Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የቀድሞ የሕወሓት አየር ኃይል አዛዥ ሜ/ጀነራል አበበ ተ/ሃይማኖት (ጆቤ) እንደገና ጻፉ |ኢትዮጵያ መንታ መንገድ ላይ ትገኛለች”

$
0
0

ታላቁ የሰላምና ደኅንነት ምሁሩ ጆሃን ጋልቱንግ ስለ ሰላም የሚከተለውን ይላል፡፡ ‹‹Peace is a revolutionary idea; peace by peaceful means defines that revolution as nonviolent. That revolution is taking place all the time; our job is to expand it in scope and domain. The tasks are endless; the question is whether we are up to them.›› (Galtung et al, 2002: xi) ትርጉም፡- ሰላም አብዮተኛ ሐሳብ ነው፡፡ ሰላም በሰላማዊ መንገድ መሆኑ አብዮቱን ከሁከት የራቀ ያደርገዋል፡፡ አብዮቱ ሁሌም የሚካሄድ ነገር ነው፡፡፤ የእኛ ሥራ መሆን ያለበት ይህንን ማስፋት ነው፡፡ ሥራው መጨረሻ የለውም፡፡ ጥያቄው ግን እኛ ለዚያ ሥራ የምንመጥን መሆናችን ላይ ነው፡፡

abebe Tekelehianot

ኢትዮጵያ መንታ መንገድ ላይ ትገኛለች፡፡ በአንድ በኩል በከፍተኛ ፍጥነት ከሚያድጉት አገሮች አንድ ሆናለች፡፡ እሰይ አገሬ እደጊ ተመንደጊ የሚያሰኝ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ አገራችንና ሕዝቦቿ የጀመሩትን የዴሞክራታይዜሽን ሒደት ከፍተኛ አደጋ ተጋርጦበታል፡፡ በዴሞክራታይዜሽንና በኢዴሞክራታይዜሽን ኃይሎች መካከል የሞት ሽረት ትግል እየተካሄደ ነው፡፡ ቻርለስ ቲሊ የተባለ የዘርፉ ተመራማሪ ዴሞክራታይዜሽንና ኢዴሞክራታይዜሽን በሚመለከት እንዲህ ይላል፡፡

‹‹Democratization means net movement towards more equal, more protected and more binding constitution. De democratization, obviously then means net movement towards narrower, more un equal, less protected and less binding constitution›› (Charles Till: 2007) ትርጉም፡- ዴሞክራታይዜሽን ማለት ወደ በለጠ እኩልነት፣ ወደ በለጠ ከለላ፣ ወደ በለጠ ሁሉንም ሊገዛ ወደሚችል ሕገ መንግሥት የሚደረግ ድምር እንቅስቃሴ ነው፡፡ ኢዴሞክራታይዜሽን ደግሞ ወደ ጠባብ፣ የበለጠ እኩል ያልሆነ፣ ዝቅተኛ ከለላ ሊሆን ወደሚችልና ተፈጻሚነቱም አነስተኛ ወደሆነ ሕገ መንግሥት የሚደረግ ድምር እንቅስቃሴ ነው ይላል፡፡

 

ዴሞክራቲክ ምኅዳሩ እየቀጨጨ ‹‹ዴሞክራሲ›› የህልውና ጥያቄ መሆኑን ጎልቶ የሚታይበት ጊዜ ነው ያለነው፡፡ ኢዴሞክራቲክ ኃይሎች በመንግሥትም ሆነ በፓርቲውም ካሸነፉ እስካሁን የተገኘውን ሰላምና ዕድገት መና ሆኖ ይቀራል፡፡ ብዙኃነትን በአግባቡ ማስተናገድ ባለባት ኢትዮጵያ ኢዴሞክራቲክ ኃይሎች የበላይ መሆን ማለት መዘዙ ከዚህ እስከዚህ ተብሎ በቀላሉ ተነግሮ የሚታለፍ አይደለም፡፡ ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲ የምርጫ ጉዳይ አይደለም፡፡

 

የአገራችን ሕዝቦች የደርግን ሥርዓት አሽቀንጥረው የጣሉት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በመከጀል ነው፡፡ ለእነዚህ ሕዝቦች ‹‹ዴሞክራሲ ይቆይልህ፣ አሁን ልማት ላይ ብቻ አተኩር›› ማለት ሞኝነት ነው፡፡ ዴሞክራሲያዊ ምኅዳሩ በጠበበ ቁጥር ልማት ይቀጭጫል፣ ሰላም ይደፈርሳል፣ በድምሩ የአገራችን ህልውና አደጋ ላይ ይወድቃል፡፡ አሁን የአደጋ ደውሎች እያቃጨሉ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የተገኙትን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እያጣጣምን፣ ሕዝቦቻችንና መንግሥታችን በቁርጠኝነት የዴሞክራሲ ሒደቱን ማስቀጠል ይኖርብናል ሲባል፣ የልማትና የዴሞክራሲ እንከኖች መሠረታዊ መፍትሔ ማግኘት አለባቸው ማለት ነው፡፡ ለዚህም ሲባል መንግሥት በታክቲክና በታችኛው አመራር ላይ ማተኮር ትቶ ከላይ ባሉት ተቋማትና አመራር፣ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች፣ እንዲሁም አደረጃጀትና አሠራር በማስተካከል አመራርነቱን ማረጋገጥ የግድ ይለዋል፡፡ ተቋማት እውነተኛ የዴሞክራሲ ተቋማት እንዲሆኑ በማድረግ ዴሞክራቲክ ብሔርተኝነት ያስፋፋል፡፡ ቁርጠኝነትና ጥበብ በተሞላበት መንገድ ከተሠራ አሁንም የማይቻል ነገር የለም፡፡ ምክንያቱም ኢሕአዴግ ከሞት አፋፍ ተነስቶ፣ አንሰራርቶ ለድል የመብቃት ባህል አለውና፡፡
የኢትዮጵያ የዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ሁኔታዎችና የመፍትሔ አቅጣጫዎች

 

በመስከረም 2008 ዓ.ም. በተሠራጨው ‹‹ብልሹ አስተዳደር የዴሞክራሲ ምኅዳርን በማስፋትና ቀጣይነት ባለው የዴሞክራሲ ተቋማት ግንባታ በወሳኝነት ይፈታል›› በሚለው መጣጥፌ ‹‹መቶ በመቶ አሸናፊነት አስቂኝና አደገኛ ነው›› ብዬ መጠቆሜ ይታወሳል፡፡ የጠቅላላ ምርጫው ውጤት ከታወጀበት ስድስት ወራት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ መቶ በመቶ ያሸነፈው ኦሕዴድ/ኢሕአዴግ ትጥቅ የተቀላቀለበት ሕዝባዊ አመፅ ተቀሰቀሰበት፡፡ ሕዝቡ በዴሞክራሲያዊ/መልካም አስተዳደር እጦት እየተለበለበ እያለ ነበር የመቶ በመቶ አሸናፊነት ጥሩንባ የተነፋው፡፡ መቶ በመቶ አሸነፍኩ ሲል አስቂኝ ሆኖ እንዳገኘነው ሁሉ የቅርብ ጊዜ ክስተቶች ደግሞ አደገኛነቱን አሳይተውናል፡፡ አማራጭ ድምፅ (Alternative Voice) የማጣት ጉዳይ እንዴት ወደተደራጀ ተቃውሞ ሊሸጋገር እንደሚችል፣ ፀረ ሰላምና ፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎች የኦሮሞና ሌሎች ሕዝቦች ለዴሞክራሲያዊ መብታቸው የሚያደርጉትን ትግል እንዴት መጥለፍ እንደሚችሉና ለአውዳሚ ዓላማቸው ሊጠቀሙበት እንደሚችሉም ፍንጭና ትምህርት የሰጠ ክስተት ነው፡፡ የኮንሶና የቅማንትም እንዲሁ፡፡ በጊዜውና በወቅቱ መልስና ሰሚ ያላገኙ ጥያቄዎች ተከማችተው ምን ዓይነት ማዕበል ፈጥረው አገራዊ ደኅንነትን ሊፈታተን የሚችል ክስተት እንደሚፈጥርም ጭምር ትምህርት መውሰድ ለሚችል ሰው የሚያስተምር ነገር ነው፡፡

 

የዴሞክራሲያዊ/የመልካም አስተዳደር ድክመቶች በሁሉም የአገሪቱ ክልሎችና በፌዴራል መንግሥት በስፋትና በጥልቀት እየተከሰቱ ያሉ ችግሮች ናቸው፡፡ መሠረታዊ ችግሮቹ በሁሉም ተመሳሳይ ቢሆኑም በመልክ (Form) እና በጥልቀታቸው (Depth) ግን ሊለያዩ ይችላሉ፡፡ ከተለያዩ ሕዝቦች የሚገኘው ግብረ መልስም በተለያዩ “Objective and Subjective” ምክንያቶች በመልክም በጊዜም ሊለያዩ ይችላሉ፡፡ ሁሉም ሕዝቦች በዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ዕጦት እየተለበለቡ ናቸው፡፡ የኦሮሞ ተቃውሞ የቀዘቀዘ ቢመስልምና በሌሎች ሕዝቦች በዚያ ደረጃ ተቃውሞ ባይታይም፣ የዴሞክራቲክ አስተዳደር ጉድለቶች ደረጃ በደረጃ መሠረታዊ መፍትሔ ካልተበጀላቸው ‹‹የተዳፈነ እሳት›› መሆናቸው አይቀርም፡፡ መቶ በመቶ አሸናፊነት የፖለቲካዊ ሥርዓቱ ችግሮች ምልክት መሆኑ ታውቆ ማስተካከል ይገባል፡፡ የሕዝቦችንና ብሎም የአገራችንን ህልውና የሚፈታተኑት መሠረታዊ ችግሮቻች በሚገባ ተጠንተው ሕዝባችንን በተሟላ መንገድ ባሳተፈ ግልጽነትና ተጠያቂነት በሰፈነበት፣ የሕግ የበላይነት በመከተልና ዴሞክራሲያዊ ሕገ መንግሥታዊ ተቋማትን በመገምገም አጠቃላይ ሥርዓቱን መፈተሽ ይገባል፡፡ በብዝኃነት አገር አንድ ፖለቲካዊ ኃይል ሁሉንም ነገር ጠቅልሎ ከያዘ አንድ አደገኛ በሽታ እየያዘው መሆኑን መገንዘብ መቻል አለበት፡፡

 

የኢትዮጵያ የውጭና የብሔራዊ ደኅንነት ፖሊሲ የአገራችንን ደኅንነት የሚፈታተኑ ዋናዎቹ የሥጋት ምንጮች ውስጣዊ (Internal) እንደሆኑና እነሱም ድህነት፣ ኋላቀርነትና፣ በዴሞክራሲ ዙርያ የሚታዩ ችግሮች መሆናቸውን በማያወላውል አቋም እንደሚከተለው ያስቀምጠዋል፡፡ ‹‹የዴሞክራሲና የኢኮኖሚ ዕድገት አለማምጣት ማለት ደኅንነት አደጋ ላይ ወደቀ ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት ጥገኞችና ድሆች መሆናችንን ራሳችንን ቀና አድርገን እንዳንሄድ ያደርገናል ማለት ነው፡፡ የመበታተን አደጋ ሊጋረጥ ይችላል፡፡›› (ኢወብድፓ፡ 18) ከዚህ መረዳት የምንችለው ነገር እንደኛ ዓይነት ፍላጎቶች በሥርዓቱ ባልተሟሉበት ማኅበረሰብ የከፋ ድህነትና ብልሹ ኢዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ማለት ተራ የፖለቲካ ጉዳይ ሳይሆን የደኅንነት አደጋ የሚደቅን ነገር መሆኑ ነው፡፡ ተመሳሳይ ችግር በገጠማቸው አገሮች እንደምናየው ደግሞ አገር ተበተነ ማለት መዘዙ የከፋ ብቻ ሳይሆን፣ መልሶ የማገገም ዕድልም ላይኖረው ይችላል፡፡ በአሁኑ ጊዜ መንግሥት ‹‹መልካም አስተዳደር የህልውና ጉዳይ ነው›› በማለት ችግሮችን ለመፍታት እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡ በ1994 ዓ.ም. በየያኔው ማስታወቂያ ሚኒስቴር ‹‹የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ጉዳዮች›› በሚል ርዕስ ባሳተመው ጽሑፍ፣ ‹‹ዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር የህልውና ጥያቄ ነው›› ይላል፡፡ አያይዞም ‹‹ምክር ቤቶች የሕዝብ ሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዴሞክራሲያዊ አስተዳደር እምብርት፣ የዴሞክራሲያዊ አገዛዝ አውራ አቋሞች›› ናቸው ይላል፡፡ የፌዴራል፣ የክልልና የወረዳ ምክር ቤቶች በዚህ መመዘኛ ምን ይመስላሉ? ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው፡፡

 

ችግር አለብን የሚለው ዕውቅና የመፍትሔው አንድ ዕርምጃ ነው፡፡ መልካም አስተዳደር የሚለው ጽንሰ ሐሳብ (Concept) በዴሞክራቲክ አስተዳደር አገላለጽ እንደ አማራጭ (Alternative concept of democratic governance) አድርጎ ካስቀመጠው ከብሔራዊ ደኅንነት ፖሊሲ ጋር ብዙም የሚጋጭ አይሆንም፡፡ መልካም አስተዳደር ከዴሞክራቲክ አስተዳደር በተለየ እንደ ቢሮክራቲክ አስተዳደር ብቻ ከቀረበ ግን፣ ከሕገ መንግሥት በመለስ ትልቅ የአገሪቷ ሰነድ ከሚባለው የብሔራዊ ደኅንነት ፖሊሲ ጋር እንዲጋጭ ያደርገዋል፡፡ የተምታቱ መግለጫዎች ባሉበት አንዴ ችግሩ የፖለቲካ አይደለም፣ ከዴሞክራሲ ጋር ተያያዥነት የለውም ሲባል፣ መንግሥት መልካም አስተዳደርና ዴሞክራቲክ አስተዳደር አንድና አንድ ናቸው እያለ እንዳልሆነ መገመት ይቻላል፡፡ እየተደረገ ባለው ግምገማ በመካከለኛና በታችኛው አመራርና ሲቪል ሰርቫንቱ ላይ እየተወሰደ ያለውን ዕርምጃ ሲታይ፣ መንግሥት ሕገ መንግሥትና የብሔራዊ ደኅንነት ፖሊሲ መሠረት አድርጎ ሰፊ ጥናት አካሂዶ እየመራ ነው ወይ? የሚል መሠረታዊ ጥያቄ እንድናነሳ ያደርገናል፡፡

 

መልካም አስተዳደር ማለት ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ማለት ነው ከተባለና የህልውና ጥያቄ ነው ከተባለ፣ መሠረታዊ ፖለቲካዊ ጉዳይ እየተነሳ (የደኅንነት (Poverty) አደጋ እንዳለ ሆኖ) የፀረ ዴሞክራቲክ እንቅስቃሴ እየጎለበተ መጥቷል ማለት ነው፡፡ የዴሞክራቲክ አስተዳደር እጥረት ነው ከተባለ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች (የግልና የቡድን መብቶች) ያለማረጋገጥ ችግር መሆኑን ያመላክታል፡፡ ኅብረተሰቡ በብልሹ አስተዳደር ሲለበለብ ሕገ መንግሥታችን ባወቀለት መብት ማለትም በጽሑፍ፣ በስብሰባ፣ በሰላማዊ ሠልፍ፣ የመረጠውን ወኪል በማስጠራት (Recall) አደጋውን ለምን በእንጭጩ አላስቀረውም? የሚል ጥያቄ ያስነሳል፡፡ መልሱ ኅብረተሰቡ በኋላ ቀር አስተሳሰብ (ደካማ የዴሞክራሲ ልምድ ስላለው) ስለተተበተበ፣ ወይም ደግሞ ዴሞክራሲያዊ ምኅዳር በመጥበቡ ሊሆን ይችላል፡፡ ሁለቱም የተሳሰሩ ናቸው፡፡ በእኔ አመለካከት የዴሞክራሲ ምኅዳሩ (Democratic Space) መጥበብ ማለት ኢዴሞክራታይዜሽን ድባብ (Environment) መግነን ነው፡፡ ዋና ችግሮችም እነኚህ ናቸው፡፡

 

ሕዝቦች በተደራጀ መንገድ የሚታገሉ ሲሆኑ ነው ውጤታማ የሚሆኑት፡፡ ዴሞክራሲያዊ ምኅዳሩ በቀጣይነት እየሰፋ እንዲሄድ ሕዝቡን የሚመሩት ሕገ መንግሥታዊና ዴሞክራቲክ ተቋማት ተጠናክረው ሕገ መንግሥቱ ያስቀመጠውን ሥልጣንና ግዴታ በአግባቡ ሲወጡ ነው፡፡ ‹‹የህልውና ጉዳይ›› የሚለው ጠንከር ያለ ሐሳብ መሠረታዊ ፖለቲካዊ ትርጉሙ እነዚህ ተቋማተ በሚገባ አልሠሩም፣ ወይም ከሕዝቦች አደራና ከሕገ መንግሥቱ አኳያ ሽባ ሆነዋል ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ሕገ መንግሥቱ ለሁኔታችን በቂ በመሆኑ በቀጣይነት ተግባራዊ እየሆነ ከሄደ ብልሹ አስተዳደር እየቀጨጨ፣ የሕዝቦቻችን ተስፋ እየለመለመ፣ የዴሞክራሲ ምኅዳሩ እየሰፋ መሄዱ አይቀሬ ይሆናል፡፡ ‹‹የህልውና ጥያቄ›› ነው ካልነው የቀበሌ/ወረዳ ወይም የዞን አመራር አካባቢ ያሉ የቀን ተቀን ሥራ አንቀሳቃሾች (Operators) እና የታክቲክ ስህተቶች ሊሆን አይችልም፡፡ በፌዴራል/ክልል ደረጃ ያለው የአስተዳደር መዋቅር እነዚህን ነገሮች በጊዜው ሊያስተካክላቸው ይችላል፡፡ ሥርዓቱ (System) ጤናማ ከሆነ ራሱን እያከመ የሚሄድና ለዚህም ሁሌም የሚሻሻል አሠራር ስለሚኖረው፣ ሥርዓቱ መላውን ሕዝብ በማሳተፍ ‹‹የህልውና ጉዳይ›› ከመሆን በመለስ ችግሮቹን ይፈታል፡፡ የፌደራል መንግሥት በቢሊዮን የሚገመት ሀብት የሚያንቀሳቅስ መንግሥት እንደመሆኑ በፌዴራል ደረጃ የሚፈጸም ሙስና፣ እንዝህላልነትና አቅም ማነስ የሚያስከትለው አደጋ ከፍተኛ ነው፡፡ ሆኖም የፌዴራል መንግሥት ይህን ከግንዛቤ ያስገባ አይመስልም? ወይስ አገሪቷ ከወረራት በሽታ ነፃ ነኝ እያለ ነው?
‹‹የህልውና ጉዳይ›› ከሆነ ሕገ መንግሥት የመተግበር ጉዳይ የፖሊሲና ስትራቴጂ፣ የመሠረታዊ መዋቅራዊ ጉድለቶች ችግር ነው ማለት ነው የሚሆነው፡፡

 

በሌላ አነጋገር በበላይ አመራር ያለ ችግር ነው ማለት ነው፡፡ የበላይ አመራሩን ሳይነካ የመካከለኛና የበታች አመራር ላይ ዕርምጃ መውሰድ ሥርዓታዊ ችግሩን የማይፈታ ‹‹ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ›› ከመሆኑም በላይ ኢሞራላዊም ነው፡፡ በፌዴራልና በክልል ሕግ አውጪ፣ ሕግ ተርጓሚ፣ ሕግ አስፈጻሚ እንዲሁም አራተኛው መንግሥት የሚባለው ሚዲያ ሽባ ሲሆኑ ነው ሥርዓታዊ የህልውና ችግር የሚባለው፡፡ የህልውና ጉዳይ ነው የሚለው የመንግሥት አነጋገርም ትርጉም የሚኖረው የሚወሰደው ዕርምጃ ጉዳዩን የሚመጥን እስከሆነ ድረስ ነው፡፡ ካልሆነ ግን በችግሩ ብያኔና (Definition of the Problem) በሚወሰደው ዕርምጃ መሀል ትልቅ ገደል አለ ማለት ነው፡፡

 

ሥርዓታዊ ችግር ማለት የሚወጡት ሕጎች ትግበራና አተረጓጎም የሕዝቦችን ተሳትፎ በማመቻቸት መሠረታዊ ችግር አለባቸው ማለት ነው፡፡ ይህ ሲባል ሕዝቦች የሚተዳደሩባቸው አማራጮች የመቀመርን፣ መረጃዎች የማግኘትን፣ የምርጫው ሥርዓት ፍትሐዊነት ጥያቄ ውስጥ ሲገባ፣ ቢሮክራሲያዊ አስተዳደሩ የሚፈጽማቸውን በደሎች በሰላማዊና በተደራጀ አግባብ ሊታገሉበት የሚያስችል ሁኔታ የሌለ መሆኑን የማያመላክት ነው፡፡ የአገራችንን ሁኔታ በዝርዝር ለማየት እንዲያስችለን የሲቪል አስተዳደርና የደኅንነት አስተዳደር በሚል ከፋፍለን እንየው፡፡

 

የሲቪል ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር

የሲቪል ዴሞክራሲ አስተዳደር ስንል ሁሉን አቀፍ አስተዳደር ማለታችን ነው፡፡ የሲቪል አስተዳደሩ ደኅንነትን ጭምር የሚመራ መሆኑ በቅድሚያ መታወቅ አለበት፡፡ ዕውቁ የዴሞክራሲ ጉዳዮች ተመራማሪ ሮበርት ዳል ለዴሞክራሲ አስፈላጊ ያላቸውን ሦስት ነገሮች ይዘረዝራል፡፡ እነዚህም የወታደራዊና የፖሊስ ኃይልን በሕዝብ በተመረጡ ሰዎች ቁጥጥር ሥር ማድረግ፣ የዴሞክራሲያዊ እምነቶችና የፖለቲካዊ ባህል መዳበር፣ ለዴሞክራሲ ተፀባኢ የሆነ የውጭ ኃይል ቁጥጥር ሥር አለመውደቅ ናቸው፡፡ ለዚህም ነው ሲቪል አስተዳደር ሁሉን አቀፍ ነው የምለው፡፡ በፌዴራልና ክልል ደረጃ ከላይ የተገለጹት ተቋማት ከመልካም አስተዳደር አንፃር በሁለት ቁልፍ መመዘኛዎች መገምገም ተገቢ ይመስለኛል፡፡ ከተጠያቂነትና ከሕግ የበላይነት አንፃር፡፡

 

“OSCE” የተባለ ድርጅት ዴሞክራሲያዊ አስተዳደርን እንደሚከለተው ይገልጸዋል፡፡ ‹‹democratic governance is a system of government where institutions function according to democratic process and norms, both internally and in their interaction with other institutionss›› ትርጉም፡- ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ማለት ተቋማት በውስጣዊ ሥራቸውንም ይሁን ከሌሎች ተቋማት ጋር የሚያደርጉትን ግንኙነት በዴሞክራሲያዊ አሠራርና ወጎች መሠረት አድርጎ የሚንቀሳቀስ መንግሥታዊ ሥርዓት ነው፡፡ እንደ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የእስያና የፓስፊክ ማኅበራዊ ኮሚሽን አረዳድ፣ መልካም አስተዳደር ስምንት ዋና ባህርያት አሉት፡፡ መግባባት ላይ ያተኮረ (Consensus Oriented) ተጠያቂነት፣ ግልጽነት፣ መልስ ሰጪነት፣ ውጤታማነትና ቅልጥፍና፣ ፍትሐዊነትና የሕግ የበላይነት ናቸው፡፡
ተጠያቂነት   

መንግሥት በአጠቃላይ ኃላፊነት በመውሰዱም ተቋማቶቻችን እንደ ተቋምና ባለሥልጣኖቻችን በየግል በተሟላና የችግሩ ክብደት በሚመጥን ደረጃ ኃላፊነት አልተወጡም፡፡ ኃላፊነታቸውን አልተቀበሉም፡፡ እንደ ተቋም ስንል ሕገ መንግሥት/ታት ያስቀመጠላቸውን ሥልጣንና ግዴታ ለመወጣት ያስቀመጡዋቸውን ፖሊሲዎችና መመርያዎች ተቀባይነትና አቅም (Legitimacy and Capacity) ለመገንባት ያደረጉት ጥረትና አባሎቻቸው (ከፍተኛ አመራሩን ጨምሮ) ለዴሞክራቲክ አስተዳደር ያላቸውን ብቃትና ቁርጠኝነት ማለታችን ነው፡፡ ለምሳሌ ሕግ አስፈጻሚው (ከሁሉም ተቋማት በተጨባጭ የበረታው ስለሆነ ነው ያስቀደምኩት) ቢያንስ ቢያንስ ለአሥራ ሁለት ዓመታት ‹‹የመልካም አስተዳደር ቁልፍ ችግር ነው›› እየተባለና እየተዘመረ ሳለ ለምን ችግሩ እየገነነ መጣ? ለምን አልተፈታም? ብሎ አጠቃላይ ሥርዓቱን ማለት ፖሊሲዎችን፣ ስትራቴጂዎችንና አሠራሮችን መፈተሽ ይኖርበታል፡፡ ያለ ተጨባጭ ድርጊት የ‹‹ችግር አለብን›› መዝሙር መዘመር ተስፋ አስቆራጭና አሰልቺ ነው፡፡ ዋናው ቁም ነገሩ ምን ተሠራ ነው፡፡

 

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስፈጻሚውን የሚኒስትሮችና የዳኞች ፕሮፖዛል ያልተቀበለበት ሁኔታ አለን? ወይስ የመጣለትን ፕሮፖዛል መሠረታዊ ለውጥ እንዲደረግለት ወደመጣበት እንዲመለስ ያደረገበት ሁኔታ ነበር? በእኔ ግንዛቤ መልሱ አሉታዊ ነው፡፡ ከነበረም ግልጽነት አልነበረውም ማለት ነው፡፡ እንዲህ ከሆነ የተወካዮች ምክር ቤት ለምን ያስፈልጋል?

 

የሚኒስትሮችና የኮሚሽነሮች ብቃትና ቁርጠኝነት መዳሰስ እንዲሁም ፖለቲካዊ፣ አስተዳደራዊና አስፈላጊ ሕጋዊ ዕርምጃ መውሰድ ይኖርበታል፡፡ ከሁሉም በላይ ግን ሕግ አውጪው ሕግ ተርጓሚውን ሽባ በማድረግ የነበረውን ሚና በግልጽ ማስቀመጥና ኃላፊነት መውሰድ ይጠይቃል፡፡ ገዥው ፓርቲ ከፍተኛ ሥልጣን በመቆናጠጡ በማዕከላዊነት (ጠርናፊ፣ Centralism) ሕገ መንግሥቱን በመናድ ሕግ አውጪው የሕግ አስፈጻሚው ተከታይ ብሎም ሕግ ተርጓሚው ተቀጥያና ማኅተም መቺ (Rubber Stamp) ያደረገበትን፣ በተለይ በመንግሥትና በገዥው ፓርቲ መካከል መኖር የነበረበትን ተነፃፃሪ ነፃነትን (Relative Independence) መጥፋቱና ከብቃት ይልቅ ለፓርቲ ተዓማኒነት ቅድሚያ በመስጠት ሲቪል ሰርቫንቱ እንዲሽመደመድ ማድረጉ፤ ፖሊሲዎችን፣ አሠራሮችን፣ የምልመላ ሹመትና ምደባ ሥርዓቱ መሠረታዊ ማስተካከያ ለማድረግ ኃላፊነትና ቁርጠኝነት ማሳየት ይኖርበታል፡፡ ሁሉም ተቋማትና የሚመሩዋቸው አመራሮች ኃላፊነት በመውሰድ የረጅምና የአጭር ጊዜ መፍትሔ ማስቀመጥ፣ ሁሉንም ተቋማት በዳሰሰ መልኩ መከናወን አለበት፡፡ ለምሳሌ የፍትሕ መጓደል አለ ብለን ምን መደረግ አለበት ስንል፣

 

ሀ) ከረጅም ጊዜ አንፃር 

በአራቱ የመንግሥት አካላት ሕገ መንግሥቱን መሠረት በማድረግ የኢትዮጵያን ሁኔታ ባዛመደ መልኩ ሰፊ ጥናት ማካሄድ፡፡ አጠቃላይ ሕጎች (Substantive Laws) በተለይም የሥነ ሥርዓት ሕጎች (Procedural Laws) ተመልሶ ማየትና ማሻሻያ ማድረግ፣ የፍትሕ አካላትን፣ ትምህርት ቤቶችን (እንደ ሕግ ትምህርት ቤቶች፣ ፖሊስና ዓቃቤ ሕጎች ማሠልጠኛ) ወዘተ. ዓላማ፣ አደረጃጀትና ብቃት ማጥናትና አስፈላጊ ማስተካከያ ማድረግ፡፡

ለ) ከአጭር ጊዜ አንፃር

–    የዳኝነት፣ የዓቃቤ ሕግ፣ የፖሊስ መኮንኖች ወዘተ ምልመላ፣ ምደባ፣ ዕድገትና ሹመት ማጥናት እና አደረጃጀቱን ማስተካከል፡፡
–    የፍትሕ መጓደል ላይ የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ሚና፣ ከሕግ አውጪው፣ ከሕግ ፈጻሚውና ተርጓሚው አንፃር መገምገምና አስፈላጊ ዕርምጃ መውሰድ፡፡
–    የዳኝነት፣ የዓቃቤ ሕግ፣ የፖሊስ መኮንኖች ወዘተ. ሞራላዊና ቁሳዊ ፍላጎቶችን ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ማስተካከል፡፡
–    የሕግ ተርጓሚው ነፃነት በግላጭና በሥውር የሚጥሱት ላይ የማስተካከያ ዕርምጃ መውሰድ፡፡
–    ለሃምሳ ዓመታት ሕዝብን አገልግለናል እያለ በትዕቢት የሚፎክረው የመንግሥት ሚዲያ ሃምሳ ዓመታት ሙሉ የፍትሕ መጓደል መሣርያ እየሆነ ስለሆነ እርምት ይደረግበት ለአፄ ኃይለ ሥላሴ ሥርዓት መለኮታዊ መዝሙር ሲያስተጋባ የኖረ፣ የደርግን አምባገነናዊ ሥርዓት መሣርያ በመሆን ‹‹የፍየል ወጠጤን›› እየዘመረ ለደም መፋሰስና ለአገራዊ ውድቀት ሲጮህ ከርሞ፣ አሁንም የሕገ መንግሥቱን አንቀጽ ሃያ ዘጠኝ በመጣስ ‹‹ያለ ኢሕአዴግ መንገድ ሁሉም የጥፋት መንገድ ነው›› የሚለውን ኢዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ በተለያዩ መንገዶች ሲያሠራጭ ፍትሕ በከፍተኛ ደረጃ እየተጓደለ ‹‹ሁሉም ነገር አበረታች ነው፣ ተስፋ ሰጪ ነው፣ አመርቂ ነው፣ ሰውም ደስተኛ ነው›› ብሎ ቱልቱላውን የሚነፋ ተቋም ነው፡፡ መሠረታዊ ባህሪውና አሠራሩ ለተመለከተው የኢትዮጵያ/የክልል መንግሥታት ሚዲያ ነው? ወይስ የኢሕአዴግ ልሳን? ወይም የአባል ድርጅቶቹ ነው? ብሎ ለመለየት አስቸጋሪ የሆነ ነገር ነው፡፡ የፍትሕ ሥርዓቱን በማኮላሸት እየተጫወተው ያለውን ሚና በድፍረት መገምገምና ማስተካከል ይገባል፡፡

 

በአጠቃላይ ሕገ መንግሥታዊና የዴሞክራሲ ተቋማቱ በዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ዙርያ ለሚታየው ችግር ኃላፊነት እንዲወስዱ፣ ከፍተኛ አመራሮቹም በግልና በቡድን ተጠያቂ የሚሆኑበትና ለሕዝቦች በግልጽ የሚታወቅበት ሁኔታ መፍጠር፣ በዚህም ሥርዓቱን እንዲያስተካክሉ ማድረግ ለነገ የማይባል ሥራ ነው፡፡
የሕግ የበላይነት ፍራንሲስ ፉኩያማ “Political Order and Political Decay” በሚለው መጽሐፉ ‹‹Rule of law should be distinguished from what is sometimes referred to as ‘rule by law’. In the latter case, law represents commands issued by the rulers but is not binding on the ruler himself.›› በአጭሩ ሲተረጎም የሕግ የበላይነትና በሕግ መግዛት የተለያዩ ናቸው ይላል፡፡ እንደሚታወቀው የሕግ የበላይነት ማለት ሕግ የበላይ ሆኖ ሁሉንም ሰው በእኩል ሲያይ ነው፡፡ በሕግ መግዛት ግን ሕግ ከመሪዎቹ የሚወርዱ ትዕዛዛት ሆነው መሪዎቹ ላይ ተፈጻሚ መሆን የማይችሉ ሲሆኑ ነው፡፡ የፌዴራልና የክልል ተቋማትና አመራሮች እንደ ተቋምና እንደ ግል ኃላፊነት ሳይወስዱና መደረግ ያለበትን ማስተካከያ ሳያደርጉ፣ በአንዳንድ የበላይ አመራር ላይ ዕርምጃ ሳይወስዱ፣ ‹‹በአዲስ አበባ አስተዳደርና በክልሎች በሺዎች የሚቆጠሩ የመካከለኛና የበታች አመራሮችና ተራ ሲቪል ሰርቫንት ላይ ዕርምጃ ወሰዱ›› ያውም በግምገማ የሚል ዜና ስሰማ በጣም ደነገጥኩኝ፡፡ ምን ዓይነት ኃላፊነት የጎደለው ዕርምጃ ነው? አልኩኝ፡፡ የውሳኔያቸውና የድርጊታቸው ምክንያት ሊገባኝ አልቻለም፡፡ የህልውና ጉዳይ ነው ለተባለው ብልሹ አስተዳደር ዋነኛ ተጠያቂዎቹ ዕርምጃ የተወሰደባቸው ናቸው ማለታቸው ይሆን? በየጊዜው በተለይ በሲቪል ሰርቪሱ የሚወሰደው ዕርምጃ መንግሥት በ25 ዓመታት ውስጥ መጠነኛ ተዓማኒነት ያለው ሲቪል ሰርቫንት ላለመገንባት የሚኖረው ሚና ምን ይሆን? የሚለው ጥያቄም ጫረብኝ፡፡

 

ፖሊሲ፣ መመርያ፣ ሕግ፣ አደረጃጀት፣ ወዘተ. የሚያወጡት አመራሮቹን የመለመለ፣ የመደበ፣ የሾመ ሥርዓት ሲኮፈሱበት የነበሩ የላይኛው አመራር እንዴት ቢሆን ነው ግምገማውና ዕርምጃው እነሱን የማይነካውና ዕርምጃ የማይወሰድባቸው? ኦሮሚያ በሁለት ከፍተኛ አመራሮች የማሸጋሸግ ሥራ የሠራ ይመስለኛል፡፡ ይህ ግን ከአጠቃላይ ሥርዓቱ አንፃር ሲታይ ከቁብ የማይገባ ቀላል ጥገናዊ ባህሪ ያለው ዕርምጃ ነው፡፡ ከአምስት እስከ አሥር ዓመት የክልል ፕሬዚዳንት/ከንቲባ፣ ካቢኔ ሆነው ሲያገለግሉ የብልሹ አስተዳደር መሪዎች እንዳልነበሩ፣ የተገኘው ኢኮኖሚያዊ ዕድገት በእነሱ መሪነት እንደመጣ እንዳልፎከሩ፣ የብልሹ አስተዳደር ችግር ሲነሳ ኃላፊነት ሳይወስዱና ሳያስተካክሉ እርስ በርሳቸው የእከክልኝ ልከክልህ ግንኙነት ፈጥረው 360 ዲግሪ ተገልብጠው የመልካም አስተዳደር አርበኞች ሲሆኑ ማየት፣ ከማስገረም አልፎ ያስቃል ያናድዳል፡፡ መቶ በመቶ አሸንፈው የለ!

 

ዕርምጃ ከተወሰደባቸው ሰዎች የእውነት ጥፋተኞች ይኖራሉ፣ በርከት ያሉ ንፁኃንም ይገኛሉ፡፡ አካሄዱ ግን አጠቃላይ ዓውዱን (Context) በሙሉ ሳይዳስስ፣ በሕግ የተረጋገጠ መረጃ ሳይኖር እንዴት ፍትሐዊ ሊሆን ይችላል? የሕግ የበላይነት እንጦረጦስ ገባ፣ ሕግ ደካማው በጉልበተኛው የሚመታበት መሣርያ ሆነ፣ ሕግ ዝሆኖችን የማትነካ የሥልጣን መከታ የሌላቸው የታችኛው አመራርና ሲቪል ሰርቫንቱ መምቻ ሆና እንደማየት ምን የሚያሳቅቅ ነገር አለ? በሕግ መግዛት እየነገሠ፣ የመልካም አስተዳደር እንቅስቃሴ ከጅምሩ እየተኮላሸ ነው፡፡ ካልተስተካከለ የውድቀት መንገድ ነው፡፡ የሕወሓት/ኢሕወዴግ የትግል ጊዜን አስታወሰኝ፡-

 

ሕወሓት/ኢሕወዴግ መሠረታዊ ችግሮችን በግለሰቦችና በተለይ በታችኛው አመራሮች ሲያላክክ የመውደቅ አዝማሚያ፣ የተስፋ መቁረጥና የመበታተን አደጋ ያጋጥመው ነበር፡፡ መሠረታዊ የችግሮቹ ምንጭ የሚሊተሪ ዶክትሪን፣ የፖለቲካ ፖሊሲ፣ አደረጃጀትና አሠራር ናቸው ብሎ ከፍተኛ አመራሩ ኃላፊነት ሲወስድ፣ በሚገርም ሁኔታ በአጭር ጊዜ ከሌሎች አጋሮቹና ሕዝቦች ጋር ሆኖ ተዓምር ሊባል የሚችል ሥራ ሠርቶ ደርግን ደመሰሰ፡፡ አሁን ከሚታየው አካሄድ ግን ሌላው ቢቀር በችግሮቹ ምንጭ ላይ እንኳን ጠለቅ ያለ ሐሳብ ሳይዳብር ነው ተገቢ ወዳልሆነው ኃላፊነት የጎደለው የማባረር ዕርምጃ የተገባው፡፡ ለዚያውም ከፍተኛ አመራሩ ራሱን ንፁህ አድርጎ የበታቹን አካል እየቀጠቀጠና እያንቀጠቀጠ፡፡

 

የደኅንነት አስተዳደር (Security Governance)

 

የዴሞክራቲክ/መልካም አስተዳደር ችግር በአንድ ፖለቲካዊ ሥርዓት እንደ ወረርሽኝ መታየት አለበት፡፡ ሁሉም የሥርዓቱ ተቋማት በአንድም በሌላ መንገድ ይነካካሉ፡፡ ደረጃቸው ይለያያል እንጂ በፖለቲካ ያለው ችግር ሁሉንም ያዳርሳል፡፡ የደኅንነት ተቋማት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በሲቪል ክፍሉ ስለሚመሩ ጠንካራ ዴሞክራቲክ አስተዳደር በሚኖርበት ጊዜ የደኅንነት ኃይሎች የተሻለ ባለሙያ፣ ለሕገ መንግሥቱ ታዛዥ፣ እንደሌላው የተጠያቂነትና የግልጽነት፣ የሕግ የበላይነት ያለበት አካል ይሆናል፡፡ በዴሞክራቲክ አስተዳደሩ ችግር በሚኖርበት ጊዜ የደኅንነት ተቋማት የሚስጥራዊነት ባህሪና በተለይ የመከላከያ ሠራዊት አጠቃላይ ዝግጅቱ ጦርነት እንዳይኖር፣ ጦርነት ሲታወጅም በአጭር ጊዜ በተነፃፃሪ በአነስተኛ ኪሳራ ለማሸነፍ የዕዝና የቁጥጥር ሥርዓቱ ጠበቅ ያለ በመሆኑ ለብልሹ አስተዳደር የበለጠ ተጋላጭ ያደርገዋል፡፡ በዕዝ ሰንሰለት የሚንቀሳቀስ በመሆኑ ለመባለግ (Abuse of Power) የተጋለጠ ይሆናል፡፡ ይህ የሚሆነው ቀደም ብሎ እንደተጠቀሰው በሲቪል አስተዳደሩ የዴሞክራቲክ አስተዳደር ችግር ሲኖር ነው፡፡

 

ችግሮቹ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፉ ከሄዱም ወታደራዊ ክፍሉ የራሱን ፖለቲካዊ ፍላጎት አዳብሮ በጡንቻው ለመንገሥ ሊፈልግ እንደሚችል ከተለያዩ አገሮች ተሞክሮ መማር ይቻላል፡፡ ይህ እንኳን ማድረግ ባይችል አንጋሽና አፍራሽ (King Maker and Breaker) የመሆን ልዩ ፍላጎት ሊያዳብር ይችላል፡፡ ወታደራዊ ክፍሉ በሲቪሎች ቁጥጥር ሥር ካልዋለ መንግሥት ባለበት አገር ሌላ ራሱን የቻለ መንግሥት (State Within a State) ሊሆን ይችላል፡፡ ልክ እንደ ግብፅ መከላከያ ሆነ ማለት ነው፡፡ ጠብመንጃ ዴሞክራቲክ አስተዳደርን የሚያዝበት ሁኔታ መኖር የለበትም፡፡ በተለይ ታዳጊና በሽግግር ላይ ያሉ የሦስተኛ ዓለም የደኅንነት ተቋማት ብዙውን ጊዜ የበለጠ የተደራጀ፣ የታጠቀ በመሆናቸው ከሌሎች መንግሥታዊ ተቋማት የበለጠ ተሰሚነት እንዲኖራቸው የሚጥሩ፣ በምርጫና መንግሥት በመመሥረት ሒደት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ተፅዕኖ የሚያደርጉ መዋቅሮች ናቸው፡፡ አንድ የፖለቲካ ኃይል የፀጥታ/የደኅንነት ኃይሎች በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ ካልደገፉት በምርጫ የማሸነፍ ዕድሉ ይጠባል፡፡ አሸናፊው ፓርቲ መንግሥት ለመመሥረት እንኳን ሊቸገር ይችላል፡፡ በዚህ መሠረት ዴሞክራቲክ ተቋማት ባልዳበሩባቸው እንደኛ ያሉ አገሮች ሙያተኛነት በጣም ያደገ ባለመሆኑ የጦር ኃይሉ ገለልተኛ ሊሆን አይችሉም፡፡ በዚህ ምክንያት በዴሞክራቲክ ሥርዓት ዘብ የመሆን ወይም የኢዴሞክራቲክ ኃይሎች መሣሪያ የመሆን ዕድል ከፍተኛ ነው፡፡ መከላከያ ሚኒስቴር ወይን መጽሔትን ስፖንሰር ማድረጉን ከሕገ መንግሥቱ አኳያ ስህተት መሆኑንና መታረም እንዳለበት ጽፌ ነበር፡፡ ይህን ተከትሎ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ወይም የመከላከያ ሚኒስትሩ ምን እንዳደረጉ ባላውቅም፣ ከዚህ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ጥያቄዎችና ሐሳቦች ተነስተው ነበር፡፡ ሐሳቦቹ የብዙ ሰዎች አስተያየቶች መሆናቸውን ተረድቼያለሁ፡፡
በመጀመሪያ ተቃውሞ ያዘለው ጥያቄ ‹‹እንዴት መከላከያን ትነካለህ?›› የሚል ነበር፡፡ ምን ማለት ነው? ብዬ ጠየቅኩት፡፡ ‹‹አለኝታችን ነው በሌላ አገላለጽ የመከላከያ ሠራዊታችን ችግሮች በአደባባይ መግለጽ ለጠላት አሳልፎ እንደመስጠት ይቆጠራል፤›› አለኝ፡፡ አዎ ሚስጥር የሚባሉ ነገሮች በጥብቅ መጠበቅ አለባቸው፡፡ ሁላችንም ጠላቶች ሚስጥሮቻችንን እንዳያውቁ በከፍተኛ ደረጃ የመከላከል ግዴታ አለብን አልኩት፡፡ ነገር ግን ሠራዊታችን ሕገ መንግሥቱን በመፃረር በፖለቲካዊ ጉዳዮችን እጁን ቢያስገባ ወይም አንዱን ፓርቲ ደግፎ ሌላውን ለማዳከም ሲሞክር ዝም እንላለን ወይ አልኩት፡፡ የኢትዮጵያ የውጭና ብሔራዊ ደኅንነት ፖሊሲ የደኅንነት ጉዳዮች፣ ሚስጥራዊ ከሚባሉ በስተቀር ኅብረተሰቡ በዝርዝር እንዲያውቃቸው ከሩቅ መከላከያን የመፍራት ጉዳይ እንዳስቀረ ገለጽኩለት፡፡ አቅማማ ነገር ግን፣ ‹‹መከላከያ ሠራዊታችን የአብዮታዊ ዴሞክራሱ ሠራዊት አይደለም ወይ?›› አለኝ፡፡ ሠራዊታችን የሊበራል ዴሞክራሲ፣ የሶሻል ዴሞክራሲ ወይም የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ፓርቲዎች ሊሆን አይችልም፡፡ የሕገ መንግሥታችን አንቀጽ 87/5/ እንዲህ ይላል አልኩት፣ ‹‹የመከላከያ ሠራዊቱ ተግባሩን ከፖለቲካዊ ድርጅቶች ወገናዊነት ነፃ በሆነ አኳኋን ያከናውናል፡፡››
ሌሎች ሁለት ሆነው፣ ‹‹በአሁኑ ጊዜ ጠባብነትና ትምክህተኝነት በትግራይ ተወላጆች ላይ በሚያነጣጥሩበት ጊዜ እንዴት መከላከያን ትተቻለህ?›› አሉኝ፡፡ እንዴት ብዬ ጠየቅኩ፡፡ ‹‹ዋስትናችን ነው›› አለኝ፡፡ ከ27 እስከ 28 ዓመት በፊት የሆነውን በመተረት ሥርዓቱ ዴሞክራሲያዊና ፍትሐዊ እስከሆነ ድረስ ዋና አዛዥ ከየትኛውም ብሔር ይምጣ፡፡ ሠራዊቱ የሕገ መንግሥት ታዛዥ እስከሆነ ድረስ የሁሉም ሕዝቦች ዋስትና እንደሚሆን፣ ነገር ግን ሥርዓቱ ፀረ ሕዝብ ከሆነ ለሁሉም ፀረ ሕዝብ እንደሚሆን አንድ ታሪክ አውስቼ አጫወትኩት፡፡ ታሪኩ እንዲህ ነው፡፡
የሕወሓት ሠራዊት መንዝ ሸዋ በገባበት ጊዜ የተከሰተ ነው፡፡ ወደ ሠራዊቱ የተቀላቀሉት አዲስ ታጋዮች መንዝ ሲገቡ የሕዝቡ የኑሮ ሁኔታ ሊገባቸው አልቻለም፡፡ የሕዝቡ ኑሮ ከትግራይ ሕዝብ በምንም ሁኔታ የማይሻል ሆኖ ሲያገኙት አንዳንዳቹ ተዋከቡ፡፡ የአማራ ገዥ መደብንና የአማራን ሕዝብ መለየት አልቻሉም፡፡ ‹‹እንዴት ነው አማራ ጠላታችን ነው ያላችሁት ተታልለን ነው የታገልነው›› አሉ፡፡ በነባሮቹና በአዲሶቹ መካከል የጦፈ ክርክር ተካሂዶ በመጨረሻ ተማመኑ፡፡ ሕወሓት ሲያስተምራቸው የነበረው ግልጽ መሆኑ እሱም፣ ‹‹የአማራ ገዥ መደቦች በአማራ ስም ሲነግዱም ለራሳቸው ካልሆነ ለአማራው ምንም እንዳልሠሩለትና አማራም እንደሌላው ሕዝብም እንደሚጨቆን›› ተማመኑ፡፡
በመቀጠልም የአማራ ዴሞክራሲያዊ ብሔርተኝነት በሚል በ1985 ዓ.ም. በተጻፈው መሠረት የነፍጠኛው ሥርዓት በአማራው ሕዝብ ላይ ያስከተላቸው መዘዝ እንዲህ እንደሚል ገለጽኩላቸው፡፡
1.    ሰፊው የአማራ ሕዝብ ለኋላቀርነት ለብዝበዛ ተጋልጧል፣
2.    የአማራ ሕዝብ የዴሞክራሲያዊ መብቶቹ ታፍነዋል፣
3.    የአማራ ሰፊ ሕዝብ የጦርነት ሰለባ ሆኗል፣
4.    ሌሎቹ ሕዝቦች በአማራ ሕዝብ ላይ ጥርጣሬ እንዲያሳድሩ አድርጓል፣ የሚለውን ገለጽኩለት፡፡
የደኅንነት አስተዳደሩ ጤናማ ሊሆን የሚችለው የሲቪሎች ቁጥጥር ተገቢና ከፍተኛ ሲሆን፣ ይህም በዋናነት ሊረጋገጥ የሚችለው በተሟላ የብሔራዊ ደኅንነት ካውንስልና በጣም በተጠናከረ የደኅንነት አስተዳደር ሴክሬታሪያት ነው፡፡ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ የብሔራዊ ደኅንነት ፖሊሲ ስለደኅንነት ማኔጅመንት የሚለው ነገር የለም፡፡ ትልቁ ድክመቱ እዚህ ነው ያለው፡፡ ያለ ግልጽ የማኔጅመንት አደረዳጀት ፖሊሲው የትኛውንም ያህል ብቁና ግልጽ ቢሆንም ጠንካራ የማኔጅመንት ሥርዓት እስከሌለው ድረስ የሲቪሎች ቁጥጥር ሊታሰብ የሚችል ጉዳይ አይደለም፡፡ ከዴሞክራሲያዊ አስተዳደር አኳያ መጀመሪያ መገምገም ያለበት የፖሊሲው ማኔጅመንት ነው፡፡ ሌላው አሠራሩ ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለው መሆኑ ነው፡፡ ጀግኖችና ብቃት ያላቸው ወደ አመራር የሚመጡበት ሥርዓት አለ ወይ? ካለስ ሥርዓቱስ በትክክል ተግባራዊ ይሆናል? ወይስ ትውውቅና ግላዊ ፍላጎት መሠረት ተደርጎ ነው እየተሠራ ያለው? ብሔራዊ አስተዋጽኦ ለማስተካከል እየተሠራ ያለው ሥራ ምን ይመስላል? ወዘተ መፈተሽ አለበት፡፡
የሲቪል አስተዳደሩ ቀጥጥር ሊረጋገጥ የሚችለው በሰፊ ትንተና የታጀቡ በርከት ያሉ አማራጭ ሐሳቦች (Scenarios) ማቅረብ የሚችል ብሔራዊ (አገራዊ) የደኅንነት ምክር ቤትና ይህንን ሥራ የየሚያስተባብር ጽሕፈት ቤት ያስፈልጋል፡፡ ይህ ሳይሆን ሲቀር ግን ወታደራዊ ክፍሉ በሲቪል አስተዳደር ቁጥጥር ሥር ለማድረግ አዳጋች ይሆናል ብቻ ሳይሆን፣ የታጠቀው ኃይል ክፍተቱን እንዲጠቀምበት ያስችለዋል፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር የኢትዮጵያ ሕዝብ ሉዓላዊ የሥልጣን ባለቤትነት ማረጋገጫ ተቋም እንደመሆኑ መጠን የጦር ኃይላችን ፖሊሲ፣ በጀት፣ ግዥ፣ ዕድገት የመከታተል ሕገ መንግሥታዊ ሥልጣኑን በመጠቀም ጭምር ነው ወታደራዊ ክፍሉ በሲቪል አስተዳደር ቁጥጥር ሥር እንዲውል ማድረግ የሚችለው፡፡ የደኅንነት አስተዳደር የሕዝቦች ሕይወት፣ እሴትና ደኅንነት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ የሚያሳድር ነገር ስለሆነ ለሥራ አስፈጻሚው ወይም ለወታደራዊ ክፍሉ ብቻ ሊተው አይገባውም፡፡ የሲቪል አስተዳደር ቁጥጥሩ ጥብቅ ካልሆነ የወታደራዊ ክፍሉ የፌዴራል ሥርዓቱን (በተለይ በታዳጊ ክልሎች የባላባታዊ ምስለኔ ዓይነት) ጣልቃ ገብነት ሊያስከትል ስለሚችል ከወዲሁ ጥንቃቄ ሊደረግበት ይገባል፡፡
የዴሞክራሲያዊ ብሔርተኝነት መጠናከር ለዴሞክራቲክ አስተዳደር መጎልበት መሠረት ነው
ዴሞክራሲያዊ ብሔርተኝነት ብዙ ብሔር ብሔረሰቦች ባሉበት አገር የአንድ ብሔር/ብሔረሰብ ብሔራዊ ጥቅም ከብሔሩ ሰፊ ሕዝብ ጥቅም ማስከበር ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ በሕዝቦች መካከል መሠረታዊ የጥቅም መቃረንና መጋጨት ስለማይኖር ደግሞ፣ የሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ብሔራዊ ጥቅም በተሟላ መንገድ መሟላት አለበት ብሎ ማመን ነው፡፡ የሌላ ብሔር ብሔረሰብ ጥቅም ወይም ጉዳት የራሱን ጥቅም ወይም ጉዳት አድርጎ የማየት አስተሳሰብ ነው፡፡ ብዙኃነትን የሚያስተናግድ ዴሞክራቲክ አስተሳሰብ ማለት ነው፡፡ የሕዝቦች ዴሞክራቲክ አንድነትና የሁሉንም ሕዝቦች ጥቅሞች የሚያረጋግጥ በመሆኑ ለአንድነት ይቆማል፡፡ በዚህ ረገድ የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት በመግቢያው ላይ የሥነ ሐሳብ ግልጽነት ባለውና በተሟላ መልኩ በብዝኃነት ውስጥ ስላለው አንድነት እንደሚከተለው ይላል፡፡ ‹‹እኛ የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የራሳችን ዕድል በራሳችን የመወሰን መብትንና በራሳችን ፈቃድ ላይ የተመሠረተ አንድ የፖለቲካ ማኅበረሰብ በጋራ ለመገንባት ቆርጠን በመነሳት…›› በዚህ መሠረት ይህንን የሕገ መንግሥቱን ዓላማ በተሟላ መንገድ መቀበል፣ ማሳደግና መተግበር ነው፡፡
አንድ የፖለቲካ ማኅበረሰብ በሚለው ሥነ ሐሳብ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መሠረታዊ የዴሞክራሲ፣ የልማትና የደኅንነት ዋስትና መሆኑን በግልጽ ያስቀምጣል፡፡ የጋራ ታሪክ (በበጎም በመጥፎም) ያላቸው ሕዝቦች እንደሆኑ እንደ አንድ ዋና መነሻ አስቀምጦ፣ ነገር ግን ዋናው ወደፊት አንድ የፖለቲካ ማኅበረሰብ በጋራ የመገንባት ነው፡፡ ሕገ መንግሥቱ የነበረውን አሃዳዊ አስተዳደር እንደ አዲስ በማደራጀት (Reengineering) ፌዴራላዊ ሥርዓት መመሥረቱ የሕዝቦችን መፃኢ ዕድል በጋራ የመገንባት መሠረት ጥሏል፡፡ ይህንን እንደ አዲስ በማደራጀት የተገኘ አዲስ የኢትዮጵያዊነት ማንነት የሽግግርና የማጠናከር ሥራን ይጠይቃል፡፡ አዲሱ የሥልጣን ግንኙነት በፌዴራልና በክልሎች ሲተገበር እንደ ማንኛውም አዲስ ሙከራ እንደመሆኑ፣ ወደ ትክክለኛ የሚዛን ምጣኔ እስከሚመጣ ድረስ ወደ ግራ ወደ ቀኝ መወናጨፍ የማይቀር ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ትዕግሥትና መቻቻልን ሕዝቦች ከተሞክሯቸው እንዲማሩ ዕድል መስጠት አስፈላጊ ነው፡፡ ሕዝቦች የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው የመወሰን መብታቸው በሚያደርጉት እንቅስቃሴ በተለይ ግትር ያልሆነ፣ ጥቅሞችን በማጣጣምና በጋራ ስምምነት የሚመራ አመራር ይጠይቃል፡፡
እንደ አለመታደል ሆኖ የእኛ አመራር (በገዥው ፓርቲም ሆነ በተቃዋሚነት ያለ ምናልባት ከኢዴፓ ውጪ) ድርቅና የሚያጠቃው፣ መቻቻል ሽንፈት የሚመስላቸውና አጥፊ ተጋፋጭነት (Destructive Confrontation) ነው ያለው፡፡ ዴሞክራቲክ ብሔርተኝነት ይኼን አመራር ይዞ ሉጎለብት የሚችልበት ዕድል ጠባብ ነው፡፡ ይህ በመሆኑም የትውልድ አመራር ለውጥ አስፈላጊነት በግልጽ ይታያል፡፡ ካለፈው የተማሩ መሪዎች፣ ብቃት ያለው አዲስ ትውልድ፣ ከ25 ዓመታት በፊት ያልነበሩ ተግዳሮቶችንና ጥያቄዎችን መመለስ የሚችል የልማት አመራር ያስፈልጋል፡፡ እያንዳንዱ ትውልድ የራሱን ፍላጎት በሚረዱ የራሱ ዘመን ሰዎች መመራት አለበት፡፡ በኢሕአዴግ አመራር የተፈጠረ አዲስ ትውልድ አለ፡፡ ይህ ትውልድ ዓለም አቀፍ ትስስር ያለው፣ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዕውቀትና ክህሎት ያለው፣ የተሻለ የትምህርት ዕድል ያገኘ፣ በሙሉ ቁመናው ካለፈው ትውልድ በብዙ መመዘኛ የሚሻል ወጣት ምሁር ትውልድ ተፈጥሯል፡፡ ይህ በኢሕአዴግ የአመራር ጊዜ የተፈጠረው ወጣት የመምራት ዕድል ሊሰጠው ይገባል፡፡ ዴሞክራሲያዊ ብሔርተኝነት ኢትዮጵያዊነትንና የብሔር ብሔረሰብና ሕዝቦችን ማንነት አጣምሮ፣ አጣጥሞ ማስኬድ የሚችል አስተሳሰብ ነው፡፡ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ኢትዮጵያዊነትን ወይም አንዱን እንዲመርጡ መገደድ የለባቸውም፡፡ ዴሞክራሲያዊ ብሔርተኝነት ኢትዮጵያዊነት የሚፃረር ተደርጎ መታየት የለበትም፡፡ የኢትዮጵያ ጥንካሬ የሚመሠረተው በብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ብርታት ነው፡፡
በኦሮሚያ የተቀሰቀሰው ተቃውሞና በአማራ ክልል አካባቢ የታየው ብጥብጥ የጠባብ ብሔርተኝነትና የትምክህት እንደገና መጎልበትና በዚህ አገር ላይ አደጋ እንደሆነ መወያያ ሆኖ ሰንብቷል፡፡ ተገቢ ሥጋት ነው፡፡ አንዳንዶቹ ፌዴራል ሥርዓቱ ያመጣው ጣጣ ነው ሲሉ በአንዳንዶቹ ዘንድ እጅግ መደናገጥ ይታያል፡፡ በእኔ አመለካከት ጠባብነት ይሁን ትምክህት በኅብረተሰቡ ውስጥ የሚኖሩ የተወሰኑ ልሂቃን በቀጣይነት ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ የሚጠቀሙባቸው አመለካከቶች ናቸው፡፡ ፌዴራላዊ ሥርዓቱ በተሟላ መንገድ እስኪጠናከር ድረስ አንዴ ብልጭ አንዴ ድርግም እያሉ፣ አንዴ ተጠናክረው አንዴ ተዳክመው የሚታዩ ክስተቶች ናቸው፡፡ በኅብረተሰቡ ውስጥ ያሉ ኋላቀር አስተሳሰቦች ቢሆኑም አብዛኛውን የኅብረተሰብ ክፍል የሚጎዱ እንጂ አይጠቅሙም፡፡ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ሥጋትና ፍርኃት በኅብረተሰቡ ውስጥ በሚያይልበት ጊዜ የሚያጎለብቱ ክስተቶች ናቸው፡፡
ትምክህት አንድ ገዥ መደብ ሕዝቦችን ለመጨቆንና ለመበዝበዝ ከሚጠቀምላቸው መሣርያዎች አንዱ ነው፡፡ ጠባብነትም ጭቆናን የመቃወም ግብረ መልስ (Reaction) ልሂቃን ወደ አንድ ጫፍ የሚወስዱበት አስተሳሰብ ነው፡፡ ሁሉም የሚጎለብቱት የፍትሕና የእኩልነት መጓደልና አጠቃላይ ጭቆና ሲነግስ ወይም ጭቆና አለ ብለው ሲያስቡ ነው፡፡ ስለእነዚህ ኋላቀር አስተሳሰቦች አደገኛነት ኅብረተሰቡን ማስተማር ተገቢ ነው፡፡ ዋናው መፍትሔ ግን ለሥጋትና ለፍርኃት የሚዳርጓቸው ተጨባጭ ወይም ታሳቢ የሚደረጉ ቅሬታዎች በሥርዓት ቀጣይነት ማስተካከል ነው፡፡ ለብቻቸው የቆሙ አስተሳሰቦች አይደሉም፡፡ ትልቁ አደጋ ግን በሕዝቦች የመብትና የዴሞክራሲያዊ እንቅስቃሴዎች ልክ እንደ ደርግ ገንጣይ አስገንጣይ ብሎ በመፈረጅ የሕዝቡን ትግል ለመጨፍለቅ የሚደረግ ሙከራ ነው፡፡
ሰሞኑን በኦሮሚያ የነበረውን ተቃውሞ ፀረ ሰላም ኃይሎች ወደ ሌላ ለመቀየር ቢሞክሩም፣ በሕዝቦች መካከል ጥርጣሬ እንዲኖር የቻሉትን ቢያደርጉም፣ የሕዝቡ እንቅስቃሴ ግን ሕጋዊና ዴሞክራሲያዊ መሆኑን፣ የሕዝቡን ጥያቄዎች ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድና ሕገ መንግሥታዊ ተቋማት በመገንባት መፈታት አለባቸው፡፡ የሕዝቡ ጥያቄ የዴሞክራቲክ አስተዳደር ጉዳይ ነው፡፡ ራሱ በራሱን የማስተዳድር መብቶችን የማጠናከር እንቅስቃሴ ነው፡፡ በአስተዳደሩ ያለውን ልፍስፍስነት የመቃወም ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ስለሆነ በመሠረቱ የኦሮሞ ጥያቄ የዴሞክራሲ ጥያቄ ነው፡፡ ለዚህም ዴሞክራሲያዊ ምላሽ ያስፈልገዋል፡፡ ከወጣት ኦሮሞ ምሁራን ጋር በዚሁ ጉዳይ ላይ የመወያየት ዕድል አግኝቼ ነበር፡፡ ከውይይታችን የተረዳሁት በመሠረቱ በኦሮሚያ ክልል ላይ ያለው ችግር በተመሳሳይ በሌሎች ክልሎች ያለ የዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ችግር ነው፡፡ ነገር ግን እስካሁን እነዚህ ጉዳዮች በኦሮሞ ልሂቃን መካከል በስፋት ውይይትና መፍትሔ የተደረገላቸው አይደሉም፡፡ ይህን ለማድረግ አገር ውስጥ ያለው ጠባብ የፖለቲካ ምኅዳር ዕድል አልሰጣቸውም፡፡
ሁለቱም እንዲህ ሲሉም ነገሩኝ፣ ‹‹የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት የኦሮሞን ሕዝብ ፍላጎት የሚያሟላ ነው፡፡ ነገር ግን አተገባበር ላይ እየሾቀ ነው፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ የተዋጋለት ሕገ መንግሥት ነው፡፡ ይሁን እንጂ እኛ በአገሪቱ በቁጥራችን ብዙ ብንሆንም የሥልጣን ማዕከል ግን መሆን አልቻልንም፡፡ ባለፉት 25 ዓመታት ኦሮሞዎች ስማዊ ብቻ የሆነውን የፕሬዚዳንትነት ሥልጣን ብቻ ነው የተሰጣቸው፡፡ እንዲሁም ወሳኝ በሚባሉ የፖለቲካ ወይም የደኅንነት አመራር ቦታ ላይ አልተደለደሉም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ የፌዴራል መንግሥት ቋንቋ እንዲሆን ፍላጎት አለ፡፡ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 49/5/ የተቀመጠው የኦሮሚያ ክልል ልዩ ፍላጎትና ጥቅም በ25 ዓመታት ውስጥ ሕግ ሳይወጣለት ቀርቶ አሁን እየተጠና ነው ይሉናል፡፡ በአዲስ አበባና አጎራባች ከተሞች ማስተር ፕላን የኦሮሚያ ልዩ ፍላጎትና ጥቅም የሚያረጋግጠው ሳይወጣ የተሠራ መሆኑ ራሱ ሕገወጥ ነው፤›› አሉኝ፡፡
በመቀጠል የመገንጠል አዝማሚያ እንደ ፍላጎት በኦሮሞ ልሂቃን አለ ወይ ብዬ ጠየቅኳቸው፡፡ ጥያቄዬን በጥያቄ መለሱት፣ ‹‹ማን ከማን ነው የሚገነጠለው?›› አለኝ፡፡ ‹‹ያው የኦነግ ፕሮግራም የሚያራምዱ ማለቴ ነው፤›› አልኩኝ፡፡ አንዱ ተናደደና፣ ‹‹ኦነግን በኦሮሞ ልሂቃን ጀግና የምታደርጉት እናንተ ሐበሾች ናችሁ፡፡ ሐበሾች አይደለንም ብንል እንኳን የኦነግ አስተሳሰብ ነው ትላላችሁ፡፡ የኦሮሞን ሕዝብ ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚደረግ ማናቸውም እንቅስቃሴ ይከፋችኋል፡፡ የኦነግ አስተሳሰብ ነው ብላችሁ ኦነግን ትሸልማላችሁ፡፡ ይህ ኢዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ በእኛ ላይ ጥርጣሬ እንድታሳድሩ እያደረገ ነው፡፡ ጥርጣሬ ደግሞ የባሰ ጥርጣሬ ይወልዳል፡፡ ዙርያ ጥምጥሙ ችግር ይኼ ነው፡፡ በእኛ አመለካከት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን በመገንባት የእኛ የኦሮሞዎች ጥቅም ያስጠብቃል ብለን እናምናለን፡፡ እንኳን የኢትዮጵያ እንብርት ሆነን፣ ትልቅ ብሔር ሆነን በአንድ የኢትዮጵያ ጫፍ የሚኖር ብሔር እንኳን በዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ይጠቀማል፡፡ ስለዚህ እናንተ ሐበሾች አንድነት ጠባቂዎች እኛ ብቻ ነን የምትሉትን አባዜ እርግፍ አድርጋችሁ ተው፡፡ ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እስካለች ድረስ ሁሉም ለዚህ አንድነት ይታገላል፤›› አለኝ፡፡ በመጨረሻም ኢትዮጵያ ከ25 ዓመታት በፊት እንደ ነበረችው ባትሆንም አሁንም የአቢሲንያ ማዕከላዊነት የሚጫናት አገር እየሆነች በመሆኑ፣ የተጀመረው የዴሞክራሲ ሒደት አደጋ ውስጥ እየወደቀ ያለባት አገር እንዳትሆን እንደሚያሰጋ ገለጸልኝ፡፡
ሕገ መንግሥቱ የኦሮሞን ሕዝብ ፍላጎት የሚያስከብር መሆኑ እሙን ነው፡፡ የእኛ ትውልድ ቢያንስ ቢያንስ ያን የመሰለ ሕገ መንግሥት አስረክቧል፡፡ ከእንግዲህ እናንተ ወጣት ምሁራን በአተገባበር ላይ ያለ ችግርን እያማረራችሁ መኖር መቆም አለበት፡፡ መሪነቱን ለመንጠቅ መንቀሳቀስ አለባችሁ፡፡ ለምሳሌ የጠቅላይ ሚኒስትር ያነሳችሁት ጉዳይ እንኳን በብዛት ከማንኛውም ብሔረሰብ ትልቁ ሕዝብ ከአናሳም የሚመረጥበት ሁኔታ አመቻችቷል፡፡ እንደምታውቁት በኢሕአዴግ ውስጥ ካሉ አራት ፓርቲዎች የውስጥ ውይይትና ማቻቻል በማድረግ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩን የሚመርጡት፡፡ እንግዲህ ይህን ሒደት ነው መመርመር ያለባችሁ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሌላ ብሔረሰብ በመሆኑ ኦሮሞ ወይም ሌላ ብሔር ይጎዳሉ ወይም ኦሮሞ በመሆኑ ሌሎችን ብሔሮች በመጉዳት ኦሮሞን ይጠቅማል የሚለው አስተሳሰብ የተሳሳተ ነው፡፡ ነገር ግን ጥያቄው ተቀባይነት (Legitimate) ያለው በመሆኑ፣ በመጀመሪያ በኢሕአዴግ ውስጥ መሪነታችሁን ማረጋገጥ አለባችሁ፡፡ ኦሕዴድ የማያሠራ ድርጅት ነው ካላችሁ በራሳችሁ ድርጅት መሥርታችሁ መታገል ነው አልኩዋቸው፡፡ ከሌሎች ወጣት ምሁራን ኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት ብታደርጉ መልካም ነው አልኩዋቸው፡፡
ዴሞክራሲያዊ ብሔርተኝነት እየተመነደገ ካልሄደ የዚህች አገር ዕጣ ፈንታ ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው፡፡ ሆኖም የዴሞክራሲያዊ ብሔርተኝነት አስተሳሰብ የበላይነት እስኪይዝ ጊዜ ይጠይቃል፡፡ ትዕግሥት ያለው ዴሞክራቲክ አመራር ያስፈልጋል፡፡ እስከዚያ ድረስ ደግሞ እየተንገራገጩ መሄድ የማይቀር ነው፡፡ በእስካሁኑ ሒደታችን ተጠቃሽ ሰላምና የኢኮኖሚ ዕድገት ማስመዝገብ ችለናል፡፡ ሆኖም በዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ዙርያ ስኬቶቻችንን ሊንድ በሚችል መልኩ ወደኋላ እየተጎተተ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝቦች መብቶቻቸውን ማስከበር አልቻሉም፡፡ የሚመለከታቸው ተቋማትም ለሕዝቡ ፍላጎት ተገቢ መልስ መስጠት አልቻሉም፡፡ ፖለቲካዊ ሥርዓቱ አደጋ ላይ ነው፡፡ መሪዎቻችን የአመራር ዘይቤያቸውና አመራራቸውን መገምገምና ችግሩ ሥርዓታዊ (Systemic) መሆኑ መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡ የሕግ የበላይነትና ተጠያቂነትም ከላይ እንጂ ከታች እንደማይጀምር መገንዘብ የግድ ይላል፡፡ በተጨማሪም ያለው ችግር ሁሉንም ተቋማት በተለያየ ደረጃ የበከለ መሆኑን መረዳት አለብን፡፡ መፍትሔውም ዴሞክራሲያዊ ተቋማት ሕይወት እንዲዘሩና ምልዓተ ሕዝቡ እንዲሳተፍ ማድረግ ነው፡፡ ሰላምና ልማት ዕውን ያደረገው አመራር ቁርጠኝነትና ብልኃት ከታጠቀ አሁን የገጠመንን ችግር መፍታት ይችላል፡፡

↧

↧

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እየሆነ ያለው ምንድነው –ሰርጸ ደስታ

$
0
0

Ethiopian Orthodox Churchesየእምነትን ጉዳይ ለሰባክያንና ለእምነት አባቶች እየተባለ ብዙ ነገሮች እየተበላሹ ያሉ ይመስለኛል፡፡ ማንኛውም እምነት የሚናገረው ሠላምን፣ የሰው ልጆችን ደህንነት ነው፡፡ በተግባር ሲታይ ግን የሰው ልጆች የደህንነት አደጋ የሚሆኑ ታላላቅ ሴራዎችና የግፍ ዕቅዶች የሚጠነሰሱት በእምነት ካባ ሥር ነው፡፡ በእኔ ግንዛቤ ለዚህ መሠረታዊ የሆነው ምክነያት በእምነት ጉዳይ ላይ ለምንና እንዴት የሚሉ ጥያቄዎች እድል አይሰጣቸውም፡፡ አመክንዮ (ሎጂክ) በእምነት አይሰራም የሚል የሁሉም ባይሆን የአብዛኛው ሀይማኖቶች አስተምህሮት ነው፡፡ በዚህም ምክነያት የእምነት መሪነቱ ቦታ ከጠቢባን ይልቅ በተራ ሰዎች እጅ ይወድቃል፡፡  ወደ ክርስትናው ስንመጣም የዚሁ አስተምህሮት ገዥ ሆኖ እናየዋለን፡፡ ይህ ግን እኔ እንደምረዳው ከመሠረቱ ያልነበረ በኋላ በመጡ ጥበብ በተፈጥሮ ገሸሽ ያደረገቻቸው ሰርጎ ገቦች የተቀላቀለ ባዕድ አስተምህሮት ነው፡፡ የክርስትናው መሠረት የሆነው ክርስቶስ ራሱ አብዛኛው ትምህርቱ አመክንዮን መሠረት ያደረገ እንደነበር እናስተውላለን፡፡ ለዛም ነበር ስላላዩት የሰማያዊ ጉዳዮች ሲያስረዳ ሰዎች በሚገባቸው በምድራዊ ምሳሌ እየመሰለ ያስተምር የነገረው፡፡ አሊያማ እንደ አምላክነቱ ለሁሉም እወቁ ብሎ እንዲያውቁ ማድረግ በቻለም፡፡ በኋላ ለሐዋሪያቱ እንዳደረገው ማለት ነው፡፡ ሌሎችን ትተን ፈላስፋው ቅዱስ ጳውሎስ አብዛኞቹን ሰዎች ሲያሳምን የነበረው በአመክንዮ (ሎጂክ) ነበር፡፡ የግሪክ ፈላስፎችን ሳየቀር ነበር እየተከራከረ የሚረታቸው፡፡ አሁንም ይሄን ስናገር ብዙዎች ግር ሊላቸው ወይም ሊቀፋቸው ይችላል፡፡ እውነታው እግዚአብሔር እኛን ሲፈጥረን ሲገባን እንድንረዳ ነው፡፡ የሚገባን ደግሞ ጭንቅላታችን የሚጠይቀው ጥያቄ መልስ ሲያገኝ ነው፡፡ አብረሃም አመነ ይላል፡፡ አብረሃም ከማመኑ በፊት የገባው አንድ ቁልፍ ጥበብ ነበር፡፡ አብረሃም እግዚአብሔርን ለማግኘት ብዙ አመክኖያዊ ሂደቶችን ሄዷል፡፡ በመጨረሻም ይሄው አመክንዮው ነው የሚነገርለት እምነት ላይ ያደረሰው፡፡ በመጽሐፍ የምናነባቸው ታላላቅ እምነት እንዳላቸው የተመሰከረላቸው ሰዎች እጅግ የመጠቁ ፈላስፎች እንደሆኑ እንረዳለን፡፡ ለዚያም ነው ሁሉን የሚያደርግ እግዚአብሔር እንዳለ ያወቁትም በፍልስፍናቸው ነው፡፡ ልብ በሉ ፍልስፍና ማለት ግን መዘባረቅ አይደለም፡፡ በእምነት በኩል ያሉ ሰዎችን ከከበዳችሁ ቢያነስ ብዙዎች በታሪክ የሚታወቁትን እነ አርስቶትልን ልብ ብላችሁ አስተውሉ፡፡ ከሎጅክ ውጭ የሚከደው ጉዙ ራስን ለአደጋ ማጋለጥ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ሁሉም ከገባው፣ ከተረዳ በኋላ ሲሆን ነው እንጂ አመነ የሚባለው ዝም ብሎ ተቀበል ተቀበል አይነት እምነት አይመስለኝም፡፡

ወደ ተነሳሁበት የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጉዳይ ስመጣ እንደሌሎቹ ሁሉ መጠየቅን የሚያኮስስ በድፍኑ ተቀበል አይነት የአስተምህሮት ስልት አለ፡፡ ከመሠረቱ ግን እንደዚህ እንዳልነበረ ተመዝግበው ያሉ መረጃዎች ይጠቁሙናል፡፡ ይሄ አመክኒዮ አልባው የማስተማር ስልት በሂደት ዋናውን ስፍራ መያዝ በመቻሉ ቀስበቀስ ጠቢባን ከቤተክርስቲያኑ እየመነመኑ መጡ፡፡ በዚህም ምክነያት አገሪቷም ጠቢባን እየነጠፉባት ዛሬ ባዶ የሚያስብል ደረጃ ደረስን፡፡ የአክሱምና ላሊበላን ሚስጢሮች ስናስብ በወቅቱ የነበረው አመክንዮ ላይ የተመሠረተ እምነት ውጤቶች እንደሆኑ እናስተውላለን፡፡ ኢትዮጵያዊው ክርስቲያን ንጉስ ከሳውዲ የመጡ ሙሲሊሞችን በእንግድነት ሲያስተናግድ አምክኒዮዊ ውሳኔ መሥጠቱን እናያለን፡፡ በወቅቱ የንጉሱ ፍልስፍና ከዚህም በላይ የሆነ ነበርና፡፡ በታሪክ አመክኒዮያዊ እምነት ወደ አመክኒዮ አልባ እምነት እየተለወጠ ሲመጣ የዛግዌ መሪዎች ስልጣንን ለሰሎሞናውያን ለሚሉ ያለአመክንዮ እንደሰጡ እናያለን፡፡ በኋላ በመጣው እምነት አድርግ የተባለውን ማድረግ እንጂ እንዴት ለምን ማለት ነውር ሆኗልና፡፡ ትንቢት ተናጋሪ ቢሆን ሌላ ቃሉን እንድንመረምር ስልጣን አለን፡፡  በዚህም ብዙ ሰርጎ ገቦች አጋጣሚውን የተጠቀሙበት እናስተውላለን፡፡  እንግዲህ በሂደት ዛሬ ላይ አመክንዮ ከነጭርሱ አያስፈልግም ሙሉ በሙሉ የመከነ እሳቤ ላይ ደረስን፡፡ በመሆኑም ለተራ ሰው እንኳን የማይታሰቡ ስህተቶች ታላላቅ ተብለው ትልቁን ቦታ በያዙ ሰዎች ሲፈጸሙ እናያለን፡፡ አሁን ማስተዋል ቦታ ስለማይሰጠው ጥበብ ከውስጥ ስለጠፋች ውጫዊ ቁስ ማለት፣ ገንዘብ፣ ሥልጣን፣ጥቅም የመሳሰሉት በይፋ ቦታውን ተቆጣጠሩት፡፡ አመክንዮ የሕሊናን ፍቃድ ስለምትጠየቅ ክፉ ነገር ማድረግን ትከላከላለች፡፡ አመክንዮ ሲጠፋ ጥበብ ጠፋች ማለት ነው፡፡ አመክንዮ ከሌለ እኮ ሰዎች ተራርደው ያልቁ ነበር፡፡ በዚህ ምክነያተም በኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ለሰው ልጅ ደንታ የሌላቸው አረመኔ ለማድረግ የማይደፍረውን በሰዎች ልጆች ላይ የሚፈጽሙ ጨካኞች ብዙ ቦታ ዋና ሆነው እናያቸዋለን፡፡ ሕዝብም ብዙ ተጎድቷል፡፡

ፈላስፋው ቅዱስ ጳውሎስ እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልፈለጉት መጠን የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው ይለናል፡፡ የአመክንዮ የመጨረሻው ግብ እግዚአብሔርን ማወቅ እንደሆነ ከአብርሃም እናያለን፡፡ ሰው ከዚች መስመር በተቃራኒው ሲሄን የት እንደሚደርስ እናስተውል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ምክነያት ሊሰጠው ለማይችላቸው ብዙ ድርጊቶች ተጋልጣለች፡፡ ከሲኖዶስ ሁለት መሆን፣ እስከ ተራ አስተዳደራዊ ግድፈት፤ ከየቧህ (የማይጠይቅ) ሕዝብ እስከ በሰዎች ልጆች ላይ ጨካኝ ሰዎችን በመናፍስት የሚያጠምዱ አጋንንት ጎታች ደብተሮች፤ ከየቧህ ለጋሽ እስከ የአገርንና የሕዝብን ገንዘብ በራራ ፀሐይ የሚዘርፉ ወሮበሎች ወዘተ፡፡  በዚህ ሁሉ አሁንም ሕዝብ አይጠየቅም፡፡ ለብዙዎችም እንዲህ ያለው ድርጊት እግዚአብሔር ስለፈቀደ ነው ተብሎ ይታመናል፡፡ ቀስ በቀስ ግን በቤተክርስቲያኗ ፍጹም እግዚአብሔር የሚጸየፈው ተግባር ቦታ እየሆነች እንደመጣች ሕዝብም ምንም ጥቅም የማያገኝበት ኦርቶዶክስ የሚል ስምን ብቻ አንግቦ አባል በመባል ለሞራል እንጂ የነፍስ ድህነት የሌለባት መካን እሆነች እንደሆነ ስጋት አለ፡፡ ሊያውም በቅርብ ጊዜያቶች ወደ መከፋፈል እንደምትሄድ ሳይዘነጋ፡፡

የእስከዛሬ የምንሰማቸው ኮተቶች ጆሮአችንን ጭው አድርገውን አሁን በዋናነት ያሉት ፓትሪአርኩ የሚያደርጓቸው ድርጊቶች ከላይ ያነሳኋቸውን ስጋቶች እንዳያፋጥኗቸው እፈራለሁ፡፡ ሂደቱ የመጨረሻው ላይ የደረሰ ይመስላልና፡፡ ፓትሪያርኩ በጤና የዚህን ያህል ስህተት መሳሳት የለባቸውም ባይ ነኝ፡፡ ሰሞኑን በተለያየ ሚዲያዎች የተተቹባቸው የማሕበረ ቅዱሳንን አውደርዕይ ማስታጎል፣ በማሕበሩም ላይ ዛቻ፣ የመምህር ግርማ ወንድሙን አገልግሎት ማገድ ትልቅ መነጋገሪያ ናቸው፡፡ ፓትሪያርኩ ጻፉት የተባለውን አንዱን ደብዳቤ ግን አይቼ እኔ ምናአልባትም ሌሎች ካላሰቡት ሌላ ስጋት ገባኝ፡፡ ደብዳቤው የራስጌ ስም (ሄዲንግ) አለው፡፡ ይሄው የራስጌ ስም ግን የቤተክርስቲያኗ ሳይሆን የፓትሪያርኩ ሙሉ ስም ነው፡፡ እኔ እንዲህ ያለ ሄዲንግ ወረቀት አይቼ አላውቅም፡፡ የግለሰብ ስም የራስጌ ስም ሆኖ አይቼ አላውቅም፡፡ የራስጌ ስም የሚተካው የራስጌ ማሕተብን ነው፡፡ ይሄ ድግሞ የተቋምን እንጂ የግለሰብን ሥም አያካትትም፡፡ ሲጀምር የግለሰብ ስም (የተቋም ሥም ካልሆነ) በየትኛውም ማሕተም የሚካተት አይመስለኝም፡፡ የኃላፊዎች ስም ከፊርማቸው ሥር በሚያርፍ ሌላ ቲተር በሚባል ይቀረጻል እንጂ፡፡ ይህ ብቻ አይደለም ሄዲንግ ወረቀት ለመጀመሪያው ገጽ ብቻ ተደርጎ ሌሎች ተጨማሪ ገጾች ካሉ በሌላ ወረቀት ነው የሚታተመው፡፡ ፓትሪያርኩ ከጻፉት እንዱ ደብዳቤ ግን ሶስት ገጽ ሲኖረው ሶስቶም በሄዲንግ የተጻፉ ናቸው፡፡ ቢያንስ ይሄን ፕሮቶኮል የሚጠብቅ ፓትሪያርክን የሚያሕል የሥልጣን ቦታ የለም እንዴ ብዬም አሰብኩ፡፡  ይሄን እንተወውና ጥቂት እዚህ ያደረሳትን የቤተክርስቲያኗን ታሪካዊ ሂደቶች ለአንባብያን እንደገባች ላካፍል ወደድሁ፡፡

የጥንታዊያኑ የፈላስፎቹ ዘመንና ቤተክርስቲያኗ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከቀድሞቹ አንዷ መሆኗ ብቻ ሳይሆን ቀደምት ተክታዮቿ ከኦሪት ወደክርስትና የገቡ በመሆኑ በእግዚአብሔር አምልኮትና በስነመለኮት ፍልስፍና ከሌሎች ክርስትናን ከተቀበሉ ሕዝቦችም መጠቅ ያሉ እንደነበሩ መዛግብቶች ይጠቁማሉ፡፡ ይሄው ሂደት ቤተክርስቲያኗን እስከዛሬም ድረስ በሌሎች ዓለማት የማይታወቁ የፍልስፍና፣ የጥበብ መዛግብቶች ባለቤት አድርጓታል፡፡ ከእነዚህም አንዱ ዛሬ ዓለምን እያነጋገረ ያለው የሄኖክ መጽሐፍ ይገኝበታል፡፡ ሆኖም ግን በቤተክርስቲያኗ ታሪክ ስናይ የጥበብ መጻሕፍት መጻፍ ቀስ በቀስ መጻፍ እያቆሞ የመጡ ይመስላል፡፡ በተለይም ደግሞ በአለፍት 1000ዓመታት አመክንዮ አዘል መጻሕፍት እየቆሙ ግራ የሚያጋቡ ጽሁፎች በምትኩ ወደ ቤትክርስቲያኗ እንደተጋበዙ እናያለን፡፡ ጸሐፊዎቹም ሥማቸው አይገለጽም፡፡ ምን ዓልባትም ከአባ ጊዮርጊስ (1000 ዐመት ገደማ) በኋላ በስም የሚታወቅ ደራሲ የጸፈው መጻፍ ላይኖር ይችላል፡፡ ከዚያ በፊት የፈላስፋውና ማሔሌታዊው ያሬድ መድብሎች አሁንም ጌጥ ሆነው እናያቸዋለን፡፡ አስደናቂው ነገር ደግሞ በዚያ ወቅት የነበሩ ሰዎች ከእኛ ብዙ ርቀት ሳይንሳዊ የሆኑ ጉዳዮችን ያውቁ ነበር፡፡ አርጋኖን በሚባለው የአባ ጊዮርጊስ የጌታ እናት ማርያም የምስጋና መጻሕፍ ላይ የጌታን ልደት በንብ መሥለውት እናነባለን፡፡ እሳቸው ምሳሌ የሰጡት ደግሞ በዚያ ወቅት ሕዝቡ በሚገባው እንደሆነ እንረዳለን፡፡ ንብ (ድንጉላው) ያለ አባት ከእናት ብቻ (parthenogenesis) እንደሚወለድ በሳይንስ የተረጋገጠው በፈረንጆቹ 1890ዎቹ ነው፡፡  መጻፈ ሄኖክ አንዱ ቢሆንም ለሎች ስለ ስነ ጠፈር ሚስጥራት የሚያወሱ መዛግብት በዚሕችው ቤተክርስቲያን እንዳሉ ይነገራል፡፡ እንደውም 16 ፕላኔትና ሌሎች ሚስጢራትን የሚናገሩ መጽሐፎች እንዳሉ ይነገራል፡፡ በኢንግሊዞች ተወሰዱ የተባሉት የመጻሕፈ ፈውስና መጻሕፈ መድሐኒት መድብሎች የእነዚሁ ዘመናት ሳይንሳዊ ሥራ በረከቶች ነበሩ፡፡  አሁን አሁን ብዙ የሀይማኖት ተመራማሪዎች በእርግጥም ስለክርስቶስ ማንነትና ሌሎች አምልኮታዊ ሚስጢራት ለመረዳት የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን ገዳሞችና ዋሻዎች እያሰሱ ነው፡፡ በቅርቡም 66 መጻሕፍትን ያካተተው መጽሐፍ ቅዱስ ሳይቀር ከኢትጵያ በተገኙ መዛግብቶች አንጻር አጠያያቂ እየሆነ መምጣቱን ለማስተዋል በየኢንተርኔቱ የሚቀርቡ ጥናቶች ማስተዋል ይቻላል፡፡ ለምሳሌ ሄኖክ በሌሎች መጽሐፈ ቅዱሳት 65 ዓመት ኖረ ማቱሳላንም ወለደ ይላል፡፡ የኢትዮጵያው መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ከሌሎች ይለያል፡፡ 165ዓመት ኖረ ማቱሳላንም ወለደ ነው የሚለው፡፡ በዛ ዘመን ሁሉም ልጅ የወለዱት የሄኖክን ልጅ ማቱሳላን ጨምሮ ቢያንስ ከ150ዓመት በኋላ ነው፡፡ ሌላው ትንቢተ ዳንኤል ላይ አንድ ጊዜ ብቻ ከተገለጸው ውጭ ስለ መሲህ (ክርስቶስ) በብሉይ መጻሕፍት ሌላ ቦታ አልተጠቀሰም፡፡ ሄኖክን ጨምሮ ብዙ በቤተክርስቲያኗ ያሉ የብሉይ መጻሕፍቶች ግን ስለክርስቶስ በብዛት ይናገራሉ፡፡ በራሱ በጌታም እንዲሁም በሐዋሪያትም እንዚህ መዛግብቶች እንደተጠቀሱ በአዲስ ኪዳን ላይ ይነበባሉ፡፡ እንግዲሕ እነዚህንና የመሳሰሉትን ሚስጢር አዘል አመክኒዮዊ የእምነት መዛግብቶች ባለቤት የሆነቸው ቤተክርስቲያን 1000ዓመት በኋላ በጣም እያቆለቆለ በሚመስል የእምነት ኪሳራ ውስት የገባች ይመስላል፡፡ ሕዘብ ዛሬ በባሕል በተለወሰ የእምነት ማነጎ ውስጥ ወድቋል፡፡

ከ1000ዓመት በኋላ ምን ሆነ

ከላይ የተጠቀሱት በዛግብቶች አይነት ከ1000ዓመት በኋላ እየነጠፉ ሌሎች ጥበብ አልባ ከዚያም በላይ የባዕድ አምልኮ አራማጆች በብተክርስቲያኗ እንደሰረጉና ከዚያ በኋላ ተጽፈው የምናያቸው መጽሐፍት ይጠቁሙናል፡፡ በተለይ የጸሎት እየተባሉ የሚወጡ መጻሕፍት ብዙ ችግር የፈጠሩና አሁንም ያልታረሙ ናቸው፡፡ በአንድ ወቅት ነገረ ማርያምን ለብሔር ማውገዣነት እንደሳተሙትም ይነበባል፡፡ እንግዲህ አመክንዮ ከሌለ ዝም ብሎ መቀበል ከሆነ አደጋው ይሄ ነው፡፡ የዚሁ ዕትም ዛሬ ድረስ ፖለቲካዊ ጥያቄ አስነስቶ ሕዝብን ከሕዝብ፣ ቤትክርስቲያኗንም ከብዙ ሕዝብ አቃቅሯል፡፡ ዋጋም እየከፈልንበት እንገኛለን፡፡ ልብ በሉ ነገረ ማርያም የተባለው መጽሐፍ ግን የተጻፋው በወንጌላዊው ዮሐንስ ነው፡፡ ይታያችሁ ዮሐንስ ስለኢተዮጵያ ብሔር እንዱን ከአንዱ አሳንሶ ሲጽፍ፡፡ ከጠቀስኩት እትምም በኋላ አሁንም ቢሆን በየፀሎጽ መጽሐፉ የሚነበበው ነገረ ማሪያም ዮሐንስ የጻፈው አይደለም፡፡ ስታነቡትም ብዙ የማይመስሉ ነገሮች ታዩበታለችሁ፡፡ እንደሂ ያሉ ተረት ተረት አይነት መጻሕፍት ምክነያተም ትክክለኛዎቹን ሁሉ በጅምላ ዋጋ እንዲያጡ አስተዋጽዖ አድርገዋል፡፡ በአንዳነዶቹ አስደንጋጭ የክህደትና የወደቁ መላዕክት ስም ከቅዱሳኖቹ ጋር ተቀላቅሎ ታያላችሁ፡፡ የማሕበረ መላዕክት ምልጃ ጸሎት በሚለው ራሙኤል የሚባል የመላዕክ ስም ታነባላችሁ፡፡ ራሙኤል ሄኖክ ከዘረዘራቸው የወደቁ መላዕክት አለቆች አንዱ ነው፡፡ እንግዲህ የማይጠየቅበት እምነት እንድህ ያሉ አደጋዎች እንዳሉት ጭምር እረዳ፡፡ በቤተክርስቲያኗ አሁንም ድረስ ጥያቄ ሆነው ያሉ ስርዓቶች ዘልቀው እንደገቡም እናያለን፡፡ ይሄን እስኪ ሌሎች እንዲናገሩት እድል ልስጥ፡፡

ዛሬ

አሁን ማንም የምዕመን የነፍስ ድህነት ጉዳይ የሚያሳስበው ያለ አይመስልም፡፡ ዋናው ፉክክር ገዥ ቦታ ይዞ ተቆጣጣሪ የለለውን ከሕዝብ የሚሰበሰብ ገነዝብ መመዘበር፡፡ እርስ በእርስ መዋጋት አንዱ አንዱን ጥሎ የሚያልፍበትን ሴራ ማቀድ ነው፡፡ ጥቂት አባቶች እንደቀሩ አውቃለሁ፡፡ ግን አሉ ማለት የሚያስችል ቁጥር የላቸውም፡፡ ስብከት፣ መዝሙሩ፣ ሁሉም አሁን ከማይጠይቅ ምዕመን ገንዘብ የሚስገኝበትን እንጂ የነፍስን ጉዳይ ማሰብ ጅልነት ነው፡፡ አንዱ  አንዱን ሲፈልግ መናፍቅ ብሎ ስብከቱን ወይም መዝሙሩን ያጣጥልበታል ወይም በይፋ እንዲታገድም የጥራል፡፡ በሰዎች ላይ የሚገኙ ስሕተቶች እንደ ትልቅ ድል ይቆጠራሉ፡፡ ሰዎችን ስለነፍሳቸው ተጨንቆ ሲሳሳቱ ማረም እርም ሆኗል፡፡ በተገኘው አጋጣሚ ሌላ ስህተት እንዲፈጽሙ በማድረግ በእልህ ሆን ተብሎ ከእምነቷ እንዲወጡ ማድረግ የተለመደ ሆኗል፡፡ አሳዛኙ ግን ተሳስተሀል የሚለው ራሱ ከሀዲና የባሰ ነውር ያለበት መሆኑ ነው፡፡ ጠንቋይና ደብተራዎች የቤተክርስቲያኗ ዋና መሪ ሆነው እንደልባቸው በቤተክርስቲያኗ ቆራጭ ፈላጭ ናቸው፡፡ መረዳት አቅቶት የተሳሳተ እንድ ተራ ሰባኪ በሉት ምዕመን ግን መናፍቅ ተብሎ ከቤተክርስቲያን ይገለላል፡፡ ጳጳሳት የተቀመጡበት መንበር ዕዳ እንደሆነ ከቶም አይረዱም፡፡ የበጎች ጠባቂ መሆን ተብለው በጎችን መጠበቅ ቀርቶ ዛሬ ራሳቸው የበጎቹ ጠላት ሆነዋል፡፡ አሜሪካና ኢትዮጵያ ሲኖዶስ ለየፊናቸው አቋቁመው በሕዝብ እየተለመኑ ከእኔ ውጭ ማን ወንድ የሚል ትምክህት የወለደው መንፈስ ተገዥ ሆነው ዋናውን ቦታ ይዘው ይገኛሉ፡፡ መንግስት ሲያጠፋ መገሰጽ አለባችሁ የሚለውን የማሉበትን ቃል ግፍ ሁሉ በሕዝብ ሲደርስ ጭራሽ የግፉ ዋና አቀናባሪ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ በአጠቃላይ ቤተክስቲያኗ በማያምኑ ግን በሂደት የቤተክርስቲያኗን ራስ ሥልጣን በያዙ መሪዎች እየተመራች እንደሆነ ስጋቴ ነው፡፡ የነዚሁ የትላልቆቹ አጫፋሪዎችም ታች ድረስ ሕዝቡን ያውኩታል፡፡

አሁን ከአገልግሎት የታገዱት መምህር ግርማ ብዙ ለዘመናት የተሰወሩ ሚስጢራትን ለሕዝብ ይፋ ያወጡት ይመስላል፡፡ ይሄው ነገር አስደንብሯቸው ነው መሰለኝ የእኝህን ሰው አገልግሎት ብዙ ትልልቅ ነን የሚሉ የቤተክርስቲያኗ ሰዎች መምህሩን ለመጣል ብዙ ሙከራ ያደርጋሉ፡፡ በቅርቡ በተለያይ ወንጀሎች ክስ እንዲመሰረትባቸው በማድረግ ለሁለት ወራት በእስር እንደቆዩ የሚታወስ ነው፡፡ አሁን ደግሞ የሀገረስብከት ጳጳስና የሲኖዶስ አባል በሁኑ የቤተከርስቲየኒቱ ኃላፊ አገልግሎት እንዲሰጡ ደብዳቤ ተሰጥቷቸው አገልግሎት ከጀመሩ በኋላ  ፓትሪያርኩ ከላይ በጠቀስኩት ደብዳቤ በጽኑ አግደዋቸዋል፡፡ ጳጳስ የፈቀደውን ፓትሪያርኩ በምን አግባብ ሊከለክሉ እንደሚችሉ አይገባኝም፡፡ የደብራት አገልግሎት ምደባ ደግሞ በፓትሪያርክ አይመስለኝም፡፡ ግፋ ቢል በሀገረ ስብከት ጳጳስ እንጂ፡፡ መምህሩም ከደብዳቤ በፊት በቃልም ሊታገዱ ይችላሉ፡፡ ሥህተት አለ ከተባለ ደግሞ መምህሩ በሚያስተምሩበት ቦታ ተገኝቶ ስሕተቱንም ለሕዝብ ነግሮ ነው፡፡ ከዚህ ባለፈ ግን ፓትሪያርኩ ያለሲኖዶስም ፍቃድ እጃቸውን ባገኙት ቦታ ባስረዝም የለባቸውም ባይ ነኝ፡፡ ነገሩ ግን እኔ እንደምለው ትክክለኛ ቅደም ተከተል የሚያስችል አይመስለኝም፡፡ እንደተባለውም ከቤተመንግስተ ተደውሎላቸው ይሆናል፡፡ ከዚህ በተረፈ ግን መምህሩ የቀደሙ አባቶችን የፍልስፍና ሚስጥር ያገኙት ይመስላል፡፡ ፓትሪአርኩና ተባባሪዎቻቸው ምናዓለባትም መምህሩ እንዲህ የሚያርበደብዱት መንፈስ አስጨንቋቸው እንዳይሆን፡፡ መምህሩ ከመታሰራቸው በፊት አንድ በሕዝብ ዘንድ የሚደነቅ እንደ ሰባኪም ፀሐፊም የሆነ ገለሰብ በመምህሩ ላይ የጸፈው ጽሑፍ ብዙ ምዕመናንን እንዳነጋገረ እናስታውሳለን፡፡ ጸሐፊው ታዲያ ሊጠቀም የሞከረው ስልት ያች ለዘመናት የደለበች አመክንዮ የማይጠይቅን እምነት ሆኖ መምህሩን ለመክሰስ ግን ብዙ ጥበብ የተራቆተቻቸው አመክንየዎችን ሊጠቀም ሞክሯል፡፡ በዚህም ይሄ ሰው ሰባኪ ነኝ እያለ ስላላወቀ ነው ወይስ ሆን ብሎ መምህሩን ለመጣል እያሴረ ሲሉ ብዙዎች ገራ ተጋብታዋል፡፡ እውነታው መምህሩ እኔን ጨምሩ የሚመሥጠኝ ፍልስፍናዊ ትምህርት ነው የሚያስተምሩት፡፡ በተለይ ለስነሕይወት ሳይንስ ቀረብ ላልንወ ሰዎች የዘመናት እንቆቅልሾችን ነው እንድናስተውል ያደረጉን፡፡ በተግባርም ይተረጉሙታል፡፡ የወሊሶው አባ ወልደ ተንሳይ (አቡነ ዲዮስቆሮስ) በቅርብ ሰዎች የሚያዎቁቸው እንደ መምህሩ መናፍስትን የሚያረበደብዱ እንደነበሩ ሰምቻለሁ፡፡ ታዲያ የሲኖዶስም አባል ስለነበሩ በአንድ ወቅት ስብሰባ ሄደው በብዙዎቹ አዝነው ስብሰባውን ትተው እንደተመለሱ ይነገራል፡፡ ያዘኑበትም ትልቁን ቦታ ይዘው አለማመናቸውን ነበር፡፡

ማህበረቅዱሳን ለቤተክርስቲያኗ ብዙ አስተዋጽዖ እንዳበረከተ ይታወቃል፡፡ ይህ ማሕበር ግን በመንግስት በኩል በበጎ የሚታይ አይመስልም፡፡ ማሕበሩ ግን በፓትሪአርኩ ጥርስ የገባበት ምክነያት ከቤተመንግስቱም እይታ በላይ ይመስላል፡፡ አጋጣሚው ቤተመንግስቱን የጠቅመው ይሆናል፡፡ እንደወሬው ደግሞ ፓትሪያርኩ ሮም ሄደው ነው መሰለኝ ሲመለሱ ዋና ጠላታቸው ማህበሩ እንደሆነ ተገለጠላቸው ነው የሚባለው፡፡ በካቶሊክና ኦርቶዶክስ መካከል ብዙም ልዩነት የለም አሉ ተብሎም ፓትሪአርኩ አንድ ሰሞን መነጋገሪያ ነበር፡፡ ማሕበሩ እንደተባለው በዚህ ነገር ተቃውሞ ይሆናል፡፡ ሆኖም ይሄ ጉዳይ መነጋገር ቢቻል እንደተባለውም ልዩነቱ የጠበበ ከሆነ እሰየው፡፡ ምኑ ችግር ሆኖ ይሄን ያህል እንደሚደረስ አላውቅም፡፡ ችግሩ እምነትን ተቀበል እንጂ አትጠየቅ በሚባልበት አስተምሮት ከባድ ነው፡፡ በአንድ ወቅት እንደውም እኮ አቡነ ጳውሎስ ከአለም አድስ አበባ ላይ ለጥምቀት ልዩነታችን ምንድነው ሲሉ ሰብስበዋቸው ነበር፡፡ በእርግጥም እኔ እንደተረዳሁት በጎ ነገር ነው፡፡ ፓትሪአርኩም ቢባሉ እንኳን ይችን ጉዳይ የውስጣቸው አድርገው ልጆቼ ብለው ሊገስጹ ስችሉ እንዴት፡፡ ብቻ ጉዳዩ የመሪዎቹ እንዲህ ሆኖ ሳለ፡፡ ዛሬ ትንሽ ጠብቆ ምዕመኑ መጠየቅ ሲጀምር ብዙ የማይመለሱ ነገሮች ይኖራሉ፡፡ ያኔ ለቤተክርስቲያኗም አደጋ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡

በአጠቃላይ ቤተክርስቲያኒቱ፣ የገጠሟት ችግሮች የተወሳሰቡ ይመስላል፡፡ የጥንታውያን አባቶችን ጥበብ የሚመስላትን  ትሻለች፡፡ ጠንቋይና ደብተራ በይፋ ሊጋለጡና ከቤተክርስቲያኗ ሊጠሩ የገባል፡፡ የተበከሉ መጻሕፍቶች እንዲጠሩ፡፡ የጠበብ መዛግብትም ለምርምር ሳይቀር ይፋ እንዲወጡና እንዲጎለብቱ ለትውልዱም የእውቀት ምንጭ እንዲሆኑ ይገባል፡፡  የዛሬ ዛሬ ጳጳስን አፍ እላፊ መናገር የተለመደ ነው፡፡ ይህ ደግሞ እየቆየ ምን ሊሆን እንደሚችል አስተውሉ፡፡ ጳጳሳቶቹ ከህዝቡ ርቀው ነው ያሉት፡፡ ሕዝቡ የሚፈለገው ለገንዘብ እንጂ ለድህነት አይደለም፡፡ ቆይቶ በአገርም ደህንነት ላይ አደጋ የሚጥል ማንነት የማጣት ችግር እንዳይፈጠር፡፡ ሕዝብ ሲቸገር አለሁልህ የሚለው ሲኖረው የሚላከው መሪ ይፈልጋል፡፡ ስለሕዝብ መንግስትን የሚገስጽ አባት አይታሰብም፡፡ ቢያንስ ግን ለሕዝብ ጠላት አለመሆን ነው፡፡

 

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!

አሜን!

 

ሰርጸ ደስታ

↧

ኮልፌ18 ማዞሪያ በደረሰ አሰቃቂ አደጋ የሰዎች ሕይወት ተቀጠፈ |የአደጋውን ፎቶዎች ይዘናል

$
0
0

Kolfe 2

kolfe

kolfe 3

kolfe 4

kolfe3
(ዘ-ሐበሻ) በአዲስ አበባ ኮልፌ 18 ማዞሪያ ዛሬ በደረሰ ከፍተኛ የመኪና አደጋ የሰዎች ሕይወት መቀጠፉን ከስፍራው የዘ-ሐበሻ የዜና ምንጮች ዘገቡ::

እጅግ አሰቃቂ ነው በተባለው የዚሁ የመኪና አደጋ መነሻ ሲሚንቶ የጫነ ቱርቦ መኪና ነው ተብሏል:: በአደጋው እስላሁን ድረስ 3 ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን እና ከ25 ሰዎች በላይ ከባድ እና ቀላል የመቁሰል አደጋ እንደረሰበትም ከስፍራው የሚመጡ መረጃዎች አመልክተዋል::

ሲሚንቶ የጫነው ይኸው ቱርቦ ከባድ መኪና በ6 መኪኖች ላይ ጉዳት እንዳደረሰ የጠቁሱት መኪኖች ይህ ከባድ መኪና ሚኒባስን ጨምሮ በሌሎቹ መኪኖች ላይ ጉዳት ያደረሰው ከዊንጌት ወደ 18 ማዞሪያ ሲጓዝ ነው ተብሏል::

የተጠቀሰው ከባድ ተሽከርካሪ ከአጠና ተራ ወደ 18 ማዞሪያ አደባባይ ሲጓዝ የነበረ ነው።
እስካሁን በአደጋው ምክንያት ሶስት ሰዎች ሲሞቱ፥ ከ20 በላይ ሰዎችም ቀላል እና ከባድ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል።

ቱርቦው ከመኪናዎቹ በተጨማሪ አደባባዩ ፊት ለፊት የሚገኝ መድሃኒት ቤት፣ የሞባይል እና የቡና መሸጫ እንዲሁም የፑል ማጫወቻ ቤቶች ላይ ጉዳት ማድረሱም ታውቋል:: በኤባ መድሃኒት ቤቱ ውስጥ መድሃኒት እየገዙ የነበሩ ሰዎችና ፋርማሲስቶች ሳይቀር ተጎድተዋል ተብሏል::

የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል ሲሉም የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታውቀዋል::

↧

አንጋፋው የሳክስፎን ተጫዋች ጌታቸው መኩሪያ አረፈ |ለህክምና 5 ሚሊዮን ብር ጨርሷል

$
0
0

Getachew mekuriya

(ዘ-ሐበሻ) ጌታቸው መኩሪያ በሳክስፎን ተጫዋችነቱ አንቱ የተባለ አንጋፋ ባለሙያ ነው፡፡ በማዘጋጃ ቤት፣ በብሄራዊ ቴአትርና በፖሊስ ሰራዊት የሙዚቃ ክፍል ከሙዚቃ ተጫዋችነት እስከ ዋና መምህርነት አገልግሏል፡፡በ1986 ዓ.ም ጡረታ ከወጣ በኋላ በሸራተን አዲስ ሆቴል ለስምንት አመታት የሰራው አንጋፋው ሙዚቀኛ፤ ከመቶ በላይ አገራትን በሥራ አጋጣሚ ዞሯል፡፡ አልቶ ክላርኔት እና ሳክስፎን አሳምሮ የሚጫወተው አርቲስቱ፤ ከሦስት አመታት ወዲህ በህመም ምክንያት ከሚወደው ስራው ርቆ የበርካታ ሆስፒታሎችን ደጃፍ ለመርገጥ ሲገደድ ነበር:: በሙዚቃ ሕይወቱ በመላው ዓለም በመዘዋወር ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ ቢያጠራቅምም ይህንን ሁሉ ገንዘብ በህክምና በመጨረሱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከፈለገ ያሳክመኝ ካልሆነ ይቅበረኝ ሲል ጥሪ አቅርቦ ነበር::

በሕይወት በነበረበት ወቅት ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ ስለሙዚቃ ሕይወቱ ሲናገር “ከ60 ዓመታት በላይ ቆይቻለሁ፡፡ በ1940 ዓ.ም ወዳጄነው ፍልፍሉ የሚባል ጓደኛዬና ተፈራ አቡነወልድን አይቼ ነው ወደ ሙዚቃው የገባሁት፡፡ ወዳጄነው ፍልፍሉ ጐበዝ ክላርኔት ተጫዋች ነበር፡፡ ተፈራም ከማዘጋጃ እስከ ብሄራዊ ቴአትርና እስከ ውጭው ዓለም ድረስ ብዙ ታሪክ የሰራ፣ ድንቅ የጥበብ ሰው ነበር፡፡ አሁን ሁለቱም በህይወት የሉም፡፡ መጀመሪያውኑ ዋሽንት መጫወት፣ ሰርግ ላይ መጨፈር እወድ ነበር፡፡ እነተፈራን ሳይ ደግሞ ፍላጐቴ ጨመረና ማዘጋጀ ቤት ገባሁ፡፡ ከዚያ ትንሽ ሰልጥኜ የመንገድ ላይ ታምቡር (ድራም) አስያዙኝ፤ በኋላ እራሴን እያሻሻልኩ ወደ ክላርኔት ተሸጋገርኩ፡፡ ከክላርኔት ወደ ሳክስፎን አሻሻልኩ ማለት ነው፡፡ ማዘጋጃ ቤት ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻልኩ ስመጣ፣ ደሞዝ የሁለት የሁለት ብር ጭማሪ ሲደረግ፣ ስንወዳደር ሁሉንም በልጬ ተቀጠርኩኝ፡፡ እነዚያ የበለጥኳቸው ልጆች ተናደው መንገድ ላይ ጠብቀው ደበደቡኝ” ሲል ተናግሮ ነበር::

የሳክስፎኑ ንጉሥ እያሉ አድናቂዎቹ የሚያሞካሹት ጌታቸው መኩሪያ የ9 ልጆች አባት ነበር:: በሙዚቃው ዓለም 60 ዓመት ቆይቷል::  ነብሱን በገነት እንዲያኖራትና ለቤተሰቦቹም መጽናናትን እንዲሰጣቸው ዘ-ሐበሻ ትመኛለች::

↧

Hiber Radio: ኢትዮጵያን የዛሬው አገዛዝ ሶሪያ ሳያደርጋት ሕዝቡ በጋራ የተሻሉ አማራጮችን አሁኑኑ እንዲያዘጋጅ ተጠየቀ እና ሌሎችም አሉን

$
0
0

Habitamu
የህብር ሬዲዮ መጋቢት 25 ቀን 2008 ፕሮግራም

ዶ/ር አባድር መሐመድ ኢብራሂም የሕግ ባለሙያና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች በሚኒሶታ ከተደረገው የኢትዮጵያ ፍትሐዊና ርትዓዊ ጉባዔ በሁዋላ ስለ ጉባዔው ከህብር ሬዲዮ ጋር ካደረጉት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)

አቶ ነጌሶ ዋቀዮ የኢትዮጵያ ፍትሐዊና ርዕታዊ ጉባዔ መስራችና የጉባዔው ተናጋሪ ስለ ጉባዔው በጋራ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)

የመጨረሻው ምሳ- ወጣቱ ባለቅኔና ደራሲ በዕውቀቱ ስዩም(ከአሜን ባሻገር ስለ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የጻፈውን ምዕራፍ የተመስገን ደሳለኝን የልደት ቀን ምክንያት በማድረግ በድምጽ አንብቦታል-ያዳምጡት)

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን ይመስል ሕይወታቸውን እየገበሩ አሰተዋሽ ያጡት የሶማሊያ ወታደሮች ወቅታዊ እሮሮ እና ምሬት(ልዩ ዘገባ)

ከአሜን ባሻገር በኢትዮጵያውያን መካከል በሀሰት የተጫረውን ዘርን መሰረት ያደረገ የጥላቻ ቅስቀሳ በታሪክ ማስረጃ ባዶ ያስቀረ ነው። ሕዝብን በፍቅር ለማቀራረብ የተጋ ፣ነገ ሊመጣ የሚችለውን ችግር ዛሬ ላይ ለማስቀረት የሚጥር ታላቅ መጽሐፍ ነው። ዛሬ ብቻ ሳይሆን ነገም ከነገ ወዲያም የሚነበብ ነው።ለነገዋ ለሁሉም እኩል የምትሆን ፍትሐዊና ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ መምጣት ምኞቱ የሆነ የዛሬው አስከፊ ጊዜ እንዲለወጥ የሚፈልግ ሁሉ በጥሞና ሊያነበው የሚገባ መጽሐፍ ነው። ህብር ሬዲዮ

ቃለ መጠይቅ በቬጋስ ሁበርን ሲያሽከረክር ጉዳት ስለደረሰበት አሽከርካሪ ከአቶ ስሜነህ ጸጋዬ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ(ሙሉውን ያዳምጡት)ሌሎችም

ዜናዎቻችን

ኢትዮጵያን የዛሬው አገዛዝ ሶሪያ ሳያደርጋት ሕዝቡ በጋራ የተሻሉ አማራጮችን አሁኑኑ እንዲያዘጋጅ ተጠየቀ

እስራኤል ለኢትዮጵያና ለኤርትራ የጦር መሳሪያ ማቅረቧ ተገለጸ

ኮ/ል መንግስቱ ሀ/ይለማሪያም ለፍርድ እንዲቀርቡ ዓለም አቀፍ ጥሪ ቀረበ

ሕዝቡ ዛሬም ኮ/ል መንግስቱ አገር ወዳድና አምባገነን ናቸው በሚል ያስታውሳቸዋል

የኦሮሞ ሕዝብ በኦህዴድ አገዛዝ ራሱን አስተዳድሮ እንደማያውቅ አንድ ምሁር ሰሞኑን ተናገሩ

በአምቦ ዩኒቨርስቲ ተቃውሞውን ተከትሎ ተደብድቦ ታሞ የነበረ ተማሪ ሕይወቱ አለፈ

የሰማያዊ ፓርቲ ፕሬዝዳንትን ጨምሮ የቀሩ ዋና ዋና አመራሮችን አገድኩ ያለው የስነስርዓት ኮሚቴ ሕገ ወጥ ውሳኔ ታገደ

ሕወሓት የአማራ ሕዝብን በጎሳ ለመከፋፈል የጀመረውን እቅድ ተግባራዊ ለማድረግ በድብቅ ያሰራጨው ሰነድ ተጋለጠ

የቅማንት ጉዳይ የሕወሓት ዋና አጀንዳ መሆኑን በተዘዋዋሪ ሰነዱ አጋልጧል

ኤርትራ ዘጠኝ የፊሊፒን ዜጎችን ሰሞኑን በቁጥጥር ስር አዋለች

በሙስና የተዘፈቁት የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማን ከስልጣን ለማውረድ የአገሪቱ ፓርላማ ማክሰኞ ለውሳኔ ሊቀመጥ ነው

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

↧
↧

ፕ/ር ጌታቸው በጋሻው  ሆድ ብሷቸው ሆድ አስባሱኝ  —    (ግዜነው ደም መላሽ)

$
0
0

 

Dr.-Getachew-Begashaw-300x173ከሶስት አመት በፊት ይመስለኛል የዩኒቲ ዩንቨረሲቲ የቀድሞው ባለቤት የነበሩት ዶ/ር ፍሰሃ እሸቱ ኢሳትና VOA ላይ ቀርበው በውጭ አዲስ የሽግግር መንግስት መመስረት እንዳሰቡና ስርሀቱን በቶሎ  (በስድስት ወር ውስጥ) አሶግደው ወደ ሙያዊ ስራቸው መመለስ እንደሚፈልጉ መግለፃቸውን አስታውሳለሁ።መንግስትን መጣል ኮመዲያኖቻች እንደሚሉት እንደ “ሙዝ መላጥ” አቅልለውብን ስለነበረ እኝህ ባለሀብትና ሙሁር የአሜሪካ ወይም የአንድ ሀያል ሀገር ድጋፍ ቢኖራቸው ይሆናል እንጂ ብለን ጠርጥረን ነበር። ይህንን ቃለ መጠይቃ ካደረጉ ከአንድ ወር ተኩሉ በኋላ ደግሞ የአቶ መለሰ ዜናዊ  ዜና እረፍት ሲሰማ ያሉትን ወደማመኑ ደርሰን ነበር።ቢያንስ ባሰቡት ፍጥነት ሳይሳካላቸው ቀረና ዶ/ር ፍሰሃ እሸቱ ም “የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሽግግር ምክር ቤት” የሚባል ድርጅት መስርተው ወደተራዘመ ትግል ውስጥ ገቡ።የሆነው ሆኖ “በቃ በስድስት ወር ውስጥ ህውሃትን ልንገላገለው ነው” ብለው ተስፋ ሰንቀው ለነበረነው ወገኖች ተስፋችን የውሀ ሽታ ከሆነ ሶስት አመት አልፎ አራተኛውን ይዘናል። ለማንኛውም  ዶ/ር ፍሰሃ   በወቅቱ ከሰጡት ቃለ መጠይቅ እንደተረዳሁት ቅንና ለሀገራቸው ጥሩ ዕራይ ያላቸው ሰው ናቸው።ተሰማርተውበት በነበረው የስራ ዘርፍም ፈር ቀዳጅና ውጤታማ ነበሩ።  እንደ እኔ ቅን ሰው ፖለቲከኛ መሆን የሚችልና ከገባበትም የሚቀናው አይመስለኝም። በተለይ እንደነ ስብሀት ነጋ ያሉ ሸፍጥና ተንኮልን የሕይዎታቸውም የትግላቸውም መመሪያ ባደረጉ ሰዎች የተፈጠረን  ስብስብ  ለመታገል ቅንነትና ሚዛናዊነት ብዙም አዋጭ አይደሉም።ቅንነትና ምክንያትዐዊ አቀራረብ ህውሃት ሰዎች ዘንድ እንደ ጅልነት ነውና የሚወሰደው።ለማንኛውም ትግል ለማድረግ የሚነሳ ቡድን ስለሚታገለው አካል በቂ የሆነ የስነልቦና፣ የሰው ሀይልና የማቴሪያል ዝግጅት ማድረግ ይገባዋል።ጠላት ለሚለው አካልም ተመጣጣኝ የሆነ   ክብደት ሊሰጥና ያንን ሊመክትና ሊያሸንፍ የሚስችል በቂ ዝግጅት ማድረግ አለበት ብየ ነው የማምነው። ይህ ማለት ጠላትን አግዝፎ በማሳየት ታጋዮችን ተስፋ ለማስቆረጥ ሳይሆን ጠላትን አሳንሶ ገምቶ ሽንፈት ላይ ላለመውደቅ ይረዳልና ነው።

ሰሞኑን ደግሞ ኢሳትና ቪዥን ኢትዮጵያ የተባለ ድርጅት የተወሰኑ የፖለቲካ ፖርቲ መሪዎችንና ምሁራኖችን አሰባስበው ስለ ነገዋ ኢትዮጵያ ለመምከር “ሽግግር ዲሞክራሲና አንድነት” በሚል እርዕስ  የሁለት ቀን ኮንፈረንስ መደረጉ ይታዎቃል። ዝግጅቱን በንግግር  የከፈቱትና የቪዥን ኢትዮጵያ መስራችና ፕሬዚዳንት የሆኑት ፕሮፌሰር ጌታቸው በጋሻው በንግግራቸው መሀል እንባ እየተናነቃቸው ንግግራቸውን  ሲያቋረጡና ሲያለቅሱ  ስመለከት በጣም ነው ያዘንከት።ሆድ ብሷቸው እኛንም ሆን እንዲብሰን አደረጉን። ኢትዮጵያ ለካ አልፎ አልፎም ቢሆን  እንዲህ ለሀገራቸው ቅን ልቦናና ብሩህ አህምሮ ያላቸው ምሁራን አሏት? እንድንልና ተስፋም እንድንሰንቅ ነው ያደረጉን። ህውሃት በተከለብን የዘርና የቋንቋ ፖለቲካ “እኛ”ና “እነሱ” በሚል ተቦድኖ ሀገሩን ለዘራፊ፣ እወክለዋለሁ የሚለውን ማህበረሰብ ለአሳሪ፣ለገራፊና ለገዳይ ትቶ በየጥጋጥጉ እንካ ሰላንትያ እየተጫወተ ያለውን ወገን ለማሰባሰብና ተቀራርቦ እንዲመክር፣ የጋራ አጀንዳ  ቀርፆ የጋራ ጠላቱ ላይ እንዲዘምት ለማስቻል እንባውን እያፈሰሰ የሚማፀን ምሁር ማየት በርግጥም ደስ የሚል ነገር ነውና የሁሉም ድጋፍ የሚያሻው  ጉዳይ ነው።

እንደተረዳሁት ከሆነ ጉባዬው ቀጣይነት አለው።በርግጥም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ውስብስብ ችግር በአንድና በሁለት ስብሰባዎች የሚፈታ ጉዳይ አይደለም። ተደጋጋሚና እልህ አስጨራሽ የሆኑና የሁሉንም ማሕበረሰብ ስሜቶች የሚያንፀባርቁ ውይይቶች ማድረግ የግድ ይላን። ዛሬ ላነሳው የፈለኩት ሀሳብ ታዲያ በኔ እይታ ኮንፈረንሱ ነበሩበት የምላቸውን መጠነኛ ክፍተቶች ለመጠቆምና ቢቻል  በቀጣይ በሚደረጉ ተመሳሳይ ምክክሮች ላይ መካተት አለባቸው የምላቸውን አንድ ሶስት ነጥቦች ለማንሳት ነው።

የመጀመሪያው ክፍተት የሚመስለኝ የጉባዬው አዘጋጆች ለፖናሊስትነት(የመወያያ ወረቀቶችን አቅራቢዎች)  ከመረጧቸው ሙሁራን መካከል የታሪክ ሰዎችን (historian) ቢያካትት መልካም የነበረ ይመስለኛል። ከቀረቡት ምሁሮች አጭር ገለፃ እንደተረዳሁቱ የኢኮኖሚክስ፣የፍልስፍና፣ የአካውንቲንግና የፖለካል ሳይንስ  ምሁራኖች ናቸው የተጋበዙትና የመወያያ ንግግሮችን ያደረጉት። ዛሬ ኢትዮጵያዊያን ካሉብን መጠነ ሰፊ ችግሮች አንዱና በእኔ እምነት ዋነኛው በቀደመው የሀገራችን ታሪክ ላይ የጋራ መተማመን ማጣታችን ይመስለኛል። ባለፋት 40ና 50 ዓመታት የታሪክ ሰዎቻችን እንዲገለሉና የኢትዮጵያን ታሪክ ፖለቲከኞቻችን እንደ ፖለቲካ አጀንዳዎቻቸው ለአላማቸው በሚያመቻቸው መልኩ ብቻ እንደፈለጋቸው ሲተርኩት መክረማቸው ይታዎቃል። ይህ ደግሞ የዛሬውን ትልድ በተቃርኖ እንዲቆምና ሁሉም በፖለቲካ መሪዎቹ የተተረከለትን ብቻ እንዲያምንና በኢትዮጵያን መካከል የጋራ መግባባት እንዳይፈጠር  ከፍተኛ መሰናከል መሆኑ ይታዎቃል።ይህንን መሰሉ ክስተትም በኮንፈረሱ ላይ ሲስተዋልም ታዝበናል።

ሀሳቡን ለማጠናከር አንዲት ምሳሌ  ለማንሳት ከፖለቲካ መሪዎች መካከል የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግምባር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑትና ድርጅቱን ወክለው የቀረቡት  አቶ ሌንጮ ባቲ አሳብ ልጥቀስ።አቶ ሌንጮ ባቲ የኢትዮጵያዊያን የችግራችን ምንጭ ነው በማለት እንደዋና መከራከሪያ ሀሳብ ይዘውት ከቀረቡት ነጥብ አንዱ “ኢትዮጵያ ከሌሎች አፍሪካ ሀገሮች በተለየ መልኩ የተሰራችው ከሰሜን በመጡ ኢትዮጵያዊያን በመሆኑ የሰሜኑ ባህል በሌሎች ላይ ተጭኖል” የሚል ሀሳብ ነው።ኢትዮጵያ የተሰራችው በኢትዮጵያዊያን ነው።ይሄ ምንም ስህተት የለበትም።እንደ ሕዝብ ልንራኮበትም የሚገባ ትልቅ የመንፈስ ሀብታችን ነው። በአለም ገናና ከነበሩት ወደ አምስት ከሚጠጉ ኢምፖየሮች የአንደኛው የአክሱም ኢምፖየር  ባለቤት እንደመሆናችን ሀገራችንን እራሳችን ለመስራት አቅምም ችሎታውም ያለን ሕዝቦች ነበርና። በኢትዮጵያ የረዥም ታሪክና በዚህም በነበረው የኢትዮጵያዊያን እንቅስቃሴ የባህል መወራረስ አይኖርም አይባልምና የባህልም ተፅኖ ሊኖር ይችላል። እኔ ያልገባኝና ምናልባት የታሪክ ምሁራን ቢኖሩ ኖሮ ማብራሪያ ይሰጡበት ነበር የምለው አቶ ሌንጮ ደጋግመው “ኢትዮጵያ የተሰራችው ከሰሜን በመጡ ፣ ከሰሜን በመጡ”  እያሉ ያቀረቡበት ትንታኔ ነው። እንደገባኝ እየጠቀሱ ያለው ከአፄ ምኒሊክ በኋላ ስለምናውቃት “ዘመናዊዋ ኢትዮጵያ” ይመስለኛል።ይህ እንግዲህ በዘመናዊዋ ኢትዮጵያ ምስረታ ወቅት የኦሮሞው ማህበረሰብ ተሳታፊ አልነበረም የሚለውን የኦነግ ትርክት ለመድገም ይመስለኛል።የዚህ አይነት የታሪክ ትንታኔ ደግሞ እን ፕሮፌሰር ጌታቸው በጋሻው  በሕዝቦች መካከል ሊፈጥሩ ላሰቡት መቀራረብ እንቅፋት የሚሆንና የተለመደው የታሪክ ማወራረድ ውስጥ የሚከት ነው።

ለማንኛውም እኔ ባለኝ መጠነኛ የታሪክ ግንዛቤ ይችን “ዘመናዊዋ ኢትዮጵያ” የሰሩት አፄ ምኒሊክ የሸዋ ንጉስ የነበሩና አያት ቅድማያቶቻቸውም ከዛው ከሸዋ መሆናቸውን ነው። ጳውሎስ እኞኞ እንደዘገበው “ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ከአባታችው ከሸዋው ንጉሥ ኃይለ መለኮት ሣህለ ሥላሴና ከእናታቸው ወይዘሮ እጅጋየሁ ለማ አድያም ነሐሴ ፲፪ ቀን ፲፰፻፴፮ ዓ.ም ደብረ ብርሃን አካባቢ አንጎለላ ከሚባል ሥፍራ ተወልደው፤ በአንጎለላ መቅደላ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ክርስትና ተነሡ “ነው የሚለው።እንግዲህ ሸዋ የኢትዮጵያ ሰሜን ነው ካልተባል አፄ ሚኒሊክ ከሸዋ እየተነሱ ነበር ወደ ሰሜንም ሆነ ወደ ሌላው ኢትዮጵያ ግዛት ያሉትን ንጉሶች ያስገበሩት። በማስገበሩ ሂደትም ወታደሮቻቸው ውስጥም ሆነ በአላፊነት ደረጃም ቢሆን የኦሮሞ ተወላጆች ነበሩባቻው። ወደ ቆየው ዘመን ከሄድን ደግሞ  በ12ኛው ክፍለ ዘመን አጼ ይኩኖ አምላክ የዘመኑን የዛግዌ ስርወ መንግሥት በመቃወም ሲነሱ ከክርስቲያን አማራዎች አገር ከሸዋ እንደተነሱ እና ቀድሞውንም የአክሱም ነገሥታት በጉዲት መነሳት ሥልጣናቸውን ሲለቁ ከዛች ንግሥት በመሸሽ ተከታዮቻቸውንና ቤተ ሰባቸውን ደብቀው የኖሩት በዚሁ በሸዋ ውስጥ እንደ ነበር ነው ታሪክ የዘገበው።እንደ  ክብረ ነገሥት (አንቀጽ 39)  አተራረክ ከወሰድነው ደግሞ ሸዋ ከክርስቶስ ልደት በፊትም ጀምሮ  የአጼ ቀዳማዊ ምኒልክ ክፍላገር የነበረ እንደሆነ ነው የሚጠቀሰ።ስለዚህ ኢትዮጵያን የሰሩት ኢትዮጵያዊያን አነሳሳቸው ከመሀል ኢትዮጵያ ከሸዋ ነው።  የወቅቱን የፖለቲካ ትርክት አሳማኝ ለማድረግ ሲባል ብቻ የሌለና ያልነበረ ነገር እያወሩ ለመጪው ትውልድ ማስተላለፉ አላፊነት የጎደለው ፣የታሪክ ሰዎች እርምት ሊሰጡበት የሚገባ ጉዳይ ይመስለኛል። ይህን መሰል የፖለቲካ ትንታኔ የሚያራርቅ እንጂ የሚያቀራርብ አይደለምና።

ሁለተኛው ክፍተት ሆኖ ታየኝ በፖናሊስትነትም ሆነ በተሳታፊነት ወጣቶችን በብዛት ያለማየታችን ጉዳይ ነው።ባብዛኛው ተሳታፊ 60ዎችን የተሻገረ ይመስለኛል።ወጣት ስል ላለፋት ወደ 30 ለሚጠጉ ዓመታት የልዩነትና የጥላቻ ፖለቲካ የተሰራበትን ወጣት ለማለት ነው። እነ ኤርሚያስ ለገሰ አይጨምርም። ከፖለቲካው ሰሪዎች ውስጥ ስለሆኑ/ስለነበሩ ።ይህንን ሀሳብ የማነሳው እነዚህ በእድሜ የበሰሉትና ለሀገራቸው ቅን አመለካከት እንዳላቸው የምንረዳላቸው ሙህራኖች የዎቅቱ የወጣቶች የፖለቲካ አሰላለፍ በርግጥ  በአግባቡ ተረድተውታል ወይ? የሚል ጥያቄ ስላጫረብኝ ነው።በሽታን ለማከም ጥሩ ሐኪም መሆን በራሱ በቂ አይደለም። በሽተኛውን አቅርቦ መመርመርና የበሽታውን ስር ማግኘት ይረዳልና ቀጣዮ ጉባዬ በፖለቲካ የተራራቀ አመለካከት ያላቸውን ወጣቶች መጋበዝና ሀሳባቸውን መረዳት ያስፈልጋል ለማለት ነው።

ይህንን ሀሳብ እዛው ውይይቱ ላይ በተነሳ አንድ ጥሩ ነጥብ ላጠናክረው።አንዲት እህት ለዶ/ር በያንና እና ለአቶ ሌንጮ የወረወረችው ጥያቄ በጣም ጠቃሚ ይመስለኛል።ባጭሩ የጥያቄዎ ሀሳብ የነበረው ወጣቶችን በርግጥ እናንተን ይሰሟችኾል ወይ የሚል አንድምታ ያለው ወሳኝ ጥያቄ ነው።ዛሬ በፖለቲካው አካባቢ ያለው ትውልድ በተለያዩ ቡድኖች ላለፋት ሶስት አስርት አመታት የጫካ ፖለቲካ ሲሰራበት የኖረ ትውልድ ነው። እንደሚታወቀው አንድ ዱር ቤቴ ያለ አማፂ ነፃ አወጣዋለው የሚለውን ማህበረሰብ ከጎኑ ለማሰለፍ ታሪኮችን ከማንሻፈፍ ጀምሮ በርካታ የፈጠራ ድርሳኖችን ወደ ሕዝብ ያሰራጫል። የህውሃትንና የሀውዜንን ታሪክ እንደ ምሳሌ መውሰድ እንችላለን። የተዛቡም ይሁኑ የተፈበረኩ የውሸት ታሪኮች ግነታቸውና ውሸትነታቸው ለመሪዎቹ (ለፈጣሪዎቹ) እንጂ ፖለቲካው ለሚሰራበት ወጣት እውነት እንሆኑ ነው የሚታመነው። ለዚህም ነው የፖለቲካ አቋምን ለመቀየር ለመሪ እንጂ ለተከታይ ከባድ የሚሆነው።ስለዚህ ዛሬ የአመለካከትና የእስትራቴጂ ለውጥ አድርገናል የሚሉን የፖለቲካ መሪዎች ወጣቱን ማስከተል እንደሚችሉ በምንም መልኩ እርግጠኛ መሆን አንችልም። እንደውም እውነታው እነዚህ የቀድሞ የፖለቲካ መሪዎች ዛሬ ባላቸው ለዘብተኛ የፖለቲካ አመለካከት ከስልጣን እንዲነሱና እንዲባረሩ የተደረጉ መሆናቸውን መዘንጋት የለብንም። በጫካ ፖለቲካ የለከፉት ትውልድ ግን የራሱን መሪ እየመረጠ ተመሳሳይ መዝሙር እየዘመረ ያለበት ሁኔታ ነውና ያለው ወጣቱን ቀጥታ ማቅረብና መመካከር ላይ ቢሰራ የሚሻል ይመስለኛል ለማለት ነው።

የመጨረሻውና ሶስተኛ ክፍተት የምለው ከሙሁራኑ በመቀጠል ድርጅታቸው የሚከተለውን የፖለቲካ ፍልስፍና እንዲያስረዱ የተመረጡት የፖለቲካ ፖርቲዎች የአመራረጥ ሂደት ላይ ይሆናል።በኮንፈረሱ ላይ የተስተናገዱት የፖለቲካ ፖርቲዎችን ዘግንና ሕብረ ብሔርን መሰረት አድርገው የተቋቋሙ ናቸው። ሕብረ ብሔር የሆኑት እንደ ግንቦት 7 አርበኞች ግንባር፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ እንዲሁም ከሀገር ውስጥ በ/ዶ መራራ ይወከላል ተብሎ ተጠብቆ የነበረው ኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (ምንም የዘውግ ፖርቲዎችን ያሰባሰበ ቢሆንም እንደ ሕብረ ብሔር ካየነው በማለት ነው) ናቸው። ሁለተኛው ደግሞ ዘውግ ላይ ከተመሰረቱት የፖለቲካ ፖርቲች የተወከሉት  አሁንም በዶ/ር መራራ ይወከላል ተብሎ ተጠብቆ የነበረው የኦሮሞ ፌደራሊስት ፖርቲ እና የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግምባር  ናቸው።ሁለቱንም የፖለቲካ እርዮት አለም የሚያቀነቅኑ ፖርቲዎችን በአንድ መድረክ ላይ ሀሳባቸውን እንዲያቀርቡ መደረጉ በራሱ ችግር ባይኖርበትም የዘውግ ፖለቲካን ስናስተናግድ ግን ውክልናን ማመጣጠኑ ጠቃሚ ነገር ይመስለኛል። ወደድንም ጠላንም ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ዘርና ቋንቋን የተመለከቱ ጉዳዮች እንዲህ በዋዛ የሚታዩ ጉዳዮች አይደሉም።ስለዚህ ይህንን አይነት መድረክ ሲዘጋጅ አግላይ መሆን ያለበት አይመስለኝም።እርግጥ ነው ሁሉንም የዘውግ ፖርቲዎች ማስተናገዱ ከባድ ነው። ነገር ግን ለአለፉት 25 ዓመታት ምናልባትም ከሁሉም ሕዝቦች በተለየ መልኩ በገዢው መንስት በጠላትነት ተፈርጆ ቁም ስቅሉን እያየ ያለውን የአማራውን ማሕበረሰብ የሚወክል ድርጅት አለማካተቱ ስህተት ነው የሚሆነው። በመሰረቱ እኔ ሞረሽ የአማራ ድርጅት በጉባዬው ላይ መጋበዙንና አለመጋበዙን የማውቀው መረጃ የለኝም። ነገር ግን የሞረሽ ሰዎች ይህንን አይነቱን መድረክ ለመጠቀም ያቅማማሉ ብየ አላስብምና ምናልባት ግብዣው ካልደረሳቸው ወደፊት ታሳቢ እንዲደረግ ለመጠቆም ነው።

ብዙ ወገኖች የአማራን ማሕበረሰብ ለኢትዮጵያ አንድነት እንቅፋት ሊሆን አይችልም የሚል አመለካከት እንዳላቸው አውቃለሁ።አንድ መረሳት የሌለበት ነገር ቢኖር በአንድ ሀገር ውስጥ ከሚኖሩ ሕዝቦች መካከል  በአንደኛው ወገን የሀገርን አንድነት አደጋ ላይ የሚጥል የአቋም ለውጥ የሚከሰተው በዛ ሕዝብ ላይ ተለይቶ በሚፈም በደል መሆኑን ነው። ያለፉትን 25 ዓመታት የኢትዮጵያን ፖለቲካ ለተከታተለና በአማራ ሕዝብ ላይ የደረሰውን መከራ ለታዘበ እንደው ዝም ብሎ “አማራ አንድነቱን አይንድም” እያሉ ይህንን መሰል አግላይ ነገሮችን ማድረግ የዋህነት ነው። የፖለቲካውን ድባብ መርዳት ጥሩ ይመስለኛል።ልዩነቱ እንደ መፍትሄ እየቀረበና የብዙዎችን ድጋፍ እያገኘ ነውና ሰዶ ማባረር እንዳይሆን ጥንቃቄ ይደረግበት ለማለት ነው።

ቸር እንሰንብት

E-mail

gizdemelash@gmail.com

 

 

 

↧

የኢትዮጵያ ቴሌኮም ቫይበርና ዋትሳፕ ተጠቃሚዎችን ሊያስከፍል ነው

$
0
0

Viber and watts up
“ቴሌ ታልቦ የማያልቅ ላም በመሆኑ ወደ ግል አላዟዙርም” ብሎ መንግስት እንቅ አድርጎ የያዘው በኢትዮጵያ ብቸኛው የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪ የሆነው ኢትዮ ቴሌኮም ኢንተርኔትን በመጠቀም የስልክ አገልግሎት የሚሰጡትን እንደ ቫይበርና ዋትሳፕ ያሉ አገልግሎቶችን በክፍያ ለማድረግ በመወሰኑ አገልግሎቶቹን የሚቆጣጠር መሳሪያ መጠቀም መጀመሩን አስታውቋል፡፡

ድርጅቱ በዋና ስራ አስኪያጁ አቶ አንዷለም አድማሴ ስም ባወጣው መግለጫ በቫይበርና ዋትሳፕ ምክንያት ድርጅቱ ማግኘት የሚገባውን ገንዘብ ማግኘት ባለመቻሉ አገልግሎቶቹን በክፍያ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ብሏል፡፡

‹‹ምንም እንኳን አገልግሎቶቹን ለመጠቀም የኢንተርኔት ግኑኝነት ክፍያ መፈጸም የሚያስፈልግ ቢሆንም ኢትዮ ቴሌኮም በአገልግሎቶቹ ምክንያት የሚያጣው ገንዘብ ለኢንተርኔት ክፍያ ከሚፈጸመው ከፍ ያለ በመሆኑ አገልግሎቶቹን መቆጣጠር አስፈላጊ ሆኗል››ማለታቸውን ለንባብ በቅቷል፡፡ድርጅቱ በተጨማሪም ቀረጥ ያልተከፈለባቸውንና ሳይቀረጡ በውጪ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጆቻቸው የሚልኳቸውን የስልክ ቀፎዎች ክፍያ እንዲፈጸምባቸው ለማድረግ በአገሪቱ የሚገኙ ህጋዊ ቀፎዎችን የሚመዘግብ መሳሪያ መጠቀም እንደሚጀምርም አስታውቋል፡፡

ቴሌ ኮም እንደሚጠቀምበት የሚናገርለት መሳሪያ ቀረጥ ባልተከፈለባቸው የስልክ ቀፎዎች ውስጥ የሚገኙ ሲም ካርዶችን መቆለፍ(አገልግሎት እንዳይሰጡ ማድረግ)ብቻ ሳይሆን የስልኩ ቀፎ ቀረጥ እንዳልተከፈለበት ከታወቀ ወዲያውኑ ስልኩን የሚቆልፍ ስለመሆኑ ተጠቅሷል፡፡

በስራ አስኪያጁ ስም የወጣው መግለጫም ሰሞኑን ብዛት ባላቸው አካባቢዎች የቫይበርና የዋትሳፕ አገልግሎቶችን ማወክ መቻሉን የኢትዮ ቴሌኮምን ብቃት ያሳያል ብሏል፡፡ በመግለጫው ባይካተትም በአገሪቱ በዋናነትም በኦሮሚያ ዋትሳፕና ቫይበርን ጨምሮ ማህበራዊ ድረገጾችን መጠቀም አለመቻሉን ለማወቅ ተችሏል፡፡

↧

ሰብለ-ወንጌል ዘአማራ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት፣ የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮና ወልቃይት ጠገዴ

$
0
0

 

welkayet - satenawአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያው ላይ የወያኔ ወኪል ነን የሚሉ ግለሰቦች የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ኢትዮጵያን እያተራመሰ ነውና ሃይ ባይ ያስፈልገዋ፥ል ስለዚህ ፒቲሽን እንፈርምና ለአሜሪካ መንግስት እናስገባ ይላሉ። እነሱ የሚወግኑለት መንግስት ዲሞክራሲን ባፍጢሙ የደፋና የመናገርም ሆነ ሌሎች ሰብዓዊ መብቶችና ነጻነቶችን የማያከብር ነው። የእነሱ እይታም ከሚወግኑት መንግስት የዘለለ ስላልሆነ የመናገር ነጻነትና ሰብዓዊ መብት ምን ማለት እንደሆነ በኢ-ሊበራል መንግስት እያታ ነው የሚያዩት። አሜሪካ ሊበራል ዴሞክርሲያው ሃገር ናት። ማህበረሰቡም ዴሞክራሲያዊ ህዝብ ነው። የመናገር ነጻነትን እዚህ ደረጃ ላይ ለማድረስ ብዙ ተለፍቶበታል። አውሮፓ ውስጥ ያሉ ሃገራት ለመናገር ነጻነት ከሚሰጡት ከለላና ጥበቃ በላይ፣ የአውሮፓ የሰብዓዊ መብት ፍርድ ቤት ለመናገር ነጻነት ከሚሰጠው ቦታ በላይ አሜሪካን ውስጥ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ትልቅ ቦታ ይሰጠዋል። ያለመናገር ነጻነት ዴሞክራሲ በሁለት እግሩ ሊቆም አይችልም፥ሊያብብም አይችልም ብለው ትልቅ ትኩረት ይሰጣሉ። ለምሳሌ የአውሮፓ የሰብዓዊ መብት ፍርድ ቤት ለመናገር ነጻነት ያለውን ቦታ ሲያሳይ እንዲህ ሲል ይገልጸዋል። Freedom of expression constitutes one of the essential foundations of [ a democratic] society, one of the basic conditions for its progress and for the development of every man. የመናገር ነጻነት የዴሞክራሲያዊ ማህበረሰብ ወሳኝ መሰረት ነው። የመናገር ነጻነት ለሰው ልጅ እድገትና መጎልበት አይነተኛ ሚና የሚጫወት መብት ነው ብሎ ፍርድ ቤቱ ሁሌም የመናገር ነጻነትን ጉዳይ የሚመለከት ውሳኔ ባሳለፈ ቁጠር ይደጋግመዋል። ፍርድ ቤቱ ሌላ ሁሌም እንደመርህ ወስዶ የሚደጋግመው አባባል ደግሞis freedom of expression is applicable not only to “information” or “ideas” that are favourably received or regarded as inoffensive or as a matter of indifference, but also to those that offend, shock or disturb the State or any sector of the population. የመናገር ነጻነት ምንም አይነት ትንኮሳ ለሌለባቸው፣ ገለልተኛ ለሆኑ ወይም መልካም (አውንታዊ) ለሆኑ ሃሳቦች (መረጃወች) ብቻ ሳይሆን የሚያገለግል መንግስትን ወይም የተወሰነ የማህበረሰብ ክፍልን ሊያናድዱ የሚችሉ፣ ሊበጠብጡ የሚችሉ ወይምሊተነኩሱ የሚችሉ ሃሳቦችም እንደሃሳብ ተቆጥረው ከለላ ይሰጣቸዋል ይላል። ነጻ የሃሳብ መንሸራሸር ሲኖር ነውና እውነት የሚወጣ፥ ባልታፈነ ማህበረሰብ ውስጥ ነውና ዴሞክራሲ ተዘርቶ የሚበቅል እንዲሁም የሰው ልጅ ተፈጥሯቂ የሆነ ራስን የመግለጽ መብት ስላለው የመናገር ነጻነት ሊከበር ይገባል ይላል። ወደ አሜሪካ የሲቭል ሊበሪቲስ (Civil Liberties) ድንጋጌዎች ስንመጣ ደግሞ የህገ መንግስቱ የመጀመሪያው ማሻሻያ የመናገር ነጻነትን የሚከለክል ምንም አይነት ህግ መውጣት እንደሌለበት ያመላክታል። ያም ሁኖ ግን የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ባዳበራቸው ኬዞች (Case Law) አንዳንድ ሃገርንና የሌላን መብት የሚጋፉ ድርጊቶች ሲከሰቱ የመናገር ነጻነት ሊገደብ ይችላል ይላል። ነገር ግን ይህም ሁኖ እንደወያኔ በፈለገው መንገድ ሳይሆን ህግና ስርዓትን ተከትሎ የመናገር ነጻነትን ማፈን የሚያመጣው ተጽዕኖና አንድ ሃሳብ ቢነገር (ለሶስተኛ ወገን፣ ለሚድያ ወይም ለህዝብ) ቢተላለፍ ምን ሊያመጣ ይችላል የሚለው ነገር ተመዝኖ ነው። በብዙ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔዎች እንደተመለከተው ለመናገር ነጻነት የሚሰጠው ከለላ አሜሪካ ውስጥ እጅግ ከፍተኛ ና ከአውሮፓም የበለጠ ነው። ለምሳሌ በ Pentagon Paper case ላይ የዋሺንግተን ፖስትና የኒዮርክ ታይምስ ጋዜጣና መጽሄት በመንግስት ጥብቅ ሚስጥር ተብሎ የተፈረጀን መረጃ ያገኛሉ። መረጃው ስለቬትናም ጦርነት ነው። ሚድያዎች ሊያትሙት ሲሉ የፕሬዚዳንት ኒክሰን መንግስት የፍርድ ቤት እግድ ትዛዝ አወጣ። መረጃው ከታተመ የሃገሪቱን ጥቅም ይጎዳል፣ ወታደሮቻችን እንዲሞቱ ያደርጋል፣ በዲፕሎማሲ ረገድ እንድንሸነፍ ያደርጋል ለጠላቶቻቸን ሃይል ይሆንና ተጋላጭነታችንን ይጨምራል ወዘተ የሚሉ የሃገራዊ ደህንነት ጉዳዮችን እንደመከላከያ አነሳ። ነገር ግን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የመንግስትን አቋም ሳይሆን የደገፈው የሚድያዎችን አቋም ነው። ከ7000 በላይ ገጽ የጥናት ወረቀቶች ያውም ጥብቅ ሚስጥር ተብለው የተፈረጁ መረጃዎች ለህዝብ ይፋ እንዲሆን ፈረደ። በዚህ ውሳኔ የተነሳ ኒክሰን impeachment ሳይመጣ ብሎ ስልጣኑን ለቀቀ። የቬትናም ጦርነትም ቆመ። ብዙ ማዕበል ያስነሳ ውሳኔ ነው።
========================================
ይህን ሁሉ ያልኩበት ምክንያት የወያኔ ጋሻ አጃግሬዎች ነጻነትን ወያኔ በሰጣቸው መነጸር ወይም እንዲያዩ በፈቀደላቸው ቁንጽል እይታ እየተመለከቱ የአሜሪካ ህዝብ የታክስ ገንዘብ ኢትዮጵያን አደጋ ላይ እየጣላት ነውና የአሜሪካ ድምጽ ራዲዩ አደብ ሊገዛ ይገባል ሲሉ ግዜ ነው። በመጀመሪያ ረገድ የአሜሪካ ድምጽ ራዲዩ ስለወልቃይት ህዝብ ሲዘግብ የታፈነ ብሶትን ነው ያወጣ። የራዲዩ ጣብያው ለዘመናት ሲካሄድ የቆየን ግዙፍ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰትን (Systemic Human Rights Violation) ለማስቆምና ለአለም ለማጋለጥ ነው የተነሳ። ያንንም ጉዳይ እያደረገ ይገኛል። ራዲዮ ጣብያው የአሜሪካ ህግና ህገ መንግስት በሰጠው ነጻነት እንጂ የወያኔ መንግስት በቀደደለት ቦይ አይደለም የሚፈስ። የራዲዩ ጣብያው ሚዛናዊ የሆነ አዘጋገብን ለመከተል ብዙ ግዜ ጥሯል። ብዙ የወያኔ ሃላፊዎች ስልክ ይደወልላቸውና በሚንተባተብ አንደበታቸው ይናገራሉ፥ ከዛም ደዋዩ ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ መሆኑን ሲነግራቸው ስልካቸውን ይዘጋሉ ወይም አያነሱም። የራዲዮ ጣብያው ለእነ “ዶክተር” ገላውዲዎስ አርያ አይነት ውሸታም ዶክተሮች እንኳ ቦታ ሰጥቷቸው ጉዳዩን ጠይቋቸዋል። ምንም እንኳ ከአካዳሚክ ቁመናቸው ጋር የማይሄድ ውሸት ቢዋሹም ቅሉ (ስለውሸታምነታቸው ነው ዶክተር የሚለውን ማዕረግ በትምህርተ-ጥቅስ ውስጥ ያስቀመጥኩት)። የራዲዮ ጣብያው ከውሸታሙ ዶክተር በፊትም ዶክተር ማሃሪ ረዳኢንና ሌሎች ሙህራንን አቅርቦ ስለጉዳዩ ጠይቋቸዋል። መሃሪ ረዳይ ትግሬ ስለሆነ ብቻ በወያኔ መንግስት የራሱን ጥቅም ለማስጠበቅ ያወጣው ህግ ተፈጻሚ መሆን አለበት አለን። በዛው ላይ አሁንም ጉዳዩን መጀምሪያ የክልል ምክርቤቶች ሊያዩት ይገባል ከዛ ነው ወደ ፌደሬሽን ምክር ቤት መምጣት ያለበት ብሎ መሰረታዊ የህግ መርሆችን ሳይናገር አለፈ። ለምሳሌ ከታች ተቋማት ላይ ያሉ የመፍትሄ አማራጮችን ሳይጨርሱ ወደላይ ወዳለ የፍትህ አካል መሄድ አይቻልም የሚል መርህ አለ (Exhaustion of available local remedies)። ዶክተር ማሃሪ ይሄንን ሲጠቅሱ የዘነጉት (ሆነ ብለው የዘለሉት ነገር አለ)። ከስር ካለው ውሳኔ ሰጪ አካል መፍትሄ ይገኛል ወይ? (Available local remedies) ጉዳዩ ያለበቂ ምክንያት ረጂም ግዜ ይወስዳል ወይ (prolongation of the case)? የመሳካትና ፍትህን የማምጣቱ ጉዳይ ምን ያህል እርግጠኛ ነው (reasonable prospect of justice)? ከነዚህ አንዱ የሚኖር ከሆነ እንኳ ከስር ያለን የውሳኔ ሰጪ አካል ውሳኔ ሳይጠብቁ ወደላይኛው አካል መሄድ የሚቻልበትን መንገድ አላስቀመጡም።
እንዲያው ለማለት ያህል አልኩኝ እንጂ የወልቃይት ጉዳይ ወያኔ ባወጣው ህግ የሚዳኝ ጉዳይ አይደለም። የአሜሪካ ነጮች ህግንና ህገመንግስትን ከለላ አድርገው የነጭ የበላይነትን ለማረጋገጥ በጥቁሮች፣ በላቲኖች፣ በቻይናና በጃፓናውያን ላይ በደል ሲፈጽሙ እንደኖሩት ሁሉ፥ የወያኔ ህጎችና ህገመንግስትም critically ከታዩ የአንድ ቡድን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ፓሊቲካዊና ወታደራዊ የበላይነትን ለማስጠበቅ የሚወጡ ናቸው። ስለዚህ በነዚህ ህጎች፥ ከነዚህ ህጎችና በነእርሱ መሰረት ከተቋቋሙ ተቋማትም ፍትህን አንጠብቅም።
=============================
ወደተነሳሁበት ጉዳይ ስመለስ የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ፍትሃዊ አዘጋገብን ለመከተል ብዙ ኳትኗል። አሁንም በወልቃይት ጉዳይ ከማንኛውም አካል የሚነሳ ጥያቄን ለማስተናገድ በራችን ክፍት ነው እያሉ ባለብት ሁኔታ ሃገር ውስጥ በለመደ አካሄዳቸው የመናገር ነጻነት ይታፈንልን ብሎ ለመጠየቅ መሞከር እብደት ነው። የአሜሪካ መንግስት የወያኔ መንግስት አይደለም። የመናገር ነጻነት እስከምን ድረስ መከበር እንዳለብት ያውቃል። የሚዲያዎችም ተግባር የታፈኑ ድምጾችን እንደገደል ማሚቶ ማስተጋባት፣ በኢ-ሊበራል መንግስትና ማህበረሰብ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ግፎችን ማጋለጥ ነው ተግባራቸው እንጂ እንደ ኢቢሲ ውሸትን እየደጋገሙ እውነት ለማስመሰል መድጣር አይደለም። የአሜሪካ ህገመንግስት የመጀመሪያው ማሻሻያ (First Amendment) ባስቀመጠው ሰፊ የመናገር ነጻነት መብት ተጠቅመው የአሜሪካ ድምጽ ራዲዩ የወልቃይት ጠገዴን ህዝብ ብሶትና እየደረሰባቸው ያለውን ግፍ ለአለም ለማሳወቅ የሚያደርጉት ጥረት ይበል የሚያሰኝ ነው። አሁንም ቢሆን በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ላይ ግዙፍ የሆኑ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች(grave human rights violations) እየተካሄዱ ስለሆአን የሚዲያ አይንና ጆሮ አይነፈጋቸው ስንል እንጠይቃለን። የሚድያ አንዱ ተግባሩ መንግስትን መቆጣጠር ነው። የሃገር ውስጥ ሚድያዎች ባያደርጉትም ቅሉ የወልቃይት ጠገዴን ህዝብ ሰቆቃ፣ ተቋማዊ በሆነ ሁኔታ በወያኔ አካላት ለሚደርስበት ሞት፣ ስደት፣ እስራት፣ ግርፋር፣ ስደት፣ እንግልት በእውነት ላይ ተመስርታቹህ ለአለም ህዝብ ታደርሱልን ዘንድ እንጠይቃለን።

4 April 2016

↧

የጎሳ ዘረኝነት (ክልላዊነት) በኢትዮጵያ –ከፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ)

$
0
0

የጸሐፊው ማስታወሻ፡ ይህ “የጎሳ ዘረኝነት/አፓርታይድ በኢትዮጵያ“ በሚል ርዕስ መደበኛ በሆነ መልኩ እያዘጋጀሁ የማወጣው ተከታታይ ትችት ሁለተኛው ክፍል ነው፡፡

Apartheid-2
የዚህ ተከታታይ ጽሑፍ ጥንድ ዓላማዎች የሚከተሉት ናቸው፡

1ኛ) በአሁኑ ጊዜ በህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ዘ–ህወሀት) አድራጊ ፈጣሪነት ተመስርቶ እየተቀነቀነ ያለው አውዳሚ የፖለቲካ ስርዓት በደቡብ አፍሪካ ውስጥ የሰፊው የጥቁሮች ህዝብ የበላይ አገዛዝ ስርዓት ከመፈጠሩ በፊት በጥቂት ነጮች የዘረኝነት የበላይ አገዛዝ ከነበረው የአፓርታይድ ዘረኛ አገዛዝ ተሞክሮ ጋር አንድ ዓይነት መሆኑን ከምንም ጥርጣሬ በላይ ለማመላከት እና

2ኛ) ጥልቀት እና ስፋት ያለው ክርክር እና ውይይት በማካሄድ ከጎሳ ዘረኝነት የጸዳች አዲሲቷን ኢትዮጵያ የመገንባቱን አስፈላጊነት ለመፍጠር እንዲቻል የኢትዮጵያን የአቦ ሸማኔ ወጣት ትውልድ ተሳትፎ ከፍ ለማድረግ ነው፡፡

በዚህ “የጎሳ አፓርታይድ በኢትዮጵያ“ በሚል ርዕስ ተቀናብሮ በሚቀርበው ተከታታይ ጽሑፍ የፖለቲካ እና የሕግ ትንተና፣ የምሁራን እና የአካዳሚክ ሁኔታን ከመመርመር ባለፈ ሁኔታ በአሁኑ ጊዜ በዘ-ህወሀት አገዛዝ ስር ወድቃ በምትገኘው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የፖለቲካ፣ የማህበራዊ እና የኢኮኖሚያዊ አጠቃላይ ሁኔታ መዳሰስን ዓላማ ያደረገ ነው፡፡ በእርግጥ በዚህ ተከታታይ ጽሑፍ ዓላማ አድርጌ የተነሳሁት ለኢትዮጵያ አቦ ሸማኔው ወጣት ትውልድ ጥሩምባ በመንፋት እንዲህ የሚል ጥሪ ለማቅረብ ነው፡ “ኢትዮጵያ በእናንተ መዳፍ ዉስጥ ናት፡፡ ጣቶቻችሁን በማስተባባር፣ በማጠንከር እና እንደ እንቁ ኢትዮጵያን በእጃችሁ መዳፍ ላይ የማድረግ ምርጫው አላችሁ፡፡ እንደዚሁም ሁሉ የእጅ ጣቶቻችሁን በማዛል እና ጥንካሪያቸውን በማልፈስፈስ ኢትዮጵያን ከእጅ መዳፋችሁ ላይ አሽቀንጥራችሁ በመጣል እንደብርጭቆ እንክትክት ብላ እንድትሰበር የማድረግ ምርጫው በእናንተው እጅ ላይ የወደቀ ነው፡፡ እያንዳንዳችሁ እጅ ለእጅ በመያያዝ እና መዳፎቻችሁን አጠንክራችሁ በመያዝ በአንድነት የመጓዝ ምርጫው የእናንተ ነው፡፡ መዳፎቻችሁን በመጨበጥ ጠንካራ ቡጢ በመፍጠር በቁጣ እና በወኔ በመነሳሳት ሀገራችሁን ከአውዳሚ አደጋ የመጠበቅ፣ ክብሯን እና ዝናዋን የማስመለስ ምርጫው በእናንተ እጅ ላይ የወደቀ ነው፡፡ የእኔ የጥሩንባ ጥሪ ኢትዮጵያ በእጃችሁ ላይ ናት፣ ሆኖም ግን “ኢትዮጵያ ኦጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘርጋለች“ የሚል ነው፡፡

ለኢትዮጵያ የአቦ ሸማኔው ትውልድ የማቀርበው ጥያቄ፣

መጀመሪያ ባቀረብኩት ትችቴ በዓለም አቀፍ የአሸባሪዎች ስም ዝርዝር የመረጃ ቋት ውስጥ ስሙ በአሸባሪነት ተመዝግቦ በሚገኘው እና በአሁኑ ጊዜ አሸባሪ ቡድን እየተባለ በሚጠራው በዘ-ህወሀት ወሮበላ አምባገነናዊ አገዛዝ በኢትዮጵያ ላይ ተጭኖ የሚገኘው “የጎሳ ፌዴራሊዝም” ትርጉም ምን ማለት እንደሆነ የሚሞግት ስልታዊ እና ወሳኝ ጥያቄ ለኢትዮጵያ ወጣቶች በማቅረብ ጀምሬ ነበር፡፡ በጎሳ ፌዴራሊዝም ላይ ያሉኝን የእኔን የመጀመሪያ የክርክር ጭብጦች አንጥሬ በማውጣት ለኢትዮጵያ የአቦ ሸማኔው ወጣት ትውልድ በማቅረብ ወጣቱ የጎሳ ፌዴራሊዝሙን ሙሉ በሙሉ በመቃወም ወደ የታሪክ ቆሻሻ መጣያ ቅርጫት ውስጥ እንዲጥለው ተማጽዕኖ አቅርቤ ነበር፡፡

በዚህ በአሁኑ ትችቴ ላይ ደግሞ በዘ-ህወሀት “የጎሳ ዘረኝነት” ወይም ደግሞ “ክልላዊነት” በማለት ሀገሪቱን በዘጠኝ ክልሎች ወይም ክልላዊ መንግስታት ከፋፍሎ ባስቀመጠው ከፋፋይ ስርዓት ላይ የኢትዮጵያ ወጣቶች የትግል መንፈሳቸውን ለማጎልበት እንዲቻል የሕግ ማስረጃ እንዲኖራቸው በማገዝ ትግሌን አጠናክሬ እቀጥላለሁ፡፡

የ21ኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያዎቹ ሁለት አስርት ዓመታት የኢትዮጵያ አንገብጋቢ ችግር የጎሰኝነት አገዛዝ ስርዓት እንደሆነ አምናለሁ፡፡ ይህ የጎሳ አገዛዝ ስርዓት ተጸንሶ ያደገው በዘ-ህወሀት ማህጸን ውስጥ ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ታላቅ ውድመትን እና ጥፋትን ለማምጣት በኢትዮጵያውያን የፖለቲካ ሰውነት ላይ ተወልዷል፡፡

የጎሳ ክፍፍል እና የጎሰኝነት ችግሮች ለኢትዮጵያ ወይም ለአፍሪካ አዲስ አይደሉም፡፡ ዋልተር ሮድነይ በአፍሪካ አህጉር የጎሳ ልዩነቶች ቢኖሩም ቅሉ የግድ የፖለቲካ ልዩነቶችን የሚያመላክቱ አልነበሩም በማለት የክርክር ጭብጣቸውን አቅርበዋል፡፡ ሆኖም ግን የጎሳ መስመርን በሚከተሉ እና ስልጣንን ጨምድደው በመያዝ እና የሀገሪቱን ሀብት ለግል እና ለተባባሪዎቻቸው ጥቅም ማጋበስ በሚፈልጉ በተወሰኑ የአፍሪካ ልሂቃን ተብዬዎች አማካይነት የጎሳ ልዩነቶች የፖለቲካ መልክ እንዲይዙ ተደርገዋል፡፡

ዘ-ህወሀት ስልጣንን በብቸኝነት ጨምድዶ ለመያዝ እና የሀገሪቱን ሀብት እርሱ እና ተባባሪዎቹ ብቻ ማግበስበስ እንዲችሉ በማሰብ የጎሳ ስርዓት መስመርን ዘርግቷል፡፡ አዲስ ነገር ነው ተብሎ ሊታይ የሚችለው ነገር ቢኖር የደቡብ አፍሪካን ሕዝብ በዘር እና በጎሳ በመከፋፈል የፖለቲካ ስርዓቱን በበላይነት ተቆጣጥሮ ብዙሀኑን የአፍሪካ ጥቁር ሕዝቦች ሲጨቁን እና የመሬትን ባለቤትነት፣ ተደራሽነት እና ጥቅም ሁሉ ሙሉ በሙሉ ይዞ ሲበዘብዝ ከነበረው ከጥቂት ነጮች ዘረኛ የበላይነት አገዛዝ ጋር በተመሳሳይ መልኩ ዘ-ህወሀትም የጎሳ መስመሩን የመከተሉ ጉዳይ ነው፡፡

በደቡብ አፍሪካ እንደነበረው እንደ ጥቂት ነጮች ዘረኛ የበላይ አገዛዝ ሁሉ ዘ-ህወሀትም በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን ሁሉንም መሬት ሰብስቦ በመያዝ (የዘ-ህወሀትን ሕገ መንግስት አንቀጽ 40 ልብ ይሏል) የእራሱን የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ኃይሉን መስርቶ ሙሉ በሙሉ የፖለቲካ ስልጣኑን ተቆጣጥሮ (እ.ኤ.አ ግንቦት 2015 ተደረገ የተባለውን የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ 100 በመቶ አሸነፍኩ በማለት እና አረመኔውን አገዛዙን በጠብመንጃ ኃይል አጠናክሮ የሚገኝ መሆኑን ያጤኗል)፣ እንደዚሁም ደግሞ የግል ዘርፉን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ (ዘ-ህወሀት በእራሱ የንግድ ድርጅቶች/ኮርፖሬሽኖቹ አማካይነት ሙሉ በሙሉ ኢኮኖሚውን ተቆጣጥሮ እንደሚገኝ ልብ ይሏል) እና የስራ ዕድል፣ የትምህርት እና ሌሎች ዕድሎችን ሁሉ ሙሉ በሙሉ ለፖለቲካ ደጋፊዎቹ እና ለታዛዥ ሎሌዎቹ በመስጠት ሰፊውን የኢትዮጵያ ሕዝብ አግልሎ በድህነት እና በስቃይ እንዲዘፈቅ አድርጎት ይገኛል፡፡

እ.ኤ.አ በ2016 በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ትልቁ ችግር የዘ-ህወሀት የበላይነት፣ የጭቆና አገዛዝ እና ጎሰኝነትን በፖለቲካ መሳሪያነት በመጠቀም ብዙሀኑን ሕዝብ በመበዝበዝ እራሱን የሁሉም ነገሮች ፈውስ አድርጎ በማቅረብ ከእራሱ የፖለቲካ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ ማዕከልነት ወደተሻለ ነገር መሻገር ከማይቻልበት ደረጃ ላይ ደርሶ ተንሰራፍቶ ይገኛል፡፡

መሬት እና የደቡብ አፍሪካ ዘረኛ የአፓርታይድ ስርዓት የሕግ መሰረት፣

የደቡብ አፍሪካ ዘረኛ/የጎሳ አፓርታይድ ስርዓት መሰረቱ መሬት ነበር፡፡ የመሬት ባለቤትነት፡፡ መሬትን የመጠቀም መብት፡፡ መሬትን የመያዝ መብት፡፡ መሬትን የመቆጣጠር መብት፡፡ መሬትን ፍትሐዊ ባልሆነ መልኩ የማከፋፈል መብት፡፡ ወደ 90 በመቶ አካባቢ የሚሆነውን መሬት በጥቂት አናሳ ነጭ ገበሬዎች እንዲያዝ የማድረግ መብት፡፡ በነጮች የመሬት ነጠቃ እና ብዙሀኑን ጥቀር ሕዝቦች ከይዞታቸው የማፈናቀል መብት፡፡ ሕገወጥ በሆነ መልኩ ለተወሰደው መሬት የሚሰጥ ካሳን በጣም አሳንሶ የማቅረብ መብት፡፡ ጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን ከቀደምቶቻቸው ጀምሮ ይዘውት ከኖሩት መሬታቸው እና እርስታቸው የማፈናቀል መብት፡፡ ይኸ ሁሉ ሕገወጥ መብት/ድርጊት በጥቂት አናሳ ዘረኛ የነጮች አገዛዝ የተሰጠ ነበር፡፡ ስለሆነም በደቡብ አፍሪካ የጥቂት ዘረኛ የነጮች አገዛዝ የመሰረት ድንጋይ እና ምሰሶ ሆኖ ሲያገለግል የነበረውን ሕግ በሕገወጥ መልክ በመሳሪያነት በመጠቀም ፍትሐዊ ያልሆነው የመሬት ክፍፍል እና ብዙሀኑ ጥቁር ደቡብ አፍሪካውን ንብረት የለሽ እንዲሆኑ በማድረግ የኢኮኖሚ ኃይልን ማዳከም ማደህዬት ነበር፡፡

የአፓርታይድ መሰረት የተጣለው “የተወላጆች መሬት ድንጋጌ፣ 1913 (አዋጅ ቁጥር 27/1913)“ ከሚለው እና ከአስርት ዓመታት በፊት እ.ኤ.አ በ1948 በይፋ ከመውጣቱ በፊት ነበር፡፡ የመሬት አዋጁ በጥቂት ዘረኛ የነጮች አገዛዝ ቁጥጥር የጥቁር ደቡብ አፍሪካውያንን የመሬት ባለቤትነት መብት ለማሳጣት የተዘየደ ዋና የሕግ መሳሪያ ሆኖ አገልግሏል፡፡ ድንጋጌው በተከታታይነት በወጡት ሕጎች እየታገዘ ብዙሀኑ ጥቁር አፍሪካውያን የመሬት ባለቤትነት መብታቸውን በእጅጉ በመገደብ ከተወላጆች መሬት በደቡብ አፍሪካ ውስጥ 14 በመቶ ብቻ የሚሸፍነውን ለጥቁር አፍሪካውያኖች በመስጠት 87 በመቶ የሚሆነውን መሬት አናሳዎቹ ነጮች ብቻ እንዲይዙት ተደርጓል፡፡

የ1950 የቡድን አካባቢዎች ድንጋጌ/Group Areas Act በኋላ በቡድን አካባቢዎች ድንጋጌ/Group Areas Act 36/1966 ተጠናክሮ በደቡብ አፍሪካ ኗሪዎች በዘር አድልኦ ላይ ተጠናክሮ ወጥቷል፡፡ ይህ ድንጋጌ አናሳዎቹን የነጮች ዘረኛ አገዛዝ የገጠር እና የከተማ መሬትን ለነጮች፣ ለፉንጋ ጥቁሮች/colored እና ለሕንዶች የብቸኝነት የመሬት ባለቤትነት መብትን አጎናጽፏል፣ ሆኖም ግን ብዙሀኑ ጥቁር አፍሪካውያን የመሬት ባለቤትነት መብት እንዲኖራቸው ወይም ደግሞ በብቸኝነት እንዲኖራቸው የሚያደርግ ምንም ዓይነት የሕግ ማዕቀፍ አልተደረገም፡፡ ሆኖም ግን ጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን ለሌሎች አካባቢዎች ቡድኖች ተብለው ከተከለሉት አካባቢዎች በተለይ መሬት ለመያዝ ወይም ደግሞ የመሬት ባለቤትነት መብት እንዳይኖራቸው ክልከላ ተደርጓል፡፡

እ.ኤ.አ በ1950 የወጣው የደቡበ አፍሪካ የሕዝብ ምዝገባ ድንጋጌ (ሕምድ)/Population Registration Act (PRA) በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ያለው እያንዳንዱ ኗሪ እንደ ዘር እና እንደ ጎሳ ቡድኑ እንዲመደብ እና እንዲመዘገብ አስፈላጊነቱን ይፋ አድርጓል፡፡ ያ ሕምድ/PRA በብዙሀኑ ጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን እና ነጭ ያልሆኑ ዜጎችን ለመከፋፈል እና የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ አድልኦን በማንሰራፋት የአፓርታይድ ስርዓትን በማፋጠን በመሳሪያነት በማገልገል ዋና መሰረት ሆኗል፡፡ (“አፓርታይድ” የሚለው የአፍሪካ ቃል ጥሬ ትርጉሙ “መለያየት“ ማለት ሲሆን ከደች/ኔዘርላንድ ቋንቋ “መለየት” ሲደመር “ጎረቤት” ከሚሉት ተጣምረው ሲነበቡ “ከጎረቤት መለየት” የሚለውን የሀረግ ትርጉም ይሰጣሉ፡፡ በሕምዳ የአመዘጋገብ ስርዓት መሰረት ግለሰቦች እንደ ዜጋ፣ ፉንጋ ጥቁሮች፣ ኢሲያዊ ወይም ደግሞ ነጭ በማለት ይመደባሉ፡፡ የማንነት ማስረጃ ሰነዶች ፍጹም የሆነውን የዘረኝነት አድልኦ እና ጭቆና ለማስፈጸም በዋናነት የሚያገለግሉ መሳሪያዎች ነበሩ፡፡

የ1951 የባንቱ ባለስልጣኖች ድንጋጌ (ባባድ)/Bantu Authorities Act of 1951 (BAA) (የድንጋጌ ቁጥር 68/1951) የባባድን ድንጋጌ ወዲያውኑ የጥቁሮች ባለስልኖች ድንጋጌ (ጥባድ)/Black Authorities Act በሚል ስያሜ ተቀየረ፡፡ ጥባድ “የጥቁር አካባቢዎች”፣ “አለቆች”፣ “የጎሳ ባለስልጣኖች” የሚል ትርጉምን በመስጠት የስልጣን ኃላፊነታቸውን፣ ስራቸውን፣ የስራ ኃላፊነታቸውን እና የሕግ ማዕቀፎቻቸውን ትርጉም በግልጽ ያስቀምጣል፡፡ ጥባድ በርካታዎቹን የጎሳ እና ቋንቋን መሰረት ባደረገ መልኩ የተደራጁትን ጎሳዎች ወደ ባህላዊ የአካባቢ ኗሪነት በመፈረጅ የጎሳ፣ የክልል እና የአካባቢ ባለስልጣኖችን ፈጠረ፡፡ የ1951ዱ የባንቱ ባለስልጣኖች ድንጋጌ (የ1951 የጥቁር ባለስልጣኖች ድንጋጌ) ጥቁሮችን ወደተመደቡላቸው ቦታዎች እንዲጋዙ በማድረግ የጎሳ፣ የክልል እና የአካባቢ ባለስልጣኖችን ፈጠረ፡፡

የ1950ው የቡድን አካባቢዎች ድንጋጌ/Group Areas Act (በ1966 እንደጸደቀው የቡድን አካባቢዎች ድንጋጌ/Group Areas Act) ሁሉ ደቡብ አፍሪካን ለነጮች እና ለጥቁሮች በሚል በመከፋፈል ሕዝቦች ካልተመደቡበት አካባቢ በተለይም ከዘራቸው እና ከጎሳቸው ውጭ መኖር እንደማይችሉ ለማባረር እንዲችል ለአገዛዙ ስልጣን ሰጠው፡፡ በዚህ ድንጋጌ መሰረት ማንም ቢሆን ባልተመደበበት “ስህተት” ቦታ ላይ የሚኖር ዜጋ ሁሉ ወደ ጎሳው/ሳዋ መኖሪያ አካባቢ ይጋዛል/ትጋዛለች፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሕጉ አፍሪካውያን ሕዝቦች በደቡብ አፍሪካ ውስጥ በማንኛውም ቦታ መሬት የመያዝ መብት የሌላቸው እንደሆኑ እና ከማንኛውም የፖለቲካ እንቅስቃሴ ሁሉ እንዲታቀቡ የሚል የሕግ ክልከላ ተጥሏል፡፡ በዚህ ሕግ መሰረት ጥቁር አፍሪካውያን በግዳጅ ይጋዙ እና እንደ ከብት በበረት ውስጥ በባንቱስታንስ የጎሳ ቡድን ይታጎሩ ስለነበር 3.5 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ህይወቶች ጠፍተዋል፡፡

እ.ኤ.አ በ1959 የወጣው የባንቱ እራስን በእራስ ማስተዳደር ማበልጸግ ድንጋጌ 1959/Promotion of Bantu Self-Government Act of 1959 (PBSA) (የድንጋጌ ቁጥር 46) 8 (ቆይቶም ወደ 10 ከፍ እንዲሉ የተደረጉ) በአሁኑ ጊዜ ካሉት እያንዳንዳቸው እራሳቸውን በእራሳቸው በምስለኔዎች፣ በአለቆች፣ በዋና አለቆች፣ እና በጥቁር አካባቢዎች ያሉ የክልል አስተዳዳሪዎች መሰረት ማስተዳደር እንዲችሉ በመፍቀድ ልዩ የሆኑ የባንቱ ክልሎችን ፈጥረዋል፡፡ የአካባቢዎች መንግስታት ውሱን የሆኑ የግብር አሰባሰብ፣ የሕዝብ ስራዎች ቁጥጥር፣ የፈቃድ አሰጣጥ ጉዳዮችን እና ውዝግቦችን በሕጋዊ መንገድ የመፍታት ስልጣን ተሰጥቷቸዋል፡፡ የPBSA ዋና ዓላማ ለአካባቢ አስተዳደሮች የመጨረሻ ስልጣን ለመስጠት፣ ከደቡብ አፍሪካ ዜግነት ለማስወገድ እና ለጥቂቶቹ የነጭ ዘረኛ ህዝቦች የብዙሀን ስልጣንን ጠቅልለው እንዲይዙ ለማስቻል ነበር፡፡ እ.ኤ.አ የ971 የባንቱ አስተዳደር ሕገ መንግስት ድንጋጌ በደቡብ አፍሪካ አፓርታይድ መንግስት በተወሰነው ውሳኔ መሰረት ለጥቂት ነጭ የበላይነት አገዛዝ ለማንኛውም አስተዳደር አካባቢ ነጻ ስልጣን ሰጥቷል፡፡ የድንጋጌው ዓላማ ግልጽ እና እንዲህ የሚል ነበር፡ “እያንዳንዱ የአካባቢ መንግስት እራሱን በእራሱ እንዲመራ እና የእራሱ መንግስት እና ነጻነት ያለው መሆኑ የመንግስት ጽኑ አቋም እና ሊቀለበስ የማይችል ዓላማ ነው፡፡“ በሌላ አባባል የአካባቢ አስተዳደሮች ድንጋጌ የተለመደውን ተፈጥሯዊ የጎሳ መሬቶች የእራስን ዕድል በእራስ መወሰን በሚል ለባንቱስታንስ መንግስታት ሙሉ ነጻነት ይሰጣል፡፡ በዚህ ድንጋጌ መሰረት በመጨረሻ ነጻነት እ.ኤ.አ በ1976 እና 1981 ለትራንስኬይ፣ ለቦፉታትስዋና፣ ለቬንዳ እና ለሲስኬይ የአካባቢ መንግስታት ተሰጥቷል፡፡

ጨካኙ የደቡብ አፍሪካ ነጮች ዘረኛ አገዛዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ሄንድሪክ ቬርወርድ እ.ኤ.አ በ1960ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ የሕዝብ ምዝገባ ድንጋጌ (ሕምድ)/Population Registration Act (PRA)ን በመጠቀም “የተናጠል ልማት” እየተባለ የሚጠራ ፖሊሲ ነድፎ በስራ ላይ አውሏል፡፡ አፓርታይድ የፖሊሲው ዋና ካርታ ሆኖ በመቅረብ የባንቱ የአስተዳደር አካባቢዎች የእየራሳቸው መንግስታት ወይም ባንቱስታን ለመሆን በቅተዋል፡፡ አናሳው የጥቂት ነጮች አገዛዝ የብዙሀኑን ጥቁር ህዝቦች ባንቱስታናዊ የማድረግ እንዲህ የሚል የፖለቲካ ስልት ዓላማ ነበረው፡

1ኛ) በዙሀኑን ጥቁር አፍሪካዊ በትንናንሽ የሕዝብ ስብስብ የመከፋፈል ስሌትን በመጠቀም የከፋፍለህ ግዛን ፖሊሲ ተግባራዊ ማድረግ ይችላሉ፡፡

2ኛ) በባንቱስታናዊ ቅኝት የተዘጋጀ የጎሳ ማንነትን ተግባራዊ በማድረጉ ጥረት ጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን እርስ በእርሳቸው ፍቅር የማይኖራቸው መሆናቸውን በማየት ስኬታማ መሆን መቻላቸውን ካረጋገጡ ማንኛውንም የጥቁር ደቡብ አፍሪካውያንን አንድነት በተጨባጭ ለማጥፋት እንደሚችሉ ያምናሉ፡፡

ባንቱስታናዊ ከማድረግም የተነሳ አናሳው የጥቀቲ ነጮች የበላይ አገዛዝ ቀደ 14 በመቶ የሚሆን የባንቱስታንን የአስተዳደር አካባቢ ለብዙሀኑ ጥቁር ደቡብ አፍሪካ ሕዝቦች በመስጠት ሌላውን ለሙን፣ የማዕድን ክምችት ያለበትን እና የከተማ ቦታዎችን በሙሉ ለነጮች ይዞታ አደረገ፡፡ ወደ 90 በመቶ ያህል የሚሆነው የደቡብ አፍሪካን የንግድ የእርሻ መሬት በሙሉ ለ50,000 ነጭ ገበሬዎች ወይም ደግሞ መንግስት ተሰጠ፡፡ በፖለቲካዊ አካሄድ ባንቱስታናዊነት ለጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን ህዝቦች የእራስ አስተዳደር መብት እና ነጻነት ይሰጣል፣ ሆኖም ግን ለእነርሱ ከተከለለላቸው አካባቢ ውጭ እንደሌላ እንደ ባዕድ ዜጋ ነበር የሚታዩት፡፡ ደቡብ አፍሪካውያን በእራሱ በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ሊኖር የሚገባውን የእኩልነት መብት ይከላከላሉ፣ የእራሳቸው የአካባቢ መንግስት የጎሳ ዜጋ ከሆኑ የዚያው የአካባቢያቸው መንግስት ዜጋ እንጅ እንደ ደቡብ አፍሪካ ሬፐብሊክ ዜጋ አይቆጠሩም፡፡

የደቡብ አፍሪካ ዘረኛ/የጎሳ አፓርታይድ ስርዓት የጥቂት ነጮች ዘረኛ አገዛዝ ውሳኔ የተመሰረተው መሬትን በብቸኝነት ለመቆጣጠር እና መሬትን ተቆጣጥሮ በመያዝ በዚያ ስር የጥቁር ደቡብ አፍሪካውያንን ማንነት፣ ዜግነት፣ ኗሪነት፣ የፖለቲካ፣ የማህበራዊ እና የኢኮኖሚ መብቶችን በመሉ ለመቆጣጠር ነበር፡፡ የደቡብ አፍሪካውያን ማንነት በዋናነት የሚወሰነው ከመሬት ጋር ባላቸው ግንኙነት ነበር፡፡ ጥቂቶቹ ነጮች ሁሉንም ምርታማ የሆነ ለም መሬት ተቆጣጥረው ሲይዙ ብዙሀኖቹ ጥቁር አፍሪካውያን ህዝቦች ግን በእርግጠኝነት ምንም ዓይነት መሬት አልነበራቸውም፡፡

መሬት እና የዘ–ህወሀት የጎሳ አፓርታይድ ስርዓት የሕግ መሰረት፣

የዘ-ህወሀት ልዩ የሆነው ጉብዝናው እ.ኤ.አ በ1995 በጸደቀው ሕገ መንግስቱ ውስጥ የጥቂት ነጮች የበላይ አገዛዝ ለበርካታ አስርት ዓመታት ያጸደቋቸውን ሁሉንም የአፓርታይድ ሕጎች እና ፖሊሲዎች ልቅም አድርገው በመውሰድ በእነርሱ ሕገ መንግስት ውስጥ ሙሉ በሙሉ በማስገባት የጎሳ የአፓርታይድ ስርዓት ለመፍጠር ያደረጉት ጥረት ነው፡፡

እ.ኤ.አ በ1995 በጸደቀው የዘ-ህወሀት ሕገ መንግስት የሕገ መንግስት አርቃቂዎቹ መሬትን እና ጎሳን በአንድ ላይ በማጣመር የደቡብ አፍሪካን ባንቱስታንስ የፖለቲካ፣ የማህበራዊ፣ የኢኮኖሚ እና የባህል ስብጥር ባህሪያትን እንዳለ በመኮረጅ ወስደው ክልሎችን ለመፍጠር ተጠቅመውበታል፡፡ የዘ-ህወሀት ሕገ መንግስት በመግቢያው መንደርደሪያ ላይ እንዲህ በማለት አውጇል፣ “ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና የኢትዮጵያ ሕዝቦች፣ መብቶቻቸውን እና ነጻነቶቻቸውን ሙሉ በመሉ ለመጠቀም፣ እስከ መገንጠል…“ ይላል፡፡ በአንቀጽ 8 (1) የዘ-ሕወሀት ሕገ መንግስት እንዲህ የሚል መብትን ያጎናጽፋል፣ “የብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና የኢትዮጵያ ሕዝቦች ሉዓላዊ መብቶች ሙሉ በሙሉ ተከብረዋል፡፡“ የዘ-ህወሀት አንቀጽ 39 እንዲህ የሚል መብትን ያጎናጽፋል፣ “እያንዳንዱ ብሄር፣ ብሄረሰብ እና የኢትዮጵያ ሕዝብ የእራሱን ዕድል በእራሱ የመወሰን መብት እስከ መገንጠል“ ተሰጥቶታል፡፡ አንቀጽ 42 (2) እንዲህ የሚል መብትን አጎናጽፏል፣ “ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ሕዝቦች በዚህ አንቀጽ በንኡስ አንቀጽ 1 በግልጽ በተመለከተው መሰረት በማናቸውም ጊዜ የእራሳቸውን መንግስት የማቋቋም መብት አላቸው፡፡“

የሚያስገርመው ነገር የደቡብ አፍሪካ ሕገ መንግስት ድንጋጌ 110/1983 እንዲህ የሚል ተመሳሳይ ዓላማን ያነገበ ድንጋጌን አጎናጽፎ ነበር፣ “ቡድኖች እና ሕዝቦች የእራሳቸውን ዕድል እራሳቸው እንዲወስኑ ውሳኒያቸውን ለማክበር፣ ለማጠናከር እና ለመጠበቅ“ ይላል፡፡

እንደ ደቡብ አፍሪካ የ1959 የBantu Self-Government Act of 1959 (PBSA) ድንጋጌ ሁሉ መጀመሪያ 8 (ቆይቶም በማስፋት 10) ባንቱስታንስ (የጥቁር ሕዝቦች መኖሪያ መንደሮች) እንደፈጠሩ ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ የዘ-ህወሀት ሕገ መንግስትም በአንቀጽ 46 (2) የአኗኗር ዘይቤዎችን፣ ቋንቋን፣ ማንነትን እና የሚመለከተውን ሕዝብ ስምምነት ከግንዛቤ በማስገባት ክሎችን ይፈጥራል ይላል፡፡ አንቀጽ 47 የአኗኗር ዘይቤዎችን፣ ቋንቋን፣ ማንነትን እና የሚመለከተውን ሕዝብ ስምምነት መሰረት በማድረግ 9 ክልላዊ መንግስታትን (ክልሎችን) መስርቷል፡፡

ለደቡብ አፍሪካ ጥቂት ነጮች ዘረኛ የበላይ አገዛዝ በአጠቃላይ መሬትን መቆጣጠር እንዳስቻለው እንደ ደቡብ አፍሪካው የአፓርታይድ ሕገ መንግስት እና ሌሎች ሕጎች ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ የዘ-ህወሀት ሕገ መንግስት በአንቀጽ 40 (3) ሁሉም የመሬት የባለቤትነት መብት በዘ-ህወሀት እና በዘ-ህወሀት ታዛዥ ሎሌዎች፣ ተባባሪዎች እና በክልል ያሉ ግብረ አበሮች አማካይነት መሬትን በብቸኝነት ለመቀራመት እና ለመቆጣጠር እንዲህ የሚል መብትን አጎናጽፏል፣ “የገጠር እና የከተማ መሬት እንዲሁም ሁሉም የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቶች የመንግስት እና የኢትዮጵያ ሕዝቦች ናቸው፡፡ መሬት የብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና የኢትዮጵያ ሕዝቦች ንብረት ነው፡፡ እናም አይሸጥም ወይም ደግሞ አይለወጥም“ ይላል፡፡ ሆኖም ግን ዘ-ህወሀት በክልሎች የሚገኘውን በመቶዎች እና በሺዎች ሄክታሮች የሚቆጠረውን አንጡራ የሀገሪቱን ለም መሬት ድብቅ ለሁኑት ሸፍጠኛ የቢዝነስ ሰዎች እየቸበቸበ በማቀራመት ላይ ይገኛል፡፡ ከጥቂት ወራት በፊት ካሩቱሪ የተባለው የሕንድ ኢንቨስተር በመሬት ቅርምቱ ያገኘውን መሬት እና የዌልስን ግዛት የሚያህለውን እና በምዕራብ ኢትዮጵያ በጋምቤላ ክልል ውስጥ የሚገኘውን ዘ-ህወሀት የሚነካበት ከሆነ የሕንድን ኃያልነት እንደሚያሳየው ድፍረትን በተላበሰ መልኩ ለህወሀት የዘራፊ ቡድን ስብስብ ነግሮታል፡፡ ወይ የካርቱርሪ በእራስ መተማመን ድፍረት እንነጋር!

ኢትዮጵያን ክልላዊ በማድረግ የዘ-ህወሀት አገዛዝ እና ታዛዥ ሎሌዎቹ በኢትዮጵያ ብዙሀን ሕዝብ ላይ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ የበላይ ጌቶች እንዲሆኑ አስችሏቸዋል፡፡ የደቡብ አፍሪካው የጥቂት ነጮች የበላይ የአፓርታይድ አገዛዝ በርካታ አስርት ዓመታትን የወሰደበት ድርጊት ዘ-ህወሀት ግን በ25 ዓመታት ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ ችሏል፡፡ ዘ-ህወሀት የኢትዮጵያን ሕዝቦች ክፍት በሆነ ከባቢ አየር ውስጥ አስሮ እና እንደ ከብት በበረት አጉሮ በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ መብት ገፍፎ ሀገሪቱን በክልላዊነት በጥጣሶ በማተራመስ ላይ ይገኛል፡፡

ሁልጊዜ እንደማቀርበው የክርክር ጭብጥ ሁሉ የጎሳ ክላልዊነት ዋና መሀንዲስ የነበረው እና አሁን በሕይወት የሌለው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ እ.ኤ.አ በ1960ዎቹ የመጀመሪያዎቹ ዓመታት አካባቢ የደቡብ አፍሪካው የጥቂት ነጮች ዘረኛ የበላይ አገዛዝ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበረው ሄንድርክ ቬርወርድ እንዳደረገው ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ በኢትዮጵያ ውስጥ የጎሳ ክፍፍልን መሰረት ባደረገ ራዕይ በመገፋፋት ሀገሪቱን በጎሳ ከፋፍሎ በስቃይ ውስጥ እንድትሆን እና ለከፍተኛ አደጋ እንድትዳረግ አድርጓታል፡፡ አምባገነኑ መለስ ለሁለት አስርት ዓመታት ገደማ ያህል የኢትዮጵያን ሕዝቦች የግንኙነት ክር ለመበጠስ እና በዘር፣ በጎሳ፣ በቋንቋ እና በክልል እንድትቀነበብ ያለ የሌለ ጥረቱን አድርጎ ነበር በተፈጥሮ ትዕዛዝ ተቀደመ እንጅ፡፡ አምባገነኑ መለስ ሙሉ በሙሉ በጎሳ እና በዘር ግንኙነት ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ ድርጅት አዋቅሯል፡፡

ከዚህ ጋር ተመሳሳይ በሆነ መልኩ ጥቂት የነጮች ዘረኛ አገዛዝ ጥቁር ደቡብ አፍሪካውያንን ከአንድ የትወልድ ቦታ ወደ ሌላ ሲያዘዋውር እንደነበረው ሁሉ ዘ-ህወሀትም አንድ ዓይነት እርምጃ በመውሰድ እና የ”አማራ” ጎሳ ቡድን አባላትን ከደቡብ ክልል (ከ9 ክልሎች አንዱ ከሆነው) በኃይል በማፈናቀል የጎሳ ማጽዳት ወንጀል ፈጽሟል፡፡ አሁን በህይወት የሌለው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ከደቡብ ክልል በኃይል ላፈናቀላቸው የአማራ ብሄረሰብ ዜጎች የሰጠው ማሳመኛ እንዲህ የሚል ነበር፣ “…በታሪክ አጋጣሚ ላለፉት አስርት ዓመታት ከምስራቅ ጎጃም የመጡ በርካታ ህዝቦች ወደ 30,000 የሚጠጉ ሰፋሪዎች በቤንች ማጅ ዞን (በደቡብ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰፍረው ይኖሩ ነበር፡፡ በጉራ ፈርዳ ወረዳ ከ24,000 በላይ ሰፋሪዎች አሉ“ ብሎ ነበር፡፡ በሰፈራ ፕሮግራም በዘለቄታዊ መንገድ ለዘመናት ቀደምቶቻቸው ሲኖሩበት ከነበረው አካባቢ ከጋምቤላ፣ ከቤንሻንጉል እና ከኦሞ ወንዝ ሸለቆ በኃይል በማፈናቀል መሬቶቻቸው በጫረታ አማካይነት ለሆዳም ስግብግብ ብዙሀን የግብርና ቢዝነስ ለሚያካሂዱ ድርጅቶች ተሰጥቷል፡፡

በዘ-ህወሀት ስቃይ እና ለመቋቋም የማይቻል ክልላዊ ደባን አስመልክቶ ዓለም አቀፍ የግጭቶች አስወጋጅ ቡድን/International Crises Group (ICG) በተባለው ዓለም አቀፍ ድርጅት አስደማሚ ጥናት ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ “ኢትዮጵያ፡ የጎሳ ፌዴራሊዝም እና ቅሬታዎቹ“ በሚል ርዕስ ባዘጋጀው ጥናቱ ICG በጎሳ ፌዴሪያሊዝም (በክልላዊነት) ምክንያት ዜጋዊነት፣ የፖለቲካ አመለካከት እና ማንነት በጎሳ መሰረት ላይ የሚሰጥ የመሆኑን ችግር ይፋ አድርጓል፡፡ ጥናቱ እንዲህ የሚል የክርክር ጭብጥ ያቀርባል፣ “የጎሳ ፌዴራሊዝም በሀገሪቱ መካከለኛው ከፍተኛ አካባቢዎች በሚኖሩት እና ከፍተኛ የሕዝብ ብዛት ያላቸው ኦሮሚያ እና አማራ በጣም ትንሽ የሆነ የሕዝብ ብዛት ካላቸው እንደ ጋምቤላ እና ሶማሊ ካሉት ጋር የማይመሳሰል ፌዴሬሽን በእኩል ተሰጥቶ ይገኛል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የጎሳ ፌዴራሊዝም ጥቂት ቡድኖችን በማጠናከር ደካማ ክልላዊ መንግስታትን በመፍጠር የብሄራዊነት ጥያቄን መመለስ ተስኖታል፡፡ በኢትዮጵያ ሕዝቦች መካከል ውይይት እና እርቀ ሰላም ለማውረድ የመለስ አምባገነናዊ አመራር ሊቀበል ባለመቻሉ ምክንያት በአሁኑ ወቅት እየታዬ ያለውን ሁኔታ እንዲባባስ በማድረግ ቅሬታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደጉ በመሄድ የኢህአዴግ የጎሳ ፖለቲካ ለስልጣን ስስ መሆን በቀጣይነት የጎሳ ግጭት ለመከሰት የሚያስችል ፍርሀትን አንግሶ ይገኛል፡፡“ የICG ዘገባ ግልጽ እንዳደረገው በረዥሙ የጊዜ እይታ የጎሳ ፌዴራሊዝም የኢትዮጵያን ሕዝብ ወደ መበተታተን እና መለያየት ሊያመራው ይችላል፡፡ አሁን ብሄራዊነት የሌለው ሀሰተኛው መሲህ መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት በኢትዮጵያ ስልጣን ሲይዝ ሀገሪቱ ወደ መበታተን አደጋ ላይ ወድቃ እንደነበር ጉራውን ቸርችሮ ነበር፡፡ እንዲህ በማለት የክርክር ጭብጡን አቅርቦ ነበር፣ “ማንም ትንታኔ የሚያቀርብ ባለሙያ እንደሚገምተው ኢትዮጵያ ዩጎዝላቪያ እና ሶቪዬት ህብረት እንደሄዱበት ባለ መንገድ ላይ ልትጓዝ ትችላለች“ በማለት መተንበይ ይችላል ብሎ ነበር፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ግን ኢትዮጵያ እንደነ ዩጎዝላቪያ፣ ሶማሌ፣ ኮንጎ ወይም ደግሞ ኤርትራ እንደሆነችው እንኳ ስትሆን አልታየም፡፡

ሀሰተኛው መሲህ የሚል ቅጽል ስም የተሰጠው መለስ ሁልጊዜ እራሱን ከፍ ከፍ ያደርጋል፡፡ ሕዝቡን በማስፈራራት ከእግሩ ስር ለማንበርከክ እንዲችል ማንኛውንም አስፈሪ የሆነ ነገረ ሁሉ እየቃረመ ያስፈራራል፡፡ እውነታው ፍርጥርጥ ብሎ ሲታይ ግን የጎሳ መለያየት፣ መበታተን፣ መከፋፈል እና ጽንፈኝነት የመለስ አገዛዝ በስልጣን ላይ እንደ መዥገር ተጣብቆ ለመኖር እና አንጡራ የሕዝብን ሀብት እየዘረፉ ለመኖር እንዲመቻቸው የሚጠቀሙባቸው መሳሪያዎቻቸው ናቸው፡፡ በእውነተኛ የፌዴሪያሊዝም ስርዓት ብሄራዊው መንግስት የክልል መንግስታት ውጤት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ክልላዊ መንግስታት የብሄራዊው መንግስት ፍጡሮች እና በዘ-ህወሀት እጅ ተጠፍጥፈው የተሰሩ መንግስታት ናቸው፡፡ በእውነተኛ ፌዴራሊዝም ብሄራዊ መንግስት ውሱን የሆኑ እና የተቆጠሩ ስልጣኖች ተሰጥተውት የክልል መንግስታት የጋራ የሆኑ ነገሮችን ማስፈጸም ብቻ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ የዘ-ህወሀት ስልጣን ሰፊ እና ያልተገደበ ነው፡፡ እናም በክልሎች ላይ ጣልቃ ለሚያስገባው ስልጣኑ ምንም ዓይነት ገደብ የሌለው በመሆኑ እንደፈለገው በማተራመስ ላይ ይገኛል፡፡ በዘ-ህወሀት ክልላዊ ስርዓት ዘ-ህወሀት እና ግብረ አበር ክልሎቹ በሕዝቦች መብቶች እና ነጻነቶች ረገጣ እና ለሚያደርጉት ጣለልቃገብነት ክልከላ ዘብ የሚቆም ምንም ዓይነት ኃይል የለም፡፡ በቀላል አገላለጽ የዘ-ህወሀት ክልላዊ ፖሊሲ የዘ-ህወሀት አምባገነናዊ አገዛዝ ቀጥተኛ ቅጅ ነው፡፡ ክልላዊነት በየራስን ዕድል በራስ መወሰን እስከመገንጠል በሚል በማስፈራሪያነት ተወሽቆ ይገኛል፡፡

በደቡብ አፍሪካው በጥቂት ዘረኛ ነጮች የበላይ አገዛዝ አፓርታይድ እና በዘ-ህወሀት የጎሳ ፌዴራሊዝም አፓርታይድ መካከል ያሉት ተመሳሳይነቶች ለመመዝገብ ከሚያስቸግር በላይ በርካታ ናቸው፡፡ ዘ-ህወሀት ሙሉ በሙሉ የፖለቲካ ስልጣኑን፣ ውክልናውን እና የውሳኔ ሰጭነት ተግባሩን እንደ ደቡብ አፍሪካው የጥቂት ዘረኛ ነጮች የበላይ አገዛዝ አፓርታይድ ብሄራዊ ፓርቲ ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ ተቆጣጥሮ በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡ ዘ-ህወሀት በክልላዊ ፖሊሲው የአማራ ብሄረተኞች (ነፍጠኛ፣ ሰፋሪ ወታደሮች እያለ የሚጠራቸው) የድሮውን ስርዓት በማምጣት በብሄረሰቦች ላይ የአማራን አገዛዝ ሊጭኑባችሁ ነው በማለት በእርሱ ክልላዊ ፖሊሲ ላይ ትችት የሚያቀርቡትን ጸጥ ለማድረግ ይጠቀምበታል፡፡ ዘ-ህወሀት ሌሎችን ተቃዋሚዎች ጽንፈኛ አክራሪዎች እና እንደ ሩዋንዳ የኢንተር ሀሞይ እልቂትን ለማምጣት ጥረት የሚያደርጉ ናቸው በማለት ይፈርጃቸዋል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ የጥቂት ዘረኛ ነጮች አፓርታይድ አገዛዝ ተቃዋሚዎቹን “የኮሙኒስት አሸባረዎች” ናቸው በማለት ይጠራቸው ነበር፡፡

ዘ-ህወሀት በደቡብ አፍሪካ የጥቂት ዘረኛ ነጮች አፓርታይድ አገዛዝ ያደርጉት እንደነበረው ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ ያደርጋሉ፡፡ የዘ-ህወሀት መንግስት በመንግስት ላይ ወሳኝ የሆኑ ውሳኔዎችን ያሳልፋል፡፡ አምባገነኑ መለስ በህይወት በነበረበት ጊዜ በመንግስት ላይ መንግስት የሚለው ሸፍጣቸው ገና ከጫካ በነበሩበት ጊዜ ይጠቀሙበት የነበረ እና ስልጣን ከያዘ ጀምሮ ታማኞቹን እና እሺ የሚሉ ሰዎችን ብቻ ከገንዘብ ገንዳው ውስጥ የሚያሳትፍ ስርዓትን ዘርግቷል፡፡ እንደ ደቡብ አፍሪካው የጥቂት ዘረኛ ነጮች አፓርታይድ አገዛዝ ሁሉ በክልሎች ስማዊ የነጻ ውሳኔ ሰጭነትን ይፈቅዳል፡፡ ሆኖም ግን እውነታው ሁሉም ውሳኔዎች በማዕከል ተሰባስበው የተያዙ እና በዘ-ህወሀት በመንግስት ላይ መንግስት ውሳኔ የሚሰጥባቸው ናቸው፡፡ የዘ-ህወሀት የደህንነት እና የስለላ ኃላፊዎች በደቡብ አፍሪካ ባንቱስታንሶች ላይ ይደረግ እንደነበረው ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ በክልሎች ላይ በመንግስት ላይ መንግስት እየሰለሉ ወሬ በማነፍነፍ ለዘ-ህወሀት አመራሮች የሚያቀብሉ ናቸው፡፡

በደቡብ አፍሪካ የጥቂት ዘረኛ ነጮች የበላይ አገዛዝ በባንቱስታንሶች ላይ ያደርግ እንደነበረው ሁሉ ዘ-ህወሀትም እንደዚሁ በተመሳሳይ መልኩ ለመሬት ቅርምቱ እና ለሌላው ሀብት እና ዘ-ህወሀትን ለመገዳደር ችሎታው ለሌላቸው እና በዘ-ህወሀት ላይ ጥገኛ የሆኑትን ክልሎችን ለመቆጣጠር እገዛና እና የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋሉ፡፡

የዘ-ህወሀት የደህንነት መዋቅር በክልል ውስጥ ያሉ ባለስልጣኖችን ሙሉ በሙሉ ይቆጣጠሯቸዋል፡፡ በእርግጥ የፖለቲካ መረጋጋት አይታይበትም በሚባል አካባቢ የዘ-ህወሀት የደህንነት እና ወታደራዊ ኃይሎች በደቡብ አፍሪካ ባንቱስታንስ አፓርታይድ ይደረግ እንደነበረው ሁሉ ከክልል ባለስልጣኖች ነጻ በሆነ መልኩ ይሰራሉ፡፡ የዘ-ህወሀት ባለስልጣኖች የደህንነት እና የወታደራዊ ኃይሉን እንቅስቃሴ በክልሎች ይመራሉ፡፡ ማንም የክልል ባለስልጣን ለዘ-ህወሀት መስመር የማያጎበድድ ከሆነ ከስልጣኑ እንዲባረር ይደረግ እና የሙስና ክስ እንዲመሰረትበት ይደረጋል፡፡

እንደ ደቡብ አፍሪካው የጥቂት ዘረኛ ነጮች አገዛዝ አፓርታይድ በባንቱስታንሶች ላይ ያደርጉት እንደነበረው ጥብቅ ቁጥጥር ሁሉ ዘ-ህወሀትም በተመሳሳይ መልኩ በክልሎች ላይ በርካታ ስልቶችን በመቀየስ ጥብቅ ቁጥጥር ያካሂዳል፡፡ ዘ-ህወሀት ፖሊሲዎቹን ሽፋን ለመስጠት፣ ለማስመሰል እና ለማስፈጸም ኢህአዴግ የሚባለውን የይስሙላ የፓርቲ ስብስብ በማስመሰያነት ይጠቀማል፡፡ ክልሎች ለበጀት እና ለሌሎች ድጋፎችም በዘ-ህወሀት ላይ ጥገኛ በመሆናቸው ምክንያት ዘ-ህወሀት ክልሎቹ እና ሌሎች በእርሱ መስመር አጎብዳጅ ሆነው እንዲኖሩ ስልጣኑን ለቁጥጥር ይጠቀምበታል፡፡

እንደአፓርታይድ ጓደኞቻቸው ሁሉ ዘ-ህወሀቶችም በተመሳሳይ መልኩ የፈጠሯቸው የጎሳ-ቋንቋ ቡድኖች አንድ ዓይነት እና ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ሆኖም ግን አንድ ዓይነት ያልነበሩ እና ቀላል በሆነ መልኩ በአኗኗ ዘይቢያቸው፣ በቋንቋ፣ በማንነት መፈረጅ እና መወሰን አልነበረባቸውም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝቦች በውልደት የተዋኸደ፣ ተመሳሳይ ባህል እና ማንነት ያላቸው ናቸው፡፡ ሁሉም ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ሕዝቦች ልብወለድ ስታሊኒናዊ ዘ-ህወሀቶች ጥሩ ሊመስል ይችላል፣ ሆኖም ግን እውነተኛውን እና ታሪካዊውን የጎሳ ልዩነቶችን እና አንድነቶችን አያንጸባርቅም፡፡ የዘ-ህወሀት የጎሳ ሀሳብ ከታሪካዊ እውነታ ጋር የሚጣረስ እና ምንም ዓይነት ወጥነት የሌለው ድልዱም አስተሳሰብ ነው፡፡

ከጥቂት ሳምንታት በፊት ንጉሳዊ አገዛዝ እስከወደቀበት እ.ኤ.አ እስከ 1974 ድረስ የትግራይ ጠቅላይ ግዛት ገዥ የነበሩት ልዑል መንገሻ ስዩም በሰሜን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የዘ-ህወሀትን ክልላዊ መዋቅር የውሸት መሆኑን አሰተባብለዋል፡፡ ልዑል መንገሻ ወልቃይት ጠገዴ ከአማራ ይዞታነት ተነስቶ ወደ ትግራይ መካለሉን አስመልከቶ ወደ ትግራይ እንዲካለል የተደረገውን የዘ-ህወሀትን ውሳኔ በጽኑ ተቃውመውታል፡፡ በሌላ አባባል በወልቃይት ጠገዴ ወደ ተግራይ መካለል ዘ-ህወሀት አኗኗር ዘይቤ፣ በቋንቋ በማንነት እና ጉዳዩ በቀጥታ በሚመለከታቸው ሕዝቦች የሚለውን የእራሱን ሕገ መንግስት እንኳ የጣሰ እና በሸፍጥ የእራሱ ግዛት ለማድረግ ያደረገው እኩይ ምግባር ነው፡፡

የኢትዮጵያ ክልላዊነት አከላል ኢትዮጵያውያንን በጎሳ መስመር በመከፋፈል ለዘ-ህወሀት አገዛዝ እንዲመቸው ዓላማ ያደረገ እና የስልጣን እድሜውን ለማራዘም የተቀየሰ የዘ-ህወሀት የጥፋት ዕቅድ ነው፡፡ ታዋቂው ኢትዮጵያዊ ፕሮፌሰር ቴደ ቬስተል “የሰብአዊ መብቶች ረገጣ በዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ፡ መንግስት አቀፍ የጎሳ ጥላቻ” በሚል ርዕስ ባቀረቡት ጽሁፋቸው እንዲህ በማለት የዘ-ህወሀትን የዘ-ህወሀትን ክልላዊ ስልት ጨምቀው አቅርበዋል፣

“የኢህአዴግ ሌላው ገጽታው [የብዙሀነት ቅርጽ ያለው ለማስመሰል በህወሀት የተፈጠረው የሸፍጥ ድርጅት] ዋና ስልት የብሄሮችን፣ ብሄረሰቦችን እና ሕዝቦችን መብት ትኩረት በሰጠ መልኩ የተዋቀረ የጎሳ ፌዴራሊዝም ስርዓት አስተዳደርን ለመመስረት ነው፡፡ ሆኖም ግን ይህ ትልቅ የሚመስል መርህ ከሌኒን የተኮረጀው ከውሶኒያን ይልቅ የማኪያቬሊንን ሸፍጥ የተላበሰ ነው፡፡ እነዚህ ብዙ መስለው የሚታዩት እና ኢህአዴግ/ኢፌዴሪን የሚዘውሩት ትግራውያን ሌሎችን የጎሳ ቡድኖች እየከፋፈሉ እና በጥልቅ የጎሳ ጥላቻ እርስ በእርሳቸው እንዲናቆሩ በማድረግ ወይም ደግሞ እነርሱ ባለቻቸው ትንሽ እውቀት ላይ በመመስረት ትናንሽ ግዛቶቻቸውን በማስተዳደር ተግባር ላይ ተጠምደው ባሉበት ሁኔታ ታላቁ የአገር ጉዳይ በአንድ ፓርቲ መንግስት እንዲካሄድ ይደረጋል፡፡ ስለሆነም ኢህአዴግ ታላቋ ኢትዮጵያ እያለ የሚያሰራጨው የውሸት የብሄራዊ ፕሮፓጋንዳ በቁጥጥር ስር ይውል እና የእርሱ ተቃዋሚዎች እንዲከፋፈሉ እና እንዲሸነፉ ያደርጋል፡፡“

የኢትዮጵያ የአቦ ሸማኔው ወጣት ትውልድ፡ “ኢትዮጵያ በእናንተ እጅ ላያ ናት፡፡”

ከአሜሪካ የሕግ ዳኞች አንዱ እና እጅግ በጣም ታዋቂ የሆኑት ጌሪ ስፔንስ በአንድ ወቅት በወንጀል ጉዳይ ላይ ያደረጉት የመዝጊያ ንግግር ውስጣዊ ስሜቴን እና ቀልቤን ስለገዛው እና የኢትዮጵያ ወጣቶች ምን ማድረግ እንደሚችሉ እና ለእራሳቸው እና ለሀገራቸውስ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ታላቅ ትምህርት ይሆናል በማለት ከዚህ በታች አቅርቤዋለሁ፡፡ ስፔንስ እንዲህ በማለት ሞግተዋል፡

“ክቡራት እና ክቡራን፣ ከእናንተ ልለይ ነው፣ ሆኖም ግን ከእናንተ ከመለየቴ በፊት ስለአንድ ብልህ ሽማግሌ እና ስለአንድ አጭበርባሪ ልጅ ታሪክ ልነግራችሁ እወዳለሁ፡፡ አጭበርባሪው ልጅ ሽማግሌው ምን ያህል ሞኝ እንደሆኑ ለማሳት ዕቅድ ነበረው፡፡ አጭበርባሪው ልጅ ከጫካ ውስጥ አንዲት ወፍ ያዘ፡፡ እርሷንም በእጆቹ ያዛት፡፡ የትንሿ ወፍ ጅራት ከጁ አልፋ ትታይ ነበር ፡፡ በእጆቹ ላይ ያለችው ወፍ በህይወት ነበረች፡፡ ዕቅዱ እንዲህ የሚል ነበር፡ ወደ ሽማግሌው እያመላከተ “ሽማግሌው በእጆቼ ላይ ምንድን ነው ያለው?“ ሽማግሌው ሰው እንዲህ አሉ፣ “ልጄ ወፍ ይዘሀል፡፡“ ከዚያም ልጁ እንዲህ ይላል፣ “ሽማግሌው ወፏ በህይወት አለች ወይስ በህይወት የለችም?“ ሽማግለው ወፏ በህይወት የለችም ሞታለች የሚል መልስ የሚሰጡ ከሆነ ልጁ እጆቹን ግራና ቀኝ በመክፈት ወፏ በነጻነት እንድትበር ሆኖ በዛፍ ላይ ታርፍ እና በደስታ መኖር ትጀምራለች፡፡ ሆኖም ግን ሽማግሌው ሰው ወፏ በህይወት አለች የሚል መልስ የሚሰጡ ከሆነ አጭበርባሪው ልጅ በእጆቹ መካከል ወፏን አጣብቆ እና ደፍጥጦ እንድትሞት በማድረግ “ሽማግሌው ይመልከቱ ወፏ ሞታለች“ ይላል፡፡ በዚህም መሰረት ልጁ ወደ ሽማግሌው በመሄድ ቀረበ እና እንዲህ አለ፣ “ሽማግሌው በእጆቼ ላይ ምን ይዣለሁ?“ ሽማግሌው እንዲህ አሉ፣ “ልጄ ወፍ ይዘሀል፡፡“ ልጁ እንዲህ አለ፣ “ሽማግሌው ወፏ በህይወት አለች ወይስ ደግሞ በህይወት የለችም?“ ሽማግሌው ምናቸው ሞኝ እንዲህ አሉ፣ “ልጄ ወፏ በእጅህ ላይ ናት“ አሉ፡፡

እኔም ለኢትዮጵያ ወጣቶች ኢትዮጵያ በእጃችሁ ላይ ናት እላቸዋለሁ፡፡ በህይወት ያለች ወይም በህይወት የሌለች ወይም ደግሞ ወደፊት የምትኖር ወይም የምትሞት ብቻ ከሆነ እናንተው ብቻ የምታውቁት ይሆናል፡፡ ለዘላለም የምትኖር መሆኗን ግን አረጋግጡ!

ይቀጥላል… (አንደትግሉ )

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

መጋቢት 27 ቀን 2008 ዓ.ም

↧
↧

የፌደሬሽን ምክር ቤት በወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ተወካዮች ለቀረበለት ሕገመንግስታዊ ጥያቄ የሰጠው ምላሽ |ደብዳቤውን ይዘናል

$
0
0

በወልቃይት ጸገዴ ህዝብ ውክልና ተሰጥቷቸው በሁለት የተለያዩ ወቅቶች ለፌደሬሽን ምክር ቤት ጥያቄያቸውን በማቅረብ የህዝቡ ህገ መንግስታዊ መብት ተከብሮ ለማንነታቸው እውቅና እንዲሰጥ ለጠየቁ ተወካዩች ምክር ቤቱ በሰጠው ምላሽ ‹‹እንዲህ አይነት ጥያቄዎች በመጀመሪያ በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ የመስተዳድር እርከኖች ቀርበው መፍትሔ የሚሰጣቸው ሲሆን ቀጥታ ለምክር ቤቱ የማይቀርቡ በመሆናቸው በአቤቱታ አቅራቢዎች የቀረበው የማንነትና ሌሎች ተያያዥ የመብት ጥያቄዎች  በክልሉ መፍትሔ እንዲሰጠው የመለስን መሆኑን እናስታውቃለን››ማለቱን ከምክር ቤቱ የወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ምክር ቤቱ የተቋቋመው እንዲህ አይነት ህገ መንግስታዊ ጥያቄዎችን በመመርመር አቤቱታዎቹን በመከታተልና የህገ መንግስት ትርጓሜ በመስጠት ጥያቄዎቹ አግባብ ባላቸው ደረጃዎች የሚመረመሩበትንና እልባት የሚያገኙበትን መንገድ ለማመቻቸት ቢሆንም ምክር ቤቱ ጉዳዩን የማንነታችን ተጨፍልቆ የሌሎችን ማንነት እንድንለብስ አድርገውናል በማለት ወደሚከሷቸው መስተዳድሮች ዘንድ ሄዳችሁ ጉዳያችሁን አሳዩ ማለቱ ነገሩን አስገራሚ ያደርገዋል፡፡

ከምክር ቤቱ የወጣውን ደብዳቤ አባሪ በማድረጋችንም ይመለከቱት ዘንድ ተጋብዘዋል፡፡

welkait

↧

“የመጨረሻው ምሳ…”–በዕውቀቱ ስዩም

$
0
0

ወጣቱ ባለቅኔ በዕውቀቱ ስዩም ከአዲሱ ከአሜን ባሻገር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን በተመለከተ በመጽሐፉ የተካተተውን ትረካ የተመስገንን ልደት በማሰብ በመጠኑ በራሱ ድምጽ አንብቦ በህብር ሬዲዮ በኩል አቅርቧል:: ያድምጡት::

“የመጨረሻው ምሳ…” – በዕውቀቱ ስዩም

↧

ኦሮሞ ጀግና ነው!

$
0
0

addis getse
አናንያ ሶሪ

‹‹ኦሮሞ ጀግና ነው!›› ማለት፡- እንደ ሕዝብ መገለጫው የሆነውን ገዢ ባህርይ መናገርና ማወጅ ነው፡፡ ለዘመናት በብዙ ፈተናና ዕድሎች ውስጥ ያለፈው ይህ ትልቅ ሕዝብ የገድሉን ያህልም ያልተነገረለት ነው፡፡

ዛሬ በዚህ ጽሁፍ፡- በግሌ ለዓመታት ከነበሩኝ ዕይታዎችና አስተውሎቶች ተነስቼ ይህን ድንቅ ሕዝብ ለማመስገን ለመዘከር እና ለማወደስ ወደድኩ…

ቢቻለኝም፡- በተከታታይ በአገራችን ስለሚገኙ ማሕበረሰቦች መጻፌን እቀጥላለሁ፡፡

ነገር ግን፡- ይህ እዚህ የሰፈረው ሃሳብ የግል ምልከታዬ እና ግንዛቤዬ ላይ የተመረኮዘ፣ ከአብሮ መኖር ባህር የተቀዳ፣ ካጋጠሙኝና ካየኋቸው ማህበራዊ ተሞክሮዎች የፈለቀ አስተያየቴ ነው፡፡ ሰፊውን የኦሮሞ ታሪክ ግን ለባለሙያዎች እተዋለሁ፡፡

በኢትዮጵያ ምስረታም ሆነ ግንባታ ሂደት ውስጥ በየዘመናቱ የራሱን አሻራ ያሳረፈው ይህ ‹‹ታላቅ ሕዝብ››፤ ከወንድም የሌላ ብሔር ህዝቦች ጋር የሰራውና የተጋራው እጅግ ብዙ ወርቃማ ታሪክ ባለቤት ነው፡፡ ከሀገሪቱ መልክአ-ምድር ውስጥም ሰፊውን ስፍራ በመያዝ ከተለያዩ ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ጋር በጋብቻ፣ በባህል፣ በእምነት፣ በግብይት፣ በጦርነት፣ በንግስና ተደባልቆ ተዋህዷል፡፡ በተለይ ለአብሮ-መኖር ሲል ረጅም ርቀት የሚጓዘው ‹‹ኦሮሞ›› ሁሌም እጅግ ያስደንቀኛል፡፡ እጅግ ሰው-ወዳድነቱ ……. ፈጣሪን አክባሪነቱ……. ተፈጥሮን ተንከባካቢነቱ ….. ብቻ ምኑ ተነግሮ ምኑ ይተዋል?!

ኦሮሞ – ዛፍ ይወዳል፤ ኦሮሞ ባህር ይወዳል ! ምድሩን ይወዳል፤ ሰማዩን ያፈቅራል! ኦሮሞ ፈጣሪንና ፈጣሪ የፈጠረውን ፍጡር ሁሉ ከልቡ ያፈቅራል! ኦሮሞ – ላሞቹን በሬዎቹን፣ እጽዋቱን አእዋፉን፣ ሳሩን ቅጠሉን ከህልውናው ጋር አዛምዶ ይኖራል፡፡

ኦሮሞ – የሕይወትን ጣዕም በሚገባ ይረዳል፡፡ ጥፍጥናን እና ምሬትንም እንዳመጣጣቸው በፀጋ ይቀበላል! ውልደቱ፣ ሰርጉና ሕልፈቱ በጀግኖች ጌረርሳ ይታጀባል! በሳቁና ለቅሶው፣ በደስታና ሀዘኑ ከልቡ የተሰማውን ከነፍሱ የፈለቀውን… መንፈስን በሚነካ ጥዑም ዜማ ያንጐራጉራል፡፡

በሰፊ ጀግንነቱ እና በሰፊ ፍቅሩ ሰፊ ግዛት የያዘው ‹‹ኦሮሞ›› የትንሽነት ስነ-ልቦና ጭራሽ አያውቀውም፡፡ በትልቁ ደክሞ… ወዙን አንጠፍጥፎ… ትልቅ ሀብት ያፈራል፡፡ ካፈራው ሀብት ሁሉ ይልቅ ግን ‹‹ዋቃ / እግዚአብሔር›› ትልቅ እንደሆነ ያውቃል፡፡ አምላኩንም እርጥብና የለመለመ ሳር ይዞ በረጋ ባህር ዙሪያ ቅዱሱ መንፈስ በረበበበት ላይ ተስብስቦ፤ ምስጋናውን ጸሎቱን፣ ምልጃውን ተስፋውን፣ ህልሙን፣ የትላንቱን፣ የወደፊቱን፣ የልቡን፣ የነፍሱን፣ መሻት ያሳርጋል፡፡ የማቲዎቹን ነገር…. የከብቶቹን ነገር… የሰብሉን ጉዳይ…. የአገሩን ነገር….. የሕዝቦቹን ሰላም…. ሁሉ አደራ ይላል! ‹‹አቤቱ….ዋቀዮ፡- አንተ በእነዚህ ሁሉ ውስጥ አብረኸን ሁን! ከጎናችን ቁም!›› ብሎ እግዚዖ ይላል… ኦሮሞ አምላኩን ጠንቅቆ ያውቃልና! ኃያልነቱም ከአምላኩ ጋር ባለው ጽኑ ፍቅር የተነሳ ነውና!

ኦሮሞ – ፍቅሩም ጀግንነቱም ‹‹ደማቅ›› ነው! ደማቅ ቀለምም ሁሉ የፅኑና ኃያል ጥልቅ-ስሜቱ /Passion መገለጫ ነው፡፡ ኦሮሞ – ለፍቅር እንጂ ለስስት ቦታ የለውም፡፡ ንፉግም አልነበር፤ ንፉግም አይደለም! የተትረፈረፈ የተፈጥሮ ሀብቱን ከማንም ጋር ተካፍሎ መብላትን ያውቅበታል፡፡ ኦሮሞ ልቡም ትልቅ ፍቅሩም ትልቅና ጥልቅ ነው፡፡ ‹‹ፍጹም ፍቅር›› እንጂ ግማሽ መውደድ የሌለው የሰው-ንፁህ ነው፡፡ በልቡ ሌላ እያሰበ ባንደበቱ አይሸነግልም – ሲወድም ሲጠላም ፊት ለፊት ነው፡፡ ድብቅነትና መሰሪነት ተፈጥሮው ውስጥ የሉም! ኃይሉም፡- ለአምላክ፣ ለተፈጥሮና፣ ለሰው-ልጆች ሁሉ ካለው ጥልቅ ፍቅር ይመነጫል! አምላኩን ያምናል፤ ተፈጥሮን ይጠብቃል፤ የሰው-ልጆችን ይወዳል! ያቅፋል እንጂ አይገፋም፤ ያካትታል እንጂ አያገልም ! የራሱ ያደርጋል……. ያላምዳል እንጂ ማንንም ባእድ/ Alien አያደርግም! ኦሮሞ ለጋስና ቸር ነው! ቸርነቱም ከቸር-አምላኩ የመነጨ ነው፡፡

ኦሮሞ – እጅግ ኃላቀር በነበረው የፊውዳል የድንቁርና ዘመን እንኳን፤ አወቅን ጻፍን ያሉት እኩይ ገዢዎችና ቀላጤዎቻቸው በአፍ ‹‹ፍቅርን›› ሲሰብኩት እሱ ግን በተግባር ‹‹ፍቅርን›› ገልጦታል፡፡ ፍቅርን ቀድሞዉኑ በኑሮው ያውቀዋልና! ኦሮሞ ‹‹ሁሉን ሰብሳቢ›› ነው፤ የሌላ የሚለው የሰው ዘር የለም፡፡ ሁሉንም እንደራሱ ያያል፡፡ ኦሮሞ የትኛውንም ሰው ይቀበላል፡፡ ኦሮሞ ያላሳደገው፤ በፍቅሩ የገዛ ገንዘቡ ያላደረገው በአራቱም አቅጣጫ ቢኬድ አይገኝም ፡፡

ኦሮሞ – ሰፊ ነው፤ ልቡም ዕይታውም ሰፊ ነው! ምስራቅ አፍሪካ ላይ ያልሸፈነው ጂኦግራፊያዊ ክልል /መልክዓ-ምድር አይገኝም፡፡ ያልተጋባው፣ ያልተዋለደው፣ ያልተዋሐደው የዘር-ግንድም የለም፡፡ በሰፊ ፍቅሩ ያልነካውና ያልማረከው የሰው ልጅ ወገን አይገኝም፡፡ ሁሉን እንደራሱ ለመቀበል የማይቸግረው የፍቅር ሀብታም የመንፈስ በረከቶች ሁሉ ባለ-ጸጋ ነው፡፡ ኦሮሞ ትልቅ ነው! ከየትኛውም ፖለቲካዊ ርዕዮተ-አለም የሚበልጥ ሀገር-በቀል ማህበራዊ ስርዓት ባለቤት ነው ፡፡ ‹‹ገዳ፣ ሞጋሳ፣ ጉዲፈቻ፣ ጉማ….›› ለዚህ ህያው ምስክር ናቸው ፡፡

ኦሮሞ ጀግና ነው! ጀግናንም ይወዳል፡፡ የኦሮሞ ጀግና ለፍቅር እንጂ ለሌላ ለምንም አይገዛምም፡፡ በተንኮል ለተነሱበትም በኃያል ክንዱ የስራቸውን ለመስጠት አንዳች አይቸግረው፡፡ ኦሮሞ ፈረሰኛም ነው! ጉግስ ጨዋታም ሁለተኛ ተፈጥሮው! ኦሮሞ – የንስር መንፈስ ያለው ኃያል ስለሆነ ‹‹ከፍታን›› ቤቱ አድርጓል! ዘሩም በምድር ላይ በዝቷል፤ የረገጠው ሁሉም ይለመልምለታል፡፡ ድልንም በአምላኩ ፈቃድ ተቀዳጅቷል፡፡ ከሰው ልጆች ሁሉም ተወዳጅቷል! ኦሮሞ አዋቂ ነው፤ አስተዋይ ነው! ፍትሀዊና ፍርድ-አዋቂ ጭምር ነው፡፡

ኦሮሞ – ሁሉም የሚጠለልበት ‹‹ትልቅ ዋርካ›› ነው! ኦሮሞ ‹‹ግንድ›› ነው፤ ቅርንጫፎቹ በሙሉ የሚያያዙበት! ኦሮሞ፡- የኢትዮጵያ አንድነት ‹‹ጽኑና ሕያው መሰረት›› ነው፡፡
ኦሮሞ – ታላቅ ማዕበል ነው! በፍቅሩና በጀግንነቱ ምድሩን ሁሉ ያጥለቀለቀ !

ኦሮሞ፡- ስለነጻነት፣ ስለእኩልነት፣ ስለማህበራዊ ፍትህ ደሙ እንደጅረት የሚፈሰው ነው!

ኦሮሞ፡- በምድሩ የሰው ልጆች ሁሉ በሰላሙ እና በጥበቃው ጥላ ስር የሚያድሩበት ታዛ ነው! ኦሮሞ ‹‹ቤቱ›› የሁሉም ነው!

ኦሮሞ፡- ‹‹አሸናፊ›› ነው! ስነ-ልቦናውም ቀዳሚ እና የከፍታው ማማ ላይ ርቆ የተሰቀለ ነው፡፡ ቁመናውም ላይ ያለን እንጂ ታች ያለን በትይዩ እንዲያይ አይፈቅድለትም! ኦሮሞ – አበበ ቢቂላ ነው! ኦሮሞ፡- ታደሰ ብሩ፣ ማሞ መዘምር ነው! ኦሮሞ፡- አብዲሳ አጋ፣ ጸጋዬ ገ/መድህን ቀዌሳ ነው! ኦሮሞ – ደራርቱ ቱሉ፣ ዋሚ ቢራቱ፣ ጥሩነሽ ዲባባ፣ ቀነኒሳ በቀለ፣ በቀለ ወያ፣ አብቹ፣ ጥላሁን ገሰሰ፣ አሊ ቢራ፣ ኤቢሳ አዱኛ፣ ይልማ ደሬሳ፣ ራስ መኮንን ጉዲሳ …… ሁሉ ናቸው!

ኦሮሞ – በጀግንነቱ ሁሌም ‹‹ከፍታው›› ላይ እንደሚገኝ የዳልጋ-አንበሳ ነው! ኦሮሞ፡- አባ ዶዮ፣ ጎበና ዳጩ፣ አባ ጅፋር፣ ጆቴ ነው! ኦሮሞ፡- ምንትዋብ፣ ጣይቱ ብጡል ወሌ፣ ‹‹ሚኒሊክ›› እና ‹‹እያሱ›› ብሎም ‹‹ኃይለ-ስላሴ››ም ጭምር ነው! ኦሮሞ – መለኛው ኃይለ-ጊዮርጊስ ዲነግዴ ነው! ኦሮሞ – መንግስቱና ገርማሜ ነዋይ፣ ተፈሪ በንቲ፣ ደምሴ ቡልቶ፣ ካሳዬ ጨመዳም ነው! የእውቀት ፋኖሱ ሰማዕት ‹‹ኃይሌ ፊዳ›› ነው! ተመራማሪና አሰላሳዩ ‹‹ሌንጮ ለታ››ም ነው! የአብሮ መኖር መሐንዲሶቹ ‹‹መረራ ጉዲና›› እና ‹‹በቀለ ገርባም›› ናቸው!

ኦሮሞ – አዛኝና ሩህሩህም ነው! ኦሮሞ የአበበች ጎበና አባት ነው፤ በክፋት የበለጡትን በፍቅር በልጦ የሚኖር የመለኮታዊ ጥበብ ባለቤትም ነው – ኦሮሞ! ስለእውነተኛ ፍቅር እንጂ ስለፍቅር ስብከትና ዲስኩር ስለማይጨነቅም፤ ይኸው ‹‹ጥልቅ አፍቃሪነቱ››፣ ‹‹ሰው ወዳድነቱ››፣ ‹‹ታሪክ ሰሪነቱ››፣ በቃየላውያን ሁሉ ሊደበቅና ሊደፈቅ ተሞክሯል፡፡

የዘመኑ ቃየላውያንና ይሁዳውያንም ስብእናውን ሊገድሉ፣ ቸርነቱንና ደማቅ ታሪኩን ክደው ሊያጠፉ ብሎም ህልውናውን ሊሰርዙ በክፋት ተነሳስተውበታል፡፡ ከመሬቱ ሊነቅሉት፣ ከቀዬው ሊፈነቅሉት፣ አምላኩን ከሚያወድስበት ሊነጥሉት፣ ምድሪቱን አርሶና በወዝ በድካሙ ጥሮ ግሮ የሚያፈራውን ፍሬ እንዳይበላ አመድ አፋሽ ሊያደርጉት የክፋት ጦራቸውን ሰብቀው እየነካኩት ነው፡፡ ስለ‹‹ትልቅነት››፣ ስለ‹‹ትልቅ ሕዝብነት››፣ እና ስለ ‹‹ትልቅ አምላክ›› የማያውቁ ዝቅተኞችና አናሳዎች የትልቅነት ካባውን ለመጎተት አድብተው በዙሪያው ተኮልኩለዋል፡፡

ነገር ግን፡- ‹‹ኦሮሞ›› በገዛ አገሩና ምድሩ ላይ የበይ-ተመልካች ሊያደርጉት ሌት-ተቀን የሚያሴሩበት መጤ-ወራሪዎችን እየመከተ ነው፡፡ ከአብራኩ በወጡና እንደገዛ አካሉ ባሳደጋቸው ከሃዲዎች አማካይነትም የተዘረጋውን ‹‹የእጁ አዙር የቅኝ አገዛዝ መዋቅር›› አውድሞታል፡፡ ለም መሬቱን፣ ላቡን፣ የላቡን ፍሬ፣ ወርቁን፣ ቡናውን፣ ውድ ልጆቹን በዘመናዊ-ባርነት ሊጨመድዱ ያሰቡ እኩያንን በገቡበት ገብቶ እየቀጣ ነው! ኦሮሞ ትዕግስቱ አልቋል፤ ኦሮሞ የቻይነት ጥጉ እጅጉን ተፈትኗል፤ ስለዚህም ኦሮሞ ተቆጥቷል!

እንደበጋ መብረቅ እየተወረወረ የጅቦችን ማንቁርት መያዝ የቀን ተቀን ስራው አድርጎታል! ትናንትናም እንዳሸነፈ ዛሬም ድል በመዳፉ ውስጥ ናት!

ይሄ የተጻፈው ሁሉ ተነግሮለትም ‹‹ኦሮሞ›› ገና ምንም ያልተባለለት ነው!

ኦሮሞ ‹‹ጀግና›› ነው! ለዛውም የፍቅር!

ክብር ለ‹‹ኦሮሞ››ይሁን!

* ይህ ጽሁፍ ለዘ-ሐበሻ የተላከ አይደለም:: በአዲስ አበባ ከሚታተመው አዲስ ገጽ መጽሔት ያገኘነው ነው::

↧

መድረክ፤ ባለፉት 3 ሳምንታት በኦሮምያ 2ሺህ 627 ሰዎች ታስረዋል አለ

$
0
0

  Oposition partyመድረክ፤ ባለፉት 3 ሳምንታት ከአዲስ አበባ ከተማ የተቀናጀ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ በኦሮምያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በተደረጉ ተቃውሞዎች የተሳተፉ 2ሺህ 627 ሰዎች በመንግስት ሃይሎች ታስረዋል ማለቱን ሮይተርስ ትናንት ዘገበ፡፡
የፓርቲው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ፤ መንግስት ተቃዋሚዎችን ያሰረው በቀጣይ ተመሳሳይ ተቃውሞዎች እንዳይደረጉ ለመከላከል በማሰብ ነው ሲሉ መናገራቸውን የጠቆመው ዘገባው፣ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ በኦሮምያ ክልል በሚገኙ 12 የተለያዩ አካባቢዎች 2 ሺህ 627 ሰዎች በመንግስት ቁጥጥር ስር ውለዋል ማለታቸውንም ገልጿል፡፡
የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ከማስተር ፕላኑ ጋር በተያያዘ በኦሮምያ ክልል በተደረጉ ተቃውሞዎች ከ200 ያህል፤ ሰዎች ሳይገደሉ አልቀሩም ማለታቸውንም ዘገባው አስታውሷል። በጉዳዩ ዙሪያ የመንግሥት ኃላፊዎችን ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረት እንዳልተሳካ ሮይተርስ ጠቁሟል፡፡

 ምንጭ – አዲስ አድማስ

↧
↧

የመተማመን  መትነን  (Trust Evaporation) –ገለታው ዘለቀ

$
0
0

trust_actionበመጀመሪያ ደረጃ መተማመን (Trsut) ስንል የአንድ ህብረተሰብ የጋራ ሃብት ወይም የማህበራዊ ካፒታል ዋና ኣካል መሆኑን እናንሳ። በአጠቃላይ ማህበራዊ ካፒታል ስንል ደግሞ ልክ እንደሌሎቹ የሰው ልጆች ካፒታል የሚታይ ነው።  ለምሳሌ የገንዘብ ካፒታል፣ የሰው ካፒታል (Human capital) እንደምንለው ማህበራዊ ካፒታልም ካፒታል ይባላል። ካፒታል ነው እንደንል የሚያስችለን ምክንያት ኣንድም ልክ እንደሌሎቹ ካፒታሎች የሚመረት (Produce የሚደረግ) መሆኑና ለተለያዩ የማህበረሰብ ልማቶች ኢንቨስት የምናደርገው ሃብት በመሆኑ ነው። እነዚህ ተፈጥሮዎቹ ከሌሎች ካፒታሎቻችን ጋር ያመሳስሉታል። የሰው ልጅ የሚያመርተውና ለተለያየ  ልማቱ የሚጠቀምበት ይህ ማህበራዊ ካፒታል ልክ ሌሎች ሃብቶችን ለማምረት አቅደን እንደምንሰራው ተጠንቅቀን ልናሳድገውና  ልንይዘው በኣስፈላጊው ቦታና ጊዜ ሁሉ በኢንቨስትመንት ላይ ልናውለው የሚገባ ትልቅ ሃብት ነው። ኣዳም ስሚዝ የተባለው እውቁ የምጣኔ ሃብት ተጠባቢ በኢኮኖሚ እድገት ውስጥ አንድ የማይታይ እጅ (Invisible hand) አለ እንደሚለው የማህበራዊ ሃብት ዋና ኣካል የሆነው መተማመን በሰው ልጆች እድገት ውስጥ ኣንዱ የማይታይ እጅ መሆኑን መገንዘብ ጠቃሚ ነው። በጠቅላላው  ማህበራዊ ካፒታል ህብረተሰብ የሚያመርተውና ለህይወቱ የሚጠቀምበትም ነው ብለናል። ታዲያ በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ማህበረሰቡ ራሱ የሚፈጥራቸው ሶስት ዓይነት ማህበራዊ ካፒታሎች እንዳሉ የማህበራዊ ካፒታል አጥኒዎች ይነገራሉ። አንደኛው አዎንታዊ ማህበራዊ ካፒታል ሲሆን  ሁለተኛው አሉታዊ ማህበራዊ ካፒታል ይባላል። ሶስተኛ ሊሆን የሚችለው ደግሞ ገለልተኛ ማህበራዊ ካፒታል  (Neutral Social Capital) ሊሆን ይችላል።  አዎንታዊ ማህበራዊ ካፒታል (Positive social capital) የሚባሉት ከህብረተሰቡ ባህል፣ ወግ ልማድ፣ ሃይማኖት አካባቢ የሚመነጩ ለሰው ልጆች ሁለንተናዊ እድገት ኣስተዋጾ ያላቸው ሃብቶች ናቸው። ለምሳሌ ስራን የሚያበረታቱ ስነቃሎች፣ እርስ በርስ መተማመን፣ የፍቅር ሃብት፣ ታማኝነት፣ ምክንያታዊ የሆነ የቁጠባ ባህል፣ የመረዳዳት ባህል ወዘተ የመሳሰሉት ናቸው። በአንጻሩ ኣሉታዊ (negative social capital) የሚባሉት ደግሞ አንድ ህብረተሰብ በግልጽም ይሁን በህቡዕ እየተለማመዳቸው ያሉ ነገር ግን ለሰው ልጆች ሁለንተናዊ እድገት ኣደናቃፊ የሆኑ ናቸው። ለምሳሌ ያህል ብናነሳ አንዳንድ ኣደገኛ ባህሎችን መጥቀስ እንችላለን። ስራን የማያበረታቱ ስነ ቃሎች፣ ሃሜት፣ የጫት ባህል፣ ሌሎች በባህሎቻችን ውስጥ ያሉ እንደ የሴት ልጅ ግርዛት፣ ግግ ማውጣት፣ እንጠል መቁረጥ፣ ሰውነትን በስለት መተልተል፣ ከባህል ጋር ተያይዞ በሴት ልጆች ላይ የሚፈጸሙ በደሎች፣ በህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ባህላዊ ግድፈቶች ወዘተ. ህብረተሰብ የፈጠራቸው ነገር ግን ለህብረተሰብ እድገትና ምርታማነት ኢንቨስት ሊደረጉ የማይችሉ እንዴውም ጎታችና ኣደናቃፊ ናቸውና ኣሉታዊ ማህበራዊ ካፒታል ሊባሉ ይችላሉ። አፍሪካ ውስጥ ተቆጥሮ የማያልቅ ኣሉታዊ ካፒታል ያለ ሲሆን ይህንን ለመቀነስ ትልቅ ዘመቻ ያስፈልጋል። ኣለበለዚያ የሰባዊ እድገትን ከፍ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ቶሎ ግቡን ኣይመታም። ሌላው ካፒታል ገለልተኛ የሚባለው ሲሆን ይሄ በሰው ልጆች ሁሉንተናዊ እድገት ላይ የጎላ ኣሉታዊ ተጽእኖ የሌለው ሊሆን ይችላል። እንዲህ ኣይነቶቹን ለጊዜው ችላ ብሎ ኣሉታዊ ካፒታሎችን የመቀነስ ኣዎንታዊ ካፒታሎችን የማሳደግ ስራ ያስፈልጋል።

 

 

ለመግቢያ ስለ ማህበራዊ ካፒታል ይችን ያክል ዳራ ከሰጠን ከማህበራዊ ካፒታል ውስጥ ኣንዱ ዋና ነገር መተማመን ነው። በዚህ ዙሪያ ጥቂት ውይይት እናድርግ። መነሻችንም ይሄው ነውና። ማህበራዊ ካፒታል ስንል፣ መተማመንን፣ የህብረተሰብ ኔትወርክን (Networks)፣ ለጋራ ጥቅም በጋራ ለመስራት መስማማት፣ መደጋገፍ(Reciprocity) ፣ ልማዶች (norms) የሚመለከት ሲሆን ከነዚህ ውስጥ መተማመንን (Trust) ብቻ መዝዘን የኢትዮጵያን ወቅታዊ  ሁኔታ ብንገመግም ጥሩ መስሎኛል።

 

በኢትዮጵያ ሁኔታ የመተማመን ሃብታችንን በሶስት ኣገራዊ የመተማመን የፍስሰት ኣቅጣጫዎች መገምገም እንችላለን። እነዘህ ሶስት የመተማመን መፍሰሻዎች

 

  1. የግለሰብ መተማመን (Interpersonal trust)
  2. ቀጥታ መተማመን (Vertical trust)
  3. የጎኖሽ የቡድን መተማመን(Cross cultural interpersonal trust)

ናቸው።

 

በነዚህ ዙሪያ የኣገራችንን የመተማመን ሃብት ወቅታዊ ይዞታ ለመገምገም ኣንዳንድ ጥናቶችን ለኣብነት ማየት መልካም ነው። የግለሰብ መተማመን ደረጃን በኢትዮጵያ ሁኔታ ስናይ  በዚህ ሃብት ኢትዮጵያ ብዙ የቀደመቻቸው ኣገሮች ኣሉ። ለምሳሌ ያህል ታዋቂው የምጣኔ ሃብት ተጠባቢ ማክስ ሮዘር ባጠናው ጥናት መሰረት የኢትዮጵያ የዜጎች  መተማመን  (interpersonal trust) ከብዙ ኣገሮች ሲነጻጸር መሃል ላይ ነው። በዚህ የመተማመን ሃብት ውድድር ኢትዮጵያ ከቀደመቻቸው ኣገሮች መካከል ፈረንሳይ፣ቡልጋሪያ፣ማሌዢያ፣ኢራን፣ሞሮኮ፣ሰርቢያ፣ማሊ፣ጆርጂያ፣ስፔንና ቱርክም ይገኙበታል።በዚህ ጥናት መሰረት ኖርወይ፣ ስዊድን፣ ፊንላንድ ከአንድ እስከ ሶስት ደረጃን የያዙና የመተማመን ሃብታቸው ሙላት ያልጎደለባቸው ሲሆን አጠቃላይ ናሙና ተወስዶባቸው ከተጠኑት ሃምሳ ስድስት ኣገራት መካከል ኢትዮጵያ ሃያ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ናት። መተማመን ከህብረተሰቡ መሃል የተነነባቸው የተባሉትና መጨረሻ ላይ የተቀመጡት ኣገራት ቱርክ፣ሩዋንዳና ትርኒዳድ እና ቶቤጎ የተሰኘችው የደቡብ ኣሜሪካ ደሴት ናቸው። ኢትዮጵያ በኣንጻራዊነት መሃል ላይ የሚገኝ ውጤት ያላት ሆኖ እናያለን። በርግጥ በግል የምንታዘበውም ይህንን ነው የሚመስለው። ይህንን ካየን በሁዋላ የቀጥታ መታመን (vertical trust) ደረጃችንስ የት ነው? የሚለውን ለመገምገም ዝንባሌ ሊያድርብን እንደሚችል እሙን ነው።ቀጥታ መታመን ስንል ህዝብ በመንግስት ተቋማት ላይ ያለውን እምነት የምንለካበት የመታመን ኣቅጣጫ ነው። ቀጥታ የሆነው የመተማመን ወይም የመደገፍ ካፒታላችን የሚገለጽባቸው አንዳንድ ኣንጻራዊ ጥናቶችን ማየት ጥሩ ነው። ከነዚህ ጥናቶች ውስጥ የትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናልን ኣመታዊ ጥናቶች ማየት ለግንዛቤ ይረዳናል። እንደ ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል (Transparency International ) ጥናት ኢትዮጵያውያን በፖለቲካ ስልጣን ኣካባቢና በህዝብ ተቋማት ኣካባቢ ያላቸውን ዝንባሌ ስናይ መታመን ተንኖ እናያለን። ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ባጠናው መሰረት ቀደም ብለን ያየናቸውና ኢትዮጵያ በእርስ በርስ መተማመን (Interpersonal trust) የቀደመቻቸው ኣገራት ሁሉ በዚህ በቀጥታ መተማመን ደግሞ እንደገና በከፍተኛ ደረጃ ቀድመዋት ይታያል። ኢትዮጵያ ውስጥ 33 በመቶ የሚሆን ህዝብ ብቻ በመንግስት ተቋማት ላይ እምነቱን ሲገልጽ ስልሳ ሰባት በመቶ የሚሆነው ህዝቧ በመንግስት ተቋማት ላይ ኣይታመንም ወይም ኣይደገፍባቸውም። በኣጠቃላይ ስናይ እንደ ሃገር መታመን በመንግስትና በህዝብ መካከል የለም ወይም ተንኖ ሄዷል ማለት ነው። ከፍ ሲል እንደጠቀስነው ለምሳሌ ፈረንሳይን ብናይ፣ ስፔንን ብናይ ተቋሞቻቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ይደገፋሉ። ፈረንሳይ ውስጥ ሰባ በመቶ የሚሆነው ህዝብ ተቋሙን መንግስቱን ያምናል። በአንጻሩ ኢትዮጵያ ደግሞ የተገላቢጦሽ ነው የሚታየው። ሌሎች ጥናቶችን ብናገላብጥ ለምሳሌ ያህል የዓለም የብልጽግና ደረጃ መለኪያ (Legatum prosperity Index) የሚያወጣውን ጥናት ብናይ ኢትዮጵያዉያን በፍትህ ላይ በጣም ዝቅተኛ መታመን (Very low confidence) ነው ያላቸው ይላል። በአንድ ሃገር ውስጥ በተለይም ዋና ዋና በተባሉት ተቋማት ላይ ማለትም፣ በፍርድ ቤት፣ በሲቪል ሰርቪስ፣ በፖሊስ፣ በወታደሩ፣ሚዲያው ላይ እምነቱ ከተነነ ያ ሀገር በኢኮኖሚም ሆነ በሰባዊ ልማት ወደፊት መራመድ ኣይችልም። ይህንን ዝቅተኛ ማህበራዊ ካፒታል ይዞ በጥንድ እያደግን ነው ማለት ኣይቻልም።

 

 

የመታመን መትነን በመንግስትና በህዝብ መካከል ሲከሰት ተቃውሞዎች ይበዛሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ በዚህ መንግስት ጊዜ በስፋት የሚታየው ተቃውሞም   በመንግስት ላይ ከፍተኛ እምነትን ከማጣት የመጣ ነው። ባለፈው ጊዜ እንደተወያየነው አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ አሁን ስልጣን ላይ ያለውን መንግስት ያለማልኛል ብሎ ሳይሆን በተቃራኒው ኣጥፊ ነው ብሎ ካመነ ያ ስርዓት ባስቸኳይ መለወጥ ኣለበት። የተነነን መታመን በቀላሉ ማዝነብ ኣይቻልም። የግድ ለውጦች መምጣት ይጠበቅባቸዋል።  አንዳንዴ ከህዝቡ መሃል ስለሚዲያ የሚነገር ነገር ኣለ። ሚዲያውን ያለማመን፣ ለመንግስት ብቻ መሳሪያ መሆኑን ማመን፣ በመንግስትና በህዝብ መካከል መተማመንን ያተነነ ኣንዱ ጉዳይ ነው። የመንግስት በፍርድ ሂደት ውስጥ ጣልቃ መግባት በከፍተኛ ሁኔታ መተማመንን የሚያተን ተግባር ነው። በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞ በሚያሰሙ ዜጎች ላይ መትረየስና ከባድ መሳሪያ የታጠቀ ወታደር ማሰማራት በመንግስትና በህዝብ መካከል መታመንን እያተነነ ኣምባገነናዊ ከባቢን የሚፈጥር ነገር ነው። የሲቪል ሰርቪሱ ሴክተር እድገት የሚሰጠው፣ የሚቀጥረው በፖለቲካ ታማኝነት መሆኑን ህዝብ ሲደርስበት መተማመን ይተናል። እንዲህ መተማመን የተነነበት ኣገር በአምስት ኣመት ትራንስፎርሜሽን እቅድ እናሻሽለዋለን ማለት ሌላ የቀረች ጥቂት እምነት ካለች እሷኑ ጨርሶ ለማትነን ነው። ቀጥታ መታመንን ከሚያሳዮ ሌሎች አንጻራዊ ጥናቶች ስናይ ለምሳሌ ፍሪደም ሃውስ የሚያወጣቸውን ጥናቶች በየጊዜው ስናይ ኢትዮጵያ ነጻ ያልሆነች ኣገር ናት። መንግስትና ህዝብ የሚደባበቁባት፣ የሚጠራጠሩባት ኣገር ናት። ይህ ኣይነት መንግስት በተለይ ብዙ ብሄሮች ያሉበትን ኣገር ሲመራ ኣደጋው ዘርፈ ብዙ ነው። ግጭቶች እንደ ጭስ ቀዳዳ እየፈለጉ ሲወጡ ኣንዳንዴ በብሄር በኩል እየፈነዱ ብሄራዊ ማንነትን እየሸረሸረ ይመጣል። የዚህን የቀጥታ መታመን ሃብታችንን ስናጤን በህዝብና መንግስት መሃል እንዲህ መታመን ተንኖ እንዴት ነው የምንኖረው? የሚል ኣስገራሚ ነገር ይነሳል። በርግጥ ያው ኣንድ ኣምባገነን ስርዓት በሃይል ያስተዳድራል። ነገር ግን ከዓመታቶች በፊት ኣዲስ ኣበባ ውስጥ ብዙ ሰው ይለው የነበረው ነገር ትዝ ኣለኝ። እኛ መንግስት የለንም ይል ነበር ህዝቡ። የምንኖረው በቤተሰብ ህግና በባህላዊ ተቋማት ነው ይሉ ነበር። መንግስት ስወለድም ስሞትም ኣያውቀኝም፣ ግብር ለመሰብሰብ ብቻ ብቅ ይላል የሚሉ ወገኖች ብዙ ናቸው።እነዚህ ወገኖች የውነትም በባህላዊ ተቋሞቻቸውና በቤተሰብ ህጎች ነው ብዙውን ህይወታቸውን የሚገፉት እንጂ ከመንግስት ጋር ያላቸው መስተጋብር እጅግ ቀጭን ነው።የማህበራዊ ዋስተና ቁጥር እንኳን የለንም።

 

በርግጥም ለአንድ ሃገር የዜጎች የእርስ በርስ መታመን መኖር ሃገርን ለመጠበቅ ይጠቅማል። ትልቁ ሃብትም ይህ ነውና መጠበቅ ኣለብን። መንግስት ዘላቂ ኣይደለም። መንግስት ሲቀየር ያ የተነነው መታመናችን ይመለሳል፣ ይዘንባል። ነገር ግን በዜጎች መካከል መታመን ሲጠፋ እሱ የበለጠ ኣደገኛ ነው። በቀላሉ ኣናመርተውም እንደ ሌሎች የፋብሪካ ምርቶቻችን በቀላሉ   የምናመርተው ካፒታል ኣይደለምና።መታመናችንን ለማደስ ብዙ ጊዜ ይፈጅብናልና።

 

 

ወደ ሶስተኛው የመታመን ኣቅጣጫ እናምራ። በእኛ ሃገር ሁኔታ የመታመን ካፒታላችን በብሄር ዘለል ደረጃም መጠናት ኣለበት። ኣንድ የብሄር ኣባል ከሌላው ጋር ሲገናኝ በምን ያህል የመተማመን ደረጃ ይኖራል የሚለውን ማጥናት በጣም ኣስፈላጊ ነው። ይህን እንድናደርግ የሚያስገድደን ኣገሪቱ ኣሁን ያለችበትን የብሄር ፌደራሊዝም ከግምት በማስገባት ነው። የብሄር ፖለቲካ በሰለጠነበት ኣገር ተዋረዳዊ የመታመንን ካፒታል ደረጃ ማጥናትና ደረጃውን እያዩ በተለያዩ ዘዴዎች ይህን ካፒታል ለማሳደግ መሞከር ለሃገር ኣንድነትና ለብሄራዊ ማንነት ለምንለው ጉዳይ ጉልህ ሚና ኣለው። ኣንድ የትግራይ ተወላጅና ኣንድ የኦሮሞ ተወላጅ በአንድ ዮኒቨርሲቲ ውስጥ በኣንድ ዶርሚተሪ ውስጥ ሲኖሩ በምን ያህል የመተማመን ደረጃ ይኖራሉ? የሚለውን ማጥናት ጠቃሚ ነው። ይህን በተመለከተ በኣሃዝ የተጠና ጥናት ማግኘት ኣልቻልኩም። ይሁን እንጂ በአንዳንዶች ዘንድ የሚታየው ጽንፈኝነትና ወገንተኝነት ይህንን ሃብታችንን እንዳያተንብንና ልብ ከልብ እንዳያራርቀን ዜጎች ሃላፊነት ወስደው ሊያስብቡት ይገባል። ባህላዊ ቡድኖች ወይም ብሄሮች በባህል ልዩነቶቻቸውና በቋንቋ ልዩነቶቻቸው መቼም ኣይጋጩም። እንደዚህ የተጋጩ ቡድኖች ኣይኖሩም። የአኙዋክ ብሄርና የኑየር ብሄር ኣባላት ወይም የጉጂና የቡርጂ ብሄረሰብ ኣባላት ያንተ ምግብ ኣይጣፍጥም የኔ ይጣፍጣል፣ ያንተ ኣለባበስ ኣያምርም የእኔ ያምራል፣ ያንተ ዳንስ ኣያምርም የእኔ ያምራል፣ ያንተ ቋንቋ ኣይገልጽም የእኔ ይገልጻል በሚል ጦርነት ኣይገቡም። የባህልና የቋንቋ ልዩነት በቡድኖች መካከል ያለን መታመን ኣያተነውም። ብዙ ጊዜ ቡድኖች ግጭት ውስጥ የሚገቡት ይህ ባህላዊ ስብእናቸው  የፖለቲካ ጥብቆ ሲለብስ ነው። ፖለቲካው የሚፈጥረው የቡድነኝነት ስሜት ልዩነትን እያራገበ ሲሄድ በኣስተዳደር ጉዳይ በተፈጥሮ ሃብት ጉዳይ ግጭት ውስጥ ይገባሉ። ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት ዘመናዊ ፖለቲካ የምታራምድ ሳይሆን ባህላዊ ፖለቲከኛ በመሆኗ ለቡድኖች ግጭት የተጋለጠች ከመሆኗም በላይ በቡድኖች መካከል የሚኖርን መታመን የሚያተን ከፍተኛ የፖለቲካ ሙቀት ስላለ ዜጎች ይህንን እንደተለመደው በሆነ ቴክኒክ መዋጋት ኣለባቸው።

 

እንደው ለአንባቢዎች ትንሽ ግንዛቤ ለመስጠት ያህል መታመን በተለያዩ ማህበራዊ ኣውዶች ውስጥ ሲታይ በሶስት ሊከፈል እንደሚችል ባለፈው ጊዜ ስለማህበራዊ ካፒታል ሳጠና ተረድቻለሁ። እነዚህ ሶስት የመተማመን ኣይነቶች የሚከተሉት ናቸው። ኣንደኛው የመታመን ኣይነት ህሊናዊ (Conscience Trust) ይባላል ። በዚህ ጎራ የሚመደቡ ሰዎች የእምነታቸው መሰረት ህሊና ነው። በቡድናቸው ውስጥ ልእልና እንዲያገኝ የሚፈልጉት ህሊናን ነው። የቡድኑ ኣባላት ለህሊና ከሰሩ ጤናማ የሆነ ግንኙነት ይኖራል ቡድኑም ትርፋማ ይሆናል ሩቅ ይሄዳል ብለው ያምናሉ። እነዚህ ወገኖች ህሊና ዋና የስጋት ኣሰውጋጅ (risk taker) ኣድርገው የሚያዩ ናቸው። በቡድናቸው መሃል ይሄን ያህል የጠነከረ ሲስተም ላይኖር ይችላል። ግን በፋይናንስ ጉዳይም ይሁን በሌሎች ጉዳዮች ህሊናን እያበረታቱ የቡድናቸውን ህይወት በጤና ሊመሩ ይሻሉ። ሁለተኛው ኣይነት ደግሞ ሃይማኖታዊ መታመን ይባላል። የዚህ ኣይነት የቡድን ኣባላት ደግሞ የመታመናቸው መሰረቱ  የሚጣለው በቅዱሳት መጽሃፋቸው ትእዛዝ ላይ ነው። ኣምላካቸው ዋና ስጋት ኣሰወጋጅ(risk taker) ተደርጎ የሚወሰድበትን ሁኔታ ያበረታታሉ። እነዚህ ወገኖች በኦዲት፣ በተጠያቂነት፣ በኣስተዳደራዊ ተሳትፎ ፈጣን ኣይደሉም። ይሁን እንጂ የተሻለ ጤናማ የመታመን ሃብት በጃቸው ይታያል። ሶስተኛው የመታመን ኣይነት ደግሞ ሲስተሚክ (Systemic trust) ይባላል። እንዲህ ኣይነት ሰዎች ስለ መታመን፣ ስለ ሞራል ጉዳይ ሲሰበክ ቢውልና ቢያድር ኣይገባቸውም። ለነሱ መታመን የሚሰራው በጠንካራ ሲስተም ላይ ሲመሰረት ነው። ቡድኖች ሲሰባሰቡ የጠራ የስራ ክፍፍል፣ መተዳደሪያ ደንብ፣ ኦዲት፣ ከፍ ያለ የኣባላት ተሳትፎ፣ ተጠያቂነት በጣም ይሻሉ። የእምነታቸው መሰረት የሚጣለው በነዚህ ጉዳዮች ጥራት ልክ ነው። እንተማመን እያሉ ቢሰብኳቸው ምንም ኣይዋጥላቸውም። ዋና ሪስክ ወሳጅ (risk taker) የሚሰራ ሲስተም በመሆኑ መሃል ላይ የሚፈልጉት ነገር ይህንን ነው። ይህንን ክፍፍል ይዘን ወደ ከፍተኛው የሰው ልጆች ስብስብ ወይም ኣገር ስንመጣ ደግሞ ህዝብ በአያሌው ሲስተሚክ ሆኖ እናያለን።ይህ ማለት ህሊናዊ መታመንን ሙሉ በሙሉ ይጥላል ማለት ኣይደለም። ነገር ግን በጅጉ ህይወት ያለውን ሲስተም የሚደገፍ ሆኖ እናያለን።  በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ በዘውዳዊ ኣገዛዞች ዘመን በንጉሱና በህዝቡ መካከል የሚኖረው የመታመን ድልድይ በኣብዛኛው ሃይማኖታዊ ነበር። ከኣምላክ የተሰጠ በመሆኑ ህዝቡ ስለተሰበሰበው ታክስ ኣይጠይቅም።ልምረጥ አይልም። ዝም ብሎ ኣምኖ ይኖር ነበር። ዘመናዊነት ሲመጣ የሰው ልጅ በእውቀቱ ሲያድግ ደግሞ ወደ ሲስተም ትረስት ነው የመጣውና ያዘነበለው። በመንግስትና በህዝብ መካከል የሚኖረው ግንኙነት በግልጽነት፣ በኦዲት፣ በተጠያቂነት፣ በምርጫ፣ በፈቃድ ላይ የተመሰረት እንዲሆን ህዝብ ይፈልጋል። ዴሞክራሲም ይህንን ወቅታዊ የሰው ልጆች ፍላጎት ለማሟላት የቆመ ካህን ነው። ዲክተተርስ የሚባሉት የዴሞክራሲን ልብስ ለብሰው ግን ደግሞ እንደ ንጉስ የሚኖሩት ዘመኑ የሲስተም ትረስት ዘመን ስለሆነ በዴሞክራሲ ስም ለመነገድ ነው። ይሁን እንጂ ህዝብ ደግሞ እውነተኛውን እምነቱን የሚጥለው የጸዳ ሲስተም ሲፈጠርና

 

የተፈጠረው ሲስተም ግልጽነት፣ተጠያቂነትን፣ የህግ የበላይነትን ማንሸራሸር ሲችል ብቻ ነው።

 

 

በዚህ ዘመን መንግስታት ህዝቡን ዝም ብላችሁ እመኑኝ ማለት ኣይችሉም። የህዝብ ሉዓላዊነትን መቀበል ኣለባቸው። በመሃል የተሻለ ሲስተም ማምጣት ኣለባቸው። ህዝብ በመንግስት በኩል ሚስጥረኝነት መኖሩ ሲሸተው፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት ሲጠፋ፣ የህግ የበላይነት ሲጠፋ፣ መንግስት ራሱ የማይጠየቅ ሲሆን ቀጥሎ የሚመጣው ነገር የመታመን መትነን አይደለም? መታመን ከህዝብና ከመንግስት መሃል ብድግ ብሎ ይተናል። ስለዚህ ነው መንግስታት ኣስር ጊዜ ስለግልጽነትና ተጠያቂነት ሲጥሩ የሚታዩት። የኢትዮጵያን ሁኔታ ስናይ ኣንዱ ለቀጥታ መታመን መትነን ምክንያት የሆነው ይሄው ነው። ግልጽነት፣ ተጠያቂነት፣ የህግ የበላይነት ስለሌሉ እነሆ ዛሬ መታመን ተንኖ ኣልቆብናል።በአጠቃላይ በአሁኑ ሰዓት በሃገራችን ያለው በመንግስትና በህዝብ መካከል ያለው መታመን በቀላሉ ሊመለስ የማይችል በመሆኑ ኣገሪቱ ቶሎ ብላ ወደ ለውጥ መሄድ ኣለባት። ወደ ሽግግር መግባትና የህዝብን እምነት የያዘ ሌላ መንግስት ማቆም ያስፈልጋል።

 

 

መተማመን ሁለት ዓይነት ትርጉም ሊኖረው ሲችል ኣንዱ ከግብረገብ (Moral) ኣንጻር ያለው መተማመን ነው። በአብዛኛው በስብከት ልንገነባው የሚገባ የሞራል እሴት ሊሆን ይችላል። በሌላ በኩል ያለው ግን ሳይንሳዊና በሚገባ ሊለካ የሚችል ነው። በዚህ ኣቅጣጫ መተማመን ሁለት ዋና ዋና ተለዋዋጮች(variables) ኣሉት። እነዚህም ዋስትና እና ስጋት ይባላሉ። በእንግሊዘኛው gurantees and risks  ማለት ነው። መታመን የነዚህ የሁለት ተለዋዋጮች ስሪት ነው። በአጭር ቃል መታመንን መገንባት ማለት ዋስታናን ማስፋትና ስጋትን መቀነስ ማለት ነው። መንግስት ዋስትናዎችን እያሰፋ ሲሄድ ስጋቶችን እየቀነሰ ሲሄድ ነው ህዝብ የሚደገፈው። በማንግስትና በህዝብ መካከል የሚኖረው የመተማመን ልክ የሚለካውም መንግስት ባሰፋው ዋትና ልክ ነው ማለት ነው። በዚህ ጊዜ ዜጎች መንግስታቸውን ይደገፋሉ። ይህ ካልሆነና ስጋቶች እየጨመሩ ሲሄዱ በመንግስታቸው ላይ ያለው መደገፍ ይቆምና ቶሎ ለውጥ ይፈልጉና ያምጻሉ። መንግስት በስልጣን ለመቆየት የሚለው ነገር እመኑኝ መልካም ኣስተዳደርን ተወያይተን እናመጣለን፣ ትንሽ ጊዜ ስጡን ነው። ይሄ ደግሞ ለህዝቡ ዋስትና አይሆንም። ሩብ ምእተ ዓመት ሙሉ ስልጣን ላይ ሆኖ በጥንድ ቁጥር ኣደግን እያለ ሲል የነበረ መንግስት አሁን በገጠሩ ከአስር ሚሊዮን በላይ በከተማውም እንደዚሁ ወደ ኣስር ሚሊዮን ህዝብ ለረሃብ ተጋልጧል። ይህ ኣንዱ የመንግስትን እምነት ያተነነ ክስተት ነው። ትናንትና መቶ ፐርሰንት ኣሸነፍን ያለ መንግስት ስድስት ወር ሳይሞላው ብዙ ቁጥር ያለው የኦሮሞ ህዝብ ሜዳ ላይ ወጣ። በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ተቃውሞ ነው። መንግስት ይህንን ሲያይ መሸነፍ ኣይወድምና የኔ የስራ ውጤት ነው ጠያቂ ማህበረሰብ ኣፈራሁ ይላል። በኣስራ ዘጠኝ ስልሳዎቹ የተነሳው ህዝባዊ ንቅናቄ ሃይለስላሴ ያፈሩት ጠያቂ ማህበረሰብ ነበር ማለት ነው? እሳቸው ይህን ሳያውቁ ነው ያለፉት። በደል የበዛበት ህዝብ ኣንድ ቀን በቁጣ ገንፍሎ መውጣቱ ተፈጥሯዊ ነው። የሆነ ነገር ሰርቶ ማሳየት ያልቻለ መንግስት ይህንን  የኔ የስራ ውጤት ነው ማለቱ ይገርማል። ህዝቡ ሰልፍ የወጣው እኔ በፈጠርኩት ዴሞክራሲ ነው ሊል ኣይችልም። እንዲያማ ቢሆን መንግስት ተቃውሞውን ባዳመጠ። በሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ ጥይት ባላፈሰሰ።

 

ኣሁን ደግሞ የተያዘው ፈሊጥ የመልካም ኣስተዳደር ችግር ነው የሚል ነገር ነው:: እውነት ነው የመልካም ኣስተዳደር ችግር ነው። የመልካም ኣስተዳደር እጦት ቀለል ያለ ችግር ነው ማለት ነው? መንግስት የሚባለው ነገር መልካም ኣስተዳደርን ካላመጣ ምን ይሰራል። መለወጥ ነው ያለበት። ስርዓቱ ራሱ በሙስና መረብ የቆመ በመሆኑ በምንም ኣይነት ሪፎርሜሽን ኣይለውጠውም። የኢትዮጵያ ህዝብም ከእንግዲህ በዚህ ገዢ መንግስት ላይ ያለችው እምነት ያለ ልክ ቀጥናለችና ለሃገር ኣሳቢ ወገኖች ሁሉ የሽግግር ጊዜ የሚፈጠርበትን ሁኔታ መምከር ይኖርባቸዋል።በህዝብና በመንግስት መካከል እምነት ከተነነ በሁዋላ የሚጠበቅ ነገር አይኖርም። ለውጥ የግድ ሊመጣ ይገባዋል።እግዚኣብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ።

 

 

ገለታው ዘለቀ

 

 

geletawzeleke@gmail.com

↧

በጅጅጋው የጎርፍ አደጋ 50 ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም –አስከሬን ፍለጋው ቀጥሏል

$
0
0

የመንግስት ሚድያዎች በጅጅጋው የጎርፍ አደጋ እያሾፉ ነው? ትናንት 23 ሞቱ አሉን ዛሬ ደግሞ 13

Gijiga jijiga 3 Jijiga

በአብዲ አሊ

የትላንቱን የጅጅጋ የጎርፍ አደጋ ተከትሎ በመንግስት ሚድያ እየቀረበ ያለው ሪፓርት ስለሁለት የተለያየ ሃገር እስኪመስለን ድረስ እርስ በርሱ እየተጋጨ ሳንፈልግ ያስቀን ሁሉ ጀምሯል::

ምሽት ላይ ቴሌቭዥኑ 23 ያደረሳቸውን የሟቾች ቁጥር፤ ንጋት ላይ ሬድዮኑ አስሩን የት አድርጓቸው እንደሆነ ባልታወቀ ሁኔታ “የሞተው ሰው ብዛት 13 ብቻ ነው” ይለናል:: አያፍሩም እኮ እነሱ ይሄኔ “መንግስ ባደረገው ከፍተኛ ርብርብ ከሞት አስመልሰናቸው ነው” ሊሉን ይሆናል:: አለ ደሞ ESTV የሚሉት የክልሉ ቴሌቭዥን ጣቢያ ነኝ ባይ፤ ያ ሁሉ ሰው በአንድ ቀን በሞተበት በዚያ አሳዛኝ ዕለት ቀኑን ሙሉ የዳንቶ ጭፈራ ሲያሳይ የዋለው::

“ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ” የሆነው ሜትሮሎጂያችንም በበኩሉ “በቀጣዩቹ ቀናትም ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ዝናብ ሊጥል ይችላል” የሚል ትንበያ አይሉት አሙቁልኝ እየሰጠ ነውና ለማንኛውም ጥንቃቄ ማድረጉ አይከፋም:: በተረፈ እነሱ ምንም ይበሉ ምን እኛ ግን እስካሁን
የደረሱበት ያልታወቀ ከ50 በላይ ወገኖቻችንን አስከሬን በማፈላለጉ ሂደት ሁላችንም የበኩላችንን ጥረት በማድረግ ርብርቡ ላይ መበርታት ነው የሚበጀን::

↧

በአምቦ ምንም ባላጠፋው ወንጀል ተደብድቦ ለአልጋ ቁረኛ የነበረው ወጣት ሕይወቱ አለፈ

$
0
0

rip

ከየኔሰው ገብሬ

በፍቶው ላይ የምትመለከቱት ለግላጋ ወጣት ተክለ ቶማ ይባላል። የአምቦ ዩኒቨርሲቲ የሶሽኦሎጅ ድፓርትመት 2ኛ ኣመት ተማሪ ነበር ። ህዳር ወር መጨረሻ አካባቢ በኣምቦ ዩኒቨርሲቲ በተነሳው የተማሪዎች ተቃውሞ ተያይዞ ምንም ባላጠፋበት ኣፍነው ከያዙ በኋላ የአጋዚ ወታደሮች ተራ በተራ እየተፈራረቁ ከፍተኛ ድብደባ አድርሰውበት ላለፉት 4 ወራት የኣልጋ ቁረኛ ሆኖ ከቆየ በኋላ መጋቢት 24 ህይወቱ ማለፍ ችሏል ።

ደማችን እንድ እስከሆነ ድረስ ሰብአዊ ፍጡር ሁሉ ይህንን አረመኔያዊ ድርጊት በጋራ ማውገዝ አለበት ። የልጁ ቤተሰቦች ምንም አይነት መረጃ እንዳይሰጡ ከሞትና ከህይወት አንድ አንድመርጡ የሚል ማስጠንቀቂያ ስለተሰጣችሁ ዝም ብለዋል ። ገዳዩች ለፍርድ እንዲቀርቡ ። ምስኪን ቤተሰቦቹ ተገቢ ካሳ እንዲከፈላቸው በጋር እንጩህ።

 

ፍትህ ለወጣት ተክለ ቶማ ቤተሰቦች ።

የወጣቱ ትውልድ ቦታ ዳውሮ ሎማ ወረዳ ደቡባዊ የኢትዮጵያ ክ/ሃገር ነው። ደማችን አንድ ነው ።

 

ዋይታ በጋራ እናሰማ!

↧

የትግራይ ነጻ አዉጪ ቡድን መከላከያ አባላት እየከዱ ነዉ

$
0
0

ከልዑል ዓለሜ
በምእራብና ደቡብ ምስራቅ እዝ ዉስጥ ባልደረባ የነበረዉና በሶማሌያ እንዲሁም በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል እየተዘዋወረ ለረጅም አመታት ያገለገለ በሐገር መከላከያ ሚኒስቴር ስልጠና ዋና መምሪያ የሜጀር ጄኔራል ኋየሎም አራአያ ወታደራዊ አካዳሚ ዉስጥ የስድስት ወር ብቻ የለብለብ የመኮንነት ስልጠና አጠናቆ የተመረቀዉ ም/መቶ አለቃ መላኩ አበበ ነጋሽ የህወሃትን ሰራዊት ተነጥሎ የሸሸ ሲሆን ብዛት ያላቸዉ የሰራዊቱ አባላት ህወሃትን የማገልገል ፍላጎት እንደሌላቸዉና አጋጣሚዎችን እየተጠባበቁ እነደሆነ ለመረዳት ችለናል።

hayelom
በአንኳርነት የትግራይ ነጻ አዉጪ ቡድን አካዳሚዎች አንድ መኮንን አሰልጥኖ ለመመረቅ የሚወስዱትን እጅግ አጭር ወቅት ከመመልከት አንጻር ምን ያህል የወያኔ መኮንኖች በብቃት እንደሚያገለግሉ እና ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናቱ በምን ያህል ግዜ የጄኔራልነት ቆቡን እንደሚጭኑት ለመገመት አመላካች መረጃ ሆኖ ከማግኘታችን በላይ የሰራዊቱን መማረርና መንቃት ለመረዳት ችለናል።


በመሆኑም በሐገር መከላከያ ሰራዊት ስም የህወሃት ጥቅም አስጠባቂ አንሆንም! ያሉ በርካታ የመከላከያ ሹሞች መብቱን በሚጠይቀዉ ጭቁኑ ህዝባችን ላይ አፈ ሙዝ አንመዝም ሲሉ በመነጠል ላይ ሲሆኑ።


በተጨማሪ የአንድ ዘር የበላይነት የነገሰበት የሐገር መከላከያ አባል መሆን አያሻንም! የወያኔ ባለስልጣናትን ኪስ ለማደለብ በሶማሌያ በከንቱ አንታረድም! ከሐገራችን ምድረ እርስት ላይ ተቆርሶ ለሱዳን መሬታችን ሲሰጥ ዝም ብለን አንመለከትም! ዝርፊያና ግፍ የነገሰበት ስርአት ጥቅም አስጠባቂ አንሆንም! በማለት ሰራዊቱ እየፈራረሰ መሆኑን እማጮች ሲሆን።
በተለይም ሌላዉን የመጨፍለቅ እራይ ያለዉን የወያኔን ወታደራዊ ስልት ከመዋጋት

አንጻር ሁሉም የመከላከያ አባልት የሚቻላቸዉን እርምጃ እንዲወስዱ እያሳሰብን !!!!!!!
በስብሶ በመደርመስ ላይ ከሚገኘዉ የትግራይ ነጻ አዉጪ ቡድን የግፍ ቤት ፍርስራሽ ሌሎች አባላት እራሳቸዉን እንዲያድኑ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።


ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !

↧
↧

ፖለቲካኛ ነኝ! (ዳዊት ዘሚካኤል)

$
0
0

ፍርሃት ስጋ ለብሶ፤
ፍቅርን ደርምሶ፤
ህሊናን አፍርሶ፤
ስስትን አንግሶ።
አንደኛው በቁንጣን፥ ሢተፋ እያደረ፤
ሌላኛው በረሃብ፥ እየተሣከረ፤
አንደኛው “የት ልብላ?”፥ ለምርጫ ሲጨነቅ፤
ሌላኛው “ምን ልብላ?” ፥ በማጣት ሲሳቀቅ፤
ሃገር ‘ወፍጮ’ ሆና መንፈሱን ብታደቅ፤
”ቤቴን አተርፍ” ባይ በስደት ሲማቅቅ፤
ባህር እየገባ ወጣት ሲተላለቅ፤
በነዲድ በረሃ፤
የሃገሬ ደሃ፤
አንገት ሲሞሸለቅ፤
ደልቶት ባለ ግዜ፥ በዕንባ ሲጨማለቅ።
ተስፋ የሸሸው ትውልድ በስጋት ደንዝዞ፤
ቁልቁል አቀርቅሮ ሲተክዝ እያየሁ፤
”ፖለቲካ በሩቅ!” እኔ እንዴት እላለሁ!?
ፖለቲከኛ ነኝ!
ወሠን አልቦ ምድር፥ ለ’ህታችን ጠቧት፤
‘ግርድና ሽጠናት’፥ የአረብ ንቀት ከቧት።
ያ! አርበኛ አባት፥ ‘ሚጦረው በማጣት፤
በሽበት ዘመኑ፥ እጁን ለምፅዋት
እንደ ‘አሮጌ አህያ’፥ ክምር ማገዶ አዝላ፤
የብዙሃን እናት፥ በመከራ ዝላ፤
ዋ!… ስትል እያየሁ፤
”እኔ ምን አገባኝ!”፥ ዛሬ እንዴት እላለሁ!?
ፖለቲከኛ ነኝ!
ፍትህ የተጠማ ሲሄድ ወደ ሸንጎ፤
‘በሆድ አደር’ ዳኛ እሪታው ተነጥቆ፤
በፍርድ አደባባይ ክብሩን ተነፍጎ፤
ለግርፋት ለእስር ሲጣል ወደ ፍርጎ!
”የምሁር” አጎብዳጅ
ከባለግዜ ፊት ሲታሽ እንደ ገረድ፤
በቀጣፊ ሸምጋይ እውነት ስትዋረድ፤
”የሀገር አብሠልሳይ” ሲቀጣ በሀሠት ፍርድ፤
እልፍ ላ’ገር አልቃሽ፥ ሀቁ ስትታረድ።
ይሉኝታችን ሻግቶ፥ እልፍ ‘ግፍ’ እያየሁ፤
”ጎመን በጤናዬን” ዛሬ እተርታለሁ!?
የድሃው መራቆት እረፍት የሚነሣኝ፤
የርሃብ ለከት ማጣት ዕንባ ‘ሚያሳረግፈኝ፤
የጨቅላዉ ሠቀቀን፥ አንጀቴን ‘ሚልጠኝ፤
ፖለቲከኛ ነኝ!
በጎጠኛ መዳፍ፥ ድንበር ሲመዠረጥ፤
‘ራሄል ሠሚ አጥታ፥ እንደ እንቧይ ስትፈርጥ
ሃገር ስትኮመሽሽ፥ እንደ ሠም ስትቀልጥ
አልጠግብ ባይነት፥ ንፍገትን አብቅላ፤
በመጠፋፋት ጫፍ፥ ‘ጦቢያ’ ተንጠልጥላ።
‘ቀዳሚት ሃገሬ’፥ ጭራ ሆና እያየሁ፤
”ፖለቲካ በሩቅ!”፥ እኔ እንዴት እላለሁ!?
ፖለቲካ ነኝ!
የእ’ህቶች ጩኸት፥ ከብዶኝ ‘ምርበተበት፤
”አይነጋም ወይ!?” እያልኩ ካምላክ የምሟገት
በነፃነት ማምለክ በቤቴ ያቃተኝ፤
በነፃነት ማሠብ ቅንጦት የሆነብኝ፤
የፍቅር ‘ረሃብ ልቤን ‘ሚያቃትተኝ፤
የሃገራችን ዕጣ፥ ዕንቅልፍ የሚነሳኝ፤
የእናታችን ዕንባ፥ አንጀቴን ‘ሚያጤሠኝ፤
ፖ.ለ.ቲ.ከ.ኛ. ነኝ!!!!!…..

↧

ከገበታ በኋላ እነዚህ ያስወግዱ..

$
0
0

የስርአተ ምግብ መፈጨት ላይ አደጋ የሚፈጥሩ ድርጊቶችን ማድረግ አይመከሩም፡፡

በዘልማድ ከምግብ በኋላ የሚደረጉ ድርጊቶች ብዙ ጊዜ ችግር ሲፈጥሩ ይስተዋላል፤ ከምግብ አለመፈጨት እስከ የጤና እክል።

እነዚህ ደግሞ ከምግብ በኋላ ባይደረጉ የሚመከሩ ናቸው፡፡
2654372_orig
ሲጋራ ማጨስ፦ ይህን ማድረግ በከፍተኛ ሁኔታ የካንሰር ተጋላጭነትን የሚጨምር ሲሆን ከዚህ ባለፈም ሰውነት ላይ ከፍተኛ ድካምን ያስከትላል፡፡

መተኛት፦ ይህን ማድረግ ደግሞ ሆድ አካባቢ ምቾት የመንሳት እና ድካም እና ጫናን ያስከትላል።

ከዚህ ባለፈም አላስፈላጊ ውፍረትን ያስከትላል፤ ይህን ከማድረግ ከተመገቡ በኋላ ከቅርብ ጓደኛዎ ወይም ወዳጅዎ ጋር መጨዋወት መልካም ነው።

ገላን መታጠብ፦ በተመገቡበት ፍጥነት ገላን መታጠብ ምግብ ለመፍጨት የሚያስፈልገውን የሰውነት ሙቀት ሌላ ስራ እንዲሰራ ያደርገዋል፤ሰውነትን ለማሞቅ።

ይህ ደግሞ በሆድ አካባቢ ያለውን ደም ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች እንዲሰራጭ በማድረግ አንጀት ላይ ከፍተኛ ችግርን ያስከትላል።

ፍራፍሬ መመገብ፦ ለመፈጨት ቀላል ቢሆኑም ምግብ ከተመገቡ በኋላ በቅጽበት ይህን ማድረግ ግን አይመከርም።

ከቻሉ ከምግብ በፊት አንድ ሰአት ወይም ከተመገቡ ከሁለት ሰአት በኋላ፤ ያ ካልሆነ ግን መደራረብ እና መጨናነቅን በማስከተል የምግብ መፈጨትን ያዘገያሉ።

ሻይ መጠጣት፦ በተመገቡበት ቅፅበት ይህን ማድረግም አደጋ አለው፤ የምግብ መፈጨትን አስቸጋሪ በማድረግ የማስጨነቅ ስሜትን ስለሚፈጥር።

ምናልባት በፕሮቲን የበለጸገ ምግብ ተመግበው ከሆነ ደግሞ ከሻይ የሚወጣው አሲድ በከፍተኛ ሁኔታ የምግብ መፈጨቱን ስለሚያስተጓጉለው አደገኛ ይሆናል።

ከምግብ በኋላ ሻይ መጠጣት ከፍተኛ የሆነ የብረት መጠን ለሚያስፈልጋቸው ህጻናትና ሴቶች ደግሞ ጭራሽ አይመከርም።

የእግር ጉዞ ማድረግ፦ ይህን ሲያደርጉ ደግሞ ከፍተኛ የሆነ የአሲድ መጠንን በመርጨት እና የምግብ አለመፈጨትን በማስከተል ችግር ይፈጥራል።

ስለዚህም ከተመገቡ ከግማሽ ሰአት በኋላ የእግር ጉዞ ማድረግ እና በተመገቡበት ፍጥነት ይህን ማስወገድ ለጤናዎ መልካም ነው።

ምንጭ፦ mavcure.com

– See more at: http://www.fanabc.com/index.php/%E1%8C%A4%E1%8A%90%E1%8A%9B-%E1%8A%91%E1%88%AE/item/13893-%E1%8A%A8%E1%8C%88%E1%89%A0%E1%89%B3-%E1%89%A0%E1%8A%8B%E1%88%8B-%E1%8A%A5%E1%8A%90%E1%8B%9A%E1%88%85-%E1%8B%AB%E1%88%B5%E1%8B%88%E1%8C%8D%E1%8B%B1.html#sthash.asLbFMpK.dpuf

↧

ተመስገንን በጨረፍታ

$
0
0

በማሕሌት ፋንታሁን
መንግሥት አሸባሪ ብሎ ከፈረጃቸው ተቋማት ጋር ማቆራኘት ሳያስፈልገው የጻፈው ጽሑፍ ብቻ ተጠቅሶበት የተከሰሰ እና የተፈረደበት ብቸኛ ጋዜጠኛ ነው – ተመስገን ደሳለኝ። በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የተመሠረተችው ፍትህ ጋዜጣ ጥቂቶቹን የግል ሕትመት ሚዲያ ውጤቶች የተቀላለችው በ2000 ነበር። ከምርጫ 97 በኋላ የተከሰተውን የግል ሚዲያ እጥረት አሳስቦት እና የበኩሉን ለመወጣት ብሎ ነው ፍትሕን ለመመሥረት የተነሳሳው። ፍትሕ ጋዜጣ ሕትመት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ እስከ 2004 ሐምሌ ወር (ላይ እስክትታገድ ድረስ) ድረስ ከዓመት ወደ ዓመት የሕትመት ብዛቷ እየጨመረ መጨረሻ አካባቢ እስከ 35ሺ ኮፒ ትታተም ነበር።
ማንኛውም ዓይነት ቅድመ ሳንሱር እንደሌለ በሚደነግገው ሕገመንግሥት መተዳደር ያለበት ፍትሕ ጋዜጣን የሚያትመው ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት፣ የሐምሌ 13/2004 ዓም እትም ላይ ስለ መለስ ዜናዊ የተጻፈ ዜና ካልወጣ እንደማያትሙ አሳወቁ። ይህን የሰማው ተመስገን እያረጉ ያሉት ቅድመ ሳንሱር መሆኑን፣ ይህ ደግሞ በሕገመንግሥቱ የተከለከለ መሆኑን ከገለጸላቸው በኋላ የታዘዙትን 30ሺ ኮፒ ካተሙ በኋላ እንዳይሰራጭ ከፍትሕ ሚኒስቴር በተላለፈ ትዕዛዝ መሠረት ማገዳቸውን እና የታተመው ጋዜጣም መወረሱን በደብዳቤ ገለፁ። ለ30ሺ ኮፒ ሕትመት፣ ለጸሐፊዎች የሚከፈል እና ለተለያዩ አስተዳደራዊ ወጪዎች የወጣው ገንዘብ ወደ100ሺ ብር የሚጠጋ ከስሯል። ነሐሴ 2 ቀን 2004 ክስ እንደተመሠረተበት ፋና ዜና ላይ እንደሰማ የሚናገረው ተመስገን፣ በዜናው እንደሰማውም በቀጣይ ቀጠሮ ነሐሴ 9 ቀን 2004 ፍ/ቤት ቀረበ። በ2003 እና በ2004 በፍትሕ ጋዜጣ ላይ በወጡ 5ት ጽሑፎች ሦስት ክስ እንደቀረበበት ተነግሮት የዋስትና መብቱንም ተነፍጎ የዛኑ ቀን ወደ እስር ቤት ገባ። ለስድስት ቀናት በቃሊቲ ጨለማ ቤት ከቆየ በኋላ ባልተጠበቀ ሰዓት እና ምክንያቱ ሳይነግው ነሐሴ 16/2004 ከእስር ተለቀቀ። በኋላ ሁላችንም እንደሰማነው ከእስር የተለቀቀው ክሱ ተቋርጦለት መሆኑን ነው።
ጋዜጠኛ ተመስገን የቀረቡበት ክሶች 1ኛ) ወጣቶች በአገሪቱ መንግሥትና ሕገ መንግሥታዊ ስርዓቱ ላይ እንዲያምፁ የመገፋፋትና ግዙፍ ያልሆነ የማሰናዳት ተግባር፣ 2ኛ) የሀገሪቱን መንግሥት ሥም ማጥፋት እና የሐሰት ውንጀላ፣ 3ኛ) ክስ የሐሰት ወሬዎችን በማውራት ሕዝብን በማነሳሳት ወይም አስተሳሰባቸውን ማናወጥ ሲሆኑ ይህን ክስ ሊያስመሠርቱበት የቻሉት ጽሑፎች ደግሞ 1) የፈራ ይመለስ (በተመስገን ደሳለኝ) 2) የሁለተኛ ዜግነት ሕይወት በኢትዮጵያ እስከመቼ? (በተመስገን ደሳለኝ) 3) መጅሊሱና ሲኖዶሱ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ማጥመቂያ (በተመስገን ደሳለኝ) 4) ሞት የማይፈሩ ወጣቶች (በተመስገን ደሳለኝ) እና 5) የብሔር ብሔረሰቦች መብት እስከመጨፈር የሚሉት ናቸው።

Temesgen Dessalegn with his foster children.

Temesgen Dessalegn with his foster children.

ፍትሕ በዚ መልኩ ከሕትመት ከታገደች በኋላ ተሜ እጅ እና እግሩን አጣጥፎ አልተቀመጠም ወይም መሰደድን አልመረጠም። በ2005 ፍትሕን በአዲስታይምስ መጽሔት መልክ፣ እሱም እንዲዘጋ ሲደረግ በልዕልና ጋዜጣ እውነትን እንድናነብ ከባልደረቦቹ ጋር በመሆን ለፍቷል። ልዕልናም ቀኗ ደርሶ ከሕትመቱ ዓለም ስትሰናበት ደግሞ በ2007 በግሉ ዘርፍ ይታተሙ ከነበሩ ተመራጭ ጥቂት መጽሔቶች እና ጋዜጦች ጋር ክስ ተመሥርቶባቸው እንዳይሠሩ ከታገዱት የሕትመት ውጤቶች መሐል አንዷ በሆነችው ፋክት መጽሔት ሥራውን ቀጥሎ ነበር።
በነሐሴ 13፣ 2004 ተቋረጠ የተባለው ክስ መቀስቀሱን አሁንም እሱ በሌለበት በታኅሣሥ ወር 2005 የዋለው ችሎት በፋና ሬዲዮ መዘገቡን ሰማ/ን። በቀጣዩ የቀጠሮ ቀን ሲቀርብ የ50ሺህ ብር የዋስትና ብር አስይዞ ክሱን ከውጪ ሆኖ እንዲከታተል ተፈቀደለት። ክሱን እየተከታተለም ነው ልዕልና ጋዜጣን እና ፋክት መጽሔትን ለኛ ላንባቢዎቹ ሲያደርስ የነበረው። ታኅሣሥ 2005 የተንቀሳቀሰበትን ክስ በዋስትና ሲከታተል ቆይቶ፤ በጥቅምት 3፣ 2007 ጥፋተኛ የተባለው እንዲሁም ጥቅምት 17፣ 2007 ላይ ደግሞ የ3 ዓመት ፍርድ የተፈረደበት።
ተመስገን የሥራ ሰዓት እና የእረፍት ሰዓት የለውም። ብዙውን ጊዜውን በመጻፍ ወይም በማንበብ ነው የሚያሳልፈው። የጻፈውን የኖረ እና እየኖረ ያለ ጋዜጠኛ ነው።
ዝዋይ ከመሄዱ በፊት ቃሊቲ በነበረበት ጊዜያትም ሆነ ዝዋይ ከሄደ በኋላ ተመስገን፣ ሌሎች እስረኞች እንዳይቀርቡት ይደረጋል። ቃሊቲ እያለ የአልሻባብ አባል ተብለው በሽብር ተከሰው ከሱ ጋር የሚኖሩ እስረኞች ከሱ ጋር ካወሩ ወይም ወክ ሲያደርጉ ከታዮ “እንዴት ከአሸባሪ ጋር ትሆናላችሁ?” ይባሉ እና የተለያዩ ማስፈራሪያዎች እንደሚደርስባቸው ነግረውታል። የዝዋዩ ደግሞ የባሰ ሆኖ ነው ያገኘው። ከሱ ጋር ያወራ ማታ ማታ እየተወሰደ ይደበደባል። ይህን በመፍራት ብዙ እስረኞች ከሱ ጋር መሆን ይፈራሉ። መጽሐፍ አይገባለትም። ሕክምና ለማግኘት ሲጠይቅ “ቆይ ያንተን ጉዳይ እየተነጋገርንበት ነው” ከሚል ውጪ ያገኘው ምላሽ ስለሌለ ከጀርባ ሕመሙ ስቃይ ጋር አብሮ ይኖራል። ምንም ዓይነት መጽሐፍት አይገቡለትም። ከሌሎች እስረኞች ተውሶ ማንበብም አይችልም። እሱ ያለበት ዞን ላይብረሪ የለም። ቤተሰቦቹ እና ጓደኞቹ እንዳይጠይቁት ይከለከላሉ። ብዙ ጓደኞቹ እና ወዳጆቹ ብዙ ርቀት ተጉዘው ከእናቱ እና ወንድሞቹ ውጪ እሱን መጠየቅ አይቻልም ተብለው ይመለሳሉ። የዛሬ ዓመት አካባቢ እናቱን እና ወንድሞቹን ጭምር ለሁለት ወር ያክል እንዳይጠይቁት ተከልክለው ነበር። በተለያዩ ጊዜያትም እነዚሁ የቅርብ ቤተሰቦቹ ገብተው እንዳይጠይቁት ተከልክለው ይመለሳሉ። በአንድ ወቅት ታናሽ ወንድሙ የሆነው ታሪኩ ደሳለኝ ሊጠይቀው በሄደ ወቅት መግባት እንደማይችል ከነገሩት በኋላ በማያቀው ምክንያት በዝዋይ እስር ቤት ፓሊሶች ተደብድቧል።
ምክንያቱን ባይገባኝም ከቅርብ ቤተሰቦቹ ውጪ መጎብኘት የሚፈቀድለትን አንዳንድ ወቅቶች ተከታትለው የሚጠይቁት ጓደኞቹ ብዙ አይደሉም። ተመስገንን የምንወደው ጓደኛችን ከሆነ ከቤተሰብ ውጪ መጠየቅ አይቻልም ብሎ ቁጭ ከማለት ዝዋይ መጠየቅ ከሚፈቀድለት ቤተሰብ ጋር ሄዶ መልዕክት መላክ ወይም መጠየቅ የሚፈቀድበትን ወቅት ጠብቆ መሄድ።
ተሜ በዝዋይ ከሌሎች እስረኞች በተለየ ብዙ ማእቀቦች ተጥሎበት እየኖረ የመንፈሱ ጥንካሬ የሚገርም ነው። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ አራት ፅሁፎችን አስነብቦናል። በእስሩ ወቅት ስላገኛቸው የኢትዮጵያ ሶማሌዎች የሚተርክ በሁለት ክፍል “የኢትዮጵያ መንግሥት ገመና ከዝዋይ እስር ቤት” እንዲሁም አሁን በኦሮሚያ ስለተነሳው ሕዝባዊ አመፅ የጻፈው “ሁለተኛው ምዕራፍ” የሚሉት ጽሑፎች ይገኙበታል።
ከዓመት በፊት በላከው በአንደኛው ጽሑፉ እንዲህ ይላል “…ግና! ይህ መንግሥታዊ የጭካኔ ተግባር፣ ዛሬም በምስኪን ዜጎች ላይ እየተፈፀመና ብዙዎችን ሰለባ እያደረገ በመሆኑ ሕዝቡ ይህን ሊሸሸግ እየተሞከረ ያለውን መከራ ተረድቶ ሥርዓቱን በአደባባይ ዓመፅ “ሃይ!” ይል ዘንድ ትርክቴን ለማጠናቀር ተገድጄያለሁ፡፡ ለእስር ያበቃኝ የጋዜጠኝነት ሙያዬም ተጨማሪ ዕዳ ጭኖብኛል፡፡”
ተሜ እንደቃሉ ጉዞውን እስከቀራኒዮ ያደረገ ጋዜጠኛ ነው። አንድ ዓመት ከአምስት ወር በእስር አሳልፏል። የሚወጣበት ቀን እየቀረበ ነው እንጂ እየራቀ አይደለም የሚሄደው። በቀሪዎቹ ጊዜዎች እና ከወጣ በኋላ በብዕሩ የሚያካፍለንን የኢሕአዴግ መንግሥት ገበናዎች ለማንበብ በጣም ነው የምጓጓው። ተሜ ከዚህ በፊት በብዙ ኮፒ ታትሞ ለገበያ ያበቃው “የመለስ አምልኮ” የተሰኘው መጽሐፍ ተወዳጅነትን አትርፎለታል። በ2007 መጨረሻ አካባቢ ደግሞ ከሙያ ባልደረቦቹ እና ከጋዜጠኛ እስክንድር ጋር (ከቃሊቲ እስር ቤት) በአንድነት በተለያየ ጊዜ የተጻፉ ጽሑፎችን በመጽሐፍ መልክ ታትሟል።

ተመስገን ደሳለኝ ከጋዜጠኝነት ሥራው በተጨማሪ ያለውን በማካፈል ይታወቃል። ለጓደኞቹ እና ለወዳጆቹ በችግራቸው ጊዜ ከጎናቸው ሆኖ ለመርዳት የሚችለውን ያደርጋል። በምስሉ ላይ ከተሜ ጋር የሚታዩት ሕፃናት ቤተሰቦቻቸው አቅመ ደካማ በመሆናቸው ወጪያቸውን በመሸፈን የሚረዳቸው ናቸው። ወጪያቸውን ከመሸፈን ባለፈም ባለው ትርፍ ሰዓት ያዝናናቸው፤ እንዲሁም በቋሚነት የሚማሩበት ት/ቤት በመሄድ የትምህርት ሁኔታቸውን ይከታተል ነበር። አሁን ጊዜው ተገልብጦ እነዚህ ህፃናት በወር አንድ ጊዜ ከእናቱ እና ወንድሙ ጋር በመሆን ዝዋይ ድረስ ሄደው ይጠይቁታል።
በነገራችን ላይ ተሜ እነዚህን ሕፃናት እና ቤተሰቡን እንደሚያስተዳድር ለፍ/ቤት ቢገልፅ የቅጣት ፍርዱ ይቀንስለት ነበር። ሆኖም ተሜ ጥፋት ስላላጠፋሁ አቅልሉልኝ ብዬ አልጠይቅም ብሎ ምንም አይነት ማቅለያ ሳያስገባ ነው 3 ዓመት የተፈረደበት።
ብርታትና ጥንካሬን ለተሜ እና ቤተሰቦቹ እየተመኘሁ ተሜን በጨረፍታዬን በዚሁ ላብቃ።

↧
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live