Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

Health: የደም ቧንቧ መስፋት በሽታ –መንስኤው፤ መፍትሄውና መከላከያው

$
0
0

 

ሁለት አይነት የደም ቧንቧዎች አሉ፡፡ ኦክስጅን የተሸከሙና ደምን ከልብ ወደ ሌላው የሰውነት ክፍል የሚወስዱ የደም ቧንቧዎች አርተሪ ይባላሉ፡፡ ጥቅም ላይ የዋለውን ደም ከሌላው የሰውነት ክፍል ወደ ልብ የሚመልሱ ቧንቧዎች ደግሞ ቬን ይባላሉ፡፡ 

ደም መልሶችም ሆኑ ደም ቅዳ ቧንቧዎች በሁሉም የሰውነታችን ክፍሎች የሚገኙ ናቸው፡፡ ደም ቧንቧን እንደ አንድ ፕላስቲክ ቲዩብ ወስደን መሀል ላይ ቆርጠን ብናየው ግድግዳውን ማየት እንችላለን፡፡ ደም ቅዳ ቧንቧ ግድግዳው ወፍራም ነው፡፡ የውስጠኛው፣ መካከለኛውና የላይኛው ተብለው የሚከፋፈሉ ሶስት ክፍሎች አሉት፡፡ በሌላም በኩል ደም መልስ ቧንቧዎች ግድግዳቸው ቀጭን ነው፡፡ ለዚህ ይመስላል፣ ከደም ቧንቧ መስፋት ጋር ለተያያዙ የጤና ችግሮች የተጋለጡ የሚሆኑት፡፡

ዛሬ በዚህ የደም ቧንቧ መስፋት ችግር ዙሪያ ለአንባቢዎቻችን ሰፋ ያለ መረጃ ለመስጠት ፈልገን አንድ የቀዶ ጥገና ህክምና ስፔሺያሊስትን ማብራሪያ ጠይቀናቸው ነበር፡፡ እንዲያነቡት ጋብዘናል፡፡

blood

ጥያቄ፡የደም ቧንቧ መስፋት ራሱን የቻለ በሽታ ነው ወይስ የሌሎች በሽታዎች ምልክት ነው? መንስኤውስ ምንድነው ይላሉ?

ዶ/ር፡- የደም ቧንቧ መስፋት (ማቆር) ራሱን የቻለ በሽታ ነው፡፡ ደም በታችኛው የሰውነት ክፍላችን ወይም ከእግራችን አካባቢ በፍጥነት ወደ ሳንባና ልብ መመለስ ሲገባው፣ ለረዥም ጊዜ እግራችን ውስጥ ከቆየ የደም ቧንቧውን እየለጠጠው እና እያሰፋው ይሄዳል፡፡ ቀላል የሆኑ  በቆዳ ላይና ከቆዳ ስር ትናንሽ ሽንትርትር ነገሮች በተለይ ሴቶች ላይ በታፋና በእግር ጀርባ አካባቢ ይታያሉ፡፡ ከዚህ ተነስቶ ከእግራችን ጀርባ አረንጓዴ (ሰማያዊ) የሆኑ ትላልቅ እብጠቶችን የሚያመጡ የደም ቧንቧዎች መቋጠር ይታያል፡፡ ይህ ችግር ገፍቶ ከፍተኛ ደረጃ በሚደርስበት ጊዜ አልሰር እስከ መፍጠር እንዲሁም የእግሮቻችንን ከለር እስከ መቀየር ሊደርስ ይችላል፡፡

የደም ቧንቧ መስፋት የራሱ የሆኑ መንስኤዎች ያሉት በሽታ ነው፡፡ ከመንስኤዎቹ አንፃር ዋና ዋና የምንላቸውን እንይ፡-

– ደም መልስ ቧንቧዎች ደምን ወደ ታችኛው የአካል ክፍል እንዳይመለስ የሚያደርጉ ቫልቮች አሏቸው፡፡ እነዚህ ቫልቮች ብዙውን ጊዜ በተፈጥሮ አለመኖር፣

– ደምን ወደታችኛው የአካል ክፍል እንዳይመለስ የሚያደርጉ ቫልቮች በተፈጥሮ ደካም በሚሆኑበት ጊዜ፤

– ለረዥም ጊዜ ቁሞ መስራት ደም እግራችን አካባ ለረዥም ጊዜ እንዲቆይ ስለሚያደርገው ደም መልስ ቧንቧዎች እየተለጠጡ ይሄዳሉ፤

– በእርግዝና ወቅት የተለያዩ አካላዊና የሆርሞን ለውጦች ይከሰታሉ፡፡ በዚህ ምክንያት በእርግዝና ወቅት የደም ቧንቧ መለጠጥ ይከሰታል፤

– ለረዥም ጊዜ የቆየ ጉበት በሽታ የደም ቧንቧ መስፋትን ያጣል፤

– የፊንጢጣ ኪንታሮት፡፡

ጥያቄ፡ከፆታ አንፃር በጤና ችግሩ የበለጠ ተጋላጭ ማነው?

ዶ/ር፡- በደም ቧንቧ መስፋት ከወንዶች ይልቅ ሴቶች የበለጠ ተጋላጭ ናቸው፡፡

ጥያቄ፡ምልክቱ ምንድነው?

ዶ/ር፡- የደም ቧንቧ መስፋት ብዙ ምልክቶችን አያሳይም፡፡ ነገር ግን ችግሩ እየጨመረ ሲመጣ ለረዥም ሰዓት በሚቆምበት ጊዜ የተወሰኑ ምልክቶችን ያሳያል፡፡

– ከፍተኛ የእግር ህመም ስሜት ይኖራል፤

– እብጠት ይኖራል፤

– ውሃ መጠራቀም ይከሰታል፤

– በተለይ ሴቶች ላይ በመቀመጫና በእግር ጀርባ አካባ ሸንተረር የመሰሉ ነገሮች በብዛት ይታያሉ፡፡

– የቆዳ ከለሩ ስለሚቀየር ለእይታ የሚማርክ አይሆንም፤

– ችግሩ መፍትሄ ካልተሰጠውና እየቆየ የሚሄድ ከሆነ እግር አካባ አልሰር ይፈጥራ፡፡

– የቆዳ ቀለም መዥጎርጎር

– የደም ዝውውር መስተጓጎል

– የተለያዩ ቁስሎች ሲፈጠሩ አለመዳን

– የቆዳ መብለጭለጭ

ጥያቄ፡ደረጃ ካለው ብናየው?

ዶ/ር፡- የደም ቧንቧ ጥበት በሽታ ራሱን የቻለ 4 ደረጃዎች አሉት፡፡ ደረጃቸውን ቀለል ባለ መልኩ ለመግለፅ የጠና ችግሩ እያለ ምንም አይነት ምልክት ሳይኖር ሐኪሙ ብቻ ሲመረምር የሚያገኘው ከሆነ ደረጃ አንድ እንለዋለን፡፡ በሽታው ደረጃ ሁለት ላይ ከደረሰ በእንቅስቃሴ ወቅት ብቻ እገራችንን የህመም ስሜት የሚሰማን ይሆናል፡፡ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል የምንለው፤ ምንም አይነት እንቅስቃሴ ሳይኖር በረፍት ላይ ሁነን የህመም ስሜት መሰማት ከመረ አስጊ ሊባል የሚችል ደረጃ ላይ መድረሱን ያመላክታል፡፡ ከዚህ ከፍ ሲልም እግር ላይ ቁስለት ሊፈጥር ይችላል፡፡ እዚህ ከደረሰ የከፋ የሚባል ደረጃ ላይ መድረሱን ያሳያል፡፡

ጥያቄ፡የደም ቧንቧ መስፋት (ማቆር) በሽታ የተከሰተ መሆኑን ለማረጋገጥ የሚካሄደው ምርመራ ምንድነው ይላሉ?

ዶ/ር፡- በሽታው መከሰቱን ለማወቅ ምንም የሚያስቸግር ነገር የለም፡፡ ምክንያቱም ደም መልስ የሚባሉ የደም ቧንቧዎች ከውጭ በግልፅ የሚታዩ በመሆኑ በዓይናችን በማየት ብቻ ማረጋገጥ እንችላለን፡፡ ለደም ቧንቧ መስፋት ምንም አይነት የማረጋገጫ ምርመራ ማድረግ የሚያስፈልገው አይደለም፡፡

ጥያቄ፡በህክምና ያለው መፍትሄ ምንድነው?

ዶ/ር፡- ለደም ቧንቧ መስፋትን እያንዳንዱ ሰው በቤቱ ውስጥ ሊያደርገው የሚገባ መፍትሄ ይኖራል፡፡ ለምሳሌ ለረዥም ሰዓት አለመቆም፣ ስራ መስራት ካለብን ቶሎ ቶሎ እየተቀመጡ እረፍትን ልምድ ማድረግና ስንቀመጥ እግራችንን ከፍ አድርገን መቀመጥ ጠቃሚ ይሆናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ወፈር ያሉ ስቶኪንጎችን በመጠቀም፣ የሰፋውን የደም ቧንቧ ጨምቀው እንዲይዙትና ደም እንዳያቁር ማድረግ ይቻላል፡፡ በእነዚህ ሁኔታዎች የማይመለስ ከሆነ፣ በህክምናው ያለው የመፍትሄ አማራጭ በቀዶ ህክምና የሰፋውን የደም ቧንቧ ቆጦ ማውጣት ብቻ ነው፡፡

ጥያቄ፡የደም ቧንቧ መስፋት በወቅቱ ካልታከመ የሚያስከትለው ጉዳት ምንድን ነው?

ዶ/ር፡-የማይድን አልሰር ወይም ሰፊ ቁስል ይፈጥራል፡፡ የተፈጠረው ቁስል የማያቋርጥ ስቃይ ያመጣል፡፡ መራመድን መከልከልና የእግር ውበትን ይቀንሳል፡፡ በተጨማሪም ጫማ አድርጎ ለመጓዝ ያስቸግራል፡፡ በስተመጨረሻም የአጥንት ኢንፌክሽን ያመጣል፡፡

ጥያቄ፡እንዴት እንከላከለዋለን?

ዶ/ር፡- ህብረተሰቡ ስለደም ቧንቧ መስፋት (ማቆር) በሽታ መኖሩንና ችግሩ በቀላሉ ሊታይ የሚችል እንዳልሆነ እንዲገነዘብ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ ውጭ የደም ቧንቧ መስፋትን ለመከላከል የሚያስችሉ ብዙ ነገሮች የሉም ማለት ይቻላል፡፡ ነገር ግን የባታችንን ጡንቻዎች የሚያጠነክሩ አካላዊ እንቅስቃሴዎችን መስራት በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ አዘውትሮ በእግር መራመድ፣ በስራ ቦታ ብዙ ከመቀመጥና ከመቆም በተወሰነ ጊዜ ውስጥ መንቀሳቀስ ጠቃሚ ይሆናል፡፡ በስተመጨረሻ ሁሉም ሰው በእግር አካባቢ የህመም ሆነ የቆዳ ለውጦች ሲኖሩ በቀላሉ ማለፍ የለበትም፡፡ ሁልጊዜም የደም ቧንቧ መስፋትን ማሰብ ይኖርበታል ለማለት እወዳለሁ፡፡


የግንቦት 20 ፍሬዎች ሲመዘኑ …. (ግርማ ሠይፉ ማሩ)

$
0
0

 

Girma-Siefu.jpgዛሬ ግንቦት 22 /2008 ዓ.ም ነው፡፡ ይህን ፅሁፍ ግንቦት 20 በሀዋሳ ከተማ ሆኜ ፃፍኩትና ለመለጠፍ ስል ፅሁፌ ሁሉ የደርግ ደጋፊ የሆንኩ አሰመሰለኝ፡፡ እውነት ከሆነ ደርግ የሰራውን በጎ ነገር መደገፍ አጢያት ባይሆንም እራሴን ከስህተት ለመጠበቅ የፅሁፉን አጭር መደምደሚያ እና የግምገማ ማዕቀፌን ለህዝብ ግምገማ እና ተጨማሪ ግብዓት በአጭሩ በፌስ ቡክ ገፄ ላይ ብለጥፈው በቂ ስድቦች እንጂ ሃሳቦች ማግኘት አልተቻለም፡፡ ሰለዚህ በእራሴ ሚዛን ይህን የግምገማ ውጤት እንደወረደ ማሰቀመጥ እንዳለብኝ ወሰንኩኝ፡፡ ለዚህ ግምገማ የተጠቀምኩበት ማዕቀፍ በብዙ ቦታዎች የተለመደ ነው፡፡ በእርግጥ ይህ ማዕቀፍ ስድስት መለኪያዎች ቢኖሩቱም አንዱ ከአንደኛው ጋር የሚገናኝ እንደሆነ ለመረዳት አያስቸግርም፡፡ በእንግሊሰኛ (PESTEL – Political, Economy, Social, Technology, Environment and legal framework ) የሚባለው ነው፡፡ በእነዚህ መመዘኛዎች የግንቦት 20 ፍሬዎችን እንመዝናለን፡፡ ለማጠቃለል እንዲመቸን ከመጨረሻው እጀምራለሁ፡፡

የህግ የበላይነትና ግንቦት 20

ደርግ በህግ የሚገዛ መንግሰት ነበር የሚል ሰው ሊኖር አይችልም፡፡ የደርግ ስርዓት ሲወድቅ ያየ ወይም እንዲወድቅ ጠብታም ያዋጣ በህግ የሚገዛ ስርዓት መጠበቁ ከእባብ እንቁላል እርግብ መጠበቅ ሊሆንበት አይችልም፡፡ ስህተትም አይደለም፡፡ የደርግ ስርዓት በተለይ የፖለቲካ ተቀናቃኞች ናቸው ያላቸውን ከህግ ስርዓት ውጭ በኮሚቴ እና በአውጫጭኝ እንደገደለ ምስክር መጥራት ወይም ማስረጃ ማቅረብ አይጠበቅብኝም፡፡ ግንቦት 20 1983 ዓ.ም የደርግ ስርዓት ሲቀየር ያለ ህግ ግድያ ይቀራል የሚል ተሰፋ በአብዛኞች ዘንድ ነበር፡፡ ነገር ግን እንደ አንባገነኑ ደርግ ገድሎ ፉከራው ቢቀርም ያለ ህግ ግድያ፣ እስራት እና ግፍ  ለኢትዮጵያዊያን የእለት ከእለት ጉዳይ መሆኑ አልቀረም፡፡ አንድ እውነትም አለ ደርግ ፍርድ ቤቶችን ለፖለቲካ ቲያትር መስሪያ አልተጠቀመባቸው፡፡ ኢህአዴግ መራሹ መንግስት የፍትህ ስርዓቱን ባጠቃላይ ለፖለቲካ ግብ ማስፈፀሚያ በማዋል ደርግን አስከንድቶታል፡፡ ሁሉም እንደሚረዳው በጥናትም እንደተረጋገጠው ዜጎች ፖለቲካው ሊበላቸው ሲመጣ “በህግ አምላክ” ብለው የሚጠለሉበት የፍትህ ስርዓት በግንቦት ሃያ ፍሬነት ያለማገኘታችን ነው፡፡ በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ዜጎች በፍርድ ቤት ውሳኔ እምነት ያጡባት ሀገር ኢትዮጵያ ብቻ ትሆናለች ብዬ እገምታለሁ፡፡ ግንቦት ሃያ ይህን ሊያረጋግጥልን አልቻለም፡፡ ዕውቀት ያላቸው የህግ ባለሞያዎች ከዳኝነት ይልቅ ጥብቅና ብለው፣ ለፖለቲካ ላለማጎብደድ ወሰነው በችሎታ ከማይመጥኗቸው ዳኞች ፊት ይቆማሉ፡፡ በእውቀት የላቁ ዳኞችን ከዳኝነት ወንበር መግፋት ፍሬ ከሆነ የግንቦት ሃያ ፍሬ አድርገን ልንወሰደው እንችላለን፡፡

ፍርድ ቤቶቻችን የሰጡት ውሳኔ እንኳን ለማሰፈፀም አቅም እንደሌላቸው በተደጋጋሚ አይተናል፡፡ በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን የህሊና እስረኞች ካሉባቸው ሀገሮች አንዷ ኢትዮጵያ ነች፡፡ ደርግ ያሰራቸውን ሰዎች መጠየቅ አይከለክልም ነበር፡፡ ይህን ፅሁፍ ከማጠናቀቄ በፊት በዝዋይ የሚገኘውን ጓደኛችንን ተመስገን ደሳለኝን መጠየቅ አይቻልም ተብለን ተመልሰናል፡፡ በህገመንግሰት የተቀመጠን መብት ማንም በመመሪያና ደንብ ሲሸረሸር አቤት የሚባልበት ቦታም ሰርዓተም የሌለበት ሀገር ኢትዮጵያ ነች፡፡ ይህን ማሻሻል የማይችል መሰዋዕትነትን ለማክበር ግንቦት 20 አደባባይ ልንወጣ የምንችልበት ምክንያት አልታይህ ብሎኛል፡፡ የሚገርመው ይህንን የግንቦት 20 ፍሬ ተብሎ እነዚሁ ታሳሪዎች እንዲያከብሩት ይገደዳሉ፡፡

ግዴታን በተመለከተ እንግዲህ ከየመስሪያ ቤቱ እየሾለከ የወጣው ግንቦታ ሃያ ካላከበርክ/ሽ ወዮልህ ማስፈራሪያ መስከረም 2 ለአብዮት በዓል ውጡ ግዴታ በምን እንደሚሻል እና ኢህአዴግ ከደርግ በምን እንደሚሻል የሚያስረዳን ቢገኝ ለመረዳት መዘጋጀት አለብን፡፡ በጭፍኑ ከደርግ እንሻላለን የሚያዋጣ አይመሰለኝም፡፡ ግንቦት 20 አላከብርም ያለ ዜጋ ምን እንደሚደርስበት እና ጉዳት እንዳይደርስበት አፋጣኝ የፍትህ ስርዓት ስለመኖሩ እርግጠኛ መሆን አይቻልም፡፡

ሲጠቃለል ግንቦት 20 “በህግ አምላክ” የሚባለውን ኢትዮጵያዊ የህግ አክባሪነት ባህል ያጣንበት ነው፡፡ ፍትህን ለደህንነታችን መሸሸጊያ ሳይሆን ለፖለቲካ መሳሪያነት የበለጠ እንድናውቃት የተደረገበት መሆኑ ጎልቶ የታየተበት ነው፡፡ ከህገ መንግሰት ድንጋጌ ይልቅ የግለሰቦች ቁጣና ግልምጫ የሚፈራበትና የሚከበርበት ሀገር ላይ መኖራቸን ነው፡፡ በተለይ ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ቃላቸው ህግ ሊሆን የተቃረበበት ወቅት ነበር፡፡

ቴክኖሎጂ እና ግንቦት 20

ይህን ሚዛን ኢህአዴግ እና የፕሮፓጋንዳ አውታሮቹ የሚጠቀሙበት ቁጥር በማነፃፀር ነው፡፡ ለምሳሌ እኔ የዛሬ 25 ዓመት 24 ዓመቴ ነበር ዛሬ 49 ስሆን ይህን በምንም መለኪያ የግንቦት 20 ፍሬ አድርጌ ለመቁጠር አልችልም፡፡ በተመሳሳይ በሚኒሊክ ጊዜ ይሁን በደርግ ጊዜ የነበረ የስልክ መስመር ቁጥር ብዛት፣ አሁን ካለው ጋር በማነፃፀር የግንቦት 20 ፍሬን ማግኘት አይቻልም፡፡ በኢትዮጵያ አሁን አሉ የምንላቸው ቴክኖሎጂዎች በተለይ የማህበራዊ ድረ ገፅ መጠቀሚያ የሆኑት መሰረተ ልማቶቸ፣ የሞባይል ስልክ፣ ኮምፒውተር፣ወዘተ ደርግ በስልጣን ቢቀጥል የኢትዮጵያ ምድር ሊረግጡ የሚችሉበት መንገድ አይኖርም ብሎ ማሰብ ይቻላል ወይ? ብሎ መጠየቅ የተሻለ ትክክለኛ ሚዛን ይሆናል ብዬ አምናለሁ፡፡ ደርግ በስልጣን ቢቀጥል ኢትዮጵያ ውስጥ ቴክኖሎጂ እንዳይገባ ያደርግ ነበር? ብዬ ለማሰብ ግን አቃተኝ፡፡

አንድ ነገር ማሰብ ቻልኩ ህወሃት እና ሻቢያ እንዲሁም ኦነግ እና ሌሎች ለመገንጠል የሚሰሩ ድርጅቶች ውጊያ ካላቆሙ፣ አሁን ይገኝ የነበረው እርዳት በገፍ የማይግኝ ቢሆን መሰረተ ልማቶቹ ሊኖሩ አይችሉም ነበር፡፡ ሰለዚህ ደርግ ይህን ሊሰራው የማይችል የነበረው አሁን በመንግሰት ላይ ያሉት ኃይሎች እንዳይስራ የማደናቀፍ ስራ ከሰሩ ብቻ ነው ሊሆን የሚችለው፡፡ ከቀዝቃዛው የዓለም ጦርነት ማክተም በኋላ የውክልና ጦርነቶች ስለማይኖሩ በሌሎቸ ሀገራትም ያሉት በመክሸፋቸው ጦርነቶቹ የሚቀጥሉበት እድል ጠባብ ነበር፡፡ እርዳታና ብድር ደግሞ እንደ ኤርትራ እንቢ ያላለ ይልቁንም በዓለም ከሚገኙ ከምስራቅም ከምዕራብም ለመውሰድ ዝግጁ የሆነ ብድር ማግኙት አይቀርም ነበር፡፡ ሰለዚህ በቴክኖሎጂ በኩል ኢትዮጵያ ከዓለም ተለይታ እንደ ኩባ እና ሰሜን ኮሪያ ትሆን ነበር ብሎ ማሰብ አይቻለም፡፡ ይልቁንም በቅይጥ ኢኮኖሚ ጅማሮ የታየው የግል ባለሀብት መስፋፋት በመቀጠል ወደ ተሻለ መሰመር ሊኬድ ይችል ነበር፡፡ ማለትም ተጨማሪ ቴክኖሎጂ የሚያቀርቡ የግል ሴክተሮች ሊኖሩ የሚችሉበት እድል ይኖር ነበር፡፡ ይህን ለማድረግ የደርግ ቅይጥ ኢኮኖሚ ከኢህአዴግ ቅጥ አንባሩን ካጣው “አብዮታዊ ዲሞክራሲ መር ኢኮኖሚ” እንደሚሻል በግሌ አምናለሁ፡፡ ሰለዚህ ግንቦት 20 በቴክኖሮለጂ መስክ ያመጣው ለውጥ ኢህአዴግ ስልጣን ባይዝ እናጣው ነበረ ብሎ ማሰብ አይቻልም፡፡

ሲጠቃለል በዓለም ላይ ሆኖ ከቴክኖሎጅ እራሱን ማራቅ አይቻልም፡፡ ሰለዚህ እኛም አሁን ካለንበት በተሻለ ልንሆን የምንችልባቸውን ወርቃማ 10 ዓመታት (1983-1993) ከተሜ ጠል በሆነ የኢህአዴግ አስተሳሰብ አምልጦናል፡፡ ከዚያም ቀጥሎ ያሉት ዓመታት ከውድድር ይልቅ የግል ዘረፋን በህዝብ ስም ለማድረግ በሚያስችል አሰራር የህዝብ ሀብት ማባከኛ ሆኗል፡፡ በቴሌ መሰረተ ልማት ብንወሰድ ዘላቂ ለመቶ ዓመትና ከዚያ በላይ ማሰብ ባለመቻል፣ በተደጋጋሚ የመሰረተ ልማት ለውጦችና ውድመቶች የደረሱባት ሀገር ነች፡፡ ስለዚህ ግንቦት 20 የሰርዓት ለውጥ ባይመጣ የምናጣው ነገር ሳይሆን ያጣነው ብዙ ነገር እንዳለ ይሰማኛል፡፡ ኢትዮጵያ የዜጎቿን ሙሉ ሀይል መጠቀም ብትችል ከዚህ የተሻለ መሆን እንደሚቻል ይስማኛል፡፡

የአካባቢ ጥበቃና ግንቦት 20

ሀገራችን ኢትዮጵያ ለረዥም ጊዜ የደን ሸፋን እየተራቆተ ሄዶ ሁለትና ሶሰት በመቶ ቀርቶዋል ስንባል ልጆች ነበርን፡፡ አሁን ደግሞ ድንገት ተነስተን ከአስራ ሁለት እስከ አስራ አምሰት በመቶ መድረሱ እየተነገረን ነው፡፡ እኔ በእድሜዬ አዲስ አበባ ከተማ ጫካ እንደነበር አውቃለሁ፡፡ ሰፈራችን መሳለሚያ አካባቢ ድረስ ጅብ ይመጣ እንደነበርም አውቃለሁ፡፡ ኮልፌ ከሚኖሩ ዘመዶቼ ከሄድኩ ከመሸ ማደር ግዴታ ነበር፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ አዲስ አበባ ውስጥ በደብሮች እና በዮኒቨርሲቲ እንዲሁም በቤተ መንግሰት እንመለከት የነበረው ደን ወደ ሲሚንቶ ክምርነት እየተቀየረ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ዋና ጊብ ልብ በሉልኝ፡፡ በክልልም ያለው ተመሳሳይ ሁኔታ ነው፡፡ በደርግ በተፈጥሮ ሀብት ልማት በሚኒሰትር ደረጃ አደራጅቶ በእርዳታ የሚገኝ ገንዘብን በነፃ ከመስጠት የአካባቢ ልማት በተለይ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ እንዲሰሩ በማድረግ እሰከ አሁን የሚታዩ ውጤቶች ተመዝግበው ነበር፡፡ አሁን ኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት የሚባለው ቦሌ ፍላሚንጎ አካባቢ ያለው ህንፃ የዚህ ተቋም ውጤት ነበር፡፡ ከግንቦት 20 በኋላ ይህ መስሪያ ቤት ፈርሶ አሁን ከ20 ዓመት በኋላ እንደ አዲስ እንዲቋቋም ተደርጎዋል፡፡ ይህ የሚያሳየን ደርግ የተፈጥሮ ሀብትን በመጠበቅ የተሻለ ሊሆን እንደሚችል መገመት ይቻላል፡፡ ከስራውና ከተገኘው ፍሬ በመነሳት ማለት ነው፡፡ በተወሰኑ አካባቢዎች የተሻለ ሰራ በኢህአዴግ እንደተሰራ አውቃለሁ፣ እነዚህ ስራዎች ግን ደርግ ሃያ አምስት ዓመት ቢቆይ አይስራውም ብዬ ለማመን ግን እቸገራለሁ፡፡ አሁንም ቢሆን በተለይ ከአባይ ግድባ ጋር ተያይዞ መሰራት ያለበት የአባይ ተፋሰስ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት መሰራት እንዳለበት ባለሞያዎች ቢናገሩም አሁንም ያለው ስራ ከወረቀት እና የውሸት ሪፖርት ከማምረት የሚዘል እንዳልሆነ በአባይ ተፋሰስ ጎግል በማድረግ ማየት ይቻላል፡፡ የሌለ ጫካ አለ ማለት በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን አይቻለም፡፡

ሲጠቃለል ግንቦት 20 መሬትን ዜጎች የኢኮኖሚ መሳሪያ አድርገው እንዲጠቀሙበት ማድረግ ባለመቻሉ ዜጎች ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ የደን ልማቶችን ሊያስራ አልቻለም፡፡ በመንግሰት የደን ጥበቃ ስራ በአግባቡ እየተሰራ አይደለም፡፡ ይልቁንም ያሉትን ባለቤት እንዳይኖራቸው በማድረግ ከህዝብ ቁጥረ መጨመር ጋር ተያይዞ ደን መመንጠር የበለጠ እየሆነ መጥቷል፡፡ ለማነኛውም ማነኛውም ኢትዮጵያዊ የሆነ መንግሰት ቢመጣ በደን ልማት ከዚህ የተሻለ ፖሊሲና ስትራቴጂ በመንደፍ የህዝብ ተጠቃሚነት ሊያረጋግጥ ይችላል ብዬ አምናለሁ፡፡ ሰለዚህ በግንቦት ሃያ ካገኘነው ይልቅ ያጣናው ያማዝናል፡፡

ማህበራዊ ልማትና ግንቦት 20

ማህበራዊ ልማትና በጤና በትምህርት መስክ ተወስኖ ይታይ ቢባል አሁን ያሉት ሸፋኖች ከደርግ ጋር ሲነፃፀር ከመቶ እጥፍ እንደሚበልጡ ይታወቃል፡፡  ይህ ግን የግንቦት 20 ፍሬ ሊሆን የሚችለው የጤና ተቋማትን እና ትምህርት ቤቶች የሚያፈርስ ኃይል በሌለበት ነው፡፡ ደርግ ትምህርት ቤት መገንባት አቅም ቢያንሰው ሁሉም ትምህርት እንዲያገኝ በሶሰት ፈረቃ እንዲማር አድርጎዋል፡፡ ይህ ደርግ ዜጎች እንዳይማሩ የሚፈልግ መንግስት ነው ብዬ ለመውሰድ ይቸግረኛል፡፡ ያለምንም የእድሜ ገደብ ወንድ ሴት ሳይባል ወደ ትምህርት ቤት እንዲሄድ በአካባቢውም የመሰረተ ትምህርት ጣቢያዎች እንዲኖሩ የተደረገበት ነው፡፡ የእኔ እናት ከመሰረተ ትምህርት ተነስታ መደበኛ ትምህርት መግባት የቻለችው ሰርዓቱ በፈጠረው በጎ ተፅዕኖ ነው፡፡ ትምህርቶች ደግሞ ይሰጡ የነበሩት ሁሉም በቋንቋው እንደነበረ ማንም ያውቃል፡፡ ከዚህ አንፃር ተገኘ የሚባል ለውጥ ካለ በኢትዮጵያ “ቁቤ” በግዕዝ ፊደል ፋንታ በኦሮሚያ እና አንዳንድ አካባቢዎች ተግባራዊ ማድረግ መቻሉ ነው፡፡ “በሬሳ” በግዕዝ ፊደልም ቢሆንም በአዲስ አበባ ከተማ ይሸጥ እንደነበር መካድ አይቻልም፡፡ በግሌ ኢትዮጵያ የብሔረሰቦች እስር ቤት ነበረች ብሎ ተረክ ሊገባኝ አይችልም፡፡ የአሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝም እኔም በደርግ የተማርን እንደነበረ መመሰከር ግድ ይላል፡፡ ዶክተር አሸበርወ/ጊዮርጊሰ ይህን ኢትዮጵያ የብሔሮች እስር ቤት ነበረች ተረክ ይወደዋል፡፡ ሩሲያ ለትምህርት የላከው ግን የደርግ ሰርዓት ነበር፡፡ ሌሎችም እንደዚሁ፡፡

የጤና ሸፋን በሀገራችን በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ደረጃ እንደጨመረ ይታወቃል፡፡ ልብ ማለት ያለብን ግን ከግንቦት 20 1983 በፊት በቅጡ ተደራጅተው የነበሩ “የወባ መቆጣጣጠር”፣ የኤች፣አይ ቪ፣ የመሳሰሉ ገዳይ በሸታዎችን በትጋት ይሰሩ የነበሩ ተቋማትን በማፍረስ በወረርሽኝ መልክ የተስፋፉበት ወቅት እንደ ነበርም የምንዘነጋው አይደለም፡፡ ያለፉት ሰርዓቶች ኢትዮጵያዊ ዜጎችን አደንቁረውና በበሸታ አማቀው ሊገዙ ፖሊሲ ነበራቸው ብዬ ለማመን አልችልም፡፡

ሲጠቃለል በማህበራዊ ልማት ግንቦት ሃያ የስርዓት ለውጥ ባይደረግ የሚቀርብን ነገር ምን አልባት “ቁቤ” ብቻ ነው፡፡ እርሱም ቢሆን በህዝበ ውሳኔ ሊደረግበት የማይችል ነገር አልነበረም፡፡

ኢኮኖሚ ልማትና ግንቦት 20

ኢህአዴግ ብዙ እንዲዘመርለት የሚፈልገው እና ሌሎች ነገሮቻችን በተለይ ነፃነታችንን አሳልፈን እንድንሰጠው የሚፈልገው ተመዘገቡ የሚላቸውን የኢኮኖሚ እድገቶች ብቻ እዪ በማለት ነው፡፡ አሁንም ደርግ ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ እንዳታድግ፣ ዜጎች በድህነት እንዲማቅቁ የሚፈልግ ሰርዓት ነበር ወይ? ብዬ እራሴን ሰጠይቅ በፍፁም እንዳልሆነ እረዳለሁ፡፡ በተለይ ደግሞ የቅይጥ ኢኮኖሚ በደርግ የመጀመሪያ ዘመን የሚያስቀስፍ እንደነበረ ሁሉ በመውደቂያው ጊዜ ደግሞ “ገንዘብ ገንዘብ ያለው ያውጣ፣ ይስራ ያሰራበት” መመሪያው ሆኖ ነበር፡፡ ደርግ የጥቂት ሰዎች መጠቀሚያ ሀገር ለመመስረት ፍላጎት ያለው መንግሰት አልነበረም፡፡ በቅርቡ ከጓደኞቼ ጋር ሆነን በቀድሞ ስርዓት ብር 500 ይከፈለው የነበረ አንድ ጀማሪ ባለዲግሪ (በዶላር 240) ማለት እንደሆነ እና አሁን ግን 240 ዶላር የሚከፈለው 10 እና 20 ዓመት የስራ ልምድ ያለው ተቀጣሪ እንደሆነ ስናስብ ነበር፡፡ ይህ በምንም ህግ እድገት ሊሆን አይችልም፡፡ የመግዛት አቅሙ የተዳከመ ብር የሚመሰረት ኢኮኖሚ ጠንካራ ኢኮኖሚ ሊሆን አይችልም፡፡ ወደፊትም በውጭ ንግድ የተሻል መሆን ካልቻልን በስተቀር የብር ምንዛሬ እየወረደ የዜጎች ሸክም እየከበደ የሚመጣበት ጊዜ እሩቅ አይደለም፡፡ ይህ ማለት ግን በዶላር ሲለካም ቢሆን የተንደላቀቀ ኑሮ የሚኖሩ ባለ ሚሊዮን ዶላር ጥቂቶች ማፍራት የቻለች ሀገር ሆናለች፡፡ ችግሩ እነዚህ ጥቂት ባለሚሊዮን ዶላር ዜጎች በግልፅ ለህዝብ የሚታወቁ እና የገቢ ምንጫቸውም የሚታወቅ ባለ ሚሊዮን ዶላር በሆኑበት ልክ ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚረጋገጥበት ስርዓት አልተዘረጋም፡፡

ኢህዴግ በሚወደው የቁጥር ጫወታ ብንጫወት ከአምሳ ሚሊዮን ህዝብ የዛረ 30 ዓመት 2 ሚሊዮን ቢራብ 4 ከመቶ መሆኑ ነው፡፡ ከዘጠና ሚሊዮን ህዝብ አሁን 10 ሚሊዮን ሲራብ ከ10 በመቶ በላይ ነው፡፡ የተሻለ የኢኮኖሚ ሰርዓት አለኝ የሚለው ኢህአዴግ ከፖሮፓጋንዳ አልፎ ዜጎችን ባስተማማኝ ሊቀልብ የሚችል ስርዓት አልዘረጋልንም፡፡ ያለ እርዳታ ዜጎች ከሞት ሊድኑ የሚያስችል ስርዓት መገንባት አልተቻለም፡፡

ሲጠቃለል ኢትዮጵያ ውስጥ በኢኮኖሚ በተለይ ሁኔታ ሊጠቀሙ የሚችሉ ቡድኖችን መፍጠር ተችሏል፡፡ አብዛኛው ህዝብ የሀገር ሀብት በፍትሃዊነት ሊጠቀም የሚችልበት አልሆነም፡፡ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት በዜጎች መካከል በብሔር በዘር መጠቃቀም ብቻ ሳይሆን፣ ከኢትዮጵያዊ ይልቅ ለውጭ ሰዎች የበለጠ ምቹ እንዲሆን የተደረገ ሰርዓት ነው፡፡ ኤኮኖሚው “በዘረኝነት” የተለከፈ ከመሆኑ የተነሳ የብዙ ሌሎች ፖለቲካ ችግሮች ነፀብራቅ ነው፡፡ ዜጎች ሰርተው ለማደግ እንዲችሉ ምቹ ሁኔታ ከመፍጠር ይልቅ ተከታትሎ ለማጥቃት የተደራጀ መሰረቱ “ምቀኝነት” የሚመሰል የኢኮኖሚ ሰርዓት ነው፡፡ የመንግሰት የገቢ መሰረት ታክስ መሰብሰብ መሆኑ ቀርቶ ከዜጎች ጋር ፉክክር የያዘ ያስመስልበታል፡፡

 

ፖለቲካና ግንቦት 20

ከላይ የዘረዘርኳቸውን መለኪያዎች ለኢህአዴግ በሚያደላ መልኩ ሊሆን ያልቻሉበት ዋናው ምክንያት ፖለቲካው፣ በመበላሸቱ ነው፡፡ በዓለም ላይ ለውጥ ሊያመጣ የሚችል ተሞክሮ ያለፈ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት በመገንባት በህገ መንግሰት ላይ የተቀመጡትን እጅግ አስደማሚ መብቶች ለማክበር ያለመቻል ውጤቶች ናቸው፡፡ ህገመንግሰትን በሚመለከት ከዚህ በፊት የነበሩ መንግሰታትም ቢሆኑ በወቅቱ የነበረውን ስርዓት የፊውዳል ይሁን፣ የኮሚኒሰት የሚመጥን ህገመንግሰት ነበራቸው፡፡ ችግራቸው መተርጎሙ ላይ ነው፡፡ አሁን ያለውም ቢሆን የፖለቲካ ሰነድ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በፍፁም ከመድበለ ፓርቲ ስርዓት ጋር የሚቃረን የአንድን ፓርቲ ብቻ ፍላጎት የሚያሟላ ተደርጎ መቀረፁ ትክክል አይደለም፡፡ ለማነኛውም ህገ መንግሰቱ ይህ ነው፣ ይህ አይደለም ከማለት ይልቅ የተፃፈውን ቢያከብሩልን ብዙ ደስታ ሊፈጥሩ የሚችሉ እና ከላይ የዘረዘርናቸውን የሌሎች መለኪያዎች የታየውን ውድቀት ማከም የሚችል ይሆን ነበር፡፡ በፖለቲካ ሰነድ ውስጥ መሬትን አስመልክቶ የተቀመጠው ድንጋጌ በአካባቢ ጥበቃም ሆነ በኤኮኖሚ መስክ ማሰመዝገብ የሚገባንን ውጤት እንዳናስመዘግብ ያደረገ ማነቆ ነው፡፡

በሀገራችን የሚደረጉ የይስሙላ ምርጫዎች ፖለቲካ በዜጎች ፍላጎት ሳይሆን በጥቂት አውቅላችኋለሁ ባዩች ብቻ እንዲመራ የሚያደርግ ብቻ ሳይሆን የገንዘብ ማባከኛም ጭምር ነው፡፡ በኢትዮጵያ ምርጫ አለ ከማለት ምርጫ የለም የተሻለ የሚገልፃት ሀገር ሆናለች፡፡ ሀገር የሚመሩ ሰዎች ተምረው በአገኙትና በያዙት እውቀት ሳይሆን ሀገር እየመራን ነው እያሉ እየተሳሳቱ የሚማሩባት ቤተ ሙከራ አድርገዋታል፡፡ ከስህተታችን ተመክሮ ወሰደናል እያሉ የሚመፃደቁበት ቦታ የፖለቲካ ስልጣን ሆኖኋል፡፡ ለማነኛውም …… የኢህአዴግ ፖለቲካ ክስረት የክስረታቸው፣ ብሎም የጋራ ክስረታችን መንስዔው እንደሆነ መረዳት ሊቅ መሆን አያስፈልገውም፡፡

ሲጠቃለል ሀገራችን ኢትዮጵያ በፖለቲካው መስረመር ዜጎች የአመለካከት ልዮነታችን ለስጋት ሳይሆን ለዜጎች ምርጫ ለማቅረብ እንደሚያስችል ምርጥ እድል አድርጎ ከመጠቀም ይልቅ፣ ዜጎች በሚይዙት የፖለቲካ አቋም በእስር፣ በግርፋት፣ ቶርቸርን ጨምሮ የሚደረግባት ሀገር ሆናለች፡፡ ግንቦት ሃያ የደርግን ቶርች ሊያስቀርልን ሳይሆን በተሻሻለ ሁኔታ ሊተገብርልን የመጣ እስኪመስለን ድረስ ዜጎች በመሃል አዲስ አባባ ውስጥ ይገረፋሉ ይስቃያሉ፡፡ ሰቃያቸውን ለፍርድ ቤት ሲናገሩ የሚያደምጥ ያለመኖሩ ሳይሆን በዚህ ዓይነት ምርመራ የተገኘን ማስረጃ ተቀብለው ዘግናኝ ውሳኔ በመስጠት የፍትህ ስርዓቱን የፖለቲካ አጋርነት ያረጋግጣለሁ፡፡ ይህ አልበቃ ብሏቸው በቁጥጥር ሰር ያዋሏቸውን እስረኞች በወዳጅ ዘመድ እንዳይጠየቁ፣ በማድረግ ማህበረሰቡን እንዳለ ለማሸማቀቅ ይጠቀሙበታል፡፡ ግንቦት 20 ያስገኘልን አዲስ ነገር ይልቅ ያጣናው ማመዘኑ የሚያስቆጭ ብቻ ሳይሆን በተለያየ ጎራ ተሰልፈው በሀገራችን ማህበራዊ ፍትህ እንዲሰፍን፣ የፖለቲካ እኩልነት እንዲኖር ዜጎች በሀገራችው ያለምንም ገደብ ተንቀሳቅሰው እንዲሰሩ፣ ወዘተ ለማደረግ መስዋዕትነት የከፈሉትን ኢትዮጵያዊያን ደምና ህይውት ከንቱ እንደቀረ የሚያስቆጥር ነው፡፡ በእኔ እምነት በሀገራችን ለብዙ ዘመናት የተከፈሉት መስዋዕትነቶች ጥቂቶችን ሚሊዮኒየር፣ ጥቂቶችን ደግሞ በስልጣን ማማ ላይ ለመስቀል አልነበረም፡፡ ግንቦት 20 1983 ተከትሎ የመጣውም ለውጥ ሀዲዱን ስቶ ያረጋገጠው ነገር ቢኖር ጥቂት ሚሊኒየሮች እና ጥቂት እምብርት አልባ የስልጣን ጥመኞችን ነው፡፡

ቸር ይግጠመን!!!

ኢትዮጵያውያን ምን እስኪፈጠር ነው የምንጠብቀው? (ስዩም ወርቅነህ)

$
0
0

3618556593_4674679485

~ 2.4 ሚሊዮን የአማራ ክልል ተወላጆች በህዝብ ቆጠራ ወቅት ጠፉ

~ ከ125 በላይ ህፃናት በጋምቤላ ክልል በሙርሌዎች ተዘረፉ
~ የእምነት ነፃነት በመጠየቃቸው ብቻ የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው እስራት፣ ግርፋት፣ ግድያና እንግልት ዛሬም ቀጥሏል።
~ ላለፉት 25 ዓመታት በስርቱ ተላላኪዎች የተቃጠሉ ገዳማትና ቤተክርስቲያን ቁጥር ቀላል አይደለም።
~ ከ2000 በላይ ከብቶች በሙርሌዎች ተዘረፉ
~ ከ225 በላይ የጋምቤላ ተወላጆች በሙርሌዎች ተገደሉ
~ ከ400 በላይ የአኟክ ተወላጆች በህወሃት/ኢህአዴግ ተወላጆች በጠራራ ፀሃይ ተገደሉ
~ ከ200 በላይ ዜጎች ከ1997 ዓ.ም ምርጫ በኋላ በህወሃት/ኢህአዴግ የፌደራልና የመከላከያ ሰራዊት ተገደሉ
~ ከ10 ዓመት በኋላ በሚደረገው ህዝባዊ ቆጠራ የጉራጌ፣ ኦሮሞ፣ አማራና የሌሎችም ዜጎች ቁጥር ቀንሷል
~ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት ከ80ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን አለቁ
~ ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ አያሌ ኢትዮጵያውያን ሶማልያ ውስጥ ሰላም ለማስከበር በሚል ተልከው ተገድለዋል። የቀድሞ ሟች ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ስንት ሰው እንደሞተ ለመግለፅ ፓርላማ ውስጥ ተጠይቀው የማሳወቅ ግዴታ የለብኝም ብለው እንቢ ማለታቸው የሚታወስ ነው።
~ አማራ ክልል ውስጥ ወላድ እናቶችን ክትባት በመስጠት እንዳይወልዱ ተደርገዋል። ያረገዙትም እንዲያስወርዳቸው ተደርገዋል።
~ ለሃገራችን የሚጠቅሙ አያሌ ኢትዮጵያውያን በሰበብ አስባቡ በእስር ቤት ታግደው ይገኛሉ።
~ ስርዓቱ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ምቹ ባለማድረጉ ምክንያት አያሌ ኢትዮጵያውያን ለስደት ተዳርገዋል። ያሰቡበት ያልደረሱትም የበረሃ ሲሳይ ሆነዋል። ሌሎችም በሜደትራኒያን ውቅያኖስ ተወስደዋል። በየበረሃው በባዕዳን ተደፍረው ለእብደት የተደራጉትና ለዘላለም የህሊና ጠባሳ እስረኛ የሆኑ ብዙ ናቸው። የዱር አራዊትና የአሳ መብል የሆኑትም ብዙዎች ናቸው።
~ 28 ኢትዮጵያውያን በISIS አንገታቸውን ተቀልተው ተገድለዋል።
~ ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ ኢትዮጵያውያን በደቡብ አፍሪካ በተቀሰቀሰው Xenophobia እስከነ ህይወታቸው ከጎማ ጋር በመጠፈር ተቃጠለው ተገድለዋል። እሚከራከርላቸው አጥተው በየቀኑ የሚገደሉትም ቁጥር ስፍር የላቸውም።
~ የመን ውስጥ በተቀሰቀሰው የርስበርስ ጦርነት በስደተኛ ካምፕ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአየር መደብደባቸው የሚታወስ ነው።
~ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መግቢያ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዋናው ቅጂ ተሰርቆ ወጥቷል።
~ በጎንደር በኩል ለሱዳን 160 ኪሎ ሜትር መሬት ወደ ውስጥ ተላልፎ ተሰጥቷል
~ ኢትዮጵያ ውስጥ ላለፉት 25 ዓመታት ወደብ አልባ ተደርጋለች
~ ላለፉት 25 ዓመታት የተገደሉትና የታሰሩ የኦሮሞ ተወላጆች ቁጥር በውን የሚታወቅ አይመስለኝም። በቅርብ ጊዜ በተፈጠረው ተቃውሞ እንኳን ከ200 በላይ የኦሮሞ ተወላጆች ተገድለዋል፣ ከ3000 በላይ ታስረዋል፣ አያሌዎች ተደብድበዋል፣ ለስደት ተዳርገዋል።
~ በየአረብ ሃገራ በእህቶቻችን ላይ የሚደርሰው ስቃይና በደል ለሁላችንም ግልፅ ነው
~ የማንነት ጥያቄ ባነሱት የወልቃይት ጠገዴ ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ኢ-ሰብዓዊ ተግባር የሚዘገንን ነው።
~ ሌላም ሌላም……..
…,……………………..……..

ይህ ሁሉ በደል አልበቃ ብሎ ምን እስኪያደርጉን ነው የምንጠብቀው??

(የፈተናው ስርቆት ጉዳይ) –ጉዳዩ ትግሉን የመቀበል ወይም ያለመቀበል ነው |ከበፍቃዱ ዘ-ኃይሉ

$
0
0

fetena

ስርቆት ነውር ነው። ግድያ ደግሞ ጭራሹኑ ተቀባይነት የሌለው ነገር ነው። የሰው ነፍስ ለማትረፍ የተፈፀመ ስርቆት፣ ለኔ ‘ቅዱስ ስርቆት’ ነው።

እኔ ‘ሞራሊስት’ አይደለሁም። ይህ ማለት ግን ጉራ ሊመስልብኝ ቢችልም እንኳ በየትኛውም መለኪያ የሞራል ከፍታዬን ተጠራጥሬው አውቃለሁ ማለት አይደለም፤ በፍፁም። የትላንቱን ፈተና ያስተጓጎለውን ስርቆትም ያለምክንያት፣ ኢሕአዴግን ስለሚያበሳጨው ብቻ ብዬ አይደለም በይሁንታ የተቀበልኩት። Here is why.

(ጋዜጠኛ በፈቃዱ ኃይሉ)

(ጋዜጠኛ በፈቃዱ ኃይሉ)

ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው መንግሥት ለኔ ሕጋዊም ሞራላዊም ቅቡልነት ያለው መንግሥት አይደለም። ሥልጣን ላይ ያለው በማጭበርበር እና በኃይል ነው። በተለምዷዊው የምርጫ አካሄድ ይወርዳልም ብዬ አላስብም። ሕዝቡ ግን የሙሉ ሰዓት ኑሮን ለማሸነፍ ተፍጨርጫሪ በመሆኑ የሙሉ ሰዓት ፖለቲከኞች ምን እየተፈፀሙበት እንደሆነ በቅጡ አያውቅም። ሕዝቡ መንግሥቱን ‘በቃኸኝ፣ አትመጥነኝም’ ለማለት የሚያስችል ፋታ ኑሮው አልሰጠውም። ‘ይሄንን ሁሉ በደልማ አልቀበልም፤ በቃኝ’ የሚለው ግን የሚችለውን ትግል ጀምሯል።

እኔ የሰው ነፍስ የሚነጥቅ ትግል ተቃዋሚ ነኝ። በሠላማዊ ትግል ስትራቴጂ ደግሞ (ጂን ሻርፕ እንዳለው) ሦስት ዐብይ ዘዴዎች አሉ። ለማሳመን መጣር (to persuaded)፣ አለመተባበር (non-cooperation) እና ጣልቃ መግባት (intervention) ናቸው። ኦሮሚያ በተቃውሞ እና በመንግሥት ኃይሎች ምኅረት አልባ እርምጃ ቢያንስ ለአራት ወራት ስትታመስ ቆይታለች። ትምህርት ቤቶች ሲዘጉ፣ ሲከፈቱ ቆይተዋል። ተማሪዎች በዚህ መስተጓጎላቸው የሚያጠራጥር ነገር አይደለም።

በኦሮሚያ፣ ተማሪዎች እና ይመለከተናል ያሉ አካላት ፈተናው ጊዜው እንዲራዘም ጠይቀው እንደነበር እና አጥጋቢ ምላሽ እንዳላገኙ ሰምተናል። ይህ ‘ለማሳመን የመጣር’ ትግል ነው። ነገር ግን እምቢታውን እንዴት መቃወም እንደሚችሉ ላያውቁ ይችላሉ። ‘አለመተባበር’፣ ምናልባትም ፈተናው ላይ አንቀመጥም ማለትን ይጠይቅ ይሆናል። ይህንን ማድረግ ቀላል ነገር አይደለም። አስተባባሪ መኖር አለበት። ይህንን ለማስተባበር የሚችል አገር ውስጥ ያለ አካል፣ ያውም ከዚያ ሁሉ የግፍ እርምጃ በኋላ እና ከወትሮው በላይ በጠበቀው ቁጥጥር መሐል የማይሞከር ነው። ስለዚህ አቅሙ ያላቸው እና አማራጩን የሚያውቁት፣ ውጪ ያሉት ሰዎች፣ ሦስተኛውን ዘዴ፣ ማለትም ጣልቃ መግባትን ተጠቀሙ እና የፈተናው ጊዜ እንዲተጓጎል አደረጉ። በኦሮሚያ አካባቢ ላሉ ተማሪዎች የተነፈገው ፍትሕ በአራማጆቹ ጣልቃ ገብነት እንደተፈፀመ ነው የምቆጥረው። Justice served.

ጉዳዩ ኢሞራላዊ ይሆን የነበረው አራማጆቹ ፈተናውን ሰርቀው፣ መልሱን በምሥጢር ተበደሉ ላሉት አካላት ቢሰጧቸው ነበር። እነርሱ ግን ያደረጉት አንጻራዊ ሠላም በነበረበት አካባቢ ያሉት ተማሪዎች ያደረጉትን ዝግጅት ያክል የመዘጋጃ ጊዜ እንዲሰጣቸው የፈተናው ቀን እንዲራዘም ነው። ኃላፊነት የሚሰማው መንግሥት ቢኖር ኖሮ ቀድሞውንም ኦሮሚያ አካባቢ ላሉት ተማሪዎች ይህንን ጊዜ ፈቅዶ ቀሪዎቹ ተማሪዎች ብቻ እንዲፈተኑ ማድረግ ይችል ነበር።

የፈተናው መስተጓጎል፣ አንደአገርም እንደግለሰብም ብዙ ምስቅልቅሎችን እና ኪሳራዎችን እንደሚያስከትል አላጣሁትም። ነገር ግን ለምስቅልቅሎቹ ተጠያቂው የችግሮቹ ሁሉ መንስኤ የሆነው መንግሥት ተብዬው ስለሆነ ይቅርታ ቢጠይቅ ጥሩ ነበር። እንደዚህ ዓይነት ነገር የማድረግ የሞራል ከፍታ ያለው ሰው በመንግሥቱ ስብስብ ውስጥ ስለሌለ ይህን አልጠብቅም።

ለሌላው ግን ፈተናውን በይፋ የመልቀቁ እና ጣልቃ የመግባቱን ጉዳይ መቀበል ወይም አለመቀበል፥ ሕገወጡን ስርዓት በሕግ እንዲገዛ ለማድረግ የሚደረገውን ትግል የመቀበል ወይም ያለመቀበል ጉዳይ ነው። To be or not to be there when you are needed.

ነበርን!!

$
0
0

Tensaye

ባንዶችን ዛቢያ አርገው በምሳር ሳይቆርጡን፣

የጀግንነት ካስማ የእምነት ዛፎች ነበርን፡፡

ልሃጫሞች ብለው ከርሳሞች ሳይሰድቡን፣

ለክብር የምንሞት ቆፍጣናዎች ነበርን፡፡

አረቦች ፈረንጆች በመረብ ሳይጠልፉን፣

ቀጥ ብለን እምንሄድ ጎምላላዎች ነበርን፡፡

ንቦች አስመስለው ዝንቦች ሳይልኩብን፣

በዘር ያልተለከፍን ጤነኛዎች ነበርን፡፡

ዝንቦች ያመጡብን የዘሩ በሽታ፣

ከኤድስ ከኢቦላ ከካንሰር የከፋ፡፡

የቅኝ ገዥዎች ጎርፍ ያላነቃነቀን፣

የዘር ቋንቋ ጅረት ጠራርጎ ወሰደን፡፡

አይ እኛ!

የፍቅር ኃይል ሳይሆን ገንዘብ አሽኮርምሞን፣

ፈረንጁ አፍሪካዊው ቻይና ሳይቀር ደፍሮን፣

አልጫ ለንቦጫም አይነ-ቆብም ሳንሆን፣

ደም ግባት የዋጠን ውበታሞች ነበርን፡፡

 

ህንድ አራሚ ቀጥሮ ምራቅ ሳይተፋብን፣

አረብ ገረድ አርጎ ልጋግ ሳይጥልብን፣

ወግድ ተዚህ ባዮች ሞገደኞች ነበርን!

አረብና ፈረንጅ ሴራ ሳይፈትሉብን፣

አህያ ፈንጅ ጭነው በጃዙር ሳይወሩን፣

ፈንጁም ፈነዳድቶ ክፍል ሳያደርገን፣

የጀብዱ ጋራዎች ተራራዎች ነበርን!

ሊደፍሩን ሲቃጡ ዝቅዝቅ ደፍተን ያየን፡፡

ነበርን!!

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

ግንቦት ሁለት ሺ ስምንት ዓ.ም.

ኮለኔል ጎሹ ወልዴ (ወታደር፤ምሁር፤ዲፕሎማት)

$
0
0

አብዮታዊዉ የደርግ መንግስት የሶሻሊስትን መንገድ ያስጠኑትን የቀድሞ ወዳጆቹን በተለያየ መንገድ ካገለለ በሗላ ልጓሟን እንደበጠሰች በቅሎ ግራ ሲጋባ ነበር ኮለኔል ጎሹ በመብራት ተፈልገዉ የመጡት። ምንም እንኳን የደርግ ዘመን የጨለማ ዘመን ቢሆንም ሰዉ በዘሩ መጠቃቀሙ የሚታሰብ ስላልነበረ ኮለኔል ጎሹም ዘራቸዉ ከግምት ሳይገባ በችሎታቸዉ ብቻ ተለክተዉ የሚገባቸዉን ወምበር አገኙ። ኮለኔል ጎሹ  ስልጣን ከተረከቡ በሗላ ኢትዮጵያን በታላቅ ክብር በየአለሙ መዲና ሲወክሉ፤ ኢትዮጵያን ከክፉ ጠላቶች ያለእረፍት ሲከላለከሉ ከቆዩ በሗላ  የደርግ መንግስት ስራዉ ሁሉ መረን የለቀቀ ከመሆኑም በላይ የምእራብ ሀገሮችም አይንህ ላፈር ስላሉት  ሊመከር  የማይችል መሆኑን የተገነዘቡት ኮለኔል ጎሹ ከሚያጓጓ ወምበራቸዉና ክብራቸዉ በታሪክና በህዝብ  ተወቃሺ ላለመሆን እንደእኔዉ ሳይወዱ በግድ ሀገራቸዉን ጥለዉ ተሰደዱ። ማንም ጤናማ አስተሳሰብ ያለዉ ዜጋ በወቅቱ ከዚህ የተለየ ምርጫ አይወስድም ነበር ።

goshu welde

ኮለኔል ጎሹ እንደሳቸዉ ትዉልድ በጥሩ ኢትዮጵያዊነት መንፈስ ታንጸዉ ለሀገራቸዉ አንድነትና ለባንድራቸዉ የማሉ መኮንን ነበሩ።  ከዉትድርና ተቋሙ በብቃትና በጥራት የፈጸሙ  ለመሆናቸዉ  አዉሮፓ በነበርኩበት ጊዜ በአንድ ስብሰባ ከአስልጣኛቸዉ ከጄነራል ነጋ ተገኝ አፍ  ሰምቻለሁ ተከታታይ ስራቸዉም ይህንኑ ያንጸባረቀም ነበር።ኮለኔሉ በወቅቱ የአዉሮፓ ጉዟቸዉ ወያኔን በሀይል ለመናጥ ያዘጋጁትን ድርጂት ለማስተዋወቅ ነበር።  በዚሁ  ስብሰባ ኮለኔል ጎሹ ከተናገሩት መሪ ቃል “ይህ ወጣት ምንም ማድረግ ቢያቅተዉ ስለ ሀገሩ እንዴት መቆጨትና መናደድ ያንሰዋል” ብለዉ የተናገሩት ለረጂም ጊዜ የመወያያ አርስት ሁኖ ሰንብቷል። በእርግጥም ጥሩ አባባል ነበር።

ኮለኔል ጎሹ ወታደር ፤ ምሁር እና ዲፕሎማት ናቸዉ  በዋሉበት ቦታ ሁሉ ድምቀት  የተሞላባቸዉ ፡ በቆሙበት ቦታ ረትተዉ ፤ተደምጠዉ፤ ተደንቀዉ ፤መክተዉ የሚመለሱ ታላቅ ኢትዮጵዮጵያዊ ነበሩ። አንባቢ ለአንድ አፍታ በስዩም መስፍን እግር የባድሜንና ሌሎች ለሻቢያ የተሰጡትን መሬቶቻችንን ክርክር ኮለኔል ጎሹ ይዘዉት ቢሆን ኑሮ ብሎ በምናቡ ያስብ። ስዩም መስፍን ከጠበቅነዉ በላይ ተሰጠን ብሎ ህዝቡን አስጨብጭቦ እሱም አጨብጭቦ በዛ በተዛባ ድርድር ምክንያት የ70 ሺህ ኢትዮጵያዊ ህይወት ተቀጠፈ ወላድ በየቤቱ ይላቀሳል አዝማቾቹ እነ ስዩም መስፍን ስብሀት ነጋ እና ሌሎቹም በየቤቱ ይስቃሉ። ስለዚህ ጉዳይ ታሪክ ወደፊት በሚገባ ያወጣዋል። በስዩም መስፍን ስንገረም ሌላዉ ትያትረኛ  ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም የ9 አመት ልጂ 8 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ አደረገችልን ብሎ ባለም ያሳቀብንን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስተራችንንም ከኮለኔል ጎሹ አንጻር አንባቢ ደምሮ ይመልከትልን :: ታድያ ወደ ጉዳዬ ስመለስ ኮለኔል ጎሹ አገልግሎታቸዉን በብቃት፤በድፍረት  እንዲሁም ፕሮፌሺናል ኤቲክስ በሚፈቅደዉ መስፈርት በጥራት የተወጡ ዜጋ እንደነበሩ  ኢትዮጵያን እንዲህ ያለ ችግር በገጠማት ጊዜ ጉዳዩን እሳቸዉ ይዘዉት ቢሆን ኑሮ ዉጤቱ ሌላ ይሆን ነበር።

ኮለኔል ጎሹ በእዉቀት ደረጃም በሁለት እጂ የማይነሱ ምሁር እንደነበሩና እስከ አሁንም አስመዝገበዉ ያለፉት ነጥብ ያልተደፈረ መሆኑን እናዉቃለን ከሚሉ ሰዎች ይደመጣል። ወደ ሗላም ወደ ባህር ማዶ ተሻገረዉ ከስመ ጥሩዉ ዬል ዩኒቨርስቲም አድናቆት የተቸራቸዉ እንደነበረ ድርሳናት ያሳያሉ። ከዉትድርና ትምህርት ባሻገር በህግ የረቀቀ እዉቀትና ችሎታ ያላቸዉ ኮለኔል ጎሹ እራሳቸዉን ከአንድ አርእስት ወደ ሌላዉ አርስት በመወረወር በተነሳዉ ነጥብ ሁሉ በሳል አስተያየትን  ሰጥተዉና አስተምረዉ የሚመለሱ ዜጋ በመሆናቸዉ ለዲፕሎማቲክ ስራ ተቀራራቢ ሰዉ ሊገኝላቸዉ የማይችሉ ኢትዮጵያዊ ነበሩ።

ኮለኔሉ በዲፕሎማሲያዊ ስራ እና ለህዝብ ይፋ ካልወጣዉ አስተዋጽዋቸዉ ሌላ ምን ሰርተዉ ነበር  ብሎ መጠየቅ የዜጋ መብት ነዉ ኮለኔል ጎሹም የህዝብ ሰዉ በመሆናቸዉ ይህ ቅር የሚላቸዉ አይመሰለኝም።

የትግራይ ነጻ አዉጭ ድርጅትና ሻቢያ አገሪቱን ከተቆጣጠሩ በሗላ ሊደርስ የሚችለዉ አደጋ ቀደም ሲል ስለገባቸዉ ጠንካራ ድርጅት አቋቁመዉ ኢትዮጵያን ከነዚህ ክፉ ጠላቶች ለማዳን ጥረት አድርገዉ ነበር:: ታዲያ እንደ ኮለኔል ጎሹ፤ፖል ትዋት፤ኢንጂነር ቅጣዉ፤ኮለኔል ታደሰ  አይነት ዜጋ የሚመራዉ ድርጅት ፈተናዉ ብዙ በመሆኑ የኮለኔል ጎሹንም ድርጅት የኢትዮጵያ ጠላቶች ከዉስጥና ከዉጭ ተረባርበዉ በለጋነቱ ጣሉት የኮለኔል ጎሹም ሀሳብ ዉጥን ብቻ ሁኖ ቀረ እንደ አንድ መሪ ግን የሚቻላቸዉን አደረጉ በዚህ ሊመሰገኑ ይገባል።

ኮለኔል ጎሹ አገር ከፈረሰ በሗላ በእጂጉ ከሚታወቁበት ትልቁ ስራቸዉ የአሜሪካን ሴናተር በጠራዉ ስብሰባ ላይ ከሻቢያና ከወያኔ ጋር  ያደረጉት ፍልሚያ ነበር።  ይህ ህዝብ የጣለዉን መንግስት ጣልን ብለዉ በለስ ቀንቷቸዉ  ሸብ ረብ በሚሉበትና እንደ መንትዬ ልጆች  ሻቢያ የጀመረዉን ወያኔ በሚጨርስበት የስብሰባ ስርአት ያደረጉት ንግግር በታሪክ ዘወትር ሲታወስ ይኖራል። ኮለኔል ጎሹ ብቻቸዉን ያለአንዳች ረዳት ይህን የበታኝ መንጋ  ሲለበልቡት አብረዋቸዉ የተቀመጡት ትንፍሺ ሳይሉ ወጥተዉ ሂደዋል የዛን ቀን ሁኔታቸዉም ከአንዱ የአፍሪካ ሀገር ለታዛቢነት የመጡም አስመስሏቸዋል። ምክንያቱም በለስ ከቀናዉ ሀይል ጥቅም አይጠፋም በሚል ምክንያት በስብሰባዉ ላይ አድፍጠዉ ተቀምጠዉ ነበር:: በሗላም እንደ አምቦ ወንድሞቻችን የኢትዮጵያ ህዝብ ጨክኖ ወያኔንና ሻቢያን እንዳይፋለም አንዴ ጊዜ ስጧቸዉ አንዴም የኛዉ ናቸዉ እያሉ ሲያጃጂሉን ከርመዉ ዛሬ ዉቃቤ ርቋቸዉ ከአንዱ ጎል ወደ ሌላዉ ጎል እራሳቸዉን እየለጉ እለተ ሞታቸዉን ይጠብቃሉ።

ታዲያ አድር ባይነትን ባእጂጉ የተጠየፈዉ  ጀግናዉ የኢትዮጵያ ልጅ ጎሹ ወልዴ ግን በዛን ስብሰባ ብቻዉን ግዳይ ጥሎ ገብቷል።

ጎሹ በዛን ቀን በሰራዉ ስራ ስሙና ተጋድሎዉ ሀገሩን በሚወድ ዜጋ እስከ ወዲያኛዉ ሲታሰብ ይኖራል።  ዛሬ ነገር አልፎ ቀላል ቢመስልም በዛን በቀዉጢ ጊዜ አባሎቻቸዉ መረን በወጡበት ዘመን ደፍሮ ሀገሩን ብቻዉን  መክላከሉ ሀገሩን በሚወድ ዜጋ ዘወትር ሲታሰብ ይኖራል። እንደዉም የእዉቀቱን ጥልቀት የተረዳዉ የስብሰባዉ ሊቀ መንበር ምን ብናደርግ ይሻላልም ብሎ ሀሳብ ጠይቆ ጎሹም ጥራት ያለዉ መልስ ሰጥቶ ነበር።በዛን ቀን ኮለኔል ጎሹ ባሳየዉ ወታደራዊ መንፈስ፤ የነገር አወራረድ፤ የሃሳብ ብስለት፤ የቋንቋ ጥራትና የታሪክ እዉቀት  የተገረመዉ ሴናተር በተመስጦ ሲመለከተዉ ደናቁርቱ ባላንጣዎቹ ደግሞ በክንድ ጠምዝ ምልልስ የጀግናዉ ጎሹን ወልዴን ሀሳብ ሊመክቱ ሲታገሉ በእጅጉ ያሳዝኑ ነበር። በዛን ቀን በተሰራዉ ስራ ኮለኔል ጎሹ ያለምንም ተቀናቃኝ እራሱን  ከታላላቁ ጎራ ቀላቅሏል። ያም ስራዉ ተቀራራቢነቱ ለሀገራቸዉ ታላቅ ስራ ሰርተዉ ካሸለቡት ዜጎች እንደ አንዱ ሊሆን ይገባዋል።  ድልንና ታላቅ ስራን  የምንመዝነዉ እንደ ዘመኑ በመሆኑ ጀግናዉ ጎሹ ወልዴም በዛን ቀን በሰራዉ ስራ ታሪክ እስከ ወዲያኛዉ ሲያስታዉሰዉ ይኖራል።  (እዚህ ላይ ነሸጥ አድርጎኝ አንተ ብያለሁ መቼም ጀግና እርሶ አይባልምና)

እንግዲህ ከአንድነት ሐይሎች ሰፈር ኮለኔል ለመገለላቸዉ  ምን  ምክንያት ሊሰጥበት ይችላል? በእርግጥ ዘመኑ የጨረባ ተዝካር የሆነበት፤ ከአዋቂ ይልቅ ተናጋሪ የተደመጠበት፤ ከአንድነት ይልቅ ልዩነት የተመረጠበት ፤ያለዉን ከመያዝ መበተን የተያዘበት፤ ከሀቅ ይልቅ  ትርፍ በሚያመጣ ነገር ላይ ማተኮር የተመረጠበት በመሆኑ ይህ ደግሞ ለኮለኔል ጎሹ ስብእና የሚስማማ ባለመሆኑ ዳር ሁነዉ መመልከትን መርጠዉ ይሆናል የሚል ግምት አለኝ። ትላንት በካድሬነት ሲያገልግሉ የነበሩ የሶሻሊስት ደቀ መዛሙርት ዛሬ ተገልብጠዉ የዘዉግ አስተዳደር ለኢትዮጵያ መፍትሄ ነዉ ብለዉ የሚሰብኩትንም ላለማየት ፈልገዉም ይሆናል ወይም ደግሞ ኤርትራ በሀይል ተገንጥላ ስትሄድ ፓርላማ ቁጭ ብለዉ ሲያጨብጭቡ ከነበሩ ፓርላሜንታሪያንም ጋር በአንድ መድረክ ላለመቀመጥም መንፈሳቸዉ ተጠይፎም ሊሆን ይችላል። ወይም ደግሞ 100,000 ጦር ኢሳይያስ አፈወርቀ ላይ አዝምቶ ዛሬ ኢሳይያስ አፈወርቅ የኢትዮጵያ ወዳጂ ነዉ የሚለዉን ላለመስማት ፈልገዉም ሊሆን ይችላል። ምሁር ተብየዎችም ኢትዮጵያ የማትጠቀምበት እምቅ ሀብት አላት ኑና ዉሰዱ ብለዉ የጥንት አፍራሺ ጓደኞቻቸዉን መታረቂያ ያደረጉት ስብሰባም ሳይመቻቸዉ ቀርቶ ይሆናል።

እንግዲህ ዛሬም እንደ ትላንቱ ለሌላ ጥፋት በየቦታዉ በሚደረገዉ ስብሰባም መገኘት ያልፈለጉበት ታሪክ እራሱን ሲደገም ድንጋይ አላቃብለም ብለዉም ሊሆን ይችላል።  ከዚህ ታክኮ የዘር ድርጅቶች በየምክንያቱ በራቸዉን ሲያንኳኩም የለም ይህ እኔን አይመለከትም ዘሬ ኢትዮጵያዊ ነዉ በጽናት እስከ ኢትዮጵያዊነቴ በክብር እንደ አንድ ወታደር እሞታለሁ ብለዉ እንደሚመልሱም ጥርጥር የለኝም። የተለያዩ የሚዲያ ተቋማትም ጎትተዉ  ባልፈለጉትና በማይመቻቸዉ  አርእሰት አስገብተዉ እንዲያዘላብዷቸዉ ሳይፈቀዱም ቀርተዉ ይሆናል።

ኮለኔል ጎሹ ኢሳይያስን ነጻ አዉጣኝ ብለዉ ያልተማጠኑ፤ለኢትዮጵያ የሚጠቅመዉ በዘር መከፋፈሏ ነዉ ከኢትዮጵያዊነት በላይ ዘራችን ቅድሚያ ሊሰጠዉ ይገባል ታሪካችንም  100 አመት አይበልጠዉም ከሚለዉ ዘመን አመጣሺ በሺታ ተከልለዉ መቀመጣቸዉ መልካም ቢሆንም ለተተኪዉ ትዉልድ የሚጠቅም ብዙ ደጎስ ያሉ መጻፍቶችን ቢያስነብቡን በሪፈረንስ መልክ አጠገባችን ይቀመጥ ነበር የሚል እምነት አለኝ። ለማንኛዉም በኔ በኩል መልካም ጤንነትና እድሜ እየተመኘሁ ከግራ ቀኝ የሚላተሙ የእርሶ ዘመን ሰዎችም የኢትዮጵያዊነትና አንድነት ማተባቸዉን ጠብቀዉ በክብር ወደማይቀረዉ ለመሄድ ቢዘጋጁ መልካም ነዉ እላለሁ።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

ሰመረ አለሙ semere.alemu@yahoo.com

በግምት የሚመራው መንግስት ትናንት የተቋረጠውን ፈተና የረመዳን ጾም ፍቺ ቀን ፈተናው ይሰጣል አለ

$
0
0

fetena 44

(ዘ-ሐበሻ) የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ሽፍራው ሽጉጤ ትናንት የተቋረጠውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በአዲስ መልክ የሚሰጥበትን ቀን ይፋ አደረጉ:: ሚኒስትሩ ፈተናው ከሰኔ 27 እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ ይሰጣል ያሉ ሲሆን ከነዚህ እለት አንዱ የረመዷን ጾም መፍቻና የኢድ አልፈጥር በዓል የሚውልበት ዕለት ነው::

ምን ያህል መንግስት ተብሎ የተቀመጠው ስርዓት ነገሮችን በግምት እንደሚመራ ያሳያል የሚሉት አስተያየት ሰጪዎች ሚኒስትርን የሚያህል አንድ ስልጣን የያዘ ሰው የፈተና ቀናትን ሲናገር እንዴት ዓመት በዓሉች እና የመንግስት በዓላት የሚዘጉበትን ቀናት ካላንደሩን ከፍቶ አይመለከትም? ሲሉ ይጠይቃሉ::

ከኢትዮጵያ ሕዝብ መካከል 33.9%, የሚሆነው የ እስልምና እምነት ተከታይ ሆኖ እያለ እንዲሁም የዘንድሮውን የሚኒስትሪ ፈተና ይወስዳሉ ከተባሉት በመቶሺዎች ከሚቆጠሩ ወጣቶች መካከል በርካቶቹ የ እስልምና እምነት ተከታዮች መሆናቸው እየታወቀ በረመዷን ጾም ፍቺ እለት ፈተና ይወስዳሉ ብሎ ማወጅ ምን የሚሉት እብደት ነው? የሚሉ አስተያየት ሰጪዎችም አሉ::

አቶ ሽፈራው ለመንግስት ቅርብ ለሆኑ ሚድያዎች እንደተናገሩት ሀገር አቀፍ ፈተናው በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጥናትና ምርምር ማዕከል አማካኝነት በከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚዘጋጅና ባለሙያዎቹ ተፈታኝ የስጋ ዘመድ እንደሌላቸው ተረጋግጦ በፈተና ዝግጅት ይሳተፋሉ ብለዋል:: አሁንም ፈተናው እንዳይሰረቅ ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ከሕትመቱ እስከ ስርጭቱ ድረስ እንደሚደረግ አስታውቀዋል::

የወያኔ ውድቀት የአደባባይ ምሥጢር መሆኑን የሚያመላክት አጋጣሚ –ማስተዋል በለጠ

$
0
0

ማስተዋል በለጠ (ከአዲስ አበባ)

Jarsoከደቂቃዎች በፊት ከአንዱ የመሥሪያ ቤቴ ቅርንጫፍ ወደ ዋናው መ/ቤት ስመጣ እንዲህ ሆነ፡፡ መኪናዋ ውስጥ  በተላላኪነት የምትሠራ አንዲት ወጣት፣ ሹፌራችንና እኔ ብቻ ነን የነበርነው፡፡ የዛሬው ቀን የከተማችን ወሬ የሆነውን የማትሪክ ፈተና መሰረቅ አነሳሁና የተለጎመውን የሦስታችንንም አንደበት በጋራ የሀገር ጉዳይ ከፈትኩት፡፡ በዚህን ዓይነት ሁኔታ እኔ ብዙውን ጊዜ ነገር እለኩስና ዋና ሥራየ ማዳመጥ፣ ማዳነቅና ማውጣጣት ነው፡፡ ቀዳሚው ሥራየ ግን የማዋራቸው ሰዎች በኔ ላይ እምነት እንዲኖራቸው ጥረት ማድረግ ነው፤ ሰው ከተጠራጠረህ የልቡን አይናገርም፡፡ ዝም ሊል ወይም ሊዋሽህና ሊያታልልህም ይችላል፡፡

ሹፌራችን ቀጠለ –  የኦሮምኛ ቅላፄው በሚነበብበት የሚጣፍጥ ዐማርኛው፡፡ “እኔ እምፈራው የማትሪኩስ መሰረቅ ቀላል ነው – እኔ እምፈራው እነዚህ ሌቦች ኃይለማርያምን ወይም ሌላውን ቱባ ባለሥልጣን እንዳይሰርቁ ነው፡፡ እንዴ! እንዲህ ያለ ነገር እኮ ተሰምቶ አይታወቅም፡፡ …” ሦስታችንም ሣቅን፡፡ ኃይማርያምን ሰርቀው ምስሉን በፌስቡክ እያሳዩ “ተላላኪ ሮቦት አሽከራችሁ እኛ ጋ ነውና ከፈለጋችሁት አንድ ሺ አምስት መቶ ብር ከፍላችሁ ልትወስዱት ትችላላችሁ” ሲሉ እየታየኝ እኔማ ፍርፍር ብዬ ነው የሳቅሁት፡፡ ደግሞስ ደብረጽዮንን ወይም ዐርከበን የሚሰርቁ ሰዎች ሰርቀው ሲያበቁ “ስብሃት ነጋንና አባይ ፀሐዬን ሰርቀናችኋል፡፡ እኛ ጋ ናቸውና ለያንዳንዳቸው አምስት መቶ ሚሊዮን ዶላር ከፍላችሁ የምትወስዱ ከሆነ በጃችን ውስጥ የሚገኙትን ተሾመ ቶጋ ሙላቱንና ደመቀ መኮንንን እንደምርቃት በነፃ እንሰጣችኋለን፡፡” ሲሉ በምናቤ እየታየኝ የብቻ ሣቄን ቀጠልኩ፡፡ – ደብረጽዮንና ዐርከበ ብልጥ ስለሆኑ በቀላሉ አይሰረቁም ብዬ ነው ሳላስፈቅዳችሁ የለወጥኳቸው፡፡

ሴቲቱም የዋዛ አይደለችም፡፡ “እንዴ! ግን ግን እዚህ አገር መንግሥት አለ ማለት ይቻላል? ይሄ ነገር እኔስ እውነት አይመስለኝም፡፡ ወዴት እየሄደች ነው አገሪቱ? ብለው ብለው ፈተና ያሰርቁ? ሌላው ዓለም ሲሰማ ምን ይለናል? ከእንግዲህስ በምን መተማመን ይቻላል? መንግሥትንስ እንዴትና በምን እንመነው? በጣም አደገኛ ጊዜ ውስጥ ነው ያለነው፡፡” ጎበዝ ተናጋሪ ናት፡፡ ከጠበቅኋት በላይ ምጡቅ የሆነ ፖለቲካዊ ግንዛቤ አላት፡፡ ሁሉም ነቅቷል፡፡

ቢሮ ገብቼ ይህችን ማስታወሻ ለመከተብ ያነሣሣኝ ግን የሹፌሩ አንድ አስተያየት ነው፡፡ ከአንድ እምብዝም ካልተማረ አሽከርካሪ በፍጹም ያልጠበቅሁትን ነገር ነው የተናገረው፡፡ ይህ ንግግሩ የብዙዎች ዜጎችን አተያይና እምነት እንደሚወክል አልተጠራጠርኩም፡፡

እንዲህ ነው ያለኝ፡፡ “አሁን በውነቱ ወንድ ጠፋ እንጂ እነዚህን ሰዎች በቀላሉ ማስወገድ በተቻለ ነበር፡፡ ግን ሰው ጠፋ፡፡ የሚደፍር ጠፋ፡፡ ቤተ መንግሥቱ እኮ አሁን ባዶ ነው፡፡ ልብ ያለው ቢገኝ በትንሽ መስዋዕትነት አንድ ወር እንኳን ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እነዚህን ቀን የሰጣቸውን ባለጌዎች ከሥልጣን ማባረር ይቻላል፡፡ ግን ማን ይድፈር? እንጂ አሁን እነሱ ምናቸው ይፈራል? ሕዝብ የጠላቸው አረመኔዎች ናቸው፡፡ ከነሱው አባሎች ውጪ አንድ ሰው አይወዳቸውም፡፡ አብሯቸው የሚንጋፈፈውም ዜጋ ለሆድ እንጂ ለዓላማ አይደለም፡፡” ጭንቅላቴ በርሮ የሚጠፋ እስኪመስል አንገቴን እያወዛወዝኩ በአንክሮ አዳመጥኩት፡፡ እውነቱን ነው፡፡ ብዙዎቻችን የምንለውም ይሄንኑ ነው – መናገርና ማድረግ ይለያያሉ እንጂ፡፡ ወያኔዎች ሞተውም እንደሚኖሩ ያረጋገጥኩት በዚህ ልጅ አነጋገር ነው፡፡ እርሱ እንኳን ባቅሙ የወያኔን ወቅታዊ ሁኔታ ጠንቅቆ አውቋል፡፡ በርግጥም እኮ ፍርሀታችንና በፍርሀታችንም ምክንት መደራጀት አለመቻላችን እንጂ እነሱ እኮ አልቆላቸዋል፤ በንፋስም የሚወድቁ ይመስለኛል፡፡ የሚጥላቸው ቢጠፋ በውነትም በራሳቸው ሳይገነደሱ አይቀሩም፡፡ ሀገሪቱ በነሲብ መሽቶ ይነጋላታል፡፡ በጠፋ ፍትህ፣ በጠፋ እህል ውኃ፣ በጠፋ መልካም አስተዳደር፣ … እንዲሁ በግምት እንኖራለን እንጂ አንድም ጠያቂም ሆነ ተጠያቂ የለም፡፡ ባዶ ሀገርና ባዶ መንግሥታዊ መዋቅር፡፡ ኢትዮጵያ መንፈሱ የላሸቀ ሕዝብና ተስፋ ያጣ ትውልድ የሚርመሰመስባት በከፍተኛ ፍጥነት እየወደመች ያለች ሀገር ናት፡፡ ለነፃነቷ ቆመናል የምትሉ ቶሎ ድረሱላት፡፡…

ሦስታችን ብዙ ተወያየን፤ ችግሩ ግን ወዲህ ነው፡፡

አንድ ወቅት ዐይጦች ተሰበሰቡ አሉ፡፡  አንድ ዕድሜ ጠገብ አረጋዊ ዐይጥም እንዲህ ሲሉ ጉባኤውን ከፈቱ አሉ፤ “ጎበዝና ጎበዛዝት ማኅበረ-ዐይጥ! እንኳን ደህና መጣችሁ፡፡ የዛሬው ጉባኤያችን የሚያተኩረው የዘመናት ባሕርያዊ ጠላታችንን የድመትን ጥቃት እንዴት መከላከል እንደምንችል በመዘየዱ ዙሪያ ነው፡፡ በድመቶች ጥቃት ያልደረሰበት ዐይጥ መቼም በመካከላችን ይገኛል ብዬ አላምንም፤ ልጁን፣ አባቱን፣ እናቱን፣ ወንድሙን፣ አክስቱን ወይ አጎቱን በድመት ያላጣ ዐይጥ በመካከላችን ይኖራል? በጭራሽ አይኖርም፡፡ እናስ? ምን ብናደርግ ይሻላል?…”

ውይይቱ ጦፎ ቀጠለ፡፡ በመጨረሻም በድመቶች አንገት ላይ ቃጭል በማሰር ዐይጦችን ሊለቅሙ ሲመጡ ቃጭሉ ይጮሃልና በዚህ የማስጠንቀቂያ ደወል ማኅበረ-ዐይጥ ወደየጉድጓዷ እንድትገባ ቢደረግ ጥሩ እንደሆነ ስለታመነበት ይህ ሃሳብ በአብዛኛው ውሳኔ-ዐይጥ አለፈና ፀደቀ፡፡ ጉባኤው በውሳኔው አጨብጭቦ ሊበተን ሲል ግን አንዲት ብልህና አስተዋይ ዐይጥ ጥያቄ እንዳላትና መናገር እንደምትፈልግ ለመድረክ መሪው የተከበረ ዐይጥ አሳወቀች፡፡ ቀጠለች – “ሃሳቡና ውሳኔው በመሠረቱ በጣም ቆንጆ ነው፡፡ ነገር ግን ማነው ይህን ቃጭል በድመቶች አንገት ላይ የሚያስር?” – ጉባኤተኛው በጥሞና ያላሰበበት ጥያቄ ነበርና ውሳኔው በእንጥልጥል እንዲቆይ ተደርጎ የዕለቱ ስብሰባ አለውጤት ተበተነ፡፡

እኛስ? ከግርጌ እስከራስጌ በዘረኝነት ደዌ በበሰበሰና በገለማ ወያኔያዊ የአፓርታይድ  ሥርዓት እየተቀጠቀጥን እንኑር ወይንስ “ከዘላለም ባርነት የአንድ ቀን ነፃነት” ብለን ሁላችንም በሰ-ሰዓት(ወታደራዊ ቃል ነው) በመነሣት ቢያንስ ለልጆቻችን የምትሆን ሀገር እንፍጠር? የአሁኑ ጥያቄ በሼክሽፒራዊ አገላለጽ የመሆንና ያለመሆን ጥያቄ ነው፡፡ ሀገራችን ከዚህ በላይ ልትዋረድ አትችልም፡፡ ወያኔዎች ጥምብርኩሳችንን አውጥተውታል፤ ያበለሻሹትን ነገር ለማቃናት ራሱ በጣም ብዙ ዓመታትን ይፈጅብናል – ዛሬ ማታ እንኳን ነፃነትን ብናገኝ ማለቴ ነው፡፡

(ትዝ ያለኝን አንድ ነገር በቅንፍ ልጡቁምና ላብቃ – ሰሞኑን ወደ አንድ የምርት ማሣያና መሸጫ መንግሥታዊ ግቢ ከጓደኞቼ ሄጄ ነበር፡፡ በግቢው ብዙ ድንኳኖች ተጥለው ንግድ ይጧጧፋል፡፡ ጥሎብኝ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሰዎችን ነገዳዊ ማንነት እቃኛለሁ፡፡ በዚህ ግቢ ውስጥ በታዘብኩት ነገር እጅግ አፈርኩ፤ ደነገጥኩም፡፡ አብሮኝ የነበረ አንድ ሰሜነኛ ጓደኛየ ራሱ በውስጡ ሣያፍር አልቀረም፤ ከሞላ ጎደል የሁሉም ድንኳኖች ባለቤቶች ትግርኛ ተናጋሪ ናቸው፡፡ ቦታው ሜክሲኮ አካባቢ የሚገኘው አነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች የሚሉት ስለሆነና ኤግዚቢሽኑም እስከ ልደታ አካባቢ ስለሚቆይ ማንም ሰው ሄዶ ማረጋገጥ ይችላል፤ በመዋሸት የምጠቀመው ነገር የለምና አልዋሸኋችሁም፡፡ ግን ለምን እንዲህ ያለ ጭፍን ያለ መድሎ ይደረጋል? ሌሎች አላመለከቱ ሆነው ነው ወይንስ ዕድሉ ተነፍጓቸው ይሆን? ጤነኛ ነን የምትሉ የሕወሓት አባላት ይህን ዓይነቱን ዐይን ያወጣና መረን የለቀቀ አድልዖ ተመልከቱና ወደኅሊናችሁ በመመለስ በመጠኑም ቢሆን ለማስመሰል እንዲሞከር ጥረት አድርጉ፡፡ በጣም ያሳዝናል፡፡ ሁሉም ያልፋል፤ ትዝብትና ማኅበራዊ ቁስል ግን ዝንታለሙን እየነፈረቀ ሲያገረሽ ይኖራል፡፡ አብረው በኖሩና በሚኖሩ ማኅበረሰቦች መካከል እንዲህ ያለ ከፋፋይ ሥርዓት አበጅቶ ዜጎች የጎሪጥ እንዲተያዩና “የኔ ጊዜ” “ያንተ ጊዜ” በሚል ጎራ ለይተው፣ ቀን ቆርጠው እንዲበዳደሉ ማድረግ ነውር ብቻ ሣይሆን በታሪክ የሚያስጠይቅ ትልቅ ወንጀል ነው፡፡ ወያኔዎች ሆይ! ምክሬ ያጥፋችና ሃይማኖትም ይኑራችሁ ግዴላችሁም፡፡ ዘመናችሁ የመሸና የጨላለመ ቢመስልም ግዴላችሁም አሁንም ቢሆን ወደኅሊናችሁ ተመለሱ፡፡ ከብቶች ብቻ ናቸው የባሕርይ ለውጥ ሳያሳዩ የሚያረጁና የሚሞቱ፡፡ እናንተ ግን ሰው ስለሆናችሁ – ከሰውም ማነስ የለባችሁምና ቢያንስ አሁን እንኳን እንስሳዊ ባሕርያችሁን ለመለወጥ ሞክሩ፡፡ ለአእምሮ ትንሽ ጊዜ ሰጥቶ እንዲያስብ ማድረግ እኮ ነው – ለዚህ ትልቅ ፍጡር ዕድል ስጡት – እስካሁን  ከርሳችሁ ውስጥ ወሽቃችሁት ስትጨቁኑት ነበር – አሁን ግን ለርሱም ፋታ ስጡት፤ ዐውሬነት ይብቃችሁ፤ ክፋትን የዘወትር ልብስ ማድረግ አይሰለችም? ከስሜት ወጥታችሁ ለአንጎላችሁ ጊዜ ከሰጣችሁት የእስካሁኑ ሸፋፋና ወልጋዳ አመጣጣችሁ ሁሉ ቁልጭ ብሎ ይታያችሁና ወደ ደጉ መንገድ ትመለሳላችሁ – እኛስ ብንሆን አናሳዝናችሁም? በጋራ ሀገራችን እናንተ እንዲህ ስትዘባነኑ እኛ ደግሞ በተቃራኒው ስናለቅስና ዕንባችንን ወደላይ ስንረጭ ለናንተስ ደግ ነው? “ልጅ አይውጣላችሁ! ጥቁር ውሻ ውለዱ! ኤ! የናንተን መጨረሻ ያሳየኝ!…” ተብሎ መረገምስ የኋላ ኋላ መቅሰፍትን እንጂ በረከትን የሚያመጣ ይመስላችኋል? በእናንተ ሰበብ ቅኑና ደጉ የትግራይ ሕዝብስ ለምን በቀጣይ ታሪክና በተከታታይ ትውልዶች እንዲወቀስ ታደርጋላችሁ? ኧረ ልብ ግዙ! ጭንቀቴ ስለናንተም ነው – ለኛ ብቻ እንዳይመስላችሁ – ‹ቀኝ ኋላ ዙሩ›ም ከአሁኑ ባልተናነሰ ሊያሳስበን ይገባል፤”የገደለው ባልሽ የሞተው ወንድምሽ – አዘንሽ ቅጥ አጣ ከቤትሽም አልወጣ” ሲባል አልሰማችሁ ይሆን? ቸር ክራሞት ለሁላችንም፡፡)

 


የወያኔ ትምህርት ሚኒስቴር መግለጫ የኦሮሞን ህዝብ የእምቢታ ኣቅም ዳግም ያስመሰከረ ድል ነው

$
0
0

ቦሩ በራቃ

እነሆ የወያኔ ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ለሌላ ጊዜ እንዲዛወር ወስኗል። ውሳኔውን ያደረገው ደግሞ ወዶና ፈቅዶ ሳይሆን በኦሮሞ ህዝብ የተቀናጀ ትግል ተገዶ ነው። እንደሚታወቀው የኦሮሞ ተማሪዎችና ኣክቲቪስቶች ላለፉት ተከታታይ ሳምንታት በሰከነ መልኩ ያሰቡበትን ጥያቄ ሲያቀርቡ ነበረ። በኦሮምያ ለወራት እየተካሄደ ካለው ህዝባዊ ኣመፅ ጋር በተያያዘ የክልሉ ተማሪዎች በተረጋጋ መንፈስ ለፈተናው ባለመዘጋጀታቸው የፈተናው ወቅት ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከተውን የክልሉን ትምህርት ቢሮ ጠይቀው ነበር። የኦሮምያ ትምህርት ቤሮ ግን ይህንን ሞራላዊና ፍትሃዊ ጥያቄ ውድቅ የሚያደርግ መግለጫ ሰጠ። ፈተናው ከጥቂት የኦሮምያ ትምህርት ቤቶች በስተቀር በተቀረው ኣብዛኛው ኣካባቢ በተያዘለት ፕሮግራም መሰረት እንደሚስጥ ነበር ያስታወቀው።

shiferaw_shigute

ከዚህ የወያኔ ባለስጣናት ትእቢት የተሞላበት ምላሽ በሁዋላ ነበር የፈተናው መልሶች ሾልከው ወጥተው እንዲበተኑ በኦሮሞ ታጋዮች እርምጃ የተወሰደው። የእርምጃው ኣላማም የኦሮሞን ተማሪዎች ያገለለ ብሄራዊ ፈተና ከቶ ተቀባይነት እንደሌለው ለማሳየት ነው። ወያኔዎቹ ተሸንፈው የፈተናውን መስጫ ፕሮግራም ለሌላ ጊዜ ለማስተላለፍ ከተገደዱ በሁዋላ የእናቴ ቀሚስ ኣደናቀፈኝ እያሉ ናቸው። የፈተናውን መልስ ኦንላይን ላይ መልቀቅ ሞራላዊ ኣይደለም ኣያሉም ማጉረምረማቸው ኣስቂኝ ነው። ሞራላዊ ያልሆነውማ የገዛ የራሳቸው ትእቢት ነው። ለኦሮሞ ህዝብ ካላቸው ንቀት የተነሳ የብዙሃኖቹን ኦሮሞ ተማሪዎች ድምፅ መስማት ተሳናቸው። ኦሮሞን በገዛ ኣገሩ ላይ ሰላም ኣሳጥተው ተማሪዎቹ ትምህርት ኣቁዋርጠው እንዲታገሉ ማስገደዳቸው ሳያንስ ኣምስት ስድስት ወር ሙሉ ክፍል ገብቶ የማያውቀውን የኦሮምያ ተማሪ ሙሉ ጊዜውን በክፍል ውስጥ ካሳለፈው የሌላ ክልል ተማሪ እኩል መፈተን ኣማራቸው። ከዚህ በላይ ኢሞራላዊ ውሳኔ የለም።

የኦሮሞ ተማሪዎች ፋና ወጊ የሆኑበት የኦሮሞ ህዝብ ትግል እንዲህ ባሉት ጠላታዊ ውሳኔዎች ሳይበገር ተጠናክሮ ይቀጥላል። እነሆ በድል ላይ ድል እየደረበ የጠላቶቹን ኣንገት ኣስደፍቶ እየገሰገሰም ይገኛል። ‘Qabbanaahu harka, gubu fal’aana (ካላቃጠለ በእጅ ካቃጠለ በማንኪያ)’ እንደሚለው የኦሮሞ ብሂል ትግሉ በህጋዊ መንገድ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች ህጋዊና ፍትሃዊ ምላሽ ከተነፈጉ እጸፋውን እንዲህ ባሉት ኣይምሬ እርምጃዎች መመለስ ሞራላዊ ኣንጂ የሚያሰወቅስ ኣያደለም።

fetena2

የዚህ ፈተና መልስ ሾልኮ መውጣት ወያኔ ብቻም ሳይሆን ለሌሎችም ኣካላት ኣንድ ከባድ መልእክት ኣስተላልፏል ተብሎ ይገመታል። ‘እንዳያማህ ጥራው፣ እንዳይበላ ግፋው’ እንዲሉ የኦሮሞ ተማሪዎች ኣፋቸውን ተለጉመው በሚቀርቡበት ብሄራዊ ገበታ ላይ ሌሎቹም ነጻ የገበታው እድምተኞች ኣንደልባቸው መመገብ ኣይችሉም። በኣጭር ኣማርኛ ኦሮሞን ያገለለ ብሄራዊ ፈተና ለሌሎቹም የሚሳካ ፈተና ሊሆንላቸው ኣይችልም። ስለሆነም ኦሮምያ ውስጥ የሚካሄደው ትግል ድሉም ሆነ ውድቀቱ ለሌሎቹም ክልሎች እንደሚተርፍ ከዚህ ምሳሌ መረዳት ጠቃሚ ይመስለኛል። ከስድስት ወር በፊት ኦሮምያ ውስጥ የተፋፋመው የእምቢታ ኣመፅ ከኦሮምያ ኣልፎ በሌሎች ክልሎች የትምህርት ሂደት ላይ ተፅእኖ ያሳድር ይሆናል ብሎ ያሰበ ኣልነበረም። እድሜ ለወያኔ ትእቢት እነሆ ሌሎቹም ተርፎ ‘ጉዳዩ የማይመለከታቸው’ ክልሎችም ሰለባ ለመሆን በቁ። ስለሆነም የኦሮሞ ህዝብን የትግል እንቅስቃሴ ከኣገሪቱ ብሄራዊ ጉዳዮች ነጥለው መመልከት ኣልያም ኣናንቀው መዝለፍ የሚፈልጉ ወገኖች ሁሉ መሬት ላይ ማየት የተሳናቸውን ሃቅ የሚመለከቱበትን መነፅር በጊዜ ቢጠቀሙ ይጠቅማቸዋል።

የላቀ ምስጋና አቀርባለሁ (ሀብታሙ አያሌው)

$
0
0

  ቀን.23.09.08 ዓ.ም

ለተከበራችሁ ወዳጆቼ

ሀብታሙ አያሌው

ሀብታሙ አያሌው

ያለፉት ሁለት ዓመታት ለኔ ከባድ የመከራ ጊዜያት ነበሩ አሳሪዎቼ በነፍሴ ላይ ስልጣን ከማጣታቸው በቀር በሥጋዬ ላይ የስቃይ ጥግ፣ የመከራ ጫፍ የቱ እንደሆነ አሳይተውኛል፡፡ በአምባገነኖች ዘንድ ሀገር እና ወገንን መውደድ መቼም ፅድቅ ሆኖ እንደማያውቅ የሀገሬ ታሪክ ምስክር ነው፡፡ ሀገሬ ሞኝ እና ተላላ ሆና ለሞተላት አፈር ከድታ የገደላትን ስታበላ ስለመኖሯም ከአርበኞቻችን ታሪክ የተሸለ መገለጫ የለም፡፡ የደጃዝማች በላይ ዘለቀ ሞት የሚነግረን ይህንኑ ነው፡፡ የማይቀመስ የጀግና ክንዱ የኋሊት ታስሮ እንደ ወንበዴ የተሰቀለው ጃንሆይን አምኖ የሰላም ጥሪውን በማክበሩ ነበር፡፡ ታዲያ የማያልቅባቸው የሀገሬ ቅኔ ዘራፊዎች በበላይ ዘለቀ ሞት ቁጭታቸውን ሲገልጡ እንዲህ ይሉ ነበር፡፡

‹‹ከበላይ ዘለቀ ከተሰቀለው

ይሻላል ሽፈራው ሶማ የቀረው

ታናሽ ነው ይሉታል እጅጉ ዘለቀን

ከበላይ እኩል ነው እሱም የከፋው ቀን››

ሶስት ሺህ ዘመን ከኖርንበት የጉልበት ፖለቲካ ወጥተን አዲስ የሰለጠነ የዲሞክራሲ ምዕራፍ እንጀምር በማለት የህዝቤ እንባ ገዶኝ የሰላማዊ ትግል አርበኛ ብሆን ብዕር ይዞ የተገኘ እጄን በካቴና አስረው ወደ ወህኒ ቤት አጋዙኝ፡፡

መታሰሬ ብዙ አልገረመኝም ወትሮም ሰላማዊ ትግል ስመርጥ መታሰርን ለመታገስ ሞትንም ለመቀበል ዝግጁ ሆኜ ነው፡፡ እንደ መፅሐፍ ቅዱሱ እዮብ በየዕለቱ ነፍሴን እስክጠላ በጭንቅ እንድኖርና በቁሜ እንድሰቃይ የሚያደርግ የበቀል እርምጃ ይወስዳሉ የሚል ግምት ግን አልነበረኝም፡፡ ነገር ግን ሁሉም ነገር ከግምቴ ውጭ ሆኖ ጤንነቴ አደጋ ላይ ወደቀ፡፡ መስሏቸው እንጂ በእውነቱ ይህም ቢሆን  ከሃገሬ አይበልጥም…

በዚህ አስቸጋሪ ወቅት እንደ ትላንቱ ሁሉ ዛሬም ከጎኔ በመቆም በራሳችሁ ተነሳሽነት የኔን ጤንነት ለመመለስ ድጋፍ ላሰባሰባችሁ እና በድጋፉ ለተሳተፋችሁ ሁሉ የላቀ ምስጋና አቀርባለሁ፡፡

በተለይ በማስተባበሩ ሂደት በኔ በኩል አንድም ድጋፍና ትብብር ሳላደርግ ሁሉንም በትዕግስት በራሳችሁ ለተወጣችሁት ሁሉ ምስጋና እያቀረብኩ በዚሁ አጋጣሚ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሀገር እንዳልወጣ የጣለውን እግድ ካነሳልኝ በቅርቡ ከሀገር ውጪ ህክምና እንደማደርግ እና ይህንኑም ስለጤንነቴ ከኔጋር ለተጨነቃችሁ ሁሉ በየጊዜው እንደማሳውቅ እገልጻለሁ፡፡

ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ

 

ሀብታሙ አያሌው

እነዛ ታጋዮች የት ሄዱ?- ከተማ ዋቅጅራ –ከተማ ዋቅጅራ

$
0
0

strugleታላቅ ወንድሜ እርግብ ያረባል። እርግቦቹም የተለያዩ ከለሮች አሏቸው ቡኒ ነጭ ጀርባው ጥቁር ረመዲ ሻቃ የሚባሉ ከለር ያላቸው ነበሩት። ኢህአዲግ አዲስ አበባ ቤተመንግስትን ከተቆጣጠረ ወራቶችን አስቆጥሯል። እናም አንድ ቀን ቡኒ ርግብ እኛ ጣራለይ ከኛ እርግብ ጋር ተደባልቃ አረፈች። እርግቦቹ ወደመሬት እንዲወርዱ እህል ወንድሜ እንደሚያደርገው በትንሽ በትንሹ መሬት ላይ እበትን ጀመር ወደመሬት እንዲወርዱ ወዲያውም ሁሉም ወደ መሬት ወረዱ እንግዳዋም ርግብ ወረደች። ከዛም በመቀጠል ወደቤታቸው እንዲገቡ እህሉን ክፍላቸውስጥ መበተን ጀመርኩኝ አሁንም ሁሉም ወደ ቤታቸው መግባት ጀመሩ አዲሲቷ ርግብ ባዶ ክፍል ውስጥ ገባች እኔም ቃስ ብዬ በሩን በመዝጋት ርግብ ስለጠለፍኩኝ ደስ ብሎኝ ለወንድሜ መጥቶ እስከምነግረው በመጓጓት እጠብቀው ጀመር። በዚህ መሃል ያላሰብኩት እና ያልጠበኩት ነገር ተከሰተ። ሶስት ኢህአዲጎች ከነመሳሪያቸው እርግብ ከተጠለፈበት ልጅ ጋር በመሆን በራችንን ማንኳኳት ጀመሩ። አባቴ ወጥቶ ከፈተ እኔ ውስጥ ነኝ እርግብ ልጥለፍ አልጥለፍ አባቴ የሚያውቀው ነገር የለም። አባቴ ሲነጋገር ድምጹን እሰማዋለው ትንሽ ከተነጋገሩ በኋላ አባቴ ይጠራኛል አቤት ብዬ ስመጣ ለኢህአዲጎቹ በጣም ትንሽ ልጅ ሆንኩባቸው። አንተ ነህ የዚን ልጅ ርግብ የሰረከው ሲሉኝ በመደናገጥ አዎ እልኳቸው በል ቶሎ ይዘህ ና ይሉኛል የዚን ግዜ አባቴ በጣም ተናዶ እንደመምታት እየቃጣው የሰው ርግብ ምን ይሰራልሃል ቶሎ ይዘህ ና ብሎኝ ይቆጣኛል። እኔም ከዘጋሁበት ክፍል አውጥቼ ርግቧን ይዜ መጣሁ እና ለልጁ ሰጠሁት። የታጠቁት ታጋዮችም ሌባን አንወድም ሌባን እናጠፋለን ወንጀለኛንም እናጠፋለን አንተ ግን ህጻን ስለሆንክ እንዳይለመድህ ብለው የጠለፍኳት ርግብ ደስታን ሳይሆን ከፍተኛ ድንጋጠን ይዛብኝ መጣች ። ከላይ የዘረዘርኩት ታሪክ መናገር ያስፈለገኝ ሌባን እናጠፋለን ወንጀለኛን እናጠፋለን የምትለዋ የታጋዮቹ ሃይለ ቃል ናት።

ታጋዮቹ የተናገሯት ቃል ሌባን እናጠፋለን ወንጀለኛን እናጠፋለን ደግመው ደጋግመው በመናገራቸው በልጅነት አእምሮዬ እንድትቀመጥ የተደረገች ቃል

እነዚህ ታጋዮች የት ሄደው ነው ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ጆሮን ጭው የሚያደርግ የስርቆት እና አሰቃቂ ወንጀሎች የሚሰማው።

ሌባን እናጠፋለን ወንጀለኛን እናጠፋለን ብለው የተናገሩት ታጋዮች በነሱ  የስልጣን ዘመን ውስጥ የገዛ ስጋቸውን እየቆረጡ እንዲበሉ ተደርጎ የተገደሉ ዜጎች እንዳሉ እና  እንዲህ አድርገው የሚገድሉ ወንጀለኖች ያሉባት አገር ኢትዮጵያ እንደሆነች ያውም በነሱ የስልጣን ዘመን እንደሆነ  ሲነገራቸው ምን ይሉ ይሆንን?

ከሰባት ቢሊዮን ብር በላይ ከአንድ ድርጅት ከስኳር ፋብሪካ ውስጥ እንደቀልድ ጠፋ  ተብሎ ሲነገር ለምን ብሎ የጠየቀ ሁሉ የዘር ሃረጉ ተመዞ አንተ ኦነግ ነህ አንተ  ግንቦት ሰባት ነህ እየተባሉ በማሸማቀቅ ዘራፊው ንጹሃኑን የሚያስርበት አገር ኢትዮጵያ እንደሆነች ሲነገር  ሌባን እናጠፋለን ወንጀለኛን እናጠፋለን ብለው የተናገሩት ታጋዮች ምን ብለው ይሆን?

88 የኮንዶምኒዬም ህንጻ ከከተማችን ጠፉ ተብሎ ሲነገር ህንጻም እንደ ሰው ተገሎ ወይንም ወይኒ ወርዶ ወይንም ተማርኮ ወደ ጎረቤት አገር ወስደውት ይሆን ወይንስ ችግር ብሶበት ተሰዶ ይሆንን? የጠፋው በማለት ህዝቡ ውስጡ እያረረ በስላቅ የተናገረበትን በኢትዮጵያ ታሪክ ታይተውና ተሰምተው የማይታወቁ ነገሮች እየሰማን ነው ህንጻ እንኳን ሰርቀው የሚሰወሩ ሌቦች አሏት ማለት ነው? ሌባን እናጠፋለን ወንጀለኛን እናጠፋለን ብለው የተናገሩት ታጋዮች ይሄንን ሲሰሙ ምን ብለው ይሆን?

ስለ ሰሞኑ ዜና ስለትምርት ጉዳይ ጥቂት ልበልና ጽሁፌን ልቋጭ

አገር ተረካቢ ትውልድ የሚፈጠረው ተቋም ከትምህርት ቤት ነው። የተማረ ሃይል ሲበዛ የእውቀት አድማሱ ይሰፋል። የእውቀት አድማሱ ሲሰፋ ሰውን በግድ አልያም በኃይል ከማሳመን  ይልቅ በመነጋገር እና በመረዳዳት ችግሮችን  መፍታት ይጀምራል። ችግሮችን በመነጋገር እና  በመረዳዳት ከተፈታ ህዝቡ ሁሉ ለአገሩ ልዩ  ፍቅር ይኖረዋል። ይህ ሁሉ የሚሆነው ትክክለኛ የመማር እና  የማስተማር የትምህርት ሂደት ሲኖር ብቻ ነው። በዚሁ ልክ ተማሪዎችን የማይመጥን ትምህርት በመቅረጽ የተበላሸ  እና ታሪክን ያፋለሰ  ትምህርት ከተማሩ ደግሞ ለአገርም ለህዝብም አደገኛ የሆነ ትውልድን እናፈራለን። ስለዚህ የትምህርት ቤት ተቋም ማስተማር ያለባቸው እውቀት ያላቸው ሆነው ለአገርም ለህዝብም የሚጠቅም ትውልድን ቀርጾ ማውጣት የሚችሉ መምህራን ቢሆኑ ጥሩ ነው።

ድሮ ድሮ የሃብታም ልጅ ወደ ቦሌ የደሃ ልጅ ወደ ጦሌ ይባል ነበረ ። ዛሬ ዛሬ ደግሞ ካድሬው ካድሬው በተሰረቀ ውጤት ባለድግሪ ሲሆኑ የተቀረው ህዝብ ደግሞ ከነ እውቀቱ ከትምህርት ተባራሪ ሲሆን… ካድሬው ካድሬው ባለድግሪ ነጻው ነጻው   ተባራሪ… የሚል ትችት ከህዝባችን ይሰማል። በግዢ ማለትም በስርቆት በሚገኝ ውጤት በመያዝ የማይገባቸውን  ቦታዎችን በመያዝ ለቦታው ስለማይመጥኑ ትላልቅ ችግሮችን በአገሪቷ ላይ እየተከሰተ የምናየው ያለ እውቀታቸው የተቀመጡ ሰዎች የሚፈጥሩት ችግር ነው። ይሄ ችግር ያንገበገባቸው የኢትዮጵያ ህዝብ አሁንም ሌላ የማስጠንቀቂያ ደውል ደውለዋል። የ12 ክፍል የፈተና  ወረቀትን ከፈተናው በፊት በማውጣት ከፈተናው በፊት ችግራችን ይሰማ  የሚል መልእክት  ይዟል። በመንግስት ደረጃ እሰውረዋለው የሚለው ሚስጢር ከህዝብ ሊሰወር እንደማይችል በማስገንዘብ ለመንግስት ትልቅ ማስጠንቀቂያ  ነግረውታል። ነገ ሊመጣ የሚችለው ለውጥ እንደዚ ቅስፈታዊ ሊሆን ስለሚችል በግድ እና  በሃይል የሚባል ነገሩን በማቆም ህዝብ መንግስትን መፍራት ሳይሆን መንግስት ህዝብን መፈራት እንዳለበት ያመላከት ትብብር ነው። ለማንኛውም ኢትዮጵያ ውስጥ የማይሰረቅ ነገር እንደሌለ  አይተናል። ነገ ምን እንደሚሰረቅ አብረን እናያለን ከላይ የዘረዘርኳቸው በ25 አመት ውስጥ ከተደረጉት 10% የማትሞላውን ትርክት በጥቂቱ ጨልፌ ነው።  ሌባን እናጠፋለን ወንጀለኛን እናጠፋለን ያሉን ታጋዮች የት ሄደው ነው  ዛሬ ከጠፋ  ውጪ፣  ከተሰረቀ ውጪ፣ ከታሰረ ውጪ፣ ከመደፈር ውጪ፣ ከመገደል ውጪ፣ ከችግር ውጪ፣ ከመሰደድ ውጪ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ መሰማት ያቆምነው። ትላንትና የነበሩት አልፈዋል… ዛሬ እንደዚህ ገዝፎ የሚታየው ችግርም እንደትላንቱ የሚያልፍበት ግዜ ይመጣል… ነገ ሌላ አዲስ ነገር ይዞ ይመጣል … መጪውን አብረን እናየዋለን መንገዱ ተጀምሯል።

ከተማ ዋቅጅራ

01.06.2016

Email- waqjirak@yahoo.com

 

 

የትረምፕ መመረጥ በአለም-በአፍሪካ-በኢትዮጵያ ፖለቲካ ያለው አንድምታ- ሰርጸ ደስታ

$
0
0

dolandl trummpብዙዎች በምረጡኝ ዘመቻቸው በሚያደርጓቸው ንግግሮች አምረው ሲያወገዟቸውና አልፎም ለአሜሪካ ፕሬዘዳንትነት ፍጹም የማይመጥኑ ብለዋቸው የነበሩት የሪፓብሊካኑ ተወካይ ከበርቴው ዶናልድ ጄ ትረምፕ በእጩነት የቀረቡትን የሪፓብሊካን ተቀናቃኞቻቸውን ሁሉ ጥለው አሁን ላይ ለቀጣዩ የአሜሪካን ፕሬዘዳንትነት ከተፎካካሪያቸው የዲሞክራቷ እጩ ሂላሪ ክሊንተን በብዙ በሚሻል ዕድል ላይ ይገኛሉ፡፡ ትረምፕ ሕዝብ ውሳኔ ለመስጠት ሙሉ እድል በአለው እንደ አሜሪካን አይነት አገር ባይሆን አሁን ያሉበት ደረጃ አይደለም ለምረጡኝ ቅስቀሳ በወጡበት በጥቂት ቀናት አገሪቱ  የሚያስጠይቃቸው ምንም አይነት ሕግ እንኳን ባይኖር እሳቸውን ለመክስስ የሚያስችል አዲስ ሕግ ወጥቶ ወደ ወሕኒም ሊጋዙ በቻሉ፡፡ ጥፋተኛ ስለሆኑ ሳይሆን እሳቸው እንደሌሎች ፖለቲከኞች ውሸት የማያውቁ  ትክክልኛ የአገርና ሕዝብ ቁጭት ያላቸው በመሆናቸው፡፡ በተለይ ኢትዮጵያዊ ቢሆኑ ጉዳቸው ነበር፡፡ አሸባሪ ተብለው እሳቸውም ወደቃሊቲ የሚካሄደውም ምርጫ 100 ፐርሰንት ገዥው ፓርቲ አሸንፎ እነ ኦባማና ቡድናቸው ፍጹም ዲሞክራሳዊ በሚል በሕዝብና አገር ላይ በተሳለቁ ነበር፡፡ ደግነቱ ትረምፕ አሜሪካዊ ናቸው ፖለቲከኞች፣ ባለስለጣን፣ የሌሎች አገር መሪ ምናምን የሚባሉት ሁሉ ተንጫጩ አልተንጫጩ እሳቸው ምን አገባቸው ሕዝቤ የሚሉት ይቀበላቸው እንጂ፡፡

ትረምፕን ለማጥላላት ተፎካካሪያቸው ብቻም ሳይሆኑ የፉክክሩን ሂደት ተጽኖ የሚያሳድሩ የኢትዮጵያን መንግስት ዲሞክራሲያዊ ያሉት የአሁኑ የአሜሪካው መሪ ኦባማን፣ የኢንግሊዙን ካሜሩንን ጨምሮ ብዙ ፖለቲከኞችና የፖለቲካ ተንታኞች ራሳቸውን  ለትዝብት የጣላቸውን ንግግር በትረምፕ ላይ ተናግረዋል፡፡ ሕዝብ  ውሸታሞች የፈለጉትን ቢሉ ትረመፕም ከመከተል ያገደው አልነበረም፡፡ ይሄኔ ነበር እንግዲህ ፌደራል ፖሊስ የሚያሰፈልገው፡፡ ሕዝብ ውሸታሞችን ጠንቅቆ ያውቃል፣ ምን እንደሚያስፈልገውም አሳምሮ ያውቃል፣ መሪውም ማን ሊሆን እንደሚችል መምረጥ ይችልበታል፡፡ ይህ የሕዝብ ባሕሪ የትም አገር ተመሳሳይ ነው፡፡ ኢትዮጵያም እንደዛው ነው፡፡ እንደውም በድምጽ የምፈልገውን እመርጣለሁ ብሎ ቀኑን ሙሉ ተሰልፎ ሌሊቱንም ቆሞ አድሮ ንጋት 10 ሰዓት ድምጽ ለመስጠት የሚታገስ ሕዝብ የታየው በአለምም ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ መሰለኝ፡፡ ምን ያደርጋል ታዲያ መዋሸት ብቻ አይደለም እውነተኞች በውሸታሞች አሸባሪ ተብለው ለሞትና እስር  በሚዳረጉባት አገር ኢትዮጵያና ሌላው  የአፍሪካም ምድር የሕዝብ ፍትሕና ሥርዓት ናፋቂነት ሕልም በሕልምም የማይታዮ ርቀቶች ሆነዋል፡፡ እንግዲህ ከለመድናቸው ፖለቲከኞች በተቃራኒው አደባባይ ላይ ወጥተው እውነትን እየጠሯት ያሉት ትረምፕ የአሜሪካ መሪ መሆን ቢችሉ  አለም ላይ ያሉ እውነት ናፋቂ ሕዝብና የሕዝብ ተቆርቋሪ መሪዎች አዲስ የዕድል ምዕራፍ ይከፈትላቸው ይሆን;

እስካሁን በተናገሯቸው ንግግሮች ትረመፕን ለትችት የዳረጋቸውና ብዙዎችም በሕዝብ ዘንድ ወዥንብር እንዲፈጠር ሰውዬው ከአእምሯቸው ያልወጣውን ሀሳብ ንግግራቸውን እንተነትናለን በሚል ሊያንሻፍፉባቸውባቸው ብዙ ቢጥሩም፤ የገዛ ፓርቲያቸው ሳይቀር ድጋፍ ሳያደርግላቸው ቢቀርም ትረመፕ አሜሪካን ከመምራት እየመለሳቸው ያለ ኃይል ያለ አልመሰለም፡፡ አሁን ፓርቲያቸው ሳይወድ በግድ የተቀበላቸው ይመስላል፡፡ በእርግጥም ፖለቲከኛ መሆን መዋሸት ሕዝብን ማታለል ካልሆነ በቀር ትረም እስካሁን የተናገሯቸው ሁሉ ለአገሩና ሕዝቡ የሚያስብ መሪ እውነተኛ መሪ የሚናገረውን ነው፡፡ የሜክሲኦውን ድንበር አጥራለሁን የሚለውን ጨምሮ፡፡ አንድ መሪ ከሁሉ በፊት የሚያስቀድመው የገዛ አገሩና ሕዝቡ ጉዳይ ነው፡፡ የአሜሪካውያን ደህንነትና ኢኮኖሚ ሥጋት ከሆነ የሜክሲኮን ድንበር ማጠር ለምን ትክክል አይሆንም፣ ከአረብና ከተለያዩ ሙስሊም ጽንፈኞች ከበዙባቸው አገራት የሚመጡ ስደተኞች ላይ ልዩ ቁጥጥር ማድረግ እንዴት ስህተት ይሆናል; ከእነጭርሱስ አላስገባም ማለትንስ ለምን ከክፋት ይቆጠራል; በምንስ መስፈርት እንዲህ ያለው ጉዳይ ዘረኝነት ያሰኛል; አሜሪካዊ ሆኖ ያለው እኮ የተለያየ የዘር ግንድ የላው ከተለያየ ዓለም የመጣ ነው፡፡ ትረምፕ አሜሪካዊ ጥቁር ከነጩ ያንሳል አላሉም፡፡ አሜሪካዊ ሜክሲካን ከአሜሪካዊው አይሪሽ ያንሳል አላሉም፡፡ እውንውም ሁሉንም እንደሚወዱ ሁሉም  ወዳጃቸው እንደሆነ ተናገሩ እንጂ፡፡ ሕዝብ ትረመፕ ያሉትን በትክክል ሰምቷል፡፡ ጥቁሩም፣ ነጩም፣ ሜክሲቻኑም፣ አይሪሹም ደጋፊያቸው ነው፡፡ ትረምፕ ባለቤታቸው መላኒያ የሌላ አገር ተወላጅ መሆናቸውና፣ ቀድሞ በሞዴልነት እርቃን የተነሱት ፎቷቸው  እንደፈተና ቀርቦባቸው ነበር፡፡ ሕዝብ እና ምን ይጠበስ ብሎ ፈታኞቹን አሳፈራቸው እንጂ፡፡   ብላክ ላይፍ ማተርስ (አማርኛው ፍች ትርጉም ስላልሰጠኝ ነው) በሚል የታየው ዘረኝነትን የሚያንጸባርቀው ትዕይንት በኦባማና ሂላሪ ሲወደስ ትረምፕ ኦል ላይፍ ማተርስ በሚል ነበር ሰው በሰውነቱ እንጂ በጥቁርነቱ በነጭነቱ ለሕየወቱ ዋስትና የተለያየ መስፈርት ሊኖረው አይገባም የሚለውን አንድምታ ያመጣ ንግግራቸውን ለሕዝብ ያደረሱት፡፡ እነ ኦባማ አዛኝ በመምሰል ሊሸውዱት የነበረውን ሕዝብ ትረምፕ ፊት ለፊት መሆን የሚገባውን ፍትሀዊ እውነት ተናገሩት፡፡ ፖለቲኞች እንደነ ኦባማ ናቸው፡፡ ሰውን የሚያሕል ክቡር ፍጡር የሚያርዱ እራሳቸውን በይፋ ሙስሊሞች ነን የሚሉ አረመኔ ሙስሊም ጽንፈኞችን፣ ለሌላው ሠላማዊው የሙስሊም ማሕበረሰብ ሞራል በሚል እነ ኦባማ፣ ካሜሩንና የመሳሰሉት ሙስሊም ጽንፈኞች ማለትን እንደ ነውር ቆጠሩት፡፡ ትረምፕ እንዲህ ያለውን ድራማ  መታገስ አልፈለጉም፡፡ አካፋን አካፋ ዶማን ዶማ እንጂ የምን ማሽሞንሞን ነው አሉ፡፡ ሙስሊም ጽንፈኞች ለማለት እንዴት ነውር ይሆናል; አረመኔዎቹ ራሳቸው እኮ እኛ ሙስሊሞች ነን እያሉ ነው፡፡ ራሱ አረሜኔው ቡድን የሚጠራበትን ሥም ትተን ከየት አምጥተን ነው ሌላ ሥም ሰጥተን ሕዝብ  የምናደናግረው፡፡ ሙስሊም ጽንፈኞች የሉም ብለው አይናችን የሚያየውን፣ ጆሯችን የሚሰማውን እኮ ነው እነ ኦባማና መሰል ውሸታም ፖለቲከኞች የሚያደነቁሩን፡፡ ሠላማዊ ሙስሊሞችን እንዲ መባሉ እንዴት ያስከፋቸዋል;  ይልቁንስ ሠላማዊ ሙስሊሞቹ ለምን ጽንፈኞቹን ለመመከት አይነሱም፡፡ የትረምፕ ለይቶ ሙስሊም ጽንፈኛ ማለት ሠላማዊዎቹን ከጽንፈኞቹ በግልጽ መለየት እንጂ እንዴት ሥሕተት ይሆናል፡፡ የተረጋጉትን የሙስሊም አገራት መንግስታቸውን በማፍረስ እኮ ዛሬ እንደልባቸው ለሚሆኑ የሙስሊም ጽንፈኞች እድል የሰጡት ሕዝብንና አገርን ሲሸውዱ የኖሩት የአሜሪካን መሪዎች ነው፡፡ የሳዳም ሁሴን ከኢራቅ የጋዳፊ ከሊቢያ የተወገዱበት ሂደት እኮ ነው አረመኔዎቹን ዕድል የሰጣቸው፡፡ ትረምፕ ያሉት እኮ ይህን እውነት ነው፡፡

ትረምፕ ከሁሉም በፊት አገሬና ሕዝቤ ያሉ ይመስላል፡፡ በውጭ ያላቸውም አቋም ግልጽነት ያለው የብዙ አገራት ሕዝብ እስከዛሬ ሲጠይቀው የነበረውን ፍትሀዊነት ያመላከተ ይመስላል፡፡ ራሱን አለም አቀፍ እስላማዊ መንግስት (አይሲስ) እያለ የሚጠራውን ቡድን እንደነ ኦባማ፣ ካሜሩንና ሌሎች የአውሮፓ መሪዎች በማሽሞንሞን የሚያልፉት አይመስልም፡፡ መወሰድ ያለበትን እርምጃ ወስደው ከምድረገፅ የሚያጠፉት እንጂ፡፡ ያኔ አሸባሪ የሚባል አይኖርም፡፡ አልሸባብ፣ አይሲስ፣ ቦኮሀራም ምናምን አይኖሩም፡፡ አልሸባብ ከጠፋ ሕዝብ ፍትሕ አጥቶ የሚያነባበቸው የኢትዮጵያ አምባገነን ባለስልጣናት የአሸባሪብት ተከላካይ በሚል በሕዝብ የተመረጡ ዲሞክራሳዊ የሚል ስም አይሰጣቸውም፡፡ ቢያንስ አምባገነንነታቸው በይፋ በትረምፕና መሰሎቻቸ ይነገራቸዋል፡፡ ኢትዮጵያም ሆነች ሌሎች አገራት የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ኃይሎች አሸባሪ የሚል ሥም አይለጠፍባቸውም፡፡

ትረምፕ  ዲፕሎማሲ ምናምን የሚባለው ጉዳይ ለሕዝብና አገር ጥቅም ትርፍ የሚያመጣ ከሆነ እንጂ ከዚያ ውጭ ያለው መሞዳሞድ አይመቸኝም የሚሉ ይመስላሉ፡፡ ትረምፕ እንዲህ እንደሚሉት የወጭ ፖሊሲያቸውን በተግባር ካዋሉ ከአሜሪካ ጋር የኢኮኖሚም ይሁን የፖለቲካ ትስስር እንዲኖራቸው የሚፈልጉ አገራት ሁሉ አማራጫቸው ፊት ለፊት ከሚናገሩትና መሠረታዊ የጋራ ጥቅምን እንጂ መሞዳሞድን በማያውቁት ትረምፕ ተጽኖ ሥር ይወድቃሉ፡፡ ዛሬ የትረመፕ አገር ከሆነችው አሜሪካ ጋር ለአለም በተለይም ለመካከለኛው ምስራቅና አፍሪካ ትልቅ የቀውስ ምክነያት የሆኑት የታላላቆቹ የአውሮፓ መሪዎችም ልጓም ይበጅላቸዋል የሚል አምነት አለኝ፡፡ አገራት በአምባገነን ባለስልጣናት እጅ ሆነው ዲሞክራሲያዊ፣ ልማታዊ፣ የአሸባሪነት ውጊያ አጋር ምናምን እየተባሉ ሕዝብን ለሞት፣ ለእስስር እና ለስደት እየዳረጉ በብዙ ሚሊዮን ዶላሮች የሚደገፉ አምባገነን የአፍሪካ መንግስታት እንደዛሬው ጉልበት የሚያገኙ አይመስልም፡፡   ከእነ ኦባማና የምዕራብ አውሮፓ አገራት በተቃራኒ ትረምፕ ከኮስታራው የራሺያው ፑቲን ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት የጠበቀ ወዳጅነት እንደሚሆን ከወዲሁ ትረምፕ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡ ያ ከሆነ ደግሞ ድሮውንም ለራሺያ የኃይልና (በተለይም የተፈጥሮ ጋዝ) የኢኮኖሚ ጥገኛ የነበሩት የጠቀስኳቸው የአውሮፓ አገራት ከፑቲን ጋር ከመስማማት ውጭ የሆነው አማራጫቸው የጠበበ ይሆናል፡፡ ትረምፕ የአሜሪካ ፕሬሰደንት ከሆኑና በቃል የተናገሯቸውን በተግባር የሚፈጽሙት ከሆነ አጠቃላይ የአለም የፖለቲካና የምጣኔ ሀብታዊ ድባብ አሁን ከምናየው መልክ የተለየ ይሆናል የሚል ግምት አለኝ፡፡ የምዕራብ አውሮፓ አገራትም አሁን ያሉትን መሪዎቻቸውን ጥለው በምትካቸው ትረምፕንና ፑቲንን የመሰሉ መሪዎችን ወደ ሥልጣን ማምጣት የሚጠይቃቸው የሚሆን ይመስላል፡፡ በተለይም ከትልቁ ቡሽ ጀምሮ አሜሪካንን ጨምሮ የብዙ አገራት መሪዎች ሕዝብን በመሸወድ እንጂ እውነትን በመጋፈጥ እየመሩ አይደለም፡፡ በእርግጥ ሕዝብ ተሸውዶም ሳይሆን መሪዎቹ ዕድሉ ስለነበራቸው በይሸወድም ሕዝቡን በብዙ መልኩ እንዲሰላች አድርገው እነሱ መሪ ሆነዋል፡፡ አሁን ያሉትን እንደምሳሌ ብንወስድ ኦባማ፣ የኢንግሊዙ ካሜሩን፣ የፈረንሳዩ ሆላንዴ ለብዙ ቀውሶች ምክነያት ናቸው የሚል እምነት አለኝ፡፡ ምን አልባት ካሜሩን በሌሎቹ ላይ ብልጥ የሆኑ ይመስላል፡፡  ጠንካራ የሚባሉት የጀርመኗ መርክልም እነዚህን ተከትለው ብዙ ስህተት ሳይሰሩ አልቀሩም፡፡ ደግነቱ የጀርመን ሕዝብና በተለያየ እርከን የሚገኙ ታላላቅ ዜጎቿ ለመርክል እንደልብ እድል የሚሰጧቸው አይደለም፡፡ መርክልም ከእነዚህ ዜጎቻቸው ማፈንገጥ አደጋ እንዳለው ይረዱታል፡፡

የእስልምና አገራቱን ነገር በይፋ እንደሚታየው በእድገት በመተኮስ ላይ ያሉት የኤሺያ አገራት (ምሳ. ሕንድ፣ ቻይና፣ ሌሎችም) አሁን ጉዳያቸው ከፖለቲካ ይልቅ ኢኮኖሚን ኢላማ ያደረገ ይመስላል፡፡ ፖለቲካውን ብዙም ትኩረት አይሰጡትም፡፡ የአፍሪካ መሪዎች ዋነኛው ትኩረታቸው ሆዳቸው ነው፡፡ አገር ሕዝብ በአሳዛኝ ሁኔታ ማሰብ የሚባል የፈጠረባቸው አይመስልም፡፡ ሰሞኑን ባይናገሩትም ትረምፕ ተናገሩት ተብሎ በተለያዩ ድረ ገጾች የተነበበውን የአፍሪካን መሪዎች ከሰው ሳይሆን ከአነሱ እንሰሶች የመደበውን አፍሪካንም እንደገና ቅኝ መያዝ የሚለውን ጽሁፍ ብዙ አፍሪካውያን ያስፈልጋል የሚል አስተያየት ሲሰጡበት ማየት ምን ያህል ዜጎች በአምባገነን ከራሳቸው ሆድ ውጭ አገርና ሕዝብ ማሰብ በማይችሉ ባለስልጣናት እንደተማረሩ ገላጭ ነው፡፡ እውነታውም ከሌላው አለም ለይቶ ለአፍሪካ ይህን የሚመስል ገጽታ እንዲኖራት አድርጓል፡፡ የትረምፕ መመረጥ በአፍሪካ ፖለቲካ ላይ የሚኖረው ተጽዕኖ ቀጥተኛም ተዘዋዋሪም ሊሆን የሚችል ይመስላል፡፡ ቀጥተኛው አሜሪካ ራሷ በአምባገነኖቹ መሪዎች ላይ ልትወስደው የምትችለው እርምጃ ነው፡፡ ትረምፕ በዚህ ፊትለፊት በሆነው አቋማቸው ከቀጠሉ በየአገራቱ ያሉ የአሜሪካ ቆንሲላዎች እንደነ ኦባማና ራይዝ ዘመን በአፍሪካ ሕዝብ ላይ አይሳለቁም፡፡ ያኔ 100 ፐርሰንት ምርጫ አሸነፍኩ ብሎ የሚደነፋ፣ ዜጎችን የሚገድል፣ የሚያስር፣ ከገዛ አገራቸው ለስደት የሚዳርግ፣  ቀጥሎም በሕዝብ የተመረጠ ዲሞክራሲያዊ መንግስት ተብሎ በአሜሪካ ፕሬዘዳንት (ትረምፕ) ምስክርነት የሚሰጠው የአፍሪካ መንግስት አይኖርም የሚል እምነት አለኝ፡፡ በተዘዋዋሪው ለአምባገነኖቹ የአፍሪካ መሪዎች አማራጭ አቅም የሚሆኑት የምዕራብ አውሮፓ አገራትም ፖለቲካ የአሜሪካ ተጽዕኖ ስለሚያርፍበት ቢያንስ አሁን አምባገነኖችን እንደሚደጉሙት የመቀጠል ፍላጎታቸው ሊቀንስ፡፡ ምን አልባትም ትረጉም ያለው ለውጥ ሊኖርበት ይችላል፡፡ በዚህ ሂደት አምባገነናቱ አቅም እያጡ ሕዝብ ጉልበቱ እያየለ ሄዶ እንደሚባለው ዲሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ መሪዎቹን የሚሾምና የሚያወርድ ሊሆን ይችላል፡፡ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿ እንደሌሎች ሁሉ ከላይ ካነሳኋቸው የትረምፕ የተስፋ በረከቶች ጥቂቶቹ ይደርሳት ይሆናል፡፡ ያም ባይሆን ከተሳለቁብን (ከአፌዙብን) አባማ፣ ራይስና ሌሎች መሰል የአሁኑ የአሜሪካ ባለስልጣናት በአዲስ አስተሳሰቦችና ልዩ አቀራረብ የመጡት ትረምፕ የአሜሪካ ፕሬሲደንት እንዲሆኑ ተመኘሁ፡፡ ትረምፕን ምረጡ!

 

እግዚአብሔር ለኢትዮጵያና ሕዝቦቿ የብርሀን ዘመን ያምጣ!

 

አሜን

 

ሰርጸ ደስታ

ሙስሊሞች የሽብር ፍጠራ ሰለባዎች |ከሳዲቅ አህመድ

$
0
0
ጦርነቶች ጥቅምን ማስከበሪያ መቅሰፍቶች ናቸዉ። በነዚሁ ጥቅምን ለማስከበር በሚከፈቱት ጦርነቶች ሰለባ ከሚሆኑት የአለማችን ዜጎች መካከል ሙስሊሞች ይገኙበታል። ይህ ልዩ ጥንቅር “ጦርነቶች እንዴት ይጀመራሉ?” የሚለዉን መሰረታዊ ሐሳብ ይዳስሳል። በተለይዩ አገራት በጦርነቶች መካከል የሚሰቃዩትን የአለማችን ዜጎች ሰቆቃ ይቃኛል።ሙስሊም ምሁራንና መሪዎች ያላቸዉን ጸረ-ሽብር አቋም ያሳያል። እንደ መፍትሔም የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ፈርጦችን አቋምን ያመላክታል። ይህ ፕሮግራም ጠቅለለ ያሉ የክፍለ ዘመናችንን ሒደቶች ይቃኛል።
 
ንጹሗን ሙስሊም የአለማችን ዜጎች በሽብር ፈጠራ በተሰማሩ አካላትና ሽብር ፈጠራን እንዋጋለን በሚሉ መንግስታት ዉግያ መካከል ሆነዉ የጦርነት ሰለባ ሲሆኑ ይታያል። ምን ይሻላል?በቀጣዮቹ ስራዎች የዚህ ፕሮግራም ጠቅለል ያሉ እይታዎች ይቃኛሉ። ለአሁኑ ሙስሊሞች የሽብር ፍጠራ ሰለባዎችን በማየት ጠቃሚ መረጃን ያገኛሉ የሚል ተስፋ አለን።

‹እኛና መንፈስ ቅዱስ› ማለት ሊቀር ነውን? ––ከዲ/ን ዳንኤል ክብረት

$
0
0

ቅዱስ ሲኖዶስ የፓትርያርኩን እንደራሴ ሹመት በተመለከተ ለመወያት የያዘው አጀንዳ የመንግሥት ተወካይ ባለበት እንዲታይ መወሰኑን ዛሬ ጠዋት ሰማን፡፡ ከብጹዐን ጳጳሳት በቀር ካህናትና ቆሞሳት እንኳን የማይገቡበት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ አማኝ ይሁን ኢአማኒ፣ ሙስሊም ይሁን ክርስቲያን የማይታወቅ የመንግሥት ተወካይ እንዲገኝበት መጋበዙ የደረስንበትን የውርደት ደረጃ የሚያሳየን ነው፡፡
H_E_Abune_Matiyas_Archbishop_of_Jerusalem_Misa
በአንድ በኩል የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያኒቱ ሃይማኖታዊ፣ ቀኖናዊና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ የመጨረሻ ወሳኝ አካል መሆኑን ስናስበው፤ በሌላ በኩል የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ የሚደረገው በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ነው፤ ውሳኔውም በሐዋርያት ሥራ እንደተገለጠው ‹እኛና መንፈስ ቅዱስ› የሚባልበት ነው(የሐዋ. 15፣29) የሚለውን ስናየው ‹የመንግሥት ተወካይ ይኑርልን› የሚለውን ውሳኔ ኢሃይማኖታዊ ነው ያሰኘዋል፡፡ ለአንድ የሲኖዶስ ጉባኤ የመንፈስ ቅዱስ መገኘት አልበቃው ብሎ ነው የመንግሥትን ተወካይ የሚጋብዘው? ‹ሱባኤ ይዘን፣ ጸሎት አድርገን፤ አንድ ገዳም ወርደን፣ ከእግዚአብሔር ጋር መክረን› አይደለም ይሉን አባቶቻችን፡፡ ‹የመንግሥትን ተወካይ ጋብዘን› ነው ያሉን፡፡ እንዲያውም ቀኖናው የሊቀ ጳጳሳቱ(ፓትርያርኩ) ጉዳይ ሲታይ ‹በመቀመጫቸው መካከል አንድ ወንበር አስቀምጠው፣ ቅዱስ ወንጌሉን በዚያ ላይ አኑረው፣ ሊቀ ጳጳሳቱ በፊታቸው ተቀምጦ፣ አንድነት ተነሥተው በሩን ዘግተው ይጸልዩ፤ የተሰበሰቡበትንም ጉዳይ በሥውር(በኅቡእ) ይመርምሩ› ነው የሚለው(ፍ.ነ. ዐ.168)፡፡ እንዴት ተደርጎ ነው የመንግሥት ተወካይ ባለበት የሚታየው? አግዚአብሔር ያየናል የሚለው ጠፍቶ ታዛቢ ቢያስፈልግ እንኳን የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች ለታዛቢነት አይበቁም? ቅዱስ ጳውሎስ ‹በወንድሞች መካከል ሽማግሌ ሊሆን የሚችል አንድ አስተዋይ ሰው በእናንተ ዘንድ አይገኝምን?› (1ኛቆሮ. 6፣5) ያለው ለዚህ ጊዜ አይሆነንም?

በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ የመንግሥት ተወካይ እንዲገኝ መጋበዙ በአንድ በኩል የቤተ ክርስቲያኒቱን ልዕልና የሚነካ በሌላ በኩልም ሕገ መንግሥቱን የሚጥስ፤ በመጨረሻም ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የሚያፈርስ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ያለ ማንም ጣልቃ ገብነትና ታዛቢነት የራስዋን ጉዳዮች በራስዋ ሕግጋት፣ ቀኖናና ሥርዓት መሠረት የመወሰን መብት አላት፡፡ አባቶቻችን ከንጉሥ ሐርቤ ዘመን ጀምረው ከግብጽ ሲኖዶስ ጋር ሲሟገቱ የኖሩት ይህን ሉዐላዊነት ለቤተ ክርስቲያናቸው ለማስገኘት ነው፡፡ ጳጳሳትን ለማግኘት የግብጽ ሡልጣኖች መለማመጥ፣ የግብጽንም ፓትርያርኮች መለመን ሰልችቷቸው፡፡ ከግብጽ ቀድማ ክርስትናና የተቀበለች ሀገር፣ የራስዋን ጉዳይ ለመወሰን አለመቻሏ አስደናቂ ስለሆነባቸው፡፡ ከቤተ ክርስቲያንዋ ታላቅነትና ከሀገሪቱ ክብር ጋር ስላልተመጣጠነላቸው፡፡

ዛሬ ያ ሁሉ ተረስቶ መንግሥትን በገዛ ፈቃዳቸው ‹አንተ በመካከላችን ካልተገኘህ አንሰበሰብም› የሚሉ አባቶች መጡ፡፡ ቀደምት አበው ‹አንተ ከኛ ጋር ሁን› የሚሉት ፈጣሪያቸው ነበር፡፡ ዘመን ተቀየረ፡፡ በቀደመው ጊዜ ‹መንግሥት ለምን በጉዳያችን ውስጥ ይገባል?› ነበር ክርክሩ፡፡ ‹አሁን መንግሥት ከሌለ ይህንን አጀንዳ አናይም› የሚባልበት ዘመን ላይ ደረስን፡፡ የፓትርያርክ እንደራሴ ጉዳይ የሃይማኖት ጉዳይ ነው፡፡ እንደራሴውም የሚፈጽመው ሃይማኖታዊ ጉዳዮችን ነው፡፡ የሥልጣን ክልሉም በቤተ ክርስቲያኒቱ የሥልጣን ክልል ነው፡፡ ታድያ ለምንድን ነው መንግሥት ያስፈለገው? ይህንን ጥያቄ ፓትርያርኩ ጠይቀውት ይሆናል፡፡ እንደመከራከሪያ ቢያቀርቡት አይገርምም፤ ቢያሳዝንም፡፡ የምልዐተ ጉባኤው መቀበል ግን ሕመም ነው፡፡

መንግሥትስ ቢሆን ምን ብሎ ነው ተወካይ የሚልከው? ምናልባት ‹ጠሩኝ፣ ሄድኩ› ካላለ በቀር፡፡ ሕገ መንግሥታችን መንግሥት በሃይማኖት ጣልቃ እንደማይገባ በግልጽ እየደነገገ እንዴት አድርጎ ነው በቀኖናዊ ስብሰባ ላይ የሚገኘው? ውሳኔውንስ ከየትኞቹ የቀኖና መጻሕፍት ጋር ሊያገናዝብ ነው? በጉባኤው የሚኖረውስ ሚና ምን ሊሆን ነው? ምን ዓይነት ወኪልስ ነው የሚወክለው? በየትኛው ሥልጣንና ሕግ ነው የሚገኘው? የዚህ ዓይነቱ አሠራርስ መጨረሻው ምን ይሆናል? በጉባኤው ላይ የሚተላለፈው ውሳኔ የማን ውሳኔ ነው? ‹የእኛና መንፈስ ቅዱስ› ወይስ ‹የእኛና የመንግሥት›? መንግሥትም ጉዳዩን ሊያስብበት ይገባል፤ ‹ሲጠሩት አቤት› ሳይሆን ‹ሲጠሩት ለምን?› መሆን አለበት፡፡

የቤተ ክርስቲያን ቀኖና ኤጲስ ቆጶስ በዚህ ዓለም መኳንንት ርዳታ አንዳይቆም ያዝዛል፡፡ በእምነቱና በእግዚአብሔር ቃል ብቻ እንዲጸና፡፡ (ፍትሐ ነገሥት፣ 176፤ረስጠብ 21) በዲድስቅልያም ላይ ‹ከቤተ ክርስቲያን ሹሞች በቀር ሕዝባዊ አይፍረድ› ይላል (ዐንቀጽ 71)፡፡ ታድያ በምን ሕግ ነው የመንግሥት ተወካይ ባለበት የቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤውን የሚያደርገው?

ዛሬ እንደዋዛ የሚከፈተው በር ነገ እንዝጋህ ቢሉት አስቸጋሪ ነው፡፡ አንድ አባት የመንግሥት ተወካይ ይገኝልኝ ባለ ቁጥር የሚፈቀድ ከሆነ፤ ነገ ደግሞ ወንድሜ ባለበት፤ እናቴ ባለችበት፤ ሐኪሜ ባለበት፣ ፖሊስ በተገኘበት ይሄ አጀንዳ ይታይ የሚል ነገር መስማታችን አይቀሬ ነው፡፡ ጋባዡም፤ ተጋባዡም ቆመው ሊያስቡበት ይገባል፡፡ መቼም እንደዘንድሮ የእንጦንስና ጳውሊ ራእይ በተግባር የታየበት ዘመን የለም፡፡

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሐኖም ግምገማ ላይ ወድቀዋል

$
0
0

Tewodros Adhanom
ከልዑል ዓለሜ

እጆቹን አስረዝሞ ለመዝረፍ ይመቸዉ ዘንድ የአለም ጤና ድርጅትን ለመምራት አዲስ አቅጣጫ የቀየሰዉ የትግራይ ነጻ አዉጪዉ ቡድን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተለያዩ የዉጭ ሐገራት በመዘዋወወር የአለም ጤና ርጅትን ለመምራት ቅስቀሳ ሲያደርግ የነበረ መሆኑ ይታወቃል።

ቅዳሜ እለት ወደ አዲስ አበባ የተመለሰዉ ቴዎድሮስ አድሐኖም ሁለት ቀላል መሳሪያ የታጠቁ ወጣቶች የሚጠብቁት ሲሆን የታርጋ ቁጥሩ ኮድ 2_69183 አአ የሆነ ዘመናዊ ላንድ ሮቨር አዉቶሞቢል ተመድቦለት ይንቀሳቀሳል።

አምባሳደር ሙሌ የካቢኔ ዋና ሹሙና አምባሳደር ቦጋለም ከቴድሮስ አድሐኖም ጋር አብረዉ አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን አቶ ህላዌ ዩሱፍ እና የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አቶ ተወልደ ከቴድሮስ አድሐኖም ጋር በአንድነት ሆነዉ በዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ዙሪያ እየደረሰ ያለዉን የአገልግሎት ኪሳራ በተመለከተ ዉይይት ከማድረጋቸዉ በተጨማሪ በህዝቦች ሽግግር ዙሪያ ከእስራኤል ዲፕሎማኦች ጋር ተወያይተዋል።

የመላዉ ሐገራችንን አንጡራ ሐብት ከግል ጥቅማቸዉ አንጻር እንዳሻ ሲጠቀሙበት ማየት እጅግ ያሳዝናል በማለት ቁጭታቸዉን የገለጹልን ባለስልጣን ከእንግዲህ ወዲህ የትግራይ ነጻ አዉጪዉ ቡድን ሐገራችንን የምምራት ብቅት እንደሌለዉና የሐገሪቷ ብሔራዊ ደንነት አደጋ ላይ መዉደቁን አሳስበዉ ኢትዮጵያን ከአደገኛ ችግር ከመታደግ አንጻር ወያኔ ስልጣኑን ለሰፊዉ ህዝብ እንዲያስረክብ አስጠንቅቀዋል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!


የሱዳን መንግሥት 442 ኤርትራውያን ስደተኞችን ወደ አገራቸው አባረረ * የግድቡ ሥራ 70 ከመቶ ተጠናቋል በማለት የወያኔው ባለሥልጣን ሀሰት ዜና አሰራጨ – (የፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ አጫጭር ዜናዎች)

$
0
0
የግንቦት 23 ቀን 2008 ዓ.ም. ዜና (May 31, 2016 NEWS)
#የግድቡ ሥራ 70 ከመቶ ተጠናቋል በማለት የወያኔው ባለሥልጣን ሀሰት ዜና አሰራጨ
#የኢትዮጵያ ፖሊቲካ እስረኞች አንድነት ኮሚቴ ላለፉት 25 ዓመታት ወያኔ ሲያካሄድ የቆየውን የመብት ረገጣ አወገዘ
#የአገር ውስጥ ሴኩርቲ ኃላፊ የነበረውን ግለስብ ለመፍታት ስምምነት ተደረሰ
#የወያኔና የሱዳን ባለሥልጣናት በፖርት ሱዳን ስብሰባ አካሄዱ
#የሱዳን መንግሥት 442 ኤርትራውያን ስደተኞችን ወደ አገራቸው አባረረ
#የቀድሞ የአቮሪ ኮስት ፕሬዚዳንት ባለቤት በሰው ማጥፋት ወንጀል ተከሰው ፍርድ ቤት ቀረቡ
#የግብጽ የጋዜጠኞች ማህበር መሪ ከሁለት ባልደረቦቻቸው ጋር ታሰሩ
#በደቡብ ናይጄሪያ ከአማጽያን በተካሄደ ግጭት ሰላማዊ ሰዎች ሞቱ
አባይ ላይ ይሰራል የሚባለው ግድብ በግብጽና በወያኔ መሀል እንደገና ንትርክን የቀሰቀሰ ሲሆን ሀሰት ዜናዎችን ማሰራጨት ሥራው የሆነው የወያኔ ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ደግሞ የግድቡ ሥራ ሰባ በመቶ ተጠናቋል ሲል መዋሸቱም ተጋለጠ። የግድቡ ሥራ በወያኔ ባለሥልጣናት ሙስና ማለትም የሜቲክ ሀላፊ ጄኔራል ክንፈ የግድቡን ትላልቅ ተርባይኖች ማሰራት በሚመለከት በፈጠረው ዕንቅፋት ያልቅበታል ከተባለው ዓመት ለሁለት ዓመት እንዲዘገይ መደረጉን የገለጹ ክፍሎች፣ ግድቡ 70 በመቶ ተጠናቋል የሚለው ሀሰት ነው ብለዋል። በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ ትገኛለች የተባለችው አዜብ ጎላም ትልቅ ልጇን ሳሊኒ እንዲቀጥርላት ጫና እያደረገች መሆንዋ ተሰምቷል፤
የወያኔ አመራር አባል ሆኖ ለተፈጸሙት ወንጀሎች ሁሉ አንደኛው ተጠያቂ የሆነው ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖምን በዓለም የጤና ድርጅት ሀላፊነት ለማሾም ወያኔ በአፍሪካ ሀገሮች ከፍተኛና በገንዘብም የታጀበ ቅስቀሳ እያካሄደ ሲሆን ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ግን ይህን በመቃወም እያደረጉ ያሉት እንቅስቃሴ ደብዛው የሚታይ አይደለም ሲሉ ታዛቢዎች ተቹ።
grand-renaissance-dam-1.jpg
የኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞች አንደነት ኮሚቴ ላለፉት 25 ዓመታት ወያኔ ሲያካሂድ የቆየውን የመብት ረገጣ አውግዞ ይህ ጸረ ሰብዓዊ መብት ድርጊት እየተባባሰና እየቀነሰ አለመሄዱንም ጠቁሟል ። ይህን የመብት ረገጣ በጋራ ከማጋለጥ አንጻር የሚደረጉትን ጥረቶች የሚያደናቅፉ አጠራጣሪ ግለሰቦች መድረኩን ማጨናነቃቸውን የጠቆመው ኢፖእአኮ የቀድሞው የጋምቤላ አስተዳዳሪ ከደቡብ ሱዳን ተጠልፎ ወይም ተገዶ አዲስ አበባ በሽብርተኝነት ሲከሰስ ይህን በመቃወም ጥገኝነትና ዜግነት የሰጠችው ኖርዌይ ያደረገችው የረባ ጥረት እንዳልነበረ ጠቅሶ አውግዟል። ኖርዌይ ከሁሉም በፊት ከወያኔ ጋር ያላትን የንግድ ጥቅም ለመጠበቅ ሆኖ በመምጣቱ ስደተኞችንም ልትጎዳ፤ ልታባርር መነሳቷንም ጠቅሷል ። እንግዝሊም ዜጋዋ የሆነውና ከየመን የተጠለፈውን አንዳርጋቸው ጽጌ ለማስፈታት ይህ ነው የሚባል ጥረት አለማድረጓ ሊደበቅ አይችልም ያለው ኢፖእአኮ የፖለቲካ እስረኞችን ዕጣ ፈንታ በተመለከተና ደብዛቸው የጠፋውን እስረኞች ጉዳይ ጨምሮ ጠንክራ የተቃውሞና የማጋለጥ እንቅስቃሴ ማድረግ የሚጠበቅም ነው ብሏል።
በቅርቡ በሙስና ክስ የ10ዓመት እስራት የተፈረደበት የወያኔ የብሔራዊ ደህንነትና ሴኩሪቲ የሀገር ውስጥ ሀላፊ የነበረው ወልደሥላሴን በዓመት ውስጥ ለመፍታት ስምምነት በወያኔ ተደርሷል የሚል መረጃ ተገኝቷል ። ብዙ ሚሊዮን ብር በህገወጥ መንገድ ያካበተውና የአዜብ ጎላ አጋር የነበረው ወልደስላሴ በቅርቡ እንፈታሃለን የሚለው ቃል ሌሎች ባለስልጣናትን እንዳያጋልጥ ወይም ምስጢር እንዳያወጣ አድርጎታል ያሉ ክፍሎች በወልደሥላሴ የሙስና እንቅስቃሴ የተሳተፉት የወያኔ ባለስልጣናት ግን አለመከሰሳቸውን ጠቁመዋል። በነጻ የምትኖረው አዜብ ጎላ ለዚህ መረጃ ናትም ተብሏል።
የወያኔ አገዛዝ እና የሱዳን ከፍተኛ ባለስልጣናት ከማክሰኞ ግንቦት 23 ጀምሮ ለሁለት ቀናት በፖርት ሱዳን ስብሰባ የተቀመጡ መሆናቸው ተነግሯል። ስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ይነጋገራል የተባለ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ በወሰን አካባቢ ነጻ የንግድ እንቅስቃሴ ለመፍጠር፤ የጋር ባንክ ስለማቋቋምና ስለድንበር መሬት ይዞታዎች የሚሉት የሚካተቱ መሆናቸው ታውቋል። ወያኔ ከዚህ በፊት ከስድስት መቶ ሺ ጋሻ በላይ ስፋት ያለው ለም መሬት ለሱዳን ለማስረከብ መስማማቱ የሚታወስ ሲሆን በነዋሪው ትግልና መስዋዕትነት ተግባራዊ ለማድረግ ሳይቻል የቀረ መሆኑ ይታወቃል። የወያኔ መሪዎችና የሱዳን ባለስልጣናት በዚህ ስብሰባቸው የህዝብን ተቃውሞ ተቋቁሞ እንዴት ስምምነቱን ተግባራዊ ማድረግ ይቻላል በሚለው ላይ እንደሚወያዩ ይገመታል።
በሚያዝያ ወር ብቻ የሱዳን መንግሥት 442 ኤርትራውያንን ወደ አገራቸው አስገድዶ የመለሰ መሆኑን ሂውማን ራይትስ ዎች የተባለው የሰብዓዊ መብት ተንከባካቢ ድርጅት ገልጿል። ድርጅቱ ሱዳን ኤርትራውያን ስደተኞችን ከሚኖሩበት በማፈን ለአምባገነኑ አገዛዝ ማስረከቡ አግባብ አይደለም ካለ በኋላ የስደተኞችን ችግር ለመቅረፍ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ክፍል ጋር መስራት ነበረበት ብሏል። የሱዳኑ አምባገነን አገዛዝ ከሻዕቢያና ከወያኔ ጋር በቅርበትና በትብብር ሲሰራ የቆየ ሲሆን በተደጋጋሚ ዜጎችን በማፈን ለአምባገኖቹ ሲያስረክብ የቆየ መሆኑ ይታወሳል። የሱዳን መንግስት ባለፉት 25 ዓመታት ሱዳን ውስጥ የነበሩ ስደተኞችን በተለይም የኢሕአፓ አባላትን ለአረመኔውና ለዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ማስረከቡ አይዘነጋም።
የቀድሞ የአይቮሪ ኮስት ፕሬዚዳንት ባለቤት ሲሞኒ ባግቦ በሰው ዘር የማጥፋት ወንጀል ተከሰው በአቢጃን ፍርድ ቤት የቀረቡ መሆናቸው ታውቋል። “ብረቷ እመቤት” የሚል ቅጽል ስም የተሰጣቸው ሚስስ ሲሞኒ በ2002 ዓም ከተካሄደው አገራዊ ምርጫ ጋር በተያያዘ ግጭት የጸጥታ ኃይሎች በገደሏቸው ከ3000 በላይ ሰዎች ቁልፍ ሚና ነባራቸው በሚል ፍርድ ቤቱ የ20 ዓመት ጽኑ እስራት ፈርዶባቸዋል። ፕሬዚዳንት ባግቦ በተመድ የሰላም አስከባሪ ኃይሎች እና ለአሁኑ ፕሬዚዳንት ታማኝ በሆኑት የፈረንሳይ ወታደሮች ጣልቃ ገብነት በቁጥጥር ስር ሲውሉ በወቅቱ የነበረው ግጭት የበረደ መሆኑና በአለም አቀፉ ፍርድ ቤት የተከሰሱ መሆናችው ይታወሳል።
የግብጽ የጋዜጠኞች ማኅበር መሪ ያህያ ካላሽ እና ሁለት ተባባሪዎቻቸው በመንግሥት ላይ ቅስቀሳ አድርጋችኋል፤ የውሸት ወሬ አሰራጭታችኋል በሚል በሲሲ አገዛዝ የጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር የዋሉ መሆናቸውን የዜና ምንጮች ገልጸዋል። የማህበሩ መሪ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የፕሬዚዳንት ሲሲ አገዛዝ ጋዜጠኞችንና የመገናኚያ ብዙሃን ባለሙያዎችን በጅምላ እያየዘ መሆኑን ገልጸው በጋዜጠኞች ላይ ጦርነት ከፍቷል በማለት ድርጊቱን አውግዘው እንደነበር ይታወቃል። የሲሲ መንግሥት በወሰደው የአጸፋ መልስ የጋዜጠኞች ማኅበር መሪን፣ ዋና ጸሐፊውንና የማህበሩን የነጻነት ኮሚቴ ኃላፊን ጽሕፈት ቤቱን ሰብሮ በመግባት በቁጥጥር ሥር አውሏቸዋል። የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶችና ተቃዋሚ ኃይሎች ድርጊቱን በጽኑ አውግዘው የታሰሩት እንዲፈቱ ጠይቀዋል።
 ማክሰኞ ግንቦት 23 ቀን በደቡባዊ ናይጄሪያ በነዳጅ አምራቿ በቢያፍራ ግዛት የናይጄሪያ ወታደራዊ ኃይል ከአማጽያን ኃይላት ጋር ባደረገው ግጭት 20 የሚሆኑ ሰላማዊ ሰዎችና ሁለት የፖሊስ መኮንኖች የተገደሉ መሆናችው ታውቋል። በሳምንቱ መጨረሻ አካባቢ የጸጥታ ኃይሎች አማጽያንን ይዞ የሚንቀሳቀስ ነው በሚል የተሳሳተ ግምት በአንድ ፈጣን ጀልባ ላይ ተኩሰው ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች የገደሉ መሆናቸውም ተዘግቧል። የአካባቢው የወጣት ማኅበር ሰላማዊ ሰዎች በወታደሮች ተገድለዋል በማለት የወነጀለ ሲሆን የአካባቢው ሰዎችም አማጽያኑ ያሉበትን ጠቁሙ በሚል ማስገደጃ በወታደሮቹ ስቃይና ድብደባ የደረሰባችው መሆኑን ገልጸዋል። “ተበቃዮች” በሚል ስም የተደራጀው የአማጽያን ቡድን በአካባቢው ነዳጅ በማውጣት ላይ የሚገኙት የነዳጅ ኩባንያዎች እስከ ግንቦት 23 አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ የሰጠ ሲሆን በተባለው ቀን ካልወጡ ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ድንገተኛ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን መግለጹ ይታወቃል። የናይጄሪያ ወታደራዊ ተቋም ሰሞኑን በአካባቢው ያደረገው ሰፋ ያለ ወታደራዊ ስምሪትና እንቅስቃሴ ከዚህ ማስጠንቀቂያ ጋር የተያያዘ መሆኑ ይገመታል።

‪#‎OromoProtests‬ ለትምህርት ሚኒስትሩ ሽፈራው ግልጽ ደብዳቤ ጻፈ –ባለ6 ነጥብ ምክረሐሳቦችን አቀረበ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ‪#‎OromoProtests‬ 6 ምክረ ሐሳቦችን የያዘ ግልጽ ደብዳቤ ለትምህርት ሚኒስትሩ ላከ:: ‪#‎OromoProtests‬ በግልባጭ ለሁሉም ኢትዮጵያ ተኮር ሚድያዎች በላከው ግልጽ ደብዳቤ አቶ ሽፈራው ሽጉጤን ” እንደክዚህ በፊቱ የኦሮሚያ ተማሪዎች እሮሮ ጆሮ ዳባ ልበስ ተብሎ ፍርደገምድል በሆነ መልኩ አሁን የተቀመጠውን የፈተና መርሃ ግብር ወደ ማስፈጸም የምትሄዱ ከሆነ በእርግጥኝነት ለሚደርሰው ዳግም ሀገርዊ ኪሳራ ተጠያቂነቱ የትምህርት ሚኒስቴር መሆኑን ከወዲሁ ልናስጠነቅቅ እንወዳለን። ” ሲል አስጠንቅቋል::

ሙሉውን ደብዳቤ እንደሚከተለው አቅርበነዋል:-

fetena2

ለክቡር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ፣ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር

ጉዳዩ: የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና (EUEE) በተመለከተ ፍትሃዊ የሆነ የመርሃግብር ምክረ ሃሳብ (program proposal) ስለማቅረብ ይመለከታል።

የተሰረዘውን ፈተና በተመለከተ መስሪያ ቤትዎ ያወጣውን መርሀ ግብር ተመልክተነዋል። ሆኖም ግን መርሃግብሩ ከታች በተገለጹት ምክኒያቶች ሊሻሻል ይገባዋል ብለን ስለምናምን የሚከትለውን ምክረ-ሀሳብ ልናቀርብ እንወዳለን። በደንብ ሊጤን የሚገባው ነጥብ ይህንን ምክረ-ሀሳብ በማጥናቀር ሂደት ውስጥ ከ5000 በላይ ተማሪዎች በግልጽ በሶሻል ሚዲያ ሀሰባቸውን ሰጥውበታል። 123 መምህራንን ከሁሉም የኦሮሚያ ዞኖች በቀጥታ አማክረናል። ተማሪዎቹም ሆኑ መምህራን በዋናው ጉዳይ ተመሳሳይ አቋም አንጸባርቀዋል። የተማሪዎቹም ሆነ የመምህራኑ ሀሳብ የሚያመለክተው በመስሪያ ቤትዎ ለድጋሚ ፈተናው የተሰጠው የአንድ ወር ጊዜ በቂ አለመሆኑንና ጊዜውን ማራዘሙ ግዴታ ነው የሚል ነው። አብዛኛዎቹ የኦሮሚያ ተማሪዎች (80%) ያመለጥንን የ6 ወራት ትምህርት ለማካካስ እና ለፈተናው ለመዘጋጀት ቢያንስ 12 ሳምንታት ወይም 3 ወራት ያስፈልግናል ብለዋል።

እንደአዲስ የወጣው የፈተና መርሀ ግብር ከጊዜ ማጠር በተጨማሪም ሌላ ግድፈት እንደለው ከተማሪዎች እና መምህራኖች ጋር ባደርግነው ምክክር ተገንዝበናል። ይሄውም መርሃግብሩ በረሞዳን ጾም ወር መጨረሻ ላይ መሆኑ በሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች ትክክል አንዳልሆነ ተረድተና።

1) ሳይንሱም እንደሚያረጋግጠው የሰው ጭንቅላት (brain) በፈተና ጊዜ በደንብ ለማሰብ ከፍተኛ የምግብ ሃይል አቅርቦት (high energy supply) ይጠቀማል። የጾም ወቅት ደግሞ የጿሚዎቹ ጭንቅላት ባንጻራዊ መልኩ ሃይል-አጠር (hypo) ስለሚሆን ጿሚ ተማሪዎችን በእንደዚህ ዓይነት ወቅቶች ለዛውም ሙሉ ቀን ረጃጅም ፈተናዎች ላይ እንዲቀመጡ ማድረግ አይመከርም። በተለይ ደግሞ ጉዳዩ ሃይማኖታዊ ሆኖ የሚጾሙና የማይጾሙ ተማሪዎች የሚወስዷቸውን ፈተናዎች በእንደዚህ ዓይነት ወቅቶች መስጠት ትክክል አይደለም ። ግልጽ የሆነ መድሎ (clear discrimination) የማድረግ ያህልም ሊቆጠር የሚችል፤ ማህበራዊ መተሳሰብን ብሎም ህገ-መንግስቱን የሚጥስ ነው።

2) በድጋሚ ባወጠችሁት መግለጫም ፈተናው የኢድ አልፈጥርን ቀን እንደሚዘል ገልጻችኋል። ይህ ማለት በኢድ ዋዜማ እና በማግስቱ ፈተና ይኖራል ማለት ነው። በማህበረሰባችን የበዓላት ሰሞን በግርግርና ለፈተና ትኩረት ፍጹም በማይመቹ (exam mood eroding) ማህበራዊና ቤተሰባዊ መስተጋብሮችና ፌሽታዎች የተሞላ መሆኑን ሁላችንም የምናውቀው ሃቅ ነው። ይህ ደግሞ ተረጋግቶ ለማጥናት የሚያስቸግር ከባባዊ ሁኔታ (distractive environment) በመፍጠር ተማሪዎች ለፈተናው ሙሉ ትኩረት እንዳይሰጡ ያደርጋቸዋል። እናም ፈተናን በእንደዚህ ዓይነት ትልቅ ዓመት በዓል ወቅት ማድረግ ለሃይማኖቱ ተከታይ ተማሪዎች ከፍተኛ ጉዳት እንደሚኖረው ግልጽ ግልፅ ነው።

የምናቀርበው ምክረ-ሃሳብ በተማሪዎቹ ምቾትና አስተያየት ላይ ብቻ በመመርኮዝ እንዳይሆን ሌሎች ባለ ድርሻዎችንም አማክረናል። አዲሱ ፈተና ተዘጋጅቶ፣ ታርሞ ውጤቱ እስኪታወቅ ድረስ ያለውን ሂደት ከግንዛቤ በማስገባት፣ ከዚህ በፊትና አሁንም በትምህርት ሚኒስቴር ውስጥ በፈተና ጉዳዮች ላይ የሰሩ ባለሟያዎችን አማክረናል። እንዲሁም ፈተናው የዩኒቨርሲቲዎችን የሚቀጥለውን አመት መርሀግብር ሊያውክ ስለሚችል ፕረዚደንቶችን ጨምሮ የተለያዩ የዩኒቨርሲቲ መምህራንና የአስተዳደር ዘርፍ ሰራተኞችን አማክረናል።

ስለሆነም ከዚህ በላይ ከገለጽናቸው ምክኒያቶችና ባሰባሰብናችው ሙያዊ አስተያየቶች ላይ ተመርኩዘን ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን የመረሃግብር ምክረ ሃሳቦችን እናቀርባለን። ለተፈጻሚነታቸውም ከእርሶ መስሪያ ቤት በኩል በጎ ምላሽ እንደሚኖር ተስፋ እናደርጋለን:

1) ለተማሪዎቹ ሁለት ወር ቢሰጣቸው እና ፈተናው ከሃምሌ 25 እስከ 28 ወይም ከዚህ ጊዜ በኋላ በሚመቻቹ ወቅት ቢሆን ፍትሃዊ ይሆናል።

2) ባሉት ሁለት ወራት ውስጥ ተማሪዎች በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ ከዚህ ቀደም ያስረከቧቸው መጽሃፍትና ሌሎች የጥናት መርጃ መሳሪያዎች ቢመለስላቸው ጥሩ ይሆናል።

3) በተለይም በኦሮሚያ ተማሪዎች ላልተማሯቸው ክፍለጊዜዎች መምህራኑ ማካካሻ (make up classes) እንዲሰጧቸው ማድረግ ያስፈልጋል። ክረምቱ የእረፍት ጊዜያቸው መሆኑን ከግንዛቤ በማስገባት ለመምህራኑ ማበረታቻ (incentives) የሚደረግበት መንገድ ቢዘጋጅ።

4) ጊዜው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለእረፍት ወደ ቤታቸው የሚመለሱበት በመሆኑ እነዚ ተማሪዎችም የየኣካባቢዎቻቸውን ተፈታኝ ተማሪዎች በቱቶር ማስጠናት ወይም በሌሎች መንገዶች ለፈተናው ዝግጅት ይረዷቸው ዘንድ የማበረታቻ መንገዶች ቢመቻቹ።

5) ለክረምቱ ወደየትውልድ ቦታቸው የሚመልሱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለተፈታኞቹ የማስጠናት (tutorial) ድጋፍ እንዲሰጡ ትምህርት ቤቶች እና የአስተዳደር ክፍሎች ሁኔታዎችን እንዲያመቻቹ ማድረግ።

6 ) በተለይም በኦሮሚያ አካባቢ በፖሊስና በመከላከያ ሃይሎች በተማሪዎች ላይ የሚደረገው ወከባና ተጽዕኖ እንዲቆም፣ እነዚ የታጠቁ አካላት ከትምህርት ቤቶች አካባቢ እንዲርቁ፣ የታሰሩ ተማሪዎችም ተለቀው ከላይ በተጠለተው መልኩ ለፈተናው ዝግጅት እንዲጀምሩ ቢደረግ።

በመጨረሻም፣ ከዚህ በፊት የወሰድናቸው እርምጃዎችም ሆኑ አሁን ያቀረብነው ምክረሃሳብ መነሻነቱ ፍትሃዊነት፣ የእኩል እድል ተጠቃሚነት እንዲሁም የተወዳዳሪነት መርህን የተከተለ የፈተና ስርዓት በሃገሪቱ እንዲረጋገጥ ማድረግ እንደሆነም ደግመን መግለጽ እንወዳለን። ለዚህም ከኛ በኩል ያለውን መልካም ፈቃድ (good faith) ይበልጥ ለማረጋገጥ በእጃችን ያሉትን ሌሎቹን የፈተና ቡክሌቶች ሚስጥራዊነት እንደምንጥብቅና አዲስ ለምታዘጋጁት ፈተናዎች ሚስጥራዊነት መጠበቅም የበኩላችንን አስተዋጽዕ እንደምናደርግ ቃል እንገባለን። ያቀረብነውን ምክረሀሰብ በሚገባ አጢናችሁ በበኩላችሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ባለጉዳዮች አማክራችሁ ፍትሃዊ ውሳኔ ላይ እንደምትደርሱ ተስፋ እናደርጋለን። ነገር ግን አሁን ያቀረብነው ምክረሀሳብ ወደጎን ተትቶ፣ እንደክዚህ በፊቱ የኦሮሚያ ተማሪዎች እሮሮ ጆሮ ዳባ ልበስ ተብሎ ፍርደገምድል በሆነ መልኩ አሁን የተቀመጠውን የፈተና መርሃ ግብር ወደ ማስፈጸም የምትሄዱ ከሆነ በእርግጥኝነት ለሚደርሰው ዳግም ሀገርዊ ኪሳራ ተጠያቂነቱ የትምህርት ሚኒስቴር መሆኑን ከወዲሁ ልናስጠነቅቅ እንወዳለን።
ከሰላምታ ጋር!

‪#‎OromoProtests‬

ግልባጭ፡
-ለኢፌድሪ ፕረዚደንት ጽ/ቤት
– ለኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት
– ለኢፌድሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ጽ/ቤት
– ለኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕረዚደንት ጽ/ቤት
– ለጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ጽ/ቤት
– ለሁሉም ክልሎች ትምህርት ቢሮዎች
– ለመላው የኢትዮጲያ ህዝብ
-ለሁሉም የ 12ኛ ክፍል ተፈጣኝ ተማሪዎች
– ለሁሉም ኢትዮጵያ ተኮር ሚዲያዎች

አስረሽ ምችው!የቁም ተዝካር(ተስካር) –አገሬ አዲስ

$
0
0

ቅጥ ባጣ፣በተሞላቀቀ፣ደንታና ይሉኝታ ቢስ በሆነ ተግባር ወይም ፈንጠዝያ ላይ ሰው ከተሰማራ ድርጊቱ አስረሽ ምችው በሚል ቃል ይገለጻል፡፤በአገራችን ልማድ አንድ ሰው በበሽታ ወይም በዕድሜ ብዛት መሞቻ ቀኑ የደረሰ መሆኑን ሲረዳና ሲገነዘብ  በቁሙ ጥሎ የሚሄደውን ንብረቱን የሚያወርሰውን አውርሶ የተረፈውን በቀሳውስት ጸሎትና በለቅሶ የታጀበ ድግስ ደግሶ  ከወዳጅ ዘመድ ጋር የመሰነባበት ግብዣ ካደረገ የቁም ተስካሩን አወጣ ይባላል።

6ሰሞኑን ሁለቱንም አይነት ድግሶች በኢትዮጵያ ውስጥ ያካሂያደው በስልጣን ላይ ያለው ህወሃት/ኢሕአዴግ ነው።ሁኔታውን በቅርበት የታዘበውና የግብዣው ተቋዳሽ የሆነው ወዳጄ ያካፈለኝን ለማካፈል እወዳለሁ።

ወዳጄን ደውዬ ሰሞኑን ምን አዲስ ነገር አለ?ብዬ ጠየኩት።እሱም ምን አዲስ ነገር አለ ብለህ ነው!የሰሞኑ እሩጫ የኢሕአዴግ የሩብ ዘመን በዓል ዝግጅት ነው ፣ለዚያም ሰፊ ግብዣ በአዲስ አበባ ብቻ ብዙ ሺህ ሰው ተጋብዟል፣እኔም አንዱ ነኝ።በቦታው ተገኝቼ ያየሁትን ጉድ ብነግርህ ይሻላል አለኝ።እንዴት በዚህ ጊዜ ብዙ ሚሊየን ሕዝብ ተርቦ በሚረግፍበት ወቅት መንግሥት ሃያ አምስተኛ ዓመቱን ብዙ ወጭ አውጥቶ ያከብራል አልኩት፤ያለው እኮ ለሥልጣኑ የሚጨነቅ እንጂ ለአገርና ለሕዝብ የሚያስብና ይሉኝታ ያለው መንግሥት አይደለም ይልቅስ ስለግብዣው ልግለጽልህ አለና ወደ ግብዣው አመራ።

የድግሱ ዝግጅት ከወራት በላይ የፈጀ ሲሆን ብዙ ሚሊየን ብርም የወጣበት ነው።በሚሊኒየሙ አዳራሽ ግቭዣ የተጋባዙት በአገር ውስጥና በውጭ አገር የሚኖሩ ለስርዓቱ ለሚቀርቡትና በጥቅም ለተሳሰሩት ግለሰቦች፣ሃብታምና የታወቁ ሰዎች እንዲሁም ያገር ውስጥ ነጋዴዎች ሲሆኑ በሌላ ቀንና በሌላ ቦታ የውጭ አገር የዲፕሎማሲ ልዑካንና ከፍተኛ ባለሥልጣኖችም ተጠርተው የደስታውና የቁም ተስካሩ ተካፋዮች ሆነዋል ሲል አጫውቶኛል።

በግብዣው ላይ የተገኙት በተለይም የነጋዴዎቹ ማህበረሰብ በብዛት የሚተዋወቁ ናቸው፣እኔም አብዛኛዎቹን አውቃቸዋለሁ፤መደበኛ ሰላምታ ከተለዋወጥን በዃላ ስለዝግጅቱ ሁሉም በመገረም መተቸት ጀመረ፤መፈራራት የሚል ነገር አልነበረም፡፤አንዳንዱ እንዴት በዚህ አገር በተራበበት ጊዜ ይህን አይነት አስረሽ ምችው ድግስ ይደገሳል? ሲል ሌላው ደግሞ አስረሽ ምችው ፈንጠዝያው ላለፉት 25 ዓመታት ካለምንም የስልጣን ተካፋይ ብቻውን በጉልበት በመግዛቱ የተሰማውን ደስታ ለመግለጽ ሲሆን ከዚያ ጀርባ ደግሞ ባለበት ውጥረትና በገጠመው ሕዝባዊ ተቃውሞ ለመሰንበቱና በስልጣን ላይ የመቆየቱ ዋስትና በሚያጠራጥር ሁኔታ ላይ በመሆኑ የቁም ተስካሩን ማውጣቱ ሊሆን ይችላልና እንዲህ ያለ ጥሪ ሊደርሰን ስለማይችልና የመጨረሻም ሊሆን ስለሚችል ሆድና ግንባር አይሸሸግም ነብስ ይማር እያልን እንብላ  የሚል አስቂኝና አሳዛኝ ትችት ሲሰነዝር ሌላውም የሕዝብ ገንዘብ ነው፣በራሳችን ገንዘብ የተዘጋጀ እንጂ ኢሕአዴግ ከየት አመጣው?ሲል ሁላችንም በአዎንታ ተቀብለን እየተሳሳቅን የቀረበልንን መብላት ጀመርን።ሰው የልቡን አውጥቶ መናገር ጀምሯል፣ፍርሃት የሚባል ነገር የቀረ ይመስላል ሲል  አቃረጥኩትና ለምን ግብዣውን ተቀበልክ? አልኩት።እሱም መልሶ ሰበብ ፈጥሬ ለመቅረት አስቤ ነበር ግን  ብቀር ከተቃዋሚ ጋር አሰልፈው ችግር ስለሚያመጡብኝ በፍርሃት ሳልወድ ሄጃለሁ ግን መሄዴን ወደድኩት፤ብዙ ለማየትና ለመታዘብ ለአንተም አሁን ሁኔታውን ለመግለጽ ቻልኩ በማለት የታዘባቸውን ነገሮች መግለጽ ጀመረ። “የአንዳንዱ አበላል እህል ቀምሶ የማያውቅ ይመስላል፣የሰው ልጅ እንዲህ በአደባባይ እንደአውሬ ሙዳ ሙዳውን እየቆረጠ ሲጎሰጉስ ማየቱ ያስፈራል።በዱሮ ጊዜ ሰው ግብዣ ቦታ ሲሄድ ግምት ውስጥ ላለመግባት ከቤቱ ቀማምሶ አሞቱን ገታ አድርጎ ነበር፣አሁን ግን የዚያ ተቃራኒ ሆኗል፤ምናልባትም ድግሱን በማሰብ ለሁለት ቀናት ሳይበላ ያደረ ወይም በጧቱ እንግሊዝ ጨው ጠጥቶ ሆዱን አጥቦና ምናምኑን አራግፎ የመጣ ይመስላል።ይሉኝታ የሚባል ነገር በቦታው የለም፤ዳሩስ ይሉኝታቢስ በሆነ መንግሥት የሚተዳደር አገርና የሚዘጋጅ ድግስ ላይ ምን ይሉኝታ ይኖራል ብለህ ነው?ሲል በብስጭት ሁኔታውን ገለጸልኝ።

ወዳጄ በዚህ ብቻ አላቆመም፣ የግብዣው ቦታና አካባቢው ምን እንደሚመስል እንዲህ ሲል ገልጾታል፣- ወደ አዳራሹ በሚወስደው ዙሪያ ገጠም መንገዶች ፖሊስ ተደርድሮ ደሃ የሚባል ዝር እንዳይል ይከላከላል።ሌላውም  ያልተጋበዘው መንገደኛ በአዳራሹ አካባቢ መቆምና መታዘብ የማይችል ሲሆን አካሄዱን ፈጠን ፈጠን አድርጎ ከቦታው እንዲርቅ ይገደዳል።ተጋባዡ የግብዣ ጥሪውን እያሳዬ ይገባል፤ ከዚያ ውጭ አካባቢው ለሌላው ኢትዮጵያዊ የባእድ አገር መሬት ሆኖበት ውሏል።እኔም ወደ አዳራሹ ስገባ፤የአስተናጋጁ ብዛት፣ወከባና የተጨናነቀው መቀመጫ፣የተለያየው የመጠጥ አይነት፣የሰው ብዛትና ሙቀት፣የሙዚቃው ጫጫታ አንድ ላይ ተደራርቦ የማየው ሁሉ ቅዠት መሰለኝና ዞረብኝ።አዲስ አበባ ውስጥ ያለሁ አልመሰለኝም፤ ሃብታሙ ለሆዱ ሰልፍ ገብቶ ሳየው እራሴን ታዘብኩት።የክት ልብሱን የለበሰው ተጋባዥ ተጀንኖ ሲራመድ፣ሴቷም ተሽቀርቅራ ስትኮፈስ(አብዛኛዎቹ የትግሬ ሹርባ የተሰሩና በወርቅ ያጌጡ ሲሆኑ የመሃል አገር ሴቶችም መስሎ ለማደር ሳይሆን አይቀርም እንደዛው ለብሰዋል) የደሃና በርሃብ ብዙ ሚሊየን ወገኖቹ የሚያልቅበት አገር ዜጎች አይመስሉም። እንዲህ ሰው የበዛበትና ሰፊ ዝግጅት ያለው ግብዣ ሳይ በህይወቴ የመጀመሪያ ጊዜየ ነው።በሌላም በኩል መጨናነቁን አይቼ አዳራሹ ቢደረመስ ምን ይውጠኛል እያልኩ በስጋት ሳወጣና ሳወርድ የምግብ መስተንግዶው ሰዓት ደረሰ።በልቤ ነፍስ ይማር እያልኩ የቀረበልኝን በንዴትም በእልህም እንክት አድርጌ በልቼ፣አንድ ማወራረጃ ከወሰድኩ በዃላ አዳራሹን ጥዬ ወጣሁ።

ወዳጄ በመቀጠል፤ይኸ መንግሥት ቀላል አይምሰልህ የሰውን ስነልቦናና ደካማ ጎን በደንብ ተረድቶታል፡፤ሆዳሙን በግብዣ፣ሴሴኛውን በዝሙት፣ሰካራሙን በአልኮል፣ቦታ ፈላጊውን በኩርማን መሬት፣ ቤት ፈላጊውን በኮንዶ፣ ሙሰኛውን(ጉቦኛውን) በገንዘብ፣ ጎሰኛውን በዘፈንና በሹመት ተብትቦ አስሮታል።አንዳንዱንም የወንጀል ተካፋይ አድርጎ ማኖ አስነክቶት በፍርሃት ተሸማቆ ታማኝ አገልጋይ እንዲሆን አድርጎታል።እውነተኛ ተቃዋሚውና አገር ወዳዱ ግን የጥይት እራት ወይም የእስርቤት ሲሳይ ሆኗል።ካለ በዃላ በመቀጠል

በአዲስ አበባ በግንቦት ሃያ ቀን ሰበብ በተደረገው ጣምራ ድግስ በሚሊኒየም አዳራሽ ተብሎ በሚጠራው ሰፊ አዳራሽ ስድስት ሽ(6000)ሰው ሲጋበዝ ለእለቱ ለቁርጥ ብቻ 60 በሬ ታርዶ እንደቀረበ ከዝግጅት ክፍሉ ሠራተኞች ሾልኮ የወጣው ማስረጃ ያረጋግጣል፡በማለት በሂሳብ ወደተደገፈው ዝርዝር ገባ።ለእያንዳንዱ በሬ በአማካይ ሃምሳ ሽህ (50,000)ብር በጠቅላላው ሶስት ሚሊየን ብር(3,000,000) ወጥቷል ማለት ነው፤ይህ ደግሞ በተመጋቢው ቁጥር ከተሰላ አንድ በሬ ለመቶ ሰው ይሆናል ማለት ነው፣በገንዘብ ለእያንዳንዱ ሰው የአምስት መቶ(500)ብር ቅርጫ ይደርሰዋል ማለት ሲሆን ከዚያ ውስጥ አጥንቱና ሌላው ቀርቶ በአሁኑ ገበያ ከ300(ሦስት መቶ ብር )በላይ የሚያወጣ ምርጥ ቁርጥ ሥጋ ይደርሰዋል ማለት ነው።ለልዩ ልዩ መጠጥ የወጣው ወጭ ምን ያህል እንደሆነ በቅጡ ባይታወቅም በሚሊየን የሚቆጠር ገንዘብ ሳይወጣ እንዳልቀረ መገመት አያቅትም።በአገር ውስጥ ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡና ለውጭ አገር እንግዶች የተለየ ግብዣ ሲደረግ ወጭውም እንደዚያው የብዙ ሚሊየን ዶላር እንደሚሆን ይገመታል፣ምክንያቱም እነሱን በቁርጥ ሥጋ መሸኘት ስለማይቻል የግዴታ የፈረንጅ አገር ምግብና መጠጥ ማቅረብ ስለሚያስፈልግ ከውጭ አገር በውጭ ምንዛሪ የሚሸመት ነው።ከአዲስ አበባ ውጭ በጠቅላላው የአገሪቱ ክፍሎች(ክልሎች)እንደአቅሙ ተመሳሳይ አስረሽ ምችውና የቁም ተስካር ድግስ በመካሄድ ላይ ነው።ላለፉት አስር ቀናት የመንግሥት መስሪያ ቤቶች በዚሁ ድግስ ዝግጅት ላይ በማተኮር መደበኛ ስራቸው ተቋርጦ ነበር።በቀጣይነት ሌት ተቀን ሲሰሩ የከረሙት የጸጥታና የፖሊስ እንዲሁም የቤት አፍራሽ ግብረሃሎች ናቸው።

ለመሆኑ አንተስ ባለህበት አገር ምን አዲስ ነገር አለ?እውጭ አገር ካላችሁት እኮ ብዙ እንጠብቃለን።እንደእኛ የቁም እስረኞች አይደላችሁም፤ለመሰብሰብና ለመወያየት ፣በነጻ ለመንቀሳቀስ ትችላላችሁ።ያገራችሁንም ሁኔታ ለዓለም ሕዝብ ልታሰሙበት የምትችሉበት መንገዱ ብዙ ነው።እዚህ ያለነው መንቀሳቀስ አንችልም፤የፖለቲካ ተቃዋሚ ድርጅቶችም በረጅም ገመድ እንደታሰረች ዶሮ ሊንቀሳቀሱ የሚችሉበት አቅጣጫና እርቀት የተወሰነ ነው፤ከዚያ ሊያልፉ አይችሉም፣ድፍረቱም የላቸውም።አንዱ ሲጠቃ ሌላው በዝምታ ያያል፣እሱም በተራው ይደቆሳል። አይችሉም፤በተጨማሪም ህብረት የላቸውም፣እርስ በርሳቸው ሲሻኮቱ ነው የሚታዩት።ሌሎቹም በተቃዋሚ ስም በመንግሥት ድጎማና ፈቃድ የሚንቀሳቀሱ አሳሳቾች ናቸው፤ካለ በዃላ ስለውጩ ትግል እንድነግረው ጠየቀኝ።እኔም ከአገር ቤት ልዩነቱ የቦታ እርቀት ከመሆኑ ባሻገር በተመሳሳይ ሁኔታ ላይ እንደሆነ፤ድርጅቶች እርስ በርሳቸው የሚጠላለፉና አንዱ ሌላውን እያወገዘ የሚሄድ፣አንድና ሁለት ሰው ይዞ ድርጅት ነኝ በማለት የየራሱን ዘውድ በኪሱ ይዞ የሚዞር፣እንተባበር ሲሉት እራሱን እያሳበጠ ጥሪውን የማይቀበል፣የተዝረከረከ ተቃዋሚ የበዛበት እንደሆነና በሌላውም በኩል አብዛኛው ለራሱ ኑሮ የሚጨነቅ፣ስለአገሩ ደንታ የሌለው፣የሚፈልገውን  ቦታና ቤት ለማግኘት ከመንግሥት ባለስልጣኖች ጋር የሚያፈደፍድ፣ለአገር ጉዳይ ከሚሰበሰበው ይልቅ በድግስና አስረሽ ምችው የሚተራመሰው እንደሚበዛ አስረዳሁት።በየጊዜው በመንግሥቱ አምባሳደሮች ተመሳሳይ ዝግጅት በሚስጥር እየተዘጋጀ ሆድ አደሩ እንደሚሳተፍ ስነግረው ታዲያ ኢሕአዴግ ለዘላለሙ ይኖራል በለኛ! ሲል በመገረም ስሜት ውስጥ እንዳለ ጨዋታችንን ሳንጨርስ የስልክ መስመራችን ተቋረጠና ተለያየን።

የሰማሁት ሲረብሸኝ አመሸ፤እንዴት መንግሥት ነኝ የሚል አካል፣ እንደሰው ማሰብ የሚችል ሰው በገዛ አገሩ ላይ ይህን አይነት በደልና ግፍ ይፈጽማል?በሚሊየን የሚቆጠረው ወገኑ በርሃብ ስቃይ ሲረግፍና የውጭ አገር በጎ አድራጊዎች እርዳታ ለመሰብሰብ ሲሯሯጡ፣በየአገሩ ቴሌቪዥን መስኮት ላይ የሞት ሲቃ የሚያጣጥሩ ህጻናትና አዛውንት እየታዩ እርሃብ መኖሩን የሚክድ መንግሥት ይህን አይነት አስረሽ ምችው ድግስ ማድረጉ ተገቢና የጤና ነው?ወይስ ወዳጄ እንዳለው ተስፋ በመቁረጥ የተዘጋጀ የቁም ተዝካር! አልኩና  ሆነም ቀረም ታሪኩን ለሌላው ማካፈል አለብኝ አልኩና በዚህ መልክ ለማቅረብ ወሰንኩ።

የህወሃት/ኢሕአዴግ ሃያ አምስተኛው ዓመት ድግስ የመጨረሻው እንዲሆን እንተባበር!!

አገሬ አዲስ

“ለትግላችን ብቸኛውን ሚና የሚጫወተውን የኤርትራ ሕዝብና መንግስትን ለማዳከም የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሚያደርገውን ሴራ ለመቃወም ይህንን ፒትሽን ፈርሙ”–ነአምን ዘለቀ (አ. ግንቦት 7)

$
0
0

Neamin Zeleke

‘ዛሬ ለትግላችን ከፍተኛ ብቸኛ ሚና የሚጫወት ሕዝብና መንግስት የኤርትራ ሕዝብና መንግስት ነው:: ይህን ሕዝብና መንግስት ለመፈታተን ለማዳከም አንዳንድ የዓለም አቀፍ ሃይሎች ብዙ ሴራ እየጎነጎኑ ነው:: ይህንን ለመቋቋም የኤርትራ ሕዝብ ከውስጥም ከውጭም የተቀነባበረ የፒትሽን ዘመቻ እያደረገ ነው:: ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ:: ይህንን ፒትሽን ዘመቻ ለመተባበር በንቅናቄያችን ዓለም አቀፍ መዋቅር በኩል የኛ አባላት እና ደጋፊዎች ፒትሽኑን እንዲፈርሙ አሰራጭተናል:: እኛም ፈርመናል”

አቶ ነአምን ዘለቀ (የአርበኞች ግንቦት 7 አመራር) – ቭዲዮን ይመልከቱ – ፒትሽኑን በቀጥታ ለመፈረም እዚህ ይጫኑ

ፒትሽኑን ለመፈረም በቅድሚያ ለምን መፈረም እንዳለብዎ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ፈተናን መስረቅ ለስብሃት ነጋ ትግል ለሌላው ወንጀል ያደረገው ማነው?

$
0
0

የአገራችን የሰሞኑ አብይ ፖለቲካ መነጋገሪያ

<<የ12ተኛ ብሔራዊ ፈተና አስቀድሞ ተሰርቆ መውጣት>> እና ተያይዞ የመጣው የስርዓቱ የተለመደ አስቂኝ መግለጫ ነው። <<ፈተና አልተሰረቀም ፣ፈተናው ተሰርቋል>>

የሚሉት መግለጫዎች በእርግጥም አገሪቱን የሚመሯትን ሰዎች አቅም ጭምር ያጋለጠ ነው። የፈተናውን መሰረቅ የትግል አካል አድርገው ላልቆጠሩ የሚያቀርቡት መከራከሪያ የተምታታ ነው። ፈተናውን መስረቅ እንደ ትግል ስትራቴጂ ለቆጠሩት ብቻ ሳይሆን ውለው አድረው ለገባቸውም ድርጊቱ ውጤታማ አንዱ የሰላማዊ ትግል ስልት አካል ነው። አገር ተጎዳ የአገር ሀብት ወደመ የሚሉት ይሄ በጥቅል የሚቀርቡ ጉንጭ አልፋ መከራከሪያዎች ለሞኑ የአገር ሀብት የሚባክነው በነማን ነው የሚል ጥያቄ ራሳቸውን እንዲጠይቁ የሚያስገድድ ነው።። ስብሃት ነጋ በአገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ታጋይነታቸውን ሲዘክሩ በረሃ ከመውረዳቸው በፊት የትምህርት ቤት ዳይሬክተር እያሉ የ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ሰርቀው፤ መልስ ተዘጋጅቶ የትግራይ ተማሪዎችን መጥቀማቸውን የተናገሩትን አንረሳም።

sebehat.jpg

ያኔ ስብሃትን ሲያሞግሱ የነበሩ የስርዓቱ ደጋፊዎች ዛሬ ስድስት ወር ሙሉ መከራቸውን ሲያዩና በባዶ እጃቸው ስለተቃወሙ ፍዳ ሲበሉ ለነበሩ የኦሮሞ ተማሪዎች ፈተና ስላልተራዘመ ለጉልበት ውሳኔ የተሰጠውን የአጸፋ ምላሽ ከትግል አለመቁጠር ያስተዛዝባል።ቤተሰብ ይጎዳል፣የተማሪዎች ሞራል እና የመሳሰለው ጉዳይ ማንሳቱ ባይከፋም የዚህ ሁሉ መዘዝ ግን ስልጣን በጠመንጃ ይዘው እኛ ያልነው ካልሆነ ለሚሉት እምቢኝ በቃን ማለት የታየበት ግልጽ እርምጃ ነው። ዛሬም ሲደናበሩ የተሰረቀውን ፈተና በሮመዳን ጾም ፍቺ ወቅት ማድረግ ያው የተለመደው እብሪት ነው። በጨዋ ቋንቋ የቀረበላቸው ግልጽ ደብዳቤ ነገ ሌላ ጫጫታ ከማምጣቱ በፊት ቆም ብለው እንዲያስቡ ይጠይቃል። የኦሮሞ ሰላማዊ ተቃውሞ አራማጆች ተከታዩን ግልጽ ደብዳቤ ጽፈዋል። ልብ ያለው ልብ ይበል ነው። እነ ለአገር ተቆርቋሪዎች አሁን ለመንግስታችሁ ጮክ ብላጭሁ ይህቺን ደብዳቤ አንብቡለት።

ለክቡር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ፣ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር

ጉዳዩ: የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና (EUEE) በተመለከተ ፍትሃዊ የሆነ የመርሃግብር ምክረ ሃሳብ (program proposal) ስለማቅረብ ይመለከታል።

የተሰረዘውን ፈተና በተመለከተ መስሪያ ቤትዎ ያወጣውን መርሀ ግብር ተመልክተነዋል። ሆኖም ግን መርሃግብሩ ከታች በተገለጹት ምክኒያቶች ሊሻሻል ይገባዋል ብለን ስለምናምን የሚከትለውን ምክረ-ሀሳብ ልናቀርብ እንወዳለን። በደንብ ሊጤን የሚገባው ነጥብ ይህንን ምክረ-ሀሳብ በማጥናቀር ሂደት ውስጥ ከ5000 በላይ ተማሪዎች በግልጽ በሶሻል ሚዲያ ሀሰባቸውን ሰጥውበታል። 123 መምህራንን ከሁሉም የኦሮሚያ ዞኖች በቀጥታ አማክረናል። ተማሪዎቹም ሆኑ መምህራን በዋናው ጉዳይ ተመሳሳይ አቋም አንጸባርቀዋል። የተማሪዎቹም ሆነ የመምህራኑ ሀሳብ የሚያመለክተው በመስሪያ ቤትዎ ለድጋሚ ፈተናው የተሰጠው የአንድ ወር ጊዜ በቂ አለመሆኑንና ጊዜውን ማራዘሙ ግዴታ ነው የሚል ነው። አብዛኛዎቹ የኦሮሚያ ተማሪዎች (80%) ያመለጥንን የ6 ወራት ትምህርት ለማካካስ እና ለፈተናው ለመዘጋጀት ቢያንስ 12 ሳምንታት ወይም 3 ወራት ያስፈልግናል ብለዋል።

እንደአዲስ የወጣው የፈተና መርሀ ግብር ከጊዜ ማጠር በተጨማሪም ሌላ ግድፈት እንደለው ከተማሪዎች እና መምህራኖች ጋር ባደርግነው ምክክር ተገንዝበናል። ይሄውም መርሃግብሩ በረሞዳን ጾም ወር መጨረሻ ላይ መሆኑ በሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች ትክክል አንዳልሆነ ተረድተና።

1) ሳይንሱም እንደሚያረጋግጠው የሰው ጭንቅላት (brain) በፈተና ጊዜ በደንብ ለማሰብ ከፍተኛ የምግብ ሃይል አቅርቦት (high energy supply) ይጠቀማል። የጾም ወቅት ደግሞ የጿሚዎቹ ጭንቅላት ባንጻራዊ መልኩ ሃይል-አጠር (hypo) ስለሚሆን ጿሚ ተማሪዎችን በእንደዚህ ዓይነት ወቅቶች ለዛውም ሙሉ ቀን ረጃጅም ፈተናዎች ላይ እንዲቀመጡ ማድረግ አይመከርም። በተለይ ደግሞ ጉዳዩ ሃይማኖታዊ ሆኖ የሚጾሙና የማይጾሙ ተማሪዎች የሚወስዷቸውን ፈተናዎች በእንደዚህ ዓይነት ወቅቶች መስጠት ትክክል አይደለም ። ግልጽ የሆነ መድሎ (clear discrimination) የማድረግ ያህልም ሊቆጠር የሚችል፤ ማህበራዊ መተሳሰብን ብሎም ህገ-መንግስቱን የሚጥስ ነው።

2) በድጋሚ ባወጠችሁት መግለጫም ፈተናው የኢድ አልፈጥርን ቀን እንደሚዘል ገልጻችኋል። ይህ ማለት በኢድ ዋዜማ እና በማግስቱ ፈተና ይኖራል ማለት ነው። በማህበረሰባችን የበዓላት ሰሞን በግርግርና ለፈተና ትኩረት ፍጹም በማይመቹ (exam mood eroding) ማህበራዊና ቤተሰባዊ መስተጋብሮችና ፌሽታዎች የተሞላ መሆኑን ሁላችንም የምናውቀው ሃቅ ነው። ይህ ደግሞ ተረጋግቶ ለማጥናት የሚያስቸግር ከባባዊ ሁኔታ (distractive environment) በመፍጠር ተማሪዎች ለፈተናው ሙሉ ትኩረት እንዳይሰጡ ያደርጋቸዋል። እናም ፈተናን በእንደዚህ ዓይነት ትልቅ ዓመት በዓል ወቅት ማድረግ ለሃይማኖቱ ተከታይ ተማሪዎች ከፍተኛ ጉዳት እንደሚኖረው ግልጽ ግልፅ ነው።

የምናቀርበው ምክረ-ሃሳብ በተማሪዎቹ ምቾትና አስተያየት ላይ ብቻ በመመርኮዝ እንዳይሆን ሌሎች ባለ ድርሻዎችንም አማክረናል። አዲሱ ፈተና ተዘጋጅቶ፣ ታርሞ ውጤቱ እስኪታወቅ ድረስ ያለውን ሂደት ከግንዛቤ በማስገባት፣ ከዚህ በፊትና አሁንም በትምህርት ሚኒስቴር ውስጥ በፈተና ጉዳዮች ላይ የሰሩ ባለሟያዎችን አማክረናል። እንዲሁም ፈተናው የዩኒቨርሲቲዎችን የሚቀጥለውን አመት መርሀግብር ሊያውክ ስለሚችል ፕረዚደንቶችን ጨምሮ የተለያዩ የዩኒቨርሲቲ መምህራንና የአስተዳደር ዘርፍ ሰራተኞችን አማክረናል።

ስለሆነም ከዚህ በላይ ከገለጽናቸው ምክኒያቶችና ባሰባሰብናችው ሙያዊ አስተያየቶች ላይ ተመርኩዘን ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን የመረሃግብር ምክረ ሃሳቦችን እናቀርባለን። ለተፈጻሚነታቸውም ከእርሶ መስሪያ ቤት በኩል በጎ ምላሽ እንደሚኖር ተስፋ እናደርጋለን:

1) ለተማሪዎቹ ሁለት ወር ቢሰጣቸው እና ፈተናው ከሃምሌ 25 እስከ 28 ወይም ከዚህ ጊዜ በኋላ በሚመቻቹ ወቅት ቢሆን ፍትሃዊ ይሆናል።

2) ባሉት ሁለት ወራት ውስጥ ተማሪዎች በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ ከዚህ ቀደም ያስረከቧቸው መጽሃፍትና ሌሎች የጥናት መርጃ መሳሪያዎች ቢመለስላቸው ጥሩ ይሆናል።

 

3) በተለይም በኦሮሚያ ተማሪዎች ላልተማሯቸው ክፍለጊዜዎች መምህራኑ ማካካሻ (make up classes) እንዲሰጧቸው ማድረግ ያስፈልጋል። ክረምቱ የእረፍት ጊዜያቸው መሆኑን ከግንዛቤ በማስገባት ለመምህራኑ ማበረታቻ (incentives) የሚደረግበት መንገድ ቢዘጋጅ።

4) ጊዜው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለእረፍት ወደ ቤታቸው የሚመለሱበት በመሆኑ እነዚ ተማሪዎችም የየኣካባቢዎቻቸውን ተፈታኝ ተማሪዎች በቱቶር ማስጠናት ወይም በሌሎች መንገዶች ለፈተናው ዝግጅት ይረዷቸው ዘንድ የማበረታቻ መንገዶች ቢመቻቹ።

5) ለክረምቱ ወደየትውልድ ቦታቸው የሚመልሱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለተፈታኞቹ የማስጠናት (tutorial) ድጋፍ እንዲሰጡ ትምህርት ቤቶች እና የአስተዳደር ክፍሎች ሁኔታዎችን እንዲያመቻቹ ማድረግ።

6 ) በተለይም በኦሮሚያ አካባቢ በፖሊስና በመከላከያ ሃይሎች በተማሪዎች ላይ የሚደረገው ወከባና ተጽዕኖ እንዲቆም፣ እነዚ የታጠቁ አካላት ከትምህርት ቤቶች አካባቢ እንዲርቁ፣ የታሰሩ ተማሪዎችም ተለቀው ከላይ በተጠለተው መልኩ ለፈተናው ዝግጅት እንዲጀምሩ ቢደረግ።

በመጨረሻም፣ ከዚህ በፊት የወሰድናቸው እርምጃዎችም ሆኑ አሁን ያቀረብነው ምክረሃሳብ መነሻነቱ ፍትሃዊነት፣ የእኩል እድል ተጠቃሚነት እንዲሁም የተወዳዳሪነት መርህን የተከተለ የፈተና ስርዓት በሃገሪቱ እንዲረጋገጥ ማድረግ እንደሆነም ደግመን መግለጽ እንወዳለን። ለዚህም ከኛ በኩል ያለውን መልካም ፈቃድ (good faith) ይበልጥ ለማረጋገጥ በእጃችን ያሉትን ሌሎቹን የፈተና ቡክሌቶች ሚስጥራዊነት እንደምንጥብቅና አዲስ ለምታዘጋጁት ፈተናዎች ሚስጥራዊነት መጠበቅም የበኩላችንን አስተዋጽዕ እንደምናደርግ ቃል እንገባለን። ያቀረብነውን ምክረሀሰብ በሚገባ አጢናችሁ በበኩላችሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ባለጉዳዮች አማክራችሁ ፍትሃዊ ውሳኔ ላይ እንደምትደርሱ ተስፋ እናደርጋለን። ነገር ግን አሁን ያቀረብነው ምክረሀሳብ ወደጎን ተትቶ፣ እንደክዚህ በፊቱ የኦሮሚያ ተማሪዎች እሮሮ ጆሮ ዳባ ልበስ ተብሎ ፍርደገምድል በሆነ መልኩ አሁን የተቀመጠውን የፈተና መርሃ ግብር ወደ ማስፈጸም የምትሄዱ ከሆነ በእርግጥኝነት ለሚደርሰው ዳግም ሀገርዊ ኪሳራ ተጠያቂነቱ የትምህርት ሚኒስቴር መሆኑን ከወዲሁ ልናስጠነቅቅ እንወዳለን።

ከሰላምታ ጋር!

#‎OromoProtests

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live