Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ኳሧ በእሳቸው እጅ ሣትሆን በሕዝብ ቁጥጥር ሥር ነች።

$
0
0

ከሎሚ ተራተራ !
መቼም የሰሞኑን ያገራችንን ጉዳይ ሁሉም በየጓዲያውና በየአደባባዩ እየመረመርና እያሰላሰለ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለውም። ማግኝትና ማጣት እንደሚያልፉ ሁሉ፤ መግፋትና መገፋትም አልፎ ታሪክ መሆኑ አይቀሬ ነው። እንደው እኔም በጓዳዬ ሆኜ ወደሖላ በመመለሰ የሀገራችንን ወቅታዊ ሁኔታ መቃኝት ሰጀምር፤ አንድ አሰገራሚ ነገር ትዝ አለኝ፤ ይኸውም ትዝ ይላችሁ እንደሆን ከምርጫ 97 ሦሰት አመት በፊት በአዲሰ አበባ ዩንቨርሰቲ ማእከል ተከናውኖ በነበረው ሰብሰባ ሟቹን መለስን ያፋጠጠው ምሁር የተናገረው ቃል………እንዲህ ነበር ያለው፡ እንዲህ…….. “”አሁን ምንድነው ልናደረግ የምንችለው ? ኳሶ በእርሦ ቁጥጥር ሰር ሰላለች የእርሶን ቅንነት ብቻ እንዳይነፈጉን ነው።”” ነበር ያለው።
የኳሰ ነገር፤ ኳሦ ከሳችው እጅ በሚያሰደንቅ ሁኔታ ሁለተኛም እጃቸው ላትገባ ምላ ተሰፈንጥራ ወጣች:: የወያኔ መሪዎቸም የኳሰ ሜዳ አሰላለፈም ሆነ አጨዋወት ባለማወቃቸው አጀሬ ኳሰ ባደባባይ አይናቸው እያየ ኳሰ ከእጃቸው አምልጣ በህዝብ ቁጥጥረ ሰር ዋለች። በመዋሏ እጀግ ደሰ ብሎኛል እንኳን ደሰ አላቸሁ።
ታዲያ አሁን ምን ይደረግ? ? ቁምነገሩ እሱላይ ነው። አዎ ኳሰ አያያዝ ይጥይቃል፤ ያጨዋወት ቴክኒክና ያሰላለፍ ሰልት እጀግ አሰፈላጊ ነው። በተለይ አሁን ወያኔ በተለያየ ሁኔታ ማለትም ( በውሰና) ወዘተረፈ…”.ማኖ..”… እየነካ በመሆኑ አሰላለፉ ሁሉ ባለም አቀፍ ደረጃ ምንም አይነት የቡድን መሪ የሌለው ተራ ቡድን እየሆነ በመምጣቱ ሕዝብ የፍጹም ቅጣት ምት( እሪጎሬ) ማግኝቱ አይቅሬ ነው።
የፈጹም ቅጣት ምቱ ግን በምንም አይነት ሁኔታ መሳት የለበትም፤ (ከመረብ መዋል አለበት) ከወዲሁ፤ የፖሎቲካ ድርጀቶችም ሆኑ ደጋፊዎች የእርሰበርሰ መጠላለፍን አቁመው በሰከነ ኢትዮፒያዊነት መንፍሰ ሕዘብን በማሰትባበር ማሊያችንን የኢትዮጲያ ባንዲራ አጥልቀን አሰላለፋችንን አሳምረን የዋንጫውን ግጥሚያ ለማድረግ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ መዘጋጀት አሰፈላጊ ነው።
የፍጹም ቅጣት ምቱን ማን እንደሚመታው ወሰነን መዘጋጀት ይጠበቅብናል እላለሁ። አራጋቢ…… ወያኔዎች ቢሆኑም የመሃል ዳኛው ግን ሕዝብ በመሆኑ ውጤቱ ያማረ…የነጻነት ጮራ እንደሚፈነጥቅ አልጠራጠርም እናንተም አትጠራጠሩ።.
አለማቀፍ የሚዲያ ዘጋቢዎች ሰለማይጠፉ ለዘገባው አታሰቡ በቻ ለውጤቱ እንዘጋጅ እያልኩ ይቺን አጭር የኳሦ በሕዝብ ቁጥጥር ሥር ነች መልክቴን አሳተላልፋለሁ። የዋንጫ ባለቤት ለመሆን ያብቃን እያልኩም….ነይ እርግብ አሞራ……ነይ እርግብ….ከሕዝብ,፣ድል..ጋራ…..ነይ..እርግብ…….በማለት እሰናበታለሁ።……..በቸር ይግጠመን፤
ከ ሎሚ ተራ,ተራ Wednesday, September-04-13 MWL200825@yahoo.com
ኳሦ…..በሕዝብ…..ቁጥጥር,,.ሥር ነች;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;ኳሦ…በሕዝብ……..ቁጥጥር….ሥር….ነች !!!!!!!
አሰተያየትም ሆነ ጥያቄ ቢኖራችሁ፦በዚህ ኢሜል አድራሻ ብትልኩ መልካም ነው። MWL200825@yahoo.com
ድል ለኢትዮጲያ ሕዝብ!!

↧

↧

በደቡብ ኮርያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በዛሬው እለት ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ በ ሰውል ኣካሄዱ።

$
0
0
pic2pic2ሰልፈኞቹ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የማያባራ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመቃወም በደቡብ ኮርያ ፕሬዚደንት ጽ/ ቤት ፊት ለፊት ፕሬስ ኮንፈረንስ በማድረግ የኮርያ መንግስት በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጫና እንዲፈጥር ተማጽነዋል። ለ ደቡብ ኮርያ ፕሬዚደንት ፓርክ  ግን-ሄ ደብዳቤም ኣስገብተዋል።
ሰልፈኞቹ  ለደቡብ ኮርያ  UNHCR  ተወካይና የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ደብዳቤዎችን ያስገቡ ሲሆን በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጫና እንዲፈጥሩ ተማጽነዋል።
ከሰልፈኞቹ መሃል ኣብዛኛዎቹ የዘማች ልጆች ሲሆኑ ባለፈው ጊዜ ለስልጠና መጥተው ገዢውን መንግስት በመቃወም ጥገኝነት መጠየቃቸው ኣይዘነጋም።

↧

አንዷለም አራጌ ከቃሊቲ ማጎሪያ የላከው መልዕክት እጃችን ደርሷል –የሐምሌ ጨረቃ

$
0
0

አንዷለም አራጌ ዋለ (ከቃሊቲ ማጎሪያ)

ክፍል ሁለት

Andualem-Aragie

አንዷለም አራጌ ዋለ

በሀገሬ ሰማይ ስር በሚደረገው የተቃውሞ ፖለቲካ እንቅስቃሴ ከኢዴፓ እስከ አንድነት ፓርቲ ድረስ በመሳተፍ ለአስራ ሶስት ዓመታት ያህል የምችለውን አስተዋጽኦ አድርጌያለሁ፡፡ ይህ ኩነትም የፓርቲዎችን ጓዳ ፈትሼ ግንዛቤ እንዳገኝ ስላመቻቸልኝ፣ በቀጣይ ህዝባችን የፖለቲካና ሰብአዊ መብቶቹ ተከብረው ነፃነቱን እንዳያገኝ እንቅፋት ሊሆኑ ይችላሉ ብዬ የማስባቸውን ነጥቦች እንደሚከተለው ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡

  1.  እንደ ገዥው ፓርቲ፣ ተቃዋሚ ድርጅቶችም ከኋላቀሩ የፖለቲካ ባህላ የተላቀቁ አለመሆናቸው ነው፡፡ እናም አዲስ የፖለቲካ ባህል ለማስጀመር ከመስራት ይልቅ ሳያውቁት ከዘመነ-መሳፍንት የተቀዳውን የፖለቲካ ባህል በተሻለ ተግባራዊ ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ ዛሬም ይታያሉ፡፡
  2.  የእስከ ዛሬውን የከሸፈ ሂደት የገመገመና የኢትዮጵያን ህዝብ ለአንዴና ለመጨረሻ ከተጫነበት የጭቆና ቀንበር ለማላቀቅ የሚያስችል በውል የታሰበበትና የተጠና የፖለቲካ ቀመር እጦት በተቀቃዋሚ ፓርቲዎች ዘንድ በጉልህ ይንፀባረቃል፡፡
  3.  የማያምኑበትን መቃወም ተገቢ የሆነውን ያህል የየራሳችንም ህፀፆች ያለርህራሄ ማየት፣ አይቶም ነቅሶ ማውጣት ተገቢ ነው፡፡ ነገር ግን በተቃዋሞ ጎራ ባለነው ፖለቲከኞች ላይ ይህንን የማድረግ ችግር ይታይብናል፡፡ ህፀፆችን ቀድሞ ማየቱ ከሌላ ወገን የሚሰነዘረው ነቀፋ ምክንያቱን ለመረዳት እድል ይሰጣል፡፡ በትችት ከመሰበርም ይታደጋል፡፡
  4. ከ1960ዎቹ ጀምሮ የኢትዮጵያ ፓርቲዎች መለያ ከሆኑት አንዱ ‹ግትርነት› መሆኑ አከራካሪ አይመስለኝም፡፡ ይህ ሁኔታ በፓርቲዎች መካከል ብቻ ሳይሆን፣ በራስ ፓርቲ አባላት ውስጥም የሚፈጠሩ ችግሮች ከግትርነት የሚነሱ ናቸው፡፡ ‹‹መሸነፍ››፣ ‹‹ማሸነፍ››፤ ‹‹መንበርከክ››፣ ‹‹ማንበርከክ›› በሚለው የጫወታ ህግ ታስረን በቆምንበት ስንረግጥ በአስከፊው የመከራ ዘመን እንድንቆይ አድርጐናል፡፡ ችግር የመፍቻ ስልትም ሆነ ባህል አላዳበርንም፡፡ እንዲያውም የትግሉ እንቅስቃሴ ከአገዛዙ ጋር መሆኑ ቀርቶ በእኛ መካከል ሆኗል፡፡
  5. የተወሰኑ ሰዎች ‹‹በሰላማዊ ትግል›› ውስጥ ቢሆኑም ‹‹በዚህ መንገድ አገዛዙን ታግሎ ማሸነፍ አይቻልም›› የሚል እምነት ስላደረባቸው በግማሽ ልብ የሚያደርጉት ትግል ትርጉም ያለው አስተዋፆ እንዲያበረክቱ አላስቻላቸውም፡፡ ሰላማዊ ትግል ራሱን የቻለ ትልቅ እምነት መስጠትና ስነ-ምግባር ያለው መሆኑን ይዘነጋሉ፡፡
  6. አንዳንድ የተቃዋሚው የትግል ጐራን የሚቀላቀሉ ግለሰቦች በስሜት ብቻ በመመራት አባል የሚሆኑበት አገጣሚ ብዙ መሆኑ ለተደራጀ ትግል እንቅፋት ሆኗል፡፡ ይህንን በምሳሌ ለማስረዳት ከአንድ የቀበሌ ካድሬ ጋር ስለተጣሉ ብቻ አባል የሚሆኑ ሰዎች፣ አገዛዙን ለመቀየር የሚጠይቀውን መስዋዕትነት ከፍሎ ከማሸነፍ ይልቅ እልሃቸው ሲበርድ የውሃ ሽታ ሆነው መቅረታቸው ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡
  7. አገዛዙ አንዳንድ ጠንካራ አባላትና አመራር ላይ ጥቃት ማድረስ ሲጀምር ተደናግጦ ማፈግፈጉም ሌላ ችግር ነው፡፡ ይህ ሁኔታ የነፃነት ትግል አልጋ በአልጋ እንደሆነ ከመጠበቅ የሚመነጭ ይመስለኛል፡፡
  8.  የፓርቲ አባላት ከአመራር እስከ ተራ አባላት፣ ከገጠር እስከ ከተማ ንቃተ-ህሊናቸውን የሚያዳብሩና የርዮተ-ዓለም ትጥቆችን የሚያስታጥቁ ስልጠናዎችንና የውይይት መድረኮችን የመፍጠር ችግርም ተጠቃሽ ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ ድንገተኛና በቂ ዝግጅት ያልተደረገበት እንቅቅስቃሴ ይደረጋል ውጤቱም አመርቂ አይሆንም፡፡
  9. የዓለም አቀፍ ሰላማዊ ትግል ተሞክሮዎችን ከኢትዮጵያ ታሪክ፣ ፖለቲካ፣ ባህል እና ተጨባጭ ወቅታዊ ሁኔታዎች አንፃር ተቃኝተው ተግባራዊ የሚያደርጉበትን ሁኔታ የመፍጠር ችግር ይታያል፡፡
  10.  የቁርጠኝነት ችግር፡- የአገዛዙ አውራዎች ወጥተው በመገናኛ ብዙሃን ፉከራና ቀረርቶ ሲያሰሙ ተደናግጦ ወደዋሻ መግባትና የትግሉን ሙቀት ማቀዝቀዝም እንዲሁ መፍትሄ የሚፈልግ ጉዳይ ነው፡፡
  11. በእቅድ የመመራት ችግር፡- በገዥው ፓርቲ ትንኮሳ ወይንም መግለጫ ላይ ተመስርቶ የእሳት አደጋ ስራ መስራት፡፡
  12. ተቀባይነት ያለውና ህዝብ በቀላሉ የሚረዳው አስተሳሰብ፣ ታማኒነት ያለው ንግግር የተጨባጭ ተግባር ባለቤት ያለመሆን ችግር፡፡
  13. ተጠራጣሪነት፡- አብሮ ታግሎ ለውጤት ለመብቃት መተማመንን መፍጠር የመጀመሪያው ተግባር ሊሆን ሲገባው መተማመን በጎደለበት ሁኔታ ፓርቲዎች አብረው ለመስራት ቢሞክሩም ሩቅ መገዝ አይችሉም፡፡ አሉባልታ ከግልፅነት ይልቅ እድል ይሰጠዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ትግሉ ያለባለቤት ይቀመጣል፡፡
  14. መናናቅ፡- ጥቂት ንብረትና ጥቂት አባላት ያሏቸው ፓርቲዎች ከሌሎች ፓርቲዎች በጥቂቱ መሻላቸው ትግሉን ያጠናቀቁ ያህል ይኮፈሳሉ፡፡ በሌላ ወገን ያሉትም ጉድለቶችን በማስተካከል ወደፊት በትጋት ሊፋታ ሲገባ ስራቸውን ትትው መዘላለፍ ውስጥ ይገባሉ፡፡
  15.  የፓርቲ አመራሮች ታላቅ የመሆን ቅዠት፡- ከዘመነ-መሰፍንት የተቀዳው የፖለቲካ ባህላችን ብዙ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችን በማስጎምዠት እንቅልፍ ይነሳናል፡፡ የፕሮግራም ሆነ የአሰራር ልዩነት ሳይኖር ለስልጣን በሚደረግ ፍልሚያ ፓርቲን የሚያህል ተቋም ለሁለት ይከፍሉታል፡፡ በቲኒኒሽ ቢሮዎች ትልልቅ ሽኩቻዎች ይደረጋሉ፡፡ ትልልቅ ስም ያላቸው አመራሮች በጥቃቅን ጉዳይና ከስልጣን ጋር በተያያዙ ችግሮች ተጠልፈው ይወድቃሉ፡፡ የማያበራ ችግርም ይፈጠራል፡፡ ዓላማችን ትልቅነት እንኳ ቢሆን ትልቅ መሆን የሚቻለው በአስተሳሰብና በተግባር ልቆ በመገኘት እንጂ በብልጣ ብልጥነት ሊቀ-መንበር ተብሎ በመሰየም አለመሆኑን ይዘነጉታል፡፡
  16. የሰላማዊ ትግልን ባህሪያት የትግል ስልቶችና ግቦቹን በሚገባ አለመተንተን ወይንም ግልብ በሆነ ግንዛቤ ተመስርቶ መንቀሳቀስ፡- ከ1960ዎቹ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እንቅስቃሴ ጀምሮ የሀገራችን የፖለቲካ ትግል በሰላማዊ መንገድ ወጣ ገባ እያለም ቢሆን ተሞክሯል፡፡ በኢህአዴግ የ22 ዓመታት አገዛዝም ለቁጥር የሚያታክቱ ፓርቲዎች በሰላማዊ መንገድ እንታገላለን ብለው ቢደራጁም አብዛኛው የትግሉን ባህሪ አለማወቃቸው በትብብር የሚመጣ ውጥን አዘግይተዋል፡፡
  17.  ትግሉን የህዝብ የማድረግ ችግር፡- በሀገራችን በተደረጉ የሰላማዊ ትግል ሙከራዎች ላይ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚያነሷቸው አጀንዳዎችን የሕዝብ በማድረግ እንዲታገልባቸው ሲያደረጉ አይታይም፡፡ ትግሉ ግብ ሊመታ የሚችለው ህዝቡ በትግሉ ከልብ አምኖ መታገል ሲችል ነው፡፡ ሆኖም ወደ ህዝብ ባለመውረዱ ጥቂት አመራሮች ሲታሰሩ ወይንም ቢሮዎች ሲዘጉ ትግሉም የመዳፈን አዝማሚያ ሲያሳይ አስተውለናል፡፡
  18. የተፅኖ ማዕከሎች ያለመኖር፡- ተቃዋሚ ፓርቲዎች እራሳቸው አፈና ውስጥ ሆነው የአፈና ቀንበር ለመስበር የሚሰሩ በመሆናቸው የአቅም ውሱንነቶች አለባቸው፡፡ ስለዚህ ያላቸውን የገንዘብና የሰው ሃይል አብቃቅተው የተሳካ ትግል ማድረግ ይችሉ ዘንድ የተወሰኑ የተፅኖ ማዕከላትን መፍጠር ይጠበቅባቸዋል፡፡ ደቡብ ህበረት በ1992 ዓ.ም. ብሔራዊ ምርጫ ሃድያ አካባቢ ያደረገው ተጋድሎ ለተነሳው ሃሳብ ጥሩ ምሳሌ ይመስለኛል፡፡
  19.  ትኩረት የተነፈገው የፓርቲዎች የገንዘብ የማሰባሰቢያ ስትራቴጂ፡-  በገንዘብ አቅርቦት ምክንያት በርካታ እቅዶች ወደተግባር ሳይለወጡ ይቀራሉ፡፡ በየክፍለ ሀገሩ ራሳቸውን ለመስዋዕትነት ያዘጋጁ አባሎቻቸውን ከማዕከል ጋር ግንኙነት እንዲኖራቸው በማድረግ ትግሉን አጠናክሮ ከመግፋት ይልቅ የቢሮ ኪራይ እንዲላክላቸው በመወትወት ጊዜያቸውን ሲያባክኑ ይታያሉ፡፡ በሂደትም እየተሰላቹ ከትግሉ ያፈገፍጋሉ፡፡ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ስትራቴጂ አዘጋጅቶ የገንዘብ ጥያቄን በማያሻማ መልኩ መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡ ይኽንን ማድረግ ሳይቻል በሰላማዊ ትግል ብዙ ርቀት መሄድ አይቻልም፡፡ የሚኖረው ዕጣ ፈንታ እንደአንዳንዶቹ ፓርቲዎች ጓዝን ጠቅልሎ ቀለብ ለማስፈር ለገዥው ፓርቲ ማደር ነው፡፡

ከሞላ ጎደል የኢትዮጵያን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ቀይደው የያዙና ሰላማዊ ትግሉን ወደፊት አላራምድ ካሉ ችግሮች ውስጥ እነዚህ ዋነኞቹ ናቸው ብዬ አስባለሁ፡፡ እናም ፓርቲዎቹ በሰላማዊ ትግል የኢትዮጵያን ሕዝብ የነፃነቱ ባለቤት እንዲሆን በሚያስችል መንገድ ለመምራት ከዚህ አንፃር ራሳቸውን ቢፈትሹ የተሻለ ነው፡፡

ይህንን ሀሳብ ከጠባቡ የእስር ክፍሌ የላኩት ፓርቲዎች፣ አመራሮቻቸውና አባላቻቸው እንዲዳከሙ ወይም ተነሳሽነታቸውን አኮስሼ ከጫወታ ለማስወጣት ከመፈለግ ሳይሆን የተሻ አቅምና ስትራቴጂ አዳብረው ለውጤት እንዲበቁ ብሎም የኢትዮጵያን ህዝብ ከአፈና አዙሪት ለማውጣት እንዲችሉ ከልቤ በቅንነት በመመኘት መሆኑን እንደምትረዱኝ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

ሌላው መረሳት የሌለበት እውነታ በፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ በተለያዩ የሀላፊነት ደረጃ ባሳለፍኳቸው እስራ ሶስት ዓመታት በፓርቲም ሆነ በግለሰብ ደረጃ ለታየው ድክመት እኔም ሀላፊነት የምወስድ መሆኔን ነው፡፡ እንዲሁም ካሉብኝ ውሱንነቶች አንፃር አቀራረቤ የጅምላ በመሆኑም ምንም እንኳን በአጠቃላይ የዴሞክራሲ ትግሉ ላይ በተናጠል ለውጥ ማምጣት ባይችሉም ሁልጊዜም የተሻለ የተደራጀ፣ የተሻለ ዴሞክራሲያዊ አሰረራር የነበራቸው ፓርቲዎች እንደነበሩ አይካድም፡፡ እናም ሁሉንም በአንድ አይነት ደረጃ ማስቀመጥ እንዲመጣ ለምንሻው መሻሻልም በጐ አስተዋፆ እያበረክትም፡፡ በግለሰብ ደረጃ ቢሆን ሁሉንም አንድ ቅርጫት ውስጥ መወርወር ተገቢ አይደለም፡፡ ለስልጣን የማይቋምጡ፣ ቀን ከሌት ሰርተው የማይሰለቹና ለሀገራቸውና ለህዝባቸው ችግር ቅድሚያ የሚሰጡ (በጣም ጥቂት ቢሆኑም) ግለሰቦች መኖራቸውን በዚህ አጋጣሚ ማስታወሱ ተገቢ ነው፡፡ የዚህ ፅሁፍ አላማም እንዲህ አይነት ግለሰቦች ተበራክተው ወደ ስብስብ ደረጃ እንዲደርሱ ማበረታታት ነው፡፡

የሆነ ሆኖ ከፍ ብዬ ያነሳዋቸው ከግማሽ ምዕተ-ዓመት በላይ ውል አልባ ያደረጉ ችግሮችን መፍታት ለነገ የማይባል ስራ ነው፡፡ ይህን ዓላማ ከግብ ለማድረስም ከዚህ በታች የምጠቅሳቸው ነጥቦች አስፈላጊ ናቸው ብዬ አምናለሁ፡፡

  1.  በየጊዜው ለምናስመዘገባቸው ለውጦች እውቅና በመስጠት በተገኘው ድልም  እየተበረታታን ነፃነት እኛ እስከታገልን ድረስ በተጨባጭ የምናሳካው ግብ መሆኑን ማመን፡፡
  2.  አገዛዙን ለማሸነፍ ተቀዳሚው ተግባር ራሳችንን ማሸነፍ መሆኑን ተገንዝቦ ህዝብን ከስሜት በፀዳ መልኩ በሀላፊነት ስሜት ማደራጀትና ለውጤት ለማብቃት መስራት፤
  3.  ሰላማዊ ትግል ለውጤት የሚበቃው በዕውነት፣ በፍቅርና ከዚያም በሚመነጭ ፅናት ላይ ተመስርተን ተግባራዊ ስናደርገው መሆኑን መገንዘብ፤
  4.  ገዥዎች በአፈ-ሙዝ ስጋን ሊገድሉ ሲያደቡ፣ ክፉ ሃሳባቸውንና ተግባራቸውን በአሳማኝ ምክንያቶችና በተገራ ሰብዕና ላይ ተመስርቶ ለመለወጥ መስራት፡፡
  5. ፍርሃትን መግደል፡- ፍርሃትን ማሸነፍ ባልቻልን ቁጥር ሰላማዊ ታጋዮች የመሆን ዕድላችን በዚያው መጠን መቀነሱ አይቀሬ ነው፡፡ የፍርሃት እስረኞች በሆንን ቀጥር አገዛዙ የጭቆና ሰንሰለቱን ለማጥበቅ ስለሚበረታ ፍርሃትን ግዴታ ማሸነፍ ያስፈልጋል፡፡ የአገዛዙን ቁንጮዎችም ሆነ ማንኛውንም ሃላፊ መፍራትና ክብሩን ማዋረድ አያስፈልግም፡፡ ትግሉ የእነርሱ አይነት የህዝብ ጌቶች ለመፍጠር ሳይሆን የህዝብ አገልጋዮችን ለመፍጠር ነውና፡፡
  6. ሰላማዊ ትግል ለውጤት የሚበቃው ከበቀልና ግብታዊ ከሆኑ እርምጃዎች እራሳችንን ስናፀዳ ነው፡፡ አላማችን የማንም ክብር የማይደፈርባትና የሁላችንም ሉዓላዊነት የሚከበርባት ልጆቻችንም በኩራት የሚኖሩበትን ሀገር መፍጠር ነው፡፡
  7. 7. የአገዛዙ የአፈና እርምጃዎችና በህዝብ ዘንድ ሽብርን ለመንዛት የሚያደርጋቸው የሀሰት ዶሴዎች ለተጨማሪ ትግል መነሳት እንዳለብን የሚያስገነዝቡ እንጂ ፈፅሞ ወደኋላ እንድናይ የሚያደርጉን አለመሆናቸው፡፡
  8. በየጊዜው የአቋማችንን፣ የትግል ስልታችንን ትክክለኛነት መፈተሽ በወቅቱም እርምት መውሰድ ወሳኝ ነው፡፡
  9. ሁልጊዜም ቢሆን ተሳስተን ገዥዎቻችን መጠላት፣ ለበቀል መዘጋጀትም ሆነ በእነርሱ ላይ በመዛት ወደፊት በሚመጣው ንጋት ስጋት እንዲገባቸው ማድረግ አያስፈልግም፡፡ አይገባምም፡፡
  10. አገዛዙ ለህዝብ ፈቃድ ለመገዛት ተነሳሽነት ሲወስድ ማበረታታት እንጂ እንደተዳከመና እንደተንበረከከ እንዲሰማው ማድረግ ተገቢ አይደለም፡፡
  11. የኢትዮጵያን ህዝብ ለዘመናት ከስብዕና ሚዛን ያወረደውን የጭቆና ስርዓት መታገል የህይወት ዘመናችን ዓላማ አልፋና ኦሜጋ ሊሆን ይገባዋል፡፡ በግለሰብ ደረጃ ያሉን ህልሞችና ጥቅሞች ሊሳኩ የሚችሉት ትልቁ ችግራችንን በጋራ ስንፈታ ነው፡፡ ሁለንተናችን አንድ ላይ የተገመደ መሆኑን ለአፍታም መዘንጋት አይገባንም፡፡
  12.  በረጅሙ ታሪካችን ተሳክቶ የማያውቀውን የድሎች ሁሉ አውራ ማስመዝገብ የምንችለው ትግሉ የሚጠይቀውን የመስዋዕትነት ደረጃ ከወዲሁ ተረድተን በስነ-ልቦናም ስንዘጋጅ ነው፡፡ ምናልባት አንዳንዶቻችን የትግሉ ፍሬ ተቋዳሾች ለመሆንም እንደርስ ይሆናል፤ መንገዳችን ላይ መታሰርና መንገላታት ብቻ ሳይሆን ሞትም አድፍጦ ሊጠብቀን ይችላል፡፡  ይኽንንም አውቀን በቁርጠኝነት መግፋት ብቻ ነው ያለን አማራጭ፡፡
  13. ሁልጊዜም በአቋራጭ እና የትግል አጋሮቻችን መስዋዕት በማድረግ ለውጤት ለመብቃት መሞከር አይገባንም፡፡ ትግላችን ግልፅነትና ንፅህና የተሟላ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ነገ ልንፈጥር የምንመኘውን መልካም ነገር፣ ዛሬ በምናደርገው መልካም ተግባሮች የተሞላ መሆን ማስመስከር አለብንና፡፡
  14. የአገዛዙን ባህሪዎችና ‹‹የእግር ቆረጣ›› ስልቶች ቀድሞ በመረዳት የተጠና አፀፋዊ እርምጃ ለመውሰድ አስቀድሞ መዘጋጀትም ያስፈልጋል፡፡
  15. በዘረኝነት ወጥመድ ተጠልፎ ላለመውደቅ መጠንቀቁም ተገቢ ይመስለኛል፡፡ አገዘዙ ስልጣን ላይ መቆየት እስከቻለ ድረስ የኢትዮጵያ ህዝብ በዘረኝነት ወረርሽኝ ቢጠቀም አንዳች ቅሬታ የሚገባው አይመስልም፡፡ ያዝ ለቀቅ እያደረገ ሲንቀሳቀስ እንደምናየው ስልጣኑን የሚነቀንቅ ከመሰለው የሃይማኖት አሊያም የዘር ግጭት ቀስቅሶ መልሶ እራሱን ግጭት አርጋቢና መፍትሄ ፈላጊ አድርጐ ለማቅረብ ይሞክር ይሆናል፡፡ በእኛ በኩል ሊያዝ የሚገባው ግልፅ አቋም በየትኛውም ዘመን ቢሆን አንዱ ህዝብ ሌላውን ጨቁኖ ባለማወቁ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ በየትኛውም ወቅት ቢሆን ኢትዮጵያውያን አማኞች የወንድሞቻቸውን የማምለክ ነፃነት ተጋፍተው አያውቁም፡፡
  16. ሕዝብ በጋራ የአምባገነን መሪዎች የአፈና ሰለባ ነው፡፡ ሰውን በአስተሳሰቡ እንጂ በዘሩ መመዘን የጀመርን ቀን ያን ጊዜ ከሰብዓዊነት ሚዛን እንወጣለን፤ ከስልጣኔ ሃዲድ እንስታለን፡፡ የሰላማዊ ትግል የመጨረሻ ግብ ፍቅር፣ ወንድማማችና አስተማማኝ ነፃነት ሆኖ ሳለ ለዘረኝነት እድል በሰጠን መጠን የትግላችን አላማ ይከሽፋል፡፡ ዘረኝነት ኢሰብዓዊነት ነው፡፡ ዘረኝነት ከትንሽና ክፋት ከተጠናወተው ሰብዕና የሚመነጭ መርዝ ነው፡፡ በዘረኝነት ሰንሰለት ተጠፍንገን ለውጤት ለመብቃት ብንሰራም ፈጣሪም ከእኛ ጋር አይቆምም፤ ዓላማው በሰው ልጆች መካከል ፍቅርና አንድነት እንጂ ጥላቻና መለያየት አይደለም፡፡ ጊዜም ከእኛ ጋር አይተባበርም፡፡ ለኢትዮጵያውያን ሁሉ እኩልነት፣ ነፃነትና ክብር ከልብ ስንቆም ያን ጊዜ የፈጣሪ ሀያል ክንድ ከእኛ ጋር ይሆናል፡፡
  17. ሚስጥራዊነትና ሰላማዊ ትግል ጋብቻ ሊፈፅሙ አይገባም፡፡ የምናደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ሁሉ ውጤታቸውም ጭምር በይፋ ማወቅ ለሚፈልግ ሁሉ ግልፅ ማድረግ ይገባል፡፡ አገዛዙ እንኳን በሚስጥር የሚደረግ እንቅስቃሴ አግኝቶ በይፋ የሚደረጉ የትግል እንቅስቃሴዎችንም እስካልተመቹት ድረስ አይኑን በጨው ታጥቦ የሽብር ካባ እየደረበ ትግሉን ለማምከን ሲሞክር እያየን ነው፡፡ የአገዛዙ ክፉ ሃሳብና ተግባር እንዳለ ሁኖ ግልፅነት በህዝብና በትግሉ መካከል ያለውን ቁርኝት ያጠብቀዋል፡፡ ህዝቡም የፕሮፓጋንዳ ሰለባ እንዳይሆን ይረደል፡፡ ስለዚህ በምንም አይነት መልኩ ከመጋረጃ ጀርባ የሚደረጉ የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴዎች ሊኖሩ አይገባም፡፡
  18.  የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴዎች ትኩረት በማዕከል በሚደረግ ዝግጅት ብቻ ሳይሆን በየአካባቢው ያሉ አባላት አጠገባቸው ባሉ አመራሮች አማካኝነት በተጨባጭ ችግሮች፣ በእውቀትና በጥሩ ዝግጅት ላይ የተመሰረቱ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ሲችሉ ለትግሉ ግብዐት ይሆናሉና፡፡ ሌሎች የፓርቲ ቅርንጫፎችም ከእነርሱ ተሞክሮ እንዲወሰዱ ማድርግ በተቻለ መጠንም በየቦታው ያሉ አባላትና ነዋሪው ህዝብ ስለሰላማዊ ትግል ተጨባጭ ትምህርት በመቅሰም እንዲንቀሳቀስ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
  19.  የሰላማዊ ትግል ፈርጦች የሆኑት ማህተመ ጋንዲና ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር በተለያየ ወቅት የተናገሩትን ተመሳሳይ ይዘት ያለውን ሃሳባቸውን አፅንዎት ሰጥተን ልንወስደው ይገባል፡፡ ማህተመ ጋንዲ ‹‹ማንም ሰው ያለፈቃዱ አንዳች ነገር እንዲያደርግ ምንም አይነት ምድራዊ ሃይል ሊያስገድደው አይችልም፡፡›› ሲሉ፣ ዶ/ር ኪንግም ‹‹እስካልተጐነበስን ድረስ ማንም ሊጋልበን አይችልም፡፡›› ማለቱ ይታወሳል፡፡ ይህ አንድ አይነት መልዕክት የሚያስተላልፈው የሁለቱም የነፃነት ታጋዮች አባባል በየትኛውም ሀገር በጭቆና ቀንበር ስር ለሚማቅቅ ህዝብ የሚሰራ እውነታ ነው፡፡ ስለዚህም ከቆምንለት ህዝባዊ፣ ዴሞክራሲያዊ መንግስት የተመሰረተባት የወንድማማችነት፣ የፍቅርና የነፃነት ማማ የሆነች ሀገር የመገንባት ግባችን ሊመልሰን የሚችል አንዳች ሃይል እንደሌለ ተገንዝበን በፅናትና በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ ይገባናል፡፡

እንደ መውጫ

ከመተኛት አልፎ እንደ ልብ መንቀሳቀስ በማይቻልበት ጠባብክ የእስር ክፍሌ ሆኜ ጎኔን ወለል ላይ፣ ጆሮዬን ወደምድር አስጠግቼ ልዳበስውና ልጨብጠው የማልችለውን ድምፅ ላደምጥ ሞከርኩ፤ እናም የአለፈው እና የአሁኑን የዘመን ዱካ ከእነአፈ እና ግሳንግሱ እየራቀ ሲሄድ፤ የመጭው ዘመን የነፃነት ድምፅና ጭቆናን የማይቀበል ትውልድ ኮቴ እየቀረበ ሲመጣ ይሰማኛል፡፡ ይህ ድምፅ ዕውን እንዲሆን ጊዜውም እንዲፈጥን፣ አባቶቻችን የዳር ድንበር ነፃነት ለማስከበር እንደዘመቱት እኛም የሰላም፣ የፍቅር፣ የወንድማማችነትና የፅናት ሰይፍ ታጥቀን የመትመም ለነገ የማያድር ሀላፊነት አለብን፡፡

ጉዞአችን ምንም ያህል አዝጋሚና በውጣ ውረድ የተሞላ ቢሆንም የምንወዳትን አዛውንት ሀገራችንን ከዘመናት የስቃይ ፅንሷ ነፃነትን የምትገላገልበት ወቅት ስለመቅረቡ ለሰከንድም አልጠራጥርም፡፡ የሐምሌና ነሐሴ ድቅድቅቅ ጨለማ፣ አጥንት ሰብሮ የሚገባ ብርድ ያኮራመታቸው እፀዋት በመስከረም ወር ከአፅናፍ አፅናፍ በሚዋኘው የብርሃን ጅረት ሁለንተናቸው ተፍታቶ ለአይን የሚማርኩ የተፈጥሮ ፀጋዎች መሆናቸውን በኩራት እንደሚያውጁ ሁሉ፣ ኢትዮጵያውያንም ዕድሜ ጠገቡን የአገዛዝ ቀንበር ከጫንቃችን አውርደን በመጣል፣ ሀገራችን ከዳር ድንበር ነፃነት ጋር ብቻ ተያይዛ የምትጠቀስ አለመሆኗን በተጨባጭ በማረጋገጥ በኩራት በሀገራችን መኖር እንጀምራለን፡፡ ሀገራችን የሰብዓዊ ክብር ማማ የምትሆንበት ዘመን እነሆ እየገሰገሰ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ያ ዘመን በመሬታችን ሲደርስ ‹‹ኢትዮጵያ የአፍሪካ መዲና…›› የሚለውን የኩኩ ሰብስቤ ዜማ ከተወሰኑ የግጥም ማስተካከያዎች ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘን ከልብ መዘመራችንም አይቀሬ እንደሆነ አምናለሁ፡፡

አዛውንቷ ሀገራችን የሰብዓዊ ክብር ማማ፣ ‹‹የአፍሪካ ገናና›› ትሆን ዘንድ ነፃነትን በእርጋታ፣ በትዕግስትና አስተዋይነት በተሞላበት ሁኔታ የምናዋልድ ጥበበኛ ሀኪሞ ልንሆን ይገባናል፡፡ ሀገራችን በተለያየ ወቅት ነፃነትን ብታረግዝም ፅንሱን ከእነነፍሱ ለማዋለድ እስከዛሬ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ ያልተሳኩ ነፃነትን የማዋለድ ጥረቶችም በባለታሪኳ ሀገራችን ላይ አገዛዙ እረግጦ በመግዛት ለመቀጠል የሚያደርገው የሞት ሽረት ትግል ሲጨመርበት፣ ሀገራችንን ፈፅሞ ወደ ማንመኘው የውድቀት አፋፍ ይዟት እንዳይወርድ ጥብቅ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል፡፡ ይኽን ማድረግ ካልቻልን በምክንያት የማንመራ፣ በስሜትና ኋላቀርነት አረንቋ የምንዳክር ልጆቻችን የሚያፍሩብን፣ መጭው ትውልድ የሚወቅሰን አባቶች እንዳንሆን ስጋቴ ፅኑ ነው፡፡

ስለዚህ በድቅድቁ የጭቆና ሌሊት ላይ ለዘላለም የማትጠልቅ የነፃነት ፀሐይ እስትከሰት ትግላችን ሊቀጥል የገባዋል፤ በድቅድቁ የአፈና ሌሊት ጨረቃ ያለማቋረጥ እስክትሰለጥን ጤፍ የሚያስለቅም ጣፋጭ ፍቅር የሚያስኮመኩም፣ ዜጐች ያለአንዳች ስጋት የሚመላለሱበትና የዱር አራዊትም ጭምር ለአደን ያለመከልከል እንዲወጡ የሚያስችል ብርሃኗን በምድራችን ላይ እስክትረጭ ትግላችን ከቀድሞ በበለጠ ደረጃ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፤ ሀገራችን የረጅም ዘመን እርግዝናዋን በሰላም ተገላግከላ የምድር ሁሉ ፈርጥ እስክትባል ድረስ የነፃነትንና የወንድማማችነት ንጋት የተራባችሁ ኢትዮጵየውያን ሁሉ የፍቅርና የፅናት ዝናራችሁን ታጥቃችሁ ትግላችሁን ቀጥሉ፡፡ አዎ! ነፃነት እንደቀትር ብርሃን ፍቅርም እንደሃይለኛ ጅረት የሀገራችን ምድር ሞልቶ ይፍሰስ!! ነፃናት፣ ነፃነት፣ ነፃነት፤ እደግመዋለሁ አሁንም ነፃነት!!!

↧

የዘ-ሐበሻ የዓመቱ ምርጥ ሰው ማን ይሁን?

$
0
0

የ2006 ዓ.ም አዲሱን ዓመት ልንቀበል የቀሩን ጥቂት ቀናት ብቻ ናቸው። በየዓመቱ እንደምናደርገው ሁሉ የዚህን ዓመት የዘ-ሐበሻን ምርጥ ሰው ስለምንሰይም የእርስዎን ምርጥ ሰው የሚሉትን በinfo@zehabesha.com ለምን ያንን ሰው ሊመርጡ እንደቻሉ ከትንሽ ማብራሪያ ጋር ይጻፉልን። ውጤቱን በአዲሱ ዓመት ዋዜማ እናሳውቃችኋለን።
ዕውነት ያሸንፋል!!
zehabesha

↧

የቀድሞው ገራፊው የደህነት ሹም በእስር ቤት እየተገረፈ ነው – (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

$
0
0

weldesilaseከአዲስ አበባ ፖሊስ ምንጮች አሁን በደረሰኝ መረጃ የአገር ውስጥ ደህንነት ሃላፊ የነበረው አረመኔው ወ/ስላሴ ወ/ሚካኤል በማእከላዊ ወንጀል ምርመራ መገረፉን አስታውቀዋል። የአዜብና መለስ ቀኝ እጅ የነበረው ይህ ጨካኝ የደህንነት ሹም በስልጣን በነበረበት ወቅት እነ ጄኔራል አሳምነውን በመደብደብ፣ አይናቸውን በቦክስ በመምታት ከፍተኛ የጭካኔ ተግባር ይፈፅም እንደነበረ ምንጮች አስታውሰዋል። በ1997-98 ዓ.ም በሺህ የሚቆጠሩ ሰላማዊ ወገኖች እንዲገደሉ፣ እንዲታሰሩና አሰቃቂ ግፍ እንዲፈፀምባቸው ያደረገው ወ/ስላሴ መሆኑን አያይዘው ገልፀዋል። በርካታ ሰዎች ከመግረፍና ከማሰቃየት ባለፈ በጥይት ደብድቦ ይገድል እነደነበረ አመልክተዋል። የቤተመንግስት የጥበቃ ሃላፊ አቶ ዘርኡ መለስ አንገታቸውን በስለት በማረድ እንዲሁም የመንገድ ት/ሚኒስትሩን አቶ አየነው ቢተውልኝን በገመድ አንቆ የገደለው ወ/ስላሴ መሆኑን ከዚህ ቀደም መገለፁ ይታወሳል። ወ/ስላሴ በትላንትናው እና በዛሬው እለት ሁለት ጊዜ መገረፉን ምንጮች አረጋግጠዋል።

↧
↧

ሰማያዊ ፓርቲ በመስቀል አደባባይ የጠራውን ሰልፍ ወደ መስከረም 12 ማዘዋወሩን አስታወቀ

$
0
0

blue party(ዘ-ሐበሻ) ሰማያዊ ፓርቲ በአዲስ አበባ ለጷጉሜ 2 ቀን 2005 ጠርቶት የነበረውን የተቃውሞ ሰልፍ ወደ መስከረም 12 ቀን 2006 ማስተላለፉን ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫ አስታወቀ።
ፓርቲው ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫ “ሰማያዊ ፓርቲ ለነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም ጠርቶት የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ በመንግስት ታጣቂ ኋይሎች ሕገ-አራዊት እርምጃ ከተደናቀፈ በኋላ ፓርቲያችን ነሐሴ 30 ቀን 2005 ዓ.ም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ጳጉሜ 2 ቀን 2005ዓ.ም ሠልፉ በድጋሚ እንደሚካሔድ አስታውቋል፡፡ ሠልፉ የተሳካና ሰላማዊ እንዲሆን በፓርቲ በኩል ልዩ ልዩ ተግባራት ከመከናወናቸው ጎን ለጎን አስፈላጊው የጸጥታ ጥበቃና የአስተዳደር ድጋፍ እንዲሰጠን በህጉ መሰረትም ሠልፉ እውቅና እንዲያገኝ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሰወቂያ ክፍል ነሐሴ 27 ቀን 2005ዓ.ም ደብዳቤ ለማስገባት በአካል ተገኝተን ጠይቀናል፡፡ ሆኖም ግን ይህ ክፍል ደብዳቢያችንን ለመቀበል ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል፡፡” ካለ በኋላ ‘በፓርቲው በኩል በሁኔታው ተስፋ ባለመቁረጥ በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት በኩል የማሳወቂያ ደብዳቤውን ከላይ በተጠቀሰው ቀን የላክን ሲሆን ውጤቱ ግን አሁንም በፖስታ ቤት በኩል የተላከውን ደብዳቤ በእንቢተኝነት አለመቀበል ሆኗል፡፡ ይህን ጉዳይ አስመልክቶ በዛሬው ዕለት የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች በአስተዳደሩ ፅ/ቤት በመገኘት ከተለያዩ ኃላፊዎች ጋር ለመነጋገር እረጅም ሰዓት የወሰደ ከቢሮ ቢሮ መንከራተት የተሞላበት ደጅ ጥናት ካደረጉ በኋላ በመጨረሻም በከንጺባ ጽ/ቤት የካቢኔ ጉዳዮች ም/ኃላፊ ጋር ለመነጋገር ተችሏል፡፡” በማለት ሰልፉን ለማራዘም የወሰነበትን ምክንያት ያብራርል።
“በዚህም ውይይት የጳጉሜ አምስቱ ቀናት በከተማው አስተዳደር ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ለጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች የገበያ እድል ለመፍጠርና እራሳቸውን እንዲያስተዋውቁ በየዓመቱ አስቀድሞ በከተማው ማዕዘናት ያሉ ቦታዎች ለዚህ አገልግሎት ስለሚያዙ በነዚህ ቀናት የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄዎችን ለማስተናገድ የማይችሉ መሆኑን አበክረው ገልጸውልናል፡፡ ፓርቲው በከንቲባ ጽ/ቤቱ የቀረበውን ምክንያት ከመረመረ በኋላ የበዓሉ ዋዜማና የዘመን መለወጫ በዓል ካካፋ በኋላ ባሉት ቀናት ሰልፉን ለማድረግ በመወሰን ለጳጉሜ 2 ቀን 2005 ዓም ጠርቶት የነበረውን የተቃውሞ ሰልፍ ወደ መስከረም 12 ቀን 2006 ዓ.ም እንዲተላለፍ ወስኗል፡፡ የዚህን ሰልፍ እውቅና ጥያቄ ወዲያውኑ ለሚመለከተው ክፍል በማቅረብ የሰልፉ ማሳወቂያ ደብዳቤ ቀሪ ላይ በማስፈረም ገቢ አድርጓል፡፡” ያለው ሰማያዊ ፓርቲ “በመሆኑም ከለይ በተጠቀሰው ምክንያት ሠልፉ ወደ መስከረም 12 ቀን 2006ዓ.ም መተላለፉን እየገለጽን ከዚህ በፊት የጠራናቸው የተቃውሞ ሰልፎች የተሳኩ እንዲሆኑ የመገናኛ ብዙኃን፣ የሲቪክ ማሕበራትና በአጠቃላይ ኢትዮጵያውያን ላደረጋችሁት ድጋፍ ፓርቲያችን ምስጋናውን እያቀረበ፤ አሁንም ቀጣዩ ሠልፍ በታሰበለት ዓላማ መሠረት የተሳካ እንዲሆን የተለመደ ድጋፋችሁን እንድታደርጉ ፓርቲያችን ጥሪውን ያቀርባል፡፡” ብሏል።

↧

‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ የሚያስተኛ አይደለም›› – (አቶ ስብሓት ነጋ)

$
0
0

(ኢትዮ-ምኅዳር ቅጽ 01 ቁጥር 34፤ ረቡዕ ነሐሴ ፳፱ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም.)

የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋራ በመተባበር በአዲስ አበባ በአፍሪካ ኅብረት አዳራሽ ከነሐሴ ፳፩ – ፳፪ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. ‹‹የሃይማኖቶች በሰላም አብሮ የመኖር እሴት በማጎልበትና ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌዎችን በማክበር የሀገራችንን የሕዳሴ ጉዞ ለማሳካት እንረባረባለን›› በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ጉባኤ ላይ ‹አቦይ› ስብሐት ነጋ በመገኘት አነጋጋሪ ሐሳቦችን ሰንዝረዋል፡፡ አንጋፋው የህወሓት/ኢሕአዴግ መሥራችና የጀርባ ሰው የሚገልጹት ሐሳብ የመንግሥትን ቀጣይ ርምጃ ያመላክታል በሚል በአጭሩ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡
sebehat nega  mehedar
አክራሪነት ይዘቱ ሃይማኖታዊ እንዳልኾነ ሕዝቡም የተገነዘበው ጉዳይ መኾኑ ተደጋግሞ ተገልጧል፡፡ ሃይማኖትን የፖሊቲካ መድረክ የሚያደርጉት የሽብርተኝነት ተግባር ለመፈጸም መኾኑ ግልጽ የኾነልን ይመስለኛል፡፡

አክራሪነትና ጽንፈኝነት በሃይማኖት ውስጥ ማስገባት የመጀመሪያው አደጋ ሲኾን በዚህ ኹኔታ ሃይማኖቱም ሃይማኖት አይኾንም፡፡ አማኞች፣ አክራሪነትና ጽንፈኝነት በየሃይማኖታቸው ውስጥ ሲታይ ሃይማኖታቸው አደጋ ላይ እንደወደቀ መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡

አቶ ካሳ ተክለ ብርሃን (የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ) እንዳለውም፣ በጣም አስደናቂ የኾነውን የኢትዮጵያ ዕድገት ማደናቀፍ ከማንኛውም ወንጀል በላይ በሕዝብ ላይ ከባድ ወንጀል መፈጸም ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለብዙ ዓመታት ሲሠቃይ የነበረ በመኾኑ አሁንም ሕዝቡን ለሥቃይ መዳረግ ተወዳዳሪ የሌለው ወንጀል ነው፡፡

በማንኛውም ሃይማኖታዊ አክራሪነት እና ጽንፈኝነት፣ በምንም ዐይነት ኹኔታ አንድም ሰው ለአንድ ደቂቃ እንኳ ተዘናግቶ መተኛት የሌለበት ሲኾን በተለይ ይህን ነገር በጥብቅ በሁሉም መንገድ መታገል አለብን፡፡

አሁን በኢትዮጵያ ያለውን ዕድገት የሚቀናቀነው የውጭ ተቀናቃኝ ነው፡፡ የእነዚህን ተቀናቃኞች ዓላማ በመያዝ በአክራሪነትና በጽንፈኝነት መልክ ታላቅ ክሕደት መፈጸም ከባድ አገራዊ ክሕደት ነው፡፡ የውጭ ጠላት ቀላል ስላልኾነ አንድም ሰው ሳይቀር በጣም ተጠናክረን መመከት ይገባል፡፡ ሕገ መንግሥቱን መሠረት ያደረገ የፖሊቲካ ልዩነት ሊኖር ይችላል፤ ሕገ መንግሥቱን የመጣስ ዝንባሌ ግን እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ መንግሥቱ ብዙ ዋጋ ተከፍሎበታል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያጸደቀው የራሱ ሕገ መንግሥት ስለኾነ ሕዝብ በመራራ ትግል ያጸደቀውን ሕገ መንግሥት መጣስ የወንጀሎች ሁሉ ወንጀል ነው፡፡

በዚህ ስብሰባ ከፍተኛ ግንዛቤ መያዙ በጣም የሚያስደስት ነው፤ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ታላቅ ተስፋ ነው፡፡ ለውጭ ጠላት ደግሞ ሲጠብቀው የነበረ ብጥብጥ መቅረቱ ሕዝብን የሚያስደስት፣ ጠላትን ደግሞ የሚያሳፍር ነው፡፡

ሌላው ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተነሣ ነበር፡፡ አንድ አባታችን ካነሧቸው ብዙ ነገሮች አንዱ፣ ‹‹መንግሥት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እጁን ያስገባል›› የሚል ነው፡፡ መንግሥት በሃይማኖት ውስጥ በእስልምናም ይኹን በኦርቶዶክስ እጁን አያስገባም፡፡ በዚህ ጉዳይ የመጀመሪያ ተጠያቂው እምነቱ ነው፡፡ ሕገ መንግሥት የሰጠው መብት ሲጣስ፣ መንግሥት እጁን ሲያስገባ ለምን ዝም አለ? ለሕገ መንግሥታዊ መብቱ ለምን አልታገለም? ሁለተኛው ተጠያቂ ደግሞ መንግሥት ይኾናል፡፡

ስለዚህ በሩን ከፍቶ ሲያንቀላፋ መንግሥት እጁን ካስገባበት እምነቱ ይጠየቃል፡፡ ይኹን እንጂ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መንግሥት እጁን እንዳላስገባ መቶ በመቶ አምናለኹ፡፡ አንዳንድ የመንግሥት ሰዎች ግን እጃቸውን አስገብተው ሊኾን ይችላል፡፡ ስለዚህ እነዚህን መመከት ነበረበት፡፡ በመጀመሪያ ተጠያቂው ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ራሱ ሲኾን እጃቸውን ያስገቡ ሰዎች ደግሞ በሁለተኛ ደረጃ ተጠያቂ ይኾናሉ፡፡

ሁለተኛ፣ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በአንድ ወጣት*የተነሣ ሐሳብ አለ፡፡ አክራሪነት አደጋ ነው ብሏል፡፡ በኋላ በእስልምና ሃይማኖት አካባቢ በአንዳንድ ሰዎች የሚታየው አክራሪነት አደጋ ነው፤ ዋናው ግን በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የተቀበረው ፈንጅ ነው ትልቁ የአክራሪነት አደጋ ብሏል፡፡ አክራሪነት ማለት እምነቱን ለፖሊቲካ ጥቅም ማዋል፣ እምነቱን ለፖሊቲካ ጥቅም ክፍት ማድረግ ማለት ነው፡፡

አንዳንድ ማኅበራት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን የፖሊቲካ መድረክ እያደረጓት ነው፤ ማኅበሩ** እንኳ ባይኾን አንዳንድ ሰዎች ብሎ ጠቅሷል፡፡ ይህን ተጠንቅቆ ያቀረበው ይመስለኛል፡፡ ማኅበሩ ነው አክራሪ ወይስ በማኅበሩ ያሉ አንዳንድ ሰዎች ናቸው? መጣራት ያለበት ጉዳይ ነው፡፡

በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ማኅበር ያሉ አንዳንድ ሰዎች ማኅበሩ ጤናው የተበከለ እንዳይኾን ማጣራት፣ ተጠንቅቆ መያዙ፣ እንደተባለው ፈንጅ ከኾነ አስቸጋሪ ነው፡፡ ወጣቱ* እና ዶክተር ሽፈራው ተክለ ማርያም (የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር) ሁለቱም ከባድ የጥንቃቄ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

እንደተባለው፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በእውነት የፖሊቲካ መድረክ እየኾነች ከኾነ፣ በዚህ አገር የትኛው አክራሪነት ነው ከተባለ፣ ትልቁ አደጋ ያለው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ነው የተባለው ትክክል ነው ወይስ ትክክል አይደለም የሚለው መጣራት የሚኖርበት ቢኾንም በሁለቱ ሰዎች የተጠቆመው ግን የሚያስተኛ አይደለም፡፡ ከእምነቱ ቦታ የኾንም መተኛት የለብንም፤ የሌሎች እምነት አማኞችም መተኛት የለባቸውም፡፡

↧

ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም በስደተኛው ሲኖዶስና በማህበረ ቅዱሳን ያሉ ምእመናንን የግንቦት 7 ከበሮ መቺ አሏቸው

$
0
0

የፌደራል ጉዳዮች ሚ/ር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም ከሰሞኑ መንግስት በአዲስ አበባ በጠራው ጽንፈኝነትን እና አክራሪነትን የሚኮንን ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር በስደተኛው ሲኖዶስና በማህበረ ቅዱሳን ውስጥ መሽገዋል ያሏቸውን ምእመናን የግንቦት 7 ከበሮ መቺ ሲሉ መናገራቸውን ሐራ ተዋሕዶ ዘገበ። ከዚህ ቀደም በሕይወት የሌሎት ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ ማህበረ ቅዱሳንን አክራሪ ሲሉ በፓርላማ መናገራቸውን ያስታወሱ ምእመናን የሚ/ሩ ንግግር እንዳስቆጣቸው ለመረዳት ተችሏል። የሐራ ተዋሕዶ ዘገባ እንደወረደ ይኸው፦

‹‹በስደተኛው ሲኖዶስ የተሸፈኑና በማኅበረ ቅዱሳን የመሸጉ የትምክህት ኀይሎች የግንቦት ሰባትን ከበሮ ሲመቱ ከርመዋል››

የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ባዘጋጁትና ከነሐሴ ፳፩ – ፳፫ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም በተካሄደው ‹‹አገር አቀፍ የሰላም እሴት ማጎልበቻ ጉባኤ›› ውይይት ከተካሄደባቸው ጽሑፎች መካከል የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም ‹‹የአክራሪነት/ጽንፈኝነት ዝንባሌዎችና መፍትሔዎቻቸው›› በሚል ርእስ ያቀረቡት ጽሑፍ ይገኝበታል፡፡

dr shiferaw tekelamariam

በሰባት ንኡሳን አርእስት ተከፋፍሎ በስፋት የቀረበው ጽሑፋቸው÷ አክራሪነትና ጽንፈኝነት ከሕገ መንግሥት አንጻር እንዴት እንደሚታይ፣ በአገራችን ይታያሉ ያሏቸውን የአክራሪነትና ጽንፈኝነት ዝንባሌዎች፣ አክራሪነትን/ጽንፈኝነትን የማስፋፊያ ስልቶችን፣ የአክራሪ/ጽንፈኛ ኃይሎች መነሻና መድረሻ ምስጢር፣ ሃይማኖትን ሽፋን ስላደረጉ የአክራሪነት አደጋዎች እና አክራሪነትን/ጽንፈኝነትን በአስተማማኝ ደረጃ ለማሸነፍ መሠራት ይገባቸዋል ያሏቸው ስድስት የመፍትሔ ሐሳቦች የተካተቱበት ነው፡፡

በሚኒስትሩ ጽሑፍ አክራሪነት/ጽንፈኝነት የሚለው ቃል የተበየነው በሦስት መንገዶች ነው፡፡ ይኸውም አክራሪነት/ጽንፈኝነት÷ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፳፯ ንኡስ አንቀጽ ፫ ዜጎች የፈለጉትን እምነት የመከተል መብት እንዳላቸው የተደነገገውን በመተላለፍ የሃይማኖትና እምነት ነጻነትን በተግባር ለመናድ መንቀሳቀስ ነው፡፡ የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፳፭ ስለ እኩልነት መብት በሚደነግጋቸው ንኡሳን አንቀጾች በሃይማኖቶች መካከል የማበላለጥ ጉዳይ እንደማይኖር የተቀመጠውን ድንጋጌ በመጣስ የሃይማኖት እኩልነትን በተግባር ለመናድ መንቀሳቀስ ነው፤ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፲፩ ስለ መንግሥትና ሃይማኖት መለያየት በግልጽ የተቀመጠውን ድንጋጌ በመፃረር መንግሥታዊ ሃይማኖት ወይም ሃይማኖታዊ መንግሥት ለመመሥረት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ነው፡፡

አክራሪው/ጽንፈኛው ኃይል ደረጃው ይለያይ እንጂ በሁሉም ሃይማኖቶች ሽፋን እንደሚንቀሳቀስ የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ዓለም አቀፋዊና ከባቢያዊ ገጽታም ያለውና የሚመጋገብ እንደኾነ ያስረዳሉ፡፡ ስለዚህ እኔን የሚመለከተኝ አይደለም የሚል ሃይማኖትና አገር ይኖራል ተብሎ እንደማይታሰብ፣ እንደየአገሩ የሕዝቦች በሰላም አብሮ የመኖር ታሪክ፣ ከድህነትና ኋላቀርነት ተጋላጭነት የመላቀቅ፣ የሕገ መንግሥታዊ ሥርዐት የብዝሃነት አያያዝ ጥበቃ ዋስትና ሊለያይ እንደሚችል ይናገራሉ፡፡

በአገራችን በሁሉም ሃይማኖቶች (በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ሽፋን፣ በእስልምና ሃይማኖት ሽፋንና በፕሮቴስታንት ሃይማኖት ሽፋን) የአክራሪነትና ጽንፈኝነት አስተሳሰብና ተግባር አራማጆች ከሃይማኖቱ መሪዎች ያልተላኩና መነሻቸውም መድረሻቸውም ሃይማኖታዊ ሳይኾን ፖሊቲካዊ መኾኑን ይጠቁማሉ፡፡

ከዚህ በታች ሚኒስትሩ ‹‹በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ሽፋን›› ይታያል ለሚሉት ‹‹የአክራሪነት እና ጽንፈኝነት አስተሳሰብና ተግባር›› በማብራሪያነት የሰጡት ገለጻ ለሐራውያን ቀጥተኛ መረጃና ማገናዘቢያ ይኾን ዘንድ በጽሑፋቸው በሰፈረበት ይዘቱ ቀርቧል፡፡

* * *

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በንጉሡ ዘመን የመንግሥት ሃይማኖት እንደኾነች በ1948 ዓ.ም. ሕገ መንግሥት የተደነገገና እስከ ንጉሡ ሥርዐት መውደቅ ድረስ የቀጠለ እንደኾነ ይታወቃል፡፡ በዚያን ዘመን ንጉሡና የገዥ መደቡ አካላት ለሥልጣን ማራዘሚያ፣ የጥቅም ማካበቻና የሌሎች እምነት ተከታዮችን በማሸማቀቅ አንድ አገርና አንድ ሃይማኖት ፍልስፍና ለማራመድ ተጠቅመዋል፡፡

በሌላ በኩል ግን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንግሥት ሃይማኖት ገጽታ የተላበሰች ብትኾንም የውስጥ ነጻነት አልነበራትም፡፡ የጳጳሳትና የዲያቆናት ሹመት ሳይቀር በመንግሥት የሚወሰንና የሚጸድቅ ስለነበር መንፈሳዊም ይኹን አስተዳደራዊ ነጻነት ያልነበራት ነበረች፡፡ በሌላ በኩል የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ ከገዥዎች አስተሳሰብ በተለየ ኹኔታ ከሌሎች ሃይማኖት ተከታዮች ጋራ አብሮ በሰላም በመኖር የሺሕ ዓመታት ታሪክ የነበረው እንደኾነ ደጋግመን አውስተናል፡፡

ይህ እንደተጠበቀ ኾኖ በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት የተረጋገጠው የሃይማኖት/እምነት ነጻነት፣ የሃይማኖቶች እኩልነት እና መንግሥትና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው የሚለው መርሕ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ክብርና ሞገስ፣ ታሪክና ጥቅም የነፈገ አድርገው የሚያስተጋቡ ግለሰቦችና ቡድኖች አሉ፡፡ እነዚህ ግለሰቦችና ቡድኖች የሃይማኖት/እምነት ነጻነትን፣ የሃይማኖት እኩልነትን፣ መንግሥታዊ ሃይማኖትም ይኹን ሃይማኖታዊ መንግሥት እንደማይኖር የተቀመጡ ድንጋጌዎችን ይጥሳሉ፡፡

ከሃይማኖት/እምነት ነጻነት አኳያ ሲታይ የሌላውን እምነት ትክክል ነው ብሎ ለመውሰድ ማንም እንደማይገደድ ቢታወቅም የሌላውን ሃይማኖት የተለያዩ ስያሜዎችን እየሰጡ የማብጠልጠልና የማሳነስ አመለካከትና ተግባራዊ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ግለሰቦችና ቡድኖች ይታያሉ፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ከሌሎች ሃይማኖት ጋራ እኩል ተደርጎ ሊወሰድ አይገባም፤ ይኽም ክብሯንና ታሪኳን የሚጎዳ ነው በሚል ይንቀሳቀሳሉ፡፡ እንደማሳያም የአማኝ ቁጥራችን ብዙ ነው፤ ታሪካችን ረዥም ነው በሚል ለመከራከር ይሞክራሉ፡፡

ሃይማኖቶች እኩል ናቸው በሚል የተቀመጠው ድንጋጌ የአማኝ ቁጥርንና የሃይማኖቶችን ታሪክ የሚደፈጥጥ ሳይኾን የአገራችን ሕዝቦች እንደ ዜጋ በነጻ ፍላጎታቸውና ምርጫቸው የያዙት አመለካከት – ሃይማኖትና እምነት ከሌላኛው እንደማይበልጥና እንደማያንስ ብሎም ሁሉም ዜጎች የዴሞክራሲያዊ መብት ተጠቃሚ መኾናቸውን ለማረጋገጥ ነው፡፡ ይህን ሕገ መንግሥታዊ መርሕ ዐውቀው በመጣስ በዙሪያው የትምክህት ኀይሎች የሚሰበሰቡበት ገጽታም የሚታይበት ኹኔታ አለ፡፡

በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ሽፋን ከሚካሄዱት ቅስቀሳዎች ‹‹የበላይነትን አጥተናል፤ ይህንኑ መመለስ ይገባናል›› የሚል ሕገ መንግሥታችን የሻረውን አስተሳሰብ የሚደግፍ ነው፡፡ በዚህ ረገድ ‹‹ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ነች››፤ ‹‹አንድ አገር አንድ ሃይማኖት›› ወዘተ. . . ጉዳዮችን በማቅረብ በአንድ በኩል የአገራችንን የሃይማኖት ብዝሃነት የሚፃረር በሌላ በኩል ደግሞ አገራችን የሃይማኖቶች ብዝሃነት ነባራዊ መገለጫዋ መኾኗን የሚቃወም አካሄድ ነው፡፡

በሃይማኖት ሽፋን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት መንግሥታዊ ሃይማኖት መኾን ይገባዋል በሚል አቋራጭ የፖሊቲካ መሣርያ ለማድረግም የሚንቀሳቀሱ አካላት ይታያሉ፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖትን ሽፋን ያደረገ የአክራሪነትና ጽንፈኝነት እንቅስቃሴ በዋናነት የሚታየው በተለያዩ የማኅበራት አደረጃጀት ውስጥ ራሳቸውን ደብቀው በሚሠሩ ግለሰቦችና ቡድኖች ነው፡፡ በእነዚህ ማኅበራት ውስጥ የመሸጉ አክራሪ ግለሰቦችና ቡድኖች በሚያሰራጭዋቸው የተለያዩ የኅትመት፣ የኤሌክትሮኒክስና የድረ ገጽ ውጤቶች በተከታታይ ሃይማኖትን ከሃይማኖት፣ ሕዝብን ከሕዝብ፣ ሕዝብንና መንግሥትን የሚያጋጩ ዘገባዎችን በማስተጋባት የኢፌዴሪ መንግሥት የኦርቶዶክስ ክርስትናን ያሳነሰና ተገቢውን ክብርና ጥቅም የነፈጋት አድርገው ለምእመናን ያቀርባሉ፡፡

መንግሥት የሚያካሂዳቸው የልማት ሥራዎች መንግሥት የሚያሳያቸውን የገለልተኝነት ሚና. . .ወዘተ መንግሥት በሃይማኖታችን ጣልቃ ገብቷል በሚል ገሃድ ፍላጎትና ድብቅ አሠራር ካላቸው የውጭ ቡድኖች ጋራ በማበር ሰላምን አደጋ ውስጥ የማስገባትና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዐቱን በሃይማኖት ሽፋን ለመናድ ይንቀሳቀሳሉ፡፡ በቅርቡ በነበረው የፓትርያርክ ምርጫና በዋልድባ ገዳም ዙሪያ የተፈጠረው ዝንባሌ የነዚህ ፍላጎቶች ጉልሕ ማሳያ ነው፡፡

* * *

የአክራሪው/ጽንፈኛው ኃይል የማስፋፋት ስልቶች

የሃይማኖት ተቋማቱን የአመራር ዕርከኖች መቆጣጠር
አክራሪነትና ጽንፈኝነትን ለማስፋፋት ከሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች አንዱ በሃይማኖት ተቋማትም ይኹን በመንግሥት መዋቅር ሰርጎ በመግባትና ደጋፊ በመምሰል በድብቅ መሠረቱንና መረቡን ማስፋፋት ነው፡፡ ይህን መሠረት የማስፋፋትና መረብ የመዘርጋት ተግባር ውጤታማ በኾነና በአጭር ጊዜ ማከናወን የሚቻለው የመንግሥትንም ይኹን የሃይማኖቶች አደረጃጀቶችን በበቂ ደረጃ መቆጣጠር ከተቻለ ነው፡፡

በእስልምናም ይኹን በክርስትና ሃይማኖቶች ሽፋን የሚካሄደው የአክራሪነት/ጽንፈኝነት እንቅስቃሴ በዋናነት እያነጣጠረ የሚገኘው የተቋማቱን የበላይ አመራር ዕርከኖች መቆጣጠር ነው፡፡ ለዚህ ጥሩ ማሳያ የሚኾነው በቅርቡ በተካሄደው የእስልምና ምክር ቤቶች ምርጫ ወቅት ለአክራሪው ኀይል ለራሱ በሚበጅ መንገድ ካልኾነ ምርጫው ትክክለኛ አይደለም በሚል የዑላማ ምክር ቤት ፋትዋ ጭምር በመቃወም ያደረገው ሙከራ ነው፡፡

ምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራዊ ኾኖ ከ8 ሚልዮን በላይ ሕዝበ ሙስሊም ወጥቶ የፈለገውን አመራር ከመረጠ በኋላ እስከ ፍርድ ቤት የሚሄድ ክሥ የመመሥረት፣ ሕዝበ ሙስሊሙ በራሱ ነጻ ፍላጎት መርጦ ያቋቋመውን መሪ ተቋም ማብጠልጠል የሚታይ የዘወትር ክሥተት አድርገዋል፡፡ አክራሪው ኀይል ‹‹የራሴ ብቻ ካልኾነ›› የሚለውን አመለካከት በግልጽ ያመላከተ ሂደት ነበር ለማለት ይቻላል፡፡ ከምርጫ ሂደቱም በኋላ ከቀበሌ ጀምሮ የተመረጡ አመራሮችን በየዕርከኑ የራሱ ለማድረግ የሌት ተቀን ሥራውን በተለያዩ መደለያዎችና ማስፈራሪያዎች እየሠራ መኾኑ በግልጽ የሚታወቅ ነው፡፡

በኦርቶዶክስ ሃይማኖት የ፮ኛው ፓትርያርክ ምርጫ ሲካሄድም በተመሳሳይ እንቅስቃሴዎች ከአገር ውስጥና ከአገር ውጭ ተስተውለው እንደነበር ይታወቃል፡፡ የሚሾመው ፓትርያርክ ጉዳይ የራሱ የአማኙ መኾኑ እየታወቀና ራሱ ሲኖዶሱ አስመራጭ አካል ሠይሞ ከየሀገረ ስብከቱ በውክልና ከ800 በላይ መራጮች እንዲሳተፉ አድርጎ ያካሄደውን ሂደት በማብጠልጠል ‹‹መንግሥት ጣልቃ ገብቷል›› ስለዚህም የፍላጎታችንን መሾም አልቻልንም በሚል ለማስተጋባት ተሞክሯል፡፡

አክራሪው/ጽንፈኛው ኃይል የሃይማኖት ተቋማቱን የአመራር ዕርከኖች መቆጣጠር የሚፈልግበት ምክንያት ሕዝባችንን በተደራጀ መንገድ በበቂ ለማደናገርና ከዚያም ከሕገ መንግሥታዊ ሥርዐታችንና ከሕገ መንግሥት ጋራ ፊት ለፊት ለማፋጠጥ ነው፡፡ ‹‹በሃይማኖትኽ መንግሥት ጣልቃ ገብቷል›› የሚለውን መፈክራቸውን የሁሉም ሕዝብ መፈክር በማድረግ በሕገ መንግሥታችንና በዴሞክራዊ ሥርዐታችን ላይ በተሳሳተ መንገድ ሕዝብን ለማዝመት ነው፡፡ ተቋማዊ ቁመናና ትስስር ተጠቅመው ገንዘቡንም ሕዝቡንም ለአክራሪነት ግባቸው ለማሰለፍ ስለሚመቻቸው ነው፡፡ የሃይማኖቱ ተቆርቋሪ መስለው አክራሪነቱን ለማስፋፋት ምርጥ ዕድል ስለሚኾን ነው፡፡

በተቃራኒው ግን ሕዝበ ሙስሊሙም ይኹን ሕዝበ ክርስቲያኑ ለአፍራሽ ፍላጎት ተገዥ እንዳልኾነ፣ ለሰላምና ልማት የቆመ ሕዝብ መኾኑን ደጋግሞ በተግባር አሳይቷቸዋል፡፡ በእነርሱ እኩይ ዓላማና ፍላጎት እንደማይገዛ፣ ሕገ መንግሥታችንና ዴሞክራሲያዊ ሥርዐትን በኃይል ለመናድ ከሚንቀሳቀሰው ኃይል ጋራ እንደማይተባበር ፊት ለፊት በሰፋፊ ሰላማዊ ሰልፎች ጭምር ነግሯቸዋል፡፡

ስለዚህ አክራሪው ኃይል ቢቻል እነዚህን የአመራር ዕርከኖች ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ካልተቻለም ደረጃ በደረጃ እየሰረገና አቋሞቻቸውን እየሸረሸረ የራሱ ተቋም ለማድረግ ሰፊ ርብርብ ያደርጋል፡፡ ንጹሓን አማኞች ሁሌም ቢኾን ይህን አደጋ በንቃት በመጠበቅ ከመንግሥት ጋራ ተባብሮ መሥራት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ጉዳዩ ፀረ ሕገ መንግሥት አቋም እንደመኾኑ የሁሉም የሰላምና ልማት ኃይሎች ርብርብ የሚፈልግ ነው፡

↧

የሥላሴዎች እርግማን (አምስት) የመንፈስ ደሀነት –ከፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም

$
0
0

ከፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም

ነሐሴ 2005

ዱሮ በአጼ ዘመን አንድ ወዳጅ መጣና አንድ ቤት ላሳይህ እንዳያመልጥህ ብሎ ይዞኝ ሄደ፤ ቤቱ ከጀርመን ኤምባሲ ፊት ለፊት ያለ ሰፊ ግቢ ያለው ቪላ ነበር፤ ባለቤቲቱ አንዲት ቆንጆ ወጣት የልጆች እናት ነበረች፤ ባልዋ በአደጋ ሞቶባት የባንኩ ዕዳ በየወሩ እያደገ ልትከፍለው የማትችለው ስለሆነባት በጨረታ ከመሸጡ በፊት ሌላ ዘዴ ሰዎች መክረዋት ነበር፤ እኔ የቀረብሁት ለዚህ ነበር፤ እስዋ ለሠራተኞች መኖሪያ በተሠራው ውስጥ ከነልጆችዋ ለተወሰነ ጊዜ እንድትኖርና አኔ የባንኩን ዕዳ ወደኔ አዛውሬ ለአስዋ ደግሞ ትንሽ ገንዘብ እንድሰጣት ነበር፤ በእኔ በኩል ዕዳውን ማዛወሩም ሆነ ለሴቲቱ የሚከፈለውን ለመክፈል በጣም ቀላል ነበር፤ የቸገረኝ ሌላ ነገር ነበር፤ እኔ ከነልጆቼ እዚያ ቤት ውስጥ ገብቼ ስኖር ባለቤቲቱ ከነልጆችዋ ለሠራተኞች በሠራችው ውስጥ ስትኖር በአየኋት ቁጥር የሚሰማኝ ኩራት ይሆናል ወይስ እፍረት? በዚች በወጣት እናት ችግር እኔ ሀብት አልሸምትም ብዬ ተውሁት፤ ጓደኞቼ የሚሉትን ሁሉ አሉኝ፤ ሌላ ሰው ይገዛዋል አንዳሉት ከጥቂት ቀናት በኋላ አንድ ፊታውራሪ ገዙት ሲባል ሰማሁ፤ እኔ ከኅሊናዬ ጋር እንበለ ቤት አለሁ፤ ባለቤቲቱ እንዴት እንደሆነች አላውቅም፤ የገዙትም ፊታውራሪ ሀብታቸው ምን እንዳተረፈላቸው አላውቅም።
Pro Mesfin
ተናግሬው የማላውቀውን ታሪክ ያወራሁት ለመመጻደቅ አይደለም፤ የሚመስላችሁም ካላችሁ ደስ ይበላችሁ፤ ምክንያቴ ‹‹የሥላሴዎች እርግማን — አዳክሞ ማደህየት›› በሚል ርእስ የጀመርኋቸው ጽሑፎች ናቸው፤ በቅርቡ በኢትዮ ምኅዳር (ሐምሌ 17/2005) ጋዜጣ ላይ ‹‹የቤተ መንግሥት ደጃፍ ግፎች›› በሚል ርእስ ተጽፎ ያነበብሁት ምን ዓይነት የመንፈስ አዘቅት ውስጥ እንደወደቅን የሚያሰየኝ በመሆኑ ነው፤ በአራት ኪሎ አምስት ትውልድ ያህል ያሳደገ የሕዝብ ሰፈር ሲፈርስ እዚያው ያደጉ የሰፈሩ ጎረምሶች ጥቅም ለማግኘት የበሉበትንና የጠጡበትን ቤት ለማፍረስ ሲሻሙ የሰው ልጅ ውሻ ያልደረሰበት ደረጃ መድረሱን ገመትሁ፤ ይህንን በደሀነት ግፊት ልናማካኘው እንችላለን፤ ደሀዎች፣ ለጫትና ለኮካ ኮላ ገንዘብ የሌላቸው የእናቶቻቸውን ቤቶች በማፍረስ ለሱሳቸው የሚገብሩ ናቸው፤ የደሀዎቹ ቤቶቹ በፈረሱበት መሬት ላይ ታላላቅ ሕንጻ የሚሠሩት ሀብታሞችስ በመንፈስ ደሀነት ከደሀዎቹ በምን ይሻላሉ? ሁለቱም እኩል የመንፈስ ደሀዎች ናቸው፤ የወገኑን ግፍ እንዳያይ ዓይኑን የጋረደውን የፎቅ ባለቤትነት ሱስ ያሳደረበትና ያደገበትንና የበላበትን ቤት እንዳያይ ዓይኑን የጋረደው የጫትና የኮካ ኮላ ሱስ ያለበት አንድ ናቸው፤ ከራሳቸው ውጭ ሰው የለም፤ በቅርቡ እኔ በምኖርበት አካባቢም የማፍረሱ ትእዛዝ በየቤቱ ሲደርሰን አንደሰማሁት የሰፈሩ ጎረምሳዎች ለአፍራሽነት እየተመዘገቡ ነበር አሉ፤ ከዚህ የባሰ የመንፈስ ደሀነት አዘቅት ምን አለ?

እናቶቻቸውንና አባቶቻቸውን፣ ዘመድና ወዳጆቻቸውን፣ ራሳቸውንም ጭምር ለጊዜያዊ ጥቅም ለውጠው፣ ኅሊናቸውን አፍነው፣ አእምሮአቸውን አደንዘው፣ መንፈሳቸውን አዋርደው፣ ሰውነታቸውን አርክሰው ነገ በእነሱና በሌሎች ላይ የሚደርሰውን ሳያውቁ በደመ-ነፍስ ለሆዳቸው መሣሪያ እየሆኑ ጥቃትንና ግፍን የሚያራምዱ ወጣቶች ተንጋሎ የተፋ ለራሱ ከፋ እንደሚባለው ይሆናሉ፤ እስከመቼ ተንጋለው ይቆያሉ? እስከመቼ በራሳቸው ላይ ይተፋሉ? በትናንሽ ጊዜያዊ ጥቅም ወይም ምቾት እየተደለሉ የራስ ሥራ በራስ ላይ ለዘለቄታው የሚያመጣውን ጉዳት ወይም ጥፋት አለመገንዘብ ትልቅ የመንፈስ ደሀነት ነው፤ እንዲያውም የደሀነት ዋናው መሠረት የመንፈስ ደሀነት ነው ማለት ይቻላል፤ አብዛኛውን ጊዜ የውጭ ጠላቶች መሣሪያ አድርገው የሚጠቀሙበት የመንፈስ ደሀነትን ነው፤ የመንፈስ ደሀነት ለማይረካ የምኞት ባርነት ይዳርጋል፤ የመጨረሻ ውጤቱም የሰውን ልጅ ወደርካሽ ዕቃነት ለውጦ በገንዘብ የሚሸጥና የሚለወጥ ማድረግ ነው፤ ነቢዩ ኢሳይያስ የሚከተለውን ይላል፡—

የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና አልቅሱ፤ ሁሉን ከሚችል አምላክ ዘንድ እንደሚመጣ ጥፋት ይመጣል፤ ስለዚህ እጅ ሁሉ ትዝላለች፤ የሰውም ሁሉ ልብ ይቀልጣል፤ ይደነግጣሉ፤ ምጥና ሕማም ይይዛቸዋል፤ እንደምትወልድ ሴትም ያምጣሉ፤ … እነሆ ምድሪቱን ባድማ ሊያደርግ ኃጢአተኞችዋንም ከእርስዋ ዘንድ ሊያጠፋ ጨካኝ ሆኖ በመዓትና በጽኑ ቁጣ ተሞልቶ የእግዚአብሔር ቀን ይመጣል፤ የሰማይም ከዋክብትና ሠራዊቱ ብርሃናቸውን አይሰጡም፤ ጸሐይም በወጣች ጊዜ ትጨልማለች፤ ጨረቃም በብርሃኑ አያበራም፤ ዓለሙን ስለክፋታቸው፣ ክፉዎችንም ስለበደላቸው እቀጣለሁ፤ የትዕቢተኞችንም ኩራት እሽራለሁ፤ የጨካኞቹንም ኩራት አዋርዳለሁ፤ የቀሩትም ከጥሩ ወርቅ ይልቅ የከበሩ ይሆናሉ፤ ሰውም ከአፊር ወርቅ ይልቅ የከበረ ይሆናል።

አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ በችጋር እየተቆላ፣ ከመኖሪያው እየተፈናቀለ በየትም ወድቆ በሚኖርበት፣ የዕለት ጉርሱን ለማግኘት ሌት-ተቀን እየደከመ የሚያገኘውን በሰበብ አስባቡ እየበዘበዙት ኑሮው ይበልጥ እያሽቆለቆለ በሚሄድበት ዘመን የጥቂቶች ሰዎች የተንደላቀቀ ኑሮ የሚያሳፍር እንጂ የሚያኮራ፣ አንገት የሚያስደፋ እንጂ የሚጀነኑበት አይደለም፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንባውን ወደሰማይ እየረጨ የሚጸልየውን ጸሎት ነፋስ ይዞት አይሄድም፤ በአምላክ ፊት እንደጎርፍ ይወርዳል፤ አምላክም ጊዜውን ጠብቆ ይፈርዳል፤ አይቀርም፤ የሥላሴዎች እርግማን ነውና!

↧
↧

የጋራ ንቅናቄው ከሰማያዊ ፓርቲ ጎን እንደሚቆም አስታወቀ

$
0
0

ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን)
ነሐሴ 30፤ 2005ዓም
የጋራ ንቅናቄው ከሰማያዊ ፓርቲ ጎን ይቆማል!
የወጣት አመራሮቹን ሰላማዊ የትግል መስመር ይደግፋል!

“ወንድሞቻችንን እና ልጆቻችንን የገደሉትን መንግስት ቢወድቅ እንኳ አንረሳም” ኦባንግ ሜቶያለፈው እሁድ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ጠርቶ በነበረው የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ላይ በህወሃት/ኢህአዴግ የተወሰደውን ጽንፈኛ፣ አክራሪና አጸያፊ የውንብድና ተግባር የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ይኮንናል፤ ያወግዛል፡፡ ፓርቲው ሰልፉን ለማካሄድ ከሁለት ወራት በፊት ፈቃድ ተሰጥቶት የነበረ ቢሆንም ቅዳሜ ነሐሴ 25፤2013 የፌዴራል ፖሊስና የደኅንነት አባላት የፓርቲውን ጽ/ቤት ጥሰው በመግባት የፈጸሙት ተራ የውብንድና ተግባር ብቻ ሳይሆን የህወሃት/ኢህዴግን ማንነት በግልጽ ያሳየ ለመሆኑ ከማንም በላይ ተግባሩ ራሱ ምስክር ነው፡፡
በዕለቱ እንደሆነው የህወሃት/ኢህአዴግ አሸባሪ ፖሊሶች የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤትን ከመውረራቸው በፊት ኤሌክትሪክ መስመሩን ቆርጠዋል፡፡ በቀጣዩም ለእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ዝግጅት እያደረጉ የነበሩትን አመራሮችና ፈቃደኛ ሠራተኞችን ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ ከደበደቡና ካሰቃዩ በኋላ ለሰዓታት አስረዋቸዋል፡፡ ወጣቶቹ ከተፈቱ በኋላ ለእሁዱ ስብሰባ ተመልሰው ዝግጅት እንዳያደርጉ የህወሃት/ኢህአዴግ አሸባሪዎች የፓርቲዉን ጽ/ቤት እስከ እሁድ ድረስ በመቆጣጠር ኮምፒውተሮችን፣ የጽህፈት መሣሪያዎችን፣ ሠንደቅዓላማዎችን፣ መፈክሮችን፣ … በማውደም፤ የሚፈልጉት በመውሰድ ሰልፉ እንዳይካሄድ አድርገዋል፡፡ ይህንን ተግባር የሚመሰክር ከበቂ በላይ የፎቶግራፍ፣ የሰው፣ … ማስረጃ ቢኖርም ህወሃት/ኢህአዴግ ሁሉንም በመካድ ለዓለምአቀፍ ሚዲያ አንዳች ነገር እንዳልተደረገ በመናገር የተለመደውን ዓይን ያወጣ ቅጥፈት ደግሟል፡፡
ጥያቄው ግን ሰላማዊ ሰልፍ እናድርግ ያሉ ቁርጠኛ ወጣቶች ያነሱት ይህ የመብት ጥያቄ ለምን ህወሃት/ኢህአዴግን ለምን አሸበረው? ለምንስ እንዲህ ያለውን ራሱን የሚያጋልጥ ተግባር እንዲፈጽም አደረገው? መልሱ ህወሃት/ኢህአዴግ ልምድ በሌለውና በማያውቅበት የሰላማዊ ትግል ጠንክረው ስለመጡበት ብቻ ነው! ለዚህ ደግሞ ለሁለት ዓመታት ያህል በጽናት መብታቸውን ለማስከበር የሚታገሉት ሙስሊም ወገኖቻችንና ሰሞኑን በአንድነት ፓርቲ የተጀመረው ሰላማዊ እንቅስቃሴዎች ማስረጃዎች ናቸው፡፡
ህወሃት/ኢህዴግ ባስቀመጠው ትዕዛዝ መሠረት የሰማያዊ ፓርቲ ለእሁዱ ሰልፍ ከሁለት ወር በፊት ደብዳቤ አስገብቶ ፈቃድ ተሰጥቶት የነበረ ቢሆንም ባለፈው ሰሞን ህወሃት/ኢህአዴግ ባቀናበረው የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ “አሸባሪነትንና አክራሪነትን” ለማውገዝ ሕዝቡ ሰልፍ እንዲወጣ ጥሪ አድርጎ ነበር፡፡ በጥሪ ብቻ ያላበቃው ዘመቻ የከተማው ነዋሪ በግድ፣ በማስፈራራት፣ በጉቦ፣ … ሰልፍ እንዲወጣ የተቀናበረም ነበር፡፡ ይህ ሰልፍ በሚካሄድበት ቀን ታቅዶ የነበረው የሰማያዊ ፓርቲ ትዕይንተሕዝብ ካልተጨናገፈ በስተቀር ህወሃት/ኢህአዴግ በጠራው በራሱ ሰልፍ ላይ የሚደርስበት ክስረት መራራ እንደሚሆን ግልጽ ነበር፡፡
ከሰልፉ ጥሪ በፊት በተካሄደው ጉባዔ ወቅት “በኢትዮጵያ ህዳሴ የሃይማኖቶች ተስማምቶ መኖር” አስፈላጊነት የተሰበከ ሲሆን ጠ/ሚ/ር ሃይለማርያም ደሳለኝ በወቅቱ “የሃይማኖት አክራሪነትን” እንዲያጋልጡ ተሰብሳቢዎቹን በመጠየቅ መንግሥት በዚህ ዙሪያ የሚወስደውን እርምጃ አንደሚቀጥልበት አስጠንቅቀው ነበር፡፡ ቅዳሜ በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት የተፈጸመው ተግባር አሸባሪና አክራሪ ራሱ ህወሃት/ኢህአዴግ መሆኑን ያጋለጠበት ነው፡፡
የሃይማኖት ተቋማት ጉዳይ ያገባኛል በማለት ጉባዔ የሚጠራው ህወሃት/ኢህአዴግ፤ “በሃይማኖታችን ጣልቃ አትግባ፤ የራሳችንን መሪዎች እንምረጥ፣ መብታችን ይከበር” በማለት ላለፉት ሁለት ዓመታት ያህል እየጮሁ ያሉትን ሙስሊም ወገኖቻችን የመብት ጥያቄ መመለስ ያልፈለገ ወይም ያልቻለ ነው፡፡ ከዚህ ይልቅ ግን የራሱን ካድሬዎች በሃይማኖት መሪነት ሽፋን በመሾምና ሙስሊሙን ኅብረተሰብ በመከፋፈል የአፈናና የመብት ረገጣ ተግባሩን ቀጥሎበታል፡፡ ይህ የህወሃት/ኢህአዴግ አሠራር በሌሎች ሃይማኖቶችም የቀጠለ ለመሆኑ በሃይማኖት ተቋማት ስም የተጠራው ጉባዔና ሰልፍ በቂ ምስክር ነው፡፡
ህወሃት ገና ከጥንስሱ የሃይማኖት ጉዳይ የማይስበው፤ በበረሃው ቆይታ በተደጋጋሚ በአሸባሪነት ተግባር ላይ ለመሠማራቱ የተመሰከረለት መሆኑ፤ ራሱን በፈጣሪ የለሽ የሌኒኒስታዊ ፍልስፍና ያጠመቀ መሆኑ ራሱ የመሰከረውና በግልጽ የሚታወቅ ሆኖ ሳለ አሁን “በኢትዮጵያ የሃይማኖት ጉዳይ ያገባኛል፤ የሃይማኖት አክራሪነትን እታገላለሁ” ማለቱ ጅብ በማያውቁት አገር ሄዶ የአህያ ቁርበት አንጥፉልኝ ያለው ዓይነት ነው፡፡
በአመሠራረቱ የተለያዩ ኢትዮጵያውያንን የሚወክለው ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በኢትዮጵያ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ እያደረጉ ካሉት “የድምጻችን ይሰማ” ሙስሊም ወገኖች፣ የአንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምጽ፣ የሰማያዊ ፓርቲና ሌሎች ወገኖች ጋር ያለውን ኅብረት ይገልጻል፡፡ የጋራ ንቅናቄው ባለው ዓለምአቀፋዊ ዕውቅናና ግንኙነት በመጠቀምም የህወሃት/ኢህአዴግን ቋት ለሚሞሉት ለለጋሽ አገራት፣ ለሕግ ተቋማት፣ ለሰብዓዊ መብት ድርጅቶች፣ ለሚዲያ ተቋማት፣ ወዘተ በአገራችን ላይ እየተፈጸመ ያለውን የመብት ረገጣ ያሳውቃል፡፡ የህወሃት/ኢህአዴግን አገዛዝ እስካሁን የፈጸመውን የሽብር ተግባርና ወደፊት ለሚያደርሰው ማንኛውም በደል በቀጥታ ተጠያቂ እንዲሆን መረጃው በሕግ ተመዝግቦ እንዲቀመጥ ያደርጋል፡፡
በአገራችን በ1997 የተደረገውን ምርጫ ተከትሎ በሟቹ ጠ/ሚ/ር ቀጥተኛ ትዕዛዝ ህወሃት/ኢህአዴግ የፈጸመው የ193 ዜጎች ግድያ፣ የፖለቲካ መሪዎች እስር፣ አፈና፣ የመብት ረገጣ፣ … ያስከተለውን ፍርሃት ለመጀመሪያ ጊዜ በመግፈፍ የፖለቲካ ትዕይንተሕዝብ ያደረገው የሰማያዊ ፓርቲ ነው፡፡ “ድምጻችን ይሰማ” የሚያደርጉት በትክክለኛ የሰላማዊ ትግል መርህ ላይ የተመሠረተው እልህ አስጨራሽና መስዋዕትነትን የሚጠይቅ ትግል እንዳለ ሆኖ የሚሊዮኖች ድምጽ እንቅስቃሴም ከዚህ ጋር አብሮ ተጠቃሽ ነው፡፡
አርቆአሳቢና ራሳቸውን በሰላማዊ ትግል ዲሲፒሊን ያነጹ ወጣቶች ተሰባስበው በሰማያዊ ፓርቲ ሥር የሚያደርጉት እንቅስቃሴ የሰላማዊ ትግል በትክክለኛው መንገድ ከተከናወነ በኢትዮጵያ እንደሚሠራ በተግባር ያስመሰከረ ነው፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን “ሰላማዊ ትግል ከኢትዮጵያ የፖለቲካ አንጻር አይሠራም” የሚለውን ስሜታዊ አስተሳሰብ ከሥሩ የመታ ትግል በመሆኑ የጋራ ንቅናቄው ለሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶችንና አመራሮች ከፍ ያለውን አድናቆት ይሰጣል፡፡ በተለይም በሰላማዊ ትግል መስመር ስማቸው በዓለም የሚጠራው መሃትማ ጋንዲ፣ ዶ/ር ኪንግ፣ ማንዴላ፣ … በወጣትነታቸው ይህንን ዓይነቱን የትግል መስመር ከመምረጣቸው አኳያ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች የተጠና እንቅስቃሴና የዓላማ ጽናት ሌሎችም የእናንተን መስመር እንዲከተሉ የሚያደፋፍር እንጂ በምንም ዓይነት መልኩ የያዛችሁትን እርግጠኛ አቋም እንድትመረምሩ ሊያደርጋችሁ እንደማይገባ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በአጽዕኖት ያስታውቃል፡፡ ለመስከረም 12፤ 2006 ዓ.ም. የተጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ሁሉም ሰላም ወዳድ ወገኖች ድጋፋቸውን እንዲሰጡት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
ከዚህ በፊት በሊቢያ በቅርቡ በግብጽ አሁን ደግሞ በሶሪያ ሕዝብን እያስተላለቀና እጅግ ደም እያፋሰሰ ያለውን ዕልቂት ተመልክታችሁ አገራችሁን በምንም ዓይነት መልኩ ወደ ደም መፋሰስና ዕልቂት እንዳትገባ የሚደርግ ሰላማዊ የትግል መስመር መምረጣችሁ የጋራ ንቅናቄው ምስክርነት የሚሰጠው ነው፡፡ ህወሃት/ኢህአዴግ ከየትኛውም የአመጽና የሽብር ተግባር ጋር በግድ በማያያዝ ሊኮንናችሁ፣ ሊወነጅላችሁ፣ ወዘተ ቢሞክርና ወደፊትም ይህንኑ ለማድረግ ቢያስብ እስካሁን የፈጸማችሁት ሰላማዊ ሥራችሁና የትግል ስትራቴጂያችሁ በገሃድ የሚመሰክረው ከመሆኑ ባሻገር የጋራ ንቅናቄው ዓለም ሁሉ ይህንን ምስክርነት እንዲያውቅ በማስረጃነት የሚያስመዘግበው ነው፡፡
ትክክለኛውን የትግል መርሆ የተከተለ ሰላማዊ ትግል ከዚህ በፊት የሠራና አሁንም ከኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ አኳያ መተግበር እንደሚችል ጠንቅቆ ያወቀው ህወሃት/ኢህአዴግ፤ በሰላማዊ የትግል መስመር የሚነሱትን ሁሉ ገና በእንጭጩ ሲቀጭ ቆይቷል፡፡ ተስፋ በማስቆረጥ፣ በመከፋፈል፣ በማሰር፣ በማሰቃየት፣ በመግደል፣ ወዘተ የፓርቲ አመራሮችን ያስወግዳል፤ ትግሉ ወደ ተራው አባል ከመዝለቁና አባሉ በራሱ አመራርና የትግሉ ባለቤት መሆን ከመቻሉ በፊት ይበታትናል፡፡ ይህንን የሚያደርገው ከባህርይውና ከለመደው የደም ማፍሰስ አገዛዝና ትግል ውጪ ያለ አካሄድ ሥልጣኑን ስለሚያናጋውና መጨረሻውን ስለሚያቃርበው ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ የትግል መስመር ተጠናክሮ ወደ ሙሉ ህዝባዊ እንቅስቃሴና እምቢተኝነት ከተቀየረ ህወሃት/ኢህአዴግ መመከት የማይችልበት ደረጃ ስለሚደርስ ህልውናው ያከትማል፡፡ “ሥልጣን ወይም ሞት” በማለት የፖሊስና የመከላከያ ኃይሉን እስካፍንጫው በማስታጠቅ ዕድሜውን እየገፋ ያለው ህወሃት/ኢህአዴግን ወደ ሙሉ ህዝባዊነት የተቀየረ ሰላማዊ ትግልን መቆጣጠርም ሆነ ማጨናገፍ አይችልም፡፡ ለዚህ ነው ሰላማዊ ትግል በህዝቡ ዘንድ በሙላት ሳይሰርጽና መርሆዎቹ ተግባራዊ ሳይሆኑና ገና በጅምሩ ማጥፋት፣ ማውደም፣ ማሰቃየት፣ ወዘተ የሚፈልገው፡፡ በወጣቶች የተገነባው የሰማያዊ ፓርቲ ላይ እየረደሰ ያለው ሁኔታ ይህንኑ የሚያመለክት ነው፡፡
ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በኢትዮጵያ የማኅበራዊ ፍትሕ መስፈን የሚታገል እንደመሆኑ በሰላማዊ የትግል መስመር ላይ ያሉ ድርጅቶችንም ሆነ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎችን ይደግፋል፤ ያበተረታታል፡፡ በሰላማዊ የትግል መስመር የሚመጣ ለውጥ በአገራችን ያለማቋረጥ ሲፈስ የቆየውን የደም ጎርፍ እንዲቀጥል፤ ቂምና በቀል እንዲስፋፋ፤ መጪውን ትውልድ በፍርሃትና በማያቋርጥ የደም መፋሰስ አዙሪት ውስጥ እንዲገባ የሚያደርግ ሳይሆን፤ በፍትሕ ላይ የተመሠረተ ዕርቅ እንዲሰፍን፤ የአንዱን ነጻነት ብቻ የሚያስከብር ሳይሆን “ሁላችንም ነጻ ካልወጣን ማንም ብቻውን ነጻ ሊሆን አይችልም” በሚል የጠነከረ ምሶሶ ላይ የሚገነባ ነው፡፡ በአገራችን ለዓመታት የተረጨውንና እስከ ቤተአምልኮዎች የዘለቀውን የዘር ፖለቲካና የዘረኝነት አመለካከት ማምከን የምንችለው በሌላ መንገድ ሳይሆን በሰላማዊ መንገድ “ከጎሣ ይልቅ ለሰብዓዊነት ቅድሚያ” እንስጥ የሚለውን ታላቅ መርህ ከፍ ስናደርግ እንደሆነ የጋራ ንቅናቄው ያምናል፡፡ ይህንን አመለካከት ከሚጋሩ ሁሉ ጋር በጋር ይሠራል፤ ይንቀሳቀሳል፡፡
በአገራችን ላይ እስካሁን በበሽታ፣ በረሃብ፣ በድህነት፣ በእርስበርስ ጦርነት፣ … ብዙ ደም ፈስሷል፡፡ ከዚህ በኋላ የምንሄድበት መንገድ ይህንኑ እንዲቀጥል የሚያደርግ በጭራሽ ሊሆን አይገባውም፡፡ ህወሃት/ኢህአዴግም ይህንኑ ሊያስተውልና “በለመድኩት የአፈና አካሄድ እቀጥላለሁ” ከሚለው ዕብሪተኛ አስተሳሰቡ ሊመለስ ይገባዋል፡፡ በውስጡ ያሉት የትግራይ ተወላጆችም ይሁኑ ሌሎች የአገራቸው ጉዳይ የሚያሳስባቸው ኢትዮጵያውያን በግልጽ የሚወጡበትና የህወሃት/ኢህአዴግ አሠራርን በግልጽ በመተቸት ሁላችንም ወደ ዕርቅ የምንመጣበት ጊዜ አሁን ነው፡፡ ሥርዓቱ “ከእንጥሉ መበስበሱን” ሟቹ ጠ/ሚ/ር የመሰከሩለት በመሆኑ ምንም የሚደበቅ ነገር ስለሌለ ጉዳዩን ይፋ ለማውጣት የሚያስፈራ ነገር የለም፡፡ የጋራ ንቅናቄው ይህንን የጥሪ ደወል እስካሁን ሲያሰማ ቆይቷል፤ አሁንም ይህንኑ ይደግማል፡፡ ሆኖም ይህ በህወሃት/ኢህአዴግ ውስጥ ላሉትና ለመሰል ድቃይ ድርጅቶች የምንሰጠው “ከሥርዓቱ ተለዩ” የሚለው ጥሪ የሚያቆምበት ወቅት ላይ ነን፡፡ ምላሽ የመስጫው ጊዜ ነገ ወይም አንድ ቀን ሳይሆን ዛሬ፤ አሁን ነው፡፡ የአፈናና የጭቆና ሥርዓት ጸንቶ አይቆይም፡፡ እንኳን እንደ ህወሃት/ኢህአዴግ ያለው ዘረኝነትን መመሪያው፤ የአገር ውርደት ክብሩ የሆነ አገዛዝ ይቅርና በህዝባዊነታቸውና ብሔረተኝነታቸው የተመሰከረላቸው አገዛዞችም ጨቋኝ በመሆናቸው ብቻ እንደማይነሱ ሆነው ወድመዋል፤ ፈርሰዋል፡፡
ፈጣሪ ሁላችንንም የማስተዋልና ትክክለኛውን መንገድ የመምረጥ ጥበብ ይስጠን፡፡ የልቦና ዓይናችንን ከፍቶ የዘረኝነትን፣ የጥፋትን፣ የብቀላን፣ የውድመትን አስከፊነት እንድናስተውልና የሰላምንና የዕርቅን መንገድ እንድንመርጥ ይርዳን፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ የመረጣችሁትን ሰላማዊ መንገድ በምንም አትቀይሩት፤ ከእርሱ የሚበልጥም ሆነ የሚሻል መንገድ የለምና!! ሌሎች የእናንተን ዓይነት መንገድ አስቀድመው ከጀመሩ ጋር በኅብረትና በመቻቻል ሥሩ፡፡
ለውጥ በአገራችን ይመጣል! ይህ የማይቀር ሃቅ ነው! ኢትዮጵያ ነጻ ትወጣለች፤ ነጻ የምትወጣው ግን በሌላ ነጻ አውጪ ሳይሆን “ነጻ አውጪ ነኝ” የሚለውን ጭምር ነጻ በሚያወጣው እውነትና ፍትህ ነው፡፡
ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ

↧

አንድነት ፓርቲና 33ቱ ፓርቲዎች በጋራ መስከረም 5 ቀን 2006 በአ.አ ሰላማዊ ሰልፍ ጠሩ (መግለጫውን ይዘናል)

$
0
0

UDJ(ዘ-ሐበሻ) እስካሁን የተቃውሞ ሰልፍ ሳያደርግ የቆየው የ33ቱ ፓርቲዎች ትብብር ከአንድነት ፓርቲ ጋር በመሆን በ”ሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” የ3ወ ር መርሃ-ግብር መጠናቀቂያ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በጋራ እንደሚሳተፍ ታወቀ። አንድነት ፓርቲ “በአንድነትና በ33ቱ ፓርቲዎች በጋራ የተሠጠ ጋዜጣዊ መግለጫ” በሚል ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት) ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል እንቅስቃሴ የበለጠ ተጠናክሮ ህዝቡ የትግሉ መሪ ተዋናይና ባለቤትነት እንዲረጋገጥ ላለፉት ሶስት ወራት ፓርቲያችን ባስቀመጠው ስትራቴጂ እቅድ መሠረት ሰፊ ህዝባዊ ንቅናቄ ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሶ “በሃገራችን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ማለትም ፖለቲካዊ፤ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መረገጥ ፓርቲያችን “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” በሚል ሰኔ 13ቀን 2005 በይፋ ለጀመረው ሕዝባዊ ንቅናቄ ፖለቲካዊ ምክንያቶች ናቸው፡፡” ብሎታል።
የአንድነትና የ33ቱ ፓርቲዎች መግለጫ መቀጠልም “ሕዝባዊ ንቅናቄው በእቅድ መመራት ከመጀመሩ በፊት ሀገራችን የምትገኝበትን ነባራዊ ሁኔታና የህዝባችን ተጨባጭ ኑሮ ላይ ጥናት በማድረግ የመፍትሄ አማራጮችን ማቅረቡ የፓርቲያችን አብይ ጥያቄ ሆኖ መገኘቱም የንቅናቄውን ወቅታዊነት ያገናዘበ አድርጎታል፡፡ በእቅዳችን መሰረት በመላው ሃገሪቱ ለመጀመሪያው ዙር በተመረጡ ቦታዎች ያደረግናቸው ህዝባዊ ስብሰባዎችና ሰላማዊ ሰልፎች በአባሎቻችን፤ በደጋፊዎቻችንና በህዝባችን ጠንካራ ትግልና መስዋእትነት ንቅናቄው የተሳካ ሲሆን ፓርቲያችን ለተከፈለው ዋጋ ሁሉ አድናቆቱን ይገልፃል፡፡” ካለ በኋላ “በገዢው ፓርቲ ካድሬዎች በመታገዝ የፀጥታ ኃይሎች እንቅስቃሴዎቻችንን ለማጨናገፍ ከህግና ሥርዓት ውጪ ማስፈራራት፤ ማሸማቀቅ፤እስራትና ድብደባ በአባሎቻችን ላይ ሰብአዊነት በጎደለው ሁኔታ ተፈፅሞባቸዋል፡፡ የቅስቀሳ ቁሳቁስም በአካባቢ የፀጥታ ሰራተኞች ተዘርፈውብናል፡፡ እንዲሁም ህዝብ በነፃ አስተሳሰብ አማራጩን እንዳይከተል በአካባቢ ካድሬዎችና አመራሮች ማስፈራራትና ዛቻ ደርሶበታል፡፡ መርሃ ግብሩም ከተፈፀመ በኃላም ቢሆን ህዝባዊ ንቅናቄውን የተቀላቀሉ ዜጎቻችን በመኖሪያ ቀያቸው ሰርቶ የማደርና በነፃነት የመኖር መብታቸው አደጋ ላይ ነው፡፡” ሲል በ3 ወር የሚሊዮኖች ለነፃነት እንቅስቃሴ ወቅት የደረሱበትን ችግሮች አስረድቷል።

(አንድነት ባለፉት 3 ወራት ካደረጋቸው ሰልፎች መካከል)

(አንድነት ባለፉት 3 ወራት ካደረጋቸው ሰልፎች መካከል)

“በተንቀሳቀስንባቸው አካባቢዎች ሁሉ ገዢው ፓርቲ ከህዝብ የተነጠለ መሆኑንና ህዝቡን እየመራሁ ነው የሚለው ህዘብን በማሸማቀቅ እንደሆነ መገንዘብ ችለናል፡፡ ከህግ ውጭ የገጠሙን መንግስታዊ ተፅእኖዎች ሁሉ ነፃነቱን በተነፈገውና በለውጥ ፈላጊው ህዘባችን ህዝባዊ እምቢተኝነት ተልኮአችን ሊሳካ ችልዋል፡፡” ያለው መግለጫው ”
የሚሊዮኖችን ድምፅ ለማሰባሰብ እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴም በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ያሉ ዜጎቻችን በንቃትና በቁጭት የተሳተፍበት በመሆኑ አመርቂ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ፊርማ የማሰባሰቡ መርሃ ግብር የሚቀጥል ይሆናል፡፡” በማለት በቀጣይ ስለሚያደርገው ትግል ሲገልጽም “የህዝባዊ ንቅናቄው የመጀመሪያው ዙር መርሃ ግብር በመዲናችን አዲስ አበባ ከተማ መስከረም 5ቀን 2006 በሚደረገው ታላቅ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡” ብሏል፡ ይህን ሲያብራራም “ይህ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ እስካሁን ካደረግናቸው ህዝባዊ ንቅናቄዎች ልዩ የሚያደርገው የ33ቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ይሁንታ ያገኘና ሰላማዊ ሰልፉን በባለድርሻነት የተሳተፉበት መሆኑ ነው፡፡ በአንፃሩ ገዢው ፓርቲ እስካሁን ካወጣቸው አፋኝ ህጎች በተጨማሪ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተጠናክሮ የመጣውን ህዝባዊ የፖለቲካ ተቃውሞ የበለጠ ለመደፍጠጥ አሳሪ ደንቦች ለማውጣት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተንቀሳቀሰ ለመሆኑ ከገጠመን መልካም አስተዳደር እጦት መገንዘብ ችለናል፡፡” ካለ በኋላ በመግለጫው ማጠናቀቂያ ላይም “የአንድነት ፓርቲና የ33ቱ ፓርቲዎች በጋራ በጠሩት በዚህ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ የነፃነት ድምፁን እንዲያሰማ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡” ብሏል።

↧

አቶ አርከበ ዑቕባይና ወንድሙ አቶ ጌታቸው ዑቕባይ ከነቤተሰቦቻቸው አሜሪካ ገብተዋል

$
0
0

አብርሃ ደስታ ከመቀሌ

አቶ አርከበ ዑቕባይና ወንድሙ አቶ ጌታቸው ዑቕባይ ከነቤተሰቦቻቸው አሜሪካ ገብተዋል። አቶ ጌታቸው በትእምት (በመስፍን ኢንዳስትሪያል ኢንጂነሪንግ በኋም በሴመንት ፋብሪካ) ሓላፊ የነበረና ከወይዘሮ አዜብ መስፍን ተጣልቶ ስራው የለቀቀ ነው።
arkabe equbay
ወደ ሰሜን አሜሪካ ተጉዘው ከነበሩ የህወሓት አባላት ግማሾቹ ፈርተው አሜሪካ መቅረታቸው ታውቋል። ከነዚህ የጠፉ ባለስልጣናት መካከል የማረት ሐላፊው አቶ ተኽለወይኒ አሰፋ አንዱ መሆኑ መረጃዎች እየጠቆሙ ነው (የተኽለወይኒ ራሴ አኣላረጋገጥኩም)።

ዓረና ትግራይ ፓርቲ ጉባኤው በደማቅ ሁኔታ እያካሄደ ነው።

↧

የሸህ ኑሩ ልጅ ለምን ታሰረ ? BBN

↧
↧

ስለእግራቸው ውጤት (የስንኝ ቋጠሮ ለብሔራዊ ቡድናችን ተጫዋቾች) –ከፋሲል ተካልኝ አደሬ

$
0
0

waliyaa2
ያልከውን አላልኩም..ሰማህ ወይ ወዳጄ?
እንዴት እበላለሁ?..እጄን በገዛ እጄ::

ክብሬን አላቀልም..እንደምን አድርጌ?
እንደሌለ አውቃለሁ..
የቁሳቁስ እንጂ..የጀግና አሮጌ::

መቼም..መቼም..መቼም አልዘነጋ
የናቤን..የማሞን..ክብርና ዋጋ::
እንዳልከው በእግራቸው..በዓለም የነገሱ
ሁሌም የሚኖሩ..በታሪክ ሲወሱ
ሕያው ጀግኖቻችን..መቼም አይረሱ!!!

ሰማህ ወይ ወዳጄ?
ፈለግ ተከትለው..ዛሬ በእግር ኩዋሱ
በፈጸሙት ገድል..ቢንቆለዻዸሱ
በእግራቸው በሠሩት..
ባስመዘገቡት ድል..አገር ስላኮሩ
በክብር ቢነሱ..በክብር ቢጠሩ
ፈጽሞ አልገባኝም..ምንድ ነው ነውሩ?!?

ሰማህ ወይ ወዳጄ?
ስቼ ያሳሳትኩት..
…አልታይህ አለኝ
ስለእግራቸው ውጤት..
እንኩዋንም ደስ አለህ!..
…እንኩዋንም ደስ አለኝ!
* * *

___ ፋሲል ተካልኝ አደሬ ___ —

↧

አንድነት በአዳማ የጠራው ሰልፍ በሰላም ተጠናቀቀ

$
0
0

udJ Adma


(ዘ-ሐበሻ) የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት በሚል በጎንደር፣ ደሴ፣ ባህር ዳር፣ ጂንካ፣ ወላይታ ፣ባሌ ሮቢ፣ ፍቼና አርባ ምንጭ ተካሂዶ የነበረው የአንድነት ፓርቲ ሰላማዊ
UDJ Dr hailu Areayaሰልፍ ዛሬ ደግሞ በአዳማ ከተማ ተደርጎ በሰላም መጠናቀቁን የፍኖተ ነፃነት ጋዜጠኛ ዳዊት ሰለሞን ከስፍራው ዘገበ። እንደ ጋዜጠኛው ዘገባ በዛሬው የአዳማ ሰላማዊ ሰልፍ መንግስት ፌደራል ፖሊሶችን በማሰማራት፣ የሰልፉን መንገድ በማስቀየርና በኢቲቪ በኩል ድራማ ለማሠራት ቢሞርክም እንዳልተሳካለትና ከምንም በላይ ሰልፉ በሰላም ተጠናቆ ሕዝቡ ድምጹን ከፍ አድርጎ ያሰማበት ነው።

በአዳማ ከተማ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ የአንድነት የምዕራብ ቀጠና ሃላፊ አቶ አስናቀ ሸንገማ በኦሮምኛ ቋንቋ፣ የአንድነት የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ስዮም መንገሻ እንዲሁም ዶክተር ሃይሉ አርአያ ንግግር ማድረጋቸውን የገለጸው ጋዜጠኛው ስልፈኛው በመፍክሩ መንግስትን የተለያዩ ጥያቄዎችን ጠየቋል፡
ከነዚህም መካከል፦
- ውሸት ሰልችቶናል
- የኢቴቪ የሃሰት ዶክመንተሪ ፊልም ከአሸባሪነት አይለይም
- ድህነት በፕሮፓጋንዳ ብዛት አይጠፋም
- ሰብዓዊ ልማት ለሁሉም
- ስራ ማግኘት የዜግነት መብት ነው
- አምባገነኖች ባሉበት የአንዷለም ቤት እስር ቤት ነው
- ርዕዮት አለሙ ጋዜጠኛ እንጂ አሸባሪ አይደለችም
- ድሌ ዛሬ ነው! ድሌ ዛሬ ነው ድሌ ድሌ ድሌ
የሚሉ መፍክሮችን እነዚሁ ከፍርሃት የተላቀቁ ኢትዮጵያውያን አሰምተዋል።

አንድነትየሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት በሚል ላለፉት 3 ወራት በመላው ኢትዮጵያ በመዘዋወር ሕዝቡን በሰላማዊ ሰልፍ በማደራጀትና ፊርማ በማሰባሰብ ሲያደርገው የቆየውን ሰላማዊ ትግል በመቀጠል የፊታችን እሁድ ከ33ቱ ፓርቲዎች ጋር በመሆን በመስቀል አደባባይ ት ዕይንተ ሕዝብ መጥራቱን ዘ-ሐበሻ ከቀናት በፊት መዘገቧ ይታወሳል።

 

 

↧

የመከላከያ ሠራዊቱ-ድምበር አስከባሪ ወይስ አሳሪና አስተዳዳሪ ?

$
0
0

  ( እምብኝ በል-ጎፍንን )         

ethiopian-troopsየደርግ ወታደራዊ መንግሥት የፖለቲካ ሥልጣኑን በለስ ቀንቶት  ሥልጣን ለመያዝ  ለበቃው ህወሃት ከለቀቀ በኋላ ህወሃት ትኩረት ሰጥቶ ያጠናክር የነበረው የካድሬውንና የመከላከያ ሠራዊቱን መዋቅር ነበር። በመከላከያ ሠራዊቱ ሥር  የአጋዚ ሠራዊት (የፌደራል ፖሊስ እያሉ የሚጠሩት) ቅጥረኛ የከተማ  ነዋርዎች ነብሰ ገዳይ ቤት ለቤት እያውደለደለ ንብረት በመዝረፍ የተሰማራ በቤተ-መንግስት በጅት ይተዳደር የነበረውን የደርግ ልዩ ጥበቃ ኃይልን ቦታ የተካውና በህወሃት የሚመራው፤ የፖሊስ ኃይል ፤ የደህንነትና ፈጥኖ ደራሽ ኃይል እንዳሉበት ግምት ውስጥ አስገብተን ማለት ነው። በመሆኑም እነዚህ መዋቅሮች እስከ ዛሬ ድረስ የሥርዓቱን እድሜ በማራዘም ረገድ የተጫወቱት ጨዋታ ቀላል አይደለም ወይም የህወሃት የጀርባ አጥንት ናቸው ቢባል ነገሩን ክብደት ሊሰጠው እንደሚችል በመግለጽ ለዛሬ ያለኝን ትኩረት በዚህ ላይ ላድርግና በመጠኑም ቢሆን  በዚህ ተቋም ላይ ያለኝን ሃሳብ ማካፈሉ ጉዳዩን በቅርበት ለሚከታትሉ ምንጭ ወይም የመነሻ ሀሳብ የሚሆን መስሎ ስለታየኝ ከዚህ የሚከተለውን የግል  አስተያየቴን ለአንባቢዎቼ አቀርባለሁ።

በሽግግሩ ወቅት የመከላከያ ሚንስትር የነበረው ስየ አብርሃ ሲሆን ከፀደቀ 18 ዓምታትን ያስቆጠረውና በሥራ ላይ ሳይውል የቀረው በህወሃት ተረግጦ የሚገኘው ሕገ-መንግስት ከመታውጁ በፊት ስየ አብርሃ -የቀጣይቷ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራስያዊት ሪፐብሊክ ሠራዊትን በሚመለከት፦ እንዲህ ብሎ ነበር ፦የመከላከያ ሠራዊቱ ከዋና መንገድ 20 ኪ/ሜትር  ከዋና ከተማ 40 ኪ/ሜትር ርቆ እንዲሰፈር እንደሚደረግ ፤ የሠራዊቱ ብሔራዊ አስተዋጾም እንደየ መጣበት ብሔር ወይም ብሔረሰብ ሕዝብ ብዛት እየታየ እንደሚመደብና ወታደራዊ ብቃቱም ፕሮፌሽናል ስታንዳርድ  (ዓለም አቀፋዊ ደረጃውን የጠበቀ) ወይም እንዲኖረው ተደርጎ እንደሚሰለጥን መሪ አቅጣጭ ተቀምጦለት ነበር። ይሁን እንጅ ስየ አብርሃ ይሁን ሌላው በመከላከያ ሠራዊቱ ውስጥ በከፍተኛ አመራር ደረጃ ላይ የነበረው አካል ይሁን አሁን ያለውም ቢሆን ይህን መርሕ እንዲተገበር ሲያደርጉት አልታዩም። በርግጥ ስየ አብርሃ በመከላከያ ሚንስትርነቱ ብዙ አልቆየበትም። ቢቆይም እዚህ ግባ የሚባል  መሠረታዊ ለውጥ ያመጣል ብየ አልጠብቅበትም ነበር። ምክንያቱም እሱም ቢሆን በህወሃት ውስጥ ለረጅም ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ በአመራር ላይ የቆየና ወደኋላ አካባቢ በጥቅምና በሥልጣን ክፍፍል ተገቢውን ድርሻ ባለማግኘታቸው በህወሃት ውስጥ ክፍፍል ሲፈጠር በሟቹ መለስ ዜናዊና በአዲሱ ለገሰ ውሳኔ ተገፍተው ከጎድና ከወጡት አንዱ ቢሆንም አሁን ህወሃት የሚያራምደውን የአንድ ጎሣ (የትግሬ) የበላይነትን ዓላማ ወደ ፊት ይገፉ ከነበሩት ጽንፈኞች ስፊ ድርሻ የነበረው በመሆኑ ለተወሰኑ ወራቶች የህወሃት ተቃዋሚ መስሎ ብቅ ቢልና ኢትዮጵያዊነቱን ለማስመስከር ቢሞክርም  እምነት እንዳንጥልበት የሚያደርጉ ብዙ ሊገልፃቸው የሚገቡ ነገሮችን አፍኖ መያዙና ለግል ሕይወቱ ቅድሚያ መስጠቱ ከትግሉ ጎራ መራቁን አመልካች ነው። ይህን ስል ግን የስየን ጠንካራ ጎኖቹን ማለትም ራሳቸውን ደብቀው (አድፍጠው) ዝም ካሉት አረጋሽ ፤ተወልደና ዓለምሰገድ እንዲሁም አብረው ብዙ ሳይራመዱ ተመልሰው የሥልጣን ጥማታቸውን ለማስታገስ ከወሰኑት ሐሰን ሽፋና አባይ ፀሀየን ከመሰሉት በእጅጉ የተሻለ መሆኑን ፤ ለሥርዓቱ አለመገዛትና ድርጅቱን ጥሎ በመውጣት ህውሃትን በውጭ ሆኖ መመልክቱ ብዙ አስተማሪ ነገር እንዳገኘበት፤ እንድሁም ይመራውና ይታገልለት የነበረው ድርጅት ቅጥረኛና ፀረ-ኢትዮጵያ ድርጅት መሆኑን፤ ከሱ በፊት የተገደሉ የታሰሩ ፤ የተባርሩ ነባር ታጋዮችን እጣም በሱ ላይ በመድረሱ አዛኝ ልቦና ሊያድርበት ይችልላ የሚለውን በታሳቢነት በማሳደር አሁንም ስየ ከሕዝብ ጎን በመሆን ትግሉን ቢቀጥል የተሻለ እንደሚሆን እግረ መንገዴን መጠቆም እወዳለሁ ምክንያቱም ኢትዮጵያ አሁን ከደረሰችበት አደገኛ ሁኔታ እንድትደርስ ካደረጉት አንዱ ስለሆነ  ከደሙ ንጹሕ ለመሆን የኢትዮጵያን ሕዝብ የሚክስ ተግባር መፈጸም ይጠበቅበታልና ህወሃትን  አለበት።

የመከላከያ ሠራዊቱ ከላይ በተቀመጠለት መርህ መስረት ስፍሮ የሀገር ሉዓላዊነትን ማስከበር ሲግባው  የሚፈጽመው ተግባር ግን በግልባጩ በየመሸታ ቤቱና ስራ አጥተው ሰውታቸውን ሸጠው በሚያድሩ ምስኪን እህቶቻችን መኖሪያ መንደር ለመንደር ትጥቁን ተጀብሎ መዋያና ማደሪያ ማድረጉን ፤ በገጠርና በየከተማው በአስዳደር ሥራ ጣልቃ ሲገባ ፤ መሬት ሲመራና ሲያካፍል ፤ በየተሰማራበት አካባቢ ሴቶችን አስገድዶ ሲደፍር ፤ በኃይል አስገድዶ የጠለፋ ተግባር ሲፈጽምና አለቆቹ  እንደ አንድ የገቢ ምንጭ ቆጥረውት ሩዋንዳ ፤ ሱዳንና ሶማሌ ድረስ እየሰደዱ ከዩኤን ወፍራም ደመወዝ በዶላር እንዲከፈለው በማስደረግ ለአለቆቹ የሀብት ምንጭ ከመሆንና መጠቀሚያ ከመሆኑ ባሻገር በሕዝቡ ዘንድ የሚያስመሰግን ተግባር ሳይሆን የሚፈጽመው አሳፋሪና የጠመንጃውን አፈሙዝ በሕዝብ ላይ በማዞር በአደባባይ ንጹሃን ዜጎችን ከመግደል ከመደብደብና ከማፈን ውጭ ኢትዮጵያዊ የአገር መከላከያ ሠራዊት መሆኑን የሚያስመሰክር ተግባር አልፈጸመም ። እዚህ ላይ እንደሰለጠነው አገር ሰራዊት የተፈጥሮ አደጋ ሲደርስ ሄዶ አላገዘም ፤አቅም ለተሳናቸው ድጋፍ አላደረገም በማለት መክሰሴ አይደለም የጠመንጃውን አፈሙዝ በምን ሂሳብ ነው ወደ ሕዝብ እንዲያነጣጥርና አልሞ እንዲተኩስ የሚደረገውና ሕዝብ የሚጨርሰነው ነው? ?

የመከላከያ ሠራዊቱ ውስጡ በሰፊ ቅራኔ ውስጥ የተሞላ ቢሆንም ከአማራው ብሔር የመጣው የመከላከያ ሠራዊት አማራውን ሲያጠቃና ሲጨፈጨፍ ተባባሪ ሆኖ ከማገልገልና ነገሩን ከማባባስ አልፎ የአማራውን ብሔር ሕዝብ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ መብት ተነካ ብሎ የአማራውን ሕዝብ ጥቃት ሲመክት አልታየም። ከኦሮሞው ብሔር የመጣው የኦሮም ተወላጅ የሆነው የመከላከያ ሠራዊት አባልም ኦሮሞው ሲንገላታ ከመተባበር የዘለለ ተግባር ሲፈጽም አልታየም። በርራ ላይም  በየግዳጁ ሲግባ በፊቱና በኋላው የሁለት ወገን እሣት የህወሃት አለቆቹና ሥርዓቱን ለመጣል በመታል ላይ ያሉት የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ጥይት እንደሚገድለው ይታወቃል።ይህ ሁሉ እየሆነ ግን የሥርዓቱን እድሜ ለማራዘምና በአለቆቹ ዘንድ ምስጉን ለመባልና በበጎ እንዲታይ ምዝብሩን ሕዝብ በማንገላታት በመግደል  ስቃዩን በማባባስ ለሰሞንም ቢሆን የህወሃት ታማኝ መስሎ እያደረ ይገኛል። የደርግ የጦር ሠራዊት በጅምላ ጨፍጫፊነት የሚታወቅ ቢሆንም የሥርዓቱ  ከአናቱ  ወይም ከላይ የተበላሸ መሆን እንጅ በጦር ሠራዊቱ ውስጥ አንድ የሚያደርግ ባህሪ ኢትዮጵያዊነትን ስንቅ የሰነቀ ነበር።  ያም ሆኖ ይህ ዛሬ የሚታየው የአገር ሉዓላዊነት መደፈር አስከፊ ጥቃትና ገጽታ በኢትዮጵያችን እንዳይመጣ ግን ሕይወቱን አሳልፎ የሰጠ፤ ደሙን ያፈሰሰ፤ አጥንቱን የከሰከሰ ነበር። ይሁን እንጅ የደርግ ሥርዓት ሲናድ በሠራዊቱ ላይ የደረሰበትን የሞራል ፤ የአካል ፤ የህይወት ዋስትና ማጣትና የጎዳና ተዳዳሪ እንዲሆን መዳረጉ በዜግነቱ ሊከበር አለመቻሉ መቼም ቢሆን የማይረሳ የህወሃት በቀልተኛነት ታሪክ በታሪክ ማህደር ተዘግቦ የሚጠብቅ ይሆናል። የአሁኖቹ ሰሞነኞችና አዲስ ናፋቂዎችም ነገ መሀሉ ዳር -ዳሩ መሀል የሚሆንበት ሁኔታ ሲፈጠር በማን ላይ ሊያሳብቡ ማንን ምክንያት ሊያደርጉ እንደሚችሉ እግዚአብሔር ብቻ የሚያውቀው ጉዳይ ይሆናል። እንደኔ የግል አስተያየት ግን ህወሃትን መከታ በማድረግ በማንኛውም አይነት መዋቅር የተፈጸመች እያንዳንዷ ግፍ ጊዜዋን ጠብቃ  ብህዝብ ፊት ለፍርድ እንደምትቀርብ ትንበያ  ወይም ጥንቆላ ሳይሆን በግልጽ እንደሚሆን በድፍረት መናገር ከእውነቱ መራቅ አይደለም።

  በሽግግሩ ወቅት በተቋቋመው ሕገ-ምንግሥት አንቀጽ 87 ላይ የመከላከያ መርሆዎች ይልና፦ከዚህ የሚቀጥለውን ደንብ ያትታል።ደንቡ ግልጽነት የጎደለውና አሻሚ ትርጓሜ እንዲሰጥ የተደረገ ውይም የያዘ ሲሆን ሆነ ተብሎ ለማጭበርበር የተዘጋጀ መሆኑን ያመለክታል። ራሱን እንደመንግሥት አደርጎ የሚቆጥረውና በማርክስዊ ሌኒናዊ ሊግ ትግራይ የሚመራው የታጠቀው የደደቢት ፖለቲካዊ ኃይል በክህደት ተወልዶ በክህደት ያደገና የፀረ-ሕዝብ ተቋም ቢሆንም በየጊዜው የሚቀያየረውን የማጭበርበሪያ ስልት ደግሞ ለይቶ ማወቅ የግድ ይሆናል ብየ አስባለሁ።

1/ የሀገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት የብሔር ብሔረሰቦችን ፤የሕዝቦችን ሚዛናዊ አስተዋፅኦ ያካተተ ይሆናል።

 እንደሚታወቀው በደርግ መውድቂያ አካባቢ ህወሃት አገር ለማጥፋት ብዙ ቁጥር ያለው ሠራዊት አስታጥቆ ነበር ። ወደ መሀል አገር ሲገባም በአምሳሉ የፈጠራቸውን ጨምሮ ይህ ኃይል የማይናቅ ቁጥር ነበረው። ከተራ ውንብድና ወደ ሕጋዊ ውንብድና ሲሸጋገርና አገር መግዛት በእጅ የተያዘና የሚቻል መሆኑ ሲረጋገጥ በቅጥፈት ያደገው ህወሃት ያሰለፈውን ኃይል የሥርዓቱ አገልገጋይና ታማኝ በማድረግ ማስቀጠል ስለነበረበት የሚጠቀምበት መንገድ መፈለግ የግድ በመሆኑ የተወሰነውን የህወሃት ኃይል የአካባቢውን ህዝብ በማስለቀቅ ዳንሻ በተባለ ቦታ ውስጥ በአንድ ማዕከል የመተዳደሪያ በጀት ስጥቶ ሲደራጅ የቀረውን ለማሸጋሸግ ደግሞ ድርጅቱ መላ መምታት ነበረበት። ይኸውም በሕጉ መሠረት የሰፈረው የሠራዊት ምደባ ሕግ እንደ ብሔሩ ወይም ብሔርሰቡ ብዛት ሚዛናዊ መሆን አለበት ስለሚል ይህን ሕግ ለመከላከል አብዝኛው የህወሃት ሠራዊት በአማራው ክፍለ ሀገራት ብዙ ጊዜ ስለቆየ አማርኛ መናገር የሚችለውን በቀጥታ የአማራ ብሔር ተወላጅ እንደሆነ አድርጎ መመደብ ነበረበት ተመደበ  ኦሮምኛ ተናጋሪ ህዝብ ባለበት ተወልደው ያደጉ ትግሬዎችም የኦሮሞውን ሠራዊት ኮታ እንዲቀላቀሉ ተደረገ ( አባዱላ ፤ዘገየ የማነብርሃን…ወዘተ የመሳስሉ)  እዚህ ላይ ለኢህአፓና ለደርግ አንምበረከክም ያሉትና ለህውሃት የተንበረከኩት ኢህዴኖች በዚህ የተግባር አፈፃፀም ወቅት ብአዴኖች የሆኑት በድጋሚ ለህውሃት ተንበረከኩ። ለህወሃት መረጃ በማቀበል፤ መንገድ በመምራት፤ በስለላና በአጠቃላይ የህወሃትን ዓላማ ስኬታማ ለማድረግ ታጥቀው ያገለገሉ ባለሟል የሆኑት እስላሙን ከእስላሙ፤ ክርስቲያኑን ከክርስቲያኑ ፤ደገኛውን ከቆለኛው፤ ሽናሻውን ከአገው ጋር፤የደቡቡን ከሰሜኑ፤ የምሥራቁን ከምዕራቡ ጋር በማጋጨት አገር ያጠፉት (አዲሱ ገለሰ ፤ ታምራት ላይኔ ፤ ተፈራ ዋልዋ ፤ ብረከት ስምኦን ፤ታደሰ ካሳ ፤ህላዊ ዮሴፍ) በዚህ መጥፎ ምግባራቸውና በአማራው ሕዝብ ላይ በፈፀሙት ሁሉም አይነት ግፍ  ሰፊው የአማራ ሕዝብ ለሁሉም ጊዜ አለውና አንድ ቀን ይፋረዳቸዋል።እዚህ ላይ ልብ ብላችሁ እንድታነቡልኝ የምጠይቀው ቢኖር ህወሃት ሕዝብና አገርን መግደል ዓላማው አድርጎ የተነሳ ሲሆን ዓላማውን ለማሳካት ለ40 ዓመታት ያህል ሥራውን እየሰራ ይገኛል ተግብሩ ወይም ዓላማው ጥፋት ነው ነገር ግን ለዓላማው አሁንም ወደፊት የሥርዓቱ እድሜ እንዲረዝም ለማድረግ ተስፋ ባለ መቁረጥ እየታገለን ይገኛል። እኛም የሕዝብና የአገር ጠላት መሆኑን ተገንዝበን በቻልነው መንገድ ሁሉ ድንጋያችን እየወረወርንበት እንገኛለን ነገር ግን ትግሉ አንድ የዘነጋው መሠረታዊ ጉዳይ አለ ይኸውም ቀደምት የኢህዴን አመራር የነበሩና ዛሬም ህወሃት በተለያዩ ከፍተኛ የኃላፊነት ደረጃ ላይ አስቀምጧቸው የሚገኙትን በዋናነት ከፍ ሲል ስማቸውን የዘረዘርኩት አደገኛ የኢትዮጵያ ጠላቶች መሆናቸውን ቅድሚያ ሰጥቶ አለመንቀሳቀሱና አሁንም ትኩረት እንዲደረግበት ለምሳሰብ ነው። ዛሬ በተለያዩ መዋቅሮች ቁልፉን ቦታ ይዞ የአማራውን ክልል በቅኝ -ገዥነት እየገዛ የሚገኘው ኃይል ምንጭ በእነዚህ በተጠቀሱ ግለሰቦችና በዙሪያቸው በተሰማሩ አሾክሿኪዎች አማክኝነት ነው። ህግ መጣስ የተጀመረው በዚህ ጊዜ ባይሆንም ኢህዴን ያሰለፈው ምስኪኑ የአማራ ብሔር ሠራዊት ግን በብር ከ3ሽህ በታች ድጎማ እየተሰጠው ወደ የመጣህበት ከብትና  ፍየል ጥበቃህ ተመለስ እየተባለ መሳለቂያ ሆኖ እንዲሄድ ተገዶ ከሠራዊቱ አባልነቱ ተወገደ። የቀረውም በህወሃት ካድሬና የሠራዊት አለቆች በየጊዜው እየተገመገመ እንዲባረር ሲደርግ ድምጣቸውን አጥፍተው ሰጥ ለጥ ብለው የተግዙት የሠራዊት አባላትም ህወሃትን የሚያስጭንቅ ውጫዊ ሁኔታ በተፈጠረ ቁጥር ወደ እሥር መወርወር ፤በድብቅ በመግድል፤ ጤና በሚነሳ መድኃኒት ተወግተው እንዲሞቱ ማድረግ የድርጅቱ መደበኛ ባህሪ እየሆነ መጣ። 1/ለምሳሌ ኮሎኔል ታደለ ገብረሥላሤ ሩውንዳ አዝማች ሆኖ ሄዶ የነበረ ህወሃትን ከደደቢት እስከ ደቡብ፤ ምእራብና ምሥራቅ ግንባር ከፋች በመሆን የሚታወቅ እንደነበር የማይካድ ነው። 2/ኮሎኔል ናቃቸው ጫቅሉ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርንት በመጨረሻ የወጣው ዝነኛ ተዋጊና አዋጊ ታመው በህክምና ላይ በነበሩበት ወቅት ህወሃት ሆነ ብሎ በመርዝ ተወግተው እንዲሞቱ ያደረጋቸው ሰለባዎች ናቸው። ይህ አድሎ እስከመቼ ይቀጥላል በሚል በመከላከያ ሠራዊቱ ውስጥ ተነስቶ የነበረው የመከለከያ ሠራዊቱ ጥያቄና አመጽ በተለይም በአማራው የመከላከያ ሠራዊት አባላት እድገቱን ጨምሮ ክልሉ በልማት ወደ ኋላ መቅረቱና በብአዴን አመራር ቦታ የተቀመጡት አማራ ያልሆኑና ለአማራው ብሔር ሕዝብ የማይጠቅሙ ጠላቶች ናቸው በማለት 1/በረከት ስምኦንና 2/ተፈራ ዋልዋን  እንዲሁም ሌሎችንም ምሳሌ አድርጎ የተነሳው እንቅስቃሴ እየተገመገመ እያለ ድንገት የኢትዮ-ኤርትራው ጦርነት ተጭሮ ሠራዊቱን ለመምታት ምቹ ሁኔታ ተፈጠረ እነሆ  ከዚያ በኋላ ገዥው ኃይል አመጹን አዳፍኖ ሠራዊቱን የሥርዓቱ አሽከር በማድረግ ሕዝብ እንዲጨርስ አሰማርቶት ይገኛል ። አሁን ይህችን መጣጥፌ እያዘጋጀሁ እያለሁ በፖሊስ ስም የሚሸቅጠው የአጋዚ ሠራዊት በመባል የሚታወቀው የሠራዊት ኃይል በሰላማዊ ፓርቲ አመራር ኃይልና አባላት ላይ ያደረሰውን ጥቃት እየተመለከትኩ በድርጊቱ እጅግ አዝኘ እስከ መቼ? በሚል ጥያቔ ስሜት ውስጥ ገብቼ ነው።

2/ የመከላከያ ሚንስትር  ሆኖ የሚሾመው ከስቪል ይሆናል።

የሕግ ባለ ሙያ ባልሆንም እስከ አሁን በመከላከያ ሚንስትር ሚንስትር ሆነው የነበሩትን ወስደን ስንመለከት በትግል ላይ የነበሩ ለፓርቲያቸው የሚያደሉ ሠራዊትን በበላይነት ሲመሩና ሲያዋጉ  ሲያዋጉ የነበሩ ሲሆን ምንጫቸውም ያው ከህወሃት እንደሆነ ይታወቃል። ከአገር አጥፊው መለስ ሞት በኋላ የመጣው ካቢኔም ለማጭበርበሪያ ይሆን ዘንድ አንዳንድ የሹመት መስጠትና የመለዋወጥ ሁኔታዎችን ያደረገ ቢሆንም ከኋላ ያሉት አስተኳሾችን እነማን እንደሆኑ ስለምናውቃቸው የተጃጃሉት እራሳቸው እንጅ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዳልሆነ ሊገነዘቡ ይገባል። ነገር ግን ቀልዱን አበዙት። እነሳሞራም ራሳቸውን አንቱ ያሉ በፀረ_ህዝብነት ታሪካቸው የታወቁ ስለሆነ ማንም የሚያዛቸው እንዳልሆኑ መግደል የሚፈልጉትን ከመግደል እንደማይታቀቡ ግልጽ  ሆኖ እያለና ነፍጥ አምላኪ ኃይልን በጎ ነገር ሊያመጣ ይችላል ብሎ ማሰብ አይቻልም። ማንም ይሾም ማንም ይህ ሥርዓት ፀረ-ሕዝብ ፤ ፀረ- ኢትዮጵያ እስከሆነ ድረስ መውወድ ብቻ ነው ያለበት።

3/ የመከላከያ ሠራዊት የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ከመጠበቅ በተጨማሪ በዚህ ሕገ-መንግሥት መሰረት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚሰጡትን ተግባሮች ያከናውናል።

ይላል። ይህን ነጥብ በሁለት ከፍለን ብንመለከተው መሰሪነቱን ለመረዳት ይቀላል፦

ሀ/ የመከላከያ ሠራዊት የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ይጠብቃል፦ አዎ!! የአንድ አገር የመከልከያ ኃይል(ሠራዊት) ተቀዳሚ ተግባሩ የአገርን ዳር ድንበር (ሉዓላዊነት) ከማንኛውም ጥቃት መጠበቅ ማስከበር ነው። በዚህ ዙሪያ ይህ የህወሃት የመከላከያ ኃይል በአገር ሉዓላዊነት ጉዳይ የተፈተነበት ወቅት ነበረ ወይ ? ካልነበረ በምን መለኪያ ሊታመን ይችላል ? ለዚህ የሚያበቃ መንፈሳዊና ብሔራዊ ሞራል አለው ወይ? በከፍተኛ ደረጃ አመራር ላይ ያሉት ከዚህ ጨዋታ ውጭ ከሆኑ እታች ያለው ኃይል አገራዊና ሕዝባዊ ፍቅር አለው ብሎ ለመናገር ዋስትና የሚሆኑት ከየት ሊገኙ ይችላሉ ? ትንሽ በኢትዮ-ኤርትራው ጦርንት ዙሪያ ልቆይና የመጨራሻ መደምደሚያየን አስቀምጣለሁ።

በ1958 የተቋመው ኤ.ኤል.ኤፍ ( የኤርትራ ነፃ አውጭ ግንባር) ቀደም ሲል ከዘውዳዊው ሥርዓት ጋር በኋላ ከወታደራዊ መንግሥት ጋር ውጊያዎችን ያካሂድ እንደነበር ይታወቃል ። ወደኋላ አካባቢ ግራ ዘመም የሚመስል ነገር ግን ያልነበረ ኢ.ኤል.ኤፍን ከሁለት እንዲከፈል አደረግ። አዲስ በተቋቋመው ኤ.ሕ.ኤል.ኤፍ (የኤርትራ ሕዝብ ነፃ አውጭ ግንባር **ሻቢያ**) እና በኤ.ኤል.ኤፍ መካከል ቅራኔዎች እያደጉ በመሄዳቸው አንዱ ሌላውን መብላት ጀመረ። በመሆኑም ሻቢያ ጉልበት እያገኘ ጀብሃ እየተዳከም መጣ ። ሻቢያ ጀብሃን ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ትጥቅ የያዙ በኤርትራ ውስጥ ይንቀሳቀሱ የነበሩትን የማዳከም አቅም አገኘ። በ1967 ዓ/ም የተቋቋመው ተጋድሎ ሀርነት ትግራይ በኋላ ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ በኤርትራ ከተከሰተው ሁናቴ ጋር የሚያገናኘው ብዙ መሠረታዊ ምክንያት ሊኖር እንደሚችል ነገር ግን ይህን ጉዳይ ቀንጭቦ ማለፍ ስለማይገባ ራሱን አስችሎ ማቅረቡን በማመን ወደ ተነሳሁበት ነጥብ ልመለስና ጀብሃም ሆነ ሻቢያ ህወሃትን በቀጥታም ይሁን በተዛዋሪ የማደራጀትና የማስታጠቁን ጉዳይ በበላይነት ይዘውት እንደነበር ይታወቃል። ደርግ በሚያደርጋቸው ዘመቻዎችም በጋራ ማለትም ሻቢያና ህወሃት በከፍትኛ ደረጃ ይተባበሩ ነበር። ይህ ግን ቀጠለ ወይስ አልቀጠለም ? ወደሚለው ስንገባ ሻቢያ የአዛዥነቱን ህወሃት የታዛዥነቱን ጉዳይ በአግባቡ ሊያደርጉ ባለመቻላቸው በመሃከላቸው የነበረው ጥብቅ ግንኙነት በህወሃት አልታዘዝም ባይነት ምክንያት ሊቀጥል አልቻለም። ለይቶላቸው የከፋ ግጭት ባይፈጥሩም ደርግ እስኪወድቅ ድረስ ይረዳዱ ነበር።ይህ በዚህ እንዳለ ግን ሻቢያ ህወሃትን ማጥመዱ አልቀረም ህወሃትም ሻቢያን የማደናቀፍ ተግብሮችን ማራመድ ጀመረ። ለምሳሌ ዴሞክራሲያዊ ምንቅስቃስ ህዝብ ኤርትራ የሚባለው ድርጅት ፀረ-ሻቢያ ሆኖ እንዲቆም የማደራጀቱን ሥራ ይመራው የነበረው ህወሃት ነበር።ሻቢያ ይህን ተግባር ቢያውቅም የተነሳበትን የመገንጠል ዓላማ ላለማደናቀፍ ህወሃትን ይጠቀምበት እንደነበርና ወደፊት ግን ወጥመድ ውስጥ ለማስገባት አለመቦዘኑን የሚያመላክቱ አንዳንድ ጉዳዮች ነበሩ። ከላይ እንደገለጽኩት ይህን ጉዳይ ባጭሩ ማሳየት ስለማይቻል ገረፍ ገረፍ አድርጌው ልለፍና ደርግ ከወደቀ በኋላ በአዲሲቷ አፍሪቃዊት አገር ኤርትራና ኢትዮጵያ ምን አይነት አንድነትና ልዩነት ነበር የሚለውን በመነካካት በጉዳዩ ሰፊ እውቀት ያላቸውን አባንኘ በሰፊው እንዲያብራሩት በመተው በበኩሌ የማውቀውን እንዲህ ለመግለጽ እሞክራልሁ።

  ወዶም ይሁን ተገዶ ኤርትራን በአማራ ገዥ መደብ በቅኝ አገዛዝ የነበረች አገር ናት በማለት አስቀድሞ እውቅና የሰጠው ህወሃት እንደሆነ ይታወቃል። ሻቢያ አስመራን ህወሃት አዲስ አበባን ከተቆጣጠሩ በኋላ ከበሮ መደለቁ ብቻ ሳይሆን ሁለቱ አገሮች በመሠረታዊ ጉዳዮች በጥቅም የሚያስተሳስራቸው ውሎችን መፈራረማቸው ይታወቃል። ከብዙ በጥቂቱ ማንኛውም ኤርትራዊ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ ፓስፖርት ወይም የመታወቂያ ደብተር እንደማያስፈልገው፤ኢትዮጵያ የጦር ካሳ ለኤርትራ መክፈል እንዳለባት፤ በኢትዮጵያ የሚኖሩ ኤርትራዊ ጡረተኞች የጡረታ ደመወዛቸው በኢትዮጵያ እንደሚከፈል፤የአስብ ወደብ ኢንሹራንስ በኢትዮጵያ እንደሚሸፍንና የመንገድ ሥራ ጥገናው በኢትዮጵያ ወጭ እንደሚከናወን፤ኤርትራዊያን ማንኛውንም ምርት ከኢትዮጵያ ሲገዙ ታክስ እንደማይከፍሉ …ወዘተ ተብለው 25 ወሎችን ዛሬ የመናፍቃን መሪ ነኝ በሚለውና የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ሲኖዶስ ከሁለት የከፈለው ታምራት ላይኔ በኩል ተፈራርመዋል።

ያ ሁሉ እከከኝ ልከክህ ከንቱ ውዳሴው ሳይውል ሳያድር ወደ ግጭት አመራ አንዴ አንዱ ሲገፋ ሌላ ጊዜ ደግሞ ተገፍቶ የነበረው ሲገፋ መቆየቱ ይታወቃል። ሸራሮ የነበረው የህወሃት ጦር ሻቢያ በኢትዮጵያ ድንበር ምሽግ እየሰራና እየተጠጋ መሆኑን ተመልክቶ የሻቢያን ምሽግ ሰብሮ በመግባት የሻቢያን ጦር በማባረር ባረንቱ ድረስ መሸኜቱንና በዚህ ጉዳይ የሠራዊቱ አመራሮች ማን አዟችሁ ነው ተብለው አዲስ አበባ ተጠርተው መገምገማቸውን አንድ የሠራዊቱ አመራር የነበረ አጭውቶኝ ነበር። ተገምጋሚዎቹ ከአዲስ አበባ ሳይለቁ የሻቢያ ጦር ተደራጅቶ በመመለስ ጥቃት መሰንዘሩና ከዚያ በኋላ የሻቢያ ጠብ አጫሪነት ግልጽ ሆኖ የሁለቱ የኢትዮ-ኤርትራው ጦርነት በሁሉም ወገን ታወጀ የህወሃት ጦር አስመራ ሲጠጋ ተመለስ ተብሎ ድርድሩ ተጀመረ ።ብዙ የአገር ኢኮኖሚ ወደመ ከሰማኒያ ሽህ የማያንሱ ውድ ኢትዮጵያውያን የጦርነት ሰለባ ሆኑ ሻቢያ በአሽናፊነት ደመደመ። እንግዲህ የመከላከያ ሠራዊቱ አገር ወዳድነት ወይም በሌላ አነጋገር ለአገሩ ለሉዓላዊነት የነበረው ወኔና ወታደራዊ ብቃቱ የታየው በዚህ ጊዜ ብቻ ነበር።

ለ/ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚስጡትን ተግባሮች ያከናውናል፦በኢትዮጵያችን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀው ህወሃት በምርጫ 97 ሲሸነፍ የምርጫ ሳጥን ለመዝረፍ ፤ በአሸባሪነት ስም የተቃዋሚ ኃይሎችን አንገት ለማስደፋት የታወጀ አዋጅ ካልሆነ በስተቀር የሕዝብን ሰላም የሚያደፈርስና ፀጥታን ሊያናጋ የሚችል ክስተት አለመፈጠሩን ብርቅም ዜና ስለማዳምጥ ስለማነብ የታየ ነገር እንደሌለ እርግጠኛ ነኝ። በነዚህ ተግባሮች የመከላከያ ሠራዊቱ እጁን አስገብቷል። ሀቁ ይህ ከሆነ የመከላከያ ሠራዊቱ የአገርን ሉዓላዊነት ያስከብራል ሲባል የማንን አገር የዚየትኛውን ሕዝብ አገር? ለህወሃት እሰየው የሚያስብል በሕዝብ ዘንድ ግን ከፍተኛ አደጋ ያደረሰ የተፈጥሮ አደጋ ደርሶ በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ቀውስ መፈጠሩን በዜና ሰምቸዋለሁ ምስሉንም አይቻለሁ። አንድ የመከላከያ ሠራዊት አባል የሆነ ግን ድጋፍ ሲሰጥ አልተመለከትኩም ወይንስ ይህ በሕግ አልተደነገገም? ይቅርታ የዚህን አገር የጦር ኃይል ተልዕኮ ስለማይ ነው።የኛዎቹ ከሕዝብ አብራክ የመጡ ቢሆኑም እንዲያልቅ በተፈረደበት ሕዝብ ጉዳይ መግባት እንደሌለበት የታዘዘ ይመስላል። እንግዲህ ከዚህ የባስ የሚመጣ ስለማይኖር ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ ያለዚያ ድንጋይ ነው ብለው ይወረውሩሃል እንደተባለው የሰላማዊ ትግሉን ወይም የትጥቅ ትግሉን መቀላቀል የተሻለ አማራጭ እንደሚሆን ያለኝን ኃላፊነትና የዜግነት ግዴታየን በዚህች ጦማሬ እንካችሁ ብያለሁ።

4/ የመከላከያ ሠራዊት በማናቸውም ጊዜ ለሕገ-ምንግሥቱ ተገዥ ይሆናል።

ሕገ መንግሥቱን አስመልክቶ ሕግ አውጭው፤ ሕግ ተርጓሚውና ሕግ አስፈፃሚው ተግባራዊ ሳያደርጉት ፤ ሳያምኑበትና ለሕገ-መንግሥቱ ተገዥ ሳይሆኑ በውል ያልተብራራን ሕግ በህዝብ ላይ መጫንና ሕዝብ ስለ ህገ መንግሥት ያለውን ግንዛቤ እንዲዛባ ማድረግ ሥርዓት አልብኝነትን በንቃት ማስፋፋት ብቻ ሳይሆን ሕዝብን በነገር እየተነኮሱ በሕገ-መንግሥት ሽፋን እያጭበረበሩ ሰጥ ለጥ ብሎ እንዲገዛና ስለ ዴሞክራሲ፤ ፍትሕና ነፃነት ስለ ዜግነት መብቱ እንዳያስብ በታጠቀ ኃይል እያስፈራሩ የሥልጣን እድሜን ለማራዘም የሚያገለግል የመከላከያ ሠራዊት እንደትስ አድርጎ ነው ለሕገ መንግሥቱ ተገዥ ይሆናል የሚባለው? ይህን ጉዳይ በሚቀጥለው  ንኡስ ማጠቃለል ስለሚቻል የመከላከያ ሠራዊቱ በማናቸውም ጊዜ ለሕገ-መንግሥቱ ተገዥ ይሆናል የሚለው መቼ በሚል? አልፈዋለሁ።

5/ የመከላከያ ሠራዊት ተግባሩን ከፖለቲካ ድርጅቶች ወገናዊነት ነፃ በሆነ አኳኋን ያከናውናል። በሰለጠነውና ዴሞክራሲ በሰፈነበት አገር የአገር መከላከያ ሠራዊት ከድርጅታዊ ፖለቲካ ወይም ለመንግሥት ከመቆም አልፎ ህግን በማስከበር እንዴት እንደሚንቀሳቀስ እየተመለከትን ወደ አገራችን ስንመለስ በተለይም በዘመነ ህወሃት የአገር መከላከያ ሠራዊቱ ለገዥው ህወሃት በመቆም ገና ትእዛዝ ሳይወርድለት አድራጊ ፈጣሪነቱን በምን አይነት ሂደት እንደሚተረጉመው በስፋት ተመልክተነዋል። የተቃዋሚ ድርጅቶችን በማዋከብ አንድ ቦታ ላይ ብቻ ተወስነው እንዲቀመጡና፡ህዝቡን እንዳያገኙት በማድረግ ቀዳሚውን ሚና የሚጫወተውም ይኸው የመከላከያ ሠራዊት ነው። የሕዝብን እምብኝ ባይነትና የውስጥ ብሶት በመሣሪያ ኃይል አፍኖ ይዞ መኖር እንደማይቻል ከዚህ በፊት በዘውዳዊው ሥርዓት፤ በወታደራዊ አገዛዝ ሕዝቡ አስመስክሯል ይህ ከሆነ የሚጠበቀው «ማየት መልካም ሁሉን እይው ግን በትዳር ቀልዱን ተይው»የሚለውን የሙሉቀን መለሰን የግጥም ስንኝ እያስታወስኩ ለህወሃት የመከላከያ ሠራዊት የመጨረሻውን ምክሬን በዚህ መጣጥፌ እደመድማለሁ። ወደፊት ሕግ ተርጓሚ የሚባለውን የኢትዮጵያ የፍትሕ ሚንስቴርና በህወሃት ጊዜ ተወልደው በህወሃት ጊዜ ተምረው ዳኛ ስለሆኑትና ዳኝነትና ዳኛ በኢትዮጵያችን በሚል ርእስ አንድ ጹሑፍ ይዥ ለመምጣት እሞክራለሁ ። እስከዚያው ደህና እንሰንብት!

አዲሱ 2006 ዓ/ም የሰላም ፤ የጤና ፤ የመተሳሰቢያ ፤ የእድገትና የድል ዘመን ይሁንልን!!

↧

ቅዳሜ ከሰዓትን ከአቶ ግርማ ሰይፉ ጋር በቶሮንቶና ኦታዋ ቆይታ ያድርጉ (Toronto City Hall)

$
0
0
↧
↧

አውስትራሊያን ከኢትዮጵያ ጋር የማመሳሰል ሕልም

$
0
0

 መስከረም 8 2013

ከታክሎ ተሾመ

 

አውስትራሊያ ቀለመ ብዙ አገር  ናት። ከ200 በላይ  ቋንቋ  የሚናገሩባት በዝንቅ ማኅበረሰብ የተመሰረተች፤በጥሬ ማዕደኗ፤ ወንድ ሴት ሳይል የሰዎች የተፈጥሮ ሰብአዊ መብት የተከበረባት አገር ማን ትባላለች ብሎ ለሚጠይቅ  መልሱ አውስትራሊያ  ናት ብሎ በድፍረት መናገር ይቻላል።

 

አዎ እርግጥ ነው አውስትራሊያ በስደት የምኖርባት አገር ናት፤ ከዚህ በፊት ዴሞክራሲ የሚባል ነገር ስላላየሁ  ከዚህች አገር ውጭ ዴሞክራሲ ያለ መስሎ ስላልታየኝ  ወደድኳት፤ ተመችታኛለች። መፋቀርና መቻላል  ስላለ ብዙ እድሎችና ሕይወትን የሚለውጡ አጋጣሚዎች  የተመቻቹ  ናቸው።

 

አውስትራሊያን  ጥሩ  አገርና  መልካም ሕዝብ ያሰኛት የተለያዩ ምክንያቶች  አሏት። አውስትራሊያ ራሷን  የቻለች አገር  ከመሆኗ  በፊት  እርግጥ ነው ብዙ ጦርነቶች  ተካሂደውባታል።  ይሁን እንጂ ራዕይ ባላቸው ሰዎች አማካኝነት ከችግር  ተላቃ  ዴሞክራሲ የሰፈነባት አገር ለመሆን የቻለቸው  ሌበርና ሊበራል  የተሰኙ ሁለት አንጋፋ ፓሪቲዎች  በመፈጠራቸው  ነው። ሁለቱ  ፓርቲዎች  የየራሳቸውን  የፖለቲካ ፕሮግራም ይዘው  ሲከራከሩ ከዚህ ቀደም የሰሩት ሥራ እየተገመገመ  ሕዝቡ የሚበጀውን  ይመርጣል።

 

በአውስትራሊያ የፌደራሊ ምርጫ ሲደረገ  ጦርሰራዊት፤ ፖሊስ ወይም ደህንነት የሚባሉ በየምርጫ ጣቢያው  አካባቢ ድርሽ አይሉም። የአውስትራሊያ ዜጋ ሁሉም የሚበጀውን ፓርቲ የመምረጥ ኃላፊትም ሆነ ግዴታ አለበት። መስከረም 7 ቀን 2013 ቅዳሜ  ከጧቱን 8 ሰዓት  ጀምሮ እስከ ምሽቱ 6 ሰዓት ድረስ  ምርጫ ተካሂዷል።  በዚህ ወቅት ለውድድር  የቀረቡ፤ የአውስትራሊያ ሌበር ፓርቲና የአውስትራሊያ ሊበራል ፓርቲ በዋናነት ሲወዳደሩ እንዲሁ አናሳ የሚባሉ 1 ናሽናል ፓርቲ 2  ግሪን ፓርቲ  3 የግል ተወዳዳሪዎች 4  ዩናይትድ ፓርቲ  የመሳሰሉት ለውድድር  ቀርበው  ነበር። ከ2007  እስከ  2013 ዓ.ም ድረስ  የአውስትራሊያ  የሠራተኞች ፓርቲ ሌበር ሥልጣን ላይ  ነበር። ነገር ግን መስከረም 7 ቀን 2013 ዓ.ም በተደረገው ምርጫ ከምሸቱ 8.45 ሰዓት ላይ ተቃዋሚ  የነበረው  የአውስትራሊያ ሊበራል ፓርቲ 88 ድምጽ ሲያገኝ ሌበር ፓርቲ 54  ድምጽ አግኝቶ የሥልጣን ባለቤት ለመሆን በቅቷል።

 

ከላይ እንዳልኩት በምርጫ ወቅት የሳጥን ስርቆት አልነበረም፤ ሥልጣን ላይ የነበረው ሥልጣን አለቅም ብሎ ጦር አላዘመተም። እንዲያውም አሸናፊውን እንኳን ደስ ያለህ በማለት ወደፊት እየተመካከሩ አገርና ሕዝብ ለመምራት ቃል ኪዳን በመግባት የእለቱ ምርጫ  ተጠናቋል።

 

ይህንች አጭር ጽሁፍ ላቀርብ የተገደድኩበት ምክንያት የአውስትራሊያው ምርጫ በኢትዮጵያ መቼ ይሆን የሚደገም የሚለው ጥያቄ  ስላስገደደኝ  ነው። እርግጥ ነው፤ አንድ አገር  እንደ አገር ሲቆረቆር ብዙ ውጣ ውረዶችን  ማለፍ ግድ  እንደሚለው  ይታወቃል። ከታሪክ  መረዳት  እንደሚቻለው አገራችን ኢትዮጵያ ከዓለም ቀደምት መሆኗን ነው የሚነግረን። ነገር ግን ረጅም  እድሜ  ብታስቆጥርም ከአብራኳ በሚፈጠሩ መንግሥታት ሕዝቦቿ  በነፃነት እንደ ዜጋ እየኖሩ አይደለም።

 

ኢትዮጵያ ከዓለም የሚወዳደሩ ምሁራን ልጆች እንዳሏት አይካድም። ነገር ግን አገርና ሕዝብን ለመታደግ የታደለች አገር  አይደለችም። በመሆኑም  በየጊዜው  እስር፤ ስደትና ሞት የዘወትር እጣ ፈንታችን  ሆኗል። ይሁን እንጂ ችግሮችን አስወግዶ ዴሞክራሲያዊ የሆነ በሕዝብ የሚመረጥ መንግሥት ለማምጣት ረጅም  ዓመታት የተለያዩ ትግሎች ተካሂደዋል። ለትግሉ ስኬት አለመበቃት የተለያዩ ምክንያቶች እንዳሉ አይካድም።  ከፓለቲካ ድርጅት  መሪዎች  እስከ ግለሰቦች ድረስ ያለውን ብሎም ከሕይወታችን ጋር በንፅፅር ማስቀመጡ ተገቢ  ይመስለኛል።

በመጀመሪያ ደረጃ ዓላማን  በትክክል በመረዳት ወደየትኛው መስመር ነው የምንጓዝ፤ የምንታገለው ለጐጂ ወይስ ለጥሩ ዓላማ የሚለው ተለይቶ ከታወቀ  ትግሉ ትርጉም ያለውና የተሟላ  ይሆናል። ይህ ማለት የትግሉ ዓላማና የጉዟችን አቅጣጫ ከታወቀ ሕዝቡ ሊከተል ይችላል። ከተለያዩ ዓለም ትግሎች ተሞክሮ መረዳት እንደሚቻለው  ትግላቸው ውጤት ከማምጣቱ በፊት  ብዙ እልህ አስጨራሽ ትግልን ማለፍ ይጠበቅባቸው ነበር።  በመሆኑም  በደቡብ  አፍሪካ፤ በሰሜን  አሜሪካና በሌሎች አገራት ለነፃነት የታገሉ ድርጅቶች ለአሸናፊነት የበቁት  ሽንፈትንና  ተስፋ  መቁረጥን በፀጋ  መቀበልን  ባለመፈለጋቸው  ነው።

 

ከዚህ በፊት የተደረጉ ትግሎች በድርጅቶችም ሆነ በግለሰቦች ላይ አስደሳችና አሳዛኝ ገጠመኞችን ተመልሰን ስንቃኝ ብዙ ትምህርቶችን መቅሰም  ይቻላል። ለአገራችውና ለሕዝባቸው ሲሉ ከዚህ በፊት የተሸነፉ ፓርቲዎች በችግሮች ተስፋ  ሲቆርጡ  አንዳንዶች  ዛሬም ድረስ  የሚችሉትን  ያህል  እየተፈረጋገጡ  ይገኛሉ።

 

 

በአገራችን የተፈጠሩ በርካታ ተቃዋሚ ድርጅቶች በውስጥና በውጭ  እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ። ይሁን እንጂ ስንቶች ናቸው መሰናክሎችን ማለፍ የሚችሉ ብለን ስንጠይቅ በጣት የሚቆጠሩ ሆነው እናገኛቸዋለን። በመጀመሪያ ደረጃ  ይጠንክሩም  ይኩሰሱ  አገር ቤት ውስጥ  የሚንቀሳቀሱ  ድርጅቶች የለውጥ ተስፋ እንደሚሆኑ እገምታለሁ።

 

ከላይ ከተጠቀሱት  የተስፋ ፓርቲዎች በተጨማሪ በውጭ የተሰባሰቡ ጅርጅቶችም እንዲሁ የአጋዥነት ግዴታ  እንዳለባቸው ብዙዎች ሲናገሩ እየተደመጠ ነው። እርግጥ ነው በውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ከጉልበት እስከ ገንዘብ ድረስ የሚችለውን ያህል ለአገሩ እያበረከተ መሆኑን ማንም አይክድም። ነገር ግን  አንዳንድ የፖለቲካ ድርጅቶች እርስ በርሳቸው በሚያደርጉት ፍክቻ  ትግሉ ወጥነት ኑሮት ስኬታማ እንዳይሆን መሰናክል መፍጠሩ አልቀረም።

 

ዋናው ነገር ግን ትግሉ ስኬታማ ሊሆን የሚችለው አገር ቤት በሚደረገው ትግል ስለመሆኑ አምንበታለሁ፤ ብዙዎችም አባባሌን  የሚስማሙበት ይመስለኛል። እነዚህ የአገር ቤት ተቃዋሚ ድርጅቶች ለአገራቸውና ለሕዝባቸው  መብት  መከበር  ሲሉ ብዙዎች የእሳት ረመጥ እስከ መሆን ደርሰዋል። እስር፤ ግርፋት ቢደርስባቸው የጀመሩትን ሰላማዊ ሕዝባዊ ተቃውሞ ትግል ከግብ ለማድረስ ቆርጠው መነሳታቸውን  በአንደበታቸው  እየሰማንና  ተግባራቸውን  እያየን  ነው።

 

እርግጥ ነው የአገር ቤት ድርጅቶች ለመስዋዕትነት መዘጋጀታቸው ቢያስደስትም የጀመሩት ትግል ውጤት እንዲያመጣ ከተፈለገ  ማበረታቻ  ያስፈልጋቸዋል። ይህ ሲባል  በስደት የተበተነው ትውልደ ኢትዮጵያዊና የፖለቲካ ድርጅቶች በሞራል፤ በገንዘብ፤ በዲፕሎማሲ፤ አገር ቤት ገብቶ አብሮ  መታገልን ግድ ይላል። እያንዳንዱ ለአገሩና ለሕዝቡ ሲል የራስ ተነሳሽነት ስሜት  ካለውና ከልብ የሚታገል ከሆነ ውጤታማ  ይሆናል። ብሎም የድርጅት መሪዎች ተነሳሽነታቸውም ቢሆን ዘላቂነት ይኖረዋል። ለዚህ ደግሞ ኃይል ሊሆን የሚችለው እምነት መሆኑ  አያጠያይቅም።  ስለሆነም እያንዳንዱ ኃላፊነትን መቀበል ሲጀምርና ወደ አንድ መመጣት ሲችል የትግሉ አቅጣጫ  ይስተካከላል ብሎ  በድፍረት  መናገር ቢያስ  ነው።

 

ከመግቢያየ ላይ  እንዳልኩት አውስትራሊያ  ዛሬ ከደረሰችበት የእድገት ደረጃ ከመድረሷ በፊት ብዙ ፈተናዎችን እንዳለፈች ከአውስትራሊያ ቤተ መጽሃፍት ውስጥ ገብቶ የታሪክ መጽሕፍቶችን ለሚያገላብጥ አስቀያሚና አስደሳች ታሪካቸው በሚገባ ተቀምጧል።  መስከረም 7 2013  በአውስትራሊ የተካሄደውን  የመንግሥት  ምርጫ በቅርበት ማየት ብቻ ሳይሆ  ተሳትፊ  እንዳየሁት ከሆነ  ተሽናፊው ለአሸናፊው ሥልጣኑን በሰላም አስረከቧል።

 

ከላይ ይህን ካልኩ ዘንዳ  ከምርጫ በኋላ   ቤቴ ቁጭ ብየ ቴሌቭዝኝ እየተመለከትኩ እግሬን ሳይሆን አእምሮየን  ኢትዮጵያ አድርጌ ጉደኛዋ አገራችንስ በምን ላይ  እንደምትገኝና የ1997 ቱን  ምርጫ ተመልሸ ስቃኝ አዘንኩ፤ ተከዝኩ እርር ትክን አልኩ። እርግጥ ነው ሃዘኔ ግን ተስፋን  ያዘለ ነው። ምክንያቱም ከዚህ ቀደም በተናጥል ይደረግ የነበረው ትግል አሁን፤አሁን በተቀናጀ መልክ  ሰላማዊ ሕዝባዊ ትግል ለማካሄድ  መስማማታቸውን እየሰማን ነው። ስለሆነም  ተስፋ ጥሩ ነው “ቸር  ተመኝ በጐ “እንድታገኝ ይሉየል በአውስትራሊያ ያየሁት  የሰላም የሥልጣን ዝውውር በኢትዮጵያም ይደገማል የሚል የተፍሳ  ስንቅ ተሸክሜአለሁ።

 

ሁሉም ፊቱን ወደ ሰላም እንዲያዞር ኃያሉ ልዑል እግዜአብዜ ይርዳን።

↧

“በስልጣን ምክንያት ህወሓት ለሁለት የተከፈለ ይመስለኛል”–አቶ ገብሩ አስራት (ቃለ ምልልስ)

$
0
0

ሐገር ቤት የሚታተመው ሎሚ መጽሔት አቶ ገብሩ አስራትን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አነጋግሯቸዋል። ዘ-ሐበሻ ለአንባቢዎቿ ይጠቅማል በሚል እንደወረደ አቅርባዋለች።

ገብሩ አስራት 1

ሎሚ፡- ባለፈው መቀሌ ላይ “አረና” ሕዝባዊ ስብሰባ አከናውኖ ነበር፡፡ የነበረው ሁኔታ በአጠቃላይ ምን ይመስል ነበር;

አቶ ገብሩ፡- እንግዲህ የመቀሌውን ስብሰባ ከሁለት ጉዳዮች አንፃር ልንመለከተው እንችላለን፡፡ አንዱ ሕዝቡ እንዴት እንደተቀበለው ስብሰባውን … ሁለተኛው መንግስት ወይም በክልሉ ያለው ፓርቲ ስብሰባው እንዳይካሄድ ያደረጉትን ጫና በተመለከተ መመልከት ይቻላል፡፡ እንግዲህ አስቀድሜም መንግስት ስብሰባው እንዳይካሄድ የፈጠረውን ጫና ነው የማየው፡፡ እንግዲህ ትግራይ ውስጥ ገዢው ፓርቲ ህወሓት ነው፡፡ ህወሓት ከእሱ ውጭ ሌላ ፓርቲ እዛ ቦታ ላይ እንዲንቀሳቀስ ፍላጐት የለውም፡፡ ይህም ባፈለው 2002 ዓ.ም. በተካሄው ምርጫ ጠ/ሚ መለስ ትግራይ ውስጥ ምንም አይነት ክፍተት መኖር የለበትም፣ ምንም አይነት የሀሣብ ልዩነት መኖር የለበትም ብለው የተናገሩበትና በርካታ ስድቦች የተሰነዘረበት በተለይም በ”አረና” ላይ በርካታ ስድቦችን ያወረዱበት ጊዜ ነበር፡፡ እንግዲህ አሁን ያለው አመራርም የእሣቸውን “ሌጋሲ” ፈለግ እከተላለሁ የሚል ስለሆነ አካሄዱ ተመሳሳይ ነው፡፡ በትግራይ ውስጥ ምንም አይነት የፖለቲካ አስተሳሰብ እንዲኖር አይፈልግም፡፡ በህገ መንግስትም ፣ በቃልም ተቃዋሚ ቢኖር አንጠላም ሊሉ ይችላሉ፡፡ ዋናው ስጋታቸው በአካባቢው የተለየ ሀሣብ ፣የተለየ አመለካከት ፣ የተለየ አደረጃጀት እንዳይኖር ስጋትና ጭንቀት ያለባቸው ስለሆነ አጠቃላይ ድርጅቱን በእነሱ ስር የተደራጀ ሲቪክ ማህበረሰብ፣ የመንግስት ድርጅቶችን አደራጅተው ነው አንድ ፓርቲ በዛ አካባቢ ስብሰባ እንዳያካሂድ የሚያደርጉት፡፡ ባለፈው ጊዜም ስብሰባ ስናካሂድ እንደውም እነሱ በሚመሯቸው ድርጅቶች ፣ ኩባንያዎች /ኢፈርት/ ሠራተኞችን ሰብስበው በዚህ ስብሰባ ላይ መገኘት ከጠላት ጋር እንደማበር ይታሰባል ብለዋቸዋል፡፡ እና ስለዚህ ስራ ለማግኘት አትችሉም፣ ስጋት ላይ ትወድቃላችሁ ፣ ከጠላት ጋር የመተባበር ያህል አድርገን ነው የምናየው ሲሉ ነው የተናገሩት፡፡

ይህንን ካሉ በኋላም በዚህም አላበቃም በኢትዮጵያ የምርጫ ሕግ መሠረት እንደተፈቀደው ማንም ፓርቲ ሊቀሰቅስ ይችላል፡፡ መቀስቀስ የማይችለው በትምህርት ቤትና በቤተ እምነት ቦታ ውስጥ እንጂ በሌላ ቦታ ድምፅ ማጉያ ተጠቅሞ መቀስቀስ ይችላል የሚል ነገር አለ፡፡ መቀሌ ላይ ግን ሌላ ህግ አውጥተዋል ወይም አውጥተናል ነው የሚሉት፡፡ እኛ ግን አላየነውም፣ ህጉ ምንድነው የሚለው ማንኛውም እንቅስቃሴን ማጉያ ተጠቅሞ መቀስቀስ አይቻልም ነው የሚሉት፡፡ ይሄ እንግዲህ ከሀገሪቱ ህግ ፣ ከፌዴራል ህግ ጋር የሚጣረዝ ህግ ነው፡፡ ህግም ቢሆን ማለቴ ነው፡፡ ማውጣትም አይችሉም፡፡ እንደዚህ ያለ የምርጫ ቦርድ ሕግ እያለ መንግስት ወይም አስተዳደር ይሄንን ህግ ሊያወጣ አይችል፡፡ እኛ ህግ አውጥተናልና መንቀሣቀስ አትችሉም እያሉ ነው የሚናገሩት፡፡ ለምን ስንላቸው ደግሞ ድምፅ ማጉያው ማለት ነፍሰ ጡሮችንና በሽተኞችን ሊያውክ ስለሚችል መናገር አይቻልም ፡፡ በዛ ምክንያት ነው የከለከል ነው ይላሉ፡፡ ያም ሆኖ ግን መስኪዶች፣ ቤተክርስቲያኖች በድምፅ ማጉያ መልእክት ያስተላልፋሉ፡፡ ራሣቸው ህውሓቶችም በድምፅ ማጉያ ዳንኪራ እየመቱ የሚያጥለቀልቁበት ሁኔታ አለ፡፡ ለተቃዋሚዎች ነው ያልተፈቀደው እንጂ ራሣቸው በማይክራፎን ከተማውን የሚያውክ ነገር ይጠቀማሉ፡፡ ስለዚህ በዚህ ምክንያት ያንን ከለከሉን፡፡ እና ይሄ ህግ ይፈቅድልናል ብለው የኛ አባላትም ተንቀሣቀሱ፡፡ ግን አሰሯቸው፡፡ ሁለት ሦስት ጊዜም ነው ይህንን ያደረጉት፡፡ ሹፌሮችንና የተከራየነውንም መኪና አገቱ፡፡ ስለዚህ በዚህ መልኩ ስብሰባ እንዳይካሄድ አግተዋል፡፡ በንጋታው ደግሞ ስብሰባ ስናካሂድ እያንዳንዱ የቀበሌ አስተዳደር ማን እንደሚገባ እንዲመለከት እዛ አሰልፈዋቸው ነበር፡፡ አብዛኞቹም ሴቶች ናቸው፡፡ /የቀበሌ ሴቶች/ እነዚህን አሠልፈው ማነው ወደዚህ ስብሰባ የሚገባው የሚል ሊስት ይዘው አስቀመጡ፡፡

ጭራሽ ስብሰባ እንዳይካሄድ ነው የሞከሩት፡፡ በሌላም እያንደንዱ ቀበሌ ለሕዝቡ ስብስባ እንዲመጣ በፅሁፍ ጭምር ደርሰው እንድትገኙ የሚል አስተላለፉ ….የምንናገረው ስለመልካም አስተዳደር ፣ ስለ ንግድ ምናምን ነው ብለው መቅረታ የለባችሁም ወሣኝ ስብሰባ ነው ብለው ፣ እኛ ስብሰባ በምናደርግበት ቀን እነሱም ስብሰባ ጠሩ፡፡ ይሄ አካሄድ ደግሞ ምንም አይነት ሰው ወደኛ እንዳይመጣ የማድረግ አላማ ያለው ነው፡፡ ያም ሆኖ ግን ሕዝቡ ፍላጐት ነበረው እንዲያውም ስብሰባውን እንድናካሂድ ግፊቱ የመጣው ከሕዝቡ ነበር፡፡ ያም ሆኖ እነሱ ባይከለክሉት ኖሮ አዳራሹም አይችልም ቦታም አይበቃም ነበር፡፡ ይሄም ሆኖ ወጣቱ ይሄን ሰብሮና ጥሶ አድራሹን ሞልቶታል፡፡ እና እዚህ ላይ ለማለት የምፈልገው በተለይ በሁለት ጉዳዮች ላይ እኛ ያቀረብነው በከተማ የሊዝ አዋጆች ላይ ፣ በነጋዴዎች የግብር ጫና፣ በዜጐች ሰብአዊ መብት እጦት እንደዚህ እንደዚህ ያሉ በርካታ ጉዳዮች ላይ ነው፡፡ ሕዝቡ ግን ትኩረት አድርጐ ያቀረበው ነፃነቱን እንደተነፈገ ነው፡፡ ትግራይም ውስጥ እንደተነፈጉ ተናጋሪዎች ናቸው፡፡ እኛ ንግግሩን ጀመርነው እንጂ የጨረሰው እዛ የተሰበሰበው ሕዝብ ነው፡፡

ገብሩ አስራት ሌላው ደግሞ ይሄ የሊዝ መሬት ዜጐችን ጭሰኛ ለማድረግ እየሞከረ እንዳለ በአፅንኦት ተናግረዋል፡፡ መሬታችንን ቀሙን፣ በወላጆቻቸው /ውርስ/ ያገኙት መሬት ላይ ዋስትና እንዳጡ ፣ ይህንንም ተናገሩ፡፡ እንግዲህ የሚገርመው ስብሰባውን በፀሎት ለመጀመር ነው ፕሮግራም የያዝነው፡፡ ሁሉም የስብሰባው ታዳሚ ተነስቶ ለሰማእታት ፀሎት ሲያደርግ አንድ ወጣት ግን ከመቀመጫው ሣይነሳ ቁጭ ብሏል፡፡ ኋላ ላይ ግን ለምን በፀሎቱ ወቅት እንደተቀመጠ ምክንያቱን ተናገረ፡፡ ይሄ ወጣት ሲናገር “እኔ እናንተ ለምን ተነስታችሁ እንደምትፀልዩ አልገባኝም፡፡ ምክንያቱም እኔ አባቴ በትግሉ ተሰውቷል፣ ወንድሜና እህቴ ተሰውተዋል፡፡ ግን ያመጡልን ምንም ነገር የለም፡፡ ለምንድነው የምፀልየው; እኔ የምፀልየው ኢትዮጵያው ውስጥ ነፃነት ሲረጋገጥ፣ መብት ሲረጋገጥ ነው እንጂ አሁን ቆሜ አልፀልይም፡፡ ቤተሰቦቼ የተሰዉበት ሁሉ ተግባራዊ እየሆነ አይደለም፡፡ አፈና ፣ ሙስና ይህንን ለማምጣት ከሆነ የተሰዉት አልፀልይም፡፡ የምፀልየው ኢትዮጵያ ውስጥ ነፃነት ሲረጋገጥ ብቻ ነው” ብሏል፡፡ ይህ ንግግር ተሰብሳቢውን በጣም ያስገረመ ንግግር ነው የነበረው፡፡በአጠቃላይ መንግስትና የክልል ፓርቲ ስብሰባ እንዳይካሄድ ሕዝቡ ሌላ አማራጭ እንዳይሰማ ቢያደርጉም ሕዝቡ ግን ከፍተኛ ፍላጐት ነበረው፡፡ እንዲያውም እኛ ካሰብነው ጊዜ በላይ ተወያይቶ በጥሩ ሁኔታ ስብሰባውን አጠናቀናል፡፡

ሎሚ፡- አንዳንድን ዘገባዎች አሉ ይህ በሕዝብ ውስጥ የሚባለው ነው መረጃውን በእርስዎ አንደበት የማስተላለፉ መልእክት ደግሞ የእርስዎ ይሆናል፡፡ አረና ጥሩ እየተንቀሣቀሰ ቢሆንም የአባላቶቹ ወደ አሜሪካ መጓዝ በፓርቲው ላይ ችግር አይኖረውም ወይ የአቶ ስዬ እና የአቶ አሰግድን የሚያነሱ ሰዎች አሉ;

አቶ ገብሩ፡- ይሄ ምናልባትም የመረጃ ጉዳይ እንዳይሆን ለመናገር እሞክራለሁ፡፡ አቶ ስዬ የአረና አባል አይደሉም፡፡ የአንድነት አባል ናቸው፡፡ አቶ አስግድም ተመልሰዋል፡፡ አሁን ትግራይ ውስጥ ነው ያሉት፡፡ ስለዚህ የእኛ አባል ሆኖ ከሀገር ውጭ የሚገኝ የለም፡፡ ስለዚህ ይህን መረጃ ሕዝብ እንዲያውቀው ይገባል፡፡

ሎሚ፡- በህወሓት ውስጥ እውነት ልዩነት አለ; ህወሓት ለሁት ተከፍሏል የሚባል ነገር አለ ይሄን እንዴት ይገልፁታል;

አቶ ገብሩ፡- እኔ እንግዲህ በፖለቲካ ምክንያት ፣ በፖለቲካ ልዩነት ምክንያት ህወሓት ውስጥ መከፋፈል አልተመለከትኩም፡፡ ያም ሆኖ በስልጣን ምክንያት ህወሓት የተከፈለ ይመስላል፡፡ ይህም የታየው መቼ ነው ባለፈው የፓርቲው ጉባኤ በተካሄደበት ጊዜ ነባሮቹን ሙሉበሙሉ ጠራርጐ አስወጥቷል፡፡ ካድሬዎቹ ይሄ የሆነው ምንድነው ህወሓት ውስጥ የተጠናከረው በካድሬ ደረጃ አባል ነው ስልጣኑን የተቆጣጠረው እንጂ ራሱ ሀሣብ ሊያመነጭ የሚችል ፣ ሀሣብን ሊቀምር የሚችል፣ ንድፈ ሀሣብን በደንብ ተገንዝቦ ሊያስረዳ የሚችል ኃይል ህወሓት ውስጥ አሁን የለም፡፡ ከፋም በጀም የተሻለ አቅም ያላቸው ሰዎች ከዚህ ተገለዋል ብሎ መናገር ይቻላል፡፡ ስለዚህ የስልጣን ሽግሽግ ነው ለዚህ ያነሱት፡፡ ይህንን መሠረት አድርገው ነባር የተባሉትን ጠራርገው አስወጡ፡፡ እዚህ ላይ ግን ነባር የተባሉትንና ተጠርገው ከወጡት እኩል በፓርቲው ረጅም እድሜ ያላቸው ደግሞ እዛው ቀርተዋል፡፡ ስለዚህ ነገሩ የስልጣን ሽኩቻ ይመስላል ብሎ መናገር ይቻላል፡፡

ሎሚ፡- አሁን የኃይል ሚዛኑ የትኛው ክፍል ጋር ነው;

አቶ ገብሩ፡- ይሄ ኢትዮጵያ ውስጥ በጣም አስቸጋሪ ነገር ነው፡፡ እንግዲህ የኢትዮጵያ ፖለቲካና ስልጣን የተመሠረተው በማን ላይ ነው የሚለውን መመልከቱ ጥሩ ነው፡፡ ሦስት አካሎችን መጥቀስ ይቻላል፡፡ አንዱ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ማየት ይቻላል፡፡ ሁለት የመንግስት አካላት፣ ሦስተኛው መከላከያና የደህንነት አካላትን ነው ማየት የሚቻለው፡፡ አቶ መለስ በነበሩበት ጊዜ እነዚህ ሦስት አካላትን ተቆጣጥረው የሄዱበት ጊዜ ነበር፡፡ እንግዲህ የአቶ መለስ መንግስት አምባገነን መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ እንደ አምባገነንነቱም ሁሉንም የስልጣን አካላት ተቆጣጥረው በእጃቸው ውስጥ አስገብተው ቆይተዋል፡፡ እንደውም አሁን ኢህአዴግ ተዳክሟል የሚያሰኘው ምንድን ነው በአንድ ሰው ተሰባስቦ ፣ የአንድ ሰው ፈላጭ ቆራጭ፣ ስልጣን የነበረው አሁን ተበታትኗል፡፡ ከስልት አንፃር ይሄ መዳከምን ያሣያል፡፡ ይህ ከሆነ በኋላ ስልጣኑ የት ላይ ነው የሚለው ነገር በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ እንደ አቶ መለስ ተጠናክሮ የወጣ ሰው የለም፡፡ የአቶ መለስ ፍላጐት ቀድሞም ምንድነው የፑቲን አይነት አስተዳደር ነው በዚህች ሀገር ላይ ፍላጐታቸው የነበረው፡፡ ደካማውን ፊት ላይ አስቀምጠው እሣቸው ከኋላ ሊነዱት ነበር አቶ ኃ/ማርያምንና ሌሎችንም ወደ ስልጣን ያመጡት፡፡ ያም ሆኖ ግን እሣቸው አልቆዩም፡፡ አቶ ኃ/ማርያም በዚህ አጋጣሚ ስልጣን ያዙ፡፡ አሁን አቶ ኃ/ማርያም መከላከያውንና ደህንነቱን በእጃቸው ለመቆጣጠር ይችላሉ 1111 የሞራል ብቃትስ አላቸወይ; የፖለቲካው ብቃትስ አላቸወይ; የሚለው ጥያቄ የሚያስነሳ ነገር ነው፡፡ ፓርቲውንስ ቢሆን እንግዲህ ነባሮች ዳግም ተመልሰዋል ብአዴን ውስጥ አቶ መለስ እያሉ ውጡ ተብለው ታዘው ወጥተው የነበሩትም እንደገና ተመልሰው መጥተዋል፡፡ እነዚህንስ ለማዘዝ ይችላሉ ወይ;ከፍተኛ ውሣኔዎች ላይ የማዘዝ አቅም ይኖራቸዋል ወይ; የሚለው አንድ ጥያቄ ነው፡፡ እንግዲህ በመንግስት የሚባሉት ፣ በፓርላማ፣ በካቤኔ ውስጥ የዚህ ነፀብራቅ ነው፡፡በደህንነቱ፣ በመከላከያው የማዘዝ ስልጣን ከሌለህ በመንግስት ውስጥም የማዘዝ ችሎታህ አነስተኛ ነው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ አሁን ችግሩ የስልጣን ክምችት በአንድ አካል ላይ አለ፡፡ ይሄ ነው የሚወሰነው፡፡ ደህንነቱም ሆነ መከላከያው ትልቅ ተፅእኖ አለው በኢትዮጵያ፡፡ እንደውም ወሳኙ እሱ ነው፡፡ እሱን ማዘዝ፣ ማሰማራት ፣ እሱን መቆጣጠር የማይችል ኃይል በኢትዮጵያ የፖለቲካ ኃይል ይዣለሁ ማለት አይችልም፡፡ ይህንንስ ማድረግ ይችላል ወይ; አሁን ያለው አመራር ለሚለው ነገር ጥያቄ ውስጥ ያስገባል፡፡ ፓርቲዎችም ቢሆን ከአቶ መለስ ሞት በኋላ የየራሣቸው ነፃነትና መብት ለማስከበር አዝማሚያም እየታየባቸው ነው፡፡ የብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ህወሓት በአጠቃላይ የፖለቲካ ሂደት ላይ ተፅእኖ ለማሣደር እየሞከሩ ነው ያሉት፡፡ በይፋ ያልወጣ ሽኩቻ እየታየ ነው፡፡ ውስጥ ለውስጥ፡፡ ድሮ የነበረው የአንድ ግለሰብ ተፅእኖ አሁን የመሰበር ሁኔታዎች ነው ያሉት፡፡ አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉንም ለመወሰን ኃይሉም አቅሙም ያለው የለም፡፡ የሚፈለገው እሱ ነው ወይ ሌላ ጥያቄ ሊሆን ይችላል፡፡ ይሄ የአቶ መለስ ሌጋሲ የሚባለው ግን እንደዛ ያለ ሰው ካልፈጠረ በስተቀር ጥንካሬ አለው ብሎ ለማለት አይቻልም፡፡

ሎሚ፡- አሁን እንግዲህ በስርአቱ ውስጥ ሙስና በከፍተኛ ሁኔታ መንሰራፋቱ ይነገራል፣ የሚታይም ነገር ነው፡፡ከሀገር ውጭም ገንዘብ የማሸሽ ሁኔታ አለ ይሄን እንዴት ይመለከቱታል;

አቶ ገብሩ፡- እንግዲህ ሁልጊዜም እንደምለው ራሱ የሙስና ምንጭ በኢትዮጵያ ያለው የሙስና ምንጭ የለሚው ነገር ካልታወቀ መፍትሄም አይገኝለትም፡፡ ኢህአዴግ ሙስናን እየታገልኩ ብሎ ለማስመሰል የተወሰኑ ባለስልጣኖችንና ነጋዴዎችን ያስራል፡፡ ይፈታል፡፡ ግን ይሄ መፍትሄ ነው ወይ; በኢትዮጵያ የሙስና ምንጭ መሠረት የሆነው እነዚህ ነጋዴዎች ናቸው ወይ; የተወሰኑ ባለስልጣናት ናቸው ወይ; የሚለውን ነገር ማንሣቱ የሚጠቅም ይመስለኛል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ሙስና ሊቀንስ፣ ሊቃለል የሚችለው ከስርአቱ ጋር በቀጥታ ተያያዥነት አለው፡፡ የአንድ ስርአት ፓርቲ አገዛዝ ከሆነ ዞሮ ዞሮ ሙስናን ነው የሚያነግሰው፡፡ደጋፊዎቹን ያጠናክራል፣ በሀብት ያጠናክራል፣ በገንዘብ ያጠናክራል፣ ፖሊሲው ነው፡፡ አባሎቼ የሚላቸውን ቢሰርቅ ፣ ቢዘርፍ ምንም ሊላቸው አይችልም፡፡ ፖለቲካውን የሚቃወሙ ሊነካኩ የሚችሉ ሰዎች አንዳንድ ጊዜም በሰውም ምንም ለውጥ አያመጣም ብሎ የሚያስባቸውን ሰዎች በሙስና ይቀጣል እንጂ ከመሠረቱ ስርአቱ ነው፡፡

እንደሚታወቀው ይሄ በውጭ ሀገር ገንዘብ አላቸው ወይ; አስቀምጠዋል ወይ; የሚለው ነገር በተለያዩ የመገናኛ ብዙሀን የአለም ተቋማት እንደሚነገረው የሸሸው ገንዘብ በርካታ ነው፡፡ ይሄ ገንዘብ የማነው የኔ ነው የሚል ባይታወቅም በኢትዮጵያ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ እየሸሸ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ግን ወደዛ መሄድ አያስፈልግም፡፡ እዚህ ሀገር ያለው ሀብት ከየት መጣ የሚለው ነገር ቢጠየቅ እኮ መልስ የለም፡፡ሰርቶ ነው ወይ; ከደሞዙ ነው; በተለይ አንድ የመንግስት ባለስልጣን ትላልቅ ቤቶችን የሚያሰራ ደሞዝ አለው ወይ; ህንፃዎችን የሚያሰራ ደሞዝ አለው ወይ; ብዙ ሀብት ቤተሰቦቹን በከፍተኛ ደረጃ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውጭ ድረስ ልኮ የሚያስተምር ደሞዝ አለው ወይ ተብለው ቢጠየቁ የኢህአዴግ አመራሮች መልስ የላቸውም፡፡ ስለዚህ ሙስናው የራሱ የስርአቱ ባህሪ ነው፡፡ ምክንያቱም ሙስናን እንታገል ቢባል፣ ኢህአዴግ በሚከተለው አግባብ እንዴት ሙስናን መታገል ይቻላል; ነፃ ማህበረሰብ ፣ ሲቪል ማህበረሰብ በሌለበት እኮ ይሄ ሙሳኝ አለ ብሎ መቃወም አይቻልም፡፡ ጠንካራ ነፃ ጋዜጦች “Invest get journalism”መስራት በማይቻልበት ሁኔታ እንዴት ነው ሙስናን መዋጋት የሚቻለው; የመንግስት ተጠያቂነት ግልፅነት በሌለበት እንዴትነው ሙስናን መታገል የሚቻለው; ሕዝብ ሰልፍ ወጥቶ መቃወም በማይችልበት፣ ተሰብስቦ መነጋገር በማይችልበት እንዴት ነው ሙስናን መታገል የሚቻለው; ስርአቱ በባህሪው አምባገነናዊ ስርአት ነው፡፡ “አብዮታዊ ዴሞክራሲ” ብሎ የአንድ ፓርቲ ፈላጭ ቆራጭነት አረጋግጣለሁ የሚል መንግስት ከሙስና አይነፃም፡፡ ነፃ ሊሆን አይችልም፡፡ በአለምም ያየነው፣ በአፍሪካም የሚታየው ፓርቲዎች የህብረተሰቡን እንቅስቃስቃሴ በሙሉ “ገዢ ፓርቲዎች” ሕዝቡ ትንፍሽ እንዳይል ፣ እንዳያጋልጥ የሚያደርጉ ናቸው፡፡ ኢህአዴግም ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡ መታየት ያለበት የአንድና ሁለት ባለስልጣን የማሰርና የማጋለጥ ጉዳይ አይደለም፡፡ ዋናው ነገር ስርአቱ በቁርጠኝነት መታገል የሚችል እስከሆነ ብቻ ነው፡፡ ይሄንን ደግሞ ኢህአዴግ አይችልም ያውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ መሬት እንደተዘረፈ ያውቃል፡፡ እሱ ነው የሚያዘርፈው፡፡ የመንግስት በጀት እንደተዘረፍ ያወቃል ግን እራሱ ነው የሚያዘርፈው፣ የመንግስት ልማት ተቋማት በሚሊዮኖች ይዘረፋሉ ያውቃል መንግስት ግን መፍትሄ የለውም፡፡ መፍትሄም ከኢህአዴግ ይመጣል ብሎ ማሰብ የዋህነት ይሆናል፡፡ ምንም ሊመጣ አይችልም፡፡

ለዚህም ነው ከአመት አመት እየተባባሰ እንደውም አሁን የስርአቱ ዋና መገለጫ እየሆነ ያለው ከዚህ በመነሣት ነውና፡፡ አንድ እንደ አቅጣጫ መታየት ያለበት፣ መረሳት የሌለበት ሙስና ከስርአቱ የሚመነጭ ስለሆነ ፣ በፀረ ሙስና በኩል የተወሰኑትን በማሰር የሚቋጭ አይደለም፡፡ሰፊ ነፃነት፣ሰፊ መብት፣ ጠንካራ የህግ የበላይነት፣ ነፃ ባለስልጣኖችን ሊጠይቅ ሊያስር የሚችል አቃቢ ህግ “ነፃነት ያለው” ፍርድ ቤት ሊወስንባቸው የሚችል ያለምንም ተፅእኖ ከሌለ ሙስናን መታገል እንዴት ይቻላል፡፡ ስለዚህ ታዩታላችሁ ሙስና ኢህአዴግ እስካለ ድረስ እየባሰበት የሚሄድ ይሆናል፡፡ አሁን ተራ ሙስና አይደለም የማፍያ አይነት የተደራጀ ሙስና ነው እየተካሄድ ያለው፡፡

ሎሚ፡- እንደታዘቡት ከሆነ ፣የሙስሊሙ ጥያቄ አለ ይሄን እንዴት ይመለከቱታል; ሌላው ከቅርብ ቀናት ወዲህ በመንግስት በኩል አክራሪነት ፣ ሽብርተኝነት፣ አሸባሪነት የሚሉ ቃላት ይሰማል ይሄስ በእርስዎ እይታ እንዴት ታዘቡት;

አቶ ገብሩ፡- እንግዲህ በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ ጊዜ ተናግረናል፡፡ እኔ እንግዲህ ኢህአዴግ አንዳንድ ችግሮች ሲነሱ የሚሄድበት አግባብ ችግሮች አሉበት፡፡ የሙስሊሙ ጥያቄ ፣ የአባይ ጥያቄ፣ የብሔር ብሔረሰቦች ጥያቄ እነዚህ በዚህ አገር ከባድ ጥያቄዎች ናቸው፡፡ በተለይ በሙስሊሞች ጉዳይ መታየት ያለበት ካለው ማህበረሰባዊ እድገት፣ አለም አቀፋዊ ሁኔታ መንገድ ነው መታየት ያለበት፡፡እንግዲህ የሙስሊሞች ጥያቄ መታየት የጀመረው እኮ መለስ በነበረበት ጊዜ ነው፡፡ እንደማስታውሰው እኔ ከተለያዩ የአለም ክፍሎች የተውጣጡ ፣ የሙስሊም አባላት መጥተው ከአቶ መለስ ጋር ተገናኝተዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የሙስሊሞች አያያዝ የሚያሳስባቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ጥያቄዎችም ያኔ አንስተዋል፡፡ ካነሷቸው ጥያቄዎች መሀል፣ የበአላት ማክበር፣ ወለድ የሌለው ባንክ የመክፈት ጉዳይ እንዲህ እንዲህ ያሉ ወደ አስር የሚጠጉ ጥያቄዎች አንስተው ነበር፡፡ በወቅቱ እናየዋለን የሚል መልስ ነው የተሰጣቸው፡፡ ከዛ በኋላ የታየም ነገር የለም፡፡ ውስጥ ለውስጥ የሚነሱ ጉዳዮች አሉ፡፡ ብዙ የመብት ጥያቄዎች፡፡ ይሄ እያለ ግን ኢህአዴግ ይሄን የሚያባብስ እርምጃ ወስዷል፡፡ ምንድነው እንደምታስታውሰው በተለይ “ፌድራል ጉዳዮች” የሚባል የመንግስት አካል የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን በሌላ ሙስሊም ለማስጠመቅ ሙከራ አደረገ፡፡ “አልሀበሽ” የሚባል ገንዘብ አውጥቶ ይሄን ተማሩት አለ፡፡ እያንዳንዱ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሙስሊም በዚህ ውስጥ እንዲጠመቅ ሙከራ አደረገ፡፡ ሙስሊሞች ተቃወሙት ፣ ሃረር ላይ ….. ሚኒስትሩ ሣይቀር ስብሰባ አደረገ፡፡ ይሄ ጣልቃ ገብነት ነው፡፡ …. አንድን ኃይማኖት በሌላ ኃይማኖት በዚህ እመን ማለት ጣልቃ ገብነት ነው፡፡ ያለጥርጥር ነገሩ ከዚህ ተነሣ ከዛ የአወሊያ ትምህርት ቤትም ተነሣ ይሄ የቆየ ነው፡፡ ድሮ የነበረ ትምህርት ቤት ነው፡፡ ያንን ለመቆጣጠር ሞከረ፣ ያም አይሆንም የሚል ምላሽ ቀረበ፡፡

እንደገና የምርጫ ጉዳይ ተነሣ፡፡ ቀላል ጥያቄ በጣም ቀላል …. ምርጫው በመስኪዶች ይሁን የሚል፡፡ ይሄ ሁሉ ኢህአዴግ የማያዝበት መንገድ ግን ሽንፈት ነው የሚመስለው፡፡ አንዳንዶቹን ጥያቄዎች መመለስ ሽንፈት ስለሚመስለው ነገሩን ያጦዘዋል፡፡ ወደ አስቸጋሪ ሁኔታ ይገፋዋል፡፡ የኢትዮጵያን ሙስሊሞች እንደማውቃቸው በመሠረቱ በጣም ተቻችለው በመኖር ተግባብተው በመኖር የሚታወቁ ሙስሊሞች ናቸው፡፡ የሱፊ እምነት ፣ ካተሚያ እምነት በኢትዮጵያ ያለው ተቻችሎ የኖረና የሚኖር ሙስሊም ነው፡፡ ያም ሆኖ ግን ልክ በክርስቲያኑ ውስጥ እንደሚታየው ድሮ የሚታወቁት ኦርቶዶክስ፣ ካቶሊክ አልፎ አልፎ የድሮ ፕሮቴስታንቶች ይታወቁ ነበር፡፡ በኋላ ላይ ግን ጴንጤዎች መጡ፣ ሌሎችም መጡ፣ ጆባ መጣ ይሄ በነበረው አይን ሲታይ ፅንፈኛ ነው እና ክርስቲያኑ ሁሉ ያኔ ተደናገጠ ግን ሊያቆመው አይችልም፡፡ ከአለም ጋር ይገናኛል፡፡ ሕዝቡ ብዙ ብዙ እምነቶች አሉ ተቀብሎ ያምናል፡፡ በሙስሊምም የሚሆነው ይሄ ነው፡፡ ዋህቢያ መጣ፣ ሳላፊ መጣ ሌሎችም ሌሎችም ሺሀ ሊነሳ ይችላል፡፡ ይሄ እንግዲህ መንግስትም ይሁን ማንም ሊያቆመው አይችልም ይሄንን ዝንባሌ፡፡ መንግስት ማድረግ ያለበት እነዚህ አስተያየቶች፣ እነዚህ መስመሮች፣ ከህገ መንግስቱ ወጥተው፣ ሰላም እንዲኖር፣ መረጋጋት እንዳይጠፋ መቆጣጠር እንጂ ከዛ ባለፈ ይሄ እምነት ነው ትክክለኛ ይሄ ደግሞ ትክክለኛ አይደለም ብሎ መናገር መብቱ አይደለም፡፡

ማስተማርም የለበትም፡፡ ግን ኢህአዴግ ትንሹን ነገር አግዝፎ ስለሚያየው ነው፡፡ ኢህአዴግ መንግስት ሆኖ ከግለሰብ ጋር እየተጣላ የሚውል መንግስት ነው፡፡ በጣም ነው የሚያሣዝነው፡፡ አይንቀውም ትንሽ ነገር ነው እቆጣጠረዋለሁ ብሎ አያምንም፡፡ ሰራዊትይዞ ፣ ስፍር ቁጥር የሌለው ፌድራል ፖሊስ ፣ የክልል ፖሊስ፣ የፀጥታ ኃይሎች ይዞ እያለ በሁለት ሦስት ሰዎች እየተሸበረ ነው ያለው፡፡ ኢህአዴግ ሽብር ነው ውስጡ ያለው፡፡ ስለዚህ በሙስሊሙ ይሄ ነገር ሲነሳ ይሸበራል፡፡ ሲሸበር ደግሞ ለዚህ ምላሽ የሚሰጠው በማተራመስ ነው እንጂ ነገሮችን ከስትራጄክ አንፃር አያያቸውም፡፡ ሰልፍ ያስወጣል፣ አገሪቱን በሙሉ በስብሰባ ያስወግዛል፣ በየቀበሌው ፣በየከተማው …. አውግዙ ይሄ መፍትሄ አይሆንም ፣ ሰልፍ ውጡ ይሄ ፕሮፖጋንዳ ነው፡፡ከፕሮፖጋንዳ በዘለለ ነው መታየት ያለበት፡፡ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ሲነሱ በስትራ ቴጂክ እንጂ በፕሮፖጋንዳ ሊፈቱ አይችሉም፡፡ ምን ማለቴ ነው የአባይ ጉዳይ ሲነሳ ያነሣነው ነገር ነበር፡፡ አባይን ስንነካ አንድ ስትራቴጂክ ጉዳይ ነው ለኛ …. ስትራቴጂክ ጉዳይ ስለሆነ በአንድ ፓርቲ ፣ በአንድ ክፍል ብቻ መፍትሄ የሚያመጣ አይደለም፡፡ መግባባት ያስፈልጋል፡፡ ተቃዋሚዎች ሁሉ ለዚህች ሀገር ኃላፊነት አለብን የሚሉ ተግባብተው መሄድ አለባቸው፡፡ ምክንያቱም ይሄንን ትልቅ ነገር ከነኩ በኋላ ተባብረው መስራት እንጂ የሚያስፈልገው እንዲሁ “አካኪ ዘራፍ” ብሎ ማሰናበት አይቻልም፡፡ የሙስሊም ጥያቄ ሲነሳ እኔ ኢህአዴግ እንደሚያየው አያስደነግጠኝም፡፡ ያን ያህል የሚያስደነግጥ ፣ የሚያስፈራ፣ የሚያሸብር ነገር የለም፡፡ መቆጣጠር የሚቻል ነው፡፡ ያም እሱ በሚያስበው ችግር ቢኖራም፣ እሱ ባወጣው የፕሮፖጋንዳ አቅጣጫ መመራት ሣይሆን ፣ እስቲ እንነጋገርበት ሙስሊሞችን ሲያነጋገር አንዱን ክፍል ብቻ ማነጋገር የለበትም፣ ሁሉንም አነጋግሮ መፍታት ይችላል፡፡ ከተቃዋሚዎችም ጋር ቢሆን መቶ በመቶ የሚቃወሙትንም ማነጋገር እንጂ የራሱን ደጋፊዎች ብቻ አንድ የዩንቨርስቲ ምሁር ማናገር ተገቢ አይደለም፡፡ ስለኔ ምን ይላል ብሎ የተለየ ሀሣብ ሊያገኝ ይችላል፡፡ ስለዚህ የሙስሊሙም ጥያቄ ከአጠቃላይ የዴሞክራሲና የሰብአዊ መብት ጋር ተያይዞ መታየት ያለበት ነው የሚመስለኝ፡፡

↧

Hiber Radio: በኑሮ ውድነቱ ሳቢያ የዓመት በዓል ገበያው ቀዝቅዟል

$
0
0

የህብር ሬዲዮ ዕሁድ ጳጉሜ 3 ቀን 2005 ፕሮግራም

እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሰዎ

በዓሉ የሰላምና የጤና እንዲሆን መልካም ምኞታችን ነው !

<...>

በሎስ አንጀለስ ዕንቁጣጣሽን አስመልክቶ የተከበረውን ዓመታዊ ፌስቲቫል አስመልክቶ ሊትል ኢትዮጵያ እንዲሰየም ጥረት ካደረጉት አምስት ሴቶች አንዱዋ ሜሮን አሀዱ ለህብር ከሰጠችው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ

>

አቶ ዳንኤል ተፈራ የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሃዝሬት/አዳማውን ሰልፍ አስመልክቶ ለህብር ከሰጡት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ።ለዲያስፖራው የአዲስ ዓመት መልክታቸውም ተካቷል።

ልዩ የበዓል መሰናዶ አካተናል

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

> አባ መላ በቬጋስ የአዲስ ድምጽ አገራዊ ጉባዔ ላይ ተገኝቶ ከሰጠው ማብራሪያ (የተወሰነውን አካተነዋል)

>

ዶ/ር ኤፍሬም መኮንን ከአትላንታ የበዓል አመጋገባችን መሰረት አድርገን አነጋግረናቸው ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)

(ሌሎችም ቃለ መጠይቆች አሉን)

ዜናዎቻችን

በኑሮ ውድነቱ ሳቢያ የበዓል ገበያው ቀዝቅዟል

ዶሮ 180 ብር፣በግ መካከለኛ 1500 ብር፣ በሬ ከ10 ሺህ እስከ 15 ሺህ ብር አንድ ዕንቁላል 2 ብር ከ70ሳንቲም ተሽጧል

አሜሪካ ሶሪያን ማጥቃቱዋ በኢትዮጵያ ንግድ ላይ ተጽዕኖ ይፈጥራል ተባለ

የኢንጂነር ሀይሉ ሻውል > የተሰኘው መጽሐፍ ነገ ለንባብ ይበቃል

የኢራን ዲፕሎማት ኦባማ ሲሪያን ካጠቁ አንዱዋን ልጃቸው ትታፈናለች ሲሉ አስጠነቀቁ

የኢትዮጵአው ዋልያ በሰሞኑ ድል የብራዚል ጉዞውን እያመቻቸ ነው

ሌሎችም ዜናዎች አሉን

↧
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live




Latest Images