Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

(ባህርዳር) የቆሰሉና የሞቱ ሰዎች ቁጥር አይታወቅም፤ ዓባይ ማዶ ኮበል በቃጠሎ ወድሟል

$
0
0

bahardar
• ከጎንደር የሚሔዱ ዐማሮች ዘንዘሊማ ላይ መታገዳቸው ለግጭቱ መንስኤ ሆኗል

ሙሉቀን ተስፋው

በጎጃም እምብርት ባሕር ዳር ዐማሮች በጠዋት ነበር ወደ ተጋድሎ ሰልፍ የወጡት፡፡ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በሰላማዊ መንገድ በዐማራ ወገኖቻቸው ላይ የሚደርሰውን በደል እና የጅምላ ግድያ በማውገዝ ወደ መስቀል አደባባይ ሕዝቡ በአንድነት ሔደ፡፡ በዚህ መካከል ከጎንደር ለተጋድሎ የሚመጡ ዐማሮች ዘንዘሊማ ላይ በወያኔ ጦር ወደ ባሕር ዳር መግባት እንዳይችሉ መታገዳቸው ተሰማ፡፡ ሕዝቡ ተመልሶ ከጎንደር አካባቢ የመጡትን ወገኖችን ለማስለቅ ወደ ዓባይ ማዶ መንገድ አመራ፡፡

የዐማራ ተጋድሎ ተሳታፊዎች እግረ መንገዳቸውን ባሕር ዳር ዩንቨርሲቲ (ፖሊ ካምፓስ)፣ ክልል ምክር ቤት፣ አማራ ብድርና ተቋምና ሌሎች መሥሪያ ቤቶች አካባቢ ያሉ የወያኔን ድሪቶ ባንዲራ የአባቶቻችን ደም በፈሰሰባት ትክክለኛ ሰንደቅዓላማ በመቀየር እንዲሁም የክልሉ ምክር ቤት ፊት ለፊት የነበረውን የመለስ ቢል ቦርድ በማቃጠል ወደ ዓባይ ማዶ ነገዶ፡፡ ባሕር ዳር ከተማ የቀረ አንድም ዐማራ አልነበረም ማለት ይቻላል፡፡

የዓባይን ድልድልይ ተሻግረው ወደ ዘንዘሊማ ለመሔድ መንገድ ሲጀምሩ አዲስ ዓለም ገበያ አካባቢ ‹‹ኮበል›› የሚባል የወያኔ ምልስ ወታደሮች ንብረት የሆነ ስጋ ቤትና ግዙፍ የእንጨትና ብረታ ብረት ውጤቶች ማምረቻ ድርጅት አለ፡፡ ይህ ድርጅት በተለምዶም ‹‹ዳሸን ቢር ጋርደን›› በመባል ይታወቃል፡፡ ከዚህ ግቢ ውስጥ በሰለማዊ መልኩ ተጋድሎውን ሲቀጥል በነበረው ሕዝብ ላይ የተኩስ እሩምታ ተከፈተ፡፡ ኮበል ማዶ ካሉ ኮንዶሚኒየም ሕንጻዎች ፎቅ ላይ የወጡ የወያኔ አልሞ ተኳሾች በተቃራኒ አቅጣጫ ከሕዝቡ ላይ ጥይት አርከፈከፉ፡፡ ባዶ እጃቸውን የነበሩ ዐማሮችን ደም ወያኔዎች አፈሰሱ፡፡

በዚህ የተበሳጨው የዐማራ ነበልባል ወጣት ከማደያ ነዳጅ እየቀዳ የኮበል ኢንዳስትሪን ሙሉ በሙሉ በእሳት አጋዬ፡፡ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ዐማሮች ሌሎችን ለማኖር ሲሉ ተሰውተዋል፡፡ በርካቶች ደግሞ ቆስለዋል፡፡ አሁን በዓባይ ማዶ መካከለኛ ክሊኒክና በአዲስ ዓለም ጠቅላላ ሆስፒታል በርካታ እስረኛና ቁስለኛ እንዳለ ነው ከቦታው ያገኘነው መረጃ የሚያመለክተው፡፡

ባሕር ዳር በአሁኑ ሰአት ዝናብ ቢሆንም ወጣቶች ተጋድሏቸውን አላቆሙም፡፡ ‹‹ደም ሰፈስ ደም ይፈላል›› እንዲሉ አበው፤ የዐማራ ወጣቶች ተጋድሎ ያለምንም ጥርጥር በሰማእት ወንድሞቻችን አጥንት ካስማ መሠረት ላይ ይገነባል፡፡


የትግራይ ነጻ አውጪ 6 ሰዎችን በባህርዳር ገደለ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በጎጃም ባህር ዳር ዛሬ ሰላማዊው ተቃውሞ ሰልፍ ሲደረግ ሰልፉ ከመሃል ከተማ እስከ ቀበሌ 10 እስከሚደረስ ድረስ ሰላማዊ ነበር:: ሆኖም ግን ቀበሌ 10 በተለምዶው አጂፕ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ሲደርስ ግን የትግራይ ነጻ አውጭ ድርጅት አስለቃሽ ጭስት ተጠቀመ:: ሰልፉ በአረጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ አላማ ያሸበረቀ ነበር:: ሰላማዊ ሰልፈኞች የርዕሰ መስተዳድሩን ጽህፈት ቤት፤ ዳሽንና ንግድ ባንክ፣ ሞይንኮ፣….ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ህንፃ ፊት ለፊት ያለውን ሃውልት ሰንደቅ አላማ አልብሰውት ነበር::

bahardar

ይህን ሰላማዊ ሰልፈኛ ዛሬ በባህርዳር ከተማ የሕወሓት ነጻ አውጭ ድርጅት በጥይት ቆልቶታል:: እስካሁን በትንሹ 6 ሰዎች መሞታቸው እየተነገረ ሲሆን የቆሰለው ሕዝብ ቁጥር አይታወቅም:: የአካባቢው ነዋሪዎች ግንች በርካታ ናቸው ይላሉ::

የመለስ ዜናዊ ፎቶግራፎች ተቃጥሏል:: ወልቃይት አማራ እንጂ ትግሬ አይደለም ሲል ሕዝብ ጮኳል:: አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈታ; ተማሪ እንጂ ትግራይ ተከዜን አልፎ እንደማያውቅ ሕዝብ ተናግሮ በአስቸኳይ ሕወሓት የሚመራው መንግስት ስልጣኑን እንዲለቅ ጠይቋል::

በባህር ዳር በትግራይ ነጻ አውጪ ዛሬ ተገዱሉት ሰላማዊ ሰዎች ቁጥር 31 ደረሰ

$
0
0

Bahardar

(ዘ-ሐበሻ) በባህርዳር አማሮች ላይ የትግራይ ነጻ አውጪ ሰራዊት የገደላቸው ሰላማዊ ሰልፈኞች ቁጥር 31 ደረሰ:: ለዘ-ሐበሻ የሚደርሱ መረጃዎች እንዳመለከቱት በባሕር ዳር የተለያዩ የጤና መስጫ ተቋማት በአስከሬኖችና ቁስለኞች ተጨናንቀው ውለዋል፡፡

በፈለገ ሕይወት ሪፈራል ሆስፒታል ካዳቨር ክፍል ያለፉ 22 አስከሬኖች ይገኛሉ:: የተቀሩት አስከሬኖች ግን ሆስፒታል ሳይገቡ ቀጥታ ወደ ቤተሰቦቻቸው እንደሔዱ ነው የተገለጸው፡፡

ስለሆነም በባሕር ዳር የታወቀ 31 ያክል ዓማራ በትግራይ ነጻ አውጪ ሲገደል ቁጥሩ ከ40 በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችል የአይን እማኞች ይናገራሉ::

የኢትዮጵያ ሕዝብ እያደረገ ያለውን ተጋድሎ የሚደግፍ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ በዋሽንግተን ዲሲ

$
0
0

DC
ለወገን ትግል የአጋርነት ጥሪ

በሃገራችን ኢትዮጵያ በሁሉም አቅጣጫ የነጻነቱ ደወል እየተሰማ ይገኛል፣ከጎንደር እስከ ሃረር፣ከጋምቤላ እስከ አዳማ ህዝባችን ከጠላት ተናንቆ እየጣለም እየወደቀም ነፃነቱን ለማውጅ የተቃረበበት ግዜ ላይ ይገኛል።

እርሶስ ነጻነቶን አያውጁም? ከሆነ ህዝባችን እያደረገ ላለው ተጋድሎ አድናቆታችንን ለመግለጽ፣ደጀንነታችንን ለማሳየት፣እንዲሁም አፋኙን የወያኔ ስርዓት አቀማጥለው ያሳደጉትን እረዳቶቹን ይብላን ለናንተ ለማለት የፊታችን ማክሰኞ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ስቴት ዲፓርትመንት ፊት ለፊት ታላቅ ሰልፍ የዋሽንግተን ዲሲ የጋራ ግብረ ሃይል ከተለያዩ የነጻነት ናፋቂዎች ጋር በመተባበር ያዘጋጀ ስለሆነ በቦታውም ሁላችንም በመገኘት ድምፃችንን እንድናሰማ ወገናዊ ጥሪውን ያቀርባል።

ቦታ ፦ Departement of State
2201 C St NW
Washington, DC. 20520

ቀን ፦ Tuesday August 9th, 2016

ሰአት ፦ 9:00 AM

የዋሽንግተን ዲሲ የጋራ ግብረ ሃይል። dcjointtaskforce@gmail.com

ዐማራው፣ ዐማራዊ ማንነቱን አረጋግጦ፤ ጀግንነቱንና ኢትዮጵያዊነቱን በደሙ እያስከበረ ነው! –ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት      

$
0
0

ሐምሌ  ቀን ፪ሺህ፰  ..             ቅፅ ቁጥር ፲፱

Moresh-901.jpgዐማራው የኢትዮጵያዊነት ዋልታና ማገር፣ ወራጅና ጭምጭም፣ ስሚንቶና አሸዋ መሆኑ ይታወቃል። ይህን ማንነቱን ጠንቅቀው የሚያውቁ፤ የአገርና የትውልድ ከኻዲዎች፣ ዐማራውን የሌሎች ነገድና ጎሣዎች ጠላት አድርገው በመሳል፣ ላለፉት ፳፭(ሃያ አምሥት) ዓመታት የዘረኛው የትግሬ ወያኔ አገዛዝ፣ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል እንዲፈጸምበት አድርገዋል። በመሆኑም በቁጥር ከአምስት ሚሊዮን የማያንሱ ዐማሮችን በልዩ ልዩ መንገዶች ከምድረ-ገጽ እንዲጠፉ አድርገዋል። አንዳንድ አወቅን የሚሉ፣ የማንነት ቀውስ ውስጥ የገቡ ሰዎችም «ዐማራ የሚባል ነገድ የለም» እስከ ማለት የደረሱ መኖራቸውን፣ ዐማራው በትዕግሥትና በትዝብት ሲያያቸው እንደኖረ ይታወቃል። ወያኔም በትዕቢት ተወጥሮ፣ ዐማራን «ፈሪ፣ ሽንታም፣ ወራሪ፣ ትምክህተኛ፣ ነፍጠኛ»፣ ወዘተርፈ እያለ የዐማራን ዘር ከመግደልና ከማንገላታት አልፎ፣ መልካም ስምና ታሪኩን ጥላሸት ሊቀባ መሞከሩ በግልጽ ይታወቃል። ሆኖም፣ ሁሉም ነገር ገደብና ወሰን አለውና፣ የዐማራው ድምፅ ከፍ ብሎ እንዲሰማ በቆራጥነት የቆሙት ልጆቹ ባሰሙት ጩኸት፣ ይኸውና የጉዳዩ ባለቤት የሆነው የዐማራው ሕዝብ ከሐምሌ 5ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ፣ በኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ፋና ወጊነት የተቀጣጠለው ሕዝባዊ አመጽ ጎንደር ከተማን፣ አዘዞን እና ደንቢያን አካቶ፣ በዛሬው ዕለት ማለትም ሐምሌ 30 ቀን 2008 ዓ.ም. ሕዝባዊ አመጹና እምቢተኝነቱ ወደ ገብርየ አገር፣ «ራስ ጋይንት» ተሸጋግሮ ውሏል። የራስ ጋይንት ሕዝብ የወያኔን የስለላና የአፈና መዋቅር በጣጥሶ፣ «ወልቃይት ጠገዴ ዐማራ ነው!»፣ «ደንበራችን ተከዜ ነው!»፣ «አላማጣ፣ ሰቆጣ የዐማራ ነው!»፣ « የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች፣ ኮሎኔል ደመቀ፣ አንዱዓለም አራጌ፣ እስክንድር ነጋ ይፈቱ! በኦሮሞ ወንድሞቻችን ላይ የተከፈተው ጥቃት ይቁም!» እያሉ፣ ዐማራዊ ማንነታቸውን አስረግጠው፣ ጀግንነታቸው በኢትዮጵያነት የተለወሰ ኅብር መሆኑን አሳይተዋል።

የዐማራዊነት ጀግንነትን እንኳን ወዳጅ ጠላቶች፣ ማለትም፦ ደርሽቦች፣ ግብፆች፣ ጣሊያኖችና እንግሊዞች የመሰከሩት ገሐድ ዕውነት ለመሆኑ ለአፍታ መጠራጠር አይቻልም። ይህ ጀግንነትና ኅብረ-ብሔራዊነት የዐማራው ማንነት መገለጫው በመሆኑ፣ ሌሎቹ አግልለውትና የሞት ፍርድ ፈርደውብት እያለ እንኳን፣ ይህንም እያወቀ፣ በእነርሱ ላይ ቂምም ሆነ ጥላቻ በልቡ አልቋጠረም። ጎንደር፣ ጋይንት፣ ደብረታቦር፣ ባሕርዳር፣ አዘዞ እና ቆላድባ በተካሄዱ የሕዝባዊ እምቢተኝነት የተቃውሞ ሰልፎች፣ «በኦሮሞ ወንድሞቻችን ላይ የሚፈጸመውን የዘር ማጥፋት እንቃወማለን!»፣ «በቀለ ገርባ ይፈታ!» የሚሉ መፈክሮችን ከራሱ ኅልውና በፊት አስቀድሞ አስተጋብቷል። ይህ የዐማራው የማንነቱ መለያ፣ የሆደ ሠፊነቱ መገለጫ፣ የትዕግሥቱ ስፋት መታወቂያ በመሆኑ፣ ሕዝባችን ላሳየው ጀግንነት፣ ቆራጥነት፣ ከሁሉም በላይ ዐማራዊ ማንነቱን ከኢትዮጵያዊነት ጋር ለንቅጦ፣ ለአገራችን ዳግም ትንሣኤ የለኮሰው የለውጥ ችቦ እኛ  በውጭ በስደት የምንኖረውን ልጆቹን አኩርቶናል።

ጎንደር፣ የኢትዮጵያ አንድነት ሲቋጠርበት እና ሲፈታበት የኖረ ታሪካዊ ምድር ነው። ዘመነ መሣፍንት የተጀመረው የትግሬው ራስ ሥዑል ሚካኤል በጎነጎነው ሤራ አማካኝነት በአገራችን በተከለው የእርስ በእርስ ጦርነት ከዚሁ ጎንደር ላይ ነው። ይህ ሤራ አገራችንን ለ70 ዓመታት ያህል ማዕከላዊ አመራር አሳጥቶ፣ ሕዝባችን እርስ በርሱ እንዳጫረሰ ይታወቃል። ይህ የብላ ተባላና፣ የፍዳ ዘመን የተቋጨውና የኢትዮጵያ አንድነት የተቋጠረው፣ ከዚሁ ጎንደር ውስጥ ከቋራ በበቀሉት፣ በአባ ታጠቅ ካሣ (ዳግማዊ ዐፄ ቴዎድሮስ) በተመራው ፀረ-ዘመነ መሣፍንት እንቅስቃሴ ነው።

ከ1520 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 1535 ዓ.ም. ድረስ በክርስትና ሃይማኖትና በፍትሐ ነገሥት ላይ የተመሠረቱን ዕሴቶችን አጥፍቶ አረባዊ ማንነት ለማለበስ የተነሳው ግራኝ አሕመድ፣ ለ15 ዓመታት ያህል አገሪቱና  ሕዝቡን ለማጥፋት ያደረገው ጥረት፣ የተገታው ጎንደር ላይ፣ ዘንተራ፣ ደጎማ ሥር በተደረገ ጦርነት ላይ ነው። ይህ በጎንደር ምድር በግራኝ ላይ የተገኘው ድል ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነት ማንሰራራትና መቀጠል ዋስትና ሆኖ ማገልገሉ ግልጽ ነው።

ልክ እንደዛሬው የትግሬ-ወያኔ ኢትዮያንና ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት እንደሚያደርገው ሙከራ፣ ከ1928 ዓ.ም. እስከ 1936 ዓ.ም. የጣሊያን ፋሽስት ኢትዮጵያውያንን በነገድ ከፋፍሎ ለመግዛት ሞክሮ ነበር። ሆኖም የፋሽስት ጣሊያኖች ቅዠት ለመጨረሻ ጊዜ ላይመለስ ያከተመው፣ ጀግኖቹ የጎንደር አርበኞች፣ ጎንደር ላይ መሽጎ በነበረው የጄኔራል ናዚ ጦር ላይ፣ በሣንቃ በር፣ በቁልቋል በር፣ በሊማሊሞ፣ እና በጭልጋ ሰራባ ላይ በተጎናጸፉት ድል ነው። ይህም የኢትዮጵያን ነፃ አገርነት እንዲረጋገጥ ወሣኝ ሚና የተጫወተ እንደሆነ ይታወቃል።

በሌላ በኩል ወያኔ ለ17 ዓመት በትጥቅ ትግል የቆየው ትግራይና ጎንደር ክፍለ-ሀገሮች ውስጥ መሆኑ ይታወቃል። በ17 ዓመቱ ግብግብ ጎንደር አያሌ ጀግኖቹን አጥቷል። የደርግ አገዛዝ በሕዝቡ አመኔታ ሲያጣ፣ ወያኔ ዲሞክራት መስሎ በአስተጋባው ፕሮፓጋንዳው፣ «ከደርግ የከፋ አይመጣም» በሚል የሞኝና አርቆ ካለመሳብ በመጣ ችግር፤ ወያኔ ባገኘው ድጋፍ ተበራቶ፣ ጎንደር ከተማን እንደያዘ፤ ማዕከላዊ መንግሥቱ በሥልጣን ላይ ለመቆየት የቻለው ሁለት ወራት አይሞላም። የጎንደር በወያኔ እጅ መውደቅ፣ ለኢትዮጵያ መበታተን ፈር ቀደደ። ስለዚህ ሰሞኑን፣ ጎንደር ላይ የተጀመረው ሕዝባዊ አመጽ፣ ያለፉት ታሪኮቻችን ፈለግ ተከታይ በመሆኑ፣ የአገራችን የአንድነት ትንሣኤ ብሥራት እንደሆነ በልበ ሙሉነት ታሪክን ነቃሽ በማድረግ መመስከር ይቻላል። በመሆኑም ዛሬም ዘረኛውን የትግሬ-ወያኔ ቡድን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ አሽንቀንጥሮ ለመጣል፣ ጎንደር ላይ የተለኮሰው የለውጥ እሣት፣ ወያኔን ለብልቦ፣ የአገራችን አንድነትና የሕዝባችን ዕውነተኛ በግለሰብ ነፃነት ላይ የተመሠረተ ነፃነትና ዕኩልነት እንደሚያጎናጽፈን ጥርጥር የለንም።

ጥሪ ለኢትዮጵያ ሕዝብ፦ በትግሬ-ወያኔ አገዛዝ በግፍ የተገደሉ ወገኖቻችን ደም ደመ-ከልብ ሆኖ የማይቀረው የሕይዎት መስዋዕትነት ከፍለው ያቀጣጠሉትን የነፃነት ትግል ወደፊት ስንገፋ ብቻ ነው። የትግሉም የመጀመሪያ ግብ እያንዳንዷ የኢትዮጵያ ግዛት ከግፈኛው የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ነፃ እስክትወጣ ድረስ መሆን ይኖርበታል። በትግሉ ወቅት ለወደቁ ኢትዮጵያዊ ሰማዕታት፣ በስማቸው መንገዶች፣ ትምሕርት ቤቶች፣ እና የመታሰቢያ ሐውልቶች ልናቆምላቸው ይገባል።

በዚህ አጋጣሚ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት፣ ላለፉት አራት ዓመታት፣ የዐማራው ድምፅ እንዲሰማ ያደረገው ጥረት፣ ሰሚ ጆሮ እና አዳማጭ ኅሊና ያገኘ መሆኑን፣ ከጎንደር ሕዝባዊ አመጽ ለማረጋገጥ በመቻላችን፣ ልፋታችን የበለል አለመቅረቱን እንድንገነዘብ አድርጎናል። ይህም የተያያዝነውን የዐማራን ኅልውና እና ማንነት የማስጠበቅ ትግላችን ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እያረጋገጥን፣  እስካሁን በቀጥታ የትግሉ አካል ያልሆኑ አካባቢዎች ትግሉን በፍጥነት እንዲቀላቀሉ ጥሪያችን እናቀርባለን።

 

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!

ዐማራነታችን የማንነት መገለጫ መታወቂያችን፣ ኢትዮጵያዊነት ኃይማኖት ማተባችን ነው!

ፈለገ-አሥራት የትውልዳችን ቃል ኪዳን ነው!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

በጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን  በንጹሃን  ሰልፈኞች ላይ መንግስት እየፈጸመውን የሚገኘውን  ግፍ ለማውገዝ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በበርሊን ለማድረግ ወሰኑ።

$
0
0
Peaceful #OromoProtests demonstrators arrested & beaten up. Police takes off shoes to prevent them from running.

Peaceful #OromoProtests demonstrators arrested & beaten up. Police takes off shoes to prevent them from running.

ዘርይሁን ሹመቴ ከጀርመን

ኢትዮጵያውያን  በጀርመን ኑረምበርግ በምትባል ከተማ ነሃሴ 1 2008 ዓም ባደረጉት ታላቅ ስብሰባ በመላው  የኢትዮጵያ ክፍል እየተቀጣጠለ ባለው የሀዝብ ለአምባገነናዊ  ስርአት አልገዛ ባይነት ምክንያት በመንግስት ታጣቂዎች  እየተፈጸመ  ያለውን ግድያ እስራት እንዲሁም ድብደባ አውግዘዋል። በተጨማሪም  በጀርመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ  ኢትዮጵያውያን በአሰቃቂ  ሁኔታ  በንጹሃን  ኦሮሞ እና አማራ ህዝብ የመንግስት ታጣቂዎች እየፈጸሙ ላሉት የነፍስ መገደል እና እስራት በመቃወም  በጀርመን በርሊን ከተማ  ድምጻቸውን ለአለም ለማሰማት ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ለማዘጋጀት ፕሮግራም  አዘጋጅተዋል።

 

በስብሰባውም  የአርበኞች ግንቦት ሰባት የኮምኒኬሽን  ሀላፊ አርበኛ ኑር ጀባ ከኤርትራ ቀጥታ  በስልክ መስመር በመግባት ለታዳሚው  ከእያንዳዱ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚነሱት ህዝባዊ አመጽ ጀርባ  የአርበኞች ግንቦት ሰባት ከፍተኛ እንቅስቃሴ አለበት በማለት ማረጋገጫ  ሰጥቶል። የኮምኒኬሽን  ሀላፊው አርበኛ ኑር ጀባ በማከልም አምባገነናዊነትን ዘረኝነትን እንዲሁም ኢፍትሃዊነትን በመቃወም  በአደባባይ በመንግስት ሀይሎች በጥይት ለረገፉት ንጹሃን የኦሮሞ እና የአማራ ተወላጆች የወያኔ መንግስት ሃላፊነቱን ሙሉ በሙሉ መውሰድ እንዳለበት አሳስቧል። እንደ አርበኛ  ኑር ጀባ  ገለጻ መሰረት አርበኞች ግንቦት ሰባት የወያኔን መንግስት በ3 ዓይነት መንገድ እየታገለ መሆኑን ለታዳሚው  ገልጸዏል። 1ኛው ህዝባዊ አመጽ በአገር ውስጥ በማነሳሳትና በመደገፍ 2ኛው ከኢትዮጵያ ውጭ  ወያኔንና የወያኔ ድርጅቶችን የማዳከም እንቅስቃሴ 3ኛው የትጥቅ ትግል ናቸው።  በተለያዩ  ጊዜያት የወያኔን ስርዓት በሀይል ለመጣል በሚደረገው  የትጥቅ ትግል በውጭ  የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እያደረጉት የሚገኘውን  የሞራል የቁሳቁስ የገንዘብ እርዳታ አርበኛ ኑር ጀባ  በሰራዊቱ ስም  ታላቅ ምስጋናውን በማስተላለፍ ፤ ይሀ ዓይነቱ  ድጋፍ  በሰፊው  እንዲቀጥል ጥሪ አስተላልፉዋል። ታዳሚውም በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች

የሚገኘው  የኢትዮጵያ ህዝብ በጨቋኞች አምባገነኖችና ከፋፋዮች መገዛት በቃኝ ብሎ  በአደባባይ ጸረ ወያኔ ትግሉን ለወራት አፏፉሞ በመቀጠሉ እና እጅግ አስገራሚ መስዋቶችን እየከፈለ በመሆኑ ለዚህ  ትግልን የተፈለገውን ግብ እንዲመታ  ለመደገፍ ወስነዋል። በዚህ የአቁዋም መግለጫ በውጭ አገር የሚኖሩ መላው ኢትዮጵያውያን በንጹሀን ህዝቦች ላይ ከፍተኛ ጭካኔ የተሞላበት ጭፍጨፋ እና ግድያ ሲፈጸም ቸል ማለት እንደሌለበት ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።

 

ይህንን ተከትሎም  ታዳሚው ለኢትዮጳያ ህዝብ  ያለውን አጋርነት ከዚሀ በታች በተዘረዘሩት እንቅስቃሲዎች ገልጸዋል።

1ኛ የወያኔ ኢህአዲግ በህዝባችን ላይ እየፈጸመ ያለውን ኢሰብአዊ ድርጊት ለአለም አቀፍ ህብረተሰብ በማጋለጥ

2ኛ በበርሊን ከተማ  ከፍተኛ የተቁዋሞ ሰልፍ በማዘጋጀት የአለም  አቀፍ ማህበረሰብ በወያኔ ላይ ተጽእኖ እንዲያደርግ በመታገል

3ኛ አለአግባብ  የታሰሩ የህዝብ ተወካዮች ጋዜጠኞች የፖለቲካና የሀይማኖት መሪዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ከፍተኛ ግፊት በማድረግ

4ኛ ወያኔ ኢህአዲግ ሃገሩንና ህዝቡን ማስተዳደር ስላልቻለ በአስቸኩዋይ  ከስልጣን የሚወርድበትን እንዲሁም ስልጣኑን ለህዝብ አስረክቦ የሽግግር መንግስት ለመመስረት  የሚያስችል ነጻና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ  እንዲካሄድ መንገዶች በመፍጠርና በማመቻቸት ናቸው።

 

ዘርይሁን ሹመቴ ከጀርመን

 

 

 

Hiber Radio: ብ/ጄኔራል ሀይሉ ጎንፋ፣ ኮ/ል አለበል አማረና ኮ/ል ደረሰ ተክሌ ሰራዊቱ ጠመንጃውን በዘረኛ አዛዦቹ ላይ እንዲያዞር ጠየቁ

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


የህብር ሬዲዮ ነሐሴ 1 ቀን 2008 ፕሮግራም

ብርጋዴር ጄኔራል ሀይሉ ጎንፋ ለህብር ሬዲዮ ከሰጡት ቃለ መጠይቅ(መጀመሪያ ክፍል)

<...>

ኮ/ል ደረሰ ተክሌ በጋራ ከብ/ጄ/ሀይሉ ጎንፋ ጋር ለህብር ሬዲዮ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ለሰራዊቱ ካስተላለፉት መልዕክት የተቀነጨበ(ክፍል አንድ -ያዳምጡት)

<... ...> ዶ/ር መረራ ጉዲና የኦፌኮ ሊቀመንበር የኢትኦጵያ የጋራ ትግል ሸንጎ ዛሬ በዋሽንግተን ባካሄደው ሕዝባዊ ውይይት ላይ ከተናገሩት(ቀሪውን አዳምጡ)

<... ...> ኢ/ር ይልቃል ጌትነት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ሸንጎ በጠራው ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ ከተናገሩት

<...> አቶ ኦባንግ ሜቶ በሸንጎ ጉባዔ ካስተላለፉት ጥሪ

ለአንድ ሳምንት በሚኒሶታ የተካሄደው የኦሮሞ ስፖርት ፌዴሬሽን ዓመታዊ የስፖርት ውድድር መዝጊያ እና በዝግጅቱ ላይ የሁሉም ወገኖች መሳተፍ ተስተውሏል (ቆይታ ከዘሐበሻ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ሔኖክ አለማየሁ ጋር ስለ ዝግጅቱ ቆይታ አድርገናል ያድምጡት)

በአገር ቤት በኦሮሚያና በአማራ ክልል የተካሄደውን ሰላማዊ ተቃውሞና የአገዛዙን የጥይት ምላሽ አስመልክቶ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ዘገባ ሲዳሰስ (ልዩ ጥንቅር)

ዜናዎቻችን

የአጋዚ የቀድሞ አዛዥ ኮ/ል አለበል አማረም ሰራዊቱ ሕዝብ ግደል ባሉት መሪዎቹ ላይ ጠመንጃውን እንዲያዞር ጥሪ አቀረቡ

ዶ/ር መረራ ጉዲና ኢህአዴግ የጀመረው አጥፍቶ መጥፋት እንደማያዋጣው ገለጹ

በአማራና በኦሮሚያ ክልል በሁለት ቀናት ብቻ ከ140 በላይ ንጹሃን በአገዛዩ ታጣቂዎች ተገደሉ

በኦሮሚያ በተካሄደው ተቃውሞ በርካታዎች በአገዛዙ ታጣቂዎች ተገደሉ

አያሌዎች ታስረዋል፣አገዛዙ ጣቱን በተቃዎሚዎች ላይ ቀስሯል

የተቃዋሚዎች የተባበረ ትግልና አመራር ሊመጣ የሚችለውን አደጋ ያስቀራል አሉ

ኢ/ር ይልቃል የሕዝቡ ጥያቄ ኢህአዴግ በቃኝ ነው ሲሉ ገለጹ

በኢትዬ-ኬኔያ ድንበር ላይ ሰሞኑን ውጥረት አይሎ የአዲስ አበባ ገዢዎች ለናይሮቢ ማስጠንቀቂያ ሰጡ

እስራኤል በኢትዮጵያ የሚገኙ ዜጌቾ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማስጠንቀቁያ አወጣች

“በአራቱም አቅጣጫ ስትዘዋወሩ ተጠንቀቁ”የእስራኤል ውጭ ጉ/ሚ/ር

የአሜሪካው ፕሬዜደንታዊ ተፎካካሪ ትራምፕ አገራቸው ጥገኝነት በሰጠቻቸው ዜግች ላይ ጥርጣሬ እንድታደርግ መከሩ

“ሙስሊም የሚለውን ቃል ከዚህ በሁዋላ አልጠቀምም”በማለት ቃል ገቡ

በቬጋስ ኢትዮጵአዊው ሆን ብሎ አስነስቶታል በተባለው እሳት ሳቢያ ሕይወት ጠፋ ለእስር ተዳረገ

አገር ለባለ አገሩ ታሪክም ለባለ ታሪኩ

$
0
0

ከአየነዉ ብርሃኑ

ዉድ አንባቢያን የመጣጥፏ መነሻ ሃሳብ የተወሰደዉ ”The Battle of Adwa, African victory in the age og Empire በሚል ከ Raymond Jonas በ 2011 ክተጻፈ መጽሃፍ መሆኑ እንዲታውቅልኝ አሳስባለሁ ።
Gonder6

አገራችን ኢትዮጵያ ትልቅ አገር ነበረች፡ ህዝቧም ለዕምነቱ ያደረ፤ስብእናን የተላበሰና ለእዉነትም ሟች እንድነበረ ከዕድሜ ጠገብ ሊቃዉንት እና ከቅሬተ መረጃዎቻችን መረዳት ይቻላል።

አያሌ አገራት ከኢትዮጵያ በኋላ እየተነሱ ዛሬ ገናናዎች ሆነዋል በአንጻሩ ግን የኛ ኢትዮጵያ እንደ አገር ኢትጵያዉያንም እንደ ህዝብ የመጨረሻ ዉዳቂዎች ሆነን ዓለም ተጠይፎናል ።ይህ ሁሉ ርካሽነት ከምን መጣ፟ ?
በኢትዮጵያዉያን ዘንድ ስብእናን ማዋረድ፤ ለእዉነት ከመቆም ይልቅ ሃሰትን መድፈር፤ ከጋራ ጥቅም ይልቅ ለግል ጥቅም መገዛት በአጠቃላይም ለኢትዮጵያዊነት እሴት እየተሟጠጠ መሄድ ምክንያቱ የዉጭ ወራሪ ሃይላት ኢትዮጵያ ዉስጥ መግባት መጀመር ሲሆን ይህ ክስተት ይበልጥ መልክ እየያዘና እየተጠናከረ የመጣዉ ግን በጣሊያን ወረራ ነዉ ይላሉ ጠበብት።

ጣሊያን ኢትዮጵያን ለመዉረር ሲያቅድ መጀመሪያ ላይ ዕግሩን ያሳረፈዉ ምጽዋ ላይ ነዉ። ከምጽዋ ወደ መሃል አገርና ወደ ደጋዉ ለመዝለቅ ግን ለጣሊያን ቀላል አልነበረም።

ዶጋሊ ላይ በራስ አሉላ መሪነት በተደረገዉ ጦርነት ወሬ ነጋሪ እንኳን ሳይቀር የጣሊያን ጦር ድምጥማጡ እንዲጠፋ በመደረጉ የጣሊያን ወይዛዝርት ከል እንዲለብሱ ፖለቲከኞች ወደ ህዝብ ፊት ለመቅረብ ሃይል ያጡበት እና የወታደር ሃላፊዎች ለማመን የሚያቅት ሽንፈት እንዲቀበሉ የተገደዱበት ሁኔታ ተፈጠረ። በጣሊያን ምድር ዋይታዉ ቀለጠ እናም እንደ ማጽናኛ ተደርጎ የተወሰደዉ ለአለቁት ጣሊያኖች ሃዉልት ማሠራት እና ሃይልን አጠናክሮ ወደ ኢትዮጵያ መመለስ ሆነ።

ጣልያን ሃይሉን አጠናክሮ ወደ ኢትዮጵያ ቢመለስም ኢትዮጵያዉያንን ፊት ለፊት መግጠም ግን አሁንም የሚሞከር አልሆነም እና ሌሎች መንገዶችን ማፈላለግ ነበረበት። ጠቃሚ ነዉ ተብሎ የታመነበትም መንገድ ለጣሊያን ያደሩ ኢትዮጵያዉያንን በመመልመል በግንባር ማሰለፍ የሚል ሆነ።በዚህም መሠረት በህብረተሰቡ ዉስጥ ችግር ያለባቸዉን ግለሰቦች ለምሳሌ ሌቦችን ፤ ቀጣፊዎችን እና በአጠቃላይ በህብረተሰቡ ዘንድ ተቀባይነት የሌላቸዉ ግለሰቦችን በመመልመል የተጀመረዉ የባንዳ ምልመላ በአጭር ጊዜ ዉስጥ አድጎ ጣሊያን አያሌ የአስካሪስ ወይም ባንዳ ባታሊዮኖች ለማቋቋም ቻለ።
ጣሊያን ይህንን ሲያደርግ ለአጭር ጊዜ ድል ብች ሳይሆን ለረጅም ጊዜ ዕቅዱ በሚያመቸዉ መንገድ ነበር። በዚህም አንድ ባንዳ ወታደር ሲቀጠር ሚስት እንዲያገባ እና ቤተሰብ እንዲመሠርት የቤተሰቡ አባላትም በወታደራዊዉ ስራ እንዲሳተፉ ከማድረግ ባሻገር የጣሊያንን ቋንቋ ባህል እና አጠቅላይ ከኢትዮጵያዉያን የሚለዩበትን መንገድ እንዲያጠናክሩ ከፍተኛ ጥረት ይደረግ ነበር ይላሉ ጸሃፍት። ይህ መሆኑ ነዉ እንግዲህ የባንዳነት መሠረቱ።

አስካሪም ይበለዉ ባንዳ ወይም ባሺ ቡዙቅ የቅጥረኛ ጥርቅም ጊዜዉ ይዘግይ እንጂ ጣሊያንን ከዉድቀት ሊያድነው አልቻለም እና ጣልያን ከመሸነፍ አልዳነም።እንዳልሆነም ሆኖ ወደመጣበት ተመልሶአል ። ጥሎት የሄደዉ ጠባሳ ግን ይሀዉ አንድ ምዕተ ዓመት ሙሉ እያመሰን እያተራመሰን እና ህልዉናቺንንም እየተፈታተነን ነዉ።

ይህ ወገንን በወገን ላይ ማነሳሳት እና እርስ በእርስ ማናከስ ስልጣንን ለማስፋፋት እና የሥልጣን እድሜንም ለማራዘም ተመራጭ መንገድ ሆኖ በመገኘቱ ከጣሊያን መባረር በኋላ በተከታታይ የተነሱ መንግሥታትም ይሁን ብለዉ ተቀብለዉ በሥራ ላይ አዉለዉታል።

የፊዉዳሉ ሥረአት ቁንጮ የነበሩት ንጉስ ወደ መንበረ ሥልጣናቸዉ ሲመለሱና መንግሥታቸዉን ሲያዋቅሩ ቅድሚያ የሰጡት ለጣልያን አገልጋይ ባንዶች ሲሆን ጣሊያንን አስጨንቀዉ ላባረሩ አርበኞች ግን መጨረሻቸዉ ስቅላት ግዞትና እንግልት እንደነበር ከታርክ ብቻ ሳይሆን ከኣይን ምስክሮች የምነሰማዉ ሃቅ ነው።

መንግሥታቸዉንም ካዋቀሩ በኋላ ቢሆን የንጉሱ የትኩረት አቅጣጫ አድርገዉ የወሰዱት ህዝብን ረግጦ መያዝ ነበርና ጀሮ ጠቢ በሚል የሥለላ መረብ በመዘርጋት ለሀገሩ እና ለወገኑ የሚያስብ ዜጋ እድሜ እንዳይኖረዉ የተቻለዉ ሁሉ ሲደረግ ቆይቶአል።

ከዚህም ባሻገር ለጣሊያን ለማደር የመጀመሪያዉን ደረጃ ለያዘዉ ለሰሜኑ ክፍል ቅድሚያ በመስጠት በትምህርት በልማት እና በመሳሰሉት ጥቅማ ጥቅሞች የአገር ሀብት ያላግባብ እንዲባክን አድርጎአል የፊዉዳሉ ሥረኣት።
የህረተሰብ የንቃተ ህሊና ዕድገት እና ለዉጥ ፈላጊነት የታሪክ ሂደት ነዉ ። በመሆኑም የብሶት መጠራቀም የፊዉዳሉ ሥረአት ከነግሳንግሱ እንዲገረሰስ አድርጎታል።

በፊዉዳሉ ሥረዓት እግር የተተካዉ ወታደራዊዉ ሥረኣትም ቢሆን የመጀመሪያ ዓላማዉ አድርጎ የተነሳዉ የሥልጣኑን መሠረት ማደላደል ነበር እና ይህንንም ለማድረግ ይሆኑኛል የሚላቸዉን የህብረተስብ ክፍሎች ከጎኑ ለማሰለፍ ጊዜ አልወሰደበትም። ለደርግ ያደሩ ምሁራንም የአቅማቸዉን ሞከሩ በህዝብ ግድያ ላይ የተሰማሩ ነፈሰ ገዳዮችም እጃቸዉ በደም ቢጨቀይም የህዝብ እምቢተኝነት እያደገ በመምጣቱ ሥልጣን ማደላደሉ ለደርግ አልጋ በአልጋ አልሆነም።ትግሉም ቀላል የማይባል የትዉልድ ጥፋት አስከትሎአል። በወታደርዊ መንግሥትና በለዉጥ ፈላጊዉ ኢትዮጵያዊ መካከል በተደርገዉ ፍትጊያ አንድ ትዉልድ አለቀ። የዚህ ፍትጊያ ጠባሳ ዛሬ አገራችን በአስካሪስ ዉላጆች እጅ ወድቃ እንዳልሆነች እንድትሆን እና ህዝቧም አዉራዉን እንድተነጠቀ ንብ ባዝኖ እንዲቀር ለማድረግ የራሱ አስተዋጸኦ አድርጎአል።

የፊዉዳሉ ሥረኣትም ሆነ የወታደራዊዉ ሥረኣት እንደነበሩበት የዕድገት ደረጃና የህብረተሰቡ የንቃተ ህሊና ደረጃ የጭቆናዉ ደረጃ ቢለያይም በጠንካራ ጎን በኩል አንድ የሚያደርጋቸዉ ዓቢይ ጉዳይ እንደነበር ግን አሌ የማይባል ሃቅ ነዉ ። በአገር እንድነት እና በብሄራዊ ስሜት በኩል በማይናወጥ መሠረት ላይ የተመሠረተ ዕምነት ነበራቸዉ።የኢትዮጵያንም ህዝብ በእኩልነት የማየት ባህሪ ነበራቸዉ። ህዝብ ከህዝብ የሚስማማበትን እንጂ ህዝብ ከህዝብ የሚናቆርበትን መንገድ ሲያሰሉ ዉለዉ አያድሩም ነበር። የፖለቲካ እንጂ ሁለቱም ሥረኣቶች የዘር ጠላት አልነበራቸዉም።

ለትግራይ መገንጥልና የዮሃንስን ሥርዎ መንግስት ለማስመለስ ወደ ጫካ የገቡት የዛሬዎችቹ የኢትዮጵያ ገዢዎች በለስ ቀንቶአቸዉ ሠፊዋን ኢትዮጵያ ለመቆጣጠር ቻሉ።የኢትዮጵያ ህዝብ የደርግን አስከፊነት አሻግሮ ሲያይ በሩን ለነዚህ ማሺንኮች ወለል አድርጎ ከፈተላቸዉ።እነሱም እግራቸዉን ካስገቡ በኋላ መሠሪ ተግባራቸዉን ቀጠሉበት።

በጣሊያን የተጀመረዉን በዘር የመከፋፈል ተንኮል እና በፊዉዳሉ ሥረአት እና በወታደራዊዉ አገዛዝ የነበረዉን አገልጋይን የማብዛት ዘይቤ አሻሽለዉ ቀጠሉበት። የፊዉዳሉ ሥረኣትም ሆነ ደረግ ባንዳን የሚመለምሉት በግልሰብ ደረጃ ነበር። እነዚህ ዘረኞች ግን ድርጅታዊ መልክ ሰጡት። በዚህም የአገሪቱን ህዝቦች በዘር ከፋፈሏቸዉ ። ባንዳነትንም አስከፊ ገጽታ አላበሱት።
አናሳዎች ናቸዉ። አገር የመምራት ራዕይ የላቸዉም። እዉቀቱም ያንሳቸዋል። ህዝብን እያጠፉ እንጂ እያለሙ የመምጣቱ ልምዱ የላቸዉም። በመሆኑም ኢትዮጵያን እየገዛን እንቀጥላለን የሚለዉ ድፍረቱ የላቸዉም። መጀመሪያዉንም ሳያስቡትና ሳያልሙት የመጣ ወርቃማ አጋጣሚ በመሆኑ እንጂ !! ከዚህም የተለየ ሊያደርጉ አይችሉም።

የሥልጣናቸዉም መቆናጠጫ የመጀመሪያዉ አድርገዉ የወሰዱት ድርጅታዊ መልክ ያለዉ የባንዳ መልመላ ነበር ። ለዚህም ነው ከጦር ምርኮኞች ዉስጥ እምነት ያሳደሩባቸዉን እና ወዶ ገብ የኢህአፓ አባላትን በማሰባሰብ መድረሻዉን እና ዓላማዉን ያላዎቁትን ኢህድንን እንደ አገራዊ ድርጅት ኦህዴድን ለኦሮም ህዝብ በኋላም ደህዴንን ለደቡብ ህዝቦች ጠፍጥፎ በመሥራት ለሥልጣን መቆናጠጫ መንገዳቸዉን አመቻቹ። ዘረኞቹ አራት ኪሎን ሲቆጣጠሩ ዛሬ ያሉበት የማይታወቅ ያኔ ግን እንደ አሸን ፈልተዉ የነበሩት እኛም ተበድለናል ባይ ግለሰቦችና ድርጅቶች ከዘረኞች ጎን ተሰለፉ በዚህም አናሳዎቹ የልብ ልብ ተሰማቸዉና ጫካ ዉስጥ የጻፉትን ታሪክ መምዘዝ ጀመሩ የኢትዮጵያም ታሪክ መቶ ዓመት ብቻ እንደሆነ ተለፈፈ።ምኒልክ ትምህርት ቤትም ሆነ መንገድ ያሠራ የነበረዉ ለወረራዉ እንዲያምቸዉ እንጂ ለኦሮም ህዝብ መማሰብ አልነበረም የሚለዉ ሠበካ በደደቢት ካድሪዎች ብቻ ሳይሆን ለዚሁ ተግባር በጥንቃቄ በተመለመሉ ባንዳዎች እንዲስተጋባ ተደረገ ።… እና ሠገራ እያደር ይገማል ፤ ትግሬና ቆርቆሮ ሳይነኩት ይጮሃል እየተባልክ ኖረሃል ዛሬ ጊዜዉ ያንተ ነዉ የሚሉት እና የመሣሰሉት ህዝብን ከህዝብ የሚያጫርሱ አደገኛ ቅስቀሳዎች በአዳራሽ ዉስጥ ስብሰባ መስበክ ተጀመረ ። በርግጥ ግን ለዚህ መርዘኛ ቅስቀሳ ሰለባ የሆነ የህብረተሰብ ቁጥር ምን ያህል እንደሆነ ጊዜ የሚፈታዉ እንቆቅልሽ ሆኖ ይቆያል ።

ዋናዉ የዚህ ጽሁፍ ትኩረት የትግራይ ዘረኞች ቢቻል ኢትዮጵያን እስከ ወዲያኛዉ በመግዛት ካልሆነም የአገሪቱን ሃብቷን በመዝረፍና ህዝቧን በማጎሳቆል ኢትዮጵያ የምትባል አገር ደግማ እንዳታንሰራራ ማድረግ ባንጻሩ ግን በሃብት የበለጸገች ፤ በፋብሪካ ላይ ፋብሪካ የገነባች የምእራብ እና ደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያን ያጠቃለለች ለም እና ታላቋን ትግራይ መመሥረት መሆኑ ባለፉት 25 ዓመታት ያከናዎኑት እና አሁንም እየገፉበት ያለዉ ተግባር መሆኑ ጸሃይ የሞቀዉ ሀቅ ሆኖ ሳለ በታሪክ ሠሪነቱ ከማንኛዉም በኢትዮጵያ ዉስጥ ከሚኖር የህረተሰብ ክፍሎች የበለጠ እንጂ ያነሰ ድርሻ የሌለዉ መሆኑ የሚታወቀዉ ፤ በጸረ ኮሎኒያል ተጋድሎ ከማንም የበለጠ ተጋድሎ መስዋዕትነት የከፈለ ህዝብና ዕዉነትኛ ማንነቱን እና የአገር ባለቤትነቱን ሃቅ ለማስጨበጥ የምሁራን ችግር አለበት ተብሎ የማይታማዉ የኦሮሞ ህዝብ እንዴት ለነዚህ መሠረተ ባንዳዎች ጠባብ ፕሮፓጋንዳ ሠለባ ሊሆን ቻለ ?

የኦሮሞ ህዝብ በጦር ሜዳ ምርኮኞች ለተመሠረቱዉ ኦህዴድ ብዙም ቁብ እንዳልሠጠዉ በኣንጻሩ ግን ዕምነቱም ተስፋዉም የኦሮሞ ነጻነት ግምባር እንደነበር ሌላዉ ቀርቶ ራሳቸዉ የወቅቱ የሥልጣን ባለቤት የሆኑት ዘረኞች የማይክዱት ሀቅ ነዉ።

የኦሮሞ ነጻነት ግምባር ምሁራን መጀመሪያ ላይ ከወያኔ ጋር መጎዳኘታቸዉ ይሁን እሺ መሰላቸዉ እንበል ። ከሻቢያም ሆነ ከወያኔ መሪዎች ጋር በነበራቸዉ ወዳጅነትና በቋመጡለት የሥልጣን ፍላጎት ያልሆነዉን ሆነ ብለዉ ተቀበሉት እንበል። ወያኔም ሆነ ሻቢያ በስልጣን ላይ ናቸዉ። የኦሮሞ ፖለቲከኞች ግን ዛሬ እንኳን አገር ሊመሩና ህዝብ ሊያስተዳድሩ ይቅርና ለራሳቸዉም መሆን ቸግⶂቸዉ ሰባት ቦታ ተበታትነዉ ለገላጋይ ባስቸገሩበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል።ወድቀት ኣዲስ ነገር አይደለም ክፋቱ ከዉድቀት ተምሮ መነሳት አለመቻል እንጂ።

ይህን ስል የኦሮሞ ምሁራንን ለማስቀየም በማሰብ እንዳልሆነ ይታወቅልኝ ይህን ጀግና ህዝብ ከታሪክና ከሀገር ባለቤትለቱ ለመነጠል የተኼደዉ እቀት እያሳዘነኝ እንጂ !!
በእርግጥ ለሩብ መዕተ ዓመት ያህል በአገር ላይ በደል በህዝብ ላይም ሞልቶ እየፈሰሰ ያለ ግፍ ተፈጽሞአል። ህዝብ ማንነቱን ካጣ ቆየ ሃብቱም ተመዘበረ በእነዚህ በልተዉ በማይጠግቡ አግኝተዉ በማይረኩ አሸንፈዉ በማያዉቁ ህዝብን በማዋረድ ብቻ በሥልጣን ላይ እንቆያለን ብለዉ አልመዉ እየተንቀሳቀሱ ባሉ ጉዶች በዓለም ላይ ያልታዩ አገራዊ በደሎች እየተፈጸሙ ነው። እያወቁም ይሁን ሳያዉቁ የኦሮሞ ፖለቲከኞች ለዚህ ሁሉ ግፍ አስተዋጸኦ አድርገዋል።

ቢዘገይም አሁን ግን ወደ ሃቅ መመለሻዉ ላይ ያለን ይመስለኛል እነዚህ ጉዶች በቃችሁ የሚባሉበት ወቅት ላይ ደርሰናል የማይናወጥ የህዝብ አቋም!!

አንድ አንድ ብልጣ ብልጥ የኦሮሙ ምሁራን ታሪኩን በማዛባት በሃቁ ላይ ሳይሆን በእነሱ ፍላጎት ላይ የተመሠረተ ታሪክ ለመጻፍ እንደሞከሩት ሳይሆን የኦሮሞ ህዝብ በዛሬይቱ እትዮጵያ ምሥረታ ላይ የጎላ አስተዋጸኦ አድርጎአል። ለኢትዮጵያ ነጻነት ከማንም በላይ ተጋድሎ ያደረገ ደሙንም ያፈሰሰ ጀግና ህዝብ ነዉ።

ይህንንም የኦሮሞ ህዝብ ጀግንነት ዮናስ በመጽሃፉ ምዕራፍ 14 ላይ ፍርሃት ሽብርና ተስፋ መቁረጥ በሚለዉ ርዕስ ሥር እንዲህ ሲል ይገልጸዋል፤
”ምኒልክ አድዋ ላይ ድል ሲቀዳጅ የተጻፈ ህግ አልነበረዉም። ወታደሮቹ አልሰለጠኑም ።ወታደራዊ ሙያም አልነበራቸዉም። ክፍያም አልነበራቸዉም። በአዋጅ የተሰባሰቡ ነበሩ። በወኔና ብኄራዊ ስሜት ተሞልተዉ መሣሪያ ያነሱ ዜጎች ነበሩ።ከቅርብ አለቆቻቸዉም ሆነ ከንጉሳቸዉ እንዲሰጣቸዉ ከሚጠብቁት መሣሪያና ከሚጠብቁት ሹመት በስተቀር ምንም ነገር አልነበራቸዉም።
ጦርነቱ ጠንክሮ ከመደበኛ ጦርነት ወደ ጨበጣ ዉጊያ ሲሸጋገር የኢትዮጵያ ወታደሮች ድል የማድረግና የመዝናናት ስሜት አልታየባቸዉም።ሃይላቸዉን በማጠናከር የጣሊያንን ወታደሮች ማባረሩን ተያያዙት እንጅ።የጣሊያን ወታደሮችም ሲሸሹ ማየት የኢትዮጵያን ወታደሮች ወኔ ከፍ አደረገዉ።በአንጻሩ የጣሊያን ወታደሮች የወደፊት እጣ ፋንታቸዉ መቁሰል መሞት እና ያላቸዉን ሁሉ ማጣት መሆኑን ቀድመዉ ስለተረዱት የሞራል ዉድቀት ደረሰባቸዉ ይህም ዉድቀታቸዉን አፋጠነው።” ይልና በመቀጠልም መበታተን እና ሺሺት በሚለዉ ርዕስ ስር ይቀጥላል፤

”አልቤርቶኒ ከብዙ አዋጊ መኮንኖቹ ጋር ከተማረከ በኋላ በእርሱ የተመራዉ ብርጌድ ፍርስርሱ ወጣ።ወታደሮቹም በተበታተነ መልኩ ሺሺት ጀመሩ።አልቤርቶኒ ከመያዙ በፊት ወታደሮቹን ለማሰባሰብ እና ለማደራጀት ሞከረ ግን አልተሳካለትም ምክንያቱም የመጀመሪያዎⶩ ሽሽት ጀመሪዎች ለጣሊያን ያደሩ ባንዶች ስለነበሩና ከአባራሪ የኢትዮጵያ አርበኞች ለመለየት አልተቻለምና። ከዋናዉ የጣሊያን ጦር ሠፈር ዳቦር ሜዳ የሚያገናኘዉ መስመር በኢትዮጵያ አርበኞች ተዘጋ። አባራሪና ተባራሪ ተቀላቀለ በጣሊያን ወታደሮች መካከልም መደናገር ተፈጠረ።ከፊታቸዉ እየተመመ ያለዉን የጦር ማዕበል ሲመለከቱ እነ አሪሞንዲና ሌሎችም የጣሊያን ጦር አዛዦች ግራ ገባቸዉ ። በአንጻሩ የኢትዮጵያ አርበኞች መተላለፊያ መንገዶችን በመዝጋት የሚሸሹትንም ወታደሮች በማሳደድ ከጦር መሪዎች ጋር በቅርብ ርቀት የጦርና ጋሻ መሞሻለቅ ሲጀምሩ የጣሊያን ጦር ተፈታ።በጁሴፔ ባዉዲኒ የሚመራዉ ባታሊዮንም ቢሆን ለዝግጀት ጊዜ አላገኘም። በኢትዮጵያ አርበኞች ተከበበና ተማረከ።ጀኔራል ባራቴሪ ያገሩን ባንዲራ እያዉለበለ በአገሩ ነገሥታት ሥም ቢማጸንም በሺሺት ላይ ያለዉን ወታደር ማስቆም አልቻለም።ሰሚ አላገኘም።ሁሉም እግሬ አዉጭኝ ወደ ኤርትራ ሆነ።በመጨረሻም ባራቴሪ ራሱ በቅሎዉን መጭ በማለት ሺሺቱን ቀጠለ።በሺሺት ላይም እንዳለ መነጸሩ ወደቀበት ለማንሳትም ጊዜ አላገኘም።ሌላኛዉ ጀኔራል እንደ ዓይን እያገለገለዉ ትዕዛዝ ለማስተላለፍ ቢሞክርም ባራቴሪ የሠራዊቱን ሽሽት ለማቆም አልቻለም።

ጭንቀት ፍርሃት እና የመጨረሻዉ ዉድቀት አይቀሬነት በጣሊያን ወታደር መካከል በነገሠበት ወቅት የኦሮሞ ፈረሰኞች በቦታዉ ፈጥኖ መድረስ በጣሊያን ጦር ዉስጥ የነገሰዉን ጭንቀት አባባሰዉ። ዉድቀቱንም አፋጠነዉ።ኦሮሞዎች ፈረሰኞች ናቸዉ።ፈጥኖ በመድረስ፤ ቦታ በመያዝና ፈጥኖም ጥቃት በማድረስ ወደር አይገኝላቸዉም።

ይህ የኦሮሞዎች ጀግንነት ወደ አዉሮፓ ይዘግቡ በነበሩ የአዉሮፓ የዜና ማሠራጫዎች ተረጋግⶏአል።ከፈረሰኛነታቸዉ ባሻገር እጨደዉ \mow them down/ የሚለዉ የኦሮሞዎቹ አዝማች ቃል በጣሊያን ምድር መደመጡ የጣሊያን ሲቪሎች በመንግስታቸዉ ላይ ጥያቄ እንዲያነሱ ብቻ ሳይሆን ለዘመቻ የተዘጋጁ ተተኪ ወታደሮችም ጭንቀት ላይ እንዲወድቁ አድርጏል።” ይላል ዮናስ በመጽሃፉ በመቀጠልም፤ ”ጣሊያኖች ፈረስ የላቸዉም ፈረስ መጋለብም አይችሉም።የነበራቸዉ አማራጭ መሣሪያን እየጣሉ መሸሽ ብቻ ነበር።የጣሊያን ጦር ሺሺት ለኦሮሞዎች ምቹ ሁኔታን ፈጠረላቸዉ።በራሳቸዉ ላይ የደፉት የአንበሳ ጎፈር ኦሮሞ የሚለዉን ስማቸዉን አጎላዉ።ጀግና ተዋጊነታቸዉን እና አስፈሪነታቸዉንም ጨመረዉ።ይህም የኦሮሞዎች አስፈሪነት የጣሊያን ጦር ሞራል እንዲንኮታኮት ጉልህ ሚና ተጫዉⶆል።የኦሮሞዎች አስፈሪ ተዋጊነት እና ኦሮሞዎች መሳሪያ ይዞ ያገኙትን የጣሊያን ወታደር ይሰልባሉ castrate የሚለዉ ማስፈራሪያ ሁሉም የጣሊያን ወታደር መሣሪያዉን እየጣለ እንዲሸሽ አግⶋኣቸዋል።

አንድ የጣሊያን ወታደር ሸሽቶ ኤርትራ ብዉስጥ ከሚገኘዉ ካምፕ ሳዉራ ቢደርስም ህሊናዉን ግን ስቶ ነበር። በካምፕ አካባቢ በመዞርና ያልተለመደ ፈገግታ በማሳየት የኦሮሞ ፈረሰኞ አስፈሪዎች አስፈሪዎች እያለ ይጮህ ነበር።”
በማለት ነበር ዮናስ የኦሮሞን ጀግንነት የገለጸዉ። በዚህ ብቻ አላበቃም እንዲ ሲል ይቀጥላል፤ ”በጀኔራል አርሞንዲ ስር የነበረ አንድ የጣሊያን ጦር የበታች አዛዥ ኦሮሞዎች በጦርነቱ ላይ የነበራቸዉን ወሳኝ ሚና እንዲህ ሲል በሚገባ ገልጾታል።”ወደ ይዞታችን እየተመመ የሚመጣዉን የኢትዮጵያን ወታደር ስመለከት ወደ ስምጥ ሸለቆ የሚፈስ የባህር ማዕበል ይመስል ነበር ብሎታል”።በዚህም ብርጌዱ በኦሮሞ ጦር ተከበበ ጣሊያኖችም ለመከላከል ሞከሩ።ከመራር ጦርነት በኋላ ግን የሰው ሃይላቸዉ እየተመናመነ መሣሪያቸዉም እያለቀ በመሄዱ በጣሊያን ጦር አዛዦች መካከል ፍርሃትና ጭንቀት ነገሠ።መሸሽ በራሱ የማይቻልና ከጦርነት የበለጠ አስፈሪ ሆነ።በኦሮሞ ተዋጊዎች ከመማረክ ራስን ማጥፋት የተሻለዉ አማራጭ ሆኖ ተገኘ። በመሆኑም የጣሊያን የጦር አዝማቾች አንዱ ከሌላዉ በፊት ራሱን ለማጥፋት መሽቀዳደሙን ተያያዙት።ጀኔራል ጋሪባልዲ የሁሉም ፍጻሜ መሆኑን በመረዳት ሞትን መረጠ።

ያለ መልዕክትም ይኸዉ ነዉና ጥሪዉ አፋጣን ምላሽ ይጠይቃል።

ያገሪቱ ምሁራን ችግር የመፍጠር እንጂ ቺግር የመፍታት ልምዱ ባይኖራቸዉም ከዘመኑ ትዉልድ ትምህርት ይዉሰዱ ። እናም አብሮነት ይሰበክ ፡ እነዚህን የትዉልድ አሽክላዎች ጠራርጎ ወደ አስቀያሚዉ የአገራችን የታሪክ ቅርጫት ለመጨመር ትግሉ ይፋፋም። ታሪክ ለባለ ታሪኩ አገርም ለባለ ኣገሩ ነዉና!!!
እግዚአብሔር እትዮጵያን ይባርክ
ህዝቧንም መንፈሰ ጠንካራ ያድርግ !!


እኔ ታዛቢ ነኝ ያነ ነው ደንበሩ

$
0
0

Screen Shot 2016-08-08 at 2.59.21 AM
“ያልረባ ጎጆዬ ቤቀርም ግድ የለኝ፤
እናቴም ልጅ የላት፣ እኔም ወንድም የለኝ።
ሲሰድቡት ዝም ያለ፤
ሲመቱትም ያው ነው።
[ተው አትሻገሩ] እሱ፣ እሱ ነው ደንበሩ
እንዳታሰኙነ እነማን ነበሩ።” … ወዘተ (ከ ህዝብ ድህረ ገጽ የተገኘ)
ላልበላነው እዳ ክፈሉ እይሉ፤
ይግባኝ እንዳንጠይቅ
ሕግ የለ ባገሩ።
ውጊያ አልፈልግም ለሚል ወገን ሁሉ
እስኪ ልጠይቃችሁ፤
ምን ይሁን ፍትሁ?
መንግሥት አለ እንዳልል
መብት አስጠባቂ አንድም አላየሁም፤
ከማቀጨጭ በቀር ገንቢም አልሰማሁም።
ከፋኝ ሲል ገበሬው አሸባሪ አንተ ነህ
ብሎ ያወግዘዋል፣
ጠረፍ ጠባቂውን “ነፍጠኛ አማራ”
ብሉ እንዲሰደብ ነጋሪት ይመታል።
ሰው ባገሩ እንዲህ እንዲሰደብ
ጭራሽም እንዲጠላ ያቁራል በክልል፤
ሰንደቅ አላማንም ጨርቅ ነው ይለዋል
አንዲት አፌ ደፍሮ መንግሥት አለ ለበል?
ሰወች እንዲጠሉ፣ እንዲህ ካስነገረ፣
እንዲት ሰውስ አይከበር በገዛ አገሩ፣
ከተወነጀለም ሰው ያለመግባሩ፤
እኔስ ሰልችቶኛል ማለት እሹሩሩ።
-2-
“ሰው በወንዙ፣ ሰው ባገሩ፣
ቢበላም እሳር፣ ቢበላም፣ መቅመቆ፤
ይከበር የለም ወይ ሰውነቱ ታውቆ።”
ባንዴራውን ሳይቀር ጨርቅ ነው በማለት
ፍጽም አዋርዶታል፣
ገበሪንም በትር ለምን ያዝህ እያለ
በጥይት ይቆላል።
መንግሥት አለ እንዳልል
ትንሽ ትልቅ፣ ውንድ እሴትን ሳይለይ፤
በጥይት ይጠብሳል፣
አንዲት አፌ ደፍሮ መንግሥት አለ ለበል?
አረ ባላህ በሉ ውይንም በየሱስ፤
እስከመቸ ድረስ እንዲህ እንታመስ?
ተው አትከልክሉኝ እኔ ላልቅስለት
ለሆነው የቁም ሙት
ወንድሙን ሲገድል እራሱን በመጥላት፤
ከጡጦ በስተቀር አያውቅ የናቱን ጡት።
ባህልንም አያውቅ እንዳላስመክረው፤
የሱ ሙዚቃ ባህል የጥያት ድምጽ ነው።
ተው አትከልክሉኝ እኔ ላልቅስለት፤
ለሆነው የቁም ሙት።
© ለምለም ፀጋው፣ ንሐሴ 1፣ 2008 (August 8, 2016
በሰሜን በደቡብና በመካከለኛው ኢትዮጵያ ብሶታቸውን በሰላማዊ ሰልፍ ስለገለጹ በመንግሥት
ለተገደሉና ለርሃብ ለተዳረጉ ሁሉ መታሰቢይ ይሁን።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከኤርትራ በቪዲዮ መልእክት አስተላለፉ

$
0
0

የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ መሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ወቅታዊውን የአማራና የኦሮሞ ሕዝብ ትግል አስታከው ከአስመራ በቪዲዮ መልእክት ላኩ:: ፕሮፌሰሩ በኢሳት ቴሌቭዥን በኩል ባስትላለፉት ቭዲዮ ተቃውሚዎች በሰከነ ሁኔታ ተነጋገረው ይተባበሩ ብለዋል:: ሙሉውን ያምድጡት::

የዐማራ ተጋድሎ ቀጣይነትና መስመር ማስያዝን በተመለከተ 7 ነጥቦች

$
0
0

ከሙሉቀን ተስፋው
(የጎበዝ አለቃ አስፈላጊነት)

የዐማራ ተጋድሎ የመኖር መብታችንና ሕልውናችን እስኪረጋገጥ ድረስ ይቀጥላል፡፡ ይህ ተጋድሎ የዐማራ ሕዝብ ነው፤ በማንም ጣልቃ ገብነት የተመራ አይደለም፡፡ ሕዝቡ ነው እየተጋደለ ያለው፤ ባለቤትነቱም የዐማራ ሕዝብ ነው፡፡
የጎንደሩ ተቃውሞ ሰልፍ የ5 ደቂቃ ቪዲዮ
በሁሉም የዐማራ አካባቢዎች (ጎንደር፣ ጎጃም፣ ወሎና ሸዋ) ተጋድሎው ተቀጣጥሏል፤ መቆም የሚችል አይደለም፡፡ ከዚህ በኋላ በምንም መልኩ ወደ ኋላ የሚል አንድም ዐማራ የለም፡፡ በያዝነው ሳምንት ሲጠባበቁ የነበሩ የወሎና የሸዋ አካባቢዎች ተጋድሎውን ለመጀመር ቀናትን ቆርጠዋል፡፡ በዚህ ሳምንት የየከተሞችን መርኃ ግብር እንደደረሰን የምናቀርብ ይሆናል፡፡ ሆኖም የዐማራን ሕዝብ ተጋድሎ ቀጣይነት ለማረጋገጥ በርካታ መሠራት ያለባቸው ነገሮች አሉ፡፡

1. በሰለማዊ ሰልፍ ሰበብ የሚሞቱ ዐማሮችን ቁጥር መቀነስ አለብን/ መኖር የለበትም፡፡ ይህም ሊሆን የሚችለው እያንዳንዱ ዐማራ ራሱን የመከላከል መብት ሲጠቀም ብቻ ነው፡፡ ሊገድለው የመጣን ጠላት እጅን አጣጥፎ በመቆም ሰውነትን ለጥይት መስጠት የእኛም የአባቶቻችንም ታሪክ አይደለም፡፡ ሒዱ በላይ ዘለቀን ጠይቁት? ፊታውራሪ ገብርየ ያደረገው ምን ነበር? ጀግናው ኃይለ ማርያም ማሞ ምን ሠራ? እያልን እንጠይቅ፡፡ ጠላታቸውን ግንባር ግንባሩን እያሉ ነው ያደባዩት፡፡ እኛስ የማን ልጆች ነን?

2. በሁሉም የዐማራ አካባቢዎች ለተጋድሎ የሚወጡ ሰዎች ጎበዝ አለቃን መምረጥ አለባቸው፡፡ እነዚህ ጎበዝ አለቃዎች ሲመረጡ አመራር የመስጠት ብስለት ያላቸው፤ ለዐማራው ሕዝብ እስከ ሞት ድረስ የታመኑ መሆን አለባቸው፡፡ ማንኛውም የዐማራ ገበሬ ያለውን ነፍጥ መጠቀም አለበት፡፡

3. የሚመረጡ የጎበዝ አለቆች ማንኛውም ዓይነት የስልክ፣ የኢንተርኔትና የመገናኛ ዘዴ ሁሉ እስከ ድል ቀን ድረስ በወያኔ እጅ ያለ በመሆኑ ሊቋረጥ እንደሚችል በመገንዘብ በቅርበት ካሉ የዐማራ ተጋድሎዎች ጋር ባሕላዊ የግንኙነት ዘዴን መፍጠር አለባቸው፡፡ ለምሳሌ በሚስጥር ደብዳቤ በመጻጻፍ ሊሆን ይችላል፡፡

4. በሁሉም የዐማራ አካባቢዎች በገጠርና በከተማ የተጋድሎ ክተት አዋጅ ነጋሪት ተመቷል፡፡ ዐማራው ሕዝብ ዘርህን ለማትረፍ በየጎጡ በሳል የጎበዝ አለቆችን በመምረጥ ቀያችንን ከወያኔ ነጻ ማድረግ አለብን፡፡ ሁሉም ዐማራ በተመሳሳይ ቀንና ሰአት፣ ለረዥም ዘመን ከተጋደለ ወያኔ ምንም ማደረግ አይችልም፤ እንዲያውም ከእግርችን ሥር ይውላል፡፡

5. ሁሉም የዐማራ ሕዝብ ከውጭ የሚመጣ ማንኛውም ዓይነት እርዳታ እንደሌለ ተገንዝቦ በራሱ ኃይልና ጥረት ተጋድሎውን ማፋፋም አለበት፡፡ ተጋድሎውን ሊያኮላሹ የሚችሉ በርካታ ኃይሎች እንዳሉ በመገንዘብ የራሱን ሕልውና ራሱ ማስጠበቅ አለበት፡፡

6. በመከላከያ ሠራዊት፣ በፌደራልና በክልል ፖሊሶች በልዩ ልዩ ቦታ ያሉ ልጆቻችሁን፣ ወንድሞቻችሁንና ዘመዶቻችሁን ሥራቸውን እያቆሙ ከወገኖቻቸው ጋር እንዲሠለፉ አድርጉ፡፡ ሆድ አደር ሆነው የሚቀሩ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ፤ ግን የትም አይደርሱም፡፡

7. በተጋድሎ ወቅት የዐማራ ሕዝብ ንብረት የሆኑ ንብረቶች ላይ የሚደርሱ ውድመቶችን መከላከል አለባችሁ፡፡ ለምሳሌ የጤና ተቋማት፣ ትምህርት ቤቶች፣ አገልግሎት መስጫ ተቋማትና የግለሰቦችን ንብረት ውድመት መከላከል አለብን፡፡ የዐማራ ሕዝብ ሊያወድማቸው የሚገባቸው የሥርዓቱ መገልገያ የሆኑ የአገዛዙም ይሁን የግለሰብ ንብረቶችን ብቻ ነው፡፡

እያንዳንዱ ማኅበራዊ ሚዲያ የሚጠቀም ዐማራ ማኅበረሰቡን ለተጋድሎ ማንቃት አለበት፡፡
በውጭ አገር የሚኖሩ ዐማሮች በአገር ቤት ወገኖቻቸው ላይ የሚደርሰውን እልቂት ለመመከት ሊኖራቸው የሚችለውን አስተዋጽኦ በተመለከተ የውይይት መድረኮች እየተዘጋጁ ስለሆነ በዚሁ በንቃት ተሳታፊ መሆን አለባቸው፡፡

ይህ ሁሉ የመጨረሻው መጀመሪያ ነው::

የኦሮሚያ እና የአማራ የህዝቦች እምቢተኝነት እውን ኢህአዴግ እንዳለው ባለቤት የለውም? –በጋዜጠኛ ቶማስ ሰብሰቤ

$
0
0

ባለቤት አለው።

እንዴት?

እንማን?

Unity-1-741x437

የትኛውም መንግስት ከስልጣን ለማውረድ ሁለት መንገዶች አሉ።አንደኛው በታጠቀ ሀይል እየተመራ የራሱ ወታደር ፣የጦርነት ስልት ያለው ፣አለቃ እና ምንዝር የሚጨንር ያልው ትግል ነው።ሁለተኛው መሪ የሌው ባለቤት ህዝባው ትግል ነው።ሁለቱም የተለያዩ ባህሪያት አላቸው።በመጀመሪያው ማለትም ታጥቀው እና ተደራጅተው ስልጣን የያዙት እንደ ደርግ እና ኢህአዴግ ያሉት ናቸው።በሁለተኛው ስልት በኢትዮጵያ ታሪክ ተሞክሮ ያልተሳካው ህዝባዊ ነው።ህዝባው ትግል ባለቤቶ እንደ ህውሃት ፣እንደ ደርግ ያሉ መሪዎች እና ድርጅቶች አይፈልግም።ትግሉ የተጨቆኑ ፣ፍትህ ያጡ ፣እኩልነት እና ዲሞክራሲ የጠማች  ህዝቦች የሚያካሂዱት ነው።

 

ዛሬም ኦሮሚያ እና አማራ ያነሳው ትግል ህዝባው ነው።ከሁለቱ ህዝቦች ጀርባ ማንም አይንቀሳቀስም።ከጀርባቸው ግን አንድ ትልቅ ሃይል አለ ህዝብ።ማንንም የማይፈራ ፣ለሀገሩ የሚሞት እና እሳት ትውልድ።ለዚህም ነው የዛሬው ትግል ባለቤቱ ማን የሚለው ለመለየት ያወዛገበን።ኢህአዴግ ባለቤት የሌለው ትግል ነው ይላል።አንዳንዴም አንዳንድ ሃይሎች የሚሉ ምክንያቶች ይሰማል።ለኢህአዴግ ግልፅ ሊሆንለት የሚገባው ይሄ ትግል በግንቦት ሃያ ወይም በኦነግ የሚመራ ቢሆን ኖሮ ለምን ህዝቡን አያግዙትም ነበር።ሄደው ሄደው ካሸነፉ ስልጣኑ የእነሱ ሰለሆነ ለምን ዝም አሉ።ግንቦት ሰባትም ሆነ ኦነግ ይህን ያህል መጠነ ሰፊ የህዝብ እንቢተኝነት አግኝተው ለምን ሊጠቀሙበት አልፈለጉም?ከኢህአዴግ ጋር የሚመጣጠን መሳሪያ እና ተዋጊ ባይኖራቸው ከሚሊየን መሳሪያ ፣ከሚሊየን ወታደር የሚበልጥ ህዝብ በቀላሉ አግኝተው እነዚያ በሳል ታጋዮች እንዴት ሊያሳልፍት ወደዱ?።መልስ አንድ ብቻ ሰለሆነ ነው በኦሮሚያ የኦነግ ፋላጎት ሳይሆን ፍትህ ነው ።በአማራ ግንቦት ሰባት ሳይሆን ብሄራዊ ጭቆና ነው።እዚህ ታጋዩ ህዝብ፤ባለቤቱ ህዝብ፤የሚሰማው ህዝብ ፤ አሸናፊው ህዝብ ይሆናል።የማይካደው በኦሮሚያ ከኦፒዲዮ የበለጠ ሌላ ባንድራ ያየነው የመገንጠል ሳትሆን የኦፒዲዮ ግፍ ሰለሂነ ሲሆን በአማራ ያየነው ባንድራ ሀገራዊ ሰሜት እንጂ ሌላ ትርጉም የለው።ለዚህ የሚመሰለው ደግሞ ህዝብ ያውቃል።

 

ህዝብ ላይ ጥይት ተኩሶ ያሸነፈ የለም።ይህ የቅርቡ የሰሜን አፍሪካን አመፅ እና ማዕበል አሳይቶናል።በቱኒዚያ ለ23 አመታት ሀገሪቱን ሲበዘብዙ የነበረው ፕሬዘዳን የጣለው ህዝብ ሲሆን አብዮቱን ያቀጣጠለው አንድ ወጣት ነው።ቱኒዚያዊው መሀመድ ቦአዚዝ ድግሪ ይዞ ስራ አጥ ሆነ።እንደ ምንም ብሎ ተበዳድሮ የፍራፍሬ ነገዴ ሆኖ ኑሮ ካሉት መቃብር ይሞቃል ብሎ ኑሮን ጀመረ።ከእለታት በአንዱ ቀን ግን የአብባገነኑ መንግስት የሆነ ወታደር ቦአዚዝን ከሚሰራበት ጎዳና አስነስቶት ፍራፍሬው በተነበት።አሁን ተሰፋ አለቀ።ቢአዚዝ እራሱን የከተማው መስተዳድር ፊት ለፊት ቆሞ ፍትህ በሌለበት ሀገር አልኖርም ብሎ እራሱን በጋዜዝ አቃጥሎ ተሰዋ።ቱኑዚያዎች ያለአንዳች የታጠቀ አይል ብሶታች  ገለፁ።አንባገነኑ መንግስት ገለበጡት።ይህ ህዝባው ትግል ነው።አንዱ ቦአዚዝ ሚሊዮኖች ተከተሉት።

 

በሊቢያ ፣ግብፅ ፣ ሱዳን እና አልጄሪያም ብዙ ቦአዚዞች መጡ።መንግስት በህዝብ ተረታ።ህዝብ ማለት እንዲ ነው።የመጨረሻው ቀን እስኪመጣ ይታገሳል።ትግስቱ ካለቀ ይጋረፋል።ህዝባው አመፅ ሲነሳ ብዙ ብሶቶች ሰላሉ ቀደም በህዝቡ ልብ ሰላለ ትንሽ ጋዝ በቂ ነው ለመቀጣጠል።ቱኒዚያ አንባገነኑን መሪ የደመሰሰችው ቦአዚዝ ብቻ ሰለሆነ አይደል በህዝቡ ዘንድ የሚታይ እውነታ ፣ጭቆናው ፣ግፍ ሰላለም ጭምር ነው።ዛሬም ለኦሮሚያ እና የአማራ ህዝብ ሲነሳ የትላንት ሰቃዮች ከጀርባው አለ።ቱኒዚያ ለቦአዚዝ ሲነሳ አማራ በወልቃይት መነሳቱ አይቀርም ጊዜ ይጠይቃል እንጂ።በኢኮኖሚ እና በስልጣን ክፍፍል የተጎዳው ኦሮሞ ይባስ ብሎ መሬቱን ሲቀማ ልክ እንድ ቦአዚዝ ያለ አብዮት ይፈጥራል።የቱኒዚያ ሆነ ግብፅ አብዮት ባለቤቱ ህዝብ ነው።ጀማሪውም ህዝብ ነበር።ዛሬም የተወሰኑ የታጠቁ ድርጅቶች ፍላጎት ሊኖራችው ይችላል ኢህአዴግን ለመጣል ያ ጊዜ ግን ዛሬ የእነሱ አይደለም ።

ዛሬ አማራ አና ኦሮሚያ የምናያቸው ህዝባዊ እንቢተኝነት  በባዶ እጅ ስርዓቱ በቃኝ ነው።የታጠቀ ሳይሆን የህዝብ ጊዜ።ዛሬም ለኢህአደግ አልረፈደም እና ይህን አሰብበት።አንድ ሰው ስትገድል እናት እና አባቱ ፣የማቱ ቤተሰቦች ፣ጓደኞቹ እና የሰፈሩ ሰዎች ልብ ውስጥ ጥላቻ እና ቁጭት ትፈጥራለህ።ህዝብ ላይ በተኮስከው እጅህ ህዝብ ይበላሀል።ዛሬ የአንተ ቢመስል መንግሰት ይነግሳል ይወርዳል ህዝብ ይኖራል።የሰሞኑን የንፁሃን እልቂት ያዊእና ጭፍጨፋ መላው ኢትዮጵያዊ ከተማሪዎች ሞት ፣ ከ77 ድርቅ ፣ከደርግ ጭፍጨፋ ፣ከ97  ጭፍጫፋ ካጣናቸው የበለጠ ቂም እና ክፋት አለው።ለምን ካልከኝ ይሄ የዘር ጭፍጨፋ ጋር ተመሳሳይ ነውና።ግን ግን ኢህአዴግ ሆይ ትግራይ  ይህን አመፅ ትግራይ ቢሆን እንዲ ትጨፈጭፍ ነበር?

 

ማኅበራዊ ሰንሰለቱ (social fabric) ተበጥሷል?

$
0
0

የጎንደሩ ተቃውሞ ሰልፍ የ5 ደቂቃ ቪዲዮ

(ኤፍሬም እሸቴ)

አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዲህ ብሏል።

«The U.S. Embassy expresses its deep condolences to those who suffered as a result of the violence and regrets the damage to livelihoods, economic development, and the social fabric that such violence brings. ከሰሞኑ በተነሣው አለመረጋጋት በሰው ልጆች ሕይወት ላይ፣ በኢኮኖሚ ዕድገት ላይ እና በማኅበራዊው ግንኙነቱ ላይ ለደረሰው ጉዳት የአሜሪካ ኤምባሲ ጥልቅ ሐዘኑን ይገልጻል» ይላል። http://ethiopia.usembassy.gov/statement-by-the-u.s.-embassy.html

ኤምባሲው በመግለጫው የተጠቀማት አንዲት ኃይለ ቃል ላይ መወያየት አስፈላጊ ይመስለኛል። መግለጫውን ያላያችሁ ሰዎች ብዙም አላመለጣችሁም። ሁልጊዜ የሚወጣ የመንግሥታት መግለጫ ላይ አንዳንድ ዐ.ነገሮችን፣ ቀኖችን መቀየር ብቻ ነው። «እንዳያማህ ጥራው፣ እንዳይበላ ግፋው» ዓይነት ነገር ናት። ያንንም ያንንም ላለማስቀየም፣ ምንም አላሉም ላለመባል የምትወረወር «እንደፍጥርጥራችሁ» የምትል መግለጫ። አንበሳንና ሚዳቋን እኩል «አንተም ተው አንተም ተው» የምትል ጉልበተኛውን እና ጉልበት የሌለውን በአንድ ሚዜን የምታስቀምጥ ግፈኛ መግለጫ። ግርማዊ ቀ/ኃሥላሴ ጣሊያን ኢትዮጵያ ላይ ክንዷን ባነሳችበት ወቅት እንዲህ ባለው የመንግሥታቱ ድርጅት መግለጫ ተከፍተው ያቀረቡት ትንቢታዊ መግለጫ ዛሬም ድረስ የሚታወስ ትንቢታዊ ንግግር ሆኖላቸዋል። ሕዝቤን ከጣሊያኖቹ ባትታደጉ ግን «እግዚአብሔርና ታሪክ ውሳኔያችሁ ያስታውሱታል “God and history will remember your judgment.” እንዳሉት ሆኗል።  https://www.mtholyoke.edu/acad/intrel/selassie.htm

ወደተነሣንበት ሐሳብ ስንመለስ ከኤምባሲው መግለጫ ትኩረቴን የሳበችው ኃይለ ቃል ያልኳት «social fabric» የምትለው ናት። በቀላሉ ማኅበረሰባዊ ሰንሰለት/ ማኅበራዊ ገመድ/፣ ማኅበራዊው ግንኙነት ብንለው ያስኬድ ይመስለኛል። (የሶሢዮሎጂ ምሁራን ሊተቹበት ይችላሉ።) የአሜሪካኖቹ መግለጫ አገራችን የገባችበት ቀውስ ይህንን ግንኙነት ጎድቶታል ነው የሚለው። እንዲህ በቀላል ነገር አስቀምጠው ማለፋቸው በርግጥ እጅጉን የሚገርም ነው። እነርሱ ተጎድቷል ያሉትን በተብራራ ሆኔታ ቢነግሩን ጥሩ ነበር። እስከዚያው ግን … የራሳችንን እንወርውር።

አንድን ማኅበረሰብ አያይዞ በአንድ ላይ የሚያኖረው የተለያየ ነገር ነው። እንደ ቀድሞዋ ሶቪየት ሕብረት፣ እንደ ሮማ ኢምፓየር ብዙ ማኅበረሰቦች በኃይል አንድ ላይ እንዲኖሩ የሚገደዱበት ጊዜ አለ። አጋጣሚው ሲመጣ እና እንደ ገል ቀጥቅጦ እንደ ሰም አቅልጦ ያዋደዳቸው ኃይል ሲዳከም አንድነቱ ይፈረካከሳል። ተፈረካሷልም። ሌሎች ማኅበረሰቦች ደግሞ አንዱ ከሌላው የሚያገኘው እጅግ ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እስካለ ድረስ አብረው ይኖራሉ። የአውሮፓን ሕብረት ወይም እንግሊዝኛ/ፈረንሳይኛ ተናጋሪ ካናዳን ማንሣት እንችላለን። ደግሞ እንደ እኛ አገር ያለው በኃይል ነው እንዳይባል ኃይል በሌለበትም ዘመን አብሮ የኖረውን፤ በኢኮኖሚ ጥቅም ብቻ ነው እንዳይባል ይህ ነው የሚባል ኢኮኖሚያዊ ጥገኝነት የማይታይበት ማኅበረሰብ ደግሞ ባለው ጠንካራ ማኅበራዊ ትስስር አብሮ ለዘመናት ኖሯል።

ማኅበራዊ ትስስሩን የፈጠረው ሃይማኖት ብቻ አይደለም። የተለያየ ሃይማኖት ስላለን። አንድ ብሔረሰብ መሆንም አይደለም። ከ80 የምንበልጥ ብሔረሰቦች ነን። መልክዐ ምድራዊ ተመሳሳይነትም አይደለም። ደጋው ወይና ደጋው ቆላው በሙሉ በኢትዮጵያ አለ። የቆዳ ሥፋታችን ትንሽ አገር ስለሆንም አይደለም። በአፍሪካ ካሉት አገራት ከትልልቆቹ ከሦስቱ መካከል ነን። የአገራችን የትስስሩ አስኳል ከላይ የተዘረዘረው ሁሉ ተደባልቆ፣ በዘመን ብዛት የፈጠረው ራሱን የቻለ ልዩ ንጥረ ነገር ነው ባይ ነኝ። ይህ ልዩ የአንድነት ገመድ በብዙ ችግር ሳይበጠስ በመቆየት ምን ያህል ጠንካራ መሆኑን አስመስክሯል።

ይሁን እንጂ በስታሊናዊ የማኅበረሰብ አንድምታ የሚመራው ግራ ዘመም የአገራችን ምሁር ላለፉት 60 ዓመታት ባቀነቀነውና «ኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦች ድምር» ብቻ እንጂ የአንድነቷ ምስጢር ከዚህ በላይ የሆነ ሌላ ምንም ነገር እንደሌለ በማበከር በሠራው ያላሰለሰ ሰበካ ይህ ማኅበራዊ ትስስር ከባድ አደጋ ሊገጥመው ችሏል። ትስስሩ ለአደጋ የተጋለጠው በተለይ መንበረ መንግሥቱን የተቆጣጠረው የግራ አክራሪው ሕወሐት ከብሔረሰቦች ውሕድነታችን ውጪ ያሉ ገመዶችን ሁሉ ለመበጣጠስ ያደረገው ሰፊ ሥራ ነው። ስለዚህም አገር ማለት የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ጥርቅም እንጂ ሌላ ምንም ነገር አይደለም የሚለውን ሐሳብ የያዘው አደገኛ ቦንብ እነሆ በመፈንዳት ልይ ይገኛል።

ሕወሐቶች ኢትዮጵያን ለመረዳት ከመጣር ይልቅ እነርሱ የሚፈልጓትን «አዲሲቱን ኢትዮጵያን» ለመፍጠር ኢንቨስት ባደረጉት አገሪቱን የማይመጥን ሥራ ራሳቸውንም አገሪቱንም ለአደጋ አጋልጠዋል። በሕዝቦች መካከል ያለውን ትስስር በጣጥሰዋል። ማንም ሰው ከራሱ ብሔረሰብ አጥር ወጥቶ መኖር እንዳይችል፣ ማሰብ እንዳይችል አድርገዋል። በሌላ ክልል የሚኖረውም በባዕድ አገር እንደሚኖር እንዲሰማው፣ ከቻለ ወደራሱ ክልል እንዲሄድ ካልቻለ ደግሞ ምንም ድምጽ ሳይኖረው በባይተዋርነት እንዲኖር አድርገዋል። ከብሔረሰቡ ውጪ ያሰበውንም እንደ ወንጀለኛ በመቁጠር የተለያየ ስያሜ በመለጠፍ ከጨዋታው ሜዳ አስወጥተውታል።

የሕዝቡን ትስስር ያጠበቁ እና በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ያልነበሩ ተቋማት ለፖለቲካ ፍጆታ በሚል በመደፍጠጣቸው፣ የተረፉትም በፓርቲው ቁጥጥር ሥር በመዋላቸው፣ ሕዝብ ተመካክሮ ችግሩን ሊፈታባቸው የሚችልባቸውን ቁልፎቹን ሁሉ አጥቷል። ዘመን ያመጣው ማኅበራዊ የትስስር ገመድ ሊሆኑ የሚችሉትን መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን (መያዶችን) እንኳን አዲስ ባወጣው «የመያዶች ሕግ» ቀርቅቦ በመያዙ፣ ገሚሶቹንም በማፍረሱ ዛሬ አገራችን በችግር ሰዓት ሊታደጋት የሚችለውን የአደጋ ጊዜ መውጫ በሙሉ እንድታጣ ሆናለች።

የምድራዊ መንግሥት እንደራሴ ያልሆኑት ሃይማኖቶች በፓርቲው ቁጥጥር ሥር ገብተዋል። የኦርቶዶክስን መንፈሳዊ የሥልጣን ተዋረድ (ከፓትርያርክ እስከ አቃቢት) በራሱ የፖለቲካ አስፈጻሚዎች ተቆጣጥሮታል። የእስልምና ተቋማትንም እንዲሁ። መዋቅራዊ ሰንሰለት የሌለባቸውን የፕሮቴስታንት ቤተ እምነቶችንም በየተናጠላቸው እንደሚያዝዝባቸው ይታወቃል። ይህ መጠን የለሽ ጣልቃ ገብነት የሕልውናው ማስተማመኛ የሆነ ቢመስለውም የቀኑ ቀን ግን ሊታደገው የሚችለውን የአደጋ ጊዜ መውጫ ድልድይ እንዳፈረሰ አልተገነዘበውም። ስለዚህም ይህንን ግራ አክራሪ ፓርቲ የሚቃወሙ በሙሉ እርሱ የሚያዝዝባቸውን የሃይማኖት ተቋማት ጭምር ለመቃወም ይገደዳሉ። ምክንያቱም በፖለቲካ ፓርቲውና በእነዚህ የቤተ እምነቶች አስተዳደር መካከል ያለው ልዩነት ስለጠፋ።

እነዚህ የሃይማኖት ቤቶች በሕዝቦች መካከል የሚፈጠሩ ችግሮችን ማብረድ፣ አደጋዎችን መቀልበስ የሚችሉበት ታላቅ ሰማያዊ ኃይል ተሰጥቷቸው ሳለ ፓለቲካው ይህን ጸጋ ቀምቷቸው ከማንኛውም ዓለማዊ ድርጅት የማይሻሉ ድኩማን አድርጓቸዋል። ስለዚህም ችግር ሲኖር ለሕዝባቸውና ለአማኛቸው ተገብተው ለመናገር ፍላጎት የላቸውም። ቢናገሩም የሚሰማቸው የለም። ልብሳቸው የሃይማኖት ከመሆኑ ውጪ አቋማቸው ግን እንደማንኛውም ዓለማዊ ድርጅት በመሆኑ በሕዝቡ ዘንድ ከበሬታም ሞገስም የላቸውም።

ስለዚህ አገራችንን ደግመን መገንባት በምንችልበት ወቅት እነዚህን ማኅበራዊ ትስስሮች ለመጠገን፣ የቆሰሉትን ለማከም ካልቻልን የመንግሥት ለውጥ ብቻ ለአገራችን አንድነት ዋስትና አይሆንም። አገራችን እንደ ሩዋንዳ ወይም እንደድሮዋ ዩጎዝላቪያ እንዳትሆን ሲባል የማይመጣ መስሎን ለነበርን በሙሉ ነገሩ ሊሆን እንደሚችል ያሰጋን በዚህ ምክንያት ነው። «አይመጣምን ትተሽ፤ ይመጣልን ያዢ» እንዲል ተረታችን። ስለዚህ ማኅበራዊ ትስስራችንን ከመበጠስ እንዲተርፍ እንሥራ። ፖለቲካዊ ለውጥ ብቻ ለአገራችን የሰላም ዋስትና አይደለም።

ጀነራል ኃይሉ ጎንፋና ኮለኔል ደረሰ ተክሌ ለሠራዊቱ የላኩት ጥብቅ መልዕክት |ያድምጡት

$
0
0


ጀነራል ኃይሉ ጎንፋና ኮለኔል ደረሰ ተክሌ ለሠራዊቱ የላኩት ጥብቅ መልዕክት | ያድምጡት

“የአጋዚ ክፍለ ጦር አባላት –እነዚህን 6 ግዴታዎችን እንድትወጣ እጠይቅሃለሁ”–ኮለኔል አለበል አማረ

$
0
0

ጥብቅ ማሳሰቢያ ለአግአዚ ኮ/ክ/ጦር አባላት……..

colenel alebel

በተለይም ለአማራና ለኦሮሞ ተወላጆች ይህንን መልዕክት ለመፃፍ የተገደድኩት ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ /ህወኃት/ የስልጣን ዕድሜውን ለማራዘም ሲል አግአዚን በገዳይነት መጠቀሙን አሁንም በመቀጠሉ ነው። በዚህ በያዝነው ስልጡን አለም ሰውን የሚያክል የተከበረ ፍጡር በየቦታው በፀራራ ፀኃይ በጥይት መግደል እጅግ የሚያሳዝንና ዘግናኝ ነገር ነው። አግአዚ እንደ ክ/ጦር በ1991 ብላቴ ላይ ከመመስረቱ በፊት መለስ ዜናዊ በቅርብ እየተከታትለው በሌ/ጄኔራል ፃድቃን ገብረትንሳኤ፣ በብ/ጄኔራል ታደሰ ጋውና፣ በጌታቸው አሰፋ /ያንጊዜ የመለስ ዜናዊ የዘመቻ ጉዳዮች ኃላፊ የነበረ ነው/ እንዲሁም የመለስ ዜናዊ የረጅም ጊዜ የጥበቃ ኃላፊ በነበረው በኮ/ል ነጋሲ ወልዳይና በእኔ ኮ/ል አለበል አማረ ሰፊና ተደጋጋሚ ውይይት በኃላ የተመሰረተ ነው። አመሰራረቱን በጥልቀት ወደ ፊት የምመለስበት ሁኖ፤ በውይይቱ በክ/ጦሩ አመሰራረት ላይ የተለያየ ሃሳብ ተነስተው ነበር በነ ጌታቸው አሰፋና ነጋሲ ወልዳይ በኩል በአነስተኛ የሰው ሃይል ሁኖ ከሶስት ሻለቆች ባልበለጠ እንዲደራጅና ግዳጁም ከመደበኛ ውጊያ ውጭ ሁኖ ጠንከር ያሉ የውጭም የውስጥም ስልጠናወች ተሰጥተውት ዘመናዊ መሳሪያ እንዲታጠቅ የፈለጉ ሲሆን በነፃድቃን በኩል ደግሞ በርከት ያለ የሰው ኃይል እንዲኖረ ትጥቁም ብረት ለበስ ተሽከርካሪወችን ጨምሮ ኤሊኮፕተሮች እንዲኖሩት ግዳጁም መደበኛ ውጊያን ጨምሮ ስፔሻል ግዳጆችንም ግምት ያስገባ እንዲሆን ይፈልጉ ነበር።

 

በመጨረሻ አደረጃጀቱ የሁለቱንም ፍላጎት በአጣጠመ መልኩ በክ/ጦር ደረጃ ሁኖ እንዲደራጅ ሲደረግ የክ/ጦሩ መሰረት ቀደም ብሎ በ1982 አጽቢ ላይ በህወኃት በኮማንዶ ደረጃ አዲስ አበባ ስንገባ ለVIP ጥበቃ ያስፈልገናል በማለት 180 የሚሆኑ አባላት አሰልጥነው በሁለት ሻለቃ አደራጅተው በኮ/ል ነጋሲ እየተመሩ ቤተ መንግስት ይጠብቁ የነበሩትን እንደመነሻ ወስደን ክ/ጦሩን እንድናደራጅ ተወሰነ። የክ/ጦሩን የሰው ኃይል ለማሟላት የምልመላ መመዘኛ ወጥቶ ከእግረኛ ሰራዊት በርካታ ወታደር ተመልምሎ ወደ ስልጠና እንዲገባ ተደረገ። በዚህ ዝግጅት ላይ እያለንም ኮ/ል ነጋሲ ወልዳይ ሸሸቢት /አዲሃኪም ላይ/ በሻቢያ መድፍ ተመቶ ሞተ። ከነጋሲ ሞት በኃላ ብ/ጄ ገብረኪዳን የሚባል / አሁን የመከላከያ ኢንዶክትሬሽን ኃላፊ/ በአዛዥነት ተመድቦ መጣ። ገብረ ኪዳንም ብዙ ሳይቆይ ሌላ ብ/ጄ ገብረመድን ፈቃዱ የሚባል በም/አዛዥነት ተመድቦ መጣ። ከእግረኛ ተመልምሎ የመጣው ኃይል ስልጠና በኃላ በነበረን በርካታ ሰው ኃይል በብርጌድና በክ/ጦር አደራጀን። በአደረጃጀት ጊዜ መነሻ የነበሩት የህወኃት /ትግሬወች/ ሰወች ሙሉ በሙሉ በየደረጃው አመራርነቱን ያዙት። ከአደረጃጀት በኃል ብ/ጄ ፍስሃ ኪዳኔ በአዛዥነት ተመድቦ መጣ፣ እንዲሁም ብ/ጄ ሙሉጌታ በርሄና ብ/ጄ መሃመድ ኢሻ እየተቀያየሩ ክ/ሩን አዘውታል። የክ/ጦሩ ስያሜና የነበረው ፍጭት በርከት ያሉ አዳዲስ አባላት በደብረ ዘይትና ብላቴ የኮማንድ ስልጠና ካጠናቀቁ በኃላ ከነባሮቹ የህወኃት ሻለቆች ጋር ውህደት ተደርጎ ክ/ጦር ሲመሰረት ስሙን እኛ እንድናወጣ ተነገረን፤ ይህንን የማስፈፀም ሃላፊነትም በተለይ ለኔ ተሰጠኝ። እኔም ስሙን እና ተያያዥ ጉዳዮችን ለመፈፀም አንድ ኮሚቴ አቆምኩ። ኮሚቴውን ከአማራ ኦሮሞና ትግሬ ተወላጆች በእኩል ደረጃ አደረኩ እና ወደ ስራው ገባን ስሙን በተመለከተ የተለያዩ አማራጩች ከነምክንያቶቹ ቀረቡ፤ ቴወድሮስ፣ ፈንቅል /የኃየሎም የበረሃ ስም ነው/ ፣ አግአዚ፣ ወልወል የተባሉ ስሞች ከነዝርዝር ምክንያታቸውና አስፈላጊነታቸው በጥቆማ ቀረቡ። ብዙ ውይይት አደረግንበት በመጨረሻ ሁለቱ ላይ ተጨቃጭቀን ተግባባን እና ሁለቱንም ለበላይ አካል እናቅርብና እነሱ ይወስኑ ብለን ተስማማን / ቴወድሮስና ፈንቅል/። ይህንኑ ለብ/ጄ ታደሰ ጋውና በወቅቱ የመከላከያ አስተዳደርና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ኃላፊ ለነበረው አቀረብኩ።

 

እሱም ከነ ፃድቃን ጋር መክረውና ወስነው በቀጠሮ ጠራኝና ለክ/ጦሩ መጠሪያ አግአዚ እንዲሆን ከነ ምክንያቱ አስረዳኝ እና ይህንኑ ተቀብየ ወደ ክፍሌ ተመልሸ ለሚመለከታቸው ሁሉ ገለፃ አደረኩ። ክፍለ ጦሩ ከተመሰረተ በኃላ በአገር ውስጥ በደርግ የኮማንዶና አየር ወለድ ባለሙያወች በነ ጄ/ል ተስፋየ ኃብተማሪያምና ሻለቃ ታምሩ እና ሌሎችም እንዲሁም በውጭ በአሜሪካኖች ሩሲያውችና እስራኤሎች በተደጋጋሚ ስልጠና ተሰጥቷል። በተለያዩ ቦታወች በተለያየ ጊዜ በሞያሌ፣ ጅማ፤ ጋምቤላ፤ አሶሳ፤ ጅጅጋ፤ አሰበ ተፈሪ፤ አሩሲ፤ ሻሼ መኔ፤ አዋሳ፤ ጎዴ፤ ቀብዲዳሃር፤ አዲስ አበባ፤ ፍቸ፤ እና በሌሎችም ህዝቡ በመንግስት ላይ የመብት ጥያቄ ባነሳበት ሁሉ የህዝቡን መብት ለማፈን ክፍለ ጦሩ ግዳጅ እንዲፈፅም ተደርጉኣል። በተለይም ነባር አባሎች እንደምታስታውሱት በ1993 ህወኃት ከሁለት ሲሰነጠቅ ክ/ጦሩ በነፃድቃን ተፅኖ ስር ስለነበር በመለስ ላይ ታስቦ በነበረው መፈንቅለ መንግስት ለመጠቀም አዘጋጅተውት ነበር። ከነ ፃድቃን ውድቀት በኃላም ጀ/ል ሳሞራ የኑስ ቂም ይዞ ስለነበረው የኮማንዶ ጥቅማጥቅሙን እና የሚገባውን ትጥቅ እንኩአን እንደማይገባው /የፃድቃን ሰራዊት/ እያለ እስከ መተረብ ደርሶ እንደነበረ የምናስታውሰው ነው። ይህን ሃሳብ ለማንሳት የፈለኩት ክፍለ ጦሩን ከመጀመሪያም ለግል የስልጣን ፍላጎት መጠቀሚያ አስበው ያደራጁት እንደነበር ለማስገንዘብ ነው። መለስ ተቀናቃኞቹን ካስወገደና የሳሞራም ስልጣን ከተረጋጋ በኃላ አግአዚን ባለበት እንዲቀጥል ፈለኩት እንዲያውም ከላይ በጠቀስኩአቸው አካባቢወችና በሌሎችም የህዝብ ቁጣ ሲነሳ አጋአዚ በፍጥነት የህዝብን ጥያቄወች በኃይል ማፈን በመቻሉ የአመራር ለውጥ በማድረግ እንደገና ለማጠናከር ተንቀሳቀሱ። ክ/ጦሩ ከሻለቃ በላይ ያለው አመራር ፍፁም የትግሬ የበላይነት ያለው ቢሆንም ከሻምበል በታችና ተራ ወታደሩ ግን እስካሁን በቀዳሚነት የአማራ ተወላጆችና በተከታይነት የኦሮሞ ተወላጆች በዝተው ይገኛሉ። ይህ ማለት ለመጥፎም ለመልካምም ነገር ዋናውን ስራ የሚሰራውና ጠመንጃውን የያዘው ግንባር ቀደም ተሰላፊው ማን እንደሆነ በግልፅ እንረዳለን ።

 

በወያኔ ስርዓት ስርዓቱን በመቀዋወምና መብቱን በመጠየቅ በቀዳሚነት እየተንቀሳቀሰ ያለው ሰፊው የአማራና የኦሮሞ ህዝብ ነው። የዚህን ህዝብ መብት በማፈን እና በመግደል ደሞ ግንባር ቀደም ሚና እየተጫወተ ያለው አግአዚ ውስጥ ያለው የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች ናቸው። በስራ ቆይታየ ከትግሬወች አንድ የተማርኩትና አሁን ላሉበት ሁኔታ ጠቅሟቸዋል ብየ የማስበው፤ በብዙ ነገር ሲጨቃጨቁ ሲጣሉ አያለው በትግራይ ህዝብ፤ ትግራዊነትና በድርጅታዊ ጉዳይ ግን አንድና አንድ ናቸው፡ ልዩነታቸውን ትተው መጥፎም ይሁን መልካም በጋራ ጉዳያቸው ላይ ብቻ ይረባረባሉ። በ1993 እነ ጀ/ል ፃድቃን ከመከላከያ በከባድ ሁኔታ ሲወጡ እነ መለስ የሚምሯቸው አይመስሉም ነበር / ሁኔታውም ከባድ ነበር እና/ ከወጡ በኃላ ግን ሁሉም በጡረታ /በክብር/ እና ዳጎስ ባለ ጉርሻ ጭምር ከነክብራቸው መሸኜታቸውን ስንሰማ ገርሞን ነበር። የ1997 ምርጫን ተከትሎ ወያኔ በምርጫ በደረሰበት ኪሳራ በተለይም የአማራውን ህዝብ ጥርስ እንደተነከሰበት ይታወቃል፤ በህዝቡ ብቻ ሳይሆን በስርዓት ውስጥ ባለን አማራወች ሁሉ ጥላቻቸው በግልጽ ይታይ ነበር። እኛም ሁኔታቸው ስላላማረን ራሳችን ለመከላከልና ሂደታቸውን ለመኮነን በፀረ-ህወኃትነት ተሰለፍን፤ ህወሃትን መክፈልም ይቻል ይሆናል ብለን በማሰብ ጀ/ል ፃድቃንን ለማነጋገር ወሰን /ጻድቃን ቀደም ሲል በሰርዊቱ የነበረውን ሁኔታ ተጠቅሞ አሁንም ተፅኖ ይፈትራል ብለን እናስብ ነበር። ሁለት ሁነን ፖሌ መድሃኒያለም ጀርባ ከፍቶት ከነበረው “የግጭትና ጥናት ምርምር” ምናምን የሚባል ቢሮ ከፍቶ ይሰራ ነበር። በደቡብ ሱዳንም የፀጥታ አማካሪ ሁኖ ለUN እና ለደቡብ ሱዳን መንግስት ይሰራ ነበር። እና ሰውየውን አግኝተን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ብዙ ከተነጋገርን በኃላ የመለስና የሳሞራ አካሄድ ወደ ጥፋትና ግጭት መንገድ እየሄዱ ስለሆነ ለምን ተባብረን አናስተካክለውም የሚል ጥያቄ አነሳንለት። እሱም ያነሳችሁት ልክ ነው ይገባኛል አሁን ግን ምንም ማድረግ አይቻልም ጊዜ መጠበቅ ይሻላል ይልቁንስ ከመከላከያ ውጡና ደቡብ ሱዳን በጥሩ ደመወዝ ልላካችሁ አለን። በዚያን ጊዜ በርካታ የትግሬ መኮነኖችን እንደላከና ተጠቃሚ እንዳደረገ እናውቃለን። እኛንም ብንፈልግ ሊልከን እንደሚችልም ተረድቶናል ግን ፍላጎታችን ያ አልነበረም።

 

በሌላ ጊዜ አንድ በጣም የምቀርበው ትግሬ ጄኔራል ጋር ስናወራ ስለ ፃድቃን አነሳን እና ጻድቃን እኮ በጣም አስተዋይ ነው እነ ገብሩ አስራት ህወኃት ላይ እንስራና መለስ እንዲወርድ እናድርግ ሲሉት እሱ ግን አይ በአሁኑ ሰዓት ለትግራይ ከመለስ የተሻለ የለም አላቸው። መለስም ይህንን ስለሚያውቅ በደቡብ ሱዳን ለUN አማካሪ መሆን እንደሚችል ፕሮፖዝ አደረገው ብሎ ነገረኝ። ሌላ ነገር ልጨምር በዚያው 93 በነበረው ልዩነት በርካታ ጀኔራሎች ፃድቃንን ተከትለው መለስን በመፈንቅለ መንግስት ለማስወገድ ከነ ተወልደ ወልደማሪያም ጋር ተሰልፈው ነበር፤ እነ ጀ/ል ገዛይ አበራ, ጀ/ል ሳረ መጆነን ጀ/ል ብርሃኔ ነጋሽ ጀ/ል አብርሃ ተወልደ ጀ/ል ዮሃንስ ገብረ መስቀል ኮል ተወልደ ፍስሃ እነዚህ ወሳኝ የአዛዥነት ቦታ ላይ የነበሩ ከነ ፃድቃን ቡድን ተሰልፈው የነበሩ ናቸው። ታዲያ ሁሉም ስህተታቸውን እንዲያምኑ ከተደረጉ በኃላ ለ3 ወር ብቻ ከነበራቸው ኃላፊነት አንዳንድ ደረጃ ብቻ ዝቅ ብለው ከቆዩ በኃላ ተመልሰው ወደ ነበሩበት የኃላፊነት ቦታ ተመለሱ። በአንፃሩ በውል እውነት መሆኑን ባላረጋገጡት ጉዳይ ላይ የእኛወቹን የአማራ መኮነኖች እነ ጀ/ል ኃይሌ ጥላሁን ጀ/ል ተፈራ ማሞ ጀ/ል አሳምነው ፅጌ ኮ/ል ደምሰው አንተነህ ኮ/ል መኮነን ወርቁ እና ሌሎችም በርካቶችን መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ አስባችኃል በሚል ሰበብ በጭካኔ ተሰቃይተዋል ታስረዋል ቤተሰባቸውን በትነዋል። የ1997 ምርጫን ተከትሎ ሰራዊቱ ውስጥ ያለው /በአግአዚም ጭምር/ አማራና ኦሮሞ በጠላትነት ተፈርጆ ስንት ስቃይና መከራ እንደነበር ታውቃለህ። በአስር ሽወች የሚቆጠሩ የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች የሰራዊት አባላት ታስረዋል በምርመራ ተሰቃይተዋል ያለምንም ጡረታና ድጎማ ተባረዋል። ይህ ሁሉ ሲደረግ የአንተ ዘር የሆነው አማራውና ኦሮሞው ተለይቶ እንጅ አንድም የትግሬ ተወላጅ ላይ የደረሰ ነገር አልነበረም።

 

ታዲያ ይህ ስርዓት የማን ነው ትላለህ? እኔም በነበረኝ የኮማንድ የአመራር አባልነቴ የትግሬ አመራሮች በክፍለ ጦሩ ይፈፀሙ የነበሩትን ዘረኝነትን ለመታገል ብዙ ብጥርም አልተሳካልኝም። የአመራር ምደባና የአደረጃጀት ለውጦች ባደረግን ቁጥር የሰው ኃይል ምደባ ላይ ከባድ ፍጭት እናደርግ ነበር። እነሱ ከላይ እስከ ታች አመራሩን ትግሬ እንዲይዘው ካላቸው ፍላጎት አንፃር ያስጨግሩኝ ነበር። እንዴውም አንዳንዴ የበላይ አካል ይወስነው ብለው እንድናልፈው ይደረግ ነበር ያው የበላይ አካሉ ሳሞራ ስለነሆነ እሱን ደግሞ እነሱ ስለሚያገኙት ጨዋታው ለነሱ ቀላል ነበር። በነሱ ጥርስ ውስጥም ሁኜ የአማራውን እና የኦሮሞውን ልጆች መብት በተወሰነ ለማስከበር የቻልኩ ቢሆንም ከኔ በኃላ ግን የአማራን እና የኦሮሞን አመራር ጠራርገው ወደ እግረኛ እንደላኩት እናንተም ታውቃላችሁ። ይህ ተጠራርጎ ወደ እግረኛ የተባረረው አመራር በብቃት ወይም በስነ-ምግባር ጉድለት ሳይሆን በዘሩና በማንነቱ ስላልተፈለገ ነበር። የትግራይ ገዥ መደብ የጭቆና አገዛዙን ዕድሜ ለማራዘም በዋነኛነት አንተን በመሳሪያነት በመጠቀም ለመብቱና ለነፃነቱ ሰላማዊ ጥያቄ ያነሳውን የአማራና የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄን ዕድታፍንና ወገንህን እንድትገድል እያደረገህ ነው። እነሱ እንወክለዋለን እንጠብቀዋለን እናበልፅገዋለን ብለው የተነሱለን የትግራይን ህዝብ በሰላም እያኖሩ አንተ የተፈጠርክበት የአማራና የኦሮሞ ህዝብ ግን በአንተና በአገዛዙ ታጣቂወች በየቀኑ ይገረፋል ይታሰራል ይገደላል።

ለምን ብለህ ማሰብና ማሰላሰል ይኖርብሃል! ከጨካኞች የባዕድ ገዥወች ወግነህ የራስክን ወገን ከመጨፍጨፍ ወገንህን መከላከል ታሪካዊ ግዴታህ ነው። እንደምትረዳው በአሁኑ ሰዓት የዘረኛው የወያኔ አገዛዝ በመንኮታኮት ላይ ሲሆን በአንፃሩ የህዝቡ የነፃነት ትግል ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል። ይህንን እየሞተ ያለ ብስባሽ ጨርሶ ለመቅበር ከአንተ ከአግአዚ የአማራና የኦሮሞ አባላት የሚከተሉትን እንድትፈፅም በሚጨፈጨፈው ወገን ስም እጠይቃለው።

 

1ኛ. አንተም ሆንክ የመከላከያ ሰራዊቱ ዋነኛ ግዳጅ ዳር ደንበር መጠበቅ እንጅ ሰላማዊ ወገንህም መጨፍጨፍ አይደለም። ስለሆነም ከተልኩአችን ውጭ ሰላማዊ ህዝባችን ላይ አንዘምትም በል።

2ኛ. የህዝብ ልጅ ነህና ህዝብ የጠየቀውን የመብት ጥያቄ አንተም ጠይቅ፣ መሳሪያህን አስቀምጠህ ከህዝቡ ጋር አብረህ ጩህ።

3ኛ. በጦር ክፍልህ ውስጥ በእርስትነት በትግሬወች የተያዘውን የአመራር ቦታ ይገባኛል በል። በቃ ሁል ጊዜ በትግሬ አልታዘዝም በል።

4ኛ. በየደረጃው ያሉት የትግሬ አዛዞች የሚፈጽሙትን ሙስና እና ብልግና ያለ ምህረት አጋልጥ ታገል።

5ኛ. በየቦታው ህዝብን እንድትጨፈጭፍ የሚሰትህን ግዳጅ እምቢ በል፣ በኃይል ፈፅም ከተባልክ መሳሪያህን በትግሬ አዛዝ ላይ አዙረው።

6ኛ. ከላይ ያልኩአቸውን ነገሮች በድፍረት ተግባራዊ አድርጋቸው፣ በዚህ የማይተረሙ ከሆነ ከሌሎች ከሚመስሉህ ጋር ተነጋገር ከነ ሙሉ ትትቅህ ወደ ህዝብህ ተቀላቀል።

ወገኖቸ እስካሁን አውቃችሁም ይሁን ሳታውቁ ወገናችሁን አድምታችኃል ገድላችኃል፣ አሁን ግን በቃን በማለት የበደላችሁትን ወገናችሁን በመካስ ታሪካችሁን አድሱ። ወያኔ እየተንኮታኮተ ያለ ወንጀለኛ ቡድን ነው፣ ለዚህ ደመኛ የህዝብ ጠላት መጠቀሚያነታችሁ ይብቃ። ዛሬውኑ ወስኑና ንስሃ ገብታችሁ ወደ ህዝባችሁ ወግኑ።  አለበል አማረ /ኮሎኔል/


የገዱ አንዳርጋቸው መነሳት የዐማራን ተጋድሎ ወደፊት ያስፈነጥረዋል • በባሕር ዳር የዐማራ ፖሊስ በንዴት አምስት ፌደራሎችን ገድሎ ራሱን አጠፋ

$
0
0

(የገዱ አንዳርጋቸው መነሳት የዐማራን ተጋድሎ ወደፊት ያስፈነጥረዋል!!)
• የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር የነበረው ድርድር ያለስምምነት ተበትኗል
• በባሕር ዳር የዐማራ ፖሊስ በንዴት አምስት ፌደራሎችን ገድሎ ራሱን አጠፋ
• ‹‹አታልቅሱ፤ ልጄ ለተቀደሰ ዓላማ ተሰውቷል›› በባሕር ዳር ልጃቸውን ያጡ እናት
• ወረታ ከተማ የመጠጥ ውኃ ውስጥ መርዝ ሊጨምር የነበረው ግለሰብ እብድ ነኝ በማለት እያጭበረበረ ነው
ኹመራ፤ በአሸባሪነት ስም የማንነት ጥያቄያቸውን ሊያደፋፍኑት ቢጥሩም እንደማይሳከ የወልቃይት ጠገዴ ዐማሮች ተናግረዋል፤

ሙሉቀን ተስፋው
ዛሬ በኹመራ፣ በዳንሻና በአዲረመጥ ከተማ ያነጋገርናቸው የወልቃይት ጠገዴ ዐማሮች እንደሚናገሩት የማንነት ጥያቄያችን ለማዳፈን የአሸባሪነት ስም እየሰጡ በየሰአቱ ይፈትሹናል፡፡ አማርኛ የሚናገር ሰው ሁሉ እንዲሸማቀቅ ከፍተኛ ጥረት ይደረጋል ብለዋል፡፡ ከኹመራ ያገኘነው ግለሰብ ‹‹አሁን የማወራህ ከፎቅ ላይ ወጥቼ ነው፤ በየቦታው እኛን የሚከታተል የትግራይ ሰው በየቦታው ነው፡፡ ያለንበትም ሁኔታ ያስጠላል›› ሲል የሚደርስበትን ጫና ገልጧል፡፡
የወያኔ ሰዎች አንዳንድ ዐማሮችን በገንዘብ በመግዛት መሣሪያ አስታጥቀው ወደ በርሃ በመላክ ከተወሰ ቀን በኋላ ‹‹ምሕረት ጠይቀናል›› ብለው ይመለሳሉ፡፡ በኋላም የወልቃይት ጠገዴ ዐማሮች እንዳስታጠቋው በመግለጽ ድራማ እንደሚሠሩ ገልጸዋል፡፡ በዚሁ አያይዘውም አንዳንድ መገናኛ ብዙሃንና የተቃዋሚ ድርጅቶች የወልቃይት ጠገዴን ዐማራ የማንነት ጥያቄ ዘገባ ሲሠሩ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ብሎም በእውነት ላይ የተመሠረተ እንዲሆን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

የብአዴን ምክትል ሊቀመንበርና የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

የብአዴን ምክትል ሊቀመንበርና የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

አርማጭሆ፤ በታችና በምዕራብ የአርማጭሆ እንዲሁም በጠገዴ አካባቢዎች ውጥረት እንዳለ ከቅራቅር ያነጋገርናቸው ሰዎች ገልጸዋል፡፡ ባለፉት ሦስት ቀናት ኩርቢ አካባቢ ከ30 በላይ የመከላከያ ሠራዊትና ሦስት መኪኖች ሙሉ በሙሉ በሕዝቡ መደምሰሳቸው ታውቋል፡፡ ከሦስት መኪና ውስጥ ከነበሩ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ውስጥ ቁጥራቸው አምስት የሚሆኑ ብቻ በከፍተኛ ቁስል መትረፋቸው ነው የተነገረው፡፡ በሳምንቱ መጨረሻ የቅራቅር ከተማ ነዋሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ መውጣታቸው ይታወቃል፡፡ ትናንት ደግሞ ‹‹ኢትዮጵያ ሰላም እንድትሆን ካስፈለገ የአርማጭሆ ሕዝብ መሣሪያ ማውረድ አለበት›› በማለት ስብሰባ ላይ የተናገረ የሕወሓት ካድሬ በምዕራብ አርማጭሆ አብርሃጂራ ከተማ ተገድሏል፡፡

ጎንደር፤ በከፍተኛ ባለሥልጣናት የተካሔደው ስብሰባ ያለ ምንም ውጤት ተበትኗል
በጎንደር ዛሬ ነሐሴ 3 ቀን 2008 ዓ.ም. በአቶ አዲሱ ለገሠ እና በአቶ በረከት ስምዖን የተመራው የከፍተኛ ባለሥልጣናት ስብሰባ ያለ ምንም ውጤት ተበትኗል፡፡ የጎንደር ከተማ እና የሰሜን ጎንደር ዞን የካቢኔ አባላት ‹‹ከዚህ በኋላ ከሕዝባችን ጎን እንቆማለን›› ብለው ስብሰባውን ረግጠው ወጥተዋል፡፡ በስብሰባው የተነሱ አጀንዳዎች ‹‹የተገደሉ ሰዎችን ኃላፊነት አገዛዙ ይውሰድ፤ የወልቃይት የዐማራ ማንነት ጥያቄ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይፈታ›› የሚሉ ሲሆኑ ከፍተኛዎች ባለሥልጣኖች ከሕወሓት በኩል የተሰጣቸውን ተልእኮ ለማስፈጸም ሙሉ በሙሉ ቢንቀሳቀሱም ተሳታፊዎች ትተዋቸው ወጥተዋል፡፡ በሽምግልና ለመፍታት የተደረገው ሴራም አልተሳካም፡፡ የካቢኔ አባላቱ ስብሰባውን ረግጠው ሲወጡ ችግር ይፈጠራል ተብሎ ቢሰጋም ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ምንም ዓይነት ነገር እንዳልነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ የሕዝቡ የእለት ተለት እንቅስቃሴም የተገደበ እንደሆነ ከቦታው የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ነገ ነሐሴ 4 ቀን 2008 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በጎንደር የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆችን በአውሮፕላን የማስወጣት ሥራ እስከዛሬም ድረስ እየተከናወነ እንደሆነ ተገልጧል፡፡
ወረታ፤ በወረታ ከተማ የመጠጥ ውኃ ውስጥ መርዝ ሊጨመር ሲል የተያዘው ሰው እብድ ነኝ በማለት ለማታለል እየሞከረ እንደሆነ ዛሬ ከቦታው በስልክ ያነጋገርናቸው ሰዎች ገልጸውልናል፡፡ ግለሰቡ ትግሬ ከመሆኑም በላይ ብዙም አማርኛ የማይችል ሲሆን የአእምሮ ጤነኝነት እንደሌለው ለማሳየት እየሞከረ ነው ብለዋል፡፡ አስተያየት ሰጪዎቹ ‹‹የአእምሮ ጤነኛ ያልሆነ ከሆነ እንዴት በድብቅ ያን ያክል ሰው ጨራሽ የሆነ ኬሚካል ለመጨመር ፈለገ? ምን ሊሠራና ማን ወረታ አመጣው?›› በማለት መገረማቸውን ገልጸዋል፡፡
ከወረታ ከተማ 25 ኪሎ ሜትር ያክል የሚገኙት የአዲስ ዘመንና የይፋግ ከተሞች እሁድ ለት የተጋድሎ ሰልፍ ከወጡ ወዲህ እስካሁን ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ እንደሌለ ነው የተገለጸው፡፡ በአዲስ ዘመንና በይፋግ በተጋድሎ የተሰው ሰዎች ብዛት ሦስት ነው ተብሏል፡፡
ደብረ ታቦር/ ነፋስ መውጫ፤ በደብረ ታቦር አንድ የኦሮሞን ሾፌር ሕዝቡ ጥበቃ አድርጎ ሸኝቶታል
በደብረ ታቦርና ነፋስ መውጫ ከተሞች እስካሁን ድረስ ውጥረት እንዳለ ነው፡፡ አንዳንድ ቅጥረኞች የተጋድሎ መሪ ናቸው ያሏውን ሰዎች በሌሊት እያሳፈኑ መሆኑን የታወቀ ሲሆን እነዚህ ግለሰቦች በቤተሰቦቻቸው እንዲመከሩ ተደጋጋሚ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ከነፋስ መውጫ ትንሽ ራቅ ብላ ባለችው የጨጭሆ መንደር ያሉ ዐማሮች እስካሁን ድረስ ተጋድሏቸውን አላቆሙም፡፡
በደብረ ታቦር ከተማ ቅዳሜ ለት በነበረው ተጋድሎ አንድ የተሳቢ መኪና የያዘ ሰው በተጋድሎው መካከል ሲመጣ ሕዝቡ መኪናውን ሊያወድም ሲል ‹‹እባካችሁ እኔ እንደናንተ የተገፋሁ ወገን ነኝ እንጅ ወያኔ አይደለሁም›› በማለት መታወቂያውን ሲያሳይ የኦሮሞ ተወላጅ ሆኖ ተገኘ፡፡ በዚህም ሕዝቡ ‹‹አንተማ የእኛው ወንድም ነህ›› በማለት ከሎሚ ዱር እስከ መሎ ድረስ ሰው ተመድቦ በሰላም እንዲሸኝ ተደርጓል፡፡
ባሕር ዳር፤ የባሕር ዳር ዐማሮች እስካሁን ትግል ላይ ናቸው፡፡ እሁድ በነበረው ተጋድሎ የዐማራ ክልል ፖሊሶች ከዱላ በቀር ምንም ዓይነት መሣሪያ እንዲይዙ አልተፈቀደላቸውም ነበር፡፡ የወያኔ ወታደሮችንና የፌደራል ፖሊሶች በዐማሮች ላይ የሚያደርጉትን ጭፍጨፋ የተመለከተ የዐማራ ክልል ፖሊስ ትናንት በንዴት አምስቱን የፌደራል ፖሊሶች ካጋደመ በኋላ ራሱን ማጥፋቱን ከቦታው በስልክ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ይህ ጀግና ለሌሎች የክልሉ ፖሊሶች ያሳየው አርአያነትን የሚያደንቁት የባሕር ዳር ወጣቶች ‹‹ራሱን ባያጠፋ ኖሮ በምንም መልኩ አሳልፈን አንሰጠውም ነበር›› ሲሉ በቁጭት ገልጸዋል፡፡
በጎጃም ሌላም የሰማነው አስገራሚ ታሪክ አለ፤ እሁድ በነበረው ተጋድሎ ልጃቸው የተሰዋባቸው እናት ለሀዘን የሚሔዱትን ዐማሮች ‹‹አታልቅሱ! የእኔ ልጅ የተሰዋው ለተቀደሰ ዓላማ ነው!! አባቶቻችን ለሕዝባቸውና ለአገራቸው ያደረጉትን መስዋትነት ስለከፈለ ደስተኛ ነኝ›› በማለት ሀዘንተኞችን ሲያጽናኑ በቦታው የነበሩ ዐማሮች በንዴትና በሚታያቸው ተስፋ የበለጠ ያነቡ እንደነበር የመረጃ ምንጫችን ከባሕር ዳር ተናግሯል፡፡
ባሕር ዳር ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ የማይታይባት ከተማ እንደሆነች የተናገሩት የመረጃ ምንጮቻችን በጢስ ዓባይና በዘጌ በኩል ያሉ ገበሬዎች ከመከላከያ በሚደርስባቸው ጥቃት ልክ አጸፋ እየሰጡ እንደሆነ ለማወቅ ችለናል፡፡ በባሕር ዳር የሞቱት ሰዎች ከ70 በላይ ደርሷል፡፡ አንድ የዐይን ምስክር ‹‹ከ12 በላይ አስከሬን ሲነሳ ተመልክቻለሁ›› ብሏል፡፡
ደብረ ማርቆስ፤ ደብረ ማርቆስ ከተማ ቀጣይ ቅዳሜ የተጋድሎ ሰለፍ ለማካሔድ ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ ለማወቅ ችለናል፡፡ የደብረ ማርቆስ ዐማሮች በቀጣይ ቅዳሜ በንጉሥ ተክለ ሃይማኖት አደባባይ ይወጣሉ፡፡
ሸበል በረንታ፤ የሸበል በረንታ ጀግኖች በወረዳው የነበረውን የጥይት መካዘን ተከፋፍለዋል፡፡ እሁድ ለት ለተጋድሎ የወጡት የሸበል በረንታ ዐማሮች በወረዳው አስተዳደር (ፖሊስ) ጽ/ቤት የነበረውን የመሣሪያ መካዘን ውስጥ የነበረውን የተለያየ መሣሪያ ዐማሮች ተከፋፍለዋል፡፡
የዐማራ ሕዝብ ትግል ያሸንፋል!!

ይድረስ «በአንድነት» ስም ለምትንቀሳቀሱ አገር አቀፍ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ድርጅቶችና የሲቪክ ተቋማት በሙሉ

$
0
0

ከአቻምየለህ ታምሩና ከሙሉቀን ተስፋው

እንደምታውቁት ከሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ የአማራ ህዝብ ከፋሽስት ጥሊያን በላይ የከፋ ከሆነው ጨካኙ የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጭ ግንባር ጋር ፊት ለፊት ገጥሞ እየተጋደለ ይገኛል። ባሁኑ ሰዓት አማራው እያደረገ ያለው ተጋድሎ ወደኋላ ላፍታ እንኳ ቢመለስ ህዝባችን የከፋ ግፍና መከራ ላይ በእርግጠኛነት ሊወድቅ እንደሚችል ቂመኛውን ወያኔ የሚያውቅ ሁሉ ያውቀዋል። ስለሆነም እየተካሄደው ያለው የአማራ ተጋድሎ የተከፈለው መስዕዋትነት ተከፍሎ ወደፊት መሄድና ማደግ አለበት እንጂ ወደኋላ ሊመለስ አይገባም።

Unity-1-741x437

የአገራችንን ሁኔታ ለሚከታተል ሁሉ ግልጽ እንደሆነው በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ በሳልሳዊ ቴዎድሮስ ወይንም በኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ችቦ ለኳሽነት የተጀመረው ይፋዊ የአማራ ተጋድሎ በአሁኑ ሰዓት ጎጃምን አዳርሶ ወደ ሸዋና ወሎ ተሻግሯል። ትናንትና በወልቃይት አማሮች የተለኮሰው የአማራ ተጋድሎ ዛሬ አድማሱን አስፋፍቶ መላውን የአማራ ህዝብ ከዳር እስከ ዳር አነቃንቋል።

ባለፉት ሶስት ሳምንታት በጎጃምና በጎንደር የተካሄደውን የአማራ ተጋድሎ በቅርበት ለተመለከተ ተጋድሎው አላማውን እያሳካ፤ ህዝባዊነትን ተላብሶ እንደሰደድ እሳት እየተስፋፋ ስለመሆኑ ነጋሪ አያሻውም። ይህ ታሪካዊ ተጋድሎ በዚህ ፍትነት ሲስፋፋና ውጤታማ ሊሆን የቻለው የአማራው ህዝብ እያካሄደ ያለው የፖለቲካ ሳይሆን የህልውና ትግል በመሆኑ ነው። በዚህ የአማራ የህልውና ተጋድሎ ጀርባ የተሰለፉም ሆነ ተጋድሎውን ከፊት ሆነው እየመሩ ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶችም ሆኑ ግለሰቦች የሉም። ከትግሉ ጀርባ የተሰለፈውም ሆነ የትግሉ መሪ ራሱ ተጋዳዩ ጀግናው የአማራ ህዝብ ነው።

ሆኖም ግን የአማራው የህልውና ተጋድሎ የፖለቲካ ትግል እየመሰላቸው የህልውና ተጋድሎውን ወደ ፖለቲካ ትግል ደረጃ ለማሳነስ የሚሞክሩ የፖለቲካ ድርጅቶች አልጠፉም። በተጋድሎው ወቅት የታዩት የፖለቲካ ድርጅቶች መፈክሮችም ሆኑ ከተጋድሎው በኋላ የተስተጋቡት «ከትግሉ ጀርባ እኛ አለንበት» ወይንም « ትግሉ የእኛ ነው» በሚል የቀረቡት የድርጅት መግለጫዎችና ዲስኩሮች የአማራው ተጋድሎ ከእውነተኛው የህዝቡ የህልውና ተጋድሎ ከፍታ ወደ ፖለቲካ ትግል ደረጃ ወርዶ ህዝባዊ ተጋድሎው የፖለቲካ ትግል እንዲመስል ጣልቃ በመግባት ለማሳነስ ተሞክሮ እንደነበር ማሳያዎች ናቸው።

የባህርዳሩ ህዝባዊ ተጋድሎ ከፍተኛ መስዕዋትነት ያስከፈለን የህዝባዊ ተጋድሎው መሪም ሆነ ስልት ነዳፊ ሰፊው የአማራው ህዝብ ራሱ ሆኖ ሳለ «የአማራ ችግር የፖለቲካ ችግርና የአስተዳደር ጉድለት እንጂ የህልውና አደጋ አይደለም» ብለው የሚያምኑና «በአንድነት» ስም «እንታገላለን» የሚሉ የፖለቲካ ድርጅቶች የፈጠሩት ጣልቃ ገብነት ነው። ይህ የድርጅቶች ጣልቃ ገብነት ወያኔ «አሸባሪ» በሚላቸው ድርጅቶች አስታኮ ህዝቡን እንዲጨፈጭፍ ሰበብ ሆኖታል።

እኔና ሙሉቀን ተስፋው ይህንን ግልጽ ደብዳቤ የምንጽፍበት ዋና አላማም ወደፊት የአማራ ህዝብ በሚያደርጋቸው ተጋድሎዎች ዙሪያ ከአማራው የህልውና አደጋዎች በላይ የድርጅታቸውን አጀንዳ ቀዳሚ የሚያደርጉ ድርጅቶች ከድርጊታቸው ይቆጠቡና ወያኔ ህዝባችንን እንዲጨርስ ሰበብ እንዳይሆኑ ወገናዊ ልመናችንን ለማቅረብ ነው።

የፖለቲካና የሲቪክ ድርጅቶች ተጋዳዩን የአማራ ህዝብ ከድርጅታቸው ሳጥን በመውጣት ከህዝቡ ጋር ሆነው እንደ ድርጅት ሳይሆን እንደ ህዝብ፤ የድርጅታቸውን አጀንዳ አንግበው ሳይሆን ህዝቡ ያነሳውን የህልውና አደጋ እንደ ህዝብ በማንሳት፤ በድርጅት ደረጃ ሳይሆን በግለሰብ ደረጃ ተሳታፊ በመሆን የአማራውን ተጋድሎ ማገዝ ይችላሉ። ይህን የሚያደርጉት ታዲያ «ከተጋድሎው ጀርባ እኛ አለንበት» ወይንም «ተጋድሎው የእኛ ነው» የሚል የሰለቸ የመግለጫ ጋጋታ ለማውጣት አይደለም።

ከዚህ በተጨማሪ ሌላ መታወቅ ያለበት አብይ ጉዳይ አለ። በአማራው ተጋድሎ ሂደት ህዝቡን ወክሎ መግለጫ የሚሰጥ፣ የሚደራደርም ሆነ ጥሪ የሚያቀርብ ራሱ ተጋዳዩ ህዝብና የአማራ በደል የወለዳቸው ልጆቹ ብቻ ናቸው እንጂ የድርጅት አጀንዳ የያዙ ግለሰቦችና የፓርቲ ስብስቦች አይደሉም።

ስለሆነም የፖለቲካ ፕሮግራማቸው በዋናነት የአማራውን ህዝብ ህልውና ማዕከል ያላደረጉ የፖለቲካና የሲቪክ ድርጅቶች መፈክርና መግለጫ እያወጡ አማራው ከተጫነበት የህልውና አደጋ በላይ የራሳቸውን አጀንዳ በማስቀደም «ከተጋድሎው ጀርባ እኛ አለንበት» ወይንም «ተጋድሎው የእኛ ነው» ቢሉ ጨካኙ ወያኔ የሚጠላውንና ሊያጠፋው የተነሳውን የአማራ ህዝብ እንዲጨርስ፤ በአሳው አሳቦ ባህሩን እንዲያደርቅ ሰበብ መሆናቸውን መገንዘብ አለባቸው።

ስለዚህ «ህዝባዊ ነኝ» የሚል ማንኛውም የፖለቲካና የሲቪክ ድርጅት ሁሉ ወያኔ አማራውን ሰበብ ፈጥሮ እንዳይጨፈጭፈው «ከትግሉ ጀርባ እኛ አለንበት» ወይንም « ትግሉ የእኛ ነው» ከሚል ህዝባዊ ያልሆነ የድርጅት መግለጫ ራሱን በመቆጠብ ህዝባዊ ተጋድሎውን በህዝቡ አጀናዳዎች ዙሪያ ብቻ እንደ ህዝብ የሚችለውን አስተዋጽኦ በማድረግ የአማራን ተጋድሎ ያግዝ ዘንድ በታላቅ አክብሮት ወገናዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

ድል ለአማራ ህዝብ!
ድል ለኦሮሞ ህዝብ!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!
የአማራ ተጋድሎ ይቀጥላል።

አባይ ማዶ ሕዝቡ ከከትግራይ ነፃ አውጪ ሠራዊት ጋር እየተጋደለ ነው * ባህርዳር የተኩስ ልውውጥ ይሰማል

$
0
0

Zehabesha-News.jpg
(ዘ-ሐበሻ) በባህርዳር እና በጎንደር አሁንም ውጥረቱ እንዳየለና በተለይም በባህርዳር ከተማ የተኩስ ልውውጥ እንደሚሰማ ከስፍራው የደረሱን መረጃዎች አመለከቱ:: እንደመረጃዎቹ ገከጻ ከሆነ የአጋዚ ሰራዊት ሕዝቡን ለማሰስ ባደረገው ሙከራ የተነሳ ሕዝብ እየታከሰ ይገኛል::

በተለይ አባይ ማዶ በሚባለው አካባቢ ህዝቡ ወደ ባህርዳር ለመግባት ሲሞክር ከትግራይ ነጻ አውጪ ሰራዊት ጋር እንደታኮሰና ቁጥራቸው በይፋ ያልታወቀ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል::

የሕወሓት ነፃ አውጪ ግምባር በተለይ በዛሬው ዕለት አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ከስልጣናቸው ካገደና ከማንኛውም የድርጅት ሥራ ውጭ ካደረገ በኋላ የሕዝቡ መነሳሳት እንደጨመረ ከስፍራው የሚደርሱን መረጃዎች ያመለከታሉ:: በተለይም የክልሉ ፖሊስም ከሕዝብ ጋር በመቆም ከትግራይ ነጻ አውጪ ወታደሮች ላይ ጥቃት እንደፈጸመም አንዳንድ መረጃዎች ተሰምተዋል::

በባህርዳር ምንም ዓይነት የንግድ ልውውጥ እንደሌለና በከተማዋ ያሉ ባጃጆችም ከአንዳንዶቹ በስትቀር በከተማዋ እንደማይታዩ ለዘ-ሀበሻ የመጣው ዜና ጠቁሟል::

ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ በአየርመንገድ በኩል በርካታ የታሸጉ ነገሮች እየሄዱ ነው

$
0
0
Addis Ababa Airport

Addis Ababa Airport

(ዘ-ሐበሻ) በአዲስ አበባ ኤርፖርት የሚገኙ የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንዳስታወቁት ካለፈው እሁድ ጀምሮ ከአዲስ አበባ ወደ ትግራይ ምንነቱ ያልታወቀ የታሸገ ፓኬጅ በብዛት ወደ መቀሌ እየተጓጓዘ ነው::

ምኝጮቹ እንደሚሉት ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ እየተጓጓዘ ያለው ምናልባትም ውድ የሆኑ የሃገሪቱ ንብረቶች; ገንዘብ እና ወርቅ ሊሆን ይችላል:: እነዚህ የታሸጉ እቃዎች በኤርፖርት በኩል ወደ መቀሌ ሲጓዙ ከፍተኛ የሆነ ጥበቃ እንደሚደረግና የሌላ ብሄር ተወላጆች እንዳያዩ እንደሚገሸሹ እነዚሁ ምንጮች አስታውቀዋል:: ፓኬጆቹን ጭነው የሚሄዱት አብራሪዎችም የትግራይ ክልል ተወላጅ የሆኑ ብቻ ናቸው ተብሏል::

በተለይ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች የተፈጠረው የሕዝብ ማዕበል ሳይበላን እቃችንን እናሽሽ ይመስላል የሚሉት እነዚሁ ምንጮች በጣም ውድ የሆኑ ነገሮች ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ በብዛት እየተሸጋገረ መሆኑ በአየር መንገዱ ውስጥ መናገገሪያ ሆኗል ብለዋል::

አስቸኳይ መልዕክት! ይድረስ ለብአዴ‬ን አመራር -ያሬድ ጥበቡ

$
0
0

‎ያሬድ ጥበቡYared Tibebu

የትግራይ ማህበረሰብ ውስጥ ለወቅቱ የኢትዮጵያ ሁኔታ ምላሽ ተደርጎ የሚታየው ብአዴን በነፍጠኞች ተይዟል፣ መሪዎች መመንጠር አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን የድርጅቱ ልሳኖች ከሰሞኑ ዘግበዋል። በመሆኑም ‪እነ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው‬ አልሰሙ እንደሆነ በመቐለ ቤተመንግስት እየ‬ተደገሰላቸው ያለውን ፍጅት ከወዲሁ አውቀው በጀመሩት ከህዝብ ጋር የመወገን ትክክለኛ ፖሊሲ ከዚህ ከተደገሰላቸው እርድ እንዴት መዳን ይቻላቸዋል? ባለፉት 40 አመታት ህወሐትን ከቅርብም ሆነ ከሩቅ እንዳጠናት ሰው የሚከተሉትን ምክሮች መሰንዘር ይጠበቅብኝ ይመስለኛል። ከተሰነዘረባቸው አደጋ ለመዳን የብአዴን መሪዎች የሚከተሉትን እርምጃዎች በአፋጣኝ መውሰድ ይኖርባቸው ይመስለኛል።

  1. የክልል ምክርቤቱን ስብሰባ ጠርተው፣ ‎ያለምክርቤቱ ጥሪ ወደክል‬ል የገቡትን የአግአዚና ፌዴራል ፖሊስ ሀይሎች ክልሉን በአፋጣኝ ለቀው እንዲወጡ ውሳኔ ማሳለፍና፣ ይህንንም ለህዝቡ በመገናኛ ብዙሀን ማስተላለፍ
  2. በዚሁ የክልል ምክርቤት ስብሰባ ወቅት ‎የመከላከያ ሰራዊቱ‬ በሃገር ውስጥ ፓለቲካ እጁን እንዳያስገባና፣ ብቸኛ ተግባሩ ሃገሪቱን ከውጪ ጠላት መከላከል መሆኑን ግልፅ ማድረግ፣ እግረ መንገዱንም የመከላከያና ደህንነት አመራሩ የሃገሪቱን ብሄራዊ ተዋፅኦ የተከተለ እንዲሆን ጥያቄ ማቅረብ፣
  3. በብአዴን ውስጥ ተሰግስገው ‎ለህወሐት የሚሰልሉ‬ እንደ ካሳ ተክለብርሀን፣ ታደሰ ካሳ፣ አለምነው መኮንን ወዘተ የመሳሰሉትን የአመራር አባላት ከአባልነታቸው ማገድና ካስፈለገም ወደ እናት ድርጅታቸው ህወሐት እንዲመለሱ ፈቅዶ ‎ማሰናበት
  4.  የኢህአዴግ አመራርና አደረጃጀት የብሄረሰቦችን ተዋፅኦ የጠበቀ እንዲሆን ማድረግና፣ የህዝብ ቆጠራውን ተከትሎ፣ የኢህአዴግ አመራር 34% ኦሮሞ፣ 28% አማራ፣ 6% ትግራዋይ ወዘተ እንዲሆን ውሳኔ ማስተላለፍና ለተግባራዊነቱ መታገል
  5. ከአማራ ክልል የተወሰዱትን ‎የድንበር መሬቶች‬ ለማስመለስ መወሰንና፣ ይህንኑ ውሳኔ የሚከታተል ከተቀሙት ቀበሌዎች ነዋሪዎች፣ ምሁራንና፣ የፖለቲካ ልሂቃን የተውጣጣ ግብረሃይል ማቋቋም
  6. የክልሉን ፕሬዚዳንትና ሌሎች ‎በህዛባዊ ወገንተኝነታቸው የሚታወቁ‬ የብአዴን አመራር ‎አባላትን‬ ካልታሰበ የህወሐት አፈናና እገታ ሊታደግ የሚችል ጥበቃ‬ እንዲደረግላቸው አስፈላጊው የሰው ሃይልና የፋይናንስ ምደባ እንዲረግ መወሰን። ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ፣ የክልሉን ልዩ ሃይል የጥበቃ አቅም ማጎልበት፣ አስፈላጊውን ሥልጠናና ትጥቅ እንዲያገኙ መወሰን፣
  7. የክልሉ ‎ህዝብ ነቅቶ ለመብቱ‬ ቀናኢ ሆኖ ዘብ ‎እንዲቆምና‬ በእለት ተእለት ህይወቱ አዛዣና ናዛዥ መሆኑ እንዲሰማው፣ ባለፉት 25 አመታት ተግባራዊ ሲደረጉ የቆዩትን ከህወሐት የተወረሱ የአፈና አሰራሮች ለማጥፋት በክልሉ ሸንጎ ላይ ለህዝቡ ቃል መግባት
  8. ብአዴን የሚመራው ክልል ተነጥሎ እንዳይቆምና፣ ህወሐት ሌሎቹን ክልሎች ይዞ እንዳያጠቃው፣ ሌሎቹን ክልሎችም የሚመሩት አባላት የቀድሞ የኢህዴን አባላት እንደነበሩ በማስታወስ፣ በተለይ የኦሮሚያ ክልል አስተዳዳሪዎች ለተመሳሳይ አላማ እንዲቆሙ የወንድማማችነት ግንኙነት መፍጠር፣ የትግል ህብረትን ማጠናከር
  9. በአንዳንድ ቦዘኔዎች ወይም በራሱ በህወሐት ሰርጎ ገቦች ‎በትግራዋዮች‬ ላይ የተናጠል ዘር ተኮር ‎እርምጃ እንዳይኖር‬ ነቅቶ መጠበቅ፣ አዝማሚያው በታየበት ሁኔታ ሁሉ እርምጃ መውሰድ፣

እነዚህንና መሰል እርምጃዎችን በመውሰድ የብአዴን አመራር የራሱን አንገት ከተሳለለት ቢላዋ ከማዳን አልፎ፣ ያለምንም ድርጅትና አመራር ጭቆና ስላስመረረው ብቻ እምቢ ለመብቴ ብሎ ለመስዋእትነት የተሰለፈውን የክልሉን ህዝብ ከእልቂት ከማዳንም አልፎ፣ ኢህአዴግ ራሱ የመፍትሄው አካል የሚሆንበትን እድል ሊከፍት ይችል ይመስለኛል።

ይህን ማድረግ አቅቶት ግን የብአዴን አመራር ካመነታ፣ ሳያታሰብ እንደ መብረቅ ብልጭ የሚለው የወያኔ ሰይፍ አናቱን ሊጨፈልቀው ይችላል። ‎ለብአዴን መሪዎች ግልፅ ሊሆንላቸው የሚገባው ነገር፣ ‎ወያኔ ከውልደቱ እስከዛሬ‬ም ድረስ የብዙ ድርጅቶችን አመራርን ደም እየጠጣ ያደገ የተመነደገ ድርጅት ነው።

በጥቅምት 1968 ዘገብላ በተባለ ቦታ ቲ ኤል ኤፍ የተሰኘውን የትግራይ ነፃ አውጪ ድርጅት አመራር አባላት “ኑ ድርጅታዊ ውህደት እንፈፅም” ብሎ ከተሰበሰቡ በኋላ እዚያው አፍኖ በመግደል ደም ከጠጣ ጀምሮ በደም አበላ እንደተዘፈቀ የኖረ ሀይል ነው። የብአዴን አመራርም ደም የመጨረሻው አይሆንም። እንግዲህ ‎ግማሽ እርግዝና የለም‬። የክልላችሁ ህዝብ ሁኔታ ኣሳዝኗችሁ መጠነኛ ወገንተኝነት በማሳየታችሁ፣ በወያኔ የተዘጋጀላችሁ መልስ እርድ መሆኑ ይፋ ተደርጓል። ባለፉት 25 አመታት እንደታዘብኩት ‎ወያኔ አንድ እርምጃ ከመውሰዱ በፊት ትግራይ ኦንላይንና አይጋ ፎረም በተባሉ አፈቀላጤዎቹ መድረክ ለፈረንጆቹ የሚሆን መረጃ መሰል ትንተና በእንግሊዘኛ ይፅፋል፣ ከዚያ በቀናት ውስጥ የማያዳግም እርምጃ ይወስዳል።

አይጋ ላይ የወጣውን የመቐለ ፅሁፍ አንብቤ ይህን ምላሽ ስፅፍ ማምሸቴ የብአዴን ወገኖቼ እጣ ስላሳሰበኝ ነው። ከህዝብ ጎን ስለቆሙ ለምን ይታረዳሉ በማለት። የብአዴን መሪዎች ዛሬ ለሚገኙበት ህዝባዊ ወገንተኝነትና በመቐለ ቤተመንግስት ለተሳለላቸው የእርድ ካራ፣ ባለፉት 25 አመታት ተስፋ ባለመቁረጥ አንድ ቀን ከህዝባችሁ ጎን እንደምትቆሙ የተመሰረታችሁበትን ህዝባዊ መሰረት እንደ ተስፋ መልህቅ በመያዝ፣ “እኔ የማውቃቸው የኢህዴን ልጆች ለጠባብ ብሄርተኝነት እጃቸውን አይሰጡም” በማለት በስደት ስመሰክርና ስከራከር ቆይቻለሁ። የጎንደር ህዝባዊ እምቢተኝነት ላይ ከወያኔ ጋር ተዳብላችሁ ሳትወገዙ፣ የናንተም ልዩ ሀይል በህዝቡ ላይ ሳይተኩስ አብራችሁ ቆማችሁ ሳይ የተሰማኝን እርካታ በቃላት የምገልፀው አይደለም። ሞትን አሸንፋችሁ እንደተነሳችሁ ያህል ነው የተሰማኝ። አሁንም የተጣለባችሁን ጋሬጣ አልፋችሁ በዓይነ ስጋ ለመተያየት ያብቃን። ከህዝቡ ጎን ቆማችሁ ሰማእት ብትሆኑም፣ ስማችሁ ከመቃብር በላይ ይውላል። ተጭበርብራችሁ ግን የወያኔ እርድ ካራ ስር እንዳትወድቁ አደራዬ ጥልቅ ነው። ከክፉ ይሰውራችሁ።

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>
<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596344.js" async> </script>