካ ተንታኝ እንደገለጹት፣ በኦሮሚያና አማራ ክልል ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለመቀልበስ ህወሃት እየወሰደ ያለውን ሃይል የተሞላበት እርምጃ ድጋፍ ለመስጠት ሆን ብሎ የተሰራ ድራማ መሆኑን ገልጸዋል። መንግስት በህዝቡ ዘንድ ተዓማኒነት ስለሌለው ሊወስደው ያሰበውን የሃይል እርምጃ በኢጋድ በኩል እያስነገረ ነው ሲሉ እነዚህ ተንታኞች ለኢሳት ተናግረዋል።
የህወሃት አመራር በከተሞች ላይ ጥቃት መፈጸሙ አይቀርም ያሉት ስማቸው እንዲነገር ያልፈለጉ የፖለቲካ ተንታኞች፣ የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር ኢትዮጵያ መሆኗን ተገን በማድረግ ጥቃቱን በአልሻባብ እንደተፈጸመ ለማስመሰል ህጋዊ ሽፋን ለመስጠት እንደታሰበ ታውቋል።
ህወሃት መራሹ መንግስት ከዚህ በፊትም በአዲስ አበባ ሶስት ቦታ ቦምብ በማንፈዳት ኤርትራንና የኦሮሞ ነጻነት ግንባርን መውቀሱን ዊኪሊክስ የአሜሪካ ኤምባሲን ጠቅሶ መዘገቡን ይታወሳል።

↧

ታላቅ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ በስዊድን ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን

$
0
0

sweedin

ታላቅ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ በስዊድን ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን

↧

አፈ ቀላጤ ጌታቸው ረዳን ባሰብነው ግዜ

$
0
0

የኦሮሞና አማራ በአንድነት መቆም የሕወሓት ተገንጣይ ቡድን ቃል አቀባይን አቃጥሏቸዋል | Video

ዩሐንስ ደሳለኝ (ከፍራንክፈርት)

ለዚህ ጹሁፌ መነሻ የሆነኝን ርዕስ የሰጠሁት ሰሞኑን በአልጅዚራ ቴሌቭዝን የተለያዩ ፕሮግራሞች ላይ የቀረበውን የTPLF አፈ ቀላጤ ጌታቸው ረዳን ሁኔታ ሳይ የተሰማኝንና አገሬ እንዴት ዓይነት ሰዎችን በአለም መድረክ እያስተዋወቀች መሆኑን ሳስብ እውነትም ይሄ መንግስት ከምራባዊያን ጋር ተባብሮ ታሪኹዋን፣ባህሏዋን፣የእውቀት የታሪክ ምሁራንና አባቶችን
በማጥፋት ላይ መሆኑን ከግዜ ወደግዜ ግልጥ እየሆነ ለመምጣቱ አስረጅ አያስፈልገውም ።
አፈ ቀላጤው ጌታቸው በተለያየ ግዜ የሚያደርጋቸውን ውይይቶች፣ ቃለ-መጠይቆችና አስተያየቶች ሳይ ያኔ አሜሪካ (2003 እኤአ) ኢራቅን በወረረች ግዜ የብዙሓን መገናኛ (Information Minister) የነበሩትን መሃመድ ሳይድ አልሳሓፍን ያስታውሰኛል፤ ሰውየው እስከመጨረሻው ሰዓት ድረስ እያሸነፍን ነው አሁን አባረናቸዋል እያሉ በመንግስት ሚዲያ ሲናገሩ ዓለም ሁሉ በአድራጎታችው ይገረም ነበር፤ እንዲያውም ከጦርነቱ በኃላ ተጠይቀው ሲመልሱ

« The information was correct, but the interpretation were not,, አያይዘውም « I did my duty up to the last minute ,, << መረጃዎቹ ሁሉ ልክ ነበሩ ስህተቱ አተረጓጎሙ ላይ ነበር ፣ እኔም እስከመጨረሻው ደቂቃ ድረስ ግዴታየን ተወጥቻለሁ» ነበር ያሉት ይገርማል በአምባገነን ስርዓት ውስጥ ያሉ መሪዎችና ተከታዮቻቸው ሁኔታ ተመሳሳይና አንድ ወጥ ነው ምንም ግዜ ቢለወጥ ዘመኑ በቴክኖሎጅ ቢያብብ ሁሉም ከአንድ አካባቢና ወላጅ የተገኙ እስኪመስል ድረስ ውሸታችውና አይነ አውጣነታቸው ግዜ አይሽረውም፣ የወያኔውም ጌታቸው ይህንንኑ ነው ሰሞኑንን የደገመልን ።
በተለያዩ ሚዲያዎች ሲቀርብ በተለይ ደግሞ ሰሞንኛውን በአልጀዚራ ላይ ባደረጋቸው የቀጥታ ውይይትና መጠይቆች ላይ
1ኛ ለተጠየቀው ጥያቄ ቀጥተኛ መልስ አይሰጥም አልያም ከጋዜጠኞቹ ጉትጎታ ሲበዛበት አድበስብሶ ያልፋል
2ኛ ሁሉንም ከእሱ ጋር የሚወያይቱን ሰዎች ይንቃል ይሄ ደግሞ የዕውቀቱንና የማንዓለብኝነቱን ጥግ ያሳያል
3ኛ ልክ እንደ ኢራቁ አፈቀላጤ እሱም እውነታውን በተለይ በዚህ የመረጃ ፍሰቱ እንደልብ በሆነበትና የስማርት ስልኮች ባለውለታነት በማይካድበት ዘመን የወያኔው ቃል አቀባይ እኛ የምንናገረው ወይም መረጃችን ትክክል ነው አተረጓጎም ካልሆን በስተቀር እያለ የሚያደነቁረን።

 

እስቲ ከላይ የዘረዘርኳችውን ተራ በተራ እንመልከት፦
አፈ ቀላጤው ጌታቸው ረዳ ለሚጠየቀው ጥያቄ ሁልግዜም ቀጥተኛ መልስ ሰጥቶ አያውቅም ቢቻል አድበስብሶ ያልፋል ካልሆነም ጋዜጠኞች ጠንከር ሲሉበት ያው ያች የTPLF ሰዎች በተደጋጋሚ የሚሏትን እኛ ዕድገት ላይ ነን፣ሰልፍ የወጡት ሰዎች ቦንብ ይዘዋል፣ የማህበራዊውን ሚዲያ ተጠቅመው የሚያነሳሱ በውጭ የሚኖሩ ጥቅም ፈላጊዎችና የሻቢያ ተላላኪዎች ናቸው ነጠላ ዜማን ይለቃል፤ኧረ እንደው ለመሆኑ ዕድገት ማለት ምን ማለት ነው? ፎቅ መደርደር ነው ወይስ ደሃውን ገበሬ ከቀየው አፍናቅሎ በምትኩ የራስን አባልና ደጋፊ ያውም የአንድ ብሄር የበላይነት ገነኖ እንዲፈነጭ ማድረግና ሌላውን የበይ ተመልካች ማድረግ? አቶ ቃል አቀባይ ምንግዜም ቢሆን በየትም ዓለም ይሁን በየትም በልማትም በለው ብትፈልግም ዕድገት በገባህ ነገር
ለካው አገር ለማ ከተባለና ካደገ ቢያንስ ሰዎች በሰላም ሰርተው በቀያችው ንፅህ አየር ተንፍሰው መኖር አለባቸው እንጅ አሁን እንዳለው እንዳንተ መንግስት የባሪያ ፍንገላ ዓይነት ሰርዓት ማካሄድ ጦሱ ያየኽው ነውጥ ነው ትርፉ ።

አዎ እኛ በውጭ የምንገኝ ኢትዮጵያዊያን እንዳንተ አንዋሽም የአንተ መንግስት እንዲቀየር በማህበራዊ ሚዲያ የቻልነውን እንጽፋለን ግን እውነታው ይሄ አይደለም አዎ ዛሬ የሚገርፍህ ወላፈን በኃላም ጠራርጎ የሚወስድህ የህዝብ ማዕበል የተቀሰቀሰው በራሱ በህዝቡ ብሶት ነው ሌላው ድግሞ የአንተ መንግስት ሲገባ የተወለዱ ልጆች ናቸው በአሁኑ ግዜ እየሞገቱህ ያሉት እንጅ
እኛማ በፊትም አገር ካጠፋ ጋር ስምምነት ወይም የተላላኪነት ሚናም የለንም ፣እሱን ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ ተላላኪው ማን እንደነበር ታውቃለህ ማለቴ ጌቶችህ ከነገሩህ አንተማ የዋህ ምን ታውቃለህ የጎረስከውን የምትተፋ ።
በሁለትኛው ነጥብ ላይ እንዳነሳሁት በጣም የሚገርመኝ የወያኔ ባለስልጣናትና ደጋፊዎች ጉደኛ ባህሪ ከሆነው አንዱ ሰዎችንንና ተቋማትን የመናቅ አባዚያቸው ነው ፣ ከአለም ዓቀፍ ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ፣ከተለያዩ በውጭም ሆነ በአገር ውስጥ ካሉ አክትቭስቶች ጋር ሲወያያዩ ክብር የላችውም በእነሱ መስፈርትና መለኪያ የህውሓትን ዕድገት የማይዘግብ ውሽታምና ተዓማኒነት
የጎደለው ነው፤ ጌታቸው ምንም እንኳ የአፈ ቀላጤነቱን ቦታ በቅርብ ግዜ ቢረከብም በተሞላው የውሽት ጎተራነቱና ጌቶቹ ካሰመሩለት መስመር ውጭ መናገር አለመቻሉ ያሳዝነኛል፣ ለነገሩ የውሽት ጎተራ የነበረው መሪያቸው መለስ አልነበር?!
ምን ይደረግ «አገር ሲያረጅ ጃርት ያፈራል» እንዲሉ ኢትዩጵያ እንግዲህ እንዲህ ሆነች ዕውቀት ያለውን የሚንቁ ባሻቸው መጠን በሚዘርፉ የዓለም አቀፍ የዕውቀት መመዘኛን ያፋለሱ ሰዎች መከበሪያ ሆናለች።
ወደ መጨረሻው ነጥቤ ስመጣ የዚሁ ሰውየን ፈጣጣ ባህሪ ስመለከተው እውነት ጌታቸው በ21ኛው ክፍለ ዘመን እየኖረ ያለ አይመስለኝም ምክኒያቱም በአሁን ሰዓት አይደለም አደባባይ የውጡ ምስጢሮች ተደበቁ የተባሉትም ገሃድ ሲውጡ እየተመለከትን ነው ሚዲያው እንደሆነ ማንም ሊገምተው ከሚችለው በላይ አድጓል ፣የኢንተርኔት አግልግሎት ዘጋን ሲሉ በሌላ ዘዴ እንዴት እንደሚገባ የሚያስረዱ አፍላ ወጣቶች በበዙበት ዘመን ካፈርኩ አይመልሰኝ በሚል የተደረተ ፕሮፓጋንዳ ሊያደነቁረን ይሞክራል ፣ የኢራቁስ አፈቀላጤ ያኔ ሲዋሹ እንዲህ እንዳሁኑ ብዙ ዓይነት ሚዲያዎች አልነበሩም ደግሞም እሳችው ቢያንስ አገራቸውንና ህዝባችውን ከወራሪ ለመታደግ ነበር የሞከሩት የኛው ጉድ ግን ዛሬ በሚያግኘው ፍርፋሪ ያሳደግውን ገበሬ
ረስቶ በተለይ የኦሮሞን ገበሬዎች « ጋኔኖች» ሲል ጥቂት እንኳን ተው የሚልና የሚቆጠቁጥ ህሊና እንዳጣ ያሳያል።

መደምደሚያ

በአጠቃላይ ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርኩት የአገሪቷ አጠቃላይ ሁኔታ እንዲህ ብተዘበራረቀና ውሉን ያጣ ልቃቂት በሚመስልበት ግዜ በሰለጠነው ዓለም በእርግጥ ባለስልጣኖች ስልጣን ያስረክባሉ ይሄን አውቃለሁ ለእኛ ቅዝት ነው ቢሆንም ግን አንዳንዴ ሊሆን ግድ የሚለውና የማይቀረው የህዝብን የቁጣ ማዕበል አስቦ መፍትሄ መፈለግ ብልህነት ነው አሊያ ጌታቸው ረዳና መሰሎቹ ለብሰው ራቁታቸውን የሚሆኑበት ግዜ ቅርብ ነው፣ ስንት ግዜ ህዝብን እየዋሽህ ትኖራለህ? ስንቴ ስለ ዕድግት ታወራለህ ህዝብ እየተራበ? ምን ያህል ግዜ ተቋማትን ፣ሚዲያዎችንንና ሰዎችን ትንቃልህ ስለ ህዝብ መፈናቅል መሰደድ መታሰር ሲነግሩህ? ደርግ ከኃይለስላሴ አልተማረም ትውልድ አበላሽቶ ሄደ እናንተ ደግሞ ተቀብላችሁ በምራባዊያን አጋዥነት ትውልድ ስደት ገባ ህዝብ ተራቆተ የአንድ ብሄር የበላይነት ቅጥ ባጣ መልኩ ሰፈነ ፣ነገር ግን 25ዓመት ሙሉ የደከማችሁበት የዘር ፖለቲካ በሁሉም ብሄሮች በተለይ በአማራውና በኦሮሞው አንድነት እውን እየሆነ መጥቶ ካባችሁን የእምቧይ ሊያደርገው ጥቂት ግዜዎች ናቸው የቀሩት እናም ጌታቸውን ባሰብን ግዜ ዋ ለመፅሂ ዕድልህ!!!!

↧
↧

“የሕዝቡ እንቢተኝነት ፣ የዘረኛውን የወያኔ አገዛዝ እያፈራረሰው ነው!”–ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

$
0
0

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት             ሐሙስ ነሐሴ ፲፪ ቀን ፪ሺህ፰  ዓ.ም.              ቅፅ ፬ ፣ ቁጥር ፳፬

የትግሬ ወያኔ አገዛዝ በኢትዮጵያ ላይ ላለፉት 25 ዓመታት ጭኖት የኖረው በዘረኝነት ላይ የተመሠረተው ያንድ ነገድ የበላይነትና የውስጥ ቅኝ አገዛዝ ሥርዓት በሕዝቡ የእንቢተኝነት እንቅስቃሴ ከመኖር ወደ አለመኖር እየተሸጋገረ ነው። የወያኔ አገዛዝ ሲጀመር ጀምሮ ደካማ «መንግሥት» እንደሆነ ይታወቃል። የድክመቱ መገለጫም፣ አንደኛ፣ የአናሳዎች መንግሥት በመሆኑ የአብዛኛውን ሕዝብ ድጋፍ ያገኘ አይደለም። ሁለተኛ፣ የሚገዛው በኃይል በጦር መሣሪያ አስገድዶ እንጂ፣ በሕግ የበላይነት ተወዶና ተፈቅሮ አይደለም። ምንጊዜም በኃይል ሕዝባቸውን የሚገዙ አገዛዞች ደካማዎች እንደሆኑ የፖለቲካ ሣይንስ ሀሁ ይነግረናል። ወያኔም ከአፈጣጠሩ፣ከሚያራምደው የዘር ፖለቲካና ከባሕሪው በሚመነጭ ምክንያት ደካማ ነው። ሦስተኛው ወያኔ ከድክመቱ ብዛት የተነሳ፣ ራሱ እመራበታለሁ ብሎ፣ «በሕዝብ ተሳትፎ አጸደቁት ላለው ሕገ መንግሥት» ተገዥ አለመሆኑ የድክመቱ ሁሉ መገለጫ ነው። ይህም በመሆኑ፣ ሲጀምር ጀምሮ የወያኔ አገዛዝ፣ ደካማ ነው። ደካማ መንግሥት ደግሞ መውደቁ የግድና አይቀሬ ነው።

file photo

file photo

የደካማ መንግሥታት የመጨረሻ እጣ ፋንታም፣ በኃይል ሥልጣን እንደወጡ፣ በኃይልም ሕዝብን ሲገዙ እንደነበሩ፣ በኃይል ከያዙት ሥልጣን መወገድ ነው። ይህ ነባራዊ ዕውነታ ነው። በወያኔም ላይ እየሆነ ያለው ይኸው ነው። ወያኔ በየትኛውም መልኩ ሕጋዊና ተቀባይነትን አግኝቶ ሕዝብን ያስተዳደረ ቡድን አይደለም። ለ25 ዓመታት በኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ ተፈናጦ የኖረው፣ በዘር ላይ ባደራጀው የመከላከያ፣ የፀጥታ፣ የፍርድ አካላት፣ በዘራው የዘረኝነት ፕሮፓጋንዳና የስለላ መዋቅር፣ በኢትዮጵያውያን አንድነትና ኅብረት ማጣት ታግዞ መሆኑ እርግጥ ነው። ይሁን እንጂ፣ ሁሉም ነገር የራሱ ወሰንና ገደብ ስላለው፣ ወያኔ ሕዝቡን በነገድ ከፋፍሎ፣ ነጣጥሎና አናክሶ የመግዛቱ፣ ባንድ ዘር ላይ በመተማመን የተገነባው የመከላከያ፣ የፖሊስ፣ የደህንነትና የፍርድ አካላት መዋቅር ከሚገባው በላይ በመለጠጡ፣ የሕዝቡን ግፊትና አመጽ ሊቆጣጠርበት ከማይችለው ደረጃ ላይ አድርሶታል።

በዚህም የተነሳ፣ በሐምሌ 2008 ዓም መግቢያ ላይ እስራኤል በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተመራው ሕዝባዊ ተቃውሞ፣ በኢየሩሳሌም ገዳም ላይ ይውለበለብ የነበረው፣ ለኢትዮጵያ ነገዶች መከፋፈልና መነጣጠል መሪ የሆነው፣ «የሰይጣን አምላኪዎች ምልክት» የያዘውን፣ በሕዝቡ አጠራር «አምባሻ» ያረፈበትን ሠንደቅ አውርደው፣ የሃይማኖት፣ የጀግንነት፣ የተስፋ፣ የልምላሜና የመስዋዕትነት ልዩ እና ዕንቁ ዕሴቶቻችን መገለጫ በመሆን የሚያንጸባርቀው አረንጓዴ፣ ብጫ እና ቀይ ደማቅ ሠንደቅችን ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ አድርጓል። ይህን ፈለግ በመከተል፣ ጀግናው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ፣ የወልቃይት-ጠገዴ የዐማራነት ጥያቄ ፊታውራሪ በለኮሰው የሕዝባዊ እንቢተኝነት እንቅስቃሴ፣ ጀግኖቹ የጎንደር ወጣቶችና አዛውንት የወያኔ/ብአዴንን እራፊ ጨርቆች አውርደው የኢትዮጵያዊነት፣ የነፃነት ዐምድ ቋሚ መገለጫ፣ ከኢትዮጵያ ድንበር አልፎ፣ የአፍሪካውያን የነፃነት ቀንዲል በመሆን ያገለገለችውን ሠንደቅ በክብር ቦታዋ መልሰው፣ ለ25 ዓመታት እጅግ ለናፈቃት የጎንደር አየር አብቅተዋታል።

 

 

 

 

በተመሳሳይ ሁኔታ የአይደፈሬው የእነ ደጃዝማች በላይ ዘለቀ፣ የእነ ፊታውራሪ ነጋሽ በዛብህ ትውልድ የሆነው ጎጃሜ በባሕር ዳርና በደብረ ማርቆስ ከተሞች ባካሄዱት መሬት አንቀጥቅጥ የተቃውሞ ሕዝባዊ አመፅ፣ ሠንደቃችን ከፍ ብላ እንድትውለበለብ አድርገዋል። ይህ ሂደት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳየው የወያኔው አገዛዝ ቋሚ መሠረት አድርጎ የሚመራበት «ሕገ መንግሥት» ተብየ በሕዝቡ ድምፅና ነፃ ውሣኔ የተሻረ መሆኑ ነው። ይህን ተከትሎም ወያኔ «ለሕገ-መንግሥቱ እና ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱ» ቆሜአለሁ እያለ ጧት ማታ ሕዝቡን የሚያደነቁረው፣ ከሕዝቡ ቀድሞ ራሱ ያፈረሰውና ለእርሱም ታማኝነት እንደሌለው ይታወቃል። ሆኖም በሰሞኑ የዐማራ ነገድ ሕዝባዊ እንቢተኝነት የቆመበትን ምድር ርዕደ-መሬት ስላናወጠው፣ ራሱ ያወጣውን ሕግ በመጣስ፣ በራሱ አሻንጉሊቶች ይመራ የነበረውን «የዐማራ ክልል ምክር ቤት» ተብየና በዚሁ ምክር ቤት ተመሠረቱ የተባሉትን ተቋሞች አፍርሶ፣ የዐማራ ክልል የተባለውን በአምስት ቀጣና ወይም የዕዝ ሰንሰለት አዋቅሯል። በምትካቸውም ከዐማራና ከትግሬ፣ ከዐማራና ከኤርትራዊ፣ ከዐማራና ከቅማንት፣ ከዐማራና ከአገው በተወለዱ፣ በፀረ-ዐማራነት ወያኔ ኮትኩቶ ባሳደጋቸው ሰዎች ሕዝቡ እንዲጨፈጨፍ አደራጅቶና ዐማራውን ባሻቸውና በፈለጉት መንገድ እንዲገሉ ገደብ የለሽ ሥልጣን ሰጥቶ አሰማርቷቸዋል።

እነዚህ አዲሶቹ የዐማራው ገዳዮችና አስገዳዮች፥ መቀመጫውን ደብረ ማርቆስ ላደረገው የምሥራቅ ጎጃም ገዳይና እስገዳይ  ዶክተር ስንታየሁ ወልደሚካኤል፣መቀመጫውን ባሕርዳር ላይ ላደረገው የምዕራብ ጎጃም ገዳይና አስገዳይ፣ ብናልፍ አንዱአለም፤ ለሰሜንና ደቡብ ወሎ ገዳይና አስገዳይ ፣ ዓለምነው መኮንንና ገነት ዘውዴ፣ ለሰሜንና ደቡብ ጎንደር  ገዳይና አስገዳይ ተፈራ ደርበውና አይለኝ ሙሉዓለም መሆናቸው ታውቋል። የእነዚህን የግድያና የአፈና ተግባር በበላይነት የሚመራውና የሚቆጣጠረው፣ በዐማራ ነገድ ጥላቻ ተወልዶ ያደገው የአክሱም ተወላጁ ትግሬው ዐባይ ፀሐዬ እንደሆነ ስንገነዘብ፣ ወያኔ ዐማራውን አጥፍቶ ለመጥፋት ቁርጠኛ ውሣኔ ላይ የደረሰ መሆኑን ለመረዳት የሚከብድ አይሆንም። በተመሳሳይ ሁኔታ፣ የጎንደር ከተማ ሹምና የፀጥታ ኃላፊ የነበሩትን አንስተው በምትካቸው የጎንደር ከተማን ወጣት ባሻቸው መንገድ ሊገድሉ የሚችሉ ቅጥር ነፍሰ ገዳዮች እያሰለጠኑ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ወያኔ ዐማራን አጥፍቶ ለመጥፋት መጠነ ሠፊ ዝግጅት አድርጎ፣ ዝግጅቱን ተግባራዊ እያደረገ ነው። ፀረ-ዐማራ የሆኑ ቡድኖችና ግለሰቦች በፊናቸው፣ ከወያኔ ግድያ የተረፈውን ዐማራ በቃርሚያ ለቀማ መልኩ ለቅመው ለማጥፋት የትብብርና የአንድነት ስምምነቶች እያደረጉ እንደሆነ እየሰማን፣ እያየን ነው። በአንፃሩ «ተማርኩ፣ አውቃለሁ» የሚለው የዐማራው ክፍል፣ አሁንም አባቶቻችን «በሬ ካራጁ ጋር ይውላል» የሚሉት አባባል እውነት ሆኖ፣ ካራጆቻቸው ጋር ለወገኖቻቸው የእርድ ቦታ ሲያዘጋጁ ይስተዋላሉ። የዐማራው ነገድ ወጣትም ሆነ አዛውንት ልብ ሊለው የሚገባው መሠረታዊ ጉዳይ፣ የሚሳሳላት የኢትዮጵያ አንድነት ጉዳይ በዐማራው ነገድ አጠቃላይ ጥፋት ላይ መመሥረት፣ ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያ ሊያደርጋት አለመቻሉን ነው። ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ መሆን የምትችለው ሁሉም ነገድና ጎሣዎቿ፣ በአጠቃላይ ሁሉም ዜጎቿ አንዱም ከቁጥር ሳይጎድል፣ በሕግ የበላይነት፣ በግለሰብ ነፃነት፣ በግል ሀብትና በነፃ ኢኮኖሚ ሕጋዊ ጥበቃነት፣ በሰብአዊና ፖለቲካዎች መብቶችና ነፃነቶች መረጋገገጥ ላይ የተመሠረተ ሥርዓት በመመሥረት እንጂ፣ ታላቁንና ለኢትዮጵያ አንድነትና ነፃነት ይህ ቀረው ያልተባለ መስዋዕትነት የከፈለውን፤ ለሕዝቡ አንድነት፣ የሙጫነትና የሲሚንቶነት ባሕሪን በመላበስ ሲያይዝ የኖረውን የዐማራ ነገድ ከምድረ ገጽ በማጥፋት አለመሆኑ ሊታወቅ ይገባል። ግለሰብ ካልኖረ፣ ቤተሰብ አይኖርም። ቤተሰብ ከሌለ ደግሞ መንግሥት አይታሰብም። በዚህ አመክንዮ፣ ዐማራ ራሱ ሳይኖር፣ የመኖር መብቱ ሳይረጋገጥ፣ ስለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን ማሰብ፣ የህልም ሩጫ ከመሆን አያልፍም።

ይህም በመሆኑ፣ በዐማራ ስም ተደራጅታችሁ የምትንቀሳቀሱም ሆነ፣ በየቤታችሁ ሆናችው ስለዐማራ ነገድ ዕልቂትና እርሱንም ለመጨረስ የታቀደው የነገዱ የፈጽሞ ጥፋት የሚያስጨንቃችሁ ወገኖች፣ ያለ የሌለ ኃይላችሁን አሰባስባችሁ፣ ከእሳና ከይሉኝታ ተርታ ወጥተን፣ ነባራዊ ሁኔታውን በግልጽ ልንጋፈጠው ግድ ከሚለን ወቅት ላይ መሆናችንን አውቀን፣ ከወያኔ ውድቀት በኋላ ለሚመሠረተው መንግሥት፣ የዐማራውን ድምፅ በሚገባ ሊወክል የሚችል ፖለቲካዊ ኃይል በአስቸኳይ ሊፈጠር በሚችልበት ጉዳይ ላይ ተወያይቶ አንድ አቋምና ውሳኔ ላይ መድረስ ግድ ይላል።

ይህን በተመለከተ፣ ይህ ጉዳይ ጉዳያችን ነው፣ ሁላችንም ያገባናል፣ የዐማራው ጉዳይ የእኔም ጉዳይ ነው የምንል ወገኖች ባሉት የመገናኛ ዘዴዎች ሁሉ ተጠቅመን ባስቸኳይ በመገናኘት ለጉዳይ አጥጋቢ ዕልባት እንድንሰጠው ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ጥሪውን ያቀርባል። ሞረሽ ወገኔ ይህን ጥያቄ ሲያቀርብ ይህ የመጀመሪው እንዳልሆነ ሁሉ፣ የመጨረሻውም አይሆንም። ምክንያቱን ሞረሽ ወገኔ የዐማራው ኅልውና መጠበቅ ለኢትዮጵያ አንድነት ዋስትና ነው ብሎ ከልብ ስለሚያምን፣ ለኢትዮጵያ አንድነትና ነፃነት የሚቆረቆር ሁሉ፣ ለዐማራው ኅልውናና ምንነት መቀጠል መቆምና መቆርቆር አለበት ብለን እናምናለን።

ይህም በመሆኑ፣ የዐማራውን ኅልውና አጽንተን፣ ኢትዮጵያነትን ለመታደግ ሳንሰለች፣ የአንድነት ጥሪ ማቅረብ ከሥራዎቻችን ሁሉ ቀዳሚውን ቦታ የሚይዝ ነው። ለዚህ ጥሪ አዎንታዊ ምላሽ ያላችሁ ወገኖች መልሳችሁን moreshsecretary@gmail.com  እንድታሳውቁን በአክብሮት እንጠይቃለን።

የዚህ ጥያቄአችን መሠረት የፉክክር ቤት የሚፈርስ እንጂ፣ የሚገነባ አለመሆንን ስለምንገነዘብ ነው። ስለሆነም የዐማራው ልጆች በተናጠል የሚያደርጉት ጉዞ፣ ከመመካከርና ከመወያየት ወጥቶ፣ ወደ ፉክክር ከገባ፣ ለዐማራው ጥፋት ተጠያቂው ወያኔና መሰሎቹ ብቻ ሳይሆኑ፣ እኛም የአንበሣውን ድርሻ የምንወስድ መሆናችንን ልንገነዘበው ይገባል።

ዐማራን ከፈፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!

በዐማራዊ ማንነትና ኅብረት ኢትዮጵያዊነት ይለመልማል!

↧

በአዲስ አበባ ለእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ወረቀት እየተበተነ ነው

$
0
0

addis ababa
ከስንታየሁ ቸኮል

በአዲስ አበባ አብዮት አደባባይ ለእሁድ ነሐሴ 15 የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ጨምሮ በሀገሪቱ ለሚደረገው ሕዝባዊ ሰልፍ የህወሓት መንግስት ጨንቆታል፡፡

በተለይ በአዲስ አበባ የተጠራው የተቃውሞ ሰልፍ እንደ ጎንደር ባህርዳር ወጣቱ በነቂስ ሊወጣ ይችላል በሚል ግራ የገባው ሲሆን ለቅዳሜ ነሐሴ14/12/08 በወቅታዊ የፀጥታ ጉዳይ በማለት አጀንዳ በመስጠት ወጣቶችን ለስብሰባ እንዲገኙ በየአካባቢው በተበተነ ካድሬ ከጠዋት ጀምሮ የጥሪ ወረቀት እየተበተነ ይገኛል፡፡

እሁድ ነሐሴ 15 በአብዮት አደባባይ የተጠራው ሕዝባዊ ትዕይንት እንዳይደገም የህወሓት መንግስት ደንግጧል፡፡ በሀገሪቱ የሚደረገውን ሕዝባዊ ተጋድሎ ለማውገዝ ቅዳሜ በአስሩም ክፍለ ከተማ በ1ለ5 የተደራጁ ጥቂት ወጣቶች ከሰበሰቡ በኃላ በአበል ወደ ሰልፍ ለመቀየር የታሰበም ሊሆን ይችላል የሚሉ ሰዎቸ ከአባላቱ እየተሰማ ይገኛል፡፡

↧

ይልቅ ወሬ ልንገርህ –ስለ ፓስተር ጥበቡ ወርቅዬ ትንቢት |ቁምነገር መጽሔት

$
0
0

መቼም ስለ ቀድሞው አርቲስት ስለ አሁኑ ፓስተር ጥበቡ ወርቅዬ ሙዚቃ ማቆምና መንፈሳዊ አገልግሎት መጀመር ሰምተሃል አይደል? ከጥቂት ሳምንታት በፊት ሐሙስ ቀን ምሳ ሰዓት ላይ እኔ ደረጄ ኮሜዲያን፤አስረስ በቀለ እና ሐብታሙ ቮካል ሪከርድስ አሹ ሥጋ ቤት ተሰይመን ነበር፤ እናስ? እናማ ገበታው ቀርቦ ሁላችንም እጃችንን መዘርጋት ስንጀምር ጥቤ ስል እያናገረ ከች ማለት፤ እሺ ከዛስ? ከዛማ የቀጠራቸው ሰዎች እስከሚመጡ እኛ ጋር መቀላቀል፤ እሺ ካዛስ? ከዛማ የቀጠራቸው ሰዎች ስዘገዩበት ከእኛ ጋር ምሳ ተቀላቀለ/ እኔ ነኝ የምከፍለው/ ብሎ፤
እሺ ከዛስ? ከዛማ ምግብ እየተበላ ጨዋታ ተጀመረ፤ ወደ ጃክሮስ አካባቢ የራሱን አዳራሽ ተከራይቶ መንፈሳዊ አገልግሎት መስጠት እንደጀመረ ነገረን፡፡ እኔ ይህን ግዜ አንድ ጥያቄ ሰነዘርኩ፤ ‹ጥቤ በፌስ ቡክ ላይ ስላንተና ስለመምህር ግርማ የተፃፈውን አይተሃል ወይ?› አልኩት፤ ‹ምንድነው?› አለ ጥቤ፤ መምህር ግርማና ጥበቡ ወርቅዬ በእርኩስ መንፈስ ከተያዙ ሰዎችን ላይ ስለያስወጡት ‹ሰይጣን› የተቀረፀ ቪዲዮ መለቀቁን ተከትሎ ‹እነዚህ ሰዎች የሚያስወጧቸው ሰይጣኖች የት ነው የሚገቡት?› መባሉን አነሳሁበት፡፡ ጥቤ ሳቅ አለና ‹የመምህር ግርማን አላውቅም፤ እኔ ግን በቅዱስ መንፈስ ነው የማባርረው፤› አለ፡፡


tibebu workiye
መንፈሳዊውን ትተን ወደ ዓለማዊው ጨዋታ ገባን፡፡ ‹ጥቤ የእውነት የድሮ ዘፈኖችህ ግጥሞች አንዳንዴ ትዝ አይሉህም ወይ?› ተባለ፤ ‹ትዝ አይለኝም አልልህም፤ ግን አሁን ሌላ መንፈሳዊ አገልግሎት ውስጥ ስለሆንኩ አላስታውሳቸውም፤› አለ፤ ጥቤ ወደ መንፈሳዊ አገልግሎቱ ከመግባቱ በፊት የመጨረሻ አልበም ሰርቶ እንደነበር በመጥቀስ‹ጥቤ የመጨረሻ ያልወጣው አልበምህ የት ነው ያለው፤ እኔ እፈልገዋለሁ?› አልኩት፡፡ ‹ለምን ፈለከው?› አለና ጥያቄዬን በጥያቄ መለሰው፤ ‹›እፈልገዋለሁ› ፤ ዳግማዊ አሊ ኮምፒዩተር ውስጥ እንዳለ እንዲጠፋ ዴሊት ተደርጓል፤ ተቃጥለዋል፡፡ጌታን የተቀበልኩት መጀመሪያ እንደዚህ አይነት ዓለማዊ ስራዎችን በማጥፋት ነው› አለ ዘና ብሎ፡፡


ወዲያው ስለ አርቲስት እዮብ መኮንን ተነሳ፤ በህይወት ሳለ ስለ ሰራውና በቅርቡ ይወጣል ተብሎ ስለሚጠበቀው አዲስ አልበም ጉዳይ ፡፡ ጥቤ በእርግጠኝነት ‹የእዮብ አልበም አይወጣም› አለ ፤ ‹ለምን?› አልነው፤ ‹እንዳይወጣ ተፀልዮበታል፡፡ ልጁ ዘፈን መዝፈን አልነበረበትም፤ መዘመር ነበር ያለበት፤ በህይወት እያለ የሰራው አልበም ይወጣል ተብሎ የነበረው እንደ ሞተ የዛሬ ሶስት ዓመት አልነበር እንዴ?› ሲል እኛኑ ጠየቀን፤ ‹አዎ› አልነው፡፡ 


‹ታዲያ ለምን አልወጣም?› ብሎ ሲጠይቀን፤ ከሙዚቃ ስራ ጋር የተያያዙ የተለያዩ ችግሮችን በመጥቀስ ላለመውጣቱ ምክንያት ደረደርን፡፡ ጥቤ ግን ይህንን አልተቀበለም፡፡‹ አይወጣም፤ ፀልየንበታል፡፡አሁንም አይወጣም፤ አለ፡፡


አልበሙ በቅዲስ ጊዮርጊስ ቢራ ስፓንሰር አድራጊነት ተሰርቶ ህትመቱ መጠናቀቁና አከፋፋዩ ቮካል ሪከርድስ ለማከፋፈል እየተዘጋጀ እንደሆነ ሐብታሙ ቢገል ፅም ጥቤ እንደማይወጣ መንፈሳዊ እምነቱን መሠረት በማድረግ ሊያሳምነን ሞከረ፡፡


ከጥቤ ጋር ከተገናኘንና አልበሙ እንደማይወጣ ከነገረን ሶስት ሳምንት ሆኖታል፤ በዚህ ሶስት ሳምንት ይለቀቃል የተባለው የእዮብ ነጠላ ዜማም አልተለቀቀም፤ ጥቤ ምን እያለ ነው…. 


በነገርህ ላይ ከጥቤ ጋር ከመንፈሳዊ ህይወቱ ጋር በተያያዘ ቃለ ምልልስ ለማድረግ ተነጋግረናል፤ ግን እንደጥቤ አይነት ሰውን ማነጋገር ያለበት ማን ቢሆን ጥሩ ነው? ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ አልክ? ልክ ነህ፤ ቴዲ ከቤት ስራው የተረፈ ጊዜ ካለው እንጋብዘዋለን፤ መጀመሪያ ግን የእዮብ አልበም መውጣት አለበት አልክ? በል ቻዎ

↧

በአማራ ክልል በሕወሓት መንግስት ወታደሮች የተገደሉ የአማሮች ስም ዝርዝር –በቤተ አማራ

$
0
0

‪ቤተ አማራ‬ በሁሉም የአማራ ምድር በሕወሓት ጥይት የተጨፈጨፈፉ ሰመአታት ወንድም እህቶቻችንን ስም ዝርዝር እያጠናከረች ነው። ለዛሬው ባህርዳር ላይ ስለ አማራነት የተሰውት ወገኖቻችን በከፊል እነዚህ ናቸው። ቁጥሩ ከዚህም ይበልጣል ። በጎንደር ፣ በደብረታቦር ፣በአለፋ ጣቁሳ ፣በወሎ ፣ በሸዋ… የተሰውትን ሰመአታት ስም ዝርዝርም እያጠናከርን ነው።
ነብስ ይማር!! ለቤተሰቦቻቸው መፅናኛ የጀመርነውን እርዳታ ማሰባሰብ እጃችሁን በመዘርጋት አግዙን!!

gonder2
‪#‎የአማራ_ተጋድሎ‬
#ቤተ_አማራ
1. እድሜአለም ዘዉዱ እድሜ 27፣ ባህርዳር
2. ገረመዉ አበባዉ እድሜ 25፤ ባህርዳር
3. ተፈሪ ባዩ እድሜ 16 ፤ ባህርዳር
4. ሰለሞን አስቻለ እድሜ 25 ፤ ባህርዳር
5. ሙሉቀን ተፈራ እድሜ 27 ፤ ባህርዳር
6. አደራጀዉ ሃይሉ እድሜ 19 ፤ ባህርዳር
7. አስማማዉ በየነ እድሜ 22 ፤ ባህርዳር
8. ታዘበዉ ጫኔ እድሜ 21 ፤ ባህርዳር
9. አስራት ካሳሁን እድሜ 24 ፤ ባህርዳር
10. የሽዋስ ወርቁ እድሜ 20 ፤ ባህርዳር
11. ብርሃን አቡሃይ እድሜ 29፤ ባህርዳር
12. ሽመልስ ታየ እድሜ 22 ፤ ባህርዳር
13. አዛናዉ ማሙ እድሜ 20 ፤ ባህርዳር
14. ሲሳይ አማረ እድሜ 24 ፤ ባህርዳር
15. ሞላልኝ አታላይ እድሜ 21 ፤ ባህርዳር
16. መሳፍንት እድሜ 22 ፤ እስቴ
17. እንግዳዉ ዘሩ እድሜ 20 ፤ ባህርዳር
18. ዝናዉ ተሰማ እድሜ 19 ፤ ባህርዳር
19. ሞገስ ሞላ እድሜ 23 ፤ ባህርዳር
20. ዋለልኝ ታደሰ እድሜ 24 ፤ ባህርዳር
21. ይታያል ካሴ እድሜ 25 ፤ ባህርዳር
22. እሸቴ ብርቁ እድሜ 37 ፤ ባህርዳር
23. ሞገስ እድሜ 40 ፤ ባህርዳር
24. አደራጀዉ ደሳለኝ እድሜ 30፤ ባህርዳር
25. አበበ ገረመዉ እድሜ 27 ፤ ጭስ አባይ
26. ማህሌት እድሜ 23 ፤ ባህርዳር
27. ተስፋየ ብርሃኑ እድሜ 58 ፤ ባህርዳር
28. ፈንታሁን እድሜ 30 ፤ ባህርዳር
29. ሰጠኝ ካሴ እድሜ 28 ፤ ባህርዳር
30. ባበይ ግርማ እድሜ 26፤ ባህርዳር
31. አለበል አይናለም እድሜ 28 ፤ ደብረ ማርቆስ
32. አብዮት ዘሪሁን እድሜ 20 ፤ ባህርዳር
33. አበጀ ተዘራ እድሜ 28 ፤ ወረታ
34. ደሞዜ ዘለቀ እድሜ 22 ፤ ወረታ
35. አለበል ሃይማኖት እድሜ 24 ፤ ወረታ
36. ሰለሞን ጥበቡ እድሜ 30 ፤ ቻግኒ
37. ፍስሃ ጥላሁን እድሜ 25 ፤ አዲስአበባ
38. ቅዱስ ሃብታሙ እድሜ 16 ፤ አዲስ አበባ
39. በረከት አለማየሁ እድሜ 28 ፤ ዳንግላ
40. ያየህ በላቸዉ እድሜ 30 ፤ ዳንግላ
41. አለማየሁ ይበልጣል እድሜ 27 ፤ ዳንግላ
42. በለጠ ካሴ እድሜ 32 ፤ ደብረታቦር
43. ይህነዉ ሽመልሽ እድሜ 30 ፤ ደብረታቦር
44. ይበልጣል እዉነቱ እድሜ 24 ፤ ጭስአባይ
45. ሃብታሙ ታምራት እድሜ 27፤ ባህርዳር
46. ታደሰ ዘመኑ እድሜ 26 ፤ አዴት
47. ሽመልስ ወንድሙ እድሜ 28 ፤ ቡሬ
48. አይናዲስ ለአለም እድሜ 24 ፤ ደብረወርቅ
49. እስቲበል አስረሳ እድሜ 19 ፤ አዴት

↧
↧

ወያኔ በንጹሃን ኢትዮጵያውያን ላይ ለሚፈጽመው ግድያ የምእራባውያን ዝምታ በጀርመኑ ግዙፍ የቴሌቭዥን ጣቢያ (ZDF) ተሰበረ

$
0
0

በዘርይሁን ሹመቴ/ ከጀርመን

የጀርመን ትልቁ የቴሌቭዥን ጣቢያ የሆነው ዜድ ኤፍ(ZDF) በ06 ቀን ነሃሴ 2008ዓም (12 Aug 2016) ባሰራጨው የዜና ዘገባ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተፋፋመ የመጣውን የህዝብ አመጸኝነትና መንግስት እየወሰደ ያለውን የግድያ የእስራት እንዲሁም የድብደባ ኢሰብአዊ ድርጊቶች በምስል በማስደገፍ ለተመልካች አቅርቧል። ይህ የዜና አውታር Äthiopien in Aufruhr – Westen schweigt፡(ቀውስ በኢትዮጵያ ውስጥ – ዝምታ በምዕራባውያን ) በሚል ርእስ በአሜሪካ ሞርገን ዩንቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ ተመራማሪና መምህር የሆኑትን ፕሮፌሰር ጌታቸው መታፈሪያን(Getachew Metaferia, Professor of Political Science, Morgan State University) አክቲቪስት ጃዋር መሃመድን (Aktivist Jawar Mohammad) አቶ ፍስሃ ተክሌ ከአምኒስቲ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ (Fisseha Tekl) እንዲሁም በናይሮቢ የሴኩሪቲ ጥናት ምርምር ሃላፊ የሆነውን ፒተር አሊንጎን (Peter Alingo) ቃለ መጠይቅ በማድረግ በመላው ኦርሚያና አማራው ክልል እየተቀጣጠለ የሚገኘውን ጸረ ወያኔ አብዮትን ተከትሎ የመንግስት ታጣቂዎች በንጹሃን ሰልፈኞች ላይ እየፈጸሙ ያሉትን ኢሰብአዊ ድርጊቶችን ለአለም ለማሳየት ችሏል።
Screen Shot 2016-08-08 at 2.59.21 AM

በጀርመን በተመልካች ብዛት ቀዳሚ የሆነው ይህ የቴሌቪዥን ጣቢያ ZDF የኢትዮጵያ ህዝቦች ለገዢው ፓርቲ አምባገነናዊነት አንገዛም በማለት ወደ አደባባይ መውጣታቸውን በተቃራኒው መንግስት ባልታጠቁ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥይት እንዳርከፈከፈ እንዲህ በማለት ለአየር አብቅቷል፡ (ተቀማጭነቱ አዲስ አበባ የሆነው አምባገነናዊው የኢትዮጵያ መንግስት ተቋውሞ በወጡት ላይ ሙሉ ሃይሉን ተጠቀመ። እንደ አምኒስቲ ኢንተርናሽናል መረጃ ወደ 100 የሚደርሱ ሰዎች ባሳለፍነው ሳምንት ተገድለዋል። የመንግስት ታጣቂዎች በኦሮምያና በአማራ ክልሎች በወጡት ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የጥይት እሩምታ ቀጥታ ከፍቶባቸዋል። በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የመንግስት ለውጥን ጠይቀዋል።)Die autoritäre Regierung in Addis Abeba schlägt die Proteste mit aller Härte nieder. Am vergangenen Wochenende kamen laut Amnesty International dabei etwa 100 Menschen ums Leben – Sicherheitskräfte hätten in der Oromia-Region nahe der Hauptstadt sowie in der nördlichen Amhara-Region mit scharfer Munition auf die Demonstranten geschossen. Tausende hatten politische Reformen gefordert. http://www.heute.de/aethiopien-in-aufruhr-westen-schweigt-44793418.html

አክቲቪስት ጃዋር መሃመድ በሰጠው ቃለ መጠይቅ የህዝባዊ አመጸኝነቱ የመንግስት ለውጥን በአጽኖት አንግቦ እየተፋፋመ እንደሆነ ገልጿል። (ተቃውሞው እየተፋፋመ ይገኛል። አሁን ሰልፈኞቹ ወይም ህዝቡ መንግስትን መገልበጥ ይፈልጋል ለዚህም በሚገባ ተደራጅቷል እንዲሁም መንግስትን ማንቀጥቀጥ ጀምሯል።) “Die Proteste nehmen zu”, sagt der im Exil lebende Aktivist Jawar Mohammed von der Volksgruppe der Oromo. “Jetzt wollen die Demonstranten das Regime stürzen. Sie sind organisiert und erschüttern die Regierung.” http://www.heute.de/aethiopien-in-aufruhr-westen-schweigt-44793418.html (“The protests are increasing, Now the protesters want to overthrow the regime. They are organized and shake the government.”) ይህንን ሃሳብ ለአምኒስቲ ኢንተርናሽናል የሚሰሩት አቶ ፍስሃ ተክሌ በመጋራት ህዝቡ በጭቆና ውስጥ እንደሚገኝና የፕሬስ ነጻነት በኢትዮጵያ እንደሌለ ለዚሁ የጀርመን የቴሌቪዥን ጣቢያ ZDF ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። (ህዝቡ መብቱ እንዲከበርለት ይፈልጋል። ይህንን ጨቁዋኝ አገዛዝ ይቃወማል የመሰብሰብና የፕሬስ መብትም እንዲከበሩ ይጠይቃል ።)”Die Menschen wollen mehr Rechte, sind gegen das repressive Regime, verlangen mehr Presse- und Versammlungsfreiheit”, sagt Fisseha Tekle von Amnesty dem ZDF. “People want more rights, are against the repressive regime, demanding more press and assembly,” http://www.heute.de/aethiopien-in-aufruhr-westen-schweigt-44793418.html

ፕሮፌሰር ጌታቸው መታፈሪያም የዚህ ሁሉ ቀውስ ተጠያቂው የወያኔ አስተዳደር እንደሆነ አብራርተዋል። የተለያዩ ብሄሮች በሚኖሩባት ኢትዮጵያ ውስጥ የአንድ ብሄር የበላይነት መንገስ ለእንደዚህ አይነት የህዝብ አመጽ መንስኤ እንደሆነ ፕሮፌሰሩ ገልጸዋል። ቁልፍ የመንግስት ስልጣን እንዲሁም የአገሪቷ መከላከያ ሃይል በአብዛኛው በትግራይ ተወላጆች ቁጥጥር እንደሆነም ይህ ጣቢያ የፕሮፌሰሩን ገለጻ በማካተት ዘግቧል።(አገሪቷ በቁጥር አናሳ በሆኑ ብሄር ህዝቦች እጅ ቁጥጥር ውስጥ ናት። እነዚሀም የራሳቸውን ፍላጎት በብዙሃኑ ብሄር ላይ በማስገደድ እያሳረፉ ይገኛሉ። እንደውም ይህ ዋንኛው የተቋውሞው መንስኤ ነው። መንግስትም ሆነ መከላከያው የትግሬ ዘር በሆኑ አባላት የተሞላ ነው ) Der Staat werde von einer ethnischen Minderheit kontrolliert, die ihren Willen der Mehrheit aufzwingt, sagt Metaferia. Dies sei ein wichtiger Grund für die Proteste. Regierung und Militär werden von Mitgliedern der Tigray dominiert,” The state was controlled by an ethnic minority that imposes its will on the majority, says Metaferia. This is an important reason for the protests. Government and military are dominated by members of the Tigray,።http://www.heute.de/aethiopien-in-aufruhr-westen-schweigt-44793418.html

ኢትዮጵያውያን በመላው አገሪቷ እያደረጉ ያሉትን የነጻነት ተጋድሎ የወያኔን መንግስት በተለያዩ ጥቅማ ጥቅም እስከ አፍንጫው ድረስ የሚረዱትን የምእራብያውያን አገራትንም እንዳሳሰበ ይህ የቴሌቪዥን ጣቢያ ጠቅሷል። በተቃራኒውም እነኚህ ምእራብያውያን የኢትዮጵያ መንግስት በብዙ የሚቆጠሩ የኤርትራን የደቡብ ሱዳንን እና የሶማሌ ስደተኞችን ወደ አውሮፓ እንዳይመጡ ስለያዘላቸው እንዲሁም በምስራቅ አፍሪቃ ሽብርን እንዲከላከልቸው ውድ ድሃ የኢትዮጵያ ወታደሮችን ነፍስ ስለሚገብርላቸው በአገሪቷ ውስጥ በንጹሃን ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ እየፈጸመ ያለውን ግድያ እስራት ድብደባ እንዲሁም የመብት ረገጣን በይፋ ለመንቀፍ መሳናቸውን ይህ የቴሌቭዥን ጣቢያ ተችቷል። http://www.heute.de/aethiopien-in-aufruhr-westen-schweigt-44793418.html የኢትዮጵያ መንግስት የኤርትራን የደቡብ ሱዳንን እና የሶማሌ ስደተኞችን አስጠግቻለው በሚል ሰበብ ከጀርመን ብቻ ወደ 30 ሚሊዮን ዮሮ ከ2015 (2007/ 2008ዓም) ጀምሮ ቢቀበልም የስደተኞቹን ህይወት ግን እንዳልተሻሻለ እንዲሁም በምግብ እንኩዋን ራሳቸውን አለመቻላቸውን ዮሃሂም ሽሚት Joachim Schmidt የሚባሉትን በኢትዮጵያ የጀርመን ዲፕሎማት ዋቢ በማድርግ ጠቅሷል።

የመንግስት ሃይሎች በንጹሃን ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ እየፈጸሙ ያሉትን ግድያ ድብደባ እንዲሁም እስራት የተለያዩ የጀርመን ጋዜጦችም እየዘገቡ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል። ከነዚህም ውስጥ ዴ ታገስ ጋዜጣ(DIE TAGESZEITUNG junge Welt) ፍራንክፉርት አልጌማይነ (Frankfurter Allgemeine) ዲ ስይት (Die ZEIT) ዲቬልት (Die Welt) ይገኙበታል።

By Zerihun Shumete
Germany
ምንጮች/ Source
ZDF heute
http://www.heute.de/aethiopien-in-aufruhr-westen-schweigt-44793418.html

http://www.zeit.de/politik/ausland/2016-08/aethiopien-demonstrationen-tote-amnesty-international

http://www.faz.net/aktuell/politik/ausland/afrika/aethiopien-blutige-proteste-gegen-die-regierung-14377891.html

https://www.jungewelt.de/loginFailed.php?ref=/2016/08-13/029.php

↧

በሚኒሶታ የትግል አንድነት የታየበት ታሪካዊ ሰላማዊ ሰልፍ ተደረገ |ቪዲዮም አለው

$
0
0


(ዘ-ሐበሻ) በሚኒሶታ ታላቋ ከተማ ሚኒያፖሊስ የኦሮሞ መንገድ ላይ መነሻውን ያደረገውና ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የመጡ በርካታ ኢትዮጵያውያን የታደሙበት ታሪካዊ ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ ተደረገ::

በኦጋዴን; ኦሮሞ እና አማራ ሕዝቦች ላይ እየደረሰ ያለው የዘር ማጥፋት እንዲቆም የጠየቀው በሰላማዊ ሰልፉ ላይ የሚገኘው ሕዝብ በተለይ ከተለያዩ ቦታዎች የመጡት ኢትዮጵያውያኑ በአንድ ላይ ቆመው ይህን ታሪካዊ ሰልፍ በማድረጋቸው በርካቶች ለዘ-ሐበሻ በሰጡት ቃለምልልስ ተናግረዋል::

ከበቀለ ገርባ – እስከ አንዳርጋቸው ጽጌ; ከ እስክንድር ነጋ እስከ ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ከ እስር እንዲፈቱ ጥሪ ያቀረበው ሕዝቡ በተለይም በሚኒሶታ ሴናተር ኤሚ ክላቫቸር ቢሮ አካባቢ ተቃውሞን በማሰማት ሴናተሯ እየሞተ ካለው የኦሮሞ; አማራና ኦጋዴን ሕዝብ ጎን በመቆም በአንድ ወር ውስጥ አቋሟን እንድታሳውቅ ጥሪ ቀርቧል::

በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ከተገኙት መካከል የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ከፍተኛ አመራር ዶ/ር ኑሮ ደደፎ ለዘ-ሐበሻ በሰጡት አስተያየት “ኦሮሞ; አማራ ኡጋዴን ሳይል ሁሉም በአንድ ላይ በዚህ ሰልፍ ላይ በማየታቸው መደሰታቸውን” ገልጸው ይህ አንድነት እንዲቀጥል ጥሪያቸውን አቅርበዋል::

ቭዲዮውን ይመልከቱ

Minneapolis Minneapolis2 Minneapolis3 Minneapolis4

ethiopia

↧

“ኢሕአዴግ ቢወርድ ማን ይተካዋል?” |ከበፍቃዱ ዘኃይሉ

$
0
0

eprdf

አገሪቱ ውስጥ “ኮሽ” ባለቁጥር የሚሰሙ የ“ይርጋ” ድምፆች አሉ። ስጋታቸው፣ ሕዝብ “ገዢው መረረኝ፣ ለውጥ አማረኝ” ባለ ቁጥር፣ ‘ገዢውን ማን ይተካዋል?’ የሚል ነው። ማስረጃቸው፣ “አንድ የረባ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ የለም” የሚለው ነው። እነዚህን ጥያቄዎች የሚያነሱ ሰዎች የችግሩን ሰፈፍ (surface) እንጂ ምንጩን የማይጠይቁ ናቸው።

 

1ኛ፣ ተቃዋሚዎች ማን እንዲኖሩ ፈቀደላቸው?

መንግሥት መመሥረት የሚችሉ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች የሉም። ምክንያቱም የገዢው ፓርቲ እንዲኖሩ አልፈቀደላቸውም። ፈቃድ ሰጪ፣ ፈቃድ ነሺ፤ ከሳሽ፣ መስካሪ፣ ፈራጅ፤ ሕግ አውጪ፣ ሕግ ተርጓሚ፣ ሕግ አስፈፃሚ የሆነው ኢሕአዴግ ተቃዋሚዎች የመደራጀት ፈቃድ ከማግኘት ጀምሮ፣ ሕዝብ የማደራጀት፣ ርዕዮተዓለማቸውን የማስተዋወቅ፣ በጀት የማሰባሰብ፣ ጽ/ቤት የመክፈት፣ ከሕዝብ ጋር የመወያየት ዕድላቸውን ሁሉ በመዝጋቱ – አዎ የምንተማመንባቸው ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሉም። የምንፈልገውን ዓይነት የተቃዋሚዎች ቡፌ እንዲኖረን የስርዓተ መንግሥቱ ፍልስፍና ሊፈቅድልን ይገባል። የአብዮታዊ ደሞክራሲ መንግሥታዊ ፍልስፍና ደግሞ ይህን አይፈቅድም። የ“ይርጋ” ድምፆች የሚያነሱት ጥያቄ ለውጥ እንዳይመጣ ለመሟገት ሳይሆን ለውጥ እንዲመጣ ለመታገል ሊያነሱት የሚገባ ጥያቄ ነው።

2ኛ፣ ኢሕአዴግ የረባ ፓርቲ መሆኑ ነው?

ኢሕአዴግ ሰባት ሚሊዮን አባላት ያሉት ፓርቲ ነው። በቀጥታ አባልነት ከተመዘገቡ እነዚህ ሰዎች ውጪ የተለያዩ የደጋፊ ሊጎችን አቋቁሟል፦ የኢሕአዴግ ደጋፊ ሴቶች፣ ወጣቶች፣ ነጋዴዎች፣ ወዘተ…። በአንድ ለአምስት ጥርነፋ በየጠረጴዛው ዙሪያ ለመገኘት ይሞክራል። በኮሙኒቲ ፖሊሲንግ ሥም ሰፈሩን ሁሉ ይሰልላል። የመንግሥት ተቋማትን ለምሳሌ ሲቪል ሰርቪሱን፣ ከዚያም በላይ መከላከያ እና ደኅንነቱን፣… እንደልቡ ያዛል፣ ፕሮግራሙን ያስፈፅምባቸዋል። የበጀትም ሆነ፣ ርዕዮተዓለሙን የማስፋፋት ምኅዳራዊ ገደብ የለበትም። እንዲያም ሆኖ ግን ሥልጣኑን በኃይል ከማቆየት በቀር ሕዝባዊ ይሁንታን ማግኘት አልቻለም፤ መፈራት እንጂ መወደድ አልሆነለትም። ነገር ግን አገር እያስተዳደረ ነው። አገሪቱን የሚያስተዳድረው በብቃት አይደለም። ቢሆን ኖሮ እዚያም እዚህም እንደፈላ ሽሮ የሚንተከተክ ሕዝባዊ አመፅ ባልበጠበጠው። ኢሕአዴግ አገር ማስተዳደር የቻለው አሁን ካሉት ተቃዋሚዎች የተሻለ ሆኖ ሳይሆን ሁሉን ባሻው መልኩ ማስኬድ የሚያስችል ሥልጣን ስለተቆጣጠረ ነው።

ሕወሓት/ኢሕአዴግ ይህን ሁሉ ሥልጣን ባይቆጣጠርና አሁን እንደሚያፍናቸው ተቃዋሚዎች የሚያፍነው አካል ቢኖር ኖሮ እንደፓርቲ ሰርተፍኬቱን እያደሰ መዝለቅ እንደሚችል እጠራጠራለሁ። እንዲያውም ግንባሩ አራት ፓርቲዎችን አቅፎ ሳምንት እንኳን መቀጠል አይችልም ነበር። የመንግሥትን ሥልጣን መያዝ በራሱ የሚሰጠው ጥንካሬ አለ። ኢሕአዴግ አገር ማስተዳደር የቻለው፣ ብቁ ስለሆነ ሳይሆን በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ያሉት ሠራተኞች ወደዱትም ጠሉትም ስለሚሠሩለት ነው። ስለዚህ የ“ይርጋ” ድምፆች ስጋት ይህንንም ከግምት ውስጥ ያስገባ ስጋት አይደለም።

3ኛ፣ ኢትዮጵያ ሰው የላትም?

ተቃዋሚዎችም፣ ኢሕአዴግም ውስጥ አንቱ የተባሉ፣ የምንተማመንባቸው ሰዎች ማጣታችን እውነት ነው። ይህ ማለት ግን ኢትዮጵያ ሰው የላትም ማለት አይደለም። መንግሥቷ እና የፖለቲካ ስርዓቷ ሰዎቿን ገፉባት እንጂ! ተቃዋሚ ፓርቲዎች የምሁራን ድርቅ አለባቸው፤ ምሁራን ተቃዋሚዎች ግን በየቤታቸው እና ተቋማቱ ውስጥ አሉ። ተቃዋሚዎች የገንዘብ እጥረት አለባቸው፤ ተቃዋሚ ባለሀብቶች ግን አሉ። የፖለቲካ ፓርቲ አባልነት ኢትዮጵያ ውስጥ በሠላም እንደማያኖራቸው ይፈራሉ እንጂ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ተቀላቅለው ለውጥ ማምጣት የሚችሉም የሚፈልጉም ሰዎች አሉ።

እነዚህ ሰዎች እንዲመጡ፣ የፖለቲካ ስርዓቱ መለወጥ አለበት። ሕዝብ በጉልበቱ መንግሥታትን ማስጨነቅ አለበት። ሠላማዊ አመፅ አንዱ የሕዝብ መንግሥትን ማስጨነቂያና የሥልጣን ሰጪና ነሺ ማን እንደሆነ ማስታወሽያ ነው። ማመፅ የሕዝብ መብት ነው፤ መግዛት ግን የመንግሥታት መብት አይደለም። ሕዝብ የሚመጥነውን መንግሥት መምረጥ ይችላል፤ መንግሥት ግን የሚገዛውን ሕዝብ መምረጥ አይችልም። የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በቀር ሕዝብ (ብዙኃኑ) ያሸንፋል። ያኔ ኢትዮጵያ የሚመጥኗትን ፖለቲካ ፓርቲዎች ማፍራት እንደምትችል እና እንደማትችል እናያለን። ያ ሳይሆን ቀርቶ ወደ እርስበርስ ጦርነት የምንገባ ከሆነ፣ መንስዔው የተቃዋሚዎች ድክመት ሳይሆን የገዢው “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” ባይነት ነው።

↧
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live