Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

በጃዋር መሃመድ ሀሳቦች ላይ! –አስራት አብርሃም

$
0
0
Asrat Abrha

አስራት አብርሃም

ጃዋር መሃመድ ሰሙኑ የሰጠውን ቃለ መጠይቅ አነበብኩት፤ እርሱ የሚታገልለትን የፖለቲካ መስመር ወደ መሬት ለማውረድና ተጨባጭ ውጤት ለማምጣት ካለው ፅኑ ፍላጎት የተነሳ በአማራና በኦሮሞ ልሂቃን መካካል የታክቲክ ትብብር ለመፍጠር የሞከረበት መንገድ፣ እንደየነባራዊው ሁኔታ ራሱን ለመለዋወጥና ፖለቲካዊ እቋሞቹን ለማመቻመች ያለውን አቅም ተመክቸለታለሁ። ይህን ጥረቱን ስታይ ልጁ የተግባር ሰው መሆኑ መረዳት የሚከብድ አይደለም፤ ቢያንስ ተስፋ ሲያገኙ ፍከራ ቀረርቶ፣ ተስፋ ሲያጡ ደግሞ ለቅሶና እርግማን ከሚያበዙ ‘ፖለቲከኞቻችን’ በእጅጉ የሚሻል እንቅስቃሴ ሲያደርግ ነው የሚታየው። ነገር ግን ጃዋር መሰረታዊ ችግር አለበት፤ አንደኛ እርሱ ራሱን እንደሚያየው ተራማጅ ፖለቲከኛ አይደለም። አሁን ካሉት ተቃዋሚዎች በተሻለ ሁኔታ የብሄር ፖለቲካን ካርድ አንስቶ መጨዋት የሚችል ሰው ለመሆኑ ግን ምንም ጥርጥር የለውም።

የጃዋር ፖለቲካ ተራማጅ አይደለም የምልበት ዋና ምክንያት አሁንም ፖለቲካው ከሶስቱ ብሄሮች (አማራ፣ ኦሮሞና ትግራይ) ጠበኛ ልሂቃን እይታ ያልወጣ መሆኑ ነው። ለእኔ አሁን ባለችው ኢትዮጵያ ተራማጅ አስተሳሰብ የምለው የተለመደውን የብሄር ፖለቲካ ካርድ እንስቶ በተሻለ ሁኔታ መጫወት ሳይሆን በዜግነት መብት ላይ የሚያተኩር፤ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን የሚመች ስርዓት ለማምጣት የሚታገል፤ ፍቅርና ወንድማማችነትን ሃገራዊነትን የሚሰብክ፤ እኩልነትና ዴሞክራሲ ለማምጣት በእምነትና በመርህ የሚገዝ ሰው፤ ወይም ተቋም ነው ወይም አስተሳሰብ ነው።

በዚህ በእኩል በሶሻል ሚዲያው ተፅዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ ኢትዮጵያዊያን ውስጥ የዜግነት ብሄርተኝነት የሚያቀነቅን፤ ቅንነትና የአቋም ያለመዋዠቅ ያለው ሰው “ከጎሣ ይልቅ ሰብአዊነትን እናስቀድም” የሚለው ኦባንግ ሜቶ (Obang Metho) እና ድርጅቱ “ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ” (Solidarity Movement for a New Ethiopia) ብቻ ይመስለኛል። አለበዚያ ስለፖለቲካዊ ለውጥ፣ ዴሞክራሲና እኩልነት አስባለሁ እያሉ፣ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ የደቡብ ኢትዮጵያ፣ የሶማሌ፣ የትግራይ፣ የአፋር፣ የጋምቤላ፣ የቤንሻንጉል ወዘተ ህዝብ ያገለለ ፖለቲካዊ ትብብር ውጤታማ ይሆናል ብሎ አያስብም። ይሄ አካሄድ ስርዓቱን በአቋራጭ ለመጣል ይጠቅም እንደሆነ እንጂ ሰላም፣ ፍትህ፣ ሃገራዊ አንድነት፣ ዴሞክራሲና እኩልነት ግን በዚህ መንገድ ፈፅሞ ሊገኝ አይችልም፤ በሀገሪቱ ያሉትን ዜጎች ያገለለ ከመሆኑ አንፃር ሃገራዊ አስተሳሰብም አይደለም። ከዚህ አንፃር የጃዋር ሀሳብ ተራማጅ ያለመሆኑ ብቻ ሳይሆን ጠቃሚም አይደለም።

ሁለተኛው የጃዋር መሀመድ ችግር ዘላቂ (consistency) የሆነ የፖለቲካ አቋም ወይም እምነት ያለመኖር ነው። በፖለቲካ ትግል ውስጥ የማትደራደርባቸውና በቀላሉ የማትለውጣቸው መሰረታዊ የሆኑ ፖለቲካዊ አቋሞች ወይም እምነቶች ወይም ራስህን የምትገልፅበት ማንነቶች ይኖራሉ። አንድ ሰው ወይም ፖለቲካዊ ድርጅት አቋሙ ለወዳጅም ለጠላትም ግልፅ ሆኖ ሲታይ ወይ ሲታወቅ ነው ለመደራደርም ሰጥቶ ለመቀበልም የተመቸ የሚሆነው። ማንነቱና ፖለቲካዊ አቋሙ የሚታወቅ ከሆነ ከእነዚህ መሰረታዊ አቋሞች ውጭ ባሉት ጉዳዮች ላይ ለመደራደር አስቸጋሪ አይሆንም። ስለዚህ በፖለቲካ ትግል ውስጥ መተጣጠፍና መገለባበጥ የሚቻለው መሰረታዊ ባልሆኑ ፖለቲካዊ አቋሞችና የትግል ታክቲኮች ላይ ብቻ ነው። ከዚህ ያለፈ መገለባበጥና መለዋወጥ መርህ አልባነት ከመሆኑ ውጪ ፖለቲካዊ ጥበብ አይመስለኝም። ምክንያቱም የራሱ የሆነ ፅኑ ፖለቲካዊ አቋም ከሌለው አካል ጋር ሌላው ለመደራደርና በሙሉ ልብ አብሮ ለመጓዝና ለመስራት ያስቸግሯል።

ለምሳሌ የአማራና የኦሮሞ ህዝብ በግጭትና በትብብር ለዘመናት አብሮ የኖረ ነው ያለው ከአሁን በፊት ይለው ከነበረው ጋር ፍፁም ተቃራኒ ነው። ከቀኝ ገዥና ተገዥ ትርክት ባንዴ ወደዚህ ጫፍ አትመጣም። አሁን መጨረሻ ላይ ይህን ሀቅ የተገጠለት ማድረግ የፈለገውን ማድረግ ስላልቻለ እንጂ ከልቡ ስለሚያምንበት ነው ለማለትም እቸገራለሁ። ይህ እውነት በኦሮሞውና በአማራው ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ልዩ ልዩ ህዝቦች ሁሉ ተመሳሳይ የግጭትና የትብብር ረጅም ታሪክ እንዳላቸው እርግጥ ነው። በትግራይና በአማራ፣ በኦሮሞውና በደቡቡ እንደዚህ ዓይነት ግንኝነቶች ነበሩ፤ አሁንም አሉ። ስለዚህ ይህን እውነት በተሸራረፈ መንገድ ሳይሆን እንዲህ በተሟላ ሁኔታ መገንዘብ ያስፈልግ ነበር፤ ነገር ግን ጃዋር ለጊዜው የአማራው ልሂቅ የታክቲክ ትብብር ስለሆነ የፈለገው የሁለቱን ህዝቦች ግንኙነት ብቻ ነጥሎ በማውጣት ሊጠቀምበት ፈልጓል ማለት ነው። እንደዚያም ሆነ በእነዚህ ሁለት ልሂቃን መካከል የሚኖርን ትብብር በምን ላይ የተመሰረተ እንደሆነ ያስቀመጠው ነገር የለም። “ፖለቲካ ማለት ማን ምን አገኘ?” የሚል ጥያቄ የያዘ በመሆኑ ሰጥቶ የመቀበል ጉዳይ ነው።

ጃዋር የኦሮሞ ፖለቲካ ወኪል አድርገን እናስበውና ለአማራ ልሂቃን የእንተባበር ጥያቄ ሲያቀርብ ከእርሱ በእኩል ምን ለመስጠት ነው የፈለገው? የሚለውን ስናይ ምንም ሆኖ ነው ያኘሁት። ህወሀትን በጋራ አስወግደን እኛ የኦሮምያን ለም መሬት ባለቤት እንሆናለን፤ እናንተ ደግሞ የመተማ፤ የጠገዴና የወልቃይት ለም መሬት ባለቤት ትሆናላችሁ ዓይነት ነገር እንጂ ኢትዮጵያ በጋራ እንጠቀማለን፣ አብረን በሰላም እንዳአንድ ሃገር እንኖራለን፤ የኢትዮጵያ የግዛት አንድነት ሳይሸራረፍ ይቀጥላል የሚል ምንም ነገር አላየሁበትም። ከእነዚህ ሁለት ክልሎች ውጨ ያለውን ህዝብና መሬት ምን እንደሚሆን የተቀመጠ ነገር የለም። ይሄ በጣም አስፈሪው ገፅታው ነው። ሁሉት ብሄሮች በዚህ ጉዳይ ሊስማሙ የሚችሉት ሁለቱም ከዋናው ሃገር ለመገንጠል በአንድ ላይ ለመዋጋት ሲስማሙ ነው ልክ እንደ ህወሀትና ሻዕቢያ። ለምሳሌ ይሄ በኦነግና በኦጋዴን ነፃ አውጪ ግንባር ማካከል የነበረው ትብብር በዚህ ዓይነቱ ስሜት የተቃኘ ነበር።

በመሰረቱ የአማራ ልሂቃን አሁን በኢህአዴግ የተሰጣቸውን ክልል ብቻ ይዘው ለመኖር የጃዋርን ትብብር የሚያስፈልጋው አይመስለኝም። ሌላው የአማራ ልሂቃን ኦሮሚያ እንድትገነጠል የሚፈልጉ አይመስለኝም፤ ስለዚህ ጃዋር ከእነዚህ ጋር ለመስራት ከፈለገ አቋሙን ነው በትክክል መቀየር ያለበት። አንደኛ በኢትዮጵያ የግዛት አንድነት ማመን አለበት፤ ሁለተኛ ህዝቦቿ የተሳሰረ የጋራ እድል እንዳላቸው፤ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለማምጣት የሁሉም ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ መቀበል ይኖርበታል። እንደዚሁም በኢትዮጵያ ጨቋኝ ስርዓቶች እንጂ በቀኝ ግዛት መልክ የገዥና የተገዥ ግንኙነት እንዳልነበረ ከልብ መረዳት ያስፈልጋል።

በሌላ በእኩል ኦፌኮ የኦሮሞ ህዝብ ወኪል እንደሆነ ገልፀዋል፤ እንደዚያ ከሆነ ደግሞ የኦፌኮ ፕሮግራም ማየት ይኖርብናል ማለት ነው። ኦፌኮ በኢትዮጵያ ትክክለኛ ፌደራሊዝምና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲኖር ይፈልጋል፤ አሁን ያለውን የኦሮሚያ ክልል ካርታ ያለመሸራረፍ እንዲከበር ይፈልጋል፤ አዲስ አበባ በኦሮሚያ ግዛት ውስጥ የሚገኝ በመሆኑ ኦሮሚያ ከአዲስ አበባ ልዩ ጥቅም እንድታኝ ይፈልጋል፤ ኦሮምኛ ልክ እንደአማርኛ የፌደራል መንግስት የስራ ቋንቋ እንዲሆን ይፈልጋል። ስለዚህ የአማራ ልሂቃን ቢያንስ በእነዚህ ከመገንጠል በመለስ ያሉትን የኦሮሞ ፖለቲካ ጥያቄዎች ለመቀበል ይችሉ ይሆናል፤ ይህን ሲቀበሉ ግን የሚያገኙት ነገር ሊኖር ይገባል። ይሄ ሲሆን ሌላው ደቡብ ትግራዩ አፋሩ ጋምቤላው ቤንሻንጉሉ ምንድነው የሚያደርገው ዝም ብሎ ያያል። ሀሳቡ ራሱ ገና ከመነሻው የከሸፈ መሆኑ የሚያሳየው እዚህ ላይ ነው።

ኦፌኮ ይህን ፍላጎቱን በተወሰነም ቢሆን በመድረክ ውስጥ ያሉትን ፓርቲዎች ለማሳመን ሙከራ ያደርጋል፤ ለምሳሌ ሁለተኛ ቋንቋ ይኑር በሚለው ጉዳይ ላይ አረና፣ የያኔው አንድነት፤ የበየነ ፓርቲዎች ተቀብለውት ነበር። ከዚህ ውጪ ከአንድ ወገን ብቻ የሚደረግ ትብብር ኢህአዴግ እስከሚወድቅ ድረስ ብቻ የሚቆይ እንጂ ዘላቂ አይሆንም። ሌላው ጃዋር እንደሚያስበው ህዝብ ዝም ብሎ ተባበር ስላልከው ብቻ አይተባበርም፤ አንድላይ ሁን ስላልከው ብቻ ተነድቶ አንድ ላይ አይሆንም፤ ሰው የከብት መንጋ አይደለምና። ይሄ ህዝብን መናቅ ነው፤ ህወሀትም እስከዛሬ ሲያደርገው የኖረውን ነገር ነው።

ሶስተኛው ነገር የትግራይ ልሂቃን ተራማጅ ለመሆን አልቻሉም ያለበት ነገር ነው። አንደኛ እውነትነት ያለው አይደለም፤ ሁለተኛ ደግሞ የእርሱ የተራማጅነት መለኪያ ምን እንደሆነ ግልፅ አይደለም፤ እሱ ሜኒሶታ ሆኖ አቧራ ባስነሳ ቁጥር ለምን ድጋፍ አልሰጡኝም ከሆነ ብዙ የሚያስኬድ አይደለም። እንደ ትግራይ ልሂቅነታቸው የራሳቸው የሆነ ክልላዊና ሃገራዊ አጀንዳዎች ይኖራቸዋል። ከዚህ ፍላጎቻቸው ተቃራኒ የሆኑ እንቅስቃሴዎች ሲደረጉ ድጋፍ ላይሰጡ ይችላሉ። ለምሳሌ እኔ በኢትዮጵያዊ ብሄርተኝነት አምናለሁ፤ ህወሀት ለኢትዮጵያ ጥሩ ስርዓት እንዳልሆነም አውቃለሁ። በዚህ ምክንያትም በተቻለኝ አቅም ሁሉ ስታገለው ኖሬያለሁ፤ ነገር ግን “የትግራይን ህዝብ ከህወሀት ጋራ ደርበን እንመታለን” የሚሉትን አንዳንድ ፅንፍ የረገጡ ኃይሎች አልቀበላቸውም።

አስር ሺህ የማይሞላ ትግርኛ ተናጋሪ በስርዓቱ ተጠቃሚ ስለሆኑ “የትግራይ ህዝብ ሁሉ ተጠቃሚ ነው” የሚለኝም አልቀበልም፤ ምክንያቱም እኔ ትግራይ ውስጥ ኖሬ ነው እውነታውን የማይቀው። ስለዚህ እኔ በትክክል ስለማውቀው ነገር አሜሪካ ወይም አውሮፓ ወይም አዲስ አበባ ሆኖ ተቃራኒው እንዲነግረኝ አልፈልግም። ሌላው የጃዋር መከራከሪያ ደካማ የሚያደርገው ምክንያት ደግሞ “አራት መቶ ሰው ሲጨፈጨፍ አንድም የትግራይ ልሂቅ ወጥቶ “አረ ይኼ ግድያ ትክክል አይደለም” አለማለቱ እንደሆነ አስቀምጠዋል።

እርሱ አልሰማም ይሆናል እንጂ ቢያንስ እራሱ “የኦሮሞ ህዝብ ወኪል ነው” ካለው ኦፌኮ ጋር አብሮ በመድረክ ጥላ ስር ያለው አረና በስራ አስፈፃሚ ደረጃ ተወክሎ አብሮ መግለጫ ሲሰጥ ተመክቻለሁ። እነ አረጋዊ በርሄ፣ ግደይ ዘርዓፅዮንና የመሳሰሉት አንጋፋ የትግራይ ፖለቲከኞች አሉበት የሚባለው ሸንጎ የተባለ በውጭ የሚኖሩ ፓርቲዎች ስብስብም ግድያውን አውግዘዋል። እንግዲህ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ኦፌኮ የኦሮሞ ህዝብ ወኪል ነው ካለ አረናም የትግራይ ህዝብ ወኪል የማይሆንበት ምንም ምክንያት የለም። ስለዚህ የትግራይ ልሂቃን ወገናቸው በሆነው የኦሮሞ ህዝብ ላይ ስለደረሰው ነገር ለጃዋር ስልክ እየደወሉ ወይም በፌስቡኩ ስር ተስልፈው አቋማቸውን ማሳወቅ የነበረባቸው አይመስለኝም። እንዲያውም እኔ አልፎ አልፎ ከትግራይ ልጆች ጋር ስንወያይ የኦሮሞ ፖለቲካ በኢትዮጵያ ባለው የኃይል አሰላለፍ እንደተፈጥሯዊ አጋር የማየት ሁኔታ ነው የማየው። ይሄ ህወሀት የፈጠረው ትፅዕኖ ሊሆን ይችላል። እንደእኔ እምነት ግን አንድ ህዝብ በአንድ ሃገር ውስጥ ከሌላው ነጥሉ አጋር አንዱን ደግሞ ጠላት ወይም ስጋት የማድረግ አካሄድ አላምንበትም።

ስለተራማጅነት ከተነሳ አረና በነበርኩበት ወቅት ኦሮምኛ ሁለተኛ ብሄራዊ ቋንቋ እንዲሆን በመድረክ መለስተኛ ፕሮግራም ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምፅ ነበር ያፀደቀው፤ ለእኔ ከዚህ በላይ ተራማጅነት የለም። ከአቶ ገብሩ አስራት በስተቀር ያለበት ጉዳይ ራሱ በጣም አስቂኝ ነው፤ አቶ ገብሩ አስራት በአረና ውስጥ ካሉት ወይም ከአረና ውጪ ካሉት የህወሀት ተቃዋሚዎች በኦሮሞ ጉዳይ ላይ የተለየ አቋም ያለው አይመስለኝም፤ “ከገብሩ በስተቀር ዓረና ውስጥ ያሉትን ወጣቶች “የአንድነት ኃይል” ተፅዕኖ አለባቸው” እየተባለ በመድረክ ኮሪደር አከባቢ የሚወራውን ነው የደገመው፤ ምንም አዲስ ነገር የለውም። መድረክን እንደ አንድ ኃይል አለመስወዱ ግን መድረክ ከሚያደርገው እንቅስቃሴ ደካማነት አንፃር ተገቢ ሊሆን ይችላል።

ሌላው የሕወሓት አወዳደቅ የትግራይ ሕዝብን ይዞ እንዳይወድቅ መጥንቀቅ አስፈላጊ ነው፤ …. ማንም ይኹን ምን ኢትዮጵያ ውስጥ የአንድ ብሔረሰብ መጎዳት ለኢትዮጵያም ኾነ ለአጠቃላዩ የምሥራቅ አፍሪካ መልካም አይደለም።” ያለው ተገቢ የሆነ ግንዛቤ ነው። ቢያንስ ምንም ምንም በማይደርስበት የውጭ ዓለም ተቀምጠው፤ በርገራቸውን እየገመጡ “የእኛ ትግል የትግራይ ህዝብ ካልደገፈ እኛ ወደ ስልጣን ስንመጣ ወዮውለት” ከሚሉት አንዳንድ የዲያስፖራ ፖለቲከኞች የተሻለ አቋም ነው።

በመሰረቱ ህወሀትንና የትግራይን ህዝብ ለይቶ የማያይ የፖለቲካ አስተሳስብም ሆነ እንቅስቃሴ መጨረሻው ውድቀትና መከራ ለሁላችን ያመጣ እንደሆነ እንጂ ለድል የሚበቃ አስተሳሰብ አይደለም። የትግራይ ህዝብ ከህወሀት የተለየ ምን ሊያደርጉለት እንደሚችሉ ማሳመን ያለባቸው እነርሱ ናቸው፤ ይህን ማድረግ ካልቻሉ የራሳቸው ችግር ነው። ገና ለገና መንግስት ሲሆኑ ሊያጠቁኝ ይችላሉ ብሎ ፈርቶ የትግራይ ህዝብ ማንምም ሊደግፍ አይችልም፤ እንደዚያ ዓይነት ታሪክም የለውም። ስለዚህ ሊማርከው ያልቻለን ፖለቲካ ያለመደገፍ መብቱ ነው፤ ህወሀት መጥፎ ስለሆነ ሌለው ሁሉ ጥሩ ነው ማለት አይደለም። እኔ የሚያሳስበኝ ነፃ ያለመሆኑ ነው እንጂ ነፃ ሆኖ ህወሀትም ቢደግፍ ህዝብ እንደህዝብ ተሳስቷል የምልበት ሞራል አይኖረኝም ነበር። እንዲያውም እንደህዝብ በህወሀት ታግቶ እየኖረ ያለ በመሆኑ ሊታሰብለት ነው የሚገባው።

ተራማጅ የሆነ ፖለቲካዊ አስተሳሰብ ያለው ማንኛውም ሃይል የትግራይ ህዝብ ነፃ ሆኖ የፈለገውን እንዲደግፍ ነው እድል ማመቻቸት ያለበት እንጂ በልዩ ልዩ ተፅዕኖና በፍራቻ ውስጥ ሆኖ እየኖረ ለህወሀት ይደግፋል ማለት እጅግ በጣም ፍርደ ገምድልነት ነው። በድንብ መሰመር ያለበት ጉዳይ እንዲህ ከሚያስቡ ኃይሎችና ግለሰቦች ጋር የትግራይ ልሂቅ ትብብር ሊኖረው አይችልም።

 

ለሁሉም ነገር አስታራቂው ሀሳብ የሚመስለኝ፤ በዜግነታዊ ብሄርተኝነት (Civic Nationalism) ሁላችንንም እኩል የምንሆንበትን ስርዓት ለማምጣት እንታገል የሚል ነው። ሁሉም ኢትዮጵያዊ ተጠቃሚ የሚያርግ፤ በህግ የበላይነት የሚመራ፤ አድልዎ የሌለበት ስርዓት ታግለን እንትከል የሚል ጥሩ ሀሳብ ነው። ይሄ ሀገር እዚህ እንዲገኝ ሁሉም አስተዋፅኡ አድርጎበታል፤ ችግር እየሆነ ያለው ሁሉም ተጠቃሚ ያለመሆኑ ነው። ይሄ ነው ማስተካከል ያለብን። ሁለተኛ ደግሞ መገንጠል መፍትሄ ያለመሆኑ ነው። ከዚያ አከባቢ ነቅለህ አይደለም የምትሄደው፤ አሳባዊ የሆነ መሬት ላይ የሌለ ድንበር አበጅተህ ነው ጎን ለጎን ተፋጥጠህ የምትኖረው። ስለዚህ እንዲህ ተፋጥጠህ ከምትኖር በሰላም ተግባብቶ መኖር አማራጭ የሌለው መፍትሄ ስለሆነ ነው።

 

 

 


የከሸፈው የብአዴን/ህወሃት/ኢህአዴግ ስብሰባ በዳላስ!

$
0
0

ባሳለፍነው ሳምንት እሁድ April 24, 2016 ወያኔ/ኢህአዴግ ጠፍጥፎ የሰራው የበአዴን ከፍተኛ ባለስልጣናት ከክልሉ ተወላጆች ጋር በልማት ዙርያ እወያያለሁ በሚል የዘወትር ዲስኩራቸው ለማሰማት ወደ ዳላስ/ቴክሳስ መምጣታቸውና ስብሰባ ማድረጋቸው የሚታወስ ነው። ስብሰባው በበአዴን የዳላስ ተወካዮችና በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኢንባሲ የተዘጋጀ ነው ቢባልም ከመግቢያው በር ጀምሮ ተቆጣጣሪ የነበሩት የህወሃት/ኢህአዴግ ሰዎች ነበሩ። የክልሉ ተወላጆች ጨምሮ አያሌ ኢትዮጵያውያን ወደ ስብሰባው ስፍራ ቢያመሩም የመግቢያ ቲኬት የላችሁም በሚል ወደ አዳራሹ እንዳይገቡ ታግደዋል።
webshet taye
የስብሰባው አዳራሽ ባዶ እንዳይሆንባቸው የህወሃት/ኢህአዴግ አባላት የተገኙ ሲሆን በቅጡ ተቆጥረው በአጠቃላይ ከ45 አይበልጡም ነበር። ከ50,000 በላይ ኢትዮጵያውያን በሚገኙበት ዳላስ ከተማ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣን መጥቶ ትንሽ ቁጥር ያለው ህዝብ ስብሰባው ላይ መሳተፉ የዳላስ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ምን ያክል በወያኔ ተስፋ የቆረጡና የተማረሩ መሆናቸውን ነው።

ስብሰባው ላይ ከተሳተፉትና ካዘጋጁት ውስጥ ተኮላ፣ ፀሃይጽድቅ፣ ኢብራሂም፣ ሙሉጎጃም ገዳሙ፣ አቶ መሰረት፣ ወ/ሮ መሰረት፣ አያሌው አርጋው፣ ወ/ሮ አለምፀሃይና ሌሎችም ይገኙበታል። ሰው በላ የሆነውን አንባገነኑና ፋሽስቱ የወያኔ/ኢህአዴግ ስርዓትን እድሜ ለማራዘም በታማኝነት ተግተው የሚሰሩት እንዚህ ጥቂት አደርባዮች ለይቶ በማወቅ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። አብዛኛዎቹ በኮሚኒቲያችን፣ በቤተክርስቲያን፣ ኢትዮጵያዊ በሆኑ የሲቪክ ማህበራት ውስጥ እራሳቸው ሸሽገው የወያኔ 52 ገፅ የዲያስፖራ ፖሊሲ ለማስፈፀም የስለላ ስራ ሲሰሩ ቆይተዋል።

እነዚህ ተላላኪ የወያኔ ተኩላዎችን ለይቶ በማወቅ እራሳችን እንጠብቅ፤ ለሌሎችም እናሳውቅ። ለሆዱ ያደረ ባንዳ ዘመድና ጓደኛው ሆዱና ሆዱ ብቻ ነውና!
የነፃነት ቀን እሩቅ አይደለም!
በፅናት እንታገል!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

የመዝናኛ ዜና: ኤፍሬም ታምሩና ዲና አንተነህ ሜይ 21 በሚኒሶታ ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ

$
0
0

epherem

ዝነኛው ድምፃዊ ኤፍሬም ታምሩ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውን የሚኒሶታ ኮንሰርቱን ይፋ አደረገ:: በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስፍራ ያለውና እጅግ የገነነው አርቲስት ኤፍሬም ታምሩ በሚኒሶታ የሙዚቃ ሥራዎቹን የሚያቀርበው ሜይ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ነው:: በርካታ የሚኒሶታና አካባቢው ስቴቶች ነዋሪዎች ይህን ታላቅ የሙዚቃ ድግስ በጉጉት ይጠብቁታል:: ከኤፍሬም ታምሩ ጋር ተወዳጇ ድምጻዊት ዲና አንተነህ አብራ የዚህ ኮንሰርት አካል ትሆናለችም ተብሏል:: ዲና አንተነህ በቅርቡ በለቀቀቻቸው የሙዚቃ ቭዲዮዎች በቀናት ውስጥ የሚሊዮን የዩቱብ ተመልካቾን ያገኘች ድምጻዊ ናት:

ቦካሃራም‬ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር የአምስት አገሮች የጋራ መከላከያ ኃይል የገንዘብ እርዳታ ያስፈልገዋል ተባለ (የፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ አጫጭር ዜናዎች)

$
0
0
ሚያዚያ 20 ቀን 2008 ዓ.ም.ዜና (April 28, 2016 NEWS)
‪#‎ቦካሃራም‬ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር የአምስት አገሮች የጋራ መከላከያ ኃይል የገንዘብ እርዳታ ያስፈልገዋል ተባለ
‪#‎በደቡብ‬ አፍሪካ ፕሬዚዳንቱ ከስልጣን እንዲነሱ የሚጠይቁ ሰላማዊ ሰልፎች ተካሄዱ
‪#‎በግብጽና‬ በሊቢያ ወሰን 16 ግብጻውያን ስደተኞች ተገደሉ
‪#‎በሊቢያ‬ የአይሲስ አሸባሪዎች በነዳጅ ማምረቻዎች ላይ እያደረሱት ያሉት ጥቃት ከፍተኛ ስጋት ፈጠረ

ሚያዚያ 20 ቀን 2008 ዓ.ም.

Ø ቦኮ ሃራምን ለመቋቋም የተቋቋመው የአምስት አገሮች የጋራ መከላከያ ኃይል አዛዥ ሚያዚያ 19 ቀን 2008  በሰጡት መግለጫ የጋራው ወታደራዊ ኃይል ውጤት ያለው ስራ እንዲሰራ የገንዘብና የማቴሪያል ድጋፍ ያስፈልገዋል ብለዋል። በመጨረሻው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ስብሰባ ላይ ረጅዎች ለጋራ ኃይሉ 250 ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት መመደባቸው የተገለጸ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ገንዘቡ ለጋራው ኃይል ያልደረሰ መሆኑኑ አዛዡ ተናግረዋል፡፡ ገንዘቡ ይሰጣል ተብሎ ቃል የተገባ ከመሆኑ ባሻገር እስካሁን የጋራው ኃይል የደረሰው የተወሰኑ የመገኛኚያ መሳሪያዎችና 11 ወታደራዊ መኪናዎች ብቻ ነው ብለዋል። 8500 ወታደሮችን የያዘው የጋራ ወታደራዊ ኃይል ተደጋጋሚ ጥቃቶችን ሰንዝሮ ቦኮ ሃራምን አዳክሟል ቢባልም ውጤት ያለው ስራ ለመስራት እርዳታ ያስፈልገዋል ተብሏል፡፤

nigeria-boko-haram-2000-feared-killed-after-baga-attacked-second-time-days

Ø ረቡዕ ሚያዚያ 19 ቀን 2008 ዓም. በደቡብ አፍሪካ በሚገኙት በጆሃንስበርግ፤ በኬፕ ታውንና በደርበን ከተሞች በርካታ የደቡብ አፍሪካ ዜጎች ፕሬዚዳንት ዙማ ከስልጣን እንዲነሱ በመጠየቅ ሰላማዊ ሰልፎች አካሄደዋል። ሰልፈኞቹ ፕሬዚዳንት ዙማ በሙስናና እና በዝምድና ስራ ውስጥ የተዘፈቁ በመሆናቸው አገራችውን ለመምራት ብቃት የላቸውም የሚሉ መፈክሮችን ሲያሰሙ እንደነበር ታውቋል። ከጥቂት ቀናት በፊት በአገሪቱ ምክር ቤት ውስጥ  ከስልጣናቸው እንዲወገዱ ተካሄዶ የነበረውን እንቅስቃሴ በድል ያሸነፉት ፕሬዚዳንት ዙማ በደቡብ አፍሪካ ነጻ ምርጫ የተካሄደበትን 22 አመት ለማክበር በተዘጋጀ ስነስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር የአገሪቱ መሪዎች የሚለወጡት በዴሞክራሲያዊ ምርጫ እንጅ በአቋራጭ እና በመፈንቅለ መንግስት አይደለም ብለዋል። በዴሞክራሲ ውህዳን የአብዛኛውን ሕዝብ ውሳኔ ተቀብሎ የመሄድ ግዴታ አለባቸው ብለዋል። በደቡብ አፍሪካ ያለው የፖለቲካ አለመረጋጋት ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ መምጣቱ እየታየ ያለ ክስተት ሲሆን ከተወሰኑ ወራቶች በኋላ የሚደረጉት የከተሞች አስተዳድር ምርጫዎች የሕዝቡን ስሜት በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ሊያሳዩ ይችላሉ በማለት ታዛቢዎች አስተያየታችውን ይሰጣሉ። በሚቀጥሉት የከተሞች አስተዳደር ምርጫዎች ገዥው ፓርቲ ከተሸነፈ የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግሬስ በአገሪቱ ላይ ባለው የስልጣን ሁኔታ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ሊኖረው እንደሚችል ብዙዎች ይተቻሉ።

 

Ø በግብጽና በሊቢያ ወሰን ከሕገ ወጥ ስደተኞች ጋር በተደረገ ግጭት 16 የሚሆኑ ግብጻውያን ስደተኞች የተገደሉ መሆናቸውን ረቡዕ ሚያዚያ 19 ቀን 2008 ዓ.ም. የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ ገልጿል። ግድያው የተፈጸመው ባኒ ዋሊድ በተባለችው ከተማ ውስጥ ሲሆን  ከአስተላላፊዎች ጋር በተነሳ ግጭት ስደተኞቹ የተገደሉ መሆናቸው ተነግሯል። በሊቢያ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የእርዳታ ተልእኮ መስሪያ ቤት መሪ በሰጡት መግለጫ  12 ግብጻዉያን እና ሶስቱ ሊቢያውያን መገደላቸውን ተናግረው ድርጊቱን በጽኑ ኮንነዋል። በሊቢያ በተለያዩ ወገኖች መካከል የእርስ በርስ ግጭት ከተጀመረና አለመረጋጋት ከተፈጠረ ወዲህ አገሪቱ ከልዩ ልዩ አገሮች የመጡ ስደተኞች ወደ አውሮፓ የሚሰደዱባት ማዕከል ሆና የቆየች ስትሆን የስደተኛ ማስተላለፍ ንግድም ደርቶ የሚገኝባት ቦታ ናት።  በሊቢያ በኩል ከሚተላለፉ ስደተኞች መካከል በወያኔው ዘረኛና አምባገነን ስርዓት አፈናና ብዝበዛ ተማረው አገራቸውን ጥለው የሚሰደዱ ኢትዮጵያን የሚገኙበት መሆኑም ይታወቃል። በዚህ አጋጣሚ ባለፈው አመት አይሲስ በሚባለው የአክራሪና የአሸባሪ ቡድን አባላት ግፍ በተሞላበት መንገድ በስለት የታረዱ  ኢትዮጵያን ሰማዕታት ወገኖችን የምናስታውሰው በከፍተኛ ሀዘን ነው።

 

 

Ø ረቡዕ ሚያዚያ 19 ቀን 2008 ዓም. በሱዳን ካርቱም የዩኒቨርስቲ የተማሪዎችን ሰልፍ ለመበተን ፖሊሶች በተኮሱት ጥይት አንድ ተማሪ ተመቶ የሞተ መሆኑ ተነገረ። በኦምዶርማን የሚገኘው የአህሊያ ዩኒቨርስቲ ቅጥር ግቢ የሚማሩ ተማሪዎች ቀደም ብሎ በተደረገ ሰልፍ ተይዘው በቁጥጥር ስር የነበሩት ተማራዎች እንዲፈቱ ለመጠየቅ ሲያካሂዱ የነበረውን ሰልፍ ለመበተን ነጭ ለባሽ ፖሊሶች በፈጠሩት ግርግር አንድ ተማሪ በጥይት ተመቶ ወዲያውኑ የሞተ መሆኑ ለማወቅ ተችሏል። ረቡዕ ማታ የገዥው ፓርቲ ቃል አቀባይ ተማሪው ከዩኒቨርስቲው ቅጥር ግቢ ውጭ በሽጉጥ ተመቶ መሞቱን አምኗል። የሟቹን ተማሪ አስከሬን በርካታ ተማሪዎች ተሸክመው ወደ መኖሪያው አካባቢ በመውሰድ እንዲቀበር ያደረጉ ሲሆን በርካታ ተማሪዎች ተማሪ መግደል አገርን እንደመግደል ይቆጠራል ብለዋል። የዩኒቨርስቲው አስተዳደር የተማሪውን መገደል አውግዞ ዩኒቨርስቲው ላልተወሰነ ጊዜ የዘጋ መሆኑን ገልጿል። የካርቱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በየጊዜው ከጸጥታ ኃይሎች ከፍተኛ ጉዳት ቢደርስባችውም አገዛዙን በመቃወም ተደጋጋሚ የተቃውሞ ሰልፎች ሲያደርጉ መቆየታቸው  ይታወቃል።

 

Ø በሊቢያ የተባበሩት መንግስታት ተልእኮ መሪ በሰጡት መግለጫ የአይሲስ አሸባሪዎች በየጊዜው በአገሪቱ የነድጅ ማውጫ አካባቢዎች ላይ የሚፈጽሙት ጥቃት ከፍተኛ ስጋት የፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል። የአሸባሪዎቹ ጥቃት የነዳጅ ምርቱን የሚያስተጓግለው መሆኑን የተናገሩ ሲሆን ጥቃቱም የአገሪቱን ኢኮኖሚና በነዳጅ ምርቱ ገቢ በሚተዳደሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የሊቢያ ዜጎችን የኖሮ ሁኔታ ይጎዳል በማለት ኃላፊው ተናግረዋል።

Ø በተያይዘ ዜና የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ከሊቢያ የአማጽያን አካባቢ ህገ ወጥ በሆነ መንገድ ነዳጅ ጭኖ መንቀሳቀሱ በተደረሰበት በአንድ በህንድ የተመዘገበ የጭነት መርከብ ላይ ማዕቀብ እንዲደርግ የወሰነ መሆኑ ታወቀ። ከሁለት ዓመት በፊት የጸጥታው ምክር ቤት በሊቢያ አማጽያን ቁጥጥር ስር ካሉ የነዳጅ ማምራቻ ቦታዎች ነዳጅ እንዳይጫን መከልከሉ የሚታወስ ሲሆን ይህንን  ህግ በመተላለፍ ነዳጅ ጭኖ ወደ ማልታ አቅንቷል የተባለው የጭነት መርከብ ማዕቀብ የተጣለበትና ጉዞው የቅርብ እየተደረገበት መሆኑ ተነግሯል። መርከቡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለማይታወቅ ሰው የተሸጠ ሲሆን ስሙም የተቀየረ መሆኑ ተነግሯል።

አላሙዲ በ”ናይጄሪያዊው ቢኒየነር ግፊት”ለመጀመሪያ ጊዜ አረጋውያንን እና የአእምሮ ህሙማንን ረዱ

$
0
0

Mohammed-Al-Amoudi-Net-Worth

Aliko-Dangote_Forbes

(ዘ-ሐበሻ) “ከታዋቂ ሰው በስተቀር ድሆችን አይረዱም” እየተባሉ የሚተቹት ሼህ መሀመድ አላሙዲ ናይጄሪያዊው ቢሊየነር አሊኮ ዳንጎቴ ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት ማድረግ ከጀመረና በርካታ አርቲስቶችና ታዋቂ ሰዎች ትኩረታቸውን ወደዚሁ ናይጄሪያዊ ካደረጉ ወዲህ ሼሁ ለመጀመሪያ ጊዜ መቄዶኒያ የአረጋውያን እና የአ እምሮ መርጃ ድርጅት 16 ሚሊዮን ብር ረዱ::

ናይጄሪያዊው ቢሊየነር ኢትዮጵያ ውስጥ ከገቡ በኋላ ወትሮ ከሼህ አላሙዲ ስር የማይጠፉ ታዋቂ ሰዎች ወደ ናይጄሪያዊው በማዞር ላይ እንደሚገኙ በተለያዩ ሚድያዎች ከዚህ ቀደም መገለጹ አይዘነጋም:: ናይጄሪያዊው ቢሊየነር ለተለያዩ አርቲስቶች የሥራ እድል ከመፍጠሩም በላይ ብዙዎችን እየረዳ ሲሆን በዚህ እልህ ውስጥ የተጋቡት አላሙዲ ፊታቸውን አዞረው ለመጀመሪያ ጊዜ አረጋውያንን እና የ አእምሮ ሕሙማንን ለመርዳት ወስነዋል::

አላሙዲ ባለፈው ዓመት በአይሲስ ለተገደሉት ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች እርዳታ ሲለመን እንዳልሰሙ ፊታቸውን ማዞራቸው በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ሲያስተቻቸው ቆይቷል:: ሼሁ ታዋቂ ሰዎችን ብቻ የሚረዱት የራሳቸውን ስም ለማስጠራትና በዛም ለመኮፈስ ነው እየተባሉ ይተቹ ነበር:: ሆኖም ግን የትንሣኤን በዓል በማስመልከት ናይጄሪያዊው ዳንጎቴ እያደረገው ባለው ተግባር ግፊትም ቢሆን 16 ሚሊዮን ብሩን መርዳታቸው አስመስግኗቸዋል:: እንደ አላሙዲ የቅርብ ምንጮች ገለጻ ሼሁ በአሁኑ ወቅት ከናይጄሪያዊው ቢሊየነር ጋር ፉክክር ውስጥ ገብተዋል:: ከ

ሜቄዶኒያ የአረጋውያን መርጃ ከዚህ በፊት በርካታ ሰዎች እርዳታ እንደሚያደርጉለት ቃል የገቡለት ቢሆንም ቃል የገቡትን ሳይፈጽሙ መቅረታቸው ይታወሳል::

የአለም ሃብታሞችን ደረጃ በየዓመቱ በሚያወጣው ፎርብስ መጽሄት ዘገባ መሰረት ናይጄሪያዊው አሊኮ ዳንጎቴ በ$16.7 ቢሊዮን ብር የዓለማችን 51ኛ ሃብታም ሲሆን የሳዑዲ ዜጋው መሀመድ አላሙዲ በ$10 ቢሊዮን ዶላር የዓለማችን 64ኛው ሃብታም ናቸው::

ዛሬ በጅጅጋ ከተማ በተከሰተ ጎርፍ የ7 ዓመት ህፃን ልጅ ሕይወት አለፈ –በሐረርም ሰው ሞቷል

$
0
0

13062142_1064834310245396_4639533248745514020_n 13125003_1064834313578729_7173675934945325962_n

(ዘ-ሐበሻ) ሐረርና ጅጅጋ ዛሬ በጣለ ከባድ ዝናብ የተነሳ በተከሰተ አደገኛ ጎርፍ በንብረት ላይ ጉዳት ሲያደርስ የ2 ሰዎች ሕይወት ማለፉን መንግስታዊ ሚዲያዎች የከተማዋን ፖሊስ ጠቅሰው ዘገቡ::

በመንግስት ቁጥጥር ሥር ያሉ ሚዲያዎች እንደዘገቡት በሐረር በጣከ ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ ሰው የአንድ ሰው ሕይወት ሲያልፍ በጅጅጋ ከተማ በደረሰው ጎርፍ ደግሞ የ7 ዓመት ልጅ ሕይወት አልፏል:: በንብረት ላይም ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ተሰምቷል::

በሐረርና በጅጅጋ በተደጋጋሚ የጎርፍ አደጋ እንደሚከሰት ይታወቃል::

የአማራ ህዝብ በጸጸት የሚተርከው የቅኝ ገዥነት ንስሃ የለውም!

$
0
0

amhara

ፕሮፌሰር ባዬ ይማም

ለአፍታ ያክል ቆም ብለን እጅግ ከመዘውተሩ የተነሳ እየቸከ የመጣውን “የአማራ የበላይነት” ሐተታ ቅቡልነት በታሪካዊ ሃቆች ማንጸሪያነት ስንመርምር፤ አስቀድሞ የበላዮቹ አማሮች እነማን ናቸው? በዚህ ቡድን ውስጥ አባልነት እንዴት ይገለጣል? የአማራ ባህል ምንድነው? ባህል ሌሎች ቅሬታዎችንና በደሎችን መሸፈኛ ትዕምርት ቃል ነውን? ወይንስ ባህል አንድ ህዝብ በሌላው ላይ የበላይ መሆኑን የሚያመላክት ቃል ነውን? በደቡብ የግዛት መስፋፋት ስለተደረገባቸው አካባቢዎች በጅምላ እንደሚነገረው በስልጣን ላይ የነበረው ሰው ሁሉ አማራ ነው ብሎ ማስረገጥና ማረጋገጥ ይቻላልን? የሚሉ መሰረታዊ ጥያቄዎች በአእምሮአችን ያጭራሉ፡፡ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት መጣጣርም ስለአማራ ትክክለኛውን ታሪካዊ እውነት ለመግለጥና ለመረዳት ያግዛል፡፡

 

ብዙ ጊዜ “የምኒልክ ታሪካዊ ድራማ መሪ ተዋንያንና ተጠቃሚዎች በዋነኛነት አማሮች” እንደሆኑ ይነገራል፡፡ ይህ አገላለጽ በእርግጥ ብዙሃኑ አማራ በጥቂቱ እንኳን ቢሆን ስማቸው የተለጠፈበት የፖለቲካ፣ የማህበራዊና የኢኮኖሚ ስርዓት ተጠቃሚዎች ናቸው ማለት ይሆንን? በዚህ አውድ ውስጥስ አማራ በትክክል ማንን ያመለክታል? ጎጃሜዎችን፣ ጎንደሬዎችን፣ ወሎየዎችን ወይስ የሸዋን ሰዎች?

 

የአማራ መንግስት በሚሉት ስርዓት ውስጥ ሸዌ አማሮች አቢይ ተጠቃሚዎች ተደርገው እንደሚታዩ የብሄረተኞችን ጽሁፎች ያገላበጠ አንባቢ ሁሉ አያጣውም፡፡ ይህ ሲባልስ ብዙሃኑ የሸዋ አማራ የጥቅመ ብዙው ገዥ መደብ አባል ነው ማለት ይሆንን? በየትኛውም መንገድ አልነበረም፡፡

 

ሌላው ቀርቶ በአብዛኛው የመንግስት አመራር መዋቅር ተሹመው፣ አብዛኛውን የኢኮኖሚ ምንጮች ተቆጣጥረው፣ ብዙውን የአገሪቱን የግዛት ክልሎች ይገዙ የነበሩ፣ በደቡብ አውራጃዎች ሰፋፊ ሁዳዶች የነበሯቸውና ለኢኮኖሚ እንቅስቃሴያቸው አዲስ አበባን ማዕከል አድርገው የመሰረቱ ነበሩ ተብሎ ቢታሰብ እንኳ የሸዋ መኳንንቶች ከአማራ ህዝብ እጅግ በጣም ጥቂቱን እጅ (አንድ መቶኛ) እንኳን የሚሸፍኑ አልነበሩም፡፡

 

በተቃራኒው ብዙሃኑ የሸዋ አማራ በድህነት የሚኖር ስልጣን አልባና እንደማንኛውም ቡድን በስርዓቱ የተመዘበረ ነበር፡፡ እንዲያውም “የሸዋ አማራ” በአንዳንድ ሁኔታዎች በደቡባዊው የሃገሪቱ ክፍል “ተጨቋኝ ከነበሩት ህዝቦች” እጅግ የከፋ ህይወት ይመራ እንደነበር የታሪክ ሰነዶች ያስረዳሉ፡፡

 

እንቆቅልሽ የሚሆነው ከችግርና ከዘራፊዎች ጋር እየተናነቁ ህይወታቸውን ባቆዩ ስለምን ጎጃም፣ ጎንደር፣ ሸዋና ወሎ ቅኝ ገዥዎችና ጨቋኞች ተደርገው በጅምላ ተፈረጁ ነው፡፡ ይልቁንም እጅግ በርካታ የሆነውን የአማራ አርሶ አደር ቅኝ ገዥ አድርገው የሚያቀርቡት ይዞታችንን አጥተናል ከሚሉ ብሄረተኞች ርካሽ ወዳጅነትን ለመሸመት የሚሹ ፀረ አማራ አቋም ያላቸው ጸሃፊዎች ናቸው፡፡

 

አማራ ሌሎች ህዝቦችን ቅኝ ገዝቷል የሚል የሃሰት አሉባልታቸውን ቢያናፍሱም የስርዓቱ ተጠቃሚ አድርገው በሚከሱትና በሚወቅሱት አብዛኛው የአማራ አርሶ አደር ቀዬ የሚታየው ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ እውነታ ፍጹም የተለየ ነው፡፡ በአካባቢው የተካሄደው የግምገማ ሪፖርትም እንደሚያመለክተው የገጠር ልማትን በተመለከተ የተሻለ እድገት አይታይም፡፡ ለምሳሌ በአማራ አካባቢ በሸዋ መንዝና ግሼ፣ ተጉለትና ቡልጋ እና መርሃቤቴ በትምህርት፣ በመንገድ ልማት፣ በጤና ማዕከላት ወዘተ ከሌላው የኢትዮጵያ ክፍል በባሰ እጅግ ኋላ ቀር ናቸው፡፡

 

የአማራ ቅኝ ገዥነት ፅንሥ ሀሳብ አቀንቃኞች ደጋግመው ወደሚያናፍሱት “የአማራ የባህል የበላይነት ወይም ጭቆና” ትኩረታችንን ስናዞርም እውነታው የተለየ መልክ አይኖረውም፡፡ “የባህል የበላይነት” የሚለው አገላለጽ ለመሆኑ በተለይ የባህሉ “አስፋፊዎች” ራሳቸው የህዝቦችና የባህሎች ውህደት ውጤት በሆኑበት ሁኔታ ከሌሎች ያልተቀየጠ የአንድ ነገድ ባህል ሊባል የሚችል ንጹህ ባህል አለን? የሚል ጥያቄ ያስነሳል፡፡ የአማራ ባህልስ ለሌሎች ግንኙነትና ልውውጥ ላደረገባቸው ባህሎች መጥፋትና መዋጥ ስጋት ሆነዋልን? ይህ ሁኔታስ በደቡብ ባሉት ልዩ ልዩ ባህሎች ላይ ተንጸባርቋልን? ለመሆኑ የሌሎች ባህሎች ተጽዕኖ የማይጋባበት ምንም ሳይለወጥ በነባር መልኩና ይዞታው ሊኖር የሚችል ባህልስ አለን?

 

አስመሮም ለገሰ “የባህል ልውውጥ ሂደት አንድ ገጽታና መልክ ያለው ስዕል ተደርጎ አይታይም፣ ለምሳሌ የአፋን ኦሮሞ ተናጋሪዎች አማራ ሆኑ ብሎ ከማጠቃለል፣ ይልቁንስ ሁኔታው ውስብስብና አያሌ የባህል ቅርጾች በሚያደርጉት የእርስ በእርስ መስተጋብር ውስጥ ፍጹም አዲስ ባህል የሚወለድበት ሂደት ነው” በማለት ይገልጻል ፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታም፣ ክላፓም “የአማራ ባህል የነገደ-ብዙ ባህል እምብርት ነው” ማለቱም በረጅሙ የአገር-ብሄር ምስረታ ሂደት በህዝቦችና በባህሎች መካከል በተደረጉ የሃሳብ፣ የልምዶች፣ የሸቀጦች ወዘተ ልውውጥ ሂደትና አብሮ መኖር ውስጥ የተፈጠረውን የባህሎች መዛነቅ መግለጹ ነው፡፡

 

ከእነዚህ ሁኔታዎች ስንነሳም ‹‹የአማራ የበላይነት›› የሚለው አተያይ በታሪክ እውነታና ሃቅ ያልተመሰረተ ምናባዊ ልቦለድና የፈጠራ ተረታ ተረት መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ ይህ ተረት አንድም አፍራሽ በሆነ መንገድ የኢትዮጵያን ታሪክ በአውሮፓ ታሪክ መነጽር ለመመልከት ከመጣጣር፣ ያለበለዚያም ይሁነኝ ብሎ የታሪክ ሃቆችን በመበረዝና በተሳሳተ መንገድ በመተርጎም የፖለቲካ አጀንዳን ከግብ ለማድረስ ከሚደረግ ጥረት የመነጨ ነው፡፡

 

እውነቱ መገለጽ ካለበት ደግሞ የአማራ ማህበረሰብ በቅኝ ግዛት ፅንሥ ሀሳብ አቀንቃኞችና በጀሌዎቻቸው ከተለጠፈበት መጥፎ ገጽታ በተጻራሪ ጠንካራ ሰራተኛ፣ ሰላም ወዳድ፣ ተባባሪና ታጋሽ ህብረተሰብ ነው፡፡ ቅኝ ገዥ ሆኖም አያውቅም፣ የበደላቸው ወገኖች ስለሌለም በጸጸት የሚተርከው የቅኝ ገዥነት ንስሃ የለውም፡፡

 

ስለዚህም የአማራ ህዝብ ያልስራው እና በውሸት የተቀባው የታሪክ ጥላሸት ሊነጻ፣ ያለ ግብሩ የተጫነበት የገዥነት አመል አለው የሚል ውግዘት ሊረሳና ሊቆም፣ በምትኩም በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ያለው ትክክለኛ ቦታና ያበረከታቸው ታላላቅ ተግባራት ሊነገሩለት ይገባል፡፡

ዓቃቤ ሕግ በአቶ ኤርሚያስ አመልጋ ዋስትና ላይ ያቀረበው ይግባኝ ውድቅ ተደረገ

$
0
0
ኤርሚያስ አመልጋ

ኤርሚያስ አመልጋ

የሚያዙበት በቂ ገንዘብ ሳይኖራቸው ቼክ የማውጣት (የመጻፍ) ወንጀል የቀረበባቸው ክስ ዋስትና እንደማያስከለክል ተገልጾ፣ የተፈቀደላቸውን የ600 ሺሕ ብር ዋስትና በመቃወም የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ያቀረበው የይግባኝ አቤቱታ፣ ማክሰኞ ሚያዝያ 18 ቀን 2008 ዓ.ም. ውድቅ ተደረገ፡፡
የሥር ፍርድ ቤት ማለትም የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ወንጀል ችሎት መጋቢት 11 ቀን 2008 ዓ.ም. ተጽፎ በቀረበለት የአክሰስ ሪል ስቴት መሥራችና የቦርድ አባል አቶ ኤርሚያስ ላይ የተመሠረተውን ክስ ተመልክቶ፣ መጋቢት 23 ቀን 2008 ዓ.ም. ውሳኔ መስጠቱ ይታወሳል፡፡ ፍርድ ቤቱ በተከሳሹ ላይ የቀረቡትን የሚያዙበት በቂ ገንዘብ ሳይኖራቸው ቼክ የማውጣት (የመጻፍ) ወንጀል መርምሮ ነው ውሳኔ የሰጠው፡፡ ለስድስት ሰዎች የጻፉት ደረቅ ቼክ የገንዘብ መጠን በድምሩ 4.8 ሚሊዮን ብር መሆኑን ጠቁሟል፡፡ አቶ ኤርሚያስ በኩባንያው ስም ከተሰበሰበ ገንዘብ ላይ ለስድስት ሰዎች የጻፉት የገንዘብ መጠን ያን ያህል የሚባል አለመሆኑን አብራርቷል፡፡
በመሆኑም ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ የወንጀል መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 67(ሀ)ን ጠቅሶ ማለትም፣ ‹‹በዋስትናው ወረቀት የተመለከቱትን ግዴታዎች አመልካቹ የሚፈጽም የማይመስል የሆነ እንደሆነ ዋስትና ይከለከላል፤›› በሚለው ድንጋጌ መነሻነት ተከሳሹ ወደፊት ጥፋተኛ ቢባሉ፣ በእያንዳንዱ ክስ የሚጣልባቸው ቅጣት ሲደመር ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችልና ዋስትና ቢፈቀድላቸው ሊጠፉ እንደሚችሉ በማስረዳት፣ የዋስትና መብታቸው እንዲታለፍ ያቀረበውን ክርክር የሥር ፍርድ ቤቱ አልፎታል፡፡ ፍርድ ቤቱ የዓቃቤ ሕግን ጥያቄ ያለፈበትን ምክንያት እንዳብራራው ዓቃቤ ሕግ ያቀረበው መከራከሪያ ሐሳብ በቂ፣ ጠንካራና አሳማኝ ምክንያቶችን አላቀረበም፡፡ በመሆኑም ዋስትና የማግኘት ግዙፍ የሆነው ሕገ መንግሥታዊ መብታቸው መከበር እንዳለበት በውሳኔው አስረድቷል፡፡ አቶ ኤርሚያስ በ600 ሺሕ ብር ዋስትና እንዲለቀቁና ከአገር እንዳይወጡ ለኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ እንዲጻፍ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር፡፡
ነገር ግን ዓቃቤ ሕግ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመቃወም ተመሳሳይ ሥጋቱን በመግለጽ፣ ውሳኔው ውድቅ ተደርጐ አቶ ኤርሚያስ በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከራከሩ አመልክቶ ነበር፡፡
ዳኛ ዳኜ መላኩ፣ ዳኛ ገበየሁ ወርቁና ዳኛ ከድር አልይ የተሰየሙበት ይግባኝ ሰሚው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሚያዝያ 18 ቀን 2008 ዓ.ም. በሰጠው ብይን ክሱ የቼክ ጉዳይ መሆኑን፣ ገንዘቡም 4.8 ሚሊዮን ብር እንደሆነ ከሥር ፍርድ ቤት የውሳኔ መዝገብና ከዓቃቤ ሕግ የመቃወሚያ አቤቱታ ሰነድ መረዳቱን ገልጿል፡፡ በመሆኑም የተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ዋስትና እንደማያስከለክል ገልጾ፣ ዓቃቤ ሕግ ግን የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ ውድቅ እንዲደረግለት በወንጀል መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 67(ሀ) መሠረት ሥጋቱን በማሳወቅ የተከራከረ ቢሆንም፣ የሥር ፍርድ ቤት እንዳልተቀበለው በመግለጽና ይግባኝ ሰሚው ችሎት ውሳኔውን ውድቅ እንዲያደርግለት መሆኑን አስታውሷል፡፡
ችሎቱ የዓቃቤ ሕግን አቤቱታና የተጠርጣሪውን ጠበቆች መልስ ሲመረምር የዓቃቤ ሕግ ሥጋት በበቂና በጠንካራ ምክንያቶች የተደገፈ አለመሆኑን በመግለጽ፣ የሥር ፍርድ ቤት በ600 ሺሕ ብር ዋስትና ተጠርጣሪው እንዲለቀቁና ከአገር እንዳይወጡ የሰጠው ትዕዛዝ የሚነቀፍ ሆኖ እንዳላገኘው በማስታወቅ የይግባኝ አቤቱታውን እንዳልተቀበለው አስረድቷል፡፡
ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የይግባኝ አቤቱታውን እንዳልተቀበለው የገለጸው ጠዋት 4፡30 ሰዓት አካባቢ በመሆኑ፣ ማስፈቻ አስጽፈው ለማስፈታት የተሰጠውን ብይን በመያዝ ወደ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የሄዱት የአቶ ኤርሚያስ ቤተሰቦች ግን እንዳሰቡት እንዳልተሳካላቸው ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ብይን ግልባጭ የደረሰው የሥር ፍርድ ቤት ቀደም ብሎ አቶ ኤርሚያስ በዋስ እንዲለቀቁ ማዘዙን ገልጾ፣ አሁን የሚጽፈው የማስለቀቂያ ወረቀት ሳይሆን ፖሊስ እስካሁን ለምን እንዳለቀቃቸው ማብራሪያ እንዲሰጠው መሆኑን እንደነገራቸው ገልጸዋል፡፡ ይግባኝ ሰሚው ችሎት የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔን ካፀደቀ እንዲፈቱም መጻፍ ያለበት እሱ መሆኑን የተረዱት ቤተሰቦቻቸው ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የተመለሱ ቢሆንም፣ ‹‹ዳኞች የሉም ነገ (ዛሬ) ተመለሱ›› በመባላቸው መመለሳቸውንና አቶ ኤርሚያስም በዕለቱ አለመፈታታቸውን ገልጸዋል፡፡
የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ስለሰጠው ብይን የተሰማቸውን የተጠየቁት የአቶ ኤርሚያስ ጠበቃ አቶ ሞላ ዘገዬ፣ ‹‹ሕግ አሸነፈ፤›› በማለት አጭር ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ምንጭ – ሪፖርተር


የኛ ሐዋርያት …በቀራንዮ መንገድ ላይ! –ዳዊት ከበደ ወየሳ (አትላንታ –አሜሪካ)

$
0
0

(በኢትዮጵያ በሚታተመው “አዲስ ገጽ” ቁጥር 10 ላይ ታትሞ የወጣ።)

ነብዩ መሃመድን ጨምሮ ሌሎች ነብያት ህዝባቸው ሃጥያት መስራት እንዲያቆም፣ መንግስት ግፍ መስራት እንዲተው ምክር ሰጥተዋል፤ ክርክር ገጥመዋል።  ክርስቶስም የሰውን ልጅ ሃጢያት በደሙ ሊያስተሰርይ በመስቀሉ ላይ ደሙን አፍስሷል፤ ስሙን አንግሷል። የኛም ክርስቶሶች የእስር ዋጋ እየተቀበሉ፤ በደማቸው አክፋይ የመስዋዕትነትን ዋጋ እየከፈሉ… ትላንት በታሪክ ነበሩ፤ ዛሬም በኛ ዘመን አሉ። የኛ ጋዜጠኞች የመሰቀያቸውን ግማድ ተሸክመው፤ እንደክርስቶስ ጉዟቸውን በቀራንዮ መንገድ ላይ አድርገዋል። ከ’ነሱም ጋር በሺዎች የሚቆጠሩ ትውልድ ብጹዓን የሚላቸው፣ ኢትዮጵያዊ ሐዋርያት አሉን። እነሆ ወደቀራንዮ የሚደረገው ጉዞ ተጀመረ እንጂ፤ አልተገባደደም። አብረን እንጓዝ።

Tensaye አቶ መለስ ዜናዊ ከመሞታቸው በፊት፤ ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትም በፊት፤ በሽግግር መንግስቱ ሰሞን… ከሓዳስ ኤርትራ ጋዜጠኛ ጋር አንድ ቃለ ምልልስ አድርገው ነበር። በዚህ ቃለ ምልልስ ላይ ጋዜጠኛው እንዲህ ሲል ጥያቄ አቀረበ፤ “እርስዎ የኢትዮጵያ መሪ ባይሆኑ ኖሮ፤ ምን ይሆኑ ነበር?” አላቸው።

አቶ መለስም… “መሪ ባልሆን ኖሮ፤ ጋዜጠኛ እሆን ነበር” የሚል ፈጣን ምላሽ ሰጡ።

እንግዲህ ይህ የጋዜጠኝነት ሙያ፤ መሪዎች ጭምር ወደፊት ይሆኑ ዘንድ የሚመኙት የነበረና የተከበረ ሙያ ነው። የተከበረ የሚያደርገው ደግሞ፤ ጋዜጠኛው ለጥቂቶች ሳይሆን ለብዙሃኑ እና ለተገፉት አንደበት ሆኖ ድምጻቸውን ስለሚያሰማላቸው ነው። እንዲህ አንገታቸውን ቀና አድርገው እውነትን የተናገሩና የመሰከሩ ጋዜጠኞች፤ እንደሻማ እየቀለጡ እና እንደብረት እየተቀጠቀጡ፤ ከአላማቸው ፍንክች ሳይሉ ሞትን ለመቀበል መዘጋጀታቸውን ስናይ… ሰማዕትነታቸው ያስቀናናል፤ መስዋዕትነታቸው ያኮራናል። እነዚህ ኩሩ ኢትዮጵያውያን እንደክርስቶስ በሃሰት ተመስክሮባቸው፤ የክብር ጌጣቸውን ተሸክመው በቀራንዮ አቀበት ላይ ናቸው። እነሆ ከስቃያቸው ስቃይ ከፍለን ሸክማቸውን ባንሸከምም፤ ዛሬ እነሱን እናስታውሳለን፤ እንዘክራቸዋለንም።

በአንድ ወቅት ለጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ወደ አውሮጳ የሚወጣበት አጋጣሚ ተፈጠረና ደውዬ እንዳናግረው ተደረኩ። ተመስገን ስለመልካሙ ሃሳባችን አመስግኖ፤ ነገር ግን ወደውጭ ወጥቶ የመቅረትም ሆነ ቀሪ ዘመኑን በስደት ለማሳለፍ ፍላጎት እንደሌለው በትህትና ገለጸልኝ። እስክንድር ነጋም ቢሆን በአሜሪካ የነዋሪነት ፈቃድ የነበረው፤ ቀሪ ኑሮውንም በአሜሪካ ማድረግ የሚችል ሰው ነበር። ነገር ግን በአገሩ ላይ መስዋዕት መክፈልን መረጠ። ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬም ቢሆን፤ በብዕሩ መንግስትን እንጂ ህዝብን እንዳላሸበረ ከሳሾቹ ጠንቅቀው ያውቃሉ። ሆኖም ጉዳዩ የፖለቲካ ውሳኔ ሆነና በክርስቶስ ስም ምለው የሚገዘቱት ጠቅላይ ሚንስትራችን ጭምር፤ “አሸባሪዎች!” ብለው የማይፈነክት ድንጋይ ወረወሩባቸው።

“እኔ የተሻልኩ ነኝ” የሚሉ ሰዎች መሻላቸውን ማሳየት ያለባቸው ፍርደ ገምድል በመሆን ሳይሆን፤ ተሽለው በመገኘት ነው። ንጹህ ዜጋን በጉልበት ወህኒ አስገብቶ መክሰሱና ፍርድ መስጠቱ፤ ለባለግዜዎች ቀላል የመሆኑን ያህል ወደፊት በታሪክ ፊት መዳኘት ራሱ ከባድ ፈተና ነው። ለነገሩ ቀዳሚው አለመታወቁ እንጂ፤ ሞትና ወህኒ ቤት ለታጋዮች መታፈሪያቸው እንጂ ማፈሪያቸው አይደለም። ይህ እንዳለ ሆኖ፤ መሪ የተባሉ መሪዎች ግን ቢያንስ፤ ጋዜጠኞችን “አሸባሪዎች ናቸው” ብለው ባይዋሹ በመጨረሻው ሰአት ከመቀሰፍ ይተርፉ ነበር።

ነገሩ አንድ ቀልድ ያስታውሰናል። እንዲህ ነው። አንድ የአገር መሪ፣ ጋዜጠኛ እና ቄስ በአንድ አነስተኛ አውሮፕላን እየሄዱ ሳለ፤ የአውሮፕላኑ ሞተር እየሞተ መጣና ፓይለቱ ፓራሹቱን ታጥቆ እንዲህ አላቸው፤ “አውሮፕላኑ ሊከሰከስ ነው። ያለን ፓራሹት ግን ሁለት ነው። ተስማምታቹህ በመጠቀም፤ በሁለቱ ፓራሹቶች እራሳችሁን አድኑ” ብሎ ዘሎ ወረደ።

በመቀጠል  የአገር መሪው፤ “ይህ የአሸባሪዎች ድርጊት መሆኑን ደርሰንበታል።” ብሎ በችኮላ አነስተኛ ሻንጣውን በጀርባው አዘለ። ከዚያም “ለማንኛውም እኔ የአገር መሪ ስለሆንኩ፤ ከናንተ ይልቅ ለህዝቡ አስፈልገዋለሁ” አላቸውና ተንደርድሮ ወደ ታች ተምዘገዘገ።

ከዚያ ቄሱ ለጋዜጠኛው እንዲህ አሉት። “እኔ ብዙ አመት ኖሬያለሁ። አንተ ግን ገና ብዙ ስለምትኖር፤ አገርህንም ወደፊት ስለምታገለግል የቀረውን አንድ ፓራሹት ተጠቀምበት” አሉት።

ጋዜጠኛውም ለቄሱ መለሰላቸው፤ “አያስቡ አባ።” አለ… “አያስቡ አባታችን። ሰውየው ፓራሹቱን ሳይሆን፤ ሻንጣውን በጀርባው ተሸክሞ ነው የወረደው።” አለና አንዱን ለራሱ ወስዶ፤ ሁለተኛውን ፓራሹት ለቄሱ ሰጣቸው።

ዘር እና ጥላቻን መሰረት ያደረገው ፖለቲካ… አገራችን በአንድ ሞተር ብቻ እንደምትበር አውሮፕላን እያስመሰላት መጥቷል። ይህ የዘር እና የቂም ፖለቲካ እየጠነከረ ሲመጣ መሪዎች ያለ ፓራሹት ከላይ ወርደው ይፈጠፈጣሉ። በአደጋው ግዜ የዳኑት ድነው፤ “አውቀናል” በሚል የዘር እና የጥላቻ ፖለቲካ ልባቸውን ያደከሙ ሰዎች፤ እንደዱባ ቁልቁል ወርደው ሲፈጠፈጡ ለመታዘብ በቅተናል። እኛ ግን ከነሱ ይልቅ የጋዜጠኞቻችን ጉዳይ፤ ብሎም ከዚያ ጀርባ ያለው የሃሰት ፕሮፓጋንዳና የፍትህ ሽል ውርጃ ያሳስበናል።

ዛሬ በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች፤ ስለኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት ስለመሰከሩ፤ ሃሳባቸውን በነጻነት ስለገለጹ ክብር እና ምስጋና ሲገባቸው፤ እስር እና እንግልት ኒሻናቸው ሆኖ ወህኒ ተወርውረዋል። ህዝቡ “ጀግና” በሚል ክብር ሲጠራቸው፤ ገዢዎች ደግሞ “አሸባሪ” የሚል ቅጽል ሰጥተዋቸዋል። ሌባ ፖሊስን እንደሚጠላ ሁሉ… እራሳቸውን ለገዢው አካል ተገዢ ያደረጉ ግለሰቦች ለጋዜጠኞቻችን ያላቸው ጥላቻ እና የጠላትነት መንፈስ መስመሩን የለቀቀ ነው። ይህ አስተሳሰብ ሊቀየር ይገባል። ለዚህ ደግሞ እንዲህ አይነት የተዛባ እና የተሳሳተ አመለካከት የሚፈጥረውን ግዙፍ አካል ማስተካከል የግድ ይላል።

እንደእውነቱ ከሆነ…  ከወንድሞቻችን መታሰር ባልተናነሰ ሁኔታ፤ ከዚህ ጀርባ ያለው ግዙፍ የቅጥፈት ፋብሪካ ያስፈራናል። ይህ የቅጥፈት ፋብሪካ ከግዜ ወደ ግዜ ራሱን እያሳደገና እየሰፋ በመምጣት ላይ ነው። ይህ ግዙፍ የመንግስት አካል ህግን እሱ በሚፈልገው መንገድ ወይም ለሱ በሚመቸው መንገድ አጣሞ ይጠቀምበታል። የራሱ የሆነ አፋኝ የደህንነት ቡድን፣ በህግ ስም አንቀጽ ጠቅሶ የሚከስ እና የሚዳኝ፣ በእስር ወቅት ተቃዋሚ የነበረ እስረኛን የሚያሰቃይ ልዩ ሃይል አለው። ጋዜጠኛ ውብሸት በጓደኞቹ እንዳይጠየቅ፤ ተመስገን ደሳለኝ ከነጀርባ ህመሙ እንዲሰቃይ፤ እስክንድር ነጋን ሰው እንዳያየው የሚያደርግ ጨካኝ የሰዎች ስብስብ አላቸው። የጋዜጠኛ እስክንድርን እናት ሃብት ወስደው፤ የሱን ንብረት እና ቤት በዳኛ ውሳኔ አስፈርደው ወርሰውበት፤ እስር ቤት ውስጥ ያለውን መጽሃፍት፣ በርጩማ እና ሌላ ቁሳቁስ… ጥርስ ብሩሽ እና ሳሙና ሳይቀር ቀምተው… ይሄ ሁሉ አልበቃ ብሏቸው በእጁ ላይ የነበረውን የመጨረሻ ሃብት መጽሃፍ ቅዱሱን ወስደውበት… የ’ስር ቤቱ ንብረት የሆነ አንድ አሮጌ ባልዲ ትተውለት፤ ይቺኑ ባልዲ እንደወንበርም እንደጠረጴዛም እንደመተከዣም ሲጠቀምባት ሲያዩ ደስ የሚላቸው ጨካኝ ሰዎችን ነው በየወህኒ ቤቱ ጭምር እያፈሩልን ያሉት። ሌላው ቀርቶ እነዚህን በአሸባሪነት ስም የታሰሩ ሰዎች እስረኛው ሲያናግራቸው ከተገኘ ከፍተኛ ቅጣት ስለሚደርስበት፤ ደፍሮና ቀርቦ የሚያናግራቸው እንዳይኖር ጭምር አድርገዋቸዋል። ይሄ ሁሉ የሚሆነው ጨቋኙንና ጨካኙን ደርግ ጨርሼዋለሁ ብለው በሚፎክሩ እንደሰው በተፈጠሩ ‘ሰዎች’ መሆኑን ልብ በሉ።

ይሄም ሁሉ ሆኖ ከዚህ ጀርባ ሌላ የሚያናድድ አመል አላቸው። ይዋሻሉ። አሁን ከላይ የተዘረዘረው ነገር ለጠቅላይ ሚንስትሩ ጭምር ቢነገራቸው፤ እውነት መሆኑን እያወቁት የህሊናቸውን አይን ጨፍነው ሽምጥጥ አድርገው ይክዳሉ። ይሄ ነገራቸው ደግሞ እንደጉንፋን ከአንዱ ወደአንዱ የሚጋባ በሽታ እየሆነ መጥቷል። ከ’ነሱ አልፎ ትውልድ ጭምር በውሸት በሽታ ተለክፎ፤ የማናውቀው የክህደት ባህል እንደአረም ሆኖ እየወረሰን ይገኛል። በየአመቱ ውሸት እና ክህደት እየጨመረ፤ ቅን ልቦና ንጹህ ህሊና ደግሞ እየመነመነ በመምጣት ላይ ነው። በየመንግስት መስሪያ ቤቱ በሃላፊነት የተቀመጡ ሰዎች፤ ከአንድ ምንጭ የተቀዱ እስከሚመስል ድረስ ብዙዎቹ ለሌላው ግድ የለሽና ጨካኝ እየሆኑ ናቸው። ይሄ ሁሉ ከአንዱ ትውልድ ወደሌላኛው እንደውርዴ በውርስ መተላለፍ ከጀመረ ሰነባበተ።

ባለፈው ሰሞን… እኛ ባለንበት አትላንታ ከተማ የትልቁ ፕሮቴስታንት ቤተ ክርስቲያን ሰባኪ፤ ፓስተር ቶሎሳ ጉዲና ምዕመናኑ ፊት ስቅስቅ ብለው አለቀሱ አሉን። “ምነው?” ብንል…

“ኢትዮጵያ ውስጥ ቅንነት እየጠፋ ነው።” ብለው አዝነው አለቀሱ አሉ። እውነት ነው። ነገሩ ያስለቅሳል። ቅን መንግስት ቢኖረን እኮ ህዝቡም ያንን ቅንነት ለመውረስ ቅርብ ይሆን ነበር። እንዳለመታደል ሆኖ ከመሪዎች የሚወረሰው መልካም ነገር እየተሟጠጠ መጥቶ ሸር እና ተንኮላቸው እንደጀብዱ የሚወራበት ዘመን ላይ ደረስን… እውነትም ይሄ ያሳዝናል፤ ያስለቅሳልም።

“ህዝብ መሪውን ይመስላል” እንዲሉ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ከነገሥታቱም ከፕሬዘዳንቱም… ወኔ እና ጭካኔን እየተማረ ዛሬም ድረስ አለ። ጨካኝ ንጉሥ ሲነሳ ህዝቡ ጭካኔን ይማራል፤ ደግ ንጉሥ ሲነግስ ህዝቡም ቅንነትን ይማራል። በዚያኑ ልክ ደግሞ ጥፉ እና ክፉ መንግስት ሲመጣ፤ ትውልድ አለቆቹን እየመሰለ – ሰው ሆኖ በአውሬ ልቦና ውስጥ ሲኖር እናያለን። ጋዜጠኛን “አሸባሪ” ብሎ ከሚከራከር ጠቅላይ ሚንስትር ወይም ሌላ ሚንስትር፤ ይህ ትውልድ ውሸት እንጂ ብዙም ሌላ የሚማረው ነገር አይኖረውም።

አሁን ባለችው ኢትዮጵያ ውስጥ ቋንቋችን እንደባቢሎን ዘመን ተዘበራርቆ፤ እኛ የምንለውን እንዳይሰሙ… እነሱ የሚሉትን እንዳንሰማ ቢደረግም፤ ደግመን ደጋግመን ኢትዮጵያዊነትን ማስተማር ይገባል። ፍቅር በመስጠት መልካም ምሳሌ መሆን ካልቻልን ወደ ቀራንዮ የሚወስደውን አቀበት መንገድ ብቻችንን ችለን አንዘልቀውም። በመተባበር እንጂ በመነጣጠል አናሸንፍም። አንድ ምሳሌ ልጥቀስ።

ኢህአዴግ አዲስ አበባ ሲገባ እድሜያችን በሃያዎቹ ውስጥ የነበርን ልጅ እግር ጋዜጠኞች፤ ዛሬ የእርጅናን ሰፈር ከቅርብ ርቀት ላይ ሆነን በማየት ላይ ነን። በትዝታ ወደኋላ መለስ በማለት ከጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ያሳለፍነውን የልጅነት ዘመን ስመለከት፤ በወጣትነት እድሜ… ለወጣቱ መልካም አርአያ ለመሆን የደከምነው  ግዜ ይበልጥብኛል። ነጻው ፕሬስ ከመስፋፋቱ በፊት፤ ኢህአዴግ አዲስ አበባ እንደገባ… ስለኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ እና ስለህዝቧ  አንድነት መመስከር ያለህግ የሚያሳፍን ወይም የሚያሳስር ነገር ሆኖ ነበር። ሰንደቅ አላማችንና ጀግኖቻችን ተዋርደው አንድነታችን ጥያቄ ውስጥ በገባበት ወቅት እስክንድር ፒያሳ ላይ በኢትዮጵያዊነት ዙሪያ የእግር ኳስ ዋንጫ ውድድር አስጀመረ።

የአካባቢውን ወጣቶች በማሰባሰብ ለቡድኖቹ ስም ሰጣቸው። አንዱን ’ምኒልክ’፣ ሌላውን ‘ቴዎድሮስ’፤ አንደኛውን ሰንደቅ አላማ፣ ሌላኛውን ‘አንድነት’ ብሎ በመሰየም በፒያሳው ሜዳ ላይ የኳስ ግጥሚያ ያካሂድ ጀመር። የምኒልክ ቡድን ሲያሸንፍ ተጫዋቹና ቲፎዞው ወደ አጼ ምኒልክ አደባባይ ሄዶ፤ “ምኒልክ ህያው ነው” እያለ መፈክር ያሰማል። የአንድነት ቡድን ካሸነፈ… “አንድ ነን” እያለ ይዘፍናል። የሰንደቅ አላማ ቡድንም የኢትዮጵያን ባንዲራ ያውለበልባል። በዚህ አይነት ዘዴ ወጣቱ ገና በጠዋቱ ስለኢትዮጵያ አንድነት እንዲነሳ የበኩሉን ያደርግ ነበር። እንዲህ አይነት መልካም ተግባር የሚፈጽመው ጓደኛችን አሁን በእስር ላይ ይገኛል። የእስክንድር እና ሌሎች ጋዜጠኞች መታሰር ሳያንስ፤ ከሌላው ወገን የምንሰማው የሃጢያት አንደበት ግን፤ ዛሬም ሳይታክት… ጋዜጠኞቻችንን “አሸባሪዎች ናቸው” ይለናል። ውሸቱን ከመለማመዳቸው ብዛት ይሄን ሁሉ ሲሉ… ህሊናቸውን አይቀፋቸውም፤ ምላሳቸውንም አያነቅፋቸውም።

“ህዝብ መንግስትን ይመስላል” ስንል ለጉዳዩ ማብራሪያ ሳያስፈልገው፤ እያንዳንዳችን በታሪክ ወደኋላ ተመልሰን የመንግስታት እና የህዝቡን ተወራራሽ ባህሪ ልናጤነው እንችላለን። መሪዎች ወደ አደባባይ ወጥተው የጥፋት ዘር ሲዘሩ፤ “የለም! ይሄ ለኢትዮጵያ አይበጅም” የሚል ወገን እና ፕሬስ ከሌለ፤ ሙሰኞች ህዝቡን እየዘረፉ፣ አምባገነኖች በጠመንጃ እየገዘፉ… ውሸታቸው እየተደጋገመ፤ ሲደጋገም ደሞ ውሸታቸው እውነት እየመሰለን ሊመጣ ይችላል። ከዚያም አልፎ የተሳሳተ እምነታቸው ጭምር በሌላው ላይ ተጽእኖ ማሳደሩ አይቀርም።

“ህዝብ መሪውን ይመስላል” ለሚለው ቃል ሌላ  ማጠናከሪያ ምሳሌ ላክል። በአጼ ምኒልክ ዘመን የሆነ ነገር ነው። አጼ ዮሃንስ ከሞቱ በኋላ… በ1880ዎቹ መጀመሪያ ላይ ኢትዮጵያ ክፉኛ በድርቅ ተጠቃች። የድርቁ ዋና መንስኤ ዝናብ ጠፍቶ ሳይሆን፤ ከብትበበሽታ በማለቁ ነበር። በዚያን ግዜ ህዝቡ ከበሬ በቀር ሌላ የማረሻ መንገድ የለውም። ከገሶ እና ዲጂኖ ውጪ እንደ ዶማ አይነት መኮትኮቻ እምብዛም አያውቅም። እናም ከብቱ ሲያልቅበት… ሞፈር እና ቀንበሩን ሰቅሎ፤ በረሃብ እሳት እየተቆላ አለቀ። በዚህን ግዜ አጼ ምኒልክ የውጭ አገር አማካሪዎችን ሰብስበው፤ “የአገሬ ሰው በሬው ቢያልቅበት፤ በእጁ አፈር እየጫረ መዝራት ጀመረ። እንደው ለመሆኑ እናንተ አገር በሬ ሳይኖር፤ መሬቱን እንዴት ነው የምታለሙት?” አሏቸው።

“ከብረት የሚሰራ መኮትኮቻ አለ” ይሏቸዋል።

አጼ ምኒልክ የተባለውን መኮትኮቻ ዶማ በብዛት ከውጭ አገር አስመጥተው፤ ገሚሱን እንጦጦ ጋራ ላይ እንዲቀመጥ ያስደርጋሉ። በንጋታው ወደ እንጦጦ ተራራ ሲወጡ መኳንንቱ እና መሳፍንቱ፤ ይሄ ‘ከውጭ አገር መጣ’ የተባለውን መኮትኮቻ ለማየት በእግር እና በበቅሎ ግር ብሎ ይከተላቸዋል። አጼ ምኒልክ እንጦጦ ጋራ ላይ ዶማዎቹ ከተቀመጡበት መጋዘን ሲደርሱ፤ ከበቅሏቸው ወርደው አንዱን ዶማ አስመጡና መቆፈር ጀመሩ። በዚህን ግዜ ሌሎቹ ተከታይ መኳንንቶች… “ኧረ አይገባም ጃንሆይ! እናግዝዎ!” በማለት ዶማውን እንዲሰጧቸው ተሽቀዳደሙ።

በዚህን ግዜ አጼ ምኒልክ፤ “ይሄ እኔ የምሰራበት ዶማ ነው። ለናንተ የሚሆናችሁን ዶማ እያመጣቹህ እንደኔ ኮትኩቱ።” አሏቸው። ከዚያም እዚያ የተሰበሰበው መኳንንት በሙሉ እየተሽቀዳደመ አንዳንድ ዶማ እያነሳ እንጦጦ ጋራን በዶማ አረሱት። በመጨረሻም የባህርዛፍ ፍሬ ተከሉና ሁሉም አንዳንድ ዶማ ወስዶ እንዲያስተዋውቅ አስገደዱ።

ከእንጦጦ ጋራው የዛፍ ተከላ በኋላ ዶማ በመላው ኢትዮጵያ ቀስ በቀስ ተዋወቀ። በርግጥ ሰነፎች እና አሽሟጧጮች ዛሬም ድረስ፤ “ከእጅ አይሻል ዶማ።” ሲሉ ከሰማቹህ ከእንጦጦ የተረፈ ተረት መሆኑን ልብ ይበሉ። ይሆነ ሆነና አጼ ምኒልክ ዶማን በዚህ መልኩ አስተዋወቁ። እንግዲህ ከመቶ አመት በፊት… እንዲህ በመስራት ምሳሌ መሆን ከተቻለ፤ በሰለጠነው ዘመን ህዝብን በመልካም አስተዳደር እጦት ማመስ እና ማተራመስ እድገት ሳይሆን ውድቀት ነው ሊሆን የሚችል።

የእንጦጦ ጋራ ነገር ከተነሳ አይቀር… እንጦጦ ጋራን ይዘን እስከ ሱሉልታ የሚወስደውን መንገድ ይዞ የሚሄድ ሰው አንድ ነገር ይታዘባል። ከአዲስ አበባ ውጪ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የነበረው መሬት በሙሉ ታጥሯል። ገበሬው እና የአካባቢው ነዋሪ ተነስቶ ቦታው የተከለለው ለልማት ተፈልጎ አይደለም። ወይም ለህዝቡ ጥቅም አይደለም። ይህ በመኪና ሄደው ሄደው የማይጨርሱት ቦታ የታጠረው ለ”መለስ ዜናዊ መታሰቢያ” የምታስቢያ ድርጅቱ ወይም ማዕከሉ የበላይ ሃላፊ ደግሞ ማነው? የሙስና እመቤቷ ወ/ሮ አዜብ መስፍን ናት። እሷና መሬት ሲገናኙ ምን ልታደርገው እንደምትችል፤ አንድ የአራተኛ ክፍል ተማሪ ቢጠየቅ አብራርቶ የሚመልሰው ስለሆነ ዝርዝር ውስጥ መግባት አያስፈልግም። እግረ መንገድዎን ግን ልጆች ጭምር ከዘመኑ መሪዎች ምን እየተማሩ እንደሆነ አስቡት። የመልካም ምሳሌነቱን ነገር እዚህ ላይ እናሳርፈውና ስለፍትህ መጓደል ትንሽ አውግተን እንለያይ።

እንደ እውነቱ ከሆነ… ኢህአዴግ የደርግን ወታደር እንጂ የኢትዮጵያን ህዝብ ልብ አላሸነፈም። ማሸነፍ ያልቻለበት ዋናው ምክንያት ደግሞ ገና ከጅምሩ ከሰንደቅ አላማው ጀምሮ፤ ታሪክን ማዛባት እና የህዝብ እሴቶችን ማናጋት ቀዳሚ አጀንዳው አድርጎ በመንቀሳቀሱ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ለብዙ ሺህ አመታት ይዞት ከቆየው እሴቶቹ መካከል ደግሞ፤ አንደኛው የተስተካከለ ፍርድ ማግኘት ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነበር።

ደሃው “ባይበላ ባይጠጣ ይቅር” ብሎ የተስተካከለ ፍርድ ለማግኘት፤ አገር አቋርጦ ንጉሡ ፊት መሬት ስሞ “አቤት” የሚልበትን ዘመን ባናየውም፤ አባቶች ለዚህ ምስክር ናቸው። የበላይ ሃላፊዎች ሲሾሙ፤ “ፍርድ እንዳታጓድል፤ ደሃ እንዳትበድል።” ተብለው ነው የመንግስት አደራ የሚቀበሉት። ይሄ የድሮ ታሪክ ሊሆን ይችላል። አሁን ያሉትን ባለስልጣናት ካየን በተቃራኒው፤ “ፍርድ አጓድል፣ ደሃን በድል” የተባሉ ይመስል ህዝቡን ሲያምሱት ይውላሉ። አንድ ሃላፊ ጋር ገብተው በአክብሮት መነጋገር አይቻልም፤ ባይጥልዎትም ሊዘረጥጥዎ ይችላል። እድገትን በፎቅ ብዛት ሳይሆን፤ በአተሳሰብ ጥልቀት ከመዘነው ብዙ ተበልጠናል።

በቅርቡ ትልቅ ድርጅት በመንገድ ሰበብ የፈረሰባቸው ዘመዶቻችን፤ “አቤት” ለማለት አዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት በብዙ ደጅ ጥናት ባለስልጣኗን ለማነጋገር ቢሮዋ ገቡ። የህወሃት አባል መሆኗ ላይገርምዎ ይችላል። ነገር ግን በችሎታዋ ቦታው ላይ ብትቀመጥ መልካም ነበር። ዘመዶቻችን ጉዳያቸውን ያስረዱ ጀመር። “ይሄን ቦታ ከጃንሆይ ዘመን ጀምሮ ሰርተንበታል። ደርግም አልወረሰብንም። አሁን ግን ካሳ እንንኳን ሳይሰጠን ፈረሰብን።” አሏት።

ባለስልጣኗ የተባለውና የፈረሰውን ቦታ የምታውቀው ትመስላለች። ግን ደግሞ ተናዳላች። “ስንት አመት ሰራችሁበት?” አለች።

“እኛ ሳንወለድ ጀምሮ የነበረ ነው። ከስልሳ አመት በላይ ሰርተንበታል።” አሏት። ከዚያ በኋላ ሴትዮዋ የጭቃ ጅራፏን አወረደችባቸው።

“ለስልሳ አመት የህዝቡን ስትመጡት ኖራችኋል ማለት ነው። እንደናንተ አይነት ፓራሳይቶች ናቸው ያስቸገሩን…” በማለት እዚህ ላይ መዘርዘር የማያስፈልጉ ስድቦች አክላበት፤ አዋርዳ ከቢሮዋ አባረረቻቸው። ሰው በአገሩ እንዲህ አይነት ግፍ እየተፈጸመበት ነው። ጉዳዩ በዚህ ቢያበቃ ጥሩ ነበር። ጭራሽ ከፈረሰ አራት አመት ለሆነው ህንጻ የአንድ ሚሊዮን ብር የግብር እዳ እንዲከፍሉ፤ ካልከፈሉ ሌላ ንብረታቸው እንደሚወረስ ማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ደርሷቸው፤ ሳይወዱ በግድ ገንዘቡን ከፈሉ።

ይሄ እንደምሳሌ ያነሳሁት ታሪክ የተጋነነ አይደለም። እንዲያውም ቦታ ላለመጨረስ በአጭሩ ያቀረብኩት፤ በቅርብ የማውቀው ታሪክ ነው። እንዲህ አይነት ታሪክ ያላቸው፤ ፍትህ የተዛባባቸው፤ “ለማን አቤት ይባላል?” እያሉ ግራ ተጋብተው ዝም ያሉ ሰዎች ብዙ ናቸው። አሁን ቅርብ ግዜ እንደሰማነው ከሆነ ደግሞ፤ ግምት ሳይሰጡ ለሚያፈርሷቸው ህንጻዎች፤ ባለጉዳዩን ካባረሩ በኋላ የካሳውን ገንዘብ ለራሳቸው ሰዎች እንደሚያስተላልፉ ሰምተን ተግርመን ዝም ብለናል።

በአሁኑ ወቅት ፍትህ አጥተው… ወዴት ‘አቤት’ እንደሚሉ ግራ በተጋቡ ህዝቦቻችን መሃል ነው ያለነው። ሰዎቹ እንደሆነ… እንኳንስ የተስተካከለ ፍርድ ሊሰጡ ቀርቶ፤ የመሃል አገሩን ህዝብ እንደጠላት በማየት፤ መንደሩን እየሸነሸኑ እና የህዝቡን የፍትህ እምነቱን እየሸረሸሩ ዛሬ ያለንበት… ይሉኝታ ቢስ ዘመን ላይ አድርሰውናል። ጠመንጃ ካነሱበት ግዜ ጀምሮ… ትምክህት መመሪያቸው፤ ጠመንጃ ሃይላቸው ሆኖ ዛሬም ድረስ አሉ። በሌላ በኩል ያለው… ሌላው ደግሞ “ኃይል የእግዚአብሔር ነው።” ብሎ መጭውን ግዜ በብርታት የሚጠብቅበትን ዘመን እንድናይ አድርገውናል።

ነገሩ ክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤል በአንድ ግጥማቸው ላይ እንደገለጹት መሆኑ ነው።

“መሬት የእግዚአብሔር ናት፣ ባለቤት የላትም፤
ኃይለኛ እየሄደ፣ ያስገብራል የትም።”

“ሆድ ለባሰው ማጭድ አታውሰው” እንደሚባለው ሆኖ ሆድ ከምናባብስ፤ ነገራችንን ወደ ማጠቃለሉ ብንሄድ ይሻለናል።

እናም ለማጠቃለል ያህል…  የኢትዮጵያ ነጻ ጋዜጠኞች ገና በጠዋቱ ስለኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት ሲያስተምሩ ነበር። “በዘር እና በብሄር መለያየት የለብንም” በማለት፤ ስለኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት ተሟግተዋል። በገዢዎቻችን ዘንድ የጥላቻ መንፈስ ሲንሰራፋ፤ የብሄር ዘረኝነት ሲስፋፋ ጋዜጠኞቻችን… “ተው – ይሄ ለህዝብ አይበጅም” ሲሉ አስጠንቅቀዋል። የመንግስት ምላሽ ግን ወንድሞቻችንን  በማሰር አርፈው እንዲቀመጡ ወይም ጋዜጠኞችን በማሸበር አገር ለቀው እንዲወጡ ማድረግ እንደዘመቻ ትኩረት ተሰጠበት።

እርግጥ ነው። ጋዜጠኞችን ማሰር እና ማሸበር ይቻል ይሆናል። የሚፈራም ከተገኘ ማስፈራራት ይቻላል። የህዝብን አንደበት ሙሉ ለሙሉ መዝጋት ግን እጅግ አስቸጋሪ ነገር ነው። ይህን አንደበት መዝጋት ማለት፤ የታፈነ የህዝብ ድምጽ ማፈን ማለት ይሆናል። የታፈነ ስሜት ሲገነፍል ደግሞ መመለሻ አይኖረውም።  ይህ ስሜት ገንፍሎ አገር ከመጥፋቱ በፊት፤ እንደተጣደ ሽሮ ‘እፍ እፍ’ እያለ ከመገነፍል የሚያድነው ፕሬሱ መሆኑን፤ በቅን ልቦና በንጹህ ህሊና መዝኖ ነጻውን ፕሬስ እንደእንቁላል መንከባከብ ብልህነት ነበር።

በድሮ ተረት እንሰነባበት። ሁለት ጓደኛሞች በርሃ አቋርጠው እየሄዱ ሳለ አለመግባባት ተፈጠረ። እናም ጉልበተኛው አቅመ ደካማውን በጥፊ መታው። በዚህን ግዜ አቅመ ደካማው ምንም አላለም። በበርሃው አቧራ አፈር ላይ”ዛሬ ጓደኛዬ በጥፊ መታኝ” ብሎ ጻፈ። ብዙ ከሄዱ በኋላ ደግሞ ወንዝ አጋጠማቸውና ከውሃው ጠጥተው መዋኘት ጀመሩ። ነገር ግን ደራሽ ጎርፍ መጣና አቅመ ደካማው በወንዙ ሊወሰድ ሆነ። በዚህን ግዜ ጉልበተኛ ጓደኛው በብዙ ጥረት የአቅመ ደካማ  ጓደኛውን  ህይወት አተረፈለት።

ከሞት የተረፈው ሰውም በትልቅ አለት ላይ፤ “ዛሬ ጓደኛዬ ከሞት አዳነኝ” ብሎ በአቧራ ላይ ሳይሆን በአለት ላይ ቀረጸው።

በዚህን ግዜ ጉልበተኛው በሁኔታው ተገርሞ “በጥፊ ስመታህ አቧራ አፈር ላይ የጻፍከውን ታውቃለህ። አሁን ደግሞ ከወንዝ ውሃ ሳተርፍህ ይህን በድንጋይ ላይ ጻፍከው። ምንድነው ሚሰጥሩ?” አለው። ጸሃፊውም እንዲህ ሲል መለሰ።

“ሃይለኛ ዝናብ ወይም ንፋስ በሚመጣ ግዜ በአፈር ላይ የጻፍኩት ነገር ይጠፋል። አንተ ያደረስክብኝ በደል ግዜያዊ ስለሆነ፤ ይቅርታ በተባባልን ግዜ እንደአቧራው ላይ ጽሁፍ ከልቤ ይጠፋል። ጸባችን ሳይሆን መልካም ተግባራችን በአለት ላይ ተጽፎ መቅረት አለበት። ይህም ውሽንፍር እና አውሎ ንፋስ ቢመጣ ጭምር አይጠፋም። እነሆ በአለት ላይ የተጻፈው ለዘላለም ይታወሳል።” አለው።

እኛ ጋዜጠኞች ፍጹም  አይደለንም። ልንሳሳት ወይም አንዳንድ ወገኖችን ልናስቀይም እንችል ይሆናል። ነገር ግን ካጠፋነው ይልቅ የሰራነውን መልካም ነገር በማየት፤ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በተለይ ለነጻ-ፕሬስ ጋዜጠኞች በልቡ ውስጥ ልዩ ስፍራ ሊሰጥ ይገባል። ሙያውን እየሰሩ ላሉትንም ሆነ ላለመስራት ለተገደዱት፤ ለታሰሩትም ሆኑ ለተሰደዱት ጋዜጠኞች ክብር ልንሰጣቸው፤ መልካም ተግባራቸውን በልባችን ጽላት ልንጽፈው የግድ ነው። እነጋዜጠኛ… ውብሸት ታዬ፣ ተመስገን ደሳለኝ እና እስክንድር ነጋ የጀመሩትን የቀራንዮ መንገድ እኛም ልናግዛቸው ይገባል – ጉዞው ተጀመረ እንጂ ገና አልተገባደደምና።

ከጎንደር ታፍኖ በቂሊንጦ የስቃይ ማጎሪያ የሚገኘው ወጣት አባይ ዘውዱ ሕይወቱ አዳጋ ላይ መድረሱ ታወቀ

$
0
0

የነጻነት ጎህ

ከሰሜን ጎንደር ታፍኖ በቂሊንጦ የስቃይ ማጎሪያ የሚገኘው የቀድሞ ኣንድነት ፓርቲ ኣመራር ወጣት ኣባይ ዘውዱ በእስር ቤት ሕይወቱ ሊያልፍ እንደሚችል በከፍተኛ ሰጋት ላይ ወድቋል፡፡ ኣባይ ዘውዱ በደረሰበት የጉበት እና ጣፊያ እብጠት ሊፈነዳ ሲሆን በተጨማሪም በቲቪ-በከፍተኛ ደረጃ መታመሙ በደረሰን ጥቆማ ዛሬ 22/08 ቂሊንጦ በመሄድ ከራሱ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡
abay
ወጣት ኣባይ ዘውዱ በህመሙ ሰውነቱ ኣልቆ በሰው ተደግፎ እያቃሰተ ማየት ያማል፡፡ የተሟላ ህክምና እንደተከለከለ ኣባይ እንባውን እያፈሰሰ ይናገራል፡፡ ይህ ለመላው ኣገር ወዳድ በተለይ የኣማራ ሕዝብ በዝምታ ተመልክቶ የወጣት ኣባይ ዘውዱ ሕይወት ልናጣው ከቻልን ለኣማራ ሕዝብ ትልቅ ውድቀት ትልቅ ዋጋ እንደሚያስከፍል መገንዘብ ያሻል፡፡ ኣባይ ዘውዱ-ሁለተኛ ድግሪውን ከቅርብ ጊዜ በፊት ያጠናቀቀ ሲሆን በከፍተኛ ትምህርት የቆይታውም ቢሆን ከባሕር ዳር ዩንቨርስቲ የማዕረግ ተመራቂ የነበረ ወጣት ምሁር ነው፡፡ ኣባይ ዘውዱ የቀድሞ ኣንድነት ፓርቲ ከተቀላቀለ በኃላ በነበረው ንቁ ተሳትፎ ከሚሰራበት ቦታ ከማባረር እንስቶ በኣካሉ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሲደርስበት የቆየ ጠንካራ ጓዳችን መሆኑ ይታወቃል፡፡ በተለይ ለሱዳን ሊሰጥ በታሰበው መሬት ዙሪያ ኣባይ ዘውዱ ከጎንደር ኣዲስ አበባ ድረስ በመምጣት በኣንድነት ፅ/ቤት ሰፊ የዳሰሳ ጥናቱን ካቀረበ ወዲህ በወያኔ አይን እንደገባ ይነገራል፡፡ ለዚህ ጀግና ጓዷችን ኣገር ወዳድ ሊደርስለት ይገባል፡፡ ኣማራ ልጆቹን በዘረኞች እያስበላ የሚኖረው እስከመቼ ነው?

ወጣት አክቲቪስቶች የሚዲያ ኣካሎች በሙሉ ወጣት ኣባይ ዘውዱ የተሻለ ህክምና እንዲሰጠው ግፊት ማድረግ ሕይወቱን መታደግ ግዴታ ኣለበት፡፡ የነቃ ተሳትፎ ያላቸው የኣማራ ተወላጅ የሚደርሰው ዘር የማጥፋት ድርጊት ሊወገዝ ኣምሮ ሊታገሉት የሚገባ ተግባር ነው፡፡ ሁሉም ወገን ወዳድ ለኣባይ ዘዉዱ ድምፁን ይሰማለት፡፡ ኣማራ ነገ ታሪኩ ሲነገር ሊያፍርበት ይችላል፡፡

ለአስራ አራት ቀን አራስ ጥይት? – (አሳዛኝ እውነተኛ የወንጀል ታሪክ)

$
0
0

crime

አቶ አስጨናቂ ደስታ፤ ተሬ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ውስጥ በእርሻ የሚተዳደሩ አርሶ አደር ናቸው፡፡ ትዳር መስርተው መኖር ከጀመሩ ደግሞ አስራ ሶስት ዓመታትን አስቆጥረዋል፡፡ ባለቤታቸው ወ/ሮ ኮከብ ወርቁ ከአቶ አስጨናቂ አራት ልጆችን አፍርተዋል፡፡ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን በቀወት ወረዳ ለረጅም ዓመታት በትዳር አብረው የኖሩት ሁለቱ ጥንዶች ትዳራቸው እንዲሁም ቤተሰባቸውን እንከን ገጥሞታል፡፡ አቶ አስጨናቂ ደስታ ታታሪ ገበሬ በመሆናቸው ነው በአካባቢው የሚታወቁት፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን አቶ አስጨናቂ ደስታ ርቋቸዋል፡፡ እርሳቸው እና ቤተሰባቸው በመጥፎ የስሜት ድባብ ውስጥ ሆነው ጊዜው እየነጎደ ነው፡፡ ይመሻል ይነጋል፡፡ ይህ የሆነበት ደግሞ ምክንያት አለው፡፡ አቶ አስጨናቂ በአጭር ጊዜ ውስጥ አራት በሬዎቻቸውን አጡ፡፡ የሚመኩባቸው የእርሻ በሬዎቻቸው ሳይታሰብ እየታመሙ ሞተው አለቁባቸው፡፡

የሀገራችን ገበሬዎች በበሬዎቻቸው በጣም ነው የሚመኩት፡፡ ዘር ዘርተው… አርመው… ጎልጉለው… አጭደውና ወቅተው ምርት የሚያገኙት የበሬዎቻቸውን ጉልበት በመጠቀም ነው፡፡ በሬ ለሀገራችን ገበሬዎች ከምንም በላይ እንደሆነ በአርሶ አደሮች አንደበት ጭምር ይነገራል… ይዘመራል፡፡

‹በሬ እረስልኝ…

በሬ ዙርልኝ

አጋዥ ባልደረባ

አራሽም የለኝ

በጥቋቁር በሬ…

መሬት ካላረሱ

ገንዘብ የት ይገኛል…

ቦርሳ ቢዳብሱ›

ከአርሶ አደሮች አንደበት የሚደመጡ የማሞካሻ ስነ-ቃሎች ናቸው፡፡ ለበሬ ማሞካሻ… ማሞገሻ… ውለታ መግለጫ የሚሆኑ ስነ-ቃሎች እነዚህ ብቻ አይደሉም፡፡

አቶ አስጨናቂ አራት ልጆቻቸውን አርሰው የሚመግቡባቸው የአራት በሬዎቻቸው ሞት ትልቅ ሀዘን እንዲሰማቸው አድርጓቸዋል፡፡ የበሬዎቻቸው ሞት ራቁታቸውን ስላስቀራቸው የኑሮ ምስቅልቅልን ፈጥሮባቸዋል፡፡

‹መሬት ያለ በሬ

ምርት ያለገበሬ› አይታሰብም የሚለው የሀገራችን ብሂል በአርሶ አደር አስጨናቂ ደርሶባቸው ዘወትር ጭንቀት ሆኖባቸዋል፡፡ በእነዚህ መጥፎ አጋጣሚዎች ውስጥ ቤተሰባቸውን እንዴት እየመሩ ነበር? ከባለቤታቸው ወ/ሮ ኮከብ ጋር ምንምን ነገሮችን ያወሩ እንደነበር ለማወቅም ወ/ሮ ኮከብን ማግኘት አልተቻለም… ለምን? ቢሉ… ምክንያቱ ወዲህ ነው፡፡

የወርሀ ሐምሌ ክረምት ወቅት ነው፡፡ ሐምሌ 4 ቀን 2001 ዓ.ም በግምት ከረፋዱ አምስት ሰዓት ላይ አቶ አስጨናቂን ‹‹ምን አስጨከናቸው?›› ያስባለ ትእይንት በመኖሪያ ቤታቸው ተከሰተ፡፡ ጎረቤትን… ዘመድ አዝማድን… የአካባቢውን ነዋሪ ያስደመመ በእጅጉ ያሳዘነ ትእይንት ነበር የተከሰተው፡፡

ወ/ሮ ኮከብ ወርቁ በትዳር ሕይወታቸው አራተኛ ልጃቸውን ከወለዱ ገና አስራ አራተኛ ቀናቸው ነው፡፡ ወገባቸው ያልጠነከረ አራስ ናቸው፡፡ በአራስ ቤት ውስጥ ሁለተኛ ሳምንታቸውን ገና አልደፈኑም፡፡ በመጫቷ ወ/ሮ ኮከብ ላይ የተፈፀመው ግን ‹‹መታረስ ነው የሚገባቸው ወይንስ ሌላ?›› የሚል ጥያቄ ያስነሳል፡፡ …ጥያቄው ደግሞ የሁሉም ሰው ነው፡፡ አቶ አስጨናቂ የአራት ልጆቻቸውን እናትና ባለቤታቸውን ‹‹…እንደ ቤታችን ምን ላቅርብልሽ?›› ብለው አልጠየቁም፡፡ በእዚህ ምትክ የሰጧቸው ጥይት ነበር፡፡ የአራት ልጆቻቸው እናት እና አራሷ ወ/ሮ ከባለቤታቸው በተተኮሰባቸው ጥይት ተመተው እስከ ወዲያኛው አሸለቡ፡፡

ለጥፋት የተዘረጋው የአቶ አስጨናቂ የጭካኔ እጅ በእዚሁ አላበቃም፡፡ ጭካኔያቸው ቀጥሏል፡፡ የሰባት ዓመት ሴት ልጃቸውንም እናቷን እንድትከተል አድረጓት፡፡ አባወራው ባለቤታቸውንና የሰባት ዓመት ሴት ልጃቸውን ጨክነው በጥይት መትተው የህይወት እስትንፋሳቸው እንዲቆም አደረጉ፡፡

ተግባራቸውን ያየ… የሰማ ሁሉ ‹‹ምንድን ነው ይህንን ያህል ጭካኔ?›› ብሎ እንዲጠይቅና እንዲወያይ አደረገው፡፡ እውነት በሬዎቻቸው ስለሞቱባቸው ተስፋ ቆርጠው ይሆን? ይህ የእኛ ጥያቄ ነው፡፡ ጎረቤቶች ግን የሚሉት አራት በሬዎችን በአንድ ጊዜ በሞት በማጣታቸው ተስፋ ቆርጠው ነው ብለዋል፡፡ ፖሊስ ጉዳዩን በማጣራት ላይ ነው፡፡ በእንስሳት ሞት የቤተሰብን ህይወት ማጥፋት ለምን አሰፈለገ? የሚለው የፖሊስም ጥያቄ በመሆኑ ምርመራው እንደተጠናቀቀ የሚታወቅ ነው የሚሆነው፡፡

አሁን አቶ አስጨናቂም በህይወት የሉም፡፡ ምክንያቱም በዕለቱ በባለቤታቸውና በሰባት ዓመት ሴት ልጃቸው ላይ ግድያውን ከፈፀሙ በኋላ በራሳቸው ላይ ፈረዱ፡፡ ራሳቸውን አጠፉ፡፡ በአራት በሬዎች ሞት የሦስት ሰዎች ህይወት መጥፋቱ ሁሉንም ያሳዘነ እንደሆነ የአካባቢው ሰዎች ይናገራሉ፡፡

ቤት ባዶ ቀረ፡፡ ሦስት ልጆችም ያለ አሳዳጊ ቀሩ፡፡ እናታቸውን፣ አባታቸውንና እህታቸውን አጡ፡፡ የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አህመድ መሐመድ እንደገለፁት የልጆቹን ህይወት ለመታደግ በአራስ ቤት ያለው ህፃን ወደ ሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር የህፃናት እንክብካቤ ተቋም በመወሰድ ተገቢውን እንክብካቤ እንዲደረግለት ተደርጓል፡፡ ቀሪዎቹ ሁለት ልጆች ደግሞ ያለ አሳዳጊ እንዳይቀሩ አሳዳጊ እንዲያገኙ ፖሊስ በጥረት ላይ ነው፡፡ የፖሊስ ጥረት ብቻውን በቂ አይደለም፡፡ ሁለቱን ህጻናት ለመታደግ ግለሰቦች፣ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች፣ መንግስትና ሌሎችም እጃቸውን ማስገባት ቢችሉ በጎ ተግባር ነውና ሁላችሁም የበኩላችሁን አበርክቱ የሚለው የዝግጅት ክፍላችን መልእክት ነው፡፡

 

ደቡብ ሱዳን ከ125ቱ ኢትዮጵያውያን ህፃናትና ሴቶች 32ን ከአጋቾቹ ተረከብኩ አለች – 93ቱ የት ናቸው? * የጋምቤላው ክልል ፕሬዚዳንት መረጃው የለኝም አሉ

$
0
0

Gambela

(ዘ-ሐበሻ) ከሁለት ሳምንት በፊት የሙርሌ ጎሳ አባላት ከ200 በላይ ኢትዮጵያውያንን ገድለው 125 የሚሆኑ ህፃናትን እና ሴቶችን አፍነው ከወሰዱ በኋላ የኢትዮጵያ መንግስት ‘ሕጻናቱ ያሉበትን ቦታ ደርሼበት ከብቤያለሁ” የሚል ዜና አሰምቶን ነበር:: ከበባው ቀናት አስቆጠረ:: ኢትዮጵያውያን ልጆቻችን የት አሉ? እያሉ ሲጠይቁ ከረመ:: ያሉበትን ቦታ ከብቤያለሁ ያለው መንግስት ልጆቹን ለማስለቀቅ ድርድር ውስጥ ገባሁ ይለን ጀመር::

ዛሬ አሶሲየትድ ፕሬስ እንደዘገበው ደግሞ ከታፈኑት 125 ህፃናትና ሴቶች መካከል 32ቱን የደቡብ ሱዳን መንግስት ማግኘቱን አስታውቋል:: የደቡብ ሱዳን ቦማ ግዛት አስተዳዳሪ አቶ ኦጋቾ ቻን ሊኩአንጎሌ በሚባል ሶስት መንደሮች ህጻናቱን እንደተረከቡ ሲገልጹ በቅርቡም 32ቱ ህፃናት ወደ ጁባ ሄደው ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ ሲሉን አስተያየታቸውን ለአሶሲየትድ ፕሬስ ሰጥተዋል:: እንደ ዜናው ዘገባ አፋኞቹ ህፃናቱን ሊኩአንጎሌ የተባለው መንደር ውስጥ ህጻናቱን ሳይለቋቸው አልቀረም::

እኚሁ አገረ ገዢ ቀሪዎቹን 93 ህፃናትና ሴቶች ካሉበት ቦታ ለማስለቀቅና ለማሰባሰብ እንሞክራለን” ብለዋል::

በሌላ ዜና ዋሽንግተን ፖስት እንደዘገበው የጋምቤላው ክልል ፕሬዚዳንት ጋትሉክ ቱት ስለልጆቹ መገኘት የሚያውቁት መረጃ የላቸውም::

የፋሲካ ገበያ |የዶሮ፣ የፍየል፣ የበግ፣ የሰንጋ፣ የቅቤና የእንቁላል ዋጋ ትንተና

$
0
0

የዘንድሮ የትንሳኤ በአል ገበያ ምን ይመስላል? | የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ዘገባ ከአዲስ አበባ

በተለያዩ የአዲስ አበባ የገበያ ስፍራዎች ተዟዙረን የበዓል ገበያ ዋጋን ለመቃኘት እንደሞከርነው፤ በአብዛኛው ከዓምና ተመሳሳይ የበዓል ገበያ ዋጋ ጋር ተቀራራቢ ነው፡፡ በአቃቂ ቄራ ገበያ የበሬ ዋጋ ከ5 ሺህ እስከ 22 ሺህ ብር ድረስ ሲሆን ዓምና በተመሳሳይ በዓል የበሬ ዋጋ ከ8 ሺህ ብር እስከ 25 ሺህ እንደነበረ ይታወሳል፡፡
sheep
በአቃቂ ቄራ፡- የበግ ዋጋ ከ700 ብር እስከ 3500 ብር ሲሆን በዓምና የፋሲካ ገበያም በግ ከ900ብር እስከ 3500 ብር ተሸምቷል፡፡ በአቃቂ የቁም እንስሳት ቄራ ገበያ፣ ከፍተኛው የፍየል ዋጋ 7ሺህ ብር መሆኑን ከነጋዴዎች የተገኘው መረጃ አመልክቷል፡፡
በገበያው ቋሚ የበግና የፍየል ነጋዴ የሆነው ወጣት መስፍን ይልማ፤ በግና ፍየሎችን ከአዳማና አርሲ አካባቢ አምጥቶ እንደሚሸጥ ገልፆ፤ ዘንድሮ ገበሬው በግና ፍየል ለነጋዴው እየሸጠበት ያለው ዋጋ ከአምናው ጋር ሲነፃፀር በአማካይ እስከ 200 ብር ቅናሽ ማሳየቱን ተናግሯል፡፡

ገበሬው ለመጪው ክረምት የሰብል ምርት የሚያስፈልገውን ማዳበሪያ መግዣ የሚሆን ገንዘብ ለማግኘት የትንሳኤ በዓል የከብት ገበያን እንደመልካም አጋጣሚ እንደሚጠቀምበት ይኸው ነጋዴ ገልጿል፡፡

በአዲስ አበባ ዋናው ቄራ ገበያ የሃረር ሰንጋ በሬዎች፡-

  • ከ18 ሺህ ብር እስከ 25 ሺህ ብር እየተሸጡ ሲሆን
  • በሰውነት አቋማቸው አጫጭር የሆኑት የጅማ ሰንጋዎች ደግሞ ከ6 ሺህ ብር እስከ 10ሺህ ብር እንደሚገኙ ታውቋል፡፡
  • በግ በቄራ አካባቢ ባሉ ገበያዎች መካከለኛው፡- ከ1300 ብር እስከ 2ሺህ ብር፣
  • ሙክት በግ እስከ 5 ሺህ ብር ይገኛል፡፡

የዶሮ ዋጋ

  • ዝቅተኛው 130 ብር፣
  • ከፍተኛው 400 ብር ሲሆን
    እንቁላል
  • – በነጠላ 3 ከ50፣
  • – ቅቤ በኪሎ፣
  • – ከ180 ብር እስከ 240 ብር እየተሸጠ ነው፡፡
  • በአስኮ ገበያ ዶሮ ከ250 ብር እስከ 350 ብር፣
  • እንቁላል በነጠላ 3 ብር 50፣
  • ቅቤ በኪሎ ከ180 ብር እስከ 250 ብር፣
  • አይብ ከ65-75 ብር በኪሎ ይሸጣል፡፡

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት በበኩሉ፤ 5ሺህ የሚሆኑ የእርድ እንስሳትን የሚያቀርብ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 2500 በሬዎች፣ 2300 ደግሞ በግና ፍየሎች እንደሆኑ ገልጿል፡፡

ከድርጅቱ ባገኘነው መረጃ መሰረት፤ ለበዓሉ ድርጅቱ በራሱ የመሸጫ ሱቅ የበግ ስጋ በኪሎ 130 ብር ይሸጣል፡፡

አመት በአል ሲቃረብ ብዙ ነገር ይናፍቀኛል|በእውቀቱ ስዩም

$
0
0

Bewketu Seyoum – Hagere Mariam (Maryland) USA [Must Listen)

አመት በአል ሲቃረብ ብዙ ነገር ይናፍቀኛል፡፡ ከሁሉም በላይ፤ እንደ አፍላ ጉም የሚሳብ የሉባንጃ እጣን – ብረት ምጣድ ላይ የሚጤስ ቡና -የጥላሁን ገሠሠ ዘፈን -ብዙ ፍቅር- ብዙ ፈገግታ ውልውል ይለኛል፡፡ ከመከረኛ ህይወታችን ማህል ብልጭ ብሎ የሚጠፋ አመት በአል የተባለ አብሪ ኮከብ ለዘላለም ይኑር!

አመት በአል ቀን ዋናው የደስታና የክብር ምንጭ መብላትና መጠጣት ነው፡፡

ግማሽ ፈረስ ግማሽ መልአክ የሆነው ሰው የተባለው ፍጡር እስኪረካ ድረስ መጠጣት፤ እስኪጠግብ ድረስ መብላት ይፈልጋል፡፡ ግን ምንዋጋ አለው? ባለማችን፤ ይልቁንም በአገራች እንደልብ የሚገኝ ነገር ቢኖር የምግብ እጥረት ነው ፡፡ ብዙ የሚበላ ሰው የሌላውን ድርሻ እንደወሰደ ስለሚቆጠር በማኅበረብ ዘንድ የተጠላ ነው ፡፡ የተፈጥሮን ጥያቄ ባግባቡ በመመለሱ  ሆዳም አጋሰስ እየተባለ ይብጠለጠላል ፡፡ በተቃራኒው ከምግብ የሚቆጠቡ ሰዎች ይወደሳሉ ፡፡ ጾመኞች ይቀደሳሉ፡፡

የተከበረ ዜጋ በጎረቤቱ ድግስ ላይ በተጋበዘ ቁጥር እንደ የሰውነቱን ፍላጎት በማርካትና የማኅበረሰቡን የክብር መመዘኛ በማሟላት መሀል ይወጠራል፡፡ ይህንን ውጥረት የሚያረግበው ማግደርደር የተባለው፤ በመጥፋት ላይ ያለ ባህል ነው፡፡ ጋባዥ እንግዳውን አፈር ስሆንልዎ በጊዮርጊስ ”እያለ ይለማመጠዋል ፡፡ ጋሽ እንግዳ“ በቃኝ!”ኧረ በቃኝ ያለ ትንሽ ሲታገል ይቆይና ይረታል፡፡ የምበላው እርስዎ አፈር እንዳይሆኑብኝ ብየ ነው የሚል ገጽታ ተላብሶ ምግቡ ላይ ይወርድበታል፡፡ ይህ ማኅበራዊ ተውኔት ሰዎች ኩራታቸውንም ራታቸውንም እንዳያጡ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡

የሆነ ጊዜ ላይ አንዱ ከገጠር ወደ ከተማ ይመጣና ከተሜ ዘመዶቹ ቤት ያንዲት ሌሊት ጥገኝነት ጠየቀ ፡፡ ማታ ዘመዶቹ አጋም የመሰለ ዶሮ አቅርበውለት እንዲበላ ጋበዙት፡፡ ሰውየው ለወግ ያህል “ ፤ አሁን በልቸ ነው የመጣሁ፤ ማርም አልስ ”ካለ በኋላ አጥብቀው እስኪያስግደረድሩት ድረስ መጠባበቅ ጀመረ:) ጋባዦች ግን በልቶ ከመጣ አናስገድደውም ብለው የራሳቸውን እየተጎራረሱ ሞሰቡን ወደ ምድረበዳነት ከቀየሩት በኋላ አነሡት፡፡ ሰውየው ባዶ ሆዱን እሪታ በሳይለንሰር አፍኖ ሲገላበጥ አድሮ ሲነጋጋ ሎንቺና ተሳፍሮ ወደ ገጠር ተመለሰ፡፡ እግሩ ገና የቤቱን ደጃፍ እንደረገጠ ሚስቱን“ አቺ! እንጀራ በጨው አምጭልኝማ ” አላት፡፡ ሚስቱ“ ዋ! በሄዱበት አገር አልበሉም እንዴ !”
ባል – “ኧሯ!አቦና ማርያም የሌሉበት አገር ህጀ ጦሜን ተደፍቸ አደርኩ እንጂ!”

ከተሜ ዘመዶቹ፤ “ ባቦ፤ በማርያም” እያሉ ለማግደርደር አለመሞከራቸው ገርሞት ነው፡፡

ባገር ቤት ጨዋታ ውስጥ ዋና ገጸባሕርይው የቆሎ ተማሪ ነው፡፡ ያገር ቤት የቆሎ ተማሪ የዶንኪሆቴ የማኪያቬሊና የካሳኖቫ ቅልቅል ነው፡፡ ገድለኝነትን ብልጣብልጥነትንና ሴትአውልነትን አስተባብሮ ይዟል ፡፡ ባንድ አመት በአል ስላውዳመቱ ብሎ ሲለምን የቤቱ አባዋራ ገብቶ እንዲጋበዝ ፈቀደለት፡፡ ራት ቀረበ፡፡ ተሜ በልቶ እንደመጥገብ ሲል ሚስትዮዋን ለማጉረስ ይንጠራራ ጀመር፡፡ አባዋራው “ተሜ አርፈህ የራስህን ብላ ፤ ሚሽቴን የማጉረስ የኔ ፋንታ ነው” ብሎ ገሰጸው፡፡ ተሜ ግን“ግዴሎትም ጌታው ላግዝዎት ብየ ነው”እያለ በባልየው ፊት በኩል አመዳም እጁን እያሳለፈ ሚስትዮዋን ማጉረስ ቀጠለ፡፡ ጉዳዩ ትንሽ እየተካረረ መጣና አባዋራውና ተሜ ትግል ተያያዙ፡፡ሚስትዮዋም በመገላገል ፋንታ ሞሰቧን አንስታ ቡናዋን እያፈላች ትግሉን በጥሞና መከታተል ጀመረች፡፡ አባዋራና ተሜ ለረጅም ጊዜ ሲታገሉ ከቆዩ በኋላ ጉልበት ወደ ተሜ እያደላ የባል መገጣጠምያ እየላላ መጣ፡፡ አባዋራው ለማሸነፍ መጣሩን ትቶ ፤ እሱንም አካባቢውንም ሳይጎዳ የሚወድቅበትን ስትራቴጂ መንደፍ ጀመረ፡፡ በተሜ ብብት መሀል ሆኖ፤ ባጭር ባጭሩ እየተነፈሰ ሚስቱን ቁልቁል እያየ “ንሽማ እቃውን አነሳሽው” አላት፡፡

ሚስት ምድጃውን እያራገበች “ሊወድቁ እንዳይሆን?”ስትል ፡፡
“አይ ነብራሬ እና አንቺ ባመጣሽው እዳ ተገትሬ ልደር?

አመት በአሉ ከገላጋይ ኣልባ ጠብ የጸዳ ይሁንልዎት!!

Health: ስኳርና መዘዙ –አዲስ የስኳር አወሳሰድ መጠን ይፋ ተደረገ

$
0
0

ስኳር የሚጨምርባቸውን ምግቦች እና መጠጦች ለአፍታ እናስባቸው፡፡ ኮስተር ያሉትን ስናዘጋጅ ብቻ ካልሆነ ዕለት ተለት በምንመገባቸውና በምንጠጣቸው ውስጥ ስኳር መጨመርን ለምደነዋል፡፡

diabetes-testing

በባህላዊ መንገድ በሚዘጋጁት ወጦቻችን፣ ጠላዎቻችንና ዳቧችን ሳይቀር እንደ ቀድሞው እናቶቻችን ባልትና የሚጠይቁ አይደሉም፡፡ ይልቁንም ጠቀም ያለ ስኳር ሊሰፈርላቸው ይገባል፡፡ የምግቦቻችንና መጠጦቻችን ቃና ላንቃን በሚያወረዙና ከምላስ በማይወርዱ ጣፋጭነታቸው ብቻ ነው ጥሩነታቸው እየተለካ ያለው፡፡ ከእናት ጡት በቀር ህፃናቶቻችንስ ስኳር ያልተጨመረባቸው ምግብና መጠጦች መች ይቀርብላቸዋል?

 

ስኳርና መዘዙ የዓለም የጤና ተሟጋቾች ትኩረት ከሆነ ሰንብቷል፡፡ ሰሞኑን እንኳን አንድ የእንግሊዝ የተመራማሪዎች ቡድን በእንግሊዝ በአሁኑ ወቅት ጥቅም ላይ የሚውለው የስኳር መጠን ቢያንስ በግማሽ እንዲቀነስ ሐሳብ አቅርቧል፡፡ ተመራማሪዎቹ ስኳር በምግብ ውስጥ የሚመርበት መጠን መወሰን ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አለመሆኑን ነው ያሳሰቡት፡፡

 

የምግብ ባለሙያዎች በቀን ከምንወስዳቸው የካሎሪ መጠን ስኳር ከ5 በመቶ ወይም ከ6 ማንኪያ ከበለጠ አደጋ አለው በሚል ነው ይሄን ዘመቻ አጠናክረው ያስቀጠሉት፡፡ በአሁኑ ወቅት ብዙ ሰዎች ከተጠቀሰው መጠን በእጥፍ የሚልቅ የስኳር ፍጆታ ነው ያላቸው፡፡ የዴቪድ ካሜሮን መንግሥትም ከባለሙያዎቹ የቀረበውን ሐሳብ እንደሚቀበልና በዚህ ዓመት በሚቀርበው የብሔራዊ የህፃናት ውፍረት መካከል እቅድ ውስጥ እንደሚያካትተው አስታውቋል፡፡

 

የአመጋገብ ኮሚቴ ተመራማሪዎቹ ያቀረቡት የቀን የስኳር ፍጆታ (6 ማንኪያ) በግማሽ መቀነስ፣ ከልክ ያለፈ ውፍረትንና የጥርስ ጤንነትን ለመጠበቅ መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑን ነው ያሳሰቡት፡፡ የኮሚቴው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር አያ ማክዶናልድ ‹‹ግኝቱ ከፍተኛ ስኳር ለጤና ጠንቅ መሆኑንና ልማዳችንን ልናስወግድ እንደሚገባ የሚጠቁም ነው ብለዋል፡፡ ፕሮፌሰሩ አክለውም ‹‹የምንወስደውን ስኳር መቀነስ የፋይበር ክምችታችንን ከፍ ማድረግና ረዥም ዕድሜ የመኖርንና በጤና የመቆየት ምስጢር ነው›› ብለዋል፡፡

 

የብሪቲሽ የምግብ ተቋም ባለሙያዋ ፕሮፌሰር ጁዲት ቡትሪስ በበኩላቸው፣ እቅዱ ‹‹ከስኳር ነፃ›› የሚል መጠሪያ ተሰጥቶታል ብለዋል፡፡ በተፈጥሯአዊዎቹ ምግቦች ማለትም ፍራፍሬዎችና ወተት ውስጥ ያለውን የስኳር ክምችት ሳያጠቃልል ተጨማሪዎቹን በመገደብ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው እቅዱ፡፡ በምግብ ውስጥ ዋነኛዎቹ የስኳር መገኛዎች ጣፋጭ መጠጦች፣ ምግቦችና የፍራፍሬ ጭማቂዎች ናቸው ተብለዋል፡፡ አንዳንድ ጋዝ ያለባቸው መጠጦች ብቻቸውን እስከ 9 ማንኪያ ስኳር መገኛ እንደሆኑ ባለሙያዋ ይናገራሉ፡፡

 

የብሪቲሽ የጥርስ ህክምና ማህበር (BDA) መንግሥት የቀረበውን ምክር ከፊት በመሆን እንዲያስፈፅም ጥሪ አቅርቧል፡፡ የማህበሩ ፕሬዝዳንት ሚክ አርምስትሮንግ እንደሚሉት፣ የምግብ ኢንዱስትሪዎች የምርቶቻቸውን ገበያ ለማስፋፋት ከፍተኛ ስኳር ጥቅም ላይ እንደሚያውሉና በአንፃሩ ግን የደንበኞቻቸውን ጤና አደጋ ላይ እየጣሉ እንደሆነ መረዳት አለባቸው ብለዋል፡፡ አንድ ሰው በቀን በሚወስደው ካሎሪ የስኳር መጠኑ ከ5 በመቶ እንዳይበልጥ የቀረበው እቅድ ለምግብ ኢንዱስትሪዎች፣ ለመንግስትና ለማህበረሰቡ ፈተና መሆኑ እንደማይቀር ነው ባለሙያዎቹ ስጋታቸውን መቀየር ይፈልጋሉ? ተፅዕኖውንስ መቋቋም ይችሉ ይሆን? የሚለው ትልቁ የክርክር ርዕሰ ጉዳይ ነው፡፡

 

በሌላ በኩል የምግብ ኢንዱስትሪዎች፣ ስኳርን የመቀነስ ኃላፊነታቸውን መተግበር መጀመራቸውን ገልፀዋል፡፡ የዓም የጤና ድርጅት መመሪያ ደግሞ አዋቂዎችና ህፃናት በቀን ወደ ሰውነታቸው ከሚያስገቡት ኃይል መካከል ስኳር ከ10 በመቶ እንዲያንስ ይመከራል፡፡ በተጨማሪነት ደግሞ የቅነሳ ዘመቻውን በቀን ወደ 5 በመቶ ወይም 6 ማንኪያ ብቻ ወደ መውሰድ ማምራት ጀግንነት ይሆናል ይላል፡፡

 

ስኳር ላይ ታክስ ይጨመር

 

ከምግብ ባለሙያዎች በተጨማሪ የህክምና ዶክተሮችን ጨምሮ ሐሳቡን የሚያራምዱ አካላት፣ በዚህ ሳምንት ስኳር ላይ ታክስ መጨመርን በሚመለከት ድጋፋቸውን አሳይተዋል፡፡

 

የብሪቲሽ የህክምና ማህበር፣ በስኳር መጠጦች ላይ ቢያንስ 20 በመቶ ቀረጥ ቢጣል፣ ውፍረትን ለመዋጋት የተያዘውን የረዥም ጊዜ ግብ ለማሳካት አንድ እርምጃ ወደፊት መራመድ ማለት እንደሚሆን አስታውቋል፡፡ የዴቪድ ካሜሮን መንግስት ግን አሁንም የስኳር ታክስን በአጭር ጊዜ ውስጥ የመጨመር እቅድ እንደሌለው አስታውቋል፡፡

 

የመንግሥት ተወካዩ ሲሞንሰቴቨንስ እንደሚሉትም፣ ቀዳሚ እርምጃ ሊሆን የሚችለው የስኳር መጠጦችን ዋጋ ማናርና የኢንዱስትሪዎቹን ሰራተኞች ደመወዝ ከፍ ማስደረግ ነው፡፡ ይሄም ቤተሰቦችን፣ ህፃናትንና ዝቅተኛ ገንዘብ ተከፋይ ሰራተኞችን የሚደግፍ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ከምግብና ከመጠጦች ውስጥ ስኳርን የማስወገድ ወይም የመቀነስ እርምጃው የማይሰራ ከሆነ ተቆጣጣሪ አካል ጣልቃ ለመግባት ይገደዳል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

 

የዓለም የጤና ድርጅት መመሪያ፣ በፍራፍሬና አትክልቶች ውስጥ እንዲሁም በተፈጥሮ ወተቶች ውስጥ የሚገኘው ስኳር በጤና ላይ ስለሚያሳድረው አሉታዊ ተፅዕኖ ያለው ነገር የለም፡፡ በአሁኑ ወቅት በተለያየ አጋጣሚ የምንወስዳቸው ስኳሮች በፋብሪካ ውስጥ በተቀነባበሩ ምግቦች ውስጥ በድብቅ ተከማችተው የሚገኙ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ጠረጴዛ ላይ የሚቀመጥ አንድ ማባያ ወይም ካችአፕ በትንሹ 4 ግራም ወይም አንድ ማንኪያ ስኳር ይገኝበታል፡፡

 

ከፍተኛ የስኳር ተጠቃሚነት ከልክ ካለፈ ውፍረት እና እሱን ተከትለው ለሚመጡት ተላላፊ ላልሆኑት እንደ ደምግፊት፣ ስኳርና የልብ በሽታ ተጋላጭነት ምክንያት ነው፡፡ በቀን ውስጥ የሚያስፈልገንን ኃይል ለማግኘት የስኳር ሚና ከ5 በመቶ በታች እንዲሆን ወይም ከ3 የሻይ ማንኪያ እንዳይበልጥ ባለሙያዎች አስገንዝበዋል፡፡


አሜሪካ በነአቶ በቀለ ገርባ ጉዳይ ሥጋቷን ገለፀች

$
0
0

0A89D816-9714-441A-ACC5-93BF048CECC1_w987_r1_sየኢትዮጵያ መንግሥት የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር በሆኑት በአቶ በቀለ ገርባና በሌሎች ላይ የሽብር ፈጠራ ክሥ ለመመሥረት መወሰኑ በጥልቅ እንዳሳሰበው የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት አስታወቀ።

አገርንና ሕዝብን እያወረዱ ትናንሾችን ትላልቅ ማማ ላይ የሚያወጡት ተቃውሞዎቻችን (ሰርጸ ደስታ)

$
0
0

በቅድሚያ እነኳን ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል አደረሳቸሁ!!

1960s and 70s Ethiopian Student movement ፋኖ ተሰማራ …..

1960s and 70s Ethiopian Student movement ፋኖ ተሰማራ …..

ከ50ዎቹና 60ዎቹ የተማሪዎች ተቃውሞ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ እያደረግናቸው ያሉትን ተቃውሞና አመጾችን ሳስብ ብዙ ነገሮች ወደ አእምሮዬ መጡ፡፡ አላማቸውም ስድብና ማዋረድን መሠረት ያደረጉ እንጂ ጥያቄን ለማቅረብና የሚቀርበውም ጥያቄ በትክክል መልስ እንዲሰጥበት የሚታቀዱ አይደሉም፡፡ ብዙዎቻችን የእነዚህ ተቃውሞና አመጽ ተሳታፊ የሆንን ስሜተኝነት እንጂ የተቀውሞዎቻችን መሠረታዊ አላማዎችን ተገንዝበን አይመስለኝም፡፡ በዚህ ግርግር ግን ምንም ላልሆኑ ትንንሽ ሰዎች ሽፋን ሆነናቸው ዛሬ ለአገርና ሕዝብ አደጋ የሆኑበትን ጉልበት የሰጠናቸው ይመስለኛል፡፡ አሁን አሁን ይባስ መደማመጥ ጠፋ፣ ትንንሾቹ ተመቻቸው፡፡ አገርና ሕዝብን የሚያስቡት አንደበት አጡ፡፡ በአጠቃላይ ዝብርቅርቅ አልን፡፡ ውሉ የጠፋን መሠለኝ፡፡ ፖለቲካኛው፣ የሀይማኖት መሪው፣ ሁሉም ብቻ የአገርና ሕዝብ ተቆርቋሪ እየመሰለ የአእምሮ ብስለትንና ማሰብን በማይጠይቀው የተቃውሞና አመጽ ቃላቶችና ድርጊቶች ራሱን ዝነኛ ሲሳካለትም ትልቁ የሥልጣን ማማ ላይ ያስቀምጣል፡፡ በእነደነዚህ ያሉ ሰዎች የሚመራን ተቃዎሞና አመጽ  እየተከተልን ግርዱን ከገለባው መለየት ተሳነን፡፡ የአገርንና ሕዝብን ክብር በሚያዋርዱ አመጾች ተሳታፊ ሆንን፡፡ ግርግሩን እያበዛን ለትናንሽ ሰዎች እድል ከፈትን፡፡

በአገር ውስጥ ያለው ሕዝብ ውስጥ ውስጡን ከማጉረምረም ውጭ ብዙም ለመቃወም ዕድሉ ስለሌለው በዚህ ጉዳይ ብዙም አይወቀስም፡፡ ሲቃወምም ተቃውሞው መሠረታዊ እውነታዎችንና የሚፈልገውን ትክክለኛ ነገር ለመጠየቅ ነው፡፡ በእርግጥ በአገር ውስጥም ብልጣብልጦች ይህንኑ አጋጣሚ ወደራሳቸው ፍላጎት ይዘውሩበታል፡፡ ብዙም ጊዜ ሕዝብን ለሞትና ሥቃይ እያጋፈጡ እነሱ ከኋላ እያጨበጨቡ በመጨረሻ ሕዝብ ያነሳውን ጥያቄ አፈር አልብሰው አጋጣሚውን ለራሳቸው ዕድል መፍጠሪያ ሲያደርጉት አይተናል፡፡  ሆኖም አነሰም በዛ የአገር ውስጡ ተቃዎሞ የተሻለ አላማና ግብ አለው፡፡ የቱንም ያህል በብልጣብልጦቹ እየተንሻፈፈ ያለ ውጤት ቢቀርም፡፡ በውጭ አገራት ኢትዮጵያውያን ነን በሚሉ የሚደረገው ተቃውሞና አመጽ ግን መነሻውም መድረሻውም ወይ ስሜት ብቻ የሆነ ወይም ሆን ተብሎ አጋጣሚውን ሊጠቀሙበት በፈለጉ ሰዎች የሚመራ ነው፡፡  ለመሆኑ እነዚህ ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን የሚያነሷቸው አመጾችና ተቃውሞዎች እውን ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን በሌላው አለም እያዋረዱ መሆኑን ምን ያህሎቻችን ተገንዝበናል; እስኪ ለማስተዋል ይረዳን ዘንድ አንዳንደ ምሳሌዎችን ልጥቀስ፡፡ በተቻለ መጠን ብዙ ሰው የሚውቃቸው ወይም በቅርቡ ተከስተው የምናስታውሳቸውን እመረጣለው፡፡

ኢትዮጵያዎያን መሪዎች ሌላ አገር ሊጎበኙ ሲሄዱ እንደሌላው ከዜጎቻቸው አበባ የሚቀበሉበትን ቀን እየናፈቅሁ እስካሁን ባለው ጉዞአቸው በገጠሟቸውን ተቃውሞዎች ልጀምር፡፡

በቅርቡ ፕሮፌሰር ዓለም ሀብቱ ከተወዳጁ ጋዜጠኛ ካሳሁን ሰቦቃ ጋር በደረጉት ቃለ ምልልስ ንጉሱ አሜሪካንን ለመጎብኘት ሄደው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ሳይቀር ታግቶ እንደ ጠበቃቸው ነግረውናል፡፡ ዓለም ይህን ሲያወሩልን በኩራት ይመስል ነበር፡፡ እኔ ግን አመጾቻችንና ተቃዎሞቻችን አብዛኛዎቹ አገርና ሕዝብን የሚያዋርዱ መሆኑን ያስተዋልኩት ይሄን ስሰማ ነው፡፡ ልብ በሉ እነ ዓለም ያደረጉት ተቃውሞ ትላልቅ የትምህርት ዕድል የፈጠሩላቸውንና እንደዛሬው በለማኝነት ሳይሆን እንድ ንጉስ ልጅ እየታዩ እንዲማሩ የላኳቸው ንጉስ እየተማሩበት ያለውን አገር ሊጎበኙ ሲመጡ የገዛ ንጉሳቸውን ለባዕዳን ለማሳጣት ነው፡፡ እኔን እንደሚገባኝ በዛን ዘመን ከዚህ በተቃራኒው እነ ዓለም ንጉሱን የሆነ መድረክ ፈጥረው በስነሥርዓቱና በክብር ሊጠይቁ የሚፈልጉትን ነግር ማቅረብ ይችሉ ነበር፡፡ ጥያቄያቸውም የሚፈለገውን ውጤት ማምጣት በቻለ ነበር፡፡ በተማሪዎቹና በንጉሱም መካከል የበለጠ መቀራረብን አገርና ሕዝብን ለመምራት ዕድል የሚፈጥሩበትን፣ በአባትና ልጅነት ሊወቃቀሱ፣ ሊተራረሙ፣ ሊወያዩ የሚችሉበትን አጋጣሚ መፍጠር ይችሉ ነበር ባይ ነኝ፡፡ አሁንም እኔን እንደሚገባኝ ንጉሱ አሁን እንዳሉት ባለስልጣኖቻችን ለሕዝባቸው ሩቅ አልነበሩም፡፡ እንኳንስ ራሳቸው ንጉሱ መርጠው የላኳቸው በሚገበኙበት የሰው አገር ያሉ እንደብርቅ የሚታዩ ጥቂት ተማሪዎቻቸውን ቀርቶ አገር ውስጥም ያሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ለማበረታታት በብዙ በድረኮች እየተገኙ ሲያናግሩ፣ ሽልማት ሲሰጡ እናያለን፡፡  ይህ አይነቱን ቅርርቦሽ ከደርግም ከኢሕአዴግም ባለስልጣናት አላየንም፡፡ እንግዲህ እንዲህ ቀርቦ የማነጋገርና ለጥያቄያቸውም ውጤታማ የሆነ መልስ ማግኘት የሚችሉት የእነ ዓለም ዘመን ተማሪዎች ነበሩ በዓም ሳይቀር ከፍትኛ ክብር የሚሰጣቸውን ለእነሱም እንደ ክብር የሆኑትን ንጉሳቸው የሚማሩበትን አገር ሊጎበኙላቸው ሲሄዱ ነበር በባዕዳን ፊት ለማዋረድ የተቃወሟቸው፡፡ እነ ዓለም አበባ በመያዝ፣ ቀይ ግምጃ በማነጠፍ ተቀብለው የሚፈልጉትን ነግር ቢጠይቁ ጥያቄያቸውም ዋጋ አግኝቶ እስከዛሬም ላለንው ተምሳሌት በሆነን፡፡ በወቅቱ እነ ዓለም ወጣትነቱም ስላለ ይህን ማስተዋል ዘንግተውታል ብዬ ለማሰብ ሞከርኩና ዛሬ ወደ አረጋዊነቱ ዕድሜ ያሉት በትምህርትም ትልቅ የተባሉት ዓለም ሀብቱ ያንን አመጽ ዛሬም እንደ ዝና ሲያወሩት አዘንኩ፡፡ በተቃራኒው ትክክል እንዳልሆኑ ቢነግሩንና ቁጭታቸውን ቢገልጹልን ለብዙዎች ትምህርት በሆነ እላለሁ፡፡

በደርግ ባለስልጣን በየትኛው ላይ በውጭ አገር ተቃውሞ እንደደረሰበት አላውቅም፡፡ ለነገሩ የደርግ ባለስልጣናት ብዙም ውጭ አገር አይሄዱም መሰለኝ፡፡ ከሄዱም ወዳጅ አገር ነው፡፡ እዛ ደግሞ መቃወም የሚፈልግ እንኳን ቢኖር የሚችል አይመስለኝም፡፡ መከባበሩም ጥሩ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ዛሬ ያሉት የኢሕአዴግ ባለስልጣናት ግን ትንሹም ትልቁም በተለይ በአውሮፓና ሰሜን አሜሪካ በሄደበት አገር ሁሉ ማት ይቻላል ያለ ተቃውሞ በደህና ወደ አገሩ አይመለስም፡፡ ሟቹ ጠ/ሚኒስቴር መለስ ወደ መጨረሻ ስልጣን ዘመናቸው አካባቢ በአሜሪካን አገር በእንድ በእንግድነት የተጋበዙበት ስብሰባ ላይ ቃለ ምልልስ እየተደረገላቸው በስብሰባው አዳራሽ በተገኘ በአንድ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ የተደረገባቸው የተቃውሞ ድምጽ ብዙዎች የምናስታውሰው ነው፡፡ በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ይህ ጋዜጠኛ እንደ አንድ ልዩ ጀግና ተወድሷል፡፡ አመጽንና ሁከትን እንዲያወግዙ የክርስቶስን ስልጣን የተሸከሙ ትላልቅ የእምነት አባቶች ሳይቀር ጀግና በሚል ምህረት በሚነገርበት አወደ ምህረት ይህን ጋዜጠኛ አቆመው ሲያወድሱት ሰምተናል፡፡ ትልቅም ተጽዕኖ እንደፈጠረ ብዙዎች ያወሩለታል፡፡ አንዳንዶች እንደውም ጠ/ሚኒስቴሩን ወደሞት የወሰዳቸው በሽታ ራሱ የለከፋቸው በዚህ ጋዘጠኛ በተፈጠረ ድንገተኛ ድምጽ ድንጋጤ ነው ብለው ያምናሉ፡፡  በወቅቱ የነበረውን ምስል በትክክል እንደተመለከትነው ግን እውነታውና አንደምታው ከዚህ በተቃራኒው ነው፡፡ ጋዜጠኛው ይህን ድምጽ ሲያሰማ መድረኩን ይመራው የነበረው የተናገረው ጋዜጠኛውን ከጤነኞች አሳንሶ ነው፡፡ እርግጥም የተለመደውን ጨፍጫፊ፣ ገዳይ፣ እነሱ እንዲሰሙት ኪለር፣ ቡቸር ምናምን የሚሉ ጩኸቶች እንጂ በትክክል የተረጋጋ ሰው የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች አይደለም፡፡ ሌላው እውነታ መለስን እንኳን ለሞት የጠራቸውን በሽታ የሚያስለክፍ ድንጋጤ የፈጠረባቸው ሳይሆን የተከሰተውን ነገር ምንም እንደሆነ ሳይቆጥሩ እየተናገሩ የነበረውን ንግግራቸውን በተረጋጋ ሁኔታ ሲቀጥሉበት ነው፡፡ በእርግጥም ስንት አስደንጋጭ ድምጽ ያለፈ ሕወት ያላቸው መለስ እንዲህ ያለ የሰው ጩኸት ቢያስደነግጣቸው ነበር የሚገርመው፡፡ ይህ እንደሆነ አድርገው በምስል በማቀናበር ያቀረቡልን አሁንም የአመጻን ውጤት ናፋቂቆች ነበሩ፡፡  እዚህም ጋር ከላይ እንዳነሳሁት እንደ ንጉሱ ቀላል ባይሆንም መለሥንም ቀርቦ ለማናገር ዕድሉ ሙሉ በሙሉ ዝግ ነበር የሚል እምነት የለኝም፡፡ እንደውም የተጋበዙበትን መድረክ እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም በክብር ቀርቦ ጥያቄዎቹን በግል ቢያቀርብላቸው መለስም ቢሆኑ ጥያቄውን የሳንሱበታ የሚል እምነት የለኝም፡፡  በወቅቱ ደግሞ መለስ እውንም ከብዙ ዘመን በኋላ ወደ ሀገርና ሕዝብ ያደሉ መስለው በሚታዩበትም በሕዝብም ዘንድ ተሰሚ እየሆኑ የመጡበት ወቅት ነበር፡፡  ብዙ አገር ቤት ያለውም ሕዝብ የጋዜጠኛውን ድርጊት የተቀበለው ሌሎች እንዳደረጉት በውዳሴ ሳይሆን በውግዘት ነበር፡፡ የቱንም ያህል ክፉ ቢሆን እንድን የአገር መሪ በባዕዳን ፊት መሳደብና ማዋረድ አገርንና ሕዝብን ማዋረድ እንጂ ግለሰቡን ነው የሚል እምነት የለኝም፡፡

በየጊዜው በተከሰቱት በኢሕአዴግ ባለስልጣናት ላይ የተደረጉ ተቃዎሞዎች ብዙ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ ባለስልጣናትን እንደውም አገር ቤት ያለው ሰው አያውቃቸውም እና ብዙም ትርጉም የሚሰጡም አይደሉም፡፡ በዚሁ ወር በዩቲዩብ ተለቆ ያየሁት በውጭ ሚኒስቴሩ ዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖም ላይ በሲዊዲን አገር የገጠመው ተቃውሞ ለግንዛቤ እንዲረዳ እዚህ ሊንክ ላይ ብታዩት ጥሩ መስሎ ታየኝ https://www.youtube.com/watch?v=WJpYqNrXCt8  ብዙ የሚያበሳጩን የኢሕአዴግ ባለስልጣናት አሉ፡፡ ቴድሮስ ግን አነዚህ ምድብ ውስጥ ናቸው የሚል እምነት የለኝም፡፡ ይልቁንም በብዙ ነገራቸው በሕዝብ ዘንድ መወደድን ያፈሩ የኢሕአዴግ ጥቂት ባለስልጣናት አንዱ ናቸው፡፡  ለብዙዎቻችን ያልተገለጸልን ድክመጽ ሊኖርባቻ ይችላል፡፡ ሆኖም መናገር የምንችለው የምናውቃቸውን ያህል ቴድሮስ ሕዝባዊ ከሁኑ በጣም ጥቂት የኢሕአዴግ ባለስልጣናት አንዱ ለመሆናቸው ብዙ በተግባር የታዩ ሥራዎቻቸውን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ቴዎድሮስ የሚታወቁባቸው ብዙ በጎ ነገሮች አሉ ከሁሉም ግን የዛሬ አመት አካባቢ በሊቢያና ደቡብ አፍሪካ በደረሰቡን አደጋዎች ከሕዝብ ጋር ለማዘን ሕዝብ መካከል የተገኙ ባለሥልጣን ቴደሮስ ነበሩ፡፡ ይሄ ጉዳይ ቴድሮስ ለማስመሰል ያደረጉት ነገር አልነበረም፡፡ ይሄ ተፈጥሮአዊ ባሕሪያቸው ወይም በብዙ ልምምድ በሕወታቸው ያዳበሩት እንጂ፡፡ በወቅቱ አንዳንደ የኢሕአዴግ ባለስልጣናት ቤተሰብ ሐዘን ተቀምጦ እያጣራን ነው ብለው ያፌዙብን በሐዘናችን ላይ ሐዘን፣ ሕመም ጨምረውብን እንደነበር እናስታውሳለን፡፡ ይህንኑ ድርጊት ለማውገዝ ሰላማዊ ሠልፍ ወጥተን ብዙ ልጆቻችን በመረረ ሐዘናቸውና በብሶታቸው ቀን የፓርቲ አባል ታርጋ ተለጥፎላቸው ለእስር ተዳረገው እንደነበርም፡፡ እንደ መንግስት፣ የሐዘኑ ባለቤት፣ የሕዝብ እንደራሴንት በእንዲህ ያለው ቀን የሚነሳ የትኛውንም የሕዝብ ተቃውሞ አሜን ብሎ መቀበልና ሕዝብን ከሐዘን ለማረጋጋት ሁሉንም አማራጭ መጠቀም ሲቻል ማለት ነው፡፡ በዚህ ወቅት ነበር ቴደሮስ ሐዘን ወደተቀመቱ የሟች ቤሰቦች በአካል ሄደው ለማጽናናት በግላቸው ትልቁን ሚና የተጫወቱት፡፡ ከዚያ በኋላ ዜጎችን ከየአገሩ ለማስመለስ፡፡ የሄ እንደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርነታቸው ግዴታቸውም ነበር፡ ግዴታውን የሚወጣ በራሱ ትልቅ ከበሬታ ይገባዋል፡፡ የግብጹ መሪ አልሲሲ የእኛን ልጆች በአውሮፕላን ጣቢያ ተገኝተው እንዳጽናኑት የእኛው ጠ/ሚኒስቴር አላደረጉትም፡፡ በወቅቱ እንደ ተባለው ቴዎድሮስ ለሕዝብ ባደረጉት ቀረቤታ ጭራሽ ከሌሎች ባለስልጣናት ወግዘት ገጥሟቸው ነበር፡፡ ብዙዎች የኢሕአዴግ ባለስልጣናት እንዲህ ያለ ሕዝባዊነት ያማቸዋል፡፡ እነሱ ሕዝቡን መቅረብ ስላልቻሉ የሚቀረበው አይመቻቸውም፡፡ ከዚህም በተረፈ ቴድሮስ በነበሩባቸው የሚኒሰቴር መ/ቤቶች ሁሉ ትልቅ ለውጥ አምጥተዋል፡፡ ቀድሞ የነበሩበት የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በርካታ ሥራዎችን ያሳከዋ በእሳቸው ነው፡፡ አሁን ያሉበት መ/ቤትም አገሪቱ ውስጥ ካሉ መ/ቤቶች ለሕዝብ ክፈትና በፍትሐዊነቱ የሚመሰገን ነው፡፡ የኢሕአዴግ ባለስልጣን በመሆናቸው ካልተባለ ቴዎድሮስ ለብዙዎች መዳን ምክነያት ሆነዋል እንጂ ሞት አልሆኑም፡፡ ኪለር፣ መርደረር፣ ምናምን የሚባሉ ቃላቶች ለቴድሮስ አይደሉም፡፡ በባዕዳን ፊት እንዲህ ያሉ አገርን ወክለው በተገኙ ባለስልጣናት ላይ እንዲህ የሉ እነሱን ያዋረድንባቸው የመሰሉን ስድቦች አገርንና ሕዝብን ራሳችንንም እያዋረድን እንደሆነ አስባለሁ፡፡ ከላይ ከአስቀመትኩት ምስል እንደምንረዳውም ቴድሮስ የሚቃወሟቸውን እጃቸውን በማውለብለብ ሰላምታ ሰጥተው ወደተዘጋጀላቸው መኪና ሲገቡ ነው፡፡  እንደ እኔ ቴድሮስ ኢሕአዴግ ውስጥ ካሉ መልካም ባለስልጣን ከጥቂቶቹ አንዱ ናቸው ባይ ነኝ፡፡ እንግዲህ እንዲህ ተቃውሟችን እንኳን እንዲህ ሁሉንም በጅምላ እየሆነ ጥሩውን ከመትፎው መለየት ሳንችል እንዴት ለውጥ ይመጣል፡፡ እኚህ ሰው የሚነቀፉበት ነገር ቢኖር እንኳን በጎ ነገራቸ ተመስግኖ የሚነቀፉበትን አብሮ ማቅረብ ሚዛናዊነት ነው፡፡

እኝሁ ባለስልጣን በቅርቡ ለተባበሩት መንግስታት ጤና ድርጅት ትልቅ ኃላፊነት እንደታጩ ሲወራ ብዙ ተቃውሞዎች ተደምጠዋል፡፡ ቴዎድሮስ ከላይ እንደገለጽኳቸው በመልምነታቸው የሚታወቁ ሲሆን፡፡ ይህም ባይሆን እንኳንና ቴድሮስ አምባገነን ሆነው እድሉ ተገኝቶ በተባለው ድርጅት ከፍተኛ ስልጣን ቢያገኙ እንደ ኢትዮጵያዊነቴ ደስተኛ ነኝ፡፡ መቼም እኚህ ሰው የለ አንዳች ነገር ለዚህ ቦታ አይታጩም፡፡ ተሳክቶላቸውም የተባለው ቦታ ላይ ቢደርሱ እኮ የሚወክሉት ኢሕአዴግን አይደለም፡፡ እንደ ኢትዮጵያዊነታቸው ኢትዮጰያን እንደ ተባበሩት መንግስታት ወኪልነታቸው ለኢትዮጰያም ክብር የሚሆናትን ኃላፊነት ነው፡፡ እንዲህ ያለውን  ነገር ታዲያ በምን መስፈርት ሊቃወሙት ይቻላል፡፡ መቃወም ልማዳችን ስለሆነ እንጂ ከአገር ክብር አንጻርስ ይህን የመሠለ እድል ለኢትዮጰያዊው መሠጠቱ የቱንም ያህል ክፉ ቢሆን ስህተት ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡

ሌላው በብዙ መልኩ የተሻለ ነበር ብዬ የየሁት ግን እሱም ያላስደሰተኝ በኦሮምያ በቀርቡ ተከስቶ የነበረውን ተቃውሞ ተከትሎ በልጆቻችን ላይ በደረሰው ግድያና እስራት ምክነያት በአንድ ስብሰባ መድረክ ላይ በአሜሪካን የኢትዮጵያ አምባሳደር በሆኑት ግርማ ብሩ ላይ የተደረገው ተቃውሞ ነበር፡፡ እንዳልኩት ጥያቄውም ስሜትን የሚነካ ከመሆኑም አንጻር የዚህን ተቃውሞ ስነስርዓት ወድጄው አሁንም መደማመጥና አመባሳደሩንም እድል የሰጠ ቢሆን መልካም ነበር፡፡ ሆኖም እስከተከታተልኩት ምስል ድረስ ስድብና ማዋረድ የሌለበት በመሆኑ አድንቄዋለሁ፡፡ ምን አልባትም እንዲህ አይነቱ ተቃውሞ በስድብና ማዋረድ  ትልቅ የሚሆኑ ለሚመስላቸው ጥሩ ምሳሌ ሊሆን ይችላል፡፡ በተለይም ተናጋሪዎቹ ጥያቄያቸው ተጽኖ ፈጥሮ ቢሆን፡፡ የዚሁኑ ልጆቻችን ለሞትና ሌሎች እንግልቶች የተዳረጉበትን የኦሮምያ አመጽን ተንተርሶ አንዳንደ ግለሰቦች የራሳቸውን ገበያ እንደፈጠሩበት ታዝበናል፡፡ ምንም እውቀት የሌላቸው ተራ ግለሰቦች ትልቅ ጆሮ አግኝተው ዋና ተንታኝና መሪ ሆነውበት አይተናል፡፡ ለዚህ ደግሞ ዋናው ምክነያቱ ኢሕዴግን መቃወም በሚል በሳልና ሰከን አስተሳሰብ ያላቸውን ምሁራንና የሕይወት ልምድ ባለቤት ግለሰቦቹን እያራቀ በግርግር የራሳቸውን ሕልም ለማሳካት ለሚጥሩ የተመቻቸ ፖለቲካ ስለምንከተል ነው፡፡ እንዲ ያሉ መርሆዎች 40 ዓመት ሙሉ ብዙ እዳ ውስጥ ከተወውን ዛሬም ማሰብ አልቻልንም፡፡

የከፋው የተቀውሞና አመጽ ልክፍት ቀስ እያለ ቀድሞ እንፈራው በነበረ አምልኮ ስፍራም አሁን አሁን መታየት የተለመደ ነገር ሆኗል፡፡ አሁንም ይህ ተቃውሞና አመጽ በዝተን በምንገኝበት በአሜሪካ የጎላ ሲሆን አገር ውስጥ ጨምሮ በሌሎች አገሮችም ይታያ፡፡ አንዳንዴ ሳስበው እንደውም ሌላ ቦታ ያሉ ተቃውሞዎቻችን ይሻላሉ፡፡ ቤተመቅደስ ውስጥ መሳዳደብ አልፎም መደባደብ እውን የምናያቸው ክስተቶች ሆነዋል፡፡ እንዲህ ነው እንግዲህ፡፡ እግዚአብሔርን ለማወቅ ባለፈለጉት መጠን የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው የሚለው የፈላስፋው የቅዱስ ጳውሎስ ንግግር ትንቢት ሆኖ እኛው ላይ ደረሰ፡፡

በአጠቃላይ ሲታይ ተቃውሞዎቻችንና አመጾቻችን የአገርንና ሕዝብን ጥያቄ የሚያነሱ ሳይሆን አጋጣሚውን ለመጠቀም አሰፍስፈው ላሉ አደገኛ ሰዎች እድል የሚሰጡ ሆነው አያቸዋለሁ፡፡ እኛ የአገርና ሕዝብ ክብር የሚለው ነገር ከአእምሮአችን የጠፋ ይመስለኛል፡፡ አሁን ያሉት የሕንድ ጠ/ሚኒስቴር ናረንድራ ዲሞዳርዳስ ሞዲ ስልጣን የያዙ ሰሞን በአሜሪካ አድርገውት የነበረው ጉብኝትና በዜጎቻቸው የተደረገላቸው አቀባበል እንዴት አስቀንቶኝ ነበር፡፡ በእርግጥ ሞዲ ፍጹም ዲሞክራሳዊ በሆነ ምርጫ ስልጣን የያዙ ሰው ናቸው፡፡ እንዲህም ቢሆን እኛ ብንሆን የሚቃወማቸው ይኖራል የሚል ግምት አለኝ፡፡ በአሁኑ ወቅት ባለስልጣኑ በተገኙበት አገር ሁሉ ፋናቸውን እየተከተል የሚቃወም እንደ እኛ ያለ አይመስለኝም፡፡ ምን አልባትም በተለይ በሰሜን አሜሪካ እንደ እኛ የአገርንና ሕዝብን ጉዳይ ያገባኛል በሚል ፖለቲከኛ የሆነ ያለ አይመስለኝም፡፡  ሌሎች ካልተደሰቱ እንኳን ዝም ይላሉ፡፡

ሌላው እኛ ከሌሎች ሕዝብች አንጻር እርስ በእርስ ምቀኞች ሳንሆን አይቀርም በዚሁ ሳምንት በተወዳጁ ጋዜጠኛ ካሳሁን ሰቦቃ ተጋብዘው የነበሩት ዶ/ር ተሾመ አበበም እርስ በእርስ ያለን ምቀኝነት ትልቁ ችግራችን እንደሆነ ይጠቁማሉ፡፡  ከብዙ ሌሎች ሰዎችም የሰማሁት ይሄንኑ ነው፡፡ ከ25 ዓመት በላይ ውጭ አገር የሚኖር እንድ ሰው በሚኖርበት አገር አግኝቼው የነገረኝ አበሻ ምቀኛ ነው ብዙም አትቅረበው የሚል ነው፡፡ አንድ እንደ ቀልድ የሚነገር የእኛ ነገር ትዝ አለኝ እግዚአቤሔር ሰውን ሁሉ የምትፈልገውን ነገር ሁሉ ጠይቀኝ ለጓደኛህ ግን ሁለት እጥፍ ነው የምሰጠው ብሎ ይጠይቃል፡፡ ሁሉም እኔ የፈለኩትን ካገኘሁ ሌላው ለምን አስር እጥፍ አያገኝም እኔን ምን አገባኝ እያለ የሚፈልገውን እየጠየቀ ድርሻውን እየወሰድ ሐበሻ ጋር ደረሰ ሐበሻው ይህን ሲሰማ እጅግ ጨነቀው፡፡ የጓደኛው እጥፍ ማግኘት አስጨነቀው፡፡ ታዲያ በደንብ አሰበና አንድ አይኔን አጥፋው ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ ይባላል፡፡ አስደንጋጭ ነው እውንም እንዲህ ያለ ባሕሪ አለን ማለት ነው፡፡ ከራሳችን ማግኘት የጓደኛችን ማጣት የሚያስደስተን ነን;

ሌሎች ከእኛ የተለየ ባሕሪያቸው በፖለቲካ እርስ በእርስ ተቃዋሚ የሚሆኑት በመሠረታዊ አላማዊ ልዩነት እንጂ ከግል ቂም በቀል ጋር አይያያዝም፡፡ መድረክ ላይ በትር ሊማዘዙ ነው ያልናቸው ተቃዋሚዎች ከሰብሰባው ሲወጡ አብረው በጓደኝነት ምሳ የሚበሉ ናቸው፡፡ እኛ ጋር ያለው እርስ በእርስ የምንተያየው በጠላትነት ነው፡፡ ሲጀምር እኛ የምናነሳቸው ጉዳዮች አብዛኞቹ የአገርና የሕዝብ ጉዳይ እንዳልሆኑ አሁን በጣም አየታዘብን ነው፡፡ ሁሉም ተማርን የሚሉ ሰዎች የየግል ወይም የቡድን ፍላጎት እንጂ አገርንንና ሕዝብን መሠረት ያደረጉ እንቅስቃሴዎች በእኛ ፖለቲከኞች አይደረግም፡፡ እውነታው ተቃዋሚውም ገዥውም ብዙ የአላማ ልዩነት የላቸውም፡፡ ሌዩነታቸው የጥቅምና የሥልጣን ሽሚያ ላይ ነው ባይ ነኝ፡፡ አገርና ሕዝብ የሚፈልጉት ግልፅ ነው፡፡ ለማት፣ፍትሕ፣ አስደዳራዊ በጎነት፡፡ ከዚህ ውጭ ያሉት የብሔረሰብም በሉት፣ ፌደራል ምናምን የሚባሉት ጥያቄዎች የኢትዮጵያና ሕዝቦቿ ጥያቄ ሆኖ አያውቅም፡፡ ፍትህ፣ መልካም አኗኗርሩን፣ ደህንነቱን የሚጠብቅለት መንግስት ሕዝቡ ይናፍቃል፡፡ እነዚህ ጉዳዮች ግን ሌሎች የሕዝቡ ባልሆኑ ተማርን በሚሉ ሰዎች በሚቀርቡ ጥያቄዎች ተጋርደው ዛሬም ድረስ ሕዝብ በሥቃይና ድህነት ይኖራል፡፡

መልካም የትንሳኤ በዓል!

እግዚአብሔር አምላክ አገራችንን ኢትዮጵያን ይባርክ! አሜን!

ሰርጸ ደስታ

 

 

 

 

 

 

 

Hiber Radio: በኢትዮጵያ በኑሮ ውድነቱ ሳቢያ በዓል ብዙሃኑን ሕዝብ የሚያሳቅቅ መሆኑ ተገለጸ፣ ኢትዮጵያ ሰራዊቷን በ/ደ/ሱዳን ግዛት ውስጥ እንዳታስገባ የአገሪው ማህበረሰብ ተወካዮች አጥብቀው አስጠነቀቁ፣ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ገዚዎች ዛሬም ቀንደኛ የነጻ ፕሬስ ጠላቶች ተብለው ተፈርጀዋል ሌሎችም

$
0
0

የህብር ሬዲዮ ሚያዚያ 23 ቀን  2008 ፕሮግራም

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


ለክርስትና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ትንሳዔው አደረሳችሁ

…በዓሉ ለብዙሃኑ ሕዝብ የሚያሳቅቅ ነው።የኖሮ ውድነቱ የሕዝቡን መቸገር ታዋለህ። ይህ ሲባል ዓመቱን በሙሉ በዓል የሆነላቸውጥቂቶች አልተፈጠሩም ማለት አይደለም። ሙስናውና ለስርዓቱ ማጎብደድ እነዚህን ፈጥሯል…የኢትዮጵያ ትንሳዔ ቅርብ ነው ሊነጋ ሲልይጨልማል የሚባለው ለዚህ ነው።ተመልከት በኢትዮጵያ አሁን ሞቱም፣እስሩም ፣ረሃቡም ሁሉም ተከታትሎ እየመጣ ነው። ከዚህ በሁዋላየሚመጣው ብሩህ ቀን ነው።ያ እንዲመጣ ግን እያንዳንዱ…; ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ የአዲስ ገጽ ዋና አዘጋጅ የዘንድሮ በዓልንና የብዙሃኑንኑሮ በተመለከተና ተያያዥ ወቅታዊ ጉዳዮችን ላይ ተወያይተናል (ሙሉውን ያዳምጡት)

…ከሁለት ሳምንት በፊት ሜዲትራኒያን ባህር ላይ ከሰጠሙ ወገኖቻችን ወዲህ ሌሎች ሁለት መቶ ሰዎች ሄደዋል ይባላል መረጃ ማግኘትይከብዳል ሰው አማራጭ ስላጣ ያንን መንገድ ይከተላል  …ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር ለኢትዮጵያውያን ስደተኞች ጉዳይ ትኩረት አይሰጥም። እኛንመስማት አይፈልግም ችግራችንን እየተረዳ አይደለም..; አቶ እንዳልካቸው ይልማ በግብጽ የኢትዮጵአውያን ስደተኞች ማህበር ም/ጸሐፊ  ለህብር ከሰጡት ማብራሪያ(ሙሉውን ያዳምጡት)

እየተሟሟቀ  እና አየተካረረ የመጣው የአሜሪካዊያን  የ እጩ ፕሬዘዳንታዊ  ምረጡኝ   የቅሰቀሳ ዘመቻ ሰሞናዊ  ውሎው ፣ የጫረውአግራሞት  ፣ቱጃሩ  ዶናልድ ትራምፕ ለተቃዋሚዎቻቸው የላኩት የመጨረሻው መልእክት ምን ይላል?፣እውን ዶናል ትራምፕ በጸረ ሙስሊሞች እና በጸረ ሰደተኖች አቋማቸው  ይገፉበት ይሆን? ፣ የቅደሞዋ  የወጪ ጉ/ሚ/ር ሂለሪ ክሊንተን  ተፎካካሪያቸው በርኒ  ሳንደረስንለምን አወደሷቸው ?(ልዩ ዘገባ)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

በኢትዮጵያ በኑሮ ውድነቱ ሳቢያ በዓል ብዙሃኑን ሕዝብ የሚያሳቅቅ መሆኑ ተገለጸ

ኢትዮጵያ  ሰራዊቷን በ/ደ/ሱዳን ግዛት ውስጥ እንዳታስገባ የአገሪው ማህበረሰብ ተወካዮች አጥብቀው አስጠነቀቁ

ከግብጽ ተጨማሪ ሁለት መቶ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በባህር ለመሻገር መሄዳቸው ተሰማ

ዓለም አቀፉ የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር ለኢትዮጵአውአን ስደተኞች ትኩረት እንደማይሰጥ ተገለጸ

በቅርቡ ከጋምቤላ ታፍነው ወደ ደ/ሱዳን ከተወሰዱት 125 ጨቅላ ህጻናት  ውስጥ 32ቱ በገፍ ተጥለው  ተገኙ

የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ገዚዎች  ዛሬም ቀንደኛ   የነጻ ፕሬስ  ጠላቶች ተብለው ተፈርጀዋል

የዞን 9 ጦማሪዎች እና ጋዜጠኞች የአምቱ የተሸላሚዎች ምርጫን አሸነፉ

16 ኪሎ የሺሻ ቱምባሆን  በህገወጥ መንገድ ወደ ም/አወሮፓ ለማሰገባት የሞከረች ኢትዮጵያዊት ለአስራት ተዳረገች

በጋምቤላ ለተፈጠረው ችግር የስርዓቱ ባለስልጣናት ግንባር ቀደም ተጠያቂ መሆናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች በስብሰባ ላይ ገለጹ

ግብጽ በተመሳሳይ ጾታ  ግንኙነት ፈጻሚዎች ላይ ከባድ ቅጣት ጣለች፥አለማቸውን ሲቀጩ የነበሩ የድርጊቱ ፈጻሚዎችንም በካይሮ ጎዳናዎች ላይ አራቁትታቸውን አንዲሂዱ  አድርጋለች

የጎርቤት ሶማሊዎች በ ኢትዮጵያ የልዩ ሃይል ታጣቂዎች  በደል እና ስቃይ አየድረሰብን ነው ሲሉ አማረሩ

ሁኔታውን ለማርገብ የአገዛዙ ባለስልጥናት ወደ ስፍራው ሊጓዙ  መሆኑ ተነገረ

ዘንድሮም የበዓል ገበያ በአገር ቤት እንደተወደደ አለፈ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Video: ኃይሌ ገብረስላሴ ጀነራል ጃጋማ ኬሎን ለዓመት በዓል ቤታቸው ሄዶ ጠየቀ |እናመሰግናለን ኃይሌ

$
0
0


Video: ኃይሌ ገብረስላሴ ጀነራል ጃጋማ ኬሎን ለዓመት በዓል ቤታቸው ሄዶ ጠየቀ | እናመሰግናለን ኃይሌ
Haile

Video: በጣም አስቂኝ የታዋቂ ሰዎች የሙዚቃ ውድድር

$
0
0

Video: በጣም አስቂኝ የታዋቂ ሰዎች የሙዚቃ ውድድር

Netsanet

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live