Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

‹ሀገር ማለት ሰው ነው›፤ እስኪ ሙት በለኝ! (በዲያቆን ዳንሄል ክብረት)

$
0
0

ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገርሙኝ ዘፈኖች አንዱ ‹ሀገር ማለት ሰው ነው› የሚለው ነው፡፡ እሥራኤላዊና ጂፕሲ ይህንን ቢሰሙ ምን ይሉ ይሆን? እላለሁ፡፡ አይሁድ በመላው ዓለም ለ1900 ዓመታት ያህል ተበታትነው ሲኖሩ በየአካባቢው ሰው ነበራቸው፤ያውም እንደ ብረት የጠነከረ ማኅበረሰብ፤ ሀገር ግን አልነበራቸውም፡፡ ሀገር ማለት ሰው ከሆነ አይሁድ ሀገር ፍለጋ ከሺ ዓመታት በላይ መኳተን አልነበረባቸውም፡፡ በአውሮፓ የሚኖሩት ጂፕሲዎች የታወቀ ማኅበረሰብ አላቸው፡፡ ነገር ግን ሀገር የላቸውም፡፡ ሀገር ማለት ሰው ቢሆን ኖሮ ጂፕሲ የሚባል ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ጂፕሲ የሚባል ሀገርም ይኖር ነበር፡፡ ግን የለም፡፡

daniel kibret
በአሜሪካ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን አሉ፡፡ ‹በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን› የምትባል ሀገር ግን የለቺም፡፡ 1.3 ሚሊዮን የሚደረሱ ግሪኮች በአሜሪካ ይኖራሉ፡፡ ‹የአሜሪካ ግሪኮች› የምትባል ሀገር ግን የለችም፡፡ ‹ግሪክ ሲሠራ አሜሪካ ይኖራል፣ ሲያረጅ ግሪክ ይጦራል› የተባለው ሀገር ሰው ብቻ ስላልሆነ ነው፡፡
ሰዎች ተሰብስበው ሀገር ሊመሠርቱ አይችሉም፡፡ በየሀገሩ የተሰበሰቡ ማኅበረሰቦች ‹ኮሙኒቲ› ይባላሉ እንጂ ሀገር አይባሉም፡፡ ሀገር ሀገር ለመሆንና ለመባል ከሰው በተጨማሪ የምትፈልገው ብዙ ነገር አላትና፡፡ ሀገርን ሀገር ለማስባል መሬትም ያስፈልጋል፤ መሬት ሳይኖርህ ሰው ስለሰበሰብክ ብቻ ሀገር ልትሆን አትችልም፡፡ ያውም የእኔ የምትለው፣ የምትሞትለትና የምትለፋለት ታሪካዊ መሬት ያስፈልግሃል፡፡ አይሁድ በ1930 አካባቢ በኡጋንዳ ኡዋሲን ጊሹ (Uasin Gishu County) በተባለ ቦታ እንዲሠፍሩና ሀገር እንዲኖራቸው ታስቦ ነበር፡፡ እንደ ቴዎዶር ኸርዝል ያሉ ታላላቅ የጽዮናዊነት መሪዎችም ለጊዜውም ቢሆን ተስማምተውበት ነበር፡፡ ብዙኀኑ አይሁድ ግን ‹ሀገር ማለት የሆነ መሬት አይደለም፡፡ ታሪካዊ መሬት ነው› ብለው ተቃወሙት፤ ሀገር ማለት የሆነ መሬት ብቻ ቢሆን ለአይሁድ ከዛሬዋ እሥራኤል ይልቅ በአየር ንብረትና በተፈጥሮ ማዕድን፣ ብሎም በአቀማመጥ ኡጋንዳ ትሻላቸው ነበር፡፡
ባድሜ ለምትባል ከጦርነቱ በፊት ብዙው ሕዝብ ሰምቷት ለማያውቅ መሬት የተደረገውን ጦርነት የረሳ ሰው ነው ‹ሀገር ማለት ሰው ነው› የሚል፡፡ ሀገር ማለት ሰው ከሆነ ለባድሜ የተደረገው ጦርነት ለማን የተደረገ ነው ሊባል ነው፡፡ በሄግ ፍርድ ቤት የነበረው ክርክርስ የመሬት ክርክር እንጂ የሰው ክርክር ነበር እንዴ?
ሀገር ማለት ሰው ቢሆን ኖሮ ሰው ስለ ሀገሩ ሲያነሣ ወንዙን፣ ተራራውን፣ ሸለቆውን፣ ሜዳውን፣ ጫካውን እያነሣ ለምን ይዘፍን ነበር ፡፡
‹ያገሬ ተራራ ወንዛ ወንዙ ለምለም
እማማ ኢትዮጵያ ኑሪ ለዘላለም› ለምን ይል ነበረ፡፡
ሀገር ማለት ሰው ከሆነ ይሄ የኔ ክልል፣ ጎጥና መንደር ነው የሚለው ክርክር ከየት ይመጣ ነበር? ሀገር ማለት ሰው ከሆነ የተለየና የታወቀ የሀገር ድንበርና ካርታ ለምን ያስፈልግ ነበረ? ሰውማ የትም ነው የሚኖረው፡፡ ካርታ አያሻውም፡፡ ሀገር ማለት ሰው ከሆነ ለምን የአብዛኞቹ ሀገሮች ብሔራዊ መዝሙር ስለ መሬቱና ስለ ድንበሩ ያወራል? ሀገር ማለት ሰው ከሆነ ለሰው ፓስፖርትና ቪዛ ለምን ያስፈልገዋል? ሰው ያለበት ቦታ ሁሉ ሀገሬ ስለሆነ ለምን እንደፈለግኩ ወጥቼ አልገባም? አንድ ሰው ወደ አንድ ሀገር ገባ የሚባለው ወደ መሬቱ ሲገባ እንጂ የሀገሩን ሰው ሲያገኝ ነው እንዴ? ምናልባትም ከአንታርክቲካ በቀር ቪዛ መጠየቅ ያለበት ሀገር አልነበረም፡፡ እርሱ ሰው የለበትምና ‹ሀገር ማለት ሰው ነው› የሚለው አይመለከተውም፡፡ ሀገር ማለት ሰው ከሆነ በሰማይ የሚሄድ አውሮፕላን ‹የአየር ክልሌን ጣሰ› ብሎ መሟገት ምን የሚሉት ሞኝነት ነው? ሰውን አልጣሰ፣ የጣሰው አየር ነው፡፡
ደግሞም አገር ማለት መሬት ብቻ አይደለም፡፡ ያማ ቢሆን ኖሮ አንታርክቲካ ሀገር ይሆን ነበር፡፡ ያማ ቢሆን ኖሮ በዓለም ላይ የሚገኙ ወደ ሃምሳ የሚጠጉ ሰው አልባ ደሴቶች(nonecumene)‹ሀገር› ተብለው በተባበሩት መንግሥታት ይመዘገቡ ነበር፡፡ ሀገር ማለት መሬት ቢሆን ኖሮ መሬት ያለው ሁሉ ሀገር ይኖረው ነበር፡፡ የአሜሪካ ሕንዶች፣ የአውስትራልያ አቦርጅኖች፣ ከጥንት ጀምሮ የሚኖሩበት መሬት አላቸው፡፡ የራሳቸው የሆነ ሀገር ግን የላቸውም፡፡ ደቡብ ሱዳናውያን የራሳቸው የሆነ የሚኖሩበት መሬት ነበራቸው፤ ሀገር ለመሆን ግን መዋጋት ነበረባቸው፡፡ ደቡብ ሱዳኖችን ያን ሁሉ ዘመን ያዋጋቸው የመሬት ጥያቄ ሳይሆን የሀገርነት ጥያቄ ነው፡፡ የራሳቸውን ፖለቲካዊ መሬት አግኝተው እንኳን ሀገር ለመሆን ገና እየተሠሩ ነው፡፡ ፍልስጤማውያን ይብዛም ይነስ የሚኖሩበት መሬት አላቸው፡፡ አገር ግን የላቸውም፡፡
አገር ከዚህ ሁሉ በላይ ነው፡፡ ሰው፣ ሰው የኖረበትና ታሪክ የሠራበት መሬት፣ ማኅበረሰብ ከማኅበረሰብ፣ ሰው ከሰው፣ ሰው ከማኅበረሰብ፣ ሰው ከመሬት፣ ሰው ከአራዊት፣ ሰው ከተፈጥሮ፣ ሰው ከወራሪ ጋር የነበረው ትግል፣ ውጊያና ወዳጅነት፤ የተረተው ተረት፣ ያወጋው ወግ፣ የፈጠረው አፈ ታሪክ፣ ያከማቸው ትዝታ፣ ሰው ለመሬቱ፣ ለወገኑና ለእምነቱ የከፈለው መሥዋዕትነት፤ የዘፈነው ዘፈን፣ ያቅራራው ቀረርቶ፣ የፎከረው ፉከራ፤ ያገኘው ድልና የተሸከመው ሽንፈት፤ ያደረሰው በደልና የደረሰበት በደል ይሄ ሁሉ ነው ሀገር፡፡
መገለጫው ቅርስ፣ መዋሐጃው ባህል፣ መታያው ልብስና መዋቢያው ጌጣጌጥ፣ መገናኛው ቋንቋ፣ መዝናኛው ጭፈራ፤ ማስተማሪያው ተረት፣ መክበሪያው ዓመት ባል፣ መጠበቢያው ምግብ፣ መቆዘሚያው እንጉርጉሮ፣ መተከዣው ልቅሶ፣ መተኪያው ልደት፣ ማሳረጊያው ቀብር፤ መገምገሚያው ምግባር፣ ማነወሪያው ነውር፤ መኩሪያ ጀግንነቱ፣ ማፈሪያ ገመናው፤ መደበቂያ ቤቱ፣ መመረሪያ ጫካው፤ ይሄ ሁሉ ነው ሀገር፡፡ ታሽቶ ተገርኝቶ ያመጣው አንድነት፣ ተጣልቶ ተባልቶ ያመጣው ልዩነት፣ እንደ ዘሐ ዘጊ የተጠላለፈው፣ እንደ እግር ሠንሠለት የተቆላለፈው፣ ሲፈተል፣ ሲገመድ፤ ሲባዘት፣ ሲዳውር፤ ሲከካ፣ ሲሰለቅ፤ ሲጣላ፣ ሲታረቅ፤ ሲያውቅና ሲማይም፤ ሲሠለጥንና ሲደኸይ፤ ሲሰፋና ሲጠብ፤ የኖረውና የኖረበት፣ የኖረለትም ነው ሀገር፡፡
ሀገር ትዝታ ነው፡፡ የትም ቦታ ስትሄድ ጠምዶ የሚያመጣህ፡፡ ምንም ሥጋ ብትቆርጥ ከብቱ ትዝ ይልሃል፤ ምንም ቢች ዳር ብትዝናና ወንዙ ትዝ ይልሃል፤ ምን በሽቱ ብትታጠን አፈሩ ይሸትሃል፤ ምን በሥጋጃ ላይ ብትሄድ ጉዝጓዙ ይመጣብሃል፡፡ በኮምፒውተር እየሠራህ ያቦካኸው ጭቃ ይናፍቅሃል፤ በጄት እየበረርክ አህያና በቅሎው ያምርሃል፤ ማንሐተን ተቀምጠህ ሰባተኛ፣ ሎንደን ተቀምጠህ ቂርቆስ፣ ኖርዌይ ሆነህ ጅግጅጋ፣ ካናዳ ሆነህ ሐረር ይወዘውዝሃል፡፡ ሀገር ማለት ትዝታ ነው፡፡
ሀገር ማለት ከምትገልጠው ብታስበው፣ ከምትኖርበት ብትሞትበት፤ ከምትስቅለት ብታለቅስለት የምትመርጥለት ነገር ነው፤ ሀገር ማለት ትተህው ብትሄድ ትቶህ የማይሄድ፣ በራቅከው ቁጥር ልብህ ውስጥ የሚቀር፣ ባወቅከው ቁጥር የምትንገበገብለት፤ በተረዳኸው ቁጥር የምትሳሳለት፣ አንተን እርሱ ውስጥ እንደምታገኘው ሁሉ እርሱንም አንተ ውስጥ የምታገኘው፤ የተሠራህበት ውሑድ፤ የተቀረጽክበት ማንነት ነው ሀገር፡፡
ሀገር ማለት ሰው ብቻ ቢሆን ኖሮ ዘመድ የሌለው ሰው ወደ ሀገሩ ለመምጣት ባልናፈቀ ነበር፡፡ ሀገር ማለት ሰው ብቻ ቢሆን ኖሮ ዘመዶቹ ሁሉ ከእርሱ ጋር ውጭ የሚኖሩለት ሰው ‹ሀገሬን ሀገሬን› እያለ መከራ ባላየ ነበር፡፡ ሀገር ማለት ሰው ብቻ ቢሆን ኖሮ ሰዎች በየዘመናቱ የበደሉት ሰው ሀገሬ በደለችኝ ባለ ነበር፡፡ ሀገር ማለት ሰው ብቻ ቢሆን ኖሮ ሰው ስለ ሀገሩ ሲያስብ ተራራውና ወንዙ፣ አዕዋፉና አራዊቱ፣ ማሳውና ቀየው ለምን ትዝ ይለው ነበር፡፡ በሀገር ማለት ሰው ብቻ ቢሆን ኖሮ ያሸነፈ አትሌት፣ ድል ያደረገ ኳስ ተጨዋች ባንዴራው ሲሰቀል ለምን ያለቅስ ነበር?
‹አዙረሀ አዙረህ ሀገሬ መልሰኝ
በሹም ታዘዘ አፈር አታልብሰኝ› ብሎ ለምን ያንጎራጉር ነበር፡፡ ዐጽሙ በአፈሩ እንዲያርፍ ለምን ይናዘዝ ነበር፡፡ ለምን ሙሾውን፣ የሠርግ ዘፈኑን፣ ወጉን ማዕረጉን ይፈልገው ነበር፡፡
ሀገር በአርምሞ እንጂ በንግግር፣ በተግባር እንጂ በዝርዝር ሊናገሩለት የማይቻል ነገር ነው፡፡ ውጥንቅጥ ሰበዞች የሰፉት ሞሰብ፣ዓይነተ ብዙ ድርና ማጎች የሸመኑት ጋቢ፣ ልዩ ልዩ ቅመሞች የሠሩት ወጥ፣ ብዙ ገባሮች የፈጠሩት ዓባይ፣ ብዙ ትውልዶች የከመሩት ተራራ፣ ከአራቱ አቅጣጫ ተሰብስቦ በአንድ ወፍጮ የተፈጨ እህል፣ ከየአበባው ተቀስሞ በአንድ ቀፎ የተሠራ ማር፣ ከየእህሉ ወጥቶ በአንድ ማድጋ የተጠመቀ ጠላ፣ ከየ እንጨቱ ተለቅሞ በአንድ ጽንሐ የታጠነ ዕጣን ነው ሀገር፡፡
ሀገር ማለት ሰው ነው? እስኪ ሙት በለኝ


ቀይስርን የመመገብ የጤና ጥቅሞች

$
0
0

(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)
*ለጉበት ጤናማነት
ቀይስር ውስጥ የሚገኝ ቤታይን የተባለ ንጥረነገር የጉበትን አገልግሎት የማነቃቃት አቅም አለው።
*ከሳንባ ጋር ተያያዥ ችግሮችን ይከላከላል
ቀይስር ቫይታሚን ሲ በውስጡ ስለያዘ የአስም ምልክቶች እንዳይነሱ ይረዳል፣ በሽታ የመከላከል አቅማችን እንዲዳብርም ያግዛል። ቤታ ካሮቲን የሚባለው ንጥረ ነገር በሳንባ ካንሰር የመጠቃት እድልን ይቀንሳል።

beets1-640x330
*ካታራክትን ይከላከላል
ቤታ ካሮቲን የሚባል ንጥረ ነገርን የያዘው ቀይስር ከእድሜ ጋር ሊመጣ የሚችልን የአይን ሞራ እንዳይከሰት ይከላከላል።
*የሃይል መጠንን ይጨምራል
ቀይስር በካርቦሀይድሬት የበለፀገ ስለሆነ ሀይል ሰጭ ከሚባሉት ምግቦች እንዲመደብ ያደርገዋል።
*ካንሰርን ይከላከላል
አንዳንድ ጥናቶች ቀይስር ከቆዳ፣ ከሳንባ እና ከአንጅት ካንሰር የመከላከል አቅም እንዳለው ያሳያሉ።

የቀዝቃዛ ሻወር በረከቶች

$
0
0

የቀዝቃዛ ሻወር በረከቶች

የብዙዎቻችን አንደኛ ምርጫ ሙቅ ሻወር መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ቀዝቃዛ ሻወርን መርጠን የምንጠቀም እምብዛም ነን፡፡ ሙቅ ሻወር ከሌለ፣ አማራጭ ሲጠፋ ነው ወደ ቀዝቃዛው ሻወር የምንገባ እንጂ የምንግዜውም የብዙዎቻችን ምርጫ ሙቅ ሻወር ነው፡፡

iStock_000015417910Small-660x330

ግን ለመሆኑ ቀዝቃዛ ሻወር ታላላቅ ጥቅሞች እንዳሉት የምናውቅ ስንቶቻችን ነን…

1. በቀዝቃዛ ውሃ መታጠብ ስብ እንዲቀልጥ ያደርጋል…፡፡ በቀዝቃዛ ውሃ ገላችንን በምንታጠብበት ጊዜ ሰውነታችን የሙቀት መጠኑን ለመጠበቅ የተከማቸውን ስብ ያቀልጣል፡፡ ይህም በፋንታው በተወሰነ መልኩ ክብደት ለመቀነስ ይረዳል፡፡

አንድ የጥናት ውጤት እንደሚያሳየው በቀዝቃዛ ውሃ ገላን መታጠብ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ 9 ፓውንድ ያህል ክብደት ለመቀነስ ይረዳል፡፡

2. በቀዝቃዛ ውሃ ገላን መታጠብ ስሜትና መንፈስን ነቃ ያደርጋል፡፡ ከእንቅልፍዎ ተነስተው ወደ ስራ ከመሄድዎት በፊት በቀዝቃዛ ውሃ ገላን መታጠብ የውሃው ቅዝቃዜ በገላዎት ላይ የሚፈጥረው ስሜት በጥልቀት ዓየር እንዲስቡ ያደርገዎታል፣ ይህም ሰውነትዎ ኦክስጅን በብዛት በመሳብ ሙቀት ለመፍጠር የሚያደርገው ነው፡፡

የልብ ምትዎም ይጨምራል – ይህም በፋንታው ደም በሰውነትዎ ውስጥ በፍጥነት እንዲዘዋወርና ቀኑን ነቃ ብለው በመልካም ሀይል እንዲጀምሩት ያደርጋል፡፡

3. በቀዝቃዛ ውሃ መታጠብ የሰውነትዎን ሜታቦሊክ ሂደት በማፋጠን የሰውነትን በሽታ የመከላከል ስርዓት ያነቃቃል፡፡

4. ከአድካሚ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በኋላም ገላን በቀዝቃዛ ውሃ መታጠብ በተለይም በበርካታ አትሌቶች ዘንድ የሚዘወተርና የሚመከር ተግባር ነው፡፡

5. በቀዝቃዛ ውሃ መታጠብ ማራኪ ጸጉርና ቆዳ እንዲኖርዎት ያደርጋል፡፡ በተለይም ቆዳ ላይ የሚወጡትን ቀያይ ብጉር መሳይ እብጠቶች እንዳይከሰቱ ለማድረግ ቀዝቃዛ ውሃ ተመራጭ ነው፡፡

ሞጋቾች ተከታታይ ድራማ ክፍል 65

የጠቅላይ ሚኒስቴሩ የይቅርታ ትርዒት |ሳዲቅ አህመድ ህወሃታዊ ሴራዎችን በመቃኘት ያዘጋጀው የድምጽ ዘገባ

$
0
0

ወርሃ መጋቢት ገና ከመግባቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለማሪያም ደሳለኝ ፓርላማ ፊት ቀርበዉ የኢትዮጵያ ህዝብን በፌደራል መንግስት ስም ይቅርታ መጠየቃቸዉ ይታወሳል። ይቅርታዉ ፓርላማ ዉስጥ ከተደረገ ትርዒት ተለይቶ አይታይም፥በህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ የሚመራዉ መንግስት የሚፈጽመዉን ብሐራዊ ጭቆና አፋፍሞ ቀጥሏል የሚሉ ብዙ ናቸዉ። ሳዲቅ አህመድ ህወሃታዊ ሴራዎችን በመቃኘትና የጠቅላይ ሚኒስቴሩን ንግግር በማጣቀስ ይህንን ፕሮግራም አዘጋጅቷል።

የጠቅላይ ሚኒስቴሩ የይቅርታ ትርዒት | ሳዲቅ አህመድ ህወሃታዊ ሴራዎችን በመቃኘት ያዘጋጀው የድምጽ ዘገባ

አቶ ኤርሚያስ አመልጋ በተመሠረተባቸው ክስና በተፈቀደላቸው ዋስትና ላይ ብይን ለመስጠት ተቀጠሩ

$
0
0

neww1661–    መታመማቸውንና የሚወስዱት መድኃኒት መርዝ እንደሆነባቸው ተናገሩ

የአክሰስ ሪል ስቴት መሥራችና የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ኤርሚያስ አመልጋ፣ በባንክ የሚያዙበት በቂ ስንቅ (ገንዘብ) ሳይኖራቸው ለስድስት ግለሰቦች በድምሩ ከ4.8 ሚሊዮን ብር በላይ ደረቅ ቼክ በመስጠት ወንጀል በተመሠረተባቸው ክስና በሥር ፍርድ ቤት ተፈቅዶላቸው በታገደው የዋስትና ጉዳይ ላይ ብይን ለመስጠት ለረቡዕና ለሐሙስ ተቀጠሩ፡፡
አቶ ኤርሚያስ በዘመን ባንክ በቂ ስንቅ (ገንዘብ) ሳይኖራቸው የግል ተበዳዮች ለተባሉት አቶ ፍጹም አስፋው 2,450,000 ብር፣ ለሳምራዊት ጴጥሮስ 822,900 ብር፣ ለጽጌረዳ አበበ 500,000 ብር፣ ለንጉሤ መንግሥቱ 500,000 ብር፣ ለሳዲቅ አብዱልዋህብ 255,534 ብር፣ እንዲሁም ለዶ/ር ኤርሚያስ ሀብቴ 343,400 ብር ደረቅ ቼክ መስጠታቸውን ገልጾ፣ ክስ የመሠረተው የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ነው፡፡

መጋቢት 15 ቀን 2008 ዓ.ም. ዓቃቤ ሕግ የመሠረተውን ክስ መጋቢት 19 ቀን 2008 ዓ.ም. የተመለከተው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት፣ ከሳሽ ዓቃቤ ሕግና ተከሳሽ ስለክሱ ያላቸውን አስተያየት እንዲሰጡ ጠይቋል፡፡ ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ በሰጠው አስተያየት ተጠርጣሪው የተከሰሱበት ደረቅ ቼክ የማውጣት (መስጠት) ወንጀል ነው፡፡ በመሆኑም የተጠቀሰባቸው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 693(1)ን ማለትም ‹‹… በቂ ገንዘብ አለመኖሩን እያወቀ ቼክ ያወጣ (የሰጠ) ከሆነ፣ በቀላል እስራት ወይም እንደ ነገሩ ክብደት ከአሥር ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራትና በመቀጮ ይቀጣል፤›› የሚል በመሆኑ፣ አቶ ኤርሚያስ ላይ የቀረበው ክስ ተነቦላቸው የእምነት ክህደት ቃላቸውን እንዲሰጡና በማረሚያ ቤት ሆነው ምስክሮቹን እንደ ክሱ እንዲያሰማ እንዲፈቀድለት ጠይቋል፡፡

የአቶ ኤርሚያስ ጠበቃ አቶ ሞላ ዘገዬ በበኩላቸው ለፍርድ ቤቱ ሲያስረዱ፣ ‹‹ክሱን አይተነዋል፡፡ እንቃወማለን፡፡ የመጀመሪያ መቃወሚያ ለማቅረብ ጊዜ ያስፈልገናል፡፡ ዓቃቤ ሕግ እንደገለጹት ክሱ ዋስትና የሚያስከለክል አይደለም፡፡ እንደነዚህ ዓይነት የክስ ጉዳዮች ዋስትና አያስከለክሉም፡፡ የተጠቀሰውም የሕግ አንቀጽ አይከለክልም፡፡ ዋስትና የግለሰብ ጥያቄ ብቻ ሳይሆን በሕገ መንግሥቱ የተሰጠ ልዩ የዜጎች መብት በመሆኑና ሊከለከል ስለማይገባ፣ አቶ ኤርሚያስ በዋስ ተለቀው ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ፤›› ሲሉ አመልክተዋል፡፡

አቶ ሞላ ዋስትናን በሚመለከት ጨምረው ሲያስረዱ ዋስትናን በሚመለከት በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 63 ላይ ከተጠቀሱት ምክንያቶች ውጪ፣ ማንኛውም ዜጋ የዋስትና መብቱ እንዲከበርለት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አስገዳጅ ውሳኔ መስጠቱንም ለፍርድ ቤቱ አስታውሰዋል፡፡ ዓቃቤ ሕግ አቶ ኤርሚያስ ዋስትና ተፈቅዶላቸው ከእስር ቢለቀቁ ወደ ውጭ ከወጡ ሊመለሱ እንደማይችሉ የገለጸው ግምት መሆኑን ያስረዱት አቶ ሞላ፣ ሕገ መንግሥት የፈቀደው የማይጣስና የማይገረሰስ መብትን የተለያዩ ምክንያቶች ማለትም ተጨባጭ ባልሆነ ነገር እየተሳበበ ሊከለከል እንደማይገባም አስረድተዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ አቶ ኤርሚያስ ስለራሳቸው እንዲገልጹ ጠይቋቸው ባለትዳርና የአምስት ልጆች አባት መሆናቸውን፣ በእናትና በአባታቸው ቤት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ አራት ውስጥ እንደሚኖሩ፣ ሁለተኛ ዲግሪ እንዳላቸውና የአክሰስ ሪል ስቴት አክሲዮን ማኅበር የቦርድ አባል ሆነው እየሠሩ እያለ መታሰራቸውን አስረድተዋል፡፡
ነጭ ባርኔጣ፣ ረዘም ብሎ ነጣ ያለ ጃኬትና ጀለቢያ (ሽርጥ) ለብሰውና ጥቁር ነጠላ ጫማ ተጫምተው ችሎት የቀረቡት አቶ ኤርሚያስ፣ አንገታቸውና እግራቸው አካባቢ በቀይ ሰውነታቸው ላይ ሽፍታና ጥቁር ነጠብጣብ የሚታይ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱ ምን እንደሆኑ ጠይቋቸው፣ ዓይነቱን ባይናገሩም ሦስት ዓይነት ሕመሞች መታመማቸውንና የሚወስዱት መድኃኒት መርዝ እንደሆነባቸው ተናግረዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም ሕክምና እንዲያገኙና ከጠበቃዎቻቸው ጋር እንዲገናኙ ትዕዛዝ ሰጥቶ፣ የክስ መቃወሚያ ለመቀበልና በዋስትና ጥያቄው ላይ ብይን ለመስጠት ለሐሙስ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

በሌላ በኩል አቶ ኤርሚያስን የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ማዕከል (ማዕከላዊ) መርማሪ ቡድን ጠርጥሬያቸዋለሁ ባለው ከባድ የእምነት ማጉደል ወንጀል ምርመራውን ሳያጠናቅቅ (ለ70 ቀናት ታስረው ከርመዋል)፣ የሥር ፍርድ ቤት በ500 ሺሕ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ በመፍቀዱ ላይ ተቃውሞ አቅርቧል፡፡ ይግባኙ የቀረበለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ሦስተኛ ወንጀል ችሎት የመርማሪ ቡድኑን አቤቱታ ካሰማ በኋላ፣ አቶ ኤርሚያስ በሌላ ክስ ለዋስትና ጉዳይ መቀጠራቸውን አስታውሶ በተቀጠሩበት የዋስትና ጉዳይ ቢፈቀድላቸው መርማሪ ቡድኑ ምን ሊያደርግ እንደሚችል ጥያቄ ቢያቀርብም፣ መርማሪ ቡድኑ ‹‹ዋስትናውን እንቃወማለን፣ ምርመራ አልጨረስንም፣ ፍርድ ቤቱ የሥር ፍርድ ቤትን የምርመራ ሒደት ይመልከትልን፤›› በማለት 37 ገጽ ግልባጭ ማያያዙን አስረድቷል፡፡

የተጠርጣሪ ጠበቃ አቶ ሞላ የሥር ፍርድ ቤትን ክርክር እንደሚያውቁ በመግለጽ ግልባጭ እንደማያስፈልጋቸው በመናገራቸው፣ ፍርድ ቤቱ መርምሮ ብይን ለመስጠት ለዓርብ መጋቢት 23 ቀን 2008 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ እስከዚያው ድረስ የሥር ፍርድ ቤት የሰጠው የዋስትና ፈቃድ ታግዶ እንዲቆይም ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

ምንጭ ሪፖርተር

ውጭ አገር ሊሄዱ ሲሉ በስህተት ተይዘው ታስረው የነበሩት ሹም ተለቀቁ

$
0
0

news

–    ስህተቱ የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ነው ተብሏል

የአዲስ አበባ የቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት የግንባታ ዘርፍ ማስተባበሪያ ምክትል ሥራ አስኪያጅ፣ በስህተት ታስረው አንድ ቀን ካደሩ በኋላ ተፈቱ፡፡
ምክትል ሥራ አስኪያጁ አቶ ተክሉ ፍቅሩ መጋቢት 17 ቀን 2008 ዓ.ም. ለ18 አጥቢያ ወደ ግሪክ ለመሄድ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንደደረሱ ፓስፖርታቸውን ለኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳዮች ዋና መምርያ ሰጥተው ወደ ውስጥ ለማለፍ ሲጠባበቁ፣ መታገዳቸው ተነግሯቸው ለብቻቸው እንዲሆኑ መደረጋቸው ታውቋል፡፡
የቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት የግንባታ ዘርፍ ማስተባበሪያ ምክትል ሥራ አስኪያጁ ግራ እንደተጋቡ፣ የቀረውን የሌሊት ክፍለ ጊዜ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ አድረው በነጋታው እሑድ መጋቢት 18 ቀን 2008 ዓ.ም. በምን ጥፋት እንደታገዱ ሲጠይቁ፣ ከአገር እንዳይወጡ ያሳገዳቸው የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን መሆኑ እንደተነገራቸው ታውቋል፡፡
ቀኑ እሑድ በመሆኑ በምን ምክንያት እንደታገዱ መጠየቅ ያልቻሉት አቶ ተክሉ አዳራቸውን በመምርያው ለማድረግ ተገደዋል፡፡ መጋቢት 11 ቀን 2008 ዓ.ም. ከአገር እንዳይዋጡ ዕግድ ያስጣለባቸው ፀረ ኮሚሽን ሲጠየቅ፣ በ2006 ዓ.ም. ከአቶ ተክሉ መሥሪያ ቤት በሙስና የተጠረጠሩ ኃላፊዎች ሲከሰሱ የሳቸውም ስም ወደ ተቋሙ ተልኮ እንደነበር፣ የተከሰሱት ከአገር እንዳይወጡ ዕግድ ሲጣል ስማቸው አብሮ መላኩን መግለጹን አቶ ተክሉ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ አቶ ተክሉ በወቅቱ ስማቸው የተላከ ቢሆንም፣ የማይፈለጉ መሆኑን አረጋጋጦ ማሰረዝ (ማስነሳት) ሲገባው ዝም ብሎ ከሁለት ዓመታት በላይ ማቆየቱ ተገቢ አለመሆኑን አስረድተዋል፡፡
አቶ ተክሉ ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የተያዙት የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ከግሪክ አቻው ጋር በውኃና ፍሳሽ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ላለው ትምህርታዊ የልምድ ልውውጥ ለመሄድ ሲሉ ነው፡፡
የልምድ ልውውጡን ለመካፈል ወደ ግሪክ የሚሄዱት አቶ ተክሉን ጨምሮ አምስት አባላት ያሉትና በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ይድነቃቸው ዋለልኝ የሚመራ ቡድን የነበረ ቢሆንም፣ ኮሚሽኑ ፈጠረው በተባለ ስህተት ምክንያት አቶ ተክሉ ሳይሄዱ ቀርተዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከግሪክ ውኃና ፍሳሽ መሥሪያ ቤት ጋር ትምህርታዊ ሥልጠናና የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ባደረገው ከፍተኛ ጥረት ዕድሉን በማግኘቱ፣ ለልዑኩ የአውሮፕላን ትኬትና ሌሎች ወጪዎችን ወጪ ማድረጉ ታውቋል፡፡ ከፍተኛ እምነት የተጣለባቸውና የልምድ ልውውጡን በመካፈል ለባለሥልጣኑ የአሠራር መሻሻልና ለውጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ የታመነባቸው አቶ ተክሉ፣ በፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የግዴለሽነት አሠራር ሊጨናገፍ መቻሉ አሳዛኝ መሆኑን፣ የውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን የሥራ ባልደረቦች ለሪፖርተር አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
አዲስ በተረቀቀውና ለፓርላማ በቀረበው የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ፣ የመመርመርና የመክሰስ ሥልጣኑ ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ እንደሚሰጥበት በቅርቡ የተገለጸው የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን፣ በአቶ ተክሉ ፍቅሩ ላይ ፈጽሞታል ስለተባለው ስህተት ማብራሪያ እንዲሰጥ ሪፖርተር ለማግኘትና ለማነጋገር ያደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡ አንድ ተጠርጣሪ በተጠረጠረበት ወንጀል ፍርድ ቤት ቀርቦ በሚደረግ ክርክር፣ የዋስትና መብቱ ተከብሮ በውጭ ሆኖ ጉዳዩን እንዲከታተል ሲፈቀድለት፣ እንደየጉዳዩ ክብደት ከአገር እንዳይወጣ ለብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት እንዲጻፍ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ የሚሰጥ ቢሆንም፣ አቶ ተክሉ በወንጀል ተጠርጥረው ሳይከሰሱ፣ ምርመራ ሳይጣራባቸውና ሳይታሰሩ ከአገር እንዳይወጡ መታገዳቸው ከማስገረምም ባለፈ፣ በእያንዳንዱ ዜጋ ላይ ጥርጣሬ የሚፈጥር መሆኑን አስተያየት የሰጡ የሕግ ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡

ምንጭ – ሪፖርተር

የማለዳው ሰማይ መረጃ! “ፈቲሐ ነገ አርብ የሀገሯን ምድር ትረግጣለች”–ነቢዩ ሲራክ

$
0
0

እህት ፈቲሐ ነገ ወደ ሐገር ቤት ትገባለች !
=================
* ለወራት በህክምና ላይ የነበረችው እህት ፈቲሐ በወገኖቿ አይዞሽ ባይነት ከትናንት ዛሬ ተሽሏታል
* ያ የተቃጠለ የሚመስለው መልኳ ዛሬ ወዝ ይታይበታል
* እህት ፈቲሐ ነገ ወደ ሐገር ቤት እንድትገባ ትልቅ ድጋፍ ያደረጉላት አረብ አሰሪዎቿ ናቸው
* አረብ አሰሪዎቿ የመውጫ ቪዛ አስጨርሰው በራሳቸው ገንዘብ ትኬት ቆርጠውላታል
* አረብ አሰሪዎቿ መራመድ የማይችለውን እህት ፈቲሐን ሐገር ቤት ደግፎ የሚያደርስ የጤና ረዳት ቀጥረውላታል
* ፈቲሐ ነገ አርብ በሳውዲ አየር መንገድ ከምሽቱ 10:30 ላይ የሀገሯን ምድር ትረግጣለች
* እህት ፈቲሐ የናፈቋት ቤተሰቦቿን እስክትቀላቀል ከአየር መንገድ ለመቀበል ያቀረብነውን ጥሪ ወዳጃችንSamuel Masresha ተቀብሏል፣ እናመሰግናለን!
* ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቲሐን ምስል ተመልክቶ በእንባ የታጠበው አንጀተ ርህሩህ ወዳጃችን ሳሙኤል ማስረሻ ለእህት ፈቲሐን በመንግስት ሐኪም ቤቶች ግብታ ህክምና እንድታገኝ እንደሚሞክር ቃል ገብቶልኛል
* የተመላሽ ስደተኞች አባት የምንለው ወዳጃችን ሳሙኤል ማስረሻ ቀይ መስቀልን አምቡላንስ ጠይቆ ተፈቅዶለታል
* እዚህም እዚያም ዝግጅቱ ተጠናቅቋል
* እህት ፈቲሐ በጤና እያለች ሰርታ ካገኘችውና በአደራ በጅዳ ቆንሰል ያስቀመጠችውን 4800 የሳውዲ ሪያል ገንዘቧን ዛሬ እንደምትረከብ ትናንት አጫውታኛለች

በእህት ፈቲሐ ለወራት በንጉስ ፉአድ ሆስፒታል ታክማ አሁን ከበፊቱ ተሽሏታል ። በጅዳና አካባቢው ያሉ ለነፍሳቸው ያደሩ በርካታ ኢትዮጵያውን ዘር ሐይማኖት ሳይለዩ ላለፉት ወራት ፈቲሐን እየጎበኙ ተስፋ ሰጥተዋታል ፣ ደግፈዋታል !

” የመንግስት ተወካዮች እርባና ያለው ድጋፍ በማያደርጉበት ሰአት ዜጎች እርስ በርሳችን እንዲህ ሲተባበሩ ማየት ደስ ይላል ! ” ያለኝ ፈቲሐን ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው እየደገፈ ያለው ወንድም ነው !
እህት ፈቲሐ ለደገፋት ለሁሉም ምስጋና አቅርብልኝ ብላኛለች ፣ ምስጋናዋ ይድረሳችሁ !

ነቢዩ ሲራክ
መጋቢት 22 ቀን 2008 ዓም


127 128

129


“ፂላ ካልሆንክ አትሠራም” –ዳግማዊ ጉዱ ካሣ (አዲስ አበባ)

$
0
0

 

ትግሬ የሆንሽ እያንዳንድሽ ጥርስሽን ነክሰሽ አንብቢና እውነቱን ተረጂ “ውሸታም፣ ዘረኛ… ምናምን” እያልሽ ራስሽን አታሞኚ- ራስን ማሞኘት ዱሮ ቀረ፤ እውነቱን ማገፈትና እመሸበት ማደር ነው ተንግዲህ እሚያዋጣ፡፡ የምልሽ ሁሉ እውነትና መነገር ከሚገባው (ስለነሱ በማፈርና በመሳቀቅ) ሊነገር የሚችለውን በጣም ትንሹንና ገራገሩን ብቻ በመምረጥ ነው የምነግርሽ፡፡ በተቀረ የወንድሞችሽ ጉድ በአንድና በሁለት ገጽ ወረቀት ይቅርና ሰማይ ብራና ውቅያሶች ቀለም ቢሆኑ ተጽፎ አያልቅም፡፡ አሁን የምነግራችሁ በአብዛኛው ከእኔና የኔ አይደለም፡፡ በቅርብ የማውቀውና  ወደሥራ ሊሄድ መንገድ ላይ ሊፍት የሰጠሁት አንድ በግል ሥራ ተዳዳሪ ወጣት ከደቂቃዎች በፊት የነገረኝን ነው የምነግራችሁ፡፡ በዚህ ዘመን ማንኛውንም ትግሬ ያልሆነ ሰው በመንገድ ወይም በመዝናኛ ሥፍራ አግኝታችሁት ስለዘመኑ የወያኔ አገዛዝ በዘር ላይ የተመሠረተ ግፍና በደል ሲናገር ብትሰሙት ታብዳላቸሁ፡፡  በሀገራችን ቀርቶ በሌላው ዓለም ታሪክ ታይቶም ሆነ ተሰምቶ የማያውቅ የሚዘገንን የዘረኝነት አገዛዝ በኢትዮጵያ በይፋ ተተክሎ ሕዝቡን ማስመረር ከያዘ እነሆ 25 ዓመታትን ሊደፍን ጥቂት ጎምዛዛ ቀናት ብቻ ይቀሩታል፡፡ ስሙን ለውጨዋለሁ፡፡ ቁም ነገሩን ብቻ ሳልጨምር ወይም ሳልቀንስ አወጋችኋለሁ፡፡

 

ሃይ ዳግማዊ፣ እንደምን አደርክ፡፡ ወደ … ነው አይደል የምትሄደው?

ሰላም ቢኒያም፣ እንደምን ሰነበትክ፤ አዎ፣ ወደ … ወደ መሥሪያ በቴ ነው የምሄደው፡፡

ቢኒያም –  እንግዲያውስ እባክህን አብሬህ ልሂድ፡፡ ታክሲ የሚባል ነገር የለም፡፡ በዚያ ላይ ለሥራ የተቀጣጠርኩት ሰው ስለሚያመልጠኝ በቶሎ መድረስ አለብኝ፡፡….

 

ችግር የለም ወጣት ቢንያም፣ ሥራ እንዴት ነው? ሠርግህን ብቻህን በላኸው አይደል? ይሁን ግዴለም፡፡ ሙሽሪት ለመደች?  ወሬ መቼም አይደበቅም እንዝርቱን ደጋኑን ላኩልኝ ማለቷን ሰምቻለሁ፡፡…

ሥራ ምንም አይልም፡፡ ግን ምን ታደርገዋለህ፡፡ እዚህ አገር ፂላ ካልሆንከ መሥራትም መኖርም  አትችልም፡፡ በጣም ተስፋ የሚያስቆርጥ ነገር ነው ያለው እባክህን፡፡ እኔ ደግሞ አንደምታውቀው ሲያቀብጠኝ ዐማራ ሆኜ ተፈጥሬ – ውይ ዳግምዬ ምነው ትግሬ በሆንኩ ኖሮ ዐማራነት ሰለቸኝ – እናማ ቅብጥ ሲያደርገኝ ዐማራ ሆኜልህ የቀባጭ ምሴን እያገኘሁ ነው፡፡ ፈጣሪን ምን በድየው ይሆን ዐማራ ያደረገኝ? ምን ቸገረው ዐድዋ መሀል ላይ ፈጥሮኝ ቢሆን ኖሮ!…

እንዴ ቢኒ … እንዲህ ባለቅኔ ሆነሃል እንዴ? ደግሞ ብለህ ብለህ ተፈጥሮን በምርጫ ልታስኬደው አማረህ? ሆ! ትግሬ ሆኖ መፈጠርም እኮ የራሱ ችግር ሊኖረው ይችላል፡፡ መቼስ ሁሌ ፋሲካ የለ ቢኒ…

ኧረ የራሱ ጉዳይ! ዛሬ ከምሞት ነገ ብሞት ይሻለኛል፡፡ አሁን እኮ ከተማውን ሁሉ ብታየው ካለትግሬ እንደልቡ የሚነግድ፣ ካለ ትግሬ እንዳሻው የሚዝናናና የሚፈነጥዝ፣ ካለትግሬ የሚዘባነን፣ ካለትግሬ ፎቅ የሚሠራ፣ ካለትግሬ ምርጥ ምርጡን የሚዘርፍና የሚቆጣጠር፣ ካለትግሬ ሥልጣን የሚይዝ፣ ካለትግሬ የሚገዛ የሚነዳ… በጭራሽ የለም፡፡ አንተ ከቢዝነሱ ዓለም የራቅህ ስለሆንክ ብዙም ላታውቅ ትችላለህ፡፡ በከተማው እየተሠራ ያለው የትግሬ ፊንታ እኮ ቀላል እንዳይመስልህ፡፡ ጨረታ ብታስገባ ትግሬ ካልሆንክ ይጥሉብሃል፡፡ የትም ቢሮ ብትባ ትግሬ ካልሆንክ ጀርባህ ይጠናና አገልግሎት አታገኝም ወይም የሎተሪ ያህል ከስንት አንዴ ይሳካልሃል – ሊያውም ወገብ የሚቆምጥ ጉቦ ከፍለህ፡፡ እባክህን አታናዘኝ ወንድሜ፡፡

አንተም የትናንቱ ቢኒያም እስከዚህ ተማረሃል ማለት ነው?

ምን መማረር ብቻ፣ የሚዋጋ ኃይል ቢነሣ ቢያንስ በሾፌርነት ለማገልገል ቆርጫለሁ፡፡ ዘረኝነቱ ጠነባኝ፤ እንዳንዳች ነገር ከረፋኝ፡፡ በናንተ ጊዜም እንዲህ ነበር እንዴ ዳጊ? ማለቴ እነሱ የሚሉት የዐማራ ገዢ ምንትስ በሚሉት ዘመን እንደዚህ ዓይነት የከረፋና የጠነባ ዘረኝነት ነበር?

አየ ቢኒ – ዐማራ እንዲህ ያለ ዐመልና ጠባይ ቢኖርበት ኖሮ ወያኔ ከደደቢት መች ትወጣ ነበር፡፡ ዐማራን የጎዳው እኮ ቦርቃቃነቱ ነው – ሀገራዊ እንጂ ጎሣዊ አስተሳሰብ የለውም፡፡ የአንድነት እንጂ በሸጥና በጎጥ ወርዶ የመወተፍ ጠባይ በዐማራ ዘንድ የለም፡፡ እንዲህ ዓይነት አስተሳሰብ ቢኖረው ኖሮማ የጎጃምና የጎንደር፣ የወሎና የሸዋ ግዛቶች ይሄኔ በፋብሪካና በዩኒቨርስዎች ይጥለቀለቁ አልነበረምን? እንኳንስ ዱሮ አሁንም ቢሆን – ከስንትና ስንት ወያኔያዊ የሥነ ልቦናና የመሣሪያ ድብደባ በኋላ ዐማራ ወደዚህ ዝቃጭ የዘረኝነት አስተሳሰብ ሊወርድ አልቻለም፡፡ የወያኔ መውደቂያ ሰበብም ይሄው በመሆኑ ወያኔዎች በዐማራ አለመኮማተር – አለመጥበብ –  ክፉኛ ይበሳጫሉ፤ ይጨነቃሉም – መፍትሔዎች በችግሮች ውስጥ ተጸንሰው እንደሚገኙና ቀናቸው ሲደርስ እንደሚወለዱ እነሱም እንዳቅሚቲ ባላቸው ግንዛቤ ያውቃሉና የዐማራ በተቆፈረለት ቦይ ያለመፍሰስ ያልጠበቁት ክስተት አጥፊያቸው መሆኑን ሳይረዱት አልቀሩም፡፡

የሆነ ሆኖ ምን ችግር ደርሶብህ ነው እንዲህ በወያኔ ዘረኝት የተንገፈገፍከው? ደግሞም ልጅ ነህ፤ እንደምገምተው እንደብዙዎች ወጣቶች ለሆድህ የምታዘነብልና በነሱ አምሳል የተቀረጽክ ትመስለኝ ነበር፡፡

እንዴ! ያን ያህልማ ለወጣቶች ዝቅ ያለ ግምት አይኑርህ፡፡ ዳግም – አታውቃቸውም እንዴ እነዚህን ምስጦች? ተመልከት – እኔ እጁን ይዤ የኔን ሥራ ያስተማርኩት ፂላ ዛሬ ከሁለት በላይ ኤሮትራክ አለው፡፡ የናጠጠ ከበርቴ ሆኗል፤ አንድ ብቻ ደግሞ እንዳይመስልህ፡፡ ዛሬ ከትግራይ ይመጡልህና አንድ አካባቢ አንገታቸውን ሰበር አድርገው አንዲት ደሳሳ ጎጆ ይከራያሉ – ከዚያ አንድ ዓመት እንኳን ሳይቆዩ ሕንፃ በሕንፃና ቦቴ በቦቴ ሲሆኑ ታያቸዋለህ፡፡ ከየት አመጡት? በአንጻሩ ደግሞ በጉ የመሀል አገር ሰው በቅጽበት ሲደኸይ ታየዋለህ፡፡ ሁሉ ነገር በደቂቃዎች ውስጥ ሲገለባበጥ ስታይ የት እንዳለህ ራሱ ሊጠፋህ ይችላል፡፡ እንደምታውቀው ይሉኝታና ትግሬ ከተለያዩ ቆዩ – ከነይሉኝታው የሚኖር ትግሬ ቢኖርም በኛም ሆነ በዘመዶቹ ዘንድ እንደሆላ በግ ነው የሚቆጠር- ዘመኑን ያልተጠቀመ ጅላጅል፤ እርግጥ ነው ይህን በማወቅ ካደረገው አስተዋይነትና ጽድቅ ነው – በሞኝነትና መንገዱን ባለማወቅ ከሆነ ግን ቢያንስ በሃሳብ ደረጃ ሞስኗልና የድርሻውን ታሪካዊ ምንዳ አያጣም፡፡

ትግሬውን ከዜሮ ሣንቲም ወደሚሊዮናት ያበቃው ብቸኛ ነገር ደግሞ ትግሬነቱ እንጂ ዕውቀቱና ችሎታው አይደለም – በልመና የትራንስፖርት ወጪ ዛሬ አዲስ አበባ የገባ አንድ ባላገር ትግሬ በወንድሞቹ ምሪትና ሁለንተናዊ እገዛ ነገ ጧት አንተን አደኽይቶና እትብትህ ከተቀበረበት መኖሪያህ አፈናቅሎ ዲታ ሲሆን ይታይህ – የኢትዮጵያ የወቅቱ ዕንቆቅልሽ፡፡ … ጨረታ ስንቀርብ የሚያሸንፈው እርሱ ነው፡፡ ባለፈው መከላከያ ባወጣው አንድ ጨረታ እኔ የመጨረሻ ትንሽ ዋጋ አቅርቤ ያ ያሰለጠንኩት ልጅ ግን ትልቅ ዋጋ አቅርቦ በትግሬነቱ ብቻ በልጦኝ አሸነፈ፡፡ እኔ ታዲያ ምንድን ነኝ? እንደርሱ እኩል ኢትዮጵያዊ ልባል እችላለሁ? አልችልም፡፡ አንዳችንን እውነተኛ ልጅ አንዳችንን የእንጀራ ልጅ እያደረጉ በአንዲት ሀገር ውስጥ የሚያበላልጡንና ታሪካዊ ባላንጣዎች እንድንሆን የሚፈርዱብን ለምንድነው? ጨረታ የሚያሸንፉት እነሱ፣ አለቀረጥ የሚነግዱት እነሱ፣ ሌላውን እያፈናቀሉ የንግድ ቤቶችን በርካሽ ዋጋና አለግብር የሚነግዱ እነሱ፣ አለምንም ቀረጥና ግብር ከውጭ ዕቃ እያ(ስ)መጡ ህጋዊ ነጋዴውን የሚያከስሩና ከሥራ ውጪ የሚያደርጉ እነሱ፣ ሰውን አለአበሳው እየከሰሱ የሚያስሩ፣ የሚያሳስሩ፣ የሚፈርዱ፣ የሚያስፈርዱ፣ የሚገድሉና የሚያስገድሉ እነሱ፣ ዐይን ዐይን የከተማ ቦታዎችን እየወሰዱ ቤት በመሥራትም ሆነ ባዶውን በሚሊዮኖች የሚቸበችቡ እነሱ .. አሁን እኮ በገንዘብ ዐብደዋል ማለት ትችላለሀ፡፡ ለይቶላቸው ዐበዱ አንጂ፡፡

ሌሎች ዜጎች ላይ ማሰሪያዎቻቸውን እያጠባበቁ በአሻንጉሊቶቻቸውና ለሁሉም እኩል በማይሠሩ ተለዋዋጭ የወንበዴ ህጎቻቸው እየቀየዱ እነሱ በኛ ላይ ተዘባነዋል፡፡ ምን እንዳዞሩብን አላውቅም፡፡ ስታያቸው ከአጠቃላዩ የሕዝብ ቁጥር አንጻር ብዛታቸው እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ ነገር ግን ዋናው ብዔል ዘቡል ከነሱ ጋር ስላበረና እግዜሩም እኛን ስለከዳን እንዳሻቸው ሲያሩብንና ሲቀዝኑብን … አዎ፣ እደግምልሃለሁ  ጥሬ አራቸውን ሲከምሩብንና ሲጨመላለቁብን … ዝምባቸውን እሽ የሚል ጠፋ፡፡ እነሱ ምን ያድርጉ? ዝምታችንና ግፍና በደልን የመሸከም ችሎታችን እነሱን እያበረታ ስቃያችን የማያባራ ሆነ፡፡ ጥፋቱ የኛው ነው፡፡ በኛ ስቃይ ተወቃሹ ማንም ሳይን እኛው ራሳችን ነን፡፡ በእስካሁኑ ሁኔታ ተጨባጭና በግልጽ ሊታይ የሚችል ነገር አደረግን ከተባለ ራሳችንን ከእሳት አውጥተን በስደት – እየተጓሸምን ጭምር – ተነጣጥለን መኖር ነው፡፡

እንዴ፣ ይህ የምትለኝ የትግሬዎች የዘረኝት መድሎ እውነት ነው?

ምን ማለትህ ነው አቶ ዳግማዊ? ሌላው ቀርቶ የሰዓሊተ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን – እዚያ ታች ጉርድ ነው ጉምድ ሾላ እሚባለው አካባቢ ያለችው – ከዘበኛው ጀምረህ እስከ ደብር አለቃው ትግሬ አይደል እንዴ ኃላፊውና ቅጥረኛው? ይሄን ሳታውቅ ቀርተህ ነው? ፖለቲካውን ብቻ ሣይሆን የአምልኮት ቦታዎችን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረውት የለም እንዴ? አንዳንዴማ ሳስበው በኔና ባንተ ይቅር እንጂ “እግዜሩንም አግተውት ይሆን እንዴ?” ብዬ እስከማሰብ እደርሳለሁ፡፡ የሚታየው ነገር ሁሉ እኮ የህልምና የቅዠት እንጂ የእውን አይመስልም፡፡ የአንዲትን አገር አጠቃላይ የሥልጣንና የጥቅም ቦታዎች ለአንድ ጎሣ አስረክቦ ባዶ እጁን እያጨበጨበ በርሀብ የሚገረፍ ሌላ ሕዝብ ትጠቅስልኛለህ? የኛ ነገር እኮ ፈጣሪንም ሳያስገርም አይቀርም፡፡

ባለፈው ሰሞን አንዱ ብሶተኛ የነገረኝን እውነተኛ ታሪክ ልንገርህ ዳጊ? …

እስኪ ቀጥል በል፤እንዴት የሚገርም ታሪክ ነው እየነገርከኝ ያለኸው!

አንድ ጓደኛዬ በአንድ የወያኔ የንግድ ድርጅት ውስጥ የሒሳብ ሠራተኛ ነው፡፡ እርሱም እንደኔው ሲቀብጥ ዐማራ ሆኖ ነው የተፈጠረው፡፡ ልጁ በሙያው ዲግሪ ያለው ሲሆን በልምድም የተመሰከረለት ድንቅ ሠራተኛ ነው፡፡ በዚህ የሒሣብ ሠራተኛ ሥር ባለዲፕሎማ የትምህርት ደረጃና በዜሮ ዓመት የሥራ ልምድ አንዲት ጀማሪ ትግሬ ትቀጠራለች፡፡ መሥሪያ ቤቱን ጦሽ ትላለህ እንጂ ሰላም ባስ ብዬ አልነግርህም፡፡ ያ ዐማራ ደሞዙ ሰባት ሺህ ሲሆን የዚያች “ምርጥ ዘር” ደሞዝ ግን 12 ሺህ አካባቢ ነው፡፡ ይህን ዐይን ያወጣ ልዩነት በመግለጽ ደሞዙን እንዲያስተካክሉለት ሲጠይቅ የተባለው ደግሞ ለቁጩም ቢሆን በአንድ ዜግነት መጠራታችንን እንድንጠየፈው ያደርገናል፤ “እዚህ ማን አስሮ ያዘህ? ልትለቅ ትችላለህ!” ነው የተባለው፡፡ በዚህ መልክ በየመሥሪያ ቤቱ እየታዩ ያሉ አድልዖዎች እጅግ ብዙ ናቸው፤ ለተመሳሳይ ዲግሪ፣ ለተመሳሳይ የሥራ መደብ፣ ለተመሳሳይ ልምድና ችሎታ… ለትግሬውና ለሌላው የሚከፈለው ደመወዝ በአብዛኛው ይለያያል – በተለይ በመንግሥት ተብዬው የምሥጢር ጓዳዎች በሚሠሩ ሠራተኞች መካከል ይህ ችግር ጎልቶ እንደሚታይ ሰዎች ሲናገሩ እሰማለሁ – ለምሳሌ ሁለት ትግሬ  የጦር መኮንኖች ባለፈው ሰሞን በገነቡት ሕንፃ ላይ የሆነ ሥራ አሠርተውኛል፡፡ ከየት አመጡት? ሌሎች ለምን እንደነሱ አልሠሩም? ይህ ዓይነት የጥቅም መለያየት የተፈጠረው ትግሬውን በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ለማድረግና ሌላው ግን ኮስምኖ እንዲቀር – ከሆዱም በላይ እንዳያስብ ለማድረግ ነው – “ኢኮኖሚውን የተቆጣጠረ ፖለቲካውንም ይቆጣጠራል” የሚሉት ጽዮናዊነት የተጠናወተው አመለካከት አላቸው ወያኔዎች፡፡ እየተሠራ ያለውን ግፍ እግዜር ከተመለከተውና የማይቀር ፍርዱን ከሰጠበት እውነት ለመናገር … ዳፋው ብዙና ተዝቆም የማያልቅ ነው – አሁንስ እንጃልን፤ እኔም ፈራሁ፡፡ እስካሁን ምንም አይመስለኝም ነበር፡፡ ሰዎች ሲናደዱ ሳይም ይገርመኝ ነበር፡፡ ዛሬ ዛሬ ግን ግርፋቱ እኔንም ውስጤን ዘልቆ ተሰማኝ፡፡ እነዚህ ወንጀለኞች እንዳንቀባበር እንኳን እያደረጉን ነው – የነጭ አፓርታይድ ቢያንስ እየመገበና በሽታህን በአግባቡ እያከመ ሰውነትህ ሳይጎዳ ያኖርሃል – እንደያ የሚያደርገውም ለራሱ ጥቅም ነው፤ ሥራ እንድትሠራለት፤ የነዚህ የጥቁር አፓርታይድ አራማጆች የሆኑ የትገሬዎች ዘረኛ አገዛዝ ግን ስም የለውም – በርሀብ ይቀጡሃል፤ በችጋር ይቀጡሃል፤ በሥነ ልቦና ጦርነታቸው ያሸማቅቁሃል፤ ህክምና እንዳታገኝ በማድረግ  ካላንዳች ጥይት በበሽታ ይረፈርፉሃል፡፡ እንዲህ እያደረጉህም ሥራህን በአግባቡ ቀጥ ብለህ እንድትሠራ ያስጠነቅቁሃል፡፡… በውነቱ ይህን ዘመን ለማስተካከል በጣም ብልኅ የታሪክ ወጌሻና ጥንቁቅ የፖለቲካ መሃንዲስ ያስፈልገናል፡፡ አለበለዚያ ሦርያና ኢራቅ በምን ጣማቸው? አሁን እንዲህ አፍረጥርጬ እውነቱን በአደባባይ ብናገር ብዙ ትግሬ አፍንጫውን እንደሚነፋብኝ አውቃለሁ፤ ግን እውነትን ለማየት ዐይንን እንደምንም መክፈትና ቢያጥበረብርም ከእውነት ፀሐይ ጋር መጋፈጥ እንጂ መሸፋፈንና መወሻሸት ለማንም አይጠቅምም፡፡ ተበልቶ እዳሪ ለሚሆን ምግብና ተጠጥቶ ሽንት ለሚሆን መጠጥ ተብሎ ሃቅ መካድ የለባትም፡፡ ኧረ ተወኝ ወንድሜ …

 

በል በደህና ዋልልኝ አቶ ዳግማዊ፡፡ አንተን ባላገኝ አራት ሰዓትም አልደርስም ነበር፡፡ እግዜር ይሁነን፡፡

comment pic

የጠቅላይ ሚኒሰትሩ የለበጣ ስብሰባዎች |ግርማ ሠይፉ ማሩ

$
0
0

ጠቅላይ ሚኒሰትር ኃይለማሪያም ሰሞኑን ስራ በዝቶባቸው እንደከረሙ ሁላችን እንረዳለን፡፡ የስራው ውጤታማነት የሚለካው ግን በሚያሰገኘው ፍሬ ነው፡፡ በእኔ ግመገማ ስራቸው ለውጤት እንዳልሆነ የተረዳሁት ዘግየት ብዬ “ከተቃዋሚ ፓርቲ” ተብዬዎች ጋር ውይይት ካደረጉ በኋላ ነው፡፡ ቀደም ሲል ከንግድ ማህበረሰብ ቀጥሎም ከምሁራን ጋር ውይይት አድረጉ ሲባል የምር እኚህ ሰው የሚመሩት ድርጅት ልብ ገዛ ብዬ ተሰፋ ማድረጌ አልቀረም ነበር፡፡ ምን ያደርጋል በተመሳሳይ ለህዝብ ግንኙነት ሲባል የሚያደርጉት መሆኑን ያጋለጠ ስብሰባ መጋቢት 14 ቀን 2008 በማድረግ ተስፋዬ አጨለሙት፡፡ የብዙ ሰው ሰሜት እንደሚሆንም ተሰፋ አደርጋለሁ፡፡ ለነገሩ ከሁሉም ጋር የሚያደርጉት ስብሰባ የኢህአዴግ ክፉ መንፈስ የተጫነው ነበር፡፡ ከአቋም ፍንክች እንደማይሉ፣ እነርሱም ሌቦች ሌላውም ሌባ (የመንግሰትና የግል ሌቦች) መሆኑን በሚያስረግጥ መንፈስ የተካሄዱ ናቸው፡፡
Girma seifu

ነጋዴዎችን ሰብሰበው ያስተላለፉት የመጨረሻ መልዕክት መንግስት ማሰር ቢፈልግ ሁሉም ከእስር ሊተርፍ እንደማይችል አስጠንቅቀው እና በተቻለ መጠንም አሸማቀው ነው፡፡ መልዕክቱ አሁንም ቢሆን ፀባይ ካሳመራችሁ የምናስረው እስር ቤት ሟቋቋም ድረስ የደረሱትን ብቻ ነው የሚሉ ይመስላሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒሰትራችን ነጋዴዎች እስር ቤት እንዳላቸው የነገሩን ነገር ብዙ የሚገርም አይደለም፡፡ በእኛ ሀገር አንድ የውጭ ኤምባሲ እስር ቤት እንደነበራው ይውራ ነበር (የኤርትራ ኤምባሲ)፤እፍኖም ይወስድ ነበር፡፡ ይህ ይሆን የነበረው ግን በመንግሰት የደህንነት ሰዎች ድጋፍና ትብብር ጭምር ነው፡፡ በእኔ እምነት አሁንም እስር ቤት ያቋቋመው ነጋዴ የደህንነት ድጋፍ አልነበረውም ብዬ አላምንም፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁንም የትኛው ነጋዴ የት ቦታ እስር ቤት አደራጅቶ ከማን ጋር ይስራ እንደነበር በግልፅ በስም ሊገልፁልን ግድ ይላቸዋል፤ በዚሁ ሁኔታም ክስ ተመስርቶ ማየት እንፈልጋል፡፡ (Name and Shame)፡፡ በዚህ አጋጣሚ ፕሮፌስር መስፍን ይህን አስመልክቶ በፌሰ ቡክ ገፃቸው ላይ ማለፊያ ነገር አስነብበውናል፡፡ የሚገርመው በጠቅላይ ሚኒስትር ደረጃ ይህ መነገሩ ነው እንጂ፤ አንባገነን ስርዓት ባበት ማንም ይህን ሊያደርግ ይቸላል የሚል ነው፡፡ ሁላችንም እንደምናውቀው በሶማሊያ ብዙ የጎበዝ አለቆች በነጋዴዎች የሚታዘዙ ማሰሪያዎች አሉዋቸው፡፡ ፀጥታም የሚያስከብሩት እነዚሁ የጎበዝ አለቆች ናቸው፡፡ እስከ አሁን ድረስ ይህ የቀረ አይመሰለኝም፡፡

የነጋዴውን ስብሰባ ጉዳይ ከመቋጨቴ በፊት “ነጋዴ በሙሉ ሌባ ነው” የሚል እንደምታ ያለውን ንግግር ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ሲያደርጉ ነፃነቱ ያለው እና ነፃነቱን የሚያስከብር የንግድ ምክር ቤት ተወካይ ቢኖር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይቅርታ እንዲጠይቁ ማስገደድ ባይችል ለወጉ ለማረጉም ቢሆን ጥያቄ ያቀርብ ነበር፡፡ ይህ ሁሉ ነጋዴ ግብር እየከፈለ ያቆማትን ሀገር ሁላችሁም ሌቦች ናችሁ፤ ማሰር ብንፈልግ የሚቀር የለም የሚል መልዕክት ማስተላለፍ በፍፁም ተቀባይነት የሌለው ከጠቅላይ ሚኒስትር የማይጠበቅ ንግግር ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትራችን አንድም ቀን በንግድ ተሳትፈው ስለማያውቅ ነጋዴዎች ትርፍ ለማሳደግ የሚወሰዷቸው የተለያዩ እርምጃዎች በሙሉ “የሌብነት ስራ” ነው ብለው ያምናሉ፡፡ ህጋዊ የሆነ የታክስ መቀነስ እንቅስቃሴ በትምህርት/በህውቀት (Legal Tax Evation) የተደገፈ መሆኑን የሚነግራቸው አማካሪ የላቸውም፡፡ አማካሪዎች ተብለው የተሰየሙት ተመሳሳይ በመሆናቸው ለውጥ ሊመጣ አይችለም፡፡

ከነጋዴዎች ቀጥለው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምሁራን ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ሰምተናል፡፡ ነጋዴዎቹን ሲያነጋግሩ እንደነበረው ሁሉ ከምሁራኑ ጋር የነበረው መንፈስም ያው የኢህአዴግ ክፉ መንፈስ የተጫነው ነበር፡፡ ይህን ስብሰባ ከነጋዴዎቹ ልዩ የሚያደርገው ነገር “ከፈለጋችሁ ፓርቲ አቋቁሙና እንጋጠም” ማለታቸው ነበር፡፡ በእለቱ ስብሰባ የተገኙ ተሳታፊዎች የዋዛ የማይባል ጥያቄ ማንሳታቸውን እኛ አድማጮች ደግሞ በተሰጠው ኢህአዴጋዊ ማብራሪያና ማፈራሪያ ሳይሆን በጥያቄዎቹ መስመር ላይ መሆናችንን ማሳታወስ ግድ ነው፡፡ ምን ማለት ነው? ብሎ ለሚጠይቅ “ይህች ሀገር ነፃነት ያለው ህዝብ መኖሪያ አይደለችም፡፡ ጋዜጣኛም፣ ነጋዴም፣ ፖለቲከኛም፣ ተማሪም፣ ወዘተ በነፃነት የሚኖርበት ሀገር አይደለም፡፡” የሚለውን የምሁራን አስተያየት የምንደግፍ መሆኑን ለመግለፅ ነው፡፡

ከምሁራኑ ስብሰባ ከተሰነዘሩት አስተያየቶች አንዱ ጠቅላይ ሚኒሰትሩ “ደረታችሁን ነፍታችሁ የምትሄዱት” በሚል ከናይሮቢ ጋር ያደረጉት ንፅፅር ሲሆን ይህ ንፅፅር በምንም መመዘኛ ትክክልም ተገቢም ሆኖ አላገኘሁትም፡፡ እውነቱን ለመናገር ለአንድ ኬኒያዊ የኬኒያ መንግሰት ስጋቱ አይደለም፡፡ እኛ ግን መንግሰታችን ስጋታችን ነው፡፡ በእኛ ሀገር ሀፈና የሚፈፀመው ሊጠብቅን በሚገባ መንግሰት ነው፡፡ ኢትዮጵያ ደግሞ እስከ ዛሬ ከሸብርተኛ ቡድን ነፃ የሆነችውን ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ስምም ፆታም አልገልፅም ብለው ነገር ግን እስከ አያት ስሟ የነገሩን ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ጉቤቦን በግፍ በማሰራቸው አይደለም፡፡ እኛ ኢትዮጵያዊያን በዚህ ደረጃ ለሸብር የደረሰ ሰነ ልቦና ስለሌለን ነው፡፡ ርዕዮትን የፈቷት በግፊት መሆንን ማመናቸው አንድ ነገር ሆኖ፤ በህገወጥ ሁኔታ በእስር እንደነበረች ግን የምንረሳው አይደለም፡፡ (የፍርድ ቤቶች ውሳኔ ልክ ነው ቢባል እንኳን የእስር ጊዜ ጨርሳ አንፈታም ብለው ከህግ ውጭ አስረው ነበር ያስቀመጧት) በኋላ ጠቅላይ ሚኒሰትሩ በግፊት እንደተፈታች ያመኑትን ማለት ነው፡፡

ከላይ የነበሩትን ስብሰባዎች የለበጣ እንደነበሩ ግምት እንድወስድ ያደረገኝ ስብሰባ የተካሄደው መጋቢት 14/2008 “ከተቃዋሚ ፓርቲ” ተብዬዎች ጋር ያደረጉት ውይይት ነው፡፡ በእኔ እምነት የውይይቱ ዋልታና ማገር የነበረው እነዚህ ፓርቲዎች በሀገራችን ከሚያመጡት የዲሞክራሲ ትሩፋት ይልቅ ለሆዳቸው መሙያ የሚሆነውን ቀለብ አስፋፈር ላይ የነበረ መሆኑ ነው፡፡ ተሳታፊዎቹ በሙሉ በሚባል መልኩ ደስተኛ የሆኑት ኢህአዴግ ከመንግሰት ካዝና ከሚደርሰው ገንዘብ ግማሹን ሊያካፍላቸው ፈቃደኝነቱን በጥቂቱም ቢሆን በማሳየቱ ነው፡፡ ለእነዚህ ተቃዋሚ ተብዬዎች ከዚህ ውጭ መልካም ዜና የለም፡፡ በስብሰባው ያልተገኙትም ቢሆን ያናደዳቸው ገንዘቡ ለፓርቲዎች የጋራ መድረክ አባላት ብቻ መሰጠቱ ነው፡፡ በክፍያው ላይ ቢካተቱ አብረው ጮቢ እንደማይረግጡ መረጃ የለንም፡፡ ከዚህ ውጭ መልካም ጅምር ብለው የኢዴፓው መሪ የገለፁት ምርጫን አስመልክቶ ይደረጋል ያሉት ለውጥ ነው፡፡ ይህ አባባል በእውነቱ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ለቆየ ሰው ፓርቲዎች ስልጣን የማይዙት ወይም ተወካይ የማይኖራቸው ህዝቡ ተቃዋሚዎችን በአብልጫ ስለአልመረጠ እና “አብላጫ ድምፅ ያገኘ ያሸንፋል” በሚለው የምርጫ ህግ ምክንያት ያስመስለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒሰትሩም “ምን አባታችን እናድርግ ህዝቡ ሲመርጠን” ያሉትን እንደመደገፍ የሚቆጠር ነው፡፡ በኢትዮጵያ ትልቁ ችግር እኩል መወዳደሪያ ሜዳ ያለመኖሩን አለመቀበል ነው፡፡ ይህ ደግሞ ከኢህአዴግ ጋር እንደመቆም የሚቆጠር ነው፡፡ ለነገሩ ኢዴፓ ከኢህአዴግ ጋር ለምን ቆመ አይባልም፣ ከዚያ ውጭ የት ሊቆም ይቸላል፡፡ ግቡም ትንሸም ቢሆን የፓርላማ ወንበር ማግኘት ነው፡፡

ለማነኛውም ጠቅላይ ሚኒሰትሩ “ተቃዋሚ ተብዬዎች” ምን እንደሚፈልጉ ገብቶዋቸዋል፡፡ ሆዳቸውን የሚሞሉበት ገንዘብ እንደሚያገኙ ቃል ተገብቶላቸዋል፡፡ “ተቃዋሚ ተብዬዎችም” ምን እንደማይችሉም አውቀዋል፡፡ መሻሻል የሚገባቸውን አዋጆች አጥኑና አምጡ በህጉ መሰረት ይታያል ብለዋቸዋል፡፡ እነዚህ አንደ ገፅ ሰርዓት ያለው መግለጫ መፃፍ ለማይችሉ ተቃዋሚዎች ጥናት አጥኑና አምጡ ከባድ ፈተና ነው፡፡ ሌላው ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ያልገባቸው ደግሞ የሰበሰቧቸው “ተቃዋሚዎ ትብዬዎች” በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ አንድም ቦታ የሌላቸው መሆኑን ነው፡፡

ሰለዚህ በቀጣይም ከህዝቡ ጋር የሚካሄትዱትም ሆነ የተካሄዱት ስብሰባዎች እንደ ከዚህ ቀደሙ የፎረም እና የኢህአዴግ ልዩ ልዩ አደረጃጀቶች ውሰጥ በንቃት የሚሳተፉ ሰዎች ተገኝተው ድራማ የሚካሄድባቸው እንደሆነ ግምት ወስደና ወይም ገብቶናል፡፡ ይህ ደግሞ የነፃነት ቀን መምጫውን ያዘገየው እንደሆን እንጂ ጨርሶ አያስቀረውም የሚል እምነት አለኝ፡፡ መፍትሄው ከዚህ በፊት ፀረ-ህዝብ፣ ጸረ -ምናም እያላችሁ ያገለላችሁትን ቡድኖችና ግለሰቦች በንቃት ማስተፍና ትክክለኛውን ሁኔታ መገንዘብ ነው፡፡ በተጨማሪ ያለምንም ቅድመ ሁኔተ ያለ አግባብ በእስር ላይ የሚገኙት ታጋዮች መፍታት ነው፡፡ ስብሰባም ካስፈለገ …….

ቸር ይግጠመን

ግርማ ሠይፉ ማሩ

ወያኔ መሞቻውን፤ እኛ መሰንበቻውን፤ –ይገረም አለሙ

$
0
0

 

tplf-rotten-apple-245x300እኔ ከምኑም የለሁበት ተቀዋሚም ደጋፊም አይደለሁም  በሚል ጭንብል ተሸፍኖ የሚኖረው ክፍል ሲቀር ሌላው በሁለቱ ጎራ ይመደባል፡፡ በወያኔ ጎራ ያለው ወገን ለአባልነትም ይሁን ለደጋፊነት ያበቃው ምክንያት ምንም ይሁን ባለው አቅም  በሚችለው መንገድ የወያኔን  ዕድሜ ለማራዘም ያስችላል ብሎ ያመነበትን ይሰራል፡፡ እንደውም አንዳንዱ ያለ ወያኔ መኖር አንደማይቸል ራሱን አሳምኖ ሞቴን ከወያኔ ጋራ ያለ ነው የሚመስለው፡፡ በዚህ ጎራ የተሰለፉ ሰዎች ሆነ ብለው አቅድው ሊገኝ የሚችለውን ውጤት ናፍቀው የወያኔን እድሜ በሚያሳጥር ተግባር ላይ አይሰማሩም፡፡ የውስጥ አርበኞች ካልሆኑ በስተቀር፡፡

 

በአንጻሩ በተቃውሞው ጎራ ያለው ወገን ለተቀዋሚነት የበቃበት ምክንያትና አንዴትነት የመለያየቱን ያህል ተግባሩም የዛኑ ያህል የተለያየ ነው፡፡ ይህም በመሆኑ መቋሰል መጓተቱን፤መወነጃጀል ጣት መቀሳሰሩን ወደ ጎን አስቀምጦ  አንድ ወጥ በሆነ መንገድ ለወያኔ እድሜ ማጠር መስራት አልቻለም፡፡  ይህም በመሆኑ ወያኔ በጥንካሬው ሳይሆን በድክመቱ፣ በእውኑ ሳይሆን በሙቱ ሲገዛ ኖሯል፣. አሁንም እየገዛ ነው ምን አልባትም ወደፊትም! ( መበስበሳቸውን ከነገሩን በኋላ በእኛ ድክመት ህይወት ዘርተው ስንት አመት ገዙን ?)

ከወያኔ ጎራ የተሰለፉት ሥልጣን ሽተውም ይሁን በዘር ተስበው፤ስኳር ልሰውም ይሁን መሬት ብናገኝ ብለው፤አያያዙን አይተህ ወደሚያደላው ብለው መስሎ ተመሳስሎ መኖርን መርጠውም ይሁን ብቻ ባሉበት በተሰለፉበት ለወያኔ ይበጃል ያሉትን በተናጠልም ይሁን በመተባበር ሲሰሩ አኛ ለተያያዝነው ትግል ይበጃል የምንለውን ምን ሰራን ብለን ራሳችንን ከመጠየቅ ይልቅ እነሱ ማውገዙ በእጅጉ የቀለናል፡፡ ዓላማው ምንም ይሁን ምን ያንን ተግባራዊ ለማድረግ ከሚመስለው ተባብሮ በራሱም ተጠናክሮ በጽናት የሚሰራ ይደነቃል፡፡ ዓላማየ የሚለውን ያውም በቃል ሲነገር የተቀደሰ አላማ ያንን ተግባራዊ ለማድረግ የማይጣጣር  የማይተባበር መወገዝ መወቀስ ካለበት እርሱ ነው፡፡

 

የተቃውሞው ጎራ ዥንጉርጉርነት በራሱ አልሞ አቅዶና ታግሎ ውጤት ማምጣት አይደለም ጊዜ የሚፈጥራቸውን አጋጣሚዎች ለመጠቀም እንኳን  የማይችል አድርጎታል፡፡ በመሆኑም ወያኔ ለሥልጣኔ ማቆያ ይበጃኛል እያለ በሚፈጽመው ኢ- ሰብአዊ ኢ- ህጋዊና  ከዴሞክራሲ ጋር ሆድና ጀርባ በሆነ ተግባሩ በየግዜው ከህዝብ እየተጣላ መሞቻውን ሲያፋጥን በአንጻሩ ተቀዋሚው መሰንበቻውን ያመቻችለታል፡፡ ( የወያኔን ዕድሜ የሚያራዝም ተግባር ይፈጽማል፡፡)

 

እንደ ተቀዋሚ ድርጅቶቹ ብዛት  እንደ መሪዎቹ ማንነት ለታቃውሞ የተነሱበት ዓላማና ምክንያት ይለያያል፡፡ ነገር ግን በወርቃማ ቃላት የተሸፈነ ድብቅ አጀንዳ እስከሌለ ድረስ የወያኔን አንባገነናዊ አገዛዝ ከህዝብ ጫንቃ ላይ ማስወገድና ኢትዮጵያን ዴሞክራሲያዊት ሀገር ማድረግ ሁሉንም ሊያስማማ የሚችል ነው፡፡ ( በድርጅት ደረጃ ከዚህ የተለየ የተጻፈና በአደባባይ የሚናገሩት ዓላማና ግብ የነበራቸው እድሜ አስተምሮአቸው መከራ መክሮአቸው  ተመልሰዋል፡፡)

 

በመሆኑም አደረጃጀታቸው ቢለያይ፤ የመረጡት የትግል ስልት ሊዛመድ የማይችል ቢሆን ከላይ በተጠቀሰው ግብ ተስማምተው  ቢችሉ ተባብረው ካልሆነም ሁሉም በየራሱ የትግል ስልትና መንገድ ወደ ግቡ መጓዝ አንጂ አንዱ የሌላኛው እንቅፋት ሲብስም ጠላት ሆኖ መሰለፍ ፍቺ ያጣ አንቆቅልሽ ነው፡፡ ይህ አንቆቅልሽ የሆነ ተግባር ነው እንግዲህ ወያኔ መቃብሩን ሲቆፍር ተቀዋሚዎች እድሜ ማራዘሚያ መድሀኒት እንዲሆኑት ያደረገው፡፡እናም ወያኔ መሞቻውን እኛ መሰንበቻውን እንሰራለን ለማለት ያበቃኝ፡፤

 

ብዙ ሩቅ መሄድ ሳያስፈልግ  ወቅታዊውን ሁኔታ እንመልከት፡፡ ከሁለት አመት በፊት ተቃውሞ አስነስቶ የብዙ ወጣቶችን የህይወት መስዋእትነት አስከፍሎ ለብዙ ወጣቶችም እስር እንግልትና ስደት ምክንያት ሆኖ ተግባራዊነቱ የቆመውን የኦሮምያና የአዲስ አበባ አጎራባች ወረዳዎች የጋራ ማስተር ፕላን ተግባራዊ አናደርገዋለን ለማደናቀፍ የሚሞክሩትንም ልክ እናስገባቸዋለን ብሎ ለህዝብ  ያላቸውን ንቀት ባሳየ መልኩ መናገር እድሜ ማሳጠሪያ እንጂ ማራዘሚያ ሊሆን አይችልም፡፡ ይህ ወያኔ ሞቱን የጠራበት የአቶ አባይ ጸሀየ ንግግር ግን ለፖለቲከኞቹ የተገለጠላቸው ህዝቡ ለተቃውሞ አደባባ ወጥቶ በጥይት መውደቅ  ከጀመረ በኋላ ነው፡፡

በኦሮምያ በአብዛኛዎቹ ዞኖች የታየው ግድያ፤ የግፍ ደብደባና የገፍ እስራት የተጠቀመበት አልተገኘም እንጂ ወያኔ መሞቻውን ያመቻቸበት ነበር፡፡ አቶ ጌታቸው ረዳ ሕዝብን ጋኔን፣ ሰይጣን ጠንቋይ በማለት የተናገሩትም ሆነ የኦሮምያ ክልል ፕሬዝዳንቱ  አቶ ሙክታር ከደር  የወያኔው ገዳይ ቡድን በኦሮምያ ክልል ተሰማርቶ የፈጸመው ኢሰብአዊ ድርጊት ሁሉ ተገቢና ትክክል እንደነበረ ገልጸው ይህን በማድረጋችሁ ትመሰገናላችሁ በማለት በመገናኛ ብዙኃን አማካኝነት ያስተላለፉት አድናቆትና ምስጋና ለወያኔ መሞቻው አንጂ መሰንበቻው ሊሆን የሚችል አልነበረም፡፡ አንዲህ አይነት ግራ ገብ ነገር ሲገጥማቸው ሟች ሞልቶ ነበር ገዳይ ጠፋ እንጂ ነው የሚሉት አበው፡፡

 

የሱዳኖችን መሬት ድንበር አልፈው ሄደው የያዙ ሽፍቶች በማለት የሀገሩን ዜጎች ከመወንጀል አልፎ  የኢትዮጵያን መሬት የሱዳን ነው በማለት በአደባባይ ለመመስከር የተበቃው ከማን አለብኝነት ንቀት በመነጨ ቢሆንም ይህ ሞቱን ሊያፋጥኑ ከሚችሉ በርካታ ተግባሮቹ አንዱ የሆነው ድርጊት ያደረሰበት ነገር አለመኖሩ ሲታይ በርግጥም የናቀን አይቶ ገምቶ ነው ያሰኛል፡፡ ያስናቁን ደግሞ በመግለጫ እንጂ በተግባር የማይታዮ ቁጥረ ብዙ ድርጅቶች ናቸው፡፡

በሀገሪቱ በብዙ አቅጣጫ ፈንድቶ የወጣ ቁጣ በሚታይበት ወቅት አዲስ አበባ ዝም በማለቱ ለአመታት ተግባራዊ ያላደረጉትን የመንገድ ሥነ- ሥርዓት ህግ ተግባራዊ እንደርጋለን ብለው የታክሲ ሾፌሮችን ለስራ ማቆም አድማ የዳረጉበትን ድርጊት ማንም ጤነኛ የወያኔ አባልና ደጋፊ ለእድሜ ማራዘሚያ የተደረገ ነው ሊለው አይችልም፡፡ ዝም ያለውን ለመቆስቆስና ተቃውሞውን አዲስ አበባ ላይም ለማቀጣጠል  የውስጥ አርበኞች የፈጸሙት ነው ከተባለ ሊያስማማን ይችላል፡፡ ነገር ግን በማንም ተፈጸመ በማን ከሌሎች ድርጊቶች ጋር ተደማምሮ  የወያኔን መሞቻ ሊያፋጥን የሚችል ድርጊት ነበር፡፡ በነበር ቀረ እንጂ፡፡

 

በሀገር ውስጥ ያሉትም ሆኑ በወጪ የሚገኙት ፖለቲከኞች እነዚህና ሌሎች በርካታ  ወያኔ ራሱ የፈጸማቸውን ሞቱን የሚያፋጥኑ ድርጊቶች  ሊያነሳሱዋቸውና ሊያስተባብሩዋቸው ቀርቶ እንደ ዓላማና አደረጃጀታቸው በየራሳቸው መንገድ    ተንቀሳቅሰው ራሱ በቆፈረው ጉድጓድ ለመቅበር ያደረጉት ነገር ባለመኖሩ እሱ ሞቱን ቢያፋጥነውም እነርሱ እስትንፋስ ሰጥተውት መሰንበት ችሏል፡፡ መሰንበቱን ሲያረጋግጥ ደግሞ  ይቅርታ የሚባል የእድሜ ማረዘሚያ መድሀኒት ራሱ ለራሱ አዞ እየወሰደ ይገኛል፡፡ ይህን ተከትሎም አንዳንዶቹ ፖለቲከኞች በእውናቸው ይሁን በህልማቸው የታያቸው ባይታወቅም ይቅርታ በተባለው እንክብል ወያኔ ሙሉ ፈውስ አግኝቶ ከደደቢት እምነቱ ይለወጣል ብለው ተስፋ እያደረጉ ነው፡፡

 

ወያኔ ከላይ ለአብነት የተጠቀሱትን ጨምሮ ለሀያ አምስት አመታት በቃልም በተግባርም መሞቻውን የሚያፋጥኑ ድርጊቶች ፈጽሟል፡፡በአንጻሩ ወያኔን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ ለማንሳት ነው የምንታገለው የሚሉ ፖለቲከኞች ሀያ አምስት አመት ሙሉ ፓርቲ ሲያፈርሱ ሲገነቡ፤ አንደ አሜባ ራሳቸውን ሲያባዙ፤ርስ በርስ ሲወነጃጀሉ የጎንዮሽ ሲታገሉ ወያኔን ታግለው የሚያሸንፉ አይደለም ራሱ መቃብሩን እየቆፈረ ሞቱን ሲያፋጥን ገንዘው ሳጥን ለመክተትም ሆነ ከቀብር ስፍራ አድርሰው አፈር ለመመለስ የሚችሉ ባለመሆናቸው ወያኔ ነበረ አለ  እስከ መቼ አንደሆነ ባይታወቅም ይኖራል፡፡ አሳዛኝ አሳፋሪ!

ኢትዮጵያ በጠቢቡ ሰለሞን ሸንጎ! (ታሪኩ አባዳማ)

$
0
0

ልተወለደ አንጀትህ ሲሉ ማንነትህን እጥር ምጥን ባለ ቋንቋ መግለፃቸው ነው። በሌላ ሰው ቁስል ጨው መነስነስ የማይቀፍህ ጨካኝ አረመኔ ነህ ማለታቸው ነው። ተቆርቋሪነት የጎደለህ ፣ ፍላጎትህን ለማርካት ብለህ ከምንም አይነት ጥፋት የማትመለስ መንፈሰ ደካማ ነህ ማለት ነው። በስግብግብነት የሌላውን ትቀማለህ ፤ ያንተ ያልሆነውን ትመኛለህ ፤ የኔ ነው ብለህ ትደርቃለህ ፣ ታፈጣለህ ለኔ ካልሆነ ሁሉም ነገር ባፍጢሙ ይደፋ ብለህ ነገር ታበላሻለህ። ሌላው ጥሮ ግሮ ያፈራውን ሀብት ፣ ያቆየውን ቅርስና ባህል ፣ ያስከበረውን ታሪክ ታረክሳለህ… ጉልበትህን መከታ አድርገህ በድርቅና ያልሆንከውን ሁሉ ‘ሆንኩ’ ብለህ ትቀጥፋለህ… ባልተወለደ አንጀት።
ባልተፃፈ ህግ ያሻህን ትፈፅማለህ ፣ ተጠያቂነት የሚሉትን ቋንቋ ትጠየፋለህ… አይን ላወጣ ዘረፋ ፣ አደባባይ የወጣን እውነት ለመካድ የማያመነታ ህሊና ተክነሀል።
ባልተወለደ አንጀት በሚያሰኝ መልክ በተራ ወሮበላ ወኔ አገርን መበደል ፣ የአገርን ሀብት መመዝበር እና ማስመዝበር ፣ ታሪክ ማበላሸት እና ማዛባት የህዝብን መሰረታዊ ጥቅም የሚፃረር አድራጎት መፈፀም ብሎም ህዝብን ወደ ጥፋት መውሰድ ባልተወለደ አንጀት የሚሉት አባዜ ነው… ይህን አይነቱን አባዜ ከህግ እና ከፍትህ ጎራዴ ሌላ የሚዳኘው መላ የለም።
ኢትዮጵያ ወያኔ በቀየሰው የጎጥ ክፍፍል መርህ እየተቸበቸበች ፣ እየተሸነሸነች ፣ እየተመዘበረች ናት… የ80 ቋንቋ ተናጋሪ ህዝቦች አገር መሆኗ ሲታሰብ አካሄዱ እየተሰነጣጠረች የሚያሰኝ አይነት ነው። አንድ ሁለት ብሎ ነገሩን በዝርዝር ሲያሰሉት ጉልበት ያርዳል። እየዋለ እያደረ ዛሬ ዘረፋው እና ቅሚያው ከመንዛዛቱ የተነሳ ዘራፊው እና ‘መዝጊያ ገልባጩ’ መንግስት ስለ ራሱ ምግባረ ብልሹነት እየወተወተ ይገኛል። በኪራይ ሰብሳቢዎች ማጥ የተዋጥኩ ቀማኛ መንግስት ነኝ “… ምናባቴ ላድርግ (ምናባታችሁ ታመጣላችሁ)” የሚሉ መሪዎች የሚያላግጡባት አገር ሆናለች። የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ ይለዋል ወገኔ…።
ባልተወለደ አንጀት አገር ያደማ ፣ አገር ያጠፋ ፣ ህዝብ የበደለ ከወንጀለኛ በምን ይለያል ፤ በወንጀለኛ ተፈጥሮው ያልተወለደ አንጀት ድርጊት የሚፈፅምስ… ወያኔን እንዴት እንግለፀው። ባልተወለደ አንጀቱ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን ላይ ወንጀል እየሰራ ወይንስ በወንጀለኛ ተፈጥሮው የተነሳ ያልተወለደ አንጀት የሚያሰኝ ወንጀል እየፈፀመ? ወይንስ በሁለቱም…
ቀልቀሎ ስልቻ ፣ ስልቻ ቀልቀሎ መሆኑ አይደለም?
መልሱን ከጠቢቡ ሰለሞን ሸንጎ የምናገኝ ይመስለኛል…
ብላቴናው የኔ ነው በሚል ሙግት የገጠሙ ሁለት ኮረዳዎች ከጠቢቡ ሰለሞን ሸንጎ የቀረቡት ከዛሬ 2500 ዓመታት በፊት ነበር። ሁለቱም ሴቶች ‘እናት እኔ ነኝ’ ሲሉ የይገባኛል ጥያቄ አቀረቡ። ሁለቱ ተሟጋቾች ባንድ ቤት ተዳብለው ይኖሩ እንደነበር የታሪኩ ጭብጥ ያረጋግጣል። አንደኛይቱ ወልዳ የሞተባትን ህፃን ለሌላዋ አስታቅፋ ፣ የሌላዋን ጤነኛ ልጅ ሰርቃ ከጉያዋ ሸጉጣ መኝታዋ ውስጥ ተጠቅልላ ተኝታለች… ሲነጋ የተፈጠረው አምባጓሮ ወደ ንጉስ ሰለሞን ሸንጎ አደረሳቸው።
ጠቢቡ ሰለሞን በጥሞና የሁለቱንም እናት ነን ባዮች አቤቱታ ካዳመጠ በሁዋላ አውጥቶ አውርዶ ብዙ አሰላሰለ፤ በመጨረሻም አንዱን ወታደር ‘ጎራዴህን ወዲህ በል’ አለው። ከሸንጎው መካከል ተነስቶ ‘ይህ ብላቴና የማናችሁ እንደሆነ ፍርድ መስጠት ቸግሮኛል ስለዚህ እኩል ለሁለት ሰንጥቄ ላካፍላችሁ’ በማለት ብይን ሰጠ።
ከፊቱ የቆሙትን ሁለቱን ወላድ ወጣት ኮረዳዎች ለመዳኘት ጠቢቡ ሰለሞን ከጎራዴ ሌላ መላ አላገኘም። ባንድ ጎጆ ጥላ ስር ዕለታዊ ኑሯቸውን ይጋሩ የነበሩ እናቶች ለዚህ ይበቃሉ ብሎ ማንም አልገመተም።
ከሁለቱ አንደኛዋ ‘እናት’ ጠቢቡ ሰለሞን የሰጠውን ብይን በደስታ እንደምትቀበል ፈጥና ገለፀች… ‘ፍትህ ዛሬ መሬት ወረደች’ ስትል ፈነጠዘች። የጠቢቡ ፍርድ ፣ ዳኝነቱ እንደተመቻት በፈገግታ አስታወቀች። ‘ህፃኑን ቆራርጡት ፣ ገነጣጥሉት ፣ በልቱት ፣ ቅርጫ አስገቡትና ድርሻዬን ስጡኝ… አሁኑኑ ገነጣጥሉት አለች።’
‘የለም ንጉስ ሆይ’ አለች ሌላዋ ሴት ተሟጋች ‘ልጄን በጎራዴ መቀራመቱ ፣ መበለቱ አይስማማኝም። ከዚህ ይልቅ ህፃኑን ለዚያች ሴት ስጧት… ልጄ ፣ የአብራኬ ክፋይ ፣ የነብሴ ቅራፊ በህይወት ይኑር ፣ አይሙትብኝ’ ስትል እናታዊ አንጀቷ ፣ እናታዊ ደመ ነብሷ ባስጨነቀው ሲቃ የጠቢቡን ፍርድ ተቃወመች። ‘ልጄ እንደ ዶሮ ብልት አይገነጣጠልም’ ስትል ድምፁዋን ከፍ አድርጋ ጮኸች… ‘የለም አትገነጣጥሉት ብላ ተማፀነች።’
ጥበብ እና አርቆ አስተዋይነትን የሚፈትን ብርቱ ጉዳይ የቀረበለት ንጉስ ሰለሞን ሁለቱም ሴቶች ያቀረቡትን ለኔ ይገባኛል ጥያቄ አመዛዝኖ አይቷል። ፍርድ ላይ ከመድረሱ በፊት ሁለቱንም እናቶች አነጋግሯል ፣ ፈትሿል ፣ ፈትኗል… ብላቴናው የማንኛዋ ሴት እንደሆነ መገንዘብ ባይሳነውም የፍርዱን ሂደት ለሚከታተለው ዜጋ የጥበቡን ዳርቻ ለማረጋገጥ ሲል ፣ ምሳሌነቱም እነሆ ምእተ ዓመታትን ተሻግሮ ዛሬ ለምንገኘው የሰው ዘሮች ትምህርት እንዲሆን አደባባይ ላይ ጎራዴውን ሰብቆ እውነት እና ፍትህ ምንኛ ተወራራሽ መሆናቸውን አረጋግጧል… ። የፍትህ መሰረቷ እውነት እንጂ ጉልበት ወይንም ጮሌነት አለመሆኑን አሳይቷል።
ንጉስ ሰለሞን የዚያ ብላቴና መፃኢ ዕድል ከወላጅ እናቱ ህይወት ጋር የተቆራኘ መሆኑንም አስተውሏል… ለህፃኑ ዘላቂ ህይወት የሚበጀው ምን እንደሆነ በፍትሀዊ ብያኔው አረጋገጧል… ።
የዚህ ታሪካዊ ፍርድ እንደምታ ዛሬ ኢትዮጵያ ለተዘፈቀችበት የህልውና አደጋ ጥልቅ ትርጓሜ አለው። ሰለሞን ዙፋን ላይ በቆየባቸው ዘመናት ብዙ ብልህነት እና ጥበብን የተላበሱ ታላላቅ ቁምነገሮችን አከናውኗል – ይህን የሁለት ሴቶች ሙግት አስመልክቶ የሰጠው ብይን ጎላ ብሎ እንዲፃፍ የተፈለገበት ምክንያት ግን በቀላሉ የሚታይ አይደለም። በቅዱስ መፅሀፍ እና በቅዱስ ቁርአን ሳይቀር ይህ ታሪክ ሰፍሯል።
በሙግቱ እና በብይን አሰጣጡ ሂደት ውስጥ የሰው ልጅ መሰረታዊ ባህሪ ውስብስበነት ተንፀባርቋል። ሰብአዊ መስሎ ጭካኔ ፣ ህጋዊ ተፋራጅ መስሎ በደለኛ ፣ አዛኝ መስሎ አረመኔነት ተመዝግበዋል። ንጉሱም ቢሆን ጎራዴ ያነሳው ያንን ህፃን ለመሸርከት ጨክኖ እንዳልሆነ ይልቁንም የማንስ ማንነት ፈተና ሲገጥመው ነጥሮ መውጣቱ አይቀሬ መሆኑን በማመዛዘን ነው።
ስለ ኢትዮጵያ አያሌ ነገሮች ተፅፈዋል ፣ ዛሬም እየተፃፉ ናቸው። የቆየ ታሪኳን ፣ የሰው ዘር መገኛ መሆኗን ፣ በስልጣኔ ቀደምት ታሪክ ካላቸው አገሮች ተርታ የመቆሟን ፣ የጥቁር ህዝብ ክብር መግለጫ የሆኑ ገድሎች የተከናወኑባት ምድር መሆኗን… እንዲሁም በድህነት አረንቋ ተዘፍቃ የቆየች እናም በረሀብ አለንጋ የተጠበሰች እናም እርስ በርስ ጦርነት ስትደማ ብዙ እንግልት የተፈራረቀባት መሆኗን የሚያትቱ ሰነዶች የተከማቹባት ናት።
ኢትዮጵያ ሚሊየኖች በማህፀኗ ተፀንሰው ሰው ለመሆን የበቁባት፤ የሞሏት ልጆቿ የብዙ ቋንቋ ተናጋሪ ፣ ዘርፈ ብዙ ባህል ባለፀጋ ሆነው ሳለ ግን አሁንም በተፃፈውም ባልተፃፈውም ረጅም ታሪኳ ውስጥ ብዙ ውጣ ውረድ አልፈው እና ዘልቀው እስከ ዘመናዊው የመንግስት አስተዳደር የደረሰችበትን ማንነት ያጎናፀፏት መሆናቸውን እንገነዘባለን። ይህ ብቻ አይደለም…
ኢትዮጵያ በልጆቿ የርስ በርስ ግጭት የተነሳ በጎ የማይባል አያሌ ክፉ ዘመናትን አሳልፋለች ፤ በጎበዝ አለቆች ፉክክር ፣ በንጉሶች ገብር አትገብር ዘመቻ ፣ በተፈጥሮ ሀብት ሽሚያ እና ከቅርብ ዘመናት ወዲህ ደግሞ በፖለቲካ ስልጣን ይገባኛል ባይ ተቀናቃኝ ዜጎቿ መካከል ቀላል የማይባል ቂም ሲያከማች የቆየ ፍጭት ውስጥ ትገኛለች።
የፍጭቱ ባህሪ መልኩን ቀይሮ ህልውናዋን ጭምር አደጋ ላይ የጣለ ፍጥጫ ላይ ደርሳለች።
ኢትዮጵያ መብት የተረገጠባት ምድር በመሆኗ ዜጎች እንደ ማንኛውም አገር ለመብት መረጋገጥ ፣ ለህግ የበላይነት ጥያቄ መሰለፋቸው ተገቢም አስፈላጊም ነው። በማናቸውም ረገድ ህዝብ የሚያነሳው የመብት ጥያቄ የአገርን ህልውና እስካልተፃረረ ድረስ አላንዳች ገደብ መልስ ሊያገኝ ይገበዋል። ትናንትም ሆነ ዛሬ ህዝብ ለሚያቀርበው የመሰረታዊ መብት ጥያቄ ገዢዎች ቀና ወይንም ቀልጣፋ መልስ ሲሰጡ አላየንም። ዛሬ ገዢው ሀይል ህዝባዊ መሰረት የቆነጠጠ ሳይሆን ውሱን የሆኑ ስግብግብ ሀይሎች የሚያሽከረክሩት በጉልበት እና ስለላ መረብ የሚተማመን ሀይል ነው። ማናቸውንም ህዝባዊ ሰላማዊ ጥያቄ በመጨፍለቅ አገዛዙን መቀጠል ይፈልጋል። ይህ ሚስጢር አይደለም – ይህን አፈና ለመቋቋም እና ለማስወገድ ብሎም በህግ የበላይነት የሁሉም ዜጎች ጥያቄ መልስ እንዲያገኝ ብሎም ኢትዮጵያ ፀንታ እንድትቆም ለማረጋገጥ ያለሰለሰ ሙግት ማካሄድ አስፈላጊ ነው።
ወያኔ ገና ከምስረታው በሰነድ ላይ አስፍሮ የዘመተው ትግራይ ተገንጥላ የራሷን መንግስት እንድታቆም ነው። አላማው በማያሻማ ቋንቋ ተቀምጧል… በቅድሚያ ‘ትግራይ ከዚያ ኢትዮጵያዊ ነኝ’ ብሎ አደባባይ የደሰኮረው የግንጠላው መሀንዲስ መሪያቸው ያረጋገጠውን ልብ ይሏል። አንቀፅ 39 የተፃፈው ከዛሬ አርባ ዓመታት በፊት ነበር። ይህ የወያኔ አላማ ለፌዝ እና ለወጉ ያህል የተጨመረ አንቀፅ ሳይሆን ኢትዮጵያ የተሰኘች አገር ህልውነዋ እንዲያከትም ይሁነኝ ተብሎ የተስማሙበት ነው። ይህን አላማ ዳር ለማድረስ ዛሬ ድረስ ተግተው እየሰሩ ለመሆኑ ከበቂ በላይ ማስረጃዎች ሲቀርቡ ቆይቷል። ባልተወለደ አንጀት ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን ላይ ሲፈፅሙ የቆዩትን የዘረፋ ፣ ግድያ ፣ በዘር መከፋፈል ብሎም ዳርድንበርን ለባእድ መቸብቸብ ድርጊቶች ማጣቀስ በቂ ይመስለኛል።
ወያኔ ባልተወለደ አንጀቱ 3ሚሊየን ሄክታር መሬት ለቱርክ ፣ ለህንድ ፣ ለሳውዲ እንዲሁም ሌሎች ባእዳን ከ30 እስከ 50 አመት ለሚደርስ ዘመን ፈርሞ አስረክቧል። ጎረቤት አገር ጂቡቲ ጠቅላላ ስፋቷ 2.3 ሚሊየን ሄክታር ነው። እንግዲህ 3ሚሊየን ሄክታር ሰነድ የሚያውቀው ለም መሬት ለባእዳን ሲሰጥ በዚህ መሬት ላይ ከትውልድ እስከ ትውልድ የኖሩ ኢትዮጵያውያን የት ደረሱ? እጃቸው ፊጥኝ እየተቀፈደደ እንደ ከብት ሲጋዙ የቆዩትን ወገኖቻችንን ወያኔ የት አደረሳቸው? ከአፅመ ርስታችን አትነቅሉንም ብለው ያንገራገሩ ኢትዮጵያውያንስ ከምን ደረሱ? ጋምቤላ በየቄያቸው የታረዱትን ገበሬዎች ደም ማን ይፋረድ? ባልተወለደ አንጀት…
ሰለማዊ የመብት ጥያቄ አንስተው የተሰለፉ ዜጎች ላይ ጅምላ ጭፍጨፋ ሲፈፅም መኖሩ ሌላው የወያኔ ማንነቱ ማረጋገጫ ነው። ድምፄን አልቀማም ብሎ አደባባይ የወጣን ሰልፈኛ በምርጫ 97 ወቅት ጨፍጭፏል። በህዝቡ ላይ የቋጠረውን ቂም ለመበቀል ሲል ባወጣው ስልት አዲስ አበባውያን ከተወለዱበት ፣ ካረጁበት ፣ እድር እና ደጀ ሰላም ከመሰረቱበት ሰፈራቸው በግድ ተፈናቅለው ገሚሱ ወደማያውቀው አንዳችም ማህበራዊ አገልግሎት ወደሌለበት ዱር እና ገደል ሌላውም ቤት አልባ የጎዳና ተዳዳሪ እንዲሆን አድርገውታል… ባልተወለደ አንጀት።
ዛሬ ድረስ አላባራ ያለው ጭፈጨፋ አፈሙዙን ወደ ኦሮሞ ህዝብ አዙሯል – መሰረታዊ ሰብኣዊ መብታችን ይከበር ፣ መሬታችንን አትቀሙን ብለው የተነሱ ዜጎች አደባባይ ተገድለዋል ፣ ከየመንደሩ እየተለቀሙ በየጉድባው ተገድለው በመጣል ላይ ናቸው። ኦሮሞ የሚኖርባት እያንዳንዷ ትናንሽ መንደር ሳትቀር የጦር ቀጠና ሆናለች… ወያኔ በመደበኛ ጦር ጥቃት እፈፀመ ነው… እናቶች ፣ አዛውንት እና ህፃናት እተጨፈጨፉ ናቸው… ባልተወለደ አንጀት።
በሰሜን ሱዳን በኩል ተቆርሶ ለባዕድ የተሰጠው መሬት ኢትዮጵያን ለማጥፋት ከታቀደው አላማ ውስጥ የሚካተት ሌላው ‘ባልተወለደ አንጀት’ የሚሰኝ ወንጀል ነው። በድንበሩ አካባቢ ኑሯቸውን ሲከውኑ የቆዩ ዜጎች እንደ ወንጀለኛ እየታደኑ ገሚሱ ተግደለዋል ቀሪዎቹ ዱር ወጥተዋል – አገራችን በታሪኳ ብዙ ክፉ እና ደግ ነገር ቢፈራረቅባትም አንዲህ አይነት ክህደት የሚፈፅም መንግስት ግን ከቶ ገጥሟት አያውቅም።
የአገሪቱ ጥሬ ሀብት ፣ ወርቅ እና ማዕድናት በነኝሁ አልጠግብ ባይ ሀይሎች አለገደብ እየተጋዘ ነው። በቅርቡ አንድ ባለሙያ እዚያው ወያኔ ፓርላማ ላይ ቀርበው ሲናገሩ ‘አገሪቱ አለርህራሄ እየተመዘበረች ነው ፣ ራቁቷን እንድትቀር እተደረገች ነው’ ብለዋል። በሌላ ቋንቋ ባልተወለደ አንጀት የሚካሄደው ዘረፋ እንኳን ለውጪው ታዛቢ ከውስጥ ሆነው ለሚያገለግሉ አንዳንድ ቅን ዜጎች ሳይቀር የሚዘገንን ነው።
እናም ለኔ ካልሆነች ድርሻዬን ቆርሼ እገነጠላለሁ የሚሉ ወገኖች ሌት እና ቀን ተዋድቀው ኢትዮጵያን ከጉያቸው አስገብተዋል። ኢትዮጵያ ላለፉት ሀያ አምስት አመታት በነሱ እቅፍ ውስጥ ናት። በውድቅት ሌሊት ሰርቃ እቅፏ ያደረገችውን ህፃን የሷ ነው ብላችሁ ካልሰጣችሁኝ በጎራዴ ቀልታችሁ ድርሻዬን ስጡኝ እንዳለችው ሴት መሆኑ ነው። እሷም ወላድ ናት ፣ እሷም ሴት ናት ግና ባልወለደ አንጀቷ የዚያን ብላቴና ቁራጭ ታቅፋ ቤቷ ለመመለስ ለምን ፈቀደች? የሚለው ጉዳይ ብዙ ያስተምራል። ኢትዮጵያ ከሰለሞን ሸንጎ ፊት ቆማ ፍትህ ትጠይቃለች።
እዚህ ላይ ‘አለበለዚያ ድርሻዬን ቆርሼ እገነጠላለሁ’ በሚሉት እቅፍ ውስጥ 25 ዓመታት የቆየችው ኢትዮጵያ ምን እየተፈፀመባት መሆኑን መቃኘቱ ጠቃሚ ነው። እነኝህ ወገኖች አትዮጵያን እና ህዝቦቿን በምን መልኩ እያሳደሩ ነው ለሚለው ጥያቄ መልስ መስጠት ተገቢ የሚሆነው ድርጊታቸው ማንነታቸውን ይበልጥ አጉልቶ የሚያሳይ በመሆኑ ጭምር ነው። ሲፈፅሙ የቆዩት ባልተወለደ አንጀት ወይንስ እንደ እናት ተቆርቋሪ በሆነ ልባዊ ፍቅር?
ያልወለደችውን ህፃን እናት ነኝ ብላ የሞገተችው ሴት እውነትም ሀሳቧ ሰምሮ ልጁን በህይወት እንድትረከብ ቢፈርድላት ኑሮ የዚያ ብላቴና ዕጣ ፈንታ ምን ይሆን ነበር? እናታዊ ፍቅር እየተመገበ ያድግ ነበር? ንጉስ ሰለሞንን ያስጨነቀው ጥያቄ ይኼ ነበር? እኛም ዛሬ የሚያስጨንቀን ይኼ ነው… ባልተወለደ አንጀት።
እናም ‘ኢትዮጵያ መገንጣጠል የለባትም – የዜጎች መብት በህግ የበላይነት ይረጋገጥ ማለት ከቶውንም ብሔራዊ ማንነትን እስከመካድ ድረስ ርቆ መሄድ አይገባውም’ በሚሉ ወገኖች ላይ የግንጠላ አቀንቃኞቹ ክስ ያቀርባሉ። ‘አሀዳዊ መንግስት ይመለስ ብለዋል ፣ ያፈጀውን የቀድሞ ስርዓት ለመመለስ የቆሙ ናቸው’ ሲሉ ይከሳሉ። ‘ዛሬ በጎጥ ዳር ድንበር ያሰመርነውን ‘ክልል’ ሊያፈርሱ ነው…’ ይላሉ።
ብትገነጣጠል አይከፋንም የሚሉት ወገኖች ያንን ‘መሬት ላራሹ’ ሲል በአንድነት ቆሞ የታገለን ትውልድ ፣ ያንን በ‘ነፃነት ለዘላለም ኑሪ’ ያለ ትውልድ ፣ ያንን ‘የብሔር ብሔረሰቦች መብት ይከበር’ ፣ ‘ህዝባዊ መንግስት ይቋቋም’ ‘የሀይማኖት እና የፆታ እኩልነት ፣ ሰብአዊ መብቶች ይረጋገጡ’ ፣ ያንን ከራሱ ምቾት እና ድሎት ይልቅ የህዝብ እና የአገር ጥቅም ይቅደም ብሎ የተሟገተ ትውልድ ይከሳሉ።
ከሳሽ እና ተከሳሽ ከሰለሞን ሸንጎ ቀርበዋል።
ሰለሞናዊ ፍትህ የሚያሻው ሙግት ላይ ደርሰናል። የተሟጋቾቹ ፍሬ ሀሳብ ፣ ያቀረቡት ጭብጥ በማያሻማ ቋንቋ ተብራርቶ ለችሎት ተሰምቷል። አብረቅራቂው ጎራዴ ስለቱን ቀስሮ ለመወንጨፍ ፣ ለመከታተፍ ተዘጋጅቷል። ንጉስ ሰለሞን ብይን ሊሰጥ ግራ ቀኙን እያማተረ ነው…
… ንጉስ ሆይ ኢትዮጵያ የማን ናት?

በኢትዮጵያና በአሜሪካ መንግሥታት የተሰጠ የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ |ሊያነቡት የሚገባ

$
0
0

በኢትዮጵያና በአሜሪካ መንግሥታት የተሰጠ የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ

የአሜሪካና የኢትየጵያ የዲሞክራሲ፣የመልካም አስተዳደር እና የሰብዓዊ መብቶች የጋራ የሥራ ቡድን የሥራ ቡድን 6ኛውን ስብሰባ በአዲስ አበባ አካሄደ

US Embassy

(PDF) አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ መጋቢት 21 ቀን 2008 ዓ.ም.:- መጋቢት 20 ቀን 2008 ዓ.ም. በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ፓትሪሺያ ሃስላክ እና በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የዴሞክራሲ፣ የሰብዓዊ መብቶችና የሥራ ረዳት ሚኒስትር ቶም ማሊኖውስኪ ከኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ጋር በመሆን 6ኛውን የሁለቱን ሀገራት የዲሞክራሲ፣የመልካም አስተዳደር እና የሰብዓዊ መብቶች የጋራ የሥራ ቡድን ስብሰባ መርተዋል፡፡ ይህ የጋራ የሥራ ቡድን ስብሰባ የሁለቱ ሀገራት መንግሥታት ተወካዮች የመልካም አስተዳደርና ሰብዓዊ መብቶችን የሚመለከቱ ጉዳዮችን በግልፅና በስፋት የሚወያዩበት መድረክነው፡፡

የጋራ ግብረ ኃይሉ ከተወያየባቸው ሰፋ ያሉ ርዕሰ ጉዳዮች መካከል ከምርጫ ጋር ተያያዥ የሆኑ ጉዳዮች፣ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ያለው ሁኔታ፣ዓመታዊው የሰብዓዊ መብቶች ሪፖርት፣መልካም አስተዳደርን በማጠናከር ረገድ የሲቪክ ማህበረሰብ ሚና ግንቦት 7፣ የመገናኛ ብዙኃን የተሳትፎና የሥልጠና ዕድሎች፤ እንዲሁም ዓለም አቀፍ የማዕድን ሀብት አጠቃቀም ግልፅነት ኢኒሼቲቭ ይገኙባቸዋል፡፡

በሀገሪቱ ሕገ መንግሥት መሠረት የኢትዮጵያ መንግሥት መልካም አስተዳደርን ለማጠናከርና የፖለቲካ ብዝሃነትን ለማስፋት እንደሚሠራ ያለውን ቁርጠኝነት የገለጸ ሲሆን፤የአሜሪካ መንግሥትም ግልጽነት በተሞላበት መንገድ የተደረገ ውይይትን የሚደግፍ መሆኑን ገልጾ፤የኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ የመልካም አስተዳደር ተግዳሮቶችን ለመፍታት ለሚያደርጉት ጥረት ሁሉ ተገቢውን ድጋፍ ለመስጠት ቃል ገብቷል፡፡

በመጨረሻም የሁለቱ መንግሥታት ተወካዮች የሚያካሂዷቸው የውይይት ፎረሞች በቀጣይነት መጨመር እንደሚኖርባቸውና ይህም ጥልቅ ውይይቶችን ለማካሄድ ዕድል የሚፈጥር መሆኑን ተስማምተዋል፡፡

###

የወቅታዊ ተግባራዊ ትግል (ወተት) መልዕክት: ጦር ሠራዊት ለለውጥ !!!

$
0
0

ዶ/ር ታደሰ ብሩ የአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር

tadesseህወሓት የጦር ሠራዊትን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል የሚል ስሜት በብዙዎች ውስጥ አለ ብዬ እገምታለሁ። በዚህም ምክንያት ሠራዊቱም “ዝመት” ሲሉት የሚዘምት፤ “ግደል” ሲሉት የሚገል ግዑዝ አካል እንደሆነ አድርገን እንወስዳለን። በዚህ ድምዳሜ ውስጥ የተወሰነ እውነት ቢኖርም ሙሉ በሙሉ እውነት ላይሆን ይችላል የሚል ጥርጣሬ ስላለኝ ይህንን የወተት መልዕክት ላቀርብ ወደድኩ።
እርግጥ ነው የሠራዊቱ ቁልፍ የኃላፊነት ቦታዎች በሙሉ በህወሓት ሰዎች ተይዘዋል። አሁን ያለው የሠራዊት አደረጃጀት ልብ ብሎ ላስተዋለው አስደንጋጭ ነው – ከላይ ሙሉ በሙሉ ህወሓት፤ ከታች ደግሞ ሙሉ በሙሉ ኢ-ህወሓት ነው። [“ህወሓት” እና “ኢ-ህወሓት” ምን ማለት እንደሆነ ለመተንተን ጊዜ ማጥፋት ያለብኝ አይመስለኝም።]
ከአዛዦች መካከል ህወሓት ያልሆነ ማግኘት የሚከብደውን ያህል ከእግረኛ ተዋጊዎች መካከል የህወሓት ሰዎችን ፈልጎ ማግኘት ከባድ ነው። ላስተዋለ ሰው ይህ ብዙ አንደምታ ያለው ሀቅ ነው። በተለምዶ “የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት” እየተባለ የሚጠራው ጦር አዛዥና ታዛዥ፤ አዋጊና ተዋጊ፤ አለቃና ምንዝር እንዲህ ተቃራኒዎች የሆኑበት ስብስብ ነው።
ትንሽ ስሌት እንጨምር። ህወሓት ስለሚመራው ሠራዊት ብዛት የተጋነነ ግምት ያለ ይመስለኛል። ተጨባጭ መረጃዎች እንደሚያሳዩት አሁን ያለው ሠራዊት የሰው ኃይል በአጠቃላይ (አየር ኃይል፣ አግዓዚንና በ UN “ሰላም ማስከበር” ላይ ያሉትን ጨምሮ) ከ 140, 000 አይበልጥም፤ ከዚህ ውስጥ 15% ያህሉ በአስተዳደ ሥራ የተያዙ ናቸው። በዚህም ምክንያት በወታደራዊ ኦፕሬሽን ውስጥ ያለው የሰው ብዛት 119,000 አካባቢ ነው። ከዚህ ውስጥ 12,000 ያህሉ በከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎች የተቀመጡ አዛዦች ናቸው – እነዚህ ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል ሁኔታ የህወሓት ሰዎች ናቸው፤ ቀሪዎቹ 107,000 ኢ-ህወሓት ናቸው። ምጣኔያቸው 1: 9 ነው። [በዚህ ምክንያት ጭምር ነው “የኢትዮጵያ የአገር መከላከያ ሠራዊት” በሚለው መጠሪያ ውስጥ “ሠራዊት” ከሚለው ቃል ውጭ አሁን ያለው ሠራዊት ሊጠራበት አይገባም የሚል እምነት ያለኝ]
ስለ 12,000 ዎቹ በጥቂቱ
ከላይ እንዳልኩት 12,000 ዎቹ ሁሉም ህወሓቶች ናቸው፤ ከዚያም በተጨማሪ ሁሉም ጄኔራሎች አሊያም ባለከፍተኛ ማዕረጎች ናቸው። ምናልባት የ Busisness Administration ወይም የ ባደግ (ILI) Institutional Leadership ዲግሪዎች ይኖራቸው ይሆናል እንጂ በወታደራዊ ሳይንስ የሰለጠኑ የሉባቸውም። የሚያውቁት ጦርነት ዱሮ በልጅነታቸው የተሳተፉበት የጎሬላ ጦርነት ነው፤ ከዚያ ጊዜ ወዲህ ችከሻዎቻቸው በማዕረግ ምልክቶች ቢከብዱም ልቦቻቸው ያሳበጠው ገንዘብ ነው። ስለሠራዊቱ ሳይሆን እየገቡት ስላለው ፎቅና በአክስዮን ስለያዟቸው ቢስነሶች ሲጨነቁ ነው የሚውሉት።
ስለ 107,000 ዎቹ በጥቂቱ
በሠራዊቱ በተዋጊነትና በዝቅተኛ የማዕረግ ደረጃ ላይ የሚገኙ 107,000 ዜጎች “ኢ-ህወሓታዊ” የሚል የጋራ ባህርይ ብቻ ነው ልሰጣቸው የቻልኩት። በኢትዮጵያዊ ሲቪል ዜጋ ላይ ያሉ ልዩነቶች (heterogeneity) እነሱ ላይ አሉ፤ በዘር፣ በሀይማኖት፣ በፓለቲካ አስተሳሰብ … ወዘተ በመከፋፈላቸው በጋራ ለመቆም ተቸግረዋል። እንደ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በህወሓት አገዛዝ ይማረራሉ፤ እንደ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ሥርዓቱ ቢለወጥ ደስተኛ ናቸው። ሆኖም ግን በዚህ ለውጥ ውስጥ የእነሱ ሚና ምን እንደሆነ ገና በትክክል የገባቸው አይመስልም። እንደ አብዛኛው ሲቪል አንጀታቸው እያረረ “እኔ ብቻዬን ምን ማድረግ እችላለሁ” እያሉ የታዘዙትን ይፈጽማሉ፤ ግደሉ ሲባሉ ይገድላሉ።
በዚህ ሁኔታ እስከመቼ ይቀጥላል? የኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት የለውጥ አካል የሚሆነው መቼ ነው? እነዚህና መሰል ጥያቄዎች መሠረታዊ እና ከባድም ናቸው። ትንሽ ለየት ባለ መንገድ ለመመለስ ልሞክር።
የተቋማት ትውስታ
ተቋማት ልክ እንደሰው ትውስታ (memory) አላቸው። የኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት በኢትዮጵያ ፓለቲካ ውስጥ ጉልህ ሚና ያለው መሆኑ በተቋሙ ትውስታ ውስጥ ያለ ነገር ነው። ሠራዊቱ በመረረው ጊዜ ሁሉ ባለስልጣኑን ፈንቅሎ ራሱን ለመሾም ሲሞክር፤ በዚህም ምክንያት የአገራችንን ፓለቲካ በብርቱ ሲወዘውዝ ቆይቷል። ይህ አሁን አይታሰብም ሊባል አይችልም። 12,000 ዎቹ አለቆች ተመሳሳይ ስለሆኑ ሠራዊቱ የረባ የፓለቲካ እንቅስቃሴ ማድረግ አይቻለውም የሚሉ አሉ። እኔ በዚህ አልስማማም፤ የተቋሙ የለውጥ ትውስታም ይህንን አይደግፍም።
ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ያልተሳኩ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራዎች ተደርገዋል። በአዕምሮዬ የሚመጡልኝ ሶስት ዋና ዋና የከሸፉ ሙከራዎች የተመሩት በጄኔራሎች ነበር – የ1953ቱ በጄኔራል መንግስቱ ንዋይ፤ የ1981 በነጄኔራል ፋንታ በላይ፣ መርዕድ ንጉሴና ደምሴ ቡልቶ እና የ 2002 ቱ በነጄኔራል ተፈራ ማሞና አሳምነው ጽጌ። በአንፃሩ፣ የተሳካው እና በኋላ የመንግሥቱ ኃይለማርያምን ደርግ ወደ ሥልጣን ያመጣው የነገሌ ቦረናውና የሀረሩ መፈንቅለ መንግሥት የተመራው በ 10 አለቆች እና በተራ ወታደሮች ነበር። ይህ የአጋጣሚ ጉዳይ ነው ብዬ አላምንም። ይህ እውነታ በተቋሙ ትውስታ (institutional memory) ውስጥ አለ።
የወተት መልዕክት
በሠራዊቱ ውስጥ ያላቸችሁ ወገኖቻችን ዓይኖቻችሁን ገልጣችሁ ዙርያችሁን ተመልከቱ፤ የተቋማችሁን ታሪክ አጥኑ። እናንተ ብዙሀን እና ጥቂቶቹ ህወሓት ሹማምንት 9 ለ 1 ናችሁ ! 9:1 !!!! ለውጥ ለማምጣት ጄኔራል መሆን አያስፈልግም፤ እንዲያውም በጄኔራል ተመርቶ ስኬታማ የሆነ ለውጥ በተቋሙ ታሪክ የለም። ስኬታማ የሆነ መፈንቅለ መንግሥት የተካሄደው በዝቅተኛ ባለማዕረጎችና ተራ ወታደሮች ነበር፤ እሱም ቢሆን መጨረሻው አላማረም።
አሁን ከእነዚህ ሁሉ የተሻለ ማድረግ ይቻላል። ጦር ሠራዊቱ የለውጡ አካል መሆን ይችላል። ጦሩ የተሳተፈበት በዲሞክራሲ ኃይሎች የተመራ ለውጥ እንዲመጣ ማድረግ ይቻላል። ያኔ 107,000 የዛሬ ጦር ሠራዊት አባላት ወገኖቻችን የህወሓቶች ጄኔራሎች የግል አሽከሮች ከመሆን ነፃ ወጥተው የምንኮራባቸው፣ የምንመካባቸው ፕሮፌሽናል የኢትዮጵያ የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ይሆናሉ። ይህ ማድረግ ይቻላል፤ ይሆናልም !!!

በኦሮሚያ እስራቱ መቀጠሉን መድረክ አስታወቀ

$
0
0

Oposition partyየሕዝብ ሰላማዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች በመልካም አስተዳደር ዕጦት ላይ ብቻ ተሳብበውና ተድበስብሰው ሊቀሩ አይገባም ያለው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ)፣ በኦሮሚያ ክልል እስራት ተባብሶ መቀጠሉን አስታወቀ፡፡
መድረክ ይህን ያስታወቀው የፓርቲው አመራሮች ዓርብ መጋቢት 23 ቀን 2008 ዓ.ም. ስድስት ኪሎ አካባቢ በሚገኘው ዋና ጽሕፈት ቤት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ነው፡፡
መልካም አስተዳደር አሳጥተዋል የሚላቸው ባለሥልጣናት ከአንዱ ሥልጣን ወደ ሌላ እየተሸጋሸጉ ናቸው የሚለው የመድረክ መግለጫ፣ ‹‹በሕዝቡ ላይ ወንጀል የፈጸመውን ተኩሶ ገዳይ ኃይልም ሆነ አስተዳደራዊ በደል እየፈጸመ ያለውን ሙሰኛ ለሕግ አቅርቦ ሳያስቀጣ፣ ይቅርታና አጥፍተናል በሚሉ ቃላት መሸንገል ዓላማው የምዕራቡን ለጋሽ አገሮች ቀልብ ለመሳብ ነው፤›› በማለት በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርላማ ይቅርታ እንደሚጠይቁ ያስታወቁበትን ሐሳብ አጣጥሎታል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርላማ መግለጫ ከሰጡ በኋላ፣ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞ ባሰሙ ባላቸው 2,627 የመድረክ አባላትና ደጋፊዎች ላይ በኦሮሚያ ክልል የተፈጸሙ እስራቶችን ዋቢ በማድረግ ተቃውሞውን አሰምቷል፡፡
‹‹ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ዜጎች ከየሥራ ቦታቸውና ከመኖሪያ ቤታቸው በገፍ ታፍሰው አብዛኛዎቹም ቤተሰቦቻቸውና ዘመዶቻቸው በማያውቋቸው አካባቢዎች ተወስደው ታስረዋል፡፡ በአሁኑ ወቅትም የሚገኙበትን ሁኔታ ለማወቅ አስቸጋሪ ሆኗል፤›› በማለት በመግለጫው አትቷል፡፡
‹‹ኢሕአዴግ በአደባባይ ባመነበት ብልሹ አስተዳደሩ ላይ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞአቸውን በማሰማታቸው ምክንያት በግፍ ያሰራቸውን አባሎቻችንና ደጋፊዎቻችን፣ እንዲሁም ሌሎች ሰላማዊ ዜጎች በአስቸኳይ እንዲፈቱ፤›› ሲል ጠይቋል፡፡
‹‹በተጨማሪም በሰላማዊ መንገድ በተቃውሞ እንቅስቃሴ የተሳተፉትን ዜጎች በግፍ የገደሉ በገለልተኛ አጣሪ አካል ተጣርቶ ለፍርድ እንዲቀርቡ፣ እንዲሁም በሕዝቡና በንብረቱ ላይ ለደረሰው ጉዳት መንግሥት ኃላፊነት ወስዶ ለተጎጂዎችና ለቤተሰቦቻቸው ተገቢውን ካሳ እንዲከፍል፤›› በማለት መድረክ ጠይቋል፡፡
‹‹መንግሥት ከመድረክና ከሌሎች ሀቀኛ ፓርቲዎች ጋር የፖለቲካ ምኅዳሩን ነፃ፣ ፍትሐዊና ተዓማኒ ለማድረግ በአስቸኳይ እንዲደራደር በአፅንኦት እንጠይቃለን፤›› በማለት መድረክ በመግለጫው አሳስቧል፡፡

ምንጭ – ሪፖርተር


በዘመነ ወያኔ ዐባይ ቢገደብ የነዳጅ ዘይት ቢገኝ ለሀገራችን በረከት ወይስ መርገም?

$
0
0

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com

ይሄንን ጽሑፍ ለንባብ ያበቃሁት ታች አምና ነው፡፡ በወቅቱ ካነሣኋቸው ነጥቦች አሁንም ጥያቄ እንደሆኑ ያሉ ብዙ ነገሮች አሉና ግድቡ ይጠናቀቃል ተብሎ ተይዞለት በነበረው ጊዜ ገና ሃምሳ በመቶ አጠናቀቅን እያሉ የሚቀልዱበትን ምክንያቶች ሁሉ ትረዱበታላቹህና አንብቡት መልካም ንባብ፡-

ከምርጫ 97ዓ.ም. በኋላ በሀገራችን በርካታ የልማት ሥራዎች ተሠርቷል እየተሠራም ይገኛል፡፡ በአስተውሎት ለማያይ ሰው እነኝህ የልማት ሥራዎች አስደሳችና አጥገቢ ናቸው፡፡ “ላንተስ?” የሚለኝ ቢኖር እውነት ለመናገር እነኝህ የልማት ሥራዎች ለእኔ እያንዳንዳቸው በእየራሳቸው የልማት ሥራ ሳይሆኑ የጥፋት ሥራዎች ናቸው፡፡
Blue Nile 2

ሁለቱን በምሳሌነት ላንሣ፡- ዛሬ ላይ በጥራት ችግር ምክንያት አገልግሎቱን ለደንበኞቹ በቅጡ መከወን አቅቶት ከፍተኛ ችግር ላይ ያለው ኢትዮ ቴሌኮም ደረጃውን ባልጠበቀ የመሣሪያ የጥራት ችግር ምክንያት ለዚህ ዓይነት ችግር እንደሚዳረግ የተረዳ አንድ ኃላፊነት የሚሰማው በዚያው መሥሪያ ቤት በኃላፊነት ደረጃ የነበረ የድርጅቱ ሠራተኛ በቢልዮኖች (በብልፎች) ዶላሮች ልብ በሉ በሚልዮኖች (በአእላፋት) ሳይሆን በቢልዮኖች (በብልፎች) ዶላር በጀት ሥራው እየተሠራ እያለ በሞያውና በኃላፊነቱ ከቻይና መጥተው ሊገጠሙ ያሉ መሣሪያዎች ከተመደበላቸው ወጪ እጅግ የወረደ ጥራት ያላቸውና ከደረጃ በታች በመሆናቸው ችግራቸውን በመግለጥ ለአገልግሎት ሊውሉ ስለማይችሉ ፊርማውን ላለማሥፈር በመቁረጡና በእንቢተኝነቱ በመጽናቱ ለአሳዛኝ ውክቢያ ተዳርጎ በመጨረሻም በገዛ ሀገሩና ሕዝቡ ፊት በቻይኖቹ በጩቤ ተወግቶ መጣሉ ከሥራም መሰናበቱ ሀገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው የአደባባይ ምሥጢር የነበረ ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ጉዳይ በወቅቱ በኅትመት የብዙኃን መገናኛዎች የተዘገበና የዜጎችን ልብ እጅግ ያሳዘነ ተግባር ነበር፡፡

ይህ ኃላፊነት የሚሰማው ዜጋ ጥራታቸው ከደረጃ በታች ነው ልንሠራባቸው አንችልም ያላቸው ዕቃዎች ተገጥመው አገልግሎት እንዲሰጡ ሲደረግ በቴሌ አገልግሎት ላይ ምን ዓይነት የተወሳሰበ ችግርና እጅግ አስቂኝና አስገራሚ እንዲህ ነው ተብሎ ሊገለጽ የማይችል የሞተ አገልግሎት እንደፈጠሩ ሁሉም የሚያውቀው ሀቅ ነው፡፡ ልብ በሉ ይሄንን እርባና የሌለው ሥራ ለማሠራት ግን በትውልደ ትውልድ ተከፍሎ የማያልቅ ዕዳ ሀገር ተዘፍቃለች፡፡ በዚህ ስም የተበደርነው ገንዘብ መበላቱ ብቻ አይደለም ብዙ ሳይጨክኑ ከፊሉን ብቻ በልተውም በተረፈው እርባና ያለው ሥራ ቢሠራበት ምንኛ ዕድለኞች በሆንን ነበር፡፡

ሌላው በመንገዶች ሥራ ላይ ያለው ጉድ ነው፡- በአጋጣሚ የተዋወኩት ሰው ነው በመንግሥት የተመደበ ተቆጣጣሪ መሐንዲስ (supervisor) ሆኖ ይሠራ የነበረ ነው፡፡ ከሥራ የተፈናቀለበትን ምክንያት ሲነግረኝ በሥራ ላይ እያለ ቻይኖቹ ቀኑ አይበቃንም ሌሊትም መሥራት እንፈልጋለንና ይፈቀድልን ብለው ጠይቀው ይፈቀድልቸውና ሌሊትም መሥራት ጀመሩ፡፡ እሱ ግን የሚከፈለው በመደበኛ የሥራ ሰዓት በመሆኑ ሌሊት ተገኝቶ ሥራውን ሊሠራ ወይም ሊቆጣጠር አልቻለም ነበር፡፡
ሥራቸውን መሥራት እንደቀጠሉ አንድ ቀን የቀን ሠራተኞቹ ለዚህ ተቆጣጣሪ መሐንዲስ አንድ ጥብቅ ጉዳይ ሹክ ይሉታል “ይሄውልህ ቻይኖቹ ቀን ያሠርነውን የአርማታ ብረት ሌሊት ሌሊት ግማሹን አስፈትተውን ካወጡት በኋላ ነው የኮንክሪት ሙሊቱን የሚሞሉት” ብለው ይነግሩታል፡፡ አጅሬ ምንም ነገር የሰማ ሳይመስል ጸጥ ብሎ ይቆያል፡፡ ቻይኖቹ ሥራውን እየሠሩ በሠሩት መጠን ሒሳብ እንዲለቀቅላቸው የሚያደርግ አሠራር ስላለ ሒሳባቸውን ለማስለቀቅ በተገቢው መንገድ ለመሠራቱ የተቆጣጣሪው መሐንዲስ ፊርማ አስፈላጊ ነበርና እንዲፈርም ተጠየቀ፡:

አጅሬው ሲጠብቀው የነበረው ጊዜ ይሄ ነበርና ተቋራጮቹን ይዟቸው ሔደና ከድልድዩ መሐል ቆሞ “ጥሩ ፊርማዬን ነው የምትፈልጉት አይደል? ምንም ችግር የለም! ብቻ እዚች ላይ ቴስት ማድረግ (መፈተሽ) እፈልጋለሁና ከልሎ እያሳየ በዚህ ስፋት እዚህ ላይ ቆፍሩልኝ!” አላቸው ቻይኖቹ ደነገጡ፣ ተሸበሩ እንደጉንዳን ወረሩት ለመደራደር ሞከሩ 200,000ብር መደለያ አቀረቡለት አጅሬ ወይ ፍንክች ያባ ቢላዋ ልጅ አለ፡፡ ቻይኖቹም “አይ እንግዲያውስ ምንም አታመጣም! የት እንደምትደርስ ምን እንደምታደርግ እናይሀለን!” አሉት፡፡ ያልሔደበት ይመለከተዋል መፍትሔ ይሰጠዋል ብሎ የገመተው የከፍተኛ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤት አልነበረም፡፡

ጭራሽ አርፎ ካልተቀመጠ በሕይወቱ እንደፈረደ እንዲቆጥረው ዛቻና ማስፈራሪያ ከየአቅጣጫው ይመጣበት ጀመር፡፡ ጭራሽም ከሥራው አውጥተው ጣሉት፡፡ የምላቹህ በትክክል እየገባቹህ ነው? በሙስና ምክንያት መንገዶቹ እየተሠሩ ያሉት ደረጃውን ባልጠበቀ ግብአትና አሠራር ነው እየተሠሩ ያሉት፡፡ በዚህም ምክንያት ነው ይሄ ከዚህ ሳይባል መንገዶቹ ጭራሽም ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ከመሆናቸው በፊት ውኃ ውስጥ እንደገባ ካርቶን ፍርክስክሳቸው የሚወጣው፣ የሚቀበሩት ቱቦዎች ለከፍተኛ መንገድ አይደለም ለመንደር ውስጥ መንገዶች እንኳን በማይበቃ ስፋት ተሠርተው የሚቀበሩትና የክረምቱን ጎርፍ የማሳለፍ አቅም አጥተው ጐርፉ አስፋልቱን አጥለቅልቆ የሚፈሰው፡፡ እነኝህን ብላሽ መንገዶች ለማሠራት ግን ሀገሪቱ በትውልደ ትውልድ ተከፍሎ ሊያልቅ ከማይችል የዕዳ ማጥ ውስጥ እንደተዘፈቀች ከማንም የተሠወረ አይደለም፡፡

የልማት ሥራ እየተባሉ በከፍተኛ ወጪ እየተሠሩ ያሉ ሥራዎች ባለባቸው የተወሳሰቡና በርካታ የጥራት ችግሮች ምክንያት ችግር ሲያጋጥም ያለባቸው ችግር ይቀረፍና እንደገና በጥራት ይሠሩ ቢባል መጀመሪያ ለአጠቃላይ ግንባታ ከጠየቁት ወጪ እጥፍ እንደሚጠይቁና ከብዙ አቅጣጫ ቀድሞውኑ አለመሠራታቸው ይመረጥ እንደነበር ባለሙያዎች አበክረው ይናገራሉ፡፡ በእነዚህ ብላሽ ሥራዎች ሀገርና ሕዝብ ምን ያህል እንደሚጎዱና እየተጎዱ እንደሆነ ለመግለጽ እጅግ ከባድ ነው፡፡

ከኪሳራው በተጨማሪ አስከትለውት የሚመጡት የችግር ዓይነት ዘርፈ ብዙ ነው፡፡ እንግዲህ የዚህ ሁሉ መንስኤው ኃላፊነት የማይሰማው ሀገሬ ሕዝቤ የሚል ቁጭትና ሐሳብ እውስጣቸው በሌላቸው የዘራፊ ቡድን (ወያኔ) የሚሠራ ሥራ መሆኑ ነው፡፡ ከዚህ ቡድን ከዚህ የዘለለ ነገር መጠበቅ የዋህነት ነው፡፡ ይሄ ይሄ ችግር ነው የተሠሩትን ሥራዎች የልማት ሳይሆኑ የትፋት የሚያደርጋቸው፡፡

በመብራት ኃይል መሥሪያ ቤት ዙሪያም ያለው ጉዳይ ከዚህ የከፋ እንጅ የተሻለ አይደለም፡፡ ለማሳያ ያህል እነዚህን ሁለት ባለሙያዎች አነሣን እንጂ በተመሳሳይ ሁኔታ በየ መሥሪያ ቤቱ ችግር ላይ የወደቁና ዜጎችና የተፈጸሙ ችግሮች ቁጥር የትየለሌ ናቸው፡፡ አቶ መለስ ዜናዊ በምን ምክንያት የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ኮርፖሬሽን ዋና ኃላፊን አቶ ምሕረት ደበበን በምን ምክንያት ከኃላፊነታቸው አንሥቶ ምን ሥራ እንደተሠራና የዚያ ውጤትም መብራት ኃይል አገልግሎቱን በብቃት ማቅረብ ሳይችል ቀርቶ በምን ዓይነት የኃይል መቆራረጥ ችግር ከቶን እንደከረመና በቢሊዮን (በብልፍ) ዶላር የሚቆጠር የሀገር ሀብት ፈሶ በሙስና በተገዙት ደረጃቸውን ባልጠበቁ የኃይል ማስተላለፊያዎች (ትራንስፎርመሮች) ወደፊትም ላሳለፍነው ዓይነት ችግር እንደሚዳርጉን፤ በዚህ መሀል ሀገርና ሕዝብ ለከፍተኛ ኪሳራና ችግር እንደተዳረጉና እንደሚዳረጉም በተለይ በአሁኑ ሰዓት የአደባባይ ምሥጢር ነውና ይሄንን መዘርዘር አይጠበቅብኝም፡፡

ወያኔ ዐባይን ለመገደብ የተነሣባቸው ዋና ዋና ምክንያቶች፡-

የሕዝብን የምርጫ ድምፅ ለመንጠቅ፡- ይሄን የምለው ወያኔ ይሄንን ግዙፍ ሥራ የጀመረው በእርግጥም የሕዝብ አቅም ይህን ፕሮጀክት (የሥራ ዐቅድ) ለመፈጸም የሚያስችል መሆኑን አውቆና አምኖ ከሆነና እውነታውም እንደዚያ ከሆነ ነው “ገንዘባችሁ ባለበት በዚያ ልባቹህ አለ” እንዲል መጽሐፍ አቶ መለስ ቦንድ ግዙ እያልኩ የእያንዳንዱን ዜጋ ገንዘብ ከያዝኩበት ለእኔ ሲል ሳይሆን ለራሱ ሲል “ገንዘቤን ይዞብኛል ተበልቶብኝ እንዳይቀር! ሲል፣ የግዱን የእኔን መኖር በሥልጣን መቆየት ይፈልጋል፡፡ ምርጫ ሲመጣ ሳያወላውል ይመርጠኛል በዚህም ዘዴ ቢያንስ ግድቡ ካለቀም በኋላ ገንዘቡ እስኪመለስለት ድረስ ለዐሥርት ዓመታት መቆየት የሚያስችለኝን ዋስትና መጨበጥ እችላለሁ፡፡ ገንዘቡ ጥሩ መያዣ ይሆንልኛል፡፡ ምርጫን ማጭበርበር ሳያስፈልገኝ በቀላሉ ማሸነፍ ያስችለኛል” በሚል ብልጣብልጥ መሰል አስተሳሰብ የሥልጣን ዕድሜን ለማራዘም የተፈጠረች ዘዴ ናት፡፡

እጥረት ወይም ችግር በመፍጠር ዐመፅን ለመቆጣጠር ከሚል የአንባገነኖች ስልት፡- ወያኔ በግድቡ ግንባታ ሰበብ የየወር ደሞዙን በመቆንደድና ሕዝቡን ለችግር በመዳረግ ሀሳቡንና ትኩረቱን በጓዳው ችግር ብቻ እንዲወሰን እንዲጠመድ በማድረግ እሱን (አገዛዙን) እንዲረሳ እንዳያስብ ማድረግ እንደሚቻል በጽኑ ያምናል፡፡ ዋነኛ የአገዛዝ ስልቱም ነው፡፡ ደስ የማይለው አዝማሚያው የማያምረው አንቅስቃሴ በተፈጠረ ቁጥር እጥረት በሌለበት ሁኔታ መብራትና ውኃን ጨምሮ ሰው ሠራሽ እጥረት በመፍጠር መሠረታዊ ፍጆታዎች እንዳይኖሩ እንዲጠፉ ያደርጋል፡፡ የፈራውንም ነገር በቀላሉ ይቆጣጠራል፡፡ ይህ አሠራሩ እስከ አሁን ቢይዝለትም እስከመቼ እንደሚያዘልቀው ግን አላውቅም፡፡ ለማንኛውም ለዐባይ ግድብ እያለ አንደኛ ዙር ሁለተኛ ዙር ሦስተኛ ዙር ገናም ይቀጥላል፡፡ ከሕዝቡ የሚነጥቀው ገንዘብም በዚህ ረገድ እንዳሰበው አድርጎለታል ሕዝቡን በየጓዳው ችግር ለመጥመድ ስላስቻለው ባሰበው መንገድ ለመቆጣጠር አብቅቶታል፡፡

አሥጊ ወቅታዊ የሕዝብ ትኩረትን ለማስቀየስ፡- እንደሚታወሰው የዐባይ ግድብ ፕሮጀክት በድንገት ታውጆ ሥራው በተጀመረበት ወቅት በተለያዩ ሀገራት ሕዝባዊ ዐመፆች እንደ ሰደድ እሳት እየተቀጣጠለና ኢትዮጵያንም እንደሚያሠጋት ይወራ የነበረበት ወቅት እንደመሆኑ መጠን የሕዝብን የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየስና ሕዝብን በመደለል ለዐመፅ እንዳይነሣሣ ለማድረግ ድንገት የተፈጠረ ፕሮጀክት (የሥራ ዐቅድ) ነው፡፡ ለዚህም ነው ይሄንን ለሚያክል ግንባታ ግንባታው ከመጀመሩ በፊት ሊከወኑ የሚገባቸው መሠረታዊ ቅድመ ሁኔታዎች ሒደቶችና ዝግጅቶች ሁሉ ሳይፈጸሙለት ሥራው የተጀመረው፡፡ ለምሳሌ አግባብነት ባለው አካሔድ ግልጽ ጨረታ፣ በእጅ ያለ በጀት፣ ሌላው ቀርቶ የመሠረት ድንጋይ ተጥሎ ሥራ ከተጀመረ በኋላም እንኳን ይሄንን የሚያህል ፕሮጀክት (የሥራ ዐቅድ) በአንዲት መለስተኛ የመቆፈሪያ ማሳልጥ (Excavator Machine) ብቻ ሥራው ከወር በላይ ሲሠራ የነበረው፡፡

ጠያቂን አካል በማስመታት ከተጠያቂነት የማምለጫ መንገድ የመፈለግ ሸር፡-ወያኔ የዐባይን ግድብ ኘሮጀክት (የሥራ ዐቅድ) ይፋ ሲያደርግ ግድቡን ለመሥራት አስቦ አልነበረም፡፡ በነገራችን ላይ ይህ የግድብ ሥራ ይፋ ሲደረግ የደነገጥኩትን ድንጋጤ እኔና እግዚአብሔር ነን የምናውቀው “መቀመጫቹህ ላይ ፈንጅ ቀበርኩባቹህ!” የተባለ ነው የመሰለኝ፡፡ ሀገራችንን ጥቅልል አድርጎ ወደ ገደል የወረወራት ነው መስሎ የተሰማኝ፣ ያለ የሌላትን በዚህ ሰበብ ጠራርገው ሲበሉት ቀልጦ መና ሆኖ ሲቀር ነው የታየኝ፡፡

ከዚህ ሐሳብ ጀርባ ሊኖሩ የሚችሉ ነገሮች ወዲያው ነበር ይታዩኝ የጀመሩት “አይ! በቃ ወያኔ ሰለቸች ታከተች ማለት ነው፣ የሚገላግላትን ነገር ፈለገች ማለት ነው” ነበር ያልኩት፡፡ ምክንያቱም ዐባይን በተመለከተ የሚሰሙ ምንም ዓይነት ሹክሹክታዎችን ግብጽ እንደማትታገስ አቶ መለስ ስለሚያውቁ በጠባብነት ፖለቲካቸው (እምነተ አሥተዳደራቸው) ታንቀው በሚዘውሩት አገዛዛቸው ቢሉት ቢሉት አልሆን ስላላቸው፣ የራሳቸውን የንግድ ድርጅቶችና የተሟሳኝ ባለሀብቶችን ዕድገት የሀገር በማስመሰል ደላላ (ሎቢ) እየገዙ የሚያሥወሩት የውሸት የሀገር እድገት የትም እንደማያደርሳቸው ስላወቁና ተስፋም ስለቆረጡ፣ የሌለን ነገር ያለ ለማስመሰል የቻሉትን ሁሉ ቢያደርጉም ገሀዳዊው እውነታ ድንገት ተገልጦ መዋጣቸው አይቀሬ መሆኑን ስለተረዱና በሌላ አማራጭ ሥልጣን ከለቀቁም የሚከተላቸውን የሚያጋጥማቸውን ያውቃሉና ይሄንን አስልተው ከዚህ ሁሉ ጣጣ ሊድኑ የሚችሉበትን ዕድል ሲያፈላልጉ የተከሰተላቸው መላ ነው፡፡

በእኔ እምነት የዐባይን ግድብ ግንባታ የወለደው ይሄ “የእኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” አስተሳሰብ ነው እንጅ ወያኔ ብሔራዊ ሐሳብ ማሰብ ችሎ የተተለመ ትልም አይደለም፡፡ ሰብእናውና ተሞክሮው ይሄን አያሳይምና አያረጋግጥምና፡፡ ነገር ግን የሚያሳዝነው ነገር በአጋጣሚ ሆኖ ግብጽ በራሷ ችግር ተመሰቃቅላ ከመጠመዷ ጋር ተያይዞ አቶ መለስ በግልጽ ግብጾችን በዓለም አቀፍ የብዙኃን መገናኛ “ወንድ ከሆናቹህ ኑ እንዋጋ!” እያሉ የጦርነት ግብዣ ቢያቀርቡም ግብጽ ልታርገው አልቻለችም፡፡ አቶ መለስ ጉዳቸው ፈላ ተጋለጡ፡፡ ያሰቡት ቀርቶ ያላሰቡት ሆነ “አይ እግዚአብሔር ደጉ!” አቶ መለስ ባላሰቡት የልማት ሥራ እንደተጠመዱ ጭንቅላታቸው ፈንድቶ አለፉ፡፡

ግንባታው እስከ አሁን ባለው ሒደት በገንዘብ እጥርት ምክንያት በጣም ተጓቷል፡፡ በተያዘለት የጊዜ ቀጠሮ መሠረት በዚህ ወቅት 60% ያህሉ መጠናቀቅ ነበረበት፡፡ የተጠናቀቀው ግን መጠናቀቅ ከነበረበት ከግማሹ የሚበልጥ አይደለም፡፡ ቀጣዩ ወቅት ትኩረት የሚስብና ልብ አንጠልጣይ ነው፡፡ ከሀገሪቱ ካዝና የለም የተባለው ገንዘብ ከየት እንደሚመጣ እግዚአብሔር ይወቀው፡፡ ብድር አልተገኘም አስቀድሞም ይገኛል ተብሎ ተስፋ አልተደረገም፡፡

በጃንሆይና በደርግ የነበረው እንቅፋት ዛሬም አለና፡፡ በቀደም ከሕዳሴው ግድብ ሦስተኛ ዓመት ክብረ በዓል አዘጋጅ ኮሚቴ እንደሰማነው እስከ አሁን 34% ቢሊዮን ብር ማለትም ለግንባታው ያስፈልጋል ከተባለው ወደ ግማሽ የሚጠጋ ወጪ እንደተደረገ እየተናገሩ ነው፡፡ አንድ ሦስተኛ ለማይሞላ ክንውን ይህንን ያህል ወጣ ማለት ግድቡን ለመጨረስ ለማጠናቀቅ ከ 113 ቢልዬን (ብልፍ) ብር በላይ የግድ ያስፈልጋል ማለት ነው፡፡

አሁን በያዙት ፍጥነት ከቀጠለ ግድቡን ለማጠናቀቅም 10 ዓመታት ይወስዳል ማለት ነው፡፡ እሱም ገንዘቡ ከተገኘ ነው፡፡ ሳያስቡት የተጠመዱበትን ነገር ከመፈጸም ውጭ አማራጭ የለም ብለው ከተመዘበረው የሀገሪቱ ገንዘብ ጥቂቷን አምጥተው ሥራውን ለማጠናቀቅ ካሰቡ ምናልባት ግድቡ ይፈጸም ይሆናል፡፡ ይህ ዕድል ከሌለ ግን ኳሷን ወደ ሕዝቡ እግር በመምታት ማስተባበርና በግድም በውድም ከጎናቸው ማሰለፍ የቻሉት የሕዝብ አቅም የታየውን ያህል እንደሆነና የማያወላዳ አለመሆኑን እያውቁ ሕዝቡን “ግድቡ ማለቅ ካለበት አውጡ አናወጣም! የለንም! አንችልም! ካላቹህ ግን ሥራው መቆሙ ነው!” ውሳኔው የናንተ ነው በማለት ኃላፊነቱን ከራሳቸው ለማውረድ እንደሚሞክሩ እገምታለሁ፡፡

አቶ ኃይለማርያም ባላቸው መረጃ ደግሞ ከላይ በኮሚቴው ከተጠቀሰው በ7 ቢሊዮብ ወርዶ ለእስካሁኑ ክንውን 27 ቢሊዬን (ብልፍ) ያህል ብር ወጪ ሆኗል ብለውናል፡፡ በዚህም መሠረትም ለማጠናቀቅ ከ90 ቢሊዬን (ብልፍ) ብር በላይ ያስፈልጋል ማለት ነው፡፡

የዐባይ ግድብ በሕወሓት ኢሕአዴግ መገደቡ ተገቢ የማይሆንበት ወይም አደገኛ መሆኑን የሚያረጋግጡ ነጥቦች፡- ጠላት ካልሆነ በስተቀር ጤነኛ አእምሮ ያለው ዜጋ ሁሉ የዐባይን መገደብ የማይፈልግ ይኖራል ብዬ አልገምትም አይኖርምም፡፡ እንዲያውም ዐባይ መገደብ ከነበረበት ዘመን በጣም ዘግይቷል፡፡ ግብጽ የምትፈጥረው እንቅፋት እየተሳካላት ቀደማዊ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ዐባይን ለመገደብ የሚያስችል ብድር አጥተው ዐባይን የመገደብ ሕልማቸው ሳይሳካ ቀረ፡፡ በደርግም ዘመን እንዲሁ ተጨማሪ የሀገር ውስጥ ሰላም እጦት ወይም የእርስ በእርስ ጦርነት እንቅፋት ሆኖበት ደርግም ሳያሳካው ቀረ፡፡ ከዚህ የእርስ በእርስ ጦርነት ጀርባ የግብጽና የሱዳን ሙሉ እጅ እንደነበረበት ይታወቃል፡፡

የግብጽንና የሱዳንን ድጋፍ ያገኘ በነበረው በሕወሓት ኢሕአዴግ ዘመን ግን እንኳን ዐባይን ስለመገደብ ሊያስብ ይቅርና በግብጽ ትእዛዝ መሠረት ደርግ ከፍተኛ ወጪ መድቦለት ሥራው ተጀምሮ በመቀጠል ላይ የነበረውን የጣና በለስን ፕሮጀክት እንዲዘጋ አድርጎት ነበር፡፡ ወያኔ ይህ አድራጎቱ ስሕተት እንደሆነ ለመረዳት የአንድ ታዳጊ ወጣት ዕድሜ አስፈልጎት ነበር፡፡ የደርግ መውደቅንና የወያኔን ሥልጣን መያዘ ተከትሎ በደርግ ዘመን በእንግሊዝ ሐሳብ አቅራቢነት የላይኞቹ የዐባይ ተፋሰስ ሀገራት የውኃ ድርሻ እንዲኖራቸው ያቀረበችው ሓሳብ ግብጽ “ያለው የውኃ መጠን ሳይታወቅ እይሆንም!” ብላ በመቃወሟ ይሄንን ጉዳይ የሚያጠና ቡድን ተቋቁሞ እየተደረገ የነበረው ጥናትና ድርድር ሳይቋጭ ደርግ በመውደቁ ተቋርጦ ወያኔም ቅጥረኛነቱና አገልጋይነቱ ገና አፍላ ነበርና ይህ ድርድር እንዲቀጥል ፍላጎት ስላለነበረው እንደተቋረጠ ቀይቶ ነበር፡፡

ከጃንሆይ ጀምሮ እስከ ደርግ ሲጠና ሲከለስ ሲጠና ሲከለስ የቆየውና በደርግ ዘመን ተነቃቅተው የነበሩት ዐባይን መሠረት ያደረጉ ፕሮጀክቶችም (የሥራ ዐቅዶች) ውኃ ተቸልሶባቸው ተዳፍነው ለመቆየት ግድ ሆኖ ነበር፡፡ ይህ ወቅት ለግብጽና ሱዳን የእፎይታ ዘመን ነበር፡፡ ወደ ኋላ ላይ አዲስ አበባ ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት ስብሰባ ሲመጡ በግብጹ መሪ ሆስኒ ሙባረክ የግድያ ሙከራ በመደረጉ ሳቢያ የሦስቱ ሀገራት ግንኙነት መሻከሩን ተከትሎ ወያኔ እንደ ማስፈራሪያ አድርጎት አዳፍኖት የነበረውን ዐባይን መሠረት ያደረጉ የሥራ ዐቅዶችን በብዙኃን መገናኛ በአለፍ ገደም ማሳየትና ማሰማት ጀመረ፡፡
በተጨማሪም አንገብጋቢ እየሆነ የመጣው የሀገሪቱ የኃይል ፍላጎት ጥያቄ ማሟላቱ ግዴታ ሲሆን የተቀያየሙት ወዳጆቹ ስለነሱ ሲል በዐባይ ላይ ምንም ዐይነት ፕሮጀክት ላለማሰብ ሥልጣን በያዘ ማግሥት ግብጽ ድረስ በመሔድ ቃል ገብቶ የነበረውን ለማጠፍ ቅያሜው ጥሩ አጋጣሚ ፈጥሮለት በደርግ ተጀምሮ የነበረውንና ሽሮት የነበረውን የጣና በለስን ፕሮጀክት ካዳፈነበት በመቀስቀስ ሥራው ተጠናቆ ከ 4ዓመታት በፊት ሥራ መጀመሩ ይታወሳል፡፡

ይህም ጉዳይ በግብጽና በሱዳን ቅሬታ አሳድሮ የተግባቡት ቃል እንዲፈርስ ጥሩ ተጨማሪ ሰበብ ሆነ፡፡ አሁን እንደምናየውም ከ 50 ዓመታት በፊት ጀምሮ ሲታሰብ የነበረው የዐባይን ግድብ እውነት የሚገነባ መስሎ እራሱ ለሚያውቀው ዓላማ ማለትም የመገላገያ ሰብብ ለመፍጠር አስቦ የጀመረው እስከአሁን እንደምናየው ከሆነ እየሆነ ያለው ያሰበው ሳይሆን ያላሰበው ነው፡፡
የዚህ ግድብ እውንነት በጃንሆይ ዘመን እንደታቀደው ተከውኖ ቢሆን ኖሮ የሀገራችንና የሕዝባችን ገጽታ ምንኛ የተቀየረ በሆነ ነበር፡፡ በዓለም አቀፍ ኅብረተሰብ ዘንድም መታወቂያችን የሆነው የ1977ቱ ዓ.ም ድርቅና ረሀብም ባልተከሰተ ነበር፡፡ ከዚያም በኋላ ለዚህ አሳፋሪ አዋራጅና ቅስም ሰባሪ ድህነት ባልተጋለጥን ነበር፡፡ በመሆኑም የዚህ ግድብ የመገደቢያ ትክክለኛ ሰዓት ቀዳማዊ ዐፄ ኃይለሥላሴ ዐባይን ለመገደብ ያቀዱበት ያ ጊዜ ነበር፡፡ አልሆነም አልተሳካም፡፡ ይህ የዐባይ ግድብ በሕወሓት ኢሕአዴግ ዘመንና በዚህ ወቅት መገደቡ ተገቢ ጠቃሚ እንዳይሆን የሚያደርጉት ስድስት ዋና ዋና ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፡-

ቀደም ሲል መግቢያዬ ላይ ካየናቸው ባለ ቢሊዮን(ብልፍ) ዶላር በጀት (የገንዘብ ምድብ) የወያኔ የልማት ሥራዎች ተሞክሮ እንዳየነው አሳሳቢና አደገኛ የጥራት ችግር ነው፡- ይሄንን ይሄንን የሚያካክል የግንባታ ሥራ በወያኔ የነቀዘ ትከሻና ክንድ፣ የተመረዘ ጭንቅላት በጥራት ይሠራል ብሎ ማሰብ እጅግ እጅግ ሲበዛ የዋህነት ነው፡፡ የቀደመው ተሞክሮው በሙሉ የሚያሳየው ይሄንን ነውና፡፡ እምነት እንድንጥልበት የሚያደርጉ አይደሉምና፡፡ የለብ ለብ እና የማታለል የዚያችው የዕለቷን ምስጋናን ማግኘት ብቻ ታሳቢ ያደረጉ ብላሽ ሥራዎች ናቸው፡፡

ወያኔ ሁሌም ሲያስብ ዛሬን እንደምንም ብሎ ማለፉን ነው እንጂ ስለ ነገ አያስብም አይጨነቅም፡፡ በዚህ ምክንያት ነው ሥራዎቹ ከባባድና ከፍተኛ የጥራት ችግሮችን እንዲያስተናግዱ የተገደዱት፡፡ እሱም አባይ ውሸታም አጭበርባሪ የሆነው፡፡ ውሸቱ እብለቱ እንደ ውሸትነቱ እንደ እብለትነቱ ሁሉ በተጋለጠ ጊዜ “ያኔ ምን ይውጠኛል!” ብሎ ፈጽሞ አያስብም አይጨነቅም፡፡ “አይነጋ መስሏት ከቆጡ ላይ ምን አለች” የሚለው ብሂላችን ወያኔን አንድም ቀን ገብቶት አስፈርቶት አያውቅም፡፡ እንዲህ ዓይነት አስተሳሰብ (mentality) ባለው ግለሰብም በሉት ቡድን ጥራት ከነ አካቴው ቦታ አይሰጠውም፡፡ ስለሆነም የጥራት ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ ስለሆነ፡፡

2. አቶ መለስ እንዳስታወቁት ይህ ግንባታ ሙሉ ለሙሉ በሕዝቡ አቅም ይገነባል በማለታቸውና የሕዝቡ አቅም የምናየውን ያህል መሆኑ፡፡ በነገራችን ላይ ሕዝቡ ይህ የልማት ሥራ ግብዣ የቀረበለት በማያምነውና በክፉ ነገር ሁሉ በቁጥር አንድ በሚጠረጥረው በወያኔ በመሆኑ እንጅ ኢትዮጵያዊ በሆነና የሕዝብ ፍቅር ባለው መንግሥት ቢቀርብለት ኖሮ ይሄንን አይደለም ሌላም ቢጨመር በስኬት ለመደምደም መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይቅርና ከሀገር ውጭ ያሉ ልጆቹ አቅም ብቻ ከበቂ በላይ በሆነ ነበር፡፡ የሀገሪቱ ካዝናም ቢሆን እዚህ ድረስ ባላሳበቀ ባላሳጣ ነበር፡፡ እናም ሀገርም ሕዝብም አቅም አልባ የሆኑት መሐንዲሱ ታማኙ ተወዳጁ ተፈቃሪው ወያኔ ስለሆነ ብቻ ነው፡፡ ሕዝቡ እንደምታውቁት ይሄንን ያህል ወገቡ ተሠብሮ አዋጥቶም ከሚፈለገው ዐሥር በመቶ እንኳን አልተገኘም፡፡ ይህ ሁኔታ ከመከሰቱ በፊት ሕዝቡ ለወያኔ ያለው መነሣሣትና እምነት ይታወቅ ስለነበረ ጊዜው አለመሆኑን መረዳት ከባድ አልነበረም፡-

3.ሙስና፡- ወያኔ ሙስናን አንዱና ዋናው የአሥተዳደር ሥርዓቱ የህልውና ስልት (strategy) አድርጎ የሚጠቀም ምናልባትም የዓለማችን ብቸኛ “መንግሥት” ነው፡፡ እያልኩ ያለሁት ሙስና የሚፈጽም አይደለም፡፡ አይፈጽምም ማለቴ አይደለም ሀገራችን ዐይታው የማታውቀው ሙሰኛ መንግሥት እንደሆነ ይታወቃልና፡፡ እኔ እያልኩ ያለሁት ወያኔ ዜጎችን የዘለዓለሙ ባሪያው አገልጋዮቹ እንዲሆኑ ተሽቆጥቁጠው እንዲገዙለት እንዲታዘዙለት ሲያስብ ሲፈልግ ሆን ብሎ ሙስና ውስጥ እንዲገቡ ያደርጋል፡፡

ከዚያ በኋላ ያችን ይይዝና በማስፈራሪያነት እየተጠቀመ ያንን ዜጋ እንደፈለገ አድርጎ የሕሊና ጥያቄ እንዳያነሣ የታዘዘውን ብቻ እንዲሠራ አድርጎ ይገዛዋል፡፡ ለወያኔ እንደ ሙስና ዋና ጠቃሚ መሣሪያ የለም፡፡ እንዲህ ዓይነት የወደቀ የዘቀጠ አስተሳሰብ አመለካከት የያዘ ቡድን እንዲህ ዓይነቱን ግዙፍ የልማት ሥራ በጥራትና በብቃት መሥራት አይደለም ማሰብም እንኳን ከቶውንም አይችልም፡፡

በዚህ ግድብ ዙሪያ የሚነሡ በርካታ የሙስና ጉዳዮች አሉ፡፡ የግድቡ ሥራ ግልጽ ጨረታ አልወጣበትም፣ የግብአት አቅራቢ ድርጅቶችን በተመለከተ ግልጽና የተለያዩ የሙስና መገለጫ ገጽታዎች በሰፊው እየታየበት ይገኛል፡፡ በመንግሥታቱ ድርጅት መረጃ መሠረት በወያኔ ዘመን 25 ቢሊዮን ዶላር ከሀገሪቱ እንደተመዘበረ ተነግሯል፡፡ ይህ ገንዘብ አንድ ብቻ አይደለም ከ5 በላይ የዐባይ ግድብ ሊገነባ የሚችል የሕዝብ የሀገር ሀብት ነው፡፡ እናም ሙሰኝነቱም ሌላው ዋነኛ ችግር ነው፡፡
የወያኔ ወያኔያዊ ባሕርይ ፡- ማለትም “ጠባብነቱ” ወያኔ በተፈጥሮው ጠባብ ነው ጎጠኛ ነው ብሔራዊ (ሀገር አቀፍ) አስተሳሰብን ሽታውንም አያውቀው፡፡ ኃላፊነት የማይሰማው ሀገሬ ሕዝቤ የሚል ሥዕል ከጭንቅላታቸው ውስጥ በሌለ ቡድን ጭንቅላት ውስጥ ከጎጥ አጥር ውስጥ ወጥቶ ከልብ (genuinely) ሀገርንና ሕዝብን ታሳቢ አድርጎ ብሔራዊ የልማት ሥራ ሊታሰብ ስለማይችል፡፡

በመሆኑም ወያኔ እንዲህ ዓይነት ግዙፍ የልማት ሥራ (mega project) አቅዶ በብቃት የመሥራት የሞራል (የቅስም) ብቃት አይኖረውም፡፡ ቅስምን ያህል ኃያል አቅም ሳይይዝ የሚሠሩ ሥራዎች ሁሉ እንደ እንቧይ ካብ ናቸው፡፡ ወያኔ የማይድን በሽታ አለበት “የጎጠኝነት ነቀርሳ” ይህ በሽታው ከጎሳው በላይ የሆነ ሐሳብ ሊያሳስበው አይችልም፡፡ ለዚህም ነው ዛሬም ከ23ዓመታት በኋላ ይሄ በሽታው ከጎንደር፣ ከወሎ፣ ከአፋር ሌላ ተጨማሪ መሬቶችን ወደትግራይ እንዲከልል ያደረገውና እያደረገው ያለው፡፡ ለምን ይምስላቹሀል? ምንስ እያሰበ? ያለ ዓላማ እንዲህ የሚያደርግ ይመስላቹሀል?

ታዲያ በእንደዚህ ዓይነት ጠባብና ጎጠኛ ጭንቅላት ላይ ነው ኢትዮጵያ እንደ ኢትየጵያነቷ ታስባ እሷንና ሐዝቧን ተጠቃሚ የሚያደርግ በብቃትና በጥራት ግዙፍ የልማት ሥራ የሚታለመው? በሽታው በየት በኩል አሳልፎት? በነገራችን ላይ ከዚህ ከጠባብነት በሽታው ሳልወጣ ወያኔ ለትግሬም ሕዝብ ቢሆን አሳቢ ተቆርቋሪ እንዳልሆነ ታውቃላቹህ? ጠቀምኩ ብሎ የሚያደርገው የሚሠራው ሥራ ሁሉ ከወያኔ “መንግሥት” ህልፈት በኋላ የትግሬ ሕዝብ ከተለያዬ አቅጣጫ ለችግር ለፈተና ለበቀል እርምጃ የሚዳርጉ ናቸውና፡፡ ወያኔ ለትግሬ ሕዝብ አሳቢ ነው ተቆርቋሪ ነው ልለው እችል የነበረው ወያኔ ኖረም አልኖረ መቸም ጊዜ ቢሆን የትግሬ ሕዝብ ከተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር በፍቅር በሰላም በመተሳሰብ መኖር የሚችልበትን ሁኔታ ቢፈጥር ኖሮ ነበር፡፡

አስተዋይነት ብልህነት አርቆ ማሰብ መሪነት ማለት ይሄ ነው፡፡ ወያኔ ግን እየኖረ ያለው በ21ኛው መቶ ክ/ዘ ይሁን እንጅ ሥራውና አስተሳሰቡ ግን ገና የድንጋይ ዘመን አስተሳሰብ ነው፡፡ ስለሆነም ወያኔ ለማን እንደሚሠራና ምን እንደሚሠራ እንኳን የማያውቅ ፍጥረት ነው፡፡ “መንግሥት” ከሆነ በኋላ ኃላፊነቱ ለሁሉም እኩል መሆኑን መቀበል ተቸግሮ ሕዝቡን እየለየ ይሄ ሕዝቤ ይሄ ጠላቴ እያለ አንድን ብሔረሰብ በጠላትነት የፈረጀ በተቻለውም መጠን ለማጥፋት የሚጥር፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ በዘርና በሐይማኖት ከፋፍሎ ለማባላት ለማፋጀት ለማስተላለቅ የሚጥር መሠሪና ክፉ አገዛዝ የኢትዮጵያን ሕዝብ ተጠቃሚ ሊያደርግ የሚያስችልን ሥራ ሊሠራ አይችልም፡፡

አቶ መለስ ምን ሲሉ እንደነበር አታስታውሱም? “አንዲት ግራም ጉልበት እስክትቀረኝ ድረስ ድርጅቴን አገለግላለሁ!” ልብ በሉ ሀገሬን አይደለም ያሉት “ድርጅቴን” ነበር ያሉት፡፡ ለነገሩማ በትክክልም ያገለግሉና ያስጠብቁት የነበሩት የሀገርንና የሕዝብን ጥቅም ሳይሆን የድርጅታቸውንና ድርጅታቸው የቆመለትን የጎሳቸውን ጥቅም በመሆኑ ሀገሬን አለማለታቸው ትክክል ነው፡፡

በዚህ መርሐቸው ሳቢያ የቱንም ያህል ለሀገር የሚጠቅምና የሚበጅ ነገር ግን ለድርጅታቸው የማይበጅና የማይጠቅም ጉዳይ ቢኖር ጥንቅር ይላል እንጂ አይ የሀገር ጥቅም ይበልጣል ይቀድማል ብለው ለሀገር ከበጀ ይሁን አይሉም፡፡ የአስተሳሰባቸው መሠረት “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” እንዳለችው እንስሳ ነውና፡፡ በአንጻሩ ደግሞ ሀገርን የማይጠቅምና የሚጎዳ ነገር ግን ድርጅቱን የሚጠቅም ቢሆን ሀገርን ሽ ጊዜ ይጉዳ እንጅ የድርጅቱ ጥቅም ቅንጣት ታክል እንኳ እንድትቀር አይፈልጉም፡፡ በዚህ ምክንያት ሀገረችን ቢዘረዘሩ የማያልቁ ብዙ አጥታ ብዙ ተጎድታለች አንዳንዶቹ ለመቸውም መልሰን ልናገኛቸው የማንችላቸው ናቸው፡፡

የጦር ኃይል አቅም ውስንነት፡- ግብጽ አሁን ለጊዜው ኃይል መጠቀም አልፈለገችም ማለት በቃ! ትታለች ማለት አይመስለኝም፡፡ ጦር ልታነሣ የምትችልበት ሥጋት ሰፊ ነው፡፡ ጦር የምታነሣበት አጋጣሚ ቢፈጠር ከወታደራዊ ትጥቋ አንጻር መመከት የሚያስችለን ተመጣጣኝ የትጥቅ ዝግጅት ሊኖረን የግድ የተገባ መሆን ነበረበት፡፡ ይሄንን የቤት ሥራ ማጠናቀቅ የቻለ መንግሥት ሲኖረን ግብጽም ራሷ ትንፍሽ ሳትል ግንባታችንን መፈጸም የምንችልበትን ሁኔታ ማረጋገጥ እንችላለን፡፡ ይህ ጉዳይ ለኔ ምሥጢር ሊሆን ይችላል፡፡ ለእንደዚህ ዓይነት ጉዳዮች ቅርብ ለሆኑ ተቋማት ግን አይመስለኝም፡፡

በቅርቡ V.O.A. “ግሎባል ፋየር ፓወር” የተባለን ድረ ገጽ ጠቅሶ እንደገለጸው ግብጽ ባላት ትጥቅና ወታደራዊ ዝግጅት ወይም አቅም ከዓለም 13ኛ ስትሆን ሀገራችን ደግሞ 40ኛ ናት ብሏታል፡፡ እንደነሱ ትንታኔ የግብጽና የእኛ ወታደራዊ ትጥቅ አቅም ጨርሶ የማይመጣጠን እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ከዚህ አንፃር ጥቃት ቢሰነዘርብን በብቃት ልንወጣው በማንችልበት ሁኔታ ዐባይን ለመገደብ መሞከር አስቀድሜ እንደገለጽኩት መደፍጠጣችን ተፈልጎ ካልሆነ በስተቀር ፍጹም ተገቢ ያልሆነና ያልበሰለ ውሳኔ ነው፡፡ “ስለሆነም ወጡ ሳይወጠወጥ ወስከንቢያው ቁጢጥ” በመሆኑ ወይም “ከፈረሱ ጋሪው” በመቅደሙ፡፡

ይህ ግድብ እንዲያው ብሎለት ከእነኝህ አሳሳቢ ችግሮቹ ጋር በዚያም በዚህም ተብሎ ቢጠናቀቅና እየተናገሩ እንዳሉት ሁሉ የሚመነጨውን ኃይል ለሀገር ውስጥ ለገበሬው ሳይሆን ለውጭ ገበያ አቅርበው፤ መቼም አሁን ለጅቡቲና ለሱዳን እየተሸጠ ያለው ከእኛ ተርፎ ነው የሚለኝ እንደማይኖር ተስፋ አደርጋለሁ እንኳን መብራት የሌላቸው አከባቢዎች መብራት ሊያገኙ ይቅርና አዲስ አበባን ጨምሮ የከተሞችን መብራት በማጥፋት ጭምር እንደሆነ ሁሉ ለጅቡቲና ለሱዳን እየተሸጠ ያለው ከዐባይ ግደብ የሚገኘው ኃይልም ለሀገር ውስጥ ፍጆታ ይውላል ተብሎ አይጠበቅም ለነገሩ እነሱም አላሉም፡፡ ከወዲሁም ውል እየፈጸሙ ቸብችበው ጨርሰውታል፡፡ እናም ከዚህ ግድብ የሚመነጨውንም ኃይል ለውጭ ገበያ በማዋል ጠቀም ያለ የውጭ ምንዛሬ የሚገኝበት ቢሆን የሚጠቅመው የሚያፈረጥመው የወያኔን ጡንቻ እንጅ ሀገርን ባለመሆኑ፡-

ወያኔ በሀገር ውስጥ የኃይል እጥረት እየፈጠረ የሀገር ውስጥ የኃይል ፍላጎትን እያስተጓጎለ ለጅቡቲና ለሱዳን በመሸጥ የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት የሚጥረው በመብራት ኃይል መቆራረጥና መስተጓጎል ምክንያት በፋብሪካዎች፣ በድርጅቶች፣ በሕክምና ማዕከላት፣ በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት እየደረሰ ያለው የሀገር ኪሳራና ጉዳት ለጅቡቲና ለሱዳን ተሸጦ ከሚገኘው አነስተኛ የውጭ ምንዛሬ እጅግ ብዙ ጊዜ እጥፍ እንደሚበልጥና እንደሚያስጎዳ ስለማያውቅ ስላልገባው አይደለም፡፡ ነገር ግን እንደ አገዛዙ አቋምና አስተሳሰብ የቱንም ያህል ሀገርንና ሕዝብን የሚጎዳ ቢሆን የአገዛዝ ቡድኑን ግን የሚጠቅም ከሆነ የማያደርጉት ነገር ስለሌለና ስለማይኖርም ነው፡፡

የሀገርና የሕዝብ ጉዳት ጉዳታቸው ስላልሆነ ነው፡፡ የሀገርና የሕዝብ ጥቅም ከእነሱ ጥቅም ጋር የማይጣጣምበት ወቅትና ሁሌታ ስላለ ነው፡፡ ወያኔነታቸው የሀገርንና የሕዝብን ጥቅም ከቡድኑ ጥቅም አስበልጠው አስቀድመው እንዲያዩ እንዲያስተናግዱ ፈጽሞ ስለማይፈቅድላቸው ነው፡፡ እናም አንድ ዐባይ አይደለም ዐሥር ዐባይ ቢገነባ ተጠቃሚው አገዛዙና ግብረአበሮቹ እንጅ ሀገርና ሕዝብ ሊሆኑ የሚችሉበት ዕድል የለም፡፡

ከዚህም ጋር በተያያዘ ለምሳሌ የነዳጅ ዘይት በሀገራችን ቢገኝና ወያኔ ፔትሮ ዶላር (የዘይት ገንዘብ) ማፈስ ቢችል ምን ሊፈጠር እንደሚችል አስባቹህት ታውቃላቹህ? “ሰብአዊ መብት ካላከበርክ” ከሚል ሊሰማው ከማይፈልገው ቅድመ ሁኔታ ጋር በሚሰጠው የእርዳታና የብድር ገንዘብ ይሄንን ያህል መፈናፈኛ መላወሻ አሳጥቶ የደቆሰን፣ የረገጠን፣ ያሰቃየን፣ የጨቆነን በአፍጢማችን ሊደፋን የተቃረበ አገዛዝ ማንም የማያዝበትን፣ ቅድመ ሁኔታ የሌለበትን፣ ለዚህ ለዚህ ጉዳይ ብቻ ሳይባል እንደፈለገ የሚያደርገውን የራሱን የካበተ ገቢ ያገኘ ጊዜ ምን ሊያደርገን እንደሚችል አስባቹህታል? ምናችንን ያስተርፍልናል? ዕኩይና እርኩም ዐቅዶቹን ሁሉ በእኛ ላይ ለመፈጸም ዕድል ያገኛል ያጠፋሀልም እንጅ አንተ ተጠቃሚ አትሆንም፡፡

እስከዛሬም እኮ የጭካኔውን የሐሳቡን የምኞቱን ያህል ሊያደርግብን ያልቻለው አቅም ገድቦት ነው፡፡ አቅም ሲያገኝስ? ያኔማ “እነሱን አያርገኝ!” ነዋ የሚለው! የነዳጅ ዘይት ለናይጄሪያ ምስኪን ሕዝብ ምን የተከረለት ነገር አለ? በድህነት ከመማቀቅ ፈቀቅ አደረገው ወይ? ጄኔራሎቹን ከማድለብ በስተቀር፡፡ ወያኔ ደግሞ ከናይጄሪያ መንግሥት ምን ያህል የከፋና መሠሪ ዕኩይ እርጉም እንደሆነ የምታውቁት ነገር ነው፡፡ እነ ኤፈርትንና የግል ኪሳቸውን ነበር የሚያደልቡበት እንጅ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንደሆነ ጠብ የሚልለት እንዲት ነገር አይኖርም፡፡

እናም ነዳጅ በወያኔ ዘመን አንዲገኝ የምትፈልጉ የምትመኙ የምትሳሉ ወገኖች ካላቹህ የዮፍታሔን ስእለት (መጽሐፈ መሳፍ. 11፤30-40) እየተሳላችሁ ነውና ወዮ ለራሳቹህ! ኢትዮጵያዊ የሆነ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ያማከለ የሕዝብ ፍቅር ያለው፣ ተጠያቂነት የሚሰማው፣ ግልጽነት ያለው መንግሥት ሲኖረን ቢወጣ ግን የእያንዳንዷ የዘይት ነጠብጣብ ዋጋ በእያንዳንዱ ደሀ ገበሬ ታርፋለችና በጅቦች ተበልቶ እምጥ ይግባ እስምጥ ሳይታወቅ ከሚቀር፣ ለእኛም መሰቃያ መሣሪያ ከሚሆን “የተባረከ መንግሥት በቶሎ ለመፍጠር ተነሥተናልና የተቀደሰ ሐሳባችንን ታሳካልን ዘንድ ቅዱስ ፈቃድህ ይሁንና ይሄንን ቶሎ እስክታስፈጽመን ድረስ እንደሠወርከው አቆይልን” የሚለው የዘወትር ጸሎቴ ነው፡፡

በመሆኑም የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! በወያኔ እየተቦጠቦጠና ሊቦጠቦጥ ያለውን የሀገር ሀብት እንዳይቦጠቦጥ ባዶ ቀፎውን ትቶልህ እንዳይሔድ በቃ ብለህ ብትሸኘውና የሀገርህ ሀብት ለሀገር የሚውልበትንና ሀገር ያላትን ሰፊ አቅም ተጠቅማ ፈጣኑን እድገት እንድታገኝ ብታደርግ ነው የሚሻልህ፡፡

እንግዲህ በእነዚህ ሰባት ዋና ዋና ፈተናዎች ችግሮች ምክንያት በዚህ ወቅትና በወያኔ እጅ የዐባይ ግድብ መሠራቱ ለሀገርና ለሕዝብ ሊሰጠው የሚችለው ጥቅም ሳይሆን ጉዳት ነው ማለት ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ግንባታ የችግሮች ቋት በሆነው በወያኔ እንዲገነባ መፍቀድ መተባበርመም ፍጹም ኃላፊነትና ማስተዋል የጎደለው ተግባር ነው፡፡

“እና መቸ ነው ጊዜው?” ካላቹህኝ የኢትዮጵያን ሕዝብ ከጎኑ ማሰለፍ የሚችል፣ የሚታመን፣ ጠባብ ያልሆነ፣ ከጎጥ ተሻግሮ ማሰብ ማየት የሚችል፣ ኃላፊነቱን በቅጡ የተረዳና የሚሰማው፣ የበቃ የኢትዮጵያ መንግሥት ሲኖር መሆኑን እናንተም ለገማቹህ ፈራቹህ ትዕግሥቱን አለቅጥ አበዛቹህት እንጂ ታውቁታላቹህ፡፡ ወያኔን የምናውቀው የሀገሪቱን ጥቅምና ሉዓላዊነት አሳልፎ በመስጠቱ ለጠላቶቻችን ቅጥረኛ ሆኖ ሲሠራላቸው እንጅ ለሀገራችን ሲሠራ አይደለም፡፡

እያልኩት ያለሁትን ነገር እየተረዳቹህ ነው? ኃላፊነት እንደሚሰማው ዜጋ እንዴት ታዩታላቹህ? ምን ይሰማቹሀል? አስኪ አሰላስሉ፡፡ ወያኔ እራሱን እንደገና መፍጠርና ኢትዮጵያዊ መሆን ካልቻለ በስተቀር እንዲህ መሆኑንም በማያሻማ ሁኔታ ሊያረጋግጥልን ካልቻለ በስተቀር ምንም ተስፋ አታድርጉ፡፡ የዐባይ ግድብም ሆነ የነዳጅ ዘይት መገኘቱ ለሀገሪቱ መርገም እንጅ በረከት አይሆኑም፡፡ ወያኔ አሁን ባለበት ማንነቱ የሚሠራ ሥራ ሁሉ ለትውልደ ትውልድ የሚተላለፍ ድርብ ድርብርብ ኪሳራ እንጂ ኪሳራና ጉዳት ብቻ ነው የሚያተርፍልን፡፡

ጭፍን ሆኜ አይለም ማሳያዎቸን መከራከሪያዎቸን ይዠ ነጥብ በነጥብ የጠቀስኩ በመሆኑ፡፡ ጨለምተኛም ሆኘ አይደለም ያልኩት ሁሉ ውሸት በሆነና እኔ ጨለምተኛ ሆኜ በዚህ አስተሳሰብ የማፍር የምዋረድ ብሆን ምንኛ ደስ ባለኝ ነበር፡፡ ጨለምታኛ (pessimist) ላለመባል ብሎ በዲያብሎስ እጅ መሆንን ወዶ ፈቅዶ እያለ አንድ ሰው ሽ ጊዜ ተስፈኛ (optimist) ቢሆን ምን ይጠቅመዋል? ምን ጠብ ይልለታል? ጨለምተኛ ማለት ተስፋ እያለ ተስፋ ለማድረግ አለመቻል ማለት እንጅ ተስፋ በሌለበት ተስፋ አለማድረግ ማለት አይደለም፡፡

የመንግሥት ሠራተኛ የሆነና የእንጀራ ምጣዱ ከመንግሥት ጋር የተገናኘ ነጻነቱን አሳልፎ ሰጥቷልና በእጁ ለማድረግን ሲንቀሳቀስ አይታይምና “ሴትዮዋ ናት አሉ የፍል ውኃ ጠበል ለመጸበል ወደ ጸበሉ ስትገባ ፍል ጸበል ነውና ለምጥጧታል ያኔ “ዋይ!” ብላ ጮኸች ጸበልተኛው “ኧረ ተይ! እንደሱ አይባልም! እሰይ እሰይ ነው የሚባለው” ብለዋታል:: ያኔ ሴትዮዋ “የግድ እሰይ የግድ እሰይ” እያለች ተጸበለች አሉ፡፡ አሁንም የመንግሥት ሠራተኛ ሆኖ ከዚህ የተለየ አቋም ለማንፀባረቅ ሠራተኛው ሊፈጥረው የቻለው ወይም የተተወለት ዕድልና ቁርጠኝነት የለምና “የግድ እሰይ” ነው ነገሩ፡፡
ደግሞ ሌሎች አሉ ዳቦው የራሳቸው ሆኖ እያለ አሳልፈው ሰተው ሲያበቁ ፍርፋሪ የሚለቃቅሙ፣ ፍርፋሪ ለመለቃቀም ተስፋ አድርገው ደጅ የሚጠኑ፡፡ እነዚህ ሁሉ ይሄ ያልኩት ሁሉ በሚገባ ቢገባቸውም ፈጽሞ የገባቸው መምሰል አይፈልጉም “ልማት” እያሉ ብቻ በአጫፋሪነት አብሮ የሚያጨበጭብ ነው፡፡ ለፍርፋሪ ብቻም ሳይሆን ያለመብሰልና ደካማ ሰብእናም ነው ጥቅምና ጉዳትን ትርፍንና ኪሳራን ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር ደምሮ ቀንሶ አካፍሎ የማስላትና የመረዳት አቅም ከማጣትም ነው፡፡ እነዚህ እነዚህ ናቸው እንግዲህ የወያኔ አገዛዝ እስትንፋሶች፡፡ እንደነዚህ ዓይነቱ ዜጋ ባይበዛ ኖሮ ወያኔ 23 ዓመታት አይደለም 23 ቀናትም እንኳን የመቆየት ዕድል ባላገኘም ነበር፡፡

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ያደባባይ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ |ፈቃደ ሸዋቀና

$
0
0

Hailemariam and Fekade Shewakena

የተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ:

ስለምልካም አስተዳደር ችግር ካንዴም ሁለቴ አምረው ሲናገሩ ሰምቼዎት የሚናገሩት እንደተለመደው ላልኩ ባይነት ያህል ነው ወይስ ቆርጠው ሊዋጉት ተነስተዋል የሚል መንታ ሀሳብ ላይ ቆሜ በተግባር የሚያደርጉትን ከሚጠብቁ የዚች አገር ልጆች እንዱ ነኝ። የተናገሩትን የሚመስል እንድ ርምጃ ወስደው አስካይዎት ድረስ ያፍዎን የልብዎ ከዚያም የተግባርዎ እንዲያደርገው እጸልያለሁ። የተናገሩትን ወደ ሥራ ለማዞር ያለዎትን አቅም ብጠራጠርም ካንጀት ካለቀሱ እንባ አይገድም እንደሚባለው ከልብዎ አስበው ከተነሱ ቢያንስ ባደባባይ እንዳላየ እያየን “መቼስ ምን ይደረግ” እያልን የምናልፋቸውን የተወሰኑትንና በቀጥታ የሚመለከቱዎትን ብልሹ ያስተዳደር ጥፋቶች በግልዎም ጥረት ቢሆን ማቆም አያቅትዎትም። ዞሮ ዞሮ ለሚደርሰው ጥፋትና ያስተዳደር ብልሹነት ሁሉ የአገሪቱ አስተዳደር አናት ላይ እንደመቀመጥዎ ለችግሩ የመጀመሪያው ተጠያቂ ርስዎ ነዎት። ዛሬ እኛ አቅም አጥተን ተጠያቂ አድርገን ባንፋረድዎትም ታሪክ ሲያብጠለጥልዎት ይኖራል። ስለዚህ ለመተማመኛም እንዲሆን ህዝብም ይህ ነገር የምር ነው እንዲል ለምሳሌ የሚሆን ርምጃ ባንድ የተበላሸ የመንግስት አሰራር ላይ ወስደው ያሳዩን።

መልካም አስተዳደር እንዲሰፍንና ብልሹ አስተዳደር እንዲወገድ ጥናት ያደረገው ግብረ ኃላችሁ ሪፖርቱን ባቀረበበት መድረክ ላይ በቪዲዮ እንዳየነው በጅጉ ጎልቶ የተሰማው የርሶ ድምጽ ነበር። ብዙ ተስፋ የቆረጡ ወገኖች የፐብሊክ ሬሊሽንስ ስራ ነው ብለው ቢያጣጥሉትም እኔ እስቲ ቀጥሎ የሚያደርጉትን እንይ በማለት ለመጠበቅ ከመረጡት ውስጥ ነኝ። በኔ አስተሳሰብ ያገራችን የመልካም አስተዳደር ችግርም መፍትሔውም ብዙ ጥናት የሚሻ ነገር አልመሰለኝም። ነገሩ ሮኬት ሳይንስ አይደለም። ብዙው የመልካም አስተዳደር ችግር ደግሞ እናንተ ባለስልጣኖቹ መሀል ላይ ቆማችሁ የምታዩት ነው። በቀደም ሀገሪቱ ውስጥ ግለሰቦች እስር ቤት አላቸው ብለው የነገሩንና ያስደመሙን ርስዎ አይደሉ?

እኔ ከሀገሮች ልምድ አገላብጬ ያገኘሁትን ዝባዝንኬ የሌለበት የመልካም አስተዳደር ማስፈኛ ትልቁን ዘዴ ልንገርዎት። የመልካም አስተዳደር መስፈን አለመስፈን ጉዳይ ከህዝብ ተሳትፎ ጋር የተያያዘ ነው። ያስተዳደር ችግር ሙስናና የስልጣን ብልግና እንዲወገድ ከተፈለገ በመንግስት ጥረት ላይ ሰፊ የህዝብ ተሳትፎ ይጠይቃል። መልካም አስተዳደር የሚመኝ ባለስልጣን የመጀመሪያ ስራ ይህንን የህዝብ ተሳትፎ መኮትኮትና ማሳደግ ነው። የግልጽነት (Transparency) ባሕል የሚዳብረው ከዚህ ጀምሮ ነው። የህዝብ ተሳትፎ ሲባል በእምነት ላይ የተመሰረተና ጥርጣሬ የሌለበት በሀገር መሪዎች አርአያነት የታገዘ ተሳትፎ ማለት ነው። ሕዝቡ በመንግስት ላይ እምነት ከሌለው ከልቡ ለመሳተፍ ይቸገራል። ባጭሩ መልካም አስተዳደርን የማስፈን ቁልፉ በእምነት ላይ የተመሰረተ የህዝብ ተሳትፎ ነው። ሌላ ብዙ ዝባዝንኬ የለውም። ሕዝቡ መንግስትንና የበላይ መሪዎችን ሲያምንና ተቆርቋሪነታቸው ከልብ የመነጨ ነው ብሎ ካረጋገጠ በህዝብ ላይ የሚባልግ የመንግስት ሹም አይኖርም። ችግሩን አጋልጬ ያገባኛል ብዬ ተጋፍጬ በኋላ ለጥቃት ብጋለጥ የሚደርስልኝ አይኖርም የሚል ዜጋ በበዛበት ሀገር መንግስት የሙሰኞች መፈንጫ ሆኖ ነው የሚቀረው።

እዚህ የምኖርበት የስደት ሀገሬ አገልግሎት ለማግኘት የመንግስትም ይሁን የግል ድርጅት ውስጥ ሄጄ አንዱ ትንሽ ቢያጉላላኝ ራሱን አለቃህን ጥራ ብዬ አፋጥጬ በደሌን ላለቃው ነግሬ ሁለተኛ

እንዳይለምደው አድረጌው የምፈልገው አገልግሎት ተቀላጥፎልኝ ነው የምሔደው። ይህን የማደርገው የኔን መጉላላት የማይቀበል ስርዓት ባገሩ ላይ መስፈኑን ርግጠኛ ስለሆንኩ ነው። እንዲህ አይነት ነገር እያሳደዱ የሚያጋልጡ ጋዜጠኞች ደግሞ ከቀበሌ አስከሀገር ደረጃ አሉ። እናንተ ባንድ በኩል ጋዜጠኛ እያስፈራራችሁና እያሰራችሁ በሌለ በኩል ስለ ማልካም አስተዳደር ስታወሩ ከልባችሁ መሆኑን እንጠረጥራለን። እቅጩን ልንገርዎት። ትችትና ነጻ የህዝብ አስተያየት እንደጦር የሚፈራ መንግስት መልከ-ጥፉ እንጂ መልካም አስተዳደር ማሰፈን አይችልም። የዚህ አይነት መንግስት ሕዝብን ብቻ ሳይሆን ራሱንም ከውድቀት አያድንም። አሁን ኦሮሚያ ፣ ጎንዳርና ኮንሶ አካባቢ ከሕዝብ ጋር ጦርነት የገጠማችሁትና ከድጥ ወደማጥ እየገባችሁ ያላችሁት በጊዜ መስማት የነበረባችሁን ነገር ንቃችሁ በመተዋችሁ ይመስለኛል። አሁን የያዛችሁት ግደለው ፣ በለው ፣ እሰረው አካሄድ ለማንም እንደማይበጅ የሚነገራችሁን ምክር ብትሰሙ ከብዙ ጥፋት መዳንም ችግሩን መቋቋምም ትችሉ ነበር።

የህዝብ ተሳትፎ እንዴት ይጎለብታል ከይትስ ይጀመራል ብለው ይጠይቁኝ ይሆናል። ህግና አዋጅ በማውጣት መስሎዎት ከሆነ ተሳስተዋል። ይህ ዝም ብሎ ድሪቶ የማብዛት ጉዳይ ነው። ባለስልጣኖቹ እንደፈለጋችሁ የምትጥሱት ጥሩ ህግ ወረቀት ላይ ሞልቷችኋል። ህዝብ ከልቡ እንዲሳተፍ ባለስልጣኖች አርአያነት ያለው ስራ ሲሰሩ ማየት ይፈልጋል። ይመኑኝ ቢያንስ እርስዎ በግልዎ ሊለውጧቸው የሚችሉ ነገሮችን ሲለውጡ ካየ ህዝቡ ተሳትፎው ይጨምራል። ትንሽ መንገድ የመቅደድ ጉዳይ ነው።

የተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስትር

እኔ በዚህ ደብዳቤ ላይ ስለዘርፈ ብዙው የሀገራችን የመልካም አስተዳደር ችግር ብዙ ለመዘብዘብ አይደለም አነሳሴ። የዚህ ደብዳቤዬ አላማ እርሶ በግል ስልጣንዎ ሊሰሩ ከሚችሏቸው ነገሮች እንዱንና ሁላችንንም ወደተራ እንስሳነት ያወረደ የመንግስትዎን አንድ የተበላሸ መልከ ጥፉ ያስተዳደር ስራ እንዲያስቆሙ ለመጠየቅ ነው። ይህን ካስቆሙ ከላይ ያነሳሁትን የአርአያነት ጥያቄ እንደጀመሩት ሊወስዱት ይችላሉ። ችግሩን ወደ መፍቻው አቅጣጫም ብዙ ማይል እንደሄዱ እቆጥረዋለሁ። ከላይ ያነሳሁትን የህዝብ አመኔታ ችግር ሙሉ ለሙሉ ባይፈታውም ይቀንስልዎታል። ሌላውንም ችግር ለመፍታት መንደርደሪያ ይሆንዎታል። በሕዝብ የሚከበሩና የሚወደዱ ሰውም ያደርግዎታል።

ህዝብና የታሪክ ፍርድ ባይፈሩ እንኩዋን እባክዎ ስለፈጠረዎ አምላክ ብለው እስረኛ ማሰቃየት (ቶርቸር) የሚባል የምርመራ ዘዴ ያስቁሙ። ሌላውን ግድያውን ፣ ማስፈራራቱን ፣ ማንገላታቱን ፣ አፈናውንና ብዙውን የመብት ጥሰትና ይፈትሕ መጓደል ያስቁሙ እያልኩዎት አይደለም። እንድ ግለሰብ በጃችሁ ላይ ከወደቀና ካሰራችሁት በኋላ በአካሉና በሕሊናው ላይ የምጥፈጽሙትን ተሰቃዩንም ራሳችሁንም ከሰብዓዊ ፍጡር ውጭ የምታደርጉበትን ሰቆቃ (ቶርቸር) ብቻ ነው የምለው። ቶርቸር በአለማቀፍ ሕግም ይሁን በእኛ ሀገር ሕጎች የተከለከለና የሚያሰቃየውን ሰውም ሆነ የሚሰቃየውን ሰው ከስብዕና ውጭ የሚያደርግ እንስሳዊ የችግር መፍቻ ዘዴ ነው። በሰለጠነው አለም ሰው ቀርቶ እንስሳት ማሰቃየት በጅጉ የተከለከለ ነው። ይህን ነውር በስፋት እያከናወኑ ስለሀገር ሕዳሴና ስለመልካም አስተዳደር ማውራት በውነቱ ፍጽም ከንቱ ግብዝነት ነው። ግፍና ሰቆቃ እንዲካሄድ በሚፈቅድ መንግስትና አገር ውስጥ ጥገና እንኩዋን ቢደረግ የሚገኝ አስተዳደር መልካም ሳይሆን መልከ ጥፉ ብቻ ነው።

በዘመናችን ሰው ከማሰቃየት የተሻሉ ብዙ የምርመራ ዘዴዎች መኖራቸውን ባለሙያዎቹ ሲናገሩ እንሰማለን። እንደሚቻልም በመረጃ ያሳዩ ብዙ ናቸው። የምኖረው ሁሉን ነገር አፍረጥርጦ ለመወያያት ገደብ የሌለበት ሀገር ነው። በዚህ የቶርቸር ጉዳይ ላይ የሚወያዩ የምርመራ ባለሞያዎች በቶርቸር የሚገኝ መረጃ አዛላቂ ጥቅም እንደሌለው እንዴውም በጣም አሳሳችና ከሰህተት ወደ ስህተት የሚወስድ ግኝት ላይ እንደሚያደርስ ብዙ ሲናገሩ እንሰማለን።

ይህን የሰቆቃ ስራ የሚሰሩት ሰዎች አንዳንድ ጊዜ እንደግል መዝናኛቸው ሊያደርጉት ወይም ግላዊና ቡድናዊ የጥላቻ ስሜታቸውን የሚያረኩበት ሊያደርጉትም እንደሚችሉ ማሰብ ይጠቅማል። በየማህበረሰቡ ውስጥ የስቃይ ደስተኞች (Sadists) መኖራቸውን ሊያውቁ ይገባል። አሁን ከሰለባዎቹ በተደጋጋሚ እንደምንሰማው አዲስ አበባ አራዳ የሚገኘው ማዕከላዊ ምርመራ መስሪያ ቤት በዚህ አይነት ሰዎች የተወረረ ነው የሚመስለው። ምናልባትም ሰዎች በጭካኔ መደሰት (sadism) የሚማሩበት ቦታ ወደመሆን ሳይዞር አልቀረም። የዚህን ምልክት ተሰቃይተው የወጡ ዜጎች ደረሰብን የሚሉት ድብደባ አዋራጅ ስድብና ዘለፋ ላይ ይታያል። የብሔረሰቤን ስም እየጠሩና እያዋረዱ ገረፉኝ እያሉ ሲናገሩ የሰማናቸው ሰዎች ቁጥር ብዙ ነው። ሁሉም ተሰቃዮች ሲወጡ ሲናገሩ እንደምንሰማው የሰቆቃው መስሪያ ቤት ሰራተኞች ካንድ ብሔረሰብ የመጡ ስዎች ናቸው ይላሉ። ይህ ሙያዊ ምርመራ ሳይሆን በመላው ታክስ ከፋይ በሚተዳደር የመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ ቡድናዊ ፍላጎትን ለመጠበቅ የሚደረግ የብልሹ አስተዳደር ምልክት ነው። ጭካኔውንም የሚያበዛው ይህ ሊሆን እንደሚችል ለመገመት አያዳግትም። ባልተወለደ እጅ የሚፈጸም ጭካኔ መሆኑ ነው። በዚህ መስሪያ ቤት ውስጥ እንደሰፈነው ስርዓት ያለ የብልሹ አስተዳደር ምሳሌ ሀገራችን ውስጥ መስጠትም ይከብዳል። ክቡርነትዎ ስለመልካም አስተዳደር ሲያሰሙ የሰማንዎት ምሬት ይህን የሚጨምር ካልሆነ ፈጽሞ ዋጋ የለውም።

ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር

እባክዎን በመጀመሪያ ይህን ያድርጉ። መሃል ከተማችን ላይ እንደጌጥ የቆመውን አራዳ ጊዮርጊስ በላይ ያለውን ይህን ማዕከላዊ የሚባለውን የሰቆቃ ማዕከል ይዝጉት። ከሳምንታት በፊት “ገራፊዬን አየሁት” በሚል ርዕስ አንዱ ሰቆቃ የተፈጸመበትና መጨረሻ ላይ ፕሬዚዳንት ኦባማ ሊመጣ ሲል በነጻ የለቀቃችሁት ወጣት ጦማሪ የጻፈውን አጥንት ድረስ ገብቶ የሚሰማ ጽሑፍ ያንቡት። እውነቱ ነው። ሰው እንዴት መሀል ከተማ ላይ ያን የመሰለ ሁላችንንም የሚያዋርድ የሰቆቃ ማዕከል ይዞ ከራሱ ጋር የታረቀ ፣ የተከበረ ህዝብና ዜጋ መሆን ይችላል? የዚህን አይነት መንግስትና ሹማምንቱን እንፈራቸው እንደሆነ እንጂ እንዴት ልናከብራቸው እንችላለን? ይህን በዋና ከተማችን መሀል አራዳ ላይ አስቀምጠን ምን አይነት የዜግነት ክብር ነው ሊሰማን የሚችለው? የሰው ልጅ ሰውነት በኤሌክትሪክ ገመድ አየተቀረደደ ፣ ወንዶች ብልታቸው ላይ ውሃ የሞላ ጠርሙስ እየሞሉ እያንጠለጠሉ ፣ ሴት ልጆችን ርቁታቸውን መርማሪዎች ፊት እንዲቆሙና ውርደት እንዲሰማቸው ማድረግን የመሰለ ግፍና ሰቆቃ የሚካሄድበት ሀገር መሪ መሆን የሚያዋርደው እርሶንና ባካባቢዎ ያሉ ባለስልጣኖችን ሁሉ ነው። ስለዚህ ነገር በተወራ ቁጥር ሹማምንቱ አውሬ እንጂ ሰው እኮ መስላችሁ አትታዩንም። በቅርቡ እንዱ ሰለባችሁ መርማሪዎቼ ሱሬዬን አስወልቀው እላዬ ላይ ሽንታቸውን ሸኑብኝ በማለት እያማረረ ሜዲያ ላይ ሲናገር እየዘገነነኝ ሰማሁት። ይህ መቼም ለምርመራ ሳይሆን ሰው በማዋርድና በማሰቃየት ደስታ ለማግኘት የሚደረግ የሳዲስቶች ስራ ነው። የተገረፈ አካልና የስረኞችን ጩኸት አየሰሙ እንዳላየ የሚያዩ ወይም ሰለባዎቹን ራሳቸውን ማስረጃ እምጡ የሚሉ ዳኞች ይዞስ ስለመልካም አስተዳደር ማውራት እንዴት ይቻላል? የስረኛ አቤቱታ የማይሰማ ዳኛ ባለበት ሀገር ምን አይነት ዳኝነት ነው የሚኖረው? ይህን ጉድ እያስተናገዳችሁ መልካም አስተዳደር ስታወሩ ማን ከልባችሁ ነው ብሎ የከተላችኋል? ይህ ሁሉ ግፍ ጭራሽ አይሠራም ብላችሁ ትክዱ ይሆናል። የመረጃው ብዛት በክህደት ሊስተባበል ከሚችልበት በላይ ሄዷል። ይህ ግፍ በተደጋጋሚ ከብዙ ሰለባዎች ዘንድ ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች እየተሰማ ነው። የመልካም አስተዳደር መበላሸት ቁንጮ ከዚህ የበለጠስ ምን አለ? ማዕከላዊ የሚባለው ትልቁ የሰቆቃ ተቋም ከቢሮዎ 5 ኪሎሜትር በመይሞላ ርቀት ላይ መሆኑን አይርሱ። አድዋ ድረስ ክብራችንን ለማስመለስ ስንዘምት አብሮን የዘመተው ታቦት አራዳ ጊዮርጊስ አጠገብ ይህን ማዕከል አስቀምጦ ስለምን አይነት ተሀድሶና ሀገር ግንባታ ነው ማውራት የሚቻለው?

የተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስትር

ይህን የግፍ ማእከል መዝጋት ቀላል ላይሆን ይችላል። ካንዳንዶች የስራ ባልደርቦችዎ መጠነኛ ፈተና ሊኖርብዎት እንደሚችል መገመት ይቻላል። መዶሻ አዘውትሮ እንደሚይዝ አናጢ ሁሉም ነገር ምስማር መስሎ የሚታያቸው ሰዎች ዞሪያዎ እንዳሉ እናውቃለን። መንግስትና ሕዝብን የሚያጋጭ ችግር መፍታት ሲባል የሚታያቸው ጥይትና ዱላ ብቻ የሆነ ሰዎች በብዛት እንዳሉ ለማረጋገጥ ባለፈው አራት ወር ሙሉ ኦሮሚያ ውስጥ ህጻን አዋቂ ሳይለዩ ሰው የሚፈጁና የሚያስፈጁ ሹሞችዎን ማይት ብቻ ይበቃል። ድርጊታቸው ተቃውሞውንና ሕዝባዊ እምቢተኝነቱን የበለጠ የሚያባብስ መሆኑን ፈጽሞ ሊገምቱ እንኳን አልቻሉም።

ይህን በየስር ቤቱ የሚደረግ ሰቆቃ ለማስቆም ከልብዎ ከሞከሩ የሚያቅትዎት አይመስለኝም። ከሁሉም በፊት ግን ይህን መሀል ከተማ ላይ የተቀመጠ የውርደት ማዕከል ሊዘጉት ይችላሉ። በዚህ ሳቢያ ሥራዎን ቢያጡም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ትልቅ ውለታ እንደሰሩ ሰው ተቆጥረው በህይወትም በታሪክም በኩራት ይኖራሉ። ብዙ ሚሊዮኖች አክባሪዎም ረዳትዎም እንሆናለን። ይህን ቦታ ይዝጉት። ከዚያ በይስርቻው ያሉትን ማሰቃያዎች መዝጋት የጊዜ ጉዳይ ይሆናል። እባክዎት ይህን ማዕከላዊ የሚባል የሰቆቃ ሰገነት ይዝጉት። ሞክረው ቢያቅትዎት እንኳን ሰቆቃን ለማስቆም የሞከረ አንድ መሪ ነበረ እየተባለ ይነገርልዎታል። ይህ የሰቆቃ ሰገንት በሰውም ብእግዚአብሔርም በሰለጠነው አለም ፊትም እንገት የሚያስዳፋ አሳፋሪ የመልከ ጥፉ አስተዳደር ምልክት ነው። እንገት መድፋት ያለብን ሰለባዎቹና ታዛቢዎቹ ኢትዮጵያውያን ብቻ ሳንሆን እናንተም ይህን ሰቆቃ የምትፈጽሙት ሹማምንት መሆናችሁን አይዘንጉ። ይህንን የምድር ላይ ሲኦል ይዝጉት። ይህን ማድረግ የማይችሉ ከሆኑ ደግሞ እባክዎን ኢትዮጵያና ሕዳሴ የሚሉትን ቃላት ባንድ አረፍተ ነገር ውስጥ መጠቀም ያቁሙ።

Fekadeshewakena@yahoo.com

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ሶማሊያን አሸነፈ

$
0
0

ethiopia

የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም ከሶማሊያ ጋር ለ2017ቱ ከ20 በታች የአፍሪካ ዋንጫ ለመግባት ያደረገውን የመጀመረ የማጣሪያ ጨዋታ በ2ለ1 አሸነፈ::

ወጣት ብሔራዊ ቡድኑ ከጨዋታ ብልጫ ጋር ይህን ድል መቀዳጀቱን የስፖርት ተንታኞች ገልጸዋል::

የኢትዮጵያ ወጣት ብሔራዊ ቡድን የመልስ ጨዋታውን ከሶማሊያ ጋር ሲያደርግ ወደ መቋድሾ አያመራም:: እዚያ ባለው የጸጥታ ስጋት የተነሳ የመልስ ጨዋታው በገለለተኛ ሃገር የሚደረግ ይሆናል:: በዚህም መሰረት ቀጣዩ ጨዋታ ጅቡቲ ላይ ይደረጋል ሲሉ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች አስታውቀዋል::

ብሄራዊ ቡድናችን በዛምቢያ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ በአዲስ አበባ ስታዲየም የሶማሊያ አቻውን አስተናግዶ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ቢያሸንፍም ሱማሊያ አንድ ጎል ከሜዳዋ ውጭ በማስቆጠሯ ጅቡቲ ላይ አንድ ለዜሮ ካሸነፈች ወደ ቀጣይ ዙር ልታልፍ ትችላለች:: ሆኖም ግን ብሔራዊ ቡድናችን ከሜዳው ውጭ የገባበትን የግብ ዕዳ ለመክፈል ጠንክሮ መጫወትና ጎል ማግባት ይጠበቅበታል::

ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊያነበዉ የሚገባ ከሕወሓት ጓዳ የወጣ ወሳኝ መረጃ –“አማራን ለመነጣጠል የተዛቡ ታሪኮችን መጻፍ”

$
0
0
(ከዚህ ቀደም ከጉራ ፈረዳ የተፈናቀሉ አማሮች፡ ፎቶ ፋይል)

(ከዚህ ቀደም ከጉራ ፈረዳ የተፈናቀሉ አማሮች፡ ፎቶ ፋይል)

ከታመነ ይህዓለም

ህወሐት የአማራን ህዝብ እንደገና በጎሳ ለመከፋፈል በትግርኛ ጽፎ ለሕወሐት አባሎችና በነርሱ ስር ላሉ ተጠርናፊዎች እያሰራጨው የሚገኘው አጭር እቅድን የውስጥ አርበኞች አደባባይ አውለውታል:: ትግረኛውንም ወደ አማርኛ እንዲተረጎም “ትንሳኤ ሃገር” አድርጎ ለሕዝብ ይፋ ሆኗል:: የትግረኛውን ከላይ – ከታች ደግሞ የአማርኛውን ትርጉም ያንብቡ::

ንዛኤኤ

‹‹መጀመርታ ህዝቢ አምሓራ ኹሉ ሸነኻት ክንምልከቶ አሎንና፤ሎሚ ግዜ አብ ውሽጢ ህዝቢ አምሓራ ብዙሕ ብሄረ ብሄረሰባት አለዋ፤እንተኾነ ግና ከይተፈላለያ ይነብራ፤እዚ ሓድነቶም ንህዝቢ ትግራይ ሐደገኛ ስለዝኾነ ህዝቢ አምሓራ ንምፍልላይ አስታት አምሓራ ግጉይ ታሪኽ መ ፅናዕትን ምርምርን እናተገብረሉ ብመልክዕ መጽሐፍ ተሰናዲኡ ሕብረተሰብ ክጥቐመሉ ዝኽእለሉ መገዲ ንምምዕርራይ ፃዕሪ እናተገብረ እዩ፡፡ብተወሳኺ ዋላ’ውን እቲ ስራሕ ብርቱዕ እንተኾነ ህወሓት እዚ መጽሐፍ ዓቕሙ ብዝፈቕዶ መጠን ብተኸታታሊ ንምህታም መደብ ከም ዘለዎ በዚ አጋጣሚ ንምግላፅ ይፈቱ፡፡ምጅምርታ ግጉይ ዘንታ ዝሐዘ መጽሐፍ ተሓቲሙ ንህዝቢ አምሓራ ክቐርብ እዩ ፤ድሕሪኡ ህዝቢ አምሓራ እንተተባእሳ ህዝቢ ትግራይ በዓለ ርስቲ ይኸውን ማለት እዩ፤እንተዘይኾይኑ ህዝቢ አምሓራ ንህዝቢ ትግራይ ምህረት ዘይብሉ እዩ!
ኣብ ርእሲ’ዚ ናይ ትግራይ ስእሊ ታሪኽ ዝሐዘ መጽሐፍ ብብእዋኑ እናተመሐየሸን እናማዕበለን ተሓቲሙ ንህዝቢ ክቐርብ እዩ ዝብል እምነት አለና፡፡እዚ መጽሐፍ ናይ ኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ካአ ብዛዕባ ታሪኸ ትግራይ ዘለዎ ርእይቶ ክብንምባል ይሕግዝ፡፡ካአ ብዛዕባ አምሓራ ዘለዎ ርእይቶ ግና ንብዙሕ መዋእል ይደቁስ፤››

አጸ

ከላይ ‹‹ንዛኤኤ›› ከታች ‹‹አጸ›› የሚሉት ምህጻረ ቃሎች ባይገቡንም በግርድፉ ልናስተረጉመው እንደሚከተለው ሞክረናል፡፡

 

“በመጀመሪያ የአማራን ህዝብ ከተለያዩ ጎኖች ማየት አለብን፤በአሁኑ ጊዜ በአማራ ህዝብ ውስጥ የተለያዩ ብሄር ብሄረ ሰቦች ይገኛሉ፤ ቢሆንም ግን ሳይነጣጠሉ እየኖሩ ነው፡፡ ይህ አንድነታቸው ለትግራይ ህዝብ አደገኛ ስለሆነ የአማራን ህዝብ ለመነጣጠል ስለአማራ የተዛባ ታሪክ ጥናትና ምርምር እየተደረገበት በመጽሃፍ መልክ ተዘጋጅቶ ህዝብ እንዲጠቀምበት ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው፤ በተጨማሪም ይህ ስራ ከባድ ቢሆንም ህወሀት ይህን መጽሐፍ አቅሙ በፈቀደ መጠን በተከታታይ ለማሳተም እቅድ እንዳለው በእዚህ አጋጣሚ መግለጽ ይወዳል፡፡ በመጀመሪያ የተዛባ ታሪክ የያዘ መጽሐፍ ታትሞ ለአማራ ህዝብ ይቀርባል ከእዚያም እርስ በእርሱ ሲጣላ ትግራይ ባለ እርስት ትሆናለች ማለት ነው፡፡ አለበለዚያ የአማራ ህዝብ ለትግራይ ህዝብ ምህረት የለውም፡፡

ከእዚህ በተጨማሪም የትግራይን ካርታና ታሪክ የያዘ መጽሐፍ በእየጊዜው እየዳበረና እየተሻሻላ ታትሞ ለህዝብ ይቀርባል የሚል እምነት አለን፡፡ ይህ መጽሐፍ የኢትዮጵያን ማህበረሰብ ስለ ትግራይ ያለውን አመለካከት ከፍ ለማድረግ ሲያግዝ ስለአማራ ያለውን አመለካከት ደግሞ ለብዙ ዘመን እንዲደቆስ ያደርጋል፡፡

ይላል አፈትልኮ የወጣው የቀቢጸ ተስፋው የሕወሓት ወንበዴ ቡድን እቅድ::

እንግዲህ ስለ አማራ ተዛብተው የተጻፉ ታሪኮችን መዝገበ-ቃላቶችን ብታነቡ እንዳይደንቃችሁ፡፡ በአማራ ክልል ውስጥ ያሉትን የአማራ
ተወላጆችም የተለያየ ስያሜ በመስጠት ለመከፋፈል ታቅደው ተዛብተው የተጻፉ የታሪክ መጻሕፍትን ብታነቡም አዲስ አይሁንባችሁ፤ ግን
ለህብረታችሁ ይበልጥ ተጠንቀቁ፤‹‹ተላላ ቃልን ሁሉ ያምናል ፤ብልህ ግን አካሄዱን አንድ በአንድ ያጤናል›› እንዲል ታላቁ መጽሐፍ ቅዱስ
በመጻፈ ምሳሌ 14፡15፣ ስለኢትዮጵያ ታሪክ እያሳተሙ የሚያድሉትን መጽሃፍ እንመርምር፡፡ ይህን በስንት ጥረት የተገኘ መረጃ ሼር በማድረግ ለኢትዮጵያ ህዝብ እናዳርስ፡፡
በእዚህ አጋጣሚ ሀከሮቻችንን አመስግኑልን! ብዙ ለአማራ የሚቆረቆሩ የውስጥ አርበኞችን ሁሉ እናመሰግናለን፡፡

ሃቻሉ ሁንዴሳ አዴካ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ፣ በደሌ ቢራና ዳሸን ቢራ በኦሮሚኛ አርቲስቶች ላይ ስለሚያደርሱት መድልዖ ተናገረ

$
0
0

ሃቻሉ ሁንዴሳ አዴካ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ፣ በደሌ ቢራና ዳሸን ቢራ በኦሮሚኛ አርቲስቶች ላይ ስለሚያደርሱት መድልዖ ተናገረ
(ዘ-ሐበሻ) በኦሮሚኛ ሙዚቃዎቹ ተወዳጅነትን ያተረፈው ድምጻዊ ሃቻሉ ሁንዴሳ ከ5 ዓመት እስር በኋላ በለቀቃቸው ሁለት የሙዚቃ አልበሞቹ በኦሮሚኛ ሙዚቃ አድማጮች ብቻ ሳይሆን በሁሉም ኢትዮጵያውያን ዘንድ ተወዳጅነትን አግኝቷል:: ድምጻዊው የመጀመሪያው አልበሙን ካወጣ በኋላ ከፍተኛ ተቀባይነትን ቢያገኝም ሁለተኛው አልበሙን ለማሳተም ሲሞክር በሃገር ቤት ስለገጠመው ፈተና ከኢትዮቲዩብ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ ተናግሯል::

በርካታ ዘፈኖችን በማሳተም የሚታውቀው አዴካ ኢንተርናሽናልን ጨምሮ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ፣ በደሌ ቢራና ዳሸን ቢራ የኦሮሚኛ ሙዚቃ ዘፋኞች ላይ ስለሚያሳዩት መድልዖ የተናገረው ሃቻሉ እነዚህ ድርጅቶች ለአማርኛ ዘፋኞች አልበማቸው ተሽጦ ከሚያገኙት ገንዘብ የበለጠ በስፖንሰር ሺፕ ገንዘብ እንደሚሰጡ ገልጾ የኦሮሚኛ አርቲስቶችን ግን ስፖንሰር ለማድረግ እንደሚቸገሩና መድልዖ እንደሚያደርጉ በቃለምልልሱ ተናግሯል::

2ኛውን አልበሙን በሃገር ቤት በኮፒራይትና እንደሌላው አርቲስት ስፖንሰር ባለማግኘቱ በውጭ ሃገር ያሳተመውና በዚህም ከፍተኛ ገንዘብ ያገኘው ሃቻሉ በየሙዚቃው አልበም ላይ ስማቸው የምናያቸውን አዴካ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ፣ በደሌ ቢራና ዳሸን ቢራ ጉዳይ ያስተዛዝባል ብሏል:: ቭዲዮውን ከኢትዮቲዩብ ካደረገው ቃለምልልስ ቀንጭበን አቅርበናል::

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live