Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባሉ ብርሃነ ኪዳነማርያም ከስልጣኑ ተባረረ

0
0

timthumb

(ዘ-ሐበሻ) የሕወሃት ማ ዕከላዊ ኮሚቴ አባልና ከአቶ ስብሃት ነጋ ጋር የቅርብ የቢዝነስ አጋር የነበረው የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮሮፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አይተ ብርሃነ ኪዳነ ማርያም ከስልጣኑ መባረሩ ተሰማ:: በዚህ ሳምንት ሌላው የሕወሓት አባልና የድህንነት ሚ/ር ምክትል አቶ ኢሳያስ መባበሩም አይዘነጋም::

በሃገረ ኤርትራ የተወለደውና የሕወሓት ታማኝ ሰዎች ማከከል አንዱ በመሆኑ ሕወሃት የሚያስተዳድረው ኤፈርት ዳይሬክተርም ነበር:: የቀድሞው የህወሃት ፕርፓጋንዳ መፈልፈያ ዋልታ ኢንፎርማሽን ማዕከልም ዋና ሰው ሆኖ ያገለግል የነበረው አቶ ብርሃነ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲና የወጋገን ባንክ የቦርድ አባል ነበር::

አቶ ብርሃነ የኢፈርት ዳይሬክተርነትን ሥራ ከወ/ሮ አዜብ ተረክቦ ይሰራ እንደነበር አይዘነጋም::

አቶ ብርሃነ ኪዳነማርያም ይህደጎ ከስልጣናቸው መባረር እንዲሁም ከጥቂት ቀናት በፊት የድህነቱ ምክትል ሰው አቶ ኢሳያስ መሰናበት በኋላ ወይዘሮ አዜብ ከነልጃቸው አሜሪካ መግባታቸው አነጋጋሪ ሆኗል::


አርሰናል በ35 ሚሊዮን ፓውንድ ሚድፊልደር አስፈረመ

0
0

arselan xhaka

ስሜነህ ታደሰ | ለዘ-ሐበሻ ስፖርት

(ዘ-ሐበሻ) ስፔናዊውን ሚካኤል አርቴታን ያጣው አርሰናል ስዊዘርላንድዊውን የመሐል ተጫዋች በ35 ሚሊዮን ፓውንድ ማስፈረሙን አስታወቀ::

አርሰናል ስዊዘርላንዳዊው ግራኒት ሳካን ከቦርሲያ ሞንቼግላባ ያስመጣው ከ35 ሚልዮን ፓውንድ የዝውውር ሂሳብ በተጨማሪ በሳምንት 110ሺህ ፓውንድ ደመወዝ ለመክፈልም በመስማማት ነው::

“ለረዥም ጊዜ ስናልመው የነበረውን ተጫዋች አግኝተናል” ያሉት የአርሰናሉ አለቃ አርሴን ዌንገር ለረዥም ጊዜ ተጫዋቹን ወደ ኤመሬትስ ስታዲየም ለማምጣት ይሰሩ እንደነበር ተናገረዋል:: የመሀል ሜዳው ተጫዋች የቡንደስሊጋ እና የቻምፒዮንስ ሊግ ልምድ እንዳለው ያወሱት ዌንገር የ23 ዓመቱን ስዊዘርላንዳዊ ክለባቸውን በሚቀጥለው ሲዝን እንደሚያጠናክረው ያላቸውን ዕምነት ገልጸዋል::

በባሴል ከ2010 – 2012 የተጫወተው ሳካ 67 ጊዜ ተሰልፎ 3 ጎሎቾን አስገብቷል:: እንዲሁም ለቦርሲያ ሞንቼግላባህ ከ2012 እስከ 2016 ለ134 ጨዋታዎችን አድርጎ 9 ጎሎችን አግብቷል:: ለ41 ጊዜያት ያህል ለስዊዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን የተጫወተው ሻካ 6 ጎሎችን አስቆጥሯል::

የራስ መንግስት መመስረትና ነጻነት ምንና ምን ናቸው? – (ሊያነቡት የሚገባ)

0
0

በአቻምየለህ ታምሩ

ዛሬ መጻፍ የፈለግሁት በእንግሊዝኛ Independence እና Freedom ስለሚባሉ ሁለት የፖለቲካ ትግል መሰረታዊ ፍሬ ሀሳቦች ነው። ወደ አማርኛ ስንመልሳቸው Independence ማለት «ተለይቶ የራስ መንግስት መመስረት» ወይንም «የራስ አገር መፍጠር» ማለት ሲሆን Freedom ማለት ደግሞ በሚኖሩበት አገር ውስጥ ነጻነት ማግኘት ወይንም ነጻ መሆን ማለት ነው። ስለዚህ ለIndependence የሚደረግ የፖለቲካ ትግል ማለት ተለይቶ የራስ መንግስት ለመመስረት ወይንም የራስ አገር ለመፍጠር የሚደረግ ትግል ማለት ሲሆን ለFreedom የሚደረግ ትልግ ማለት ደግሞ በሚኖሩበት አገር ውስጥ ለነጻነት ወይንም ነጻ ለመሆን የሚደረግ ትግል ማለት ነው።
Tensaye

በአገራችን ላለፉት ሃምሳ አመታት በብሄረሰብ ማንነት የተሰባሰቡ የዘር ድርጅቶች ያደረጉት የLibration ፍልሚያ [ዛሬም እያደረጉት ያለው የፖለቲካ ቁማር ጭምር] ለነጻነት የተደረገ ንቅናቄ ሳይሆን ተለይቶ የራስን መንግስት ለመመስረት ወይንም የራስን አገር ለመፍጠር ያካሄዱት ትግል ነው። በመሰረቱ ለነጻነት መታገል በብሔረሰብ መደራጀትን አይጠይቅም። በብሄረሰብ ተደራጅቶ መታገል ሊያስገኘው የሚችለው ብቸኛ ግብ የራስ መንግስት መመስረት ወይንም የራስ አገር መፍጠር ብቻ ነው። በብሄረሰብ ተደራጅቶ የራስ መንግስት ለመመስረት መታገል ነጻነትን ሊያጎናጽፍ አይችልም። የራስ አገር ለመመስረት በሚደረግ ትግል የኦሮሞ ገበሬ የመሬት ባለቤት ሊሆን አይችልም። የኦሮሞ ገበሬ የመሬት ባለቤት ሊሆን የሚችለው ለነጻነት በሚደረግ ትግል ብቻ ነው። የራስ አገር ለመመስረት በሚደረግ ትግል የመሬት ባለቤት መሆን የሚቻል ቢሆን ኖሮ ዛሬ የትግራይና የኤርትራ ገበሬ የመሬት ባለቤትና ባለ መብት በሆነ ነበር።

የአገራችን የብሔረሰብ ድርጅቶች ትልቁ ስኬት እናቱ ገበያ የሄደችበትን የብሔረሰባቸው አባል እናትህ ሞታለች ብለው ማስለቀስ መቻላቸውና «ጭቆና እየደረሰበኝ ያለው ስልጣን ላይ ያሉት ሰዎች [ማለትም ጨቋኞቹ] የብሔረሰቤ አባላት ስላልሆኑ ነው» ብሎ የሚያምን ትውልድ መፍጠራቸው ብቻ ነው። ይህን ስብከታቸውን ለማንበርም «ተጨቆነ» በሚሉት ብሔረሰብና «ጨቋኝ» ነበር ባሉት ብሔረሰብ መካከል ምንም አይነ ግንኙነት ወይንም ዝምድና እንደሌለ የፖለቲካ ታሪክ ፈጥረዋል። «ተጨቆነ» በሚሉት ብሔረሰብ መካከልና «በጨቋኙ» ብሔረሰብ መካከል የነበሩትን ትስስሮችና አንድ የሚያደርጉትን ክሮች ሁሉ በጥሰዋል። በአንድነቱ ጊዜ «የኔ ብሔረሰብ አባላት ናቸው» የሚሏቸው ሰዎች የነበራቸውን አስተዋጽኦ አሳንሰዋል፤ አኮስሰዋል። ሰዎቹንም ጭቃ ቀብተዋቸዋል። የነበራቸውን ሚናም እንዳልነበረ አድርገውታል። ራስ አበበ አረጋይ፣ ጄኔራል ሙሉጌታ ቡሊ፣ ጄኔራል ደምሴ ቡልቶ፣ገረሱ ዱኪ፣ ይልማ ደሬሳ፣ ራስ መንገሻ ስዩም፣ ራስ ስዩም መንገሻ፣ ሀረጎት አባይ፣ ሎሬንሶ ታዕዛዝ ወዘተ የራስ አገር ለመፍጠር በታገሉና አሁንም እየታገሉ ባሉ የዘር ፖለቲከኞች ፕሮፓጋንዳ ዶግ አመድ ሆነዋል።

ዛሬም ድረስ የአገራችን የዘር ድርጅቶች «የምንጨቆነው ጨቋኞቹ የኛ ብሄረሰብ አባላት ስላልሆኑ ነው» የሚሉት የዘር ቅስቀሳ የራሳቸውን አገር ለመመስረት ሲሉ የብሔረሰቦቻቸው አባላት የሆኑ ወገኖቻቸው ትግል እንዲያደርጉ የሚያነሳሱበት ዋነኛ ዘዴያቸው ነው። ተከታዩም ስላልነቃ ጥሪያቸውን ሰምቶ አብሯቸው ይጎተታል። እነዚህ የራሳቸውን አገር ለመመስረት የሚታገሉ የዘር ድርጅቶች «ስልጣን ላይ ያሉት ጨቋኞች የሚጨቁኑኝ የብሔረሰቦቻችን አባላት ስላልሆኑ ነው» የሚለውን ያረጀ ስብከታቸውን የበለጠ ለማሳመን ደግሞ በአንድነቱ ጊዜ የነበሩ የብሔረሰባቸው አባላት የሆኑ ልሂቃን ለአገራቸው ሲሉ ያደረጉትንም አዲስ ትርጓሜ በመስጠት ስራዎቻቸውንና ሰዎቹን አሳንሰዋቸዋል።

ባለ ቅኔው ጸጋዬ ገብረመድህን የዚህ የማሳነስ ዘመቻ ሰለባ ነው። ባለ ቅኔው ጸጋዬ «በማናቸውም የአለም ህዝብ ታሪክ ውስጥ የሚገኝ የየአገሩ ወንዝ ጉዞ የየአገሩ ሰፊ ህዝብ የየትውልድ ጉዞ ተምሳሌት ሆኖ ይቀረጻል» በማለት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙት እንደ አባይ፣ አዋሽ፣ ዋቢ ሸበሌ፣_ ተከዘ፣ መረብና ሌሎቹንም ወንዞች ከኢትዮጵያ አፈጣጠር ጀምሮ የኢትዮጵያን ታሪክና ትውልዶች ጉዞ በተምሳሌትነት ለማሳየት በኢትዮጵያውያንና በባዕድ የስነጽሁፍ ሰዎች ሳይቀር እንደተቀረጹ ያስረዳና ከባዕድ አገራትም ኤፍራጦስና ጤግሮስ በሜሶፖታሚያ፤ ቴምስ በእንግሊዝ፤ ሚሲሲፒ በአሜሪካና ዶን በሩሲያ የየዘመኑ ታላላቅ ጸሀፍት ዘንድ የየአገራቱን ህዝብ ታሪክና የየትውልድ ጉዞ ለማሳየት በተምሳሌትነት እንደቀረቡ አውስቶ እሱም በብዕሩ የኢትዮጵያን ታሪክና የየትውልድ ጉዞ በአዋሽ ተምሳሌትነት የጻፈውን አስደማሚ ግጥም ኦነጋውያን «ስለኦሮሞ ህዝብ እጣ ፈንታና መጻኢ እድል» የጻፈው አድርገው በማሳነስ አዲስ ትርጓሜ ሰጥተውበታል።

ከዚህ በተጨማሪ እነዚህ የራሳቸውን አገር ለመመስረት የሚታገሉ የዘር ድርጅቶች በአንድነቱ ጊዜ የነበሩ አንዳንዶቹን የብሔረሰባቸው አባላትና አስተዋጿቸውን ደግሞ እንዳላዩ አልፈዋቸዋል። የክቡር ዘበኛ ኦርኬስትራ የዘፈናቸውን በርካታ የኦሮምኛ ዘፈኖች፤ዳግማዊ ምኒልክ ቤተ መንግስት ደጃፍ ላይ ቁጭ ብለው እነ ጥላሁን ገሰሰና ብዙነሽ በቀለ የዘፈኑትን ያንን ሁሉ የኦሮምኛ ዘፈን ኦነጋውያን እንዳልነበረ ቆጥረውታል። ሻዕብያም በበኩሉ ከጥላሁን ገሰሰና ብዙነሽ በቀለ እኩል የትግርኛ ዘፈናቸው ሸክላና ካሴት ይሸጥላቸው የነበሩትን እነ በረኸት መንግስተዓብንና ትበርህ ተስፋሁነኝን እንዳልነበሩ፤ በኢትዮጵያ ማዕቀፍም ያ ሁሉ ነገር እንዳነበረ በመቀስቀስ በውሸት አገር ፈጥሯል።

የራሳቸውን አገር ለመመስረት የሚታገሉ የዘር ድርጅቶች ከዚህ በከፋም በአንድነቱ ጊዜ የነበሩና እስከመጨረሻው ድረስ በኢትዮጵያዊነት አቋማቸው ጸንተው የቆሙትን የብሔረሰባቸው አባላት ስለኢትዮጵያ ያደረጉትን ሁሉ የከሀዲዎች ድርጊት አድርገው አጣጥለውታል። ራስ ጎበና ዳጨ፣ ጄኔራል ጃጋማ ኬሎና አስፍሀ ወልደ ሚካዔል የዚህ የዘረኞች የከሀዲነት ክስ ሰለባዎች ናቸው። በቤተ ኦነግ «ጎበና» የሚለው ስም ሲጠራ የክህደት፣ የጸረ ኦሮሞነትና የጥፋት ተላላኪነት መገለጫ ሆኗል። ይህ ሁሉ ትርክት «የምንጨቆነው ጨቋኞቹ የኛ ብሄረሰብ አባላት ስላልሆኑ ነው» የሚለውን በብሔረሰቦቻቸው አባላት ላይ አስርጸው የራሳቸውን አገር ለመመስረት የሚያደርጉትን ትግል ለማቃናት ነው።

ዛሬ ዛሬ ደግሞ «ብዝሀነትን» ወያኔና ኦነግ ከደደቢት በረሀና ከሞቃድሾ ቤተ መንግስት ስበው ያመጡት አንዳች አዲስ ጽንሰ ሀሳብ ሆኖ እየተሰበከ ይገኛል። ላስተዋለው ግን በተለይ በኢትዮጵያ ንጉሳዊ ቤተሰብ ውስጥ ብዝሀነት አዲስ አይደለም፤ በቤተ መንግስት ደግሞ በጉልህ ይታይ ነበር። አዎ ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ በቤተ መንግስታቸው ከነ ራስ አበበ አረጋይ፤ከነ ራስ ስዩም መንገሻ፤ ከነ ዋቆ ጉቱ፣ ከነ ጄኔራል ሙሉጌታ ቡሊ፤ ከነ ራስ መስፍን ስለሺ፣ ከነ ጀኔራል ጃጋማ ኬሎ፣ከነ ተድላ ባይሩ፣ ከነ ሐረጎት አባይ፣ወዘተ ጋር ሲገናኙ በአማርኛ ያወሩ ነበር። እንኳን ያንድ አገር ሰዎች የተለያዩ አለም መሪዎች እንኳ ዋይት ሀውስ ሲሄዱ ከአሜሪካን ፕሬዝደንቶች ጋር የሚነጋገሩት በእንግሊዝኛ ነው። ሁለት ሰዎች ይግባቡ ዘንድ በአንድ ቋንቋ ማውራታቸው ግድ ነው። «የብዝሀነት አባት» ተደርጎ በካድሬዎቹ የሚሰበክለት መለስ ዜናዊም ከነ አባዱላ ገመዳ፣ ከነ አባተ ኪሾ፣ ከነ ኩማ ደመቅሳ፣ ከነ አብዱል መድጅ ሑሴን፣ ከነ ግርማ ብሩ፣ ከነ ጁኔይድ ሳዶ፣ከነ አልማዝ መኩ፣ ከነ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጋር በዳግማዊ ምኒልክ ቤተ መንግስት ሲገኛኝ የሚያወራው በአማርኛ ነበር።

ሌንጮ ለታም በመስ ዜናዊ ቦታ ቢቀመጥ ኖሮ ከነ ስዬ አብርሀ፣ ከነ ካሱ ኢላላ፣ ከነ አብዱል መጂድ ሑሴን፣ ከነ መብርሀቱ ገብረሕይወት፣ከነ ተኽሉ ተኽላይ ጋር ሲገናኝ የሚያወራው በአማርኛ ነበር። ልዩነቱ ወንበሩ ላይ የሚቀመጡት ሰዎች እንጂ የብዝሀነት አይደለም። ሆኖም ግን ታሪክ የሚጻፈው በየዘመኑ አሸናፊዎች ነውና የኢትዮጵያ ብዝሃነት በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቤተ መንግስት ያልነበረ፤ በመለስ ዜናዊ ቤተ መንግስት ግን ከደደቢት ተስቦ እንዳዲስ የተጀመረ ተደርጎ ተጻፈ። ዛሬ በአፍ የሚሰበከው «ብዝሀነት» የነጻነት ፍቺ ቢሆን ኖሮ «ብዝሃነት ተከበረ» በተባለበት በመለስ ዜናዊ ዘመነ መንግስት የኦሮምያ ምስለኔ ከነበረው ከኦሮሞው አባዱላ ገመዳ በላይ በኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግስት የሸዋ ጠቅላይ ግዛት እንደራሴ የነበሩት ኦሮሞው ራስ መስፍን ስለሺ የተሻለ ነጻነት አይኖራቸውም ነበር።

የራሳቸውን አገር ለመመስረት የታገሉት ኤርትራውያን ለነጻነት ስላልታገሉ ለሰለሳ አመታት ያህል ታግለው የራሳቸውን አገር መመስረት ከቻሉ በኋላ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የነበራቸውን ነጻነት ጭምር ለኢሳያስ አስረክበው ከሰላሳ አመት የበረሀ ትግል በኋላ ያገኙት ነገር ቢኖር ነጻነት ሳይሆን በባርነት የሚኮሩበት የራስ ቴምብርና ባንዲራ ብቻ ነው። በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግስት ኤርትራ ነጻ ፓርላማ ነበራት። ኤርትራ ወደናት አገሯ ከተቀላቀለች በኋላም ኤርትራውያን እንደራሴዎች በኢትዮጵያ ፓርላማ ውስጥ እንዴት ንቁ ተሳታፊ እንደነበሩ የአስመራ ከንቲባ የነበሩት የደጃዝማች ሐረጎት አባይ ልጅ ኤርትራዊው ስዩም ሀረጎት «The Bureaucratic Empire Serving Emperor Haile Selassie» በሚል ርዕስ በጻፉት ድንቅ መጽሀፋቸው በሰፊው አቅርበውታል። ኤርትራውያን ጫካ የገቡት በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የነበራቸው ነጻነት አነሰን በሚል ነበር።

የራሳቸውን አገር ለመመስረት ባደረጉት ትግል ግን በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የነበራቸውን መብትም ከናካቴው አጥተዋል። «የነበራቸው ነጻነት አነሰን፤ ይጨመርልን» ብሎ ዱር ቤቴ ያለው የኤርትራ ህዝብ ለሰላሳ ዓመታት ያህል ታግሎ የራሱን መንግስት ሲመሰርት የነበረውንም ነጻነት አጣ። የኤርትራ ህዝብ ለሰላሳ ዓመታት ያህል የራስ አገር ለመመስረት ባደረገው ተጋድሎ የነበረውን ነጻነት ሽጦ ያገኘው ጥቅም የኢሳያስ ቴምብርና ባንዲራ ብቻ ነው። ለኤርትራውያን ይህ የኢሳያስ ቴምብርና ባንዲራ ከመለስ ዜናዊ ቴምብርና ባንዲራ ጋር በምን እንደሚለይ አላውቅም። እንዴውም በዘር ሀረግ ከኢሳያስ በላይ መለስ ዜናዊ ኤርትራዊ ነው።
የሆነው ሆኖ ነጻነት የራስ አገር ለመመስረት በሚደረግ ትግል አይገኝም። እንዴውም በተግባር እንደታየው ከሆነ የራስ አገር ለመመስረት የታገሉ ህዝቦች የነበራቸውን አንጻራዊ ነጻነት አጥተዋል። ኤርትራውያን የዚህ ትራጀዲ ዋና አብነቶች ናቸው። ኦነግ በሚያደርገው የራስ አገር የመመስረት ትግልም ቢሆን የሚገኘው የነጻነት «ትሩፋት» ኤርትራውያን ካጋጠማቸው የከፋ፤ ምናልባትም ሶማሊያ ውስጥ እንደተከሰተው አይነት የርስ በርስት መተላለቅ ሊሆን እንደማይችል ዋስትና የለም። ኦነግ የሚመሰርታት ኦሮምያ የምትባለዋ «አገር» ከሶማሊያ የከፋ ሁኔታ ሊያጋጥማት የማትችልበት ዋስትና እስካሁን ያቀረበ ኦነጋዊ አላጋጠመኝም። ዛሬ ኦሮምያ ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለች ብቻ የማይታይ የሚመስለው የጎሳ፣ የባህል፣ የርዕዮተ አለምና የእምነት ልዩነቶች ኦነግ የኦሮሞ አገር ሲመሰርት ያቆጠቁጡና እንደሶማሊያ ጎሳዎች የፖለቲካ መሳሪያ ሆነው እንደማያገለግሉ ዋስትና የለም።
አንዳንዶቹ ኦነጋውያን ያለ ኦሮምያ ኢትዮጵያ ትፈርሳለች ይላሉ። ያልገባቸው ነገር ቢኖር ያለ ኢትዮጵያ ኦሮምያም እንደማትኖር ነው። ኢትዮጵያ በመኖሯ ኦሮምያ ውስጥ ያሉት የጎሳ፣ የባህል፣ የርዕዮተ አለምና የእምነት ልዩነቶች የግጭትና የርስ በርስ መከሳከስ መንስዔዎች አልሆኑም። ኢትዮጵያ ባትኖር ኦሮምያ ውስጥ ያሉት የጎሳ፣ የባህል፣ የርዕዮተ አለምና የእምነት ልዩነቶች ገንትረው እንደ ሶማሊያ የመከሳከሻ፣ የመፈረካከሻና የሞት ማንገሻ መሳሪያዎች አለመሆናቸው ዋስትና የለም። ስለዚህ የኦሮምያ መኖር ለኢትዮጵያ አስፈላጊ የሆነውን ያህል የኢትዮጵያ መኖርም ኦሮምያ እንደሶማሊያ እንዳትሆን ትልቅ ዋስትና ነው። ይህን የሚጠራጠር ካለ ያስብበት።

የባሮ ቱምሳ ሞት ለዚህ አንድ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። ክርስቲያኑ ባሮ ቱምሳ በጭንቅላቱ የሳለውን የኦሮሞ አገር ይዞ ለመታገል ሀረር ሲመሽግ የእስላሚክ ኦሮምያ ታጋዮች «ክርስቲያን ነጻ አያወጣንም» በሚል አርደውታል። ኢትዮጵያ ባትኖር ኖሮ በበባሮ ላይ የደረሰው በሌንጮ ለታና በገላሳ ዲልቦ ላይ ላለመድረሱ ዋስትና የለም ነበር። በሌንጮ ለታና በገላሳ ዲልቦ ላይ የሚደርሰው በኦሮሞ ክርስቲያኖችና በዋቄ ፈታ ስርዓት አማኞች ላይ ላለመድረሱ ዋስትና የለም።

ዛሬ ላይ የኦነግን ሀሳብ የሚያቀነቅኑ የኦሮሞ ኤሊቶች በተለይ ኢትዮጵያዊ ብሔርተኝነትን በሚያራምዱ ምሁራን ላይ የሚያካሂዱትን የጥላቻ ፖለቲካና መረን የለቀቀ ቀፋፊ ንግግር ለተመለከተ ኦነግ በለስ ቢቀናው በሚፈጥረው አገር የሚገዛቸው ህዝቦች እድል ፈንታ ከኤርትራውያን ይዞታ የከፋ ሊሆን እንደሚችል መገመት አያዳግትም። የሚገርመው ግን አብዛኛው የነዚህ ዘረኛ የኦነግ ኤሊቶች ተካታይ የሆኑ ወጣት ኦሮሞዎች ዘረኞቹ ኦነጋውያን ኢትዮጵያዊ ብሔርተኞችን ለማሸማቀቅ የጥላቻ መርዝ በሚተፋው ምላሳቸው የሚረጩትን መረን የለቀቀ ስድነት እያዩ «አበጃችሁ፤ ጎሽ፤ ጀግኖቻችን ናችሁ» ማለታቸው ነው። አላወቁትም እንጂ ይህ መርዘኛ ምላስ ነገ በለስ ቀንቶት አዲስ አገር ሲመሰርት ቀድሞ የሚበላው እነሱን ነው። ኢሳያስ አፈወርቂ ሻዕብያን ለመንግስትነት ከማብቃቱ በፊትም ጫካ እያሉ «ማንካ» በሚባለው የሻዕብያ «የህንፍሽፍሽ» እንቅስቃሴ በሃሳብ የተለዩትን የትግል አጋሮቹ የሆኑትንና በቀማዳዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የተማሪዎች እንቅስቃሴ የፊት ተዋናይ የነበሩትን እነ ዮሀንስ ስብዓቱን በሀሳብ ስለተለዩ ብቻ ገድሏቸዋል። ዮሀንስ ስብዓቱን ግን ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግስት ታስሮ በይቅርታ ምህረት ተሰጥቶት ከእስር የተነቀቀ ነበር።

እንግዲህ ይታያችሁ ዮሀንስ ከኢሳያስ በሀሳብ ስለተለየ ለነጻነት ታገልሁ በሚለው ኢሳያስ ተረሸነ። ዮሀንስ ስብዓቱ ግን ዲሞክራሲ የለበትም በተባለበትና ዘመንና «ሪያክሽነሪ» በተባሉት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ምህረት የተሰጠው ነበር። ኢሳያስ አፈወርቂ በተማረኩ የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላት ላይም ይለማመድባቸው የነበረውን የግፍ አይነት በወቅቱ ባይናቸው ያዩ የነበሩ የትግል ጓዶቹ የወዲ አፈወርቂን ድርጊት ከጀግንነት ቆጥረውት ነበር። የኢሳያስ ጓዶች ኢሳያስ በኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ የፈጸመውን ግፍ በኛ ላይ ሊፈጽመው ይችላል ብለው አላሰቡም ነበር። በአንድ የተወሰነ የታሪክ ወቅት የሚከሰት የጭካኔ ድርጊት ግን ሁሌም Precedence አለው። ቶላና ጫላ አብረው ሳሉ ጫላ በበየነ ላይ የሚፈጽመውን ዘግናኝ ድርጊት ጫላ በቶላ ላይ ላለመፈጸሙ ዋስትና የለም። እንዴውም ጫላ በበየነ ላይ የፈጸመው ዘግናኝ ድርጊት በቶላ ላይ ሊፈጸመው እንደሚችል precedence አለ። ኢሳያስ አፈወርቂም በነዮሀንስና በተማረኩ የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላት ላይ ያደረገውን ግፍ የራሱን አገር ሲፈጥር ከሁሉ አስቀድሞ ያስቀጠለው አብረውት በነበሩ፤ ግፍ ሲፈጽም እያዩ «አበጀህ፤ ጎሽ፤ ጀግኖቻችን ነህ» ባሉት የእድሜና የትግል አጋሮቹ ላይ ነው።

በኢትዮጵያዊ ብሔርተኛ አራማጆች ላይ መርዝ ከመርጨት የማይቦዝነው የኦነግ የምሁር ሊጎች ምላስም ነገ አገር ሲመሰርት ቀድሞ የሚበላው ዛሬ አጅበው «አበጃችሁ፤ ጎሽ፤ ጀግኖቻችን ናችሁ» የሚሉትን ጭፍን ደጋፊዎች ነው። እነዚህ ኦነጋውያን ኢትዮጵያዊ ብሔርተኞች ጋር በኢትዮጵያ ውስጥ አብረው እያሉ ማምጣት ያልቻሉትን ነጻነት የራሳቸውን መንግስት መስርተው ሊያመጡት አይችሉም። «የምጨቆነው ጨቋኞቹ ወገኖቻችን ስላልሆኑ ነው» በሚል ያስተሳሰብ ዝንፈት ያሰለፉት ኃይል ይህንን እውነት ያስተዋለው አይመስልም። የራሳቸውን አገር ቢመሰርቱ ጨቋኝ እንጂ ጭቆና እንደማይቀየር የተገነዘቡት አይመስልም። ጨቋኑ መሬት ነጣቂ ከሆነ የራሳቸውን አገር ቢመሰርቱ መሬት ነጣቂው ቢቀየር እንጂ መሬት ነጠቃው እንደማይቀር አላጤኑትም።
እንዴውም በሚመሰርቱት የራሳቸው አገር በንጉሱ ዘመን ከነበረውና «የማንም ንብረት ለግለሰብ ተብሎ አይነካም» ከሚለው ህገ መንግስታዊ መብት አኳያ ካየነው ደግሞ ቁልቁለቱ በጣም ቁልቁል ነው። የራሳቸውን አገር ቢመሰርቱ ገራፊ ቢቀይሩ እንጂ ግርፊያ አይቀርም። በኢትዮጵያዊ ብሔርተኞች ላይ ዛሬ መርዝ የሚተፋው የኦነጋውያን ዶክተሮች ምላስ ነገ ላይ አገር ስለመሰረቱ precedenሱ ጥሩ ሊሆን አይችልም። ኤርትራ የሆነው ኦነግ በሚፈጥረው አገር አይሆንም ብሎ ማሰብ ቂልነት ነው። ኤርትራ ላይ የምናየውን ፊልም ኦነግ በሚፈጥረው አገር የማናይበት ምንም ምክንያት የለም። ለምን ቢባል የራስ መንግስት ለመመስረት የሚደረግ ትግል እንደማትጨቆን፤ እንደማትገደል፤ ንብረትህን እንደማታጣ፤ ነጻነትህን እንደማትገፈፍ ዋስትና ሊሰጥ አይችልምና ነው። በኤርትራና በደቡብ ሱዳን እንደታየው የራስ መንግስት ለመመስረት የሚደረግ ትግል ላለመጨቆን፤ ላለመገደል፤ ንብረትን ላለማጣት፤ ነጻነትህን ላለመገፈፍ ዋስትና አይሆንም።

ከዚህ በተጨማሪ የራስ መንግስት ለመመስረት የታገሉት ኤርትራውያንና ደቡብ ሱዳናውያን ለመውቀውስ የሚያዳግት ጨካኝ አገዛዝ «ተጎናጽፈዋል»። ለመውቀስ የሚያዳግት ያልሁት ስለ አንድ ነገር ነው። ኤርትራውያንና ደቡብ ሱዳናውያን በርሀ ሲወርዱ «ጭቆና እየደረሰብን ያለው ስልጣን ላይ ያለው የኔ ዘር ስላልሆነ ነው፤ የኔ መንግስት ስላልሆነ ነው» በሚል መነሻ ስለሆነ ዛሬ በትግላቸው የኔ የሚሉት መንግስት አቁመው ሲጨቁናቸው «የኔ መንግስት ጨቁኖኛል» ብለው ለመውቀስ፤ የነበራቸው ነጻነት እንዳጡ ለመናገርና ለመታገል ያሳፈራቸው ይመስላል። የራስ መንግስት ለመመስረት ያታገሏቸው ፋኖዎች ነጻነት ሊሰጧቸው እንደማይችሉ በሚጭኗቸው የጭቆና ቀንበር ውስጥ ገብተው ሲገነዘቡት ፋኖዎቹ እንደሸወዷቸው ቢገባቸውም የውሽማ ለቅሶ እያለቀሱ እንዳይነወሩ የከፋ የራስ የግፍ አገዛዝ ተሸከመው መኖርን ይመርጣሉ።

ስለዚህ የነጻነት አንኳሮች የሆኑት የንብረት መብት፣ በራስ ሀብት የማዘዝ ሙሉ መብት፣ ሀሳብን የመግለጽ መብት፣ንብረት የማፍራት መብት፣ በእኩልነት የመተዳደር መብት፣ወዘተ የራስ መንግስት ለመመስረት በሚታገሉ ቡድኖች ሊረጋገጥ አይችልም።
የራስ መንግስት ለመመስረት የሚታገሉት ፋኖዎች አላማቸው የራሳቸውን ባንዲራ ፈጥረው፤ የክብር ዘብ አሰልፈው የህይወት ዘመን ፕሬዝደንት ሆነው የሚገዘግዙት አገር ለመፍጠር እንጂ ትክክኛ የህዝብን የመናገር፣ የመወከልና የንብረት መብት ነጻነት ለማምጣት አይደለም። ለዚህ ቢሆን ኖሮ የታገሉት የየለቱ ንግግራቸውና ተግባራቸው ሁሉ በራስ ሀብት ስለማዘዝ፣ ስለመናገር፣ ስለመወከልና ስለንብረት ማፍራት መብት ነጻነት ምስክር ሆኖ ይታይ ነበር። ኦነጋውያንም የሚታገሉት ለነጻነት ቢሆን ኖሮ የተለየ አስተሳሰብ ባላቸውና በሰላ በሚሞግቷቸው የኢትዮጵያ ብሔርተኞች ላይ አይን ያወጣ ስድብ፣ ዘለፋ፣ ማዋረድ፣ ተክለ ስብዕና ገደላ፣ ጥላቻና ርኩስ መንፈስ የተሞላበት ንግግር በማራባት አይጠመዱም ነበር። ለነገሩ ነጻነት ለማምጣት የራስ መንግስት ለመመስረት መታገል አያስፈልግም። የራስ መንግስት ለመመስረት ሳትነሳ በአንድነት እየኖርህ አብረህ እስከታገልህ ድረስ ነጻነትህ ታገኛለህ። የኦነጋውያን መንፈስ ግን የዚህ ተቃራኒ ነው። የራሳቸውን መንግስት ለማቆም ሲሉ ከሰይጣንም ጋር ቢሆን የሚተባበሩ ይመስለኛል። ከሰይጣን መንፈስ ነጻነት ሊቀዳ አይችልም። ከሰይጣን መንፈስ የሚቀዳው ሁሉ ብሩቁ የሆነ ጨካኝ አገዛዝ ብቻ ነው።

ከፍ ብዬ በአንድነት እየኖርህ አብረህ እስከታገልህ ድረስ ነጻነትህ ታገኛለህ ብያለሁ። ይህን ስል በአንድነት ለነጻነት መታገል የራስ መንግስት መስርቶ ለነጻነት ከመታገል በብዙ እጥፍ ይቀላል ለማለት ነው። ዛሬ ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል ብትሆን ኖሮ 95 ሚሊዮን ህዝብ ለነጻነት አብሮ ይታገል ነበር። 95 ሚሊዮን ህዝብ ለነጻነት አብሮ ሲታገል የነጻነት ቀን ሩቅ አይሆንም። ዛሬ የራሳቸውን መንግስት የመሰረቱት ኤርትራውያን ብቻቸውን ቢታገሉ ግን ከአምስት ሚሊዮን ኤርትራውያን ግማሹ ያልህ እንኳ ለነጻነት ለመታገል መነሳቱ ያጠራጥራል። ከፍ ብዬ ኤርትራውያን ለመውቀስ የሚያዳግታቸው አገዛዝ አቁመዋል ብዬ ነበር። ዛሬ ምንም እንኳ በባርነት እየኖሩ ቢሆንም የታገሉለት አገዛዝ ስለሆነ ብቻ ግን የኢሳያስን አገዛዝ «የኛ መንግስት ነው» ብለው ተቀብለው ለመኖር የቆረጡና ለነጻነት ትግል የማይደፍሩ ቁጥራቸው የማይናቅ መሆኑ እሙን ነው። ይህንን አጥር ሰብሮ ለነጻነት ለመታገል የሚነሳው ኤርትራዊ ቁጥር ግፋ ቢል ግማሹ የኤርትራ ህዝብ ቢሆን ነው። በዚህ ስሌት መሰረት የኤርትራ ህዝብ ለነጻነት ሊታገል ቢነሳ 2.5 ሚሊዮን ኤርትራዊ ለነጻነት ሊታገል ይችላል ማለት ነው። 2.5 ሚሊዮን ኤርትራዊ በአገሩና 95 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊና ኤርትራዊ በአንድነት በሚያደርጉት የነጻነት ትግል መካከል ያለው የነጻነት ቀን ርዝማኔ ልዩነት ግልጽ ነው። 95 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊና ኤርትራዊ በአንድነት አይደለም ታግሎ ተራራ ላይ ወጥቶ ሽንቱን ቢሸና የማይቆም ናዳ ይፈጥራል። በአድነት ለነጻነት የመታገል ጥቅሙ ይህንን ያህል ጥልቅ ነው።

«እየተጨቆንን ያለነው ስልጣን ላይ ያሉት ጨቋኞች የብሄረሰባችን አባላት ስለልሆኑ ነው» በሚል የነጻነት ጥማትን የራስ መንግስት በመመስረት ለማስተንፈው መሞከር መዳረሻው እንደ ኤርትራና ደቡብ ሱዳን ለነጻነት ዋስትና የማይሰጥ የራስ መንግስት ማቆም ብቻ ነው። ውጤቱም የነበረውን አንጻራዊ ነጻነት በባርነት ቀይሮ ለማማረር የሚቸግር ጨካኝ አገዛዝ ተከናንቦ የሚገኘው ነገር ጥቅም ከተባለ ብጣቂ የቴምብር ወረቀትና የራስ ባንዲራ ብቻ ነው። ትርፉም የነበረን አንጻራዊ ነጻነት መጨረሻው በማይታወቅ ባርነት መቀየር ብቻ ነው።

ስለዚህ «የምንጨቆነው ጨቋኞቹ የኛ ብሄረሰብ አባላት ስላልሆኑ ነው» በሚል ቅስቀሳ ዘረኛ ድርጅቶችን የምትከተሉ የኔ ትውልድ ወጣቶች አትሸወዱ። «የምንጨቆነው ጨቋኞቹ የኛ ብሄረሰብ አባላት ስላልሆኑ ነው» በሚል የራስ መንግስት ለመመስረት ድርጅት አቁመው እየታገሉ ያሉት የብሔረሰባችሁ አባላት የሆኑ ፖለቲከኞች ነጻነትን ሊሰጧችሁ አይችሉም። ነጻነት የሚገኘው በአንድነት በሚደረግ የነጻነት ትግል ብቻ ነው። የብሔረሰባችሁ አባላት የሆኑ ፖለቲከኞች ነጻነትን ሊሰጧችሁ ከፈለጉ አገር መመስረት ሳይነሱ በአንድነት ታግለው ሊሰጧችሁ ይቻላቸዋል። የራስ መንግስት ለመመስረት ቢነሱ ግን ግፋ ቢል የሚያቆሙላችሁ አገዛዝ እንደ ኢሳያስ አፈወርቂ አይነት መንግስት ነው። ይህም ሲደላ ነው። እንደ ሶማሊያ መሆን አለና። ስለሆነም እነሱን በጭፍን ከመከተል ከጥላቻ ወጥታችሁ ዛሬ በሌሎች ላይ እያደረጉት ያለውን ክፋት ነገ አገር ሲመሰርቱ በማይመቻቸው የብሔረሰባቸው አባል ላይም ዛሬ በሌሎች ላይ እያደረጉት ያለውን ሊያደርጉ እንደማይችሉ ዋስትና የላችሁም። የዛሬ ድርጊት የነገ precedence አለው፤ የዛሬ ድርጊት የነገን ቁልፍ ይይዛልና። በአንድነት እየኖርህ አብረህ እስከታገልህ ድረስ ነጻነትን የማታገኝበት ምንም ምክንያት የለም። የራስ መንግስት የመመስረት አባዜ የተጠናዎታቸው ዘረኛ ግለሰቦች ትናንሽ ኢሳያስ አፈወርቂዎች ብቻ ናቸው። ኢሳያስ አፈወርቂ የራስ መንግስት በመመስረትና በነጻነት መካከል አንዳች ግንኙነት እንደሌለ፤ እንዴውም ተቃራኒ እንደሆኑ ፐርፈክት የሆነ ምሳሌ ነው። አበቃሁ!

በሐረርጌ የተቀሰቀሰው የተማሪዎች አመጽ ወደ ሌሎች ቦታዎች ተዳረሰ (የፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ አጫጭር ዜናዎች)

0
0

 በተመድ ስር የሚሰሩ ወታደሮች ደሞዛቸው በወያኔ ባለስልጣናት እንደሚበዘበዝ ተጋለጠ
 ስደተኞች ለመቆጣጠር የተቋቋመው የአውሮፓ ህብረት ግብረኃይል የሊቢያን ጠረፍ ጠባቂዎች
እንዲያሰለጥን መመሪያ ተሰጥተው
 በኬኒያ ኩሱሙ በምትባለው ከተማ የተቃውሞ ኃይሎች ያካሄዱትን ሰላማዊ ሰልፍ ለማፈን
ፖሊሶች በወሰዱት እርምጃ ቢያንስ አንድ ሰው ተገደለ
 በዳርፉር መስጊድ ውስጥ የነበሩ ስምንት ሰዎች በአረብ ሚሊሺያዎች ተገደሉ

13254093_10102296231320823_8172214177964234618_n
ዝርዝር ዜናዎች

 ለሳምንታት ጋብ ብሎ የነበረው የተማሪዎች ተቃውሞና የሕዝብ እንድቅስቃሴ እንደገና መቀስቀስ
መጀመሩ ታወቀ። በሐረጌ በዓለማያ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ያገረሽው የተማሪዎች ተቃውሞ እንቅስቃሴ
ለማፈን የወያኔ አግአዚ ጦርና የፌዴራል ፖሊስ ወደ ዩነቨርስቲው ግቢ ውስጥ በመግባት
የተማሪዎችን የመኝታ ክፍሎች ከቀላል መፈንከት እስከ አጥንት ስብራት የደረሰ ድብደባ
መፈጸማችው የሚታወቅ ሲሆን በዚህ የጭካኔ ድብደባ ምክንያት ተቃውሞና ሕዝባዊ ንቅናቄው
በሌሎች የኒቨርሲቲዎናች ከተሞች የተዛመተ መሆኑ ይነገራል። በወለጋ በነቅምት ዩኒቨርሲት
ተማሪዎች ተቃውሟቸውን እንደገና ማሰማት የጀመሩ ሲሆን ወያኔም እንደተለመደው ነፍሰ ገዳይ
አግአዚ ወታደሮችን አሰማርቷል። የሆሩ ጉድሩና የከምቦልቻ ከተማ ነዋሪዎችም ዳግም የመብት
ጥያቄን አንግበው አደባባይ መውጣት ጀምረዋል።
 የወያኔ አገዛዝ ዓለም አቀፍ አስዳሪዎቹን ለማስደሰትና እግረ መንገዱንም ጠቀም ያለ ገንዘብ
ለመሰብሰብ በማሰብ በተመድ ስር በሺህ የሚቆጠሩ ወታድሮች ያሰማራ መሆኑ ይታወቃል። ተመድ
ከፍተኛ የሆነ ደምዝ ለወታደሮቹ በየጊዜው ቢከፈልም የወያኔ የጦር አለቆች ገንዘቡን በመረከብ
ወታደሮችን እየበዘበዙ መሆናቸው ታውቋል። ወታደሮቹ የሞት አደጋ ሲደርስባቸው በግልጽና በይፋ
የማይነገር ሲሆን የተመድ የህይወት ካሳ ክፍያንም ባለስልጣኖቹ እንደሚቀራመቱት ይታወቃል።
ተመድ ባለፈው ሳምንት የተመድ የሰላም አስከባሪዎች ቀንን ምክንያት በማድረግ በተመድ ተልእኮ
ስር ሆነ የተገደሉ ስምንት የወያኔ ወታደሮችን የሸለመ ሲሆን የተለያዩ አገሮች ዜጎች የሆነ 128
ወታደሮቹን ተልእኮውን በመፈጸም ህይወታቸው በማለፉ ክብርና ሚዳሊያ ሰጥቷል።
 በኬኒያ ምዕራባዊ ግዛት በምትገኘው ኩሱሙ በምትባለው ከተማ የተቃዋሚ ኃይሎች ደጋፊዎች
ትዕንተ ሕዝብ ያካሄዱ ሲሆን ከፖሊሶች ጋር በተካሄደው ግጭት ቢያንስ አንድ ሰው የሞተ መሆኑን
የዜና ምንጮች ዘግበዋል። ሟቹ የተገደለው ከፖሊሶች በተተኮሰ ጥይት ነው የሚለውን ዜና የፖሊሱ
ክፍል አስተባብሎ ግለሰቡ ወድቆ መሞቱን ገልጿል። ባለፈው ሳምንት በኬኒያ ዋና ከተማ
በተደረገው የተቃውሞ ስልፍ ፖሊሶች ሰልፉን ለመበተን የኃይል እርምጃ መውሰዳቸው ይታወሳል።
በኩሱሙ የተደረገው ስልፍ የተቃዋሚ ፓርቲዎች የምርጫ ኮሚሽኑን የአድልዎና ብልሹ አሰራር
በመቃወም በተከታታይ ካደረጓቸው ስለፎች ውስጥ አራተኛ መሆኑ ነው።

 የአውሮፓው ኅብረት ሰኞ ግንቦት 15 ቀን ባደረገው ስብሰባ ስደተኞች የሚዲትራኒያን ባህር
አቋርጠው ወደ አውሮፓ እንዳይዘለቁ ለመከላከል የተቋቋመው የባህር ኃይል ግብረ ኃይል የሊቢያ
ጠረፍ ጠባቂዎችን በማሰልጠን ተግባር ላይ እንዲሰማራ ተጨማሪ ኃይላፊነት የሰጠው መሆኑ
ተገልጿል። አፕሬሽን ሶፊያ በመባል የሚታወቀው ይኸው ግብረኃይል በሚቀጥለው ሐምሌ ወር
ውስጥ ኃይላፊነቱ የሚያበቃ መሆኑ የታወቀ ሲሆን በብራስል የተሰበቡት 28 የአውሮፓ አገሮች
የግብረኃይሉን እድሜ ለአንድ ዓመት እንዲራዘም አድርገዋል። ግብረኃይሉ ከተቋቋመ ጀምሮ
ያስገኘው ውጤት አነስተኛ ነው በሚል በተደጋጋሚ ወቀሳ የቀረበበት ሲሆን ኃይሉ እንዲጠናከርና
በማሰልጠን ተግባር ላይ እንዲሰማራ የተወሰነው ድክመቱን አርሞ ውጤት እንዲያስገኝ ነው
ተብሏል።

 በዳርፉር የአረብ ሚሊሺያ አባሎች በአንድ መስጊድ ውስጥ በተሰበሰቡ ሰዎች ላይ በወሰዱት ጥቃት
ቢያንስ ስምንት ሰዎች መገደላቸው ታውቋል። ቀደም ብሎ በአንድ የገበያ ቦታ አንድ የአረብ
ብሔረሰብ አባል የሆነና አንድ የመሳሊት ማህብረሰብ አባል የግል አለመግባባት ፈጥረው በተደጋጋሚ
በዱላ የተመታው መሳሊት አረቡን በስለት ገድሎት እንደነበር ከቦታው የተገኘው ዜና ይገልጻል።
የአረቡ ሚሊሺያ አባሎች ለአረቡ መገደል በወሰዱት የበቀል እርምጃና በአካሄዱት የእሩምታ ተኩስ
በመስጊድ ውስጥ የተሰበሰቡ ስምንት ነዋሪዎችን መግደላቸውንና ከእነዚህ ውስጥ ሁለቱ ልጆች
መሆናቸውን የዜና ምንጮች ገልጸዋል።

 በደቡብ አፍሪካ በፕሬቶሪያ ከተማ ሰሜናዊ ክፍል በህገ ወጥ መንገድ የተሰሩ ቤቶችን ለማፍረስ
የጸጥታ ኃይሎች የወሰዱትን እርምጃ በመቃወም ነዋሪዎቹ የተቃውሞ እንቅስቅስቃሴ
ማድረጋቸውን ከስፍራው የተገኘ ዜና ያስረዳል። ሰኞ ግንቦት 15 ቀን በነበረው ግጭት ቤቶች
ለማፍረስ ከተላከው የአፍራሽ ግብረኃይል አባላት ውስጥ ቢያንስ ሁለቱ መገደላችውን የደቡብ
አፍሪካ ባለስልጣኖች ገልጸዋል። ባለስልጣኖቹ ሃማንስክራል በሚባለው የከተማው አካባቢ በሺ
የሚቆጠሩ ሰዎች በህገ ወጥ መንገድ የሚኖሩ መሆናቸውን ጠቁመው ቦታውን ለማጽዳት ከፍርድ
ቤት ፈቃድ የተሰጣቸው መሆኑን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያዊው በሚኒሶታ ሕይወቱ አልፎ ተገኘ

0
0

Abel

(ዘ-ሐበሻ) ነዋሪነቱ በሚኒሶታ የሆነው ኢትዮጵያዊው ወጣት አቤል ሺሻይ ሕይወቱ አልፎ ተገኘ:: በድንገተኛ ትናንት ሕይወቱ አልፎ የተገኘው ይኸው ኢትዮጵያዊ የቀብር ስነ ስርዓቱን ለማስፈጸም ወዳጅ ዘመዶቹ እየተሯሯጡ ይገኛሉ::

የወጣቱ አቤል ቤተሰቦች ሐዘን የተቀመጡ ሲሆን በሚኒሶታና አካባቢው የምትገኙ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያውያን ወዳጆች ለቅሶ ለመድረስ አድራሻው 1821 University Ave W, St Paul, MN 55104 ሲሆን ለቅሶ መድረስ የሚቻለውን ከጠዋቱ 10 ሰዓት እስከ ምሽቱ 10 ሰዓት ድረስ መሆኑ ታውቋል::

በወጣቱ አቤል ዙሪያ ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሱን ለማቅረብ እንሞክራለን::

ጋዜጠኛው አበበ ገላው ያደረገውን በፌስቡክ ጠቅሰህ ሕዝብን ለማነሳሳት ተጥቅመህበታል በሚል በሽብር ተከሰሰ

0
0

Negere-Ethiopia-edtor-Getachew-Assefa-300x200.jpg

(ዘ-ሐበሻ) የኦሮሚያ ተማሪዎች አመጽ በተቀጣጠለበት ሰሞን መንግስት አስሮ ለረዥም ጊዜ ክስ ሳይመሰርትበት የቆየው ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ጋዜጠኛ አበበ ገላው ያደረገውን አድንቀህ ሕዝብን ለማነሳሳት ተጠቅመህበታል እና ከኢሳት ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም ጋር በፌስቡክ እና በስልክ አውርተሃል በሚል የሽብርተኝነት ክስ ቀረበበት::

እንደ ክሱ ዝርዝር ከሆነ

“ተከሳሽ (ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው) በሚጠቀምበት ማህበራዊ ድህረገአጽ በተለይም ፌስቡክ አድራሻው ተጠቅሞ በውጭ ሃገር የሚገኝ የሽብር ቡድኑ አመራር እና አባል ከሆነው አበበ ገላው በልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት በጸረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ተከሶ በመዝገብ ቁጥር 112546 የጥፋተኝነት ውሳኔ ከተሰጠው ጋር ግንኙነት በመፍጠር በቀን 01/9/2006 ዓ.ም በአቶ መለስ ላይ ያደረገው ተቃውሞ መስቀል አደባባይ ላይ ከሚደረግ አንድ ሚሊዮን ሕዝብ የተሳተፈበት የተቃውሞ ሰልፍ የማይተናነስ ነበር:: አሁንም እንዲሁ ኦባማ ላይ ደግሞታል:: የአቤ ጩኸት ዝም ብሎ ያለመገዛት አንድ ድምጽ ብትሆን ለውጥ እንደምታመጣ በጽኑ የማመን ለውጥ አይመጣም ብሎ በተስፋ መቁረጥ ከመቀመጥ የራስን አስተዋጽኦ ማድረግ የተግባር ሰው መሆን ነው በማለት ከሽብር ቡድኑ አባል ጋር የአመጽ ጥሪ በማስተላለፉ”

የሽብር ክስ ተመስርቶበታል ይላል::

ሙሉውን የክስ ዝርዝር ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ዛሬም በቦሌ ክፍለከተማ ወራ ጋኑ አካባቢ 2 ሰዎች በፌደራል ፖሊስ ተገደሉ * በርካታ ሰዎች የደረሱበት ጠፋ

0
0
(ቤታቸው የፈረሰባቸው ወገኖች በአደባባይ እንዲሁም ፌደራል ፖሊሶች አካባቢውን ወረውት)

(ቤታቸው የፈረሰባቸው ወገኖች በአደባባይ እንዲሁም ፌደራል ፖሊሶች አካባቢውን ወረውት)

(ቤታቸው የፈረሰባቸው ወገኖች በአደባባይ እንዲሁም ፌደራል ፖሊሶች አካባቢውን ወረውት)

(ቤታቸው የፈረሰባቸው ወገኖች በአደባባይ እንዲሁም ፌደራል ፖሊሶች አካባቢውን ወረውት)

(ቤታቸው የፈረሰባቸው ወገኖች በአደባባይ እንዲሁም ፌደራል ፖሊሶች አካባቢውን ወረውት)

(ቤታቸው የፈረሰባቸው ወገኖች በአደባባይ እንዲሁም ፌደራል ፖሊሶች አካባቢውን ወረውት)

(ዘ-ሐበሻ) በአዲስ አበባ ከተማ በቦሌ ክፍለ ከተማ ስር ባለው ወራ ጋኑ በተባለው አካባቢ የመንግስት ሃይሎች የአካባቢውን ነዋሪዎችን መኖሪያ ቤቶች በማፍረስ ለሃብታሞች መሬቱን እየቸበቸቡት ሲሆን ዛሬም ቤቶቹን ለማፍረስ ከሄደው ግብረሃይል ጋር የነበረው ፌደራል ፖሊስ 2 ሰዎችን መግደሉን የአካባቢው ሰዎች አስታወቁ::

ከስፍራው የሚመጡ መረጃዎች እንደጠቆሙት በዚሁ አካባቢ ሰሞኑን መሬቱን ለባለሃብቶች መሸጡን ተከትሎ ከ6 ሺህ የማያንሱ ቤቶች ህገወጥ ናቸው በሚል ፈርሰዋል::

ፌደራል ፖሊስ ባለፈው ሳምንት እንዲሁ በዚሁ አካባቢ ቤቶችን ሲያፈርስ በህዝቡ ተቃውሞ ሲደርስበት ከ10 በላይ ሰዎችን መግደሉን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ የማይዘነጋ ሲሆን ዛሬም ድርጊቱን የተቃወሙና የት ሄደን እንኑር ያሉ ወገኖች ከመደብደባቸውም በተጨማሪ 2ቱ ሲገደሉ ከ20 በላይ ሰዎችም ታፍነው መወሰዳቸውና የት እንደደረሱ እንደማይታወቅ የአካባቢው ሰዎች ገልጸዋል::

የትዝታ ፈለግ –ዓለም ፀሐይ ወዳጆ

0
0

ALEM-PIC2_coverሚያዚያ 21,2008 የአቶ አስፋ ጫቦን” የት ዝ ታ ፈለግ” መጽሐፍ ለመመረቅ ጣይቱ የባሕልና ትምህርት ማዕከል አዳራሽ Civic Building, 1 Veteran Plaza,Silver Spring,Maryland ያደርግኩት የመከፍቻ ንግግር ነው የተወደዳችሁ እንግዶች በቅድሚያ የዛሬው እንግዳችን አቶ አሰፋ ጫቦን “የትዝታ ፈለግ” በሚል ርዕስ ያሳተመውን መጽሐፍ ለምርቃት በማብቃቱ በጣይቱ የባህልና የትምህርት ማዕከል ስም “‹እንኳን ደስ አለህ !” እላለው—–ሙሉውን ጋዜጣ በፒ.ዲ.ኤፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ—-

 


ለአስገድዶ ደፋሪዎች ከልብ ያዘንኩላቸው ልዩ ዕለት!

0
0

         ADDIS ABABA    

ፍርዱ ዘገዬ (ግንቦት 20 ቀን 2008ዓ.ፍ.)

ይህችን ማስታወሻ እጽፋለሁ ብዬ በልሜም በውኔም አላሰብኩም፡፡ ዛሬ ቀኑ በዓል በመሆኑና የተወዘፈ ሥራ ስላለብኝ ቢሮ ገብቼ ለመሥራት በማቀድ ከጧቱ ሁለት ሰዓት አካባቢ ወደ መሥሪያ ቤቴ መጓዝ ጀመርኩ፡፡ ጥቂት እንደሄድኩ ግን ጉዞዬ ጉዞ ፍትሓት ሆነና እንዳሰብኩት መሆን አቃተኝ፡፡ ምክንያቱም በግንቦት 20 ምክንያት የአዲስ አበባ መንገዶች በተለይም መሀል ከተማ ተዘጋግቷል፡፡ በካዛንችስ ስሄድ ዝግ ነው፤ በአራት ኪሎ ስሄድ ዝግ ነው፤ በቴዎድሮስ አደባባይ በኩል ስሄድም ዝግ ነው፤ በተክለ ሃይማኖት በኩልም ዝግ ነው፡፡ እንደምንም ብዬ ወታደሮችንና ትራፊክ ፖሊሶችን በመለማመጥ ዲአፍሪክ ሆቴል አካባቢ ደረስኩና መኪናየን እዚያ ጥዬ ከአንድ ኪሎ ሜትር የሚበልጠውን የመሥሪያ ቤቴን መንገድ በእግር ተያያዝኩት – ግንቦት ሃያን በልቤ እየረገምኩ፡፡ መንገዱን ሁሉ የሞላው ከየወራዳውና ከፍተኛው በሃይገርባሶችና በከተማ አውቶቡሶች እንዲሁም  በሌሎች ልዩ ልዩ የመንግሥትና የግል ተሽከርካሪዎች በግዳጅ እንዲመጡ የተደረጉ በዓል አክባሪዎች ናቸው፡፡ እነዚህን በግዳጅና በገንዘብ ኃይል የተሰባሰቡ ዜጎች ጠጋ ብላችሁ ስትመለከቷቸውና ስትጠይቋቸው የምታገኙት ነገር ልባችሁን ይሰብረዋል፡፡ ነገረ ሥራቸው ያሳዝናል፤ ድህነት እንዴቱን ያህል እንደሚያዋርድና የጭራቅንም እጅ ሳይቀር እንደሚያስቀላውጥ ትረዳላችሁ፡፡

እኚህ ዜጎቻችን በኑሮ እጅግ የተጎሳቆሉ መሆናቸውን በአለባበሳቸውና በሁኔታቸው መገንዘብ ይቻላል፡፡ አንድም ደህና ሰው የለባቸውም – ደህና ሰው ስል ከምድራዊ የደህና ሰውነት መለኪያ አንጻር ማለቴ እንጂ በፍጡርነት ሁሉም እኩል መሆኑን ዘንግቼው አይደለም፡፡ በአለባበስ፣ በትምህርት ደረጃ፣ በስብዕናን አያያዝ (personality)፣ በሥራና በኑሮ ወዘተ. በእጅጉ የተበሰቋቆሉ መሆናቸውንና እነዚህን ዓይነት ዜጎች ገንዘብ ካሳዩዋቸው ምንም ዓይነት የራሳቸው ዓላማና አቋም ቢኖራቸው እንኳን ለገንዘቡ ሲሉ አድርጉ የሚባሉትን እንደሚያደርጉ መረዳት አይከብድም – የተማረ ሰው መቼም በዚያ መልክ ውራጅ ለብሶና ሞጋና ነጠላ ጫማ አድርጎ ለወያኔ ሠርግ ሲል በራሱ ሞት አይጨፍርም፡፡ ይህን ትርዒት ባይኔ በብረቱ ስመለከት በዜግነቴ አፈርኩ፤ የወቅቱ ኢትዮጵያዊነቴ ራሴን ከሰው በታች አድርጌ እንድመለከተው አስገደደኝ፡፡ የት እንዳለሁም ማወቅ ተሳነኝ፡፡ “እኔ ነኝ ወይንስ አካባቢየ እንዲህ ቆሽሾ የሚታየኝ? እንደሀገርም ሆነ እንደማኅበረሰብ ከየት ወዴት እየተጓዝን ነው? በእነዚህ ሰዎችና በኔ መሀል ምን ልዩነት ቢፈጠር ይሆን ያለሁበት ሥፍራ  በመጥፎ ጠረን ተበክሎ ኅሊናየን የሚያሰቃየው?” በሚል በሃሳብ ናወዝኩ፡፡ ዙሪያ ገባየን ተፀየፍኩት፤ እሱም ተጠየፈኝ መሰለኝ ገፈታትሮ ከዚያ አካባቢ አስወጣኝና ወደቢሮየ አስገባኝ፡፡

እንዲህና እስከዚህ የተዋረድነው ለምን ይሆን? ፈጣሪን ምን ብንበድለው ይሆን ወደዚህ የዘቀጠ ደረጃ አውርዶ የፈጠፈጠን? ምንድነው በሀገራችን ውስጥ እየተካሄደ ያለው? እስኪ ቆም ብለን እናስበው!

ምስኪኖቹ ወገኖቼ የሚዘፍኑትም ሆነ ጉሽ ጠላ ጠጥቶ እንደሰከረ ሰው የሚያብዱት ለምን እንደሆነ የሚያውቁ አይመስለኝም፡፡ በየፒካፑና አይሱዙው ተንጠልጥለው ከሞንታርቮ በሚለቀቁ ዘፈኖች ሥልት በሌለቀው ዳንስ አይሉት ጭፈራ ይንጠራወዛሉ፡፡ የአካባቢውም ሰው አፉን እየሸፈነ ሳይሞቀው ሳይበርደው በትዝብት ዐይን ይመለከታቸዋል – አንዳንዱም ስለነሱ እያፈረ፡፡ ሲዖል ውስጥ በዕረፍት ሰዓት እንዲደነክሩ ለአፍታ የተፈቀደላቸው የሚመስሉት እነዚያ  በሰው አምሳል የሚንቀሳቀሱ የተኮነኑ ነፍሳት ወያኔ በጨው እያታለለ ለዓላማው ስኬት የሚጫወትባቸው ቀን የጣላቸው ዜጎች ናቸው፡፡

ከዚህ ወዝ የለሽ ድራማ በመነሳት እኔን የታየኝ ሌላ ነገር ነው፡፡

በዓለም ላይ እጅግ ብዙ አስገድዶ ደፋሪዎች አሉ – ሴትን ብቻ ሣይሆን ወንድንም ጭምር፡፡  ልዩ የርኩሣን መናፍስት ኃይል የተጠናወታቸው እነዚህ ሰዎች – ሰዎች ማለት እንኳን ይከብደኛል – የሚያደርጉትን ባለማወቅ ከሕጻናት እስከዐዋቂ – ከጤነኛ እስከ በሽተኛ ያገኙትን ሁሉ ባገኙት ቦታ ይደፍራሉ፤ በዚህም ጠያፍና ወንጀለኛ ድርጊታቸው ብዙዎችን ለአካላዊ፣ ለኅሊናዊና ለአእምሯዊ በሽታዎች ይዳርጋሉ፡፡ ያልተፈለገ እርግዝናም በማስከተል ብዙዎችን ለቁም ስቅል ይዳርጋሉ፡፡ ወያዎችም እንደነዚህ ብልሹ ፍጡራን ናቸው፤ በምንም ነገር አይለዩም፡፡ ወያኔዎች አካልንም መንፈስንም፣ አእምሮንም ኅሊናንም አስገድዶ በመድፈር የሚታወቁ ናቸው፡፡ ዓላማቸው ሰውን በአካል ብቻ ሣይሆን በቁምም መግደል ነውና፡፡

በፈረንጅኛው Stockholm Syndrome የሚሉት አባባል አለ፡፡ ምን ማለት ነው – ተጎጂው ለጎጂው የሚያዝንለት ሁኔታ ማለት ነው፡፡ ክርስቶስም የሚሰቅሉትን የዚያን ዘመን ፈሪሣውያን ወያኔዎችን “የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” ሲል አብ እንዲምራቸው ጸልዮላቸዋል፡፡ ሰሞኑን ደግሞ ፓኪስታን ውስጥ አክራሪ እስላሞች አንዲት ሕጻን ክርስቲያን በመሆን “ኃጢኣቷ” ብቻ ተረባርበው ከደፈሯት በኋላ ሲገድሏት በሚገርም ሁኔታ “እግዚአብሔር ሆይ ይቅር በላቸው” እያለች ነፍሷ እንደወጣች አንብቤያለሁ፡፡ ይህን የሚሉ ብፁዓን ናቸው፡፡ ፍጹም አምላክና ፍጹም ሰው የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ጨምሮ ከሰው ልጆችም ውስጥ ይህ የከፍተኛ አእምሯዊና መንፈሣዊ ዕድገት ምልክት የሆነ ለጠላት ምሕረትን የመለመን መልካምነት አልፎ አልፎ ይታያል፡፡ ጥሩ ነው፡፡ ምክንያቱም አንድ ሰው የሚዘገንን ኃጢኣትም እንበለው ወንጀል የሚሠራው በሆነ ኃይል ተገድዶ እንጂ በጤናው ሊሆን አይችልምና፡፡ ወያኔዎችም ይህን የመሰለ አጸያፊና ነውረኛ ተግባር የሚፈጽሙት እነዚህ ምስኪኖች ከተማ ውስጥ በግዳጅ ወጥተው ስለተንጫጩ የሚያገኙት ጠቀሜታ ኖሮ አይደለም፡፡ ሰዎቹ ጮኹ አልጮኹ የወያኔን ዕድሜ አያረዝሙ ወይ አያሳጥሩ፡፡ እርግጥ ነው ወያኔዎች እንዲህ የሚያደርጉት “ብዙ ደጋፊ አለን” የሚል ምስል በተለይ ለእስስታውያኑ የዳብል ስታንዳርድ አራማጅ የዓለም ኃያላን አገሮች ለማስተላለፍ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ያረጀ ያፈጀ ሥልት ነው፡፡ ሁሉም የወያኔን ጠባይና ተፈጥሯዊ ባሕርይ ስለሚያውቀው – ማወቁንም ወያኔዎች ራሳቸው ስለሚያውቁ – ይህን ያህል በሕዝብና በሀገር ሀብት መቀለድ አያስፈልጋቸውም ነበር፡፡ ይልቁንም እንዲህ የሚጫወቱበትን የሀገር ሀብትና ንብረት ዜጎችን አለፍላጎታቸው እየዘረፉ ገሚሱን ለሙስና ገሚሱን ለግንባታ በሚል እንዳሻቸው ለሚመዘብሩበት ለዚያ መከረኛ የአባይ ግድብ ቢያውሉት ይሻል ነበር፡፡

እኔ ግን አዘንኩላቸው፡፡ ድሆችን አስገድደው አእምሯቸውን በመድፈር ለዚህ ለኢትዮጵያ ውድቀትንና ውርደትን ላስከተለ የግንቦት 20 በዓል በማሰለፋቸው ለነሱም አዘንኩ፡፡ አስገድደው የሚደፍሩ ሰዎች በዚያ ሰዎችን እያስለቀሱና ደም እያስነቡ በሚፈጽሙት ወሲብ እንዴት እንደሚደሰቱ ለማወቅ እርግጥ ነው እነሱን መሆንን ይጠይቃል፡፡ ነገር ግን ደስታቸው ሰይጣናዊ እንጂ ቅዱስ እንደማይሆን መረዳት አይከብድም፡፡ ግልጽነት በተወሰነ ደረጃ መጥፎ አይመስለኝም፤ ይህን ጉዳይ በሚመለከት በራሴ ሕይወት ማረጋገጥ የምችለው አንድ ነገር አለ – እርሱም በተለይ በወጣትነት ዘመኔ ባለቤቴ ዳቦ አልሰጥም ብላ እምቢ ስትለኝና በእልኽ ተነሳስቼ ዳቦዋን አለፍላጎቷ ስቀማት፣ ከበላሁት በኋላ ምንም ያላገኘሁ ያህል ይሰማኝ እንደነበር አሁን ድረስ ትዝ የሚለኝ ልዩ ትውስታ ነው፡፡ ምክንያቱም ጉድለቱ ወደራሴ ስመለስ እየቆዬ ይሰማኛል፡፡ ፈቅዳና ወድዳ ስላልስጠችኝ ብበላም አልረካም፤ እናም የጥፋተኝነቱ ስሜት እውነተኛ ደስታን እንዳገኝ አያስችለኝም ነበር – እንኳንስ የማታውቀውን ሰው ማስገደድ ይቅርና የራስህንም ቢሆን በፍቅር እንጂ በጠብና በእልህ አይሆንም ለማለት ፈልጌ ነው እንዲህ የራሴን ምሥጢር ፀሐይ ላይ አውጥቼ የማሰጣው፡፡ ይቅርታ ደግሞ፡፡ ሆ!

ስለዚህ ወያኔን ይቅር የሚለው ይቅር ይበላቸው፡፡ የሚያደርጉትን አያውቁምና ኅሊናቸውን ይመልስላቸው፡፡ በሽተኞችንና የአእምሮ ዘገምተኞችን ሣይቀር በየወረዳውና በየቀበሌው እንዲሁም በየከፍተኛው ከፍተኛ የኃላፊነት ሥራ ላይ ሳይቀር እየመደቡ ሕዝብንና ሥራን እንደሚበድሉ በበኩሌ አውቃለሁ፡፡ የተማረ ሰው እነሱ ጋ መሥራት ስለማይፈልግ አብዛኛው ሠራተኛቸው ከፊደል ዘር የተጣላ ማይም መሆኑንና  ያገኘውን አግበስበስብሶ ዘወር ለማለት የሚፈልግ እንደነሱው ወሮበላ መሆኑን አውቃለሁ፡፡ በወያኔዎች መንግሥት የሥራ መዋቅር በየደረጃው የተሰገሰገው የሰው ኃይል ለሆዱ እንጂ ለሀገራዊ ጥቅምና ዓላማ እንዳልሆነም የታወቀ ነው፡፡ ብዙው ሠራተኛቸው ዛሬ ከምሞት ነገ ልሙት ብሎ ቆርጦ የተነሣና ለማንም ለምንም የማይሞቀው የማይበርደው መሆኑም እውነት ነው፡፡ በዚህም ሳቢያ ኢትዮጵያ በብላኔ እየተነዳች እንዳለች ሁላችን እናውቃለን፡፡ ቢሆንም ምን እያደረጉ እንዳሉ ማወቅ የማይፈልጉትን ወያኔዎች ፈጣሪ ይማርልንና የኛ የሚላቸውን ሰዎች በቶሎ ይስጠን፡፡

ማሳሰቢያ፡- ዓ.ፍ  – ዓመተ ፍዳ ለማለት ነው፡፡ ዓ.ዓ. ብል ኖሮ ደግሞ ዓመተ ዓለም በሆነ ነበር፡፡

የኢ/ር ግደይ ዘርዓጽዮን ቃለምልልስ ክፍል 2 –“በኢትዮ-ሶማሊያ ጦርነት ወቅት ሁለቱም ጠላቶቻችን ናቸው የሚል አቋም ነበረን”

0
0


ኢንጂነር ግደይ ዘርዓጽዮን፤ መሥራችና የቀድሞው የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ፖሊት ቢሮ አባል ስለ ድርጅቱ አመሰራረት፣ የትግል እንቅስቃሴ ታሪክና ሚናዎች ይናገራሉ።

“የትግራይን የብሔር እኩልነት እስከመገንጠል ድረስ፤ የራሱንም ሪፐብሊክ ለመመሥረት ይታገላል የሚል በፕሮግራሙ ነበር። Sensitivity አልነበረንም ለዛ።” – ኢንጂነር ግደይ ዘርዓጽዮን

hqdefault

ጎንደር ህብረት አስቸኳይ መግለጫ –“የወልቃይት ጠገዴ፣ ቃፍቲያ፣ ሁመራና ጠለምት ህዝብ ፈጥኖ ደራሽ አጋር ይሻል”

0
0

Gondor Hibret

ወያኔ ገና ካፈጣጠሩ ጀምሮ፤ አገር ሸንሽኖ፤ ህዝብን ከፋፍሎ፤ ለዘለዓለም የሥልጣን ዘመኑን ለማራዘም አለሞ እና ሸርቦ የተነሳውን ህልሙን ለማሳካት፤ የመጀመርያ የጥቃት ኢላማው ያደረጋት የጎንደር ክ/ሀገርን ነው። የዚም የመጀመርያው የግፍ ሰቆቃን እየተጋቱ ያሉት፤ ደግሞ ሰሜን ምዕራብ ክ/ሀገራችን ኗሪ የሆኑት የወልቃይት፤ ጠገዴ፤ ፀለምት ወገኖቻችን ናቸው።

ይሁን እንጂ፤ ከሰላሳ ዓመት በላይ የአካባቢዋን እና የዘር መሰረታቸውን ታሪክ ነጋሪ እንኳ እንዳይኖር፤ አንድ በዓንድ ለቅሜ አጥፍቻለሁ፤ ብሎ ያስብ የነበረውን ከንቱ የወያኔ ቅዠት አዲሱ ትውልድ፤ ለማንነቱ፤ ፍርሃትን ሰብሮ ወደ ትግል ከወጣ ውሎ ቢያድርም፤ አሁን ግን የነዚህ ወገኖቻችን የትግል ምዕራፍ የመጨረሻው የሞት ሽረት ደረጃ ላይ ደርሷል።

(ሁመራ ከተማ)

(ሁመራ ከተማ)

የዚህም አንዱ እና ዋንው ሀቅ፤ ወያኔ በጎንደር ህዝብ ላይ በጉልበት የጫነዉ የመስፋፋት እና የመሬት ቅርምት አባዜን ለመገደብ፤ በሁሉም የጎንደር ሕዝብ ቆራጥነት ድጋፍ ማግኘቱ ነው። ከእንግዲህ በኋላ፤ የቃፍቲያ ሁመራ፤ ወልቃይት ጠገዴ እና ጠለምት ህዝብ የወያኔን የዘር አጥፊ በደል መሸከም ከሚችለዉ በላይ በመሆኑ፤ ትግስቱን ጨርሶ በአንድ ድምጽ ተማምሎ “የትግራይ ነፃ አዉጭ ግንባር ተከዜን ተሻግሮ አያስተዳድረንም” ከሚል ዉሳኔ ላይ ደርሶ፤ የራሱን መሪና የጎበዝ አለቃ መርጧል። በጎንደሬነቱ፤ በአማራነቱ፤ በባህሉ፤ ለዘመናት በኖረበት መሬቱና በጠቅላላ ማንነቱ ላይ ግፍና መከራ ስለተፈጸመበት፤ በአንድ ድምጽ በቃለ መሃላ ነጻነቱን አዉጇል። ተወደደም፤ ተጠላም፤ ይህ የቃፍቲያ ሁመራ ወልቃይት፤ ጠገዴ፤ እና የጠለምት ህዝብ “ጎንደሬም አማራም ነን” በሚል መፈክር ለነፃነቱ ያቀጣጠለውን ትግል፤ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በቅንነት መቀበል ሰባአዊነት ነው። በተለይ ደግሞ፤ ለዘመናት የጎንደር እና የትግራይ ሕዝብ፤ በጉርብትና ሲኖሩ፤ ተዋደው እና ተፈቃቅረው ያጋኙትን ተካፍለው ከመኖር ባሻገር፤ አንድም ቀን እንኳ፤ የመሬት ይገባኛል ግጭት አድርገው እንደማያውቁ እየታወቀ፤ በአሁኑ ሰዓት፤ የትግራይ ወገኖቻችን፤ ዘመን ካሳበጣቸው፤ ጥቂት ከውሥጣቸው በወጡ ቡድኖች ምክንያት፤ የተጠነሰሰውን፤ ታሪክን መሰረት ያላደረገ፤ የመሬት ሥግብግብነት፤ ተንኮል፤ በዝምታ፤ መመልከት፤ እጅግ አሳዛኝ የሆነ፤ የታሪክ ስህተት መሆኑን ለማስገንዘብ እንወዳለን።

ስለሆነም፤ የትግራን እና የጎንደርን ሕዝብ የወደፊት አብሮነት ታሪክ ለማስቀጠል ሲባል፤ ማንኛውም የትግራይ ተወላጅ፤ ወገኖቻችን ይዘው የተነሱበትን የማንነት ጥያቄ፤ የታሪክ እውነት መሆኑን፤ ማክበር እና መቀበል እንዳለበት ከወዲሁ ልናሳስብ እንወዳለን። አፈጣጠሩ እና ባህሪው አይፈቅድለትም እንጂ፤ ልብ ሰጥቶት የገዥዉ መደብም ቢሆን፤ ይህን የሕዝብ ውሳኔ ማከበር የጎንደርን ህዝብ ማክበር ነዉ የሚል እምነት አለን። ለዓመታት የጠዬቀዉ የጎንደሬነት ጥያቄ ምላሽ ባለማግኘቱ ጭቆናዉ በዝቶበት እራሱ በመረጣቸዉ መሪወች ለመተዳደር መወሰኑ ፍህታዊ እና ህዝባዊ እርምጃ ነዉ። መከበር ይገባዋል!!

ከእንግዲህ ይህንን ህሊናዉ የቆሰለ እንግዳ ተቀባይ ደግ ህዝባቸን ላይ፤ ተከዜን ተሻግሮ ከአድዋ በመጣ ፀረ ሽምቅ ሰራዊት ተኩሶ በመግደል፤ የበለጠ ሕዝባችንን ወደከፋ መተላለቅ የሚገፋ መሆኑን ተገንዝቦ፤ ጣቱን ከመሳሪያ ምላጭ አንስቶ፤ የወገኖቻችን ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ ምላሽ እንዲሰጥ እናሳስባለን።

ይህ ግፍ እና በደል የወለደውን፤ የጎንደሬ/የአማራ ማንነት ጥያቄ፤ ቆመንለታል ብላችሁ፤ ለ25 ዓመት በወያኔ፤ እየተሽከረከራችሁ ያላችሁ፤ የብ.አ.ዴን አባላት እና ካድሬዎች፤ የማንነታችሁ መፈተኛ ወቅት ላይ በመሆናችሁ እና፤ የመጨረሻ እጣ ፈንታችሁ ወቅት ላይ በመድረሳችሁ፤ ከእንቅልፋችሁ የምትነቁበት ደወል፤ እየተደወለ ነው። በዚያው እንዳታሸልቡ፤ ከወገኖቻችሁ ጋር ለማንነታችሁ አብራችሁ በመቆም እስካሁን የበደላችሁትን ወገናችሁን ልትክሱ የግድ ነው። እንዲሁም፤ የሰባቱ አዉራጃ የጎንደር ህዝብ፤ ጥያቄው፤ የራሱ ማንነት ጭምር መሆኑን በማመን፤ በአስቸኳይ፤ በሚፈለገው ሁሉ ትብብሩን ማሳየት፤ የግድ እሚልበት ደረጃ ላይ በመሆኑ፤ እስቸኳይ ታሪካዊ ምላሽ፤ ለወልቃይት ጠገዴ፤ ጠለምት ወገኖቻችን እንዲያሳይ የጎንደር ሕብረት ታሪካዊ እና ወቅታዊ ጥሪያችንን ለማስተላለፍ እንወዳልንለን። የጎንደር ሕብረት የተመሰረተበት ቋሚ ዓላማም፤ ሁላችንም በሰላም እና በፍቅር ታሪካዊ፤ መልካዓ ምድራችንን ጠብቀን በጋራ እንድንኖር የሚያስችለንን ታሪክ ለማስጠበቅ ነው። በመሆኑም፤ ስማችን ጎንደር ነክ ይሁን እንጅ፤ ለትግራይም ሆነ፤ ለመላ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን እኩል ፍቅር፤ እኩል፤ ተቆርቋሪነት እና ኃላፊነት ይሰማናል።

ሌላዉ ሳንጠቅስ የማናልፈዉ እጅግ አሳዛኝ ሁኔታ ደግሞ ባለፈው ወር የጋምቤላ ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመዉ የጀምላ ጭፍጨፋ ነዉ። የኢትዮጵያን መሬት አሳልፎ ለመስጠት በተሸረበ ሴራ ምክንያት ወያኔ፤ ጠረፍ ጠባቂ፤ ፀጥታ አስከባሪ፤ የነበሩትን የታጠቁትን የአካባቢ ሚሊሻዎች፤ ትጥቃቸውን አስፈትቶ፤ ካምፕ ውስጥ እንደከብት በመዝጋቱ ምክንያት፤ አካባቢዉን ክፍት መሆኑን የተረዱ፤ ከ እንሰሳት ዝርፊያ አልፈው የሰው ህይወት ለማጥፋት ተዳፍረው የማያውቁ የደቡብ ሱዳን ኗሪ የሙርሊ ብሔረሰቦች በወሰዱት አሰቃቂ ርምጃ ከ200 በላይ ኢትዮጵያዊያን ተጨፍጭፈዉ፤ 150 ታፍነዉ ሲወሰዱ፤ እጅግ ብዛት ያላቸውን ቤት እና ንብረት አቃጥለው፤ በሺ የሚቆጠሩ የቀንድ እና የጋማ ከብቶችም ተዘርፈው ተወሥደዋል።

እንዲሁም በተመሳሳይ መልኩ በመተከል ቁጥራቸዉ ወደ 70 የሚደርሱ አርሶ አደሮች በሱዳን መንግስት ተጠልፈዉ መዳረሻቸዉ ጠፍቶ፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ የቀንድ ከብቶችም ተዘርፈው ሲወሰዱ፤ እርምጃ የሚወስድ ቀርቶ፤ የሚጠይቅ መንግስት እንኳ አልተገኘም።

ይህ የሚያሳየው፤ አገራችንም ሆነ ሕዝባችን፤ መንግሥት ተብዬ አገር በቀል ጠላት ቅንብር፤ በውጭ ታሪካዊ ጠላቶቻችን የጥቃት አደጋ እንደተደቅነብን ነው። በመሆኑም፤ ኢትዮጵያ አገራችንም ሆነ የህዝባችን ደህንነት የሚጠብቅ መንግስት እንደሌለ አዉቀን በሞቱት ወገኖቻችን መሪሪ የሆነ ሃዘናችንን በሃገራዊ ቁጭት እየገለጽን፤ ለዘመድ አዝማድ ሁሉ መጽናናትን ይስጥልን እንላለን። የደቡብ ሱዳንም ሆነ የሰሜን ሱዳን መንግስት በወያኔ ቅጥረኞች ታፍነዉ የተወሰዱ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን ከነንብረታቸዉ ወዳገራቸዉ በአስቸኳይ እንዲመለሱ፤ ወንጀለኞችም ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን። የመላዉ ኢትዮጵያ ህዝብም፤ በዬአካባቢው የራሱን መሪ መርጦ፤ ደህንነቱን ጠብቆ፤ ዳር ደንበሩን እንዲያስከብር ጥብቅ መልክታችን እናስተላልፋለን። ከዉጭ አገር ጋር ተባባሪ የሆነዉ የወያኔን መንግስት እንደ አገር መሪ ቆጥሮ ህዝባችን እንዳይዘናጋ አደራ እንላለን።

በመጨረሻም በጎንደር ክፍለ ሀገር በቋራ ወረዳ የጓንግን ወንዝን ተሻግሮ ከኢትዮጵያ መሬት የሰፈረዉ የሱዳን ወታደር በአስቸኳይ እንዲለቅ እንጠይቃልን።

ጀግናዉ የጎንደር ህዝብ ዳር ድንበሩን ያስከብራል!!!

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!

ጎንደር ህብረት

ከ5ኛው ዙር የማኅበረ ቅዱሳን ዐውደ ርእይ ከፍቶኝ አዝኜም ወጣሁ!

0
0

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

5ኛው ዙር የማኅበረ ቅዱሳን ዐውደ ርእይ!

በብዙ ትግል ጥረትና ድካም ስንት ወጪ ወጥቶበት የተዘጋጀው የማኅበረ ቅዱሳንን 5ኛው ዙር ዐውደ ርእይ እንደጠበኩት አላገኘሁትም፡፡ ጎበኘሁት ከፍቶኝ አዝኘም ወጣሁ!

ከዐውደ ርእዩ ሥያሜ ተነሥቸ በዚህ ዐውደ ርእይ ላይ ቤተክርስቲያን አሁን ያለችበትን እጅግ አሳሳቢ ሁኔታ ማለትም ከደረሱባት ከባባድ ፈተናዎች የተነሣ የደረሱባትን ጉዳቶች፣ በግንባር የሚጠብቃትን ከባባድ ችግሮችና ፈተናዎች ለጎብኝዎች በሚገባ ያስገነዝባል የሚል ግምት ነበረኝ፡፡
አገዛዙ “የኦርቶዶክስን አከርካሪ ሠብረናል!” በማለት እስከመግለጽ ያደረሰውን የጥፋት ድል “ወያኔ ይሄንን ይሄንን አደረገ” ባይሉም እንኳ የደረሰውን ጉዳት ግን መናገር ማሳወቅ ይጠበቅባቸው ነበር ሊያደርጉት ግን አልቻሉም፡፡ ይሄ ቀርቶ እኔ ምን እንደሆኑ አላውቅም ሌሎች ሊገለጹ የሚችሉ ነገሮችን እንኳ መግለጽ አልቻሉም፡፡

ተሽለው ያየሁት በዐውደ ርእዩ ላይ ሊገለጽ የሚገባውን ያህል ባይሆንም በተሻለ ሁኔታ የተሐድሶ መናፍቃንን ሕገወጥና አጋንንታዊ እንቅስቃሴን ተኩሎቻቸውን እያሰለጠኑ እንዴት ወደ ቤተክርስቲያን አስርገው እንደሚያስገቡ በምስለ ትዕይንት (በቪዲዮ) በተደገፈ መረጃ ማሳየታቸው ነው፡፡

የሚገርመው ይሄንን ያደረጉ ሆኖ እያለ የቤተክርስቲያን አባላት (የምእመናን) ቁጥር ያሽቆለቆለበትን ምክንያት ሲገልጹ ግን ምን ይላሉ “ሩቅ የሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎችን መድረስ ባለመቻሉ ነው!” በማለት ትክክለኛውን የችግሩን መንስኤ ወይም ምክንያት ከመግለጽ በመታቀብ አስቂኝ የሆነ ምክንያት ሰጥተው አረፉት፡፡
ቤተክርስቲያን በብዙ ሚሊዮን (አእላፋት) የሚቆጠሩ በጎቿ በተኩሎቹ በመናፍቃን እንደተበሉባት በግልጽ የሚታወቅ ጉዳይ ሆኖ እያለ ማኅበረ ቅዱሳን ይሄንን እውነት ለመግለጽ ለማሳወቅ ለማስረዳት አንደበቱ ከተሸበበ ካልቻለ በግልጽ መረዳት እንደሚቻለው ዐውደ ርእዩ እየተደረገ ያለው በከባድ ፍርሐትና ጫና ውስጥ ነው ማለት ነው፡፡

ሌላው ያስከፋኝ ነገር ቢኖር “የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ቅዱሳን ሐዋርያት ምንትስ እያለች ሰዎችን ትሰብካለች፣ የሰዎችን ታሪክ ትተርካለች፣ በስማቸው ዝክር ዘክሩ ምንትስ እያለች ታስተምራለች እንጅ ኢየሱስን አትሰብክም!” ለሚለው ከወንጌል የሚጻረር የመናፍቃን ክስ በተደጋጋሚ እየተነሣ አባቶች ሳይቀሩ እልህ በተናነቀው ስሜት የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ክርስቶስን እንደምትሰብክ ማሳያዎችን እየጠቀሱ ለማስረዳት ጥረት ሲደረግ ተመልክቻለሁ፡፡ ይሄ በጣም አስከፍቶኛል ስሕተትም ነው፡፡ ስሕተት የሚሆነው ለዚህ ክስ መልስ በሚሰጥበት ወቅት “ኧረ እኛም እንሰብካለን!” የሚል ቅኝት ስላለው በተዘዋዋሪ መናፍቃኑን “ክርስቶስን ትሰብካላቹህ!” የሚል እውቅና የሚሰጥ አኪያሔድ ያለው በመሆኑ ነው፡፡ ክርስቶስ አንድ ነው እንጅ የክርስትና ሃይማኖት ነን በሚለው ድርጅት ቁጥር ልክ “ክርስቶስ እንዲህ ነው! እንዲህ አይደለም!” እያሉ እንደሚሰብኳቸው የተለያዩ ዓይነቶች ክርስቶሶች መዓት ዓይነት ክርስቶስ የለም!

“የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው። ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው። ልዩ ልዩ ዓይነት በሆነ በእንግዳ ትምህርት አትወሰዱ፤ ልባችሁ በጸጋ ቢጸና መልካም ነው እንጂ በመብል አይደለም፤ በዚህ የሚሠሩባት አልተጠቀሙምና” ዕብ. 13፤7-9

“…ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ። እነሆ፥ አስቀድሜ ነገርኋችሁ። እንግዲህ። እነሆ፥ በበረሀ ነው ቢሉአችሁ፥ አትውጡ፤ እነሆ፥ በእልፍኝ ነው ቢሉአችሁ፥ አትመኑ፤ መብረቅ ከምሥራቅ ወጥቶ እስከ ምዕራብ እንደሚታይ፥ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና” ማቴ. 24; 24-27

ሲጀመርም ጥያቄው ወይም ክሱ የኢየሱስ ክርስቶስን አስተምህሮ የሚጻረር አጋንንታዊ ጥያቄ ወይም ክስ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የነቢያት የቅዱሳን ሐዋርያት እያለች ገድላቸውን መተረኳ በስማቸውም ዝክር (መታሰቢያ) መዘከሯ ክርስቶስ በወንጌሉ “እኔን የመቀበላቹህ ማረጋገጫው ይሄ ነው!” ስላለና ኢየሱስ ክርስቶስን ለመቀበላችን ማስረጃ ምስክር ማረጋገጫ ስለሆነ ነው፡፡ መናፍቃኑ ደግሞ ይሄንን አለማድረጋቸው እንደ ክርስቶስ ቃል ክርስቶስን ያለመቀበላቸው ማረጋገጫው ነው፡፡ ይሄንን ያልኩት እኔ ሳልሆን በቅዱስ ወንጌሉ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፡፡ ሐዋርያቱን ትዕዛዝ ሰጥቶ ወደ ዓለም በላከበት ባሰማራበት ወቅት፡፡

“እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል። ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል። ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋው አይጠፋበትም” ማቴ. 10፤40-42

እንግዲህ የኢየሱስ ወንጌሉ የሚለው ይሄንን ነው፡፡ ይሄም በመሆኑና የኢየሱስንም ቃል ሳትሸራርፍ አሟልታ መፈጸም ማክበር መጠበቅ ስላለባት ነው ቤተክርስቲያን በነቢያቱ፣ በደቀመዛሙርቱ፣ በቅዱሳን ሐዋርያቱ ስም ዝክር የምትዘክረው ስለ ክርስቶስ ሲሉ የተጋደሉትንም ገድል (በሕይዎት የተተረጎመ ወንጌል) ጽፋ የምትተርከው፡፡ ከላይ እንዳነበባቹህት የኢየሱስ ክርስቶስ ቃል እነሱን ሳይቀበሉ፣ በስማቸው ሳይዘክሩ ኢየሱስን መቀበል ስለሌለ ስለማይቻል ነው፡፡
ስለሆነም ነው ከላይ ክሳቸውን ከክርስቶስ ወንጌል ጋር የሚጻረር አጋንንታዊ ክስ ነው ያልኩት፡፡ ላይ ላዩን ሲያዩት ለክርስቶስ ኢየሱስ የመቆርቆር ስሜት ያለው ይመስላል ውስጡ ግን የክርስቶስን ቃል ወንጌልን የሚጻረር በመሆኑ መርዝና አጋንንታዊ ነውና “እኛም…” በማለት ይሄንን ክስ እያነሡ ማንጸባረቅ ክሱን ከትክክለኛ ቦታ እንደተነሣ ትክክለኛ ጥያቄ ስለሚያስመስል መልሱ መሰጠት ካለበትም በዚያ ቅኝት መሆን ስለሌለበት ይሄም መታረም ይኖርበታል፡፡
ሌላው ገለጻ በሚያደርጉበት ጊዜ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን፣ የምንትስ ቤተክርስቲያን የሚል የቃላት አጠቃቀም ተመልክቻለሁ፡፡ ቃሉ የሚለው አንዲት ቤተክርስቲያን፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንድ መንገድ ብቻ መኖሩን ነው፡፡ ኤር. 6፤16 ኤፌ. 4፤5 ይሁ. 1፤3

kidusan

በመሆኑም እነሱን መጥራት ካስፈለገ ካቶሊካዊያን፣ ፕሮቴስታንታዊያን ወዘተረፈ. በማለት መጥራት ይገባል እንጅ በኑፋቄ እየተጠለፈ በየዘመኑ እየተገነጠለ የወጣውን ሁሉ የምንትስ ቤተክርስቲያን፣ የምንትስ ቤተክርስቲያን ካልን ቤተክርስቲያንንም እራሳችንንም ማስዋሸት የእግዚአብሔርንም ቃል ማስተባበል ነውና ይሄም ሌላው መታረም ያለበት ጉዳይ ነው፡፡

ሌላው እዚያ ቦታ ሊቀርቡ የሚችሉ ንዋዬ ቅድሳት በሙሉ የቀረቡ ሲሆን ትእምርተ ኪዳኑን (የቃልኪዳን ምልክቱን ማለትም ሰንደቅ ዓላማውን) ግን አላቀረቡትም፡፡ ይሄም ወያኔን ያስከፋብናል ተብሎ ወያኔን በመፍራት ከቀሩት ነገሮች አንዱ መሆኑ ነው፡፡ በመጀመሪያዎቹ ዐውደ ርእዮች ግን በሚገባ ከበቂ ማብራሪያ ጋር ቀርቦ እንደነበረ የሚታወስ ነው፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥታት ሰንደቅ አላማውን ከቤተክርስቲያን ወሰዱ እንጅ ቤተክርስቲያን አይደለችምና ከእነሱ የወሰደችው ይሄ መደረጉም ስሕተት ነው፡፡

በቤተክርስቲያን ከጥንታዊ የብራና መጻሕፍት አንሥቶ እስከ ጉልላቷና መንበረ ታቦቷ ድረስ ከጥንት ጀመሮ የእነዚህ ሦስት ቀለማት ማኅተም በተለያዩ መልኩ አሠራሩና ጥበባዊ ስልቱ እንዲያርፍበት ይደረጋል፡፡ የዚህ ምክንያቱ ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ በዘፍ. 9÷8-17 ላይ እንደተገለጸው እግዚአብሔር በኖሕ በኩል ለሰው ልጆች ሁሉ ዓለምን ዳግመኛ በጥፋት ውኃ ላያጠፋት ቃል ሲገባለት ለገባው ቃል ኪዳን ምልክትና ምስክር ትሆን ዘንድ “ቀስቴን በደመና ላይ እዘረጋለሁ የምሕረት የቃል ኪዳን ምልክት ትሁን!” እንዳለው እናያለን፡፡

አንዳንድ ሰዎች ታዲያ ሰንደቁ ቀስተ ደመና ከሆነ ለምን ሦስት ቀለማት ብቻ ሆነ? በቀስተ ደመና ውስጥ ያሉት ቀለማት ሰባት ናቸውና የሚሉ አሉ፡፡ እርግጥ ነው አትኩረን ላየነው በቀስተ ደመና ውስጥ ያሉ ቀለማት ሰባት ናቸው፡፡ ነገር ግን አራቱ ቀለማት የሚፈጠሩት በውሕደትና በውርርስ እንጅ እንደ ሦስቱ ቀለማት ማለትም እንደ ቀዩ ቢጫውና አረንጓዴው በራሳቸው ህልው ሆነው አይደለም፡፡ ቀዩ ከቢጫው ቢጫው ከአረንጓዴው ጋር ባለው መጋጠሚያ መጋጠሚያቸው ላይ በንክኪው ውሕደት ሲፈጥሩ የሚፈጠሩ ሁለት፡፡ እንዲሁም ከቀስተ ደመናው ላይና ታች ከሰማዩና ከመሬቱ ቀለማት ጋር ባለው መወራረስ ደግሞ ሌላ ሁለት የሚፈጠሩ ናቸው፡፡ በድምሩ 4ቱ ቀለማት ከአረንጓዴው ከቢጫውና ከቀዩ ውጭ ያሉት በራሳቸው ህልው የሆኑ ሳይሆኑ በእነዚህ በሦስቱ ቀለማት ተጽዕኖ የሚፈጠሩ በመሆናቸው ቤተክርሲቲያን ሦስቱን ዋነኛ የቀስተ ደመናውን ቀለማት ብቻ ልትወስድ ችላለች፡፡ በመሆኑም የቀስተ ደመናው ቀለማት በጉልህ የሚታዩት ቀይ ቢጫ አረንጓዴ ሦስቱ ቀለማት ናቸው እንጅ ሰባት ቀለማት አይደሉም ማለት ነው፡፡

በተጨማሪም ሦስቱ ቀለማት ሦስት መሆናቸው በቤተክርስቲያን ካላቸው የምሥጢር ትርጉም አንዱን ብቻ ስጠቅስ የምሥጢረ ሥላሴ ምሳሌ መሆኑ ወይም መሆናቸው ነው ትላለች ቤተክርስቲያን፡፡ ማለትም ሥላሴ (እግዚአብሔር) አንድም ሦስትም ናቸው ወይም ነው፡፡ የሚለውን ምሥጢረ ሥላሴን ለማጠየቅ ነው፡፡ ቀስተ ደመና ከቃል ኪዳን ምልክትነቱም በላይ የልዑል እግዚአብሔር የክብሩ መገለጫም ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስና ነቢዩ ሕዝቅኤል በየራእዮቻቸው ልዑል እግዚአብሔር በክብርና በሚያስፈራ ግርማ በዙፋኑ ላይ ሆኖ ዙሪያውን በሚያምርና ኅብር ባለው የቀስተ ዳመና ጸዳል ተከቦ ተመልክተውታል፡፡ ራዕ ዮሐ 4÷2-3 ትን ሕዝ 1÷26-28

እንግዲህ እግዚአብሔር የቃል ኪዳን ምልክት ነው ያለውን በጉልህና በግልጽ የሚታዩትን በራሳቸው ህልው የሆኑትን ሦስት ቀለማት በመውሰድ ቅድስት ቤተክርስቲያን ከእግዚአብሔር እንደተሰጣት የቃል ኪዳን ምልክቷ አድርጋ በመውሰድ ለተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎት ትጠቀምበታለች፡፡ ለምሳሌ በሀገር ላይ አንዳች ችግር፣ መዓት፣ ቁጣ በሚከሰትበት ጊዜ ማለትም ጦርነት፣ ረሀብ፣ ድርቅ፣ በሽታ፣ ቸነፈር የመሳሰሉት ችግሮች ሲፈጠሩ ምንም እንኳ ቀይ ቢጫ አረንጓዴው ትእምርተ ኪዳኑ (የቃል ኪዳኑ ምልክት) የተሰጠው “መላ ዓለምን የሚያጠፋ የጥፋት ውኃ ዳግመኛ በሰው ልጆች ላይ ላያመጣ” ቢሆንም ይህችን የቃል ኪዳን ምልክት አንድ ጊዜ “የምሕረት የቃል ኪዳን ምልክት” ብሏታልና እነዚህ ችግሮች በሚከሰቱበት ጊዜም በምሕላ ጸሎት (ወር በገባ ከ1-7 ባሉት ቀናትና ከላይ የተገለጹት ችግሮች በሀገር ላይ ሲከሰቱ የሚጸለይ የጸሎት ዓይነት) ጊዜ ፈጣሪን ከቁጣህ ተመለስ፣ በምሕረትህ አስበን፣ በቸርነትህ ጎብኘን፣ ቃልኪዳንህን አስብ! ለማለትና ለምሕረት የገባውን ቃል አስቦ ምሕረት እንዲሰጠን ለማድረግ በጸሎቱ ሰዓት ትእምርተ ኪዳኑን ከሥዕለ አድኅኖና ከመስቀሉ ጋር ተይዞ በዐውደ ምሕረት ላይ እየተወጣ ሥርዓተ ጸሎቱ ይደረጋል፡፡

ቤተክርስቲያን በዚህ መልኩ ከጥንት ጀምሮ ስትገለገልበት እንደቆየች በአድዋ ጦርነት ጊዜ በተንቀሳቃሽ ድንኳን እየተቀደሰ አብሮ ዘምቶ ከነበረው የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ድሉን እንዳገኙ ዐፄ ምኒልክ ቀይ ቢጫ አረንጓዴውን የቃል ኪዳን ምልክት ሰንደቅ (ትእምርተ-ኪዳን) አንሥተው “ከዛሬ ጀምሮ ይህች ሰንደቅ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ትሁን!” ብለው እዛው ካሉበት አድዋ አወጁ፡፡

kidusan 2

በእርግጥ በአዋጅ በይፋ አይሁን እንጅ ከዚያ ቀደም የነበሩ ነገሥታትም በጣም ከጥቂቶቹ በስተቀር ካህናት ማለትም ቢያንስ ዲያቆን ያልነበረ የለምና በዚህ ቅርበታቸው ይህንን ትእምርተ ኪዳን (ሰንደቅ) እንደ ሀገር ሰንደቅ አድርገው ይጠቀሙበት እንደነበረ ይታወቃል፡፡ ቀረብ ያሉትን ለማንሣት ዐፄ ቴዎድሮስን ከሳቸውም በኋላም ዐፄ ዮሐንስ 4ኛንም መጥቀስ ይቻላል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ይሄ ለቤተክርስቲያን ከንዋየ ቅድሳት የመጀመሪያው የሆነው ንዋየ ቅዱስ በግልጽ በይፋ በአደባባይ በበዓላትም ሆነ በአዘቦት ቀን አገልግሎት እየሰጠ ያለው ጎንደርና አክሱም ብቻ ነው፡፡ በሌሎቹ ግን በወያኔ ካድሬ ካህናት የተነሣ ጠፍቷል፡፡ የአጋንንት አምላኪዎችና የአሕዛብ ምልክት የሆነው ኮከብ የተለጠፈበት ነው አብያተክርስቲያናቱን ሁሉ ሞልቶት ያለው፡፡ እናም በዐውደ ርእዩ ላይ እንደ ከዚህ ቀደሞቹ ዐውደ እርዮች ሁሉ ይህ ንዋየ ቅዱስ አለመቅረቡ ስሕተት ነው፡፡

ወያኔ በገዛ ሕገ መንግሥቱ ላይ እንዳስቀመጠው “መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም!” ይላልና ለሃይማኖታዊ አገልግሎት የምንገለገልባቸውን ንዋየ ቅድሳቶቻችንን ይሄንን ተጠቀሙ ይሄንን አትጠቀሙ ሊል የሚችልበት መብት ፈጽሞ ስለሌለው በዚህ ንዋየ ቅዱስ ከመገልገል መታቀብ አይገባም ነበረ፡፡ እንዲያው ነገሩን አልኩ እንጅ ወያኔ የትኛውን ሕግ አክብሮ ያውቅና!

ሌላው በቤተክርስቲያን ታሪክ እንደሚታወቀው ሁሉ ከዚህ ቀደም በነበሩት ዐውደ ርእዮች የምሥራቅ አብያተክርስቲያናት ወይም አኃት አብያተክርስቲያናት በመባል የሚታወቁት አምስት ነበሩ፡፡ እነሱም የኢትዮጵያ፣ የግብጽ፣ የአርመን፣ የሶሪያና የሕንድ ናቸው፡፡ እዚህኛው ዐውደ ርእይ ገለጻ ሲደረግ ስንሰማ ግን ስድስት አድርገዋቸው አረፉት፡፡ ግራ ገብቶኝ ቆየሁና “ደሞ ማን ተጨምሮ ነው ስድስት የተሆነው?” ብየ ገለጻው ካለቀ በኋላ ባነሩን (የማስታወቂያ ሸራውን) ተጠግቸ ተመለከትኩት፡፡ ስድስተኛ ተብላ የተጠቀሰችው “የኤርትራ ቤተክርስቲያን” ተብሎ ተጽፏል፡፡ ስሜቴን መቆጣጠር አልቻልኩም ገለጻ ለሚሰጡት ወንድሞች ፍጹም ስሕተት መሆኑን ገለጽኩላቸው፡፡

ይሄ እንግዲህ ሌላኛው ወያኔን በመፍራት የተፈጠረ ለውጥ መሆኑ ነው፡፡ አሁን ላይ በጊዜያዊ የታሪክ አጋጣሚ የግዛት አንድነቱ ስለፈረሰ ብቻ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንም እንደተከፈለች እየቆጠርን አኃት እያልን ቁጥር የምንጨምር ከሆነማ በአውሮፓ፣ በአሜሪካ፣ በመካከለኛው ምሥራቅና በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ያሉ የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናትንም ያሉበትን ሀገር ስም እየጠራን የእከሌ የእከሌ እያልን አኃት አብያተክርስቲያናት እያልን እንጥራቸዋ ታዲያ!

ይሄንን ስል እዚያ ኤርትራ ያሉ ሀገሪቱ ከመከፈሏ በፊት የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ገዳማት አብያተክርስቲያናት አባቶችና ምእመናን የነበሩት ዛሬ ላይ ፓትርያርክ ሠይመው እየተገለገሉ መሆኑን አጥቸው አይደለም፡፡ ነገር ግን ይሄ የሆነው በፖለቲከኞች ጫናና ግፊት በመሆኑ ለዚህ ሕገ ወጥ ተግባር እውቅና ሰጥቶ እነሱ የሚሉትን ተቀብሎ ማስተጋባት ፍጹም ፍጹም ስሕተት ነው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የኢትዮጵያን ካርታ (ምስለ ምድር) በሚያሳዩበት አጋጣሚ ሁሉ የተገነጠለችውን ኢትዮጵያን ነበር የሚያሳዩት፡፡

ይሄንን ማድረግ አልነበረባቸውም፡፡ ምክንያቱም የትኛውንም ሙዚየም (ቤተ ቅርስ) ብትጎበኙ ተሰቅለው የሚታዩት የኢትዮጵያ ካርታዎች (ምስለ ምድሮች) ሙሉው ወይም ያልተቆረጠችውን ኢትዮጵያን ነው፡፡ ሙዚየሞች (ቤተ ቅርሶች፤ ቤተ መዘክር የሚለው ቃል ትክክለኛ ቃል ስላልሆነ ነው፡፡ ቤተ መዘክር ማለት የመታሰቢያ ቤት ማለት ስለሆነ) ካላቸው ቅርስን የመጠበቅና ጠብቆም የማኖር የማስጎብኘት የማስዋወቅ ተግባርና ኃላፊነት የተነሣ ነው ይሄንን ማድረግ የቻሉት፡፡
ማን እንዳወናበዳቸው ባላውቅም ከሁለት ሦስት ዓመታት ወዲህ ተውት እንጅ አርበኞችም በየበዓላቶቻቸው ይዘውት ይወጡት የነበረው ሙሉዋን ኢትዮጵያና ንጹሑን ሰንደቅ ነበረ የታሪካቸው አካልና የተጋደሉለት እሴት በመሆኑና ታሪካቸውን መዘከር ካለባቸው ማድረግ የሚገባቸውና ያለባቸው ይሄንኑ በመሆኑ መብታቸውም ስለሆነ ነው፡፡
ቤተክርስቲያንም ከማንምና ከምንም በላይ ሙዚየም (ቤተ ቅርስ) ቢሏት ሙዚየም (ቤተ ቅርስ) አርበኛ ቢሏት አርበኛ ናትና ሙሉ የኢትዮጵያን ምስለ ምድር የማሳየት መብት ነበራት፡፡ የምትመራበት ሱታፌን (አንድነትን) መሠረት ያደረገው የክርስቶስ አስተምህሮ በመሆኑም ከቤተቅርሶቹና ከአርበኞቹ በላቀ የሚመለከታት የሚገዳት እሴት ነውና ሙሉዋን ኢትዮጵያን መጠቀም ትችል ነበረ፡፡ መብት የሚጠበቅባት ሀገር አይደለችም እንጅ ሀገራችን፡፡
ሌሎችም እዚህ ልገልጻቸው የማልፈልጋቸው አንዳንድ ያልወደድኳቸው ገለጻዎችንም ታዝቤያለሁ፡፡ አንድ ግን ሳላስተላልፈው ማለፍ የማልፈልገው መልእክት ቢኖረኝ፡- እራሱን የቤተክርስቲያን ግንባር ቀደም ጠላትነት ባሰለፈ የጥፋት ኃይል በወያኔ ፍላጎትና ፈቃድ እየፈሰስን ታዲያ እንዴት ብለን ነው ቤተክርስቲያንን አፍጥጦ ከመጣባት የመጥፋት አደጋ ልንታደጋት፣ የቤተክርስቲያንን ጥቅም ፍላጎት ልናስጠብቅ የምንችለው? የውሽማ ለቅሶ እያለቀስን ወደ መቃብሯ ለመሸኘት ካልሆነ በስተቀር፡፡

ለዚህ ጥያቄ ተገቢ ምላሽ መስጠት እስካልቻልን ጊዜ ድረስ መልሱ “ፈጽሞ ቤተክርስቲያንን መታገድ አንችልም!” የሚለው ነው የሚሆነው፡፡ አሁን በዚህ ጊዜ ቤተክርስቲያን እንዲህ ተሰባብራ መላወስ አቅቷት በምትንጠራወዝበት ሰዓት ጉዳት ሕመሟን፣ ጭንቅ ችግሯን ደፍረን መናገር መጮህ ያልቻልን መቸ ልንናገረው ነው?
ይሄ ቤተክርስቲያንን ከጥፋት የመታደግ ተልእኮ በቁርጠኝነት ደፍሮ በመውጣት በቆራጥነት ካልሆነ በስተቀር ራስን ለአደጋ ለጉዳት ለእንግልት ላለበዳረግ እጅግ እየተጠነቀቁ በሚደረግ እንቅስቃሴ ሊወጡት የሚቻል ተልእኮ ነው ወይ? መልሱ በፍጹም አይደለም ለሚለው ነው፡፡ የቤተክርስቲያንን ታሪክ አገላብጠን ብናይ የምንረዳው እውነት ቢኖር ይሄንን ነው፡፡ ቤተክርስቲያን ከብዙ የአውሮፓ ሀገራት ልትጠፋ የቻለችውና በመናፍቃን የተወረሰችው በዚህ ዓይነት ራስ ወዳድነትና ፍርሐት ሳቢያ ነው፡፡ እንዲህ ብለንማ ነው ይሄው ለዚህ ስብራቷ ሕመሟ ድቀቷ የዳረግናት፡፡ ከዚህ መማር እንችላለን በዝምታችን፣ ዓይተን እንዳላየን ሰምተን እንዳልሰማን በማለፋችን፣ ኃላፊነታችንን ግዴታችንን መወጣት አመለቻላችን ቤተክርስቲያንን ሲጠቅማት፣ ሲያሰፋት፣ ሲያሳድጋት ነው እያየን ያለነው??? ይሄ አኪያሔድ እንዳላዋጣ ቤተክርስቲያንን እየገደላት እንደሆነ እያወቅንም ሞታ እስክትቀበር ድረስም በዚህ እንቀጥል ነው እያልን ያለነው???

ልብ የሚለው የለም እንጅ ይሄ ሁኔታ በዐውደ ርእዩ ላይ መታየቱ ራሱ የዐውደ ርእዩ አንድ አካልና ቤተክርስቲያን በምን ዓይነት ፈተናና ችግር እንዳለች የሚያሳይ አንዱ ትዕይንት ነው፡፡ “የዚህ ዐውደ ርእይ ስኬት ምንድን ነው?” ከተባለም ይሄንን ችግር በሚገባ ማሳየት መቻሉ ይመስለኛል፡፡

በመጨረሻም ይሄንን ዐውደ ርእይ እንድትጎበኙት እየጋበዝኩ በመጀመሪያው ዐውደ ርእይ ላይ ያጋጠመኝን አንድ አሳዛኝ ገጠመኝ ባጭሩ ጋብዣቹህ ልጨርስ፡፡ ከዛ በፊት ግን ከዐውደ ርእዩ አንጀቴን ከበሉኝ ትዕይንቶች አንዱን ልጥቀስ፡፡ የማኅበረ ቅዱሳን ጠንካራና አስመስጋኝ የሥራ ክንውን ከሚታይበት ለቅድስት ቤተክርስቲያን ህልውና የጀርባ አጥንት የሆኑት በሀገራችን በተለያየ ስፍራ የሚገኙ የአብነት ትምህርት ቤቶች ያውም የማስመስከሪያዎቹን መምህራንና ተማሪዎችን በአካል አቅርቦ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያኑ እንዴት ባለ ሁኔታ የመማር ማስተማር ሒደቱን እንደሚከውኑ፣ ያሉባቸው ችግሮች፣ ከማኅበረ ቅዱሳን እየተደረገላቸው ያለው ቋሚ ድጋፍ ምን ያህል ከመጥፋት እንደታደጋቸው አንጀት ከሚበላውና እጅግ ከሚያስቆጨው የዐውደ ርእዩ ክፍሎች አንዱ ነበር፡፡

በመጀመሪያው ዐውደ ርእይ ላይ የእኔ ሦስት ሥዕለ አድኅኖዎች ቀርበው ነበር፡፡ ከሦስቱ አንዱ ከዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ 12ን እና 13ን መሠረት ባደረገ የተሣለ የቅዱስ ሚካኤል አውሬውን 666ን በእሳት ሰይፉ አንገቱን ቆርጦ ሲዖል ሲወረውር የሚያሳይ ሥዕል ነበር፡፡

እና እላቹህ ይህ ሥዕለ አድኅኖ ቦታውን ይዞ እንዳለ ዐውደ ርእዩን መርቀው ሊከፍቱ አባ ጳውሎስና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት መምጣት፡፡ መርቀው ከከፈቱ በኋላ እየተዘዋወሩ በሚጎበኙበት ወቅት ከዚህ ሥዕል ጋር ፊት ለፊት መፋጠጥ፡፡ አባ ጳውሎስ ሥዕሉን እንዳዩት የመረበሽ ስሜት ይታይባቸውና ሥዕሉ እንዲነሣ አዘው ይሔዳሉ፡፡ አባ ጳውሎስ የአውሬው መንፈስ ያለባቸው የአውሬው አገልጋይ አልነበሩ? ለዛ ነው መረበሻቸውና ሥዕሉን መጥላታቸው፡፡ እናንተ ኢሉሚናቴ የምትሉት ማለቴ ነው፡፡

ff

በማግስቱ ስሔድ ሥዕሉ የለም፡፡ ልጆቹን ስጠይቃቸው ዲ/ን ዳንኤል ነው ያነሣው አሉኝ፡፡ እዛው ነበረና ጠየኩት፡፡ የት ወስዶ ወሽቆታል መሰላቹህ ከተከፋች በሩና ከአዳራሹ ግድግዳ ጣብቂያ እንደ ቆሻሻ ክርታስ ወስዶ ወሽቆታል፡፡ በጣም ደነገጥኩ! “ምነው? ለምንድን ነው የተነሣው እዚህስ የተጣለው?” ስል ጠየኩት፡፡ “አይ አባቶች ይነሣ ስላሉ ነው” አለኝ “ለምንድነው ይነሣ ያሉት?” ስል ጠየኩት “የቤተክርስቲያናችን ሥዕል አይደለም! ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን አልጠበቀም! ብለው ነው” አለኝ በምን ምክንያት ነው የቤተክርስቲያናችን ሥዕል አይደለም፣ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን አልጠበቀም! ያሉት?” ብየ እንደገና ጠየኩት መልሱ አጭር ነበረ “እኔ እንጃ!” አለኝ፡፡

ከዚያ በኋላ ይሄ ሥዕል ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ቤተክርስቲያን ዐውደ ምኅረቱ ላይ ተሰቅሎ አገልግሎት ይሰጥ ነበር፡፡ ታሪኩ ረጅም ነው ላሳጥርላቹህ አባ ጳውሎስ ትዕዛዝ ሰጥተው የወያኔ አገልጋይ እንደሆኑ የሚታወቁ የልደታ ቤተክርስቲያን ካህናት ሥዕሉን ከቦታው አውርደው ነዳጅ አርከፍክፈው አቃጠሉት፡፡ አቤት የአባ ጳውሎስ ድፍረትና ኃጢአት የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል አቃጠሉት፡፡

ይሄንን ሥዕል ብዙዎቻቹህ የምታውቁት ይመስለኛል፡፡ በፖስተር (በተለፋጭ ወረቀት) ወጥቶ ነበር፡፡ ታዋቂው መምህር የናቴ ልጅ ቀሲስ መንግሥቱም “ተዐቀብ ዉሉደ እምየ!” በሚለው ስለ አውሬው 666 ማንነትና የጥፋት ሥራ በተነተኑበት መጽሐፋቸው የውስጠኛው ገጽ ላይ ሥዕሉ አለ፡፡ ስለ ሥዕሉም ግሩም የሆነ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተውበታል፡፡

እናም እባካቹህ ያለው ሁኔታና ውጊያው ከማን ጋር እንደሆነ እባካቹህ ይግባን! ቆራጦች እንሁን! ይሄንን የቤተክርስቲያን ፈተና ቆራጦች ሆነን ቆራጥ እርምጃ በመውሰድ ካልሆነ በስተቀር በማስታመም በመለማመጥ በፍጹም የምንወጣው የምናሸንፈው አይደለም እንንቃ! እንንቃ! እንንቃ! እንቁረጥ! እንቁረጥ! እንቁረጥ!
መድኃኔዓለም ክርስቶስ የቅድርስ ቤተክርስቲያንን ጠላቶች እንደጉም አብንኖ እንደጢስ አትንኖ ያጥፋልን! ጉልበታቸውን ቀጤማ ያድርግልን! ቅድስት ቤተክርስቲያንን ከጥፋት ይታደግልን! ቤተክርስቲያን በሌሎች ሀገራት ጠፍታ በመናፍቃን ተወርሳ “ነበረች” እየተባለ እንደሚወራው ሁሉ በሀገራችንም ጠፍታ በመናፍቃን ተወርሳ “ነበረች” ተብሎ ከመነገር ያውጣልን! እኛም አሁን እያደረግነው እንዳለው ኃላፊነታችንን ከመወጣት ታቅበን ርቀን ተሰብስበን ለቤተክርስቲያን ጥፋት ተጠያቂዎች ከመሆን ሠውሮ ታድጎ እንደ እዱሳን አባት እናቶቻችን ኃይልን፣ ጽናትን፣ እልህን፣ ቅንአትን፣ ፍቅርን፣ ቁርጠኝነትን ሰጥቶን አስታጥቆን ሞልቶን ኃላፊነታችን እንድንወጣ ያድርገን ያስችለን ያብቃን አሜን!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com

ሜ/ጄኔራል አበበ ተ/ሃይማኖት ለኢሕአፓ፣ መኢሶን፣ ኦነግ፣ ሲነግ ክሬዲት ሰጡ –“ተወልደ፣ ፃድቃን፣ ስዬና ተፈራ ዋልዋ ስለአሰብ ጥያቄ ያነሱ ነበር”አሉ

0
0

abebe Tekelehianot

(ዘ-ሐበሻ) በሕወሓት ክፍፍል ወቅት ስልጣናቸውን እንዲያጡ የተደረጉት የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ኃይል አዛዥ ሜጀር ጄኔራል አበበ ተክለ ሃይማኖት ደርግን ለመጣል ለተደረገው ትግል ኢሕአፓ፣ መኢሶን፣ ኦነግ፣ ሲነግና ወዘተ አስተውጽኦ እንደነበራቸው ተናገሩ:: ጄነራሉ ከሪፖርተር ጋዜጣ ጋር ግንቦት 20ን በማስመልከት ባደረጉት ንግግር ስለአሰብ ወደብ ጉዳይም ተናግረዋል::

“ድሮም ቢሆን የኤርትራን ነፃነት ተቀብለው የአሰብ ጉዳይ ላይ ጥያቄ የሚያነሱ ሰዎች ነበሩ። እንደነ አቶ ተወልደ ወልደ ማርያም፣ ሌተና ጄኔራል ፃድቃን ገብረ ትንሳኤ፣ አቶ ስየ አብርሃ፣ አቶ ተፈራ ዋልዋ፣ እኔም ጥያቄዎች የምናነሳበት ሁኔታ ነበር፡፡ በዝርዝር ባንወያይበትም። አሜሪካ ሄጄ ሁለተኛ ዲግሪዬን ስሠራ ግን በዚህ ላይ ጥናት አካሂጄ የባህር በር መብታችንን በሕጋዊ መንገድ ማስመለስ እንደምችል የሚያረጋግጥ ድምዳሜ ላይ ደረስኩ። ባለማወቅና በመታበይ (Ignorance and arrogance) ያጣነው መብት ነው፡፡ አሁንም ግን ሕጋዊ መሠረት አለን፡፡”

ያሉት ጀነራሉ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል::

አሁን እየተነሱ ባሉት የህዝብ እንስቅቃሴዎች ዙሪያ ከሪፖርተር:-

“ሕዝባዊ አመፅ እየታየ ያለው በተካሄደው ምርጫ ገዢው ፓርቲ መቶ በመቶ ማሸነፉን በገለጸበት ማግሥት ነው፡፡ ይህን ያህል የሕዝብ ተቃውሞ መነሳቱ በምርጫ ሒደቱ ላይ ጥያቄ አያስነሳም?” የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው ሜጀር ጀነራል አበበ ” የመንግሥትና የፓርቲ መዋቅሮች መደባለቅ አንዱ ትልቅ ችግር ነው። ኢሕአዴግ የመንግሥት ሚድያ፣ የመንግሥት ቢሮ፣ ገንዘብና አሉ የሚባሉ እርከኖችን ለፓርቲ ሥራ ስለሚያውል የፉክክር ሜዳው ዴሞክራሲን የሚያስችል (democracy enabling) እንዳይሆን አድርጎታል። ቻርለስ ቲሊ የሚባል ታላቅ የፖለቲካ ሳይንቲስት አንድ ፓርቲ ከሰባ አምስት በመቶ በላይ የፓርላማ መቀመጫዎችን ለብቻው ከያዘ ገና ከወዲሁ ዴሞክራሲያዊና ፍትሓዊ ያልሆነ፣ በሕዝብ ተቀባይነት የሌለው ምርጫ ነው ማለት ይቻላል ይላል። ምክንያቱም አንድ ሕዝብ ከፋብሪካ እንደሚወጣ ወጥ ምርት አይደለም። የተለያየ ፍላጎት፣ ምርጫና ዝንባሌ ስለሚኖረው። አሥር በመቶ እንኳ ተቃዋሚዎች ቢያሸንፉ መሬት ላይ ያለውን ሀቅ አያንፀባርቅም። የፌዴራሊዝም ባለሙያዎችና አገራዊ የውክልና ተቋማት ሕዝቡ ውስጥ ያሉ ልዩነቶችን ማንፀባረቅ አለባቸው ይላሉ። ስለዚህ ኢሕአዴግ አሽነፍኩ ያለበት ሒደትም የታወጀው ውጤትም አስቂኝ ብቻ ሳይሆን አደገኛም ጭምር ነው። ውጤቱ ሲነገር ስቀን ነበር፡፡ አሁን ደግሞ አደጋው ፈጦ እያየነው ነው። ኢሕአዴግ ማሸነፍ አይችልም ነበር እያልኩ አይደለም፡፡”

ብለዋል::

ቃለምልልሱን እንደወረደ ለግንዛቤ እንዲረዳዎ እንደሚከተለው አቅርበነዋል:-

 

ሪፖርተር፡- መድበለ ፓርቲ ሥርዓትና ተቋማዊ አሠራር ከመገንባት አንፃር አሁን መሬት ላይ ያለው አሠራር ከሕገ መንግሥቱ ጋር ሲታይ ምን ይመስላል?

ጄኔራል አበበ፡- በጣም ዘመናዊ ሕገ መንግሥት አለን። ሕገ መንግሥቱ ግሎባላይዜሽን፣ የሌሎች አገሮች ተሞክሮና የራሳችን ሁኔታ ታሳቢ አድርጎ የወጣ ነው። ነገር ግን ፍፁም ነው ማለት አይደለም። በመሠረቱ ሲታይ ግን ሕገ መንግሥቱ የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ፍላጎትን ያሟላ ነው። መስተካከል ያለበት ነገርም ሊኖር ይችላል። አሁን ትልቁ ችግር ያለው በተግባር ማዋል ላይ ነው። የሕገ መንግሥት ተቋማት ነፃነት የተጠበቀ አይደለም። በእኔ ግምገማ ሁሉንም ሥልጣን የያዘው አስፈጻሚው አካል ነው። የተወካዮች ምክር ቤት ከሚጠበቀው አንፃር ሲታይ ብዙ መሠረታዊ ችግሮች አሉበት። በሕገ መንግሥቱ የበላይ አካል ተቆጣጣሪ ሆኖ እያለ በተግባር ግን ሥራ አስፈጻሚ የሚያዘውን የሚፈጽም ነው፡፡ በተመሳሳይ ፍርድ ቤትም እንደዚያው ነው። በተለይ መንግሥትና ፓርቲ አንድ የሆኑበት አሠራር ነው ያለው። መለያየት አለበት። ይህ በጠቅላላ ሕገ መንግሥቱን የሚንድ አሠራር ነው። ለመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ህልውናም ትልቅ አደጋ ነው። ኢሕአዴግ መንግሥት በመያዙ ለአደጋው ዋና ድርሻ ቢኖረውም በአጠቃላይ ሲታይ ግን አብዛኛዎቹ ተቃዋሚዎችም ተመሳሳይ አመለካከት ያላቸው ናቸው። ሕገ መንግሥትን መሠረት አድርገው፣ በሕገ መንግሥቱ ያሉት ተቋማትን ተግባራዊ ከማድረግ አኳያ ትልቅ ክፍተት ይታያል። አሁን ያለው መንግሥት ‹‹ከእኔ በላይ ማን አለ?›› የሚል እብሪትም ያለበት መንግሥት ነው። የዴሞክራሲ ምኅዳር እያጠበበ እያጠበበ ሄዷል። ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት እየተገደበ ነው ያለው። አሁን ያሉትን ተቃዋሚ ፓርቲዎች እንደ ፀጋ አያይም፡፡ ኢሕአዴግ የተደራጀ የሕዝብ እንቅስቃሴ ሥጋት ይሆንበታል። ስለዚህ ፓርቲዎችን የማዳከም ሥራ ነው የሚሠራው። ይህም ለመድበለ ፓርቲ ሥርዓት አደጋ ነው።

ከተቋማት አኳያ ሲታይም በተለይ ፖለቲካዊ ተቋማት እንደ ፓርላማ፣ ፀረ ሙስና ኮሚሽን ጠንካራ ናቸው ለማለት የሚከብድ ነው። ተቋማቱ ያረጁ ናቸው። ይኼ ለሕገ መንግሥታዊ ሥርዓትና ለዴሞክራሲ አደገኛ ነው። ስለዚህ ገዢው ፓርቲ ተቃዋሚዎችን እንደ ፀጋ ዓይቶ አብሮ የሚሠራበትንና ተቃዋሚዎች የሚጠናከሩበትን ሁኔታ መፍጠር አለበት። የፕሬስ መብትን ማረጋገጥም አለበት፡፡ በተለይ የተደራጀ ሕዝብ ተቃውሞ በሚያሰማበት ጊዜ ይህን እንደ ትልቅ ሀብት ዓይቶ መደገፍና ሕዝቡን ሰምቶ የሕዝቡን ፍላጎት በተሻለ ለሟሟላት መንቀሳቀስ አለበት። አሁን የስኳር ኮርፖሬሽንን ስናየው 77 ቢሊዮን ብር ያህል የሚያንቀሳቅስና በቀጥታ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራ ድርጅት ነው፡፡ እንዴት ነው አንድ ትልቅ በጠቅላይ ሚኒስትር የሚመራን ድርጅት ማን ነው የሚያስፈራራው? እነዚህ ሰዎችስ ማን ናቸው? በስኳር ያለው ችግርም በሌሎች ትልልቅ ፕሮጀክቶች ላይ እንዳለ ባለሙያዎች መረጃ አላቸው። ለምሳሌ ግልገል ጊቤ ሦስት እስከ አሁን ለምን ተጓተተ? የሥራው ጥራትስ ምን ያህል ነው? አሁን የምንፈልገውን ኃይልስ አግኝተናል ወይ? በህዳሴ ግድብ ላይም ቢሆን ብዙ ባለሙያዎች ጥያቄዎችና ሥጋቶች ያነሳሉ።

ሪፖርተር፡- የትጥቅ ትግል ከማካሄድና ሲቪል መንግሥት ሆኖ ዴሞክራሲያዊርዓትመገንባት የቱ ይከብዳል ይላሉ?

abebe

ጄኔራል አበበ፡- የትጥቅ ትግል የፀረ ዴሞክራሲ ዘበኛን ለማስወገድ የሚካሄድ ትግል ነው፡፡ ስለዚህ የትጥቅ ትግል በኃይል የሚደረግ በመሆኑ በባህሪው ከዴሞክራሲ ጋር ግጭት ሊኖረው ይችላል። ምክንያቱም ማስገደድ ይኖረዋል።  ይህ የፀረ ዴሞክራሲ ዘበኛ በሕዝባችን ትግል ከተወገደ በኋላ በሽግግር መንግሥት ቻርተርና ቀጥሎ በመጣው ሕገ መንግሥት በኩል ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መንደርደርያ የሚሆን ሥራ ተሠርቷል። በዚህም የሕዝቦች መሠረታዊ ጥያቄ ለመፍታት ትልቅ ሥራ የተሠራ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ብዙ ያልተሻገርናቸው ፈተናዎች አሉ። በመጀመርያ ኢሕአዴግ ራሱን መቀየር ነበረበት። የትጥቅ ትግል አስተሳሰብና የአገር ግንባታ አስተሳሰቦች መሠረታዊ ልዩነት አላቸው። ኢሕአዴግ ራሱን ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ግብዓት ከሆኑ እሳቤዎች ጋር አጣጥሞ የሄደ አይመስለኝም። ኢሕአዴግ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የእኛ ትውልድ የአማፂ ትውልድ ነው። የአማፂ ትውልድ የዴሞክራሲ ትውልድ መሆን አይችልም። ስለዚህም ሌሎች ፓርቲዎችም ራሳቸውን በሕገ መንግሥቱና በዓለም ላይ ካሉ ዘመናዊ እሳቤዎች ጋር ማጣጣም ይኖርባቸዋል። የእኛ ትውልድ ከራሱ እሳቤና ተግባር ውጪ ያለን አካል መብት የማያከብር ‹‹እኔ ብቻ ነኝ ልክ›› የሚል አክራሪነት የሚታይበት ትውልድ ነው። ተማሪ ሆነን ሰላማዊ ሠልፍ እንውጣ በምንልበት ጊዜ እምቢ የሚል ተማሪ ካለ ይመታል፡፡ ይህ በመሠረቱ ኢዴሞክራሲያዊ አካሄድ ነው። እንጭጭነትም ነው። ስለዚህ የኛ ትውልድ የዴሞክራሲ ትውልድ አይደለም፡፡ የአመፅ ትውልድ ነው፡፡ የፀረ ዴሞክራሲ ዘበኛ የነበረን ሥርዓት ግን በማስወገዱ እኮራበታለሁ።  ከዚያ በኋላ  አዲሱ ትውልድ ተረክቦ መሄድ ነበረበት፡፡ ሆኖም የእኛ ትውልድ አሁንም ሥልጣንን የሙጥኝ ብሎ አልለቅም በማለቱ አሁን ለሚታየው ቀውስ ምክንያት ሆኗል።

ሪፖርተር፡- ምን ማለት ነው ‹‹የሙጥኝ ብሏል›› ሲሉ? ለምሳሌ ኢሕአዴግ ውስጥ መተካካት እየተደረገ እንደሆነ ይሰማል፡፡ የመተካካቱን ሒደት አላመኑበትም?

ጄኔራል አበበ፡- መተካካት ሲባል የትውልድ መሆን አለበት፣ የግለሰቦች አይደለም። የአሁኑ ትውልድ ብቃት ያለው ትውልድ ነው። ገና ሲወለድ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የሚያውቅ፣ ከመንግሥት የተለዩ ጋዜጦችንና መጽሔቶችን የሚያነብ፣ የተለያዩ ሐሳቦችን የሚያውቅ፣ ዓለም አቀፍ ትስስር ያለው፣ በምርምር ብዙ ነገር ማድረግ የሚችል ትውልድ ነው። ስለዚህ መተካካት ሲባል የትውልድ መጎራረስ ነው። ካለፈው ትውልድ በጎ በጎውን ተምሮ የራሱን ጥበብ ጨምሮበት እንደ ትውልድ አገሩን ሲረከብ ነው መተካካት የሚባለው።

ሪፖርተር፡- ‹‹የዴሞክራሲ ምኅዳሩ እየጠበበ ነው›› ብለዋል፡፡ ‹‹ኢሕአዴግን ባልመጣበት የሰላማዊ ትግል መድረክ ማሸነፍ ስለማይቻል አዋጪው የትጥቅ ትግል ነው››የሚሉ ተቃዋሚዎች አሉ። የእርስዎ ግምገማ ምን ይመስላል?

ጄኔራል አበበ፡- ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ለውጥ እየተመዘገበ ነው። ይህ ለዴሞክራሲው ምን ማለት ነው የሚለው በደንብ መታየት አለበት። መንገድ ተሠራ ሲባል ሕዝቦች የሚገናኙበት፣ አንዱ የአንዱን ባህል የሚማርበት ዕድል ሰፋ ወይም ተፈጠረ ማለት ነው። ስለዚህ የትብብርና የአስተሳሰብ አድማሱ የሚሰፋበት ዕድል አለ ማለት ነው። የውኃ አገልግሎት ተሠራ ማለት ያቺ ሚስኪን ሴት አራት አምስት ሰዓታት ለውኃ የምታጠፋውን ጊዜ ትቆጥባለች ማለት ነው። ጤና ኬላ ተሠራ ማለት ጤንነቱ የተጠበቀ ልጅ መማር ይችላል ማለት ነው። የአንደኛ ትምህርት መስፋፋት ማለት እኮ ለዴሞክራታይዜሽን ሰፊ ምንጣፍ እየተነጠፈ ነው ማለት ነው። አባትም፣ እናትም ልጅም ለፖለቲካዊ ተሳትፎ የሚሆን ጊዜ አገኙ ማለት ነው። በአጠቃላይ ማኅበረ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታው እየተቀየረ ነው፡፡ ፖለቲካዊ ፍላጎቱ የሚጨምር ትውልድም እየተፈጠረ ነው። እዚህ ላይ ቅራኔ አለ፤ ሆኖም ይህንን ቅራኔ መፍታት የሚችል ትውልድ እየመጣ ነው፡፡ ይህ ትውልድ ያጣው ቦታ ብቻ ነው። በትጥቅ ትግል ዴሞክራሲን ማስፈን የሚለው ነገር አስቂኝ ነው። ትጥቅ ትግል ለዚህች አገር አይረባም፣ በጣም አደገኛ ነገር ነው። የዴሞክራሲ ምኅዳሩ እየጠበበ መሄዱ ወደ ትጥቅ ትግል እንድትገባ ምክንያት ሊሆን አይችልም። በዚህ ጠባብ ሁኔታም ጭምር ጠንካራና እውነተኛ ፖለቲካዊ አመራር መስጠት የሚችል ካለ መታገል ይቻላል፡፡ ስለዚህም ነው በርካታ ዜጎች አገር ውስጥ እየታገሉ ያሉት። ምክንያቱም ሕዝቡ በቦታው ነው።

የኢትዮጵያ ዴሞክራታይዜሽን በኢሕአዴግ ፈቃድ ላይ የሚመሠረት ነገር አይደለም። በተወሰነ ሁኔታ ኢሕአዴግ ጥሩ በሚሆንበት ጊዜ ሒደቱን ሊያፋጥነው ይችላል ወይም በተቃራኒው ሊሆን ይችላል። የኢትዮጵያ ሕዝብ የኢሕአዴግን ፈቃድ መጠየቅ የለበትም። ሕዝቡ ይህንን ሥርዓት ያመጣው በራሱ ትግል ነው፡፡ የሚያስቀጥለውም ሕዝቡ ራሱ ነው። የ1997 ዓ.ም. ክስተት ሕዝብ ካመፀ ምን ማድረግ እንደሚችል ደንበኛ ማሳያ ነው። አሁን በኦሮማያና በትግራይ እምባሰነይቲ አካባቢ እየታየ ያለው የተደራጀ ሕዝባዊ የመብት ጥያቄ አለ። በሁሉም የሚታይ ባይሆንም አሁንም ኢሕአዴግ ውስጥ ሁሉንም ነገር በኃይል ለመፍታት የመፈለግና የመሞከር አዝማሚያ ይታያል። ይህንን የትጥቅ ትግል አስተሳሰብ አሽቀንጥረው መጣል አለባቸው። ምኅዳሩም ፍፁም ዝግ አይደለም፡፡ ጠባብ በመሆኑ ግን ብዙ መስዋዕትነትና ዋጋ ይጠይቃል።

ሪፖርተር፡- ሕዝባዊ አመፅ እየታየ ያለው በተካሄደው ምርጫ ገዢው ፓርቲ መቶ በመቶ ማሸነፉን በገለጸበት ማግሥት ነው፡፡ ይህን ያህል የሕዝብ ተቃውሞ መነሳቱ በምርጫ ሒደቱ ላይ ጥያቄ አያስነሳም?

ጄኔራል አበበ፡- የመንግሥትና የፓርቲ መዋቅሮች መደባለቅ አንዱ ትልቅ ችግር ነው። ኢሕአዴግ የመንግሥት ሚድያ፣ የመንግሥት ቢሮ፣ ገንዘብና አሉ የሚባሉ እርከኖችን ለፓርቲ ሥራ ስለሚያውል የፉክክር ሜዳው ዴሞክራሲን የሚያስችል (democracy enabling) እንዳይሆን አድርጎታል። ቻርለስ ቲሊ የሚባል ታላቅ የፖለቲካ ሳይንቲስት አንድ ፓርቲ ከሰባ አምስት በመቶ በላይ የፓርላማ መቀመጫዎችን ለብቻው ከያዘ ገና ከወዲሁ ዴሞክራሲያዊና ፍትሓዊ ያልሆነ፣ በሕዝብ ተቀባይነት የሌለው ምርጫ ነው ማለት ይቻላል ይላል። ምክንያቱም አንድ ሕዝብ ከፋብሪካ እንደሚወጣ ወጥ ምርት አይደለም። የተለያየ ፍላጎት፣ ምርጫና ዝንባሌ ስለሚኖረው። አሥር በመቶ እንኳ ተቃዋሚዎች ቢያሸንፉ መሬት ላይ ያለውን ሀቅ አያንፀባርቅም። የፌዴራሊዝም ባለሙያዎችና አገራዊ የውክልና ተቋማት ሕዝቡ ውስጥ ያሉ ልዩነቶችን ማንፀባረቅ አለባቸው ይላሉ። ስለዚህ ኢሕአዴግ አሽነፍኩ ያለበት ሒደትም የታወጀው ውጤትም አስቂኝ ብቻ ሳይሆን አደገኛም ጭምር ነው። ውጤቱ ሲነገር ስቀን ነበር፡፡ አሁን ደግሞ አደጋው ፈጦ እያየነው ነው። ኢሕአዴግ ማሸነፍ አይችልም ነበር እያልኩ አይደለም፡፡

ሪፖርተር፡- እየታየ ያለው የአስተዳደር ቀውስ የሥርዓት ችግር (Systemic Problem) ነው ብለው በቅርቡ በጻፉት ጽሑ ላይ ተከራክረው ነበር። በመፍትላይም የሰጡት አስተያየት ነበር። ሥርዓታዊ ችግር ሲሉ ምን ማለትዎ ነው?

ጄኔራል አበበ፡- መንግሥት ችግራችን የመልካም አስተዳደር ነው ብሎ ትልቁን ምሥል ወደ ጎን ትቶ ነገሩን ወደ ቴክኒካዊ ደረጃ አውርዶ ነው እያየ ያለው። እየተወሰደ ያለው ዕርምጃም ሥርዓቱን እንደ ሥርዓት የሚገመግምና የሚያስተካክል ሳይሆን፣ ታችኛው አመራርና ሲቪል ሰርቫንቱን ማዕከል ያደረገ ቁንፅል ነገር ነው። እኔ ደግሞ የምለው ‹‹ችግሩ ተራ የአስተዳደር ችግር ሳይሆን አጠቃላይ የዴሞክራሲ እጥረት የሚባል ነገር ነው፣ በአጭሩ ጉዳዩ የዴሞክራታይዜሽን ችግር ነው፤›› ነው። ጉዳዩ ሕገ መንግሥታዊ ተቋማትና አሠራሮች ከመሥራት ወይም ካለመሥራታቸው የተያያዘ ነው። ቀላል ነገር አይደለም። መዋቅራዊ ችግርን አድበስብሶ ማለፍ ውጤቱ እስከ አገር ማፍረስ ሊዘልቅ ይችላል፡፡ ነገርየውን መመርመርና መፈተሽ ያለብንም ከዚህ አቅጣጫ ነው። ከሁሉም በላይ ግን የሕዝቡን የተደራጀና የተናጠል ትግል ለማፈን የሚደረጉ ነገሮች ስለችግራችን ስፋትና ዓይነት ብዙ ነገር ይነግሩናል።

ሲቪል ማኅበረሰቡም ቢሆኑ የፓርቲ ተቀጥያ እንዲሆኑ እየተደረገ ነው ያለው፡፡ ሥራ ለማግኘት አባልነትና ድጋፍ መለኪያ ሲሆን ጉዳዩ የሕገ መንግሥት ጥሰት መሆኑን መገንዘብ አለብን። ለምሳሌ ኦሮሚያ ውስጥ የተነሳውን ሕዝባዊ አመፅ ብንመለከት ለዴሞክራሲ ትልቅ ግብዓት ይሆን ነበር፡፡ መንግሥት ብስለቱና ብልኃቱ ስለሌለው በተወሰነ መልኩም ቢሆን ፅንፈኞችና አክራሪዎች ሕዝቡ በማይፈልገው መንገድ ለመጠቀም ችለዋል፡፡

እነዚህ ኋላቀር ፅንፈኞች ደግሞ ይህንን ተገቢ ትግል በሕዝቦች መካከል ጥርጣሬ እንዲሰፍንና ግጭት እንዲቀሰቅሱበት ለመጠቀም ሞከሩ፡፡ በተወሰነ ደረጃም ተሳካላቸው። ጥያቄው ሕዝቡ ወዳልፈለገው አቅጣጫ ለመውሰድ የሞከሩ ፅንፈኞች የአቅማቸውን ያህል ቢጥሩም የሕዝቡ ጨዋነት ግን የሚገርም ነበር፡፡ ይህ ጨዋ ሕዝብ ላይ የደረሰው ሞት፣ የአካል ጉዳትና ውድመት በጣም አሳዛኝ ነው። ከዚህ ሒደት የምንማረው በገዢው ፓርቲና በሕዝቦች መካከል ትልቅ ክፍተት እንዳለ ነው። ሕዝቦች በገዢው ፓርቲ መሪነት አንድ ትልቅ ደረጃ ላይ ደርሰዋል፡፡ ኢሕአዴግ ግን  ቆሟል ወይም ወደኋላ እየነጎደ ነው። ከሕዝቦች ፍላጎትና ዕድገት ጋር አብሮ መሄድ አልቻለም።

ሪፖርተር፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ‹‹ሕዝቡን አስለቅሰነዋል፣ በድለነዋል›› ብለዋል። ይቅርታምጠይቀዋል።

ጄኔራል አበበ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ እንደዚያ ማለታቻው የሚመሠገን ተግባር ነው፡፡ አንድ ዕርምጃ ወደፊት መሄድ ነው። በኮሙዩኒኬሽን ሚኒስትሩ በኩል የሚገለጸው ነገርም አንዳንዴ ተስፋ የሚሰጥ ነው። ይቅርታ ማለት ሕዝብን ማክበር ነው፣ ትልቅነት ነው። ይቅርታ ማለት መጀመሩ በራሱ እንደ ትልቅ ነገር አድርጌ ነው የምቆጥረው። ለዚህም ማመስገን እፈልጋለሁ። ይቅርታ ብቻውን ግን በቂ አይደለም፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት ችግሩ መላውን ኢትዮጵያ የሚያስለቅስ ከሆነ ነገሩ ሥርዓታዊ ነው ማለት ነው። ዋናው ጥያቄ መሆን ያለበትም ይህ ችግር ከየት ይመነጫል የሚለው ነው። የፍትሕ መጓደል፣ ሙስና፣ አስተዳደራዊ በደል በተለያየ መጠን ይኖራሉ፡፡ ሆኖም የዴሞክራሲ ምኅዳሩ ሲጠብ ችግሮቹ ይጎለብታሉ፡፡ በተቃራኒው የዴሞክራሲ ምኅዳሩ ሲሰፋ ችግሮቹ ይቀጭጫሉ፡፡ ምክንያቱም ሕዝቡ ይሳተፋል፡፡ በሰላማዊ ሠልፍ፣ ሐሳቡን በነፃነት በመግለፅ፣ በነፃ በመደራጀትና በመሳሰሉት ይሳተፋል። ኢዴሞክራሲያዊ ኃይሎችና ክራይ ሰብሳቢዎችን ይታገላቸዋል ማለት ነው፡፡ ለግላዊና ለቡድናዊ መብቱ ዘብ ይሆናል ማለት ነው። ስለዚህ ችግሩን ሲገመግሙ ከላይ ከቁንጮው ነበር መገምገም የነበረባቸው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት የቀረበው ጥናት ጥሩ ነበር፡፡ ቀጣይ ዕርምጃዎቹ ግን መሠረታዊ ስህተት ነበረባቸው፡፡ ከላይ መጀመር ሲገባው የሆነው በተገላቢጦሽ ነበር።

ሪፖርተር፡- ‹‹በተገላቢጦሽ›› ሲሉ ምን ለማለት ነው?

ጄኔራል አበበ፡- ጥናቱ መገምገም የነበረበት መዋቅራዊ ጉዳዮችን በማንሳት ነበር። በፓርቲና በመንግሥት መካከል ያለው ግንኙነት፣ የዳኞች አሿሿም፣ የከፍተኛ ባለሥልጣናት የምልመላና የግምገማ ሥርዓት፣ በፓርላማውና በሥራ አስፈጻሚው መካከል ስላለው ግንኙነት፣ የሚዲያው ሁኔታ፣ የፍርድ ቤቶች ነፃነት ነበር መገምገም የነበረበት፡፡ በፓርቲውና በሕገ መንግሥቱ መካከል የሐሳብ ቅርበት ወይም ልዩነት አለ ወይ ብሎ መገምገም ነበረበት። ነፃ የሆኑ የሕዝብ አደረጃጀት አለ ወይ? የግል ፕሬሱና ሲቪል ማኅበረሰቡ በነፃ ይንቀሳቀሳሉ ወይ? ፓርቲዎቹስ መተንፈሻ አግኝተዋል ወይ ብሎ መታየት አለበት። ሲጠቃለል ሕዝቡ ትርጉም ያለውና በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ተሳትፎ እንዲያደርግ የሚያስችል ሁኔታ አለ ወይ ብሎ ነው መገምገም ያለበት። በአስገዳጅ ስብሰባዎች እጅ እንዲያወጣ ማድረግ አይደለም ተሳትፎ ማለት። አንዳንድ በጎበኘሁዋቸው አካባቢዎች ‘አንድ ለአምስት’ የሚባል አደረጃጀት አደገኛ የስለላ መዋቅር እየሆነ ነው። ማኅበራዊ እሴቶቻችንን የሚበጣጥስና ማኅበራዊ ኑሮን ሊያናጋ በሚችል መንገድ ሥራ ላይ እየዋለ ሳይ በጣም ደንግጬያለሁ። ባልና ሚስት፣ ልጆችና ወላጆች በአጠቃላይ ቤተሰብ ቤተሰቡን የሚሰልልበትና የሚያስፈራራበት አሠራር እየሆነ ያለበት አጋጣሚ ስላለ ቆም ብሎ ማሰብ ይጠይቃል። ቤተሰብን ይበትናል። አደረጃጀቱም በኃይል ስለሆነ ግለሰባዊ ቅንነትንም ይገድላል። ስለዚህ ኢዴሞክራሲያዊ እየሆነ የመከባበር፣ የመተማመንና የአብሮነት እሴቶችን ይገድላል። በዘመናት የተገነባ እሴት በዓመታት ዋጋ ቢስ ሆኖ ብዙ ዋጋ እንዳያስከፍለን እሠጋለሁ።

ሪፖርተር፡- በቅርቡ በትግራይ ክልል የእምባሰነይቲ ሕዝብ ‹‹ወረዳችን ይመለስልን›› የሚል ጥያቄ አንስቷል። ይህ ሕዝብ የሕወሓት ኮር ቤዝ የሚባል ነበር። በድርጅቱየተሰጠው መልስና ጥያቄው እንዴት ያዩታል?

ጄኔራል አበበ፡- በመጀመርያ የእምባሰነይቲ ሕዝብ እንደዛ ጨዋነት በተሞላው፣ የሞራል ልዕልናውን ባረጋገጠ መንገድ ጥያቄውን በተደራጀ መንገድ ማቅረቡ ሊያስመሰግነው ይገባል፡፡ እኔም በግሌ ያለኝን ልባዊ አክብሮት መግለጽ እወዳለሁ። በዚህ ሒደት ሁለት ነገሮች አሉ። የሕዝቡ ተገቢ ጥያቄ እንዳለ ሆኖ መንግሥትም ያገባኛል ማለቱ የግድ ነው፡፡ የበጀትና ተያያዥ ነገሮች ስላሉ። መንግሥት ግን ሲያገባው እንዴት ነው መልስ የሚሰጠው የሚለው መታየት አለበት። መጀመሪያ ጥያቄ ለምንድነው ወረዳ የሚፈልገው የሚለው ከሕዝቡ ፍላጎት ጋር አስተሳስሮ መመለስ ነበረበት፡፡ ይህ ለሃያ ዓመታት የቆየች ችግር በጥናት በተረጋገጠ መንገድ አልተመለሰም። የሕዝቡን ጥያቄ አክብሮ ከማዳመጥ ይልቅ የት ትደርሳላችሁ የሚል የትዕቢት መልስ መንግሥት መስጠቱን ሕዝቡ በሰላማዊ ሠልፉ ላይ ገልጿል፡፡ ይህ አሳፋሪና አሽማቃቂ መልስ ነው። ይህ ሕዝብን መናቅ ነው፡፡ ሕዝብን ማዳመጥ እየጠፋ ነው ማለት ነው፡፡ ከሕዝብ ጋር ሆነህ መፍትሔ መሻት የሚባል ነገር የለም ማለት ነው። ሰማንያ አንድ ወረዳ ቢፈጠር ለልማት እንቅፋት ይሆናል የሚል ሥጋት እንኳን ቢኖራቸው፣ ሥጋታቸውን ከሕዝቡ ጋር ሆነው ተመካክረው ወረዳ መሆን የሚሰጠውን ጥቅም በሆነ አሠራር ሕዝቡ እንዲያገኝ ለማድረግ ፍላጎት አለማሳየታቸው ያሳዝናል። ነገሩን ከባድ የሚያደርገው ደግሞ ጥያቄው የእምባሰነይቲ ብቻ አለመሆኑን እያወቁ ማስፈራራትን እንደ መፍትሔ መውሰዳቸው ነው።

ችግሩ የኪራይ ሰብሳቢ፣ የጥገኛ አመራር፣ የተቃዋሚ ፓርቲ ሴራ አድርገው ማየታቸው ምን ማለት እንደሆነ የገባቸው አይመስለኝም፡፡ ሕዝቡን ሞኝ ነህ፣ ተታለህ ነው፣ ስለራስህ ምንም አታውቅም እያሉት ነው። ይህ ደግሞ ከማሳዘን አልፎ ከባድ አላዋቂነት ጭምር መሆኑን ነው የሚያሳየው። በኦሮሚያም የተባለው ተመሳሳይ ነው፡፡ በሁሉም ክስተቶች የእገሌ የእገሌ እየተባለ ሕዝብን ማሸማቀቅ ፀረ ዴሞክራሲያዊነት መሆኑ መታወቅ አለበት። ሲጀመር መንግሥት የት ነበርና ነው?

ሪፖርተር፡- ከኦሮሚያ ቀጥሎ በቅርቡ የታጠቀ ኃይል በሕገ መንግሥታዊ ተቋማት ላይ የበላይነት ከያዘ፣ የፖለቲካ ፍላጎት ሊያሳድር ይችላል የሚል አስተያየትም ሰጥተው ነበር፡፡ ዕውን በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲህ ዓይነት ሥጋት ይኖራል?

ጄኔራል አበበ፡- የደኅንነትና የዴሞክራሲ እጥረት ዋናው የድህንነታችን ጥያቄ ነው። በአፍሪካ እንደምናየው የታጠቀው ኃይል ከትጥቅ በላይ ከፍተኛ የፖለቲካ ተፅዕኖ አለው። በሲቪል ቁጥጥር ሥር ካልዋለ ራሱን ንጉሥ ወይም አንጋሽ የመሆን ፍላጎት ሊያዳብር ይችላል። ሕገ መንግሥታዊ ተቋማት ሕጉ በሚያስቀምጠው መንገድ መሥራት ካልቻሉ አጠቃላይ መዛባት ይፈጠራል። ሕገ መንግሥቱ በተለያዩ ተቋማት መካከል ሊኖር ስለሚገባው ግንኙነት በሥርዓቱ ደንግጓል፡፡ ሕጉ በተገቢ መንገድ በማይተገበርበት ጊዜ ግን መዛባት ይፈጠርና ጉልበት የበላይነት ያገኛል። ሥልጣን አስፈጻሚው ዘንድ ሲጠቃለል የመጀመሪያው የአደጋ ምልክት ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። ከአስፈጻሚው ጋር ደግሞ ሲቪልና የደኅንነት አካላት አሉ። እዚህ ጋ መዛባት ሲፈጠር ጠቅላላ ኃይሉ ወደ ታጠቀው ይጠቃለላል። ካልተዛባ ቦታውን ይይዛል፣ አገሩንም ይጠብቃል፣ የውጭ ጠላትን ይመክታል ይከላከላል። ካልሆነ ግን ፖለቲካዊ ፍላጎት አዳብሮ ተፅዕኖ ማሳደር ይችላል። ሕገ መንግሥቱ መሠረት ተደርጎ ካልተኬደ ሲቪሉ በታጠቀው ኃይል ሥር ይወድቃል። አሁን አንዳንድ ምልክቶች እየታዩ ነው። ከስኳር ኮርፖሬሽን ጋር ተያይዞ የተሰማው ነገር የዚህ ምልክት ነው እንዴ? እንድትል ያደርጋል።

ሪፖርተር፡- ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በየመን የሳዑዲ ዓረቢ እንቅስቃሴ አለ፡፡ ከደቡብ ሱዳን የመጡ ታጣቂ ቡድኖች በጋምቤላ ክልል ነዋሪዎች ላይ ብዙ ጉዳት አድርሰዋል፡፡ቀጣይነት ያለው ከኤርትራ የሚመጣ አደጋ አለ። እርስዎ እንደ የሰላምናደኅንነት ባለሙያና የቀድሞ ጄኔራል እንደመሆንዎ መጠን በዚህ የደኅንነት ጉዳይ ላይ ምን ይላሉ?

ጄኔራል አበበ፡- ባለሙያ ለመባል እንኳን ያስቸግረኛል። ጋምቤላ ላይ የተፈጠረው ትልቅ ጉዳይ ነው። ብዙ ሰው ነው የሞተውና የተጎዳው። ለቤተሰቦቻቸውና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ፅናቱን እንዲሰጣቸው እመኛለሁ። ለብቻው ስታየው የሚያጋጥም ነገር ነው ለማለት የሚቻል ይሆናል። ነገር ግን ብዙ ጥያቄዎች ያሉበት ነው። ሙርሌዎች እንዴት ብለው ነው ልባቸው ሞልቶ ለቀናት ተዘጋጅተውና ሠልጥነው ያጠቁት? እንዴት ብለው ነው የደፈሩት? እዚያ አካባቢ ያለው የደኅንነትና የመከላከያ ኃይሎች ምን ይሠሩ ነበር? በአካባቢው ሠራዊት ነበር? አልነበረም? ለምንድነው በአጭር ጊዜ ምላሽ ያልተሰጠው? ሕፃናቱን ማስመለስ ለምንድነው የዘገየው? ሲደጋገምና ተመሳሳይ ክስተቶች በርከት ብለው ሲታዩ ጥያቄ መነሳቱ የግድ ነው። ይኼ ነገር የሥርዓቱ ችግር ሊሆን ይችላል ተብሎ ከብሔራዊ የደኅንነትና የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ፣ ከፖሊሲው ማኔጅመንት፣ ከሥራ አስፈጻሚውና ከተወካዮች ምክር ቤት ሚና ጋር አያይዞ ማየት ያስፈልጋል። የሥርዓቱ በሽታ ማሳያ ሊሆን ይችላል። ፓርላማው ሐዘን ከማወጅ የዘለለ ለምን ተከሰተ ብሎ አስፈጻሚውን መጠየቅና ማጣራት አለበት፡፡ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥንም ቢሆን ይህ ነገር ለምን ተከሰተ ተብሎ ሊጠየቅና ማብራርያ ሊሰጥ ይገባዋል። መከላከያ ሚኒስትሩም እንዲሁ። ይህ ክስተት ሥርዓቱን እያስተካከልን እንሄዳለን የሚል በጎ አስተሳሰብ ካለ አጠቃላይ ሥርዓቱን ለመፈተሽ ይጠቅመናል፡፡ ክስተቱ የውድ ዜጎችን ሕይወት የቀጠፈ አሳዛኝ ድርጊት መሆኑ ሳይረሳ።

ሳዑዲዎች የኤርትራ ባህር ዳርቻዎች ላይ የጦር መርከቦቻቸው ሲያሰፍሩ ኢትዮጵያን አንነካም፣ ዓላማችን የመን ላይ ነው እያሉ ይምላሉ ይገዘታሉ፡፡ እኛ እንደ ሞኞች ብለውናል ብለን ነው መሄድ ያለብን? የፈለጉትን ነገር ለማድረግ ተፅዕኖ እየፈጠሩ ነው? ሳዑዲ ዓረቢያ አሥራ አምስት ቢሊዮን ዶላር አካባቢ በሱዳን ኢንቨስት እያደረገች ነው፡፡ ለሱዳን ወታደራዊ ድጋፍ እየሰጠች ነው፡፡ ሱዳን ሠራዊትዋን ወደ የመን ልካለች፡፡ በሳዑዲና በኢራን መካከል ከነበረው ፍጥጫ ተነስተው ሱዳንና ሶማሊያ ከኢራን ጋር የነበራቸውን ግንኙነት አቋርጠዋል። ይኼ የሱዳንና የኢራን እንጂ እኛ ጋ ሊከሰት አይችልም የሚባል ነገር ልክ አይደለም። አጠቃላይ ሁኔታው ምን ይመስላል የሚለው ነገር መጤን አለበት። የኤርትራም ጉዳይ ከዚህ ጋር ተያይዞ ነው መታየት ያለበት።

ሪፖርተር፡- በቀጣናው እየታየ ያለውን የደኅንነት ሥጋት ለመቆጣጠር ከውስጥ ምን መደረግ አለበት ይላሉ?

ጄኔራል አበበ፡- በዚህ ጊዜ ደግሞ ለዘመናት የኢሕአዴግ ባህል የነበረው የጋራ አመራር እየጠፋ ነው፡፡ ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት ባልተቋመበት፣ ሁሉን አቀፍ የሆነ ጽሕፈት ቤት ባልነበረት ሁኔታ አደጋ ተከስቷል። በዚህ ላይ አንድ የጻፍኩት ጽሑፍ አለ። በጥናቴ ያገኘሁት ነገር ቢኖር ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት በአዋጅ ቢቋቋምም፣ ሴክሬታሪያት የሌለውና አልፎ አልፎ እንደሚሰበሰብና የተጠናከረ አደረጃጀት እንደሌለው ነው። የዚችን ትልቅ አገር ደኅንነት በዚህ መልኩ መያዝ የለበትም፡፡ ጥንቃቄና ጥልቅ ትንተና የግድ ነው። ከየዘርፉ ምሁራን መሰብሰብ አለባቸው፡፡ ሥጋቶችና ፀጋዎች በደንብ መለየት አለባቸው፡፡ ትንበያዎችና ቅድመ ዝግጅቶች መደረግ አለባቸው። ነገሮች ከተፈጠሩ በኋላ እሳት ለማጥፋት አይደለም መሮጥ ያለብን፡፡ ሊፈጠር እንደሚችል መገመት የሚያስችል አቅም ልንገነባ ይገባናል፡፡ ታላቅ አገር ይዘን ንህዝላል መሆን አንችልም። የሁሉም የትምህርት ተቋማት፣ ኤምባሲዎችና ቆንፅላ ጽሕፈት ቤቶች፣ የደኅንነትና የወታደራዊ መረጃ፣ የቲንክ ታንኮችና ዓለም ላይ ሊገኙ የሚችሉ መረጃዎችን መሠረት እያደረገ ሴናርዮዎች (ቢሆኖች) ማቅረብ የሚችል በትልቅ አቅም የሚንቀሳቀስ የደኅንነት ሴክሬታሪያት ያስፈልገናል። ለምሳሌ ከተቋማዊ አሠራር አቅጣጫ ብናየው በተከታታይ የኤርትራ መንግሥት ሉዓላዊነታችንን እየደፈረ ዜጎቻችንን ይጠልፋል፣ አልፎ አልፎ ይመለሳሉ፡፡ ፓርላማው ግን አንድም ቀን ቢሆን አስፈጻሚውን ለምን እንዲህ ሆነ ብሎ ሲጠይቅ ዓይተን አናውቅም። ሙርሌዎች እንደዚህ ሲያበሳብሱን ፓርላማው ለምን ማለት ነበረበት፡፡ የሚመለከተው አካል መጠየቅና ኃላፊነት መውሰድ ነበረበት።

ሪፖርተር፡- ከኢሕአዴግ ነባር አመራሮች ወጣ ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ያጣችው ‹‹በኢሕአዴግ አላዋቂነት ነው›› ብለዋል፡፡ በጥናታዊ ጽሑፍዎ ድምዳሜምሰፍሮ ይገኛል። እውነትጋዊ መሠረት አለን ማለት ነው?

ጄኔራል አበበ፡- ድሮም ቢሆን የኤርትራን ነፃነት ተቀብለው የአሰብ ጉዳይ ላይ ጥያቄ የሚያነሱ ሰዎች ነበሩ። እንደነ አቶ ተወልደ ወልደ ማርያም፣ ሌተና ጄኔራል ፃድቃን ገብረ ትንሳኤ፣ አቶ ስየ አብርሃ፣ አቶ ተፈራ ዋልዋ፣ እኔም ጥያቄዎች የምናነሳበት ሁኔታ ነበር፡፡ በዝርዝር ባንወያይበትም። አሜሪካ ሄጄ ሁለተኛ ዲግሪዬን ስሠራ ግን በዚህ ላይ ጥናት አካሂጄ የባህር በር መብታችንን በሕጋዊ መንገድ ማስመለስ እንደምችል የሚያረጋግጥ ድምዳሜ ላይ ደረስኩ። ባለማወቅና በመታበይ (Ignornace and arrogance) ያጣነው መብት ነው፡፡ አሁንም ግን ሕጋዊ መሠረት አለን፡፡ ዝርዝር ነገር የሚፈልግ ካለ የመመረቂያ ጽሑፌ ላይ አስፍሬዋለሁ፡፡

ሪፖርተር፡- በአሰብ ጉዳይ ላይ ካደረጉት ጥናት ውጪ በተግባር የመሥራትቅድ አለዎት?

ጄኔራል አበበ፡- አዎ፡፡ የአገር ጉዳይ ስለሆነ ነው። በእኔ አረዳድ የባህር በር ሳናውቅ ያጣነው አገራዊ ፀጋችን ነው። በእርግጥ የባህር በር ጉዳይ ከአጠቃላይ ሕገ መንግሥታዊና ፖለቲካዊ ሥርዓቱ አንፃር ካልታየ የወራሪነት ባህሪ ያለው አደገኛ ነገር ነው የሚሆነው፡፡ ስለዚህም ተጠንቅቄ የማነሳው ጉዳይ ነው። የባህር በር ጉዳይ በጣም አስፈላጊ ነው ስል የሞት ሽረት ጉዳይ አድርጌ አላየውም። ከኢኮኖሚም ከፀጥታም አኳያ በጣም ያስፈልገናል፡፡ ግን ሕጋዊና ሕገ መንግሥታዊ በሆነ መንገድ ነው መሆን ያለበት። አሁን ያለውን ሥርዓትና መሠረታዊ የፖለቲካ እሴቶቻችን በሚንድ መልኩ መሆን የለበትም። አሁን ያለን ሕገ መንግሥት ለሌሎች ሕዝቦችና አገሮች አርዓያ መሆን የሚችል የዳበረ ሕገ መንግሥት ነው። ስለዚህም የአሰብ ጉዳይ ተነስቶ ሕገ መንግሥቱን ለመሸርሽርና ለመናድ በሚደረግ እንቅስቃሴ አልሳተፍም። ይህ ሕጋዊ መብታችን ግን መረጋገጥ አለበት ብዬ ስለማምን በቻልኩት መጠን እንቅስቃሴ አድርጋለሁ።

ሪፖርተር፡- ኢሕአዴግ ከክፍፍሉ ከ1993 ዓ.ም. በፊትና በኋላ እንደ ድርጅት ውስጣዊ ጥንካሬው እንዴት ያዩታል?

ጄኔራል አበበ፡- ኢሕአዴግ በ1993 ዓ.ም. ቀውስ ውስጥ ሲገባ የድርጅቱ አባል አልነበርኩም፡፡ የአየር ኃይል አዛዥ ነበርኩ። ስለዚህ ድርጅት ውስጥ የነበረውን ነገር በዝርዝር አላውቅም፡፡ ሆኖም ከሁለቱም አንጃዎች በኩል የትጥቅ ጊዜ ጓደኞቼ ስለነበሩ በሁለቱም ጎራ የነበረውን ሁኔታ እሰማ ነበር። ከድርጅቱ ጋር በነበረን ሥነ ልቦናዊ ትስስርም ድርጅቱ እንዲፈርስ አንፈልግም ነበር። ቁውሱን ለመፍታት የተደረገው ድርጊት ግን በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ከፍተኛ ጠባሳ ያሳደረ ነበር። ሒደቱ እልባት ያገኘው ኢዴሞክራሲያዊና ኢሕገ መንግሥታዊ በሆነ መንገድ ነበር። የመንግሥት ሚዲያ የአሸናፊው አንጃ ሚዲያ ሆኖ ተሸናፊው አንጃ ሐሳቡን የሚገልጽበት ዕድል ተነፍጎ፣ ጄኔራሎችም ጭምር በጉዳዩ ፖለቲካዊ መግለጫ የሰጡበት ሕገ መንግሥታዊነት፣ ፌዴራሊዝምንና የድርጅትን ሕገ ደንብ ገደል የከተተ ሒደት ነበር። ለስዬ ተብሎ ሕግ እስከማውጣት ድረስ ተኪዷል፡፡ ፍርድ ቤት ሲለቀው ፖሊስ በጉልበት ይዞታል። በአጠቃላይ የቀውስ አፈታት ሒደቱ ኋላቀር ብቻ ሳይሆን የተወው ትምህርትም አደገኛ ነው። በውስጥ የፓርቲዎችን መብትም የናደ ነበር። በተለይ ኦሕዴድና ደኢሕዴን ላይ የተሠራው ሥራ ህልውናቸውንና ነፃነታቸውን በሚንድ መልኩ ነበር የተካሄደው። በዚያ መልኩ መለያየታችን ያሳዝነኛል።

ሪፖርተር፡- በ1993 ዓ.ም. የተከሰተውን ቀውስ በመፍታት ረገድ የታየው ፀረ ዴሞክራሲ አሠራር ከዚያ በፊት አልነበረም ይላሉ?

ጄኔራል አበበ፡- መለያየቱ ራሱ የነበረውን አቅም የበተነ ነበር፡፡ ትልቅ ብቃትና ዕውቀት የነበራቸው ሰዎች በአገር ግንባታ እንዳይሳተፉ ያደረገ ነገር በመሆኑ ያሳዝነኛል። በተጨማሪም አሸናፊው አንጃ የደኅንነት መዋቅሩን የሰው መብት በሚጥስና ፍራቻን ለማንገሥ ባለመ ሁኔታ ነበር ሲያንቀሳቅስ የነበረው። እንዲህ ዓይነት ዝንባሌዎች ከዚያ በፊት አልነበሩም ማለቴ አይደለም። ምናልባት እኛ ላይ ስለተፈጸመ ሊሆን ይችላል ያስተዋልነው ወይም መጠኑ ከፍ ብሎ ሊሆን ይችላል። በሰዓቱ የነበረን አስተሳሰብ ‹ከኢሕአዴግ መስመር ውጪ ሁሉም የጥፋት መስመር ነው› ብሎ የሚያምን ስለነበር ተቃዋሚዎችን እንደ ፀጋ የማያይ፣ እግራቸውን እንዳይተክሉ የሚያደርግ አስተሳሰብ ነበር፡፡ ጎልቶ የታየን ግን እኛ ላይ ሲደርስ ነው። ስለዚህ 1993 ዓ.ም. ብቻውን መለያ አይሆንም። እንደኔ አመለካከት ኢሕአዴግ የተሻለ ዴሞክራቲክ ድርጅት ነበረ ብልም ሙሉ በሙሉ ዴሞክራቲክ ነበር ለማለት አልችልም። ከቀውሱ በፊት ፓርላማው ማኅተም መቺ ነበር፡፡ ፍርድ ቤቶች ነፃነት አልነበራቸውም፡፡ ‹ቼክ ኤንድ ባላንስ› የነበረበት የሥልጣን ክፍፍል አልነበረም፡፡ ከዘጠና ሦስት በኋላ ግን ባሰበት።

ሪፖርተር፡- ለወጣቱ ትውልድ ምን ይመክራሉ?

ጄኔራል አበበ፡- ወጣቱ ትውልድ ያለፈው ትውልድ የሠራውን ሥራ ዕውቅና እየሰጠ ሲያበላሽ ደግሞ አታበላሽ ማለት መቻል አለበት፡፡ ያለውን ብልሽት ለማስተካካል መሥራት አለበት፡፡ ማማረር ብቻ መፍትሔ አይሆንም። በምሬት መጀመር ባህርያዊ ነው። ወጣቱ ትውልድ በሚያምንበት አደረጃጀት እየገባ መታገል አለበት። በግልና በመንግሥት መዋቅር ውስጥ የተሸሸጉ ማፊያዎችን መታገል አለበት። አገሪቷ በመስቀለኛ መንገድ ነው ያለችው፡፡ የወጣቱ ፖለቲካዊ ተሳትፎ የግድ የሚልበት ጊዜ ላይ ነው ያለነው። በፌስቡክም፣ በትዊተርም፣ በየጋዜጣና በየመጽሔቱ በትጋት የሚሳተፉ ወጣቶችን በርቱ ማለት እወዳለሁ።

የኢትዮጵያ የ12ኛ ክፍል ፈተና ተሰርቆ በኢንተርኔት ተሰራጨ

0
0

fetena 44 fetena fetena2

(ዘ-ሐበሻ) በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ የ12ኛ ክፍል ፈተና ዛሬ ሰኞ እንደሚካሄድ ቀነ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረ ሲሆን ሆኖም ግን ፈተናው ተሰርቆ ቀድሞ በኢንተርኔት መሰራጨቱ ታወቀ::

በDropbox አማካኝነት እንዲሁም በፌስቡክ እና በሌሎች ሶሻል ሚድያዎች ፈተናው ተሰራጭቶ የሚገኝ ሲሆን መንግስት ግን ምንም ዓይነት ፈተና አልተሰረቀም ሲል በሚያዛቸው ሚዲያዎቹ አውጇል::
የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን “የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ የ12ኛ ክፍል ፈተና ነገ ሰኞ ግንቦት 22 ቀን 2008 ዓ.ም ይሰጣል ፡፡ ይሁንና ፈተና ተሰርቋልና ሌሎች መሰል አሉባልታዎች እየተናፈሱ መሆናቸው ተደርሶበታል፡፡ ነገር ግን የተሰረቀ ፈተና እንደሌለ፣ እንዲሁም በፈተና ዝግጅትና ስርጭት ላይ ምንም ዓይነት ችግር የሌለ በመሆኑ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተፈታኞች በአሉባልታ ሳይረበሹ ተረጋግተው ፈተናቸውን እንዲወስዱ የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡” ሲል ለማሰባበል የዘገበ ቢሆንም አብዛኛው የትምህርት ዓይነቶች ፈተናዎች ከነመልሶቻቸው በሶሻል ሚዲያዎች ተለቀዋል::

በተለይም ፈተናው የተሰራጨበት የDropbox ሊንክ በከፍተኛ ትራፊክ (ጎብኚዎች) መጨናነቅ ምክንያት ለጊዜው መታገዱ ቢገለጽም ብዙዎች ፈተናዎቹን ከነመልሱ በሶሻል ሚዲያዎች ማሰራጨታቸውን ቀጥለዋል:: ለጊዜው ፈተናውን ለማየት Dropbox ሲገቡ የሚከተለውን ያሳያል::

exam ethiopia

የሕወሓት መንግስት “እንቁልልጬ”የተሰኘ ዶክመንታሪ ፊልም በኤርትራ መንግስት ላይ ለቀቀ |ለምን በፊልሙ ላይ ግንቦት 7ን መጥራት አልፈለገም?

0
0

አርበኞች ግንቦት 7 በአርባምንጭ 20 የመንግስት ወታደሮችን ገደልኩ ባለበት ማግስት ዘ-ሐበሻ ሕወሓት መራሹ መንግስት በአርበኞች ግንቦት 7 ላይ የራሱን ሰዎች አስጠንቶ ዶኩመንታሪ ፊልም እየሰራ መሆኑን ምንጮቿን ጠቅሳ መዘገቧ አይዘነጋም:: ዛሬ የግንቦት 20 ማግስት የአርበኞች ግንቦት 7ን ስም ሳያነሳ በኤርትራ መንግስት ላይ ዶክመንታሪ ቪዲዮ በፖሊስ ፕሮግራም ላይ ለቆታል:: ለግንዛቤና አስተያየት ይሰጡበት ዘንድ አቅርበነዋል::

ይህን ፊልም ከማየታችሁ በፊት ከዚህ ቀደም ትግራይ ሆቴልን አፈነዱ ተብለው በቴሌቭዥን የታዩትን እና አፈንድተናል ብለው የተናገሩትን የ’ኦነግ አባላት’ ተብለው በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ታይተው በኋላም ተስፋዬ ገብረአብ ደቡብ አፍሪካ ሲሰደድ እነዚህን ወገኖች እዛው አገኘኋቸው ማለቱን ያስታውሷል::

የሚገርመው በቪዲዮው ላይ ተያዙ ተብለው የቀረቡት የጺማቸው አቆራረጥ እስረኛም አያስመስላቸውም። አንዱ ደግሞ “[መያዛችንን] ባውቅ ኖሮ እዚህ ውስጥ አልገባም ነበር” እያለ ድራማው ድራማ መሆኑን ይነግረናል::

በነገራችን ላይ በዚህ ዶክመንታሪ ፊልም ላይ መንግስት የአርበኞች ግንቦት 7 ለአርባ ምንጩ ጥቃት ኃላፊነቱን ወስዶ እያለ ለምን የግንባሩን ስም ለምን መጥራት አልፈለገም?


AG 7


አርከበ እቁባይ የራሳቸውን ሞራል እየገነቡ ነው

0
0

equbai
(ዘ-ሐበሻ) “የመለስ ራዕይ የሚባል በቃ” ሲሉ እየተከራከሩ ቆይተዋል የሚባሉት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ‘ልዩ’ አማካሪ አቶ አርከበ እቁባይ “Made in Africa industrial policy in Ethiopia” የተሰኘውና በርሳቸው ስም ይጻፍ እንጂ እርሳቸው ይጻፉት አይጻፉት ያልተረጋገጠውን መጽሐፋቸውን ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማስተማሪያነት በስጦታ መልክ አብርክቻለው በሚል ዜናውን በሚያዟቸው ሚዲያዎች በማስነገር በመገባት ላይ ናቸው::

“Made in Africa industrial policy in Ethiopia” የተሰኘውና በአቶ አርከበ ስም የወጣው መጽሐፍ አቶ አርከበ እንዳልጻፉት እየተነገረ ቢሆንም ዘ-ሐበሻ ለዚህ ጉዳይ ማረጋገጫ ማግኘት አልቻለችም:: ሆኖም ግን የመጽሐፉ ጸሐፊ ነኝ ያሉት አቶ አርከበ ከ20 በላይ ለሚሆኑ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት “መጽሐፋቸው” ለማስተማሪያነት እንዲውል ማበርከታቸውን በከፍተኛ የመንግስት ሚድያዎች እንዲዘገብ አድርገዋል::

ከዚህ ቀደም በርካታ ጥልቅ እውቀትን የያዙ መጽሐፍ የጻፉ ወገኖች መጽሐፍቶቻቸውን ለክፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለማስተማሪያነት ቢያበረክቱም እንደ አቶ አርከበ የመንግስት ሚዲያ ሽፋን ሳያገኙ ቀርተዋል::

መንግስት የ12ኛ ክፍል ፈተናው መሰረቁን አምኖ ዛሬ ሊሰጥ የነበረው ብሔራዊ ፈተና እንዲቋረጥ አደረገ

0
0

fetena2
(ዘ-ሐበሻ) በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች ባለፉት 4 ወራት በነበረው የሕዝብ ተቃውሞ ተማሪዎች በአግባቡ ትምህርታቸውን ሳይማሩ ቀርተዋል:: ይህን ተከትሎም ያልተምሩትን እንዳይፈተኑ; ለፈተናም በቂ ዝግጅት ባለማድረጋቸው እንዲራዘም ለትምህርት ሚኒስቴር ጥያቄ ቢያቀርቡም ጥያቄው ውድቅ በመደረጉ በስርዓቱ ውስጥ ያሉት የውስጥ አርበኞች ተቃውሟቸውን ለማሳየት ፈተናውን በኢንተርኔት ለቀውት ነበር::

shiferaw-shigute
ትናንት የትምህርት ሚኒስትሩ ሽፈራው ሽጉጤ “የተሰረቀ ፈተና የለም; ብሔራዊ ፈተናው በታሰበለት እና በታቀደለት ጊዜ ይካሄዳል” ቢሉም ፈተናው ግን በሶሻል ሚድያዎች መራባቱን ቀጥሎ ነበር:: ዛሬ ጠዋት እንደገና እኚሁ የትምህርት ሚኒስትሩ በሰጡት መግለጫ “እንደማንኛውም ሰው ፈተናው በኢንተርኔት ቀድሞ መበተኑን አይቻለሁ” በሚል ፈተናው እንዲቋረጥ መታዘዙን አስታውቀዋል::

ፈተናው ከመቋረጡ በፊት ዛሬ ጠዋት የተወሰኑ የትምህርት ዓይነቶች ፈተና ተስጥቶ እንደነበርም ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ይጠቁማል::

እንደ አቶ ሽፈራው ገለጻ በሃገሪቱ 800 የፈተና ጣቢያዎች እንዳሉና ከየትኛው ቦታ ተሰርቆ እንደወጣ መንግስት የሚጣራ ይሆናል::

በምስራቅ ወለጋ የማትሪክ ፈተና ከተሰረዘ በኋላ ተማሪዎቹ መንግስትን አወገዙ

0
0

Jarso

Jarso1
(ዘ-ሐበሻ) የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተሰርቆ በሶሻል ሚዲያዎች ከተሰራጨ በኋላ ፈተናው ተጀምሮ እንዲቋረጥ ሲደረግ ተማሪዎች በተለያዩ አቅጥጫዎች በመንግስት ላይ ያላቸውን ተቃውሞ በመግለጽ ላይ ናቸው::

ወትሮም ፈተናው እንዲራዘምላቸው ጠይቀው የነበሩት ተማሪዎች መንግስት በግድ ፈተናውን ማቋረጡን ተከትሎ አደባባይ በመውጣት ብሶታቸውን ተናግረዋል:: በምስራቅ ወለጋ ጃርሶ ወረዳ ተማሪዎቹ “ብለን ነበር ብለን ነበር” የሚሉ ድምጾችን በማሰማት በስርዓቱ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ከነዩኖፎርማቸው በወረዳዋ እየተዟዟሩ አሳይተዋል::ተማሪዎቹ መንግስት ሳይወድ በግዱ ፈተናውን በመሰረዙ የተሰማቸውን ደስታም ገልጸዋል::

በሃገሪቱ በሌሎችም አካባቢዎች የተማሪዎች ጉምጉምታ እንዳየለ መሆኑን የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ::

በሌላ ዜና የትምህርት ሚኒስቴር የኢንተርኔት አገልግሎት በሌለባቸው አካባቢዎች የተሰረቀው ፈተና አልተዳረሰም በሚል ፈተናውን ያስቀጠለበት ሁኔታም እንዳለ መረጃዎች ደርሰውናል::

Hiber Radio: ጌታቸው ረዳ በአባይ ግድብ ዙሪያ የሰጡት ያልተገራ አስተያየት የካይሮ ባልስልጣናትን አስቆጣ * ከጋምቤላ የታፈኑት ህጻናት በደ/ሱዳን ለሽያጭ ሳይቀርቡ እንዳልቀረ ተሰግቷል

0
0
ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

<...> አቶ ግርማ በቀለ የኦሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ሕብረት ሊቀመንበር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከአገር ቤት ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)

<...> አቶ ማሙሸት አማረ የሕጋዊው መኢአድ ፕሬዝዳንት ለህብር ከሰጡት ቃለ መጠይቅ (ሙሉውን ያዳምጡት)

በቬጋስ ተጠርቶ ውቴታማ ያልሆነው የሁበር አሽከርካሪዎች ተቃውሞና ተያያዥ ጉዳዮች

የዛሬ ስድስት ዓመት በኡጋንዳ ከሚገኝ የኢትዮጵያ ሬስቶራንት ላይ ጥቃት በማድረስ የሰው ሕይወት የቀጠፉ አሸባሪዎች ሰሞዩን የተላለፈባቸው ውሳኔ ሲዳሰስ(ልዩ ዘገባ)

በኢሚግሬሽን እስር ቤት ስላሉት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ በዝዋይ እስር ቤት የጻፍከው ጽሑፍ ተገኘ በሚል ጨለማ ቤት እንዲገባ ተደረገ

ከጋምቤላ የታፈኑት ጨቅላ ህጻናት በደ/ሱዳን ውስጥ ለሽያጭ ሳይቀረቡ እንዳልቀረ ተሰግቷል

የአሜሪካ ሴኔተሮችና ዲፕሎማቶች በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ዙሪያ የተሰማቸውን ስጋትጋት ገለጹ

በተለጣፊው መኢአድ ስም የተጠራው ጉባዔ የስርዓቱ ሕገ ወጥ ተግባር አካል መሆኑን ተቃባይነት እንደሌለው ሕጋዊው የፓርቲው ፕሬዝዳንት ገለጹ

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን ለዓለም ጤና ድርጅት መሪነት እሾማለሁ ማለት በአገሪቱ ለሚደረገው የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና በጤና ስም ሲደረግ የነበረውን ሙስና መደገፍ ነው ሲሉ ከአገር ቤት አንድ የተቃዋሚ መሪ ገለጹ

የኢህአዲጉ የኮሚኒኬሽን ሚኒስተር ጌታቸው ረዳ በሕዳሴው ግድብ ግንባታ ላይ የሰጡት ያልተገራ አስተያየት የካይሮ ባልስልጣናትን አሰቆጣ

የኢትዮጵያው አገዛዝ የኤርትራ ተቃወሚዎችን በገንዘብ ለመርዳትና ለማደራጀት መወሰኑ ታወቀ

በሜዲትራኒያን ባህር ሰሞኑን የሰጠሙት ስደተኞች ቁጥር ከሰባት መቶ በላይ ሊሆን እንደሚችል ስጋት አለ

የስፔኑ ሃያል የእግር ኳስ ቡድን ሪያል ማድሪድ ኣትሌቲኮ ማድሪድን በማሸነፈ በአውሮፓ ሻምፒዮና ውድድር ታሪክ ሰራ

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የባፍሎ ዓመታዊ የማራቶን ውድድር አሸናፊ ሆኑ

እና ሌሎችም ዜናዎች አሉን

ስኬት እና ተምሳሌት! |“በዛሬው ዕለት በታሪክ ተመዝግቦ የሚኖር አኩሪ ድል በደማቅ ተጽፏል!!!”

0
0
ይድነቃቸው ከበደ

ይድነቃቸው ከበደ

ይድነቃቸው ከበደ (እርገጤ)

ብልህነት የተሞላበት ስትራቴጂ ከተነደፈ፣ አምባገነናዊ ሥርትዓት እና የሥራዓቱ አራማጆችን በአነስተኛ መሰዋዕትነት ትልቅ ድል ማስመዝገብ ይቻላል።ለዚህም በዛሬው ዕለት በታሪክ ተመዝግቦ የሚኖር አኩሪ ድል በደማቅ ተጽፏል። አምስት ወር ሙሉ ትምህራትቻውን ባአግባቡ ሳይከታተሉ፣ በአገዛዙ ጠባቂዎች ሲገደሉና ሲንገላቱ የነበረ ተማሪዎች፤ በግዳጅ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የብሔራዊ ፈተና እንዲፈተኑ የታቀደው እቅድ፣ በሰለጠነ የሰላማዊ ትግል ዜዴ ማስቀረት ተችሏል ።ይህን መሰል አኩሪ ድል ለፈጸሞት ምስጋና ሲያንስባቸው እንጂ አይበዛባቸውም።


“የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላን”የሚል ስያሜ የተሰጠው የመሬት ነጠቃ እና ወረራ ፤የህዝብ ጥቅም እና ፍላጎትን ያልጠበቀ መሆኑን ተከትሎ ፣በተደረገ ህዝባዊ ጥያቄ እና በገዢው መንግሥት በኩል በተሰጠው ምላሽ ፣ መተኪያ የሌለው የሰው ልጅ ሕይወት እንዲጠፋ ፣የንብረት ውድመትና ኪሳራ እንዲደርስ ምክንያት ሆኗል።ለህዝብ አቤቱታ እና ተቃውሞ ፣ተገቢውን ክብርና ምላሽ የመስጠት የአቅም ውስንነት ብቻ ሳይሆን አፈጣጠሩ ጭምር የማይፈቅድለት የህውሓት/የኢህአዴግ አንባገነን መንግሥት ዓይኑን በጨው አጥቦ ፣ከሞትና ከእስራት የተረፉ ታዳጊ ወጣቶችን፣ በከፍተኛ ትምህርት መግቢያ በብሔራዊ ፈታና ለመቅጣት ሲዳክር ፣ የአገዛዙ ስርዓት ለብቀላ አንድም ሣይቀር ምን ያህል ርቀት እንደሚሄድ የሚያመላክት ነው።

shiferaw_shigute
የከፍተኛ ትምህርት የብሔራዊ ፈተና፣አንድ ተማሪ በቀጣይ የትምህርት ሂደቱ እና በወደፊት የስራ መስክ ላይ ቀጥተኛ ውሳኔ የሚወስንበት የዓመታት የልፋት ውጤት ነው። የፈተና ውጤቱ የሚያስከትለውን አሉታዊ እና አወንታዊ ተጽእኖ ቀላል የሚባል አይደለም ። በዚህ ላይ አሻሚነት እንደሌለው የጋራ እምነት ካለ፤በአንድ ተማሪ ላይ የዚህን ያህል ተፅእኖ ካለው፤ በአገራችን በተለያየ ክፍለ አገር በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ተማሪዎች ላይ ድርጊት ቢፈጸም ፣የጉዳቱ መጠን ምን ያህል አስደንቃጭ ሊሆን እንደሚችል ግልፅ ነው፡፡

አሁንም እየተጠየቀ ያለው ፣ተማሪዎች ለአምስት ወራት ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዳይከታተሉ ተደርጓል ፣ለዚህም የመንግስት እጅ አለበት።በመሆኑም ፈተናው አገር አቀፍ እንደመሆኑ መጠን ፣አመቱን ሙሉ ሲማር እና ለአምስት ወር የተማረ ተማሪ እኩል ፈተና ላይ መቀመጥ የለበትም ።ስለዚህም በቂ የፈተና ጊዜ እና የማካካሻ ት/ት ተሰጥቶ ፤ብሔራዊ ፈተና መካሄድ እንዳለበት ነው።ይህ ጥያቄ የማንም መብት የማይጋፋ፣ከምንም በላይ የፈተናው ሚዛናዊነት እንዲጠበቅ የሚያደርግ ነው፡፡

የህውሓት/የኢህአዴግ አንባገነን መንግሥት “የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላን” የሚል ስያሜ ሰጥቶ የነበረው እቅድ ተግባራዊነቱ እንዲቆም፣ በህውሓት የሞግዚት አስተዳደር የሚመራው ኦህዴድ መዕከላዊ ኮሚቴ መወሰኑ የሚታወቅ ነው። ድርጅቱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የህዝብ ተቃውሞና አለም አቀፍ ማህበረሰብና የውጪ መንግስታት ከፍተኛ ጫና ተከትሎ ነው።በተለይ በአገራችን በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች የህይወት መሰዋዕትነት ሁሉ ከፍለውበታል።

አቶ ኃ/ማርያም ዳሳላኝ በተለያየ ወቅት በመንግስት የመገናኛ ብዙሃን ቀርበው ፣እሳቸውና እና መንግሥታቸው ፤የኦሮሚያ ልዩ ዞን ማስተር ፕላን አስመልክቶ በተከሰተው ነገር ይቅርታ ከመጠየቃቸው በላይ ፣ለይስሙላ የተወሰኑ ባለስልጣናት ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ እና እንዲጠየቁ አስችለናል ሲሉ ተደምጠዋል።ይህን ማድረግ ከተቻለ መንግስት ነኝ ባዮም ኃላፊነት ወስጃለሁ ካለ ፣ለተማሪዎች ተጨማሪ የፈተና ጊዜ እና የማካካሻ ትምህርት ለምን አይስጥም ?! ብሎ መጠየቅ አግባብነት አለው።ተገቢውን መልስ የሚሰጥ የመንግስትነት ቅርጽ ያለው ስርዓት ስለመኖሩ ዋና መሰረታዊ ጥያቄ ነው።የሆነዉ ይሁንና ተብሎ የማይታለፈው ፣ዛሬ የሆነው ነገር ስኬቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ተምሳሌታዊነቱ ለአማራጭ የሰላማዊ ትግል ዘዴ ትልቅ ቦታ ይኖሯዋል።
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!
ግንቦት 22 ቀን 2008 ዓ.ም

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live