Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

በአሜሪካ እየተካሄደ ያለው የእጩ ፕሬዝዳንታዊ ተፎካካሪዎች ምርጫ እና ያሰከተለው እንድምታ ሲዳሰስ | Audio

$
0
0


አሜሪካዊያን ሙስሊሞች፣ ጥቁሮች እና ላቲኖች ሰለ ምርጫው ምን የሚሉት ነገር አለ?(ልዩ ጥንቅር)
በአሜሪካ እየተካሄደ ያለው የእጩ ፕሬዝዳንታዊ ተፎካካሪዎች ምርጫ እና ያሰከተለው እንድምታ ሲዳሰስ


ህዝባዊ ትግል ማገዝ እንጂ ማደናቀፍ የሃቀኛ ፓርቲ መገለጫ አይደለም |ከይድነቃቸው ከበደ

$
0
0

በተለይ ሰማያዊ ፓርቲ ህዝባዊ ትግል ለማገዝ እና ለመምራት በእውነተኛ የለውጥ ፈላጊ አመራሮች እና አባላቶች ፣በተከፈለና ወደፊትም በሚከፈል መሰዋዕትነት የቆመ ፓርቲ ነው።ይህ ሁሉ የሚሆነው የህዝብ ጥያቄ ትክክለኛ ምላሽ እንዲያገኝ ነው። ይህም በመሆኑ በአገራችን በአራቱም አቅጣጫ በአገዛዙ ሥርዓት ላይ የተነሣው ህዝባዊ ተቃውሞ “የእኔ ነው ፣የእኔ” ዓይነት ለአምባገነኑ አገዛዙ የሚመች፣ የለውጥ ፈላጊው አንድ ስንዝር የማያራምድ ባለህበት እርገጥ፣ አሰልቺ ፓለቲካ የእኔን ትውልድ የማይመጥን ፤ከምንም በላይ ደግሞ የአገራችንን ነበራዊ ሁኔት እንደ-መርሳት የሚቆጠር ጭምር ነው።

bahardar
ሰማያዊ ፓርቲ በውስጣዊ ችግሮቹ ለላፋቱ ወራት ታች-ላይ ማላቱ ለማንም ግልፅ ነው። አሁን ላይ ችግሮቹን ለይቶ ህዝባዊ ትግሉን ለማገዝና ለመምራት ሥራዎቹን እያጠናቀቀ ይገኛል።ከችግሮቹ ወጥቶ ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲደርስ የፓርቲው ከፍተኛ አመራርና አባላት ያደረጉት በጎ አሰተዋአዖኦ ወደፊት በፓርቲያችን ታሪክ እንደ ማሳያ የሚጠቀስ ነው። በፓርቲያችን ውስጥ ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት ሲያስጨንቃቸው እና ሲያሳስባቸው የነበረ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊን ስለ ፓርቲያችን መልካም ዜና የሚሰሙበት ቀን እሩቅ አይደለም ። ከላይ ለገለጽኩት ለመልካሙ ዜና እና ለበጎ ምኞቴ የአመራሩና የአባላቱ ጥረት ታሳቢ በማድረግ ብቻና፣ ብቻ! ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ወደ ተነሳውበት ሃሳብ ስመለስ፣ ህዝባዊ ትግል ማገዝ እንጂ ማደናቀፍ የሃቀኛ ፓርቲ መገለጫ አይደለም! የሚለው የጽሑፊ መግቢያ፣ ለሰማያዊ ፓርቲ ሙሉ በሙሉ የሚያገለግል ነው። ፓርቲያችንም የአገዛዙ ሥርዓት ከምስረታው ጀምሮ ከህዝብ ጎን በመቆም ሲታግልና ሲያትግል እንጂ ለደቂቃም ቢሆን ያደናቀፈበት የትኛው ዓይነት አጋጣሚ የለም፣ወደፊትም አይኖርም። በዚህም መሰረት በአገራችን የሚካሄደው ህዝባዊ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፎች ፓርቲያችን እንደ-አግባቡ እና አስፈላጊናቱ እውቅና በመስጠት ፣ ህዝብ በራስ ተነሳሽነት የጀመረውን ሰላማዊ የትግል እንቅስቃሴ ለእራሱ ለባለቤቱ (ለህዝብ) ቅድሚያ መሰጠት አለበት ብዬ አምናለሁ ። ምክንያቱም ጥቅሙ ብዙ ስለሆነ። ፓርቲ ህዝብን እንጂ፣ እንዴት ህዝብ ፓርቲን ይመራል፤ ከሚባለው ሃስተሳሰብ ይሄኛው መንገድ በብዙ መልኩ ይለያል። መንገዱ አይለይም ቢባል እንኳን አሁን ላይ ያለው ተጨባጭ ሁኔታ ታሣቢ መደረገ አለበት።

በዚህም መሰረት ፓርቲያችን የህዝቡ ሰላማዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴ በንቃት በመከታተል፣ ተገቢውን ድጋፍ በመስጠት ፣ጠንካራና ደካማ ጎን በመለየት ፓርቲው በራሱ ለሚያደርጋቸው እንቅስቃሴ እንደ-ማመላከቻ ሊወስዳቸው ይገባል የሚል (የግል) ምልከታ አለኝ። ምልክታዬን ለሚጋራኝ ይሄን ለማድረግ አሁንም ጊዜው አልረፈደም ! የፓርቲው የሥራ አስፈፃሚ አባላት ወቅታዊ የአገራችን ሁኔታ እና የህዝቡ ሰላማዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴ በአግባቡ መርምረው ፤በፓርቲያችን ላይ የተፈጠረውን ብዥታ በማከም ፣ በአገራችን በሁሉም አካባቢ የተጀመረው ህዝባዊ እንቅስቃሴ ከፓርቲያችን ፕሮግራም ጋር በተጣጠመ መልኩ የሚያግዝ እና አቅጣጫ የሚያሲዝ ውሳኔ በአስቸኳይ እንደሚያሳልፉ ተስፋ አደርጋለሁ ።

የኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!

  ትዝብት-የሰሞኑ እይታዬ –አገሬ አዲስ

$
0
0
comment symbol icon

comment symbol icon

ሃምሌ 25 ቀን 2008 ዓ.ም.(01-08-2016)

በትዝብት ዓምድ ሳቀርብ የነበረው ተከታታይ ጽሁፍ ለተወሰኑ ወራቶች ቢሰወርም አሁን በሰሞኑ ባየዃቸውና አሳሳቢ ሆነው ባገኘዃቸው አንዳንድ ሁኔታዎች ላይ ሃሳብ እንዲንሸራሸር ማድረጉ አስፈላጊ መስሎ ስለታየኝ እነሆ አምዷን ለዳግመኛ ንባብ እንድትበቃ ይዤ ቀርቤአለሁ።

ትንተናው የሚያጠነጥነው ለወራቶች በተለይም በሰሞኑ በአገራችን የሚካሄደውን ሕዝባዊ አመጽ አስመልክቶ በውጭ አገር በስደተኛ ስም የሚኖረው ወጣት ያለውን አገራዊ ስሜትና ተሳትፎ በሚመለከተውና ሰሞኑን በሆላንድ ውስጥ ከደንሃግ ወጣ ብላ በምትገኘው ሌይድሰከንዳም በተባለች አነስተኛ ከተማ(ትልቅ መንደር ማለት ይሻላል) በተከናወነው የኢትዮጵያውያን የስፖርት በዓል ዙሪያ ይሆናል።

በዓለም ዙሪያ ተበትኖ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ቁጥር ከአራት ሚሊየን እንደማያንስ የሰሞኑ ጥናት ያመለክታል።ከዚህ ውስጥ አብዛኛው ከአርባ ዓመት በታች የሆነ ወጣትና ጎለምሳ ነው።በቀላሉ የማይገመትም አዛውንትና በዕድሜ የገፉ መኖራቸው አይካድም።ሁሉም በየአገሩ ሲገቡ ምክንያት ያደረጉትና የመኖሪያ ፈቃድ አግኝተው ኑሯቸውን የጀመሩት በአገራቸው በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ስርዓት ሊያኖራቸው ባለመቻሉ፣መብትና ነጻነታቸው በመገፈፉ,ለህይወታቸው አደገኛ የሆነ ሁኔታ እንደተፈጠረ፣በፖለቲካ እምነታቸው እንደታሰሩና መከራ እንደደረሰባቸው የመሳሰለውን ምክንያት በመዘርዘር  እንደሆነ አይዘነጋም።ጥቂቶች በጋብቻ፣በትምህርት፣በሥራና በቤተሰብ ቅልቅል ከአገራቸው ለመውጣትና በውጭ አገር ለመኖር እንደቻሉም የሚካድ አይደለም።ሆኖም ግን ሁሉም የሚጋሩት ነገር ቢኖር አንድ አገር ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ነው።

ይህን የጋራ እሴት በተለያየ መልኩ ሲያንጸባርቁ ይታያል፤በባህሉ፣በእምነቱ፣በማህበረሰብ ስብስቡ፣በድግሱ፣በሃዘንና ደስታው ተሰባስበው አብረው ያሳልፋሉ።ወፍ እንዳገሩ ይጮሃል እንዲሉ በያሉበት አገር ያደጉበትንና ይዘው የመጡትን ወግና ልማድ ሳይረሱ ከአዲሱና በእንግዳነት ከሚኖሩበት አካባቢ ባህልና ቋንቋ ጋር አዋህደው ለመኖር ይጥራሉ።ጥቂቶችም በጥረታቸውና በችሎታቸው ከተቀበላቸው አገር ተወላጅ በልጠውና ተሽለው የሃላፊነት ቦታ ለመረከብ በቅተዋል።ብዙዎችም ያገሩ ዜጋ በተሰለፈበት ሙያና ዕድልና ሁኔታ በፈቀደላቸው መስክ ተሰልፈው የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።ኑሯቸውን ይገፋሉ።

ጥቂቶችም ለዝቅተኛ ኑሮና ስቃይ የተጋለጡ አልጠፉም።የአካልጉድለት ከደረሰባቸው ሌላ በልዩ ልዩ ሱስ ተጠምደው ከማህበረሰቡ የተገለሉ፣ቤት አልባ የሆኑ፣በአእምሮ መቃወስ ህመም በማገገሚያ ጣቢያና በወንጀል ተግባር በእስርቤት የሚማቅቁ ኢትዮጵያኖችም መኖራቸው አይካድም።

በውጭ አገር የተወለዱት ከሚኖሩበት ህብረተሰብ ጋር፣እንደ ነባሩ ያገሬው ሰው መስለውና ተቀላቅለው የመኖር ዘይቤን ወርሰዋል።በቤተሰብ ብርታት ያገራቸውን ቋንቋ ለመናገር የሚችሉት ጥቂቶች እየሆኑ መጥቷል። ሂደቱ ከቀጠለ ከሁለት ትውልድ በዃላ ከኢትዮጵያና ከኢትዮጵያዊነት ጋር የሚኖራቸው ንክኪ የሚከስም ይመስላል፣ቀለማቸው ሳይቀር እየተከለሰ ለመምጣቱ ምልክቶች እየታዩ ነው።አሁን ጥቁር አሜሪካውያን በወሬ ከአፍሪካ መምጣታቸውን እንደሚናገሩት ምናልባት ከኢትዮጵያውያን የተወለዱት የልጅ ልጆች ከአፍሪካ ወይም ከኢትዮጵያ እንደመጡ በቃል ደረጃ ሊናገሩ፤ወይም እስከነ አካቴው የሚረሱበት ደረጃ ላይ ይረሱት ይሆናል።ያንን ለነገው ትተን ወደዛሬው ፊታችንን መለስ አድርገን የወጣቱን አዝማሚያ ማየቱ የሚሻል ይመስለኛል።

አንድ አገር የእድገት ተስፋውና የመኖሩ ዋስትናው የሚለካው በወጣቱ ትውልድ ምግባርና አገራዊ ስሜት እንደሆነ የሚያጠያይቅ አይደለም።አገር ትውልድ እየተቀባበለ የሚኖርበት፣መስዋዕት ተከፍሎበት ለተተኪ ትውልድ የሚተላለፍ ክብር ያለው አንጡራ የወል ንብረት ነው።አገር የሌለው ሕዝብ ማለት ሲደክመው የሚያርፍበት ዛፍ(ጎጆ) የሌለው ወፍ ወይም ውሃው ደርቆበት የሚሞት አሣ ማለት ነው።

የአገርን ጥቅም ከአዲሱ ትውልድ ስንት ስንተኛው ያምንበታል?ለአገሩስ ጉዳይ የሚቆረቆረው ምን ያህሉ ነው?ብለን ብንጠይቅ መልሱን ለማግኘት አንቸገርም።እስከአሁን ድረስ የአገራችን ነጻነት ተከብሮ የኖረው የየዘመኑ ትውልድ በከፈለው መስዋእትነት ነው።ያ መስዋእትነትና የአገር ነጻነት ምንም እንኳን አደጋው ቢያንዣብብበትም በአሁኑ ጊዜም ቢሆንሊጠፋ አልቻለም።ብዙ ወጣቶች በሚያምኑበትና በሚችሉት መንገድ አገራቸውን ከአደጋ ለመከላከል ቆርጠው ተሰለልፈዋል፣ ወራሪንና የአገር አንድነትን የሚቀናቀን የውጭና የውስጥ ጠላት ሲነሳ በመከላከል መስዋእት ሆነው ህይወታቸውን ሰጥተዋል፤አሁንም ለመስጠት ዝግጁ የሆኑና በየእስር ቤቱም የሚማቅቁ ብዙዎች ናቸው።ሁኔታ ፈቅዶላቸው ህይወታቸው ተርፎ በየአገሩ ለስደት ኑሮ የተገደዱትም ለሚገጥማቸው ችግርና ፈተና እጅ ሳይሰጡ ያገራቸውንና የወገናቸውን ጉዳይ፣የተሰደዱበትን ዓላማ ሳይዘነጉ በቻሉት አቅም እያበረከቱ ነው።የተወሰኑት ኢትዮጵያውያን በየአገሩ ተሰባስበው የወገናቸውን በደል ለውጭ ዓለም በማሰማት የተሳተፉ ሲሆን በአገር ቤትም ያለው ሕዝብ እስከ ጥርሱ የታጠቀ የመከላከያ ሃይል ያለውን ጨቛኝ ቡድን የሚመራውን መንግሥት እየተጋፈጠ ከዳር እስከዳር እየተዋደቀ ይገኛል።በውጭ አገር ስደተኛ ነኝ ብሎ የመኖሪያ ፈቃድ ተሰጥቶት የሚኖረው  አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በተለይም ወጣቱ በዚህ አገር አድንና የመብት ማስከበር ትግል ውስጥ ምን ያህል ድርሻ እንዳለው ብንመለከት የሚያሳፍርና የሚያሳዝን ሆኖ እናገኘዋለን።የመኖሪያ ፈቃድ ያገኘበትን ጉዳይና የሰጠውን ምክንያት ዘንግቶት ምን አገባኝ በሚል አቋም ከዳር ቆሞ የሚታየው ብዙ ነው።ከአገሩ የተሰደደው ለመዝናናትና ለአስረሽ ምችው ኑሮ እጁን እንደሰጠ፣ለአገርና ለወገኑ ግዴለሽ እንደሆነ የሚያደርገውን አድራጎትና ምግባረ ብልሹነት ሲያዩት ያስደነግጣል።በአገር ጉዳይ ለመወያየት ስብሰባ ሲጠራ የሚገኘው አዲስ መጡ ሲሆን እሱም መኖሪያ ፈቃዱን ለማግኘት የፖለቲካ ተሳትፎውን በፎቶ ግራፍ ለማሳየት ሲል ነው።መኖሪያ ፈቃድ ካገኘ በዃላ “ፖለቲካና ኮረንቲ በሩቁ” ብሎ ድራሹን ያጠፋል።እንደውም በፖለቲካ የሚሳተፉትን እንደጠላትና የሰላም ጠር አድርጎ ይቆጥራቸዋል።ለእንደዚህ አይነቶቹ ስለሃገር፣ስለባህልና ታሪክ ማውራትና መጨነቅ ዃላ ቀርነት ነው።ትልቁ እውቀትና ዘመናዊነት በምንም መንገድ ይሁን በምንም ገንዘብና ንብረት ማግበስበሱ ነው።በፍቅረ ነዋይ የተለከፈው ከስርዓቱ የወረሰው በመሆኑ አይፈረድበትም።ሰው እንደመሪው ነው ይባል የለ!

ሰሞኑን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከጁላይ 27 እስከ 30 ድረስ፣ለአራት ቀናት ያህል በሆላንድ አገር በተካሄደው በአውሮፓ የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል በዓል ላይ ያየሁትን ሌላው በቦታው ያልነበር እንዲያውቀው በጥቂቱ ላቅርብ። ይህ አይነት ዝግጅት በአውሮፓ ውስጥ ከተጀመረ አስራ አራት ዓመት አስቆጥሯል። ከእግርኳስ ውድድሩ በተጓዳኝ በየዓመቱ ከተለያዩት የአውሮፓ አገሮች፣ከኢትዮጵያና ከሰሜን አሜሪካ፣እንዲሁም ከመካከለኛው ምስራቅ የመጡ ኢትዮጵያውያንና ቤተሰባቸው ከዘመድ አዝማድና ጓደኛ ጋር ተገናኝተው አብረው መልካም ጊዜ የሚያሳልፉበት፣እንደእረፍትም የሚዝናኑበት ወቅት ነው።ጎን ለጎንም መንግሥት የማያውቀው የንግድ ስራ የሚጧጧፍበት የድንኳን ውስጥ ጉልት ገበያ እየሆነ መጥቷል።ማስተሳሰሪያ ክሩ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ነው። ኢትዮጵያ ከሌለች ኢትዮጵያዊነትና የኢትዮጵያውያን የስፖርት በዓል የሚል ድግስ ሊኖር አይችልም።ስለሆነም ለኢትዮጵያ መኖር ሁሉም የየድርሻውን ማበርከት ይኖርበታል ማለት ነው።

በዚህ በዓል ላይ ከእስፖርቱ ውጭ የኪነት እንቅስቃሴዎች የሚካሄዱበት ወቅት ነው።በአብዛኛው የገበያ ድንኳን ውስጥ ለሽያጭ የቀረበው ከምግብ ጋር የተያያዘ ሲሆን በሁሉም ማለት ይቻላል ስኒ ተደርድሮ ጀበና ከበው ቡና እየጠጡ የሚያወሩ ብዙዎች ናቸው።ታዲያ ሁሉም ነገር እንዳማረበት ያልቃል ማለት አይደለም፤ግጭትና ንትርክ አልፎ አልፎ አልጠፋም። በበዓሉ አዘጋጆችና በንግድ ዘርፉ በተሳተፉት መካከል በተለይም በዳንኪራው ዙሪያ ውዝግብና የጥቅም ግጭት ተከስቶ እንደነበረ ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ።የተሰባሰበው በሚመስለው የደስታ ዘርፍ ውስጥ እራሱን ለማስደሰት የሚችልበት ዕድል ተከፍቶለታል።ከመልካምና ከማይጎዱ እንቅስቃሴዎች በተጨማሪ አእምሮንና አካልን በሚጎዱ መስኮች የተሰማሩም ነጋዴዎች የሚታዩበት መድረክ ነው።አልኮል፣ጫት እንዲሁም አዲስ መጡ ሺሻ የሚባለው  የጋያ (ትምባሆ) ሱስ በግላጭ የሚስተናገድበት ቦታ ሆኗል።በዚህ የሺሻ ሱስ  የተለከፉት አብዛኛዎቹ  በየአረብ አገሩ ተሰደው የኖሩ ለጋ ወጣት ሴቶች በመሆናቸው የበለጠ ልብ ይሰብራል።፣የተለያዩትን ጎጂ ሱሶች በእስፖርቱ ሜዳ ዙሪያ በተተከሉት ድንኳኖች እንዲከናወኑ የፈቀደው የእስፖርት ፌዴሬሽኑ በመሆኑ ከገንዘብ በቀር ሌላ ማህበረሰብአዊ ደህንነትንና ጤናን በማስከበሩ እረገድ ፍላጎት የሌለው ሆኖ ታይቷል።እስፖርት ለጤና መሆኑ እየታወቀ ፣ያንን የሚጻረሩ ድርጊቶች መፍቀድና ድንኳን አከራይቶ ከንግድ ገቢው እጠቀማለሁ ማለት በወገን ጉዳት ላይ እየነገዱ ወጣቱ ለአደጋ ሲጋለጥ በምን ቸገረኝነት መመልከትና ማበተረታታት ነው።እንደ ነጻነትና ስልጣኔ መቆጠር የለበትም።

በዚህ ወቅት ስለአገራቸው የወቅቱ ሁኔታ የሚጨነቁ ድርጅቶችና ግለሰቦች ተሰባስበው የሚወያዩበትም አጋጣሚ ነበር።በዚህ በሆላንዱ ዝግጅት ወቅት በአውሮፓ የኢትዮጵያውያን የውይይት መድረክ(ፎረም) በሚል ስያሜ የሚንቀሳቀሰው አካል ስብሰባ አዘጋጅቶ ነበር።በስብሰባው ላይ ከወደፊቱ እይታ ጠቃሚ እርእሶች ማለትም ኢትዮጵያዊነት የብሔር/ብሔረሰብ ጥያቄና ፌዴራሊዝም(በዶር.ፈቃዱ በቀለ)፣የማንነት ፖለቲካ ጠንቆችና አኗኗር የአብሮነት መፍትሔ ፍለጋ (በአቶ የሱፍ ያሲን) የቀረቡ ሲሆን ለወቅቱ ችግር ማለትም አሁን በአገራችን ውስጥ ከዳር እስከዳር በተቀጣጠለው ሕዝባዊው አመጽ ላይ ግን ትኩረት የሰጠ ውይይት አልነበረም።

በዚህ ስብሰባ ላይ ከሰላሳ የማይበልጡ ታዳሚዎች ሲገኙ በስፖርት ሜዳው ውስጥ፣ በዙሪያው በተተከሉ የምግብ፣የጫት፣የቡና፣የመጠጥ፣የሺሻ፣የሸቀጣ ሸቀጥ ድንኳኖች ውስጥ ግን በሺህ የሚቆጠር ኢትዮጵያዊ ይርመሰመስ ነበር። የሚሆነውን አጢኖ ለተከታተለውና ለተመለከተው ስደተኛ ነኝ የሚለው ወገን አገሩ ኢትዮጵያ በቀውስ ውስጥ መኖሯን የዘነጋ ወይም ደንታ የማይሰጠው የራሱንም ስደተኝነት የረሳ ይመስላል።በጣም የሚያስገርመው ደግሞ የውይይት ስብሰባ ያዘጋጁት ወገኖች ስብሰባ መኖሩን ለማስታወቅ የሜዳውን ድምጽ ማጉሊያ እንጠቀም ብለው ላቀረቡት ጥያቄ አዘጋጆቹ “ይህ የእስፖርት እንጂ የፖለቲካ ሜዳ አይደለም”ብለው መከልከላቸው ነው።ታዲያ ኢትዮጵያውያን የተሰበሰቡበት የስፖርት ሜዳ በዚህ አሳሳቢ ወቅት ስለአገራቸው ጉዳይ እንዳያውቁ፣በአገራቸው ጉዳይም ላይ በውይይት እንዳይሳተፉ መከላከልና ኢትዮጵያኑን በሚጎዳ ለጫት፣ለአልኮልና ለሲሻ ገበያ ማስፋፊያ እንዲሆን ቅድሚያ መስጠትና መፍቀዱ የጤነኛ አስተሳሰብ ነው?ከስደተኛስ ይጠበቃል?ይህን የስፖርቱ አዘጋጆች መልስ ሊሰጡበት ይገባል።የኢትዮጵያ ሕዝብ በጨቛኝ ስርዓት ላይ እምቢ ብሎ ሲነሳ ፣መስዋእትነት እየከፈለ ባለበት ወቅት አለመተባበርና አለመደገፍ ከጨቛኙ ስርዓት ጋር ከመወገንሌላ ትርጉም የለውም።በደፈናው ፖለቲካና እስፖርት የተለያየ ነው ብሎ ከአገር ጉዳይ እራስንና ሌላውን ማግለል ከአንድ የስደተኞች ስብስብ የሚጠበቅ አይደለም።እስፖርተኛ አገረቢስና ስለአገሩ የማያስብ ከዃስ የተወለደ ልዩ ፍጡር ተደርጎ እስካልተቆጠረ ድረስ የተሰጠው ምክንያት ውሃ አይቋጥርም።

ይህን አይነቱን አዝማሚያና አድራጎት፣በመካከላችን ያለውን ድክመት አሶግደን ለተወለድንባትና ለመኖሪያ ፈቃድ ሰበብ ላደረግናት አገርና ለቁም ነገር ላበቃን ሕዝብ ውለታ የምንከፍልበትን መንገድ ብንከተል ለወጣቱ ትውልድም ምሳሌ ብንሆን ጠቃሚ ነው።ወጣቱን ትውልድ በሚቀጥፉ ጎጂ ልማዶችና አድራጎቶች እንዳይጠመድ ማህበረሰባዊ መፍትሄ ሊፈለግበት ይገባል።በነጻነት ስም ወጣቱ ትውልድ ገደል ሲገባ እያዩ አበጀህ!ቀጥልበት! አይባልም።በአመለካከትና በዕድሜ በሰል ያለው ወገንም የመጣበትን አስታውሶ ለአገሩ ጉዳይ ቦታ ሊሰጠውና በአገር ውስጥ የሚካሄደውን አገር አድን ሕዝባዊ ትግል መርዳትና ማገዝ ይገባዋል።ምንም እንኳን በግል ኑሮው ላይ ማተኮሩ የኑሮ ግዴታ በመሆኑ የሚያስወግዘው ባይሆንም ጎን ለጎን ከአንድ ዜጋ የሚጠበቅበትን ማበርከት ተገቢ ነው።

ጥቂት የማይባለው ኢትዮጵያዊ አሰደደኝ ከሚለው መንግሥት ተወካይ ቢሮ(ኤምባሲ) ደጃፍ እየተደረደረ ህሊና ቢስ ሆኖ ከደሃ ወገኖቹ እየተነጠቀ በሚቸበቸበው በመሬት ቅርምቱ በመሳተፉ ይቅርታ የማይገባው ጥፋት በመፈጸም ላይ ይገኛል።ይህ የጥፋትና በደሃው ሕዝብ ላይ በሚፈጸም ወንጀል ተባባሪነት እንጂ ለእድገትና ለልማትም አስተዋጽኦ ማድረግ አይደለም።በዚህም አላበቃም፤በስርዓቱ የሚፈጸመውን ግፍና በደል እንደሌለ በመካድ አደባባይ ወጥቶ የስርዓቱ አወዳሽና ተከላካይ በመሆንም ያዙኝ ልቀቊኝ የሚል ስደተኛም አልጠፋም።ምርጫው የየግለሰቡ ቢሆንም ሕዝብና አገር ለመበደልና ለመበታተን ሌት ተቀን ከሚሠራ አምባገነን ቡድን ጋር መሰለፍ ብሔራዊ ክህደት እንደሆነና እንደሚያስጠይቅም ሊታወቅ ይገባል።በስርዓቱ የሚኮራና የሚተማመን ሰው የስደተኛ ካርዱን መልሶ ወደ አገሩ ቢመለስ ይሻለዋል።ይህ ስርዓት መውደቁ አይቀርም፣ይወድቃል።አሁን እያንዳንዱ የሚወስደው አቋምና የሚፈጽመው ተግባር ወደፊት የሚያፍርበት ወይም የሚኮራበት ይሆናል።

በዘንድሮው የሰሜን አሜሪካኑ(በቶሮንቶ ከተማ)የእስፖርት በዓል ላይ ባለመገኘቴ ልተችበት አልችልም።በቦታው የነበሩ ትዝብታቸውን ቢያካፍሉ መልካም ነው።

ለሚመጣው ዓመት በሰሜን አሜሪካም ሆነ በአውሮፓ በሚዘጋጁት የስፖርት በዓላት ላይ እስከአሁን ድረስ የታዩ ጥፋቶችና ድክመቶች ታርመውና ተወግደው፣የአገራችንን ጉዳይ ባካተተ መልኩ እንደሚከናወን ተስፋ አደርጋለሁ፤የዛ ሰዎች ይበለን።

እግረመንገዴን ከሰሞኑ እይታዎቼ የመድረክ መሪ ዶር.መረራ ጉዴናና የሰማያዊ ፓርቲ መሪ ኢንጅነር ይልቃል በአሁኑ ጊዜ አሜሪካን አገር ውስጥ መገኘታቸውን ተገንዝቤአለሁ።በአሁኑ ጊዜ ደግሞ በአገራችን ውስጥ የጦፈ ሕዝባዊ አመጽ እየተካሄደ ነው።አወጣጣቸው የውጩን ለመቀስቀስ ፣የገንዘብ እርዳታ ለመሰብሰብ ወይስ የአሜሪካንን መንግሥት ለመማጸን? ወያኔን ለማዳን ወይም በተመሳሳይ ስርዓት ለመተካት ከአሜሪካኖች ጋር ውል እንደማይገቡ ተስፋ አደርጋለሁ።

አገሬ አዲስ

 

 

ሰላማዊ ሰልፉ የጥፋት መልዕክቶች የተላለፉበት ሰልፍ ነው! “ብአዴን!”–ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

$
0
0

13882497_10206705956951835_2221566154745392193_nየሕውሐቱ አሻንጉሊት ድርጅት ብአዴን፤ በነገራችን ላይ ብአዴንን አሻንጉሊት ብለን ስንል እውነት እንጅ ስም ለማጉደፍ እንዳልሆነ ለማንም ግልጽ ይመስለኛል፡፡ ለዚህ ማረጋገጫውም በለፈው ጊዜ ወያኔ ሥልጣን ከያዘ ጊዜ ጀምሮ ብአዴን በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በአማራ ሕዝብ ላይ ለተፈጸሙ ግፎችና ኢሰብአዊ ድርጊቶች ምንም ዓይነት ምላሽ ሰጥቶ ያለማወቁን ከገለጽኩት በተጨማሪ ሌላ ማረጋገጫ መጥቀስ ቢያስፈልግ፦ እስከ የወያኔ የመጀመሪያዎቹ የአገዛዝ ወቅት ድረስ ሥያሜው ኢሕዴን (የኢትዮጵያ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቅ) የነበረው የዛሬው ብአዴን (ብሔር አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ) ሥያሜው ትግርኛ መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ ይህን ሥያሜ አማርኛ እናድርገው ብንል ይሆን የነበረው አሕዴን (የአማራ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ) ነበር የሚሆነው፡፡

እናም ይህ ድርጅት ከሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲነት (የእምነተ አሥተዳደር ቡድንነት) ወደ ብሔር (ብሔረሰብ) ተኮር ሲቀየር የክልሉ ተወላጅ ያልሆኑትን ወደየክልላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች መሸኘት ሲኖርባቸው የፌዴራላዊ (የራስ ገዛዊ) አወቃቀርን ሥርዓት መብትንና ግዴታን በቀጥታ በሚጻረር መልኩ የአማራ ተወላጆች እንዳልሆኑ በይፋ የሚታወቁ ግለሰቦችን ይዞ መቀጠሉ (ኦኦ ይቅርታ አማርኛውን ላስተካክለው) የአማራ ተወላጆች ያልሆኑ ግለሰቦችን ይዞ እንዲቀጥል መደረጉ ወይም መገደዱና እነኝህ ግለሰቦችም የብአዴንን ከፍተኛ የወሳኝነት ሥልጣን መያዛቸው የብአዴንን አሻንጉሊትነትና የፌዴራል (የራስ ገዝ) አሥተዳደሩንም የይስሙላነት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ጉዳይ ነው፡፡ ድርጅቱ የአማራ ከተባለና ራስ ገዛዊ ከሆነ ሊመራ ሊተዳደር የሚገባው በአማሮችና በአማሮች ብቻ ነበር፡፡ ትግሬም አገውም ሌላም ሊካተት አይችልም፡፡ ይህ የአሐዳዊ መንግሥት አሠራር እንጅ የራስ ገዛዊ አሠራር አይደለምና፡፡
እንከተለዋለን የሚሉት ሥርዓት ራስ ገዛዊ ከሆነ ትግራይ ከአምስት ተከፍላ ኢሮቡም ኩናማውም ሌሎቹም ራስ ገዝ መሆን ይኖርባቸዋል በሌሎች ክልሎች ያሉ ጎሳዎችና ብሔረሰቦችም እንደዚያው፡፡ ይህ ሲሆን ብቻ ነው ሥርዓቱ ፌደራላዊ (ራስ ገዛዊ) ነው ማለት የሚቻለው፡፡
በስተቀረ ግን በውስጥ ያሉ ጎሳዎችንና ብሔረሰቦችን እንደሌሉ ቆጥሮ ያሉበትንና ሀገራቸውን በአንዱ ብሔረሰብና ጎሳ ስም ብቻ “የትግራይ ክልል” የአንድ ቀበሌ ሰው የማይሞሉትንም በክልል ደረጃ በማዋቀር “የሐረሪ ክልል” እያሉ ማላገጥና ከሐምሳ በላይ ብሔረሰቦችና ጎሳዎችን በአቅጣጫ ሠይሞ “የደቡብ ክልል” ማለት ፈጽሞ የፌዴራል (የራስ ገዝ) አሥተዳደር ሥርዓትን አያሳይም፡፡
“አይ ስለማይመች ነው! የሚቻል ስላልሆነ ነው!” ከተባለ ደግሞ ቋንቋንና የብሔረሰብ ወይም የጎሳ አሠፋፈርን መሠረት ያደረገ የራስ ገዝ ሥርዓት ለሀገራችን አይሆንም ማለት ነውና የፌዴራል (የራስ ገዝ) አወቃቀሩ ከዚህ ውጭ የደርግን ወይም የዐፄ ኃይለሥላሴን ክፍላተ ሀገር ወይም ጠቅላይ ግዛት መውሰድ ይኖርበታል ካለሆነም በሌላ አከፋፈል አሐዳዊ ሥርዓትን መከተል ይኖርብናል ማለት ነው፡፡
በመሆኑም ይህ የብአዴን ውጥንቅጥ የሚያሳየው ዐቢይ ቁምነገር ቢኖር አገዛዙ የራስ ገዝ ሥርዓትን ከሥያሜው በስተቀር የሥርዓቱን ዘይቤ ሊተገብረው ፈጽሞ የማይፈልግና የማይፈቅድ ይሄንን የሥርዓት ዓይነት ለማወናበጃነት ከመጠቀም ውጪ ለሥርዓቱ በፍጹም ታማኝ አለመሆኑን ነው፡፡
በመሆኑም ነው አቶ በረከትን ጨምሮ በርካታ ትግሬዎችን የአማራ ነው በተባለው ድርጅት ሰግስጎ ድርጅቱ እያየነው እንዳለነው የአማራ ሕዝብ ጉዳይ ጨርሶ የማይገደው የማያሳስበው ይልቁንም የወያኔ መሣሪያ በመሆን የአማራን ሕዝብ የሚያጠቃና የሚያስጠቃ ሊሆን የቻለው፡፡
የብአዴን አባላትን የምጠይቀው ጉዳይ ቢኖር እንደሚሉት ድርጅቱ የአማራ ከሆነ ከቀበሌ እስከ ብአዴን ከፍተኛ የሥልጣን ደረጃ ያሉት የትግሬ (የተግሬ) ተወላጆች እነ በረከት ምን ይሠራሉ???
መቸም እናንተ እኮ አታፍሩም! “እኛ አማሮች እራሳችንን ማሥተዳደር ስለማንችልና ብቃት ያለው ሰው ስለሌለን ሊረዱን ነው” ሳትሉ አትቀሩም!

እናም ድርጅቱ እንዲህ በትግሬ ተሞልቶ የአማራን ሕዝብ ሳይሆን የወያኔን (የትግሬን, የተግሬን፤ ከዚህ ቀደም መረጃዎችን ጠቅሸ ዐፄ ካሌብ በተደረገላቸው የድረሱልን ጥሪ የናግራን ክርስቲያኖችን ከአይሁድ ጥቃት ለመታደግ የመን ዘምተው በነበሩበት ጊዜ ከድላቸው በኋላ ለባርነት ወይም ለአገልጋይነት ከየመን ይዘዋቸው የገቡ በመሆናቸው እንደሆነ ተግሬ በጊዜ ሒደት ተቀይሮ ትግሬ የተባሉት ማለቴ ይታወሳል) እናም ብአዴን የነሱ ጥቅም አስጠባቂ ሆኖ ይሄንንም በጸጋ ተቀብላቹህ ከራስ ገዛዊው ሕግና ሥርዓት ውጪ እያስተናገዳቹህ “ብአዴን የራስ ገዛዊው የአማራ ድርጅት ነው” ስትሉ ትንሽ እንኳን አታፍሩም?
ወያኔ የአማራን ሕዝብ ካለማመኑና ለመጨቆንና ለመቆጣጠር ካለው ዕኩይና ጽኑ ፍላጎቱ የተነሣ ከመንግሥት መዋቅር ውጪ ያሉ እንደ እድር፣ የሰበካ ጉባኤ፣ ማኅበር የመሳሰሉ በክልሉ ሕዝብ ያሉ የማኅበራዊ መዋቅሮች የአሥተዳደር ቦታዎች እንኳን አይቀሩም በትግሬ እንዲያዙ ሲያደርግ፡፡ ወያኔ ሥነልቡናዊ ወንድነቱ ቆራጥነቱ ወይም ቆፍጣናነቱ የተሰለበ እንደ እንስሳ ሆዱ ብቻ የሚያሳስበው እንደፈለገ የሚያሽከረክረውንና የሚረግጠውን ኅሊናውን የሸጠ ሆዳም መሆኑን ካላረጋገጠ በስተቀር ወያኔ በብአዴን ውስጥ በሥልጣንም ሆነ በአባልነት አንድንም የአማራ ተወላጅ አይቀበልም አያካትትም፡፡
ሰዎች ብአዴን ውስጥ ያሉ ባለሥልጣናትን እየጠቀሱ “አቶ እከሌ ተቆርቋሪ ነው፣ አቶ እከሌ እንደዚህ ነው” ሲሉ እኔ ይገርመኛል! የወያኔን ዘዴ አለማወቃቸው ነው፡፡
ወያኔ ሁሌም የቸገረ ነገር ሲያጋጥመው ሁለት ዓይነት ገጸ ባሕርያትን ይዞ ነው የሚቀርበው፡፡ አንደኛው አጥቂ ሌላኛው ተቆርቋሪ ሆነው ይቀርባሉ፡፡ አጥቂና ግትር አቋም የያዘው አካል የማይሆንለት ከሆነ ተቆርቋሪና ለዘብተኛ መስሎ በቀረበው አካል ያጋጠማቸውን ወይም የተጋፈጡትን ችግር ለመፍታት ለማለዘብ ለማስቀየስ ጥረት ያደርጋሉ፡፡
እስከ አሁን ድረስ “አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ለአማራ ለማንነታቸው ተቆርቋሪ ናቸው…” የሚባለውን ነገር ሊያረጋግጥልኝ ሊያሳምነኝ የሚችል አንዳች ነገር ላገኝ አልቻልኩም፡፡
እኔ የሚመስለኝ ሰውየው ተቆርቋሪ መስሎ የሁለተኛውን የወያኔ የአቀራረብ ገጸባሕርይ እየተጫወተ ወይም እየተወነ ያለ ነው የሚመስለኝ፡፡ እንዲህ እንዲያደርግ የተፈለገበት ምክንያትም የአማራ ሕዝብ በብአዴን ተስፋ ቆርጦ ጉዳዩን በራሱ በመወጣት በራሱ ቆራጥ እርምጃ መፍትሔ ወደ መሻት እንዳይሸጋገር ዝም ብሎ ተስፋ እያደረገ እንዲቀመጥ ለማድረግ ነው እንጅ የገቢዎች ሚንስትር የነበረውን አቶ መላኩ ፈንታን ከጉራፈርዳ የተፈናቀሉ ወገኖቻችን ጉዳይ በብአዴን እንዲታይ በመጠየቁ ከብአዴን ስብሰባ በመመለስ ላይ እንዳለ ቦሌ ከአውሮኘላን (ከበረርት) ሲወርድ ተቀብሎ ወዲያው የፈጠራ ክስ መሥርቶ ወኅኒ የወረወረ አገዛዝ አቶ ገዱ የተወራውን ነገር እያደረጉ ይታገሳል ብሎ ማመን ሲበዛ ቂልነት ነው የሚመስለኝ፡፡
ሲጀመር አቶ ገዱ ይሄንን ያህል ቁርጠኝነቱ ተቆርቋሪነቱና እልሁ ካላቸው በወያኔ አሻንጉሊት ድርጅት ውስጥ ተቀምጠው የወያኔ አገልጋይ የመሆን አቅል ስሜት ፍላጎትና ትዕግሥት ይኖራቸዋል ብየ አልገምትም፡፡
ሲቀጥል አነሧቸው የሚባሉት አቋሞች ብአዴን ውስጥ እንዳልተሠራባቸው እያዩ በአገዛዙ ሕገወጥ ጣልቃገብነት ሲሻሩ እየተመለከቱ ወይ ሥልጣናቸውን በመጠቀም የማስተካከያ እርምጃ ለመውሰድ ጥረት ያደርጉ ነበር እንጅ እንዲህ እየሆኑ በሥልጣን መቆየትን ሊሹ የሚፈልጉበት አንዳችም ምክንያት አይታየኝም፡፡
በእርግጥ የወያኔ ቅጥ ያጣና መረን የለቀቀ ስድብ ንቀት ዘለፋ ግፍና ጥቃት ያስቆጫቸውና ያንገበገባቸው ከዚህም የተነሣ በወያኔ ላይ ፊታቸውን ያዞሩ ማንነታቸውን ወደማሰብ ለሕዝባቸው ወደመቆርቆሮ የተመለሱ አንዳንድ የብአዴን አካላትን አውቃለሁ፡፡ ይሁንና አቶ ገዱ ግን ከእነኝህ ውስጥ አንዱ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥልኝ መረጃ አላገኘሁም፡፡ ስለሆነም የሚባለውን ነገር ለማመን እቸገራለሁ፡፡
ወደቀደመው ነገራችን እንመለስና የአማራ ሕዝብ ድርጅት ነኝ ባዩ የወያኔ አሻንጉሊት ድርጅት ብአዴን ትናንት 25,11,2008 ዓ.ም. በሁለት ባለሥልጣናቱ በኩል ከአሜሪካ ራዲዮ (ነጋሪተ ወግ) የአማርኛ ድምፅ አገልግሎት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጹት “ምንም እንኳ ሰልፉ ዕውቅና የሌለው ሕገወጥና የጥፋት መልዕክት የተላለፈበት ቢሆንም ሰላማዊ ስለነበር ለዚህ ዕውቅና እንሰጣለን” በማለት ብአዴን አቋሙን እንደገለጸው ጎንደር ከተማና በጎንደር የተለያዩ ወረዳዎች በ24,11,2008ዓ.ም. የተደረጉትን ደማቅ የአማራ ሕዝብ የተቃውሞን ሰልፍ እንዲያ በማለት ፈርጇል፡፡
እስኪ መጀመሪያ “ዕውቅና የሌለው ሕገወጥ” የሚለውን እንይ፦ ብአዴን ወይም ወያኔ ይሄንን ሰልፍ “ዕውቅና የሌለው ሕገወጥ!” ሲል ሊጠራው በፍጹም አይችልም፡፡ ምክንያቱም አንድን የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የአገዛዙ ፈቃድ እንደሚያስፈልግ የሚያዝ ወይም የሚጠይቅ ወይም የደነገገ ሕግ በሀገራችን የለምና ነው፡፡ ሕገ መንግሥታቸው የሚለው “አስታውቅ” ነው፡፡ የማሳወቁ አስፈላጊነትም አገዛዙ ዕውቅና ሰጥቸዋለሁ ሰልፉን አድርጉ ፣ አልሰጠሁትም አታድርጉ እንዲል ሳይሆን ሥነሥርዓት የሚያስከብሩ የጸጥታ አካላትን እንዲመድብ፣ ሰላማዊ ሰልፉ ሊደረግ በታሰበበት ቦታ ላይ በተመሳሳይ ቀን ተመሳሳይ ሌሎች ኩነቶች ለማድረግ እንዳይታቀድና የኩነቶች መደራረብ ችግር እንዳይፈጠር ሥርዓት ማስያዝ እንዲችል ለማድረግ ብቻ ነው፡፡
በዚህም መሠረት ሰልፉ እንደሚደረግ እንዲያውቁ ተደርጓል፡፡ ነገር ግን ሰልፉ እንዲደረግ በፍጹም ፈቃደኛ አልነበሩም፡፡ ሰልፉ እንደሚደረግ ስላወቁማ ነው በነሱ አማርኛ ሰልፉን ከመደረጉ ከሳምንት በፊት ጀምረው ሕገ ወጥ እንደሆነ ሲለፍፉ የሰነበቱት፡፡ ይሄ ልፈፋቸው ሰልፉ እንደሚደረግ ማወቃቸውን ያረጋግጣል፡፡
ያለው ሀቅ እንዲህ በሆነበት ሁኔታ ወያኔ በምንም ተአምር ሰልፉን “ዕውቅና የሌለው” ስለዚህም “ሕገወጥ” ሊል የሚችልበት አንድም ዓይነት ሕግና አሠራር የለም፡፡ በገለጽኩት መልኩ ሕጉን ተከትሎ የተከናወነን የተቃውሞ ሰልፍን “ሕገወጥ” ካሉ ሕገወጦቹ በሕግ መሠረት የማይሠሩት እነሱ እንጅ ሕዝብ አይደለም፡፡
ሕዝብማ የተቃውሞ ሰልፍ ማድረግ ብቻም አይደለም በተቃውሞ ሰልፉ እንዲስተካከሉ እንዲፈጸሙ የጠየቃቸው ጉዳዮች በአፋጣኝ ካልተፈጸሙና ካልታረሙ አንባገነን አገዛዙን በዐመፅ የማስወገድ መብት ኃላፊነትና ግዴታም አለው እናደርገዋለንም፡፡
ከላይ እንደገለጽኩት አሻንጉሊቱ ብአዴን ሰልፉን “… የጥፋት መልዕክት የተላለፈበት” ሲል ጠርቶታል፡፡ ለመሆኑ የትኛው መልዕክት ነው የጥፋት መልዕክት? የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄው ነው የጥፋት መልዕክት?፣ የወያኔ ሀገርና ሕዝብ በታታኝነት መወገዙ ነው?፣ ወያኔ በአማራ በኦሮሞና በሌሎችም የሚፈጽመው ግፍና በደል እንዲቆም መጠየቁ ነው? የቱ ነው የጥፋት መልዕክት? የጥፋት መልዕክት ማለትስ ራሱ ምን ማለት ነው? ሕዝብ ከተጨባጭ እውነቱና ሕይዎቱ ተመሥርቶ ያንጸባረቀውን ሐሳብ ወይም አስተሳሰብስ የጥፋት መልዕክት ማለት ይቻላል ወይ? ብአዴን እወክለዋለሁ የሚለውን የአማራን ሕዝብ ሐሳብ፣ ጩኸትና ጥያቄ ሳይጋራ፣ ሳያንጸባርቅ፣ ሳያራምድ፣ ሳይይዝ ተቀጣሪ ወይም አሻንጉሊት እንጅ “የአማራ ሕዝብ ድርጅት ነኝ” ሊል ይችላል ወይ??? በሚሉ ጥያቄዎች ብአዴንን ብንመረምረው ብንፈትሸው ብንሞግተው በኢትዮጵያ ውስጥ ግፈኛው ወያኔ ብቻ እንጅ ብአዴን ምንትስ የሚባል ከነአካቴው እንደሌለ ልናረጋግጥ እንችላለን፡፡
ከሰልፉ ቅር ያሰኙ ጉዳዮችን ሳነሣ፦ ሰልፉ የራሱን አጀንዳ (ርእሰ ጉዳይ) ይዞ የተጠራ ሰልፍ ቢሆንም ማዕከላዊነትን በጠበቀ መልኩ የተደራጀ ሰልፍ ስላልነበረ በዚህ ክፍተት ምክንያት ከፊሎቹ በራሳቸው ተነሣሽነት የእነ አቶ በቀለና የአቶ ሀብታሙ ጉዳይ በሰልፉ መነሣቱ የአማራ ሕዝብ የዜጎች ሰብአዊ መብቶች እንዲከበር ካለው ጽኑ ፍላጎት አኳያ ነው እንጅ አቶ በቀለና ጓዶቻቸው እያራመዱት ላለው ዘውግን መሠረት ላደረገው ፖለቲካዊ አስተሳሰባቸው ድጋፍ ለመስጠት ወይም ደግሞ ሰውየው ከዚህ ቀደም የአማራን ሕዝብ በተመለከተ “የአማራ ሕዝብ ቀድሞ ገዥዎች ለፈጸሙብን በደል ይቅርታ ሊጠይቀን፣ ካሳ ሊከፍለን ይገባል! ካልሆነ ግን አብሮ ለመኖር ይቸግረናል!” በማለት ለመሠረተው የፈጠራ ክስና ላስተላለፈው የተሳሳተ ኦነጋዊ የጥፋት አስተሳሰቡ ሰውየው እራሱ ይቅርታ ሳይጠይቅና ሳይታረም እኛ ይቅርታ አድርገንለታል ለማለትም አይደለም፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዳለ ሰቆቃ በሚያይባት ሀገር ወያኔ በአቶ ሀብታሙ ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍ ነጥሎ አውጥቶ ማንጸባረቁም በዚሁ ወቅት በተለያዩ ቦታዎች ተመሳሳይና ከዚህም የከፋ ግፍና በደል እየተፈጸመባቸው ያሉ ወገኖችን ዋጋ ማሳነስና እንደሌሉ መቁጠር፣ ከሩቅ ለሚያይ ታዛቢም በዚህ ወቅት ወያኔ የፈጸመው ግፍ ይህ የሀብታሙ ብቻ እንደሆነ ስለሚያስመስል በመሆኑ የሀብታሙ ጉዳይ ተነጥሎ መውጣቱም ትክክል አልነበረም፡፡
በተረፈ በመጪዎቹ ቀናትና ሳምንታት በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ሊደረጉ በታቀዱ የተቃውሞ ሰልፎች በነቂስ በመውጣትና ለወያኔ ሕገወጥ ፍረጃ ባለመበገር የመጨረሻውን ሕዝባዊ ማስጠንቂያችንን እንድናሰማ ወንድማዊ መልዕክቴን ማስተላለፍ እወዳለሁ፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com

 

“አማራው ዘሩ በሕወሓት ከመጥፋቱ በፊት በአንድነት ይነሳ”ሲል የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ ጥሪ አቀረበ

$
0
0

ከአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ

ወያኔ ህወሃት ዘርን መሰረት አድርጎ በአማራ ህዝብ ላይ የሚፈጽመውን የጥቃት ፖሊሲ ለመመከት በአንድነት እንነሳ!

የአማራ ህዝብ በቅድመ ዘመነ መሳፍንት ኢትዮጵያ አንደ ሆና እንድትቀጥል ከፍተኛ መስዓውትነት ሲከፍል የቆየ ህዝብ ነው፡፡ ዘመነ መሳፍንት እንዲከስምና ሰሜናዊና ደቡባዊ ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ ከፍተኛ መስዋትነት በመክፈል ለሀገሩ ያለውን ፍቅር አሳይቷል፡፡

(ፎቶ ከፋይል)

(ፎቶ ከፋይል)

አማራ በሀገሪቱ የመንግስት ስርዓት ለውጦች እንዲመጡ በኢትዮጵያዊ ብሄርተኝነት ስሜት መስዓውትነትን የከፈለ አርቆ አሳቢ ህዝብ ቢሆንም ጨፍጫፊው ዘረኛ ቡድን ህወሃት ወያኔ ገና ከውልደቱ ጀምሮ የአማራን ህዝብ በመሰረታዊ ጠላትነት ፈርጆ በኢትዮጵያ ውስጥ ይህን ህዝብ እንዴት ማዳከም እንደሚችልና ከቻለም አጠቃላይ ህዝቡንና ሀገሪቱን በህወሃት ዘላለማዊ አገዛዝ ስር ማስገባት ነው፡፡ ይህን ካልቻለ ደግሞ የታላቋ ትግራይን ሪፐብሊክ እውን ማድረግ የሚል የፖለቲካ ፕሮግራም መሰነቁና ለዚህም ያለ ድካም መልፋቱ ነው፡፡
ሆኖም ይህን አጉል ምኞቱን ተግባራዊ ለማድረግ በሚያደርገው ግስጋሴ በዋነኛነት እንቅፋትና የስጋት ምንጭ አድርጎ የፈረጀው ኢትዮጵያዊነቱን ኩራቱና የማንነቱ መገለጫ አድርጎ የሚያምነውን የአማራ ህዝብ በመሆኑ ብዙ ጥቃቶችን ሲፈጽም ቆይቷል።

በዚህም እንቅስቃሴው የኢትዮጵያዊ የብሄርተኝነት ጠንካራ ምሽግ ሲል በጠላትነት የፈረጀውን የአማራ ህዝብ በጅምላ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ማዳከምና ከምድረ ገጽ ለመደምሰስ በሰራ መጠመዱ ነው።
ይህም ህወሃት መሰረታዊ ጠላቴ ሲል የፈረጀውን አማራ ከወልቃይት ጽገዴ ህዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ እስከ አሁኗ ስዓት ድረስ በጎንደር እያካሄደ ያለው ጸረ አማራ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ዋናውና አንገብጋቢው መሆኑ በግልጽ ይታያል፡፡
ህወሃት የወልቃይት ፀገዴ በርካታ ንጹሃን ወገኖቻችንን በዘር አማራ ስለሆኑ ብቻ ጅምላ ከመረሸን አልፎ አፍኖ በመውሰድ አድራሻቸው እንዲጠፋ ብሎም ወደ አደገኛና ዘግናኝ እስር ቤቶች የወረወራቸው በመሆኑ ይህን አደገኛ ዘር ላይ ያነጣጠረ ናዚያዊና ፋሽስታዊ ጥቃት መላው የአማራ ህዝብ በጋራ ታጥቆ ከአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ ጎን በመሰለፍ ሊመክተውና ሊደመስሰው ይገባል። ይህ በአማራነት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በአማራነት ታጥቆ በመነሳትና በመደራጀት ብቻ የሚመከትና የሚመታ በመሆኑ ማነኛውም አማራ ዘሩ በህወሃት ሴራ ከምድረ ገጽ ከመጥፋቱ በፊት የህወሃትን ሴራና አሻጥር ለመደምሰስ በአንድነት እንዲነሳ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ (አ ዴ ሃ ን) የትጥቅ ትግል ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

አማራ ዘሩ በህወሃት ሳይጠፋ ለትጥቅ ትግሉ እንነሳ!

በኦሮሚያ ክልሎች ለሚገኙ ሙስሊም ወጣቶች በአጠቃላይ የተላለፈ አስቸኳይ ጥሪ

$
0
0

oromia

የወያኔ መንግስት ኦሮሞ በመሆናችን ብቻ እያሸበረን፣ እየገደለን፣ እያሰረን እና ከሀገረ እያባረረን ይገኛል። በሀይማኖታችንም ቢሆን እየደረሰብን ያለው ጭቆና እና አፈና በቀላሉ የሚታይ አይደለም። መጠን ያለፈው የብሄርና የሀይማኖት ጭቆናው ሊቆም የሚችለው ስርዐቱ ህዝቦች ውሳኔ የሚሰጡበት ዲሞክራሲያዊ ሲሆን ብቻ ነው።

መንግስት በሙስሊሙ ላይ ይፋ የሆነ ጦርነት ከጀመረ 5 አመት አስቆጥሯል ።

በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ ሲደርስ የነበረው ጭቆና ያለ ልዩነት የነበረ በመሆኑ የኦሮሞ ሙስሊምም ከገፈቱ ቀማሽ ብቻ ሳይሆን በሰላማዊ ትግሉ ላይ ጉልህ ተሳትፎ እያደረገ ይገኛል። በሙስሊም ለይ የተቃጣውን ግፍ በመቃወም ብዙዎች ህይወታቸውን ሰውተዋል ፣ታስረዋል ፣ተደብድበዋል፣፣ ተገለዋል ፣ተሰደዋል።

መንግስት በሀገሪቱ በአጠቃላይ የሙስሊሙን የመብት ጥያቄ መልስ ከመስጠት ይልቅ በእብሪት እና በማን አለብኝነት በሙስሊሙ ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ አጠናክሮ እስካሁን እንደቀጠለ ይገኛል።

ሰለሀገራችን እያደረግነው ያለው ትግል እስካሁን የከፈልነው መስዋእትነት በታሪክ ላይ የራሱን አሻራ ያሰረፈ በመሆኑ የሚረሳ እና የሚዘነጋ አይደለም።

በሀይማኖታችንም ቢሆን የከፈልነው መስዋእትነት በተምሳሌነትነት የሚዘከር ነው።

ስለሆነም በሚቀጥለው ቅዳሜ ሀምሌ 30 /2008 በኦሮሚያ ክልሎች በሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ በነቂስ በመውጣት የሀገር ባለቤትነታችንን እና በእምነታችን ላይ የሚደርሰውን ግፍ የሚያወግዙ መፈክሮችን በማዘጋጀት በዚህ ታሪካዊ ሰልፍ ላይ እንደንገኝ ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። ጥያቄዎቻችን ሊመለሱ የሚችሉት ዛሬ በምንከፍላቸው መስዕዋትነት ብቻና ብቻ ነው።

በተጨማሪ የኦፒዲኦ ባለስልጣናት ህዝብን ከዚህ ታሪካዊ ሰልፍ ለማደናቀፍ ለመስጂድ ኢማሞች በጁምአ ኹጥባ ላይ ሙስሊሙ በሰልፍ እንዳይገኝ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጡ መልክዕት ማስተላለፋቸውን መረጃው የደረሰን ሲሆን በየትኛውም መስጂድ ኢማሙ ስለሰልፉ መናገር ሲጀምር በተኪቢራ በማቋረጥ የትግሉ አጋርነታችንን እናረጋግጥ።

ትግላችን በሀይል አይገታም!!!

ድምፃችን ይሰማ

“የዘረኛው ሥራዓት በሕዝባዊ ኃይል ይደመሰሳል”–የጎንደር ሕብረት

$
0
0

የጎንደሩ ተቃውሞ ሰልፍ የ5 ደቂቃ ቪዲዮ

የፍርሃት ከፈን፤ በጎንደር ተቀደደ፤ የጎሕ ብርሃን በኢትዮጵያ ፈነጠቀ! ልዩ መግለጫ፤

በቅድሚያ የአምባ ገነኖችን ፉከራ ደፍሮ፤ ከፊት ለፊቱ የተደገነውን መሳሪያ ተረማምዶ፤ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ላዉለበለበዉ ጀግናዉ የጎንደር ህዝብ ያለንን አድናቆት በደስታ እና በከፍተኛ ክብር ልንገልጽ እንወዳለን። የትግራይ ነፃ አዉጭ ግንባር በማስፈራራት ለዘመናት ቀፍድዶ የያዘውን የፍህራት ጨለማ ዘመነ ሐምሌ 24 ቀን 2008 ዓ/ም በጎንደር ህዝባዊ ሃይል ተገፈፈ። ትግራይ ላይ ተወልዶ፤ የሕዝብ ደምን በከንቱ እያፈሰሰ፤ ጎንደር ላይ አድጎ፤ ምኒልክ ቤተ መንግሥት የገባው የወያኔን ሥራዓት የዉድቀት፤ ግባ ከመሬቱ ጎንደር ላይ ተቆፍሮ፤ ሊቀበር የአንድ ጀምበር ያክል ጊዜ ቀርቶታል። ወያኔ ቀበርኩት ያለው አንድነታችን፤ በዳግማዊ ቴውድሮሶች፤ ዛሬም እንደገና ሁለተኛውን ምእራፍ በጥንታዊት ጎንደር ከተማ ላይ መፃፍ ጀምሯል። ከህዝቡ አብራክ የወጣው መደበኛ ሰራዊት፤ ፖሊስና ልዩ ሃይል፤ ህዝባዊ ሚሊሻ የህዝቡ ደስታ ተካፋይ መሆኑን፤ ከላይ በተጠቀሰው ቀን ሥንታዘብ ደግሞ፤ የአገራችን ኢትዮጵያ ታሪካዊ ክብር ቀጣይነትና፤ የነ ስብሐት ነጋ “እኛ ከሌለን ኢትዮጵያ ትፈርሳለች” ከንቱ ቅዠት መሆኑን እና ለዉጥ የተጠማዉ የህዝብ አንድነት አስተማማኝ ደረጃ መድረሱን ስናረጋግጥ ደስታችን መጠን የለዉም። ትግሉ ያለማቋረጥ ይቀጥላል። “የነብርን ጅራት አይዙም፤ ከያዙም አይለቁም” እንዲሉ ከዚህ በኋላ፤ ለዚህ ዘረኛ እና ቂመኛ ቡድን ጊዜ መስጠት እጅግ አደጋ ነዉ።

በመሆኑም፤ የወያኔው ቡድን በተፈጥሮው፤ እውነትን መቀበል የማይችል፤ ከራሱ ጥቅም በቀር ለኢትዮጵያችን የሚያስብ ቡድን ሥላልሆነ፤ ሁሉም የትዮጵያ ህዝብ የጎንደር ወንድም /እህቱን የትግል ቆራጥነት ፈለግ ተከትሎ ሳይዉል ሳያድር፤ በመላ አገራችን፤ ከዋና ከተማ እስከ ወረዳ እና ቀበሌ ድረስ በአን ድምጽ ለህዝባዊ ትይንት በመዉጣት ከመለዮ ለባሹ ጋር ተባብሮ ይህን ዘረኛ መንግስት ለደቂቃ ያህል ፋታ ሳይሰጥ፤ የጥፋት እጆቹን በመቁረጥ፤ አዲሱን ዓመታችን፤ ሁሉም ዜጋ በነፃነቱ፤ ኮርቶ እና ተከባብሮ የሚኖርባትን ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን እንድንመሰርት፤ ጥሪያችን እናስተላልፋለን። ከአሁን በፊት በተግባር፤ እንዳየነው፤ የትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር ጊዜ ለመግዛት የእርቀሰላም ጨዋታ ሊጠይቅ ይችላል። ብዙ ድርጅቶችንም በመድረክ ወጥታችሁ አረጋጉ፤ ካሃናትንም ይህን ጨዋ ህዝብ አስታርቁን፤ ገዝቱልን ማለቱ አይቀርም። የኢትዮጵያ ህዝብ የተማመነበት አንድ ሃቅ ግን አለ። ያም! ወያኔ ሰላም የሌለዉ፤ ሊጠገን የማይችል፤ የበሰበሰ የሳር ጎጆ መሆኑን ብቻ ነዉ። ይህን ቂመኛ ቡድን አምኖ የሚደራደር ሁሉ፤ በአንገቱ ላይ ገመድ እንደማስገባት የሚያስቆጥር ሲሆን፤ ለማደራደር፤ የሚሞክሩ ደግሞ ኢትዮጵያዊነታቸውንም ሆነ፤ ኢትዮጵያችን ቆፍረው እንደቀበሩ ይቆጠራል። የወያኔ ሥርዓት የህዝብ አመኔታ አቶ ያከተመ ዘረኛ ስርዓት ነዉ። በየአካባቢ ተደራጅተህ ጀግና መሪህን መርጠህ ኢትዮጵያዊነትህን እና ታሪካዊ ፍቅር ያለህ ህዝብ መሆንህን አሳይተሃል እና ማንም ዓላማህን ወደኋላ እንዳይጎትት በቆራጥ ጀግንነትህ አረጋግጥ። በጎንደር አደባባይ ያውለበለብከውን፤ የኢትዮጵያዊነት ምልከት የሆነዉ ሰንደቅ ዓለማንን በሌሎች ሁሉም የኢትዮጵያ አደባብዮች፤ አዉለብልብ። ወያኔን አስወግደን ህዝባችን መክሮ ያመነበት መንግስት በእርግጠኛነት ይቋቋማል። በመቶ የሚቆጠሩ ድርጅቶች ባንዲራ አንግቦ “እኛን ተከተሉን መሪያችሁ ነን” ማለት ለ82 ነገዶች ለተዋበችው ብርቅየ ኢትዮጵያችን ምንም አይነት ፋይዳ የለዉም። መላዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ተባብሮ እጅና ጓንት ሁኖ ሳይዉል ሳያድር የትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባርን ስርዓት ለማስወገድ በቆራጥነት የጎንደር ህዝብን ተጋድሎ አጋዥ መሆን ችላ የማይባል የትግል ጥሪ ነዉ። በዚህ የነጻነት ትግል መሃከል ለስልጣንና የግል ጥቅማቸውን ለማራመድ የሚስበደበዱ ሁሉ፤ የትግሉ አጋር አይደሉም እና በመንገድህ ላይ ደንቃራ እንቅፋት እንዳይሆኑህ፤ እየጠራርክ፤ ወደ ድል አጥቢያህ ገሥግሥ።

በሌላ በኩል፤ የትግራይ ተወላጆች፤ በወያኔ ግዳጅም ይሁን፤ ነገርን አርቆ ካለማዬት፤ ከእውነት በራቀ ድርቅና፤ የወልቃይት መሬት የኛ ነው በሚል፤ የምታደርጉት ሰላማዊ ሰልፍ እና ወያኔያዊ ድጋፍ፤ አገራችንን ወደ ባሰ ቀውስ የሚከት ከመሆኑም  በላይ፤ በመላ አገሪቱ ኮራ እና ዘና ብለው፤ ሰርተው ለሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች፤ ችግር እየፈጠራችሁ መሆኑ ተገንዝባችሁ፤

በአስቸኳይ፤ ከመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን እንድትቆሙ፤ ልናሳስብ እንወዳለን።

አስቸኳይ አገራዊ ጥሪ፦

አገር ውስጥ ያላችሁም ይሁን፤ ውጭ አገር ያላችሁ፤ ለአገራችሁ አንድነት፤ ለሕዝባችሁ መብት የቆማችሁ፤ የፖለቲካ ድርጅቶች፤ የስባዊ መብት ተከራካሪ ብዙሃን ድርጅቶች፤ የሃይማኖት እና የሙያ ተቋማት፤ ለአገር ተቆርቋሪ የሆናችሁ ሁሉ፤ ያላችሁን ጥቃቅን ልዩነቶች ወደ ጎን ትታችሁ፤ ኢትዮጵያችን ካለችበት ተረክበን፤ በተረጋጋ ሁኔታ እንድናስቀጥል፤ በፍጥነት፤ ወያኔን ሊተካ የሚችል፤ ብሄራዊ እርቅን መሰረት ያደረገ የሽግግር መንግሥት እንድታቋቁሙ፤ በኢትዮጵያ አምላክ እንማፀናለን።

በመጨረሻም፤ እ. ኢ. አ በ07/24/2016 ዓ.ም በጎንደር ከተማ በተደረገው፤ ሰላማዊ ሰልፍ፤ እናቶች ለተሰላፊው ውሃ በማቅረብ፤ መለዮ ለባሹ፤ ከአብራኩ ለወጣው ህዝብ ያሳየውን ክብር፤ ተሰላፊው፤ ያሳየውን ጨዋነት እና አገራዊ ፍቅር፤ ያነገባቸው መፈክሮች እና የተሸከመው ዓላማ ፍጹም ኢትዮጵያዊነት፤ ከመሆኑም በላይ፤ ወያኔን ከትግራይ ወገኖቻችን ለይቶ ማየቱን፤ እያደነቅን፤ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፤ ሊከተለው የሚገባ ቀጣይ ፈለግ መሆኑን ልናሳሥብ እንወዳለን።

የዘረኛው ሥራዓት በሕዝባዊ ኃይል ይደመሰሳል! የኢትዮጵያ አንድነት እንደገና ይገነባል!!
ጎንደር ሕብረት

በጎንደር ቆላድባ ከባድ ውጊያ እየተደረገ ነው –አጋዚ በአወዳይ 3 ሰላማዊ ሰዎችን ገድሎ 70 አቆሰለ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በጎንደር ቆላድባ ሕዝብ ከሕወሃት ወታደሮች ጋር እየተዋደቀ እንደሚገኝ የሚደረሱን መረጃዎች አመልክተዋል:: በአወዳይ የሕወሃት ሰራዊት በንጹሃን ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ባወረደው ጥይት 70 ሰዎችን ሲያቆስል 3 ሰዎች መገደሉ ተዘግቧል::

bbn
የጎንደር ቆላድባ ከተማ በአሁኑ ወቅት የጦር አውድማ ትመስላለች የሚሉት የአካባቢው ነዋሪዎች ሕዝቡ ቁጣውን ለመግለጽ ፍርድ ቤት; የክልሉን የመንግስት መስሪያቤቶች እና ከ14 በላይ የመንግስት መኪኖችን በማቃጠል ተቃውሞውን ገልጿል::

በተለይም በቆላድባ ከተማ የሚገኘውን የመንግስት መሳሪያ ግምዣ ቤትን በመስበር ሕዝቡ ራሱን አስታጥቆ መከላከያ ሰራዊቱ ን በጦርነት ገጥሞታል::

ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ደብረታቦር እና ጋይንትም አለመረጋጋቱ እንዳለ ነው::

ይህ በ እንዲህ እንዳለ በአወዳይ ዛሬም ሰላማዊ ሰዎች ተገደሉ:: 70 የሚሆኑ ንጹሃንም ቆስለዋል:: በአወዳይ ላይ ጥቃት ሲፈጽም የነበረው ህወሃት መራሹ መንግስት ዛሬም ጥቃቱን ቀጥሏል ያሉት ነዋሪዎች ለቢቢኤን እንደገለጹት ገና በማለዳዉ ከመስጊድ ሶላት ሰግደዉ የሚወጡን የእድሜ ባለጸጋ የሐይማኖት አባት አጋዚ በጥይት መመታታቸዉ አወዳይን እልህ ዉስጥ የከተተ መሆኑን ገልጸዋል።
ሁሌም አጋዚዎችን በቁርጠኝነት የሚጋፈጠዉ ነዋሪ ዛሬም አጋዚን ሲጋፈጥ መዋሉን ገልጸዋል። ህዝቡ ተቃዉሞን በሰላማዊ መንገድ ቢያሰማም አጋዚዎች ቀጥታ ወደ ህዝብ በመተኮሳቸዉ እስከ ሰባ የሚደርሱ የአወዳይ ነዋሪዎች መቁሰላቸዉ ለማወቅ ተችሏል። የህዝቡ ቁጣ በአወዳይ ዉስጥ ተጠናክሮ ቀጥሏል። በማለዳ ሶላት ሰግደዉ ከመስጊድ ሲወጡ የነበሩት የሐማኖት አባት በጥይት መገደላቸዉ ዉጥረቱን ወደ ጦርነት ሳይቀይረዉ አይቀርም በማለት የአወዳይ ነዋሪዎች ስጋታቸዉን ገልጸዋል።
ስርዓቱ በጣረሞት ዉስጥ ነዉ በማለት ለቢቢኤን የገለጹት ነዋሪዎች እርምጃዎቹ የደመነፍስ እንደሆኑ አስረድተዋል። በስተመጨረሻ ድል የተጨቆነ ህዝብ በመሆኑ ለድል በጋራ እንነሳ የሚል ጥሪ አስተላልፈዋል።


የባሌ ሮቤ ውሎ –በፎቶ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) እንደማንኛውም የኢትዮጵያ ከተሞች በባሌም ሰላማዊ ሰልፍ ተጠርቶ ነበር:: ሕዝቡም በሰላም ጥያቄዎቹን እየጮኸ ሲያሰማ ነበር:: ሆኖም ግን የሕወሃት መንግስት ተላላኪ ወታደሮች የሆኑት አጋዚዎች ሕዝቡን ከሰላማዊው ጥያቄው ለመበተን ጥይት ተኮሱ:: ሕዝቡም ሰላማዊውን ተቃውሞ ወደ አመጽ አሸጋገረው:: የሞቱ እና የቆስሉ ሰዎች እንዳሉ እየተነገረ ነው:: ከተማዋ ግን በፎቶ ይህን ትመስል ነበር::
Bale Robe 2 Bale Robe 3 bale robe

።።።።።ተነስ ድረስለት።።። (እንስማው ሃረጉ)

$
0
0

።።።።።ተነስ ድረስለት።።።

መሬቱን ሲነጥቁት ስለታገሳቸው፣
ቤቱንም ሲያፈርሱት ቢሰደድላቸው፣
ማንነቱን ቀሙት አቤት ክፋታቸው፣
ጠባብ ትምክህተኛ ሲከፈት አፋቸው፣
በዚያ ተሳዳቢ ምርቃኑ ጌታቸው፣
ለካ መስሏቸዋል ህዝቡ የፈራቸው፣
መካሪ ባገኙ ህዝቡ እንደጠላቸው፣
ጀምበርም ጠልቃለች ብርሃን የላቸው፣
ቢአመልጡ ይሻላል እንዳማረባቸው፣
መውጫም አያገናኙ ሲከበብ ዙሪያቸው።

ወልቃይት ጠገዴ ሁመራ ጎንደር፣
ለ25 ዓመት ሊያጠፋሽ ሲጥር፣
ለካ ረቂቅ ነበርሽ የጏዳ ሚስጥር፣
ተርፈሻል ከመጥፋት ያለጥርጥር።

ወገን ደርሶልሻል ስጋ መንፈስሽ፣
የተቆራኘሽው አማራ እትብትሽ፣
ትናንትናም ዛሬ ምንግዜም ጎንደር ነሽ።

ባድማው ተነጥቆ የትም ሲንከራተት፣
ነጥቆት ማንነቱን በግፍ ዘረኝነት፣
ያያቶቹን አገር ወያኔ ቀምቶት፣
እጅህን ስጥ አለው መስሎ አስፈርቶት፣
እጅ ላይሰጥ ከንቱ ጎንደሬው ወልቃይት፣
ድሮም ያውቅበታል በታሪክ ለመኩራት፣
ጎንደሬው አምሯል ሊዋጋ በትጋት።

በጥንቱም ዘመን ኃያል የነበር፣
የሰው ልጅ መገኛ የታሪክ ማህደር፣
ፍልስፍና በጁ የፊደል ዝክር፣
ዘመን ተሻጋሪ የማያጠራጥር፣
ጠብቆ ያቆዬ የሃበሻን ምድር፣
ሃገርን ያኖረ ከዳር እስከዳር፣
ለወራሪ አይመች የጠረፍ ወታደር፣
ነጭን የቀጣ ነው ኩራቱ ለጥቁር፣
እጥንቱ ይዋጋል በጀግኖቹ ምድር፣
ነፍሱም ትጣራለች ከመካነ ቀብር፣
ዛሬም እንደ ጥንቱ ትውልዱም ደፋር፣
ጀግንነት ውርሱ ነው ያያቶቹ ክብር፤
ወሰን አስከባሪው ሳተናው ወታደር፣
አንዴ ወግድ ካለ መች ይሸሻል ጎንደር፣
ከዘውድ ተወልዷል ከመይሳው ዘር፣
ንጉሱን አይሰጥም ኮ/ል ወታደር።

ምታ ነጋሪት አዋጅ አስነጋሪ፣
ክተት ሰራዊት ፈረስህን አስጋሪ፣
እንገናኝ ብሏል በታሪኳ መንደር፣
በጀግኖች ባድማ ባፄዎቹ ሰፈር፣
ጎንደር አይታማም ቃሉን በማክበር፣
እዚያው እንገናኝ ጉና ደብረ ታቦር፣
አዳርህም ማዶ ነው ወደ ባህር ዳር።

ታቦር ከነፈሰ ከተነቃነቀ፣
መሄዱ ነው ለካ ድብርቱን ለቀቀ፣
ዳሞት ይቀበላል ጨዋታው አለቀ፣
ከዚያም ይከተላል እየነቀነቀ፣
ጎጃም ይሻገራል የበላይ ዘለቀ፣
ምንድነው ዝምታው ወገን እያለቀ፣

አርበኛው ጎጃሜ ያባኮስትር እገር፣
የጊዮን በረኛ የጥንቱ ወታደር፣
ማርቆሴም ተነሳ እጅግ አትደበር፣
ወንድምህ ሲዋደቅ ካባይ ማዶ ጎንደር፣
አይሏል ንፋሱ ጉና ደብረ ታቦር፣
ጭሱን እያጨሰ ከወልቃይት ጎንደር፣
ግለቱ ይፋጃል መላ ቤጌምድር፣
በሌሊት ምጣለት ክተት ከባህር ዳር፣
አማኑኤን አልፈህ ደምበጫን ተሻገር፣
ሸበልም አትስነፍ የተኳሾች አገር፣
የእንጭቅ ልጅ በልና ተነሳ ለሀገር፣
ሞጣና ቢቸና ዳንግላ አቸፈር፣
ፈረስ ቤት ያደርሳል ዳንግላ ባህር ዳር፣
ደጀን ትሆናለህ ለወንድምህ ጎንደር፣
በሸዋም ይጨሳል አባመላ መንደር፣
በቡልጋ ከመንዜው ተሻግሮ አንኮበር፣
ደርሷል አሉ ቡንጋ ከየጁዎች ሰፈር፣
በጠገዴም አግድም ወደታች ታቦር፣
ከመከም እያለ አባይን ሲሻገር፣
ገና ከጅምሩ ወያኔን ሲያሸብር፣
በቀላሉ ላይቆም ገድል ሳያዘክር፣
እየተመመ አይደል ካዋሽስ ባሻገር፣
ወያኔ ቢዶልት ቢያድር ሲመካከር፣
መግባቱስ አይቀርም መናገሻው ሸገር።እንስማው ፣ ነሐሴ 29/ 2008 ዓ:ም

አርሲ

የባሕር ዳሩ ሰላማዊ ሰልፍ ዝግጅት ተጠናቋል • “አንድ የሕወሓት ደጋፊ 3 አማሮች ላይ ቦምብ ወርውሮ በመግደሉ ከነቤቱ ተቃጥሏል” (የዛሬው ውሎ ዜና ዘገባ)

$
0
0
ባህርዳር ከተማ ነገ እሁድ ጠዋት በሰልፈኞች ትጥለቀለቃለች ተብሎ እየተጠበቀ ነው

ባህርዳር ከተማ ነገ እሁድ ጠዋት በሰልፈኞች ትጥለቀለቃለች ተብሎ እየተጠበቀ ነው

• ጎንደር የሚኖሩ ትግሬዎች በአየር መንገድ እንዲወጡ እየተደረገ ነው
• የደብረ ታቦር፣ ጋይንትና አካባቢው ያለው የዐማራ ተጋድሎ አሁንም አልበረደም

በሙሉቀን ተስፋው
ባሕር ዳር፡ እሁድ ነሐሴ 1 ቀን 2008 ዓ.ም. በጎጃም እምብርት የሚደረገው የዐማራ ተጋድሎ ሰልፍ ሊጀመር ሰአታት ብቻ ቀርተውታል፡፡ ከቦታው በስልክ ባደረግነው የመረጃ ልውውጥ ሁሉም የባሕር ዳር ከተማና አካባቢው የሚኖሩ ዐማሮች በጠዋት መስቀል አደባባይ ለተጋድሎ ይገናኛሉ፡፡ ባነሮችና ቲሸርቶች ታትመው አልቀዋል፤ የአባቶቻችን ሰንደቅ ዓላማም ተዘጋጅቷል፡፡ በመታተም ላይ የነበረ በርካታ መጠን ያለው ቲ ሸርት በባንዳ ደኅንነቶች ጥቆማ የታሸገ ቢሆንም በቂ መጠን ያለው ታትሞ ወጥቷል፡፡ የባሕር ዳር ሕዝብ በገንዘብና በሞራል ያደረገው አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ ሰልፉን እየመሩ የሚገኙት ዐማሮች በራሳቸው ተነሳሽነት ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሲሆን ከዐማራነት ውጭ የሚነሱ ጥያቄዎችን የሚያስቆሙ ብሎም በእነሱም ላይ እርምጃ የሚወስዱ ኮሚቴዎች ተዋቅረዋል፡፡

ጎንደር፡ የጎንደርና አካባቢው ችግር እየተወሳሰበና በቀላሉም ሊፈታ የማየችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን ከቦታው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ዛሬ ሐምሌ 30 ቀን 2008 ዓ.ም. አንድ የትግራይ ተወላጅ የሆነ የሕወሓት ደጋፊ ለተጋድሎ በወጡ ዐማሮች ላይ ቦንብ በመወርወር ከሦስት በላይ ሰዎችን ገደለ፡፡ የወያኔ መከላከያ ሠራዊት ይህን ነፍሰ በላ ሰው ተከላክለው ለማዳን ቢሞክሩም አልቻሉም፤ ከነቤቱ መቃጠሉን ለማወቅ ተችሏል፡፡ 


በተመሳሳይ በአዘዞ ትናንት የተሰው ሰማእታትን ለመቅበር በሚሔዱ ሰዎች ላይ የተኩስ እሩምታ የከፈተው መከላከያ ሠራዊት ሞትን የማይፈሩት የዐማራ ወጣቶች አዘዞ የሚገኘውን የመከላከያ ሠራዊት ካምፕ መቆጣጠራቸው ተሰምቷል፡፡ የሥርዓቱ አገልጋይ የሆኑ ግለሰቦች የሆኑ የንገድ ተቋማት በብዛት መውደማቸው የታወቀ ሲሆን ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የተኩስ ልውውጥ መኖሩን ለማወቅ ችለናል፡፡ 


ይህን ተከትሎ የሥርዓቱ አገልጋይ የሆኑ የትግራይ ተወላጆችን መንግሥታቸው በአየር መንገድ በኩል ሲያጓጉዝ መዋሉን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ዛሬ ከጎንደር አጼ ቴዎድሮስ አየር ማረፊያ ወደ መቀሌና አዲስ አበባ በርካታ የትግራይ ተወላጆች መውጣታቸውን ለማረጋገጥ ችለናል፡፡ 


ቆላድባ፡ በደንቢያ ወረዳ የቆላ ድባ ዐማሮች ተጋድሎ ከሁሉም ያየለ እንደነበርም ሰምተናል፡፡ በሌሊት በቁጣ የወጣው የደንቢያ ዐማራ ማንም የሚያቆመው ኃይል ሳይኖር የሥርዓቱ መገልገያ የነበሩ ተቋማትንና ተሸከርካሪዎችን ዶጋ አመድ አድርጓል፡፡ እስካሁን ባለመን መረጃ መሠረት ከዐሥር ያላነሱ መኪናዎች ተቃጥለዋል፤ የብአዴን፣ የአብቁተና ሌሎችም መሥሪያ ቤቶች ወድመዋል፡፡ ከወያኔ መከላከያ ሠራዊት ጋር በበነበረ ተጋድሎ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ዐማሮች የቆሰሉ ሲሆን የሞቱ ሰዎች መኖር አለመኖራቸው የደረሰን መረጃ የለም፡፡ በተመሣሣይ ከጭልጋ ሰራባ ካምፕ ወደ ጎንደር በመጓዝ ላይ ከነበረ የትግሬ መከላከያ ጋር በተደረገ ተጋድሎ አይባ ላይ ሁለት ያክል ዐማሮች ተሰውተዋል፡፡ 


አርማጭሆ፡ በላይ፣ ታችና ምእራብ አርማጭሆ፣ በጠገዴና በጠረፍ አካባቢዎች ዐማሮች አካባቢያቸውን ነጻ ማውጣታቸውን የተሰማ ቢሆንም የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ በመቋረጡ ማረጋገጥ አልተቻለም፡፡ የሱዳን መንግሥት በምዕራብ አርማጭሆ በኩል ከዐማሮች ላይ ጦርነት መጀመሩን የተሠማ ቢሆንም እስካሁን በስልክ ችግር ማረጋገጥ አልተቻለም (ዜናውን የጠናቀረው ሰው ማረጋገጥ አልቻለም)፡፡ 


ደብረ ታቦር፡ በደብረታቦር የተካሔደው የዐማራ ተጋድሎ ሰልፍ በከተማዋ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ነበር፡፡ ለተጋድሎ የወጣው ሰው ብዛት እስከ 5 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን እርዝመት ነበረው ተብሏል፡፡ ቀሳውስት፣ አዛውንቶች፣ ሴቶች፣ ወጣቶችና በሁሉም የእድሜ ክልል የሚገኙ ሰዎች ተሳትፈውበታል፡፡ የአጼ ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ ‹‹ዘመዶቻችን አገር መሸጥ አላስለመዱንም!›› እያሉ ወጣቶች የአባቶቻቸውን ሰንደቅ ዓላማ ያውለበለቡ ሲሆን ሰንደቅ ዓላማዋን ለመቀየር ከመጣ የአጋዚ ጦር ጋር በነበረ ተጋድሎ ከአራት ያላነሱ ሰዎች ተሰውተዋል፡፡ የተሰው ዐማሮች አስከሬን የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ለብሶ በክብር መሸኘቱን ለማወቅ ችለናል፡፡ ከክምር ድንጋይና ጋሳይ አካባቢ ገበሬው ፈረሱን ሸልሞ የመጣ ቢሆንም የአጋዚ ጦር እንዳይገባ ለመከላከል ሞክሯል፡፡ አንድ የፌደራል ፖሊስ አልሞ ዐማሮችን ለመምታት ሲሞክር ሞት የማይፈሩት የፋርጣ ዐማሮች መሣሪያውን ነጥቀው እርሱንም መተው መሔዳቸውን አውቀናል፡፡ የክልሉ ፖሊሶች ከሕዝብ ጎን እንደነበሩም ታውቋል፡፡ ከቀኑ በስምንት ሰአት ሰልፉ ተጠናቋል፡፡ 


ጋይንት፡ የነፋስ መውጫ ከተማ ዛሬ ከዝናብ ጋር ተጋድሎዋን በጠዋት ነበር የጀመረችው፡፡ ነፋስ መውጫ ዐማሮች ትናንት የታሰሩ ዐማሮችን አስፈትተው ንብረትነቱ የወያኔ የሆነን የእንጨት ክምር አቃጥለዋል፡፡ የክልሉ ፖሊስ አብሮ ለተጋድሎ መሠለፉን ብንሰማም በኋላ ላይ ቁጥራቸው ያልታወቀ ለተጋድሎ የወጡ ወጣቶች መሰዋታቸው ተነግሯል፡፡ ዜናውን ያጠናቀረው ስንት ሰዎች መስዋት እንደሆኑ ሊያወቅ አልቻለም፡፡

ደም ሳይፈስ ስርየት የለም! –ያሬድ በላይነህ ከ ብራሰልስ

$
0
0

Bale Robe 3

በእምነት ፍርሃት አንገቴን ቀብሬ እሰማው ከነበረው የሰንበት ስብከት ውስጥ አንድ ሃይለ ቃል ጎንትላ አነቃችኝ።”ደም ካልፈሰሰ ስርየት የለም” የምትል ጠጣር ቃል።ይህች ቃል እንደጥቅምት ብርድ ውስጤ ገብታ ልታንዘፈዝፈኝ ቃጣት።በመንፈሳዊው ምኩራብ ስር ቁጭ ብዬ ስጋዬ ተጎልቶ መንፈሴ ጸጥ ያለውን አዳራሽ ለቆ ወጣ።ቼበለው የሃሙሱ ፈረስ ነው ያለችው ዘፋኟ? ቼ ብዬ ሄድኩኝ ወደ ሰሜኑ የሃገራችን ክፍል የወልቃይትን የማንነት ጥያቄ ተቆናጦ የሩብ ዘመን የዝምታ እልፍኝን ሰብሮ ከወጣ የህዝቤ መንፈስ ጋር ልገናኝ።በእነ ወልቃይት ጠገዴ፣ጸለምት አርማጭሆ የጥንቱ የበጌምድር ጎንደር መንደር የጥንቶቹ ጀግኖች አናብስት መንፈስ በዚህ ትውልድ ደም ውስጥ ሲሯሯጥ ታየኝ።የዘረኞችን፣የጎጠኞችን ድንኳን ከስሩ ነቅሎ ሊጥል እንቢኝ ለሃገሬ እንቢኝ ለነጻነቴ ብሎ ሲወጣ ታየኝ።የዛ የቋራው አንበሳ የመይሳው ካሳ መንፈስ ቀስቅሶት የመከራውን ቀንበር ከጫንቃው አውርዶ ሊጥል ተማምሎ የወጣ ህዝብ ድምጽ በጎንደር አደባባዮች ላይ ሲያስገመግም ተሰማኝ።

በረጅሙ ተነፈስኩ የጎንደሩ የህዝብ ማእበል የጨቋኞችን አንገት አስደፍቶ አፈሙዛቸውን እንደሽመል አንከርፈው ሊውጣቸው የቀረበውን አይቀሬውን የህዝብ ቁጣ የሚጋፈጡበት የምጥ ቀን መድረሱን ሲመለከቱ ታየኝ።ሰልፍ ባዩ ቁጥር ንጹሃንን ለመቅጥፍ ቃታ ለመሳብ ይፈጥን የነበረ የገዳዮች ጣት አርፎ መቀመጡ ደነቀኝ።እነዛ ያለርህራሄ ቆመጥና ጥይትን ያዘንቡ የነበሩ እጆች ምን አዚም አግኝቷቸው ይሆን እንዲህ ደርቀው የቀሩት ስል ራሴን ጠየኩ።ላለፉት ሃያ አምስት አመታት በግድ ሊያጠልቁልን የሞከሩት የዘር ቡልኮ ተቀዳዶ በጎንደር አደባባዮች ላይ ነትቦ ተበጣጥሶ ሲወድቅ ታየኝ።”አረ ጥራኝ ጫካው አረ ጥራኝ ዱሩ ላንተም ይሻልሃል ብቻ ከማደሩ” እያለ ድንበር ተሻግረው ደጁን የረገጡትን ወራሪዎች ሲያርበደብድ የነበረ ያ የፋኖዎች የአልገዛም ባዮች መንፈስ በጎንደር ሰማይ ስር ዳግም ነግሶ ሳየው ኩራት ነገር ተሰማኝ።

ከፋፍለው ለመግዛት እንዲያመቻቸው ከኢትዮጲያዊነት ማማ አውርደው የጎጥ ስርቻ ስር የወተፉንን እኝህን የእፉኝት ልጆችን እስከመጨረሻው ሊጋፈጣቸው የወጣውን ህዝብ በምናቤ መልሼ አየሁት።ዘረኝነት በቃኝ፣ስደት በቃኝ፣ድህነት በቃኝ ብሄራዊ ውርደት መሸከም በቃኝ የሚል የብዙሃን የሃገሬ ህዝቦች ድምጽ ከየፈፋው ሲሰማ በብሄራዊ እንቢተኝነት የእብሪተኞችን ቅጥር ሲነቀንቅ ታየኝ።በኦሮሚያ የተለኮሰው የመብት ትግል አድማሱን አስፍቶ ወደሰሜን ተራሮች አናት ሲንጠራራ በጨቋኞቹ የእብሪት ልሳን አከርካሪውን ሰብረን ቀብረነዋል የተባለው አማራ ማንነቴን መልሱ፣የወገኖቼ የኦሮሞዎች ሞት የኔም ሞት ነው፣የፈሰሰው ደማቸው የኔም ደም ነው በማለት የዘረኝነት እርሿቸውን መልሶ የጨቋኞቹ አይን ላይ ሲደፋ ታየኝ።ከወደምስራቅ ኢትዮጵያም በአወዳይ አመጹ ሲቀጣጠል አሁንም በመሰዊያው ላይ የንጹሃን ፍትህን ጠያቂ ኢትዮጵያውያን ደም ሲፈስ ታየኝ።

የመብት ጩኸት፣ህዝባዊ እንቢተኝነት በቃኝ የሚል የተጨቋኞች የጋራ ድምጽ፣በግፈኞች አረር የሚፈስ የእንቢ ባዮች ደም ድምጽ ወደጸባኦት ሲጮህ ተሰማኝ።እውነት ነው “ደም ካልፈሰሰ ስርየት የለም” ነጻነት ካለመስዋእትነት አትገኝም።ካለትግል ድል የለም።ማንም ነጻነትን በወርቅ ዋንጫ ከጨቋኞች እጅ በስጦታ ተችሮ አያውቅም ከጨቋኞቹ የብረት መዳፍ በሃይል ፈልቅቆ ይወስዳታል እንጂ።መንፈሴ አላረፈም ይህ እንቢታ የእሩብ ዘመንን ቀንበር ሲሰብር፣የግፈኞችን የእብሪት ግንብ ሲነቀንቅ፣ለነጻነት ሲሉ በግፍ የታሰሩትን እግረሙቅ ሲፈታ ታየኝ።እስከመቼ የጥቂቶች የበላይነት፣እስከመቼ በሃገር ባይተዋርነት፣እስከመቼ ስደትና ጉስቁልና እስከመቼ የዘረኞች የእብሪት አገዛዝ ተጭኖብን መንፈሴና ነፍሴ አላረፉም ዳግም በኦሮምያ እንቢተኝነት፣በአማራ፣በደቡብ፣በጋምቤላ… ይህ ትግል አይቆምም አልኩ ለራሴ የጭቆና ቀንበር ሳይሰበር፣እብሪተኞች ሳይንበረከኩ፣የህግ የበላይነት በሃገሬ ምድር ሳይሰፍን የለም…አይሆንም…አልኩ ለራሴ።መንፈሴ የትግሉን ጎራ አዳርሶ በድን ስጋዬ ወደተወዘፈበት የሰንበት ምኩራብ ስመለስ ካህኑ”ደሙ ስርየትን ሞቱም ትንሳኤን ያመጣል እስቲ ተመልከቱ ዛሬ በቀራንዮ ተራራ ላይ የመስዋእቱ የድል ታሪክ እንጂ ሽንፈት አይታወጅም በጎልጎታ ትንሳኤ እንጂ ሞት አይነገርም”ሲሉ እውነት ነው አባ አልኩኝ እውነት ነው ዛሬ ህዝቤ የግፍ አገዛዝ በቃኝ ብሎ ከመሰዊያው ላይ ቆሟል ጨቋኞችን ሊፋለም፣የግፍ ቀንበሩ አሽቀንጥሮ ሊጥል፣ረሃቡን፣ስደቱን የዘመናት ጉስቁልናውን ጥሎ በትግሉ ነጻ ሊወጣ አሻፈረኝ ብሏል።አዎ ዛሬ ትንሳኤ ቀርቧል የፈሰሰው የብዙሃን የሃገሬ ልጆች ደም ስርየትን ሊያመጣ ቀርቧል።ሁሉም ተባብሮ የሚቆምበት የጎጠኞችን እግረሙቅ ሰብሮ የሚወጣበት የድል ቀን ቀርቧል።ሃገር ውስጥ ያለው ሰላማዊ ትግሉን በእንቢተኝነት ገፍቶ የዚህን አጥፊ ስርአት ግብአት ሊያፋጥን፣በውጭ ያለውም ስደተኛ የዚህ ትግል አጋርነቱን በተግባር የሚያረጋግጥበት፣ስደቱ የሚቆምበትን ቀን እውን ለማድረግ ሳይከፋፈል በጋራ የሚቆምበት የድል አጥቢያ ላይ ነው ያለነው።

በጥቃቅን አጀንዳዎች ተለያይቶ ለስርአቱ የመከፋፈል ሴራ እጅ ሰጥቶ የሃገሩን ጉዳይ ችላ የሚልበት ሁኔታ መቆም አለበት።ካለበለዚያ የዲያስፖራው የስደት በሰው ሃገር የባይተዋርነት ህይወት ማብቂያ አይኖረውም።ጭቆና የወለደው ድህነት፣ረሃብና ስደት በቃ ሊባል ይገባል በጋራ በመቆም። የካህኑ ስብከት አብቅቶ የትንሳኤ መዝሙር ሲያስተጋባ መንፈሴ ከመነነበት የሃሳብ አለም ነቃ።ደም ሳይፈስ ስርየት ወይም ፈውስ የለም በሚለው የስብከት ጀልባ ተሳፍሬ ከቀዘፍኩበት የሃሳብ አለም የመለሰኝ የትንሳኤው የድል መዝሙር የሃገሬ ትንሳኤ መቅረቡን አሳየኝ ልቤ የሃሴት ድቤውን እየደለቀ እግሬ የቤተክርስትያኑን አጸድ ለቆ ወጣ።መንፈሴ ግን እንደ ግብጹ ታህሪር አደባባይ በመጥለቅለቅ ላይ ያሉትን የሃገሬ የብሶት አንባዎችን ሊቀላቀል ነጎደ።የብዙሃንን ህዝብ አመጽ ሊገቱ ያልቻሉት የሙባረክ ታማኞች ግመላቸውን እየጋለቡ ህዝቡን በጅራፍ እየገረፉ ሊበትኑ ሲባክኑ ህዝቡ ከግመላቸው ላይ እየገለበጠ ሲረመርማቸው በሩቁ ታየኝ።የኛዎቹም ከተቀመጡበት የእብሪት ማማ ላይ የሚገለበጡበት ቀን መቅረቡን እያየሁ እግሬ ወደመራኝ ተጓዝኩ።መንገዶች ሁሉ ወደ ሃገሬ የብሶት አደባባዮች፣የእንቢታ የአልገዛም ባይነት አንባዎች ያመራሉና ካለጥርጥር ጉዞዬ ወደ ድል ጎዳና ነው።የታሉ እኒያ ተርብ የሃገሬ ልጆች የታሉ እኒያ የጠባቦችን የዘር ጥብቆ ለባለቤቶቹ ወርውረው የሙስሊም ኮሚቴዎች ነጻ ይውጡ፣እነበቀለ ገርባ የነጻነት ድምጽ የሆኑን ነጻ ይውጡ በማለት የከፋፋዮችን ወገብ በድንጋጤ ከፍለው የጣሉ አንበሶች?የታሉ እኒያ ሞት እና እስራት ያልፈታቸው ሌንጫ ኦሮሚያ የኦሮምያ አንበሶች የገዳዮችን የእብሪት ክንድ የሰበሩ በሞታቸው የሃገር ትንሳኤን እያቀረቡ ያሉ ወገኖቼ፣የታሉ እነዛስ ከባህር ማዶ ሆነው የውጩ አለም ምቾትና የሩጫ ህይወት ሳይገታቸው ለታፈነው ድምጽ የሆኑት ስደተኛ ወገኖቼ፣በዚ ወሳኝ የቁርጥ ቀን ላይ የተገፊዎች የድረሱልን ጩኸት ሊቀሰቅሳቸው ይገባል።ጥሩልኝ የሃገሬን ልጆች እስከመቼ የመከራን ቀንበር ሸሽተን ተሰደን እናመልጠዋለን።ጭቆናን በተባበረ ክንድ ታግሎ የመጣያው የድል ቀን ቀርቧል እኔ መንፈሴም እግሬም ወደ ሃገሬ አደባባዮች ነው እንደህዝቤ እናንተም ተከተሉኝ በውጭም በውስጥም ያላችሁ የሃገሬ ልጆች።

06/8/2016
ያሬድ በላይነህ ከ ብራሰልስ

የፃድቃን ገብረተንሣይ፤ የሙታን ኑዛዜ፣ –ተክሌ የሻው

$
0
0

8/1/2016
tekele Yeshaw
ወያኔን አምጠው ከወለዱት አንዱ የሆነው ፃድቃን ገብረተንሣይ ሰሞኑን «የሃ[ሀ]ገራችን ፖለቲካዊ ሁኔታና የመፍትሔ ሃ[ሀ]ሳቦች» በሚል ርዕስ የሙታን ኑዛዜ ቃሉን ሰጥቷል። በዓለም ላይ ያሉ ሰዎች  ኑረው፣ የሕዎታቸው ፍጻሜ ሲቃረብ፣ ወይም በድንገት ሕይዎታችን ቢያልፍ በሚሉ ምክንያቶች ውስጥ ሲሆኑ፣ ሀብት፣ንብረታቸውን፣ አንዳንዶቹ ደግሞ የሥልጣን ተረካቢያቸውን (ወራሻቸውን) በቃል ወይም በጽሑፍ ይናዘዛሉ። በአገራችን በኢትዮጵያም ይህ እንደ ባህል ሆኖ ሲፈጸም ኖሯል። ወደፊትም ሕግን መሠረት በማድረግ እንደሚቀጥል ይታመናል። ኅብረተሰብ በመወለድና በመሞት ሂደት ውስጥ እስካለ ድረስ ይህ ምንጊዜም የሚቀጥል ነው። ለውጥ ካለ ሊኖር የሚችለው የአወራረሱ መንገድድና ስልት ብቻ ነው የሚሆነው።

በአገራችን በኢትዮጵያ እስከ ቅርብ ጊዜ ድርስ ኑዛዜ የሚጸፈመው፣ ተናዛዡ፣ በፀና ታሞ፣ በሕይዎት የመቆየቱ ጉዳይ አጠያያቂ ደረጃ ላይ ሲደርስ  እንደሆነ ይታወቃል። አሁን አሁን ግን ትውልዱ ከልማዳዊ አሠራር እየወጣ፣ በዕውቀትና በሕግ መመራት በመጀመሩ፣ ውርስም  በወራሾች መካከል አጨቃጫቂ እየሆነ በመምጣቱ፣አውራሾች የጤንነታቸው ሁኔታና የማገናዘብ አቅማቸው ጥያቄ ውስጥ ሳይገባ፣ የማውረስ ልምድ መጀመሩ ይታወቃል። ባህላዊ አወራረሱ፣ በእያንዳንዱ ተናዛዥ የነፍስ  አባት አማካኝነት፣ የተናዛዡ ሰው የቅርብ ሰዎች የሆኑ ሽማግሌዎች በተገኙበት ፣በከፍተኛ ሚስጢር የሚደርግ እንደሆነ ይታወቃል። ኑዛዜ የሙት ቃል በመሆኑ ተከባሪነቱ ከሞራልና ከሃይማኖት አንፃር ከፍተኛ እንደሆነ ይታመናል። ይህ ግን ተፈጻሚ የሚሆነው፣ ንዝ ተቀባዮቹ ከፍተኛ የሆነ የሞራል ብቃትና ደረጃ የጨበጡ፣ የጠነከረ የሃይማኖት ፍቅር ያላቸው የሆኑና የተናዛዦቹን ስም በክፉ አናስጠራም ብለው የሚያምኑ ከሆነ ብቻ ነው። ከሁሉም በላይ የተናዛዡ ሀሳብ የጸና የሚሆነው፣ በሚናዘዝበት ወቅት የነበረው የማመዛዘን ብቃት የተዛባ አለመሆን፣ የአናዛዦቹ  በንዝ ተቀባዮቹ ላይ ያላቸው ታማኒነት ከፍተኛ መሆንን ይጠይቃል። እነዚህ ሁኔታዎች አልተሟሉም ብሎ ያሰበና የገመተ የንዝ ተቀባይ፣ ኑዛዜውን አልቀበልም በማለት ኑዛዜውን ውድቅ ያደርገዋል። ይህም ክርክርና ብጥብጥ ይጋብዛል። ትውልዱን ሆድና ጀርባ ያደርጋል። አልፎ አልፎም ደም ያቃባል።  ተራውን ቤተሰባዊ ኑዛዜ ትተን፣ ታላቆቹን የሥልጣን ሽግግር ኑዛዜዎችን ስናጤን፣ የምንመለከተው ይኸንኑ ነው። ይህን በተጨባጭ ምሳሌ እንፈትሸው።

በ1880-81 ላይ ዐፄ ዮሐንስ 4ኛ፣ ከድርቡሾች ጋር መተማ ሲዋጉ፣ በጽኑ እንደቆሰሉና መትረፍ እንደማይችሉ ሲረዱ፣ መኳንንቶቻቸውን ሰብስበው፣ የአልጋ ወራሼ ራስ መንገሻ ነውና እርሱን ተከተሉ ብለው ተናዘዙ። ይህ ኑዛዜ ግን፣ ከ1857 እስከ 1874 ዓም ድረስ «የኢትዮጵያ ንጉሠነገሥት ወአዳል ወጋ ጋላ» የሚል ማኅተም አሳትመው ሲንቀሳቀሱ ለቆዩት፣ በኋላም በ1874 ዓም ልቼ ላይ ከዐፄ ዮሐንስ ጋር ባደረጉት ስምምነት፣ ለጊዜው የሸዋ ንጉሥ እንዲሆኑ፣ ንጉሠ ነግሥትነቱ ለዮሐንስ እንዲሆን፣ ከእርሳቸው ሕልፈት በኋላ ምኒልክ እንዲነግሡ፣ ለዚህም ሲባል ተከታዮቹ ነጋሢዎች ከዮሐንስና ከምኒልክ ዘር እንዳይወጣ ልጆቻቸውን አርኣያ ዮሐንስንና ዘውዲቱ ምኒልክን ማጋባታቸው ይታወቃል። ይህን ውልና ቃል በመዘንጋት ወይም በሌላ ምክንያት ዐፄ ዮሐንስ  «ወራሼ መንገሻ ነው» ማለታቸው፣የልቼን ስምምነት ለተዋዋሉት ንጉሥ ምኒልክ የሚዋጥ አልሆነም። በሌላ በኩል፣ ምኒልክ ከቀዳማዊ ምኒልክ ሲወርድ ሲዋረድ ከመጣው የነጋሢ ትውልድ የሚወለዱ፣ የንጉሥ ሣህለሥላሴ የልጅ ልጅ በመሆናቸው፣ የእርሳቸው ንግሥና የዘመኑ የሕጎች ሁሉ የበላይ የሆነው ፍታነገሥት የሚቀበለው፣ በሕዝቡም ዘንድ ታማኒነትና ተቀባይነት ያለው ስለነበር የዮሐንስ ኑዛዜ ተፈጻሚ የሚሆንበት ሁኔታ አልነበረም። ከዚሁ ጋር በተጓዳኝ፣ ምኒልክ ከ1857 ዓም ጀምሮ ለዚህ ዙፋን ኃይላቸውን ሲያደራጁና አቅማቸውን ሲፈትሹ መኖራቸው እየታወቀ፣ ንዛዜውን ወደው ይቀበሉታል ለማለት የሚቻል አይደለም። የሆነውም ይኸው ነው።

ምኒልክ ኑዛዜውን ባለመቀበል «ሕጋዊ  የዙፋኑ ወራሽ እኔ ነኝ፣ የልቼው ስምምነትም ሥልጣኑን የሚሰጠው ለኔ ነው» ብለው ተነሱ።  ይህን በኃይል የሚቃወም ካለም፣ አለሁ! ብለው ጦራቸውን ሰብቀው ትግራይ ገቡ። የዮሐንስ መኳንንቶች አቅማቸውን መዝነው ለምኒልክ አደሩ። የዐፄ ዮሐንስ ኑዛዜ አስከባሪ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊና ወታደራዊ ኃይል ስላልነበረው ፣ተራ ኑዛዜ ሆኖ መቅረቱን ታሪካችን ይነግረናል። ኑዛዜው አደረገ የምነለው ነገር ቢኖር፣ አንደኛው ነገር፣ የመንገሻን ልብ በማሻከር  በምኒልክ አገዛዝ ላይ ለሦስት ተከታታይ ጊዜአቶች እንዲያምጹና ለእስራት እንዲዳረጉ ማድረጉ አንዱ ነው። ሁለተኛው የወያኔ ትውልድ ሥልጣናችን በምኒልክ ተነጠቅን ብሎ የትግራይን ሕዝብ በዐማራ ነገድ ላይ በጠላትነት እንዲሰለፍ ያበረከተው የፕሮፓጋንዳ መሣሪያ መሆኑ ነው።

በተመሳሳይ ሁኔታ ፤ዐፄ ምኒልክ በ1906ዓም ሕመመቸው ጠንቶ፣ የአልጋ ቁራኛ ሲሆኑ፣ ወጣቱን የልጅ ልጃቸውን የዙፋናቸው ወራሽ እንዲሆን፣ ተናዘዙ። ንዙን ግን ፣ንዝ ተቀባዩ ከዕድሜ ለጋነት ጋር ተያይዞ፣ በተከተለው የአገዛዝ ዘይቤ ከምኒልክ ያፈነገጠ መሆን ጋር ተያይዞ፣ ከወቅቱ ሥልጣን ተሻሚዎች በተከፈተበት ፕሮፓጋንዳ፣ የምኒልክን ኑዛዜ የተቀበሉት የቤተክህነት አባቶችና የምኒልክ መሣፍንቶችና መኳንቶች፣ የኑዛዜውን ቃል ሽረው፣ ልጃቸውን ዘውዲቱን ንግሥተ ነገሥታት ብለው በዙፋኑ በማስቀመጥ፣ የወቅቱን ደጃዝማች ተፈሪ መኮንን ንጉሥ ብለው ባለሙሉ ሥልጣን እንደራሴ በማድረግ ለሥልጣን እንዳበቁ ይታወቃል።

የሁለቱ ንጉሦች ኑዛዜዎች በሕይዎታቸው መጨረሻ ላይ ፣ንዝ ተቀባዩ ባላደራም ሆነ፣ የንዝ ተቀባዩን ፍላጎትና ዓላማ ተሸካሚ የሆነውን የሕዝብ ፍላጎት ያላገናዘቡ፣ ንዞቹ ሲደረጉ ከተለያየ አቅጣጫ ያልታዩ፣ ሊከተሉ የሚችሉ ሁኔታዎችን ግንዛቤ ያላስገቡ፣ በሞራልና በሃይማኖት ላይ የተንጠለጠሉ በመሆናቸው፣ የሙታኖቹ ቃሎች/ኑዛዜዎች በሥራ ሳይውሉ መቅረታቸውን እንገነዘባለን። ንዞቹ በተናዛዦቹ ሕይዎት ፍፃሜ ላይ የተሰጡ፣ ሞራልና ሃይማኖት እንጂ፣ ሌላ አስገዳጅ ኃይል ያልነበራቸው በመሆኑ፣ በባለኃይሎች ሳይፈጸሙ ቀርተዋል። ተናዛዦቹ ግን፣ የተመኙትን ለታሪክም ቢሆን፣ የፈለጉትንና የተመኙትን ተናግረው አልፈዋል።

ስለንዝ ይህን ሁሉ ለማለት የወደደኩት፣ ሰሞኑን ፃድቃን ገብረተንሣይ የተባለው የወያኔ ባለሥልጣን፣ከላይ በመግቢያው በተጠቀሰው ርዕስ የጻፈው ከኑዛዜ ቃል አልፎ፣ የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ ችግር የማይፈታ፣ ግን ወያኔ ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትን፣ የዐማራውን ነድንና ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖትን ፈጽሞ ለማጥፋት የጀመረውን የጥፋት ጉዞ አጠናክሮ እንዲቀጥል «ጊዜ እንስጠው» የሚል መልዕክት የያዘ ሰሚና አስፈጻሚ የሌለው የኑዛዜ ቃል በማንበቤ ነው።

ከዚህ ላይ አንባቢ እንዴት ሰሚና አስፈፃሚ የለውም? ብሎ ሊጠይቅ እንደሚችል መገመት ይቻላል። ሰሚ የለውም የተባለበት ምክንያት፣ ወያኔ፣ከደደቢት በረሃ እስከ ምኒልክ ቤተ መንግሥት ድረስ ባደረገው ጉዞ፣ ችግሮች በገጠሙት ቁጥር ቆዳውን እየቀያየር፣ ብይ ተጫዋቾች፣ «ሰይብል፣ ብከረባበስ» እንደሚሉት እየተንከረባበሰ ከዚህ የደረሰ በመሆኑ፣ የሕዝቡን አመኔታ ፈጽሞ ባጣበትና ፀረ-ወያኔ እንቅስቃሴው በመላ አገሪቱ እንደሰደድ እሳት በተቀጣጠለበት ወቅት የተደረገ ኑዛዜ በመሆኑ ነው። ሕዝባዊ ቁጣው ከከተማ እስከ ገጠር፣ ከመሀል እስከ ጠረፍ ገንፍሎ፣ ሕዝቡ ብሶቱን፣ በአደባባይ እያሰማ ነው። የወልቃይት የማንነት ጥያቄ ያስከተለው ሕዝባዊ ቁጣ በጎንደር አደባባይ ከወያኔ ዕውቅናና ፈቃድ ውጭ እንደ ሐምሌ ጎርፍ ገንፍሎ ወጥቶ ፍላጎቱን ገልጿል። በአዲስ አበባ የመስፋፋት ጥያቄ የአዲስ አበባና የአካባቢው ነዋሪ ወጣት፣ አቋሙንና ፍላጎቱን በግልጽ  አሳይቷል።  የወለጋ፣ የሐረር፣ የከፋ፣ የሸዋ፣ የወሎ፣ የጎንደር፣ የጎጃም፣  የሲዳሞ፣ የባሌ፣ የኢሉባቡር እና የጋሞጎፋ ነዋሪ ሕዝብ አቋሙን በተለያዩ ጊዜ በግልጽ አሳይቷል። ሕዝቡ እንድትናንቱ በወያኔ ተረግጦ ለመገዛት ፍላጎት የሌለው መሆኑን በአደባባይ አሳይቷል። በመሆኑም የወያኔን አገዛዝ ለማራዘም የሚደረግን የኑዛዜ ቃል፣ ሕዝቡ መስሚያ ጆሮ የለውም።

ወያኔ ፍላጎቱን ሲያስፈጽም የኖረው፣ በገነባው የስለላ መዋቅር፣ በዘር ላይ በመሠረተው የጦር ሠራዊት፤ ፍርድ ቤት፣ አቃቢ ሕግ፣ የአስፈጻሚ አካላት፣ በቋንቋ ላይ ለያያቶ ባደራጃቸው የዘር ድርጅቶች እንደሆነ ይታወቃል። እነዚህ ክፍሎች በአሁኑ ወቅት፣ ግማሾቹ አካላቸው በሥጋ፣ ኅሊናቸው በገንዘብ ታስሮ እንደድሮው ተራውጠው የወያኔን ፍላጎት ለማስፈጸም የሚችሉበት ወኔውም ሆነ፣ ጉልበቱ የላቸውም። ቱባ ባለሥልጣኖቹ  የሕዝቡን ቁጣ ፈርተው ሚስቶቻቸውንና ልጆቻቸውን ከአገር አስወጥተዋል። የቆሙት ባንድ እግራቸው ነው። ይህም በመሆኑ በሙሉ ልባቸው መስዋዕትነት ለሚጠይቀው ትግል ፈጽሞ ፈቃደኞች አይደሉም። ይህ የጎንደር እና «በኦሮሚያ ክልል» በተካሄደው ሕዝባዊ አመጽ አስፈጻሚ አካሎቹ እንደድሮው ገድለው፣ አስረውና አስፈራርተው አመጹን ማስቆም አለመቻላቸው፣ ባንፃሩ ከሕዝቡ ጎን መቆማቸው በግልጽ ተስተውሏል። ባንድ ቃል፣ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ፣ የትግሬ ወያኔዎች እንደጥንቱ መግዛት፣ መንዳትና መግድል የማይችሉበት፣ ተገዥዎች ደግሞ፣ እንደጥንቱ ተጨቁነውና ተረግጠው ለመገዛት ፈቃደኛ ያልሆኑበት አብዮታዊ ወቅት ላይ ያለች በመሆኑ፣ የፃድቃንን የሙታን ኑዛዜ የሚሰማ ጆሮም ሆነ፣ ኑዛዜውን የሚያስፈጽም ኃይል የለም። ይህን በተመለከተ ማለትም የወያኔ መንግሥት ተብየ የማፈኛና የመቆጣጠሪያ መዋቅር ሽባ መሆኑን ፃድቃን እንዲህ ሲል ውስጥ አዋቂነቱን ገልጿል።

«አሁን አገራችን ያለችበት ሁኔታ የህዝብ አመኔታ በመንግስት ላይ በጣም ዝቅተኛ የሆነበት፣ በህዝቦች መካከል ያለው መቀራረብና መዋደድ የቀነሰበት፣ጥላቻ እየበረታና በግልጽ እየተነገረ፣ የህዝቦች የእርስ በርስ መናቆር እንዳይመጣ የሚፈራበት ስለሆነም ውስጣዊ አንድነታችን በጣም የላላበት፣ የመንግስት መዋቅር የመፈጸም አቅሙ ደካማ የሆነበት፣ከዚህ የተነሳም ህዝቡ ተስፋ የቆረጠበት፣በየአካባቢው ፖለቲካዊ ችግሮች ሲነሱ በታጠቀ ሃይል (ፖሊስና መከላከያ) የሚፈታበት፣ህዝቡ አሁን የሚታየው ችግር ይፈታል፣ አይፈታም፣ እንዴት ይፈታል እያለ ከፍተኛ ጥርጣሬ ውስጥ  የገባበት ሁኔታ ውስጥ ነው ያለው።» በማለት የወያኔ አገዛዝ የመጨቆኛ ተቋሞች ሽባ መሆናቸውንና ሕዝቡ ለለውጥ መነሳሳቱን ሳይደብቅ፣ ግን ወያኔና ግብረ አበሮቹ በከፍተኛ ፍርሃት ውስጥ መሆናቸውን በፍርሃት ተውጦ ነግሮናል። ይህ ከፍተኛ ፍርሃት የወለደው የፃድቃን ኑዛዜም ግብ፣ ወያኔና ግብረ አበሮቹ ከሕዝብ የዘረፉትን ሀብትና ንብረት ተጠብቆ የሚዘልቁበት፣ በአገርና በሕዝብ ላይ ክህደት የፈጸሙ ወንጀለኞች ለፍርድ አደባባይ እንዳይቀርቡ፣ ለዚሁ መድህን ይሆናል ያለውን፣ ራሱ ጽፎ፣ሕዝብ አጸደቀው ያለውን  ሕገመንግሥት በሥራ ላይ ማዋል ያልቻለውን አገር አፍራና የችግሮች ሁሉ ምንጭ የሆነውን ሕገመንግሥት ተብየ እንጠብቀው ይለናል።

ፃድቃን ገብረተንሣይ በዚህ የሙታን የኑዛዜ ቃሉ ሊያስተላልፍ የፈለጋቸው መልዕክቶች የሚከተሉት ናቸው።

(1) ወያኔ በትጥቅ ትግሉ ዘመን አብዮታዊና ዴሞክራት እንደነበር፣ በሂደት ይህ አቋሙ መሸርሸሩን፤

(2) የወያኔ የትጥቅ ትግል መቋጫው«በሕዝብ የፀደቀው ሕገመንግሥት» መሆኑና፣ ይህ ሕገመንግሥትም ዲሞክራሲን፣ ዕኩልነትን፣ ነፃነት፣ አንድነትን የሚያረጋግጥ ፍቱን መሣሪያ እንደሆነ አምኖ፣ ግን በሂደት በመመሪያዎችና በፖሊሲዎች እየተሻረ፣ አገሪቱና ሕዝቡ አሁን ለሚገኙበት ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ መግባታቸውን፤

(3) አገሪቱና ሕዝቡን ከገቡበት ችግር መውጫው ብቸኛ መንገድ ሁሉም በኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ኃይሎች ተሰባስበው ሕገመንግሥቱና ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱ በሚፈቅደው መሠረት ችግሮቹን መፍታት እንደሚቻል እምነቱና ፍላጎቱ መሆኑን፤

(4) የትግራይ ሕዝብ ለወያኔ ሥልጣን መጨበጥ ባበረከተው ይህ ቀረሽ ያልተባለ ድጋፍና ለዚህ ውለታም ወያኔ ለአባላቱና ለደጋፊዎቹ የአገር ሀብት ዘርፈው እንዲበለጽጉ ያደረገው ድርጊት፣ በሌሎች ነገዶች ላይ ቅሬታና ምሬት ያስከተለና ይህን የትግራይ ሕዝብ የጥላቻና የመገለል ሰለባ እንደሆነ አምኖ፣ ሕዝባዊ አመፁ በዚህ ከቀጠለ በትግራይ ሕዝብ ላይ የሚከተለው ጉዳት ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል በመገመት፣ ይህ ጥፋት እንዳይከተል ተቃዋሚዎችን ለማለዘብ፣ የትግራይንም ሕዝብ ለማንቃት የተላለፈ  መልዕክት ነው። የመልዕክቶቹ ግብም፣ ወያኔ የዘረጋው የዘር ፖለቲካና በቋንቋ ላይ የተመሠረተው ፌደራሊዝም በወያኔ የበላይነት እንዲቀጥል፣ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን አፍራሽ የሆነውን ሕገመንግሥት  ተጠብቆ እንዲዘልቅ፣ ለዚህም ወያኔና የወያኔ ትውልድ የዚህ ባለውለታ ሆኖ እንዲቆጠር የሚፈልግ ነው። አገሪቱ ለገጠማት ችግር ብቸኛው መፍትሔ  ሕገ-መንግሥቱን በሥራ ላይ ማዋል  እንደሆነ ፣የአገሪቱን ብሔራዊ  ጥቅም፣ የሕዝቡን አንድነትና ተንቀሳቅሶ የመሥራት ነፃነት የገፈፈውን፣ አጥፊ ሕገመንግሥት መጠበቅ እንዳለበት እምነቱና ፍላጎቱ መሆኑን ሳያፍርና ሳይሸማቀቅ ነግሮናል። በዚህም የተነሳ በ20 ገጽ ጽሑፉ ውስጥ 60 ጊዜ ሕገ-መንግሥት የሚለውን ቃል ተጠቅሟል። እንዲህም ሲል የሕገ-መንግሥቱን ፍቱን መሣሪያነት ሊነግረን ሞክሯል። እንዲህም ይለናል፦

አንደኛ፦ «የትጥቅ ትግሉ ከተጠናቀቀ በኋላ ያኔ ሁኔታው በፈቀደው መሰረት በህዝብ ተሳትፎ ሕገ መንግስት አፅድቀን በዚህ ሕገመንግስት እየተመራን መጓዝ ከጀምርን ሁለት አስርት ዓመታት በላይ አስቆጥረናል።» (ስርዝ የተጨመረበት)

ማንም እንደሚያውቀው፣ ሂደቱም እንዳረጋገጠው ፃድቃን «በህዝብ ተሳትፎ ፀደቀ» ያለው ሕገመንግሥት፣ ሕዝብ የተቃወመው እንጂ፣ የተሳተፈበት አይደለም። ቢሳተፍበትማ ኖሮ፣ ይህ ሁሉ ተቃውሞ ከወያኔ ልደት እስከ ምንኩስና ዘመኑ ባልቀጠለ ነበር። በግልጽ እንደሚታወቀው፣ ለሽግግር ጊዜው ቻርተርና በኋላም ለሕገመንግሥት ተብየው መነሻ መሠረት የሆነው ሰነድ፣ ሻዕቢያ፣ ወያኔ እና ኦነግ ተሰኔ ላይ ተሰብስበው፣ የማዕከላዊ መንግሥት (ደርግን) ጥለው እንዴት ኢትዮጵያን በዘር ከፋፍለው እንደሚያስተዳድሩ፣ ኤርትራ በምን ሁኔታ መገንጠል እንደምትችልና ዕውቅና እንደሚሰጣት የተስማሙበት፣«የተሰኔ ማንፌስቶ» በመባል የሚታውቀው ሰነድ ነው። የዚህ ሰነድ አዘጋጅ ደግሞ የኦነጉ ሌንጮ ለታ እንደሆነ ራሱ በብዙኃን መገናኛ መሣሪያዎች ነግሮናል። ዕውነቱም ይኸው ነው። በዚህ ሰነድ ሕዝብ ያለመሳተፉን ያልህል፣ የሽግግር መንግሥቱም ቻርተር ሲጸድቅ፣በሻዕቢያ፣ በወያኔና በኦነግ ዕውቅናና ፈቃድ የተጣቸው የነገድ ነፃ አውጭነን ያሉ፣ ግለሰቦች የሰነዱን ጥቅምና ጉዳት፣ ወደፊት ሊያስከትል የሚችለውን ሳይመዝኑና ለሕዝብም ሳይቀርብ በሦስት ቀን ስብሰባ ጸደቀ የተባለ መሆኑ ይታወቃል። ይህ በሕዝብ ተሳትፎ ፀደቀ የሚያስብለው አንዳችም መሠረት የለውም። ከሁሉም በላይ ይህ የሽግግር ቻርተር ፀደቀ ሲባል፣ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ከ35% በላይ የሚሆነው የዐማራ ነገድ፣ በድርጅትም ሆነ በግለሰብ  በውሳኔው ላይ ለውጥ ማምጣት ባይችልም ለስም እንኳን ተወካይ አልነበረውም። በመሆኑም ቻርተሩ በዐማራው ነገድ ላይ ተገዶ የተጫነበት እንጂ፣ የፈቀደውና የተስማማበት አይደለም። ይህን ፃድቃን የኢትዮጵያን የሦስት ሺ ዘመን ታሪክ በመካድ በመቶ ዓመት እንደገደቡት፣ ካልካደ በቀር፣ ዐማራው ተወክሏል ሊል የሚችልበት ማስረጃ የለውም።

የሽግግር ጊዜ ተብየው ተጠናቆ፣ ሕገመንግሥት ተብየው ሲዘጋጅም ሆነ ሲፀድቅ ፣ የሕዝብ ተሳትፎ አልነበረም። የተደረገው፣ የወያኔ ፍላጎት የሆነው ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትን፣ የዐማራ ነገድንና ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ሃይማኖት ለማጥፋት ፍላጎት ያላቸው የነገድ ድርጅት አባሎች የመለስና የቡድኑ ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦች ተሰብስበው፣በኋላይ እንደታየው፣ ፃድቃንም እንዳመነው፣ በሥራ ላይ የማይውሉ፣ ግን ለወያኔ የምዕራባውያንን ድጋፍ ሊያስገኙ ይችላሉ የተባሉ፣ ኢትዮጵያ ቀደም ሲል የተቀበለቻቸውን የሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችና ነፃነቶችን የሕገመንግሥቱ አካል እንዲሆኑ በማድረግ፣ፀረ-ኢትዮጵያ አንድነት የሆኑ ግለሰቦች የተስማሙበት እንጂ፣ ሕገመንግሥቱ ለሕዝብ ቀርቦ ውይይትና ክርክር የተደረገበት አለመሆኑን ፃድቃን ይስተዋል አይባልም። ሕዝብማ ቢያጸድቀውና ቢስማማበት ኖሮ፣ ዛሬ ወያኔን ያራደው ሕዝባዊ አመጽ ሊቀሰቀስ ቀርቶ የሚታሰብ አልነበረም።

ሁለተኛ፦«— ይህ አሁን የምንገኝበት ፖለቲካዊ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ስለሆነ በሰለጠነ መንገድ ተወያይተን ከፍተኛ ጉዳት ከመድረሱ በፊት እንፍታው። ችግሩን ለመፍታት ደግሞ በኢህደአዴግና (በኢሕአዴግ ለማለት ይመስላል)  ድርጅቱ በሚመራቸው የመንግስት ይሁን የፖርቲ (የፓርቲ ለማለት ይመስላል) መዋቅሮች ታጥረን በምናደርገው እንቅስቃሴ ብቻ መፍትሄ ማምጣት አይቻልም። ከዚህ በላይ ከተጠቀሰው መዋቅር በተጨማሪም ከየፖርቲና (ከየፓርቲና ለማለት ይመስላል) የመንግስት መዋቅር ውጭ ያሉ ፖለቲካዊ ሃይሎችና ምዕላተ ህዝቡ በስፋትና በንቃት ሲሳተፍበት ነው በእርግጠኝነት ችግሩን መፍታት የሚቻለው ከሚል መነሻ ሃሳብ የሚነሳ ነው። ይህ ደግሞ በከፍተኛ የህዝቦች  መስዋዕትነትና ተሳትፎ የፀደቀውን ህገመንግስታችንን መሠረት አድርገን በህገመንግስቱ የተቀመጡትን ሰብአዊና(ስርዝ የተጨመረበት) ፖለቲካዊ መብቶችን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ በማድረግና በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ ፖለቲካዊ ሃይሎችም ያለምንም ተፅዕኖ ያልተገደበ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ አድርገው በመጨረሻም በገለልተኛ በዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ነፃ ዲሞክራሲያዊና ያለምንም ተፅዕኖ የተከናወነ ምርጫ መሆኑ ተረጋግጦ የተካሄደ ምርጫ የሚሰጠንን ውጤት ተቀብለን ለመጓዝ ቆርጠን ስንነሳ ነው በሚል አስተሳሰብ ላይ ያጠነጥናል።»

ይህን ዓይነት ጥሪ የተቃዋሚው ጎራ በተከታታይ ሲያቀርበው የነበረ ነው። «የአማራጭ ኃይሎች»፣ «ፓሪስ አንድና ሁለት»፣ «ቅንጅት»፣ «ኅብረት»፣ «መድረክ»፣ ወዘተ የተሰኙ ስብስቦች ላለፉት 25 ዓመታት ሳይታክቱ ሲያቀርቡት የነበረ ጥሪ ነው። ለነዚህ ጥሪዎች ፃድቃንን ጨምሮ የወያኔው ቡድን የሰጠው አዎንታዊ መልስ የለም። መልሱ «እኛ ትክክል ነን! ለኢትዮጵያ ሕዝብ ከእኛ የተሻለ፣ሀሳብም ዕውቀትም ያለው የለም» የሚል እንደነበር እናስታውሳለን። ፃድቃንም ዛሬ እርሱ እንደ አዲስ ላቀረባቸው ጥሪዎች፣  በግሉም ሆነ በቡድ  እንደዛሬው በግልጽ ሀሳቡን ሲሰጥ አልተደመጠም፤ አልታየም። ሆኖም« የናቁት ያስቀራል ራቁት» ነውና የሕዝቡ ትዕግሥት ተሟጦ፣ ግፉ ገደቡን ጥሶ ሲፈስ፣ ማዕበሉ ማንን ሊጠራርግ እንደሚችል፣ ከመሸም ቢሆን፣ የባነነው ፃድቃን፣ በተቀጣጠለው ሕዝባዊ ቋያ ላይ ውኃ ለማፍሰስ፣ ነባሩን የሕዝብ ጥያቄ፣ በማር ለውሶ፣ «ሕዝብ የተሳተፈበት» የሚለውን ሕገ አራዊት ሕገመንግሥት ነፍስ ዘርቶ፣ የወያኔን አገዛዝ ዕድሜ ለማራዘም የትብብር ጥሪ አቅርቧል። ጥሪው አዲስም ባይሆን፣ የወያኔው ከፍተኛ ባለሥልጣን፣ ያውም «ጦር ሠሪ» ከሚባሉት አንዱ የሆነው ፃድቃን የችግሩን መኖር ማመኑ በራሱ ትልቅ ነገር ነው። በዚህ ረገድ ለጻድቃን የሚቀርብለት ጥያቄ፣ ለችግሩ መፍቻ መሣሪያ እንዲሆን ያቀረበው «በሕዝብ ተሳትፎ የጸደቀ» የሚለው ሕገመንግሥት፣ ሕዝቡ የማያውቀው፣ የኛ ነው የሚሉትም ያላከበሩትና የማይገዙበት ስለሆነ፣ አሁን አገሪቱ ለገጠማት ችግር ዋናው የችግሯ ቋጠሮ ይኸው ሕገመንግሥት ተብየ የዘረጋው በነገድ ላይ የተመሠረተ ፌዴሬሽንና የሚመራበት የዘር ፖለቲካ ስለሆነ፣ የችግራችን መፍቻ አይሆንም የሚል ነው። የችግሮች አካል የሆነ፣ የመፍትሔ አካል ሊሆን አይችልምና የወያኔው ሕገመንግሥት አገሪቱ ለገጠሟት ዘርፈ ብዙ ችግሮች መፍቻ መሣሪያ አይሆንም የሚለው፣ በአንፃሩ የፈራቸው ችግሮች እውን እንዳይሆኑ ከፈለገና ካመነ፣ ብሔራዊ ዕርቅ የሚያወርድ፣ መሠረቱ ለሠፋና በሕዝቡ ቀጥተኛ ተሳትፎ ለሚጸድቅ ሕገመንግሥት ዝግጅትና ይህኑ ለሚያስፈጽም ሁሉንም የፖለቲካ ድርጅቶች ያሳተፈ የሽግግር መንግሥት የሚመሠረትበትን መንገድ ማመቻቸት እንዲቻል፣ የበኩሉን አዎንታዊ ተጽዕኖ በወያኔው አባሎች ላይ ለማሳደር የምትችለውን አድርግ ነው መባል ያለበት።

ሦስተኛ፦በአገሪቱ ውስጥ የተከሰተው ከፍተኛ ችግር መፍታት የሚቻለው«–ሃገር ወዳድ የሆኑ ፖለቲካዊ ሃይሎች በሚያማማቸው (በሚያስማማቸው ለማለት ይመስላል) ፖለቲካዊ መድረሻ ተገናኝተው በመጀመሪያ የሀገራችንን የራሳችንን ችግሮች ስናስወግድ ነው የሚል እምነት አለኝ። ይህንን ደግሞ ህገመንግስቱን መነሻ (ስርዝ የተጨመረበት) በማድረግ ሊጀመር ይችላል ብየ አስባለሁ።»

የአገሪቱ የፖለቲካ ድርጅቶች በሚያስማሙዋቸው መዳረሻዎች ላይ ተወያይተው የጋራ ውሣኔ ላይ ለመድረስ በቅድሚ መጫዎቻ ሜዳውን የተቆጣጠረው ወያኔ በሀሰት ከሶ ያሰራቸውን የፖለቲካ መሪዎች፣ ጋዜጠኞች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ግለሰቦችን በከፍተኛ ይቅርታ በነፃ መፍታት አለበት። ፃድቃን ያመናቸውን ሕገመንግሥቱን ሻሪ የሆኑ መመሪያዎችንና ፖሊሲዎችን በይፋ መሻር አለበት። የጠረሽብር ሕጉ፣ ሰዎችን በነፃ የመንወሳቀስና የመኖር ነፃነት የሚገፉ ደንቦችን ማንሳት አለበት። አገር እንዳይገቡና በነፃነት እንዳይንቀሳቀሱ ያገዳቸውን ድርጅቶችና ግለሰቦች ሕጋዊ ዋስትና ሰጥቶ ወደ አገር እንዲገቡ በግልጽ ማወጅ አለበት። ይህ በሌለበት ሁኔታ በጋራ ለመወያየትና የጋራ መፍትሔ ላይ መድረስ ስለማይቻል። ፃድቃን ይህን የቤት ሥራ ሠርቶ መድረኩ ለውይይት ሲመቻች፣ የሀሳብ የበላይነት ያለውና የሕዝቡን ዕውነተኛ ድጋፍ ያገኘ ድርጅት አገሪቱን ሊመራበት የሚችለው ሕጋዊ ሥርዓት ዘርግቶ ወደፊት መራመድ ይቻላል። ከዚህ ባለፈ የወያኔ ጊዜ መግዣና አፍኝ ሥርዓት መቀጠያ የሆነው ሀሳብ፣ ገዥ ሊሆን አይችልም።

አራተኛ፦ ፃድቃን በአገራችን የተከሰተው ዘርፈ ብዙ ችግር ለማለፍ ብዙ ፈተናዎችን ማለፍ ግድ እንደሚል ጠቅሶ፣ ችግሩን ለመፍታት ተጨባጭ ሁኔታውን አውቆ ፣ከዚሁ ሁኔታ ጋር «የተጣጣመ ፖሊሲና ስትራቴጂዎችን አውጥቶ ተግባራዊ ማድረግ ይገባል። ለዚህ ዋና መነሻ ሕገ መንግስት ነው ብየ አምናለሁ።» ይህን ሀሳቡን ሲያጠናክር ፃድቃን እንዲህ ይላል። « —የሃገራችንን ሁኔታ ያገናዘበ በማንኛውም ደረጃ በጣም ጥሩ ሊባል የሚችል ህገ መንግስት አለን። ይህ ሕገመንግስት ህዝቦች ፈቅደው እንዲመሩበት ያወጡት የሃገሪቱ የመጨረሻ ህግ ነው።» (ስርዝ የተጨመረበት) ይላል።

ይህ  አባባል ከክህደት ያለፈ ፍሬ ነገር የለውም። እንኳን ተቃዋሚው ወገን፣ ተራው ዜጋ ሊቀበለው የማይችል ተራ ቅጥፈት ነውየሀሳቡን አቀራረብና መዳረሻው ምን እንደሆነ በግልጽ ስለሚታይ፣ የሕዝቡን ቁጣ ከማባባስ ውጭ፣ አባባሉን የሚገዛው ቀርቶ፣ሊሰማው የሚፈልግ የለም። ግቡ ኢትዮጵያን ከገጠማት ችግር ለማውጣት ሳይሆን፣ ወያኔና ደጋፊዎቹን ከሚጠብቃቸው የሕዝብ ቁጣ ማውጫ፣ ከሕዝባዊ ማዕበል ማፈትለኪያ ስልት ስለሆነ፣ ሰሚ ጆሮ የለውም። ምክንያቱም በአገር አንድነትና ሉዐላዊነት፣ ብሔራዊ ጥቅምና ዳር ድንበር ላይ ክሕደት የፈጸሙ ቡድኖችና ግለሰቦች ለፍርድ ሳይቀርቡ፣ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን የገደሉ፤ ያፈናቀሉ፣ ያሰሩና ያሰቃዩ ወንጀለኞች ሳይጠየቁ፣ በዳይ ሳይክስ፣ ተበዳይ ሳይካስ፣ ከሁሉም በላይ የነዚህ ወንጀሎች ሁሉ መሣሪያ ሆኖ ያገለገለው ሕመንግሥት ይቀጥል ማለት የሕዝባዊ ተቃውሞውን ዓላማና ግብ ካለመረዳት ሳይሆን፣ ሆን ተብሎ ለወንጀለኞች መከታ ለመሆን የታሰበ በመሆኑ ሰሚ የለውም።

አምስተኛ፦ «ሕገመንግስቱ በህዝባዊ የትጥቅ ትግሉ ውስጥ አብዮታዊና ዴሞክራሲያዊ መንፈስ የተላበሰ ኢህአዴግ በሚመራው መንግስት እንዲኖር የሚፈለገውን የመንግስት አሰራርና ባህርይ መለኪያ (Standard) ይሆናል ብለን ያስቀመጥነው የትጥቅ ትግሉ ድሎች መቋጫ ነበር እላለሁ።»

ወያኔ የኢትዮጵያ ተማሪዎች እንቅስቃሴ አካል መሆኑ ይታወቃል። ማንም  እንደሚገነዘበው የ1960ቹ የኢትዮጵያ ተማሪዎች እንቅስቃሴ ግራዘመም ሶሻሊስታዊ እንጂ፣ ዲሞክራሲያዊ አለመሆኑ ግልጽ ነው። በመሠረቱ አብዮት የነበረን ማጥፋት፣ ማንነትን ማስለወጥና ማስካድ፣ የራስን ወርቅ መለያና መታወቂያ ጥሎ ፣ የሌሎችን መዳብ ማንነት መላበስ በመሆኑ፣ ከዲሞክራሲ ጋር የሚጣጣም አይደለም። ምክንያቱም ዲሞክራሲ በሂደት ፣ባለውና በነበረው መልካም ዕሴቶች ላይ ቀስ በቀስና ደረጃ በደረጃ እየተጨመረ በሕዝቡ ፍላጎትና ነፃ ውሣኔ የሚዳብር እንጂ፣ የተወሰኑ  እናውቅልሃለን በሚሉ ቡድኖች ከላይ የሚጫን አይደለም። የዲሞክራሲ ዋልታዎችም፣ የብዙኃን ውሳኔ ገዥነት፣ የጥቂቶች መብት ተከባሪነት፣ የሰብአዊና ዲሞክራዊያ መብቶች ደረጃ በደረጃ ተከባሪነት፣ መሪዎችን የመምረጥና የመመረጥ ነፃነት መረጋገጥ፣ የሕግ የበላይነት መስፈን፣ ሥልጣን የሕዝብ መሆንና ባለሥልጣኖች ለሕዝብ ተጠሪዎች መሆን፣ ወዘተ መሆን ናቸው። በዲሞክራሲ የሰዎች የማምለክ ነፃነት የተረጋገጠና የሃይማኖቶች ዕኩልነት ዕውን የሚሆንበት እንደሆነ ይታመናል። የመድብለ ፓርቲ ፖለቲካና የሰዎች የሀሳብ ነፃነት የተከበረበት ነው። በአጠቃላይ ሰብአዊነት ከፍተኛ ቦታ የተሰጠው አመለካከት ነው። እነዚህ መብቶች እንኳን በዘረኛው የወያኔ ድርጅት ቀርቶ በየትኞቹም የፖለቲካ ድርጅቶች ተግባራዊ ሆነው አያውቁም። የነበረው ዲሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት የሚባለው፣ ጠቅላላ አባላቶቹ መብትና ነፃነታቸውን «ማዕከላዊ ኮሚቴ» ለሚሉት የሚሰጡበት፣ ማዕከላዊ ኮሚቴ የሚባለው ደግሞ፣ ከአባላቱ ተሰጠኝ ያለውን መብትና ነፃነቶቹን «ለሥራ አስፈጻሚ »ለሚባሉት ከ7 እስከ 11 ለሚሆኑ ሰዎች የሚሰጡበት፣ ሥራ አስፈፃሚው በበኩሉ፣ ከማዕከላዊ ምክር ቤት ተሰጠኝ ያለውን መብትና ነፃነቱን ላንድ «ጸሐፊ ወይም ሊቀመንበር ወይም ሰብሳቢ» ለሚሉት የሰጡበት በመሆኑ፣ ምንጊዜም ቢሆን፣ በሕዝብ ስም የሚወሰኑ ውሣኔዎች የጠቅላላ አባላቱን አብዛኛውን ፍላጎት የሚወክሉ ሳይሆኑ፣ የሊቀመንበሩን ብቸኛ ፍላጎት የሚገልጽባቸው እንደሆነ ይታወቃል። በመሆኑም ወያኔ አብዮታዊ እንጂ፣ ዲሞክራት አልነበረም። ዲሞክራት ሆኖም አያውቅ። ሊሆንም ፍላጎት የለውም።

ከሁሉም በላይ ወያኔ ዘረኛ ከመሆኑም አልፎ ፀረ-ሃይማኖት እንደነበር፣በርሃ ሳሉም ሆነ በሥልጣን ላይ ሆነው፣ በክርስትናና በእስልምና ሃይማኖት ተካታዮችና ተቋሞች ላይ የሚፈጽሙት ግፍ በግልጽ እየታየ ነው። በባዶ ስድስት እስር ቤቶቻቸው ሰዎችን በቁመናቸው በመቅበር ያጠፉትን ሕዝብ ቁጥር የግፉ ተቃባይ ቤተሰቦችና የተቀበሩባቸው ቦታዎች ብቻ ናቸው የሚውቁት። ወያኔ ጠባብና ዘረኛ፣ ፀረዲሞክራሲና ፀረ-ብዙኃን አስተሳሰብ መሆኑን ከሚያመላክቱን ማስረጃዎች መካከል ኢሕአፓን ከአሲንባ ያስለቀቀበትና የትግራይ ነፃ አውጭ ድርጅት አባሎችን በስምምነት ስም በግፍ ያረደበት ሁኔታ አፍ አውጥተው የሚናገሩ ዘመን ተሻጋሪ ነቃሾች ናቸው።

ፃድቃን በሕዝብ ተሳትፎ ጸደቀ የሚለን ሕገመንግሥት፣ ቋሚ መሠረቱና ዋልታው ዲሞክራሲያዊ ሳይሆን፣ ዲሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ነው። ይህም በመሆኑ፣ ፀረ-ሕዝብና ፀረ-አገር ነው። ከሁሉም በላይ የአልባኒያው ኤንቨር ሆጃ (Enver Hoxha) ተከታይና አምላኪ የነበረው ወያኔ፣ ዲሞክራት ነበር ማለት ከማሳቅ አልፎ ያሳፍራል። የወያኔን ሕገመንግሥትም ሕዝቡ የሚጠላው በሚከተሉት ምክንያቶች ነው።

አንደኛ፦ ሕገመንግሥቱ ሕዝቡ የመከረበትና የተስማማበት አይደለም። በመሣሪያ ኃይል የተጫነበት ነው።

ሁለተኛ፦ አገሪቱን በነገድ ከፋፍሎ ለዘመናት በሥጋ ልደት፣ በደም ውሕደት፣ አንድ የሆነውን ሕዝብ በቋንቋ ከፋፍሎ ሆድና ጀርባ ከማድረግ አልፎ፣ ፃድቃን እንዳለው በሕዝቡ መካከል መራራቅና መነጣጠል የፈጠረ መሆኑ ነው።

ሦስተኛ፦ ሕገመንግሥቱ የዲሞክራሲያዊ ማዕከላዊነትን የውሣኔ አሰጣጥ በሕዝቡ ላይ የጫነ ኮሚኒስታዊ አሠራር በመሆኑ ነው። ስለሆነም በወያኔ የተዘጋጀው ሕገመንግሥት የምዕላተ ሕዝቡን ይሁንታና ፈቃድ ያላገኘ ብቻ ሳይሆን፣ ዲሞክራሲያዊ ማዕከላዊነትን ማለትም የግለሰቦችንና ያንድ ድርጅትን የበላይነት ያሰፈነ በመሆኑ መለወጥ ያለበት ነው። ዲሞክራሲያዊ ሕገመንግሥት በሕዝቡ ቀጥተኛ ተሳትፎ በግልጽ ውይይትና ክርክር መዘጋጀት አለበት። ይህ ካልሆን፣ ፃድቃን የፈራው የአንድ ነገድ ከምልዓተ ሕዝቡ መገለል የማይቀር መሆኑን መናገር ነቢይነትም ሆነ ክፉ አሳቢነት አይሆንም።

ስድስተኛ፦ ፃድቃን በትግሬ ወያኔ አገዛዝ ባለፉት 25 ዓመታት ለወያኔ ትውልድና ዘር በዘረፋና በንጥቂያ የተገኘውን ጥቅም  ምዕላተ ሕዝቡ የተጠቀመ ያስመሰሉትን የመንገዶችና የከተሞችን ዕድገት በማሳያነት በመጥቀስ፣ በእርሱ እይታ ችግር የሚለውን እንዲህ ይገልጸዋል። « በአጭር አነጋገር ዴሞክራሲያዊ ስርዓቱ እንዲሰፋ ይፈላጋል። ቢያንስ በሕገመንግስቱ ዕውቅና የተሰጣቸው መብቶች ሳይሸራረፉ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲሆኑ ይፈልጋል። ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ መንግስት እነዚህን በሕገ መንግስቱ እውቅና የተሰጣቸው መብቶች የሚገድቡ አሰራሮችና መመሪያዎች በማውጣት ዴሞክራሲያዊ ምህዳሩ እያጠበበው ይገኛል። ይህ ሁኔታ በሃገራችን ውስጥ ላለው ፖለቲካዊ ቀውስ አንድ ትልቅ ምክንያት ነው።» (ስርዝ የተጨመረበት)

ከዚህ ላይ ፃድቃን ከፍ ሲል ለመግለጽ እንደተሞከረው ከመሸ ቢሆንም፣ የወያኔ አገዛዝ፣ ፀረ-ሕዝብ ነው የምንለው፣ ራሱ ላጸደቀው ሕገ መንግሥት ተገዥ አለመሆኑ አንዱ የሆነውን ማመኑ ነው። እንዳለውም ወያኔ በራሱ ሕገ መንግሥት አለመገዛቱ የችግሩ አንዱ አካል ቢሆንም፣ የችግሮቹ ዋነኛ ምንጭ ግን ሕገመንግሥቱና በርሱ ላይ የተመሠረተው የአገዛዝ ሥርዓት ወይም ዘይቤ ነው። የዚህ ችግር መፍትሔውም የችግሩን ምንጭ ማድረቅና ሥርዓቱን ከነአገዛዙ ማስወገድ ነው። ፃድቃን ለወያኔ አገዛዝ መቀጠል ባለው ከፍተኛ ፍላጎት፣ ወያኔ ሆን ብሎና አስቦ ክርችም አድርጎ የዘጋውን የዲሞክራሲ ምኅዳር፣ «እያጠበበው ይገኛል» በሚል ይገልጸዋል። መጀመሪያውኑ  ወያኔ ዴሞክራት አልነበረም። የዲሞክራሲም ምኅዳር አልከፈተም። ያልተከፈተና ያልነበረ እንዴት እየጠበበ መጣ ይባላል? ዞሮ ዞሮ የፃድቃን ጥሪ ልንጠፋ ነውና ከመጥፋታችን በፊት መውጫ ቀዳዳ እንፈልግ፣ መውጫውም የሞትንለት፣ የታገልንለት፣ በትግላችን ያገኘነው ሕገመንግሥት በሥራ ላይ ይዋል የሚል፣ ተሂዶበት ውጤት ባላስገኘ መንገድ፣ ደጋግመን ለ25 ዓመታት እንድንላቅጥበት የቀረበ ፣እናንተ ሙቱ፣ ተራቡ፣ ተሰደዱ፣ ተሰቃዩ፤ እኛ እንኑር፣ እንብላ፣ እንበልጽግ፣ ጠያቂም አይኑረን፣ እንዳሻን ኢትዮጵያና ሀብቷን እንጠቀምባት የሚል «የጅል ዘፈን ሁልጊዜ አበባዬ» አይነት ጥሪ ነው።

ሰባተኛ ፦ ፃድቃን ወያኔ የምዕራባውያንን ለጋሺና አበዳሪ መንግሥታት ልብ ለማማለል ፣ ከሁሉም በላይ የነፃ ገብያና የዲሞክራሲ ፊታውራሪ ነኝ የሚለውን የምዕራቡን ዓለም ሠፊና ያልተቋረጥ ድጋፍ ለማግኘት ሲል፣ በሕገመንግሥቱ የሸነቆራቸውን አንቀፆች ተግባራዊ አለማድረጉን ጠቅሶ፣ ለዚህም  ምክንያቱ እርስ በርሳቸው የሚደጋገፉ ምክንያቶች እንዳሉና እነዚህም «የፖለቲካ ስርዓቱ እና መንግሥት በኢኮኖሚው ውስጥ ያለው ወሳኝ ድርሻ» እንደሆኑ ገልጿል።

በፃድቃን እምነት የፖለቲካ ስርዓቱ ዋነኛ ችግር በገዥው ፓርቲና በመንግስት መካከል ያለው ግንኙነት ፈጽሞ ጠፍቶ፣ ገዥው ፓርቲና መንግሥት አንድ ከመሆናቸው የሚመነጭ እንደሆነ ይነግረናል። በተመሳሳይ ሁኔታ፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴና ታሪካዊ አስተዳደጉ የዜጎች በመንግሥት ላይ ተፅዕኖ የመፍጠር አቅም የሌለው መንግሥት፣ በአጠቃላይ የሥራ አስፈጻሚው ክፍል ደግሞ በተለይ የፈለገውንና ያመነበትን ለማድረግ የሚከለክለው የሌለበት ሁኔታ እንዳለ ያምናል። ይህንም እምነቱን ሲያጠናክር እንዲህ ይላል፤ «የስራ አስፈጻሚው አካል የፈለገውን ነገር ከማድረግ የሚያግደው ተቆጣጣሪ አካል የለም።» በማለት ወያኔ ያሻውን ያደረገ እና እያደረገም እንደሆነ ነግሮናል። ይህ ደረቅ ሐቅ ነው።

የየአካባቢው ሕዝባዊ አመፆች መነሻና መዳረሻም ይኸው ወያኔ ያላንዳች ተቆጣጣሪና ሀግ ባይ አገርና ሕዝብ የማጥፋት ድርጊቱ ከገደብ አልፎ በመፍሰሱ ምክንያት ነው። ፃድቃን ያልተገነዘበውና ሊገነዘበውም የማይፈልገው ጉዳይ፣ በእርሱ አገላለጽ «የፖለቲካ ስርዓቱና መንግሥት በኢኮኖሚው ውስጥ ያለው ወሳኝ ድርሻ» የመያዝ ጉዳይ በድንገት ወይም በሂደት የተፈጠረ አለመሆኑን ነው። ይህ በተከታታይ ድርቅና ድርቁ ባስከተለው ረሃብና መሰደድ ተማረው መሣሪያ መልጠው ዱር ቤቴ ያለው የወያኔ ትውልድ፣ የዘመናት ምኞቱን ዕውን ለማድረግ፣ ይህ ወያኔ መራሹ መንግሥት በኢኮኖሚው ላይ የበላይነቱን መያዝ የማይታለፍ እንደሆነ አምኖ በዕቅድ የተንቀሳቀሰ ነው። ዛሬ መቀሌ ውስጥ ሕዝቡ «አፓርታይድ» ብሎ የሰየማቸውን ሰማይ ጠቀስ ፎቆችና የተንጣለሉ ቪላዎች የገነቡ፣ ሰባራ ጫጩት ከቤተሰብ ሳይወርሱ ቢሊየነሮችና ሚሊየኖሮች የሆኑ፣ አዲስ አበባ ቦሌ ክፈለ ከተማ «ሕዝቡ መቀሌ» ብሎ በሰየመው አካባቢ በተገነቡ ፎቆችና ቪላዎች፣ የሚሽሞነሞኑ ሰዎች፣ ካለዚህ ቁርኝት ሊታሰቡ የሚችሉ አይሆኑም።  በሽግግር ወቅት ተብየው «በጦርነት ለተጎዱ ክልሎች ቅድሚያ ልማት ይሰጥ» የሚል ሕግ አውጥቶ ትግራይ በአገሪቱ ሁለንተናዊ ሀብት ለ8 ተከታታይ ዓመታት እንድትገነባና ኢኮኖሚዋ ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ እንዲሸጋገር የተደረገው በዚሁ በፖለቲካ ሥርዓቱ ውስጥ መንግሥት ተብየው  በኢኮኖሚው ውስጥ የበላይነቱን እንዲይዝ በመደረጉ እንደሆነ ግልጽ ነው። ይህ ደግሞ ታስቦና ታቅዶ የተሠራ ነው። ዛሬ የወያኔ ጄራሎች ፃድቃንን ጨምሮ ለገነቧቸው ፋብሪካዎች፣ ሕንፃዎች፣ ለያዙት ሠፋፊ የእርሻ መሬቶችና የከተማ ቦታዎች ምንጩ ይኸው ወያኔ መራሹ መንግሥት ተብየ በኢኮኖሚው ውስጥ በያዘው የበላይነት  ከሕዝብ ተነጥቆ የወሰዱት መሆኑን ፃድቃን አይገነዘብ ለማለት ያስቸግራል።

ዛሬ ፃድቃን በድንገት ሳይሆን፣ ከመሰሎቹ ጋር አውጥቶ አውርዶ፣ ይህን ሊለን የፈለገው፣ለሕዝብና ለአገር ተቆርቋሪ ሆኖ፣ ወይም ለዲሞክራሲዊ ሥርዓት ግንባታ አስቦ ሳይሆን፣ በወያኔ አገዛዝ እርሱና መሰሎቹ ከአገርና ከሕዝብ ዘርፈው ያከማቹትን ሀብት በብቸንነት የሚጠቀሙበት ሁኔታ የማይኖር መሆኑን ሕዝቡ በየአቅጣጫው የሚያስተጋባቸው መፈክሮችና እየወሳዳቸው ያሉት እርምጃዎች ሰላም ስለነሳቸው ነው። በመሆኑም ፃድቃን፣የጥፋቱ ሁሉ ምንጭ የሆነውን ወያኔና እርሱ  ያራመደውን  የዘር ፖለቲካና የተከለውን አገር አፍራሽ ሕገመንግሥት ተብየ፣ ከማውገዝ ተቆጥቦ፣ ግዑዙን ኢሕአዴግንና አስፈጻሚ አካሉን የጥፋቱ ተጠያቂ ለማድረግ ሞክሯል። ይህ ደግሞ «ዶሮን ሲያታልሏት፣ በመጫኛ ጣሏት» ከሚባለው አባባል ተለይቶ የሚታይ አይደለም። የአገራችን የችግር ቋጠሮው ወያኔ የተከተለው የዘር ፖለቲካና የተከለብን በዘር ላይ የተመሠረተ «ሕገመንግሥት» ነው። መፍትሔውም  በተጋጋለው ሕዝባዊ አመጽ  ወያኔንና ሥርዓቱን ማስወገድ ነው።

ስምንተኛ፦ ፃድቃን ገብረተንሣይ አገሪቱና ሕዝቧ አሁን ወዳሉበት የውድቀት ጉዞ እንዴት ሊደርሱ እንደቻሉ ምክንያቶቹን እንዲህ ሲል ይደረድራቸዋል። «የትጥቅ ትግል እና ከዚያም በኋላ በነበሩ ጥቂት ዓመታት ፀረ-ዴሞክራሲያዊ የሆኑ አስተሳሰቦችና ተግባሮች አልነበሩም ባልልም መሰረታዊ ባህሪው ግን ህዝባዊና ዴሞክራሲያዊ ነበር የሚል እምነት አለኝ። የዚህ ዴሞክራሲያዊ ባህሪ መቋጫ በህዝብ ተሳትፎ የፀደቀው ህገመንግስት ነው እላለሁ።» ካለ በኋላ፣ወያኔ የመንግሥት ሥልጣን ከጨበጠ በኋላ፣«የኢህአዴግን ዴሞክራሲያዊነት እሚፈታተኑ ሶስት ትልልቅ ክንዋኔዎች ተጽመዋል። እነዚህም ክንዋኔዎች የተፈቱበት መንገድ የኢህአዴግን ፀረ ዴሞክራሲያዊነት ያጎሉ ከዛም በላይ ተቋማዊ (Institutionalize) እንዲሆን ያስቻሉ ናቸው ብየ አምናለሁ።» በማለት የወያኔ አገዛዝ አሁን እየደረሰበት ላለው ቀውስና ሕዝባዊ አመጽ ያበቁት ችግሮች፣ « አንደኛ፦ ከኦነግ ጋር  ቅራኔ አፈታት፣ ሁለተኛ፦ በህወሃት ውስጥ የተፈረውን የውስጠ ፓርቲ ቀውስ አፈታት፣ ሶስተኛ፦ የ1997 ዓም ምርጫ ተከትሎ በተፈጠረው ቀውስ የተፈታበት አግባብ ናቸው።» በማለት የችግሩን መገለጫ ክስተቶች ወያኔ/ኢሕአዴግ ለገባበት ቀውስና አገሪቱ ለገጠማት ዙሪያ ገብ ችግሮች መሠረታዊ ምክንያቶች እንደሆኑ ለማስረዳት ሞክሯል። እነዚህ ፃድቃን ችግሮች ናቸው ብሎ የደረደራቸው፣ አገሪቱ አሁን ለምተገኝበት ደረጃ ያደረሳት መሠረታዊ ችግሮች ሳይሆኑ፣ መሠረታዊ ችግሩ ከተከሰተባቸው አያሌ ክስተቶች ጥቂቶቹ ናቸው። ከፍ ሲል ማሳየት እንደተሞከረው፣ የአገሪቱና የሕዝቡ መሠረታዊ ችግር፣ ወያኔ የተከተለው የዘር ፖለቲካና በዚህ ላይ የመሠረተው የጎሣ ፌደራሊዝምና የዚሁ ማስፈጸሚያ የሆነው ሕገመንግሥት ተብየው ናቸው።

ችግሩን በቅጡ ሳያውቁ፣ መፍትሔ ላይ መድረስ አይቻልም። የኢነግና የወያኔ ቅራኔ መሠረቱ የሥልጣን ክፍፍል ነው። ኦነግ በሰው ብዛት፣ በተሰጠኝ ክልል ባለኝ የተፈጥሮ ሀብት እኔ ወያኔ የኔ ከሚለው የበለጠ ስለሆነ፣ የወሳኝነቱ ቦታ ለእኔ ይገባኛል የሚል ጥያቄና አቋምr ነው ያለው። ወያኔ ደግሞ፣የለም እኛ ታግለን ባገኘነው ድል የሰጠንህንና የፈቀድልንህን ይዘህ ተቀመጥ የሚል ነው። ይህ የአገሪቱ መሠረታዊ ችግር አይደለም። የወያኔ ከሁለት መከፈልም የወያኔ የውስጥ ጉዳይ እንጂ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጉዳይ አይደለም። ወያኔ በዚህ መልክ ሲከፋፈል ይህ የመጀመሪያው አይደለም። የመጨረሻውም አይሆንም። በመሆኑም የአገሪቱ መሠረታዊ ችግር አይደለም። በተመሳሳይ ሁኔታ የ1997ቱ ምርጫ ውጤት መቀበልና አለመቀበል፣ ያገሪቱ መሠረታዊ ችግር ሳይሆን፣ ወያኔ ላፀደቀው ሕገመንግሥት ተገዥ አለመሆን በመሆኑ፣ መሠረታዊ ችግር ሊሆን አይችልም። ይህም በመሆኑ ፣ፃድቃን መሠረታዊ ችግርን ከስበቦችና ከክስተቶች የመለየት አቅም ያንሰዋል ወይም ዕውቀት የለውም ለማለት አይቻልም። ማለት የሚቻለው የችግሮቹ  ምንጮች ከመሠረታቸው ከታወቁ፣ ወደ ግማሽ መፍትሔአቸው ስለሚያመራ፣ ያ እንዲሆን ባለመፈለጉ ብቻ ሳይሆን፣ እርሱ በሕዝብ ተሳትፎ የፀደቀው ሕገመንግሥት የሚለው ከተሻረ ለዘመናት እርሱና ቡድኑ ሲቋምጡለት የነበረው በዘረፋ ሀብታም የመሆን ጉዳይ፣ ተጠያቂነትን አስከትሎ ወደ ድህነት የሚያመራ መሆኑን ጠንቅቆ በማወቁ ነው።

ዘጠንኛ፦ ፃድቃን የትግራይ ሕዝብ ኢትዮጵያዊ እንደሆነና ኢትዮጵያዊ ሆኖ እንደሚኖርም ሊሰብክ ሞክሯል። አዎ! የትግራይ ሕዝብ ኢትዮጵያዊ ነው። ይህን ከወያኔ በቀር ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ የለም። ወያኔ ግን ኢትዮጵያዊ አይደለህም ብሎ፣ በቋንቋ አጥር አስገብቶ ወያኔ በኢትዮጵያ ላይ በሥልጣን  የመቆየት አጋጣሚ ካጣ ሊገነጥለው እንደሚችል መንገዶችን እያመቻቸ እንዳለ በግልጽ ይታያል። ይህን ሁኔታ የትግራይ ሕዝብ አይሆን ሲል አይደመጥም። ይህን የልጆቹን ጉዞ ካልገታ፣ ኢትዮጵያዊነቱን ጥያቄ ውስጥ ያስገባው ወያኔ እንጂ፣ ሌላ ኃይል አለመሆኑን ፃድቃን ይስተዋል አይባልም።

ከዚሁ ጋር አያይዞ፣ ፃድቃን «በመሃል አገር ከሌሎች የኢትዮጵያ ሕዝቦች በትግራይ ተወላጆች ላይ ጥላቻ ይንጸባረቃል። የትግራይ ሕዝብ በስርዓቱ እላፊ ተጠቃሚ እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል፤ ይታያል። ተጨባጭ ሁኔታው ደግሞ ከዚህ የተለየ ነው።» በማለት የአደባባዩን  በጆሮ ሊነግረን ሞክሯል። ልብ በሉ፣ ይህ አባባል «የገብርኤልን ግብር የበላ ለፍልፍ ለፍልፍ ይለዋል» ይባላል። ይህ ጥላቻ በትግራይ ተወላጆች ላይ እንዲፈጠር ማን የጠቡን ዘር ዘራ? ብለን ብንጠይቅ የምናገኘው መልስ ወያኔ/ሕወሓት የሚል ነው። በመጀመሪያ ደረጃ በ1968 ዓም ወያኔ ባወጣው ፕሮግራሙ፣የትግራይ ሕዝብ አውራ ጠላት ዐማራው ነው ብሎ የትግሬ ነገድ በነቂስ ዐማራን እንዲያጠፋ ቀስቅሷል፤ አደራጅቷል። ዐማራውን ነፍጠኛ፣ ትምክህተኛ፣ ገዥ፣ ወዘተ የሚሉ ስሞች ለጥፎ፣ በመላ አገሪቱ በሚኖሩ ነገዶች በጠላትነት ተፈርጆ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል እንዲፈጸምበት ሠራዊቱን አዝምቷል። በዚህም ባለፉት 25 ዓመታት 5 ሚሊዮን ዐማሮች ከምድረ ገጽ እንዲጠፉ አድርጓል። ወያኔ ራሱ ሤራ አድርቶ በቁጥጥሩ ሥራ ያዋላቸውን ዐማሮች ፣ በነፍሰ ገዳይ ጀሌዎቹ የነገዳቸውን እየጠራ «ሽንታም ዐማራ» «ፈሪ ዐማራ» «ልሀጫም ዐማራ፣ ልጋጋም ዐማራ» የሚሉ ስድቦች በምላተ ነገዱ ላይ የሚያወርደው ወያኔ፣ ሌላው ቢቀር ጥላቻውን መግለጹ ለፃድቃን ምኑ ታምር ሊሆንበት እንደቻለ የሚያስገርም ነው። ሰዎች የዘሩትን ያጭዳሉ። የትግሬ ተወላጆችም ወያኔ የዘራላቸውን ማጨዳቸው የማይቀር ነው። «ጥንት ነበር እንጂ፣ መጥኖ መደቆስ፣ አሁን ምን ያደርጋል ወጭት ጥዶ ማልቀስ» የሚባለው አባባል ለዚህ ለፃድቃን የተጠላን እሮሮ ተገቢ ቦታው ሳይሆን አይቀርም።

በሥርዓቱ ትግሬ አልተጠቀመም ለሚለው አጭሩ መልስ « ግመል ሰርቆ አጎንብሶ» የሚለው የአባቶቻችን አባባል ከበቂ በላይ ምላሽ ይሆናል ብየ እገምታለሁ። ባይጠቀምማ፣ ትናንት ከኢትዮጵያ ሕዝብ በተለየ ሁኔታ በደል ሳይፈጸምበት ተበደልን ብለው በርሃ የገቡት ልጆቹ ወደ በርሃ ለመግባት የሚቀድማቸው ባልነበር!

ፃድቃን በማጠቃላያ ሐሳቡ እንዲህ ይላል።« —-አሁን የሚታየው ፖለቲካዊ ችግር ከፖለቲካዊ ስርዓቱ አወቃቀርና የኢኮኖሚ ሁኔታው የሚነሳ ስለሆነ፣ስርዓታዊ (Systematic) ነው የሚል እምነት አለኝ። ስለሆነም ነው ኢህአዴግ ችግሩን እያየ እያወቀ እየተነጋገረበት እያለም ለመፍታት ያስቸገረው ብየ አምናለሁ። ለወደፊቱም በገዥው ፓርቲ መዋቅርና ገዥው ፓርቲ በቀየሰው የህዝብ እንቅስቃሴ ብቻ አይፈታም የምለው።» በማለት የችግሩ አካል እና ፈጣሪ የሆነው ወያኔ ለችግሩ ብቻውን መፍትሔ ማስገኘት እንደማይችል እምነቱ መሆኑን አስረድቷል። ፃድቃን በዚህ የማጠቃለያ ሀሳቡ፣እስካሁን እየገነባ የመጣውን ማለትም፣ በሕዝብ ተሳትፎ የፀደቀው ሕገመንግሥት ለችግሮቹ ሁሉ መፍቻ ይሆናል ያለውን ሐሳቡን የሻረው እንደሆነ እንገነዘባለን። ወያኔ/ኢሕአዴግ ከሕዝባዊና ከዲሞክራሲያዊ እምነቱ እያፈነገጠ የሄደባቸውና ለዚህም ማሳያ ብሎ የጠቀሳቸው የኦነግ ቅራኔ አፈታት፣ የ1997 ምርጫ ውጤት ያስከተለው ችግር፣  እንዲሁም በወያኔ መካከል ለተፈጠረው ችግር ፣ችግሮቹን ለመፍታት የተጠቀሙበት ስልት፣ የችግሮቹ ሁሉ መሠረት ነው ሲል የቋጨውን ሀሳብ ከዚህ ላይ የቀደመ አቋሙን ሽሮ፣ የችግሩ ምንጭ ሥርዓታዊ እንደሆነ አረጋግጧል። ይህም ችግሩ  ዕውነተኛው  ቋጠሮ ሥራዓታዊ መሆኑንና የሥርዓቱ  መሠረት ደግሞ በሕገመንግሥቱ እንደሆነ መጠራጠር አይቻልም። መፍትሔውም ሥርዓቱን ከመሠረቱ መቀየር ነው። ይህም ሕዝቡን በቋንቋ የከፋፈለውን ሕገመንግሥት ተሽሮ፣ አገራችን፣ የግለሰቦች ነፃነትና የግል ሀብት የተከበረባት፣ ነፃ ገበያ እና የሕግ የበላይነት የሰፈነበት፣ ሥልጣን የሕዝብ ሆኖ፣ ባለሥልጣኖች ለሕዝብ ተጠያቂ የሚሆኑበት፣ ወዘተ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መዘርጋት ስንችል ነው።

 

ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ፡ አሁን ውሳኔው ከሰው ሳይሆን ከእግዚአብሔር ነው!- ሰርጸ ደስታ

$
0
0

Woyane

ኢትዮጵያ እንደ ሕወሐት/ኢሕአዴግ ያለ የአገር ጠላት የሆነ አገዛዝ ገጠሟት አያውቅም፡፡ ሕወሐት መጀመሪያውንም ዓላማው ኢትዮጵያ የምትባለውን አገር ለማጥፋት እና ትግራይን ከኤርትራ ጋር በመገንጠል መንግስት መሆን ነበር፡፡ ቀስ ብሎ የመጣ የሐሳብ ለውጥ ነው ትግራይን ከመገንጠል ለምን ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን  ለማጥፋት ሰፋ ያለ ዕቅድ አናቅድም በሚል ወደ ኢትዮጵያ ሥልጣን የመጣው፡፡ ዛሬ በሕዝቡ ዘንደ በይፋ እንደተባለው ዋናው የሻቢያ ቅጥረኛ ሕወሐት እንደሆነ ለሁላችንም ግልጽ ነው፡፡ ሕዝቡን በዘር መከፋፈልና አንድነት እንዳይኖረው ማድረግ ሕወሐት  ከሻቢያ ከተሰጠው ትዕዛዝ አንዱ ነው፡፡ ኋላም ይሄው ስልት አገርን በመከፋፈል በሕዝብ ላይ እንደፈለገው መሆን ስላስቻለው የራሱ አድርጎ ወሰደው፡፡ ሕወሐት/ኢሕአዴግ በመጀመሪየዎቹ የስልጣን ዘመኖቹ በሻቢያ መሪዎች ቀጥተኛ አዛዥነት ነበር ኢትዮጵያን ሲመራ የነበረው፡፡ ሆኖም ሕወሐት ውስጥ ይህን የማይቀበሉ በኢትዮጵያዊነታቸውም የሚኮሩ ሰዎች እንዳነበሩ አንዘነጋም፡፡ እንደምሳሌ በጀግንነቱ የሚታወቀውን ኃያሎም አረዓያን ማንሳት ጥሩ ግንዛቤ ይሰጣል፡፡ የሕወሐት መሪዎች ሻቢያ በሐኒሽ ደሴቶች ምክነያት ከየመን ጋር ጦርነት በገባ ጊዜ ወታደር ለሻቢያ ሊልኩ አስበው ቀድሞውንም የሻቢያን ነገር የማይወደው ኃያሎም ይህ ሊሆን አይችልም በማለት መቃወሙ አይዘነጋም፡፡ በዛን ወቅት ኃያሎም ከሠራዊቱ ጋር የደቡብ እዝ ኃላፊ ነበር፡፡ ያችን ሻቢያን የተቃወመበትን ቂም ይዘው የሕወሐት ባለስልጣናት ከሻቢያ ጋር በመሆን ኃያሎምን የሚያጠፉበት ተንኮል መሸረብ ያዙ፡፡ ከዛም የሎጂስቲክ መምሪያ በሚል ከሠራዊቱ ነጥለው አዲስ አበባ አመጡት፡፡ በመጨረሻም በአንድ ሻቢያ እንዲገደል ሆነ፡፡ ሻቢያም እስከ ኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ጊዜ ድረስ በኢትዮጵያ ቆራጭ ፈላጭ ሆኖ አገልጋዩ ሕወሐትን በሞግዚትነት አሳደገው፡፡ እግዚአብሔር ጊዜው ሲደርስ ሻቢያና ሕወሐት ተጣሉ፡፡ ሆነ፡፡  ማንም ያ ይሆናል ብሎ አልገመተም፡፡ ቀድሞውንም ሻቢያ አስቦት የነበርው የኢትዮጵያ ሕዝብ በዘር ስለተከፋፈለ ትግራይን ወርሬ ሕዝቡን አንድፈለኩ አደርገዋለሁ ብሎ አስቦ ነበር፡፡ ጦርነቱንም ከትግራይ እንጂ ከሌው ኢትዮጵያ ጋር እንዳልሆነ በስፋት ነገረ፡፡ የትኛውም ያህል ከትግራይ በወጡ የሻቢያ ቅጥረኞች የሕወሐት ባለስልጣናት የኢትዮጵያ ሕዝብ ልቡ ቢደማም የትግራይ ወገኖቹን ለመታደግና የአገርን ዳር ድንብር ለመጠበቅ አንድ ሆኖ ተነሳ፡፡ ሻቢያና ወያኔ በታትነንዋል አንድ አይሆንም ብለው ያሰቡተ ሕዝብ ይህ አጋጣሚው ለኢትዮጵያውያን አንድ መሆን ትልቅ ክስተት   ሆኖም የኢትዮጵያውያን አንደ መሆን ሕወሐትን ትልቅ ሥጋት ፈጠረበት፡፡ ለዛም በዘር የመከፋፈሉን ሥራ አጠናክሮ ቀጠለበት፡፡ ሕዝቡንም በማይፈልጋቸው ራሱ በቀጠራቸው ቅጥረኞች መሰቃየቱን ቀጠለ፡፡

በ1993 የዩኒቭረሲቲ ተማሪዎች ዓመፅ ምክነያት የአዲስ አበባ ሕዝብ ባሳየው ተቃውሞ ምክነያት አሁንም ሕዝቡ ለፖሊስ ሳይቀር የማይበገር አንድነት እንዳለው ተራዳ፡፡ ለወደፊት እንዲህ ያለ ተቃዎሞን የሚያፍንበትን ሕዝብን የሚገድልበትን ልዩ ኃይል እንደሰው የማያስቡ መደብደብና መግደል ብቻ የተማሩ ፌደራል ፖሊስ በሚል አንደ ቡድን አቋቋመ፡፡

በ1997 ምርጫ ተከትሎ በነበረው የሕዝብ ተቃውሞ ላይ በይፋ በጦር ሰራዊቱ ሕዝብ ፈጀ፡፡ ከዛ በኋላ አንድም እድል እንዳይኖር ጭራሽ ሁሉንም ነገር ዘግቶ ሕዝቡን በዘር በሐይማኖት እየከፋፈል አፋኝነቱን አጠናከረ፡፡ ሕወሐትን የሚናገር ሁሉ አሸባሪ፣ ሕገመንግስቱን በኃይል ለመናድ የሚል ታበፔላ እየተለጠፈበት ለእስርና ለሞት ሆነ፡፡ በመጨረሻም አንድም የተደራጀ የፖለቲካ ቡድን ሳይዝ ፓርላማውን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠርኩት፣ ሕዝብ መረጠኝ እያለ ያለመረጠውን ሕዝብ ጭራሽ ማበሳጨቱን ቀጠለ፡፡ አሁን ሕዝብ የሚያደራጀው አካል የለም፡፡ የግፉና ጫናው ብዛት ሞልቶ ሲፈስ ሕዝቡ ያለምንም ቀስቃሽ በራሱ ጊዜ ተነሳ፡፡ በኦሮምያ ይሄው ዛሬ 9 ወር ሆነ፡፡

ከላይ ያነሳሁት ትንሽ መንደርደሪያ እንዲሆነኝ ነው፡፡ በጥልቀት ላየው በደሉ ብዙ ነው፡፡ ዛሬ በኢሕአዴግ መዋቅሮች ሁሉ የሕወሐት ተወካይ የሌለበት የለም፡፡ ብዙ ገቢ የሚያስገኙ የአገሪቱ ድርጅቶች የኢትዮጵያ አየር መንግድን፣ ጉምሩክን ጨምሮ ሙሉ በሙሉ የሕወሐት ተከታዮች ናቸው የሚመሯቸው፡፡ የመከላከያን የሥልጣን እርከን  እርሱት፡፡ የመከላከያ አምራች ድርጅቶችም እደዛው በተለያየ አገራት ያሉ የአገሪቱ ቆንሲላዎችን ለማሰብ እንኳን ይከብዳል፡፡ እንዚህ ሁሉ በትግራይ ተወላጆች መወረራቸው ሳያንስ እንዚሁ የትግራይ ተወላጆች በሕዝቡ ላይ ይደነፉበታል፣ ይገድሉታል፣ ያስሩታል፡፡ ይህ ትግራይ ላለው ሕዝብም የተለየ አይደለም፡፡ ከትግራይ የወጣው የትግራይ ተወላጅ በብዛት በአንድም ይሁን በሌላ የዚሁ የሕዝብና አገር ጠላት የሆነው ሕወሐት ደጋፊዎችና የሥረዓቱም ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡

አሁን ያለውን ሕወሐትን ለማስወገድ የሚደረገውን ፍልሚያ እየመራው ያለ አንድም የተደራጀ ኃይል የለም፡፡ የፍልሚያው ባለቤት ሕዝብ ነው፡፡ ሕዝቡ ለድርጅቶችም ያለው መተማመን ጎድሏል፡፡ አሁን ችግሩን በራሱ ሊወጣው የቆረጠ ይመስላል፡፡ ሕዝብ እንደ ሕዝብነቱ በየትኛውም የአገሪቱ አካባቢ በሕወሐት አፋኞች እየሞተ፣ እየተሰቃየ ነው፡፡ በትግራይ በሕዝብ ላይ ያለው አፈና ከሌላው ቢብስ እንጂ የተሻለ አይደለም፡፡ ግን እሰከ አሁን ባለው ሁኔታ ምንም እድል አልነበረውም፡፡ አሁን አገሪቱ ውስጥ እየሆነ ያለው አገሪቱ የኢትዮጵያውያን ሳትሆን የሕወሐት ባለስልጣናትና፣ የሐወሐት ደጋፊዎች በሕዝቡ ስቃይ ላይ እንደልባቸው የሚኖሩባት አገር ሆናለች፡፡ ለዚህ ከትግራይ የወጡ የትግራይ ተወላጆች ግንባር ቀደም ናቸው፡፡ የሌሎች ብሔረሰብ ተወላጆችም በአነስተኛ ዳረጎት በሎሌነት ለሕወሐት ሕልውና እያገለገሉ ናቸው፡፡

ሕወሐት አስደግሞ ያሳተመው ሕገ መንግስት የሚባዙ ሰነዱ ለብዞዎች ሞትና ሥቃይ ምክነያት እንደሆነ አንድም ምሁር ይሁን የፖለቲካ መሪ ደፍሮ ሊናገረው አልወደደም፡፡ እንደውም ሕገ ምነግስቱ ወድር የማይገኝለት እየተደረገ ይሞገሳል፡፡ ሲጀምር ይሄ ሕገ መንግስት የሚባው የሕወሐት የጥንቆላ ሰነድ የኢትዮጵያ ሕዝብ በግድ እንዲቀበለው የተደረገ እንጂ ሕዝብ ወዶና ፈቅዶ የተዘጋጀ አይደለም፡፡ ሕወሐትና ሌሎች የታሪክ ነቀርሳዎች በሕዝብ ላይ እንደልባቸው ለመሆን ያዘጋጁት ሰነድ ነው፡፡ ወደር የሌለው እየተባለ የሚወደሰው ሕገ መንግስት ከተለያዩ ዓለም ዓቀፍና አገሮች የተቀዱ (በቀጥታ የተኮረጁ) ደንቦችንና ሕጎችን ማካተቱ አንድ ነገር ሆኖ ሳለ ልክ በሳል ሰዎች ያወጡት እንደሆነ መወደሱ አሳዛኝ ነው፡፡ ልብ በሉ እነዚህ ሕገ መንግስተ በሚባለው ሰነድ የተካተቱ ነጠቦች አንድ መንግስት ጻፈውም አልጻፈውም ማድረግ የሚገባው መሠረታዊ የሰዎች የህልውና መብታት እንጂ ጽፌልሀለሁ እያለ የሚደነፋበት አይደለም፡፡ እነዚህን መሠረታዊ የሆኑ መብቶችን በአጃቢነት ተጠቅሞ ሕወሐት ለሕዝብና አገር አደገኛ ጠንቅ የሆኑ አንቀጾችን በዚህ የጥንቆላ ሰነዱ አካቶታል፡፡ አንቀጽ 39 ወደድንም ጠላንም ሆን ተብሎ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ እንደገባ ብዙዎች እናውቃለን፡፡ ከዚህ ውጭ የሰንደቅ ዓላማን መልክ ዛሬ የሕገ መንግስት አካል እያስመሰለ ሕዝብን ሊከስበት ሊገድልበት የሚመክረው ሕወሐት በታሪክ የማይታወቅና የራሱና የራሱ ብቻ የሆነ የፓረቲውን ማንነት እንጂ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሊወክል አይችልም፡፡ ሕዝብ ከመሠረታዊ የሰንደቃላማዎቹ ቀለማት ውጭ ማንም ጠንቋ እየነገረው ድሪቶ ምልክት የመቀበል ግዴታ የለበትም፡፡ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለም ያለውን ባንዲራ መያዝ ወንጀል የሆነበት የታሪክ ምዕራፍ ላይ መድረሳችን ራሱ አሳዛኝ ነው፡፡ ለዘመናት አባቶቻችን የአገር ማንነት ምልክት አድርገውት የሞቱለት አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላማ እንጂ ሕወሐት አስጠንቁሉ ድሪቶ የደረተበትን ጨርቅ አይደለም፡፡ ደግሞስ ሕወሐት ስለ ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ለማውራት የትኛው ሙራልስ ሲኖረው ነው፡፡ የጨው መቋጠሪያ ጨርቅ ነው ብሎ የአገርን ክብር ምልክት የሆነውን ሰንደቅ ዓላማ ያጣጣለው ሕወሐት ለኢትዮጵያውያን የራሱ በደብተራ አስመትቶ ያመጣውን ድሪቶ እንድንቀበል አስገድዶ ዛሬም አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላማውን የሽበረቶኞች ምልክት ይለናል፡፡ ጉድ ነው ዘንድሮ፡፡ ለዚህም ሰዎች ሕገመንግስቱን በመጻረር ተብለው ዜጎች ይከሰሳሉ ይገደላሉ፡፡ ሌላው ይሄው የሕወሐት የጥንቆላ ሰነድ ሕገ መንግስት ምንም ሚና የሌለውን የአገር ርዕሰ ብሔር ተብዬውን (ፕሬሲደንት) የስልጣን ገደብ ያስቀምጣል፡፡ 6 ዓመት ቢበዛ ደግሞ 12 ዓመት ይላል፡፡ አገርን ለመምራት ትልቁን ስልጣን የተሸከመውን ጠቅላይ ሚኒስቴር ተብዬውን ግን ምንም ገደብ ሳያበጅለት ያልፈዋል፡፡ እዚህ ጋር ስታነቡት ሟቹ ጠ/ሚኒስቴር ለራሳቸው እንዲመቻቸው ጠንቋዮቻቸውን አማክረው የደረሱት ሰነድ እንደሆን በደንብ ታስተውላላችሁ፡፡ ዛሬ ላይ ሁሉም ሕገ መንግስቱ በሚያዘው መሠረት እያለ ሲቀርብ ይገርመኛል፡፡ አዚም የዞረበት ሁሉ ሕገመንግስቱ ሕገመንግስቱ እያለ ያልቃል፡፡ እንግዲህ ይህ ሰነድ ነው ድንቅ እየተባለ ዛሬ ድረስ ለሕዝብና አገር ጥፋት ምክነያት እየሆነ እየታየ ሁሉም ፈዞ የሚያሞግሰው፡፡ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ያለ መጀመሪያ መቃወም ያለበት ይህን የሕወሐት መርዘኛ ሰነድ ነው፡፡ ጨው ለራስሕ ስትል ጣፍጥ ነው፡፡

ሌላው ሕወሐት ባለፉት 25 ዓመታት በሕዝቦች መካከል መቀራረብ እንዳይኖር በደንብ ለያይቷል፡፡ ከሁሉም በላይ ግን ሕወሐትና ሌሎች ኦሮሞን እንወክላለን የሚሉ ድርጅቶች የኦሮሞን ሕዝብ ከኢትዮጵያዊነቱ እንዲመክን በማድረግ ፍጹም አቅም የሌለውና እንደልባቸው የሚፈነጩበት አድርገውታል፡፡ ይህን ማድረግ የግድ ነበረባቸው፡፡ ኦሮሞ በሙሉ በማያወላዳ ኢትዮጵያዊነቱ ካለ የእነሱ ሕልውና እንማይኖር አሳምረው ያውቁታል፡፡ አስገራሚው ነገር በኢትዮጵያ ታሪክ የኦሮሞ ከፍተኛ ተሳትፎ የነበረበትን የታላቁን የሚኒሊክን ዘመን ከምንም በላይ አክፍተው እእምሮውን በርዘውታል፡፡ የኢትዮጵያም ሆነ የኦሮሞ ሕዝብ ጉልበት እዛ ታሪክ ላይ እንዳለ አሳምረው ያውቁታል፡፡ ያ ታሪክ ለሕወሐትና ለደጋፊዎቻቸው ምን ያሕል እንደሚያስፈራቸው ለማወቅ በቅረቡ አንድ የሕወሐት ደጋፊ የሆኑ ግለሰብ የተናገሩትን ማዳመጥ በቂ ነው፡፡ አኖሌና ጨለንቆ ለኦሮሞ የዚህ ዘመን ትውልድ በደንብ ተጋነውን ከፍተው አእምሮው ውስጥ ተቀረጾለታል፡፡ የዛ ዘመን ጀግኖች አባቶቹ ታሪክ ውርደት ሆኖበታል፡፡ አሳዛኝ ነው፡፡ ከኦሮሞ ወገን የሆነው የልጅ ልጃቸው ኢያሱ ንጉስ እንዲሆን ሚኒሊክ አልጋ ወራሽ ማድረጋቸው  ለምንድነው ብሎ እንዳያስብ ሕወሐቶችና አጋሮቻቸው በኦሮሞ ሕዝብ ላይ አዚም አድረገውበታል፡፡ የትኛውም ዘመን በደል ለኦሮሞ ሕዝብ ከአሁኑ በከፋ እንዳልነበረ መረዳት እንኳን እንዳይችል ተጋረዶበታል፡፡ ምኒሊክ ነበሩ እኩ ኦሮሞን ስልጣን እንዲይዝ ዙፋናቸውን ያስረከቡት፡፡ በሚኒሊክ ዘመንም ነበረ እኮ ታላላቅ የሚባሉ የአገሪቱ ስልጣኖች በኦሮሞ ልጆች እጅ የነበረው፡፡ ያ ታሪክ ለኦሮሞ ሕዝብ ብሎም ለኢትዮጵያውያን ሁሉ ታላቅ ጉልበት እንደሆነ የሚያውቀው ሕወሐትና አጋሮቹ እናገረዋለሁ የቀድሞ የኦነግ አመራሮች ፍጹም ከኦሮሞ ሕዝብ አእምሮ እንዲመከን ከመደረግም አልፎ እጅግ የከፋ ሆኖ እንደያየው አደረጉት፡፡ ያ የጀግኖች ታሪክ ለሕወሐትና አጋሮች ቢያስፈራቸው አይገርምም፡፡ የዛ ዘመን ጀግኖች ዛሬም መንፈሳቸው አስፈሪ ነውና፡፡ የአባቶቹን ደም ያረከሰው የዛሬው የኦሮሞ ተወላጅ የቱ ጋር ጉልበቱ እንመከነ ዛሬም ሊረዳው አልቻለም፡፡ የቀድሞው ዘመን ናፋቂዎች የሉታል፡፡ ያስፈራሩታል፡፡ የቀድሞውን ዘመን የመሩት አባቶቹ እንደሆኑ ሳያውቅ የቀድሞውን ዘመን ይፈራዋል፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ ከሥልጣን እየወጣ የሄደበት የአጼ ኃይለስላሴ ዘመን አይነገርም፡፡ ከፍቶ የሚነገረው ኦሮሞ ትልቁን ስልጣን የያዘበት የታላቁ ሚኒሊክ ዘመን ታሪክ ነው፡፡ በአኖሌና ጨለንቆ አእምሮውን ደፍነው ዛሬ እንሱ የፈነጩበታል፡፡ አሳዛኝ ነው፡፡ ከመቼውም ዘመን ለኦሮሞም ሆነ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንደዚህ ዘመን ያለ ውርደት አልገጠመውም፡፡ አንድ ሰው በጣም የሚወደው ልጁ ይሞትበትና እየመሰለ የልጁን አባት ከሐዘን እንዳይወጣ ለብዙ ወራት አንድ ተንኮለኛ የሆነ ጎረቤቱ ጠዋት ጠዋት እየመጣ የልጁን ነገር እያስታወሰ እንዴት ያለ ልጅ አጣሕ እያለ ብሶቱን እያነሳ ሲያስለቅሰው የውላል፡፡ የልጁ አባት ከልጁም ከኑሮውም ሳይሆን ጭራሽ ብዙ ችግር ይደርስበታል፡፡ መስራት ባለመቻሉም ይደኸያል፡፡ በዚህ ያ ተንኮለኛ ጎረቤቱ ደስ ይለው ነበር፡፡ ከእለታት አንድ ቀን አንድ ቅን ሌላው ጎረቤቱ ወደ ልጁ አባት ይሄድና የሄ ጎረቤትህ ሆን ብሎ አንትም በሀዘንና በድህነት እንድትሞት እያደረገህ ነውና ወዳጄ ራስህን ጠብቅ ይለዋል፡፡ ያም የልጁ አባት ነገሩ እውንም ገባውና ወደራሱ ተመልሶ ኑሮውን መኖር ቻለ ይባላል፡፡ ዛሬ አኖሌና ጨለንቆ የሚዘከሩለት የኦሮሞ ሕዝብ ለኦሮሞ የሚያዝኑ መስለው ኦሮሞ ፍፁም አቅም ያጣ ሊያደርጉት የሚያሴሩ ጠላቶቹ እንደሆኑ ዛሬም አልተረዳም፡፡

የኦሮሞ ሕዝብ የኢትዮጵያን ሕዝቦች ሁሉ መሪ በመሆን ሊንቀሳቀስ ይገባው ነበር እንጂ እንደዛሬው በትንንሽ ጉዳዮች ታስሮ ባልኖረም ነበር፡፡ ከኢትዮጵያዊነቱ እጅግ ስለራቅ በገዛ አገሩ ባይተዋር ነው፡፡ ሰልፍ ሲወጣ አባቶቹ የሞቱለት አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ ትቶ ለዛሬው ሞት እንግልትና ባርነት ያበቁትን ድርጅቶች አርማ ይዞ ይወጣል፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ ከከሕወሐት ሚስጢረኛ አጋር ከሆነው ኦነግና መሰሎቹ የአእምሮ ባርነት ራሱን ነጻ አድርጎ በኢትዮጵያዊነቱ የነጻነቱ መሪ ተዋናይ እስካልሆነ ድረስ እሱም በባርነት ይቀጥላል ሌሎችም ኢትዮጵያውያን ያለዚህ ሕዝብ ነጻ ሊወጡ እይችሉም፡፡

ዛሬ የተደረገውን ሠላማዊ ሰልፍ በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ፍፁም ኢትዮጵያዊነት አጅቦት ቢሆን መላው የኢትዮጵያን ሕዝብ የሚያነቃንቅ ክስተት ሊያደርገው በቻለ ነበር፡፡ ሞትም ቢኖር አብረውት ብዞዎች በሞቱም ነበር፡፡ ያ አልሆነም፡፡ የጎንደርን ሰልፍ ስኬታማ ያደረገው ቁርጠኛ ኢትዮጵያዊነቱ እንጂ መሣሪያ ስለያዘ ብቻም አደለም፡፡ መሣሪያ መያዝ በራሱ ሌላ ችግር በፈጠረም ነበር፡፡ አሁንም እላለሁ የኦሮሞ ሕዝብ ወደ ሙሉ ኢትዮጵያዊነቱ ተመልሱ ተግሎን ሊመራው ካልቻለ ነጻነት የለም፡፡ ጉልበት የለም፡፡ ዛሬ ማም ማን መለማመጥ አያስፈልገውም ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ ነው የምለው፡፡ እስከዛሬ ብዙ ማባበሎችና ማደባበሶች ነበሩበት አሁን ጥርት ያለ አቋም ላይ መቆም ይገባል፡፡

በየ ቦታው ያሉ የትግራይ ተወላጆች ሕወሐትን እንጂ የትግራይ ሕዝብን እንደማይወክሉ በአጽዕኖት ሊታሰብበት ከሚገባቸው ጉዳዮች አንዱ ነው፡፡ የትግራይ ሕዝብ ከሌላው ኢትዮጵያ ሕዝብ የተለየ ጥቅምም ሆነ የአስተዳደር ፍትሕነት የለውም፡፡ ምን ዓልባትም ከሌሎች በከፋ ሁኔታ ዛሬ ባርነት ይኖራል፡፡ በሌሎች አካባቢዎች የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ግን በአብዛኛው በሚያሰኝ የሕወሐት ደጋፊዎች እንደሆኑ በተግባርም በቃልም እያሳዩን ነው፡፡ ሌላውንም በግፍ ለማኖር የበኩላቸውን እያደረጉ ነው፡፡ እነዚህ ወገኖች ዛሬ በሌላ ሕዝብ አደጋ ላይ ቢወድቁ ተጠያቂ የሚሆኑት ራሳቸው እንጂ አደጋውን የሚያደርሱባቸው አይደሉም፡፡ በግልጽ እንደምናየው እነሱ ሌላውን ለሞትና ለእንግልት ለሕወሐት እየሰለሉ እያስገደሉ በሠላም እንኖራለን ብለው ካሰቡ ጭንቀላታቸው በጥቅም መታወሩን ከማስተዋል ሌላ ምንም አይባልም፡፡ በግልጽም እንዳየንው ሕወሐት ከምንም በላይ እነዚህን ደጋፊዎቹን ይጠብቃል፡፡ የሌላው ሕዝብ ሕይወት ለሕወሐት እንደ ድል ነው የእነዚህ ደጋፊዎች ቁሳዊ ንብረት ግን ትልቅ ጥፋት ተደርጎ የሕወሐትን ሚዲያዎች ያጨናንቁታል፡፡ ከዚህ በኋላ ለእነዚህም ወገኖች እላለሁ ጨው ለራስሕ ስትል ጣፍጥ….. ዛሬ ንብረቴን ነኩብኝ የምትል ነገ ራስህም ለመኖርህ እርግጠኛ አይደለህም፡፡ ከምንም በላይ አደገኛ የሆነውን ምርጫ አለህና፡፡ በየትኛውም እይታ ግን እነዚህ የሕወሐት የግፍ አገዛዝ ተጠቃሚዎች መከራውን እየበላ ላለው የትግራይ ሕዝብ ምሳሌ ሊሆኑ አይችሉም፡፡

በየሥልጣኑ እርከን ላይ ያላችሁ ባለስልጣኖችም የሕወሐት ባርነታችሁ ይበቃ ዘንድ እስከዛሬ የበደላችሁትም ቢሆን ዛሬም ሕዝቡ ይቅር ይላችኋልና ራሳችሁን ከሕዝቡ ቀላቅሉ፡፡ የታጠቃችሁ ኃይላትም እንዲሁ፡፡ እየተለመናችሁ ሳይሆን ከሚመጣው ማዕበል ትድኑ ዘንድ ለሕዝብ ያላችሁን ወገንተኝነት ዛሬ በድፍረት ለመግለጽ ወስኑ፡፡ ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ …. በመጨረሻም ከሕዝቡ ጎን ቆማችሁም አልቆማችሁምም መውደቃችሁ እውነት ነው፡፡ ይህ ከላይ ከኃያሉ እግዚአብሔር የመጣ እንጂ የሰው አድርጋችሁ አትዩት!

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ! ይጠብቅ!

 

አሜን

 

ሰርጸ ደስታ

 

 

ድምፃዊ ፋሲል ደሞዝ ስለጎንደር ወልቃይት ይናገራል –“ለትግሉ በሙያዬ አስተዋጽኦ አደርጋለሁ”

$
0
0


ድምፃዊ ፋሲል ደሞዝ ስለጎንደር ወልቃይት ይናገራል – “ለትግሉ በሙያዬ አስተዋጽኦ አደርጋለሁ”
ድምፃዊ ፋሲል ደሞዝ ስለጎንደር ወልቃይት ይናገራል – “ለትግሉ በሙያዬ አስተዋጽኦ አደርጋለሁ”


 ነፃነት ለኢትዮጵያ——— በጋዜጠኛ ቶማሰ ሰብሰቤ

$
0
0

Freedomነፃነት የሌለው ህዝብ ሁሌም አይተኛም።በየትኛውም መንገድ ይተነፍሳል።ነፃነት የፈለገ ያክል አንፀራዊ ቢሆንም ሰው ሰለ ማንነቱ አና ሰለ ሀገሩ በነፃነት የማውራ መብት አለው።ህዝብ ያልተመቸውን አልተመቸኝም ብሎም መናገር ይችላል።በሀገር ጉዳይ ሁሌም ያገባዋል።ከህዝብ የበለጠ መንግስት ስለ ሀገር ነፃነት አይጨነቀም።ኢህአዴግ የፈለገ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚጠቅም ነገር ቢመጣ እሱ የማይጠቀም ካልሆን አይወደውም።ለምን?መንግሰት ለራሱ ነው የሚኖረው።ህዝብ ለሀገሩ። ጃ ፣ደርግም እና ኢህአዴግም የሚሰቁት ስለ ራሳቸው መልካም ነገር ስነግራቸው ነው።ይህ ሀገር ይጎዳል ብለን በኢትዮ ያዊነታችን ከጠየቅን እኔ አውቅላችዋለው ብለው ንፁሃን ይጨፈጭፋሉ።

 

አሁን ያለው ነፃነት እንዴት ይገለፃል?

 

ባለፉት 25 አመታት  ኢህአዴግ ነፃነት ሰፍሮ ሰቶናል።ሰለዚህም የሰፈራ ነፃነት ነው ።በነፃነት ብዙ ቦታዎች መሄድ እንድትችል ያደረገው ኢህአዴግ በወሳኝ ቦታዎች ነፃነት የለህም።ኢትዮጵያን ከኢህአዴግ ውጪ ለውጥ ያሰፈልጋታል ካልን ይህ የትኛውን ህዝብ አይመለከተውም ኢህአዴግ በስናይፐር ቋፐ ያደርግሃል። በነፃነት ችግራችን ለአለም እናሰማ ካልክ ሀገር ከሀዲ ነህ ተብለ ዘብጥተያ።የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ መወዳደር እንጂ ማሸነፍ አልተፈቀደላቸውም።፣ነፃ ሀገር ፣ ነፃ ፕሬስ ፣ነፃ ፖለቲካ ፣ ነፃ አመለካከት በኢህአዴግ ሰፈር ክልክል ነው።በየትኛውም የኑሮ ደረጃ ፖለቲካ አለ።በዚህ ፖለቲካ ደግሞ ካድሬ አለ።ኢህአዴግ ሰካራም ከጠጣ በሃላ እንኳን ሰለ እሱ ፖለቲካ ብቻ እንዲያወራ ሰርቷል።የኢህአዴግ የነፃነት አናት ላይ ቷ« የትኛውም ነፃነት ወያኔን የማይነካ መሆን አለበት » የሚል ነው።

 

ሚሰት ከባሏ ከጋር ምሳ እየበላች «አየህ ውዴ ቆይ መንግስት ምን ያደርግ እሺ ።ህዝቡ ቤት ያቃጥላሉ።ንብረት ያወድማሉ።እነዚህ እማ አሸባሪዊች ናቸው ኢህአዴግ እውነቱን ነው» ስትለው ለባሏ።ባል «እረ ልክ ብለሻል» አላት እና የ25 አመት ሚሰቱን እያየ በሆዴ« ያለኩትን ሰንምተሽ ልታሳፍሽኝ ነው »አላት ይባላል።የኢህአዴግ ነፃነት እንኳን ኦሮሞን ከአማራ ሊያግባባ ይቅር እና  ባል እና ሚስትን እርስ በእርስ በቁራኛ አስቀምተጣል።

 

ነፃነት ለምን ተፈለገ?

 

ዲሞክራሲ ያለ ነፃነት ቀለሀ እንደ ሌለው ጥይት ነው።ዲሞክራሲን ሰጠው ካሉ ደግሞ ከእነምናምኑ ነው እንጂ መርጦ አይደለም።ነፃ ትውልድ ካለ ሌብነት ፣ሀገር ክህደት ፣አንባገነንነት ፣ አድርባይነት ፣ ግፍ እና ጭፍጨፋ ያለም።ነፃ ትውልድ ለማምጣት ነፃነት ቆጥሮ አይሰጥን።ለዚህም ነው ትላንትም ዛሬም ነፃነት ኢህአዴግ ቆልፎ ያሰቀመጣት።ግን ህዝብ ነፃነት ይወልዳል እና ዛሬም እያየን ነው።ወያኔ የመልካም አሰተዳደር ችግር አለብኝ ፣ብዙ ባለ ስልጣኖቼ እውነት ነው ዘራፊዎች ናቸው ቢልም ፤ እኛ በቤተ መንግስር እናተ በቤተ ድህነት ውስጥ ናቹ ብለው ብነግሩንም እኛ ደግሞ በነፃነታችን ሰርዓቱ በቃን ፤ አዲስ ሰርዓት ያሰፍልገናል ማለት እንቀጥላል።

 

ኢህአዴግ ምን ያሰፈራዋል?

 

ብሶቴን ፣ችግሬን ፣ማንነቴን ፣ ሰቃዬን በአደባባይ ላይ ልናገር ለኢህአዴግ ሁሌም ራሰ ምታቱ ነው።አደባባይ እና ጎዳናዎች የመንግስት ውዳሴ ማሰነገሪያ እንጂ የህዝብ ጥያቂ ማቅረቢያ እንዳይሆኑ ሰርቷል።በየትኛው ቦታ በነፃነት የሚያወራ ሲጨልምቷ ወደ ቤቱ ሲገባ የሰራውን ይህ በው ብሎ ግድያ።ሁሉም ህዝቦች ለነፃነት ዘብ ከቆሙም ያመዋል።ኢህአዴግ የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ ያመዋል።የአማራ አመፅ ያሰኮርፈዋል።አንዱም እንዳይሳካ እየሰራ ነው።

 

 

 

ነፃነት ጠያቂው ማነው?

 

በኢህአዴግ ሁሉም  ህብረተሰብ ብዙ ጥያቄ አለው ።ከሁሉም ከባዱ ወያኔ ከስልጣን ውረድልን ሲባል ነገሮች አለቁ።የትኛውም ህዝብ ወያኔን በቃኝ ካለ አሸባሪ ነው።ተልዕኮ አለው።ብዙ ድራማ ይሰራል ።ሰው ይጨፈጨፋል ከዚያን እድሜ ማራዘም።ከዚያ ለሀገሬው ህዝብ ውሸት መንገር።ይህ የተነሳው ህዝብ አሸባሪ ነው ለእናተ አይበጅም ይሉናል።ልንግራቹ የምወደው የተነሳው ህዝብ ከኢህአዴግ እንጂ ለኢትዮጵያ መልካም አሳቢ ነው።ኢህአዴግ የሚኖረው ኢህአዴግ እሰካከ ነው።ኢትዮጵያ ግን ህዝቦቾ ናቸው ሀብቶቾ።

 

የጎንደር ነፃ ሰላማዊ ሰልፍ ምን አሰተማረን?

 

የጎንደር ህዝባዊ ኢህአዴግ ትክክል አለመሆኑን አሳይቷል።በቃኝም እንዴት እንደሆነ አይተናል።ከጎንደር ሶስት ነገሮችን በትንሹ ወስደናል።

አንደኛው ህዝብ የትኛውን ጥያቄ ለማንሳት ከመንግስት ፍቃድ እንደማያስፈልገው ያሳየ ነው።መቶ በመቶ ሰላማዊ ሰልፍ በተከለከለበት ሀገር ወደ በአዴን ቢሮ ሄዶ አንተብ ልቃወምህ ነውና ሰልፍ ፍቀድልኝ እንኳን ጎንደሬ ሌላውም አይቀልድም።ሁለተኛው ኢህአዴግ የሚከለክለው ባንዲራ ይዞ መውጣት።ሶስተኛ ጎንደሬዎች አማራነትን ሳይሆን ኢትዮጵያዊነትን አሳይተዋል።ስለ ኦሮሚያ ጠይቀዋል።ስለ ሙስሊም አሰምተዋል።የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱልን ብለዋል።በአንድ ቀን ህዝብ ሲቆጣ አሳዪን።

 

ኦሮሞ ለኦሮሞ ሳይሆን ከዛም በላይ ነው

 

የኦሮሞ አመፅ ኦሮሚያን መገንጠል ነው ብለው ለሚያወራ ሰው ምላሽ የሰጠ ሰልፍ ኦሮሞ አካሂዳል።አማራ ወንድሜ ነው።ሁላችንም ጠላት ገዥው ፓርቲ ነው ብለዋል።ይህ ነው እውነቱ በቃን ፣ሰለቸህን ፣ለውጥ በአዲስ መንግስት ነው ህዝብ ያለው።

 

ህዝቡ ምን ይላል?

 

ከኢህአዴግ ነፃ መውጣት የህዝቡ ጥያቄ ነው።ህዝቡ ያለው በቃኝ ኢህአዴግ ነው።በምዕራቡ አለም የአንድ ሰው መፈንከት የሚያሰደነግጠው ፣ የሶሪያ ነውጥ በእየሰዓቱ የሚያወራው ሚዲያ ስለ ወንድሙ መሞት እና መከፋት ስለምን አያወራም።The nearest is the best የሚለው የጋዜጠኝነት መሰታዊ መርህ ማን ወሰደው ?ወይስ ለሚዲያዎቹ ከኦሮሚያ እና አማራ ሶሪያ ይቀርባል? በዚህ ነው ህዝቡ ያፈረባቹ ።የኢህአዴግ ድግስ አጃቢ ሚዲያ ፤ በህዝብ ድግስ  ያለመገኘት አለ ነገር አሰባለ።

 

 

 

 

ምክትል ጠቅላይ ሚ/ር ደመቀ መኮንን በእስራኤል የሚታከሙበት ሆስፒታል አድራሻ ታወቀ

$
0
0

demeke
(ዘ-ሐበሻ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በ እስራኤል ሃገር ባለው ትልቁ የግል የቱሪስትሆስፒታል ውስጥ እየታከሙ እንደሚገኝ ታወቀ:: ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን እኚህን የደም በላ ስርዓት ተላላኪ ምክትል ጠቅላይ ሚስትር የሚገኙበት ቦታ ሄደው እንዲያሸማቅቋቸው በሶሻል ሚዲያዎች ጥሪ ማቅረባቸው ታውቋል::

አሱታ (Assuta – Israel’s largest and leading private hospital) ውስጥ በከፍተኛ ገንዘብ ወጪ እየታከሙ የሚገኙት አቶ ደመቀ መኮንን በስኳር በሽታና በደም ግፊት ክፉኛ እየተሰቃዩ መሆኑ ታውቋል::

የሆስፒታሉ አድራሻ: HaBarzel St 20, Tel Aviv-Yafo ነው:: ስልክ ቁጥሩም +972-3-7643247 ነው:: በዚህ የግል ሃኪም ቤት ለመታከም ከፍተኛ ገንዘብ ይጠይቃል::

በሶሻል ሚድያዎች እየተሰራጨ ያለው መልዕክት የሚከተለው ነው::

እስራኤል ለምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን

የሕወሓት መንግስት ተላላኪ የሆነው ምክትል ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን በስኳር በሽታና በደም ግፊት የጤና መታወክ ምክንያት እስራኤል የሚገኝው አሱታ በተባለ የግል ሆስፒታል እንደሚገኝ ተሰምቷል:: ሆስፒታሉ ሙሉ አድራሻ HaBarzel St 20, Tel Aviv-Yafo ስለሆነ በኦሮሚያና በአማራ ምድር ሕወሓት ያፈሰሰው የንጹሃን ደም ያንገበገባችሁ ሁሉ እዚያ በመገኘት ተቃውሟችሁን እንድታሰሙ; እንዲሸማቀቅ እንድታደርጉት አደራ እንላለን::

ሐገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን

የሰማያዊ ፓርቲ ነገር መደገፍ፣ ወይንስ ማደናቀፍ ? –ይገረም አለሙ

$
0
0

blue-party.jpgአንደ መነሻ፤ አሁን በሥራ ያለውና ወያኔዎች በማጥቂያ መሳሪያነት የሚጠቀሙበት ነገር ግን እነርሱ የማያከብሩትና የማይገዙበት ህገ መንግስት ሰላማዊ ሰልፍን በተመለከተ እንዲህ ይላል፡፡
አንቀጽ 30 ንኡስ አንቀጽ 1 “ ማኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በመሆን መሳሪያ ሳይዝ በሰላም የመሰብሰብ ፣ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነጻነትና አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው፡፡ ከቤት ውጪ የሚደረጉ ሰብሰባዎችና ሰለማዊ ሰልፎች በሚንሳቀሱባቸው አካባቢዎች በህዝብ አንቅስቃሴ ላይ ችግር እንዳይጥሩለማድረግ ወይም በመካሄድ ላ ያለ ስብሰባ ወይም ሰላማዊ ሰልፍ ሰላምን ዴሞክራሲያዊ መብቶችን የህዝብን የሞራል ሁኔታ አንዳይጥሱ ለማስጠበቅ አግባብ ያላቸው ሥርዓቶች ሊደነገጉ ይችላሉ፡ ”
ነገር ግን አግባብ የላቸው ሥርዓቶች የተባሉት እስከ ዛሬም አልወጡም፡፡ በመሆኑም ጉዳዩ የሚስተናገደው ከህገ መንግስቱ አስቀድሞ በ1983 ዓም በወጣው የሰላማዊ ሰልፍና የፖለቲካ ስብሰባ ሥነ ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 31/1983 ድንጋጌ ነው፡፡ የዚህ አዋጅ አንቀጽ 6/2 ስብሰባ ወይንም ሰላማዊ ሰልፍ የሚያደርገው አካል ከ 48 ሰዐት በፊት አስቀድ ለአካባቢው የመስተዳደር አካል አንዲያሳውቅ ነው ግዴታ የሚጥለው፡፡ ለአካባቢው መስተዳድር ደግሞ የጸጥታ ጥበቃ የመመደብን ኃላፊነት ይሰጥና ስብሰባውም ይሁን ሰላማዊ ሰልፉ አዘጋጆቹ ባሰቡት ቀን አንዳይካሄድ የሚያደረግ በቂ ምክንያት ሲኖር ይህንኑ ገልጾ ለሌላ ቀን እንዲተላለፍ ከመንገር ያለፈ ሥልጣን አይሰጠውም፡፡
በተግባር ስናይ እንደኖርነው ግን በጠያቂም በተጠያቂም ዘንድ ይህ የሚታወቅ አይመስልም፡፡ በመሆኑም ፖለቲከኞች አይደለም ሰላማዊ ሰልፍና ህዝባዊ ስብሰባ የምክር ቤት ስብሰባቸውን በሆቴል ለማድረግ የፈቃድ ደብዳቤ ሲያስገቡ ተጠያቂውም ሲከለክል ነው ስንሰማም ስናይም የኖርነው፡፡ ነገሩ ያልተጻፈ ነገር ግን በሁሉም ዘንድ ተግባራዊ የሚሆን ልማዳዊ ህግ ሆነና ጋዜጠኞችም ፈቃድ ጠይቃችኋል፣ ተፈቅዶላችኋል ወዘተ እያሉ ሲጠይቁ መስማት የተለመደ ሆኗል፡፡ይህም በመሆኑ በወያኔ ፈቃድ ያልተሰጠው ሰልፍም ሆነ ስብሰባ በፖለቲከኞች ተካሂዶ አያውቅም፡፡ ወያኔ ደግሞ አይፈቅድም፡፡
አሁን ግን ይህ ህገ መንግስታዊ መብት ጎንደር ላይ ተግባራዊ ሆነ፡፡ ጎንደሬዎች ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ማሳወቅ አንጂ ማስፈቀድ አይጠበቅብንም ፣ህግ አክብረን የምናደርገውን ሰልፍ በህገ ወጥ መንገድ ለመግታት ከተሞከረ እኛም ህገ ወጥ አንሆናለን ( ብትተኩሱ አንተኩሳለን) በማለት መብታቸውን ብቻ ሳይሆን ህገ መንግስቱንም አስከብረው ዋሉ፡፡ ሰላማዊ ሰልፍም ሆነ ስብሰባን በተመለከተ የፖለቲካ ፓርዎች ታሪክ ይህ መሆኑ እየታወቀ ሰማያዊ ለእሁድ ነሀሴ 1/2008 በባህር ዳር ሰላማዊ ሰልፍ ጠራሁ ማለቱ ወቅታዊውን የህዝብ ተቃውሞ ለመደገፍ ወይንስ ለማደናቀፍ ብሎ መጠየቅ ግድ ይሆናል፡፡ አንዲህ አይነት ነገሮች በይሉኝታ ለፓርቲዎች ባለ ስስት ወይንም ለአመራሮቹ ባለ ቅርበት ወዘተ በዝምታ እየታለፉ ብዙ ጉዳት ደርሷል፡፡ የሀገራችንን ፖለቲካና ፖለቲከኞች በቅርብ ሲከታተል ለኖረ የሰማያዊ የሰልፍ ጥሪ ከፕሮፓጋንዳ ፍጆታ አልፎ ተግባራዊ እንደማይሆን መረዳት አይገደውም፡፡ አስቀድሞ ለምን ብሎ መጠየቅ ለሚያወሩት ግን ተግባራዊ አንደማያደርጉት ራሳቸውም ለሚያውቁት ነገር አደናቃፊ ተደርጎ መታየት ስለሆነ ነው አስተያየቴን ከውጤት በኋላ ማድረጉን የመረጥኩት፡፡
የአዳራሽ ስብሰባ ያልተሳካላት የአደባባይ ሰልፍ መጥራት ለምን?
ሰማያዊ ፓርቲ ከወር በፊት በባህር ዳር የአዳራሽ ሕዝባዊ ሰብሰባ መጥራቱን ነገሮን ብዙም ሳይቆይ የአካባቢው መስተዳደር ለሌላ ግዜ አስተላልፉት ስላለን የቀረበውን ምክንያት ተቀብለን አስተላፈናል ተብሎ ቀን ተቆርጦ ተነገረን፡፡ አስተዳደሩም በሁለተኛው ቀን ተስማቶ እውቅና መስጠቱን ነግረውን ውጤቱን ሰንጠብቅ ለቅስቀሳ የተሰማሩ አባሎቻችን ታሰሩ ተብሎ ነገሩ የውኃ ሽታ ሆነ፡፡ በአካባቢው አስተዳደር እውቅና ያገኘ ስብሰባ በማን ነው የተከለከለው? አባላቱን ያሰረው ማነው?ለምንና በምን ምክንያት ነው የታሰሩት? ወዘተ ሰማያዊዎች ይህን እንኳን መከታተል መጠየቅ ቀርቶ ያንኑ የቢሮ መግለጫ እንኳን አለወጡም፡፡ አባላቱ የተፈቱት አሳሪው ሲበቃው ነው፡፡ ታዲያ የአዳራሽ ስብሰባ አዘጋጀሁ ብሎ ያልተሳካላትና ይህንንም በዝምታ ያለፈው ሰማያዊ ፓርቲ ድንገት ተነስቶ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱ መደገፍ ወይንስ ማደናቀፍ የሚል ጥያቄ አያስነሳም ትላላችሁ?
የሰላማዊ ሰልፉ ጥሪ ግብታዊ መሆን፤
ሰማያዊ ባህር ዳር ላይ ሰላማዊ ሰልፋ መጥራቱን የነገረን የጎንደሩ ሰልፍ በስኬት በተጠናቀቀ ማግስት ነው፤፡፡ሰላማዊ ሰልፍ የሚደረገው ዓላማው ታውቆ የሰልፉ ግብ ተለይቶ ሊገጥም ይችላል የሚባል ችግር ተተንብዮና መፍትሄ ተተልሞ በሰፊው ታቅዶና በቂ ዝግጅት ተደርጎ ነው፡፡ በተለይ በፖለቲካ ፓርቲዎች የሚጠራ ሰላማዊ ሰልፍ ታስቦ ታቅዶ በቂ ዝግጅት ተደርጎ የሚከናወን እንጂ ኮሽ ባለ ቁጥር አለን ለማለት፣ የህዝቡ ትግል ሲቀጣጠል የድል አጥቢያ አርበኛ ሆኖ ለመታየት፣ በህዘብ መስዋዕትነት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ወዘተ ለፕሮፓጋንዳ የሚጠራ መሆን የለበትም፡፡
ተግባራዊ እንደማያደርጉት እያወቁ ጣልቃ መግባት ለምን ?
ከላይ በመግቢያው የተገለጸውን የህገ መንግስቱንና በ1993 ዓም የወጣውን አዋጅ ድንጋጌዎች ተግባራዊ በማድረግ ለአደባባይ የበቁት ሰልፎች ( በኦሮምያም በአማራም) በፖለቲካ ድርጅቶች ያልተዘጋጁ ናቸው፡፡ፓርቲዎቹ አይደለም የአደባባይ ሰልፍ የሆቴል ስብሰባም ተፈቅዶላችኋል ካልተባሉ የማያደርጉ ለመሆናቸው እነርሱም አይክዱም የወያኔን አንባገነንነት በመከራከሪያነት ያቀርባሉ እንጂ፡፡ ታዲያ አሁን ምን ተገኝቶ ምን ታስቦ ምን የተለወጠ ነገር ኖሮ ነው ሰማያዊ ባህር ዳር ላይ ሰልፍ ጠራሁ ማለቱ ?
እዛው ባህር ዳር ላይ አይደለም የአደባባይ ሰልፍ የአዳራሽ ሰብሰባ ማድረግ ያልቻሉት የሰማያዊ አመራሮች ሰላማዊ ሰልፍ ሲጠሩ በአካባቢው መስተዳድር በኩል ምን የተለወጠ ነገር አይተው ነው? ወይንስ እኛም እንደ ጎንደሮች ማሳወቅ አንጂ ማስፈቀድ አይጠበቅብንም ብለን መብታችንን ተግባራዊ እንደርጋለን የሚል ወኔ በአንድ ጀንበር ተላብሰው? ብለን ጠይቀን ምላሽ ለማግኘት እንዳንሞክር ውጤቱ ከሁለት አንዱንም አላሳየም፡ እንደውም ከከንቲባው ጽ/ቤት ምላሽ እንዳገኙና መቼ የተጀመረና በየትኛው ህግ የተደነገገ አንደሆነ የማይታወቅ የስምምነት ሰነድ ለመፈራረም እንደተቀጠሩ ነበር የተናገሩት፡፡ መጨረሻ በምክትል ሊቀመንበሩ በኩል የተነገረውም ከወትሮው ለየት ለ ነው፡፡ እስከ ዛሬ የምንሰማው ፈቃድ ተከለከልን የሚል ነበር፤ የአሁን ግን ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ሰልፉን ሰርዘናል የሚል ነው፡፡ ሳይመክሩ ሳይዘክሩ ሳያቅዱና ሳይዘጋጁ ጠሩ፣ በዛው መልኩ ሰርዘናል አሉ፤ ታዲያ ይህን ምን ይሉታል፡፡ ሰማያዊዎች ምላሽ ቢሰጡበት መልካም ነው፡፡አባላትና ደጋፊዎችም ለምን ብላችሁ ጠይቁ፡፡ያለፈው ይበቃል፡፡

በኦሮምያ ዉስጥ ተቃዉሞ ተደርጓል፥ህወሃት ተንገዳግዷል –ጻዲቅ አህመድ

$
0
0
ከሁለት መቶ በላይ በሚሆኑ ከተሞች የተደረገዉ የኦሮምያ ተቃዉሞ የተሳካ ነበር። ህዝቡ ሰልፉን በሰላማዊ ምንገድ ቢያደርግም የህወሃቱ የሽብር ጦር አጋዚ 67 ሰዎችን ገድሏል። ከ 500 በላይ የሚሆኑን አቁስሏል። ሰልፉ በተለያኡ ከተሞች ባንድ ግዜ በመደረጉ ታሪካዊ ነበር። ይህ ሰልፍ ህወሃትን ያንገዳገደ ቢሆንም አምባገነናዊዉ ስርዓት በኦሮሞ ህዝብ ላይ ያለዉ ጭካኔ የተስተዋለበት ነዉ።


በኦሮምያ ዉስጥ ተቃዉሞ ተደርጓል፥ህወሃት ተንገዳግዷል – ጻዲቅ አህመድ

በኦሮምያ ዉስጥ ተቃዉሞ ተደርጓል ፥ ህወሃት ተንገዳግዷል ፥ አጋዚ 67 ሰዎችን ገድሏል

$
0
0

ከሁለት መቶ በላይ በሚሆኑ ከተሞች የተደረገዉ የኦሮምያ ተቃዉሞ የተሳካ ነበር። ህዝቡ ሰልፉን በሰላማዊ ምንገድ ቢያደርግም የህወሃቱ የሽብር ጦር አጋዚ 67 ሰዎችን ገድሏል። ከ 500 በላይ የሚሆኑን አቁስሏል። ሰልፉ በተለያኡ ከተሞች ባንድ ግዜ በመደረጉ ታሪካዊ ነበር። ይህ ሰልፍ ህወሃትን ያንገዳገደ ቢሆንም አምባገነናዊዉ ስርዓት በኦሮሞ ህዝብ ላይ ያለዉ ጭካኔ የተስተዋለበት ነዉ።

በኦሮምያ ዉስጥ ተቃዉሞ ተደርጓል ፥ ህወሃት ተንገዳግዷል ፥ አጋዚ 67 ሰዎችን ገድሏል

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live