Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ወያኔን ኢንቡልኑ። –ዳዊት ዳባ

$
0
0

Woyane

አገሬው በሺዎች ልጆቹን እየቀበረ፤ በአስር ሺዎች ወደማጎርያ እየተጋዘ። በሚሊዬኖች አደባባይ ወጥቶ እየታገለ ነው። አሁን ላይ መሸፋፋኛው ተገላልጦ ፍንትው ብሎ የወጣው  ታላቁ የህዘብ ጥያቄ “ የህዋዋት የበላይነት በቃ” የሚለው ነው። ይህ ማለት “የስርአት ለውጥ ነው”። ህዘብ በቃ ሲል በጠቅላላ በአገሪቷ ላይ ካሰፈኑት ፈፁም የበላይነት በተጨማሪም    ኢህአዲግ በሚለው ስብስብ ውስጥ ያለው የበላይነትና አድሏዊነት ይብቃም እያለ ነው። ይህ ድምፅ ከውጪ ብቻ አይደለም እየተሰማ ያለው።  እዛው ከውስጣቸውም እያየለ እየመጣ ነው።  አዎ የደርግን ስርአት በጦርነት አሸንፋዋል።  አሸናፊነት የሚሰጠውን ሁለንተናዊ ጉልበት ውስን ለሆኑ አመታት በተለየና በነበረው ነባራዊ ሁኔታ ውስጥ ለሚዛኑ መዛባት ምክንያት አድርጎ መውሰድ ይቻል ይሆናል። ይህም እንኳ ለከት ባለው ሁኔታ ተደርጎ ቢሆን ኖሮ ነው።

ለኦሮሞዎች ድርጅት እንፍጠር ብለው ከምርኮኞች ሰርተዋል። ለአማራዎች ድርጅት እንፍጠር ብለው ደግሞ እንዲሁ ፈጥረዋል። እንዲህ እንዲህ እያሉ ለሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች   ድርጅቶች ፈጠሩ።  እነዚህ ድርጅቶች በሰዎች ነው የተሰሩት። እንዳሻቸው ጢቢ ጢቢ እንዲጫወቱባቸውና ለሀያ አምስት አመት መጠቀሚያ ሊያደርጓቸው መቻላቸው የሚሰግርም ነው። ያም ሆኖ  የፈለገውን አይነት ክትትል ግምገማና ጥቅም ይኑር። ቋንጃቸው አልተሰነኮለም። አንገታቸው ላይ ሰንሰለት አልታሰረም። ሁሌ መሳርያ የያዘ አካል ማማ ላይ ቆሞ አይጠብቃቸውም። ይህም ተደርጎ ቢሆንም እንኳ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ የትግሬ ወያኔዎች አገዛዝ  ፍፃሜ ላይ ይህ ክፍል የሚኖረው ትልቅ ሚና ቀድሞ ማየት መቻል አለመቻል ካልሆነ  ሳይታለም የተፈታ ነበር።

እነዚህ ድርጅቶች ውስጥ ድርሻ ያደረጉ ከላነሰ ምን አልባትም ከተሻለ ማህበረሰባዊ እሴት ካለው ህዘብ ውስጥ የወጡ ናቸው። የበዙት በእድሜያቸውማ ሆነ በጉልበታቸው ካሳዳሪዎቻቸው የበረቱ ናቸው። በአይምሮም ሆነ በመማር ካገኙት እውቀትም በልጠዋቸዋል። በቁጥር አጥፈዋል። በድርጅት ጥንካሬም  እንዲሁ። በአግባቡ አልተጠቀሙበትም እንጂ ከወከሉት ማህረሰብ ብዛት አኳያ ሊሰጣቸው የሚችለው ጉልበትም  የትየለሌ ነበር። እርቀን ካለነው በተሻል በቅርብ ሆነው ብልግና ቆሞ ሲሄድ አይተዋል። ወገንታዊነት ሊኖራቸው አይችልም አያማቸውም ብሎ ማሰብ የአቦይ ስበሀት ድንቁርና ብቻ ነው። ዛሬ የምናየው የነዚህ ጉዳዬች ድምር ውጤትን ነው። ከአመት በፊት ኦፒዲዬዎች የተመከሩት  ህወሀት እራሱን ችሎ  የኦሮሞን ህዘብ አፍኖ ሊገዛ በጭራሽ አይችልም። የታፈነ የኦሮሞ ህዘብ ማለት ጢቢ ጢቢ መጫወቻ  ስትሆኑ መኖር ነው። ሊገባችሁ ከቻል ቀላሉ መንገድ  ህዝቡን ልቀቁት ነበር። ከምትግመቱት በላይ ጉልበት ይሆናችሗል ነበር።  ይህ በሌሎች አጋር  ድርጅቶች ዘንድ የተወሰደ ተሞክሮ ነው።

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ አነድ ጊዜ ላይ ቀለል አድርገው  አመላካችና የምታድግ ግን የማትመስል አሳብ ጣል አድርገዋል። “እንቢ ካሉ  ሌሎቹ  እራሳቸውን ችለው መንግስት መሆን ይችላሉ” የምትል።

መሳርያ የያዘው ላይ በመለጠፍ መትረፍ ይቻላል የሚለውም ህልም ነው። ጉዞው የሗልዬሽ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ጀነራሎቹ እንጂ አብዛኛው ሰራዊት የናንተ አይደለም። ህዘብ ነው። የደሀ እናት ልጆች ናቸው። የወገኖቹ ደም በመላው አገሪቱ የሚንዥረዥር። ለራሱም ያልተመቸው። ጠቀላላ የአገሩና የወገኑ ሁኔታ የሚያመው። አዎ ቁጭ ብሎ የመምከር አማራጮችን የማየት በአጠቃላይ ትግሉን በጋራ ለማድረግ በአፈናው ምክንያት ክፍተቶች አሉበት። የማይሞሉ ወይ ሊሞላቸው የማይቻለው ግን አይደሉም። ፈዛዛ ተቃዋሚ መኖሩ ነው እንጂ ድሮ በቀላሉ ሊሞላ የሚችል ነበር። አሁንም ቢሆን ሌላው ቀርቶ የጊዜ፤ አጋጣሚና ቦታ መመቻቸት በራሱ  ደህና ሁኑን ለሁሌው ሊያመጣ ይችላል። ይህ የህዘብ ትግል በሁሉም አገሪቷ ክፍል ባንድ ጊዜና ሰዓት በአገር አቀፍ ደረጃ መደረጉ አይቀርም። የዚህ አይነት ሁኔታዎች ከዛሬ ጀምሮ ሁላችንም ነፃ ነን የሚለውን መናበብና ስሜት መፍጠሩ አይቀርም። የአገሪቷ ጠቅላላ ሁኔታ የሚሻውም ይህንኑ ነው።

የኦሮሞ ተቃውሞ ጥንካሬ አንዱ መገለጫ  ስርአቱ ውስጥ ያሉ ወገኖቻቸውን መዚገብ ገልጠው የለውጡ አካል የሆነውን ካልሆነው መናገር መቻላቸው ብቻ ሳይሆን ከበዙት ጋር አስፈላጊ ሲሆን ሊደርሷቸው የመቻልን አቅም መገንባታቸው ነው። በግሌ ከአመታት በፊት የኢላሞ ሞልሞሌ ቀበሌ ሊቀመንበር ስሙ ማነው? ባለቤቱስ ማን ትባላለች? የጅ ስልኩስ? ብዬ ነበር። ምን እናድርገው? ድክመት ሆኗል። አሁንም ሊሰራ የሚቻል ነው። ቀድሞ አስቦ መስራት የብልሆች ነው። አንዳንዴ ደግሞ ግድ ሲል በዘመቻ በሳምንታት ይሰራል። ሁሉን ያቀፈ ትብብር ማቆሙም እንዲሁ።  ይህ ሀሳብ በዜጎች ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው መሰረቱ የተጣለ ነው። አንዳንዴ አሜሪካኖች ጠርተው ኑ እዚህች ላይ ፈርሙ እስኪሉ የሚጠበቅ ይመስላል።

እውነት ለመናገር ዲሞክራሲያዊት ፤ ፍትህና እኩልነት የሰፈነባት የሁሉንም ፍላጎትና ጥያቄ ማስተናገድና ብሎም መሸከም የምትችል አገር እንዲኖረን አሁን የተፈጠረውን አይነት አጋጣሚ መቼም ተፈጥሮ አያውቅም። ከወያኔ በሗላ ጦር ሀይል ፖሊቲካው ውስጥ የለም። ደርግ ጦር ነበረው። ወያኔ ጦር ይዞ ነው የገባው። አሁን ማንም ፍላጎቱን አቻችሎና ተደራድሮ፤ በዜጎች ፍላጎት ተዳኝነቶ  ካልሆነ ፍላጎቱን በጦር ሐይል መጫን የሚችልበት ሁኔታ የለም። ወያኔን ባዶ እጁን ታግሎ የጣለ ህዘብ ለትናንሽ  ባለመሳርይዋች ወይ ጉልበታሞች ይገብራል መጃጃል ነው። አጉል ፍርሀትና ጥርጣሬ ካልሆነ መጪው ጊዜ ለሁሉም ብሩህ ነው። መተባበር አብሮ መታገል ሽግግሩንም መስራት ይቻላል። {የዚችን ፓራግራፍ ይዘት የያዘ አነጋገር ረፋዱ ላይ አቶ ሌንጮ ለታ ኦ.ሜ.ኔ ላይ ያደረገው ቃለ መጠይቅ ላይ ሲጠቀም ሰማው}። በነገራችን ላይ የትብብሩ ፋይዳ ለወደፊት እነሌንጮ ድርጅታዊ ጥንካሬ ሊገነቡ ከቻሉ ካልሆነ አልታየኝም። እንደውም ጊዜው ለሚሻው ትልቅ ነገር ዝም ብሎ አፍ ማዘጊያና መከፋፈያ አድርጌ ነው የወሰድኩት።

ያም ሆኖ በሽግግሩ አዳልጦን ማጥ ውስጥ እነዳንገባ መጠንቀቅ ያስፈልጋል። አይደለም ከፈላጭ ቆራጭ አንባገነን ወደዲሞካራሲያዊ ሁሌም ቢሆን መንግሰት መቀየር እንደተባለው ያው ዳይፐር መቀየር ነው። ሲቀይሩ ላለማነካከትም ሆነ ቶሎ ቶሎ በአዲስ ይቀየር የሚባለውም ለዚሁ ነው። መቀየሩ ጥሩ ግድም ሆኖ እያለ ያገለገለ ከቆሻሻ ውስጥ አውጥቶ  አድርግ አታድርግ በሚል ግብ ግብ አገሩን በሙሉ አር እንዳናናካካውም መጠንቀቁም አይከፋም። ለፈለገ ከድል በሗላ ይህም ሀሳብ ችግር የለውም። ከድል በፊት ትግሉ ውስጥ ማስሮጥ ግን ህዘብ መራራ መሰዋትነት ከፍሎ ወደፊት ያስኬደው ትግል ላይ መከፋፈያ ታኮ ይሆናል። ምንጩ ደግሞ ይታወቃል ድክመት ነው። በመጀመርያ እናሸነፍ። ከዛ ያሉ ፖለቲካዊ ፍላጎቶችና ልዩነቶች ሰላማዊ ህጋዊና መዋቅራዊ በሆነ መንገድ እንደባደብባቸው።

ጊዜው የኔን መንገድ በትንሹ። ብዙ የጋራ ስራን ግድ የሚል ነው። አገዛዙ የፈለገውን ያህል ቢዳከም ፍፃሜውን ማድረግ ብዙ ስራን ይፈልጋል። ከዛም ባጭር ጊዜ ውስጥ ሰላም መረጋጋትን ማስፈንና አልፎም ህግና ስርአት በቶሎ እንዲጠበቅ የሚያስችል ብቃት ላይ ማቀድ፤ በዝርዝር መዘጋጀትና የመተግበር ዝግጁነትን መፍጠር ደግሞ አለ። ይህን አለማድረግ እንዝላልነት ብቻ ሳይሆን አስጠያቂም ነው። በግልሰብ ደረጃ ሎተሪ ቢደርሰኝ ብሎ ከዛ ተነስቶ ማለም ወይ ማቀድ ይቻላል። በአገርና በሕዝብ ግን አንባገነን እየታገልክ ላዛውም የኛዎቹን እያወቅናቸው ፖለቲካዊ ማሻሻያ እንዲያደርጉ ሲጠብቁ መዘናጋት ሀላፊነት የጎደለው ይሆናል። ከአንዷለም ይፈታም ሆነ ፖለቲካዊ ማሻሻዬዎችን አስቀምጦ መታገያ ማድረጉ ማለፊያ ሊሆን ይችላል። ይህ አያከራክርም። ከዛ ባለፈ ሰላም የሰፈነባት የተረጋጋች ዲሞክራሲያዊ ኢትይጵያ ያለነሱ በጎ ፍቃድ አይመጣም ካልን መታገል ሳይሆን ቤተ መንግስት በር ላይ እየሄድን ምህላ መያዙ ይሻል ነበር። በዛ ላይ ልናገኝ የምንችልው ውጫው ድጋፍ ለውጡን መሸከም መቻላችን ላይ የሚታይ፤ ሊተገበር የሚችል ዝግጅት በዝርዝር አስቀምጠን ማሳመን ከመቻላችን ጋር በቀጥጣ ይገናኛል። ይሄ ሁሉ በተናጠል በሚደረግ እሩጫ ሊሰራ አይችልም። ሽግግር ግድም፤ ሀላፊነትም፤  ስራም ነው።

ዳዊት ዳባ

Saturday, August 20, 2016

dawitdaba@yahoo.com

 

 

 

 


የአዲስ አበባ ተቃውሞ ሰልፍ –የቀጥታ ዘገባ | Live Coverage

$
0
0

addis ababaየአጋዚ ሰራዊት እና የፌደራል ፖሊሶች ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ ማናቸውንም መንገዶች ዘጋግተዋል:: መኪኖችም እንዳያልፉ በመከልከል ላይ ናቸው:: (ፖሊሶች ፎቶ)

addis ababa

______

“በመላ ሀገሪቱ በመካሄድ ላይ ያለው ህዝባዊ ንቅናቄና በተለይ ዛሬ በአዲስ አበባ ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀው ተቃውሞ ስጋት ላይ የጣላቸው የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ከፍተኛ ባለስልጣናት መቀሌና ደብረዘይት የሚገኘውን የአየር ሃይል ምድብተኛ በአንደኛ ደረጃ ተጠንቀቅ እንዲሆን ማዘዛቸው ተሰማ።” – ኢሳት አሁን ያስተላለፈው ሰበር መረጃ

————

በጥቁር አንበሳ አካባቢ ወደ መስቀል አደባባይ እየተመመ የሚገኘው ሕዝብ እና አታልፉም ብሎ መንገድ ከዘጋው የትግራይ ነጻ አውጪ ሰራዊት ጋር ተፋጠዋል:: ወታደሮቹ ሕዝቡን ለመመለስ ኃይል እየተጠቀሙ ነው::

——–

የአዲስ አበባ ህዝብ ወደ አብዮት አደባባይ ጉዞ ጀምሯል።  አዲስ አበባ በአሁኑ ሰዓት ሁሉም መንገዶች ወደ መስቀል አደባባይ እያመሩ ነው:: የትግራይ ነጻ አውጪ ሰራዊትና አጋዚዎች ሕዝቡን ለማፈን እየጣሩ ነው::

addis ababa

 

መስቀል አደባባይ በፌደራል ፖሊስ ተከቧል:: ፎቶግራፉን አሁን ከአዲስ አበባ የደረሰን ነው:: የፌደራል ፖሊሶቹ መኪኖቻቸውን በአደባባዩ አቁመውታል::

ገና ሰልፉ ሳይደረግ ፌደራል ፖሊሶቹ መስቀል አደባባይ ሰፍረው አካባቢውን በማጠር ላይ ናቸው:: አዲስ አበባ በአሁኑ ወቅት ተወጥራለች::

meskel adebabay

————–

የመንግስት ሚዲያዎች ከትናንት ምሽት ጀምሮ ዛሬም በጠዋቱም “በአዲስ አበባ የተጠራ ሰልፍ የለም” በሚል ህዝቡን ለማደናገር እየሞከሩ ነው:: አሁንም በየሰፈሩ ያለው ፍተሻ ከመጠናከሩም በላይ ጦር መሳሪያ የታጠቁ የትግራይ ነፃ አውጪ ሰራዊት ወታደሮች ብዛት ቁጥሩን ለመጥራትም ይከብዳል:: በተለይም ተቃውሞው ሊነሳባቸው ይችላሉ በተባሉ ሰፈሮች አካባቢ እነዚሁ የአጋዚ ወታደሮች መንገዶችን ዘጋግተው እየጠበቁ ነው:: ዘ-ሐበሻ ካነጋገቻቸው የተለያዩ ግለሰቦች መረዳት እንደቻለችው በፈረንሳይ ለጋሲዮን፣ በመካኒሳ፣ ቤልኤር፣ ጉለሌ፣ አዲሱ ገበያ፣ መገናኛ፣ ወሎ ሰፈርና ሌሎችም አካባቢዎች የጦር መሳሪያ በታጠቁ በትግራይ ነጻ አውጪ ወታደሮች ተከቧል::

 

———-

ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች እየተፈተሹ ነው

አዲስ አበባ አሁን ከጠዋቱ 2:08 ነው:: ከአዲስ አበባ ያነጋገርናቸው ወገኖች እንደሚገልጹት ከጠዋቱ 10 ሰዓት ጀምሮ ወደ ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎችን የአጋዚ ወታደሮች እያስቆሙ ሲፈትሹ ነበር:: የትግራይ ነጻ አውጪ ወታደሮች በየሰፈሩ ሰፍረው ቢገኙም በከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ እንዳሉ የሚያደርጉት ነገር ያሳብቅባቸዋል ሲሉ ያነጋገርናቸው ወገኖች ገልጸውልናል::

———

 

እንደምን አደራችሁ:: በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል እየተባለ እየተጠበቀ ነው:: ፈጣን መረጃዎችን ለናንተ በማድረስ የምትታወቀው ዘ-ሐበሻ ከአሁን ጀምሮ በዚህ ገጽ ከአዲስ አበባ አዳዲስ መረጃዎችን እየተቀበለች ታደርሳለች:: አዳዲስ መረጃዎችን ቶሎ ቶሎ ስለምናደርሳችሁ ይህን ገጽ ደጋግመው Refresh እያደረጉ ይጎብኙት::

በባህርዳር ከቤት ያለመውጣትና የሥራ ማቆም አድማ ተጀመረ

$
0
0
(የባህር ዳር ከተማ File Photo)

(የባህር ዳር ከተማ File Photo)

(ዘ-ሐበሻ) የአማራው ክልል ዋና ከተማ በሆነችው ባህር ዳር ከተማ የሥራማቆም እና ከቤት ውስጥ ያለመውጣት አድማ ተጀመረ::

በከተማዋ በአሁኑ ወቅት የሚታየው ፖሊስ ብቻ ሲሆን ሕዝቡ ለቀጣይ 3 ቀናት እንዲደረግ በታቀደው ከቤት ያለመውጣትና የሥራማቆም አድማ ተሳታፊ ለመሆን በዛሬው እለት ጀምሮታል::

በባህርዳር ምንም ዓይነት ንግድ እንቅስቃሴ ካለመኖሩም በላይ ሆቴሎችን ጨምሮ ትናንሽ ምግብ ቤቶች ዝግ ናቸው::

የአዲስ አበባን ሰልፍ በተመለከተ – ‪ግርማ ካሳ‬

$
0
0

ዛሬ በአዲስ አበባ ሊደረግ ታስቦ የነበረው ሰልፍ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶችን ሁሉ አገዛዙ ስለዘጋና ቁጥሩ እጅግ በጣም ብዙ የሆነ የታጠቀ ሃይል በመረጨቱ ሳይደረግ ቀርቷል።፡

addis ababa

ሕዝብ ድምጹን የማሰማት ሙሉ መብት እንዳለው ሕገ መንግስቱ ይናገራል። ሆኖም ሕወሃት በድጋሚ በአዲስ አበባ ሕዝቡ ድምጹን የማሰማት መብቱ ገፏል።

የሕወሃት መሪዎች ብዙ ጊዜ እንደ አልጃዚራ ባሉ ሜዲያዎች እየቀረቡ ሕዝቡ ድምጹን የማሰማት መብት እንዳለው ይናገራሉ። ሆኖም ግን ሕዝብ ድምጹን እንዳያሰማ፣ አዲስ አበባ የጦር ቀጠና እንድትመስል ማድረጋቸው ሰዎቹ ምን ያህል በርግጥ ከሕዝቡ እንደተጣሉ የሚያመለክት ነወ።

አንዳንድ ወገኖች ያንን የአገዛዙ አፈና ሰብሮ ለምን እንደ ባህር ዳርና እንደ ጎንደር ህዝብ አልወጣም በሚል አላስፈላጊና እንጭጭነት ያለበት አስተያየትም ሲሰጡ እያነበብኩ ነው። ለነዚህ ወገኖች ዘጠና ሰባትን እና በቅርቡ ደግሞ አይሰስን በመቃወም በተጠራው ሰልፍ የነበረዉን ሁኔታ እንዲያስቡ እመክራቸዋለሁ። አሁን ብቻ አይደለም ሕወሃት አዲስ አበባ ሲገባ እንኳን. ይሄንን ዘረኛ አገዛዝ ከጅምሩ የተቃወመ ሕዝብ ነው። የአዲስ አበባ ህዝብ በአገዛዙ ከፍተኛ ስቃይ የደረሰበትና የመረረው፣ ለአገርና ለነጻነትም ብዙ ዋጋ የከፈለ ነው።

ይልቅ የአዲስ አበባ ህዝብ ነቅሎ ለምንድን ነው ያልወጣው የሚል ጥያቄ በመጠየቅ ሁኔታዉን መረዳት ያስፈለጋል።

ሕወሃቶች የአዲስ አበባ ሕዝብ ሰልፍ ስላልወጣ፣ “እኛን ደግፎ ነው፤ የጸረ-ሰላም ሃይሎችን ስለተቃወመ ነው” የሚልዝ ዝባዝንኪ ሊያወሩ ይችላሉ። በሜዲያቸው ትልቅ ሽፋን ሰጥተዉት። እኔ እነርሱን ብሆን ግን ዛሬ፣ ሕዝብ አልተነሳም ብለው ከሚመጻድቁ፣ ቢነሳ ኖሮ ግን ምን እንሆን ነበር ብለው፣ ለገ፣ ከነገ ወዲያ ሊነሳ እንደሚችልም በማሰብ በቶሎ ለብሄራዊ እርቅ እንዲዘጋጁ የሽግግር መንግስት በማቋቋም የአገር ችግሮች በሰላም እንዲፈቱ እሰራ ነበር።የአዲስ አበባ ሕዝብ ነገሮችን እንዲያስተካክሉ ሌላ እድል እንደሰጣችው ቢያስቡት ጥሩ ነው።

addis ababa

የአዲስ አበባ ህዝብ ለምን ዛሬ ሰልፍ አልወጣም? በኔ እይታ ሁለት ትላልቅ ምክንያቶች ነው ያሉት፡

1. የአዲስ አበባ ህዝብ በበቂ ሁኔታ አልተደራጀም። በሶሻል ሜዲያ ሰልፍ ስለተጠራ ሰልፍ ይወጣል ማለት አይደለም። በባህር ዳርና በጎንደር የተደረጉ ሰልፎች፣ እዚያው በህዝቡ መካከል ያሉ ወገኖች ድርጅታዊ ሥራ ሰርተው ያቀረቡትን የሰልፍ ጥሪ ነው ፣ በሶሻል ሜዶያ የበለጠ ተደራሽነት እንዲኖረው የተደረገው። ሶሻል ሜዲያ አጋዥ እንጅ ወሳኝ አይደለም። የአዲስ አበባው ሰልፍ ግን የተለየ ነው። መነሻው ህዝብ ሳይሆን ሶሻል ሜዲያው ነው። በሶሻል ሜዶያ የተወሰኑ ዳያስፖራ ያሉ ሃይሎች በስሜት ሰልፍ ጠርተው፣ ሰልፉ ከተጠራ በኋላ ነው ሕዝቡን ለማደራጀት የተሞከረው። ትልቅ ስህተት ነበር። በዚህ መልኩ ህዝብ ሳይደራጅ በሶሻል ሜዶያ ዘመቻ፣ ወይንም በኢሳት ቅስቀሳ ለዉጥ እንደማይመጣም በሚገባ አስተምሮናል። ይሄ አንዱ ነጥብ ነው።

2. በአዲስ አበባ እንቅስቃሴ እንዲኖር ሕዝብ መደራጀት አለበት ካልን እንዴት ነው ህዝቡን የምናደራጀው የሚል ጥያቄ ይነሳል። ሕዝቡን ለማደራጀት ደግሞ የአዲስ አበባ ህዝብ ጥያቄዎችም መስተናገድ አለባቸው። ኦሮሞ፣ አማራ የሚለው ሰሞኑን ፖለቲካችንን አጡዞታል። የአዲስ አበባ ሕዝብ ኦሮሞ፣ አማራ የሚል ነገር፣ የዘር ነገር አይመቸውም። በዘር ዙሪያ የሚደረግ እንቅስቃሴን ለመደገፍ ይከብደዋል።

ትግሉ ተጀመረ እንጅ መጨረሻ አይደለም። የዛሬው ሰልፍ በመጠኑም ቢሆን በአዲስ አበባ ለሰልፉ ተብሎ በሜዳ የተሰሩ ሰራዎች አሉ። ይህ ሰራ በተጠናከረ መልኩ መቀጠል አለበት ባይ ነኝ። የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እየተመካከሩ፣ እየተነጋገሩ በየቀበሌዉና በየወረዳው መስባሰብ አለባቸው። ሁሉም ነገር የሚጀመረው ከሰፈር ነው። በዚህ መልክ በአጭር ጊዜ ውሱጥ ከህዝቡ ክራሱ ትልቅ ድርጅታዊ ጉልበት ያለው ሃይል ሊፈጠር ይችላል፡ ጎንደር የተደረገው እንደዚያ ነው።

እንግዶህ ወገኖች ..እንበርታ ….ትግሉ ይቀጥላል !!!!

ኢትዮጵያዊው ፈይሳ ላሊሳ በሪዮ ኦሎምፒክ ማራቶን የብር ሜዳሊያ አገኘ –እጁን ወደላይ በማጣመር ለትግሉ ያለውን አጋርነት አሳየ

$
0
0

Lalisa Feysa Lalisa

lalisa(ዘ-ሐበሻ) በሪዮ ኦሎምፒክ በወንዶች ማራቶን ኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ አገኘች:: ኢትዮጵያዊው ፈይሳ ላሊሳ በኬኒያዊው አትሌት ኤሉድ ኪፕቾጌ ተቀድሞ 2ኛ ቢገባም ውድድሩን በሚያጠናቅቅበት ወቅት የኢትዮጵያ ሕዝብ  ባለፈው 10 ወራት ካለማቋረጥ እየተጠቀመበት ያለውን እጅን ወደላይ ማጣመር በማሳየት ለትግሉ ያለውን አጋርነት አሳይቷል::

በዚህ የማራቶን ውድድር አሜሪካዊው ግሌን ሩፕ 3ኛ ሲወጣ ኤርትራዊው አትሌት ግርማይ ገብረስላሴ 4ኛ ሆኖ አጠናቋል::

ኬንያዊው አትሌት ውድድሩን ለመጨረስ 2:08:44 ሲፈጅበት ኢትዮጵያዊው ፈይሳ 2:09:54 ገብቷል:: 3ኛ የወጣው አሜሪካዊው ግሌን 2:10:05 በመግባት 3ኛ ሆኗል::

ፈይሳ ዛሬ በብዙ ሚሊዮኖች በተከታተሉት የኦሎምፒኩ ሜዳ ላይ እጁን ወደላይ አጣምሮ መንግስትን መቃወሙና ከሕዝብ ጎን አጋርነቱን ማሳየቱ በኢትዮጵያ ውስጥ የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት በሕዝቦች ላይ እየፈጸመ ያለውን ግድያና የሰብ አዊ መብት ጥሰት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ትኩረት እንዲያደርጉበት የራሱን ጫና ያሳድራል::

lalisa

“ወደ ኢትዮጵያ ከተመለስኩ ይገሉኛል”አትሌት ፈይሳ ላሊሴ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በሪዮ ኦሎምፒክ በማራቶን ሩጫ ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ ያስገኘው አትሌት ፈይሳ ላሊሴ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሰ የመንግስት ኃይሎች ሊገድሉት እንደሚችሉ ተናገረ::

ውድድሩን ሲጨርስ እጆቹን ወደላይ በማጣመር ተቃውሞውን የገለጸው ላሊሴ በኢትዮጵያ ባለትዳር እና የ2 ልጆች አባት ነው:: አትሌቱ ፕሬስ ኮንፍረንሱን ከጨረሰ በኋላ በሰጠው ቃል ሃገር ቤት ከዚህ በኋላ ሊኖረው የሚችለው ሕይወቱን ሲያስብ እንደሚሰጋ ገልጿል:: ሆኖም ግን በዚያው ጥገኝነት ይጠይቅ አይጠይቅ የታወቀ ነገር የለም::

የፈይሳ ለሊሳ እጆች ~ ከ1968 ወዲህ በኦሎምፒክ መድረክ የታየ የመጀመሪያው ተቃውሞ

አዲስ አበባ ሰሞኑን የጦርነት ቀጠና ሆናለች።በተለይ ዛሬ ስርዓቱ ቀዩዋን ያ ሲል ውሎዋል።ተደናብሮ ተደናግሮ ፈርቶ ሕዝቡን አስፈራራሉ ብሎ ውሎ አምሽቷል። ይሄ ሰላማዊ ሰልፉን አድርጎ ቀይ ካርድ የማሳየትን ያክል አይሳካ እንጂ በራሱ የሌላ ታላቅ ተቃውሞ ድል ዋዜማ ነው።ይሄ ሁሉ ሰራዊት ይሄ ሁሉ ወከባ ይሄ ሁሉ ፍርሃት ስልጣን ላይ ያሉት ሰዎች ስጋት ምን ደረጃ እንደደረሰ ማሳያ ነው። ቀሪው ኳሱዋን በመሬት ላይ የሚጫወቱት የለውጥ ሀይሎች ቀጣይ ስትራቴጂ ነው። የዛሬውን የአዲስ አባባ የጦር አውድማ ያስመሰለው የቀይ ካርድ ተቃውሞ ቢከሽፍም አትሌት ፈይሳ ለሊሳ በሪዮ ኦሎምፒክ ሁለት ሰዓት ከዘጠኝ ደቂቃ ከ54 ሰኮንድ በመግባት የብር ሜዳሊያ አስገኝቷል።   ድርብ ድል እንዲሉ የሕዝብ አጋርም ሆኗል።ተቃውሞን በተገኘው ሁሉ መድረክ ላይ ማሰማት ጊዜው የጠየቀው ነው። በኦሎምፒክ አደባባይ አጋዚ ማይደርስበት ወያኔን አንገት ያስደፋ እርምጃ ወስዷል። ለሞቱ ወገኖቹ በድሉ ሳይኮራ አጋርነቱን አሳይቷል። አሁን የቀረው የነ ጌታቸው ቅርሻት ብቻ ነው <ኦሎምፒክ ላይ ምንትሴ..> ያበደ ስርዓት ያበደ ቃል አቀባይ።ለሁሉም የኦሎምፒክ መድረክ ከዚህ ቀደም ያስተናገደውን ጨምሮ የትነበርክ በገጹ የከተበውን ያንብቡት። 

Lalisa Feysa

(የትነበርክ ታደለ)

በዝያ አመት በሜክሲኮ በተካሄደው የኦሎምፒክ ውድድር ቶሚ ስሚዝ እና ጆን ካርሎስ የተባሉ ሁለት ጥቁር አሜሪካውያን ወርቅና ነሀስ በማግኘት ለሽልማት መድረክ ላይ ቆመዋል። የሽልማቱ ስነ-ስርአት ተጀመረ። የአሜሪካ ብሄራዊ መዝሙር ተከፍቶ በስታዲየሙ የሚገኙ አሜሪካውያን ሁሉ ከመቀመጫቸው ተነስተው እጆቻቸውን በደረታቸው ላይ ጭነው ከፍ ባለ የብሄራዊ ስሜት መዝሙሩን ያስተጋቡ ጀመር….

ነገር ግን ሜዳሊያዎቹን በወዛቸው ያገኙት ሁለቱ አትሌቶች ቶምና ጆን አንገታቸውን ደፉ፣ እጆቻቸውን ወደ ላይ ሰቀሉ፣ በዝምታም ብሄራዊ መዝሙሩን ሳይዘምሩ ጸጥ ረጭ አሉ!!

በወቅቱ በጥቁር አሜሪካውያን ላይ ለሚደርሰው በደል እና የዘር መድልዎ እነዚህ ሁለት ወጣቶች በዚህ መድረክ በኩራት ደረታቸውን ሊያስነፋቸው በደስታ ሊያስቦርቃቸው አልቻለምና አንገታቸውን በመድፋት ለአለም ህዝብ ተቃውሞዋቸውን አሰሙ። ይህም ለብዙ የነጻነት ታጋዮች ዳግም የመነቃቃት ስሜትን ፈጠረ።….

ቶም ስሚዝና ጆን ካርሎስ ከዝግጅቱ በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይም “ዛሬ ምን አይነት ታላቅ ስራ እንደሰራን አሜሪካውያን ሁሉ ያውቃሉ!” ሲሉ በኩራት ተናግረዋል። “ድላችን የህዝባችንን ድምጽ ለአለም ህዝብ ማሰማት መቻላችን ነው” ብለዋል።

lalisa

ዛሬ ከ46 አመታት በኋላ ደግሞ የኛው የማራቶን ጀግና በሪዮ ኦሎምፒክ የህዝብ ልጅነቱን ደገመው። ዛሬ ኢትዮጵያውያን ከዳር ዳር የነጻነትና የእኩልነት ጥያቄ እያቀረቡ ባለበት ወቅት፣ ለጥያቄያቸውም ምላሹ የጥይት ባሩድ በሆነበት በዚህ ወቅት፣ መንግስት የተባለው የጥቂቶች ስብስብ ነገሮችን አረጋግቶ ሀገራዊ ፋይዳ ያለው ውሳኔ ከመወሰን ይልቅ ህዝብን ከመጤፍ ሳይቆጥር ቀንና ማታ እያሸበረ ባለበት በዚህ ወቅት…….

….ፈይሳ ለሊሳ ኢትዮጵያ አይታው የማታውቀውን ታሪክ ሰርቷል። ማሸነፍ ሩጫን ብቻ አይደለም፣ ማሸነፍ አንድ የተሰለፉበትን የሙያ መድረክ ብቻ አይደለም፣ ማሸነፍ ማለት የሀገርና የወገንን ጥቅም ማስቀደም ማለት ነው።

እናም ፈይሳ በሪዮ ዴጄኔሮ የኦሎምፒክ የሽልማት አውድ ላይ ሲቆም ታሪክ የሚዘክረው ባስገኘው የብር ሜዳሊያ ብቻ አይሆንም። የብዙዎችን ዝምታ መስበር የቻለበት እና ለአለም ህዝብ ድምጻችንን ያሰማበት እጆቹም እንዲሁ ይዘከራሉ። ታሪክ ለመስራት ሁሉም ጊዜ አመቺ ነው!! ረዥም እድሜ ለፈይሳ ለሊሳ!!!

አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ቃለምልልስ ሰጠ “ከባለፉት 9 ወራት ብቻ ከ1 ሺህ በላይ ኦሮሞዎች በኢትዮጵያ ተገድለዋል –ወደዚያ አልመለስም”

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ በሪዮ ኦሎምፒክ በማራቶን ውድድር የብር ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ ካመጣ በኋላ እጁን ወደላይ በማጣመር መንግስትን የተቃወመው ባለፉት 9 ወራት ብቻ ከ1 ሺህ በላይ ኦሮሞዎች በመንግስት ጸጥታ ኃይሎች በመገደላቸውና በርካቶችም በመታሰራቸው ነው አለ:: አትሌቱ በቃለምልልሱ ላይ እንዳለው ወደ ኢትዮጵያ ቢመለስ ለህይወቱ አስጊ በመሆኑ ወደ ኢትዮጵያ እንደማይመለስ አስታውቋል:: ቃለምልልሱን በቭዲዮ ይመልከቱት::

Lalisa Feysa copy

አትሌት ፈይሳ ለሊሳ ሪዮ ላይ ታሪክ ሲሰራ

$
0
0

ከጌታቸው በቀለ

ዛሬ ነሐሴ 15፣2008 ዓም ኢትዮጵያ ጭንቀት ላይ ነበረች።የህወሓት አጋዚ ወታደሮች ከጎንደር እስከ ባሌ፣ከባህርዳር እስከ አርሲ በመቶ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ሕይወት በሕዝብ ገንዘብ በተገዛ ጥይት ሕዝቡን ሲፈጁት ከርመዋል። በሁለተኛው የዓለም ጦርንነት ወቅት አይሁዶችን ጀርመኞች እንደሚያጉሩት በትግራውነታቸው የምመፃደቁት ህወሓቶች በሺህ የሚቆጠሩ የአማራ እና ኦሮሞ ወጣቶችን በኢየቦታው አጉረዋል።ይህ ሁኔታ ያሳሰባቸው ኢትዮጵያን አክትቪስቶች በአዲስ አበባ በገዢው ህወሓት ላይ ሰልፍ እንደሚደረግ ገለፁ።ከቅዳሜ ምሽት ጀምሮ ግን የህወሓት ወታደሮች የአዲስ አበባ ወጣት በተኛበት እየያዙ ወደ እስር ቤት ወሰዱት።እናቶች እያለቀሱ ልጆቻቸውን እያዳፉ ወደ እስር ቤት ወሰዷቸው።ምሽት ላይ እና እሁድ ጧት ለቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ የሚሄዱ ካህናት ሳይቀሩ ሲፈተሹ አረፈዱ።የአዲስ አበባ ዋና ዋና መንገዶች እና መንደሮች ሁሉ በአጋዚ ወታደሮች ተትለቀለቁ።መስቀል አደባባይ በከባድ የጦር ካሚዮኖች አጠረው።የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ እንጂ ጦርንት አይደለም በሚል ኢትዮጵያውያን ህወሓት ካለ ጦርነት ሰላም የሚባል ቃል እንደማታውቅ ደግመው አረጋገጡ።
Lalisa
ይህ ሁሉ በሆነበት ወቅት ነበር።በብራዚሏ ከተማ ሪዮ ዲጀነሮ የሚደረገው የ2016 እኤአቆጣጠር ኦሎምፒክ ላይ በማራቶን የሚወዳደረው አትሌት ፈይሳ ለሊሳ 42 ኪሎ ሜትሩን ማራቶን 2ኛ ሆኖ በመጨረስ የብር ሜዳልያ ማሸነፉን ባረጋገጠበት ቅፅበት የኢትዮጵያንን በዘረኛው እና አምባገነኑ ህወሓት መረገጥ በቀጥታ ቴሌቭዥን ከ3 ቢልዮን በላይ ሕዝብ የሚመልከተው ስርጭት ላይ ለዓለም አጋለጠ። ህወሓት ከጎሳው ውጭ ለሆኑ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈፅመውን ግፍ ለመላው ዓለም ነገረው።አዲስ አበባ ላይ ታንክ ደግነው በቴሌቭዥን ህዝቡ ተስማምተነዋል እያሉ ሲሳለቁ ለነበሩ አረመኔዎች በሳሎናቸው ሶፋ ፊት ለፊት ባለው ቲቪ ፊት ለዓለም አጋለጣቸው።በልጆቻቸው፣ቤተሰባቸው ፊት አረመኔነታቸውን ነገራቸው። ቃል አቀባዩ አቶ ጌታቸው ”አሁን የምሳ ሰዓት ደረሰ”እያሉ በአዲስ አበባ ወጣት ላይ እንዳልተሳለቁ ምሳ በልተው እራት ሳይደግሙ በዓለም ፊት ከጀርመኑ ናዚ የማያንሱ መሆናቸውን ነገራቸው።

አትሌት ፈይሳ ከኦሎምፒክ ሜዳ በኃላ በጋዜጣዊ መግለጫው መድረክ ላይም በደላችንን አሰምቷል።

በኦሎምፒክ አደባባይ ዘረኛ መንግስት ማጋለጥ ትልቅ መልዕክት ያለው ብቻ ሳይሆን ቀጣይ መዘዝ ለወያኔ ይዞ ይመጣል። ጋዜጠኛ ካሳሁን ይልማ የእዚህ አይነቱ ተግባር ከእዚህ በፊት በኦሎምፒክ አደባባይ መደረጉን እና ውጤቱን በፌስ ቡክ ገፁ ላይ የጠቀሰውን እንደሚከተለው አስቀምጠዋለሁ።
”አሜሪካዊያን አትሌቶች ጆን ካርሎስ እና ቶሚ ስሚዝ በ1968ቱ የሜክሲኮ ኦሊምፒክ በ200 ሜትር ሩጫ ውድድር የወረቅ የብር እና የነሐስ ሜዳሊያ ካሸነፉ በኋላ ባገኙት ድል መፈንጠዝ ሳይሆን በቆዳ ቀለም ልዩነት ብቻ በጥቁር ሕዝብ ላይ የሚፈጸመውን ጭቆና እና ዘረኝነት በመቃወም ጥቁር ጓንት አጥልቀው እጃቸውን ወደላይ ከፍ በማድረግ የጥቁር ኃይል ምልክትን አሳይተዋል። የለበሱት ጃኬት ላይ የሰብአዊ መብት ባጅ ለጥፈዋል። ጫማቸውን አውልቀው ጓንት ባለደረጉት እጃቸው ይዘዋል።

ከዚያ በኋላ በኦሊምፒክ ኮሚቴ እና በተለያዩ አካላት ከፍተኛ የትችት ውርጅብኝ ወርዶባቸዋል። ከናዚ ሰላምታ ጋር አመሳስለው እንዲሸማቀቁ የሞከሩ ሁሉ ነበሩ። ከአሜሪካ ቡድን እንዲገለሉ ቅጣት ተጥሎባቸዋል።ሆኖም ሁለቱ እንቁ አትሌቶች በዓላማቸው ጸንተው ተምሳሌት ሆነው ዛሬ ድረስ ይወሳሉ። በሳንሆዜ ዩኒቨርሲቲ የድል ሰላምታ ተብሎ ሐውልት ቆሞላቸዋል።የነርሱ ለእውነት መቆም ከሺህ ሰላማዊ ሰልፍ በላይ ለጥቁሮች መብት የሚያስፈልገውን መልዕክት ለዓለም አስተላልፏል። ከጎናቸው የቆመው ለህሊናው ያደረውና የወቅቱን የጥቁሮች ጭቆና የተገነዘበው ነጩ አውስትራሊያዊ ፒተር ኖርማን የብር ሜዳሊያውን ሲያጠልቅ የሁለቱ አትሌቶችን ዓላማ በመጋራት የሰብአዊ መብት ምልክት የሆነውን ባጅ ደረቱ ላይ አኑሮ አጋርነቱን አሳይቷል።
ነጭ ቢሆንም የነጮችን ዐይን ያወጣ በደል፣ ጭቆና፣ ዘረኝነት፣ አድልዎ…ተረድቷል።ትግሬ በመሆናቸው የሌላው መረገጥ መሰደድ መገደል የሚያስደስታቸው ህወሓትን የሚደግፉ ሰዎች ስለ ሌሊሳ ምን ይሉ ይሆን?”እዚህ ሀገር አይገባትም፣ ተመልሶ ከመጣ ደግሞ ይገባታል፣ ይኼ ኦነግ…ከልቢ…” ምን እያሰባችሁ ነው?እኛስ ለሌሊሳ የክብር ሐውልት በልባችን ተክለናል። ነፃነት በምታገኘው ኢትዮጵያም ለትውልድ ትምህርት የሚሆን ሐውልት ይቆምለታል።” የጋዜጠኛ ካሳሁን ፅሁፍ መጨረሻ።

ወያኔ ዘረኛ መሆኑን ከአይሮፕላን አብራሪ ካፕቴን ገብረመድህን እስከ የአልጋ ላይ ቁራኛ ሀብታሙ አያሌው የመሰከሩት ነው።ፈይሳን የአዕምሮ በሽተኛ ነው እንዳትሉ ጤናው በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመርምሯል።እረስታችሁ እንዳትሉ ብዬ ነው። ዛሬ ታሪካዊ ቀን ነው።ሪዮ ኦሎምፒክ ታሪክ ተሰራ! ሌሊሳ ስለ ሁሉ ተሰለፈ! ታሪክ የምለው ዝም ብዬ ለማዳነቅ አይደለም።ለልጅ ልጆቻችን ስለ ኦሎምፒክ እና ኢትዮጵያ ትምህርት ቤት ሲማሩ የፈይሳ ተጋድሎ ይወሳል።ሲቀጥል ኢትዮጵያ ወያኔ በሚባል ዘረኛ ቡድን ምን ያህል ተጨቁና እንደኖረች ይማራሉ።ታሪክ ማለት ይህ ነው።የቅርብ ጊዜው ታሪክ ግን የምናየው ነው።

ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com


የሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ በወቅታዊው የሃገራችን ጉዳይ ባለ8 ነጥብ የአቋም መግለጫ አወጣ

$
0
0

Minnesota church Ethiopian
ጋዜጣዊ መግለጫ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ፤ አሜን!

ሁላችንም እንደምናውቀው እና በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን እንደምንሰማውና እንደምናየው በአሁኑ ጊዜ ቅድስት ሃገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላማዊ ጥያቄ ባቀረቡ ወገኖች እና በንጹሃን ዜጐች ላይ በመንግሥት የጸጥታ ሃይሎች እየተካሄደ ያለው ግድያ፣ እስራት፣ አፈና እና እንግልት ከምንግዜውም የከፋ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

አስደሳች ዜና –ዶ/ር ሼክስፒር ፈይሳ ብራዚል ድረስ ሄደው ለአትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ጥብቅና እንደሚቆሙ ቃል ገቡ

$
0
0

feyyisa
ጴጥሮስ አሸናፊ እንደዘገበው

ጀግናው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ በሪዮ ኦሎምፒክ በማራቶን ታላቅ ድል ካስመዘገበና ህወሃትና ታማኝ ጦሩ የሆነው አጋዚ በኢትዮጵያውያን በተለይም በታላላቆቹ የኦሮሞና አማራ ብሔረሰቦች ላይ የሚያካሂዱትን የዘር ማጥፋት፣ የመግደል፣ የማሰር፣ የመጨፍጨፍ፣ የማዋከብና የማሳድድ ተግባርን በአለም አቀፍ መድረክ በቢሊዮን ለሚቆጠሩ የአለማችን ህዝቦች በኦሎምፒክ አደባባይ ከፍ አድርጎ በማሳየቱ የሃገራችን ሕዝቦች፣ የሃገራችን ወዳጆችንና በአምባገነኖች የሚረገጡና የሚጨቆኑ ጥቁር አፍሪካውያንን ያኮራ ታሪካዊ ጀግንነትን በመፈፀሙ ገድሉ በአለም አቀፍ ደረጃ በአራቱም መዐዘን በመገናኛ ብዙሃን እየተነገረለት ይገኛል።

የወንዶች ማራቶን ውድድር በታላቁ የኦሎምፒክ መድረክ የመዝጊያ ቀን የሚካሄድ እንደመሆኑና ከውድድሩ መጠናቀቅ በኋላ የተሳታፊ ሃገሮች ተወዳዳሪዎችና የልዑካን ቡድን አባላትም ወደየሃገራቸው ለመመለስ የሚዘጋጁበት ጊዜ በመሆኑ የኢትዮጵያን ኦሎምፒክ ቡድን የሚመሩት የህወሃት አባላት ጀግናውን አትሌት እንዳያዋከቡትና ወደ ሃገር ቤት እንዲመለስ ጫናና ግፊት እንዳያደርጉበት ኢትዮጵያውያንና አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ተቋማት አፋጣኝ እንቅስቃሴ እንዲጀምሩ በመላው አለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በመጎትጎት ላይ ይገኛሉ።

የጉዳዪን አሳሳቢነትና የሕዝባችንን ስጋት በመረዳት አሁን ማምሻውን በአጭር ጊዜ የተዋቀረ አለም አቀፍ ግብረ ሃይል አስቸኳይ ውይይት በማድረግ ላይ ሲሆን በቀጣይ ቀናትም ያለውን የሙያተኞች ስብስብ በማስፋት ለጀግናው አትሌት የአለንልህ ጥሪውን ለማሰማት የሚቻለውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን በታላቅ ደስታ ይገልፃል።

እስካሁን መቀመጫቸውን በአሜሪካን ሃገር ሲያትል ዋሺንግተን ያደረጉት የሕግ ባለሙያ ዶ/ር ሼክስፒር ፈይሳ እንደ አጋጣሚም ፓስፖርታቸው ላይ የብራዚል ቪዛ ስላላቸው በራሳቸው ወጪ ወደ ሪዮ በመሄድ ለጀግናው አትሌት በነፃ ጠበቃው ለመሆን ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል ሌሎችም የሕግ ባለሙያዎች እንዲቀላቀሏቸው ጠይቀዋል።

የህወሃት መንግስት በነገው ዕለትና በመጪዎቹ ቀናት ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮችን ወደ ብራዚል እንደሚልክና ከብራዚል መንግሥት ተወካዮችም ጋር ግንኙነቶችን እንደጀመረ ምንጮች እየጠቆሙ ቢሆንም የብራዚል መንግሥት ሰላማዊ ዜጎችን በአደባባይ በጥይት ለሚገድለው ህወሃት አዎንታዊ መልስ ይሰጣል ተብሎ አይገመትም።

የህወሃት መንግሥት ከሁለት አመት በፊት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነውን የመንገደኞች አውሮፕላን በመጥለፍና ጄኔቫ ስዊዘርላንድ በማሳረፍ የሥርአቱን ገመና ያጋለጠውን ረዳት አብራሪ ኃይለመድኅን አበራን ከስዊዘርላንድ ወደ ኢትዮጵያ በማስመለስ ለማሰቃየትና ለመግደል አድካሚ የዲፕሎማሲ ጥረት ቢያደርግም በስዊዘርላንድ መንግሥት ጥያቄው በተደጋጋሚ ውድቅ እንደተደረገበትና የስዊዘርላንድም ከፍተኛው ፍርድ ቤት ኃይለመድኅንን በነፃ እንዳሰናበተው የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው።

በጠራራ ጸሀይ አገር ሲዘረፍ |ከአቻምየለህ ታምሩ

$
0
0

በያዝነው የፈረንጆች ዓመት በወርሀ ጥር የወያኔ ካድሬዎችና የአገዛዙ የፕሮፓጋንዳ ተቋማት የሆኑት እነ ኤ.ቢ.ሲ.፣ ዋልታ፣ ፋና፣ ኤ.ዜ.አ. ወዘተ ትግራይ በታሪኳ ለብሔራዊ ባንክ አቀረበችው ስላሉት የወርቅ ምርት መጠን በስፋት ዘግበው ነበር። የአገዛዙ ልሳን ኢ.ቢ.ሲ. እ.አ.አ. ጥር 07 ቀን 2016 ዓ.ም. ባቀረበው ርዕሰ አንቀጽ፤ ዋልታ እ.አ.አ. ጥር 09 ቀን 2016 ዓ.ም. ባስደመጠም የዜና እወጃ ፤ ኤ.ዚ.አ. ጥር 16 ቀን 2016 ዓ.ም. ባስነበበን ሪፖርት ትግራይ እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ድረስ 597.7 ቶን ወርቅ [በባህላዊ መንገድ] እንዳመረተችና ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እንዳቀረበች ነግረውናል።

 

gold
ይህንን «ልማታዊ ዜና» የሰሙ ብዙ ሰዎች «ትግራይ ከየት አምጥታ ነው ይህንን ያህል ወርቅ አምርታ ለብሔራዊ ባንክ የምታቀርበው?» በማለት ከቁጥሩ ጀርባ ያለውን የምጣኔ ሀብት ትርጉም ሳያጤኑ አጣጥለውት አልፈዋል። ሆኖም ግን ከቁጥሩ ጀርባ ወያኔ ትልቅ አገራዊ ዘረፋና ወንጀል ፈጽሟል። ወያኔ በቁጥሩ ቁማር ተጫውቶ የኢትዮጵያን የሁለት አመት ባጀት ያህል ብሔራዊ ሃብት በአንድ ግብይት ብቻ ወደ ትግራይ አሸሽቷል ወይንም አሻግሯል። ነገሩ እንዲህ ነው።

ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ድረስ 597.7 ቶን ወርቅ ከትግራይ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ቀረበ ማለት በ42 ወር ውስጥ 597.7 ቶን ወርቅ ከትግራይ ለብሔራዊ ባንክ ቀረበ ማለት ነው። ይህ ማለት ትግራይ በአመት በአማካኝ 171 ቶን ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አቅርባ ነበር ማለት ነው። በኢትዮጵያ የንግድ ህግ መሰረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ብቸኛው ወርቅ ገዢና አስቀማጭ ተቋም ነው። ክልሎች በየክልሉ የተመረተውን ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ሲያቀርቡ ብሔራዊ ባንክ ክልሎች ላቀረቡት የወርቅ መጠን ክፍያ ይፈጽማል። ለምሳሌ ትግራይ 597.7 ቶን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ስታቀርብ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለትግራይ ክልል የ597.7 ቶን ወርቅ ክፍያ በገንዘብ ይፈጽማል። ያልቀረበ ወርቅ ሪፖርት ተደርጎ ብሔራዊ ባንክ ላልቀረበ ወርቅ እንደቀረበ ተደርጎ ክፍያ ቢፈጽም ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ የሀብት transfter ይኖራል ማለት ነው።

ወያኔ የነገረን ትግራይ ለብሔራዊ ባንክ ያቀረበችው 597.7 ቶን ወርቅ ማለት 597,700 ኪሎ ግራም ወርቅ ማለት ነው።ይህ ማለት ደግሞ 19,216,473 ወቄት ወርቅ ማለት ነው። ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ድረስ በነበሩት አመታት ውስጥ አማካኝ የአንድ ወቄት ወርቅ ዋጋ 1,100 የአሜሪካን ዶላር ነበር። ይህ ማለት ትግራይ አቀረበችው የተባለው 597.7 ቶን ወርቅ ዋጋ 21. 376 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ይሆናል ማለት ነው።

ይህ ማለት [በወያኔ ዜና መሰረት] ትግራይ ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ድረስ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ላቀረበችው 597.7 ቶን ወርቅ ብሔራዊ ባንክ 21. 376 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከፍሏታል ማለት ነው። የኢትዮጵያ ያለፈው አመት ባጀት አስር ቢሊዮን ዶላር ነው። ይህ ማለት ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ድረስ ትግራይ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አቀረበችው ለተባለው 597.7 ቶን ወርቅ የተከፈላት 21. 376 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከኢትዮጵያ የሁለት አመት በጀት በላይ ነው ማለት ነው።

ዋናውና ቁልፉ ጥያቄ እውነት ትግራይ ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ድረስ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 597.7 ቶን ወርቅ ወይንም ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. በየአመቱ 171 ቶን ወርቅ አቅርባለች ወይ? የሚለው ነው።

ይህንን ጥያቄ ለመመለስ የአለም አገሮችን የወርቅና የሌሎች ማዕድናትን አመታዊ ምርት ማስረጃ የሚሰበስበውንና የሚያደራጀውን የUnited States Geological Survey (USGS) Minerals Resources Program አመታዊ የአለም ማዕድናት ምርት ሰንጠረዥን ማየት በቂ ነው። ይህ የአሜሪካ ተቋም በአለም ላይ ያሉ ማዕድን አምራች አገሮችን የማእድን አመታዊ ምርት አሃዝ ሰብስቦ ደረጃ ያወጣና የአለም አገሮችን በማዕድን ምርት ያወዳድራል። በዚህ መስሪያ ቤት ማስረጃ መሰረት ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ድረስ በአለም ላይ በወርቅ ምርት አንደኛ ቻይና ስትሆን አመታዊ የወርቅ ምርት መጠኗ 403 ቶን ነው። ሁለተኛዋ የአለም ወርቅ አምራች አገር ደግሞ አውስትራሊያ ስትሆን አመታዊ የምርት መጠኗ ደግሞ 250 ቶን ወርቅ ነው። ሶስተኛ አሜሪካ [235 ቶን ወርቅ በአመት] ፤አራተኛ ሩስያ ፌድሬሽን [217.8 ቶን ወርቅ በአመት] ፤ አምስተኛ ፔሩ [161 ቶን ወርቅ በአመት] ፤ስድስተኛ ደቡብ አፍሪካ [160 ቶን ወርቅ በአመት]፤ ሰባተኛ ካናዳ [103 ቶን ወርቅ በአመት] ፤ ስምንተኛ ሜክሲኮ [96.7 ቶን ወርቅ በአመት] ፤ ዘጠነኛ ኡዝቤኪስታን [ 93 ቶን ወርቅ በአመት] እና ጋና [86.5 ቶን ወርቅ በአመት] በአለም ላይ አስሩ ከፍተኛ ወርቅ አምራች አገሮች ናቸው። የዚህ ምንጭ የሚከተለውን ትር መክፈትና መመልከት ይቻላል… http://www.indexmundi.com/minerals/…።

ወያኔ ኢትዮጵያ ትግራይ ብቻ ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ድረስ በየአመቱ 171 ቶን ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አቅርባለች ያለው እውነት ቢሆን ኖሮ ኢትዮጵያ በወርቅ ምርት በአለም ደረጃ ፔሩን ቀድማ ሩስያን ተከትላ አምስተኛ ደረጃ ላይ ትሆን ነበር። ልብ በሉ ከአንድ እስከ አስር የወጡ አገሮች ሁሉ ወርቅ የሚቆፍሩት በጣም ዘመናዊ በሆነ መሰርሰሪያ ማሽን ነው። ወያኔ ግን ትግራይ በየ አመቱ 171 ቶን ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አቅርባለች የሚለን በባህላዊ መንገድ አምርታ ነው።

ከፍ ብዬ በለጠፍሁት የUnited States Geological Survey (USGS) Minerals Resources Program አመታዊ የወርቅ ምርት እውነተኛ ደረጃ መሰረት የኢትዮጵያ አመታዊ የወርቅ አምራችነት ደረጃ 29ኛ ሲሆን አመታዊ የወርቅ ምርቷ ደግሞ 12 ቶን ብቻ ነው። ልብ በሉ ይሄ አመታዊ የኢትዮጵያ የወርቅ ምርት ዶዶላ፣ መተከል፣ ለገደንቢና ወለጋ ሜድሮክ በዘመናዊ ቴክኖሎች ታግዞ የሚያመርተውን ይጨምራል። ወያኔ ግን የትግራይን አመታዊ ምርት ብቻ 171 ቶን ነው ይለናል።

ሜድሮክ በዶዶላ፣ በመተከል፣ በለገደንቢና በወለጋ የሚያመርታቸውን ዜሮ አድርገን ኢትዮጵያ ያመረተችውን 12ቱን ቶን ወርቅ ከትግራይ ብቻ ለብሔራዊ ባንክ የቀረበ የወርቅ መጠን አድርገን ብንወስድ፤ ብሔራዊ ባንክ ከትግራይ በየአመቱ 171 ቶን ወርቅ እንደቀረበለት ተደርጎ ለትግራይ በጠቅላላ ከከፈለው 21.3 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ ውስጥ በያመቱ ላልቀረበ 158 ቶን ወርቅ ክፍያ ፈጽሟል። ይህ ማለት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከትግራይ ቀረበ ተብሎ ከፍያ ከፈጸመበት 597.7 ቶን ወርቅ ውስጥ ባንኩ የተረከበው ወርቅ 42 ቶብ ብቻ ነው። የተቀረው 555.7 ቶን ወርቅ ወርቁ ከትግራይ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሳይቀርብ ብሄራዊ ባንክ ግን ከትግራይ ወርቅ ሳይቀርብ ክፍያ እንዲፈጽም የተደረገበትና የአገር ሀብት ዘረፋ የተካሄደበት የውሸት ቁጥር ነው።

ይህ ማለት ብሔራዊ ባንክ ለትግራይ ከከፈለው 21.3 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ ከ20 ቢሊዮን ዶላር በላይ ለትግራይ የተከፈለው የአገር ሀብት ላልቀረበ የወርቅ መጠን እንደቀረበ ተደርጎ ነው ማለት ነው። ይህ ማለት ወያኔ ያልቀረበ ወርቅን አስታኮ 20 ቢሊዮን ዶላር በላይ ያገር ሀብት ወደ ትግራይ wealth transfter አድርጓል ማለት ነው። ይህ ማለት የሁለት አመት የኢትዮጵያ አመታዊ በጀትን የሚያህል የአገር ሀብት ትግራይ ለብሔራዊ ባንክ ወርቅ እንዳቀረበች ተሳቦ እንድትወስድ ተደርጓል ማለት ነው። ይህ ማለት የሁለት አመታት የኢትዮጵያ አመታዊ ሀብት ወደ ትግራይ እንዲሄድ ሲባል ዘረፋ ተፈጽሟል ማለት ነው። ወገኖች this is a huge wealth transfter. ወያኔ ከጥር ወዲህም ማራኪ ቁጥር እያቀረበ የአገር ሀብት ወደ ተስፋዋ ምድሩ እያሸጋገረ ይገኛል። በሌላ ጊዜ ከሌሎች ቁጥሮች ጀርባ ስለሚፈጸም አገራዊ ዘረፋ የምለው ይኖረኛል።

የሚገርመው ትግራይ በየአመቱ 171 ቶን ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አቀረበች በተባለ በወሩ የቀረበው ሌላ ዜና የስርዓቱ ዜና ነው። ፋና በየካቲት 11 ቀን 2008 ዓ.ም [እ.ኢ.አ.] ያቀረበው ዜና ርዕስ እንዲህ ይላል…«ለብሄራዊ ባንክ እየቀረበ ያለው ወርቅ በከፍተኛ ደረጃ እየቀነሰ ነው።» ዜናው በዚህ ብቻ አያበቃም። ከ2004 ዓ.ም. እስከ 2008 ዓ.ም.[እ.ኢ.አ.] በየአመቱ 171 ቶን ወርቅ ትግራይ ለብሔራዊ ባንክ አቀረበች እንዳልተባለ «ብሄራዊ ባንክ ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል በባህላዊም ሆነ በዘመናዊ መልኩ ተመርቶ የሚቀርበለት ወርቅ በእጅጉ ቀንሷል። በ2005 ለባንኩ የቀረበለት 8.1 ቶን ወርቅ ነበር። በ2006 ዓ.ም ደግሞ 7.4 ቶን ሆነ፤ በ2007ም በጣም አሽቆልቁሎ 5.4 ቶንድረስ ወርዷል።» አሉን። ይህ ሁሉ የሚሆነው ከትግራይ ብቻ ለብሔራዊ ባንክ በአመት 171 ቶን ወርቅ ቀረበ ተብሎ 20 ቢሊዮን ዶላር እንደቀላል ወደ ትግራይ transfter እንዲሆን ባደረጉ በአንድ ወር ውስጥ ነው።

አይ አንቺ አገር! ማፍያዎች የውሸት ቁጥር እየቀቀሉ ሌላውን ጾም ደፍተፍና አራቁተው የድሆችን ሀብት ወደ መንደራቸው ያግዛሉ። በአንድ ማጭበርበር ብቻ ሀያ ቢሊዮን ዶላር የአገር ሀብት ወደ መንደራቸው አሸሹ! በቁጥር ሊሸውዱን ሲሞክሩ በትንተና እንዲህ ባጋለጥናቸው ጉዳይ ብቻ ሀያ ቢሊዮን ዶላር በድብቅ ባልተወለደ አንጀታቸው ከገፈፉ ሰው ሳያውቀው የዘረፉት የአገር ሀብት ቢታወቅ ለሌላው ኢትዮጵያ ምን ያህል ያተርፉለት ይሆን?

በጠራራ ጸሀይ አገር ሲዘረፍ –አቻምየለህ ታምሩ

$
0
0

TPLF 1በያዝነው የፈረንጆች ዓመት በወርሀ ጥር የወያኔ ካድሬዎችና የአገዛዙ የፕሮፓጋንዳ ተቋማት የሆኑት እነ ኤ.ቢ.ሲ.፣ ዋልታ፣ ፋና፣ ኤ.ዜ.አ. ወዘተ ትግራይ በታሪኳ ለብሔራዊ ባንክ አቀረበችው ስላሉት የወርቅ ምርት መጠን በስፋት ዘግበው ነበር። የአገዛዙ ልሳን ኢ.ቢ.ሲ. እ.አ.አ. ጥር 07 ቀን 2016 ዓ.ም. ባቀረበው ርዕሰ አንቀጽ፤ ዋልታ እ.አ.አ. ጥር 09 ቀን 2016 ዓ.ም. ባስደመጠም የዜና እወጃ ፤ ኤ.ዚ.አ. ጥር 16 ቀን 2016 ዓ.ም. ባስነበበን ሪፖርት ትግራይ እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ድረስ 597.7 ቶን ወርቅ [በባህላዊ መንገድ] እንዳመረተችና ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እንዳቀረበች ነግረውናል።

ይህንን «ልማታዊ ዜና» የሰሙ ብዙ ሰዎች «ትግራይ ከየት አምጥታ ነው ይህንን ያህል ወርቅ አምርታ ለብሔራዊ ባንክ የምታቀርበው?» በማለት ከቁጥሩ ጀርባ ያለውን የምጣኔ ሀብት ትርጉም ሳያጤኑ አጣጥለውት አልፈዋል። ሆኖም ግን ከቁጥሩ ጀርባ ወያኔ ትልቅ አገራዊ ዘረፋና ወንጀል ፈጽሟል። ወያኔ በቁጥሩ ቁማር ተጫውቶ የኢትዮጵያን የሁለት አመት ባጀት ያህል ብሔራዊ ሃብት በአንድ ግብይት ብቻ ወደ ትግራይ አሸሽቷል ወይንም አሻግሯል። ነገሩ እንዲህ ነው።

ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ድረስ 597.7 ቶን ወርቅ ከትግራይ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ቀረበ ማለት በ42 ወር ውስጥ 597.7 ቶን ወርቅ ከትግራይ ለብሔራዊ ባንክ ቀረበ ማለት ነው። ይህ ማለት ትግራይ በአመት በአማካኝ 171 ቶን ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አቅርባ ነበር ማለት ነው። በኢትዮጵያ የንግድ ህግ መሰረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ብቸኛው ወርቅ ገዢና አስቀማጭ ተቋም ነው። ክልሎች በየክልሉ የተመረተውን ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ሲያቀርቡ ብሔራዊ ባንክ ክልሎች ላቀረቡት የወርቅ መጠን ክፍያ ይፈጽማል። ለምሳሌ ትግራይ 597.7 ቶን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ስታቀርብ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለትግራይ ክልል የ597.7 ቶን ወርቅ ክፍያ በገንዘብ ይፈጽማል። ያልቀረበ ወርቅ ሪፖርት ተደርጎ ብሔራዊ ባንክ ላልቀረበ ወርቅ እንደቀረበ ተደርጎ ክፍያ ቢፈጽም ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ የሀብት transfter ይኖራል ማለት ነው።

ወያኔ የነገረን ትግራይ ለብሔራዊ ባንክ ያቀረበችው 597.7 ቶን ወርቅ ማለት 597,700 ኪሎ ግራም ወርቅ ማለት ነው።ይህ ማለት ደግሞ 19,216,473 ወቄት ወርቅ ማለት ነው። ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ድረስ በነበሩት አመታት ውስጥ አማካኝ የአንድ ወቄት ወርቅ ዋጋ 1,100 የአሜሪካን ዶላር ነበር። ይህ ማለት ትግራይ አቀረበችው የተባለው 597.7 ቶን ወርቅ ዋጋ 21. 376 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ይሆናል ማለት ነው።

ይህ ማለት [በወያኔ ዜና መሰረት] ትግራይ ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ድረስ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ላቀረበችው 597.7 ቶን ወርቅ ብሔራዊ ባንክ 21. 376 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከፍሏታል ማለት ነው። የኢትዮጵያ ያለፈው አመት ባጀት አስር ቢሊዮን ዶላር ነው። ይህ ማለት ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ድረስ ትግራይ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አቀረበችው ለተባለው 597.7 ቶን ወርቅ የተከፈላት 21. 376 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከኢትዮጵያ የሁለት አመት በጀት በላይ ነው ማለት ነው።

ዋናውና ቁልፉ ጥያቄ እውነት ትግራይ ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ድረስ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 597.7 ቶን ወርቅ ወይንም ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. በየአመቱ 171 ቶን ወርቅ አቅርባለች ወይ? የሚለው ነው።

ይህንን ጥያቄ ለመመለስ የአለም አገሮችን የወርቅና የሌሎች ማዕድናትን አመታዊ ምርት ማስረጃ የሚሰበስበውንና የሚያደራጀውን የUnited States Geological Survey (USGS) Minerals Resources Program አመታዊ የአለም ማዕድናት ምርት ሰንጠረዥን ማየት በቂ ነው። ይህ የአሜሪካ ተቋም በአለም ላይ ያሉ ማዕድን አምራች አገሮችን የማእድን አመታዊ ምርት አሃዝ ሰብስቦ ደረጃ ያወጣና የአለም አገሮችን በማዕድን ምርት ያወዳድራል። በዚህ መስሪያ ቤት ማስረጃ መሰረት ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ድረስ በአለም ላይ በወርቅ ምርት አንደኛ ቻይና ስትሆን አመታዊ የወርቅ ምርት መጠኗ 403 ቶን ነው። ሁለተኛዋ የአለም ወርቅ አምራች አገር ደግሞ አውስትራሊያ ስትሆን አመታዊ የምርት መጠኗ ደግሞ 250 ቶን ወርቅ ነው። ሶስተኛ አሜሪካ [235 ቶን ወርቅ በአመት] ፤አራተኛ ሩስያ ፌድሬሽን [217.8 ቶን ወርቅ በአመት] ፤ አምስተኛ ፔሩ [161 ቶን ወርቅ በአመት] ፤ስድስተኛ ደቡብ አፍሪካ [160 ቶን ወርቅ በአመት]፤ ሰባተኛ ካናዳ [103 ቶን ወርቅ በአመት] ፤ ስምንተኛ ሜክሲኮ [96.7 ቶን ወርቅ በአመት] ፤ ዘጠነኛ ኡዝቤኪስታን [ 93 ቶን ወርቅ በአመት] እና ጋና [86.5 ቶን ወርቅ በአመት] በአለም ላይ አስሩ ከፍተኛ ወርቅ አምራች አገሮች ናቸው። የዚህ ምንጭ የሚከተለውን ትር መክፈትና መመልከት ይቻላል…http://www.indexmundi.com/minerals/…

ወያኔ ኢትዮጵያ ትግራይ ብቻ ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ድረስ በየአመቱ 171 ቶን ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አቅርባለች ያለው እውነት ቢሆን ኖሮ ኢትዮጵያ በወርቅ ምርት በአለም ደረጃ ፔሩን ቀድማ ሩስያን ተከትላ አምስተኛ ደረጃ ላይ ትሆን ነበር። ልብ በሉ ከአንድ እስከ አስር የወጡ አገሮች ሁሉ ወርቅ የሚቆፍሩት በጣም ዘመናዊ በሆነ መሰርሰሪያ ማሽን ነው። ወያኔ ግን ትግራይ በየ አመቱ 171 ቶን ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አቅርባለች የሚለን በባህላዊ መንገድ አምርታ ነው።

ከፍ ብዬ በለጠፍሁት የUnited States Geological Survey (USGS) Minerals Resources Program አመታዊ የወርቅ ምርት እውነተኛ ደረጃ መሰረት የኢትዮጵያ አመታዊ የወርቅ አምራችነት ደረጃ 29ኛ ሲሆን አመታዊ የወርቅ ምርቷ ደግሞ 12 ቶን ብቻ ነው። ልብ በሉ ይሄ አመታዊ የኢትዮጵያ የወርቅ ምርት ዶዶላ፣ መተከል፣ ለገደንቢና ወለጋ ሜድሮክ በዘመናዊ ቴክኖሎች ታግዞ የሚያመርተውን ይጨምራል። ወያኔ ግን የትግራይን አመታዊ ምርት ብቻ 171 ቶን ነው ይለናል።

ሜድሮክ በዶዶላ፣ በመተከል፣ በለገደንቢና በወለጋ የሚያመርታቸውን ዜሮ አድርገን ኢትዮጵያ ያመረተችውን 12ቱን ቶን ወርቅ ከትግራይ ብቻ ለብሔራዊ ባንክ የቀረበ የወርቅ መጠን አድርገን ብንወስድ፤ ብሔራዊ ባንክ ከትግራይ በየአመቱ 171 ቶን ወርቅ እንደቀረበለት ተደርጎ ለትግራይ በጠቅላላ ከከፈለው 21.3 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ ውስጥ በያመቱ ላልቀረበ 158 ቶን ወርቅ ክፍያ ፈጽሟል። ይህ ማለት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከትግራይ ቀረበ ተብሎ ከፍያ ከፈጸመበት 597.7 ቶን ወርቅ ውስጥ ባንኩ የተረከበው ወርቅ 42 ቶብ ብቻ ነው። የተቀረው 555.7 ቶን ወርቅ ወርቁ ከትግራይ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሳይቀርብ ብሄራዊ ባንክ ግን ከትግራይ ወርቅ ሳይቀርብ ክፍያ እንዲፈጽም የተደረገበትና የአገር ሀብት ዘረፋ የተካሄደበት የውሸት ቁጥር ነው።

ይህ ማለት ብሔራዊ ባንክ ለትግራይ ከከፈለው 21.3 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ ከ20 ቢሊዮን ዶላር በላይ ለትግራይ የተከፈለው የአገር ሀብት ላልቀረበ የወርቅ መጠን እንደቀረበ ተደርጎ ነው ማለት ነው። ይህ ማለት ወያኔ ያልቀረበ ወርቅን አስታኮ 20 ቢሊዮን ዶላር በላይ ያገር ሀብት ወደ ትግራይ wealth transfter አድርጓል ማለት ነው። ይህ ማለት የሁለት አመት የኢትዮጵያ አመታዊ በጀትን የሚያህል የአገር ሀብት ትግራይ ለብሔራዊ ባንክ ወርቅ እንዳቀረበች ተሳቦ እንድትወስድ ተደርጓል ማለት ነው። ይህ ማለት የሁለት አመታት የኢትዮጵያ አመታዊ ሀብት ወደ ትግራይ እንዲሄድ ሲባል ዘረፋ ተፈጽሟል ማለት ነው። ወገኖች this is a huge wealth transfter. ወያኔ ከጥር ወዲህም ማራኪ ቁጥር እያቀረበ የአገር ሀብት ወደ ተስፋዋ ምድሩ እያሸጋገረ ይገኛል። በሌላ ጊዜ ከሌሎች ቁጥሮች ጀርባ ስለሚፈጸም አገራዊ ዘረፋ የምለው ይኖረኛል።

የሚገርመው ትግራይ በየአመቱ 171 ቶን ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አቀረበች በተባለ በወሩ የቀረበው ሌላ ዜና የስርዓቱ ዜና ነው። ፋና በየካቲት 11 ቀን 2008 ዓ.ም [እ.ኢ.አ.] ያቀረበው ዜና ርዕስ እንዲህ ይላል…«ለብሄራዊ ባንክ እየቀረበ ያለው ወርቅ በከፍተኛ ደረጃ እየቀነሰ ነው።» ዜናው በዚህ ብቻ አያበቃም። ከ2004 ዓ.ም. እስከ 2008 ዓ.ም.[እ.ኢ.አ.] በየአመቱ 171 ቶን ወርቅ ትግራይ ለብሔራዊ ባንክ አቀረበች እንዳልተባለ «ብሄራዊ ባንክ ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል በባህላዊም ሆነ በዘመናዊ መልኩ ተመርቶ የሚቀርበለት ወርቅ በእጅጉ ቀንሷል። በ2005 ለባንኩ የቀረበለት 8.1 ቶን ወርቅ ነበር። በ2006 ዓ.ም ደግሞ 7.4 ቶን ሆነ፤ በ2007ም በጣም አሽቆልቁሎ 5.4 ቶንድረስ ወርዷል።» አሉን። ይህ ሁሉ የሚሆነው ከትግራይ ብቻ ለብሔራዊ ባንክ በአመት 171 ቶን ወርቅ ቀረበ ተብሎ 20 ቢሊዮን ዶላር እንደቀላል ወደ ትግራይ transfter እንዲሆን ባደረጉ በአንድ ወር ውስጥ ነው።

አይ አንቺ አገር! ማፍያዎች የውሸት ቁጥር እየቀቀሉ ሌላውን ጾም ደፍተፍና አራቁተው የድሆችን ሀብት ወደ መንደራቸው ያግዛሉ። በአንድ ማጭበርበር ብቻ ሀያ ቢሊዮን ዶላር የአገር ሀብት ወደ መንደራቸው አሸሹ! በቁጥር ሊሸውዱን ሲሞክሩ በትንተና እንዲህ ባጋለጥናቸው ጉዳይ ብቻ ሀያ ቢሊዮን ዶላር በድብቅ ባልተወለደ አንጀታቸው ከገፈፉ ሰው ሳያውቀው የዘረፉት የአገር ሀብት ቢታወቅ ለሌላው ኢትዮጵያ ምን ያህል ያተርፉለት ይሆን?

[የግርጌ ማስታወሻ፡ ከላይ ለትንተና የተጠቀምሁባቸውን ማስረጃዎች ሁሉ ከታች ካለው የአስተያየት መስጫው ሳጥን መመልከት ይቻላል!]

ለአትሌት ፈይሳ ሌሊሳ በቀናት ውስጥ 25 ሺህ ዶላር ለማሰባሰብ ታስቦ በ4 ሰዓት ውስጥ 23 ሺህ ዶላር ተሰባሰበ

$
0
0

Lalise23

(ዘ-ሐበሻ) ትናንት እሁድ በተዘጋጀው የሪዮ ኦሎምፒክ የወንዶች ማራቶን ውድድር ላይ እጆቹን ወደ ላይ በማጣመር በመንግስት ላይ ተቃውሞውን ያሰማው አትኬት ሌሊሳ ፈይሳ ወደ ኢትዮጵያ እንደማይመለስ ከገለጸ በኋላ በጎ ፈንደ ሚ በኩል አትሌቱን ለማጠናከር በወጣ የገቢ ማሰባሰብ ኢትዮጵያውያን በ4 ሰዓታት ውስጥ ከ23 ሺህ ዶላር በላይ አዋጡ:: ይህ የገንዘብ መጠን ይህ ዜና እየተጻፈ ባለበት ወቅት ሊጨምርም ይችላል::

ለአትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ካሁኑ ዶክተር ሼክስፒር እና ሌሊሳ የተባሉ ጠበቆች በነጻ እንደሚቆሙለት ቃል የተገባ ሲሆን በገንዘብም ሆነ በሞራል አትሌቱን ለማጠናከር ኢትዮጵያውያን ተግተው እየሰሩ ነው:: በ ጎ ፈንድ ሚ በኩል ለአትሌቱ በቀናት ውስጥ 25 ሺህ ዶላር ለማዋጣት ታስቦ የነበረ ቢሆንም በ4 ሰዓታት ውስጥ ብቻ ከ23 ሺህ ዶላር በላይ መዋጣቱና እቅዱን ለምታት ከ2 ሺህ ያላነሰ ዶላር መቅረቱ በጣም አበረታታች ምላሽ ነው እየተባለ ነው::

ለአትሌቱ የሚቻላችሁን ለማገዝ በዚህ ሊንክ በመግባት ይክፈሉ

ዶ/ር ጸጋዬ ረጋሳ አራርሳ፤ ስለ ወቅታዊው የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ሁነት፤ የብሔራዊ ዕርቅ አስፈላጊነትና አካሄድን አስመልክተው ይናገራሉ

$
0
0

 

tsegaye_22“አገሪቱ ትፈርሳለች፤ ሕዝብ በሕዝብ ላይ ይነሳል የሚል ስጋት የለኝም። ይኼ እንደማይሆን እርግጠኛ ነኝ።” – ዶ/ር ጸጋዬ ረጋሳ

“ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ በአንድ መሪ የማትመራበት ጊዜ እየመጣ ነው። አንድ መሪ አይበቃትም። ሊይስተዳድራት የሚችለው ቡድን ነው” – ዶ/ር ጸጋዬ ረጋሳ

Hiber Radio: በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የለውጥ አብዮት ትውልድ አቀፍ ነው ተባለ –ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ ስለ አዲስ አበባ ሁኔታ ይናገራል –የኦባንግ ሜቶና አብርሃ በላይ ቃለምልልስን ይዘናል

$
0
0

habtamu05
የህብር ሬዲዮ ነሐሴ 15 ቀን 2008 ፕሮግራም

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ዛሬ በአዲስ አበባ ስለታሰበው ተቃውሞና በከተማው ስለፈሰሰው ሰራዊት ከህብር ሬዲዮ ተጠይቆ ከሰጠው ምላሽ የተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)

<...> አቶ ኦባንግ ሜቶ ከጋዜጠኛ አብርሃ በላይ ጋር በጋራ ለህብር ሬዲዮ ከሰጡት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ክፍል አንድ አድምጡት)

<... ...> ጋዜጠኛ አብርሃ በላይ ከአቶ ኦባንግ ሜቶ ጋር በጋራ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ክፍል አንድ ያድምጡት)

ኢትዮጵያዊው አርቲስት እና የታክሲ ሹፌር በአሜሪካ ሎስ አንጀለስ ውስጥ የተፈጸመበት አሳዛኝ ግድያ እና የቅርብ ጎደኞቹ እይታ/ልዩ ጥንቅር/

<...> አክቲቪስት ገረሱ ቱፋ(ካለፈው የቀጠለ ውይይት-ክፍል ሁለት) <...> አክቲቪስት መስፍን አማን(ካለፈው የቀጠለ ያድምጡት) ሌሌችም

ዜናዎቻችን

ኢትዮጵያዊው የማራቶን ጀግና በኦሎምፒክ መድረክ በአገር ቤት የሚፈጸመውን ግፍ መቃወሙ ታላቅ ብሔራዊ ጀግና አሰኘው

አሜሪካዊው ከፍተኛ ዲፕሎማት በኦሮሚያና በአማራ ክልል የተነሳው ተቃውሞ ለኢትዮጵያው አገዛዝ ብርቱ ፈተና መሆኑን ገለጹ

አትሌት ፈይሳ ለሊሳ አገዛዙ ወገኖቼን እየጨፈጨፈ ነው ሲል ገለጸ

አገር ቤት ቢገባ ሊገደል ወይ ሊታሰር እንደሚችል ና ጥገኝነት እንደሚጠይቅ አስታወቀ

የትግራይ ሕዝብ በስሙ ወገኖቹን በሚገለውን ስርዓት ላይ እንዲነሳ ተጠየቀ

በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የለውጥ አብዮት ትውልድ አቀፍ ነው ተባለ

አቶ ኦባንግ የትግራይ ልሂቃን ለሕዝቡ የሚአስቡ ከሆነ ከቀረው ወገናቸው ጎን የሚሰለፉበት ወሳኝ ወቅት መሆኑን ገለጹ

በተቃውሞ የሚታወቁት የእነ ዶ/ር አረጋዊ መግለጫ ብቻ በቂ አለመሆኑን አስታወቁ

በብራዚሉ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያኖችን አንገት ያስደፋው አትሌት በቶኪዮ ኦሎምፒክ እንገናኝ አለ

አትሌት አልማዝ አያናና ገንዘቤ ዲባባ ስለቀረበባቸው ክስ ምላሽ ሰጡ

በሚኒሶታ የሚገኘው ደብረ ሰላም መድሓኒዓለም ቤተ ክርስቲያን በአገር ቤት እየተፈጸመ ያለውን ግድያ አውግዞ መግለጫ አወጣ

ሌሎችም


አስገራሚ ቪዲዮ: ከአንበሳ ባንክ ብር በጆንያ ታጭቆ ሲወጣ የሚያሳይ

$
0
0

ቀጥሎ የምትመለከቱት ቪዲዮ የተነሳው በኢትዮ-ኬንያ ድንበር አካባቢ በምትገኘው ሞያሌ ከተማ ከሚገኘው አንበሳ ባንክ ብር በ2 ጆንያ ከባንክ ውስጥቶ ወደ ቶዮታ መኪና ሲጫን ነው:: ቪዲዮውን ቀርጸው ለሕዝብ በሶሻል ሚዲያ የለቀቁት ይመሰገናሉ:: አንበሳ ባንክ የሕወሓት ባለስልጣናት በአክሲዮን የከፈቱት ባንክ እንደሆነ ይታወቃል:: ይህ ሁሉ ገንዘብ ከባንክ ወጥቶ ወዴት ይሆን የሚሄደው?

Anbesa Bank

በባህር ዳር ከቤት ያለመውጣት አድማው ለ2ኛ ቀን ቀጥሏል |ሱቆቻቸውን ለዘጉ ባለሃብቶች ማስጠንቀቂያ እየተለጠፈባቸው ነው

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ባህርዳር ከትናንት ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ከቤት ያለመውጣት አድማው በተሳካ ሁኔታ እንደተካሄደ ተዘገበ:: በርካታ የከተማዋ ሱቆች ተዘጋግተው የዋሉ ሲሆን ትራንስፖርትም የለም::

በባህርዳር መንግስት እያደረሰ ያለውን ገድያ እና አፈና በመቃወም ሕዝቡ ትናንት የጀመረውን ተቃውሞ ዛሬም መቀጠሉ ያስደነገጠው ሕወሓት የሚመራው መንግስት ዛሬ ሱቆቻቸውን ለ2 ቀናት ለዘጉ ባለሃብቶች በየሱቆቻቸው በር ላይ በአስቸኳይ እንዲከፍቱ የሚያስጠነቅቅ ደብዳቤ ሲለጥፍ ውሏል:: (ደብዳቤውን ይመልከቱ)

ሕዝብ ከቤት በለመውጣት በሚያደርገው ሰላማዊ ትግል ኢኮኖሚውን ክፉኛ እንደሚጎዳው ባለሙያዎች በተደጋጋሚ ሲገልጹ መቆየታቸው ይታወሳል::
letter

በፌስቡክ ቪዲዮ ኦሮሞውን እና አማራውን ለይታ የዘር ጥላቻና ዛቻ ንግግር ያደረገችው ወጣት በአሪዞና ፖሊስ ጉዳይዋ እየተመረመረ መሆኑ ተሰማ

$
0
0

Screen Shot 2016-08-22 at 10.41.58 PM
(ዘ-ሐበሻ) ከምትሰራበት አሪዞና ፌኒክስ ኤርፖርት በቀጥታ በቭዲዮ ራሷን በመቅረጽ የኦሮሞን እና የአማራን ሕዝብ በጸያፍ ቃላት ስትሳደብ የነበረችው የትግራይ ነፃ አውጪ መንግስት ደጋፊ የሆነችው ወጣት ሄለን ኃይሉ (ዮዲት ወልደሩፋኤል) በአሪዞና ፖሊስ በምርመራ ላይ እንደምትገኝ የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ኦባንግ ሜቶ አስታወቀ::

ኦባንግ በፌስቡክ ገጹ እንዳስታወቀው በዛሬው ዕለት እጅህ በሚዘግንን ሁኔታ አማራውን እና ኦሮሞውን ሕዝብ እንቀጠቅጥሃለን; እናጠፋሃለን; አፈር ውስጥ ግቡና ሌሎችም ለመጻፍ የሚከብዱ ጸያፍ ቃላትን በመናገር በፌስቡክ የለቀቀችው ወጣት በአሪዞና ህግ መሰረት ፖሊስ ምርመራ እያደረገባት ነው::

ወጣቷ የሕወሓት መንግስት ደጋፊ ሥራ ላይ ሆና እንዲህ ያለውን ቭዲዮ መልቀቋ ለመስሪያ ቤቷም መልካም ገጽታን የማያሳይ በመሆኑ በርካታ ኢትዮጵያውያን ለምትሰራበት መስሪያ ቤት በፌስቡክ የለቀቀችውን ቭዲዮ በማያያዝ እንደከሰሷት ታውቋል:: መስሪያ ቤቱም የሄለን ጉዳይ እየመረመረ መሆኑን እና ሥራዋን እስከማጣት የሚያደርሳት ቅጣት እንደሚጥልባት ከላከው ኢሜል መረዳት ተችሏል:: መስሪያ ቤቱ እንዲህ ያለውን የጥላቻ ንግግር በሥራቦታዎች ላይ እንዲነገር መስሪያ ቤታችን አይፈቅድም እናወግዘዋለንም ሲል በልጅቷ ላይ ክስ ላቀረቡ ወገኖች ምላሽ ሰጥቷል::

የሕወሓትን መንግስት መደገፍ መብት ቢሆንም እንደዚህ አማራውን እና ኦሮሞውን በሃገር ቤት ውስጥ ብቻ ሳይሆን ውጭ ሃገር ያሉትንም በጨለማ እየጠበቅን እንቀጠቅጣለን ስትል በቭድዮ ላይ መደመጧ የምትኖርበትን ሃገር ህግ አለማወቋን ያሳያል ሲሉ አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች ተናግረዋል::

ስድብ ያዘለው ቭዲዮን ካላያችሁት ይኸው

ኦባንግ ሜቶ ስለአትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ይናገራሉ |ቪዲዮ ይዘናል

$
0
0

ኦባንግ ሜቶ ስለአትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ይናገራሉ | ቪዲዮ ይዘናል
ኦባንግ ሜቶ ስለአትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ይናገራሉ | ቪዲዮ ይዘናል

በአዲስ አበባው ከተጠራው ሰልፍ ምን ተጠብቆ ነበር? የሕዝቡ ምላሽ ለምን እንዲህ ሆነ? ያ ሁሉ ወታደር ምን ይሰራል? ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ ከአ.አ. ይተነትናል

$
0
0

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ዛሬ በአዲስ አበባ ስለታሰበው ተቃውሞና በከተማው ስለፈሰሰው ሰራዊት ከህብር ሬዲዮ ተጠይቆ ከሰጠው ምላሽ የተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)

በአዲስ አበባው ከተጠራው ሰልፍ ምን ተጠብቆ ነበር? የሕዝቡ ምላሽ ለምን እንዲህ ሆነ? ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ ከአዲስ አበባ ይተነትናል

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live