Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ሸንጎ በአዲስ አበባ የተጠራውን ሰላማዊ ሠልፍ እንደሚደግፍ አስታወቀ

$
0
0

የሸንጎ መግለጫ፦

ሸንጎ በአዲስ አበባ የተጠራውን ሰላማዊ ሠልፍ ይደግፋል
ጳጉሜ ፪፣ ፪፼፭
September 7, 2013

shengoህገመንግስታዊና ተፈጥሮአዊ መብታቸውን ተጠቅመው ሰላማዊ የፖለቲካ ተሳትፎ ለማድረግ የሚጥሩ የፖለቲካ ድርጅቶችን ህወሓት/ኢህአዴግ ቀንተቀን እያጠበበው ከመጣው የፖለቲካ ምህዳር ሊያስወጣቸው የሚያደርገውን ጥረት ሸንጎ እያወገዘ፣ የተቃዋሚ ድርጅቶች የሚደርስባቸውን አስከፊ እንግልትና በደል ተቋቁመው ህዝባዊ እንቅስቃሴውን ማስቀጠላቸውን ያደንቃል።
ያለውን አምባገነን አገዛዝ ታግሎ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ለመፍጠር የታጋይ ድርጅቶችን አንድ ላይ መቆም ግድ የሚል በመሆኑ በነጠላ የሚደረጉ ትግሎችን በማስተባበር ትግሉን ውጤታማ ማድረግ ወደሚቻልበት ደረጃ ማድረስ አስፈላጊ ነው። አንድነት መስከረም አምስት በአዲስ አበባ የጠራውን ሰላማዊ ሠልፍ 33ቱ ፓርቲዎች በጋራ ለማዘጋጀት መወሰናቸው እሰየው የሚያሰኝና ትግሉ ጥሩ አቅጣጫ ይዞ መጓዝ እንደጀመረ የሚያመላክት ነው። ይህም ትብብር ከፍወዳለ ደረጃ እንደሚደርስ ትስፋችን ነው።
የፖለቲካ ድርጅቶች እንዲህ ተባብረው በሚቆሙበት ወቅት ህዝቡም በነቂስ በመውጣት የተባበረ ጠንካራ ጉልበት እንዲፈጥር ሸንጎው ያሳስባል።
በተባበረ ትግል ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን እንገነባለን!


አዲስ ዓመት –በነተበ ሥርዓት

$
0
0

(ሩት ዳግም)

COEEFMesganaDancersCA4

Enqutatash -Happy New Year

      ጊዚያቶች  ክንፍ  አውጥተው የሚበሩ ይመስላሉ። 2005 አምና ለመሆን በቅቷል። የተፈጥሮን ህግጋት ጠብቆ በዳመና የጠቆረው ዳመና  እየገለጠ፣   አበቦች እየፈኩ መድሪቷ የመስከረም ወር መጥባቱን ብታበስርም፤ በክፉ የወያኔ አገዛዝ ቀንበር ስር ለሚማቅቀው የአገሪትዋ ህዝብ ዛሬም እንጉርጉሮው የሀዘን ነው። የኑሮ ውድነቱ፣ የሰብአዊ መብት ጥስቱ፣ ፍትህ ማጣት እና በመሳሰሉ ስር በሰደዱ ችግሮች እግር ተወርች ተቀፍድዶ ነገን በተስፋ ተሞልቶ አዲስ ዓመት ይጠብቃል ማለት ዘበት ነው። ይልቁንም አዲስ ዓመት ይዞት በሚመጣው የኑሮ ጣጣ የሚቆዝመው ህዝብ ቁጥር እልፍ ነው።

     ‹‹ትራንስፎርሜሽን›› የሚባል የወያኔ ዕድሜ ማራዘሚያ የተዘጋጀው እቅድ እንደተወራለት በአምስት ዓመት ውስጥ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ  ህዝብን የሚያሰልፍ አለመሆኑን ሁሉም ተገንዝቦታል። ይልቁንም የህውሃት ግዙፉ ድርጅት ኤፈርት በያዛቸው ትላልቅ ፕሮጀክቶች አመቻቺነት ጥቂት የወያኔ ባለስልጣናትን በሙስና ፈጣን ባቡር ወደ ሚልኒየር፣ ቢልየነር ተርታ  መላውን ህዝብ ደግሞ በድህነት ቀፍድዶ ወደአዘቅት የሚያደርስ ሆኗል። በዚህ አሳዛኝ ህይወት ላይ  ለሚገኝ ህዝብ አዲስ ዓመትን በአዲስ ተስፋ መጠበቅ የቀን ቅዠት ነው። ወትሮስ በዘረኝነት፣ በሙስና በሀገር ክህደት ብል እንደበላው ነጠላ የነተበ መንግስት የአገርን ገበና በምን አቅሙ ይሸፍናል??

     በአይነ ህሊና የዘመን አሮጌ ልብስ የደረበውን የዘንድሮ ዓመት መለስ ብላችሁ ብትቃኙት ቅንጣት ያህል አስደሳች ነገር ለማግኘት ይከብዳል። በ2005 ዓ.ም. በወያኔ መንግስት የስልጣን ሽኩቻና ሹም- ሽር ያየለበት፤ እስርና ግድያ በአደባባይ የተፈጸመበት፣ ፍትህ ማጣት ያየለበት፤ በኑሮ ወድነት፣ በመብራት መጥፋትና መምጣት፣ በውሃ መቋረጥ፣ በታክሲ፣ ዘይት፣ የስኳርና የስንዴ በመሳሰሉ ሰልፎች መሽቶ እስኪነጋ ህዝብ የሚደክምበት ተስፋ አስቆራጭ የቀን ጨላማ ነበር። በመንግስት ሚድያ ደግሞ “የታላቁ መሪ” አቶ መለስ ውዳሴ “ውርሳቸውን/ሌጋሲያቸውን” እናስቀጥላለን በሚል የማያባራ የቆሸሸ ፖለቲካ ህዝብን ማሰላቸት ሥራዬ ብለው ከርመውበታል። ይሁንና ይህ ወቅት አልፎ የመለስ እኩይ ተግባር፣ ክህደትና ተዘርዝሮ የማያልቅ ክፉ ተግባር ትውልድ ሁሉ በሚማርበት መልኩ በዚያው በሀገራችን፤ በዚያው ሚድያ የሚነገርበት ዕለት ይመጣል።

አሁን ባለው የጨለመ ድባብ አዲስ አመት ሲመጣ ህዝቡ እንደ ወግ ልማዱ

“ከብረው ይቆዩ ከብረው

በዓመት ወንድ ልጅ ወልደው

ሠላሳ ጥጆች አስረው

ከብረው ይቆዩ ከብረው” የሚል የልጆቹን ዜማ ተቀብሎ እያዜመ ነገን በተስፋ ያልማል ማለት የአብዛኛውን ህዝብ ኑሮና የተጫናበትን መከራ ያለማወቅ ነው።

 

ይሁንና ይቺን መከራኛ አገር ላይ ተፈናጠው እንዳሻቸው ደንገላሳ ለሚጋልቡዋት የህውሀት ባለስልጣናትና ጋሻ ጃግሬዎቻቸው  ግን ሁሌም አዲስ ዓመት፤ ሁሌም በዓል ነው ያቺ ቀን እስክትመጣ . . . በሙስና በዘር ፖለቲካ ውርስ በተባለ አስማታዊ ብልሃት ከባዶ ኪስ ተነስተው በአንድ ሌሊት ከሚልኒየር ተርታ የሚሰለፉ የዘመናችንን ጉዶች ማየት የተለመደ ሆኗል።

ግና በመዲናችን በየመንገዱ ዳር ተገጥግጠው ከሚታዩት በመስተዋት ካሸበረቁት ህንጻዎች ጀርባና በየመንገዱ ዳርና በየጎዳናው ድህነት ጠልፎ እንደ ጉድፍ የጣለውን በርካታ ህዝብ ማየት ያማል። እናም የሀገሪቱን የሁለት ዲጂት ዕድገት ቱልቱላና የሆነውን በማመዛዘን የአዲስ ዓመት ፌሽታ ባይገባው ይደንቃል? እፍረት አልባው መንግስት ሀገራችን ኢትዮጵያ በአፍሪካ ብቻ ሳይሆን በዓለም ፈጣን እድገት እያስመዘገቡ ካሉ ሀገራት ተርታ ተመድባለች እያለ እውን ያልሆነውን ህልም ሊያሳይ ቢሞክርም ዩናትድ ኔሽን ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርት በ Multidimensional Poverty Index መሰረት ኢትዮጵያ ከመንግስት አልባዋ ሱማሌ ጭምር ተበልጣ ከመጨረሻው የድሀ አገር ተሰልፋለች። የበለጠችው አገር ኒጀርን ብቻ መሆኑ ነው። “ጉድ ሳይሰሙ መስከረም አይጠባም !” እንዲሉ።

በሥራ አጥነት፣ በየተልካሻ ምክንያት ከሥራ በተባረሩ፣ በዘራቸው ሳቢያ በተሰደዱ፣ በሃይማኖታቸውና በፖለቲካ አመላካከታቸው ሳቢያ ለእንግልትና ስቃይ በተዳረጉ በርካታ ቤተሰቦች ባሉበት አገር ደስታን ለማጣጣም እንዴት ህሊና ይቀበላል? ለእውነትና ለህሊናቸው ብቻ ስለቆሙ በአሰቃቂ እስር ቤት ታጉረው ከሚወዱት ቤተሰብ በግፍ የተነጠሉ ወገኖቻችንን አስበልተን ምን አይነት የበዓል ድግስ ይኖረናል??

ሀገራችን ኑሮ፣ የመልካም አስተዳደር ችግር፣ የፍትህ ማጣት እንደ ጎርፍ ጠራርጎ ጎዳና ላይ ካወጣቸው እጅግ በላቀ ሁኔታ ለልመና መውጣት አፍረው በየቤታቸው በችግር አለንጋ የሚገረፉት እጅግ እጅግ በርካታ ናቸው፤ ዛሬ ልጆቻውን በቀን አንዴ እንኩዋን ለመመገብ የማይችሉ ቤተሰቦች የተበራከቱበት ሃገር ሆናለች። ታዲያ ዓለምን ያነጋገረው በስደት በየበረሃውና በአረብ ሀገራት  የሚያልቀው ወጣት የሁለት ዲጅት ዕድገት ውጤት ይሆን?

በየቤታቸው በችግር የሚጠበሱትን ወገኖች ካነሳሁ ከጥቂት ወራት በፊት ያጋጠመኝን ልጥቀስ አዲስ አበባ ኡራየል አካባቢ አንዲት አነስተኛ ሱቅ የምፈልገውን ዕቃ በመሸማመት ላይ ነበርኩ፤ እናም ከሁዋላዬ አንዲት በእድሜና በኑሮ ጉስቁልና ወገባቸው የጎበጠ ጠይም እናት ብዙ ደቂቃ መቆማቸው ስለሰቀቀኝ “እናቴ እርሶ ግዙና እኔ እቀጥላለሁ” አልኩዋቸው። ሽቁጥቁጥ በሆነ ትህትና መርቀውኝ ባለሱቁን “ቡና ይኖርሃል?” አሉት

“ቡና አለ! ኪሎ ባለመቶ ሃምሳ፣ ባለምቶ ሃያ ወይም ባለመቶውም ጥሩ ነው . . .” በእጁ እየዘጋገነ ሊያሳየቸው ሞከረ

ዓይናቸው ዓይኖቻችንን የሚሸሹ መሰለኝ፣ ጥቂት አሰቡና “ የአስር ብር አድርግልኝ”

“እማማ አያዋጣኝም…’’

“እንግዲያውስ የሩብ ሩብ ስጠኝ’’ ሀዘን፣ ሸንፈት የኑሮ ድካም በደማቁ ጠይም ፊታቸው ላይ ይነበባል።

“በዚህስ ዘይት ትሸጥልኝ?’’ በፌስታል የያዙትን ትንሽ የዘይት ጠርሙስ አውጥተው እያሳዩት

“እኔ ጋር በችርቻሮ የለኝም። እታች ካለው ሱቅ ይሞክሩ” አላቸው

ተስፋ በቆረጠ መንፈስ “ዘይቱ ቢቀርም ግድ የለም። ብቻ ይቺ ቡና ሱስ  ነው ያስቸገረች . . .’’ አሉና ወገባቸው ላይ ክታሰረችውን መቀነት ፈትተው ብሩን ቆጥረው ከፍለው ሄዱ።

በዓይኔ ተከተልኳቸው ይህ የበርካታ የሀገራችን እናቶች ኑሮ መሆኑን ባውቅም፤ ያለፉትን የኑሮ ውጣውረድ ወለል አድርጎ የሚያሳይ ገጽታቸው፤ ሽቁጥቁጥነታቸው ለልመና እጃቸውን ለመዘርጋት ያልተረታ መንፈሳቸው፤ ነገር ግን ድህነት አንገዝግዞ ሊጥላቸው ያቃረበው የተጎዳ አካላቸው ከፊቴ ላይ እየተጋረጠ ፋታ ነሳኝ .  . . ለምን አንድ ኪሎ ቡና እንኩዋን ሳልገዛላቸው. . . ቁጭት ያዘኝ፤  ደጋግሜ ራሴን ወቀስኩ፤ አሮጊትዋ  ግን ከዓይኔ ርቀዋል።  ባለሱቁን መኖሪያ ቤታቸውን ጠየኩት። አልፎ አልፎ ወደ ሱቁ እንደሚመጡ ቤታቸውን ግን እንደማያውቀው ነገረኝ። በሌሎቹ ቀናት ደጋግሜ ባለሱቁን ብጠይቀውም አይቶአቸው እንደማያውቅ ነገረኝ። ለባለሱቁ ይህ ደጋግሞ የሚያየው የህይወት ትዕይንት ስለሆን ቁብ አልሰጠውም።

እንግዲህ “ሁለት ዲጂት…” ይህን መሰል የበርካቶችን ህይወት ያለመዳሰሱ ቀልድ ህሊናን ይኮሰኩሳል? በየመንገዱ በጠኔ በህመም ወድቆ በአደባባይ ያለምንም ረጂ ሊሞት የሚያጣጥር ወገን እንደ ዋዛ ማየት በተለመደበት አገር፤ ከየመንገዱ የበቀሉ ደሃውን በግፍ አፈናቅለው በበቀሉ ህንጻዎች መመዘኛ ዕድገትን መለካት ፌዝ ነው። የለየለት ቧልት ነው። በየመንግስት ትምህርት ቤቱ ደጃፍ ብትቆሙ ርሃብ ጉስቁልና እንደለበሱት ልብስ አመድ ያስመሰላቸው ልጆችን በመቶ ሳይሆን በሺዎች የሚቆጠር ታያላችሁ። ከዚህ ሁሉ የኑሮ ቀዳዳ ጥቂቱን አለመድፈን ደግሞ ሌላ ስቃይ ነው። በአንዲት ትንሽ ብልቃጥ ለምትለካ መጠጥ ብቻ 2 እና 3 ሺህ ብር በመክፈል በየዕለቱ ሸራተን በመሳሰሉ ትላልቅ ሆቴሎች በዘረፉት ገንዘብ የሚምነሸነሹ የሞሉበት አገር መሆኑ ደግሞ የአገሪቷ ሥርአት ለመኮላሸቱ ሌላው ማሳያ ነው። በየኮንፌሽየስ  እንደተገለጸው በመጥፎ አስተዳደር ስር በሚገኝ አገር የጥቂቶች ብልጽግና የሚያሳፍር ነው። ሰሞኑን የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ኑሮ ጠንቆች ሲል ባስጠናውና ይፋ ባደርገው መረጃ መሰረት ከሚልዮን የሚልቁ በልመና የሚተዳደሩ አሉ። እውነታው ከዚህም ይከፋል።

ይባስ ብሎ የመጨረሻ በሌለው ድህነት ተውጠን  አንድ  ቁጥር ዘረኛና አምባገነን ስርአት የተጫነብን ምን ፍርጃ ነው ያሰኛል። ኢትዮጵያን በዘር ፣ በቋንቋ እና በሃይማኖት ከፋፍሎ የህዝቡን አንድነት ለማጥፋት የሚጥረውን አገዛዝ መቃወም ደግሞ “አሸባሪ’’ የሚል ታርጋ አስለጥፎ ዘብጥያ ያስወረውራል። በወያኔ እኩየ ስራዓት የህግ የበላይነት የለም፤ ዲሞክራሲ ተደፍጥጡዋል፤ የደህንነት ዋስትና የለም፤ ነፃ ፕሬስ ተረት ሆኗል፣ የብዙሃን ፓርቲ ያልምንም እፍረት ተገፍትሮል። የሲቪክና ሙያ ማህበራት የማሽመድመዱ ተግባር ተከናውኗል።

ይለቁንም ዘረኞች ግፈኞች፣ ወንጀልኞች፣ አምባገነኖች፣ ሙሰኞች እንዳሻቸው ዛሬም እየፈነጩ፤  በተቃራኒው ፍትህና እኩልነት ለህሊናቸው፣ የሚታገሉና የሚዋረዱበት፣ የሚሰደዱበት የሚታስሩበት አገር መሆኑ ያስቆጫል።

በርግጥ የታፈኑ ብሶት ገንፍሎ የነጻነት ደማቅ ፀሐይ የምናይበት ጊዜ እንደሚመጣ ቅንጣት አልጠራጠርም። ያኔ በርግጥም ክረምቱ ያልፋል፣ ምድሪቱም በነጻነት ጸበል ይለመልማል፤ ሰማያችን ከክፉ የዘረኝነት ዳመና ይጠራል። ከተራራ ተራራ “አበባ አየሆሽ” ዜማ ይናኛል።

“የእማምዬን ቤት

ወርቅ ይዝነብበት

የአባብዬን ቤት

ወርቅ ይዝነብበት” በርግጥም ትርጉም ይኖረዋል። መልካም ዘመን ያምጣልን። አሜን!!

የሐምሌ ጨረቃ! (ክፍል አንድ) –ከአንዱዓለም አራጌ ዋለ (አንድነት ም/ሊቀመንበር ከቃሊቲ ማጎሪያ)

$
0
0

የሐምሌ ጨረቃ!

ከአንዱዓለም አራጌ ዋለ (አንድነት ም/ሊቀመንበር ከቃሊቲ ማጎሪያ)

ክፍል አንድ

(ሊያነቡት የሚገባ)

andu_udj

ከጉልበተኞች ጠመንጃ የሚወጣ ጥይት ስጋን እንጂ እምነትን ሊገድል እንደማይችለው ሁሉ፣ ከቤተሰብና ወዳጅ ዘመድ ተነጥሎ ቅዝቃዜ በዋጠው ጠባብ ክፍል ውስጥ መታሰርም አካልን እንጂ ምናብን (ህልምን) ሊያስር የሚችልበት ጉልበት የለውም፡፡ ከቶስ እንደምናብ ሜዳውን፣ ተራራውን፣ ቁልቁለቱን፣ ዳገቱን፣ ሸለቆውን፣ ኮረብታውን በሰከንድ ክፍልፋዮች ከብርሃን ፈጥኖ በመምዘግዘግ ያለመዛነፍ ያሰበበት የሚደርስ ምን ኃይል አለ? ከጠባቧ ክፍል ውስጥ ‹‹ድርሻህ›› ተብላ በተሰጠችኝ 90 ሴንቲ ሜትር ላይ ቀሪ ህይወቴን አሳልፍ ዘንድ በግፍ ፍርድ ብታሰርም ዕረፍት ለማያውቀው ምናቤ ገለታ ይድረሰውና ይዞኝ ይከንፋል፤ ወደ ምፈልገው አድርሶ ይመልሰኛል፡፡

አንዳንዴ ከጁፒተር ማዶ ያሉ ተንሳፋፊ ዓለማቶችን ቢያስቃኘኝም፣ አብዛኛውን ጊዜ ግን በሀገሬ ሰማይ ስር በጥቅጥቅ ደመና ላይ አንሳፎ ታላላቅ ወንዞቿን፣ ሃይቆቿን፣ የተንጣለሉ መስኮቿንና ሰማይ ጥግ የሚደርሱ ተራሮቿን በመንፈስ ያስጐበኘኛል፡፡ በተራሮቿ ግርጌና በመስኮቿ እምብርት ላይ ችምችም ብለው የተሰሩ ጐጆ ቤቶችንና በውስጣቸው ለሺ ዓመታት በፍቅር የኖሩ ደሃ ኢትዮጵያውያንን እንደጓደኞቻቸው ከሚመለከቷቸው የቤት እንስሳቶቻቸው ጋ ይታዩኛል፡፡ በየከተሞቹ ከድህነትና ከአፈና ጋር ግብግብ የገጠሙ፣ ከድህነትና ከፖለቲካ አፈና ነፃ ለማውጣት በዓለም ዙሪያ የተበተኑ ወገኖቼን ሳይቀር በአይነ- ህሊና ያስጎበኘኛል፡፡ አንዳንዴ ውሸትን እንደብልህነት፣ አፈናን እንደ አገዛዝ ስልት የወሰዱ አሳሪ ወንድሞቼና እህቶቼ የህሊና ጓዳ ውስጥ ይዞኝ ዘው ይልና ያረበበውን እብሪት፣ ፍርሃት፣ ጭንቀት፣ እርስ በእርስ የሚላተሙ ሃሳቦቻቸውን ፍልሚያ… ያሳየኛል፡፡

እነዚህ ምን አይነት ኢትዮጵያውያን? ምን አይነትስ ወላጆች ናቸው? ብዬ ራሴን እጠይቃለሁ፡፡ የምናብ ፈረስ ጋልቤ የምጐበኘው የዚህን ዘመን ክንዋኔ ብቻ ሳይሆን የተደራረበውን የዘመን ጉም እየጠራረጉ ያለፉ አያሌ ዘመናትን ወደ ኋላ አስጉዞ ያሳየኛል፡፡ የኢትዮጵያን የከፍታ ዘመናት፡- አክሱምን፣ ላሊበላን፣ ጐንደርን፣ ያልዘመርንለትን የገዳ ዴሞክራሲ ስርዓትንና ሌሎች የጥንት ስልጣኔዎችን በብላሽ ያስኮመኩመኛል፡፡ የኢትዮጵያን የዳር ድንበር ነፃነት ለማስከበር አባቶቻችን ያደረጓቸውን የጀግንነት ውሎዎች በተለይም የጀግንነታችን ማማና የጥቁር ህዝብ ሁሉ ኩራት የሆነውን የአድዋን ጦርነት ደጋግሜ አየዋለሁ፡፡ አድዋና መሰል የጀግንነት ማማዎች ላይ ቆሜ ኢትዮጵያውያን በየቀያቸውና በየዘመኑ ሰብዓዊ ክብራቸው ተረግጦ፣ በጭቆና አዘቅት ውስጥ ወድቀው ሲዘቅጡ ይታዩኛል፡፡ አንዳንዴ ኢትዮጵያውያን ሰብዓዊ ልዕልናቸውንና ነፃነታቸውን ለመጐናፀፍ ያደረጉትን ትግል ያሳየኝና መንፈሴን ያበረታዋል፡፡

ታሪክ እንደሚዘክረው ከኋላ ቀሩ የፊውዳል አገዛዝ ነፃ ለመውጣት (በትክክል ወዴት ያመራ እንደነበር መናገር ባይቻልም) የመጀመሪያ አብሪ ጥይት የተተኮሰችው የ1953ቱ የእነ ጄኔራል መንግስቱና ገርማሜ ንዋይን የመፈንቅለ-መንግስት ሙከራ በተደረገበት ዕለት ነው፤ አቤት! እርሱን ተከትሎ የተሻለ ንቃት ያለው ኢትዮጵያዊ በሙሉ ‹‹ሕዝባዊ መንግስት›› ለመመስረት ያሳየው እንቅስቃሴ! የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለዓመታት የሞቱለት፣ የተጋዙለት፣ የተደበደቡለት፣ የተሰደዱለት… ሰላማዊ ትግል እና ያነሷቸው ጥያቄዎች ጆሮዬ ላይ ደጋግመው አስተጋብተዋል፡፡ በወቅቱ የዘውዳዊ ስርዓት ገበሬዎች፣ ተማሪዎች፣ ሰራተኞችና ልዩ ልዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተቃውሞአቸውን በሰላማዊ መንገድ አሰምተው፣ በሰላም ወደ ቤታቸው እንዲገቡ የነበረውን ትዕግስት አሁን ካለው ሁኔታ ጋር ባነፃፀርኩት ቁጥር እንደ አዲስ እደመምበታለሁ፡፡ ንጉሳዊውን ስርዓት በመቃወም ተደጋጋሚ ሰልፎች ላይ ይሳተፉ የነበሩት እና ዛሬ ለድል የበቁት የቀድሞዎቹ ተማሪዎች፣ የአሁኖቹ ገዥዎች የትምህርት ነፃነትን ከመርገጣቸውም በላይ ቅሬታ በተነሳ ቁጥር የተማሪዎች መኝታ ቤት ድረስ በመዝለቅ ደም ማፍሰሳቸውን ሳስብ፤ ለተቃውሞ አደባባይ የሚወጡ ንፁሃን ላይ ከውሃ ይልቅ ጥይት ማዝነብ የሚቀናቸውና ተቃዋሚዎቻቸውን በውሸት ድሪቶ ዘብጥያ የሚያወርዱ አምባገነኖች መሆናቸውን ሳስብ የማይፈታ እንቆቅልሽ ይሆንብኛል፡፡

ዘውዳዊ ስርዓቱን የተቃወሙ ሰዎች ከነገስታቱ በላይ ከዘመን ጋር የማይዘምኑ፣ ከአፈሙዝ ጋር የተጋቡ እንዴት ሊሆኑ ቻሉ? የሚል ጥያቄ አነሳለሁ፡፡ የምናብ ፈረሴ ኢትዮጵያውያን ወደዚህ ዓለም በመጣሁበት ሰሞን ከነበረው የጭቆና አገዛዝ ነፃ ለመውጣት አልመው ወደ ከፋ የአምባገነንነት ገደል የወደቁበትን የእልቂትና የዋይታ አብዮት እየደጋገመ ያስቃኘኛል፡፡ በተፋላሚዎች መካከል የርዕዮተ-ዓለም ልዩነት ባይኖርም አፈ-ሙዝን በአፈ-ሙዝ ለማሸነፍ የተደረገው ደም መፋሰስና ወንድም በወንድሙ አስከሬን ላይ ቆሞ የፎከረበት የእርስ በርስ ጦርነትም ሌላኛው እረፍት የሚነሳው ጉዳይ ነው፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ የግፍ ቋት የነበረውን ደርግ በኢትዮጵያ ሕዝብ ድጋፍ አሸንፎ በድል አድራጊነት ወደ ምኒሊክ ቤተ-መንግስት ሲገባ ሌላ የግፍ ቋት ይሆናል ብለው ያልጠበቁ አያሌዎች ነበሩ፡፡ ረጅሙ የመከራ ሌሊት መልሶ ላይጨልም ነግቷል ብለው ለተሻለ ነገር የተዘጋጁ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ትንሽ የሚባል አልነበረም፡፡ በአሁኑ አገዛዝ ከቀደሙት ህገ-መንግስታት የተሻለ ህገ-መንግስት ቢፀድቅም ቃልና ተግባር ሳይገናኙ ይኸው 22 ዓመታት አልፈዋል፡፡

እነሆም የሌላ ዙር የአፈና ሰለባ ሆኜ ወደምማቅቅበት እስር ቤት የምናቤ ፈረስ መልሶ አደረሰኝ፡፡ ሌላ ዙር እስር፣ ሌላ ዙር አፈና፣ ሌላ ዙር የህፃናት ለቅሶ፣ ሌላ ዙር የወላጆች ሰቆቃ፣ ሌላ ዙር ውርደት፣ ሌላ ዙር የአጤዎች ቀረርቶ፣ ሌላ ዙር የህዝብ እንባ፣ ሌላ ዙር… ባለንበት መርገጥ ቀጥለናል፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ የከበረና ከፍ ያለ መስዋዕትነት በመክፈል የዳር ድንበር ነፃነቱን ማስከበር ቢችልም በአገሩ ሰብዓዊ ክብሩንና ነፃነቱን ከራሱ ገዢዎች አስከብሮ መኖር የቻለበት ዘመን የለም፡፡ አንዴ ሞቅ ሌላ ጊዜ ቀዝቀዝ እያለ የቀጠለው የኢትዮጵያ ህዝብ የነፃነት ትግል በድቅድቁና ዝናባማው የሐምሌ ጨለማ የምትወጣውን ‹‹ጨረቃ›› ይመስላል፡፡ በተለይ የኤሌክትሪክ ብርሃን በሌለበት የገጠሩ የሀገራችን ክፍል የልጅነቱን የመጀመሪያ ዓመታት እንደእኔ ላሳለፈና የኢትዮጵያን የፖለቲካ ትግል በአንክሮ ለተከታተለ ሁሉ ስርዓቱና ጨረቃዋ የአንድ አባት ልጆች ይሆኑበታል፡፡ የሐምሌ ወር ጨለማ ጥቁር ነው፡፡ እንደግድግዳ ፊት ለፊት ቆሞ ነፍስን ያስጨንቃል፡፡ ጫፉ የማይታይ የጥላሸት ቁልል ይመስላል፡፡ ከጨለማው መደቅደቅ የተነሳ በቅርብ እርቀት ያለ ቁስን እንኳን ለመለየት የሚያስችል ብርሃን የለም፡፡ ወደሰማይ ለሚያንጋጥጥም በጥቁር የደመና ከል የተጋረደ ነው፡፡ በዚህ መሃል ግን ህልቆ መሳፍርት ለሌላቸው ዘመናት የሐምሌ ወርን እየጠበቀች እየደጋገመች የምትወጣው ጨረቃም ወቅቷን ጠብቃ መውጣቷን አላቋረጠችም፡፡ ከአንድ ጥቁር የደመና ኮረብታ ወደሌላው ስትወረወር ለቅፅበት ትንሽ ብርሃን ብትፈነጥቅም ምድሩን እንደቡልኮ የሸፈነውን ድቅድቁን ጨለማ ሰንጥቆ ለማለፍ የሚችል የብርሃን ፍንጣቂ በመልቀቅ የጨለማውን ሀይል መግፈፍ የሚችል አቅም የላትም፡፡ እንዲያውም በብርሃን ጅረት የተሞላው መላ አካሏ በጨለማው ፅልመት ጠልሽቶና ከጨለማው ጋር ተመሳስሎ ይታያል፡፡ የሐምሌ ጨረቃ ወይ ድቅድቁን አትገፋ፣ ወይም የሐምሌን ወር አትዘል በየዘመኑ፣ በየአመቱ ፍሬ አልባ ዑደቷን ቀጥላለች፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግልም እንዲሁ፡፡ እንደ ሐምሌ ጨረቃ ሁሉ የኢትዮጵያ ሕዝብም የሀገሩን የህላዌ እድሜ ያህል ከጭቆናው ሌሊት ጋር በየወቅቱ ግብግብ ይገጥማል፡፡ በተለይም ከ1953 ዓ.ም ወዲህ ያሉት 50 ዓመታት ህዝባችን ከአብራኩ ከወጡ አምባገነን ገዥዎች መዳፍ ነፃ ለመውጣት ተደጋጋሚ ትግል አድርጓል፡ ፡ አሁንም እያደረገ ነው፡፡ ይሁን እንጂ የሰብዓዊ ልዕልናው ባለቤት ለመሆን የሚያስችለውን የተጠና፣ በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት የሚመራና ህዝብ የራሱ ያደረገው የፀና ሰላማዊ ትግል በማድረግ ለውጤት አልበቃም፡፡

ለምን? በረጅሙ የሀገራችን ታሪክ የሀገርን ዳር ድንበር ማስከበርን የመሳሰሉ ገንቢ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ፣ ፍልስፍናዎች ማዳበር የመቻላችንን ያህል፤ በሌላ መልኩም አሉታዊ የሆኑ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ስነ-ልቦናዊ ፍልስፍናዎች እንዳዳበርን መረዳት ይቻላል፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች ፖለቲካዊ መስተጋብራችን የተፋለሰ እንዲሆን አስተዋፆ አድርገዋል፡፡ በተለይም ከዘመነ-መሳፍንት በኋላ ያለውና በዚያ ዘመን የፖለቲካ ብሒል የተቃኘው ፖለቲካዊ ፍልስፍናችን ከምህዋሩ የወጣ ነው፡፡ በአመዛኙ በፍርሃት፣ በአድርባይነትና በጊዜያዊ ጥቅም የተለወሰ ፍርሃት፣ የማያምኑበትን መናገር፣ በአርምሞ ማሳለፍ፣ ያልሆነውን ሁነን መታየት፣ ነገሮችን በሚስጥር መያዝ፣ ተጠራጣሪነትና በውል ባልታሸ ሁኔታ እራስን ማዕከል ያደረገ አስተሳሰብ ማራመድ የመሳሰሉትን ለአብነት ያህል ማንሳት ይቻላል፡፡ በየዘመኑ የሚነሱ አምባገነኖችና የጎበዝ አለቆች ጥላ ስር ለመጠለል መሞከር እነርሱን አይነኬ አድርጐ መቁጠር እራስን ፍፁም አቅመ-ቢስ አድርጐ መረዳት ለገዥዎች ማሸርገድና ቅዳሴ-ማህሌት መቆም አያሌ ኢትዮጵያውያን በየዘመኑ እንደ ፖለቲካ-ጥበብ የሚቆጥሩት አካሄድ ነው፡፡ ይህም ሁሉ በጥልቅ አስተሳሰብና ከዚያም በሚመነጭ እምነት ላይ ቢመሰረት ችግር አልነበረውም፡፡ የተሳሳተ እምነት በማንገብ የጨለማ አገዛዞችን የነፃነት ንጋት ናቸው ብለው የሚዘምሩ፤ በረሃብ ስንሞት በቁንጣን ነው ብለው ሊያሳምኑን የሚዳዳቸው፤ የአገዛዞች ዋልታና ማገር የሆኑ ኢትዮጵያውያንን በየዘመኑ አይተናል፡፡ እያየንም ነው፡፡

ከዘመናት የአፈና አገዛዝ ነፃ ልንወጣ ይገባናል ብለን የምንታገል ወገኖች እንደመኖራችን ሁሉ፤ አገዛዙ የፀሐይ መውጫ ምኩራብ ነው ብለው የሚያምኑ ወገኖች እምነታቸውን ያራምዱ ዘንድ መብታቸው ነው፡፡ ከስሜታዊነት በፀዳ መልኩ ጨለማው በእርግጥም ጨለማ መሆኑን አይኖቻቸውን ገልጠው እንዲያዩና እንዲመለሱ ማድረግ ይገባል፡፡ ሞታችን ከጨለማው ጋር ነው ብለው በጨለማው አካልነታቸው መቀጠል የሚፈልጉ ከሆነ ደግሞ ታግሎ ማሸነፍና እነርሱም ከጨለማ ነፃ እንዲወጡ ማድረግ ነው፡፡ ከባዱ የቤት ስራና እስከአሁንም ነፃነት ከእኛ እንዲርቅ ትልቁን አስተዋፆ እያበረከተ ያለው ከፍተኛ ቁጥር ያለው ‹‹መሃል ሰፋሪው›‹› ኢትዮጵያዊ ይመስለኛል፡፡ እውነቱን ለመናገር በፖለቲካ ትግል ባሳለፍኳቸው ጥቂት ዓመታት ከባዱ ፈተና የገጠመኝ ከቤተሰቤ፣ ከወዳጆቼና ከቅርብ ጓደኞቼ ነው ብል ማጋነን አይሆንም፡፡ እነዚህ ወገኖች ፖለቲካ ውስጥ ገብቼ ከአገዛዙ ጋር ግብግብ ከመግጠም ይልቅ አንገቴን ደፍቼ ልጆቼን እንዳሳድግ ምክራቸውን በተደጋጋሚ ለግሰውኛል፡ ፡ ለነገሩ ትዳር ባልያዝኩበት፣ ልጆች ባልነበሩኝ ወቅትም ‹‹አርፈህ ተቀመጥ!›› የሚለው ምክራቸው አልተለየኝም ነበር፡፡ ትግል ውስጥ እንዳልገባ የሚሰጡኝ ምክንያቶች ሁለት ናቸው፡፡ የሀገራችን ፖለቲካ በደም መፋሰስና በሸፍጥ የተሞላ መሆኑ አንደኛው ሲሆን በተጨማሪም ከኢኮኖሚ አዋጭነት አንፃር ፖለቲካ ፈፅሞ የማይመከር መሆኑን ያስረዱኛል፡፡ በመሆኑም አንገቴን ደፍቼ፣ ገዥዎች ወደአጋዙኝ ተግዤ እንድኖር፤ ልጆቼንም እንዳሳድግ ምክራቸውን ለግሰውኝ ነበር፡፡ አሁን እንኳን በእስር ላይ እያለሁ እንደሳይቤሪያ ብርድ አጥንትን ሰብሮ የሚገባና ነፍስን የሚወጋ ምክራቸውን ይልኩልኛል፡፡ ‹‹ነግረነው አልሰማንም››፣ ‹‹ህፃናት ልጆቹን ያለአባት ትቶ እንዴት ይታሰራል?›› ይላሉ፡፡ አንዳንዶቹ ከመበሳጨታቸው የተነሳ የመጐብኘት መብቴ ቢከበር እንኳን ሊጐበኙኝ እንደማይፈልጉ ይናገራሉ፡፡ ወንጀልሰርቼ እንዳልታሰርኩ፣ ለመስራትም እንደማላስብና ሰላማዊ የትግል ስልትን የሃይማኖት ያህል እንደማምንበት ወዳጆቼም ሆኑ አሳሪዎቼ እኔ የማውቀውን ያህል ያውቃሉ ብል ያጋነንኩ አይመስለኝም፡፡

ያም ሆኖ ግን ወዳጆቼ ስርየት እንደሌለው ሃጢያት፣ የአገዛዙ ዋናዎችም የሰማይስባሪ እንደሚያክል ወንጀል የቆጠሩት የተቃውሞ ፖለቲካ ጐራ መቀላቀሌን፣ በሀገሬ አንገቴን ቀና አድርጌ በመራመዴና የማምንበትን በቀጥታ በመናገሬ ነው፡፡ አገዛዙም ይኽን አይነት በፍርሃት የተሸበበ ማህበረሰብ እንዲፈጠር ይፈልጋል፤ ወዳጆቼም አገዛዙ በግፍ ስላሰረኝ የነቢይነት ደረጃቸውን በመደመምያስባሉ፤ እርስ በእርሳቸው ይመጋገባሉ፡፡ የትችት ጦራቸውን እስር ቤት ድረስ የሚወረውሩት አብዛኞቹ ጓደኞቼ በታላላቅ ዩኒቨርስቲዎች የተማሩና የሚያስተምሩ፣ በመደበኛ ትምህርት ልህቀታቸው በሊቀ- ጠበብትነት ጐራ የሚሰለፉና ይህች ደሀ አገር ከውስን ጥሪቷ ቆንጥራ ያስተማረቻቸው ናቸው፡፡ የሆነ ሆኖ ዛሬ ወዳጆቼ ያሉት ደርሶብኛል፤ ትንቢታቸው ሰምሯል፡፡ አዎ! ልጆቼ በድንገት ከቤት ወጥቶ እስከአሁን ወደቤት ስላልተመለሰው አባታቸው በህፃንነት የአእምሮ ጓዳቸው ውስጥ እያንሰላሰሉና እየተጐዱ መሆኑን በሚገባ እረዳለሁ፡፡ በተለይ ልክ የታሰርኩ እለት የትምህርት ቤትን ደጃፍ የረገጠው የልጄ የሩህ ጥያቄዎች ከዕለት ወደ ዕለት እየበረከቱ መጥተዋል፡፡ ‹‹ማሚ፣ እኔ አባት የለኝም እንዴ?››፣ ‹‹አባባ መቼ ነው ቤት የሚመጣው?››፣ ‹‹የአንተ ስራ መቼ ነው የሚያልቀው?›› የሚሉ ናፍቆት ያንገበገባቸውን ጥያቄዎች ያነሳል፡፡

እኔ የምከፍለው ዋጋ ይቅርና ልጆቼም በውል በማይረዱት ነገር ትልቅ ዋጋ እየከፈሉ መሆኑን በጥሞና እገነዘባለሁ፡፡ ቀድሞውንም ያልጠበኩትም አልነበረም የሆነው፡፡ ግና! በልጆቼ ሰብዕና ላይ የከፋ ስብራት እንዳይደርስ እውነተኛ ፈራጅ ወደሆነው ፈጣሪ ከመፀለይ በቀር ምን ማድረግ ይቻለኛል? ይህችን ምድር ለመጀመሪያ ጊዜ የተቀላቀለው በእስር ቤት ነው፤ ይኸው አሁን ደግሞ ባልጠኑ እግሮቹ፣ ክፉ ደግ ባለየ ህሊናው ከሚያፈቅረው አባቱ ተለይቶ በባዕድ ምድር የፖለቲካ ስደተኛ ሆኖ የሚንከራተተው የናፍቆት እስክንድር ነጋ ህይወት ለዚህ የበቃው አባቱ እንደኔ የወዳጆቹን የአርምሞ ጥያቄ ባለመቀበሉ ጭምር ነው፡፡ አባታቸውን ተመላልሰው መጠየቅ በማይችሉበት እርቀት ላይ የታሰረባቸው የናትናኤል መኮንን ልጆች እንባም ሰብዓዊ ፍጡርን በተለይም የወላጆችን ልብ ምንኛ እንደሚሰብር ግልፅ ነው፡፡ ከሚያስተምርበት አዲሰ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ ከግቢ ውጭ እንደሚፈለግ በስልክ ሲነገረው የጠመኔውን ብናኝ ከእጁ ላይ አራግፎ የወጣው የኦሮሞ ፌዴራሊስ ኮንግረስ /ኦፌኮ/ ም/ሊቀመንበር በቀለ ገርባ ‹‹የኦነግ አባልና የፌደራላዊ አገዛዙን በኃይል ማስገንጠል አሲረሀል›› በሚል ክስ ተፈርዶበት ከህፃናት ልጆቹ ተለይቶ በዝዋይ እስር ቤት የግፉን ፅዋ እየተጎነጨ ነው፡፡ በእርግጥ አቶ በቀለም እንደ እኛ አርፎ ልጆቹን እንዲያሳድግ ተነግሮት ነበር፡፡ ሌሎች አያሌ ኢትዮጵያውያንና ልጆቻቸውም ተመሳሳይ የመከራ ህይወት እየገፋ ይገኛሉ፡፡ ልጆቻችንና የትዳር አጋሮቻችን እየከፈሉ ያሉት ዋጋ እኛ በእስር ቤት ከምንከፍለው የከፋ ይመስለኛል፡፡

ለጓደኞቼና ለወዳጆቼ የማነሳላቸው ጥያቄዎች ይኖሩኛል፡፡ ነፃነት አልቦ ህይወት ምን ምን ይላል? ለመሆኑ ነፃነትን በገዥዎች ችሮታ የተጐናፀፈው የየትኛው ሀገር ህዝብ ነው? በየትኛው ክ/ዘመን ይሆን? …አባቶቻችን ዳር ድንበራቸውን ለማስከበር ልጆቻቸውን፣ ሚስቶቻቸውንና ዘመድ አዝማዶቻቸውን ከኋላቸው ጥለው ወደ አድዋ መዝመታቸው ስህተት ነበር እያላችሁን ይሆን? ቴዎድሮስ በመቅደላ፣ ዮሐንስ በመተማ ለሀገር ክብር መውደቃቸው ትርጉም የለሽ ነበር ማለት ነው? ሌሎች አባቶቻችንስ በጉራ፣ በጉንደት፣ በማይጨው እና በአያሌ የጦር አውድማዎች ለሀገር ክብር እንደወጡ ሲቀሩ የሚናፍቋቸው ሚስቶችና የሚሳሱላቸው ህፃናት ልጆች ያልነበሯቸው ይመስሏችኋል? አሉላ አባ ነጋ እስከ እርጅና ዘመኑ ድረስ ለሀገሩ ዳር ድንበር አጥር ሆኖ ጣሊያንና ግብፅን በማስጨነቅ ዛሬ የምንኮፈስበትን ታሪክ ማጐናፀፉ ስህተት ነበር እያላችሁ ይሆን? የእነ በላይ ዘለቀ፣ የእነ አብዲሳ አጋ፣ የእነዘርአይ ደረሰ፣ የእነ ራስ ደስታ ዳምጠው፣ የእነ አቡነ ጴጥሮስና የሌሎችም ስመ-ጥር ጀግኖቻችን ውሎ በከንቱ ጀብደኝነትና ግብታዊነት የተሞላ ነበር ማለት ነው? እነዚህ ጀግኖች የሀገራቸውን ዳር ድንበር ክብር ለማስጠበቅ ከቀያቸው ርቀው ሲጓዙ ሞትን ከፊት ለፊታቸው እያዩት የቆሙለት እውነት አመዝኖባቸው እንደነበር ዘንግታችሁት ይሆን? አባቶቻችን በየተራራውና ኮረብታው ስለሀገር ክብር ባይቀበሩ ኖሮ የዛሬዋን ኢትዮጵያ ማግኘት የምንችል ይመስላችኋል? ወይስ የዳር ድንበር ነፃነት ከተከበረ፣ ዜጐች በጭቆና ቀንበር ቢማቅቁ ምንም ክፋት የለውም እያላችሁ ነው? ወይስ ጭቆና ከአብራካችን በወጡ ሰዎች እስከሆነ ድረስ እንደክብር ይቆጠራል እያላችሁ ነው? የሀገርን ዳር ድንበር ለማስከበር የተከፈለው ዋጋ ጠጋ ብለን ስናየው የህዝብን መሰረታዊ የሉዓላዊነት ጥያቄ እንደሚያነሳ ሳታችሁት? አባቶቻችን ለሀገር ነፃነት የከፈሉት ዋጋ ተገቢ አልነበረም ካላላችሁ በስተቀር ለዜጐች ሉዓላዊነትና ለዕውነተኛ ዴሞክራሲያዊ መንግስት መታገል ስህተት ሆኖ የሚገኘው በምን ቀመር ነው? በዩኒቨርስቲዎች ስለ- ሰብዓዊ ፍጡር ልዕልና የምትማሯቸውና የምታስተምሯቸው ትምህርቶች ‹ነፃነት›ን በተመለከተ ምን ነበር ያሏችሁ? ወይስ ዲሞክራሲና ነፃነት ለእኛ ሀገር አይሰራም እያላችሁ ነው? የጥቁር ህዝብ ኩራት የሆነውን የአድዋን ድል ያስመዘገቡ አባቶች ልጆች ሉዓላዊነታችን ከገዥዎቻችን መዳፍ ነጥቀን ማስከበር ካልቻልን ‹የእሳት ልጅ አመድ› መሆን አይመስላችሁም? ሌላው ቢቀር ኢትዮጵያ የቅኝ ግዛትን ቀንበር እንዲሰብሩ የረዳቻቸው የአፍሪካ አገሮች በዴሞክራሲ ጐዳና በርቀት ጥለውን ሲተሙ፤ የእኛ በጭቆና አረንቋ ውስጥ መዳከር እንዴት ቁጭት አይፈጥርባችሁም? ወይስ የእናንተ ድርሻ ትችትና ታዛቢነት ብቻ ነው? እነዚህ ከፍ ብዬ ያነሳኋቸው ጥያቄዎች ለምወዳቸው ጓደኞቼ ብቻ ሳይሆን ‹‹የመሃል-ሰፋሪነት›› ሚና ለመረጡ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ ሁሉ የተሰነዘሩ ናቸው፡፡

ኢትዮጵያውያን በፖለቲካ ባህላችን ውስጥ ያሉ ሸንኮፎችን አስቀድመን መግረዝ ካልቻልን፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ትግል እንደ ሐምሌዋ ጨረቃ አሁንም በከንቱ ብቅ ጥልቅ ከማለት የዘለለ ፋይዳ አይኖረውም፡ ፡ ምናልባት የሀሳባችሁ ማጠንጠኛ ባለፈው ግማሽ ምዕተ-ዓመት ማሳካት ያልተቻለው እንዴት አሁን ይቻላል? የሚል ከሆነ ይኸንን ጥያቄ ማንሳት፣ ለጥያቄውም መልስ መስጠትና በመልሱም ላይ ተመስርቶ በእውነተኛ ነፃነትና ህዝባዊ ልዕልና ላይ የተመሰረተች ኢትዮጵያን ለመፍጠር መታገል እንደሚያስፈልግ መተማመን ላይ መድረስ ይጠበቅብናል፡፡ የተወሰኑ ጥያቄዎችን አክዬ ላንሣ፡ ፡ ሁሉም የግል ጥቅሙንና የአብራኩን ክፋዮች ብቻ በሚያስቡባት ሀገር እንዴት ህዝብ ከአገዛዝ ነፃ ሊሆን ይችላል? በየማጀቱ አገዛዙን በመርገም ነፃ መውጣት ቢቻል ኑሮ ከረጅም ዘመናት በፊት ነፃ አንወጣም ነበር ትላላችሁ? አባቶቻችን ለነፃነት መስዋዕት መሆናቸው ትክክል ነበር የምትሉ ከሆነ የስብዕና መሰረትና የነፃነቶች ሁሉ የበላይ ለሆነው የሰብዓዊ መብት መታገል ትክክል የማይሆንበት አሳማኝ ምክንያት ምንድን ነው? ከገዥዎች መዳፍ ለመውጣት አሳማኝ ምክንያት ምን ሊሆን ይችላል? ይኽን ከገዥዎች መዳፍ ለመውጣት የሚደረግን ትግል እንዳላየን አይተን ብናልፍ ለሁላችንም የማይቀረው ሞትን ተጋፍጠን ወደመቃብር ስንወርድ በምን አይነት ክብርና የህሊና እረፍት ማሸለብ እንችል ይሆን? የዘወትር ህልማችን ሰብዓዊ ልዕልናችን ተጠብቆ የምንኖርበትንና ልጆቻችን የማያፍሩበትን ሀገር ማውረስ ሆኖ ሳለ የአገዛዙን የጭቆና አርጩሜ በመፍራት ከእምነታችን ውጭ የሆኑ ተግባሮችን ስንፈፅም የምንበጀው እስከመቼ ነው? ለዘመናት እላያችን ላይ ቤት የሰራብንን የጭቆና ቀንበር መስበር በረጅሙ የኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ያልተከወነ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲንከባለል የመጣ የቤት ስራ ነው፡፡ በውዝፍ ያደረ ቁምነገር ከቅርሶቻችን ሁሉ የገዘፈና የታሪካችን ፈርጥና የማንነታችንም መደምደሚያ ነው፡፡ በዚህ የሰብዓዊ ልዕልና ጉዳይ ላይ መታገል ሰው የመሆንና ያለመሆንን ጥያቄ መመለስ ነው፡፡ በነፃነት አለመታገል የቤት ስራውን ለልጆቻችን ወዝፎ ማሳደር በጭቆና ቀንበር ለመገዛት ህዝበ ውሳኔ የመስጠት ያህል ይቆጠራል፡፡ በሌላ በኩል ነፃ ለመውጣት እንደቀድሞ ነፃ አውጭ አበጋዞችን መጠበቅ አይገባንም፡፡ ይኽን የምናደርግ ከሆነ ሰማያችን በጭቆና ደመና እንደተሸፈነ ይቀጥላል፡፡ ጥቂቶችን አንጋጠን ስንጠብቅ በውስጣችን ያለውን ትልቅ የነፃነት ሃይል እንዳናይ ግርዶሽ ይሆንብናል፡፡

ይኽን በመሰለው የነፃነት ትግል የሚጀምረው የራስን የከረመና የተሳሳተ ፖለቲካዊና ማህበራዊ አስተሳሰብ ከመሞገት ነው፡፡ ከዚያም ከፍ ሲል እንደ ፖለቲካ ባህልና የብልህነት ቁንጮ በመውሰድ ለህፃናት ልጆቻችን ሳይቀር በምክር መልክ የምንለግሳቸው ልዩ ልዩ ያልተሰለቀቁ አሉታዊ አስተሳሰቦችን በቅድሚያ ታግሎ መጣል ያስፈልጋል፡፡ እያንዳንዱ ስለሁሉም ፤ሁሉም ስለእያንዳንዱ ግድ በማይሰጠው ሀገር ውስጥ አምባገነኖች የሚዘውሯቸው አገዛዞች መኖራቸው የግድ ነው፡፡ በዚህ ዘመን ስለነፃነት ክብርነት ለማንም ማስረዳት እምብዛም አይጠበቅብንም፡፡ ነፃነት እንደ እንጉዳይ በየዛፉ ስር ያለትልቅ መስዋዕትነት በቅሎ የሚገኝ አይደለም፡፡ ይኸንን የነፃነትን ውድነት ስንረዳ የሀገርን ዳር ድንበር ለማስከበር እንደዘመቱት አባቶቻችን ሁሉ ያለነፃነት ከመኖር ይልቅ ህፃናት ልጆቻችን ጥለን፣ ከሞቀ ቤታችን ወጥተን በእስር ቤት የሲሚንቶ ወለል ላይ መጣልን እንመርጣለን፡፡ በነገራችን ላይ ደጋግሜ ከምጠቅሳቸው ጀግኖች ጋር እራሴን እያወዳደርኩ አለመሆኑን አንባቢዎች ልብ እንድትሉልኝ እወዳለሁ፡፡ በታሪክ ኮረብቶች ላይ ከድንቅ የጀግንነት ውሎዎቻቸው ጋር ከፍ ብለው የሚታዩ ጀግኖች ጫፍ የሚደርስ አንዳች ስራ እንዳልሰራሁ ጥሩ አድርጌ እገነዘባለሁ፡፡ አላማዬ የዳር ድንበርን ሉዓላዊነት ከሰብዓዊ ሉዓላዊነት ጋር ማነፃፀር ነው፡፡

ሌላው የአገር ውስጥ ገዥዎችንን እንዴት ከውጭ ሀገር ወራዎች ጋር ያነፃፅራል? የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡ ሁለቱም የዘመቱት በነፃነታችንና ሰብዓዊ ክብራችን ላይ ነው፡፡ የነፃነት ትርጉም ከሀገር ልጅነትም በላይ ነው፡፡ በሰላማዊ ትግል መንገድ ስንጓዝ ትግላችን ጨቋኝ ወንድሞቻችን ወደልባቸው እንዲመለሱና ሁላችንም በነፃነት የምንኖርባትን የጋራ ሀገር እውን እንድትሆን ከማድረግ ጋር ነው፡፡ ከዚህ በዘለለ እንዲታመሙና እንዲሞቱ አይደለም ፡፡ በእኛና በልጆቻችን ላይ እያደረሱት ያለው በደል በእነርሱም ላይ እንዲደርስ ፈፅሞ የምንመኘው ነገር አይደለም፡፡ ነ ፃነትን ከውጭ ሀገር ወራሪም ሆነ ከሀገር ውስጥ ጨቋኝ መጠበቅ መቼም በይደር የሚያዝ ተግባር አይደለም፡፡ ስለሁላችን ነፃነትና ሉዓላዊነት የተዘረጋ የተማፅኖ ቃል እንጂ፡፡ በሀሰት ‹‹አሸባሪ›› ተብለን ዘብጥያ ብንወርድም ትግሉን ከመቀጠል ውጭ ሌላ አማራጭ የለም፡፡ ነፃነትን መጠየቅና መታገል ነፃነቱን የተጠማ የነፃነት ታጋይ ሁሉ ድርሻ መሆን ይኖርበታል፤ ይሁንና የናፈቃችኋትን ነፃነት አታገኟትም ብለው ወህኒ መወርወር የአፋኞች የአፈና ተግባር ቢሆንም መንበርከክ ለከፋ መከራ፣ ለበረታ ጭቆና ከማገለጥ ውጪ ትርፍ አልባ ነው፡፡ የአሁኖቹ ገዥዎች እንደ ቀድሞዎቹ ሁሉ የተሳሳተ የፖለቲካ ባህላችን ያበቀላቸው መሆኑን መረዳት ይገባል፡፡ የፖለቲካ ባህላችንና አስተሳሰባችን ካልተቀየረ እንደ እስከ አሁኑ ሁሉ ሌሎች አምባገነኖችንም ማብቀሉን ይቀጥላል፡፡

በአምስት አመት ውስጥ ማዕከላዊ እስር ቤት ሁለት ጊዜ ስታሰር፤ ሃላፊዎች ተለዋውጠው ባገኛቸውም የሁለቱም ዋና ኃላፊዎች ቃልና ተግባር ግን ትንሽ እንኳ ልዩነት አልነበረውም፡፡ በሚገርም ሁኔታ ሁለቱም እንዳገኙኝ የጠየቁኝ አንድ አይነት ጥያቄ ነበር፡፡ ‹‹ወንድ ከሆንክ ለምን ጫካ አትገባም?›› የሚል፡፡ ወንድነት ማለት አፈ-ሙዝን፤ በማይናወጥ የፍቅርና የወንድማማችነት መንገድ መጋፈጥ፤ ተጋፍጦም ሳይገሉ መሞት ነው ወይንስ በራሳችን ጥላ ሳይቀር እየደነበርን ንፁሃንን መግደል? የሚገርመው እኮ ለአፈ-ሙዝ ፍልሚያ የጥሪ ካርድ የሚበትኑት ወገኖች የደሃ ኢትዮጵያውያን ወንድማማቾችን ደም ለማፍሰስ እንጂ እነርሱማ ከመኪና ተደግፈው ለመውረድ ምንም የማይቀራቸው ናቸው፡፡ አንዳንድ በተለይም የአገዛዙ ዋነኛ ሰዎች ይችን ሀገር ለሁላችን ወደሚበጅ ንጋት ይዘዋት ለመውጣት እድሉን ለዓመታት ቢያገኙም ሊጠቀሙበት አልቻሉም፡፡ ይልቅስ እብሪት የሁለንተናቸው ማጠንጠኛ ምህዋር ሆኖአል፡፡ አንዳንዶቹን በጨረፍታ በማየት ለወንድማማችነትና የኢትዮጵያን የባጁ ችግሮች ለመፍታት በጐ አስተዋፆ ሊያደርጉ ይችሉ ይሆናል፣ ሕዝብን እንኳን ባይፈሩ ፈጣሪን ይፈሩ ይሆናል ብለን ተስፋ ብናደርግም ሁለቱንም እንደማይፈሩና የኢህአዴግ ዋና ሰዎች መለያ የሆነውን እብሪትና ሃኬት የሙጥኝ ብለው መንጐድ ቀጥለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ታሪክ አገዛዞች ከዚህ የተለየ ሲያደርጉ አልታዩም፡፡ ይኸኛው አገዛዝ ከቀድሞዎቹ ለመለየት የሚሞክረው በእውነት ላይ ያልተመሰረተ የፕሮፓጋንዳ ደመራ በማቀጣጠል ነው፡፡ የፕሮፓጋንዳ ደመራው ህዝቡንም ሆነ አገዛዙን በብርሃን እንዲመላለስ አላደረገውም፡፡ ሊያደርገውም አይችልም፡፡ አገዛዙም ሆነ ህዝቡ ከፍርሃትና ከጨለማ ጉዞ ነፃ ሊወጣ የሚችለው የእውነት ችቦ ለኩሶ ከዚያም በሚገኘው ብርሃን ዙሪያ ተሰባስቦ መወያየት ሲቻል ነው፡፡ ለዜጐች ሉዓላዊነት ክብር የሚሰጥ አገዛዝ ቢኖር የፕሮፓጋንዳ ደመራ አቀጣጥሎ በዙሪያው መጨፈር ባላስፈለገ ነበር፡፡ ምክንያቱም ተግባር ከቃላት በላይ ይናገራልና፡፡ የአገዛዙን አምባገነናዊ ባህሪዎችና ተግባሮች በመተንተን ከዚህ በላይ ጊዜ ልናጠፋ አይገባንም፡፡ ምንስ የማይታወቅ ነገር አለ? እንኳን የአፈናው ሰለባዎች ኢትዮጵያውያን ቀርቶ ዓለምም በቅጡ ተረድቶታል፡፡ አገዛዙ ለህዝብ ፈቃድ የሚገዛ ቢሆን ለመቃወም ከቤታችን መውጣት ባላስፈለገን ነበር፡፡

ትልቁ መፈተሽ ያለበት ጉዳይ ከ50 ዓመታት በላይ የአገዛዝ ስርዓትን ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዋር ለማስወገድ የተደረገው ጥረት፣ የተከፈለው የህይወትና የአካል መስዋዕትነት እንዴት እስካሁን ለፍሬ ሊበቃ አልቻለም? የሚለው ነው፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲዎች እስከ አሁን ቢያንስ ወደተሻለ ምዕራፍ ትግሉን ለማሸጋገር አልቻሉም? እስከ አሁን በተደራጁ የፖለቲካ ትግል ውስጥ ገብቶ ከመታገል ይልቅ በተለየና የራሳችን በሆነ መንገድ አስተዋፆ እናበረክታለን ብለን በተለያየ መስክ ተሰልፈን የምንገኝ ሰዎችም ምን ያህል አስተዋፆ አበረከትን? ብለን ራሳችንን መፈተሽ ይገባናል፡፡ ጊዜው በተግባር የማይደገፍና የተጠጋገኑ ምክንያቶችን በመደርደር ብቻ ከተጠያቂነት የምናመልጥበት አይደለም፡፡ ኢትዮጵያውያን የአፈናው ሰለባዎች መሆናችንን አለም በቅጡ ተረድቶታል፡፡ አገዛዙ ለህዝብ ፈቃድ የሚገዛ፣ የህግ የበላይነትን የሚያከበር ቢሆን ኖሮ ለመቃወም ከቤታችን መውጣት ባላስፈለገን ነበር፡፡ ትልቁ መፈተሽ ያለበት ጉዳይ ከ50 ዓመታት በላይ የአገዛዝ ስርዓትን ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዋር ለማስወገድ የተደረገው ጥረት፣ የተከፈለው የህይወትና የአካል መስዋዕትነት ዛሬም ለፍሬ ሊበቃ ያልቻለበትን ምክንያት ነው፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲዎችስ ስለምን ትግሉን ወደተሻለ ምዕራፍ ማሸገር ተሳናቸው? ዛሬም ድረስ የተደራጀ የፖለቲካ ትግልን ተቀላቅሎ ከመታገል ይልቅ በተለየና የራሳችን በሆነ መንገድ አስተዋፆ እናበረክታለን ብለን በተለያየ መስክ ተሰልፈን የምንገኝ ሰዎችም አበርክቶአችን ምን ያህል እንደሆነ ራሳችንን መፈተሽ ይገባናል፡፡ ጊዜው በተግባር የማይደገፍና የተጠጋገኑ ምክንያቶችን በመደርደር ብቻ ከተጠያቂነት የምናመልጥበት አይደለም፡፡ የነፃነት ጉዳይ ‹ለነገ…› ተብሎ በይደር የሚቆይ አይደለም፡፡

 

- See more at: http://www.fnotenetsanet.com/?p=5640#sthash.q1MeZSR5.dpuf

ሀሳብን አወላግዶ ትርጉም መስጠት ከሀሳብ ነጻነት ሊመደብ አይገባም (ሰመረ አለሙ)

$
0
0

ሰመረ አለሙ

ቀደም ሲል ዳግማዊ ጉዱ ካሳ በሚል ስም ለልጂ ተክሌ የጻፈዉን ከግምት በማስገባት እሱ በጠቃቀሳቸዉ ጉዳዮች ላይ መጠነኛ ግንዛቤ ለመስጠት ብእር መምዘዝ ግድ ብሏል።

Freedom of Speechበመጀመሪያ ደረጃ ጸሀፊዉ ቋንቋዉ ላይ ያለዉን የበላይነት ለመግለጽ እወዳለሁ (ሃሳቡን አላልኩም ልብ በሉልኝ)  ወረድ ብዬ ደግሞ ጽሁፉን በስሱ ሳጠናዉ ጽሁፉ በቀጥታ የተነጣጠረዉ ልጅ  ተክሌ ላይ  ሁኖ ዶ/ር ብርሀኑን አስመልክቶ ልጂ ተክሌ የዘገበዉ በእጅጉ እንዳበሳጨዉ ከጽሁፉ ለመረዳት ከመቻሉም በላይ የጉዱ ካሳ ጽሁፍ ሀሳብን በነጻነት መግለጽ ላይ የተመዘዘ ሰይፍ ነዉ ተብሎ ቢነገር ለክርክር አይዳርግም የሚልም አመለካከት አለ። ጉዱ ካሳ ዲማቶ ከመዉደቃቸዉ በፊት ዘሎ መሀል ገብቶ የቁርጥ ቀን ወዳጂ መሆኑንም አሳይቷል ለዚህም አድናቆት ይቸረዋል።

ብቻ ሲያመጣዉ አንዴ ነዉ የጉዱ ካሳንና፡የልጂ ተክሌን ጽሁፍ  ካነበብን በሗላ ደግሞ በጥሩ ኢትዮጵያዊ አቀራረብ ስለ ዶ/ር ብርሀኑ ሌላዉ እንደ ልጂ ተክሌ አንጀቱ የበገነ አንድ ጽሁፍ አስነበበን። አዎ ዶ/ር ብርሀኑ እና አቶ አንዳርጋቸዉ ሊሸፈኑ የሚችሉ ካለመሆናቸዉም በላይ ሊሸፈቱም ግድ ይላል ሁኔታዉን እስከዛሬ በቅርብም በሩቅም ስንከታተለዉ ነበር። መለሰ ዘራዊ በህይወት ቢኖር እና ቢፈልግ እነዚህን ሰዎች የሚፈልጉትን  ሰጥቶ ይመልሳቸዉ ነበር ይጠቅማሉ ብሎ ከገመታቸዉ ይህም ግለሰቦቹ ላይ ካለን ጥላቻ ሳይሆን የህይወት ታሪካቸዉን በሚገባ ከመበርበር የተወረወረ አስተሳስብ ነዉ።

ወደ ጉዱ ካሳ ሌላዉ ክፍል ስንሸጋገር ዶ/ር ብርሀኑ ስለ ዋሂቢሰቶቹ ያላቸዉን አመለካከት አስመለክቶ በመደገፍ “ኢትዮጵያዉስጥ የሸሪያ ህግ ተቋቁሞ ኢትዮጵያ የእስላም አገር ትሆናለች የሚል እብድ ነዉ” የሚለዉን የሀጂ ነጂብን ማረጋገጫ ሰጥቶናል። እዚህ ላይ ጉዱ ካሳ  እስላም ይሁን ሌላ  እርግጠኛ ባንሆንም  ይህን ማረጋገጫ አምነን  ዶ/ር ብርሀኑን እንድናምን የተፈለገበት ምክንያት ግን ግልጽ አይደለም። እዉነታዉ ግን ሓጂ ነጂብ በጣም ጥበበኛ እንደኛዉ አገላለጽ ደግሞ ጩሉሌ ብለዉ ሊጠሩ የሚገቡ ሰዉ ናቸዉ። ብዙ ንግግራቸዉን ባለፈዉ አምስት አመት ተከታትለነዋል አንዳንድ ስብሰባቸዉንም ተሳትፈናል። ሐጂ ነጂብ እስላሞች ስብሰባና ሌሎች ስብሰባዎች ላይ የሚያወሩት የተለያየ ሃሳብም ነዉ። የህዋትንም መንግስት እንደዛሬዉ ከመጣላታቸዉ በፊት መንግስታችን ነዉ በማለት ሙሉ ድጋፋቸዉን ሲሰጡ የነበሩም ሰዉ ነበሩ። የሀጂ ነጂብ ሚስት ወ/ሮ ዘይነብ ይባላሉ እሳቸዉ የተናገሩትን ሙሉዉን ቃልም ቀድተነዋል “ኢትዮጵያ የእስላም አገር ትሆናለች ማሺ አላህ; አቶ መለሰ ወደ እስልምና ቢመለሱ ይሻሎታል ኢትዮጵያ በሸሪያ ትተዳደራለች” ይላል ቅንጫቢዉ ከዚህም የባሰ አባባል ታክሎበታል። ወ/ሮ ዘይነብ እና ሀጂ ነጂብ አንድ ሀይማኖት አንድ እምነት አንድ የኢስላም አይዲዮሎጂ የሚጋሩ ባልና ሚስት ናቸዉ በየስብሰባዉም ተከታትለዉ የሚሄዱ ናቸዉ።የሚለያዩት ሐጂ ነጂብ እንዲህ ያለ ቋንቋ የሚናገሩት በእስላሞች ዝግ ስብሰባ ነዉ እነ ጁሀርን የመሳሰሉ ጸረ ኢትዮጵያ ሀይሎችን በክብር ሲጋብዙ።

በጉዱ ካሳ ጽሁፍ አቶ አንዳርጋቸዉ ተደጋግመዉ ተነስተዋል እዉነታዉ ግን አቶ አንዳርጋቸዉ ህወአት ሲደናብር እጅ እና እግር ቀጥለዉለት ነብስ ዘርተዉበት ተሸልመዉ ተሸኝተዉ የሚኖሩ ሌላዉ ጩሉሌ ሰዉ ናቸዉ። አቶ አንዳርጋቸዉ ሕወአት ኢትዮጵያን ሲወርር የፕሮፓጋንዳ ሀላፊ ሁነዉ የሰሩ የህወአት የቁርጥ ቀን ልጅ ናቸዉ እንዲህ ያለዉ ስልጣን ለትግሬዎችም ቢሆን ለመስጠት ደጋግሞ ማሰብን የሚጠይቅ ነበር ለትግሬዉ ድርጂት። ዶ/ር ብርሀኑን በተመለከተ የህወአት ልዩ አድናቂ ከመሆናቸዉም በላይ ለመለስ፤ ለበረከት ስምኦን ለሰየ አብረሀ ልዩ አመለካከት የነበራቸዉ ከመሆኑም በላይ ኢትዮጵየ በነበሩበት ጊዜ ከፕራይቬታይዜሺን ፕሮግራም ምን ያህል ሊያተርፉ እንደሚችሉ ሲያሰሉ የነበሩ  ግለሰብ ናቸዉ። ታዲያ ሁኔታዉ ይህ ሁኖ ሳለ እነ ጉዱ ካሳ  በ ኢቫንጀሊካን ሰበካ መንገድ ተጉዘዉ ኢሳትን፤ ከረንት አፌይርስን እና ሌሎች ደካማ የሚዲያ ተቋማትን በመጠቀም ግንቦት 7ን ከምንም በላይ አገዝፎ ለኢትዮጵያ አሳቢ አስመስሎ መሪዎቹ አንዳርጋቸዉ ጽጌና ብርሀኑ ኢትዮጵያን ካለችበት የሚያድኑ አድርገዉ አቅርበዉልናል። ይህ እንዴት ይተገበራል? ቀላል ነዉ ጸረ ኢትዮጵያን ሀይሎችን አስተባብሮ ኢትዮጵያ ላይ መዘመት (ኦነግ፤ኦብነግ፤ሻቢያ፤ግብጽ………………) እንግዲህ እነዚህ ሀይሎች ናቸዉ ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ ሊያደርጉ የሚችሉት ጎበዝ ተደፍረናል ትዉልዱን እያዩም መቀለጃ አድርገዉናል ቀደም ያለ ጊዜማ ቢሆን እንዲህ ያለ ቀልድ ለ አሳቢዉም ያስፈራ ነበር።

እንደእዉነቱ ከሆነ አንድን የሚዲያ ተቋም ተቆጣጥሮ እንደ ሂትለር ፕሮፓጋንዳ ህዘብን አደንዝዞ አማራጭ አሳጥቶ ህዘብን ዉዥምብር ዉስጥ መጨመር ለአንድ ህዝብ አማራጭ አይሆንም አለፍ ሲልም ወንጀል ይሆናል። ዛሬ ሁኔታዎች ተለዉጠዋል በኢትዮጵያ ስም ተቋቁመዉ ከላይ የተመለከትነዉን አይነት የተወላገደ አስተሳሰብ እኛ ዉሰጥ ፈጥረዉ የራሳቸዉን እቅድ ለሚያሳኩ ዜጎች ወገን ዞር በሉ ብሏል። ይህን ክስረት የተረዱ የዜና ድርጅቶችም ከሉበት ከፖለቲካ አቅዋም እና ትርፍ ሊያመጣልኝ ይችላል ከሚለዉ አመለካከት ተላቀዉ በመጠኑ በራቸዉን ከፍተዋል መሆንም ያለበት ይኸዉ ነዉ። ኢትዮጵያ ዉስጥ በሚደረገዉ እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ ጥቃት የሚመለከትን ዜጎች ሁሉ ያገባናል። አለም አቀፍ የፖለቲካ ተልእኮ ያለዉ የዋሃቢስቶች  እንቅስቃሴ በማጭበርበር ፖለቲካ ኢትዮጵያዉያንን ሲያምስ ይህ ነገር ሊታሰብበት ይገባል እያልን በጽሁፍም በቃልም ሀሳብ ስናቀርብ ከወያኔ በላይ ወያኔ ተብለን ዉርጅብኝ ቀርቦብናል። ይህ ማንንም አይረዳም እዉነት ከአጀማመሯ ብትቀጥንም በሗላ ግን እየገዘፈች እንደምትሄድ የተፈጥሮ ህግ ያሳያል። ኢትዮጵያ ዉስጥ ይህ የአዲሱ እስላም እንቅስቃሴ ያደረገዉን የቤተ ክርስቲያን ቃጠሎ፤ የንብረት ዉድመት፤አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ዜጎችን መግደል ነጻ የሆኑ የሚዲያ ተቋማት ዘግበዉታል ታድያ እነሱን ኪሳራ ዉስጥ የሚከት ሁኔታ ሲፈጠር ወያኔ ነዉ ያደረገዉ የሚለዉ የፌዝ አነጋገር እየተለመደ መጥቷል።  እነዚህ ማስረጃዎች ህዝቡ ዘንድ እንዳይደርሱ ቢደረግም፤የኢትዮጵያ ሚዲያዎችን በማጭበርበር እና ግፊት በማድረግ ህዝቡ ዘንድ እንዳይደርስ ጫና ቢደረገም  ለሀገራቸዉ በጎ የሚያስቡ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ለእይታ አቅርበዉታል አንባቢ በጉግል ከተመለከቱት ከብዙ በጥቂቱ ተመልካቹን የማያሳቅቀዉን ብቻ መርጠን አዉጥተነዋል ቀሪዉን ብርታት እና ጥናቱ ያላችሁ ዜጎች የዚህን ኢሰብአዊ ስራ መመልከት ትችላላችሁ።1.

እዚህ ላይ እነዚህን ሰዎች ኮትኩቶ እዚህ ያደረሳቸዉ የህወአት መንግስት መሆኑን አንባቢ እንዲረዳዉ ያስፈልጋል ሆኖም የህወአት ትግራይ ቢኮተኩታቸዉም አድራጊዎቹ እነሱ በመሆናቸዉ ለዚህ ወንጀል በህብረት ተጠያቂ መሆናቸዉም ሊሰመርበት ይገባል። እዚህ ላይ ታማኝ በየነም ምንም እንኳን ቀደም ባለዉ ጊዜ ለሀገሩ ብዙ ዉለታ የዋለ ዜጋ ቢሆንም በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በነ ዶክተር ብርሀኑ ተጋልቦ የኦነግ ወዳጂ ሁኖ ወደ ኢትዮጵያን መንደር የተኮሰዉን ሳናነሳ ልናለፍ አንፍለግም።ይህንን ነገር አስመልከተዉ ታማኝ በየነን አንዳንድ ጥንቃቄና ትምህርት የሚያስፈለገዉን ጉዳይ  የዘገቡ ወገኖች  (ዲ/ን ሙሉጌታ) በመኖራቸዉ ታማኝ በየነም ከዚህ ይማራል ብለን እንገምታልን ሌሎች ታማኝ በየኖችም ጥንቃቄን ያደርጋሉ ብለን እናምናለን።

ዛሬ ነገሮች ተለዉጠዋል ኢትዮጵያን የሚጎዳ ማንኛዉም አይዲዮሎጅ፤እምነት፤እይታ የሚዲያ ተቋማትን በሞኖፖሊ ይዞ ኢትዮጵያዊነትን የማፈን እንቅስቃሴ ጊዜዉ አልፎበታል ተጎጂዎቹም ከማንም በላይ የሚዲያ ተቋማት እና ይህን የሚያራምዱ ድርጂቶች እና ቡድኖች ይሆናሉ። በጊዚያዊ ጥቅም ተገፋፍተዉ ታላቁን ኢትዮጵያዊነትን እና ኢትዮጵያን ማጣት ከጥቅም ጉዳቱ ስለሚያመዝን ቆም ብለዉ ማሰብ ይጠበቅባቸዋል።  ይህንን ኪሳራ በብዙ የኢንተርኔት  የዉይይት መድረክም ጭምር ተመልክተናል በብዙ መቶዎች ያስተናግዱ የነበሩ በወረደና በጸረ ኢትዮጵያ አቋማቸዉና ተልእኮዋቸዉ ዛሬ ክፍላቸዉን ሬሳ የወጣበት  ቤት አስመስሎታል። ህዝቡ የሚፈልገዉን ስለሚያዉቅ ዛሬም ተቋማት በጊዜያዊ የቴርሞ ሜትር መለኪያ ብቻ ሳይወሰኑ የረጅም ጊዜ እይታችሁን መዝኑ እንላለን።

እንግዲህ መባል ያለበት ተብሏል ካጠፋሁም በዚህ ተቆጡኝ  semere.alemu@yahoo.com

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

የሼኽ ኑሩ ወንድ ልጅ በእስር ላይ እንደሚገኝ ተነገረ! (ድምፃችን ይሰማ)

$
0
0

ድምፃችን ይሰማ

ከሁለት ወራት በፊት በሰው እጅ ሕይወታቸው የጠፋው ሼኽ ኑሩ ወንድ ልጅ በመንግስት ደህንነቶች ታፍኖ ተውስዶ መታሰሩ ተሰማ፡፡ በደሴ አረብ ገንዳ አካባቢ ነዋሪ የነበሩትና መንግስት ለፖለቲካ ጥቅም ሲል ገድሏቸዋል ተብሎ በስፋት የሚታመነው ሼኽ ኑሩ ወንድ ልጅ በመንግስት ደህንነቶች ታፍኖ ከተወሰደ በኋላ አሁን ያለበት ቦታ በውል መታወቅ አልቻለም፡፡ እንደ አከባቢው ምንጮች ከሆነ የሼኽ ኑሩ ልጅ የታሰረው ከአባቱ ግድያ ጋር በተያያዘ ‹‹አባቴን ያስገደለው መንግስት ነው!›› በሚል በዙሪያው ላሉ ሰዎች በመናገሩ ነው ተብሏል፡፡ ይህ ወጣት ተመሳሳይ እስር ሲያስተናግድ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን ከጥቂት ሳምንታት በፊትም ተመሳሳይ ንግግር በመናገሩ በደህንነቶች ለቀናት ታፍኖ ከተወሰደ በኋላ ማስፈራሪያና ምክር ተለግሶት ተፈቷል፡፡ ሆኖም ከተፈታ በኋላም የመንግስት ደህንነቶች ያስጠነቀቁትን ‹‹ከአሁን በኋላ አባቴን መንግስት አስገድሎታል እንዳትል!›› የሚል ምክር ጥሶ በመገኘቱ ለድጋሚ እስር ተጋልጧል፡፡

 

Ethiopian Musilms

መንግስት ከሼኽ ኑሩ ግድ ጋር በተያያዘ ለሳምንታት የዘለቀ ከፍተኛ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ሲያካሄድ መቆየቱ የሚታወቅ ሲሆን በዚህ ዘመቻ ኢሕአዴግ ውስጥ ያሉ ፓርቲዎችን ጨምሮ በርካታ የመንግስት ተቋማት መግለጫ በማውጣት ከፍተኛ የሚዲያ ሽፋን ለመስጠት ተሞክሯል፡፡ በተጨማሪም በበርካታ የገጠር ከተሞች በተሌም በአማራ ክልልና ደቡብ ወሎ ‹‹ሕዝቡ የሼኽ ኑሩን ግድያ እንዲቃወም›› በሚል የግዳጅ ሰልፍ እንዲወጣ ከመደረጉም በላይ ‹‹ግድያውን የፈጸሙት ሙስሊሞች ናቸው›› በሚል ‹‹መንግስት እርምጃ ይውሰድ!›› የሚል መልእክቶች በተከታታይ በመንግስት ሚዲያዎች ሲያሰራጭ ነበር፡፡ ሆኖም ከሼኽ ኑሩ ግድያ ጋር በተያያዘ ሙስሊሙ ኅብረተሰብ ምንም ንክኪ እንደሌለውና ሙስሊሙ ኅብረተሰብ የሚያደርገው ተቃውሞ ፈጽሞ ይህን መሰል ጸየፍ ድርጊቶችን የሚስተናግድበት መርህ እንደሌለው በማስረገጥ፤ በዋነኝነትም የእንቅስቃሴው መርህ የሆነው ‹‹የምንሞትለት እንጂ የምንገድልበት አላማ የለንም›› መፈክር ተደጋግሞ ተጠቅሷል፡፡ ሙስሊሙ ህብረተሰብም በሃይል እርምጃዎች የማያምንና የሚሰነዘርበትን ዱላ በጸጋ ከመቀበል ውጪም አጸፋ የሰጠበት አጋጣሚ እንደሌለ በአስረጂነት ቀርቧል፡፡

አሁን የት እንደታሰር በውል የማይታወቀውና ከቤተሰብ ጋር እንዳይገኛኝ የታቀበው የሼኽ ኑሩ ወንድ ልጅ የገለጸው ሀሳብ አብዛኛው ህብረተሰብ የሚያምንበትና በተለይም በደሴ ከተማ ሕዝብ ዘንድ ግድያውን መንግስት እንደፈጸመው በስፋት የሚታወቅ እውነት ነው፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞም በተለያዩ ወቅቶች ከሼኅ ኑሩ ግድያ ጋር በተገናኘ የመንግስት ረጅም እጆች መኖራቸው የሚያመላክቱ መረጃዎች ወጥተዋል፡፡ ሼኅ ኑሩ ከመንግስት ሀላፊዎች ጋር በቅርበት ሲሰሩ የቆዩ ቢሆንም በሞታቸው የመጨረሻ ወቅቶች ግን ከአካባቢው አስተዳደር ሀላፊዎችና የጸጥታ ሹሞች ጋር በአካሄድና መርህ ላይ ባለመስማማታቸው ስብሰባ ረግጦ እስከውጣትና ዳግም አብሮ የመስራት ፍላጎት እንደሌላቸውም ሲገልጹ ነበር፡፡ መንግስት ሞታቸውን ተከትሎም የአስከሬን ምርመራ እንዳይደረግና የቀብር ስነ ስርአቱ በአፋጣኝ እንዲፈጸም በማስደረግ የግድያው ሁኔታ ተሸፋፍኖ እንዲቀር ለማድረግ ጥረት አድርጓል፡፡ የሼህ ኑሩ ግድያ ‹‹በመንግስት የተፈጸመ ድራማ ነው›› ሲል ሕብረተሰቡ ደጋግሞ መግለጹ ይወሳል፡፡

አላሁ አክበር!

አያ ተክሌ ምነዉ አህያዉን ትተዉ ፈረሱን ቢጋልቡ

$
0
0

 በደርብ ከፈለኝ

አዋቂ መስሎኝ ሰምቼዉ
ትልቅ ሰዉ መስሎኝ ተጠግቼዉ
በቃኝ . . . በቃኝ  አወቅኩትና  ናቅኩት
ለካስ ወዳጄ ኖሯል ፈረስ እየናቀ አህያ የሚጋልብ
በሬ እያቀጨጨ ጅብና ድብ የሚያደልብ

comment picከላይ አያ ተክሌ ብዬ የጀመርኩህ ተሳስቼ ነዉ። ከአሁን በኋላ ግን አቦይ ተክሌ ብዬ ነዉ የምጠራህ። አይዞህ “አቦይ” ያልኩህ እንደ አቦይ ስብሐት አርጅተህብኝ አይደለም። አወቃለሁ አንድ ፍሬ ልጅ ነህ . . .  አዎ ልጅ ነህ . . .  አሁንም ልጅ!  “አቦይ” ብዬ ሹመት የሰጠሁህ  አነጋገርህ፤ አስተሳሰብህና እንዳዉ አኳኋንህ ሁሉ ከአቦይ ስብሐት ጋር ስለተመሳሰለብኝ ነዉ፤ ወይም እንደ አቦይ ስብሐት ቀላማጅ ነህ ትቀለማድለህ ማለቴ ነዉ። አቦይ ተክሌ ምንም ቢሆን የቅርብ ጓደኛዬ ነህና የጓደኝነቴን ምክር ቢጤ ልሰጥህ እስኪ ስማኝ። አቦይ ስብሐት ሃያ ሁለት አመት ሙሉ ቀላምደዋል፤ ከአሁን በኋላ ልቀላምድ ቢሉም አንድ ሐሙስ ነዉ የቀራቸዉ። አንተ ግን አንድ ፍሬ ልጅ ነህ፤ እንግዲህ ይታይህ 35 አመት፤ 40 አመት፤ 50 አመት፤ ስልሳ አመት እያልክ ወዳጅና ጠላት፤ዘመድና ባዳ ፤ ጎረቤትና የማዶ ሰዉ ሳትለይ ይህንን ሁሉ አመት እየቀላመድክ ልትኖር ነዉ . . .  ያዉም በዚህ እንደ አሞራ በሚበርረዉ የዳያስፖራ ኑሮ። ምነዉ ተክሌ ቢቀርብህ!  መዶሻ የያዘ ሰዉ ሁሌም የሚመለከተዉ ሚስማር ብቻ ነዉ ሲባል ሰማሁና መዶሻ የያዘ ሰዉም መሰልከኝ፤ አሁን ግን በደንብ አድርጌ ሳይህ መዶሻ የያዘ ሰዉ ሳይሆን ጭራሽ መዶሻዉን እራሱን መሰልከኝ።

 

“ዬት ይደርሳል የተባለ ጥጃ ሉካንዳ ታየ” . . .  አያ ተክሌ . . .  ይቅርታ አቦይ ተክሌ ማለቴ ነዉ . . . ይህ ስንኝ የተቋጠረዉ ለሌላ ለማንም ሳይሆን ላንተ ብቻ ይመስለኛል። እስኪ ንገረኝ ተክሌ ምነዉ የነካሄዉ ነገር ሁሉ አይበረክት ወይ አንተ አትበረክት። እስኪ መለስ ብለህ አስበዉ ECADF፤ EHSNA፤ ESAT TV ፤ ESAT Radio ሁሉንም ነካ ነካ ግን አንዱንም ሳታረካ አንተም ሳትረካ እንዳዉ ዉኃ ላይ እንደተንሳፈፈ ኩበት ባክነህ ቀረህ። ምነዉ ወንድሜ ተክሌ እንዲህ ነበር እንዴ እኔና አንተ የምንተዋቀዉ? ምን ላድርግ እንደዛ ማታ ማታ እንደምንጫወትበት ካርታ ተበዉዝክብኝኮ። ምነዉ ተክሌ የተደበቀዉ ጸባይህ እየወጣ ነዉ ወይስ ድሮ ሳዉቅህም እንዲህ ወናፍ ነበርክ? ተክሌ ከሁሉም ከሁሉም የምታናድደኝ ደርሶ አዋቂ ለመመሰል  ቱግ ቱግ ስትል ነዉ፡፡ ዉድ ጓደኛዬ ተክሌ እባክህ ተረዳኝ እኔ አዋቂ አትሁን ማለቴ አይደለም፤ ግን አዋቂ ለመሆን አዋቂ ሁን እንጂ አዋቂ አትምሰል። ደግሞም ቱግ ቱግ እንኳን ባንተ በእንደኔ አይነቱ አንድ ክንድ ከስንዝር በማትሞላዉ ባንተ በሸበላዎቹም አያምርም። ስለዚሀ ተክሌ እባክህ እንዳቅምህ . . .  አዎ እንዳቅምህ!

 

በያ ሰሞን በየድረ ገጹ እየገባሁ  ያገኘሁትን ሁሉ ሳነብ አንተም የሞነጫጨርከዉን አገኘሁና አንብቤዉ በጽሁፍህ ሳይሆን በጓደኝነትህ አፈርኩ። እስኪ ንገረኝ ተክሌ ምን ይሁን ብለህ ነዉ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዉን ፖለቲካ አትተንትን ያልከዉ፤ እናስ ምን ይተንትንልህ? እኮ ንገረኝ ተክሌ የፖለቲካ ፓርቲ መሪ ፖለቲካ ካልተነተነ ሌላ ምን ይተንትን?  ለመሆኑ ያልተተነተነ ፖለቲካ ምን አይነት እስትራቴጂ ነዉ የሚወጣለት? ምነዉ ተክሌ “አወቅሽ አወቅሽ ሲሏት” የምንላትን ሴትዮ ሆንክብኝ! የፖለቲካ ፓርቲ መሪ ሆኖ የአገሩን የፖለቲካ ሁኔታ የማይተነትንና መጻኢዉን እዉነት በስዕል ቀርጾ የማያሳየን ከሆነ ምኑን የፖለቲካ ፓርቲ መሪ ሆነ . . .  እንደሱ አይነት የፖለቲካ ፓርቲ መሪማ ካንተ ጋር የዋለ ሰዉ ማለት ነዉ። አይዞህ ተረት ጎበዝ ነህ ብዬ ነዉ (ከአህያ ጋር የዋለች . . . )  አቦይ ተክሌ ችኩልነትህን ድሮም አዉቀዋለሁ፤ ከተናገርክ በኋላ የምታስብ ሰዉ መሆንህም ለእኔ አዲስ አይደለም፤  ግን ምነዉ ተክሌ . . .  ያንተ እዉነት የሰዉ ሁሉ እዉነት ይመስልሃል እንዴ? እንደዚህማ ከሆነ እዉነት የሚባል ነገር ምድር ላይ የለም ማለት ነዉኮ!  ተክሌ እባክህ በዚህ “ካፍ ከወጣ አፋፍ” በሆነበት አለም ከመናገርህና ከመጻፍህ በፊት አስብ። ፈረንጆቹ (Think twice before you speak once) ይላሉ። ተክሌ አንተ ግን የሚጽፈዉ እጀህ ደራሽ የሚናገረዉ አፍህ ነካሽ ነዉና እባክህ እንዳዉ በዚያች በምታከብራት በወላዲት አምላክ ይዤሃለሁ ከመናገርህ  በፊት አምስቴ አስብ (Think five times before you speak once).

 

መቼም የኛ ነገር “አፍ ያለዉ ጤፍ ይቆላል” ነዉና አንድ ሰሞን ይችኑ የምትንጣጣዉን አፍህን አይተዉ  ኢሳቶች ወያኔ ላይ ብትንጣጣላቸዉ ብለዉ አስጠጉህ አንተ ግን ጠላትና ወዳጅ ሳትለይ ሁሉም ላይ የምትተኩስ ጉድ ነህና ኢሳቶች ላይ እሳት ሆንክባቸዉና እሳት አደጋ ጠርተዉ በግዜ ተገላገሉህ። ተክሌ ልክ እንደ ቁመትህ ምን ያህል ትንሽ ሰዉ እንደሆንክ ያየሁት በስራ አጋጣሚ የምታዉቀዉን ነገር ሁሉ ድረ ገጽ ላይ እንዳላዋቂ ሳሚ መለቅለቅህ ነዉ። አሁን ይህ ምን ይባላል? አዋቂነት ወይስ ጅልነት? መልሱ ቀላል ነዉ፤ ተክሌ አንተ አዋቂነት የሚባል ነገር በአጠገብህ ያለፈም አይመስለኝም። ጅልን ለማወቅ ደሞ ጅል መሆን የግድ ይላልና እስኪ እዚያ የሞነጫጨርከዉ መጣጥፍ ላይ የከተብከዉን ዝባዝንኬ እንዳለ ላሳይህ

 

“ይሁን እንጂ፤ የኢሳት አስተዳዳር የሆነው ወዳጄ ነአምን ዘለቀ የዛሬ አመት አካባቢ እንዲህ ያለው ተመሳሳይ ስብሰባ ሲዘጋጅ፤እባክህን መሪዎቹ ንግግር ያሳጥሩና ለሰዉ እንዲተነፍስ ግዜ ይስጡት ብዬ አሳስቤው ነበር። ነአምን አንዳንዴ አይሰማም። ወይም ቢሰማም አያደምጥም” አቦይ ተክሌ

 

“ነአምን አንዳንዴ አይሰማም። ወይም ቢሰማም አያደምጥም” . . . ወይ ጉድ! አንተንስ ምን እንበል? . . .  ተክሌ የሚባል ስም ከተሸከምክ ጀምሮ ሰምተህም አዳምጠህም የማታዉቀዉን ጆሮም አፍም የሌለህ እንግዳ ፍጥረት! ለካስ አለምክንያት መዶሻ አልተባልክም!  ነአምንማ እንተም እንደመሰከርክለት አንዳንዴ ነዉ እንጂ አብዛኛዉን ግዜ ይሰማልኮ፤ እንደዚህ ብዙ ግዜ የሚሰሙ ኢትዮጵያዉያን ደግሞ ብርቅዬ ናቸዉ . . . የሉማ! እስኪ ንገረኝ ተክሌ ምንድነዉ እየነገርከን ያለኸዉ፤ አንተ ሁሉን ነገር  አዋቂዉ ተናግረህ ነአምን አላዋቂዉ አለመስማቱን ነዉ ወይስ ከዚህ ሌላ የምትለን ነገር አለ? ደሞኮ ከብዙ ጉድ ያዳነን የነአምን አንዳንዴ አለመስማት ነዉ እንጂ ሰምቶህማ ቢሆን ኖሮ የዛሬዉ ትግላችን ከወያኔ ጋር መሆኑ ቀርቶ አንተ የቀደድከዉን ቀዳዳ መቋጠር ላይ ይሆን ነበር። ችግሩ ዲሲ ላይ አትቅደድ ብለዉ ሲያባርሩህ ቶሮንቶ ሄደህ ደሞ እንደገና ትቀድዳለህ . . .እስኪ ንገረን የሚቀደድ የሌለበት ዬት አገር እንስደድህ?

 

አቦይ ተክሌ  . . . ዶ/ር ብርሐኑ በሐይማኖት ጉዳዮች ላይ የጻፉት ሰፋ ያለ ጽሁፍ አልገባህ እንደሆነ መጠየቅ አንድ ነገር ነዉ፤ አለዚያ ስምም፤ሀሳብም ጸባይም  እንደምትጋራቸዉ እንደ አቦይ ስብሐት ህዝብ አንዳለ ባኮረፈበት አገር “ያኮረፉ ሰዎች እንጂ ያኮረፈ ህዝብ የለም” ብትል አባባሉ ለግዜዉ ሊያምርልህ ይችል ይሆናል፤ እመነኝ የሚሰማህ ግን አታገኝም። የዶ/ር ብርሀኑ ጽሁፍ ላይ ገጽ 16 መጨረሻና ገጽ 17 መጀመሪያ ላይ የቀረበዉ ሃሳብ ጥልቅ ወይም ሐቀኛ አይደለም ብለሃል። እስኪ ንገረኝ ተክሌ ምንድነዉ መለኪያህ? ጥልቀቱን ባንተ ስንዝር ሐቀኝነቱን ባንተ ሚዛን ነዉ የለካኸዉ? ከሆነ… አብረን ስለኖርን ዝንዝርህንም ሐቅህንም በሚገባ አዉቃለሁና አልፈርድብህም። አቦይ ተክሌ እንዳዉ ያንተ ነገር “አህያ ማር አይጥማት” ሆኖብህ ነዉ እንጂ እስኪ አሁን ምኑ ላይ ነዉ ያ ጽሁፍ ጥልቀት ያጣዉ ምኑስ ላይ ነዉ ሀቅ የጎደለዉ? አንድን ሰዉ ደደብ ነዉ ብሎ አንድ ሙሉ መጽሐፍ መጻፍ ይቻላልኮ፤ ለዚህ ደግሞ የሚያስፈልገዉ ብዙ ጥረትም አይደለም አንድ ያንተ አይነት ጭንቅላት ይበቃል። ችግሩ የሚመጠዉ የሰዉየዉን ደደብነት ዋቢ ጠቅሶና መረጃ አስይዞ ማቅረቡ ላይ ነዉ፤ እንደዚህ አይነቱ መረጃ ደግሞ እንኳን አንተ አያገባዉ ይገባል ያልከዉ ሰዉ ላይ ቀርቶ የእርጎ ዝንብ የሆንከዉ አንተ ላይም ማቅረብ አስቸጋሪ ነዉ። አይህ ወንድሜ ተክሌ አንተም እንደዚሁ ነህ። ሰዉን “ደደብ” ለማለት አፍህ ይቀድማል መረጃ ተብለህ ስትጠየቅ የምታሳየን ግን ያንኑ የምናዉቀዉን ባዶነትህን ነዉ . . .እሱ ደግሞ ሰለቸን . . .  አዎ ሰለቸን! ሰማህ ተክሌ ሰለቸን።

 

አቦይ ተክሌ ደሞ ብለህ ብለህ አንተም እንደ ወያኔ ምሁራን ተቃዋሚዉን ሁሉ “ሊብራል” ልትለዉ ነዉ እንዴ! መቼም አንዳንዴ ነካ ሲያደርግህ እንደ ዕብድም መሆንም ያምርሃል እንጂ በወያኔነት እንኳን በፍጹም የምትታማ ሰዉ አይደለህም፤  ግን . . . ግን ጠንቀቅ በል ልጄ ዉኃኮ ሲወስድ እያሳሳቀ ነዉ . ..  እንግዲህ ይታይህ ተክሌ ባንተ መንቀዥቀዥኮ መወሰድህ ነዉ!  ብሉይን በመቀበል ከዚያ ክርስትናን፤ ከዚያ እስልምናን፤ ከዚያ ካቶሊክን፤ ከዚያ ፕሮቴስታነንስዝምን፤ በመቀበልና በማቻቻል የኖረች አገር ናት ብለሀል አገራችን ኢትዮጵያን። እርግጥ ነዉ፤ ግን ለመሆኑ ብሉይ የሚባል ሐይማኖት አለ አንዴ ወይስ አንተዉ ወደኋላ ሄደህ ልትጀምር ነዉ? ደግሞስ ክርስትና፤ ካቶሊክና  ፕሮቴስታነንስዝም ስትል ካቶሊክና ፕሮቴስታንት ምን መሆናቸዉ ነዉ? ክርስትና አይደሉም እንዴ? ወይስ ኢትዮጵያ ዉስጥ ከምንም ተቋም ጋር የማይገናኝ “ክርስትና” የሚባል ሐይማኖት አለ? አየህ ተክሌ ምን አይነት የተበላሸ ጭንቅላት እንዳለህ የሚያሳየዉ እንደዚህ አይነት ቆሻሻና ወደ አንድ ወገን ያጋደለ ትንተናህ ነዉ። ይልቅ ምነዉ እንዲህ አይነቱን ጭንቅላት የሚፈልገዉን ትንተና ለዚያ አትችልም ላልከዉ ሰዉ ብትተዉለት! ማቻቻል የሚል ቃልም ተናግረሃል፤ ምን ማለትህ ነዉ? ኢትዮጵያ ዉስጥኮ ማን ማንን ችሎ እንደኖረ ግልጽ ነዉ . . .  እና አሁንም በዚያዉ እንቀጥል ነዉ እንዴ የምትለን? ዶ/ር ብርሀኑኮ በዚያ ጸሁፉ ዉስጥ ያስነበበን የተለያየ ሐይማኖት ቢኖረንም እንዴት ሁላችንም ያሰኘንን ሐይማኖት ባሰኘን መንገድ እያመለክን (ይግባህ መቻቻል አይደለም) በእኩልነት ተከባብረን መኖር እንደምንችል ነዉ። ይህንን ደግሞ ሊብራል ዲሞክራሲ በሚገባ ተንትኖ አስቀምጦታል። አየህ ተክሌ  ፖለቲካ ተንትን ተብሎ ስራ ሲሰጥህ አንደጋይኮ ኮሜርሻል ነገር ትደባልቃለህ፤ አዋቂ ሲተነትን ደሞ አትተንትን ብለህ ትወርድበታለህ፤ ምነዉ ተክሌ . . .  “ያግቡብሽ እምቢ ያዉጡብሽ እምቢ” ሆንክሳ!

 

ኦባማ ሲመረጥ ምሁር ነበር ብለሃል. . . . አይደለም ብዬ ብከራከርህስ?  ምነዉ ተክሌ የማታዉቀዉ ዉስጥ ገብተህ ትፈተፍታለህ! አባማ ፕሬዚዳንት ሆኖ ሲመረጥ የፖለቲካ ሰዉ (ሴኔት) ነበር፤ ዛሬም የፖለቲካ ሰዉ ነዉ። በእርግጥ ኦባማ የምሁር ችሎታዉም ተሰጥኦዉም አለዉ፤ ግን በምሁርነት የሚበልጡት ሺዎች አሉ፤ ኦባማን አባማ ያሰኘዉ በምሁርነት ችሎታዉ ላይ አዳብሎ የያዘዉ ከፍተኛ የፖለቲካ ችሎታዉ ነዉ (ይህ ችሎታ የፖለቲካ ትንተናዉንም ያጠቃልላል)። አለዚያ ለምሁርነቱማ ሀርቨርድና ፕሪንስተን ዉስጥ አባማን የሚያስከነዱ ብዙ ምሁራን አሉኮ። ተክሌ አንተኮ አንዳንዴ የምትናገረዉንም የምታዉቅ አይመስለኝም፤ ለዚህ ይመስለኛል ‘ተክሌ’ ከተናገረ በኋላ ነዉ የሚያስበዉ እየተባልክ የምትታማዉ። ምሁር ምሁርነቱ ሲቀንስ ወደ “ቡሽነት” ይለወጣል ነዉኮ ያልከዉ? የፈጣሪ ያለህ!  . . .  ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም አሉ፤ ዕድሜ ላንተ ዘንድሮ ሊጣባ ነዉ። አየህ ተክሌ በዚህ አንተ ባልከዉ ስሌት ከሄድንኮ ኢሳት ዉስጥ ዜና ያነበበ ሰዉ ሁሉ ወናፍነቱ ሲጨምር ‘ተክሌ’ ይሆናል ማለት ነዉኮ . . .  እንዴ! እኛ አነተ አንዱም አላስቀምጥ ብለኸናል ደሞ ስንት ተክሌ ሊኖረን ነዉ?  ከዚህስ ቸሩ ፈጣሪ ይጠብቀን!!

 

“የፖለቲካ ተንታኝ የምለው፤ በፖለቲካ ውስጥ በቀጥታ በአድራጊ-ፈጣሪነት ሳይሳተፍ ወይም መሳተፍ ሳይጠበቅበት፤ የአንድን ፖለቲካዊ ስብስብ/ማህበረሰብ ፖለቲካዊ ሁኔታ እየቃኝ፤ ከአካባቢያዊና አለማቀፋዊ ሁነቶች ጋር እያጣቀሰ የሚናገር ነዉ” ብለሀል። ለመሆኑ ይህ የተናገርከዉ ነገር ያንተ ህግ ነዉ ወይስ የሁላችንም?  ያንተ ከሆነ ያንተ ነገር ሁሉም ግራ የተጋባ ነዉና አልፌሃለሁ። ግን ምነዉ ተክሌ ሰሜን አሜሪካ ዉስጥ እየኖርክ ፖለቲካ በምሁርና በፖለቲከኛዉ ሲተነተን ልዩነቱ አልገባህ አለ? እስኪ የሚገባህ ከሆነ ምሳሌ ልስጥህ . . .  ፕሮፌሰር ላሪ ሰባቶ (ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ቨርጂኒያ) አንተ ያልከዉ አይነት የታወቀ ምሁርና ፖለቲካ ተንታኝ ነዉ፤ ግን ፖለቲካ አድራጊም፤ፈጣሪም አይደለም ። ተሳትፊ ግን ነዉ። አንተ ከዬት እንዳመጣኸዉ አላዉቅም አንጂ  ሰዉ ሆኖ ፖለቲካ  ላይ የማይሳተፍ የለም፡፡ ፕሬዚዳንት ኦባማ  ፖለቲካ አድራጊም፤ፈጣሪም  ተሳታፊም ናቸዉ፤ ዋናዉ ስራቸዉ  ፖለቲካ መተንተን ላይሆን ይችላል፤ ግን አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የአሜሪካንን ፖለቲካ ተንትነዉ ለህዝብ ማቅረብ ግዴታቸዉ ነዉ።  ህዝቡም ጆሮዉን በአብዛኛዉ የሚሰጠዉ ለፖለቲካ ኤክስፐርቱ ለላሪ ሰባቶ ሳይሆን ለፖለቲከኛዉ ለኦባማ ነዉ። አየህ ተክሌ ባንተ አባባል ፕሬዚዳንት ኦባማ ፖለቲካ ትንተናዉን ለላሪ ሰባቶ መተዉ አለባቸዉ ማለት ነዉ፤ ወይም የኦባማ ፖለቲካ ትንታኔ ያልጠራ የላሪ ሰባቶ ትንታኔ ግን የጠራ ነዉ ማለት ነዉ . . . እንዴት ሆኖ!  እርገጠኛ ነኝ ይህንን ጽሁፍ አንብበህ ስትጨርስ በራስህ ቅዠት ይምትስቅ ይመስለኛል። በነገራችን ላይ የኢትዮጵያም ፖለቲካ እንደዚሁ ነዉ፤ ጋዜጠኛዉም፤ የዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰሩም፤ ሌላ ሌላዉም ሊተነትነዉ ይችላል፤ ግን ህብረተሰቡ (አንተን ላይጨምር ይችላል- አዋቂ ነሃ!) በብዛት ጆሮዉን የሚሰጠዉ ፖለቲካዉን የፖለቲካ መሪዎች ሲተነትኑት ነዉ። ደሞ ማነዉ ምሁር ሁሉ ፖለቲካ መተንተን ይችላል ብሎ የነገረህ?  አቦይ ተክሌ ሌላዉ ትልቁ ችግርህ ሰዉ ያለማክበር ነቀርሳ አለብህ፤ ለምሳሌ ዶ/ር ብርሀኑን አንዴ ዲባቶ ብርሀኑ ፤ አንዴ ብርሀኑ ነጋ፤ ሌላ ግዜ ደግሞ ልክ እንደ ቆሎ ጓደኛህ “ብሬ” ብለህ ጠርተዋኸል። ዶ/ር ብርሀኑ በዕድሜ ይበልጥሃል ደግሞም አስተማሪህ ነዉ፤ ስለዚህ አጠገቡ ስትሆን ዶ/ር ብርሀኑን እንዳሰኘህ መጥራት ትችላህ እሱ ያንተና የሱ ጉዳይ ነዉ፤ ለኛ ስትጽፍልን ግን ኢትዮጵያዊ ባህላችን ነዉና ማክበር ግዴታህ ነዉ። ይህንን ታላቆችህን የመዘርጠጥ ነቀርሳ በግዜ ካልታከምከዉ ብዙ ታዳጊ ልጆቻችንን ታበላሻለህና አንተዉ  ጽሁፍህ ላይ በጠቀስካት በእመ ብርሀን የዤሃለሁ እባከህ ታላቆችህን አክብር።

 

ኢትዮጵያ ዉስጥ ሙስሊም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ያነሱትን የመብትና የነፃነት ጥያቄ ሙሉ በሙሉ የምንደግፍ ኢትዮጵያዉያን፤ የምንደግፍ ግን ንቅናቀዉን በጥርጣሬ አይን የምንመለከት ኢትዮጵያዉያንና ጭራሽ ንቅንናቄዉን የምንቃወም ኢትዮጵያዉያን አለን። አቦይ ተክሌ አንተም የሙስሊሙን ህብረተሰብ እንቅስቃሴ መጠራጠር መብትህ ነዉ፤ ያ እዚያ ሙንጭርጭርህ ላይ የወረድክበት የፖለቲካ ተንታኝም አትጠራጠሩ አላለምኮ! መቼም ያንተ ዱላ ልክ እንደ ወያኔ ፌዴራል ፖሊስ ዱላ ያገኘዉ ሁሉ ላይ ይመዘዛል እንጂ ዶ/ር ብርሀኑማ እንድያዉም የሙስሊሙን እንቅስቃሴ የሚጠራጠሩ ሰዎችን በመንግስት ፕሮፓጋንዳ የተደለሉና የሐይማኖት አክራሪነትን የሚፈሩ ብሎ በሁለት ከፍሎ ነዉ ያስቀመጣቸዉኮ። አንተ ግን በዚያ በተከፈተ ቁጥር አንደ “ታድፋለች ቅጥ” በሚሰፋዉ አፍህ “ብሬ አድበሰበሰው” ብለህ አረፍከዉ። መቼም በባህላችንም ቢሆን ነዉር ነዉና አደባባይ ላይ “ባለጌ” ብዬስ አልሰድብህም!

 

ምንም ቢሆን ተሰድደህ ዳያስፖራዉን የተቀላቀልከዉ ለትግል ነዉና አስኪ አንድ ነገር ልጠይቅህ . . . . ክርስቲያኑ የሙስሊሙን የመብትና የነፃነት ጥያቄ በጥርጣሬ የጎሪጥ ከተመለከተዉ፤ ሙስሊሙ ደግሞ ይህንን እሱን በጥርጣሬ የሚለከተዉን ክርስቲያን በትግል አጋርነቱ ካላመነዉና ካልተቀበለዉ እንዴት ሆኖ ነዉ የኛ ትግል ግቡን መትቶ አገራችን የምንገባዉ? ይሄዉልህ ተክሌ በዚያ አስቀያሚ የፖሊስ ዱላህ ደጋግመህ የጨረገድከዉ ሰዉ እንዲህ አይነቱን አንተ አይቶ ለመረዳት አመትና ሁለት አመት የሚፈጅብህን ነገር እሱ በግዜ አይቶና ተንትኖ ለህዝብ ያቀረበ ሰዉ ነዉኮ! ምነዉ የልጅነት ገደኛዬ እንዲህ ገብስ ሆንክብኝ ከገብስም የነፈዘዉ! ለመሆኑ ጽሁፉን በደምብ አንብበኸዋል ወይስ ለትችት የሚመችህን ቦታ ብቻ ነዉ እየመረጥክ ያነበብከዉ፤ ለዚያዉምኮ አንተኑ ለትችት የሚያጋልጠዉን ቦታ ነዉ የመረጥከዉ። ለነገሩ አንተ መምረጥ መች ታዉቅበታለህ? ብታዉቅ ኖሮ አንዳቅምህ ትኖር ነበር። ዶ/ር ብርሀኑኮ እንደ ማንም ሰዉ የሚተች ሰዉ ነዉ፤ እንዳዉም እንደሱ ለትችት የተጋለጡ የፖለቲካ መሪዎች በጣት የተቆጠሩ ናቸዉ፤ በየቀኑ እንደሰሩ ነዋ! አንተ ግን ወይ አትሰራ፤ ወይ አታሰራ እንዳዉ “ዝናር በቅፌን” ይመስል መናኛ መናኛዉን ኮተት ተሸክመህ ከሚሰሩ ሰዎች ጋር ትቀላቀላለህ። አሁን እስኪ ተክሌ በሞቴ ንገረኝማ . . .  ተክሌ እንዴት ጎበዝ ነዉ፤ ዶ/ር ብርሀኑን እኮ አገኘዉ፤ ልክ ልኩን ነገረዉ ብለዉ ያንተ ብጤ ጥቅት ወናፎች ቢያናፍሱልህ እዝያ ቁመትህ ላይ ስንዝር ይሚጨምሩልህ ይመስልሃል? ቢጨምሩስ?

 

አየህ አቦይ ተክሌ ጽሁፍኮ ፊደልና ፊደል ማገናኘት ስለምንችል ብቻ የምንገባበት የጨረባ ተዝካር አይደለም። መጻፍ ማሰብ፤ ማሰላሰል፤ ማንበብና ነገሮችን የማመዛዘን ችሎታን የሚጠይቅ ትልቅ ስራ ነዉ፤ አንተ ደሞ ነገሮችን መቀላቀል ነዉ እንጂ ከእነዚህ እሴቶች ጋር በተለይ ከማሰብና ከማመዛዘን ጋር ጭራሽ የምትተዋወቅም አይመስለኝም። እዩኝ እዩኝ ትላለህ፤ አወቅኩ አወቅኩ ታበዛለህ። አንዳንዴማ ጭራሽ ካንተ በላይ የሚያዉቅ ሰዉ ያለም አይመስልህም። የሰዉ ልጅ የማዉቁ ትልቁ ምልክት አለማወቁን ማወቁ ነዉ። ኦይ ተክሌ ላንተ ግን ይህ የጠቢባን አባባል ተረት ነዉ የሚመስልህ። እባክህ የማታዉቀዉን ነገር አላዉቅም በል። በተለይ በተለይ የማተዉቀዉ ነገር ላይና በደምብ ያልገባህ ነገር ላይ አትጻፍ፤ አትተች አስተያየትም አትስጥ። ዉድ ጓደኛዬ ተክሌ አንግዲህ አንድም ገና የምታድግ ሰዉ ነህና ደሞም ሰዉ እፈር ተብሎ የሚነገረዉ ዉድቀቱን ሲረዳ ስለሆነ “እፈር “ ብዬህ አፌን አላበላሽም። እስከዛሬ እንዳየሁህ አንተም እንጣጥ እንጣጥ ማለት ነዉ እንጂ እፍረት የሚሰማህ ሰዉ አይደለህም። እንጣጥ የሚያበዛ ሰዉ ደግሞ ያመለጠዉ ለታ ዕድሜ ልኩን ያፍራል። እንግዲህ ይህ መጥፎ ቀን ሳይመጣብህ ከአቅምህ በላይ መዝለሉን አቁም። እርግጠኛ ነኝ ተክሌ ይህንን ጽሁፍ አንብበህ “ዲሞክራሲ” የማይገባቸዉ ሰዎች ሀሳቤን የመግለጽ መብቴን ሊቀሙኝ ነዉ እንደምትል፤ ሆኖም የዚህ ጽሁፍ ጥረት የዲሞክራሲ ጽንሰ ሀሳብ አንዲገባህና ከሰዎች ጋር በቡድን ስትሰራ ሌሎችን ሳትጋፋና ሳታስቀይም ሀላፊነት ተሰምቶህ ግዴታህን እንድትወጣ ነዉ እንጂ የሁላችንም ትግል ለመብት መከበር ነዉና መብትህን የነካም የደፈረም የለም። የፖለቲካ መሪዎቻችንን መተችትና ስህተት ሲሰሩ ተከታትሎ ማጋለጥ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነገር ነዉ፤ ነገር ግን የሌለ ስህተት እየፈጠርክ፤ ያልተጻፈ  እያነበብክና ሰዎች ደፋር ተቺ ነዉ እንዲሉህ ብቻ የሚሰሩ ሰዎችን ባትቦጫጭቅ ጥሩ ይመስለኛል። አንድ ሰዉ ባጠፋዉ ጥፋት የሚያዝነዉ ለሌሎች ካለዉ ክብርና ፍቅር ነዉና . . .  ተክሌ እስኪ እባክህ ለህዝብ ክብር ስትል ጥፋትህን ተረዳና ከራስህም ከወገንም ጋር ታረቅ። የምትመኘዉን ትልቅ ሰዉ ለመሆን ከፈለግክ የትልቅነት መንገዱ ይህ ነዉ። እግዜር ይርዳህ!

የዓመቱ የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች ምርጥ ሰው –የሕይወት ገድል

$
0
0

በ1997 ዓ.ም ኢዴፓ /ቅንጅትን ወክሎ በተወለደበት ክ/ሀገር ፋርጣ ወረዳ ለተወካዮች ም/ቤት ተወዳድሯል:፡ በምርጫው ውጤት ቅንጅት ቢያሽንፍም ከፍተኛ አመራሩና አባላቱ በተለያዩ እስርቤቶች ሲታሰሩ እሱም አብሮ ቃሊቲ እስር ቤት ለሁለት ዓመታት ቆይቷል፡: በሁለት ዓመት ቆይታውም የብረት ግድግዳ በመሆን ፅናቱን አስመስክሯል:፡ ከእስር ቢለቀቅም ከፖለቲካው ወደ ኋላ አላፈገፈገም፡ አንድነት ፓርቲን በመቀላቀል የብሔራዊ ም/ቤትና የሥራ አሥፈፃሚ አባል በመሆን ለዋና ጸሐፊነት ተመርጦ ላንድ ዓመት በቆራጥነት አገልግሏል፡: ብቃቱን በማስመስከሩም በም/ሊቀመንበርነት የሕዝብ ግንኙነት ሐላፊ ሆኖ ተመርጦ በማገልገል ላይ እንዳለ፤ በተጨማሪም የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር እንዲሆን ብዙዎች እየቀሰቀሱ ባለበት ወቅት ነው ርምጃው ያልጣመው ገዥው ፓርቲ ከግንቦት 7 ጋር በማገናኘት የሽብርተኝነት ጥላሸት በመቀባት መስከረም 3 ቀን10 ሰዓት ላይ ከመንገድ የታጠቁ ኃይሎች ከመኪና አስወርደው ይዘውት በመሄድ አሁን እድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ይገኛል።
Andualem Arage
አንዱዓለም አራጌ ማነው? ለሚለው ጥያቄ ለአንባቢያንና ለውጥ ለማምጣት ለሚታገልለት የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሕይወት ታሪኩ ትንሽ ጨለፍ አድርገን ለመፈንጠቅ እንሞክራለን።

የትውልድ አካባቢና የልጅነት ጊዜ አቶ አንዱዓለም አራጌ በጎንደር ክ/ሀገር በደብረታቦር አውራጃ በፋርጣ ወረዳ ጉና ተራራ ሥር ወይንም ግርጌ ክምር ድንጋይ ከተባለ ቦታ በ65 ዓ.ም ጥቅምት25 ቀን ተወለደ፡፡ የኢትዮጵያ አብዮት ሊፈነዳ ሁለት ዓመት ሲቀረው በምጥ ዋዜማ ማለት ነው፡፡ “ሰው አካባቢውን ይመስላል” እንደሚባለው አንዱዓለም አራጌ በክ/ሀገሩ ከራስ ዳሽን ተራራ ቀጥሎ በሁለተኛደረጃነት ከሚጠቀሰው ጉና ተራራ ስር በመወለዱ ለኢሕአዴግ እንደ ጉና ተራራ ኮርቶና ከብዶ ታይቶታል፡፡ እናም አስሮ በሽብርተኝነት በመወንጀል አሞቱን ያፈሰሰ መስሎታል፡፡ አንዱዓለም አራጌ ግን እንዲህ በቀላሉ የሚፈታ አይደለም፡፡ ለምንም ነገር የማይበገር፣ ችግር የማይፈታው፣ ለቆመለት ዓላማ ወደ ኋላ የማይል፣ ከሁሉም በላይ ቅጥፈትንና እብለትን አጥብቆ ይጠየፋል፡፡ባጭሩ ትክለ ሰውነቱ ወይንም nስብእናው በቁም ነገር የታነፀ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ለቆመለት ዓላማና ላመነበት ነገር ያላንዳች ይሉኝታና ፍርሃት ሽንጡን ገትሮ ይከራከራል፡፡
በዚህ አቋሙና ፅናቱም ነው ገና በለጋ እድሜው ሩጦ ሳይጠግብ፣ ሠርቶ ሣይደክም በተደጋጋሚ የእሥር ሰለባ ለመሆን የበቃው፡፡

አ ን ዱ ዓ ለ ም አራጌ አሥራ አንድ ዓመት እስከሚሞላው ድረስ ክምር ድንጋይ ከወላጆቹ ጋር ቆይቷል፡፡ አባቱ የቤተ ክህነት ሰው በመሆናቸው ልጃቸው በፅኑ የግብረገብ ሥነ ምግባርኮትኩተውና ገርተው ከማሣደጋቸውም በላይ የቤተክህነት ትምህርት እንዲማርላቸው በመሻት ካንድ ከታወቁ መርጌታ ልከውት በተመላላሽነት እየተማረ እንዳለ አዲስ አበባ የሚኖሩ አያቱ ክምርድንጋይ ይሄዳሉ፡፡ እሳቸውም የቤተክህነት ሰው ነበሩና ንቃቱን፣ ጨዋነቱን፣ ትህትናውንና አርቆ አስተዋይነቱን በዚያች አጭር ጊዜ ቆይታቸውአስተዋሉና “ይኸ ልጅ ዘመናዊ ትምህርት መማርአለበት” ብለው ወደ አዲስ አበባ ይዘውትይመጣሉ፡፡ሕይወት በአዲስ አበባአንዱዓለም አራጌ ካያቱ ጋር አዲስ አበባ ከመጣ በኋላ መስከረም መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በመግባት ከ1-8ኛክፍል ድረስ ሁለት ጊዜ ደብል ወይንም አጥፎ በማለፍ በ6 ዓመት ውስጥ ስምንተኛ ክፍልን አጠናቀቀ፡፡

Andualem Arage kids
ዘጠንኛና አሥርኛ ክፍልን የተማረው ኮከበ ጽባህ ሲሆን የደረጃ ተማሪ ስለነበር 11ኛና 12ኛ ክፍልን የተማረውና ከፍተኛ ውጤት አምጥቶ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለመግባት የበቃው በሳንጅዮሴፍ ት/ቤት በመማር ነበር፡፡ አንዱዓለም አራጌ በከፍተኛ ውጤት አ.አ.ዩ በመግባት በታሪክ የመጀመሪያ ዲግሪውን አግኝቷል፡፡በዩኒቨርስቲ ቆይታውም በተለያዩ ክበባት በመግባት በኃላፊነትም ሆነ በአባልነት ካንድ ንቁ ተማሪየሚጠበቅበትን ግዴታ ተወጥቷል፡፡ በዩኒቨርስቲው ውስጥ በአራት ዓመት ቆይታው የት/ቤት ጓደኞቹ በሚያደርጋቸው ክርክሮችና በአቋሙ ፅናት እጅግ አድርገው ያደንቁት እንደነበር ዛሬ በቅርብየሚያውቁት ይናገራሉ፡፡

አንዱዓለም አራጌ ከሚታወቅባቸው ቁም ነገሮች መሀከል ባገራችን ገና የሰላማዊ ትግል ፅንስ ሐሳብ በቅጡ ባልታወቀበት ወቅት እሱ ሰለሰላማዊ ትግል ይሰብክ ነበር፡፡ ይህንንም ሲያደርግ የአንጋፋሰላማዊ ታጋዮችን አርማ በማንሳትና መርሃቸውን እንደ ምርኩዝ በመጠቀም ነው፡፡ ማርቲን ኪንግ፣ ማንዴላ፣ ማኅተመ ጋንዲን ታሪካቸውን በማጥናትና የሄዱበትን መንገድ በመከተል በዩኒቨርስቲቆይታው መርሃቸውን መርሁ በማድረግ የትግል ብቃቱን እንዳዳበረ በቅርብ የሚያውቁት በአጽንኦት ይናገራሉ፡፡ የአንዱዓለም አራጌ ልዩ ባህሪውና ተሰጥኦው ወይንም ትክለ ሰውነት ከላይ ለመጥቀስእንደሞከርነው በሰላማዊ ትግል ገና ከወጣትነቱ ዕድሜው ጀምሮ ቆርቦ እያለ ገዥው ፓርቲ “ሽብር አራማጅ” ብሎ በመወንጀል ጥላሸት ሲቀባው ማየትና መስማት ያለንበትን ዘመንና ሥርዓት ምንያህል አስጨናቂና አስከፊ እንደሆነ መገመቱ ከባድ አይሆንም፡፡ እያንዳንዳችንም ውለን ስለመግባታችን ዋስትና የለንም፡፡ ሁላችንም የሱ እጣ እንደሚጠብቀንና ጥላሸት እንደምንቀባም በርግጠኝነትመናገር እንችላለን፡፡

የሥራ ዓለምአንዱዓለም አራጌ ከአ.አ.ዩ ትምህርቱን ጨርሶ ከወጣ በኋላ በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ እየተቀጠረ ሠርቷል፡፡ ከነዚህ ውስጥ የዓለም ባንክና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች መኅበርበግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

የፖለቲካ ሕይወቱ

አቶ አንዱዓለም አራጌ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቆይታው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የፖለቲካ ሀሁን ከመቁጠር ጀምሮ በማዳበር ብስለቱን ያስመስከረ ቢሆንም በድርጅትውስጥ ታቅፎ መታገል የጀመረው ግን በ1992 ዓ.ም የኢዴፓ መሥራች አባል በመሆን ነበር፡፡ በኢዴፓ ውስጥ በቆየባቸው ዓመታትም ከቋሚ ኮሚቴ አባልነት ጀምሮ ደረጃ በደረጃ አድጎ ም/ዋናጸሐፊ በመሆን በከፍተኛ ኃላፊነት ሠርቷል፡፡ በመሆኑም በ1997 ዓ.ም ኢዴፓ /ቅንጅትን ወክሎ በተወለደበት ክ/ሀገር ፋርጣ ወረዳለተወካዮች ም/ቤት ተወዳድሯል። በምርጫው ውጤት ቅንጅት ቢያሽንፍም ከፍተኛ አመራሩና አባላቱ በተለያዩ እስር ቤቶች ሲታሰሩ እሱም አብሮ ቃልቲ እስር ቤት ለሁለት ዓመታት ቆይቷል፡፡ በሁለት ዓመት ቆይታውም የብረትግድግዳ በመሆን ፅናቱን አስመስክሯል፡፡ ከእስር ቢለቀቅም ከፖለቲካው ወደ ኋላ አላፈገፈገም፡፡ አንድነት ፓርቲን በመቀላቀል የብሔራዊ ም/ቤትና የሥራ አሥፈፃሚ አባል በመሆን ለዋና ጸሐፊነት ተመርጦ ላንድ ዓመት በቆራጥነት አገልግሏል፡፡

ብቃቱን በማስመስከሩም በም/ሊቀመንበርነት የሕዝብ ግንኙነት ሐላፊ ሆኖ ተመርጦ በማገልገል ላይ እንዳለ ነው ርምጃው ያልጣመው ገዥው ፓርቲ ከግንቦት 7 ጋር በማገናኘት የሽብርተኝነት ጥላሸት በመቀባት መስከረም 3 ቀን 10 ሰዓት ላይ ከመንገድ የታጠቁ ኃይሎች ከመኪና አስወርደው ይዘውት የሄዱት፡፡
Andualem 2-10-2 (2)
የቤተሰብ ሁኔታ
ወጣቱ ፖለቲካኛ አንዱዓለም አራጌ ባለትዳርና የሁለት ህፃናት አባት ነው፡፡ አንዱዓለም አራጌ ትዳር የመሠረተው ከእስር ከተፈታ በኋላ በ2000ዓ.ም ከዶ/ር ሰላም አስቻለው ጋር በሥርዓተ ተክሊልነው፡፡

አንዱ ዓለም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ባደረገው የነፃነት ትግል ወህኒ ተወርውሮ ጠባብ ክፍል ውስጥ ቢቀመጥም በፍርድ ቤት የሚከተለውን ተናግሮ ነበር፦
“መንግሥት ለኢትዮጵያ ሕዝብ የአፋና ሥራ እየሠራ ነው፡፡ እኔም አንዱ የዚህ ሰለባ ነኝ፡፡ ፍ/ቤት ነፃ ሆኖ የራሱን ሂደት ያያል የሚል እምነት ስለሌለኝ እስከመጨረሻው የሞት ፍርድ ድረስ ቢደርስብኝም ከመቀበል ሌላ የምከራከረውም ሆነ የምናገረው ነገር የለኝም”
አንዱዓለም አራጌ መስከረም 4 ቀን2004ዓ.ም፡፡

የሕሊና እስረኛው አንዷለም አራጌ የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች የ2005 ዓ.ም ምርጡ ሰው ተብሎ ተመርጧል።

የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች የ2005 ዓ.ም የዓመቱ ምርጦች ታወቁ

$
0
0

New Picture (5)
Andualem 2-10-2 (2)(ዘ-ሐበሻ) ዘ-ሐበሻ ጋዜጣና ድረገጽ በየዓመቱ አንባቢዎቻቸውን በማሳተፍ “የዓመቱ ምርጥ ሰው” በማለት ይሰይማሉ። ከ2 ዓመት በፊት መምህር የኔሰው ገብሬ በዘ-ሐበሻ አንባቢዎች ምርጥ ሰው ተብሎ የተሰየመ ሲሆን ባለፈው ዓመት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አሸንፎ እንደነበር ይታወሳል። በዚህ ዓመት ዘ-ሐበሻ ለአንባቢዎቿ ባቀረበችው ጥያቄ መሠረት 598 ሰዎች በዓመቱ ውስጥ ተጽዕኖ ፈጣሪ ያሉትን ምርጥ ሰው ጠቁመዋል። በተለይ አንባቢዎች እስር ቤት የሚገኙ ወገኖችን አንዱን ከአንዱ ማበላለጥ እንዳይሆን የሚል ፍራቻቸውን እየገለጹ የነበረ ቢሆንም በምርጫው ሕዝቡ እስር ቤት ያሉትን ሰዎች አስታውሶ መምረጡ በራሱ የታሰሩት ወገኖች እንዳልተረሱ ያሳያል የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች በሌላ በኩል ነበሩ።
የዘ-ሐበሻ 598 መራጮች ባደረጉት ምርጫ የዘ-ሐበሻ የዓመቱ ምርጦች የሚከተሉት ናቸው። (ይህ ማለት ግን ሌሎቹ ምርጥ አይደሉም ማለት ሳይሆን ብዙ ድምጽ ያገኙ ለማለት ነው)

የዓመቱ ምርጥ ሰው፦ አንዷዓለም አራጌ

የዓመቱ ምርጥ ሰላማዊ ትግል፡ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች

የዓመቱ ምርጥ ጋዜጠኛ (ከወንዶች)፡ ፡ ተመስገን ደሳለኝ

የዓመቱ ምርጥ ጋዜጠኛ (ከሴቶች) ፡ ርዕዮት ዓለሙ

የዓመቱ ምርጥ አክቲቪስት ታማኝ በየነ

የዓመቱ ምርጥ ስፖርተኛ መሐመድ አማን

(አጠቃላዩን ውጤት በPDF ይመልከቱት)


የማለዳ ወግ …አምላክ ሆይ ! የአዲሱ አመት ተስፋና ምኞታችን አሳካው !

$
0
0

YeMaleda Weg
ነብዩ ሲራክ ከሳዑዲ አረቢያ

አንድየ ሆይ! ያላንተ እዚህ መድረስ አይታሰብምና ከሁሉ አስቀድሜ ለከበረው ስምህ ፣ ለማይደፈር ለማይገሰሰው ሰማያዊ ክብርህ ፣ ለቸርነት ፣ ምህረት ይቅርታህ ምስጋና ይድረሰው ! አባታችን አዳም ትዕዛዝክህ ተላልፎ ታላቁን ስህተት ፈጸመ ፣ ከገነትም ተባረረ ! አባት ሆይ ! አዳም አጠፋ ብለህ አልተውከንም ! የምህረት አምላክ ነህና መንግስትህን እንወርስ ዘንድ በህግ ትዕዛዛትህ እንድንመራ አዘዝከን! ዳሩ ግን ትዕዛዛት ህግ ቀኖናህን ስንጥስ ኖርን … ይህ ሆነ ብለህም አልተውከንም …
ያለባላ በዘረጋህው ሰማይ ፣ ያለመሰረት ባነጠፍከው ምድር ፣ በእጹብ ስራህ የምድር መቀነት አድርገህ ባንሰራፋህው ውቅያኖስ እና ወንዝ ደምቀን ስታኖረን የምንበላው የምንጠጣውን የምንለብስ የምንጠለልበት በመለኮታዊ ስልጣን ከቸርነት እና ከምህረትህ ጋር ያልተውከን አንተው ብቻ ነህ ! እናም እናመሰግንሃለን ! ዘመን በዘመን ሲተካ ፣ ትውልድ በትውልድ ሲታደስ የዛሬ ባለተሮች ሆነናልና ለቀኖና ህግ የምንገዛ ለሰማያዊ ትዕዛዝህ የምናከብር አድርገን ! በይቅርታ ቸርነትህ ተጠብቀን አዲሱን አመት ስንቀበል የአዲሱ አመት ምኞታችን ብዙ ነው …ከሁሉም በላይ የሰው ልጅን ኢትዮጵያን እና ህዝቧን አንድነታችን ከሚያናጋ ፣ ህብረታችን ከሚንድ እኩይ ስራ ሁሉ ትጠብቃት ዘንድ ምኞቴ ነው ! በአዲሱ አመት መባቻ አሮጌው አመት ለመሸኘት ስንሰናዳ የሃገር የወገናችን ጉዳይ የሚያሳስበን የሚያስጨንቀን ተጠራርተን እንዲህ ብልን የህብረት ምኞት ተመኘን … አዲሱ ዓመት ሲጠባ፣ በአዲስ መንፈስ አዲስ ሕልም ለአገራችን ብሩህ እድገት ለወገኖቸቻችን ሰላም ጤና ህብረት ጥንካሬ የማለሙንቀዳሚ የምኞት ህልም ለማጠናከር ቃል ገባን። ኢትዮጵያ የብሔር፣ የሃይማኖት፣ የሃብት፣ የትምህርት፣ የፖለቲካ አመለካከት እና ሌሎችም ልዩነቶች አብሮነታችንን የማያደናቅፉባት፤ ከነልዩነታችን በጋራ እድገት የምንጠቀምባት፤ ለሁላችንም እኩል ዕድል እና ተጠቃሚነት የሚቀርብባት፤ ሁላችንም እንደ የችሎታችን ለጋራ ነጻነታችን፣ ደኅንነታችን እና ብልፅግናችን የምንሠራባት ሃገር ትሆን ዘንድ ተመኘን . …ለሃገራችን ብሩህ መጻኤ ህይዎት በጋራ ስኬታማ የምንሆንባት፤ እንዲሁም ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚያፈቅራት፣ በዜግነቱ የሚደሰትባትና የሚኮራባት ኢትዮጵያ እንድትሆን በጋራ የአዲስ አመቱን አዲስ ምኞት ተመኘን ! አቤቱ የጭንቀት ምልጃ ልመናችን ተቀበለው ! ተስፋ ምኞታችን አሳካው !
ስደት ክፉ ነገር ነው … በስደት ረክሰናል ፣ በስደት ተዋርደናል ፣ በስደት መልካሙ ገጽታችን ከፍቷል ! ለስደቱ የከፋ መከራ አማኝ ለመሆኔ የአረብ አለም የገፋሁት ህይዎት አማኝ ምስክር መሆኔን በፊትህ ስመሰክር አንተ አታውቀውም ብየም አይደለም ! እናም ለቀሩው ትምህርት ቢሆን ደግሜ ደጋግሜ እናገረዋለሁ !

ለአመታት በከተምኩበት የአረቡ አለም የስደተኛ የከፋ መከራ የከፋ ነው ! የተሻለ ኑሮን ለመግፋት ከሚለው የተሻለ ኑሮ ፈላጊ ይልቅ የኑሮ ውድነት እና ድህነቱ አፈናቀሏቸው ወደ አረብ ሃገራት የሚሰደዱት ወገኖች ስቃይ በቃላት ሊገልጹት የሚቻል ያለመሆኑ ምስጥር ስደቱ ከሞት ጋር ተፋጦ የሚከወን ነው! ይህ በመኖርና አለመኖር መካከል በሚደረገው አሰቃቂ ስደት በሶማሌና በጅቡቲ እና በሳውዲ በቀይ ባህር ማዕበል እና ጭልጥ ባሉ በርሃዎች እልፍ አእላፍ ዜጎች ውሃውና በርሃው እየበላቸው በሃዘን ተለይተውናለል ! በራሳችን አዘዋዋሪ ዜጎች በንዋው ፍቅር ተለክፈው ጨክነው ጎድተውናል! ዜጎች በዘላን ሴሰኛ አረቦች እየተደፈሩ ሊናገሩት የሚሰቀጥጥ ግፍ እየተፈጸመባቸው እስከ ወዲያኛው አሸልበዋል ! ነፍሳቸውን ይማረው ! በባህር እና በበርሃዎች የቀሩትን ዜጎችስቃይ ህልፈት እያመመን ሲቀጥል በውል በማይታይ የማይጨበጥ የሃገራት የህግን ማዕቀፍ ወደ አረብ ሃገራት በኮንትራት ስራ ስም የሚሰደዱ ዜጎች ሰቆቃም ከህገወጡ ስደት ባልተለ የከፋ ሆኗል! ያሳለፍነው አሮጌ አመት ዜጎች ያለ ጠባቂ መብት አስከባሪ እንደጨው ሲበተኑ የሚሰደርስባቸው ፈተና ቀላል አልሆነም! ድህነትንና የኑሮ ውድነትን ሸሽተው የመጡ እድሜ ያልጠገቡ እህቶች እና ወንድሞች መሪር የመከራ ጩኸት ከፍ ብሎ ተሰምቷል ! ብዙዎች ድምጻቸው ሳይሰማ በግፍ ጠፍተዋል ፣ ከሞት የተረፉት በአካልና በመንፈስ ሁከት ደዌ ተሸብበው አብደውና ጨርቃቸውን በአደባባይ ጥለው ያየንበት አሰቃቂ ሰቆቃ ተስተናግዷል ! ይህ ሁሉ ግፍ ሲፈጸም ለመብት ማስጠበቁ የተሰየሙ ምስለኔዎቻችን የፈየዱልንን የመብት ጥበቃ ከማውሳት የበደሉንን በቁጭት ማዘከሩ ይቀላል ! ይህ ሆነ ብለን ግን አንተን ከማመስገን እና በጎ በጎውን ከመመኘት አንቦዝንም !
አቤቱ አምላክ ሆይ ! የምህረት የቸር አምላክ ነህና በአዲሱ አመት በስደት የተሰበረ ልባችን አጽናው ! ለሃገሩ ለወገኑ ቀናኢ መንግስት ስጠን ! ከተሰየሙለትና ከቆሙለት ሃገር ወገናዊ በጎ አላማ ይልቅ በቡድናዊ ስሜት ኑሯችን ያጨለሙትን ልብ አቅናው ! በመዋዕለ ንዋይ ታውረው በወገን ደም የሚበለጽጉትን አዘዋዋሪ ደላሎች በጭካኔ የታበለ ልብ አራራው !
ከህብረት ይልቅ መለያየትን ፣ ከሰላም ይልቅ ብጥብጥን ከመመኘት ሰውረን ! ክፉ ክፉ ከሚያሳስበን እኩይ ሰይጣናዊ ምግባር እቅበን ! ልዩነታችን ከፍቷልና በህብረት አንድነት ትስስር አሽረው ! አንድ አድርገን ! አዲሱን አመት በአዲስ ተስፋ እጀምረው ዘንድ በማወቅና ባለማዎቅ ያስቀየምኩ ፣ ያስከፋኋቸው ይቅርታየን ይቀበሉ ዘንድ ልባቸውን አራራው ! አቤቱ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ ! አንተም በይቅርታህ ጎብኘን ! ዘመኑን የምህረትና የይቅርታ ዘመን አድርግልን !
አቤቱ ሁሉንም ማድረግ የማይሳንህ አምላክ ሆይ ! የአዲሱ አመት ተስፋና ምኞታችን አሳካው !
አሜን ! ! !
ነቢዩ ሲራክ
መስከረም 1ቀን 2006 ዓ.ም
ከሳውዲ አረቢያ

ርዕዮት ዓለሙ በ እስር ቤት የረሃብ አድማ ጀመረች፤ በሙስና የታሰሩት ኮ/ል ሃይማኖት እያስፈራሯት መሆኑን ተናገረች

$
0
0

 ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ

ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ

የ2005 ዓ.ም በዘ-ሐበሻ አንባቢዎች የዓማቱ ምርጥ የሴት ጋዜጠኛ በሚል የተመረጠችውና በእስር ቤት እየማቀቀች የምትገኘው ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ከትላንት ጀምሮ ከእናት ከአባት እና ከነፍስ አባት ውጪ እንዳትጠየቅ በመከልከሏ የረሃብ አድማ ላይ መሆኑና ጋዜጠኛ በፍቃዱ ኃይሉ በፌስቡክ ገጹ ባሰራጨው መረጃ ገለጸ።

በቅርቡ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ክስ ከተመሰረተባቸው ውስጥ አንዷ የሆኑት ኮ/ል ሃይማኖት (በተመሳሳይ ወንጀል ክስ የተመሰረተባቸው እና የጉምሩክ አመራር የነበሩት አቶ ገ/ዋህድ ባለቤት)፤ ርዕዮት ያለችበት ክፍል እንዳሉና፤ ከኮ/ል ሃይማኖት በተደጋጋሚ ዛቻ ፣ ስድብ እና ማስፈራሪያ እየደረሰባት እንደሆነ በዛሬው እለት ሊጠይቋት ለተፈቀደላቸው ለእናቷ ገልፃለች፡፡ እንዲሁም ከማረሚያ ቤቱ የሴት ፖሊሶችና እና ደህንነቶችም ተመሳሳይ ማስፈራሪያ፣ ስድብ እና ዛቻ እየበረታባት እንደሆነ ተናግራለች፡፡

ዛሬ ለበዓል ሊጠይቋት ከሄዱ ቤተሰቦቿ እና ጓደኞቿ መሃል እናቷ ብቻ እንዲያዩአት የተፈቀደላቸው ሲሆን፤ እየደረሰባት ያለውን የሰብአዊ ጥሰትም በመቃወም ከትላንት ጀምሮ የምግብ አድማ ላይ መሆኗን በመግለጿ፤ ይዘውላት የሄዱትን ምግብ መልሰውታል ያለው ጋዜጠኛው “በዚህ ስሜት ውስጥ ያሉትን የርዕዮት ቤተሰቦች ለማፅናናትም የሚከብድ ነገር ነው፡፡” ሲል ስሜቱን ገልጿል።

2005 እንዴት አለፈ? –የአመቱ አበይት ክንውኖች –በማህሌት ፋንታሁን Zone 9

$
0
0

ዶ/ር መሠረት ቸኮል

ዶ/ር መሠረት ቸኮል

በማሕሌት ፋንታሁን

ክቡራት የዞን 9 ነዋሪዎች ዓመቱ ከማለቁ በፊት እንዴት እንዳለፈ ለማስታወስ እንዲረዳን በማሰብ በ2005 የተከናወኑ አበይት ተግባራትን በዓመቱ የጊዜ መሥመር ላይ እንደሚከተለው ለማሳየት ሞክረናል፡፡ መልካም አዲስ ዓመት ይሁንላችሁ፡፡
መስከረም
•  መስከረም 11/2005 የተከበሩ ኃ/ማርያም ደሳለኝ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ሆነው፣ የተከበሩ ደመቀ መኮንን ደግሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ቃለ መሐላ ፈፀሙ፣
•  መስከረም 17 ቀን 2005 ድምፃዊ ቴድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በሒልተን ሆቴል አንድ ሺሕ ያህል ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ጋብቻውን ፈፀመ፣
ጥቅምት
•  ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ አሜሪካን ሃገር ከሚገኘው የዓለም አቀፉ የሴቶች ሚዲያ ፋውንዴሽን የ2012 ‹ፅናት በጋዜጠኝነት ሥራ› የተሰኘ ሽልማት አገኘች፣
•  የ2005 የእስልምና ምክር ቤት /መጅሊስ/ ምርጫ በየቀበሌው ተካሄደ፣
ሕዳር
•  የጋዜጠኝነት እና የኮሚውኒኬሽን ባለሙያ ዶ/ር መሠረት ቸኮል ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፣
•  ጠ/ሚኒስቴር ኃ/ማርያም ደሳለኝ አቶ ቴድሮስ አድሃኖምን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤አቶ ሙክታር ከድር እና ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በጠ/ሚኒስቴርነት ማዕረግ የሲቪል ሰርቪስ፣ የትራንስፖርት እና ቴክኖሎጂ ሚኒስተር፤ አቶ ከበደ ጫኔን የንግድ ሚኒስቴር እንዲሁም ዶ/ር ከሰተብርሃን አድማሱን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አድርገው ሾሙ፣
tewedrosታኅሳስ
•  በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ የወንጀል ችሎት በቀረበባት የሽብርተኝነት ወንጀል 14 ዓመታት እስርና 33 ሺሕ ብር ቅጣት የተጣለባት ጋዜጠኛና መምህርት ርዕዮተ ዓለሙ፣ በይግባኝ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የእስር ጊዜዋን ወደ አምስት ዓመታት በመቀነሱ ምክንያት ለሰበር ችሎት “በሥር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል” ስትል አቤቱታ አሰምታ፤ ሠበር ሰሚ ችሎቱ በሰጠው የመጨረሻ የቅጣት ውሳኔ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያስተላለፉትን የቅጣት ውሳኔ አፀና፣
•  የአውሮፓ ፓርላማ አባላት ለጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በጻፉት ግልጽ ደብዳቤ፤ ከሽብርተኝነት እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ክስ ተመስርቶበት የ18 ዓመት እስር የተፈረደበት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በአፋጣኝ ከወህኒ ቤት እንዲለቀቅ ጥያቄ አቀረቡ፣
•  አራት በፍ/ቤት እስር የተፈረደባቸው የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች የ2012 የሄልማን/ሃሜት ሽልማት መሸለማቸውን፤ ተሸላሚዎቹ በእስር ላይ የሚገኙት እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት ዓለሙ፣ ውብሸት ታዬ እንዲሁም በሌለበት የተፈረደበት የቀድሞዋ የ“አዲስ ነገር” ጋዜጣ አዘጋጅ መስፍን ነጋሽ ሲሆኑ ጋዜጠኞቹ ሽልማቱን ያገኙት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሐሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን ለማስጠበቅ ላደረጉት ጥረት መሆኑም ተጠቅሷል፣
ጥር
•  የ33ቱ ፓርቲዎች ኅብረት በሚያዚያ ወር የተካሄደውን የአዲስ አበባ መስተዳደር እና በመላው ሃገሪቱ በሚካሄደው የወረዳና የክልል ምክርቤቶች ምርጫዎች ላይ ላለመሳተፍ ውሳኔ አሳለፉ፣
•  በአሠልጣኝ ሰውነት ቢሻው የሚመራው ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከ31 ዓመታት ቆይታ በኋላ በደቡብ አፍሪካ በሚካሄደው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ በቃ፤ በዚሁ የአፍሪካ ዋንጫ ላይ አዳነ ግርማ ከ37ዓመት በኋላ የመጀመሪያ የሆነችውን ብቸኛ ጎል ለኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ አስቆጠረ፣
•  ኢትዮጵያ የራሷን ሳተላይት ለማምጠቅና የሰው ኃይሏን ከቴክኖሎጂው ጋር ለማስተዋወቅ የሚያስችል የሙከራ ሥራ መጀመሯን፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የኢኮኖሚ ዘርፍ አስተባባሪና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ደብረ ፅዮን ገብረ ሚካኤል አስታወቁ፣
•  በ2004 ከሃያ ዓመት እስር በኋላ የተፈቱት ከፍተኛ የደርግ አመራር የነበሩት ኮሎኔል ደበላ ዴንሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፣

አቡነ ማቲያስ

አቡነ ማቲያስ

የካቲት
•  ድምፃዊ ታምራት ሞላ ለረጅም ዓመታት ሕክምና ሲከታተል በነበረበት የደም ካንሰር ሕመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፣
•  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክርስቲያን 6ኛውን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስን አድርጋ መረጠች፣
•  የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ተባባሪ ፕሮፌሰር የነበሩት ዶክተር ዮናስ አድማሱ በ69 ዓመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ፣
•  በአዲስ አበባ በባሕል ሕክምና ታዋቂ የነበሩት ሐኪም ማሞ ኃይሌ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፣
•  ከሁለት ዓመት በፊት በአምባሳደርነትና በምክትል አምባሳደርነት ማዕረጐች ተሹመው በተለያዩ አገሮች ከተመደቡ የቀድሞ ከፍተኛ ባለሥልጣናት መካከል ዐሥራ ስምንት የሚሆኑት ወደ አገር እንዲመለሱ ተደረገ፤ ሁለቱ በድጋሚ ሹመት ወደሌሎች አገሮች ሲመደቡ የተቀሩት ግን በአገር እንዲቀሩ ውሳኔ ተላለፈ፣
መጋቢት
blue party•  በኢትዮጵያ ሕዝብ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት ኮሚቴ፣ በሰማያዊ ፓርቲ እና በባለራዕይ ወጣቶች ማኅበር አስተባባሪነት፤ በጣሊያን አፊሌ በተባለ ቦታ የተገነባውን የግራዚያኒ ኀውልት እና መታሰቢያ ቦታ በመቃወም፤ ከሰማእታት ኀውልት (6 ኪሎ) አንስቶ እስከ ጣሊያን ኤምባሲ የሚዘልቅ የእግር ጉዞ መጋቢት 8/2005 ጥሪ ተላለፈ፤ ሰልፉን ለማካሄድ የተገኙ አባላት እና የሰልፉ ዓላማ ደጋፊዎች ሰማእታት ኀውልት መሰባሰብ እንደ ጀመሩ ፖሊስ ሰልፉን ሕጋዊ አይደለም ብሎ በኃይል በመበተን እና 40 የሚሆኑ በሰልፉ የተገኙ ሰዎች ለአንድ ቀን ታስረው ተፈቱ፣
•  የኢሕአዴግ ዘጠነኛ ጉባዔ በባሕር ዳር ከተማ ለአራት ቀናት ተካሄደ፣
•  ‹ኢትዮትዩብ› በአሜሪካ አምስተኛ ዓመቱን አከበረ፣ በዕለቱም ‹ለፕሬስ ነፃነት የተጋ› በሚል ዓመታዊ ሽልማት ለጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ተሸላሚ በወኪል ተበረከተለት፣
•  የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ መታሰቢያ “መለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን” መሥራች ጉባኤ በአፍሪካ ኅብረት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሄደ፣
ሚያዚያ
abune_petros•  ላለፉት አምስት ዓመታት በተደረገ ኮንትራት አማካኝነት በአሜሪካ ስትጎበኝ የነበረችው ሉሲ (ድንቅነሽ) ጉዞዋን ጨርሳ ወደ ሃገሯ ተመልሳ ለሕዝብ ዕይታ ክፍት ሆነች፣
•  ፒያሳ አራዳ ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ጀርባ የሚገኘው የአቡነ ጴጥሮስ ኀውልት፤ በአዲስ አበባ በመሠራት ላይ በሚገኘው የቀላል ባቡር ግንባታ ምክንያት ከነበረበት ቦታ ተነስቶ ብሔራዊ ሙዚየም እንዲገባ ተደረገ፣
•  በጋምቤላ ክልል አኙዋክ ዞን አቦቦ ወረዳ ልዩ ቦታው ቁርጫ በሚባል አካባቢ 17 ተማሪዎችንና በኢንቨስትመንት ሥራ ላይ የተሠማራው ሳዑዲ ስታር ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ሠራተኞች የሆኑ ስድስት ሰዎችን፣ በድምሩ 23 ሰዎችን በጥይት ደብድበው በመግደልና በሽብር ወንጀል ተከሰው ከነበሩት 14 ግለሰቦች መካከል፣ ዘጠኙ በሞት እንዲቀጡ ተወሰነባቸው፣
•  ጋምቤላን ለሰባት ዓመታት በፕሬዚዳንትነት የመሩት አቶ ኡሞድ ኡቦንግ የጋምቤላ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን) እና የክልሉ ምክር ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ከፓርቲው ምክትል ሊቀመንበርነትና ከክልሉ ፕሬዚዳንትነት እንዲነሱ በመወሰኑ፣ ምክትል ፕሬዚዳንቱ አቶ ጋትሉዋክ ቱት በምትካቸው የክልሉ ፕሬዚዳንትነት ሆነው ተሾሙ፣
•  የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰኔ 20 ቀን 2004 ዓ.ም. የሰጠውን የጥፋተኝነት ብይንና ብይኑን ተከትሎ የተጣለባቸውን የቅጣት ውሳኔ በመቃወም፣ ከነሐሴ ወር 2004 ዓ.ም. ጀምሮ በተለያዩ ጊዜያት ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የይግባኝ አቤቱታ አቅርበው በነበሩት፣ እነ እስክንድር ነጋ ላይ ሚያዝያ 24 ቀን 2005 ዓ.ም. የመጨረሻ ውሳኔ ተሰጥቶ ይግባኝ ካሉት ፍርደኞች ውስጥ ከክንፈሚካኤል ደበበ (አበበ ቀስቶ) በስተቀር የሁሉም የሥር ፍርድ ቤት ቅጣት ውሳኔ እንዲፀና ተደረገ፤ በመሆኑም ክንፈሚካኤል በሥር ፍርድ ቤት ተጥሎበት የነበረው የ25 ዓመት ፅኑ የእስራት ቅጣት ማቅለያው ሲያዝለት ወደ 16 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀነሰ፣
•  የፌዴራሉ ዋና ኦዲተር በ124 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች የ2004 ዓ.ም. ሒሳብን ኦዲት በማድረግ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲያቀርብ፣ መንግሥት ሊያገኘው የሚገባ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ አለመታወቁንና በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ደግሞ መንግሥት ማጣቱን አሳወቀ፤ ከዚህ ውስጥ ትምህርት ሚኒስቴር 401.757 ሚሊዮን ብር የሚሆነውን ከፍተኛ ድርሻ የያዘ ሲሆን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር 173.756 ሚሊዮን ብር፣ የግብርና ቴክኒክ ሙያና ትምህርት ሥልጠና ፕሮጀክት ማስተባበሪያ 155.597 ሚሊዮን ብር የታየባቸው መሥሪያ ቤቶች መሆናቸው ተገለፀ፣
ግንቦት
Melaku-Fenta-and-Gebrewahid-Woldegiorgis•  የፌደራል ፀረ ሙስና እና የሥነ ምግባር ኮሚሽን የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መላኩ ፋንታን ጨምሮ ሌሎች የባለሥልጣኑ ኃላፊዎችና ባለሀብቶች በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር በመዋላቸው የክስ የፍርድ ሒደቱ ተጀመረ፣
•  በባሕርዳር ከተማ የፌደራል ፖሊስ አባል የሆነ ግለሰብ በከፈተው ተኩስ 10 የሚሆኑ ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ ወንጀለኛው ፖሊስም ራሱን አባይ ወንዝ ውስጥ ወርውሮ ሕይወቱን አጠፋ፣
•  በኢትዮጵያ የአውሮፓ ኅብረት አምባሳደር ዣቪየር ማርሻል በ61 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፣
•  በከፍተኛ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር በዋሉት በሚኒስትር ማዕረግ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ ምትክ፣ የአዳማ ከተማ ከንቲባ የነበሩት አቶ በከር ሻሌ ተሾሙ፣
•  በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በመምህርነት፣ በተመራማሪነት እና በልዩ ልዩ የኃላፊነት ቦታዎች ያገለገሉት እና “ቤተ ክሕነትና መንግሥት በኢትዮጵያ ከ1262-1527” (Church and state in Ethiopia 1262-1527) በተሰኘው መጽሐፋቸው የሚታወቁት ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፣
•  አዲስ አበባ የሚከበረውን የአፍሪካ ሕብረት 50ኛ ዓመት የወርቅ እዮቤልዩ በዓል ላይ ሰማያዊ ፓርቲ ታላቅ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ቢያደርግም የአ.አ መስተዳድር ሰልፉን ጥበያ የሚያደርግ የፖሊስ ኃይል እጥረት አለብን በማለት ለሌላ ጊዜ እንዲያዘዋውሩት ጠየቀ፣
•  የአፍሪካ አንድነት ድርጅት/የአፍሪካ ኅብረት የተመሰረተበትን 50ኛ ዓመት በተለያዩ ዝግጅቶች ዋናው ጽ/ቤት በሚገኝበት በኢትዮጵያ አከበረ፣
•  የሕዳሴው ግድብ ቀጣይ የግንባታ ምዕራፍ የሆነው ወንዙን አቅጣጫ የማስቀየስ ሽራ ተከናወነ፣ ይህን ተከትሎም ከሃገሪቷ ፖለቲከኞች ጋር በቀድሞው የግብፅ ፕሬዝዳንት ሙርሲ የተመራ ውይይት ሲካሄድ የግድቡ ሥራ እውን እንዳይሆን የሚያደርጉ ሐሳቦች መሰንዘራቸው፤ ይህ ውይይትም በስህተት በሃገሪቱ የብሔራዊ ቴሌቭዥን ጣቢያ በቀጥታ ተላለፈ፣
•  ሰማያዊ ፓርቲ በአዲስ አበባ ከተማ መነሻውን የፓርቲው ፅ/ቤት፤ መድረሻ ቦታውን ኢትዮ-ኩባ አደባባይ ያደረገ፣ በርካቶችን ያሳተፈ እና ከ97 ምርጫ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄደ፣
UDJ Candlelight vigilሰኔ
•  አንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ‹‹ሚሊዮን ድምፆች ለነፃነት›› የተሰኘ፣ ለሦስት ወራት የሚቆይ ሕዝባዊ ንቅናቄ ጀመረ፤ በንቅናቄው ሕዝባዊ ስብሰባዎች፣ ሠላማዊ ሰልፎችና በፀረ-ሽብር ሕጉ ላይ የተቃውሞ ፊርማ እንደሚሰበሰብ ተነግሯል፣
•  ለቀደሙት 20 ወራት በሽብር ወንጀል ተፈርዶበት ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚገኘው ጋዜጠኛ፣ ጦማሪ እና አራማጅ እስክንድር ነጋ፤ ከባለቤቱ እና ልጁ ውጪ በሆኑ ቤተሰቦቹ፣ ወዳጆቹ እና አድናቂዎቹ እንዲጎበኝ ሲፈቀድለት የሚጎበኝበት ሰዓትም እንደማንኛውም በማረሚያ ቤቱ የሚገኙ ታራሚዎች እንደሆን ተደረገ፣
•  በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው የ2013ቱ የቢግ ብራዘር አፍሪካ ውድድር ከኢትዮጵያ የሄደችው ቤቲ የወሲብ ትእይንና አነጋጋሪ መሆን፣
•  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ሦስተኛውን ጨዋታ በሃገሩ አድርጎ ተጋጣሚውን ደ/አፍሪካን 2-1 በመርታት የቀሪውን ጨዋታ ነጥብ ሳያሳስበው ምድቡን በአንደኝነት መምራቱን ቢያረጋግጥም በማግስቱ በፌዴሬሽኑ ስህተት ብሔራዊ ቡድናችን ሦስት ነጥቦችንና ሦስት ጎሎች የሚያስቀጣውን ጥፋት ማጥፋቱን ተነገረ፣
•  ፓርላማው በ2005ዓ.ም የሥራ ዘመን ማጠናቀቂያ ላይ የሥልጣን ሹም ሽር በማድረግ አስር አዳዲስ ሚኒስተሮች ሾመ፣
betty-bba-chase-ethiopia•  የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ወደ ኮንፌደሬሽን ካፕ የምድብ ማጣሪያ ያለፈ የመጀመርያ ክለብ መሆኑ፣
ሐምሌ
•  ወጣት የፖለቲካ ተንታኙ ጃዋር መሐመድ አልጀዚራ የቴሌቪዥን ጣቢያ በሚያዘጋጀው ‹ዘ ስትሪም› በተሰኘ ፕሮግራም ላይ ስለ ኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ እና ተያያዥ ጉዳዮች የብዙዎችን (በተለይም ማኅበራዊ አውታር ተጠቃሚዎችን) ትኩረት የሳበ እና ያነጋገረ ንግግር አደረገ፤
•  አንድነት ፓርቲ በጎንደርና ደሴ ከተሞች በተመሳሳይ ቀን (ሐምሌ 7/2005) ‹‹ሚሊዮን ድምፆች ለነፃነት›› በተሰኘው ሕዝባዊ ንቅናቄው ሠላማዊ ሰልፎችን አካሄደ፣
•  አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገ/ሥላሴ ከሁለት ዓመት በኋላ በሚካሄደው በ2007ቱ ጠቅላላ ምርጫ አዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ በመወዳደር ወደ ፓርላማ ለመግባት ማቀዱን በቃለ ምልልሶች አረጋገጠ፣
ነሐሴ
merara gudina•  የአምስት ፓርቲዎች ጥምረት የሆነው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ አንድነት መድረክ ዶ/ር መረራ ጉዲናን ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ፣
•  1434ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በእስልምና እምነት ተከታዮች በተለይ በአዲስ አበባ ብሔራዊ ስታዲየም ሲከበር፣ ፌደራል ፖሊስ በዓሉን ለማክበር የተገኙትን በርካታ ሰዎች ላይ እስር እና አካላዊ ጥቃት ፈፀመ፣
•  ሞስኮ በተዘጋጀው የ14ኛው የዓለም አትሌትክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ 3ት የወርቅ፣ 3ት የብር እና 4ት የነሃስ ሜዳሊያ በማግኘት ከዓለም 6ኛ ከአፍሪካ 2ኛ ሆና አጠናቀቀች፤ ወርቁን ያስገኙት ዝነኞቹ የረጅም ርቀት ተወዳዳሪዎች ጥሩነሽ ዲባባ እና መሰረት ደፋር እንዲሁም በታሪካችን ለመጀመሪያ ጊዜ የሆነውን የ800ሜ ርቀት አሸናፊ መሐመድ አማን ናቸው፣
•  የአቡነ ጳውሎስ እና የቀድሞ ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ሙት ዓመት በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበሩ፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሙት ዓመት ለማክበር መንግሥት አረንጓዴ ዘመቻ አደረገ፣ በርካታ ፓርኮችንም በስማቸው ተሰየመላቸው፣
•  ወጣቱ ድምፃዊ ኢዮብ መኮንን ባደረበት ድንገተኛ ሕመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፣
•  የ33ቱ ፓርቲዎች ዐቢይ ኮሚቴ ባደረገው የጋራ ስብሰባ፣ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት በየጋዜጣው ላይ የሚሰጡት መግለጫ የፓርቲው አቋም መሆኑ በመረጋገጡና በጋራ ለመሥራት ከተስማሙበት የጋራ ሰነድ ውጪ ሆነው መርሖችን በመጣላቸው ምክንያት ፓርቲው ከኅብረቱ መታገዱን አሳወቁ፣
•  ሰማያዊ ፓርቲ ነሐሴ 26/2005ዓ.ም በአዲስ አበባ ሊያካሂድ ያቀደውን እና ከሦስት ወር በፊት ሲያስተዋቅ እንዲሁም ዝግጅት ሲያካሂድ የከረመበትን ሠላማዊ ሰልፍ፤ የአዲስ አበባ ፖሊስ ሰልፉ እንዳይካሄድ ከለከለ፣
•  በተለያዩ የእምነት ተቋማት ኅብረት ጠሪነት፤ በመንግሥት ወኪሎችና የኢሕአዴግ አባላት ቀስቃሽነት የሃይማኖት አክራሪነትና ፅንፈኝነትን ለመቃወም በሚል ነሐሴ 26/2005ዓ.ም በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሠልፍ ተካሄደ፣
Ethiopia national teamጳጉሜ
• የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ የምድብ ማጣርያ ከሴንትራል አፍሪካ ሪፐብሊክ ጋር ኮንጎ ብራዛቪል ላይ ገጥሞ ተጋጣሚውን 2 ለ 1 በመርታት፤ ምድቡን በመሪነት በማጠናቀቅ አፍሪካን የሚወክሉ 5 ቡድኖች ተለይተው ለሚወጡበት 10 ብሔራዊ ቡድኖች ለሚያደርጉት የደርሶ መልስ ጥሎ ማለፍ ከገቡት ውስጥ መካተት ቻለ፡፡

Health: ኮሌስትሮልዎ ከፍ ያለ ከሆነ ዓመት በዓሉን የግድ በሥጋ ብቻ ማክበር የለብዎትም

$
0
0

ከዶ/ር ዓብይ ዓይናለም
ኮሌስትሮል ከተለያዩ ምግቦች ወደ ሰውነት ዘልቆ እና ከመጠን አልፎ ሲጠራቀም የደም ባንቧዎች ግድግዳና መንገዳቸው ላይ በመለጠፍና መንገዱን በማጥበብ ደም እንደልቡ ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች እንዳይደርስ ያግዳል፡፡ ይህም ለህዋሳቶች በህይወት መቆየት ወሳኝ የሆኑት ንጥረ ነገሮችና ኦክስጅንም አይሄዱም ማለት ነው፡፡ በጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስና ኦክስጅን ማጠርን ተከትሎ የሚመጣው እንደኩላሊት ድክመት አይነት ክፉ ህመሞችም ከሚከሰቱባቸው መንስኤዎች ዋነኛውም ይኸው የኮሌስትሮል ጠንቅ ነው፡፡ ኮሌስትሮል በተፈጥሮው ክፋት ያለው ቅባት አይደለም፡፡ የተለያዩ የፆታ ሆርሞኖችን ጨምሮ የሚዘጋጁበት ንጥረ ነገር በመሆኑ ለሰውነታችን እጅግ በጥቂት መጠኑ ያስፈልገዋል፡፡ ነገር ግን በተለያዩ ምግቦች ስንወስደው ይጠራቀምና መዘዝ ያመጣል፡፡ እሾህን በእሾህ ነውና ባለሞያዎች ዋነኛዎቹ ኮሌስትሮልን ከደም ውስጥ በከፍተኛ ምጣኔ ለማውረድና ከመዘዞቹ ለመጠበቅ ከሚመክሩዋቸው ማርከሻዎች ውስጥ ዋናኛዎቹ ምግቦች ሆነው ተቀምጠዋል፡፡ በተለያዩ በሳይንስ በተረጋገጡ መንገዶች ከመድኃኒት ይልቅ ቅድሚያ ተሰጥቷቸው የኮሌስትሮል ምጣኔያቸው ከፍተኛ ለሆኑ ሰዎችና ለሌሎች ወደዚያው እየተንደረደሩ ላሉትም እንዲያዘወትሩዋቸው የተመከሩ ምግቦች ላይ በዛሬው ሜዲካል ፊቸራችን ትኩረት አድርገናል፡፡ እነዚህ ከመድኃኒት ይልቅ የተመረጡት የኮሌስትሮል መቀነሻ ምግቦች የትኞቹ ይሆኑ? በምን አይነት አሰራር? – አዲሱ ዓመት ኮሌስትሮላችንን የምንቀንስበት ይሁን!
aokado
1. አፕል
አፕል በተለይ መጥፎ የሚባለውን አይነት የኮሌስትሮል አይነት ከሚቀንሱ ፍራፍሬዎች ይመደባል፡፡ አፕል ሟሚ የሆነ ፔክቲን የተባለ ቅመም ያለው ሲሆን ኮሌስትሮልን ከደም የመምጠጥ ባህሪ ስላለው ደም ውስጥ ያለውን ኮሌስትሮል ይቀንሳል፡፡ ይህ ብቻ አይደለም አፕል ውስጥ ያሉት ፍላቪኖይድስ የሚሰኙ ፀረ መርዛማ ኬሚካሎች ኮሌስትሮል ቅባት በደም ውስጥ እንደልቡ እንዳይንቀሳቀስ መንገዱን በመቁረጥም ይሳተፋል፡፡ አንድ አፕል ዶክተርን ያስጥል የሚባለው ብሒል እውነት ከሚሆንባቸው የአፕል የጤና ጥቅሞች አንዱ ይኸው የኮሌስትሮልን መጠን የመቀነስ ተግባሩ እንደሆነ በጥናት መረጋገጡን ሃርቫርድ ኒውስሌተር የሐምሌ ወር እትም በዝርዝር ያትታል፡፡
2. ቡናማ ሩዝ
ቡናማው የሩዝ አይነት በውስጡ ልዩ ዘይት አለው፡፡ ይህ ዘይት ነው ኮሌስትሮልን የመቀነስ ብቃት ያአለው፡፡ በተለይ ቡናማ ሩዝን እንደ አተር እና መሰል ጥራጥሬዎች ጋር ቀላቅሎ መመገብ ምርጥ የፕሮቲን ቅልቅል እንደሆነ እና ኮሌስትሮልንም መዋጊያ መሆኑን ባለሞያዎቹ ይጠቁማሉ፡፡ ቡናማ ሩዝ ማግኒዥየም፣ ቫይታሚን ቢ እና ፋብየርን የያዘ በመሆኑም ከልብ ጋር ተስማምቶ የሚዋሃድ ለልብ ጤና የሚጠቅም እንደሆነ በስፋት ይገለፃል፡፡
3. ቀረፋ
ስለቀረፋ ጠቀሜታ የቀደሙት ሰዎችም በስፋት ሲያወጉ እና ከበረከቱም ሲካፈሉ ቆይተዋል፡፡ የህክምናው ሳይንስ ሰዎችም ያደረጉት ጥናት ይህንን ያረጋግጣል፡፡ ጆርናል ዲያቤትስ ኬር የተሰኘ የምርምር ውጤቶች ማስፈሪያ መጽሔት ላይ የወጣ ጥናት እንደሚለው በቀን ግማሽ ማንኪያ ቀረፋ መጠቀም በስኳር ህሙማን ዘንድ አብዝቶ የሚታየውን የደም ግፊት ህመም በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ይቻላል፡፡ መጥፎ የሚባለውን አይነት ኤልዲኤል ኮሌስትሮልም ከደም ውስጥ ማውረድ መቻሉን ማረጋገጣቸውን አጥኚዎቹ በመጽሔቱ አስፍረዋል፡፡ ስለሆነም በሻይም ይሁን በሌላ የአመጋገብ መልክ ቀረፋን ማዘውተር ኮሌስትሮልን ይዋጋል፣ ከምግብ ዝርዝርዎት ይጨምሩት ይላሉ ባለሞያዎች፡፡
4. ነጭ ሽንኩርት
ስለነጭ ሽንኩረት ጥቅሞች ዘርዝሮ መጨረስ ይከብዳል፡፡ በነጭ ሽንኩርት ውስጥ ታምቀው ከሚገኙ ንጥረ ነገሮች አንዱ የሆነው አሊሲን ባክቴሪያ እና ፈንገሶችን ከመግደሉ በተጨማሪ ለአንዳንድ የጨጓራ ችግሮችም ሁነኛ መፍትሄን ይሰጣል፡፡ የደም መርጋትን ማስቀረቱም ልዩ ጥቅሙ ነው፡፡ ከእነዚህ ቀደም ብለው ከሚታወቁ ጥቅሞች በተጨማሪ በምን አይነት ስርዓት እንደሆነ ባይታወቅም ለጤና ጎጂ የሆነውን ኮሌስትሮልን መጠን የመቀነስ ጥቅም እንዳለው ሳይንቲስቶች በቅርቡ በጥናት ጽሑፎቻቸው አሳይተዋል፡፡ ግምቶች እንደሚያሳዩት ግን ነጭ ሽንኩርት ኮሌስትሮልን የሚቀንሰው የጉበትን ኮሌስትሮል የማምረት አቅም በማዳከም ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ነጭ ሽንኩርትን የማይደፍሩ ከነበረና የውፍረትና የኮሌስትሮል ጉዳይ የሚያሳስበዎት ከሆነ ወደ ነጭ ሽንኩርት ቢያዘነብሉ ከጠቀሜታውን ይቋደሳሉ፡፡
5. አጃ
አጃን በተለያየ መልክ ለሚጠቀሙት ኢትዮጵያውያን ጠቀሜታዎቹ ብዙም እንግዳ ላይሆኑ ይችላሉ፡፡ ከኮሌስትሮል ቅነሳ ጋር ስለመያያዛቸው ግን ብዙም የሚታወቅ አልነበረም፡፡ እንደ ጥናቶች ጥቆማ ግን አጃ ውስጥ ያሉ ፋይበሮች የኮሌስትሮልን ምጣኔ በከፍተኛ መጠን ይቀንሳሉ፡፡ አጃ ውስጥ ያሉት ግሉካጎን የሚሰኙ ንጥረ ነገሮች ይህን ቁልፍ ስራ ይሰራሉ፡፡ ቀን ከ5 እስከ 10 ግራም አጃ መውሰድ የኮሌስትሮልን መጠን በቀን ቢያንስ በ5 በመቶ እንደሚቀንሰው ባለሞያዎቹ ይገልፃሉ፡፡ በየትኛውም መልክ ቢወስዱት በጣም እሳት ሳያጠቃው ሲወሰድ አጃ ውጤቱ ከፍተኛ ነው ይባላል፡፡ አሜሪካን ጆርናል ኦፍ ክሊኒካል ኒውትሪሽን ላይ የሰፈረው ጥናት ይህን ያረጋግጣል፡፡
6. ኦሜጋ ፋቲ አሲድ ከነጭ ዓሣ
ቅባት ያላቸው ዓሣዎች በተለይ ኦሜጋ ፋቲ አሲድ በብዛት ያላቸው ሲሆን ይህም ለልብ በሽታ፣ ለመዘንጋት ችግር እና ለሌሎችም ጭምር በመዋጋት በኩል ከፍተኛ ጠቀሜታዎችን ስለመስጠቱ ከዚህ ቀደም ብዙ የተባለለት ነው፡፡ ሳይንቲስቶች ጥቅሞቹ በዚህ ብቻ እንደማይቆም ጠቁመው ለኮሌስትሮል ቁጥጥርም ሚናው የላቀ እንደሆነ እየገለፁ ይገኛሉ፡፡ በአሜሪካው የሎማ ሊንዳ ዩኒቨርሲቲ የተሰራ ጥናት እንደጠቆመው መጥፎ ቅባቶችን ከዓሣ በሚገኙ ጤናማ ቅባቶች መተካት የጥሩውን አይነት ኮሌስትሮል ምጣኔ በ6 በመቶ ጨምሮ ተገኝቷል፡፡ ይህም በተዘዋዋሪ መጥፎው አይነት ኮሌስትሮል ምጣኔ እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡
7. ሻይ
ሻይ ካንሰርን በመከላከል በኩል ያለው አስተዋፅኦ ከታወቀ ረዘም ያሉ ጊዜያትን አስቆጥሯል፡፡ በቅርቡ የተደረጉ ተጨማሪ ጥናቶች ደግሞ በደም ውስጥ የሚገኝ ኮሌስትሮል መጠንን በመቀነስ የደም ፍሰትን የማቀላጠፍ ሚናውም አቻ የማይገኝለት መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ በተለይም ጥቁር ሻይ ላይ በተደረገው ጥናት በሶስት ሳምንታት በተከታታይ ጥቁር ሻይን የጠጡ ባለከፈተኛ ኮሌስትሮል ሰዎች ደም ኮሌስትሮል ቅባት መጠናቸው በ10 በመቶ ሊቀንስ መቻሉ በዩኤስዲኤ የምርመራ ውጤቶች ላይ ሰፍሮ ይገኛል፡፡
8. ጎመን
ጎመንና ሌሎቹም አረንጓዴ ቅጠል ያላቸው ምግቦች ዘንድ የሚገኘው ሊውቲን የተባለው ንጥረ ነገር ከማርጀት ጋር በተያያዘ ለሚመጣ የአይን ጡንቻዎች መድከም ሁነኛ መፍትሄ ሆኖ ያገለግላል፡፡ በዚህም በርካቶችን ከአይነ ሰውርነት ሲጠብቅ መኖሩን ባለሞያዎች በጽሑፎቻቸው አስፍረውታል፡፡ ተጨማሪ ጥቅሞቹ ደግሞ የልብ በሽታን ከመዋጋት ጋር የሚያያዝ ነው፡፡ ይህንንም የሚያደርገው የደም ቧንቧ ግድግዳ ላይ ተለጥፈው የሚገኙ የኮሌስትሮል ቅባት ክምችቶችን እያጠበ በማውጣት ብቃቱ ነው፡፡ በሚቀጥለው ጊዜ ወደ ገበያ የሚወጡበት ምክንያት ካለ ከፌስታልዎ ውስጥ ጎመን አብሮ ተገዝቶ መምጣቱን ያረጋግጡ፡፡ ለልብዎ ጤና ወሳኝ ቅመሞች አሉትና፡፡ በዚህ መልክ ከኮሌስትሮል ጥርቅምና ተያይዘው ከሚመጡት በሽታዎች ራስዎን ይጠብቃሉ፡፡ የቤተሰብ ኃላፊ ከሆኑም ለቤተሰብዎ አባላት ይህን በረከት እንዲያካፍሉ ባለሞያዎች ይመክራሉ፡፡ ታዲያ ጎመኑ ለዛው እስኪሟጠጥና ጠቃሚው ቁልፍ ንጥረ ነገር ተጠቃሎ እስኪሄድ አያብስሉት፡፡
9. አቮካዶ
አጎካዶ ሞኖሳቹሬትድ የሚሰኙት ጤናማ ቅባቶችን በብዛት የያዘ ፍሬ ሲሆን ይህ ተፈጥሮውም ጤናማ የሚባለውን የኮሌስትሮል አይነት ከደም ውስጥ ለመጨመርና መርዛማውን ባለዝቅተኛ ግዝፈት ኮሌስትሮል ለመቀነስ ይረዳዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ሲቶስትሮል የተባለ ከምግብ የምንወስደውን ከፍተኛ ኮሌስትሮል መጥጦ የማስቀረት ከፍተኛ ብቃት ያለው ንጥረ ነገር ስለሚይዝ ጠቀሜታውን ከፍ ያደርገዋል፡፡ ይሁንና አቮካዶ ከፍተኛ የቅባትና ካሎሪ ይዘት ያለው ፍሬ ስለሆነ ማዘውተሩ ለውፍረት ሊዳርግ ስለሚችል አለፍ አለፍ እያሉ ቢጠቀሙበት የበለጠ እንደሚመከር የሐምሌው ወር 2011 የሃርቫርድ ህክምና ትምህርት ቤት ኒውስ ሌተር ያሳስባል፡፡
10. ቸኮሌት
ቸኮሌት ቅባት እንዳለው በብዛት ቢነገርም በውስጡ ያለው የፀረ መርዛማ ኬሚካሎች (አንቲኦክሲዳንትስ) ምጣኔ የሚበልጥ በመሆኑ ጠቀሜታው የበለጠ ይጎላል፡፡ በተለይ ጥቁር ቸኮሌት ይህን በብዛት ስለሚይዝ የኮሌስትሮል ቁጥጥር ውስጥ የራሱን ጠቃሚና ጣፋጭ ሚና ይወጣል፡፡ የአሜሪካ ክሊኒካል ጆርናል መጽሔት ይህን በማስረጃ አስደግፎ ጽፎታል፡፡ ጥቁር ቸኮሌት በ12 ሳምንታት ጊዜ ውስጥ 24 ከመቶ የሚሆነውን የኮሌስትሮል መጠን ሊቀንስ መቻሉ በጥናቱ ታውቋል፡፡ የደም መርጋትንና የህዋሳት መጣበቅን የመግታት ተጨማሪ ጥቅሞቹንም የሚያስታውሱት ባለሞያዎች ከወተት የተደባለቀው ቸኮሌት ጠቀሜታው ያን ያህልም ስለሆነ ጥቁሩን ቸኮሌት የሙጥኝ ይበሉ ብለዋል፡፡ ቸኮሌት ለፍቅረኛ ብቻ ያለው ማነው? ለራስዎም ጤንነት ሁነኛ መፍትሄ ነው፡፡ መጥፎ ሙድን በመለወጥ ዘና የማድረግ ብቃቱን ታዲያ እንዳይዘነጉ፡፡ ትንሽ ድብርት ቢጤ ከሞካከረዎት ቸኮሌት ጥሩ መፍትሄ ነው፡፡µ

በህገ-ወጥ ርምጃ ሕጋዊው ሰላማዊ ሰልፋችን አይቀለበስም!!! ሲሉ አንድነትና በ33ቱ ፓርቲዎች በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ

$
0
0

በአንድነትና በ33ቱ ፓርቲዎች በጋራ የተሠጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ላለፉት ሦስት ወራት ‹‹የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት›› በሚል መሪ ቃል በመላ ኢትዮጵያ ህዝባዊ ንቅናቄ ሲያደርግ መቆየቱ የሚታወቅ ነው፡፡ በዚህም መሰረት በጎንደር፣ በደሴ፣ በባህርዳር፣ በአርባ ምንጭ፣ በጅንካ፣ በፍቼና አዳማ ከተሞች ሕዝቡን ያሳተፉ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፎች ያጋጠሙ የገዥው ፓርቲ እንቅፋቶችን እየተራመደ በተሳካ ሁኔታ ያደረገ ሲሆን በተለያዩ ከተሞች ሕዝባዊ ስብሰባዎችንም አከናውኗል፡፡

ፓርቲያችን የመጀመሪያውን ሕዝባዊ ንቅናቄ ለማጠናቀቅም በአዲስ አበባ ከተማ መስከረም 5 ቀን 2006 ዓ.ም የሚካሄደውን የመጀመሪያው ምዕራፍ የማጠቃለያ የተቃውሞ ሰልፍ ከ33ቱ ፓርቲዎች ጋር ለማካሄድ ወስኖ ይህንንም ውሳኔ ለኢትዮጵያ ህዝብ በማሳወቅ ሰፊ እንቅስቃሴ ውስጥ ገብቷል፡፡ በዚህ ሂደትም አመራሩና የፓቲው አባላት በከፈሉት መስዋዕትነትና ግፊት ህዝቡን ያሳተፉ የተቃውሞ ሰልፎች እንደጅምር አበረታች ናቸው ብለን ብናምንም የህዝቦች መብት ሳይሸራረፍ እስከሚከበር ድረስ፣ ነፃነታችን እስከሚረጋገጥ ድረስ የሚቀጥል እንደሆነ ለማረጋገጥ እንወዳለን፡፡

በአዲስ አበባ የምናካሂደውን የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ለማከናወን ከማሳወቅ ጀምሮ የገጠመን ውጣ ውረድና ማደናቀፍ ትልቋ ከተማችን ሃላፊነት በማይሰማቸው አስተዳዳሪዎች የምትመራ መሆኑንም ያረጋገጥንበት አጋጣሚም ነው፡፡

ሰላማዊ ሰልፍና ሕዝባዊ ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል ደብዳቤ ላለመቀበል ከማስቸገርም በላይ የቢሮ ሓላፊዎችና ሌሎች በቀጥታ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ስልጠና፣ ስብሰባ፣ እንግዳ ለመቀበልና ሌሎችን ተልካሻ ምክንያቶች በመደርደር ለማደናቀፍ ጥረት አድርገዋል፡፡ ደብዳቤ ፈርሞ መቀበል የማይችል አካል ሃላፊነት የማይሰማው ነው ከማለትም ባለፈ በህግ የሚያስጠይቅ ሀላፊነትን ባግባቡ አለመወጣትን የሚያመለክት ድርጊት ነው፡፡

ከንቲባውና የከንቲባው ፅ/ቤትም በአግባቡ ካለማስተናገድም በላይ የአንድነትን ከፍተኛ አመራሮች (ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳና አቶ አስራ ጣሴን) ሀላፊነት በጎደለው ሁኔታ ስለሰላማዊ ሰልፉ እንደራደር በማለት አመላልሰዋል፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ማሳወቅ በቂ ቢሆንም ከከንቲባው ጋር መነጋገር ያስፈለገበት ዋና ምክንያት ለፖሊስ በሚሰጥ የውስጥ መመሪያ እየተካሄደ ያለው ማደናቀፍ እንዲቆም፣ መስተዳድሩ መመሪያ ብሎ ያወጣውና ለወረቀት ብተና፣ ፖስተር ልጠፋ፣ የመኪና ላይ ቅስቀሳና ፔቲሽን ለማስፈረም ልዩ ፈቃድ እንደሚያስፈልግ የሚያዝ፤ ይህ ካሆነ ፖሊስ ርምጃ እንዲወስድ የሚያደርገውን ሕገ-መንግስት የሚጥስ መመሪያ በተመለከተ ነበር፡፡

ምንግዜም ህጋዊ መስመር ተከትሎ ከማስተዳደር ይልቅ በህገ-ወጥ መንገድ ማፈንና ማደናቀፍ የሚመርጠው ገዥ ፓርቲ ለህጋዊ የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄያችን የመረጠው መንገድ ህገ-ወጥነትን ነው፡፡ ይህ ህገወጥነትም መንግስትን ዋጋ ያስከፍለዋል፡፡ ስለዚህ፡-

1ኛ. ሰላማዊ ሰልፋችንን ለማድረግ ከነሐሴ 21 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ ያሳወቅን በመሆኑ በታቀደው ቀን መስከረም 5 ቀን 2006 ዓ.ም ከጠኋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ ይደረጋል፡፡

2ኛ. ለሰላማዊ ሰልፉ ቅስቀሳና ሂደት ላይ ለሚከሰቱ ማናቸውም ጉዳቶች ተጠያቂው መስተዳድሩና መንግስት ነው፡፡

3ኛ. ሕገ-መንግስቱን የማስከበር ተልዕኮ ያለው ፖሊስ በህገ ወጥ መመሪያ አባሎቻችንን ከማሰርና ማዋከብ እንዲቆጠብ እንዲሁም ህጋዊ መሰረት ያለውን ሰላማዊ ሰልፋችንን ፀጥታ የማስከበር ሃላፊነት እንዳለበት እያሳሰብን ቅስቀሳ በሚደረግበት ወቅት ተገቢውን ጥበቃ በማድረግ ሃላፊነቱን እንዲወጣና የህግ የበላይነትን እንዲያስጠብቅ ከአደራ ጋር እናሳስባለን፡፡ ህዝቡም መስከረም 5 ቀን 2006 ዓ.ም ወደ አደባባይ በመውጣት የተቃውሞ ድምፁን በሰላማዊ መንገድ እንዲያሰማ ሃገራዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

 

             ዘላለማዊ ክብር ለኢትዮጵያ!!!

የአንድነት ፓርቲና የ33ቱ ፓርቲዎች

መስከረም 1 ቀን 2006

አዲስ አበባ

MILLIONS OF VOICE FOR FREEDOM !

የሙስና ነገር (ክፍል ሁለት) በዳዊት ከበደ ወየሳ

$
0
0

የሙስና ነገር (ክፍል ሁለት)
በዳዊት ከበደ ወየሳ

እውነት የማይመስሉ ግን እውነት የሆኑ የሙስና ታሪኮች – በኢትዮጵያ።

አሁን በኢትዮጵያ አቆጣጠር ወደ 2006 ተሻግረናል። ከአመት ወደ አመት ስንሸጋገር ደግሞ ያለፈውን አመት የሙስና ነገር በገደምዳሜ ዳሰስ አድርገን ብናልፍ ክፋት የለውም። በመሆኑም የስራ ባልደረባዬ ክንፉ አሰፋ “ክፍል አንድ” ብሎ በጀመረው የሙስና ጉዳይ… “ክፍል ሁለት” ብዬ እኔ ቀጠልኩበት፤ አንብቡት።

የጉምሩክ ከፍተኛ ሃላፊዎች ሲታሰሩ፤ በየፊናው የነበሩ ጉምቱ ባለስልጣናት መደንገጣቸው አልቀረም። “እገሌስ መቼ ነው የሚታሰረው ወይም የምትታሰረው?” የሚለው ሹክሹክታም ከቢሮ አልፎ በአደባባይ የህዝቡ መነጋገሪያ ሆኖ ሰንብቷል። በዚያኑ ሰሞን ከኢትዮጵያ የመጣ አንድ ዘመዴ ጋር ቁጭ ብለውን ስናወራ፤ “ገብረዋህድ የሚባለውንስ እንኳንም አሰሩት።” አለኝ።

“ምነው?” አልኩት።

“በጣም መጥፎ ሰው ነው” ብሎ ጀመረልኝ – ፊቱን አጨፍግጎ። “መጥፎ ሰው ነው። አንዳንዴ እንደተራ ሰው ሻይ ቤት እና ቡና ቤት ገብቶ፤ የሆነ ነገር አዝዞ ይቀመጣል። ከዚያም አንዱ ተስተናጋጅ፤ ሂሳቡን ከፍሎ ሲወጣ፤ ድንገት ደረሰኝ ይዞ ካልወጣ…  ከመቀመጫው ተነስቶ፤ ‘ሌቦች አጭበርባሪዎች’ ብሎ ይሳደብና ፖሊስ ወዲያው ጠርቶ የንግድ ቤቱን ያሳሽጋል።” (ደረሰኝ ለደንበኛ አለመስጠት ሙስና መሆኑን እዚህ ላይ ጠቅሰን እንለፍ)… እናም ይህ የጉምሩኩ ምክትል ሰውዬ ያላስለቀሰው ነጋዴ የለም።

ደግሞም በነጋዴዎቹ ቢበቃው ጥሩ ነበር። የመስሪያ ቤቱን ሰራተኞች በሙስና እየወነጀለ ያላሳሰረው ሰራተኛ እንዳልነበር፤ የቅርብ ሰዎች ያወራሉ። እዚህ ላይ አንድ አስቂኝ ነገር አለ። ይሄ ለሰማይና ለመሬት ከብዶ ህዝቡን ሲያስለቅስ የነበረ ሰውዬ በመጨረሻ የሱም ቀን ደረሰና ሊታሰር ሆነ። እናም በቁጥጥር ስር በዋለበት ቀን፤ ሁለት የፌዴራል ፖሊስ አባላት ወደ ቢሮው ገብተው በቁጥጥር ስር ሊያውሉት ሲሉ ይደነፋል።

“ማን እንደሆንኩ ታውቃለህ?” ይላል።

“አዎ እናውቃለን!” አሉት። አንድ ሁለት ቃል ከተለዋወጡ በኋላ፤ ልክ እንደ ነጋ ገብረእግዚአብሄር – አንቱ ወደተባሉ ከፍተኛ የህወሃት አባላት ስልክ መደወል ይጀምራል። ከባለስልጣናቱ የሚሰማው ነገር ያልጠበቀው ነበር። በመሃል ፌዴራል ፖሊሶቹ ከቢሮው እንዲወጡ ያደርግና ከውስጥ በኩል የቢሮውን በር ይቆልፈዋል። ፖሊሶቹ ቢያንኳኩ – ቢያንኳኩ የሚከፍት ሰው ጠፋ። የጉምሩክ መስሪያ ቤት ተጨነቀ። በቢሮ አካባቢ ያሉት “በቃ ይሄ ሰውዬ እንደ አጼ ቴዎድሮስ የራሱን ህይወት ሊያጠፋ ነው” ብለው በመስጋት፤ ከአሁን አሁን የተኩስ ድምጽ በጉጉት ይጠባበቃሉ። ሌሎች የግቢው ጥበቃ ሰራተኞች ደግሞ፤ ‘ከፎቅ ላይ ራሱን ወርውሮ ይገድላል’ በሚል ስጋት አንገታቸውን ወደ ፎቁ አንጋጠው፤ ድንገት ከፎቅ ላይ ሲወድቅ ሮጠው እንደኳስ ሊቀልቡት ተዘጋጅተዋል። ይሄ ሁሉ ሲሆን፤ ሰውየው ቢሮውን ቆልፎ ከህወሃት ባለስልጣናት እስከ ጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ ድረስ ስልክ እየደወለ ነበር።

የደወለላቸው ባለስልጣናት በሙሉ ለራሳቸው በመስጋት የተለያየ ምክንያት እየሰጡ ስልኩን ጆሮው ላይ ዘጉበት። በዚህች ቀውጢ ወቅት በመከላከያ ውስጥ የኮሎኔል ማዕረግ የተሰጣት፤ እጩ ጄነራል ሚስቱም ልታድነው አልቻለችም። ፌዴራሎቹ ጉዳዩን አስመልክተው ወደ አለቆቻቸው ደወሉ። “ሰውየው እራሱን እንዳያጠፋ ስለሰጋን ነው” አሉ።

ከአለቆቻቸው የተሰጣቸው መልስ አጭር ነበር። “እራሱን አያጠፋም። ተጨማሪ ትዕዛዝ እስከሚሰጥ ድረስ እዚያው ቆዩ”።

“ሰራተኛ ሲወጣ፤ እሱ ከቢሮ ካልወጣ ሰብራችሁ ትገባላችሁ” ተባሉ። ፖሊሶቹም ሰራተኛው ከስራ እስኪወጣ መጠባበቅ ጀመሩ። ሰራተኛው ከወጣ በኋላ፤ ፌዴራሎቹ በር የሚሰብሩበትን መሳሪያ እያፈላለጉ ሳለ ገብረዋህድ ከተደበቀበት ቢሮ ሹክክ ብሎ ወጣ።

“ምነው ብዙ የምታስጠብቀን?” ብለው ጠየቁት ፌዴራሎቹ።

“በሰራተኛው ፊት ታስሬ መሄድ ስላልፈለኩ ነው” አላቸው።

ገብረዋህድ በማግስቱ የፈራው ደረሰበት።  ለፖሊስ ቃሉን ከሰጠ በኋላ፤ በሚቀጥለው ቀን የመንግስት ንብረት እንዲያስረክብ ወደ ጉምሩክ ሲወሰድ፤ በሰራተኞቹ ፊት ሁለት እጁን ተጠንጎና በፌዴራል ፖሊሶች እየተጎነተለ መጣ። “ከዚህ በላይ ውርደት?” ብለን ቃሉን አለመጨረሹ ይሻለናል።

ሌላም የሚገርም ነገር አለ። ይሄ ሰው ከመታሰሩ አንድ ወር በፊት በመላው አገሪቱ የሚገኙ የጉምሩክ ባለስልጣናትን በኮንፈረንስ ስብሰባ አድርጎ ነበር። የፈረደበትን የሟቹን ጠቅላይ ሚንስትር ፎቶ በመለጠፍም “በሙስና ለምትጨማለቁት እንደደርግ ጥይት አናጎርሳችሁም፤ እናስራችኋለን።” እያለ ስለመለስ ራዕይ ሲያወራ ነበር። በንግግሩም መጨረሻ፤ (ያን ሰሞን የመለስ ሚስት የምኒልክን ቤተ መንግስት ለቅቃ ነበርና…) “በአሁኗ ደቂቃ የመለስ ዜናዊ ልጆች መኖሪያ ቤት እንኳን የላቸውም። ሜዳ ላይ ነው የቀሩት።” ሲል የዋሆቹ ሲያለቅሱ፤ ነገሩን የሚያውቁ ግን ስቅስቅ ብለው ይስቁ ነበር።

ገብረዋህድ ከታሰረ በኋላ በስሙ የአርሲን ቆዳ ስፋት የሚያህሉ የቤት ካርታዎች ሲገኙ፤ “ምናለበት አንዱን ቤት ሜዳ ላይ ለወደቁት ለመለስ ዜናዊ ልጆች ቢሰጣቸው ኖሮ?” መባሉ አልቀረም።

ወደ አዲስ አበባ ከተማ ሲገቡ፤ ቦሌ መንገድ ላይ ያሉትን ህንጻዎች ከተመለከቱ፤ ህዝቡ ራሱ እንደጎበዝ አስጎብኚ ይነግርዎታል። “ይሄ ህንጻ የጄነራል ጻድቃን ነው። ይሄኛው የጄነራል እገሌ ነው እያሉ፤ መድሃኔአለም ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት ከሚገኘው ኤድናሞል ህንጻ ጋ ሲደርሱ ደግሞ “ከጎኑ ያለው የሚያምር ህንጻ የጄነራል አባ ዱላ ነበር።” ይሏችኋል።

“አሁንስ የማነው?” ካሉ አስጎብኚዎ የሙስናን ነገር እያጣቀሰ ወሬውን ሊቀጥል ይችላል። እኛም እንንገርዎ – የነ አባ ዱላን ነገር። አባ ዱላ ገመዳ አሁን የፓርላማው አፈ ጉባዔ ነው። ከዚያ በፊት የኦሮሚያ ፕሬዘዳንት፡ ከዚያም በፊት የመከላከያ ሚንስትር፡ ከዚያ በፊት በሻዕቢያ የተማረከ የደርግ ወታደር ነበር… መቼም አንድ ወታደር ለሻዕቢያ እጅ ሰጥቶ ከተማረከ ከዚያ በፊት ምን ነበር? ተብሎ አይጠየቅም። እናም አባዱላ እና በሙስና ስለተሰራው ትልቅ ቤተ መንግስት የመሰለ ቤታቸው ከማውራታችን በፊት፤ ሰውየው ሌሎቹን ጄነራሎች ጭምር እንዴት በሙስና እንዳነካኩ ላጫውታችሁ።

በአንድ ወቅት ለጄነራሎቹ (ያው ከአባ ዱላ በቀር ብዙዎቹ ህወሃቶች ናቸው) አዲስ አበባ ውስጥ መኖሪያ እንዲሰሩ መሬት ተሰጣቸው። የሲሚንቶ እና የሌላ ሌላው ነገር ዋጋ መጨመርን ተከትሎ የብዙዎቹ አቅም የሚችለው አልሆነም። እናም የኦሮሚያ ፕሬዘዳንት የነበሩት አባ ዱላ ገመዳ ከሌሎቹ ጄነራሎች ጋር በመመሳጠር በኦሮሚያ የሚገኙ መሬቶች፤ እየተሸነሸኑ ለጄነራሎቹ በስጦታ መልክ እንዲሰጣቸው አደረጉ። ይህ የተደረገው ያለ ምክንያት አይደለም። በኋላ ላይ ጄነራሎቹ በኦሮሚያ ባለስልጣናት የተሰጣቸውን መሬት እየሸጡ፤ አዲስ አበባ ላይ በተሰጣቸው መሬት ላይ ህንጻ

ከቢሾፍቱ እስከ አዳማ፤ አልፎም እስከ ሻሸመኔ ድረስ ያሉ መሬቶች በዚህ አይነት የሙስና ቅብብሎሽ ለጄነራሎቹ ታደሉ። አባ ዱላ ገመዳ ይሄንን ሁሉ ሲያደርግ፤ ለሱም ትንሽ ጉርሻ ይሰጠው ነበር። ያቺ በጉቦም በ እጅ መንሻም ያገኛትን ገንዘብ ሰብስቦ ቦሌ መድሃኔአለም ፊት ለፊት የተንጣለለ ህንጻ መገንባት ጀመረ።

እንግዲህ ልብ በሉ። በቦሌ መንገድ እርስዎ ብቻ አይደሉም የሚሄዱት- ሟቹ ጠቅላይ ሚንትርም በዚያ መንገድ ብዙ ጊዜ ተመላልሰው ነበር – ያውም መንገድ እየተዘጋ። እናም አስጎብኚው ለርስዎ እንደሚነግርዎ ለመለስ ዜናዊም፤ “ይሄ የእገሌ ነው። ይሄኛው የጓደኛችን እገሌ ነው።” መባሉ አልቀረም። ነገር ግን ሟቹ ጠቅላይ ሚንስትርም ቢሆኑ፤ የስርአቱ ዋነኛ መገለጫ የሆነውን የሙስና አደጋ በዝምታ ሲያልፉት ነበር። የኢህአዴግ ሰዎች ሙስናን እንደጥፋት የሚያዩት ከዚያ ሰውዬ ጋር እስከሚጣሉ ድረስ ነው። እናም ከአባ ዱላ ጋር እስከሚጣሉና የጄነራልነት ማዕረጉን እስከሚገፈፍ ድረስ ምንም አላሉም። በኋላ ላይ ግን… አባ ዱላ ከህወሃት ሰዎች ጋር ሳይሆን ከራሱ ሰዎች ጋር መጋጨት ጀመረ። በተለይም በኦህዴድ ውስጥ ካለው ከነ ግርማ ብሩ ቡድን ጋር ክፉኛ ተጋጨ – የቁርጡ ቀን ሲመጣም በመታሰር፣ ክብርን በማጣት እና ንብረቱን በመስጠት መካከል ዋዠቀ።

በመጨረሻ አባ ዱላ ገመዳ ያሰራውን እና ሊኖርበት የነበረው በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የወጣበት ባለ ትልቅ ግቢ ቪላ ጥያቄ ውስጥ ገባ። ጸቡ እየከረረ ሲመጣ፤ በመጀመሪያ ደረጃ ያሰራው ትልቅ ህንጻ በሙስና መሆኑን ነገሩት። መጀመሪያ ሊከራከር ፈለገ። በኋላ ላይ ግን ደሞዙና የወጣው ወጪ እንደማይመጣጠን ሂሳቡን ሰርተው ሲያሳዩት፤ “አይ እኔ እንኳን Surprise ላደርጋችሁ ብዬ ነው” አለ።

ኦህዴዶቹም በመገረም፤ “ምንድነው Surprise የምታደርገን?” ሲሉ ጠየቁት።

“ይሄንን ቤተመንግስት የመሰለ ቪላ የሰራሁት ለኔ ሳይሆን፤ ለድርጅታችን ነው።” ብሎ የቤቱን ቁልፍ ሲያስረክብ፤ አጨብጭበው ዝም አሉት። አሁን በቦሌ በኩል ስታልፉ፤ “ይሄኛው የጄነራል አባ ዱላ ነበር” ይሏችኋል። ከርክክቡ በኋላ ግን የኦህዴድ ዋና ጽህፈት ቤት ሆኗል – እውነት የማይመስል የአገራችንን ታሪክ ነው እያወጋናችሁ ያለነው።

ባለስልጣናቱ “Surprise” ከመባላቸው በፊት፤ እዚያው ቤት ምሳም እራት ተጋብዘው በልተዋል። የቤት ምርቃቱ ጊዜ፤ ስጦታ ይዘው መጥተዋል። ጸቡ ሲመጣ ዝምድናው ወደ ሙስና ተቀይሮ፤ አባ ዱላ ገመዳ ቪላ ቤቱን ከነ ሙሉ እቃው የኦሮሚያ ቤተ መንግስት እንዲሆን ሰጥቶ ከመታሰር አመለጠ። የጄነራልነት ማዕረጉን ከመቀማት ግን አልዳነም። ከመከላከያ ሚንስትርነትም ሆነ ከኦሮሚያ ፕሬዘዳንትነት በጥፋት ተወንጅሎ ከተነሳ በኋላ ይህንን ታማኝ ሰው ሙስና የሌለበት ቦታ ሊመድቡት ፈልገው ክፍት የስራ ቦታ ፓርላማ ውስጥ ተገኘ። እናም የፓርላማው አፈ ጉባኤ በመሆን፤ ኢህአዴግን በማገልገል ላይ ይገኛል – አባ ዱላ (ምናሴ ገብረማርያም )።

እንግዲህ ይህ ሙስና የምንለው ነገር… ዋናዎቹን ሰዎች እስካላስከፋ ድረስ፤ በኢህአዴጎች ዘንድ እንደባህል የሚቆጠር ነውር ያልሆነ ተግባር ነው። የሙስና ነገር አውርተን… የኢህአዴግ ሙስና እመቤት ስለሆነችው ወ/ሮ አዜብ መስፍን ሳንጨዋወት ብንቀር እሳቸውም ቅር ይላቸዋልና ስለ ወይዘሮዋ ትንሽ እንዙር።

በአንድ ወቅት ለጄነራሎቹ መሬት ሲታደል ወይዘሮዋ ቦታ አምልጧቸው ኖሮ ተናደዋል። ወደ አዳማም ሆነ ቢሾፍቱ ደውለው ቢጠይቁ፤ “መሬት ተወዲ’ዩ” አሏቸው። ቆይተው ግን በኦሮሚያ ሰበታ ከተማ መሬት መሰጠት መጀመሩን ሰምተው፤ እንዲሰጣቸው ጠየቁና ተሰጣቸው። ከዚያም የሚያውቋቸውን ሰዎች እየላኩ መሬት ያሳድሉ ጀመር። በኋላ ላይ… የሰበታ ከተማ አስተዳዳሪዎች ሁኔታው ሲበዛባቸው፤ በወ/ሮ አዜብ አማካኝነት የሚላኩትን ሰዎች መሬት ከለከሏቸው። በዚህን ጊዜ ወ/ሮ አዜብ መስፍን እሳት ለብሰው፣ እሳት ጎርሰው ለከተማው አስተዳዳሪ ደወሉና ከፍ ዝቅ አድርገው ተናገሩት። በመጨረሻ የሆነው ነገር ነው የሚገርመው… ወይዘሮዋ ዛቻ ቢጤ አሰሙ። እንዲህ ሲሉ።

“እንዲያውም በሰበታ አካባቢ ሙስና አብዝታችኋል ማለት ነው! ሙስና ስላበዛችሁ ግምገማ መደረግ አለበት።”

ወ/ሮ አዜብ እንዳሉትም በህወሃት ሰዎች ታጅበው ሰበታ ከተማ በመገኘት የመንግስት ሃላፊዎችን ከላይ እስከታች አተረማመሷቸው። ለሳቸው መሬት የሰጧቸው ሰዎች ሳይቀር፤ በሙስና ተወንጅለው እየተለቀሙ ታሰሩ። መሃንዲሱ እና መሬት ፈቃጆቹ ሁሉ ተቀፈደዱ። ከዚያም የራሳቸውን ታማኞች ሹመው ሰበታ ከተማን ለቀው ተመለሱ። ባለፈው አመት ኢቲቪ ስመለከት እነዚያ በሰበታ ከተማ “ሙስና ውስጥ አላችሁበት” የተባሉ ሰዎች እያንዳንዳቸው ከአስር አመት በላይ እንደተፈረደባቸው ሰማሁ። በርግጥ ሰዎቹ ሙስና ውስጥ ነበሩበት። ቢሆንም ግን ለወ/ሮ አዜብ መስፍን እና ለሌሎች መሬት ሲሰጡ፤ ሙስና አልተባለም… የአዜብን “ትዕዛዝ አንቀበልም” ሲሉ ግን የጨዋታው ህግ ተቀይሮ፤ ሰዎቹ በሙስና ወንጀል እየተለቀሙ ወህኒ ወረዱ።

መቼም የወ/ሮ አዜብ መስፍን ታሪክ ማለቂያ የለውም። ባለፈው ሰሞን ደሞ፤ አቶ አያሌው የተባሉ ትልቅ ባለሃብት ፍርድ ቤት ቀርበው ሲናገሩ፤ “ክቡር ፍርድ ቤት እኔ ምንም ጥፋት እንደሌለብኝ አቃቤ ህጉም ያውቀዋል። የኔ ጥፋት ከወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋር በሽርካነት እንድሰራ ተጠይቄ እምቢ ማለቴ ነው።” ብለው ነበር። አቶ አያሌው በተከበሩበት አገር አስራ ስድስት አመት ተፈርዶባቸው ወደ እስር ቤት መወርወራቸውን ከጥቂት ወራት በፊት ስንሰማ ማዘናችን አልቀረም። እንግዲህ አቶ አያሌው በደርግ የሶሻሊዝም ዘመን ሳይቀር በንግድ ሙያ ውስጥ የቆዩ ናቸው። የደርግ ዘመን አልፎ በዘመነ – ነጻ ገበያ ሲታሰሩ ያልገረመው ሰው የለም።

እዚህ ላይ የምናወራው ላይ ላዩን የምናውቀውን… እውነት የማይመስል፤ ነገር ግን እውነት የሆኑ የሙስና ታሪኮችን ነው። ውስጥ ውስጡን የማናውቀው ብዙ ነገር ሊኖር እንደሚችል ምንም አያጠያይቅም። ሌላ ነገር ትውስ አለኝ። የዛሬ 12 አመት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ወደ አሜሪካ ሲመላለሱ፤ ብዙም አይን የሚገቡ ሰው አልነበሩም። ሃብታቸውም ሰማይ አልደረሰም ነበርና ብዙዎች ትኩረት አንሰጣቸውም ኖሯል። ሆኖም እዚሁ አሜሪካ ኮሎምበስ ኦሃዮ ለምትገኘው እህታቸው፤ 250 ሺህ ዶላር ካሽ ከፍለው ቪላ ቤት ሲገዙ ብዙዎቻችን ማመን አቃተን። እናም ‘አዜብ ሙስና ውስጥ የለችበትም’ እያለ ለሚጨቀጭቀኝ ዘመዷ ስልክ ደወልኩና ጠየኩት።

“የምንሰማው እውነት ነወይ?” አልኩት።

“ምኑ?” አለኝ።

“ዘመድህ ካሽ ከፍላ ለእህቷ ቪላ ቤት የመግዛቷ ነገር…” ብዬ ሳልጨርስ፤ የነገሩን እውነተኛነት አረጋግጦ በትህትና ሊያስረዳኝ ሞከረ።

“እሷም ሆኑ ልጆቿ ሲመጡ የሚያርፉበት ቤት ያስፈልጋቸዋል። … ታዲያ ይህን ማድረጓ ምን ያስደንቃል?” የሚል አይነት ምላሽ ሰጠኝ። ለነገሩ ከደጃዝማች ጎላ የሚወለዱ፤ የነአዜብ መስፍን የቅርብ ዘመዶች ብዙ ናቸው። ድርጊቷን የሚደግፉ እንዳሉ ሁሉ፤ በግልጽ የሚቃወሟትም አሉ። ለገንዘብ ሳይሆን ለህሊናቸው ላደሩ ዘመዶቿ አክብሮት እንዳለኝ በዚህ አጋጣሚ ጠቅሼ የውጪ ሃብት ግዢውን ነገር እዚህ ላይ ገታ ላድርገው።

          የ”ደቡብ ክልል” ፕሬዚዳንት የነበሩት የአቶ አባተ ኪሾ ጉዳይም አለ። አባተ ኪሾ  ከወያኔ ሳይጣሉ ከደቡብ በጀት ተመላሽ የሆነ ሰባ ሚሊዮን ብር (70.000.000) ለመንግስት ተመላሽ ሊያደርጉ ሲሉወዲህ በል! የምን መንግስት ነው?” በማለት ወ/ሮ አዜብ ተቀብለው ወስደዋል።  ብሩ ወደ አዜብ ካዝና ይግባ እንጂ የፖለቲካ ቂም የተቋጠረባቸው አቶ አባተ ወደ ወህኒ ከመወርወር አልዳኑም። አቶ አባተ ኪሾ ይህንን ጉዳይ /ቤትም ጭምር ምስክር ሰጥተውበት ነበር።

 

የወ/ሮ አዜብን ጉዳይ ጨርሼ ወደሌሎቹ መሄድ ብፈልግም። ብዙ እውነት የማይመስሉ፤ ነገር ግን እውነት የሆኑ አስገራሚ ነገሮች ታወሱኝ። ስለሁሉም ነገር ምንም ማለት ስለማልችል ጥቂት ነገር ብዬ የሴትዮዋን ነገር ልቋጭ። በኢትዮጵያ የፀረ ሙስና ኮሚሽን ሲቋቋም በዋናነት እንዲሰራ ከታዘዙት ነገሮች አንዱ፤ የመንግስት ባለስልጣናት ሃብታቸውን እንዲያስመዘግቡ ማስደረግ ነው። ይህ ስራ እንደተጀመረ… “አሻፈረኝ አላስመዘግብም” ካሉት ውስጥ ወ/ሮ አዜብ እና የህወሃት ጄነራሎች መሆናቸውን ከዚህ በፊት በሌላ ጉዳይ ላይ ጠቅሼው ነበር። አሁንም ልድገመው። እናም የወ/ሮ አዜብ መስፍን የሃብት መጠንም ሆነ ምንጭ እስካሁን ድረስ በመንግስት ደረጃ አልተመዘገበም። አሁንማ ሴትዮዋ ጥቁር ሲለብሱ፤ ጥቁር ለብሰው የሚያጅቧቸው፤ ሲያስነጥሳቸው መሀረብ የሚያቀብሉ አሽከሮች አላቸው። ሴትዮዋ ከመለስ ዜናዊ ሞት በኋላ እንደጎማ ተንፈስ ብለዋል። ሜጋ ሚሊዮን ዶላር ከሚያንቀሳቅሰው የህወሃት ኤፈርት ሊቀመንበርነት ተነስተው፤ የመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን ዛፍ አስተካይ ከመሆን ያለፈ ስልጣን እንደሌላቸው እየስማን ነው።

 

በሌሎች ላይ የሚደረገውን የሙስና ክስ አመሰራረት እያየን… “የሙስና እመቤቷ ወ/ሮ አዜብ እና ሌሎች የኢህአዴግ ሰዎችስ ተራ መቼ ይሆን?” ማለታችን አልቀረም። ደግሞም “የጉምሩክ ባለስልጣናት ሲታሰሩ ዋነኛውን ሃላፊ አቶ መላኩ ፈንታን ወንጀል አግኝተውበት ይመስላችኋል?” አይደለም። ነገሩ የህወሃቱን ገብረዋህድ ብቻውን ቢያስሩት በህወሃት አካባቢ ከፍተኛ ጫጫታ መምጣቱ አይቀርም። ስለዚህ ከብአዴንም “የአማራ ድርጅት አባል አስረናል” በማለት ነገሩን ለማብረድ የተጠቀሙበት ነው የሚመስለው።

 

ባለፈው አመት ብቻ ምን ያህል ሙስና እንደተፈጸመ እናውጋ እና እንለያይ። ባለፈው አመት (እ.ኢ.አ 2005) ከ1 ሺህ 500 በላይ ጥቆማዎች ለፀረ ሙስና ኮሚሽን ደርሰው በ200 ያህሉ ላይ ክትትል አድርጓል። የሚገርመው ግን ከሁለት ሺህ በላይ ጥቆማዎች ደግሞ፤ ከስልጣኔ በላይ ነው በማለት ባሉበት ትቷቸዋል። (ይህንን መረጃ ያገኘነው ከራሱ ከፀረ ሙስና መስሪያ ቤት ነው።) እነዚህ ከፀረ ሙስና ኮሚሽን አቅም በላይ የሆኑት እንግዲህ፤ የጄነራሎቹ፣ የነአዜብ እና የህወሃት ከፍተኛ ንብረት እና የመከላከያ ጉዳይ መሆኑ ነው።

ለመሆኑ መከላከያ ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ በሙስና ተወዳዳሪ ያልተገኘለት፤ ከፌዴራል መንግስት ውጪ የራሱ ባለ አምስት ሆቴል እና ሌሎች የንግድ ስራዎችና ገቢዎች እንዳለው ያውቃሉ? የምናወራው እውነት ስለማይመስሎት፤ የሙስና ታሪካችን ስለሆነ አብረውን ይቆዩ።

 

ፀረ ሙስና ኮሚሽኑ ከስልጣኑ ውጪ ያሉትን ሙስናዎች አይከታተልም። እናም ከዚህ በታች ያሉት ኮሚሽኑ እርምጃ ስለወሰደባቸው ጉዳዮች ነው።

 

ባለፉት ሁለት አመታት ከአንድ ሺህ በላይ የሙስና ክሶች ተከፍተው፤ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ታይቷል ወይም እየታየ ነው። እውነት ከማይመስሉ መካከል አንዳንዶቹን እንጥቀስ። በየሰፈሩ ወጣቶችን ሳያደራጁ፤ ያደራጁ አስመስለው መሬት የወሰዱ የኢህአዴግ  አባላት ብዙ ናቸው። የሃሰት የማህበራት ማደራጃ ሰነድ በማዘጋጀት ግምቱ 25 ሚሊዮን ብር የሆነ መሬት በነዚህ ሰዎች እንደአባት ውርስ ። ከሰላሳ ሚሊዮን ግምት በላይ ያለው 4ሺህ ካሬ መሬትም በ’ነዚህ የኢህአዴግ ሰዎች ያለአግባብ ወደ ግል ይዞታነት ተቀይረዋል ወይም ካርታ ወጥቶባቸዋል፤ አልፎ ተርፎም የገንዘብ ብድር ተወስዶባቸዋል። ግምቱ 842 ሚሊዮን ብር የሆነ መሬትም ያለአግባብ በግለሰቦች እጅ ገብቶ፤ የፀረ ሙስና ኮሚሽኑ የሚያደርገው ጠፍቶት፤ ግራ እንደተጋባ 2006 ዓ.ም. ገብቷል።

 

የኢህአዴግ አባላትና ሹመኞች በመሬት ቅርምት ብቻ አያበቁም። ጉምሩክ መስሪያ ቤት ዋነኛ የገቢ ምንጫቸው ነበር። በኮንትርባንድ የተያዘን ለዋስትና የተያዘን ቦንድ ሰነድ በማጥፋት ገንዘቡን ቅርጥፍ አድርገው ይበሉታል። የኢህአዴግ ወዳጆች ወይም ጉቦ የሚሰጡትን አነስተኛ የታክስ መጠን በማስከፈል ከመቶ ሚሊዮን ብር በላይ ወደ ግለሰቦች ኪስ ገቢ ሆኗል።

 

በመንግስት መስሪያ ቤቶች ትላልቅ ግዥና ሽያጭ ሲደረግ ያለው ማጭበርበር ደግሞ አይን ያወጣ ነው። የአፋር መስተዳድር ቻይናዎች መንገድ እንዲሰሩ ከተዋዋሉ በኋላ የፌዴራሉ መንግስት የሰጣቸውን 10.7 ሚሊዮን ብር እጃቸው አስገብተው ከመብላታቸው በፊት ተይዘዋል። እንዲህ አይነት ብዙ ታሪክ  መዘርዘር ይቻላል። ባለፈው አመት ብቻ ልዩ ልዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ባወጧቸው ጨረታዎች እና የሃራጅ ሽያጮች 3 መቶ ሚሊዮን ብር ተጨበርብሮ የተያዙም የተፈቱም ሰዎች አሉ።

 

ከፊንጫ ስኳር ፋብሪካ 75 ሚሊዮን ብር መሰረቁን እንንገርዎና በየመስሪያ ቤቱ እንዲህ ያለው ማጭበርበር ምን ያህል ሊሆን እንደሚችል እርስዎ ይገምቱ።

 

“በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል የሚመጡ ተጓዦች ንብረት መጥፋቱንስ ሰምተው ይሆን?” አዎ ባለፈው አመት ብቻ፤ ከሰባት ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ንብረቶች እና ሻንጣዎች ጠፍተዋል።

 

“ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም” ነው የሚባለው… እንዲህ እንዲህ እያልን፤ የዳኛውንም፣ የጉቦኛውንም ታሪክ እያወራን ከቀጠልን ጊዜና ምሽቱ ላይበቃን ነው። ስለዚህ የሰማነውን በልቦናችን ያሳድርልን በማለት ልንለያቹህ ነው። ጊዜ አግኝተን እንደገና ከተጨዋወትን ከአጼ ምኒልክ ቤተመንግስት ስለተሰረቁት የወርቅ ሹካ እና ማንኪያዎች ጭምር እናወጋለን። እንደገና ከተገናኘን የአጼ ኃይለስላሴ የወርቅ ቀለበት ስርቆት እንጨዋወታለን። አረ ሌላም አለ። የአጼ ምኒልክን ሽጉጥ ሰርቆ፤ መጠጥ ቤት ሲፎልል የነበረን አንድ የኢህአዴግ ኮሎኔል ኢትዮጵያ ውስጥ በሚታተመው ጋዜጣዬ ላይ አጋልጠነው ነበር። በአገራችን የሚፈጸመው እውነት የማይመስለን የኢህአዴግ ሙስና ማብቂያ ያለው አይመስልም። በዚሁ እንሰነባበት… መልካም አዲስ አመት።

 

Pen

በበዓል የረሃብ አድማ!! –ርዕዮት ምን ልትነግረን ነው?

$
0
0

ከዳዊት ሰለሞን (ጋዜጠኛ)

በብሄራዊ በዓላት ቀን በአብዛኛው ከወደ እስር ቤት የሚሰማው ዜና አስደሳች ነበር፡፡ይህንን አጼዎቹ ፣ሰው በላው የደርግ ስርዓትና ብሶት ወለደኝ ያለን ኢህአዴግ ሲያደርጉት ቆይተዋል፡፡በዘንድሮው አዲስ አመትም የመንግስትን ይቅርታ በማግኘት ከወዳጅ ዘመዶቻቸው የተቀላቀሉ ስለመኖራቸው ተሰምቷል፡፡በአዲሱ ዓመት ይቅርታ ከተቸራቸው እስረኞች መካከል ታዋቂ ፖለቲከኞች፣አክቲቪስቶችና ጋዜጠኞች አለመኖራቸው ተፈቺዎቹ በደረቅ ወንጀል ታስረው የነበሩ መሆናቸውን ለመናገር ብዙ መድከም አይጠይቅም፡፡
መንገስት ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ፣ሂሩት ክፍሌና ዘሪሁን ገ/እግዚአብሄር አቅርበውት ለነበረ የይቅርታ አቤቱታ የእምቢታ ምላሽ መስጠቱም ይቅርታ የሚገባውና የማይገባው በመንግስት ማውጫ ውስጥ ስለ መኖሩ ማሳያ ነው፡፡የይቅርታው ጉዳይ ለጊዜው ይዘግይልንና በጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ ላይ በበዓል ቀን ስለ ተፈጸመ ግፍ ላካፍላችሁ፡፡

 ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ

ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ


ጋዜጠኛዋን በበዓሉ ዋዜማ ለመጠየቅ ወደ ቃሊቲ አምርተን ነበር፡፡በመጠየቂያ ሰዓት መድረስ የቻልን ቢሆንም ጥበቃዎቹ ‹‹ርዕዮት የምትጠየቀው በዋናው በር ሆኗል፡፡ስለዚህ ወደ ዋናው በር ሂዱ›› አሉን፡፡ዋናው በር ፈጣን ተራማጅ በ10 ደቂቃ የሚደርስበት በመሆኑ ሰዓቱ እንዳይረፍድና እንዳንከለከል በማለት መሮጥ ጀመርን፡፡
ዋናው በር ግብረ ገብነት አልያም ፖሊሳዊ ስነ ምግባር በዞረበት ለሰላምታ እንኳ አግኝቷቸው የማያውቁ የሚመስሉ ጠባቂዎች ‹‹በዚህ በኩል እስረኛ አይጠየቅም ሂዱ ››አሉን፡፡ግትር ብለን በዚህ በኩል ግቡ ተብለናል አልን፡፡ሰዓቱ እየሄደ ፖሊሶቹም በአቋማችን የበለጠ በመበሳጨት እየዛቱ ነው ፡፡በመካከሉ የርዕዮት ታናሽ እህት እስከዳር አለሙና እጮኛዋ ስለሺ ሀጎስ ከግቢው ውስጥ እየተጣደፉ ወጡ፡፡
ስለሺ አንገቱን አቀርቅሮ እጆቹን እያወናጨፈ ብቻውን ያወራል፣እስከዳርን በሙሉ አይን ማየት ያስፈራል፡፡ ፊቷ በርበሬ መስሎ በእንባ ጎርፍ እየታጠበች ነው፡፡አብሮኝ የነበረው ሰውና እኔ ለመግባት እናደርግ የነበረውን ትንቅንቅ በመተው ሁለቱን ለማጽናናት እና ምን እንደተፈጠረ ለማወቅ መወትወቱን ተያያዝነው፡፡
ርዕዮት ቤተሰቦቿን እንዳገኘች‹‹ያለሁበት ሁኔታ አስቸጋሪ ነው፣ችግር ውስጥ ነኝ››ትላቸዋለች፡፡በዚህ ወቅት በዙሪያዋ የነበሩ ሴት ፖሊሶች ጋዜጠኛዋ ላይ በመጮህ ‹‹ስለ ራስሽ ብቻ አውሪ››ይሏታል፡፡
‹‹የነገረችን እኮ ስለ ራሷ ነው››የእስከዳር ምላሽ ነበር፡፡በዚህ መሃል በጊዜያዊነት የሴቶች ዞን ሃላፊ የሆነች ፖሊስ ‹‹እናንተ አቅማችሁ ጋዜጣ ላይ ነው ከፈለጋችሁ ሂዱና እንዳንጠይቃት ተከለከልን በሉ፡፡››በማለት በዚህ ቦታ ለመጥቀስ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት የሚያቅበንን የስድብ መዓት በስለሺ ፣በርዕዮትና በእህቷ ላይ ታወርዳለች፡፡

ርዕዮት ሁኔታውን መቋቋም ተስኗት ሃላፊዋን ለምን እንዲህ አይነት በደል እንደምትፈጽምባት ለመጠየቅ ስትሞክር እየገፈታተሩ ወደ ውስጥ እንድትገባ በማድረግ እነ ስለሺን ግቢውን እንዲለቁ ያደርጋሉ፡፡
በንጋታው መስከረም 1/2006 ነው፡፡የመንግስት ሃላፊዎችና የሃይማኖት አባቶች የቴሌቭዥኑን መስኮት በአዲስ አመት ቀና መልዕክት አጨናንቀውታል፡፡አዲስ ቀን አዲስ ገጠመኝ እንደሚፈጥር ተስፋ ያደረጉት የርዕዮት ቤተሰቦች ከቃሊቲ አልቀሩም፡፡ነገር ግን የሰሙት ነገር በቀኑ እንጂ በአስተዳደሩ መካከል ለውጥ ወይም ዕድሳት አለመኖሩን ነው፡፡ለካ የአዲስ አመት በጎ መልእክት የሚያስተላልፉልን መሪዎቻችን ያሉት‹‹በድሮው ቀን ነው፡፡››
ርዕዮትን እንዲጠይቁ የተፈቀደላቸው ‹‹እናቷ፣አባቷና የነፍስ አባቷ ብቻ ናቸው››እነ ስለሺ ከቃሊቲ ሃላፊዎች ዛሬ ያደመጡት መንፈስ ሰባሪ ቃል ነው፡፡የህግ ባለሞያው አቶ አለሙ ጌቤቦ ድርጊቱ ህገ መንግስታዊ ጥሰት እንደሆነ በመግለጽ ቃሊቲ ደርሰው ልጃቸውን ሳይጠይቁ ተመልሰዋል፡፡ወላጅ እናቷ ያመጡትን ምግብ ለማስገባት ቢሞክሩም ርዕዮት በቃሊቲ የሴቶች ዞን ጊዜያዊ ሃላፊ እየደረሰባት የሚገኘውን ህገ ወጥ ድርጊት ለመቃወም የርሃብ አድማ በመጀመሯ እናት ያመጡትን ምግብ የሚቀበላቸው አላገኙም፡፡
ወዳጄ ስንቶቻችን ነን አዲሱ ዓመት በጾም ቀን ዋለ ብለን የተከፋን?ይህው እንግዲህ በዓሉን ርዕዮት በርሃብ አሳልፋዋለች፡፡
የርዕዮት የርሃብ አድማ መልእክቱ ግልጽ ነው፡፡አቅም ያላት በራሷ ላይ በመሆኑ ራሷን በመቅጣት ህገ ወጦችን እምቢ አለቻቸው በዚህ ሰላማዊውን ታጋይ ማህተመ ጋንዲን መሰለችው፡፡ሰዎቹ እየበሉ በርሷ ላይ የሚፈጽሙት በደል እየተራበች በምታስተላልፈው መልእክት የህሊና ርሃብተኞች መሆናቸውን ይነግራቸዋል፡፡
ከቃሊቲ ውጪ ያለንም ምግብ ወደ አፋችን ባስጠጋን ቁጥር ርዕዮት የቃሊቲ አጥር ሳይበግራት ትመጣብናለች፡፡በምግብ ብቻ በማይኖርባት አለም በምግብ ብቻ ለመኖር ለምናደርገው ከንቱ ሩጫም ርሃቧ ትልቅ ደወል ይሆንብናል፡፡


ገድሎ ለቅሶ የሚደርሰው ስርዐት ሞቶ ቀብር የምንወጣለት አዲስ አመት ይሁልን

$
0
0

Melak addis  ametመቸም የዘመን ዑደት ማለት አሮጌው አልፎ አዲሱ የሚተካበት፣ ዘር አፈር ቅሞ ወሀ ጠጥቶ በቅሎና አብቦ የሚያሸትበት መስከረም ማለትም አይደል? አዎ አዲስ ዘመናችን ምድሪቱ ጭጋግን ለብሳ፣ አራዊቱ ያጠራቀሙትን ስብ እያቀለጡ የሚኖሩበት፣ አእዋፍ ስደት የሚጀምሩበትና የሰው ልጅ አንደ በቆሎ በልብስ የሚጠቀለልበት የበረዶ ወቅት ባለመሆኑ እርግጥም አዲስ አመት ነው። በምንም መስፈርት በማንም መለኪያ ዘመን አቆጣጠራችን ለኛ ተገቢም ትክክልም ነው። አዲስ አመት ማለት ለኛ ለኢትዮጵያውያን ተስፋ ማለትም ነው።

ታድያ ተስፋ ላይ ለቅሶና ቀብር እንዴት ርዕስ ሆነ ማለታችሁ አይቀርም። አዎ ሸፍጥ ሞቶ ሀቅ ቀብር ቢወጣና ለእውነት ኖረን ስለ ዕውነት ብናልፍ፤ በዚህ የአመታት ቅብብሎሽም እንደ አደይ አበባ ሁሉ የተስፋ ብስራት ቢያሸትልን ምን ይለናል? የሚል መንደርደርያ ነው የዚህን አይነት ርዕስ ያስመረጠኝ። አዎ እነዚህ አዲሶቹ ገድሎ ቀብር ወጪዎች ‘ተረትና ማቅራራት’ የአማራ ነው እንዳለው አስተኳሻቸው ገድለው አያቅራሩም። በፊት በረሃ እያሉ እርግጥ ነው በአንድ ጥይት 10 ሰው መደዳውን እንደሚገድሉ ተራራው እንደሚንቀጠቀጥላቸው ነግረውን ነበር። ‘ፍሬንድሊ ፋየር’ የምትለውን ብልጥ ቃል መጠቀም የጀመሩት ግን ያኔ ‘ፍሬንዶቻቸውን’ እያጋደሙ ሲያርዱ ነበር። እድሜ ለገብረመድህን አርአያ አስገድሎ አሸርጦ ማልቀስን በሜጋ የፊልም ቅንብር ሀውዜን ላይ መተወናቸውን ነግሮናል። አተረፉበት ነው የሚባለው! ከበሩበት እንጂ ሸገር ይዞአቸው የገባው ሞት የሀውዜኑም አይደል? ከዚያ በሁዋላ ያፈነገጠውን ሁሉ እርድ ያደርጉና ጉድ ተሰራን? ገዳዩን ለማግኘት የማንፈነቅለው ድንጋይ የለም ብለው አደባባይ ይምላሉ።

በሁዋላ ግን የፈነቀሉትን ድንጋይ መቃብሩ ላይ ቆልለው ወሬውንም ያጠፉታል። አይንአውጣ ስለሆኑ ለቅሶ ሁሉ ይደርሳሉ። ስፍስፍ ብሎ የሚያለቅስና ሁዋላ አደጋ የሚያመጣ የሚመስላቸውን መንጥረው ለማባረር የሚጠቀሙበትም ይመስላል። ይህ ወንጀላቸው ወደ ህግ ባይመጣም እንኳ ሕሊናን መበጥበጡና ነገም ለኔ አይመለሱም የሚለው ፍርሀት መኖሩን ከሰዎቹ ፊት ማንበብ ይቻላል። ይህ ጥርጣሬና ፍርሃት ፊታቸውን አበላሽቶታል።

የሆነ እርኩስ መንፈስ የተጠናወተው የሚመስል ቅብዝብዝ ዐይኖች አላቸው። የተሸበረ ፊ የሌለው ባለስልጣን እኮ የለም። አዎ የሰው ደም ያቅበዘብዛል። እነዚህ በጎደለ የተተኩ ከበረሀኞቹ በላይ በረሀኛ የሚመስሉትም ቶሎ የደለበ ግን መታረጃውን ያየ ሰንጋ መስለዋል የሚሉም አሉ። አሁን በቀደም ሼክ ኑሩን መስዋዕት ሲያደርጓቸው ገድሎ አልቃሾቹ መስጊድ እንደጧፍ ሲነድ ቤተክርስትያን እንደ ደመራ ቦግ ሲል ሕዝቡ ሲተራረድና እነሱ ገላጋይ ሆነው ሲወጡ የሚያሳይ ባለቀለም ሕልም አይተው ነበር። ሕዝቡ ግን አረ ቀልዳችሁን አቁሙ ብለው ‘የሞኝ ለቅሶ መልሶ መላልሶ’ የሚል የአማራ ተረት ተረተባቸው ሲባልም ሰምተናል። አዎና አርባ አመት ሙሉ ገድሎ ማልቀስ እንዴት ይቻላል? ማነው ስሙ አንድ አስለቃሽ ጋዜጠኛ ወደ ወሎ ሄዶ የ’አይዶል ሾው’ ቢሆን “ለዛሬው አልተሳካልህም” የሚያስብል ሳይጀመር ያለቀ ዘገባ አቅርቦ ነበር። ከዚህ የበለጠ ጭካኔ መቸም የለም።

ለቅሶ ላይ መፈክር ሲያሰሙ እንዲውሉ አደረጋቸው። ውሸታቸው ወንዝ የመሻገር አቅም ስለሌለው ውሸቱን በውሸት ለመሸፈን አሁን መዘዙ ለሼኩም ልጅ አልቀረለት መታሰርና መጋዝ ውስጥ ወስጡን ሌላ ሞት መደገስ ሆነ። የሰለቸንም ይኸው ነው! ዘዴውም ጃጀ እንደ ተሰነጣጠቀ ሽክላ በድምጽ ሲፈርስም አየነው። አሁን አስተኳሹ ብቻ ሳይሆን ስርዐቱም ሞቱን በጸጋ ሊቀበል ይገባዋል። ብዙ የለቅሶን ወሬ ወደ የመልካም ምኞት መግለጫ እንቀይረውና በሚቀጥለው አመት ገድሎን ለቅሶ የሚወጣው ጎጠኛና ወሮበላ ስርዐት ሞቶ ቀብር የምንወጣለት ይሁን ብለን እንመራረቅ። እንዲህ እያልን ምክርም እንምከር “ከነሱ ጋር በልቶ በሰላም ተኝቶ ማደር የለምና በቁልቋል የተመሰልክ ተላላ ሆይ ይህንን አጋም ተጠግተህ እድሜ ልክህን አታልቅስ።” ብለን። የፍቅር አደይ አበባ የተነጠፈባት፣ የተስፋ ቀስተ ደመና የተዘረጋባት፤ ፍትህ፣ ነፃነትና እኩልነት መለያዋ የሆነች ውብ ኢትዮጵያ የመልካም አዲስ አመት ምኞታችን ትሁንልን እውነትም እናድርጋት።
ዳኛቸው ቢያድግልኝ
biyadegelgne@hotmail.com

የአርቲስት ሻምበል በላይነህ አገራዊ ስራዎች አርአያነት –“ወጣቱ አንበሳ ላገርህ ተነሳ…” (ከሉሉ ከበደ)

$
0
0

shambel belayeneh
ሉሉ ከበደ (ጋዜጠኛ)

ውድ ኢትዮጵያን ወገኖቼ እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ። እዲሱ አመት ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ታላቅ ብስራት ይዞ የሚመጣ ይሁን። ያለምንም ደም መፋሰስ ይህ ዘረኛ የወያኔ ገዢ ቡድን መቃብር ገብቶ፤ ዘረኝነት፤ ጎጠኝነትና በታኝነት ከምድራችን ጠፍቶ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ተፋቅሮ ተከባብሮ፤ ሲያጠፉ የሚቀጣቸውን የሚሽራቸውን፤ ሲያለሙ የሚሾማችውን የሚሸልማቸውን መሪዎች በድምጹ መርጦ፤ የሚኖርበት፤ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከዘር ማንነቱ በፊት በኢትዮጵያ ሲምል ሲገዘት የምናይበት፤ ዜጎች ሁሉ ለሀገሬ፤….. ለወገኔ.. እያሉ ሲተጉ፤ ለጋራ እድገትና ብልጽግና ሲጓጉ….አንተ ትብስ አንቺ ትብሽ እያሉ አንዳቸው ላንዳቸው ሲሞቱ የምናይበት የተአምር ዘመን ይሁንልን,….ዘረኞች ለአንዴና ለመጨረሻ የሚጠፉበት ዘመን ይሁንልን….2006. አሜን!
አርቲስቶች የተሰጥኦና የህዝብ ሁለንተናዊ ባህልና ወግ፤ እናም የህዝብ ድጋፍና አድናቆት ውጤቶች እንደ መሆናቸው፤ ስራዎቻቸው ሁሉ የህብረተሰብ ህይወት ነጸብራቆች የመሆን ተፈጥሮአዊ ግዴታ አለባቸው። ሰላምና ጦርነት፤ ድልና ሽትንፈት፤ ደስታና ሀዘን፤ ፍቅርና ጥላቻ ምን ጊዜም ከሰው ልጅ ጋር የሚኖሩ ክስተቶች በመሆናቸው፤ ሰውም በጥብበ ስራዎቹ ውስጥ እነዚህን ባህሪያት እያንጸባረቀ፤ ይማማርባቸዋል። ይዝናናባቸዋል። ያስተላልፋቸዋል። ለሚከታተል ትውልድ የታሪክ መንገሪያም ያደርጋቸዋል ።
ጥበብ የአንድ ህብረተሰብ የስልጣኔ፤ የባህል፤ የሳይንስ፤ የፖለቲካ፤ የሁለንተናዊ እድገት ነጸብራቅና ማሳያም ነው። ጭቆናን ለመታገል፤ ፍትህ ርትእ እንዲሰፍን ህዝብን መቀስቀሻና ማስተማሪያ መሳርያም ነው። ትያትር፤ ስነጽሁፍ፤ ሙዚቃ፤ወዘተ…የህዝብን ንቃተ ህሊናና ታሪካዊ ሁለንተናዊ እውቀት እንደሚያጎለብቱ የሚያጠያይቅ ነገር የለውም።
በሀገራችን የወኔ ስራት ከሰፈነ ያልፉት ሀያ ሁለት አመታት ወዲህ ኢትዮጵያውያን አርቲስቶች አድሎን፤ ዘረኛነትን፤ የመብት ረገጣን በመታገል ረገድ ማን ምን አስተዋጾ አበረከተ ብለን የመረመርን እንደሆን፤ የተወሰኑ ጠንካራ አርቲስቶች እንዳሉን ብናውቅም፤ አሰሩትም ፤አንገላቱትም፤ ሰደቡትም አዋረዱት፤ ስለመከረኛው የኢትዮጵያ ህዝብ አለቀሰ አንጎራጎረ፤ መከረ አስተማረ፤ አጽናና እንጂ ለወያኔ ስራት አድሮ የወያኔ ፕሮፓጋንዳ ማይክራፎን አልሆነም። የሚወዳት ሀገሩንም ጥሎ አልሄደም….ማን?… ሀዋርያውን ብላቴና ቴዲ አፍሮን ዙፋኑ ላይ እናስቀምጠዋልን።
አርቲሥቶች ህዝባዊ ሀላፊነት አለባቸው። ይህም ማለት በጥበብ ስራዎቻቸው የሚያገለግሉትን ህብረተሰብ የሞያ ስነምግባርን በጠበቀ መልኩ፤ ማህበራዊ፤ ባህላዊ፤ ኢኮኖሚያዊ፤ ከባቢያዊ ብሎም ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ ህጸጾችን እያፈነፈኑ፤ ነቅሰው እያወጡ፤ በብሩሽ በዜማ በግጥም እያዋዙ ማዝናናት፤ ህብረተሰብን ማስተማር፤ ማንቃት፤ የሞራልና የዜግነት ግዴታ ሊሆንባቸውም ይገባል።

አርቲስት በአድናቂዎቹ ልብ ውስጥ የዘራው ፍሬ በአንድ ወይ በሌላ መልኩ ውጤት ማፍራቱ አይቀርም። የህውሀት ካድሬዎች ፖለቲካ አስተምረው፤ አንቅተው፤ ካሸፈቱት የትግራይ ወጣት፤ በዘፈን በጭፈራና በቀረርቶ የሸፈተው ሳይበለጥ አይቀርም።
ተወዳጅ አርቲስቶች ከአንድ ጠንካራ ፖለቲከኛ የበለጠ ድምጣቸው በአድናዊዎቻቸው ዘንድ ይሰማል።
ክቡር ለሆነው የሰው ልጅ ሰባዊ መብትና ነጻነት ጥብቅና የቆሙ የጥበብ ሰዎች እንደ ነጻ አውጭ አርበኛ ሲሞገሱ፤ ሲወደሱና ሲመለኩ ይኖራሉ።
በሌላ መልኩ አድርባይ ፤ እበላባይ አርቲስቶችን፤ አንባ ገነኖች፤ ህዝብን በዜማና በጥበብ እንዲያደነዝዙላቸው ማበረታታት ማስገደድም የተለመደ ነው። እንዲመለኩ እንዲዘመርላቸው፤ መልካቸው አምሮ እንዲሳልላቸው፤ የሚገዟት አገር በምስላቸው እንድትሸፈን ያስደርጋሉ። የተለመደ ነው። የመለስ ዜናዊ ፎቶ ከዚያች ቅዱስ ምድራችን ተለቅሞ ይልቆ ይሆን?
ወያኔ ወደ ስልጣን የመጣ የመጀመሪያዎቹ አመታት እንደነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞች በርካታ አርቲስቶች ማለት ይቻላል፤ የአንድነትን ጥቅም፤ በዘር የመከፋፈልን ጉዳት፤ በዜማዎቻቸው ለማስገንዘብ ሞክረዋል። ከፊሎቹ ከልባቸው በራሳቸው ሰብእና ውስጥ ካላቸው ኢትዮጵያዊ ስሜት ተነስተው እንደቴዲ አፍሮ አይነቶቹ በሀገራቸውና በህዝባቸው ጉዳይ ላይ የማይናወጥ ጠንካራ ወገንተኝነት እንደያዙ ዘልቀዋል።
አንዳንዶች ደግሞ በወቅታዊ የህዝብ ብሶት ላይ ያተኮረ ስራ ማቅረብ ገበያ ያስገኛል ብለው በማመንም ሊሆን ይችላል፤ የህዝቡን ብሶት የሚኮረኩሩ ስራዎችን አቅርበው የተቸራቸው ድጋፍና ጭብጭባ ሳያባራ፤ ሶስት መቶ ሰላሳ ዲግሪ ተሽከርክረው፤ በአንዲት ቀን ጀንበር ወደ ካድሬነት የተለወጡ አሉ። ሰለሞን ተካልኝ ተገፋን ሲል በዘመረበት አፉ ነው ስለመለስ ዜናዊ ቅንድብ ማማር ማላዘን የጀመረው።
ገናናዋ የደቡብ አፍሪካ ተወላጅ ማሪያ ማኬባ እንደ አውሮፓውያኑ ዘመን አቆጣጠር 1963 ዓ ም ለተባበሩት መንግታት ድርጅት የደቡብ አፍሪካው የነጮች መንግስት ያሰፈነው የአፓርታይድ ስራት፤ በሀገሬው ተወላጅ ላይ እያደረሰ የነበረውን ስቃይ በመመስክሯ ነበር የገዛ አገሯን የዜግነት መብት ገፏት፤ ካገሯ እንድትሰደድ ያደረጋት አፓርታይድ። ማሪያ ለስርአቱ ያጎበደደችበት ጊዜ አልነበረም። በዜማዎቿ ህዝቡ ለነጻነቱ እንዲታገል ታበረታታ ትቀሰቅስ ነበር።
ከዚያ በኋላ ለሰላሳ አመታት በኖረችበት የስደት ዓለም፤ በዜማዎቿ ፤ በንግግሮቿ፤ አፓርታይድ ምን አይነት ስራት እንደሆነ፤ በደቡብ አፍሪካ ህዝብ ላይ ምን አይነት ግፍ እንደሚፈጸም ስትነግር፤ የደቡብ አፍሪካውያንን ባህሎችና ልምዶች ስታስተዋውቅ ኖረች።
ቁጥራቸው በቀላል የማይገመት ኢትዮጵያን አርቲስቶች ሀገራቸውን ጥለው በውጭው ዓለም ለመኖር ሲወስኑ ጥቂቱ፤ የስራቱን እኩይ ተግባራት እየኮነኑ የህዝባቸውን መከራና ስቃይ በማስተጋባታቸው የዘረኛው ህውሀት ቡድን ሰለባ በመሆናቸው ለስደት ተዳርዋል። ከነዚህም ታማኝ በየነ በዋናነት ይጠቀሳል። ሌሎችም የተሻለ ህይወትና ኑሮ ፍለጋ ያተርፈናል ወዳሉት አህጉር ተሰደዋል። ይሁንና እነዚህ አርቲስቶች ሀሳብን እንደልብ መግለጽ በሚቻልበት ሀገር ውስጥ የመኖራቸውን ያህል ኢትዮጵያ ውስጥ እየደረሰ ያለውን ሁለንተናዊ ጥፋትና የሰብአዊ መብት ረገጣ፤ በጥበብ ስራዎቻቸው በመዋጋት ረገድ የዜግነት ግዴታቸውን እየተወጡ ነው ወይ?
ከቅርብ አመታት ወዲህ ሀገር ቤት ያሉ አርቲስቶች እጅግ በሚያሳፍርና ለማመን በሚያዳግት መልኩ፤ የኢትዮጵያን ህዝብ ክደው፤ የወያኔ የፕሮጋንዳ እቃና አጫፋሪ ሆነው፤ የገዛ ሀገሩን ባንዲራውንና ወገኑን ክዶ፤ ስለ ዲሞክራሲ የተናገረውን፤ ስለመብት የተናገረውን፤ የጻፈውን ሁሉ በመጨፍጨፍና ወህኒ በማጋዝ አለም አቀፍ ዝና ላተረፈው መለስ ዜናዊ ፤ የወርቅ ብእር ሽልማት መስጠት ፤ የኢትዮጵያን መፍረስና የአንድን ዘር የበላይነት ተቀብሎ፤ በሎሌነት ለማደር ከመዘጋጀት ውጭ ምንም አይነት መልእክት ያለው ተግባር አልነበረም። ስመጥሩና እጅግ ተወዳጅ የነበሩ አርቲስቶች ዛሬ ወደ ነፈሰበት አዘንብለው፤ ስለወያኔ ስራት ና መሪዎች መልካምነት የምስክርነት ቃላቸውን ሲሰጡ መስማት ጥበብ በኢትዮጵያ ውስጥ መዝቀጧንና ተጠባቢውም በአድርባይነትና እበላባይነት ሰብእና ውስጥ መስጠሙን ያመለክታል።
በራሱ ሩጫና ጥረት የሚተዳደር አዝማሪ የህዝብ ግጥም እየተቀበለ ዜጎችን ማዝናናት ያልቻለበት ደረጃ ላይ መደረሱ፤ ያስደነግጣል። ልማታዊ ግጥም እንጂ መቀበል አለመቻሉ፤ ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ ምን ያህል አካሉንም ህሊናውንም እንደገዛው አመላካች ነው። ይህ ቡድን እምን ድረስ ዝቅ ብሎ የኢትዮጵያን ህዝብ ለመቆጣጠረ እየሞከረ እንዳለ የሚያስገነዝብ ሁኔታ ነው።
ሀተታውን እዚሁ ላይ ላቁመውና ዋናው የርእሴ ጉዳይ ወደ ሆነው እንደ ማሪያ ማኬባ በተሰደደበት የባእድ አገር ፤ በሚያውቅበትና በሚችለው ሙያው እናት ሀገር ኢትዮጵያን የወረራት ህውሀት ዘረኛ አስተዳደር በሀገርና በህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን አደጋና ጥፋት በዜማው እየነገረ፤ እየመከረ፤ የሚበጀውን እያመለከተ ትግሎን ስለተያያዘው አርቲስት ሻንበል በላይነህ ስራዎች ላወሳ እሻለሁ።
ውድ አንባቢያን አርቲስቱ ባልፉት አመታት የተጫወታቸውን በርካታ ቀስቃሽ ዜማዎች ሁሉ በዚህ አጭር ጽሁፍ ውስጥ አካቶ ለማመላከት አይቻለኝም ። ለዛሬ በቅርቡ ካወጣቸው ሲዲዎች “ በቁም እንዋደድ እናም ሀይለስላሴ” የሚል መጠሪያ ከሰጣቸው ሁለት አልበሞቹ ውስጥ በሀገራችን ባለው ወቅታዊ እውነታ ላይ ያጠነጠኑ ቀስቃሽ ግጥሞቹን፤ ከየዘፈኑ የተወሰኑ ስንኞች እያወጣሁ ያሰውን ሁኔታ እንዴት ቁልጭ አድርጎ እንዳስቀመጠው ለማመላከት እሞክራለሁ፤ ሌሎች አርቲስቶቻችንም ወቅታዊውን ሁለገብ ትግል ለማገዝ በዜማዎቻቸው ህዝቡን ለነጻነት ማነሳሳት እንዲጀምሩ ጥሪ ለማቅረብ እሻለሁ። ከንግዲህ ኢትዮጵያውያን በሚችሉት ሁሉ ወደ ትግሉ በመቀላቀል የወያኔን ስርአት እስትንፋስ ማሳጠር ግድ ይላል።
ይሰማ ድምጻችን…. ግጥም አይገልጥም፤ ዜማ..ሻንበል በላይነህ
….እኛ አንበተንም፤ እኛ አንበተንም፤ ሙስሊም ክርስቲያኑ ልዩነት የለንም።
ዛሬም ቢሆን እንደበፊታችን፤ ተጠናክሮ ይህ አንድነታችን፤
ሙስሊም ክርስቲያኑ በለቅሶም በሰርጉም፤ አብረን እንኖራለ በክፉም በደጉም። …..
አዎ!.. “..ተነሱ ውጡና እስላም ወንድሞቻችሁን ስደቡ፤ እርገሙ፤ መንግስት ሊሆኑባችሁና ሊያጠፏችሁ ነው “ እያለ የኢትዮጵያን ክርስቲያኖች እያስፈራራና እየዛተ አደባባይ የሚያወጣ፤ በመንግስት ቅርጽ መደራጀት የቻለ የወንጀለኞች ቡድን፤ ምናልባትም በዛሬዪቱ አለማችን በአይነቱ የተለየ የሆነ፤ መንግስት የሚመስል የወንጀለኞች ቡድን ፤ ሀገር በተቆጣጠረበት፤ ሻንበል በላይነህ በምርዋ ድምጹ በጣፋጭ ዜማው ያንቆረቆረልን መልእክት ህዝባዊ እንጉርጉሮ መሆን ያለበትና ሁሉም ኢትዮዝፕያዊ ሊያንጉራጉረው የሚገባ የሙስሊም ክርስቲያኑን መተላለቅ ለሚናፍቀው ወያኔ ጠንካራ ምላሽ ነው።

ህዝበክርስቲያን፡ መስሊሙ፤
ሁሌም በውኑ፡ በህልሙ፤
ያስባል ስለሰላሙ ….
ችግሩ የኢትዮጵያን ህዝብ ከማሸበር ተግባሩ ያልታቀበው የወያኔ ቡድን ነው እንጂ፤ ህዝቡ ስለሰላሙ ያስባል። በአስራ አምስተኛው ክፍለ ዘመን ግራኝ አህመድ ሙስሊሙን ይዞ ያን ያክል ጥፋት ሲያደርስ፤ ሙስሊሙን የድጋፍና የሀይል ምንጭ አድርጎት ለራሱ የመንግስትነትን ስልጣን ለመቀዳጅት ተዋጋ እንጂ፤ ነብዩ ሙሀመድ ያላዘዙትን፤ እስልምናን በሰይፍ በኢትዮጵያ ውስጥ ሊያስፋፋ አልነበረም ጦርነቱ ፤ “አህባሽ የሚባለውን እስልምና ፤ እኔ ያመጣሁልህን ተቀበል ፤ ለሺዎች ዘመናት ይዘህ የተጓዝከውን እምነትህን ጣል” እያለ በኢትዮጵያዊው ሙስሊም ላይ ከጂሀድ ያልተናነስ ስራ እየሰራ ያለው ወያኔ ነው። ማሰር መግደል። ኢትዮጵያዊው ሙስሊም ክርስቲያን ወንድሞቹን ያሸ በረበት ዘመን የለም። አርቲስቶቻችን እንደሻንበል በላይነህ በዜማቸው ደግመው ደጋግመው ሊናገሩት የሚገባ እውነታ ነው።
አማራ… ግጥም፤ አይገልጽም። ዜማ፤ የህዝብ…
……ምነው ምን በደለ ደጉ ያገሬ ሰው፤ አረ የሰው ያለህ ፡አረሰው፡ አረ ሰው። እሳት ቢያንቀላፋ ገለባ ጎበኘው፤ ዘመን አረጀና ይሄ ቀን አገኘው። ከባህር ይሰፋል አማራ ማለት፤ ያንድነት ሀረግ ነው ኢትዮጵያዊነት ……
በፋሸሽት ወረራ ዘመን ተፈጸመ ያልተባለ ግፍ፤ አማሮች እስከወዲያኛው እንዲጠፉ፤ በሽታ ገብቷል ብለው የወያኔ ጤና ጥበቃ ሀላፊዎች ወጣት የአማራ ታዳጊዎችን በክትባት ዘመቻ እንዳይወልዱ ያመከነ አውሬ ቡድን የጁን ማግኘት አለበት። ይህ በጥይት ተጨፍጭፎ አላልቅ ያለ ህዝብ፤ እንደሌሎቹ ኢትዮጵያውያን እንደኦሮሞው፤ እንደትግሬው፤ እንደአፋሩ እንደ ደቡቡ እንደ ሁሉም….. ደሙን እያፈሰሰ ፤ ኢትዮጵያን ሲያቀና ዳር ድንበር ሲያስከብር ኖረ እንጂ፤ ወያኔ ሻእቢአና መሰሎቻቸው እንደሚያወሩት ተረት፤ ሌሎቹን ሲገዛና ሲጨቁን አልኖረም። ይልቁን ከማንም በክፋ መልኩ ሲረገጥ ነው የምናየው። የጎጃምን ድሀ አርሶ አደር፤ ከትግራይ ደሀ አርሶ አደር፤ የትግራይን ድሀ አርሶ አደር፤ ከሀረርጌ ድሀ አርሶ አደር ባጠቃላይ የኢትዮጵያን ድሀ ህዝብ አንዱን ካንዱ የተለየ የሚያደርገው የትኛው ኑሮው ነውና ነው አማራው ተለይቶ እንዲጠፋ የተፈረደበት? የህውሀት በሽተኞች አማራውን የበቀል ኢላማ ያደረጉበት ምክንያት እንደሎሎቹ ሁሉ ለኢትዮጵያ ቀናኢ በመሆኑ ነው። ወያኔ አማራን በማጥፋት ኢትዮጵያን የሚያጠፋ ሊመስለው ይችል ይሆናል፤ ግና ለኢትዮጵያ ደሙን ያፈሰሰላት ከሰሜን ምጽዋ ጫፍ እስከ ደቡብ ዶሎ፤ ከምስራቅ ፌርፌር ጫፍ እስከ ምእራብ ኢሎባቡር ጫፍ ያለ ህዝብ ሁሉ ነው። አሁንም ከወያኔ የማጥፋት ዘመቻ ያድናታል። ኢትዮጵያን ይታደጋታል።

ዘንድሮ… ግጥም፤ ተስፋዬ ለማ። ዜማ፤ ተስፋዬ ለማ
……ህጻናት ሲሸጡ ወተው በማደጎ፤ ያለቅሳል ባመቱ ወላጅ አደግድጎ…. ሻንበል በላይነህ በዜማው የነገረን የምናየው ነገር ነው። በማደጎ ስም ህጻናቶቻችንን እየቸበቸበ ያለው ወያኔ ህጻናቱ ካገር ከወጡ በሗላ የት ወደቁ ያለበት ጊዜ የለውም። በስርቆትና በዘረፋ ስለተጠመደ ስለዜጎች የሚያስብበት ገዜ የለውም። ሽያጩ ግን በስፋት እንደቀጠለ ነው። በየ አለሙ ያሉት ኢምባሲዎቹም ድለላውናንና ዶላር ማቀባበሉን እንጂ ስለኢትዮጵያውያን መብትም ሆነ ህይወት የሚያገባቸው ነገር የለም። ዓለም ደቻሳ ቤይሩት ወያኔ ኢንባሲ ፊት ለፊት ነበር ኡ ኡ እያለች በባእድ ጫማ ስትረገጥ መሬት ለመሬት ስትጎተት በዚያው የራሷን ህይወት ያጠፋችው። የኢትዮጵያ ኢምባሲ ተብሎ ወያኔዎች እዚያው ነበር አድፍጠው በዚያች ኢትዮጵያዊ ድሀ ላይ ይደርስ የነበረውን የሚመለከቱት። እነዚህን ነው ሀያ ሁለት አመት ተሸክመን የተቀመጥነው።
…..ጥያቄ ባነሳ መብቱን ያስከበረ፤ ጸረ ሰላም ሲሉት በህግ ሽብር፤ እውነቱን አውጥቶ ስለተናገረ፤ ስንቱ ጋዜጠኛ እስር ቤት ታጎረ… ዘንድሮ
ፍርሀት አሽነፈን…. ግጥም፤ ተስፋዬ ለማ። ዜማ፤ ተስፋዬ ለማ
….ፍራት አሽመድምዶን ጥሎን ባደባባይ፤ ክፉንም ደጉንም ሁነናል ተቀባይ፤ የቆረቆረንን ምቹ ስናስመስል፤ ስንጨስ እንኖራልን ስንጠቁር ስንከስል……
አዎ .. ኢትዮጵያውያን በባህላችንም በተፈጥሮአችንም፤ ለህግ የመገዛት፤ የማክበር፤ በይሉኝታ መገዛት መፍራት፤ ስለሚያጠቃን፤ አንዳንድ ጌዜ ስንገፋና መብታችን ሲገፈፍ፤ ይህ ተፈጥሮ ከልክ ያለፈ ትግስት እንዲኖረን ያደረገ ይመስላል። ለዚህ ስርአት ያሳየነው ከልክ ያለፈ ትግስት ፍርሀት ነው የሚመስለው። አርቲስት ሻንበል በበላይነህ ምናልባትም ይህንኑ ታዝቦ ሳይሆን አልቀረም በዜማው እየነገረን ያለው። ሆድ ይፍጀው ወይም የባሰ አታምጣ እያልን ይኸው ሀያ ሁለት አመታት ጉዳት ተሸካሚዎች ሆነን በዚያው ጉዞ ቀጥሏል።
….. በጥቅም ሲፈረድ፤ በወገን ሲሰራ፤ አይተን እያለፍን ስንጠብቅ ወር ተራ፤ ፍርሀት እንደውሀ ወኔያችን አፍሶት፤ ይዘን ኖራለን የማይወጣ ብሶት…
መለስ ስብሀት ሰራሹ የወያኔ ገዢ ቡድን ወደስልጣን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ በመንግስቱም ሆነ በግላ ተቋማት፤ ያሻውን ሲሰራ ስንቱን ሺህ ሰራተኛ በገፍና በግፍ እያባረረ የወደደውን የራሱን ምልምል እስከ አሁን ድረስ ሲሰገስግ፤ ሁሉም ተራው ሲደርስ ሜዳ ላይ እየተጣለ ከማልቀስ በቀር ዛሬ በወገኔ ላይ የደረሰ ነገ በኔ ነው ብሎ አምርሮ ስራቱን ለመዋጋት የተነሳ እስካሁን የለም።
የቀድሞው ሰራዊት….. ግጥም ይልማ ገብረአብ። ዜማ ሻምበል በላይነህ ….ጊዜ ተለውጦ ቀን እስከሚከዳው፤ አንጠፍጥፎ ቀምሶ ውሀውን ከኮዳው፤ ያገር መሰረቱ ህብረቱ እንዳይናድ፤ ኑሮውን አድርጎ በቀበሮ ጉርጓድ፤ ታግሎ ወድቆልናል ስላንድነታችን፤ ውለታው ይዘከር የሰራዊታችን። ሳያጓድል ያባት አደራ፤ ያስጠበቀ ያገር ባንዲራ፤ እንዳናጣ የባህር በር፤ ነፍሱን ከፍሏል ለኛ ክብር……
የወደቀ ዛፍ ምሳር ይበዛበታ እንደሚባለው ; የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጦርሰራዊት መበተኑ ሳያንሰው ፤ ለወያኔ የፕሮፓጋንዳ ሰለባ እንደሆነ እስካሁን በመቆየቱ እድሜ ልኩን ሲዘመርለትና ሲሞገስ ሊኖር የሚገባው ጀግና ሰራዊት፤ ባልፉት ሀያ ሁለት አመታት እንደዋዛ ተዘንግቶ ቆይቶ ነበር። ሻንበል በላይነህ ምስጋና ይድረሰውና ዛሬም እንደትናንቱ የዚያን ክቡር ሰራዊት ገድል አንስቷል። ይበል የሚያሰኝ ነው። የኢትዮጵያን ሰራዊት ሀያል ክንድ አጣጥመው የሚያውቁት ገንጣይና አስገንጣይ እንዳላሸነፉት ልቦናቸው ያውቀዋል። ሰራዊቱን በአካልና በሞራል ከውስጥ ይገልላቸው የነበረው መንግስቱ ሀይለማርያም ባለውለታቸው ነው። በዚያ በውሸት ፕሮፓጋንዳቸው እውነት ለዲሞክራሲና ለእኩልነት የሚዋጉ መስሎት በገፍ እየሄድ ሲቀላቀላቸው፤ ያልተቀላቀለውም መሳሪያውን አውርዶ ባዶ እጁን የቆመ ወታደር በመትረየስ እያጨዱ ነበር ተሯሩጠው ድፍን ኢትዮጵያን እንደ ወባ ትንኝ የወረሯት። መልካሙ ነገር ኢትዮጵያውያን ጀግኖቻችንን መሸለም መጀምራቸው ነው። ያየር ሀይል፤ የምድር ጦር የባህር ሀይል ጀግኖቻችን አሁንም ሊዘፈንላቸው ሊሸለሙና ሊወደሱ ይገባል።

ታሪክ ይፍረደን፤ ግጥም፤ ተስፋዬ ለማ። ዜማ፤ ተስፋዬ ለማ
…የነበረው ቀርቶ ያልነበረው ሆነ፤ የሰራነው ሁሉ እንደቀልድ ባከነ….. ……… .የራሳችን ቋንቋ የራሳችን ፊደል፤ የራሳችን እምነት የራሳችን ባህል፤ የነሉሲ ሀገር፤ የሰው ልጅ መገኛ፤ በራሱ የተሟላ ማን ነበር እንደኛ……
እርግጥ ነው። በራሱ የተሟላ እንደኛ ማንም አልነበረም:: ምን ያደርጋል፤ በመካከላችን የበቀሉ፤ በዚችው ምድር ላይ የተፈለፈሉ፤ ለራሳቸው ታሪክ ባእድ ሆነው፤ አባቶቻቸው የባእድ ጠላት አሽከሮችና ባንዳዎች፤ ያ ጠላት በወላጆቻቸው እአምሮ ውስጥ ባሰረጸው እኩይ አስተሳሰብ ተኮትኩተው ያደጉ፤ ጊዜ ለነሱ አድልታ ኢትዮጵያ እጃቸው ላይ ወደቀች። በማግስቱም … የአድዋው ታሪክ ለአማራው፤ ለደቡቡ ምኑ ነው፤ የኢትዮጵያ ባንዲራ ጨርቅ ነው፤ እንኳን ከትግራይ ተወለድኩ፤ የሚል ሰው መሪ ተብሎ ባደባባይ የሚናገር፤ ሚኒሊክ ቤተ መንግስት መኖር የቻለ አጥፊ አየን። መልካሙ ነገር እግዚአብሄር ባጭር አስቀረው። የጀግኖቻችን ሀውልቶች ፈረሱ። በባንዳ ልጆች ስም ተተኩ። በዘመናት አብሮ መኖር የተገነባ የደምና የስጋ ውህደት እንዲለያይ የዘር አጥር ግርግዳ የሚገነቡ፤ በስጋ ፤ ኢትዮጵያውያን፤ በመንፈስና በገቢር ባእዳን የሆኑ ገዢዎችን ለማስተናገድ በቃን። የሻምበል በላይነህ ዜማ ይህንን ነው ልብ ብሎ ለሰማ የሚነግረው።
ኢትዮጵያ…. ግጥም፤ ይልማ ገብረአብ። ዜማ፤ ይልማ ገብረአብ
…….ኢትዮጵያ ህይወታችን፤ ኢትይጵያ ኩራታችን፤ ኢትዮጵያ እምነታችን፤ ያገር ፍቅር ጽናት የምንማርብሽ፤ በፈጠርሽው ትውልድ ይመርብሽ፤ ዛሬም ትላንትም የምልሽ ህይወቴ፤ ውዳሴ ነሽ ለኔ የዘላለም ሀብቴ…. ከዳሽ በሞትሽ ለማትረፍ፤ በሚኒሊክ ጅራፍ ልገረፍ….
ውድ አንባቢያን እነዚህ ሁሉ መልክቶች ሻንበል በላይነህ በቁም እንዋደድ በሚለው አልበሙ ውስጥ ያካተታቸው ስራዎቹ ናቸው። ሀይለስላሴ የሚል ርእስ የተሰጠው ሲዲም ብዙ ታሪካዊና ወቅታዊ መል እክቶች አሉት፤ በተለይም በከፍጠኛ ሁኔታ ወጣቶችን ለትግል የሚያነቃቃ መልእክቶችም አሉ። እራሱን ማዳመጡ የተሻለ ነው። የሻንበል በላይነህ ስራዎች ለአርቲስቶቻችን በአርአያነት የሚጠቀሱ ናቸው። ተመሳሳይ ስራዎች ከየአቅጣጫው ብቅብቅ ቢሉ የህዝባችንን ንቃት እጥፍ ድርብ ያሳድጉታል። ሻንበልም የነጻነት ቀን እስከሚመጣ በያዘው መንግድ እንደሚጓዝና ሌሎችንም እንደሚያስከትል ተስፋ አደርጋለሁ።
ኢትዮጵያ ለዘለአለም ትኑር
lkebede10@gmail.com

የደርብ ከፈለኝ አስተያየት በእኔ እይታ –መሠረት ከቴክሳስ

$
0
0

‘አህያውን ፈርቶ ዳውላውን’ በሚል ርእስ በተክለሚካኤል ላይ የስድብ ውርጅብኝ ያወረዱት ደርብ ከፈለኝን ሳስብ በእኛ በኢትዮጵያውያን ውስጥ በብዙ ሰዎች ዘንድ የማየው በሽታ ታወሰኝ። ይኸውም ታዋቂን፣ሀብታምን፣ባለስልጣንን እንደው ብቻ በማናቸውም መልኩ በማህበረሰቡ አይን ውስጥ የገባን ሰው ማሞካሽት፤ ቢሳሳት እንኳን ስህተቱን ስህተት ነው ብሎ ደፍሮ ከማረም ግለሰቡ ከተናገረው ይዘት ጋር በማይገናኝ ሁኔታ አቃንቶ እንዲህ ለማለት ፈልጎ እኮ ነው ብለው የሚሉ ብዙ ሰዎችን አውቃለሁ። እንዲህ አይነት ሰዎች ከባለ ጉዳዩ በላይ ተቆርቋሪ ሆነው ከስህተቱ እንዳይማር መንገድ የሚዘጉ፣እንደዚያ አይነት ሰው ስህተት ቢፈጽም እንኳን ይቅርታ መጠየቅ የማይገባው መሆኑን እስከመግለጽ ይደርሳሉ።

             ይህን መሰል አንድ እውነተኛ ታሪክ ላጫውታችሁ። በአሜሪካን አገር ውስጥ አንድ የአበሻው ብዛት ከሁለት ሺህ አይበልጥባትም በምትባል ከተማ ውስጥ አበሾች ተሰባስበው ቤተክርስቲያን ይተክላሉ። ቤተክርስቲያኗም የምትተዳደረው አቡነ ይስሐቅ በሚባሉት ጳጳስ ስር ነበር። አቡነ ይስሐቅ ነፍሳቸውን እግዚአብሔር በገነት ያኑርልንና በዘመናቸው የኢትዮጵያን ቋንቋ የማይናገሩ ህዝቦችን አስተምረው የእኛን ኦርቶዶከስ እምነት አለማቀፋዊ ይዘት ያላበሱ ትልቅ አባት ነበሩ። እሳቸው ከሞቱ በሁዋላ ቤተክርስቲያኗ ከአገር ውስጥም ከውጨውም ሲኖዶስ ሳትሆን ከምእመናን በተውጣጡ የቦርድ አባላት እየተመራች ባለችበት ሁኔታ ውስጥ የቤተክርስቲያኗ ካህን ምእመኑን ለመከፋፈል እራሳቸውን አንዴ የወሎ ሰው ነኝ ብለው ወሎዬውን ሲሰብኩ ሌላኛውን ጎጃሜነኝ ሲሉ ሌላውንም ሌላ እያሉ ምእመኑን እየፈተሹ ባሉበት ሂደት ውስጥ አንድ ቀን ያልታሰበ ዱብዳ ተፈጠረ ። ይኸውም ካህኑ ከአራት አባት ምአመናን ጋር የቆመችውን ሴት የተናገሩትን ለመድገም በሚያሸማቅቅ ቃላት ዘለፉዋት። መንፈሳዊው አባት ሲሳደቡ ምእመን አባቶች ቆመው ታዘቡ። በትዝብት ማለፉ አስተማሪነት የለውም በሚል በአደባባይ በደፈናው ስህተት መፈጸማቸውን አምነው ይህቺን ሴት በቤተመቅደስ ቆመው ይቅርታ እንዲጠይቁ ከ4ምእመናን ሶስቱ ጠየቁ። አራተኛው ግን ይህ ነገር በእኛው መሀል ይቅር፣ ሴትየዋን እኛ ይቅርታ ጠይቀን ለሌላም ሰው እንዳትናገር እናግባባት በሚል አቋም ይይዛሉ። የተቀሩት ሶስቱ ግን ይህ በተአምር አይደረግም ብለው ጉዳዩን ምእመኑ ፊት ይዘውት ቀረቡ። ብዙዉ ምእመን ካህን ቢያጠፋ እግዜር ይጠይቀው እንጂ ሰው ምን አገባው ባይ ሆነና ለካህኑ የቆመው ሰው ጉልበት አገኘ። እነኝህኞቹ እውነትን ይዘው ካህኑን ሞገቱዋቸው። ካህኑም ስለ እውነት ስንት ነገር እያስተማሩ ፊትለፊታቸው እውነት ሲያፈጥባቸው አልቻሉምና ልክናችሁ ልጆቼ ብለው ለይቅርታ ንስሀቸውን መናዘዝ ሲጀምሩ ከአራቱ አንዱ የሆነው ሰው ‘ልጅ እንጂ አባት ይቅርታ እንዴት ይጠይቃል’ በማለት ሌላውን ምአመን ምን ዝም ትላላችሁ በማለት ሲያነሳሳ ካህኑም ወዲያው ሀሳባቸውን ገልብጠው ጥፋተኛ አይደለሁም በማለት ጉባኤው በብጥብጥ ተበተነ። ይህቺ አጋጣሚ ለካህኑ የትልቌ እድል በር ከፈተችና ለእውነት ሲሙዋገቱ የነበሩት ምእመናንና ተከታዮቻቸው ሲቀሩ የተቀሩትን ይዘው ቤተክርስቲያኗን ለአባ ጳውሎሱ ሲኖዶስ የእጅ መንሻ አድርገው በማቅረብ እሳቸውም የጳጳስነት ሹመታቸውን በማግኘት ሂደቱ ተጠናቀቀ።

መቼም ይሄ ጥፋት ህሊና ለአለው ሁሌም ሲያሳፍር የሚኖር ነው። ዛሬ በዚያ አካባቢ ለአንድ ቤተክርስቲያን የማይበቃ ህዝብ በአለበት፣ ሁለት ቤተክርስቲያን ተሰርቶ ሰዉም ቂም ቋጠሮ ያንን ክፉ ቀን በሁለቱም ወገን የማይረሱት ታሪክ ሆኖ ተቀምጧል። የያኔው ቄስ የዛሬው ጳጳስ እድሜ ሰጥቷቸው ይህን ማስተዋል ከቻሉ የህሊና ቁስል እንደሚሆንባቸው አልጠራጠርም። የእሳቸው ተቆርቋሪ ነኝ ብሎ ትልቅ ስህተት ውስጥ የጨመራቸውን ሰው ግን ያ ሰይጣን ባያሳስተኝ ኖሮ እኮ እንደሚሉ አሁንም በድጋሚ አልጠራጠርም። ሰውየው ካህን ተሳስቷል ከሚለው ሃሳብ ተሻግሮ ይቅርተቀ ይጠይቅ  የሚለው ሃሳብ  አሳፋሪ አድርጎ በውስጡ በማመኑና እምነቱን ከእራሱ አልፎ ለሌሎችና ባለጉዳዩንም የሃሳቡ ተጋሪ በማድረጉ  እራሱ መሳሳቱ ሳይበቃው ካህኑንና ሌሎችንም ከእውነት ጋር አጣልቱዋቸው ለብዙዎች የተረፈ የታሪክ ጠባሳ ጥሎ አልፉዋል። ደርብ ከፈለኝ በጽሁፎት ላይ ማጋነን ባይሆንብኝ ከ90 በመቶ በላይ ትችቱ ተክለሚካኤልን መዝለፍ  ነው። አንባቢም ሆነ ተተቺ እንዲሁም ተቺ እርሶ ትችቱን ስር በያዘና በጥሩ ምክንያቶች የእራስዎትን እይታ ቢሰጡ መልካም ነበር። መቼም ዶ/ር ብርሃኑ እንደቄሱ ደጋፊ ከአገኘሁ ብሎ ሽምጥጥ አድርጎ የእርስዎ ደጋፊ ሊሆን እንደማይችል እገምታለሁ። የእኔ ጽሁፍ አላማ በተክሌ ጽሁፍ አስተያየት ለመስጠት ባይሆንም ዶ/ር ብርሃኑ ግን የተክሌ ሀሳብ የእሱ ብቻ አለመሆኑን ሊገነዘበው እንደሚገባ አሳስባለሁ። ባለራዕዩ፣  ምሁሩ ፣ የምርጫ 97 ሞተሩ፣የእስርቤቱ ታሪክ ጸሐፊው እንዲሁም የግንቦት 7 ፈጣሪው ብርሃኑ እንደ ሰው ለፍጹምነት ሲሮጥ ያልፋል እንጂ ፍጹም አይደለም። እንደ ሰው የሚጎለውን ፊትለፈት ነግረነው አድመጭ መሪያችን እንዲሆን ማድረግ ይኖርብናል።  መተቸትን ዛሬ በቅርብ ሆኖ ካላስለመድነው ነገ ስልጣን የመያዝ አጋጣሚው ቢፈጠርና  አውሬ ሆኖ ቢበላን ጥፋቱ የእኛ እንጂ የእሱ አይሆንም። ለማንኛውም ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እባክህን አስተያትህን ስጠን። ካልሆነ ግን ኢሳት ላይ ጠይቁት ከተባለ ይህቺ ጥያቄ የእኔ ናት።

መሠረት ከቴክሳስ

 

Pen

 

ሕዝብን የሚያሸብር ሥርዓትና የህዝቡ መከራ -አበራ ሽፈራው /ከጀርመን/

$
0
0

አበራ ሽፈራው /ከጀርመን/

ዛሬ አለማችን በከፍተኛ ስልጣኔ ላይ ትገኛለች። በዚህም ስልጣኔ ውስጥ በኢንተርኔትና ተያያዥ የመገናኛ ዘዴዎች ተጠቅሞ የሰው ልጅ የሚፈልገውን መረጃ መፈልግ፣ማግኘት፣መለዋወጥና ማሳወቅም ሆነ ማወቅ የሚችልበት ጊዜ ላይ ደርሰናል።

ጊዜው ለውሸታሞች ፣ ለአታላዬች፣ ለግፈኞች እና ለበዝባዦች የሚመች አይደልም፤ ዓለም መድረስ ወደሚፈልግበት እየሔደ  ነው፤ጊዜው ወደፊት መሄድን እንጂ እንደኃለኛው ዘመን ማሰብን አይፈቅድም፤ ስለዚሀ ከጊዜው ጋር አብሮ መሄድ ካልሆነም ውሸታሞች ውሸታቸውን ሊድብቁ የሚችሉብትን አዳዲስ መሳሪያዎችን መፈብረክ ይጠይቃል።አለመታደል ሆነና ህወሓቶች  ስለእነሱና ስለተግባራቸው ማንም የሚያውቅ አይመስላቸውም። ትልቁ የሚያውቁትም ቃታን እየሳቡ ሰውን መግደል ብቻ መሆኑን ድርጊታቸው እያሳየን ነው፤ በዚህም ድርጊታቸው እንደ ትልቅ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች እራሳቸውን ከመሪዎቻቸው ጀምሮ ሲያጋንኑ፣ ከበሮ ሲያስደልቁ ኖርዋል አሁንም በሰብዓዊ ፍጥረት ላይ ግድያን መፈጸም፣መስረቅ፣መንጠቅ፣ማሸማቀቅ፣እያሰሩ ማሰቃየት፣በአጠቃላይ ግፍን መፈጸምና ማሸበር እንደትልቅ ሙያና ተግባር ተያይዘውታል።

ህወሃት /TPLF/ እ.ኤ.አ ከ1976-1991 በሰው ልጆች ላይ በፈጸማችው የሽብር ወንጀሎችና ጥቃቶች በአሸባሪነት ተመዝግቦ የነበረ ቡድንም ነበር። ህወሓት ሽብርን ለመፈጸም ለ39 ዓመታት ያካበተው ልምድ ቢኖረውም ከዚህ በላይ መሽበር ግን የህዝቡ ግዴታ ሊሆን አይግባም።

ህወሓት ዛሬ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልን ሽብር፣የሃይማኖት ነጻነት ጥያቄን ሽብር፣ጋዜጠኝነትን ሽብር፣መደራጀትን ሽብር ፣ሃሳብን በነጻነት መግልጽን ሽብር በማለት ህዝብን ሲያሸብር ሲታይ ህወሓት ስሙንና ተግባሩን ለሌላ ለመስጠት የፈለገ ይመስላል።

በየጊዜዉ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬድዮ ድርጅት አማካኝንት የሚነዙትን ፕሮፓጋንዳ ላየና ለሰማ ሁሉ ሽብርተኝነት ህወሃትን ያስመረረው ይመስላል። ይልቁንም የኢትዮጵያ ህዝብ በህወሃት መሸበሩንና መማረሩን፤ የሽብርተኝንት ታሪክም የህወሓት የራሱ የ39 ዓመታት ታሪክ እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብ ታሪክ እንደልሆነ ለህወሓት ለራሱ ሊነገረው ይገባል።

  1. 1.    ህወሓት መንግስት ከመሆኑ በፊት የፈጸማቸው የሽብር ተግባራት ምን ነበሩ ?

ሀ. ህወሓት አሸባሪ ድርጅት የነበረና የተመዘገበም መሆኑ፡-

በዩ.ኤስ.ኤ አሜሪካ በአገር ውስጥ ደህንነት መስሪያ ቤት አማካኝንት በሜሪላንድ ዩንቨርስቲ በአለም አቀፍ ደረጃ የአሸባሪዎችን እንቅስቃሴና ድርጊታቸውን የሚመዘግበውና የሚተነትነው የመረጃ ማዕከል ማለትም The National Consortium for the study of Terrorism and Responses to Terrorism/START/ ለመረጃ መሰብሰቢያ ባዘጋጀው ዳታ ቤዝ  ወይም  GTD/Global Terrorism Data Base/ ክፍት በሆነው የመረጃ ፍልሰቱ ውስጥ እ.ኤ.አ ከ1976-1991 ድረስ አሥር/10/ ልዩ ልዩ የሽብር ጥቃቶች በህወሓት/TPLF/ መፈጸማቸውን መዝግባል፤ በነዚህ የሽብር ድርጊቶቹ ህወሓት አሸባሪ ድርጅት ተደርጎ ተመዝግባል። ይህ የመረጃ ማዕከል ህወሓት የፈጸማቸውን የሽብር ድርጊቶች የዘረዘረ ሲሆን በዚህ መረጃ ላይ ድርጊቱ የተፈጸመበት ቀን፣ ቦታ፣የአደጋው ብዛት፣ የአደጋው አይነት፣የተጠቀማቸውን የመሳሪያ ዓይነት ለመመዝገብ ሞክሯል፤በዚህ መረጃ መሰረት በራያ ቆቦ፣በትግራይ ቦታዎች፣በላሊበላ፣በጅሬ፣በኮረም፣በወርቅ አምባ፣በአክሱምና በሌሎች ቦታዎችም የሽብር ድርጊቱ የተፈጸመ መሆኑን ጽፋል፤በነዚህም ጥቃቶች የሃይማኖት ተቃማትና መሪዎች፣በግለሰብ ህይወት እና ንብረት ላይ፣ በመንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ላይ፣በንግድ ተቃማት ላይ ፣በጋዜጠኞች እና ሚዲያዎች ላይ ሽብሩ መፈጸሙን ዘርዝሯል። ስለዚህ ህወሓት አሸባሪ ድርጅት እንደነበረና ተግባሩም ሽብር እንደነበረ ለማወቅ ይቻላል። ለበለጠ መረጃ http://www.start.umd.edu/start/  ይመልከቱ።

 

ለ. ህወሓት ልዩ ልዩ ሽብሮችን ሲፈጽም እንደነበረ አባሎቹ የነበሩ መመስከራቸው፡-

የህወሃትን እኩይ ተግባር በማጋለጥ የሚታወቁት አቶ ገብረመድህን አርአያ ስለ ህወሓት ያለፈው ታሪክ ላይ በጻፋቸው ጽሁፎች ላይ ህወሓት ግልጽ አሸባሪ መሆኑን በተደጋጋሚ ከመግለጻቸውም በላይ አሁንም ካዩትና ከሰሙት እዉነታዎች ተነስተዉ ይህንን አሽባሪ ድርጅት እያጋለጡም ይገኛሉ።

ህወሓት ከምስረታው ጀምሮ የተነሳው የራሱን የህወሓትንና የኢትዮጵያን ህዝብ ጥቅም ለማስጠብቅ ሳይሆን ጥቂቶች በስውር ይዘዉት የተነሱትን ስውር የዘረኝነት፣የብዝበዛና የጭቆና ዕቅዶቻቸውን ከግብ ለማድረስ እንደህነ ተግባራቸው ያሳየና፤ ይህንንም ግባቸውን ለመፈጸም የትኛውንም ሽብር ከመፈጸማቸው ጋር ተያይዞ ህወሓቶች በዓለም ከሚታወቁ የሽብርተኛ ቡድን ተርታ ተሰልፈው የነበረ ቢሆንም ከቀዝቃዛው ጦርነት ማብቃት ጋርና ከደርግ መንግስት መንኮታኮት ጋር ተያይዞ አገራችን በአሸባሪዎች እጅ ወደቀች፤ ደርግና ባለማሎቹም እንዲሁም ዋና ዋናዎቹም የዓለም መንግስታትም ህዝቡንና አገራችንን አሳልፈው ለሽብርተኞች  ሰጡ ። ይለወጣል ብለው ብዙዎች ቢጠብቁትም ተግባሩ ያለቀቀው ህወሓት/ኢህአዴግ መንግስት ከሆነም በኃላ ከቡድናዊ ሽብርተኝንት ወደ መንግስታዊ ሽብርተኝነት ተሸጋገረ።

  1. 2.   የህወሓት/ኢህአዴግ  የመንግስት ስልጣን ከያዘ በኃላ ወደ መንግስታዊ ሽብርተኝነት መቀየር /State Terrorisim/

ሀ . ለመሆኑ የመንግስት ሽብርተኝንት/ State Terrorisim/ ምንድ ነው? 

ጸሃፊዎች የሽብርተኝነት መሰረታዊ ዓላማ ሽብርተኞቹ የሚፈልጉትን ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊና ሃይማኖታዊ ግቦችን ተግባራዊ ለማድረግ ልዩ ልዩ መንገዶችን ተጠቅመው በህዝቦች ላይ ከሚገባው በላይ ፍርሃትን በመፍጠርና በማስገደድ ዓላማቸውን ከግብ ማድረስ እንደሆነ ይገልጻሉ።

በ acadamia.org ላይ የመንግስት ሽብርተኝነትን እንደዚህ ጽፎታል፡- State terror refers to the use or threat of violence by the state or its agent or supporters,particularly against civilian individuals and population,as a means of poletical intimidation and control.

የፖለቲካ የበላይነትን ለመያዝና ጫናን ለመፍጠር በተለይም በሰላማዊ ግለሰቦችና ህዝቦች ላይ ተገቢ ያልሆነን ጥቃትን በራሱ በመንግስት፣በተወካዮቹና በደጋፊዎቹ  ሲፈጸም ይህንን ጥቃት መንግስታዊ ሽብር ብሎታል።

እንግዲህ ህወሓት/ኢህአዴግ  ምንም እንካን የመንግስትን ሥልጣን የያዘ ቢሆንም ሌሎች አሸባሪ ድርጅቶች የሚፈጽማቸውን ተግባራት በግልጽና በአደባባይ ይፈጽማል። ከነዚህም ውስጥ ፍንዳታን ይፈጽማል ፣ያፍናል፣ህጋዊ ያልሆኑ እስራትን ይፈጽማል፣በሰብዓዊ ፍጥረት ላይ የማይፈጸሙ ድብደባዎችን፣ በወንዶችም ሆነ በሴቶች የመራቢያ ብልቶች ላይ አደጋን ማድረስ፣አካለ ስንኩል ማድረግ፣ ቤተሰቦች እንዲለያዩ ማድረግ፣ ስውርና የአደባባይ ላይ ግድያዎችንና ሌሎችም ተግባሮችን ይፈጽማል።ከዚህም ድርጊቱ አንጽር ህወሓት/ኢህአዴግ  ከአሸባሪነት መገለጫዎች የዘለሉ ተግባሮችን የሚፈጽም ቡድን መሆኑን ያሳያል።

ህወሓት/ኢህአዴግ  በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚፈጽመውን የሽብር ጥቃቶችን ኢትዮጵያውያን በግልጽ የሚያውቁት ጉዳይ መሆኑ ፣የልዩ ልዩ ሃገራት መንግስታትና በኢትዮጵያ የሚኖሩ የልዩ ልዩ ሃገራት አምባሳደሮችም ሳይቅሩ በግልጽ የሚያውቁት መሆኑና ይህንንም የሚያግዙ የተለያዩ መረጃዎች እየወጡ መሆናቸው፤በተለይም የዩ.ኤስ.ኤ አሜሪካንና ሌሎችንም መረጃዎችን በመሰብሰብ እና በማጋለጥ የሚታወቀው ዊኪሊክስ ይፋ ባደረጋቸው መረጃዎች መሰረት እነዚህ እውነታዎች ግልጽ እየሆኑ መምጣታቸውና በተለይም ህወሓት የራሱን የሽብርን ጥቃት ለመፈጸም እንዲያግዘው ኢትዮጵያ ውስጥ የሽብር ጥቃት እንዳለ ለማስመሰል ሲጠቀምባቸው የነበሩትን የማታለያ እንቅስቃሴዎች ማለትም የሽብር መሳሪያዎችን በራሱ ወታደሮችና የደህንነት ሰዎች በልዩ ልዩ ቦታዎች በማስቀመጥ መልሶ በራሱ የደህንነት ሰዎች እንደተገኙ በማስመሰል ያደርገዉ የነበረውን ተግባር አጋልጧል፤ እነዚህም ድርጊቶቹ  አስቀድሞም ብዙዎች  የነበራቸውን ጥርጣሬም አጠናክሮታል።

 

ለ. ህወሓትኢህአዴግ የፈጸማቸው የሽብር ጥቃቶችስ ምንድ ናቸው?

ህወሓት/ኢህአዴግ የመንግስትን ሥልጣን ከያዘ በኃላ መጠነ ሰፊ የሽብር ጥቃቶችን በህዝቡ ላይ በተለያዩ ጊዜያትና ቦታ የፈጸመ ሲሆን ዋና ዋናዎቹን በጥቂቱ እንመልከት፡-

  1. በወልቃሪት ጠገዴ ህዝቦች ላይ የተፈጸሙት የዘር ማጥፋት ዘመቻና የዚህንም ህዝብ ህልዉና በማጥፋት የራሱን መስፋፋት ከግብ ለማድረስ በህዝቡና በትውልዱ ላይ የተወሰደዉ የዘር ማጥፋት ተግባር እጅግ ዘግናኝ ተግባር የሆነና ጉዳዩ ገና መፍትሄ ያልተገኘለት ይልቁንም ገና ብዙ ቀውስን ሊፈጥር የሚችል ተግባር መሆኑም እራሱም ህወሃትም ያልተረዳው ግፍ ነዉ።ለበለጠ መረጃ http://ethio-wolqait.blogspot.de/. እና ሌሎችንም ተያያዥ ጽሁፎችን ይመልከቱ::
  1. በጋምቤላ በአኟኮች ላይ እ.ኤ.አ በዲሴምበር 13/2003 በጋምቤላ ከተማ የተደረገው የጅምላ ግድያ/Gonocide/ 424 ስዎችን በጅምላ በመግደል ታሪክ የማይረሳው የመንግስት ሽብር የተፈጸመ ሲሆን ብዙዎችም አገራቸውን ጥለው እንዲሰደዱ ተደርገዋል፣የአኟክ ሴቶች በወታደሮች ተደፍረዋል፣በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤቶች ወድመዋል፣የሚመገቡአቸው ምግቦችና የቤት እንሥሣቶችም እንዲወድሙ ተደርጓል።ይህ ሽብር  ህወሓት በዚህ ክልል ውስጥ ለመስፋፋት ብሎ በህዝብ ላይ የተፈጸመ ግልጽ ሽብር ነው።ለዚሀም ድምዳሜ ላይ ያደረሰኝ ጉዳይ አብዛኛው የጋምቤላ ሰፋፊ መሬቶች በህወሃቶችና የጥቅም ተጋሪዎቻቸው ቁጥጥር ውስጥ መሆኑና እየተበዘበዘ መሆኑ ነው። በዚሁ ክልል  ስለተፈጸመው ጅምላ ግድያና ህወሓት  በዚሁ ክልል ስለሚፈጽማቸው የሃብት ብዝበዛ ለማውቅ ከፈለጉ የአኟክ የፍትህ ካውንስልን ዌብ ሳይት “http://www.anuakjustice.org/”  ይመልከቱ።
  1. የሲዳማ ህዝቦች ሰላማዊ ጥያቄዎች በማንሳታቸው እና ህገ-መንግስታዊ መብቶቻቸውን ተግባራዊ ለማድረግ በመነሳታቸው ብቻ ከ 11 ዓመታት በፊት እ.ኤ.አ ሜይ 24/ 2002 በአዋሳና አካባቢው ከ100 በላይ የሲዳማ ተወላጆችን በጅምላ በመግደልና ከ250-300 የሚሆኑትን በማቁሰል የተፈጸመው ዘግናኝ ሽብር ለታሪክ የማይረሳና የህወሓትን ግልጽ ሽብርተኝነት የሚያሳይ ሌላው ሀቅ ነው። ለበለጠ መረጃ http://sidamaliberation-front.org/ ይመልከቱ።
  1. በኢትዮጵያ አቆጣጥር ከ1997 ዓ.ም ምርጫ በኃላ በህዝብ ምርጫ የተሸነፈው ህወሓት/ኢህአዴግ ከህጻናት እስከ አዋቂ በጠራራ ጸሃይ በመቶዎች የሚቆጠሩትን ንጹሃን ግንባር ግንባራቸውን ብሎ በመግደል፣ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩትን አካለ ስንኩል በማድረግ፣በሽዎች የሚቆጠሩትን ደግሞ በእሥር ቤቶች ውስጥ በማሰርና በማሰቃየት በኢትዮጵያ ህዝብና በዓለም ማህበረሰብ ፊት ግልጽ ሽብር የፈጸመ ቡድን መሆኑ የቅርብ ግዜ እውነታዎች ናቸው።
  1. በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ውስጥ በተወሰኑ በኦሮሞና በትግራይ ተማሪዎች መካከል በተደረግ ግጭት ግልጽ በሆነ መድሎና በማን አለብኝነት በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ ከትምህርት ገበታቸው እንዲባረሩ ተወስኖ የነበረውን ውሳኔ ሰንመለከት እጅግ የሚያሳዝን ተግባር መሆኑና ድርጊቱ በአዲሱ ትውልድም ላይ የተቃጣ ሽብር ከመሆኑም በላይ ኢትዮጵያውያን በአገራችን በግልጽ መድሎ ውስጥ መሆናችንን ያሳያል።
  1. በኦሮሞ ህዝቦች ውስጥ የሚደረጉትን ትግሎች በሙሉ ከኦነግ ጋር በማያያዝ የኦሮሞ ህዝቦች በእስር ቤቶች ውስጥ እንዲማቅቁ መደረጉና አብዛኛው የአገሪቷ እስር ቤቶች ኦሮሚኛ የሚነገርባቸው እስከ መሆን መድረሳቸውን ከፖለቲከኞች አፍ መስማታችን እጅግ ከባድ ችግሮች በህዝቡ ላይ መኖራቸውንና በኦሮሞ ህዝብ ላይ ሽብር እየተፈጸመ መሆኑን ያሳየናል።
  1. ህወሓት/ኢህአዴግ ሊፈጽመው የሚፈልገውን ሽብር በሽብር ህግ ድጋፍ እንዲደረግለት በህዝቡ ሳይሆን ለህወሓት የብዝበዛና የጭቆና መሳሪያነት በሚያገለግለው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አማካኝነት አጽድቆ የሽብር ጥቃቱን እየፈጸመ ሲሆን በዚህ ጥቃትም ልዩ ልዩ አካላት የህወሓት የሽብር ጥቃት ስለባዎች ሆነዋል። በዚህም ውስጥ ጋዜጠኞች፣የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላት፣ የነጻነት ተማጋቾችና ልዩ ልዩ ግለሰቦች በሙሉ በዚሁ ጥቃት ውስጥ ወድቀዋል።

ከጋዜጠኞች መካከልም፡- ርዮት አለሙ፣ውብሸት ታዮ፣እስክንድር ነጋ፣ በተለያዩ ጊዜያት በፍርድ ቤት የሚመላለሰው ተመስገን ደሳልኝ እና ሌሎችም ከሃገር ውስጥ ፣ የስውዲን ጋዜጠኞች ጀሃን ፕርሰን/Johan person/ እና ማርቲን ሽብዮ/Martin Schibbye/ ከውጭ ይገኙባቸዋል።

ከፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላትም ውስጥ አንዱዓለም አራጌ ፣በቀለ ገርባ፣ኦርባና ሌሊሳና ሌሎች በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ በእሥር ቤቶች የሚማቅቁ ይጠቀሳሉ።

በተለይም ተዋቂ ጋዜጠኞችን በሽብርተኝነት ሰበብ አስሮ ሌሎች በአገራቸው በሚደረገው የነጻነት እንቅስቃሴ ላይ ምንም እንዳይናገሩ በማድረግ በነጻው ሚድያ ላይ ግልጽ የመንግስት ሽብር እንዳለ ሁሉም የሚያውቀውና እ. ኤ. አ ከ2007-2012 ድረስ ብቻ 49 የሚሆኑ ጋዜጠኞች በዚህ የህወሓት የሽብርተኝነትን ድርጊት በመፍራትና በግዳጅ ከሃገር መሰደዳቸውን ለጋዜጠኞች መብት የሚከራከረው ሲፒጄ/Commitee to Prtect Jornalists / በተለያዩ ጊዜያት ገልጸዋል፤በዚህም ምክንያት አገራችን ለጋዜጠኞች ህይወት አደገኛ አገር መሆናንና ከሱማሊያና ከኢራቅ ቀጥላ  ለጋዜጠኞች የስደት ምክንያት በመሆን ታዋቂ ሆናለች ።

  1. በተለያዩ ጊዜያት በአፋር፣በሶማሊያና በጋምቤላ ክልሎች የህወሓት የመሬት መስፋፋትን ተግባራዊ ለማድረግ በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ የእነዚህን ህዝቦች የመሬት ሃብት ተጠቃሚነትን በመንጠቅ የህወሓት የብዝበዛ ቡድን አባላትና ጀሌዎቻቸው በህዝቦች ህይወት ላይ ተደጋጋሚ አደጋ በመፍጠርና በማፈናቀል አስከፊ ተግባር እየተፈጸመ ያለው በዚሁ ተስፋፊ  የህወሓት/ኢህአዴግ ቡድን አሸባሪነት መሆኑም ሊሰመርበት ይገባል።
  1. በአማራ ተወላጆች ላይ ከደቡብ ከጉራፈርዳ፣ከቤንሻንጉል ጉምዝና ከሌሎችም ክልሎች በማፈናቀል፣መሬት በመንጠቅና በማሳደድ የዘር ማጽዳትን ተግባርን የሚያቅደው እራሱ ህወሓት መሆኑንና ከትግሉ ጀምሮ ይዞት የመጣው በማኔፌስቶውም ላይ በግልጽ ያስቀመጠውና እየተገበረ ያለው ተግባር ነዉ፤በዚህም ብዙ ጭቁን አማሮች የሚከላከልላቸው አጥተው የዚሁ የሽብር ጥቃት ሰለባ ሆነው ተቀምጠዋል።
  1. ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በተለይም ከአንድ ዓመት ወዲህ በሙስሊም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ላይ የሚፈጸመው የአደባባይ ላይ ድብድባ፣እስራትና ግድያዎች የህወሓት/ኢህአዴግ ሌላው ህዝብን የማሽበር ተግባሩ አካል እንደሆነ ብዙዎች ይስማሙበታል።
  1.  በሃገር ውስጥ ባሉ ሰላማዊ ትግልን አማራጭ ትግል በማድረግና ህግን ተከትለው የሚታገሉትን የተቀዋሚ ፓርቲዎች አመራርና አባላት ላይም እየደረሰ ያለው ወከባና እንግልት ሰላማዊ ትግሉን እጅግ መራራ አድርጎታል፤ለዚህም ማስረጃ ይሆን ዘንድ በቅርቡ በሰማያዊ ፓርቲ ላይና በአንድነት ፓርቲዎች አመራሮችና አባላት ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ ህወሓት/ኢህአዴግ በፍጹም ማን አለብኝነት መቀጠሉንና ሰላማዊ ትግሎችንም ጭምር ለማጥፋት መቀጠሉ ይህ ሥርዓት በግልጽ በመንግስታዊ ሽብርተኝነት መቀጠሉን ግልጽ አድርጎልናል።
  1. 3.   ህወሓት/ኢህአዴግ የሽብር ጥቃትን ለምን ይፈጽማል ?

ወሓት/ኢህአዴግ በየትኛውም የታሪክ አጋጣሚ ኢትዮጵያዊነትን የተላበሰና ለእውነተኛ ዲሞክራሲና ፍትህ የቆመ ቡድን ሳይሆን በጥቂቶች ጠባብና ዘረኞች የተዋቀረ የማፍያ ቡድን መሆኑን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያውቃል። የህወሓት ዓላማና ግብ በእርግጥም የነጻነትና የዲሞክራሲ ሳይሆን ጥቂቶች የአገሪቷን ወታደራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መዋቅሮችን በሙሉ ተቆጣጥረው ለዓመታት የተመኙትን የኢኮኖሚና የመሬት መስፋፋትን ዕውን ለማድረግ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ አካልና፤በኢትዮጵያ ህዝብ ደምና ሀብት ለመክበር በሚቋምጡና በሚተገብሩ የህወሓት መሪዎችና ጀሌዎቻቸው አማካኝነት ይህንን ስውር ተግባር ለማስፈጸም የሚፈጸም የሽብር ተግባር ነው።

የዚህን እውነታዎች ለማወቅ ለሚፈልጉ ሁሉ አሁን በተጨባጭ የሚታየውን እውነታን ማየት ይቻላል።አጠቃላይ የኢኮኖሚው ክፍል በሙሉ ማለት ይቻላል በህወሓት ቁጥጥር ስር መውደቁና፤ የወሓት የንግድ ድርጅቶች ሙሉውን የአገሪቷን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችን በሙሉ ለመቆጣጠር ሩጫ ላይ መሆናቸውና፤ እነዚህን ሁኔታዎችን የሚያመቻቹ የመንግስት መዋቅሮች በእነዚሁ በህወሓት ሰዎች እጅ ቁጥጥር ስር መዉደቁ ግልጽ ማስረጃ ሆኖ ይገኛል፤ለምሳሌ ኢፈርት በሁሉም የአገሪቷ የንግድ ሴክተሮች ተጽዕኖን እንዲፈጥርና ሌሎችን ከገበያ ውጭ እንዲሆኑ የሚያደርገው እንቅስቃሴና በብሄራዊ ባንክ፣በግሙሩክ፣በአየር መንገድ፣በአገር ዉስጥ ገቢ መስሪያ ቤቶች፣በወታደራዊ ተቋማት፣በፖሊስና ደህንነት መስሪያ ቤቶች ተሰግስገው አገሪቷን ለመበዝበዝ የሚያስችሉአቸውን ሁኔታዎች በቁጥጥር ውስጥ ያስገቡ በመሆኑ፤ ይህንን ብዝበዛ የሚቃወምም ሆነ የሚነካ ሃይል በሙሉ የጥቅሞቹ ተቀናቃኝ አድርጎ በመቁጠሩና፤ ይህንን የህወሓትን ቡድን ስውር ዓላማን ለማስፈጸመ መንግስታዊ ሽብርን አንዱ አማራጭ አድርገው የያዙት መሆኑ፤ ህወሓትን የሚያሳስበው የፍትህና የዲሞክራሲ ጉዳይ ሳይሆን ይህንን የብዝበዛ መዋቅራቸውን የሚነካ ሃይል ሁሉ በአሸባሪነት በመፈረጅ የብዝበዛ ተግባራቸውን ከግብ ለማድረስ የመንግስት ሽብርተኝነትን  እያቀጣጠሉ መሆኑ ነው።

  1. የህወሓት/ ኢህአዴግ የሽብር ተግባራት በህዝቡ ላይ የፈጠራቸው ችግሮች ምንድን ናቸው ?

 

የህወሓት/ኢህአዴግ ቡድን በሚፈጥራቸው የሽብር ተግባራት የተነሱ በህዝቡና በአገሪቷ ላይ የፈጠሩት ተጽዕኖዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡-

  1. በህዝቡ ላይ ፍርሃት መንገሱና በብዙዎች ላይ የስለልቦናም  ችግር ያስከተለ መሆኑ፤
  2. ስደትና በስደትም የተነሳ ወጣቶች በጎረቤት አገራትና በየበረሃው ለሞት መዳረጋቸው፤
  3. እስራትና ሞት፤
  4. ግልጽ የህወሓትንና የጥቅም ተጋሪዎቻቸውን ልዩ ልዩ ብዝበዛዎችን ከፍርሃት የተነሳ በዝምታ ማየት፤
  5. በህዝቡ ላይ ሰብዓዊ ጥሰቶች በብዛት እየተፈሰሙ መምጣታቸው፤
  6. የመሬትና የተፈጥሮ ሃብቶች ብዝበዛ መቀጠሉ፤
  7. የሃገሪቷ ሃብቶች በጥቂቶች እጅ እየወደቁ መምጣታቸው፤
  8. ህዝቡ መብቶቹን እንዳይጠይቅ መገደዱ፤
  9. የስራና የትምህርት እድሎች መድሎዎች መፈጠራቸው ይህንንም መድሎ በዝምታ ለመቀበል መገደድ፤
  10. የስራና የመኖሪያ ቦታዎች ችግር መፈጠሩ፤
  11. የሙስና መስፋፋት መባባሱ፤
  12. የህግ የበላይነት ቀርቶ የህግ  መድሎ መፈጠሩ፤
  13. ግልጽ የንግድና የስራ ቦታዎች መድሎ መኖሩ፤
  14. ህዝቡ ከተቀዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እንዳይቀላቀልና መብቶቹን እንዳያስከብር መሆኑ፤
  15. በንሮ ውድነት መማቀቅ፤
  16. ህዝቡ በሃገሩ ላይ የበይ ተመልካች መሆኑ፤
  17. የንብረት መነጠቅ ችግሮች መደራረብና ሌሎችም:-

 

  1. 5.   ከፖለቲካ ፓርቲዎች ፣ከስቪክ ማህበራትና ከኢትዮጵያ ህዝብ አጠቃላይ ምን ይጠበቃል ?

ህወሓት/ኢህአዴግና የጥቅም ተጋሪዎቹ ይዘው የተነሱትን የኢኮኖሚ፣የንግድና የመሬት መስፋፋት ከግብ ለማድረስ በሚያደርጉት የብዝበዛና የዝርፊያ እንቅስያሴ ዉስጥ ማናቸውንም ሰላማዊና ህጋዊ ትግሎች ሳይቀሩ በሽብርተኝነት ሰበብ መግደል፣ማሰር፣ማሳደድ፣ማሸማቀቅና ማስፈራራት የህወሓት የየዕለት ተግባር ሆኗል። ይሁንና ይህንን ሁኔታ ለመለወጥ እራሳችን ለመታገል ካልቆረጥንና መሰዋዕትነትን ለመክፈል ካልተነሳን ችግሩ ማብቂያ እንደማይኖረው ሊሰመርበት ይገባል።

በሃገራችን ታሪክ ህዝብንና አገርን በማሽበር በኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን በዓለም የሽብርተኝነት መዛግብት ውስጥ የተመዘገበውን ይህንን ሽብርተኛን የህወሓትን ቡድን ከድርጊታቸው እንዲያቆሙ ማድረግ ወይም እራስን የመከላከል ተፈጥሮአዊና ህጋዊ መብቶችን ተጠቅሞ ወደ መከላከል መግባት፣ የህወሓት ፍጹም አምባገነንነት እንዲያበቃና የአገራችንና የህዝቦቻ ነጻነት እንዲረጋግጥ ማድረግ ለነገ የሚባል ጉዳይ አይደለም።

በእርግጥም ህዝብን በማሸበር ህወሓት ለዓመታት በህዝቦች መብቶችና ህይወት ላይ የሚፈጽማቸው የሽብር ጥቃቶች እንዲያበቁ አስፈላጊዉ ሁሉ ባለመደረጉ ዛሬ ህዝባችን በመከራ ውስጥ መሆኑ ለሁሉም የተሰወረ አይደለም።ትግሉ አሁን የመንግስት ስልጣን ይዘው በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ግፍን ከሚፈጽሙ የመንግስት ሽብርተኞች ጋር እንጂ ከህገ መንግስት ጋር አይደለም፤ህግ በትክክል እየተጣሰ ያለው በእነዚህ እኩይ ተግባርን በሚፈጽሙ የህወሓት/ኢህአዴግ በዝባዥ ሥርዓትና የሥርዓቱ መሪዎች ነው፤ ይህንን አስከፊ ሥርዓት ለማስወገድ መነሳት፣ መታገልና አስፈላጊውን መስዋዕትነት ከፍሎ በድል ማጠናቅቀ ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም።

 

በሃገራችን የበይ ተመልካች ሆነን መቀጠል ያብቃ፤ጥቂቶች ብዙሃኑን የሚዘርፉበትና የሚጨቁንበት ሊያበቃ ይገባል፤የተወለድንባቸውና ያደግንባቸው ቦታዎች የራሳችን እስር ቤቶች ሊሆኑ አይገባም፤ወታደሩ፣ፖሊሱና የደህንነት ሀይሉ ኢትዮጵያውያንን የሚወክል መሆን ይኖርበታል እንጂ ለጥቂት ዘረኞች ቅጥረኛ ሆኖ የሚያገለገለበት ጊዜ ሊያበቃ ይገባል።

 

ህወሓት/ኢህአዴግን መታገልና ማስወገድ የተቀዋሚ ፓርቲዎች፣የስቪክ ማህበራት፣ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎችና ለእውነት የቆሙ ጋዜጠኞች ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያዊ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያሉ ሁሉ  ትግል ሊሆን  ይገባል።

 

 

ለዚህም ይረዳ ዘንድ የሚከተሉት ሁኔታዎችን ማየት ይኖርብናል ብዮ አስባለሁ፡-

 

 

  1. ነጻነቱን የተነጠቀዉ ሁሉም መሆኑና ነጻነቱን ማስመለስ የሁሉም መሆኑ፤ ስለሆነም ትግሉም የሁሉንም ተሳትፎና መስዋዕትነትን የሚጠይቅ በመሆኑ ሁሉም በመረጠዉ የትግል መንገድ ወደ ትግሉ መቀላቀል ይጠበቅበታል።ድልን የሚጠብቅ ሁሉ የትግሉም አካል ሊሆን ይገባል፤
  2. የህዝቦች መቀራረብና በጋራ ጠላት ላይ የጋራ ትግልን ማፋጠን ለነገ የማይባል መሆኑ፤
  3. የተማሩና የህዝባቸው ሮሮ የሚሰማቸው ሁሉ ዛሬ ህዝቡ የሚፈልጋቸው በመሆኑ ያስተማራቸውን ህዝብ ለማገልግል የሚቆርጡበት ጊዜ መሆኑ፤
  4. የፖለቲካ ፓርቲዎች ልዩነቶችን በማጥበብና ለትዉልዱ በማሰብ በጋራ ጠላት ላይ በጋራ መነሳት መቻልና ለህዝቡ የትግል ፍላጎት መዳረሻ ሊሆኑና ሊያታግሉ ይገባል፤
  5. የስቪክ ማህበራትም ያላቸዉን ትስስር በማጠናከር ትግሉን ማገዝ ይኖርባቸዋል፤
  6. አዲሱ ትውልድም ለራሱ ሲል ወደ ትግሉ መቀላቀል ይኖርብታል፤
  7. በውጭ የሚገኙም የዚህን ዘረኛና አሸባሪ መንግስታዊ ቡድን ተግባር በማጋለጥና በዲፕሎማሲው ዘርፍ አስፈላጊውን እንቅስቃሴ በማድረግ ዕርቃኑን ማስቀረትና አገራትና መሪዎቻቸው ከተጨቆነው ህዝብ ጋር እንዲወግኑ ጥረት ማድረግ፤
  8. በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል፣ በስቪክ  ማህበራት መካከል፣ በሰብዓዊ ድርጅቶች መካከል በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያሉት የእርስ በእርስ ግንኙነቱን በአህጉራት መካከልና በዓለም አቀፍ ደረጃ በማጠናከር የህወሓትን የመከፋፈል አቅምን መስበር መቻል፤
  9.  በውጭ ያሉ ምሁራንም የተለያዩ ሙያዊ ድጋፍ እንዲያደርጉ ማበረታታትና ተነሳሽነት መፍጠር፤
  10. የህወሓት የንግድ ድርጅቶች ምርቶችን ባለመግዛትና የንግድ አገልግሎቶቹን ባለመጠቀም ጭምር የህወሓትን የብዝበዛ መስመሮች መዝጋትና
  11. ልዩ ልዩ ትግሎችን  በሃገር ውስጥና በውጭ ማቀጣጠልና ተግባራዊ ማድረግ ግድ ይላል።

 

እነዚህንና ሌሎች ተግባራትን በመፈጸም ይህንን ሽብርተኛ ቡድን ከሃገራችንና ከህዝባችን ላይ ማንሳት ይጠበቅብናል።

 

 

  1. 6.  ማጠቃለያ

 

ከላይ ከተዘረዘሩትም ሆኑ ሌሎች በዚህ ጽሑፍ ካልተጠቀሱ የህወሓት/ኢህአዴግ ተግባራት ስንነሳ ግዜው መሰባሰባችንን ይጠይቃል። ከራሳችን ይልቅ ለደሃው ህዝባችን ልናስብና የመከራውን ግዜ ልናሳጥር የሚገባን ሰዓት ላይ ነው ያለነው፤ ስልሆነም አስፈላጊውን ሁሉ ማድረግ ይጠበቅበናል።

 

ህወሓት/ኢህአዴግ በሰላማዊ ትግል ላይ ባሉ የሰላማዊ ትግል አራማጅ ፓርቲዎች ላይም  ሳይቀር መንግስታዊ ሽብርን ቀጥል። ይህንን የፓርቲዎችን ትግል ማገዝና ችግራቸውን መጋራት ለነገ የሚባል ሳይሆን ዛሬ የሚተገበር ተግባር ነዉ። በሩቁ ሆኖ ፓርቲዎቹ ብቻቸውን እንዲታገሉ  መፈልግ ትግሉን ይጎዳዋል እንጂ አይጠቅመዉም፤ ስለሆነም ትግሎችን መደገፍና ከውጤት ላይ ማድረስ የሁሉም ተጠቂ ሁሉ ሃላፊነት ነው ።

 

በመጨረሻም አንድ ነገርን ሳልል አላልፍም ይኽውም ትግሎቻቸን ግቦቻቸውን እውን የሚያደርጉ ግለሰቦችን፣ ቡድኖችንና አስተሳሰቦችንና ፖሊሲዎቻቸውን ማየት ይኖርባቸዋል ፤ እነዚህም ቢሆኑ የብዙሃኑን ተሳትፎ ይጠይቃሉ ። ይኽንን ያልኩባቸው ምክንያቶችለመመልከት ያህል በዓለማችን እንደሚታየው አብዛኞች ትግሎች ግባቸውን እንዲስቱ የሚደረጉበት አጋጣሚዎች ተፈጥረዋል፤ ትግሎች በልዩ ልዩ ምክንያት በድሎቹ ዋዜማና አስቀድሞ የራሳቸው ስውር ግብ ባላቸው ግለሰቦችና ቡድኖች እጅ በመውደቃቸው ብዙ መስዋዕትነት የተከፈለባቸው ትግሎች ግቦቻቸውን እየሳቱ ሌሎች ትግሎችን የሚጠይቁበት ሁኔታዎች ታይተዋል።ለምሳሌም በሃገራችን የተደረጉት የተማሪዎች ትግል በደርግ እጅ መውደቅና የኢህአዴግ ትግል በጥቂቶች የህወሓቶች እጅ መውደቁ፣አሁን በአረቡ ዓለም የሚደረጉ ትግሎችንም ስንመለከት ደግሞ እንዲሁ ብዙ መስዋዕትነት ከተከፈለባቸው በኃላ ባልታሰቡና ወይም ያልተጠበቀ ግብ ባላቸው እጅ እየወደቁ ሌላ ተጨማሪ መከራን ሲፈጥሩ ተስተውላል፤ስልሆነም ትግሎች ግቦቻቸውን የሚተገብሩ ሰዎችንና ቡድኖችን ማንነት ማወቅ ይኖርባቸዋል ለዚህም የብዙሃኑ ተሳትፎዎች ወሳኝነት ይኖረቸዋል

 

 

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ።

 

 

 Pen-4

aberashiferaw.wordpress.com

ኤርትራን በአቋራጭ (ከኤፍሬም እሸቴ)

$
0
0

በሰሜን ምዕራቧ የአሜሪካ ከተማ በሲያትል ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን የሚርመሰመሱበት አንድ ሰፈር አለ። ንግድ ቤቶቹ፣ ጋራዦቹ፣ ሬስቶራንቶቹ እና እዚያ አካባቢ የሚቆሙት መኪናዎች አብዛኛው የኛ ሰዎች ንብረት ናቸው። ከመንገዱ አንዱ ኮርነር ላይ “ስታርባክስ” ቡናመጠጫ ደረቱን ሰጥቶ መንገዱን ቁልቁል ይመለከታል። ወደ ውስጥ ሲገባ አንዱ ጥግ “የኢትዮጵያውያን ጥግ” ነው፤ ሌላው ደግሞ “የኤርትራውያን ጥግ”።

 

አንድ ኢትዮጵያዊ ሲገባ እግሩ የሚመራው ወደራሱ አገር ጥግ ነው። መቀመጫ ባይኖርና በኤርትራው ጥግ በኩል ባዶ ቦታ ቢገኝ፣ ወደዚያ ለመሔድ አይሞክርም። ድንበር አይሻገርም። አንድ ኤርትራዊም እንዲሁ ወንበር ቢሞላበት ወደ ኢትዮጵያው ጥግ ለመሔድ አይሞክርም። ይህንን የሚነግረኝ ወዳጄ እየሳቀ ነው። ስታርባክሱ የባድመ ግንባር (ጦርነት የሌለበት፣ ነገር ግን ወታደሮቹ የተፋጠጡበት) አሊያም የአሰብ ቡሬ ግንባር መሰለኝ። ለመግባት አልፈለግኹም።

 

ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን በየሄዱበት ድንበርተኛ ሆነው መኖር ይፈልጋሉ ልበል? የተለያየን አገሮች ነን ብለው እንደሚለፍፉት ሳይሆን ተለያይተውና ተቆራርጠው ለመኖር አይፈልጉም።  ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ። የሚገርመው ግን ድንበርተኛ መሆን ሲፈልጉ ባድመ ግንባርንም አብረው እየገነቡ ነው። ጦራቸውን ሰድረው። የአበባ መስክ ያለበት ድንበር አይመቻቸውም – ሁለቱም። “አብረው ለመኖር የማይችሉ፣ ተለያይተው ለመኖርም የማይችሉ” የተባለው ለእነርሱ ሳይሆን አይቀርም። ይህንን የሚያፈርስ ገጠኤርትራን በአቋራጭ

መኝ ያገኘኹት ደግሞ ከሰሞኑ ወደ ሰሜን ካሊፎርኒያ ጠቅላይ ግዛት ሳን-ሖዜ ከተማ በሔድኩበት ወቅት ነውና ገጠመኙን በደስታ (ከልቤ ደስስስስ እያለኝ) ላጫውታችሁ።

 

በሰሜን አሜሪካ የተለያዩ ስብብሰቦች አሉ። ከሰፈር ልጅና ዕድር ጉባኤ እስከ ሃይማኖትና ፖለቲካ፣ ከብሔረሰብ ስብስብ እስከ ስፖርት ቡድኖች ድረስ። ከነዚህ ውስጥ በአሜሪካ የሚገኙ ወጣቶች ያቋቋሙትና ባለፈው ሳምንት 13ኛ ዓመቱን ያከበረው “የሰሜን አሜሪካ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ” አንዱ ነው። ከመላው አገሪቱ የሚሰባሰቡ ወጣቶች የሚካፈሉበት የሦስት ቀናት ኮንፈረንስ አካሂዷል።

 

ዝግጅቱን ያዘጋጁት በሳንሆዜ እና በአካባቢው የሚገኙ ወጣቶች እና እነርሱ የሚያገለግሉባቸው አብያተ ክርስቲያናት ናቸው። ኋላ ግን እንደሰማኹት ዝግጅቱን አብረው ያከናወኑት ከሳንሆዜ ወጣ ብለው ከሚገኙት ከተሞች (ለምሳሌ ከኦክላንድ) የመጡ ኤርትራውያን ወጣቶች ጭምር መሆናቸውን ተረዳኹ። ለካስ አለማወቄ ነው እንጂ እዚያው አብረውኝ ከሚውሉት መካከል አንዳንዶቹ ኤርትራውያን ነበሩ። አንዱ ወጣት መልከ መልካም ልጅ ራሱን አስተዋውቆ እስኪነግረኝ ድረስ አላወቅኹም ነበር።

 

አማርኛው ለክፉ አይሰጥም። በእጁ የያዘው መጽሐፍ የአማርኛ ነው።

“የት ለመድክ አማርኛ” አልኩት።

“እዚሁ ነው የለመድኩ”።

“ስንት ጊዜ ፈጀብህ?”

“አንድ ስድስቲ ምናምን ወር ይሆናል”።

 

ዲያቆን ነው። የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ይማር ነበረው ከአንድ ኢትዮጵያዊ መሪጌታ ኖሯል። እሳቸውን ሁል ጊዜ “ደህና ነሽ” ይላቸው እንደነበር “ነሽ ለሴት፣ ነህ ለወንድ” እያሉ እንደሚያርሙት እየሳቀ ነገረኝ። ገና ለጋ ወጣት። 19 ዓመቱ ነው። በዚህ ዓመት የመጀመሪያ ዓመት ትምህርቱን ተከታትሏል። ወደ ሁለተኛው ተሸጋግሯል። በዕድሜ እኩያ ከሚሆኑት ኢትዮጵያውያኑ ጋር ቶሎ ተላምዷል። ወጣት አይደል?

 

ሌላው ወጣት ወደ ሃያዎቹ አጋማሽ ነው። እዚሁ አሜሪካ ያደገ ሳይሆን የስደትን መከራ ቀምሶ የመጣ ስክን ያለ ልጅ ነው። እንደ ሌሎቹ ስደተኛ ወገኖቹ በሱዳንና የመን አልተጓዘም። በከባዱ የኢትዮ-ኤርትራ ድንበር አልፎ ኢትዮጵያ በሰላም ለመግባት የቻለ “ዕድለኛ ልጅ”። ቃሉን ተውሼ እንጂ “ዕድለኛ ልጅ” ያለው ራሱ ነው። አማርኛ ጥሩ አድርጎ ይናገራል። “መጻፍ ነው ችግሬ”  ብሎኛል። ታሪኩ ደግሞ ልብ ይነካል።

 

ወጣቱ ብሔራዊ ውትድርናውን ጨርሷል። ከአንዱ የጦር ግንባር ወደ ሌላው ጦር ግንባር ሲዟዟር አሳልፏል። ጦርነት ባይኖርም። “ዓይንህን ለአፍታ እንኳን ከምሽጉ እንድትነቅል አይፈቀድም” ብሎኛል። “አንድ ቦታ አያስቆዩንም። መቀያየር ነው። አንዴ ቡሬ፣ አንድ ባድመ፣ አንዴ ….”። ከዚያ ሲመርረው አገሩን ጥሎ ለመሰደድ ወሰነ።

 

“አገሩ ውስጥ ወጣት የሚባል የለም’ኮ። አንድ ልጅ 16፤ 17፣ 18 ዓመት ከሆነ የሚያስበው መጥፋት ነው። አባት ከሆንክ ግን የት ትሔዳለህ። መማረር ብቻ። ሰዉ አይናገርም። ዝ…..ም ብቻ”። (‘ም’ን ላላ አድርጎ እየጠራት።)

 

ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ ሽሬ አካባቢ ወደሚገኝ የስደተኞች ካምፕ እንዲገባ ተደረገ። እርሱ ብቻ ሳይሆን ከሌሎች ብዙ የአገሩ ሰዎች ጋር። ለአራት ዓመታት ኖረ።

 

“ምን ታደርግ ነበር?” ጠየቁት።

“ለእኔ ስኮላርሺፕ ማለት ነበር። አማርኛ ተማርኩ። መጻሕፍት ማንበብ ቻልኩ። የሚገርምህ ወደ አሜሪካ ስመጣ ሻንጣዬ 50ኪሎ ይመዝናል። 48ቱ ኪሎ መጽሐፍ ነው።”

“ሌሎቹስ ጓደኞችህ ምን ይሠሩ ነበር?”

“ሌሎቹም ዝም ብለው አልተቀመጡም። ቅኔ፣ ዜማ፣ መጻሕፍት ለመማር ወደ ጎጃም፣ ወደ ጎንደር፣ ወደ ሸዋ ሄዱ።”

“ኢትዮጵያ መጥተህ አታውቅም አይደል ከዚያ በፊት?”

“አላውቅም። ናጽነት ከመጣ በኋላ ደግሞ ችግር ሆነ። ኢትዮጵያ ማለት ሰይጣን ማለት ነበር የሚመስለኝ።”

ገታ አደረገና አንገቱን ነቀነቀ። እኔም “ለምን እንደዛ አሰብክ ምናምን” ወደሚል ጥያቄ ውስጥ መግባት አልፈለግኹም። ከሚናገረው ይልቅ በአካላዊ እንቅስቃሴው የሚያሳየው ብዙ ይናገር ነበር።

 

ወጋችንን ሳናጠናቅቅ የራት ሰዓት ደረሰና ወደ ማዕዱ ታደምን። ቀስ በቀስ ጠረጴዛችን ሞላች። ሁሉም ኤርትራውያን ናቸው። ወንዶችም ሴቶችም። ገና ወጣቶች። ሁሉም አማርኛ ይሰማሉ፣ ይናገራሉ። የተማሩት ግን በቅርብ ነው። አንዲቱ ልጅ ብቻ ገና አማርኛ አልተማረችም። አንዱ ኢትዮጵያዊ እየሳቀ “ጆሮሽን ቢቆርጡሽ አትሰሚም ማለት ነው?” አላት። ሌሎቹ የአገሯ ልጆች ሳቁ። ትርጉሙ ሲነገራት እሷም ሳቀች። የዛሬ ዓመት እሷም አማርኛ የምትችል ይመስለኛል።

 

“አማርኛ መማር ይሄን ያህል ቀላል ነው ማለት ነው?” አልኳቸው። አዎንታዊ መልስ አገኘኹ። በውስጤ “ለምን ትግርኛ አልተማርኩም ነበር? የመማር ዕድል ነበረኝ? ልማረው የምችለው ሌላ የአገራችን ቋንቋ  ነበር?” እያልኩ አሰላሰልኩ።

 

“አስመራ፤ ቤት ሙዚቃ ውስጥ አማርኛ ዘፈን እኮ መክፈት አይቻልም” አለኝ ቅድም ታሪኩን ያጫወተኝ ልጅ። ለካስ ክልከላው ጠንከር ያለ ኖሯል። ግን አልሰራም። ወጣቶቹ የፖለቲካ ድንበርን በፍቅር እየተሻገሩት ነው። ለብዙ ዘመናት ሲዘራ የነበረው የጥላቻ ዘር በጥቂት ግንኙነቶች ሲመክን ማየት እጅግ ያስደስታል። ወጣቱ በትግራይ ስላጋጠመው መልካም ነገር ሁሉ ተናግሮ አይበቃውም።

 

“አዲስ አበባ የቆየኹት አንድ ሳምንት ብቻ ነው። አሜሪካ ልመጣ ስል።” . . . ትንሽ ቆየት ብሎ ቢያየው ተመኘኹ። አዲስ አበባ የብሔረሰቦች ሁሉ መናኸሪያ፣ የኢትዮጵያዊነት ናሙና ማሳያ። ክትፎውን ቢበላ፣ ጠጁን ቢጠጣ፣ ከወያላው ጋር ቢላከፍ፣ ቆጮውን ቢሞክር፣ ቡላውን፣ ጨጨብሳውን፣ ዶሮ ወጡን …። “አብሮ የበላን ቅዱስ ዮሐንስ አይሽረውም” ይሉ የለ አባቶቻችን?

 

የሄድንበት ኮንፍረንስ እሑድ ማታ ሲጠናቀቅ ከሲያትል በመጡ ወጣቶች እና በሳንሆዜ አካባቢ በሚገኙበት መካከል ትልቅ የጨረታ ፉክክር ተጀምሮ ነበር። የሳንሆዜዎቹ ቁጥራቸው አነስተኛ በመሆኑ ውድድሩ ሲከብዳቸው ኤርትራውያኑ ወጣቶች ያግዟቸው ጀመር። በዚያ ውስጥ የምመለከተው የተለያዩና ለጦርነት የሚፈላለጉ ድንበርተኛ አገሮች ሳይሆን ወጣትነትና ፍቅር ያስተሳሰራቸው ፍጡራንን ነበር። ጠቢቡ ሰሎሞን እንዳለው ሆነ፤ “የጐመን ወጥ በፍቅር መብላት የሰባ ፍሪዳን ጥል ባለበት ዘንድ ከመብላት ይሻላል።” (መጽሐፈ ምሳሌ 15፥17)

Moving-picture-Ethiopia-flag-flapping-on-pole-with-name-animated-gif

ይቆየን – ያቆየን

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live