Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ 10 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ለእለት የሚበሉት እንዳማይኖራቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለጸ

$
0
0

_88107348_hi031231902ኢሳት ዜና ፦ በቀጣዮቹ ሶስት ወራቶች ውስጥ አለም አቀፍ እርዳታ ወደ ኢትዮጵያ መላክ ካልጀመረ ከ10 ሚሊዮን ሰዎች ለእለት የሚበሉት እንዳማይኖራቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በድጋሚ አሳስቧል። የበጋ ወቅቱ እየተጠናከረ መምጣቱንና የእርዳታ አቅርቦት ባለመኖሩ ምክንያት የድርቁ አደጋ ወደ አሳሳቢና አስከፊ ድረጃ እየተሸጋገረ መሆኑንም ድርጅቱ ገልጿል። በአሁኑ ወቅት ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ የተጋለጡ ከ10 ሚሊዮን በላይ ሰዎችም የግንቦት ወር ከመግባቱ በፊት አለም አቀፍ እርዳታ ሊቀርብላቸው እንደሚገባ የተባበሩትመንግስታት ድርጅት አመልክቷል። ይሁንና ለዚሁ ድጋፍ በተደጋጋሚ ጥሪ ቢቀርብም በቂ ምላሽ አለመገኘቱ ስጋትን ፈጥሮ እንደሚገኝ የድርጅቱ ባለስልጣናት ይፋ አድርገዋል። የመንግስት ባለስልጣናት በበኩላቸው የአለም አቀፍ ማህበረሰብ ለኢትዮጵያ የእርዳታ ጥሪ በቂ ምላሽ ባለመስጠታቸው የድርቁ አደጋ ትኩረት እየሳበ መምጣቱን በመግለጽ ላይ ሲሆን፣ አንዳንድ የእርዳታ ተቋማት ድርቁ ወደ ረሃብ ሊለወጥ ይችላል የሚል ስጋት መኖሩንም አስታውቀዋል።

The post በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ 10 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ለእለት የሚበሉት እንዳማይኖራቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለጸ appeared first on Zehabesha Amharic.


ፖሊስ በሐይማኖት አስተምህሮ ሰበብ የታመመች ልጇን ወደ ሀኪም ቤት ያልወሰደችን እናት አሰረ

$
0
0

12631557_10205785783304680_5747023594850496573_n

ዳዊት ሰሎሞን

የኬንያ ፖሊስ መካከለኛ እድሜ ላይ የምትገኝን አንዲት እናት ለወራት በህመም ስትሰቃይ የነበረችን ልጇን ወደ ሐኪም ቤት ለመውሰድ ፈቃደኛ ሳትሆን በመቅረቷ በቅጥጥር ስር በማዋል ታማሚዋን የህክምና ምርመራ እንድታደርግ መርዳቱን አስታወቀ፡፡እናትየዋ ልጇን ሆስፒታል ያልወሰደቻት ‹‹ፈውስ ከእግዚአብሄር ብቻ ነው ››በማለትና አምልኮ የምትፈጽምበት ቤተክርስቲያን አስተምህሮም ወደ ሆስፒታል መሄድን ስለሚቃወም መሆኑን ተናግራለች፡፡
የታማሚዋ ወላጆች የአንደኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራን መሆናቸውን የጠቀሰው ፖሊስ ህመምተኛዋን ከሁለት ወራት በላይ በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ አስተኝተዋት ቆይተዋል ብሏል፡፡ ወይዘሮዋ ሐይማኖቷን የምትከታተልበት ቤተክርስቲያን አገልጋዩችና ምዕመናኖቻቸው የወሊድ መከላከያን መጠቀም፣ህጻናትን ማስከተብና የህክምና አገልግሎት ማግኘትን የማይቀበሉ ስለመሆናቸውም ተወስቷል፡፡
‹‹ሴትየዋን ከስራ ቦታዋ በመያዝ ወደቤቷ በማምራት የታመመችውን ልጅ ቤት ተቆልፉባት አግኝተናታል››ያሉት የፖሊስ ኃላፊው ኢውኒቼ ኪማ ‹‹የልጅቷ መምህራን ስልክ በመደወል ከህዳር ወር ጀምሮ ክፍል አለመግባቷንና በምን ሁኔታና የት እንደምትገኝ አለማወቃቸውን ከነገሩን በኋላ እርምጃውን ወስደናል››ማለታቸውን ዴይሊ ኔሽን ጋዜጣ ዘግቧል፡፡

ልጅቷ ከህዳር ወር ጀምሮ በህመም ስትሰቃይ መቆየቷም ታውቋል፡፡
ልጇን ለምን ህክምና እንዳታገኝ እንዳደረገቻት ተጠይቃም ‹‹በምንታመምበት ወቅት ሊፈውሰን የሚችለው አምላክ ብቻ ነው፡፡ልጄ ከታመመችበት ቀን ጀምሬ ፈውስ እንድታገኝ ስጸልይላት ነበር፣ምንም አይነት መድኃኒት ሳትወስድም ሙሉ ጤንነቷን እንደምታገኝ አምናለሁ››ብላለች፡፡
እናትየው በምትገኝበት ቤተክርስቲያን የሚገኙ ወላጆች ልጆቻቸው ሲታመሙባቸው ወደ ህክምና ከመውሰድ ይልቅ የታመሙትን ለብቻ በመነጠል ‹‹የጸሎት ክፍል››በማለት በሰየሙት ቤት ውስጥ ህመማቸው እስከሚሻላቸው እንደሚያቆያቸው ፖሊስ አስታውቋል፡፡
የታማሚዋ ወላጅ እናት ከ1976 ጀምሮ ሆስፒታል ሄዳ ወይም መድኃኒት ወስዳ እንደማታውቅ በመግለጽ ‹‹ባመመኝ ወቅት ሁሉ በመጸለይ ፈውሴን አገኛለሁ››ማለቷ ተሰምቷል፡፡

ከእምነታቸው ውጪ በሐይል ተገፍተው ወደ ሆስፒታል እንዲወሰዱ በመደረጋቸው የሚያመልኩት አምላክ ይህንን ባደረጉት ላይ የቅጣት በትሩን እንደሚያሳርፍ ሴትየዋ ተናግረዋል፡፡ለሐይማኖታቸው ያላቸውን ታዛዥነት ለማሳየት ሲሉ ልጃቸውን ለወራት ለስቃይ ስለዳረጓት ቤተሰቦች አስተያየት የሰጡት የአካባቢው የፖሊስ ኃላፊ ‹‹ሰዎቹ የተማሩ ብቻ ሳይሆኑ አስተማሪዎች ጭምር መሆናቸው ነገሩን አስገራሚ ያደርገዋል››ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያም በሁሉም የሐይማኖት ቤቶች ለማለት በሚያስደፍር መልኩ እንዲህ አይነት አቋም የሚያንጸባርቁ መምህራን፣ወላጆችና ምዕመናንን ማግኘት አያስቸግርም፡፡የታመሙ ሰዎችን ከህክምና መስጫ ተቋማት ይልቅ ወደ ጸበል ቦታዎች እንዲሄዱ የሚገፉ፣የተጀመሩ መድኃኒቶችን እንዲያቋርጡ የሚመክሩና ፈውስ ከአምላክ ብቻ በመሆኑ ህመምን ከኃጢአት በማገናኘት በሽታቸው ስር ሰድዶ ለሞት የሚዳርጋቸውና የዳረጋቸው አይታጡም፡፡

ኬንያስ በሀይል ጭምር ታዳጊዋ ህክምና እንድታገኝ አድርጋለች፣የታከመ ሁሉ ይድናል ባይባልም ቢያንስ በሽታን በሳይንሳዊ መንገድ በማስወገድ የቀደመ ጤንነትን ማግኘት ይመከራል፡፡ወላጆች፣መምህራንና ማህበረሰቡ ታማሚዎችን ወደ ህክምና ከመምራት ይልቅ በሽታን ኃጢአት በማድረግ በሽተኛውን ወደ ጸሎትና ጸበል መምራታቸውን እንዴት ያዩታል?እንዲህ አይነት ሁኔታዎች ሲፈጠሩስ ፖሊስ ጣልቃ በመግባት ታማሚውን ወደ ሆስፒታል መውሰዱን ይደግፋሉ?

 

The post ፖሊስ በሐይማኖት አስተምህሮ ሰበብ የታመመች ልጇን ወደ ሀኪም ቤት ያልወሰደችን እናት አሰረ appeared first on Zehabesha Amharic.

በጋምቤላ የተከሰተው ግጭት የወያኔና የደቡብ ሱዳን እቅድ መሆኑን የታህሳስ 3 ሊቀመንበር ተናገሩ

$
0
0

ጥር 26 2008 ዓ/ም
በጋምቤላ የተከሰተው ግጭት በሕወሓትና በደቡብ ሱዳን አመፀኛ መሪ ርየክ መቻር መካከል የተደረገ ድርድር መሆኑን የታህሳስ ሶስት መታሰቢያ ዲሞክራሲያዊ እንቅስቃሴ ሊቀ መንበር አቶ ጊቭሰን ኡበንግ ገለጹ። ጉዳዩን በቅርብ ሲከታተሉት የነበሩትና ለስጋታቸው በሚል ፎቶግራቸው የማይወጣው አቶ ሳይመን ቹዎል ጋትበል በፈስ ቡክ ላይ እንደፃፋት፣ ጋምቤላ ለርየክ መቻር መለገሷን በማጋለጥ፣ ይህን እቅድና ውል የተነደፈው በአለፈው ዲሴምበር በናይሮቢ ኬንያ ሲሆን፣ በውሉ ላይ ተሳታፊ የነበሩ መካከል የሕወሓት ተወካዮች፤ የቀድሞ የኢሰፓ አንደኛ ፃፊ የነበሩት ጓድ ቱዋት ፓል፤ የቀድሞ የጂንካው አውራጃ የኢሰፓ አንደኛ ፃፊ የነበሩት ቢቾክ ዋን፤ በጎንደር ስደተኛ ሆኖ የጤና ትምህርቱ የጨረሰ ዶክተር ኮንግ ቱት፤ የወያኔ የግድያ አስፈፃሚ እንዲሆን የተሾሞው ስደተኛው የርየክ መቻር የቅርብ ዘመድ ፕሬዝዳንት ጋትሉዋክ ቱትና የደቡብ ሱዳን አመፀኛ ተወካዮች እንደተገኙበት በግልጽ ተናግሯል ሲል ታህሳስ 3 ገልጿል::

Simon

እንደታህሳስ 3 ገለጻ “ይህ የሚያሳን የወያኔ ሠራዊት በአኝዋኩ ላይ የተፈፀመው ጭፍጨፋ እየታዘበ፣ ኑዌሩ የወያኔን ሰንደቅ አላማ በማቃጠል፣ በምትኩ የደቡብ ሱዳኑን በማውለበለብና ለጭፍጨፋ ማፋጠኛ እንዲሆን ለወያኔ በሙስና የተሰጠው ገንዘብ የዚህች ውል የጠለቀ ማስረጃዎች ናቸው::”
“በአሁኑ ወቅት የጋምቤላ ሀኔታ እንደተረጋጋ ቢያስመስልም፤ ወያኔ በህዝባችን ላይ የሚያቀጣጠለዉ ግጭት ደንታ የሌላቸዉ ቢሆንም፣ ስደተኛው ኑዌር በአኝዋኩ ኢትዮጵያዊ ላይ እንዲነሳ በመመልመል፤ አኝዋኩ ሆነ አጠቃላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ የዚህ አይነቱ የረከሰ የክፍፍል አረመናዊ አገዛዝ በግልጽ ስለተረዱ፣ ሕዝባችንና አገራችን ለደቡብ ሱዳን ለመሸጥ ወያኔ የሚያካሂደውን ስልት ዝም እንደማንል እናሳዉቃለን። ወያኔ በደም የተነከረ እጃቸውን እንዳአዘቀቱበት ስንዘግብ፣ ታች የተፃፈውን በግልጽ ያረጋግጣል ስሉ አቶ ጊቭሰን ጨምሮ ገልፆል።

አቶ ጊቭሰን፥ በፀረ ደርግ ትግል ወቅጥ የጋምቤላ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር (GPLM) መሪ በነበሩበት ጊዜና ከነአባይ ፀሐይ፣ ስዬ አብርሃ፣ ስብአት ነጋ፣ ስዩም መስፍን፣ አዲሱ ለገሠና የተቀሩት የወያኔ መሪዎች በትግራይ ያደረጉት ቆይታ፣ ያኔ ሲያራምዱት የነበረው የአገሪቷን የማውደም አላማ አሁንም እንዳልተቀየሩ ሲገልፁ፥ በመቀጠል፥ ወያኔ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የሚያካሂደዉን የዘር ማጥፉት ዘመቻ በማውገዝ፤ ጠቅላላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እጅ ለእጅ ተያይዞ በጎሳ ሳይከፉፈል ይህን ጨቋኝ መንግስት ለማስወገድ መታገል እንደሚገባቸው አቶ ጊቭሰን በጥብቅ ተናግሯል።
“በሰላም እንዳይኖር የተገደደው ፤ መሬቱ እየተዘረፈና፤ በመጨፍጨፍ ላይ የሚገኘው የአኝዋኩ ብሄረሰብ መሆኑን መገንዘብ አስፈላጊ መሆን ሲታሰብ፣ ያለ ሕዝቡ ፍቃድ በግድ የሰፈሩትን ስደተኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጋምቤላ እንዲነሱ የተባበሩት መንግሥታ የስደተኛች ጉዳይ ጽህፈት ቤትና ለሰላምና ለነፃነት የሚቆሙ ኢትዮጵያዊያን የከረረ አቤቱታ እናስተላልፉለን።” ያለው ታህሳስ 3 “በወያኔና በስደተኛው መካከል የተደረገው ሽር ጉድ፣ በአዲስ አበባ የሚገኙት ከፍተኛ እስር ቤቶች የሚሰቃዩ የአኝዋክና የመጀንግር ብሄረሰብ አባላት በአስቸኳይ እንዲፈቱ እናሳስባለን።” ብሏል::
­”ስደተኛውን እስከ አፍንጫው ድረስ ያስታጠቁት የጦር መሣሪያ ሳይፈቱ፣ ከቤታቸውን የተፈናቀሉና ልጆቻቸው የተገደገለባቸውን ወገኖቻችን ሳያማክሩ፣ ጣልቃ እየገቡ በግድ የፈጸሙትን የማሥታረቅ ተግባር በጸና እምነት አለመደረጉ ስገልጽ፣ ለወደፊቱ የታቀደው ተመሣሣይ ግድያ የወያኔ መንግሥትና የርየክ መቻር አስፈፃ መሪዎች በቀንደኛነት እንዲጠየቁ በሕዝቡ ስም እናሳስባለን።” የሚሉት አቶ ጊብሰን ” በናይሮቢ የተከናወነው የግድያ እቅድ የተሳተፋት ግለሰቦች በነፃና ገለልተኛ አካል እንዲጠየቁ እንጠይቃለን። በግድያ እቅድ የተሳተፋትና የአስፈፀሙ ጋትሉዋክ ቱትና የወያኔ ሠራዊት መሪዎች በመሆናቸው በአስቸኳይ ያለአንዳች አድሎ በኢትዮጵያ የፀጋ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ በጠቅላላው የአኝዋኩና የኢትዮጵያ ሕዝብ ስም በጥብቅ እንጠይቃለን ” በማለት ደምድመዋል።

The post በጋምቤላ የተከሰተው ግጭት የወያኔና የደቡብ ሱዳን እቅድ መሆኑን የታህሳስ 3 ሊቀመንበር ተናገሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የምስክርነት ቃሉን ሰጠ |‹‹የህሊና እስረኛ ነኝ›› እስክንድር ነጋ

$
0
0

(ነገረ ኢትዮጵያ)  በሽብርተኝነት ወንጀል ጥፋተኛ ተብሎ 18 አመት እስር ተፈርዶበት በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የመከላከያ ምስክርነት ቃሉን ሰጥቷል፡፡

Eskinder Nega
በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ አንደኛ ተከሳሽ ለሆነው አቶ ዘላለም ወርቃገኘሁ መከላከያ ምስክር ሆኖ ልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ከእስር ቤት የቀረበው ጋዜጠኛ እስክንድር ዛሬ ጥር 27/2008 ዓ.ም ምስክርነቱን ሊያሰማ ችሏል፡፡
ያለጠበቃ በግሉ የሚከራከረው ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ ጋዜጠኛ እስክንድር እንዲያስረዳለት የሚፈልገው ጭብጥ ጡመራ ምንድነው፣ ከወንጀል ጋርስ ግንኙነት አለው ወይ፣ እና ሰብዓዊ መብት እና ዴሞክራሲ ላይ ስልጠና ስለሚሰጡ ድርጅቶችና የስልጠናው ይዘትን በተመለከተእንደሆነ ቢያስታውቅም በጭብጡ ላይ አቃቤ ህግ ተቃውሞውን አሰምቷል፡፡ በዚህም አቃቤ ህግ ጡመራ ምንድነው፣ ወንጀልስ ነው ወይ የሚለው በምስክር ሳይሆን በህግ ድንጋጌዎች የሚረጋገጥ እንደሆነ በመግለጽ ተቃውሟል፡፡ ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን ከሰማ በኋላ ጡመራ ወንጀል ስለመሆን አለመሆኑ የተያዘውን ጭብጥ ውድቅ በማድረግ ስለ ስልጠናውና አሰልጣኝ ተቋማት የተመዘገበው ጭብጥ ላይ ምስክሩ እንዲመሰክሩ ብይን ሰጥቷል፡፡ 


ብይኑን ተከትሎ ምስክሩ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ችሎት ፊት የቀረበ ሲሆን በመጀመሪያ በፍርድ ቤቱ የቀረቡለትን ጥያቄዎች መልሷል፡፡ ምስክሩ ሙሉ ስሙን፣ እድሜውን፣ ስራውንና ለምን እንደመጣ፣ እንዲሁም ከተከሳሾች ጋር ስለመተዋወቁ ለቀረቡለት ጥያቄዎች መልስ ሰጥቷል፡፡ እስክንድር ‹‹ስራ›› ተብሎ ሲጠየቅ፣ ‹‹ጋዜጠኛ ነበርኩ›› ብሏል፡፡ ‹‹አሁንስ›› የሚል ጥያቄ ፍርድ ቤቱ አቅርቦለት፣ ‹‹አሁን የህሊና እስረኛ ነኝ›› ሲል መልሷል፡፡


ተከሳሹ ዘላለም ወርቃገኘሁ በዋና ጥያቄ ተከሳሹ ውጭ ሀገር ሊወስደው ነበር ተብሎ በክሱ ላይ ስለተጠቀሰው ስልጠና ምስክሩ እንዲያብራሩለት ጠይቋል፡፡ ምስክሩም ‹‹ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ሀገራትንም የሚያሳትፍ ስልጠና በሰብዓዊ መብት፣ በሚዲያ ‹ኢቲክስ›፣ እና በዴሞክራሲ ላይ ይሰጣሉ፡፡ ድርጅቶቹ የተለያዩ ቢሆንም በሰብዓዊ መብት ጉዳይ ላይ መርሃቸው ተመሳሳይና ዓለም አቀፍ ነው›› በማለት መስክሯል፡፡ 


ድርጅቶቹን በስም መጥቀስና የሚገኙበትንም ሀገር ለፍርድ ቤቱ መግልጽ ይቻል እንደሆነ ምስክሩ ተጠይቆ ‹‹የተቋማቱ መገኛ ምዕራቡ ዓለም ነው፡፡ በዴሞክራሲ የዳበሩ ሀገራት ነው ዋና መቀመጫቸው፡፡ ሲ.ፒጄ፣ ፍሪደም ሀውስ፣ አምንስቲ ኢንተርናሽናል እና አርቲክል 19 የመሳሰሉትንም በስም መጥቀስ ይቻላል፡፡ እኔም ከነዚህ ተቋምት ውስጥ በአንዱ የተሰጠ ስልጠና አዲስ አበባ ላይ ተካፍየ ነበር፡፡ ስልጠናው ስለ ሰብዓዊ መብት፣ ስለ ሚዲያ፣ ስለ ዴሞክራሲ የሚያስተምር ነው፡፡ ስልጠናው ከሽብር ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፤ ይህ እንደማስረጃ መቅረቡ ኢትዮጵያን ትዝብት ውስጥ የሚከትና የሚያሳዝን ነው›› ሲል ምስክርነቱን ሰጥቷል፡፡ 


ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ መቼ እንደታሰረ በመስቀለኛ ጥያቄ ተጠይቆ ‹‹መስከረም 2004 የሀሰት ክስ ቀርቦብኝ፣ በግፍ ተፈርዶብኝ ታስሬ እገኛለሁ›› ሲል መልሷል፡፡ እስክንድር ነጋ ጥቁር ሱፍ በደብዛዛ ሸሚዝ ለብሶ፣ ሙሉ ጥቁር መነጸር አድርጎና ነጠላ ጫማ ተጫምቶ ችሎት ፊት ቀርቧል፡፡ 


አንደኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ ምስክሩ ምስክርነቱን ማጠቃለሉን ተከትሎ በመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡለት የጠራቸው ሌላኛው ምስክር አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በተደጋጋሚ እንዲቀርቡለት ትዕዛዝ እንዲሰጥለት የጠየቀ ቢሆንም እስካሁን አለመቅረባቸው መንግስት ግለሰቡን ለማቅረብ ፍላጎት እንደሌለው ያሳያል ሲል ቅሬታውን አሰምቷል፡፡ ‹‹አሁን የተረዳሁት ነገር ከሳሼ የሆነው መንግስት አቶ አንዳርጋቸውን ከሚያቀርብ እኔን በነጻ መልቀቅ እንደሚቀለው ነው›› ብሏል ተከሳሹ፡፡


ተከሳሹ ከአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጋር በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች እንደተገናኜ አቃቤ ህግ መጥቀሱን በማስታወስ ምስክሩ መቅረባቸው ያለውን ተገቢነት አስረድቷል፡፡ ‹‹ምስክሩ እንዲቀርቡልኝ እፈልጋለሁ፡፡ ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ፍርድ ቤቱ ከምስክሩ ጋር በተገናኘ ያለውን የክሱ ፍሬ ነገር አውጥቶ በቀሪው ላይ ብይን ይስጥልኝ›› ብሏል ተከሳሹ አቶ ዘላለም፡፡ 


ፍርድ ቤቱም ምስክሩ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲቀርቡ ትዕዛዝ በመስጠት ምስክርነታቸውን ለመስማት በሚል ለየካቲት 16/2008 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

The post ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የምስክርነት ቃሉን ሰጠ | ‹‹የህሊና እስረኛ ነኝ›› እስክንድር ነጋ appeared first on Zehabesha Amharic.

የወያኔ ኢኮኖሚ፣ የገበያ ኢኮኖሚ፣ የካፒታሊስት ኢኮኖሚ፣ በመንግስት የሚደገፍ ኢኮኖሚ፣ ወይስ ሌላ? |ፈቃዱ በቀለ፣ ዶ/ር

$
0
0

በቅድሚያ ለዚህ ጽሁፌ መነሻ የሆነኝ፣ በአለፉት ሃያ አምስት ዐመታት በአገራችን ምድር „የነፃ ገበያ ፖሊሲ“ ተግባራዊ መሆን ከጀመረ ወዲህ በተሳሳተ መልክ የሚናፈሰውንና በአንዳንድ መጽሄቶች የሚወጣውን የተሳሳተ አመለካከት ለመዳሰስ ነው። በተለይም በገዢው መደብ አንዳንድ አባላት ወይም ሚኒስተሮችም ሆነ በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ስለ ነፃ ገበያ የተሳሳተ አባባል ስለሚነፍስ እንደዚህ ዐይነቱን የተዛነፈና የአንድን አገር ዕድገት የሚያዛባ አነጋገር ማስተካከል ስለሚያስፈልግ የግዴታ ይህንን አጭር ጽሁፍ ለመጻፍ ተገደድኩኝ። በተጨማሪም ውጭ አገር የሚኖሩ በኢኮኖሚክስ ሙያ የሰለጠኑ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ምሁራን የገበያን ኢኮኖሚ ልቅ እንደሆነ ስርዓትና፣ ለሁሉም ተዋናይ የሀብት ክፍፍልን በእኩልነት ደረጃ እንደሚያዳርስ አድርገው ስለሚያቀርቡ የገበያ ኢኮኖሚ ምን እንደሚመስልና በምንስ ዐይነት ውስጣዊ ህጎች እንደሚገዛ ማሳየቱን አመንኩበት።

national bank of ethiopia

በሳይንስና በህብረተሰብ ዕድገት ታሪክ ባልተደገፈ መረጃ፣ በአንዳንድ የመንግስቱ ተጠሪዎችም ሆነ በሌላ የነፃ ገበያ ኢኮኖሚ ናፋቂዎች፣ “ በነፃ ገበያ መርህ እዚህ አምርተህ እዚህ ሽጥ የሚባል ነገር የለም። አምርቶ የፈለገበት መሸጥ ይችላል።“ የሚለው አነጋገር ሃላፊነት የጎደለው አባባል ብቻ ሳይሆን ልቅነትን የሚያስፋፋ ነው። ድህነት እንዳይቀረፍና ጠንካራ ኢኮኖሚ እንዳይገነባ የሚያግድ እጅግ አደገኛ አነጋገር ነው። በሌላ ወገን ደግሞ እንደዚህ ዐይነቱ አባባልና ተግባራዊ መሆን ጥቂት ሰዎችን የሚጠቅምና የሚያደልብ ነው። በተግባርም እንዳየነው በዓለም አቀፍ ኢንስቲቱሽኖችና የምዕራብ መንግስታት የተደገፈው ነፃ የገበያ ፖሊሲ አዳዲስ ችግሮችን በመፍጠርና፣ በድሮው ላይ በመደረብ ህዝባችን የባሰውኑ እንዲደኸይ መደረጉ ብቻ ሳይሆን፣ ሌላ ኃይል ስልጣን ቢጨብጥ እንኳ ችግሩን ለመፍታት እንዳይችል ብዙ ምስቅልቅል ሁኔታዎችን የፈጠረ ነው። ዛሬ በአገራችን ምድር የተስፋፋው ድህነትና የጥቂቶች ማበጥ የዚህ የተሳሳተ ግንዛቤና የፖሊሲው ውጤት ነው ማለት ይቻላል። አንዳንድ ባለስልጣናት ይህንን በደንብ ሳይታኘክ፣ ፈረንጆች እንደሚሉት ከጭንቅላት ሳይሆን ከሆድ የወጣ አነጋገር የትኛው የኢኮኖሚክስ መጽሀፍ ላይ ተጽፎ እንዳነበቡ ቢነግሩን በጣም ጥሩ ነበር። ሃሳቡን ከዚህኛው መጽሀፍ ላይ ነው የወሰድነው ቢሉን እንኳ፣ ይህ ዐይነቱ አባባል የተፈጥሮ ህግ፣ ወይም ደግሞ እንደ እግዜአብሄር ቃል ተደርጎ መወሰድ የለበትም። ትምህርት ቤት ገብተን የምንማረው ዝም ብለን የሚነገረንን እንደ ዕምነት ለመቀበልና እሱን መልሰን ለማስተጋባት ሳይሆን፣ ከኮመን-ሴንስም ሆነ ከሳይንስ አንፃር አንድ ነገር ትክክል መሆኑንና አለመሆኑን በመመርመር የራሳችንን ፍርድ ለመስጠትና ትክክለኛውን መንገድ ለመያዝና ለሌላው ደግሞ ለማሳየት ነው። የተማሩ ሰዎችም ዋናው ተግባርና ኃላፊነት አንድን ነገር ከሳይንስና ከተጨባጩ ሁኔታ በመመርመርና በማጥናት ለሰፊው ህዝብ ዕውነትን ከውሸት ለመለየት ይችል ዘንድ ትክክለኛውን መንገድ ማሳየት ነው።

በተለይም ባለፉት ስድሳ ዐመታት የኒዎ-ክላሲካል፣ ወይም በዘመኑ አባባል የኒዎ-ሊበራል የኢኮኖሚክስ ትምህርት የበላይነትን ከተቀዳጀ ወዲህ፣ በብዙ መቶሺህ የሚቆጠሩ ምሁራንን በማሳሳት ለብዙ የሶስተኛው ዓለም አገሮች ድህነትና ኋላ-መቅረት ዋና ምክንያት እንደሆነ፣ በየአገሩ የሰፈኑት ተጨባጭ ሁኔታዎች ብቻ ሳይሆኑ እሱን የሚቀናቀኑ አያሌ መጽሀፎችም ያረጋግጣሉ። በተለያዩ አዋቂዎች ታትመው የወጡትን የተለያዩ አስተሳሰቦችን ያዘሉና፣ በየአገሩ የሰፈኑትን በጣም አስከፊ ሁኔታዎች ግንዛቤ ውስጥ አስገብቶ ማወዳደርና እንዲሁም ደግሞ ማውጣትና ማውረድ ባልተለመደበት አገር ከአንድ ወገን የሚቀርቡ ትምህርቶችን ትክክል ናቸው ብሎ መቀበልና እነሱን ማስተጋባቱ እንደልማድና ዕምነት ተደርጎ ይወሰዳል። ይህን የመሰለ የተሳሳተ አባባል በተፈጥሮ ሳይንስም ውስጥ ተቀባይነትን በማግኘት የሳይንስን ዕድገት ሁለት ሺህ ያህል ዐመታት አፍኖ እንዳስቀረ ይታወቃል። ለምሳሌ የፕላኔቶችን፣ ምድርንም ጨምሮ በፀሀይ ዙሪያ መሽከርከር በብዙ የግሪክ ፈላስፎች የታወቀ ቢሆንም፣ አርስቲቶለስና ፖትሌመዎስ ደግሞ ይህንን በመገልበጥ፣ ፀሀይ ሳትሆን በአንድ ቦታ ቆማ የምትገኘው ምድር ናት በማለትና፣ ፀሀይና ሌሎች ፕላኔቶችም በምድር ዙሪያ ነው የሚሽከረከሩት ብለው የሳይንስን ዕድገት እንደጎተቱትና፣ የአውሮፓም ህዝብ ለሰባት መቶ ዐመታት ያህል በጨለማ ዓለም ውስጥ እንዲኖረ የበኩላቸውን አስተዋፅዖ አድርገዋል። ይህ ዐይነቱ የተሳሳተ አመለካከት ምርምር ፣ በተለይም በካቶሊክ ሃይማኖት መሪዎች ተቀባይነት ያገኘው የተሳሳተ ዕምነት በኮፐርኒከስ ውድቅ እንዲሆን ከተደረገ ወዲህ፣ ጳጳሶች በሳይንቲስቶች ላይ በመነሳት አንዳንዶችን እንዳቃጠሏቸውና፣ ጋሊልዮን ደግሞ እስር ቤት እንደወረወሩት ይታወቃል። በህብረተሰብ ታሪክ ውስጥ ዕውቀትን በሚመለከት የተለያዩ አመለካከቶች እንደመኖራቸው ሁሉ፣ በአንድ የታሪክ ወቅት የበላይነትን የተቀዳጀው ኃይል የሰው ልጅ ዕውነተኛውን የነፃነት መንገድ እንዳይከተልና፣ ሰላምና ብልጽግና የሰፈነበት ኑሮ እንዳይመሰርት በተወሰኑ ምሁራን እንደ ዕውቀት የዳበሩትን ወደ ርዕዮተ-ዓለምነት በመለወጥ የሰውን ልጅ አስተሳሰብ እንዲጠብ ያደርጋሉ። ወደ ውስጥ ጠልቆ እንዳይመራመር በማድረግ ለህብረተሰብአዊ ውዝግብ ዋና ምክንያት ይሆናሉ። ዕውነተኛ ስልጣኔን የመቀዳጀቱ ጉዳይ እየተራዘመና እየጨለመ እንዲሄድ ያደርጋሉ።

ወደ ኢኮኖሚክስ ስንመጣ ዛሬ በየትምህርት ቤቱ የሚሰጠውና እንደቀኖና የተወሰደው የኒዎ-ክላሲካል ኢኮኖሚክስ ትምህርት ከመፍለቁ በፊት ብዙ የአውሮፓ መንግስታት፣ ኋላም አሜሪካ ህብረ-ብሄርን(Nation-State) መገንባት የቻሉት የኔዎ-ክላሲካል ወይም የኒዎ-ሊበራልን የኢኖሚክስ ቲዎሪን መሰረት በማድረግ ሳይሆን -በጊዜው እንደዚሁ ዐይነቱ ቲዎሪ በፍጹም አይታወቅም ነበር- የመርከንታሊዝምን ወይም ቀጥተኛና ንቁ የሆነን የኢኮኖሚ ፖሊሲ መመሪያና ተግባራዊ በማድረግ ነው። የኋላ ኋላ ሌሎች የኢኮኖሚክስ ቲዎሪዎችና ፖሊሲዎች ቢፈልቁም፣ ከአስራአምስተኛው እስከ አስራዘጠነኛው ክፍለ-ዘመን ማገባደጃ ድረስ የብዙ አውሮፓ መንግስታት የኢኮኖሚ ፖሊሲ በማኑፋክቱር ግንባታ ላይ የተመሰረተ ሲሆን፣ የውስጥ ገበያን በጠንካራ መሰረት ላይ ለመገንባት፣ ከተማዎችን ማስፋፋት፣ የካናል ሲይስተሞችንና የባቡር ሃዲድን በመስራትና በመገንባት ህዝቡን ማስተሳሰር ነበር። በ18ኛው ክፍለ-ዘመን የአዳም ስሚዙ የነፃ ገበያ መመሪያ ተቀባይነት እንዲኖረው በተለይ እንግሊዝ ከፍተኛ ትግል ብታካሂድም፣ የጀርመን ፈላስፎች፣ የህብረተሰብ ሳይንስ ምሁሮችና ኢኮኖሚስቶች ይህንን ዐይነቱን ልቅ የሆነና ለእንግሊዝ ብቻ የሚያመቸውን የነፃ ገበያ በመቃወምና የራሳቸውን ቲዎሪ በማፍለቅና በማስፋፋት ጀርመን በጠንካራ የኢኮኖሚ መሰረት ላይ እንድትገነባ መሰረት መጣል ችለዋል።

የዩሊታሪያን አስተሳሰብ ከተስፋፋ በኋላ የነፃ ገበያ ፍልስፍና እንዳለ ለሰላሳ ዐመት ያህል እንግሊዝ አገር ተግባራዊ ቢደረግም ከፍተኛ ህብረተሰብአዊ ቀውስ በመፈጠሩና ድህነትም ስልተስፋፋ በጊዜው የድህነት ፖሊሲን መዋጊያ (Poor Law) በማውጣት፣ ሊሰራ የሚችል ሰው ሁሉ ስራን ሳያማርጥ በዝቅተኛ ደሞዝ እንዲሰራ ተገደደ። ልቅ የሆነ የነፃ ገበያ ፖሊሲ ውድቅ ከተደረገ በኋላም እንግሊዝም ሆነች ሌሎች የአውሮፓ አገሮች በመንግስት የተደገፈን የኢኮኖሚ ፖሊሲ እንዲከተሉ ተገደዋል። በሌላ ወገን ግን በ19ኛው ክፍለ-ዘመን በእንግሊዝ፣ በፈረንሳይና በጀርመን መሀከል የነፃ ንግድ ስምምነት ቢደረግም፣ ይህ ዐይነቱ የነፃ ንግድ ስምምነት በጀርመንና በፈረንሳይ ኢኮኖሚ ላይ ጉዳት ስላደረሰ ሁለቱም አገሮች ስምምነቱን በማፍረስ ወደ ውስጥ ያተኮረ የኢኮኖሚ ግንባታ ላይ እንዲሰማሩ ተገደዋል። የኢኮኖሚክስ ታሪክን ሊትሬቸሮችና፣ በተለይም በኋላ በማርክስ የተደረሰውን የዳስ ካፒታልን ስራና፣ የሹምፔተርን የኢኮኖሚ ዕድገት መጽሀፍና፣ እንዲሁም ሌሎች ትችታዊ አመለካከት ያላቸውን መጽሀፎች ላገላበጠ የሚረዳው በአውሮፓ ምድር ውስጥ የተካሄደው የኢኮኖሚ ግንባታ በፍጹም አዳም ስሚዝም ሆነ በኋላ የወጣው የትምህርት ቤት ኢኮኖሚክስ እንደሚነግሩን አይደለም። ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ሊታይ የቻለው በስምምነት ላይ ወይም ደግሞ እያንዳንዱ ግለሰብ የራሱን ጥቅም በማስቀደምና ኢኮኖሚያዊ „ግለሰብአዊ አርቆ-አሳቢነትን“ መመሪያ በማድረግ አይደለም። የካፒታሊዝም ዕድገት፣ ወይም ደግሞ በማሳመር የነፃ ገበያ ተብሎ ስም የተሰጠው ኢኮኖሚያዊ ስርዓት ብዙ ውጣ ውረድን አሳልፎ እዚህ የደረሰና፣ በተወሰኑ ህብረተሰቦች ውስጥ ብቻ ተግባራዊ የሆነ ክንውን እንደሆነ የኢኮኖሚክስ ታሪክ መጽሀፎችና የህብረተሰብ ታሪክ ግንባታ ሊትሬቸሮች ያረጋግጣሉ። በተለይም የኢንዱስትሪ አብዮት በተካሄደባት እንግሊዝ አገር ውስጥ የካፒታሊዝም አፀናነስና አስተዳደግ ከውስጥ ገበሬውን በማፈናቀልና ወደ ከተማ እንዲሰደድ በማድረግ በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ እንዲኖር አስገድዶታል። ካፒታሊዝም ወደ ገጠር ሲስፋፋ በእርሻ ላይ የተሰማራው የፊዩዳል መደብ በዕድገት ላይ የሚገኘውን የሱፍ(የልብስ) ኢንዱስትሪ የጥሬ-ሀብት ፍላጎት ለማሟላት ሲል በበግ እርባታ ላይ ተሰማራ። ይህ ሁኔታ የትናንሽ ገበሬዎችን አስተራረስ እንዲቀይር ማድረጉ ብቻ ሳይሆን፣ አብዛኛው ገበሬ ከሚያርስበት እንዲፈናቀል በመደረጉ፣ በተለይም እንደለንደን ወደ መሳሰሉት ከተማዎች እንዲሰደድ ተገደደ። በኢንዱስትሪ ውስጥ ተቀጥሮ የመስራት ዕድል ያገኘው ሰራተኛ ደግሞ የስራው ሁኔታ እጅግ አሰቃቂና አሰልቺ፣ እንዲሁም ደግሞ በጣም አድካሚ እንደነበር በኢኮኖሚክስ የታሪክ ምሁራን በደንብ ተተንቶን ተቀምጧል። ይህ ብቻ ሳይሆን በኢንዱስትሪ ውስጥ ተቀጥሮ የመስራት ዕድል ያላገኘው ሰፊ የሰራተኛው ወታደር(reserve army) የግዴታ በመንገድ ስራ፣ በካናልና በድልድይ እንዲሁም ትላልቅ ቤተመንግስቶችንና ካቴድራሎችን ለመስራት ይገደድ ነበር። ዛሬ በብዙ ምዕራብ አውሮፓ ዋና ዋና ከተማዎች የምናያቸው የሚያማምሩ ትላልቅ ህንፃዎች በሰፊው ህዝብ ደም የተገነቡ ናቸው። የትምህርት ቤት ኢኮኖሚክስ እንደሚለን እያንዳንዱ ግለሰብ የራሱን ጥቅም ከፍ ለማድረግ ሲል በኢኮኖሚ ክንዋኔ ውስጥ በመሳተፍ የገነባው አይደለም። በሌላ ወገን ደግሞ አንድ መታወቅ ያለበት ነገር በኒዎ-ክላሲካል የትምህርትቤት ኢኮኖሚክስ ውስጥ ከተማዎችና ህንፃዎች ምን እንደሆኑ አይታወቁም። ምክንያቱም ኢኮኖሚያዊ ክንውን ካለቦታና ጊዜ የሚካሄድ ነው ተብሎ ስለሚታመን ነው። ይህ ዐይነቱ አመለካከት ደግሞ ፀረ-ሳይንስና ፀረ-ታሪክ ነው። ይሁንና በሪናሳንስ አማካይነት የተካሄደው ጭንቅላትን የማደስ ሰፋ ያለ እንቅስቃሴ ለግለሰብአዊ ፈጣሪነት መንገዱን እንዳመቻቸ የማይታበል ሀቅ ነው። የገበያ ኢኮኖሚ እንደ ኢኮኖሚ ፖሊሲ መመሪያ ከመወሰዱ በፊት ታውቆም ይሁን ሳይታወቅ በተለይም በብዙ የምዕራብ አውሮፓ አገሮች የተካሄደው ቅድመ-ስራ የአሪስቶክራሲውንም ሆነ በማደግ ላይ የነበረውን የከበርቴ መደብ፣ እንዲሁም ደግሞ ሰፊውን ህዝብ ጭንቅላቱን በአዲስ ዕውቀት አድሶታል። ኋላ-ቀር ከሆነ የፊዩዳልና ሌሎች ስልጣኔን ከሚቀናቀኑ አስተሳሰቦች እንዲላቀቅ ከፍተኛ የጭንቅላት ስራ ይሰራ ነበር። ስለሆነም ስለካፒታሊዝም ወይም ደግሞ በብዙዎች አነጋገር ስለገበያ ኢኮኖሚ ሲወራ ከላይ ባጭሩ የሰፈረውን ሀተታ ከቁጥር ውስጥ ሳያስገቡ ዝም ብሎ የነፃ ገበያ እያሉ መወትወት እንዲያውም የባሰውን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እንዳይመጣ እንደመታገል ነው የሚያስቆጥረው። ይህም ማለት፣ ስለ ገበያ ኢኮኖሚ ከመወራቱ በፊትና፣ ካለዚህ ፍቱን መፍትሄ የለም እያሉ ከመወትወት በፊት በመጀመሪያ ለካፒታሊዝም መፀነስ ቅድመ-ሁኔታዎች ከሆኑ ነገሮች ጋር መተዋወቅ ያስፈልጋል። በሁለተኛ ደረጃ፣ ካፒታሊዝም ደረጃ በደረጃ ያለፈባቻውን የታሪክ ሂደቶች መመርመርና፣ ዛሬ ደግሞ እንዴት አድርጎ የብዙ ሚሊያርድን ህዝቦች ዕድል መወሰን እንደቻለ በሰፊው ማጥናት ያስፈልጋል። በህብረተሰብ ዕድገት ታሪክ ውስጥ የተደረገውን ትግልና ጥረት፣ እንዲሁም ደግሞ የተለያየ አስተሳሰብ በነበራቸው ምሁራን ዘንድ የተደረገውን የጦፈ ክርክር ሳያጠኑ ተግባራዊ የሚሆኑ የኒዎ-ሊበራል የነፃ ገበያ ኢኮኖሚ ፖሊሲዎች ከፍተኛ ህብረተሰብአዊ ምስቅልቅልነትን ነው የሚያስከትሉት። የኒዎ-ሊበራል ኢኮኖሚ ፖሊሲን ተግባራዊ ያደረጉ የላቲንና የአፍሪካ አገሮች ሁኔታ የሚያረጋግጠው፣ በውጭ የተደነገገና ምሁራዊ ክርክር ሳይደረግበት ተግባራዊ የሆነ የኢኮኖሚ ፖሊሲ አንድን አገር የቱን ያህል መቀመቅ ውስጥ እንደሚከት ነው።

ነፃ ገበያ ወይስ ካፒታሊዝም !

የነፃ ገበያ የሚለው ጽንሰ-ሃሳብ ብቅ ከማለቱና ከመስፋፋቱ በፊት ብዙ ህብረተሰቦች ከሞላ ጎደል የገበያን ኢኮኖሚ እስከተወሰነ ደረጃ ድረስ አዳብረዋል። ገበያ ከህብረተሰቦች ዕድገትና ከስራ-ክፍፍል መዳበር ጋር የተያያዘ ነው። ህዝቦች እንደማህበረሰብ ሲደራጁና ፍላጎታቸውም እያደገ ሲመጣ፣ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ተመሳሳይ ምርቶች ስለማያመርቱ፣ እያንዳንዱ ፍላጎቱን ለማሟላት ሲል አንደኛው የህብረተሰብ ክፍል ማምረት የማይችለውን ለማግኘት ሲል ከሌላው ጋር መገበያየት ተገደደ። በገበያ ውስጥ በሚደረግ የተለያዩ አምራቾች ግኑኘነትና፣ በኋላ ደግሞ በነጋዴዎች አማካይነት እያንዳንዱ ግለሰብ፣ በመጀመሪያ ዕቃን በዕቃ(Natural Exchange)፣ በኋላ ደግሞ ገንዘብ የዕቃዎች ወይም እህል መለዋወጫ መሳሪያ ሆኖ ሲዳብር ተጠቃሚው የፈለገውንና የቻለውን በመግዛት ፍላጎቱን ያሟላ ነበር። እንደዚህ ዐይነቱ የገበያ ልውውጥ እንደ አገር በማደግ ላይ በሚገኙ አገሮች ውስጥ በተወሰነ ክልል በመካሄድና በማደግ፣ በኋላ ደግሞ በተለያዩ አገሮች መሀከልም በመስፋፋት የሩቅ ንግድ እየተባለ ለሚጠራው በር ከፈተ። በሩቅ ንግድ አማካይነትም በተለያዩ ማህበረሰቦች ዘንድ የዕቃ ልውውጥ ብቻ ሳይሆን፣ የባህልም ግኑኝነት በመፈጠር፣ በጋብቻና በመዋለድ ለአንዳንድ አገሮች የህብረተሰብአዊ ለውጥ እምርታን አምጥቷል። በተለይም በእንደዚህ ዐይነቱ የሩቅ ንግድ ግኑኝነትና የዕቃዎች ልውውጥ ተጠቃሚና፣ ህብረተሰብአዊ ለውጥን ማምጣት የቻለው የምዕራብ አውሮፓ ነው። በምዕራብ አውሮፓ ውስጥ ነው በሩቅ ንግድ አማካይነት ቀስ በቀስ የስራ-ክፍፍል መዳበር የቻለውና፣ ነጋዴዎችም ብዙ ገንዘብ በማከማቸትና የዕደ-ጥበብ ስራዎችን በመቆጣጠርና የፊዩዳሉን መደብ በዕዳ በመተብተብና፣ ልዩ የፍጆታ አጠቃቀም በማስለመድ ቀስ በቀስ ወደ ኢንዱስትሪ ከበርቴነት ሊለወጡ የቻሉት። በአውሮፓ የኢኮኖሚ ግንባታ ታሪክ ውስጥ ከፊሉ የነጋዴ መደብ ወደ ኢንዱስትሪ ከበርቴነት ሲቀየር ዋና ተግባሩ ዝም ብሎ ሀብት ማጋፈፍ ብቻ ሳይሆን፣ በባህላዊ እንቅስቃሴና በከተማ ግንባታዎች ስራ በመሰማራት የህብረተሰቡ አኗኗር በዕውቅ(Rationalize) ላይ እንዲገነባና እንዲንቀሳቀስ ማድረግም ነበር። በዚህም ምክንያት በዕውቅ ላይ ያልተመሰረተው የፊዩዳሉ ስርዓት፣ በከተማዎች ግንባታ፣ በዕደ-ጥበብ ሙያ መስፋፋትና በንግድ ማበብ እየተዳከመና፣ ለሌላና ለተሻለ የአኗኗር ስርዓት መንገዱን እንዲለቅ ተገደደ። ፍልስፍና፣ ድራማና አርክቴክቸር ሲያብቡ፣ በተለይም የከበርቴውና የአርስቶክራሲው የአኗኗር ስልት ከራስ በማለፍ ህብረተሰቡ ሊተሳሰር የሚችልበትን ሁኔታ እንዲያዘጋጁ ተገደዱ። በነሼክስፔር፣ በሼሊና የኋላ ኋለ ደግሞ በጀርመን ክላሲኮች የድራማና የክላሲካል ሙዚቃ አማካይነት በማደግ ላይ የነበረውን የከበርቴ መደብና የአርስቶክራሲ አገዛዝ ጭንቅላት እንዲታነጽ በማድረግ የከበርቴው ሰብአዊነት ቀስ በቀስ ሊስፋፋ ቻለ። ከዚህን ጊዜ ጀምሮ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ከህብረተሰብአዊ ዕድገት ተነጥሎ ሊታይ የማይችል ሆኖ ተቀባይነትን በማግኘት ስራዎች በሙሉ ጥበብንና(aesthetic) ስርዓትን እንዲይዙ ተደረጉ።

ከዚህ ባሻገር፣ በምዕራብ አውሮፓ ውስጥ በየጊዜው የህዝብ ቁጥር እያደገ ሲሄድና ፍላጎትም ሲጨምር ብዙ የምዕራብ አውሮፓ አገሮች በአንድ ዐመት ውስጥ ሶስት ጊዜ ሊያመርቱ የሚችሉበትን ሁኔታ(The Three Field Farming System) አዳበሩ። በተጨማሪም በበሬ ከማረስ ይልቅ በፈረስ እየታገዙ በማምረት ምርት ሊያድግ የሚችልበት ሁኔታ ተዘጋጀ። በአገር ውስጥ ምርት ብቻ የህዝብ ፍላጎት ማሟላት ባልተቻለበት አገሮች ውስጥ መንግስታት ከውጭ እህል በማስመጣት የህዝቡን ፍላጎት ያሟሉ እንደነበር የተገደዱበት ጊዜ ነበር። ይህንን ጉዳይ ፕሮፌሰር ሚስኪሚን ሃርይ የመጀመሪያውና የመጨረሻው ዘመን የሬናሳንስ ኢኮኖሚ(The Economy of Later Renaissance Europe, 1460-1600) በሚለው መጽሀፋቸው ውስጥ በዝርዝር ያስረዳሉ። በተጨማሪም ፕሮፌሰር ጞልድትዋይት፣ የሬናሳንስ ኤኮኖሚ በፍሎሬንሰ( The Economy of Renasissance Florence) በሚለው ግሩም መጽሀፋቸው የኢጣሊያን ኢኮኖሚ በዘፈቀደ ሳይሆን በዕውቅ ላይ የተገነባና፣ ጣሊያንም በተለይም በኢንዱስትሪ ምርት አይላ ትገኝ እንደነበር ነው የሚነግሩን። ከነዚህ መጽሀፎችም ሆነ ከሌሎች አያሌ የኢምፔሪካል ጥናቶች መረዳት የሚቻለው፣ በነፃ ገበያ አማካይነት ሁሉም እንደፈለገው እህሉን ውጭ እያወጣ መቸብቸብ ይችላል የሚባል አነጋገር የተለመደ ሳይሆን፣ በዕውቅና በመጀመሪያ ደረጃ የየህብረተሰቡን ፍላጎት ማሟላት ያስፈልጋል የሚለውን መመሪያ በመውሰድ ነው ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ህብረተሰብአዊ ግንባታ ሊካሄድ የተቻለው። ማንም እንደፈለገው መሸጥ ይችላል እየተባለና የውጭ ከረንሲ ለመቃረም ሲባል በአገር ውስጥ የሚመረትን ምርትም ሆነ ፍራፍሬዎች እየሟጠጡ ወደ ውጭ በመላክና መሬትን ለውጭ „እንቬሰተሮች“ በማከራየት አልነበረም በአውሮፓ ምድር ውስጥ ካፒታሊዝም ማደግ የቻለው። በአውሮፓ ምድር ውስጥ የካፒታሊዝም ዕድገት በውስጥ ኃይሎች የተካሄደ ሲሆን፣ ከውጭ የመጣውን አስተሳሰብ ደግሞ ቀስ በቀስ ውስጣዊ ባህርይ(internalize) እንዲኖረው በማድረግና በማገናኘት ለህብረተሰብና ለኢኮኖሚ ግንባታ ጠቃሚ እንዲሆን ተግባራዊ ማድረግ ነበር። ይህም ማለት የውጭው ባህልና የአሰራር ኖርሞች፣ እንዲሁም ከውጭ የተቀዱ የተክኖሎጂ አሰራርና ፈጠራ የግዴታ በሰው ጭንቅላት ውስጥ እንዲቀረጹ ከፍተኛ ትግል ይደረግ ነበር። ከውጭ የሚመጡ አሰተሳሰቦች የራሳቸውን ደሴት በመስራት በራሳቸው ክልል ብቻ እንዲሽከረከሩ የሚደረጉ አልነበሩም። የአውሮፓን የካፒታሊዝም ዕድገት ለተመለከተ፣ አንደኛው አገር ከሌላው አገር እየኮረጀ ሁለ-ገብ ዕድገትን እንዳመጣ መገንዘብ እንችላለን። እንደአገራችን ዕውቀት የጋን መብራት በመሆንና የራስን ዓለም በመመስረት ከሰፊው ህዝብ ጋር ሳይገናኙ አይደለም ካፒታሊዝም በአውሮፓ ምድር ውስጥ ማደግ የቻለውና፣ ዓለምን መቆጣጠርና ማዳረስ የቻለው። ካፒታሊዝም ውስጣዊ ኃይል ሊያገኝ የሚችለውና የሀብት ክምችትም በከፍተኛ ደረጃ ሊያድግ የሚችለው ምርቶች በመመረታቸው ብቻ ሳይሆን፣ አብዛኛው የሚመረተው ምርት አገር ውስጥ ገበያ ላይ የመገዛትና የመሸጥ ዕድል ካገኘና፣ በዚህም አማካይነት የገንዘብ መሽከርከር በከፈተኛ ሁኔታ እየጨመረ የመጣ እንደሆን ብቻ ነው።

ገበያ በህብረተሰብ የታሪክ ዕድገት ውስጥ ግዴታ የሆነውን ያህል፣ የኋላ ኋላ በተለይም የእነ ጆን ሎክና የሌሎች ዩቲላቴሪያን አስተሳሰብ በአሸናፊነት ሲወጣ፣ ካፒታሊዝምና የግል ሀብት ተያይዘው በመውጣት በህብረተሰብ ውስጥ የመደብ አከፋፈል ግልጽ እየሆነ መጣ። የምርት መሳሪያዎችና ሌሎች ሀብቶች የሌለው የግዴታ የስራ ጉልበቱን እንዲሸጥ ተገደደ። ተቀጥሮ በመስራት ብቻ ገንዘብ በማግኘት የቀን ተቀን ፍላጎቱን ማሟላት ቻለ። አዲስ በተፈጠረውና ውስብስብ እየሆነ በመጣው ግኑኝነት መሰረት፣ የተለያዩ የህብረተሰብ ኃይሎች በምርት የስራ ቦታና በገበያ የሚገናኙ ሁኑ። ገንዘብም ከዕቃ ባህርዩ(Commodity Character) በመላቀቅ እቃዎችን በፍጥነት ማሽከርከሪያ መሳሪያ በመሆን ህብርተሰብአዊ ኃይል እየሆነ መጣ። ለብዙ መቶ ዐመታት ወርቅ፣ ብርና መዳብ እንዲሁም ሌሎች ለፍጆታ ጠቀሜታ የሚያገለግሉ እንደገንዘብም በማገልገል ለገበያ ዕድገት ዕምርታን መስጠት ችለዋል። ካፒታሊዝም እያደገና እየተወሳሰበ ሲመጣ ግን እነዚህ የፍጆታ ባህርይ ያላቸው ገንዘቦች እያደገ የመጣውን ፍላጎት ማሟላት አልቻሉም።ለዕቃዎች በሰፊው መሸከርከር የሚያመች፣ በቀላሉ ካለብዙ ወጪ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ሊሽከረከር የሚችል በመንግስት የተደገፈ የወረቀት ገንዘብ አስፈላጊ እየሆነ መጣ። ስለሆነም፣ በመንግስት የተደገፈ የወረቀት ገንዘብና ሳንቲም በብዛት በመታተም የካፒታሊዝምን ዕድገት ማፋጠን ቻሉ። የወረቀት ገንዘብ የበለጠ ተቀባይነትን እያገኘ ሲመጣም የሰው በሰው ግኑኝነትም እየተለወጠ መጣ። ገንዘብ የህበረተሰብአዊ ግኑኝነት መለኪያ ሆነ። ተራ የገበያ ኢኮኖሚ ወይም የነፃ ገበያ የሚለው አባባል አዲስ በተፈጠረው የሀብት ቁጥጥርና የህብረተሰብ ግኑኝነት አማካይነት ወደ ካፒታሊዝምነት ተለወጠ። ካፒታሊዝምም ህብረተሰብአዊ ስርዓትን መግልጫና ብዙ ነገሮችን ያካተተና የያዘ ሆነ። ለዚህ ነው ማርክስም ሆነ ሹምፔተር ካፒታሊዝምን ዝም ብለው ነፃ ገበያ ወይም የገበያ ኢኮኖሚ ብለው የማይጠሩት። ምክንያቱም እንደዚህ ዐይነቱ አባባል ያልተሟላና ብዙ ነገሮችን ስለማያካትት ነው። ይህም ማለት ካፒታሊዝም ህብረተሰብአዊ ግኑኝነትንም ሲገልጽ፣ በህብረተሰቡ ውስጥ በገቢ አከፋፈልና ምድባ የሚገለጽና፣ አንዲሁም በህብረተሰብ የኑሮ ሁኔታ(Social Status) የሚታይ ህብረተሰብአዊ አወቃቀር የካፒታሊዝም አንደኛው ገጽታ መሆን ቻሉ። በሌላ ወገን ግን የእነ አዳም ስሚዙ አገላለጽ ታሪካዊ አይደለም፤ የማርክስም ሆነ የሹምፔተር እንዲሁም የሌሎች የታሪክን ዕድገት ያካተተና ካለ ምርት ኃይሎች ዕድገት(Production Forces)፣ ማለትም ካለቴክኖሎጂ ምጥቀት ሊገለጽ አይችልም። በተጨማሪም የአዳም ስሚዙ የገበያ ኢኮኖሚ፣ በተለይም ደግሞ የኒዎ-ክላሲካል የገበያ ኢኮኖሚ ፅንሰ-ሃሳብ ውስጣዊ ኃይል የሌለውና፣ ከዝቅተኛ ወደ ከፍተኛ የማይሸጋገር ሲሆን፣ የማርክስም ሆነ የሹምፔተሩ በዚያ ባለህበት ቆሞ የሚቀር አይደለም። ውስጥ ባለው ኃይልና ውስጣዊ ቅራኔ የአረጁ ኢንዱስትሪዎችን በማፈራረስና በተሻሉና ምርታማቸው ከፍ ባሉ ማሺኖች በመተካት አዲስ ዐይነት የፍጆታ አጠቃቀምንና ህብረተሰብአዊ ግኑኝነት እንዲፈጠር ያደርጋል። በዚህም አማካይነት የሰው ከሰው ግኑኝነት የበለጠ ገንዘባዊ እንዲሆን በማድረግና ቀጥተኛ አምራቹንም የበለጠ ጥገኛ በማድረግ የሰው አስተሳሰብ በቀጥታ ከፍጆታ አጠቃቀም ጋር እንዲያያዝ ያደርጋል። ለዚህም ነው የአራት መቶ ዓመትን የካፒታሊዝምን ዕድገት በጥብቅ የተከታተለ፣ ምርት በዐይነትና በብዛት መመረቱ ብቻ ሳይሆን፣ የምርት ማምረቻ መሳሪያዎችም ምጥቀትን በማግኘት የሰው ልጅ ከቴክኖሎጂ ጋር ያለውን ግኑኝነት መለወጥ እንዲችል የተገደደው። በቴክኖሎጂ መሻሻል የስራ ሰዓት መቀነሱ ብቻ ሳይሆን፣ ሰራተኛው ከአዲሱ ቴክኖሎጂ ጋር ለመስተካከል ሲል በፍጥነት መስራት ተገደደ። አጠቃላይና የተስፋፋ የሀብት ክምችት (Expanded Capital Accumulation) በመዳበር ካፒታሊዝም በአገር ብቻ እንዳይወሰን ተገደደ። ቀሰ በቀስ እያለ ዓለም አቀፋዊ ባህርይ እየያዘ መምጣት ቻለ።

አዲሱና የተሻሻለው የቴክኖሎጂ ለውጥ አሰራር አንድ ሰው ብቻውን ሆኖ የተወሰኑ በተኖችን ብቻ በመንካት የምርትን ሂደት እንዲያፋጥን አስቻለው። በዚያውም መጠን በአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች አማካይነት የሰው ኃይል ትርፍ(Redundant) እየሆነ እንደመጣ እንመለከታለን። በቴክኖሎጂዎች ምጥቀትና ውድድር አማካይነት የካፒታል ክምችትና(Concentration of Capital) የኢንዱስትሪና የባንክ ካፒታል እየተቆላለፉ በመምጣት፣ ፋይናንስ ካፒታል የኢንዱስትሪን ዕድገትና የቴክኖሎጂን ምጥቀት መወሰን ቻለ። በተጨማሪም፣ የኢንዱስትሪ ካፒታል እየመጠቀ ሲያድግና የካፒታል ክምችትም እየተስፋፋ ሲመጣ፣ በአንድ በኩል መጠነኛና ማዕከለኛ ኢንዱስትሪዎች ወይም ባህላዊ የዕደ-ጥበብ ስራዎች እየተዳከሙና እየጠፉ ሊመጡ ችለዋል። ከዚህም በላይ የማዕከለኛ ኢንዱስትሪዎች ዕድገት፣ መኖርና ያለመኖር በትላልቅ ኢንዱስትሪዎች ውስጠ-ኃይለ የሚወሰን ሆነ። ምክንያቱም መጠነኛና ማዕከለኛ ኢንዱስትሪዎች ተለዋዋጭ ዕቃዎችንና(Spare parts) መጠገኛዎችንም ሆነ ዋና ዋና ክፍሎችን አምራች ስለሆኑ፣ ለምሳሌ የመኪና ገበያ በሚቀዘቅዝበት ጊዜ ትናንሽ ኢንዱስትሪዎችም ይዳከማሉ ማለት ነው። ይህም የሚያመለክተው የተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ርስበራሳቸው የተያያዙና(Value-added Chain)አንደኛው በሌላው ላይ የተመካና፣ የአንደኛው መዳከም ወይም መጠንከር በሌላው ላይ ተፅዕኖ ይኖረዋል ማለት ነው። ይሁንና ግን በዘመነ-ግሎባላይዜሽን፣ ለምሳሌ የአንድ መኪና የተለያዩ ክፍሎች እዚያው ፈጣሪው አገር ብቻ አይመረቱም። የማምረቻን ዋጋ ለመቀነስ ሲባል የተወሰነው የመገጣጠሚያ ክፍል በተለያዩ አገሮች በመመረት የመጨረሻ መጨረሻ ዋናው አምራች አገር ምርቶቹ በመገጣጠም የመጨረሻው ምርት ውጤት ገበያ ላይ ይቀርባል። ስለሆነም የዛሬው የገበያ ኢኮኖሚ ወይም ደግሞ ካፒታሊዝም ከሶስት መቶና አራት መቶ ዐመት በፊት ከነበረው በብዙ መቶ እጅ ልቆ የሚገኝ ነው።
ካለምንም የጭንቅላት ማስጨነቅ ዛሬ የቴክኖሎጂዎችን ዕድገት ስንመለከትና የፍጆታ ዕቃዎችንም ስንጠቀም ሁሉም ነገር በጤናማ መልክና ካለ ውስጣዊ ቅራኔ የሚካሄድ ነው የሚመስለን። በመጀመሪያ በምዕራብ አውርፓ የካፒታሊስት አገሮች የሰራተኛው መደብ መብቱን ለማስጠበቅ ሲል በሙያው ማህበሩ አማካይነት ከፍተኛ ትግል አድርጓል። የሳምንት የስራ ሰዓት ወደ 42ና ወደ 40 ሰዓት እንዲቀነስ ማድረግ፣ እንዲሁም ደግሞ በሰራተኛ ማህበርና በኢንዱስትሪዎች ውስጥ በግሩፕ በመደራጀት ከከበርቴው መደብ ጋር የሚደራደር ተጠሪ መምረጥ መቻል፣ እነዚህ ሁሉ በትግል የተገኙ ናቸው። በሌላ ወገን ደግሞ ቴክኖሎጂዎች ምጥቀትን ባገኙ ቁጥር የሰራተኛው የመከራከርና የመደራደር ኃይል እየተዳከሙ እንደመጡ መገንዘብ ይቻላል። በመሆኑም ባለፉት ሰላሳ ዐመታት በካፒታሊዝም ዕድገት ውስጥ የታዩት አሉታዊ ክስተቶች የሰራተኛውን መደብ በከፍተኛ ደረጃ እንዲዳከም አድርገውታል። ትላልቅ ኩባንያዎች ትርፍ ለማካበት ሲሉ የተወሰነውን የኢንዱስትሪ ክፍል ርካሽ የስራ ጉልበት ባለበት አገር እየወሰዱ በመትከል ወደ ውስጥ ብዙ ስራተኞች እንዲባረሩና የባህልም ውድቀት እንዲመጣ አድርገዋል። የትራዲሽናል ኢንዱስትሪዎች በግሎባላይዜሽን አማካይነት መዳከማቸው ብቻ ሳይሆን፣ ኢንዱስትሪዎች ወደ ሌሎች አገሮች ተወስደው እንዲተከሉ በማድረግ በየአገሮች ውስጥ ከኢንዱስትሪ መስክ ጋር የተያያዙ ሌሎች የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችም እንዲዳከሙ ተደርገዋል። በዚያው መጠንም በተለይም በትናንሽ ከተሞች ውስጥ በኢንዱስትሪዎች መፈናቀልና በሰራተኛው ከስራው ቦታው መባረር የተነሳ የሎካል አስተዳደሮች ከህዝብ የሚሰበስቡት ግብር(Tax) እጅግ እየቀነሰ መጥቷል። ይህ ማለት ደግሞ ትምህርት ቤቶችን ለማደስ፣ ከተማዎችን ለማፅዳትና ሌሎች የሶሻል መስኮችን ለመደጎም የሚያስፈልገው ወጪ እየቀነሰ ሊመጣ ችሏል ማለት ነው።

በተለይም የፊናንስ ካፒታል በከፍተኛ ደረጃ ማደግና ራሱን ከኢንዱስትሪ አግልሎ በገንዝብ አማካይነት ብቻ ትርፍ ማካበት መቻል ብዙ መንግስታትን ከቁጥጥር ውጭ እያደረጋቸውና፣ በተራ የሞኔተሪ ፖሊሲ አማካይነት ብቻ የኢኮኖሚውን ዕድገት ሊቆጣጠሩና የኢኮኖሚውን መዛባትም ሊያርሙ የሚችሉበት ሁኔታ እጅግ እየጠበበ መጥቷል። የዚህ ዐይነቱ የፊናንስ ካፒታል ማደግና በተለያዩ ዐይነቶች መገለጽ፣ ለምሳሌ ሄጅ ፈንድስ ወይም ኢንቬስሜንት ካፒታል በሚባሉት መልኮች የሚሽከረከረው የፊናንስ ካፒታልና፣ ይህ ደግሞ እንደገና ከትላልቅ ባንኮች ጋር መቆላለፍ የብዙ የሶስተኛው ዓለም አገሮችንና አንዳንድ የደቡብ አውሮፓን ኢኮኖሚዎችንም ከመቆጣጠር አልፎ እያፈራረሰቸውም እንደመጣ እንመለከታለን። ዛሪ ግሪክን እዚህ መቀመቅ ውስጥ የከተታት ከራሷ የውስጥ ኢኮኖሚ አወቃቀር ድክመት ባሻገር የፊናንስ ካፒታል አይሎ መውጣትና በዕዳ ወጥመድ ውስጥ እንድትገባ በማድረጉም ጭምር ነው። በተጨማሪም እጅግ ልፍስፍስ የሆነ የፖለቲካ ኤሊት ለፊናንስ ካፒታል አጎብዳጅ በመሆኑም ጭምር ነው። የአውሮፓው አንድነትን የአንጀት አጥብቅ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ጠጋ ብሎ ለተመለከተ የባሰውን የግሪክን ኢኮኖሚ የሚያዳክምና የባሰ የውስጥ ካፒታል ወደ ውጭ እንዲወጣ የሚያግዝ ነው። ግሪክ ከፋይናንስ ገበያ ላይ የምትበደረው ተጨማሪ ብድር ወይም ከአውሮፓ አንድነት የምታገኘው ብድር የጀርመንንና የፈረንሳይ ባንኮችን ከኪሳራ ለማዳን የሚውል ነው። በዚህ መልክ ብዙ አገሮች መቀመቅ ውስጥ እንዲገቡና እንዲራቆቱ ሆነዋል።

ይህ የካፒታሊዝም አንደኛው ገጽታ ሲሆን፣ በምርት አማካይነት በብዙ የሶስተኛው ዓለም አገሮች የተስፋፋው የምርት ክንውን ለእነዚህ አገሮች በምንም ዐይነት ዕድገትንና ስልጣኔን ሊያጎናጽፋቸው አልቻለም። ከአስራዘጠነኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ የሚካሄደውን የካፒታሊዝምን በዓለም አቀፍ ደረጃ መስፋፋት ስንመለከት ዋናው ዓላማው ስልጣኔና እንዲሁም ደግሞ ሳይንስንና ቴክኖሎጂዎችን ማስፋፋት ሳይሆን የጥሬ ሀብትን መዝረፍና ወደ ኢንዱስትሪ አገሮች እንዲጫን ማድረግ ነው። ለዚህ ደግሞ በተወሰኑ መስኮች ላይ ብቻ መረባረብ ሲሆን፣ እንዲዚህ ዐይነቱ በጥሬ ሀብት ማውጣት ላይ ያተኮረ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ በብዙ የሶስተኛው ዓለም አገሮች ውስጥ፣ በተለይም በአፍሪካ ውስጥ የሀብት ዘረፋ በማካሄድ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እንዳይመጣ አግዷል። ህብረተሰብአዊ መመሰቃቀልና፣ ከተማዎች ካለምንም ዕቅድ መሰራትና መቆሽሽ የብዙ አፍሪካ አገሮች ዕጣ ሆኗል ማለት ይቻላል። በዚያው መጠንም እንዲዚህ ዐይነቱ የግሎባል ካፒታሊዝም መስፋፋት በአፍሪካ ምድር ውስጥ በማኑፋክቱር ላይ የተመሰረተ የውስጥ ገበያ እንዳይዳብርና እንዳይስፋፋ አግዷል። በየአገሮች ውስጥ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች በተወሰኑ ቦታዎች ብቻ እንዲካሄዱ መደረጉ ደግሞ ከገጠር ወደ ጥቂት ከተማዎች ውስጥ የሰውን ፍሰት በማስከተል፣ ከተማዎች የዕድገትና የብልጽግና ቦታዎች ከመሆን ይልቅ በጣም ጥቂት ሀብታምና፣ ሰፋ ያለ ደሃ ፊት ለፊት የሚፋጠጡበት መድረክ በመሆን ህብረተሰብአዊና ማህበራዊ ቀውስ በማስከተል የህብረተሰብና የህብረ-ብሄር ትርጉም እንዲወድሙ ተደርገዋል።

በዚህም የተነሳ ከኢንዱስትሪ አገሮች እየተነቀሉ የሶስተኛው ዓለም አገሮች የሚተከሉት ኢንዱስትሪዎች ከውስጥ ዕውነተኛ ሀብት ፈጣሪዎች ያልሆኑና ህዝቡም ቴክኖሎጂን እንዳይማር ያገዱና የሚያግዱ ናቸው። በመጀመሪያ ደረጃ፣ ኢንዱስትሪዎቹ በትላልቅ ኩባንያዎች ቁጥጥር ስር ያሉና ከላይም የሚቀመጡ ማኔጀሮች የራሳቸው ነፃነት የሌላቸው ናቸው። በሁለተኛ ደረጃ፣ ቴክኖሎጂዎቹ ከምርምርና ከዕድገት ጋር የተያያዙ አይደሉም። ቀጥታ ግኑኝነታቸው ከእናት አገሮቻቸው ጋር ነው። በሶስተኛ ደረጃ፣ የሚመረቱት ምርቶች ለዓለም ገበያ ተብለው ስለሆነ ወደ ውስጥ በእነዚህ አገሮች ውስጥ ለገበያው ማደግና መስፋፋት የሚያበረክቱት አስተዋፅዖ እጅግ ዝቅተኛ ነው። በአራተኛ ደረጃ፣ በየፋብሪካው ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰራው ሰራተኛ ደሞዙ በጣም ዝቅተኛ ስለሆነ ሰራተኛው ምርቶችን ገዝቶ የመጠቀም ኃይሉ በጣም አነስተኛ ነው። በአምስተኛ ደረጃ፣ በብዙ የሶስተኛው ዓለም አገሮች ውስጥ የሚከተሉት ኢንዱስትሪዎች ከየአገሩ ባንክ ጋር ምንም ግኑኝነት የላቸውም። ይህ ማለት ደግሞ የገንዘብን በፍጥነት መሽከርከርና ህብረተሰብአዊ ኃይል ማግኘት በከፍተኛ ደረጃ ያግደዋል ማለት ነው። በኢንዱስትሪና በባንክ ማሀከል ግኑኝነት ሲኖር ብቻ ነው የገበያ ኢኮኖሚ ማደግ የሚችለው። በስድስተኛ ደረጃ፣ የሰራተኞችንና የስራ ቦታዎችን ሁኔታ ለተመለከተ፣ ሰራተኞች እጅግ በአሰቃቂ ሁኔታ ነው የሚሰሩት። የምንለብሳቸው ጂንሶችና የምንጠቀምባቸው የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በሙሉ በርካሽ ጉልበት የተመረቱ ብቻ ሳይሆኑ፣ ብዙ ወጣት ሴቶች ጤንነታቸው በከፍተኛ ደረጃ እየተቃወሰ የሚመረቱ ምርቶች ናቸው። አብዛኛዎቹ በሰላሳና በአርባ ዐመታቸው በጤንነት መቃወስ የተነሳ ከጥቅም ውጭ ይሆናሉ። ኑሮን ሳይኖሩ ይሞታሉ። ብዙዎችም የአልጋ ቁራኛ በመሆን ፍዳቸውን ያያሉ። ይህንን ነው እንግዲህ የዛሬው ካፒታሊዝም የሚመስለውና፣ በአገራችን ደግሞ ዘመኑ የግሎባላይዜሽን ዘመን ነው እየተባለ የሚወደስለትና ካለቡዙ ቅራኔዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ይስፋፋ ይመስል የሚነዛው። ብዙዎች ካለማወቅ በሚያናፍሱት ወሬና በፊናንስ ካፒታል ግዳጅ በሚያካሂዱት የኢኮኖሚ ፖሊሲ የተነሳ የብዙ መቶ ሚሊዮኖች ህዝብ እየተረበሸና ጤናማና ለስልጣኔ የሚያመች ረጋ ያለ ኢኮኖሚ እንዳይገነቡ እየታገዱ ነው። የአንድ ትውልድ ዕድል ብቻ ሳይሆን የሶስትና የአራት ትውልድ ዕድል የሚበላሽበት ሁኔታ ዛሬ ተነጥፏል ማለት ይቻላል። ዛሬ በአገራችን ምድር ውስጥ የኢኮኖሚ ፖሊሲ የሚያወጡትና እነሱ የሚሉትን የገበያ ኢኮኖሚ የሚያራምዱ በነሱ ባልበሰለ ሁኔታ በሚካሄድ ፖሊሲ አማካይነት የተፈጸመውና የሚፈጸመው ወንጀል የማይታያቸው ይህንን የካፒታሊዝምን ውስጣዊ ቅራኔና ሂደት በቅጡ ካለመራዳት የተነሳ ነው። አላዋቂ ሳሚ … እንደሚሉት አነጋገር።

ውድድርንና የካፒታሊዝም ዕድገት !

የገበያ ኢኮኖሚ ወይም ካፒታሊዝም እንደ አገራችን በተራ ነጣቂነት ወይም ዐይን ባወጣ ዘራፊነት የሚደነገግና ውስጠ-ኃይል የሚያገኝ አይደለም። ማርክስ እንደሚለውና በትክክልም እንደሚረጋገጠው ውድድር(Competition) የካፒታሊዝም ዋናው አንቀሳቃሽ ኃይል ነው። ቴክኖሎጂያዊ ምጥቀትም የሚታየው በውድድር አማካይነት ብቻ ነው። ለዚህ ደግሞ በከፍተኛ ምርምርና ፈጠራ እየታገዙ ማምረት ያስፈልጋል። እያንዳንዱ በገበያ ላይ ምርት እያመረተ የሚያቀርብ ካፒታሊስት ተወዳዳሪውን በመርዝ ወይንም በአንዳች ነገር ህይወቱን ለማጥፋት ወይም ለመግደል ተንኮል የሚያብሰለስል ሳይሆን፣ በምን መንገድና እንዴት አድርጌ ምርት ባመርት ተወዳዳሪዬን ለማሸነፍ እችላለሁ፣ ወይም የበለጠ የገበያ ድርሻ ይኖረኛል ብሎ ታጥቆ በመነሳት የእንቬስትሜንት ስትራቴጂውን ይቀይሳል። ከዋጋ አንፃር የማምረቻ ዋጋን በመቀነስና ምርትን በነፍስ ወከፍ ሲተመን በማሳደግ(Productivity)፣ እንዲሁም ደግሞ ምርቱ ጥራት እንዲኖረው በማድረግ ብቃትነቱን በማሳየት በገበያ ውስጥ ለመቆየት ጥረት ያደርጋል። በየጊዜው የምርቱን ሁኔታ ይለዋውጣል። ለምሳሌ በአንድ ወቅት የተወሰነ ምርት፣ መኪና ወይም ማቀዝቀዣ የተወሰነ የፍጆታ ዘመን ነው ያላቸው። በመጀመሪያው ወቅት አዲስ ምርት ገበያ ላይ ሲወጣ እንደብርቅ ይታያል። ቀስ በቀስም ሰው እየለመደው ሲሄድ ገዝቶ ይጠቀማል። በገበያ ላይ የመሸጡ ኃይል እያደገ ይመጣል። ሌላው ተመሳሳይ ምርት የሚያመርት ካፒታሊስት ውበቱንና የአጠቃቀሙን ዘዴ በመለወጥ ተመሳሳይና የተሻሻለ ምርት ለገበያ ያቀርባል። የድሮውም ምርት ገበያ ላይ ተገዢነቱ እየቀነሰ በመምጣት ከገበያ ላይ እየተስፈናጠረ ይወጣል። በዚህ መልክ በስድሳኛውና በሰባኛው ዓ.ም ይመረቱ የነበሩ መኪናዎችም ሆነ ማቀዝቀዣዎች ዛሬ በፍጹም አይገኙም። በተጨማሪም የኃይልን አጠቃቀምና የአካባቢን ብክለት ለመቀነስ ሲባል በተለይም የረዥም ጊዜ ዕድሜ ያላቸው ምርቶች በጥራትም ሆነ በአጠቃቀም ደረጃ እጅግ እየተሻሻሉና ለምቾትም አጋዥ እየሆኑ መጥተዋል።

ውድድር ለካፒታሊዝም ዕድገት አንቀሳቃሽ ኃይል የሆነውን ያህልና፣ የገበያ ኢኮኖሚ የሚለው ተራ አነጋገር በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት ያገኘውን ያህል፣ ይህ ዐይነቱ በውድድር ላይ የተመሰረተ የገበያ ኢኮኖሚ ከህግ ውጭ የሚሰራ ነው ማለት አይደለም። በአምራችና በነጋዴ መሀከል ያለው ግኑኝነት በአንድ ወገን፣ በሌላ በኩል ደግሞ በነጋዴውና በተጠቃሚው መሀከል ያለው ግኑኝነት በህግ ላይ ተመርኩዞ የሚንቀሳቀስ ነው። በመጀመሪያ አምራቹ ካለምንም ማጭበርበር ምርቱን አምርቶ ለነጋዴው ያቀርባል። ነጋዴው በአምራቹ ላይ ሙሉ ዕምነት አለው ማለት ነው። የሚያጭበረብር አምራችና ነጋዴ በህግ ተጠያቂዎች ብቻ ሳይሆኑ፣ ምናልባት በምርቱ አጠቃቀም ላይ የተወሰነ ኖርምን ተከትሎ ያልተሰራ ምርት አደጋ የሚያደርስ ከሆነ አምራቹ እንደ አደጋው ዐይነት ፈቃዱን እስከመነጠቅ ይደርሳል። ይህ ዐይነቱ ህግ ጠቅላላውን የገበያ ሂደት የሚመለከትና ብዙ ነገሮችን የሚያካትት ነው። ከዚህም በላይ በአለፉት ሰላሳና አርባ ዐመታት ተጠቃሚው በዕውቀት እየዳበረ ሰለመጣና፣ የተጠቃሚዎችም ማዕከል(Consumer Protection Agency) ወይም ድርጅት ስላለ፣ ተጠቃሚው በምርት አጠቃቀም ምክንያት የተነሳ የሚደርስበት ጉዳትም ሆነ ያልተስተካከለ አጠቃቀም ዘዴ አቤቱታ ሊያሰማና ሊከስም ይችላል። ይህም ማለት በአገራችን በዘልማድ አነጋገር እንደሚናፈሰውና እንደሚሰራበት ልቅ የሆነ የገበያ ኢኮኖሚ ሳይሆን፣ የምዕራቡ የገበያ ኢኮኖሚ ስርዓትን ይዞ የሚጓዝና በጣም የተወሳሰበ ነው። ከዚህም በላይ በስርዓቱ ውስጠ-ኃይልነትና የሰዎችም የፈጠራ ችሎታ የተነሳ ከአንድ ዐይነት ነገር የተለያዩ ብዙ ነገሮችን ማምርት ይችላል። ለምሳሌ ከእንጨት፣ እንደ ባህርይው ከልጆች መጫዎቻ አንስቶ የተለያዩና የሚያማምሩ መቀመጫዎችና ወንበሮች፣ እንዲሁም ልዩ ልዩ ነገሮች ማምረት ይቻላል። እንዲሁም ከተለያዩ የፍራፍሪ ወይም ጥራጥሬ ነገሮች በመቶዎች የሚቆጠሩ ለመቀቀያና ለሌሎች አገልግሎቶች የሚያገለግሉ የዘይት ጭማቂ ማምረት ይቻላል። እንደ አገራችን በካፒታሊስት አገሮች ኑግን፣ ተልባን፣ ሰሊጥን፣ ሱፍንና ሌሎች ነገሮችን የውጭ ከረንሲ ለመቃረም ሲባል እስከነነፍሳቸው የመላክ ባህል የለም። ይህንን የሚያደርግ ስለኢኮኖሚ ዕድገት ምንነትና በኢንዱስትሪዎች መሀከል ስለሚኖረው ውስጣዊ ግኑኝነትና የሀብት ክምችት ምንጭነት የማያውቅ መሆን አለበት። እንደዚህ የሚያደርግ መንግስት በዚያውም መጠንም የውስጥ ገበያን ዕድገት ይዘጋል። ነጋዴው እዚያው ቀጭጮ እንዲቀር ያደርገዋል። በአጠቃላይም ህብረተሰብአዊ ለውጥ እንዳይመጣ መንገዱን ሁሉ ያፍናል። የህዝቡን የፈጠራ ስራ ከማፈኑም በላይ ኑሮው የተዘበራረቀ እንዲሆን ያደርጋል።

ስለዚህም ስለውድድር በምናወራበት ጊዜ የኢኮኖሚው ኤጀንቶችን የፈጠራ ችሎታና በየጊዜው እንደገበያው መለዋወጥ ከሁኔታው ጋር ሊኖር የሚችለውን መጣጣምና በፍጥነት መጓዝ ማጤን ያስፈልጋል። በዚህ ላይ ለውድድሩ መጧጧፍ የጊዜ ኢኮኖሚና ቦታ(Time &Space) ከፍተኛ ሚናን ይጫወታሉ። አንድን ዕቃ አምርቶ ወደ ሌላ ቦታ በፍጥነት ለማድረስ ፈጣንና በቀላሉ አደጋ ሊያደርስ የማይችል የትራንስፖርቴሽን ማገልገያ ያስፍልጋል። እንደዚሁም በመርከብ፣ በባቡርና በመኪና ሊጫኑ የሚችሉ ዕቃዎችን መለያየት ያስፈልጋል። ጤናማና ጥንቃቄ የተሞላበት የማከማቻ ቦታ ለዕቃዎች መከማችትና ለረዥም ጊዜ መቆየት ወሳኝ ሚናን ይጫወታሉ። ወደ ቦታ ስንመጣ ይህ ዐይነቱ አገላለጽ በደንብ ከተደራጀ ገበያና መደብር ጋር የተያያዘ ነው። በሚያማምሩ ከተማዎችና መንደሮች የሚገለጽ ነው። ስርዓት ያለው የቤት አሰራርና የተለያዩ ተግባር ያላቸውን ቤቶችና አዳራሾች የሚመለከት ነው። የገበያ አዳራሾች ውብና ሰፋ ብለው እንዲሁም ማራኪ ሆነው መሰራት አለባቸው። በዘመኑ ሁኔታ ደግሞ ከመናፈሻና ከልጆች መጫዎቻዎች እንዲሁም በአካባቢው ማራኪ ከሆኑና ሰውን ከሚጋብዙ ቡና ቤቶች፣ የቲያትርና የሲኒማ እንዲሁም ልዩ ልዩ የመዝናኛ ቦታዎች ጋር የመሰራትንና የመዘጋጀትን እንዲሁም መያያዝን ጉዳይ ይጠይቃል። በዚህ መልክ የሚዘጋጅና በአካባቢው አንድ ወጥ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ የምርት ዐይነቶች ተደራጀተው የሚገኙ ከሆነ ለገበያው ዕድገትና ለውድድር ከፍተኛ ዕምርታን ይሰጣል ማለት ነው። ከዚህ ስንነሳ በአገራችን ምድር የሚነዛው ስለገበያ ኢኮኖሚ ሳይንሳዊ ባህርይ የሌለው በተራ ችርቻሮ ላይ የተመረኮዘና ተዋንያኖችን የበለጠ የሚያንቀዠቅዥና አጭበርባሪ የሚያደርጋቸው ነው። ወያኔዎች እንደዚህ ዐይነቱን ኢኮኖሚ ነው አንዳንዴ የነፃ ገበያ ኢኮኖሚ እያሉ የሚነግሩን። አልፎ አልፎ ደግሞ የለም እኛ ኒዎ-ሊበራሊዝምን የምንዋጋና በመንግስት የተደገፈ(Developmental State) የኢኮኖሚ ፖሊሲን ነው የምንከተለው እያሉ እዚያው በዚያው የሚያላግጡብንና ግራ ለማጋባት የሚሞክሩት። ይህም የሚያመለክተው የገዢው መደብና ተከታዮቹ የቱን ያህል በህዝብ ላይ እንደሚያላግጡ ነው።

ከዚህ ባሻገር ተመሳሳይ ምርት በሚያመርቱ ካፒታሊስቶች መሀከል የሚካሄደው ውድድር በአገር ውስጥ ብቻ ተወስኖ የሚቀር አይደለም። እንደሚታወቀው ካፒታሊዝም በዓለም አቀፍ ደረጃ መስፋፋት በምርት ክንውን ብቻ የሚገለጽ ሳይሆን፣ የፍጆታ አጠቃቀሞች፣ የፊናንስ ግኑኝነትና ደካማ አገሮችን በዕዳ መተብተብ አጠቃላዩ የካፒታሊዝም የሀብት ማካበቻ ዘዴዎችና፣ በተለያየ መልክ የሚገለጽ ሀብት ከሶስተኛው ዓለም አገሮች ወደ ካፒታሊስት አገሮች የሚተላለፍበት የብዝበዛና የድህነት መፈልፈያ መሳሪያም ነው። ይህም ማለት በአገር ውስጥ የሚካሄደው የካፒታሊስት የሀብት ክምችትና ዘዴ በአገር ውስጥ ገበያ ብቻ የሚመካ አይደለም። እያንዳንዱ የካፒታሊስት አገር ህብረተሰቡ ገዝቶ ከሚጠቀመው በላይ ስለሚያመርት ትርፍ ምርቱን ለመሸጥ ሲል የውጭ ገበያ ያስፈልገዋል። ስለሆነም ይህ ዐይነቱ ሁኔታ በተለያዩ አገሮች መሀከል ባሉ ካፒታሊስቶች ዘንድ የግዴታ ውድድር ይፈጥራል። የተለያዩ ካፒታሊስት አገሮች ምርቶቻቸውን፣ ለምሳሌ መኪና ወይም የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በዓለም ገበያ ላይ ለመሸጥ ይችሉ ዘንድ በተቻለ መጠን ለምርት የሚያወጡትን ወጪ እንዲቀንሱ ይገደዳሉ። በሌላ ወገን ደግሞ አንዳንድ ምርቶች የውጭ ገበያ ላይ ለመሸጥ እንዲችሉ መንግስታት ከኤክስፖርት ቀረጥ ነፃ ያደርጉላቸዋል። የማምረቻን ዋጋ እንደልባቸው አገር ውስጥ መቀነስ ስለማይችሉ፣ ለምሳሌ የሰራተኛውን ደሞዝ በመቀነስ፣ የተለያዩ አካሎች(Spare parts) ሌሎች የሰራተኛ ደሞዝ ርካሽ የሆኑ ሌሎች አገሮች ውስጥ እንዲመረቱ በማድረግ ምርቶቻቸውን በርካሽ ዋጋ ሊሸጡ የሚችሉበትን ሁኔታ ያመቻቻሉ። ስለዚህም የዛሬው ካፒታሊዝም ከሁለት መቶ ዐመት ከነበረው ሁኔታ ጋር ሲነፃፀር በብዙ እጅ ይለያል። ውድድሩ በትናንሽ ካፒታሊስቶች መሀከል የሚደረግ መሆኑ ቀርቶ የዓለምን ገበያ ለመቆጣጣር በሚሽቀዳደሙ ጥቂት ያበጡ ካፒታሊስቶች(Oligopolies) በመሆን የዓለም ገበያ ከቁጥጥር ውጭ በመውጣት፣ የሶስተኛው ዓለም አገር ኢኮኖሚዎችም እየተዘበራረቁ ሊመጡ ችለዋል። ይህ ዐይነቱ በተወሳሰበ የአደራጃጀትና የአመራረት ስልት የሚንቀሳቀስ የምርት ክንውን እንዲያው በተራ የነፃ ገበያ ሊገለጽ የሚችል አይደለም።

ከዚህም በላይ፣ የዛሬው ዓለምን የሚቆጣጠረው ካፒታሊዝም የሶስተኛውን ዓለም አገሮች የጥሬ-ሀብት በመቆጣጠርና የሰውን ጉልበት በመብዘብዝ ነው በመጀመሪያ ደረጃ ጥንታዊ የሀብት ክምችትን(Primitive Capitalist Accumulation) ማዘጋጀትና ለኢንዱስትሪ አብዮት መጠቀሚያ ማድረግ የቻለው። በመጀመሪያ ደረጃ በባሪያ ንግድ የተነሳ ወደ አውሮፓና ላቲን አሜሪካ፣ በኋላ ደግሞ ወደ ኃያሉ አሜሪካ የተሸጡ አፍሪካውያን በፕላንቴሼን ኢኮኖሚ ውስጥ እንዲሰማሩና እንዲሰሩ በመገደድ ለካፒታሊዝም የሀብት ክምችትና ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅዖ አድርገዋል። ከዚያ በኋላ ደግሞ በቅኝ ግዛት አማካይነትና አዲስ በተፈጠረው ዓለም አቀፋዊ የስራ-ክፍፍል አማካይነት ብዙዎቹ የአፍሪካ፣ የላቲንና የሴንትራል አሜሪካ አገሮች የጥሬ-ሀብትና የእርሻ ምርት አምራቾች እንዲደረጉ በመገደድ የኢንዱስትሪ አገሮችን ህዝቦች በርካሽ ዋጋ መመገብ ብቻ ሳይሆን፣ ለጠቅላላው የሀብት ክምችት ከፈተኛ አስተዋፅዖ በማበርከት ላይ ናቸው። ዛሬም ቢሆን አብዛኛዎቹ የካፒታሊስት አገሮች ከሶስተኛው ዓለም አገሮች በሚመጡ የጥሬ-ሀብቶችና የእርሻ ምርት ውጤቶች የሚመኩና፣ ይህ ሁኔታም እንዳይቀየር የተለያዩ ኢንስቱትሽኖችን በመፍጠር ዕድገታቸውን የሚቆጣጠሩ ናቸው። ከዚህ ስንነሳ ይህ ነፃ ገበያ እየተባለ የሚጠራው የካፒታሊዝም የምርት ክንውን እስከዚህም ድረስ ነፃ እንዳልሆነ መረዳቱ ከባድ አይደለም።

ካፒታሊዝም፣ ሳይንስና እንዲሁም ቴክኖሎጂ !

የኒዎ-ክላሲካል ኢኮኖሚስቶች አብዛኛውን ጊዜ ስለኢኮኖሚ ዕድገት ሲጽፉና ሲያወሩ በተለይም ሳይንስና ቴክኖሎጂ በኢኮኖሚ ዕድገት ላይ ያላቸውንና የሚኖራቸውን ሚና ቁጥር ውስጥ ባለማስገባት ነው። የኢንዱስትሪ አብዮት ከተጀመረና ቀስ በቀስ እየተስፋፋ ሲመጣ፣ ኢኮኖሚ በሁሉም አቅጣጫ ሊስፋፋና ስር ሊሰድ የቻለው በሳይንስና በቴክኖሎጂ መደገፍ ከጀመረ በኋላ ነው። ከባቡር ሃዲድ መሰራትና ጥራትን እያገኘ መጥቶ ፍጥነቱ ከቀድሞው ጋር ሲወዳደር በከፍተኛ ደረጃ መጨመር፣ የአይሮፕላን ስራና እየረቀቀ መጥቶ የዓለምን ህዝብ ማገናኘት መቻል፣ ዛሬ የምንገናኝባቸው የኮሙኒኬሽን መሳሪያዎች… ወዘተ፣ እነዚህ ሁሉ ለኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅዖ አበርክተዋል። ይህ ብቻ ሳይሆን የምርት ዕድገትና ጥራት፣ እንዲሁም የኢንዱስትሪዎች ምርታማነት ከሳይንስና ከቴክኖሎጂ ጋር የተያያዙ ናቸው። በተፈጥሮ ውስጥ የሚከሰቱትን በሽታዎችና ቫይረሶች ሁሉ መዋጋትና መቋቋም የሚቻለው በሳይንስና በቴክኖሎጂ አማካይነት ብቻ ነው። ከዚህ ስንነሳ ሳይንሳዊ ምርምርንና የቴክኖሎጂ ፈጠራን ቦታ የማይሰጥ ህብረተሰብ በተራ የነፃ ገበያ አማካይነት ብቻ የትም ሊደርስ በፍጹም አይችልም። ዕጣው ድህነትና ረሃቭ፣ የመጨረሻ መጨረሻ እንደ አገርና እንደ ህብረተሰብ አለመኖር ይሆናል። እስከዛሬ ድረስ ቀድመው የተነሱ ስልጣኔዎች የመጨረሻ መጨረሻ ሊፈራርሱና የታሪክ ትዝታ ሆነው መቅረት የቻሉት በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተደገፈ ሰፋ ያለ ኢኮኖሚ መገንባት ባለመቻላቸው ነው። ስለዚህ ስለ ኢኮኖሚ ዕድገት በሚወራበት ጊዜ የግዴታ ከሳይንስና ከቴክኖሎጂ መስፋፋት ጋር ማያያዝ ያስፈልጋል። ካፒታሊዝም እንበለው ሌላ ስርዓት የግዴታ በሳይንስና በቴክኖሎጂ መደገፍ አለባቸው።

በመጀመሪያ ደረጃ ሳይንስ መዳበር የቻለው በታላላቅ ተመራማሪዎች፣ በአስራአምስተኛው፣ በአስራስድስተኛውና በአስራሰባተኛው ክፍለ-ዘመን ሲሆን፣ ወደ ቴክኖሎጂ ማፍለቂያነትና ወደ ተግባራዊነት እየተለወጠ ሊመጣ የቻለው ከአስራስምንተኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ ነው። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ነው ሳይንሳዊ ግኝት ብቻ ሳይሆን ተግባራዊነትና ቴክኖሎጂዎችን ፈጥሮ ወደ ምርት ማምረቻ መሳሪያነት መለወጥ የታቸለው። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ነው ምርት በዕውቅ መመረትና ምርትን ማሳደግና እንዲሁም የተለያዩ ምርቶችን ማምረት የተቻለውና፣ ቀስ በቀስም ዛሬ ለማየት የበቃነውን ቴክኖሎጂያዊ ምጥቀት ማየት የቻልነው። በአንዳንዶች አባባል ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ነው በቴክኖሎጂ አማካይነት ተፈጠሮን እስከተወሰነ ደረጃ መቆጣጠርና በተፍጥሮ ውስጥ ተደብቀው የሚገኙ ነገሮችን በልዩ መሳሪያዎች መመርመርና ማየት የተቻለው። ስለሆነም ሰለ ገበያ ኢኮኖሚ ወይም ስለ ካፒታሊዝም በምናወራብት ጊዜ ከሳይንስና ከቴክኖሎጂ፣ እንዲሁም ደግሞ በየጊዜው ከሚካሄድ ፈጠራ(Innovation) ውጭ ማየትና ማተት ስህተት ብቻ ሳይሆን እጅግ አደገኛም ነው። ስለሆነም የካፒታሊስት ኢኮኖሚ በከፍተኛ የሳይንስና የቴኮኖሎጂ (A Science and Technology Driven Economic Development) መሰረት ላይ በመመርኮዝ የሚንቀሳቀስና፣ ከተወሰኑ ዐመታት በኋላ ደግሞ አሮጌው ከገበያው በመውጣት በአዲስ የሚተካበት ልዩ ዐይነት ኢኮኖሚያዊ ክንውን ነው። ስለሆነም ነው ታላቁ የአውስትሪያው ኢኮኖሚስትና የሶሻል ሳይንስ ምሁር ፕሮፌሰር ሹምፔተር በካፒታሊዝም ዕድገት ውስጥ የሚፈጠረውንና ተግባራዊ የሚሆነውን ቴክኖሎጂ ክሪአቲቭ ዲስትራክሽን(Creative Destruction) ብሎ የሚጠራው።

የሳንይንስና የቴክኖሎጂ ዕድገት በተለይም በካፒታሊዝም ስርዓት ውስጥ ለምን ከፍተኛ ትርጉም ሊሰጠው ቻለ? በእርግጥስ የነፃ ገበያ በራሱ ለሳይንስና ለቴክኖሎጂ ዕድገት አመቺ ነው ወይ ? የሳይንስና የቴኖሎጂ ዕድገት የብዙ መቶ ዐመታት ወይም ሺህ ዐመታት ዕድሜ ያለው ሲሆን፣ ለአውሮፓው የሳይንስና የቴክኖሎጂ ዕድገት በተለይም፣ የግብጽ ስልጣኔ፣ የባቢሎናውያን፣ የግሪክ፣ ቀጥሎም ቻይናዎች በበኩላቸው አስተዋፅዖ አድርገዋል ማለት ይቻላል። በመሰረቱ የሳይንስና የቴክኖሎጂ ምርምር የየግለሰቦች ጥረት ሲሆን፣ ከብዙ ትግል፣ ውጣና ውረድ በኋላ ነው ተቀባይነትን እያገኘ መምጣት የቻለው። የኢንዱስትሪ አብዮት እየተስፋፋና ስር እየሰደደ ሲመጣ የከበርቴውም መደብ በኢኮኖሚ ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ተፅዕኖ በማድረግ የሳይንስና የቴክኖሎጂ ምርምር ኢንስቱትሽናላዊ መሆን ጀመሩ። በተለይም ከሁለተኛው ዓለም በኋላ የተፈጠረው አዲስ ሁኔታና፣ የምዕራብ አውሮፓ መንግስታት በኢኮኖሚ ግንባታ ውስጥ በቀጥታ መሳተፍና አመቺ ሁኔታዎችን መፍጠር ለሳይንስና ለቴክኖሎጂ ምርምርና ምጥቀት አመቺ ሁኔታን ፈጥሯል ማለት ይቻላል። በቀጥታ በመንግስት የሚደገፉ የሳይንስና የቴክኖሎጂ ምርምር አካዳሚዎች በግለሰብ ካፒታሊሶች ብቻ ሊካሄዱ ወይም በገንዘብ ሊደጎሙ የሚችሉ አልነበሩም። ስለሆነም፣ በአንድ በኩል አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎችን የምርምርና የቴክኖሎጂ ማፍለቂያ መድረክ በማድረግ ከኢንዱስትሪዎች ጋር እየተባበሩ እንዲሰሩ ማድረግ፣ በሌላው ወገን ደግሞ በቀጥታ በመንግስት የሚደገፉ ኢንስቲቱሽኖችን በማቋቋም ባጀት በመመደብ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እንዲፈጠሩና ተግባራዊ እንዲሆኑ ማድረግ ለካፒታሊዝም ዕድገት ከፍተኛ ድጋፍ ሰጥቶታል ማለት ይቻላል። አንዳንድ ኢንዱስትሪዎች እያደጉና ራሳቸውን እየቻሉ ሲመጡ ደግሞ በአጠቃላይ ሲታይ ትላልቅ ኩባንያዎች የየራሳቸውን የምርምር ጣቢያ በመክፈትና በመደገፍ በቀጥታ ቲክኖሎጂን ለምርት ዕድገትና ጥራት ማምረቻ መጠቀሚያ መሳሪያ ማድረግ ችለዋል። ከዚህ አጠቃላይና አጠር መጠን ያለ ትንተና ስንነሳ የነፃ ገበያ መኖር በራሱ ለቴክኖሎጂ ዕድገት አመቺ ሁኔታን ሊፈጥር በፍጹም አይችልም። የቴክኖሎጂ ዕድገትና ምጥቀት ትርጉም ሊኖራቸውና ተግባራዊ መሆን የሚችሉት ኢንስቲቱሽናዊ፣ ፖለቲካዊ፣ መንግስታዊ፣ ባህላዊና ህብረተሰብአዊ አመቺ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ብቻ ነው። ቶሎ ቶሎ ገንዘብ ለማግኘት ጥድፊያ በሚደረግበት እንደኛ ባለ አገር፣ ሁሉም ነገር ተዘበራርቆ በሚገኝበት፣ መንግስትና ቢሮክራሲው ሳይንሳዊ ምርምርንና የቴክኖሎጂ ዕድገትን ዐይነተኛ ቦታንና ትርጉምን በማይሰጡበትና በማይረዱበት አገር ውስጥ የሳይንስና የቴክኖሎጂ አብዮትን ለማካሄድ በጣም ያስቸግራል።

ያም ሆነ ይህ፣ የሳይንስንና የቴክኖሎጂን አስፈላጊነት ከተራ የኢኮኖሚ ስሌት አንፃር ማየቱ ብቻ ከፍተኛ ስህተት ነው። ይህ ዐይነቱ ውስን አመለካከት ሳይንስና ቴክኖሎጂ ለአንድ ህብረተሰብ አጠቃላይ ሁኔታ፣ ደህንነትና አደጋ መከላከል ያላቸውን ሰፋ ያለ ትርጉም እንዳንረዳ ያግዱናል። ሳይንስና ቴክኖሎጂ በቀጥታ ልንጠቀምባቸው የምንችላቸውን የፍጆታ ዕቃዎች ለማምረት የሚያገለግሉ ብቻ ሳይሆኑ፣ ከአደጋ የሚከላከሉንን፣ ለምሳሌ እንደ እሳት አደጋ መኪና፣ ውሃ ሲሞላ መምጠጫና ሰውን በቀላሉ ማዳኛ፣ ልዩ ልዩ ለመንገድ ስራ የሚያገለግሉ መኪናዎችንና መዳመጫዎች፣ እንዲሁም አፈር ዛቂዎች፣ ዲንጋይ ተሽካሚዎች፣ በሀይድሮሊክስ እየታገዙ ከባድ ከባድ እቃዎችን ማንሳትና፣ በተለይም በገደላማ ቦታ ድልድይን መስራት የሚቻለው የሳይንስን ትርጉም የተረዳን ከሆነ ብቻ ነው። ከዚህም በተጨማሪ፣ ዘመናዊ የህክምና መስሪያ መሳሪያዎችን፣ መድሀኒቶችንና ልዩ ልዩ ለሰው ልጅ ሊያገለግሉና ከአደጋም ሊከላከሉ የሚችሉትን መሳሪያዎች መስራት የሚቻለው፣ በተለይም የፊዝክስንና የኬሚስትሪን ህግና ምስጢር የተረዳን ከሆን ብቻ ነው። ስለዚህም ስለ ኢኮኖሚ ዕድገት ወይም ደግሞ በአጠቃላይ ሲታይ ስለህብረተሰብና ስለሁለገብ ኢኮኖሚያዊ ስርዓት በሚወራበት ጊዜ የግዴታ ከሳይንስና ከቴክኖሎጂ ጋር ማያያዝ ያስፈልጋል።

ከዚህ ስንነሳ በአገራችን ምድር ኢኮኖሚው በአስራአንድ በመቶ አድጓል፣ የነፃ ገበያ ኢኮኖሚ እያካሄድን ነው የሚለው ተራ አባባል ሳይንሳዊ መሰረት የለውም። ይህ ዐይነቱ አነጋገር የኢኮኖሚ ፖሊሲ አውጭዎቻችንን ስለነፃ ገበያ ኢኮኖሚ ያላቸውን የተሳሳተ ግንዛቤ የሚያሳይ ብቻ ሳይሆን፣ እንደዚህ ዐይነቱ የሽቃዮች ኢኮኖሚ የቱን ያህል በሚሊዮን የሚቆጠረውን ታዳጊ ወጣት አእምሮውን እንዳበላሸውና እንደሚያበላሽው መረዳቱ ከባድ አይሆንም። እንደዚህ ዐይነቱ ግራ መጋባትና አላዋቂነት የፈረንጆች መጫወቻ፣ መሳቂያና መሳለቂያ እንድንሆን አድርጎናል። የተለያዩ ግን ደግሞ ሳይንሳዊ ይዘት የሌላቸው የኢኮኖሚ ፖሊሲ የሚባሉ ነገሮች ተግባራዊ በመሆን ከፍተኛ የሆነ የውንብድና ስርዓት ተዘርግቷል። ድህነት ተስፋፍቷል። ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ሳይሆን፣ ገንዘብ ከዚህና ከዚያ በመቃረምና ትላልቅ ኢኮኖሚያዊ መሰረት የሌላቸው ሆቴል ቤቶችና ቡና ቤቶች በመስራት ውድ እናት አገራችን ወደ አስረሽ ምችውነት ተለውጣች።

ኢኮኖሚያዊ ዕድገት፣ የሀብት ክምችትና ካፒታሊዝም !

አብዛኛውን ጊዜ በአገራችን ኢኮኖሚው ይህን ያህል በመቶ አድጓል ሲባል ከስሌት ውስጥ የማይገቡ ብዙ መሰረታዊ ነገሮች አሉ። ይህ ጉዳይ ተቃዋሚ ነኝ የሚለውንም አስተሳሰቡን እንዲዛባ አድርጎታል ብል እንደተራ ውንጀላ አይቆጠርብኝም። ስለ ካፒታሊዝም ዕውነተኛ ዕደገት በደንብ ሳንመረምር በተራ የጂዲፒ(GDP) አሰላል የሚቀርበው የኢኮኖሚው አደገ አላደገም እያሉ መከራከር የካፒታሊዝምን ዐይነተኛ ባህርይና ውስጠ-ኃይል ከግንዛቤ ውስጥ ካለማስገባት ጋር የተያያዘ ነው።

ከላይ ለማሳየት እንደሞከርኩት፣ ካፒታሊዝም ካለ ንፁህ ውድድርና የቴክኖሎጂ ምጥቀት እንዲሁም ደግሞ ተከታታይነት ከሌለው የሳይንስና የምርምር ውጤት ውጭ በፍጹም ሊሰራ አይችልም። ከዚህ በተረፈ ግን ስለካፒታሊስት ኢኮኖሚ ዕድገት በምናወራበት ጊዜ ሌላ እጅግ አስፈላጊ መሰረታዊ ቅድመ-ሁኔታዎችም አሉ። ይኸውም ማርክስ ክፍል አንድና(Department I) ክፍል ሁለት(Department II) እያለ የሚጠራቸው የተለያዩ ምርቶችን የሚያመርቱ መሳሪያዎች ወይም ማሽኖች ናቸው። ይህንን የማርክስን፣ የሹምፔተርንና የሎነርጋንን የዕድገት ኢኮኖሚ አሰላል ወደ ሶስትና አራት ክፍሎችም ማስፋፋት ይቻላል። ለምሳሌ ጥሬ ሀብቶችን የሚያጣሩና ወደ መጀመሪያው የምርት ክንውን የሚለውጡ ኢንዱስትሪዎች፣ ወይም ደግሞ ልዩ ዐይነት የቅንጦት ምርቶች የሚያመርቱ እያልን ልናስፋፋው እንችላለን። በተጨማሪም ኢንዱስትሪዎችን ዲዛይን የሚያደርጉና ለምርት ክንውን እንዲሆን የሚያቀርቡ ዘርፎችን ልናክልበት እንችላለን። አንባቢን ግራ ላለማጋባት በሁለቱ ክፍሎች(Departments) ብቻ ላይ ማትኮሩ ነገሮችን ለመረዳት ቀላል ይሆናል።

ማርክስ እንደሚያስተምረውና በትክክልም እንደሚያብራራው ክፍል አንድ(Department I) ብሎ በሚጠራው ውስጥ የምርት ማምረቻ መሳሪያዎች ይመረታሉ። ማሽኖች ማለት ነው። እነዚህ ቀደም ብለው በኢንጂነሪግ ዴፓርትሜንት ዲዛይን ይሆናሉ። ለምርት ማምርቻ እንዲያገልግሉ ሆነው ይቀረጻሉ፤ ይዘጋጃሉ ማለት ነው። በዚህ ዴፓርትሜንት አማካይነት ነው የፍጆታ ዕቃ አምራቾች አስፈላጊው የምርት ማምረቻ ኢንዱስትሪዎች ተዘጋጅቶ የሚቀርብላቸው። በሁለተኛው ክፍል ወይም ዴፓርትሜንት ሁለት እየተባለ በሚታወቀው ውስጥ የተለያዩ የፍጆታ ዕቃዎች፣ ከረዥም ጊዜ እስከ አጭር ጊዜ ዕድሜ ያላቸው የተለያዩ ምርቶች ይመረታሉ። መኪናዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ልብስና ጫማ፣ የልጆች መጫዎቻዎችና እንዲሁም ምግብና መጠጥ በክፍል ሁለት ውስጥ ነው የሚመረቱት። በሁለቱ ዴፓርትሜንቶች መሀከል ዲያሌክታዊ ግኑኝነት አለ ማለት ነው። አንደኛው ካለሌላው በፍጹም ሊያድግና ሊንቀሳቀስ አይችልም።

ይህ ማለት ምን ማለት ነው? የምርት ማምረቻው ክፍል በተከታታይ እንዲያመርት የግዴታ በፍጆታ ምርት ማምረቻ ተሰማርቶ የሚንቀሳቀስ ውስጠ-ኃይሉ ከፍተኛ የሆነ የካፒታሊስት መደብ መኖር አለበት። በዴፓርትሜንት ሁለት የምርት መሳሪያዎች ሲገዛ በባንክ አማካይነት አካውንቱ ላይ ለዴፓርትሜንት አንድ ገንዘብ ይተላለፍለታል። በዚህ አማካይነት በሁለቱ ክፍሎችና(Departments) በባንክ መሀከል የሶስትዮሽ ግኑኝነት ይፈጠራል። ይህ ልዩ ግኑኝነት ለባንኮች መጠናከርና ለገንዘብ በፍጥነት መሽከርከር አመቺ ሁኔታን ይፈጥራል። ይህ አንደኛው ጉዳይ ሲሆን፣ በምርት ማምረቻ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰራው ሰራተኛ በሚያገኘው ገቢ በክፍል ሁለት የሚመረቱትን የረዥምና የአጭር ጊዜ ዕድሜ ያላቸውን ዕቃዎች ወይም ምርቶች እየገዛ ይጠቀማል። ገንዘብ በባንክም ሆነ በቀጥታ ለዴፓርትሜንት ሁለት ይተላለፋል። በዚህ መልክ በጠቅላላው ኢኮኖሚክ ውስጥ ልክ እንደ ደም ዝውውር የማያቋርጥ ግኑኝነትና መሽከርከር ይፈጠራል። ስለሆነም ይህ ሁኔታ አጠቃላይ የሀብት ክምችትና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እንዲፈጠር በማድረግ ለጠቅላላው ስርዓት ልዩ ዕምርታን ይሰጠዋል። ይህ ዐይነቱ የአመራረት ስልት ሲደራጅና ኢንዱስትሪዎች በዚህ መልክ ሲቀናጁ ስለ አጠቃላይ ኢኮኖሚ ዕድገት ማውራት ይቻላል። ይህ ዐይነቱ የተስፋፋ የሀብት ክምችት ዘዴ(Expanded Accumulation) በመባል ይታወቃል። በዚህ ዐይነቱ ተከታታይነት ያለው የሀብት ማከማቻ ዘዴ ውድድር ከፍተኛ ቦታን ይይዛል። ቀደም ብሎ እንደተተነተነው በካፒታሊስቶች መሀከል ባለው ፉክክርና የማምረቻን ዋጋ ቀንሶ ገበያ ላይ ለመቆየት ሲባል ካፒታሊስቶች በየጊዜው አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እንዲተክሉ ይገደዳሉ።

ገንዘብና የገንዘብ ሚና እንዲሁም የገንዘብ ወደ ፊናንስ ካፒታል የመለወጥ ሂደት !

ዛሬ የጥቂት አገሮች በተለይም፣ የአሜሪካን ዶላርና ኦይሮ ገንዘቦች ወይም ከረንሲዎች ዋናዎቹ የዓለም ንግድ መገበያያና የሬዘርብ ወይም የሀብት መከማቻ ዘዴዎች መሆናቸው የአብዛኛዎች የሶስተኛውን ዓለም አገር ገንዘቦች ትርጉም እንዳሳጣ የማይታበል ሀቅ ነው። በተለይም በአብዛኛው የዓለም ህዝብ ላይ ዶላር ህሊናዊ ተፅዕኖ ማሳደሩ ደካማ አገሮች ወደ ውስጥ የራሳቸውን ገንዘብ በተለያየ መሳሪያ በማንቀሳቀስ ለመዋዕለ-ነዋይ ተግባራዊ እንዳያደርጉ እንቅፋት ሆኖባቸዋል። ይህም የሆነበት ምክንያት በብዙ የሶስተኛው ዓለም አገሮች የካፒታሊዝም ዕድገትና ቴክኖሎጂያዊ ምጥቀት፣ ከዚህም ጋር ተያይዞ የጥቂት አገሮች ከረንሲዎች አይሎ መውጣት ተፈጥሮአዊና፣ ለጥቂት አገሮች የተሰጠ ችሮታ ተደርጎ በመወሰዱ ነው። ይህንን የተዛባ ሁኔታና አመለካከት ለመረዳትና በመጠኑም ቢሆን መልክ ለማሲያዝ ገንዘብ በካፒታሊስት ህብረተሰብችም ሆነ በሌሎች አገሮች የኢኮኖሚ ዕድገት ውስጥ የተጓዘባቸውን ደረጃዎችና ዛሬ የደረሰበትን የዕድገት ደረጃ ጠጋ ብሎ መመልከቱ ጠቃሚ ይመስለኛል።

እንደሚታወቀው በገበያ ኢኮኖሚ ዕድገት ታሪክ ውስጥ የገንዘብ በተለያየ ዐይነት ብቅ ማለትና የንግድ መለዋወጫ መሳሪያ መሆን ከስራ-ክፍፍል መዳበር ጋር በቀጥታ የተያያዘ ነው። በሌላ አነጋገር ከስራ-ክፍፍል መዳበርና፣ ገበያ የእህልና አንዳንድ የዕደ-ጥበብ ስራ ውጤቶች መለወዋጫ መድረክ ሆኖ ከመፈጠሩ በፊት ገንዘብ ቀደም ብሎ አልተፈጠረም። አንዳንድ ማህበረሰቦች እንደኮሙኒቲ ሲሰባሰቡና የስራ-ክፍፍል ማዳበር ሲችሉና፣ በዚያውም አማካይነት ገበያ የሚለውን መድረክ ሲፈጥሩ፣ በተለያየ ኮሙኒቲና በግለሰቦች የሚመረተውን የተለያየ ምርት ለመለወጥ ወይም ለመሸጥ እንዲያስችል በመጀመሪያ አንድን ዕቃ ወይም ምርት በሌላ ተመሳሳይ ባልሆኑ ዕቃዎች ሲለውጡ፣ ይህ ዐይነቱ የልውውጥ ዘዴ አመቺ ሆኖ ስላላገኙት፣ ለሁሉም ገበያተኛ ተቀባይነት ያለው የሁሉም ዕቃዎች መለኪያ ሊሆን የሚችል ገንዘብ የሚባል ነገር ፈጠሩ። በመጀመሪያ ደረጃ እንደዚህ ዐይነቱ የመገበያያ መሳሪያ ራሱ የፍጆታ ባህርይ ሲኖረው፣ ለምሳሌ ፣ አሞሌ ጨው፣ ወይም ብረትና ልብስ እንዲሁም ሌሎች እቃዎች የገንዘብን ሚና በመጫወት እስከተወሰነ ጊዜ ድረስ ለገበያ ዕድገት የበኩላቸውን አስተዋፅዖ አድርገዋል። ቀስ በቀስ አገዛዞች ሲቋቋሙና ስልጥናቸውን አስፋፍተው የተወሰነ ሀብት መቆጣጠር ሲጀምሩ፣ በጊዜው የተቋቋሙት መንግስታት ማህተም ያለበት ሁሉም ማሀብረሰብ ሊቀበለው የሚችል ገንዘብ አትመው የመገበያያ መሳሪያ ማድረግ ይችላሉ። ይህ ዐይነቱ ማሀተም ያለበት የገንዘብ ዐይነት(Coined Money) እንደየሁኔታው ከመዳብ፣ ከነሃስ፣ ከብርና ከወርቅ የሚሰራና፣ አማካይ ሆኖ የዕቃዎች መለዋወጫ ወይም የንግድ ልውውጥ መሳሪያ በመሆን የንግድ ፍጥነትንና የገበያ ኢኮኖሚ መዳበርን ማፋጠን ችሏል። ብዙ አገሮች ወደ ተወሳሰበ ስርዓት ከመሸጋገራቸው በፊት እንደዚህ ዐይነቱን፣ በመጀመሪያ ደረጃ የዕቃ በዕቃ ልውውጥ ላይ የተመሰረተ የገበያ ዕድገት በኋላ ደግሞ የንጉሶች ስዕል ያለበት፣ ከነሃስ፣ ከመዳብ፣ ከብርና ከወርቅ የተሰራ ገንዘብ ሲጠቀሙበት ነበር።

የገበያ ኢኮኖሚ ቀስ በቀስ እያደገ ሲመጣ ብርና ወርቅ በመፈራረቅ ዋናው የገንዘብ ዐይነት በመሆንና የንግድን ልውውጥ በማፋጠን ዐይነተኛ ሚና ተጫውተዋል። ይሁንና ሁለቱም የገንዘብ ዐይነቶች የተፈጥሮ ውጤቶች በመሆናቸው እንደልብ የማይገኙ ስለነበር፣ በተለይም ወርቅ እንደልብ በማይገኝበት ጊዜ አንዳንድ መንግስታት የወርቅን ይዘት በመቀነስ የመግዛት ኃይሉ እንዲቀንስና የዋጋ ግሽበትም የታየበት ወቅት ነበር። በኢንዱስትሪ አብዮትና በማኑፋክቱር ማበብ የተነሳና የገበያውም መጠን እየሰፋ ሲመጣ ወርቅና ብር በማደግ ላይ ያለውን የንግድ ልውውጥ ሊያግዙና ሊያፋጥኑ አልቻሉም። በዚህም ምክንያት በማደግ ላይ ያሉ እንደ ኢንግላንድ የመሳሰሉ አገሮች ከረጅም ጊዜ ጥናት በኋላ በወርቅ የተደገፈ የወረቀት ገንዘብ ወደ ማተምና ዋናው የመገበያያና የምርት ክንዋኔ አጋዥ መሳሪያ ለማድርግ በቅተዋል። የሁለተኛው ዓለም ጦርነት ለመፈንዳት እስከተቃረበበት ጊዜ ድረስ የእንግሊዝ ፓውንድ ዋናው የመገበያያና የሀብት ክምች(Reserve Currency) መሳሪያ በመሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ የንግድ ልውውጥን ማፋጠን ችሏል። በሌላ ወገን ደግሞ እንግሊዝ በጊዜው የነበራትን የበላይነት ተጠቅማ ብዙ አገሮችን የነፃ ንግድ ፖሊሲን እንዲከተሉ በማድረግና በዚህ አማካይነትም የብዙ አገሮች የውስጥ ገበያ ማደግ ስላልቻሉ፣ በተለይም ፈረንሳይና ጀርመን የመሳሰሉት ከእንግሊዝ ጋር የነበራቸውን የነፃ ንግድ ስምምነት በከፍተኛ ደረጃ በማቀዝቀዝና ወደ ውስጥ በማትኮር የእንግሊዝ የውጭ ንግድ ሚዛን ሊዛባ ችሏል። በተጨማሪም እንግሊዝ ብዙ ቅኝ ግዛቶች ስለነበሯትና እዚያ ያለውንም አስተዳደር መደጎም ስለነበረባት ከእንግሊዝ ወደ ሌሎች አገሮች የሚፈሰው ወርቅ እንግሊዝን እየጎዳት መጣ። በዚህም ምክንያት ፓውንድ እንደ ቀድሞው በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ዋና የመገበያያና የሀብት ማከማቻ ዘዴ መሆኑ እያከተመ ይመጣል። ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ በጦርነትና በኢኮኖሚ ብዙም ያልተጎዳችው አሜሪካ የእንግሊዝን ሚና ትወስዳለች። በ1944 ዓ.ም በብሬተንስ ውድስ ላይ በእንግሊዙ ታላቅ ኢኮኖሚስት ኬይነስና የአሜሪካኑ ተወካይ ኋይት መሀከል የጦፈ ክርክር ይደረጋል። በተለይም ኬይንስ የአሜሪካን ዶላር የዓለም አቀፍ የንግድ መለዋወጫና ሬዘርብ ከረንሲ እንዳይሆን አጥብቆ ቢከራከርምና፣ ከማንኛውም መንግስት ተፅዕኖ ውጭ የሆነ ባንኮር የሚባል አርቲፊሻል ከረንሲ ተግባራዊ እንዲሆን ቢሞክርም፣ ከአሜሪካኑ ተወካይ ከፍተኛ ቅዋሜ ስለደረሰበት ሳይወድ በግድ ዶላር ዋናው የንግድ መለዋወጫና የሪዘርብ ከረንሲ መሆኑን አምኖ ተቀበለ።

ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት ማብቂያ በኋላ አብዛኛው የኢንዱስትሪ አገሮች ወደ ውስጥ ኢኮኖሚያቸውን ሲገነቡና ቀስ በቀስም የውስጥ ገበያን ሲያስፋፋ፣ በዚያው መጠንም ወደ ውጭ የሚልኩት የኢንዱስትሪ ውጤት በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ተወዳዳሪ እየሆነ መጣ። በተለይም ምዕራብ ጀርመንና ጃፓን ወደ ውጭ የሚልኩት ዕቃ ተቀባይነት እያገኘ በመምጣቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከአሜሪካን ጋር በመወዳደር፣ የአሜሪካ የውጭ ንግድ እየተዳከመና፣ የአሜሪካን ዶላር ክምችትም በእነዚህ አገሮችና እንዲሁም በፈረንሳይ እየበዛ ሲመጣ፣ የአሜሪካን የወርቅ ክምችትም እየተናጋ ይመጣል። በብሬተንስ ውድስ ስምምነት፣ አሜሪካን ውጭ የተከማቸውን ዶላሯን በተለይም በከፍተኛ ደረጃ የንግድ ልውውጥ ከምታደርግባቸው አገሮችና በከረንሲ ከረጢት ውስጥ በተጠቃለሉ አገሮች ጋር ባደረገችው ስምምነት ዶላርን በወርቅ መተካት ነበረባት። በዚህም ምክንያት ከአሜሪካን ማዕከላዊ ባንክ ወርቅ ወደ ፈረንሳይና ጀርመን እየፈሰሰ በመምጣት ካዚናውን ማራቆት ይጀምራል። ስለሆነም በ1971 ዓ.ም አሜሪካን በራሷ ኃይል ስምምነቱን በማፍረስ ከእንግዲህ ወዲያ ዶላር በወርቅ እንደማይደገፍ ታስታውቃለች። በዚህም ምክንያት የተነሳ የዶላር ሚና ቀስ በቀስ እየተዳከመ ይመጣል። ይሁንና አሁንም ቢሆን የአሜሪካ ኢኮኖሚ ወደ ውስጥ ሰፋ ያለ ስለሆነና፣ አሜሪካንም በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን የፖለቲካና የሚሊታሪ ተፅዕኖ በመጠቀም ዶላር የበላይነቱን ይዞ እንዲቆይ ለማድረግ ችላለች። በዚህም ምክንያት በተለይም የብዙ የሶስተኛውን ዓለም አገሮች ዕድገት ቆልፋ ለመያዝ ኢኮኖሚው ከሚፈቅደው በላይ ዶላርን እያተመች በማስፋፋቷ በብዙ አገሮች ውስጥ ከየአገሩ የውስጥ ገንዘብ ይልቅ ዶላር የበለጠ ማምለኪያ ገንዘብ ሊሆን ችሏል ማለት ይቻላል።

ይህንን ትተን ወደ ዋናው መሰረተ-ሃሳብ ስንመጣና፣ ገንዘብ በካፒታሊስት ኢኮኖሚ ውስጥ ያለውን ሚና ስንመለከት ከአብዛኛዎቹ የሶስተኛው ዓለም አገሮች የተለየ ሆኖ እናገኘዋለን። ይህም የሆነበት ምክንያት አብዛኛዎቹ የምዕራብ አውሮፓ ኢኮኖሚዎች፣ የአሜሪካ፣ የጃፓን፣ አሁን ደግም የቻይና ኢኮኖሚ ወደ ውስጥ ሰፋ ባለ መልክ የተደራጀና በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ስለሆነና፣ አብዛኛውም ህዝብ ተቀጥሮ የሚሰራ በመሆኑ፣ ገንዘብ በአንድ በኩል ከአንድ ኢኮኖሚ መስክ ወደ ሌላና እንዲሁም ወደ ባንክ፣ ደሞዝ ተቀባይ ከሆነው ደግሞ በንግድ አማካይነት፣ ከንግድ መስክ ወደ ኢንዱስትሪና ወደ ባንክ በፍጥነት በመሽከርከርከር ለገንዝብ ዕድገትና ባህርይ ልዩ መልክ ሰጥቶታል። በሌላ አነጋገር በውስጡ ገበያ መስፋፋትና፣ በተለያዩ የኢኮኖሚ መስኮች መሀከል ባለው መተሳሰርና የንግድ ልውውጥ የተነሳ ከሶስተኛው ዓለም አገሮች ጋር ሲወዳደር የገንዘብ ሚና በብዙ የካፒታሊስት አገሮች ልዩ ዐይነት አካሄድና ያለውና፣ በኢንዱስትሪና በተለያዩ መልኮች የሚገለጽ የሀበት ማከማቻ መሳሪያ ሊሆን ችሏል። በቁጠባ መልክና በልዩ ልዩ ዘዴ ከህዝቡ የሚሟጠጠው ገንዘብ ወደ መዋዕለ-ነዋይነት ስለሚለወጥ በተለይም እንደ ዶላርና ኦይሮ፣ እንዲሁም የጃፓኑ ዬን በጣም ጠንካራ ገንዘብ ሊሆኑ በቅተዋል።

ወደ ሶስተኛው ዓለም አገሮች ስንመጣ ግን የውስጥ ገበያ ስነ-ስርዓት ባለው መልክ ሊስፋፋ ባለመቻሉ ከረንሲዎቻቸው በጣም ደካማ ናቸው። የኢትዮጵያና የተቀረው የአፍሪካ ኢኮኖሚ ቀስ በቀስ ከታች ወደ ላይ እያደገ የመጣ ባለመሆኑ፣ የገንዘብም ዕድገት እንደዚሁ ከታች ወደ ላይ ከኢኮኖሚው ዕድገት ጋር ተያይዞ ያደገ አይደለም። በዚህም ምክንያት ገንዘብ በመጀመሪያ ደረጃ እንደካፒታሊስት አገር ኢኮኖሚዎች ቀስ በቀስ ከሌሎች ለፍጆታ ዕቃ ከሚውሉ ዕቃዎች ተላቆ በወርቅ አማካይነት በመገለጽና፣ የወረቀት ገንዘብም በወርቅ በመደገፍ ታትሞ ገበያ ላይ ሊቀርብ ባለመቻሉ፣ የገንዘብ ዕድገት የኢኮኖሚ ዕድገት ነፀብራቅ አይደለም ማለት ነው። ዝም ብሎ ከላይ ወደ ታች የተጫነ ነው ብሎ አፍን ሞልቶ መናገር ይቻላል። ከዚህም በላይ የአብዛኛው የአፍሪካ አገር ኢኮኖሚዎች፣ የአገራችንንም ጨምሮ በተሰበጣጠረና እርስ በርሱ ባልተያያዘ የኢኮኖሚ ክንዋኔ ስለሚገለጽ ገንዘብ በፍጥነት ሊሽከረከር አይችልም። አብዛኛው ህዝብም ተቀጥሮ የማይሰራና፣ የሚሰራውም የሚያገኘው ገቢ በቂ ስላልሆነ፣ ገንዘብ በባንክ አማካይነት የሚተላለፍ አይደለም። የአብዛኛዎችም የንግድ ባንኮች ተግባር ኤክስፖርትና ኢምፖርትን ፋይናንስ ስለሚያደርጉና ለኢንዱስትሪ ተከላ መዋዕለ-ነዋይ ስለማያቀርቡ፣ ገንዘብ ማከናወን ያለበትን ተግባር እንዳያከናውን ተደርጓል። አብዛኛዎችም የአፍሪካ አገሮች ወደ ወደ ወጭ የሚልኩት ዕቃ የእርሻ ውጤትና የጥሬ-ሀብት በመሆኑ ከኢንዱስትሪ አገሮች ጋር በሚያደርጉት የንግድ ልውውጥ ለአደጋ የተጋለጡ ናቸው። በሌላ አነጋገር አንድ የኢንዱስትሪ የምርት ውጤት ለማስገባት ብዙ ቶን ቡና ወይም ሌላ ያለተፈበረከ የጥሬ-ሀብት ማስተላለፍ ስላለባቸው ከውጭ ንግድ የሚያገኙት ገቢ የሚያመረቃና፣ ለውስጥ ገበያ መስፋፋት የሚያግዝ አይደለም። በዚህም ምክንያት አብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገሮች በካፒታሊዝምና በተራ ገበያ መሀከል ያለውን ልዩነት ለመረዳት ችግር አለባቸው። ስለሆነም አገዛዞች ወደ ውስጥ ሰፋ ያለና፣ ህዝቦቻቸውን የሚያስተሳስርና፣ እንዲሁም ሰላምንና መረጋጋትን ሊያመጣ የሚችል ኢኮኖሚ እንዴት እንደሚገነባ ያልተገነዘቡ በመሆናቸው ያለውን ችግር የሚያባብስ በገበያ ኢኮኖሚ ስም የሚመጣ ፖሊሲ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ተገደዋል። ይህ ዐይነቱ ግራ መጋባትና መዘበራረቅ ለብዙ ዐመታት እንደሚቆይ መናገር ይቻላል። ከዚህ ዐይነቱ የተወሳሰበ ችግር ለመውጣት የሚቻለው ቢያንስ ለሰላሳ ዐመት ያህል ወደ ውስጥ ያተኮረ በመንግስት የተደገፈ የአገር ውስጥ ግንባታ የኢኮኖሚ ክንዋኔ ሲካሄድ ብቻ ነው። ለዚህ ደግሞ በየአገሩ ያለው የውስጥ ኃይል በመንግስት አስተባባሪነት በአንድነት መነሳት አለበት። የየአገሩም ምሁር ከራሱ ስሜትና ፍላጎት በመላቀቅ በቆራጥነት በአንድነት በአገር ስሜት በመነሳሳት ወደ ውስጥ ያተኮረ ሁለ-ገብ የኢኮኖሚና የህብረተስብ ግንባታ ማካሄድ አለበት። ይህ ብቻ ሲሆን የየአገሩን ኢኮኖሚ በፀና መሰረት ላይ በመገንባት በሃማኖትና በጎሳ የሚናቆረውን ህዝብ መንፈስ በመሰብሰብ አትኩሮውን ወደ አገር ግንባታ እንዲያተኩር ማድረግ ይቻላል። በዚህም አማካይነት ቀስ በቀስ የአገር ውስጥ ገንዘብ በአንድ አገር ኢኮኖሚ ግንባታ ላይ ሊኖረው የሚችለውን ሚና መረዳት ይቻላል።

የመንግስት ሚና በካፒታሊስት ኢኮኖሚ ውስጥ !

በአብዛኛዎቹ ለዩኒቨርሲቲ ተብለው በተዘጋጁ የኢኮኖሚ መጻህፍቶች ውስጥ፣ ለምሳሌ ስለ ማክሮና ስለ ሚክሮ ኢኮኖሚክስ የሚያትቱ መጽሀፍቶችን ለተመለከተ፣ የካፒታሊስት ኢኮኖሚ ካለምንም የመንግስት ጣልቃ-ገብነት በራሱ ኃይል እንዳደገና፣ እዚህ ደረጃ ላይ እንደደረሰና እንደሚንቀሳቀስ ተደርጎ ነው የተማርነው። የሚሰበከውምና የሚለፈፈውም ሁሉንም ገበያው ይቆጣጣረዋል፤ ያስተካክለዋል፤ ኢኮኖሚው ሲዛባ ራሱ ውስጥ ባለው ኃይል ሚዛናዊ እንዲሆን ያደርገዋል እየተባልን ነው የተማርነው። እንደሚነገረንና ለማሳመንም እንደሚሞከረው የመንግስት ጣልቃ ገብነት የገበያን ኢኮኖሚ ያዛባል፤ በተለይም በፊስካል ፓሊሲ የሚወሰድ ኢኮኖሚያዊ ጣልቃ-ገብነት የዋጋ ግሽበትን ያስከትላል። መንግስት ከባንክ ወይም ከካፒታል ገበያ ላይ እየተበደረ በኢኮኖሚው ውስጥ ጣልቃ መግባቱ የግዴታ ከካፒታሊስቶች ጋር እንዲወዳደር ያደርገዋል። በካፒታሊስቶች ላይ ግፊት(Crowding out) ስለሚያደርግ ከገበያው እየተስፈናጠሩ እንዲወጡ ይገደዳሉ እየተባልን ነው ሲነገረን የከረመው።

ሀቁ ግን በኢኮኖሚ የግንባታ ታሪክ ውስጥ በተለያዩ መልኮች መንግስት ጣልቃ ሳይገባ አጠቃላይ የሆነ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የታየበት የምዕራብ አውሮፓ አገር የለም። በተለይም አንዳንድ የአውሮፓ አገሮች ከሰላሳ ዐመት ጦርነት በ1648 ዓ.ም ከተላቀቀቁ በኋላ ሆን ብለው የያዙት ወደ ውስጥ ያተኮረ ሰፋ ያለ ኢኮኖሚ መገንባት ነው። በጊዜው የከበርቴው መደብ ያደገ ስላልነበረና፣ የአብዛኛዎቹ ምዕራብ አውሮፓ አገሮች ኢኮኖሚዎች በአማዛኙ በእርሻ ላይና በዕደ-ጥበብ ላይ የተመረኮዘ ስለነበር፣ ይህ ዐይነቱ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ለህብረ-ብሄር ግንባታና፣ ህዝቡን ለማስተሳሰርና ብሄራዊ ስሜት እንዲኖረው ለማድረግ በፍጹም አያመችም ነበር። በመሆኑም የተገለጻለቸው ምሁራን የመንግስትንና ርስ በርሱ የተሳሰረ ኢኮኖሚ ሚናን በመረዳት በመንግስት ላይ ከፍተኛ ጫና ያደርጉ ነበር። ለዚህ ደግሞ፣ 1ኛ) የነቁ ኃይሎችን መደገፍ፣ 2ኛ) ወደ ውስጥ በማኑፋክቱር ላይ የተመሰረተ ሁለ-ገብ ኢኮኖሚ መገንባት፣ 3ኛ) የውስጥ ገበያን ለመከላከልና በተለይም በማደግ ላይ ያሉ ኢንዱስትሪዎች ከውጭ በሚመጣ ተመሳሳይ ምርት እንዳይጠቁ የታሪፍ ዕገዳ ፖሊሲ ማካሄድ፣ 4ኛ)ወደ ውጭ ደግሞ የተፈበረኩ ዕቃዎች በመላክ ወደ ውስጥ ወርቅ እንዲፈስ ማድረግ፣ 5ኛ) የዕደ-ጥበብ ስራዎችን ማስፋፋት፣ 6ኛ) መንገዶችንና ካናሎችን መስራት፣ የኋላ ኋላ ደግሞ የባቡር ሀዲድ በመዘርጋት ህዝቡ እንዲገናኝና የንግድ ልውውጥ እንዲፋጠን ማድረግ፣ 7ኛ) ከተማዎችንና መንደሮችን ጥበባዊ በሆነ መልክ መስራት፣ ይህ በራሱ የአንድ ህዝብ መንፈስ የተረጋጋ የሚሆን ስለሚያደርግ የቤቶች አሰራር የተወሰነ የጂኦሜትሪ ቅርጽን ተከትለው እንዲሰሩ ማድረግ፣ እነዚህና ሌሎች ለአንድ አገር ግንባታ ይጠቅማሉ ተብለው የታሰቡ ነገሮች በሙሉ ተግባራዊ በመሆን ለሁለ-ገብ ዕድገት መሰረት መጣል ችለዋል። በጊዜው የነበረውም ክርክር ኢኮኖሚያዊ ዕድገት አንድን አገር ሁለንታዊ በሆነ መልክ ከማሳደግ ተነጥሎ መታየት እንደማይችልና፣ ህብረ-ብሄር፣ ህብረተሰብ፣ ባህል፣ ስነ-ምግባር፣ ሞራልና ሌሎች ህብረተሰብአዊ እሴቶች ተነጣጥለው ሊታዩ እንደማይችሉ በምሁራን የታመነበትና ትግል የሚካሄድበት ነበር። ስለሆነም መንግስት ብሄራዊ ኢኮኖሚ እንዲገነባ አስፈላጊውን እርምጃ የሚወስድና፣ የአገርም አለኝታ የነበረ ነው። በምንም ምክንያት የየግለሰቦችን ተሳትፎ ሃሞት ለማፍሰስ የሚከተለው ተንኮላዊ ስራ አልነበረውም። በአጠቃላይ ሲታይ ራሳቸው ነገስታትም በከፍተኛ ዕውቀት የተካኑና፣ አማካሪዎቻቸውም ፈላስፋዎችና የከተማ ገንቢዎችና ሳይንስቲስቶች ስለነበሩ አገርን ለመገንባት ይህን ያህልም ከባድ አልነበረም። በተለይም ደግሞ የትኛው ዐይነት የኢኮኖሚ ሳይንስና ፖሊስ ነው ለአገር ግንባታ ሊጠቅም የሚችለው በሚለው ላይ ሙሉ ስምምነት የነበረና፣ የተማረውም ለአገሩ ዕድገት ግንዛቤ ስለነበረው የአገሩን ጥቅም ለማስጠበቅና ህብረተሰብአዊ ስምምነት ለማምጣት ቀን ከሌሊት የሚሰራ ምሁራዊ ኃይል ነበር። በዚህም ምክንያት ጥበባዊ አገር ለመገንባት ከባድ አልነበረም።

ወደ አሜሪካ ስንመጣ ደግሞ በመጀመሪያ ደረጃ የነፃ ንግድ ፍልስፍናን በሚያራምዱና፣ ወደ ውስጥ ደግሞ በማኑፋክቱር ላይ ያተኮረ ኢኮኖሚያዊ ግንባታ ያስፈልጋል በሚሉ ኃይሎች መሀከል የጦፈ ትግል ይካሄድ ነበር። የመጀመሪያው የእንግሊዝን ጥቅም የሚያስጠብቅ ሲሆን፣ ሁለተኛው ግን ብሄራዊ አጀንዳ የነበረውና አሜሪካንን ታላቅ አገር አድርጎ ለመገንባት የሚታገል ነበር። በመጨረሻ ላይ ብሄራዊ ስሜት ያለው የእነ ሃሚልተን ክንፍ በማሸነፍ የአሜሪካንን ኢኮኖሚ በአጭር ጊዜ ውስጥ በመገንባት ቀስ በቀስ የበላይነት እንድትቀዳጅ መስመሩን ማስያዝ ቻለ። ጃፓንና ደቡብ ኮሪያም፣ ከሞላ ጎደል ይህንን ዐይነቱን በመንግስት የተደገፈ ሁለንታዊ የኢኮኖሚ ግንባታ በመከተል ነው በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ብሄራዊ ኢኮኖሚነት ለመሸጋገርና፣ ዛሬ ደግሞ በቴክኖሎጂ በዓለም አቀፍ ደረጃ መወዳደር የቻሉት። ከሜጂ ዲይናስቲ በፊት የነበረው ቶኮጋዋ የሚባለው አገዛዝ የበለጠ በንግድ ላይ ያተኮረ ስለነበር፣ የሜጂ ዲይናስቲ ስላጣን ሲወስድ ቀስ በቀስ የቶኮጋዋን ደጋፊዎች በመግፋት የግዴታ ለውስጥ ገበያ የሚያመች የኢንዱስትሪ ፖለቲካ ማካሄድ ይጀምራል። በተለይም ጃፓን በዚያው ዘመን በእንግሊዝና በተቀሩት ኃያል መንግስታት ተከባ ስለነበር የዚህን አደጋነት የተረዳው የሜጂ ዲይናስቲ የግዴታ አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ ነበረበት። በመጀመሪያ ወጣቶችን ወደ ውጭ ልኮ ማስተማር፣ ሁለተኛ የቴክኖሎጂ መማሪያ ኮሌጆች ማስፋፋት፣ በሶስተኛ ደረጃ፣ ለዕድገት አመቺ የሆነ የኢኮኖሚ ፖሊሲን ማጥናትና እሱን ተግባራዊ ማድረግ፣ በአራተኛ ደረጃ፣ ኢንስቲቱሽናል ሪፎርም ማድረግ ነበር። ለፈጣን ዕድገት ተስማሚ ርዕዮተ-ዓለም የነበረው ሱማራይ የሚባል በከፍተኛ ዲሲፕሊን የሰለጠነ የሰው ኃይል በቆራጥነት በመነሳት ጃፓን ሁለት ትውልድ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የቴክኖሎጂ ባልቤት በመሆን ኢኮኖሚዋ እንዲያድግ ከፍተኛ አስተዋፅዖ አበርክቷል። ካለፉት ሰላሳ ዐመት ጀምሮ ደግሞ ቻይና በመንግስት ጣልቃ ገብነት ነው የተወሳሰበና አጠቃላይ የኢኮኖሚ ዕድገት ማሳየት የቻለችውና ወደ ብሄራዊ ኢኮኖሚ ለመሸጋገር የበቃችው ።

ከዚህ ስነነሳ የምንገነዘበው ለካፒታሊስት ኢኮኖሚ መሰረት የተጣለው በማኑፋክቱር አብዮት አማካይነት በፍጹም ሞናርኪዮች ነው። በኢኮኖሚው ውስጥ ጣልቃገብነታቸውም ዕውቅና ለራሳቸው የግል ሀብት ለማካበት ሳይሆን፣ ንቁ የህብረተሰብ ክፍሎች ውስጣዊ-ኃይል እንዲያገኙ በክሬዲትና በኢንስቲቱሽናዊ የጥገና ለውጥ መስመር በማሲያዝና በመደገፍ ነው። በጊዜው የነበረው አመለካከትና ዕምነት ጠንካራ ህብረ-ብሄርን የመመስረቱ ጉዳይ እንደ ቅድመ-ሁኔታ በመታየቱና፣ በተለያዩ የምዕራብ አውሮፓ አገሮችም ዘንድ ውድድር ስለነበር፣ ሁሉም በየፊናው የአገሩን ገበያና የአገሩን ከበርቴ ማጠናከር ነበረበት። ስለሆነም የአገር ውስጥ ገበያ እንዲዳብርና ጠንካራ ኢኮኖሚ እንዲገነባና ዕቃዎችና ካፒታል ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ በቀላሉ እንዲሽከረከሩ ለማድረግ እንቅፋት የሆኑ ነገሮች ሁሉ ቀስ በቀስ መወገድ ነበረባቸው። የሰው አስተሳሰብ ከክላዊነት ወጥቶ ወደ ማዕከላዊነት እንዲያተኩር በማድረግ ኢኮኖሚው ህብረ-ብሄራዊ ባህርይ እንዲኖረው ማድረጉ ብቻ ሳይሆን፣ ህዝቡም በተለያዩ ድሮች መተሳሰርና እንደ አንድ ህዝብ መነሳት አለበት የሚለው አመለካከት የታመነበት ጉዳይ ነበር። ካፒታሊዝምና ጠንካራ የውስጥ ገበያ ክልላዊ አስተሳሰቦች በሰፈኑበት አገር ውስጥ ማደግ አይችሉምና። ይህ በሞናርኪስቶች የተመራው የመርካንትሊዝም የኢኮኖሚ ግንባታ ነው የኋላ ኋላ ለእነ አዳም ስሚዙ የረቀቀው እጅ(Invisible Hand) መንገድ የከፈተው። የእነስሚዝ የነፃ ገበያ መሰበክ ከተጀመረም በኋላ የመንግስታት ጣልቃ ገብነት እየተወሳሰበና መልኩን እየቀየረ መጣ እንጂ፣ መንግስት ኢኮኖሚውን ለተዋንያኖች ብቻ በመልቀቅ ምሽግ ውስጥ የገባበት ጊዜ አልነበረም።

በመሀከሉ የተወሰዱትን እርምጃዎች ሁሉ ትተን፣ የሁለተኛው ዓለም ጦርነት ከተገባደደ በኋላ በመንግስታት የተወሰዱትን መልሶ የመገንባት እርምጃ ስንመለከት ኢኮኖሚው መንሰራራት የጀመረው እንደሚነገረን በገበያ ተዋንያን አማካይነት አይደለም። በመጀመሪያ ደረጃ፣ የምዕራብ አውሮፓ መንግስታት የፈራረሱ ከተማዎችን መልሰው በመገንባት ለህዝቡ መጠለያ መስጠት ነበረባቸው። በሁለተኛ ደረጃ፣ የምግብን ችግር መቅረፍ ነበረባቸው። ቀጥሎም የንጹህ ውሃና የኃይል(Energy) ጉዳይ መፍታት ነበረባቸው። እነዚህ መሰረታዊ ነገሮች ሲሟሉ ብቻ ነበር ኢኮኖሚውን መገንባት የሚቻለው። ይህንን መሰረታዊ ጉዳይ የተረዱት የምዕራብ አውሮፓ መንግስታት ስራ ለመስራት የሚችለውን ኃይል ሁሉ ማሰማራት ነበረባቸው። ለዚህ የሚሆን ደግሞ ልዩ ዐይነት የክሬዲት ሲስተም ማቋቋም ነበረባቸው። ስለሆነም ምዕራብ ጀርመን ብቻ ከ70-80% የሚጠጋው ከተማዎቿና ኢንዱስትሪዎቿ እንዲሁም ድልድዮቿ ከወዳደሙ በኋላ ከአስራአምስት እስከ ሃያ ዐመት ባለው ጊዜው ውስጥ ነው አገሯን መልሳ መገንባት የቻለችው። አገዛዞች የገበያ ተዋንያን መልሰው ይጠግኑታል ብለው እጃቸውን አጣጥፈው አለተቀመጡም። ለዚህ ሁሉ ደግሞ ዋናው መሰረታዊ ጉዳይ ከፍተኛ ዲሲፕሊን፣ ለስራ ታጥቆ መነሳት፣ የአገርን ክብር ለውጭ ኃይል ለመሸጥ አለመነሳት፣ የተከበረ አገር መገንባት የሚለው መመሪያ ነበር። በጊዜው የተለያዩ ፓርቲዎች ቢኖሩም፣ በሁሉም ዘንድ የነበረው ስምምነት ጠንካራ ኢኮኖሚና የተከበረች አገር መገንባት በሚለው ላይ ነው።

ይህ ዐይነቱ ኢኮኖሚውን መልሶ የመገንባት እርምጃ ቀጥተኛና ግልጽ ነበር። ኢኮኖሚው እያደገና ውስጠ-ኃይል እያገኘ ሲመጣ ደግሞ በሞኔተሪና በፊስካል ፖሊሲ አማካይነት የእርማት እርምጃዎች መውሰድ ጀመሩ። እዚህ ላይ ነው ብዙ የሶስተኛው ዓለም አገር ተማሪዎች የሚምታታበቸውና ስልጣን ላይ ቁጥጥ ሲሉ ብዙ ነገሮችን የሚያበላሹት። ያም ሆነ ይህ የመንግስት ሚና የተወሰነውን ሀብት ከመቆጣጠር አልፎ በፖሊሲ አማካይነት ጣልቃ እስከመግባት ድረስ ለካፒታሊዝም አጠቃላይ የሀብት ክምችት አመቺ ሁኔታዎችን የሚፈጥር ነበር። ለምሳሌ የምዕራብ ጀርመንን ኢኮኖሚ ስንመለከት፣ እስከ 90ዎቹ መግቢያ ድረስ፣ የአየር መንገድ(ሉፍታንሳ)፣ ፓስታ ቤት፣ የውሃ ክፍፍል፣ የመብራት ስርጭት፣ የባቡር ሃዲድ፣ ትምህርት ቤቶችና ሆስፒታሎች፣ ስልክ… ወዘተ በመንግስት ቁጥጥር ስር ሆነው በአውቶነመስ ደረጃ በግሩም ሁኔታ የሚንቀሳቀሱ ነበሩ። አሁንም በአብዛኛዎቹ ላይ መንግስት ከፍተኛውን ድርሻ ሲይዝ፣ ወደ ግላዊነት የተዘዋወሩት ደግሞ ከሃያ ዐመት ሙከራ በኋላ በተለይም በሎካል ደረጃ ያሉት የሎካል አስተዳዳሪዎች እንደገና መልሰው እየገዟቸው ነው። ምክንያቱም እንደ ንጹህ ውሃ ስርጭት፣ መብራትና ጋዝ የመሳሰሉት ካፒታሊስቶች ዋጋውን ስለሚያስወድዱና ትርፋማ ያልሆኑትን ስለሚዘጓቸው ይህ ጉዳይ አስቸጋሪ ሁኔታ ስለፈጠረና የህዝብንም ጩኸት ለመቀነስ ሲባል የግዴታ መልሶ መግዛቱ አስፈላጊነቱ ታየ። ከዚህም በላይ፣ በጀርመን አገር ብቻ ሶስት ዐይነት የባንክ አደረጃጀትና የአሰራርና ዘዴዎች አሉ። 1ኛ) በግል ቁጥጥር ስር ያሉ ባንኮች(Private Banks)፣ 2ኛ) በጋርዮሽ ስር ያሉ(Cooperative Banks)፣ 3ኛ) በመንግስት ቁጥጥር ስር ያሉ። ከዚህ በተረፈ ልዩ ዐይነት በዝቅተኛ ወለድ ብድር የሚሰጥ በመንግስት ቁጥጥር ስር ያለ፣ ከሃምሳኛው ዓ.ም ጀምሮ የሚንቀሳቀስ የባንክ ሲስተም አለ። በዚህ መልክ እነዚህ የተለያዩ ባንኮች የተለያየ ተግባር በመውሰድ ደንበኞቻቸውን ያስተናግዳሉ። በመንግስት ቁጥጥር ስር ያሉ ባንኮች ለትናንሽና ለማዕከለኛ አምራቾች ከረጂም ጊዜ አንፃር በዝቅተኛ ወለድ የሚከፈል ብድር ያበድራሉ። በጋርዮሽ ስር ያሉት ደግሞ ለአባሎቻቸው ብድር የሚያበድሩ ናቸው። ማንኛውም ማህበራዊ ነክ የገንዘብ እንቅስቃሴዎች በሙሉ በጋርዮሽ ባንክ አማካይነት ነው የሚንቀሳቀሱት።

ከላይ በአጭሩም ቢሆን የተዘረዘረው ጉዳይ የሚያሳየው ካፒታሊዝም በንጹህ መልክ በገበያ ኢኮኖሚ ህግ ብቻ የሚካሄድ ኢኮኖሚያዊ ስርዓት አይደለም። የተወሳሰበና ብዙ ተዋንያን በህብረተሰብ ውስጥ ባላቸው ቦታ አማካይነት የሚካፈሉበትና፣ ሁሉም የተሻለ ድርሻ ለማግኘት ሲሉ በግልጽም ሆነ በይፋ ትግል የሚያደርጉበት መድረክ ነው። እዚህ ላይ ነው ብዙ የሶስተኛው ዓለም መንግስታት እስከዚህም የካፒታሊዝምን ውስጣዊ ባህርይና እንቅስቃሴ በሚገባ ሳይረዱ በዓለም አቀፍ ኢንስቲቱሽኖች እየተመከሩ የሚወስዱት ፖሊሲ ህዝቦቻቸው መቀመቅ ውስጥ ሲገቡ አንድ ቦታ ላይ ቆም ብለው ለመጠየቅ የማይችሉት። ከላይ አንድ ቦታ ላይ እንደተተነው ካፒታሊዝም ኢኮኖሚያዊ ክንውን ብቻ ሳይሆን ፓለቲካዊ፣ ማህበራዊና ርዕዮተ-ዓለማዊ እንደመሆኑ መጠንና፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የእያንዳንዱን የሰው ህይወት ሰለሚነካና ስለሚወስን የሚወሰዱት እርምጃዎች በሙሉ በዘፈቀደ አይደለም። በጉልበትና በአወቅኹኝ ባይነት በሚወሰዱበት ቦታ ደግሞ የግዴታ የሲቪክ ማህበራትን እንቅስቃሴና ጩኸት ያስከትላሉ። ስለሆነም እንደኛ አገር ዐይነቱ መንግስታት በየዋሁ ህዝባችን ላይ እንደሚጭነውና አገርን እንደሚያተራምሰው ዐይነት ፓሊሲ አይደለም በካፒታሊስት አገሮች የኢኮኖሚ ፓሊሲ ተግባራዊ የሚሆነው። ከዚህ በመነሳት ነው የአገራችንን የኢኮኖሚ ሁኔታና አደገ የተባለውን ኢኮኖሚ ማየትና ማንበብ ያለብን።
የወያኔ ኢኮኖሚ ፖሊሲ፣ የኒዎ-ሊበራል፣ አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ወይስ ሌላ ዐይነት !

ወያኔ ስልጣን ከያዘ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ተግባራዊ ያደረገው የኢኮኖሚ ፖሊሲ በግልጽ ለውይይት የቀረበ አይደለም። እስከቅርብ ዐመታት ድረስ አገዛዙ የሚከተለው የኢኮኖሚ ፖሊሲ ለብዙዎቻችን ግልጽ አይደለም። አገዛዙ በሚያካሂደው የተምታታ ፖሊሲና፣ በተለይም ደግሞ „ስትራቴጂክ የሚባሉ መስኮችን“ ራሱ በመሰረተው ኩባንያና በአንዳንድ ከአገዛዙ ጋር በተቆላለፉ ሰዎች ቁጥጥር ስር በመዋላቸው ወደ ውስጥ ምን ዐይነት የኢኮኖሚ ፖሊሲ እንደሚከተል ለማወቅ አስቸጋሪ ሆኗል። በተለይም ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ከመሞቱ በፊት ያናፈሰው „የዴቬሎፕሜንታል መንግስት” የኢኮኖሚ ፖሊሲ ብዙዎቻችንን እንዳዘናጋና፣ በእርግጥም አገዛዙ በመንግስት የተደገፈ የኢኮኖሚ ፖሊሲ የሚያካሂድ ይመስል አንዳንዶቻችንን ሲያጨቃጭቀን ሰንብቷል። በመንግስት የተደገፈ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ምን መምሰል እንዳለበት ከአገዛዙ ጋር ክርክር ባለመደረጉ፣ እስካሁን ድረስ አገዛዙ ሰፊውን ህዝብ ለማዘናጋት ይሰብክ ይነበረው እሱ የሚያካሂደው ፖሊሲ አማራጭ የሌለውና፣ ይኸኛውም ብቻ „ የዴቬሎፕሜንታል ስቴት“ መንገድ ሲሆን፣ ተቃዋሚው ደግሞ የኒዎ-ሊበራል የኢኮኖሚ ፖሊስን የሚናፍቅና እሱን ተግባራዊ ለማድረግ የሚታገል ነው በማለት ዘመቻ ሲያካሂድ ቆይቷል። ይሁንና ግን ለአልተማረው ሰፊው ህዝብ ቀርቶ ለተማረው እንኳ የኒዎ-ሊበራል የኢኮኖሚ ፖሊሲ ምን እንደሚመስል ግልጽ አይደለም። ሰፋ ያለ ምሁራዊ ክርክር በማይደረግበት፣ የህዝብና የአገር ተቆርቋሪ በሌለበት አገር እንደወያኔ የመሳሰሉ ጮሌዎች ህዝብን ለማደናበር በቀላሉ ያመቻቸዋል።

ሀቁ ግን ወያኔ ስልጣን ከያዘ ከአንድ ዐመት በኋላ ከዓለም አቀፍ ኮሙኒቲው ጋር ባደረገው ስምምነት መሰረት ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅትና ከዓለም ባንክ ተጽፎ የመጣለትን „የተቅዋም ማስተካከያ የኢኮኖሚ ፖሊሲ“(Structural Adjustment Program) እየተባለ የሚታወቀውን፣ ከ1980 ዓ.ም መጀመሪያ ጀምሮ ለአፍሪካ አገሮችና ለተቀሩት የሶስተኛው ዓለም አገሮች የቀረበላቸውንና ተግባራዊ ያደረጉትን፣ በጠቅላይ መለሰ ዜናዊ የሚመራው አገዛዝ ተግባራዊ አድርጓል። የዚህም ፕሮግራም ዋናው ዓላማ ለአንዴም ለመጨረሻም ጊዜ የገበያን ኢኮኖሚ በኢትዮጵያ ምድር ተግባራዊ አድርጎ፣ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ተወዳዳሪ ማድረግ ነው። ስለሆነም ፕሮግራሙን ተግባራዊ ለማድረግ፣ ለኢኮኖሚው አለመንቀሳቀስ እንቅፋት ናቸው ተብለው የተገመቱትን ማስወገድ ነበር። የፕሮግራሙ ዋና መሰረተ-ሃሳብ የመንግስትን በኢኮኖሚ ውስጥ ጣልቃ መግባት በከፍተኛ ደረጃ በመቀነስ ለኢኮኖሚ ተዋንያን(Invisible Hand) ገበያውን መልቀቅ ነው። በዚህም መሰረት፣ 1ኛ) በመንግስት ቁጥጥር ስር ያሉ ፋብሪካዎችንና የንግድ ድርጅቶችን ወደ „ግል በወድድር ማዘዋወር ወይም መሸጥ፣“ 2ኛ) መንግስት ለማህበራዊ መስክ የሚያወጣውን ወጪ መቀነስ፣ 3ኛ) የውጭውን ኢኮኖሚ ሊበራላይዝ ወይም ልቅ ማድረግ፣ 4ኛ) ወደ ውስጥ በገበያ ላይ የሚደረገውን የዋጋ ቁጥጥር አንስቶ፣ የዕቃዎች ዋጋ በአቅራቢና በጠያቂ እንዲደነገግ ማድረግ፣ 5ኛ) የብርን የመግዛት አቅም ከአሜሪካን ዶላር ጋር በማነፃፀር ዝቅ (Devaluation) ማድረግ፣ ወዘተ… ናቸው። በዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅትና በዓለም አቀፍ ኮሙኒቲው ዕምነት መሰረት እነዚህ የተቅዋም ድክመቶች(structural weakness) ሲሆኑ፣ እነዚህ ፖሊሲዎች ተግባራዊ ሲደረጉ የገበያ ኢኮኖሚ በንጹህ መልኩ ተግባራዊ በመሆን፣ ሰፊው ህዝብ የስራ መስክ ያገኛል፤ ገቢ ሲያገኝ በገበያ ላይ የሚሸጠውን ዕቃ ገዝቶ ይጠቀማል፤ የተወሰነውን በመቆጠብና ባንክ ውስጥ በማስቀመጥ፣ በአጠቃላይ ሲታይ ለገበያው ኢኮኖሚ ዕምርታን በመስጠት ኢኮኖሚው እንዲያድግ ያደርጋል የሚል ቀላል የኒዎ-ሊበራል ኢኮኖሚስቶች ፎርሙላ ነው።

በመጀመሪያ ደረጃ የተቅዋም መስተካከል(Structural Adjustment) የሚለውን ጽንሰ-ሃሳብ ጠጋ ብለን እንመልከት። እንደሚታወቀው የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅትና፣ ይህንን ፖሊሲ የሚደግፈው ዓለም አቀፍ ኮሙኒቲ የሚባለው እንደዚህ ዐይነቱን ፕሮግራም በብዙ የሶስተኛው ዓለም አገሮች ላይ ሲጭኑ መነሻቸው ሁሉም አገሮች ተመሳሳይ ችግር አላቸው ከሚለው ቀላል ውሳኔ፣ ግን ደግሞ ሳይንሳዊ መሰረት ከሌለው ግምት በመነሳት ነው። እነዚህን ከላይ የተዘረዘሩትን ፖሊሲዎች እንደስትራክቸር ማየቱም ትክክል አይደለም። ምክንያቱም እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ፖሊሲዎች የአንድን ህብረተሰብ የኢኮኖሚ ድክመት ማሳየት ቢችሉም፣ የስትራክቸራል ድክመቱ ዋና ምክንያት የጠቅላላው የኢኮኖሚ አወቃቀር ነው። ይህም ማለት የዳበረ የስራ ክፍፍል አለመኖሩ፣ በአጠቃላይ ሲታይ ኢኮኖሚው ስነስርዓት ባለው መልክ አለመደረጃቱ፣ ለዚህ ደግሞ እጅግ የተበላሸ ለኢኮኖሚ ዕድገት የማያመች የፖለቲካና የመንግስት አወቃቀር መኖሩ፣ በተጨማሪም የባህልና የህብረተሰብ ችግር አንድ ላይ ተደማምረው ኢኮኖሚው ውስጠ-ኃይል እንዳያገኝ ሊያደርጉት በቅተዋል። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ አገራችንና ሌሎች የአፍሪካ አገሮች ለሃምሳ ዓመታት ያህል የተከተሉት ለሁለ-ገብ የኢኮኖሚና የህብረተሰብ ግንባታ የማያመች የኢኮኖሚ ፖሊሲና፣ በዓለም አቀፍ የስራ-ክፍፍል ውስጥ በመካተት እንደ ቡናና ሌሎች ጥሬ-ሀብቶችን እንዲያመርቱ መደረጋቸውና ለገበያ እንዲያቀርቡ መገደዳቸው ወደ ውስጥ ኢኮኖሚያዊ አወቃቀሩ ውስጠ-ኃይል እንዳይኖረው ለማድረግ በቅቷል። በዚህና በሌሎች በተሰበጣጠሩ አያሌ ምክንያቶች የተነሳ በተለያየ ጊዜያት ስልጣንን የጨበጡ አገዛዞች አንድ ወጥና በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተደገፈ ኢኮኖሚ መገንባት አልቻሉም። ከዚህ ስንነሳ እነ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅትና የዓለም ባንክ ያቀረቡት የስትራክቸራል ሬፎርም ፕሮግራም የነበረውን ውስጣዊ ድክመት (Structural Weakness) የባሰውን ጥልቀት እንዲኖረውና እንዲጠናከር ያደረገ እንጂ መፍትሄ ሊሆን እንደማይችል በተግባር ከተመነዘረ በኋላ ማረጋገጥ ችሏል።

እንደገና ወደ አጠቃላዩ ጽንሰ-ሃሳብ ስንመጣ፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከማን ጋር አድጀሰት ወይም መስተካከል እንዳለበት ግልጽ አይደለም። በሌላ አነጋገር ወደ ውስጥ ያተኮረ ሰፋ ያለ፣ በማኑፋክቱር ላይ የተመሰረተ ኢኮኖሚ ለመገንባት፣ ወይስ ወደ ውጭ የዓለም ገበያንና ተዋንያኖችን ፍላጎት ለማሟላት በሚችል መልክ ማደራጀት ? እንደገባኝና ፖሊሲው በተግባር ላይ ከዋለ በኋላ ማየት እንደቻልነው፣ ወደ ውስጥ ሰፊውን የህብረተሰብ ክፍል የሚያደኸይና በመንፈሱም ሆነ በአካሉ ደካማ ህዝብ ማፍራት ሲሆን፣ በሌላ ወገን ደግሞ ከላይ በተገለጹት ፖሊሲዎች አማካይነት ጥቂቱን አደልቦ በዓለም አቀፍ ሂራርኪ ውስጥ በማካተት አጠቃላይ የሆነ ዕድገት እንዳይኖር መንገዱን መዝጋት ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ አጠቃላይ የሆነ ማህበራዊ፣ ህብረተሰብአዊ፣ ባህላዊና የህሊና ቀውስ እንዲፈጠር አድርጎ ለብዙ ዐመታት ህብረተሰብአዊ መረጋጋት(Social Stability) እንዳይኖር ማድረግ ነው። ይህ ነው የኢኮኖሚ ፖሊሲው ዋና ዓላማ። በሌላ አነጋገር የኢኮኖሚው ፖሊሲ ሰፋ ያለ በማኑፋክቱር ላይ የተመሰረተና ሊዳብር በሚችል ኢኮኖሚያዊ ክንዋኔ ላይ ያተኮረ አይደለም።

ፖሊሲው ተግባራዊ ከሆነ በኋላ ለማረጋገጥ የተቻለው ድህነትን መቅረፍና ወደ አጠቃላይና ሁለ-ገብ ኢኮኖሚ ግንባታ ማምራት ሳይሆን የባሰ ድህነትን መፈልፈልና የአገር ውስጥ ገበያ በጠንካራ መሰረት ላይ እንዳይገነባ ማድረግ ነው። በመጀመሪያ ደረጃ አገዛዙ የህዝብን ንብረት „ሲሸጥ“ ንብረቱ በቀጥታ በኢፈርት ስርና በአንዳንድ ከወያኔ ጋር የተቆራኙ እጅ ውስጥ ነው የወደቀው። ኢፈርትና አንዳንድ ግለሰቦች ገንዘብ ከንግድ ባንክ በርካሽ ወለድ በመበደር ፋብሪካዎችንና የንግድ ኩባንያዎችን በመግዛት በአጭር ጊዜ ውስጥ በብዙ መቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ሀብት ማካበት ችለዋል። በአሁኑ ወቅት በኢፈርትና ከወያኔ ጋር በተሳሰሩ ግለሰቦች እጅ ወደ ስድሳ የሚጠጉ ፋብሪካዎችና የንግድ ኩባንያዎች አሉ። በዚህ አማካይነት አገዛዙና አንዳንድ ገለሰቦች የሞኖፖል ቦታ በመያዝ እጅግ ወደ ኋላ በቀረ ኢኮኖሚ ውስጥ ነፃ ውድድር እንዳይኖር ለማገድ በቅተዋል። ስለሆነም እንደተገመተው የተቅዋም መስተካከያ ፖሊሲው ነፃ ገበያን ሳይሆን ያመጣው የጥቂት ሰዎችንና የአንድ ኩባንያን ዘረፋንና መደለብን ነው። በዚያው መጠንም ወደ ውስጥ ሰፋ ያለ በብዙ መልኩ ሊገለጽ የሚችል የስራ-ክፍፍልና የውስጥ ገበያ(Home Market) እንዳይዳብሩ ነው ያገደው። ስለሆነም ለስራ ፈላጊው የስራ መስክ መክፈት አልተቻለም። በአንፃሩ ግን የውጭው ገበያ ልቅ በመሆኑ የሞባይል ስልክና የኢንተርኔት ሱቆች በመስፋፋት ከተማዎችን ማጠባብ ችለዋል። ወደ ገጠር ከተማዎች ሲኪድ ደግሞ ሳልቫጅና ከቻይና የመጡ ዕቃዎች በመፍሰስ ሰውን ባልባሌ ነገር ላይ እንዲሰማራ አድርገውታል። ይህ አጠቃላዩ ሁኔታ ደግሞ የባሰ ጥገኛና ለማኝ እንድንሆን አድርጎናል።

በእኛ ኢትዮጵያውን ምሁሮች በምንባለው ዘንድ የአገዛዙን የኢኮኖሚ ፖሊሲ በሚመለከት የተዛባ አመለካከት አለ። አንዳንዶች አገዛዙን እዚያው በዚያው እየተቃወሙ፣ በሌላ ወገን ደግሞ በመንግስት የተደገፈ ፖሊሲ በአገራችን ምድር እንድሚካሄድ ይነግሩናል። ከላይ ለማሳየት እንደሞከርኩት በመንግስት የሚደገፍ ፖሊሲ በመጀመሪያ ደረጃ ሁለ-ገብ መልክ ያለው ሲሆን፣ መሰረቱም ማኑፋክቱር ነው። በሁለተኛ ደረጃ፣ በህብረተሰብ ግንባታ ታሪክ ውስጥ እንደተረጋገጠው፣ በመንግስት የሚደገፍ የኢኮኖሚ ግንባታ የግለሰብ ተሳትፎን በፍጹም አይቃወምም። እንዲያውም የሚያበረታታና በዝቀተኛ ወለድ ብድር የሚያቀርብ ነው። በሶስተኛ ደረጃ፣ በመንግስት የሚደገፍ ፖሊሲ በመጀመሪያ የሚወስደው እርምጃ መሰረታዊ ፍላጎቶችን(Basic Needs) ማሟላት ነው። ይህም ማለት፣ ለምግብ የሚሆኑ ልዩ ልዩ የእህል አይነቶችን መትከልና በማስፋፋት በዚያውም መጠንም ሰፊው ህዝብ በምግብ ራሱን እንዲችል ማድረግ ነው። ከዚህ ቀጥሎ የንጹህ ውሃን ማቅረብ፣ ትምህርትቤቶችና የጤና መስኮች በየቦታው እንዲስፋፉ ማድረግ፣ ከዚህም በላይ ደግሞ ሰፊው ህዝብ ስነ-ስርዓት ያለው ኑሮ እንዲኖር በአገሪቱ ምድር ከአገራችን አየር ጋር የሚስማማና ዘላቂነት የሚኖራቸው ቤቶች እየሰሩ ለዝህቡ ማዳረስና፣ ህዝቡም በቤት ስራ ሊሰማራ የሚችልበትን ሁኔታ ማዘጋጀት መሰረታዊ የህዝብ ፍላጎቶች ናቸው። የወያኔ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ግን መሰረታዊ ፍላጎቶችን መሟላት ያልቻለ ነው። በአራተኛ ደረጃ፣ በመንግስት የተደገፈ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ብሄራዊ ባህርይ ሲኖረው፣ ከውጭ የሚመጡ ተመሳሳይ ምርቶች የአገርን ኢንዱስትሪ እንዳያዳክሙ የእገዳ ፖሊሲ መከተል አለበት። ወያኔ ግን ይህንን አላደረገም። ባጭሩ የዛሬው አገዛዝ የኢኮኖሚ ፖሊሲ በመንግስት የተደገፈ(Developmental State Ecnomy) ሳይሆን፣ በጥቂት ሰዎች የሚዘረፍ ኢኮኖሚ ወይንም መንግስትን ተገን አድርጎ ዝርፊያ የሚያካሄድና(Predotary State)፣ አገራችን ከውስጥም ከውጭም እንድትጠቃ ያደረገና የሚያደርግ በዘረፋ ላይ የተመሰረተ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ነው።

በየቦታው የተተከሉትን የኢንዱስትሪ ዘርፎች ስንመለከት ደግሞ በመሰረቱ ህብረተሰብአዊ ሀብት ሊፈጥሩ የሚችሉ አይደሉም። የህዝቡን ፍላጎት ለማሟላት ተብለው ታስበው የተተከሉና የሚተከሉ ሳይሆን ጥቂት ሰዎች ቶሎ ቶሎ ብለው በሀብት እንዲደልቡ የሚያመቹ የኢንዱስትሪ ተከላዎች ናቸው። አዲሱ የኢንዱስትሪ አተካከል ዘመቻ በ50ኛውን በ60ኛው ዓ.ም በብዙ የአፍሪካ አገሮችና በኛም አገር ይካሄድ የነበረውን ዐይነት በዚያው እንዲቀጥል ያደረገ የኢንዱስትሪ ተከላ ፖሊሲ ነው። እነዚህም እንደ መጠጥ የመሳሰሉ ፋብርካዎችን ማስፋፋት፣ ቀላል የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ተከላዎች፣ የስኳር ተከላና ፋብሪካን ማስፋፋት… ወዘተ፣ የመሳሰሉት በመሰረቱ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ዕድገትን የሚቀናቀኑ የኢንዱስትሪ ተከላዎች ናቸው። እነዚህ አስፈላጊ ቢሆኑም ተከታታይነት ላለውና ለፈጠራ የሚያመች የኢኮኖሚ ግንባታ የሚስማሙ አይደሉም። ከዚህም በላይ በተለይም በአዲስ አበባና በአንዳንድ ከተማዎች የተስፋፋው ብዙ ውሃንና ኃይልን የሚጋራና የሚጨርስ የሆቴል ቤቶች መስራትና ማስፋፋት ከአገራችን ስትራቴጂያዊ ፍላጎትና ከሰፊው ህዝብ ጥቅም ጋር የሚጣጣሙ አይደሉም።
ባጭሩ የወያኔን የኢኮኖሚ ፖሊሲና የትራንፎርሜሽን ዕቅድ ከላይ በየቦታው በተዘረዘሩት መሰረተ-ሃሳቦች መነፅርና በአንዳንድ አገሮች ውስጥ በልምድ ውጤትን ካስገኙ፣ በመንግስት በተደገፉ የኢኮኖሚ ክንዋኔ ሚዛን ነው መመርመርና መለካት ያለብን። በመንግስት የተደገፉ የካፒታሊስት የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች የሚያረጋግጡት፣ ፖሊሲዎቹ ብሄራዊ ባህርይ ሲኖራቸው፣ በመሰረቱ በካፒታሊስት የኢኮኖሚ ፖሊሲ ሎጂክ ላይ ያተኮሩ ቢሆኑም የመጨረሻ መጨረሻ ለሰፊው ህዝብ የስራ መስክ የሚከፍቱና ህብረተሰቡንም በብዙ ሺህ ድሮች የሚያስተሳስሩ ናቸው። በመሆኑም ጠንካራና የተከበረ አገር መገንባት ነው ዋና ዓላማቸው። ይህም ደግሞ በብዙ አገሮች በተግባር ተረጋግጧል። ከዚህ ስንነሳ ለብሄራዊ ኢኮኖሚ ግንባታ የሚያመቹ ቅድመ-ሁኔታዎች ቀስ በቀስ መዘርጋት ሊታለፉ የማይችሉ መሰርተ-ሃሳቦች ናቸው። ጤናማና ነፃ ውድድር፣ ሳይንስና የቴክኖሎጂ ምጥቀት፣ ከዚህም ባሻገር መሰረታዊ የሆኑ ለሀብት ክምችት የሚያገለግሉ ሁለት የኢንዱስትሪ መስኮች መኖር፣ እነዚህ ደግሞ በማሺን ኢንዱስትሪ መደገፍ ለአጠቃላይ የሀብት ክምችት ዋናው ቁልፍ እንደሆኑ በፖሊሲ አውጭዎችና በመንግስታቱ የታመነበት ጉዳይ ነው። እነዚህ መሰረታዊ ነገሮች በጭንቅላት ውስጥ ሲቋጠሩና እንደ ፖሊሲ መመሪያ ሆነው ደረጃ በደረጃ ተግባራዊ ሲሆኑ ብቻ ነው ሰፋ ያለ ህብረተሰብአዊና አገራዊ ሀብት መፍጠር የሚቻለው፤ ለሰፊው ህዝብም የስራ መስክ ሊፈጠር የሚችለው። እንደሚታወቀው ሰፋ ያለ የስራ መስክ መክፈት የማይችል ኢኮኖሚ ደግሞ ውስጠ-ኃይሉ ውስን ብቻ ሳይሆን፣ የህዝቡም የመግዛት ኃይል ደካማ ስለሚሆን ኢንዱስትሪዎች ሊስፋፉና አዳዲሶችንም በመትከል ወደ አጠቃላይና ሁለ-ገብ ኢኮኖሚ መሸጋገር በፍጹም አይቻልም። የህዝቡ የመግዛት ኃይል በደከመበት ኢኮኖሚ ውስጥ ደግሞና፣ ኢንዱስትሪዎች ርስ በርሳቸው ባልተያያዙበት አገር ውስጥ ገንዘብ ከአንድ የኢኮኖሚ መስክ ወደ ሌላው በመሽከርከር ህብረተሰብአዊ ኃይል(Social Power) ሊያገኝ አይችልም ማለት ነው። የአንድ አገር ገንዘብ መጠንከርና የመግዛት ኃይሉም ሊወሰን የሚችለው የውስጡ ኢኮኖሚ ከላይ በተዘረዘረው መልክ የተደራጀ እንደሆን ብቻ ነው። የተገላቢጦሽ ሊሆን በፍጹም አይችልም። የገንዘብን የዕድገት ታሪክ ለተከታተለ ከስራ-ክፍፍል መፈጠርና ማደግ፣ እንዲሁም መዳበር ቀደም ብሎ ገንዘብ አለተፈጠረም። ዕድገቱ፣ በፍጥነት መሽከርከሩና ጥንካሬው ከጠቅላላው ኢኮኖሚ ዕድገት ጋር የተያያዘ መሆኑን ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል። በገንዘብ ጥንካሬ ውስጥም የሳይንስና የቴክኖሎጂ ምጥቀት፣ የከተማዎች ማደግና መስፋፋት፣ እንዲሁም በልዩ ልዩ የመገናኛና የመመላለሻ ዘዴዎች መገናኘት ለገንዘብ ጥንካሬና በፍጥነት መሽከርከር የራሳቸው ሚና አላቸው። እነዚህ ግን በገንዘብ አተማመን ስሌት ውስጥ ስለማይገቡ ስለአንድ ገንዘብ ጥንካሬ የሚኖራቸው ውስጣዊ አስተዋፅዖ ግልጽ ሆነው አይቀመጡም። ለዚህ ሁሉ ዋናው ምክንያት ምንድ ነው? ዋናው ምክንያት ብዙ ነገሮች ተነጣጥለው ስለሚታዩ፣ አንዱ የኢኮኖሚ ዘርፍ ከሌላው ጋር ምንም ግኑኝነት ሳይኖረው ሊያድግ እንደሚችል ተደርጎ ስለሚወሰድ ነው። በዚህም ምክንያት በአንድ በኩል በገንዘብ መጠንከርና በኢንዱስትሪዎች ዕድገትና ርስበርስ መተሳሰር፣ በሌላ ወገን ደግሞ በገንዘብ የመግዛት ኃይል ድክመትና በጠቅላላው ኢኮኖሚ አወቃቀር ድክመትና የውስጥ ገበያ አለመዳበር መሀከል ያለውን ዲያሌክቲካዊ ግኑኝነት መገንዘቡ ለወደፊቱ የአገር ግንባታ የተወሰነ ግንዛቤ ሊኖር ይችላል ብዬ እገምታለሁ።

ተጨባጩ የአገራችን ኢኮኖሚ ሁኔታና አማራጭ መፍትሄ !

እንደምንሰማው በአሁኑ ጊዜ በአገራችን ምድር በአንዳንድ ቦታዎች ከፍተኛ ረሃብ ገብቷል። ከ10-14 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ ለረሃብ ተጋልጧል። ለዚህ ዋናው ምክንያት አገዛዙ ለ25 ዐመታት ያህል፣ በዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት፣ በዓለምን ባንክና በዓለም አቀፍ ኮሚኒቲው በመገደድና በመታገዝ ያካሄደው የኢኮኖሚ ፖሊሲ ነው። ዛሬ አገራችን ለገባችበት አጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ ቀውስና ረሃብ የዓለም አቀፍ ኮሚኒቲው እጅ የሌለበት አስመስሎ ለማቅረብ መሞከር እጅግ አደገኛ አካሄድ ነው። ከላይ በዝርዝር እንደ ተተነተነው በዓለም አቀፍ ኮሚኒቲው የተደነገገው „የንጹህ ገበያ” ኢኮኖሚ ፖሊሲ ተግባራዊ መሆን ከጀመረ ወዲህ ነው አገራችን የባሰውኑ መቀመቅ ውስጥ እየገባች ልትመጣ የቻለችው። አገዛዙ ስልጣን ላይ ሲወጣ እዚህ ድረስ ደርሼ የአገሪቱን ሀብት ለመቆጣጠር እችላለሁ የሚል ዓላማ ባይኖረውም፣ የተቅዋም መስተካከያን የኢኮኖሚ ፖሊሲ ተግባር ማድረግ ሲጀምርና፣ ከምዕራቡ ዓለም የበለጠ ዕርዳታ ሲፈስለት የአገሪቱን ስትራቴጅክ ሀብቶች መቆጣጠር ጀመረ። በውጭ አማካሪዎችም እየታገዘ የሆቴል ቤቶች እንዲሰሩ ሁኔታዎችን አመቻቸ። በዚህም መሰረት ህገ-መንግስቱ ከሚፈቅደው ውጭ በተለይም የከተማ ቦታዎችን በማከራየትና የአየር ባየር ንግድ እንዲጦፍ በማድረግ ትላልቅ ህንፃዎችን በመስራት ለመሬት ኪራይና ሺያጭ የዋጋ ንረት እንዲኖር አደረገ።

ወደ ገጠር ስንመጣ ደግሞ የውጭ አገር „ኢንቬስተሮች“ ለሚባሉት የሚሰጠው መሬት ገበሬውን ማፈናቀል ጀመረ። ለውጭ ከበርቴዎች የተሰጠው መሬት ላይ ደግሞ አበባ የሚተከለውና እርሻ የሚታረስበት ለውጭ ገበያ ተብሎ እንጂ የሰፊውን ህዝባችንን ፍላጎት ለማሟላት አይደለም። በተለይም በለምለም መሬት ላይ አበባ እየተተከለ ለውጭ ገበያ እንዲሸጥ መደረጉ ከፍተኛ የታሪክ ወንጀል እንደመስራት ይቆጠራል። በዚህ ለምለም መሬት ላይ ልዩ ልዩ ሰብሎች በመትከል የህዝቡን የምግብ ፍላጎት ማሟላት በተቻለ ነበር። ከዚህ ጋር ተያይዞ ባለፉት አስራ አምስት ዐመታት የአገራችን ዘር በመዘረፉ፣ ገበሬው ከውጭ በሚመጣ ዘር ላይ እንዲመካ ተደርጓል። ምናልባትም ከውጭ የሚመጣው ዘርና ማደባሪያ እንዲሁም ደግሞ የተባይ ማጥፊያዎች ዛሬ ለተከሰተው ረሃብ ምክንያት ሳይሆኑ የሚቀሩ አይመስለኝም። በዚህ ላይ ደግሞ በራሱ በአገዛዙ ካድሬዎችና በውጭ ተባባሪዎቻቸው እየተቆረጡ ወደ ውጭ የሚጋዙ ዛፎች ለአየሩ መዛባትና ለዝናብ አለመዝነብ የበኩላቸውን አስተዋፅዖ አድርገዋል ማለት ይቻላል። በተጨማሪም በአገሪቱ ውስጥ የመሬት አያያዝ ስርዓት ስለሌና በዘፈቀደ ስለሚታረስ ለችግሩ መባባስ በራሱ እንድ አንድ ምክንያት ሊታይ ይችላል። ይህ በእንደዚህ እያለ ነው የአገዛዙ ካድሬዎችና ትላልቅ ሹማምንቶች በየቦታው መሬትን በመቀራመት ዘመናዊ ፊዩዳሊዝምን በአገራችን ምድር ውስጥ እንደገና ለመትከልና ለማስፋፋት የሚሽቀዳደሙት። ይሁ ሁሉ የሚያሳየው አገዛዙ የቱን ያህል ለስልጣኔና ሁለገብ ለሆነ የኢኮኖሚ መሰናክል እንደሆነ ነው። ከዚህ ስንነሳ አገዛዙ ልማታዊ መንግስት የሚያሰኘው ምንም ነገር የለም። ስለሆነም የአገራችንን ዕድገትና መሻሻል፣ እንዲሁም ህብረተሰብአዊ መረጋጋት ከወያኔ ባሻገር ማየት ያስፈልጋል። ከዚህ ጋር ተያይዞ ማንኛውም ተቃዋሚ ነኝ የሚል ኃይል በውጭ ኃይሎች ላይ ያለውን አመለካከት ማስተካከል ይገባዋል። በውጭ ድጋፍ አንድ ጠንካራ አገር መገንባት አይቻልም። የሳይንስና የቴክኖሎጂ ባለቤትም መሆን አይቻልም። ከዚህም በላይ በጭንቅላት ውስጥ መቋጠር ያለበት መሰረታዊ ጉዳይ፣ ትግላችንና ህልማችን እነ ጋና፣ ኬኒያና ቬትናም የደረሱበት „ የዕድገት ደረጃ“ ላይ ለመድረስ ሳይሆን፣ ከነሱ እልቀን ለመሄድ ነው። በሌላ አነጋገር ዕውነተኛ ስልጣኔን ለማምጣት ነው። ስለሆነም የዕውነተኛ አገር ወዳዶች መመዘኛ ወይም መለኪያ፣ ስዊዘር ላንድ፣ አውስትሪያና ስዊድን ናቸው እንጂ ጋናና ቬትናም ሊሆኑ በፍጹም አይችሉም።

አማራጩ መንገድ በመንፈስ ተሃድሶ ላይ የተመሰረተ ሁለገብ የኢኮኖሚ ግንባታ ማካሄድ ብቻ ነው የሚያዋጣው። ለዚህ ደግሞ የመንግስቱ አወቃቀርና ሚና፣ እንዲሁም የቢሮክራሲው ሁኔታ መመርመር አለባቸው። በታሪክ ውስጥ እንደታየው መንግስታዊና ኢንስቲቱሽናዊ ሪፎርሞች ሳይደረጉ ጤናማና ሁለገብ ኢኮኖሚ በፍጹም መገንባት አይቻልም። ከዚህም በላይ ከኒዎ-ክላሲካልና ከኒዎ-ሊበራል የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች ተላቆ ግልጽ የሆነ ሰፊውን ህዝብ ወደ ስራ ሊያሰማራውና የአገርን ሀብት ለማንቀሳቀስ የሚያስችል የኢኮኖሚ ፖሊሲ ላይ ማተኮሩ የማይታለፍ ጉዳይ ነው። በተጨማሪም፣ በቀላሉ ተግባራዊ የሚሆኑና የህዝቡን መሰረታዊ ነገሮች ሊፈቱ በሚችሉ የቮኬሽናል ትምህርቶች ላይ መረባረብ እጅግ ጠቃሜ ነው። በመሆኑም፣ በጠቅላላው አገሪቱ ውስጥ ሊስፋፉ የሚችሉበትን ሁኔታ ማዘጋጀት። ለዚህ ጥሩ ልምድ ካላቸው እንደ ስዊዘርላንድ፣ አውስትሪያና ጀርመን ጋር የጠበቀ ግኑኝነት መመስረት። በዚህ መሰረት ሁሉም ነገር ለአገር ግንባታ በሚለው ላይ በመረባረብ፣ በተለይም የውጭ ካፒታልን እንቅስቃሴ መቆጣጠርና፣ ወደ ውስጥ ደግሞ ባንኮች ለአገር ግንባታ ፋይናንስ እንዲያደርጉና፣ ይህም ከምርት ክንዋኔ ጋር እንዲያያዝ ማድረግ። በአገር ግንባታ ለመሳተፍ ለሚፈልገው ገንዘብ ላለው ልዩ ስልጠና በመስጠት በትናንሽና በሚዲየም ሳይዝ ኢንዱስትሪዎች ላይ እንዲያተኩሩ ማድረግ። የመንግስት ዋናው ተግባር እነዚህን ሁሉ መልክ መልክ ማሲያዝ ሲሆን፣ በተለይም መሰረታዊ ነገሮች(Basic Needs) የሚሟሉበትን ሆኔታዎች ማዘጋጀትና መረባረብ። የአንድ መንግስትና የምሁሩ ታሪካዊ ኃላፊነት አገርን በጠንካራ መሰረት ላይ መገንባት ነው። ይህ ሲሆን ብቻ ነው ዕውነተኛ ነፃነት ሊገኝ የሚችለው። ኢኮኖሚያዊ ድቀት በሰፈነበት፣ ሰፊው ህዝብ ካለምንም ኔትወርክ ተሰበጣጥሮ በሚኖርበት አገር፣ የኮሙኒቲ ኑሮ እንዳይመሰረት እንቅፋት በተዘረጋበት አገር፣ እዚህና እዚያ ለነፃነታችን እንታገላለን የሚሉ „ድርጅቶች“ አንድን ህዝብ ራሱን እንዲችል ማድረግ አይቻልም። ከዚህ ስንነሳ የአገራችን የወደፊቱን ዕድል ከሶስት መሰረተ-ሃሳቦች አኳያ መንደፍና መመልከት የሚያስፈልግ ይመስለኛል። ይኸውም፣ 1ኛ) ጠንካራ-ህብረ ብሄር መመስረት፣ 2ኛ) አንድ ጠንካራ ህብረተሰብ ለመገንባት የሚያስችሉ እርምጃዎችን መውሰድ፣ 3ኛ) ለዚህ ደግሞ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ሰፋ ያለ የአገር ውስጥ ገበያ መገንባት። እነዚህ መሰረተ-ሃሳቦች በኢንፍራስትራክቸር፣ በከተማና በመንደሮች ግንባታዎች ተግባራዊነት የሚገለጹ መሆን አለባቸው። በእነዚህ አማካይነት ብቻ ነው አንድ አገር ከድህነትና ከልመና ልትላቀቅ የምትችለው። ለዚህ ደግሞ በየጊዜው የሃሳብ ልውውጥ፣ ጥናትና ክርክር ማድረግ ያስፈልጋል። ሃሳቦች በሚዳፈኑበት አገር፣ ጥቂት ግለሰቦች የሃሳብ ሞኖፖል በያዙበት አገር ዕውነተኛና ፍቱን ዕቅድ መንደፍ አይቻልምና።

ከሁላችንም የሚጠበቀው መሰረተ-ሃሳብ !

ከሶስት ሺህ ዓመት ጀምሮ ለስልጣኔና ለነፃነት የተደረገውን ትግል ስንመለከትና ስንመረምር የፍልስፍና፣ የሳይንስና የቲዎሪ መሰረት የሌለው ትግል አንድን ህዝብ የስልጣኔ ባለቤት ማድረግ እንደማይችል ነው። ይሁንና ግን አንድን ህዝብ የስልጣኔ ባለቤት ለማድረግ በሚደረገው ትግል ውስጥ ሁልጊዜ በሁለት መስመሮች መሀከል የጦፈ ትግል ይካሄዳል። ይኸውም ዕውነተኛ ስልጣኔና ስላምን በሚፈልገውና፣ ይህንን በሚጻረረው መሀከል የጦፈ ትግል መካሄዱ እንደ ተፈጥሮአዊ ህግ ሆኗል። በሌላ በኩል በቲራኖች ወይም ስልጣንን ላለመልቀቅ ያላቸውን ኃይል ተጠቅመው የህዝብን ትግል ለማፈንና ይህንን በሚቃወሙ መሀከል ያለው ትግል ግልጽ ነው። በታሪክ ውስጥ የሚያስቸግረው ትግል ቲራኖችን ወይም ጨፍጫፊዎችን ማጋለጡና መቋቋሙ አይደለም። ሁልጊዜ አስቸጋሪው ትግል በአንድ ጎራ የተሰለፉ ይመስል፣ ግን ደግሞ ዕውነተኛውን የስልጣኔ ፈለግ ለማሳሳትና፣ በዚህም በዚያም ብለው ስልጣን ላይ በመውጣት የአንድን ህዝብ የድህነት ዘመን በተዘዋዋሪ የሚያራዝሙትን ማወቁ ላይ ነው። በተለይም ምሁራዊና ሳይንሳዊ የውይይት ዘዴና ክርክር ባልተለመደበት እንደኛ ባለው አገር ውስጥ ሀቀኛውን የስልጣኔ አራማጅ፣ ሀቀኛ ካልሆነው ለመለየት በጣም አስቸጋሪ ነው። ሁለቱም አንድ ቋንቋ የሚናገሩ ስለሚያስመስላቸው፣ የዋሆች ሀቀኛውን መንገድ ካሳሳቹ ለመለየት የሚቸገሩበት ጊዜ አለ። ስለሆነም ነው በእኛ አገር ብቻ ሳይሆን በብዙ የሶስተኛው ዓለም አገሮች የህዝቦች ትግል የመጨረሻ መጨረሻ ሊወድሙና ህዝቦች እንደገና ለሌላ የትግል ዙር እንዲዘጋጁ የሚደረገው። ከደቡብ አፍሪካና ከሌሎች የነፃነት ትግል ከተካሄደባቸው የአፍሪካ አገሮች መማር የምንችላቸው ነገሮች አሉ። በተለይም በፐርሰናሊት ከልት አካባቢ ተገን የሚደረጉ ትግሎች አንድን ህዝብ በምንም ዐይነት ነፃ እንደማያወጡት ነው።

ስለሆነም ረጅም ጊዜ ቢፈጅም በሃሳብ ዙሪያ ከሚደረግ ትግል ውጭ ሌላ አማራጭ የትግል ዘዴ የለም። በተለይም አሁን ባለንበት በተወሳሰበ ዘመን፣ እንደ ዲሞክራሲ፣ መብትና ነፃነት የመሳሰሉት ጽንሰ-ሃሳቦች በዝርዝር መተንተን ያለባቸው መሰረተ-ሃሳቦች ናቸው። ከዚህ በመነሳት ነው ወደ ትልቁ የህብረተሰብ፣ የማህበረሰብ፣ የህብረ-ብሄር፣ የብሄራዊ ኢኮኖሚና የብሄራዊ ነፃነት ጉዳዮች ላይ መምጣት የምንችለው። በሌላ ወገን ግን የዲሞክራሲ፣ የመብትና የነፃነት ጥያቄዎች ከህብረተሰብና ከህብረ-ብሄር አስተሳሰቦች ውጭ ወጥተው ለብቻቸው ቢተነተኑና ትግል ቢደረግባቸው ትርጉም ሊኖራቸው አይችልም። ምክንያቱም ማንኛውም ግለሰብ መብቱንና ነፃነቱን በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ ብቻ ነው ተግባራዊ ሊያደርግ የሚችለው። በሌላ አነጋገር፣ የዲሞክራሲና የነፃነት ጥያቄ ወደ ብሄረሰብ ደረጃ ዝቅ ብለው የሚታዩ ሳይሆን፣ ምንነታቸው ግልጽና ተግባራዊ ሊሆን የሚችለው እንደ ህብረተሰብና እንደ ማሀበረሰብ በተደራጀ ህዝብ ውስጥ ብቻ ነው። ከዚህ ስንነሳ አንድ ግለሰብም ሆነ ህዝብ ዕውነተኛ ነፃነቱን ሊቀዳጅ የሚችለው እንዲያው ከአንድ አረመኔያዊ አገዛዝ በመላቀቁ ብቻ ሳይሆን፣ የመጨረሻ መጨረሻ ኑሮውን ለማሻሻል የግዴታ በሳይንስና በቴክኖሎጂ የተመሰረተ ኢኮኖሚ ሲገነባለት ብቻ ነው።

በመሆኑም ትግላችን በብሄረሰብና በቡድን ዙሪያ የሚደረግ ሳይሆን፣ ህብረተሰብአዊና አገራዊ ባህርይ እንዲኖረው ያስፈልጋል። በአንድ አካባቢ የሚደረግ እንቅስቃሴም ትርጉምነቱ ግልጽ ሊሆን የሚችለው ብሄራዊና ህብረተሰብአዊ ባህርይ ሲኖረው ብቻ ነው። በክልል ደረጃ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች በሳይንስና በፍልስፍና እንዲሁም በቲዎሪ በመደገፍ ከአጠቃላዩ የህብረተሰብ ጥያቄ ጋር መቀናጀትና መስመር መያዝ አለባቸው። ማንኛውም ታጋይ ነኝ እያለ ብሄረ-ሰቡንና ሃይማኖትን ተገን አድርጎ እዚህና እዚያ ቢንቀሳቀስም፣ ትግል ሳይንሳዊና ፍልስፍናዊ መሰረት እስከሌለውና ከሌሎች የህብረተሰብ ጥያቄዎች ጋር እስካልተቀናጀ ድረስ አንድ ብሄረሰብ የፈለገውን ያህል ቢንቀሳቀስም የመጨረሻ መጨረሻ ትግሉ በጥቂት ጮሌዎች ተነጥቆ የድህነተ ዘመኑ እንዲራዘም መደርጉ የማይቀር ጉዳይ ነው።

ስለሆነም የአገራችንን ጉዳይ በሚመለከት፣ ከህብረተሰብ እስከ ማህበረሰብ፣ ከብሄራዊ ነፃነት እስከ ህብረ-ብሄርና እስከብሄራዊ ኢኮኖሚ ድረስ የምንከራከርባቸው አያሌ ነጥቦች አሉ። በተለይም የዛሬው አገዛዝ ከወደቀ በኋላ ህብረተሰብአችን በምን መልክ መደራጀት አለበት፣ ከመሰረታዊ ፍላጎቶች መሟላት አልፈን እንዴት አድረገን በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ጠቅላላውን ህዝብ የሚጠቅም ኢኮኖሚ መገንባት እንችላለን? በሚሉት መሰረተ-ሃሳቦች ላይ መወያየትና መከራከር አለብን። በእነዚህ ሃሳቦች ላይ ከሞላ ጎደል ግልጽነት እስከሌለ ድረስ ህዝባችን የሚመኘውን ዕውነተኛውን ነፃነት ሊጎናጸፍ በፍጹም አይችልም። ከዚህ ስንነሳ ወደ ውጭ ወጥተንና እየተገናኘን በአያሌ ነጥቦች ላይ መከረካርና መወያየት አለብን። ሀቀኛውን የትግል ዘዴና ውጤት አምጭውን ከአሳሳቹ ለይተን ለማወቅ ፊት ለፊት ተገናኝተን መከራከር አለብን። ይህ አንደኛው ሲሆን፣ በሁለተኛ ደረጃ መታወቅ ያለበት ጉዳይ ዕውነተኛ ብሄራዊ ነጻነትና ኢኮኖሚያዊ ድል ለመጎናጸፍ የሚቻለው ይኸኛውን ወይም ያኛውን ኃይል በመለማመጥ አይደለም። በተለይም በእኛ በኢትዮጵያኖች ዘንድ ፈረንጆችን መለማመጥ ትልቁ የትግል ስልት እየሆነ መጥቷል። በሌላ ወገን ደግሞ ይህንን ባደረግን ቁጥር እየተናቅን እንደመጣን የገባን አይመስለኝም። ከዚህ ዐይነቱ „ዲፕሎማሲያዊ“ ከሚባለው አሳሳችና ድህነትን ከሚያራዝመው የትግል አካሄድ የግዴታ መላቀቅ አለብን። ደጋግሜ ለማሳየት እንደሞከርኩት ዓለም አንደኛው ኃይል ወይም ጥቂት ኃይሎች የባላይነትን ይዘው ለመቆየት የሚታገሉባት መድረክ ነች። አንደኛው አገር ወይም መንግስት ለሌላው አገር ነፃነትና ብልጽግና ጠበቃ ወይም አለኝታ ሊሆን አይችልም። በታሪክም ውስጥ ታይቶ አይታወቅም። አንድ ህዝብ ነፃነቱን ሊቀዳጅ የሚችለው በራሱ ጥረትና ኃይል ብቻ ነው። ለዚህ ደግሞ በምሁሩ ዘንድ፣ በተለይም በግንባር ቀደምትነት እታገላለሁ በሚለው ዘንድ የሃሳብ ጥራት ያስፈልጋል። በተለይም ይህ ዐይነቱ ግንዛቤ ለአንድ አገር ብሄራዊ የኢኮኖሚ ግንባታ መሰረታዊ እንደመሆኑ መጠን፣ በዚህ ዙሪያ ጠለቅ ያለ ሰፊ ውይይትና ክርክር ማድረግ ያስፈልጋል። በየትኛው የኢኮኖሚ ሳይንስ አማካይነት ነው ጠንካራ ብሄራዊ ኢኮኖሚ መገንባት የምንችለው? የሚለው መሰረታዊ ጥያቄ የመመለሱ ጉዳይ እጅግ አስፈላጊ ነው።
ፈቃዱ በቀለ
fekadubekele@gmx.de

The post የወያኔ ኢኮኖሚ፣ የገበያ ኢኮኖሚ፣ የካፒታሊስት ኢኮኖሚ፣ በመንግስት የሚደገፍ ኢኮኖሚ፣ ወይስ ሌላ? | ፈቃዱ በቀለ፣ ዶ/ር appeared first on Zehabesha Amharic.

“መሬትን መሸጥ፤ መለወጥ የኢትዮጵያን መሠረታዊ ችግር ይፈታል ብዬ ፍጹም አላስብም።” –ዶ/ር ፈቃዱ በቀለ

$
0
0

SBS Amharic Radio | አቶ አበራ የማነ አብ፣ ዶ/ር ፈቃደ በቀለና አቶ ገለታው ዘለቀ፤ “ኢትዮጵያ አዲስ የመሬት ስሪት ማሻሻያ ለውጥ ያስፈልጋታልን?” የሚለው የውውይት መድረክ አጀንዳችን ተሳታፊዎቻችን ናቸው። የግል አተያዮቻቸውን ያንጸባርቃሉ።

Part 2

Part 1

The post “መሬትን መሸጥ፤ መለወጥ የኢትዮጵያን መሠረታዊ ችግር ይፈታል ብዬ ፍጹም አላስብም።” – ዶ/ር ፈቃዱ በቀለ appeared first on Zehabesha Amharic.

“I Can’t Lie Anymore!“ |“ከዚህ በኋላ በቃኝ . . . ውሸት ሰለቸኝ”

$
0
0

alwashim
በጥላሁን ዛጋ fikireyohanis@yahoo.com

የካዛኪ ተወላጇ ኩዳይቤርጌኖቫ ልክ የዛሬ 12ዓመት በጸደይ ወር መገባደጃ ላይ እንደ አውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር በ2003 ዓም በሁለት የሃገሪቱና በአንድ የውጭ ቋንቋ ስርጭቱን ለ24 ሰዓታት በEutelsat አማካይነት በሚያስተላልፈው የካዛኪስታን ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ስትቀጠር ምኞቷ፣ ፍላጎቷና ህልሟ በሙያዋ ሃገሯን፣ ህዝቧንና የወጣችበትን ማህበረሰብ ማገልገል እንደሆነ ትናገራለች።

ካሃባር በሚባለው በቀጥታ በመንግስት ሹመኞች በሚዘወረው የዜና አገልግሎት ኤጀንሲ ውስጥ ለሚተዳደረው የካዛኪ ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ የብሪታኒያ ለንደን ዘጋቢ ለመሆን፣ በወቅቱ መዋቅራዊና ሌሎች የዜና ማሰራጫ ግብዓቶችን አደራጅቶ ዝግጅቶቹን በራሺኛ፣ በካዛኪና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች ከጀመረ ገና አንድ ዓመቱ በሆነው የካዛኪ የቴሌቪዥን ጣቢያ ስትቀጠር፣ ሩሲያ ዋና መዲና ከሚገኘው ሎሞኖሶቭ የሞስኮ ብሄራዊ ዩኒቨርሲቲ በፍልስፍና የዶክትሬት ትምህርቷን ባጠናቀቀች ማግስት ነበር።

በሩሲያዋ አስትራካን ክፍለ ሃገር ተወልዳ፣ እድገቷን በቤተሰቦቿ የስራ ጠባይ ምክንያት በዋና ከተማዋ ሞስኮ ያደረገችው የካዛኪ ብሄር ተወላጇ ቤላ ኩዳይቤርጌኖቫ፣ ላለፉት 12ዓመታት በዘጋቢነት፣ በሪፖርተርነት እንዲሁም በለንደንና አካባቢዋ የሚከናወኑ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ብሎም ዓለም ዓቀፋዊ ዜናዎችን እየሰራች ያሳለፈችበትን የጋዜጠኝነት ስራዋን፣ በፌስቡክ ገጿ ላይ በጻፈችው አንድ ሃረግ፣ እርግፍ አድርጋ መተዋን ገልጻለች።
እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በታህሳስ ወር 2015 የሚከበረውን የካዛኪስታን የነጻነት በዓል አስመልክቶ የሃገሪቱን እድገት፣ ልማትና አሁን ያለውና በፕሬዚዳንት ኑርሱልጣን የሚመራው መንግስት የሄደበትን የልማትና መልካም አስተዳደር ጎዳና የሚያንጸባርቅ ሰፋ ያለ ዘገባ እንድትሰራ ከሃገሪቱ የኢንፎርሜሽን /መረጃና/ ዜና ሚኒስቴር ቀጥተኛ ትእዛዝ ይደርሳታል፣ ለዚህ “የሃገርን ገጽታ ለሚገነባና” የመንግስታቸውን ህያውነት ለሚያረጋግጥ “ጮማ የቴሌቪዥን ዘጋቢ“፣ በሶሺዮሎጂ /በማህበረሰብ ጥናት/ የመጀመሪያ እንዲሁም በፍልስፍና ደግሞ የዶክትሬት ዲግሪዋን የጫነችው ኩዳይቤርጌኖቫን የሚያህል ተመራጭ ጋዜጠኛ እንዳልነበር የተረዱት በሚኒስቴር ማእረግ የሃገሪቱ የዜናና መረጃ ሚኒስቴር የሆኑት ጉምቱ ባለስልጣን በቀጥታ ወደለንደን ስልካቸውን መቱ።

ኩዳይቤርጌኖቫ ወዲያው መልስ አልሰጠችም፣ ጥቂት ላስብበት፣ ጊዜ ይስጡኝ አለች . . . ሚኒስቴሩ ዲስኩራቸውን ቀጥለዋል . . . ይህ ዘጋቢ ፊልም የሃገራችንን ገጽታ የሚገነባ፣ ምን ያህል በልማት እንደገሰገስን የሚያሳይ፣ መንግስታችን ደግሞ ለዚህ ምን ያህል ቁርጥኛ እንደሆነ ማሳየት የሚችል መሆን ይኖርበታል። ከዚህ በላይ መስማት አልፈለገችም፣ እሺ በቃ እስከነገ ላስብበት ብላ መልስ ሰጠች፣ ሚኒስቴሩ እርግጠኛ ናቸው . . . ትሰራዋለች . . . እሳቸውን ያህል ሰው ደውለው?

ሚኒስቴሩ በደወሉ በማግስቱ በኩዳይቤርጌኖቫ የግል የፌስቡክ ገጽ ላይ የሰፈረው የጋዜጠኛዋ ጽሁፍ ግን . . . ከቅርብ ወዳጆቿ አልፎ፣ ከ253 ሚሊዮን ህዝብ በላይ ይከታተለዋል ለሚባለው አድማጭ ተመልካች አስደንጋጭ፣ አነጋጋሪና በተቃውሞው ጎራ ያሉትን ወገኖች ደግሞ ጮቤ ያስረገጠ ዜና ነበር። “Enough is enough, I could not force myself to do a report saying Kazakhstan is a prosporous country with a brilliant leader . . .“

ካዛኪስታን ከቀድሞዋ የሶቪየት ሶሻሊስት ሪፐብሊክ ህብረት /USSR/ ራሷን ነጻ ያደረገችው ከሌሎቹ 14 የህብረቱ አባል ሃገራት ዘግይታ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1991 ዓም ነበር፣ ሃገሪቱ ነጻነቷን ካገኘችበት ዓመት ጀምሮ ላለፉት 26 ዓመታት በስልጣን ላይ በሚገኘውና በፕሬዚዳንት ኑርሱልጣን ናዛርባዬቭ በሚመራው አውራ ፓርቲ ሙሉ ቁጥጥር ስር ትገኛለች።

በልማታችን ኢዩሮኤዢያ ከሚባሉትና ራሺያን፣ ኡዝቤኪስታንን፣ ቤላሩስን፣ አርሜኒያንና ሌሎችን አስከትለን በቀዳሚነት እየገሰገስን ያለን ልማታውያን በመሆናችን ሃገሪቱን ለቀጣዮቹ ክፍለ ዘመናት መምራት ይገባናል በሚለው ዲኩራቸው የሚታወቁት ኑርሱልጣን፣ ተቃዋሚዎቻቸውን በማሳደድ፣ በማሰርና በሰብዓዊ መብት ይዞታ አስከፊነት ከዓለም ሃገራት የሚተካከላቸው እንደሌለ “ሪፖርተርስ ዊዝ አውት ቦርደርስ“ የተሰኘው ዓለም ዓቀፉ በሰብዓዊ መብቶችና በጋዜጠኞች መብት ዙሪያ የሚንቀሳቀሰው ተቋም የ2015ቱ ጥናት ሪፖርቱ ከ180 ሃገራት 160ኛ አስቀምጧቸዋል።

ሃገሪቱ ያሏት የዴሞክራሲ አቀንቃኝ ጋዜጠኞች በሙሉ ተሰደዋል፣ ተቃዋሚዎቻቸውም እኩሉ እስር ቤት ሲሆኑ ገሚሱ ደግሞ ከሃገር ወጥተዋል። ሃገሪቱ ለዜጎቿ የበረሃ እሳት ሆናባቸዋለች፣ ዜጎች የመናገር፣ የመሰብሰብና በነጻነት የመምረጥ መብት የላቸውም። ጋዜጠኞች ስራቸውን በነጻነት እንዳይሰሩና እራሳቸውን ሳንሱር እንዲያደርጉ አንዳንዴም በቀጥታ በመንግስት አካላት ሳንሱር እንዲያደርጉ ትእዛዝ ይወርዳል። ይልቁንም በ2012 በሃገሪቱ በExtrimisim /ጽንፈኝነት/ ስም የወጣው የጸረ ጽንፈኝነት አዋጅ ተቃዋሚዎችንም ጋዜጠኞችንም ለማዋከብ፣ ስራዎቻቸውን በአግባቡና በነጻነት እንዳይሰሩ ለመገደብና ለማፈን ሆን ተብሎ የወጣ አዋጅ ነው።

ስለዚህም ትላለች ኩዳይቤርጌኖቫ . . . “አሁን የወሰድኩት አቋም በቀጥታ ለብሪታኒያ መንግስትና ለዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ . . . አሁን በዚች ደቂቃ በሃገሬ ካዛኪስታን ምን እየተከናወነ እንደሆነ ለማሳየትና መልእክት ለማስተላለፍ ነው። 6 አባላት ያሉት የዘጋቢዎች ቡድን በብሪታኒያ ውስጥ እንገኛለን፣ በዚህ ስራ ውስጥ እስካለን እውነቱን መካድ ይኖርብናል፣ ካዛኪስታን በመልካም ሁኔታና በማደግ ላይ የምትገኝ ሃገር እንደሆነች በየእለቱ መደስኮር አለብን፣ ልክ እንደበጎች ወደተነዳንበት መጓዝ ነበረብን፣ የምንባለውን ሁሉ ለመቀበል ሁልጊዜ ዝግጁ መሆን ይጠበቅብን ነበር . . . እኔ ሃገሬን እወዳታለሁ ህዝቤንም እንዲሁ፣ ህዝባችን የተሻለ ህይወት እንደሚገባው አምናለሁ እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትና እውነተኛ የህዝብ ወኪሎች ያስፈልጉናል እውነተኛ የህዝብ እንደራሴዎች . . . “ዞምቢዎች ያልሆኑ“፣ እናም አሁን በቃኝ . . . ውሸት ሰለቸኝ . . . “ . . . ትላለች፣ የካዛኪስታኗ ጋዜጠኛ ቤላ ኩዳይቤርጌኖቫ . . . እኛስ ምን ትምህርት እንውሰድ ይሆን . . . ?

“ወኩሉ ዘተጽህፈ ለትምህርተ ዚአነ ተጽህፈ“ . . . “የተጻፈው ሁሉ ትምህርት ይሆነን ዘንድ ተጻፈ“

The post “I Can’t Lie Anymore!“ | “ከዚህ በኋላ በቃኝ . . . ውሸት ሰለቸኝ” appeared first on Zehabesha Amharic.

Sport: የአድናን ያንዩዣይ መመለስ  |ለማንቸስተር ዩናይትድ የሚያስገኙለት 5 ቁልፍ ጠቀሜታዎች

$
0
0

 

ቤልጂየማዊው ኢንተርናሽናል አድናን ያንዩዣይ የዘንድሮ ሲዝን የጀመረው ለማንቸስተር ዩናይትድ ጎል በማስቆጠር የታጀበ ጥሩ እንቅስቃሴን በማሳየት ቢሆንም በሆላንዳዊው አሰልጣኝ ሉዊ ቫንሃል ግን ከፒ ኤስ ቪ አይንደንሆቨን የገዙት ሜምፌስ ዴፓይን ውጤታማ ፉትቦልን ለማጉላት በመጓጓት ያንዩዣይን በውሰት ውል ወደ ቦሪሽያ ዶርትሙንዱ የመልቀቅ ውሳኔ ላይ ደርሰዋል፡፡ ያንን ውሳኔያቸውን በማስመልከት ቫንሃል በተደጋጋሚ በሰጡት መግለጫዎች ከጀርመን ቡንደስሊጋ ውድድር በመሳተፍ በቂ ልምድን አግኝቶ እንደሚመለስልኝ በመጓጓት ነው ቢሉም በተግባር ከታየው ለመረዳት ያስቻለው ግን የያንዣይ በውሰት ውል ማምረት ሶቱን አካሎች ማለትም ቦሪሽያ ዶትሙንድ ማንቸስተር ዩናይትድና ራሱ ተጫዋቹን ያልጠቀመ ሆኗል፡፡

januzai

ምክንያቱም ያንዩዣይ ለቦሪሽያ ዶርትሙድ የተሰለፈው በአራት ግጥሚያዎች ብቻ ነው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ብቻ የቡንደስሊጋ ግጥሚያው ነው ሌሎቹ ሶስት ጨዋታዎችን ያደረገው በዩሮፓ ሊግ ውድድር ነው፡፡ የዶርትሙንዱ አሰልጣኝ ለያንዣይ በበቂ ግጥሚያዎች የመሰለፍ እድልን ያልሰጡበት ምክንያት የሚገልኑት ግጥሚያዎችን ለማድረግ የስነ ልቦና ጥንካሬ አልታየበትም በማለት ነው፡፡

ይህ አባባላቸው በ20 ዓመቱ ቤልጅየማዊው ኢንተርናሽናል በቫንሃል ችሎታው ሙሉ እምነትን ባለማሳደሩ መጠነኛ የሆነ የመረበሽ መንፈስ እንደተፈጠረበት ነው ባሳለፍነው ሳምንት ውስጥ ግን ዶርትሙንድ የያንዩዣይን ለአንድ ዓመት የሚዘልቅ የውሰት ውልን ለማቋረጥ በመስማማት ሉዊ ቫንሃል ወደሚወደው ክለቡ ማንቸስተር ዩናይትድ መልሰውታል፡፡ ይህንን ተከትሎም የያንዩዣይ ወደ ኦልድትራፎርድ መመለስ ከጉዳቱ ይልቅ ጠቀሜታው የሰፋ እንደሚሆን በማመን አስተያየታቸውን የሚሰጡ ባለሙያዎች ተበራክተዋል፡፡ በተለይም የዛሬ ሁለት ዓመት ከማንቸስተር ዩናይትድ ፉትቦል አካዳሚ ወደ ዋናው ቡድን ለመሸጋገር የቻለው ቤልጅየማዊው ወጣት ወደ ኦልድትራፎርድ መመለሱ በአሁኑና በሲዝኑ መጨረሻ መካከል ለሉዊ ቫንሃል ቡድን የሚኖረውን ጠቀሜታዎችን የዴይሊ ሚረር የፉትቦል ተንታኞች ከዚህ በታች ባለው መልኩ ዘርዝረዋቸዋል፡፡

1. ጎል የማስቆጠር ተሰጥኦው

ማንቸስተር ዩናይትድ የዘንድሮን ሲዝንን ያጋመሰው ከዚህ በፊት በነበረው በተለይ ሁኔታ በበቂ ጎሎችን የማስቆጠር ረሃብ ተፈጥሮበት ነው፡፡  ለዚህ አንዱ ችግሩ የቡድኑ የአጥቂና አማካይ ክፍል ተጨዋቾች የጎል ማስቆጠር ሙከራዎችን የማድረግ ድርጊትን እያጡ ሲመጡ መታየታቸው ነው፡፡ ይህ ዥ ችግራቸው ማንቸስተር ዩናይትድ በእስካሁኑ ሲዝን ባደረጋቸው 20 የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያዎች 24 ጎሎቹ ብቻ እንዲኖሩት መንስኤ ሆኖታል፡፡ ያንዩዣይ ግን በሚፈጠሩለት ጎል የማስቆጠር እድሎችን ካለምንም ማመንታት ለመጠቀም ከርቀት ሳይቀር ጠንካራ ሹትን በመምታት ከፍተኛ ድፍረትን የተላበሰ ተጨዋች ነው፡፡

2. የሚያስገኘው ከፍተኛ ፍጥነት

በሉዊ ቫንሃል ስር በማንቸስተር ዩናይትድ የማጥቃት እንቅስቃሴ በመታየት ላይ ያለው ችግሮች ውስጥ ከፍተኛ ፍጥነቱ በጣት አንዱ ነው፡፡ ይህንን ችግሩን ለመቅፈረፍ ሲሉም ቫንሃል በዘንድሮው ሲዝን ዝውውር መስኮት ፔድሮ ባርሴሎና ለመግዛት ተቃርበው ነበር፡፡ ሆኖም ግን ፔድሮ በመጨረሻው ሰዓት ወደ ቼልሲ ማምራትን ምርጫው በማድረጉ ጥረታቸው ሳይሰምርላቸው ቀርቷል፡፡ ከዚህ አንፃር ሌላው ከፍተኛ ፍጥነትን የተላበሰ የማጥቃት እንቅስቃሴ ያለው ያንዩዠይን የውሰት ውሉን አቋርጦ እንዲመለስ ባደረጉበት ውሳኔያቸው ፔድሮን ሲያስፈርሙበት የቀሩበት ስህተታቸውን መጠነኛ የሆነ እርምትን የሚያስገኙለት እንደሚሆን ይታመናል፡፡

3. በተጋጣሚ ላይ የሚፈጠረው ጫና

ያንዩዣይ በተፈጥሮው በተጋጣሚ ቡድን የተከላካይ መስመር ተሰላፊዎች ላይ የኳስ ቁጥጥርን ይዞ በመሮጥ ከፍተኛ ጫና እንዲፈጠርባቸው የማድረግ ተሰጥኦው ከፍተኛ ነው፡፡ ይህ ተሰጥኦው የክለቡ ደጋፊዎች በመነቃቃት ለቡድናቸው ለሙሉሃይሉ የማጥቃት ተነሳሽነት እንዲኖው የማያቋርጥ ድጋፍን እንዲሰጡት የሚያስገድዳቸው ይሆናል፡፡

ምክንያቱም ያንዩዣይ በከፍተኛ ፍጥነት የታጀበ ድሪብሊንጎችን በሚያደርግበት ወቅት በኦልድትራፎርድ ተደናቂ ድባብ እንዲፈጠር ምክንያት ሲሆን መታየቱ የተለመደ ነው፡፡

4. ለማን.ዩናይትድ ስኬት ያለው ተቆረቋሪነት

ሉዊ ቫንሃል ከተተቹበት ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ማንቸስተር ዩናይትድ በፉትቦል አካዳሚ ያፈራቸው ዳኒ ዌልቤክና ቶም ክሌቨርሌይን የመሳሰሉት የራሱ የሆኑ ተጨዋቾችን ወደ ሌሎች ከክለቦች እንዳይመሩ ያደረጉበት ተግባራቸው ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ግን ያንዩዣይን የመሰሉበት ተግባራቸው ከዚህ ወቀሳ ራሳቸውን ማዳን እንዲጀምሩ የሚረዳቸው እንደሚሆን ይታመናል፡፡

ደግሞም ቤልጅየማዊው ኢንተርናሽናል በማንቸስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች በከፍተኛ ደረጃ የሚፈቀር ለክለቡ ስኬታማነት ከፍተኛ የሆነ የተቆርቋሪነት መንፈስን በመላበስ በእያንዳንዱ ግጥሚያዎችን ከፍተኛ በሆነ በማሸነፍ ወኔ የማድረግ ባህል ያለው በመሆኑ ነው፡፡ የቤልጅየማዊው ከፍተኛ የማሸነፍ ወኔ በዙሪያው ላሉት የቡድኑ ጓደኞች በድል የመነሳሳትን መንፈስን የሚፈጥርላቸው እንደሚሆን ይታመናል፡፡

5. ለማታ የሚሰጠው ጠቀሜታ

ሉዊ ቫንሃል በስፔናዊው ኢንተርናሽናል ሁዋን ማታ ተደናቂ ኳሊቲዎችን በግራ ክንፍ በኩል እንዲሰለፍ በማስገደድ እያባከኑት ይገኛሉ፡፡ ምክንያቱም ለማታ ይበልጥ ተስማሚ የሚሆንለት ጨዋታ ሚና ከፊት አጥቂ ጀርባ ባለው ቦታ ወደመሃል ገብቶ የሚጫወትበት ነፃነትን የሚያገኝበት ነው፡፡ በአንፃሩ ያንዩዩይ የበለጠ ውጤታማ ግልጋሎትን የሚሰጠው በግራ ክንፍ በኩል ግጥሚያዎችን በመጀመር ወደ መሃል ሰንጥቆ በመግባት በጠንካራ ቀኝ እግሩ የጎል ማስቆጠር ሙከራዎችን የሚያደርግበት ነው፡፡ ከዚህ አንፃር የያንዩዣይ መመለስ የማንቸስተር ዩናይትድ ግራ ክንፍን በመረከብ ወደ ማታ በሚመርጠው የጨዋታ ሚና በመሰለፍ ዕድልን ፈጠሮለት ነፃ እንዲወጣ የሚረዳው እንደሚሆን ይታመናል፡፡

 

The post Sport: የአድናን ያንዩዣይ መመለስ  | ለማንቸስተር ዩናይትድ የሚያስገኙለት 5 ቁልፍ ጠቀሜታዎች appeared first on Zehabesha Amharic.


በሐዋሳ የተቃውሞ ወረቀቶች ተበትነው አደሩ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በሐዋሳ ከተማ ትናንት ለሊት የተቃውሞ ወረቀቶች ሲበተኑ አደሩ:: በተለይ በመንግስታዊ ተቋማት; ፖሊስ እና ወታደሮች በሚኖርባቸው ቦታዎች እንዲሁም በየትምህርት ቤቱ የተበተነው ወረቀት እንደሚያሳየው የሕዝቡን መቆጣትና በ ስር ዓቱ መሰላቸቱን ነው::

Hawasa

የተለያዩ መፈክሮችን የያዘው ይኸው ወረቀት “ሙሰኛ መንግስት መልካም አስተዳደር የማስፈን አቅም የለውም!” “የዜጎች ጅምላ ፍጅት ዛሬውኑ ይቁም!”; “በግፍ ለተገደሉ ንፁሀን ዜጎቻችን ቤተሰቦች የደም ካሳ ይከፈል”; “የኢትዮጵያ ህዝብ ከወንጀለኛው ፋሽሽት የወያኔ መንግስት ጋር አይደራደርም!” ; “የኦሮሚያ ነፃነት ትግል የሁሉም ክልሎች ትግል አካል ነውና በሰላማዊ ሰልፍ እንደግፍ” እና “ህዝባዊ መንግስት ይቋቋም” የሚሉ መል ዕክቶችን የያዘ ነው::

አንዳንድ ወገኖች ወረቀት መበተኑ ዋጋ የለውም በማለት በየቦታው የሚደረጉትን ወረቀት ብተናዎች ቢቃወሙም መንግስት ሚድያውን ዘጋግቶና ተቆጣጥሮ ሕዝብ ድምጹ ሲታፈን በ እንዲህ ያለው ሁኔታ ወረቀት እየበተኑ ድምጽን ማሰማት የሚደገፍ ነው የሚሉ በርካቶች ናቸው::

The post በሐዋሳ የተቃውሞ ወረቀቶች ተበትነው አደሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

ፕ/ር ብርሃኑ ከቢቢኤን ራድዮ ጋር: በተለይ በሙስሊም ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ተናግረዋል |“ወያኔ የሙስሊሙን ጥያቄ መመለስ ያቃተው ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ስላልሆነ ነው”

በኢትዮጵያ ውስጥ ህዝቡ ፔፕሲ እንዳይጠጣ ተጠየቀ

$
0
0

12654111_767726366661154_1300336201884149680_n
(ዘ-ሐበሻ) በኢትዮጵያ ውስጥ አላግባብ የሕዝብን ሃብት ከሕወሓት መንግስት ጋር በመተባበር ዘርፈዋል እየተባሉ በሰፊው ተቃውሞ የሚቀርብባቸው ሼህ መሀመድ አላሙዲ ንብረት የሆነውን ፔፕሲን እና የፔፕሲ ምርቶችን ሕዝቡ ያለመጠጣት ተአቅቦ እንዲደረግ እንቅስቃሴ ተጀመረ::

በሶሻል ሚድያዎች እና በስልክ መል ዕክቶች በሃገሪቱ በሰፊው እየተካሄደ ባለው በዚህ ቅስቅሳ ‘ቦይኮት ፔፕሲ’ የሚል ጽሁፍ ያለበት እና ከአጠገቡም የአላሙዲን ምስል ያለበት ነው:: የዚህ ቅስቀሳ አስተባበሪዎች በአሁኑ ወቅት የኦሮሞ ሕዝብን እንቅስቃሴ እያካሄደ ያለው ሕዝብ መሆኑ ታውቋል::

በአማራ ክልል ከዚህ ቀደም አቶ አለምነው መኮንን የአማራውን ሕዝብ በስብሰባ ላይ ክብሩን በሚነካ መንገድ ከተሳደቡ በኋላ ሕዝቡ የብ አዴን ንብረት የሆነውን ዳሸን ቢራን አንጠጣም በሚል ቦይኮት መጥራቱ ይታወሳል:: አሁን አላሙዲ በኦሮሚያ የወርቅ ማዕድኑን ሳይቀር መውሰዳቸውን ተከትሎ በተጠራው ሕዝባዊ የአላሙዲንን ምርቶች የመጠቀም እቀባ በሌሎችም ላይ እንደሚቀጥል ይጠበቃል ተብሏል::

በሶሻል ሚድያዎች እና በኢትዮጵያ በተለያዩ ከተሞች ሕዝቡ ፔፕሲ እንዳይጠጣ/ መጠጣት እንዲያቆም የሚጠይቀው በራሪ ወረቀትን ከላይ ለግንዛቤ አቅርበነዋል::

በምርቶች ላይ ያለመጠቀም ተአቅቦ (ቦይኮት) የሰላማዊ ትግል አንዱ አካል መሆኑን ፖለቲከኞች ያሰምሩበታል::

The post በኢትዮጵያ ውስጥ ህዝቡ ፔፕሲ እንዳይጠጣ ተጠየቀ appeared first on Zehabesha Amharic.

በጋምቤላ ውጥረቱ አይሏል * እናት እና ህፃን ልጇ ተገደሉ * ፒኙዶ ከተማ የጦር አውድማ መስላለች (ፎቶዎች ስላሉ ከ18 ዓመት በታች ያሉ እንዳያነቡት)

$
0
0

Gambela 2(ዘ-ሐበሻ) የፌደራል መንግስት የኑዌር እና የአኝዋክ ብሄረሰቦችን ለማስታረቅ ከጋምቤላ በስተደቡብ 105 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው ፒኙዶ ከተማ ላይ ስብሰባ ጠርቶ ስብሰባው እየተካሄደ ባለበት ወቅት የኑዌር ብሄረሰብ አባላት ድንገት በወሰዱት እርምጃ እናት እና የ2 ዓመት ህፃን ልጇ ዛሬ መገደላቸውን የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ከስፍራው አስታወቁ::

ዘ-ሐበሻ በስልክ ያነጋገረቻቸው የዓይን እማኞች እንደሚገልጹት ፒኙዶ ከተማ የደቡብ ሱዳን አማጽያን የሪክ ማቻር ወታደሮች የሚኖሩባትና የስደተኞች ካምፕ የሚገኝበት ቦታ እንደሆነ ገልጸው ድንገት ስብሰባው እየተደረገ እርምጃውን የወሰዱት እነዚሁ የሪክ ማቻር ወታደሮች የሆኑ የኑዌር ብሄረሰብ አባላት ናቸው ብለዋል::

የአይን እማኞቹ በፎቶ ግራፍ አስደግፈው በላኩት መረጃ የከ እናት እና ልጅ በተጨማሪ ሌላም አንድ ሰው ሕይወቱ ማለፉን እና በርካታ ሰዎች መቁሰላቸውን ገልጸዋል:: የፌደራል መንግስት ሁለቱን ብሄረሰቦች ለማስማማት ስብሰባ ጠርቶ ኑዌሮች ድንገት እርምጃ ሲወስዱ የፌደራል ወታደሮች ግጭቱን ከማብረድ ይልቅ ዳር ቆመው ይመለከቱ ነበር ሲሉ እነዚሁ የአይን እማኞች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል::

በሌላም በኩል በጋምቤላ ኦሚንጋ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር ከ2 ቀናት የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት በጠሩት ስብሰባ ላይ ሕዝቡን ወክሎ በስብሰባ ላይ ሲናገር የነበረውና በቅጽል ስሙ ሶኒ ተብሎ የሚታወቀው ወጣት ዛሬ ባልታወቁ ሰዎች ወገቡን ተምትቶ በጋምቤላ ሆስፒታል ህክምና ላይ እንደሚገኝ ከስፍራው ያገኘነው መረጃ አመልክቷል::

በጋምቤላ በተለይም ከፓንጋ ወደ ፒኙዶ የሪክ ማቻር ስደተኛ ወታደሮች በከGambelaፍተኛ ሁኔታ የጦር መሳሪያዎችን እያመላለሱ እንደሚገኝም ለዘ-ሐበሻ የመጣው መረጃ ጨምሮ ገልጿል::

የጋምቤላውን ጉዳይ ደጋግመን እየተከታተልን እንዘግባለን::

 

 

The post በጋምቤላ ውጥረቱ አይሏል * እናት እና ህፃን ልጇ ተገደሉ * ፒኙዶ ከተማ የጦር አውድማ መስላለች (ፎቶዎች ስላሉ ከ18 ዓመት በታች ያሉ እንዳያነቡት) appeared first on Zehabesha Amharic.

በአውስትራሊያ ቭክቶሪያና አካባቢው ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች የቀረበ ሃገራዊ ጥሪ

“ኢትዮጵያ ሄጄ እናቴንና ልጄን በአይን የማገናኝበት ቀን ናፍቆኛል”–ዲና አንተነህ

$
0
0

በአገውኛ የሙዚቃ ስልት “በል ፈጥነህ ናማ” የሚለው ነጥላ ሙዚቃዋ እጅግ ተወዳጅ ያደረጋትና ከዚህ ቀደምም “ጋሜ ” እንዲሁም “አልችልም” የሚል ነጠላ ዜማዎቿን ለህዝብ አቅርባ የተሳካላት ዲና ከኢቢኤስ ቴሌቭዥን ከ እንጨዋወት ፕሮግራም ጋር ያደረገችውን ቃለምልልስ ያድምጡት::

The post “ኢትዮጵያ ሄጄ እናቴንና ልጄን በአይን የማገናኝበት ቀን ናፍቆኛል” – ዲና አንተነህ appeared first on Zehabesha Amharic.

በጋምቤላ ኢታንግ ወረዳ በተፈጠረ ግጭት በርካታ ጎጆ ቤቶች ተቃጠሉ

$
0
0

Zehabesha News
(ዘ-ሐበሻ) በጋምቤላ ክልል በኑዌሮች እና በአኝዋኮች መካከል የተፈጠረው እርስ በ እርስ ግጭት ካለ ፌደራል ፖሊስ ገላጋይነት እንደቀጠለ በአካባቢው የሚኖሩ ወገኖች ለዘ-ሐበሻ በስልክ ገለጹ::

ትናንት ዘ-ሐበሻ ባወጣችው መረጃ መሰረት የኑዌር ዘር ያላቸው የሪክ ማቻር ወታደሮች በስተኞች ካምፕ በሚኖሩባት ፒኙዶ ከተማ በተወሰደ እርምጃ 3 ሰዎች መገደላቸውን የዘገብን ሲሆን ዛሬ ባደረግነው የስልክ ውይይት የሟቾች ቁጥር ወደ 5 ማደጉን ለማወቅ ችለናል::

ይህን ተከትሎ በጋምቤላ ከፍተኛ የሆነ አለመረጋጋት ተፈጥሯል:: በዚህም መሠረት ከትናንት ማምሻውን ጀምሮ በኢታንግ ወረዳና በሌሎችም አካባቢዎች የአኝዋኮች ንብረት የሆኑ የማሽላ እና የበቆሎ እርሻዎች በ እሳት ጋይተዋል:: በተጨማሪም በመቶዎች የሚቆጠሩ ጎጆ ቤቶች በ እሳት ነደዋል::

በሌላ በኩል አኝዋኮችም እንዲሁ ጥቃት እንደፈጸሙ የሚገልጹት ዘገባዎች የሪክ ማቻር ወታደሮችና የደቡብ ሱዳን ስደተኞች የሚገኙበት አካባቢም እንዲሁ ቤቶች መቃጠላቸው ተዘግቧል::

የፌደራል መንግስት ጉዳዩን ለማረጋጋት ስብሰባ ከመጥራት ውጭ የወሰደው እርምጃ የለም የሚሉት እነዚሁ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች በሚቆጣጠራቸው ሚድያዎች ጋምቤላ መረጋጋቷን እና ሁሉም ሰላም መሆኑን እየዘገበ ነው::

የጋምቤላን ወቅታዊ ሁኔታ አሁንም ተከታትለን እንዘግባለን::

ላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ በግምት 3000 አካባቢ የሚደርሱ የአኝዋክ መኖሪያ ቤቶች በኑዌር በእሳት ተቃጥለዋል ፎቶ አለኝ እንዴት ልሰጣችሁ እችላለሁ ?

The post በጋምቤላ ኢታንግ ወረዳ በተፈጠረ ግጭት በርካታ ጎጆ ቤቶች ተቃጠሉ appeared first on Zehabesha Amharic.


አቡነ መልኬጼዲቅ በወቅታዊው ንትርክ ዙሪያ በቴሌ ኮንፈረንስ ማብራሪያ ሊሰጡ ነው

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በካሊፎርኒያ ውስጥ በሚገኝ አንድ ቤተርክርስቲያን ውስጥ ከሕዝብ ጥያቄ ቀርቦላቸው ሲመልሱ “በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ በኦርጋን መዘመር አለበት” ያሉትና ይህን ተከትሎም በርካታ ውይይት እንዲፈጠር ምክንያት የሆኑት አቡነ መልኬጼዲቅ በቴሌ ኮንፈረንስ ለህዝቡ ገለጻ እንደሚሰጡ ለዘ-ሐበሻ የተላከው በራሪ ወረቀት አመለከተ::

“በህጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ መሰረት ሰሞኑን በተዋሕዶ ሃይማኖት ሽፋን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ለማፈራረስ የተነሳውን በስም ማህበረ ቅዱሳን ተብሎ የሚጠራውን የግል ድርጅት ስውር አጀንዳውን የሚያጋልጥ እና ም ዕመናንን የሚያደናብሩበትን አንዳን ነጥቦችን ማብራሪያ የሚሰጥ ጉባኤ ተዘጋጅቷል” በሚል የተበተነው ይኸው ፍላየር ጉባኤው የካቲት 3 ወይም በፈረንጆች አቆጣጠር ፌብሩዋሪ 11, 2016 እንደሚደረግ ይገልጻል::

ፍላየሩን አስተናግደናል:- 12660316_802427726551884_117080678_n

 

The post አቡነ መልኬጼዲቅ በወቅታዊው ንትርክ ዙሪያ በቴሌ ኮንፈረንስ ማብራሪያ ሊሰጡ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

ደቡብ አፍሪካ ኢትዮጵያዊያን ሳይገደሉ የማይዉሉበት ሐገር መሆኑን ያዉቃሉ??

$
0
0
File Photo

File Photo

ከጉድሽ ወያኔ 
በደቡብ አፍሪካ ቢያንስ በአንድ ቀን ዉስጥ አንድ ወይም ሁለት ወገኖቻችን በዘራፊዎች ወይም እርስ በእርስ በሚነሳ ጸብ ወይም ተንኮል ሳይገደል አይዉልም።
ባለፈዉ ሳምንት እጅግ አሳዛኝ የሆነዉ ክስተት ቴምቢሳ ላይ የተፈጸመ ሲሆን ይህዉም የአጎቱን ልጅ ሰርግ ሰርጎ ነገ ሰርጉ ላይ መገኘት ሲኖርበት ዛሬ የተገደለዉ አነሞ የተባለዉ ወንድማችን ብዙዎችን አሳዝኖአል በወቅቱ አነሞ መኪናዉ ዉስጥ ሊገባ ሲል ዘራፊዎች ደርሰዉ መሳሪያ ግንባሩ ላይ ደቅነዉ መኪናዉን እንዲያስረክባቸዉ ሲጠይቁት ፍቃደኛ ሆኖ ሊሰጥ ባለበት ወቅት ላይ ሌላዉ ኢትዮጵያዊ ጓደኛዉ ተመልክቶ መሳሪያ አዉጥቶ ዘራፊዎቹ ላይ በመተኮሱ ሌቦቹ አነሞ ላይ ጥቃት የፈጸሙ ሲሆን ህይወቱም ያኔዉኑ አርፋለች።

በመሆኑም ባሳለፍነዉ ሳምንት እሁድ የአነሞ የአጎት ልጅ በሐዘኑ ማግስት የሰርግ ስነ ስረቱን በጸጋ ተቀብሎ ሊያሳልፍ ችሏል።

በተለያየ ስፍራ እየደረሰ ያለዉ ግድያ እየተባባሰ ባለበት በዚህ ወቅት ላይ ሌንዲላ በተባለዉ እስር ቤት በመኖሪያ ፍቃድ ሰበብ ታስረዉ የሚሰቃዩ ኢትዮጵያዊያን የድረሱልን ጥሪ መልስ አልባ ሆኖ አይምሯቸዉን እየሳቱ የሚንገላቱ ወገኖቻችን መበራከታቸዉን ከስፍራዉ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።


በተለይም የትግራይ ነጻ አዉጭ ቡድን ኢንባሲ በኒንዴላ በእስር ላይ ለሚገኙ ወገኖቻችን ሊሴ ፓሴ ወይም የምጓጓዣ ወረቀት ለምስጠት ባለመቻሉ እና አፋጣኝ ምላሽ ባለማድረጉ በየወቅቱ ኢትዮጵያዊያን እንደሚሰቃዩ የደቡብ አፍሪካ የስደተኞች ቢሮ ( DEPARTMENT HOME AFFAIRS ) ቅሬታዉን ማሰማቱን ቀጥሏል።


ደቡብ አፍሪካ በከፍተኛ ደረጃ የወያኔ ተቃዋሚዎች የሚንቀሳቀሱበት ሐገር ስትሆን ኢትዮጵያዊያን የፖለቲካ ስደተኞችንም በብዛት ተጠልለዉባት ይገኛሉ::  በዚያ የሚኖሩ ወገኖቻችንን በተቻለን ሁሉወደ ሐገራቸዉ በሰላም ይመልሳቸዉ ዘንድ የወያኔን መንግስት ግበአተ መሬት ያፋጥነዉ ዘንድ ተግተን እንድንሰራ ጥሪያችንን በኢትዮጵያ ስም እናቀርባለን!!
ድል ለኢትይጵያ ህዝብ ! !

The post ደቡብ አፍሪካ ኢትዮጵያዊያን ሳይገደሉ የማይዉሉበት ሐገር መሆኑን ያዉቃሉ?? appeared first on Zehabesha Amharic.

ሰማያዊ ፓርቲ በነገው ዕለት ሐውልቱ ሲመለስ ህዝቡ በቦታው እንዲገኝና ክብሩን እንዲገልጽ ጥሪ አቅርቧል

$
0
0

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

በአዲስ አበባ ቀላል የከተማ ባቡር ግንባታ ምክንያት ሚያዝያ 24/2005 ዓ.ም ፒያሳ ማዘጋጃ ቤት አካባቢ ከነበረበት ቦታ እንዲነሳ ተደርጎ የነበረው የአርበኛ አቡነ ጴጥሮስ የመታሰቢያ ሐውልት ከሦስት አመት ገደማ በኋላ ነገ ጥር 29/2008 ዓ.ም ወደነበረበት ቦታ እንዲመለስ የህዝቡ ትግልና ያላቋረጠ ጥያቄ አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ሰማያዊ ፓርቲ ገለጸ፡፡

abune_petros_statue_addis_ababa

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት የአቡነ ጴጥሮስ መታሰቢያ ሐውልት መጀመሪያውንም ከቦታው እንዳይነሳ ህዝቡ አሳስቦ እንደነበር በማስታወስ ሐውልቱ ወደነበረበት ቦታ እንዲመለስም በተከታታይ ጥያቄውን በማንሳት ለታሪኩና ለባለውለታዎቹ ያለውን ተቆርቋሪነት እንዳሳየ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ የቀላል ባቡሩ ስራ ሲታሰብ ዲዛይኑ ቅርሶችን በማይነካ መልኩ መሆን እንደነበረበት የተናገሩት ሊቀመንበሩ፣ ነገሩ ከሆነም በኋላ ቅርሱ ወደነበረበት ቦታ እንዲመለስ ህዝቡ ያደረገው ትግል የሚመሰገን ነው ብለዋል፡፡

መንግስት የባቡር ስራው ተጠናቅቆ ወደስራ መግባቱን ተከትሎ ሐውልቱ እንደሚመለስ ያስታወቀው ከህዝቡ የተነሳበትን ጥያቄ ተከትሎ እንጂ ለቅርሱ ከመቆርቆር እንዳልሆነ ከመጀመሪያው በባቡር ዲዛይን ስራው ወቅት (ቅርሱን እንደሚነካው እየታወቀ) ያሳየው ግዴለሽነት አመላካች መሆኑን ኢ/ር ይልቃል ገልጸዋል፡፡ ሐውልቱ በነገው ዕለት ወደቦታው ሲመለስ ህዝቡ ከ5፡00 ጀምሮ ፒያሳ አቡነ ጴጥሮስ አደባባይ በመገኘት ለሀገር ባለውለታው አርበኛ እና ለታሪኩ ያለውን ክብር እንዲገልጽም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አቡነ ጴጥሮስ በፋሽስት ጣሊያን ወረራ ወቅት ለጣሊያን እንዲገዙና ኢትዮጵያውያንም ለጣሊያን አሜን ብለው እንዲተዳደሩ እንዲቀሰቅሱና እንዲያሳምኑ በፋሽስት ቢጠየቁም እምቢ ለሀገሬ እና ለሐይማኖቴ በማለት እንኳንስ የኢትዮጵያ ህዝብ ምድሩም ለፋሽስት እንዳይገዛ በማውገዝ መስዋዕት የሆኑ ታላቅ አርበኛ ናቸው፡፡ አቡነ ጴጥሮስ ለዚህ የተጋድሎ ተግባራቸው ሐምሌ 16 ቀን 1938 ዓ.ም ዛሬ አቡነ ጴጥሮስ አደባባይ እየተባለ በሚጠራው ስፍራ መታሰቢያ ሐውልት ሊቆምላቸው ችሏል፡፡

The post ሰማያዊ ፓርቲ በነገው ዕለት ሐውልቱ ሲመለስ ህዝቡ በቦታው እንዲገኝና ክብሩን እንዲገልጽ ጥሪ አቅርቧል appeared first on Zehabesha Amharic.

“ኬንያ ከሚረዳኝ ሱዳን ከሚረዳኝ ደቡብ ሱዳን ከሚረዳኝ እንኳንም እንደወገኔ የማየው የኤርትራ ሕዝብ ረዳኝ”|ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ስለኤርትራ ይናገራሉ | Video

$
0
0

“ኬንያ ከሚረዳኝ ሱዳን ከሚረዳኝ ደቡብ ሱዳን ከሚረዳኝ እንኳንም እንደወገኔ የማየው የኤርትራ ሕዝብ ረዳኝ” | ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ስለኤርትራ ይናገራሉ

The post “ኬንያ ከሚረዳኝ ሱዳን ከሚረዳኝ ደቡብ ሱዳን ከሚረዳኝ እንኳንም እንደወገኔ የማየው የኤርትራ ሕዝብ ረዳኝ” | ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ስለኤርትራ ይናገራሉ | Video appeared first on Zehabesha Amharic.

ፊት ለፊት: ሳዲቅ አይመድ ይጠይቃል ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ይመልሳሉ | Video

$
0
0

ፊት ለፊት:
ሳዲቅ አህመድ ከፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጋር

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ለምን ከአሜሪካ ተነስተዉ በርሃ ገቡ?
የፕሮፌሰሩ ኤርትራ መግባት በአርበኞች ዘንድ ያመጣዉ ለዉጥ አለ?
በአርበኞች ግንቦት 7 አመራር ዉስጥም ይሁን አባልነት ለምን ብዙ ሙስሊሞች የሉም?
አርበኞች ግንቦት 7 የሙስሊሙን ሰላማዊ ትግል እንዴት ይመለከተዋል?
አርበኞች ግንቦት 7 በምን መልኩ የእምነት ነጻነቱን የተነጠቀዉን ሙስሊም መተባበር ይችላል?
አርበኞች ግንቦት 7 ሙስሊሞች በብዛት ባሉበት ክልሎችና ዞኖች መሬት ላይ ምን እያደረገ ነዉ?
ዜጎች በእኩልነት ታግለዉ ያላመጡት ዲሞክራሲ ለወደፊቱ አደጋ አይኖረዉምን?
ነጻነትን በሁለገብ ትግል ለማምጣት በሚደረገዉ ትግል ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ምን ይጠበቃል?

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live