Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

“ልጄ በምግብ እጥረት ምክንያት ታሟል”የሦስት ዓመት ልጅ የታቀፈች እናት | VOA

$
0
0

(VOA Amharic) በኢትዮጵያ በተከሰተው ድርቅ ዋና ተጠቂዎች ሕናት በመሆናቸው፤ከስድስት ሚሊዮን በላይ ሕጻናት ለምግብ እጥረት፣ለበሽታና ለትምህርት መስተጓጎል ተጋልጠዋል። የአሜሪካድምጽ ዘጋቢ ማርታ ቫን ደርዎልፍ በድርቁ ምክንያት የተጎዱና አሁን በሚሰጣቸው ሰብአዊ ርዳታ የሚተዳደሩ ሰዎች የሚኖሩበት መተሐራ አካባቢ ተዘዋውራ ያጠናቀረችውን ዘገባ ጽዮን ግርማ ታቀርበዋልች።

mom
ዋሽንግተን ዲሲ — በኢትዮጵያ በተከሰተው አስከፊ ድርቅ ምክንያት ወደ 10 ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ አስቸኳይ የምግብ ርዳታ ይፈልጋል። ከእነዚህ ውስጥም ሕፃናት በከፍተኛ ሁኔታ በምግብ እጥረት ተጠቅተዋል።

በሪቲ ሃዋስ ትባላለች የሦስት ዓመት ልጇ በምግብ እጥረት በመጎዳቱ ታሞ ሆስፒታል ተኝቷል።”ምንም የሚበላ ምግብ ስለሌለን ልጄ ታሞብኛል።” ትላለች የሦስት ዓመት ልጇን እንደታቀፈች።

ልጆች ትምሕርት ቤት መሄድ አቁመዋል። እቤት ውስጥ ቁጭ ብለው በድርቁ ምክንያት ከብቶቻቸው ያለቁባቸው ቤተሰቦቻቸውን ይረዳሉ። የኢትዮጵያ መንግሥት በተለይ ከድርቁ ጋር በተያያዘ ለረሃብ የተጋለጡትን ሕፃናት ለመታደግ ረደኤት ከሚሰጡ ድርጅቶች ጋር እየሠራ መሆኑን ይናገራል።

የሕፃናት መርጃ በጎ አድራጎት ድርጅት ሠራተኛ ሳሙኤል ተፈራ ሕፃናቱ በምግብ እጥረት ምክንያት ለበሽታ እንደሚጋለጡ ይነገራል።

“የተመጣጠነ ምግብ እጥረትና ረሃብ በሚከሰትበት ጊዜ የሕፃናቱ የአዕምሮ ዕድገት ይቀንሳል። የማሰብ ብቃታቸው ዝቅተኛ ይሆናል እንዲሁም ለበሽታ ይጋለጣሉ።” ይላል ሳሙኤል ተፈራ።

እስካሁን ከ800 ሚሊዮን ዶላር በላይ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ተገኝቷል። ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግሥትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 1.4 ሚሊዮን ዶላር ለዚህ ዓመት ያስፈልጋል ብለዋል። ይህ ገንዘብ የሚያስፈልገውም ምግብ ለማቅረብ እንደሆነ ታውቋል።

“በድርቁ ምክንያት መንግስት ከሚሰጠን ርዳታ ውጪ ምንም የሚላስና የሚቀመስ ነገር አጥተናል። በቤታችን ውስጥ ምንም የለም። ልጆቻችንን የምናበላው ምንም ነገር የለንም፡፡ የምንጠጣው ውሃም የለንም”

የአሜሪካ ድምጽ ዘጋቢ ማርታ ቫን ደርዎልፍ በድርቁ ምክንያት የተጎዱና አሁን በሚሰጣቸው ሰብአዊ ርዳታ የሚተዳደሩ ሰዎች የሚኖሩበት መተሐራ አካባቢ ተዘዋውራ ያጠናቀረችውን ዘገባ ጽዮን ግርማ ታቀርበዋልች።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ።


ኃይለማርያም ደሳለኝ ለህክምና ጀርመን ገቡ

$
0
0

Hailemariam Desalegn

(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር ኃይለማርያም ደሳለኝ ለህክምና ጀርመን መግባታቸው ተሰማ:: በጀርመን ግራንድ ደቺ ባደን ከተማ ውስጥ መኖሪያ ቤት ገዝተው እንዳስቀመጡ የሚነገርላቸው ኃይለማርያም ከኢትዮጵያ የወጡት ለ እረፍትና ለህክምና በሚል በግል አውሮፕላን በመከራየት ነው::

ጠቅላይ ሚኒስተሩ በጀርመን ቆይታቸው ዓይናቸው አካባቢ ቀዶ ጥገና (Aesthetic surgery) በማድረግ ፊታቸውን በፕላስቲክ ሰርጀሪ ያስተካክላሉ ተብሏል:: እንደ ዜና ምንጮች ገለጻ በታዋቂ የዓይን እና የፕላስቲክ ቀዶ ጥገና ሃኪሞች ክሊኒክ ውስጥ ዓይናቸውን እና ፊታቸውን ውበት እንደሚያሰሩ ገልጸዋል::

ሁለት ሚሊዮን ሕዝብ የሚኖርባት ባደን ከተማ ሃብታሞች የሚኖሩባት ከተማ ስትሆን ቤትና ንብረት በዚህ ከተማ ለማፍራት በጣም ሃብታም መሆን ቢያስፈልግም ሃይለማርያም ግን በዚህ ከተማ ውስጥ የቤት ባለቤት ናቸው::

ከአውሮፓ ኢትዮጵያ ኑሮውን ለማድረግ የገባው ወጣት በሳንጃ ተወግቶ ተገደለ

$
0
0

በፈትያ አንዋር
ዓመት በዓል ከመድረሱ ሳምንት በፊት ጀምሮ የተለያዩ ውክቢያዎች፣ ፈንጠዚያዎች እንዲሁም ደስታና ሳቅ፣ በሌላ ጎኑ ደግሞ ሀዘንም ሊኖር እንደሚችል እሙን ነው፡፡

haba
ባሳለፍነው የፋሲካ በዓል ዋዜማም በጣም አስደንጋጭ ነገር ተፈጥሯል፡፡ መቼም ሰው ነንና በበዓል ዋዜማ ደስታችንን ለመግለፅ ወደተለያዩ መዝናኛ ቦታዎች ማምራታችን የማይቀር ነው፡፡ በዋዜማው በአዲስ አበባ መብራት ሀይል ኮንዶሚኒየም ውስጥ ሁለት የዛው አካባቢው ነዋሪዎች ሊዝናኑ በወጡበት ባልታሰበ ፀብ በሳንጃ የአንደኛው ሰው ሕይወት ሲያልፍ ሌላኛው ደግሞ ሳንባው ተወግቶ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በህክምንና ላይ ይገኛል ፡፡


የሟች ስም ለይኩን እሸቱ(ራስ ይኩኖ) ሲሆን እድሜው 35 ነው፡፡ ከወራት በፊት ከአውሮፓ ኑሮውን ትውልድ ሀገሩ ላይ ለማድረግ ነበር የመጣው ፡፡ የእሱ ጓደኛ ዳንኤል ንጉሴ ሲሆን እድሜው 36 ነው፡፡ በግል ስራ የሚተዳደር ነበር፡፡ በግድያው የተጠረጠሩት አምስት ግለሰቦች ደግሞ በፖሊስ እየተፈለጉ ሲሆን የሟች ለይኩን ስርአተ ቀብር በፋሲካ ዕለት ከተፈፀመ በኋላ ቀብርተኛው በቀጥታ ጎተራ ፔፕሲ አካባቢ ወደሚገኘው ፓሊስ ጣቢያ በማምራት ፖሊስ ተጠርጣሪዎችን በአስቸኳይ እንዲዝ ጠይቋል ።


የፀቡ መነሻ እንደ እንደ ሰማነው የተጎጂ ኮፋያ በጎጂዎች መወሰዱ እና ሟች ለምን ትወስዳላችሁ በማለቱ በተነሳ አምባጓሮ ነበር።የፀቡ መነሻ ምንም እንኳ አጥጋቢ ባይሆንም ለአንዳንድ ግብዞች ግን ከበቂ በላይ ነው፡፡ 


ከላይ የምትመለከቱት የሟች ለይኩን እሸቱ(ራስ ይኩኖ) ፎቶ ነው ።

ዶላሩ ስድስት ነው ግን …(እስረኞችን በተመለከተ) –ግርማ ካሳ

$
0
0

13087831_10209092917670839_7103252007685623458_nኢትዮጵያ ዉስጥ ለአገርና ለህዝብ ብለው ትልቅ ዋጋ እየከፈሉ ያሉ ወገኖቻችን እጅግ በጣም ብዙ ናቸው። ለምሳሌ ሁለት እስረኞች አሉ፤ ቤተሰቦቻቸው የአንዱ በአርባ ምንጭ የሌላው ደግሞ በሰሜን ጎንደር ነው የሚኖሩ። አንዱ የሰማያዊ፣ ሌላው ደግሞ የአንድነት አባል የነበሩ ናቸው። አምስት ልጆች አሏቸው። ሚስቶቻቸው ሥራ አይሰሩም።

እነዚህ ወገኖች የታሰሩት ወንጀል ሰርተው አይደለም። የታሰሩት ለሕዝብ ብለው ነው እንጂ። በማእከላዊ፣ በቂሊንጦ ..በመሳሰሉ ወህኒ ቤቶች ሲሰቃዩ ከጎናቸው ማን እንደቆመ፣ ልጆቻቸውን ማን እንደደገፈ እግዚአብሄር ነው የሚያውቀው።

የፖለቲካ መሪዎች ከመታሰራቸው በፊት እና ታስረው ከተፈቱ በኋላ “ሆይ ሆይ” የምንል ብዙ ነን። ግን እሥር ቤት እያሉ የሚያስባቸው ሰው ፣ ከጎናቸው የሚቆምሙ ግን በጣም ጥቂቶች ናቸው ።

የሚታወቁ የሕሊና እስረኞች ብዙ ጊዜ ስማቸው ይጠራል፤ ግን ለትግሉ ዋጋ የከፈሉ ተረስተው የሚማቅቁ ፣ ያልተዘመረላቸው እስረኞች ግን እጅግ በጣም ብዙ ናቸው።ስለ ተመስገን ደሳለኝ፤ ስለ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ ስለ አብርሃ ደስታ ..ብዙ ይጻፋል። ግን ማን ነው እስቲ ስለ አስቴር ስዩም፣ ስለ እንግዳው ዋኘዉ፣ ስለ በላቸው አወቀ፣ ስለ ሉሉ መለሰ …. የሚያውቀዉና የሚጽፈው ?

አያችሁ ወገኖች፣ በትግል ዉስጥ ከጎናችን የወደቁትን እየረሳን ፣ የታሰሩትን እየረሳን፣ የሚደረግ ትግል የዉሸት ትግል ነው። ታጋዮች ሰልፍ ሲመሩ ማድነቅ ብቻ አይደለም፤ ታጋዮች ለትግሉ ከፊት ፊት ሲቀድሙ ማድነቅ ብቻ አይደለም። ታጋዮች ሲታሰሩ ከጎናቸው መቆም ያስፈልጋል። ትግሉ የትም ሊደርስ ያልቻለው ፣ አሁንም ትግሉ ድንክ ሆኖ የቀረው ጀግኖቻችንን አሳሰረን፣ ዝም የምንል አደርባዮች በመሆናችን ነው። ራስ ወዳዶች፣ ፈሪዎች በመሆናችን ነው። ሌላው ሞቶ በሌላ ሬሳ ላይ ተረማምደን እንዲያልፍልን የምንፈለግ ደካሞች በመሆናችን ነው …..በጣም በጣም ነው የምናዛዝነው።

ይህን ስጽፍ በየጊዜው እስረኞችን ሄዳችሁ የምትጠየቁ፣ የእስረኞች ቤተሰቦችን በገንዘብ የምትደገፉ፣ ቤተሰቦችን የምታበረታቱ ፣ የእስረኞች ሁኔታ እየተከታተላችሁ ለሕዝብ የምታቀርቡ እንዳላችሁ አውቃለሁ። እናንተን እግዚአብሄር ያክብራችሁ። ትልቅ ሰዎች ናችሁ። ግን እናንተ ከባድሊ በማንኪያ እንደሚቀዳ ዉሃ ናችሁ። ከሚሊዮኖች መካከል እጅግ በጣም ጥቂቶች ናችሁ። አብዛኞቻችን እናንተ እያደረጋችሁት ያለዉን ጥቂቷን ጥረት ብናደርግና የድርሻችንን ለመወጣት ትንሽ መነሳሳት በዉስጣችን ቢኖር፣ ይሄን ጊዜ የትናየት በደረሰን ነበር። እኛ ግፍ ሲሰራ ዝም ባንል ኖሮ ወያኔዎች አይቀልዱብንም ነበር። ኢሰብአዊ የሆነ ግፋቸው ማስቆም እንችል ነበር።

ወገኖች መሰረታዊ የአስተሳሰብ ለዉጦች ያስፈልጋሉ። ፕራዮሪታችንን በጣም ማስተካከል አለብን። ይሄ ዝባዝንኪ ፣ ወሬ ብቻ የሆነ የፖለቲካ ስብሰባዎች፣ ዉይይቶች ላይ ጊዜና ገንዘብ ማጥፋት የለብንም። አንዱ ደርጅት ይነሳና ስብሰባ ይጠራል፤ ሌላው ድርጅቶ ደግሞ ይነሳና ሌላ ስብስባ ይጠራል። በቃል ወሬ ብቻ !!!!!! ኤዲያ…..

ያ መቆም አለበት።፡ ፈረንጆች እንደሚሉት we have to go to the drawing board.

በዚህ አጋጣሚ ማመስገን የምፈልጋቸው አካላት አሉ። ወንድም ሃብታሙ አያሌው እስር ቤት እያለ በተለይም በማእከላዊ የደረሰበትን ሁላችንም የምናወቀው ነው። ከዚያም የተነሳ ከፍተኛ ሕመም ሸምቶ በስቃይ ላይ ነው የሚገኘው። ሃብታሙ ሕክምና ያገኝ ዘንድ ፣ የገንዘብ ማሰባሰብ ሂደት እየተደረገ ነው። ወደ 256 የሚሆኑ ኢትዮጵያዉያን ተባብረዋል። የቃሌ ፕላቶክ ክፍል ፣ የአዲስ ድምጽ ራዲዮ እና የ ሳተናእ ድህረ ገጽ (satenaw.com) በዚህ ዙሪያ ላሳዩት እጅግ በጣም የሚያኮራ ኢትዮጵያዊ ሥራ በጣም ላመሰግናቸው እና አድናቆቴን ልግልጽላቸው እወዳለሁ።

ሌላ ልቤን በጣም የነካው ነገር አለ። ከ256 ሰዎች መካከል ስድስት ዶላር ያዋጡ ነበሩ። ስድስት ዶላር …!!! ሰው የአቅሙን ነው። የዶላሩ ማነስ መጠን አይደለም። ግን ትንሽ ብትምስልም፣ የድርሻን ለማበርከት መነሳቱ በራሱ ትልቅነት ነው። ስድስት ዶላር ምን ታደርጋለች ተብሎ ምንም አለማድረግ ይቻል ነበር። የኔ ደርሻም ለዉጥ አያመጣም ብለን ተስፋ ቆርጦ ዝም ማለት ይቻል ነበር። ግን ስድስት ዶላር ከሌሎች ጋር ተደምራ ነው ሺሆች የደረሰችው፡ እኛ ሚሊዮኖች ነን። ጥቂቶች ብዙ መስዋኣትነት ከፍለው ለዉጥ እንዲያመጡ ከምንጠብቅ፣ ትንሽም ትሁን የድርሻችንን ለማበርከት እያንዳንዳችን ብንነሳ ተዓምር እንሰራ ነበር።

ቴዎድሮስ ካሳሁን ገርማሜ |በመስፍን ወልደማርያም አርኣያ

$
0
0

Mesfin

አሁን አሁን ይሕ የፌስ ቡክ ዥዋዥዌ ግልፍታዊ፣ ወቅታዊ፣ በብዛት እየሰማን ነው፤ /”ጤዛዊነት” ብንለው የተሻለ ሳይገልጸው አይቀርም- ጤዛዊነት የትውልድ ደዌ ነው!!
ከጋምቤላ እልቂት ወደ አንድ ግለሰብ ጡዘት ይሕንን ያክል የሚያሸጋግር ወጀብ መኖሩ ሳያስደንቀን አይቀርም፡፡
ይሕንን በማሰብ አለባቸው ተካ ጋር ያደረገውን ቃለ ምልልስ ለመመልከት እና የልጁን የብዙሃን አውታር (ምሕዋር) /ሚዲያ ላለማለት ነው/ ለመመልከት ወደ ዩቱብ ውቅያኖስ መግባት ነበረብኝ፡፡ የዚህ ልጅ ብዙ ወጀብ የበዛበት ምክንያቱ ምን ይሆን? በሚል ሐሳብ መጠነኛ ምልከታ ለማድረግ ጣርሁ፡፡
“ቴዎድሮሰ ካሳሁን ዊዝ አለቤ ሾ” የሚል ጽሑፍ ስጠይቀው በርካታ አማራጮችን አመጣልኝ፤ በደቡብ አፍሪቃ ያደረገውን አጭር ቃለምልለስ (የኢትዮጵያን የእግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ለመደገፍ የሄደበትን)፣ ከዚያም ወደ ኋላ ተመልሶ የፖሊስ እና ሕብረተሰቡ ጋዜጠኛ ከኃይሌ ገብረ ሥላሴ ጋር ያደረገውን ቃለ ምልልስ-1994 ዓ.ም በ97 ፣ ከዚያም በአሜሪካን አገር፣ ከዚያም “ካሳ ሾው” የሚባል ከበርካታ ዓመታት የቃለምልስ እድል በኋላ “ኢቢኤስ” ባለውለታ ሆኖ መቅረቡን፤ ከዚያም በድጋሜ “ኢቢኤስ” የፋሲካ በዓል ላይ ክብር እንግዳ ማድረጉን፤ አሁንም ለዚህ ሁሉ ወጀብ የሆነውን የፋሲካ በዓል በድጋሜ የተቀረጸ ወደ መድረክ ሥራ ያዳርሰናል፡፡(በዚህ ላይ በጣይቱ ሆቴል የጥቁር ሰው ትዕይንት ምረቃ ላይ ተመስገን ደሳለኝን ስመለከት ለነዚህና መሠል ሰዎች መዝፈኑ ይቀር ይሆን ማለቴ አልቀረም…)
በዚህ ሁሉ የቃለ መጠይቅ ሂደት ውስጥ ልጁ ከተለመደው የሙዚቀኞች ማንነት የተለየ መመሆኑን ከሚናገራቸው የአስተሳሰብ ልኬቶቹ መገመት አይከብድም፤ ሆኖም የዚህ ልጅ ብዙ ወጀብ የበዛበት ምክንያቱ ምን ይሆን? ወደሚለው ጥያቄ አዘነበልሁ፡፡ “ጥቁር ሰው”ን ምኒሊክን ብንወስድ የአብዛኛው ወጀብ ምክንያት መሆኑን እናስታውስና፤ በጥቁር ሰው ሙዚቃው ውስጥ “ምኒሊክ ሆይ ኦሮሞን ወላይታን ገደልክልኝ” ሲል እንዳልገጠመ፣ እንዳላሰበም ጭምር ማሰብ ከቻልን በኋላ፤ ‹‹አድዋ››ን ያሳየበት አቅጣጫ ብቻ ማየት እንችላለን፡፡ የአድዋ ጠላት ማን ነው? በማናቸውም መልኩ የኢትዮጵያ ጠላት ዓላማ ሊሆን እንደሚችል ተገንዝበን፤ የዚህ ልጅ ብዙ ወጀብ የበዛበት ምክንያቱ ምን ይሆን ብለን እንጠይቅ እና እንመካከር…
ተራ አሉባልታ እና ሥርዓት አልበኝነት በግድግዳው ላይ የመዋል አቅም አይኖረውም… በጨዋነት እስኪ ሐሳባችን እንመነዝር እና ወደ አንድ መዳረሻ እንሂድ… ጥያቄው ይደገም፡-
የዚህ ልጅ ብዙ ወጀብ የበዛበት ምክንያቱ ምን ይሆን?

የጣና ዳሩ ጉባኤ |በዘላለም ክብረት

$
0
0

 kofi-anan

(በሃገር ቤት ታትሞ ከወጣው ውይይት መጽሔት ላይ የተገኘ)

አምስተኛው የጣና መድረክ ሚያዝያ 8 እና 9፣ 2008 በባሕር ዳር ተካሒዷል። ዘላለም ክብረት መድረኩ የተቋቋመለትን ግብ ይመታል ወይ ሲል ይጠይቃል።

ቅዳሜ ሚያዚያ 08/2008 ባሕር ዳር ላይ በየዓመቱ የሚደረገው የጣና መድረክ (Tana Forum) አምስተኛውን ዙር ውይይት የጀመረ ሲሆን፤ ሁለት ቀናት በፈጀው ውይይት አፍሪካ በዓለም የፀጥታ ሁኔታ ላይ ሊኖራት ስለሚገባት ቦታ አፅንኦት ሰጥቶ ተነጋግሯል። ከአምስት ዓመታት በፊት በሚያዚያ 2004 በይፋ የተጀመረው የጣና መድረክ በየዓመቱ ከተለያዩ የአፍሪካ አገራት መሪዎችና ምሁራንን በማሰባሰብ በጣና ሐይቅ ዳር እየተካሄደ ያለ መድረክ ነው። በዘንድሮው አምስተኛው ጉባኤው ላይ ንግግር እንዲያደርጉ ከተጋበዙት ታላላቅ ስብዕናዎች መካከል ‹የፓናማ ፔፐርስ› እየተባለ እየተጠራ ባለው የሙስና ቅሌት ጋር በልጃቸው ምክንያት እየተብጠለጠሉ የሚገኙት የቀድሞው የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ ጋናዊው ኮፊ አናን አንዱ ናቸው። ኮፊ አናን በፎረሙ ላይ ተገኝተው ከእስከ አሁኑ የመድረኩ መንፈስ ለየት ባለ መልኩ ‹ሥልጣን ላይ ሙጭጭ ብለው የተቀመጡ የአፍሪካ መሪዎች የግጭቶች ዋነኛ መነሻ ምክንያቶች ናቸው። ሠላምና ደኅንነት ያለ የሕግ የበላይነትና የሰብኣዊ መብቶች መከበር ሊሳካ አይችልም› እና ‹በአፍሪካ ያለው ግጭትና የሠላም ማጣት ዋነኛው መነሻ የወጣቶች ሥራ አጥነት ነው› የሚል ጠንከር ያለ ንግግር አድርገው ነበር። አናን አያይዘውም ምርጫ በአፍሪካ ለደንቡ የሚደረግ ነገር መሆኑ ጣጣ ያለው መሆኑን የሕጋዊነትን (legality) እና ቅቡልነትን (legitimacy) ልዩነት በመግለጽ ለማስረዳት ሞክረዋል። አናን ይሄን ሲናገሩ የመድረኩ መሪ የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴድሮስ አድሃኖምና የመድረኩ ተጋባዥ ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከፊት ሆነው ያዳምጧቸው ነበር።

‹ከየካቲት ለሚያዚያ›

ላለፉት አምስት ዓመታት በሚያዚያ ወር መጀመሪያ ሲካሄድ የቆየው የጣና መድረክ በተጀመረበት ሚያዚያ 2004 ላይ ‹የመድረኩ ወላጅ አባት ናቸው› የሚባሉት ሟቹ መለስ ዜናዊ ስለ መድረኩ ያላቸውን ተስፋ ሲገልፁ ‹የእኔ ፍላጎትና ተስፋ እንግዲህ ይህ ተቋም እያደገና አየተመነደገ ሄዶ እኔ የማውቀውንና በዘርፉ ላይ አተኩሮ ዓመታዊ ውይይት የሚያደርገውን የሙኒክ ደኅንነት ኮንፈረንስ የሚቀናቀን፤ ብሎም የሚበልጥ ተቋም እናደርገዋለን የሚል ነው› በማለት ነበር የገለጹት። መድረኩ ሞዴል አድርጎ የተነሳው ከሃምሳ ዓመታት የሚልቅ ረጅም ዕድሜ ያስቆጠረውንና በየዓመቱ በየካቲት ወር ጉባኤ የሚያካሂደውን የሙኒክ የደኅንነት ኮንፈረንስ መሆኑን የመድረኩ አመራሮች በተለያዩ ጊዜ የገለፁ ሲሆን፤ አፍሪካን የትኩረት ማዕከል ያደረገ ተቋም ማቋቋምንም ዓላማ ብለው የያዙት መሆኑን ይገልጻሉ። ከዚህ ሁኔታ አንፃር መለስ ዜናዊ በወቅቱ ያደረጉት ንግግር ከሙኒክ የደኅንነት ኮንፈረንስ ጋር  የፉክክር መንፈስ የነበረው መሆኑ ትንሽ ግራ አጋቢ ነበር። ይህ ከሆነ ከአምስት ዓመታት በኋላ የመለስን የፉክክር ዓላማ ገሸሽ አድርጎ ዘንድሮ የሙኒክ የደኅንነት ኮንፈረንስም በየካቲት ወር ዋነኛ ጉባኤውን በሙኒክ ጀርመን ካደረገ በኋላ ንዑስ ጉባኤውን በያዝነው ሚያዚያ ወር በአዲስ አበባ ሲያደርግ፤ ጣና መድረክም ወደ ‹ጣና ፋውንዴሽን› ልቀየር ነው ብሏል።

የመድረኩ አፍሪካ ኅብረትነት

የአፍሪካ ኅብረት ከተመሠረተ ግማሽ ምዕተ ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ድርጅት ቢሆንም እስከ አሁን አጥብቆ እየተተቸበት የሚገኘው ጉዳይ የዴሞክራሲ ጉዳይ ነው። ዴሞክራሲ አህጉሪቱ መሥራት ያልቻለችው የቤት ሥራዋ ሆኖ፤ በተለያዩ ዓለማቀፍ መመዘኛዎች የአህጉሪቱ Cዴሞክራሲያዊነት አሁንም እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው። ጣና መድረክ የተመሠረትኩት ‹የአፍሪካ ኅብረት በትሪፖሊ በ2009 ባሳለፈው ‘Tripoli Declaration on elimination of Conflicts in Africa and the Promotion of Sustainable Peace’ መሠረት ነው› የሚል ሲሆን፤ ያነሳቸውን አጀንዳዎችና የስብሰባዎቹን መሪዎች ተመልክተን ‹ጣና መድረክ የአፍሪካ ኅብረት ተቀጥላ ነው እንዴ?› ብለን መጠየቃችን አይቀርም። የአህጉሪቱ ደኅንነትና ፀጥታ በዴሞክራሲያዊነቷ ላይ ተንጠልጥሎ ያለ ቢሆንም መድረኩ እስከ አሁን ድረስ ዴሞክራሲን የተመለከተ አጀንዳ ላይ በመሪነት ለመወያየት ብዙም ፍላጎት አላሳየም። ለዚህም ነው ለብዙ ሰዎች መድረኩ ኅብረቱን መስሎ መታየቱ።

‘Anglophile’ የልኂቃን ቤት

መድረኩ ከአምስት ዓመታት በፊት ሲመሠረት በአንዳንዶች ዘንድ የእንግሊዘኛ ተናጋሪ አገራትን ብቻ መሠረት ያደረገ ተቋም በመሆኑና ‹ከግማሽ በላይ ለሆኑት የአፍሪካ እንግሊዘኛ ተናጋሪ ላልሆኑት አገራት ትኩረት አይሰጥም፤ በተለይም ፈረንሳይኛ ተናጋሪ የሆኑትን አገራት ያገለለ ነው› የሚል ትችት ይሰነዘርበት ነበር። መድረኩ በሒደት ‹ባለ ሁለት ቋንቋ (እንግሊዘኛ እና ፈረንሳይኛ) ተቋም ነኝ› በማለት ይሄን አካሄድ ለማስተካከል ጥረት ማድረግ መጀመሩም የዚህ ትችት ውጤት ነው። ነገር ግን አሁንም ቢሆን ከእንግሊዝኛ ተናጋሪዎች ጋር የበዛ ፍቅር ያለው ተቋም መሆኑ አልቀረም። ከዚህም ባለፈ እንግሊዝኛ ተናጋሪ ጥቂት ልኂቃን ከአምባገነን አፍሪካዊያን መሪዎች ጋር በዓመት አንድ ጊዜ ለሁለት ቀናት ተሰብስበው ለአፍሪካ የሠላምና የደኅንነት ችግር መፍትሔ ማምጣታቸውን የሚጠራጠሩ ብዙዎች ናቸው።

የአፍሪካ ለአፍሪካዊያን ሐቲት

ምንም እንኳን የኋላ ረጅም ታሪክ ያለው ቢሆንም በደረጀ መልኩ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2007 በኢንተርናሸናል ሰኪዩሪቲ ስተዲስ (Institute of Security Studies – ISS) አማካኝነት በአጀንዳነት ብቅ ያለው የአፍሪካዊና መፍትሔዎች ለአፍሪካዊያን ችግሮች (African Solutions for African Problems – ASAP) ፅንሰ-ሐሳብ አሁን አሁን ከብዙ የአፍሪካ መሪዎች እንዲሁም ከአንዳንድ ምዕራባዊያን ለጋሾች አፍ የማይጠፋ ሐረግ ነው። ‹አፍሪካዊያን ያለማንም ጣልቃ ገብነት ለራሳቸው ችግሮች ራሳቸው የመፍትሔ አፍላቂዎች መሆን አለባቸው› የሚለውም ነው የሐሳቡ ግንዛቤ። ይህ ሐሳብ በብዙ መልኩ የሚወደሱ ነገሮች ያሉት ነው። ጣና መድረክም ከተነሳባቸው ዋነኛ ዓላማዎች አንዱ ‹ለአፍሪካ የፀጥታ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔዋች በራሳቸው በአፍሪካዊያን አመጣለሁ› የሚል አንደሆነ የፎረሙ ሊቀመንበር የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዘደንት የሆኑት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ በተደጋጋሚ ይገልጻሉ። ነገር ግን ይህ ‹አፍሪካዊያን ለአፍሪካዊያን ሐቲት (rethoric)› ከመልካም ጎኑ ባለፈ በውስጡ ከትችት መሸሽንና መሬት ላይ ሊወርድ የማይችል ነገር ማቀንቀን ነው የሚል ትችት ሲቀርብበት ይስተዋላል።

አፍሪካዊያን ለአፍሪካዊያን ይዞ የተነሳው ጣና መድረክም ትችቶች ማምለጫ መሆንን በማሰብ ‹ሮማንቲክ› የሆነውን የአፍሪካ ለአፍሪካዊያን ሰንደቅ እያስቀደመ፤ ነገር ግን በውጤቱ ለተርታው አፍሪካዊ ምንም ጥቅም አይሰጥም የሚለው  ሐሳብም ነው የትችቱ መደምደሚያ። ከዚህም ባለፈ ፎረሙ ‹አፍሪካዊያን ለአፍሪካዊያን› ቢልም የመድረኩ የድጋፍ ምንጮች የተለያዩ የአውሮፓ አገራትና የቻይና መንግሥት መሆናቸውን ስንመለከት የሐቲቱን እውነተኝነት አጠራጣሪነት እንረዳለን።

የመለስ ጥላ ያጠላበት መድረክ

ስለ ጣና መድረክ ተናግረው የማይጠግቡት ሊቀመንበር ኦባሳንጆ ስለመድረኩ አመሠራረት እና መግፍኤ ሲናገሩ ‹መለስ ይሄን መድረክ መመሥረት እንዳለብኝ ነገረኝ› ይላሉ። ከኦባሳንጆ ጋር በመሆን የመድረኩ መሥራች የሆነው የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የሠላምና ፀጥታ ኢንስቲቲውትም መለስ ይመሩት በነበረው መንግሥት ስር ለዚህ ዓይነት ጉዳዩች የተዘጋጀ ተቋም መሆኑን መረዳት ብዙም ከባድ አልነበረም። መድረኩ ከተመሠረተ በጥቂት ወራት በኋላ የሞቱት መለስ ግን ከሞታቸውም በኋላ ከመድረኩ ብዙም አልራቁም።

መድረኩ በየዓመቱ በተሰበሰበ ቁጥር ለመለስ ‹የሕሊና ፀሎት› ማድረጉን ከመቀጠሉም ባሻገር ‹የመለስ ዜናዊ ሌክቸር ሲሪየስ› በተባለው የጉባኤው ፕሮግራም አማካኝነት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መወያየቱን ቀጥሏል። እነዚህን ሁኔታዎች ስንመለከትም ‹መድረኩ መለስ ጋር ቆርቧል› ልንል እንችላለን። ለመለስ ተችዎች ይህ የተቋሙ ከመለስ ጋር መቆራኘት ተቋሙን በጥርጣሬ እንዲመለከቱት የሚያደርግ ሲሆን፤ ‹መድረኩ የኢትዮጵያ መንግሥት የፈለገውን አጀንዳ ወደፊት መግፋት እንዲችል የሚያግዝ የጭቆና መሣሪያ ነው› ወደሚል መደምደሚያ ላይ እንዲደርሱ የሚያደርግ ገፊ ምክንያት ሆኖ አግኝተውታል።

የመድረኩ ቀጣይ ፈተናና ተስፋ

የጣና መድረክ ለአምስት ዓመታት በመወያያ መድረክነት ቆይቶ ዘንድሮ ወደ ‹ጣና ፋውንዴሽንነት› ሊቀየር መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በአምስተኛው ጉባኤ ላይ አሳውቀዋል። መድረኩ ወደ ፋውንዴሽንነት ሲቀየር የአቋምም ሆነ የቅርፅ ለውጥ ያሳይ ይሆናል የሚለውም የብዙዎች ግምት ነው። ነገር ግን ‹መድረክም› ሆነ ‹ፋውንዴሽን› ራሱን ከላይ ከተጠቀሱት ትችቶች ካላላቀቀ እና ነጻ ተቋም መሆኑን በተግባር እስካላወጀ ድረስ መሬት ላይ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ጥናቶችንም ሆነ ውይይቶችን ማድረጉ አጠራጣሪ ነው።

በሌላ በኩል ከዚህ ተቋማዊ ፈተና ባለፈ በመግቢያችን የጠቀስናቸው ኮፊ አናን በመድረኩ ላይ ተገኝተው ‹ሥልጣን ላይ ሙጭጭ ብለው የተቀመጡ የአፍሪካ መሪዎች የግጭቶች ዋነኛ መነሻ ምክንያቶች ናቸው። ሠላምና ደኅንነት ያለ ሕግ የበላይነትና የሰብኣዊ መብቶች መከበር ሊሳካ አይችልም […] ምርጫ ማካሔድ ማለት ተቀባይነት ማግኝት ማለት አይደለም› እያሉ ሲናገሩ ከፊት ቁጭ ብለው የሚሰሟቸው አፍሪካዊያን መሪዎች እና ሹማምንቶች ይሄን ንግግር ከምንም ሳይቆጥሩትና እና ሳይጎረብጣቸው ራሳቸው በመድረኩ ላይ ወጥተው ‹ለአፍሪካ ፀጥታ መፍትሔ ሐሳብ አለኝ› ቢሉ ሐሳባቸውን መስማት ጊዜ ከመግደል ያለፈ ጥቅም አይሰጥም፤ መድረኩም የጥቂቶች ዓመታዊ የፌሽታ ድግስ ከመሆን አያልፍም።

Source: ውይይት መጽሔት

የኢትዮጵያ ወይንስ የትግራይ አየር መንገድ? |ይሄይስ አእምሮ

$
0
0

የ2008ን የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ አንድ የኢትዮጵያ ይሁን የትግራይ ውሉ ባልታወቀ አየር መንገድ ውስጥ የሚሠራ ሰው በቤቱ ምሣ ጋበዘኝ፡፡ ተራ ጎረቤቱ እንጂ የሰማሁትን በሆዴ የማላሳድር ወሬ አራጋቢ መሆኔን አያውቅም፡፡ በሀገር ተቆርቋሪነት ስሜት በቀድሞው አጠራር ስለኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁኑ ደግሞ ስለ”ትግራይ አየር መንገድ” እየተንገፈገፈ ሲናገር እንደማንኛውም ተጋባዥ አደመጥኩ፡፡ የምፈልገውን ወሬ ከጨበጥኩ በኋላ የተከፈተልኝን ቢራ እንኳን በቅጡ ሳልጨርስ ወደቤቴ አመራሁ –  እንደልማዴ ልጫጭር፡፡ ኢትዮጵያዊ የሆንክና አሁን የምነግርህን ከአሁን በፊት ያልሰማህ ሁሉ ይህን የወያኔዎች ቅሌት ልብ ብለህ ስማ! ኢትዮጵያ ዳግመኛ እንዳታንሠራራ ሆና በወያኔ መዶሻ እየተቀጠቀጠች መሆንዋንም አስተውል፤ ልጆችህ ሀገር አለን ብለው የማይኮሩባት አዲስ ኢትዮጵያ መፈጠሯንም ተገንዘብ፤ በተበተንክበት የስደት ዓለም ጠፍተህ እንድትቀር የተፈረደብህ ተስፋቢስ ትውልድ መሆንህን አትርሣ፡፡ ስለአየር መንገዱ የሚነገረው በባሰ ሁኔታ በሌሎች ላይ የሚሠራበት ወያኔያዊ አሠራር ነው – ለ25 ዓመታት የተሠራበት፡፡ በዚህ ተቋም እንዲህ የተሠራ በሌላው ምን ሊያቅታቸው?

Ethiopian Airline

ባለፈው ሰሞን አየር መንገዱ 27 ሆስተሶችን (የሴት አስተናጋጆችን)  አስመርቋል፡፡ በሚያስገርም ሁኔታ ሃያ ሰባቱም ትግሬዎች ናቸው፡፡ አዲስ አበባን የማያውቁና ብዙዎቹ አዲስ አበባ ውስጥ ቤተሰብ የሌላቸው ፍጹም ባላገር ሴቶች ናቸው፡፡ የተቀጠሩት ሁሉም ከትግራይ ምድር ነው፡፡ ለመሃላ እንኳን አንድም የሌላ ዘውግ አልተቀላቀለባቸውም – ቴክኒሻንና አብራሪም ሲመለመል እንዲሁ ነው፡፡ ከነዚህ ሆስተሶች ብዙዎቹ ዐማርኛ ቋንቋ አይችሉም፤ እርግጥ ነው – ከልጅነት እስከ ዕውቀት ዘመናቸው ዐማርኛ ከሚወገዝበት ክልል ተወልደውና አድገው የመጡ ወጣቶች በመሆናቸው በነሱ አይፈረድም፡፡ ነገር ግን የአየር መንገዱ አንደኛው የሥራ ቋንቋ የሆነውን ዐማርኛን ባለመቻላቸው ችግር እየፈጠሩ ይገኛሉ – ማኅበራዊነት (ሶሻላይዜሽን) ስለሚጎድላቸው ደግሞ ከሌሎች ሠራተኞች ጋር በቀላሉ መግባባት ካለመቻላቸውም በተጓዳኝ ቋንቋ አለመቻላቸው ሥራቸው ላይ ትልቅ አሉታዊ ጫና እየፈጠረባቸው ነው፡፡  አንድ ተጨባጭ ምሣሌ እንይ፡፡ በውነቱ ሕወሓት የትግራይ ሕዝብ በቀጣይ ታሪኩ እጅጉን የሚያፍርባቸው ብዙ ሰቅጣጭ ተግባራትን እየፈጸመ ነው፡፡ ስለወያኔ ትግሬዎች ሁላችንም ማፈር አለብን፡፡ ሃያ ሰባቱም ትግሬ? ውይ …ው ይ….ውይ…

ባለፈው አንድ ጊዜ ወደ አፋር ዋና ከተማ ወደ ሠመራ አንድ የሀገር ውስጥ በረራ ነበር፡፡ አንዷ ዐማርኛ እንደቁመት ያጠራት አስተናጋጅ ትግሬ “ህጅ አሥመራ ስለተቃሪብና ለቀቦቷቹ አጣብቁት” በማለት ለተሣፋሪዎች ማስታወቂያ በመናገሯ ተሣፋሪዎች አውሮፕላኑ ተጠልፎ አሥመራ ገብቶ ነው በሚል ተደናግጠው ክው ይላሉ፡፡ በኋላ ግን የቋንቋ ችግር መሆኑ ተነግሯቸው አሥመራ ሣይሆን ሠመራ እንደደረሱ ተገልጾ ይቅርታ ተጠይቀዋል – ተሣፋሪዎች፡፡ ሀሰት እንዳይመስልህ ሁሉም የአየር መንገዱ ሠራተኛ ሰምቶ የሚያላግጥበት እውነተኛ ታሪክ ነው፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ራሱ “የትግሬ” ወይም በተወራራሽ የቃላት አጠቃቀም “የትግራይ አየር መንገድ” ነው የሚባለው፡፡ በዚህ ዓይነት መንገድ በኢትዮጵያ ውስጥ ትግሬነትን አስጠልተውት እንዳይቀሩ እፈራለሁ – ከአሁኑ አንዳንድ ሁኔታዎች ተነስቼ እንደምታዘበው ይህን ጉዳይ በሚመለከት ችግር የለም ብሎ ራስን ማታለል የዋህነትና ከኃላፊነትም የመሸሽ ዝንባሌ ይመስለኛል፡፡ ብዙ ነገር መሠራት ሊኖርበት ነው – እንዴ? አያያዛቸው በጣም ያሣፍራል እኮ!

ከ27 አስተናጋጅ አንድ ሰባት ያህል እንኳን ለማስመሰል ከሌላው ብሔር ቢቀላቀል ምን ነበረበት? ይህን ምን ይሉታል? ምን ዓይነት መታወር ነው? ጭንቅላታቸው ውስጥ ጭቃ ነው ንፍጥ የታጎረው? የምትቀርቧቸው በተለይም ጤናማ ነን የምትሉ ትግርኛ ተናጋሪ  የሆናችሁ የትግራይ ልጆች እስኪ ጠይቋቸው፡፡ ከሰው አይደለም ከእንስሳም እንዲህ ዓይነት ድንቁርና አይጠበቅም፡፡ በስመ አብ!

በሌላ ቦታ በዐይኔ በብረቱ ያየሁትን ነገር ሳልረሳው ጣልቃ ላስገባ መሰለኝ፡፡ ቦታው ሲቭል ሰርቪስ ዩንቨርስቲ የሚባለው ድንጋይ ማምረቻ የትምህርትና የ“ኢንዶክትሪኔሽን”ማዕከል ነው፡፡ ከአንድ የመንግሥት ተብዬ መሥሪያ ቤት በስኮላርሽፕ ወደዚህ ማዕከል የተላኩ ሰዎች ስም ዝርዝር ተለጥፎ አየሁና ማንበብ ጀመርኩ፡፡ አንብቤ ስጨረስ ደነገጥኩ፡፡ ከተኮለኮለው ወደ ሃያ የሚጠጋ የስም ዝርዝር ውስጥ አንድም ዐማራ ዜጋ የለም፡፡ ሦስት ይሁኑ አራት ገደማ የደቡብና የኦሮሞ ስሞች አሉ – ቀሪው በሙሉ ከሐጎስና ከአብረኸት ውጪ ሌላ የለም፡፡ አዘንኩላቸው፤ አንዳንዴም አእምሮው በዘረኝነት ልምሻ፣ በጠባብነት ምችና በድንቁርና መብረቅ ለተመታ ሰውም ማዘን መጥፎ አይደለም – “እንደነዚህ አታድርገኝ” ብሎ መጸለይ ከተመሣሣይ የአስተሳሰብ መካንነትና የአመለካከት ድውይነት ይሠውራል፡፡ ረጋ ብለው ሲያስቡት እነዚህ ወንድሞቻችን የገቡበት የዘረኝነት አዘቅት ከመለኮታዊ መቅሰፍት የማይተናነስና በቁም ነፍስ ይማር የሚያሰኝ ትልቅ አደጋ ነው፡፡ እናም ለነሱም እንዘን፡፡

የአየር መንገዱ ዘበኛና ሴኪዩሪቲ ሁሉ ከትግራይ ነው የሚቀጠረው – ሁሉም የአየር መንገዱ የሥራ ዘርፍ  ሙሉ በሙሉ በትግሬ ሊሸፈን የቀረው ጥቂት ጊዜ ነው – ጥረቱም በስፋትና በጥልቀት ቀጥሏል፡፡ የመለስን ራዕይ እውን ለማድረግ የአየር መንገዱ የትግሬዎች የማኔጅመንት አካል ሌት ከቀን እየደከመ ነው፡፡ ጥቂት ወታደሮች ከጋምቤላ ተቀጥረው የብሔር ተዋፅዖ ያለ ለማስመሰል ይሞክራሉ እንጂ ሌላው ሁሉ ከትግራይ ነው የሚመጣው፤ እነዚህ ወታደሮችም አዲስ አበባንና የትግሬውን አገዛዝ መላመድ ስለሚቸግራቸው በየጊዜው ይጠፋሉ፡፡ እግዚኦ የሚያስብል ዘመን ውስጥ እንገኛለን፡፡ የሚገርመው ደግሞ ሌላው ዜጋ ሁሉ ለነዚህ እፍኝ ለማይሞሉ አጭበርባሪና ዘረኛ ትግሬዎች ሁሉን ነገር አስረክቦ እግሩ ባወጣ በመሰደድ በተዋራጅነት ለመኖር ራሱን ዝግጁ ማድረጉ ነው፡፡ ቆንጆ ሀገሩን ለወሮበላ አስረክቦ ራሱን የሚያጠፋና በከንቱ ማስኖ የሚቀር ዜጋ ቢኖር ኢትዮጵያዊ ዜጋ ብቻ ነው፡፡ የነሱን ዘረኝነት ስናገር እኔም ዘረኛ የሆንኩ እየመሰለኝ አፍራለሁ – እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ የሚያምን ሰው ዘረኛ ሊሆን እንደማይችል ሳስብ ግን እጽናናለሁ፡፡ በተለይ ዐማራ እስካሁን ያልሆነ ካሁን ወዲያ ዘረኛ ይሆናል ብዬ አልገምትምና ከኢትዮጵያዊነት ብቸኛ የመታገያ ሥልትና መንገድ ውጪ በወያኔ ቦይ ገብቶ እንዳይዳክር አደራችሁን እላለሁ፡፡ በርግጥ ዐማራ ሆኖ ስለዐማራ አለማሰብ ብልኅነት አይደለም፤ ወዶና ፈቅዶ ባልተፈጠረበት፣ ይሁነኝ ብሎ ባልሆነበት ማንነቱ ሲጨፈጨፍና ሲሳደድ እንኳንስን ተመሣሣይ ዕጣ የተፈረደበት ዜጋ ሌላውም ሊረዳውና ከዕልቂት ሊታደገው ሰብኣዊና ዜግነታዊ ግዴታ አለበት፡፡ ዐማራን እያስጨረሰው ያለው በዐማራነት ራሱን ለመፈረጅ መቸገሩ ነው፤ ከጥንት ከጧቱ ሰውነቱና ሥነ ልቦናው ሲታነፅ በኢትዮጵያዊነት እንጂ “ትግራይ አደይ፣ ዐምኻራ ሀድጊ፣ ዐምኻራን ተመንን እንተረከብኻ ቀዲምካ ንዐምኻራ በሎ…” እየተባለ በዘፈንም በሽለላና በቀረርቶም በወንድሞቹ ላይ እንዲዘምት በዐማራ ታሪካዊ ጠላቶችና በጣሊያን የባንዳ ልጆች እንደተገደደው የትግራዩ ወንድሜ ከልጅነቱ ጀምሮ የሚኮተኩተውና የሚያበረታታው አክራሪ ሰው ቢኖር ኖሮ ዐማራ ምን ሊሠራ እንደሚችል እኔ ሣልሆን ወያኔዎች ራሳቸው አሣምረው ያውቃሉ፡፡ ተኝቷል የሚባለው የዐማራው ልሂቅ እንኳን ይህን በዐማራው ላይ እየወረደ የሚገኘውን ወያኔያዊ ውርጅብኝ በማመንና ባለማመን መካከል ሆኖ በስማም እንደተባለበት ሰይጣን ዝም ብሎ ተቀምጧል – አብዛኛው፡፡ ስለዐማራው መብት ቢጮኽ ከወያኔዎቹ ያነሰ መስሎ ስለሚታየው ይመስለኛል በዝምታው ጸንቷል፡፡ ለማንኛውም የነበረ ያልነበር ይሆናል – ምንም ነገር ባለበት አይቀጥልም፤ የመደንቆሪያ ጊዜ አለ – የመስሚያ ጊዜም አለ፤ የልደት ቀን እንዳለ ሁሉ የመሞቻ ቀንም አለ፤ ለጥጋብ ቀን አለው – ለርሀብም እንዲሁ፡፡ አሁን ያለ የሚመስለውም ነገ የለም፡፡ ሞኝነትም ብልጥነትም ያረጃሉ፤ ይሞታሉም፡፡… የልብ መደፈንን በጊዜ ካልደረሱበትና መድሓኒት ካላገኙለት ግን ዳፋው ተዝቆ አያልቅም፡፡

ከአዲስ አበባ መቀሌ ስትገባ እዚያ ያሉ የአየር መንገዱ ሠራተኞች በግልጽ “እንኳን ወደ ኢትዮጵያ ዋና ከተማ በሰላም መጣችሁ” ይሉሃል፡፡ አፍረህ ዝም ትላለህ፡፡ አንድ ሰው ቢናገራቸው በቀጥታ ለዋናው የአየር መንገዱ ሥራ አስኪያጅ ለአቶ ተወልደ ይደውሉና የፈለጉትን እርምጃ ያስወስዱብሃል፡፡ አየር መንገዱ የተወልደ የግል ንብረት ያህል – በዚያውም የወያኔ የግል ሀብት ያህል እንጂ የኢትዮጵያ እንዳልሆነ ለማወቅ ብዙ ጉድ ትሰማለህ፤ ታያለህም፡፡ ጆሮህንና ዐይንህን ማመን እስኪያቅትህ በትንግርቱ ትገረማለህ፡፡ ለካንስ ዕድሜ የሰጠው ብዙ ያያል? በበኩሌ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ይህን ሁሉ ወያኔያዊ ድራማ አያለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር፡፡ በጣም ቸኮሉ፡፡ ይገርማል – ሰው ሲቸኩል ይሉኝታንና ሀፍረትን ጨርሶ ይረሳል ማለት ነው፡፡

ሠራተኛ ከየትም ሊቀጠር ይችላል – ከጎንደርም፣ ከባሕር ዳርም፣ ከድሬ ዳዋም ተቀጥሮ ሊመጣ ይችላል፡፡ ነገር ግን ከየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ቢመጣ ወያኔዎች ያን ምልምል ተቀጣሪ ትግሬ መሆኑን ሳያረጋግጡ የአየር መንገዱን ግቢ አያስረግጡትም፡፡ እጅግ፣ እጅግ በጣም የሚገርሙ “ሰዎች” ናቸው፡፡

በሁሉም የሥራ ዘርፍ የነሱን ሰው ያሰለጥኑና ሌላውን አበሳጭተው ወይም አባረው በነሱ ይተካሉ፡፡ የሚተኳቸው ትግሬዎች ደግሞ በአብዛኛው ችሎታም ሆነ ዕውቀት ስለሌላቸው ሥራውን ያበላሻሉ፤ የብዙ ዓመት የሥራ ልምድና በቂ ሥልጠና የሚፈልግን አንድ ሥራ በለብ ለብ ለጥቂት ጊዜ በ”ሰለጠነ” ትግሬ መተካት ደግሞ በተለይ አየር መንገድን በመሰለ ተቋም ሊያስከትል የሚችለው ችግር ከባድ ነው፤ የሰውን ሕይወት በአየር ይዞ ለሚቀዝፍ የአየር ላይ መርከብ የወያኔ ዓይነት አሠራር ሀገራዊ ኪሣራን ማስከተሉ አይቀርም፡፡ ኦ..ኦ..ኦ… በጣም ንቀውናል ጎበዝ! “ትንሽ ሰው አያሸንፍህ” የሚባለው ምርቃት እንዴት ትክክለኛ ነው እባክህን! ትንሽ ሰው አሸንፎ አገር ያቀናበት ዘመን ደግሞ የትም የለም፡፡ ትንሽ ሰው ሲያሸንፍ ሁሉ ነገር ብርቅ ይሆንበትና አገር ምድሩን መቆሚያና መቀመጫ ያሳጣል፡፡ ወያኔዎችም እንዲህ ናቸው፡፡ ትንሽ ሰው ስል ግን በሰውነት አቋም ወይም በሥነ ተፈጥሯዊ የፍጥረታት ደረጃ ምደባ ሣይሆን በአስተሳሰብና ርዕዮተ ዓለም ረገድ ማለቴ ነው፡፡ በጅስምማ ሁላችን እኩልና የአዳምና የሔዋን ልጆች ነን፤ ግን አንዳችን ቃየልን ሌላኛችን አቤልን እየሆን ለዚህች አጭር ምድራዊ ዕድሜ እንባላለን፡፡

በዚሁ ሰሞን አንዱን የአየር መንገዱን ነባር ባለሙያ እንዲህ አሉት አሉ፡፡ “ይህን የያዝከውን ቦታ ልቀቅልን – በጣም እንፈልገዋለን፡፡ ደሞዝህን ግን አንቀንስብህም፤ ወደሌላ ቦታ እናዛውርህ፡፡…” እርሱም እምቢ የሚልበት አቅም የለውምና ሳይወድ በግዱ ለቀቀላቸው፡፡ ሥራውን ግን እያበለሻሹት ነው ይባላል – ወሬ ተደብቆ አይቀርም መቼም – ከዚያው አካባቢ የሚናፈስ ትኩስ መረጃ ነው፡፡ ሥራ ሲበላሽ ማየት ደግሞ አያስችልምና ባለሙያው በዳር ሆኖ እያገዛቸው ነው፡፡ እነሱ ስለሀገር ባይጨነቁ እርሱ ግን እነሱን አልሆነም፡፡

ኧረ ሌላ በኢሳት የሰማሁትን ጉድ ደግሞ ልንገራችሁ – ያልተከታተላችሁ ካላችሁ፡፡ አንድ ወልቃይቴ ከወንድማገኝ ጋሹ ጋር እየተወያዬ ነው፡፡ ወያኔዎች ስላደረሱበት በደልም እያብራራ ነው፡፡ እንዴት አምልጧቸው እንደተሰወረባቸው ሲናገር አልደረስኩበትም ወይም አልፎኛል፡፡ ያደረሱበት ስቃይና መከራ እጅግ የሚዘገንን መሆኑ እንዳለ ሆኖ ወደ አንድ ገደል ወስደው ምን እንዳሉት ሲናገር ብትሰሙት ከነዚህ ሰዎች ጋር ወደፊት እንዴት እንደምንኖር ግራ በመጋባት ትጨነቃላችሁ፡፡ “አየኸው ይሄን ገደል? ዘመዶችህን (ወልቃይቶችን ማለቱ ነው) እያመጣን የምንጥለው እዚህ ገደል ውስጥ ነው፡፡ አጥንታችሁ እዚህ ይከማቻል፡፡ ትግራይ ነፃ ስትወጣ በማሽን እየፈጨን ለትግራይ የእርሻ መሬቶች ማዳበሪያ እናደርገዋን … ምን አስቸኮለህ፤ አንተንም ገድለን እዚሁ እንጥልሃለን…” ነበር ያለው – ልበ ድፍኑ የወያኔ ካድሬ፡፡ ለመሆኑ ይህን ሁሉ ጭካኔ ማን አሰረጸባቸው? ለዐማራ ያላቸውስ ጥላቻ እንዴት አይበርድም? ትግራይስ ነፃ የምትወጣው ከማን ነው? ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን በምዕራቡ ዓለም ያልተቋረጠ ልዩ እገዛ ማሸነፋቸው ከ25 ዓመታት በኋላም እንደህልም የማይታመን ሆኖባቸዋል ማለት ይሆን? ጥልቅ እንቅልፉን የሚደቃው ዐማራ በህልማቸው እየመጣ እንዴት ቢያስፈራራቸው ይሆን እንዲህ አቅላቸውን ስተው የሚበረግጉትና በዚህን መሰል የማሰቃያ “ጥበብ” ዐማራውን የቁም ስቅል የሚያሣዩት?

እነዚህን ጉዶች ሰው ቢያቅተው ፈጣሪ እንዴት አቃተው? በኢትዮጵያና ሕዛቧ ላይ አለ አንዳች ዕረፍት ከ25 ለሚበልጡ ዓመታት ጥሬ እንትናቸውን ሲለቁብን፣ በትዕቢትና በዕብሪት ተነፍተው እንዲህ ሲያስታውኩብን ምን ነው ሃይ የሚላቸው አንድም ምድራዊም ይሁን ሰማያዊ አካል ጠፋ? “የኢትዮጵያ አምላክ” እየተባለ የሚንቆለጳጰሰው አምላከ ሰማይ ወምድር ምን ሆኖ ነው እንዲህ በኛ ላይ የጨከነው? ምን ኃጢኣተኞች ብንሆን  አለርህራሄ እንደክርስቶስ ይህን ያህል እንድንወገር መፍቀዱ ለምን ይሆን? ሀገረ ማርያም ኢትዮጵያ በነዚህ ጥፍራም ወያኔዎች ስትጠፋ፣ ባልተገራ ብልግናቸው እንዲህ ሲጨመላለቁብን በውነቱ ፈጣሪ በመንበሩ ካለ እንዴት አስቻለው? በትምህርትም ሆነ በልምድ እዚህ ግቡ የማይባሉ 27 ባላገር ትግሬዎች በዘረኝነት ከአንድ ክፍለ ሀገር ተለቅመው ይህን በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የነበረ አየር መንገድ እንዲቀላቀሉና በዘረኝነት ግማት እንዲያከረፉት ከተደረገ በሌላው ማኅበራዊና መንግሥታዊ ተቋምማ ከዚህ የበለጠ ወንጀል እንዴት አይሠራ? የድፍረታቸው ምንጭ ምን ሊሆን ይችላል? የኛ ፍርሀት ወይንስ የነሱ “ጀግንነት”? የኛ “ትግስት” ወይንስ የነሱ ጀብድ? ምሥጢሩ ምን ይሆን?  ጥቂት ሺዎች በብዙ ሚሊዮኖች ዘንድ እንዲህ ግፍ ሊሠሩ የሚችሉበት አገባብ አልገባህ ብሎኝ ተቸግሬያለሁና የሚያብራራልኝ ባገኝ እጅግ በጣም ደስ ይለኛል፡፡ ሕይወት ብቻ ሣትሆን ኢትዮጵያም ዕንቆቅልሽ ሆነችብኝ – መፈቻው የራቀ ዕንቆቅልሽ፤ ሀገር የማይሰጥበት ክፍለ ዘመናዊ ምሥጢር፡፡  ጥቂቶች በአንደርባቸው ሚሊዮኖችን አፍዝዘው ወደ ተናጋሪ ዕቃነት(ዞምቤነት) የለወጡባት የምትገርም ሀገር – ኢትዮጵያ! ሁሉም ነገር ግራ የሚያጋባበት ሁኔታ የተፈጠረባት አስገራሚ ሀገር፡፡ እንደብልኅ በዐርባ ቀን ቀርቶ እንደሞኝ እንኳን በዐርባ ዓመት ልብ መግዛት ያልተቻለባት የዘመናችን ባቢሎንያውያን ሀገር – ኢትዮጵያ፡፡ ወደኋላ እንጂ ወደፊት የማይሮጥባት፣ ባሉበት ቆሞ መቅረትም ራሱ ዕርም ሆኖባት ወዳልነበረችበት የጥፋት ዘመን የኋሊት ሽምጥ የምትጋልብ ሀገር – አቢሲንያ፡፡

ለኢትዮጵያ ቆመናል የምትሉ የሰላማዊም ሆናችሁ የብረት ትግል ተቃዋሚዎች፣ የሰብኣዊ መብት ተሟጋቾች፣ በውጪም ሆነ በውስጥ የምትገኙ የነፃነት ፋኖዎች፣ … አሁንና ዛሬ ወዴት አላችሁ? ከዚህ የበለጠ ውርደት የት አለ? ከዚህ በላይስ ምን እስኪያደርጉን ትጠብቃላችሁ? ሥጋችንን እስኪበሉ? ደማችንን በስሪንጅ እስኪመጡ? እነዚህ ቫምፓየሮች ከዚህ በላይ ምን እስኪያደርጉን ትጠብቃላችሁ?

“ወደሽን ቆማጢት…” እንዳትሉኝ እንጂ ሁሉም የመንግሥት ሠራተኛ ትግሬ ይሁን – ለጊዜው ግዴለም እንበል፡፡ ግን የተማረና በአግባቡ የሠለጠነ ትግሬ ቢሆን ምናለበት? ወያኔዎች ሆይ! ሁሉንም ዜጎች ከሥራ አውጡና በትግሬ ተኩ፤ ጀምራችሁ እያጠናቀቃችሁት እንደምትገኙት ከዳር እዳር ሁሉንም ሙያዎችና የጥቅም ቦታዎች እናንተው ያዙ – ግን እባካችሁን ሰዎቻችሁ በቂ ሥልጠናና የማኅበራዊ ተግባቦት ችሎታ እንዲኖራቸው አድርጉ – የምትቃዡባትን የትግራይ “ሪፓፕሊክ”ን መሥርታችሁ እስክንገላገላችሁ ድረስ ያው እናንተም እንደኛው ኢትዮጵያውያን መባላችሁ አይልቀረምና ስለናንተ ፀያፍ የዘረኝነት ተግባር እኛም እያፈርንባችሁ ነው – ከሚደርስብን ቁሣዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት ባልተናነሰ በእናንተ ምክንያት ሀፍረቱም አሸማቀቀን – እውነቴን ነው – ከናንተ ጋር የአንዲት ሀገር ዜጋ መባሉ ራሱ በበኩሌ ቃላት ከሚገልጹት በላይ እያሣፈረኝ ነው – 27 ሆስተስ ከትግራይ ብቻ? ይህ ተግባር ብቻውን አይደለም ኢትዮጵያውያንን በእንስሳዊነት የጋራ ተፈጥሮ ምክንያት ዓሣማና ጅቦችንም በሀፍረት አንገት ሊያስደፋ የሚችል አጸያፊ ወያኔያዊ ድርጊት ነው(እናንተን እስፖንሰር ያደረጉ ምዕራባውያን ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች ይህን ተግባራችሁን አያውቁም አልልም፤ ከነሱም ሆነ ከናንተ ከዚህ የሚብስ ግፍ እንጂ መልካም ነገርን አልጠብቅም – ተፈጥሯችሁን ለአፍታም አትዘነጉምና)፡፡ በዋናነት ታዲያ ዐውሬ ትግሬዎችን ከጫካና እልም ካለ ገጠር እያመጣችሁ በአንጻራዊነት ሻል ባለ የሥልጣኔና የንቃተ ኅሊና ደረጃ በሚገኝ ሕዝብ ላይ እንደውሻ ጃዝ አትበሉ፡፡ ሕዝቡን እያስመረሩና እያስለቀሱ፣ የሀገሪቱንም ምስል እያበላሹ ነውና በጣም እየተዋረድን ነው፡፡ እርግጥ ነው – ኢትዮጵያን ማዋረድና ከምድረ ገጽ ማጥፋት ትልቁ አጀንዳችሁ መሆኑን እናውቃለን – ግን በቅጡ አጥፉን እባካችሁን፡፡ ፕሮፌሽናል በሆነ ሥልጡን መንገድ አጥፉን እንጂ ይህን ያህል የለዬላችሁ ‹ፋራ› አትሁኑ፡፡

ወያኔዎች ፈጣሪንም አግተው እንደያዙ አሁን አሁን መጠራጠር ጀምሬያለሁ፤ እንዲያ ባይሆን ይህን ሁሉ ግፍ እየሠሩ ሃይ የሚላቸው ባልጠፋ ነበር እላለሁ፡፡ …. በርግጥም ለኢትዮጵያ አሁን ያልታዘነ መቼም አይታዘንላትም፡፡ 27 ሰው ከአንድ ቀየ? የመንግሥት ተቋማትን ሁሉ በአንድ ክልል ሰዎች ማስያዝ? ማን ናቸው … እኚያ ስመጥር ፕሮፌሰር አሁን የት ነው ያሉት? የለም፣ የለም… እርግጥ ነው … ትግሬ ሣይሆኑ የሆኖሉሉ ዜጎች ናቸው በወያኔ እየተጠቀሙ ያሉት፡፡ ትግሬዎች ምን በወጣቸው? 27… ወይ መድሓኔ ዓለም… ምኑን አመጣህብን፤ ምን ጉድ ነው እያሳየኸን ያለኸው… ለማንኛውም እግዜሩን እግዜር ይይለት፡፡

“ሰውነት ቢያብጥ በምላጭ ይበጣል – ምላጭ ቢያብጥ በምን ይበጣል?….”  አዎ፣ አሁንም እውነት ነው –  “እህል ቢያንቅ በውኃ ይዋጣል፤ ውኃ ቢያንቅስ በምን ይዋጣል?” ፍርዱን ለራሱ ለፈጣሪ ሰጥቻለሁ፡፡

ታላቅ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ –በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ

$
0
0

13124744_594917307344027_5817391705741433452_n

በጋምቤላ እየደረሰ ያለውን እንዲሁም ሕወሓት በመላ አገሪቱ በንፁሀን ዜጎች ላይ እያደረሰ ያለውን መጠነ ሰፊ የሰብአዊ መብት ጥሰት ለማውገዝ የተጠራ!

ቀን: ሰኞ ሜይ 9/ 2016

አገር ወዳድ የሆነ ኢትዩጵያዊ ሁሉ በሰልፋ በመገኘት የተቃውሞ ድምፁን ያሰማ ዘንድ ተጋብዟል!

የዲሲ ግብረሀይል


የህብረብሄራዊ ድርጅቶች ኪሳራ እና የብሄረተኛ ድርጅቶች ስኬት ምክንያቶችና ለአማራ መፍትሄው |ከመልህቅ ሐራ

$
0
0

Amhara
በኢትዮጵያ ህብረ ብሔራዊ ፖለቲካ ትግል ውስጥ ጎልቶ ሲስተዋል የቆየ ችግር አለ፡፡ እርሱም የኢትዮጵያን አንድነት ለማስጠበቅ ህብረ ብሄራዊ አደረጃጀቶች የግድ ያስፈልጋሉ የሚለው ልማዳዊ አስተሳሰብና አሰራር ነው፡፡ እንደገባኝ መጠን የህብረብሄራዊ እና ብሄረተኛ ድርጅቶችን ውድቀትና ስኬቶችን በመዳሰሰ ለአሁኑ ወቅት ለአማራ ትግል የሚበጅ መንገድ ለመጠቆም እሞክራለሁ፡፡

ባለፉት 40 አመታት የተካሄዱ ትግሎችን ስንገመግም የብሄረተኛ ድርጅቶች በተደጋጋሚ ስኬት ሲጎናጸፉ ህብረብሄራዊ ድርጅቶች በተደጋጋሚ ሲሰናከሉና ሲፈርሱ ታይቶአል፡፡ አንዱም ህብረብሄራዊ ድርጅት ስኬት ላይ አልደረሰም፡፡ በተቃራኒው ብሄረተኛ ድርጅቶች ተሳክቶላቸዋል፤ ያልተሳካላቸውም ቢሆኑ ምንም እንኳ ከስኬት ቢርቁ ጨርሰው አልጠፉም፡፡ የተሸነፉ ህብረብሄራዊ ድርጅቶች በተጻራሪው ዱካቸው እንኳ እንዳይገኝ ሆነው ነው ሲጠፉ የቆዩት፡፡ ለአብነት ያህል ከህብረብሄራዊ ደርጅቶች ኢህአፓን፤ ደርግን፤ መኢሶን፣ ኢዲዩን እና በዘመኑ ከነበሩት ብሄረተኛ ድርጅቶች ህውሀት፤ ሻእብያ እና ወያኔን እንውሰድ፡፡

ኢህአፓ ሰፊ አደረጃት እንደነበረው እና የተቀባይነት አድማሱም ሰፊ እንደነበር ይታወቃል፡፡ በውስጡም የተለያየ ብሄር ተወላጆች እንደነበሩበት ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጅ ይህ ድርጅት በከተማ በደርግ እና በመኢሶን በደረሰበት መሳደድ ወደበርሀ ገብቶ ነበር፡፡ ይሁንና በበረሀ በብሄረተኛው ድርጅት ህወሀት ተሸነፈ፡፡ ለሽንፈት የዳረገው ምክንያት ብዙ ሊሆን ይችላል፡፡ በበኩሌ ግን ህብረብሄራዊነቱ ለውድቀት እንደዳረገው አምናለሁ፡፡ በውስጡ የነበሩት ህብረብሄራዊ አባላት ብሄረተኛ ስሜታቸው ስላመዘነባቸው ለየብሄራቸው ድርጅቶች ምስጢር እያሾለኩ አዳከሙት ብሎ መከራከር ይቻላል፡፡ ብሄረተኛ ድርጅቶች በተቃራኒው በብሄር ስሜት ስለሚጫወቱ በተጻራሪነት የቆመባቸውን እንኳ በስሜት ማሸፈት ይችላሉ፡፡ ያው የዘር ጉዳይ ከባድ ነው፡፡ እናም የኢህአፓ አባላት ከሻእብያ፤ ህወሀት እና ሌሎች ድርጅቶች ጋር በመተባበር ለኢህአፓ ሙሉ ትግል ባለማድረጋቸው፤ ይልቅም ወደብሄራቸው ድርጅቶች በማድላታቸው ኢህአፓ ሊንኮታኮት ችሏል፡፡ ለዚህ ማረጋገጫው ከኢህአፓ የተራረፉት አባላት ኢህድን ተብለው ቢቋቋሙም የኋላ የኋላ ትግሬያዊ ስሜትና እምነታቸው አሸንፏቸው በአንድ ጀንበር ህብረብሄራዊ ካባቸውን አውልቀው ብሄረተኛ ድርጅት ሆነዋል፡፡ ያም ማለት ህወሀት ህብረብሄራዊ አስተሳሰባቸውን በብሄረተኛ አስተሳሰብ ቀይሮ በብአዴን ጭንብል የራሱን ቅርንጫፍ ድርጅት መሰረተ ማለት ነው፡፡ ለዚህም ነው ብአዴንን ቁጥር ሁለት ህወሀት ብለን የምንገልጸው፡፡ ከትግሬዎች አባላት በተጨማሪ እንደሀድያ፤ ሲዳማ፣ ኦሮሞ የመሳሰሉ አባላትም ነበሩበት፡፡ እነዚህም ህብረብሄራዊ እምነታቸውን (ጭራሽ ኖሮአቸው ከሆነ) አውልቀው በጸረ አማራው ብአዴንነት ተጠፍጥፈው ሲሰሩ ያላንገራገሩት ከተማሪነታቸው ጀምሮ የተጠናወታቸው የአማራ ጥላቻ ነው፡፡ ፊውዳል ወይም ከበርቴው መደብ በሚሉ የሽፋን ቃላት ሲወገዝ የነበረው አማራ እንደነበር እናውቃለን፡፡ ስለዚህ ገሚሶቹን የትግሬ ብሄረተኝነት ስሜት አሸንፎአቸው የተቀሩትን ደግሞ የአማራ ጥላቻ ገፋፍቶአቸው በብሄረተኛው ህወሀት ጸረ አማራ ብሄረተኛ ድርጅት ሆነው ተጠፍጥፈው ተሰርተዋል፡፡ ያለማንገራገር፡፡

ደርግ በ120 አባላት ተመስርቶ መጨረሻ 40 አባላት ብቻ ይዞ ቀርቷል፡፡ ያም የሆነው ምንም እንኳ ደርግ ህብረብሄራዊ ድርጅት ቢሆንም ውስጡ የነበሩት አባላት ለየብሄራቸው ይሰሩ ስለነበረ ያንን ተከትሎ በየጊዜው በተፈጠረው ችግር ይገዳደሉ ስለነበር ነው፡፡ ደርግ ውስጥ የህወሀት፤ የሻእብያ እና የኦነግ ፍትጊያ ነበር፡፡ አባላቱ ለየብሄራቸው ድርጅቶች በነበራቸው አዝማሚያ ደርግ የቆመለት ህብረብሄራዊ አላማ ችግር ላይ ወደቀ፡፡ በተለይ የትግሬና ሀማሴን ተወላጆች ደርግን በመሸርሸር ወደር አልነበራቸውም፡፡ ያም ከደርግ ማእኮላዊ ኮሚቴ ወርዶ እስከታችኛው የሰራዊት እርከን ድረስ የተንሰራፋ ችግር ነበር፡፡ በዚህ በኩል ሰራዊት እና አቅርቦት ሲላክ በተጓዳኝ መረጃ ለጠላት ይላካል፡፡ ደርግ እንደ ፖለቲካዊ ፓርቲ እና ሰራዊቱ እንደሀገራዊ ጦር ሆኖ በህብረ ብሄራዊ አደረጃጀት ስለተዋቀረ እነዚህን ለየብሄራቸው የሚያደሉ ችግሮች መከላከል አልተቻለም፡፡ በዚህ ሳቢያ የደርግ ቤት የባቢሎን ግንብ ሰራተኞች መስሎ አረፈውና በመጨረሻ ሳይግባባ የህብረብሄራዊው አላማም አደጋ ላይ ወደቀ፡፡ ደርግም ከአመሰራረቱ ህብረብሄራዊ በመሆኑ ዱካው እንኳ እንዳይገኝ ሆኖ ወደቀ፡፡ በውስጡ ተሰግስገው ሲቦረቡሩት የነበሩትም ሰርጎገቦች በአዳዲሶቹ አሸናፊ ብሄረተኛ ድርጅቶች ውስጥ የአገልግሎታቸው እየተከፈላቸው ተቀላቀሉ፡፡

ኦሮሞ ቢበዛበትም ህብረብሄራዊ ባህርይ የነበረው መኢሶንም ተመሳሳይ እጣ ገጥሞት ድራሹ ጠፋ፡፡ በውስጡ ለኦነግ በተለይ እና ለሌሎች ድርጅቶች የሚሰሩ ሰዎች የነበሩበት በመሆኑ ወደቀ፡፡ ከወደቀ በኋላ ለስሙ ማስታወሻ እንኳ አልተገኘለትም፡፡

ቅንጅት በአጭር ጊዜ እንደማእበል ህዝብ አንቀሳቅሶ ወዲያው ሲከስም የአገዛዙ ጫና ዋናውን ድርሻ ቢወስድም ለታሪክ እንኳ ሊቀር አልቻለም፡፡ ለየብሄራቸው ማንነት የሚያደሉ ሰዎች በውስጡ ስለሚኖሩ እና ምስጢር አጠባበቅና ታማኝነት ስለሚላላ እንዲሁም ከዚህ የተነሳ ለሰርጎ ገቦች ስለሚጋለጥ ነበር ያ ሁሉ የሆነው፡፡ አንድነትም እንዲሁ፡፡ የአሁኑ ሰማያዊም በተመሳሳይ ሁኔታ ነው ያለው ማለት ይቻላል፡፡ መኢአድም ከዚህ ችግር አላመለጠም፡፡ በእርግጥ እነዚህ ሰላማዊ ታገዮች ስለሆኑ ለዚህ ጽሁፍ የሚረዳ ክርክር ለማቅረብ አይመቹ ይሆናል፡፡ ህብረብሄራዊነታቸው በውስጣቸው በሚካተቱት አባላት ብሄረተኛ አዝማሚያ ችግር ሲፈጠርባቸው እንደቆየና ለወደፊቱም እንደሚፈጠርባቸው ግን ግልጽ ነው፡፡

ከህብረብሄራዊ ድርጅቶች በተቃራኒ ብሄረተኛ ድርጅቶች ስኬታማ ሆነዋል፡፡ ሻእብያና ወያኔ ለድል የበቁት ብሄረተኛ አስተሳሰባቸው ስለረዳቸው ነው፡፡ ኦነግም ተሳክቶለት የመንግስት ስልጣን እስከመጋራት የደረሰው ከጥንስስ እስከፍጻሜው የነበረው ትግል በብሄረተኛ ማንነትና ስሜት ላይ የተገነባ ስለነበረ ነው፡፡ አሁን ተሸንፎ እንኳ ስምና አስተሳሰቡ ሊጠፋ ያልቻለው በዚሁ አፈጣጠርና አቀራረጽ መነሾነት ነው፡፡ ወያኔ በተለይ የመንግስት ስልጣኑንም በአስተማማኝ ይዞ የቀጠለው የብሄረተኛ አደረጃጀትና ስሜቱን በፖለቲካው፤ በደህንነቱ፤ በሰራዊቱ ውስጥ ስላሰረጸ እና በትግሬ ብሄረተኝነት ማንነት ዙሪያ ስላዋቀረ ነው፡፡ ሁሉም ነገር በትግሬ ብሄረተኛ አባላት ቁጥጥር ስር ስለወደቀ እስካሁን አገዛዙ ይህ ነው የተባለ ስጋት ሳያጋጥመው 25 አመት ቆይቷል፡፡ ህወሀት ሊወድቅ የሚችለው ይህንን ብሄረተኛ አደረጃጀቱን ትቶ ህብረብሄራዊ የሆነ እለት ነው፡፡ ያችን ደግሞ አይሞክራትም፡፡ በዚህ መንገድ የማይወድቅ ከሆነ ደግሞ ሌላ መንገድ መንደፍ ያስፈልጋል፡፡ ራሱ በመጣበት መንገድ መጓዝ የሚችል ጥብቅ የብሄረተኝነት አቋም ያለው ሌላ ድርጅት ብቻ ሊጥለው ይችላል፡፡ ያ ድርጅትም በትግሬ ብሄረተኝነት ዙሪያ የገተነባውን ስርአት መገዳደር የሚያስችል ተቃራኒ ሀይል ሲኖረው ብቻ ያሸንፋል፡፡ ከዚህ ውጭ በህብረብሄራዊ ድርጅቶች ሊሸነፍ ይችላል ብሎ ማሰብ ይከብዳል፡፡ ህብረብሄራዊ ድርጅቶች እንኳን የተሸነፈውን የኢትዮጵያ አንድነት ሊያመጡ ደርግ ራሱ ተከላክሎ ሊያድነው አልቻለም፡፡ በሌላ አነጋገር ህብረብሄራዊ ድርጅቶች ከደርግ በላይ አቅምና አደረጃጀት ያስፈልጋቸዋል ማለት ነው–ብሄረተኛውን አገዛዝ አሸንፎ በህብረብሄራዊ አገዛዝ ለመቀየር፡፡ ባጭሩ ህወሀትን ለመገዳደር እና ለማንበርከክ የሚቻለው ሌላ ብሄረተኛ ሀይል በመፍጠር ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ይወድቃል ከተባለ እንግዲህ በፈጣሪ ቁጣ ነው የሚሆነው፡፡

ለምንድነው ህብረብሄራዊ ድርጅቶች እየተሸነፉ ብሄረተኛ ድርጅቶች የሚያሸንፉት? ከላይ ለመጠቋቆም ተሞክሯል፡፡ ሰፋ አድርገን እንየው፡፡ ህብረብሄራዊ ድርጅቶች ሲዳከሙ ብሄረተኛ ድርጅቶች የሚጎለምሱበት ምክንያት የሰዎች ድርጅት በመሆናቸው ውድቀትና ስኬታቸውም የሚመነጨው ከሰው መሰረታዊ ስነፍጥረታዊ ባህርይ የተነሳ በመሆኑ ነው፡፡ ትንሽ ስጋ እንደመርፌ ትወጋ፤ አጥብቀህ ጎርሰህ ወደዘመዶችህ ተመለስ፤ የዘሬን ነገር ብረሳ ያንዘርዝረኝ የሚሉት እድሜ ጠገብ ፍልፍስፍናዎች ለዚህ ትልቅ ትምህርት የሚሰጡ ናቸው፡፡ እነዚህ አባባሎች በዘመናት መሀል ተፈትነው እውነት ሆነው የተገኙ የማህበረሰባዊ ጥናት ውጤቶች ናቸው፡፡ ሰዎች አፈጣጠራችን ለየራሳችን የዘር ሀረግ ወይም ቀበሌ እንድናደላ ያደርገናል፡፡ ይህ የሆነው የተፈጠሮ ግዴታ በመሆኑ እንጅ የተረገምን ስለሆነ አይደለም፡፡ በእርግጥ በኢትዮጵያ ልዩ ሁኔታ ብሄረተኛ ስሜትን በህብረብሄራዊ ወይም ሁሉን አቀፍ ሰብአዊነት አስተሳሰብና እምነት የቀየረ ህዝብ አለ፡፡ እሱም አማራ ነው፡፡ እንዳለመታደል ግን ይህ ህዝብ ዙሪያውን የተከበበው ብሄረተኛ ስሜትና እምነት ባልለቀቃቸው ህዝቦች ነው፡፡ ስለዚህ ይህንን ህዝብ ሁሉን አቀፍ ሰብአዊ ስሜትና እምነቱ እደተጠበቀ ሆኖ ወደራሱ ተመልሶ በብሄራዊ አወቃቀር እንዲደራጅ ማድረግ የግድ አስፈላጊ የሆነ የድል መንገድ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ስለሆነም የአማራን የሰውነት ተፈጥሮአዊ ስሜት ወደራሱ አማራዊነት እንዲቀየር ማድረግ የግድ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት እስካሁን ያደረጋቸው ህብረብሄራዊ አደረጃቶች በብሄረተኛ ሰርጎ ገብ ሰዎች እየተጠለፈበት ለሽንፈት ሲዳረግ ስለቆየ አዲስ የትግል ስልት መንደፉ የማያከራክር ሆኖ በመገኘቱ ነው፡፡

ከዚህ መሰረታዊ እሳቤ ተነስተን አንዳንድ ምሳሌዎችን እንይ፡፡ ብሄረተኛ ድርጅቶች ውስጥ የሚታገሉ ሰዎች ምስጢር አሳልፎ የመስጠት እድላቸው አናሳ ነው፡፡ ምክንያቱም የገዛ ዘመድ አዝማዳቸውን ለሌላ ወገን በአብዛኛው ጠላት ተብሎ ለሚታሰብ ህዝብ ወይም ድርጅት ታጋዮች መስጠት ራስን እነደመካድ መስሎ ስለሚሰማቸው ነው፡፡ አባትን ወይም እናትን ለአክስት ልጆት ፍላጎት አሳልፎ መስጠት ከባድ እንደሆነው አይነት አድርጎ መረዳት ይቻላል፡፡ ባጭሩ የገዛ ዘርን እንደመክዳት ስለሚቆጥሩት ድርጅታቸው ላይ ክህደት አይፈጽሙም፡፡ በዚህም ምክንያት ያ ድርጅት ደህንነቱ ተጋላጭ የመሆኑ እድል ያንሳል ማለት ነው፡፡ በተቃራኒው ህብረብሄራዊ ድርጅቶች ውስጥ የሚሰሩ ሰዎች ለየብሄራቸው የድርጅታቸውን ምስጢር የማካፈል እድላቸው ሰፊ ነው፡፡ ይህም አንድ አባል በራሱ ዘሮች እና በሌሎች ዘሮች መካከል እንዲመርጥ ጥያቄ ስለሚቀርብለት የዘር ነገር ያሸንፈዋል ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ መዐሕድ የብሄረተኛ አደረጃጀት አዝማሚያ ስለነበረው ወደመጀመሪያዎቹ አካባቢ ለውጦችን ማስመዝገብ ችሎ ነበር፡ በኋላ ግን በሌሎች ብሄሮች በተለይ ቅይጦች ሆነው ሳለ ራሳቸውን በአማራዊ ማንነት ይገልጡ በነበሩ ሰዎች ምክንያት እየተዳከመ ሄደ፡፡ በኋላም ወደህብረብሄራዊ ድርጅትነት ተቀየረና ከነአካቴው ጠፋ፡፡ ከጅምሩ እንደታየው በአማራ ብሄር ብቻ ተዋቅሮ ቢሆን ኖሮ ታሪክ ባይሰራ እንኳ የራሱ ታሪክና ህልውና ጨርሶ እስከመጥፋት ባልደረሰም ነበር፡፡ በተመሳሳይ አነጋገር ህብረብሄራዊ ድርጅቶች ውስጥ የሚታገሉ ሰዎች ለአማራ ባላቸው ጥላቻ ወይም ጥርጣሬ የተነሳ የየድርጅቶቻቸውን ምስጢሮች ሲያሾልኩ መቆየታቸውን መገመት ይቻላል (ኧረ ጠቅላላ እውቀት ነው እንዴውም)፡፡ በቅርቡ ያየናቸው ምሳሌዎች ይህንን በበቂ ሁኔታ ያስረዳሉ፡፡የሞላ አስገዶም መክዳት፤ የጃዋር መክዳት፤ የዳዊት ከበደ መክዳት ወዘት ለዚህ ክርክር ደጋፊ ምሳሌዎች ናቸው፡፡

ለአማራ መፍትሄው ምንድነው ታዲያ? ከላይ የተዘረዘረው እንግዲህ በቂ ትምህርት ነው ብየ አስባለሁ፡፡ አማራው በተለወጠ የፖለቲካና ማህበራዊ ሁኔታ ውስጥ ባልተለወጠ ዘዴ መታገል የለበትም፡፡ ትግል ብቻውን እንደግብ መታየት አለበት ካልተባለ በቀር ህብረብሄራዊ አደረጃት ውስጥ ገብቶ መታገል ለድል እንዳላበቃ ተደጋግሞ ታይቷል፡፡ ስለዚህ ራስን ከተለዋዋጭ ሁኔታዎች ጋር በማላመድ ለአዳዲስ ችግሮች አዳዲስ ዘዴዎች መቀየስ የግድ ያስፈልጋል፡፡ የተዘጋ በር ስንደበድብ ከምንውል ሌላ ያልተዘጋ በር መፈለግ ወይም ስስ የሆነውን የግድዳ ክፍል ፈልጎ መደርመስ ይሻላል፡፡

እንደምናሸንፍበት እርግጠኛ ያልሆንበትን ትግል መጀመርም የለብንም፡፡ ሩቅ የሚያደርስ ግብ መተለም ያስፈልጋል፡፡ የአላማ ግልጽነት፤ የግብ ተጨባጭነት እና የመስመር ጥራት ዋና ዋና ሊተኮርባቸው የሚገቡ ጉዳዮች ናቸው፡፡ እንግዲህ በእነዚህ እሳቤዎች በመመርኮዝ የአማራን ብሄረተኝነት መስርተናል፡፡ በዚህ አስተሳሰብ እና በዚሁ ዙሪያ በሚፈጠር አደረጃጀት ብቻ በመጓዝ ሙሉ በሙሉ አማራዊ የሆነ አደረጃጀት በመከተል ለድርጅት ታማኝነትን ማጎልበት እንችላለን፤ ምስጢር ለሌላ ወገን ተላልፎ የመሰጠቱን እድል እንቀንሳለን፡፡ ከዚህ ውጭ ያለው ህብረብሄራዊ መንገድ ግን ራስን ለጠለፋ ማጋለጥ ነው የሚሆነው፡፡

ዶናል ትራምፕ በጸረ- ሙስሊም እና በጸረ-ስደተኛ አቋማቸው ይገፉበት ይሆን? |ዜና ትንታኔ በታምሩ ገዳ (የሚደመጥ)

$
0
0

እየተሟሟቀ እና አየተካረረ የመጣው የአሜሪካዊያን የእጩ ፕሬዘዳንታዊ ምረጡኝ የቅሰቀሳ ዘመቻ ሰሞናዊ ውሎው ፣ የጫረው አግራሞት፣ ቱጃሩ ዶናልድ ትራምፕ ለተቃዋሚዎቻቸው የላኩት የመጨረሻው መልእክት ምን ይላል?፣እውን ዶናል ትራምፕ በጸረ- ሙስሊም እና በጸረ-ስደተኛ አቋማቸው ይገፉበት ይሆን? ፣ የቀድሞዋ የወጪ ጉ/ሚ/ር ሂላሪ ክሊንተን ተፎካካሪያቸው በርኒ ሳንደረስን ለምን አወደሷቸው? (ልዩ ዘገባ)

የሕዝብ ማእበልና ሱናሚ በመስቀል አደባባይ –ይገረም አለሙ

$
0
0

የፊታችን ቅዳሜና እሁድ የሚውሉት ሚያዝያ 29 እና 30 ከአስር ዓመት በፊት በ1997 ዓም በተመሳሳይ ቀናት ነበር የዋሉት፡፡ እነዛ ሁለት ቀናት በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ጉልህ ሥፍራ ይዘው የሚኖሩ ትእይንቶች የታዩባቸው ነበሩ፡፡ በተለይ ሚያዝያ ሰላሳ በዚህ ትውልድ ዳግም ይታያል ተብሎ ለመገመት የማይቻል ትእይንት ነው አሳይቶን ያለፈው፡፡
elc
የምርጫ 97 ዋንኛ ተፎካካሪ የነበረው የአራት ፓርቲዎች ጥምረት ቅንጅት ከድምጽ መስጫው ግንቦት 7/97 እለት አስቀድሞ በሚውለው እሁድ የምርጫ ዘመቻ ማጠናቀቂያ ሕዝባዊ ትእይንት በመስቀል አደባባይ እንደሚያደርግና የትዕይንቱ መሪ ቃልም ለዴሞክራሲ እናዚም/እንዘምር የሚል አንደሆነ ቀደም ብሎ አስታወቀ፡፡ ይህን አንደሰማ ኢህአዴግም ለሚያዝያ 29 ቅዳሜ ፕሮግራም አንዳለው ገለጸ፡፡

የኢህአዴግ ትዕይንት ሕዝብ፤

የፖለቲካ ፉክክር አንድም አስቀድሞ አቅዶ በሚፈጸም ተግባር በልጦ መገኘት፣ ሁለትም የተፎካካሪዎችን እንቅስቃሴ እግር በእግር እየተከተሉ የሚሰሩትን በማየትና የሚናገሩትን በመቅለም አጸፋዊ ተግባር መከወን እንደመሆኑ የቅንጅት የምርጫ ዘመቻ ማጠቃለያ ትእይንተ ሕዝብ ፕሮግራም እንደተሰማ ወይኔ በጥድፊያ ተዘጋጅቶ ለሚያዝያ 29 በመስቀል አደባባይ ጥሪ አደረገ፡፡ በእለቱም በየቀበሌው የተለመደውን የካድሬ ስራ ሰርቶ፤ ንብ የታተመችበትን ካናቴራ አድሎ፣ ራቅ ላሉ ቀበሌዎችም የህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት አቅርቦ ሰዉን መስቀል አደባባይ አወጣው ወይንም አስወጣው፡፡ በዚህ ሁኔታ አደባባዩ በሕዝብ ተጥለቀለቀ፡፡ አቶ መለስም አይተውት የማያውቁትን የህዝብ ብዛት በአደባባይ ሲያዩ እንዴትና በምን ሁኔታ እንደወጣ ሳይረዱ በጥይት መከላከያ መስተዋት ጀርባ ሆነው ባሰሙት ንግግር ስሜት ፈንቅሎአቸው ይህ የህዝብ ማእበል ምንም ማጭበርበር ሳያስፈልገው ምርጫውን ማሸነፍ ይችላል አሉ፡፡ በዚህም ድርጅታቸው በምርጫ ተወዳድሮ ለማሸነፍ ሳይሆን አጭበርብሮ ለማለፍ የተዘጋጀ መሆኑን አጋላጡ፡፡ መሪዎች በአደባባይ የሚያደርጉት ንግግር ተጽፎ የሚሰጣቸው እንዲህ በስሜት ተገፍተው አደጋ የሚያመጣ ነገር እንዳይናገሩ ይመስለኛል፡፡ አቶ መለስ የተነፈሱትን ማናፈስ ስራቸው የሆኑት የመገናኛ ብዙኃንም በመስቀል አደባባይ የህዝብ ማእበል ታየ በማለት እያጋነኑ አቀረቡት፡፡

ይህ በመስቀል አደባባይ የታየውና ማዕበል ተብሎ የተገለጸው የህዝብ ቁጥር ኢህዴጋዊያንን ሲያስፈነድቅ( ለአንድ ቀንም ቢሆን) በአንጻሩ ለቅንጅት አመራሮች ብቻ ሳይሆን ለአባላቱና ለደጋፊዎቹም ትልቅ ጭንቀት ፈጠረ፡፡ የጭንቀቱ ምክንያትም በማግስቱ ሚያዝያ ሰላሳ ቢያንስ ተመጣጣኝ የሆነ የህዝብ ቁጠር ይገኝ ይሆን የሚለው ነበር ፡፡

የቅንጅት ትዕይንተ ሕዝብ

እሁድ ሚያዝያ ሰላሳ ጠዋት ቀይ መስቀል፣ በመስቀል አደባባይ ዝግጅት ነበረው፡፡ የቅንጅት ጥሪ ደግሞ ከሰአት በኋላ ነው፡፡ አምስት ሰአት ተኩል አካባቢ መስቀል አደባባይ ስንደርስ ቀይ መስቀሎች ጓዛቸውን እየጠቀለሉ ሲሆን አደባባዩ በሰው እየተሞላ ነበር፡፡ ሰአት ገና ነው ብለው ወደ አደባባዩ የደረሱት ቅንጅቶች ከጥሪው ቀድሞ የሰዉን መጉረፍ ሲመለከቱ መድረክ የማዘጋጀቱንና የድምጽ መሳሪያ የመዘርጋቱን ሥራ ማጣደፍ ጀመሩ፡፤ ፌዴራል ፖለሶች ደግሞ ጎን ለጎን ተያይዘው በመቆም ሰዉ ወደ መኪና መንገዱ እንዳይገባ ለማደረግ አጥር ሰሩ፡፡ ነገር ግን የሰዉ ቁጥር ሲጨምር ሲያፈገፍጉ በዚህ መልኩ እየተገፉ ሄደው መጨረሻ ክቡር ትሪቡኑ ስር በሚገኘው ምሽጋቸው ውስጥ ተጠቃለው ለመግባት ተገደዱ፡፡ መንገዱ ሙሉ በመሉ በህዝብ ተሟላ፡፡

ወደ መስቀል አደባባይ የሚያደርሱት ስድስቱም መንገዶች በህዝብ ተጨናነቁ፤ከፒያሳ አቅጣጫ የሚመጣው ከፖስታ ቤት፤ከሜክሲኮ አቅጣጫ የሚመጣው ከቡናና ሻይ፤ ከሳሪስ የሚመጣው ከአራተኛ ክፍለ ጦር፤ ከቦሌ የሚመጣው ከፍላሚንጎ፤ ከመገናኛ አቅጣጫ የሚመጣው ከባምብሲ፤ከአራት ኪሉ የሚመጣው ከታላቁ ቤተ መንግሥት ማለፍ አልቻለም፡፡ የቅንጅቶች መድረክ በሕዝብ ተውጣ እንኳን ከሩቅ ከቅርብም የማትታይ ሆነች፡፡ ከመድረክ የሚነገረውም የሚሰማው በመድረኩ ዙሪያ ላሉት ብቻ ሆነ፡፡

ማእበል ለመባል ከበቃው በኢህአዴግ ትእይንተ ሕዝብ ላይ ከተገኘው የህዝብ ብዛት ይህኛው በሁለት ምን አልባትም በሶስት እጥፍ የሚበልጥ በመሆኑ ሱናሚ ተባለ፡፡ በወቅቱ በወያኔ አደገኛ ቦዘኔ ከመባል አልፎ ህግ ወጥቶ እየታደነ ይታሰር የነበረው ወጣት አደገኛ ቦዘኔ ራሱ ወያኔ፤ ወጣቱ ስራ አጥ አንጂ ቦዘኔ አይደለም በማለት በየምርጫ ቅስቀሳ መድረኮች ሲያሰማው የነበረውን መፈክር በአደባባዩ ከማሰማት አልፎ አደገኛ ቦዘኔ ያለመሆኑን ያሳየበትን ተግባር ፈጸመ፡፡ በአደባባዩ የተተከሉ የጌጥ መብራቶች ስስ ከመሆናቸው የተነሳ በቀላላ ሊሰበሩ የሚችሉ ቢሆኑም ወጣቱ ባደረገው ጥንቃቄና መከላከል በዛ የህዝብ መጨናነቅ ውስጥ አንድም ጉዳት ሳይደርስ ቀረ፡፡ የእጅ ስልኮች ወድቀው ተገኝተው ወደ መድረክ ተላለፉ፡፡ ሰልፉ ከተበተነ በኋላ በህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ሲሳፈሩ ራሳቸው ስርአት አስከብረው አንድ ሰው ሳይከፍል አንዳይሳፈር ገንዘብ ያልያዘ ካለ ያልያዛ አንዲከፍልለት እያደረጉ ወጣቶች ኢትዮጵያዊ ጨዋነታቸውንና ህግና ሥርዓት አክባሪነታቸውን በተግባር አሳዩ፡፡ ትናንት ለእንጀራችን ዛሬ ለእምነታችን፤ ትናንት ለካናቴራ ዛሬ ለባንዲራ ወዘተ የሚሉ መፈክሮችም በየቦታው ተሰሙ፡፡ እነዚህ ኢህአዴጋዉያንን በእጅጉ ያበሳጩ እንደነበሩ ለማተዘብ ተችሏል፡፡
የቅንጅቶችም ጭንቀት ለኢህአዴግ የወጣውን ያህል ህዝብ ይወጣልን ይሆን ከሚለው ይህ ሁሉ ሕዝብ በሰላም በየቤቱ ይገባ ይሆን ወደሚል ተለወጠ፡፡ ቢያንስ በጥንቃቄና በኢትዮጵያዊ ጨዋነት ወደየቤቱ እንዲሄድ መልእክት ለማስተላለፍ አለመቻሉ የቅንጅቶችን ጭንቀት እንዳበረታው በመድረኩ እቅራቢያ የነበርን ታዝበናል፡፡ ነገር ግን ፕሮግራሙ አንዳለቀ ከየት መጣ ያልተባለ ዝናም ድንገት ወረደና በተነን፡፡ ከፊሉ መጠለያ ፍለጋ ሲሯሯጥ በተለይ ወጣቱ በቡድን በመሆን እያዜመ ዝናቡ ምንም ሳይመስለው ጉዞውን ቀጠለ፡፡ምሽት ላይ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን የተለመደውን ተቃራኒ ዜና ሰሩ፡፡ ይህ ደግሞ ህዝቡን ይበልጥ አበሳጨው፡፡
የሀያ ዘጠኙ ትእይንተ ሕዝብና የተሰራው ፕሮፓጋንዳ በሰላሳ ሕዘቡ ነቅሎ አንዲወጣ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ አንድ ምሳሌ ልጥቀስ ከሰፈሬ አንድ በእድሜ ጠና ያሉ ሰው ትእይንተ ሕዝቡ ላይ ተገኝተው አንደነበረ ሲያጫውቱኝ፤ የቅንጅቶችን ጥሪ አስቀድሜ ብሰማም የመውጣት እቅድ አልነበረኝም፤ የቅዳሜውን ሰው ሳይ ግን አንዴት እንዲህ ይሆናል አልኩ፤ፕሮፓጋንዳቸው ደግሞ ይበልጥ አበሳጨኝና ለመውጣት ወሰንኩ፡፡ግን ከፖስታ ቤት ማለፍ አልቻልኩም፤ ባየሁት የህዝብ ብዛት ግን በጣም ነው የተደሰትኩት ነበር ያሉኝ፡፡

ዳግም ይታይ ይሆን!

ከዚህ ማእበልና ሱናሜ ከተባለ ተእይንተ ህዝብ ወያኔ በሚገባ መማሩን ተግባሩ ይመሰክራል፡፡ ተቀዋሚው ግን የተማረ አይመስለኝም፡ወያኔ ቅዳሜ ያን ያህል ሕዝብ ወጥቶ አቶ መለስንም ምስጢር አስወጥቶ በማግስቱ በሁለት እጥፍ መውጣቱ በህዝብ ልብ ውስጥ አለመኖሩን እንዲገነዘብ አስችሎታል፡፡ በህዝብ ካልተወደደና ተቀባይነት ከሌለው ደግሞ በህጋዊ አግባብ ፍላጎቱና ማሳካት፣ ወንበሩንም ማስጠበቅ አይቻለውም፡፡ ስለሆነም ህገ ወጥ ህጎችን ማውጣት፣ ማናቸውንም አንቅስቃሴዎች በጠመንጃ ጸጥ ማሰኘት፣ ፓርቲዎች ከቢሮአቸው መግለጫ ማውጣት ያለፈ እንቅስቃሴ አንዳይኖራቸው ማድረግ ወዘተ ስራው ሆነ፡፡

ወያኔ ያን መሰል የሕዝብ እንቅስቃሴ ዳግም በኢትዮጵያ እንዳይኖር ለማድረግ ያስቻለውን ስራ ቢሰራ ከታገለለት ዓላማና ከሥልጣን ወይንም ሞት መርሁ አንጻር ተገቢ ነው፡፡ ተቀዋሚዎች ግን ወያኔ ለሥልጣኔ አስጊ ብሎ የፈራው ይህ የህዝብ ተነሳሽነት አስፈላጊነቱን አምነው አንዲቀጥል ለማድረግ የሚያስችል ስራ ለመስራት አለመቻላቸው ነው እንቆቅልሹ፡፡

በምርጫ 97 ለታየው የህዝብ ተነሳሽነት የሚጠቀሱ እንደየሰው አስተሳሰብ የሚለያዩ ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩም አንዱ ምክንያት አራት ፓርቲዎች ቅንጅት ፈጥረው አንድ ሆነው መቅረባቸው እና በቅንጅት አመራር ውስጥ ከዛ በፊት ብዙም በፖለቲካው መድረክ ያልታዩ ሰዎች ብቅ ማለታቸውና የህዝቡን አመኔታ ማግኘታቸው መሆኑ ሁሉም ሰው የሚስማማበት ይመስለኛል፡፡

በአንድ ዓላማ ተሳስሮ በልዩነት ተከባብሮ ህብረት ፈጥሮ በአንድ የትግል መስመር ላይ መቆም አንዲህ ተአምራዊ የህዝብ ተነሳሽነት አንደሚፈጥር በተግባር ታይቶ እያለ ለዚህ መሳካት የየግል ፍላጎትን በመክላትና ድብቅ አጀንዳን በማስወገድ መስራት ሲገባ ፖለቲከኞቻችን ከራስ በላይ ማሰብ እየተሳናቸው ትብብር ሊፈጥሩ ቀርቶ የጀመሩትንም እያፈረሱና እየበተኑ ለወያኔ እድሜ ማራዘሚያ መድሀኒት ይሆናሉ፡፡

የፖለቲከኞቻችን ችግር ከዚህም ይዘላል፡፡አለመተባበር ብቻ ሳይሆን መቀናናትም አለ፤ አንዱ የተሻለ መስራት ከቻለና የህዝብ አመኔታና ድጋፍ ካገኘ ሌላው እሱም ሰርቶ ለመታመን ከመጣር ይልቅ ለሚሰራው እንቅፋት ይሆናል፡፡ቅንጅት ሚያዝያ 30/97 ያን ያህል ሰው አደባባይ ስለወጣለት በቅናት ያረሩ በተበለጥን ሰይጣናዊ ስሜት የተቃጠሉ ስሜታቸውን መቆጣጠር እየተሳናቸው ይህን የሚያጋልጡ ቃላት ከአፋቸው ሲያመልጡ እየሰማን ታዝበናል፡፡ ይህን ደግሞ ስም ግዜና ጋዜጦችን እየጠቀሱ ማስረጃ ማቅረብ ቢቻልም ቢያንስ ለዛሬ ጠቀሜታ የለውምና ይቅር፡፡

በአጠቃላይ ሚያዝያ 29 እና 30/97 ያየነው ትእይንት ዳግም ሊታይ መቻሉ አጠራጣሪ ነው፡፡ ይህም የሆነው ወያኔ ሕዝብን አደባባይ ቢያወጣ ወደ ተቃውሞ ተቀይሮ በራሱ ጥሪ ራሱ አንዳይወገዝ ተቃውሞ አንዳይደርስበትና በህዝቡም ዘንድ አዲስ መነሳሳት እንዳይፈጠር ስለሚሰጋ ሲሆን በተቃውሞው ጎራ ደግሞ ያንን ለማድረግ የሚያስችል እቅም ያለው ፓርቲም ሆነ ህብረት ባለመኖሩ ነው፡፡

የብአዴን አመራር ጎንደር ውስጥ የማንነት ጥያቄ ያነሱት ዜጎች ለማጥቃት ያስተላለፈው ውሳኔ ውድቅ ሆነ – (የፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ አጫጭር ዜናዎች)

$
0
0

#ኃይለማሪያም ደሳለኝ ለፕላስቲክ ቀዶ ጥገና ወደ ጀርመን ሄደ ተባለ
#በመተከል አካባቢ ኦሜድላ ላይ የሱዳን ታጣቂዎች ንብረት ዘርፈው ዜጎችን አፍነው ወሰዱ
#የብአዴን አመራር ጎንደር ውስጥ የማንነጥ ጥያቄ ያነሱት ዜጎች ለማጥቃት ያስተላለፈው ውሳኔ ውድቅ ሆነ።
#የግብጽ የጋዜጠኞች ማህበር አጠቃላይ የስራ ማቆም አድማ ጠራ
#በሱዳን ግብጽ የወሰደቻቸውን ቦታዎች ለማስመለስ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው
#የአለም የገንዘብ ድርጅት በዚህ አመት የአፍሪካ የኢኮኖሚ እድገት ይቀንሳል አለ
#በናይጄሪያ 15 ሚሊዮን ዶላር በሙስና ተሰረቀ ተባለ

የብአዴን ምክትል ሊቀመንበርና የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

የብአዴን ምክትል ሊቀመንበርና የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

ሚያዚያ 25 ቀን 2008 ዓ ም
ርዕሰ ዜና
 ኃይለማሪያም ደሳለኝ ለፕላስቲክ ቀዶ ጥገና ወደ ጀርመን ሄደ ተባለ
 በመተከል አካባቢ ኦሜድላ ላይ የሱዳን ታጣቂዎች ንብረት ዘርፈው ዜጎችን አፍነው ወሰዱ
 የብአዴን አመራር ጎንደር ውስጥ የማንነጥ ጥያቄ ያነሱት ዜጎች ለማጥቃት ያስተላለፈው ውሳኔ ውድቅ ሆነ።
 የግብጽ የጋዜጠኞች ማህበር አጠቃላይ የስራ ማቆም አድማ ጠራ
 በሱዳን ግብጽ የወሰደቻቸውን ቦታዎች ለማስመለስ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው
 የአለም የገንዘብ ድርጅት በዚህ አመት የአፍሪካ የኢኮኖሚ እድገት ይቀንሳል አለ
 በናይጄሪያ 15 ሚሊዮን ዶላር በሙስና ተሰረቀ ተባለ
ዝርዝር ዜና
 የወያኔ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ለቅንጦት ህክምና ወደ ጀርመን
ማምራቱን የዜና ምንጮች ገልጸዋል። ኃይለማሪያም ደሳለኝ የፊት ገጹን ለማስተካከል
እና ለማስዋብ የፕላስቲክ ቀዶ ጥገና እንደሚያደርግ ታውቋል። ኃይለማርያም ደሳለኝ
ወደ ጀርመን የተጓዘው በግል አውሮፕላን መሆኑ ሲታወቅ በባደን ከተማ በገዛው ቤት
ውስጥ እንደሚያርፍ ተገልጿል። ሁለት ሚሊዮን ነዋሪ ያለው የባደን ከተማ የጀርመን
ሃብታሞች የሚኖሩበት ውድ ከተማ መሆኑ ይታወቃል። የወያኔው ጠቅላይ ሚኒስትር
ለህክምና በማለት ወደ ጀርመን ማቅናቱ ሲነገር በኢትዮጵያ በመሰረታዊ የጤና እጦት
የተነሳ በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ በሚሰቃይበት በድርቅና በረሃብ አንድ አምስተኛው
የሚሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ የዓለም አቀፉን ሕብረተሰብ እጅ በሚያይበት ሰዓት መሪ
የተባለው ኃይለማሪያም ደሳለኝ ለቅንጦት ህክምና ወደ አውሮፓ መጓዙ ግብዝነነትና
ለሕዝብ ደንታ ቢስነትን የሚያሳይ ነው ተብሏል።

 የኢትዮጵያ ዳር ድንበር እየተደፈረ፣ ዜጎችም በወራሪ ኃይሎች እየተወረሩና እየታፈኑ
መመጣቱን መቀጠሉን የሚገልጹ መረጃዎች ከመተከል አካባቢ ከኦሜድላ እየመጡ
መሆናቸው ይነገራል። ባለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ በመተከል ኦሜድላ አካባቢ
አድፍጠው የነበሩ የሱዳን ወታድሮች በኢትዮጵያ ግዛት ዘልቀው በመግባት ወረራ
መፈጸማቸውና ንብረት በማውደም ሰባ ዜጎችን አፍነው የመውሰድ ወንጀል
መፈጸማቸው ታውቋል። ይህ ካለፈው አርብ ጀምሮ በቀጠለው ወረራ በአቅራቢያ
የነበረው የወያኔ የምዕራብ ጦር አባላትም የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ በማለት ነዋሪው በባዕድ
ኃይል እንዲወረር አድርጓል።

 የወያኔ የበኩር ጥፍጥፍ የሆነው ብአዴን ጎንደር ውስጥ የማንነት ጥያቄ ያነሱ ዜጎችን
ስልታዊ በሆነ መንገድ ለማጥቃት ላማስር ያወጡትን እቅድ የጎንደር አስተዳድሪዎችና
ሹማምንት አንቀበልም ማለተታቸው ተሰምቷል። በማንነት ጥያቄ ዙሪያ ሕዝብን
ያስተባበሩ ናቸው የተባሉትን ሰዎች የማዳበሪያ ዕዳ ወይም ጥቃቅን አበዳሪ ተቋማት
እዳ ካለባቸው እንዲከፍሉ ማስገደድና ካልከፈሉ እንዲታሰሩ የሚጠይቀውን ትእዛዝና
መመሪያ የጎንደር ባለስልጣናትና ሹማምንት አሻፈረኝ ማለታቸው ታውቋል። ብአዴን
ከወያኔ የሚሰጠው ትእዛዝ ሕዝብን ለማሸበር የሚያደርገው ጥረት ከፍተኛ ካድሬዎችና
መካከለኛ አባላት ተግባራዊ አናድርግም ማለታቸው በበአዴን አመራር መካከል ክፍተት
ሳይፈጥር እንዳልቀረ ተገምቷል።

 የዓለም አቀፍ የፕሬስ ቀን ሊከበር አንድ ቀን ሲቀረው እሁድ ሚያዚያ 23 ቀን ለሰኞ
አጥቢያ ሁለት የግብጽ ጋዜጠኞች በጸጥታ ኃይሎች ተይዘው በመወሰዳቸውና ጽህፈት
ቤቱ ያለምንም ማስጠንቀቂያ በጸጥታ ኃይሎች በመወረሩ ምክንያት የግብጽ የጋዜጠኞች
ማህበር አጠቃላይ የስራ ማቆም አድማ የጠራ ከመሆኑ ባሻገር የየግብጽ የአገር ውስጥ
ጉዳይ ሚኒስትር ከስራቸው እንዲነሱ ጠይቋል። የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር
የማህበሩን ጽሕፈት ቤት መውረሩን ቢክድም ሁለቱ ጋዜጠኞች አመጽ የሚያነሳሳ
ጽሑፍ በመጻፋቸው መታሰራቸውን አምኗል። ሁለቱ ጋዜጠኞች የፕሬዚዳንት ሲሲ
አስተዳድርን በመንቀፍ ለሚታወቀው ባዋቤት ያነያር (የጥር በር) ለሚባለው ድረ ገጽ
የሚሰሩ ነበሩ። የጋዜጠኞቹ ማህበር ሰኞ ሚያዚያ 24 ቀን 2008 ዓም. ባወጣው
መግለጫ የጸጥታ ኃይሎች የማህበሩን ጽቤት ወረረው የጋዜጠኞችን ክብር በሚያጎድፍ
ሁኔታና መብታቸውን በሚጻረር መንገድ አሰቃይተው ያሰሯቸው መሆኑን ገልጾ
ድርጊቱን በጽኑ አውግዟል። የማሕበሩ ጠቃላላ ስብሰባ ረቡዕ ሚያዚያ 26 ቀን
እስከሚካሄድ ድረስም ጋዜጠኞች በማህበሩ ጽ/ቤት ዙሪያ በመሰብሰብ ላይ የቁጭ በሉ
አዳማ እንዲያደርጉ ጥሪ አስተላልፏል። ከአስራ አምስት ቀን በፊት የሲሲ አገዛዝ ለሳኡዲ
አረቢያ የግብጽን ደሴቶች ማስረከቡን በማውገዝ 2000 የሚደርሱ ጋዜጠኞች
በማሕበሩ ጽ/ቤት ዙሪያ የተቃውሞ አንቅስቃሴ ማድረጋቸው ይታወሳል።

 የግብጽ መንግስት ሁለት ደሴቶችን ለሳኡዲ አረቢያ ካስረከበ ወዲህ ግብጽ ከሱዳን
የወሰደቻቸውን ሁለት ቦታዎች ለማስመለስ እንቅስቃሴ የተጀመረ መሆኑ ታውቋል።
ሱዳን በ 1948 ዓም ነጻነቷን ስታገኝ አለአግባባ ለግብጽ ተሰጥተዋል የሚባሉቱን
ሃይላቢን እና ሸላቲን በሚል ስም የሚጠሩ በቀይ ባህር ዳርቻ ላይ ያሉ ቦታዎች ለሱዳን
መመለስ አለባብቸው በማለት በተደጋጋሚ ጥያቄ አቅርባ ከግብጽ አዎችንታዊ መልስ
ሳታገኝ መቆየቷ ይታወቃል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ጥያቄው እንደገና ተነስቶ መወያያ
የሆነ ሲሆን በቅርቡ በይፋ ጥያቄ ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል። የሱዳኑ የውጭ ጉዳይ
ሚኒስትር ሰኞ ሚያዚያ 24 ቀን ለሱዳን ምክር ቤት አባላት ባሰሙት ንግግር ሱዳን
ግዛቶቿ እንዲሰጧት መጠየቋን የማታቋርጥ መሆኑን ገልጸው ይህንንም ተግባራዊ
ለማድረግ የተለያዩ ህጋዊና ፖሊቲካዊ መንገዶችን እየተወሰዱ መሆናቸውን ገልጸዋል።

 በዚህ ዓመት አፍሪካ የምታሳየው የኢኮኖሚ አድገት ባለፉት አስራ አምስታት ከነበሩት
ዝቀተኛ ሊሆን እንደሚችል የአለም የገንዘብ ድርጅት ገለጸ። ባለፈው ዓመት አፍሪካ
በአማካይ ያሳየችው የኢኮኖሚ እድገት 3.5 ከመቶ ሲሆን በዚህ ዓመት 3 ከመቶ ብቻ
ይሆናል የሚል ግምት ተሰጥቷል። የአፍሪካ የህዝብ ቁጥር እድገትም ሶስት ከመቶ
አካባቢ በመሆኑ እድገቱ የዜጎችን ህይወት በመለወጥ ረገድ ለውጥ ሊያመያ
እንደማይችል ተገምቷል። የሸቀጦች ዋጋ መቀነስና የመዋእለ ንዋይ መጠን መዳከም
ለእድገቱ ዝቀተኛ መሆን ምክንያቶች መሆናቸው ተገልጿል። ናይጄሪያና አንጎላ
በከፍተኛ ደረጃ የእድገት መቀነስ የታየባቸው ሲሆን ዛምቢያ እና ደቡብ አፍሪካም
መጎዳታቸው ተነግሯል።

 የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዚዳንት ሰኞ ሚያዚያ 24 ቀን 2008 በሰጡት መግለጫ ባለፈው
አስተዳድር ወቅት ናይጄሪያ 15 ቢሊዮን ዶላር በሙስና ተስርቃለች ብለዋል። ገንዘቡ
የተሰረቀው በተለያዩ ምክንያቶች ቢሆንም አብዛኛው ገንዘብ በሙስና መልክ የጠፋው
ወታደራዊ መሳሪያዎችን ለመግዛት ከተመደበው ወጭ ነው ብለዋል። ምክትል
ፕሬዚዳንቱ የተበዘበዘው የገንዘብ መጠን በጣም የሚያስደነግጥ መሆኑን ገልጸው
ምርመራው እየተካሄደ መሆኑን አስረድተዋል።

የሕዝብ ማእበልና ሱናሚ በመስቀል አደባባይ –ይገረም አለሙ

$
0
0

Kinijitየፊታችን ቅዳሜና እሁድ  የሚውሉት ሚያዝያ  29 እና 30   ከአስር ዓመት በፊት በ1997 ዓም በተመሳሳይ ቀናት ነበር የዋሉት፡፡  እነዛ ሁለት ቀናት  በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ጉልህ ሥፍራ ይዘው የሚኖሩ ትእይንቶች የታዩባቸው  ነበሩ፡፡ በተለይ ሚያዝያ ሰላሳ በዚህ ትውልድ ዳግም  ይታያል ተብሎ ለመገመት የማይቻል ትእይንት ነው አሳይቶን  ያለፈው፡፡

የምርጫ 97 ዋንኛ ተፎካካሪ የነበረው የአራት ፓርቲዎች ጥምረት  ቅንጅት ከድምጽ መስጫው ግንቦት 7/97 እለት አስቀድሞ በሚውለው እሁድ የምርጫ ዘመቻ ማጠናቀቂያ ሕዝባዊ ትእይንት በመስቀል አደባባይ እንደሚያደርግና የትዕይንቱ መሪ ቃልም ለዴሞክራሲ እናዚም/እንዘምር  የሚል አንደሆነ ቀደም ብሎ አስታወቀ፡፡ ይህን አንደሰማ ኢህአዴግም ለሚያዝያ 29 ቅዳሜ ፕሮግራም አንዳለው ገለጸ፡፡

የኢህአዴግ ትዕይንት ሕዝብ፤

የፖለቲካ ፉክክር አንድም አስቀድሞ አቅዶ በሚፈጸም ተግባር በልጦ መገኘት፣ ሁለትም የተፎካካሪዎችን እንቅስቃሴ እግር በእግር እየተከተሉ የሚሰሩትን በማየትና የሚናገሩትን በመቅለም አጸፋዊ ተግባር መከወን እንደመሆኑ የቅንጅት የምርጫ ዘመቻ ማጠቃለያ  ትእይንተ ሕዝብ ፕሮግራም እንደተሰማ ወይኔ በጥድፊያ  ተዘጋጅቶ ለሚያዝያ 29 በመስቀል አደባባይ ጥሪ አደረገ፡፡ በእለቱም በየቀበሌው የተለመደውን የካድሬ ስራ ሰርቶ፤ ንብ የታተመችበትን ካናቴራ አድሎ፣ ራቅ ላሉ ቀበሌዎችም የህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት አቅርቦ ሰዉን መስቀል አደባባይ አወጣው ወይንም አስወጣው፡፡ በዚህ ሁኔታ አደባባዩ በሕዝብ ተጥለቀለቀ፡፡ አቶ መለስም አይተውት የማያውቁትን የህዝብ ብዛት በአደባባይ ሲያዩ  እንዴትና በምን ሁኔታ እንደወጣ ሳይረዱ በጥይት መከላከያ መስተዋት ጀርባ ሆነው ባሰሙት ንግግር ስሜት ፈንቅሎአቸው ይህ የህዝብ ማእበል ምንም ማጭበርበር ሳያስፈልገው ምርጫውን ማሸነፍ ይችላል አሉ፡፡ በዚህም  ድርጅታቸው በምርጫ ተወዳድሮ ለማሸነፍ ሳይሆን አጭበርብሮ ለማለፍ የተዘጋጀ መሆኑን አጋላጡ፡፡ መሪዎች በአደባባይ የሚያደርጉት ንግግር ተጽፎ የሚሰጣቸው እንዲህ በስሜት ተገፍተው አደጋ የሚያመጣ ነገር እንዳይናገሩ ይመስለኛል፡፡ አቶ መለስ የተነፈሱትን ማናፈስ ስራቸው የሆኑት የመገናኛ ብዙኃንም በመስቀል አደባባይ የህዝብ ማእበል ታየ በማለት እያጋነኑ አቀረቡት፡፡

ይህ በመስቀል አደባባይ የታየውና ማዕበል ተብሎ የተገለጸው የህዝብ ቁጥር ኢህዴጋዊያንን ሲያስፈነድቅ( ለአንድ ቀንም ቢሆን)  በአንጻሩ ለቅንጅት አመራሮች ብቻ ሳይሆን ለአባላቱና ለደጋፊዎቹም ትልቅ ጭንቀት ፈጠረ፡፡ የጭንቀቱ ምክንያትም በማግስቱ ሚያዝያ ሰላሳ ቢያንስ ተመጣጣኝ የሆነ የህዝብ ቁጠር ይገኝ ይሆን የሚለው ነበር ፡፡

የቅንጅት ትዕይንተ ሕዝብ

እሁድ ሚያዝያ ሰላሳ ጠዋት ቀይ መስቀል፣ በመስቀል አደባባይ ዝግጅት ነበረው፡፡ የቅንጅት ጥሪ ደግሞ ከሰአት በኋላ ነው፡፡  አምስት ሰአት ተኩል አካባቢ መስቀል አደባባይ ስንደርስ  ቀይ መስቀሎች ጓዛቸውን እየጠቀለሉ ሲሆን አደባባዩ በሰው እየተሞላ ነበር፡፡ ሰአት ገና ነው ብለው ወደ አደባባዩ የደረሱት ቅንጅቶች ከጥሪው ቀድሞ የሰዉን መጉረፍ ሲመለከቱ መድረክ የማዘጋጀቱንና   የድምጽ መሳሪያ የመዘርጋቱን ሥራ ማጣደፍ ጀመሩ፡፤ ፌዴራል ፖለሶች ደግሞ ጎን ለጎን ተያይዘው በመቆም ሰዉ ወደ መኪና መንገዱ እንዳይገባ ለማደረግ አጥር ሰሩ፡፡ ነገር ግን የሰዉ ቁጥር ሲጨምር ሲያፈገፍጉ በዚህ መልኩ እየተገፉ ሄደው መጨረሻ ክቡር ትሪቡኑ ስር በሚገኘው ምሽጋቸው ውስጥ ተጠቃለው ለመግባት ተገደዱ፡፡  መንገዱ ሙሉ በመሉ በህዝብ ተሟላ፡፡

ወደ መስቀል አደባባይ የሚያደርሱት ስድስቱም መንገዶች በህዝብ ተጨናነቁ፤ከፒያሳ አቅጣጫ የሚመጣው ከፖስታ ቤት፤ከሜክሲኮ አቅጣጫ የሚመጣው ከቡናና ሻይ፤ ከሳሪስ የሚመጣው ከአራተኛ ክፍለ ጦር፤ ከቦሌ የሚመጣው ከፍላሚንጎ፤ ከመገናኛ አቅጣጫ የሚመጣው ከባምብሲ፤ከአራት ኪሉ የሚመጣው ከታላቁ ቤተ መንግሥት ማለፍ አልቻለም፡፡ የቅንጅቶች መድረክ በሕዝብ ተውጣ እንኳን ከሩቅ ከቅርብም የማትታይ ሆነች፡፡ ከመድረክ የሚነገረውም የሚሰማው  በመድረኩ ዙሪያ  ላሉት ብቻ ሆነ፡፡

ማእበል ለመባል ከበቃው በኢህአዴግ ትእይንተ ሕዝብ ላይ ከተገኘው የህዝብ ብዛት ይህኛው በሁለት ምን አልባትም በሶስት እጥፍ የሚበልጥ በመሆኑ ሱናሚ ተባለ፡፡ በወቅቱ በወያኔ  አደገኛ ቦዘኔ ከመባል አልፎ ህግ ወጥቶ እየታደነ ይታሰር የነበረው ወጣት አደገኛ ቦዘኔ ራሱ ወያኔ፤ ወጣቱ ስራ አጥ አንጂ ቦዘኔ አይደለም በማለት በየምርጫ ቅስቀሳ መድረኮች ሲያሰማው የነበረውን መፈክር በአደባባዩ ከማሰማት አልፎ አደገኛ ቦዘኔ ያለመሆኑን ያሳየበትን ተግባር ፈጸመ፡፡ በአደባባዩ የተተከሉ የጌጥ መብራቶች ስስ ከመሆናቸው የተነሳ በቀላላ ሊሰበሩ የሚችሉ ቢሆኑም ወጣቱ ባደረገው ጥንቃቄና መከላከል በዛ የህዝብ መጨናነቅ ውስጥ አንድም ጉዳት ሳይደርስ ቀረ፡፡ የእጅ ስልኮች ወድቀው ተገኝተው ወደ መድረክ ተላለፉ፡፡ ሰልፉ ከተበተነ በኋላ በህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ሲሳፈሩ ራሳቸው ስርአት አስከብረው አንድ ሰው ሳይከፍል አንዳይሳፈር ገንዘብ ያልያዘ ካለ ያልያዛ አንዲከፍልለት እያደረጉ ወጣቶች ኢትዮጵያዊ ጨዋነታቸውንና ህግና ሥርዓት አክባሪነታቸውን በተግባር አሳዩ፡፡ ትናንት ለእንጀራችን ዛሬ ለእምነታችን፤ ትናንት ለካናቴራ ዛሬ ለባንዲራ ወዘተ የሚሉ መፈክሮችም በየቦታው ተሰሙ፡፡ እነዚህ  ኢህአዴጋዉያንን በእጅጉ ያበሳጩ እንደነበሩ ለማተዘብ ተችሏል፡፡

የቅንጅቶችም ጭንቀት  ለኢህአዴግ የወጣውን ያህል ህዝብ ይወጣልን ይሆን ከሚለው ይህ ሁሉ ሕዝብ በሰላም በየቤቱ ይገባ ይሆን  ወደሚል ተለወጠ፡፡ ቢያንስ በጥንቃቄና በኢትዮጵያዊ ጨዋነት ወደየቤቱ እንዲሄድ መልእክት ለማስተላለፍ አለመቻሉ የቅንጅቶችን ጭንቀት እንዳበረታው በመድረኩ እቅራቢያ የነበርን ታዝበናል፡፡ ነገር ግን ፕሮግራሙ አንዳለቀ ከየት መጣ ያልተባለ ዝናም ድንገት ወረደና በተነን፡፡ ከፊሉ መጠለያ ፍለጋ ሲሯሯጥ በተለይ ወጣቱ በቡድን  በመሆን እያዜመ ዝናቡ ምንም ሳይመስለው ጉዞውን ቀጠለ፡፡ምሽት ላይ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን የተለመደውን ተቃራኒ ዜና ሰሩ፡፡  ይህ ደግሞ ህዝቡን ይበልጥ አበሳጨው፡፡

የሀያ ዘጠኙ ትእይንተ ሕዝብና የተሰራው ፕሮፓጋንዳ በሰላሳ ሕዘቡ ነቅሎ አንዲወጣ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ አንድ ምሳሌ ልጥቀስ ከሰፈሬ አንድ በእድሜ ጠና ያሉ ሰው ትእይንተ ሕዝቡ ላይ ተገኝተው አንደነበረ ሲያጫውቱኝ፤ የቅንጅቶችን ጥሪ አስቀድሜ  ብሰማም የመውጣት እቅድ አልነበረኝም፤ የቅዳሜውን ሰው ሳይ ግን አንዴት እንዲህ ይሆናል አልኩ፤ፕሮፓጋንዳቸው ደግሞ ይበልጥ አበሳጨኝና ለመውጣት ወሰንኩ፡፡ግን ከፖስታ ቤት ማለፍ አልቻልኩም፤ ባየሁት የህዝብ ብዛት ግን በጣም ነው የተደሰትኩት ነበር ያሉኝ፡፡

ዳግም ይታይ ይሆን!

ከዚህ  ማእበልና ሱናሜ ከተባለ ተእይንተ ህዝብ ወያኔ በሚገባ መማሩን ተግባሩ ይመሰክራል፡፡ ተቀዋሚው ግን የተማረ አይመስለኝም፡ወያኔ ቅዳሜ ያን ያህል ሕዝብ ወጥቶ አቶ መለስንም ምስጢር አስወጥቶ በማግስቱ በሁለት እጥፍ መውጣቱ በህዝብ ልብ ውስጥ አለመኖሩን  እንዲገነዘብ አስችሎታል፡፡ በህዝብ ካልተወደደና ተቀባይነት ከሌለው ደግሞ በህጋዊ አግባብ ፍላጎቱና ማሳካት፣ ወንበሩንም ማስጠበቅ አይቻለውም፡፡ ስለሆነም ህገ ወጥ ህጎችን ማውጣት፣ ማናቸውንም አንቅስቃሴዎች በጠመንጃ ጸጥ ማሰኘት፣ ፓርቲዎች  ከቢሮአቸው መግለጫ ማውጣት ያለፈ  እንቅስቃሴ አንዳይኖራቸው ማድረግ ወዘተ ስራው ሆነ፡፡

ወያኔ ያን መሰል የሕዝብ  እንቅስቃሴ ዳግም በኢትዮጵያ እንዳይኖር ለማድረግ ያስቻለውን ስራ ቢሰራ  ከታገለለት ዓላማና  ከሥልጣን ወይንም ሞት መርሁ አንጻር ተገቢ  ነው፡፡  ተቀዋሚዎች ግን ወያኔ ለሥልጣኔ አስጊ ብሎ የፈራው ይህ የህዝብ ተነሳሽነት አስፈላጊነቱን አምነው አንዲቀጥል ለማድረግ የሚያስችል ስራ ለመስራት አለመቻላቸው  ነው እንቆቅልሹ፡፡

በምርጫ 97 ለታየው  የህዝብ ተነሳሽነት የሚጠቀሱ እንደየሰው አስተሳሰብ የሚለያዩ ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩም  አንዱ ምክንያት አራት ፓርቲዎች  ቅንጅት ፈጥረው አንድ ሆነው መቅረባቸው እና በቅንጅት አመራር ውስጥ  ከዛ በፊት ብዙም በፖለቲካው መድረክ ያልታዩ ሰዎች ብቅ ማለታቸውና የህዝቡን አመኔታ ማግኘታቸው መሆኑ  ሁሉም ሰው የሚስማማበት  ይመስለኛል፡፡

በአንድ ዓላማ ተሳስሮ በልዩነት ተከባብሮ ህብረት ፈጥሮ በአንድ የትግል መስመር ላይ መቆም አንዲህ ተአምራዊ የህዝብ ተነሳሽነት አንደሚፈጥር በተግባር ታይቶ እያለ ለዚህ  መሳካት የየግል ፍላጎትን በመክላትና ድብቅ አጀንዳን በማስወገድ መስራት ሲገባ ፖለቲከኞቻችን ከራስ በላይ ማሰብ እየተሳናቸው  ትብብር ሊፈጥሩ ቀርቶ የጀመሩትንም እያፈረሱና እየበተኑ ለወያኔ እድሜ ማራዘሚያ መድሀኒት ይሆናሉ፡፡

የፖለቲከኞቻችን ችግር ከዚህም ይዘላል፡፡አለመተባበር ብቻ ሳይሆን መቀናናትም አለ፤ አንዱ የተሻለ መስራት ከቻለና የህዝብ አመኔታና ድጋፍ ካገኘ ሌላው እሱም ሰርቶ ለመታመን ከመጣር ይልቅ  ለሚሰራው እንቅፋት ይሆናል፡፡ቅንጅት ሚያዝያ 30/97 ያን ያህል ሰው አደባባይ ስለወጣለት በቅናት ያረሩ በተበለጥን ሰይጣናዊ ስሜት የተቃጠሉ ስሜታቸውን መቆጣጠር እየተሳናቸው ይህን የሚያጋልጡ ቃላት ከአፋቸው ሲያመልጡ እየሰማን ታዝበናል፡፡ ይህን ደግሞ ስም ግዜና ጋዜጦችን እየጠቀሱ ማስረጃ ማቅረብ ቢቻልም  ቢያንስ ለዛሬ ጠቀሜታ የለውምና ይቅር፡፡

በአጠቃላይ ሚያዝያ 29 እና 30/97 ያየነው ትእይንት ዳግም ሊታይ መቻሉ አጠራጣሪ ነው፡፡ ይህም የሆነው  ወያኔ ሕዝብን አደባባይ ቢያወጣ ወደ ተቃውሞ ተቀይሮ በራሱ ጥሪ ራሱ አንዳይወገዝ ተቃውሞ አንዳይደርስበትና በህዝቡም ዘንድ አዲስ መነሳሳት እንዳይፈጠር ስለሚሰጋ  ሲሆን በተቃውሞው ጎራ ደግሞ ያንን ለማድረግ የሚያስችል እቅም ያለው ፓርቲም ሆነ ህብረት ባለመኖሩ ነው፡፡

 

የ“ከአሜን ባሻገር” —- ጥቂት ውሸቶች?!  –ተጻፈ ከዶኖ ኢበሮ

$
0
0
beyondamenየበዕውቀቱ ስዩምን “ከአሜን ባሻገር” የመጀመሪያ እትም ለማግኘት ባለመቻሌ ሁለተኛው እስኪታተም በከፍተኛ ጉጉት ስጠባበቅ ቆየሁኝ፡፡ ስለ መጽሐፉ የተሰነዘሩ ሙገሳዎች (ለምሳሌ አዲስ አድማስ ጥር 14 እና የካቲት 5 ቀን 2008 እትሞች) ጉጉቴን ጨመሩት። ከብዙ ያልተሳኩ የመጽሐፍት በረንዳ ጉብኝቶች በኋላ መጽሐፉ የካቲት አጋማሽ 2008 ከእጄ ገባች፡፡
ስለ ራስ ጎበና የተጻፈውን የጎበና ቅኝት የተሰኘውን የመጽሐፉን ክፍል እያነበብኩ ሳለ ከሚከተለው አንቀጽ ጋር ተፋጠጥኩ፡፡ እንዲህ ይላል፡-
“በከፋ አንድ ሰው በጥንቁልና ከተወነጀለ ከነቤተሰቡ ይቃጠል ነበር፡፡ የከፋው ንጉስ ምግቡን በእጁ ቆርሶ መብላትን እንደ ውርደት ስለሚቆጥረው አጉራሽ ሎሌ ነበረው፡፡ አጉራሹ ባርያ ንጉሡን ከማጉረስ ሌላ የሕይወት ተልዕኮ ስላልነበረው፣ ንጉሡን የሚያጎርስበት እጁን በከረጢት ጠቅልሎ መኖር ነበረበት፡፡ በንጉሡ ዓይን ይህ ሎሌ ሰው ሳይሆን ተንቀሳቃሽ ማንካ ነበር፡፡ ስለዚህ በኒያ ግዛቶች ሲኖሩ የነበሩ ህዝቦች ነፃነታቸውንና ሰላማቸውን በጎበና ምኒልክ እንደተቀሙ ሊቆጠር አይገባም፡፡ ሲጀመር ከሰላምና ከነፃነት ጋራ መች ይተዋወቁና፡፡”
የዚህ ጽሑፍ ዋና ዓላማ ከላይ በሰፈረው አንቀጽ ላይ የተቀመጡት የበዕውቀቱ ውሸቶችና ዘለፋዎች ላይ ቅሬታዬን ለመግለጽና ስህተቶቹን የማውቀዉን ያህል ለማሳየት ነው፡፡ መጽሐፉን የሚያነቡ ወገኖቼንም ከተዛባ አሉታዊ አመለካከት በመከላከልና በመመለስ የበኩሌን ለመወጣት ነዉ፡፡ እንደ ካፋ ብሔር ተወላጅነቴም (ትክክለኛው አጠራር ካፋ እንጂ ከፋ አይደለም) ሆነ ኢትዮጵያዊነቴ በዝምታ ባልፈው የህሊና ወቀሳው ዘወትር አይለቀኝም፡፡
የጎበና ቅኝት ጎበናን ለማወደስ የተጻፈ ከሆነ፣ ከላይ የተቀመጠው አንቀጽ አላማውን የሳተ ለመሆኑ አመዛዛኝ አንባቢ የሚገነዘበው ሀቅ ነዉ፡፡ አንባቢ ሆይ፤ ይህ አንቀጽ የጎበናን ታላቅነት ምን ያህል ያሳያል? ለእኔ በካፋና በሌሎች የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ላይ የተሰነዘረ በውሸት የታጀበ ስድብ ነዉ፡፡ ጎበናን ለማወደስ የፈፀማቸውን መልካም ተግባራትና ጀግንነቱን ማሳየት ይበቃል፡፡ በነገራችን ላይ ከላይ የተቀመጠው አንቀፅ ሙሉ በሙሉ ማስረጃ ያልተጠቀሰለት መሆኑን ልብ ልንል ይገባል፡፡ በዕውቀቱ ስዩም፤ በካፋ ንጉስና ህዝብ ላይ ያቀረባቸው ውንጀላዎች ከተዛባ አስተሳሰቡና ከአላጋጭነቱ የመነጩ ስድቦችና ውሸቶች ናቸዉ፡፡
በከፋ አንድ ሰው በጥንቁልና ከተወነጀለ ከነቤተሰቡ ይቃጠል ነበር ያለው ማስረጃ ያልጠቀሰለት ውንጀላ ነዉ፡፡ በተቃራኒው በካፋ ግዛተ ዓጼ፣ ቃልቾች ከፍተኛ ከበሬታና ስልጣን ነበራቸው፡፡ ሩስያዊዉ ወታደር አሌክሳንደር ቡላቶቪች፣ በካፋ አረማዊ (ፓጋን) እምነት እንደነበርና ከክርስትና እና አይሁድ እምነቶች ድብልቅ ድርጊቶች ይፈጽሙ እንደነበር ዘግቧል፡፡ የመጨረሻዎቹ ስድስት ነገስታት እምነት ይህ ነበር፡፡ (ከዚያ በፊት ንጉሡም ሆነ የካፋ መንግስት የክርስትና እምነት ተከታይ ነበር፡፡) በተጨማሪም እምነታቸውን አጥብቀዉ ሲከተሉ የነበሩ ኦርቶዶክስ ክርስትያኖችና በሚሲዮናዊያን (አባ ማሳያ) የተለወጡ ካቶሊኮችም እንደነበሩ ቡላቶቪች ጽፏል። ሙስሊሞችም ሆኑ ዐረቦችም ነበሩ፡፡ ጥቂትም ቢሆኑ (ጥንታዊውን የባሃ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስትያንም ጨምሮ) ጥንታዊ አብያተ ክርስትያናት ነበሩ፡፡ (አሁንም አሉ።) በካፋ አንፃራዊ የእምነት ነፃነት እንደነበረ ከቡላቶቪች መረዳት ይቻላል፡፡
የካፋ ንጉስ ምግቡን ከሰው እጅ መጉረሱ ለበዕውቀቱ እንዴት ከጭፍጨፋና ባርያ ፍንገላ እኩል ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ሆኖ እንደታየው ሊገባኝ አልቻለም። ኢትዮጵያዊ እንደመሆናችን አጉራሽ ማለት የፍቅርና አክብሮት መግለጫ ነዉ፡፡ እኔ እንደሚገባኝ ከአንድ ሰው እጅ መጉረስ ላጉራሹ ያለንን ፍቅር፣ እምነትና አክብሮት ያመለክታል፡፡ የካፋው ንጉሥም ቆርሶ መመገብን እንደ ዉርደት ስለሚቆጥር ተብሎ ሊወገዝ አይገባም፡፡ ይህ ስርአት ንጉሱን ራሱን ሊጎዳ የሚችልበት እድል እንዳለ ግልጽ ነዉ፡፡ ነገስታት የገዛ ቤተሰቦቻቸውን እንኩዋን በማያምኑበትና ለስልጣናቸው ሲሉ ወንድም እህት፣ እናት አባት በሚያግዙበትና በሚያጠፉበት ዘመን፣ የካፋው ንጉስ ምግቡን ከሎሌዉ እጅ መጉረሱ ላጉራሹ ያለውን እምነትና ክብር የሚያሳይ፣ የሚገርምና የሚያስደንቅ ስርአት ነዉ፡፡ ምክንያቱም አጉራሹ ታማኝነት የጎደለው ከሆነና ንጉሡን መጉዳት ከፈለገ ምን ሊያደርግ እንደሚችል ግልፅ ነዉ፡፡
የካፋው ንጉሥ መጋቢ፣ ባርያ ሳይሆን በታማኝነቱ የተመረጠ ሹም ነበር፡፡ ንጉሱ ግብር በሚያበላበት ጊዜ ከታዳሚው ከሚለየው መጋረጃ፣ ከንጉሱ ጋር ገበታ የሚቀመጠው ይህ ሰዉ ብቻ ነበር (ቡላቶቪችም እንዳስቀመጠዉ)፡፡ የንጉሡ መጋቢ ንጉሱን የሚያጎርስበትን እጁን በጨርቅ የሚሸፍነዉ በዕውቀቱ አጣሞ እንዳቀረበው፣ ሌላ የሕይወት ተልዕኮ ስላልነበረው አይደለም፡፡ ቡላቶቪች እንደጻፈዉ፡-
‘During the time when he was away from his main duties, his right arm was tied in a canvas sack, in order that this arm, which fed the king, not contract some illness or be bewitched.’ ትርጉሙም፡- ‘ከዋና ግዳጆቹ የተለየ እንደሆነ ንጉሡን የሚያጎርስበትን ቀኝ እጁን ከበሽታና ከክፉ ድግምት (ጥንቆላ) ለመከላከል በጨርቅ ይሸፍን ነበር፡፡’ ይህ የቡላቶቪች ዘገባ በራሱ ግለሰቡ ሌሎች ስራዎች (duties) እንደነበሩት የሚያሳይና የበዕውቀቱን ውሸት የሚያስረዳ ነወ፡፡ ይህ የስራ ድርሻ ከፍተኛ ዋጋ የነበረዉ መሆኑን ቡላቶቪች ዘግቧል፡፡ ;This post was considered very important in the court hierarchy. This dignitary had to be distinguished for the best moral qualities so as not to in any way harm the king.; ትርጉሙም፡ ይህ የስራ ድርሻ በንጉሱ / ቤተመንግስቱ በጣም ከፍ ያለ ስልጣን ነበረ፡፡ ሹሙም ንጉሱን በምንም አይነት የማይጎዳ መሆኑ በመልካም ምግባሩ ልቀት የተረጋገጠ ነበረ፡፡
በንጉሡ ዐይን ይህ ሎሌ ሰዉ ሳይሆን ተንቀሳቃሽ ማንካ ነበር ማለቱ የበዕውቀቱ ተሳዳቢነትን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡ ይህ ሰው አብሮት ማእድ የሚቀመጥ የሚያከብረው ሰው ነበር እንጂ ንጉሱ እንደ ባርያ ወይም ግኡዝ እቃ የሚያየው አልነበረም፡፡ በዕውቀቱ፤ ንጉሡ ስለ አጉራሹ ይህ አመለካከት ነበረው ለማለት እንዴት ቻለ? ከየትስ አመጣው? ምንጭ ሳይጠቅሱ የራስን አስተሳሰብና የተዛባ ሚዛን በመያዝ መሳደብና ማላገጥ ስለፈለገ ብቻ ይመስለኛል፡፡ ይህን ስርአት ጥፋት ብሎ ከመፈረጅ በፊት የዚህ ስርአት መነሻ ምንድነው፣ ንጉሡ ስለ ግለሰቡ የነበረው አመለካከትስ፣ ሰውየውስ በህብረተሰቡ ዘንድ ያለው ክብርና ቦታ ምንድነው፣ ይህ ተግባርስ ሁሌ ነው ወይስ አንዳንዴ ነው የሚፈጸመው፣ ስራውስ በአካልና በስነልቦናው ላይ ያስከተለው ጉዳት ነበር ወይ፣ ድርጊቱንስ በፍላጎት ነዉ ወይስ በግድ ነበር የሚፈፅመው፣ የራሱ ቤተሰብና ሕይወትስ ነበረው? የሚሉትንና ሌሎች ጥያቄዎችን መመለስ ያስፈልጋል፡፡ በዕውቀቱ ይህን ሳያደርግ መዛለፉ ከተለመደው ጨዋነት የተፋታ ለመሆኑ አብይ ማረጋገጫ ነዉ፡፡
ሌላዉ በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ “በኒያ ግዛቶች ሲኖሩ የነበሩ ህዝቦች ነፃነታቸውንና ሰላማቸውን በጎበና ምኒልክ እንደተቀሙ ሊቆጠር አይገባም፡፡ ሲጀመር ከሰላምና ከነፃነት ጋር መች ይተዋወቁና፡፡” ብሎ መፃፉ ነዉ፡፡ ይህ አባባል ፈፅሞ ሀሰት ነዉ፡፡ ላገራችን ህዝቦችም ያለውን ታላቅ ንቀት ያሳያል፡፡ ለመሆኑ ሰላም ምንድነው? ነፃነትስ? በዕውቀቱ አላብራራም፡፡ ሰላም ማለት ከጦርነት፣ ከግጭትና ብጥብጥ ነፃ መሆን ነዉ፡፡ ነፃነትም ሰዎች በምርጫቸውና ፍላጎታቸዉ መኖር ማለት ነዉ፡፡ በተለይ ነፃነት አንፃራዊ ነዉ፡፡ በዕውቀቱ፤ ሲኖሩ የነበሩ ሲል አሁንም ያሉ መሆናቸውን መዘንጋቱን ያሳያል፡፡ ለመሆኑ የተለየ ልማድ የሰላምና ነፃነት መጥፋት ማሳያ ነዉ እንዴ? እንዲያ ከሆነማ ኢትዮጵያውያን በርካታ ልዩ ልማዶች ስላሉን፣ ከሰላምና ነፃነት ጋር አንተዋወቅም ማለት ነዉ፡፡
የካፋ፣ ጎማ፣ ሸካና ሌሎች የደቡብ ምዕራብ አትዮጵያ ህዝቦች የራሳቸው አስተዳደር፣ ባህል፣ አኗኗር የነበራቸው ሲሆኑ በራሳቸው ሀገር በሰላምና በነፃነት ይኖሩ ነበር፡፡ እንደማንኛዉም መንግስት የራሳቸው ጠንካራና ደካማ ጎኖች ነበራቸው፡፡ በየትኛውም ዘመንና ስርዓት ስህተት አይጠፋም። በአሉባልታና ድርጊቶችን አዛብቶ በማቅረብ ከሰላምና ነፃነት ጋር የማይተዋወቁ ማለት ስህተት ነዉ፡፡
በካፋ ለብዙ ምዕተ ዓመታት ፀንቶ የኖረ ጠንካራ የንጉስ አስተዳደር ነበር፡፡ ካፋ በ12 ወራፎዎች (ክፍለ ሀገር) ተከፋፍላ ትተዳደር ነበር፡፡ እያንዳንዱም የራሱ አስተዳዳሪ (ራሻ) ነበረው። በወራፎዎችም ስር አካባቢያዊ አስተዳደሮች ነበሩ፡፡ ንጉሱም እለታዊ አስተዳደራዊ ስራዎችን የሚያከናውኑ ሰባት ሹሞች (ሚኪሬቾ) ነበሩት
ሰባቱ ሚክረቾ ከስድስት ቶሞ (ጎሳዎች/clan) የሚመረጡ ናቸው፡፡ እርሻና እደ-ጥበብም በሰፊዉ ይካሄዱ ነበር፡፡ ካፋ ከፍተኛ የንግድ ማዕከል እንደነበረች በስፋት የሚታወቅ ነው፡፡ ቡና፣ ሰብል፣ ማር፣ ቅመማ ቅመም፣ የእደ-ጥበብ ዉጤቶች፣ የዝሆን ጥርስ ወዘተ የሚገበይባት ነበረች፡፡ እነዚህ እውነታዎች የሰላምና ነፃነት ማሳያ ናቸዉ። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ከሰላምና ነፃነት ጋር የማይተዋወቁ ማለት ያፈጠጠ ውሸት ነው፡፡ በአንጻሩ በወራሪው ሰራዊት ብዙኃን ተገድለዋል፡፡ ዝርፍያና ውድመትም ተካሂዷል፡፡ እጅግ ትልቅ የነበረው የዋና ከተማዉ የአንደራቻ ቤተ መንግስትም በራስ ወ/ጊዮርጊስ ከተያዘ በኋላ በቃጠሎ አውድመውታል። የቦንጋ ቤተ መንግስትም በወራሪው ወድሟል፡ ረሃብና ባርያ ፍንገላ በመስፋፋታቸው ለምና ምቹ የነበረችው ምድር ሰው አልባ ሆነች፡፡ (ይህን ከቡላቶቪች መጽሀፍ ማግኘት ይቻላል፡፡ Alexander Bulatovich: With the Armies of Menelik II Emperor of Ethiopia. Translated by Richard Seltzer)
የመጨረሻው የካፋ ንጉስ ታቶ ጪኒቶ ጋሊቶ (ጋኪ ሻረቾ) ከ9 ወራት ጦርነት በኋላ ነሐሴ 1897 ተይዞ በአንኮበርና አዲስ አበባ በእስር ሲማቅቅ ቆይቶ በ1919 ህይወቱ አልፏል፡፡ (ተመርዞ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል) ምኒሊክ የካፋን ታሪክ ለማጥፋት የካፋውን ንጉስ ዘውድ ወደ ስዊዘርላድ እስከመላክ ደርሰዋል፡፡ ካፋና ህዝቧ ከዚያ እልቂትና ጉዳት እስካሁን አላገገሙም፡፡ ይህን ነው በዕውቀቱ አንፃራዊ ሰላም ሰፍኖ ነበር የሚለን፡፡ ከግራኝ ወረራ በፊት ከኢትዮጵያ ነገስታት ጋር ግኑኙነት የነበረውና ንግስናው የተከበረለት የካፋው ንጉስ፣ ከዐፄ ምኒልክ የቀረበለት የሰላም ጥሪ ሆነ እውቅና የነበረ አይመስለኝም፡፡ (ከተሳሳትኩ በማስረጃ ልታረም እችላለሁ) ይልቁንም ተደጋጋሚ ወረራ በማካሄድና በላዩ ላይ ሌላ ንጉስ በመሾም በጦርነት ማስገበርን መርጠዋል፡፡ (ራስ ወልደ ጊዮርጊስ የካፋ ንጉስ ተብለው ተሹመው ነበር ወደ ካፋ የዘመቱት፤አፄ ዮሐንስም የጎጃሙን ንጉስ ተክለሐይማኖት በካፋ ላይ ሾመዋል፡፡) በዚህም የምኒልክ አካሄድ ስህተት እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል፡፡ በካፋ ለደረሰው ጥፋትና እልቂትም ምኒሊክ ተጠያቂ ናቸው፡፡
ጎበና በካፋ ተሸንፎ መመለሱ የታወቀ ነዉ፡፡ ራስ ወልደጊዮርጊስም በመጀመሪያ ሙከራቸው ተሸንፈው ወደ ሸዋ ተመልሰዋል፡፡ የካፋ መንግስት የተሸነፈው በራስ ወልደ ጊዮርጊስ በተመራውና ራስ ተሰማ፣ ደጃዝማች ደምሰው እና የጅማዉ አባ ጅፋር በተሳተፉበት ጦርነት ነዉ፡፡ ያኔ ራስ ጎበና በህይወት አልነበረም፡፡ ስለሆነም በዕውቀቱ ታሪክ ሳያውቅ ስለ ታሪክ መፃፉን አንባቢው ሊረዳ ይገባል፡፡ ሌሎች ግድፈቶችም አሉ፡፡ መዘርዘሩ የዚህ ፅሁፍ አላማ ስላልሆነ ትቸዋለሁ፡፡
በዕውቀቱ፤ አፈወርቅ ገብረየሱስንና ገብረሕይወት ባይከዳኝን ስለ ሌላው ህዝብ በጣም ግልብ እውቀት ያላቸው ብሎ ይዘልፋል፡፡ የራሱ ዘለፋዎችና ውሸቶች “ከጥልቅ እውቀቱ” የመነጩ መሆናቸው ነው? በዕውቀቱ መረጃ በእጅ ጫፍ (A click away) በሆነበት በዚህ ዘመን፣ ለዚያውም አሜሪካ ቁጭ ብሎ (ሌላዉ ቢቀር ዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘዉ ኮንግረስ ላይብረሪ የአለማችን ትልቁ ቤተ መጻህፍት ነዉ) ይህን የዘለፋና ውሸት ስብስብ መፃፉ አሳፋሪ ተግባር ነው፡፡ በአንድ አዳራሽ የተነገሩ ብሔር ተኮር ቀልዶችን የወቀሰው በዕውቀቱ፣ የርሱ በጽሁፍ የተቀመጡ ስድቦችስ ምን ይባሉ ይሆን? የራስ ዐይን ውስጥ ያለ ግንድ ሳያዩ ከሌላ አይን ጉድፍ ማውጣት ይሏል ይህ ነዉ፡፡ ስለ ታሪክ ለመፃፍ ሰፊ የታሪክ ዕውቀት፣ ጥናትና ምርምር ይጠይቃል፡፡ የታሪክ አፃፃፍም የራሱ ስርአት አለው፡፡ በሀገራችን ያልተፃፈ ታሪክ የበዛ እንደመሆኑ በርካታ ሰዎችን ማነጋገር ያስፈልጋል፡፡ ከሁሉም በላይ ሚዛናዊነትንና አክብሮትን ይጠይቃል፡፡ በዕውቀቱ ስዩም የፈጸመው ድርጊት ግን በተቃራኒው ከስነምግባር ውጭ የሆነና በጥብቅ ሊወገዝ የሚገባው ነዉ፡፡ በዕውቀቱ በዚህ መጽሐፉ ከባድ ጥፋት እንደፈጸመ ለመጠቆም ሞክሬያለሁኝ፡፡ በኔ እምነት ሀሳብን የመግለፅ ነፃነት፣ ስድብንና ውሸትን በሌሎች ላይ መሰንዘርን አይጨምርም፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ በቂ የሆነ ምላሽ ሰጥቻለሁ ብዬም መሉ በሙሉ አልተማመንም፡፡ ስለሆነም ሌሎች በተለይም የታሪክና የህግ ምሑራን አስተያየት ቢሰጡበት መልካም ነው እላለሁ፡፡

በርካታ ኢትዮጵያውያን የሚኖሩባት የካናዳዋ ፎርት ማክማሪ ከተማ በእሳት እየነደደች ነው

$
0
0
ነዋሪዎች በዚህ መልኩ ነው ከከተማዋ እየሸሹ የሚገኙት

ነዋሪዎች በዚህ መልኩ ነው ከከተማዋ እየሸሹ የሚገኙት

(ዘ-ሐበሻ) የካናዳ የነዳጅ ዘይት እምቅ ሃብት ያላት ፎርት ማክማሪ ከተማ በ እሳት እየነደደች መሆኑና ሁሉም የከተማው ነዋሪ ከተማዋን ለቆ እንዲወጣ መደረጉን ኤንቢሲ የዜና አውታር ዘገበ::

የከተማዋ አውራ ጎዳናዎች ከተማዋን ለቅቀው በሚወጡ ሰዎች ተጨናንቆ እንደነበር የገለጸው የዜና ምንጩ በተለያዩ ካምፖች ተጠልለው እንደሚገኙ አስታውቋል::

በከተማው እየደረሰ ባለው ቃጠሎ የተነሳ ነዋሪዎች ከተማዋን እየለቀቁ ሲወጡ የ እሳቱን እና ጭሱን እያለፉ ለመንዳትና ለመሸሽ እንደተገደዱ የገለጸው የዜና ምንጩ በጠቅላላ የከተማዋ ነዋሪዎች ለቀው እንዲወጡ ት ዕዛዝ መተላለፉንም ዘግቧል::

ከትናንት ማታ ጀምሮ በከተማዋ በተነሳው እሳት በርካታ ንብረቶች ሲወድም እስካሁን በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት ስለመድረሱ የተዘገበ ነገር አላገኘንም::

 ነዋሪዎች በዚህ መልኩ ነው ከከተማዋ እየሸሹ የሚገኙት


ነዋሪዎች በዚህ መልኩ ነው ከከተማዋ እየሸሹ የሚገኙት

በፎርት ማክማሪ ከተማ ቤከን ሂል መንደር 80 በመቶ የሚሆኑ ቤቶች በቃጠሎ ነደው ወድመዋል:: መላው የካናዳ የ እሳት አደጋ ተቆጣጣሪዎች ከተማዋን ለማትረፍ እሳቱንም ለማጥፋት እየተረባረቡ ነው::

በሰሜን አልበርታ ካናዳ ግዛት ስር የምትገኘው ፎርት ማክማሪ ከተማ የሃገሪቱ ከፍተኛ የነዳጅ ዘይት ማውጫ ከተማ ስትሆን በርካታ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራዊያን እንደሚኖሩባት ይታውቀዋል::


በትግራይ ቓፍታ ሑመራ ከ2 ሺ በላይ ወጣቶች ታሰሩ

$
0
0

(አምዶም ገብረሥላሴ ከመቀሌ እንደዘገበው)

በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ከ2 ሺ በላይ ወጣቶች በፀረ ሽፍታ ልዩ ሃይል ታድነው ታስረዋል።

(ሁመራ ከተማ)

(ሁመራ ከተማ)

ከ2 በላይ ወጣቶች ታድነው የታሰሩት በቓፍታ ሑመራ ወረዳ የሚገኙ በባህላዊ መንገድ ወርቅ የሚወጣባቸው ቦታዎች ነው።
የወርቅ የሚወጣበት ቦታ ከዓዲ ጎሹ እስከ ዓደባይ የሚገኝ ሰፊ መሬት ከሸረ ወደ ሑመራ ሲጓዙ ወደ ሰሜን ኣቅጣጫ የሚገኝ ሲሆን እስከ ኢትዮ_ኤርትራ ድንበር የሚያዋስን የተከዘ ዳርቻዎች የተዘረጋ ነው።
ኣፈሳው የተካሄደው በጠበቖ(ኣንድ ወጣት ሙቶ የተገኘበት)ገዛ ግርማይ፣ መቓብር ዓንደማርያም፣ እነይ ቕበፅኒ ከሚባሉ በወርቅ የበለፀጉ የተከዘ ደንደሶች ነው የተያዙት።(ከዚ በፊት 85 ወጣቶች የታገቱበት ቦታ ነው።) በሺ የሚቆጠሩ ወጣቶች ከፀረ ሽፍታ ልዩ ሃል እንዳመለጡ ታውቀዋል።
ቦታው ወርቅ የሚወጣበት ብቻ ሳይሆን ታጣቂዎች ከኤርትራ እየተሻገሩ በሺ የሚቆጠሩ ወጣቶች ኣግተው የሚወስዱበትና የሚገድሉበትም ጭምር ነው።
የፀረ ሽፍታ ሃይሉ በወጣቶቹ ላይ ዘመቻ የጀመረው ከ17 እስከ 20 /08/08 ዓ/ም ሲሆን ከ2 ሺ በላይ ወጣቶች ኣድኖው ከተያዙ በኋላ በሑመራ ከተማና ሌሎች 13 ቀበሌዎች በተሰሩ ግዝያዊ እስር ቤቶች እንዲታሰሩ ኣድርገዋል።
የዞኑ ሃላፊዎች ወጣቶቹ ለመቅጣት በርካታ የዳኞች መድበው በዘወቻ መልክ የተፈረዱባቸው ሲሆኑ እያንዳንዱ ወጣት ከ700 ብር እስከ 1500 ብር እየከፈልክ ልትወጣ ትችላለህ ተብለዋል። ወጣት ገብርሃንስ ይልማና(700 ብር) ሃለቃ ሓጎስ ገብሩ(1000 ብር) እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል።
መክፈል ያልቻሉ ወጣቶች “ከቤተሰቦቻቹ ኣስልኩ ወይም ተበደሩ” እየተባሉ እየተገደዱ ይገኛሉ። ወርቅ በማውጣት ስራ የተሰማሩ ወጣቶች ድሆች ሲሆኑ በኣገራቸው ስራ ለመስራት ዕድል ያላገኙ፣ ወደ ኣውሮፓ ለመኮብለል ቤተሰቦቻቸው ለሕገ ወጥ ደላሎች(የህወሓት ባለስልጣናት ሸሪኮች) ለሚከፈል ብር ኣቅም ያነሳቸው ናቸው።
ወደ ቦታው ሲመጡም ሁለት ዕድል ግምት ውስጥ ኣስገብተው ነው።
ሀ) ወርቅ የማግኘት ተስፋና ወርቁን ሽጠው ራሳቸውና ቤተሰቦቻቸውን መርዳት
ለ) ከኤርትራ በሚሻገሩ ታጣቂዎች ታግተው ወደ ኤርትራ ተወስደው በባርነት መማቀቅ ነበር።
ሌላ ያልጠበቁት ሶስተኛ ኣደጋ ደሞ
፦ በህወሓት መሪዎች ታድነው መያዝ፣ መታሰርና በገንዘብ መቀጣት የሚለውን ነው።
በኣሁኑ ሰዓት የህወሓት መሪዎች ተግባር ወጣቱ ከህገ ወጥ ደላሎች ጋር በመመሳጠር ከመላ ትግራይ ከተሞችና ገጠሮች ወጣቶች እያማለሉ ለሊብያ መላክና ወላጆቻቸው ተገድደው የሚልኩት 14000(መቶ ኣርባሺ ብር) ተካፍለው መብላት ነው።
ሰሞኑ በማይካድራ ያጋጠመ ምሳሌ የህወሓት ባለስልጣናት በዚ ሕገወጥ ተግባር እጅ እንዳለባቸው ያመላከተ ነው። በኮብላይ ወጣቶች ” ልጆቻችን መልስልን ኣለበለዚያ እናጋልጠሃለን” ተብሎ በወላጆች የተደወለለት ብርሃነ ኣሸብር የተባለው ኣስከውላይ “…በሉ እርማቹ ኣውጡ እኔ የትም ኣታገኙኝም። የኔ ብር ያልቀመሰ የትግራይ ባለስልጣን የለም። ስለዚ ኣርፋቹ የሚጠበቅባቹ ብር ክፈሉ። ካልሆነ ልጃቹ ወደ ኩላሊት ነጋዴዎች ይላካል…” ሲል ዝተዋል።
በሉ እዩልኝ ! እነዚህ ባለስልጣናት በትግራይ ያለው ድሃው ወጣትም በ13 ግዝያዊ ማጎርያዎች ኣግተው በመያዝ ያለ ደላላ ብር ውለድ እያሉ እያስጨነቁት ይገኛሉ።
ወጣቱ ትውል እሳት ትርያንግል ሰርቶ እየለበለበው ይገኛል።
የህወሓትና ባለ ስልጣናት=====> ህገ ወጥ ደላሎችና ኩላሊት ነጋዴዎች(ስደት)====> ከኤርትራ የሚሻገሩ ታጣቂዎች ናቸው።
ወጣቶቻችን ከእልቂት እናድን።
ነፃነታችን በእጃችን ነው።

ወያኔ በሕገ-ወጥ ሰዉ ዝዉዉር ሰንሰለት ዉስጥ

$
0
0

ከልዑል ዓለሜ

 የኢኳዶር ፖሊስ (  Ecuadorean police ) የኮሎምቢያ የጸረ አጋች ቡድን ወይም ኽዉላ (Colombia’s elite anti-kidnapping squad, known as GAULA ) የአሜሪካዉ ሆም ላንድ ሴኪዉሪቲ ( us  Home land security )   የብራዚል የህገ ወጥ ሰዉ ዝውውር ቁጥጥር ፖሊስ ( Brazilian migration police ) እና የሩቅ ምስራቅ ሀገራት ፖሊስ መረጃዎች እንዲሁም አለማቀፍ ፖሊስ ( Interpol  )  በመተባበር የህገ ወጥ የሰዉ ዝዉዉርን ለማኮላሸት በጋራ መስራት ከጀመሩ ሰንበትበት ብለዋል::

dawittttttttt

እነዚህ መጠነ ሰፊ አሰሳ ላይ የሚገኙት ሐይሎችን ሆም ላንድ ሴኪዉሪቲ በበላይነት ሲመራቸዉ ከእነዚህ የትብብር ሀይሎች የወጡ መረጃዎች ጣታቸዉን ወደ ሐገራችን ኢትዮጵያ ቀስረዋል አዎ  እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሐገራት ባለስልጣናት፣ ኢሚግሬሽን እና ቦርደር ፖሊሶች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ እጃቸዉ በህገ ወጥ የሰዉ ዝዉዉር ዉስጥ አሉበት ኢየተባለ ይገኛል።

  ኢላይ ዳዊት ታደሰ ትዉልደ ኢትዮጵያዊ ሲሆን በ ( 05 May 2011  ) ኢኳዶር ላይ በእነዚህ ሐይሎች ቁጥጥር ስር ዉሏል ዳዊት ታደሰ አብዛኛዉን ንብረቱን ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚያስቀምጥና ከኢትዮጵያ እና ከተለያዩ የአፍሪካ ሐገራት ብዛት ያልቸዉ ስደተኞችን ወደ አሜሪካ አሸጋግሯል ዳዊት 66 የሚጠጉ አጋሮቹ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን የሆሳማ ቢን ላዲን ቀኝ እጅ የሆኑ ባልደረቦችም  አብረዉት ተይዘዋል  ዳዊትና ግብረ አባሮቹ ( 12 March  2011 ) ለሐያሏ አሜሪካ ተላልፈዉ ተሰጥቷል።

 ሰብለ አማረ ትዉልደ ኢትይዮጵያዊ ስትሆን በኮሎምቢያና በብራዚል መካከል ሀገ ወጥ የሰዉ ዝዉዉር በማካሄድ ወንጀል በ 2014 በቁጥጥር ስር ዉላ በህግ ክትትል ላይ ትገኛለች በኮሎምቢያ በጥገኝነት የምትኖረዉ ሰብለ ኢትዮጵያዊ ስትሆን በህገ ወጥ መንገድ ከኢትዮጵያ ኢሚግሬሽኖች ጋር በመተባበር ሰዉ እንደምታሻግር እንዱሁም ከቦርደር ፖሊሶች ጋር አብራ እንደምትሰራ መረጃዉ ያመላከተ ሲሆን በሆምላንድ ሴኪዉሪቲ ክትትል ስር ትገኛለች።

ሳራ ሳህሌ በትዉልድ ኢትዮጵያዊ ስትሆን በ 2015 በኮሎምቢያ በህገ ወጥ የሰዉ ዝዉዉር ወንጀል እጅ ከፍንጅ ተይዛ በቁጥጥር ስር የዋለች ሲሆን ከኢትዮጵያ ባለሳልጣናት ጋር ትብብር እንዳላት መረጃዎች አመላክተዋል።

 ሰለሞን . . በ 2013 በብራዚል ፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለ ኢትዮጵያዊ ሲሆን የተያዘበት ወንጀል ህገ ወጥ የሰዉ ዝዉዉር ሲሆን ኢትዮጵያ ከሚገኙ ኢሚግሬሽን እና ቦርደር ፖሊሶች ጋር የተበቀ ግንኙነት እንዳለዉ መረጃዎች ሲያመላክቱ፡፤

በተያያዘ ሁኔታ ወደ እሩቅ ምስራቅ ሐገራት የሚደረጉ ተመሳሳይ ወንጀሎች በወያኔያዊያን የህግ ጥላ ተሰጥቷቸዉ ወንጀሉን በበላይነት የሚፈጽሙ አካላት ላይም ከፍተኛ ጥናት እየተደረገባቸዉ ይገኛሉ።

ባጠቃላይ ከአፍሪካ ከ18 በላይ ግለሰቦች በተመሳሳይ ወንጀል ተጠርጥረዉ በቁጥጥር ስር ለማዋል ህጋዊ ማረጋገጫ እየተፈለገባቸዉ ሲሆን አብዛኞቹ ከትግራዩ ነጻ አዉጪ ቡድን ጋር ትስስር እንዳላቸዉ ምንጮች ጠቁመዋል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !

በቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ አመራር ዮናታን ረጋሳ ላይ የተመሰረተው ክስ ቻርጅ እጃችን ገባ –ፌስቡክ ላይ በጻፋቸው ጽሁፎች አሸባሪ ተባለ

$
0
0

Yonatan Regas - Satenaw

(ዘ-ሐበሻ) የኦሮሞ ሕዝብ ንቅናቄ ስር ዓቱን በነቀነቀው ወቅት ከታሰሩት በርካታ ሰላማዊ ታጋዮች መካከል አንዱ የሆነው የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ አመራር ወጣት ዮናታን ረጋሳ ላይ የሽብርተኝነት ክስ ተመሰረተበት::

“ተከሳሽ የፖለቲካ; የአይዲዮሎጂ ዓላማን ለማራመድ በመንግስት ተጽ ዕኖ ለማሳደር ሕብረተሰቡን ወይም የህብረተሰቡን ክፍል ለማስፈራራት እና የሃገሪቱን መሰረታዊ; ፖለቲካዊ; ሕገመንግስታዊ; ኢኮኖሚያዊ ወይም ማህበራዊ ተቋማትን ለማናጋት እና ለማፈራረስ አስቦ ራሱን የኦሮሞ ነፃነት ግምባር (ኦነግ) ብሎ በሚተራ አሸባሪ ቡድን በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ዞኖች እና ወረዳዎች ህብረተሰቡን የአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ ክልል ልዩ ዞኖች የተቀናጀ ማስተር ፕላን ሽፋን በማድረግ ከህዳር ወር 2008 ዓ/ም ጀምሮ የተጠቀሱትን አመጽና አድማ መሰረት በማድረግ ከህዳር 24 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ በሚጠቀምበት ድህረ-ገጽ በተለይም በፌስቡክ ተጠቅሞ በሽብር ቡድኑ የተጀመረውን አመጽና ብጥብጥ በማስቀጠል” በሚል በቀረበበት ክስ ዮናታን ፌስቡክ ላይ በተለያዩ ጊዜያት የጻፋቸው ጽሁፎች ተጠቅሰው አሸባሪ ተብሎ ተከሷል::

ሙሉ የክሱን ቻርጅ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ስንት ትውልድ እስኪጠፋ እንጠብቅ? –ፍርዱ ዘገዬ                       

$
0
0

Freedomዳዊት በመዝሙሩ – “አቤቱ ጌታ ሆይ ጸሎቴን ስማ፤ ጩኸቴም ወዳንተ ይድረስ፣ በመከራየም ቀን ፊትህን ከኔ አታዙር” ሲል ፈጣሪውን ተማጽኗል፡፡ እኛስ? ከልበ ድንጋዮቹ ወንድሞቻችን ግፍና በደል የሚታደገንን ሙሤ እንዲልክልን እንደዳዊት እየጮኽን ነው ወይንስ እንደኖኅና እንደሎጥ የቅጣት ዘመናት በአሥረሽ ምቺው የኃጢኣት ባሕር ከተዘፈቁት ጋር አብረን ፈጣሪን ረስተናል?

እግዚአብሔር የኖኅ ዘመን ሰዎችን በውኃ ቀጣ፡፡ ኋላ ላይ ግን ለፍጡራኑ አዘነ፡፡ በዚያ መልክ ዓለምን ዳግም በውኃ ንፍር እንደማይቀጣም ቃል ገባ፡፡ እግዚአብሔር በሎጥ ዘመን ሶዶምንና ገሞራን በድኝ የእሳት ዝናብ ቀጣ፡፡ ሁለተኛውም ከመጀመሪያው ባሰ፡፡ የሰው ልጅ ግን ከሁለቱም አልተማረም፡፡ እናም በጥፋቱ ቀጠለ – እስካሁኒቷ ወያኔያዊት ዘመነ ፍዳ ወፃማ ቅጽበት ድረስ፡፡ ፈጣሪም የቅጣት ዓይነቶችን በመጠንም በዓይነትም በደረጃም እየለዋወጠ ፍጡራኑን – በአባይ ፀሐይ ትዕቢታዊ አገላለጽ “ልክ ማስገባቱን” እንደቀጠለ እስካሁን አለ፡፡ ግን ማን ልክ ገባ? ማንም! ሰውና ፈጣሪ ያልተገባ ፉክክር ውስጥ ገብተውና እልህ ተጋብተው በተለይ በአሁኑ ዘመን የለዬለት የጨበጣ ውጊያ ውስጥ የገቡ ይመስላል፡፡

ሦስተኛ ዓይነት መለኮታዊ ቅጣት በኢትዮጵያ በግልጽ ከታወጀ እነሆ 25 ዓመታትን ሊደፍን ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተውታል፡፡ ከውኃና ከእሳት ቀጥሎ ወደዚህች ዓለም የመጣው የቅጣት ዓይነት በሀገራችን ኢትዮጵያ ብቻ ለሙከራ ያህል በሚመስል አኳኋን ተግባራዊ የሆነ ሲሆን እሱም ትውልድን በትምህርትና በዕውቀት ማደደብና በቋንቋና በጎሣ መከፋፈል ነው፡፡ ይህ በተከታታይ ትውልዶች ላይ የተቃጣ ገሃነማዊ ቅጣት ከቀደሙት የውኃና የእሳት ቅጣቶች በበለጠ የሚያቃጥልና የሚፋጅ ነው፡፡ ሰዎች እንደቀላል ሊመለከቱት ይችሉ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ቅጣቱ ጥይት ሳያባክን ትውልድን ማምከን የሚችል ከኒዩክሌር ቦምብ የበለጠ እጅግ አውዳሚና በቀላሉ ማንሠራራትም የማይቻልበት ነው፡፡

ዛሬ በአዲስ አበባ ሂልተን አንድ የመጻሕፍት ምረቃ መርሐ ግብር ነበር፡፡ እዚያ ስብሰባ ውስጥ የነበረ አንድ ወዳጄ በአስቸኳይ እንደሚፈልገኝ ነገረኝና ምን ሆኖ ወይም ምን አጋጥሞት ይሆን ብዬ ተጣድፌ ላገኘው ሞከርኩ፡፡ ቀኑ ብሔራዊ የነፃነት ክብረ በዓል የሚከበርበት እንደመሆኑ ሥራ የለኝምና አንድ ቦታ ተገናኝተን ማርፈጃውን ስለታዘበው ነገር በቁጭት እየተንገበገበ ቀጣዩን ነገር አጫወተኝ፡፡

በሰባት የኢትዮጵያ ቋንቋዎች የተዘጋጁ የልጆችና ሕጻናት መጻሕፍት ሜጋ የመጻሕፍት አሣታሚና በቅርብ እንደተመሠረተ የተነገረለት ስፖትላይት የተባለ ድርጅት በጥምረት ዛሬ ጧት አስመረቁ፡፡ በዚህ የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ በርካታ የሥነ ጽሑፍ ባለሙያዎችና ጋዜጠኞች እንዲሁም በንባብ ዙሪያ የሚሠሩ መጻሕፍት አሣታሚዎችና አከፋፋዮች ተጋብዘው ብዙዎቹ ተገኝተዋል፡፡ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የሚሠራው ታዋቂው የፎክሎርና የሥነ ጽሑፍ ምሁር ዶክተር ፈቃደ ትዛዙም (አዘዘ?) ተገኝቶ ንባብን በሚመለከት ከሕይወት ተሞክሮው በጥቂቱ የተጨለፈ አጠር ያለ ገለጻና ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡ ታዋቂ ደራሲያንና የመድረክ ሰዎችም ተጋባዥ ነበሩ፡፡ በጣም ደስ የሚል ነበር፡፡…

ወዳጄ ይህን ሲነግረኝ ቀዝቀዝ አልኩ፡፡ ነገር ግን ለዚህ ብሎ በጥድፊያ እኔን መፈለጉ አላሳመነኝምና በአስቸኳይ ለምን ሊያገኘኝ እንደፈለገ ጠየቅሁት፡፡ ጓደኛዬ ንዴት እንጂ ንግግር ብዙም አይሆንለትም፡፡ ከፍ ሲል የነገረኝን በእርጋታ ከነገረኝ በኋላ በንዴት እየተንጨረጨረ እኔንም የሚያናድዱ ብዙ ቁም ነገሮችን ዘከዘከልኝ፡፡ የመጣጥፌ መሠረትም ይህ የነገረኝ ነገር ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ከወዳጄ ተሰናበቱ – ከኔ ጋር ጥቂት እንቆይ፡፡

ከጓኛዬ እንደተገነዘብኩት ዐማርኛን ጨምሮ ሰባት የልጆች የንባብ መጻሕፍት ተዘጋጅተው ለምረቃ በቅተዋል፡፡ ይህ በራሱ እሰዬው የሚያስብል ትልቅ መልካም ነገር ነው፡፡ ይሁንና የመጻሕፍቱ ይዘትና ቅርጽ እንዲሁም የመጻፊያ ሆሄያት ምርጫ ብዙ ማነጋገሩ አልቀረም፡፡ በሥፍራው ግን ይህን ነገር ማንም ደፍሮ እንዳላነሳ ወዳጄ ነግሮኛል፡፡

እንዲህ ያለ ነገር ውስጥ መግባት ጣጣው ብዙ መሆኑን ሁሉም ሳይረዳ አልቀረም፡፡ በዚህ ወያኔ በገነነበትና ያሻውን በሚያደርግበት አደገኛ ወቅት ሰዎች ትክክለኛ መስሎ የሚሰማቸውን ነገር በግልጽ ከመናገር ይልቅ (“ሽብርተኛ” ሆኖ ዘብጥያ ላለመውረድ ሲባል) አድምጡና ተመልከቱ የተባሉትን ብቻ አድምጠውና ተመልክተው ወደየመጡበት መሄድ የተለመደ ሆኗል – ጎመን በጤና፡፡

ከዐማርኛና ከትግርኛ በስተቀር በኦሮምኛ፣ በወላይትኛ፣ በሲዳምኛ፣ በሃዲይኛና በሶማሊኛ የተዘጋጁት መጻሕፍት የተጠቀሙት ሆሄያት የላቲኑን ነው፤ ያሳየኝ ብሮሸርም ይህን ይጠቁማል፡፡ ይህ ነገር በርግጥ የየቋንቋዎቹ ተናጋሪ ኅብረተሰብ ምርጫ ቢሆን ችግር ባልነበረው፤ ምርጫው የወያኔ መሆኑን ለመረዳት ደግሞ እነዚህን መሰል መጻሕፍትና በራሳቸው ቋንቋ የራሳቸውን ቋንቋ ተምረው ሲያበቁ መጨረሻ ላይ የሚሰጧቸውን የፈተና ወረቀቶች ከፈተናው አዳራሽ እንደወጡ በመቀዳደድ አካባቢውን ጨረቃ በጨረቃ ማስመሰላቸው አንዱ ምሥክር ነው፤ እንዲያውም “ ልጆቻችን በአንድ የአካባቢ ቋንቋ ብቻ ተወስነው እንዲቀሩ የሚያደርጉት የትም ሄደው ሥራ እንዳይዙና እዚሁ እንደኛው ገበሬ ሆነው እንዲቀሩ ነው” በሚል የየአካባቢው ሕዝብ እንደሚጮህ የታወቀ ነው – ሰሚ የለም እንጂ፡፡ በመሠረቱ አንድ ዜጋ የራሱን አንድ እና ለሁሉም የሚያገለግል ደግሞ አንድ በድምሩ ቢያንስ ሁለት ቋንቋዎችን ቢለምድ ሕዝብና ሀገር ይበልጥ ይጠቀማሉ እንጂ ጉዳት የለውም፡፡ ዜጎች በአንድ ክልል ተኮድኩደው ከአድማስ ወዲያ ሕይወት መኖሩን እንዳያውቁ ሆን ተብሎ በወያኔ የሚሸረበው ተንኮል ወያኔ አወራርዶ ሊጨርሰው የማይችል የታሪክ ዕዳ ተሸካሚ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሣያል፡፡ ሁሉም ሕዝብ የነዚህን እባቦች ተንኮል በእኩል ደረጃ በሚረዳበት ወቅት ሊከሰት የሚችለውን በጣም አደገኛ ሁኔታ ከአሁኑ ሲያስቡት አስጨናቂ ነው፡፡ የሕዝብ መገናኛ ድልድዩ ሁሉ ፈራርሷል፤ ሃይማኖት፣ ባህል፣ ቋንቋ፣የጋራ ማኅበራዊ ሥነ ልቦና… የመሳሰሉት ዕሤቶች የሕዝብ መገናኛ ድልድዮች ናቸው፡፡ ወያኔዎች እንዚህን ማስተሳሰሪያ ገመዶች በጣጥሰው አንዱ ከሌላው እንዳይገናኝና በምትኩ ሁሉም ፉዞ ሆኖ የነሱ አሽከርና ባሪያ እንዲሆን በከፍተኛ ደረጃ እየሠሩበት ነው – አብዛኛው ሕዝብም የተኛ ይመስላል፡፡ ችግሩ ታዲያ የተኛ የነቃ እንደሆነ ነው፤ የጊዜ ጉዳይ እንጂ መንቃቱም የማይቀር ነውና፡፡

አንድ ማሳሰቢያ ልስጥ፡፡ እኔ በዘሬ ኢትዮጵያዊ ነኝ – ይህን ስል ግን ወያኔና የወያኔን ፍልስፍና የሚከተል ማንኛውም ወገን “ይህ ሰው ዐማራ ነው” ብሎ እንደሚፈርጀኝ እገምታለሁ፡፡ የማነሳው ጉዳይ ግን ከኔ ማንነትና ምንነት በዘለለ ትልቅ ሀገራዊ ውድመት የሚያስከትል መሆኑን ሁሉም ልብ ሊል ይገባዋል፡፡ እናም እኔ አሁን የምለው ከተቻለ ሀገሪቱን ከመፈራረስ የምናድንበትን መንገድ በጋራ እንፈልግ፣ አለበለዚያ ግን ማንም ተጠቃሚ የማይሆንባት ጥቂት ጮሌዎች ብቻ በሀብትና በሥልጣን ሊያውም ለተወሰነ አጭር ጊዜ ተምነሽንሸውባት በቅርብ ለይቶላት የምትጠፋ ሀገር ውስጥ እየኖርን እንደሆነ እንገንዘብ እያልኩ ነው፡፡ ዐማራን ለማዳን ወይ ስለዐማርኛ ተጨንቄ ወይ ወያኔ በ“ካህናትና ጳጳሣት” ካድሬዎቹ ድራሹን ስላጠፋው ሃይማኖት ተጠብቤ… እንዳይመስላችሁ፡፡ እንዲያውም በዐማራ ምክንያት ወያኔና ግብረ አበሮቹ ኢትዮጵያንና ቀሪውን ወደ 70 ሚሊዮን የሚጠጋውን ሕዝብ ከሚያጠፉ በ20 ሚሊዮን ገደማ የሚገመተው ከወያኔ ጭፍጨፋና ዕልቂት የተረፈው የዐማራ ሕዝብ በሌላ ሀገር ውስጥ ባዶ ቦታ ተፈልጎለት እዚያ ሄዶ ቢሠፍር የምመርጥ ሰው ነኝ – ለእሥራኤላውያን ታስቦ እንደነበረው፡፡ እስኪ ሌሎቻችሁ እንኳን ራሳችሁን አድኑ፤ ሁሉም ተያይዞ ሞኝ አይሁን፤ የዚህን ዐውሬ የትግሬዎች ቡድን አንደርባዊ ድግምቱንና ትብታቡን አፍርሱበትና ራሳችሁን ነፃ አውጡ፡፡ ለመሆኑ ማን ነው ከወያኔ የጥፋትና የውድመት አዙሪት ነፃ የሆነ? የትኛው ጎሣ ወይም አካባቢ ነው ከወያኔ ቀረቤታና በወያኔ ችሮታ የተጠቀመ? ኦሮሞ? ሶማሌ.? አፋር? ጋምቤላ? ቤንሻንጉል? ከድንጋያማ የተራቆተ መሬት የመጡ ቀጫጭንና ከሲታ ወንድሞቻችን ዛሬ እኛን እርስ በርስ እያባሉ እንደጉማሬ በልተው እንደዝኆን ሲወፍሩ ባይናችን በብረቱ እየተመለከትን የምንገኝ አንዳንድ ቂሎች በጋራ ጠላቶች መሠሪ የፈጠራ ወሬ እየተነዳን አሁንም የፈረደበት ዐማራ ላይ እንረባረባለን፤ የሞተን ፈረስ መጋለብ – የደረቀን ወንዝ መሻገር የጀግንነት መገለጫ አይሆንም፡፡ ትኋንን በጠበንጃ፣ ቁንጫን ደግሞ በርግጫ መግደልም የሚያስፎክር ጀብድ አይደለም፡፡ እውነትን ከሀሰት አበጥሮ በመለየት ሁነኛ ዘመድን ማወቅ አንዱ የጀግንነት ምልክት ነው፡፡ እንደቦይ ውኃ በነዱት መነዳትና እንደክርስቶስ ዘመን “ስቅሎ፣ ሰቅሎ” ብሎ በንጹሕ ዜጎች ላይ “ሆ!” እያሉ መዝመትም በትንሹ ቂልነት ነው፡፡ ጠላትንና ወዳጅን አለመለየት ለከፋ ችግር ይዳርጋል፡፡

ዐማሮችን መጥላትና ማጥፋትም ይቻላል፤ ቀላልም ነው፡፡ እንግሊዞችን መጥላትና – ቢያንስ በንድፈ-ሃሳብ ደረጃ – ማጥፋትም ይቻላል፤ ይህም ቀላል ነው፡፡ ዐማርኛንና እንግሊዝኛን ግን ማጥፋት ይቅርና ለማጥፋት ማሰብ በራሱ ዕብደትና ትልቅ ዋጋ የሚያስከፍልም ነው – ኢትዮጵያን በሚመለከት እየታዘብነው እንዳለነው ይህ ዓይነቱ የወፈፌ ሥራ የትውልድን መቃተት ያስከትላል፡፡

ዐማርኛን ማጥፋት ዐማሮችን እንደማጥፋት ቀላል ቢሆን ኖሮ እስካሁን ትግርኛ ቋንቋ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቋንቋ ሆኖ ነበር፡፡ ወያኔዎች ግን የለየላቸው ደንቆሮና ልበ-ሥውራን በመሆናቸው ይህ ታሪካዊ ኹነት እንኳን ሊገባቸው አልቻለም፡፡ የነሱን ልጆች ሸገር ላይ ለምን ዐማርኛና በዐማርኛ ያስተምራሉ? ለምን ወደ ቻይና፣ እንግሊዝና አሜሪካ እየላኩ ለሥልጣኔ ቅርብ ያደርጓቸዋል? ለሌላውስ ድንቁርናን ለምን ይፈርዱበታል?

ከሌሎች ክልሎች በተሻለ ሁኔታስ በትግራይ ክልል ለምን ዐማርኛ ይነገራል? ገዢዎቸ ራሳቸው ለምን ዐማርኛን ይለምዳሉ? አሃ! ተረዱታ! ጀምጀምንና ጃንጀሮን – ኮንሶና ሙርሲን፣ አሪና በርታን  ለማስገበር፣ ሲዳማንና ወላይታን እንደልብ ለማዘዝ፣ ጠምባሮንና ደራሳን ለማሽቆጥቆጥ፣ አኝዋክንና ኑዌርን ለመቦጥቦጥ፣ ቦንጋንና ቤንቺ ማጂን ለመርገጥ፣ ሃዲያንና ሐረሪን ለመንዳት፣ ኦሮሞንና ሶማሌን ለመግዛት፣… ከዐማርኛ የበለጠ መሣሪያ እንደማያገኙ ዐወቋ! ግን ግን የቋንቋው ጥቅም ገብቷቸው ሲያበቃ ለተናጋሪዎቹ ያላቸው ንቀትና ጥላቻ አላፈናፍን ብሏቸው ይሄውና ይህን ቋንቋ ለማጥፋት – የሚበሉበትን ወጪት ሰባብሮ ለመጣል – ያቺ ሞኝ ሴት በተረቱ አደረገች ተብላ እንደምትታማበቱ ያለ አስቂኝ ግን አጓጉል ነገር እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ሞኟ ሴት ግን ምን አደረገች በል? እሷማ ባሏን የጎዳች መሰላትና ሰውነቷን በጋሬጣ ዘነጣጠለችዋ፡፡ ጅል ሴትና ደንቆሮ ወያኔ አይግጠማችሁ፡፡

ዐማርኛ የሙጃ ሣር ነው፡፡ ዐማርኛ ሰንሰልና ሸምበቆ ነው፡፡ ዐማርኛ ባማርኛ አንፋር ወይም ነጭሎ ብለን የምንጠራው የተክል ዓይነት ነው፡፡ የትም ቢሄድ አካባቢውን በቀላሉ ይለምዳል፤ ሞኛሞኝ ቢጤ ነው፡፡ ዐማሮች የሚባሉ ወገኖቻችን እንደዐማርኛ ገርና ለማዳ ስለመሆናቸው አታስወሹኝ እምብዛም አላውቅም፡፡ ዐማርኛ ግን ቀደም ሲል በተፈጠረለት ታሪካዊ አጋጣሚ የተነሣ በመላው ኢትዮጵያ ተሠራጭቶ ሕዝቡን አንድ ለማድረግ ከጥንት ጀምሮ እየደከመ ይገኛል፡፡ ትርፉ ድካም ብቻ ሆኖ መቅረቱ ግን ያሣዝናል፡፡ ለዚህ ልፋቱ – ለዚህ ከ80 በላይ ለሚገመቱ ጎሣና ነገዶች የጋራ የመግባቢያ መሣሪያ ሆኖ ማገልገሉ ባለቤቶቹን ሊያስወድስና ሊያሸልም ሲገባ በተገላቢጦሽ ሽልማታቸው ውግዘትና ጥይት መሆኑ ምን ዓይነት የታሪክ ምፀት እንደገጠመን ጠቋሚ ነው፡፡ ወያኔ በጨለማ ውስጥ የሚኖር የድንጋይ ዳቦ ዘመን ፍጡር ሆኖ እንጂ እያንዳንዱ የኢትዮጵያ ንጉሥ – ለሀፄ ዮሓንስ ጮሙሮ –  ትግሬም ይሁን ኦሮሞ ወይ ዐማራና ቅልቅል ሁሉም የተጠቀሙት ዐማርኛን ነው – ዐማርኛ ኮከቡ ሰምሮለት ላገዛዝ ሳያመች የሚቀር አይመስለኝም – ለተናጋሪዎቹ ጠንቅ ሆነ እንጂ፡፡ ሁሉም ነገሥታትና ገዢዎች ዐማርኛን መጠቀሙ ስላመቻቸውና ስላተረፉበት እንጂ ወደውትም ላይሆን እንደሚችል ቢያንስ በጥርጣሬ ደረጃ መጠርጠር ይቻላል፡፡

የቋንቋ ልደት፣ ዕድገትና ሞት የራሱ አካሄድ አለው – እንደወያኔ በዐዋጅና በጦርነት አንድ ቋንቋ አይወለድም ወይም ተወልዶ እንኳን ቢሆን አያድግምና ለተፈለገው ቁም ነገር አይበቃም፤ ለዚህ ነባራዊ እውነት ዋናው ምሥክር ወያኔዎች ራሳቸው ናቸው፡፡ እንደነሱ ፍላትና ምኞት ቢሆን ኖሮ ትግርኛ የአሁኒቷ ኢትዮጵያ የጋራ ቋንቋ ሆኖ ነበር – ግን እባብ ልቡን ዐይቶ … እንደሚባለው በፈለጉት መሣሪያ ቢወጉት ዐማርኛ አልሞት አላቸው – እንደነሱው አፍር ልሶ ከመቃብሩ ይነሣል፤ እንዲያውም ይባስ ብሎ እየገነነ መጣና በዋሽንግቶን ከተማ ሣይቀር የሥራ ቋንቋ እስከመሆን ደረሰ፡፡ እንጂ እንደነሱ ጥረት – እንደነሱ የባህል ወረራ – እንደነሱ መፍጨርጨር አዳሜ በአሁኑ ሰዓት አብዚሎ ቅብዚሎ እያለች ሁሏም በትግርኛ ትግባባ ነበር – በመሠረቱ ትግርኛ ብሔራዊ ቋንቋ መሆን አለመሆኑ አያሳስበኝም፤ የሚያሳስበኝ የመሆኛውና ያለመሆኛው ሥልት ነው፤ እንጂ እንኳንስ ጠንቅቄ የምናገረው የእናቴ ወገኖች ቋንቋ በአግባቡና በደንቡ ከሆነ የዝንጀሮም “ቋንቋ” ብሔራዊ ቀርቶ የዓለምም ቢሆን በደስታ እቀበላለሁ፡፡

የትግርኛን ቋንቋና የትግራይን ባህል በሌላው ላይ በግዴታ ለመጫን የሚያደርጉት ሙከራ ቀላል አይደለም – ይህ ደግሞ በጣም ያናድድሃል፤ የምትወደው ብትሆን እንኳን እንድትጠላው ሊያደርጉህ ይችላሉ – ፈቃዳችሁ ከሆነ እዚች ላይ አንዲት ፈረንጅኛ አባባል ልጥቀስ መሰለኝ – “A man can take a horse to a river, but twenty cannot make it drink.” አዎ፣ ሙዚቃውን ልትከፍት ትችላለህ – ግን ማን ነው በፍቅር የሚያዳምጥልሀ? እንዴ፣ ከዚህ ከጀመርኩላችሁ ከዘፈን አቅም እንኳን ሚዲያው ሁሉ በዐዋጅ የተገደደ ይመስል ብዙውን ጊዜ ካለትግርኛ ሌላ ዘፈን አይከፍትም – ቲቪውም፣ ኤፍ ኤሙም፣ የባዛርና የንግድ ትርዒት ዝግጅቱም፣ ዕድሩም ሰምበቴውም ምኑም ምናምኑም… ኮበለይና ተበራቢረይ ሲል ነው የምታደምጡት – ይቅርታችሁንና ብዙዎቻችን ደግሞ ማሽቃበጥ ስንወድ! እነዚህን የ simple  psychology ተጠቂ ዶንኪሾታዊ ወንድሞቻችንን በቀላል ነገር የመደሰትና በትንሽ ድል የመኮፈስ ተፈጥሮ የምናውቅ አጎብዳጆች እነሱን ለማስደሰት የምናደርገው አንዳንድ ነገር ለትዝብት ሲዳርገን አስተውላለሁ – ያ ዓይነቱ ራስን ያለመሆን ችግር ደግሞ በጣም ያሳዝነኛል – እነሱ ራሳቸውም ሳይታዘቡን የሚቀሩ አይመስለኝም – ነገ ደግሞ በሌላው ቀን በቅጽበት ሌላ እንደምንሆን ግልጽ ነው፡፡… የትምህርት ቤቶች ሚኒ ሚዲያዎች እንኳን ባቅማቸው ካለበት የተጋባበት ሆነው በዕረፍት ሰዓታቸው የሚለቋቸው ዘፈኖች ብዙዎቹ ትግርኛ ናቸው፡፡ ሰው ደግሞ ጥልት! በኃይል የመጫን አሉታዊ ጎኑ እንግዲህ ይህ ነው፡፡ ወደህ ከሆነ ትጨፍርበታለህ፣ ትፎክትበታለህ ማነው ትፎክርበታለህ፣ ታገባበታለህ፣ ትፈታ…. አይ፣ አይ መፍታትስ ይቅር… ብቻ ከልብህ ትወደውና በሙዚቃው እንደልብህ በፍቅር ትመላለስበታለህ፡፡ ስትገደድ ግን ትጠላዋለህ፡፡ ተገድደህ እንድትቀበል ከሚደረግ ነገር የበለጠ የሚጠላ ነገር የለም፡፡ ስለዚህ እንኳንስ ትልቁን የማንነትህን መገለጫ ይቅርና ከረሜላም ቢሆን በፈቃድህ እንጂ ተገድደህ ብላ ብትባል እንደኔ ሆዳም ካልሆንክ በስተቀር ያቅርሃል ወይም ቢያንስ ሊያቅርህ ይገባል፡፡

መጠጥ ቤቶች ካለትግርኛ አያዘፍኑም – ለነገሩ እነሱ እንኳ አብዛኛው ደምበኛቸው ትግሬ በመሆኑ ሊሆን ይችላል፤ እርግጠኛ ነኝ – የዚህ ዘመን የሆቴልና የመዝናኛ ሥፍራዎች ደምበኛ ሲታይ በአነስተኛ ግምት ከ60 በመቶ በላይ ትግሬ ነው፡፡ ጎበዝ መደባበቅ ብሎ ነገር የለም፡፡ እንዲህ የምለው ደግሞ አንዱን በመጥላት ወይም ሌላውን በመውደድ እንዳይመስላችሁ፡፡ ከዘር ሐረግ አንጻር ዐማራ ቢቀቀል አይሸተኝም፡፡ በተቃራኒው አንድን ትግሬ አንድ ሰው – ምናልባትም ዐማራ – አላግባብ ሲበድለው ባይ ያን ዐማራ እኔ ነኝ ቀድሜ የምፋረደው፡፡ እኔ እንዲህ ነኝ፡፡ ሁሉም እንዲህ ይሁን፡፡ ሰውን በሰውነቱ እንጂ በሰው ሰራሽ ነገሮች ፈርጀን በእንስሳዊ ባሕርይ አንነዳ፡፡ ማን ነው በፈቃደኝነት ዐማራ ወይ ትግሬ የሆነ? እኔ በተወለድኩበት ቤተሰብ ውስጥ እንድወለድ ለእግዜር ያስገባሁት ማመልቻ የት ነው የሚገኘው? ምን ዓይነት የሚጎመዝዝ ቀልድ ነው ይሄ ኦሮሞ፣ ዐማራ፣ ጉራጌ፣ ሽናሻ… የሚሉት ፈሊጥ? ማን ይሆን ይህን የሰው ግርድና አመሳሶ የሚለይ ቆሻሻ ነገር ወደዚች ምድር ያመጣብን?

እደግመዋለሁ – ዐማሮች በዐማርኛ ተጎዱ እንጂ አልተጠቀሙም፡፡ ይህ ቋንቋ እንዲያውም ከናካቴው ባይፈጠር ይሻላቸው ነበር፡፡ ለጥፋትና ውድመታቸው፣ ለስደትና መከራቸው ዋና ምክንያት ሆነ እንጂ የጠቀማቸው አንዳችም ነገር የለም – በስማቸው የተጠቀመ የየትኛውም ዘር ሹምባሽና አገረ-ገዢ ሁሉ ጥቁር ጠባሳውን ወደነሱ እያላከከ ጦሱጥምቡሱ ተረፋቸው እንጂ ዐማሮች ባማርኛ አልተጠቀሙም፡፡ ይህ በጣም አሣዛኝ ነገር ነውና ሁላችንም ለዐማሮች እንዘንላቸው፡፡ በዚህ ሩዋንዳዊና አርመናዊ የዕልቂታቸው ዘመን ካለኛ ማን አላቸው?

ቋንቋ በመሠረቱ ከሸሚዝና ከኮት የዘለለ ጥቅምም ሆነ አስፈላጊነት የለውም፡፡ ሁላችንም ከኅሊና መታወር የተነሣ “ያንተ ቋንቋ፣ የኔ ቋንቋ” እንላለን እንጂ የማንም ቋንቋ የሁሉም ነው፤ የሁሉም ቋንቋ ደግሞ የማንም ነው፡፡ ያንተ ሊባል ይችል የነበረው በትውልድ እንደ አንድ ባሕሪያዊ ስጦታ ብታገኘው ነበር – ለምሣሌ በጄኔቲክ ውርስ ከአባትህ ልትወርሰው እንደምትችለው ሸፋፋ አረማመድ ማለቴ ነው፡፡ ቋንቋን ግን ከሚነገርበት አካባቢ ከራቅህ አታገኘውም – ወይም በሕጻንነትህ ወደሌላ ቦታ ብትወሰድ የዚያን አካባቢ ቋንቋ እንጂ የዘመዶችህን ቋንቋ ጆሮህን ቢቆርጡት አትሰማም፤ጭራሹንም ያለ ቋንቋ ቀርተህ እንደሌሎች እንስሳት ጓደኞቻችን ለምሣሌ እንደላም “እምቧ” እያልክ ልትኖርም ትችላለህ – በከብቶች መሀል ከነሱ ጋር ብቻ እንድታድግ ከተደረገ፡፡ ወያኔዎች ግን ይህን እውነት አያውቁም ወይም ሊያውቁ አይፈልጉም፡፡ ስለዚህም ትግርኛ ተናጋሪ (ትግሬ) ሰው ለነሱ እግዚአብሔራቸው ነው – ዘረኝነት የፈጣሪን ቦታ የተካላቸው የአምልኮት ጽላታቸው መሆኑን መርሳት የለብንም፤ ትግሬ ማለት ለነሱ በምንም ነገር የማይደራደሩበት አካላቸው አምሳላቸው ነው – አጠፋ አላጠፋ፣ ንጹሕ ሆነ ወንጀለኛ ያ ሌላ ጉዳይ ነው፡፡ የጠባብነት ወረርሽኝ የሚያሰቃየው ሰው በዘመናዊ ፈሊጥ ከ”ዕውቀት የፀዳ” በመሆኑ ልክ እንደከብት መሰሉን እየፈለገ እንደከብት ይተሻሻል፤ ሌላውን ደግሞ በጠላትነት ፈርጆ ባገኘው ቀንድ ሁሉ እያሳደደ ይወጋዋል፡፡ ለዚህ ነው ወያኔዎች የነሱን ቋንቋ የማይናገርንና ትግሬ ያልሆነን ሰው ፍዳውን እያሣዩ መፈጠሩን እንዲጠላ የሚያደርጉት፡፡ እንምንታዘበው የዕውቀት አድማሳቸውም ከአፍ እስከ አፍንጫቸው እንኳን አይደርስም፡፡ ተማሩ ተብለው ዶክተርና ፕሮፌሰር ሆነዋል የተባሉትም ቢሆኑ ዕውቀታቸው ያን ያህል ነው – እንዳብዛኛው የወያኔ “ምሁር” ድግሪውን በግዢ ካላመጡት ነው ያውም፡፡ ትምህርት ደግሞ የውስጥ ዐይንን – እንደሎብሳንግ ራምፓ አባባል ሦስተኛውን ዐይን – ካልከፈተ ዋጋ የለውም፡፡ ያ ሁሉ በትምህርት ያሣለፈው ጊዜ ልፋትና ጊዜን መግደል ብቻ ነው፡፡ ብዙ ዓመት ተምሮ መደንቆርን ነው ያተረፈው፡፡ ተማረ የተባለ ሰው በትንሹ ዘረኝነትን መፀየፍ ይኖርበታል፤ በሰው ልጆች እኩልነት ማመን ቀዳሚው የመማር ጥቅም ሊሆን ይገባል – አለዚያ ያ ተማርኩ የሚል ሰው ደደበ እንጂ አልተማረም፡፡ ለነገሩ መማር ማለት መደንቆርም እንደሆነ የሚያምኑ ፈላስፎች አሉ፡፡

ጠባብነትና የግንዛቤ ዕጥረት ደግሞ ጓደኛሞች ናቸው፤ ብዙ ነገርም ያሳጡሃል – ለምሣሌ ማኅበራዊ እንስሳነትህን በማስረሳት የሁሉምነትህን ትተህ የጥቂቶች ወገን ብቻ እንድትሆንና ለጥቂቶች ልብህን ለብዙዎች ግን ጥርስህን እንድትሰጥ ያስገድዱሃል፤ ሃይማኖትህን ያስክዱህና በዘረኝነት ልምሻ ኮድኩደው በከረፋ መሬት ላይ የዘውግ አባላትህን ትፈልግ ዘንድ የእንፉቅቅ ያስኬዱሃል፤ ከሌላ ዘውግ ጓደኛና ወዳጅ ቢኖርህ እሱንም ያስክዱህና በጠባቧ የዘውግ ክፍልህ አውርደው የገማ የገለማ የአጥንትና ደም ጭቃ ውስጥ እንድትንቦራጨቅ ያደርጉሃል፡፡ ዘረኝነትን ምናልባት ከሆነልህ በጸሎትና በጸበል እንጂ በትምህርትና በሕይወት ተሞክሮ በቀላሉ አትገላገለውም፡፡ ቀያጅ ነው፤ ባሪያው ካደረገህ እንደ አደንዛዥ ዕፅ ሱስ፣ እንደሀሽሽና ሱረት ፍዳህን ሳያበላህ አትገላገለውም፡፡ ብቻ ጠባብነትና ዘረኝነት መዘዛቸው ብዙ ነው ወንድሜ፡፡ እግዜር ይጠብቅህ እንጂ በተወርዋሪ ኮከብ የብርሃን ብልጭታ በምትመሰል በዚህች ቅጽበታዊ የምድር ሕይወት ውስጥ የዘረኝነትን ደዌ ጨምሮ የማይታይ አበሳ የለም፡፡

በነገራችን ላይ ኢትዮጵያ ጠፋች ማለት ምን ማለት ነው? ብዙ ሰው ላይገባው ይችላል፡፡

በደምቢ ዶሎ ከተማ በእንግሊዝኛ ቋንቋ በቢኤ ዲግሪ የተመረቀ አንድ ኦሮምኛ ተናጋሪ ወጣት በዚሁ በወያኔ ዘመን ለሥራ ፍለጋ አዲስ አበባ ይመጣል፡፡ ማስታወቂያ ያነብና እኔ የማውቀው አንድ ትምህርት ቤት ሄዶ ለእንግሊዝኛ አስተማሪነት ያመለክታል፡፡ የመመረቂያ ውጤቱ ኤ በኤ ስለነበር ለቃለ መጠይቅ ከተመረጡት ውስጥ ስሙ ይካተትና በቀጠሮ ይጠራል፡፡ ፈታኞቹ አንድ ፈረንጅና ሁለት ሀበሾች ናቸው፡፡ (የዘመናችንን የውጤት መግለጫ ካርድ ስናይ “ቢ” “ሲ”ና “ዲ” የት ገቡ ብለን መጠየቃችን አይቀርም፤ በተግባር ግን ዜሮ! በተለይ አንዳንድ የግል የትምህርት ተቋማት ተማሪን ለመሳብ ሲሉ …)

ብቻ የሚያሣዝን ነው፡፡ ጠፍተናል፡፡ ወያኔዎች ድራሻችንን አጥፍተውናል፡፡ ሰው ግን አላወቀም ወይም ጥልቅ የሆነ ክፍለ ዘመናዊ እንቅልፍ ውስጥ ነው፡፡ ያ ልጅ ራሱን እንዲያስተዋውቅ ዕድል ይሰጠዋል – በእንግሊዝኛ፡፡ ምንም ነገር መናገር ያቅተዋል፡፡ ፍርሀት እንዳይመስላችሁ – የችሎታ ማጠር ነው፤ ቋንቋውን ከየት ያምጣው? ዲግሪን እንደጠበል መርጨት እኮ በጣም ቀላል ነው – ደርግ የከፍተኛ መኮንንነትን ማዕረግ በ“ከዚህ መልስ ሻምበል፤ ከዚያ ታች ወዲህ ደግሞ ሻለቃ” እያለ በለብ ለብ ሥልጠናና አለልክ በተጋነነ ባዶ ጀብድ ያድል አልነበር? – አሁን የነወዩ ብሶ ቁጭ አለ እንጂ! ከበረሃ ትግል በቀጥታ ወደ ጄኔራልነት)፡፡ መቶ ዩንቨርስቲ መክፈት እኮ እጅግ ቀላል ነው – ለዚያውም በቢከፍቱ ተልባ የሚታወቁ ዩንቨርስቲዎችን ለታይታና ለዕቅድ ማስፈጸሚያ ብሎ መክፈት – ባገር ሀብትም መቀለድ፡፡ … ልጁ በዐማርኛ ራሱን እንዲገልጽ በአስተርጓሚ ይጠየቃል፤ ዐማርኛውስ ከየት መጥቶ? በምን ይግባቡ? ፈረንጁም አፉን ይዞ ከተደመመ በኋላ እንዲህ ተብሎ እንዲነገረው መከረ፤” አየህ፣ አሁን እኛ ብንቀጥርህ የ4ኛ ክፍል ተማሪዎች እንደመሆናቸው አንተን ያሣቅቁሃል፤ እነሱ ካንተ መቶ በመቶ ይበልጣሉ… ስለዚህ አዲስ አበባ ውስጥ ካሉት የግል የቋንቋ ት/ቤቶች በአንደኛው ተመዝገብና ራስህን አሻሽል፡፡ ማሻሻልህን እርግጠኛ ስትሆን ለመቀጠር አመልክት፡፡ አሁን ግን እናዝናለን አልተገናኘንም…”፡፡

ዛሬ የተመረቁት መጻሕፍት በላቲን ነው የተጻፉት ተብሏል፡፡ በላቲን ሆሄ እንዲጠቀሙ የተሸረበውን ወያኔያዊ የፖለቲካ ሤራ ለጊዜው እንተወውና ወደ ወጪው እንሂድ፡፡ በዐማርኛ ቢጻፍ በ100 ገጽ ያልቅ የነበረ መጽሐፍ በላቲን ሲሆን በትንሹ 300 እንደሚሆን ታውቃላችሁ? ካላወቃችሁ ዕወቁ፡፡

ምሣሌ ማየት እንችላለን፡- “ወላይትኛ” ሊባል ሲችል  Wolayttotto Doonaa ተባለ ተሠልጥኖ ተሙቶ፡፡ ማየት ማመን ነውና ወላይታዎች የሆናችሁ ራሳችሁ ፍረዱት፡፡ 7 ፊደል በ17 ፊደል ተመነዘረ፡፡ እኔ በመሠረቱ አይደለም በላቲን በዐረብኛና በቻይንኛም ቢጻፍ ግድ የለኝም – ቋንቋውን ዱሮውንም አላውቀውምና፡፡ የወያኔ መሠረታዊ እሳቤ ግን ወላይታውንና ሌላውን ዘውግ ከኢትዮጵያዊነት የማስተሳሰሪያ ገመድ ለመነጠል ነው፡፡ እንጂ ወላይትኛ በዐማርኛ መጻፍ አለመጻፉ ያን ያህል አጨቃጫቂ ሆኖ እንዳይመስላችሁ፡፡ ወያኔ ደግሞ ቅራኔና ግጭትን እንደመፍጠር የሚያስደስተው ነገር የለም፡፡

ሌላውና ከዚሁ የሚያያዘው ነገር ጎሣዎች ሁሉ በየራሳቸው ቋንቋ እንዲማሩ ተደርጎ ዐማርኛን ሲቻል እንዲጠሉትና በመላ አቅማቸው እንዲዋጉት ያ ባይቻል ከዐማርኛ ርቀው እንዲያድጉና ከሌላው ዜጋ ጋር በምንም ዓይነት የጋራ ገመድ እንዳይገናኙ ማድረግ ነው፡፡ ይህ ዕቅድ በሚገባ ተተግብሮ ፍሬ እያፈራላቸው ነው፡፡ አንድ የፌዴራል ተብዬ ሠራተኛ ከአዲስ አበባ በአራቱም አቅጣጫ ሲወጣ የክልሉን ቋንቋ የሚያውቅ ዐማርኛ ተናጋሪ ይዞ መሄድ አለበት፡፡ ሁሉንም ክልል ፀረ-ዐማርኛና ፀረ-አንድነት አድርገውታል፡፡

አብዛኛው የሥራ ዘርፍ በወያኔዎች በተያዘው አዲስ አበባ ውስጥ በየግንባታው ‹ሳይት› ሥራ ለመቀጠር የሚፈልግ ዜጋ ትግሬ ሆኖ መገኘት ይኖርበታል – በተፈጥሮ ወይም በገዢ – ዲቪ ይገዛል – ትግሬነትም ካወቅህበት ይገዛል፡፡ ትግሬ ካልተሆነ በቀላል መቀጠር የለም (የቅንፍ ጨዋታ፡- አንዲት አሮጊት በአንድ ረጂም ሠልፍ ገብተዋል፡፡ ምግብና ልብስ ለመቀበል ነው ሰዎቹ የተሰለፉት፡፡ ሴትዮዋ ግን ሠልፉ ውስጥ ለመገኘት መሥፈርት መኖሩንም ሆነ የመሥፈርቱን ዓይነት አያውቁም፡፡ ተሠላፊዎቹ የኤች አይቪ ተጠቂዎች ናቸው፡፡ ሴትዮዋ ተራቸው ደረሰና ማስረጃቸውን ተጠየቁ፡፡ ምሥጢሩን ካለማወቃቸውም በተጨማሪ ምንም ማስረጃ የላቸውም፡፡ ያኔ “አይ ፈጣሪየ፣ ለምንድነው ይህን በሽታ እንኳን ያልሰጠኸኝ?” በማለት እግዜር በሽታውን ስላልሰጣቸው አማረሩት አሉ – ሆድ መጥፎ ነው፤ ከሰው በታች ያደርጋል- ያዋርዳል፤ እንደምናየው እንኳንስ ትግሬነትን የማይድን በሽታን ያስመኛል፡፡…) ሁሉም እንደውሻ ዘሩን እያነፈነፈ ነው ወዛደርና ኩሊ እንኳን የሚቀጥር፡፡ እናም መንጓለል አለ – አዳሜ የቀባጭ ምሷን እያገኘች ነው፡፡ በዚህ መልክ ሁሏም ዋጋ እየከፈለች ነው፡፡  በቀጣፊዎች ሸር በተፈጠረ ታሪካዊ ስህተት ለተጎዳ ዜጋ መቼም እሰይ አይባልም እንጂ ሁሉም ይህን ችግር መረዳቱ ጥሩ ነው ባንልም ክፉ አይመስለኝም – ትልቅ ዋጋ ከፍለህ የቀሰምከውን ትምህርት በቀላሉ አትረሳውምና፡፡

አዲስ አበባ የምትመጣ የክልል ሰው ፍዳዋን እያየች ነው፡፡ ከትምህርት ትምህርት የላት፤ ከችሎታ ችሎታ የላት፤ ከቋንቋ ቋንቋ የላት… ባዶዋን ትመጣና ዘበኝነትና ግርድና ባቅማቸው በቀላሉ የማይገኙ እየሆኑ ክፉኛ እየተቸገሩ ናቸው፡፡ ምክንያቱም ቋንቋ ዋና መሣሪያ ነውና፡፡ ዘመናውያኑ ትግሬዎች ቋንቋቸው ከዐማርኛ እምብዝም ስለማይለይና ሥረ-መሠረታቸው አንድ ግንድ በመሆኑ ለመልመድ ብዙም አይቸገሩም፡፡ ከትግራይ ገጠር በመጡ በሁለትና ሦስት ወር ውስጥ ዐማርኛን አቀላጥፈው በመናገር ይሄን የዋህ የመሀል አገር ሰው በአሽከርነትና በግርድና ያንቆራጥጡታል – ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ አይደለም ብረት ይሰብራል፤ በተግባር አየን፡፡

አሁን ምን ይደረግ? እኔ እንጃ፡፡

The post ስንት ትውልድ እስኪጠፋ እንጠብቅ? – ፍርዱ ዘገዬ                        appeared first on Zehabesha Amharic.

«የእሣት ልጅ አመድ» የሆነው የዘመኑ ኢትዮጵያዊ ታሪካዊ ማንነቱን ያስከብር! –ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

$
0
0

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት             ሐሙስ ሚያዝያ ፳፯ ቀን ፪ሺህ፰  ዓ.ም.         ቅፅ ፬ ፣ ቁጥር ፲፬

Moreshከዛሬ ሰማኒያ ዓመታት በፊት የነበሩት ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን እና እናቶቻችን፣ ከትግራይ እና ከኤርትራ ምድር በበቀሉ ባንዶች አጋዥነት በፋሽስት ጣሊያኖች ጦር ማይጨው ላይ ድል ሲመቱ «እሺ፣ አሜን፣ እንገዛለን» ብለው እጃቸውን አጣጥፈው አልተቀመጡም። ራሣቸው ፋሽስቶችም እንዳመኑት፥ በተለይ በሰሜን ሸዋ፣ በጎጃም፣ በጎንደር፣ በወሎ፣ በጉራጌ፣ በጅባት እና ሜጫ እንዲሁም በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች የነበሩት አርበኞች በመረጧቸው የጎበዝ አለቆቻቸው እየተመሩ፣ ለአምሥት ዓመታት የፋሽስት ጣሊያንን ጦር ከእነ ባንዳ ግሣንግሱ መውጫ መግቢያ አሣጥተውታል። ከዚያም ከየካቲት1933 ዓም ጀምረው ጀግኖች አርበኞቻችን ባደረጉት የተቀነባበረ የጥቃት ዘመቻ ልክ የዛሬ 75 ዓመት ሚያዝያ 27 ቀን 1933 ዓም በቀዳማዊ ኃይለሥላሤ መሪነት በድል አድራጊነት ዋና ከተማችንን አዲስ አበባን ለመቆጣጠር በቅተዋል። ሆኖም ዛሬ ላይ ሆነን ስናየው ያ ሁሉ መስዋዕትነት ያስገኘልንን ብሔራዊ ክብር እና ልዕልና እንዲህ አሽቀንጥረን እንድንጥል ያደረገንን ምክንያት ለመገንዘብ ትልቅ እንቆቅልሽ ይሆንብናል።

የአምሥቱ ዓመት የፋሽስት ኢጣሊያ ወረራ በአገራችን በኢትዮጵያ ላይ ታላቅ የትውልድ ስብራትን ፈጥሮ አልፏል። ብዙ ጀግኖች አርበኞቻችን መሥዋዕት ሆነውብናል። በተቃራኒው ደግሞ ለፋሽስት ጣሊያኖች በባንዳነት ያገለገሉ አያሌ ከሃዲዎች ተፈልፍለዋል። በመሆኑም ፋሽስት ጣሊያኖች በጀግኖች አርበኞቻችን ከፍተኛ ተጋድሎ ከኢትዮጵያ ምድር ተጠራርገው ቢወጡም፣ እነርሱን በባንዳነት ሲያገለግሉ የነበሩት የእናት ጡት ነካሾች ግን ተንሠራፍተው ለመኖር በቅተዋል። ለዚህም የረዳቸው በተለይ ቀዳማዊ ኃይለሥላሤ ሥልጣናቸውን ለማደላደል ሲሉ በአገሪቱ የመንግሥት መዋቅር ውስጥ አብዛኞቹን የጣሊያን ሎሌ ባንዶች በመሾማቸው ነው። በሚያሣፍር ሁኔታ ንጉሠ-ነገሥቱ ይባስ ብለው አርበኞችን እያደኑ በእሥር፣ አልፎም በግድያ ቀጧቸው። የአርበኞችን ቤተሰቦች አጎሣቆሉ። በተቃራኒው የባንዶች ልጆች በምርጥ ምርጥ የውጭ አገር ትምህርት ቤቶች እና ዩኒቨርሲቲዎች እንዲማሩ አደረጉ። የተዘረጋውም ሥርዓተ-ትምህርት ተተኪውን ትውልድ ስለአገሩ እንዲያውቅ ሣይሆን የምዕራቡን ሥልጣኔ የበላይነት እንዲቀበል የሚሰብክ እንዲሆን ተደርጎ ተቀረጸ። የእነዚህ ድምር ውጤት አገሩን የማያውቅ፣ በኢትዮጵያዊ ማንነቱ የሚያፍር፣ ዐይቶት የማያውቀውን የውጭውን ዓለም የሚቀላውጥ መጢቃ ትውልድ ፈጠረ። ስለዚህ ዛሬ ላይ ሆነን ስናየው ጣሊያኖች በ1888 ዓም ዐድዋ ላይ ድል ሆነው ቢመለሱም፣ ከማይጨው ውጊያ በኋላ ግን የረዥም ጊዜ ዕቅዳቸውን እንዳሣኩ መገንዘብ ይቻላል።

ከፋሽስት ጣሊያን ወረራ በኋላ ዘመናዊ ትምህርት የቀመሰው ትውልድ፣ በወቅቱ እንደ ወረርሽኝ በመላው ዓለም በመሠራጨት ላይ የነበረው የኮሚኒስት ርዕዮተ-ዓለም ተከታይ ለመሆን ጣረ። «ያ ትውልድ» ለአገሩ ቀና ያሰበ መስሎት ጎትቶ ያመጣው ርዕዮተ-ዓለም ግን ከራሱ አልፎ የታላላቆቹን እና የታናናሾቹን ትውልዶች ቀርጥፈው የሚበሉ አምባገነን ሥርዓቶችን ፈጠረ። በዚህ ረገድ ወታደራዊው ደርግም ሆነ የትግሬ-ወያኔ ሥርዓቶች ምንጫቸው «የተማሪዎች እንቅስቃሴ» እየተባለ የሚጠራው ክስተት ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። በእርግጥ በአገራችን ላይ የደረሰውን እና አሁንም በመድረስ ላይ ያለውን መዓት ሁሉንም በዚያ ትውልድ የተሣሣተ የፖለቲካ አቅጣጫ ብቻ ማሳበብ ባይቻልም፣ ግዙፉን ድርሻ እንደሚወስድ ግን መጠራጠር አይገባም። ስለዚህ ዛሬ በኢትዮጵያዊነቱ የሚያፍር ትውልድ ቢፈጠር ሊደንቀን አይገባም፥ አባቱን አያውቅ፣ አያቱን ናፈቀ ተብሏልና።

ትውልድ በትውልድ ሲተካ በጎም ሆነ መጥፎ ነገሮች ይከሰታሉ። የአሁኑ ወጣት ትውልድ ያለፉት ትውልዶች ያከማቹት ጥሪት ውጤት ነው። ባንዳነት እንደ መሠልጠን እየተቆጠረ፣ በጥራዝ-ነጠቅነት ከውጪ «አዲስ መጣ» የተባለውን ርዕዮተ-ዓለም ስላነበነቡ ብቻ «አዋቂ» የሚያስብል ባህል እንዲስፋፋ እየተደረገ፣ ስለ አገር ታሪክ እና ስለ ሕዝብ ባህል ከማወቅ ይልቅ በምዕራቡ ዓለም የሚፈበረኩ ርካሽ የባህል ሸቀጦች ማራገፊያ መሆን የዘመናዊነት ምልክት ተደርጎ እየታየ፣ ዓለም በቴክኖሎጂ እየተመነደገ ሲሄድ የእኛ አገር ገዢዎች ሕዝብን በማስራብ እና በጅምላ በመፍጀት ከፍተኛ መዋዕለ-ንዋይ ሲያከማቹ እንድ ብልጠት እየተቆጠረ፣ ወዘተርፈ፤ ይህ አዲሱ ወጣት ትውልድ ከማን ያየውን እና የተማረውን የመልካም የዜግነት ምግባር እንዲያሣይ ይጠበቃል? ስለዚህ ከታሪክ ተወቃሽነት፣ ከትውልዱም ፈፅሞ መጥፋት እንድንድን በአንድነት ለትክክለኛው ኢትዮጵያዊ ማንነታችን ልዕልና እንነሣ!

 

ኢትዮጵያ በጀግኖች እና ቆራጥ ልጆቿ መስዋዕትነት ለዘለዓለም ፀንታ ትኖራለች!

The post «የእሣት ልጅ አመድ» የሆነው የዘመኑ ኢትዮጵያዊ ታሪካዊ ማንነቱን ያስከብር! – ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live