Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ተቆርቋሪ የሌላት ኢትዮጵያ ወደ የት? –ትብብር ወይንስ ውድድር?- አክሎግ ቢራራ (ዶ/ር)

$
0
0

Dr. Aklog Birara
የብዙ ሽህዎች አመታት ተከታታይ ታሪክ፤ መንግሥታትና ዝና ያላት ኢትዮጵያ የምትታወቀው ከሁሉም ብሄር፤ ብሄረሰብና ሕዝቦች ተወጣጥተው ግዛታዊ አንድነቷን፤ ነጻነቷን፤ ክብሯን፤ ዘላቂ ጥቅሟንና ሉዐላዊነቷን ባስጠበቁት ጀግኖቿ መስዋእት ነው ብል የተሳሳትኩ አይመስለኝም። አፍሪካ፤ የመካከለኛው ምስራቅ፤ የላቲን አሜሪካና ካሪቢያን እና የኤዥያ አገሮች በቅኝ ገዢዎች እጅ ወድቀው ሲማቅቁ፤ ድሃና ኋላቀርም ብትሆን፤ ኢትዮጵያ ነጻነቷንና ሉዐላዊነቷን በራሷ አቅም አስከብራ ለተከታታይ ትውልድ አስተላልፋለች። በጀግኖቿ ትግል ከፋሽስት ወረራ ነጻ ከሆነች በኋላ በዓለም ደረጃ እውቅና ያገኘችው ከሰማይ የወረደ አይደለም። አገር ወዳድ የሆኑ ልጆቿ ጠንክረውና ተባብረው ስለሰሩ ነው።

Read Full Story in PDF


የኖርዌይ መንግሥት 800 ኢትዮጵያውያን እና 60 ሕፃናትን ወደ ኢትዮጵያ ሊመልስ ነው | VOA

$
0
0

norway
የኖርዌይ ከለላ ጠያቂዎች ድርጅት ከፍተኛ አማካሪና የሕግ ባለሞያ በፖለቲካ ውስጥ ተሳትፎ ያላቸው ስደተኞች ስጋታቸው ተገቢ ነው ይላሉ።
ዋሽንግተን ዲሲ —
ያቀረቡት የጥገኝነት ጥያቄ ተቀባይነት ያላገኘላቸው 800 ኢትዮጵያውያን እና 60 ሕፃናትን የኖርዌይ መንግሥት በግዳጅ ወደ ኢትዮጵያ እመልሳለሁ ማለቱ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንደከተታቸው ተናገሩ።

የኖርዌይ ከለላ ጠያቂዎች ድርጅት ከፍተኛ አማካሪና የሕግ ባለሞያ በፖለቲካ ውስጥ ተሳትፎ ያላቸው ስደተኞች ስጋታቸው ተገቢ ነው ይላሉ።

ጽዮን ግርማ ስደተኞችንና የሕግ ባለሞያውን አነጋግራ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች።

በተግባር ያልተደገፈ ይቅርታ የጊዜ መግዣ ፕሮፓጋንዳ ብቻ ነው |በቀለ ጅራታ

$
0
0

ኦቦ በቀለ ጅራታ

ኦቦ በቀለ ጅራታ

ገዢው የኢህአድግ መንግስት ለሃያ ኣራት ኣመታት የሃገሪቱን ህዝቦች በማን ኣለብኝነት መብታቸውን ገፎ ሲያሰቃይ በኖረባቸው ዘመኖች ኣንድም ጊዜ ኣስተዳድራለሁ የሚለውን ህዝብ ድምጽ ሰምቶ ኣያውቅም እንኳን ይቅርታ ሊጠይቅ ይቅርና። ሰሞኑን ግን ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ያልተለመደ ኣዲስ ዜና ኣሰምተዋል። ይሄውም ባለፉት ኣራት ወራት በኦሮሚያ ህዝብ ላይ ጦርነት ኣውጀው ከ 500ያላነሱ ንጹሃን የኦሮሞ ልጆችን በገፍ ካስጨፈጨፉ በኋላ የኢትዮዽያን ህዝቦች ይቅርታ እጠይቃለሁ ማለታቸው ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያምና ግብረኣበሮቻቸው የህዝባችንን ህጋዊ የመብት ጥያቄ

የኣሸባሪዎችና ስልጣንን በኣቋራጭ ለመያዝ የሚፈልጉት ሴራ ነው ብለው እንዳልፈረጁ ሁሉ ዛሬ ጥፋቱ የመንግስታቸው ብልሹ ኣስተዳደር ነው በማለት እየመረራቸውም ቢሆን እውነትን ሊውጡ ተገደዋል። ይህ ለህዝባችን ትልቅ ድል ነው።

የኢትዮዽያ ህዝቦችና የፖለቲካ ተቃዋሚዎች ባለፉት ኣመታት ሲጠይቁ የነበሩትን ኣስተዳደራዊ በደሎች ከማስተካከል ይልቅ ትችት ኣቅራቢ የፖለቲካ ፓርቲዎችን እንደጠላት በመቁጠር ጸረ ሰላምና ጸረልማት ኣድርገዉ ሲኮንኑ የነበሩት የመንግስት ባለሥልጣናት ዛሬ በራሳቸዉ ኣንደበት በህዝቦች ላይየፈጸሟቸውን በደሎች ኣምነው ለመቀበል ተገደዋል። እውነት ትቀጥናለች እንጂ ኣትበጠስም እንደተባለው እውነትን በዉሸት መሸፈን ስላልቻሉ እያነቃቸውም ቢሆን ለመቀበል ተገደዋል።
enqilf Hailemariam
ሆኖም ኣቶ ሃይለማሪያም ለደረሰው የግፍ ጭፍጨፋ ሃላፊነት ከወሰዱም በኋላ ግዲያው፣ ድብደባውና እስሩ ቀጥሏል። ይህም ይቅርታው ከልብ ያለመሆኑን የሚያሳይ ኣንዱ ምልክት ነው።ኣንድ መንግስት በህዝቡ ላይ እንደዚህ ኣይነት ግዙፍ በደል ከፈጸመ ቢበዛ ስልጣኑን ይለቃል ቢያንስ ደግሞ ተጨባጭ የሆኑ የማስተካከያ እርምጃዎችን ይወስዳል። ሰሞኑን በኣውሮፓዊቱ ሃገር ቤልጅየም ኣሸባሪዎች ላደረሱት ጥፋት ሰበብ የሃገር ውስጥ ሚኒስትሩ ወዲያውኑ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የስልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ ኣቀረበ። የኣሸባሪዎቹ ጥቃት የሰውዬው ጥፋት በመሆኑ ሳይሆን የዜጎቹን ሰላምና ደህነነት በተገቢው መንገድ ኣልጠበኩም የሚል የህሊና ወቀሳ ተስምቷቸው መሆኑ ግልጽ ነው። የጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ መንግስት ግን ይቅርታ በጠየቀ ማግስትም ጥፋቱን ቀጠለበት እንጂ የሰራው ነገር የለም። እየወሰደ ያለው እርምጃ ቢኖር የኦሮሞ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ኣባላትን ከስራ ማባረር ነው። ለጠፋው የኦሮሞ ተወላጆች ህይወት ተጠያቂው የራሳቸው መንግስት መሆኑን እያመኑ ድርጊቱን ለመፈጸም ኣቅምም ሆነ ስልጣን ያልነበራቸውን ከስራ ማባረር የእምዬን ወደ ኣብዬ እንደሚባለው ነው።

የተጠራቀመ የበርካታ ኣመታት የኣስተዳደር በደል ቢኖርም ለኣሁኑ ህዝባዊ ተቃውሞ መነሻ

የሆነው የኣዲስ ኣበባ ማስተር ፕላን መሆኑ ይታወቃል። የኦሮሚያ መንግስት ደግሞ ስለማስተር ፕላኑ ምንም እውቀት እንደለሌው በቅርቡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኦህዲድ ኣባላት ስብሰባ ላይ ኣቶ ኣባ ዱላ በግልጽ ቋንቋ ገልጸዋል። ኣቶ ኣባዱላ እንደተናገሩት ስለማስተር ፕላኑ ኣንዳች የሚያውቁት ነገር እንደለሌ ጭራሹኑ ነገሩ እስካሁንም እንዳልገባቸው ሲናገሩ ተሰምቷል። ከእራሳቸው ኣልፈውም ሌሎች የኦህዲድ ከፍተኛ ባለስልጣኖችም እንደማያውቁ ተናግረዋል። ታዲያ የኦህዲድ ባለስልጣናት በምን ወንጀላቸው ነው የሚቀጡት ? ኣቶ ኣባ ዱላ ገመዳ በኦህዴድ ውስጥ ከፍተኛ ቦታ ያላቸው ስለማስተር ፕላኑ ኣላውቅም ካሉ ሌላ ከእሳቸው የተሻለ ሊያውቅ የሚችል ማነው ? በትክክልም ነገሩ ይፋ የሆነው ኣቶ ኣባይ ጸሃዬ የተባሉ የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሓት) ባለስልጣን በኣዳማ ላይ ለኦሮሚያ የከተማ ልማት ሃላፊዎች ጉዳዩን ሲያሳውቁ ተቃዎሞ የተነሳ ጊዜ ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ በኦሮሚያ ለተፈጠረውም ሆነ በኣጠቃላይ በሃገሪቱ ለተፈጠሩት ችግሮች ዋናው ምክንያት እሳቸው የሚመሩት መንግስት የተበላሸ ኣስተዳደር እንዲያውም የተጨማለቀ ኣስተዳደር ነው ካሉ ለምንድነው በኦህዴድ ባለስልጣናት ላይ ብቻ ጥፋቱን የደፈደፉትና ከ ሶስት መቶ በላይ ሃላፊዎችን ከስልጣን እንዲባረሩ ያደረጉት?

ኣቶ ሃይለማሪያም እራሳቸው የኦሮሚያን ክልል የመንግስትነት ስልጣን በመጋፋት ወይም በመግፈፍ የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን ብለው የኣጋዚና የፌደራል ፖሊስ ያሰማሩ ሆኖ እያለና የኦሮሚያ ፖሊስም ትጥቁን እንዲፈታ በተገረገበት የኦሮሚያ ባለስልጣኖች ወንጀለኞች የሚሆኑበት ኣሰራር ጉልበተኛ እራሱ ደብድቦ ማልቀስ ይከለክላል እንደሚባለው ኣይነት መሆኑ ነው። በሃገሪቱ ህገመንግስት ኣንቀጽ 51(14) የፌደራል መንግስቱ ከክልል ኣቅም በላይ የሆነ የጸጥታ መደፍረስ ሲያጋጥም በክልሉ መስተዳደር ጥያቄ መሰረት የሃገሪቱን የመከላከያ ሃይል ያሰማራል ይላል። ኣቶ ሃይለ ማሪያ ግን የሃገሪቱን ጦር ወደ ኦሮሚያ ሲያዘምቱ የክልሉ መንግስት በጠቃቸው መሰረት ብለው ያሉት ነገር የለም። የክልሉ መንግስትም ጥያቄ ማቅረቡን ያሳወቀበት የለም።

በመሆኑም የፌደራሉ መንግስት ቀድሞውኑ ህገ መንግስቱን በመጣስ ገዳይ ስኳድ በኦሮሚያ ኣሰማርቷል። ይህ ገዳይ ስኳድ ዜጎችን ያለ ርህራሄ ህይወታቸው እንዳይተርፍ ከወገብ በላይ ኣልሞ በመተኮስ እንደፈጃቸው በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ለማየት ትችሏል። የሰብዓዊ መብት ጉባኤ ሪፖርትም ይህንኑን ኣረጋግጧል። የሰብዓዊ መብት ጉባኤ (ሰመጉ) በጥቂት ወረዳዎች ላይ ባደረገው ጥናት ሪፖርት ላይ እንደገለጸው 157 የኦሮሞ ልጆች በሙሉ ግንባራቸውን፣ ደረታቸውንና ጭንቅላታቸውን በጥይት ተመተው እንደተገደሉ ገልጿል። ይህንን በስው ልጆች ላይ የተፈጸመውን ወንጀል (Crimes against Humanity) የፈጸሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም የማያዳግም እርምጃ እንዲወስዱ ያሰማራቸው ናቸው እንጂ የኦህዴድ ባለስልጣኖች ኣልነበሩም። የኦህዴድ ባለስልጣናት ወንጀል ኣልሰሩም ማለቴ ኣይደለም ። የእነሱ ወንጀል ከዚህም የባሰ የሚሆነው የኦሮሞ ህዝብ ውክልና ሳይኖራቸው ባለፉት ሃያ ኣራት ኣመታት የኦሮሞን ህዝብ በመግደል፣ በማሰርና ከሃገር እንዲሰደድ በማድረግ ሃብት ለመዝረፍና ለመክበር የመጡትን የትግራይ ነጻ ኣውጪ ታጋዮችን መንገድ መርተው በማስገባታቸውና የኦሮሞን ህዝብ ሰብዓዊ መብት በመርገጥና በማስረግጥ በፈጸሙት ወንጀል ይጠየቁበታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ባለፉት ሃያ ኣራት ኣመታት በኢትዮዽያ ህዝቦች ላይ ኣሁን እሳቸው የሚመሩት መንግስት ላደረሰው የመብት ረገጣ፣ እስርና ሲቃይ በተለይም ከሁለት ኣመት በፊት ለደረሰውም ሆነ ካለፈው ህዳር 2008 ጀምሮ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ለደረሰው ታላቅ የግዲያና የመብት ረገጣ ሃላፊነቱን ከወሰዱና ይቅርታ ከጠየቁ የሚከተሉትን ተጨባጭ እርምጃዎችን በኣስቸኳይ በመውሰድ ማሳየት ይኖርባቸዋል።

ኣንድ፤ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ መንግስታቸው በፈጸመው የማስተር ፕላን እቅድ ሰበብ በተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ኣነሳሳታችዋል ተብለው የታሰሩትን እንደነ በቀለ ገርባና ደጀነ ጣፋ፣ በኣጠቃላይ በዚህ ሰበብ የታሰሩትን በሙሉ በኣስቸኳይ ይፍቱ ። ለደረሰባቸዉ ጉዳት የሞራል ካሳ እንዲከፈላቸዉ እዲያደርጉ፣

ሁለት፣ በኦሮሚያ የተሰማራውን የፈደራል ጦርና ፖሊስ በኣስቸኳይ ከኦሮሚያ ክልል እንዲያስወጡ።

ሶስት፣ በኦሮሚያ የተፈጸመውን ግዲያና ድብደባ በቀጥታ የመሩት፣ ትእዛዝ የሰጡ፣ ኣልመው ተኩሰው የገደሉ በሙሉ፣ በህገወጥ መንገድ የታቀደውን ማስተር ፕላን ወደዳቹም ጠላቹ ይተገበራል ያሉት እንደነ ኣቶ ኣባይ ጸሃዬ ያሉትና እንደነ ጌታቸው ረዳ ያሉት ህዝቡ ን ጋኔን ብለው የተሳደቡ በኣስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ እንዲያደርጉ፣

ኣራት፣ መሬታቸው የተወሰደባቸው የኦሮሞ ኣርሶ ኣደሮች በዝርዝር ታውቀው ወይ መሬታቸው እንዲመለስላቸው ኣለበለዚያም የመኖርያ ቤት እንዲሰራላቸውና ለዘለቄታው ለህይወታቸው ኣስፈላጊ የሆነ መተዳደርያ ካሳ እንዲከፈላቸው እንዲያደርጉ፣

ኣምስት፣ በኦሮሚያ፣ በኣማራ፣ በጋምቤላ፣ በደቡብ በኮንሶ፣ በሱርማ ፣ በሱማሌ ክልል በኣጠቃላይ በመላ ሃገሪቱ በመንግስት የደረሰውን ጊዲያና የመብት ረገጣ የሚያጣራ ገለልተኛ ኣለም ኣቀፍ ኣጣሪ ኮሚሽን እንዲቋቋምና እንዲያጠና እንዲደረግ።

ስድስት፣የኦነግ ደጋፊዎች ናችሁ ተብለው ታስረው በመሰቃየት ያሉትን እንደነ ኦልባና ሌሊሳ ያሉትን የኦሮሞ ልጆች በኣስቸኳይ ከእስር ፈተው የሞራል ካሳ እንዲከፈላቸው እንዲያድርጉ፣ ስባት፣በኣጠቃላይ ያለ ምንም ወንጀል መንግስትዎን ባለመደገፍ የሌሎች ፖለቲካ ፓርቲዎች ኣባልበመሆናቸው፣በመምረጣቸውና በመደገፋቸው ታስረው ያሉትን የፖለቲካና የህሊና እስረኞች ከእስር እንዲለቀቁና ለደረሰባቸው በደል ካሳ እንዲከፈላቸው ። የታሰሩ ጋዜጠኞችን እንደነ

እስክንድር ነጋ፣ ተመስገን ደሳለኝና ሌሎችን በሙሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከእስር እንዲፈቱ እንድያደርጉ፣

ስምንት፣ መንግስት በሃይማኖታችን ጣልቃ ኣይግባ በማለት በሰላማዊ መንገድ የጠየቁትንና ለዚህም መፍትሄ ኣፈላላጊ ኮሚቴ መርጠው ከመንግስት ጋር እንዲነጋገሩ የላካቸውን በፈጠራ የሽብር ክስ የታሰሩት የሙስሊም ማህበረሰብ ተውካዮችን እንዲፈቱና በእነሱና ቤተሰቦቻቸው ላይ ለደረስው ጉዳት ካሳ እንዲከፈላቸው።

ዘጠኝ፣ ባለፉት ሃያ ኣራት ኣመታት በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ክትትልና ማሳደድ ምክንያት በሃገራቸው ለመኖር ባለመቻላቸው ከሃገር ተሰደው በጎረቤት ሃገሮች በስቃይ ላይ የሚገኙ የኦሮሞና የሌሎች ብሄረሰብ ኣባላት ወደ ሃገራቸው ተመልሰው በሰላም ለመኖር እንዲችሉ ዋስትና የሚሰጣቸው መሆኑን መንግስት በይፋ እንዲያውጅ እንዲደረግ።

ኣስር፣ ከሁሉም በላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ እራሳቸው በገለጹት መሰረት የተጨማለቀው መንግስታቸው ከዚህ በላይ በስብሶ ሃገሪቷን ወደ ከፋ መንገድ ከመውሰዱ በፊትና ሌላ የቀረው ነገር ባለመኖሩ ከእንግዲህ ተሻሽሎ ሃገሪቷን ወደ ሰላምና ብልጽግና ሊመራት ስለማይችል ሁሉን ያቀፈ መንግስት እንዲመሰረት የጊዜ ገደብ ተወስኖ በፓርላማዎ ኣዋጅ እንዲወጣ እንዲያደርጉ፣ በዚሁ ፓርላማው በሚያውጀው ኣዋጅ ለሚመለከታቸው የኢትዮዽያ የፖለቲካ ተቃዋሚዎችና የሲቪክ ድርጅቶች የሀገር ውስጥና ከሃገር ውጭ ላሉት ጥሪ እንዲደረግ። ይህ እርስዎንም ሆነ ሌሎችን ሊጠቅም የሚችል በመሆኑ ጊዜ ሳያባክኑ ተግባራዊ እንዲደረግ። በአጠቃላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለ ማሪያም ደሳለኝ የሚመሩት መንግሥታቸዉ ከላይ የተዘረዘሩትንና ሌሎች የማስተካከያ እርምጃዎችን ካልወስዱና የኢትዮዽያን ህዝቦች እውነተኛ ይቅርታ ጠይቆ በሀገሪቱ እርቅና ሰላም እንዲመጣ ካላደረገ ከእውነተኛው ተጠያቂነት የማይድን መሆኑን ማወቅ ኣለበት።

ይህ ካልሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለ ማሪያም ደሳለኝ በሃገሪቷ ህዝቦች ላይ በተለይም በኦሮሞ ህዝብ ላይ ለደረሰው ከባድ ወንጀል ሃላፊነት እወስዳለሁ ያሉትም ሆነ ይቅርታው ጊዜ ለመግዛትና የተለመደውን ጥፋት ለመቀጠል የፕሮፓጋንዳ ስራ ብቻ ይሆናል። ያ ከሆነ ደግሞ ከኣጥፍቶ መጥፋት የተለየ ሊሆን ኣይችልም። ሃገርንም ሆነ እራስን ከጥፋት ለማዳን መንግስትዎ ልቦና የመግዣው ጊዜ ኣሁን መሆን ኣለበት።

በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ከሚፈጸሙ ጥቃቶችና ጨርሶ የማጥፋት ዓላማ ጀርባ ያሉት እነማን ናቸው?

$
0
0

abune Matias
6ኛ ፓትርያርክ እናስመርጣለን ተብሎ የይስሙላ ምርጫ በማድርግ አባ ማትያስን ለመሾም ሽር ጉድ በሚባልበት ወቅት ይህ ሒደት ሕገ ቤተክርስቲያንን የጣሰ ወይም ያልተከተለ ከመሆኑ የተነሣ ማኅበረ ቅዱሳን የዚህ አስቂኝ ጨዋታ ተካፋይ መሆኑ በእጅጉ አስከፍቶኝ በወቅቱ እስኪ ግልጽ ያልሆነልኝ ነገር ካለ ብየ ዋና ጸሐፊውን ሔጀ አናግሬው ነበር፡፡
ምላሹ ምንም ሊያሳምነኝ አልቻለም፡፡ ብዙ አወራን ተከራከርንም፡፡ የገባኝ ነገር ምንድን ነው ማኅበሩ የሰጥቶ መቀበልን ጨዋታ ለመጫወት መገደዱን ነው፡፡ ስለሆነም ምን አልኩት የሰጥቶ መቀበል መርሕ የሚሠራው ለፖለቲካ እንጅ ለቤተክርስቲያን አይደለም፡፡ ምክንያቱም ሰጥቸ እቀበላለሁ ሲባል መርከስ፣ መንጠብ፣ የማይገባ ነገር መፈጸም፣ ከማይገባ ግብር ጋር መተባበር ይመጣልና በእነዚህ ድርጊቶችም እግዚአብሔር የሚቀየምበት ሁኔታ ይፈጠራል፡፡ ከእሱ እጅ ያጣነውን ከሌላ እጅ ልናገኘው የምንችል ይመስል እንዲህ ማሰብ በፍጹም ክርስቲያናዊ አስተሳሰብ አይደለም፡፡

ስለሆነም ይህ ጨዋታ ለፖለቲካ (ለእምነተ አሥተዳደር) እንጅ ለቤተክርስቲያን አይሠራም አያዋጣም፡፡ ቤተክርስቲያን ላይ የሚሠራው “በጊዜውም አለጊዜውም ጽና” 2ጢሞ. 4፤2 በሚለው ቃሉ መሠረት ጸንቶ የእግዚአብሔርን መጠበቅ ነው፡፡ ለማየት ያብቃህ እኒህ ሰውዬ ከአባ ጳውሎስ የባሱ የከፉ ቤተክርስቲያንን አዋኪ፣ ችግር ፈጣሪ ነው የሚሆኑት፡፡ ብየው ነበር፡፡ ያልኩት አልቀረም ሰውየው ማሰብ ማገናዘብ የሚባል ነገር የሌላቸው አቅለ ቀላል ተኩላነታቸውን ማሳየት ሲጀምሩ ብዙም አልቆዩም ነበር፡፡
ከሦስት ሳምንታት በፊት ባለፈው ወር ሚያዚያ 23 ቀን የማኅበረ ቅዱሳን የጥናትና ምርምር ክፍል የአድዋን ድል አስመልክቶ አንድ ያዘጋጀው ዝግጅት ነበር፡፡ በዝግጅቱ ሁለት ጥናት አቅራቢዎች ጥናታቸውን እንዲያቀርቡ ተደርጎ ነበር፡፡ አንደኛው በጎንደር ዩኒቨርስቲ የታሪክ መምህር ሲሆኑ ሌላኛው እዛው ከማኅበሩ ነበሩ ያቀረቡት፡፡ጥናት አቅራቢዎቹ በተሰጣቸው ርእሰ ጉዳይ ላይ በጥሩ ሁኔታ ጥናታቸውን አቅርበዋል፡፡
• የቅኝ ገዥዎችን ቅኝ የመግዛት ፍላጎት ሊፈጥሩ የቻሉ ምክንያቶች
• የቅኝ ገዥዎች ዓላማና ፍላጎት
• የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ነጻነታችን ላለማስደፈር ለመጠበቅ ያደረጉት ተጋድሎ
• የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አስተዋጽኦ በአድዋ ድል ላይ
በሚሉ ነጥቦች ላይ ባላቸው አጭር ጊዜ ጥሩ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ጥናት አቅራቢዎቹ ጥናታቸውን ካቀረቡ በኋላ ከታዳሚው ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀረቡና ምላሽ እንዲሰጡም ተደርጎ ነበር፡፡ በርከት ያሉ ታላላቅ ሰዎች ግሩም ግሩም የሆነ የየራሳቸውን ሐሳብ አስተያየት ሰጥተው ነበር፡፡ ከጥያቄዎችና አስተያየቶች በኋላም እኔ አንድ ያስተላለፍኩት ማሳሰቢያ ነበር፡፡ ማሳሰቢያውም በወቅቱ ያልታወሱኝን አኃዞች ጨምሬበት ይሄንን ይመስል ነበር፡-
““ እኛ ኢትዮጵያዊያን ነጻነታችንን ለመንጠቅ የተደረጉብን ተደጋጋሚ የጠላት ወረራዎች ጦርነቶች ውጊያዎች ተደርገው ተፈጽመው ነገር ግን ሳይሳኩ ቀርተው ከሽፈው ያለፉ ያበቃላቸው ውጊያዎች ጦርነቶች ወረራዎች እንደሆኑ ማሰባችን ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈለን ነው፡፡ ይህ አስተሳሰባችን ልናደርገው የሚገባንን መከላከልና የመልሶ ማጥቃት ዝግጅት እንዳናደርግ አድርጎ እያስማረከን ውድ ዋጋም እያስከፈለንም ይገኛል፡፡

የአድዋውም ሆነ የኋለኛው የማይጨው ጦርነቶች ያኔ ተፈጽመው ያለቁ አይደሉም! እስከአሁንም የቀጠሉና ግባቸውን እስኪመቱ ድረስም ወደፊት የሚቀጥሉ ናቸው፡፡ እርግጥ ነው የሚጮህ የመሣሪያ ድምፅ የለም፡፡ ጦርነቱ ግን ተጧጡፎ ቀጥሏል እየተሸነፍንባቸውም ነው፡፡

በዚህም ምክንያት እንደምታዩት በአሁኑ ሰዓት እኛ ኢትዮጵያዊያን እንደ አንድ ሀገር ሕዝብ ሁሉ በሀገር ጉዳይ ላይ የጋራ መግባባትና የጋራ ጥቅም እንዳይኖረን አድርገውናል፡፡ ሌላው ቀርቶ ዓለም በሚያደንቀውና በቅኝ ገዥዎች በተገፉ የዓለም ሕዝቦች ዘንድ በከፍተኛ ደረጃ አክብሮት በተቸረውና በሚደነቀው በዚህ እያከበርነው ባለነው የአድዋ ድል እንኳን አንዳይነት የሆነ አመለካከትና አስተሳሰብ እንዳይኖረን አድርገውናል፣ በሀገራችን ታሪክ እሴቶች ማንነት ጉዳይ ላይ ምንቅርቅራችንን አውጥተውት ብዙዎቹን በሀገር ታሪክ ማንነት እሴቶች ላይ በጠላትነት እንዲሰለፉ ማድረግ ችለዋል፣ ከገዛ ዩኒቨርስቲዎቻችን (መካናተ ትምህርት) የታሪክ ትምህርት እንዲሰረዝ ማድረግ ችለዋል፣ የሀገሪቱን ሕልውና በቋፍ እንዲሆን አድርገዋል ሌላው ቀርቶ የሚገርማቹህ ነገር ለየካቲስ 12 የሰማእታት መታሰቢያ የቆመውን ሐውልት ገላጭ አካላቱን ሁሉ እያወላለቁ እየሸራረፉ አጉድለውታል አበላሽተውታል እዚህ ድረስ ወርደው ነው ሥራቸውን እየሠሩ ያሉት፡፡

በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ከሁለት አቅጣጫ (ከቤተ ክህነትና ከቤተ መንግሥት) እየተሰነዘረ ያለው ጥቃትም የዚህ ጦርነት አንዱ አካል ነው፡፡ የእነዚህ ጥቃቶች የማዘዣ ማዕከላት የሮማ ቤተመንግሥትና የቫቲካን ቤተክህነት ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በጣሊያን ወረራ ከባድ ኪሳራ ደርሶባታል፣ ከባድ ዋጋ ከፍላለች፣ከሁለት ሽህ በላይ አብያተክርስቲያናት እንዲቃጠሉ ተደርጓል፣ በገዳማቶቿ የነበሩ ከዐሥር ሽህ በላይ መነኮሳቷ በፋሽስት ጣሊያን ወታደሮች በጥይት ተደብድበው ወይም በሰይፍ ተቀልተው እንዲገደሉ ተገርገውባታል በቁጥር ከሚታወቁት ውስጥ መጥቀስ ቢያስፈልግ በደብረ ሊባኖስ 732፣ በማኅበረ ሥላሴ 515፣ በደብረ ዳሞ 2116፣ በዝቋላ 211፣ በመርጦለማርያም 363፣ በአሰቦት 91፣ በአዲስ ዓለም 143፣ በምድረከብድ 60 ያለቁ ሲሆኑ የነበሩባቸው ገዳማትም በፋሽስቱ ወታደሮች ተመዝብረዋል ተዘርፈዋል፣ ቁጥራቸው ከማይታወቁት ደግሞ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው በጣና ሐይቅ ገዳማት የነበሩ መነኮሳት፣ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሚከበርበት ወቅት በተለያየ ቦታ በአውሮፕላን (በበረርት) ቦምብ (ፈንጅ) ዘንቦበት ያለቀው ሕዝብ ለምሳሌ በጎጃም ደብረ መዊዕ ወዘተረፈ.
ከሁሉም ደግሞ ቤተክርስቲያንን የጎዳት ካለቁት አባቶች ውስጥ ቤተክርስቲያን እስከዛሬ ልትተካቸው ያልቻለቻቸው ወደፊትም ይተካሉ ተብለው የማይታሰቡ ሊቃውንቶቿ በተሸከርካሪ እየተጎተቱ፣ በጥይት እየተደበደቡ፣ በሰይፍ እየተቀሉ አረመኔያዊ በሆነ ሁኔታ ተፈጅተው እንድታጣቸው መደረጉ ነው፡፡

ቫቲካን በሰጠችው ቡራኬ በተፈጸመው የግፍ ወረራ ይህ ሁሉ ግፍ እንደተፈጸመ ስለሚታወቅ እንዲሁም ቅዱስ ቃሉ “ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው? ክርስቶስስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው? ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው?” 2ኛ ቆሮ. 6፤14 በሚለው ሐዋርያዊ ግዝት፣ ከዚያም በኋላ እነ ዲዮስቆሮስ ቄርሎስና አትናቴዎስ ታላላቅ የቤተክርስቲያን መሪዎችና ሌሎችም ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ባስተላለፉት ግዝት ምክንያት የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ከቫቲካን ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት አልነበራትም፡፡

ከሁለት ዐሥትት ዓመታት ወዲህ ግን መጀመሪያ አባ ጳውሎስ አሁን ሰሞኑን እንዳያቹህት ደግሞ አባ ማትያስ ከዚህች እጇ በዐሥር ሽዎች በሚቆጠሩ ንጹሐን ዜጎቻችን ደም ከተጨማለቀ የቫቲክን “ቤተክርስቲያን” ጋር ቅዱስ ቃሉን እንዲሁም የእነ ቅዱስ ዲዮስቆሮስን ቅዱስ ቄርሎስና ቅዱስ አትናቴዎስን እንዲሁም የሌሎችን ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንን ግዝት በመተላለፍ ዓላማውና ተልዕኮው ግልጽ ያልሆነ ግንኙነት መሥርተው ድብቅ የጥፋት ሥራቸውን ሲሠሩ ቆይተዋል እየሠሩም ይገኛሉ፡፡ ጭራሽም አባ ማትያስ በአደባባይ “እኛና ካቶሊኮች ልዩነት የለንም!” እስከማለት መድረሳቸው የሚታወቅ ጉዳይ ነው፡፡

በነዚህ ነውረኛ ግለሰቦችና አባሪዎቻቸው ተግባርም ቤተክርስቲያን ጥቅሟን እንድታጣ፣ ክብሯ እንዲደፈር፣ ያለቁ የንጹሐን ደም ደመ ከልብ ሆኖ እንዲቀር ተደርጓል፣ አስተምህሮዋ እየተቆነጻጸለ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በታሪኳ የገዛ አባቶቿ ናቸው በሚባሉ ግለሰቦችና ቡድኖች ክህደት ሲፈጸምባት ይሄ ክህደት የመጀመሪያው ነው፡፡
ቤተክርስቲያን በቫቲካን ቡራኬ በተፈጸመው ወራራና በአምስት ዓመቱ የወረራ ወቅትም በካቶሊክ ካህናት ለተፈጸመባት አረመኔያዊ ግፍና በደል ይቅርታ አልተጠየቀችም፣ ካሳም አልተከፈላትም፡፡ ይህ ባልተፈጸመበት ሁኔታ ከላይ የጠቀስኳቸው የቤተክርስቲያን መሪዎች አስቀድሞ የቅዱሳን አባቶች ግዝት ያለ በመሆኑና ቅዱስ ቃሉም ስለሚከለክል የእኛ ቤተክርስቲያን ቫቲካንን እንደ አቻ ቤተክርስቲያን ቆጥራ ልትመሠርተው የምትችለው ምንም ዓይነት ግንኙነት ባይኖርም እንደ ማንኛውም ተቋም እንኳን ቆጥረን እውቅና ሰጥተን ግንኙነት የመሠረትን ቢሆንም እንኳን ሀገርንና ቤተክርስቲያንን ውርደት ለማሸከም ታስቦ ካልሆነ በስተቀር ለቤተክርስቲያንም ሆነ ለሀገር ምንም ዓይነት አግባብነትና ጠቀሜታም የለውም፡፡

ሰዎቹ በመግለጫቸው ግልጽ እንዳደረጉልን ግንኙነቱ የተፈጸመው የቤተክርስቲያናችንን ግዝት በመተላለፍ የአቻ ላቻ ግንኙነት እንደፈጠሩ ነው ያስታወቁት፡፡ ሥጋታችንም ይሄ ነው፡፡ ግዝት ከመጣሱም በላይ ዕድሜ ዘመኗን ይህችን ቤተክርስቲያን ለማጥፋት ያልጣረችው የጥረት ዓይነት ከሌላት የጥፋት አካል ጋር ምን የሚያገናኝና የሚያወዳጅ ጉዳይ ኖሮ ነው ግንኙነቱ የተመሠረተው? የዓላማ አንድነት ከሌለ በስተቀር! ይሄም ግልጽ ሆኗል “እኛና ካቶሊክ ልዩነት የለንም!” በሚል ተገልጾ፡፡

እጅግ የሚገርመው ነገር ይሄ ሁሉ ሲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ ተብየው በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም ያለው ነገር አለመኖሩ ነው፡፡ ይህ ዛሬ በጨረፍታ በፈራ ተባ የተነገረ ቃል ነገ በይፋ በድፍረት መነገሩ የማይቀር መሆኑ ነው አሳዛኙ ዜና፡፡ ያኔ እንደ ማኅበረ ቅዱሳን ያሉ ተቋማት አስቀድመው እንዲጠፉ ካልተደረገ በስተቀር ታላቅ እንቅፋት የሚሆኑ በመሆናቸው ነው ከወዲሁ የግድ ማኅበረ ቅዱሳንን ማጥፋት እንዳለባቸው አምነው ታጥቀው የተነሡት፡፡ ለዚህም ነው ከላይ “በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ከሁለት አቅጣጫ (ከቤተ ክህነትና ከቤተ መንግሥት) እየተሰነዘረ ያለው ጥቃትም የዚህ ጦርነት አንዱ አካል ነው፡፡ የእነዚህ ጥቃቶች የማዘዣ ማዕከላት የሮማ ቤተመንግሥትና የቫቲካን ቤተክህነት ናቸው” ስል የገለጽኩት፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን ይሄንን የሚያውቅ ይመስለኛል፡፡ የሚያውቅ ከሆነ የጦርነቱን ክብደትና ውስብስብነት በሚገባ በተረዳ መልኩ እየደረሰብን ያለውን ውጊያና ጥቃት ለመመከት በሚያስችል በቂ ዝግጅት ጥንካሬና ብቃት መሰለፍ እንችል ዘንድ ያለውን የተጋፈጥነውን ችግር ለሕዝበ ክርስቲያኑን አሳውቆ ያለብንን ጦርነት እንድንመክት የሚያስችል ዝግጅት እንዲያደርግና እንዲያሰልፈን አጥብቄ ማሳሰብ እወዳለሁ”” በማለት ነበር ማሳሰቢያውን የተናገርኩት፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን ጥርስ ውስጥ የገባው አሁን አይደለም፡፡ “ለምን?” ለሚለው ጥያቄ በየመድረኩ የወያኔ ካድሬዎች የሚናገሩት “በሀገሪቱ የአንድነት ኃይል የሆነ መኖር አይችልም!” የሚል ሕግ ያለ ይመስል ካድሬዎቹ የሚናገሩት “ማኅበረ ቅዱሳን የአንድነት ኃይል (አንድነትን የሚሰብክ) ስለሆነ ነው እንዲጠፋ የምንፈልገው እንዲኖር የማንፈቅደው!” የሚል ነው፡፡ አያይዘውም “የአንድነት ኃይል ከሆኑት በፖለቲካው (በእምነተ አሥተዳደሩ) መስክ ያሉትን በሙሉ አዳክመናል ሰብረናል በትነናል፡፡ ከአንድነት አቀንቃኞች የቀረን ማኅበረ ቅዱሳን ብቻ ነው እሱን ሳንበትን ሳናጠፋ እንቅልፍ አንተኛም!” ሲሉ ይደመጣሉ፡፡

በእርግጥ እንዳሉትም ወያኔ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ጥርሱን የነከሰበት ምክንያት ይሄ ሊሆን ይችላል፡፡ ብቸኛው ምክንያት እንዳልሆነ ግን እርግጠኛ ነኝ፡፡ የቫቲካንና የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ግንኙነት እንዲፈጥሩ ትዕዛዝ ሰጥቶ እያስፈጸመ ያለው አገዛዙ እንደሆነ በግልጽ ይታወቃልና፡፡

በዛም ሆነ በዚህ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ እየተሰነዘረ ያለው ጥቃት ምንጩ ከምዕራቡ ዓለም ዕኩያን እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ “ማኅበረ ቅዱሳን ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሕግ ሥርዓትና ቀኖና መጠበቅ፣ ትውፊቶቿን እንዳይጠፉ ጠብቀው ለያዙት የአብነት ትምሕርት ቤቶች ህልውና ቀጣይነት የጸና አቋም ስላለውና አንዳች ነገር ብሎ ሕዝብ እንዲቃወም ለማድረግ ቢፈልግ ተደማጭነት ስላለው እሱ ባለበት ሁኔታ ምንም ዓይነት ሥራ ልንሠራ አንችልም!” የሚል ግንዛቤ ወስደዋል፡፡

ማኅበሩ እየደረሰበት ያለውን መከራ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ይፋ ሳያደርግ ብዙ ተቀጥቅጧል፡፡ ይፋ አለማድረጉና ዋጋ እየከፈለበት ያለበት ጉዳይ ባለቤት ሕዝበ ክርስቲያኑ መሆኑን ለሕዝበ ክርስቲያኑ አለማሳወቁ ብዙ ዋጋ እያስከፈለው ይገኛል፡፡ ብዙ ከመቀጥቀጡ የተነሣም ዝሏል፡፡ ከመዛሉ የተነሣም በርካታ ዕንቁዎቻችንን ከእጁ ጥሏል፡፡

ለምሳሌ ለቤተክርስቲያን ከንዋዬ ቅድሳት የመጀመሪያው የሆነውን ዘፍ. 9፤9-17 መንግሥት ከቤተክርስቲያን ወስዶ የሀገሪቱ ሰንደቅ ዓላማ ያደረገውን ትእምርተ ኪዳኗን (ሰንደቅ ዓላማዋን) እንዲጥል እንዲተው ተደርጓል፣ እንደ “አንድ ሃይማኖት! አንዲት ጥምቀት! አንድ ጌታ!” ኤፌ. 4፤5 እና “ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ” ይሁ. 1፤3 ያሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን እንዳይጠቀም ተደርጓል፣ ቤተክርስቲያን ለዚህች ሀገር ባለ አደራ እንደመሆኗና የሀገርንና የሕዝብን አንድነት መስበክ ዐቢይ ተግባሯና ከሐዋርያዊ ተልእኮዋ አንዱ በመሆኑ ማኅበሩ የሀገር አንድነትን በሚሰብክበት ጊዜ “ፖለቲካ ነው በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም ማለት አትችሉም!” እየተባለ ሊገናኙ የማይችሉ ነገሮች በግድ እየተገናኙ የሀገረ እግዚአብሔርን አንድነት እንዳይሰብክ በማዕቀብ ታስሯል፣ በወያኔ ካድሬ መሞላቱን እያየ ይሄም ለህልውናው አደጋ መሆኑን እያወቀ በዝምታ እንዲመለከት ተደርጓል ወዘተረፈ.

እነ አባ ማትያስና ይሄንን ዕኩይና ሰይጣናዊ ተልእኮ አንግበው አብረው እየተንቀሳቀሱ ያሉት መናፍቃኑ ግን “ለምንድን ነው ማኅበረ ቅዱሳንን እንዲህ ጠምዳቹህ የያዛቹህት እሱን ሳናጠፋ አንተኛም! የሚያሰኛቹህ ቤተክርስቲያንን ምን ስለበደለ ነው?” ብለው “ቤተክርቲያንን እንዲህ እንዲህ አድርጎ ስለበደለ!” ብለው ሊጠቅሱት የሚችሉት አንዲትም ምክንያት ሊናገሩ አልቻሉም፡፡ ይሄም በመሆኑ ነው የማኅበሩ አመራር “ጥፋታችን ምንድን ነው? እባክዎን ያነጋግሩን?” ብሎ አባ ማትያስን ለማነጋገር በተደጋጋሚ ላቀረበው ተማጽኖ ያዘለ ጥያቄ በጎ ምላሽ ሊያገኝና ሰውየውን ለማናገር ዕድል ሳያገኝ የቀረው፡፡

ሰውየው ከመናፍቃኑ ጋር ግንባር ፈጥረው ይሄንን ሁሉ ጥቃት ሲፈጽሙ ለአንድም ጊዜ እንኳን “የሲኖዶሱን” ይሁንታና ፈቃድ ሳያገኙ እንዲያውም “የሲኖዶሱን” ወይም የቤተክርስቲያንን አቋም ዓላማና ጥቅም በተጻረረ መልኩ ነው ይሄንን ሕገ ወጥና ሥርዓት አልበኝነት የተሞላበት የውንብድና ድርጊት እየፈጸሙ ያሉት፡፡
ይሄም ምንን ያሳያል የዚህ የጥቃት ተልእኮ ፍላጎትና ትእዛዝ ከቤተክርስቲያን ውጪ መሆኑንና ባለቤቱ እራሳቸው አለመሆናቸውን ትእዛዝ ፈጻሚ መሆናቸውን ያሳያል “ትእዛዝ ሰጪውና የጥፋት ዓላማው ባለቤት ማን ነው?” የተባለ እንደሆን የጋራ ጥቅም ያስተባበራቸው መናፍቃኑና ወያኔ ናቸው፡፡

እንግዲህ ያለው ሀቅ ይሄ ነው፡፡ ሕዝበ ክርስቲያኑ ቤተክርስቲያን የተጋፈጠችውን አደጋ ጠንቅቆ በመረዳት አደጋውን ሊያከሽፍ በሚችል ደረጃ እራሱን አዘጋጅቶ እንቅስቃሴ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳንን ለማፍረስ ለማጥፋት የሚወሰድን ማንኛውም ዓይነት እርምጃ በቸልተኝነት ተመልክተን በዝምታ ለማሳለፍ ከፈቀድን ግን ያለ ምንም ጥያቄና መልስ ይህችን ቤተክርስቲያን ካቶሊካዊትና ፕሮቴስታንታዊት እንድትሆን ፈቀድን ማለት እንደሆነ እያንዳንዱ ክርስቲያን ጠንቅቆ ሊውቅ ይገባል፡፡
እኛ ምእመናን ከግብጽ ቤተክርስቲያን ምእመናን ልንማረው የሚገባ አንድ ተቃሚ ተሞክሮ አለ፡፡ በአምስተኛው መቶ ክ/ዘ እንደኛ ዓይነት ችግር ገጥሟቸው ነበር፡፡ የቁስጥንጥንያው ንጉሥ መርቅያንና የሮማው ፓፓ ተማክረው ፓትርያርካቸውን ዲዮስቆሮስን አንሥተው አሰሩትና ፕሮቴሪየስ የተባለ የራሳቸውን ሰው ፓትርያርክ አድርገው ሾሙላቸው፡፡ ምዕመናን አንቀበልም ብለው አባረሩት፡፡

መርቅያን በምእመናን ምላሽ ተቆጥቶ ሁለት ሽህ ያህል ሠራዊት ላከባቸውና በግድ እንዲቀበሉ ለማድረግ ጥረት አደረገ ምእመናን ግን ቁጣቸው አይሎ በተፈጠረው ሁከት አዲስ የተሾመው ፓትርያርክ ተገደለ፡፡ በዚህም መሀል ዲዮስቆሮስ በእስር እንዳለ አረፈ፡፡ ለሦስት ዓመታት ያህል መንበሩ ክፍት ሆኖ ከቆየ በኋላ እራሳቸው ምእመናኑ ጢሞቴዎስን ሾሙት፡፡ እሱም ጥሩ አባት ሆኖ አገለገላቸው፡፡ የታወከችው ቤተክርስቲያንም ተረጋጋች፡፡ እኛ ግና እራሳችንን ወደን ለሥጋችን አድልተን ቅድስት ቤተክርስቲያንን ለጭራቆች አሳልፈን ሰጠን፡፡ ከእንግዲህ ግን ቢበቃስ?

ሕዝበ ክርስቲያኑ አስቀድሞ በአባ ጳውሎስ አሁን በአባ ማትያስ እየተደረገ ያለውን የእብደትና የጠላት ሥራ ማመን ተቸግሮ በሰፋ ትዕግሥት ማሳለፉ ቤተክርስቲያንን በርካታ ዋጋ እያስከፈለ ሰዎቹንም ለመለጠ ድፍረትና የዕብደት ሥራ እያበረታታ ይገኛል፡፡ ይህ ሁኔታ በዚህ መቀጠል የለበትም!

ለዚህች ሀገርና ሕዝብ ተቆርቋሪ ቤተክህነትና ቤተ መንግሥት በዚህች ሀገር ቢኖር ኖሮ ትውልዱ እንዲህ በሱስ ማጥ ውስጥ ሰምጦ ሀገር ተረካቢ ትውልድ አጥታ በመከኑ ዜጎች እየተሞላች እየከሰረች ባለችበት ዘመን ከማንም ምንም ሳይጠብቁ በራሳቸው መዋጮ ማኅበር መሥርተው ሀገራዊና ሃይማታዊ የዜግነት ግዴታቸውን ለመወጣት የሚታትሩ የተማሩ ወጣቶች ማኅበር በዚህች ሀገር መኖሩ ጮቤ ሊያስረግጣቸው ሊያስደስታቸው ሊያረካቸው ምን እንርዳቹህ? በምን እንደግፋቹህ? ሊያሰኛቸው እንጅ ሊያበሳጫቸው ሊያስከፋቸው እንዴት አድርገን? ምን አሳበን? ባጠፋናቸው ሊያሰኛቸው ባልቻለ ነበር፡፡ አእምሮ ቢኖራቸው ማሰብ ቢችሉ ማኅበረ ቅዱሳን በቢሊዮኖች (በብልፎች) የሚቆጠር ብር ቢፈስ ሊገነባ የማይችል የሀገር ሀብት መሆኑን መረዳት በቻሉ ነበር፡፡

እንግዲህ ውሳኔው የሕዝበ ክርስቲያኑ ነው፡፡ ኧረ ባያድለን እንጅ እንደዜጋ የሌላውም ዜጋ ጉዳይ ነበር፡፡ ሕዝበ ክርስቲያን ሆይ! ቤተክርስቲያንንና ሀገርህን ለዚህች ሀገርና ሕዝቧ ጥንተ ጠላቶች ለባዕዳንና ለተቀጣሪ ባንዶች አሳልፈህ ሰተህ ታስበላታለህ ወይስ እንደ እናት አባቶችህ ዋጋ ከፍለህ ትታደጋታለህ?
እስኪ እባካቹህ በሀገሩ የምትታፈሩ የምትፈሩ ታላላቅ ሰዎች አረጋዊያን ሽማግሎች ካላቹህ ቤተክህነቱንም ሆነ ቤተ መንግሥቱን “ማኅበረ ቅዱሳን እንዲጠፋ ያስፈረደበት የተላለፈው በሕግ የሠፈረ ወንጀሉ ምንድን ነው?” ብላቹህ እስኪ ጠይቁ እባካቹህ!፡፡ እኛ ዜጎች ሀገራችንን ሕዝባችንንና ቤተክርስቲያናችንን እንዳናገለግል “አትችሉም!” የማለት መብትና ሥልጣን ያለው ማንና እንዴትስ ሆኖ? በምንስ ምክንያትና በየትኛውስ ሕግ ነው? ቤተክርስቲያንና ሀገር የሕዝብ ሆነው ሳለ እንደግል ንብረቱ ቆጥሮ ከቤተክርስቲያንና ከሀገር ጥቅም በተጻራሪ ለግል ጥቅሙ ሲል ሕገ ወጥና ሥርዓት አልበኝነት የተሞላ የግፍ ድርጊት እየፈጸመ እንዲፋንንብን መብት የተሰጠው ማንና ከማንስ ነው? ይሄንን ዓይን ያወጣ ግፍና በደልንስ ሕዝብ እንዴት ነው ሊታገስ የሚችለው???

ልዑል እግዚአብሔር የዚህችን ሀገርና ቤተክርስቲያን ሰላምና ደኅንነት ይመልስልን!!! ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com

የህወሓት አገዛዝ የ24ኛ ክፍለ ጦር በርካታ ወታደራዊ አዛዦችን በቁጥጥር ስር አዋለ

$
0
0

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ) ከሰሞኑ በቁጥጥር ስር ከዋሉት በርካታ የህወሓት የጦር መኮንኖች መካከል ኮሎኔል ባምላኩ እና ሻለቃ ተካ የተሰኙት ይገኙበታል፡፡ህወሓት የ24ኛ ክፍለ ጦር አዛዦችን እየለቀመ ያሰረው በክፍለ ጦሩ ውስጥ በተፈጠረው ውስጣዊ አለመተማመንና ጥርጣሬ መሆኑ ታውቋል፡፡
clash
ከታሰሩት የህውሓት የጦር መኮንኖች መካከል ስሙ ከላይ የተጠቀሰው ኮሎኔል ባምላኩ ከዚህ ቀደም በ2007 ዓ.ም ከመተማ እና አካባቢው 9 ወጣቶችን በቁጥጥር ስር በማዋል ሁመራ ወደሚገኘው በመቶ አለቃ ይስሃቅ የሚመራ የዚሁ የ24ኛ ክፍለ ጦር ክፍል የሆነ ገዳይ ቡድን በማስረከብ ተረሽነው አስከሬናቸው በተከዜ ወንዝ አቅራቢያ እንዲቀበር ያደረገ ጨፍጫፊና ወንጀለኛ ነው፡፡

አርቲስት ዳንኤል ተገኝ ተፈረደበት |ሙሉ የፍርድ ቤት ትዕዛዙን ይዘናል

$
0
0

Daniel

(ዘ-ሐበሻ) በመዝገብ ቁጥር 234974 በልደታ ምድብ አምተኛ ፍትሃብሔር ችሎት ሲታይ የቆየው ወ/ሮ ፍሬሕይወት ኃይሉ በአርቲስት ዳንኤል ተገኝ ላይ የመሰረቱት ክስ እልባት አገኘ:: ፍርድ ቤቱ አርቲስት ዳንኤል የወሰደውን ገንዘብ እንዲመለስ ት ዕዛዝ ሰጥቷል::

ፊልም እስራለሁ ብሎ ገንዘብ ወስዶ ፊልሙንም ሳይሰራ ገንዘቡንም ሳይመልስ ቀርቷል በሚል ክስ የቀረበበት አርቲስት ዳንኤል በ24/11/2007 ዓ.ም በተደረገ የገንዘብ ውል ስምምነት 75 ሺህ ብር መውሰዱና በ15 ቀን ውስጥ ገንዘቡን ለመመለስ ፈቃደኛ አለመሆኑን ፍርድ ቤቱ በፍርድ ት ዕዛዝ ላይ ጽፏል::

ዘ-ሐበሻ በደረሳት የፍርድ ት ዕዛዝ መሰረት መረዳት እንደተቻለው አርቲስቱ በቀረበበት ክስ ምንም ዓይነት መከላከያ አላቀረበም:: በዚህም መሰረት ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ አድርጎ በይኖበታል:: በዚህም መሰረት ከ75 ሺህ ብሩ በተጭርማሪ ከሳሽ ለዳኝነት የከፈሉትን 2600; ለቴምብር ቀረጥ የተከፈለውን 10ብር እንዲሁም ለጥብቅና አገልግሎት ጉዳዩ ከወሰደው አጭር ጊዜ አክይያ በጥብቅና አገልግሎት ውሉ ላይ የተመለከተውን መጠን በማሻሻልክስ ከቀረበበት ገንዘብ 9% ብር 6750 አርቲስቱ ለከሳሽ እንዲከፍል ታዟል::

ሙሉ የፍርድ ቤት ትዕዛዙን ይዘናል ያንብቡት
daniel1

daniel 2

daniel3

daniel 4

ፈርዖናዊው የወያኔ አገዛዝ በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ሲደገም ምን ይመስላል?

$
0
0

19 መጋቢት2008 /

በ24 አመታት ውስጥ በተለያዩ የኢትዮጵያ አከባቢ ጥቂት የሚባሉ መልካም ለውጦች ቢኖሩም እንኳ ጀግናው የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ አይደለም የመልካሙን ለውጥ ሊያጣጥም እንዲያውም በተቀነባበረ ሁኔታ የዛሬ 24 አመት ከነበረበት የህልውናና  ኑሮ ብዙ እጥፍ አሽቆልቁሎ ተምዘግዝጎ ወርዶበታል፤ ወያኔ አሰቃይቶታል፤ ህይወቱና አኗኗሩ አመሰቃቅሎበታል፤ ለብዙ መከራና ስቃይ ሞትና እንግልት መታሰርና ደብዛ መጥፋት መሰደድና መሸማቀቅ ዳርጎታል። የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ከ1972 ጀምሮ የወያኔ መርዝ የተርከፈከፈበት ህዝብ ነው። አሳዛኙ ነገር ወያኔ የፈጠረው ችግር በሁሉም የኢትዮጵያ መርዙን ከመትፋቱ ጋር ተያይዞ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ወገኑ የየራሱን ህመም ሲያዳምጥ ስለኖረ ከህመም ሁሉ ህመም፣ ከእልቂት ሁሉ እልቂት ሲፈጸምበት፣ በእስራኤላውያን ላይ በኦሽዊትስ ካምፕ በናዚዎች የተቀነባበረው የዘር ማጥፋት በ21ኛው መ.ክ.ዘ በወያኔዎቹ በግልጽና በድብቅ ሲደገም የሚዲያ ሽፋን ስለማይደርሰው ኢትዮጵያዉያን ወገኖቹ ሊያውቁለትና ሃይ ሊሉት አልቻሉም መከራዉን ከ1972 አ/ም ጀምሮ ወገኖቹ ሳይደርሱለት ብቻውን ሲጎነጭ ኖሯል።

Wolqite News

እዚህ ላይ ለማሳሰብ እምፈልገው ዋና ነጥብ  በአማራነታችን እየደረሰብን ያለው የዘር ማጥፋት ዘመቻ ህወሃት በመልካም አስተዳደር ስም ለማስተባበል መሞከር በፍጹም አይቻልም፤   የመልካም አስተዳደር ችግርማ አሜሪካም ውስጥ ቢሆን ይኖር ይሆናል። እኛ አንደላቃችሁ አኑሩን አይደለም እያልን ያለነው። ዋናው ጥያቄያችን የወልቃይት ጠገዴ ህዝብና መሬት አማራ ስለሆነ ወደ እናት አገራችን ወደ ጎንደር ወደ አማራነታችን መልሱን የሚል ነው። ሰላምን ፈልገው ከመለሱን እጅግ ደስ ይለናል ካልሆነ ደግሞ የእነርሱ ፈቃድና ምስክርነት ሳያስፈልገን በራሳችን ራሳችንን አማራነታችንን አስረግጠን እንመልሳለን።በቃ ይሔው ነው!!! ይህ በትግራይ ተስፋፊና ነጻ አውጭ ቡድን፣ በትግራይ ፖሊስ፣ በትግራይ ልዩ ሃይል፣ በአጋዚ ወታደር፣ በትግራይ አስተዳደር አመራሮችና ካድሬዎች ማዳፈን የማይቻል የሚፋጅ ረመጥ ጥያቄ ነው።

የኢትዮጵያ ወገኖቻችን ሆይ ታሪክ የሚመሰክረስው እውነት የወልቃይት ጠገዴ ህዝብና መሬት የአማራ እንጂ የትግሬ ሆኖ እንደማያውቅ እንድታውቁሉን ነው። የታሪክ  መዛግብት ከሚመሰክሩት እውነት በተቃራኒ ታሪኩን በማዛባት እንደማጣቀሻ ከሚያቀርቡ የትግራይን ህዝብ ከማይወክሉ የወያኔ ባንዳ የሆኑ የታሪክ ሙሁር ነን ባዮች ለምሳሌ እንደ ዶክተር  ገላውዲዮስ ያሉ የውሸት ታሪክ አጣቃሾች ታሪክ ይፋረዳቸዋል። በነገራችን ላይ ገላውዲዮስ በትግሬኛ የአሜሪካን ድምጽ ሬድዮ ቃለ ምልልስ ሲያደርጉ ያጣቀሱት መጽሓፍ መጽሓፉ ከሚለው በተቃራኒ ስለሆነ ክስ ለመመስረት  ዲግሪያቸውን ለማስነጠቅና ሌላም ህጋዊ ቅጣት እንዲወሰድባቸው ሙሁራኖች እየሰሩ ነው። በዉሸት የህዝብን ጥያቄ አዳፍኖ ዘሩን መጨረስ እንደማይቻል ሊማሩ ይገባቸዋል እነዚህ ከንቱና ጠፊ ዘራፊዎች።  ሌላው የተማረ ኢትዮጵያዊ  ያለ የማይመስላቸው ጠባቦቹና ዘረኞቹ የትግራይን ምስኪን ህዝብ የማይወክሉ ወረበሎች የኢትዮጵያ ህዝብ በቃችሁ ሊላቸው ይገባል። በዚህ አጋጣሚ የታሪክ እውነተኛ ሙሁር አቻምየለህ ታምሩን ስለሚያደርጉት የውሸተኞች ካድሬ ሙሁሮችን ሴራ ማጋለጥ በእጅጉ የወልቃይት ጠገዴ  ህዝብ ልባዊ ምስጋና እንዳስተላልፍላቸው ይፈቀድልኝ። እንዲሁም ክቡር ልኡል ራስ መንገሻ ስዩም፣ክቡር አቶ ገብረመድህን አር አያ፣ ክቡር አቶ ያሬድ ጥበቡንና ሌሎች ውድ  የኢትዮጵያ አንድነት የሚገዳቸውና አጥብቀው የሚሰሩ እውነተኛ  ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ  አብዛኛው ሙሁር በወልቃይት ጠገዴ ዝምታውን መርጦ  የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ህዝብ እንደበግ ለመታረድ ወያኔ የውሸት ታሪክን እንደቅመም እየተጠቀመበት ባለበት ስአት እውነተኛ ቃላቸውን ስለሰጡ በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ልዩ ምስጋናየን አቀርባለሁ። ሌሎች ሙሁራን ተሳትፎ እንዲያደርጉ አሁንም ህዝቡ የግረሱልኝ ጥሪውን በማስተጋባት ላይ ነውና እባካችሁ ድረሱልን።ተሳትፎ ያደርጋችሁ ሙሁራንም  ሳይለየን የአገራችን ህግ በወያኔ ምክንያት ካልዳኘን ወደ አለማቀፍ ህግ ጉዳያችን ወስዳችሁ ከሞት እንድትታደጉን እርዳታችሁ እንዳይለየን በእግዚአብሔር ስም አደራ እንላለን።

ወያኔ ይህ ሁሉ ስቃይ የሚፈጸምበት ምክንያት ህዝቡ ፍጹም ኢትዮጵያዊነት የሚታይበት ከዘረግኝነት የጸዳ ኢትዮጵያዊ  ህዝብ ስለሆነ ነው። ይህም  ማለትም እስከቅርቡ ድረስ በኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያየ ብሔር  ያላቸውን ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በአሁኑ ግዜም ቢሆን ለአፍሪካዉያንም  ጭምር ማለትም  ሰሜንም ደቡብም ሱዳናዉያን የመሳሰሉ የአፍሪካ ዜጎችም ሰርተው ህይወታቸውን ቀይረውበት በሰላምና  በፍቅር ደስ ብሏቸው የሚኖሩበት  ከኢትዮጵያዊነቱ  በዘለለ በአፍሪካዊነቱም የማይታማ ህዝብና በጣም ለምና በተፈጥሮ ሃብት በኢትዮጵያ ግንባር ቀደም የሆነ አካባቢ በመሆኑ ዘረኞቹ ወያኔዎችና ትግሬዎቹ የተፈጥሮ ሃብቱን ቋመጡት፤ ኢትዮጵያዊ ስሜቱንም አልወደዱትም። የሚገርመው ነገር ህዝቡን አጥፍተው ‘ታላቂቷን ትግራይ’ በመመስረት ከሱዳንና ኤርትራ ጋር እንዋሰናለን አማራም እናጠፋለን ብለው ተነሱ።  የሚገርመው ነገር ላለፉት 36 አመታት እነርሱ የሚፈጸሙት ስቃይ አላረካ  አልበቃ ብሏቸው በሱዳን ልዩ ሃይሎች ከፍተኛ የአፈናና ግድያ አስፈጸሙበት።  የስንቱ የሃገር ጀግናና የአገር አልኝታ ህይወት ቀጠፉት አስቀጠፉት መሰላችሁ። ጀግናው ህዝብም የሚቻለውን ያህል ታገለ ቢሆንም ግን ወያኔ ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረ ብሗላ ወታደራዊ ሃይሉን አጠናክሮ በመምጣት ቦታውን ተቆጣጠረ ህዝቡንም በተለይም ወንዶችን ልክ እንደፈርዖን እያደነ ማሰር፣ ማሳደድ፣ ማሰቃየትና መዝረፍ ጀመረ በተለይ ከ1983 አ/ም ጀምሮ።

የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ይህ ሁሉ ግፍ፣ መከራና እልቂት ሲጎነጭ፤ ህዝብ እንደህዝብ በመስቀል ሲሰቀል ኢትዮጵያዊያን ወገኖቹም አላወቁለትም። ኢትዮጵያን ለማፈራረስ በተነሳው ገንጣይ የወያኔ ቡድንና ግብረ አበሮቹ ህጻን አዋቂ፣ ወንድ ሴት፣ ገበሬ ነጋዴ፣ቀይ ጥቁር፣ አጭር ርዥም፣ ገጠር ከተማ፣ ሃብታም ድሃ ፣ያገባ ያላገባ፣ ቆላ ደጋ  ሳይለይ ሌት ተቀን ለ24 አመታት በተቀነባበረና ሳይንሳዊ አካሄድ በተሞላበት መንገድ ሞት፣ ስቃይና እንግለት ተፈጽሞበታል። ይህ ሁሉ ሲሆን ግን አሁንም ኢትዮጵያዊያን ወገኖቹ አላወቁለትም፤ ከህመም ሁሉ ህመም ይሉሃል እንዲህ ነው። እ ንዲያውም ከዚህ በተቃረነ መልኩ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ትግሬ አይደለም እንዴ ወያኔ በኢትዮጵያ ህዝብ የሚያደርሰው ስቃይ በሌሎች ብሔር ብቻ አይደለም በእኛ በትግረዎቹ ላይም ይፈጸመዋል ለማለት ፈልጋቹህ ነው?” የሚሉ አንዳንድ ሁኔታውና መሰረታዊ ችግሩ ያልገባቸው ወገኖችም አልጠፉም። በወያኔ የፖለቲካ ሴራ ተጠልፎ መውደቅ ማለት ይሔ ነው። እውነታው ግን ፍጹም እንደዛ አይደለም፤ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ጠለምትም ጨምሮ ትግሬ ሳይሆኑ አማራ ናቸው። ይህ ሁሉ ግፍና የዘር እልቂት የሚፈጸምበት ስለ ሁለት አበይት ምክንያት ነው። እነርሱም፦

1ኛ. የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ የብጌምድር የጎንደር አማራ ህዝብ እንጂ ወያኔና ካድሬዎቹ እንደሚሉት ትግሬ ባለመሆኑ ነው፤ ለዚህም ስለእውነት ይመስከር ቢባል ወያኔና ካድሬዎቹ ጥሩ ምስክር ይሆኑ ነበር። ትግሬም እንዳልሆነ ስለሚያውቁም ነው ይህ ሁሉ የእልቂት ግፍ ለ36 አመት የፈጸሙበታና አሁንም እየፈጸሙበት ያሉት። ሌላኛው ነጥብ ደግሞ ህዝቡ ትግሬ ቢሆን ኖሮ ትግሬነት በራሱ ጥቅም በሚያሰጥበት ወቅት ለምን ታድያ እውነትኛ የትግሬ ማንነቱን ጥሎ አማራነትን ይመርጣል? ለዛውም አማራነት ማለት “ወንጀል” አማራነት ማለት “ሞት፣ ስደትና መፈናቀል” ማለት በሆነበት ስአት፤ በአንጻሩ ደግሞ ትግሬነት ማለት “ቁጥር አንድ ምርጥ ዘር” ሆኖ በስርአቱ በተቆጠረበት ግዜ በዚህም ምክንያት ትግሬነት ማለት “ሃብታምነት፣ምርጥ ዘር፣ የበላይ ገዥ፣ ባለስልጣን” ማለት ሆኖ የተለያየ ጥቅም በሚያስገኝበት ስ አት እንዴት አንድ ህዝብ አማራ ነኝ ትግሬ አይደለሁም ብሎ ይነሳል። ይሔን ጥያቄ አንድ ደረጃ ከፍ እናድርገውና በኢትዮጵያ እውነታው እንዲህ በሆነበት ግዜ ጭራሽ እነርሱ እንደሚሉት እንዴት ትግሬ ሆኖ ሳለ አማራ ነኝ ይላል። አያችሁ ወያኔ በጣም ወንበዴና ህሊና-ቢስ ነው። ህዝቡ  ንጹህ አማራ እንጂ ትግሬ ባለመሆኑ ምክንያት ነው እኔ ትግሬ ሳልሆን አማራ ነኝ ያለው። ይህን ህጋዊ የህዝቡ ጥያቄ በማዳፈን ማለፍ አይቻልም አሁን ማለት ትላንት ማለት ስላልሆነ። የሚደንቀው ባለፈው መጋቢት ሁለተኛው ሳምንት 14ና 15 ላይ በሁመራ አባይ ወልዱና አባዲ ዘሞ ካድሬዎች ሰበሰበው ይህ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ የማንነት ጥያቄ ለማዳፈን 80 ሚሊዮን ብር ወጭ እንዳደረጉና ይህም እስካሁን ድረስ ማስቆም ስላልተቻለ እርምጃ እንደሚወስዱ በድጋሚ በድፍረት ተናገሩ። ተወላጆቹ ካድሬዎቹ ግን ይህን አንመክርም የለንበትም በማለት በድፍረት እዛው ስብሰባው ላይ እቅጩን ነገሯቸው። ህዝብ ለማጫረስ የሚደረግ የድንቁርና ውሳኔ ካልሆነ በቀር የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ በፍጹም ማስቆም እንደማይችሉ ይሔው አረደሗቸው። በአሁኑ ስአት ለሞት ምንም የሚፈራበት ምንም ምክን ያት የለውም መፍራት ካለባቸው በድሎት ያሉት እነርሱ ናቸው፤ እኛማ ለየትኛው ህይወትና ኑሮ ብለን ሞትን እንፍራ?

2ኛ. አንድ ካድሬ በ1984 አ/ም እንዳለው ለታላቂቷ ትግራይ እጅ መንሻ “የወልቃይት ጠገዴ መሬቱና ሴቱ ስለሚፈለግ” ብቻ ነው። ይህም በድብቅ ሳይሆን በየስብሰባ መድረኮች ተናግረው በተግባር ሲፈጸም አይተናል።

በዚህ ጽሑፍ በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ከደረሱት የሰብአዊ መብት ጥሰቶችና ግፎች መካከል ለኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ለግንዛቤ ያህል ጥቂቶቹን እጠቅስላቸሗለሁ። ይህም  ለኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ያለንበት አጣብቂኝ ሁኔታ ተረድተው ጨርሰው ሳያጠፉን እንዲደርሱልን ለማሳሰብ ነው እንጂ በሌላ ግዜ ለአለማቀፍ ማህበረሰብ የሚሆን ጽሑፍ በሰፊው አዘጋጅቼ እመለስበታለሁ። አሁን ሳይንሳዊ  በሆነ መንገድ ወያኔ በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ሙሉ የዘር ማጥፋት እቅዳቸውን እንዴት ሲያከናውኑ እንደቆዩና አሁንም አይከናወኑ እንዳሉ  ከዚህ ጽሑፍ ተነስታችሁ መተንበይ አያቅታችሁም። አሁን ግዜ ሳልወስድባቸሁ ወደ ነጥቦቹ ላሸጋግራችሁ።

1ኛ. የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ እንደለሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ በጣም ሃይማኖተኛ የሚባል ህዝብ ነው፤ ቢሆንም ግን ከልቡ ያለውን እምነት እምኳን መፋቅ ባይችሉም እምነቱ እንዲጠፋ ተደርጓል። ታዋቂ ታሪክ አዋቂ  ሙስሊም  አባቶች ታስረዋል ንብረታቸው ተዘርፏል። ክርስቲያኖች ሙሉ ለሙሉ ማለት በሚቻልበት ሁኔታ የቤተ ክርስቲያኖቹ  ቅርሶች እጅግ በጣም በተቀነባበረ ሁኔታ በወያኔ ካድሬዎች ተዘርፎ ለውጭ አገሮች ተሽጧል ተበርብሯል እንዲሁም ታዋቂ ታሪክ አዋቂ ቀሳውስቶች ተገድለዋል። የዋልድባ ገዳምም ሳይቀር ተደፍሯል ተበርብሯል።

ለልማት እየተባለ ህዝቡ የእርሻ መሬቱ ከነፍሬው፣ ከብቶቹ የሚያሰማራበት ቦታውንና ቤቱን ሳይቀር ያለካሳ ተነጥቆ ምንም የጤና አገልግሎት ሰጪ ድርጅት በሌለበት በሃይል በወታደር እየተጠበቀ እንዲሰፍር ተደርጎ በወባና በካላዛር በሚአሳዝን ሁኔታ እንዲያልቅ ተደርጓል።

2ኛ. በወልቃይት ጠገዴ ሶስት አይነት የትግራይ ሰፋሪዎች አሉ። በጠቅላላ ወደ 800,000 የሚሆኑ የትግራይ ሰፋሪዎች ነው ህዝቡን ሳያማክር መሬቱን እየነጠቀ በህዝቡ ላይ አምጥቶ ያፈሰሳቸው:: አንደኞቹ በ1983 አ/ም የሰፈሩ የወያኔ የቀድሞ ወታደሮቹ ሲሆኑ ወደ 30,000 የሚጠጉ በዳንሻ አካባቢ እንደገና እስካፍንጫቸው አስታጥቆ ያሰፈራቸው ናቸው። ሌሎቹ ደግሞ በ1985 አ/ም እና  1989አ/ም ከሱዳን የተመለሱ ላጅን የሚባሉ ሲሆኑ በሁመራ፣ ዳንሻ፣ ባዕከር፣ በረከት፣ ራዉያን፣ አዲጎሹ ያሰፈራቸው ወደ 70, 000 የሚጠጉቱ ናቸው:: ሶስቶኞቹ ደግሞ አዲሶቹ ሰፋሪዎች ሲሆኑ ከ1996 አ/ም ጀምሮ የመጡ የታጠቁ ሰፋሪዎች ናቸው። አዲሶቹ ሰፋሪዎች ከ630,000 በላይ ቁጥር ያላቸው ናቸው::ነገሩን የእብደት የሚያደርገውና በእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ የሚያስብለው ደግሞ  ተጨማሪ ሌላ 70 ሺ ለማስፈር እቅዱን አቅደው ለተግባርዊነቱ መዘጋጀታቸው ነው። ይምጡ ችግር የለም ለመተራረድ ይምጡ!

እዚህ ላይ ለወልቃይት ጠገዴ ህዝብ በጣም አስደንጋጭ የሆነው ነገር የሶስትዮሽ ጎን የአሰላለፍ ዘመቻ (Triangular Campaign) የሚባል ሚስጥራዊ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ የማጥፋትና የታላቂቷ ትግራይ የተስፋፊነት ህልም እውን የሚያድርግ እቅድ ይዘው ነው የተነሱት። አሰላለፉ እንዴት ነው ቢሉ አንደኛው መስመር ትግራይን ተሻግረው ከተከዜ እስከ ሁመራ በ15 የሰፈራ ማእከሎች የሰፈሩ ሲሆኑ ከጥርጊያ በታች የወልቃይት ሰው እንዳይወድ በማድረግ ወደ ደጋው እየገፉ የሚወጡ ተስፋፊ ነጻ አውጭ ቡድን ናቸው። ሁለተኛው መስመር በሁመራ አከባቢ ያሉ አዳዲስ ከተማዎች ማቋቋምን ጨምሮ ከሁመራ ዳንሻና ሹመሪን ጨምሮ እስከ የጎንደር ድንበር ሶሮቃ ድረስ ጥርጊያውን ተከትለውና ከጥርጊያው በታች በሙሉ የሰፈሩ ሲሆኑ እነዚህም ከድሮ ሰፋሪዎች ጋር አንድላይ በመሆን የእርሻና ከብት ማርቢያው ሙሉ ለሙሉ በመቆጣጠር ወደ የወላቃይት ጠገዴ ደግማው አከባቢ በሂደት እየገፉ የሚዘልቁ አደገኛ ቡድኖች ናቸው። ሶስተኛው መስመር ደግሞ በአጭር ግዜ ውስጥ ወልቃይት ጠገዴን ህዝቡን አጥፍቶ ለመቆጣጠር የመጨረሻው የድል መስመር ብለው የሚጠሩት ከሽሬ ጀምሮ ወልቃይት ጠገዴን ለሁለት ከፍሎ ሱዳን ድረስ የሚወስደው በፍጥነት ያለቀው እጅግ በጣም ዘመናዊው የአስፋልት መስመር  ተከትለው ማንም ሳያውቅ የሰፈሩ በጣም ጥጋበኛና ግፍ ፈጻሚ ተስፋፊዎች የሰፈሩበት ነው። ይህኛው መስመር አንድም ወልቃይት ጠገዴን ለሁለት ከፍሎ እንዳይገናኙ ለማድረግ ይልቁኑ በአዳዲስ የሰፈራ ከተሞች ምክን ያት በማድረግ ወደ ወልቃይትና ጠገዴ ከላይኛው የደጋ በኩል ወደ ቆላዎቹ ቦታዎች በመግፋት በቆላዎቹ ከሚመጡ ተስፋፊ ቡድኖች ጋር በቀላሉ ለመገናኘት የታሰበ እ ጅግ በጣም ቀጥተኛውና አድገኛው የሞት መስመር ነው። ይህን የጥርጊያ መስመር እንዲሰራ አንፈልግም ያሉ ከ129 ሰዎች በላይ ታፍነው ተወስደው የት እንዳሉ አይታወቅም። እጅግ በጣም አዉዳሚ መስመር ነው። ከዚህ በተረፈ ወልቃይት በሚገኘው የስኳር ፋብሪክ ፕሮጀክት አማካይነት የሰፈሩ ከ30,000 በላይ አተራማሽ ተስፋፊ ቡድኖችም በህዝቡ ህልውናና ንብረት እንዲሁም ተፈጥሯዊ ሃብት ያደረሱትናእያደረሱት ያሉት ጭካኔና ግፍ ለመናገር ሌላ ጽሑፍ የሚጠይቅ ነው። እንግዲህ በዚህ መልኩ ነው ወያኔዎች የወልቃይት ጠገዴ ህዝብን እየገደሉ፣ እያሰሩ፣ እያሰደዱ፣ እያፈናቀሉ፣ ንብረቱን እየዘረፉ ለመስፋፋት እየሞከሩ ያሉት። ወገኖቻችን ሆይ ስቃያችንን ተመልከቱ፤ ይህ የአስተዳደር ችግር አይደለም የማንነትና የህልውና ጉዳይ ነው እንጂ። አማራነታችን እንዲከበርና ለዘር የሚተርፍ ትውልድ እንዲኖረን እርዱን ድረሱልን።

ኢትዮጵያዉያን ወገኖቼ ሆይ ስለዚህ ጉዳይ በጥልቀት ለመረዳት በቅርቡ “የህወሓት ሴራ በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ” የሚል ከእጃቸው በአገር ወዳድ ኢትዮጵያዉያን የተጋለጠው ሴራዊ ዶክመንት እንድታነቡ በትህትና እጋብዛለሁ። ይህ ጽሑፍ በድረ-ገጽ ታገኙታላችሁ።

ከአብዛኞቹ የሱዳን ተመላሾች በቀር ሰፋሪዎቹ ብዙ ግዜ ነገር ነገር የሚሸታቸውና ታጥቀው የሚጓዙ ናቸው። ከህዝቡ ጋር ይጣላሉ፣  አንዳንዴም ሴቶችን ይደፍራሉ፣  የህዝቡን ክብትና በግ ዘርፈው ወደ ሱዳን ይሸጣሉ። ለህዝቡ ፍጹም በጥላቻ መነጽር ብቻና ብቻ የሚያዩ ናቸው። ምን አይነት የጥላቻ የፖለቲካ ትምሀርት ለስንት ግዜ በምን አይነት ሁኔታ እንደተሰጣቸው እግዚአብሔር ብቻ ነው የሚያውቀው። ከጥርግያ በታች ወይንም ቆላው አካባቢ የነበሩ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ንብረቱ የሚያቆይባቸው ቦታዎች ሁሉ ለእነዚህ ሰፋሪዎች ስለተሰጠ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ንብረቱንም ስለሚዘረፍበት ህዝቡ ያለው አማራጭ ንብረቱን በዋነኝነት ከብቶቹ፣ በጎቹና ፍየሎቹ መሸጥ ስለሆነ ንብረቱን ሽጦ ከተማ ገብቶ አንዳንድ የኑሮ እንቅስቃሴ ሲጀምርና የተካነበት የእርሻ ሙያውን ባለችው መሬት ማረሱን ሲቀጥል በተለያይዩ ምክን ያቶች ተስፋ እንዲቆርጥ በማድረግ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴው ሁሉ ያለምንም ተቀናቃኝ በቆዩና በአዲስ ሰፏሪዎቹ እንዲሁም በአዲስ ከትግራይ በሚመጡ ሰፋሪ ያልሆኑ የትግራይ ልጆችና የባለስልጣን ዘመዳሞች ቁጥጥር ስር ወድቋል። የወልቃይት ጠገዴ ህዝብም ይህ ወልቃይት ጠገዴ እኮ እኛም ተወልደንበታል ኢትዮጵያውያን ነን ሲል “እንኳን ቆላው ደጋውና ሴቶቻችሁ ገና እንረካበአችሗለን” በማለት ህዝቡን እንደ ቄሳር መንግስት ያስጨንቃሉ። በዚህ መልኩ ህዝቡ ነፍጥኝነት ሲያነሳ ቤተሰቦቹን የነፍጠኛ ዘር እያሉ ሲጨርሱት ስለቆዩ በራስ ላይ ሞት ከማምጣትና ቤተሰብ ከማስጨረስ በቀር ምንም ለውጥ እንደማያመጣ ከባለፉት ግዝያቶች በህይወቱ ስለተማረ ምንም እንኳን ውስጡ ባይሸነፍም የበይ ተመልካች ሆኖ እየኖረ ይገኛል።

ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ የሚሰራው ግፍ በዞህ ብቻ የሚያበቃ እንዳይመስላችሁ ከታች  ለመጠቃቀስ እንደሞከርኩት እንዲህ እየባሰ ክፋቱና መልኩ እየቀያየረ እየቀጠለ ነው እንጂ።

3ኛ. ሴት ተማሪዎች በአስተማሪዎቻቸው፣ በወታደሮቻቸው፣ በግብርናና በህክምና ባለሙያ ነን ባዮችና ጓደኞቻቸው ገና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እያሉ ይደፈራሉ፣ ያረግዛሉ፣ ትምህርት ያቋርጣሉ፣ ይኮበለላሉ። አሳዛኙ ነገር ይሔን የሚያደርጉት የትግራይ ሰዎቻ አብዛኞቹ በትግራይ ባለትዳርና ባለልጅ መሆናቸው ነው። እንዲህ አይነት አጸያፊ ስራ በህዝባችን እንደነውር ስለሚቆጠር የተደፈሩ ህጻናት ልጆች ለቤተሰቦቻቸው ያጋጠማቸው የልብ ስብራት አይናገሩም አንድም ቢናገሩ በደፋሪዎቹ ቤተሰቦቻቸው አንድ ነገር ቢያደርጉ ቤተሰቡ እንደሚፈርስ በማሰብም ዝም የሚሉ አሉ፣ አንዳንዶቹ ራሳቸውን ያጠፋሉ ሌሎቹ ደግሞ ካራገዙ ብሗላ እውነቱን ይናገራሉ።

አብዛኞቹ ይህን መከራ የደረሰባቸው ለጋ ህጻናት ከወላጆቻቸው ጋር ተጣልተው ትምህርታቸውን አቋርጠው አባት የሌለውን ልጅ ታዳጊዎቹ አሳዳጊ ይሆናሉ። ምንም እንኳን በመጨረሻው ቤተሰቦቻቸው አዝነው በዝሙት ተዳድረው ከሚኖሩ ብለው ቢቀበሉዋቸውም በቤተሰብ ውስጥ ግን ሰላም የለም። ወንድ ተማሪዎችም የተለያዩ ምክንያት በመፍጠር መምህራኖቻቸው ትምህርት እንዲያቋርጡ ያደርጋሉ።

ይህን ሁሉ ግፍ ለሚያደርጉ በህግ ተጠያቂ እንደማድረግ የሚበቃውን ወንጀል የፈጸመን አካል ቦታ በመቀየር አበጀህ በሚል ስውር የሞራል አሰጣጥ የተሻለ ስልጣንና ደሞዝ ተደርጎላቸው በትግራይ የአስተዳደር ስራ ውስጥ ይቀመጣሉ አንዳንዴም በአከባቢው ይሾማሉ።

ለምሳሌ ይሆነን ዘንድ የዚህ ችግር ቀማሽ የሆነችው አታላ የተባለች የ13 አመት የ6ኛ ክፍል ተማሪ ከዳንሻ ከተማ መጥቀስ ይቻላል።  አስተማሪዋ ከደፈራት ብሗላ ደብድቦ የስነልቦና ጫና በማሳደር ፍርሃት እንዲሰማት ካደረገ ብሗላ ህጂና ከቤተሰብ ብር ሰርቀሽ ነይ ይላታል። ልጅቷም ሃብታም ቤተሰብ ስለ ነበሯት ሳጽን ሰብራ 60,000 ብር ወስዳ ከሰጠችው ብሗላ አፍኖ ወደ ትግራይ ወስዶ የሚፈልገውን ሁሉ ከፈጸመ ብሗላ ሆቴል ውስጥ ያስቀጥራታል። ለምን ስትለው ባለትዳር እንደሆነ ነግሮ ወደ አግርሽ ጥፊ ብሏታል። በቤተሰቡ ሊደርስ የሚችለው የልብ ስብራትና የሰላም መጥፋት ምን ሊሆን እንደሚችል ለእናንተ እተወዋለሁ። ህጻኗ እንዴት ወደ አገሯ መመለስ እንዳለባት እንኳን አታውቅም ነበር! የጭካኔው ብዛት ምክን ያቱ ምን እንደሆነ ባናውቅም ካስረከበችው 60 ሺ ብር እናኳን ለመሳፈሪያ የሚሆን ሰጥቶ ቢልካት ምን ነበረበት? ተመሳሳይ ችግር የደረሰባቸው ልጆች እግዚአብሔር ይቁጠራቸው። ታዳጊዎቹ አጋዥ የሌላቸውን ዲቃላ ህጻናትን እያስረከቡ ማህበረሰቡ ላይ ነገ አባቴን የሚል መርዝ ችግኝ እየተከሉ ይሔዳሉ፤ በጣም ያማል ወገኖቼ። የወልቃይት ጠገዴ ህዝባዊ ስብጥሩ በግድ ለመቀየር የሚአደርጉት ታሪክ ይቅር የማይለው ሴጣናዊ ድርጊታቸው ነው። የህዝቡን ህልውና የካዱ የሴጣን መንፈስ የሞላባቸው እርጉማን ሰዎች!!! በዚህ ጉዳይ በቅርቡ ዘግቤ አጋልጨ አስነብባችሗለሁ፤ ግፍን ማጋለጤን እቀጥልበታለሁ ከዛ ብሗላም ብሞትም እንኳን ሊቆጨኝ ደስ ብሎኝ ነው እምሞተው። ህዝቤንና አገሬን የሚታደግ ሰርቼ ስሞት ለእኔ የክብር ሞት ነውና!  ለመወሰን አንቸኩልም እንጂ ቆርጠን ከተነሳን ደግሞ ማን እንደሆንና ወደሗላ እንደማንል በደምብ ያውቁናል፤ ፈጣሪም ከእኛ  ከጭቁኖቹ ጋር እንዳለ በፍጹም መተማመን ላይ በሙሉ ልብ እንናገራለን። እኛ ግን ከህሊናችን ጋር ስላለን የማንነት ጥያቄው ይመልሳሉ ብለን አሁንም ቢሆን በትዕግስት እየጠበቅናቸው ነው፤ ካልሆነ ግን በኮሚቴው ላይና በህዝቡ ላይ እየፈጸሙ የሚያደርጉት  አፈናና ዛቻ ካላቆሙ ወደ እርስ በርስ ጦርነት እንደምናመራ የተረጋገጠ እውነት ነው። ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ሆይ የማንነት ጥያቄያችንን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲመልሱልን እርዳታችሁ አይለየን።

4ኛ. ይሔን ሁሉ ፈተና አልፈው ዩኒቨርስቲ ወይንም ኮሌጅ ገብተው የተመረቁ አንዳንድ የወልቃይት ጠገዴ ልጆች በመንግስት ስራ አይመደቡም ቀደም ብለው የተመደቡትም መቶ በመቶ ማለት ይቻላል ከተመደቡበት ስራቸው ተባረዋል። የመንግስት መስሪያ ቤቶች ሁሉ በአድዋ ልጆች አለፍ ካለም በአክሱም ልጆች ተተክተዋል። አንዳንድ በስራ የሚገኙ በዲፕሎማ ሙያ በአስተማሪነት ቢመደቡም እነዚህም ባሎቻቸው ፖሊስ ወይንም ስልጣን ያላቸው የትግራይ ተወላጆች ከሆኑ ብቻ ነው።

አንዳንድ የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆች ፖለቲካዊ ማግለሉና አስተዳደራዊ ጫናው ተቃቁመው ለመስራት ቢወስኑም ጫናውና ማስጠንቀቂያው ከባድ በመሆኑ ወይንም በራሳቸው ስራቸው ለቀው ያለስራ ይቀመጣሉ ወንም ደግሞ በአድዋና አክሱም አለቆቻቸው ይግባኝ በሌለው የስንብት ደብዳቤ ይሸኛሉ። አይ የመጣ ይምጣ ብለው ለመስራት ወስነው የነበሩ ጥቂት የመንግስት ሰራተኞችም ወንጀል ሰርተዋል ተበለው ማረሚያ ቤት የገቡም ነበሩ አሁንም ያሉ አሉ።

5ኛ. ከላይ በ ተራ ቁጥር 4 እንደነገርኳችሁ ማንኛውም የመንግስት መስሪያ ቤቶች መቶ በመቶ በአድዋና በአክሱም ተወላጆች የተያዙ ናቸው። እናም የተለያዩ አስተዳደራዊም ሆነ ግላዊ ችግር የደረሰባቸው የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆች “የመንግስት ያለህ” ብለው ብሶታቸውን ለማሰማትና ፍትህ ለማግኘት ሲሔዱ ገና በንግ ግራቸውና በቋንቋቸው ለዛ ስለሚያውቋቸው እንኳን ብሶታቸው ሊሰሙላቸው ሌላ ችግርና ብስጨት መርቀው ይመልሷቸዋል። በጣም ተናዶ ለሄደ ወጣት ወይ ጎልማሳ ሰው በተካኑበትና ሴራ በተሞላበት መፍትሔ በሌለው “ችግሩን እናየየዋለን” ወይንም የኔ ቢጤ አቅም የሌለው ሰው ከሆነ ደግሞ በማፌዝ ፍትህ አጓድለው ህዝቡን እግዚአብሔር የሰጠውን ነጻነቱን ቀምተው በሓዘንና በቁጭት እንዲኖር አድርገዋል። የ80ና የ90 አመት አዛውንት በደረሰባቸው ችግር እንኳን ልጆቻቸውን ወክለው መክሰስና መሟገት አይችሉም፤ ነገሩ ከምነግራች ሁ በላይ እጅግ በጣም አሳዛኝ ነው።

ብዙ ግዜ “ለምን እንዲህ ይሆናል፤ ለምን እውነትን ትግደሏታላችሁ ተው ኧረ ተው ስለ እግዚአብሔር ብላችሁ ይሔ ነገር አይጠቅማችሁም ለእኛም አይበጅ!!” ብለው የተናገሩ አባቶችና እናቶች ከዚህ መጣ በማይባል በፖሊስ ታፍነው ይጠፋሉ። ኧረ እንትና የት ገባ ሲባል ኧረ መቀሌ ማረሚያ ቤት እኮ ነው ያለው ይባላል ከሳምንታት ብሗላ። ማን ከሶት ታሰረ?  ለስንት ግዜ ነው የተፈረደበት? መልስ የለም። ኧረ ለመሆኑ ለምንስ እዚህ ቤተሰቦቹ ባሉበት አላሰሩትም? ኧረ እንዲያው ምንስ ብለው ነው ያሰሩት? አሁንም መልስ የለም። በነገራችን ላይ ቤተሰቦቻቸው እንዲጠይቋቸው የሚፈቀድላቸው አይሆንም።

6ኛ. አንዳንድ ባለቻቸው ንብረት በግላቸው በንግድ ስራ የሚንቀሳቀሱት የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆች ገቢን መሰረት ያላደረገና በጣም ከፍተኛ የግብር ክፍያ አንዳንዴም ከጠቅላላ ካፒታላቸው በላይ የሆነ ክፍያ እንዲከፍሉ በማድረግ ከገብያ ውጭ ሆነው በብስጭት እንዲታመሙና ራሳቸውን እንዲያጠፉ ይደረጋሉ። ለገሚሶቹ ደግሞ መሰረትነት በሌለው የውንጀላ ስራዎችና ማስፈራሪያዎች ተደርጎባቸው የንግድ ስራቸው እንዲዘጉ ይደረጋሉ ይታሰራሉም። በዚህ መልኩ ከጨዋታ ውጭ ይደረጋሉ!! ከዛም ቤተሰቦቻቸው በሓዘንና በብስጭት እንዲሁም በእጦት ምክን ያት በአይነቱ ልዩ ልዩ ወደ ሆነ ስቃይ ገብተው እንዲኖሩ ይደረጋሉ።

እዚህ ላይ በወልቃይት ጠገዴ የሚሰሩት ከዚህ ጋር የተያያዘ ግፍ በጥቂቱም ቢሆን መንገር የግድ ይለኛል። በንግድ ሙያ የገቡ እነዚህ ሰፋሪ ትግሬዎቹ  በጣም ሃብታም ናቸው። ሃብታም የሚሆኑት ታድያ በወራት ውስጥ ነው፤ ግብር አይከፍሉም ልዩ ብድር ይመቻችላቸዋል። በአመት ውስጥ ከተማ ውስጥ ሶስት አራት ቦታ ላይ ቤት የሚሰሩና ባለመኪና ናቸው እነዚህ ሰፋሪዎች ናቸው። ወደ ጉዳይ እንመለስና እኒህ ሰፋሪ ነጋዴዎች ምን ያደርጋሉ ብትሉኝ ከላይ በጠቀስኩት አይነት ከፍተኛ የግብር ክፍያ የሚሰቃዩትን የወልቃይት ጠገዴ ነጋዴዎችን ጭንቀታቸውን ያዩና ቀረብ ብለው “አንተ ሞኝ ነህ እንዴ፤ለእኔ እኮ እንዳንተ ከፍተኛ ግብር ክፈል ብለውኝ ይሄን ያህል ለሻይ ይሁንህ ብየ ስሰጣቸው አንድ ሶስተኛውን ብቻ ነው ያስከፈሉኝ” በማለት ሹክ ብሎ ተወላጆቹ ሙስና እንዲከፍሉ ያበረታታቸዋል። ሌላ መንገድ እንደሌለ እቅጩን በዚህ መልኩ ይነገራሉ ፤ በህግ እሔዳለሁ የሚል ተወላጅ ካለ በተራ ቁጥር 5 የገልጽኩት ሂደት እንዳለ ስለሚያውቁ ለተደገሰላቸው የሙስና ጥያቄ ለዛውም ተሸማቀው እንዳይያዙ በመፍራት በጭንቅ ደጅ ጠንተው ህሊናቸው ሳያምነበት ከራሳቸው ጋር እየተጣሉ ይከፍላሉ። አብልግ ወይ በሰርግ የተዛመዳቸው ካለ ከእንደዚህ አይነት ስቃይ ነጻ ነው ግን እንዲህ ያደረጉ ትንሽ ተወላጆች ናቸው። ይህ ለምን ይደረጋል ብትሉ  ፈቅዶ ስለማይዛመዳቸው በግድ እንዲዛመዱት ለማድረግም ጭምር ነው። ዋናው አላማ ይህ ቢሆንም ከርሳቸውም ለመሙላትም ጭምር ነው እንጂ።

እንዲህ ከሚሉት የተወሰኑቱ  የሙስና በይዎቹ ቀንዳኛ ወዳጆች፣ ደላሎችና ተጠቃሚም ናቸው። ሌላው ከግብር ጋር በተያያዘ የሚሰሩት ድራማ ደግሞ ለሰፋሪዎቹ የትግራይ ተወላጆች “ይህን ያህል ብር በዚህ ግዜ ወደ ቢሮ ገቢ ካላደረክ ከዛሬ ጀምሮ የንግድ ስራህ ታሽጓል” ብለው ይዘጉቧቸዋል፤ ተመሳሳይ የንግድ ዘርፍና ካፒታል መጠን ያላቸው የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆቹንም እንዲሁ ካደረጉ ብሗላ የትግራይ ሰፋሪ ተወላጆቹን የግብር መጠን ግን ከፍ ያደርጉባቸዋል። እንዲህ የሚያደርጉት የወልቃይት ጠገዴ ተወላጅ ነጋዴዎች ግብር የመክፈል ችግር ኖሮባቸው ሳይሆን ያለምንም ድርድር ከፍተኛው የግብር ተመኑ እንዲከፈሉ ለማድረግ ነው፤ ከዛ የትግራይ ተወላጆች እየተጣሉ እየተጨቃጨቁ ከተወላጁ በላይ እንዲከፍሉ ካደረጓቸው ብሗላ ለትግራይ ተወላጆች ብሩ ይመለስላቸዋል።

እንዴ በጣም እኮ የሚአስደንቅ እኮ መአት ነው የተጣለብን፤ በሁለትና ሶስት ትራክተር ሲያርሱ የነበሩ ኢንቨስተር ተወላጆች በዚህ መልኩ ደህይተው ግብር የተተመነላቸው ከፍተኛ  ግብር መክፈል ብ አለመቻላቸው ወደ ሱዳን ሲሰደዱ በየወሩ በየቤቱ እየዞሩ የዉሃ ሒሳብ የሚያስከፍሉ የትግራይ ተወላጆች ደግሞ በአንጻሩ ባለሁለት ፎቅ ቤት አሰርተው አከራይተው ሲኖሩ ታያላችሁ በጣም አይን ያወጣ ኢኮኖሚያዊ ዘመቻ (economic ‘genocide’) እኮ ነው።

ተመልከቱ ወገኖቼ ከሞት ከእስራት የተረፉት የወልቃይት ጠገዴ አማራ ህዝብ በምን አይነት ስቃይ ህይወታቸው እየመሩ እንዳለ። ከእነዚህ ሰዎች ጋር ነው 25 አመታቶችን ሙሉ የኖርነው፤ እነዚህ ሰዎች እኛን ትግሬ ናቹህ የሚሉን ማርና ወተት የምናፈልቅላቸው የሰውም የምድርም ከንዓን ስለሆንላቸው ነው እንጂ አማራነታችን እኮ ከኛ በላይ ሲመሰክሩልን ነው የኖረነው።

ታድያ እኛ ከእነርሱ ጋር ስንኖር ከሞቱት በላይ በዚች አለም ካሉት ሰዎች ሁሉ በታች ሆነን ነው!!!

7ኛ. የትኛውም አይነት ክፍት ስራ በመንግስት መስሪያ ቤት ካለ ብዙ ግዜ የስራ ማስታወቂያ ሳይለጠፍ ወገናቸውን ያስገቡበታል። የስራ ማስታወቂያ የሚለጠፍ ከሆነ ደግሞ ስራው ካለበት ከወልቃይት ጠገዴ ውጭ በትግራይ ከተሞች ነው የሚለጠፈው። አንዳንዴ ቀለል ላሉ ግዜያዊ ስራዎች ለምሳሌ ለጉልበት ስራ ኩንትራት እዛው አካባቢው ላይ ቢለጥፉም የሚላስ የሚቀመስ የሌለው በጣም ድሃ የተባለ የወልቃይት ጠገዴ ተወላጅ ሄዶ እንኳን አያመለክትም። የሆነ ግዜ ላይ ለእንደዚህ አይነት ስራ ሊያመለክት የሔደን የአካባቢው ተወላጅ ምን ልታደርግ ነው የመጣኸው ተብሎ በመዝጋቢዋ ተሹፎበታል። የቅጥር ዉሳኔው ከውድ ድሩ በፊት ማለትም ከምዝገባው በፊት በድፍረት እንዲህ ይናገራሉ!!! የትግሬዎቹ ጥጋብ እጅግ በጣም ልኩ ያለፈ ነው:: ይህን የሚያደርጉት እኛ ተማረን አገራችን ጥለንላቸው እንድንሔድ ነው። በነገራችን ላይ እጅግ በጣም አሳዛኝ ስግብግብ አንበጣዎች ናቸው።

8ኛ.  በወልቃይት ጠገዴ ተወላጅና ነገር ነገር በሚሸታቸው እንዳበደ ውሻ በሚክነፈነፉት የትግራይ ተወላጆች መካከል ተወላጁ ትዕግስቱ ተሟጦበት ችግር ከተፈጠረ ያለምንም ማጣራትና ያለምንም  ምንም ጥርጥር ለትግራይ ተወላጁ ስለሚፈረድለት ብዙ ግዜ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ከእነርሱ ጋር በሰቀቀን ነው የሚኖረው፤ አመላቸው ራሱ የምትይዘው የምትጨብጠው አይነት ስላልሆነ ተወላጁ የቤተሰቦቹን ሰላም ለመጠበቅ ሲል ትንኮሳቸውን በመፍራት በጣም ርቋቸው ነው የሚኖረው። ለንግድና ለኑሮ የመጡ ትግሬዎች እንኳን ሲቪል ቢምስሉም አላማቸው ግልጽ ያልሆነ የፈርዖን አብጋዞች ናቸው። የሚደንቀኝ እርስ በርሳቸውም እንዲሁ ነው የሚበላሉት! አዎ ፍቅር የሚባል ነገር በመሃላቸው የለም፤ አንድ የሚሆኑት በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ብቻና ብቻ ናቸው። እናም የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ በሃገሩ ወንጀል እንደሰራ አይነት ህዝብ ሆኖ እንደሁለተኛ ዜጋ በቁም እስር ነው የሚኖረው። ይህ በራሱ የሚያሳየው እነርሱ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ እንደጠላታቸው ማሰባቸው ለወረራ መምጣታቸውና በግድ እኛን ትግሬ ለማድረግ ስላልቻሉ አላማቸው ባለመሳካቱ ምክን ያት የመጣ ንዴታቸው ነው፤  አማራነታችን ብንፈተንበታም ገና አንገታችን ቀና ብሎ ኮርተንበት በደስታ እኖራለን። አዎ አማራነት ወንጅል አይደለም አማራነታችን ይከበረልን!!!

9ኛ.  የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ በአያቶቹና ቅድመ አያቶቹ የመሰረቷትን የሁመራ ከተማ ውስጥ ወልቃይት ጠገዴ ተወላጅ ማግኘት እንደትልቅ የምስራች የተቆጠረበት የግዜ ደፊ ላይ ነው የምንገኘው፤በቃ ያለነው ጥቂት ተወላጆችን ስንገናኝ በሓዘን ድባብ ሆነን ቆይ ግን ይህ ሁሉ ህዝብ በምን መልኩ ነው የጨረሱን ተባብለን እንላቀሳለን። ከዚህም የተነሳ ሰፋሪ ትግሬዎቹ የልብ ልብ ተሰምቷቸው ሁመራ የኛ ናት በማለት የወልቃይት ጠገዴ ተወላጅን ጸጉረልውጥ ይሉታል። ምናለ ሁመራን የሁላችን ነች ቢሉ እንኳ። በተለያየ ግዜ በተለያየ የኢትዮጵያ ቦታ በዋነኝነት ከአዲስ አበባና ጎንደር ቆይተው የሚመለሱ የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆችን ሲያዩን “ፀጉረ-ልውጥ” አይተናል ብለው ለፖሊሶቻቸው በነፋስ ፍጥነት ሄደው ሪፖርት ያደርጋሉ። ፖሊስ ነን ባዮችም እኛን ተወላጆችን ይዘው “አንተ ማን ነህ”፤ “ከየት መጣህ”፤ “ለምን መጣህ” እያሉ ካዋከቡና የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆች መሆናችንን ካረጋገጡ ብሗላ “አንተ የመስፍን ዘር” ፤ “አንተ የነፍጠኛ ዘር”  ብለው ያንገራግራሉ፣ ይሳደባሉ፣ ያስፈራራሉ፣ ይደበድባሉ እንዲሁም ያስራሉ። እንዲህ ስለሚያደርጉን ብዙ ግዜ ወደ ቤተስቦቻቸው የማይመለሱ ብዙ ናቸው። “ምን ሆንክ? ይህ እኮ ትግራይ ነው!” ይልሃል ፖሊሱ። በጣም አሳሳቢ ጉዳይ ነው በአገራችን መኖሪያ እንጣ። በነገራችን ላይ በዚህ መሃል ያለ ውጣ ውረድና ወከባ ተዉት። ይህ እውነታ በሁሉም የወልቃይት ጠገዴ አካባቢ የነበረና አሁን ደግሞ በባሰ ሁኔታ ያለበት ችግር ነው። እኛ የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆች ማንነታችን የሚያረጋግጡበት መንገድ በመታወቂያችን ሳይሆን ወላጆቻችና የሚታወቁ ቤተሰቦቻችንን ፖሊስ ጣብያ ጠርተን ካመጣን ብሗላ ነው። ይህ ጉዳይ ለእኛ ከፍተኛ የሆነ ስነልቦናዊ ስብራት ነው አብሶ ደግሞ ለወላጆቻችን!!! ይህ ችግር በቋንቋ ከምገልጸው በላይ በጣም በተቀነባበረ ሁኔታ ነው የሚፈጸመው። በልዩ ልዩ ስራና በትምህርት ምክን ያት ከአካባቢው ርቀው የቆዩ ሰዎች መታወቂያችንን ለማደስ የማንችልበት ሁኔታ ነው ያለው። ይህን የሚያደርጉት ህጋዊ ኗሪ አይደለህም ለማለትና ከአካባቢው እንድንለቅ ለማድረግ ታስቦ የሚፈጸም ዘግናኝ ድርጊት ነው።

በጣም አሳዛኙ ነገር ፖሊሶቹ በራሳቸው ለአካባቢው አዲስና በእነርሱ ቋንቋ ከዚህ በተያያዘ ታድያ በየቀኑ አዳዲስ የትግራይ ተወላጆች ማየት አዲስ ነገር አይደለም:: ተመልከቱ በእነርሱ የወረደ ኢትዮጵያዊ  ባልሆነ የዘረኝነትና ተስፋፊነት ቋንቋ እንድናገር አንዴ ፍቀዱልኝና “ፀጉረ-ልውጥ” እነርሱ ሆነው ሳለ እኛን ተወላጆቹን “ፀጉረ-ልውጥ” ብለው ያንገራግራሉ!!! የአካባቢው ተወላጆች ሌላው ቀርቶ 25 አመት ሙሉ የመኖሪያ ጎጇቸውን የሚሰሩበት ቦታ እንዲሰጣቸው እድሜ ልካቸው ጠይቀው ያልተሰጡ እነዚህ ከላይ የጠቀስኳቸው ሰፋሪዎች የትግራይ ተወላጆች ግን ተወላጆቹ ገና ስማቸው  እንኳን ሳያውቅ ከመኖሪያ ቤት ባለቤትነት በዘለለ በተለያዩ የልማት አደረጃጀት በሌላ አገላለጽ የፖለቲካ አደረጃጀት ተደራጅተው በወራት ውስጥ ሃብታም ሆነው የህዝቡ ፈላጭ ቆራጭ ሆነው ማየቱና ከዚህ በላይ ደግሞ የፍትህ ማጓደላቸው ስራቸው ስትታዘቡ እንዴት ያማል መሰላችሁ።  በነገራችን ላይ የአካባቢው ተወላጅ የሆነ ማንም ሰው ወደ እንደዚህ አይነት አደረጃጀት እንዲገባ አይፈቀድለትም ህዝቡም ደግሞ በፍጹም መግባትም አይፈልግም።  ህዝቡን ተገልብጠው “አንተ ማነህ” የሚሉት እነዚህ የቀን ሃብታሞች  የሆኑ ዘራፊና ወራሪ “ኢትዮጵያውያን” ነን የሚሉ “የትግራይ ሰዎች” ናቸው። ግዜ አንገት ደፊ ያደርጋል፤ በእርግጥ የእኛ አንገታችን ብቻ ሳይሆን ስብእናችንንም ሕይወታችንም ለማስደፋትና ለመድፋት ጥረዋልም ይጥራሉም ግን ግን ከአሁን በፊትም አልቻሉም ከአሁን ብሗላም አይችሉም እንጂ። በዚህ ታላቅ፣ሀቀኛና ጀግና ኢትዮፕያዊ የጎንደር ህዝብ የሞራል ድቀት ለማምጣት ግን እንዲህ በብስጭቱ፣ ቁጭቱና ሃዘኑ ይስቁበታል ይሳለቁብታል።

10ኛ.  የህክምና አገልግሎት በአብዛኛው የኢትዮጵያ አካባቢ ከዛሬ 24 አመት ሲነጻጸር በተሻለ ደረጃ እንደሚገኝ ማንም ኢትዮጵያዊ የሚያስበው እውነት ይመስለኛል። የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ግን የህክምና አገልግሎት መዝጋት የህዝቡ ማለቂያ መሳሪያ ሆኖ ነው ያገለገለው፤ይህን መሰረታዊ ሰብ አዊ መብቱ ላለፉት 24 አመታት በትግራይ አስተዳደር እርምህ ይሁን ተብሏል።

ዛሬ የወልቃይት ጠገዴ  ህዝብ በአለም ተረት በሆኑ በሽታዎች እንደኩፍኝና ኮሌራ በየግዜው ህይወቱን ሲቀጥፉት ማየት የተለመደ ነው። በእነዚህና ሌላ ዉሃ ወለድ ሽታዎች በህዝቡ ውስጥ በወረርሺኝ መልኩ እየተነሱ የብዙ ህጻናትና አዋቂዎች ህይወት የሚቀጠፍበት አሳፋሪ ሁናቴ ነው ያለው።

የወልቃይት ጠገዴ እናቶች እጅግ በጣም በከፍተኛ ሁኔታ በወሊድ ምክን ያት ከንህጻናቸው ጋር ይሞታሉ። ለ10,000 የትግራይ ሰፋሪዎች ሆስፒታል ተሰርቶላቸው አንቡላንስ ሲመደብላቸው ተወላጅ እናቶች ግን ህክምና ባለማኖሩ እንዲሁም መንገድ ባለ መኖሩ ምክን ያት በመንገድ በቃሬዛ ሳሉ ህይወታቸው ያልፋል። ይህ በትግራይ አስተዳደር በደምብ የሚታውቅ ግን ሆን ተብሎ የተደረገ ነው። እንዲሁም የኛን ቤቶች ንብረቶች በሙሉ እየወረሱ ካስወጡን ብሗላ በአሁኑ ስአት 99.9% እነርሱ በተቆጣጠሯት ሁመራ ከተማ የቆየ ሆስፒታል ቢገኝም ህዝቡ በቀላሉ ሄዶ የሚታከምበት ሁኔታ አይደለም ያለው። ከዛ ገብተህ ለመታከም ብዙ ውጣ ውረድ አለበት እናም ለሰፊው ወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ግን ሆስፒታል ይቅርና አገልግሎቱን የሚወጣ የተሻለ ጤና ጣብያና ኬላ እንኳን የለውም። በእነዚህ የማይረቡ የሬሳ መጋዘን የሆኑ የጤና ድርጅቶች የሚገኙ የህክምና ባለሙያ ነን ተብዬ ሰራትትኖች እጃቸው የሚፈቱት በህዝቡ ስለሆነ የጠናበት ሰው ሲመጣባቸው ታዲያ ምን እናድርግህ አክሱም ወይ መቀሌ ሄደህ ታከም ይሉታል። እሺ በቃ እድሌን ልሞክር የሪፈር ወረቀት ወደ ጎንደር ጻፉልኝ ስንላቸው ‘አይ የሪፈር ወረቀት የምንጽፈው በትግራይ ወደሚገኙ ሆስፒታሎች የምትሄዱ ከሆነ ነው እንጂ ወደ ጎንደር የሪፈር ወረቀት አንጽፍም’ ይላሉ የራሳቸው ሰው በጠና ሲታመም ግን በአንቡላንስ ወደ ጎንደር ሪፈር አሲዘው ይወስዱታል። እኔ እንኳን በግሌ ቤተሰብ ታማብኝ  ህመሟ ሲጠናባት ‘ለምን ወደ ጎንደር ሪፈር አይጻላትም’ ብዬ የጠየኳት ባለሙያ ‘ህጉ አይፈቅደልንም’ ነበር ያለችኝ። ‘እንዴት ማለት’ ስላት ‘በቃአሰራሩ እንደዛ ስለሆነ’ አለችኝና በስጨት ብላ ‘ከፈልክ ለመንግስት መጠየቅ ትችላለህ’ ነበር ያለችኝ።ሰውኮ በጭንቀት ውስጥ ሆኖ ወደ ጎንደር ሪፈር ጻፉልኝ ብሎ ደጅ የሚጠናቸው ጎንደር ሆስፒታል ቅርብ ስለሆነ ነው እንጂ ሆስፒታሉ ህዝቡን በነጻ ስለሚያክም አይደለም።

በነገራችን ላይ እንዲህ የሚያናግሩት የጤና ‘ብሩካኖቹ’ ናቸው፤ አለዚያማ ሰው ኪሱ እስቲያልቅ ድረስ ወይንም ተስፋ ቆርጦ ሞቱን እስቲጠባበቅ ወይንም ደግሞ እስቲሞት ድረስ ‘ይሻልሃል’ እየተባሉ ስንቶቹ ወደ መቃብር እንደወረዱ የፈጠራቸው አምላክ ያወቃል ህዝቡም አይረሳቸውም እስከመቼውም ድረስ። እየሳቁ መግደል ይሉሃል ይሔን አይነቱን ነው።

ብር ያለው ተሎ ጎንደር ሄዶ ይታከማል፤ የሌለው ደግሞ ሞቱን ይጠባበቃል። የትግራይ ሰፋሪዎቹስ ብትሉኝ የወልቃይት ጠገዴ  በሚከፍለው ግብር ሁሉም ልጆቻቸውን ጨምሮ በነጻ ነው የሚታከሙት። እናማ የወልቃይት ጠገዴ በሽተኛ ግን ወገን ያለው ከሆነ ይህን ችግር ስለሚያውቅ ብር አዋጥቶ ወደ ጎንደር ወስዶ ሲያሳክም በብዛት ተዳክመው ስለሚደርሱ ወገኖቹ ሬሳ ወይንም ወደ ሬሳነት የቀረበ በሽተኛን ይዘው ይመለሳሉ። እና ህዝቡ ጎንደር  ሄዶ መታከም ማለት ሬሳ ሆኖ ከመመለስ ጋር ስላገናኘው በሽተኛው ስቃይ በዝቶበት ወደ ጎንደር ሊሄድ ነው ከተባለ የብሽተኛው ዘመዳሞችና ጎረቤታሞች በእንባ ተራጭተው ነው የሚሸኙት።  የሚገርመው ጉዳይ ታድያ እነኝህ የጤና ባለሙያ ነን ባዮች የትግራይ ነጻ አውጭ ቡድን አባሎች ታድያ ልታምኑት ከምትችሉት በላይ ሃብታም ናቸው። ለምን ብትሉ ስራ ቦታቸው ሳይገኙ በአቋቋሙት የግል ክሊኒካቸው ድሃውና የጨነቀው የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ወደ የመቃብር መጋዝን ክሊኒካቸው ስለሚጎርፍላቸው የጎንደር ሃኪሞች ከሚያስከፍሉት በላይ እያስከፈሉ አዎ በጣም ሃብታም ናቸው።

እነዚህ የጤና ባለሙያ ነን ባዮች እጅግ ስርዓተ ቢስ ናቸው። ለምሳሌ እንኳን ለመጥቀስ ያህል በወልቃይት ውስጥ በአዲረመጥ የሆነውን አሳዛኝ ክስተት ልንገራችሁ። ወላጅ አባት ዲያቆን ልጃቸውን ሊያገባ ስለነበር የዲያይቆኑ አባት ከዲያይቆኑ ልጃቸው የልጅቱ አባትም እንዲሁ ለጃቸውን ይዘው ለሁለቱ ኤች አይ ቪ ምርመራ እንዲደርግላቸው ለልጅቱ ደግሞ ድንግልናዋ እንዲረጋገጥ ወደ ጤና ጣብያው ይመጣሉ። የደም ምርመራ እንዲደረግላቸው ደም ከተወሰደ ብሗላ የልጅቱ ድንግልና ምርመራ የሚያደርገው የጤና ባለሙያ ልጅቱን ደፍሮ በመስኮት ዘሎ አምልጦ ሁመራ በማደር ከዛ ወደ ትግራይ ሄዷል። የልጅቱ ቤተሰብ ሃኪሙ በመዘግየቱ ተጨንቀው ለሌላ ሴት ሃኪም ነግረው ሃኪሟ ስታንኳኳ የሚከፍትላት ስላጣች በመስኮት በኩል ስት ሄድ ሃኪሙ የለም ልጅቱ ግን አለች። ከዛ ሁለት ሃኪሞች ገብቶ ህ በመስኮት ገብተው  ልጅቱን ሲያናግሯት ሃኪሙ እንደደፈራትና ወጥቶ ሲያመልጥ ግን ራሷን ስታ እንደነበር ተናገረች። ቀስም የሚሰብር ታሪክ በልጅቱና በሁለቱ ቤተሰብ እንዲህም በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ተደረገ። ሌላም በጣም ብዙ ተመሳሳይ ግር አለ። እንዲህ ያደረገው ሃኪም በትግራይ ውስጥ የፖለቲካ አመራር ውስጥ እስከቅርብ ግዜ በደቡብ ዞን እንደነበር እናውቃለን ይገኛል።

የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ በዚህ የጤና አገልግሎት ሰጭ ድርጅት እጦት ምክንያት የጎንደር ሃኪሞችን እንደነ ዶክተር ፍስሃ ያሉትን የተካኑ የበረሃ በሽታ ሃኪሞች እንዳደርጓቸው እነዚህ ሃኪሞች የሚያውቁ ይመስለኛል። ምንም እንኳን የህዝቡን ችግር ተረድተው ካላቸው በሽተኛ ብዛት የተነሳ በደምብ ባያክሙትም።

11ኛ. ታሪክ ነጋሪ ታላላቅ አዛውንት አባቶችንና እናቶችን በህይወት እንዳይኖሩ ገና ከጧቱ ብዙ አዛውንት አባዎራዎችና እማዎራዎች  ታፍነው ተወስደው ይሔው እስከዛሬ ድረስ መቃብራቸው እንኳን የት እንዳለ አልታወቀም። በአንድ ቀን እንኳን 43 አዛውንት ነበር ወስደው ያጠፏቸው።  ከ43 አዛውንት መጥፋት ብሗላም በፊትም ታሪክ የሚያውቁ የሱዳንን ታሪክ እንኳን ሳይቀር የሚተርኩ ሙስሊምና ክርስቲያን አዛውንቶች እየለቀሙ ደብዛቸውን ነው ያጠፏቸው። በህይወት እስከቅርብ ድረስ የነብሩትን ታሪክ አዋቂዎችንም “መስፍን ነበርክ”፤”ነፍጠኛ ነበርክ”፤ “የነፍጠኛ ሚስት ነሽ” ፤ “የነፍጠኛ አባት ነህ” እያሉ በዚህች ምድር በሰቀቀን እንዲኖሩ በማድረግ ፈጠሪያቸውን አሟሟታቸውን እንዲአይሳምርላቸውና የህዝቡን ስቃይ እንዲያይና በቃ እንዲል በጸሎት በማሳሰብ ነው ያለፉት። ወያኔዎች እንዲህ የሚያደርጉት ታድያ እሊህ አዛውንት በደል ኖሯቸው ሳይሆን አካባቢውን ትግሬያዊ ለማድረግ የሚያቀልላቸው ስለመሰላቸው ነው። በነገራችን ላይ እንዚህ የትግራይ ተወላጆች ሃይማኖት አላቸው፤ በፈጣሪ ያምናሉ ለማለት ለወልቃይት ጠገዴ ህዝብ በጣም ይክብደዋል።

12ኛ. የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ለ25 አመት ባህሉን፣ዘፈኑን፣ ቋንቋውንና የአነጋጋአር ዘዬውን በግድ እንዲተው ተደርጎ በትግራይ ባህልና ቋንቋ እንዲተካው በክፈተኛ ዛቻና ስልታዊ አሰራር ተዘምቶበት ቆይቷል። ህዝቡ በትግራይ ትግሬኛ እንዲጽፍና እንዲናገር ካልሆነ ግን ምንም አይነት የመንግስት አገልግሎት እንዳያገኝ፣ ልጆቹንም እንዳያስተምርና ብሎም ከተወለደባት ወልቃይት ጠገዴ ለቆ እንዲጠፋ ተገዷል፤ እንዲወጣም መመሪያ ሲሰጠው ኖሯል። የወልቃይት ጠገዴ ልጆችም በትምህርት ቤት በግድ በትግሬኛ እንዲማሩ ተደርጓል። ስንቶቹ የአካባቢው ተወላጅ ተማሪዎች የትግሬኛ ትምህርት እንደወደቁ ትምህርት ቤት ይቁጠራቸው። አዎ አስተማሪዎቻቸው ይቁተሩዋቸው እንዳልል አስተማሪዎቹም ያው ነጻ አውጪ ታጋዮች ናቸው። በነገራችን ላይ በ25 አመት ውስጥ በወልቃይት ጠገዴ ከተመደቡት አስተማሪዎች አንድ ሴትና 3 ወንዶች አስተማሪዎች ጥሩ ሰዎች ነበሩ፤ ሃይማኖተኛም ነበሩ። ለእነዚህ ጥሩ አስተማሪዎች ጓደኞቻቸውና አመራሩ በጣም ያገሉዋቸው ነበር ምንም እንኳን በመጨረሻ የጽዋ ተራቸው ከወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ጋር ብ አመሆናቸው ብቻ ለተለያየ አይነት ስቃይ ሰላባ ቢሆኑም እግዚአብሔር ውለታቸውን እንደሚካፍላቸው ግን እኔ በግሌ አምናለው። ከእነዚህ 4 አስተማሪዎች በተቀራኑ ደግሞ ስራን የሚሰሩ በዱላቸውም ተማሪዎችም የገደሉ አሉ፤ ይሔው ሁሉን ነገር ለእግዚአብሔር ሰጥተን ልጆቻችንን በዱላ መተው ከገደሉ፣ ከደፈሩ፣ አላግባብም ከትምህርት እንዲያቋርጡ ካደረጉ አስተማሪዎች ጋር እየኖርን ነው። ከዚህ ከወልቃይት ባህልና ዘፈን በተያያዘ ምልኩ ምንም አይነት የአማርኛ ዘፈን እንዲሰማና አዝማሪ እንዲታይ አይፈቀድለትም። ይልቁንስ አሸንዳን ሴቶቹ በጥቅማ ጥቅም አንታለልም አሸንዳ አንልም ቢሏቸው በግድ እንዲወጡ በማይክሮፎን እየለፈፉ በማስፈራራት ቅጣት እንዳለ ጀሯችን ያደነቁራሉ። ለአሸንዳና ጥጋቡ የእነርሱ ልጆች ይበቁ ነበር፤ እኛም ተሸማቀን  በየቤታችን ሆነን ቀን እስቲወጣልን ድረስ “እህህህ…እህህ”  እያልን መከታተሉን ባላቆምን ነበር። ተመልከቱ ወገኖቼ እንዴት በቁም እስር እንዳለን። የኛን ውቡ አማርኛ ባህላችን እየቀበሩ የእነርሱን በግድ ህይወት እንዲኖረው ይጥራሉ። በነገራችን ላይ በዚህ ፩ አመት የጀመሩት ሌላው አሳዛኙ ድራማ ደግሞ በሰርጋችና በማንኛውም ይደስታችንም የሃዘናችንም ግዜ የምናሳየው ባህላዊው የአማርኛ ዘፈንና ለቅሶ ተዘዋዋሪ በሆነ መንገድ በትግርኛ አድርጉት እያሉን ይገኛሉ።  “ሰርጉን በአማርኛ የደገሰ ማን ነው” በማለት ይሔን ባደረጉ አንዳንድ ተወላጆች የተለያየ ምክንያት እየፈጠሩ ልዩ ልዩ ግፍና ስቃይ መስራት ጀምረዋል። ተስፋፊዎቹ የዘራችን ማጥፋት (Genocide and Ethnic Cleansing) ብቻ ሳይሆን  የማንነታችን መገለጫ በሆነው ባህላችን ላይ የባህል ዘመቻ (Cultural ‘Genocide’ and Extinction) እየፈጸሙብን እንገኛለን። በዚህ አልበቃ ብሏቸው የድፍረታቸው ድፍረት ኑ በግ ውጡ ለውቢቷ ታላቂቱ  ትግራይ መወድስ አቅርቡ ይሉናል። አይ ግዜ እንድግዜ ያለ ድል አድራጊ ጀግና በአለም ውስጥ ማን ይኖር ይሆን። አማራነት ወንጀል ሆኖ እንዴት እንደሚያሰቃዩን ተመልከቱ።

13ኛ. ሌላው አሳዛኙ ድርጊት ደግሞ የወልቃይት ጠገዴ የአካባቢ ስሞች በትግራይ ከተሞች ስም፣ በትግራይ የአካባቢ ስሞችና ጀግኖቻችን ብለው የሚጠሩዋቸው ሰዎች ስም እንዲጠሩ የተደረገበት የክልሉ የአዋጅ ድራማ ነው። አንድ ምሳሌ ለመስጠት ያህል እንኳን ድሮ “እንዳይቀዳሽ” እየተባለ የሚጠራው  አሁን “ፍረወይኒ” ብለው አጋሜ በሚገኘው ከተማቸው ስም ጠርተውታል።   በወልቃይት ጠገዴ የሚገኙት የወንዞቹ፣ የተራሮቹ ፣የበርኻዎቹ፣ የትምህርት ቤቶቹ፣ የሽንተረሮቹና የከተማቹ ስሞች አጋዚ ፍሬ ስዋት ስብሓት አዲአህፈሮም ምናምን እየተባለ አዲስ ስም ተሰጥቷቸዋል። ይህን ጉዳይ በተመለከተ በሌላ ጽሑፍ እመለስበታለሁ።

የአካባቢው ተወላጅ ከዚህ ከአዲስ ከተሰጣቸው ስም ውጭ አካባቢውን በድሮ ስማቸው ሲጠራ ቢሰማ “ትዕቢተኛ አምሓራይ” እና “ወዲ አድጊ” በማለት የሚጠብቀው የመልስ ምት ቅጣት አንድም ማታን ጨለማን ተገን አድርገው ይገድሉታል አለዚያ ደግሞ በፖሊስ የስድብና ማስጠንቀቂያ ወርጅብኝ ተሰጥቶት ከዚያ ብሗላ ምንም አይነት የመንግስት መስሪያ ቤት አገልግሎት እንዳያገኝ ተደርጎ ጥፋት ፈጽሟል ተብሎ ዘብጥያ እስኪወርድ ድረስ በአይነ-ቁራኛ ክትትል ይደረግለታል። የዚህ ሴራዊ አሰራር ድርጊት በጣም ያማል በቃ እበድ እበድ ይልሃል፤ በጣም ያሳዝናል። ፈጣሪ የያዘላቸው ጥፋት ስላለ ነው እንጂ እንዲህ በማድረግ የሚያጠፉን ከመሰላቸው በፍጹም የሚታሰብ አይደለም ይልቁንስ አብረን እንተላለቃታለን እንጂ። በዚህ በወልቃይት ጠገዴ ስም ሲኖሩ የትግራዩ የስምና የባህል ድባብም እያጣጣሙ አለማቸውን ያያሉ፤ ቆይ ግን አለማሰብ ነው እንጂ እስከመቼ ድረስ እንዲህ ሆኖ ይቀጥላል ብለው አስበው ነው።

14ኛ. የእያንዳንዱ የወልቃይት ጠገዴ ተወላጅ የትውልድ ሃረጉና የአያቶቹ ታሪክ ይጽፋሉ፤ ታድያ ይሄን የሚደርጉት የህዝቡን ታሪኩና ቅርሱን ለትውልድ እንዲያሰተላልፉለት እንዳይመስላች ሁ። የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆች የሚያስሩበትና የሚያሰቃዩበት ምክን ያት ሲያጡ በአባቱ፣ አባቱ ንጹህ ቢሆን በአያቱ፣ አያቱ ንጹህ ቢሆን በልጆቹ፣ በልጆቹ ንጹህ ቢሆኑ ባሉና በነበሩ አዝማዶቹ ሽፍታ ነበረ፤ መስፍን ነበር፤ ነፍጠኛ ነበር፤ ለትግራይ ህዝብ የነበረው አመልካከት እንዲህ እንዲያ እንደዛ እንደዚህ ወዘተርፈ ነበረ ለማለት ነው እንጂ። የአካባቢው ተወላጅም እንደዛ አልንበረም ወይንም እነርሱ እንደዛ ቢሆኑ እና እኔ ምን አደረኩ ሲል ድሮም አንተ የእነርሱ ዘር ሆነህ ለትግራይ ምን መልካም ነገር ይገኝብሃል፤ እንዴትስ ትግሬ ነኝ ብለህ እንድታምንና ልጆችህን ትግሬኛ እንድታስተምር እንጠብቃለን ይሉና አንዳንዱን በማስፈራራት ይለቁታል፤ ሌላውን ደግሞ ደስ ላላቸው ቀን ዘብጥያ ያወርዱታል። የታሰሩትን ለመጠየቅ የሚሄድ ዘመድ አዝማድና ወዳጅም ሁኔታቸው እየታየ ብዙ ስነልቦናዊ ሰለባ ይደርሰባቸዋል።

ሌላው ታሪኩንና ዝምድናውን የሚያጠኑበት አሳዛኝ ምክን ያት ስነግራች ሁ በጣም በከፍተኛ የልብ ስብራት ሆኜ ነው። ወልቃይት ጠገዴ አንድ ጎጂ ባህል አለ ደምነት የሚባል። ታድያ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ይህን ጎጂ ባህል የሚገራበት ሃይማኖታዊና ባህላዊ መንገድ በተሎ ዕርቅ መፈጸም ነው። ደምነት ውስጥ የገቡ ሰዎች ካሉ ዕርቅ ይፈጸማሉ፤ ከዕርቅ ብሗላ የገዳይ ቤተሰብ ከሟች ቤተሰብ ጋር በትዳር ይተሳሰራሉ ከዛም ደምነቱ ቀርቶ በፍቅር ይተካል ደሙም በቀሉም በዚህ መልኩ እንዲደርቅ ይደረጋል። ይህን ዕርቅ ያፈረሰ ወይንም በልቡ ለማፍረስ ያሰበ ወገን ካህናቱ ውጉዝ ከመአርዮስ ብለው በፍጹም ያወግዙታል። ከዛም ያን የገዳይ ቤተሰብ ሄዶ መግደል ራስን እንደመግደል ስለሚቆጠርና ቤተሰባዊ ፍቅርም ስለሚያሸንፈው ጊጂ ባህሉ ዘላቂ መፍትሔ ያገኛል ማለት ነው።

እናም አረመኔዎቹ ደም የጠማቸው የትግራይ ተወላጆቹ ግን ማን ከማን ቤተሰብ ጋር ያልተከፈለ/ያለተመለሰ ደምነት አለው የሚለውን ለማወቅ የእያንዳንዱ የወልቃይት ጠገዴ አዋቂ ተወላጅ ታሪክ ያጠናሉ። ይህን ካጠኑ ብሗላ በዕርቅ የቆመን ደምነት በተለይ ደግሞ ዕርቅ ያልተፈጸመለትን የደምነት እዳ ወያኔዎቹ አንዳቸውን ቤተሰብ ማጥቃት ሲፈልጉ ግዜ የትግራይ ተወላጆቹ በተለይም ፖሊሶቹ ሄደው የገዳይ ቤተሰብን የሟች ቤተሰብ እንደገደለው በማስመሰል ይግደላሉ። ይሔን ለማስመሰል በጥይት ከመቱት ብሗላ ተጠቂው ሰው ለመሞት እያጣጣረ ከሆነ ገዳይህ እኔ ደመኛህ እንትና ነኝ ብለው ድሮ እሱ ወይንም የእሱ ቤተሰብ የገደሉትን ሰው ስም ይነግሩታል ወይንም ደግሞ ቢሞትም ባይሞትም ማን ለምን እንደገደለው ወረቀት ጽፈው መልእክት ጥለው ይሄዳሉ። ከዚህ ይበልጥ ነገሩን በጣም አሳዛኝ የሚያደርገው ደግሞ በግልጽ የህግ አካል ሆነው ምስክር አቁመው የገዳይ የተባለው ቤተሰብን ደግሞ መጥተው ያስራሉ። የተገደለበት ቤተሰብ ደግሞ ውሎ አድሮ መግደሉ አይቀርምና ደግሞ ተመልሰው እነርሱንም እድሜ ይፍታህ ብለው ያስራሉ። በእንደዚህ አይነት አረመኔያዊ ስውር የሴጣን አሰራራቸው የወልቃይት ጠገዴ ጎጂ ባህሉን እያጠኑ ስንቱን ጀግና ጨረሱት መሰላችሁ። አሁን ግን ህዝቡ በከፊልም ቢሆን ስላወቀባቸው ቢአይንስ ለመግደል አይሯሯጥም ለዕርቁ እንጂ። ተመልከቱ ኢትዮጵያዉያን ወገኖቻችን እየደረሰብን ያለው ግፍን እልቂት። ይህ ሁሉ ሲሆን ታድያ እኛ ለእነርሱ ክፉ ሆነን ሳይሆን እንዲያውም ሲራቡ የምናበላቸው፣ሲጠሙ የምናጠጣቸው፣ ሲሰደዱ የምናስጠጋቸው፣ ስራ ቢፈልጉ ሰርተው የሚቀየሩብን፣ ሲያጡ የሚጠጉብን እውነተኛ እትዮጵያውያን ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ነበርን። ለምን እንዲህ ይህ ሁሉ ግፍ እንዳደረሱብና እያደረሱብን እንዳለ በጥቂቱ ቢገባንም ለእኛ ግን እንደታላቅ መቅሰፍት ከመቁጠር ውጭ ለታላቂቱ ትግራይ ምስረታ ብለው ይሔን ሁሉ ግፍ በኢትዮጵያውያን ሰው ልጆች ማድረስ ምንም አሳማኝ አልሆነልንም።

15ኛ. የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ አብሮ መኖርና አብሮ ተካፍሎ መብላት ለቸገረው ሰው መርዳትና የዋህነት ማህበረሰባዊ ባህሉ ነውና በወልቃይት ጠገዴ መጥተው ያለፈላቸው የትግራይ ተወላጆች ግን እውነትነትና መሰረት በሌለው በጥቅማጥቅም ተደልለው ህዝቡን በውሸት መረጃነትና ስለላ እያሰቃዩት ይገኛሉ። የእነዚህ ህዝቦች ባህሪ ምን አይነት በጣም እጅግ በጣም ለመረዳት ከባድ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ለእኛ አስገራሚ የህይወት እንቆቁልሽ ናቸው። ለህዝቡ ወዳጅ መስለው በውሸት መረጃ ስንቱን ንጹህ ተወላጅ እንዳስጨረሱት እነርሱ መቁጠር የሚከብዳቸው ይመስለኛል፤ በእርግጥ ለእነርሱ ቢከብድም ቤተሰቦቻቸው አንረሳቸውም ከዚህም አለፍ ሲል ፈጣሪያቸው ያውቃቸዋልና ደማቸው በፊቱ እየጮኸ ነው ግፋቸውን ትተው ለህዝቡ መበደሉን ካላቆሙ እርሱም መፍረዱ አይቀርም። ለምሳሌ ያክልም፦ በዳንሻ ከተማ የሚገኝ የታጋዮች የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያ የዛሬው ኢንቨስተርና ደህንነት አቶ ተላ፤ የትላንትናው የስአትና ሬድዮ ጠጋኝ የዛሬው ኢንቨስተርና ደህንነት ወዲ ሃጎስ፣ የትላንትናው ባለፉል ቤት የዛሬው ኢንቨስተርና ዋና ደህንነት ወዲ ሃበሽ እንዲሁም በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ እሟሃይ እናቱና ወንድሙን እየተረዱ በዚህ መልኩ አድጎ እስከ ዩኒቨርስቲ ድረስ   የሂሳብ ባለሙያው ህዝቡ ያስተማረው የዛሬው ዋና ደህንነትና ነጋዴ ገብረግዚአብሔር ነጋሽ የሚጠቀሱ ናቸው። በዚህ ጉዳይ በንጹሃን የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ግፍ የፈጸሙትን የጡት ነካሾችን አሳዛኝ ታሪክ የሚያጋልጥ ለእናንተው ለኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በቀጣይ በስፊው ይዘን እንመለሳለን።

16ኛ. የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ገጽታን አጥቁረው በወልቃይት ጠገዴ የማይኖሩና የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ሁሉ ያለ አንዳች ምህረት እንዲያሰቃዩ በማሰብ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ጠላታቸው እንደሆነና ትግል ውስጥ እንዳሉ ለህዝባቸው ይስብካሉ። እኔ እንኳን ሽፍታ ብለው የገደሏቸውን የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆችን በአንድ መኪና ሁለት ሶስት መኪና አስረው ሲጎትቱ አይቼያለሁ፤ በመሃል ከተማ አምጥተው ከጣሏቸው ብሗላ ጭንቅላታቸውን በጥይት ሲያፈራሩሱት በአይኔ አይቻለሁ። እስከቅርብ ግዜ ድረስም ሳስታውሰው እጨናነቅ ነበር፤ አሁንም ይሔን ስጽፍ እንባዬን እየረጨሁ ነው። ማለት አይሲስ የሚባለውስ ከዚህ ውጭ ምን አደረገና። ብዙ ታሳሪዎች ናቸው ያሏቸውን የወልቃይት ጠገዴ ሰዎች በሩቅ ጫካ ወስደው ካሰሩዋቸው ብሗላ ጅብ እንዲበላቸው የተደረጉም ነበሩ በ1985/6። እዚህ ላይ ሳልጠቅስ ማለፍ የማላልፈው የአንድ ዘመዴ አሟሟት ልንገራቹህ። ሰውየው የ63 አመት ሃብታም አባወራ ነው። እና ጫካ ወስደው አሰሩት እኛም ጠፍቶ ስንፈልግ ስንፈልግ ካንድ የደረቀ እንጨት የሗሊት ታስሮ ትክሻው ላይ ሆኖ አንድ ትልቅ አሞራ ያንገቱን ስጋ እየዘነጠለው ነው ያገኘነው። ሌላም አንድ በጣም ሃብታም የነበር ዘመዳችንም ጎረቤታችንም ከብቶቹ ለማየት ወደበረሃ ሄዶ አራት እረኞቹ ጋር ምሳ ስአት ቁጭ ብለው ሳለ መጥተው ወሰዱት።   ብሗላ አመሻሽ ላይ ግን ሶስቱን እረኞች ከገደሉ ብሗላ አንዱ ያመልጣቸዋል። ለሰዉየውም ካንገቱ በታች ጉድጓድ ቆፍረው ከቀበሩት ብሗላ ከ700 በላይ የሆኑት የግዛ ራሱ ከብቶች በራሱ ላይ መልሰው መላልሰው ነዱበት። ከብቶች እየተጨነቁ ‘እምቧእምቧ እምቧ’ እያሉ ሲጨነቁና  እንስ ሳዊ ለቆሷቸውን እያሰሙ ሲበረግጉ ሊያመልጡ ያሉትን ከብቶችም ጭምር በጥይት ይጥሏቸው ነበር። የጌታቸው ጭንቅላት እንደሊጥ እየፈረጠ እንደማስቲካ ሽሆናቸው ላይ ተለጠፈ:: የተቀሩትንም ገሚሶቹ ወደ ሱዳን ገሚዞቹ ደግሞ ወደ ትግራይ ነዷቸው። የሁለቱም ሰዎች ስም ያልጠቀስኩበት ዋናው ምክኛት ለቤተሰቡ ደህንነት ብዬ ነው። እንግዲህ እሊህ የትግራይ ሰዎች ከእንሰሳ በታች የሆነ ልቦና ነው ያላቸው አረመኔ ናቸው እምለው ለዚህ ነው። እንግዲህ እኒህ ሰዎች ናቸው እኛን ትግሬ ናቸውና ከእኛ ጋር ይሁኑ የሚሉን፤ እጅግ በጣም የሚገርም ነገር እኮ ነው። የፌደረሽን ምክር ቤት እንግዲህ አሳልፎ ዘራችን እንዲጠፋ እነደማይተወን ተስፋ አደርጋለሁ፤ ለነገሩ ተስፋስ ያለው በአንዱ በአዳኙ በኩል ነውና እርሱ ይርዳን። ኦ አምላቼ ምነው ምን በደልነህ ብለን እኛስ አናማርም ግን እባክህን ከንዚህ አላቀን ወደ ወገኖቻችንም ጨምረን::

ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና እንደዚህ ሁሉ እያደረጉ ለህዝባቸው ጥላቻን ቢያስተምሩዋቸውም በተለያየ ስራ ወይንም ዘመዶቻቸውን ጥየቃ በለው የመጡና ብሗላም ኗሪ የሆኑ አንዳንድ ደግ ኢትዮጵያውያን የትግራይ ተወላጆች ከህዝቡ ኖረው ህዝቡን የተረዱ ሰዎች አይደለም ደሞዝ ተጨምሮልን በነጻ ለዚህ ህዝብ ብናገለግልስ፤ ምርጥ ህዝብ አይደል እንዴ፤ አገርቤት የሚወራውኮ እንደዛ አይደለም ተቃራኒው ነው የሚደመጡ አሉ። ታድያ ከእነዚህ ደግ ኢትዮጵያውያን የትግራይ ተወላጆች እንዲህ ሆነው ቃላቸውን በዚሁ ንግግራቸው የሚያጸኑ በጣም ላጭር ግዜ ብቻ ነው፤ ለምን ቢሉ ጽዋቸው ከወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ጋር እንዳይሆን ፖለቲካዊ ዛቻ ስለሚደርስባቸው ሳይወዱ በግዳቸው ሰልፋቸው ከማይመስሏቸው ከአረመኔዎቹ ጋር ይሆንና ህዝቡን እያዘኑ ሲበድሉ ይታያሉ። እነዚህ እንኳን በከፊል ያሳዝኑናል ቢያንስ የህሊናቸው እስርኞች ናቸውና። ሰልፋቸው ከእነርሱ ጋር ሆነው በተለያየ መልኩ ቢበድሉንም እንኳን የተሴረውን የሴጣን ምክር ለተጠቂው ህዝብ አንዳንዴ ሹክ ብለው የሚያስመልጡ ደግነታቸው ያልተለያቸው ጥሩ ኢትዮጵያዊ ስለሆኑ ፈጣሪ ዋጋቸው እንደሚከፍላቸው አንጠራጠርም። በወልቃይት ጠገዴ ምድር ቸር የሆነ የትግራይ ተወላጅ ማግኘት ለእኛ በጣም ብርቅ የሆነን ሰዎች ነን።

17ኛ. ሌላው የወያኔዎቹና ሰፋሪ ትግሬዎቹ አሳዛኝም አብሳጭም ባህሪ ደግሞ ማንነታቸውንና በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ብሎም በኢትዮጵያው ያላቸውን አመለካከት የሚያሳየውን ነው። እነዚህ አረመኔዎች የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ጠላት ብቻ ሳይሆኑ የተፈጥሮም ጠላት ናቸው።

የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ለዘመናት እንደ አካሉ፣ እንደአይን ብሌኑና ውርሱ አድርጎ ጠብቆት የኖረውን ተፈጥሯዊ ሃብቶቹ ለምሳሌ እንደወርቅ፣ እጣን፣ ጥንታዊ ደኖችና እደሜ ጠገብ እጽዋቶች ከህዝቡ እጅ ተነጥቆ የተሰጡት ለሰፋሪዎቹ ናቸው። በእርግጥ እጣን ለተወላጁ ቢሰጥም አሁን ደግሞ ለሰፋሪዎቹ ለመስጠት እቅድ አውጥ ተው እየተንቀሳቀሱ ነው። ለምለሚቷ ጎጆ እያሉ የሚቋምጣትን ወልቃይት ጠገዴ ከአረንጓዸው ልማት ልፈፋና የዝርፊያው የመለስ ፓርክ መላ በተቃረነ ሁኔታ የረዥም እድሜ ባለጠጋ የነበሩትን ግ ርማ ሞገስ የተላበሱትን እጅግ በጣም ጥንታዊና አግርኛ እጽዋቶቿ በመቁረጥና በመጨፍጨፍ የግብርናው ባለሙያ እንኳን ሳይቀር ከሙያቸው በተቃረነ ሁኔታ በትግራይ ልዩ ልዩ ከተሞችና በአዲስ አበባ የሃብታም  የትግራይ ሰዎች ልዩ ልዩ ቤቶች መስሪያ ሆነዋል። ቀሪውም በየግዜው በመቶዎች በሚቆጠሩ  መኪኖች እያጓጓዙ በአዲግራት፣ በአድዋ፣ በአክሱም፣ በመቀሌና ሽሬ ይሸነሽኑታል ይቸበችቡታል። በዚህ ሃብታም ሆነው ወደ ከፍተኛ ኢንቨስተርነት የተሸጋገሩ የትግራይ ተወላጆች በጣም ብዙ ናቸው ቢሆንም ዝርዝራቸው ያለን የ193 ዘራፊዎች ግን ወንጀላቸው ከነሙሉ ስማቸውና አድራሻቸው ታሪክ እንደከተበው ሊያውቁት ይገባል።

ከእነዚህ ሰዎች በላይ ሰፋሪዎቹ በየቀኑ ከስራቸው ሳይቀር መዘው እያወጡ ስራቸው የሚቆፍሩ የአካባቢው ግርማ ሞገስ የነበሩ ደኖች ምስክር ይሁኑባቸው፤ በእውነት እንዚህ ሰዎች አገር አጥፊ ናቸው።ይህን ያልኩበት አስተሳሰብ ትግራይ ውስጥ ችግኝ ሁሌ ከመትከል ተቆጥበው አያቁም ቢሆንም አንድም ተራራ እንኳን በተከሉት እጽ መሸፈን አልቻሉም፤ እንዲህ ሲሆንባቸው በቃ ዝም ብለን እንተወውና የሚሆነውን እኝ ብለው ይሔው ይጠብቁታል አንድም እጽ ግን ሲወጣ አላየንም በቴሌቭዥናቸው ትግራይ ለመለመች ብለው እንደሚያሳዩን ከሆነ። እንዲህ በሆነበት ሁኔታ ታድያ ለምንድን ነው በወልቃይት ጠገዴ የሚገኘውን አዝማናትን ያሻገረን ደን የሚጨፈጭፉት። በእውነት ከንቱ ምቀኞ ናቸው፤ የህዝቡን ትግሬ ያለመሆን ሁኔታ ስለተረዱ ትግራይ እንዳልሆነ ስለሚያውቁ ነገ ጥለነው ለምንሄድ ብለው አማራውን ህዝብ የተበቀሉ መስሏቸው በተፈጥሮ ላይ ግፍ የሚፈጽሙ ዲንጋይነታቸውን የሚያሳይ የአረመኔ ግብራቸውን ነው የሚነግረን።

ለነገሩማ እንደነርሱ ነፍስና ስጋ ያለውን የሰው ህይወት ያላሳዘናቸው ስለተፈጥሮ እንዴት ሊያስቡና ሊያዝኑ ይችላሉ። ፈጣሪ አይፈቅደላቸውም እንጂ እንደየበርኻው እቅዳቸው እኮ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ሙሉ ለሙሉ ጨርሰው አጥፍተው ወልቃይት ጠገዴ የትግራይ ቢአይደርጉ እንኳን ደኑ አሁንም ይጠቅማቸው ነበር ባይ ነኝ። ግን እነርሱ አይምሯቸው አርቆ የሚያስበው ለጥፋት እንጂ ለልማት አይደለምና ይሔንን እቅዳቸው የዋልደባ አምላክ እንደማይፈቅድላቸው ስለሚያውቁ የወልቃይት ጠገዴ ተፈጥሮ ይሔው እንዲሁ በቀላሉ ሲያጠፉት ነበር አሁንም ያጠፋሉ። ከታች እስከላይ ያው እነርሱ ስለሆኑ ህዝቡን እንኳን የተፈጥሮ ጸጋ ስጦታውን ህይወቱን እንኳን መታደግ ስላላቻለ ወልቃይት ጠገዴ ክዳኗን አውልቀው በባዶ ገላዋ ራቁቷን አቅሟዋታል። ለነገሩ ምን ይገርማል ኢትዮጵያን የምታህል ቅድስት ሃገርንስ ለአለም ልጆቿን ቸብቸበው እራቁቷን አቁመው ለዝሙት አየቸበቸቧት አይደል እንዴ። ወገኖቼ ኢትዮጵያውያን ሆይ የነዚህ ግፋቸው ከሰው ልጅ ከቋንቋ በላይ ነው።

18ኛ. እያንዳንዷ የሚፈጽሟት ግፍ፣ የሰብ አዊ መብት ጥሰት፣ አፈናና ግድያ አንሰላስለው አቅደው  ስለሆነ ህዝቡ እንደጠቀየማቸው ስለሚያውቁ ከፍርሃታቸው የተነሳ ዝም ብለው ብድግ ብለው “ምንም አታመጡም፤ ገና ስታስቡት ልክ ትገባላችሁ፤ አሁንኮ ትላንት አይደለም ዛሬ ነው  መሸፈቻ ቦታ የለም፤ ኢትዮጵያ እንደሆነች በእጃችን ነች የትም አትገቡም ብትገቡም አታመልጡንም፤ አንድ ነገር ብትሉ እስከነ ልጆቻቹህ እንጨርሳቹሗለን” ብለው በድፍረት በአደባባይ በየስብሰባው ህዝቡን በስሜት ሆነው ይወርፋሉ ይናገራሉ። ኧረ እናንተየ  ሆይ ፈጣሪ ከሰው ልጅ ሲለይ የሰው ልጅ እንዲህ ከንቱ ይሆናልን? እናማ እንዲህ እያሉ ህዝቡን ስሜት ውስጥ እንዲገባና እርምጃ እንዲወስድ ይገፋፋሉ፤ እያንዳንዷን ቀን ያለመረጋጋት ህይወት እንዲኖረው ጠክንረው ሲሰሩ ይታያሉ። ህዝቡ ደግሞ ተንኮላቸውን ስላወቀ የአየር ሁነታው እስቲስተካከል ድረስ በተቻለው መጠን በትዕግስት በአርምሞ ለማሳለፍ ይሞክራል። ግን ዝምታው ደግሞ ብርድ ብርድ እስከሚላቸው ድረስ ሲያንቀጠቅጣቸው ታያላችሁ፤ የፈጣሪ ስራውና  ግብሩ እንዴት እጅግ ግሩም ነው። ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ ሆይ በእርግጠኝነት የምነግራቹህ በወልቃይት ጠገዴ መጥታቹህ ለአንድ ቀን ብትውሉና ብታድሩ በጣም የሚያሰጠላና የሚያምምም ስሜት ይሰማችሗል። ኑና እዩት ብየ እናንተን ዉድ ወገኖችቸን አልረግማችሁም። በነገራችን ላይ የሌላ ብሔር ኢትዮጵያዊ በወልቃይት ጠገዴ ውስጥ እንዲኖር ቀርቶ ለቀናት እንዲገኝ አይፈቀድለትም። ለምን እንደሆነ ለእኛ እ ስካሁን ድረስ ግልጽ የሆነ ነገር የለንም።

19ኛ. በአካባቢው ማለት በወልቃይት ጠገዴ ምንም አይነት ሌላ አካል ለምሳሌ እንደ ግብረሰናይ ድርጅቶች፣ ጋዘጠኞች፣ በህዝቡ ሊቋቋሙ የሚችሉ ማህበራት፣ የሌላ ብሔር ያለው ኢትዮጵያዊ እንዲገኝ አይፈቀድም። እነዚህ የጠቀስኳቸው ነገሮች እጅግ በጣም በጥብቅ የተከለከሉ ናቸው። ሌላው ይቅር በተለያየ ስራ የወጡ የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆች እንኳን እንዲመለሱ አይፈቀድላቸውም።

እኛ ጋር ብትመጡና ብታስተዉሉት የተወላጁ ድባቡና መንፈሱ ሶሪያ ውስጥ በጦርነት መሃል ያላችሁ ያህል ነው የሚሰማችሁ። በአንጻሩ ደግሞ ትግሬዎቹ አንድን ከተማ መሉ በሙሉ ደምስሶ ድል አድርጎ የተቆጣጠረን ሰራዊት በሚመስል መንፈስ እዚህና እዚያ በደስታ ሲወራጩ ታዩዋቸዋላች ሁ። በጣም የሚያስገርም ነው፤ ወሬያቸው ሁሉና ደስታቸው የሚመነጨው ከአማራው ህዝብ የህዘን ድባብ ነው እንዴ የሚል ጥያቄ መልሱን አዎ ብላችሁ እንድትሄዱ የሚያደርግ ገራሚና አስጥሊታ ድባብ።

20ኛ. በአጠቃላይ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ በፈርዖን አገዛዝ ስር ነው ያለው። ወያኔና ካድሬዎቹ የፈርዖንን አገዛዝ ከዛም በላይ ካለ እነዚህ አረመኔዎችን በሚገባ ይገልጻቸዋል  ምንም እንኳን ቢያንሳቸውም። እነዚህ የዘመኑ አዶልፍ ሂትለርና ስታሊን ናቸው። በእርግጥ ከፈርዖን የሚለያቸው አንድ ነገር አለ። አዎ ፈርዖን እስራኤላውያንን ያስጨነቀው በሀገሩ ነው፤ ግብጽ ድረስ ሄደውበት ነው የዘመኑ ፈርዖኖች ወያኔዎች ግን የወልቃይት ጠገዴን ህዝብ በአጠቃላይ ደግሞ የኢትዮጵያን ህዝብ እንደፈርዖን የሚያስጨንቁት በሀገሩ ነው።

21ኛ. ቢሆንም አዎ ቢሆንም ጀግናውና ቆራጡ የወልቃይት ጠገዴ የጎንደር ህዝብ ግን የተደገሴትን የሞት ጽዋ ለ36 አመታት እንደኢየሱስ ክርስቶስ ሞቱን እየተጎነጨ ቃሌ አንድ ነው፤ እውነት አይቀየርም ይላል። አሁንም እንዲህ ሆኜ ህያው ሆኜ ኢትዮጵያን እታደጋለኡ ይላል። ምንም እንኳን በሞት ቀይ ባሕር መካከል ለማለፍ ለ36 አመታት ወደ ቀይ ባሕር ፊት ለፊት ለመቆም ሲጓዝ ቢቆይም አሁን ከቀይ የሞት ባሕር ተፋጦ ቆሟል።  ሙሴን ወክሎ ይሔን የሞት ባሕር የሚባርክ የኢትዮጵያ ወገኖቹን ትእዛዝ እንዲሰጥ ይሔው በተጠንቀቅ ቆሞ ይጠብቃል። የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ጠላቴ ሆይ ደስ አይበልህ ይሔው ህያው ነኝ ህያው ሆኜ እየተሻገርኩኝ ነው አለ። ሰልፉ የሁላችን ነውና ኑ ተቀላቀሉኝ ይላችሗል፤ “አዋጅ!”“አዋጅ!!”“አዋጅ!!!” ኑ ህያው ሆነን እንሻገር ይላችሗል። አዎ “አዋጅ!”“አዋጅ!!”“አዋጅ!!!”…….ጀሮ ያለው ይስማ፤ ልብ ያለው ልብ ይበል!!!…..የሞት ሰማያዊ ያይደለ  ቀይ ባሕሩን ተሻግረን ወደ ነጻነትና ፍትህ የሞላባት አገር  በደስታና በአንድነት ተሰባስበን ኑ በሓሴት እንዘምር ይላችሗል። ፈርዖን ታሪክ እንደሆነ አረመኔው ወያኔና ህዝባዊ ያልሆኑት ካድሬዎቹም ታሪክ ይሆናሉ። ኢትዮጵያ ለዘላለም ከልጆቿ ጋር በሰላም በክብር ትኑር፤ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ፤ አሜን።

ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ አንዳንድ ነገር በጥልቀት ለመረዳት “የማያልቀው ወያኔያዊ_የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ስቃይ” የሚለውው ንጽሑፍ ከwelkait.com ወይንም ecad forum.com ድረ ገጽ እስቲ አንብብሉኝ።

በዚህ ጉዳይ በባለፈው መጣጥፌ ላይ ካሰፈርኩት የለቅሶ ጽሑፍ እስቲ ቀንጨብ አድርጌ እስቲ ላስነብባችሁ። አንድ የወልቃይት አባት የተናገሩት ነው።

እነዚህ ሰፋሪ ነን ወራሪዎች ለወልቃይት ጠገዴ ህዝብ እጅግ በጣም የመረረና የከረረ ያላቸው ናቸው። ወያኔ ለስንት ግዜ በምን አይነት ዘዴ ለምን አላማ ኮትኩቶ እዚህ ደረጃ ለደረሰ አመለካከት እንዳደረሳቸው እግዜር ብቻ ነው የሚያውቀው።

በገዛ ሃገራችን ሁሉን ነገር አሳጡን የቀራችው ያችው ማንነታችን ለመዝረፍም ይሔው አሁንም ያሰቃዩናል፣ያስሩናል፣ ይገድሉናል፣ ያሳድዱናል፣ ይደበደቡናል ፤ ሴቶቻችንን ይደፍራሉ።  እንኳንስ አማራ ሆነን ወደ ፈለግነው መሆን ምርጫው የኛው አይደል እንዴ? ለምንድን ነው የሚያሰቃዩን። ይህ ሁሉ ግፍ የሚደርስብን አማራ በመሆናችን ብቻ ነው፤ ዘር ወንጀል የሆነበት አገር በዚህ መንግስት በኢትዮጵያ ብቻ:: አሁን ደግሞ ትግሬ ነን ካላላችሁ ይሔን አገር ለቃችሁ ጥፉ ይሉናል፤ አይ የእግዜሩ ትዕግስት። በትዕግስት እንደቆየነው አንልም እንጂ በጄ እሺ ትግሬ ነን ብንል እንኳ በሕይወት እንደማያስኖሩን በደምብ እንረዳለን፤ ወገን ምነው ኢትዮጵያ እንዲህ ስቃይ ሞላባት?

እሊህ አባት ይህ “አልበቃ ብሏቸው ደግሞ ” ይላሉ “የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ በግድ ትግሬ ነን በሉ እያሉ በየቤታችን እየዞሩ ያስፈራሩናል” ይላሉ….“ከእንግዲህስ እንተላለቅ እንደሆን እንጂ በቀረችን አንዷ ሃብታችን በማንነታችን እንኳ ከንግዲህ ብሗላ አንደራርደርም” ብለው ማስጠንቀቂያ ያዘለ ሃሳባቸውን ይገልጻሉ።

በመጨረሻም እሊህ አባት  “እግዚአብሔር ስቃዩና ስቅላቱ በቃቹህ ብሎን ከወገኖቻችን ጋር በሰላም የምንኖርበት ግዜ ያምጣልን” በማለት የጥልቅ ሃዘናቸውን መርሻ የሆነውን ተስፋቸውን በቃላቸው ገልጠዋል።

እባክዎ ይህቺን ጠቃሚ ጽሑፍ ለሌሎች ኢትዮጵያውያን እንድትዳረስ በማድረግ የወልቃይት ጠገዴን ህዝብ ዘር መጥፋት እንዲቆም የማንነት ጥያቄው እንዲመለስለት ይረዱን ዘንድ በዋልደባው አምላክ በትህትና እንጠይቃለን። ፈጣሪ ውለታዎትን ይክፈል!!!

 

ሰላም ሁኑ፤ የዋልድባ አምላክ ቸር ወሬ ያሰማን!!!

አንበሳው የመይሳው የቴዎድሮስ ዘር  ወልቃይት ጠገድቼው ነኝ

ከወልቃይት ጠገዴ ብጌምድር ፤ጎንደር  ኢትዮጵያ

19 መጋቢት 2008 አ/ም

 

የጠቅላይ ሚኒሰትሩ የለበጣ ስብሰባዎች!!! –ግርማ ሠይፉ ማሩ

$
0
0
girma seifu

ግርማ ሠይፉ ማሩ

ጠቅላይ ሚኒሰትር ኃይለማሪያም ሰሞኑን ስራ በዝቶባቸው እንደከረሙ ሁላችን እንረዳለን፡፡ የስራው ውጤታማነት የሚለካው ግን በሚያሰገኘው ፍሬ ነው፡፡ በእኔ  ግመገማ ስራቸው ለውጤት እንዳልሆነ የተረዳሁት ዘግየት ብዬ “ከተቃዋሚ ፓርቲ” ተብዬዎች ጋር ውይይት ካደረጉ በኋላ ነው፡፡ ቀደም ሲል ከንግድ ማህበረሰብ ቀጥሎም ከምሁራን ጋር ውይይት አድረጉ ሲባል የምር እኚህ ሰው የሚመሩት ድርጅት ልብ ገዛ ብዬ ተሰፋ ማድረጌ አልቀረም ነበር፡፡ ምን ያደርጋል በተመሳሳይ ለህዝብ ግንኙነት ሲባል የሚያደርጉት መሆኑን ያጋለጠ ስብሰባ መጋቢት 14 ቀን 2008 በማድረግ ተስፋዬ አጨለሙት፡፡ የብዙ ሰው ሰሜት እንደሚሆንም ተሰፋ አደርጋለሁ፡፡ ለነገሩ ከሁሉም ጋር የሚያደርጉት ስብሰባ የኢህአዴግ ክፉ መንፈስ የተጫነው ነበር፡፡ ከአቋም ፍንክች እንደማይሉ፣ እነርሱም ሌቦች ሌላውም ሌባ (የመንግሰትና የግል ሌቦች) መሆኑን በሚያስረግጥ መንፈስ የተካሄዱ ናቸው፡፡

ነጋዴዎችን ሰብሰበው ያስተላለፉት የመጨረሻ መልዕክት መንግስት ማሰር ቢፈልግ ሁሉም ከእስር ሊተርፍ እንደማይችል አስጠንቅቀው እና በተቻለ መጠንም አሸማቀው ነው፡፡ መልዕክቱ አሁንም ቢሆን ፀባይ ካሳመራችሁ የምናስረው እስር ቤት ሟቋቋም ድረስ የደረሱትን ብቻ ነው የሚሉ ይመስላሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒሰትራችን ነጋዴዎች እስር ቤት እንዳላቸው የነገሩን ነገር ብዙ የሚገርም አይደለም፡፡ በእኛ ሀገር አንድ የውጭ ኤምባሲ እስር ቤት እንደነበራው ይውራ ነበር (የኤርትራ ኤምባሲ)፤እፍኖም ይወስድ ነበር፡፡ ይህ ይሆን የነበረው ግን በመንግሰት የደህንነት ሰዎች ድጋፍና ትብብር ጭምር ነው፡፡ በእኔ እምነት አሁንም እስር ቤት ያቋቋመው ነጋዴ የደህንነት ድጋፍ አልነበረውም ብዬ አላምንም፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁንም የትኛው ነጋዴ የት ቦታ እስር ቤት አደራጅቶ ከማን ጋር ይስራ እንደነበር በግልፅ በስም ሊገልፁልን ግድ ይላቸዋል፤ በዚሁ ሁኔታም ክስ ተመስርቶ ማየት እንፈልጋል፡፡ (Name and Shame)፡፡  በዚህ አጋጣሚ ፕሮፌስር መስፍን ይህን አስመልክቶ በፌሰ ቡክ ገፃቸው ላይ ማለፊያ ነገር አስነብበውናል፡፡ የሚገርመው በጠቅላይ ሚኒስትር ደረጃ ይህ መነገሩ ነው እንጂ፤ አንባገነን ስርዓት ባበት ማንም ይህን ሊያደርግ ይቸላል የሚል ነው፡፡ ሁላችንም እንደምናውቀው በሶማሊያ ብዙ የጎበዝ አለቆች በነጋዴዎች የሚታዘዙ ማሰሪያዎች አሉዋቸው፡፡ ፀጥታም የሚያስከብሩት እነዚሁ የጎበዝ አለቆች ናቸው፡፡ እስከ አሁን ድረስ ይህ የቀረ አይመሰለኝም፡፡

የነጋዴውን ስብሰባ ጉዳይ ከመቋጨቴ በፊት “ነጋዴ በሙሉ ሌባ ነው” የሚል እንደምታ ያለውን ንግግር ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ሲያደርጉ ነፃነቱ ያለው እና ነፃነቱን የሚያስከብር የንግድ ምክር ቤት ተወካይ ቢኖር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይቅርታ እንዲጠይቁ ማስገደድ ባይችል ለወጉ ለማረጉም ቢሆን ጥያቄ ያቀርብ ነበር፡፡ ይህ ሁሉ ነጋዴ ግብር እየከፈለ ያቆማትን ሀገር ሁላችሁም ሌቦች ናችሁ፤ ማሰር ብንፈልግ የሚቀር የለም የሚል መልዕክት ማስተላለፍ በፍፁም ተቀባይነት የሌለው ከጠቅላይ ሚኒስትር የማይጠበቅ ንግግር ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትራችን አንድም ቀን በንግድ ተሳትፈው ስለማያውቅ ነጋዴዎች ትርፍ ለማሳደግ የሚወሰዷቸው የተለያዩ እርምጃዎች በሙሉ “የሌብነት ስራ” ነው ብለው ያምናሉ፡፡ ህጋዊ የሆነ የታክስ መቀነስ እንቅስቃሴ በትምህርት/በህውቀት (Legal Tax Evation) የተደገፈ መሆኑን የሚነግራቸው አማካሪ የላቸውም፡፡ አማካሪዎች ተብለው የተሰየሙት ተመሳሳይ በመሆናቸው ለውጥ ሊመጣ አይችለም፡፡

ከነጋዴዎች ቀጥለው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምሁራን ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ሰምተናል፡፡ ነጋዴዎቹን ሲያነጋግሩ እንደነበረው ሁሉ ከምሁራኑ ጋር የነበረው መንፈስም ያው የኢህአዴግ ክፉ መንፈስ የተጫነው ነበር፡፡ ይህን ስብሰባ ከነጋዴዎቹ ልዩ የሚያደርገው ነገር “ከፈለጋችሁ ፓርቲ አቋቁሙና እንጋጠም” ማለታቸው ነበር፡፡ በእለቱ ስብሰባ የተገኙ ተሳታፊዎች የዋዛ የማይባል ጥያቄ ማንሳታቸውን እኛ አድማጮች ደግሞ በተሰጠው ኢህአዴጋዊ ማብራሪያና ማፈራሪያ ሳይሆን በጥያቄዎቹ መስመር ላይ መሆናችንን ማሳታወስ ግድ ነው፡፡ ምን ማለት ነው? ብሎ ለሚጠይቅ “ይህች ሀገር ነፃነት ያለው ህዝብ መኖሪያ አይደለችም፡፡ ጋዜጣኛም፣ ነጋዴም፣ ፖለቲከኛም፣ ተማሪም፣ ወዘተ በነፃነት የሚኖርበት ሀገር አይደለም፡፡” የሚለውን የምሁራን አስተያየት የምንደግፍ መሆኑን ለመግለፅ ነው፡፡

ከምሁራኑ ስብሰባ ከተሰነዘሩት አስተያየቶች አንዱ ጠቅላይ ሚኒሰትሩ “ደረታችሁን ነፍታችሁ የምትሄዱት” በሚል ከናይሮቢ ጋር ያደረጉት ንፅፅር ሲሆን ይህ ንፅፅር በምንም መመዘኛ ትክክልም ተገቢም ሆኖ አላገኘሁትም፡፡ እውነቱን ለመናገር ለአንድ ኬኒያዊ የኬኒያ መንግሰት ስጋቱ አይደለም፡፡ እኛ ግን መንግሰታችን ስጋታችን ነው፡፡ በእኛ ሀገር ሀፈና የሚፈፀመው ሊጠብቅን በሚገባ መንግሰት ነው፡፡ ኢትዮጵያ ደግሞ እስከ ዛሬ ከሸብርተኛ ቡድን ነፃ የሆነችውን ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ስምም ፆታም አልገልፅም ብለው ነገር ግን እስከ አያት ስሟ የነገሩን ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ጉቤቦን በግፍ በማሰራቸው አይደለም፡፡ እኛ ኢትዮጵያዊያን በዚህ ደረጃ ለሸብር የደረሰ ሰነ ልቦና ስለሌለን ነው፡፡ ርዕዮትን የፈቷት በግፊት መሆንን ማመናቸው አንድ ነገር ሆኖ፤ በህገወጥ ሁኔታ በእስር እንደነበረች ግን የምንረሳው አይደለም፡፡ (የፍርድ ቤቶች ውሳኔ ልክ ነው ቢባል እንኳን የእስር ጊዜ ጨርሳ አንፈታም ብለው ከህግ ውጭ አስረው ነበር ያስቀመጧት) በኋላ ጠቅላይ ሚኒሰትሩ በግፊት እንደተፈታች ያመኑትን ማለት ነው፡፡

ከላይ የነበሩትን ስብሰባዎች የለበጣ እንደነበሩ ግምት እንድወስድ ያደረገኝ ስብሰባ የተካሄደው መጋቢት 14/2008 “ከተቃዋሚ ፓርቲ” ተብዬዎች ጋር ያደረጉት ውይይት ነው፡፡ በእኔ እምነት የውይይቱ ዋልታና ማገር የነበረው እነዚህ ፓርቲዎች በሀገራችን ከሚያመጡት የዲሞክራሲ ትሩፋት ይልቅ ለሆዳቸው መሙያ የሚሆነውን ቀለብ አስፋፈር ላይ የነበረ መሆኑ ነው፡፡ ተሳታፊዎቹ በሙሉ በሚባል መልኩ ደስተኛ የሆኑት ኢህአዴግ ከመንግሰት ካዝና ከሚደርሰው ገንዘብ ግማሹን ሊያካፍላቸው ፈቃደኝነቱን በጥቂቱም ቢሆን በማሳየቱ ነው፡፡ ለእነዚህ ተቃዋሚ ተብዬዎች ከዚህ ውጭ መልካም ዜና የለም፡፡ በስብሰባው ያልተገኙትም ቢሆን ያናደዳቸው ገንዘቡ ለፓርቲዎች የጋራ መድረክ አባላት ብቻ መሰጠቱ ነው፡፡ በክፍያው ላይ ቢካተቱ አብረው ጮቢ እንደማይረግጡ መረጃ የለንም፡፡ ከዚህ ውጭ መልካም ጅምር ብለው የኢዴፓው መሪ የገለፁት ምርጫን አስመልክቶ ይደረጋል ያሉት ለውጥ ነው፡፡ ይህ አባባል በእውነቱ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ለቆየ ሰው ፓርቲዎች ስልጣን የማይዙት ወይም ተወካይ የማይኖራቸው ህዝቡ ተቃዋሚዎችን በአብልጫ ስለአልመረጠ እና “አብላጫ ድምፅ ያገኘ ያሸንፋል” በሚለው የምርጫ ህግ ምክንያት ያስመስለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒሰትሩም “ምን አባታችን እናድርግ ህዝቡ ሲመርጠን” ያሉትን እንደመደገፍ የሚቆጠር ነው፡፡ በኢትዮጵያ ትልቁ ችግር እኩል መወዳደሪያ ሜዳ ያለመኖሩን አለመቀበል ነው፡፡ ይህ ደግሞ ከኢህአዴግ ጋር እንደመቆም የሚቆጠር ነው፡፡ ለነገሩ ኢዴፓ ከኢህአዴግ ጋር ለምን ቆመ አይባልም፣ ከዚያ ውጭ የት ሊቆም ይቸላል፡፡ ግቡም ትንሸም ቢሆን የፓርላማ ወንበር ማግኘት ነው፡፡

ለማነኛውም ጠቅላይ ሚኒሰትሩ “ተቃዋሚ ተብዬዎች” ምን እንደሚፈልጉ ገብቶዋቸዋል፡፡ ሆዳቸውን የሚሞሉበት ገንዘብ እንደሚያገኙ ቃል ተገብቶላቸዋል፡፡ “ተቃዋሚ ተብዬዎችም” ምን እንደማይችሉም አውቀዋል፡፡ መሻሻል የሚገባቸውን አዋጆች አጥኑና አምጡ በህጉ መሰረት ይታያል ብለዋቸዋል፡፡ እነዚህ አንደ ገፅ ሰርዓት ያለው መግለጫ መፃፍ ለማይችሉ ተቃዋሚዎች ጥናት አጥኑና አምጡ ከባድ ፈተና ነው፡፡ ሌላው ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ያልገባቸው ደግሞ የሰበሰቧቸው “ተቃዋሚዎ ትብዬዎች” በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ አንድም ቦታ የሌላቸው መሆኑን ነው፡፡

ሰለዚህ በቀጣይም ከህዝቡ ጋር የሚካሄትዱትም ሆነ የተካሄዱት ስብሰባዎች እንደ ከዚህ ቀደሙ የፎረም እና የኢህአዴግ ልዩ ልዩ አደረጃጀቶች ውሰጥ በንቃት የሚሳተፉ ሰዎች ተገኝተው ድራማ የሚካሄድባቸው እንደሆነ ግምት ወስደና ወይም ገብቶናል፡፡ ይህ ደግሞ የነፃነት ቀን መምጫውን ያዘገየው እንደሆን እንጂ ጨርሶ አያስቀረውም የሚል እምነት አለኝ፡፡ መፍትሄው ከዚህ በፊት ፀረ-ህዝብ፣ ጸረ -ምናም እያላችሁ ያገለላችሁትን ቡድኖችና ግለሰቦች በንቃት ማስተፍና ትክክለኛውን ሁኔታ መገንዘብ ነው፡፡ በተጨማሪ ያለምንም ቅድመ ሁኔተ ያለ አግባብ በእስር ላይ የሚገኙት ታጋዮች መፍታት ነው፡፡ ስብሰባም ካስፈለገ …….

ቸር ይግጠመን

ግርማ ሠይፉ ማሩ


‘እስመ ሥሙ ይመርሖ ኀበ ግብሩ’ –በበፍቃዱ ኃይሉ

$
0
0
(ጋዜጠኛ በፈቃዱ ኃይሉ)

(ጋዜጠኛ በፈቃዱ ኃይሉ)

በፍቃዱ ኃይሉ

የሥም ነገር ሳልወድ በግዴ ያፈላስመኛል። ሥም ተራ መለያ መጠሪያ ብቻ ነው ብዬ አልቀበልም። ምናልባት መጀመሪያ ላይ እንዲያ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን አሁን፣ ሥም በባሕልና የሥልጣኔ ዝግመተ ለውጥ ሒደት (evolution of civilizations) ውስጥ ብዙ ውስብስብ ነገሮችን እያነገበ በጊዜ ባቡር ተሳፍሮ ውስብስብ ደረጃ ላይ ደርሷል። ሥም የባሕል መገለጫ፣ የፖለቲካ አመለካከት መንፀባረቂያ፣ የወላጆች ለልጆች ውርስ ነው። ለዚያም ይመስለኛል “ሥምና ማንነት” የሚለው ጉዳይ የመጽሐፍ ምዕራፍ እና የጥናት ርዕስ ለመሆን እየበቃ ያለው።  አባቶቻችን በፈረንጆች ‘የሊትሬቸር’ አጻጻፍ ደምብ ስላልጻፉልን ፍልስፍና መስለው ያልታዩን አፈላሳፊ አባባሎች አሏቸው። የሊቃውንቱ “ሥሙ ይመርሖ ኀበ ግብሩ” (ሥሙ ተግባሩን ይመራዋል) የምትለው አባባላቸው አሁን ምዕራባውያን እያጠኑት ያሉት ጉዳይ ላይ እነርሱ የደረሱበት ድምዳሜ ነው። በነገራችን ላይ በተቀራራቢ ሮማውያንም ‹nomen est omen› (ሥም ዕጣፈንታ ነው) የሚሉት አባባል አላቸው፡፡ ሳይንቲስቶች «ሰው ወደሥሙ ወይም ከሥሙ ወዲያ (እየተጎተተ ወይም እየተገፋ) የሚኖር ብኩን ፍጡር ነው» ወደማለቱ እየዳዳቸው ነው። ለመሆኑ አንድ ሰው ለመለያ ይሆነው ዘንድ የተሰጠው ሥም ማንነቱን ያሳብቃል? ባሕሪው ላይ ወይም ተግባሩስ ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል?

የሥም ቅርፅ

ሥም ከአገር አገር ብቻ ሳይሆን ከዘመን ዘመን ቅርፁና ፀባዩን እየቀያየረ ይሄዳል። ለምሳሌ ምዕራባውያን ‘የቤተሰብ ሥም’ የሚሉት እኛ የለንም፤ አንዳንዶች የጎሳ ሥም እሱን ይተካል ይላሉ። በጊዜ መሥመር ደግሞ ለምሳሌ በኢትዮጵያ በ19ኛው ክ/ዘመን (ከ1900ቹ በፊት) የኢትዮጵያውያን ሥም የሚጻፈው (የሚገለጸው) ‘ከአያት ሥም➡ የአባት ሥም ➡ የልጅ ሥም’ በሚለው ቅደም ተከተል ነበር። ከዚያ ወዲህ ግን (‘የእከሌ ልጅ’ ዘመን አልፎ፣ ‘የእከሌ አባት’ ዘመን ሲጠባ) በተቃራኒው ተደርጓል። በቱርክ እ.ኤ.አ. ከ1943 በፊት የቤተሰብ ሥም የሚባል ነገር አልነበረም። አንዱን ሰው ከሌላኛው ለመለየት ሲባል እስከ ሦስት ሥሞች ድረስ ይወጡለትና በዚያ መደዳ (በእኛ እስከ አያት ሥም በምንለው መንገድ) ይጠራ ነበር። በዚህ የአሰያየም ስርዓት የአባትና የልጅ ሥም ምንም የሚያዛምዳቸው ነገር የለም። ለምሳሌ የቱርክ አባት የሚባለው አታቱርክ (Atatürk) ሥሙ ሙስጠፋ ከማል ነበር። አታቱርክ የተጨመረው ኋላ ለክብሩ ሲባል ነው። የአባቱ ሥም ደግሞ አሊ ሪዛ ነበር። በቱርክ የተጠፋፉ ዘመዳሞች በሥም ተፈላልገው የመገናኘት አማራጭ አልነበራቸውም ማለት ነው። በሌላው ባሕል የልጅ ሥም፣ የአባት ሥም፣ የቤተሰብ ሥም… የምንለው ነገር ዝምድና መቁጠሪያም ጭምር ነው ማለት ነው፡፡

በአገራችን በተለያዩ ማኅበረሰቦች የተለያየ ዓይነት የሥም አወጣጥ አላቸው። ለምሳሌ በጋምቤላ የአኙዋክ ብሔረሰብ ሥም አወጣጥ ሥሙን ሰምቶ ስለሰውዬው ጥቂት ቤተሰባዊ መረጃ ማግኘት ይቻላል። በአኙዋክ፣ የመጀመሪያ ልጅ ኡመድ ይባላል፤ ሁለተኛ ኡጁሉ፣ ሦስተኛ ደግሞ ኦባንግ እያለ ይቀጥላል። አንዳንዴ አባትና ልጅ አንድ ዓይነት ሥም ሊኖራቸው ይችላል። ታላላቆቹ ሴቶች ሆነው መጀመሪያ የሚወለድ ወንድ ኦማን ይባላል። ለምሳሌ እኔ ከአኙዋክ ቢሆን የተወለድኩት ኦማን እባል ነበር እንደማለት ነው።…

በአማራ ተወላጆች ዘንድ ደግሞ ትንሽ ለየት ይላል። ለምሳሌ መንዞች “ርስትና ውትድርና ይወዳሉ” ይባልላቸዋል። ይህም በሥማቸው ሳይቀር ይስተዋላል። ለምሳሌ “ሸዋጉልቱ” የመንዜ ሥም ነው። አምበርብር፣ ደምሰው፣ ዳምጠው፣ አሸብር፣ የመሳሰሉትም የመንዜ ሥሞች ናቸው። ጎንደሬ ደሞ “ሹመት ይወዳል” ይባላል። የጎንደሬ ሥሞች ሹመቴ፣ መኳንንት ወይም መኮንን የመሳሰሉት ናቸው (ወይም ነበሩ)። ቀደም ብዬ እንዳልኩት የሥም አወጣጥ እንደጊዜው ይለዋወጣል። ጎጃም የሄድን እንደሆነ ደግሞ ከልጅ እስከ አባት (ወይም አያት) ያለው ሥም ተገጣጥሞ ዓረፍተ ነገር የሚሰጥበት ጊዜ አለ። በጣም ታዋቂ ከሆኑት መካከል ብንጠቅስ እንኳ ሐዲስ ዓለምአየሁ፣ በዕውቀቱ ሥዩም፣ ፍቅር ይልቃል፣ እያደር አዲስን ማግኘት ይቻላል።

ሥም እና ፖለቲካ

ሥም የፖለቲካ መሣሪያም ነው። የአብዮቱ ሰሞን የተወለዱ ልጆች ‘አብዮት’፣ ‘ትቅደም’… የሚል ሥም ተሰጥቷቸው ዕድሜያቸውን እንኳ እንዳይደብቁ ሆነዋል። አሁንም ያ ባሕል ቀጥሎ “ሕዳሴ” ከሥም ዝርዝሮች ውስጥ ገብቷል። የኦሮሞ ብሔርተኞች ‘የአማራ’ ሥማቸውን እየቀየሩ ቢሊሱማ (ነፃነት)፣ ኒሞና (አሸናፊ) የመሳሰሉት የወጣት ‘አክቲቪስቶች’ ተመራጭ ሥሞች እየሆኑ ነው። ኦቦ ሌንጮ (“አንበሳው” እንደማለት) ለታ (ከዮሐንስ ለታ) እና ብዙዎቹ የኦነግ አንጋፋዎችም ሥሞቻቸውን በመቀየር ነው ትግላቸውን የጀመሩት። በዕውቀቱ ሥዩም የአያቱ ቀዳማይ ሥም በዻዻ መሆኑን መጥቀሱ የኦሮሞ ብሔርተኝነትን ለመተቸት እንደነፃ ፈቃድ ሆኖለታል (ወይም ተጠቅሞበታል)። ዮናታን ተስፋዬ ደግሞ የአባቱን ቀዳማይ ሥም (ቴሬሳ) ፈልጎ የተጠቀመው የኦሮሞ ብሔርተኝነትን በአዎንታዊ መንገድ መረዳቱን ለማመልከት ነበር። በተመሳሳይ በ‘ያ ትውልድ’ ዘመን ሥምን ለፖለቲካ ዓላማ ራስን ለመደበቅ ሲባል መቀየር የተለመደ ነበር። ሕወሓቶች የሞቱ ጓዶቻቸውን ሥም ይወርሱ ነበር። ለገሰ ዜናዊ መለስ ዜናዊ እንደሆኑት ማለት ነው። በሕወሓት ለፖለቲካ ዓላማ ስዩም መስፍን ከአረቦች (ሶርያዎች) እርዳታ ለማግኘት ራሳቸውን ሙስሊም አስመስለው ለማቅረብ የአባታቸውን ሥም ሙሳ ነው ብለዋል። ብዙዎቹ የኦህዴድ ሰዎችም ከምርኮ ወደትግል ሲገቡ የ“አቢሲኒያ” ሥሞቻቸውን ወደ “ኦሮሞ” ቀይረዋል።

ሥምን ለፖለቲካ አገልግሎት መቀየር በዓለም ዙሪያ የተለመደ ነው። አምባገነኑ ሞቡቱ ሴሴ ሴኮ ‘የአውሮጳውያን’ ነው ያሉትን ሥማቸውን ቀይረው ነው ሴሴ ሴኮን በማስጨመር የትግል ሥም ያገኙት። በአገራቸው ዛየር (የአሁኗ ኮንጎ) የክርስቲያን ሥም (Middle Name የሚባለው) ‘የእብራይስጥን ሥም’ ለአፍሪካውያን ሲሰጥ የተገኘ ቄስ እስከ 5 ዓመት የሚደርስ እስር እንዲቀጣ የሚያደርግ ሕግ አውጥቷል። ጥቁር አሜሪካዊው ታጋይ ማልኮም ኤክስ የቤተሰቡን ሥም በ‘X’ የተካው እና ሌሎችም አጋሮቹ እንደዚያው ያደረጉት “የነጮች” ነው ያሉትን የክርስትና ሥም ለመቃወም ነበር።

ሥም እና ሃይማኖት

መጤ ሃይማኖት ነባር ባሕሎችን ሁሉ ደምስሶ የመተካት አቅሙ ኃያል ነው። ክርስትና እና እስልምና የዓለም ሥም አወጣጥ ቅርፅን የለወጡት በዚሁ ኃይላቸው ነው። በዓለማችን ላይ በብዛት ወንዶች የሚጠሩበት ሥም ‘መሐመድ’ ነው የሚል ነገር ማንበቤ ትዝ ይለኛል። በአገራችን ወላጆች ለልጆቻቸው ሥም ሲያወጡ ወይ አምላካቸውን መጥቀስ ወይም ከቅዱስ ባለታሪኮቻቸው የአንዱን ታሪክ መጥቀስ ይቀናቸዋል። በሱፍቃድ (በእግዜር ፍቃድ)፣ ዋቅጅራ (እግዜር አለ)፣ ገብረእግዚኣብሔር (የእግዜር ሥራ)… ጥሩ ምሳሌዎች ናቸው።

በቅዱሳን ባለታሪኮች ልጅን መሰየም በተለይ አሁን አሁን ፋሽን እየሆነ መጥቷል። አገር በቀል ሥሞችን ለልጆች ማውጣት ልጆቹን “ፋራ” (ወይም “አራዳ” ያልሆኑ) የሚያሰኝ ይመስላል።

በሌላ በኩል በቀድሞ ጊዜ ለንግሥና ሲባል ሥምን መቀየር የተለመደ ነበር። ብዙ ጊዜ ንግሥናን በጳጳሳት ተቀብቶ ለማፅደቅ ሲባል በክርስትና ሥም መጠራት ደንብ ነበር። (ነገሥታት ራሳቸውን ሥዩመ-እግዚአብሔር ይሉ ነበር። ስለዚህ ንግሥና ፖለቲካዊ ብቻም ሳይሆን ሃይማኖታዊም ነበር) ተፈሪ መኮንን [ቀዳማዊ] ኃይለሥላሴ የተባሉት በዚያ መንገድ ነው። “ቴዎድሮስ የተባለ ንጉሥ እስከ እስራኤል ይገዛል” የተባለውን ትንቢት ወይም ጥንቆላ ተከትሎ ነው ካሣ ኃይሉ ራሳቸውን [ዳግማዊ] ቴዎድሮስ ብለው ያነገሡት። ቀዳማዊ ቴዎድሮስም ሥማቸውን ያገኙት በትንቢቱ መሠረት እሰከ እስራኤል የመግዛት (ካልሆነም ትንቢቱን ሰምተው በሥም የሚግገዙላቸው እንዲያገኙ) ተመኝተው ነው። አውሮጳውያን አፍሪቃዊ ኃያል የክርስቲያን መንግሥት መሥርቷል ብለው በአንዲት ደብዳቤ መነሻ ብዙ ያወሩለት የነበረውን ቄስ ዮሐንስ (Prester John) ለመሆንም ሲባል ነው እስከ አራተኛ የተደረሰው። ዐፄ ዮሓንስ እና የወሎ ሙስሊሞች የገቡበት ቁርሾ መነሻም የዐፄው እንደሥማቸው የማደር ምኞት ይመስለኛል።

ሥም እና ስርዓተ—ፆታ

ሥም ስርዓተ-ፆታን የሚገልፅበት ሁኔታም ቀላል አይደለም። ወንዶች በአማራው ተወላጅ ዘንድ በጥቅሉ ምናባዊ ጀግንነትን የሚያጎናፅፍ ሥም ይሰጣቸዋል። ለምሳሌ ወንዳፍራሽ፣ ናደው፣ ሺመክት፣ መኩሪያ፣ የመሳሰሉትን ሥሞች መጥቀስ ይቻላል። በኦሮምኛ ሌንጮ (አንበሳው)፣ ኬራንሶ (ነብሩ፣ ደፋሩ)፣ ዋንጎ (ቀበሮው) የሚሉ በኃይለኛ አራዊቶች ሥም ለወንዶች የሚሰጡ ስያሜዎች ጀግንነትን ለወንድ የማልበሱ ማኅበራዊ ትውፊት አካል ናቸው። ጫላ (ቀዳሚው)፣ ሁንዳራ/ኢራና (የበላይ)፣ ኩማራ (ሺመክት) የመሳሰሉትም የተጠቀሰውን ምናባዊ ጀግንነት አልባሽ ኦሮምኛ ስያሜዎች ናቸው። በሲዳምኛ አዳቶ (ደፋሩ)፣ ዳፉርሳ (የማይዳፈሩት) የመሳሰሉት ሥያሜዎች የላይኞቹ ዓይነት ሚና አላቸው። በሌሎቹም ቋንቋ እና ባሕሎች ውስጥ ተመሳሳይ አጠራሮች አሉ።

ለሴቶች ሲሆን ውበታቸውን፣ ወይም በቁስ የሚተመን ዋጋቸውን የሚገልፅ ሥም ይሰጣቸዋል፦ መድፈሪያሽ ወርቅ፣ ሺብሬ፣ ወርቂቱ፣ ብሪቱ፣ ሸጊቱ፣ ቆንጂት…የሴቶች ሥም አወጣጥ ሴቶችን በአትክልትና ፍራፍሬ የሚመስልበትም ጊዜ ቀላል አይደለም፤ አበባ፣ ወይኒቱ፣ ትርንጎ፣ ብርቱኳን፣ ሸዊት (በትግርኛ “እሸት” ማለት ነው) ጥቂት ምሳሌዎች ናቸው። በኦሮምኛ ቢፍቱ (ብሩህ፣ ፀሐይቱ/ጣይቱ)፣ ፋኖሴ (መብራቴ)፣ መጋሌ (ጠይም/ቆንጆ)፣ ዱንጉጄ (ሽንኩርት፣ አጭር ቆንጆ)፣ በከልቻ (ኮኮብ፣ ለዓይነ ቆንጆ) የመሳሰሉት ሥሞችና በሲዳምኛ ዳንቺሌ (ቆንጆ፣ ፀባየ ሸጋ)፣ ደራርቱ (አበባ፣ ፍካት (ኦሮምኛም ነው)) ሴትን በውበቷ የመግለፅ ትውፊታዊ ወግ ያሳያሉ።

ሥም እና የቤተሰብ ታሪክ

ሥም አንዳንዴ የሐዘን መግለጫ ነው። አባቱ (ተፀንሶ እያለ ወይም በልጅነቱ) ወይም ታላቅ ወንድሙ የሞተበት ልጅ ለምሳሌ በአማርኛ ምትኩ፣ ማስረሻ… ይባላል፤ በትግርኛ ካልኣዩ፤… ታላላቆቹ ሲወለዱ እየሞቱ እሱ ግን ያንን መሰናክል ያለፈ ልጅ ለምሳሌ በአኙዋክ ኞም ይባላል፤ በሲዳማ ሪቂዋ ይባላል።

ሥም አወጣጥ ልጁ በተወለደ ጊዜ ወላጆች የነበራቸውን ግንኙነት፣ የኢኮኖሚ ሁኔታ እና ወዘተ የሚናገርበትም ሁኔታ አለ፤ ለምሳሌ አስማማው፣ አስታርቄ… የመሳሰሉት ሥሞች ብዙ ጊዜ የሚወጡት እየተጥጣሉ (በተለይ በልጅ እጦት) የነበሩ ጥንዶች የልጅ መገኘቱን ተከትሎ ሲስማሙ ነው። ወላጆች ልጅ ሲወልዱና የጥሩ ዕድል (በተለይ የሀብት) መምጣት ከተገጣጠመ ልጃቸውን ሀብታሙ፣ ጥጋቡ፣… ብለው ሊሰይሙት ይችላሉ። በተቃራኒው ከገጠማቸው ደግሞ ያንኑ የሚያንፀባርቅ ሥም ይሰጡታል፤ ለምሳሌ ‘በድሉ’ የሚለው ሥም በዕድሉ ይደግ ከሚለው የመጣ ነው፤ ወይም ሳይታቀድ ከመጣ ነው። በኦሮሞ ትውፊት ተጨማሪ ልጅ የማይፈልጉ መሆኑን ለመግለጽ ወላጆች ለ“መጨረሻ” ልጃቸው ጉታ የሚል ሥም ያወጣሉ።

«ሥምህን ንገረኝና ማንነትን እነግርሃለሁ»

የኒው ሳይንቲስት ጋዜጠኛ ጆን ሆይላንድ “nominative determinism” (ሥም አመጣሽ ቁርጠኝነት) የሚለው ነገር አለው። ‘ሥም አመጣሽ ቁርጠኝነት’ የሚወክለው በሥማቸው ተገፍተው ለስያሜያቸው የሚስማማ ሙያ ሲከተሉ ነው። ለምሳሌ በዕውቀቱ ሥዩም ኃይለኛ ቦክሰኛ ቢሆን ኖሮ ሥሙ ከሙያው ጋር አይሰምርም እንል ነበር። በቡጢው ሥዩም ይሆን ነበርና። ስለዚህ የበዕውቀቱ ‘ሥም አመጣሽ ቁርጠኝነት’ ኋላ ቀር የሚለውን ስርዓት (social order) በነውጥ/ነፍጥ ሳይሆን በዕውቀት በመሞገት መንገሥ/መሰየም ነው።

ብዙ መንግሥቱ፣ ንጉሡ የተባሉ ሰዎች መራኄ መንግሥትነት ማዕረግ ሳያገኙ አንድ መንግሥቱ ኃይለማርያም ቦታውን መቆናጠጡ ብቻ መንግሥቱ የተባለ ሰው ሁሉ የመንግሥት ኃላፊ ይሆናል ማለት ባይቻልም ሥማቸው ግብራቸውን ቀድሞ እንዲመራው በማድረጉ ረገድ ተፅዕኖ መፍጠር ይችላል በሚለው ግን መስማማት እንችላለን፡፡

በአማራው ማኅበረሰብ ዘንድ ‹ደመላሽ› የሚለው ሥም የሚሰጠው “ደም የተቃቡ” ቤተሰቦች መካከል ከአንደኛው ወገን ተበቃይ ባልነበረበት ጊዜ ለተወለደ ልጅ ነው፡፡ የዚህ ልጅ ዕጣፈንታ ባስተዳደግ ይወሰናል፡፡ ሥሙን ያወጡለት ሰዎች ሥሙን ለምን እንዳወጡለት ብቻ ሳይሆን ምን እንዲያደርግላቸው እንደሚፈልጉም ጭምር እያስተማሩት ነው፡፡ ስለሆነም፣ አድጎ “ጠላት” የሚለውን ወገን ለመግደል መሠማራቱ ሰፊ ዕድል ያለው የሕይወቱ ምዕራፍ ነው የሚሆነው፡፡

ሥም እና ማንነት ግንኙነት አላቸው የሚሉ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት፣ “ሥማችን – ወይም ሰዎች ሥማችንን ሲሰሙ በሚያሳዩት ግብረ-መልስ ወይም የማንነት ግምት ላይ ተመሥርቶ ባሕሪያችንን ይወስናል፡፡” ወደድንም ጠላንም በሥማችን ብቻ ሰዎች ዘውጋዊ ማንነታችንን፣ የቤተሰባችንን ሁኔታ፣ እና ሌሎችም መሠረታዊ ግምቶችን ስለኛ ያሳልፋሉ፡፡ እኛም ይህንኑ ስለምንረዳ የሰዎቹን ግምት ለማጠናከር ወይም ለማስተባበል የበኩላችንን ጥረት በማወቅም፣ ባለማወቅም ማድረጋችን አይቀርም፡፡

ሥም በባለቤቱ ላይ የሚያመጣውን ማንኛወንም ዓይነት ተፅዕኖ ለመቀነስ የተለመደ-ሥም (popular name) መስጠት እንደመፍትሔ ይጠቆማል፡፡ ልጆች በሥማቸው ማንነታቸው እየተገመተ፣ እነሱም በምላሹ በሥማቸው እና ሥማቸውን ሰምተው ሰዎች በሚያሳልፉት ግምት ተፅዕኖ ሥር እየወደቁ ‹የሥማቸው ፍሬ› እንዳይሆኑ ሲባል ለልጆች በሚያድጉበት አካባቢ የተለመደ የሚባለው ዓይነት ሥም ቢሰጣቸው የገዛ ሥማቸው ሰለባ ከመሆን ይድናሉ፡፡


እንደ ዋቢ:-
– የነጋድራስ ገ/ሕይወት ባይከዳኝ ድርሰቶች፣
– Atatürk (biography), by Andrew Mango
– Wax and Gold, by Donald Levine
– ፍቅር እስከ መቃብርን የጻፉት «ሐዲስ» ናቸው ወይስ «ዓለማየሁ»? (የሚከራዩ አማት እና ሌሎች)፣ በዳንኤል ክብረት
– ሉኣላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ፣ በገብሩ አሥራት
– ሥምና ማንነት (ከአሜን ባሻገር)፣ በበዕውቀቱ ሥዩም
– Typology of Oromo Personal Names, by Tesfaye Gudeta Gerba
– እና የተለያዩ ድረገጾች እና ሌሎችም…

– በፍቃዱ ይህን ጽሁፍ በራሱ ብሎግ http://befeqe.blogspot.com/2016/03/blog-post_28.html ላይ ለጥፎት የነበረ ሲሆን የጸሐፊውን ፈቃድ አግኝተን ለዘ-ሐበሻ አንባቢዎች አካፍለናል::

በዉስጥ አርበኞች የተቀናጀ ስልት በተለያዩ ክልሎች በአጋዚ ጦር ላይ እርምጃዎች ተወሰዱ

$
0
0

ከልዑል ዓለሜ

በአማራዉ ክልል ላይ በቋራ ወረዳ በንፋስ ገበያ ግንቦት 21/2008 ዓ/ም ከሱዳን መንግስት ጦር ጋር በመተባበር 24 የኢትዮጵያ ገበሬዎችን የእርሻ ቦታ በማቃጥል 13 የአማራ ተወላጅ ወጣቶችን በመግደል እና 34 ሰላማዊ ነሪዎችን በማገት ግፍ የሰራዉ የአጋዚ ሰራዊት ላይ የዉስጥ አርበኞች ከህዝብ ጋር በመተባበር እርምጃ የወሰዱበት ሲሆን 3 ቀንደኛ የህዝብ ጠላቶች ተወግደዋል።

Breaking News zehabesha
በተያያዘ መረጃ አድማሱን እያሰፋ የሚገኘዉ የዉስጥ አርበኛ ሐይል ከኦሮሚያ ጀግና አርበኞች ጋር በመቀናጀት በምእራብ ወለጋ ጉደር ከተማ ስምሪት ጥቢያ ካምፕ አድፍጦ በሚገኘዉ የወያኔ አጋዚ ጦር ላይ በተመሳሳይ ጥቃት በመፈጽም ከአርባ በላይ ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ግምቱ ባልታወቀ የወያኔ ንብረት ላይ ጉዳት አድርሰዋል።
በአርሲ ክልል የዉስጥ አርበኞች አካል የሆነ አንድ ጀግና የኦሮሚያ ፖሊስ ክልል አባል 5 የአጋዚ ጦር ወራሪዎች ላይ እርምጃ ከወሰደ በኃላ እራሱን አጥፍቷል።
በትግራይ ክልል በሰሞኑ በተደረገ የመከላከያ ሰራዊት አመራሮች ድብቅ ስብሰባ ላይ
” የትግራይ ህዝብ የወደፊት እጣ ፈንታ ምንድን ነዉ? የወደፊቷ ትግራይ ማለት በፈንጅ የተከበበች ደሴት ናት! የህዝቡን ህልዉና ዛሬ በስልጥን ላይ ያለዉ የትግራይ አማጺ ቡድን ድባቅ መትቶታል ” በማለት የተናገረ አንድ በ10 አለቃ ማእረግ የሚገኝ የትግራይ ተወላጅ ከስብሰባዉ ቦኃላ እራሱን በመግደል ተቃዉሞዉን በአሳዛኝ መልኩ ገልጿል።
በኦጋዴን እና በምስራቅ ኢትዮጵያ ተሰማርቶ የሚገኝዉ የመከላከያ ሰራዊት በአዛዦቹ በመማረሩ ምክንያት እርምጃ እየወሰደባቸዉ፣መልቀቂያ እየጠየቀ እንዲሁም እየተሰወረ በመመናመን ላይ መሆኑን ከዉስጥ የወጡ መረጃዎች እና በሰት ወደተለያየ አፍሪካ ሐገር የተጠለሉ ወገኖቻችን አመላክተዋል።
እራሱን ብሄራዊ መረጃ እያለ የሚጠራዉ አካል በመረጃ ፍሰት ወይም ማፈትለክ ምክንያት በአባላቶቹ ላይ እርምጃ እየተወሰደበት ሲሆን ባጠቃላይ በአጭር ግዜ ዉስጥ ከመረጃ ሰራተኞች ዉስጥ 21 ባለመተማመን ምክንያት ለእስር ተዳርገዉ 18 ያህሉ ከሐገር ለመኮብለል ሲገደዱ ፣ 8 የሚጠጉት ደግሞ በህዝብና በተለያዩ አካላት እርምጃ ተወስዶባቸዋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !
( ጉድሽ ወያኔ )

ለኤርሚያስ አመልጋ የተፈቀደው ዋስትና ታገደ

$
0
0

Ermias-Amelga

ከእሸቴ አሰፋ

የአክሰስ ሪል ስቴት መሥራችና ሊቀመንበር አቶ ኤርሚያስ አመልጋ ከእሥር እንዲፈቱ የተፈቀደላቸው የዋስ መብት ታገደ፡፡

የአራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በ500 ሺህ ብር ዋስትና ከእሥር እንዲለቀቁ የሰጠው ብይን የታገደው መርማሪ ቡድኑ ለፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ባቀረበው ይግባኝ ነው፡፡

አቶ ኤርሚያስ አመልጋ ከ 2 ሺህ 500 በላይ ከሚሆኑ የቤት ገዢዎች በቢሊየን የሚቆጠር ገንዘብ ለተባለለት አላማ አላዋሉም ተብለው በእሥር መቆየታቸው ይታወቃል፡፡

አቶ ኤርሚያስ አመልጋ በተጨማሪ ከስድስት በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ደርቅ ቼክ ፅፈዋል ተብለው ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡

 

ትንሳኤ ለፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ – አንተነህ ገብርየ

$
0
0

የተወሰኑ ፊዲዮዎች ለግንዛቤ እንዲረዱ ቀርበዋል ይመልከቷቸው

23 (1)ትንሳኤ የሚለውን የግእዝ ቃል ትርጉም ተነሳ ማለት ሲሆን ተንስአ ለጸሎት፤ ተንስአ ለሥራ፤ተንስአ ለምሥጋና እየተባለ ይነገራል የሁሉም መልእክት ቀጥታ አባባል ልዩ ልዩ ተግባር ለመፈጸም መነሳት ማለት ነው በሁሉም መልኩ የቃሉ ትርጉም መጠን መገኘትን ጠቋሚ ነው። ከዚሁ ጥሬ ቃል የሚወጣው ስም ትንሳኤ ሲሆን ያለ የተገኘ ያልሞተ ማለት ነው ይህ እንግዲህ ከዚህች ዓለም እኛን ለማዳን ከመጣውና በሰው ልጅ ሕይወቱ ያለፈው ጌታችን ከመድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ይጀምራል።ክርስቶስ በአይሁዶች ተወግሮ ከተገደለ በኋላም በሦስተኛው ቀን ተነሳ በዚህ ምክንያት ትንሳኤ እንጀምራለን ትርጉሙም ሞቶ ያልቀረ በሌላ መልክ የተነሳ መሆኑን በማሳየት ነው።ተግባራቸው ከመቃብራቸው በላይ ሕያው ሆኖ ያሉ ግለሰቦችም ምንም እንኳን በአካል ባይኖሩም ከትውልድ ትውልድ እየተዘከረ በመሆኑ ትንሳኤ ግብራቸው ይነገራል።

አነሳሴ ትንሳኤ የሚለውን ቃል በዚህ ጹሑፍ ለመተንተን ወይም ለመዘርዘር ሳይሆን ቃሉ የማይሞት ግብርን ለማሳየት ፈረንጆች እንደሚሉት (Immortal)የሚለውን ቃል ጽንሰ ሀሳብ ለማሳየት ነው።ይህን ጉዳይ ይበልጥ ለማሳየት የተነሳሁት በርዕሱ የተገለጸውን የፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ አይበገሬነትና ትንሳኤ ምንድን ነው የሚለውን ለማብራራት ነው።እኔ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን በአካል አላውቃቸውም በሕይወት እያሉ በተግባራቸው የፈጸሙትን ግን በተለያዩ ሁኔታውች ለማወቅ ችያለሁ።በተለይ በእርሳቸው እጅ ታክመው የዳኑ፤አብረዋቸው ያደጉ፤ አብረዋቸው የሰሩ ስለፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ሲናገሩ ሁሉን አይነት ስሜት የሚነካ ተፈጥሮ እንደነበራቸው ለመግለጽ አያዳግትም።(ደግነት፤ትሕትና፤ወንድነት፤አትንኩን ባይነት፤ብልሃት፤ጥበብ፤ፈገግታ፤አርቆ አስተዋይነት፤ለጋሽነት፤ፈዋሽነት…ወዘተ.)ነበሩ ዛሬ በሕይወት እኛ ጋር ባይሆኑም ጀምረውት ያለፉት ራእያቸውን ትተውልን አልፈዋልና ሁልጊዜ አብረውን እንዳሉ ልንወስደው ይገባል።የተቀደሰ ዓላማቸው ግቡን እንዲመታ ማድረግን የሚያክል ኃላፊነት ተጥሎብናል።

ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ሕዝብን በእኩል አይን የሚመለከቱ ለሁሉም እጃቸውን የሚዘረጉ በልብ ቀዶ ጥገና በዓለም የታወቁ ሊቅ ነው የነበሩት።እንደሚታወቀው ህወሃት ከበርሃ ጀምሮ የሚቀናቀኑትን በተለይም ደግሞ አማራን ነገር በማፈላለግ እያጠፋ የመጣ ስለነበር ወደ መሐል አገርና ከተማ ሲገባም ያን አውሬያዊ ባህርዩን ይዞ ነው የገባው።ሻእብያ አስመራ ህወሃት አዲስ አበባ መንግሥት መሆናቸውን በግንቦት 16/83 እና በግንቦት 20/83 ካወጁ በኋላ በሰኔ ወር 1983ዓ/ም ህወሃት ልማዳዊ ባህርዩን ተግባራዊ ለማድረግ በየደረጃው የሚካሄድ ስብሰባ በማዘጋጀት የኤርትራን የአገርነት ጉዳይ የመወያያ አጀንዳ በማድረግ አስቀድሞ የኢትዮጵያ ምሁራንን አወያየ በዚህ አጋጣሚ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ በአንዱ ስብሰባ በመገኘት ሁኔታውን ካዳመጡ በኋላ 1/ኤርትራ አገር እንዳለመሆኗ 2/ኢትዮጵያ ወድብ አልባ መቅረት እንደሌለባት 3/የጎሳ ግዛት አስፈላጊ አለመሆኑንና በሕዝብ መሐከል አላስፈላጊ ቅራኔ ስጋትና አለመተማመን ያስከትላል በሚል ብዙው ተስብሳቢ አድፍጦ ዝም ሲል ፕሮፌሰር አስራት ተቃውሟቸውን በምሬት የገለጹ ሰው ነው የነበሩ።ክዚህች ቀን ጀምሮ ፕሮፌሰር አስራት ከህወሃትና ሻእብያ አይን ውስጥ ገቡ።

ከዚህ በኋላ የቀጠለው የበርሃው መፈክር በከተሞች እንዲሉ አማራና አማራነትን ማጥፋት የሚል መርሃ ግብር ወጥቶ በሐረር የተለያዩ ቦታዎች፤በአርሲ፤ወተር፤አርባጉጉ፤ቤንችማጅ፤ በደኖ ፤ጉራፈርዳ፤ጋቤላ፤ቤንሻንጉልና በመላው ኢትዮጵያ አማራን አሰቃቂና በጣም ጨካኝ በሆነ ዘግናኝ ሁኔታ መግደል፤በሳት ማቃጠል በገደል መስደድ፤ሳይሞቱ በሕይወት እያሉ ቆዳቸውን መግፈፍ በአጠቃላይ ይህ ቀረሽ በማይባል ሁኔታ የአማራው ነገድ ሕዝብ እንዲያልቅ ተደረገ።እንግዲህ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን ወደ ፖለቲካው ዓለም ብቅ ያደረጋቸው ይኸው ድርጊት ነው።በመሆኑም ወቅቱ አንድ ለአምስት የምትለዋ የህወሃት መዋቅር ገና ስለነበረች የሚተዋወቁ አብረው ያደጉና የሚተማመኑ በጋራ መክረው የመላው ዐማራ ድርጅት በሚል መዐድን መሠረቱ ፕሮፌሰር መስራች ነበሩ በኋላም ድርጅቱን በሊቀመንበርነት መርተዋል።ከዚህ ጎን ለጎን ደግሞ ህወሃት፤ሻእብያና ኦነግ አማራነትን አማራን ማጥፋት በሚለው መርህ አንድ በመሆን ዘመቻው በአማራው ላይ ሲነጣጠር ቀዳሚው ተግባር በስብሰባ ላይ የሞገቷቸውን ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን ሥነ-አእምሯዊና ሥነ-ልቦናዊ ተጽዕኖ ከማድረግ የዘለለ ጥቃት በመሠንሰር ታዋቂው ኃኪም ኃኪም አጥተው ከዚህ ዓለም በሕይወት ተለዩን።

መዐድ ፕሮፌሰር ከሞቱ በኋላ በድሮው ጥንካሬው ሊዘልቅ አልቻለም አሁን እየተባለ እንዳለው አማራ የሚባል የለም የሚሉ ከሃዲ ትውልዶች በአንድ በኩል በሌላ ወገን ደግሞ አማራው በጎሳ ከተደራጀ የህወሃትን ፈለግ መከተል ማለት ነው ስለዚህ አማራው በጎሳ መደራጀት የለበትም ብለው ሞገቱ መዐድ በመኢዐድ ሆነ በመኢዐድ ላይ ያረፈውን ዱላና ድርጅቱ አሁን በምን ሁኔታ ላይ እንዳለም እያየነው ያለ ጉዳይ ነው።የህወሃትን መንገድ የማይከተሉ በርካታ ድርጅቶች መመስረታቸው ይታወቃል ቁጥራቸው ብዙ ለጥቃት የተጋለጡ ሲሆን ህወሃት በሚጭረው ተንኳሽ ሁኔታ የተቃውሞ ድምጽ የሚያሰሙ ከተገኙ በቅድሚያ የሚለቀሙት የዚሁ ሞት የተፈረደበት የአማራው ነገድ ተወላጆች ናቸው።አብነት እንውሰድ ከተባለ በአንድነት ፓርቲ፤መኢዐድ፤ሰማያዊ ፓርቲ የተገደሉ የታሰሩ እነማን እንደሆኑ ሁላችንም የምናውቀው ጉዳይ ነው።እነ አንዷአለም፤የሽዋስ፤ሀብታሙ…….ወዘተ አማራ ሆነው ስለተገኙ ብቻ ነው ይህን የመሰለ መራራ ጽዋ እየተጋቱ የሚገኙት።

ህወሃት የሰላማዊ ትግሉን በር ዘግቶ አላፈናፍን ሲል የግፍ ጽዋው ሞልቶ ሲፈስ ብዙ መንገዶችን መከተል የግድ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን ትግሉን በተለያየ ስልት ጀምረዋል።የፊት ለፊት ሰላማዊ ትግል፤ዲፕሎማሲያዊ ትግል በውጭ አገር፤የትጥቅ ትግል…ወዘተ ይሁን እንጅ ሁላቸውም ሊሄዱበት የፈለጉትን መንገድ ፈትሾ ይህ ነው ማለት ይቻላል ይህን ለማለት የአዋቂነት መሥፈርት ማሟላት የግድ አይልም በዙ ጊዜ በትግሉ ዓለም የቆየ ሰው በቀላሉ ሊረዳው የሚችለው ጥሬ ሐቅ ነው።አንድ አጠር ያለች ምሳሌ ጠቅሼ ላሳያችሁ፦ፋሽስት የህወሃት መሪዎች አዘውትረው የሚናገሩት ስለ እድገት ነው።ሞጋቾች ደግሞ እድገት የሚለካው ከታች ያለውን የሕብረተሰብ ክፍል ሕይወት በመቀየሩና ባለመቀየሩ፤ሁሉም ዜጎች አገር ባፈራው ሀብት እኩል ተጠቃሚ በመሆንና ባለመሆን፤በመልካም አስተዳደርና የፍትሕ መረጋገጥ በማስፈንና ባአለመስፈን..ወዘተ አባባሉ ትክክል ነው ይህን የሚሰማው ሲኖር ነው።መጀመርያ እየተገዛን ያለው ህወሃትና ሻእብያን ኦነግ በለስ ባይቀናውም እነኝህን ፀረ-ኢትዮጵያ የሆኑ ድርጅቶችን አደቁነው ባቀሰሱ(ቄስ)ባደረጉ የምእራብና የዐረብ አገሮች ሲሆን እኛው ራሳችን በምንከፍለው ታክስ የአፋኙ ሥርዓት የበለጠ እንዲደራጅ በማድረግ በቀጥታ እየገዙን ያለ ሲሆን እኛው ተባብረን ሥርአቱን ካልገፋነው እነኝህ ጠላቶቻችን ወደሰውነታቸው ይመለሳሉ ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው። ኃይለማርያም ደሳለኝ ድርቁና ርሃቡ አሣሥቦኛል ሲል ይህን በል ያለው ይኖራል ወይም ኃላፊነት ተሰምቶት ሊሆን ይችላል ግምገማ እስከሚገባ ድረስ ።በሌላ በኩል አርከበ በምግብ ራሳችን ችለናል ርሃቡ ወይም ድርቁ አያሰጋንም በቁጥጥር ሥር እናውለዋለን ወይም አባይ ጸሐየ የኦሮሞን ሕዝብ ልክ እናስገባዋለን፤አባይ ወልዱ ወልቃይቶች የማንነት መብታችን ይከበር እኛ አማራ እንጅ ትግሬዎች አይደለንም ሆነንም አናውቅም ሲሉ የማዳግም እርምጃ እወስዳለሁ ማለቱ የሚያመላክተው እነዚህ ሰዎች ምን ያህል ከሕግ በላይ ርቀው መሄዳቸውን እንገነዘባለን።

ጠባቦች ናቸው ጎጠኞች ናቸው ካልን እንዲህ አስተሳሰቡ ስንኩል የሆነ በሌሎች ጥላቻ በተለይም በአማራው ነገድ ህዝብ ላይ በመከፋት ካደገ አመለካከተ ኩድኩድ ቡድን የምንጠብቀው ነገር ከዚህ በፊት የፈፀሙትን አሁን እየፈፀሙት ያለውን ወደ ፊት ሊፈጽሙ ያሰቡትን ብቻ ነው የሚሆነው።ልብስ ስንገዛ ወይም ምግብ ለመጉረስ ስንፈልግ ልቡሱን እንለካዋለን የምንጎርሰውን መጠንም በእጃችን ለክተን እንጎርሳለን የአጭር ወይም የረጅም ጊዜ ታክቲክና ስትራቴጅ ስንነድፍ የስተሳሰብ አድማሳችን ስፋትና ጥልቀቱን ማየት እንችላለን ህወሃቶች ሊያስቡ የሚችሉት ወርድና ቁመቱም እየተናገሩ ያሉትን ነው።አርከበ ወይም አባዮቹ የሚያስቡት የዘረፉትን የሀብት ክምችት ፤የገነቡትን ፎቅ ውጭ አገር ሰደው የሚያስተምሯቸውን ልጆቻቸውን በውጭ ያስቀመጡትን የገንዘብ መጠን ከሞት የሚታደጋቸውን የአጋዚ ሠራዊት መከላከያ ሠራዊት ፖሊስና ደህንነቱ የሚያቃሳዩትን ኃይል የተሞላበት ርምጃ ነው፤አቃቢ ሕግ የህወሃት ጠበቆች የሚፈጽሙትን የሀሰት ውንጀላ መሠረት ያደረገ ሥልጣን ከአንዱ ወደ ሌላው እየተላለፈ እስከ ዘልዓለሙ ሊገዙን የሚችሉበትን ነው የሚያስቡት የኢትዮጵያን ህዝብ የሚያስቡበት አዕምሮ በፍጹም አልፈጠረላቸውም የአዲስ አበባው መስፋፋት ፤በጎንደር ቅማንቶችን አደራጅቶ ከአማራው ጋር እንዲጋጩ ማድረግና ቅማንቶች ግዛታቸውን እስከ መተማና ቋራ እንዲያሰፉት ማድረግ ከዚያም የአንበሳውን ድርሻም እንዲያስረክቡ የማድረግ፤የወልቃይቱ ያልጠበቁት የማንነት ጥያቄና ሕወሃትን ከተከዜ ማዶ የማድረግ ከለሙ ሰሊጥ ጥጥና ማሽላ ሌላም የሚያመርተውን መሬት የሚያሳጣ ትግል ሲጀምር  ለህወሃት አደገኛ ምጻት ነው።ስለዚህ ሕገ አራዊትን ከሚከተል ሾተላይ ጋር እሰጥ አገባ ከማለት እስከ ወዲያኛው ድረስ እንዳያንሠራሩ አድርጎ የሚያሽልቡበትን መላ በጋራ ከመፍጠር ውጭ ሌላ ምርጫ የለም።

የህወሃት ዱላ እንዳያርፍባቸው የፈሩ ወይም ህወሃት የሚጥልላቸውን ፍርፋሪ በልቶ ለማደር ለሆዳቸው ብቻ የሚገዙ አማራዎች አማራ አይደለንም ቢሉ መልካም ሆኖ ሳለ አማራ የሚባል የለም የሚሉ አማራዎች አንዳንድ የቃጁ ምሁር ነኝ ባዮችና ጸሐፊያን ይህን የሚሉት ከጥላቻ በመነጨ መሆኑን ማወቅና ምላሹን መስጠት ሲገባ ከማንም ተጓዥ ጋር አብሮ መንጎድን ስለመረጡ ወዳጅ ዘመድ የሆነ ሊያዝንላቸው ይገባል የቻለም ቢጸልይላቸው የተሻለ ነው በግሌ ግን እንዲህ አይነት አባዜ ያለው ሰው ወይም ቡድን ይህን ፀያፍ አነጋገር ከፊቴ ቢናገር አማራነቴ የማንነቴ መገለጫ በመሆኑ ከምር የምጣላው መሆኔን ሊያውቅ ይገባዋል ለምን እሱን ወይም እሷን በማንነታቸው የሚያሳፍር ነገር አልተናገርኩምና።የአማራ ሥጋ እንደ በግና ፍየል በሚበላበት በዚህ ወቅት አማራ የሚባል የለም ወይም አማራ በጎሳ ከተደራጀ ጠባብነት ነው የሚሉ ከመስተኋላ ደግሞ ለህወሃትም ሆነ ለሌሎች በአማራ ላይ ጥላቻ ላላቸው ዱላ የሚያቀብሉና የአማራውን ዘር ለማጽዳና ለማጥፋት ከተሰለፉ ኃይሎች ጋር መተባበር የሚያስከፍለው እዳ ከበደ ያለ መሆኑን ከወዲሁ ሊያስቡበት ይገባል።

በአማራ ላይ ፎክረው የተነሱ ግልጽና የታወቁ ጠላቶች በመሆናቸው ምንም አይደለም ነገር ግን የነዚህ ጠላቶቻችን የጥቃት ሰለባ እንድንሆን ያዘናጉን ወይም እኛን መስለው እጃችን እየጠመዘዙ ተራ በተራ ታርደን እንድናልቅ ያደረጉ እንዲሁ በዋዛ ሊታለፉ የሚገባቸው አይደሉም።በለሳ ከሪጅን 3 በኢህአፓ ላይ አንጃ ፈጥረው ወደ ትግራይ በመሄድ የህወሃትን ቡራኬ ተቀብለው ኢህዴን የሚባል ስም ወጥቶላቸው ወደ አማራው ክፍለ ግዛት በመዝለቅ አማራ መስለው አማራውን በሁለት ወገን ጥይት እንዲንገበገብ ያደረጉት አማራዎች አይደሉም በርግጥ በውስጣቸው አማራዎች ነበሩ እነዚያ ግን አማራ ስለነበሩ ሁሉም በህወሃት አዛዥነት በኢህዴን ገዳይነት አልቀዋል።በዚህ ድርጊት ፊታውራሪዎች፦ታምራት ላይኔ፤ተፈራ ዋልዋ፤ህላዊ ዮሴፍ፤በረከት ስምኦን፤ታደሰ ካሣ(ጥንቅሹ)፤አዲሱ ለገሰ፤ካሣ ሸሪፎ የሚጠቀሱ ሲሆን ህወሃትን እየጎተቱ ወደ መሀል አገር ያስገቡበት ሂደትም በሌላ ወገን በደንብ አልተፈተሸም አሁን ደግሞ ብአዴን የሚል ስም ለጥፈው የአማራውን ነገድ ሕዝብ በከፋ ሁኔታ ዜግነቱን ገፈው ከአማራ ነገድ ጋር ምንም የማይገናኙ ገዥዎች ከላዩ ላይ ጭነው የቁም ስቅሉን እያሳዩት ይገኛሉ።

ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ይህን በአማራ ላይ የሚደርሰውን ክፉ ድግስ አስቀድሞ በመገንዘብ ነበር የመላው ዐማራ ድርጅት መመሥረት አለበት ያሉት የመሠረቱትም ይሁን እንጅ እሳቸው በነበሩበት ወቅት የነበረውን ጥንካሬ እንደያዘ ሊዘልቅ ባለመቻሉ በመሃሉ ብርድ ገባ አማራውን የሚታደገው ጠፋ በየደረሰበት ተዋከበ።ተሰደደ፤በግፍ ተጨፈጨፈ፤ሀብቱ ተዘረፈ፤መሬቱን ተቀማ በጥቅሉ በአማራ ላይ ያልተሞከረ መጥፎ ድርጊት አለማለት አይቻልም።እሳት ከነበረበት ረመጥ አይጠፋም እንደሚባለው ይህ በአማራ ላይ የሚፈጸመውን ግፍና በደል ታግየ አስቆመዋለሁ በትግሌ እበቀለዋለሁ የሚሉ ውድ የአማራ ነገድ ሕዝብ ቆራጥ ልጆች ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅትን በመመሥረት የፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን ራእይ ከግቡ ለማድረስ አማራውን ከሁለንተናዊ ጥቃት ለመታደግ የዘር ማጽዳቱና ማጥፋቱ አባዜ እዚህ ላይ ማክተም አለበት በሚል እነሆ እንቅስቃሴ ከጀመሩ ሦሥተኛ አመታቸውን ተያይዘውታል።በነዚህ 3ዓመታት ውስጥም ያልተጠበቁና አበረታች ተግባሮችን በመፈፀም የበለጠ ተጠናክሮ ለመራመድ አመች የትግል ስልቱን በመንደፍ እየገሰገሰ ይገኛል።ከዚህ ጎን ለጎን ግን ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ሥራዎቹ አልጋ በአልጋ ሆነውለት ነው የተጓዘው ማለት አይደለም። የሌሎቹ እንዳለ ሆኖ ራሱ አማራው ሞረሽን ተፈታትኖታል አሁንም እጅ እግራቸውን መስብሰብ ያልቻሉት እያደናቀፉ ይገኛሉ።በማህበር ላይ ማህበር፤በድርጅት ላይ ድርጅት መፍጠር የዘመኑ ፋሽን ቢሆንም ሞረሽ ወገኔ በከፍተኛ ደረጃ ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ተጠንቶ ለሕዝብ ይፋ የተደረገው በአማራ ላይ የተፈፀመ ግፍ በፍጹም ሊሰማቸው ያልቻሉ አማራዎችን ማየት እጅግ የሚያሳዝን ሰይጣናዊ ባህርይ ነው።

በመጨረሻም ፁሑፌን ከመቋጨቴ በፊት አማራ የለም ወይም አማራ አይደለሁም ብንልም የዘር ቆጠራ መሀንዲሱ ህወሃት እንደ እህል አበጥሮ ያውቃችኋልና ህወሃት እየደወለ ያለውን የአማራ ሞት ደወል ሰምታችሁ ራሳችሁን ከሞት ለማዳን ተነሱ ታጠቁ ይህ ፋሽስትና ቅጥረኛ ድርጅት በወገናችሁ ላይ ያደረሰውን ግፍ አጸፋው ለመመለስ ጥርስን ነከስ ወገብን ጠብቅ አድርጎ ታጥቆ ልኩን ማሳየት እንዲቻል ከሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት ወግኑ በያላችሁበት ሁለት ሦሥት ብትሆኑም ተሰባሰቡ ተደራጁ ኦሮሞችን እዩዋቸው እየሞቱም ትግላቸውን አላቋረጡም ጠንክሮ የታገለ ደግሞ ማሸነፉ አይቀሬ ነው ስለዚህ ይህን ግማሽ አካሉ መቃብር ላይ የገባ አውሬያዊ ስርአት አንዱ ሲታገል ሌላው እያረፈ በተራ በሚካሄድ ትግል አይደልም ከሥሩ ነቅሎ መጣል የሚቻለው።በአንድ ጊዜ በሁሉም ቦታ መዋከብና ሰላም ማጣት አለበት በተለይ ወልቃይት ላይ የተደቀነው አደጋ በቀላሉ የምንመለከተው አይደልም።1/የህወሃት ህልውና የማክተም ወይም የመቀጠል ጉዳይ ስለሆነ 2/ ጦርነት ቢጫር በመላ ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በየትኛውም አገር ሌሎች የሚወስዱት ርምጃ አስጊ በመሆኑ በዚህ ወቅት ያልተደራጀ ኢትዮጵያዊ ዜጋ አማራ ብቻ ስለሆነ አማራ ተጠንቀቅ።

  

የህወሓት 17 + 25 አመት የትግል ታሪክ በ200 ሚሊየን ብር ባጀት ተመድቦለት ሊጻፍ ነው ተባለ |ከአሥገደ ገ/ሥላሤ መቀለ

$
0
0

TPLF leaders

የህወሓት ታሪክ በመሪዎቹ አይጻፍም!!
ከአሥገደ ገሥላሤ መቀለ በ1997 /06/2008

የሀወሓት 17 + 25 አመት የትግል ታሪክ በ200 ሚሊየን ብር ባጀት ተመድቦለት ሊጻፍ ነው ተባለ::
መጽሀፉ ለመጻፍ የሚያሥተባቡሩ የበላይ ኮሚቴ አቶ አባይ ጸሀዬ ሥዩም መሥፍን ሥብሓት ነጋ ጀ/ ሣሞራ የኑሥ ገብረአበ ባርነባሥ ሌሎቹም ሆው ከነሡ በተጨማሪ ከከተሞች እሥከ ቀበሌ መረጃ የሚያሣባሥቡ የነሥብሀት የቅርብ ሠዎችና ታዛዞች ተወቅረዋል::
በአሁኑ ጊዜ መጽሓፉ ለመጽሀፍ የተገደዱበት አላም :
1ኛእነዚህ መሪዎች የየግላቸው የትግል ታሪክ በቤተሠቦቻቸው አድርገው ኳኩለው አጽፈው ነበር ነገርግን በህዝብም በታጋዮች ተቀባይነት በማጣታቸው አሁን ብዙሀኑ የተሣተፉበት ተበሎ ተቀባይነት አግኝተው የራሣቸው የግላላቸው አምልኮት በህዝብ ለማሠረጽና የሌላቸው ታሪክ ወረው የሀሦት ታሪክ ለመገንባት የሚያደርጉት ሥግብግብነት ነው::
2 የህዝብና የህወሓት ታሪክ ልንጽፍ ነን ብለው እጅግ ብዙ ገንዘብ ከህዝብ ለመበዝበዝና ሀብት ለመካበት:: ለዚሁ የሀብት መደለብ ኣላማቸው ለማሣካት በትግራይ ያለ የመንግሥት ሠራተኛ ዘቅተኛ ሠራተኛ የጥዳትና ዘበኛ ከ50 ብር እሥከ100 ብር: ሌላው ሠራተኛ ግመሽ የወር ደሞዙ እንዲከፍል : የትግራይ አርሦአደር ድሀና ሀብታም በማይለይ ገንዘብ እንዲዋጣ: በመላው የሀገራችን መአዝን የሚገኙ የትግራይ ነጋዴዎች:የመንግሥት ሠራተኞች ነዋሪዎች በሞቶዎች ሚሊዮን ብር እየተሠበሠበ ይገኛል:: እንዲሁም በውጭ አገር ከሚገኙ ወገኖች ከአጋር ፓርቲዎች ጭምር ገንዘብ ለመሠባሠብ ዘመቻ ተያይዘውታል :: በሌላ በኩል ከትግራይ ተወላጆች ውጭም ከህወሓት መሪዎችና ካድሬዎቹ ተጠቃሚዎች የሆኑ ኢትየጱያውያን እጅግ ቡዙ ገንዘብ እየተሠበሠበ ነው :: በአጠቃላይ በዚሁ መጸሀፍ ማሣተም በሚል ምክንያት የሀወሓት መሪዎች ቡዙ የህዝብ ገንዘብ እየበዘበዙ እንዳሉ ታውቋዋል ::
ለሚታተም መጽሀፍ ማሣተምያ የሚሠበሠብ ገንዘብ ገንዘብ ያዥ ህወሓት ከተፈጠረች ከገንዘብ ያዥነት ተለይቶ የማያውቅ ሥብሀት ነጋ ነው::
የመጽሀፍ ማሣተምያ ምክንያት አድርገው ለግላ ቸው ሀብት ሢሠበሥቡ የትግራይ ህዝብ ከነ እንሥሣ ዘቤቱ በድርቅ ምክንያት በረሀብ በውሀ ጥም እየተሣቃዬ አየሞተ እየተሠደደ ተበታትኖ እያለ መሆኑ መዘንጋት የለበንም :: በዋናነት ግን መላው የኢትዮጱያ ህዝብ ከመቸውም ጊዜ በከባድ ድርቅ እያለቀ እንዳለ የሚታወቅ ቢሆንም እነዚህ ሠዎች ይቅርና ለ90 ሚለዮን ህዝብ ሊየሥቡሥ ለዛ 17 አመት ታግሎ እሽኮኮ ብሎ 4 ኪሎ ቤተመንግሥት ላሥገባቸው ልጆቹ ወደ እሣት የማገዱበት ህዝብ እንካን አልሆኑም ሥሥታሞች ናቸውና::
3 ኛእነ አባይጸሀዬ ሥብሀት ሥዩም በአሁነ ጊዜ የህወሓት ታሪክ ሊያጽፉ መሯሯጧቸው ቡዙ ሙሁራን ወገኖች ተመራማሪዎችና ለታሪኩ በዋናነት በቅርበት የሚያውቁ ቅን ታጋየች እና ወጣቶች ሀቁን እየመዘዙ ቡዙ መጻህፍቶች ጽፈው ለንባብ በማድረሣቸው: አነዚህ ምርምሮች ለሀወሓት መሪዎች ማንነት እያጋጡ በመሆናቸው : በነዚህ መሪዎች ጭንቀት እየፈጠሩ ሥለመጡ ተመራማሪዎች የጻፉት ሀቀኛ አይደለም በሚል ለህዝብ ለመደናገር አላማ ያለው በሚሌኖች መጽሀፍት ለህዝብ ለመሠራጨት ታሣቢ በማድረግ ነው::
4ኛመጽሀፉ በአፋጣኝ ለመጻፍ እንዲሯሯጡ ያሥገደዳቸው በአዴን ባለፈው አመት የበአዴን የ35 አመት የትግል ታሪክ ብለው አብዛኛውን የመጽሀፉ ይዘት የትግራይ ሀዝብና ታጋይ ልጆቹ የሠሩት ታሪክ ማጡጦ ወሮ የራሡ ታሪክ አድርጎ የውሼት ታሪክ በመጻፉ በትግራይ ህዝብና ታጋዮች ቅር ሥላሠኜ ያን የህዝብ ሥሜት ተጠቅሞው መጽሀፉ ከጻፉት ተቀበይነት እናገኛለን ብለው እያጻፉት ያሉ መጽሀፍ ነው ::
5ኛ ይህመጽሀፍ አነማን ነው የሚጽፉት ? እሥከአሁን አንድ የታሪክ ሙሁር ከአክሡም ዩንቨርሢቲ ሥድሥት የታሪክ ሙሁራን ያልሆኑ አሥተማሪዎች ናቸው:: ከመቀሌ ዩንቨርሢቲ ናቸው :: እነዚህ መሁራኖች ከሥራቸው ሣይለቁ ደሞዛቸው እየበሉ ከነሥብሀት ነጋ በወር 15000 ብር እየተከፈላቸው በሁለት አመት ጌዜ መጽሀፉ ጽፈው ሊያሥረክቡ ነው የተዋዋሉት:: አነዚህ ጸሀፊዎች ሁሉም የህወሓት ታማኝ ካድሬዎች ሆነው የሀወሓት የመካከለኛ አማራር ልዩ ሥልጠና የተሠጣቸው ናቸው: :
ሥለዚህ የመጽሀፍ ከሚቴ ማነነተ ይጥላል::
ከጠሥገደ ገብረሥላሤ መቀለ

“ከክፉ ተወልጂ ስፈጭ አደርኩ”|በኢ/ር ይልቃል ጉዳይ ከይድነቃቸው ከበደ የተሰጠ ምላሽ –“ትናንት የግንቦት 7 ሰው ነው ስትሉኝ እንዳልነበር ዛሬ አትወይኑኝ”

$
0
0

Yidenekachew Kebede
ብዙ ነገር እየተባለ ነው ፤ የተባለው ሁሉ ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የእራስ አረዳድ የሚኖረው አሰተዋአዖኦ ቀላል አይደለም። ከዚህ በኃላ የፓርቲያችን አባላት እና ደጋፊዎች ማወቅ የሚገባቸውን እንዲያውቁት መደረግ አለበት።
.

ይድነቃቸው ከበደ

ይድነቃቸው ከበደ

በፓርቲያችን ለተፈጠረው ችግር ከመነሻው ጀምሮ እስካሁን ስላለው ሁኔታ በእያንዳንዱ ጉዳይ ላይ ምስክርነቴን እሰጣለው። ከጀርባ ሆኖ በብዕር ስም እንዲሁም እኔ ካልበላሁት ይደፋ አይነት መሰሪ ተግባር ወደ ጎን ትቶ በምክንያት እና በእውነት ላይ የተመሰረተ የሃሳብ ሙግት ለሚገጥመኝ ዝግጁ ነኝ።
.
በተለይ የጉዳዩ ቀጥተኛ ባለቤት የሆነው ሁላችንም ከፓርቲያችን ሊቀመንበር ጀምሮ የምናቀውን እውነት በአደባባይ የምንገልፅበት ትክክለኛው ጊዜ አሁን ነው።
.
በጋዜጠኝነት ሙያ ላይ የምትገኙ (ሁሉንም ማለቴ አይደለም) የራሳቸውን ፍላጉት እና ምኞት ከመጻፉ ባለፈ፥በእያንዳንዱ ጉዳይ ላይ ሲሆን ሲሆን”የምርመራ ጋዜጠኝነት”መሰረት ያደረገ ፤ ካልሆነ ደግሞ ቀለል ባለ ቃለ መጠይቅ የነገሮችን ሂደት በአግባቡ በማጤን ተገቢውን መረጃ ለህብረተሰቡ ማድረስ የሙያ እንዲሁም የህሊና ግዴታ ጭምር ነው ብዬ አምናለሁ ።
.
የማህበራዊ ሚዲያ ወዳጆቼ፤ የነገሩን ሥረ መሠረት በአግባቡ በማጤን፣ ገንቢ አሰተያየት በመስጠት፣ ለምንፈልግው የለውጥ ሂደት እና ለፓርቲያችን ግባት አጋዥ የሚሆን ትችትና ማበረታቻ በመስጠት የተለመደው ድጋፋችሁ ሊለየን አይገባም።
.
በዚህም መሠረተ ለዛሬው የምለው ነገር ቢኖር የሥነ-ሥርዓት ኮሜቴ በፓርቲያችን ውስጥ የተፈጠሩ ችግሮች በአግባቡ መርምሮ ውሳኔ የመስጠት አቅም እንደሌለው አረጋግጫለው።የሥነ-ሥርዓት ኮሚቴ በተሰጣቸው የኃላፊነት ቦታ የግል ፍላጎታቸውን እየፈጸሙበት ይገኛሉ።
.
ለዚህ እንደ ማስረጃ የማቀርበው ከ1 ወር 14 ቀን በፊት እኔ ከሳሽ ባልሆንኩበት በእኔ ስም የሚደረጉ የደብዳቤ ልውውጦች ተገቢ እንዳልሆነ በጻፍኩት ግልጽ ዳብዳቤ ገልጬላቸዋለው፤ይሁን እንጂ በትላንትናው እለት ባስተላለፉት ውሳኔ የከሳሽ ተወካይ እኔን በማድረግ ፣ተከሳሾች ባልቀረብበት ሆነ ተብሎ የፓርቲውን ደንብ ያልተከተለ ህግ ወጥ ውሳኔ አስተላልፈዋል።
.
በዚህ ጉዳይ ላይ 21የምክር ቤት አባላት፣የሥራ አስፈጻሚ ኮሜቴ፣ የኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን አባላት በተገኙበት የምክር ቤት ስብሰባ ላይ “በእኔ ስም የሚደረጉ ማናቸውም የክስ ሂደቶች እኔን የማይመለከት ነው፣ከዚህ በኃላ ምክር ቤቱ የሚፈልገውን ተወካይ መመደብ ይችላል”በማለት ጥር 29 ቀን 2008 በነበረን ስብሰባ ላይ ተናግሪያለው። ይህን ሁሉ እውነታ ወደ ጎን በማድረግ ለፓርቲያችን የማይጠቅም ሂደቱን በአግባቡ ያልጠበቀ ተደጋጋሚ ውሳኔዎች፤ በሥነ-ሥርዓት ኮሜቴ እየተላለፈ ይገኛል።
.
በተጨማሪ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፤ መጋቢት 16 ቀን 2008 ዓ.ም ለብሔራዊ የኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን በጻፉት ደብዳቤ ፤በሥነ-ሥርዓት ኮሜቴ ላይ ያላቸውን ቅሬታ ከገለጽበት መካከል ” ከሳሽ የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት መሆኑ በማስርጃዎች መረጋገጡ እየታወቀ፤በምክር ቤት ሰብሳቢ ስም አቶ ይድነቃቸው ከበደ ነው የከሰሳችሁ መባሉ “ተገቢነት የሌው እንደሆነና የሥነ-ሥርዓት ኮሚቴ ከወቀሱበት መካከል አንዱ ጉዳይ ነው።
.
በመሆኑም ይህን ኮሜቴ ያቋቋመው የሰማያዊ የኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን ነው፤ የኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን ጉዳዩ በአግባቡ መርምሮ ተገቢ ውሳኔ ማሳለፍ ይኖርበታል ብዬ አምናለሁ ።
.
የዛሬውን ለማጠቃለል ፤ትላንትና የግንቦት 7 ትልቅ ተልእኮ የተሰጠው ፣ዋንኛ የግንቦት 7 ሰዉ ነው ሲሉኝ የነበሩ ፤አሁን ደግሞ እነሱ ወይነው እኔን ሲወይኑኝ ስመልከት፤በልጆቹ የሃሳብ ልጅነት እንደትላንትናው ዛሬም መታዘቤ እንደቀጠለ ነው።
.
በነገራችን ላይ “ከክፉ ተወልጂ ስፈጭ አደሩኩ ” ብዬ ለዚህ ጽሁፍ አርእስት የተጠቀሙት ለምን እንደሆነ በቃጣይ እመለስበታለው።ባለፈውም “እውነቱን ማወቅ ለሚፈልግ”በሚል የጀመርኩት ክፍል አንድ ፤ለንባብ ከበቃ በኃላ ክፍል ሁለት ያልቀጠልኩት የሚቀጠለ ሳይኖር ቀርቶ አይደለም ፣ለውስጥ ጉዳይ ቅድሚያ ልስጥ ብዬ ነው።አሁም እንደ-አመጣጡ ቅድሚያ እሰጣለሁ ።

የቤልጂየም የሽብር ጥቃት ጠንሳሾች ማንነት እና ዓለማቀፋዊ ምላሾች |የታምሩ ገዳ የድምጽ ትንታኔ

$
0
0

የአውሮፓ ሕብረት እና የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን አገሮች (ናቶ) መዲና በሆነችው ቤልጂየም ብራስልስ ከተማ የሰሞኑ የሽብር ጥቃት ጠንሳሾች ማንነት እና ዓለማቀፋዊ ምላሾቹ ሲቃኙ (ልዩ ጥንቅር)


የቤልጂየም የሽብር ጥቃት ጠንሳሾች ማንነት እና ዓለማቀፋዊ ምላሾች | የታምሩ ገዳ የድምጽ ትንታኔ


የማለዳ ወግ…“ የልጀን ነገር አደራ እባክህ ነፍሴን አሳርፋት ”እናት ሎሚ ረጋስ

$
0
0

hana

Lomi regasa
===============================================
* በሐዘን የሚላዎስ እንስፍስፍ የእናት አንጀት
* የኮንትራት ሠራተኛዋን እህት ቤዛን አፋልጉኝ !

ሆዴን ያላወሰው የእማማ ሎሜ አደራ !
========================
የእናትን መሪር ሐዘን ሰምቸ ሆዴ ተላውሷል፣ የእናትን ጥልቅ ጭንቀቷ፣ ያለ አባት በአሳር በመከራ ያሳደገቻት የእናትን ሎሜ መሪር ሐዘን ተረድቸ ህመም መታመሜ እውነት ሳለ በዝምታ እየቆሰልኩ ማስረጃ መረጃ ፍለጋ መዋተቴ ህመሜን አክብዶታል፡፡ ከጉያዋ ወሽቃ፣ በትንፋሿ አሙቃ፣ ስታገኝ በደስታ፣ ስታጣ ተከፍታ ድሃ አደግ ቤቷን አሟሙቃ ነገን ልጆቿን ለወግ ለማዕረግ የማድረስ ምኞት ተስፋን ሰንቃ ተስፋዋን የተነጠቀች እናት እንባ ውስጤን አድምቶ አቃጥሎታል። እናት ዛሬ ማለዳ በላኩልኝ መልዕክት እንዲህ ይላል “ የልጀን ነገር አደራ እባክህ ነፍሴን አሳርፋት ” … ሰው ሆዬ ሲጨንቀው እኔ መረጃን ከምንጩ ከማሰራጨት ባለፈ ሁሉን ማድረግ የሚቻለኝ አድርጎ ይስለኛል ፤ እኔ ግን አቅሙ የለኝም ! መረጃዎችን ለወገናቸው ጥቅም ቅድሚያ ከሚሰጡ የመንግስትና የድርጅት አባላት በሚስጥር ፤ ከቀሩት ወገኖች በአደባባይ የሚደርሰኝ መረጃ የተጣሰው የስደተኛ መብት ይከበር ዘንድ ሁሌም የመረጃ ጉልበቴ ነው ! ያገኘኋቸውን መረጃዎች እያጣራሁ ሰሚ ቢገኝ አቀርባቸዋልሁ ! ከዚህ ባለፈ ጉልበት የመርዳት አቅሙ እንደሚገመት የለኝም !

በተለያዩ አቅጣጫዎች መረጃን ፈላፍየ የማግኘቴን ያህል ግን ለመብት ማስከበሩና ለመፍትሔው የመንግስት ተወካይ የቆንስልና ኢንባሲ ሰዎች እንጅ እኔ አቅም ስልጣኑ የለኝም …በመንግስት ተወካዮቻችን በኩልማ መረጃን ለማግኘት እንኳ ከአንድ ተራ ዜጋ ያነሰ መብት እንዳለኝ ስንቶች እንደሚረዱ አላውቅም ! መረጃ በማቀበሌ ብቻ “መንግስትን አትወድም ፤ ተቃዋሚ ነህ ” የሚሉኝ ካድሬዎች አንድ መረጃ ሳቀርብ በአካልና በዋትሳፕ በቡድን ተሰባስበው “ በነቢዩ ጽሁፍ ላይ እንዝመት ፤ መልስ እንስጠው ! ”እኔ የማነሳቸውን ጉዳዮች እንኳ መርምረው ስለሰብዐና ብለው ፣ ፈጣሪን ፈርተው በስደት የተጨነቀ ወገናቸውን አይደግፉም ፣ ስለሰብዕና የቆመው ፣ ወገኑን የደገፈውን በስውር ያሳድዱታል ፣ ለእነሱ ሁሉም ነገር ድርጅታቻው ነው እነሱ እንዲህ ናቸው… !

እኔ የሆነና የተጨበጠ ግልጽ ያለ መረጃ ሳቀርብ እነሱ የተንሸዋረረ ስም ማጥፋቱ ልማድ አድርገውታል ! … በዚህ መካከል የተገፋው ወገን ድምጽ ከፍ ብሎ ይሰማኛል ! የእናት ሎሜ ረጋስ የአደራ መልዕክት ደግሞ የእኔን የጨካኙን ልብ አርዶታል ፤ ሆዴን ያላውሶታል … እኒህን እናት ምን ላድርጋቸው ? ከሰሞኑ በውስጤ እየተብላላ ሰላም የነሳኝ እንደ እናት ሎሜ ረጋስ እዚህ ደረጃ ያልደረሱ በሺዎች የሚቆጠሩ ልጆቻቸውን በኮንትራት ልከው ደብዛው የጠፋባቸውን በገጠር ያሉ እናቶችን አስብኳቸው … ታምሜ ሰንበትኩ ፤ በቤቴ ውስጥ ሳይቀር ሰላም አጣኝ ፤ ህመሜን ተረድቶ የሚያክመኝ ባጣም ችየው የእናት ሎ ሜን አደራ ለመወጣት የቤዛን ታሪክ በጨርፍታ አሳውቃችኋለሁ !

እህት ቤዛን ሳውዲ ያደረሳት መንገድ … !
===============================
በሃያዎቹ የእድሜ ክልል የምትገኘው እህት ቤዛ አሸናፊ እንግዳ ከአሰላ ተነስታ በቦሌ አየር መንገድ በኩል ለተሻለ ኑሮ ፍለጋ ወደ ሳውዲ አረቢያ ያቀናችው ከሶስት አመት በፊት ነበር ። ከዚያ ወዲህ ብዙ ጊዜ ከቤተሰቧ ጋር ትገናኝ ነበር፤ መስከረም 18 ቀን 2008 ዓም ከእህቷ ጋር ከተገናኘች ወዲህ ግን ድምጿ ጠፍቷል። ቤተሰቦችዋ ከወሰዳት ኤጀንሲ እስከ ሳውዲ አሰሪዋ ድረስ በየአቅጣጫው ሲያፈላልጓት ሰንብተው ለመጨረሻ ያገኘኋት በአሰሪዋ በኩል መረጃ ተገኘ። አሰሪዋ የቤዛን ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷን አስረድተው በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሞቷን እንዲያረጋግጡ አሳወቋቸው፡፡ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርም ስለ አሟሟቷ ምንም ማስረጃ ሳያቀርብ ቤዛ ራሷን ሰቅላ መግደሏን ለቤዛ ቤተሰቦች አረዷቸው። እናትና የቀሩት ቤተሰቦች ከሀዘኑ በላይ ሞተች የተባለበት መንገድና ስለመሞቷ የፎቶም ሆነ የሰነድ መረጃ አለመቅረቡ ሓዘናቸውን መሪር አደረገው። የቤዛ ቤተሰቦች በዚህ ሁኔታ የሚይዙ የሚጨብጡት አጥተው “ሬሳዋ ይላክልን አስመጡልን” ብለው ሲጠይቁ የቤዛ አስከሬን ተቀብሯል“ የሚል መልስ ተሰጣቸው። ሞተች የሚለውን ማመን የገደዳቸው እናት ሎሜ ረጋስ መላው ቤተሰብ በቤዛ ዙሪያ የሆነውን በጥርጣሬ ማየት ጀመሩ፡፡ ወላጅ ቤተሰብ ሳይጠየቅና ሳይፈቅድ ምን ሲባል የቤዛ አስከሬን ሳውዲ ላይ ተቀበረ? ለምን? እንዴት? ይህን የቤተሰብ ውል ያለው ጥያቄ ነው ፤ ቤተሰብም እኛም ወላጅ ቤተሰብ ሳይጠየቅና ሳይፈቅድ ምን ሲባል የቤዛ አስከሬን ሳውዲ ላይ ተቀበረ? ለምን? እንዴት? እንጠይቃለን !

የቤዛ ቤተሰቦች በተለይም እናት ሎሜ እርማቸውን ሊያወጡ በማይችሉበት መንገድ ከሀዘን ላይ ሐዘን ተደራረበ፤ ተጫነባቸው፡፡ ቤዛ ራሷንና ድሃ አደግ ቤተሰቧን ለመደገፍ ሕጋዊ በተባለው ኤጀንሲ ቪዛ ይዛ ለስራ ወደ ሳውዲ መላኳ እውነት ነው ። በተላከችበት ሃገር በስራ ላይ እንዳለች ስለመሞቷ ቤተሰብ ፈለገው ባይጠይቁ የተገኘው መረጃም ላይገኝ ይችል እንደነበር ቤተሰቦችዋ ያስረዳሉ። ሞታለች የሚለው መርዶም ድፍንፍን ያለ መሆኑ ቤተሰቡን ግራ አጋብቶታል። የተነገራቸው መረጃ የተዛባ ነው እስከ ማለት ደረሰዋል። በዚህ የመከራ አጣብቂኝ ለወደቁ ቤተሰቦች ከቀናት በፊት የለቀቅኩት የአሚናት መረጃ ተስፋን አጭሮባቸው እኔኑ ማፈላለግ ጀመሩ። በእርግጥም ሞታለች ተብሎ ተነግሯቸው በሐዘን ተቀምጠው እርማቸውን ባወጡ በሁለት ዓመታት አሚናት መዲና በሚገኝ አንድ ሆስፒታል ተገኝታለች። በውል የማይታወቅ የመኪና ግጭት አካሏ ጉዳት ከደረሰባት ከሁለት ዓመት በኋላ አሚናት በአብሮ አደጓ በእህት ሀድያና በቀሩት ወገኖቿ ትብብር ሐገር ቤት ገብታለች፣ ለሀገሯ ምድር በቅታለች። ከእናቷና ቤተሰቦቿን ተቀላቅላለች። የአሚናት እውነት የቤዛን ቤተሰቦች ልጃቸው በተመሳሳይ መንገድ እንደ አሚናት ትመጣ ይሆናል የሚል ተስፋን አጭሮላቸዋል፡፡ እናትና እህት የአሚናትን ታሪክ ከሰሙ በኋላ ቤዛ አለች ብለው ተሰፋ አድርገዋል፡፡ “ራሷን ሰቅላ ሞተች ”ተብሎ የተነገራቸው አላምን በለው ትተውታል፤ በአንጻሩ ያችን የደስ ደስ ያለት የሚያውቋት ቤዛ “ትመጣለች” ብለው ዓይናቸው በተስፋ ይዋትት ይዟል፡፡… የቤዛ ነገር ግን የውሃ ሽታ ሆኖ ቀርቷል፡፡ የቤዛ ቤተሰቦች እንደ አሚናት ሁሉ ቤዛ የፈለገውን ጉዳት ደርሶባትም ይሁን በሕይወት ትቀላቀላቸው ዘንድ ጓጉተዋል … የልጃቸውን ጉዳይ አጣርቸ እንዳሳውቃቸው ደግሞ እኔኑ ፍለጋ ይዘዋል …

ስለ እህት ቤዛ ዝርዝር መረጃ !
==========================
ከተባበሩት ኢምሬት አድራሻየን አግኝታ ልብ ሰባሪውን የቤዛ ታሪክ ያጫዎተችኝ እህት የቤዛን እናት እና የመላ ቤተሰቡን ሐዘን ጫፍ ጫፉን ነበር። ስለሆነው ሁሉ ሙሉ መረጃን አደንደሚያስፈልገኝ ገልጨላት ብዙም ሳይቆይ ከቤዛ እህት እህት ከመአዛ አሸናፊ ጋር አገናኘችኝ፡፡ ከመአዛ በዋትሳፕ ተገናኝተን ስለ ቤዛ ብዙ አጫዎተችኝ ፤ መአዛና ቤዛ መስከረም ሲጠባ በፊስ ቡክ ይገናኙና ያወሩ እንደነበር ፣ ቤዛ ወደ ሃገር ለመምጣት ዝግጅት ላይ እንደነበረች እህት መአዛ ገላልጣ አወጋችኝ ፡፡ የእናቷን መከራና ቤተሰቡ የገባበትን የሐዘን ማጥ ስትናገረው ደግሞ ልብ ይሰብራል፡፡ የቤዛ እናት ወ/ሮ ሎሚ የልጃቸውን መሞት በመረጃ አስረግጦ የነገረቸው ስለሌለ እንደ አሚናት እናት ወ/ሮ ወርቅነሽ ልጃቸው አደጋ ደርሶባት ተደብቀው እንጅ “ሞተች” ብለው ለማመን ገዷቸዋል። እናም ሌት ተቀን “እህህ” እያሉ እንባቸውን በማዝራት በር በሩን በማየት ቤዛን ይጠብቃሉ … የእናት አንጀት! ምስኪኗ እናት የወ/ሮ ሎሜ ረጋስ ከዓመታት በፊት ወደ ሳውዲ የመጣች አንድ ፍሬ ልጃቸውን በመላከ ሞት የመነጠቃቸው መርዶ እንደ ቀላል፣ እንዳአልባሌ ነገር “ልጅሽ ቤዛ ራሷን ሰቅላ ሞታለች” ተብለው ጎረቤት፡ ዘመድ አዝማድ፤ እድርተኛ ተሰብስቦ፣ ደረት ተመቶ ፣ ሙሾ ተደርድሮ ሀዘን ቢቀመጡም “ቤዛ ሞታለች” ብለው አላመኑም፡፡ በሐዘን ላይ መሪር ሐዘን ተደራርቦባቸዋል፣ ቅስማቸው ተሰብሯል፡፡

የቤዛ ቤተሰቦች ቤዛ ሞተች በተባለበት የጅዳ ከተማ የምገኘው ለእኔ አፋልገን ብለውኝ ፈቃደኛ መሆኔን አሳውቄያቸዋለሁና በእኔ ላይ ተስፋ ጥለዋል፤ እንዲህ አሉኝ “ነቢዩ ቤዛ ጤነኛ ነች፣ ራሷን ስታ አትታነቅም፣ ግን ሞታም እንደሁ ስለአሟሟቷ መረጃ ሰባስበህ ሞተች በለን ! ካለችም አለች ብለህ የደስታ ብስራት አሰማን፤ እኛ የምንፈልገው በልጃችን ላይ የሆነውን ማወቅ ብቻ ነው፤ እባክህ ተባበረን፡ እባክህ እርዳን” የሚለው መልዕክት ደጋግመው አድርሰውኝ ነበርና ተጨናንቄያለሁ፡፡ ወላጅ ቤተሰብ በውጭ ጉዳይ በኩል የመቅበሪያ ውክልናና ካልላኩ ማስቀበር እንደማይቻል አሳምሬ ባውቅም ፡የቤዛ ከቤተሰብ እውቅና ውጭ መቀበር በእርግጥም አሳሳቢ ነው፡፡ የቤዛ ቤተሰቦች ቤዛ የሆነችውን አፈላልገህ፤ አጣርተህ አሳውቀን ቢሉኝም ፤” ሞተች“ ተብሎ ፎቶም ሆነ ተዛማጅ መረጃ አልቀረበላቸውምና ”ቤዛም ትመጣልናለች“ ብለው በተስፋ እየተጠባበቁ መሆኑ ደግሞ ከብዶኛል፡፡ የከበደኝ ያለ ነገር አይደለም፣ ወላጅ ዘመድ ሳይሰማ፣ ማንነታቸው ሳይረጋገጥ እንደወጡ የቀሩ ብዙ የስደት ታሪኮችን መስማት ሳይሆን አይቻለሁና የወላጅ ህመሙ ዘልቆ ያማል !

የቤዛ ቤተሰቦች ”እባክህ ቤዛን አፋልገን!” እናት ተማጽኖ ካቀረቡልኝ ሳምንት አለፈው ፤ ሰምቸው እንዳልሰማሁ ተረጋግቸ ጉዳዩን ውስጥ ውስጡን ማጣራት ይዣለሁ ፤ የቤዛን እህት በተደጋጋሚ ፎቶ እንድትልክልኝ አድርጌ እያቀረብኩና እያራቅኩ በመጠለያው በር ላይ በተደጋጋሚ ወድቀው ካነሳኋቸው እህቶቸ ፎቶዎች ጋር ባመሳስለውም ቤዛን አላገኝኋትም ። ቤዛ አዕምሮዋ ታውኮ ራሷን መሰቀሏን በሰበር መረጃ አቅርቤው ነበርና እሱንም ተመለከትኩት ፤ ራሷን ሰቀለች የተባለችው እህት ደግሞ የልጆች እናት መሆኗን ከመጠለያው በወቅቱ ያገኘሁት ያስረዳል ። ይህም ከቤዛ ጋር አልገናኝ አለኝ … ሌላ መረጃ አስታወስኩ ፤ ራሷን ሰቀለች የተባለችው እህት ከመሞቷ ከቀናት በፊት በጀዳ ቆንስል የቅርብ ርቀት ግቢ አትግቢ በሚል የነበረውን ግርግር የሚያሳይ በሚስጥር የተነሳ ተንቀሳቃሽ ምስል በእጀ ይገኛልና እሱኑ እያቀረብኩና እያራቅኩ ማየቴን ቀጠልኩ … ጩኸት ግርግሩ ይታያል ! የዚያች እህት ምስል ግን ብዙም ግልጽ አይደለም ፤ ከቪዲዮው ፎቶ አንስቸ ለቤዛ ቤተሰቦች ላኩላቸው ። ለመለየት ተቸገሩ … እንዲህ እንዲህ እያልኩ ሳምንት ገፋሁት … ተደጋግሞ የሚደርሰኝ የቤዛ ቤተሰቦች ጭንቀትና ተማጽኖ አላስቀምጥ አለኝ ! ሰምቸው ጉዳዩን እስካጣራ ብየ ለጊዜው የዘለልኩት ፣ ግን ሰላም የነሳኝን የቤዛን እናት ጭንቀት የቤዛ ቤተሰቦች የሚያስረዳውን ከእህቷ ከቤዛ የደረሰኝ አንዱን የድምጽ መልዕክት ከፍቼ መስማቴን ቀጠልኩ… እንዲህ ይላል !

“እባክህን ነበዩ ከጎናችን ሁን፣ ይህን የመጣብንን ነገር ተባብረህን የሆነ ነገር ላይ እንድንደርስ እፈልጋለሁ፣ እባክህን! በቃ ከምነግርህ በላይ ነው፡፡ በተለይም እናቴ በጣም እየተጎዳች ነው :: ምን ማድረግ እንዴት ማድረግ እንዳለብኝ እንኳን ግራ እስኪገባኝ ድረስ በጣም ተጎድታለች፡፡ እሷ ነች ያሳደገችን ፣ አባታችን ልጅ ሆነን ነው የሞተው ፡፡ በመጨረሻም የእሷ ክፍያ ይሄ ሆነ፡፡ እና የሚሰጡን መረጃ እንዳልኩህ በጣም የተለያየ ነው፣ እ …ጓደኛዋን ሳናግራት ነበር ፤ እዛው ዘመድ ቤት የምትሰራ ልጅ ነችና ሰውየየ የነገረኝ ከመዲና፣ የሚኖሩበት መዲና ነው፣ ወደ ጅዳ ስትጠፋ ነው፣ እ …ዱርየዎች አግኝተዋት ተጫውተውባት ከዚያ ውጭ ላይ የጣሏት፣ ዓይነት ነገር ነው የነገረኝ የእኔ ሰውየ፣ ሰውየየ አይዋሽም ብላ ነው የነገረችኝ፡፡ ከኢንባሲ (ከጅዳ ቆንስል ለማለት ነው) በኩል ደግሞ የምትሰማው ያው እንደነገርንህ ራሷን እንዳጠፋች ነው የሚናገሩት፡፡ በጣም እኔ እንጃ ዝብርቅርቅ ነው ያለብኝ፣ በምትችለው ነገር ተባብረህ የሆነ ነገር ላይ እንድትደርስልን እለምንሃለሁ ! በቃ በምትችለው ነገር!! የሆነ ብቻ ትክክለኛውን ነገር ቢያንስ ቢያውቅ ሰው አዕምሮው ያርፋል ፡፡ ሁለተኛ ነገር የአስከሬኑ ጉዳይ ራሱ እንዴት? ማን? መጠየቅ እንዳለብኝ አላውቅም ነብዩ፡፡ ከሥራህ በተጨማሪ እንደወንደምነት ነው የምጠይቅህ፣ እንዴት ማድረግ እንዳለብን አላውቅምና ካንተ ራሱ ምክር እፈልጋለሁ በቃ ፡፡ ማንም የለም ከጎናችን ፣ እንዳልኩህ እናታችን ነው ያሳደገችን ሌላ ከጎናችን ሆኖ የሚረዳን የሚያግዘን እንደዚህ እንደዚያ አድርጉ ብሎ የሚነግረን የለም! እዚህ ካሳንችስ ሄደን ነበረ፣ ምንም ዓይነት መረጃ የለም፣ እንዲጠየቅላችሁ የምትፈልጉት ካለ ፎርም ሙሉ ብሎ ነግሮኛል ሰኞ ሒጀ እሞላለሁ፣ እስኪ የሚያመጡትን ነገር ከዚያ ካለ አያለሁ ! እኛጋ ወረቀት ተቀብሎ ቁጭ ማድረግ ነው፣ እኔ “ እህቴ ድምጿ ጠፍቶ ወር ከ15 ቀን ሳይሞላ ነበር ለሄደችበት ኤጀንሲ ያሳወቅኩት፣ ጠፍታብኛለችና እናንተ መጠየቅ በሚገባችሁ በኩል ጠይቁልኝ ”ብየ ሰጠሁት፣ ግን ምንም ዓይነት መልስ አልሰጠኝም፡፡ በእኛም ጥረት ላይ ነው እዚህ ላይ ያለው፡፡ ግን እየተሰጠን ያለው ኢንፎርሜሽን ደግሞ የተለያየ የተዘበራረቀ ነው፣ እባክህን እ ባ ክ ህ ን አንተ አንድ እንድታደርግ እፈልጋለሁ፣ በቃ ! እግዚአብሔር ይርዳህ አንተንም፡፡ ምንድነው ማድረግ ያለብን ነገር? ከዚህ ውጭ ደግሞ የራስህ የሆነ ስለሠራህበት ስለምታውቅ ስለሠራህበት የተወሰነ ምክር እንድትሰጠኝ !” ይላል ሙሉ መልዕክቱ…

እናም የቤዛን ቤተሰብ አቤቱታና የጭንቀት የድረሱልን ጥሪያቸውን ይድረሳችሁ፤ ስለ እህት ቤዛ አሸናፊ እንግዳ መኖርና መዳረሻ ዙሪያ የተጨበጠ መረጃ ያላችሁ ወገኖች ታሳውቁን ዘንድ አደራየ የጠበቀ ነው ! ” እህት ቤዛን አፋልገን ” በማለት አደራ የሰጡኝ የሚማጸኑኝ የእናትና የቤተሰቡን ጭንቅ ተረድታችሁ ያላችሁን መረጃ ታቀብሉን ዘንድ በትህትና እንማጸናልን !

ቸር ያሰማን !

ነቢዩ ሲራክ
መጋቢት 21 ቀን 2008 ዓም

አንድ ሰሞን ከሙኒኮች ጋር |በኤፍሬም ማዴቦ

$
0
0

Ephrem-Madebo-DC
አባባ . . . አባባ . . . . ስማ አባባ ረሳህ እንዴ አለኝ ያ ባለፈዉ ነኃሴ ወር ስንለያይ ያስለቀሰኝ ልጄ። ምኑን አልኩት። ቅድም ምሳ ላይ የነገርኩህን . . . እንዴ! እሱንማ እንዴት እረሳለሁ። Please don’t አባባ! …… I will not! ሲረጋጋና ደስ ሲለዉ ታየኝና ልቤን ደስ አለው። ልጄ ኮሌጅ የሚገባበት ቀን እኔ ደግሞ ከትግል ጓደኞቼ ጋር የምንገናኝበት ቀን ናፍቆናል። አባባ Good luck አለኝ። እኔም ይቅናህ አልኩት። Good luck እና ይቅናህ የተባባልነው እኔ እሱ የሚመኘዉ ኮሌጅ እንዲገባ እሱ ደግሞ እኔ በድል ኢትዮጵያ እንድገባ ነበር። ሁለታችንም ይቅናን . . . አሜን!!!

አዉሮፕላን ዉስጥ ገብቼ ከተረጋጋሁ በኋላ ኢር ፎኑን ጆሮዬ ውስጥ ሰክቼ አይፎኔ ላይ “Play” የሚለዉን ስጫነዉ ጥላሁን ገሰሰ “አራዊቱ ሁሉ መጥቶ ቢከበኝ” እያለ ጀመረኝ። የምወደው ዘፈን ነበርና ደጋገምኩት። ጥላሁንኮ ድምጻዊ ብቻ አይደለም ነቢይም ነዉ፤ የዛሬ ስንትና ስንት አመት በአራዊቶች እንደምንከበብ ተንብዮ ነበር። የሚቀጥለው ዘፈን ገና ሲጀምር ምን መሆኑ ታወቀኝና. . . . . ኧረ በፍጹም. . . እንዴት ተደርጎ አልኩና አይፎኔን ዘግቼዉ ኪሴ ዉስጥ ከተትኩት። “መለያየት ሞት ነዉ” የሚለዉን የጥላሁን ገሰሰ ሙዚቃ ብወደዉም የጠነከረዉ ሆዴ እንዲባባ በፍጹም አልፈለኩም። አይፓዴን አወጣሁና የአስናቀች ወርቁን ሰዉነት እየሰረሰር ገብቶ አንጀት የሚያርስ ክራር መኮምኮም ጀመርኩ። አስናቀች ኢትዮጵያን ጨምሮ ብዙ ቦታ ወሰደችኝ፤ ደግነቱ ዬትም ትዉሰደኝ ዬት መልሳ መላልሳ እዚያዉ አዉሮፕላኑ ውስጥ ታመጣኝ ነበር . . . አለዚያማ!

አዉሮፕላኑ ወንበር ላይ አንደተኛሁ ከአንድ ጎኔ ወደ ሌላዉ ጎኔ ስገላበጥ ሁለት የተለያዩ ድምጾች ተራ በተራ ጆሮዬ ዉስጥ ገቡ። ከአይፓዴ የሚወጣዉ ድምፅ “እልም አለ ባቡሩ” ይላል፥ የአዉሮፕላኑ ድምጽ ማጉያ ደግሞ “Welcome to Munich” ይላል። እንቅልፋም አይደለሁም፥ እንቅልፌን ሳልጨርስ የሚቀሰቅሰኝ ሰዉም ሆነ ምንም አይነት ድምጽ ግን ጠላቴ ነዉ። ደግሞም የእንቅልፍ ነገር ሆኖብኝ ነዉ እንጂ ሙኒክ መድረሴን ወድጄዋለሁኮ።

እኔንና ሌሎች ከ180 በላይ መንገደኞችን የጫነዉ ዩናይትድ አየር መንገድ በረራ ቁጥር 106 አዉሮፕላን ጎማዎች ከሙኒክ አዉሮፕላን ማረፊያ ወለል ጋር ሲላተሙ ያ ለካሳ ተሰማ ዘፈን አልበገር ያለዉ እንቅልፌ ዳግም አይመጣ ይመስል እልም ብሎ ጠፋ። እኔም የምን እንቅልፍ አልኩና ሙኒክን ለማየት ቸኮልኩ። ሙኒክ ሲባል ከልጅነቴ ጀምሮ እሰማለሁ እንጂ እቺን ዉብ የባቫሪያ ከተማ ሳያት የመጀመሪያዬ ነበር። አይፎኔን አወጣሁና ከአስመራ አሜሪካ ከገባሁ ጀምሮ ስልክ እየደወለ ሙኒክ ካልመጣህ እያለ ለሚጨቀጭቀኝ የአገሬ ሰዉ ስልክ ደወልኩ. . . . ጋሼ ደረስክ እንዴ አለኝ። አዎ እናንተን እየጠበኩ ነዉ አልኩት። ጋሼ እኛ መግባት አንችልም ስትወጣ ታየናለህ አለኝ። ሁለት ተንጠልጣይ ሻንጣዎቼን ግራና ቀኝ ትከሻዬ ላይ አንጠልጥዬ ሻንጣ የጫንኩበትን ጋሪ እየገፋሁ ወደ መዉጫዉ አመራሁ። የሁለቱ ሻንጣዎች ክብደት ትከሻዬን ሲያጎብጠዉ ግዜ ሁለተኛ ለማንም ሰዉ ዕቃ አላደርስም ብዬ ማልኩ። ሁሌም እየማልኩ የምረሳዉ መኃላ ቢኖር ይህ ብቻ ነዉ። ወደ መዉጫዉ ስጠጋ በሩ ወለል ብሎ ተከፈተ። ታክሲዉና አዉቶቡሱ፤ ሸኚዉ፤ እንግዳ ተቀባዩ፤ እኔን መሰሉ ወደ ሙኒክ የሚመጣዉና ሙኒክን የሚለቀዉ መንገደኛ እዚህም እዛም ይተራመሳል። ከዚህ ሁሉ የሰዉና የመኪና ትርምስ ዉስጥ አይኔ ተሽቀዳድሞ ያረፈዉ በዚያ በዉበቱና በድምቀቱ የባንዲራዎች አዉራ በሆነዉ የአገሬ ባንዲራ ላይ ነበር። ሊቀበሉኝ የመጡ ሁለት ኢትዮጵያዉያን ያንን በትንሽነቴ “ደሙን ያፈሰሰ” ብዬ የሰቀልኩትንና ማታ “ተጣማጅ አርበኛ” ብዬ ያወረድኩትን የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ይዘዉ ሲመጡ አየሁና ተጠጋኋቸዉ። ሰንደቅ አላማዉ “አምባሻ” ስለሌለበት አመንኳቸዉ። አለዚያማ ፊቴን አዙሬ ጉዞዬን ወደ አስመራ እቀጥል ነበር እንጂ አምኜ አልጠጋቸዉም ነበር። ወይ ጉድ …… ዘመን አያመጣዉ ነገር የለም. . . . . . የምንተነፍሰዉንም አየር መጠርጠር ጀመርንኮ!

ሙኒክ የገባሁት ሐሙስ ጧት አስር ሰአት ተኩል ላይ ነበር። እሁድ ጧት ለስራ ጉዳይ ሲዊዘርላንድ እስክሄድ ድረስ ከሁለት ቀን ተኩል በላይ ሙኒክ ዉስጥ ቆይቻለሁ። ግን እንኳን ሁለት ቀን ተኩል ግማሽ ቀንም የቆየሁ አልመሰለኝም። ነገሩ ምንድነዉ ብዬ ተገረምኩ። ሚስጢሩ የገባኝ አስመራ ገብቼ ከእንቅልፌ ስነቃና የቀረብኝን ሳዉቀዉ ነዉ። ሙኒኮች በልቼ የምጠግብ፥ ጠጥቼ የምረካ አይመስላቸዉም። ያገኙኝ ሰዎች ሁሉ ብላ፤ጠጣ፤ እንሂድ፤ እንዉጣ፤ ምን እንግዛ፤ ምን እናምጣ፤ ምን ትፈልጋለህ፤ ምን አነሰ ነዉ ጥያቄያቸው። የሙኒክ ወገኖቼ ከኑሯቸዉ በላይ ሲያስቡልኝና ከራሳቸዉ በላይ ሲሳሱልኝ አይቼ እንደ ዐለት የማይነቃነቅ ደጀን አለኝ ብዬ ተመክቼባቸዋለሁ። በተለይ ሙኒክ ውስጥ ያየኋቸዉ ሴቶች እህቶቼ መጥተን እንቀላቀላችሁ እንጂ ከተማ ዉስጥማ ምን እናደርጋለን ነበር ጥያቄያቸዉ። የሙኒክ ሴቶች ደሜ ዉስጥ የቀረዉን የመጨረሻ የፍርሃት ጠብታ ጠራርገዉ ሲወስዱት ታወቀኝና ድፍረቴ ከአናቴ አልፎ ሲያንሳፍፈኝ ተሰማኝ። እቴጌ ተዋበች ለቋራዉ አንበሳ እቴጌ ጣይቱ ደግሞ ለዳግማዊ ምንሊክ ጉልበት፤ ብርታትና ጽናት እንደሆኗቸው ሁሉ ለኔም የሙኒክ ሴቶች ደሜ ዉስጥ ገብተዉ ብርታት፤ ልቤ ዉስጥ ገብተዉ ጽናት ሆኑኝ። አደራ. . . . ሴት የላካዉ ሞት አይፈራም ብላችሁ ለቆራጥ እህቶቼ የምሰጠዉን ምስክርነት እንዳታሳንሱብኝ። የሙኒክ ሴቶች የልብ ልብ የሰጡኝ ዕቃችንን ጠቅልለን ካልተከተልንህ እያሉ ነዉ እንጂ አይዞህ በርታ አለንልህ እያሉ ብቻ አልነበረም።

ቀኑን እንደ ደዋሪ ከወዲህ ማዶ ወዲያ ማዶ ስሽከረከር ዉዬ ስለደከመኝ አርብ ዬካቲት 26 ቀን (Feb 26) አልጋዬ ዉስጥ የገባሁት በግዜ ነዉ። ከሆቴሉ ሰራተኛ ቁልፍ ተቀብዬ መኝታ ክፍሌ ስደርስ አልጋዋ እንኳን ሙሉዉን ኤፍሬም አንድ እግሩንም ተሸክማ የምታድር አልመሰለችኝም። ትንሽዬ አልጋ ናት። ሽንት ቤቱና መታጠቢያ ቤቱም እንደዚሁ። ብቻ ምን አለፋችሁ አዉሮፓ ዉስጥ ትልቅ ነገር ያለም አይመስል። መንገዱ፤ መኪናዉ፤ ሀንጻዉና መኖሪያ ቤቱ ሁሉም ነገር ትንሽ ነው። አዉሮፓዉያን አንድ ነገራቸዉ ግን ትልቅ ከትልቅም ትልቅ ነዉ። ለሀይል ቁጠባና (Energy Conservation) ለአካባቢ ጥበቃ የሚሰጡት ቦታ እጅግ በጣም ትልቅ ነው። አዉሮፓ ስሄድ ሁለት ጉዳዮች ነበሩኝ። አንደኛዉ የሙኒክ ኢሳት ቤተሰቦች ባዘጋጁት የገንዘብ ማሰባሰብ ስብሰባ ላይ ለመገኘት ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ የትግል ጓደኛዬን የአንዳርጋቸዉ ጽጌን 61ኛ አመት የልደት በዐል ሲዊዘርላንድ ዉስጥ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ወገኖቼ ጋር ለማክበር ነዉ።

አርብ ማታ በግዜ ቆጤ ላይ ስለተሰቀልኩ ቅዳሜ ዬካቲት 27 ቀን ከእንቅልፌ ስነቃ እንደልማዴ እየደጋገመ አላዛጋኝም ወይም ተኛ ተኛ አላሰኘኝም። ፈጣን ሻወር ወስጄ ልብሴን ለባበስኩና ያደርኩበት ሆቴል በነጻ ብላ ያለኝን ቁርስ መቆርጠም ጀመርኩ። ከቁርሱ ይልቅ የጣመኝ ቡናዉ ነበርና አንዴ ደግሜ ሶስተኛዉን ይዤ ጠረቤዛ ቀየርኩና አይፓዴን ከፍቼ ዜና መቃረም ጀመርኩ። ኦሮሚያ ዉስጥ ከሦስት ወራት በፊት የተቀሰቀሰዉ ሀዘባዊ ቁጣ አለመብረዱ፤ የአዲስ አበባዉ ታክሲ ሾፌሮች አድማና ጎንደር ዉስጥ በየቦታዉ የሚፈነዳዉ ህዝባዊ አመጽ ትኩረቴን ከሳቡ ዜናዎች ዉስጥ ዋና ዋናዎቹ ነበሩ። ዜና ማንበቡን ጨርሼ ቀና ስል ጋዜጠኛ ሀይሉ ማሞና ጓደኛዉ መጡና . . . ጋሼ ምሳ እንብላ እንጂ ብለዉኝ ተያይዘን ወጣን።

ፉጨቱ፤ ሆታዉ፤ መዝሙሩና አዳራሹ ዉስጥ በየማዕዘኑ የሚዉለበለበዉ ሰንደቅ አላማችን ገና ስብሰባው አዳራሽ ዉስጥ ሳልገባ በሩቁ የአዳራሹን ስሜት ነገረኝ። አዳራሹ ዉስጥ ያሉት ኢትዮጵያዉያን አላማቸዉ አላማዬ ምኞታቸዉ ምኞቴ እንደሆነ ካውቅኩ ቆይቷል። አዳራሹ ዉስጥ ገብቼ ስሜታቸዉን ሳይ ግን ልባቸዉ ከልቤ ተገናኘና ደሜ ደማቸዉ፤ ሞቴ ሞታቸዉ መሆኑ ዉስጤ ድረስ ዘልቆ ተሰማኝ። ከሰዉነቴና ከሰዉነታቸዉ የአካል ፍላጭ ወጥቶ አዲስ አካል ሲፈጠር ታወቀኝ። አዎ. . . ዜግነት መሰረቱ፤ እኩልነት ማዕዘኑ፤ ነጻነት ጣራዉ፤ ፍትህ ወለሉ፤ አንድነትና ዲሞከራሲ ድርና ማጉ የሆነ ፍጹም አዲስ አካል ሲፈጠር ተሰማኝ። ፍጹም ልዩ ስሜት ነበርና ወደድኩት። አዳራሹ ዉስጥ ገብቼ ብዙም ሳልቀመጥ እኛ በህይወት እንድንኖር የሞት መስዋዕትነት ለከፈሉልን ጀግኖች የሂሊና ጸሎት እናድርስ ሲባል አዳራሹ ዉስጥ ያለዉ ሰዉ በሙሉ ከመቀመጫዉ ተነሳ። አዳራሹ ላንዳፍታ ሰዉ የሌለበት ኦና ቤት መሰለ። ያንን ሰው የሞላበት የስብሰባ አዳራሽ የዝምታ ጽላሎት ዋጠዉ። ሁላችንም በአንድ አፍንጫ እንተነፍስ ይመስል ትንፋሻችን እራሱ አንድ ሆነ።

ሁለቱ የኢሳት ጋዜጠኞች አፈወርቅ አግደዉና ሀይሉ ማሞ ማይክሮፎናቸዉን ጨብጠዉ መድረኩ ላይ ቦታ ቦታቸዉን ይዘዋል። አዳራሹን የሞላዉ ህዝብ እነሱን እነሱ ደግሞ ህዝቡን ያዩታል። ጋዜጠኛ ሀይሉ ማሞ ለእለቱ ጨረታ የቀረበዉን ዉብ የኢሳት አርማ ለተሰበሰበዉ ህዝብ ሲያሳይ ያ የሂሊና ፀሎት ሲደረግ ዝምታ የዋጠዉ አዳራሽ በጭብጨባ ጩኸት የፈረሰ መሰለ። ጨረታዉ በአንድ ሺ ዩሮ ተጀመረ። አፈወርቅ አግደዉ መድረክ ላይ ወጣና በዚያ ጀት ድምጹ ንግግሩን ሲጀምር አዳራሹ ዉስጥ ኢሳት ቴሌቭዥን የተከፈተ መሰለኝ። ከጋዜጠኛ አፈወርቅ አግደዉ አፍ እንደ አብሪ ጥይት እየተወረወሩ የሚወጡት ቃላት አድራሻቸዉ ጆሮ ሳይሆን የተሰበሰበዉ ሰዉ ኪስ ዉስጥ ይመስል ሁሉም እየተነሳ ያለዉን ይለግስ ጀመር። በአንድ ሺ ዩሮ የተጀመረው ጨረታ ብዙም ሳይቆይ አምስት ሺ ዩሮ ደረሰ። አዳራሹ ዉስጥ የነበርኩት ብቸኛ የበረሃ ሰዉ ጨረታዉ አምስት ሺ ዩሮ ላይ የሚቆም መስሎኝ ነበር። ምን ላድርግ እዉነቴን ነዉ። በረሃ ዉስጥ ብቸኛዉ የገንዘብ ቋንቋ ናቅፋ ብቻ ነው። አምስት ሺ ዩሮ ደግሞ እጅግ በጣም ብዙ ናቅፋ ነዉ። ለሁሉም ጨረታዉ እኔ እንዳሰብኩት አልቆመም፤ እንዲያዉም የማሸነፍ እልህ ዉስጥ በገቡ ከተሞችና ግለሰቦች መካከል ፉክክር ፈጠረና 6 ሺ፤ 7 ሺ፤ እና 8 ሺ እያለ ቀጠለ።
የሙኒክ ጨረታ ትዉስታቸዉ በበጋው ፀሐይና በክረምቱ ዝናብ የማይደበዝዝ ሶስት ትዝታዎች ጥሎብኝ አልፏል። ለወትሮዉ እኔ ጨረታ የማዉቀዉ ግለሰቦች በቡድን ወይም በግል ሲጫረቱ ነዉ። የሙኒኩን ጨረታ ለየት ያደረገብኝ አንዱ ነገር የጀርመን ኢትዮጵያዉያን ሙኒክ፥ በርሊን፥ ፍራንክፈርትና ኑረምበርግ. . . ወዘተ እያሉ በከተማ ጭምር ያደረጉት ጨረታ ነዉ። እንግዲህ ይታያችሁ አዉሮፓ ዉስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ጨረታ በተካሄድ ቁጥር የሚጫረቱት በግል፥ በቡድንና በከተማ ጭምር ከሆነ እነዚህ ኢትዮጵያዉያን ለፍትህና ለነጻነት ለሚደረገዉ ትግል የሚያደርጉት አስተዋጽኦ ከሌሎቻችን ይበልጣል ማለት ነው። ሌላዉ የሙኒክ ትዝታዬ የጀርመን ኢትዮጵያዉያን ወያኔን ለማጥፋት በሚደረገዉ ትግል ዉስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ባደረጉ ጀግኖች ኢትዮጵያዉያን በነ አንዳርጋቸው ጽጌ፤ ርእዮት አለሙ፤ እስክንድር ነጋ፤ ኡስታዝ አቡበከር፤ በቀለ ገርባና አንዱአለም አራጌ . . . ወዘተ ስም መጫረታቸዉ ነዉ። በእነዚህ ጀግኖች ስም የተደረገዉ ጨረታ የጀግኖቹ ስምና ህያዉ ስራቸዉ ከልባችን እንዳይጠፋ ማድረጉ ብቻ ሳይሆን የእነሱን ፈለግ እንድንከተል የሚገፋፋ ነበርና ለሙኒኮች ያለኝ አድናቆት ከፍተኛ ነው። Dank u München!

ሶስተኛዉ ትዝታዬ ሙኒክን ለቅቄ አስመራ ከገባሁ ከሶስት ሳምንታት በኋላ አሁንም ፊቴ ላይ አለ። ካሁን በኋላም ቢሆን እየረሳሁ ብዉልና ባድር ሶስተኛዉን ትዝታዬን የምረሳ አይመስለኝም። ይህ እንደ አፍላ ፍቅር ልቤ ዉስጥ ተተክሎ የቀረዉ ትዝታ የሶስት ሰዎች ትዝታ ነዉ። በአንድ በኩል ፊት ለፊት የመጀመሪያዉ ረድፍ ላይ ተቀምጦ ከተሸነፍኩ ሞቼ እገኛለሁ የሚል ዶክተር አለ። በሌላ በኩል ደግሞ አዳራሹ ኋላ ሆነዉ አንሸነፍም ብለዉ የመሸጉ ባልና ሚስት አሉ። እነዚህ ሶስት ሰዎች ኋላና ፊት ተቀምጠዉ ያካሄዱት ለሰአታት የዘለቀ ፉክክር ተሰብሳቢዉን እንደ ልብ ሰቃይ ድራማ ከፍና ዝቅ ያደረገ ልዩ ትርዕት ነበር።

ዶክተሩ የህክምና ዶክተር ነዉ። ታላቄ ነዉ ሆኖም በቁመት እንጂ በዕድሜ ብዙ አንበላለጥም። የምፈልገዉን ነገር አድርግልኝ ስለዉ ያደርጋል፤ ና ስለዉ ይመጣል። ከሙኒክ ሲዊዘርላንድ እንሂድ ስለዉ ሳያቅማማ ስራዉን ጥሎ ነዉ የተከተለኝ። ቀልዱ፥ጨዋታዉና ቁምነገሩ አይጠገብም፥ በተለይ ከአፈወርቅ አግደዉ ጋር ሲተራረቡ የአራት ሰአቱ የሙኒከ ሲዊዘርላንድ መንገድ እንኳን ያለቀ የተጀመረም አይመስልም ነበር። ብቻ ምን ልበላችሁ ዶ/ሩ ለኔ የነበረዉ አክብሮትና ለእናት አገሩ ለኢትዮጵያ ያለው ፍቅር በኔ ደካማ ብዕር የሚገለጽ አይደለም።

ባልና ሚስት ናቸዉ፥ የተቀመጡት አዳራሹ የመጨረሻ ረድፍ ላይ ነዉ። አይቸኩሉም ደግሞም አይዘገዩም። ፈጣሪ ያደላቸዉ ስጦታ ነዉ መሰለኝ ትክክለኛዉን ግዜ ያዉቁታል። ሲማከሩ ጆሮና አፍ ገጥመው ያንሾካሽካሉ። ሲስማሙ ስምምነታቸዉን የሚናገረዉ ባልየዉ ነዉ። የእነዚህ ባልና ሚስት ፍላጎት ጨረታዉን ማሸነፍ ሳይሆን ኢሳትን መርዳት መሆኑን የሁለቱም ፊት በግልጽ ይናገራል። ከላይ ባስተዋወቅኳችሁ ዶክተርና በእነዚህ ባልና ሚስት መካከል የተደረገዉ የጨረታ ፉክክር አዳራሹ ዉስጥ የተሰበሰበዉን ኢትዮጵያዊ ልብ ሰቅዞ የያዘ ፍጹም ልዩ ድራማ ነበር። ፉክክሩ ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን የአገር ፍቅርና እኛነት የታየበት እንዲሁም የማይቀረዉን ብሩህ የአገራችንን ተስፋ ከወዲሁ በናሙና መልክ ፈንጥቆ ያሳየ ዉብ መድረክ ነበር። በገንዘብ አስተዋጽኦ መልኩም ቢታይ ባልና ሚስትና ዶክተሩ ያደረጉት ፉክክር የጨረታዉን ጣሪያ ከሃያ ሺ ዩሮ በላይ አድርሶታል። በነገራችን ላይ እዚህ መጣጥፍ ዉስጥ ስማቸዉን ጠቅሼ ብጽፍ ደስ የሚለኝ ብዙ ኢትዮጵያዉያን አሉ። የማላደርገዉ ክፉ ብቻ ሳይሆን ጭራሽ ደንቆሮ የሆነ ጠላት ስላለን ነዉ። ይህ ጠላት የደደብነቱ ብዛት የሥልጣን ክልል ያለዉም አይመስለዉም፤ አዉሮፓና አሜሪካ ዉስጥ የጻፈ፥ የተናገረና ሀሳቡን የገለፀ ኢትዮጰያዊ ላይ እድሜ ልክ እስራት ይፈርዳል። ደሞስ ጭንቅላታቸዉ በንፍጥ ብቻ የተሞላና ሰዉነታቸዉ በተዘረፈ ሀብት የደለበ ሰዎች ከዚህ የተለየ ምን ሊያደርጉ ይችላሉ?

ከሙኒክ የሲዊዟ መናገሻ ቤርን ድረስ የአራት ሰአት መንገድ ነዉ። በረጂም በረራና በቅዳሜዉ የአዳራሽ ዉስጥ ቆይታ የተዝለፈለፈዉ ሰዉነቴ እየከዳኝ ቢሆንም የግድ ሲዊዘርላንድ መሄድ ነበረብኝና ተንገዳግጄ መኪናዉ ዉስጥ ገብቼ የአራት ሰአቱን መንገድ ተያያዝኩት። የሙኒከ ሲዊዘርላንድ መንገድ የሚያልፈዉ በኦስትሪያ በኩል ነዉ። ከጀርመን ወጥቼ ኦስትሪያ መግባቴን ያውቅኩት ሁለቱ አገሮች ድንበር ላይ የቆሙትን ፖሊሶች ስመለከት ነዉ፤ ለዚያዉም ባይነገረኝ ኖሮ አላዉቅም ነበር። መኪናዉ ዉስጥ እንቅልፍ ብጤ ሞካክሮኝ ነበር ግን የጋዜጠኛ አፈወርቅ አግደዉና የዚያ ደግ ዶክተር ጨዋታ እንኳን እንቅልፍ ሌላም ነገር የሚያስረሳ ነበርና ጨዋታቸዉ እንቅልፌን አባረረዉ። የመኪናዉ ዉስጥ ቀልድ፥ ተረብና ጆክ ከአካባቢዉ የተፈጥሮ ዉበት ጋር ሆነዉ መንፈሴን እያደሱት ድካሜን አስረሱኝ። አፈወርቅን የምትወዱት በቴሌቭዥን መስኮት ዉስጥ ብቻ አይታችሁት ከሆነ ብዙ ገና ብዙ ይቀራችኋል . . . ምኑን አያችሁና። አፈወርቅ ሲቀርቡት ጨዋታዉ፤ ቀልዱና ቁም ነገሩ አይጠገበም። ስለምንም ነገር ሲናገር የራሱ የሆነ ልዩ ዜማና ቃና አለዉ። ታሪክ ሲናገር በታሪኩ ዉስጥ ይዟችሁ ያልፋል። የታሪኩን መቸትና የተዋንያኑን ስም ከአባት ስም ጋር ሲናገር መጽሐፍ የሚያነብ እንጂ በቃሉ የሚናገር አይመስልም። የአማርኛ ቋንቋ በተለይ የቅኔ ችሎታዉ ይኸ ሰዉ ዋልድባ ነዉ ጋሙጎፋ ተወልዶ ያደገዉ ያሰኛል።

ከሙኒክ ተወጥቶ ኦስትሪያ እስኪገባ ድረስ ከመንገዱ ግራና ቀኝ የሚታየዉ ዘመናዊ እርሻ ከሳንሆዜ ሳንታክላራ ሲኬድ የሚታየዉን ሜካናይዝድ እርሻ አስታወሰኝ። የአዉሮፓና የአሜሪካ መመሳሰል ገረመኝ። በሃሳቤ ረጂም ርቀት ወደኋላ ተጓዝኩና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስማር ከአዋሳ አዲስ አበባ በአዉቶቡስ ስጓዝ አዉቶቡሱ ቆቃን እንዳለፈ አርሲ ነጌሌ እስኪደርስ ድረስ አልፎ አልፎ የማያቸዉ ትናንሽ እርሻዎች ፊቴ ላይ መጡ። አስናቀች ወርቁ “እንደ መቀነቴ ዞሬ ዞሬ እዚያዉ” ብላ የተጫወተችዉ ዘፈን ትዝ አለኝና ሆዴ በቁጭት ተሞላ። አዎ የኛ ነገር ዞሮ ዞሮ እዚያዉ ነዉ። እርሻው እዚያዉ፤ ገበሬዉ እዚያዉ፤ ፋብሪካዉ እዚያዉ ባጠቃላይ የኑሮ ደረጃዉ እዚያዉ ነዉ። እዚያዉ ድሮ የነበረበት ቦታ። ወደፊት እናያለን እንጂ ወደፊት አንሄድም። ይህንን ሳስብ ተቆጨሁ . . . ተናደድኩ። ለምን አልናደድ ለምንስ አልቆጭ . . . እኛና ድህነት፤ እኛና ኋላቀርነት፤ እኛና እየረገጡ ከሚገዙን ጋር መሞዳሞድ ሞት ካልለየን በቀር ላንለያይ የቆረብን ይመስላልኮ!

እኛ ኢትዮጵያውያን ከአዉሮፓና ከአሜሪካ ለምንድነዉ ይህን ያህል የምናንሰው ብዬ እራሴን ጠየኩና መልሳ ሳጣ የአዉሮፓን ዉበት ማድነቄን ቀጠልኩ። እዉነቱን ለመናገር የኋላ ቀርነታችን ምክንያት ጠፍቶኝ አይደለም። ለምን መናጢ ደሃዎች እንደሆንም ጠፍቶኝ አይደለም። ችግሩ. . . የኋላ ቀርነታቸንን ምክንያት ባሰብኩ ቁጥር ከዚህ አሳፋሪ ኋላ ቀርነት ለመላቀቅ የምናደርገዉ ጥረት እምብዛም መሆኑን ስለማዉቅ ማሰቤን አቆምና ንዴትና ቁጭት ዉስጥ እገባለሁ። የኔ ነገር ደግሞ ጉድ ከጉድም ጉድ ነው፤ አራሴን ስጠይቅ የማገኘዉ መልስ ቁጭትና ንዴት ነዉ። ቁጭትና ንዴት ደግሞ እንደገና ጥያቄ ያጭሩብኛል። ይገርማል .… አገሬ ከድህነት ኡደት እኔ ከጥያቄ ኡደት ላንላቀቅ የተማማልን ይመስላል። የራሱ ፊደል፥ ስነጽሁፍና የራሱ የሆነ የዘመን መቁጠሪያ ቀመር ያለዉ ሀዝብ እንዴት ያልሰለጠነ ህዝብ ተበሎ ይጠራል? አባይን፤ አዋሽን፤ ሸበሌን፤ዴዴሳን . . . ወዘተ ይዞ አገር እንዴት ይራባል? አክሱምን፤ ላሊበላንና ፈሲለደስን የገነባ ህዝብ ለምን ከኋላ ቀሮች ተርታ ስሙ ይጻፋል? ለምን? ለምን? ለምን?

ኦስትሪያ ስደርስ እርሻዉ፤ መኪናዉ፤ ከተማዉ፤ የሰዉ መልክና ቋንቋዉ ምንም አልተለየብኝም። ልዩነት አለ ቢባል ጀርመንን ለቅቄ ኦስትሪያ የሚባል አገር መድረሴ ብቻ ነዉ። ኦስትሪያን ለቅቄ ሲዊዘርላንድ ስገባም ፊት ለፊቴ ላይ ጉብ ጉብ ብለዉ ከሩቁ ከሚታዩኝ ተራራዎች ዉጭ ከተማዉ የጀርመንን ከተሞች ይመስላል፤ ብዙዎቹ መኪናዎች ጀርመን ዉስጥ የተሰሩ መኪናዎች ናቸው፤ ቋንቋዉም ጀርመንኛ ነዉ። ከአሜሪካ ተነስቼ ሲዊዘርላንድ እስክደርስ ድረስ በአራት አገሮች ዉስጥ አልፍያለሁ (አሜሪካ፥ ጀርመን፥ ኦስትሪያና ሲዊዘርላንድ) – ማነህ ተብዬ ፓስፖርት የተጠየኩት አሜሪካንን ስለቅና ሙኒክ ስገባ ብቻ ነው።

ሽፍታዉ ልቤ መሸፈት አይታክተዉ ነገር አሁንም ሸፈተ። ደግሞስ ይሸፍት አንጂ. . . . ለምን አይሸፍት? የተወለድኩት ኢትዮጵያ ዉስጥ ነዉኮ! እኛ ሰዎች እግዚአብሄር በአምሳያዉ እኩል አድርጎ ፈጥሮን አንዱ መሪዉን መርጦ ሲሾም ሌላዉ በገዛ መሪዉ ሲጎሸም፤ አንዱ በልቶ ጠግቦ ሲያምርበት ሌላዉ የሚበላዉ አጥቶ ህይወት ሲከዳዉ፤ አንዱ ሁሌም አሳሪ ሌላዉ ሁሌ ታሳሪ፤ አንዱ የበላይ አንዱ የበታች ሲሆን እንኳን የሰዉ ልብ ከሳር ዉጭ ሌላ የማያዉቀዉ በሬም ይሸፍታል። ጀርመንን፤ ኦስትሪያንና ሲዊዘርላንድን ሳይ በገዛ አገራቸዉ ማናችሁ እየተባሉ በየኬላዉ የሚጉላሉት ምስኪን ወገኖቼ ትዝ አሉኝ። ቤንች ማጂ ዉስጥ ወደ ክልልህ ተመለስ ተብሎ የተገፋዉ ወገኔ በርቀት ታየኝ። ቤኒሻንጉል ዉስጥ አለክልልህ ምን ታደርጋለህ ተብሎ ንብረቱን ተቀምቶ እየተረገጠ የተባረረዉ ኢትዮጵያዊ ወገኔ ትዝ አለኝና ሆዴን አመመኝ። ጋምቤላ ዉስጥ የአያት ቅድም አያቶቹ መሬት ጠመንጃ ባነገቱ ጉልበተኞች ተቀምቶ ሲታርስ እሱ ተመልካች የሆነው አኝዋክ ወገኔ ትዝ አለኝ።

ከጀርመን ሲዊዘርላንድ ስንጓዝ መኪናዉ ዉስጥ የነበርነዉ አምስት ሰዎች ሁላችንም ኢትዮጵያዉያን ነን። አዉሮፓ ዉስጥ አገሮችን በሚያሳስብ ደረጃ ከፍተኛ የስደተኛ ቀዉስ አለ። ሆኖም ከጀርመን ወጥተን በኦስትሪያ በኩል ሲዊዘርላንድ እስክንደርስ ድረስ አንድም ግዜ ማናችሁ የሚል ጥያቄ አልቀረበልንም። ተመልሰን ጀርመን ስንገባም እንደዚሁ። እትብቴ በተቀበረባትና የዚህ አለም ጉዞዬን ስጨርስ የመጨረሻ ማረፊያዬ እንድትሆን በምፈልግባት ምድር እንደ ቆሻሻ ነገር የሚረገጠዉ መብቴ በባዕድ አገር ሲከበር አየሁና “ኢትዮጵያዊነት” ምን ያደርጋል ብዬ አማረርኩ። ችግሩ ኢትዮጵያዊነት ላይ ሳይሆን ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት ቆርጠዉ በተነሱ ከሃዲዎች ላይ መሆኑ ገባኝኛ እነዚህን ከሃዲዎች ማጥፋት አለብኝ አለኩ። አዎ! እነዚህን ከሃዲዎች ማጥፋት አለብኝ ። “ማጥፋት” አለብኝ ሲባል አባባሉ በተግባር ካልተተረጎመ የባዶ ቃላት ጫጫታ ወይም የሞተ ሰዉ ዛቻ ነዉ። አንተ/አንቺ አንባቢ አስተዉል/አስተዉይ። ነፃነትና ፍትህ የሌሉበት አገር ሁሉ የአጥፊዎችና የጠፊዎች መድረክ ነዉ። ጠፊና አጥፊ ባሉበት ቦታ ደግሞ ሁለቱም ያጠፋሉ። አጥፊ ስራዉ ማጥፋት ነዉና ያጠፋል። ጠፊ ደግሞ ላለመጥፋት የሚያደርገዉ ምንም ነገር ስለሌለ እራሱን በማጥፋት ከአጥፊዉ ጋር ይተባበራል። የኛ የኢትዮጵያዉያን ችግርም ይኼዉ ነዉ. . . ጠፊዉም አጥፊዉም እኛዉ እራሳችን ነን። ከዛሬ በኋላ ግን እኛ አጥፊዎች ጠላታችን ጠፊ መሆን አለበት። ተፈላሲፌባችሁ ከሆነ ይቅርታ . . . እንደዚህ የሚያንበለብለኝ ዉስጤ ያለዉ ላለመጥፋት የማጥፋት ፍላጎት ነዉ። ሲዊዘርላንድ መናገሻ ቤርን መድረሴን ያወቅኩት መኪናዋ ቆማ . . . ጋሼ እንዉረድ ስባል ነው።
የኢትዮጵያን የቁርጥ ቀን ልጅ የአንዳርጋቸዉ ጽጌን 61ኛ አመት የልደት በዐል ለማክበር ሲዊዘርላንድ ዉስጥ የሚኖረዉ ኢትዮጰያዊ ከያለበት ተሰባስቧል። አዳራሹ ከመሙላቱ የተነሳ መቀመጫ ያጣዉ ሰዉ ያዳራሹን ዳር ዳር አጨናንቆታል። በየማዕዘኑ የሚወዛወዘዉ የኢትዮጰያ ሰንደቅ አላማ ለአዳራሹ ልዩ ዉበት ሰጥቶታል። የእንኳን ደህና መጣህ ጩኸቱ፥ ጭብጨባዉና ፉጨቱ አዳራሹ የእግር ኳስ ስታድዩም እስኪመስል ድረስ ቀለጠ። አጠገቤ የቆመው ጋዜጠኛ አፈወርቅ አግደዉ ጭብጨባዉ ለኔ ነዉ ላንተ ብሎ ጠየቀኝ . . . ለኛ ነዉ አልኩት። ሳቅ አለና ሁለት እጆቹን ዘርግቶ ተሰብሳቢዉ እንዲቀመጥ ተማፀነ። እኔም እጆቼን ዘርግቼ አብሬዉ ተማፀንኩ። ከእግራቸዉ ጣት እስከ ጸጉራቸዉ ጫፍ ድረስ ፍቅር በፍቅር የሆኑት የሲዊዝ ኢትዮጵያዉያን የምን መቀመጥ አሉና ሆታዉና ጭብጨባዉ ቀጠለ። ጧት ሙኒከን ስለቅ ድካም በድካም የነበረዉ ሰዉነቴ ዉስጥ አዲስ ሀይል እየገባ ሲያጠነክረኝ ተሰማኝ። ለካስ እኛ ሰዎች ምናብ ለምናብ ስንናበብ ዉጤቱ ፍቅር፥ ሀይልና ብርታት ነዉ። ብቻ ምን አለፋችሁ የሲዊዘርላንድ ኢትዮጵያዉያን እንደ ሲዊዝ ቸኮለት የሚጣፍጥ የአገር ልጅነት ፍቅር አቀመሱኝና በወገን ፍቅር ሰከርኩ። ሲዊዞች፥ ቸኮለታቸዉና ፍቅራቸዉ በጣም ተመቸኝ…….. ግን ብዙ ስራ ስላለብኝ የአንዲን ልደት ሻማ አብርተንና ኬኩን ቆርሰን “መልካንም ልደት” አንዲ ብለን ከዘመርን በኋላ ተለያየን። ጉዞ እነሱ ወደ ቤታቸዉ እኔ ወደ ሙኒክ ሆነ።

ረቡዕ መጋቢት 2 (March 2) ቀን በጧት ተነስቼ ቁርስ ከበላሁ በኋላ ከአዲሶቹ የሙኒክ ጓደኞቼ ጋር ተያይዘን ጉዞ ወደ ኦሎምፒክ መንደር ሆነ። ሙኒክ ኦሎምፒክ ልጅነቴን ይዞ የሚመጣ ብዙ ትዝታ አለዉ። የሜክሲኮዉ ኦሎምፒክ ጀግና ሻምበል ማሞ ወልዴ የመጨረሻዉን የኦሎምፒክ ማራቶን፤ ሻምበል ምሩፅ ይፍጠር ደግሞ የመጀመሪያዉን የኦሎምፒክ ሩጫ የሮጡት ሙኒክ ኦሎምፒክ ላይ ነዉ። ምሩዕ ይፍጠር ሙኒክ የሄደዉ ለ10ሺና ለ5ሺ ሜትር ዉድድሮች ሲሆን በ10ሺ ሜትር ሦስተኛ ከወጣ በኋላ የ5ሺ ሜትር የመጨረሻዉ ዉድድር ከተጀመረ በኋላ በመድረሱ ያሸንፋል ተብሎ በጉጉት ይጠበቅ በነበረዉ ዉድድር ላይ ሳይሳተፍ ቀርቷል። ሙኒክ ኦሎምፒክ አሳዛኝ ታሪክም አለዉ። ጨለማዉ መስከረም (Black September) በመባል የሚታወቀዉ የፍልስጥኤማዉያን አክራሪ ቡድን ኦሎምፒክ መንደር ዉስጥ አሸምቆ ገብቶ በእስራኤል አትሌቶች ላይ አደጋ ያደረሰዉ በዚሁ እንደ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር በ1964 ዓም በተካሄደዉ ሙኒክ ኦሎምፒክ ላይ ነበር። በነገራችን ላይ ሙኒክ ኦሎምፒክ የተካሄደዉ ጥቁር አሜሪካዊዉ ጆዜ ኦዉንስ በርሊን ኦሎምፒክ ላይ የወርቅ ሜዳሊያዎች አሸንፎ የናዚ ሂትለር መሪዎች ጥቁር ስለሆንክ ከኛ እጅ ሜዳሊያ አትቀበልም ካሉት ከ36 አመታት በኋላ ነበር።
ሙኒክ ዉስጥ በመጨረሻ የጎበኘሁት ከከተማዋ 19 ኪሎ ሜትር ወጣ ብሎ የሚገኘዉንና በ1944 ዓም የተሰራዉን የዳሁ ናዚ ማጎሪያ (Concentration Camp) ነበር።

ዳሁን ጎብኝቶ ለመጨረስ ወደ ሦስት ሰአት አካባቢ ፈጅቶብኛል። እነዚህ ሦስት ሰአቶች ወደፊትም ወደኋላም እየወሰዱኝ ዳሁ የጭካኔና የእልቂት ቦታ የመሆኗን ያክል የይቅርታና የመማማሪያ ቦታም እንደሆነ አሳይተዉኛል። ዳሁ ለሰዉ ልጅ ቁስሉም መድኃኒቱም ሰዉ መሆኑ የታየበትና የሰዉ ልጆች ጭካኔ መድረስ የሚችልበት የመጨረሻዉ ከፍታ ላይ የደረሰበት ቦታ ነዉ። ዳሁ አሁንም ድረስ ሲያዩት ጣረ ሞትን የሚጣራ የጨለማና የብርህን፤ የሞትና የህይወት፤ የጭካኔና የምህረት ቦታ ነዉ። ዳሁ የናዚ ግፍና ጭካኔ እማኝ ነዉ። ዳሁ የዘግናኝ ታሪክ ቅርፊት፡ የብሩህ ዘመን ትዉፊት፥ ቂምና ጥላቻን አብናኝ ይቅር ብሎ ይቅርታ ለማኝ ቦታ ነዉ። ዳሁ አይዋሽም . . . እንኳን ሊዋሽ ጭራሽ ዉሸት የሚባል አያዉቅም። ዳሁ ከአንዱ ክፍል ወጥተን ወደ ሌላዉ ክፍል በገባን ቁጥር የሚነግረን እዉነት ግን እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ ያሰኛል። ያቆስላል፤ ያደማል፤ ልብ ይሰብራል፤ ሆድ ይቆርጣል። እስረኞች ከመኝታ ቤታቸዉ እየተነዱ ገላችሁን ስለምትታጠቡ ልብሳችሁን አዉልቁ ተብለዉ ወደ ሌላ ክፍል ይወሰዳሉ። የሚቀጥለዉ ክፍል ዉስጥ የሚጠብቃቸዉ የመታጠቢያ ገንዳ ሳይሆን የመርዝ ጋዝ ገንዳ ነዉ። እስረኞቹ በመርዝ ጋዝ ከተገደሉ በኋላ እሬሳቸዉ ወደሚቀጥለዉ ክፍል ይወሰድና አገር የሚያክል ምድጃ ዉስጥ እየተጣለ ይቃጠላል። ይህ ግፍና ጭካኔ የተፈፀመዉ በሰዉ ልጆች ላይ ነዉ፤ ይህንን ግፍና ጭካኔ የፈፀሙትም የሰዉ ልጆች ናቸዉ። ጀርመንና ፖላንድ ዉስጥ ስላሉ የናዚ ጀርመን ማጎሪያ ካምፖች ከሰማሁ ቆይቷል። ይህንን በተለያዩ መጽሐፍት ላይ ያነበብኩትን ታሪክ ታሪኩ የተፈጸመበት ቦታ ላይ ቆሜ ስመለከት ግን አእምሮዬ ማሰብ አቆመና በድን ሆኜ ቀረሁ። ሁለት እጆቼን ዘርግቼ አማተብኩና . . . . . እንዲህ አይነት ክፉ ጭካኔ ዬትም ቦታ መደገም የለበትም ብዬ የዳሁ ጉብኝቴን ጨረስኩ።

ጀርመን፥ ኦስትሪያ፥ ሲዊዘርላንድና ዳሁ ስለ አሁኗና ስለወደፊቷ ኢትዮጵያ በየራሳቸዉ መንገድ የሚነግሩን ብዙ ነገር አለ። ዳሁ በሚባለዉ የናዚ ሂትለር ማጎሪያ ካምፕ ዉስጥ የተፈጸመዉን ግፍና ጭካኔ የፈጸሙት እኛን የመሰሉ የሰዉ ልጆች ናቸዉ እንጂ ከጥልቅ ባህር ዉስጥ የወጣ ዲያብሎስ አይደለም። ጀርመን፥ ኦስትሪያና አራት የተለያዩ ቋንቋዎች የሚነገሩባት ሲዊዘርላንድ ድንበር፤ ቋንቋ፤ባህልና ሐይማኖት ሳያግዳቸዉ ከአንዱ አገር ወደ ሌላዉ እንዳሰኛቸዉ እየተዘዋወሩ በኤኮኖሚ ተሳስረዉ በሰላም የሚኖሩት አርቆ አስተዋይ መሪዎቻቸዉ በወሰዱት መልካም እርምጃ ነዉ እንጂ እግዚአብሄር ከሰማይ ወርዶ የልዩነት ግድግዳቸዉን አፍርሶላቸዉ አይደለም። ክፉዉም ስራ የሰዉ ልጆች ስራ ነዉ፥ መልካሙም ስራ የሰዉ ልጆች ስራ ነዉ።እኛ ኢትዮጵያዉያን ምርጫችን ምንድነው? አዉሮፓ ዉስጥ ሰዉ ከአባቱ ገዳይ ጋር ተስማምቶ ሲኖር እያየን እኛ ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን ጋር በሠላም ጎን ለጎን መኖር ለምን አቃተን? አዉሮፓዉያን በየአገሮቻቸዉ መካክል ያለዉን ድንበር አፍርሰዉ በአንድ ገንዘብ ሲገበያዩ እኛ በአንድ አገር ዉስጥ ለዘመናት አብሮ በኖረ ህዝብ መካከል አጥር የምንሰራዉ ለምንድነዉ?

ሙኒክ ከመሄዴ በፊት አሜሪካ ሜሪላንድ ዉስጥ አንድ ትልቅ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ተገኝቼ ነበር። እዚህ ስብሰባ ላይ የእምነት አባቶች፤ የሲቪክና የፖለቲካ ድርጅቶች መሪዎች፤ አባቶች፤ እናቶችና ወጣቶች ተገኝተዉ ነበር። የሁሉም ፍላጎት አንድ፤ አንድና አንድ ብቻ ነበር። እሱም ፍትህ፤ እኩልነትና ነጻነት የሰፈነባት ኢትዮጵያ እዉን ሆና ማየት ነዉ። አዉሮፓ መጥቼ ጀርመንና ሲዊዘርላንድ ዉስጥ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ወገኖቼ ጋር ስገናኝ የተሰማኝ ስሜት አሜሪካ ዉስጥ ከተሰማኝ ስሜት ጋር ፍጹም ተመሳሳይ ነበር። እርግጠኛ ነኝ ኢትዮጵያዉያን በሚኖሩበት የአለም አካባቢ ሁሉ ፍላጎታቸዉ ፍትህ፥ ነጻነትና ዲሞክራሲ ነዉ። ግን ፍትህና ነጻነትን ስለፈለግናቸዉ ብቻ አናገኛቸዉም። የተናጠል ትግል ደግሞ ተራ በተራ የወያኔ ምሳና ቁርስ ያደርገናል እንጂ ነጻነታችንን አያስገኝልንም። በእርግጥ ነጻነት ስንደሰትበት ደስታዉ በግለሰብ ደረጃ ነዉ፤ ሆኖም ነጻነታችንን ጠላት እንዳይቀማን የምንጠብቀዉና ከተቀማንም ታግለን የምናስመልሰዉ በጋራ ነዉ። ስለዚህ ጽኑ የሆነዉ የፍትህና የነጻነት ፍላጎታችን ጽናት ባለዉ የጋራ ትግል ካልተደገፈ ያለን አማራጭ እየተረገጥን መኖር ብቻ ነዉ።

ወያኔ የበላይ በሆነባት በዛሬዋ ኢትዮጵያ ዉስጥ እንደዳሁ አይነት በሰዉ ዘር ላይ የተፈጸመ ወንጀል ሊፈጸም አይችልም የምንል ሰዎች ካለን ወደ ኋላ ዞር ብለን አኝዋክንና ኦጋዴንን ልንመለከት ይገባል። ዛሬ ወያኔ ኦሮሚያ ዉስጥ መብቴ ይከበር ብሎ በጮኸ ኢትዮጵያዊ ላይ የሚወስደዉ ፍጹም አረመኔያዊ የሆነ እርምጃም የሚያሳየን ወያኔ የስልጣን ገመዱ ባጠረ ቁጥር የማያደርገዉ ምንም ነገር እንደሌለ ነዉ። የወደፊቷ መልካም ኢትዮጵያ የምትናፍቀን ኢትዮጵያዉያን ከጀርመን፥ ከኦስትሪያ፥ ከሲዊዘርላንድና ከዳሁ የምንማረዉ ጠቃሚ ትምህርት አለ። ዛሬ በማድረግ ወይም ባለማድረግ የምንፈጽማቸዉ ብዙ ስህተቶች አሉ። እነዚህ ስህተቶች የጠላታችንን የወያኔን የሥልጣን ዘመን ማራዘማቸዉ ብቻ ሳይሆን ወያኔ ከተወገደ በኋላም ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት በምናደርገዉ ጥረት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያደርጋል። ለምሳሌ ኦሮሚያ ዉስጥ ለወራት የዘለቀዉ ህዝባዊ ቁጣና እምቢተኝነት በሌላ አገር የሚካሄድ ይመስል ብዙዎቻችን ከጎን ቆመን ተመልክተናል። ይህ አጉልና የማያዋጣ ቸልተኝነት ነገ በአማራ፤ በሲዳማ፤ በሃዲያና በኮንሶ … ወዘተ አካባቢዎች የሚነሱ ህዝባዊ እንቅስቃሴዎችን ኦሮሞዉ በቸልተኝነት እንዲመለከት ያደርገዋል። ኢትዮጵያ ዉስጥ አማራዉ ለኦሮሞ ካልጮኸና ኦሮሞዉ ከአማራዉ ጋር አብሮ ካልታገለ አማራዉ፤ ኦሮሞዉ ባጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ከወያኔ ባርነት ነፃ አይወጣም። ወደድንም ጠላን ታሪክ ኢትዮጵያ ዉስጥ ሲዳማን በወላይታ፤ ጉጂን በጌዲኦ፤ ትግሬን በአማራ፤ አማራን በኦሮሞ . . ወዘተ አዉድ ዉስጥ ጠቅልሎ አስቀምጦናል። ከዚህ ጥቅልል ዉስጥ በተናጠል አንዱ ብቻዉን ነፃ መሆን አይችልም። ወያኔ ጨፍልቆ የሚረግጠን አንድ ላይ ነዉ፤ ነፃ የምንወጣዉም አንድ ላይ ነዉ። ኢትዮጵያና አንድነቷ አደጋ ላይ ወድቀዋል። ኢትዮጵያዊነት የምንለዉ ክቡር ማንነትም ከፍተኛ አደጋ ላይ ነዉ። እነዚህን ጣምራ አደጋዎች ማቆም የዚህ ትዉልድ ሃላፊነት ብቻ ሳይሆን ግዴታም ነዉ። የወደፊቷ ኢትዮጵያ ዉስጥ ዳሁን የመሰለ የመታሰቢያ ቦታ እንዲኖራት በፍጹም መፍቀድ የለብንም። ይህ እዉን የሚሆነዉ ግን እኛ ኢትዮጵያዉያን እጅ ለእጅ ተያይዘንና ትከሻ ለትከሻ ተደጋግፈን የዛሬዋን ኢትዮጵያ ከእልቂት አድነን የነገዋን ኢትዮጵያ በፍትህ፤ በነጻትና በዲሞክራሲ መሰረት ላይ መገንባት ከቻልን ብቻ ነዉ። ሌላ ምንም መንገድ የለመልኩም። ቸር ይግጠመን።

አፍሬም ነኝ ከአርበኞች መንደር – ebini23@yahoo.com

የፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ አጫጭር ዜናዎች

$
0
0

ርዕሰ ዜና
– ኖርዌይ የፖለቲካ ጥገኛነት የጠየቁ ኢትዮጵያውያንን ወደ አገራቸው ልትልክ ነው
– የታክሲ ነጅዎች አድማ እንደገና ሊጀምር ይችላል ተባለ
– በትግራይ የቤት መስሪያ የቦታ ስፋት እንዲጨምር ተደረገ
– የሶማሊያ መንግስት 115 የአልሸባብ አባላት የተገደሉና ሌሎች 110 የተማረኩ መሆናቸውን ገለጸ
* የግብጽ የመንገደኛ አውሮፕላን ተጠለፈ
– በመከካለኛው አፍሪካ ሪፕብሊክ ተጨማሪ የተመድ የሰላም አስከባሪ አባላት በወሲብ ወንጀል ተከሰሱ

መጋቢት 20 ቀን 2008 ዓ.ም.

Ø የኖርዌይ መንግስት የፖሊቲካ ጥገኝነት የጠየቁ 800 ኢትዮጵያውያንን ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ የተዘጋጀ ሲሆን ከሚላኩት ውስጥ 60ዎቹ ህጻናት እንደሆኑ ተገልጿል። መንግስቱ ስደተኞች ያቀረቡት የፖሊቲካ ጥገኝነት ጥያቀ ተቀባይነት አላገኘም በማለት በግዳጅ ለመመልስ ይወስን እንጅ የስደተኛ ከለላ ጠባቂ የሆኑ ድርጅቶች ግን ስደተኞቹ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ በአካላቸውና በመንፈሳቸው ጉዳት ከማምጣቱ በተጨማሪ ለህይወታቸው አስጊ እንደሚሆን በመጥቀሰ መንግስት ጉዳዩን እንደገና እንዲመለተው ውትወታ በማድረግ ላይ ይገኛሉ። በቅርቡም በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የኖርዌይን መንግስት ውሳኔ በመቃወም ኦስሎ ላይ ታላቅ የተቃውሞ ስለፍ ማድረጋቸው ይታወሳል። የወያኔ ቡድን መሪዎች በሀገር ውስጥ ሕዝብን በዘረኛ አምባገነን አገዛዝ ረግጦ መግዛት ብቻ ሳይሆን በውጭ ሀገር የሚኖሩትም ገጽታችንን ያበላሻሉ በማለት ከየቦታው ለማስወጣት ከየአገሮቹ ጋር ልዩ ልዩ ስምምነት እየፈጠሩ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከፍተና መከራና ስቃይ እየደረሰባቸው ነው።

Taxii

Ø ከጥቂት ቀና በፊት በአዲስ አበባ ከተማ የታክሲ ሹፌሮችና ባለንብረቶች አዲስ የወጣውን የትራፊክ ህግ በመቃወም የሥራ ማቆም አድማ በማድረጋቸው የወያኔ መሪዎች ሕጉ እንደገና እንደሚታይና ለሶስት ወር ተግባራዊ እንደማይሆን በመግለጽ የሥራ ማቆም አድማውን ለጊዜውም ቢሆን ማስቆማቸው ይታወሳል። ሰሞኑን ውስጡን አዲሱን የተራፊክ ሕግ ተግብራዊ እያደረጉ በመምጣታቸው ምክንያት አንዳንድ የታክሲ ሹፌሮች ትናንት መጋቢት 19 ቀን 2008 ዓም ለአገልግሎት ሳይወጡ የቀሩ መሆናቸው የታየ ሲሆን በወያኔ ካድሬዎች ለታክሲዎቹ መጥፋት የገብርኤል በዓል እንደምክንያት ሲሰጥ ውሏል ። በዛሬው ዕለት መጋቢት 20 ቀን 2008 ዓም በስራ መግቢያ ሰዓት ላይ ከፍተኛ የታክሲ ዕጥረት እንደነበር ታውቋል፡፤ ይህ የታክሲ ዕጥረት የተከሰተው በርካታ አሸከርካሪዎች ለሥራ ባላመውጣታቸው መሆኑ ሲታወቅ ምናልባት የታክሲ ማኅበራቱ አጥቃላይ አድማ ሊጠሩ ይችላሉ ተብሎ ተገምቷል። አሁን ያለው የታክሲ ሥራን የማቀዝቀዝ አድማ አዲስ አበባ ከተማን ውጥረት ውስጥ ከቷል።
OPDO 5

Ø ከምርኮኛ ወታደሮች ወያኔ በአምሳሉ ጠፍጥፎ የሰራው ኦህዴድ የመሠረተበትን 24 ኛ ዓመት አከብራለሁ ይበል እንጅ እንደታሰበውና እንደታቀደው መከበሩ አጠያያቂ እየሆነ ነው። የወያኔው ኦህዴድ በዓሉን ምክንያት በማድረግ በተዋረድ ታች ያሉትን አባላትና ደጋፊዎች ሰብስቦ ለማነጋገር ይታቀድ እንጅ ከሕዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተገናኘ ከሕዝብና ከታች አባላት ጋር መገናኘቱ አስቸጋሪ እንደሚሆን ከወያኔው ኦህድዴ ጽሕፈት ቤት አካባቢ የተገኘው መረጃ አመልክቷል። ኦህዴድ ቀደም ሲል በያዘው መርሀ ግብር መሠረት የድርጅቱ ባለሥልጣናት በየቦታውና በየአዳራሹ እየተገኙ የኦህዴድን በዓል እንዲያስከብሩ የታቀደ ቢሆንም የወገኖቻችንን ደም በአግአዚ ወታድሮች እያፈሰሰ እንዴት በዓልና ፌስታ ይኖራል? ኦህዴድ የአሰገዳይና የገዳዮች ተባባሪ ሆኗል በማለት ካድሬዎቹ እርስ በርስ መነጋገራቸው የኦህዴድ በዓል መከበሩ አጠያያቂ ሆኗል። ከዚህ በዓል አካባበር ጋር በተያያዘ ዋና የተባሉ ካድሬዎች በዓሉ ከተከበረ ላለመገኘት የዓመት ፈቃድና የህክምና ፈቃድ እየጠየቁ ከስራ እየወጡ መሆናቸው ታውቋል።

Ø የወያኔ ቡድን መሪዎች በኢትዮጵያ ውስጥ ለከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲያቸው እንዲያመች አድላዊና ዘረኛ አምባገነን አገዛዝን ከመሠረቱ ጊዜ ጀምሮ የትግራይ ሕዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለመነጠል የኢኮኖሚ የፖሊቲካ የወታደራዊ የትምህርት የልማትና የኢንቨስትመንት የሚዲያዎች ወዘተ ሥራዎች ለትግራይና ለትግራይ ተወላጆች ሲሰጥ መቆየቱ ይታወሳል። ሰሞኑን ደግሞ በሌላው የኢትዮጵያ ክፍል የማይታሰበውን በትግራይ አዲስ ቤት የሚሰራበትን ቦታ ስፋት በመጨመር መመሪያ አውጥቷል። በመመሪያው መሠረት ቀደም ብሎ ቤት ሰሪዎች ከ180 ካሬ ሜትር በላይ የማይፈቅድላቸው የነበረ ሲሆን አሁን ከዚያ በላይ በሆነ የቦታ ስፋት ላይ መስራት እንደሚችሉ ተፈቅዶላቸዋል። የወያኔ ቡድን መሪዎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመላ ኢትዮጵያ እየተቀጣጠለ የመጣውን የተቃውሞ እሳት በትግራይ ሕዝብ ኪሳራ ለማዳፈን ትግራይ ውስጥ አንድ ግዙፍ የኬሚካል ፋብሪካ ለማቋቋም ከወስኑ ወዲህ አሁን ደግሞ የቤት ሠሪዎችን የቦታ መጠን ለማስፋት መፍቀዱ የትግራይ ሕዝብ ከጎኑ ለማሰልፍ የሚደርግ ጥረት መሆኑ ታውቋል። ብዙ ሀገር ወዳድ ዜጎች ወያኔ ከትግራይ ውጭ ባሉ ኢትዮጵያያኖች ላይ የሚፈጽመው ግድያ እስር በደልና አድልዎችን በትግራይ ሕዝብ ላይ ለለላው መጠን እንዲፈጽም ፍላጎት ባይቦራቸውም እንደ ትግራይ ግን ልማትና እንክብካቤ ቢኖራቸው እንደማይጠሉ ይናገራሉ።

alshebab

Ø ሰሞኑን በሰሜን ሶማሊያ በአልሸባብና መንግስቱን በሚደግፉ ወታድሮች መካከል በተካሄደ ውጊያ 115 የአልሸባብ ወታድሮች መገደላቸውን የሶማሊያ መንግስት ቃል አቀባይ አስታውቋል። 110 የአልሸባብ ታጣቂዎች መማረካቸንና ሌሎች ወደ ገጠር ማምለጣቸውን መግለጫው ጨምሮ ገልጿል። ታጣቂዎቹ ሽንፈት የገጠማቸው ለአራት ተከታታይ ቀኖች በተደረገ ጦርነት መሆኑ የተገለጸ ሲሆን የሶማሊያ መንግስት በውጊያ ስለደረሰበት ጉዳይ የሰጠውም መግለጫ የለም።ይህ የመንግስት መግለጫ በሌላ በሶስተኛ ወገን አልተረጋገጠም። አልሸባብ በደቡብ ሶማሊያ በርካታ ሽንፈት ስለገጠመው በሰሜን የጦር ሰፈር ለመመስረት እየሞከረ ነው ተብሏል። 22000 የሚደርሱ የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ኃይል በሱማሊያ የሚገኝ ሲሆን የሶማሊያ መንግስትን አልሸባብን ለመደምሰስ የቆረጠ መሆኑን በተደጋጋሚ ቢዝትም የቡድኑ እንቅስቃሴ ጎላ እያለ መምጣቱን ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ሰዎች ይጠቁማሉ።

Ø አሌክሳንድሪያ ከምትባለው የወደብ ከተማ ወደ ካይሮ ሲበር የነበረው የግብጽ የመንገደኛ አውሮፕላን ተጠልፎ ወደ ቆፕሮስ (ሳይፕረስ) መወሰዱ ተነገረ። ጠለፋው ከሽብረተኛነት ጋር የተያያዘ አይደለም የተባለ ሲሆን አውሮፕላኑ በቆፕሮስ አውሮፕላን ማረፊያ እንዳረፈ ተሳፋሪዎቹ በሙሉ ተለቀዋል። በአውሮፕላኑ ውስጥ ከነበሩት 55 መንገደኞች መካከል 21 ዱ የውጭ አገር ሰዎች መሆናቸው ተገልጿል። ጠላፊው በእጁ ላይ የያዘው ምንም ዓይነት ፈንጅ ወይም መሳሪያ ያልተገኘ ሲሆን ጠለፋውን ለመፈጸም ያስገደደው በቆፕሮስ የምትኖረውን ፍቅረኛውን ለማይት መሆኑን ገልጿል። ጠላፊው በቁጥጥር የተደረገ ሲሆን በቆፕሮስ የፖሊቲካ ጥገኛነት ጠይቋል።

Ø በአይቮሪ ኮስት ሰሜናዊ ግዛት ባለፈው ሳምንት ረቡዕ መጋቢት 14 ቀን 2008 በአርብቶ አደሮችና በአካባቢው ገበሬዎች መካከል በግጦሽ ምክንያት በተነሳ የእርስ በርስ ግጭት የአስራ ሰባት ሰዎች ህይወት የጠፋ ሲሆን ከ 1300 የሚሆኑ ሰዎች በላይ የሆኑ ሸሽተው ወደ ቡርኪና ፋሶ የገቡ መሆናቸው ተገልጿል። ከተሰደዱት መካከል አብዛኞቹ ሴቶችና ህጻናት ናቸው። በአይቮሪ ኮስት በዘላኑ ህብረተሰብ እና በገበሬዎች መካከል በግጦሽና በውሃ አጠቃቀም ብዙ ግጮት ሲደደሩ የቆዩ ቢሆንም የአሁኑ ከፍተኛ የነበረ መሆኖ ተገልጿል።

Ø በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፕብሊክ የሚገኙ ሁለት የተመድ የሰላም አስከባሪ ኃይል አባላት በወሲብ ወንጀል የተከሰሱ መሆናቸውን የተመድ ቃል አቀባይ ሰኞ መጋቢት 19 ቀን ለጋዘጠኞች በሰጡት መግለጫ ገለጹ። ተጠርጣሪዎቹ አንዱ የብሩንዲ ሌላው የሞሮኮ ወታደሮች ሲሆኑ በማዕካለአዊ አፍሪካ ሪፕብሊክ ሴቶችን አስገድዶ በመድፈር ክስ የተመሰረተባችደውን የተመድ የሰላም አስከባሪ ኃይል አባላት ቁጥር ወደ 25 ከፍ አድርጎታል። በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ውስጥ ብሩንዲ 1128 ወታድሮች ሞሮኮ ደግሞ 741 ወታድሮች ሲኖሯቸው ሞሮኮ በወታደሩ ላይ የተሰነዘረውን ክስ የምትመረምር መሆኗን ገልጻለች። ባለፈው ሳምንት አስፈላጊ ከሆነ በቻድ ውስጥ የሚገኘው ወደ 12 000 የሚደረሰው የተመድ የሰላም አስከባሪ ኃይል በሙሉ በለላ ኃይል ሊለውጥ እንደሚችል የተመድ ዋና ጸሀፊ ባንኪ ሙን መግለጻቸውና ይህንን አስመልክቶ በመጋቢት 2 ቀን 2008 ዓም ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል፡

Ø በምግብ እጥረት ምክንያት ከደቡብ ሱዳን ወደ ሱዳን የሚሰደደው ሕዝብ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መሄዱ ተነገረ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን ዛሬ ማክሰኞ መጋቢት 20 ቀን 2008 ዓም እንዳስታወቀው በደቡብ ሱዳን ውስጥ በሰሜን ምዕራብ ግዛቶች ብቻ 38000 ሺ የሚሆኑ ስደተኛች ወደ ምስራቅና ደቡብ ዳርፉር ግዛት የተሰደዱ መሆናቸውን ገልጿል። ኮሚሽኑ የስደተኞቹ ሁኔታ በጣም አሳሳቢ እንደሆነ ገልጾ ልጆች ከወላጆቻቸው የተለዩ መሆናቸውንና ከፍተኛ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው መሆኑ አብራርቷል። ባለፉት ሶስት ዓመታት በደቡብ ሱዳን በተከሰተው የእርስ በርስ ጦርነት 2.3 ሚሊዮን የሚሆን የደቡብ ሱዳን ዜጋ ከሚኖርበት ተነቅሎ ወደ ሌሎች ቦታዎች የተሰደደ መሆኑ ይታወቃል።

Ø በደቡብ አፍሪካ በጆሃንስበርግ ከተማ የኖርዝ ዌስት ዩኒቨርስቲ ለአንድ ወር ያህል ከተዘጋ በኋላ እንደገና መከፈቱ ተነገረ። ከጥቂት ወራት በፊት በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የትምህርቱ ክፍያ እንዲቀንስ፤ የኖሮ ሁኔታ እንዲሻሻልና ለነጮች ፍላጎት የተዘጋጀው የትምህርት ሥርዓት እንዲሻሻል በመጠየቅ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ሲካሄድ መቆየቱ የሚታወቅ ሲሆን ባለፈው ወር የኖርዝ ወስት ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ባደረጉት ተቃውሞ የአስተዳድሩን ቢሮና የሳይንስ ማዕከሉን ማቃጠላቸው ይታወሳል። ሁኔታው ተረጋግቶ በዛሬው ዕለት ትምህርት መጀመሩ ተነግሯል።

Oromo

Ø የአዲስ አበባን አጎራባች ከተሞችን ወደ አዲስ አበባ ለመጠቅለል የወጣውን ማስተር ፕላን በመቃወም በተለያዩ ቦታዎች ሕዝባዊ ተቃውሞ ሲካሄድ የቆየ መሆኑ ይታወቃል። ለዚህ ሕዝባዊ ተቃውሞ አስፈላጊውን እርምጃ አልወሰዳችሁም፤ ተባባሪ ነበራችሁ በማለት ከወያኔ መሪዎች በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ኦህዴድ ከፍተኛ ባለስልጣኖችን ከፓርቲው የኃላፊነት ቦታ ማባረሩም ይታወሳል። ሰሞኑን ከሚደመጡና ከሚነበቡ ሪፖርቶች ደግሞ የወያኔው ፓርላማ አፈ ጉባዔ አባዱላ ገመዳና የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ የተባለው ዲሪባ ኩማ እንቅስቃሴያቸው በወያኔ ደህንነት ራዳር ስር መውደቁ ተዘግቧል። ሁለት ከፍተኛ የአገዛዙ ባላሥልጣናትና የወያኔ ኦህዴድ መሪዎች ከተነሳው ሕዝባዊ ተቃውሞና ቁጣ ጋር በተያያዘ በዓይነ ቁራኛ ውስጥ እንዲወድቁ መደረጉ ሲታወቅ ወደ ውጭ ሀገራም እንዳይወጡ ፓስፖርታቸውን መነጠቃቸው ተገልጿል። የወያኔ መሪዎች ላጠፉት ህይወትና ላወደሙት ንብረት አገልጋዮችና አሽከሮች የሆኑትን ከፍተኛ የኦህዴድ ካድሬዎችና መሪዎች ጭዳ ለማድረግ መዘጋጀታቸው ቀደም ሲል መገለጹ ይታወሳል።

 

Ø የወያኔ መሪዎች የሥልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም እንዲያስችላቸው በውጭ ሀገራት የማግባቢያ ሥራ (የሎቢ ሥራ) ለሚሰሩላቸው ኩባንያዎች የአገሪቱን ሀብት ማዕድኗን እንዲበዘብዙ መንገዶችን ሲያመቻቹ መቆየታቸው ይታወቃል። ከአፋር ግዛት ከሰመራ የሚመጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከአስር ዓመት በፊት ለቀድሞ የወያኔ መሪና ጠቅላይ ሚኒስትር ለመለሰ ዜናዊ ሽልማት የሰጠው ያራ የተባለው የኖርዌይ የማዳበርያ አምራች ድርጅት በአፋር ዳሎል የሚገኘውን የፖታሽ ክምችት እንዲያወጣ ፈቃድ ተሰጥቶታል። ከኖርዌይ ያራ በተጨማሪ አንድ የእንግሊዝ የማዕድን ኩባንያም ይህንኑ የአፋር ማዕድን እንያወጣ ተፈቅዶለታል። ኢትዮጵያ በከርሰ ምድሯ ያላትን ሃብት የወያኔ መሪዎች ከንግድ ሸሪኮቻቸውና ከባለውለታና አጋር ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ጋር በመሆን እየበዘበዙና በባዕድ ሀገርም ከፍተኛ መጠን ያለው ሀብትና ንብረት እያከማቹ መሆናቸው ይታወቃል። የኖርዌይና የእንግሊዙ ማዕድን አውጭዎች በቅርብ ጊዜ ወደ ማዕድን ቁፋሮ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Ø ከጎንደር የሚመጡ ሪፖርቶችና መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ የጎንደር ሕዝብ የወልቃይት ጠገዴ ነዋሪ ያነሳውን የማንነት ጥያቄ በመደገን ለወያኔ አገዛዝ ያለውን ተቃውሞ ባገኘው አጋጣሚና ሁኔታ እየገለጸ መሆኑ ታውቋል። መጋቢት 18 ቀን 2008 ዓም በጎንደር ከተማ በጎንደር ስታዲዩም ለብሔራዊ ሊግ በጎንደር ከነማና በአዲግራቱ ውልዋሎ ክለብ መሃል የእግር ኳስ ግጥሚያ በሚደረግበት ሰዓት የስታዲየሙ ተመልካች በቦታው መሰብሰቡን እንደ አጋጣሚ በመጠቅም ተቃውሞን ሲያሰማ፤ ብሶቱን ሲገልጽ ቁጣውን ሲያሳይ ውሏል። በዕለቱ በስታዲየሙ የነበረው ተመልካች “የወያኔ ኖር ይለያል ዘንድሮ”፤ “ወልቃት ይመለስ”፤ “አማራ ነን”፤ “የትግራይ የበላይነት ያብቃ”፤ “አፈና ይቁም” የሚሉትን መፈክሮችና ልዩ ልዩ የተቃውሞ መዝሙሮችን ሲያሰሙ ውለዋል። ወያኔ ህዝብ እንዳይሰበሰብና ተቃውሞውን እንዳይገልጽ ቢገድብም በስፖርት ሜዳና በጸሎት ቦታ ሳይቀር ሕዝብ ሲሰባሰብ ብሶቱን መግለጽ መጀምሩ ምናልባት ነገ ተሰባስቦ አደባባይ መውጣቱ የማይቀር ነው የሚሉ ታዛቢዎች አሉ።

Ø የወያኔ አጃቢና ሻማ ያዥ የሆኑት የፖሊቲካ ፓርቲ መሪ የተባለት ግለሰቦች ከወያኔ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር መነጋገራቸውን ወያኔ አስታውቋል። ይህ በወያኔ መሪዎች ትዕዛዝ በኃይለማርያም ደሳለኝ ፈጻሚነት የተካሄደው የብሔራዊ መግባባት የተባለለት ስብሰባ ከፕሮፓጋንዳ ወፍጮነት ባለፈ እንደ ስሙና አጀንዳው ምንም የተግባር ምላሽ ያልሰጠና ይልቁንም በወያኔ የምርጫ ድራማ ወቅት ስለሚከፈላቸው የገንዘብ መጠን የተጨነቀ ንግግር ሲያደርጉ መዋላቸው ታውቋል። የወያኔ ፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ግን ለመልካም አስተዳድር ችግር ብሔራዊ መግባባት ዋና መሳሪያ ስለሆነ ከተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ጋር ውይይት ተደረገ ቀጥሎ ከሕዝብ ጋር ይሆናል በማለት ሲያናፉ ሰንብተዋል። የፓለቲካ ታዛቢዎች ወያኔ በአራቱም ማዕዘና የተነሳበትን ተቃውሞና አገዛዙ በቃን በማለት ሕዝብ እያካሄደ ያለውን የአመጽ እንቅስቃሴ ለማዳካም አንዴ ይቅርታ ተጠየቀ ሌላ ጊዜ ስለ መግባባት ንግግር ተደረገ በማለት ለማወናበድና ዕድሜ ለማስረዘም የሚያደርገው ጥረት አካል መሆኑን ይጠቅሳሉ። የወያኔ መሪዎች የሰላምና የዕርቅ ብሩን ከዘጉ ዓመታት ማስቆጠራቸውን ገልጸው በአሁኑ ወቅት የተባለው የብሔራዊ መግባባት ንግግር የተደረገው የወያኔ አጃቢና ሻማ ያዥ ፓርቲዎችን ከቀውሱ ጀርባ የቤት ስራ ሊሰጣቸው ታስቦ መሆኑን ሕዝቡ ይገነዘባል በማለት ተጨማሪ አስተያየት ይሰጣሉ።

Ø ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ከአፍሪካ ወደ አውሮፓ አገሮች ለመሰደድ ሙክራ ሲያደርጉ የነበሩት 600 ስደተኞች በየሊቢያ የወደብ ጠባቂዎች የታገዱ መሆናቸው ታወቀ። ስደተኞቹ ከተለያዩ የአፍሪካ አገሮች የመጡ ሲሆን ህጻናትና እርጉዝ ሴቶች እንደሚገኙባችውም ተነግሯል። መቀመጫው ትሪፖሊ የሆነውና የዓለም አቀፍ እውቅና ባያገኝም ራሱን መንግስት ብሎ የሚጠራው አካል ስር የሚገኘው የሊቢያ ባህር ኃይል ስደተኞችን ያገተው ከትሪፖሊ ምዕራብ 70 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሳብራታ በምትባለው ወደብ ነው። ሊቢያ ውስጥ ከ800 000 በላይ ስደተኞች እንደሚገኙ ቀደም ብሎ በፈረንሳዩ የመከላከያ ሚኒስትር የተሰጠውን መረጃ የሊቢያ ባለስልጣኖች የተጋነነ ነው በማለት ውድቅ ቢያደርጉትም ባለፉት ሶስት ዓመታ እስከ 300 000 ስደተኞች ሊቢያ መግባታቸውን አልካዱም። ከአምስት አመት በፊት የጋዳፊ መንግስት ተገርስሶ ሊቢያ ውስጥ ቀውስ ከተፈጠረ ጀምሮ ከፍተኛ ገንዘብ በማስከፈል ስደተኞች ከቦታ ወደ ቦታ የማስተላለፍ ስራ በጣም አትራፊ የሆነ የንግድ ስራ መሆኑን ብዙዎች ይናገራሉ።፡

Ø የሩዋንዳ መንግስት ያለፈበትን የሰው እልቂት ወደ ብሩንዲ በመላክ የአገሪቱ ዜጎች እርስ በርስ እንዲጫረሱ በማድረግ ላይ ነው በማለት የብሩንዲ የገዥው ፓርቲ መሪ ከሰሱ። የፓርቲው ፕሬዚዳንት ፓስካል ንያቤንዳ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ለተባለው የዜና ወኪል በጽሁፍ በላኩት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለጹት የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት የብሩንዲን ዜጎች በወታደራዊ ትምህርት አሰልጥነው ወንድሞቻቸውን እንዲገድሉ ወደ ብሩንዲ ይልካሉ የሚል ክስ ከሰነዘሩ በኋላ የአውሮፓ አገሮችም መሳሪያና ገንዘብ በመስጠት እየተባበሩ ነው ብለዋል። በቅርቡ በሩዋንዳ እና በብሩንዲ መንግስታት መካከል የእርቅ ውይይት እንዲካሄድ ግፊት ስታደርግ የነበረችው የካቶሊክ ቤተክርሲያን ከወቀሳው ያልዳነች ስትሆን የፓርቲው መሪ አሸባሪዎች የሚሏቸውን የአማጽያንን ዓላማ በማራገብ የሀሰት ዜና ያስፋፋሉ በማለት በውጭ ጋዜጠኞች ላይም የከረረ ሂስ ሰንዝረዋል። በብሩንዲ የፖሊቲካ ቀውስ መከሰት ከጀመረ ወደ አንድ ዓመት ገደማ እየተጠጋ ሲሆን እየተካሄደ ባለው የእርስ በርስ ግጭት ከ400 ሰዎች በላይ መገደላቸውና ከ250 000 ሰዎች በላይ ቤት ንብረታቸውን ጥለው መሰደዳቸው አይዘነጋም።

Ø የጣሊያን ዜጋ የሆነውን ወጣት ገዳዮች ናቸው ተብለው የተጠሩ የቡድን አባሎች በአሰሳ ተገድለዋል በማለት የግብጽ መንግስት መግለጫ መስጠቱ የሚታወቅ ሲሆን በወጣቱ ግድያ ላይ የግብጽ ባለስልጣኖች ያሉበት መሆኑን የሚጠረጥረው የጣሊያን መንግስት የግብጽ ባለስልጣኖችን መግለጫ ያልተቀበለ ከመሆኑም ሌላ በጉዳዩ ላይ የጣሊያን መርማሪዎች በሚገኙበት የምርመራ ቡድን ተመስርቶ ምርመራው እንዲቀጥል የጠየቀ መሆኑ ታውቋል። የግብጽ መንግስት በጣሊያን መንግስት ግፊት ወንጀለኞቹ ተገድለዋል ካለ በኋላ ምርመራው የቀጠለ መሆኑን እንዲሁም ሌሎች ተባባሪዎች መያዛቸውን የሚገልጽ መግለጫ ቢሰጥም የጣሊያን መርማሪዎች ምርመራ ውስጥ ይሳተፉ ለሚለው ጥያቄ ገና መልስ ያልሰጠ መሆኑ ተነግሯል።

Ø ከጥቂት ቀናት በፊት በአይቮሪ ኮስት የወደብ መዝናኚያ ከተማ ለ19 ሰዎች መገደል ምክንያት የሆነው የሽብር ጥቃት ውስጥ ተሳትፈዋል የተባሉ ሁለት የእስላማውያን አክራሪ ድርጅት አባላት በማሊ ውስጥ የተያዙ መሆናቸውን የማሊ የስለላና የጸጥታ ክፍል ባለስልጣኖች ገለጸዋል። ከተያዙት መካከል አንደኛው ሾፌር በመሆን ጥቃቱን ለፈጸሙት ግለሰቦች የትራንስፖርት አገልግሎት የሰጠ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የእርሱ ተባባሪ መሆኑ ተነግሯል። ግንቦት አራት ቀን ግራንድ ባሳም በተባለው የአይቮሪ ኮስት የቱሪስት መዝናኚያ ቦታ ላይ የተካሄደው የሽብር ጥቃት በጥቂት ወራት ውስጥ ከተካሄዱት መካከል ሶስተኛው ሲሆን በሰሜን አፍሪካ የአልቃይዳ ቅርንጫፍ ለጥቃቱ ኃላፊነቱን መውሰዱ ይታወቃል።

ወያኔዎች በሴይጣን ታስረዋል

$
0
0

 

| አባ ቢያ የባለሀገር ንቅናቄ

ለጋብቻ በማይመረጥበትና በማይታጭበት: ለቤት መስሪያ ዛፍ በማይቆረጥበት ጎዶሎ ወር ውስጥ የተወለደው ወያኔ: ዋጋው በቁና እየተሰፈረለት ነው:: ይህ የኃጥአት ልጅ ስብስብ ድርጅት የያዘው የዛር ፈረስ አምጥቶ እሞቱ ደጃፍ ላይ አድርሶታል:: ይኸው የሴይጣን መጫወቻ የሆነው ወያኔ በግድያ: በስርቆት: በዝርፊያ: በቅሚያ: በማጭበርበር: በማታለል: በመዋሸት አገርን ከነድንበሩ ትውልድን ከነባህሉ አበላሽቶአል:: ወያኔ ጫካ በነበረበት ጊዜ ሽፍቶቹን ለማነቃቃትና ለማዋጋት ሲል በሱዳን አማካሪነት Rhamnus Prinodes የተባለ ዕጸ-ፋሪስ ወይም የጌሾ ቅጠል በተለያየ ምግብና መጠጥ ውስጥ ጨምረው ወያኔ ሠራዊትን ያጠጡና ያበሉ ነበረ:: አመራሮች ሁሉ ጭምር ይጠቀሙ ነበረ:: በጎጃም የአብነት ተማሪዎች እንደዚሁም የአስኩዋላ ተማሪዎች ለትምህርት አእምሮን ያነቃቃል:: አንጎልን ይከፍታል እያሉ የሚወስዱትንና ከወሰዱ በሁዋላ በመጨረሻም አሳብዶ ከሰውነት ተራ የሚያወጣውን አብሾ ወይም በባዮሎጂ አጠራር ካናቢስ ሳቲቫ ወይም ማሪዋና በባህላዊ አጠራር ዕጸ-ፋሪስ ወይም አጤ-ፋሪስ ተብሎ የሚታወቀውን መርዘኛ ዕጸዋት ወያኔዎች ይጠቀሙ ስለነበር ዛሬ የወያኔ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ሁሉ አእምሮ ትክክል አይደለም:: ነገር ግን ማንም አልተረዳላቸውም እንጂ አእምሮአቸው ደንብሾአል ::ተቃውሶአል::

TPLF Ethiopian Leaders

በዚህ የተነሳ ከጫካ የመጡ ነባሮቹ ወያኔዎች እርኩስ መንፈስ አጠናግሮአቸዋል:: ቁራና የተባለው ዲሞንስ ወይም መጥፎ መንፈስ የተጠናወታቸው ሰዎች ናቸው:: የሱዳን ቆሪጥ :ሌጌዎን: ጠጠር ጣይ: ዊቃቢ እና ከዘር ጭምር ወደልጅ የሚሸጋገረው Hobgoblins-Imps በአማርኛ አጠራር የዛር ውላጅ በወያኔዎች ላይ ሠልጥኖአል:: ዛሩ ባሪያዎቹ አድርጎአቸዋል:: እንደሚታወሰው ሁሉ ባለፈው ጊዜ የመንግሥት ቃለ-አቀባዩ የኦሮሞ ተቃዋሚዎችን ጋኔን የጠራቸው ብሎ ሲናገር ተደምጦአል:: ይህም ማለት ወያኔዎች በነዚህ እርኩስ መንፈስ ቁጥጥር ሥር ስለሆኑ ሁሉ ሰው እንደእነሱ ይመስላቸዋል:: የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ የሴይጣን መጫወቻ የሆነ ይመስላቸዋል:: እነሱ አንዴ የመጥፎ ማጂክ ባሪያ ስለሆኑ ::They are Slave Zar and they fear all bad magics. for example fools, Vagabond, mad poor,sick etc….ይህ ዓይነት አደጋ ያመጣብናል ብለው ስለሚጨነቁ በምድር ላይ ያለውን ወንጀል ሁሉ ይሠራሉ:: ጋኔን የጠራቸው ብሎ የተናገረው አፈ- ቀላጤው ጋኔን ጎታች The Demons puller የሆነው አለቃ መለስ ሁሉንም ወያኔ የገራው በዚህ መልክ ስለሆነ ነው:: ስለዚህ ወያኔዎች የሰው ህይወት የሚያጠፉት: የሰው ደም የሚያፈሱት: የሰው ልጅን የሚያሰቃዩት በጌቶቻቸው በእርኩስ መንፈስ እየታዘዙ: ለድፍረት ይሆናቸው ዘንድ አጤ ፋሪስ በጥብጠው እየጠጡ ስለሆነ ወደ ድርጊቱ የሚገቡት የሚያደርጉትን በሙሉ ለበጎ ያደረጉ ይመስላቸዋል:: ለዚህም ነው በሚዲያ ያለምንም ፍራቻ: ያለምንም ይሉኝታ ደረቅ ውሸት የሚዋሹት:: በዛር ፈረስ ላይ ስለሆኑ ሚሊዮን ሕዝብ አስር ሰዎች ብቻ መስለው ይታዩአቸዋል:: ሲገድሉ ደግ ያደረጉ ያህል ኮርተው ይናገራሉ:: ሲያሰቃዩ ያስታመሙ ይመስል ደረት ነፍተው ሕዝብ መኃል ይሄዳሉ:: ስለዚህም ነው ደህና ሰው ሳይታሰብ በድንገት ወያኔ ቤት አንድ ቀን ካደረ በዚያው ተበላሽቶ የሚቀረው:: ድምጻዊ ንዋይ ደበበ : ድምጻዊ ሰለሞን ተካልኝ እናም በርካታ አርቲስቶችና ጋዜጠኞች የወያኔ ባሪያ ሆነው የሚቀሩበት ዋናው ምክንያት በዚህ መሠረት ስለሚበላሹ ነው:: የተማሩ ስዎች ወያኔ ከሥራቸው ብታባሪራቸው እንኩዋን በየትም አገር ተቀጥረው መስራት የሚችሉ እንደነ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና ዓይነቶቹ የሱዳን ባህለዊ ጥበብ ሰለባ በመሆናቸው ነው:: እንደነ ልደቱ አያሌው ዓይነት የሴይጣን ተላላኪ ሆነው የቀሩት በዚህ መልክ ነው ::

ስለሆነም የኢትዮጵያ ሕዝብ ከነዚህ ሰዎች ጋራ ሰዎች ናቸው ብሎ ጤነኛ ንግግር ለማድረግ ሠላማዊ ድርድር መጀመር ዕርቅና ርትዕ ይኖራል ብሎ ማመን የሴይጣንን ችሎታና ባህርይ አለመረዳት ነው::

ማንኛውም ወያኔ አሙዋሙዋቱ ድንገት ነው:: ተቀጨ በሚባል ደረጃ ነው ሕይወታቸው የሚያልፈው:: ጄኔራል ኃየሎም ዐረአያ በመሸታ ቤት አንድ ተራ ሰው በዛገ መሣሪያ ተገደለ :: ሰላዩ ክንፈ ገብረ መድኅን በአንድ ረፋዱ ላይ ሰው ፊት ተደፋ:: ታምራት ላይኔ በመንግስት ምክር ቤት ፊት ቁጭ ብሎ እንደሕጻን ስመከር ስገጸጽ አልመለስ ብዬ ሰለነበረ እርምጃው ተገቢ ነው ብሎ መበላሸቱን ተናግሮ ከርቸሌ ተከረቸመ:: እሱ እንኩዋን የታሠረበትን የጋኔን ሰንሰለት በንስሀ ና በጸሎት በጥሶ ዛሬ ሰው ሆኖአል:: የአቶ መለስ እና የአባ ጳውሎስ ጉዋደኝነትና የሠፈር ልጅነት በዚያ ላይ ቅዱስ አባት በሚያስብል ከፍተኛ ማዕረግ ላይ ሆነው ሲሠሩ የነበረው ክፉ ሤራና ሥራ የአቶ መለስ ጠቅላይ አዛዥነት ሚና ተደምሮ ኢትዮጵያ በእነዚህ በሁለቱ አደዋኛዎች ጫማ ሥር እንደወደቀች ሲታሰብ ሴይጣን በተቀደሰችው ኢትዮጵያ ላይ ምን ዓይነት ሹመት እንደነበረው መረዳት አያስቸግርም:: ነገር ከሴይጣንና ከጋኔን ጋራ ጨዋታው የሚባለው:: ከመቃብር

መጨረሻ አያምርም እና ሁሉቱም ሞቱ ሳይሆን ተቀሰፉ ነው የሚገርም ነገር ደግሞ አንዱ አንዱን እንዳይቀብር ሆነው ነው የወረዱት ::

የሴይጣን ሥራ ይኸው ነው:: ሴይጣን ውለታ አያውቅም:: ሰይጣን ቤት ምህረት የለም :: ሰብዓዊ ስሜት ጋኔን ቤት ከተገኘ ሰብዓዊ ስሜት የተሰማው ሰው ወዲያው ይቀሰፋል:: እነዚህ የቀሩቱ ጋኔን የሚጋልባቸው ወያኔዎች ከሰውነት ውጭ ናቸው:: ሲቀኑ: ሲጨክኑ: ሲዋሹ :ሲያታልሉ: ሲገድሉ :ሲያሰቃዩ: ሲጠጡ: ሲሰከሩ: ሲያመነዝሩ በጤናቸው አይደለም:: እላያቸው ላይ ያረፈው የጋኔን አለቃ እየተጫወተባቸው ነው:: በየቀኑ ጠርሙስ ሙሉ ዕስኪ መጨረሰ: በየቀኑ ከተለያየ ሴት ጋራ መተኛት ና እርካታ ማጣት የበረሃ አጋንንት ባህርይ ነው:: በዚህ ላይ የወያኔዎችን ፊት ተመልከቱ እስቲ:: እህልና ውሃ ከቀመሱ ወራት ያለፋቸው ወይም ለኮሶ ሽረት እንቆቆ የሚጠጡ የሚመስል ፊት ነው የሚታየው:: የጤናማ ሰው ፊት እኮ አይደለም ፊታቸው:: የበረከትንና የሰብሀት ነጋን ፊት ተመልከቱ:: በደርግ ዘመን በሕብረት ዘመቻ የተሠራ እርከን ነው የሚመስለው:: አርከቤን ተመልከቱት:: ኦፋይት ዑቃቢ ያለበት ይመስላል:: ሁሎቹም ወያኔዎች በየቀኑ ገርጥጠው እና ገርኝተው ይታያሉ :: የሰው ልጅ ሀመልማል ፊት የላቸውም ::

እናም ኢትዮጵያ በሴይጣን በአጋንንት አገዛዝ ሥር ስለሆነች ከተቻለ በእግዚ- ኦታ በጸሎት ካልሆነም በአንድነት ተነስቶ ይህንን ደም መጣጭ የሴጣን ጋማዎችን ማስወገድ ይኖርብናል :: እንደሰው እያዩ ለምን ህግን ጣሱ? ለምን እግዚአብሄርን አልፈሩም? ለምን ባህላችንን ተጻረሩ? ብሎ መታለል ይብቃ:: ምንም ዓይነት ከስይጣና ባሪያዎች ጋራ ንግግርና ድርድር አለማድረግ ትልቅ ውሳኔ ነው ::

 

“የሰማዕቱ ፕ/ር አስራት የሞቱለትን ዓላማ አንግበን የአማራውን ሕዝብ ትግል ከግብ ለማድረስ እንታገላለን”|ከዳግማዊ መዐሕድ የተሰጠ መግለጫ

$
0
0

AAPO !!

ከዳግማዊ የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት (ዳግማዊ መዐሕድ ) የተሰጠ መግለጫ

በኢትዮጵያ ውስጥ ላለፉት ሃያ አምስት የሰቆቃ ዓመታት፣ በዘረኛው የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባርና አባሮቹ በዐማራ ሕዝብ ላይ የፈጸሙት ግፍና በደል የሰው ልጅ ሊሸከመው ከሚችለው ያለፈ ሆኗል። በፖሊሲ ተቀርጾ፣ ደረጃ በደረጃ በሚፈፀም የዘር ማጥፋት ዘመቻ ዐማራው እየተጠቃ ይገኛል።

በተለያዩ ግዚያት በበደኖ ፣ በአርባጉጉ ፣ በወተር ፣ በአርሲ ፣ በነጌሌ ፣ በአሰቦት ገዳም፣ በአሶሳ ፣ጎንደር በአደባባይ እየሱስ፣ በወልቃይት ፣ በጠገዴ፣ በጌዲኦን፣ በጉጂ ፣በምስራቅ ወለጋ ፣በጅጅጋ፣ በጉሙዝና በቤንቺ ማጂ ዞን፣ በጉራ ፈርዳ ወረዳና በሌሎችም አካባቢዎች ዐማራውን ዒላማ ያረገ ኢሰባዊ ጭፍጨፋ ተካሂዶ ከፍተኛ እልቂት ተፈጽሟል።

ሙሉ መግለጫውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live