Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ለሰማያዊ እና አንድነት ፓርቲ ድጋፍ ለማሳየት ነገ በዋሽንግተን ዲሲ ሰላማዊ ሰልፍ ተጠራ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በአሁኑ ወቅት በሃገር ውስጥ ትግልጉልህ ሚና እየተጫወቱ ላሉት የሰማያዊ ፓርቲ እና የአንድነት ፓርቲን ለመደገፍ እንዲሁም በኢትዮጵያ ውስጥ ካለማቋረጥ እየተፈጸመ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት ለአለም ሕዝብ እና ለአሜሪካ መንግስት ለማሳወቅ ነገ ማክሰኞ ሴፕቴምበር 3 በዋሽንግተን ዲሲ የሰላማዊ ሰልፍ ተጠራ። የሰላማዊ ሰልፉ ጥሪ ፍላየር ሁሉንም መረጃ ይዟል – ይመልከቱት።
Rally to show solidarity to Semayawi and Andinet party members and protest Human Rights Violations by the regime – Tuesday Sept 3-2013 9AM US Department of StateSemayawi and Andnet solidarity and human rights vioaltions rally (2)


በሰማያዊ ፓርቲ ላይ የተወሰደውን ህገ-ወጥ ርምጃ አጥብቀን እናወግዛለን!!! ከአንድነት ለዴሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ (አንድት) የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

$
0
0

ከአንድነት ለዴሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ (አንድት) የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም ሰማያዊ ፓርቲ የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ አስመልክቶ የተወሰደበትን ሕገ-ወጥ ርምጃ አጥብቀን የምንቃወም ሲሆን፤ ይህንን የፈፀሙ አካላትም በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን፡፡

እንደሚታወቀው ሰማያዊ ፓርቲ ከአንድ ወር አስቀድሞ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱን እንዳሳወቀ የሚታወስ ሲሆን በተመሳሳይ ቀንም የሀይማኖቶች ጉባኤ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱ መገለፁ አደናጋሪ ነበር፡፡ ይህንን የሁለት አካላት የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄ በሰከነ መንገድ የአዲስ አበባ መስተዳድር መፍታት ሲገባው ችግሩ እንዲከር አድርጓል፡፡ ይህም የገዥው ፓርቲ የፖለቲካ ምህዳሩን የመዝጋትና የማናለብኝነት አንዱ መገለጫ ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ቅዳሜ ምሽት በሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ላይ የተፈፀመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት በሰላማዊ ትግሉ ላይ እየተፈፀመ ያለ ርምጃ ነው፡፡ የፀጥታ ሃይሎች የወሰዱት የማገት፣ የማፈንና የመደብደብ ርምጃ አሳፋሪ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ ፀጥታ አስከብራለሁ የሚለው የፖሊስ አካል መብትን በድብደባ ለማስቆም የሄደበት መንገድም ህገ-ወጥ ነው፡፡ ስለዚህ ፓርቲያችን አንድነት መንግስት እያካሄደ ያለውን የአፈናና የጉልበት ርምጃ አቁሞ አሁንም ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታና ለሰብዓዊ መብት መጠበቅ ቅድሚያ እንዲሰጥ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብም ህገወጥነትን መቃወሙን አጠናክሮ በመቀጠል የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ እየተካሄደ ያለውን ሰላማዊ ትግል እንዲደግፍ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

ዘላለማዊ ክብር ለኢትዮጵያ!!!
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ
ነሐሴ 27 ቀን 2005 ዓ.ም

አዲስ አባባ

UDJ

በመንግስታዊ ውንብድና ትግላችን አይገታም! ሰማያዊ ፓርቲ

$
0
0

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም. ባካሄደው ታላቅ ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ለመንግሥት ያቀረባቸው ጥያቄዎች አስፈላጊው ምላሽ እንዲሰጣቸው በመጠየቅ ይህ ካልሆነ ግን ከሦስት ወር በኋላ ተቃዉሞውን ከፍ ባለ ደረጃ እንደሚያቀርብ በመጋለፅ ሰልፉን አጠናቋል፡፡ ለተነሱት ጥያቄዎች የተገኘ ምላሽ ባለመኖሩ ፓርቲው ለሕዝብ በገባዉ ቃል መሠረት ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም. ታላቅ የተቃዉም ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሔድ በመወሰን በሕግም ሆነ በሥራ የሚያስፈልጉ ነገሮችን በማጠናቀቅ እለቱን በመጠበቅ ላይ እያለ ምንም አይነት መለዮ ባልለበሱ ግለሰቦች የሚመራ የፖሊስ መለዮ ለባሽ ታጣቂዎች ከሕግ ውጭ ነሐሴ 25 ቀን 2005 ዓ.ም. ከምሽቱ 12 ሰዓት አካባቢ የፓርቲውን ቢሮ ጥሰው በመግባት ፓርቲው ይጠቀምባቸው የነበሩ የቅስቀሳ ቁሳቁሶችና ሌሎች የፓርቲውን ንብረቶች ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ወርሰዋል፡፡ በፓርቲው ፅ/ቤት የነበሩ አባላትን እና መሪዎችን በጠመንጃ በማስገደድ ወደተለያዩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያዎች ከፋፍሎ በመውሰድ አስረዋል፣ ዘልፈዋል፣ አስፈራርተዋል እንዲሁም አረመኔያዊ በሆነ መንገድ ደብድበዋል፡፡ አንዳንዶችን በጭቃ ላይ ጭምር አንከባለዋል፡፡ ይህ ሁሉ ሕገ ወጥና አረመኔያዊ ድርጊት ሕገ መንግስታዊ የሆነውን መብታቸውን በሚጠቀሙ ዜጎች ላይ ሲፈፀምና በሕግ ማስከበር ስም በቁጥጥር ሥር በዋሉ ዜጎች ላይ የግል ጥላቻን መወጣጫ እስኪመስል ድረስ ማንኛዉንም የማንአለብኝነት ድርጊት ሲፈፅሙ ማየት ያልታጠቁ ዜጎችን አቅመ ቢስነትና የሕግ ከለላ ማጣትን ገሃድ አድርጎታል፡፡ ይሕ አይነቱ የጡንቻ ሥራ በአንድ በኩል ልብን በሐዘን የሚሰብር ድርጊት ሲሆን በሌላ በኩል ለነፃነትና ለፍትህ የሚደረገው ትግል እጅግ ትክክለኛና ወቅታዊ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ሕጋዊ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ሁሉ አድረጓል፡፡ የአስፈፃሚው አካላት በሕግ ከተሰጣቸው ስልጣንና ተግባር በመውጣት የፈለጉትን ለማድረግ መብት እንደሌላቸው ማሳዬት ፓርቲያችን ከተመሰረተባቸው አብይ መርሆች አንዱ በመሆኑ፤

blue party
1ኛ. በአዲስ አበባ ከተማ ከቤት ውጭ የሚደረጉ ስብሰባንና ሰላማዊ ሰልፍን አስመልክቶ ጥያቄዎችን ተቀብሎ በሕግ በተወሰነው መሰረት አስፈላጊውን ሁሉ ማከናወን የሚገባው በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት የሕዝባዊ ስብሰባና የሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል ኃላፊነቱን ባለመወጣቱ በፓርቲው ላይ ለደረሰው የአካል፣ የንብረትና የሞራል ጉዳት ምክንያት በመሆኑ በሕግ እንጠይቃለን፤

2ኛ. የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የፓርቲ መሪዎችን በማስፈራራት ከሰልፍ ለማስቀረት የሚያደርገው ድርጊት ከህግ ውጭ በመሆኑና በፖሊስ መለዮ ለባሾች ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የፓርቲውን ቢሮ በመውረር ለፈፀሙት የንብረት ዘረፋና ውድመት እንዲሁም ፓርቲው ባቀደውና በተዘጋጀበት ጊዜ የተቃውሞ ሰልፉን እንዳያካሂድ በማደናቀፉ በሕግ እንጠይቃለን፤

3ኛ. በሐገራችን ፓርቲዎችን እንዲያስተዳድርና እንዲከታተል ስልጣን የተሰጠው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እውቅና ሰጥቷቸው በሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ላይ እንዲህ አይነት ሕገ ወጥ ድርጊት እየተፈፀመባቸው መሆኑን እንዲያውቀው እናደርጋለን፤

4ኛ. የፖለቲካ ትግላችንን በመቀጠል ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብታችንን የትኛውም የአስፈፃሚ አካል የመከልከል መብት ስለሌለው የተቃውሞ ሰልፈችንን ቅዳሜ ጳጉሜ 2 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ እንደምናከናውን ለአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት የሕዝባዊ ስብሰባና የሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል በዛሬው ዕለት አሳውቀናል፡፡
በመሆኑም ከዚህ ቀደም ለመንግስት ያቀረብናቸው ጥያቄዎች እንደተጠበቁ ሆነው በተደጋጋሚ እንዳስተዋልነው በዚህች ታሪካዊት ሐገር የሕግ የበላይነት ግብዓተ መሬት ከመፈፀሙ በፊት እንድንደርስላት ለዘመቻ የሕግ የበላይነት ትግላችን የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማሕበራትና ዜጉች በአጠቃላይ ከጎናችን እንዲሰለፉ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

በመንግስታዊ ውንብድና ትግላችን አይገታም!!!!
ነሐሴ 27 ቀን 2005 ዓ.ም.
አዲስ አበባ

ከመንግስት የቤቶች ግንባታ ጀርባ ያለው ትክክለኛ ዓለማ ሲገለጥ

$
0
0

ግርማ ሠይፉ ማሩ

Girma-Seifu2ሰሞኑን ከፀረ አሸባሪነት ህግ በማስቀጠል የአዲስ አበባን ከተማ ነዋሪን በተለ ሲያምስ ከርሞ አሁንም በማመስ ላይ ያለው የመኖሪያ ቤት ጉዳይ ነው፡፡ በእዲስ አባባ የመኖሪያ ቤት ችግር እንዳለ አሌ የሚባል አይደለም፡፡ ይህ ችግር እዚህ እንዲደርስ ደግሞ ዋናው ተዋናይ መንግሰት እንደሆነ መዘንጋት የለበትም፡፡ ምክንያቱም ለቤት መስሪያ የሚሆነውን ቦታ በቁጥጥሩ ስር አድርጎ ለዜጎች እንዳይደርስ በማድረጉ ነው፡፡ አንደኛው በቁጥ-ቁጥ ቦታ በሊዝ ጨረታ እያወጣ በውድ ዋጋ እየሸጠ የመሬትን ዋጋ በማስወዳድ እና የመኖሪያ ቤት ውድ እንዲሆን በማድረግ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ ለመኖሪያ ቤት ግንባት የሚውል የብድር አገልግሎት የተለየ አቅርቦት ባለማዘጋጀቱ ሲሆን፣ የመንግሰት ሹሞች ደግሞ በተለየ ሁኔታ የተመረጠ ቦታ እያገኙ በሽያጭ እንዲከብሩ በተቃራኒው ዜጎች ከከተማ ወጣ ባሉ ቦታዎች በህገወጥ መንገድ እንዲሰፍሩ በማድረግ ነው፡፡

በቅርቡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ልዩ ወዳጅነት የመሰረቱ ይመስላል፡፡ ባንኩ በተለይ መመሪያ የሚቀበለው በቀጥታ ከብሔራዊ ባንክ መሆኑ ቀርቶ ከሚኒስትር መስሪያ ቤቱ እስኪመስል ድረስ ግራ አጋቢ ሆኖብናል፡፡  በእኔ አምነት በቅርቡ መንግሰት ዜጎች ቤት እንዲኖራቸው ለቤቶች ግንባታ በሚል 10/90፣ 20/80፣ 40/60፣ አና ሌለችም በቁጠባ ላይ መሰረት ያደረገ ዜጎችን የማመስ ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡ ይህን ጉዳይ ዛሬ ላይ ሆኜ የምፅፈው ከዓመት እና ሁለት ዓመት በኋላ ለውይይት ይጠቅማል በሚል ነው፡፡ አቋሜን ግልፅ ለማድረግ የኢህአዴግ መንግሰት በምንም ዓይነት መለኪያ ለኢትዮጵያ ህዝብ የመኖሪያ ቤት ሰርቶ የመስጠት አቅምም ሆነ ፍላጎት የለውም፡፡ ስለዚህ የፕሮግራሙ ዓላማ ምንድነው? የሚለውን ጥያቄ ማየት ተገቢ ነው፡፡

የኢህአዴግ መንግሰት በዓለም ላይ ካሉ መንግሰታት በተለየ ሁኔታ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ቤቶችን አንደኮንትራከትር ለመገንባት ሙከራ እያደረገ ያለ መንግሰት ነው፡፡ መንግስት እንደ መንግስት ሊሰራቸው የሚችለው ብዙ ተግባራት ወደ ጎን በመተው ዜጎች እንደፍላጎታቸው እና አቅማቸው ቤታቸውን መስራት የሚችሉበትን ሁኔታ ማመቻቸት ሲገባው መንግስት በፈለገው እና በተወሰኑ የቤት ዓይነቶች ውስጥ ታጥሮ እንዲኖር ለማድረግ እየሞከረ ነው፡፡ ወደ መጨረሻ ላይ ይህን መንግሰት ለምን እንደሚያደርግ የግል ምልከታዬን አሰቀምጣለሁ፡፡

የመንግሰት ቤቶች ግንባታ ዋና ዓላማ መንግሰት በ2006 በጀት መግለጫ ላይ እንዳስቀመጠው የሀገር ውስጥ ቁጠባን ለማሳደግ ከተያዙት ዕቅዶች አንዱ ነው፡፡ ይህ የሀገር ውስጥ ቁጠባን ማሳደግ የተቀደሰ ሃሳብ ነው፡፡ ይህን ቁጠባን በፈቃደኝነት ማሳደግ በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያገኘ አይመስለም፡፡ ለዚህ ብዙ ምክንያት ስለአለው ዝርዝር ውስጥ አልገባም፡፡ መንግሰት ግን ለዚህ እንደመፍትሔ አድርጎ ያስቀመጠው ዜጎች ቤት ይስራልናል በሚል በተስፋ ላይ መሰረት ያደረገ ገንዘብ ተቀማጭ እንዲያደርጉ ማድረግ ነው፡፡ እግረ መንገዱንም መንግሰት ለተለያየ ሰራ የሚፈልገውን ገንዘብ ለማግኘት እንዲችል ዕድል መፍጠር ነው፡፡ ይህ በቁጠባ የተሰበሰበ ገንዘብ በግል ባንኮች ቢቀመጥ፣ የግል ባንኮች ለግል ባለሀብቶች በብድር መልክ ሊሰጡት ስለሚችሉ መንግሰት የሚፈልገውን ገንዘብ ላያገኝ ስለሚችል ይህ ገንዘብ ተጠቃሎ ወደ ንግድ ባንክ እንዲገባ ማድረግ አማራጭ የሌለው መፍትሔ ሆኖ ተገኝቶዋል፡፡ በዚህ ፖሊሲው መንግስት በሀገሪቱ ውስጥ ያሉትን ተቋማትን እና ዜጎችን በአንድ ዓይን እንደማይመለከት ግልፅ ማሳያ ነው፡፡

ብዙ ሰዎች የመንግሰት ዋና ዓላማ የገባው አይመስልም፡፡ ይልቁንም መንግሰት ቤት መስራት ለማይችሉ ሰዎች ቤት ቢሰራ ምን ችግር አለው? የሚሉ አሉ፡፡  መንግሰት እንደሚያወራው ቤት መስራት ያልቻሉ ዜጎች በተመጣጣኝ ዋጋ ቤት ለመስራት እንዳልሆነ የሚያሳብቀው ግን በተነፃፃሪ የተሻለ አቅም ያላቸው በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንም ቢሆኑ በዚሁ ፕሮግራም እንዲሳተፉ ዕድሉ ክፍት ነው ይባላል፡፡ ይህ ዕድል ግን ክፍት የተደረገው በውጭ ምንዛሪ መቆጠብ ሲችሉ ነው፡፡ ገባችሁ አይደለም የውጭ ምንዛሪ ችግር ለመቅረፍ የተያዘ ዕቅድ ነው- ትክክለኛውም ዕቅድ ይህ ነው፡፡ ተሰፋን እየመገቡ ዶላር መሰብሰብ፡፡ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በሀገራችን ላለው የውጭ ምንዛሬ እጥረት መፍትሔ መስጠት መቻል ተገቢ ነው፡፡ ነገር ግን የሚገኘው የውጭ ምንዛሬ ዜጎች ለጋራ ልማታችን የሚያውሉት እንጂ መንግስት ብቻ ለሚያቅደው ዕቅድ መዋል አለበት የሚል እና የግል ባለሀብት ከጫወታ የሚያስወጣ ዕቅድ ለመተግበር መሆን የለበትም፡፡

ሌላው የመንግሰት እቅድን ፊት ለፊት ከሚያወራው በተቃራኒው መሆኑን የሚያሳብቀው በአርባ ስልሣ ሙሉ ክፍያ የከፈለ ቅድሚያ ያገኛል የሚለው መመሪያ ነው፡፡ ቅድሚያ መክፈል የሚችል ማለት አርባ ስልሳ (አርባ ቆጥቦ ስልሳ በብድር የነበረ ፕሮግራም) ሳይሆን መቶ ዜሮ (መቶ ቆጥቦ ዜሮ ብድር ሆኖዋል) ፕሮግራሙ መባል ያለበት፡፡ በእርግጥ መንግሰት ቤት በተመጣጣኝ የመስራት እቅድ አለው ብለን እንድናምን የሚያደርግ ነገር አለወይ? ነው የእኔ ጥያቄ፡፡ መልሱ በፍፁም መንግስት ይህ እቅድ የለውም፡፡ ዕቅዱ በጭፍን አለው ብለን ብንወሰድም አቅሙ የለውም፡፡

የመንግሰት አቅም እንዴት እንለካው? የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡ ሁሉም እንደሚያውቀው ኢህአዴግ በ1997 የአዲስ አበባ ህዝብ ያለበትን ችግር ለመቅረፍ ቅድሚያ የሚሰጠው የመኖሪያ ቤት ነው በሚል ከአራት መቶ ሃምሳ ሺ በላይ ቤቶችን በአምስት ዓመት ለመገንባት ብሎ ምዝገባ አድርጎ ነበር፡፡ ዛሬ ላይ ቆመን ውጤቱን ስንመለከተው በስምንት ዓመት ውስጥ በጅምር ላይ ያሉትን ጨምሮ አንድ መቶ ሺ ቤቶችን ነው መገንባት የተቻለው፡፡ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዳሉት መቶ ሺ ቤቶች የገነባ ሌላ መንግሰት የለም፡፡ ምክንያቱም የሌላ ሀገር መንግሰታት በማያገባቸው አይገቡም፡፡ ስለዚህ ይህን ያህል ቤት አይገነቡም፡፡ እስራኤል አወዛጋቢ በሆኑ ቦታዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤቶች ስትገነባ እንኳን ለግል ኮንትራክተሮች ነው የምትሰጠው፡፡ መንግሰታት የተሰጣቸውን ኃለፊነት ያውቃሉ እርሱን በቅጡ ይተገብራሉ፡፡ የእኛ መንግሰት ለአምስት ዓመት ከያዘው ዕቅድ ውስጥ በስምንት ዓመት ውስጥ ከሃያ በመቶ በታች ብቻ በማከናወን ሌላ ሶስት ዕጥፍ የሚሆን ሌላ ዕቅድ ይዘው ብቅ ብለዋል፡፡ ይህ ዕቅድ ዝርክርክ እንደ ሆነ ለማወቅ በምዝገባ ወቅት ብቻ የሚለዋወጠውን መመሪያ ማየት በቂ ነው፡፡ ለድሃ ነው የምንሰራው ብለው፣ መሉ በሙሉ ለከፈለ ቅድሚያ ይስጣል ይሉናል፡፡ በዚህም ተባለ በዚህ መንግሰት የመኖሪያ ቤት ችግርን ለመፍታት የሚያሰችል መላው ዜጋውን እና በተለይም የግሉን ዘርፍ የሚያበረታታ ዕቅድ ማውጣት ግድ ይለዋል፡፡

ሌላው በጥቂቱም ቢሆን የተሰሩት ቤቶች ዓላማ ምንድነው ካላችሁ በልማት ስም የተነሱ የቀበሌ ቤቶችን በመተካት ዜጎችን ለቁጥጥር በሚመች መልኩ ማስፈር ነው፡፡ ለዚህ ዋነኛው ማሳያ የኮንዶሚኒየም ቤቶች በህጋዊ መንገድ በሽያጭ ማዛወር አይቻለም፡፡ ዜጎች ይህን የመንግሰት ቁጥጥር መስመር ለማለፍ የተለያዩ ዘዴዎችን የሚጠቀም ሲሆን ይህን ለማድረግም የተለያዩ ተገቢ ያልሆኑ ድርጊቶችን ይፈፅማሉ፡፡ ይህ ብቻም አይለም የመንግሰት የቁጥጥሩ አባዜ በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንም የሚቀር አይደለም፣ ገንዘባቸውን ገቢ ካደረጉ በኋላ መንግሰትን በሚቃወም ተግባር ቢሳተፉ በቁጠባ ያስቀመጡት ገንዘብ አደጋ ላይ ስለሚወድቅ ጭጭ ማለት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ነፃነታችንን ከፍለን ሽጠናል የምለው ለዚህ ነው፡፡ በሀገራችን ቤት እናገኛለን ብለው ነፃነታቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል፡፡ በቅርቡ ሁሉም እንደሚታዘበው ኢትዮጵያዊያን ለሁለት ተከፍለናል ግማሹ ለነፃነት፣ ቀሪው ለኮንዶሚኒየም እየተሰለፍ ነው፡፡

ኢህአዴግ የቀበሌ ቤቶችን በመንግሰት ቁጥጥር ስር እንዲቆይ ያደረገው በምንም ዓይነት በቀበሌ ቤት ለሚኖሩት ሰዎች አዝኖ አይደለም፡፡ ዋና ዓላማው በገጠር ገበሬውን በመሬት ጭሰኝነት እንደያዘው ሁሉ በከተማ ደግሞ በቀበሌ ወይም በኪራይ ቤት እንድንኖር ታቅዶ እየተተገበረ መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ የቀበሌ ቤቶች በዕድሜ ምክንያት ከጫወታ ሲወጡ ይህ ተግባር በኮንዶሚኒየም በኩል ነብስ እንዲዘራ ዕቅድ አለ፡፡ ይህ ዕቅድ የለም የሚሉ ከሆነ ለዜጎች በነፃነት ቤታቸውን ሽጠው እንዳይንቀሳቀሱ ማድረግ ትክክል አይደለም፡፡

 

 

Hiber Radio: በኩዌት ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሳንባ በሽተኛ ዜጎቹ ተጨናንቋል መባሉ ባለስልጣናቱን አስቆጣ

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

>

አቶ ከባዱ በላቸው የሰማያዊ ፓርቲ የሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ቻፕተር የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ

>
አባ ገብረስላሴ ጥበቡ በስደት የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ ሀላፊ ሰሞኑን በቬጋስ ያደረጉትን የአንድነት ጉባኤ መሰረት አድርገን ካደረግንላቸው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡ)

(ሌሎችም ቃለ መጠይቆች አሉን)

ስለ ሶሪያ ወቅታዊ ሁኔታ ልዩ ዘገባ ይዘናል..

ዜናዎቻችን

- ከታሰሩት ከመቶ በላይ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ጥቂቶቹ ተደብድበው ተለቀቁ

- መንግስት አሸባሪነትን አወግዛለሁ ብሎ የጠራው ሰልፍ በውጥረት ተጠናቀቀ

- ለጥበቃ ታንክ ጭምር ማሰለፉ የስርዓቱን ፍርሓት ያሳያል ተብሏል

- ከሰልፉ ላይ የታሰሩት ሙስሊሞች አልተለቀቁም

- በኩዌት ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሳንባ በሽተኛ ዜጎቹ ተጨናንቋል መባሉ ባለስልጣናቱን አስቆጣ

- በኢትዮ-ኬኒያ ድንበር አዲስ ግጭት ተቀስቅሶ ከሃያ በላይ ሕይወት ጠፋ

- ኬኒያ የአጸፋ እርምጃ እወስዳለሁ ብላለች

- አንድነት ፓርቲ በኢትዮጵያ ለውጥ ለማምጣት የሚደረገውን ትግል ዲያስፖራው በተግባር እንዲደግፍ ጥሪ አቀረበ

- ጆርጅ ዚመርማን የ17 ዓመቱን ትራይቮን ማርቲንን የገደለበትን ሽጉጥ ፋብሪካና መሳሪያ መሸጫ መጎብኘቱ ቅሬታ ፈጠረ

ሌሎችም ዜናዎች አሉን

የአብዮቱ የምፅአት ቀን ምልክቶች! –ከተመስገን ደሳለኝ (ጋዜጠኛ)

$
0
0

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

‹‹በአፍሪካ ትልቁ አምባገነን›› የሚል ተቀፅላ የተሰጣቸው የሊቢያው ኮሎኔል መሀመድ ጋዳፊ እና የግብፁ ሆስኒ ሙባረክ በህዝባዊው እምቢተኝነት ከስልጣን መነሳታቸው በመሰል አገዛዞች ስር ያደሩ ሕዝቦችን ለለውጥ ማነቃቃቱ የሚጠበቅ ነው፡፡ በተለይም ከራሳቸው መንግስት ተኳርፈው አስተማማኝ የዲሞክራሲ ተቋማትን በገነቡ የምዕራብ ሀገራት በብዛት የሚኖሩ ዜጎች ላሏት ኢትዮጵያ ንቅናቄው የፈጠረው ተመሳሳይ መነሳሳት ቀላል ባለመሆኑ ኢህአዴግን ሊወጣው ከማይችለው ቅርቃር ውስጥ ከቶታል፡፡ የዚህ ተጠየቅም ቀድሞ እንዲህ አይነት ችግሮች ሲፈጠሩ ድርጅቱ ‹እሳት ማጥፊያ› ያደርጋቸው የነበሩ አጀንዳዎቹ ያለፈባቸው (Expired) መሆናቸውን
ማሳየት ነው፡፡
ሰባቱ ‹‹ቀኖና››ዎች
ስርዓቱ ከሃያ ሁለት ዓመታት በላይ በስልጣን የመቆየቱ ምስጢር ከሁለት ምንጭ የሚቀዳ ነው፡፡ አንዱ የታዘዘውን ሁሉ ያለ ምንም ማንገራገር የሚፈፅመው ጠመንጃ አንጋቹ (መከላከያ ሰራዊት፣ ፌደራል ፖሊስ እና የደህንነት መዋቅሩ) ሲሆን፤ ሌላኛው ደግሞ ከፖለቲካው ፍልስፍና የሚወረሱ አጀንዳዎቹ ናቸው፤ ይሁንና ለጊዜው የታጠቀውን ኃይል ወደ ጎን ብለን ስርዓቱ ‹‹የፖለቲካዬ መገለጫዎች›› ብሎ እንደ ቀኖና ይዟቸው የነበሩትን ሰባት ጉዳዮች በደምሳሳው ብንቃኝ የመቃብር አፋፍ ላይ የቆመ ስርዓት ስለመሆኑ የማመላከት አቅም አላቸው ብዬ አስባለሁ፡፡
፩. የገጠር ፖሊሲ
ኢህአዴግን የሶስት ፓርቲዎች ግንባር አድርጎ በመመስረቱ ሂደት የአንበሳውን ድርሻ የሚወስደው፣ በሀገሪቱ ከሚገኙ የገጠር ከተሞች ከሽሬ ጋር በሚዋሰነው ‹‹ደደቢት በርሃ›› ላይ የተመሰረተው ህወሓት ሲሆን፣ መስራቾቹም ሆኑ አብዛኛው አባላቱ ከአርሶ አደሩና የገጠር አካባቢዎች የወጡ ናቸው፡፡ የህወሓት የታሪክ ንባብ እንደሚያረጋግጠው ትጥቅ ትግል ያስፈለገበት ዋነኛ ምክንያቶች ሁለት ነበሩ፤ የብሄር ጭቆናን እና የትግራይ አርሶ አደር ለአስከፊ መከራ ተዳርጓል የሚል፡፡ ድርጅቱ ለትግል ካሰለፋቸው አባላቱ ሁለት ሶስተኛው ከእርሻ ሥራ በቀጥታ የተቀላቀሉ ስለመሆናቸው ድርሳናቱ ያወሳሉ፡፡ በወቅቱ በተድበሰበሰ መልኩ የቀረፁት የፖለቲካ ፕሮግራም በመሬትና በብሄር ጥያቄ ላይ የተንጠለጠለ እንደነበር ይታወቃል፤ ይሁንና ከትምህርት ገበታ ተሰውረው፣ በረሃ የገቡት ወጣቶች ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ምናልባትም ‹‹‹መሬት የመንግስት ነው› የሚለው ፖሊሲያችን የሚቀየረው በመቃብራችን ላይ ነው›› ወደሚል ኦሪታዊ የፖለቲካ አቋም (ቀኖና) የተመለሱት የኢትዮጵያ ተማሪዎች የ‹‹መሬት ላራሹ››ን ትግል ጠልፎ ወደስልጣን የመጣው ደርግ፣ ህወሓት በተመሰረተ ልክ በአስራ አራተኛው ቀን የካቲት 25 ቀን 1967 ዓ.ም መሬትን በተመለከተ መሬትን ያራሹ ባደረገው አዋጅ የሰጠው ምላሽና ያገኘው ድጋፍ ሌላ አማራጭ የነፈጋቸው ይመስለኛል (ህወሓት
የተመሰረተው የካቲት 11 ቀን 1967 ዓ.ም መሆኑን ልብ ይሏል) በነገራችን ላይ ለኢትዮጵያውያን ፖለቲከኞች መሬት ከኢኮኖሚ ይልቅ ፖለቲካዊ ጠቀሜታው እንደሚበልጥ በርካታ ማሳያዎች አሉ፡፡
የሆነ ሆኖ ከኢህዴንና ኦህዴድ ጋር ተጣምሮ ኢህአዴግን የመሰረተው ህወሓት በ1983 ዓ.ም ለመንግስታዊ ስልጣን መብቃቱን ተከትሎ ራሱን ‹የኢትዮጵያ አርሶ አደር ነፃ አውጪ› አድርጎ አስተዋውቋል፡፡ በተጨማሪም ‹‹በቅዱስ መፅሀፌ ‹አብዮታዊ ዲሞክራሲ› መርህ መሰረት የቀመርኩት›› የሚለውን ‹‹ገጠርን እና ግብርናን ማዕከል ያደረገ የልማት እስትራቴጂ›› በፖሊሲ ደረጃ ከማውጣቱም በተጨማሪ በተለያየ ጊዜ ባሳተማቸው መጻህፍት እና ጥናቶች የአርሶ አደሩን ህይወት በከፍተኛ ደረጃ እየቀየረው እንደሆነ ለማስረዳት ሞክሯል፡፡ በአናቱም ሀገሪቱ ያላት ሀብት የሰው ኃይልና መሬት መሆኑ ለሚከራከርበት ንድፈ-ሃሳብ ቅቡልነት አስተዋፅኦ ያደረገ ይመስለኛል፡፡
በቀዳሚዎቹ ሶስት ሀገር አቀፍ ምርጫም አፅንኦት ሰጥቶ የተሟገተው ‹‹ለአርሶ አደሩ የምታገል ፓርቲ ነኝ›› እና ‹‹አርሶ አደሩ ይደግፈኛል›› የሚል እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ይሁንና በምርጫ 97 በከተሞች በደረሰበት ያልተጠበቀ ሽንፈት እንዲያ ከበሮ የደለቀለትን ‹‹ገጠርና ግብርናን ማዕከል ያደረገ የልማት ስትራቴጂ›› ለድንገቴ (አልቦ ቅድመ-ዝግጅት) ለውጥ ይዳርገ ዘንድ መገደዱን የሚጠቁሙ ምልክቶች እየታዩ ነው (የትራንስፎርሜሽን እቅዱ፣ የአባይ ግድብ፣ የመከላከያ ኢንዱስትሪ እና የኮንዶምኒየም ቤቶች ግንባታ የተበጀተላቸው ባጀት ስርዓቱ በአዋጅ የነገረንን የገጠር ልማት ፖሊሲ፣ ያለኮሽታ መቀየሩን ያመላክታል) የአብዮቱን የምፅአት ቀን
ካቃረቡት ዋነኛ ምክንያቶች አንዱ ነው፡፡
፪. የብሔር ጥያቄ
የህወሓት መስራቾች በርሃ ለመግባት ሌላኛው ዋና ምክንያት ‹‹ነፃ የትግራይ ሪፕብሊክ››ን ለመመስረት ቢሆንም በጊዜውበአቅራቢያቸው የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ ይህንን ሴራ ኢትዮጵያዊ ብሄርተኝነትን ለሚያስቀድመው የአካባቢው ህዝብ በማጋለጥ ትልቅ የፖለቲካ ኪሳራ ስላደረሰባቸው የ‹‹ነፃነት›› ጥያቄያቸውን ወደ‹‹የብሄር ጭቆና›› እንዲቀይሩ መገደዳቸውን በጉዳዩ ዙሪያ የተዘጋጁ በርካታ ድርሳናት አጋልጠውታል፡፡ ከድርጅቱ በተለያዩ ምክንያቶች የወጡ የአመራር አባላትም በፃፏቸው ‹ገድሎች› እንደአተቱት ከዚህ በኋላ ነው ‹‹በሀገሪቱ የአንድ ብሄር የበላይነት ነግሷል›› የሚለው ተረታ ተረት በማርክሲዝምና ሌኒንዝም አስተምህሮ ተተንትኖ በማጎን
የድጋፍ መቀስቀሻ የተደረገው፡፡ የሆነ ሆኖ ለህወሓት መደርጀት ዋናው ምክንያት ተጋኖ የተቀነቀነው የጎጠኝነት ፕሮፓጋንዳ ሳይሆን፣ የወታደራዊው ደርግ ጭካኔ የተሞላበት ጭፍጨፋና አፈና ያስመረረው በሙሉ በቅርብ ያገኘውን የፋኖዎች ድርጅት መቀላቀል መምረጡ እንደነበር ከጊዜው ንባብ መረዳት ይቻላል፡፡
ከድል በኋላ ኢህአዴግ የቀድሞውን ‹‹አሀዳዊ መንግስት›› በብሔር ላይ ወደ ተመሰረተ የ‹‹ፌደራል መንግስት›› ያስቀየረኝ መግፍኤ ‹‹በኢትዮጵያ አስከፊ የብሄር ጭቆና መንበሩ ነው›› የሚለው መከራከሪያውን ዛሬም ድረስ እንደ በቀቀን ሲደጋግመው ይደመጣል፡፡ የግንቦት ሃያ ድልን ተከትሎ ሀገሪቱን የአፍ መፍቻ ቋንቋን መስፈርት ባደረገ ቀመር በዘጠኝ ክልላዊ መንግስት እና በሁለት ራስ ገዝ ከፍሎ ማስተዳደሩ ለብሄር ጭቆና የማያዳግም መፍትሄ ቢያስመስለው፣ ዛሬም ድረስ በምርጫ ቦርድ ተመዝግበው በሰላማዊ መንገድ ከሚታገሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል አርባ አራቱ ‹‹የብሄራችን ጥያቄ ገና አልተመለሰም›› በሚል ሀቲት በብሄር የተደራጁ መሆናቸው፤ በኦሮሚያ፣ በሶማሊያ እና ጋምቤላን መሰል አካባቢዎች ደግሞ ጠመንጃ ያነሱ የብሄር ድርጅቶች መኖራቸው ስርዓቱ በብሄር ጥያቄ ረገድ የታሪክ ፈተናን ማለፍ እንደተሳነው መረዳት ይቻላል፡፡
በኢትዮጵያ ሰማይ ስር የብሄር ጥያቄ ‹ዳግም ላይነሳ መልስ አግኝቷል› ትርክት ምፀት የሚሆነው በሀገሪቱ ከሚገኙ ክልሎች በብዙ እጥፍ ያነሰ የህዝብ ቁጥር ያለው ሐረሪ፣ የኢህአዴግ አጋር የሆነው ‹‹የሐረሪ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት-ሐዲድ››ን ጨምሮ ‹‹የሐረሪ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ-ሐሕዴፓ›› እና ‹‹የሐረሪ ብሔራዊ ሊግ-ሐብሊ›› የተሰኙ የፖለቲካ ድርጅቶች መኖራቸው ነው (በአፋርም አራት ህጋዊ የፖለቲካ ድርጅቶች አሉ) እነዚህ እውነታዎች ለስርዓቱ ክሽፈትና የአብዮቱ የምፅአት ቀን በጣም የተቃረበ ለመሆኑ በቂ ምልክቶች ናቸው፡፡
፫. የኢኮኖሚ ዕድገት
ኢህአዴግ ስልጣን ላይ በወጣበት የመጀመሪያዎቹ ዓመታት የቀድሞ ሊቀ-መንበሩ ‹‹ህዝባችን በቀን ሶስቴ እንዲበላ እናደርጋለን›› ብሎ በአደባባይ ቃል መግባቱም ሆነ ‹‹በአጭር ጊዜ ውስጥ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ያቆመኛል›› በሚል ሽፋን ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን የደፈጠጠበት የ‹‹ልማታዊ መንግስት›› ጩኸቱ አለመሳካት ሌላኛው የአደባባይ ተቃውሞን የሚጋብዝ ነው፡፡ የስራ አጥ ቁጥር አለቅጥ መጨመር እና የዋጋ ንረትን መቆጣጠር አለመቻሉም የምፅአት ቀኑን መቃረብ አብሳሪ ‹ሰይጣን› ከአንዳች ሸለቆ መቀሰቀሱ አይቀሬ ነው፤ የዶ/ር መረራ ጉዲና ‹‹የሚበላውን ያጣ ህዝብ መሪዎቹን ይበላል›› ትንቢትም የሚያመላክተው ይህንኑ ነው፡፡
፬. የእስልምና እምነት
በሀገሪቱ ከፍተኛ ተከታይ ካላቸው ዋነኛ ኃይማኖቶች መካከል እስልምና አንዱ ነው፡፡ እንደኃይማኖቱ ልሂቃኖች ምስክርነት ኢህአዴግ የእምነቱን ተከታዮች መብት ለማክበር ከቀድሞ አገዛዞች የተሻለ ውጤት አለው፡፡ ይሁንና በምትኩ ከምዕመኖቹ ያገኘው ጠንካራ የፖለቲካ ድጋፍ ብቻውን ያረካው አይመስልም፡፡ ምክንያቱም ከተባባሪዎቹ የመጅሊስ መሪዎች ጋር በመመሳጠር ኃይማኖቱን ‹አጋር ፓርቲ› አድርጎ እስከ መቁጠር ደርሷልና፡፡ በርግጥ አብዛኛው ሙስሊም ያለፉትን አራት ሀገር አቀፍ ምርጫዎች ግንባሩን ከመምረጥ አልፎ በየመስጂዱ ከሶላትና ፀሎት በኋላ ‹‹ኢህአዴግን ምረጡ›› የሚሉ ድምፆች በርክተው እንደነበር ዛሬ በአገዛዙ ላይ የመረረ ተቃውሞ ከሚያሰሙ ምዕመናን አረጋግጫለሁ፡፡ …‹ታሪክ ራሱን ይደግማል› እንዲሉ የዘርፉ ምሁራን አገዛዙ እንደነገስታቱ ዘመን በእስልምና አስተምህሮት ላይ ጣልቃ በመግባቱ ከ2003 ዓ.ም ታህሳስ ወር ጀምሮ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የእምነቱ ተከታዮች ‹‹መንግስት በሃይማኖታችን ጣልቃ መግባቱን ያቁምልን!›› በማለት
ላቀረቡት ጥያቄ ምላሹ በታጠቀው ኃይል በመሆኑ ለከፋ መስዋዕትነት ተዳርገዋል፡፡ ይህ አይነቱ መንግስታዊ ሽብርተኝነት ከቀን ቀን እየሰፋና እየጠነከረ በመሄድ ላይ ነው፡፡ እውነታውን የሚያብራራ አንድ ገጠመኜን እዚህ ጋ ላንሳ፡፡ ይኸውም ባለፈው ቅዳሜ (ነሐሴ 14 ቀን 1967 ዓ.ም) ከጠዋቱ አራት ሰአት ተኩል አካባቢ የቤቴ በር ጠንከር ባለ መዳፍ ተደጋግሞ ሲቆረቆር ከፈትኩት፤ የፖሊስ መለዮ ከለበሰ ወጣት ጋር ተፋጠጥን፤
‹‹ምን ነበር?››
‹‹የቤቱ ባለቤት አንተ ነህ?››
‹‹አይ! እኔ ተከራይ ነኝ››
‹‹የሚሞላ ፎርም ስለያዝኩ ጥቂት ጥያቄዎችን ላቀርብልህ ነው!››‹‹ግባ!›› ገብቶ ከተቀመጠ በኋላ ስለመጣበት ጉዳይ ከማውራቱ በፊት እንዲህ አለኝ፡-
‹‹አንድ ነገር ልምከርህ፤ የደንብ ልብስ የለበሰውን በሙሉ መታወቂያ ሳታይ አመነህ ወደ ቤትህ አታስገባ!››
‹‹ለምን?››
‹‹አክራሪዎቹ የፖሊስ ልብስ ለብሰው ወንጀል እየፈፀሙ ነው››
…በጣም አዘንኩ፤ ይህ አገዛዙ ከእስልምና ውጪ ያለውን ህዝብ በእምነቱ ላይ በጥላቻ እንዲነሳሳ (እርስ በእርስ እንዲበላላ) ምን ያህል ዕርቀት እየተጓዘ እንደሆነ የሚያሳይ ሀላፊነት የጎደለው ድርጊት ነው፡፡ …ሁሉም ጉዳይ ጊዜው ያለፈበት መሆኑ በጀ እንጂ፣ የባለስልጣናቱ ፍላጎት ግልፅ ነው፡፡ ኩነቱ ግን ለግንባሩ መዳከም ከፍተኛ አስተዋፅኦ ሲያደርግ፣ ለለውጥ ፈላጊው ደግሞ ታላቅ ድል መሆኑ ነው፡፡
፭. የምዕራብ ሀገራት ድጋፍ
በ1980ዎቹ መጨረሻ አካባቢ የአሜሪካ ዲፕሎማቶች መለስ ዜናዊን እና ኢሳያስ አፈወርቂን ‹‹አዲሱ የአፍሪካ መሪዎች ትውልድ›› የሚል ካባ ይደርቡላቸው የነበረበት ያ ‹‹ደግ›› ዘመን እንደዋዛ አልፏል፤ ኢህአዴግ፣ የሻዕቢያን ያህል ከምዕራባውያኑ ጋ ወደለየለት ጠላትነት ደረጃ ባይደርስም፣ እንደቀድሞ ባደናቀፈው ቁጥር ‹‹እኔን!›› ብለው በሚነጠፉለት አይነት ‹ፍቅር› ላይ አለመሆኑ ግን እርግጥ ነው፤ በተለይም የ1997ቱን ድህረ ምርጫ ተከትሎ ከቅንጅት አመራርና አባላት ጋር የተከሰተው አለመግባባት የፈታበት መንገድ፣ ሀገራቱ በኢትዮጵያ ላይ የሚከተሉትን የግንኙነት ፖሊሲ ቆም ብለው እንዲከልሱ አድርጓቸዋል፡፡ የአውሮፓ ህብረት፣ ስዊዲንና ኖርዌይ ደግሞ ጠንከር ያለ አቋም እንዲይዙ አስገድዷቸዋል፡፡ ይህ ሁኔታ ኢትዮጵያን በመሰለ ነጭ ደሀ ሀገር ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ‹በሌላ መንገድ እቀርፈዋለሁ› ወይም ‹ራሴ እወጣዋለሁ› የሚሉት አይነት አይደለም (ከባጀቱም አብዛኛው በእነርሱ እርዳታ እና ብድር ላይ የተመሰረተ መሆኑ ሳይዘነጋ ማለት ነው) ከአንድ ወር በፊት በአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ‹‹የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ንዑስ ኮሚቴ››ን ወክለው በኢትዮጵያ ከሰብዓዊ መብት መጣስ ጋር ተያይዘው የሚሰሙ ችግሮችን ለመፈተሽ የአራት ሀገራት ተወካዮች ያሉበት አንድ የልዑካን ቡድን መጥቶ ነበር፤ ይህ ቡድን ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር በተወያየበት ጊዜም ለፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር አንድ ጥያቄ አቀረበ፡፡ ‹‹ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚገኙ የህሊና እስረኞችን መጎብኘት እችላለሁን?›› የሚል፡፡ ጥያቄውም ተቀባይነት በማግኘቱ ቡድኑ ወዳዘው አመራ፤ ይሁንና ቃሊቲ ያሉ የፖሊስ ባለስልጣናት የልዑኩን ቡድን ጉብኝት እንዳያደርግ በመከልከል ‹ኩም› አድርገው በመጣበት እግሩ መልሰውታል፡፡ በሁኔታው በእጅጉ የተበሳጩት የቡድኑ አባላትም ዕለቱኑ በሂልተን ሆቴል ‹‹›› በሚል ርዕስ በበተኑት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በስርዓቱ ተፈፅመዋል ያሏቸውን ወደ ስምንት የሚደርሱ አንኳር ችግሮች ከዘረዘሩ በኋላ፤ በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላት፣ እንዲሁም ከሀይማኖት ጋር በተያያዘ የታሰሩ ሰዎች እንዲፈቱ ጠንከር ባሉ ቃላት ጠይቀዋል፡፡ ይህ ሁኔታም ከአሜሪካ ጋር የነበረው የሲሲሊያ ማፊያ ‹‹የጡት አባት›› አይነት ግንኙነቱ ወደ መናፈቅ እየተቀየረ ለሄደበት ስርዓት ፍጻሜውን ለማቅረብ መልካም የሚባል አጋጣሚ ይመስለኛል፡፡
፮. የዲሞክራሲ ተቋማት ያለመኖር
ዲሞክራሲን ባህል ባደረጉ ሀገራት የሚኖሩ ህዝቦች ለደህንነትም ሆነ ለህግ የበላይነት ዋስትና የሚያገኙት በምርጫ ካርድ ውስን ለሆነ ጊዜ በስልጣን ላይ የሚፈራረቁ ፓርቲዎች ሳይሆን ቀድመውንም ተደላድለው በታነፁ የዲሞክራሲ ተቋማት ነው፡፡ በኢትዮጵያ አስቸጋሪ ጉዳዮች አንዱ በዚህ በኩል የተሰራ ሥራ አለመኖሩ ነው፡፡ ኢህአዴግ ለዲሞክራሲ ተቋማት ያለመታከት እየሰራ እንደሆነ ለማደናገር ይሞክርበት የነበረው መክራከሪያው መክሸፉን ለማረጋገጥ፡- ህገ-መንግስቱን ራሱ በጠራራ ፀሀይ ደጋግሞ መገርሰሱ፣ ነፃ የፍትህ ስርዓት አለመኖሩ፣ ራሱ የፈጠረውን ነፃ ፕሬስ መልሶ መብላቱ፣ የነፃ ምርጫ ቦርድ እጦት፣ እያቆጠቆጠ የነበረው የብዙሃን ፓርቲ ስርዓት በ2002ቱ ምርጫ በአውራ ፓርቲ መተካቱ፣ የሲቪክና ሙያ ማህበራት ከተፅእኖ ነፃ መሆን አለመቻል… ከበርካታ ማሳያዎቹ ጥቂቶቹ ናቸው (በነገራችን ላይ አገዛዙ ድሮውንም በአንደበቱ እንጂ በልቡ ግራ ዘመም በመሆኑ እነዚህ ተቋማት ‹አስፈላጊ ናቸው› ብሎ ሊያምን የሚችልበት ምክንያት አይኖረውም፤ ምዕራባውያንን ሲሸነገል ካልሆነ በቀር ማለቴ ነው፤ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ደግሞ ሀሳዊ- መሲሂነቱ በመጋለጡ ለእንዲህ አይነት ጉዳዮች ብዙም ሲጨነቅ አይታይም)
፯. የመለስ ህልፈት
መቼም የመለስ ዜናዊ ህልፈት ለኢህአዴግ፣ አቦይ ስብሃት ነጋ እንዳሉት ‹‹በቀለ መጣ፣ በቀለ ሄደ፤ ፋጡማ መጣች ፋጡማ ሄደች፤… አይነት ፖለቲካ ነው›› ብሎ የሚያምን የዋህ የሚኖር አይመስለኝም፤ እኛ ኢትዮጵያውያን ብቻ ሳንሆን፣ የፖለቲካ ጉዳዮቻችንን የሚከታተሉ የሌላ ሀገር ዜጎች በሙሉ መለስ ለድርጅቱ ሁሉም ነገር እንደነበር ጠንቅቀው ያውቃሉ፤ በስልጣን ላይ ባሳለፋቸው ሃያ አንድ ዓመታትም የውስጥንም ሆነ የውጪን ተቃውሞ እና ጫናን ያለ ኪሳራ እንዴት መፍታት እንዳለበት ተክኖታል፤ ከምዕራቡ ሲኳረፍ ወደ ምስራቅ ምን ይዞ እንደሚሄድ ያውቃል፤ የሰጣቸውን ትዕዛዝ ያለአንዳች ማመንታት የሚቀበሉ እልፍ አዕላፍ ታጣቂዎቹንም የግል ታዛዦቹ ማድረግ ችሎ ነበር፤ ባልተመረጠበት አካባቢም የድምፅ ቆጠራው እንዴት እንደሚስተካከል ጠንቅቀው የተረዱ ‹‹ምርጫ አስፈፃሚዎች››ን ከጎኑ ማሰለፉ ተሳክቶለታል፤ ፍትህን እንዴት ማዛባት እንደሚችሉ የገባቸው ስፍር ቁጥር የሌላቸው ዳኞችም አሰልጥኗል፤… ግና! (ምናልባትም ኢትዮጵያን አምላኳ ሲታደጋት) እነዚህን ሁሉ አንድ ላይ አጣምሮ የሚቆጣጠር እርሱን መሳይ ተተኪ አላስቀመጠም፤ ይህ ነው ሶስተኛውን አብዮት (ሕዝባዊ ንቅናቄ) የተሳካ ከሚያደርጉ (መደላድል እንደተፈጠረ ከሚያመላክቱ) ቁልፍ ጉዳዮች አንዱ፡፡ የፓርቲው ቀሳውስትና ዲያቆናትም ‹የምፅአት ቀኑን በአርማጌዶ ዘመቻ ለመቀልበስ ማን ይመራናል?› የሚለው ጥያቄ ዕብሪት ያደነደነውን መንፈሳቸውን አልፈስፍሶታል፡፡
በጥቅሉ ከላይ የተጠቀሱት ሰባቱ የስርዓቱ ‹‹የማዕዘን ድንጋይ›› በነበሩበት አለመገኘት ወይም የማጭበርበሪያ አጀንዳ መሆናቸው ተጋልጠው ከአገልግሎት ውጪ መሆን የለውጡን አብዮት የህዝብን ፍላጎት በመጨፍለቅ ሊገድብ የሚችል ኃይል እንዳይኖር ያደረገው ይመስለኛል፡፡ አገዘዙ እንደለመደው ዛሬም ‹አርሶ አደሩ መረጠኝ›፣ ‹ብሔር ብሔረሰቦች አከበሩኝ› ‹የሃይማኖት ነፃነትን አስከብሪያለሁ›፣ ‹ሀገሪቱን በልማት ባቡር አከነፍኳት›… የመሳሰሉት ለተጭበረበረ ምርጫ መከራከሪያ ሆነው የሚቀርቡት ‹ካርዶች› ተበልተውበታል፡፡
የነፃነቱ ደውል
ከዚህ በኋላ በኢትዮጵያ ጠረቤዛ ላይ የተቀመጠው አማራጭ አንድ ብቻ ነው፤ በጥቂት ወራት አሊያም በአንድና ሁለት ዓመት ውስጥ ውጤቱን አስቀድሞ ማወቅ ከማይቻልበት ህዝባዊ ንቅናቄ የሚፈጥረው አብዮት ጋር መፋጠጥ ወይም ህዝብንና ህግን በማክበር የ2007ቱን ምርጫ ተዓማኒና ተቀባይነት ባለው መንገድ አካሄዶ ከታሪክ ጋር ማበር፡፡ በእኔ እምነት ሁለተኛው መንገድ በምንም መልኩ ከየትኛውም አማራጭ ጋር ሊነፃፀር አይችልም፡፡ ሀገሪቱን ማረጋጋት የሚችለውም ሆነ በእውነተኛው የለውጥ ባቡር የሚያሳፍረው ይህ ነው፡፡ እርግጥ ነው እንዲህ አይነት ጉዳዮችን ደፍሮ በአደባባይ መነጋገሩ ከስርዓቱ በኩል እንደተለመደው ‹አመፅ ናፋቂ› ወደሚል ጠርዝ
ያስገፋል፣ አገዛዙን አግዝፈው በሚያዩት ደግሞ ከምኞት የሰረፀ ባዶ-ተስፋ መምሰሉ አይቀሬ ነው፤ ይሁንና ኢህአዴግ እንደማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ከታሪክ ዑደት ውጭ ሊሆን የሚችልበት ተዓምር አለመኖሩን ወይም ‹የምመጣበት ቀን አይታወቅምና ተዘጋጅታችሁ ጠብቁኝ› እንደሚለው የመፅሀፉ ትእዛዝ አይነት ድንገቴ በሚፈጠሩ ኩነቶች መፃኢ ዕድሉ የሚወሰን አይደለም ብሎ መከራከሩ ብዙ አያስኬድም፤ ምክንያቱም እንደ መንግስት ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ በስልጣን ላይ ስለቆየ ኃይል ነውና የምናወራው፡፡ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር በአንድ ወቅት በምክር ቤት ውስጥ ‹‹መንግስት ማየት የተሳነው አይደለም ያያል፤ መስማት የተሳነው አይደለም ይሰማል›› ሲል እንደተናገረው ሁሉ መንግስትም በግልባጩ ከስሩ ባደረ ህዝብ ይመዘናል፣ ይፈተናል፣ ውጤቱም በሰራው ልክ ይሆናል፡፡
ዘመኑን የኢህአዴግ የመጨረሻ ወቅቶች እንድለው የሚያስገድደኝ ከዚህ ግምገማ የተነሳ ነው፡፡ የሆነ ሆኖ የዲሞክራሲን መሰረት የሚጥለው የአብዮት ምዕራፍ መከፈቻው ዕለት በጣም ተቃርቧል፤ የነፃነቱ ደውልም በጥሪው የተኙትን ሊያነቃ ከደጅ ደርሷል፤ በሀገሬ ተራሮችና ኮረብቶች የነፃነት ጅረት ያለ ከልካይ የሚፈስበት ያች የተቀደሰች ዕለት ደርሳለች፤ በርግጥም በሁሉም የሀገረ ጥቅም እና በሁሉም ዜጋ መብት በደል የፈፀመው የጉልበት አገዛዝን ከመሰረቱ ፈነቃቅለው ፍትህ የሚሰበክባቸው፣ ዲሞክራሲ የሚሰፍንባቸው፣ ሰብዓዊ መብት የሚከበርባቸው የሙክራቦቻችንን ቅፅር የሚገነባው የለውጥ ንፋስ፣ ከፍታቸው ሰማይ ጥግ ከሚደርሱት ተራሮቻችን፣ ቁልቁል ሊንደርደር ሲያኮቦኩብ ይታየኛል፡፡ (ከለውጡ በኋላስ? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ፣ ሊከሰት የሚችለውን ‹ፖለቲካል ፓራዳየም› እና ራሳቸውን ‹አማራጭ ኃይል› ያደረጉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተስፋ ሊጣልባቸው ይችላሉ? ወይስ ከዚህም ወደ ከፋ መከራ የሚያደርሱን ‹የዳቢሎስ ፈረስ› ናቸው? የሚሉትን
ጥያቄዎች ከፓርቲዎቹ ስንስክሳር ጭምር መፈተሹን ሳምንት እመለስበታለሁ፤ አንዳንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እንደሚያስቡት ዓላማችን ኢህአዴግን ሽረን፣ እንርሱን ማንገስ እንዳለሆነ ይረዱ ዘንድ መምከሩ አስፈላጊ ነው፤ ይህ መፈንቅለ መንግስት እንጂ አብዮት ሊሆን አይችልምና)

የ12 ሚሊዮን ብር ወሬ: መንግስት ይህን ዘገባ በአዋሽ ባንክ ዙሪያ ለምን ማቅረብን ፈለገ?

$
0
0

AWASH_INTERNATIONAL_BANK_LOGOመንግስታዊ ሚድያዎች በአዋሽ ባንክ ዙሪያ ዘመቻ የጀመሩ ይመስላል። መቼም ስም መስጠት ስለምንወድ በተለምዶ በሃገራችን የኦሮሞዎች ባንክ ተብሎ የሚፈረጀው አዋሽ ባንክን በሚመለከት በምርመራዊ ጋዜጠኝነት ያገኘነው መረጃ ነው በሚል “ልዩ የምርመራ ዘገባ የአዋሽ ባንክ ፕሬዚዳንቶች የ12 ሚሊዮን ብር ብድር ጉዳይ አነጋጋሪ ሆኗል” ሲሉ ያቀረቡት ዘገባ ከጀርባው ምን እንዳለ አነጋጋሪ ሆኗል። የሕወሓቱን ወጋገን ባንክ ለመፈተሽ ድፍረት የሌላቸው መንግስታዊ ጋዜጠኞች ይህን ምርመራ ለምን ሊያቀርቡ ቻሉ? ምላሽ ያላችሁ በአስተያየት ላይ ጻፉት መንግስታዊ ሚዲያዎች ያቀረቡትን ግን ለግንዛቤ እንደወረደ እንካችሁ።
በአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዚዳንቶች ከባንኩ የተወሰደው 12 ነጥብ 35 ሚሊዮን ብር ብድር አነጋጋሪ ሆኗል።
የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ፀሐይ ሽፈራው 6 ነጥብ 65 ሚሊዮን ብር የመኖሪያ ቤት ብድር የወሰዱ ሲሆን፤ የብድርና ሪስክ ማኔጅመንት ምክትላቸው አቶ ባጫ ጊና ደግሞ 5 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ተበድረዋል።
ፕሬዚዳንቶቹ ብድሩን የወሰዱት ባለፈው ዓመት ነሐሴና ዘንድሮ በጥቅምት ወር ቢሆንም ጉዳዩ በባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ዘንድ የታወቀው በጥር ወር አንድ የባንኩ ባለአክስዮን መረጃውን ከሰጡ በኋላ መሆኑን የቦርዱ ሰብሳቢ አቶ ወሌ ጉርሙ ተናግረዋል።
እንደ አቶ ወሌ ገለጻ፤ የፕሬዚዳንቶቹንም ሆነ የሌሎች የሰራተኞችን ብድር በተመለከተ የቦርዱ እውቅናና ፈቃድ አያስፈልግም። ያም ሆኖ ቦርዱ የፕሬዚዳንቶቹ የብድር ጉዳይ እንደደረሰው በተለያዩ አካላትና ኮሚቴዎች አስመርምሮ በባንኩ የብድር ፖሊሲ አግባብ የተወሰደ ብድር መሆኑን እንዳረጋገጠ አቶ ወሌ ገልጸዋል።
የአገሪቱን ባንኮች የመከታተልና የመቆጣጠር ስልጣን ያለውና የአዋሽ ባንክ ቃለ ጉባዔ በእጁ የሚገኘው ብሔራዊ ባንክ ጉዳዩን ማጣራት የጀመረው ሰዎች ስለ ብድሩ ቅሬታ ካደረሱት በኋላ መሆኑና ጉዳዩ ከስምንት ወራት በላይ ቢያስቆጥርም እስካሁን በማጣራት ሂደቱ የደረሰበት ደረጃ አለመታወቁ ነገሩን ይበልጥ አነጋጋሪ አድርጎታል።
አዲስ ዘመን ጉዳዩን በመመርመር መረጃ በማሰባሰብ ላይ እያለ ፕሬዚዳንቱ ቤቱን ሸጠው ብድሩን መመለሳቸው ከአቶ ወሌ ጉርሙ የተገለጸለት ከመሆኑም በላይ ጋዜጣውም ይህንኑ አረጋግጧል።
የብድር ውሎቹ እንደሚያሳዩት ፕሬዚዳንቶቹ ገንዘቡን የወሰዱት «የሰራተኞች የመኖሪያ ቤት ብድር» በሚል በሰባት በመቶ ወለድ ቢሆንም፤ አቶ ጸሐይ በብድሩ የገዙት ቤት ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሠራተኞች መከራየቱን አዲስ ዘመን ጋዜጣ ቤቱ ከሚገኝበት ወረዳ ገቢዎች ጽህፈት ቤት ጋር በመሆን ደርሶበታል። አቶ ጸሐይ ቤቱን አከራይተው የቆዩ ቢሆንም ከቤት ኪራይ ከተገኘው ገቢ ግብር እንዳላስገቡም የገቢ ጽህፈት ቤቱ አረጋግጧል።
ቤቱ ለኪራይ አገልግሎት ከዋለ ደግሞ ባንኩ እንደሌሎቹ የቢዝነስ ብድሮች በ16 በመቶ ወለድ ገንዘቡን ማበደር እንደነበረበት ተገልጿል።
ፕሬዚዳንቱ ዓምና በሰባት ሚሊዮን ብር የገዙትን ቤት በቅርቡ በ11 ሚሊዮን ብር የሸጡት ቢሆንም፤ በገቢ ግብር ዓዋጁና በደንቡ መሰረት የመኖሪያ ቤቱን በማስተላለፍ ከተገኘው ጥቅም ግብር እንዳልከፈሉ ተረጋግጧል።
ጋዜጣው በጉዳዩ ላይ ባደረገው ጥልቅ ምርመራ በተለይም የፕሬዚዳንቱ የብድር መያዣ በህግ ፊት የማይጸና መሆኑንና ብድሩም የተወሰደው ያለመያዣ እንደነበር አረጋግጧል።
የባንኩ የኮምፒዩተሮችና የተሽከርካሪዎች ግዥም እየተመረመረ ይገኛል። የፕሬዚዳንቶቹ ብድር ለቦርዱ መታወቁን ተከትሎ በቦርድ አባላት መካከል በተፈጠረው ውጥረት አንድ የቦርድ ዳይሬክተር ከቦርዱ ራሳቸውን አግልለዋል።

በዚህ መንግስታዊ ሚድያዎች ባቀረቡት ዘገባ ላይ አስተያየትዎ ምንድን ነው?

የሙስናው ጉዳይ –ከክንፉ አሰፋ (ጋዜጠኛ)

$
0
0

ክንፉ አሰፋ
በተንጣለለ ቪላ ውስጥ ከበድ ያሉ እንግዶች “ጸዳ” ባሉ ምግብና መጠጦች እየተስተናገዱ ነው። ታዋቂ ግለሰቦች፤ ባለስልጣናት እና አርቲስቶች የቀረበላቸውን ብፌ በልማታዊ ወጋቸው እያወራረዱ ሳሉ አንድ እንግዳ ነገር በመሃላቸው ተከሰተ። ሞቅ ባለው የአይቴ ነጋ ገብረእግዚአብሄር ድግስ ላይ ያልተጋበዙ ሁለት ሰዎች ዘው ብለው ከግብዣው ክፍል ገቡ። የፌዴራል ፖሊስ አባላት ነበሩ።

ጄነራል ባጫ ደበሌ

ጄነራል ባጫ ደበሌ


በዚህ ያልተለመደ ክስተት የአቶ ነጋ እንግዶች አልተደናገጡም ነበር። ይልቁንም የፌዴራል ፖሊሶቹ ለተጨማሪ ጥበቃ የመጡ ነበር የመሰላቸው። አንድ ብርጌድ ያህል ጦር አስከትለው የመጡት ፖሊሶች ግን አቶ ነጋ ገብረእግዚአብሄርን አስጠሯቸው። አቶ ነጋም ለጥሪው እንደወትሮው በመወጣጠርና ፍጹም ትእቢት በተሞላበት አነጋገር ምላሽ ሰጡ። በፖሊስ አባላቱ እና በአቶ ነጋ መካከል የሃይለ-ቃል ልውውጥ ተጀመረ። እሰጥ እገባው አንድ፣ ሁለት እያለ ሄደና በመጨረሻ ተካረረ። በዚህ ሰዓት አቶ ነጋ ስልክ መደዋወል ያዙ። ከፍተኛ የሚባሉ ባለስልጣናትና ምኒስትሮች ጋ ደወሉ። ከዚያም በመቀጠል፣ ጀነራሎች ጋ ደወሉ… የጦር መኮንኖች፣ የፓርቲ ባለስልጣናት… ሁሉም ጋ ተደወለ። የባለስልጣናቱ ምላሽ ግን ጥሩ እንዳልነበር ከአቶ ነጋ ፊት ላይ ይነበብ ነበር። ወዳጆቻቸው ሁሉ እንደ ቱኒዚያው ቤን አሊ በአንድ ጊዜ ከዷቸው።
“በል – ና – ውጣ!” አለ አንደኛው የፖሊስ አባል፣ የስልኩን ሽርጉድ በጥሞና ከተከታተለ በኋላ።
“ምን ማለትህ ነው? እኔኮ ነጋ ነኝ። ነጋ ታሪኩ!” አሉ። አነጋገራቸው የጀምስ ቦንድን ይመስል ነበር። በዚህ ጊዜ ታዲያ እጃቸውም አላረፈም። ከጎን ያሸጎጡትን መሳርያ ለማውጣትም ዳዳቸው።
በቅጽበት ግን ፌዴራል ፖሊሱ ቀደማቸው። በድንገት “ጯ!” የሚል ድምጽ አዳራሹን አናጋው። የፖሊሱ አይበሉባ የግራ መንጋጭላቸው ላይ ሲያርፍባቸው ጊዜ፤ አይቴ ነጋ ነገር አለሙ ተደበላለቀባቸውና እጅ መስጠትን መረጡ። ግብር ሊያበሉ በጠሯቸው የክብር እንግዶቻቸው ፊት፣ ከዚህ በላይ መዋረድ አልፈቀዱም። ሁለት እጃቸውንም ወደ ፖሊሱ በመዘርጋት ለብረት ማሰርያው ራሳቸውን አመቻቹ። እጃቸው የኋሊት ከተጠፈረ በኋላም አቶ ነጋ እንዲህ አሉ። “በቃ! ህወሃት አበቃለት!”
“ባለሃብቱ” በዚህ ሁኔታ በፖሊስ መኪና ተጭነው ወደ እስር ቤት ሲሄዱ፣ ተጋባዥ እንግዶቹም እግሬ-አውጭኝ እያሉ ከስፍራው አፈተለኩ። ይህ ታሪክ ድራማ ሊመስል ይችላል። ግን በእውን የተፈጸመ ሃቅ ነው። ታሪኩን ያጫወተኝ ሰውም እዚያ ግብዣ ላይ ግብር ሊበላ ተገኝቶ ነበር። እንደ አግራሞቱም “ይህ መቼም የፈጣሪ ስራ ነው።” ከማለት ውጪ ስለ ጉዳዩ እንድምታ የሰጠው ማብራሪያ የለም።
ነጋ ገብረእግዚአብሄር የነፃ ትሬዲግ ኃላፊነቱ የተወሰነ (ሰዎች ያልተወሰነ ይሉታል) የግል ማህበር ባለቤት ነበሩ። ድርጅታቸውም እንደስሙ ከሁሉም ነገር ነጻ ነበር። ከግብር ነጻ፤ ከቁጥጥጥር ነጻ፤ ከፍተሻም ነጻ። በመቶዎች የሚቆጠሩ የጭነት መኪናዎች እቃ ጭነው በየኬላው ሳይፈተሹ እንዲያልፉ የተሰጠ ልዩ መብት ሁሉ እንደነበራቸው ይነገራል። ዛሬ ፈጣሪ ሲፈርድባቸው በኢፍትሃዊ መንገድ ቢልየነር ያደረጋቸው ስርዓት፤ ያው ስርዓት ሰለባ አደረጋቸው… ነጋ ገብረእግዚአብሄር ለአቶ መለስ ዜናዊ እና ለባለቤታቸው ለወ/ሮ አዜብ መስፍን ቅርብ – በጣም ቅርብ ነበሩ። ለጉምቱ ባለስልጣናት ይሰጡት የነበረው እጅ መንሻ ከዚህ አይነት ውርደት እና እስራት ሊያድናቸው አልቻለም። በትግራይ ውስጥ ከ40 ሚሊየን ብር በላይ አውጥተው በስማቸው ያሰሩት የቴክኒክ ኮሌጅም እንደ ውለታ አልተቆጠረላቸውም።…
AWASH_INTERNATIONAL_BANK_LOGOይህችን አጭር መጣጥፍ ለመጫር እንደተቀመጥኩ አንድ ዜና በኢሜይል ደረሰኝ። የዜናው ርእስ “ጀነራል ባጫ ደበሌ የአዋሽ ባንክ ሰራተኞችን ከሥራ እንዲባረሩ አደረጉ!” ይላል። ባጫ ደበሌ የባንክ ሰራተኞቹን ያባረሩዋቸው ‘’እኔ ጀነራል ባጫ ደበሌን እንዴት አታውቁኝም?’’ በሚል በሰራተኞቹ አለመታወቃቸው አበሳጭቷቸው ነበር። ወደ ፌስ ቡክ ጎራ ስልም አንዳንዶች በዜናው ላይ ሲወያዩ አስተዋልኩ። ይህ እኮ አዲስ ክስተት አይደለም። ለብዙ ጊዜ የሚደጋገም እና የተለመድ ነገር ዜና ሊሆን አይችልም። ውሻ ሰውን ሲነክስ ዜና አይሆንም። በተቃራኒው ግን ሰው ውሻን ከነከሰ ዜና ይሆናል። እንዲህ አይነቱ ክስተት ስር የሰደደ የስርዓቱ ባህርይ ነው። ባጫ ደበሌ እነዚያን ሰዎች ማስገደል የሚያስችልም ስልጣን እና መብት ያላቸው የአዜብ ሰው መሆናቸውን አንዘንጋ። ጀነራል ባጫ በተልእኮ ትምህርት ከአንድም ሁለተኛ ዲግሪ እንዲገዛላቸው ካደረጉ በኋላ፣ ለምርቃታቸው ስነ-ስርዓት፣ ሰንጋዎች ጥለው፣ የሙዚቃ ባንድም አስመጥተው፣ መንገድ ሁሉ እንዲዘጋ አድርገው ሲያበቁ፤ በተለመደው ብሬክ ዳንሳቸው መንደሩን የቀወጡ ሰው ናቸው። በብርሃን ፍጥነት ከኪነት ጓድነት ወደ ጀነራል የተሸጋገሩት ባጫ ደበሌ በመደበኛ የስራ ጊዜያቸው ጫት ይነግዳሉ። በትርፍ ጊዜያቸው ደግሞ በዜጋው ላይ እንዲሁ እንደዋዛ እየቀለዱ እስካሁን አሉ። የነገውን አንድዬ ብቻ ነው የሚያውቀው። የፍትህ ሳይሆን የግለሰቦች የበላይነት የሰፈነበት ሃገር ስልጣንን ያላግባብ መጠቀም ሙስና ሊደንቀን አይገባም። የፍትሃዊ ስርዓት መጥፋት ነው ሙስና።
ፕሮፌሰር አል ማርያም ባለፈው መጣጥፉ ስለሙስና ሲጽፍ ከሙስና ሁሉ በላይ ሙስና የሚሆነው የፍትህ መጓደል እንደሆነ አስነብቦናል። የፍትህ መጥፋት ስብእናን፣ ነጻነትንና ንብረት ማጣትን ያስከትላልና። In my view, denial of due process (fair trial) is the highest form of corruption imaginable in the “justice sector” because it results in the arbitrary deprivation of a person’s life, liberty and property. (Al Mariam)
ከሰሞኑ ደግሞ ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም ምንጩ ያልታወቀ ሃብት አፍርተሃል በመባል ተወንጅሎ ወህኒ የወረደው የወልደስላሴ ወልደሚካኤልም ዜና በስፋት እየተሰራጨ ነው። ወልደስላሴ ሌላኛው የአዜብ መስፍን የቅርብ ሰው ነበር። በዚህ ጉዳይ ላይ ዳዊት ከበደ በስፋት ትንታኔ ስለሰጠበት እዚህ ላይ አልደግመውም። ወልደስላሴ ግን ከህወሃት የጫካ ትግል ጀምሮ ቀልፍ ቦታዎች ላይ ተመድቦ የሰራና – የመለስ ቀኝ እጅ የነበረ ሰው ነው። ታማኝ አገልጋይም ስለነበረ በህወሃት ውስጥ ወሳኝ ቦታ ነበረው።
ከወልደስላሴ እስር በኋላ ብዙዎች በህወሃት ውስጥ ውጥረት እንዳለ መናገር ጀምረዋል። ውስጥ ለውስ እየተንከባለለ ያለው ውጥረትማ ከከረረ ትንሽ ዘግየት ያለ ይመስላል። በውጥረቱ የተነሳም በባለስልጣናቱ መካከል እርስ በርስ መተማመን ከጠፋ ቆየ። አንድ ውስጥ አዋቂ ስለዚህ ሁኔታ ሲያጫውተኝ አባላቱ በምሽት ሲወጡ እንደ ጅብ ጎን ለጎን ነው የሚሄዱት። ጅብ ስለሚፈራ ብቻውን አይሄድም። ሁሌም ተጠራርቶ በቡድን ይሄዳል። ከባልንጀራው ጋር አብሮ ሲሄድ ደግሞ ጎን ለጎን መሆን አለበት። ፊትና ኋላ ከሆኑ እርስበርስ ይበላላሉ።
በአሁኑ የህወሃት አሰላለፍ ግን አንደኛው ወገን ከኋሊት መጥቶ የቀደመ ይመስላል። ከፊት ያለው የኋላውን መብላት ጀምሯል። ተገላቢጦሽ የሆነው ይህ አስገራሚ ክስተት ነው ውጥረቱን ይበልጥ ያከረረው። የአዜብን ቡድን የማጥፋቱ ሂደት ላይ ግን ከፍተኛ ጥናት ሳይደረግ አልቀረም። የፖለቲካ ሃይል አሰላለፉ ላይ ሚዛን የደፋው አንደኛው ቡድን ከደሙ ንጹ ባይሆንም የሙስናውን ወንጀል ለብቀላ መጠቀምያ ማድረጉ የአደባባይ ምስጢር ነው።
አንዳንድ የዋሆች ታዲያ ይህ የጸረ-ሙስና ዘመቻ አቶ መለስን ለማሳጣት እየተደረገ ያለ ድራማ እንደሆነ ይናገራሉ። አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝንም የሚያመሰግኑም አልጠፉም። አቶ ሃይለማርያም ብዙውን ክስተት እንደ ተራው ሰው በዜና እንደሚሰሙ የሚያውቁት በቅርብ ያሉት ሰዎች ብቻ ናቸው። ለነገሩ እሳቸውም አስቀድመው “የእኔ ስራ ከፊትም ሆነ ከኋላ የሚሰጠኝን ትእዛዝ እየተቀበሉ ማስፈጸም ብቻ ነው።” ብለዋል። ከፊትና ከኋላ ብቻ ሳይሆን ከላይና ከታችም መመርያ እየተቀበሉ ያስፈጽማሉ። በሙስናው ስም የሚካሄደው ጨዋታ ከሳቸው ራዳር ውጭ ያለ መሆኑን ለመረዳት የፖለቲካ ጥበብን አይጠይቅም።
አቦይ ስብሃት በአንድ ቃለ-መጠይቅ ላይ ስለዚህ ጨዋታ ሲናገሩ የ10 ሚሊዮኑ ዘራፊ ቁጭ ብሎ የ10 ሺው መታሰር የለበትም ብለው ነበር። አቦይ ስብሃት እውነት ብለዋል። ከሌላው ጋር ሲነጻጸር ከአቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ ቤት ተገኘች ተብላ በኢቲቪ ጭምር ስትታይ የነበረችው 26 ሺ ኢሮ ኢምንት ናት። Global Financial Integrity (GFI) በመባል የሚታወቀው አለማቀፍ የገንዘብ ግልጸኝነት ተቋም ከ 2001 እስከ 2010 ብቻ ከኢትዮጵያ ተዘርፎ ወደውጭ የወጣው ገንዘብ 16.5 (አስራ ስድስት ነጥብ አምስት) ቢሊየን ዶላር ነው ሲል መረጃውን ከነማስረጃው ይፋ አድርጓል። ይህ ድርጊት ደግሞ በሙስና ከዘቀጡ ሃገራት ኢትዮጵያን በመጀመሪያው ደረጃ ላይ አስቀምጧታል። ልብ በሉ! 16.5 ቢሊየን ዶላር ከአራት በላይ የ”ህዳሴ” ግድቦችን ያሰራል። ከሁለተኛው አለም ጦርነት በኋላ መላው አውሮፓን ከውድቀት ያስነሳው የማርሻል ፕላን በጀት 20 ቢሊየን ዶላር ነበር። ከኢትዮጵያ በስምንት አመታት ጊዜ ውስጥ ብቻ የወጣው 16 ቢሊየን ዶላር ደግሞ አፍሪካ ካለችበት ውድቀት ሊያስነሳት የሚችል ገንዘብ እንደሆነ የኢኮኖሚ ጠበብት ይናገራሉ።
ኤ.ቢ.ሲ ኢንተርናሽናል የተባለው የማድሪድ ጋዜጣ ወ/ሮ አዜብ መስፍን በአንድ ቀን ግብይት ብቻ ለልብሷ 1.5 ሚሊዮን ዶላር እንዳወጣች ዘግቧል። አዜብ መስፍን ባለፈው የህወሃት ስብሰባ ላይ ተገኝታ ስትናገር ግን የአቶ መለስ የወር ደሞዝ 250 ዶላር እንደሆነ ነበር የተናገረችው። አዜብ የ1.5 ሚሊዮን ዶላር ልብስ በአንዲት ምሽት ስትሸምት መንግስት ድጎማ አድርጎላት ከሆነ ይኸው በይፋ ይነገር። በ250 ዶላር የወር ገቢ በሚሊዮን ዶላር ወጪ ማድረግ የሚቻልበት ሚስጥር የአባባ ታምራት ገለቴ ምትሃት ካልሆነ ታዲያ ምን ሊሆን ይችላል? ይህንን መራራ ሃቅ የጸረ-ሙስናው ኮሚሽንን የሚነዳው ቡድን እንዴት ችላ ሊለው ቻለ? በዚህ ጉዳይ ላይ በርካታ ታዛቢዎች የሚሰጡት አስተያየት የሚያስኬድ ይመስላል። ቡድኑ በቅድሚያ ወደ እነ አዜብ ሰፈር የሚወስደው መንገድ ላይ ያሉ ከእንቅፋቶችን ሁሉ ማጥራት አለበት።
በዛሬይቱ ኢትዮጵያ እንደ ቀልድ የሚነገሩ አንዳንድ እውነታዎች ለማመን የሚከብዱ ናቸው። አንዱ ‘ልማታዊ ባለሃብት’ በሪል ስቴት ስም የተመራው ቦታ ሲሰላ ከጅቡቲ የቆዳ ስፋት በልጦ ተገኘ። ይህ ሰው ትንሽ ቆይቶ ህገ-መንግስታዊ መብቱን በመጠቀም የመገንጠል ጥያቄም ሊያነሳ ይችላል እያሉ ያወሩ ነበር – በዚያ የቀኑት ባልንጀራዎቹ። በመጨረሻ ግን “ባለሃብቱ” በሙስና ታሰረና ይዞት የነበረው መሬት ለነ ቱሬ ዘመዶች በሄክታር ሁለት ብር ሂሳብ ተቸበቸበ። ለነገሩ 3.5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ከዜጋው እየተቀማ ለውጭ ዜጎች በተቸበቸባት ሃገር ይህ ምንም ላይደንቀን ይችላል።
የሙስና ሰለባ የሆነው የሌላኛው ባለስልጣን ቤት ሲበረበር ደግሞ ብሄራዊ ባንክ ይመስል ነበር። እዚያ ቤት ውስጥም የአለም መገበያያ ገንዘብ ተገኘ። ዶላር፣ ኢሮ፣ ድራም፣ የን፣ ፓውንድ፤ ክሮን፤ ፍራንክ፣ ዲናር፣ ረንቢኒ … እንዲያውም የኤርትራ ናቅፋ በገፍ ነበር። ከአቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ 26 ሺ ዶላር ተጋንና በቲቪ ስትቀርብ የዚህኛው ንግድ ፈቃድ የሌለው ባንክ በግል እጅ ሲገኝ ሜዲያም ዝም ማለትን መረጠ። በዚህ ጊዜ ነበር የአሳሪው ቡደን ሃላፊ የኮሎኔል መንግስቱን ንግግር የተጠቀመው። “ደፍረውናል፣ ንቀውናል።.. ብታምኑም ባታምኑም በቁም ሞተናል።”
አነጋገሩ ለምን ሃገር ተዘረፈ ሳይሆን እኛ ታግለን ለዚህ የደረስን የቁርጥ ቀን ታጋዮች ቁጭ ብለን እንዴት ከኋላ የመጣው ሊበልጠን ቻለ ለማለት ነበር። የሙስናው ዘመቻ ድራማ ቁልፍ እዚህ ላይ ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ ወደፊት በሰፊው እሄድበታለሁ። ለአሁን ግን በአቶ ኤርምያስ አመልጋ የሚደነቅ ታሪክ ጽሁፌን ልቋጭ።
በዚያ ሰሞን የአክሰስ ሪል ስቴት ሥራ አስኪያጅና የቦርድ ሰብሳቢ የነበሩት አቶ ኤርምያስ ጠቅል አመልጋ፣ በተለይ በውጪ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለመኖሪያ ቤት ግንባታ ከ1.4 ቢሊዮን ብር በላይ ከሰበሰቡ በኋላ፣ ከሃገር መጥፋታቸው ተዘግቦ ነበር። ታዲያ አቶ ኤርምያስን የሚረግሙ ጌጃ ዲያስፖራዎች እንዳሉ ሁሉ እሳቸውን የሚያደንቁም አልጠፉም። ስለአቶ ኤርምያስ በቀልድ እየተመሰለ ብዙ ነገር ይወራል። የተከበሩ ሎሬት አፈወርቅ ተክሌን እና አቶ ኤርምያስን የሚያመሳስላቸው ነገር ቢኖር ሁለቱም የተዋጣላቸው ሰአሊያን መሆናቸው ነው ተብሏል። ለላሜ ቦራው ዲያስፖራ እንዲሰሩ ገንዘብ የተከፈለባቸው ቤቶች ሁሉ ባማሩ ስዕሎች በወረቀት ላይ ዱቅ ብለዋል። በንዴት ገንዘቡን ሊያስመልስ የሚሄደው ሁሉ በስእሎቹ እና በአቶ ኤርምያስ ምትሃታዊ ንግግር እየተማረከ እንዲያውም ለሁለተኛና ሶስተኛ ቤት የከፈለው ዲያስፖራ ቁጥር ትንሽ አይደለም። አቶ ኤርምያስ በአንድ በኩል በሙስና ክስ እየተፈለጉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ከሃገር በቦሌ አድርገው እንዲወጡ የተደረጉ “ጀግና” ባለሃብት ናቸው።
ለፖለቲካው እንግዳ ለሆኑ ሰዎች፤ እነዚህ ሁሉ ፈጠራ ሊመስሉ ይችላሉ። ግን የኢትዮጵያ ህዝብ የእለት ተለት ገጠመኞች ውስጥ አንድ እጅ እንኳን የማይሞሉ እውነታዎች ናቸው።


የሃማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ አስፈላጊ ነበር??? (በይበልጣል ጋሹ)

$
0
0

በይበልጣል ጋሹ

የሃይማኖት ጉባኤ ሰላማዊ ሰልፍይህ ጉባኤ በዋናነት የተቋቋመው ለአገር ሰላምና በእምነት ተቋማቸው ለሚያስተዳድሩት ህብረተሰብ(የእምነት ተቋም) ደህንነት እንጂ ለመንግሥት ወይም ለአንድ የፖለቲካ ድርጅት አይደለም። በተለይ ደግሞ ይህ ጉባኤ በእምነት ትቋማት መካከል አለመግባባት እንዳይፈጠር እና ወደ አልተፈለገ ግጭት/እሰጣ ገባ/ ውስጥ እንዳይገባ ሁሉም የየራሱን የሃይማኖት አስተምሮ በመቻቻል እንዲሁም ሰላምና ፍቅር በተሞላበት መንገድ እንዲያካሂዱ ለማድረግ አመስለኝም።

በትናትናው እሁድ ማለትም በ26/12/2005 ዓም የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ግን ከዓላማው በእጅጉ የራቀ እና ሁኔታዎችን ያላገናዘበ መስሎ ይታያል። እርግጥ ነው ይህ ጉባኤ አገራዊ ሰላም ሊያደፈርሱ ይችላሉ ብሎ ያመነባቸውን ጉዳዮች ለህዝብ ይፋ ማድረጉ የሚበረታታና ለወደፊትም ሊቀጠልበት የሚገባ ተግባር ነው። ነገር ግን ይፋ ከማድረጉ በፊት የሃይማኖት ኮሚቴ እንደመሆኑ መጠን በርካታ ቅድመ ስራዎች ሊኖሩት ይገባል። የህብረተሰቡን ነባራዊ ሁኔታ፣ የእምነት ተቋማት አመለካከትና የፖለቲካ አቅጣጫን በሚገባ ማጤን ከዚህ ትልቅ ከሚቴ ቀርቶ ከአንድ ግለሰብ ሊሰወር የማይገባ ነገር ነው።

የህብረተሰቡን ነባራዊ ሁኔታ በትክክል መገንዘብ ያስፈልጋል ሲባል የተፈጠረውን ችግር ህብረተሰቡ በምን መልኩ ነው የተረዳዉ፣ ሰላማዊ ሰልፍ ሊያስወጣ በሚችል መልኩ ነው? ውይስ የግንዛቤ እጥረት አለበት? ወይስ በሌላ አቅጣጫ ነው የተረዳው? የሰላማዊ ሰልፍ አስፈላጊነት? እና መሰል ጥያቄዎችን በማንሳት ህብረተሰቡ ያላበትን የግንዛቤ ደረጃ መለካት፣ ማጤንና መመልከት ይገባል። እንዲሁም ህብረተሰቡን ግንዛቤ ከማስጨበጥ አንጻርም ይህ ኮሚቴ ትልቅ ኃላፊነት አለበት። ሰላማዊ ሰልፍ ወይም ውሳኔ ከመወሰኑ በፊት የችግሩን አሳሳቢነት ማለትም በአገርና በሃይማኖት ተቋማት ላይ ሊያመጣ የሚችለውን ችግር በሚገባ በተለያየ መልኩ ማስረዳትና ማሳወቅ፣ መግለጽና ማስተላለፍ ይኖርበታል። ምናልባት ኮሚቴው ይህን አድርጊያለሁ ቢልም በቂ ነው ብዬ አላምንም። በዚህ መልኩ ህብረተሰቡን ማንቃትና ወደ አንድ የግንዛቤ መንፈስ እንዲመጣ ሳያደርጉ ውሳኔ መወሰን ይባስ ብሎ አገራዊ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራት ከጥቅሙ ጉዳቱ እጅግ የከፋ ይሆናል።

የእምነት ተቋማት አመለካከት ምን ይመስላል የሚለውንም በሚገባ መረዳት የኮሚቴው ተቀዳሚ ተግባር ነው። የዚህን ኮሚቴ የእያንዳንዱ አባል የወከለው የእምነት ተቋሙ ነው። ስለዚህ ከእምነት ተቋሙ ጋር መነጋገር፣ መወያየት፣ የችግሩን አመጣጥና ሁኔታ፣ በተቋሙ ላይ ሊያስከትለው የሚችለውን ችግር በሚገባ ማየትና ተደጋጋሚ ውይይቶች ያስፈልጋሉ። ችግሩ ተፈጠረ ከተባለበት ተቋም ወይም ቦታ ድረስ በመሄድ ችግሩን በውውይት ለመፍታት መሞከር ይኖርበታል። በእኔ አመለካከት የሃይማኖት ተቋማት ከመንግሥትም በላይ ለሰላምና ለህብረተሰቡ ደህንነት የሚቆሙ ናቸው። ስለዚህ ችግሩን በውይይት፣ በትምህርትና በተግሳጽ ለመፍታት መጣር ያስፈልጋል። ኮሚቴው እንደኮሚቴ ከመወሰኑ በፊት ከወከለው የእምነት ተቋም ጋር ግልጽ ውይይት አድርጎ ችግሩን ሊፈታ በሚችል መልኩ አንድ አቋም መያዝ ይኖርበታል። በእውነት የትናቱ ሰላማዊ ሰልፍ ግን የተፈጠረውን ችግር ሊፈታ ይችል ነበር??? መልሱን ለእናንተ ትቸዋለሁ።

ይህ ኮሚቴ ከፖለቲካ ነጻ እንደመሆኑ መጠን / በወረቀት ደረጃ ማለቴ ነው/ አንድ ውሳኔ በሚወስንበት ጊዜ የፖለቲካ አቅጣጫውን መመልከት ያስፈልገዋል። ምንም እንኳ ሃይማኖትና መንግሥት የተለያዩ ናቸው ቢባልም መንግሥት ከሃይማኖት ነጻ ሁኖ ስለማያውቅ አቅጣጫውን እና ሂደቱን ከውሳኔ በፊት መረጃዎችን መሰብሰብና መፈተሽ ያስፈልጋል። የህብረተሰቡ የፖለቲካ አመለካከት ምን ይመስላል? የገዢው ፓርቲ ያለበት ደረጃ? የተቀዋሚ የፖለቲካ እንቅስቃሴና ሌሎችንም ተያያዝ ነገሮችን መፈተሽ ይኖርበታል። እነዚህ ሁኔታወችን ሳይገነዘብ ወደ ውሳኔ ከገባ ግን በአንድ ተጽዕኖ ውስጥ ሊገባ ይችላል፤ ይኸው ገባም። የሃይማኖት ተቋም የሰላም ኮሚቴ ተብሎ  በአንድ ተጽዕኖ ውስጥ ዥው ብሎ መግባት ግን ችግሩ እንዲበባስ ያደርገዋል፤ በተጫማሪም ሌላ ችግር ይፈጥራል እንጂ መፍትሔ ሊያመጣ አይችልም።

ጉባኤው መመልከት ያልቻላቸው ግልጽ ነገሮች፦

  1. ችግሩን፦ ጉባኤው በአዲስ አበባ በ10 ክፍለ ከተሞችና በ116 ወረዳዎች በተካሄደው ህዝባዊ የሰላም ኮንፈረንስ እንዲሁም ከፍትህ ቢሮ ጋር በመተባበር ከነሐሴ 15-16 በተካሄደው የሰላም ኮንፈረንስ ላይ የሃይማኖት መሪዎችና ተከታዮቻቸው «ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከተማችን እየታየ ያለው የአክራሪነትና የፅንፈኝነት እንቅስቃሴ የሀገራችንን ሰላምና ልማት የሚያውክ፣ በሰላም አብሮ የመኖር እሴቶቻችንን የሚያናጋና የሃይማኖት መልክ የሌለው የጥፋት እንቅስቃሴ ከመሆኑም በላይ በህገ መንግሥታችን የተደነገገውን የሃይማኖት እኩልነትና የእምነት ነፃነት የሚፃረር ስለሆነ በሰላማዊ ሰልፍ ተቃውሟችንን ማሰማት እንፈልጋለን» ተብሎ በአቋም መግለጫ የተላለፈውን መሰረት በማድረግ ሰልፉ እንደተዘጋጀ በጋዜጣዊ መግለጫ ስለሰልፉ አስፈላጊነትም በማብራራት ሰላማዊ ሰልፉ በመጪው እሁድ ከንጋቱ 12 ሰዓት በመስቀል አደባባይ የሚካሄድ ሲሆን፤ በከተማው ውስጥ ያሉ የሃይማኖት ተቋማት በሙሉ በጋራ በመሆን ለሰላም፣ ለልማት፣ ለመቻቻልና ለአብሮነት ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚገልጹበት የሰላም መድረክ ነው//፤ በማለት የጉባኤው ኮሚቴ በገለጸልን መልኩ ችግሩን ሙሉ በሙሉ እንውሰደው ብንል እንኳ የሃይማኖት አክራሪነት ከመቼ ወዲህ ነው በሰላማዊ ሰልፍ ሊገታ የሚችለው። ኃያላን አገራት እንኳ በተደራጀና ዘመናዊ ስልትን በመጠቀም አክራሪነትን ማቆም ሳይችሉ እኛ እንዴት ነው በሰላማዊ ሰልፍ ልናቆመው የምንችለው። እንደ አገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ሰላማዊ ሰልፍ ለሰላማዊ ትግልም ልንጠቀምበት አልታደልንም። ስለዚህ ጉባኤው የሃይማኖት አክራሪነትን በሰላማዊ ሰልፍ ለመግታት መሞከሩ የችግሩን ምንነት አለመረዳት ነው። ችግሩን በሚገባ ሳይረዱ ደግሞ ውሳኔ መወሰኑ ከመፍትሔው ይልቅ ጉዳቱ እንደሚያመዝን ብዙ መናገር የሚያስፈልግ አይመስለኝም። ችግሩም መቶ ፐርቸንት/100%/ አክራሪነት ነው ብሎ ለመፈረጅ ማስረጃ የሚያጥር ይመስለኛል። በግሌ አክራሪነት የለም፣ አይኖርም የሚል አመለካከትና ግንዛቤ የለኝም። ቢሆንም ግን በሰላማዊ ሰልፍ ከችግሩ እንወጣለን የሚል እምነት ፍጽሞ አይኖረኝም።
  2. ስዓት፦ ሰላማዊ ሰልፉ እንዲጀመር የተደረገበትን ስዓት እንኳን ስንመለከተው ጉባኤው ከወከለዉ የእምነት ተቋም ጋር ጥብቅ ውይይት አለማድረጉን በቀላሉ መመልከት እንችላለን። በተለይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ያን እና ሌሎችም ማለት ይቻላል በየሳምንቱ እሁድ ጥዋት የአምልኮት ስርዓታቸውን የሚፈጽሙበት ስዓት ነው። ስለዚህ ስዓቱን እንኳ ያገናዘበ ሰላማዊ ሰልፍ አለመጥራት የግደለሽነት ያስመስላል። ወይም በሌላ ተጽዕኖ ውስጥ መሆኑን በግልጽ ለመረዳት አያዳግትም። በተጽዕኖዎችና በግደለሽነት የሚደረጉ ማንኛውም ነገሮች ደግሞ ችግርፈጣሪ እንጂ ችግር ፈቺ መቸውንም አይሆኑም።
  3. ቀን፦ በሰላማዊ ሰልፉ አስፈላጊነት ጉባኤው ካመነ በቀላሉ ሊመለከተው የሚገባው ነገር የሚደረግበትን ቀን ነው። በዚያ ቀን ምን ተያያዥ ነገር አለ? ቀኑ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል፣ ለእምነት ተቋማትና ለፖለቲካ ፓርቲዎች ምቹ ነው? የሚለውን ጥያቄ ጉባኤው ከመወሰኑ በፊት መመልከት ይኖርበት ነበር። ጉባኤው ግን በተቃራኒው የተጓዘ ይመስላል። ይህ ቀን ማለትም 26/12/2005 ዓ.ም ግን ሰማያዊ ፓርቲ የአገር ሰላም እንዲሰፍን፣ ሰባአዊ መብት እንዲከበር፣ ዲሞክራሲ እንዲሰፍን፣ ከአላግባብ የታሰሩ ዜጎች እንዲፈቱ፣ እኩልነት እንዲረጋገጥ፣ ሙስናና አገርን ወደ ኋላ ሊጎትቱ የሚችሉ ችግሮችን ለመቅረፍና ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ለመፍጠር ከመንግሥት እንኳ ሳይቀር ፍቃድ ጠይቆ ለ2ተኛ ጊዜ  ሰላማዊ ሰልፍ የጠራበት ቀን ነበር። ጉባኤው ግን ይህን ሳያገናዝብ በመጥራቱ ለፓርቲው አባላት እስራት፣ እንግልትና ድብደባ ምክንያት ሁኗል። ፓርቲው የጠራው ሰላማዊ ሰልፍም በእስራትና በድብደባ እንዲቀየር አድርጎታል። ሙሉ በሙሉ ጥፋቱ የመንግሥት ቢሆንም የጉባኤው አባላት ለዚህ ተግባር ተባባሪ በመሆናቸው ተጥያቂ አድርጓቸዋል። ሌሎችን እናተ ጨምሩበት…….

በአጠቃላይ የጉባኤው ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ አስፈላጊ ነበር የሚለውን ሁላችንም በራሳችን አስተያየት እንስጥበት እና እንማርበት። አስፈላጊ አልነበረም ለምንል ሰዎች ወደፊት እንዲህ አይነት ተያያዥ ክስተቶች እንዳይፈጠሩ ምን እናድርግ ለማለት ሃሳብ መለዋወጡ መልካም ስለሚሆን ለመነሻ ያክል የግሌን ሃሳብ አቅርቢያለሁ።

ሰላማዊ ትግል በካዮች እና መከላከያ ምክሮች! (ግርማ ሞገስ)

$
0
0

ግርማ ሞገስ (girmamoges1@gmail.com)
ማክሰኞ ነሐሴ 28 ቀን 2005 ዓ.ም. (Tuesday, August 03, 2013)

 

(ግርማ ሞገስ)

(ግርማ ሞገስ)

ህውሃት (መንግስት) ህዝብን የሚገዛበት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ አቅሙ ከሰማይ የሚወርድለት ወይንም በተፈጥሮው ከውስጡ የሚንጠፈጠፍለት ሳይሆን ከህዝብ የሚነጭለት ነው። ፖሊሱም፣ ደህንነቱም፣ የኢቲቪ ሰራተኛውም፣ የቃሊቲ አስተዳዳሪውም፣ የኢምባሲ ሰራተኛውም፣ ወ.ዘ.ተ. ከህዝብ የሚመለመሉ ናቸው። ለህውሃት በደሞዝ ክፍያ ያገልግሉ እንጂ የሰዎቹም ሆኑ የደሞዛቸው ምንጭ ህዝብ ነው።በግብር እና በሌሎች ምክንያቶች ከህዝብ የሚሰበሰብ ነው ደሞዛቸው። አሊያም በኢትዮጵያ ህዝብ ስም ከውጭ በዕርዳታ፣ በብድር ወይንም በሌሎች ስምምነቶች የሚያገኘው ነው ደሞዛቸው። የፋብሪካ፣ የኢንዱስትሪ፣ የመገናኛ፣ የትራንስፖርት፣ የአየር መንገድ፣ የመድህን ሰራተኞች፣ የንግድ እና አገልግሎት ድርጅቶች ወ.ዘ.ተ. በሙሉ ስራ ቢያቆሙ ከህዝብ መንጭቶ ወደ ህውሃት የሚፈሰው ሃብት ብር ይቋረጣል። ህውሃት ለፖሊስ፣ ለደህንነት እና ለመሳሰሉት ሽብርተኛ ስልጣን ጠባቂዎቹ የሚከፍለው ደሞዝ ያጥረዋል። እነሱም ደሞዝ ካልተከፈላቸው አያገለግሉትም። ስለዚህ የህውሃት የፖለቲካ አቅም ይዳከማል። ብሎም አቅሙ ከምንጩ ይደርቃል ማለት ነው። በመጨረሻ ተርቦ ይሞታል ህውሃት። እንደምናስተውለው ከሆነ ከዚህ በፊት በፈጸማቸው ይቅርታ በማናደርግለት የተለያዩ የፖሊሲ ስህተቶች ላይ ህውሃት ዛሬም በቀጣይነት በህዝብ ላይ ተከታታይ መብት ረገጣዎች እና የኢኮኖሚ ቀውሶች እየፈጠረ ነው። ሰላማዊ ዜጎችን ሽብርተኞች እያለ ሽብርተኛው እራሱ መሆኑን ለኢትዮጵያ ህዝብ ግልጽ እያደረገ ነው። ህውሃት የፖለቲካም ሆነ የሞራል ብቃት እንደሌለው የኢትዮጵያ ህዝብ እያወቀ ነው። ባቡር ሃዲዱንም፣ ህንጻዎቹንም፣ መንገዶቹንም፣ ግድቦቹንም ህዝቡ እራሱ ለራሱ በራሱ የገነባል። ህውሃት አያስፈልገውም። ተቃዋሚውም ከምንጊዜውም የተሻለ በስሏል። ቀጣይነት ያለው ሳይኮሎጂያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ፈርጆች ያሉት ሰላማዊ ትግል በማድረግ ላይ ይገኛል።

 

የሰላማዊ ትግል ማራመጃ መሳሪያዎች (በጠብ መንጃ ምትክ) በቁጥራቸው 200 ያህል ሲሆኑ በጸባያቸው ተዛማጅ እና ውስብስብ ናቸው። ይሁን እንጂ የአልበርት አነስታይን ሰላማዊ ትግል ምርምር ተቋም ባልደረቦች እነ ጅን ሻርፕ የመሳሰሉት የዘመናዊ ሰላማዊ ትግል የፖለቲካ ሳይንስ ጠበብቶች እነዚህን 200 ሰላማዊ ትግል ማራመጃ መሳሪያዎች ማጥናት እንዲቻል ለማድረግ በሶስት አብይ ክፍሎች ከፍለዋቸዋል። እነሱም (1ኛ) ተቃውሞ እና ማግባባት (Protest and Persuasion) ፣ (2ኛ) የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ትብብር መንፈግ (non-cooperation) እና (3ኛ) ጣልቃ መግባት (intervention) ይባላሉ። እስካሁን በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ የሚገኘው ሰላማዊ ትግል በ(1ኛው) ክፍል የሚመደብ ነው። ይሁን እንጂ ህውሃት (መንግስት) በተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ በገበሬው፣ በሰራተኛው፣ በተማሪው፣ በእስረኛው፣ በነፃ ጋዜጠኞች፣ መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ አይግባ በሚል መርኽ እንከን የለሽ ሰላማዊ ትግል በማኪያሄድ ላይ በሚገኙት ኢትዮጵያውያን ሙዝሊም ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ላይ የሚፈጽመው ወከባ፣ ድብደባ፣ እገታ፣ ግድያ ሰላማዊ ትግሉን ወደ (2ኛው) ደረጃ እንዲሸጋገር እየገፋው ነው።

የሆነው ሆኖ ሰላማዊ ትግል ውስብስብ ነው። በረጅም ማስተዋልን፣ በረጅም ማስላትን፣ የትግል ብስለትን፣ ትዕግስትን፣ ጀግንነት፣ ፅናትን ሁሉ ይጠይቃል። ያ ብቻም አይደለም። ሰላማዊ ትግል ከጀብዱኛነት ነፃ መሆንን፣ ለግል ስም እና ዝና ከሚደረግ ሽሚያ መራቅን፣ እራስን ሳይሆን ህዝብን የመንግስት ስልጣን ባለቤት በማድረግ ላይ ማትኮርን ይጠይቃል። ያ ብቻም አይደለም። የህውሃት ሰርጎ ገቦች ሰለባ አለመሆንን፣ ከቀረው ተቃዋሚ እኔ እሻላለሁ ከሚል ደካማ ስሜት መራቅን፣ ለክፍፍል ቀዳዳ አለመስጠትን እና የመሳሰሉትን ሁሉ ይጠይቃል ሰላማዊ ትግል። ያ ብቻም አይደለም። በሌሎች አገሮች ስለተደረጉ (የተሳኩም ያልተሳኩም) ሰላማዊ ትግሎች ተመክሮዎችን በስፋት እና በጥልቀት ማወቅም ይፈልጋል። ከእነዚህ ከተዘረዘሩት ውስጥ አንዱ ወይንም ሁለቱ ቢከሰቱ ወይንም ቢጓደሉ ሰላማዊ ትግል ይበክላል።

 

በምርጫ ጊዜም ብክለቶች ሊከሰቱ ይችላሉ። የምርጫው ውጤት አንድ አምባገነን አውርዶ በአዲስ አምባገነን መተካት ወይንም ለመፈንቅለ መንግስት ቀዳዳ መክፈት እንዳይሆን አስፈላጊውን ፕላን ቀደም ብሎ ማስላት ያስፈልጋል። አሊያ በግብጽ ያየነው ሊከሰት ይችላል በኢትዮጵያ። የግብጽ ሰላማዊ ትግል የሙባረክን አምባገነን መንግስት ካስወገደ በኋላ በተደረገው ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ አራት ግለሰቦች እንደተወዳደሩ እናስታውሳለን። በቅርብ ከስልጣን የወረደው ሞርሲ (ሃይማኖትን ከፖለቲካ ጋር የሚቀላቅለው) በምርጫ ያገኘው የህዝብ ድምጽ 12 ሚሊዮን ግድም ሲሆን የቀሩት ሶስቱ (ሃይማኖትን ከፖለቲካ የማይቀላቅሉት) ግለሰቦች ያገኙት የህዝብ ድምጽ ድምር 21 ሚሊዮን ግድም ነበር። ሶስቱ አርቆ ማየት ስለተሳናቸው፣ የግብጽን ህዝብ የመንግስት ስልጣን ባለቤት ማድረግን ከማስቀደም ፈንታ እራሳቸውን (ፓርቲያቸውን) በማስቀደማቸው በህብረት መቆም ተሳናቸው። ስለዚኽ ሶስቱ ያገኙትን የህዝብ ድምጽ ለሶስት ሲካፈሉት ሞርሲ አሸነፋቸው። ዛሬ ላይ ቆመን ሁኔታውን ወደ ኋላ ስንመለከተው ግብጽ አጭሩን የዴሞክራሲ መሸጋገሪያ ድልድይ የሳተቸው ያን ጊዜ ነበር ማለት ይቻል ይሆናል። ዛሬ እንደምናየው ግብጽ እረጅሙን መንገድ በመጓዝ ላይ ነች።

 

በተቃራኒው ከፍ ብለን ያነበብናቸው በምርጫ ጊዜ ሊከሰቱ የሚችሉ ብክለቶችን በዘዴ ያስወገደች አገር ሰርቢያ ናት። በሰርቢያ ሰላማዊ ትግል ሲያደርጉ የነበሩት የተቃዋሚ ፓርቲዎች ቁጥራቸው 16 ነበሩ። እነዚኽ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከምርጫ ቀደም ብለው ህብረት በመፍጠር የሞልሶቪችን አምባገነን መንግስት ህገ-መንግስት እንዲያከብር ሲታገሉት ቆይተዋል። የሆነው ሆኖ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2000 ዓ.ም. በተደረገው ምርጫ የሰርቢያ 16 ተቃዋሚ ፓርቲዎች ህብረታቸውን ጠብቀው የሞልሶቪችን አምባገነን መንግስት ተፎካክረው በቀላሉ አሸነፉ። ሞልሶቪች ግን ድምጽ ሰርቆ ምርጫውን አሸንፌያለሁ አለ። በህብረት የቆሙት 16 ፓርቲዎች “የህዝብ ድምጽ ይከበር” የሚል ሰላማዊ ትግል ጥሪ አደረጉ። ህዝቡም “ድምጻችንን ካላከበርክ እኛም መንግስትህን አናከብርም” ብለው ሰላማዊ ትግሉን ተቀላቀሉ። ከዚያ መሸነፉን ከመቀበል በስተቀር የተሻለ አማራጭ እንደሌለው ሲገነዘብ ሞልሶቪች ሽንፈቱን ተቀብሎ ሰላማዊ የመንግስት ሽግግር ተደረገ። 16 ተቃዋሚ ፓርቲዎች የህብረት መንግስት መሰረቱ። ቀደም ብለው ባደረጉት ስምምነት መሰረት የሞሊሶቪችን አምባገነን መንግስት ካስወገዱ በኋላ ለተወሰኑ አመቶች በህብረት ገዙ። በህብረት ለመግዛት የተስማሙበት ዘመን (ሁለት ወይንም ሶስት አመቶች መሰለኝ) ሲያልቅ ነፃ ምርጫ ጠሩ። ለመጀመሪያ ጊዜ በሰርቢያ ታሪክ ነፃ ምርጫ የተደረገው በዚህን ጊዜ ነበር። አብላጫ የህዝብ ድምጽ ያገኘው ፓርቲ አገር አስተዳዳሪ (ገዢ ፓርቲ) ሲሆን ዝቅተኛ የህዝብ ድምጽ ያገኙት ፓርቲዎች ተቃዋሚ ፓርቲ በመሆን የፓርላማ ትግላቸውን ጀመሩ። በዚኽ አይነት ሰርቢያዎች የአገራቸውን የዴሞክራሲ ሽግግር አጭር እና ከውጣ ውረድ የጸዳ ማድረግ ችለዋል። ስልጣን ከለቀቀ በኋላ ብዙም ሳይቆይ በዘር ማጥፋት ወንጀል ተከሶ በአለም አቀፍ ፍርድ ቤት እስር ቤት ሳለ ሞተ ሞልሶቪች።

 

ኢትዮጵያችን ከግብጽም ከሰርቢያም መማር አለባት። ስለዚህ በኢትዮጵያ በዘልማድ ሰላሳ ሶስቱ ተብሎ የሚጠራው ቡድን፣ መድረክ እና አንድነት ከግብጽም ከሰርቢያም ከሌላም ይማራሉ ብለን እንገምታለን። የኢትዮጵያን ህዝብ የመንግስት ስልጣን ባለቤት ማድረግ ቀዳማይ ግባቸው ነው ብለን እናምናለን። ግባቸው ይኽ ከሆነ ደግሞ በመካከላቸው የሚኖረው ልዩነት ሁሉ-በጁ ሁሉ-በደጁ ከሆነው ከህውሃት መንግስት ጋር ካላቸው ልዩነት ጋር ሲነጻጻር እጅግ የደበዘዘ መሆን አለበት። በመድረክ እና በአንድነት ወይንም በ33 መካከል ያሉትን የመርህ ልዩነቶች እናውቃቸዋለን። ከህውሃት ጋር ካላቸው ልዩነት ጋር ሲነጻጸሩ ግን ጊዜ የሚሰጡ ናቸው። እስከዛሬ ድረስ ደክማችሁ የገነባችሁትን ህብረት እንደ ሰርቢያዎች ከብክለት ጠብቃችሁ ሰላማዊውን ትግል እንደምትመሩ ተስፋ እናደርጋለን። ከህውሃት መንግስት በኋላ የተወሰኑ አመቶች በህብረት ገዝታችሁ ነፃ ምርጫ መጥራት ትችላላችሁ ብለን እናምናለን። ከውስጣችሁ አብላጫ የህዝብ ድምጽ ያገኘው ፓርቲ ገዢ ፓርቲ ይሆናል። የቀራችሁት ተቃዋሚ በመሆን በፓርላማ ትግላችሁን መቀጠል ትችላላችሁ ሰርቢያዎች እንዳደረጉት። ይኽ የምር የህልውናችን ጉዳይ ነው።  ኢትዮጵያ እያስተዋለቻችሁ ነው። ዜጎችም ዝም ብለን ተመልካቾች አንሆንም።

ስለዚህ በላንበት መሄዳችንን አቁመን ከአምባገነን ገዢ ህውሃት ነፃ ለመውጣት እና የኢትዮጵያን ህዝብ የመንግስት ስልጣን ባለቤት የማድረግ ምኞታችንን ከፍጻሜ ለማድረስ ከፈለግን ሰላማዊ ትግላችንን ሊበክሉ የሚችሉ ተግባሮችን፣ አሰራሮችን እና ሁኔታዎችን ማወቅ እና ማስወገድ ይጠበቅብናል።

 

የሰላም ትግል አቀንቃኝ ሮበርት ሃርቬይ (Robert L. Harvey) “ስትራተጂያዊ ሰላማዊ ትግል” በሚል ርዕስ በአልበርት አነስታይን ተቋም ድረገጽ [www.aeinstein.org] ላይ ባተመው የጥናት ጽሑፉ ውስጥ የሰላማዊ ትግል በካዮች (Contaminants of Peaceful Struggle) በሚል ጽፏል። የሰላማዊ ትግልን መበከል ከመኪና ነዳጅ መበከል እና ከመኪናዋ እንጂን መቃጠል ጋር እንደሚከተለው ያመሳስለዋል። ለጥቆም በርካታ ምክሮችን ይለግሰናል። የሮበርት ሃርቬይ ፍሬ አሳብ እንደሚከተለው በአጭሩ ሊቀርብ ይችላል፥

 

“የመኪና ነጃ (ቤንዚን) ውስጥ ውሃ ከጨመርክ ነዳጁን እንደበከልከው ማወቅ አለብህ። በውሃ የበከልከውን ነዳጅ  ተጠቅመህ መኪናዋን ከቆመችበት ለማስነሳት ብትሞክር ጤናማ ያልሆነ ድምጽ ልትሰማ ትችላለህ። መኪናዋን ማስነሳትም አስቸጋሪ ሊሆንብህ ይችላል። ነዳጁ ውስጥ የከለስከው የውሃ መጠን ከፍ ካለ ደግሞ መኪናዋ ፍጹም ላትነሳ ትችላለች። አልፎም የመኪናዋ ኢንጂን (ሞተር) ሊቃጠል ይችላል። የተበከለ ሰላማዊ ትግልም እጣው እንደዚሁ እንደመኪናዋ ኢንጂን (ሞተር) መቃጠል ወይንም መሞት ነው” ይለናል። ይኼን ካለን በኋላ ሰላማዊ ትግልን ሊበክሉና ለአደጋ ሊያጋልጡት አልፎም ሊገሉት የሚችሉ ተግባሮችን፣ አሰራሮችን እና ሁኔታዎችን በሰፊው ያብራራል። ሙሉውን ጽሑፍ ከፍ ብዬ ከጠቀስኩት ከልበርት አነስታይን ሰላማዊ ትግል ምርምር ተቋም ድረገጽ ማግኘት ይቻላል።

 

ሮበርት ሃርቬይ በጽሑፉ ከጠቀሳቸው በካይ ተግባሮች፣ አሰራሮች እና ሁኔታዎች ውስጥ ጥቂቱን እና ከሌሎች ምንጮች የተወሰዱ ተዛማጅ በካይ ሁኔታዎችን እና መከላከያ ምክሮችን ከኢትዮጵያ ሁኔታ ጋር በማዛመድ በዚህ ጽሑፍ በአጭር በጭሩ ለውይይት ቀርበዋል፥

 

(1) ኃይል እና ክፉ-ቃሎች በማንኛውም መልካቸው ቢሆን ሰላማዊ ትግልን ይበክላሉ። የኢትዮጵያ ሰላማዊ ትግል ሰራዊት የማሳመን እና የማግባባት ማለትም ሰላማዊ ሰልፍ፣ ህዝባዊ ስብሰባ፣ የህዝብ ፊርማ ማሰባሰብ፣ ወ.ዘ.ተ. ሰላማዊ ትግሎች ሲያደርግ ኃይል አይሻም። ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ ትብብሮች የመንፈግ ትግል ሲያደርግም ሰላማዊ የሚሆነው። የህውሃት (የመንግስት) የፖለቲካ ድጋፍ ሰጪ ምሶሶዎችን ማለትም የሃይማኖት ተቋማት፣ የመምህራን እና ሰራተኛ ማህበሮችን፣ ወ.ዘ.ተ. ከህውሃት ካድሬዎች ቁጥጥር ነፃ ለማውጣት ወይንም በሌሎች ለመተካት የሚደረግ ትግልም ሰላማዊ ነው። የውጭ ለጋሽ አገሮችን ዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ ከውሃት ለመንጠቅ የሚደረጉም ዲፕሎማሲያዊ ትግሉችም ሰላማዊ ናቸው። እነዚህን ሁሉ ትግሎች ሲያደርግ የሰላማዊ ትግል ሰራዊት ኃይል አይጠቀመም። እንኳን ኃይል ክፉ ቃል አይጠቀመም። ይኽ ሁኔታ ሰለሰላማዊ ትግሉ የሚዘገቡ ዜናዎች እና የሚሰጡ መግለጫዎችን ይጨምራል። የሰላማዊ ትግል ዘገባዎች እና መግለጫዎች ከጀብዱኛ ፉከራ እና ቀረርቶ ነፃ ሊሆኑ ይገባል። ገና ምኑም ሳይያዝ ስለድል አድራጊነት መጻፍ የሚወዱ ሰዎች አሉ። ያን ማድረግ አስፈላጊም ጠቃሚም አይደለም። መንግስትን ወይንም የመንግስት ካድሬዎችን ለማበሳጨት ተብሎ የሚጻፍ ከሆነም ስህተት ነው። እንዲያውም ከተቻለ ካድሬዎችን ሳይቀር ሰላማዊ ትግል ይስባል (PULL ያደርጋል) እንጂ አይገፋም (PUSH አያደርግም)። የሰላም ትግል ሰራዊት ስለጀግንነቱ ማውሪያ ጊዜም የለውም።

 

(2) ሰላማዊ ትግላችን ወደ ኃይል ከተንሸራተተ ተበከለ ማለት ነው። ሰላማዊ ትግል አምባገነኖችን የሚገጥማቸው በደካማ ጎናቸው እንጂ በጠንካራ ጎናቸው አይደለም። ይኽን መሰረታዊ መርህ መዘንጋት እና በጀብዱኛነት የኃይሉን መንገድ መቀላቀል ሰላማዊ ትግላችንን ሊበክል እና ሊገድለው ይችላል። በሶሪያ እንደሆነው። የኃይሉን መንገድ ህውሃት የተካነበት እና እስከ ጥርሱ ድረስ የታጠቀበት መንገድ መሆኑን መርሳት የለብንም። በመንግስት ወይንም በመንግስት ደጋፊዎች አማካኝነት ለሚፈጸሙ የድንጋይ፣ የዱላ፣ የስድብ፣ የማዋከብ፣ የማንጓጠጥ፣ የጫጫታ ረብሻ፣ የትንኮሳ፣ የግድያ እና ሌሎች ጥቃቶች የሰላማዊ ትግል ሰራዊት እና ደጋፊዎቹ ምላሻቸው ሰላማዊ ነው። የኃይል ምላሽ ከሰጠን መንግስት እና የመንግስት ደጋፊዎች የሚመኙትን አገኙ ማለት ነው። በለመዱት ሃሰተኛነታቸው ጉዳዩን ጸጥታ የማስከበር ጉዳይ በማድረግ ሰላማዊ ትግሉ ቶሎ እንዳይነሳ አድርገው ሊመቱት ይችላሉ። ሰላማዊ ትግል ወደ ኃይል ከተንሸራተተ በሰላማዊ መንገድ ለነፃነት መታገል የጀመረው ህዝብ እምነት ይተናል። በትግሉ ከመቀጠል ፈንታ ስደተኛ መሆንን ይመርጣል። ከዚያ ትግሉ በታሪካችን የተለመደው በቡድኖች የሚመራ የርስ በርስ ጦርነት ይሆናል። አሸንፎ ስልጣን የሚጨብጠውም አዲስ አምባገነን ይሆናል። ኢትዮጵያ የሶሪያን ወይንም የቀድሞውን የርስ በርስ ጦርነት መንገድ አትወስድም።

(3) ሴቶችን በብዛት በሰላማዊ ትግል ሰራዊት ውስጥ አለማስገባት ሰላማዊ ትግሉን ሊበክል ይችላል። ጉልበተኛነት ተወግዶ ሁሉንም ነገር በሰላማዊ መንገድ እንዲፈጸም ማድረግ ለአብዛኛዎቹ ሴቶች ተፈጥሮዋቸው ነው። የዚህ ህግ ተገዢዎች ናቸው። በተፈጥሮዋቸው ለጉልበተኛነት ተፃራሪዎች ናቸው። ይኽን ተፈጥሮዋዊ ባህሪያቸው በየቤታችን ሳይቀር የምናስተውለው ነው። ብርቱነትም (ጥንካሬም) ቢሆን ሰላማዊ ትግል የሚፈልገው ብርቱነት የመንፈስ እና የሞራል አቅም ነው። የሴቶች የመንፈስ እና የሞራል ጥንካሬ ሊተመን አይችልም። በሰላም ትግል ሂደት ውስጥ ረጋ ብሎ በማመዛዘን ደፋር እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል። ሴቶች ያን ማድረግ ይችላሉ። የሴቶች በሰላም ትግል ውስጥ መሳተፋቸው ለሰላማዊው የፖለቲካ ትግል ስብዕናን እና ግብረ ገባዊ ባህሪ ይሰጠዋል። ይህ ባህሪ ደግሞ ዲሞክራሲን ለመገንባት እጅግ አስፈላጊ ጉዳይ ነው። ሴቶች ዱላ ለማንሳት ስለማይጣደፉ ብቻ በነፃነት ትግል ላይ ያላቸውን ጀግንነት ከወንዶች ዝቅ አድርገው የሚያዩ ካሉ ተሳስተዋል። በተጨማሪ የኢትዮጵያ ህዝብ ግማሽ ያህሉ ሴቶች ናቸው። ስለዚህ ይህን ኃይል ወደጎን ከተውን ሰላማዊ ትግል አቅማችን ግማሽ ብቻ እንደሆነ እና ለድል አድራጊነት የሚበጅ ግማሽ ያህል ተጨማሪ ኃይል ትግሉን እንዳልተቀላቀለ ማወቅ አለብን።

 

(4) ሰማዕታትን እና በእስር ቤት የሚጉላሉ ጓደኞችን በሚመለከት የሚፈጸም ሰላማዊ ትግሉን ሊበክል ይችላል። ለምሳሌ በዚህ ወይንም በዚያ ቀን የሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ እነእከሌ የታሰሩበትን ቀን ማስታወሻ ነው ብሎ ማውራት በፖለቲካም ሆነ በሞራል ትክክል አይደለም። ሰላማዊ ትግልንም ይበክላል። ወዳጅ ያርቃል። ስለሆነም ሰላማዊ ትግሉን አብረው የጀመሩ የሰላም ትግል ሰራዊት ባልደረቦች በሙሉ አብረው ከመጨረሻው የነጻነት ቀን ላይደርሱ እንደሚችሉ በቅድሚያ በግልጽ መታወቅ አለበት። በርካታ የሰላም ትግል ሐዋሪያቶች እና ሰራዊቶች በተለያዩ ቀናት፣ ወራት እና አመተ ምህረት ሊታሰሩ እና መስዋዕት ሊሆኑ ይችላሉ። ቀሪው በትግል ላይ የሚገኘው የሰላም ትግል ሰራዊት በእስርም ሆነ በመስዋዕትነት የተለዩትን ጉዋደኞቹን እኩል ያከብራል። እኩል ያስታውሳል። እኩል ይዘክራል።

 

(5) በሰላማዊ ትግል ሚስጢር ማብዛት ሰላማዊ ትግልን ሊበክል ይችላል። ምስጢር መሆን የማይገባውን ሚስጢር ማድረግ በሰላም ትግል ሰራዊት ውስጥ ጥርጣሬ እና እርስ በርስ አለመተማመን ለፈጠር ይችላል። የሚስጥር ስራ በድርጅት ውስጥ መፍቀድ እና እንዲለመድ ማድረግ አንዳንድ አባሎች አደጋ ሊያመጡ የሚችሉ የሚስጢር ስራዎችን እንዲፈጽሙ ሊያበረታታቸው ይችላል። ሰላማዊ ትግል ግልጽነትን ይሻል። ህጋዊ መንገዶችን ይከተላል።

 

(6) ዘመቻ መቼ ማቆም እንደሚገባ በቅድሚያ ማወቅ ያስፈልጋል። ማፈግፈግ ሲያስፈልግም መቼ ማፈግፈግ እንደሚያስፈልግ ማወቅ ያስፈልጋል። ይኽ መርህ መሆን አለበት። ማፈግፈግ አስፈላጊ ሲሆን አለማፈግፈግ ጀግንነት ሳይሆን ጀብዱ ወይንም ሌላ ምክንያት ሊኖር ይችላል። ዘመቻዎች ፕላን ሲደረጉ የዘመቻዎቹ አድማስ፣  እስከከየት ድረስ መሄድ እንዳለባቸው እና በሂደት ላይ የተገኙትን ውጤቶች እንደ ድል መቆጠር እንዳለባቸው እና የተጀመሩት ዘመቻዎች መቼ መቆም እንዳለባቸው በግልጽ መታወቅ አለበት። ዘመቻዎቹ ከመጀመራቸው ቀደም ብሎ ለህዝብ እና ለመንግስት እስከ ዝርዝር መርሃ-ግብራቸው ማሳወቅ ሰላም ትግልን ከብክለት ያድናል። በዘመቻው የተወሰኑ ግቦች ተፈጻሚ ከሆኑ በኋላ ተጨማሪ ግቦችን ተፈጻሚ ለማድረግ ሲባል የተጀመረው ዘመቻ ቀደም ብሎ ከታቀደለት አድማስ እና ጊዜ ገደብ አልፎ እንዲሄድ ማድረግ አንዳንዴ ብልህ እርምጃ ላይሆን ይችላል። ሰላማዊ ትግሉንም ሊበክለው እና አልፎም ሊገድለው ይችላል። ይኽን ጉዳይ አስመልክቶ ሮበረት ሃርቬይ እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ1989 ዓመተ ምህረት በታይናሜን አደባባይ የተፈጸመውን በማስታወስ እንደሚከተለው ይተነትናል፥ “በአደባባይ የወጡት ቻይናውያን ተማሪዎች የጀመሩት ዘመቻ ከመንግስት በኩል ያስገኘላቸውን መለስተኛ እሺታ እንደ ድል በመቁጠር የመንግስት ጦር ኃይል በታንክ እና በእግረኛ ወታደር ጥቃት መፈጸም ከመጀመሩ ቀደም ብሎ ዘመቻውን አቁመው መበተን ነበረባቸው። ያን ሁሉ ታንክ እና ጦር ኃይል ገጥመው ከማለቅ ቀደም ባሉት ሳምንቶች ያገኙትን ድሎች ይዘው ማፈግፈግ ነበረባቸው” ይለናል። ማፈግፈግ ፍራቻ አይደለም። ጀግኖች ያፈገፍጋሉ። አላንዳች ጥቅም ሰራዊትህን ማስጨረስ የለብህም። አልፎም ሰላማዊ ትግሉን አታስገድልም። ይኸው ከ1989 ወዲህ እስከ አሁን ድረስ ለ23 አመቶች በቻይና ያን አይነት ሰላማዊ ትግል ገና አልተጀመረም። ለምሳሌ የአንድነት ፓርቲ የጀመረውን የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ አስመልክቶ ግቦቹን፣ አገር አቀፍነቱን፣ ከተሞቹን፣ የከተሞች ዘመቻዎችን ቅደም ተከተል፣ የዘመቻው እድሜው ሶስት ወሮች እንደሆነ በቅድሚያ ማስታወቁ ትክክል ነው። ለጊዜውም ቢሆን በመቀሌ እና በባሌ ሮቢ ያደረገው ማፈግፈግም ስህተት አይደለም።

 

(7) የሰላማዊ ትግል መሪዎች አንድ እርምጃ ለመውሰድ ሲያስቡ በቅድሚያ እርምጃው የሚያስገኘው ጥቅም እና እርምጃው የሚያስከፍለውን ዋጋ መገምገም እና ማነጻጸር አለባቸው። ዋጋው በድርጅቱ የሚመራውን ሰላማዊ ትግል ቀጣይነት የሚፈታተን ከሆነ እርምጃው ውድቅ መደረግ አለበት። ስለዚህ ሁልጊዜ የሰላማዊ ትግል መሪዎች ምንም አይነት እርምጃ ከመውሰዳቸው ወይንም መግለጫ ከማውጣታቸው በፊት ዋጋ እና ጥቅም (Cost/Benefit) ትንታኔ ማድረግ አለባቸው።

 

(8) የሰላም ትግል አመራር በወጣቶች ብቻ ከተሞላ ሰላማዊ ትግል ሊበከል ይችላል። እርግጥ ወጣት ከግል ጥቅም ነፃ በመሆኑ ህይወቱን ሙሉ በሙሉ ለትግል ይሰጣል። ወጣት የድፍረት፣ የአቅም፣ የተነሳሽነት እና የተስፋ ምንጭ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ወጣት ወጣት ነው። ተመክሮ ያንሰዋል። ዳኝነቱ አርቆ ያላስተዋለ እና ብስለት የጎደለው ሊሆን ይችላል። ከአዕምሮ ይልቅ ወደ ስሜት ሊያዘነብል እና ጀብዱኛነትን ጀግንነት አድርጎ ሊወስድ ይችላል። እራሱን ከሁሉ የተሻለ አድርጎ ሊገምት ይችላል። እነዚኽ ሁሉ የወጣትነት ባህሪዎች ሰላማዊ ትግልን ሊበክሉ ይችላሉ። ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ከምርጫ 97 በኋላ ፓርላማ እንግባ አንግባ በሚለው ውይይት ላይ ‘አትግቡ’ የሚለው አቋም በአብዛኛው በወጣቱ የተደገፈ ነበር። ፓርላማ አለመግባት ስህተት ነበር። ፓርላማ የገቡት በማርላማ ውስጥ ህግ በማስቀረጽ እና በማጸደቅ ለኢትዮጵያ ብዙ ሊያደርጉ ይችሉ ነበር ከሚል እምነት ሳይሆን እዚያው በትግሉ ሂደት ውስጥ እንዲቆዩ እና ትግሉ ቀጣይነት እንዲኖረው ለማድረግ ይጠቅም ነበር ከሚል ጽኑ እምነት የተነሳ ነው። ከትግሉ ሂደት ውጭ ሆነህ ድል አድራጊ ልትሆን አትችልም። ይኸው ግንቦት 25 ቀን የተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ከስምንት አመቶች በኋላ የተደረገበት ዋንኛው ምክንያትም ተቃዋሚው ከሂደቱ በመውጣቱ ትግሉን ማስቀጠል በለመቻሉ ነው። በቅርብ ዶክተር ያዕቆብ ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ጥያቄ ተጠይቆ ሲመልስ ዛሬ ላይ ሆኖ ወደኋላ ሲመለከት ፓርላማ አለመግባት ስህተት ነበር ማለቱን አንብቤያለሁ። ትክክለኛ ግምገማ ነው። ያም ሆነ ይኽ በተለይ አገራዊ ሰላማዊ ትግልን አስመልክቶ ወጣቱ በእድሜና በተመክሮ ከበሰሉ እና የኢትዮጵያን ውስብስብ ታሪክ ከሚያውቁ የሰላም ትግል መሪዎች ጋር ተቀይጦ መስራት አለበት። በዚኽ በወጣቶች ጉዳይ ላይ ሮበርት ሃርቬይ (Robert L. Harvey) “ስትራተጂያዊ ሰላማዊ ትግል” በሚል ርዕስ በአልበርት አነስታይን ተቋም [www.aeinstein.org] ድረገጽ ላይ ባተመው የጥናት ጽሑፉ ውስጥ በርካታ ገጾች ሰጥቶ ጽፏል። እንድታነቡት ጋብዣችኋለሁ።

 

(9) የሲቪክ ድርጅቶች አመራሮች በአምባገነኖች ቁጥጥር ስር ከሆኑ የሰላም ትግል በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ተበክሏል ማለት ይቻላል። ለምሳሌ የመምህራን፣ የሰራተኛ፣ የወጣቶች ማህበራት አመራሮች በገዢው ቡድን ቁጥጥር ስር ከሆኑ እነዚህ ተቋሞች የመጨቆኛ አጋዥ ምሶሶዎች ሆነዋል ማለት ነው። ነፃ ማውጣት አሊያም ሌላ ትዩዩ (Parallel) ድርጅቶች መመስረት ያስፈልጋል። እነዚህ ተቋሞች የነፃነት ትግልን ኃላፊነት ለእያንዳንዱ የህብረተሰብ ክፍሎች ለማከፋፈል ይጠቅማሉ።

 

(10) አግላይነት ሰላማዊ ትግልን ሊበክል ይችላል። በሰላም ትግል ኃይሎች ወይንም ድርጅቶች የሚሰጡ መግለጫዎች ሌላውን የሰላም ትግል ኃይል ወይንም ድርጅት የሚያገሉ ከሆኑ የተገለለ የመሰለው ወገን ወደ ጸበኛነት ሊሄድ እንደሚችል ቀደም ብሎ መገመት እና መግለጫዎች ሌሎችን እንዳያገሉ ተደርገው መጻፍ አለባቸው። ለምሳሌ የአንድ ተቃዋሚ ድርጅት አባል ሲታሰር የሁሉም ተቃዋሚ ድርጅቶች ጉዳይ መሆን ይገባዋል። መንግስት ሁሉንም በወዳጅ አይን እንደማያያቸው እና ቢቻል ሁሉም ቢጠፉለት እንደሚፈልግ መዘንጋት የለብንም። ጥቃቱ ተራ ጠብቆ የሁሉንም በር እንደሚያንኳኳ ማወቅ ያስፈልጋል። አንዱ ላይ ጥቃት ሲደርስ ጥቃቱን የሁሉም ጥቃት አድርጎ መመከት ያስፈልጋል።

 

(11) ፖሊሶች ከከተማው ህዝብ ጋር ተቀላቅለው ስለሚኖሩ ጥሩዎቹን ልናርቃቸው አይገባም። ለምሳሌ ጎረቤቴ ፖሊስ ቢሆን እና እኔ ፍጹም የሰላም ትግል አማኝ መሆኔን እንዲያውቅ እና እንዲያምንበት አደረኩት እንበል። ከዚያ አለቃው ከፖሊስ ጣቢያ እከሌ (እኔን) ሽብርተኛ ነው እና ይዘህ አምጣ የሚል ትዕዛዝ ቢሰጠው ለአለቃው ሽብርተኛ አለመሆኔን ሊናገር ይችላል። ውይይታቸው እዚያ ላይ ላያቆምም ይችላል።

 

(12) መለዮ ለባሾች ለሰላማዊ ትግል ድጋፋቸውን የሚለግሱት ህገ-መንግስቱን በማክበር ብቻ እንደሆነ በተደጋጋሚ በአደባባይ መገለጽ ያስፈልጋል። መፈንቅለ መንግስት ወይንም ሌላ የኃይል መንገድ ሰላማዊ ትግልን ይበክላል። ስለሆነም ሰራዊቱ፣ ፖሊስ፣ ደህንነት ለህገ-መንግስቱ ተገዢ የመሆን ህገ-መንግስታዊ ግዴታ እንዳለባቸው የሰላማዊ ትግል ሰራዊት በአደባባይ መስበክ እና ማስተማር አለበት። ህዝብም ይህን ሃቅ እንዲያውቅ ማድረግ ያስፈልጋል። በሰላማዊ ሰልፎች ላይ ነጭ አበባ ለፖሊሶች መስጠት ግን የሰላምነት እና የወዳጅነት ምልክት ነው።

 

(13) ሰላማዊ ትግል በሚያራምዱ ተቃዋሚ ድርጅቶች መካከል የሚፈጠር የአሳብ ፉክክር አለጊዜው ወደ የፖለቲካ ባላንጦች ፉክክር ካደገ ሰላማዊ ትግሉን ሊበክል ይችላል። በባላንጣነት ፉክክር የተጠመዱ በሙሉ ይሰምጣሉ። በህዝብ ዘንድ የፖለቲካ ካፒታላቸውን ያጣሉ። ተፎካካሪነት ባላጣነት መሆን የለበትም። መርህ የለሽ ፉክክር ግን ወደ ባላንጣነት ሊያመራ ይችላል። በተፎካካሪ ሰላማዊ ትግል ድርጅቶች መካከል የሚፈጠሩ ግጭቶችን በፍጥነት ለመፍታት የሚያስችል የጋራ መወያያ እና መደራደሪያ መድረክ ሊኖር ይገባል። በሆነ ባልሆነው መጋጨትን ማስወገድ ያስፈልጋል። ትልቁን ህዝብን የመንግስት ስልጣን ባለቤት የማድረግ ጉዳይ (ግብ) አለመርሳት ያስፈልጋል። ጥቃቅን ነገሮችን ቸል ማለት ይመረጣል። በማኪያሄድ ላይ ያለነው ሰላማዊ ትግል መሆኑን እና በሰላማዊ ትግል ደግሞ ስልጣን የሚመነጨው ከምርጫ ሳጥን እንጂ በመጠፋፋት እንዳልሆነ ማስታውስ ተገቢ ነው።

 

(14) በሰላማዊ ትግል ድርጅቶች መንደር መንግስት ሰርጎ ከገባ ሰላማዊ ትግልን ሊበክል ስለሚችል መጠንቀቅ ያስፈልጋል። ተጨባጭ መረጃ ካለ በስውር የመንግስት አገልጋይ የሆኑ አስመሳይ ተቃዋሚ ድርጅቶችን ማጋለጥ ተገቢ ነው። በስህተት ሰም እንዳናጠፋም መጠንቀቅ የግድ ነው። ከመጠን ያለፈ ተጠራጣሪዎችም መሆን እና ከሌሎች ጋር በህብረት ከመስራት  መራቅም ሰላማዊ ትግሉን ይበክላል።

 

(15) ከሰላም ትግል ድርጅቶች አመራር ውስጥ ህሊና ደካማዎቹ ግለሰቦች በመንግስት እየተመለመሉ ሰላማዊ ትግሉን ሊበክሉ ይችላሉ። እነዚኽን ህሊና ደካማ ሰዎች መንግስት በጥቅማ ጥቅም በመደለል እና በማግባባት ህሊናቸውን  በመግዛት ወሬ እንዲያቀብሉት (informants) ያደርጋል። በዚህም ጉዳይ ላይ ቀደም ብሎ ሊታሰብበት እና አደጋ መከላከያ ወይንም መቀነሻ ዝግጅት ማድረግ ያስፈልጋል። እነዚህ ወደ መንግስት ወሬ አቀባይነት የተለወጡት የሰላም ትግል ድርጅት አመራር አባላት  ለውይይት በሚነሱ ጉዳዮች ላይ ሆን ብለው ስምምነት እንዳይኖር ያደርጋሉ። ዞር ብለው ደግሞ ለሰላማዊ ትግል ሰራዊት እና ለታጋዩ ህዝብ ስምምነት ጠፋ ይሉታል። ህዝብ ስምምነት ጠፋ ብሎ እንዲያምን እና በትግሉ እምነት እንዲያጣ ለማድረግ። የተለያዩ የሃሰት ዜናዎች እየፈጠሩ በማሰራጨት ህዝቡ ከፍራቻ ወጥቶ እንዳይታገል ለማድረግ ይጥራሉ።

 

(16) የመንግስት መልክተኛ ቆስቋሾች (agent provocateurs) ሰላማዊ ትግልን ለመበከል እና ለማስመታት በመንግስት ወይንም በፖለቲካ ባላንጣዎቻችን የተተከሉ አሊያም ሊሆኑ ይችላሉ። እነዚኽ ሰዎች ሆን ብለው የኃይል እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋሉ ወይንም እራሳቸው ድንጋይ ይወረውራሉ። ወይንም ፈንጂ ያፈነዱ እና ህግ አክባሪው ሰላማዊ ትግል ሰራዊት (ሰልፈኛ) እንዲመታ ያደርጋሉ። ብጥብጥ ያነሳሳሉ። ጀብዱኛነትን ጀግንነት አስመስለው ያራምዳሉ።

 

(17) ከውጭም ሆነ ከውስጥ የሚነሱ ጸብ ጫሪዎች (provocateurs) እንዲሁም በትግል ስም የህዝብ እና የመንግስት ንብረት አውዳሚ ተግባሮች ሰላማዊ ትግል ይበክላሉ። ሰላማዊ ትግል (የተቃውሞ ሰልፍ፣ ህዝባዊ ትብብር፣ ስራ ማቆም፣ ወይንም ሌላ) ሲካሄድ በሰላማዊ ትግል ድስፕሊን የታነጸ የሰላም ትግል ሰራዊት በጸታ ተቆጣጣሪነት ተግባር መሰማራት አለበት። ይኽ በድስፕሊን የታነጸ የሰላም ትግል ሰራዊት ከውጭም ሆነ ከውስጥ የሚነሱ ጸብ ጫሪ ተግባሮችን ይከታተላል። በፍጥነት ያጋልጣል። ሰላማዊውን ተሳታፊ ያረጋጋል። ሰላማዊ ትግል በማኪያሄድ ላይ ካለው ህዝብ ተቀላቅሎ በፖሊሶች፣ በመንግስት ንብረት፣ በህዝብ ንብረት ላይ አደጋ ለመፍጠር የሚሞክር ወዲያውኑ መጋለጥ እና ለፖሊሶች መሰጠት ያስፈልጋል።

 

 

በመስቀል አደባባይ እጅ ለእጅ ተያይዘን “በመጨረሻ ነፃ ወጣን!” “በዴሞክራሲ አደባባይ!” ብለን በደስታ የምንዘምርበትን ቀን ህውሃት እራሱ እያቀረበው ነው። 

 

መልካም ውይይት!

 

 

የኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ በዋሽንግተን ዲሲ

“ደረቅ ራዕይ”–“ደረቅ ትግል”

$
0
0

ሚኪያስ ሙሉጌታ ግዛው ከኖርዌ

ሠማይ ጠቅስ ሕንፃዎች ተደርድረዋል ይባላል። ሠፊው ጎዳና የሠማዩን አድማስ አቋርጧል ይባላል። ወንዙ ተገድቦ ውሃው ተንጣሎ ተኝቷል ይባላል። ማዶ ከተራራው ሥር ዘመናዊ የእርሻ ልማት ይታያል ይባላል። የእድገቱ አሃዝ ጨምሮ የሕዝቡ ኑሮ መሻሻሉን የሚዘግብ ዶኩሜንተሪ ፊልም በቴሌቪዥን ይታያል። የአቶ መለስ ራዕይ ሠምሯል ማለት ይሆን? – ግናስ ሀገሬ ኢትዮጵያ ምን ነካት? – ምነው ኩርምት አለች? – ምነው ገጿ ደበዘዘ?
Moving-picture-Ethiopia-flag-flapping-on-pole-with-name-animated-gif

የአቶ መለስ ራዕይ ሉዓላዊነቷን ያስደፈረ፣ ኅልውናዋን የተፈታተነ፣ ታሪኳን ያንቋሸሸ “ደረቅ ራዕይ” ስለነበር ነዋ። እምዪ ኢትዮጵያ ምነው ታድያ ኩርምት አትል? ምነው ገጿ አይደበዝዝ`? ራዕዩ የሕንድና የአረብ ከበርቴዎችን ያስፈነጠዘ፣ ሼሁንና ሎሌዎቹን ያወፈረ፣ የቅኝ ገዢዎችን ምኞት ያሳካ፣ በርካታ ቀን የሰጣቸውን ባለስልጣናትና ዘመዶቻቸውን ያባለገ ራዕይ ነበር። በአለም ባንክ ርዳታ የተነጠፈው ጎዳና ረጅም – ግን ደረቅ የሙስናውንና የኤፈርቱን የዘረፋ ሸቀጥ በተሸከሙ ከባድ መኪኖች የተጨናነቀ ጎዳና ነው። በየመስኩ የተንጣለሉት ሌብነትና ጉቦ ወለድ ፋብሪካዎቹ የሕዝቡን ኑሮ አላሽቀውታል። ራዕዩ ሃይማኖትን ሳይቀር የተፈታተነ ሕዝብን ያጠወለገ የክፋት ምንጭ ነበር። ዛሬ ከአቶ መለስ ሞት በኋላ ቀድሞ ተንሰራፍቶ የነበረው ሙስና ገሃድ ወጥቶ ሙስናውያኑን እያባረረ ነው። በቅርቡ በኦሮምያና ትግራይ ክልሎች ባሉ ትልቁ የሙስና ዋሻ የመሸጉ ሁሉ ሙቅ ውሃ እንደተደፋባቸው አይጦች ይራወጣሉ። የስባዓዊ መብት ጥሰቱ ይቁም (Stop human rights violation)፣ አምባገነንነት ይውደም (Down with Dictatorship)፣ ሙስናው ያብቃ (Stop Corruption)፣ የሚሉ ሰላማዊ መፈክሮች ይዘን ስለወጣን ለስደት የዳረጉን ከቀበሌ እስከ መንግስት አመራር ያሉ ሁሉ ነገ ተጠያቂዎች ናቸው።

በእርግጥ ሙስናው ያደለባቸው አምባገነኖች ደረቅ ተቃውሞን አይፈሩም። ደረቅ ከደረቅ ቢጋጭ ለውጥ እንደማይመጣ ተንኮሉን ጫካ እያሉ አውጠንጥነውታል። አምባገነኖቹ ደረቅ ወሬን፣ ደረቅ ጽሁፍን፣ ደረቅ ጩኸትን፣ ደረቅ አመጽን አይፈሩም። ደረቅና ውሸት ጋጋታዎች የእድሜአቸው ማራዘምያ ኪኒኖች ናቸው። ወያኔነዎቹ በበርሃ ላይ ድንገት ፍልቅ እንደምትለው ምንጭ ርጥብ ነገርን ከተመለከቱ ነው ክው የሚሉት። ታድያ መልሰው እስኪያደርቋት ድረስ እንቅልፍ አይወስዳቸውም። ዓይነተኛ ባህርያቸው ይህ ነው። ወያኔዎች እስክንድር ነጋንና አንዷለምን እንደ ጦር ይፈራሉ። ወደፊት ሌላ እስክንድርና አንዷለም ዓይነቶች እንዳያብቡም ነው ዛሬ በሰማያዊ፣ በአንድነትና በመኢአድ ፓርቲዎች ላይ ከፍተኛ ወከባ የሚያደርጉት። አቶ መለስን ትንሿ የእስክንድር የብዕር ጠብታ ለፍርሀቱ ስትዳርጋቸው – የአበበ ገላው ድምጽ ደግሞ ኃይል አግኝቶ አንገታቸውን አስደፍቷቸው ነበር።

ዛሬ ሃገሬን ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን የቀሰፈው ትልቁ በሽታ ፍርሃቱ እንጂ የኢሕአዲግ ብርቱነት አይደለም። ደረቅ ትግሉ ተስፋ አስቆርጦ አድርባይነትን አስፋፍቷል። ድርቀቱ የተግባር ብኩንነቱን አስፋፍቶ “እስኪ ልኑርበት” የሚሉ ግለሰቦችን አብዝቷል። ድርቀቱ “ቤቴን ልስራበት – ልጆቼን ላሳድግበት” የሚሉ ፈሪዎችን አበራክቷል። እምነት ደርቃ ቤተክርስትያን ሂያጁ የትለሌ አስኪሆን ድረስ “ደረቅ ትግሉ” የአስመሳዮች ምሽግ ሆኗል። ጸሎቶች ደረቅ ጸሎቶች ሆነዋል። ድርቀቱ የሕዝቡን አንድነትም ሆነ የተቃውሚውን የፖለቲካ ስልት አወላግዷል። ታድያ ለዚህ ሁሉ ከንቱነት የዳረገንን አዚም ሳጤን – “በርግጥ አቶ መለስ ለካ – የደረቁ ምጣኔ ኃብት ፈላስፋ፣ የአፈናና ስውር ግድያ መሃንዲስ፣ የታላቁ ሤራና የደረቁ ትግል ስትራቴጂስት፣ የክፉ አደረጃጀት ስልት ቀያሽና ሕዝብ ከሕዝብ – ዘር ከዘር እሚናከስበትን መላ ጠንሳሽ፣ የመሃይማንና የደናቁርት ስብስብ መሪና – የኃጢዓት ሥራ ዋና ተዋናይ ነበሩ” – ለማለት እደፍራለሁኝ። ብቻ ፍርዱን ለእግዚአብሔር እንተወው።

የሚያሳዝነው ታድያ እስካሁን ድረስ በአቶ መለስ መተት ለተቀሰፈው የውስጡም የውጭውም ደረቅ ትግል ማርጠብያ መድሃኒት አለመገኘቱ ነው። መፈክሮቻችን፣ ሰልፎቻችን፣ ስብሰባዎቻችን፣ ጽሑፎቻችን የታንክ ጥይት ቢሆኑ ኖሮ የሕወሀት ዘመን አጭር በሆነ ነበር። እንደተዋጊ ጄቶች የፈጠኑት ድኅረ ገጾች፣ ጋዜጦችና መጽሄቶች ቦንብ ተሸካሚዎች ቢሆኑ ኖሮ ሕወሀትና ሻዕቢያ መቀመቅ ወርደው ሕዝቦች ነጻ በወጡ ነበር። በገቡ በጥቂት ቀናት መወገድ ስለነበረባቸው ኢሕአዲጋውያን በማውሳት ሕዝቡ – “ሳንፈልጋቸው ሀያ ሞላቸው” – በማለት ብሶቱን አች አምና በታላቁ ሩጫ ወቅት አሰምቷል። ትግሉ እጅግ ለመዘግየቱ ከዚህ ሌላ ምን ማስረጃ አለ?

የአቶ መለስ መንፈስ በተቃዋሚው ጎራ ሳይቀር ሰርጎ ገብቶ ተግባር በሌለው ምላሳቸው ሰብዓዊ መብት ተገፈፈ፣ ምርጫው ተዛባ፣ ሙስና ተስፋፋ፣ ዲሞክራሲ የለም – እያሉ የሚያስተጋቡ ልሳናቸው የኢትዮጵያን ክብር የማያውጅ ደረቅ አስመሳይ ተባባሪዎችን ሳይቀር አፋፍቷል። ባጠቃላይ “ደረቅ ትግሉ” የኢትዮጵያ የቀድሞ ክብሯና ገናናነትዋ ዳግም እንዳይመለስ ለሚፈልጉት ምዕራብያውያን እፎይታ፣ ለኢሕአዲጎቹ እድሜ ማራዘምያ ኪኒን፣ ለሻዕቢያ – ለኦነግና ለአልሻባብ ጊዜ መግዢያ አሞሌ ጨው እንዲሁም በዝርፊያና በወንጀል ተጠያቂ ለሆኑት ግለሰቦች ሽፋን ሠጪ ተኩስ ከመሆን በቀር ለኢትዮጵያና ለሕዝቦቿ አፋጣኝ መድህን መሆን አልቻለም፣።

ልብ በሉ! ኢሕአዲጎቹን ማስወገድ ያለብን የቅኝ ገዢዎች ተባባሪዎች፣ ለሀገሪቱ ሉዓላዊነት፣ ክብርና ታሪክ ፈጽሞ የማይጨነቁ፣ ሃገሪቱን ወደብ አልባ ያደረጉ፣ ኃይማኖትን የበከሉ፣ ሕዝቡን ለ”ስደት ሞት”ና ለ”ዳግም ክፉ” ቀን የዳረጉ ሰው መሰል ጨካኝ አራዊቶች ስለሆኑ ነው። ይህ ደግሞ በኢንተርኔት፣ ፓልቶክ፣ ሬድዮና ቴሌቪዥን በሚተላለፍ “ደረቅ ትግል” ብቻ አይሞከርም። ዛሬ በአቶ መለስ የሙት መንፈስ ምስል እየተመራ በመበታተኑ ጣዕረ ሞት የሚያቃስተውን ኢሕአዲግ ገፍትረን መጣል ካልቻልን ነገ አገግሞ ለሌላ መቅሰፍት ይዳርገናል። እንዲህ ተበታትነን፣ መስዋዕትነት የከፈሉትን ጀግኖች ገለል እያደረግን፣ ለወንጀለኞችና ለበታኞች ፍሪዳ እያረድን፣ የጓደኝነቱን፣ የአበልጅነቱን፣ የሚዜነቱን “ስውር አብዮት” በየመሸታው እያጠናከርን – በደረቅ ትግሉ ብቻ ተቃውሞን ከቀጠልን የሀገሪቱ መጪ እድል መገነጣጠል፣ መፈረካከስ – የሕዝቡ ዕጣ ደግሞ መራብ መታረዝ ብሎም – የ”ስደትን ሞት” – እንደ ብቸኛ አማራጭ አድርጎ መቀበል ብቻ ነው።

ወያኔን ለማስወገድ መፍትሄው አንድ ብቻ ነው። መፍትሄው የመንፈስ ፅናት ነው። እንደ አለፈው ትውልድ የጠላት ፈረስና ሰረገላ ማኅተማቸውን ሳያላላ፣ በእግዚአብሄር ኃይል ራሳቸውን አበርትተው፣ በባህሩ በደረቅ መሬት፣ በሸለቆና በተራራው ተሰማርተው የሃገሬን ቁስለቷን እንደ ሻሩላት ጀግኖች ምሳሌ ለመሆን አስቀድሞ የፅናቱ ቅባ ቅዱስ እንዲነካን በይቅር ባይነትና ፍቅር ዳግም መደራጀት ይኖርብናል። ፅናት አቋምን ትወልዳለች። ውጤት የምናመጣው የሕዝብ ወገን የሆንን ሁሉ በሕብረት ተደራጅተን እንደ አንድ ሰው ሆነን ስንታገል ብቻ ነው።

አለበለዝያማ ጽናትን የሚያጎለብተውን፣ የጀግኖቹን ፈለግ መከተሉን ትተን፣ ጋጋታና አጀብ ስናበጃጅ ዘመኑ በከንቱ እንዳያልፍ እንጠንቀቅ። የመስመር ልዩነት የሌላቸው ፖለቲካ ፓርቲዎች በቶሎ ወደ አንድነቱ መምጣት አለባቸው። ለሃገሪቱ ርጥብ ራዕይ ያላቸው ድርጅቶች ሁሉ መቀራረብ አለባቸው። ኢትዮጵያ የምታገግመው ከትግሉ ሜዳ በተለያዩ ምክንያት የራቁትን ጀግኖቿን በፍቅር ተማጽኖ ትግሉን እንደገና እንዲቀላቀሉ ሲደረግ ነው። ማዕከላችን ኢትዮጵያ ነች። ሁላችንም ለኢትዮጵያ እናስባለን። ልዩነታችን ውበታችን ነው። አንድነታችን አምባገነንነትን ያንበረክካል። ሙስናን ያጠፋል። ኢትዮጵያ የሰው ልጆች መብት የማይረገጥባት ሀገር ትሆናለች።

አምላክ ኢትዮጵያን ይጠብቃት።

አድራሻዬ michyas.ethio@yahoo.com ነው።

ልማት ምንድነው? እውን የወያኔ መንግሥት ልማታዊ ነው? (ታደሰ ብሩ)

$
0
0

ከታደሰ ብሩ

“ሰላም ምንድነው?” በሚል ርዕስ ለፃፍኩት መጣጥፍ ከደረሱኝ በርካታ አስተያየቶች ውስጥ “በነካ እጅህ ልማት ምን  ማለት እንደሆነ ብትገልጽልን” የሚለው ጥያቄ ለዚህ ጽሁፍ ምክንያት ሆኗል።

What is developmentከአሰልቺ የወያኔ ካድሬዎች ክርክሮች አንዱ “ልማታችን፣ ልማታችን” መሆኑ የማውቀውና በራሴም ላይ ከተራ ማሰልቸት በላይ የመብት ጥሰቶች ያደረሰብኝ ጉዳይ ነው። ወያኔ በአገራችን ላይ ላሰፈነው አገዛዝ ተቀባይነት  (ligitimacy) ዋነኛ መከራከሪያው “ለኢትዮጵያ ልማትን ያመጣሁ፤ አሁንም በማምጣት ላይ ያለሁ መንግሥት ነኝ።  ለወደፊቱም ኢትዮጵያን ለማልማት ከኔ የተሻለ የለም” የሚል ነው። በዚህ ክርክር ውስጥ (1) ከዚህ በፊት በአገሪቱ  ውስጥ ልማት የሚባል ነበር አልነበረም፤ (2) እኔ ልማትን እያመጣሁ ነው፤ ሌላውን ቻሉት፤ እና (3) ለወደፊቱም ከኔ  የተሻለ ኢትዮጵያን ማልማት የሚችል የሌለ በመሆኑ ለኢትዮጵያ ሲባል እኔ ለረዥም ጊዜ በስልጣን መቆየት አለብኝ  የሚል መልዕክት አለው። ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ  

በቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ መስቀል ከሰማይ ወረደ መባሉ አነጋጋሪ ሆኗል

$
0
0

(....ከሰማይ ወረደ የተባለውን መስቀል ይዘው)

(….ከሰማይ ወረደ የተባለውን መስቀል ይዘው)

(ዘ-ሐበሻ) “ገላን ጉራ ፈለገ ግዮን ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ብርሃን የተሞላ መስቀል ከሰማይ ወረደ” በሚል እየተወራ ያለው ዜና በኢትዮጵያ ዋነኛ መነጋገሪያ መሆኑ ታወቀ።

ከአዲስ አበባ የመጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በገላን ጉራ ፈለገ ግዮን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ተከሰተ በተባለ ተአምር መስቀሉ ወረደ የተባለው ሐሙስ ለአርብ አጥቢያ ከለሊቱ 9፡00 ሰዓት አከባቢ ነሐሴ 23 ቀን 2013 ሲሆን ካህናት አባቶች እና ምእመናን የክርስቶስ ሳምራን የበአል ዋዜማ ማህሌት ቆመው እንዳለ መስቀሉ ወርዷል ተብሏል።

ከስፍራው የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው ማህሌት ቆመው የነበሩት አባታኦች ከሰማይ የወረደውን መስቀል ድምጽ ድምፅ ሲሰሙ ካህናትና የቤተክርስቲያን አስተዳደሩ ከቤተመቅደስ ወጥተው ሁኔታውን ሲመለከቱት ብርሀን ከሰማይ እንደወረደና አከባቢውን በብርሀን እንደሞላው ተመልክተዋል ተብሏል። መስቀሉ የጌታ ስቅለት ያለበት ነውም ተብሏል።

በኢትዮጵያ ውስጥ ሕዝቡ ጉዳዩን በጥርጣሬ በማየት እየተነጋገረበት ሲሆን ለማመን የተቸገሩ ሰዎች እንዳሉ ሁሉ የመስቀሉን መውረድ የሚያምኑ ሰዎችም ቁጥራቸው አናሳ አይደለም።

በቅርብ ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያ ውስጥ አንዲት ሴት ድንግል ማርያም ነኝ በሚል ብዙ ሰዎችን አጭበርብራለች ተብላ መታሰሯ ይታወሳል። ከዚያ ቀደምም ባህታዊ ገብረ መስቀል የተባሉ ሰው ራሳቸው ታቦት አስቀብረው ሕዝቡን ‘ራዕይ ታይቶኛልና እዚህ ቦታ ብትቆፍሩ ታቦት ታገኛላችሁ” በሚል በማጭበርበር መጋለጣቸው ይታወሳል።

አንባቢዎች የእናንተ አስተያየት በዚህ ጉዳይ ምን ይመስላል?

ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ይቅርታው ተቀባይነት እንዳላገኘ የሚገልጽ ደብዳቤ ከፍትህ ሚኒስቴር ደረሰው

$
0
0

webshet taye
በፋኑኤል ክንፉ (ሰንደቅ ጋዜጣ) በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ለፍትህ ሚኒስቴር በይቅርታ እንዲፈታ ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት አለማግኘቱን ከፍትህ ሚኒስቴር በደብዳቤ እንደተገለፀላቸው ባለቤቱ አስታወቁ።
የጋዜጠኛ ውብሸት ባለቤት ወይዘሮ ብርሃኔ ተስፋዬ ለሰንደቅ እንደገለጹት፤ “ባለፈው ማክሰኞ ዕለት ከፍትህ ሚኒስቴር የይቅርታ ቦርድ ጽ/ቤት በተፃፈ ደብዳቤ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ፈርሞ ተረክቧል። በደብዳቤው የጠየቀው ይቅርታ እንዳልተፈቀደለት በሁለት መስመር ከመግለፁ ባለፈ ይቅርታው ለምን ተቀባይነት እንዳላገኘ የሚገልፅ ኀሳብ አልያዘም” ብለዋል።
አያይዘውም፣ “ከዚህ በፊት የአቶ ኤልያስ ክፍሌ እህት የሆኑት ወ/ሮ ሂሩት ይቅርታ ተቀባይነት ሳያገኝ ሲቀር ምክንያቱ ተገልፆ ነበር። ለውብሸት ግን ምክንያቱ አልተገለጸም። ጉዳዩን ለማወቅ ለፍትህ ሚኒስቴር ጥያቄ አቅርቤ ነበር። የውብሸት ደብዳቤ ወጪ ተደርጓል። አድራሻው ለማረሚያ ቤት ስለሚል እኛ ምን እንደተፃፈ አላወቅንም። ስለዚህም ማረሚያ ቤት ጠይቂ ብለውኛል። ማረሚያ ቤት የመጣው ደብዳቤ ሁለት መስመር ላይ የሰፈረ ነው። ይዘቱም የይቅርታ ጥያቄው ተቀባይነት አላገኝም የሚል ነው” ሲሉ ለሰንደቅ ገልፀዋል።
ጋዜጠኛ ውብሸት ከታሰረ ሁለት አመት ከሶስት ወራት የሞላው ሲሆን፤ የተፈረደበት የእስር መጠን አስራ አራት ዓመት ነው። ጋዜጠኛ ውብሸት የአንድ ወንድ ልጅ አባት ነው።¾


Art: የዘመኑ ቀልብ ቀልባሽ ድምጻዊያኖች

$
0
0

በተስፋሁን ብርሃኑ

ዘመናዊ ሙዚቃ በኢትዮጵያ ከተጀመረ አራት አስርት ዓመታትን አሳልፏል፡፡ በነዚህ ዓመታት በርካታ ዘመን አይሽሬ ድምፃውያን በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ነግሰውበታል ዘመን አይሽሬ ከሚባሉት ድምፃውያን በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱ ድምፃውያን መካከል ጥላሁን ገሠሠ፣ ሚኒሊክ ወስናቸው፣ መሀሙድ አህመድ፣ አለማየሁ እሸቴ፣ አስቴር አወቀ፣ ኩኩ ሰብስቤ ከብዙ በጥቂቱ ናቸው፡፡
በቀደሙት ዓመታት የነዚህ ድምፃውያን ስራዎች በሰፊው ይደመጡ ነበር፡፡ ካሴቶቻቸውም በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ትልቅ ተቀባይነትን አግኝቶ ነበር ምክንያቱ ደግሞ የግጥሙ ይዘት ዜማውና ድምፃውያኑ የእውነት ዘፋኞች በመሆናቸው ሙዚቃቸው አሁን ድረስ ከመደመጡ ባሻገር ለአዳዲስ ድምፃውያን የድምጽ ማሟሻ እየሆናቸው ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ እነዚህ ድምፃውያን ለገንዘብና ለዝና ሲሉ ሳይሆን የእውነት ሙዚቃ ጠርታቸውና መርጣቸው በመሆኑም ጭምር ነው፡፡

አሁን አሁን ገና ለገና ገንዘቡንና አጋጣሚውን ያገኙ በርካታ ድምፃዎያን ነን ባዮች ግራ የገባው ግጥምና ዜማ ይዘው በመምጣታቸው በርካታ የሙዚቃ ወዳጆችን የኢትጵያ ሙዚቃ ወደየት እየሄደነው እንዲሉ እያስገደዳቸው ነው፡፡ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ በአዳዲስ ድምፃውያን የሚወጡ ሙዚቃዎች አንድ ዓይነት ማለት ይቻላል ሴቶችን የሚያባብሉ፣ ብሶቶችና ‹‹የዛሬን ተደሰት የነገን ነገ ያወቃ›› የሚል መንፈስ በመያዛቸው አገር ተረካቢውን ወጣት ምንም እንዳይሰራና የጨለምተኛ አስተሳሰብ እንዲያዳብር እያደረጉት እንደሚሄዱ ምንም አያጠያይቅም፡፡ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ብዙ ሺህ ኮፒዎች ከአንድም ሁለት ጊዜ የተሸጡለትና የቀደሙትን
ዘመን አይሽሬ ድምፃውያንን ይተካል የሚባልለት ቴዲ አፍሮ /ቴዎድሮስ ካሳሁን/ ከሰባት ዓመታት በኋላ በ2004ዓ.ም ሚያዚያ ወር ላይ ካወጣው ‹‹ጥቁር ሰው›› አልበም በፊት በርካታ ነባርና አዳዲስ ድምፃውያን ስራዎቻቸውን ለአድማጭ ቢያቀርቡም የበርካታ ሙዚቃ አፍቃሪያንን ቀልብ መግዛት ሳይችሉ ቀርተው ነበር፡፡ ይህ ጥቁር ሰው› አልበም በእውነትም እጅግ ተቀዛቅዞ የነበረውን የኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ አነቃቅቷል ማለት ይቻላል ምክንያቱ ደግሞ ካሴቱ ከወጣ ሰዓት ጀምሮ በሰልፍ ተሽጧል በሙሉ ማለት ይቻላል ዘፈኖቹ ታሪክን፣ አንድነትን ፍቅርን በመስበኩ በእጅጉ ተወዶ ነበር ብራቮ ቴዲ፡፡

በዚህ በያዝነው 2005 ዓ.ም በርካታ አንጋፋና ወጣት ድምፃውያን ስራዎቻቸውን ለአደማጭ አቅርበዋል፡፡ ነገር ግን በለስ ቀንቷቸው የአድማጮችን ቀልብ የገዙት በጣት የሚቆጠሩ ናቸው በዚህ ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት በቀሩት ዓመት ከተወዳጅ ድምፃውያን መካከል ጃሉድ፣ አቤል ሙሉጌታ፣ ሚካኤል በላይነህ፣ ጃኖ ባንድ፣ ፀጋዬ እሸቱ የቀደመውን ዜማዎቹ እንደ አዲስ ያቀረበበት እንዲሁም አሁን በሰፊው እየተደመጠ ያለው ‹‹ስጦታሽ›› የሸዋንዳኝ ሀይሉ ካሴት በእጅጉ የሙዚቃ አፍቃሪያንን ቀልብ ገዝቷል፡፡ በዚህ በያዝነው ነሐሴ ወር ሌላ አዲስ አልበም ወጥቶ በሰፊው እየተደመጠ ይገኛል፡፡ ‹ሲያ ሲያ› ፣ ‹አልችልማ› በሚባል ክሊፓቹ ከፍተኛ ዝናን ያገኘው ተመስገን ገ/እግዚሐብሄር /ተሙ/ አዲስ ካሴት አሳትሟል የመጀመሪያ ካሴቱን በራሱ ወጪ አሳትሟል፡፡ ይህ ካሴት በወጣ በአጭር ጊዜ የመጀመሪያው ህትመት በጥቂት ጊዜያት ተሽጠው በማለቃቸው በድጋሚ እንደታተመ ተነግሯል፡፡ በሌላ በኩል ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት በቀሩት በዚህ ዓመት በርካታ ነባርና አዳዲስ ድምፃውያን ስራዎቻቸውን ለአድማጭ አቅርበዋል፡፡ ካሴቶቻቸውን አውጥተው ብዙም ተደማጭነትን ካላገኙት ተወዳጅ ድምፃውያን መካከል አስቴር ከበደ፣ ነፃነት መለሰ፣ አበባ ደሳለኝ፣ ይገኙበታል፡፡ ከዓስር ዓመት በፊት የህበረተሰቡ አዲስ ካሴት ሲወጣ የመግዛት ዝንባሌው በእጅጉ ከፍተኛ ነበር ለማለት ይቻላል አሁን አሁን ግን
አዳዲስ የሚወጡ ካሴቶችን በተለያዩ ሚዲያዎችና ድህረ ገጾች ካሴቶቹ በወጡ በጥቂት ቀናት በመለቀቃቸው ምክንያትና በዘፈኖቹ ጥራት አብዛኛው ህብረተሰብ አዲስ ካሴት ገዝቶ የማዳመጥ አዝማሚያ አይስተዋልም፡፡ የህብረተሰቡ ካሴት ገዝቶ የማድመጥ ባህሉም ከጊዜ ወደጊዜ እየቀነሰና ነጠላ ዜማዎችን ብቻ የማየትና
የማድመጥ አዝማሚያ እያሳየ ነው፡፡ ነገር ግን በዚህ መሀልም አንጋፋና ወጣት ድምፃውያን አንዳንዶቹ ስራዎቻቸውን ማቅረባቸው አልቀረም ከነዚህ ውስጥ ታዲያ በግጥሞቹ በሳልነትና በድምፁ እስከ አሁን እየተደመጠ ያለው አቤል ሙሉጌታ አንደኛውነው፡፡
ይህ ወጣት ድምፃዊ በቤተክርስቲያን አካባቢ በማደጉ ለግጥምና ለዜማ እንዲሁም ለድምፅ ታላቅ አስተዋጽኦ እንዳደረገለት ይመሠክራል አንጋፋው ፀጋዬ እሸቱም ከቀድመው ተወደውለት ከነበሩት ሙዚቃዎቹ መካከል መርጦ በሙሉ ባንድ ያወጣው ካሴትም እጅግ ተወዶለታል፡፡ ከሰባት ዓመት በኋላ ‹‹ ስጦታሽ›› በተሰኘው አዲስ
አልበም የመጣው ሸዋንዳኝ ሀይሉ አንጀት የሚያርስ ሙዚቃ እንደሰራ ብዙ የሙዚቃ አፍቃሪያንና የሙዚቃ ባለሙያዎች እየተናገሩ ይገኛሉ፡፡ በዚህ አልበም ውስጥ በርካታ ስመጥር ገጣሚያን የተሳተፉበት ሲሆን እንደከዚህ ቀደሙ የቴዲ አፍሮ ግጥም በአልበሙ ተካቷል፡፡ ወጣቱ ድምፃዊ ተመስገን ገ/እግዚሐብሄር
ተሙ ሌላው 2005 ዓ.ምትን ካደመቁት ድምፃውያን መካከል አንዱ ነው ይህ ወጣት ድምፃዊ በሦስት ነጠላ ዜማዎቹ የብዙ ሙዚቃ አፍቃሪያንን ቀልብ ገዝቶ ቆይቶ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ በአዲስ አልበም ብቃቱን አሳይቷል፡፡ ካሴቱ በወጣ በጥቂት ቀናት ለሁለተኛ ጊዜ የታተመለት ይህ ድምፃዊ ሙሉ የካሴቱን ወጪ በራሱ ማሳተሙ ለሙዚቃው የሰጠው ትኩረት ከፍተኛ መሆኑን አስመስክሮለታል ይህን ካሴት በርካታ አቀናባሪዎች የሰሩት ሲሆን ማስተሩን ታዋቂው አበጋዝ ሺዌታ ሰርቶለታል፡፡ በ2005 ዓ.ም እጅግ ካሴቶቻቸው የተደመጠላቸው ጃሉድ፣ ሚካኤል በላይነህ፣ አቤል ሙሉጌታ ፣ፀጋዬ እሸቱ፣ ሸዋንዳኝ ሀይሉ እንዲሁም ተመስገን ገ/እግዚሐብሄር ነበሩ፡፡ በሚቀጥለው ዓመት በርካታ አንጋፋና ወጣት ድምፃውያን ስራዎቻቸውን ጨርሰው ለማውጣት በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡

ኤርያልን የገደለው!!!! ………

$
0
0

(ቴዲ ከአትላንታ)

ኤርያል ካስትሮ ከአስር ዓመት በፊት ሶስት አሜሪካውያን ወጣት ሴቶችን አፍኖ ቤቱ አስቀመጠ። ለ 10 ዓመት ያህልም የፈለገውን እያደረገ ሲያሰቃያቸው ኖረ። ዋጋ የማይተመንለትን ወጣትነታቸውን ወሰደባቸው (ሰረቃቸው)፣ በዚያ ጨለማ በምድር ቤቱ ውስጥ አስቀምጧቸው አስር ዓመት ያህል ሲቆዩ ፣ እንወጣለን ብሎ ማሰብ ረስተው ነበር። ቦ ጊዜ ለኩሉ (ለሁሉም ጊዜ አለውና) አንድ የተመረጠች ቀን ምክንያት ተፈጥሮ ነጻ ወጡ።
arial castro
ከዚያ ኤርያል ካስትሮ ተያዘ፣ አሜሪካም የቀረውም ዓለም ጉድ አለ ! ጨካኙ ካስትሮ ፍርድ ቤት ቀረበ፣ የገዛ ወንድሞቹና ልጁ ሳይቀሩ አይንህን ላፈር አሉት፣ የሰው ዓይንና ርግማን ሳይገድለው ቀረና፣ ፍርድ ቤት ቀርበ ውሳኔ ተሰጠው፣ የፍርድ ቤቱም ውሳኔ – ሞትን አስቀረና ዕድሜ ይፍታህ ፈረደበት። እዚያም ሞትን አመለጠ። ከዚያ እስር ቤት ገባና የ እስር ኑሮውን ሀ ብሎ ጀመረ። ለካ ከዚህ ሁሉ ከውጭ ሊመጣ ይችል ከነበረው የሞት ፍርድ ያምልጥ እንጂ፣ ህሊናው ፈርዶበት ነበር። ከሁሉም የህሊናው ፍርድ፣ ጸጸቱ፣ የጥፋተኝነት ስሜቱ፣ የበደለኝነት ግለቱ አላስቀምጥ ቢለው …..፣ የ እስር ቤት ምግብ እየበላ፣ ቴሌቪዥን እያየና ካርታ እየተጫወተ መኖር ሲችል ዛሬ ንጋት ላይ ራሱን አንቆ የራሱን ህይወት አጠፋ ተባለ።

…. በምንሰራው ግፍና በደል ከሌላው ዓለም ፍርድ እናመልጥ ይሆናል፣ ከራስ ህሊና ግን የት እናመልጣለን? ሰዎች ላይ ግፍና በደል ሰርተን ፣ አገር በመቀየር ፣ በገንዘብ ፍርድ በመግዛት፣ ስማችንን በመቀየር፣ በትልቅ ግንብ በመከለል የምናመልጥ ይመስለን ይሆናል፣ ትልቁ ፈራጅ ህሊናችንን ግን የትም አናመልጠውም። በደል፣ ግፍ፣ ተንኮል፣ ምቀኝነት …. ይቅርብን። ነገ የሚጸጸተንን ዛሬ ለምን እናደርጋለን ?

“ቀጣዩ ፕሬዚዳንት ኦሮሞ ሙስሊም ይሆናል የሚል ግምት አለኝ”–የፓርላማው አባል አቶ ግርማ ሰይፉ

$
0
0

ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ የፓርላማ አባል የሆኑት የተከበሩ ግርማ ሰይፉ ከሎሚ መጽሔት ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አውግተዋል፡፡ ዘ-ሐበሻ ለአንባቢዎች ግንዛቤ እንደወረደ አስተናግዳዋለች።
ሎሚ፡- የዘንድሮው ፓርላማ ምን ይመስል ነበር;
ግርማ፡- ባለፈው አንድ ጋዜጣ ጠይቆኝ ነበረ፤ እንዴት ነበር ሲለኝ አሠልቺ ነው ስለው…እንዴት እንደዚህ ይላሉ ከሰለቸዎ ለምን ለቀው አይወጡም የሚል አስተያየት ሰምቼ ነበር፡፡ እንዲህ እያሉ ቅሬታ የሚያቀርቡ ሰዎች ለምን ጥለውት አይወጡም? ከሰለቻቸው አዛ ቁጭ ብለው ደሞዝ ይበላሉ? የሚል ነገር አለ፡፡ የኔ አስተሳሰብ ግን ሌላ ነው፡፡ በእንደዚህ አይነት አሠልቺ ሁኔታም ቢሆን ነጥብ ማስያዝ የምንችልበትን ስራ መስራት አለብን፡፡ እኔ አሠልቺ ነው ያልኩበት ምክንያት፣ ኢህአዴግን አውቀኸው ገብተህ ምንም ነገር እንደማይመጣ…ለምሣሌ አዋጅ ሲቀርብ እንደሚፀድቅ ታውቃለህ፤ አዋጁ ላይ የኔ የግሌ አስተያየቶች አሉ፡፡ እነዚህን አስተያየቶች ይዘህ ሄደህ ለመቀየር የሚያስችል አቅም አለመኖሩን ስታይ ትሰላቻለህ፡፡ ይህን ለመግለፅ ነው አሰልቺ ነው ያልኩት፡፡ ሦስቱም አመታት የመጡ አዋጆች በሙሉ የሚፀድቁበት ነበር፡፡ በዚህ አመት በነበረው ፓርላማ፣ ሀሣቦች መነሣት ጀምረው ነበር፡፡ በቀረቡት ጉዳዮች ላይ ሣይሆን እንዲሁ ውይይቱን ሞቅ ደመቅ የማድረግ ሁኔታ ነበር፡፡ ከዛ በፊት ጠያቂው እኔ ብቻ ነበርኩ፡፡ ይሄ ብቻ አይደለም፤ እነሱም አንዳንድ ለታሪክ የሚሆኑ ነገሮች እያስመዘገቡ መሄድ ጀምረው ነበር፡፡ እንደዚህ አይነት ነገሮች ይመዘገባሉ፡፡ እነዚህ ነገሮች ልዩ ያደርጉታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በፓርላማው መዝጊያ አካባቢ አንድ የተወካዮች ም/ቤት አባል ያለመከሰስ መብት ለማንሣት የተደረገው ነገር “አስቆጭ” ነበር፡፡ እና ‹‹እንዳይከሰስ›› የሚለውን ነገር አስተካክለው እንዲመጡ፣ እንደዛ ካልሆነ እንዳይሆን ብለው ለመጀመሪያ ጊዜ ተቃውሞ የተነሣበት ሁኔታ ነበር፡፡ በማግስቱ ባልታወቀና ባልተለመደ ሁኔታ ተገልብጦ ሌላ ነገር ተፈጠረ፡፡ ለምን ተከሰሱ ለምን እንደዚህ ሆኑ አይደለም፡፡ ፖለቲካው ለረጅም ጊዜ የሚዘልቅና የሚቆይ ነው፡፡ አንዳንድ ትንተና የሚሰጡ ሰዎች አሉ፡፡ ኢህአዴግ እንደ ፓርቲ በስራ አስፈፃሚ ደረጃ እኩል ነው፡፡ በምክር ቤት ደረጃ ግን እኩል አይደለም፡፡ ስለዚህ እኩል በሆኑበት የስራ አስፈፃሚ ደረጃ የሚወሰነው ውሣኔ፣ በም/ቤቱ እኩል ያልሆነ ወንበር ያላቸው ሰዎች መወሰን አለባቸው የሚለው ነገር በትክክልም የህገ-መንግስትና የሕዝብ ውክልናን ይዘው ምክር ቤት የገቡትን ሰዎችን የሚጐዳ ነው፡፡ ባላቸው ድምፅ እኩል መልስ የማይሰጡበት ስለሚሆን ማለት ነው፡፡ እነዚህ የዚህ አመት የፓርላማ ጨዋታዎች ነበሩ፡፡
ሎሚ፡- ከጠ/ሚ መለስ ሞት በኋላ ፓርላማው መቀዝቀዝ ታይቶበታል ይላሉ;
ግርማ፡- መቀዛቀዝ ነው መነቃቃት…;
ሎሚ፡- እርስዎ ቢመልሱት አይሻልም?…
Girma Siefuግርማ፡- ጠ/ሚኒስትሩ ከሞቱ በኋላ ፓርላማው ተነቃቅቷል የሚሉ ሰዎች አሉ፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ ከሞቱ በኋላ ፓርላማው ተኝቷል የሚሉም አሉ፡፡ ተፋዟል የሚሉም እንዲሁ አሉ፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ ይሰጧቸው የነበሩ ትንሽ “ድምቀት” መሳይ መልሶች አንዳንዴ ፓርላማውን የሚያስቁ ወይም ደግሞ የሚያሸማቅቁ ነበሩ፡፡ ግን በሙሉ ልብና ስልጣን ባለመኖራቸው ተቀዛቅዟል የሚሉ ሰዎች አሉ፡፡ ሁለተኛው ቡድን ደግሞ ጠ/ሚ መለስ ከሞቱ በኋላ የፓርላማው አባላት የተለያዩ ሀሣቦችን በስፋት የማንሸርሸር አዝማሚያ ታይቶባቸዋል ይላል፡፡ እውነቱን ለመናገር በመለስ ጊዜ የስራ አስፈፃሚ አካሎቹ ትንሽ ሸምቀቅ ብሎ የመምጣት ሁኔታ ይታይባቸው ስለነበር አሁን ተነቃቅቷል የሚል ነገር አለ፡፡ ለኔ ሁለቱም ትርጉም የላቸውም፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ መጥተው ደመ ሞቃት የሆነ መልሣቸውን የሚናገሩበት ነገር አለመኖሩ ለኔ የተለየ አይደለም፡፡ “ለኔ የቀረብኝ ነገር ብዬ የማስበው ነገር የለም፡፡” የምጠብቀው ነገር ስላልሆነ ማለት ነው፡፡ እኔ ከኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር የምጠብቀው በእውነት የሚመጥን፣ ረጋ ያለ፣ ነጥብ ያለው መልስ እንጂ ተረት ተረት እያነሱ፣ የፈለጉትን እያሉ በተለይ ደግሞ ለልጆችም ጭምር የማይመጥን ቃላት እንዲናገሩ አልፈልግም፡፡ ከዚህ አንፃር የጠ/ሚ ኃ/ማርያም ደሣለኝን እመርጣለሁ፡፡ ያው እሣቸውም ሲናገሩ የሚፈልጉት ነገር ያለ ቢመስልም፣ እሱ እንዲታረም እየጠየቅኩ ቁጥብነታቸውንን ነው የምወደው፡፡ ፓርላማው ተቀዛቅዟል የሚለው ብዙም ትኩረት አይሰጠኝም፡፡ መሟሟቁ ትርጉም ከሌለው ተጠያቂነትን የማያመጣ ከሆነ ቢቀዛቀዝስ?…ፓርላማ ዋና ስራው የሕዝብን ተጠያቂነት ማምጣት ነው፡፡ የሕዝብ ወኪል የሆነ ፓርላማ ፈፃሚ አካሎችን መጠየቅ አለበት፡፡ ተጠያቂነትን ማረጋገጥ አለበት፡፡ ያጠፉ ሰዎች አይ ምንም አይደለም እየተባሉ የሚታለፉበት ሁኔታ መኖር የለበትም፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ እርምጃ መውሰድ እስካልቻለ ድረስ ሁሉም ጥያቄ ጠይቆ ቢወጣ፣ ምንም ለውጥ አልመጣም፡፡ እኔም አንዱ ሆኜ እጠይቃለሁ፡፡ እነሱም 300 ሆነው ጥያቄ ጠይቀው ለውጥ የማይመጣ ከሆነ ምን ትርጉም ይኖረዋል? ስለዚህ አንድ እኔ እበቃ ነበር፡፡ ፓርላማው የሕዝብ ውክልና የሚኖረውው፣ ትክክል የሚሆነውም ተጠያቂነት ሲኖረው ብቻ ነው፡፡ እያንደንዳችን መታገል አለብን፡፡ በፀሎት ከሆነ በፀሎት፣ ሌላ መንገድም ካለ ደግሞ ሌላ መንገዶችን እየተጠቀሙ ፓርላማው በሚቀጥለው የተሻለ እንዲሆን የፖለቲካ ፓርቲዎች ልንሰራ የሚገባን ይሄን ነው፡፡ አሁን ባለው ፓርላማ ግን ይሄ ይሻሻላል ብዬ አልጠብቅም፡፡
ሎሚ፡- በርግጥ ለብቻዎ ፓርላማ መግባትዎ የፈጠረው ተፅዕኖ አለ;
ግርማ፡- ምን ዓይነት ተፅዕኖ;
ሎሚ፡- ለብቻዎ ስለገቡ የተፈጠረ ነገር አለ;
ግርማ፡- እኔ ምንም እንዲፈጠር አይደለም ፓርላማ የገባሁት፡፡ ምክር ቤቶች ሁለት ዋና ዋና ተግባራት አላቸው፡፡ ህግ ማውጣት፣ አስፈፃሚ አካላትን መቆጣጠር ነው፡፡ የነዚህ ሁለቱ ስራዎች ሕግ በማውጣት አስፈፃሚ አካላትን መቆጣጠር ነው፡፡ ህግ በማውጣቱ ረገድ መቶም ሆነን ብንገባ ህግ የማውጣት ስልጣን የሚኖረው አብላጫ መቀመጫ የያዘው ነው፡፡ ግን ስምምነት ይደረጋል፡፡ ሌሎቹም ቢሆኑ ድምፃቸው ለአብላጫው ባይደርስም እንደዚህ አይነት ነገር ያደርጋሉ ተብሎ ይታሰባል፡፡ ‹‹ብሎክ ስቲንግ›› በሚታሰብበት ቦታ ነው፡፡ ይህ በሌለበት ሁኔታ በፓርላማ ውስጥ የሚገቡ ሰዎች በሕገ መንግስቱ መሠረት ተጠያቂነታቸው ለመራጩ ሕዝብ ነው የሚሆነው፡፡ በዚህ አይነት የሚመረጡ ቢሆን ኖሮ እኔ ጥሩ ሀሣብ ባቀርብ ለጥሩ ሀሣብ ይገዙና እዛ ውስጥ ያሉ ሰዎች ይመረጣሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ተፅዕኖ አሣድሪያለሁ ብዬ ላስብ እችላለሁ፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ግን ኢህአዴግ ድምፃችንን የመዝጋት ሁኔታ ነው የሚጠቀመው፡፡ የፓርቲውን ብቻ አይደለም፤ የአጋሮቹን ስብስብ ጭምር ነው የሚጠቀምበት፡፡ ስለዚህ ከዚህ አንፃር ለውጥ አመጣለሁ ብዬ አስቤ አይደለም የገባሁት፡፡ ያመጡት ሁሉ ነው የሚፀድቅላቸው፡፡ ፓርላማው 15 ቋሚ ኮሚቴዎች አሉት፡፡ ከነዚህ 15 ቋሚ ኮሚቴዎች ውስጥ እኔ ልሣተፍ የምችለው አንድ ቋሚ ኮሚቴ ውስጥ ነው፡፡ የምሠራበት ቋሚ ኮሚቲ ውስጥ 16 ሰዎች አሉ፡፡ አንድ ነኝ፤ ስለዚህ እዚህም ውስጥ በድምፅ ብልጫም ይሁን… በእውነቱ እኛ ድምፅ ሰጥተን ስለማናውቅ አብዛኛው በስምምነት የሚያልፍ ነው፡፡ ስለዚህ ይሄ ነው የሚባል ተፅዕኖ አመጣለሁ ብዬ ገምቼ አላውቅም፡፡ በዋነኝነት የኔ ስራ ኢህአዴግ አንድ ሕዝብን የሚመለከት ጉዳይ በሚያመጣበት ጊዜ፣ የሕዝብ ስሜት ይሄነው ብዬ ይኸኛውን ነገር ለማሣየት ነው፡፡ አላየንም ነበር እንዳይሉ፤ አልሰማንም ነበር እንዳይሉ ማለት ነው፡፡ ሰምተው በራሣቸው አንግል እንደወሰኑ እንዲያውቁት ነው ፓርላማ የገባሁት፡፡ ከዚህ አንፃር ተሣክቶልኛል፡፡ በታሪክ ውስጥ ሊመዘገቡ የሚችሉ ኢህአዴግ እየሰማ አውቆ ሳያስተካክላቸው ያወጣቸው አዋጆች አሉ፡፡ እንግዲህ የታሪክ ፍርድ ነው፡፡ ተፅዕኖውም የሚለካው ያኔ ነው፡፡
ሎሚ፡- ከፕ/ር በየነ ጋር ያለዎት ልዩነት ምንድን ነው;
ግርማ፡- በእኔና ፕ/ር በየነ መካከል አለ የሚባል ልዩነት ካለ እኔ ፓርላማ መግባቴ ነው፡፡ ፓርላማ መግባቴ ልክ ነው እላለሁ፡፡ ፕ/ር በየነ ደግሞ የኔ ፓርላማ መግባት ልክ አይደለም ብለው ያምናሉ፡፡ ይሄም ልዩነት ተገቢ ነው፡፡ ችግር የለውም፡፡ ተገቢ የማይሆነው “ፓርላማ ግርማ የገባው ኢህአዴግ አስመርጦት ነው” የሚለው ነው፡፡ ኢህአዴግ አስመርጦኝ ከሆነ ፓርላማ የገባሁት፣ እሣቸው ፓርላማ ሲገቡ ኢህአዴግ አስመርጧቸው ነበር ወይ? ነው የምለው፡፡ እነዚህ ናቸው ልዩነቶቻችን፡፡ እኔ ደግሞ ለነዚህ ልዩነቶች ብዙ ጊዜ መልስ ሰጥቼ አላውቅም ነበርና በጣም ሲደጋገም መልስ መስጠት በነበረብኝ ጊዜ መልስ ሰጥቻለሁ፡፡ እንጂ ሌላ የሀሣብ ልዩነት የለንም፡፡ ፓርላማ መግባት አለብኝና ፓርላማ መግባት የለብኝም በሚለው ልዩነት እከራከራለሁ፡፡ ችግር የለብኝም፡፡ ያለስምህ ስም ሲሰጡህ ግን ትክክል አይደለም፡፡ የዛኔ ነው ፓርላማ የገባሁት በኢህአዴግ ድራማ አይደለም ያልኩት፡፡ ኢህአዴግ ብዙ ድራማ ይሰራል፡፡ ይህንን ድራማ ግን አልሰራም ስላቸው ማመን አለባቸው፡፡ ካለመኑ ግን እኔ የመድረክ አባል ድርጅት መሪ ነኝ፡፡ ያ ድርጅት የመድረክ አባል ነው፡፡ ስለዚህ መድረክ ውስጥ ኢህአዴግ አለ ማለት ነው፡፡ በኢህአዴግነት የሚያስፈርጀኝ መረጃ ካላቸው ለመድረክ አቅረበው ከኢህአዴግ ጋር የሁለትዮሽ ጥምረት አንፈጥርም ብለው ወይ እኔ እንድወጣ ወይ ደግሞ ያ ፓርቲ እንዲወጣ ማድረግ አለባቸው፡፡
ሎሚ፡- በአሁኑ ወቅት ከመለስ ሞት በኋለ ያለውን ኢህአዴግ እንዴት ይመለከቱታል?…እንደሚታወቀው አንደኛ አመታቸው እየተዘከረ ነው፡፡ እናም የአንድ አመት ቆይታው ምን ይመስል ነበር;
ግርማ፡- ይሄ ጥያቄ ለኢህአዴግ ለራሱ አይሻልም ነበር? ….(ሳቅ)….እንዴት ከረማችሁ ማለት ለእነሱ ነው፡፡…. ጠ/ሚኒስትሩ ከሞቱ በኋላ ኢህአዴግ ቤቱን በጣም ይቆጣጠር የነበረበት አመት ነው፡፡ ሁሉን በእጁ ጠቅልሎ ይዞ ይመራ የነበረ አባት ሲሞት የሚፈጠር ቀውስ አለ አይደል፡፡ ውይ ቢዝነሱን ማን ይምራው; ልጆቹ እንዴት ይሁኑ; የውርስ ጉዳይ እንዴት ይሁን; ኢህአዴግ እንደዛ ነው የሆነው፡፡ ቤቱን ቀጥ አድርጐ የያዘ ጥሩ አባት የነበራቸውን እና ውርሱ ይሄ ይሄ ነው ብሎ በትክክል ሣያስረክብ ድንገት የሞተባቸውን ቤተሰቦች አስብና ኢህአዴግን በዛ መልኩ ተመልከተው፡፡ በይፋ ያልወጣ ይመስላል እንጂ በውርስ በምናምና የሚጣሉበት ሁኔታ አለ፡፡ እኔ ነኝ የአባትን ‹‹ሌጋሲ›› የምወስደው፤ እኔ ነኝ ይህን የማደርገው እያሉ የሚጣሉበት ሁኔታ አለ፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ኢህአዴግ እንዳለ ሆኖ ህወሓት የበኩር ልጅ በመሆኑ ብኩርናውን የሚመጥን ደረጃ ላይ አይደለም የሚገኘው፡፡ ድንገት ነው የሞቱባቸው፡፡
ሎሚ፡- የስልጣን አወቃቀሩን እንዴት ይመለከቱታል;
ግርማ፡- የፓርቲ መዋቅሩን ከዚህ በፊት በግልፅ ነው ያስቀመጥኩት፡፡ እውቀትን መሠረት አድርጐ አይደለም፡፡ ፓርርቲን መሠረት አድርጐ ነው እየተከፋፈለ ያለው፡፡ ይህንን ነው ቅድምም ያልኩህ፡፡ ‹‹ውርሱ›› በትክክል ያልተከፋፈለበት ሁኔታ አለ፡፡ በውርስ ጉዳይ ጠብ አለ፡፡ በትክክል የተከናወነ ነው ብዬ አላስብም፡፡ ድሮ በኔ እምነት ጠ/ሚኒስትሩ በደንብ ጠቅላይ ነበሩ፡፡ አሁን ግን በእውነት የቡድን አመራር ነው ያለው ብዬ አምናለሁ፡፡ ይሄ የቡድን አመራር በሁሉም ስር ነው ያለው፡፡ ይሄን በቀጥታ የምታየው አዲስ አበባ ውስጥ ነው፡፡ አዲስ አበባን የሚያስተዳድረው ኃላፊነት ያለው ከንቲባ አይደለም፡፡ ኮሚቴ የሚያስተዳድርበት ሁኔታ አይነት ነው ያለውና፡፡ ያው ኮሚቴ ደግሞ በማስ (በሒሳብ) ነው የሚሰራው፡፡
ሎሚ፡- የእናንተ አመራሮችን ጨምሮ ሌሎችም በእስር ላይ የሚገኙ የፖለቲካ እስረኞች አሉ፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ዓይነት እንቅስቃሴዎች እያደረጋችሁ ነው? እንቅስቃሴዎቻችሁስ ምን ዓይነት ምላሽ እያገኙ ነው (ከኤምባሲዎች);…
ግርማ፡- በመጀመሪያ ደረጃ ከኤምባሲዎች እኛ ምንም አንጠብቅም፡፡ ጉዳያቸውንም የሚከታተል ኤምባሲ መኖሩን አናውቅም፡፡ በኛ ደረጃ ሚና አላቸው ብለን አናምንም፡፡ አዎ! ያውቃሉ፡፡ ለዚህች ሀገር የሚሰሩት ነገር እንዳላቸው እናውቃለን፡፡ ከዛ ውጭ ግን ሚና አላቸው ብለን አናምንም፡፡ ከኛ አንፃር ትግል ውስጥ ሲገባ እስር እንዳለ እናውቃለን፡፡ እነዚህ ታሳሪዎች በሚታሰሩበት ጊዜ ምን እንደሚጠብቃቸው እናውቃለን፡፡ ተከታይም የሚገባው ሰው ምን እንደሚጠብቀው ያውቃል፡፡ ዋናው ስራ የእስረኞች ጉዳይ አይደለም፡፡ የፖለቲካ ጉዳይ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር የሁላችንም እስር ቤት ሆና ባለችበት ሁኔታ ላይ ሌሎች የተወሰኑ ሰዎች እስር ቤት ውስጥ ስለገቡ የተለየ የምናደርገው እንቅስቃሴ የለም፡፡ እነዚህ ፖለቲከኞች የፖለቲካ እስረኞች መሆናቸው እንዲታወቅ፣ ያለጥፋት የታሰሩ መሆናቸው እንዲታወቅ ብዙ እንቅስቃሴዎች እናደርጋለን፡፡ በማህበራዊ ዘርፍ ደግሞ ሌላው ቀርቶ ቤተሰቦቻቸው ማህበራዊ ችግር ውስጥ እንዳይወድቁ የተለያዩ ድጋፎችን ለማድረግ እንዲቻል የሕዝብ ግንኙነት ስራዎችን እንሰራለን፡፡ ከዛ ውጭ ግን ዋናው መፍትሄ የሚገኘው እስረኞች ይፈቱ በሚል መፈክር አይደለም፡፡ አጠቃላይ የስርዓቱ፣ ስርዓት መያዝ ነው መፍትሄ የሚያመጣው ብለን ስለምናምን ነው ትግል የምናደርገው፡፡ እስረኛ የማስፈታት ትግል አናደርግም፡፡ ምናልባትም ይህን አቅጣጫ እንደ አቅጣጫም ያስቀመጠው አንዱአለም ነው ብል ስህተት አይደለም፡፡ ምክንያቱም ከዚህ በፊት ብርቱካን ታስራ ፖለቲካው በሙሉ ‹‹ብርቱካን ትፈታ›› እስከሚመስል ድረስ የተደረገበት ሁኔታ ነበርና ነው፡፡ አሁን ፖለቲካችንን በሙሉ አንዱአለም ይፈታ የሚል ብናደርገው አንዱአለም ከኛ ጋር ይጣላል፡፡ ስለዚህ እኛ ደግሞ አንዱአለምን ማስቀየም አንፈልግም፡፡ የአንዱአለም ትግል ስርአቱ ስርአት እንዲይዝ እንጂ የተለየ ነገር በእስረኞች ላይ እንድናደርግ አይደለም፡፡ ግን የሕግ ጉዳዮቻቸውን እንከታተላለን፡፡ ለታሪክ የሚመዘገቡ ነገሮችን ማለት ነው፡፡
ሎሚ፡- የአውሮፓ ሕብረት የሰብዓዊ መብት ተወካዮች እንዲሁም የአሜሪካ ከፍተኛ ሹማምንት (የቀድሞ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሣደርን ጨምሮ) ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ነበር፤ እነሱን የማግኘት እድል አላጋጠማችሁም;
ግርማ፡- ያገኘናቸው ሰዎች አሉ፤ እኔ አልነበርኩኝም እንጂ፡፡
ሎሚ፡- ምን አዲስ ነገር ነበረው;
ግርማ፡- ምንም የለውም፡፡ በይፋ የሰጡት መግለጫ ነው፡፡ የተረጋገጠው ነገር ግን እኛ እስር ቤት ስንሄድ የሚደርስብን ውክቢያና እንግልት እነሱም ላይ ስልታዊ በሆነ መንገድ መከናወኑ ነው፡፡ እኛን አያምኑንም ነበር፡፡ እስረኞችን መጠየቅ ተከለከልን ስንል ውሸት ሊመስላቸው ይችላል-ውጭ ያሉ ሰዎች፡፡ አሁን ግን በትክክል በዘዴ እነሱንም እንዳይጐበኙ እንዳደረጓቸው አይተው ሄደዋልና ይህ ጥሩ አጋጣሚ ነው ብዬ ነው የማምነው፡፡ እኛ ግን ዕለት በዕለት የምናየው ነገር ነው፡፡
ሎሚ፡- እንደሚታወቀው የሙስሊሙ ጉዳይ በጣም እየሰፋ መጥቷል፣ ላለፈው አንድ አመት የነበረው ሁኔታ በሰላማዊ ተቃውሞ የተገደበ ነበር፡፡ አሁን ግን ደም የፈሰሰበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ የመንግስትን እርምጃ እንዴት ያዩታል? መፍትሔውስ ምንድን ነው ይላሉ;
ግርማ፡- መፍትሄው ውይይት ነው ብዬ ነው የማምነው፡፡ ሌላ መፍትሄ የለውም፡፡ በኢሳት ቴሌቭዥን አንድ ቃለ-መጠይቅ በዚህ ጉዳይ ላይ እያየሁ ነበር፡፡ ልክ እኛ እዚህ ሀገር ውስጥ የሚገጥመንን አይነት የሙስሊም መሪዎችንም የሚገጥማቸው ሁኔታ አለ፡፡ በሙስሊሙ ውስጥ ያለውን የኃይማኖት ጥያቄ ለምንድነው ወደ ሕብረተሰቡ ወስዳችሁ ፖለቲካ የማታደርጉት ተብለው ይጠይቃሉ፣ ተጠይቋል፡፡ ተመሳሳይ የሆነ ጥያቄ እኛም ጋር የመጣ አለ፡፡ ለምንድነው የሙስሊሙን ጉዳይ የፖለቲካ ጉዳይ አድርጋችሁ የማታራግቡት ተብለን ተጠይቀናል፡፡ እነዚህ ሁለቱም ትክክል አይደሉም፡፡ እኛም ይህንን አጀንዳ አድርገን የፖለቲካ ስራ ለመስራት እቅድም ፕሮግራምም የለንም፡፡ በጣም ደስ ያለኝ ነገር ከነሱም በኩል ይህ ነገር የለም፡፡ ይህንን ኮረንቲ ለማገናኘት ግን ኢህአዴግ ተግቶ እየሰራ ነው፡፡ ኢህአዴግ ግን ገብተውበታል እያለ በሌለንበት ቦታ ውስጥ እያገናኘን ሰበብ መፍጠር ይፈልጋል፡፡ ከኛ አንፃር የመርህ ጉዳይ ነው፡፡ የፖለቲካ ጥያቄ በሚነሣበት ቦታ ላይ ሙስሊሞች መብታችን ተጣሰ ብለው ሀሣባቸውን ሊያቀርቡ ይችላሉ፡፡ አንድነት በጠራው ስብሰባ ላይ ለምን ሙስሊም ተገኘ ብለው ይንጫጫሉ፡፡ ሙስሊም ኢትዮጵያዊ አይደለም እንዴ; አንድነት በጠራው ስብሰባ ላይ ሙስሊም መምጣቱ እኛን ያስደስተናል፡፡ ለምን ከዚህ በፊት በብዛት የማይሣተፉ የነበሩ ሙስሊሞች አሁን መብታቸው በደንብ እየተነካ ስለሆነ በፖለቲካ ፕሮግራሞች ላይ መንቀሣቀስ ጀምረዋል፡፡ ምርጫ በመስጊድ እናድርግ ማለት ምን ስህተት አለው; በመስጊድ አይደረግም የሚለውን ክርክር እነሱ ናቸው ከመጅሊሣቸው ጋር መነጋገር ያለባቸው፡፡ መንግስት ምን አግብቶት ነው በዚህ ላይ መግለጫ የሚሰጠው፡፡ መንግስት ምን አግብቶት ነው አህባሽ፣ ሰለፊ ምናምን እያለ ማብራሪያ የሚሰጠው?…ይሄንን እነሱ ያብራሩ፤ እነሱ ይህንን እንዲያደርጉ መተው ነው፡፡ ከዚህ ቀደም አሸባሪ ድርጅት ምናምን ሲሉ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ የተወሰነ ማሻሻያ አድርገውበታል፡፡ “አክራሪ” ወደሚል መጥተዋል፡፡ አክራሪ ብለው አታክርሩ ተብሎ ለመነጋገር የሚቀል ከሆነ ወደ ቀለል ወዳለው መምጣታቸው ክፋት አለው ብዬ አላምንም፡፡ ስለዚህ አሁንም ቢሆን አክርረዋል የተባሉት ሰዎች ጋር አታክርሩ ተብለው መነጋገርና መፍትሄ ማበጀት ነው፡፡ መፍትሄው ሁሉንም ላያስደስት ይችላል፡፡ ግን መፍትሄ እያበጀንለት ነው ብለው መናጋር ቢጀምሩ አብዛኛው ሙስሊም ይሄ የመነጋገሩ ነገር ያበርደዋል፡፡ በሰላም ሶላታቸውን ሰግደው የሚመለሱበት ሁኔታ ይኖራል፡፡ ከዛ ውጭ አንዳንዶቹ ለምንድነው በሶላት ሰዓት ላይ ሌላ ጥያቄ የሚያቀርቡት ይላሉ፡፡ ሶላታቸውን በስርዓት ነው የሚሰግዱት፡፡ ሶላታቸው ካለቀ በኋላ ግን በአጋጣሚ የሚገናኙበት ቦታ ያ ስለሆነ መልዓክታቸውን ለማስተላለፍ ቢጠቀሙበት ጥፋቱ አይታየኝም፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ፖለቲካ ርኩስ ነው ያለው ማነው; ስለዚህ መብታቸውን፣ የእምነት ጥያቄያቸውን ከመስጊድ ውጭ የት ያቅርቡ? የፖለቲካ መሪዎች ቢሮ መጥተው ነው የሚያቀርቡት; ቆይ መጂሊሱ ይለወጥ ብለው አንድነት ፓርቲ ቢሮ ቢሰበሰቡ ምንም ትርጉም የለውም? በእርግጠኝነት የምነግርህ አንድነት ፓርቲ እንደ ፓርቲ እንደዚህ አንድ አጀንዳን ይዞ እዛ ላይ ገብቶ የፖለቲካ ጉዳይ ለማድረግ አይፈልግም፡፡
ሎሚ፡- ጠ/ሚ ኃ/ማርያም ከዋልታ ጋር ቃለመጠይቅ አድርገዋል፡፡ በቃለ መጠይቁ ላይ አንዳንድ ፓርቲዎችን ከሙስሊሙ ጉዳይ ጋር አያይዘው ተናግረዋል፤ ይህን እንዴት ያዩታል;
ግርማ፡- የፈለጉትን አንዳንድ ፓርቲ ሊገምቱ ይችላሉ፡፡ የቀድሞው ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ በፓርላማ ከሻዕቢያ ጋር እንደምትሰሩ ማስረጃ አለን፤ የእንትና ተላላኪ ምናምን ይሉ ነበር፡፡ የዛኔ ምን አይነት ደካማ መረጃ ነው ያላቸው ብለን ነው እንጂ የምንጠራጥራቸው ብዙም በዚህ ጉዳይ አንረበሽም፡፡ አሁንም እንደዚህ ያደርጋሉ የሚሉ ከሆነ እኛ በመርህ ነው የምንሰራው፡፡ ከመርህ ውጭ የምንሆነው ነገር የለም፡፡ ከዚህ መርህ ውጭ ሰዎች ቢጠረጥሩ፣ ሲጠራጠሩ ቢውሉ የሚደክሙት እነሱ ናቸው፡፡ ይሄ ማለት ግን እኛ ላይ እንቅፋት የለውም ማለት አይደለም፡፡ እንቅፋቶች ይፈጥራሉ፡፡ አሁን ፋንፍሌቶች እንበትናለን፤ የእለት ተእለት የፖለቲካ ስራዎች እየሰራን እያለ ፖሊሶች በየመንገዱ ላይ ይይዙህና ‹‹እናንተ አሸባሪዎች›› ምናምን ይላሉ፡፡ ቀልዴን እንዳይመስልህ፡፡ ‹‹አሸባሪዎች›› ይሉናል፡፡ በምን አይነት የፖሊስ አስተሳሰብ ውስጥ አንዳለን የሚያሣይ ነው፡፡ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት የሚለውን ፕሮግራም መጀመራችን የኢትዮጵያን የፖሊስ ተቋም እንድንታዘብ አድርጎናል፡፡ እያንዳንዱ የፖሊስ ተቋም ሕገ መንግስቱን ጥንቅቅ አድርጐ ቃል በቃል ማወቅ አለበት፡፡ ትራፊኮች ታርጋ ቁጥር ለቅመው እንደሚይዙት ፖሊሶችም ሕገ መንግስቱን ጠንቅቀው ሊያውቁ ይገባል፡፡ ግን ኮከብ ትከሻቸው ላይ ያደረጉ በሙሉ የፀረ ሽብር ህጉን ለምን ትቃወማላችሁ? ‹‹አሸባሪዎች›› ናችሁ ይሉናል፡፡ ይሄማ ህገ መንግስቱን መናድ ነው ይሉናል፡፡ ተመልከት፤ ህገ መንግስት እንዴት እንደሚናድ እንኳን አያውቁም፡፡ ሎሚ፡- በመስከረም ወር የፓርላማው የመጀመሪያ ስራ ርዕሰ ብሔር መምረጥ ነው፡፡ ሦስት ሰዎች ለፕሬዚዳንትነት ተገምተዋል፡፡ አንደኛ ዶ/ር አሸብር፣ ሁለተኛ ኃይሌ ገ/ስላሴ እንዲሁም ሶሎሜ ታደሰ፤ ይሄን እንዴት ያዩታል? በተለይ ኃይሌ እንደሚሆን ነው በርግጠኝነት እየተነገረ ያለው፡፡ እርስዎ በፓላማ ካለዎት ቆይታ ከሚያዩት የኢህአዴግ አሠራር ምን ይገምታሉ;
ግርማ፡- ዶ/ር አሸብር አይሆኑም፡፡ እኔ ድሮም ይሆናል የሚል ግምት የለኝም፡፡ በጣም ብዙ ሰዎች ናቸው በእሱ ጉዳይ የሚሳሳቱት፡፡ የአሁኑ ፕሬዚዳንት የግል ተወዳዳሪ ስለነበሩ አሁን ያለው የግል ተወዳዳሪ ዶ/ር አሸብር ስለሆነ፣ በዚህ ምክንያት እሱ ሊሆን ይችላል የሚል ግምት ይንጸባረቃል፡፡ ዶ/ር አሸብር ፕሬዚዳንት አይሆንም ስልህ እሱ አይፈልግም ማለት አይደለም፡፡ እሱ ሊፈለግ ይችላል፤ ግን አይሆንም፡፡ ቅድም እንዳልኩህ የስልጣን አወቃቀሩ ፓርቲን መሠረት ያደረገ ነው፡፡ ስለዚህ ከደቡብ የሚሆንበት ሁኔታ ሚከብድ ነው፡፡ ጠ/ሚኒስትሩም ከደቡብ፣ ፕሬዚዳንቱም ከደቡብ ሲሆን የኃይል ሚዛኑ ወደታች ይወርዳል፡፡ በዚህ ቀመር ስለሚሰሩ ዶ/ር አሸብር የሚሆን አይመስለኝም፡፡ ይሄ የኔ ግምት ነው፡፡ ኃይሌ የመሆን ዕድል ይኖረዋል፡፡ ኃይሌ ለዚህች ሀገር ከዚህ የበለጠ ሊሣተፍ የሚችልበት ሌላ ቦታዎች አሉት፡፡ ባለፈው አንድ ጋዜጣ ላይ ሪዞልቱን ቢያስተዳድር ይሻላል ብሏል፡፡….አዎ ሪዞልት ማስተዳደር የበለጠ ለዚህች ሀገር የሚጠቅም ስራ ነው፡፡ ወይም በአመት አንድ ማራቶን የበለጠ ሊሆን ይችላል፡፡ በሚቀጥለው ምርጫ ተወዳድሬ ምክር ቤት እገባለሁ ብሏል፡፡ ኃይሌ ፕሬዚዳንት ከሆነ በፕሮቶኮል ታጥሮ ምንም ስራ አይሰራም ማለት ነው፡፡ በዶ/ር ነጋሶ ጊዜ አንበሳ ጊቢ ነበር የሚባለው፡፡ አንበሳ ጊቢ ገብቶ ከአንበሶች ጋር ተቀምጦ ምን አይነት ሕይወት እንደሚኖር አስበው እስኪ፡፡ ለኃይሌ ይሄ አይመጥነውም፡፡ ስለሰሎሜ አስተያየት መስጠት አልፈልግም፡፡ ግን ሌላ አማራጭ ሞልቷል፡፡ ኦህዴድ ብዙ ቦታዎችን አላገኘንም ከሚለው ቅሬታው አንፃር የፕሬዚዳንትነቱ ቦታ ለኦሮሞ ሊሰጥ ይችላል የሚል ግምት አለኝ፡፡ ኦሮሞ ብቻም አይደለም፤…ፕሬዚዳንቱ የኦሮሞ ሙስሊም ሊሆን ይችላል የሚል ግምትም አለኝ፡፡ ምናለ ለአንድ ሱማሌ ቢሰጠው? ለአፋር ቢሰጠው? ለቤንሻንጉል ቢሰጠው? ከአጋር ድርጅቶች ለአንዱ ቢሰጥ ምን አለበት? ልክ ለግል ተወዳዳሪ ለግርማ ወ/ጊዮርጊስ እንደተሰጠው ከአጋር ድርጅቶች ለአንዱ ቢሰጠውስ? ግን ፖለቲካዊ አማራጭ አለው፤ ትልቁ ግምቴ ግን ፕሬዚዳንት ሊሆን የሚችለው ኦሮሞ ሙስሊም ነው፡፡

ፖሊስ 4 የአንድነት አባላትን በአዳማ በማሰር የሚበትኑትን ወረቀት ነጠቀ

$
0
0

አዳማአንድነት ፓርቲ እያደረገ ያለውን የሰላማዊ ትግል በመቀጠል የፊታችን እሁድ በአዳማ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ መጥራቱ የሚታወስ ሲሆን ለዚህ ሰላማዊ ሰልፍ መሳካት ሕዝብ እንዲያውቅ ወረቀት በመበተን እየቀሰቀሱ የሚገኙ የድርጅቱን አባላት ገዢው ፓርቲ ማዋከቡን ቀጥሏል። በዚህም መሠረት የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ለዘ-ሐበሻ በላከው መረጃ እንዳመለከተው በቅስቀሳ ስራ ላይ የነበሩ አራት የአንድነት ፓርቲ አባላት አዳማ ከተማ ውስጥ ታስረዋል።
ፖሊስ ከ5ሺ በላይ በራሪ ወረቀቶችን እንደቀማቸው የገለጸው የሚሊዮኖች ድምጽ ፖሊስ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ እውቅና ተሰጣችሁ እንጂ በራሪ ወረቀት የመበተን ፍቃድ የላችሁም በሚል
1ኛ. ዳንኤል ፈይሳ፣
2ኛ. ደረጄ መኮንን፣
3ኛ. አስናቀ ሸንገማ
4ኛ ደረጄ ክበበው የተባሉት አባላት ወረዳ አንድ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ታስረው ከሰዓታት በኋላ መለቀቃቸውን የቅስቀሳ ቡድኑ አባላት አስታውቀዋል፡፡ ከትራፊክ ፖሊስ፣ ከፖሊስ፣ ከደህንነት፣ከ ደንብ አስከባሪና ከሚሊሻ የተውጣጡ ስምንት ግለሰቦች የአንድነት አባላትን በማሰሩ ተግባር እንደተሳተፉና የተወሰኑት ደህንነቶችና ፖሊስ የድብደባ ሙከራ ማድረጋቸው ታውቋል፡፡
የአንድነት ፓርቲ በመጪው እሁድ በአዳማ ከተማ ለሚያካሂደው ሰላማዊ ሰልፍ ስኬታማ የቅስቀሳ ስራ እያከናወነ እንደሚገኝ የሚሊዮኖች ለነፃነት እንቅስቃሴ ገልጿል።

የኢቲቪ ሽርፍራፊዎች (በሃብታሙ አያሌው)

$
0
0

በሃብታሙ አያሌው (የአንድነት ፓርቲ ምክትል የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ)

እንደ መግቢያ

Habitamu Ayalew


ሃብታሙ አያሌው (የአንድነት ፓርቲ ምክትል የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ)

የፀረ ሽብረ አዋጅና የፓርቲዎች አቋም ሲል ወይም ኢ.ቲ.ቪ በላከው ደብዳቤ መስረት የሶስት ሰዓታት በእጅጉ የተጋጋለ ውይይት ከተካሔደ በኋላ ውይይቱ በዜና እንኳን ሳይዘገብ ከሳምንት በላይ ለሆነ ግዜ በመራዘሙ ተወያይ ፓርቲዎች በተለያየ መንገድ ቅሬታቸውን ሲገልጹ የግል ኘሬስና ማህበራዊ ገፆችም የፓርቲዎቹን ክርክር ኢቲቪ የውሀ ሽታ ሊያደርገው ይችላል ከሚለው መላምት ባሻገር በተለያየ መንገድ አገኘን ያሉትን መረጃም ሲለቅቁ ሰንብተዋል፡፡ አንዳንዶች ተቃዋሚዎች ውኃ የሚቋጥር ኃሣብ ማንሳት እንዳልቻሉ የውስጥ መረጃ አገኘን ሲሉ ሌሎችም በተከራካሪዎች ላይ አለ የሚሉትን የአቅም ማነስ ሳይቀር በመዘርዘር ኢህአዴግ ከውይይቱ ትርማማ ይሆናል ሲሉ ተነበዩ ከዚህ አስተሳሰብ በመጠኑ እንለያለን የሚሉም ውይይቱ ፋይዳ የለውም ኢቲቪ ቆራርጦ መቅኖ ያሳጣዋል ሲሉ ስጋታቸውን ሲገልፁ ስንብተዋል፡፡ ለፓለቲካ ነፅሮት ልዬ ተስጦ ያላቸወ በሳል ተንታኞች በበኩላቸው ኢህአዴግ ውይይት ማድረጉን ለምን መረጠ? ለምን ይህንን ወቅት መረጠ? ውይይቱ ለተቃዋማው ያለው ፋይዳ ምንድነው? አዋጁ እንዲሰረዝና በዚህም ምክንያት የታሰሩ እንዲፈቱ ከማድረግ ባሻገር ይህ አፋኝ ስርአት እንዲለወጥ የትግሉ አቅጣጫ ምን ያህል የተጠና ነው? የሚሉ በርካታ ጥያቄዎችን በማንሳትና መፍትሔዎችን በማመላከት የበኩላቸወን ጥረዋል፡፡ በጥቅሉ በፀረ ሽብር አዋጁ ዙሪያ የተደረገው ክርክር ለህዝብ እይታ ከመቅረቡ አስቀድሞ አጓጊ ሆኖ ሰንብቷል፡፡ የብዙዎቹ የሆነው የጋራ ስጋት የሚመነጨው ኢቲቪ በህዝብ እነት ያጣ ድርጅት ከመሆኑ ጋር በቀጥታ የሚያያዝ በመሆኑ ውይይተ በስርጭት ላይ ውሎ የብዙሀኑን ቀልብ የሳበ ቢሆንም ኢቲቪ ቆርጦባችኋል? የሚለው ጥያቄ ግን አሁንም አላቋረጠም እና ኢቲቪ የሽራረፋቸውን የኢትዮ ምህዳር ጋዜጣ በኩል ላቀብላችሁ ወደድኩ፡፡

ከመሸራረፍ ባህሪው ያልታረመ ቢሆንም ኢቴቪ ገለታ ይደረሰው ለማለት ግን አልሰስትም፡፡ ስለ ሽብር ያወያየን አሸብር ፊሽካ ይዞ ለመዳኘት ስንፈቅድለት ያንን ክብር ትቶ ኳስ አቀባይነት፣ ሲያኘው አጥቂና ተከላካይ እየሆነ ምላስ ቦታ በመርገጡ የተሰማኝን ቅሬታ መግለፁም እውነታ ነውና ነውር የለውም፡፡

አንድ ጋዜጣና ሚዛን አልባ ሆኖ ለሚደግፈው ካራገበ፣ የማይፈልገውን ሃሳብ ከጨቆነና አንዳንዴም ሀሳብን በፈለገው መንገድ ከቆረጠ ጋዜጣኛ ሊባል የሚችልበት ምንም ምክንያት የሌለ ሲሆን በመስኩ ሊገኝ የሚገባውን ጤናማ ውጤት ሁሉ የሚያበላሽ ይሆናል፡፡

ከዚህ እረገድ የኢትቪው አሸብር ጌትነት እራሱን መፈተሽ እና ለሙያው መታመንን መምረጥ ተቀዳሚ ተግባሩ ሊያደርግ የሚገባው ይመስለኛል ይህም በማሳሰብ ሳይሆን ይልቁንም በመምከር ነው፡፡

ሽርፍራፊዎች
ኢቲቪ ለአየር ያበቃው የውይይቱ ክፍል የተቆራረጠ ሀሳብ እና የማጠቃለያ ቅደም ተከተል መዛባት ቢኖረውም ገለታ ይድረስው ለማለት አልሳሳም ያልኩበት ምክንያት አንባቢ እንደሚገነዘበው ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ይህውም ቢሆን ከእባብ እንቁላል እርግብ እንደማግኘት የሚያስገርም በመሆኑ ነው፡፡
1. በአቶ ሸመልስ ከማል የቀረበ አስተያየት
ፍርድ ቤትን ፓሊስን እያጣጣላችሁ በማስረጃ ተረጋግጦ ቦንብ ሊያፈነው የመንግስትን ተቋማት ሊያወድሙ ሲሉ ተይዘው በማስረጃ የተረጋገቀባቸውን ሰዎች ይፈቱ እያላችሁ፣ እንደሰማዕት ከየአደባባዩ ከመጥራትም አልፋችሁ እዚህ ሳይቀር እየደገማችሁበት ባለችሁበት ሁኔታ እናንተ እንዴት ሰላማዊ ታጋይ ልትሆኑ ትችላላችሁ፡፡

የተቆረጠብኝ ምላሽ እነዚህን አሸባሪዎችን ሰማዕት ማስመሰልና ማበረታታት በሙሉ አሸባሪነት ነው፡፡

እናንተ ያስራችኋቸው እኛ ጀግና ሠላማዊ የነፃነት ታጋይ የምንላቸው እና አንዷለም አራጌ፣ በቀለ ገርባ፣ ሌሊሳ ኣልባና ናትናኤል መኮንን፣ አንዱአለም አያሌው አለም አቀፍ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ጋዜጠኛ ርዮት ዓለሙና የመሳሰሉትን የታሰሩት ነፃነት የሌላው የፓርቲ አገልጋይ ነው ይሞግቱት በነበረው ፍ/ቤት ነው፡፡ እንደፓርቲ ፍ/ቤት ነጻ እንዳልሆነ እናምናለን ይህም ከእኛ በላይ በመንግስት ተቋም በተደረገ ጥናት የተረጋገጠ ነው፡፡ በዚህ ታማኝና ነጻ ባልሆነ ፍ/ቤት አሸባሪ ስለታባሉ እኛ አሸባሪ አንላቸውም፡፡ ለእኛ ጀግኖች ናቸው፡፡

እነዚህ ጀግኖች ፈንጂ ሊያፈነዱ ነበር ተቋማት ሊያወድሙ ነበር የተባሉት በኢቲቪ አኬልዳማ ዶክመንተሪና በኢህአዲግ ባለስልጣናት እንጂ በፍ/ቤት የቀረበባቸው የክስ ቻርጅ እና መረጃ ይህ አይደለም ዛሬም እንደትናንቱ ህዝብ አታታሉ፡፡ በቃ የሚል ጽሁፍ ያለበት ወረቀት ፎቶ አነሳሽ፣ የወንድምህን ደህንነት፣ በስልክ አወራህ፣ ኢሚል ተጻጻፍክ ወዘተ በሚል ተልካሸ ምክንያት ከኢህአዴግ የተለየ አስተሳሰብ በመያዛቸው ምክንያት ብቻ የህሊና እስረኞች ናቸው፡፡

ይህንን ሀቅ መናገር አሸባሪነትን ማበረታታት ነው ብላችሁ ለማሸማቀቅ የምታደርጉት ሙከራ ተቀባይነት የለውም፡፡ ዛሬም ነገም በየአደባባዩ ስማቸውን እንዘክራንለ ነጻ እስኪወጡም እንታገላለን፡፡

2. አቶ ሸመልስ ከማል በሀገር ውስጥ ተከውኖአል ያሉትን የሽብር ተግባር ሲዘረዝሩ የበደኖን ጭፍጨፋ በማንሳን ኦነግ ጨፍጭፎአል ሲሉ ላቀረቡት መከራከሪያ

የተቆረጠው የእኔ ምላሽ
ብዙዎቹ የኢህአዴግ ባለሥልጣናት ደፍረው የማያነሱትን የበደኖ ጭፍጨፋ በማንሳትዎ አቶ ሸመልስን አመስግናለሁ፡፡ የበደኖን ጭፍጨፋ ለኦነግ በማቀበል ዘወር ማለት ግን አይቻልም፡፡ ኦነግ ከሀገር ሳይወጣ አሸባሪም ብላችሁ ሳትፈርጁት በሽግግር መንግስትነት ከህወሀት ኢህአዴግ ጋር ሀገር እየመሩ ባሉበት ወቅት የተፈፀመ ጭፍጨፋ መሆኑ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ ሌላው ይህንን የበደኖ ጭፍጨፋ እርስዎ በመሰሎት መንገድ ሲናገሩት ወንጀል አይደለም ከፖርቲዎ ሞራል ያሰጥዎታል፡፡ ይህንን የበደኖ ጭፍጨፋ ዘርዝሮ በመጻፍ ለእውነት በመትጋቱ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሣለኝ ክስ ተመስርቶበት ፍ/ቤት እየተመላለሰ ነው፡፡ እንግዲህ ህግ አለ የምትሉት ይህንን ነው፡፡ ለዜጋ ሳይሆን ለካድሪ የሚፈርደውን የእናንተን ህግ የምንሟገተውም ይህ ብልሹ አሰራር እንዲቀየር የህግ የበላይነት እንዲከበርና የስርአት ለውጥ እንዲመጣ እንጂ እናንተ እንደምትፈርጁን ለሁከት አይደለም፡፡
3. አቶ ጌታቸው እረዳ በአንድ ወቅት አስታውሳለሁ ሀብታሙ የማደራጃ አዋጅን ከእኔ በተሻለ ብቃት ይተነትን ነበር አሁን መንገዳችን ለየቅል ቢሆንም ሲሉ ለሰነዘሩት የትናንት አብረን ነበርን ሾርኒ …

የተቆረጠው የእኔ ምላሽ
የኢህአዴግ ባለስልጣናት ለተቃዋሚ እውቅና መስጠትና ይበልጠኛል ማለት ሞታቸው ነው፡፡ አቶ ጌታቸው በዚህ መድረክ ከእኔ በተሻለ የመተንተን ብቃት አለህ ብለው ምስክርነት በመስጠትዎ አከብራለሁ አመሰግናለሁ፡፡
ነገር ግን “በእኔ እምነት ከስህተቱ የማይማረው ፈንጂ አምካኝ ብቻ ነው” ሲያመክን ከተሳሳተ ይሞታል የመማሪያ እድል የለውም እርስዎና የኢህአዴግ ባለስልጣናት እንደእኔ ከስህተት ለመማር አልረፈደባችሁም፡፡ አሰላለፋችሁም እንደእኔ ከህዝብ ጋር በማድረግ እንድትማሩ እመክራለሁ፡፡

4. አቶ ሸመልስ ከማል መንግስት ደጋግሞ ቢያሳስባችሁም ከስህተታችሁ ለመማር አልፈለጋችሁም እናንተ ህገ ወጦች ናችሁ፡፡ በማለት ቁጣ ቀላቅለው ለሰነዘሩት ዛቻ

የተቆረጠው የእኔ ምላሽ
አቶ ሸመልስ ሳይቀር መንግስትን የተለየ አካል አድርገው አሳስበናችኋል፣ አደጋ አለው፣ታግሰናችኋል በማለት ለማስፈራራት መሞከር እና ዛቻ መምረጥዎ ያሳዝናል በእርግጠኛነት የምነግርዎ እናንተና እኛ በህግ ፊት እኩል ነን እናንተ ከእኛ የምትለዩት የመንግስት ስልጣን በመያዛችሁ እኛ ደግሞ ነገ መንግስት ለመሆን የምንወዳደር ፓርቲ ነን ሁለታችንም ሊዳኘን የሚገባው ሰርአትና ህግ እንጂ እናንተን አሳሳቢና አስፈራሪ ያደረጋችሁ ማነው? ትልቁ ችግራችሁ ከእዚህ ይመነጫል የተቃወማችሁን ሁሉ ለማጥፋት አሸባሪ የምትለውን ታርጋ መጠቀም የመረጣችሁትም ከዚህ ባህርይ በመነሳት በመሆኑ ሊታረም ይገባል፡፡

ጥቅል ቆረጣ የተካሄደበት
ውይይቱ የተላለፈው በሶስት ክፍል ሲሆን ክፍል አንድ በኢህአዴግ ተጀመረ የመጨረሻ ሰፊ ሀተታ በኢህአዴግ ከቀረበ በኋላ የተቃዎሚዎች ምላሽ ሳይቀጥል ክፍል ሁለት ይቀጥላላ ተባለና ክፍል ሁለትን በአዲስ ጥያቄ በመጀመር የተቃዎሚውን መልስ ሙሉ በሙሉ አስቀረ ክፍል ሁለት ሲጠናቀቅ እንዲሁ በተመሳሳይ ከኢህአዴግ ማብራሪያ በኋላ ያለው የተቃዎሚዎች ማብራሪያ ተቆርጦ በአዲስ ጥያቄ ተጀመረ፡፡ የክፍል ሶስት ማጠቃለያም በኢህአዴግ ማብራሪያ እንዲጠናቀቅ ተደረገ፡፡

የማጠቃለያው ሀሳብ
ውይይቱ ሲጠቃለል የመጨረሻው ተናጋሪ አቶ ሸመልስ ከማል ሆነው ማብራሪያ ሲሰጡ አንቀጽ በአንቀጽ መረጃ ማቅረብ አልቻላችሁም በማለት መከራከሪያ ሀሳብ እንደአጠረንና አንቀጽ ለመጥቀስ እንደተቸገርን በማስመሰል መደምደሚያ አድርገው ሊያጠናቅቁ ሲል የተቃውሞ ሀሳቤን ሰነዘርኩ፡፡ አንቀጽ በአንቀጽ እንወያይ ብለን ስናነሳ አወያዩ የፓለቲካ አቋም ላይ ተወያይተን በአንቀጹ በኋላ እንመለስበታለን በማለት ካቆየ በኋላ ሰአት አልቋል አለን፡፡ ባልተወያየንበት ጉዳይ መረጃ አላቀረባችሁም ብለው መደምደሚያ መስጠቱ ስህተት ነው፡፡ አቶ ጌታቸው ሀብታሙ ትክክል ነው ይህ ያልተወያየንበት በመሆኑ ሁለተኛ ቀጠሮ ተይዞ ውይይት ይጠራ የሚለው ሀሳብ ማጠቃለያ ሆነ፡፡ ለኢቲቪ ሲተላለፍ ግን ይህ ማጠቃለያ ውይይት ተቆርጦ የአቶ ሸመልስ ሀሳብ ወደ መሀል ተወስዶ መሀል ላይ ለማደናገሪያ ገባና ከመሀል የአቶ ጌታቸው ንግግር ተቆርጦ ማጠቃለያ እንዲሆን በማድረግ ኢቲቪ በኤዲንግ ጥበቡ አጠቃለለው፡፡

የግል አስተያየት
የተቆረጡ ሀሳቦች በሚል የማስታውሳቸውን ስጽፍ የሌሎች ተከራካሪዎች ሀሳብ አልተቆረጠም በማለት ሳይሆን በራሳቸው አገላለጽ እንደሚጽፋት በማሰብ ንግግራቸውን እንዳላበላሽ በመስጋት የተውኩት ነው፡፡ የተቆረጡ ሀሳቦችን መጻፍ ያስፈለገውም በርካታ ህዝብ የተቆረጡ ሀሳቦችን ለማወቅ ከአቀረበው ጥያቄ በመነሳት እና ኢቲቪ በጐውን እንዲቀጥልበት እኩይ ተግባሩንም እንዲተው ለመቃወምና ለማስጠንቀቅ እንዲረዳ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

Part 2


// ]]>
Part 2

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live