ሚያዚያ 27 ቀን 2008 ዓ.ም.ዜና (May 05, 2016 NEWS)
#በደሴ ከተማ ያሉ ነጋዴዎችና ባለሱቆች የስራ ማቆም አድማ አደረጉ
#ከጋምቤላ ተጠልፈው የተወሰዱ ከ100 በላይ የሚሆኑት ህጻናት ያሉበት ቦታ ታወቀ
#ከወያኔ ጋር ግንኙነት ያላቸው ስደተኛ አስተላላፊዎች ተያዙ ተባለ
#የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት በደቡብ ሱዳን ወንጀል የፈጸሙ ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀ
#በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ የአገሪቱ የፍርድ ሚኒስተር በተቃዋሚ ፓርቲዎች እጩ
#ተወዳዳሪ በመሆኑ እንዲወዳደሩ በተወከሉት ግለስብ ላይ ክስ ሊመሰርት እንደሚችል ገለጸ
#በደቡብ አፍሪካ ምክር ቤት ረብሻ ተፈጠረ
#ከስድስት ቀን በኋላ በኬኒያ ከፈረሰው የመኖሪያ ህንጻ ውስጥ አንዲት ሴት በህይወት ተገኘች
ዝርዝር ዜናዎች
በወሎ ደሴ የስራ ማቆም ያደረጉ ነጋዴዎችና ባለ ሱቆች ዛሬ ሶስተኛ ቀናቸው መሆኑ ታውቋል።
በደሴ ከተማ የሚገኙት ባለሱቆችና ነጋዴዎች የስራ ማቆም አድማ ለማድረገ የተገደዱት ከአቅም
በላይ የግብር ክፍያ የተጠየቁ በመሆናቸው የተነሳ ሲሆን ከሚያዚያ 24 እስከ ሚያዚያ 26 ድረስ
ባለሱቆችን ሁሉ ያሳተፈ የሥራ ማቆም አድማ መደረጉ ታውቋል። ነጋዴዎች ከአቅም በላይ የሆነ
የግብር ክፍያ መጠየቃቸውና ሁሉም ባለሱቅ የገንዝብ መሰብሰብና መመዝገቢያ እንዲያስገባ
በመጠየቃቸው ምክንያት ተቃውሟቸውን በሥራ ማቆም አድማ ከመግለጻቸውም በላይ
የተጣለባቸው የግብር ክፍያ ለመክፈል አቅም የሌላቸው ነጋዴዎች የንግድ ፈቃዳቸውን ለመመለስ
ቢያመለክቱም 20 ሺህ ብር እንዲከፍሉ መጠየቃቸው ተገልጿል። የወያኔ ባለሥልጣኖች የደሴ
ነጋዴዎች ላቀረቡት ጥያቄ አግባብ ያለው መልስ አለመስጠታቸው ሲታወቅ በዛሬው ዕለት
አንዳንዶቹ ወደ ስራ መመለሳቸው ታውቋል።
Dessie (ደሴ)
ከትውልድ ቦታቸውና ከቀያቸው በግዳጅ ተጠልፈው የተወሰዱ ከ100 በላይ የሚሆኑ የጋምቤላ
ህጻናት ያሉበት ቦታ መገኘቱን የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ቃል አቀባይ አስታውቋል። እንደ ቃል
አቀባዩቹ ከሆነ ከጋምቤላ ታግተው የተወሰዱት ህጻናት ከደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ 300 ኪሎ ሜትር
ርቀት ሰሜናዊ ምስራቅ ግዛት ውስጥ እንዳሉ የታወቀ ሲሆን የአካባቢው ነገድ መሪዎችም ህጻናቱ
በቦታው ያሉ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። ሰላሳ ሁለቱ ሕጻናት እንዴት እንደተፈቱና እንደተለቀቁ
የተሰጠ መረጃ የለም።
የወያኔን ዘረኛና አምባገነን አገዛዝ በመጥላትና በኢትዮጵያ ያለውን አስከፊ ድህንነት በመሸሽ ወደ
አውሮፓ ወደ አረብ አገራትና ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚደረገው ስደት ለአንዳንድ ግለሰቦችና ለወሮበላ
ቡድኖች በርካታ ገንዘብ የሚያስገኝ ስራ መሆኑ ሲታወቅ በዚህ ሰውን የማዘዋውር የወንጀል ስራ
ላይ ተሰማርተዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች በየአገሩ በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆናቸው ታውቋል።
በሚዴትራኒያን ባህር አቋርጠው በማልታ በኩል ወደ ጣሊያንና ሌሎች የአውሮፓ አገሮች
ኢትዮጵያውያንና የአፍሪካ ስደተኞችን በማሻገር ወንጀል ተከሶ የዋስ መብቱን ተጠቅሞ ተሰውሮ
የነበረው ሃዲሽ ኪዳኑ በቁጥጥር ስር መዋሉ ሲነገር በደቡብ አሜሪካ አገሮች በኩል ስደተኞች ወደ
አሜሪካ የሚያዘዋውሩ ወንጀለኞች እየተያዙና እየታደኑ መሆናቸውና ከተያዙት ውስጥ በኢትዮጵያ
ውስጥ ንብረትና የንግድ ሥራ ያላቸው እንዲሁም ከወያኔው ጋር ቀጥተኛ የነበራቸው መሆኑ
ታውቋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ረቡዕ ሚያዚያ 26 ቀን 2008 ዓ.ም. ባደረገው
ስብሰባ የተለያዩ ተጻራሪ ቡድኖችን ያካተተ የአንድነት መንግስት በደቡብ ሱዳን መመስረቱን አድንቆ
በግጭቱ ጊዜ ከፍተኛ ወንጀልና የሰብአዊ መብት ረገጣ ያካሄዱ ግለሰቦች ባስቸኳይ ለፍርድ
እንዲቀርቡ ጠይቋል ። ምክር ቤቱ የደቡብ ሱዳን የአንድነት መንግስት ተቋቁሞ ስራ መጀመሩ
በአገሪቱ ውስጥ ሰላምን ለማስፈን ትልቅና የመጀመሪያ እርምጃ መሆኑን ገልጾ በግጭቱ ወቅት የዓለም
አቀፍ ህጎችንና ደንቦችን በመተላለፍ የተደረጉትን የጭካኔ ርምጃዎችና የሰብአዊ መብት ረገጣዎች
ለፍርድ ለማቅረብ አስቸኳይ ርምጃዎች መወሰድ አለባቸው ብሏል። በሪክ ማቻርና በሳልቫ ኬር
መካከል ባለፈው ዓመት በተካሄደው ድርድር ከሁሉም የተወጣጣ አንድ ገለልተኛ የሆኑ የፍርድ
አካል ለማቋቋምና እንዲሁም አንድ የእርቅን የእውነት ፈላጊ ኮሚሽን ለመመስረት ስምምነት
የተደረገ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን በትናንት የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ አሜሪካና
ሌሎች የምክር ቤቱ አባላት በአፍሪካ ህብረት የሚደገፍ የፍርድ አካል ባስቸኳይ እንዲቋቋም
ጠይቀዋል።
በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ በሚቀጥለው ብሔራዊ ምርጫ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ወክለው
በእጩ ተወዳዳሪነት እንዲቀርቡ የተሰየሙት ሚስተር ካቱምቢ ኃላፊነቱን የሚቀበሉ መሆናቸውን
ተናግረዋል። ሚስትር ካቱምቢ በሰጡት መግለጫ ኃላፊነቱን በደስታና በክብር የሚቀበሉ መሆኑን
ገልጸው የተሰጣቸውን ኃላፊነት በድል ለማጠናቀቅ የሚቻለቸውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ቃል
ገብተዋል። በሌላ በኩል በዚሁ ዕለት የአገሪ የፍርድ ሚኒስተር ሚስተር ካቱምቢ የውጭ አገር ዜግነት
ያላቸው ቅጥረኛ ወታደሮችን በጠባቂነት አሰማርተዋል የሚለውን ስሞታ እየመረመረ መሆኑን ገልጾ
ምርመራው ሲጠናቀቅ ክስ የሚመሰርት መሆኑን አስታውቋል። ሚስተር ካቱምቢ ለተሰነዘረባቸው
ክስ በሰጡት መልስ በመንግስት በኩል ሊቀርብ የተፈለገው የፈጠራና የውሸት ክስ እሳቸውን
ከውድድር ለማስቀረት የተደረገ ሴራ መሆኑን ገልጸው ኃላፊነታቸውን ለመወጣት እንቅፋት
እንደማይሆንባቸው ተናግረዋል። በሰላማዊ የስልጣን ሽግግርና በህግ የበላይነት የሚያምኑና
መሆናቸውን አስምረው የውጭ ዜግነት ያላቸው የግል ወታደሮች እንዳልቀጠሩ ገልጸዋል። ከአምስት
ዓመት በፊት በአገሪቱ የተካሄደው ብሔራዊ ምርጫ ነጻና ገለልተኛ ያልሆነ ማጭበርበርና ኃይል
በተቀላቀለበት ሁኔታ የተካሄደ ስለነበር የአሁኑ ፕሬዚዳንት የሚስተር ካቢላ አስተዳደር በከፍተኛ
ውጥረትና አለመረጋጋት ውስጥ አገሪቱን ሲመራ የቆየ መሆኑ ይታወቃል።
በደቡብ አፍሪካ አንዲት ሴት የ19 ወር ህጻን ልጇን በኢንተርኔት አማካይነት በ340 የአሜሪካን ዶላር
ለመሸጥ ስትስማማ ተይዛ የአምስት ዓመት እስራት የተፈረደባት መሆኑ ታውቋል። የተወሰነባት
ቅጣት ለሶስት ዓመት ያህል በቤት ውስጥ ተገድባ ትምህርት እንድተወስድ የሚደረግ ሲሆን ሁለቱን
ዓመት ግን በእስር ቤት ታሳልፋለች ተብሏል። ሴትየዋ ልጇን ለመሸጥ የተገደድችው የህጻኑ አባት
ለልጁ ማሳደጊያ የሚከፍለውን ገንዘብ በማቋረጡና ችግር ላይ በመውደቋ ምክንያት መሆኑን
ገልጻለች። በደቡብ አፍሪካ የሰውን ልጅን በገንዘብ መሸጥ የእድሜ ልክ እስራት ወይም 6.7 ሚሊዮን
ዶላር መቀጫ የሚያስከፍል ሕግ ያለ ሲሆን የሕጻኑ እናት ቀለል ያለ ቅጣት እንዲሰጣት የተደረገው
ልጁን ለመሸጥ ያደረገችው ሙከራ የገንዘብ ትርፍ ለማግኘት ሳይሆን ከችግር መሆኑ ስለታመነበት
ነው ተበርካታ ገንዘብ ለማግኘት ባለመሆኑ ነው ተብሏል።
ትናንት ረቡዕ ሚያዚያ 26 ቀን 2008 ዓ.ም. በደቡብ አፍሪካ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሚስተር ዙማ ስለ
በጀት ጉዳይ ለምክር ቤቱ አባላት ንግግር ለማድረግ በሚዘጋጁበት የኢኮኖሚ ነጻነት ታጋዮች ፓርቲ
የሚባለውን የተቃዋሚ ፓርቲ የሚወክሉ 10 የምክር ቤቱ አባላት ፕሬዚዳንቱ መናገር የለባቸውም
የሚል ድምጽ በማሰማት እንዳይናገሩ እክል በመፍጠራቸው የጸጥታ ኃይሎች ሰዎችን ከምክር ቤቱ
መሰብሰባያ አዳራሽ ለማስወጣት ሙከራ ባደረጉበት ወቅት ቦክስ እና እርግጫ የተቀላቀለበት ድብደባ
ተካሄዶ እንደነበር ታውቋል። ተቃዋሚዎቹ ከምክር ቤቱ እንዲወጡ ከተደረገ በኋላ ፕሬዚዳንቱ
ያቀደቱን ንግግር ለማደረግ ችለዋል። ቀደም ብሎ የደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሚስተር ዙማ
የአገሪቱን ሀብት ያለአግባብ ተጠቅመዋል ብሎ የፈረደ መሆኑ ይታወቃል። አንድ ሌላ ፍርድ ቤት
4
ደግሞ በሚስተር ዙማ ላይ ቀርበውና በኋላ ተሽረው የነበሩ ከ800 በላይ የሚሆኑ ክሶች እንደገና
እንዲታዩ በመወሰኑ ዙማ በሚመሩት የደቡብ አፍሪካ አስተዳደር ላይ ከፍተኛ ውጥረትና ጫና
የፈጠረ መሆኑ ይታወሳል።
በኬኒያ ባለፈው ሳምንት አንድ የመኖሪያ ህንጻ ከተረደመሰ ከስድስት ቀን በኋላ በተደረገው ፍለጋ
አንዲት ሴት በህይወት ልትገኝ የቻለች መሆኗን የኬኒያ መንግስት ባለስልጣኖች ሐሙስ ሚያዚያ 27
ቀን 2008 በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል። መናገር የምትችለውና በጥሩ መንፈስ ላይ ትገኛለች
የተባለችው ይችው ሴት ከህንጻው ፍርሽራሾች ገና ያልወጣች ስትሆን በአካብቢው የሚገኙ የሕክምና
ባለሙያዎች ግሎኮስና ኦክሲጅን እየሰጧት መሆኑ ታውቋል። በትናንትናው ዕለትም አንዲት
የስድስት ወር ህጻን ከእነህይወቷ መትረፏ የተነገረ ሲሆን ዘግይቶ እናትየዋ ሞቷ መገኘቷ ተነግሯል።
የህንጻው መደርመስ ስድሰተኛ ቀኑን ያስቆጠረ ሲሆን እስካሁን 36 ሰዎች መሞታቸውና የ70 ሰዎች
ሁኔታ ምን እንደሆኑ አለመታወቁ ተገልጿል።
ዝርዝር ዜናዎች
የወያኔ አገዛዝ ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ እንደ አሸን የፈሉትን ቡና ቤቶችንና የጭፈራ ቤቶችን
ምዝገባና ቆጠራ ሊያካሂድ መሆኑ ታውቋል። ከዚህ በተጨማሪ የአስጎብኝ ድርጅቶች እየተባሉ
የተከፈቱት የንግድ ድርጅቶች ምዝገባና ቆጠራ ይካሄድባቸዋል። ቆጠራውና ምዝገባው ለምን እንዳስፈለገ
ወያኔ የገለጸው ነገር ባይኖርም ምናልባት የአገልግሎት ክፍያ ጭማሪ ሊያደርግባቸው በማሰብ ሊሆን
እንደሚችል ተገምቷል። ምዝገባውና ቆጠራው ከግንቦት 1 ቀን እስከ ግንቦት 20 ቀን 2008 ዓ.ም ድረስ
በአዲስ አበባ የሚካሄድ ሲሆን በሌሎች ከተሞች ቀጣይነት ይኑረው አይኑረው የታወቀ ነገር የለም።
የወያኔ መሪዎችና ባለስልጣኖች ሌላ ዜጋ የማይገባበት የራሳቸው መስከሪያ ቡና ቤቶችና መዝናኛ
ሆቴሎች እንዳላቸው ይታወቃል።
ሰላሳ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ከዱባይ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ወደ አዲስ አበባ
እንዲመለሱ መገደዳቸው ታወቀ። ኢትዮጵያውያን ሴቶቹ ቲኬት ገዝተው በፋላይ ዱባይ አየር መንገድ
ተሳፍረው ዱባይ ይግቡ እንጅ ዱባይ እንደደረሱ ትክክለኛ የመጎብኚያ ቪዛ የላችሁም ተብለው
በአውሮፕላን ጣቢያው እንደሚገኙ ታውቋል። የፋላይ ዱባይ አየር መንገድ ቃል አቀባይ የተወሰኑ
የኢትዮጵያ መንገደኞች ቡድን ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ እንደሚደረግ ማረጋገጫ ሰጥተዋል። ይሁን
እንጅ ትክክለኛ ቪዛና የመጎብኚያ ፈቃድ የሌላቸው ሴቶች እንዴት ከሀገር ወጡ የሚለው ጥያቄ አነጋጋሪ
ሆኗል።
የኢትዮጵያው ድርቅና ረሃብ አየከፋ መምጣቱና በተለይም በሕጻናት ላይ አስጊ ሁኔታን እየፈጠረ መሆኑን
የዕርዳታ ድርጅቶች አስታውቀዋል። ስድስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ህጻናት በዚህ የድርቅና የረሀብ
ሰለባ እንዳይሆኑ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን ድርቁና ረሃብ ከአሳሳቢነት ወደ አስጊነት መሸጋገሩ በተለይም
ለሕጻናት መድረሻው ጊዜ አሁን ነው ብሏል።
የወያኔ አገዛዝ ፖለቲካውን የጦር ኃይሉን የፖሊስና የደህንነት መስሪያ ቤቱን በትግራይ ተወላጆች ብቻ
ካደራጀ ወዲህ በንግድ ዓለምም በሙስናዋ እመቤት በአዜብ መስፍን የሚመራ የነጋዴ ቡድን በተለይ
የቡና ንግዱን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠራቸውና ቡና ላኪነት በትግራይ ተወላጆች እጅ እንዲወድቅ
መደረጉ ይታወሳል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቡና ላኪነት የተመዘገቡ ቡና መላክ የጀመሩ ላኪዎች ከ 19
ሺ ሜትሪክ ቶን በላይ ቡና ደብቃችኋል በመባል ከንግዱ ዓለም እንዲታገዱ መደረጉ ታውቋል።
እንዲታገዱ የተደረጉት የቡና ላኪዎች 54 እንደሆኑና ደበቁት የተባለውም ቡና 7.6 ሚሊዮን ዶላር
የሚያወጣ ነው ተብሏል። ቡና ለወያኔ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ማስገኛ የነበረ ሲሆን የወያኔ ነጋዴዎችና
መሪዎች በሚሰሩት አሻጥርና ገንዘብ የማሸሽ ሚስጥር የአበባ ሽያጭ የቡና ገቢውን እየተካ መምጣቱ
ይታወሳል።
የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች በጋምቤላ ወረራ በመፈጸም ከ200 በላይ ገድለው ከመቶ በላይ አፍነው ንብረት
አውድመው ከጠፉ ከሁለት ሳምንታት በኋላ የወያኔ ወታደሮች በደቡብ ሱዳን እንቅስቃሴ መጀመራቸው
ታውቋል። የአይን ምስክሮች ለሱዳን ትሪቡን ጋዜጣ እንደገለጹት ብዛት ያላቸውና በ 20 ታንኮች የታጀቡ
የወያኔ ወታደሮች በፓቼላ በኩል ወደ ደቡ ሱዳን እየገቡ መሆናቸውንና የጦር አውሮፕላኖችም የቅኝት
በረራ እያደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል። የደቡብ ሱዳን ባለስልጣኖች የወያኔን ወታደራዊ እንቅስቃሴ
መስማታቸውን ገልጸው ዝርዝር መርጃ ግን የለንም ብለዋል።
የሱማሊያ አማጺ ኃይልና ከአልቃይዳ ጋር ንኪኪ ያለው አልሸባብ ማክሰኞ ዕለት በሞቃዲሾ አውሮፕላን
ጣቢያ ባለው የአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ኃይል የጦር ሠፈር ላይ የሞርታር ጥቃት ማድረሱን
አምኗል። አልሸባብ ሞቃድሾ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ውስጥ ባለው የጦር ሰፈር ላይ ድብደባ
ማካሄዱንና በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን በደፈናው ይግለጽ እንጅ ስለደረሰው ጉዳት
ዝርዝር መግለጫ አልሰጠም። በሶማሊያ የተመድ የሰላም አስከባሪ ኃይል ቃል አቀባይ በበኩላቸው
የአልሸባብ የሞርታር ጥይቶች ከጦር ሰፈራቸው ውጭ ማረፋቸውን በመግለጽ በሰውና በንብረት ላይ
የደረሰ ምንም ዓይነት ጉዳት አለመድረሱን ተናግረዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአልሸባብ መሪዎችና
ኮማንደሮች በአሜሪካ ድሮን በመገደላቸው ብቻ አልሸባብ ተዳክሟል የሚል አስተያየት ይሰጥ እንጅ
የአልሸባብ ጥቃት መቀጠሉ የድርጅቱን ጥንካሬና የሶማሊያ የሰላም ጊዜ ገና ሩቅ መሆኑን ያሳያል
ተብሏል።
በላቦራቶሪ ውስጥ የተሰራ አንትራክስ የሚባልን ተላላፊ በሽታ በማሳራጨት የሽብር ተግብር ላይ
ለመሰማራት ያቀደውንና ከአልካይዳ ጋር ግንኙነት አለው ተብሎ የሚንጠረጠረውን መሀምድ አብዲ
አሊ የተባለውን ግለሰብ ከሚስቱ እና ከሌላ አንዲት ሴት ጋር በቁጥጥር ስር ያደረገ መሆኑን የኬኒያ
ፖሊስ ገልጿል። ሽብሩን ለማካሄድ በእቅዱ ላይ ተባባሪ የነበሩ ሌሎች ሁለት ሰዎች አምልጠው
እየተፈለጉ መሆናቸውም ተገልጿል። በኬኒያ ሆስፒታል የነጻ ህክምና አገልግሎት ይሰጥ የነበረው
መሀመድ አብዲ አሊ ኬኒያውያንን በመቀስቀስ ለሽብር ተግባር ሲያዘጋጅ የቆየ ነበር የተባለ ሲሆን
የህክምና ባለሙያዎችን በማሳተፍ በላቦራቶሪ የተሰራ የአንትራክስ በሽታ ለማሰራጨት እቅድ
እንደነበረው ተደርሶበታል። ሚስቱና የቅርብ ተባባሪ የነበረችው ተማሪዋ ኑሰይባ መሀመድ ሃጂ
የተባለችውና ጓደኛዋ ፋጡማ መሀመድ ከሚኖሩበት ከኡጋንዳ የተያዙ መሆናቸውም ተነግሯል።
የመሀመድ አብዲ ሌሎች ተባባሪዎች አምልጠው የተደበቁ ሲሆን ሰዎቹን ይዞ ላመጣ ወይም ያሉበትን
ለጠቆመ የኬኒያ መንግስት 20 ሺ የአሜሪካ ዶላር ለመክፈል ዝግጁ እንደሆነ ገልጿል። ቡድኑ በሊቢያ
በሶሪያ ካሉ የአልካይዳ ቡድኖች ጋር ግንኙነት እንዳለው ተደርሶበታል።
በተያያዘ ዜና ባለፈው ሳምንት አርብ ሚያዚያ 21 ቀን ከፈረሰው አንድ ህንጻ ውስጥ በህይወት ያሉ ሰዎችን
ለማውጣት ፍለጋው የቀጠለ ሲሆን ማክሰኞ ሚያዚያ 25 ቀን 2008 ዓም አንዲት የስድስት ወር ህጻን
በህይወት የተገኘች መሆኑ ታውቋል። በህንጻው መደርመስ 23 ሰዎች መሞታቸውና በርካታዎች
መቁሰላቸው ሲነገር ከ93 በላይ የሚሆኑ ሰዎች መዳንና አለመዳናቸው አልታወቀም ተብሏል። ከአራት
ቀን በኋላ የስድስት ወር ሕጻን በህይወት መገኘቷ ሌሎች በህይወት ሊኖሩ ይችሉ ይሆናል የሚለውን
ተስፋ ከፍ አድርጎታል። ሕጻኗ ከፈሳሽ እጥረት በስተቀር ምንም ጉዳት ያልደረሰባት መሆኑ የታወቀ ሲሆን
አብራት የነበረችው እናቷ በህይወት ትኑር አትኑር እስካሁን አልታወቀም። በሌላ ቦታ ስራ ስለነበር
ከአደጋው ያመለጠው አባቷ የልጁን በህይወት መገኘት ከፍተኛ ተአምር ነው ብሎታል።
በምስራቅ ኮንጎ ሶስት የቀይ መስቀል ሰራተኞች ተጠልፈው የተወሰዱ መሆናቸውን አንድ መንግስታዊ
ያልሆነ ድርጅት ማክሰኞ ሚያዚያ 25 ቀን ገለጸ። ሶስቱም ሰዎች ሾፌሮች ሲሆኑ ጎማ ከተባለችው
የምስራቅ ኮንጎ ከተማ ክብሪዚ ወደ ተባለች አንድ ሌላ ከተማ እቃ የያዙ መኪኖችን እያሽከረከሩ
በነበሩበት ወቅት ነው። ጠላፊዎቹ የታጠቁ ሚሊሺያዎች መሆናቸው የአካባቢው ሰዎች የተናገሩ ሲሆን
መኪናዎቻቸውን መንገድ ላይ ትተው እነሱን ወደ ጫካ ይዘዋቸው እንደገቡ ገልጸዋል። ማዕከሉ ጄኒቫ
የሆነው የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ተቋም ዳይሬክተር ዶሚኒክ ስቲል ሃርት ማክሰኞ ዕለት በሰጡት
8
መግለጫ ድርጅቱ ሰዎቹን ለማስፈታት የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል ብለዋል። በምስራቅ ኮንጎ የመንግስቱ
ተቃዋሚ የሆኑ የተለያዩ የታጠቁ ቡድኖች የሚንቀሳቀሱ መሆናቸው ይታወቃል።
በተያያዘ ዜና በዚሁ በምስራቅ ኮንጎ ማንነታቸው ያልታወቀ ሰዎች ማክሰኞ ሚያዚያ 25 ቀን 2008 ዓም
ከምሽቱ 2 ሰዓት እስከ 4 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ አንድ መንደር ላይ ወረራ አካሂደው በቆንጨራና
በመጥረቢያ 16 ሰዎች የገደሉ መሆናቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም አስከባሪ ኃይል እና
የኮንጎ መንግስት ባለስልጣኖች ገልጸዋል። ባለስልጣኖቹ ዛሬ ረቡዕ ሚያዚያ 26 ቀን በሰጡት መግለጫ
አሸባሪዎቹ ለጥበቃ ከተሰማራው ኃይል ተሰውረው ወደ መንደሩ የመጡ መሆናቸው ጠቅሰው ሰዎቹ
አላይድ ዴሞክራቲ ፎርስ (ADF)የተባለው የዩጋንዳ አማጺ ቡድን አባላት መሆንና አለመሆናቸው
አልታወቀም ብለዋል፡፤ አላይድ ዴሞክራቲክ ፎርስ የተባለው ድርጅት ተደጋጋሚ የሽብር ተግባሮችን
የፈጸመ ሲሆን በፈረጆቹ አመት 2014 ብቻ በአካባቢው ከ500 የሚበልጡ ሰዎችን መግደላቸው
ተዘግቧል።
ናይጄሪያ ከሌጎስ ግዛት ነዳጅ ማውጣት የጀመረች መሆኑ ተነገረ። ከ25 ዓመት የፍለጋ፣ የጥናትና
የግምባታ ሥራ በኋላ ማውጣት የተጀመረው የነዳጅ ክምችት በቀን 40 ሺ በርሜል የማውጣትና ከ
750 ሺ በርሜል በላይ የማከማቸት አቅም እንዳለው ተገልጿል። እስካሁን ናይጄሪያ ነዳጅ ስታወጣ
የነበረው ከደቡብ ዴልታ ግዛት ሲሆን ከነዳጁ ገቢ ተመጣጣኝ ገንዝብ አለተሰጠንም በማለት የተለያዩ
ቡድኖች የአመጽ እንቅስቃሴዎች ሲካሄዱ መቆየታቸው የሚታወቅ ነው። የነዳጅ ሽያጭ የናይጄሪያ
መንግስትን በጀት በከፍተኛ ደረጃ እየሸፈነ ቢሆንም በቅርቡ በነዳጅ ላይ የነበረው የዋጋ ማሽቆልቆል
የበጀቱን መጠን ዝቅተኛ አድርጎት እንደነበር ይታወቃል።
The post በደሴ ከተማ ያሉ ነጋዴዎችና ባለሱቆች የስራ ማቆም አድማ አድርገው ነበር (የፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ አጫጭር) appeared first on Zehabesha Amharic.