Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

በሚ/ር ደኤታ ማዕረግ ከሚገኝ የልብ ወዳጄ ጋር በሃገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ያደረግኩት ሚስጢራዊ ውይይት


ከልቤ ሰው ጋ በአማኑኤል ሆስፒታል –ከወሰን ሰገድ ገ/ኪዳን (ጋዜጠኛ)

$
0
0

==== እንደ መግቢያ ====


ትናትና ያልጠበቅኩትንና ያልገመትኩትን “ዜና” ሰማሁ፡፡ የክፉ ቀን ጓደኛዬ ችግር ውስጥ መሆኑን እና አማኑኤል ሆስፒታል መግባቱን፡፡ ይህ ጓደኛዬ በእኔ ህይወት ውስጥ ልዩ ቦታ ያለው ነው፡፡ በጭንቅ ጊዜ፣ በመከራ ጊዜ፣ “የሰው ያለህ” በሚያሰኝ ጊዜ የሰውም ሰው መሆኑን በተግባር ገልፆ ያሳየኝ የልቤ ሰው ነው፡፡ የጭንቅ ጊዜ ወዳጄ፣ ጭንቅ ውስጥ ሆኖ እኔን ማግኘት ይፈልጋል፡፡ ግን ምን ያደርጋል!? መሽቷል፡፡ መንጋት አለበት፡፡
አይነጋ የለም ነጋ፡፡

ከዕንቅልፌ ስነሳ መንጋት ብቻ አይደለም፤ ረፋድ ሆኗል፡፡ ፊቴን ለመታጠብ ደጃፌን ከፍቼ ስወጣ በአጋጣሚ የተጎራበትኩት ጋዜጠኛ ብርሃኑ በላቸው “በለሊት አማኑኤል ሆስፒታል እሄዳለሁ ብልህ አልነበር እንዴ?” አለኝ፡፡
“ልሄድ ነው፤ ለሊቱን ሙሉ በሃሳብ ስናውዝ አድሬ ሲነጋጋ እንቅልፍ ጣለኝ” አልኩት ሰዓት እያየሁ፡፡ ከጠዋቱ 3 ሰዓት ሆኗል፡፡
“ሲሳይ ምን ሆኖ ነው?… ለማንኛውም የምንተጋገዘው ነገር ካለ ንገረኝ” አለኝ ብርሃኑ ወደ ውጪ በር
እያመራ፡፡ ልክ ነው የዚህ ወዳጄ ስም ሲሳይ ነው፡፡ ከዚህ በፊት አስተዋውቄያቸዋለሁ፡፡ ሲሳይ በቀለ ይባላል፡፡ በ”የቃሊቲ ምስጢሮች” ትረካ ውስጥ ስሙን ያልገለፅኩት ለ”ጥንቃቄ” ብዬ ነው፡፡ አሁንም ስሙን መግለፄ ትክክለኛ ተግባር ይሁን አይሁን እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ግን ….
የሆነ ሆኖ የቁርጥ ቀን ወዳጄ ሲሳይ በቀለ ከእውቅ የዜማና ግጥም ደራሲዎች መሃል የሚመደብ ነው፡፡ በሕዝብ ልብ ውስጥ የቀሩ ምርጥ ምርጥ የግጥምና የዜማ ድርሰቶች አሉት፡፡ በአንጋፋና በወጣት ድምፃውያን አንደበት የናኙ፡፡ ይህ ሰው ነው አማኑኤል ሆስፒታል ለመግባት የተገደደው፡፡ ለምን!? ምን ገጥሞት ይሆን!?

==== በአማኑኤል ቅጥር ግቢ ====
ከቀኑ 5 ሰዓት የሆስፒታሉን ዋና በር አልፌ እየዘለቅኩ ሞባይሉን አወጣሁና ደወልኩለት፡፡ ስልኩ ይጠራል፤ አያነሳም፡፡ ሞባይሌ አምስት ጥሪ ያህል እንዳስተላለፈ አንድ የህሙማን ልብስ የለበሰ ሰው እጁን ከፍ አድርጎ ምልክት አሳየኝ፡፡ እሱ ነው፡፡ ሲሳይ በቀለ ነው፡፡
ገፅታዬ ላይ ምንም ለውጥ እንዳይታይ እየጣርኩ እጄን ዘረጋሁለት፡፡ ጨበጠኝ፡፡ ትከሻ ለትከሻ ተገጫጨን፤ ከዚያም ተቃቀፍን፡፡ ….ከሠላምታ በኋላ እጅ ለእጅ ተያይዘን ሳለ አጠገባችን ወደሚገኝ የሃኪም ቤቱ አንድ ጥጋት መራሁት፡፡
“ና! ወደ እኔ ክፍል እንሂድ፡፡” አለኝ ግቢው ውስጥ ወደሚገኝ የተከለለ ሌላ ግቢ እየመራኝ፡፡
ቀፈፈኝ፤ ቢቀፈኝም ምንም ማድረግ አልችልም፡፡የምንገባበት ግቢ ውስጥ ዱላ ይዘው ወዲያ ወዲህ የሚያወናጭፉ ታካሚዎች ይታዩኛል፡፡ ሞባይል ይዘው እየተጯጯሁ የሚነጋገሩ፤ ብቻቸውን የሚያወሩ፤ በዝምታ የሚንጎራደዱ…የሆነ ሰው ላይ የሚዝቱ፣ የሚሳደቡ ..ወዘተ ታካሚዎች ይታዩኛል፡፡
እነዚህን መሰል ታካሚዎች በሥጋት ዓይን እያየሁ ጓደኛዬን ተከተልኩት፡፡ ግቢው ውስጥ የሚገኝ ትልቅ ሕንፃ ሥር ወደ ታችኛው ክፍል ይዞኝ ወረደ፡፡
“አንተ ሻንጣ ስለያዝክ ሐኪም ነው የምትመስለው” አለኝ የያዝኩትን ላፕቶፕ እየጠቆመኝ – እናም የተኛበትን ክፍል በር አልፎ ገባ፡፡ አልጋው ላይ አረፍ ብሎ እኔም አረፍ እንድል ጋበዘኝ፡፡ ከጎኑ ተቀምጬ ክፍሉን ቃኘሁት፡፡ ፅዱ ክፍል ነው፡፡ 20 ያህል በሥነ ሥርዓት የተነጠፉ አልጋዎች ተዘርግተዋል፡፡ አልፎ አልፎ የተነጠፉት አልጋዎች ላይ ጋደም ያሉ ታካሚዎች አሉ፡፡ አንዳንዶቹ ሞባይል ለብሰዋል፡፡ አንዳንዶቹ የሆስፒታሉን ሳይሆን የራሳቸውን ልብስ የለበሱ ናቸው፡፡
“አሪፍ ክፍል ነው፤” አልኩት ወሬ እንዴት እንደምጅምር ግራ ገብቶኝ፡፡
“ይኼኛው ክፍል የሳይኪክ ችግር የሌለባቸው ነው፡፡” አለኝ፡፡ ሌላም ሌላም ነገር ነገረኝ፡፡ አነጋገሩ ጤነኛ መሆኑን እንድረዳለት የሚያሳብቅ ነው፡፡እናም ዝም ብዬ ሰማሁት፤ ዓይን አይኑን እያየሁ ሰማሁት፡፡ ይህቺን የማዳመጥ አስፈላጊነት የተማርኩት አንድ የእርዳታ ድርጅት ለሳምንታት “ፒር ካውንስለር” የተባለ ኮርስ በሰጠን ጊዜ ነው፡፡ “እንዲህ ዓይነት ችግር ያለበት ሰው ችግሩን ሲነግርህ ከልብህ አድምጠው፤ ከልብህ ማዳመጥህን እንዲረዳልህ ዓይን ዓይኑን እየው፡፡ ዓይኑን ከማየት በተጨማሪ ማዳመጥህን እርግጠኛ ሆኖ ችግሩን በራሱ ፍቃድ ዘክዝኮ እንዲነግርህ ‹እህ! እህ!› እያልክ አበረታታው” የሚል ዓይነት ነው የኮርሱ ይዘት፡፡
እናም የሚነግረኝን “እህ!” ብዬ አዳመጥኩት፡፡ ልናገርስ ብል ምንድነው የምናገረው? ንግግሬንስ ከየትና እንዴት ነው የምጀምረው!?…ግራ ግብት የሚል ነገር ነው፡፡ ደግነቱ እሱ ራሱ ወደዋናው ጉዳይ ገባልኝ፡፡
“እዚህ ከገባሁ አንድ ወር አለፈኝ፡፡ ወዲያውኑ አንተን ማግኘት ነበር በጥብቅ የፈለግኩት፡፡ ትናንት እንደነገርኩህ ስልኬ ጠፍቶ ስለነበር ላገኝህ አልቻልኩም፡፡ የአንተን ቁጥር ለማግኘት የደወልኩላቸው ሁሉ የበፊቱን ስልክ ቁጥርህን ነው የሚሰጡኝ፡፡ ….አሁን እንዴት እንዳገኘሁህ ታውቃለህ!? በመዝሙር ዮሐንስ (ድምፃዊ) በኩል ነው፡፡”
“መዝሙር እንዴት ስልኬን አገኘ?”
“ሁለት ቀን ሙሉ ስልክህን ማግኘት ሞክሮ አልተሳካለትም ነበር፡፡ እንዳልተሳካለት ሲነግረኝ የድምፃዊ ትዕግስት ፋንታሁን ወይም የባለቤቷን ስልክ ካወቅህ እነሱን ጠይቃቸው አልኩት፡፡ በዚህ ሁኔታ ነው የአንተን ስልክ ትናንትና ያገኘሁት” አለኝ፡፡
የነገረኝ ነገር አልደነቀኝም፡፡ ድምፃዊ ትዕግስት ፋንታሁን በ2002 ዓ.ም “ና” በሚል ርዕስ ለአድማጭ ባቀረበችው አልበም ውስጥ የሁለቱን ግጥሞች የፃፍኩት እኔ ነኝ፡፡ (ሃሃሃሃ ይህቺ ነገር እንደማስታወቂያ እንዳትቆጠርብኝ) ያኔ ከትዕግስት ፋንታሁን ጋር ለሥራ እንገናኝ ነበር፡፡ (ከትዕግስትም ሆነ ከባለቤቷም ጋር አብሮ አደግ ነን) …እንዲያም ተባለ እንዲህ ያንን አስታውሶ እኔን ማግኘት መቻሉ አስደሰተኝ፡፡ ጤንነቱ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተረዳሁ፡፡ የልቤ ሰው የከፋ ሁኔታ ላይ ባለመሆኑ ተፅናናሁ፡፡ የሆነ ሆኖ ስለ ዘፈን ካነሳሁ ዘንዳ ዛሬ አማኑኤል ሆስፒታል ስለሚገኘው የልቤ ሰው ሲሳይ በቀለ የግጥምና የዜማ ደራሲነት ጥቂት በምልሰት ላውራ፡፡

====== ምልሰት =======
“እኔን ናፍቀሽኛል – አልናፈቅኩሽም ወይ
መራራቁ ቀርቶ – አንገናኝም ወይ
ፍ…ቅ …ር …..
ፍቅር አይገድሽም ወይ”

” አማላጅ ማን ይሁን፤ ማንን ልላክብሽ
ህመሜ ተሰምቶሽ – ፍቅር እንገድሽ….”
የዘፈኑን ግጥም በትክክል መከተቤን እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ የዜማው ለዛ እና ፍሰት ግን እስካሁን በጆሮዬ ይሰማኛል፡፡ ዘፈኑን ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማሁት በሬድዮ ነው፡፡ ከ20 እና ከ25 ዓመት በፊት፡፡ ድምፃዊው ማን እንደሆነ በስም አላስታውስም፡፡ የዜማና የግጥሙ ደራሲ ግን ሲሳይ በቀለ ነው፡፡
ሲሳይ በቀለ ከበርካታ ዕውቅና ድንቅ ድምፃውያን ያለ የጥበብ ሰው ነው፡፡ ከበርካታ የጥበብ ሰዎች ጀርባ ያለ ጥበበኛ ነን፡፡ ለጊዜው ለእነማን ለእነማን ሥራዎቹን እንደሰጠ ማውጋት አልፈልግም፡፡ ነገር ግን ሁለቱን ወንድማማቾች ታዋቂ ድምፃውያን ልጥቀስ፡፡ ፀሐይዬ ዮሐንስን እና መዝሙር ዮሐንስን፡፡
ለእነሱ ከሰጣቸው ሥራዎች ውስጥ አብዛኛው ሰው የሚወድለትን የመዝሙር ዮሐንስን “ልጅነቴ”ን ዘፈን ብቻ ላስታውስ፡፡ የ”ልጅነቴ” ዘፈን ዜማና ግጥም ደራሲ ይኸው የልቤ ጓደኛ ሲሳይ በቀለ ነው፡፡
“….ውሃ ሽቅብ ላይወጣ
ኑግ እንደሱፍ ላይነጣ
ልጅነቴ ናፈቀኝ ተመልሶ ላይመጣ….”

“ፊደል ይዤ በጉያዬ
ተቃቅፌ ከእኩያዬ….”
ይህንን የመዝሙር ዮሐንስን “ልጅነቴ” ሰምቶ በትዝታ የማይመሰጥ የለም፡፡ እነሆ የዚህ ዘፈን ግጥምና ዜማ ደራሲ ነው የልቤ ሰው፡፡ ዛሬ አማኑኤል ሆስፒታል የሚገኘው፡፡

===== ምን ሆኖ ነው!?====
የሆነው ብዙ ነው፡፡ ታሪኩም ረዥም ነው፡፡ 6 ዓመታት ያህል ወደ ኋላ የሚያስጉዝ ነው፡፡ ቤተሰቡ ተበትኗል፤ ልጆቹን አጥቷል፤ ቤቱም በእሱና በባለቤቱ ግጭት የተነሳ በሌላ ሰው እጅ ነው ያለው፡፡ ….ህይወት ፊቱን ካዞረችበት ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ይኸው ነው፡፡ ከዚህ በላይ ማለት አልችልም፡፡ እንዲያም ሆኖ ፊቱን ሙሉ በሙሉ ወደ ጥበብ አዙሮ ቤት ተከራይቶ ራሱን እያስተዳደረ ህይወትን መቀጠል ችሎ ነበር፡፡
ከወራት በፊት ግን “ሰው ጠላሁ፤ ሰው ፈራሁ፤ መሸሽ ጀመርኩ” አለኝ፡፡
“ለምን?”
“የሚታመን ሰው ማግኘት አልቻልኩም፡፡ ያሰብኩት ቀርቶ ያላሰብቡት ሲሆን ግራ ገባኝ፡፡ ጨነቀኝ፡፡ ሰው መሸሽ ጀመርኩኝ፡፡ ሰው ለመሸሽ ብዬ ትንሽ አልኮል አበዛሁ መሰለኝ ታመምኩኝ፡፡” አለኝ፡፡
“ሰው ይጠላል እንዴ?” ስል ጠየቅኩት እየፈራሁ እየተባሁ፡፡ “ትናንትና እንኳ አንተ ያለህበትን ከነገርከኝ በኋላ ይህንን ፃፍኩኝ” አልኩት ኮምፒውተሬን እየከፈትኩ፡፡ ፌስ ቡክ ላይ የፃፍኩትንና የተሰነዘረውን አስተያየት ጭምር አስነበብኩት፡፡ “ይህ ሁሉ ሰው አንተ እዚህ በመገኘትህ አዝኗል፡፡ የማያውቅህ ሰው ያንተን ጤንነት ተመኝቷል፡፡ እና እንዴት ሰው ይጠላል፤ ሰው ለሰው መድሃኒቱ ነው ይባል የለ እንዴ”
የፌስ ቡክን አስተያየት ካነበበ በኋላ ፊቱ ፈካ አለ፡፡ ወዲያው ደግሞ ተኮሳተረ፡፡
” ምን ላርግ? የሚታመን ሰው አጣሁ፤ በእምነት የሰጠኋቸውን ሥራ የእኔ ነው ብለው ያሳትሙታል፡፡ ገንዘቡ ይቅር ስሜን እንኳ ለመፃፍ (ለማንሳት) አይፈልጉም፡፡ …ሌላው ሌላውን ተወው፤ አሁን በቅርቡ የወጣው ዘፈን እንኳ የኔ ሥራ ነው፡፡ እኔ አልብላ፤ አልጠጣ ስሜን እንኳ መፃፍ ማንን ገደለ!?”
ዝም አልኩኝ፤ ዝም፡፡ ዝም ከማለት ሌላ ምን ማለት እችላለሁ፡፡ ሲሳይ በቀሌ “የኔ ፈጠራ ነው” እያለ የሚነግረኝ ዘፈን ሀገር ሁሉ ትከሻውን የሚሰብቅበት፣ የሚወዛወዝበት እጅግ ተወዳጅ የሆነ ዘፈን ነው፡፡ ይህ የእሱ ነው፤ የእሱ አይደለም ለማለትም ላለማለትም ድምፃዊውንና አሳታማውን ማነጋገር ያስፈልጋል፡፡
“መልካም፤ እንዲህ ዓይነት ነገር ያጋጥማል፤ ደግሞም ላንተ አዲስ አይደለም፡፡ አሁን እሱን እንተወውና እኔ እንድረዳህ የምትፈልገው ነገር ምንድነው? የምችለው ከሆነ ልረዳህ ዝግጁ ነኝ፡፡”
“አሁን በጣም ደህና ነኝ፡፡ በቅርቡ ከዚህ እወጣለሁ፡፡ ስወጣ የት እንደምኖር አላውቅም፡፡”
አመመኝ፡፡ የልብን ስር ጠቅ የሚያደርግ ህመም ተሰማኝ፡፡
“እዚህ እስካለሁ ድረስ መንግስት የሚያቀርብልኝን እንጀራ በልቼ ማደር እችላለሁ፡፡…”
ከዚህ በላይ መስማት አልቻልኩም፡፡ አቋረጥኩት፡፡
“ምን ችግር አለው!? አሁን እኔ ቤት ተከራይቻለሁ፤ ከእኔ ጋር ትኖራለህ፡፡ ከኔ ጋ ኖርክ ማለት የምትበላው አታጣም ማለት ነው፡፡ ይኼ ሊያስጨንቅህ አይገባም፡፡ ከዚያ በኋላ ደግሞ የሚሆነው ይሆናል፡፡…” አልኩት፡፡
“አዎ ካንተ የምፈልገው ይኼን ነው፡፡ የልጄን ት/ቤት የከፈለልኝ ሰው ነው፡፡…”
“ግዴለም የምንችለውን እናደርጋለን፤ ዋናው ጤና ነው፡፡ ካንተ ጤንነት በኋላ ነው፤ አሁን አታስብ” አልኩት፡፡ “አታስብ” ይባላል እንዴ!!? አለማሰብስ ይቻላል እንዴ!!? እንጃ!!!!
እነሆ ለአንድ ሰዓት ያህል እንዲህ እና እንዲያ አብረን ቆየን፡፡ ልንሰነባበት ሆነ፡፡ ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ከክፍሉ ለመውጣት በዝግታ ማዝገም ጀመርኩ፡፡ ተከተለኝ፤ ሊሸኘኝ፡፡ እየሸኘኝ
“ደግሞ በዚያው እንዳትጠፋ፡፡ እየመጣህ ጠይቀኝ፡፡ እስካሁን መዝሙር ዮሐንስ ብቻ ነው እየመጣ የሚጠይቀኝ!!”
“አልጠፋም፤ እመጣለሁ፡፡ በጣም የምትፈልገኝ ከሆነ ደውልልኝ፤ እመጣለሁ፡፡” አልኩት ዋናውን የግቢው መውጫ በርቀት እያየሁ፡፡
በመጨረሻም ተሰነባበትን፡- ነገን እያለምን፡፡ ነገም ሌላ ቀን ነው!!

Pen

 

“ከሰማይ ወረደ ለተባለው መስቀል የሳይንስ ምርመራ አይፈቀድም ተባለ”– (አዲስ አድማስ ጋዜጣ)

$
0
0

(ፎቶ ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ)

(ፎቶ ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ)


አለማየሁ አንበሴ ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ለታተመው አዲስ አድማስ ጋዜጣ እንደዘገበው፦

በአቃቂ ቃሊቲ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን ከሰማይ ወረደ የተባለው መስቀል ፓትርያርኩ በተገኙበት ለህዝብ እንዲታይ መግቢያ መንገድ እስኪሰራ ድረስ የተራዘመ ሲሆን፣ በመስቀሉ ላይ የሳይንስ ምርመራ እንደማይፈቀድ ተገለፀ፡፡ ከሶስት ሳምንት በፊት በፍንዳታ ድምፅና በብርሃናማ ቀስተደመና ከሰማይ ወረደ የተባለው መስቀል፣ በሚቀጥለው ሳምንት መስከረም 19 ቀን ለህዝብ ይታያል ተብሎ የነበረ ቢሆንም፣ ፓትርያርኩ የሚገኙበት ስነስርዓት ለማዘጋጀት ጊዜው እንደተራዘመ የቤተክርስቲያኗ አስተዳዳሪዎች ተናግረዋል፡፡ መስቀሉ ለህዝብ የሚታየው ቅዱስ ፓትሪያርክ አቡነ ማቲያስ በተገኙበት ስነስርዓት መሆን አለበት መባሉን አስተዳዳሪዎች ጠቅሰው፤ መንገዱ ጭቃ ስለሆነ ጠፈፍ ብሎ ለመኪና እስኪስተካከል ድረስ ቀኑ መራዘሙን ገልፀዋል፡፡ ቀኑ ገና እንዳልተወሰነና ለፓትሪያርኩ ጋር ውይይት እየተደረገበት ነው ያሉት የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳዳሪዎች፤ ስነስርዓቱን ህዳር 11 ቀን ለማካሄድ እንደታሰበ ጠቁመዋል፡፡

ከአዲስ አበባና በአቅራቢያዋ ከሚገኙ አካባቢዎች በየእለቱ ከ3ሺ በላይ ሰዎች ቦታውን እየጎበኙ መሆናቸውን የገለፁት የቤተክርስቲያኗ መጋቢ ሃዲስ ፍሰሃ፤ እኛም በየእለቱ ከ15 ጊዜ በላይ ስለ ተከሰተው ተዓምር ገለፃ እናደርጋለን ብለዋል፡፡ መስቀሉ ባረፈበት ሳር ላይ እንዲሁም ወደ ቤተ መቅደሱ ከገባ በኋላ የተነሱ ፎቶዎችን የያዘ ካርድ ታትሞ ለምዕመናን በ10 ብር እየተሸጠ ነው፡፡ በፎቶግራፍ ላይ የሚታየው መስቀል በሰው የተሰራ የዕደ ጥበብ ውጤት እንደሚመስል በመጥቀስ ከሰማይ ወረደ መባሉን የሚጠረጥሩ መኖራቸውን በተመለከተ መጋቢ ሃዲስ ፍስሃ፣ እውነቱን የሚያውቀው ፈጣሪ ነው ብለዋል፡፡

በምድራችን የተሰራ የሚመስል መስቀል ከሰማይ ሊወርድ አይችልም የምንል ከሆነ፣ በምድራችን የምናረባው አይነት በግ ለአብርሃም ከሰማይ ወርዶለታል የሚለውን የመፅሃፍ ቅዱስ ቃል መጠራጠር ይሆናል ብለዋል መጋቢ ሃዲስ ፍስሃ፡፡ የመስቀሉን ስሪት እንዲሁም መስቀሉ አረፈበት የተባለውን ሳርና አፈር ለመመርመር ሃሳብ ተነስቶ እንደሆነ ተጠይቀው መጋቢ ሃዲስ ሲመልሱ፤ “ይህ መስቀል የቤተክርስቲያኒቱ የክብር መገለጫ ነው” በማለት ተቃውመዋል፡፡

እስካሁን በስፍራው የተፈፀመውን ተአምር ሰምተው የሚያደንቁ እንጂ በመስቀሉና በቦታው ላይ እንመራመራለን የሚሉ ምሁራን አላጋጠሙኝም ያሉት መጋቢ ሃዲስ፤ “እንዲህ ያለ ጥያቄ ያላቸውም ካሉም፣ የማይሞከር ነው” ያሉት መጋቢ ሃዲስ፤ የሃይማኖት ጉዳይ ስለሆነ ቦታውን እንፈትሻለን፣ የወረደውን መስቀል እንመረምራለን ለሚሉ የሳይንስ ባለሙያዎች ፈፅሞ አይፈቀድም ብለዋል፡፡ መስቀሉ ከሰማይ ከመውረዱ አስቀድሞ ራዕይ ታይቶኛል የሚል ሰው እስካሁን አላጋጠመን ያሉት መጋቢ ሃዲስ፤ ቤተክርስቲያኒቱን ያቋቋሙት አባት ግን፣ ቦታው የእግዚአብሔር ክብር መገለጫ እንደሚሆን በራዕይ እንደታያቸው ተናግረው ነበር ብለዋል፡፡

የተወልደ በየነ (ተቦርነ) በዘፈን እናውራ ሲዲ የፊታችን ማክሰኞ ይመረቃል

$
0
0

Teborne CD Release Flayer (2)
(ዘ-ሐበሻ)፡ በተለያዩ የራድዮ ጣቢያዎች አዝናኝ የሙዚቃ ሥራዎችን በማቅረብ ተወዳጅነትን ያተረፈው ጋዜጠኛና የሙዚቃ አማካሪ ተወልደ በየነ በአይነቱ ልዩ የሆነው “በዘፈን እናውራ” የተሰኘ አስቂኝና ቁምነገር የያዘ ሲዲ ይዞ ቀረበ። ይህ በሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትን ያገኛል በሚል ከወዲሁ ግምት የተሰጠው ሲዲ የፊታችን እሁድ በቨርጂኒያ መዓዛ ሬስቶራንት እንደሚመረቅ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመልክቷል።

ከዚህ ቀደም ሽገር ሬዲዮ አሁን ደግሞ በኢሳት ራድዮና ቴኤቭዥን በሚያቀርባቸው የመዝናኛ ዝግጅቶች ተወዳጅነትን ያተረፈው ዜጠኛና የሙዚቃ አማካሪ ተወልደ በየነ በአይነቱና በአቀራረቡ ለየት በሚል መልኩ ይዞት የቀረበው የሲዲ ሥራ “በዘፈን እናውራ” ይሰኛል። በዚህ አዝናኝ ሲዲ ተወዳጁ ጋዜጠኛ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ከመሪ ጅምሮ እስከ ተቀዋሚ ያሉትን በዘፈን እያወራቸው ያስቃል፤ ያዝናናል ተብሏል።

ከመሪዎች በተጨማሪም ድምፃዊያኑንም በዘፈን እንደሚያወራቸው የተጠቀሰ ሲሆን በስራቸው ለተጠየቁት ምላሽ ከሰጡት ድምፃዊያን መካከልም ጥላሁን ገሠሠ፣ አስቴር አወቀ፣ ነዋይ ደበበ፣ ቴዎድሮስ ካሳሁን፣ ይገኙበታል ተብሏል:
የተቦርነ በየነው ይህ በአይነቱና በአቀረቡ የመጀመሪያ የሆነው ሲዲ ሴፕቴምበር 24 በመአዛ ሬስቶራንት ከ 8:30pm ጀምሮ ከተመረቀ በኋላ በመላው ዓለም ለአድማጭ እንደሚሰራጭ ይጠበቃል። በሲዲው ምረቃ ላይ መገኘት ለምትፈልጉ የመአዛ ሬስቶራንት አድራሻ 5700 Columbia Pike Falls Church, VA 22941 ነው። የሬስቶራንቱ ስልክ ቁጥርም (703) 820-2870 ነው።
መልዕክቱን በድምጽ ያድማጡ፦

ኦሮማይ ትግሉ በሚቻለውና በማንኛውም መንገድ!

$
0
0

ከቴዎድሮስ ሓይሌ (tadyha@gmail.com)

Oromayሠሞኑን የግንቦት ሰባት ዋና ፀሐፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ስለ ኤርትራ ቆይታቸውና ስለድርጅታቸው ቀጣይ የትግል እንቅስቃሴ ሠፊ ገለጻና ማብራሪያ በኢሣት ቴሌቪዠን ከሠጡ ወዲህ የዘረኛው የትግሬ ነጻ አውጪ ግንባር ደጋፊ የሆኑት መርገማዊ ልሳኖች( አይጋ ፎረም ፤ ትግራይ ኦላይንና አውራንባ ታይምስ) እና አንዳንድ ተንበርካኪ የመንደር ሬድዮኖች ሰፊ የውግዘትና የህዝብን መንፈስ ያሸብርልናል በተቃዋሚዎችም ላይ ጥርጣሬ ይዘራልናል በሚል ደካማ ግንዛቤ እያካሄዱ ካለው አሰልቺና ኋላቀር ፕሮፓጋንዳ እጅግ ተጋኖ እየቀረበ ያለው ከሻብያ ጋር አብሮ መስራት ታላቅ የሃገር ክህደት ስለመሆኑ እፍረት የለሽ ኡኡታ በማሰማት ላይ ይገኛሉ። ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

አፍሪካዊያን ከአይሲሲ በደቦ ወሙጣታቸውን ኢትዮጵያ ትደግፋለች

$
0
0

ቪኦኤ ዜና

የአፍሪካ ሃገሮች ከዓለምአቀፉ የወንጀል ችሎት – አይሲሲ አባልነት በደቦ እንዲወጡ ለማድረግ ኬንያ የጀመረችውን ጥረት እንደምትደግፍ የአፍሪካ ኅብረት የወቅቱ ሊቀመንበር ኢትዮጵያ አስታውቃለች፡፡

578A83

በዓለምአቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ተከስሰው ጉዳያቸው እየታየ ያለው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታና ምክትል ፕሬዚዳንቱ ዊልያም ሩቶ /የተከሰሱባቸው ‘አቀናብረዋቸዋል’ ወይም ‘ተሣትፈውባቸዋል’ ተብለው የተጠረጠሩባቸው ‘በሰብዕና ላይ የተደረጉ ወንጀሎች’ የተፈፀሙት እንደስማቸው ቅደም ተከተል የኬንያ የገንዘብ ሚኒስትርና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር በነበሩበት እአአ በ2007 ዓ.ም ነው፡፡

አፍሪካዊያን ከአይሲሲ በደቦ ወሙጣታቸውን ኢትዮጵያ ትደግፋለች
የአፍሪካ ሃገሮች ከዓለምአቀፉ የወንጀል ችሎት – አይሲሲ አባልነት በደቦ እንዲወጡ ለማድረግ ኬንያ የጀመረችውን ጥረት እንደምትደግፍ የአፍሪካ ኅብረት የወቅቱ ሊቀመንበር ኢትዮጵያ አስታውቃለች፡፡

ዓለምአቀፉ የወንጀል ችሎት በኬንያው ምክትል ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ ላይ በሰብዕና ላይ በተፈፀሙ ወንጀሎች ክሥ መሥርቶ ጉዳያቸው ጄኔቫ ላይ እየታየ ሲሆን ፕሬዚዳንቱ ኡሁሩ ኬንያታ ደግሞ የፊታችን ኅዳር

የአፍሪካ ኅብረት በመጭው ወር ውስጥ በዚሁ የኬንያ ባለሥልጣናት ክሥና የፍርድ ሂደት ጉዳይ ላይ ልዩ ስብሰባ እንደሚያካሂድ የኅብረቱ ሥራ አስፈፃሚ አካል ምክትል ኃላፊ የሆኑት ኬንያዊው ኤራስቱስ ሞኤንቻ ለፈረንሣዩ የዜና ወኪል ገልፀዋል፡፡

ጉዳያቸው በዓለምአቀፉ የወንጀል ችሎት በተያዘው ከፍተኞቹ የኬንያ ባለሥልጣናት የፍርድ ሂደት ጉዳይ ላይ ኬንያዊያን የተለያየ አስተያየት አላቸው፡፡
በአይሲሲ እየታደኑ ያሉት ኦማር ሁሴን አል-በሽር – የሱዳን ፕሬዚዳንት
በአይሲሲ እየታደኑ ያሉት ኦማር ሁሴን አል-በሽር – የሱዳን ፕሬዚዳንት
በሌላ በኩል ደግሞ ዩናይትድ ስቴትስ የሱዳኑን ፕሬዚዳንት ኦማር ሁሴን አል በሽርን የመግቢያ ቪዛ ጥያቄ እያጠናች መሆኗን ገልፃለች፡፡

ለዝርዝር ዘገባው የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የቀይ ባሕር ሴራ፤ መጣ እያጓራ ! ከሎሚ ተራ

$
0
0

 

ምን አለ ብትተዉኝ መሬቴን ባለማ

ምን አለ ብታርፉ ወገኔ ቢሰማማ

             ……..

ወገን ደራሽ መሰሎ ሆዱን እየሞላ

ጎርፍ ሆኖ ሊወሰደው የቀይባሕር ሞላ

 

ምን አለባት የዚህ ግጥም መንደርደሪያ  አንባቢያንን ግራ ሊያጋባ ይችል ይሆናል ብዬ ሰግቼ ነበር፤ ሆኖም ኢትዮጲያዊያን ወገኖቼ በርካታዎቹ ““ድጓ ጾመዱጓ ፤ የደገሙ““በመሆናቸው መልዕክቱ በቀጥታ ምን ማለት እንደሆነ እንደሚረዱ አምናለሁና  ልቀጥል።

 

“”ይቺ፤ ምራቅ ሳትደርቅ፤”” ይባል ነበር አሉ ድሮ፤  ይግርማል” ሰለ ሻአቢያ ደባ አውርትን ሳንጨርሰ፡ እንደተመለከታችሁት የሻአቢያው መሪ በኤርትራው ቲቪ መሰኮት ብቅ ብለው በሁለት እጃቸው ወገባችውን ይዘው ጥርሳቸውን እያንቀጨቀጩ አንዳንዴም ጠያቂው (ጋዜጠኛው)  መግቢያ መውጫ እሰኪጠፋው፤ አይናችውን እያጉረጠረጡ  ለመሆኑ ኢትዮጲያ ማን ናት ? ?;;;;;;፤  ይቺ ከሁለተኛው አለም ጦርነት ማግሰት የተፈጠረች አገር  ? ? ;;;;;;;’  ኤርትራን ኮሎኒ ;;;;;;፤  አድርጋለች እየተባለ የሚወራው ? ? ;;;;፤  ይሄማ ለ ኢትዩጲያዊያን ትልቅ ክብር መሰጠት ነው። በሚል  ፌዛዊ አነጋገር ኢትዬጲያ ትላንት ወያኔ ሲገባ እንደተፈጠረች አይነት አድርገው ለማሰቀመጥ ሲሞክሩ መሰማት ምን ያኸል አሳዛኝና አሁንም ኢትዬጲያን የማጥፋት አባዚያችው እንዳልበረደላቸው አሰረግጠውልናል።

 

እንግዲህ ልብ በሉ ከእኚህ የ ኢትዬጲያ ሰም ሲጠራ ከሚያንገሸግሻችው ሰው ጋራ ነው ለኢትዮጲያ አሳቢ ናቸው፤  በሙሉ ልባቸው ወያኔ በኢትዬጲያ ሕዝብ ላይ የሚደረሰውን ግፍ ድጋፍ ለመሰጠት ቆርጠዋል። ድጋፋቸውም ወደር የሚገኝለት አይደለም ። እየተባለ ጠዋትና ማታ የሚለፈፈው። እኔ በበኩሌ እንዲገባኝ ለማድርግ ብዙ ጥረት አደረግኩ ። ብዙም ወደሖላ ተመልሼ ለመመልከት ሞከርኩ። አንዱም የሻአቢያ ተግባር ለ ኢትዬጲያ በጎ ነገር እንደሌለው እንጂ አንድም በጎ ተግባር እንደሌለው ነው መረጃው በሙሉ እሰካሁኗ ደቂቃ ድረሰ የሚያሳየኝ እና አንባቢያን ሆይ እባካችሁ እንደገና ቆም ብለን እንመርምር  በሻአቢያ እርዳታ አገር ነፃ አይወጣም። ሻአቢያ ከወያኔ ጋር ተባብርው ቀይባሕር እንዳይከቱን እንጠነቀቅ።

 

ይልቅ አገርውሰጥ ያለውን የሰላማዊ ትግል መደገፉ ጠቃሚና አሰፈላጊነቱን በሚከተሉት ሦሰት ነጥብ ለማሰቀመጥ ልሞክር እንሆ፦———

 

1ኛ)    የሰላም ትግል ማለት እኮ የሕብረተሰብን አሰተሳሰብና አመለካከት በጠመንጃ ሣይሆን በተሻለ አሰተሳሰብና አመለካከት የዲሞክራሲ ሰርአት እንዴት ማምጣት እንደሚቻል ማሰተማርና ማደራጀት ነው። ኢትዮጲያ በአለም ላይ ደሃ አገሮች ተብለው ከሚጠሩት አንዶና፤ ሕዝቦ በድህነትና ፍትሕ በማጣት፤ በጉሰቁልናና በሰደት፤ በበሽታ፤ በመፈናቀል፤ የምትታወቅ በመሆኗ፤ ይኸን አለማቀፍ ጉሰቁልና ለመቅረፍና የዲሞክራሲን ሂደት ለማምጣት በ አገር ውሰጥ የተጀመረው የሰላም ትግል ከጦርነት ትግል በላይ ዋጋ የሚያሰከፍል እንደሆነ የተረዱ ወጣት ታጋዬች ዋጋ እየከፈሉ እናዳለ በውል መረዳትና አንዳሰፈላጊነቱም ከያለንበት እንዳወጣጣችን ወደህገር በመመለሰ የሰላሙን ትግል በመቀላቀል በሐገር መሬት ላይ አሰፈላጊውን ዋጋ ለመክፈል የቆረጥን መሆን እንጂ በሻአቢያ ብብት ሰር ለመውደቅ መዘጋጀት መፍትሄ አይሆንም”። ከሁሉ በላይ የሰላሙ ትግል ሙሉ የሕዘብ ዽጋፍ ያለው ሲሆን ጦርነት ግን እንኳን እንደኛ ያለ ድሃ አገር ቀርቶ ዛሬ ባለማቀፍ ደረጃ ተደጋፊነት የለውም።

 

2ኛ)  ሻአቢያ ሲጀመርም፤ አሰካሁኖም ደቂቃ ደረሰ ለኢትዬጲያ መፈረሰ እንጂ፤ ግንባታ ሰርቶ አያውቅም ሊሰራም አይችልም።  ባገር ውሰጥ እየተካሄደ ያለውን የሰላም ትግል ባገር ውሰጥ ያሉት የመንግሰት አካላትም ሆኑ በሚሊቴሪው ክፍል፤ የሚገኙ አካላት ፖሊሱንም ጨምሮ በየቀኑ እየተከታተሉና፤ የወያኔ ግፍ አገዛዝ ምን ያኸል ሰርአተ አልበኛ እንደሆነ  እየተገነዘቡና ሊቆጣጠሩት ከሚችሉት በላይ እንደሆነና የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በሰተቀር ይኸንኑ የሰላም ትግል እንደሚቀላቀሉ በተለያየ ሁኔታ ምልክቶች እየታየ እንደሆነ በማሰተዋል መመልከት አሰፈላጊ ነው። ለምሳሌ በቅርቡ አገር ኮብልለው የወጡት ቱባ ቱባ የመንግሰት ባለሰልጣናትና የጦር ኦፊሻልሰ መመልከት አሰፈላጊ ነው።  ያኮበኮቡትን  አግዚአብሔር ይቁጠረው። ይኸ ሁሉ የሰላሙ ትግል ውጤት እንጂ ሻአቢያ በሰጠው ድጋፍ የተገኝ ውጤት እንዳልሆነ መረዳት በጣም አሰፈላጊ ነው።

 

3ኛ)  ወያኔ በሰላሙ ትግል በከፍተኛ ደረጃ ተዳክሟል። ለዚህ መረጃዎቹ መንግሰትነኝ ተብዬው አንዴ የሰላማዊ ሰልፍ ፍቃድ መሰጠትና ትርጉም በማይሰጥ ምክነያቶች መልሦ መከልከልና፤ ቀን ማራዘም ከብዙው በጥቂቱ ናቸው። ሌላውና ሊሰመርበት የሚያሰፈለገው ነጥብ ወጣቶቹ የሰላም መሪዎች በየጊዜው ከአንደበታቸው የሚሰማው የቆራጥነት አቆም አገራችን ምን አይነት ብርቅና ድንቅዬ ቆራጥ የሰላም ታጋዬች እንዳሏትና ምንም እንኳን የድሉ ጊዜ ቢረዝም ኢትዬጲያ  በቆራጥ የሰላም ታጋይ መሪዎቾ ተሰፋዋ የለመለመ እነደሆነ ያረጋግጣል። በ ሺ፤ የሚቆጠሩ ተከታዬችም እያፈሩ እንደሆነ በመረዳት ይኸንን የሰላም ትግል መደገፍና የሰላም መሪዎችን ማበረታታት እጅግ ጠቃሚና ወቅታዊ ነው እላለሁ።

 

ኢትዮጲያ’’’’’’’በሰላም ‘’’’’’’’’ታጋዮች’’’’’’’’ቆራጥ’’’’’’’አመራር’’’’’’’ድል’’’’’’ትቅዳጃለች ! !

 

በቸር ይግጠመን ፤   Saturday, September-21-13

 

Eriteria

የሰልፉ ዝግጅት ተጠናክሮ ቀጥሏል : Tomorrow at Meskel Square


የ ኢትዮጵያውያን ማህበረስብ በቤልጅግ በአምስተርዳም ከተማ ሕዝባዊ ስበስባ ጠራ

የአንድነት ፓርቲ ቀጣይ እጩ ሊቃነመናብርት ተለይተው ታወቁ

$
0
0
 ከግራ ወደ ቀኝ - ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው፣  አቶ ተክሌ በቀለ ፣ አቶ ግርማ ሰይፉ

ከግራ ወደ ቀኝ – ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው፣ አቶ ተክሌ በቀለ ፣ አቶ ግርማ ሰይፉ

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ፓርቲውን ለቀጣዮቹ 3አመታት በሊቀመንበርነት ለመምራት ከተወዳደሩት 5 ከፍተኛ አመራሮች ውስጥ 3ቱን ለመጨረሻው ዙር ውድድር እንዲያልፉ በዴሞክራሲያዊ መንገድ መርጧል፡፡ ፓርቲውን በሊቀመንበርነት ለመምራት የተወዳደሩት አቶ ትግስቱ አወሉ፣ ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው፣ አቶ ግርማ ሰይፉ፣ አቶ ሽመልስ ሀብቴ እና አቶ ተክሌ በቀለ ናቸው፡፡

ዛሬ የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባላት በሚስጥር ድምፅ አሰጣጥ ስርአት ባደረጉት ምርጫ 1ኛ.ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው 2ኛ.አቶ ተክሌ በቀለ 3ኛ.አቶ ግርማ ሰይፉ ለመጨረሻው ዙር ውድድር አልፈዋል፡፡

ለመጨረሻው ዙር ሳያልፉ የቀሩት አቶ ትግስቱ አወሉ እና አቶ ሽመልስ ሀብቴ ምርጫው ዴሞክራሲያዊ መሆኑን ተናግረው አንድነትን ለመምራት ከሚመረጠው ቀጣይ ሊቀመንበር ጋር ትግሉን ለማፋጠን እንደሚተጉ ለምክር ቤቱ ቃል ገብተዋል፡፡

1262887_516932691725003_368242465_o

የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባላት

- See more at: http://www.fnotenetsanet.com/?p=5718#sthash.mnRx1QXg.dpuf

 

ሳዑዲ አረቢያ ሪያድ ከተማን ከባድ ዝናብ መታት፤ መንገዶች በጎርፍ ተጥለቅልቀዋል

$
0
0

Heavy Rain
(ዘ-ሐበሻ) ኢትዮጵያውያን በስቃይ ላይ ያሉባት የሳዑዲ አረቢያዋ ሪያድ ከተማ ዛሬ ቅዳሜ ማታ በጣለ ከባድ ዝናብ የተነሳ ከተማዋ በጎርፍ ተጥለቀለቀች፣ መንገዶች በጎርፍ ተዘግተው በሥራ ላይ እና በ እለት ተለት ተግባር ላይ ችግር እንደፈጠረ አረብ ኒውስ የተባለው የዜና ወኪል አስታወቀ። የአረብ ኒውስን ጠቅሶ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢ እንደጠቆመው በነገው ዕለት እሁድ በሳዑዲ አረቢያ ትምህርት ቤቶች እና አንዳንድ የመንግስት መሥሪያ ቤቶች ዝግ ሆነው ይውላሉ።

በሪያድ ከተማ የጣለው ከባድ ዝናብ በመኪኖች ላይም ጉዳት ያደረሰ መሆኑን የዘገበው የአረብ ኒውስ በተለይ ሩዳህ፣ ናሲም እና ናጂም በተባሉ የሪያድ አካባቢዎች በጎርፍ ተመተው መንገዶች በውሃ ተጥለቅለቀዋል።

ይህ ከባድ ዝናብ በከተማዋ የመብራት አገልግሎት ላይም ችግር እንደፈጠረ የዘገበው አረብ ኒውስ መኪናዎች በጎርፍ እንደተወሰዱ በአንዳንድ ሰዎች ላይም ጉዳት መድረሱን ዘግቧል።

በሳዑዲ አረቢያ ከ35ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገራቸው ለመመለስ በፖሊስ እጅ ያሉ ሲሆን እነዚህ ወገኖች በቤት ጥበት ሳቢያ በውጭ እንዲያድሩ በመደረጉ ዝናብ ሲደብደባቸው እንደነበር መግለጻቸው ይታወሳል። ኢትዮጵያውያኑ አሁንም በሳዑዲ አረቢያ በከፍተኛ ችግር ላይ ናቸው።

ሳዑዲ አረቢያ በዝናብ እና በጎርፍ ከተመታች በኋላ ያሉ ፎቶዎች

$
0
0

ተማጽኖ ለጠ/ሚ ኃይለማሪያም: ሳዉዲን በተመለከተ (ግርማ ጌታቸዉ ካሳ)

$
0
0

ግርማ ጌታቸዉ ካሳ
(muziky68@yahoo.com)

ኖቬምበር 16 2013 ዓ.ም
MESSAGEአይኖቼ በደም ቀሉ። ልቤ ተሰበረ። ከሳዉዲ አረቢያ፣ ከባህር ማዶ፣ የወገኖቼ  ጩኸትና ሮሮ፣  ከጣራዬ በታች የመነጨ ይመስል፣ በጆሮዬ በቅርበት ያቃጭላል። በርግጥ እንደ አገር፣ እንደ ሕዝብ ፣ እንደ ኢትዮጵያዊ መዋረዳችንን አየሁ። በተለይም ደግሞ በአሁኗ ሰዓት፣ እንደ ወገን ምንም ማድረግ ባለመቻሌ ዉስጤ ደበነ። የማድርገዉን ሳጣ መሬት ተንበረከኩ። አይኖቼን ወደ ላይ አንስቼ፣ እጆቼን ዘረጋሁ። «ሄሮድስ ሊገድልህ ፈልጎ በነበረ ጊዜ፣  በልጅነትህ ከእናትህና እናታችን ቅድስት ማሪያም እንዲሁም ቅዱስ ዮሴፍ ጋር ተሰደሃል። የስደትን ኑሮና መከራ ምን ማለት እንደሆነ ታውቃለህ። አንተ መድሃኔአለም ኢየሱስ ክርስቶስ፣  እባክህ እነዚህ ስደተኞች ወገኖቼን አስባቸው። አንተ ድረስላቸው» እያሉ ጮኽኩኝ።

ትላንትና በአገራቸው መከራ ሲያጋጥማቸው፣  የኢትዮጵያ ንጉስ ነበር  በክብርና  በሰላም፣ ኢትዮጵያ መጠለያ እንድትሆናቸው ያደረገዉ። ዛሬ ፣ እነርሱ በእዉቀታቸዉና ጭንቅላታቸው  ሳይሆን ፣ ከመሬት በታቸ ፈረንጆች ባገኙላቸው፣ ዘይት «ሃብታም» ሆኑና፣ አሸዋ ላይ ከመተኛት ዳኑና፣  ይኸዉ ኢትዮጵያዉያንን  እንደ እንስሳ እያሰሩ ሲገርፉ እያየናቸው ነዉ። በርግጥ ይህ እንደ ኢትዮጵያዊ አንገት የሚያስደፋ ነዉ። የኢሕአዴግ ደጋፊ እንሁን፣ የኢሕአዴግ ተቃዋሚ፣ እንደ ኢትዮጵያዊ ሁላችንም ተዋርደናል።

ይህ በኢትዮጵያዉያን ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት፣ በርግጥ፣ ያለ ምንም ማጋነን፣ በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት ከማወጅ ያነሰ ተደርጎ ሊቆጠር አይገባም።

በመሆኑም የኢትዮጵያ መንግስት ሳዉዲ አረቢያ ለፈጸመችው ግፍ፣  ኦፌሴላዊ ይቅርታ እስክትጠይቅና ግፍ ለፈጸመችባቸው ወገኖች ሙሉ ካሳ እስክትከፍል ድረስ፣ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ማቋረጥ ይኖርበታል። የሳዉዲ አምባሳደር፣ ዲፕሎማቶች በአስቸኳይ ከአዲስ አበባ መባረር ይኖርባቸዋል።

ያ ብቻ አይደለም። ኢትዮጵያዉያን ብቻ ሳይሆኑ በርካታ ቀለማቸው ጠቆር ያሉ አፍሪካዉያን ተመሳሳይ  እድል ገጥሟቸዋል። ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ለጥቁር ሕዝብ በሙሉ፣  ያላትን ንቀት ነዉ ሳዉዲ አረቢያ ያሳየችው። ሌሎች የአፍሪካ አገራትን በማስተባበር፣ በአፍሪካ ሕብረት ዘንድም፣ ጠንካራ አቋም እንዲወሰድ ማድረግ ያስፈልጋል። በዚህ ረገድ፣ መንግስት የራሱ በሆኑ ምክንያቶች ማቅማማት ካሳየ፣  ከሁሉም ማእዘናት ኢትዮጵያዉያን በመንግስት ላይ ግፊትና ጫና እንዲያደርጉ እጠይቃለሁ።

ወደ ሁለተኛዉ ነጥቤ ልመለስ። ሳዉዲ አረቢያን ማዉገዝ በራሱ በቂ አይደለም። ከማዘን፣ ከመናደድ፣ ከማዉገዘና ሰልፍ ከመዉጣት ያለፉ እርምጃዎችን ፣ እንደ ሕዝብ መዉሰድ ያለብን ይመስለኛል።

በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ወደ አገር ቤት ሊመለሱ ነዉ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጎናቸው ሊሰለፍ ይገባል። አረቦቹ እንደዚያ ቢያዋርዷቸውም ፣ ወገንና ሕዝብ ያላቸው መሆናቸውን ማሳየት ይኖርብናል። አገራቸው መመለሳቸው የተሻለ ነእንጂ የባሰ እንደማይሆን የሚያመላክት ተስፋ፣ በትንሹም ቢሆን ጭል ጭል ማለት ይኖርበታል።

በዚህ አጋጣሚ ለተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሃይለማሪያም  ደሳለኝና ጓዶቻቸው፣  ኢትዮጵያዊ፣ ወንድማዊና አክብሮት የተሞላበት ተማጽኖ ማቅረብ እፈልጋለሁ። ትልቅ ሃላፊነት አለባቸው። በአገራዊ ጉዳይ ላይ ህዝብን ማሰባሰብ ያስፈልጋል። ለአባይ ትኩረት እንደተሰጠዉ፣ በሳዉዲ የተጎሳቆሉ ወገኖቻችንን ለማቋቋም ከፍተኛ ገንዘብና ርብርብ ይጠይቃል። በዉጭ አገር የሚገኘው፣ የገንዘብ አቅም ያለዉ ኢትዮጵያዊ፣ አገር ቤት ያሉ ባለሃብቶች፣  ሁሉም የድርሻዉን መወጣት ይኖርበታል። አገር ቤት ካሉ ተቃዋሚዎች ጋር በጋራ በመነጋገር አንድ ጠንካራ፣ ገለልተኛ፣  የሳዉዲ ስደተኞች ኮሚሽን እንዲቋቋም እመክራለሁ። ይህ ኮሚሽን ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለበት መልኩ፣ በሕግ፣ በኢኮኖሚክስ፣ በሲሻል ዎርክ ባለሞያዎች፣ ከሃይማኖት አባቶች በተወከሉ ኢትዮጵያዉያን  በመሳሰሉት ተዋቅሮ፣ በቅርበት ከመንግስት ጋር እየሰራ፣ በስፋት የገንዘብ ማሰባሰብ እንቅስቃሴዎች በማድረግ፣  ስደተኞችንም የማቋቋም የሚሰራ ይሆናል። በአለም አቀፍ ፍርድ ቤቶች ስደተኞችን ወክሎ በሳዉዲ አረቢያ ላይ ክስ የሚመሰረትበትንም ሁኔታ ሊያመቻችም ይችላል።

ኢትዮጵያዉያን መጀመሪያውኑ ከአገር ለመሰደድ የሚሞክሩት እንዲሁ በባዶ አይደለም። የኑሮ ዉድነት፣ የኢኮኖሚ ችግር፣ የሰብአዊ መብት ረገጣ፣ የመልካም አስተዳደር እጦት የመሳሰሉ ናቸው ለስደት ሰዉን የዳረጉት።  መንግስት በዚህ ረገድ አዎንታዊና ስር ነቀል ለዉጦች ቢያደርግ፣  የታሰሩ የሕሊና እስረኞች ቢፈታ፣ ብሄራዊ እርቅ እንዲኖር፣ ቅንነት ያለበት ዉይይት፣ ቢያንስ ቢያንስ፣ አገር ቤት ካሉ ተቃዋሚዎች ጋር ቢያደርግ፣ የሕግ ስርዓቱ የመጨቆኛ ዱላ ሳይሆን ፍትህ የሚገኝበት ስርዓት ቢሆን፣ የአገራችን አየር የራቁትን የሚስብ እንጂ በቅርብ ያሉትን የሚያርቅ አይሆንም ነበር።

በዚህ አጋጣሚ፣  አገር ቤት ላሉ ተቃዋሚዎች ፣ የሳዉዲን ኢሰብዓዊ እርምጃዎች በማዉገዝ፣ ለጠሩት ሰላማዊ  ሰልፎች ያለኝን ታላቅ ድጋፍ እየገለጽኩ፣ አብሮ መስራት በሚቻልባቸዉ ጉዳዮዎች ዙሪያ፣ ከኢሕአዴግ ጋር ለመነጋገር ፍቃደኝነቱን እንዲያሳዩም እጠይቃለሁ። መቃወም መልካም ነዉ። ግን ከመቃወም አልፍዉ በአገር ጉዳይ ከገዢዉ ፓርቲ ጋር አብሮ መስራት ያስፈልጋል።

እሰከምቼ ነዉ አገር እያለን የምንሰደደው ? እስከመቼ ነዉ ምግብ እያለን የምንራበዉ ?  እስከመቼ ነዉ ክብር እያለን የምንዋረደው ? እስከመቼ ነዉ ወገን እያለን ብቸኞች የምንሆነዉ ? ሳዉዲዎች ዘይት አላቸው። እኛም እኮ ፍቅር አጥተን ነዉ እንጂ፣ ማንም የሚመኘው የተፈጥሮ ሃብት አለን። እንደ ምሳሌ ያሉንን በርካታ ወንዞች መጥቀስ ይበቃል። ደግሞም ማን ያወቃል ?  ዛሬ ሳዉዲዎች የተመጻደቁበት ዘይትም እኮ አገራችን ሊገኝ ይችላል። መቼ በስፋት ተፈልጎ ?

በሕዝብ ብዛት ከሳዉዲዎች ሶስት አራት እጥፍ ነን።  እጅግ በጣም በርካታ ምሁራን፣ ጠበብት፣ ሳይንቲስቶች አሉን። ሳዉዲዎቹ ሁሉንም ነገር የሚያሰሩት በነጮች ነዉ። እኛ ግን ለእኛዉ እንበቃለን። የጎደልን ፍቅር ብቻ ነዉ !!!!!

በነገራችን ላይ ፍቅር ሲኖረን፣ ይቅር ስንባባል፣ ፊታችንን ወደ ኢግዚአብሄር ስናዞር፣ ምድራችንንም አምላክ ይባርካታል። እንኳን ለኛ ለሌሎችም የምንተርፍ እንሆናለን።  እንግዲህ እግዚአብሄር  ፍቅሩን ይስጠን ! ጮሮ ያለው ይሰማ ፤ ልብ ያለው ያስተዉል።

(ይሄን ጽሁፍ ለአንባቢያ ከመበተኔ በፊት፣  የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እግር ኳስ ጨዋታን ተመለከትኩ። እርግጥ ነው ለአለም ዋንጫ አልበቃንም። ነገር ግን  ለተጨዋቾቻችን፣ ለአስለጣኙ ያለኝን ትልቅ አክብሮትና አድናቆት መግለጽ እፈልጋለሁ። እዚህ መድረሳቸው በራሱ ትልቅ ዉጤት ነዉ። ኮርቼባቸዋለሁ። በዚህ ጉዳይ ላይ ወደፊት በስፋት እመለስበታለሁ)

 

መንግስት መድረክ ዛሬ በአ.አ በሳዑዲ አረቢያ ኢምባሲ የጠራውን ሰልፍ ከለከለ (የክልከላውን ደብዳቤውን ይዘናል)

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ባለፈው አርብ በሳዑዲ አረቢያ በወገኖቻቸው ላይ እየደረሰ ያለው ስቃይ ያመማቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ቢገኙም የመንግስት ፌደራል ፖሊሶች በሳዑዲ አረቢያ ላይ ተቃውሞ ሊያሰሙ የወጡትን ኢትዮጵያውያን በቆመጥ በመምታት ሰልፉን በመበተን በርካታ ሰዎችን ማሰራቸው ይታወሳል። ኢትዮጵያውያን “እየመራን ያለው የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ነው ወይ?” እስኪሉ ድረስ በቅርቡ ከሳዑዲ የተመለሰች ወጣት ሳትቀር ሁለተኛውን ዱላ ከራሷ መንግስት ቀምሳለች። ይህ የመንግስት ለሳዑዲ ጥብቅና መቆም ቀጥሎ በዛሬው እለት መድረክ በሳዑዲ አረቢያ ኢምባሲ ፊት ለፊት የጠራውን የተቃውሞ ሰልፍ በደብዳቤ መከልከሉን ድርጅቱ ለዘ-ሐበሻ በላከው መረጃ አስታውቋል።
መንግስት በሳዑዲ አረቢያ ኢምባሲ ፊት ለፊት የተጠራውን ሰልፍ የከለከልኩት በቂ ጥበቃ ስለሌለኝ ነው በሚል ነው። ደብዳቤው ይኸው”-
medrek

ከሳዑዲ አረቢያ መንግስት እየበደለን ያለው የኢትዮጵያ መንግስት ነው – የሚለውን የነብዩ ሲራክን ትንታኔ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

በጅዳ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ደጃፍ “ከዛሬ ጀምሮ አገልግሎት አቁመናል”የሚል ፖስተር ተለጠፈ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በሳዑዲ አረቢያ ከ35 ሺህ የማያንሱ ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገራቸው ለመመለስ እየተጠባበቁ ባለበት ወቅት የኢትዮጵያ ኢምባሲም ችግር ያለባችሁን እንረዳለን እያለ ስልኮቹን ሲለጣጥፍ ቆይቶ በዛሬው እለት በጅዳ የቆንስላ ጽህፈት ቤቱ ደጃፍ ላይ “ከህዳር 8 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ ቆንስላ ጽ/ቤቱ ላልተወሰነ ጊዜ አገልግሎት የማይሰጥ መሆኑን እንገልጻለን” የሚል ደብዳቤ ለጥፏል። ዘ-ሐበሻ ይህ ፖስተር እንደደረሳት ወደ ኢምባሲው በመደወል ጉዳዩን ለመጠይቅ ብትሞክርም ስልክ የሚያነሳ የለም። በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያውያን ስቃይ አሁንም እንዳየለ ነው። አሁንም ማብራሪያውን ለማግኘት እንሞክራለን።
jida embassay


ዋ! አንቺ የሳውዲ ምድር !.ዋ! አንቺ የሳውዲ ምድር

ሀገራዊ ውርደት እንዲያበቃ ወያኔን ማስወገድ- በዳዊት መላኩ (ከጀርመን)

$
0
0

በዳዊት መላኩ (ከጀርመን)
tplf-rotten-apple-245x300ኢትዮጵያውያን የወያኔ ባናዳዎች ባፈሙዝ ሀይል ስልጣን ላይ ከወጡበት እለት አንስቶ በርካቶች ለስደት፤ለእስራት፤ለሞት እና ለእንግልት ተዳርገዋል፡፡የሰሃራን በረሃ አቋርጠው ለማለፍ ሲሞክሩ የበረሃ እራት ሁነዋል፡፡ሌሎች ደግሞ ኩላሊታቸው ሳይቀር እየተዘረፉ ለከፋ አካላዊ እና አእምፘዊ ጉዳት ተዳርገዋል፡፡በባህር ሲያቋርጡ የተሳፈሩበት ጀልባ በሞገድ እየተመታ በብዙ ሺ የሚቆጠሩት ለዓሳ እራት ሁነዋል፡፡በታንዛኒያ እና በኡጋንዳ ሲያልፉ በኮንቴነር ታፍነው የሞቱትን ቤት ያቁጠራቸው፡፡ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነው አውሮፕላን የመን ውስጥ ተጠልፎ በውስጡ የነበሩት የአየር መንገዱ ሰራተኞች እና ተሳፋሪዎች ባሰቃቂ ሁኔታ ሕይወታቸው አልፏል፡፡

ይህ ሁሉ ህይወት እንደቅጠል ሲረግፍ የወያኔ ባለስልጣኞች አንድም ቀን ብለው የተጎዱ ቤተሰቦችን አጽናንተው አሰከሬናቸው በክብር እንዲያርፍ አላደረጉም፡፡በሰው ሰራሽ አደጋ ለሞቱትም ጥፋተኞችን ለፍርድ ለመቅረብ ተንቀሳቅሰው አያውቁም፡፡ዲፕሎማሲያዊ በሆነ መንገድም ዳግም ስህተቶች እንዳይፈጸሙ ስምምነቶችን ተፈራርመው ያውቁም፡፡በየሀገራቱ የሰገሰጉዋቸው ዲፕሎማት ተብየዎችም ቤተሰባቸውን እንዴት አንደላቀው እንደሚያኖሩ ፤ከነማን ጋር የንግድ ሽርክና እንደሚፈራረሙ እንጂ በስደት ለሚንገላታው ዜጋቸው መብት ተከራክረው ፡ የሀገሪቱን ጥቅም ለማስጠቀም አንዳች ስራ ሰርተው አያውቁም፡፡

ዲፒሎማቶች ከሙያ ብቃት ጀምሮ ህዝባዊ ወገንተኝነትም ስለሚጎድላቸው የፓርቲውን ህልውና ለማስጠበቅ ካልሆነ በስተቀር ለህዝብ የሚጠቅም ስራ ይሰራሉ ብሎ መገመት ያዳግታል፡፡የወያኔ ዲፕሎማቶች በውጪ የሚኖሩት ኢትዮጵያውያን እርስ በርስ እንዲከፋፈሉ ከላይ በሚሰጣቸው መመሪያ መሰረት ብዙ የመከፋፈል ስራዎችን ሲሰሩ እነደቆዩ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ዛሬ በ40/60 የኮንደሚኒየም እና በዓባይ ግድብ ግንባታ ሰበብ በውጪ ከሚኖሩት ኢትዮጵያውያን ዶላር ለመሰብሰብ ደፋ ቀና የሚሉት ዲፕሎማቶች ለይስሙላ ያክል እንኳን አንድም ቃል መተንፈስ አልቻሉም፡፡
በወያኔዎች ዘንድ ብሔራዊ የሀዘን ቀን የሚታወጀው እና ህዝቡ በግዳጅ እየወጣ የመንግስት አገልግሎች መስጫ ድርጅቶች ሳይቀሩ ለሁለት ሳምንተ ያልክ ተዘግተው ስራቸው ሀዘን ብቻ እንዲሆን መመሪያ የሚተላለፈው የስልጣን እና የጥቅም አጋራቸው ሲሞት እንጂ ሌላው ተራ ዜጋ እማ ሞቱን እንኩዋን የሚዘግበለት የሀገሩ የመገኛኛ ብዙሀን የለውም፡፡ ግብር የሚከፍልበት ቴሌቭዥን እንዲህ ያሉ ዜናዎችን ለህዝቡ እንዳያቀርብ እነሽመልስ ከማል አፉን ጥርቅም አድርገው ይዘውታል፡፡የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሜዲያዎች የዘገቡትን እውነት በወያኔ ቁጥጥር ስር የሚገኘው የሀገሪቱ ቴሌቭዥን የቁጥር ጨዋታ ያዟል፡፡የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተብየው ዶ/ር ቴወድሮስ አድሀኖም ችግሩ ተጋኖ ቀረበ ነው ሲሉ ተዘባበተውብናል፡፡

ሀገሪቱን እመራለሁ ብሎ የተቀመጠ ሀይል እንዴት እንዲህ ሀገራዊ ውርደት ሊያከናነብ ቻለ? መልሱ ቀላል ነው፡፡ መጀመሪያም ወያኔዎች ከሆዳቸው ባለፈ ሀገር እና ህዝብ ብሎ ነገር አይገባቸውም፡፡አሰራ ሰባት ዓመት ተዋጋንለት የሚሉትም የስልጣን ጥማቸውን ለማርካት እንጂ ለህዝብ የሚጠቅም አንዳች ሀገራዊ አጀንዳ ኑፘቸው አደለም፡፡የወያኔዎች ዋነኛ መገለጫቸው እና ግባቸው ሀገራዊ ውርደት ማሰፈን ነው፡፡ ይሕን ደግሞ ባለፉት አመታት ሁላችንም በደንብ የምናውቀው ነው፡፡ለግራዚያኔ ሀውልት ማቆምን የተቃወሙ ህዝቦችን አስረዋል፡፡ሰላማዊ ሰልፉን በትነዋል፡፡የሀገሪቱን ቅርስ እና ታሪክ በማወደም ታረክ- አልቫ አድርገዋል፡፡የሀገሪቱን ብሄራዊ ጥቅም በተደጋጋሚ ለባእዳን አሳልፎው ሰጥተዋል፡፡አርሶ አደሮችን እያፈናቀሉ ለም መሬታችንን በርካሽ ዋጋ ሲቸበችቡት ቆይተዋል፡፡ዳር ድንበራችንን ለሱዳን አሳልፎው ሰጥተዋል፡፡በሰላም ማሰከበር ስም ወታደሮች በሶማሊያ መንገድ አስክሬናቸው እንዲበተን አድረገዋል፡፡ዜጎች እምነታቸውን በነፃነት እንዳያመልኩ አድርገዋል፡፡ሌላው እና መሰረታዊው ነገር ራሱ ወያኔ ዜጎችን አደህይቶ፤አደንቁሮ፤አዋርዶ መግዛት የአስተዳደር ስትራቴጅው ዋነኛ ማጠንጠኛው ነው፡፡

በሰሞኑ ያየነውም በአረብ ሀገራት የያኔን አንባገነን ስርዓት ሸሽተው የተሰደዱ ዜጎች በሳዉዲ ወሮበላ ፖሊሶች እንደ በግ ሲታረዱ ሰማያዊ ፓርቲ ሕዝቡን በማስተባበር ሐገራዊ ውርደት እንዲያቆም፤በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ግድያ ፤አሰገድዶ መድፈር እና እንግልት እንዲቆም በሰላማዊ መንገድ ድምፃቸውን ለማሰማት አደባባይ የወጡ የወገን ተቆርቋሪ ዜጎችን በፌዴራል ፖሊስ ማስቀጥቀጥ፤የፓርቲውን አመራሮች ማሰር የወያኔ ብሄራዊ ውርደት ለፍተኛው ማሳያ ነው፡፡ሰማያዊ ፓርቲ የሰራው መንግስት ሊሰራው የሚገባውን የዜጎችን ደህንነት የማስጠበቅ ስራ ነው፡፡
ምን እናድርግ?

የእነዚህ ሁሉ ችግሮች ምንጭ ወያኔ ነው!ስለዚህ መፍትሄውም የችግሩን ምንጪ ከመሰረቱ ማድረቅ ነው፡፡ወያኔን ለማሰወገድ ደግሞ የሁሉንም ርብርብ የሚጠይቅ ተግባር ነው፡፡ በሀገር ውስጥም ይሁን በውጪ የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ሀዘናችንን አቁመን በልበ ሙሉነት ለዚህ ሀገራዊ ውርደት የዳረገንን አንባገነናዊ ስርዓት ማስወገድ ይኖርብናል፡፡ዛሬ በሳውዲ ማጎሪያ ክምፕ ያለኸውም ሀገርህ ብትገባም ሊያስኖርህ የሚችል መንግስት አደለም ሀገሪቱን የሚመራት፡፡ያው ከመውጣትክ በፊት የምታውቀው በአንድ ዘር የበላይነት የተገነባው አብዛኛው ጾም የሚያድርበት ተቂቶች በብዙሀኑ ደም የሚንደላቀቁበት ነው፡፡ገብተህ ድምጽህን የምታሰማበት ምንም መንገድ የለህም፡፡ምናልባትም የሚጠብቅህ ሰበብ ተፈልጎ ቃሊቲ መወርወር ሊሆንም ይችላል፡፡ስለዚህ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ የነፃነት ታጋዮችን በመቀላቀል ነፃነታችንን፤የተዋረደው ክብራችንን ፤በአለም አደባባይ የጎደፈው ስማችንን በጋራ ማደስ ይኖርብናል፡፡እግዚያብሄር አምላክ የሞቱት እህት እና ወንዶሞቻችን ነፍስ በገነት ያሳርፍልን፡፡የጠላቶቻችንን ልብ ያራራልን፡፡

ሞት ረግጠው ለሚገዙን አንባገንን መሪዎች !ድል የነፃነትን ብርሀን ለመፈንጠቅ በየበረሀው ለምትንከራተቱ የቁርጥ ቀን ልጆች!

 

 

ወደአይምሮአችን እንመለስ!ቆም ብለንም እናስብ! –በአበራ ሽፈራው /ጀርመን/

$
0
0

 በአበራ ሽፈራ /ጀርመን/

በአረቡ ዓለም ከፍተኛ ተሰሚነትና የመላው ዓለም አይን ሁሉ በተለየ መልኩ በሚያያት ሳውዲአረቢያ በወገኖቻችን ላይ የደረሰው አሰቃቂ ግፍና መከራ ለትውልድ የማይረሳ ክፉ ታሪክ ጥሎብናል ፤ ዛሬም ሰቆቃው ቀጥሏል፡፡

ድረሱልን የሚለው የወንድሞቻችንና በተለይም የእህቶቻችን ጩኸት በእየቀኑ ከዚህች የሳውዲ አረቢያ ከተማዎች ለብዙሃን መገናኛዎች እየጎረፈ ይገናል። አልታደልንምና የእኛዎቹ ጉልበተኛ መሪዎች ይህንን እኩይ የሳውዲ አረቢያን ተግባር ከመኮነን ይልቅ በአገር ውስጥ ሌላ ተጨማሪ  ሃዘንን የሚፈጥሩ የቃላት፣ የዱላንና የእስርን ጉዳይ በግልና በጅምላ ተያይዞታል ።

ሳውዲዎች እየጎዱንም ያሉት በብሄራችን አይደለም፣ በቋንቋችንም አይደለም፣ በኢትዮጵያዊነታችን ብቻ ነው ። ዛሬ ወደአይምሮአችን እንመለስ፤ ለማሰብ እንነሳ፤ በቋንቋችንና በብሄራችን እየከፋፈለ  በግልና በቡድን የሚያጠቃን ህወሃት ብቻ ነው፤ አሁንም ትንሽ ቆም ብለን እናስብ።

የኢትዮጵያ ሳይሆን የጥቂት ጎጠኛና ጉልበተኛ ቡድን ብዝበዛናንና ጭቆናን ለመጠበቅ ሲባል በኢትዮጵያ ህዝብ ደምና ላብ ከሽጉጥ እስከ ተዋጊ አይሮፕላን የታጠቀው ወታደራዊ ሃይልና የፌደራል ፖሊስ በሚል የሚጠራው ኃይል ከቆመጥ እስከ ካራቴ ሲያልፍም በጥይት በራሱ ወገን ላይ ድብደባንና ግድያን ሲያደርስ መመልከት በአገሩ ያልተከበረ ህዝብ እንዴት በውጭዎች ይከበራል? እጣ ፋንታችንም በአገራችን ውርደት፤በውጭ ሃገራትም ውርደት ሆኗል።

ከሳውዲዎች ጋር የሰው ዝውውር/Human Trafficking/ና የንግድ ትሥሥርን የፈጠሩት ህወሃቶች በወኪላቸው ሺህ መሐመድ አላሙዲን እና በሌሎች የህወሃት የንግድ ሰዎችና በኢትዮጵያውያን ስም በአረቡ አገራት ኢንባሲዎችና ቆንስላዎች በተቀመጡ የህወሓት ወኪሎች አማካኝነት የሰውን ዝውውርን በንግድ ትርፍነት ይዘው የሚጠቀሙበት መሆኑና ለዚህም በማስረጃነት በዚሁ የድለላ ሥራ የተሰማሩት ብዙዎቹ የህወሃት ሰዎች መሆናቸውና በሃዋላ መልክ በእነዚሁ ጭቁን እህቶቻችን የሚላኩትንም ገንዘቦች ዝውውር የሚፈጸመው በነዚሁ ሰዎች መሆኑ ፤ በቅርቡም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ እህቶቻችንን በተመሳሳይ መልክ ለመላክ ተዘጋጅተው የነበሩ መሆኑ፤ ከዚህም በላይ ደግሞ በኢትዮጵያ ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችንና ልዩ ልዩ የንግድ ተቋማትን የያዙት የሳውዲ ሰዎች ዛሬ ህወሃትን ባይተማመኑና በህወሃት አንባገነንዊ ሥርዓት ሥር መውደቃችንን ባያውቁ ኖሮ እንዲህ ባልተጠቃን ነበር ።

እነዚህ ሃገራችንንና ህዝባችንን የሚበዘብዙና የሚያዋርዱ ኃይሎች ይባስ ብለው በአገራችን ተቃውሞ እንዳይደረግ ለመከላከል መዘጋጀታቸውና ህዝቡን በዱላ መደብደባቸው፣ ማሰራቸውና መቀጥቀታቸው ቢያሳዝንም ዛሬ ወደአይምሮአችን እንድንመለስና ህወሃት ከዚህ በላይ ምን እስኪያደርገን እንደምንጠብቅ እንድናስብ ይጠበቅብናል።ግልጽ የአገራችንና የህዝባችን ጠላቶች ህወሓቶች መሆናቸውን ያለፉት 22 ዓመታት የህወሃት ድርጊቶች ምስክሮቻችን ናቸው ።

ለእውነቱ ከሆነ በዓለም ሁሉ ሁሌም በተቃውሞ ሰልፍ እንታወቃለን። አሁን ያሉትን ችግሮች ለመቅረፍና መፍትሄ ለማምጣት የሚደረገው ሰልፍ ተገቢና መቀጠል እንዳለበትና ሰልፎቹም ግቦቻቸውን ሊመቱ በሚችሉበት ሁኔታ በተጠና መልኩ መቀጠል እንዳለባቸው ግን አምናለሁ። አዋጩ መንገድ ግን ለዘለቄታው ማሰብና ተግባራዊ እንቅስቃሴን በአገር ውስጥም ሆነ በውጭው አለም መፍጠርና ለተግባራዊነቱ ለመነሳት መመካከር ይመስለኛል፤ ደግሞም ነው ብዮም አምናለሁ፤ የተጀመሩም ካሉ እንዲበረታቱ ድጋፍ ማድረግ ይኖርብናል ።

በህወሓቶች መሰሪ ተንኮል መለያየትን በህዝቦች መካከል በመፍጠር በፍጹም አምባገነናዊ ሥርዓት እንድንተዳደር የተደረግንበትን የህወሃቶችን እኩይ ተግባርን አሁንም ለመቀልበስ  እንድንችል ወደአይምሮአችን እንመለስ።

 

የሃገሬ ወጣቶች ፣ የተማራችሁ ኢትዮጵያውያን፣ ገበሬው፣ ሰራተኛው፣የሃይማኖት ተቋማትም ሁሉ ለእውነት ልትነሱና ፍትህን ልትናገሩ፣ ሁላችን እውነትን ልንጋፈጥና ለእውነት መስዋዕት ልንሆን፤ በወደፊትም የአገራችን እጣፋንታ ላይ ልንነሳና ይገባናል።

የኢትዮጵያ ወታደሮችና ፖሊሶች እየተባላችሁ ለጥቂት የህወሃት በዝባዥና ዘረና ኋይሎች በመሳሪያነት የምታገለግሉ የኢትዮጵያ ልጆች ለህዝባችሁ ወገንተኝነታችሁን ለማሳየት ወደአይምሮአችሁ ተመለሱ ፤ ተገቢውን ተቃውሞ በማሰማት ባለታሪክ እንድትሆኑና ለዚህም መልስ ለመስጠት ከወገኖቻችሁ ጋር እንድታብሩ እመክራለሁ። ካልሆነም ግን ጊዜ ሊፋረዳችሁ ከፊታችን ቀርቧል።

በልዩ ልዩ የኢሕአዴግ ፓርቲዎች ውስጥ ሆናችሁ በህወሃት በዝባዦች ውክልናን ተቀብላችሁ፤ህዝቡን ለመጨቆን እንደመሳሪያነት የምታገለግሉና የምታሰቃዩ፤ ወደአይምሮአችሁ ተመለሱ ወደህዝቡም ትግል ተቀላቀሉ፤ የሰውም የአምላክም ፍርድ ከፊታችሁ መጥቷል አመናችሁም ጠላችሁም የህዝቡ እንባ ለፍርድ ወጥቷል።

በልዩ ልዩ ሃገራት በዲፕሎማሲው ዘርፍ ኢትዮጵያን ወክላችሁ በስራላይ ያላችሁና ይህንን የኢትዮያውያንን መከራ አይናችሁ እያየ እንዳላየ የምትሆኑ ሁሉ አሁን ከኢትዮጵያውያን ትግል ጎን ለመሰለፍና ለመወሰን ወደአይምሮአችሁ ተመለሱ። ብዙዎቻችሁ የህዝባችንን፣ የአገራችንንና የወገኖቻችንን ጥቅምና ተስፋዎች ለህወሃት አሳልፋችሁ በመስጠት ሁሌም ህዝብን እንደበደላችሁ የሚሰማችሁ ፤ የህዝቡ መከራ የሚያንቀጠቅጣችሁ ሁሉ ዛሬ ወስኑ፣ አቅዱ፣ ተግብሩ፤ በቃ! ከህወሃት እኩይ ተግባር ተባባሪነት እራሳችሁን እግልሉ ። ሰውም አምላክም ይቅር ይላችኋል፤ ለዚህም የኢትዮጵያ ህዝብ ልብ ለይቅርታ የተዘጋጀ ነውና ቁረጡ። ቸር ይግጠመን።

 

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!

 

aberashiferaw.wordpress.com

pen

ሻማ ማብራት ምሽት ስነ-ሥርአት በሚኒሶታ

Hiber Radio: በሳውዲ ሪያድ ስድስት ኢትዮጵያውያን በጥይት ተገደሉ፤ አንዱ በመኪና ገጩት

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ ዕሁድ  ህዳር 8 ቀን 2006 ፕሮግራም

<<…ሳውዲ በወገኖቻችን ላይ የፈጸመችውን ግፍ በመቃወም ነው ሰልፍ የወጣነው ሰልፉ እንዳይደረግ ቢሮ አካባቢ አንዳንድ አመራሮችነ ሲያግቱ ቦሌ ቶሎ ሄድኩ እዛ ስንደረስ ሕገ ወጥ ሰልፍ ብለው ደብድበውና…በእርምጃው በጣም አዝኜያለሁ…>> አቶ ወረታው ዋሴ የሰማያዊ ፓርቲ የፋይናንስ ሀላፊ ሳውዲን ለመቃወም ወጥተው ስለደረሰባቸው እስርና ድብደባ ከገለጹልን የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

 <<…የሳውዲ መከላካያዎች ይዘውን ለመሄድ መጡ ኤምባሲ ካልመጣ አንሄድም አልናቸው ።አንዱን ኢትዮጵአዊ በመኪና ገጩተት ቆይተው ደግም ስድስት በጥይት ገደሉ።የኤምባሲው ተወከኢ ጋር ደውዬ አንስቶ ስልኩን ዘገአ ቆይቶ ሞባይሉን አጠፋው…>>

ሳሮን ጸጋዬ ባለፈው አርብ በኢትዮጵያውያን ላይ ስለተወሰደው የግድያ እርምጃ ለህብር ሲገልጽ( ቃለ መጠይቁን አዳምጡት)

<<…ተፋፍገን በአንድ ሰርግ በሚደግሱበት ቦታ ሶስት ሺህ ሴቶች ሆነን ነው ያለነው። ድምጻችን መዘጋት ጀምሯል ።  በቂ መጸዳጃ የለም ውሃ ይዘጉብናል፣ኤምባሲው ምንም አላደረገልንም።ድምጻችንን አሰሙልን…>>  ከጅዳ  ማቆያ ኢትዮጵያዊቷ ስለ ችግሯ ከገለጸችልን

<… በአገር ቤት በሳውዲ የሚደርሰውን ግፍ ለመቃወም ዜጎቻችን በአገራቸው ወጥተው በመደብደባቸው እዚህም በችግር ውስጥ ያሉትም እኔም በጣም ሀዘንና ሐፍረት ነው የተሰማን…>>

ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ከሰጠን አስተያየት የተወሰደ

የምዕራባውያን በኢትዮጵያ ያለውን እውነታ አውቆ ዝምታን መምረጥ በመረጃ ሲገለጥ…>>

ሌሎችም ዝግጅቶች

ዜናዎቻችን

በሳውዲ ሪያድ ስድስት ኢትዮጵያውያን በጥይት ተገደሉ

አንዱ በመኪና ገጩት

ሀያ ሺህ ኢትዮጵአውያን በአንድ ስፍራ ተጉረዋል

የተላላፊ በሽታ ስጋት አለ

 በሳውዲ የጎርፍ አደጋ ስምንት ሰዎችን ገደለ

ኢትዮጵያውያን በወገኖቻቸው ለተፈጸመው ግፍ የፈጣሪ ምላሽ እንደሆነ የሚያስቡ አሉ

የኢትዮጵያ ጦር በሶማሊያ ከአፍሪካ ህብረት ሀይል ጋር ልጣመር ያለው በፋይናንስ ችግር መሆኑ ተገለጸ

አልሸባብ ስማርት ፎንን አገደ

<<..መንግስት ለሳውዲ አግዞ ለሰልፍ የወጡትን በመደብደቡ አገርም መንግስትም የለንም…>> አብርሃ ደስታ ከመቀሌ

የሰውዲ ፖሊስ ለምርመራ በሚል ኢት ጵአ አንን ማሰር ቀጥሏል

ከኢትዮጵያ ተነስተው አውስትራሊያ ለመግባት ያሰቡ ኤርትራውያን ኢንዶኔዢያ ላይ ተጣሉ

አሰልጣኝ ሰውነት ከናይጄሪያ ጋር ለደረሰው ስንፈት ዳኛውን ተጠያቂ አደረጉ

 ሌሎችም ዜናዎች አሉን

 

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live