Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የሰሞኑ ህወሃት ሕዝቡን አቅጣጫ የሚያስቀይስበት ዘዴ ከሽፏል ወይስ አልከሸፈም? –ከአንተነህ ገብርየ

$
0
0

TPLF 1ከሞላ ጎደል በዚህ ዓመት ህወሃት የሚያደርገውን ማምታታት አቅጣጫ የማስቀየስ ስልት ሕዝቡ የነቃበትና ርምጃውን በጥንቃቄ ያካሄደበት ስለሆነ በኃይል ከሚወሰድ የጉልበትና የግድያ ድርጊት በስተቀር ዓላማው ከሽፏል የሚል እምነት ስለአለኝ ይህችን መጣጥፌ ለንባብ አቅርቤያለሁ›

ህወሃት የሚመራው አገር አጥፊ ቡድን አንዱን ከሌላው ጋር በማናከስ፤በሃይማኖት፤በጎሳ እርስ በእርሳቸው እምነት እንዲያጡና በጥርጣሬ እንዲተያዩ ማድረግ የተቋሙ ዋና ፕሮግራም ሆኖ እየተሰራበት የመጣ ቢሆንም ከምርጫ 1997(2005)በኋላ በስውር ይካሄድ የነበረው ግድያ(silent killing methods) ተቀይሮ ወጣት ሽማግሌ ሴት ሕጻን የማይለይ ሕገ-አራዊት የሆነ መርህ በመከተል በኃይል አንበርክኮ ለመግዛት ከተጀመረ እነሆ አሥር አመታት አለፉት።

ከእውነት ጋር በፍጹም ላይገናኙ ወይም እውነትን ላለመናገር ጨክነው ቃል የገቡት የህወሃት መሪዎችና ግብረ-በላዎች ጧት የተናገሩትን በምሳ ሰአት ሲንዱት በምሳ ሰአት የተናገሩትን በእራት ሰአት እየካዱ የመገናኛ ብዙሃንን በቁጥጥር ስር አድርገው ዝባዝንኬ የበዛበትን የቅጥፈት ላዛናቸውን ሲያላዝኑ ተመልክተናቸዋል።ይህ መዋቅር ከላይ እስከ ታች ድረስ በነፍሰ ገዳዮች የሚመራ ሲሆን በሰላም ቀን ከሕዝብ ጋር አብሮ ለመኖር እንደማይችሉ ስለሚያውቁት በትንሹም በትልቁም አጋጣሚ ሁሉ ቀዳሚው መፍትሄያቸው መግደል ነው። የድርጅቱ አወቃቀር የኮሚኒስት ርዕዮት ዓለም ይከተሉት የነበረው አይነት ልክ እንደ (Joseph Stalin red terror system) ሲሆን የምእራቡ አለም አገራትም በህወሃት ተጭበርብረው ድጋፋቸውን እየቸሩ ዘልቀዋል። አያውቁትም ማለቴ አይደለም እያወቁ ግን ጥቅማቸውን የሚያስጠብቅ እስከተገኘ ድረስ ስለኢትዮጵያና ስለኢትዮጵያ ህዝብ እስራት ሞት ስደት ርሃብ አጠቃላይ የዲሞክራሲያው ስርአት መጨለሙ ምናቸው አይደለም።

ከርእሱ እንዳልወጣ ጥቂት ነገሮችን ማከል ስለአለብኝ  ይቅርታ፦ባለፈው በአንድ ጹሑፍ ላይ ብቅ አድርጌ የተውኳት ነገር ነበረች እንደሚታወቀው በዓለማችን ሙስና ተስፋፍቷል(corruption is spreaded in the world )  በተለይ ደግሞ በአፍሪቃ አንድ እንኳን ከዚህ ግባ የሚባል ጤናማ የአገር መሪ አለመኖሩ ግልጽ ነው። በመልካቸው እኛን የሚመስሉት ከአንድ ጎሳ የበቀሉ ጠባቦችና ዘረኞች ከሁሉም በላይ ሥልጡንና እንደፍልፈል የሀገር ሀብት ዘርፈው ወደ ትግራይ ወይም ሰርአቱ አገግሞ መሰንበት ከቻለ እስከ እለተ ሞታቸው በዝርፊያ ለመኖር የተሰማሩ ናቸው። እንደምናውቀው በየመን ፤ደቡብ ሱዳን ፤በሱዳን በኬኒያ ፤ እንዲሁም በመላው የአፍሪቃ አገሮች ማለት ይቻላል የህወሃትን ስርዓት ተቃውመው ወደ ጎረቤት አገር የሚሸሹ የፖለቲካ መሪዎችና አባላት፤ጋዜጠኞች፤የኢኮኖሚ ስደተኞች ሁሉም እየተለቀሙ ተመልሰው ለህወሃት ይሰጣሉ ከህወሃት ምን እንደሚጠብቃቸው ይታወቃል። እዚህ ላይ አንድ ነገር አስታውሻችሁ ልለፍ አዲሱ አበበ ከአሜሪካ ራዲዮ ጣቢያ የአማርኛው ክፍል ዝግጅት አንድን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኃላፊ ሲያነጋግር በግባባት ሳይችሉ ቀሩና ፖሊሱ አምጥቸ እዘጋሃለሁ አይነት ነገር ተናገረ አዲሱ እኔ እኮ ያለሁት አሜሪካ ነው ሲለው ከሰማይ ብትወጣም አምጥቸ እዘጋሃለሁ ብሎት አረፈ።እንደዚህ አይነቱ ነው እንግዲህ የሕዝብን ደህንነት ይጠብቃል ተብሎ በኃላፊነት ተቀምጦ የምናገኘው።

 ለምንድን ነው ይህ የሚሆነው ሲባል የህወሃት ደህንነት መምሪያ በሚስጢር የያዘው ጉዳይ ነው የሚባለው። የአፍሪካ መሪዎች ወደ አዲስ አበባ ሲባል ለአፍሪቃ ሕበረት ስብሰባም ሆነ ለተየያዩ ጉዳዮች የሚያስኬድ ምክንያት ሲገኝ በጣም ደስተኛ ሆነው ለመዝናናት እንደሚመጡ አንድ ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቅ በቅርቡ ከኢትዮጵያ የመጣ ሰው አጫውቶኛል።ይህ  ቸርነት ወይም ድግስ ለአፍሪቃ መሪዎች ብቻ አይደለም ለምእራባውያንና ለዐረቦችም የሚደረግ ነገር ነው።ለሁሉም መሪዎች በሚኖሩበት ቆይታ አስፈላጊው ነገር ሁሉ በኢትዮጵያ ሕዝብ ሀብት ይሟላላቸዋል።ከስብሰባ በኋላ በአፍሪቃ ሕብረት አዳራሽ ከቆንጆም ቆንጆዎቹ ሴቶች ተመርጠው በጋድም ይቀመጣሉ እያንዳንዱ የአፍሪቃ መሪ የፈለጋትን ሴት እንደ ዕቃ አንስቶ ይወስዳታል ያማግጣታል።የገንዘብ ችግር የለም ያች ስጋዋን የሸጠች ሴት ከመኪና የተለየውን ከቤትም ትልቅ ዋጋ የሚያስከፍለውን ይገዛላታል።ገንዘቡ የተገኘው ከአፍሪቃ ምስኪን ሕዝብ እንደሆነ አይዘነጋም።ለዚህ አይነቱ መስተንግዶ ምላሹ ደግሞ የህወሃት አረመኔያዊና አምባገነናዊ ስርአት እንዲቆይ የአፍሪቃ መሪዎች ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እያነቁ ለዚህ ሰው በላ ቡድን ማስረከብ ነው አበቃ ተከተተ።

ወደ ርእሴ ስመለስ የኢትዮጵያ ሕዝብ በ1997 ምርጫ ህወሃትን ሲያሰናብት የተወሰደው ርምጃ ሁላችንም የምናውቀው ነው ከዚያም ተከትሎ ህወሃት ኮሮጆ በመዝረፍ በጉልበት ተመርጫለሁ አለ። ሕዝቡ ድምጻችን ተሰርቋል ይመለስ ብሎ ጠየቀ መልሱ ግድያ እስራት ስደት ሆነ ይህን ለማዘናጋት ሲባል አቅምን ያልመጠነ ሙያዊ ጥናት ያልተደረገበት ከአጎራባች አገሮች ጋር ጦርነትን የሚያጭር እቅዶች ወጥተው በአዋጅ ተነገሩ የሕዳሴው ግድብ፤የስኳር ፋብሪካ ኮርፖሬሽን ኧረ ምኑን ብየ ልጥቀሰው?ያ! የሕዝብን ሀብት ጨርሶ ለማሟጠጥ የሕዝቡ አመለካከት በዚህ ላይ እንዲያተኩር ለማድረግ ነበር።ሊሆን አልቻለም።የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳም እንዲሉ ሕዝቡ ሳንፋረድ እንዴት ብሎ አላቸው።ያ እያደገ ስር እየሰደደ በልብ የታመቀው እምቢኝተኝነት እግር አውጥቶ መንቀሳቀስ በጀመረበት ዓመት ዘንድሮም እንደዚሁ አስደንጋጭ ድርቅና ርሃብ በመላ አገሪቱ ሲያንዣብብ የሚያስከትለውን መዘዝ የተገነዘቡት ገዥዎቻችን የኢትዮጵያን ለም መሬት ለሱዳን አሳልፈን መስጠት አለብን ብለው አገር ይያዝልን ዑዑታቸውን ለቀቁት፤አዲስ አበባን ማስፋት አለብን ብለው ሕዝቡን ማፈናቀል ጀመሩ።ያለ ወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ሕዝብ ፍላጎትና ውሳኔ የወልቃይት የጠገዴ የጠለምት መሬት ወደ ትግራይ እንዲካለል ያደረገው ኢፍትሃዊና አፋኝ በዘር ማጥፋት ጉዳዩን አዳፍኘ አስቀረዋለሁ ያለው ህወሃት እሣት ከነበረበት ረመጥ አይጠፋውም እንዲሉ የቀደሞቹም ሆነ የአሁኖቹ የአካባቢው ተወላጆች ፋና ወጊ መፈክራቸውን ከፍ አድርገው ይዘው እኛ ጎንደሬዎች ነን ፤እኛ አማራ እንጅ ትግሬዎች አይደለንም ብለው ሞገቱ ።ለሱዳን ይሰጣል የተባለው ለም መሬትም ወልቃይትን ጨምሮ በመሆኑ ሁሉም ነገሮች ተያይዘው ሕዝቡን ማሰባሰብ ማስተሳሰር ጀመሩ ገዥዎች ተራወጡ አስፈራሩ ሕዝብ ጥያቄውን እስካልተመለሰ ድረስ እረፍት የለም መብታቸን ለማስከበር የሚከፈለውን ዋጋ እንከፍላለን በለው እንቅጩን ተናገሩ። ሕዝብ አምኖባቸውና ጥያቄየን አቅርበው መፍትሔ ያመጡልኛል ያላቸውን ኮሚቴዎች መርጦ ከላይ እስከ ታች ላለው ይህወሃት ቡድን አቀረበ ኮሚቴዎቻችንን አስረው ለማስፈራራት ሞከሩ፤ይቅርታ ጠይቁን አሉ ማን ነበርይቅርታ መጠየቅ የነበረበት?? ግድ የለም የሚሆነውን እናያለን ትግሉ ግን አይቆምም። የቅማንት ሆዳሞችን በማሰለፍ ከአማራው ጋር ለማጋጨትና ትኩረት ለሱዳን በሚሰጠው መሬት ጉዳይ ላይ እንዳይሆን አላስፈላጊ ደም አፋሰሰ ዘመዶቼ ብልጦች ናቸው እኛ በደምና በሥጋ የተዋህድን ስለሆንን ጣልቃ አትግቡብን ብለው ሞገቱ አገር ቤት ያሉትን ሆዳሞችን ሆነ በውጭ የተደራጁ የህወሃት አጫፋሪ የቅማንት ተወላጆችን አፋቸውን አስያዙዋቸው።

እያንዳንዳቸውን ለይተን ስንመለከት፦አዲስ አበባን ለማስፋት የተዘጋጀው እቅድ(master plan) ብዙ ሲመከርበት ቆይቶ ከአመት በፊት በዚህ እቅድ ምክንያት በርካታ የአምቦ ወጣቶችና ተማሪዎች ተቃውሞ አድርገው በርካታ ለጋ የሆኑ ወጣቶች ተገደሉ በአመቱ ደግሞ ዘንድሮ ይህን ጉዳይ ይዘው ብቅ አሉ በመላው ኦሮሞ ክልል የሚገኙ ተማሪዎችን አስነሳ በአንድ ጊዜ እንደ ሰደድ እሣት ተቀጣጥሎ መላ ኢትዮጵያውያንን አስቆጣ የበርካታ ወጣቶችን ሴቶችና ሕጻናት ሕይወት ቀጠፈ ማስተር ፕላኑ ቆሟል ተባለ እስከመቼ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ወይስ ለተወሰነ ጊዜ ጥርት ያለ መልስ ሳይሰጡ እያድበሰበሱ ለማቆየትና በሌላ ስልት ገብቶ የተፈለገውን ጥቅም ለማሟላትና አዲስ አበባ የጥቂት የህወሃት ባለሥልጣናት መናኸርያ እንድትሆን ለማድረግ ወይም በሌላ መንገድ ብጥብጡ ከቁጥጥር ውጭ እንዲሆንና ሥርአት አልበኝነት እንዲሰፍን በዚህም ምክንያት አንዳንድ የመገንጠል አባዜ ላለባቸው በሩን ለመክፈት ያለመ ይመስላል።ለዚህ ይመስለኛል ሌንጮ ለታ ከየትም ከርሞ ወጣቶች ባስመዘገቡት ድል ባለቤት ለመሆንና አመራር እየሰጠ ያለ ለመምሰል ብቅ ማለት የጀመረው። አያ ጅዋርም በካድሬው በሠራዊቱ በደህንነቱ ትግሉ እንዲደገፍ ተገቢውን ሥራ ሠርተናል ብሎናል ያም ሆነ ይህ ሌንጮ ለታ ያሰበው ኦሮሞን የመገንጠሉ ቅዥት ይሁን አባይ ጸሐየ የኦሮሞ ተወላጆችን በማፈናቀል ከሕዝብ በዘረፈው ገንዘብ ዘመናዊ ፎቆችን እያሰራ የማከራየቱ ሥስታም አስተሳሰብ ነቄዎቹ የኦሮሞ ወጣቶች ቀልድህን ወደዚያ በል አገራችን ጥለን የት እንድንሄድ ትፈልጋለህ? በማለት ሞትን ተጋፈጡት አሁንም እየሞቱ ነው ሞታቸው ግን የውሻ ሞት አይደለም።ነጻነትን ሊያስጨብጥ የሚችል ትግል ነው እየተካሄደ ያለው።ይህ ትግል የሚፈልገው አንድ ነገር ብቻ ነው እሱም ትግሉ አገር አቀፋዊ እንዲሆን በሳል በሆኑ የፖለቲካ መሪዎች አቅጣጫ እየተሰጠው እንዲጓዝ ማድረግ ነው።

ህወሃት ጠዋት ከመነሻው ጀምሮ የራሱ ከሆነው የኢኮኖሚ ችግርና የትግራይ ምድር ለምርት የታደለ ባለመሆኑ ምክንያት ለም የሆኑትን የኢትዮጵያ ክፍሎች በቅድሚያ በቅርብ ያሉትን ከዚያም የሩቆቹን ለመያዝና የኢኮኖሚ ችግራቸውን ለማራገፍ ከማሰብ በዘለለ ሌላ ከኢትዮጵያ ሕዝብ የተለየ የደረሰ ጭቆና አለመኖሩና ለትግል የሚያበቃ ምክኒያታዊ አጀንዳ ሳይኖረው በቅጥረኝነት የተነሳና የባእዳንን ፍላጎት ስኬታማ ለማድረግ ስለሆነ ለኢትዮጵያ የሚበጅ ነገር ይኖረዋል ተብሎ የሚታሰብ አልነበረም ልክ እንደ አዲስ አበባው የመሬት ወረራ በሰ/ውሎና ጎንደር ትግራይን የማስፋፋትና የእዚህ አካባቢ ነዋሪዎችን በማፈናቀል ትግሬዎችን በማስፈር ትልቋን ትግራይ የመገንባት ጉዳይ ጋር በተያያዘ መተከልን ከጎጃም ራያ አዘቦ ከወሎ ጠለምት ጠገዴ ወልቃይት እንዲሁም የምእራብ አርማጭሆ በከፊል ከጎንደር ወደ ትግራይ አስገብቶ ትግሬዎች ሆናችኋል በማለት የተስፋፊነት ተግባሩን መፈጸም ነበር። የሕዝብ ይሁንታ ባያገኝም በቁርቁስ ተፋጠን ያለንበት ሰአት ነው። ይባስ ብሎ ሰፊና ውሃ ገብ የሆነውን ለም መሬት ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት ከመቸውም ጊዜ በላይ ህወሃት ፍጥነት የጨመረበት ወቅት አሁን ነው። ይህ ሁሉ የሚሆነው ለምንድን ነው ሲባል የሁላችንም የተለያየ ምክንያት ሊኖረን ይችላል ህወሃት እውን ይህን መሬት ለሱዳን አሳልፎ የመስጠቱ ጉዳይ በጊዜያዊነት ወይስ በቋሚነት? የሚለውን ጥያቄ ትተን በድርቁና ድርቁ ባስከተለው ርሃብ ምክንያት አንዳንድ ያልተጠበቁ ድንገተኛ የሕዝብ ቁጣዎች መሪዎቻቸውን ለማስወገድ የተነሱበት ሁኔታዎች ስለነበሩ የሕዝብን አስተሳሰብ አቅጣጫ ለማስቀየስ ጉዳዩ አሁን ቢነሳ ብዙ ጨዋታ ልንጫወት እንችላለን ከሚል ስልት ነው ብየ አምናለሁ።1966እና 1977 እንመልከት።የመስጠቱ ጉዳይ እንደተጠበቀ ሆኖ ማለቴ ነው።

የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጉዳይ የጎንደር ሕዝብ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ጉዳይ በመሆኑ ሱዳን እኛ የምንጠይቃት  እንጅ ከኢትዮጵያ የምትወስደው ኢትዮጵያን የምትጠይቅበት ምንም አይነት መሬት የላትም እኔ ከዚህ አካባቢ ከበቀሉት ተወላጆች አንዱ ነኝ አካባቢውን አበጥሬ አውቀዋለሁ የእኛና የሱዳኑ ድንበር የት እንደሆነ በሚገባ የማውቀው መሆኔን ህወሃቶች ጠንቅቀው ያውቁታል በዚህም ምክንያት ለመጀመርያ ጊዜ ከሱዳኑ ልኡክ ጋር የጋራ ድንበር የሚባለውን ለማየት በ1977 ዓ/ም ምህረቴ መለሰ ከሰሜን(ደባርቅ) የዞኑ ክንስትራክሽን ዘርፍ ኃላፊ ፤ታረቀኝ እማኙ ከአለፋ ጣቁሳ የዙኑ የብአዴን የጋራ ኮሚቴ አባል ፤ደሳለኝ አሰሜ እስቴ  የታች አርማጭሆ ወረዳ ም/ ሊቀመንበር ፤ሌላው ደሳለኝ ደብረታቦር የመተማ ወረዳ ሊቀመንበር ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ሱዳን መሶሎኒ የሚባል ትግሬ በመስፍን አማረ እንዲመራ ሲዋቀር የመሬቱ ባለቤት ይህን ጉዳይ የሰማሁት ቡድኑ ሲመለስ ከአዘዞ አየር ማረፊያ ስልክ ተደውሎ ለቡድኑ አልጋ እንዲያዝላቸው እንዳደርግ ካደረጉ በኋላ ነው ጉዴን የሰማሁት እዚህ ላይ ጠቁሜ ማለፍ የምወደው ቢኖር መስፍን አማራ የሰሜን ምእራብ የኮር አዛዥ እኔ ለምን በኮሚቴው ውስጥ እንዳልገባሁ ሲጠይቅ አንዱ የአዲሱ ለገሰ ግብር ሰብሳቢ ፈጠን ብሎ እሱን በዚህ ኮሚቴ ውስጥ ማስገባት ማለት ሄደህ ጦርነት ግጠም ማለት ነው ብሎ ለመስፍን መለሰለት።ዛሬ እንዲህ ሊርቀኝ ያኔ ግን ይጀምሩትና እንተያያለን ድንበሩ ሲካለል የሚፈላውን ጉድም ራሳቸው ጠንቅቀው ያውቃሉ ለጊዜው በመከላከያ ኃይል ተመክተው ድንበሩን ሊከልሉት ይችሉ ይሆናል በሚል ነበር የምመለከተው ። ይህ ጉዳይ ወደ ተግባር አፈጻጸሙ ከተገባ መጀመርያ ሱዳንን በጣም ይጎዳታል ቃታ ከተከፈተ ማቆሚያው የት እንደሆነ ያውቃሉ።የእኛ ሕዝብ በህወሃትየመከላከያ ሠራዊትና በሱዳን ጦር በሚጠመድ ሴራ ጉዳት ይደርስበታል ድንበሩን ግን በኃይል ይከብራል ። ህወሃት ያኔ የሜዳ ጦጣ ነው የሚሆነው ከኢትዮጵያ ሕዝብ ሥር ነቀል በሆነ መንገድ ይነጠላል፤ከሱዳን ጋር ያለው ወዳጅነትም ያከትማል የወልቃይቱ ጉዳይ ትልቅ የትግል መድረክ ከፍቷል ከሁኔታው እንደሚታየው የወልቃይት ሕዝብ በድል አድራጊነት እንደሚዘልቅ ደፍሮ መናገር ይቻላል።

አማራውን ለዘመናት አብረውት ከኖሩት ቅማንቶች ጋር ለማጋጨት የህወሃት ቡድን የሄደበት መንገድ ከሁለቱም ወገን ደፍሮ የሚገባበት ባለመኖሩ እንጅ ያ ሕዝብ ለህወሃት ጀሮ የሚሰጥ አልነበረም ጥቂት እበላ ባዮች ደግሞ ያሰቡት ሳይሳካ እኛ ሳንደርስባቸው ራሱ ህወሃት እንደሚውጣቸው ግልጽ ነገር ነው።በተመሳሳይ ሁኔታ በኑዌሮችና በአኝዋኮች ላይ ሰሞኑን የተጫረው የህወሃት እሳትም እንዲሁ የአቅጣጫ ማሳሳቻ ዘዴዎች ድጋፍ ሰጭ እንዲሆን የታሰበ ቢሆንም ሁለቱ ክፍሎች ሊነቁና በፍጥነት ችግሩን ሊያበርዱት ይገባል ምክንያቱም ህወሃት አሁን ያለበት ደረጃ አንድ እግር ከውጭ አንድ እግር ጉድጓድ ውስጥ ስለሆነ በዚህ በሞተ ሰአት የታሪክ ጠባሳ ጥሎ ማለፍ ከኢትዮጵያውያን የሚጠበቅ ተግባር አይደለምና።ሀሳቤን ለማጠቃለል አንኳር አንኳር የሆኑትን ላስቀምጥ።

*ጣሊያን ኢትዮጵያን ለመውረር በወሰደችው ርምጃ ተዋርዳ ተመልሳለች፤እንግሊዝም በአፄ ቴዎድሮስ ዘመን ጥሩ ሆነው ተኮርኩመዋል፤ሱዳኖች በመሃዲስት ወረራ ተሸንፈው ተመልሰዋል፤ቱርኮችና ግብጻውያን በተደጋጋሚ ያደረጉት ሙከራ ከሽፏል የሌሎችም እንዲሁ ከዚህ አንጻር ለዚህ የበቀል ፍላጎት አገር በቀሉና ለም ሆኖ የተገኘው ቡድን በጣሊያንና በእንግሊዝ ፕሮግራም የሚመራው ህወሃት የተሰለፈበትን የቅኝረኝነት ግዳጅ ለመወጣት ኢትዮጵያን ወደብ አልባ ማድረግ ነበር ተሳክቶላቸዋል።አሁን ደግሞ በክብር ተጠብቆና ታፍሮ የኖረውን የሀገራችን ድንበር ለማስደፈርና ለም መሬታችን ለጠላት(ሱዳን)አሳልፎ በመስጠት ዳሩ መሐል መሃሉ ዳር እንዲሆን ዝግጅቱ የተጠናቀቀ በመሆኑ የድንበር ማካለሉ ከመጀመሩ በፊት መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መሬቱ የጎንደር ብቻ ስላልሆነ ለጠላት ይሰጣል ወደ ተባለው አካባቢ ለመሄድ ስንቁን መሰነቅ ዝግጅቱን ማጠናቀቅና የማካለሉ ሥራ ሲጀመር ኢትዮጵያዊነቱን በማሳየት የአያት ቅድመ አያቶቹን ታሪክ መድገም አለበት።

*ድርቁና ድርቁ ያስከተለው ርሃብ ፋታ የሚሰጥ ባለመሆኑ በችግር ላይ የሚገኘውን ወገናችን ለመታደግ በስቪክ ማህበራት ሆነ በፖለቲካ ድርጅት ዙርያ የተደራጀን ሕዝባችንና ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች የተፈጠረውን አደገኛ ሁኔታ በማስረዳት ድጋፍ መስጠት ወገነን መታደግ ይገባናል፡፤ራሳቸውን እንደ መንግሥት ቢቆጥሩም በኢትዮጵያ ውስጥ መንግሥት ሳይሆን በውጭ ኃይሎች ትዕዛዝ የሚንቀሳቀስ ቅጥረኛና ዘራፊ ቡድን ርሃቡን እንደ አንድ የሕዝብ ክንድ የሚዝልበት እየተራበ እንዲገዛ የማጥቂያ መሣርያ አድርጎ ስለሚጠቀምበት በዚህ ቡድን ላይ ዘመቻ መክፈት ካስፈለገም ሕዝብ ሲርበው መሪውን ይበላል እንደሚባለው በሀገር ስምና ከሕዝብ የዘረፉትን ገንዘብ እስከ ማውጣት እንዲሄዱ ማስገደድ ድረስ መሄድ አለብን።

*የኦሮሞ ወጣቶች ያቀጣጠሉት ትግል በኦሮሞ ክልል ብቻ ተወስኖ መቅረት የለበትም ቢቻል በተመሳሳይ ጊዜና ሰአት በሁሉም ክልሎች የሚቀሰቀስ አመጽ እንዲካሄድ ማድረግ፤መሪ መፈክሮችም አገር አቀፋዊ እንዲሆኑ ማድረግ ድርቁና ርሃቡን ህወሃት መጠቀሚያ እያደረገው እንደሆነ፤የኢትዮጵያ ድንበር ለጠላት ተላልፎ መሰጠት እንደሌለበት፤ህወሃት ራሱን ከሕግ በላይ አድርጎ ንጹሐን ዜጎችን መብታቸውን አፍኖ ዜግነታቸውን ገፎ የመሬት ቅርምት ማድረጉን አቁሞ ሥልጣን ለሕዝብ እንዲያስረክብ፤መሬት የሕዝብ ነው ወዘተ.መፈክሮችን መጠቀም ፤የተቃዋሚ ኃይሎች ተገደው ወደ ሕብረት እንዲመጡ ማድረግ ያስፈልጋል።

*እነዚህን ሁሉ ስናደርግ አንዱ ሌላውን እንዲያጠናክር ተያያዥነትና ትሥስር እንዲኖራቸው ለማድረግ መሪ ሚናውን የሚጫወቱት ሚሥጥራዊና ሕቡአዊ መስመር ዘርግተው ግንኙነታቸው ሳይቋረጥ አመጹን እንዲመሩት ማድረግ ጠቃሚ ነው።አሁን ባለው ሁኔታ እንዲጓዝ ከፈቀድን ግን መጥፎ አደጋ ላይ ሊጥለን እንደሚችል ልንገነዘብ ይገባል።የእያንዳንዱን የተቃዋሚ ኃይል የፖለቲካ ፕሮግራም በደንብ ከተመለከትን አንዱ በሌላው ላይ አሽከላ ለመጣልና ጥሎ ለማለፍ ያነጣጠረ እንጅ መላ ኢትዮጵያውያን በእኩልነትና በጋራ የሚኖሩባትን አገር ለመገንባት ያለመ አይደለም።ይህን ደግሞ እኛው ፈቅደን አሻግረን በመመልከታችን ድርጅቶችን ደፍረን ቁሻሻ ተሸክማችኋል እኛን ከመምራታችሁ በፊት ቁሻሻችሁን አራግፉ ለማለት መድፈር አለብን።ምክንያቱም እኛ በውጭም ይሁን በአገር ውስጥ ያለነውን ድጋፍ ካላገኙ አንድ ርምጃ መሄድ አይችሉም።

*የአማራው ነገድ ሕዝብ በማንኛውም አካባቢ ሠርቶ  መብላትና መኖር እንዳይችል ድብቅ አጀንዳ ይዞ የተደራጀው  የአማራውን ዘር እያጠፋ ያለው አገር መራሹ ህወሃት 80% የትግራይ ሕዝብ በመላው ኢትዮጵያ ሀብት ለማካበት የህወሃትን ኮቴ እየተከተለ በሚያፈራው ሀብት ትግራይ ስንትና ስንት ግንባታ እየተካሄደ ሌሎች አካባቢዎችን ግን ድሮ በጫካ እያለ ይዞት በነበረው የአፍራሽና የማውደም አመለካከት ተመርኩዞ ሁሉም ተቋዋማት መደበኛ ተግባራቸውን መፈጸም ከማይችሉበት ደረጃ ለማድረ ተግባራዊ  እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል።አሁን ትግራይ ውስጥ የሚገኘው ሕዝብ የሚበዛው ሕፃናትና ሴቶች ሲሆኑ ሌላው የመንግሥት ሥራ የሌለው በሱዳን ፤በሶማሌ፤በደቡብ ሱዳን እንዲሁም የህወሃት ስርአት በየትኛውም የአለም አገር ዳቦ ፍለጋ እንዲሰደዱ ያደረጋቸውን እንዲሰልሉ አብሮ በማሰደድ በእናትና ልጅ፤በወንድማማች፤በእህትማማች፤በእድር፤በመረዳጃ ማህበራት፤በኮሚቲዎች፤በሲቪክ ማህበራት፤በእምነት ማእከሎች በሥራ ቦታዎች ሁሉ በማሰማራት ከፈተኛ የሀገሪቱ ሀብት ተመድቦ ለብጥብጥና የሕዝብን ሰላም እንዲነሱ የተሰማሩበት ይገኙበታል።ሌሎች 80% ያልኳቸው ዳቦ ያቀብሉናል ማለት አይደለም እነሱ ቀድመው ተደራጅተው በመጠበቅ አስተናጋጆች ናቸው።ከዚህ ላይ በዚህ ሀሳብ መሠረት የትግራይ ሕዝብ በህወሃት ሥርዓት ተጠቃሚ አይደለም እል የነበርኩት ሀሳቤን ሙሉ በሙሉ አንስቻለሁ።

*ሕዝቡን ተወልዶ ካደገበት ርስትና ጉልቱ በማፈናቀል ለድህነት መዳረግ፤አገር ጥሎ እንዲሰደድ ማድረግ ሠርቶ የመብላት እድሉን በመንፈግ ኢ-ሰብአዊ የሆኑ ድርጌቶችን በመፈጸም በማናለብኝነት ሕዝብን በመገናኛ ብዙሃን የስድብ ናዳ ማውረድ ሠርተው የሚበሉ ንጹሕ አርሶ አደሮችን ሽፍታ፤ጥጋበኛ እያሉ መዘለፍና በጭፍን የሱዳንን መሬት ተሻግረው እንደሚያርሱ አስመስሎ ማቅረብ ጠቅላይ ሚንስትሩን ተጠያቂ የሚያደርግ ሲሆን ከኋላ ይህን አድርግ ይህን ተናገር እያሉ የሚገፉት (አዲሱ ለገሰ፤ታደሰ ካሣ፤በረከት፤ካሣ ተክለብርሃን፤ሕላዊ ዮሴፍ፤ ደመቀ መኮንን ከብአዴን)፤ (ስብሃት ነጋ፤ስዩም መስፍን፤አርከበ እቁባይ፤ፀጋየ በርሄ፤አባይ ጸሐየ፤ቴዎድሮስ አድኅኖም፤ደብረጽዮን ሳሞራ የኑስ፤ጌታቸው አሰፋ ከህወሃት) ፤ኩማ ደመቅሳ አባዱላና ሙክታር እንዲሁም ሽፈራው ሽጉጤና የመሳሰሉት ስለሆኑ ሕዝቡ በዋዛ እንዳይመለከታቸውና አገሪቱን እያጠፉ ያሉት የመጀመርያዎቹ ተጠያቂዎች መሆናቸው እንዲታወቅ በነዚህ ሰዎች ማንኛውም ተንቀሳቃሽ ንብረት ላይ እርምጃ እንዲወሰድና የማእቀብ ማለትም ማንናውንም አገልግሎት አለመጠቀም ምሳሌ፦ምግብ፤መጠጥ፤ትራንስፖርት፤ባንክ ሌሎችንም በነዚህ ግለሰቦች የሚቀርቡ ምርቶችን አለመግዛት በመጠኑም ቢሆን ከጥጋባቸው ሊያበርዳቸው ይችላል”።

ወገኖቼ! ቢቻል ዋናውን ሁላችንም ሊጠቅም የሚችለው አንድነት ለማምጣት እንግባባ ይህ ጊዜ የሚወስድ ከሆነ ደግሞ ቢያንስ ሕብረት በመፍጠር በሕዝባችን ላይ የተቃጣውን ማንኛውም አይነት ጥቃት ለመመከት ሕዝቡን በየደረጃው ራሱን ሊከላከል እንዲችል የማደራጀት ሥራ እንሥራ።ህወሃት እንዳለ ሆኖ ከየካቲት 1966 አብዮት ጀምሮ ከህወሃት ባልተናነሰ መልኩ የአገርን ሉዓላዊነት፤የሕግ የበላይነት የሚረግጡ፤የዜግነት መብትን የሚያፍኑ በጥቅሉም አንድ ነፃ ሕዝብ ሊያገኝ የሚችለውን መሠራታዊ መብት እንዲያጣ ጠንክረው እየሰሩ እስከ አሁን የዘለቁ ድርጅቶች ጣልቃ እየገቡ እንዳያምሱን ለይተን ልናውቃቸውና ልናጋልጣቸው ከዚህ የጥፋት ተግባራቸው እንዲታቀቡ ልናደርግ ይገባናል።

                    ድል ለኢትዮጵያ ግፉአን ሕዝብ!!

                     ሞት ለህወሃትና ግብረ-በላዎቹ!!

                                        ከአንተነህ ገብርየ


ዝምታው ይሰበር –በውቢት ዘውዱ ታደለ፤

$
0
0

 

Colነፃነት እና ልማት ተነጣጥለው የሚታዩ ሳይሆኑ፤ የአንድ ሳንቲም ግልባጮች መሆኑን ያልተረዳው የኢህአዴግ መንግስት፤ የኦሮሞን የማስተር ፕላን ጥያቄ ለማጣጣል አፀፋውን በእስር እና በድብደባ ገፋ ሲልም በደም አጥለቅልቆታል፡፡ ትላንት የእልፍ ወገናችንን ነፍስ ቅርጥፍጥፍ አድርጎ የበላውና በደም የተፃፈው ‹‹የመሬት ላራሹ›› ጥያቄ ዛሬም ሳይመለስ አርሶ አደሩ ወገናችን መሬቱን እየተቀማ ሞፈሩን በጨበጠበት ለልመና እጁ መዘርጋቱ በገዛ እርስቱ ጭሰኛ መሆኑ ተባብሶ ቀጥሏል፡፡ ቢሆንም የኦሮሞ ህዝብ ይህንን አቋም ለመጣስ መሬቴን አልሰጥም ብሎ ቆርጦ መነሳቱ የኢህአዴግን መንግስት ፈተና ውስጥ ከቶታል፡፡

የኦሮሞ ህዝብ ከኢትዮጵያ ህዝብ ገሚሱን የሚሸፍን ሲሆን ከተቀሩት ብሔር ብሔረሰቦች ጋር ተባብሮ እና ተስማምቶ በመኖር ብዙ ጊዜን አስቆጥሯል፡፡ እንዲሁም በሌባነት እጁ በተጨማለቀው የኢህአዴግ መንግስትን የሚቃወም ድብደባም ሆነ ሞት የማይበግረው ድንበሩን ለቀማኛ አሳልፎ የማይሰጥ ጀግና ትውልድ ዛሬም ከኦሮሞ ትውልድ ፈልቋል፡፡ በአንባገነናዊ ስርዓቱ ቀጣይነቱን ሊያርጋግጥ የሚፈልገውን የኢህአዴግን መንግስት መቃወም ብቻ ሳይሆን ድንበሬን አሳልፌ አልሰጥም ብሎ ግብ ግብ ከፈጠረው የኦሮሞ ህዝብ ጋር ዛሬም እኛ አንድ ላይ መቆም አለብን፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ጥያቄ ሲሆን ዘር፣ ብሔር፣ ቋንቋ፣ ሀይማኖት ሳንለይ ወንድሞቻችን ለከፈሉት ዋጋ ከጎናቸው ሆኖ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊደግፍ ይገባል፡፡

ጉዳዩ የአንድ ብሔር ጥያቄ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጥያቄ ነው፡፡ ህዝብ ማለት ሀገር ነው፤ ሀገር ማለት ዳር ድንበር፣ መሬት ነው፡፡ አምባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት መሬታችንን ቆርሶ ሊሸጥ፣ ሲሸነሽን፣ ነዋሪዎች ሲገፉ፣ ህዝቦች በብሔራቸውና በሚናገሩት ቋንቋ ያለአግባብ ከመኖሪያቸው ሲፈናቀሉ  . . . እያየን ዛሬም ነፃነት አለ ብሎ ስለዲሞክራሲና ነፃነት እየሰበከ የዲሞክራሲና የነፃነት ጥያቄ ደም መፋሰስን ካመጣ ድንቄም ነፃነት!! የኦሮሞ ህዝብ ነፃነት ይመለከተኛል ብቻ ሳይሆን የእኔም ጉዳይ ነው ብለን ሳናየው በመቅረት ጆሮ ዳባ ልበስ ብለን ዛሬም እንደትላንቱ በዝምታ ልናልፈው አይገባም፡፡ ዝምታ ምን ፈየደ? ስንቶቻችን ለነፃነት ቆምን? መሬት ተሸጠ፣ ህዝብ ተራበ፣ ህጻናት በረሀብ ሞቱ፣ ወጣቶች ታሰሩ፣ ወገን ተሰደደ . . .  .

ድሮ ልዩነታችን ውበት እንዳልነበር ዛሬ ኢህአዴግ የስልጣን እድሜውን ለማራዘም በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ የሚዘራውን የብሔርተኝበት ጥያቄ በቃ ልንለው ይገባል፡፡ ትላንት አባቶቻችን በአንድነት ሆነው አስከብረው የሰጡን አንድ ኢትዮጵያ ዛሬም በቆራጥነት አለሁሽ እንበላት፡፡ ይበቃል በል ወገን! እናት ልጇን በረሀብ እያጣች፣ መስኖዎች እየደረቁ፣ መሬት እየተሸጠ፣ ሰው እየሞተ፣ እየታሰረ፣ ሀገር በሰቆቃ እየታመሰች ሳለ ዝምታው ዝምታው ምንድነው? ይበቃል በል ወገን! ዝምታን በቃ ብሎ ከሰበረው የኦሮሞ ህዝብ ጋር እንነሳ፡፡ የኢህአዴግ የፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ ያሴረውን የብሔርተኝነት ሴራ ወደኋላ ትተን ለአንድ ኢትዮጵያ ቃላችንን እናሰማ፡፡

ውቢት ዘውዱ ታደለ፤ ጥር፤ 2008 ዓ፤ም. ቶርንቶ፤ ካናዳ

ጸሀፊዋ ውቢት ዘውዱ ከአዲስ አበባ ዪኒቨርስቲ በቋንቋ በጋዝጠኝነትና ፎክሎር የመጀመሪ ድግሪዋን የወሰደች ሲሆን፤ በአሁኑ ሰዓት በቶሮንቶ ካናዳ በስደተኝነት ትኖራለች፡፡

በአትላንታ መርሃዊት ሺበሺ ከጠፋች 6 ቀን ሆኗታል –ቤተሰብ አፋልጉኝ እያለ ነው

$
0
0

merehawi
Admas News:- Habesha Woman missing in Clarkston, GA መርሃዊት ሺበሺን አፋልጉኝ ሲል የክላርክስተን ጆርጂያ ፖሊስ ጥሪ አቀረበ።

According to Clarkston Police a, 26-year-old woman. Merhawit Shibeshi is missing since Feb. 2/2016.
…. .. የ 26 ዓመቷ መርሃዊት ሺበሺ ክላርክስተን ጆርጂያ ውስጥ ከጠፋች ቢያንስ 6 ቀን ሆኗታል። 5″5 ኢንች ቁመትና 140 ፓውንድ ትመዝናለች የተባለችውን ይህችው ወጣት ያያችሁ ለፖሊስ አመልክቱ ወይም ቤተሰቦቿን ዘ-ሐበሻ ልታገናናችሁ ትችላለች። ቤተሰብ በጭንቀት ላይ ነው።

She is said to be suffers from Schizophrenia and her family is concerned. She is about 5 feet 5 inches and weighs about 140 pounds.

If you recognize her, you’re asked to call the police.

በጉጂ በሃራ ቃሎና አካባቢው በአላሙዲን እና በመንግስት ላይ ሰፊ ተቃውሞ እየተሰማ ነው –ሕዝቡ አደባባይ ወጥቷል

$
0
0

guji
(ዘ-ሐበሻ) በኦሮሚያ የተቀጣጠለው ሕዝባዊ አመጽ ተጠናክሮ በተለያዩ ከተሞች መቀጠሉ እየተዘገበ ነው:: እንደ ምንጮች ዘገባ በተለይ ከሕወሓት መንግስት ጋር በመዛመድ የሃገሪቱን ንብረት እየዘረፉ ነው በሚል ተቃውሞ የሚደርስባቸው ሼህ መሐመድ አላሙዲን የሚመሩት ሜድሮክ ኢትዮጵያ የሕዝብ ንብረትን ወስዶ እየበዘበዘ ነው በሚል ተቃውሞ እየደረሰበት ነው::

ዛሬ በጉጂ ዞን በሀራ ቃሎ ከተማና በተለያዩ የዞኑ ከተሞች በአላሙዲ ንብረት በሆነው ሜድሮክ ኢትዮጵያ እና በመንግስት ላይ ከፍተና የሆነ ተቃውሞ ሲሰማ ነው የዋለው:: ለተቃውሞ አደባባይ የወጣው ሕዝብ ለአላሙዲ በአካባቢው የተሰጠው መሬት የሕዝብ ሃብት ከመሆኑንም በላይ በርካታ የአካባቢውን ተወላጆች እና ነዋሪዎች የበይ ተመልካች እንደሚያደርግ በተቃውሞው እየተገለጸ ነው::

ሼህ መሐመድ አላሙዲ በሃገሪቱ ላይ የያዙትን የመሬት ቅርምት እንዲሁም ከሕወሃት መንግስት ጋር በመተባበር በሕዝቡ ላይ እያደረሱት ነው በተባለው የሃገር ሃብት ዝርፊያን በመቃወም በኢትዮጵያ እርሳቸው የሚያስዳደሩትይን ፔፕሲ እንዲሁም ሾላ ወተት እንዳይጠጣ ቦይኮት እንደተጠራባቸው መዘገቡ አይዘነጋም::

አላሙዲ የሃገር ሃብት የሆኑትን በጉጂ ዞን ለሻኪሶ እና ለአዶላ ከተማ አቅራቢያ አካባቢ የለገደንቢ የወርቅ ማዕድን እንዲሁም ከዚሁ ከለገደቢ ወርቅ ማዕድን ማውጫ 3 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ሳካሮ የተባለ የወርቅ ማዕድን ማውጫዎችን ተቆጣጥረዋል:: በተጨማሪም በመተከል ቤኒሻንጉል ጉምዝም እንዲሁ የህዝብ ሃብት የሆነውን የወርቅ ማዕድን ማውጫ ተጣጥረዋል::

መልስ ለአቶ ብርሃነመስቀል የ”ኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄዎች” ባሉት ላይ –ግርማ ካሳ

$
0
0

አቶ ብርሃኑ መስቀል አበበ፣ በኦሮሞ ብሄረሰብ መብት ዙሪያ በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ጽሁፎችን ይጽፋሉ። ቢቢሲ በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ስርጭት እንዲኖረው ፔቲሽኖችን በማስፍረም አንድ ዘመቻ እንደነበረ የምናስታወሰው ነው። ይሄንን ዘመቻ ይመሩ ከነበሩት መካከል አቶ ብርሃነመስቀል አንዱ ነበሩ። እኔም ሆንኩም በርካታ ኢትዮጵያዊያን ፔቲሽኑ ላይ ፊርማችንን በማስፈር ፣ ፔቲሽኑ ያልፈረሙ እንዲፈረሙ በማበረታታት እንደነ አቶ ብርሃነ መስቀል ባይሆንም፣ የድርሻችንን አበርክተናል።

ላለፉት ሶስት ወራት በኦሮሚያ በተነሳው ተቃዉሞ ዙሪያ፣ አቶ ብርሃነመስቀል “የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄዎች ናቸው” ያሉትን ስድስት ጥያቄዎች አስቀምጠዋል።

“የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄዎች ለልመናም ሆነ ለድርድር የሚቀርቡ አይደሉም። ጀግናው እና ደጉ የኦሮሞ ሕዝብም የልመና ባህልም ሆነ የለማኝ ተወካይ የለውም፣ ኖሮትም አያውቅም። መብቱንም ያስከብራከል እንጂ አይለምንም።” ሲሉ በጥያቄዎቹ ዙሪያ ድርድር እንደሌለ በአድን በኩል ይጽፉና ወረድ ብለው ፣ አቶ ብርሃነመስቀል ድርድር እንደሚያስፈለግ ይገልጻሉ። እርስ በርስ የሚቃረኑ አባባሎች።

አንደኛ “የልመና ባህል የለዉም፣ አይለምንም …” የሚሉት አይነነት አባባሎች መንፈሳቸው ጤናማ አይደለም። አቶ ብርሃንመስቀል ይሄን አይነት፣ “እኛ ያልነው ካልሆነ “ የሚመስል አባባል በመጠቀም ሌላውን ለማስፈራራት መሞከሩ ጠቃሚ አይመስለኝም። ሁለተኛ አቶ ብርሃነመቀል የኦሮሞ መሬት የሚሉት የኦሮሞዎች ብቻ እንዳልሆነ የዘነጉትም ይመስላል። የኦሮሞ መሬት የሚሉት የሁሉም ኢትዮጵይያዊ ነው። ሌላውም መሬት የኦሮሞዎች እንደሆነው። ሶስተኛ የኦሮሞ ሕዝብ አይለምንም እንዳሉትም፣ የሶማሌ ሕዝብ፣ የጉራጌ ሕዝብ፣ የሲዳማ ሕዝብ፣ የአዲስ አበባ ህዝብ ..ሌላውም አይለምንም።

”የኦሮሞ ሕዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ወገኖቹ ጋር በጋራ የመኖር ጠቀሜታና አስፈላጊነትን በሚገባ ስለሚገነዘብ በእኩልነትና በጋራ ጥቅም ላይ በተመሠረተ የሰጥቶ መቀበል የድርድር ሕግ ያምናል” ያሉት አባባል ግሩም አባባል ነው። እዚያ ላይ በማተኮር ላሉ ችግሮች ፣ ሁሉም አሸናፊ የሆነበት መፍትሄ መፈለጉ ላይ የበለጠ ቢሰሩበት ጥሩ ይሆናል ብዬ አማናለው። አቶ ብርሃኑ መስቀል ባቀረቧቸው ሐሳቦ ላይ ግን መቀበል እንጅ መስጠትን አላየሁበትም። በአንድ ወግን ያለውን ፍላጎት ብቻ ያንጸባረቀ እንጅ በሌላው ወግን የሚነሱትን ጥያቄዎች ከግምት ያስገባ አይመስለኝም። እንግዲህ ሰጥቶ የመቀበል መርህ ማለት መቀብል እንዳለበትም ሁሉ መስጠት አለበት።

አቶ ብርሃነመስቀል የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄዎች ናቸው ብለው ሲጽፉ፣ አንደኛ በምን መስፈርትና ሚዛን እነዚህ ጥያቄዎች የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄውም ስለሞሆናቸው የገለጹልን ነገር የለም። እንዴት አወቁ የኦሮሞ ሕዝብ ያሉት ጥያቄዎቹ እነዚህ እንደሆኑ ? ሁለተኛ የኦሮሞ ሕዝብ የሚሉት የትኛውን ሕዝብ ማለት እንደሆነ የጠራ መመዘኛ ያቀረቡ አይመስለኝም።፡የኦሮሞ ሕዝብ የሚባልው በኦሮሚያ የሚኖረው ወይንም የክልሉ ነዋሪዎች ማለቱ ነው ? ወይስ አፋን ኦሮሞ አንደኛ ቋንቋዉ የሆነው ማህበረሰብ ማለታችቸው ነው ? ወይስ ራሳቸዉን ኦሮሞ ነን ብለው የሚጠሩ ወገኖች ስብስብን ነው የኦሮሞ ሕዝብ የሚሉት ?

ይሄን ስል ግን ጥያቄዎቹ መነሳት የለባቸው ማለቴ አየደለም። ግን አቶ ብርሃነመስቀል የ”ኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄዎች ናቸው” ብለው ከሚያቀርቧቸው “ያሉ ችግሮችን ለመፍታት መመለስ አለባቸው የምላቸውም ወይንም የኦሮሞ ጥያቄዎች ናቸው ብዬ የማስባቸው ጥያቄዎች ናቸው” ብለው ቢያቀርቡት መልካም ይሆን ነበር። እኔም ጥያቄዎች እንደ ኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄዎች ሳይሆን በአቶ ብርሃነ መስቀል የተነሱ ጥያቄዎች አድርጌ ሐሳብ እሰጥባቸዋለሁ፡

1. “በጉልበት እና ሕግን ሽፋን በማድርግ የተዘረፈው የኦሮሞ ሕዝብ መሬት እንዲመለስ፣ የወረራው መሠረት የሆኑት ሕጎች እንዲሻሩና የዘረፋ ተቋማቶቹ እንዲፈርሱ፣” ይላሉ አቶ ብርሃኑ መስቀል።

ትክክል ብለዋል። ሆኖም የኦሮሞ ሕዝብ መሬት የሚለው አባባል አይመቸኝም። ከላይ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት፣ ይህ አባባል የተወሰኑ ቦታዎች የኦሮሞ መሬት፣ ሌላው ደግሞ የሌሎች መሬት እንደሆነ የሚያመላክት አባባል ይመስለኛል። ሁሉም የኢትዮጵያ መሬት የኦሮሞዎች መሬት ነው። ሁሉም የትግሬዎች መሬት ነው። በመሆኑም በምትኩ “በጉልበትና ሕግን ሽፋን በማድረግ ከመሬታቸው የተፈናቀሉ ወገኖቻችን መሬታቸው እንዲመለስ” የሚል አባባል ቢጠቀሙ ጥሩ ይሆን ነበር።

“የመሬት ነጠቃዉ መሰረት የሆኑ ሕጎች እንዲሻሩም” ሲሉ ጽፈዋል። ይሄንን ሲጽፉ፣ በሕገ መንግስቱ የተቀመጠውን “መሬት መሸጥና መለወጥ አይቻልም፣ መሬት የመንግስት ነው” የሚለውን አባባል ለምን እንዳልጠቀሱ አልገባኝም። አንዱና ትልቁ ችግር መሬት የአራሹ አለመሆኑ ነው። ገበሬው የመሬቱ ባለቤት መሆኑ በህግ እስካልተቀመጠ ድረስ ገበሬዉን እና ድሃ ከተሜዎች እንዳይፈናቀሉ ሊያስቆም የሚችል የሕግ መሰረት አይኖርም። ብዙ የኦሮሞ ብሄረተኞች ገበሬዉ የመሬቱ ባለቤት እንዲሆን አይፈለጉም። መሬቱ የመገርሳ፣ የቶላ፣ የቀልቤሳ፣ የቱሉ ..ከሆነ መሬቱ የነዋሪዎቹ እንጂ የኦሮሞ ብሄረሰብ መሆኑ ይቀራል። በኦሮሚያ ዉስጥም እነ ጎይቶም፣ እነ ሸምሹ፣ እነ አበጋዝ ፣ እነቤርሳሞም የመሬት ባለቤት ይሆናሉ። ያንን የኦሮሞ ብሄረተኞች አይፈልጉም። እንደ ኦፌኮ ያሉ ደርጅቶች በዚህ ምክንያት ነው መሬት ለአራሹን የማይደገፉት።

2. “ኦሮምኛ ከአማርኛ ጎን ለጎን የኢትዮጽያ ፌድራል መንግስት የሥራ ቋንቋ እንዲሆን” ሲሉ በሁለተኛነት አቶ ብርሃነመስቀል ያስቀምጣሉ።

ይሄም የሚደገፍ ሐሳብ ነው። አፋን ኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ሶማሌኛና ትግሪኛም ቢጨመሩ ጥቅም ይኖረዋል ብዬ አስባለሁ። በተለይም ሶማሌኛ ተናጋሪ ከሆኑት ከሶማሊያ፣ ከሶማሌላንድና ጅቡቲ ጋር እንዲሁም ትግሪኛ ተናገሪ ከሆንችው ኤርትራ ጋር መቀራረቡን የበለጠ ለማጠናከር ይረዳል።

ቋንቋ በመሰረቱ ጠቃሚ ነገር ነው። ብዙ ቋንቋዎችን ማወቅ ጸጋ ነው። ብዙዎች የተለያዩ ቋንቋዎች ቢችሉ ጥቅም አለው እንጂ ጉዳት የለዉም። ቋንቋ የመለያየት ምክንያት ሊሆን አይችልም፣ አይገባምም። በቅንነት ነገሩን ካየነው ከአማርኛ ቀጥሎ ሌሎች ቋንቋዎችም ፌዴራል ቋንቋ መሆናቸው ተቃዉሞ ሊያስነሳ አይገባም።

ሆኖም በኦሮሚያ ክልል፣ ከአፋን ኦሮሞ ጎን አማርኛም የሥራ ቋንቋ የመሆኑ አስፈላጊነት ሊሰመርበት ይገባል። አቶ ብርሃነ መስቀል በዚህ ረገድ ጥቂት ቢሉ ጥሩ ነበር። በአዳማ ከ75% በላይ የሚሆነው ነዋሪ አማርኛ ተናጋሪ ሆኖ ፣ የክልል መንግስት አገልግሎት በአማርኛ መነፈጉ፣ አፋን ኦሮሞ ባለመቻሉ የኦሮሚያ ክልል መንግስት መስሪያ ቤቶች ተቀጥሮ የመስራት፣ የመመረጥ መብቱ መረገጡ ተገቢ ነው ይላሉን ? አዳማን እንደ ምሳሌ ጠቀስኩ እንጂ በቡራዩ ከ45% በላይ፣ በሻሸመኔ፣ ቢሾፍቱ ፣ ጂማ ባሉ ከተሞች ከ60% አፋን ኦሮሞ የማይችሉ ኢትዮጵያውዉያን ይኖራሉ። አዲስ አበባን ጨመሮ በአራቱም የኦሮሚያ የሸዋ ዞኖች ከ44% በላይ ሕዝብ አፋን ኦሮሞ አይናገረም። ታዱያ ይሄን ያህል እጅግ በጣም ትልቅ ማይኖሪቲ “አፋን ኦሮሞ ብቻ” በሚል ፖሊሲ መገፋት አለበትን ?

3. “አድስ አበባ እንደ ሌሎቹ ትላልቅ የኦሮሚያ ዞኖች የዞን ደረጃ ተሰጥቷት፣ አማርኛ እና ኦሮምኛ የሥራ ቋንቋ ሆነው በኦሮሚያ ሥር እንድትተዳደር፣” ሲሉ በአዲስ አበባ ዙሪያ ከዚህ በፊት ያልሰማሁት ሐሳብ አቅርበዋል። ከዚህ በፊት በሰጠሁት አስተያየት አዲስ አበባ በዙሪያዋ ያሉትን አካባቢዎች ያካተተ፣ አፋን ኦሮሞና አማርኛ የሥራ ቋንቋ የሆነበት፣ 10ኛ ክልል ቢኖር ጥሩ የሚል ሐሳብ አቅርቤ ነበር። እኔ ያቀርብኩት ሐሳብ አቶ ብርሃነመስቀል ካቀረቡት ሐሳብ ጋር ይመሳሰላል። ልዩነቱ እርሳቸው አዲስ አበባ ብቻ ሲሆን ያሉት እኔ ደግሞ አዲስ አበባ እና አካባቢዋንም እጨምራለሁ። እርሳቸው ኦሮሚያ ዉስጥ ተኩኖ በዞን ደረጃ ይሁን ሲሉ እኔ ደግሞ ራሱን የቻለ ክልል ይሁን እላለሁ።

ሆኖም አቶ ብርሃኔ መስቀል ያቀረቡት ሐሳብ በጊዜያዊነት ተግባራዊ ቢሆን ችግር ይኖራል ብዬ አላስብም። እደግማለሁ እጊዜያዊነት። ይሀእን ስል ግን ሁለት ነጥቦችን በማስቀመጥ ነው። አንደኛ አዲስ አበባን ለብቻ ዞን ከማድረግ ፣ የቡራዩ ልዩ ዞንና የሰሜን ሸዋ ዞንን ከአዲስ አበባ ጋር በማዋሃድ፣ አንድ ትልቅ ዞን በመፍጠር የዞኖኑ ቆዳ ስፋት ማስፋት ጥቅም አለው። ይህም ዞን በፌዴራል መንግስት ሥር የሚሆንን ሳይሆን፣ ተጠሪነቱ ለኦሮሚያ ክልል መንግስት ይሆናል። ሁለተኛ በሂደት ሕዝቡ ከፈለገ ዞኖችን ማዋሃድ፣ ወይንም ዞኖች የራሳቸው ክልል የመሆን መብት እንደሚኖራቸው ስምምነት መደረሰ አለበት። አሁን ያለችው ኦሮሚያ የምትባለው ክልል በሕዝብ ፍላጎት የተመሰረተች ክልል አይደለችም። “ኦሮሚያ ወይም ሞት” የሚለው የአንዳንድ ኦሮሞ ብሄረተኞች አባባል ተቀባይነት የሚኖረው አባባል አይደለም። ሕዝቡ በፈለገ ጊዜ እንዴት መተዳደር እንዳለበት የመወሰን ሙሉ መብት አለው። ኦሮሚያን መቀየር አይደለም፤ ሕዝቡ ከፈለገ ፌዴራሊዝምን አልፈለግም ማለት ይችላል።

4. “በግፉ ለተገደሉና ለታሰሩ የኦሮሞ ልጆች ካሳ ተከፉሎ ገዳዮችና አሳርዎች ለፉርድ እንድቀርቡ” በማለት ተጠያቂነትን እና ፍትህ መኖር እንዳለበት አቶ ብርሃነ መስቀል ይጽፋሉ። 200% እስማማለሁ።፡በትክክል መሆን ያለበት ነገር ነው።

5. “ የኦሮሞ ሕዝብን ለ140 ዓመታት ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የለየው ሥረዓት ተሽሮ ፣ ሕዝቡን ተጠቃሚ የሚያደርግ ፖሊሲ እንዲወጣ” ሲሉ አቶ ብርሃነመስቀል በጻፉት ላይ ትንሽ ያልተመቸኝ ነገር አለ። ለ140 አመታት ያሉት ምን ለማለት እንደፈለጉ ቢዘረዝሩት በስፋት ሐሳብ ለመስጠት ይረዳ ነበር። ይመስለኛል፤ በአይምሯቸው አጼ ሚኒሊክን እያሰቡ መሰለኝ። አንደኛ እርሳቸው ምናልባት ወደሌሎች የኢትዮጵያ ግዛቶች ሄደው የሕዝቡን ሁኔታ ቢመለከቱ ጥሩ ሊሆን ይችል ነበር። በይፋት፣ በመንዝ፣ በቆቦ፣. በኣጽቢ፣ በአሳይታ ምን ያህል ሌላው ማህበረሰብ በድህነት የማቀቀ እንደሆኑ ይረዱ ነበር። ኦሮሞው ብቻ የኢኮኖሞ ተጠቃሚ እንዳልሆነ አድርገዉም አያቀርቡም ነበር። ሁለተኛ ታሪክን እያነሳን እንነጋገር ከተባለ ከመቶ አመት በፊት ሆነ የተባለውን ብቻ ሳይሆን ከሁለት፣ ሶስት፣ አራት መቶ አመታት በፊት በኢትዮጵያ ዉስጥ የተደረገዉን ልናነሳ እንችላለን። ይልቅ ተጣሞ የቀረበን ታሪክ እያነበበን ከመወነጃጀል፣ የወደፊቱን ላይ ብናተኩር የሚበጅ ይመስለኛል። ሂሳብ መተሳሰብ ከተጀመረ፣ ሌሎችም ሊመነዝሩት የሚችሉት ብዙ ነገር በእጃቸው እንዳለ እነ አቶ ብርሃነመስቀል መረዳት ያለባቸው ይመስለኛል።

6. “የኦሮሞ ሕዝብ በክልል ደረጃ ከፌዴራል ተላላኪዎ እጅ ወጥቶ ራሱን በራሱ እንዲያስተዳድርና በፌዴራል ደረጃ ኢትዮጵያን በድርሻው ልክ ተወክሎ እንዲያስተዳድር” ሲሉ አቶ ብርሃነመስቀል ስድስተኛ ነጥባቸዉን ያስቀምጣሉ።

የፌዴራል ስርዓት እስከሆነ ድረስ ያለው በአገሪቷ የፌዴራል ስርዐት የተቀመጡ ሕጎች መከበር አለባቸው። ሕግ የበላይ ካልሆነ የፌዴራል ስርዓት ተግባራዊ ሊሆን አይችልም። አምባገነናዊ ስርዓት ብለበት ሁኔት ፌዴርሊዝም አይሰራም።፡በመሆኑም እዉነተኛ ፌዴራሊዝም እንዲኖር ሕግ የበላይ የሆነበት ስርዓት መኖር አለበት። የፌዴራል መንግስት ከሕግ ውጭ በክልል ዉስጥ ጣልቃ መግባት የለበትም። ክልሎችም በዞን እና በወረዳ አስተዳደሮች ሕጉ ከሚፈቅድላቸው ዉጭ ጣልቃ መግባት የለባቸው። ላችንንም ሕግ ከገዛን ነገሮች ይስተካከላሉ።

Comment

“ደንቆሮ የሰማ ዕለት ያብዳል” አሉ . . . ወይ ብሔረ-ጽጌ! –አከለው የሻነው ደሴ

$
0
0

ጥር 28 ቀን 2008 ዓ.ም. ወደ ብሔረ-ጽጌ መናፈሻ ጎራ ብዬ ነበር። ከቤት ለምን ወጣሁ መሰላችሁ ሕዝባችን ከጎረቤቶቹ፣ ከአካባቢው ሰዎች ነፃነት ይልቅ የራሱን ትንሽ ጉዳይ፣ ፌስታ፣ ደስታ፣ ጩኸት የሚያስበልጥ ገና ኋላቀር እና ጥንታዊ ስለሆነ። በተጨማሪም አገሪቱ አንድ ሰው ከጎረቤቶቹ እና ከአካባቢው ኗሪዎች ረብሻ ነፃ የሚሆንበትን አስተማማኝ ሥርዐት ስላላሰፈነች ይመስለኛል። በአጭሩ ኮንዶሚኒዬማችን ውስጥ አንድ ጉዳይ ያለው ሰው ካለ ከአካባቢው ጠፍቶ መዋል ግድ ነው። አይቻልም እንጅ ሌሊትም ጠፍቶ ማደር ይሻል ነበር። ምክንያቱም ያለው ጩኸትና ዘፈን በፍፁም ሊያስተኛ አይችልምና።

የዛሬ ሳምንት አካባቢ መብራት ለብዙ ቀኖች በጠፋበት ጊዜ እኛ ብሎክ አራተኛ ፎቅ ላይ ሰርግ ነበር። እውነት ለመናገር ሁለት ቀን ሙሉ ቀንም ሌሊትም ሰዎች ጄኔሬተር ተከራይተው በድለቃ፣ በጭፈራ፣ በዘፈን፣ በጨኸት ሕንፃውን ሲያንቀጠቅጡት ውለው አደሩ። ለመሆኑ ኢትዮጵያ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ደንነት፣ሰላምና ፀጥታ በሚመለከት ሕግ የላትምን ከሌላት በጣም ያሳፍራል፤ ካላት ግን መንግሥት በተግባር እንዲያውለውና እንዲታደገን እንማፀናለን። ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ አራተኛ ፎቅ ላይ ባለሰርጎቹ ሲዘሉ ልክ አናታችን ላይ የሆነ ነገር የፈነዳ ይመስለን ነበር። እንዲህ ዐይነት ተግባር ለሕንጻውስ ዕድሜ ጥሩ ነው ወይ ሰው በሰላም የመተኛት መብቱ የሚከበርለት መቼ ነው የጋራ መኖሪያ ሕንፃ ላይ አንድ ሰው የፈለገ ጉዳይ ቢኖረው ፎቅ ላይ መጨፈር፣ መዝለል፣ መጮህ፣ ማቅራራት ይገባዋልን ሕዝቤ ሰልጥኖ ከራሱ የግል ጉዳይ አልፎ ስለ ሰዎች ነፃነት እና ሰላም ማሰብ የሚጀምር መቼ ይሆን መንግሥትና ፖሊስስ አንድን ነገር እንደ ጥፋት (ወንጀል) የሚያዩት ሰው አናቱን ሲገመስ፣ ሲደማ ወይም ሲሞት ብቻ መሆን አለበት ትላላችሁ

እኔ ግን ከዚያ ሌላ የሚያሳስበኝ ብዙ ነገር አለ። አንድ ሰፈር ውስጥ (ኮንዶሚኒየም መሃል) መኪና አቁሞ ጆሮ እሚሰነጥቅ ዘፈን (መዝሙር) ከፍቶ ሰው መረበሽ፣ መንገድ ላይ አላፊ አግዳሚውን ስለ ሃይማኖት በመስበክ ነፃነቱን መጋፋት፣ እግዚአብሔር ያለ ድምፅ ማጉያ ካልተነገረው የማይሰማ ይመስል አገር እስቲናጋ እና እቤቱ በሰላም የተኛ ሰው እስቲንቀጠቀጥ ድረስ ከየእምነት ቤቶች የሚለቀቀው ድምፅ ሁሉ በኔ ግምት ከኋላ ቀርነት እና ከኔ ውጭ ስላለው ሰው ምናገባኝ ከሚል በራስ ዙሪያ ብቻ ከታጠረ አስተሳሰብ ጋር የተያያዙ ተግባራት ናቸው። እናም እኔ እነሱ ሁሉ አካላዊ ባይሆኑም መንፈሳዊ ጥፋቶች ናቸው ባይ ነኝ። በመሆኑም እነሱን ሥርዐት የሚያስይዝ ዘመን አንድ ቀን እንደሚመጣ አምናለሁ፤ ዛሬም አጥብቄ እመኛለሁ። ያን ጊዜ ከሚናፍቁት ምስኪን ኢትዮጵያዊያን አንዱ ነኝ ማለት ነው።
ከትናንት ወዲያ ቅዳሜ ከቀኑ ሰባት ሰዓት ላይ ባለሰርጎች ሙሽሪትን ምላሽ ጠርተው እና ደግሰው ለምሳ እንድንገኝ ጋብዘውን ነበር። የምላሹ ድግስ ከፎቅ ወደ ምድር ተዛወረ። እኛ እምንኖርበት ሕንፃ ላይ የልብስ ማስጫ ቦታ አለ። ከዚሁ ጠባብ ቦታ በስተግራና በስተቀኝ ሁለት መሽሎኪያ መውጫ መግቢያዎች አሉ። ለዝግጅቱ ሲባል ግን ተጠርቅመው ተዘጉ-በሸራ ታጠሩ። መሃል ለመሃል ልብስ ማስጫውን ሰንጥቆ የሚያልፈው መንገድ በድንኳን ታጥሮ የዝግጁት ዋና መድረክ ሊሆን ተወስኖበታል። እናም ቀኑን ሙሉ በጩኸት ከምሰቃይ እና መውጣትና መግባት ስፈልግም መንገድ አጥቼ ከምቸገር በሚል የተጠራሁበትን ግብዣ ትቼ መዋያዬን በሃሳብ አፈላለግኩ።
በዚህ አጋጣሚ እዚያው አጠገቤ በእግር ሃያ ደቂቃ ብቻ በመጓዝ የማገኘው መናፈሻ ስላለ፤ ወደሱ ለመሄድ ወሰንኩ። በቆስጣ ሠፈር የአቃቂን ወንዝ ግማት እየሳብኩ እና እዚች አገር ላይ የየፋብሪካው ቆሻሻ የማይለቀቅበት ወንዝ ማየት የምንችልበትን ዘመን ከየረር ተራራ ባሻገር እያየሁ ቀይ አፈር በሚባለው ሰፈር ወደላይ ወጣሁ። በአብዮት ፋና ትምህርት ቤት እና በሃይላንድ ውኃ ፋብሪካ (በሃገራችን የመጀመሪያው ፋብሪካ በመሆኑ ውኃ የሚታሸግበት ጠርሙስ መጠሪያ የሆነ ፋብሪካ ነው-ሃይላንድ) መካከል ተጉዤ ብሔረ-ጽጌ መናፈሻ ደረስኩ።

በር ላይ ሁለት ብር ከፍዬ የተሰጠኝ ቲኬት ‹‹በየካ ክፍለ ከተማ የፈረንሳይ ፓርክ፣ መግቢያ ዋጋ አንድ ብር›› ስለሚል፤ ትንሽ ቆም ብየ በማሰብ የካ ሳይሆን ነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ መሆኔን አረጋገጥኩ። መናፈሻውም ፈረንሳይ ሳይሆን ብሔረ-ጽጌ እንደሆነ ለራሴ ምስክርነት ሰጠሁ። የመግቢያ ዋጋው አንድ ብር ተብሎ ሳለ ሁለት ብር መክፈል ኢትዮጵያ ውስጥ እና ለአንድ ኢትዮጵያዊ ምንም ማለት እንዳልሆነ ራሴን አሳመንኩ። ከዚህ ውጭ ጥያቄ ማብዛት ቅብጠት እንደሚሆን በተጨማሪም በአስተናጋጁ፣ በፖሊሱ ወይም በደንብ አስከባሪው ባህርይ እንዲሁም በሰሞኑ የአየር ጠባይ እና በሃገራችን የፖለቲካ ስሜት የሚወሰን በመሆኑ አልፎ አልፎ ሊያስገላምጥ እንደሚችል ስላላጣሁት ዝም ብዬ ወደውስጥ ገባሁ።

መናፈሻው ውስጥ የማየው ነገር እንግዳ እና አስደንጋጭ ሆነብኝ። ብዙ ዕድሜ ጠጋብ ዛፎች እየተገነደሱ ከወደቁ በኋላ ተቆራርጠው ተነስተዋል። ከሥር ያለው ሣርና ቅጠላቅጠልም በእሳት ይቃጠላል። ግራ ገባኝ። ዛፎች ለዚውም መቶ ዓመታትን የዘለቁ አንጋፋ ዛፎች ምን አጥፍተው እንደሚቆረጡ መገመት አቃተኝ። እዚያው እመናፈሻው ውስጥ አቃቂን ወንዝ ተሻግሬ ታችኛውን የመናፈሻውን አካባቢ ተዘዋውሬ አየሁት። በጣም ያሳዝናል፣ ያሳፍራል። ዛፎች አልቀዋል፤ አካባቢውን ለማፅዳት የተመደቡት ሰዎች በመቁረጥ፣ በማቃጠል እና በማንሳት እጅግ ይባትላሉ። ቸኩለዋል፤ ቢጠሯቸው አይሰሙም። ምናልባት መናፈሻውን ሜዳ ሆኖ የሚያዩበት ጊዜ ሳይርቅባቸው የቀረ አልመሰለኝም።

ለጊዜው እዚያ ቁጭ ብዬ ለመጻፍ ያሰብኩት ጉዳይም አልመጣልኝ ስላለ ዝም ብዬ ወዲያ ወዲህ መዘዋወር አበዛሁ። አልፎ አልፎ በመካከለኛ ዕድሜ ላይ ያሉ እና ታላላቆቻቸውን ያጡ ዛፎች በፍርሃት ድርቅ ብለው ቆመዋል፤ አይንቀሳቀሱም። ውስጡም ከምድረ በዳ አይሻልም። የድሮው ብሔረ-ጽጌ ዛሬ የለም። እሚገርው ግን በገላጣው ቦታ ላይ ተቃቅፈው እግር አንስቶ ዋናውን ጨዋታ መጀመር እስቲቀራቸው ድረስ ወንዶችና ሴቶች አልጋ ላይ የተኙ ያህል በፍቅር ዓለም ሲንከባለሉ ማየቱ ዐይን ማድከሙ ነው። ብሔረ-ጽጌ የድሃ የፍቅር ቦታ መሆኑ ዛሬም አልቀረም-ነገ ግን እንጃ!
ለምሳ ወደ ሳሪስ ደረስ ካልኩ በኋላ እንደገና ቲኬት ቆርጬ ተመልሼ ገባሁ። አሁን አመጣጤ ከመጀመሪያው የተለዬ ነው። የማገኘውን ሰው ሁሉ መጠየቅ እንዳለብኝ ወስኛለሁ።

“ይኸ ፈረንሳይ መናፈሻ ነው እንዴ” ቲኬት የሰጠችኝን ሴትዮ ጠየቅኳት። ቦታ የጠፋብኝ መስሏት (አበሾች ስንባል ከማዳመጥ ለመናገር ለምን እንደምንሮጥ አይገባኝም) “አደለም፣ አደለም። ብሔረ-ጽጌ ነው!” ብታዩአት በአፏ ይቅርና በእጇ፣ በእግሯ፣ በጠጉሯ ምን አለፋችሁ በልብሷ ሁሉ ለመናገር ተጥደፈደፈች።
“ታዲያ ቲኬቱ ለምን ፈረንሳይ ፓርክ ይላል”

“ቲኬት አልቆብን ተውሰን ነው።” ይቅርታ አድርግልን አጥፍተን ነው የሚል ስሜት ቢጠበቅም እሷ ግን የማይገባ ነገር እንደተጠየቀች ሁሉ ቆጣ ብሎ በከንፈሯ ወደ ውስጥ ገፈተረችኝ። ቀስ ብዬ እየተራመድኩ “ዛፉ ደሞ ለምንድነው የተቆረጠ የሚያቃጥሉት ለምንድነው” ጥያቄ ጨመርኩ።
“ወንጀለኛው በዛ፤ የወንጀለኛ መደበቂያ ሆነ።” ስትለኝ ተናደድኩ። ለምን ተናደድኩ መሰላችሁ-የአፍሪካን ፖለቲካ ለመረዳት ገና ሕፃን ስላልሆንኩ። ትክክለኛው ነገር ሰዎች በሉ ተብለው የሚያወሩት እና የሚያስተጋቡት ሳይሆን ከጀርባ የተደበቀው እንደሆነ ስለምገምት።
“እንዴ! መንግሥት የት ሄደ መንግሥት አለ አደል እንዴ” ስል አፏን በጣቷ እየተመተመች “እኔ እንደሰማሁ ሌላ እንዳይሰማ በል ሂድ ግባ!”አለችኝ።
“የኛ መንግሥት መሃል አዲስ አባባ ብሔረ-ጽጌ ላይ ወንጀልን የሚከላከልበት ኃይል አጥቶ መቶ ዓመት የኖሩ አንጋፋ ዛፎችን ይቆርጣል” እያልኩ ሳላስበው የሰጠችኝን ቲኬት ቆራርጬ ጣልኩት።

“ኧረ ቲኬቱን ቀደድከው! ኧረ ቲኬቱ!” ስትል ጥዋት የቆረጥኩትን ከሱሪዬ ምስጢር ኪስ አውጥቼ አሳየኋትና ወደ ውስጥ ገባሁ።
መሃል አካባቢ ቅጠላ ቅጠሉን እና ርጋፊውን እያግበሰበሱ የሚያቃጥሉ፣ የተቆራረጠውን ግንድ የሚያነሱ እና ከእሳት የተረፈውን ልቅምቃሚ የሚጠራርጉ ወጣቶች አየሁ። ስንት ሊከፈላቸው ቃል እንደተገባላቸው ባላውቅም ፍጥነታቸው አስደንቆኛል። ከመንገዱ ሰበር አልኩና ተጠጋኋቸው። “ዛፉ ምን አርጎ ነው የሚቆረጥ” አልኩኝ። “ወንጀለኛ በዛ፤ የወንጀለኛ መደበቂያ ሆነ።” ሥራቸው እንዳይደናቀፍ ለጥያቄዬ ብዙም ትኩረት ሳይሰጡ መለሱልኝ። ኃላፊ የሚመስል በዕድሜ ከአባዛኞቹ ከፍ ያለ ሰውዬ “ምንድነው የሚል” አለ በንቀት። ጠጋ አልኩና “ዛፉ ለምነድነው የሚቆረጥ” ስለው፤ “ወንጀለኛ አስቸገራ!”

ነገሩ የገባኝ እና በራሴ ግምት ዛፉ ለምን እንደሚቆረጥ የራሴን መልስ ያገኘሁ ስለመሰለኝ ከዚያ በላይ መጠየቅ አላስፈለገኝም። ብዙ ሰዎች ተቀድቶ የተቀመጠ የሚመስል ተመሳሳይ ነገር ከተናገሩ ምስጢሩን ለማወቅ ቀመሩ ከባድ አይሆንም። አንዳንድ የቴሌቪዥን እና የሬዲዮ ጣቢያዎችን መከታተል የማልወድበት ምክንያትም ምናልባት ይኸው ሳይሆን አይቀርም። ለማንኛውም ቁጥሮችንም እንመልከት ካልን የኢትዮጵያ የመሬት ስፋት 1,127,000 ካሬ ኪሎ ሜትር ሲሆን የብሔረ-ጽጌ መናፈሻ የመሬት ስፋት 0.4 ካሬ ኪሎ ሜትር ብቻ ነው። ታዲያ እዚች የበሬ ግንባር እምታህል ትንሽ መናፈሻ ላይ ወንጀልን መቆጣጠር ከዐቅም በላይ ሆኖ መቶኛ ዓመት ልደታቸውን ያከበሩ ጥንታዊ ዛፎችን ካስቆረጠ፤ ቢያንስ ቢያንስ ማዘን ግድ ይሆናል። እናም አዘንኩ-በጣም አዘንኩ። መንግሥቴን ለማገዝም ፖሊስ መሆን አማረኝ!

ዝም ብዬ ሳስበው፤ በዛሬው ጊዜ ከሁለት ሺ ዓመት በፊት ከነበረው ኋላ ቀር የኦሪት ሕግ ጭራሽ ወደኋላ መሄድ ሥልጣኔ አልመስለኝ አለ። የኦሪት ሕግ አንድ ሰው (ዛፍን ተገን አድርጎም ቢሆን) ሰው ከገደለ ገዳዩን ግደለው ይላል እንጅ ዛፉን ቁረጠው አይልም። ዛሬ ወንጀለኛ ዛፉን ተገን አድርጎ ወንጀል ስለሠራ ዛፉ ይቆረጥ የሚል ያልተጻፈ ሕግ እንዴት በኢትዮጵያ ምድር ይፈጸማል ከምኖርበት ሠፈር በወፍ በረራ አንድ ኪሎ ሜትር በማይሞላ ርቀት ላይ ይኸ ሁሉ ሲፈጠር ገና ዛሬ ማየቴ “ደንቆሮ የሰማ ዕለት ያብዳል” እንድል ገፋፋኝ፤ ይኸን ሁሉም አስጻፈኝ። ስንቶቻችሁ ግን ይኸን ነገር ካሁን በፊት ሰምታችሁት ነበር ማጠቃለያዬ እንደሚከተለው ይሆናል። እንቅልፋችንን የጤና አድርጎ፤ “ብሔረ-ጽጌ ይባል እነበረው መናፈሻ ላይ የተገነባው ኮንዶሚኒየም ተመረቀ” የሚል ህልም ወይም “አቶ ሃብቱ ፈጠነ የተባሉ ልማታዊ ባለሀብት ብሔረ-ጽጌ ላይ የገነቡት ፋብሪካ ተመረቀ” የሚል ቅዠት ከመስማት ይሰውረን። በምትኩም “ብሔረ-ጽጌ መናፈሻ ውስጥ አርጅተው የተቆረጡት ዛፎች አቅጥቅጠው ጫካው እንደገና ለምልሞ ሕዝቡ እየተጠቀመበት ነው” የሚል ዜና የምንሰማበትን ጊዜ አያርቅብን።

comment pic

በምስራቅ ጎጃም ደብረ ወርቅ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራን የስራ ማቆም አድማ አደረጉ

$
0
0

news

ቀጣዩ እንደወረደ የቀረበው ዘገባ የነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ነው::

‹‹የትምህርት ጥራት ይጠበቅ!›› ተማሪዎች

በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን የሚገኘው የደብረ ወርቅ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡

ምንጮቹ ዛሬ ጥር 30/2008 ዓ.ም እንደገለጹት በትምህርት ቤቱ የሰሚስተሩን አጋማሽ ረፍት ጨርሰው ተማሪዎች ወደትምህርት ቤቱ ቢመጡት መምህራኑ በስራ ገበታቸው ላይ ባለመገኘታቸው ተማሪዎቹ ‹‹የትምህርት ጥራት ይጠበቅ!›› በማለት መፈክር እያሰሙ ወደቤታቸው ተመልሰዋል፡፡

የደብረ ወርቅ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ካለፈው ዓመት የካቲት ጀምሮ በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ከርሟል ያሉት ምንጮቹ በዋናነት ከመመሪያ ውጭ በርዕሰ መምህርነት የሚሾሙት አካላትና የወረዳው የት/ት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ፍቅረአዲስ ሙሉሰው ለችግሩ መባባስ አስተዋጽኦ አላቸው ተብሏል፡፡

‹‹በክልሉ የሌለ አሰራር በመከተል በት/ቤቱ 4 ምክትል ርዕሰ መምህራን ተሹመውብን ቆይተዋል፤ ይህ መመሪያ ይጥሳል ብለን ታግለን አስወረድናቸው፡፡ ነገር ግን ከወረዱት መካከል አንዱን ርዕሰ መምህር አድርገው እንደገና ሾሙት፡፡ በዚህም ችግሩ ተባብሶ ቀጠለ፤ እኛም ድርጊቱ ትምህርትን ይጎዳል ብለን ከዛሬ ጀምሮ አድማ ልናደርግ ችለናል›› ብሏል አድማ ከመቱ መምህራን አንዱ፡፡

በት/ቤቱ 141 መምህራን እንዳሉ የጠቆሙት ምንጮቹ፣ ከእነዚህ መካከል ከ100 በላይ የሚሆኑት የአድመውን ተካፋይ ናቸው ተብሏል፡፡ የትምህርት ቤቱ አስተዳደርና የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት መምህራኑን ‹‹ሰማያዊ ፓርቲን እንጂ ኢህአዴግን አትቀበሉም›› እያለ ችግሩን ለመግፋት እየሞከረ እንደሆነም ምንጮቹ አክለው ግልጸዋል፡፡

– See more at: http://www.satenaw.com/amharic/archives/12564#sthash.DNnywcVH.dpuf

ድንቄም የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ? ማስተር ፕላኑማ የዘ-ህወሀት ነው!

$
0
0

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

የጸሐፊው ማስታወሻ፡ መለያ ምልክት ምንድን ነው? ደህና፣ “በስም ውስጥ ያለው ምንድን ነው? ያ ጽጌረዳ እያልን የምንጠራው/በሌላ በማንኛውም ስም ቢጠራም ያው ጣፋጭ ሽታው መሽተቱ አይቀርም…“ ብሎ ነበር ሸክስፒር:: “ካራቱሪ እና የሕንድ ኃያልነት በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ በቅርቡ ባቀረብኩት ጽሑፍ በካራቱሪ ዓለም አቀፍ ከኢትዮጵያ በተነጠቀው መሬት ላይ የበቀሉት ጽጌረዳዎች በእርግጥ ጽጌረዳዎች አይደሉም የሚለው እውነት ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ በኢትዮጵያ የመሬት ነጠቃ እና ዘረፋ እያካሄድኩት ያለው ጽሑፍ ለሶስተኛው ጊዜ ያዘጋጀሁት ትችቴ ነው፡፡

ባለፈው ሳምንት ዘ-ህወሀት በሚሊዮን ሄክታር የሚቆጠር መሬት ከነጠቀ፣ ከዘረፈ እና ለውጭ ሸፍጠኛ ኢንቨስተሮች እና ለጎረቤት ሀገሮች ካደለ በኃላ ለኢትዮጵያውያን ምን የተረፈ ሀገር ይኖራል የሚል ጥያቄ በማንሳት ጥያቄ አቅርቤ ነበር፡፡ በዚህ ትችቴ ላይ ደግሞ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን እየተባለ የሚጠራው ፕላን ለዘ-ህወሀት ማስተር ፕላን የመሬት ዘረፋ በብልጣብልጥነት ተሸፍኖ የቀረበ የህዝብ ግንኙነት የተንኮል ስራ ስለመሆኑ ጥያቄ አቀርባለሁ፡፡

“የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን” ከዚህ በኋላ ሊኖር ይችላልን?

AddisAbaba

ከጥቂት ሳምንታት በፊት የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ የዘራፊ ቡድን (ዘ-ህወሀት) ስብስብ ከህዝብ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ ካጋጠመው በኋላ መናገሻ ከተማዋን ወደ አካባቢው የእርሻ መሬት የማስፋፋት ድርጊቱን የሚያቆም መሆኑ ታውጆ ነበር፡፡ “የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን” የማዘጋጃ ቤቶችን እና በመናገሻ ከተማይቱ ያልታቀፉ አካባቢዎችን ስልታዊ በሆነ መልኩ በማካተት ፈጣን የሆነ ግዙፍ የምጣኔ ሀብት የያዘ ከተማ ለመገንባት ነው የሚል ስልትን መርህ አድርጎ የተነሳ ነበር፡፡

ሆኖም ግን ዘ-ህወሀት ከአካባቢው ኗሪዎች ከባድ ተቃውሞ የደረሰበት በመሆኑ ተቃውሞውን ለመጨፍለቅ እና ሁኔታውን ለመቆጣጠር ሲል ተቃውሞው በተነሳባቸው አካባቢዎች የግድያ እና የአፈና ዕኩይ ድርጊቱን ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡

ሂዩማን ራይትስ ዎች የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት እ.ኤ.አ ከህዳር 2015 አጋማሽ ጀምሮ በዘ-ህወሀት የተካሄደውን እልቂት በማስመልከት እንዲህ የሚል ዘገባ አቅርቦ ነበር፣ “የደህንነት ኃይሎች በምዕራብ አዲስ አበባ በሚገኙት በሸዋ እና በወለጋ ዞኖች እንዲሁም በወሊሶ ከተማ በደርዘኖች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ተኩስ በመክፈት የንጹሀን ዜጎች እሬሳዎች በአደባባይ በመንገዶች ላይ እንዲዘረሩ አድርገዋል፡፡“

ዛር እንደሰፈረበት የአዕምሮ ህመምተኛ የሚለፈልፈው እና የዘ-ህወሀት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር የሆነው አዞው ጌታቸው ረዳ እውነተኛ የማስተር ፕላን እንደሌለ አሳፋሪ በሆነ መልኩ በመካድ እንዲሁም ፕላኑን ምንም የሚረባ ነገር እደሌለው በመግለጽ እውነተኛ ፕላን ቢኖር ኖሮ ሁከት ፈጣሪዎች ይቃወሙት እንደነበር እንደህ በማለት ተናግሯል፡፡ ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት መደረጉን ተከትሎ የተዘጋጀ እውነተኛ ፕላን አልነበረም፡፡ የመጨረሻ የፖለቲካ ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችል ሙያዊ በሆነ መልኩ የተነደፈ ወይም ደግሞ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የተዘጋጀ ፕላን አልነበረም፡፡” ብሎ ነበር በገሃድ ሲሸፍጥ::

ረዳ በዘ-ህወሀት እልቂት የተፈጸመባቸውን የጦር መሳሪያ ያልታጠቁ ንጹሀን ዜጎች እና የጥቃት ሰለባዎች ሁከት ፈጣሪ ወሮበሎች በማለት እንዲህ ፈርጇቸዋል፡ “የተፈጠረውን አለመግባባት እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመውሰድ ሁከት ፈጣሪዎች በአሁኑ ጊዜ ወደለየለት በትጥቅ ወደተደራጀ ወሮበላነት ከፍ በማለት የግለሰቦችን ህንጻዎች በተደጋጋሚ ማቃጠል እና የመንግስትን መሰረተ ልማት ማውደሙን ቀጥለውበታል፡፡“ አይን ያወጣ ዘራፊ ሌባ ምንም ዓይነት የጦር መሳሪያ ያልታጠቁትን ዜጎች ወሮበላ ብሎ ይጠራል!)

የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን እየተባለ በሚጠራው ፕላን ላይ የተቀጣጠለው ህዝባዊ አመጽ በዘ-ህወሀት ስልጣን ላይ አስደንጋጭ ማዕበልን የፈጠረ ሲሆን የዘ-ህወሀት አለቆችን ጭራ እየተከተሉ ያሉ ጥገኛ ምሁር ተብየዎች ቁጥሩ እየጨመረ ከመጣው መሬት አልባ፣ ተስፋ የለሽ፣ ድምጽ አልባ እና ኃይል የለሽ ደኃ ገበሬዎች ላይ መሬት እና ሀብትን ያግበሰብሳሉ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በመሬት ነጠቃ ቅርምቱ የዘ-ህወሀትን ዙፋን የነቀነቀው ሌላ ምንም ሳይሆን እናንተ እንደምትገምቱት ምህረት የለሽ የሆነ የገንዘብ ቀያሪ ወሮበላው የዓለም ባንክ እና እኔ በግልጽ “የድህነት አቃጣሪ” እያልኩ የምጠራው እና ለበርካታ ዓመታት ሳጋልጠው የቆየሁት ዓለም አቀፍ ድርጅት ነው፡፡ እ.ኤ.አ ህዳር 2015 “ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ ውሸቶች እና ተራ አሀዛዊ ቅጥፈቶች“ በሚል ርዕስ ያዘጋጀሁትን ትችት ይመልከቱ፡፡)

እውነት ለመናገር የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በከፍተኛ ደረጃ እንደ አዲስ አበባ ባለ ትልቅ ከተማ እያደገ የመጣውን የመሬት ነጠቃ፣ ደኃውን ህዝብ በኃይል ማባረር እና ማፈናቀል ለመሸፈን ሲባል በዓለም ባንክ የተፈበረከ ትረካ ነው፡፡ የዓለም ባንክ የወደፊት የከተሞች እድገት እንደ አዲስ አበባ ያሉት ከፍተኛ የሆነ መልክዓ ምድራዊ እና የቦታ መስፋፋት ምክንያት ከያዙት የከተማ ድንበር አልፈው ወደ ጎረቤት ማዘጋጃ ቤቶች እና አካባቢዎች የመስፋፋት አስፈላጊነትን በማቅረብ ይሞግታል፡፡ የመስፋፋቱ ሁኔታ ባካባቢው ላሉት ተጠቃሚዎች ቀልጣፋ የሆነ አገልግሎት ለማቅረብ እና የከተሞች ቀጣይነት ባለው መልኩ በመተግበር የከተማውን አካባቢ ማስፋፋት ነው፡፡

oromia

ግልጽ በሆነ መልኩ ለማስቀመጥ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ደኃ አርሶ አደሮችን ከይዞታቸው በማፈናቀል ለዘ-ህወሀት፣ ለስርዓቱ ተጣቃሚዎች እና  ለጥገኛ ምሁር ተብዬ ነቀዞች የግል ይዞታ ለማድረግ በዓለም ባንክ/ዘ-ህወሀት የተቀየሰ ደባ እና ሽረባ ነው፡፡

በእርግጥ የዓለም ባንክ ከዘ-ህወሀት ጋር እጅ እና ጓንት በመሆን በልማት ስም የአካባቢውን ህዝብ ሲያፈናቅል መቆየቱ አዲስ ነገር አይደለም፡፡ ባንኩ የመሰረታዊ አገልግሎቶች ጥበቃ ፕሮጀክት እየተባለ የሚጠራውን አካሄድ ዘ-ህወሀት እንዲጠቀምበት በማድረግ በመንደር በማሰባሰብ (ደህና የሚመስል እና ዜጎችን የሚያፈናቅል፣ ጠራርጎ የሚያባርር፣ ከይዞታቸው የሚነቅል እና ለዘላለም ነባር ኗሪ ህዝቦችን ከኖሩበት ቦታ የሚያፈናቅል) በምዕራብ ኢትዮጵያ የጋምቤላ ህዝቦችን (እና ሌላ አካባቢዎችን) ህዝቦች መሬት በመንጠቅ ለኢንቨስተሮች በመስጠት በመጨረሻም እነዚህ ነጣቂዎች ዋና ሸፍጠኞች በመሆን መሬቱን ነጥቀው ወስደዋል፡፡ (“በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ የሞራል ኪሳራ“ በሚል ያዘጋጀሁትን ትችት ይመልከቱ፡፡)

እ.ኤ.አ ግንቦት 2014 የዓለም ባንክ እንዲህ በማለት ይፋ አድርጓል፣ “ከተሞች በፍጥነት በሚያድጉበት ጊዜ ቀልጣፋ እና ዘላቂነት ያለው አገልግሎት ለማቅረብ እንዲቻል በከፍተኛ ደረጃ የተዘጋጀ ስልታዊ ዕቅድ አስፈላጊ ጉዳይ ነው፡፡“

እ.ኤ.አ የካቲት 2015 ከዓለም ባንክ የተዋቀረ የባሉሙያዎች ቡድን ከመንግስት ባለስልጣኖች፣ ከባለሙያዎች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በቅድሚያ መሰራት ያለባቸውን እና የከተማዋን ችግሮችን የመቋቋም አቅም ለማጎልበት እና የከተማ ፕላንን ለመተግበር በአዲስ አበባ በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ ቡድኑ ያልተጠበቀውን የከተማዋን ዕድገት ለማፋጠን አዲስ የተቀናጀ የከተማ ፕላን በማዘጋጀት በፍጥነት ተግባራዊ መደረግ ይኖርበታል፡፡

እ.ኤ.አ ሀምሌ 2015 የዓለም ባንክ “አዲስ አበባ ኢትዮጵያ፡ የከተሞችን ችግር የመቋቋም አቅም ማጎልበት“ በሚል ርዕስ አንድ ዘገባ አውጥቷል፡፡ ያ ዘገባ አዲስ አበባ ችግርን መጋፈጥ የምትችል ከተማ መሆን አለባት የሚል የክርክር ጭብጥ አቅርቧል፡፡ እናም የከተማዋ የመቋቋም አቅምን ለማጎልበት ሁለገብ፣ የብዙሀን ዘርፎች እና ለከተማ ዕድገት ተለዋዋጭ መንገድን መከተል አስፈላጊ ነው፡፡ አዲስ አበባ እንዴት ነው አደጋን የበለጠ መቋቋም የምትችለው? ዘገባው የተቀናጀ የልማት ዕቅድ እና ተዛማጅነት ያላቸውን ህጎች እንዲሁም በመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ መዋዕለ ንዋይ ለማፍሰስ ከተማዋ የመጀመሪያ እና ቀዳሚ ዓላማ አድርጋ መውሰድ ይኖርባታል የሚል ዘገባ አውጥቷል፡፡

የተቀናጀ የልማት ዕቅድ ማለት ህዝብን በፍጥነት እያደጉ ከመጡት ክልሎች ጋር ማገናኘት እና ትናንሽ ከተሞችን እና ክልሎችን በትራንስፖርት እና በኤሌክትሪክ መረብ በማገናኘት በጣም ትላልቅ ከተሞች ውስጥ ፋብሪካ ማቋቋም ውድ ስለሆነ ትናንሽ ከተሞች ኢንዱስትሪዎችን መሳብ ይችላሉ፡፡

በቀላል አባባል ለማስቀመጥ የተቀናጀ ልማት ማለት በከተማዋ አቅራቢያ ያለውን መሬት እያግበሰበሱ ለኪስ ማድለቢያ በማዋል በከተማው ውስጥ ስርዓት የለሽ ሁኔታ እንዲፈጠር እና የላሸቀ ሞራል እንዲፋጠን ማድረግ ነው፡፡

በአዲስ አበባ አካባቢ ያለውን ማህበረሰብ በማካተት በዘ-ህወሀት የሙስና አገዛዝ የተቀናጀ የልማት ዕቅድ ለማምጣት እንዲያው ከቅንነት አኳያ በህልወት ደረጃ እንኳ ተግባራዊ ሊሆን ይችላልን?

ደህና፣ እንግዲህ ይህ ይሆናል ብለን የምናስብ ከሆነ በገሀነም በረዶ ላይ ሰይጣን ሸርተቴ ይጫወታል እንደ ማለት ነው?

የዚህ መልስ “በኢትዮጵያ ሙስናን መመርመር“ የዓለም ባንክ ባዘጋጀው ሰነድ ከገጽ 285 – 326 ላይ ሰፍሮ ይገኛል፡፡ በዚያ ዘገባ ላይ እ.ኤ.አ በ2013 በርካታ ትችቶችን ያዘጋጀሁ ሲሆን almariam.com በሚለው ድረ ገጽ ላይ ይገኛል፡፡

የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ የመሬት ሙስና ጥናት የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በአካባቢው ህዝብ ላይ አሉታዊ የሆነ እንደምታ ሊያስከትል እንደሚችል በግልጽ አስቀምጧል፡፡ ያ ጥናት እንዲህ በማለት ደምድሟል፣ “መከፋፈል የሌለበት መሬት በመከፋፈል ላይ ይገኛል፡፡ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ቀርቷል፣ እናም አብዛኞቹ አረንጓዴ አካባቢዎች እና በማስተር ፕላኑ ላይ የነበሩት መንገዶች ለግል ጥቅም እንዲውሉ ተደርጓል፡፡“ (ገጽ 303፡፡)

ሆኖም ግን ሰላማዊ አመጽ በማድረግ እና የማስተር ፕላኑ ለጊዜው እንዲቆም የደፋሮቹ ኢትዮጵያውያን መስዋዕትነት ባይታከልበት ኖሮ ኦሮሚያ ተጨማሪ 36 ትናንሽ እና ትላልቅ ከተሞችን ታጣ ነበር፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ታስቦ የነበረው ዕቅድ የአዲስ አበባን ወሰን ወደ 1.1 ሚሊዮን ሄክታር ከፍ እንዲል ያደርገው ነበር፡፡ ይህም አሁን ካለበት ስፋት ሀያ ጊዜ እጥፍ እንዲበልጥ ያደርገው ነበር፡፡

በቀላል አገላለጽ በመቶዎች እና በሺዎች የሚቆጠሩ አርሶ አደሮች እና ኗሪዎች ብቻ ሳይሆኑ ከዚህም በላይ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ጉዳት ከደረሰባቸው አካባቢዎች በኃይል እንዲባረሩ እና እንዲፈናቀሉ ይደረጉ ነበር፡፡

የዘ-ህወሀት የመሬት ነጠቃ ዕቅድ፣

የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን እየተባለ የሚጠራው የሚያስከትለውን እንደምታ በውል በመገንዘብ በኢትዮጵያ የመሬት የባቤትነት መብት ባህሪ ምን እንደሚመስል መገንዘብ ይቻላል፡፡

እ.ኤ.አ በ1995 ዘ-ህወሀት ያዘጋጀው ህገ መንግስት እንዲህ በማለት ያውጃል፣ “የገጠር እና የከተማ መሬት የባለቤትነት መብት እንዲሁም ሁሉም የተፈጥሮ ሀብት በብቸኝነት የመንግስት እና የኢትዮጵያ ህዝቦች ነው፡፡ መሬት የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሶበች እና ህዝቦች የጋራ ሀብት ነው፡፡ እናም አይሸጥም ወይም ደግሞ በማንኛውም መንገድ አይለወጥም፡፡“ (አንቀጽ 40 (30)፡፡)

መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ የገጠር እና የከተማን መሬት በብቸኝነት የባለቤትነት መብት ቢኖረው ኖሮ ግልጽ የሆነው ጥያቄ እንዲህ የሚል ነው፡ “በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በብቸኝነት እና በአጠቃላይ የመንግስት ባለቤትነት ያለው ማን ነው? ባለፉት 25 ዓመታት የመንግስት መዋቅሩን በብቸኝነት ተቆጣጥሮ መንግስቱን ሲዘውረው የቆየው ማን ነው?“ መልሱ ከዚህ ጥያቄ ጋር የተያያዘ ነው: እ.ኤ.አ ግንቦት 2015 የተካሄደውን የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ በ100 ፐርሰንት ያሸነፈው ማን ነው?

በኢትዮጵያ ሁሉም መሬት በመንግስት ቁጥጥር ስር የመዋሉ ጉዳይ ለመሬት ሙስና ዋና ምንጭ ለመሆን በቅቷል፡፡

የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ የሙስና ዘገባ እንዲህ በማለት ይገልጻል፣ “በኢትዮጵያ የመሬቱ ዘርፍ በተለየ መልኩ ለሙስና እና ለኪራይ ሰብሳቢነት የተጋለጠ ነው፡፡ ይህም ማለት ምንም ዓይነት አዲስ ሀብት ሳይፈጠር የነበረውን ሀብት በማህበራዊ ወይም በፖለቲካ ተቋማት አማካይነት ለተለያዩ የህብረተሰብ ቡድኖች ማከፋፈል ነው፡፡“

ሀብታሞቹ እና ተጽዕኖ ፈጣሪዎቹ የዘ-ህወሀት ግለሰቦች፣ ዝምድና ያላቸው ቡድኖች እና ሆድ አምላኩ ጥገኛ ምሁራን ተብየዎች የድሆችን መሬት በመያዝ በግዳጅ በማፈናቀል ሆኖም ግን በህጋዊ መንገድ ማስወገድ እና የማየቀረውን ድርጊት በመፈጸም ዜጎች እንዲገለሉ ያደርጋሉ፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ በዘ-ህወሀት እና በዓለም አቀፍ መዋዕለ ንዋይ አፍሳሽ ሸፍጠኞች ሲካሄድ የነበረውን ደባ ለዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና ለአካባቢ ጥበቃ ድርጅቶች ስራዎች ምስጋና ይግባና ጉዳዩ በዓለም አቀፍ ደረጃ ታላቅ ትኩረት እንዲያገኝ እና እንዲጋለጥ ተደርጓል፡፡ የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ የሙስና ሰነድ እንዲህ በማለት ጠቁሟል፣ “በርካታ የሆነ የተወሰደው መሬት የግል ፍላጎት ላላቸው ሰዎች እንዲዛወር ተደርጓል፣ ሆኖም ግን አነስተኛ ይዞታ ላላቸው ዜጎች አይደለም፡፡“

አነስተኛ የመሬት ይዞታ ያላቸውን አርሶ አደሮች ማፈናቀል እና ወደ አዲስ ቦታ እንዲሰፍሩ ማድረግ ጠቀሜታው ሰፋፊ የንግድ እርሻ ለሚያካሂዱ የአበባ እርሻዎችን፣ ባዮ ፊዩል እና ሌሎችን ሸቀጦች ለሚያመርቱ ሰዎች ነው፡፡

በዘ-ህወሀት እየተካሄደ ያለው የውስጥ የመሬት ዘረፋ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ብዙም ትኩረት አልተሰጠውም፡፡ ሆኖም ግን ከፍተኛ የሆነ ውድመትን እያስከተለ ነው፡፡

በቀረበው የሙስና ዘገባ መሰረት የውስጥ የመሬት ዘረፋው ሂደት ትንሽ ቁራጭ መሬትን ለይቶ በማውጣት ይጀምርና ከማዘጋጃ ቤቱ ጋር የሊዝ ስምምነት ማድረግ ይጀመራል፡፡ ለዘ-ህወሀት ምቹ እንዲሆን ምንም ዓይነት መመሪያዎች የሉም፡፡ ይህም በመሆኑ በዘገባው ገጽ 302 ላይ እንዲህ ይላል፡

“በርካታ ሙስና አለ…መሬት ለማግኘት ያሉት ህጎች ግልጽ አይደሉም፣ እናም ጥቂት ሰዎች በአብዛኛው ባላቸው ግንኙነት ወይም ደግሞ ጉቦ በመክፈል ከሌሎች የተሻለ መሬት የማግኘት ዕድል አላቸው፡፡ የግሉ ዘርፍ በዚህ አይተማመንም ወይም ደግሞ ሊዙን ይጠባበቃል ወይም የጨረታ ሂደቱን ይከታተላል፡፡ ስለሆነም ሁልጊዜ ሌሎች አማራጮችን ይመለከታል፡፡ የማዘጋጃ ቤቱን መሬት ህገወጥ በሆነ መልኩ አሳልፎ ለሌላ ለመስጠት የሚጠቀሙበት ቁልፍ መንገድ በአልሚዎች ቁጥጥር ስር ላሉት የቤት ስራ ማህበራት በመደልደል ከዚያ በኋላ በህገወጥ መልክ መሬቱን ይሸጡታል፡፡ መሬቱን የሚገዙት ሰዎች ስለመሬቱ የህጋዊነት ሁኔታ የሚያውቁት ነገር የለም፡፡“

እንግዲህ መልሱ ከዚህ ላይ ይገኛል፡፡ የመንግስቱን ስልጣን የያዙት ሰዎች የመሬት ባለቤትነቱንም ይይዛሉ፡፡ የመሬት ባለቤትነቱን የያዙት እና መንግስት እስከ አጥንታቸው ድረስ በሙስና የበከቱ ናቸው፡፡ የዓለም ባንክ ይህንን ዓይነት ድርጊት ፈጽሟል አላልኩም!

በመሬት ላይ እየተካሄደ ያለ ሙስና በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የሁሉም ሙስናዎች ሁሉ ዋና ስር ነው! ታላቁ የመሬት ሙስና በከፍተኛው የስልጣን እርካብ ላይ ካሉት ቡድኖች እና ከግሉ ዘርፍ የሚመነጭ ነው፡፡ ኃይለኞቹ የዘ-ህወሀት የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ልሂቃን ህገወጥ አሰራርን፣ የዘፈቀደ አካሄድን፣ ሚስጥራዊ አያያዝን፣ ተጠያቂ ያለመሆንን እና የአስተዳደር ስርዓቱን ግራ በማጋባት ሽባ እንዲሆን በማድረግ የእራሳቸውን የሙስና እና የኪራይ ሰብሳቢነት መረባቸውን ይዘረጋሉ፡፡

የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ የሙስና ዘገባ መሰረት በመሬት ዘርፉ በኢትዮጵያ ውስጥ ውስብስብ የሆኑ በርካታ የሙስና መንገዶች እንደሚፈጸሙ ግልጽ ያደርጋል፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ልሂቃን እና ከፍተኛ ባለስልጣኖች በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን ተፈላጊ የሆነ መሬት ለእራሳቸው ነጥቀው ይወስዳሉ፡፡ እነዚህ የዘ-ህወሀት ወፍራም ድመቶች በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን ደካማ ፖሊሲ እና የሕግ ማዕቀፍ እንዲሁም ያሉትን ፖሊሲዎች እና ህጎች ደካማ አፈጻጸም ለእራሳቸው ጥቅም እንዲውሉ ያደርጓቸዋል፡፡ በሁሉም የከተማ እና የገጠር አካባቢዎች፣ ከቤት ስራ ማህበራት እና ከከተማ አካባቢ አልሚዎች ጋር ግንኙነት በመፍጠር የሙስና ስራ በመስራት መሬቱን ለእነርሱ እንዲመደብ ያደርጋሉ፡፡ እነዚህ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች እና በጥብቅ የተሳሰሩ ግለሰቦች ያሉትን ሕጎች እና ደንቦች በመጣስ ለእነርሱ መሬት እንዲመድቡ ያደርጋሉ፡፡

ሌላው የመሬት ሙስና ቁልፍ ዘዴ የማዘጋጃ ቤትን መሬት ህገወጥ በሆነ መንገድ በአልሚዎች ቁጥጥር ስር ለተያዙት የቤት ስራ ማህበራት እንዲሰጡ በማድረግ ግልጽ ባልሆነ መንገድ እንዲሸጥ ያደርጋል፡፡ ሁልጊዜ መሬት የገዙ ሰዎች የተሸጠላቸውን መሬት ህጋዊነት አያውቁትም:: በመጨረሻም እነዚህ ገዥዎች በሙስና ከተዘፈቁት ባለስልጣኖች አጋሮች ጋር ከፍትህ አካል ፊት ይቆማሉ፡፡

ሌላው ቁልፍ የመሬት ሙስና ቁልፍ መንገድ ባለስልጣኖች የሀሰት ሰነዶችን በማዘጋጀት ሙስና የሚሰሩበት መንገድ ነው፡

“ትክክለኛውን ነገር ለመመዝገብ የሚያስችል ስርዓት ውስንነት በተለይም በከተማ አካባቢዎች እና ውስን ምልከታ በመኖሩ ምንክያት ባለስልጣኖች የሀሰት ሰነዶችን ለማዘጋጀት በርካታ የሆኑ ዕድሎች አሏቸው፡፡ አንድ ቁራጭ መሬት ለበርካታ ሰዎች የመስጠቱ ሁኔታ የተለመደ ነው፡፡ ከዚህም ሂደት ባለስልጣኖች እና አቀባዮቻቸው በርካታ የልውውጥ እና የአግልግሎት ክፍያዎችን ይሰበስባሉ፡፡“

የሊዝ የጨረታ አወጣጥ ሂደቱን በሚያዩት በቦርድ አባላት መካከል ያለ ዓይን ያወጣ የፍላጎት ግጭት፣ ለሊዝ አሰጣጡ እና አከፋፈል የክትትል ስርዓት ያለመኖር እና የመሬት አጠቃቀም ሕግ ባለመኖሩ ምክንያት በኢትዮጵያ ውስጥ እየተስፋፋ የመጣውን ሙስና እንዲፋጠን አድርጎታል፡፡

የሀገሪቱ መናገሻ ከተማ በሆነችው በአዲስ አበባ ለከተማው አስተዳደር ባለስልጣኖች ጉቦ ሳይሰጥ ቁራጭ መሬት ማግኘት ፈጽሞ የሚቻል ጉዳይ አይደለም፡፡ እነዚህ ባለስልጣኖች ግዙፍ የሆነ ጉቦ ብቻ አይደለም የሚጠይቁት ሆኖም ግን ከዚህም በተጨማሪ ለግዙፍ የመሬት ቅርምት እንዲመቻቸው ከመሬት ዋጋ ተንባዮች ጋር እና የህገ ወጥ የሸፍጥ ስራውን ከሚያቀላጥፉላቸው የቤት ስራ ማህበራት ጋርም ደባ ይሰራሉ፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ባለፉት አምስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ብቻ 15,000 የተጭበረበሩ ስያሜዎች እንደታተሙ ይገመታል፡፡

ይህንን ነው እንግዲህ የዓለም ባንክ በእርግጠኝነት የተናገረው!

ስለሆነም የትኞቹ የመንግስት ባለስልጣኖች ናቸው ግዙፍ የሆነ ጉቦ የሚጠይቁት? ደህና፣ እነማን ናቸው የመንግስትነት ስልጣኑን የያዙት ባለስልጣኖች?

በተመሳሳይ መልኩ የገጠር መሬት አስተዳደርም በዘ-ህወሀት ሙስና ጥልቅ በሆነ መልኩ ተበክሏል፡፡ በገጠር አካባቢዎች ባለስልጣኖች የሕዝብ መሬትን ትርጉም የመንግስት መሬት በማለት አዛብተው ያቀርቡታል፡፡ ባለስልጣኖች ሕዝብን ለማፈናቀል ሲፈልጉ እና በመጨረሻም ለመሬት የለሽነት ለሚዳርገው ተግባር ለህዝብ ጥቅም ዓላማ የሚል ትርጉም ይሰጣሉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ባለስልጣኖች ለሌሎች ብዙም እርባና በሌለው ተግባር ላይ ተሰማርተው ለሚገኙ ባለስልጣኖች መሬት ነጥቀው በመስጠት ተግባራት ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ሲሆን ይህ ድርጊት በወረዳ ደረጃ ላይ የሚፈጸም ሲሆን ይህም ድርጊት በተመሳሳይ መልኩ በቀበሌ ደረጃ በተመረጡ የኮሚቴ አባላት ደረጃ እንዳለ ተቀድቶ ተግባራዊ ይሆናል፡፡ እንደ የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ የሙስና ዘገባ ከሆነ ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ከመሬት ጋር በተያያዘ ሁሉም የልውውጥ ስራዎች ሁልጊዜ ሙስናን ያካትታል፣ ምክንያቱም መሬትን በሚመለከት ግልጽ የሆነ ፖሊሲ ወይም ደግሞ ግልጽ የሆነ ሕግ የለም፡፡

ቀላል በሆነ መንገድ ለማስቀመጥ የህዝብ የሚባል መሬት የለም፡፡ ያለው የመንግስት መሬት ብቻ ነው፡፡ ደህና፣ ማን ነው የመንግስት ስልጣንን እና መሬትን የያዘው?

ዘ-ህወሀት በጣም ተራ የሆነውን የመሬት አስተዳደር ስርዓት በስራ ላይ ያላዋለ መሆኑን ከዓለም ባንክ ዘገባ መማር በጣም አስደናቂ ነገር ነው፡፡ የዓለም ባንክ ዘገባ እንዲህ ይላል፡

“የገጠር አካባቢዎች የተመዘገበ የመሬት ይዞታ ካርታ የላቸውም…በከተማ አካባቢዎች ጥቂት የተመዘገቡ ንብረቶች ካርታ አለ፡፡ ዕዳዎች እና ክልከላዎች በመመዝገቢያ ሰነዱ ላይ አይመዘገቡም፡፡ ሆኖም ግን ዕዳዎች የሚመዘገቡ ከሆነም እራሱን በቻለ በሌላ ሰነድ ላይ ነው የሚመዘገቡት፡፡ የመሬት አጠቃቀም ክልከላዎች በመመዝገቢያ ሰነዱ ላይ አይመዘገቡም፡፡ የህዝብ መሬት ቆጠራ የለም፡፡ ይህም ደካማ የሆነ የህዝብ መሬት አስተዳደር ህገወጥ በሆነ መልኩ የህዝብን መሬት ለግል ቡድኖች እና ግለሰቦች መሬት የማግኘት ዕድልን ይፈጥራል፡፡“

በአሁኑ ጊዜ ያሉት ተ ቋማት እና ሕጎች የተሸረሸሩ፣ የተተው እና ለግል ጥቅም ሲባል የሚፐወዙ በመሆናቸው ምክንያት የመሬት አስተዳደር ስርዓቱ ሙሉ በሙሉ ውድቀት ደርሶበታል፡፡ ይህም በመሆኑ በስልጣን ላይ ያሉት ባለስልጣኖች እየፈጸሟቸው ላሉት የሙስና ተግባራት  ተጠያቂ መሆን አልቻሉም፡፡

ሆኖም ግን ይህ ቀውስ የበዛበት የመሬት አስተዳደር ስርዓት ሆን ተብሎ የዘ-ህወሀትን የመሬት ነጠቃ አዳኝነት ተሞክሮ ለማሳደግ እና ለማፋጠን ተብሎ ነውን?

መሬት መዝረፍ ወይም የግል ሀብት መንጠቅ፣

የዘ-ህወሀት ህገ መንግስት “ለህዝብ ጥቅም ሲባል የግል ሀብት በሚወሰድበት ጊዜ አስቀድሞ በቂ የሆነ የካሳ ክፍያ በመክፈል ይሆናል“ በማለት ለዘ-ህወሀት ስልጣን ይሰጣል፡፡ (አንቀጽ 40፡1)፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ዘ-ህወሀት ለሕዝብ ጥቅም በሚል ሰበብ መሬትን ለመዝረፍ እንዲችል አዋጅ ቁጥር 455/2005ን አውጥቷል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ከዚህ ጋር በተያያዘ መልኩ በመሬት ይዞታ ላይ ያለን ሀብት ለመውረስ በሚፈለግበት ጊዜ የካሳ ክፍያ ለመክፈል በሚል የይስሙላ አካሄድ የካሳ ክፍያ እና የምኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 135/2007ን አውጥተቷል፡፡

እነዚህ ሁሉ ሕጎች በእውነት ጥርስ አላቸውን? ወይስ መሳቂያ ናቸው? ወይም ደግሞ ዘ-ህወሀትን በገንዘብ የሚያንበሸብሹት እና የመሬት ዘረፋው እንዲካሄድ የሚያግዙትን ዓለም አቀፍ የድህነት አቃጣሪዎችን ደስ ለማሰኘት ሲባል ዝም ብለው ለቃላት ፍጆታ (እንደ ዘ-ህወሀት ሕገ መንግስት) በወረቀት ላይ የተጻፉ ናቸው?

የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ያደረገው የሙስና እና ሌሎች ጥናቶች በግልጽ እንደሚያመላክቱት እደዚህ ያሉ ሕጎች ከተማን ከመስፋፋት፣ የኢንዱስትሪ ዞኖችን እና ሌሎች ፕሮጀክቶችን ከማመላከት አንጻር የአካባቢ ማዘጋጃ ቤቶች በቂ የካሳ ከፍያ ገንዘብ የሌላቸው በመሆናቸው ፋይዳ የሌላቸው ትርጉመ ቢስ ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት የከተማ መስፋፋት ሂደት ባብዛኛው ያለምንም የካሳ ክፍያ ወይም ደግሞ በቂ ያልሆነ የካሳ ክፍያ በመስጠት ወይም የመሬት ባለይዞታዎችን ያለምንም ማቅማማት ከይዞታቸው ኃይልን በመጠቀም ያለምንም የሕግ የይግባኝ አቤቱታ ማባረር  ነው፡፡ ግልጽ በሆነ መንገድ ለማስቀመጥ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን የዘ-ህወሀት የመሬት ዘረፋ ማሰተር ፕላን ነው!

ዘ-ህወሀት መንግስትን ከመሬት ባለቤትነት ለማስወገድ ወይም ደግሞ መሬት በግሉ ዘርፍ በግል ሀብትነት እንዲያዝ ዕቅዱም ፍላጎቱም የለውም፡፡ የገንዘብ ማካበቻ እና ማግበስበሻ ምንጫቸውን በፈቃደኝነት ለምን ብለው ይለቃሉ?

ዘ-ህወሀት የኢትዮጵያ ፊውዳል ታሪክ ከኋላ ቀሩ ባህላዊ የመሬት ይዞታ ስሪት ጋር በመቀላቀል ጠፍተው የነበሩት የመሬት ከበርቴዎች እንደገና ተመልሰው ይቆጣጠሩታል፣ እናም መሬት የሌላቸውን ህዝቦች ይበዘብዛሉ፣ ወዘተ በማለት ይሰብካሉ፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ዘ-ህወሀት የመሬት አስተዳደሩን በተሻለ ሁኔታ መያዝ እንደሚችል ይናገራል፡፡ እኮ ለማን ነው የተሻለ የሚያደርገው?

በእርግጥ ዘ-ህወሀት የኢትዮጵያን መሬት ለኢትዮጵያ ህዝብ ጥቅም እንዲያስተዳድረው መጠበቅ ማለት ቀበሮ የዶሮዎችን ማደሪያ ቤት ወይም ደግሞ ተኩላ የበግ ለምድ በመልበስ የበጎችን ጋጥ ማስተዳደር እና መጠበቅ እንዲችሉ መፍቀድ ማለት ነው፡፡ ይህ ምንም እርባና የሌለው ፋይዳቢስ ጉዳይ ነው!

በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ የመንግስት የመሬት ባለቤትነት ማለት በተጨባጭ የዘ-ህወሀት የመሬት ባለቤትነት ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ዘ-ህወሀት በብቸኝነት የመንግስት መዋቅርን ተቆጣጥሮ ይገኛል፡፡ ለዘ-ህወሀት በኢትዮጵያ የመሬት ባለቤትነት መብትን መልቀቅ ማለት የመንግስት ስልጣንን የመልቀቀቅ ያህል ከባድ ነገር ነው፡፡ በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን መሬት በብቸኝነት በይዞታ ከመያዝ ውጭ ዘ-ህወሀት ምንም ዓይነት ምርጫ የለውም፡፡

ለዘ-ህወሀት የመሬት ይዞታ ባለቤትነት ማለት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖረውን የእያንዳንዱን 100 ሚሊዮን ህዝብ ህልውና መቆጣጠር ማለት ነው፡፡

መሬት ለዘ-ህወሀት ጉቦ እየተባለ የሚጠራው ስጦታ መስጠት ማለት ነው፡፡

መሬትን መቆጣጠር ማለት የገጠሩን ህዝብ ድምጽ መያዝ ማለት ነው (ድምጽ መስረቅ ማለት ነው)፡፡

ለዘ-ህወሀት መሬት የመጨረሻ የሆነውን ፍጹም ስልጣን የመያዝ ምንጭ ነው፡፡ ስልጣን ያባልጋል የሚለው እውነት ከሆነ በመሬት ላይ የሚፈጸም ሙስና በስልጣን መባለግን ያስከትላል፡፡

ዘህወሀት ወደ ታሪክ ቆሻሻ ቅርጫት እስከሚጣል ድረስ ከእያንዳንዷ ቁራጭ መሬት ጋር እንደ መዥገር ተጣብቆ ይቆያል፡፡

እውነታው ፍርጥርጥ ተደርጎ ሲታይ ዘ-ህወሀት የህዝብን ድምጽ መቶ በመቶ ተቆጣጥሮ ይገኛል፡፡ የህዝብ ተወካዮች እየተባለ የሚጠራውን ይስሙላውን ፓርላማ ተብዬ መቶ በመቶ ተቆጣጥሮ ይገኛል፡፡

ዘ-ህወሀት በሀገሪቱ ውስጥ መሬትን መቶ በመቶ ተቆጣጥሮ ይገኛል፡፡

እንግዲህ ይኸ ሁሉ ሁኔታ ዘ-ህወሀት በአሁኑ ጊዜ በዘመናዊት ኢትዮጵያ አዲስ ምስለኔ፣ ገዥ እና አድራጊ ፈጣሪ መኳንንት ሆኖ ይገኛል፡፡

በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ያለው የጎሳ ፌዴራሊዝም በመካከለኛው  ክፍለ ዘመን እንደነበረው ዓይነት ስያሜ ሊኖረው አይችልምን?

የመካከለኛው ክፍለ ዘመን የፊውዳል ንጉስ በሀገሪቱ ውስጥ የሚገኘውን ሁሉንም መሬት ይቆጣጠራል፣ እናም የሚፈልገው ብቻ መጠቀም እንዲችል ይፈቅዳል፡፡ ሁልጊዜ በሚባል መልኩ ንጉሱ መሬቱን ለሚያምናቸው እና ለእርሱ በቃለ መሀላ ታማኝ ለሆኑ ሎሌዎቹ ብቻ ይሰጣል፡፡ የንጉሱ ሰዎች ባሮን እየተባሉ የሚጠሩ ሲሆን ለንጉሳቸው ይዋጉ ነበር፡፡ ባሮኖች በጣም ሀብታሞች፣ ኃይለኞች እና ከንጉሱ ላይ በሊዝ በያዙት መሬት ላይ ሙሉ በሙሉ ተቆጣጣሪ ሆኑ፡፡

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ በክልል መንግስታት እየተካሄደ ያለው ይኸ አይደለምን ወይም ደግሞ በትክክለኛው ስማቸው የማዘጋጃ ቤት ኃላፊዎች ብለን ልንጠራቸው አንችልምን?

ለዘ-ህወሀት ሌቦች (አለቆች ማለቴ ነው) ጽናቱን ይስጣቸው፡፡

የዘላለማዊ ቁጥጥር አስፈላጊነት፣

ዘ-ህወሀትን አሻፈረኝ ብለው ከባድ የህይወት መስዋዕትነት በመክፈል ያባረሩት እና የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ዜሮ እንዲሆን ያስገደዱት በአሁኑ ጊዜ ከፍተኛ በሆነ የደስታ ስሜት ውስጥ ሊገኙ እንደሚችሉ እና የአይበገሬ የአሸናፊነት ስሜት ይሰማቸዋል፡፡ ከዚህም በላይ ዘ-ህወሀትን ሙሉ በሙሉ ድል እንዳደረጉት ያህል ሆኖ ይሰማቸዋል፡፡

እንደዚህ ያሉ ስሜቶች ዝም ብለው የየዋህነት ስሜቶች ብቻ አይደሉም ሆኖም ግን ለመጨረሻ ጊዜ የተሳሳቱትን ስሌቶች በተጨባጭ ስህተት መሆናቸውን የሚያረጋግጡ እንጅ፡፡

ጸሐይ ነገ ትወጣለች ከሚለው እርግጠኝነት አኳያ የዘ-ህወሀት የመሬት ተቀራማች ዘራፊዎች በፍርሀት በመዋጥ ጥንብ አንስተው እንደሚበሩ አሞራዎች (ጆቢራዎች) እንደገና ተመልሰው ይመጣሉ፡፡ በእርግጥ የተነሳውን እና የቦነነውን አቧራ ለማረጋጋት ሲሉ ጸጥ በማለት ካሰለፉ በኋላ በከፍተኛ የበቀልተኝነት ስሜት ታጅበው እንደገና ብቅ ይላሉ!

በእርግጥ የዘ-ህወሀት አለቆች በኃይል ወደኋላ እንዲያፈገፍጉ በመደረጋቸው ግራ ተጋብተዋል፡፡ ከስርዓቱ አፈቀላጤ ከጌታቸው ረዳ የሚወጡ የቅጥፈት ቃላት ዘ-ህወሀት እንደ ድሮው ሁሉ እንደፈለገው መሬት እየዘረፈ ሊኖር እንደማይችል እና የዘ-ህወሀት አለቆች ምን ያህል እንደተደናገጡ እና ይይዙት ይጨብጡት እንዳጡ የሚያመላክት ነገር ነው፡፡ (የዘ-ህወሀት አለቆች ተመልሰው ወደ ላይ ከፍ እንደማይሉ እና በሰሩት ነገር ላይ ምንም ዓይነት ገለጻ ማድረግ እንደማይችሉ ፍጹም ፍጹም በሆነ መልኩ እና ሊሆን በማይችልበት ደረጃ እርግጠኛ ሆኘ መናገር እችላለሁ፡፡ ወያኔዎች ሁልጊዜ እንደ ጌታቸው ረዳ ወይም ደግሞ እንደ ሬድዋን ሁሴን ያሉ ለእራሳቸው ብቻ ንግግር ከሚያደርጉት የወደቁ ሙትቻ የስርዓቱ አፈቀላጤዎች ጀርባ ይቆማሉ፡፡) ኃይለማርያም ደሳለኝስ እንደዚህ ዓይነት ተመሳሳይ ድርጊት እየፈጸመላቸው አይደለምን?)

ዘ-ህወሀት እንደገና በአንድ ወቅት ይመለስ እና ይህንኑ መሬት ሊዘርፍ ይችላል፡፡

ይህ ጉዳይ የዱሮውን አስቸጋሪ የቃላት ድርደራ ስርዓት ሊያስታውስ አይችልምን? እንጨት ቆርጣሚ ዓይጥ እንጨት መቆርጠም የሚችል ከሆነ ምን ያህል እንጨት ሊቆረጥም ይችላል?

ደህና፣ የዘ-ህወሀት መሬት ዘራፊዎች መሬት መዝረፍ የሚችሉ ከሆነ ምን ያህል መሬት ሊዘርፉ ይችላሉ?

ሊካድ የማይችለው ዋናው ነገር የዘ-ህወሀት አለቆች እና ወፍራም ድመቶች በአዲስ አበባ አካባቢ የሚገኘውን መሬት ለመቀራመት እና ለመዝረፍ ምራቆቻቸውን ከምላሶቻቸው ላይ በማንጠባጠብ ላይ የሚገኙ የመሆናቸው ጉዳይ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ሁሉንም ነገር ለማግኘት ማንኛውንም ነገር ያደርጋሉ፡፡ ጊዜ ተበድረው ቢሆን ይሰራሉ፡፡

ዘ-ህወሀት በሚቀጥለው ጊዜ የበለጠ ውስብስብ ሆኖ ይቀርባል፡፡ በሚቀጥለው ጊዜ በማስተር ፕላኑ ላየ ዘ-ህወሀት ተከታታይነት ክርክር ወይም ደግሞ የህዝብ ትችት እና ተቃውሞ እንዲሰማ አያደርግም፡፡ መሬትን ለመዝረፍ በዝረራ አይሸነፉም፣ ድርጊቱን በማዘግት ለመፋለም ጥረት ያደርጋሉ፡፡ ሁሉንም ነገር በሚስጥር፣ ስልታዊ በሆነ መንገድ እና በውል ሊታይ በማይችል መልኩ ይሰራሉ፡፡

ዘ-ህወሀት ማስተር ፕላኑን እንደተውት የሚመስል ግንዛቤ በህዝቡ ላይ በማሳደር እያንዳንዱን ሰው ጸጥ ለማድረግ ጥረት ያደርጋል፡፡ ለውጤቱ የበለጠ የፕሮፓጋንዳ ስራ ይሰራሉ፡፡ እስከ አሁን ሲኖር የነበረው ማስተር ፕላን ሞቶ ተቀብሯል ብለው ያስወራሉ፡፡ ለኦሮሞ ህዝብ ሌላ የማህበረሰብ ፕሮጀክት (ዕቅድ ሳይሆን) በማዘጋጀት ከህዝቡ ጋር አብረው ለመስራት ቃል ይገባሉ፡፡ (ከዚህ በኋላ ዘ-ህወሀት “ማስተር” የሚለውን ቃል በማንኛውም ለህዝብ በሚያቀርቡት ዕቅድ ውስጥ በፍጹም አይጠቀሙም በማለት በእርግጠኝነት እናገራለሁ፡፡)

ዘ-ህወሀት ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች የሚኖረው ህዝብ ጠባቂዎች እስኪወድቁ ድረስ ጊዜ በመሸመት ዝም ብሎ ይመለከታል፡፡

“በሚፈላ ውኃ ውስጥ ያለ እንቁራሪት“ የሚለውን አሮጌ ስልት ይጠቀማሉ፡፡ እንቁራሪትን በፈላ ውኃ ውስጥ ብትጨምራት ወዲያውኑ ከመቅጽበት ዘላ ትወጣለች፡፡ ሆኖም ግን እንቁራሪትን በቀዘቀዘ ውኃ ማሰሮ ውስጥ ብትጥላት እና ቀስ በቀስ ሙቀት በመስጠት በዝግታ እየፈላ እንዲሄድ ብታደርግ እንቁራሪቷ እዚያው ተቀቅላ እስክትሞ ድረስ ልትቆይ ትችላለች፡፡

ዘ-ህወሀት በአንድ ጊዜ ሁሉንም መሬት ለመዝረፍ ሙከራ አደረገ፣ እናም ህዝቡ በአንድ ጊዜ ገንፍሎ ወጣ እና ተቃውሞውን አሰማ፡፡

ሆኖም ግን የመሬት ቅርምት ዝርፊያው ቀስ በቀስ የሚከናወን ቢሆን ኖሮ ህዝቡ ዓይኑን ርግብ አያደርግም ነበር፡፡ ችግሩ ተከስቶባቸው በነበሩት አካባቢዎች ህዝቡ የአመጹን አስተባባሪዎች አጋልጦ ይሰጣል ብዬ እሰጋለሁ፡፡

እስከዚያው ድረስ ግን ዘ-ህወሀት እጆቹን አጣምሮ ዝም ብሎ አይቀመጥም፡፡ ማስተር ፕላን ቢን (ማስተር ፕላን እንዳላቸው ባታውቁም እንኳ) ወይም ደግሞ የመሬት ዘረፋቸውን በመቃወም የሚያኮላሹባቸውን ስልታዊ እና ዘዴ በተመላበት መልኩ ከጥቅም ውጭ በማድረግ ተግባራዊ ያደርጋሉ፡፡

ዘ-ህወሀት የማስተር ፕላኑን ተግባራዊነት የሚቃወሙትን በማስወገድ ማስተር ፕላን ቢን ተግባራዊ ለማድረግ የሚከተሉት ዘዴዎች አሉት፡

1ኛ) የሚቃወሙትን ሰዎች በገንዘብ መግዛት፣

2ኛ) የሚቃወሙትን ሰዎች ጸጥ በማድረግ፣

3ኛ) የሚቃወሙትን ሰዎች በማስፈራራት እና በማሸበር ከድርጊቱ እንዲወጡ በማድረግ፣

4ኛ) የሚቃወሙትን ሰዎች በማሰር እና በማሰቃየት፣ እና

5ኛ) የሚቃወሙትን ሰዎች በመግደል (በመፍጀት) ነው፡፡

ይኸ አካሄድ ዘ-ህወሀት ሲጠቀምበት የቆየው እና ትክክለኛው የአካሄድ ስርዓት ነው በማለት የሚተገብረው ዘዴ ነው፡፡

ጥቃቱ በተፈጸመባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች ዘ-ህወሀት ጅራቱን በእግሮቹ መካከል በጉያው ወትፎ ተመልሷል ብለው ለአንዲት አፍታም ቢሆን የሚያስቡ ሰዎች ካሉ ብልሀት የሌለው ድፍረትን እያካሄዱ ነው፡፡

የዘ-ህወሀት የጥፋት ሰለባዎች ዘ-ህወሀት አጭበርባሪ፣ ሚስጥራዊ፣አታላይ፣ ደባ ሰሪ፣ ዲያብሎስ፣ ህገ ወጥ፣ ኃይለኛ፣ ሰይጣናዊ፣ በጣም መጥፎ፣ ድብቅ እና ማቻቬሌናዊ አካሄድን የሚከተሉ የዕኩይ ምግባር አራማጅ የፖለቲካ መሰሪዎችን የሚያራምድ አንደነሱ አንደሌለ መረሳት የለበትም፡፡

እነዚህ ሰዎች ከመሬት ቅርምት ዘረፋው እና ከማይነጥፈው የገንዘብ ማግበስበሻ ምንጫቸው በቀላሉ የሚሄዱ አይደሉም፡፡ በአዲስ አበባ አካባቢ ያለውን መሬት በአንድ ጊዜ አግበስብሰው ለመውሰድ የማይችሉ ከሆነ ቀስ በማለት አንድ በአንድ እያሉ መውሰድ ይችላሉ፡፡ምንም ዓይነት ችግር የለም፡፡ የዘ-ህወሀት መሪዎች ደኃ ገበሬዎችን በአንድ ጊዜ ከይዞታ መሬታቸው ላይ በአካል በማባረር መሬታቸውን ካልዘረፉ ጋህነም በማታለል እና በማጭበርበር ከመሬታቸው ላይ የሚያስወግዳቸው መስሎ ይታያቸዋል፡፡

ዘ-ህወሀት ማንኛውንም መንገድ የአካባቢ ግንባር ቀደም ሰዎችን እና ገንዘብ ሰብሳቢዎችን ጨምሮ በኋላ እንዲያስተላልፉላቸው በማሰብ መሬት እንዲገዙ የሚያደርጉ ለመሆናቸው ምንም ዓይነት ጥርጥር የለኝም፡፡ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ከአካባቢው ሰዎች ጋር በመሆን ከግል አልሚዎች ጋር ሽርክና በመፍጠር ለማስመሰል ይሞክራሉ፡፡ ቁርጥራጭ መሬት በተናጠል ለማግኘት እንዲመቻቸው እዩልኝ እመኑኝ ዓይነት ፕሮጀክቶችን ያቀርባሉ፡፡ ማስተር ፕላኑን በሌላ ጣፋጭ በሚመስል የአካባቢ ስም ስያሜ በመስጠት ድብቅ አድርገው ይይዛሉ፡፡ መሬቱን ለመዝረፍ ያለ የሌለ ጥረታቸውን ሁሉ ያደርጋሉ፡፡ ከሁሉም በላይ ፕላናቸው የሚሰራ ከሆነ በአዲስ አበባ አካባቢ የሚገኙትን 36 ትናንሽ እና ትላልቅ ከተሞች እንዳለ ይውጣሉ፡፡ ይኸ እንግዲህ በርካታ የሆነ የመኖሪያ ቦታ ነው!

ዘ-ህወሀት የዘረፈውን መሬት በመያዝ ምላሱን አውጥቶ በማሾፍ ይጓዛል፡፡ ይህም ማለት የዘረፉትን ጥንብ በመያዝ እንደሚበሩት አሞራዎች ዓይነት ማለት ነው፡፡

“የነጻነት ዋጋ ዘላለማዊ ምልከታ ነው“ ይባላል፡፡ የአንድን ሰው መሬት የመጠበቅ ዋጋም ዘላለማዊ ምልከታ ነው እላለሁ፡፡ በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ዘላለማዊ ምልከታ ማድረግ እና በአካባቢው የሚደረጉ ማንኛቸውንም ዓይነት ግብይይቶች በንቃት የመጠበቅ ዕድሎቻቸውን በመጠቀም መሬቶቻቻው ከነጣቂዎች በመጠበቅ የወደፊቱን የልጆቻቸውን ዕድል ማመቻቸት ይኖርባቸዋል፡፡

በቅድመ ፕላን እና በቴክኖሎጂ የታገዘ ችግሮችን በማስወገድ የከተማ ልማትን ማምጣት መቃወሜ አይደለም፡፡ የአዲስ አበባን ማስተር ፕላንን አንብቤዋለሁ እናም በጥንቃቄ አጥንቸዋለሁ፡፡ እ.ኤ.አ ከ2006 – 2030 ድረስ የሚዘልቅ የአዲስ አበባ እና የኦሮሚያ አካባቢ ልዩ ዞኖች በሚል የተዘጋጀ ማስመሰያ ነው፡፡

በአዲስ አበባ አስተዳደር እና በኦሮሚያ ክልል መንግስት የተዘጋጀ የማስመሰያ የሸፍጥ ሰነድ ነው፡፡ ዕቅዱ በተቀናጀ ልማት የአዲስ አበባን ችግሮች መቋቋም በማስመልከት በበርካታ የዓለም ባንክ ዘገባዎች እና የመፍትሄ ሀሳቦች ላይ የተነሱ ጉዳዮችን በመያዝ በጥልቀት እና በዝርዝር ያቀርባል፡፡ ስለመሰረተ ልማት፣ ስለትራንስፖርት፣ ስለአገልግሎቶች፣ ስለኢንዱስትሪ ዞኖች፣ ስለስነምህዳር ክብካቤ፣ ስለአረንጓዴ ልማት ቦታዎች፣ ስለመስኖ እና ስለሌሎች ነገሮች  ይናገራል፡፡ የወደፊት የፓርኮችን፣ የአየር ማረፊያዎችን፣ የክልል ልማት ቦታዎችን በካርታው ላይ ያመላክታል፡፡ እንደ የቴክኒክ ሰነድ ዕቅዱ ልዩ በሆነ መልኩ ዝርዝር ጉዳዮችን በማከተት በዓለም ባንክ የከተማ ፕላን አወቃቀር ተቃኝቷል፡፡

የማስተር ፕላኑ ፍጹም በሆነ መልኩ የተወው ነገር ቢኖር በፕላኑ ምክንያት ጉዳት የሚደርስባቸው ዜጎች ግብዓት ምን ሊሆን እንደሚችል ያለመነካቱ ብቻ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ከተለጠጠ እና የእርሻ እና የግጦሽ መሬቶቻቸውን ሁሉ ከወሰደባቸው በኋላ በዚያ አካባቢ የሚኖሩ አርሶ አደሮች ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል? እነዚህ የጉዳት ሰለባዎች ቤተሰቦቻቸውን እንዴት ነው ሊረዱ የመችሉት? እነዚህ ዜጎች ለዘ-ህወሀት ትርፍ ዜጎች እና በክልል ታዛዥ አጋሮቻቸው እንደፈለጉ የሚጣሉ ዜጎች ናቸው ማለት ነው?

የጀርመን ብሄራዊ ሶሻሊስት የሰራተኞች ፓርቲ በመኖሪያ ቦታ ላይ አውዳሚ የሆነ ደርጊት በመፈጸም እና የኃይል ግዛት የማስፋፋት ዕቅዱን ለመተግበር ህዝብን በመጨረስ፣ በማፈናቀል፣ እና እንደ አርአያኖች ዝርያ ያልሆኑትን በአንተርሜንስቸን ህዝቦች የተያዙትን ህዝቦች በማፈናቀል በጎረቤት ሀገሮች ላይ ጭምር የመስፋፋት ዕቅዳቸውን አካሂደው ነበር፡፡ ብሄራዊ ሶሻሊስቶች ሁለት ቀዳሚ ዓላማዊች ነበሯቸው፡፡ እነርሱም፡

1ኛ) የመኖሪያ ቦታዎችን በኃይል ተቆጣጥሮ መያዝ፣

2ኛ) አይሁዶችን ዘላለማዊ በሆነ መልኩ ማጥፋት ነበር፡፡

በመጨረሻም ብሄራዊ ሶሻሊስቶች ተሸነፉ፡፡

ዘ-ህወሀት ኢትዮጵያን ለመቅበር የጎሳ ፌዴራሊዝምን ጉድጓድ ቆፈረ፡፡ በአሁኑ ጊዜ የጎሳ ፌዴራሊዝም እራሱን ዘ-ህወሀትን ለመቅበር በመዘጋጀት ላይ ይገኛል፡፡

በኦሮሚያ ላይ እንደተደረገው ሁሉ እያንዳንዱ በዘ-ህወሀት የተፈጠረ ክልል ወደ ኋላ የሚገፋ ከሆነ ከዘ-ህወሀት የሚተርፈው ምንድን ነው?

“ጉድጓድ የሚቆፍር ሁሉ እራሱ ይገባበታል፣ እንደዚሁም ሁሉ ድንጋዩን ማንከባለል የሚጀምር ሁሉ እራሱ ድንጋዩ በእራሱ ላይ ይጫነዋል“ ተብሎ ተጽፏል፡፡

ይህ እውነተኛ አምላካዊ ቃል ነው፡፡ ከዚህ ጋር ስምምነት አድርጉ!!!

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!         


ሸገር ራድዮ የባለዲግሪዋ ቆሎ ሻጭ ሐና አዋሽን እናስተዋውቃችሁ ይላል |እኛ ደግሞ በዛውም የኢህአዴግን የትምህርት ፖሊሲ ታዘቡት እንላችኋለን

$
0
0

(ከአዘጋጁ) ቀጣዩ በድምጽና በጽሁፍ የተቀናበረው ዘገባ የተወሰደው ከሸገር ራድዮ ነው:: በሸገር ራድዮ ስለባለዲግሪዋ ቆሎ ሻጭ ሐና አዋሽ ይናገራል:: ዲግሪ ይዛ ቆሎ ሽያጭ ውስጥ ለገባችው ሃና ዋነኛው እና ግንባር ቀደሙ የኢህአዴግ ትምህርት ፖሊሲ ውጤት ነው:: ኢትዮጵያ በርካታ ዜጎች ተምረው ሥራ የማያገኙባት ሃገር ከሆነች ሰነባብታለች:: ታሪኩን ያድምጡ/ያንብቡና አስተያየትዎን እንጠብቃለን::

በ2003 ዓ.ም በታሪክና ቅርስ ትምህርት ከአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ በዲግሪ የተመረቀችው ሐና፣ ለአንድ ዓይኗ መጥፋት እንዲሁም ለፊቷ ማበጥ ሰበብ በሆነባት ሕመም ሳቢያ በተመረቀችበት ሙያ ሥራ ማግኘት አልቻለችም፡፡ ስለዚህም ኑሮን ለማሸነፍ ሐና በደጃች ውቤ ሰፈር ጠጅ ቤቶችና ግሮሰሪዎች እየተዘዋወረች ቆሎ መሸጡን ተያያዘችው፡፡
Hana
የሸገር ልዩ ወሬ አዘጋጁ ወንድሙ ኃይሉ ያነጋገራት ሐና፣ የሰፈሩን መፍረስ ተከትሎ የቆሎ ገበያው ሲቀዘቅዝባት አሁን ላይ ለታክሲ ረዳቶች፣ ተራ አስከባሪዎችና ለሌሎችም የተቀቀለ ድንች በዳጣ ወደመሸጡ ዞራለች ይለናል፡፡

የትምህርት ማስረጃዎቿን ይዛ በየመሥሪያ ቤቱ ብታመለክትም የፊቷን ማበጥ እያዩ ከንፈር ከመምጠጥ ውጪ ማንም ሊቀጥራት የፈቀደ እንደሌለ የምትናገረው ሐና፣ እሷ ግን ላጋጠማት ችግር እጅ እንደማትሰጥ ትናገራለች፡፡

ሐኪሞች የሐና ሕመም የካንሰር ዘር እንደሆነ ነግረዋታል፡፡

ተቸግረው ያስተማሯት እናቷ፣ ሐና ላይ የደረሰውን አንስተው በእንባ እየታጠቡ ሐዘናቸውን ለወንድሙ ኃይሉ ነግረውታል፡፡

ሐና … ይህን የያዘችውን ንግድ የሚደግፍላት አልያም በተማረችበት ሙያ የሚቀጥራት ብታገኝ ደስታዋ እንደሆነ ትናገራለች…

ድህረ-ኢህአዴግ ኢትዮጵያ፤ ከታሪክ ምን እንማራለን? |ደስታው አንዳርጌ (ዶ/ር)

$
0
0

ደስታው አንዳርጌ (ዶ/ር) የካቲት ፩ ቀን ፪ ሺ ፰

ሆ ብለን ተነስተን ወያኔን እናስወግድ ይላሉ። ለውጥ መፈለግ ተፈጥሮሯዊ ነው። ወያኔን የመሰለ መሰሪና አደገኛ ቡድን ይቅርና በጎ የሚባል መንግስትም ቢሆን እድሜው ሲንዘላዘል ያንገሸግሻል። ለውጥ ግን በራሱ ግብ አይደለም። ለውጥማ ተፈጥሯዊ ነው፤ ጊዜውን ጠብቆ ይመጣል። ተፈጥሮ ግን ለውጡን መልካም የማድረግ ግዴታ የለባትም። ለውጥን በሚፈለገው መንገድ መቀየስ የሰወች ድርሻ ነው። ያ ደግሞ ጥበብ፣ አርቆ አሳቢነትና ጠንካራ አደረጃጀት ይጠይቃል። ከምንም በላይ ዘላቂ አገራዊ ጥቅምን ከስልጣን ጥም ማስቀደም የግድ ይላል። ያ ካልሆነ ለውጥ የከፋ አደጋም እንደሚጋብዝ ታሪክ ቁልጭ አርጎ ያሳየናል (ከታሪክ እንማራለን ወይ ራሱን የቻለ ጥያቄ ሆኖ ማለቴ ነው)። የራሳችን ታሪክ ለጊዜው ወደኋላ እናቆየውና ለንጽጽር ያህል የቅርብ ጊዜ ምሳሌ ላንሳ፤

12651089_10205997771163674_7322304711962946875_n

ሀ. ከአረብ ጸደይ ምን እንማራለን?
የዛሬ አምስት አመታት ገደማ የአረብ ስፕሪንግ በቱኒዝያ፣ ግብጽና ሊብያ ድንገት ተቀጣጠለና ለውጥ ወለደ። አሁን ቱኒዝያውያን ቤን አሊን ሊናፍቁ አይችሉም። ማህበራዊ ችግሮቻቸው ባይፈቱም ቢያንስ የፖለቲካ ነጻነት አግኝተዋል። ግብጾችም ለነጻነት ነበር የታገሉት፤ ነጻነት ግን ላም አለኝ በሰማይ እንደሆነባቸው ነው። ሊቢያውያን በአንጻሩ የፖሊቲካ ነጻነት ሊያገኙ ቀርቶ በጋዳፊ ጊዜ የነበራቸው ምቾትና በሰላም ውሎ የመግባት ነጻነት አጡ። ከምንም በላይ አሁን ሊቢያ የለችም። ወደፊትም ላትመለስ ትችላለች። አገሪቱን ተቀራምተው የሚፈነጩባት ምን አይነት አውሬወች እንደሆኑ መቸም ልንረሳው አንችልም።

ቱኒዝያውያን አተረፉ፣ ግብጾች ሌላ ሙባረክ አገኙ፣ ሊቢያውያን ከሰሩ። ምን ለያያቸው? ብዙ ውጫዊና ውስጣዊ ምክንያቶችን መጥቀስ ይቻላል። ለማሳያ ግን ሶስት ምክንያቶችን እንይ። በመጀመሪያ ምዕራባውያን በሶስቱም አገራት ላይ ያላቸው ፍላጎት የተለያየ ነው። ከዚህ አንጻር ለምሳሌ ግብጽ ውስጥ መረጋጋት እንጂ ዲሞክራሲ እንዲኖር አይፈለግም። አሜሪካ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ለዚያች አገር ጦር ሀይል የምታፈሰው ዲሞክራሲ እንዲያብብ በማሰብ አይደለም። ግብጻውያን በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ በፈቃዳቸው በመረጡት መሪያቸው ላይ ምን እንደደረሰ አይተናል። የማይጠበቅ ግን አልነበረም (፹ በመቶው ግብጻዊ የአለም ቀንደኛ የሰላም ጸር አሜሪካ ነች ብሎ ያምናል)። ሊቢያ በበኩሏ የነዳጅ ሀብቷ መርገምት ሆነባት። በዋነኝነት ግን የሊቢያ ህዝብ ከሌሎች ሁለት አገራት በተለየ መልኩ በጎሳ የተቧደነ በመሆኑ የጋራ ራዕይ መንደፍ አልቻለም። ከመጀመሪያው እንደ ቱኒዝያውያን በሰለጠነ መንገድ መብታቸውን ከመጠየቅ ይልቅ በጎሳ ተቧድነው ጋዳፊን በየትኛውም መንገድ ጥሎ የአገሪቱን የነዳጅ ሀብት መቀራመት ላይ ያነጣጠረ ነውጥ ውስጥ ገቡ። እነዚህ ቡድኖች ለስልጣንና ሀብት መቀራመት እንጂ ለአገራቸው እንደማይገዳቸው ግልጽ የሆነው ከጅምሩ መሳሪያ አንስተው ምእራባውያን አገራቸውን በአየር እንዲደበድቡላቸው ሲማጸኑ ነበር።

የአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ የቱን ይመስላል?
የሶስቱን አገራት ምሳሌ ያነሳሁት ወያኔ ቢወድቅ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ለመገመት እንዲረዳን ነው። መነሻዬ ወያኔ የሞት አፋፍ ላይ ነው የሚል የዋህ ግምት አይደለም፤ ወያኔ በዋዛ ስልጣን ይለቃል ብለው የሚያስቡ ወያኔን አያውቁትም። ግን አንድ ቀን መውደቁ አይቀርም። ወያኔ የወደቀ ለታ ምን እንደሚፈጠር መገመት የሚችል አለ? እንደ ቱኒዝያውያን እናተርፋለን ወይንስ እንደ ሊቢያውያን (የመንንና ሶሪያንም ጨምሩ) ወደ ትርምስ እንገባለን? ኢትዮጵያ እንደ አገር ትቀጥላለች? በሌላ አነጋገር የአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ከሶስቱ አገራት ውስጥ ከየትኛው ጋር ይቀራረባል? ስለ ኢትዮጵያ ለሚገደው ሁሉ አስጨናቂ ጥያቄ ነው። የአገር ህልውና ጉዳይ ነውና ከስሜት ነጻ ሆኖ ማሰብ ያስፈልጋል። መለስ ኢህአዴግ ከሌለ አገሪቱ ትበታተናለች ሲል ሟርት ወይ ደግሞ የስልጣን ማራዘሚያ ማስፈራሪያ ብቻ የሚመስለው ይኖራል። ግን አይደለም። ወያኔና መሰሎቹ ባለፉት 􏰀􏰁 ዓመታት ሲዘሩት የኖሩት እኮ የአንድነትን ፍሬ አይደለም። የተቃዋሚ ፓርቲ ነን የሚሉት አብዛኞቹ በጎሳ የተቧደኑ መሆናቸን አስተውሉ (ከወያኔ የሚለዩት አቅመቢስ በመሆናቸው ብቻ ነው)። የትጥቅ ትግል ሲያካሂዱ ከቆዩት ቡድኖች ውስጥም ቢሆን ጠንከር ያሉትና የውጭ ድጋፍ ያላቸው ሁሉ ተገንጣዮች ናቸው።

በሩቅ ተቀምጦ ደሀ ኢትዮጵያዊያን የአጋዚ ጥይት ራት እንዲሆኑ መቀስቀስ አርበኛ አያሰኝም። እንዲያውም የለየለት ነውረኝነት ነው። ወያኔን ማውገዝ ስለ ኢትዮጵያ ማሰብ፤ ከወያኔ መሻል አይደለም። ወያኔን መጥላት አንድ ነገር ነው፤ ስለ ኢትዮጵያ ማሰብ ግን ፍጹም ሌላ ጉዳይ ነው። ከወያኔ መሻል ከወያኔ የተሻለ አማራጭ ማቅረብ ነው። ከወያኔ መሻል ከጭፍን ጥላቻ ወጥቶ ወያኔ ድንገት ቢወድቅ የኢትዮጵያ እጣ ምን ይሆናል ብሎ ማሰብ፣ መደራጀትና መስራት ነው። የወያኔን መውደቅ አሰፍስፈው የሚጠብቁ ጸረ-ኢትዮጵያ ሀይሎች መኖራቸውን ለአፍታም አለመዘንጋት ነው። በድፍረት እውነቱን መነጋገር፣ ሀሳብ ማመንጨት፣ መደራጀት፣ ህብረትና ከምንም በላይ ማስተዋል ይጠይቃል። ዲሞክራሲን ርሱት፤ ሲጀመር ኢዲሞክራሲያዊነት ወያኔ ያመጣው ችግር አይደለም፤ ስለዚህ ወያኔ ቢወድቅ ዴሞክራሲ ያብባል ማለት አይደለም። እንደ እውነቱ እኮ ዴሞክራሲያዊ አደረጃጀት ያለው የፖለቲካ ቡድን በአገራችን ኖሮ አያውቅም፤ አሁንም የለም። አንድ የፖለቲካ ቡድን ስታስቡ አንድ ሰው ብቻ ነው ትዝ የሚላችሁ። ያ ዴሞክራሲ አይደለም። በዚያ ላይ አብዛኛው በየጎሳው ተኳርፎ ነው ያለው፤ በጎሳ ተቧድኖ ስለ ዴሞክራሲ ማውራት ራስን መቃረን ነው። ወይ የሰወችን ምርጫ ታከብራለህ ያለዚያ እንደ ወያኔ ማንነት የሚለካው በቋንቋ አጋጣሚ ብቻ የሚል ተረት ተረት ስታወራ ትኖራለህ። በአንድ ጊዜ ጎሰኛም ዲሞክራትም መሆን አይቻልም። ዋናው ጉዳይ ግን ያለው ተጨባጭ ሁኔታ ቢያንስ ኢትዮጵያ እንደ አገር እንድትቀጥል የሚያስችላት ነው ወይ የሚለው ነው። ሌላው ሁሉ ዝርዝር ጉዳይ ነው።

ለ. ከራሳችን ታሪክ ምን ተማርን?

የንጉሱ ዘመን አክትሞ ደርግ መጣ። ብዙ ኢትዮጵያውያን ለውጡን በደስታ እንደተቀበሉት ጥርጥር የለውም። ለውጡ ግን ወደ ቅዠትነት ሲለወጥ ጊዜ አልፈጀም። ለምን ቢባል ንጉሱን ከስልጣን ከማውረድ ባለፈ ለውጡን በተፈለገው መንገድ ለመምራት ይህ ነው የሚባል ዝግጅትም ሆነ መግባባት አልነበረምና ነው። ግብታዊ አብዮት ነበር የሚሉ ልክ ናቸው። የመግባባት አለመኖር ሁምናን ይጋብዛልና በወቅቱ የተሻለ ጡንቻ የነበረው ደርግ ክፍተቱን ተጠቅሞ ስለጣኑን በጁ አስገባና ስጋት የመሰሉትን ሁሉ መመንጠር ጀመረ። በንጉሱ ጊዜ የነበረው የፖለቲካ አስተዋይነት በአንዴ ገደል ገባ። ምናልባትም በታሪካችን ምርጡን ጠቅላይ ሚኒስትር ጨምሮ ብዙ የአገር ባለውለታወች ያለፍርድ ታረዱ። በአገራችን ፖለቲካ ያኔ ነው የሞተው። የመጀመሪያው ኪሳራ ያ ነበር። ከዚያ ኪሳራ አሁንም አልወጣንም። አደጋው ግን ያ ብቻ አልነበረም። ደርግ አገር ለመምራት ዝግጁነት ያልነበረው ከመሆኑ በላይ የስልጣን ተቀናቃኞቹን ማጥፋት ላይ ተጠመደ። የገብያ ግርግር…እንዲሉ ሶማሊያ ባቅሟ ፈነጨችብን። የውጭ ድጋፍ ባናገኝ ኖሮ ማይጨው ሊደገም በቻለ ነበር። ቪቫ ካስትሮ!

በአጠቃላይ የ 􏰂􏰃ቱ ለውጥ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ኪሳራ ነበር። ከዚያ ታሪካችን ምን ተማርን? ምንም። ደርግ የቻለውን አጥፍቶ በተራው በበለጡ በጉልበተኞች ተሸነፈ። ሌላ ለውጥ። በዚህ ጊዜ ግን ዘውዳዊው መንግስት ሲገረሰስ የነበረው አይነት ተስፋ አልነበረም። ሲጀመር ደርግን ያሸነፉት ኢትዮጵያን ነጻ ለማውጣት ሳይሆን ከኢትዮጵያ ነጻ ለመውጣት በሚል በተቧደኑ ጉዶች ናቸው። የሚገርመው ቅኝ ገዢ የሚሏትን ትልቅ አገር የመግዛት አጋጣሚ ሲያገኙ አገሪቱን ከመካፈል የተሻለ መንገድ አልታያቸውም። በስልጣን ጥም ያበደ ብዙ መንገድ አይታየውም። ደርግ አስተዋይነትን ገድሎ አውሬነትን ተከለ ብያለሁ። ያሁኖቹ ጉዶች ደግሞ ኢትዮጵያዊነትን ገድለው ጎሰኝነትን ተከሉ። ሁለቱም ለውጦች ይሄ ነው የሚባል የፖለቲካ ጥያቄ ያልፈቱ፤ በተቃራኒው በፊት ያልነበሩ የፖለቲካና ማህበራዊ ችግሮች የፈጠሩ ነበሩ። ለነገሩ በሀይል የመጣ ለውጥ ዴሞክራሲ ሲተክል በታሪክ ታይቶ አያውቅም። የሚቀጥለው ለውጥ ሌላ ተጨማሪ ችግር እንደማያመጣ ርግጠኛ መሆን አይቻልም፤ ዙሪያችሁን ተመልከቱ። አሁን 􏰂􏰃 ወይም 􏰄􏰅 ዓ.ም አይደለም። በ􏰂􏰃 የውጭ ጠላት ካልሆነ በስተቀር የአገር አንድነትን በተመለከተ ያን ያህል ስጋት አልነበረም(የሰሜኑ ገና አልደረጀም)። በ􏰆􏰅ም ቢሆን ድል አድራጊወቹ ተባብረው ታላቅ አገር መግዛት ቢፈልጉ ኖሮ የአሪቱን አንድነት ለመጠበቅ የሚያስችል ጠንካራ ወታደራዊና የጸጥታ ሀይል ባለቤቶች ነበሩ። አሁን ግን ማን አለ? ወያኔ ድንገት ቢወድቅ ሌላው ቢቀር ለእለት ጸጥታ ለማስከበር የሚችል አለ? የኢትዮጵያ ህልውና ከመቸውም ጊዜ በበለጠ አስጊ ሁኔታ ላይ እንደሚወድቅ ማሰብና ያ እንዳይሆን ከአደጋው ግዝፈት በበለጠ መዘጋጀት ያስፈልጋል። አንድ ትውልድ ስለ ኢትዮጵያ ሳይሰማ ብሄር ብሄረሰብ እያለ አድጓል።

ሐ. ምን እናድርግ?
የፖለቲካ ለውጥ በራሱ ቁም ነገር አይደለም ብያለሁ። ጭብጡ ለውጥ መምጣቱ ሳይሆን ለውጡ የሚፈለገው አይነት መሆኑ ላይ ነው። በአገራችን እንዲመጣ የምንፈልገው ለውጥ መልካም እንዲሆን ምን ማድረግ አለብን? በመጀመሪያ ባለፉት ሁለት የመንግስት ለውጦች የደረሰውን ኪሳራ መቀልበስ ያስፈልጋል። ደርግ ካመጣው ኪሳራ እንጀምር፤ የፖለቲካ ትንሳኤ የግድ ይላል። ይኸውም፤

፩. በምንም ምክንያት ላለመገዳደል ቃልኪዳን መግባት
በመጀመሪያ ኢትዮጵያ እንደ አገር መቀጠል ይኖርባታል። ቀጥለን ምን አይነት ዴሞክራሲ እንደሚያስፈልገን መነጋገር ያስፈልገናል። ይሄ ሁሉ የሚሆነው ከአውሬነት ከፍ ብለን መነጋገር ስንችል ብቻ ነው። ስለዚህ ከአሁን በኋላ በፖለቲካ አመለካከቱ ምክንያት የሚገደል ኢትዮጵያዊ አይኖርም የሚል ቃል ኪዳን ብንገባስ? ከዚህ በኋላ ጠበንጃ የምናንሳው የውጭ ወራሪ ከመጣ ብቻ ነው ብለን ብንማማልስ? ትልቅ ታሪክ ያለን ህዝብ ሆነን የፖለቲካ ልዮነታችን በሰለጠነ አግባብ መፍታት ያለዚያም ማቻቻል አያቅተንም ብለን ከልባችን ብናምንስ? መነጋገር አያቅተንም ብለን ቆራጥ አቋም ብንወስድስ? ለመጀመሪያ ጊዜ እውነተኛ ብንሆንስ? የኢትዮጵያ ህዝብ መሰረታዊ ችግር ድህነት፣ ኋላቀርነት፣ የፍትህ መጓደል፣ የዲሞክራሲና ነጻነት እጦት ወዘተ ናቸው። ከነዚህ ውስጥ በጦርነት ሊፈታ የሚችል አለ? የለም። በየጎሳ በመኳረፍ ሊፈታ የሚችል ችግር አለ? መልሱ አሁንም የለም ነው። ታዲያ የፖለቲካ ቡድን ነን የሚሉት ሁሉ ተበጣጥሰውና ተኳርፈው ያሉት ለማን ብለው ነው? ከስልጣን ህልምና ጥቅም ያለፈ ራዕይ ካላቸው በመነጋገርና በመተባበር ቢያሳዩንስ?

ይሄ ማለት ወያኔ ጋርም ቢሆን አንዋጋም ማለት ነው። ኢህአዴግን የመፍትሄው አካል ማድረግ ማለት ነው። አውቃለሁ ይሄ ለብዙወች አስቸጋሪ ነው። ነገር ግን የትኛውም ሀሳብ ትርጉም የሚኖረው ከእውነታ ጋር ሲታረቅ ነው። ምን አልባት እንደ ወያኔ ኢትዮጵያን የበደላት ቡድን የለም። የባህር ወደብ ከግመል ማጠጫነት ያለፈ ጥቅም የለውም እያሉ በሚገዟት አገር የቀለዱ እነሱ ብቻ ናቸው። ግን ሌላም እውነት አለ፤ ወያኔወችም ኢትዮጵውያን ናቸው። በዚያ ላይ ስልጣን ላይ ናቸው። የሞቱት ለኢትዮጵያ ህዝብ ሳይሆን ለስልጣን ነውና ስልጣናቸውን እንደዘበት አይለቁም። ወያኔ አሁን ስጋ የያዘ አንበሳ ነው። በመጀመሪያ ብዙ ሰው ገለዋል፣ አገር ቆርሰዋል፣ ብዙ በደል ፈጽመዋል። ሲቀጥል ስልጣናቸውን ተጠቅመው ብዙ ህገወጥ ሀብት ሰብሰበዋል። ስልጣን ወይም ሞት እንደሚሉ ማንም አያጣውም። በዚያ ላይ በጣም ጠንካራ ወታደራዊና ደህንነት መዋቅር አላቸው። የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ልምዳቸውም ጠንካራ ነው። በየጊዜው ዋሽንግተን ዲሲ የሚሰለፉ ኢትዮጵያውያን የሚያስቁኝ ለዚህ ነው፤ አሜሪካ እንደ ወያኔ የሚመቻችትና የምትተማመንበት ቡድን እንደሌለ አለማወቃቸው። እውነታው በጉልበት ወያኔን ለማቸነፍ ሽራፊ ዕደል ያለው ሀይል በሩብ ምዕተዓመት አልታየም። አሁንም የለም። ግን ነጥቡ እሱ አይደልም። ከምንም በላይ ሰላምና ብልጽግና የሚኖረው ማንም ኢትዮጵያዊ ከወደፊቷ ኢትዮጵያ እንደማይገለል ቃል ስንገባ ብቻ ነው። ስልጣን ላይ ያለውን ቡድን ያላካተተ ለውጥ ቢሳካ እንኳን አደጋ አለው። አላማችን አንድን የፖለቲካ ቡድን በሌላ መቀየር ሳይሆን የፖለቲካ አብዮት (ማንም ዜጋ በፖለቲካ አመለካከቱ የማይከሰስበት ምህዳር) መፍጠር ከሆነ ከወያኔወች ጋር መነጋገር ይቻላል። ጥያቄው መሆን ያለበት ወያኔወች ለድርድር ዝግጁ ናቸው ወይ የሚለው ነው። ወያኔን ወደ ድርድር ጠረጴዛ ማምጣት በጣም አስቸጋሪ እንደሚሆን ግልጽ ነው፤ የማይቻል ግን አይደለም። ይቻለል! የሚቀጥለው መንግስት ወያኔ ባለው የጸጥታና የዲፕሎማሲ ልምድ ላይ መገንባት እንጂ እንደልማዳችን ከዜሮ መጀመር የለበትም። ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ ህዝብ እናስብ እስቲ። በህይወቴ ብዙ አገር አይቻለው፤ ኢትዮጵያ በእውነት ውብ አገር ናት። ችግሩ እንደ ህዝብ ማሰብ አለመቻላችን ብቻ ነው።

፪. አንድነታችን ማጽናት
ትልቅና ለምለም አገር አለችን። ለማኝ የሆንነው፣ የአረብ ገረድና ሎሌ የሆንነው፣ ዲግሪ ይዘን የፈረንጅ መኪና ጠባቂ ይምንሆነው ተረግመን አይደለም። እንደ ህዝብ ማሰብ ባለመቻላችን እንጂ። በሌላ አነጋገር ተባብረን አገራችን እንደገና ታላቅ ከማድረግ ይልቅ ውርደትን መርጠን ነው። ያን የግድ መቀየር ይኖርብናል። መነጋገር ከቻልን እኮ ምንም አይነት መሰረታዊ ልዩነት የለንም። ኢትዮጵያውያን መልካችን ብቻ አይደለም የሚመሳሰለው፤ ችግራችን፣ ፍላጎታችን፣ እጣችን ሁሉ አንድ ነው። ከልብ መነጋገር ከቻልን ችግሮቻችን ያን ያህል ግዙፍ አይደሉም። ግን ከጠባብ ከጎሰኝነት መውጣት የግድ ይላል። ይሄ ማለት ሁሉም ኢትዮጵያዊ አንድ አይነት ቋንቋ ይናገሩ፣ ተመሳሳይ ቀሚስና ሱሪ ይልበሱ፣ ለአንድ አምላክ ይስገዱ፣ ወይ ደግሞ አንድ አይነት የፖለቲካ ዕምነት ይኑራቸው ማለት አይደለም። ልዩነት የህይወት ሀቅ ነው። በሁለት ወንድማማቾች መካከል አንድ ሺ ልዩነት ሊኖር ይችላል። ከባልሽ ባሌ ይበልጣል ከሌለ ግን ልዩነታቸው ወንድምነታቸውን አያቀጭጨውም። በአንጻሩ መከባበርና ማስተዋል የተሳነው ህዝብ አንድ አይነት ቋንቋ ስለተናገረ ወይ ደግሞ ለአንድ አምላክ ስለሰገደ ከመበታተን አይድንም። ሶማሊያን ይመለከቷል። ከመኳረፍና መገዳደል ወጥተን መነጋጋርና በጋራ መስራት ከቻልን ታላቅ ህዝብ መሆን እንችላለን። በእውነት እንችላለን!

ሰላም ሁኑ።

በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ ኮሜቴ የሥርዓቱን የለየለት አምባገነንነትና ቀማኝነትን ተቃውሞ በማሰማት ላይ ይገኛሉ።

$
0
0

በርሃብ እየሞተ ታሞ ስለመዳን የሚያስብ የለም!!!

ff4d3-screen2bshot2b2015-05-272bat2b6-04-312bpmየተሰጠ መግለጫ

በርሃብ እየሞተ ታሞ ስለመዳን የሚያስብ የለም!!!
የአዛኝ ቅቤ አንጓች!
ለሕዝብ ደንታ ቢስ የሆነውና ኃላፊነት የማይሰማው አምባገነኑ የወያኔ/ኢህአዴግ አገዛዝ ጤናማውን የሕብረተሰብ ክፍል የመብት ጥያቄ ስላነሱ ብቻ በጥይት እየገደለ፣ እያቆሰለ፣አካለጎዶሎ እያደረገ፣ እየደበደበና በጭካኔ አያያዝ በእስር እያማቀቀ ህክምና እንኳን እንዳያገኙ እየከለከለ ዛሬ ደርሶ ለሕዝብ ጤና የተጨነቀና ያሰበ መስሎ ለመታየት በጤና ዋስትና ስም ከመንግሥት ሠራተኛው፣
ከጡረተኛው፣ ከገበሬውና ከነጋዴው ገንዘብ ለመሰብሰብ የጀመረው እንቅስቃሴ ከፍተኛ ተቃውሞ እየገጠመው ነው።
በአጠቃላይ የመንግሥት ሠራተኞች በተለይ መምህራን የጤና መድህን ዋስትና አስገዳጅ ሕጉን በመቃወም ፔትሽን እየተራረሙ ለአሰሪ መስሪያ ቤቶች በማስገባት ላይ ይገኛሉ።በደሴ፣ በወልድያ ፣ በአዲስ አበባ፣ በሐረር፣ በአዋሳ፣ በደብረማርቆስ፣ በባሕር ዳር – —በመሳሰሉና በአብዛኛው የአገሪቱ ከተማዎች የሚያስተምሩ መምህራን ከጥር ወር ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል የተባለው አስገዳጅ የጤና መድህን ዋስትና ለሰራተኛው የሚሰጠው የሕክምና አገልግሎት እስከምን ድረስ እንደሆነ ሠራተኞች ሳይወያዩበትና ፈቃደኞች መሆናቸው ሳይረጋገጥ በአስገደጅ ሕግ ከደመወዛቸው በየወሩ 3% ለመቀነስ በዝግጅት ላይ መሆኑ የሥርዓቱን የለየለት አምባገነንነትና ቀማኝነትን የሚያጋልጥ ነው በማለት ተቃውሞ በማሰማት ላይ ይገኛሉ።
ዛሬ መምህራንም ሆኑ ባጠቃላይም ሠራተኞች በልተው ለማደር በተቸገሩበት ፣ የኑሮ ውድነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ የመጨረሻው ጫፍ ላይ በደረሰበትና የዋጋ ግሽበት (ንረት) እየጨመረ በሚገኝበት ፣በሀገሪቱ በተከሰተው ድርቅ ሳቢያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ለረሃብ አደጋ በተጋለጡበትና የወገኖቻቸውን ድጋፍ በሚሹበት ወቅት የጤና መድህን ዋስትና በሚል ሽፋን ከመንግሥት ሠራተኞች በየወሩ 3% ከደመዛቸው ለመቁረጥ መወሰኑ የአዛኝ ቅቤ አንጓች እንዲሉ ነው።ከዚያም በላይ ድብቅ የሆነውን የሥርዓቱን አጀንዳ ለማስፈጸምና ከአዲስ አበባ የተቀናጃ ማስተር ፕላን ጋር በተያየዘ በኦሮሚያ ክልል ፣ ከቅማንት ማንነት ጥያቄ ጋር በተገናኘ በጎንደር የተነሳበትን የሕዝብ አመጽ አቅጣጫ ለማስቀየር፣ እንዲሁም ያለ በቂ ጥናት የሕዝብን የትኩረት አቅጣጫ ለመለወጥ ተብሎ ከ2010 እ.አ.አ ጀምሮ እየተገነባ ያለው የአባይ ግድብ ግንባታ የገንዘብ ዕጥረትን ለመወጣት አገዛዙ የቀየሰው ዘዴ ከመሆን ባለፈ የሠራተኛው የጤና ሁኒታ አስጨንቆት እንዳልሆነ መገመት አያዳግትም።
አገዛዙ የአገሪቱን ሀብትና ንብረት እየዘረፈና እያስዘረፈ፣ ሕዝቡን በድህነት አረንቋ ውስጥ እየከተተ ፣ ለሀገራቸውና ለወገናቸው ነፃነት የሚታገሉ የቁርጥ ቀን ልጆችንና ነፃ ሚዲያን ለማሳፈን በሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ እያፈሰሰ፣ ለአፋኙ የመከላከያ ሠራዊትና የደህንነት ተቋም ለልማት መዋል የሚገባውን የሀገሪቱን በጀት እያባከነ ላጋጠመው የበጀት እጥረት ማካካሻ ይሆነው ዘንድ በልቶ ማደር ከተሳነው ሠራተኛ በጤና ዋስትና ስም የወር ደመወዙን በአስገዳጅ ህግ ለመቀነስ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ ለሕዝብ ያለውን ንቀትና ማናለብኝነትን የሚያሳይ ነው።
ከዚህ ሕገወጥ የወያኔ ተግባር አንፃር መምህራን በሁሉም የአገሪቱ ክልሎች ተቃውሞአቸውን እየገለጹ እንደሆነ ታይቷል።ስለሆነም የደሴ ከተማ መምህራንን ተቃውሞ ለአብነት አቅርበነዋል።
“(1)የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 9 መሰረት ማለትም የሕግ የበላይነት በሚለው ስር መንግሥት የሚያወጣቸው መመሪያዎች ሕገ መንግሥቱን ከተፃረረ ተቀባይነት እንደሌላው፣”
“(2) በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 43 የልማት መብት በሚለው ስር ብሔራዊ ልማትን በሚመለከት የሚወጡ ፖሊሲዎችና ፕሮጃክቶች ላይ ዜጎች ሐሰባቸውን እንዲሰጡ የመጠየቅ መብት አላቸው የሚል ቢሆንም መንግሥት ሠራተኛውን ሳያወያይ የመድህን ክፍያውያን መጠን ራሱ ወስኖ ማሳወቁ ሕገመንግሥቱን የሚጋፋ መሆኑ፣”
“ (3) በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 40 ንዑስ አንቀጽ 2 መሰረት መንግሥትም ይሁን ሌላ አካል ዜጎች ያፈሩትን ሀብት የመቀማት መብት እንደሌለው ይገልጻል” ይህ እየታወቀ አገዛዙ ሰራተኞች ተሳትፈው ሳይወያዩበት ከደመዛቸው በግዴታ 3% መቁረጥ የሕግ የበላይነትን መጣስ ነው ብለው በተቃውሞ የፔቲሽን ፊርማቸው አረጋግጠዋል።
ከዚህም በተጫማሪ በዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች በተለይ በዓለም አቀፍ ሠራተኞች ድርጅት ( International Labor Organization, ILO)ስምምነት (Convention) የፀደቁትን መብቶች ማለትም ስራ ማቆም አድማና ሰላማዊ ሰልፍ ወጥቶ ብሶትን የማሰማት መብት በመጠቀም እንዲዘጋጁና አገር አቀፍ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ ለመምህራንና ለሁሉም ሠራተኞች ጥሪ ያዳርጋል።እስከ መቼ ነው ዝም የምንለው? ምን ቀረብን?
በአሁኑ ጊዜ በኦሮሚያ የአገራችን ክፍልና በሌሎች አካባቢዎች እየተደረጉ ያሉት ሕዝባዊ እምቢተኝነት በክልል የተወሰነና የአንድ አካባቢ ችግር መገለጫ ሆኖ እንዳይቀር መፍትሔው በጋራ መነሳትና ትግሉን በማቀናጀት ብሔራዊ አጀንዳ ይዞ የአገሪቱን ሕልውና መጠበቅ የሕዝቡን ነፃነትና አንድነት ማረጋገጥ ላይ ያተኮረ እንዲሆን እናሳስባለን ።
በረሃብ እየሞተ ታሞ ስለመዳን የሚያስብ የለም !!!

የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ተገልብጦ የ18 ሰዎች ሕይወት ጠፋ | 25 ሰዎች ተጎድተዋል

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በኢትዮጵያ በየቀኑ የሚደርሱ የመኪና አደጋዎች ብዙ አምራች ዜጋዎችን ሕይወት እየቀጠፈ ይገኛል:: በዘ-ሐበሻ ድረገጽ እንኳ በየጊዜው እየደጋገመን በሃገሪቱ በተለያዩ ስፍራዎች የሚደርሱ የመኪና አደጋዎችን ስንዘግብ ቆይተናል:: ትናንት በአርሲ ዞን ጎለልቻ የደረሰው የመኪና አደጋም ከአስፈሪዎቹና አሳዛኞቹ የመኪና አደጋዎች መካከል አንዱ ነው::

ፎቶው የተገኘው: ከራድዮ ፋና

ፎቶው የተገኘው: ከራድዮ ፋና

በመንግስት ቁጥጥር ስር ያለው ራድዮ ፋና እንደዘገበው ትናንት ምሽት የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ 200 ሜትር ጥልቀት ባለውና ጨነኒ ወንዝ አካባቢ ልዩ ስፍራው የተፈጥሮ ድልድይ የሚባለው ቦታ ገደል ውስጥ ገብቶ የ18 ሰዎች ህይወት አልፏል::

በዚህ አደጋ 25 ሰዎች ከባድ እና ቀላል ጉዳት ቢደርስባቸውም ስድስት ተሳፋሪዎች ግን ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው በሰላም መትረፋቸው ተዘግቧል::

በኢትዮጵያ ሹፌሮች ጫት ቅመው; መጠጥ ጠጥተው መኪና ይነዳሉ:: ሹፌሮች የትራፊክ ሕጉን ሳይሆን ፖሊስን ነው የሚፈሩት:: ይህም ማለት ትራፊክ ፖሊሶች ባሉባቸው አካባቢዎች ብዙ ጉዳት አይፈጠርም:: ሆኖም ህግን የማያከብሩ ሹፌሮች ፖሊስ በሌለባቸው አካባቢዎች በግድ የለሽነት ስለሚነዱ ብዙ አደጋዎች ይፈጠራሉ:: ፖሊሶችም በሙስና የተጨማለቁ በመሆናቸውና ጥፋት በሚያጠፉ ሹፌሮች ላይ አስተማሪ ቅጣት ስለማይጣልባቸው ለአደጋዎች መባባስ አንዱ ምክንያት እንደሆነ ዘ-ሐበሻ ታምናለች::

የማይንበረከክ መንፈስ –ገጣሚ አንዱዓለም አራጌ –ከቃሊቲ (ትርጉም መስፍን ማሞ ተሰማ –ሲድኒ)

$
0
0

Andualem Family

ይህ ከቃሊቲ መቀመቅ የወጣ የታጋዩ አንዱዓለም አራጌ የፅናት፤ የተስፋና የትግል ጥሪ ነው። ጥሪው ሥነ ቃል ነው። ሥነ ሕይወት። ሥነ ትግል! ቃል የዕምነት ዕዳ ነው – እንዲሉ። ይህ ሥነ ቃል አስቀድሞ የወረደው በፈረንጅ ቋንቋ በእንግሊዝኛ ነው። ሥነ ቃሉን ከሰፈረበት ድረ- ገፅ እንዳነበብኩት – ሰቀዘኝ። እያደር ደግሞ አስማጠኝ። ምናለ በሀገርኛ ቋንቋ ብመልሰው? ግና እንደገጣሚው ውስጠ ህመም ህመሙን ምን ያህል ማስተላለፍ እችላለሁ? እስከምንስ ጠልቆ ይሰማኛል? ወይስ አሞኛል?….ለማንኛውም እነሆ! የነፃነት አርበኛው አንዱዓለም አራጌ ከቃሊት መቀመቅ እንዲህ ይላል…  ……የማይንበረከክ መንፈስ —–

 

 

The post የማይንበረከክ መንፈስ – ገጣሚ አንዱዓለም አራጌ – ከቃሊቲ (ትርጉም መስፍን ማሞ ተሰማ – ሲድኒ) appeared first on Zehabesha Amharic.

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ፤ መንግሥታዊ ወይስ ሃይማኖታዊ ?! –ይድነቃቸው ከበደ

$
0
0
ይድነቃቸው ከበደ

ይድነቃቸው ከበደ

“የእስልምና ጠቅላይ ጉዳዮች ምክር ቤት (መጂሊስ) እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን (ሲኖዶስ) የሃይማኖት መሪዎች ለእምነታቸው ካላቸው ተገዢነት ይልቅ ፣ በሥልጣን ላይ ላለው መንግሥት ታማኝነታቸውና አገልግሎታቸው የበዛ እንደሆነ ይነገራል፡፡”

በአገራችን በሥራ ላይ ያለው ሕገ መንግሥት፣ የሰው ልጅ መሠረታዊ መብቶችን ከሚያስከብሩ ሰነዶች መካከል፣ ሃይማኖትን አስመልክቶ የያዘው ድንጋጌ ከመብት አንፃር ሲቃኝ ጤናማ የሆኑ የሰው ልጅ መሠረታዊ መብቶች በውስጡ ይገኛል፡፡ይህ ማለት በተፈፃሚነታቸው ላይ የሚታየው ፣ መንግሥታዊ ዳተኝነት ታሳቢ በማድረግ ነው፡፡ በዚህም መሠረት በሕገ መንግሥቱ ተደንግጎ የሚገኝ ለዚህ ጹሑፍ ተዛማጅ የሆኑቱ እንደ መነሻ ሃሳብ ሊያገልግል ይችላል፡፡

  1. ‹‹ መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም፤ሃይማኖትም በመንግስት ጣልቃ አይገባም፡፡ ›› አንቀጽ 11 ንዕሱ አንቀፅ 3 ፡፡
  2. ‹‹ ማንኛውም ሰው የማሰብ፤የሕሊና እና የሃይማኖት ነጻነት አለው ፡፡ይህ መብት ማንኛውም ሰው የመረጠውን ሃይማኖት ወይም እምነት የመያዝ ወይም የመቀበል ሃይማኖቱንና እምነቱን ለብቻ ወይም ከሌሎች ጋር በመሆን በይፋ ወይም በግል የማምለክ፣ የመከተል፣የመተግበር ፣የማስተማር ወይም የመግለጽ መብትን ያካትታል፡፡››አንቀጽ 27 ንዕሱ አንቀፅ 1 ፡፡
  3. ‹‹ ማንኛውም ሰው የሚፈልገውን እምነት ለመያዝ ያለውን ነጻነት በኃይል ወይም በሌላ ሁኔታ ማስገደድ ወይም መከልከል አይቻልም፡፡ ›› አንቀፅ 27 ንዕሱ አንቀፅ 3 ፡፡

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ በውስጡ ስድስት ቤተ እምነቶች በጋራ የሚንቀሳቀሱበት ተቋም ነው፡፡ተቋሙ ዋና አላማዬ የሚለው “ልዩነታችንን ጠብቀን በሃገር ደረጃ ሰላምና መረዳዳት እንዲኖር በጋራ ለመስራት፣በሃገራችን ለዘመናት የኖረው የሃይማኖት መከባበርና መቻቻል ተጠብቆ እንዲቀጥል ለማድረግና አክራሪነት”ን ለማውገዝ፣ ሁሉም ሃይማኖት በእኩል የሚሳተፉበት” እንደሆነ ስለጉባዔ ሲነሳ ሁሌም “የጉባዔው” መልዕክተኞች የሚናገሩት አላማቸው ነው፡፡

ጉባዔው እንቅስቃሴ አደረኩ በሚልበት በማናቸውም ወቅት፣በመንግሥት የመገናኛ ብዙሃን፣  ተያይዞ የሚዘገበው ዜና “የጋራ ጉባዔው በፌዴራል ደረጃ ከተመሰረተ በኋላ በዘጠኙ ብሔራዊ ክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች መዋቅሩን በማስፋት ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ በተለይም በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ ወደ ዞንና ወረዳ የሰፋበት ሁኔታ ተፈጥሯል። በቀጣይም በሌሎች ክልሎች ማዋቅሩን ለማስፋት በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛል።”እየተበላ በተደጋጋሚ የዜና ሽፋን ተሰጥቷል፣የሁኔታዎች ለውጥ እስካልመጣ ድረስ የዜናው ዘገባ በዚህ ሊቀጥል ይችላል፡፡

ይሁን እንጂ የሃይማኖት ተቋማቱ ከገለጹት ዓላማ እንዲሁም ቤተ እምነቶቹ ከሚመሩበት  ሃይማኖታዊ ትእዛዝ ውጪ ፣የመንግሥት ሥራ በጉያቸው ሸሽገው ፣ሲመቻቸው በአስተምህሮት ሳይሳካ ሲቀር በመግለጫ የተቋቋሙለትን ዓላማ ሳይሆን ፣ያቋቋማቸውን የመንግሥት ሥራ እየፈጸሙና ለማስፈጸም እየጣሩ ይገኛሉ፡፡ለዚህም ተግባራቸው ከጠቅላይ ሚኒሰትር ኃይለማርያም ደሳላኝ ጀምሮ የጉዳዩ ቀጥተኛ አስፈፃሚ የሆኑት የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም ጨምሮ በይፋ “የቤት ሥራችንን ካልሠራን አክራሪነት በድህነት አረንቋ ላይ የሚወልደውን ብጥብጥ ነው፡፡ የአክራሪነትና የጽንፈኝነት አመለካከት ለመዋጋትና በእንጭጩ ለመቅጨት” የሃይማኖት  ጉባዔው ወሳኝ ሚና አለው፡፡በማለት በመንግሥታዊ ልማታዊ ቃል፣ የመንግሥት እና የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የጠበቀ ግንኙነት እንዳላቸው በተደጋጋሚ በሚኖራቸው ስብሰባ እንዲሁም በጋራ በሚሰጡት መግለጫ አረጋግጠዋል፡፡

የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የሚባለው ስብስብ ፣የትኛውንም ቤተ እምነቶቾ የሚወክሉ ትክክለኛ ተወካዮች ስለመሆናቸውም፣ የቤተ እምነቶቾ ተከታዩች በጥርጣሪ ብቻ ሣይሆን በእርግጠኝነት አይወክሉንም ሲሉ መግለጻቸው የአደባባይ ሚስጥር ከሆነ ቆይቷል፡፡ለዚህም እንደ መሳያ የእስልምና ጠቅላይ ጉዳዮች ምክር ቤት (መጂሊስ) እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን (ሲኖዶስ)፣በእምነነቱ ተከታዮች፣ የሃይማኖት መሪዎች ለእምነታቸው ካላቸው ተገዢነት ይልቅ ፣በሥልጣን ላይ ላለው መንግሥት ታማኝነታቸውና አገልግሎታቸው  የበዛ እንደሆነ ይነገራሉ፡፡መንግሥትም ቢሆን እጁን አስረዝሞ በእምነት ተቋማት ውስጥ የሃይማኖት መሪዎችን እስከ-መምረጥና እስከ-ማስመረጥ መድረሱ ለቤተ እምነታቸው ቅርብ የሆኑ አማኞች የሚመሰክሩት ሐቅ ነው፡፡

የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ፣በአገራችን በደካማ የመንግሥት አስተዳደር እንዲሁም ተፈጥሯዊ በሆኑ ምንያቶች ለሚከሰቱ ችግሮች ፣በቤተ እምነታቸው የእምነቱ ተከታይ፣ሃይማኖታዊ ይዘት ጠብቆ የመፍሔ አካል እንዲሆን ከማስተማርና ከማስተባበር ይልቅ ፣ፖለቲካዊ ውሳኔዎችን ባልተወከሉበት እነሱ ግን እንወክለዋለን በሚሉት አማኞች ስም በድፍረት ጉዳዮችን ሁሉ፣ መንግሥታዊ አቅጣጫ እንዲይዝ ጥረት ሲያደርጉ ተስተውሏል፡፡መንግሥትም ለአገዛዙ ሥርዓት አይበጀኝም ብሎ የሚያስባውና የሚያሰጋው ማናቸውም ነገር ቅድመ ትእዛዝ ማስተላለፊያ መንገድ የሚጠቀመው የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔን ነው፡፡

ለዚህ እንደ-ማመላከቻ ይሄን ማስታወስ በቂ ነው፡፡ ባላፉት አራት አመታት “የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች” ሕገ ወጥ እስር በመቃወም፣ በሰለማዊ መንገድ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄውን እያቀረበ ይገኛል፡፡ መንግሥትም ለሠላማዊ ጥያቄ እየሰጠ ያለው ምላሽ ምን-እንደሆነ ይታወቃል፡፡በመንግሥት ቀጥተኛ ትእዛዝ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ “አክራሪነትና ጽንፈኝነትን እናወግዛለን” በሚል መሪ ቃል መግለጫ እና ማሳሰቢያ ከመስጠት ባለፍ ለችግሩ የመፍትሔ አካል ሲሆኑ አልተገኙም፡፡ ይባስ ብሎ የመንግሥትን ድርጊት በመደገፍ ሠልፍ እስከመጠራት ደረጃ ደርሰዋል፡፡ይሄን ማድረጋቸው የሚያስገርም ባይሆንም የተቋቋሙለት ዓላማ ምን እንደሆነ የሚያረጋግጥ ነው፡፡

ይህ አይነቱ ድርጊት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን (ሲኖዶስ) እና በማኅበረ ቅዱሳን መካከል፣ወቅቱን እየጠበቀ በሚደረገው ንትርከ እና እሱን ተከትሎ በሚመጣው ነገር ሁሉ ፤መንግሥት ከጀርባ በመሆኑ ሥራውን ሲሰራ ቆይቷል፣አሁንም እየሰራ ይገኛል፡፡በዚህም መሐል የእምነቱ ተከታዮች የጉዳዮ ባለቤት በመሆን ለችግራቸው ትክክለኛ መፍትሔ እንዳያመጡ፣ ካስፈለገ በቀጥታ ሳይሆን ሲቀር በሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ስም የመንግሥትን ፍላጎት ለመፈጸም ጥረት ይደረጋል፡፡

መንግሥት ከየትኛውም ሃይማኖት ወገንተኛነት የተገለለ መሆኑ ከላይ በመግቢያ ላይ በተገለጸው ሕገ መንግሥት ላይ ተጽፎ ይገኛል፡፡ይሁን እንጂ ባሁን ወቅት መንግሥትና ሃይማኖት መለያየት በሚያስቸግር ሁኔታ ፣መንግሥት ሰተት ብሎ በሃይማኖት ተቋማት ውስጥ ገብቷል፡፡ይህ አይነቱ አሳፋሪ ተግባር ሽፋን ለመሰጠት እየተሞከረ ያለው፣ በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አማካኝነት ነው፡፡

ይህም በመሆኑም እንደኔ የግል እይታ፣ የቤተ እምነት ተከታዮች ፣ፖለቲካዊ አወቃቀር እና ይዘት ያለው “የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ” እየተባላ የሚጠራው ተቋም፣ የሚያደርጋቸው ማናቸውም እንቅስቃሴ ፣በንቃት በመከታተል ሃይማኖታዊ ይዘቱን ጠብቆ እንዲንቀሳቀስ ከአወቃቀሩ ጀምሮ እስከ-ሚወከሉት የሃይማኖት መሪዎች ድረስ እነማን እንደሆኑ ዋነኛ ተግባር ሊሆን ይገባል የሚል እምነት አለኝ፡፡

 

 

The post የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ፤ መንግሥታዊ ወይስ ሃይማኖታዊ ?! – ይድነቃቸው ከበደ appeared first on Zehabesha Amharic.

Sport: ባስቲያን ሽዌንስታይገር ‹‹ማንቸስተር ዩናይትዶች በመሆናችን በእስካሁኑ የተሻለ ስኬት ሊኖረን ይገባል››

$
0
0

 

schweinsteiger

በኪንግስ ፓወር ስቴድየም ቅዳሜ ምሽት በሌሲስተር ሲቲና በማንቸስተር ዩናይትድ መካከል በተደረገው የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያዎች የተቆጠሩበት ጎሎች ለሁለት ተጨዋቾች የየራሳቸው የሆኑ አዳዲስ ታሪክን ለማስመዝገብ የቻሉባቸው ሆነዋል፡፡ የመጀመሪያው የ23 ዓመቱ እንግሊዛዊ አጥቂ ጃሚ ቫርዲ ለ11ኛ ተከታታይ የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያው ጎል በማስቆጠር ከዚህ በፊት በማንቸስተር ዩናይትዱ ዝነኛ ጎል አዳኝ ሩድ ቫንኒስተልሮይ በ2003 በአስር የሊጉ ግጥሚያዎች በተከታታይ ጎሎችን በማስቆጠር ይዞት የነበረው ከ12 ዓመታት በላይ የዘለቀውን ሪከርድ የሰበረበት ነው፤ ሌላኛው ደግሞ ጀርመናዊው ኢንተርናሽናል ባስቲያን ስዌንስቲገር በ2015 ፕራሲዝን ዝውውር መስኮት ባየር ሙኒክን በመልቀቅ ለማንቸስተር ዩናይትድ ከፈረመ ወዲህ ለአዲሱ ክለቡ ለመጀመሪያ ጊዜ ጎል ያስቆጠረበት ግጥሚያ መሆኑ ነው፡፡ በኪንግስ ፓወር ስቴዲየም በተደረገው ግጥሚያ ጃሚ ቫርዲ በጨዋታው 24ኛ ደቂቃ ላይ 11ኛዋን የፕሪሚየር ሊግ ጎሉን ከመረብ በማሳረፍ ሌሲስተር ሲቲን 1ለ0 በሆነ ውጤት በመምራት እንዲጀምር ቢያስችለውም እረፍት ከመውጣታቸው በፊት ሽዌንስቲገር የዳሊ ብሊንድ የመዓዘን ምት በግንባሩ በመግጨት የማንቸስተር ዩናይትድን የአቻነት ጎል ከመረብ አገናኝቷል፡፡

 

ከማንቸስተር ዩናይትድ በሁለተኛው ግማሽ የታየችው ብቸኛዋ ኢላማዋን ያገኘች ጎል የማስቆጠር ሙከራንንም ሽዌንስቲገር አድርጎ በሌሲስተር ሲቲው ግብ ጠባቂ ካስፐር ሽማይክል ተመልሳበታለች፤ ሆኖም ግን ሽዌንሲቲገር ከግጥሚያው መጠናቀቅ በኋላ በሰጠው መገለጫ በማንቸስተር ዩናይትድ ተጨዋችነቱ የመጀመሪያ ጎሉን በማስቆጠሩ ከመደሰት ይልቅ በተመዘገበው የአቻ ውጤት ማዘኑን በማረጋገጥ ለሌሎች የቡድኑ ጓደኞቹ በአርአያነት የሚጠቀስ አስተያየት ሲሰነዝር ተደምጧል፡፡

‹‹ቡድናችን ሙሉ ሶስት ነጥቦችን በማስመዝገብ የፕሪሚየር ሊግ ሰንጠረዥ የመሪነት ስፍራን መቆጣጠርን በማድረግ እንደመሆኑ ከግጥሚያው አንድ ነጥብ ብቻ መጋራታችንን እንደ መጥፎ ውጤት ቆጥሬዋለሁ›› በማለት ለማንቸስተር ዩናይትድ ቲቪ መግለጫውን መስጠት የጀመረው የ31 ዓመቱ ጀርመናዊ አማካይ በመቀጠልም ‹‹አብዛኛውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ የሳለፍነው ሰፊ የኳስ ቁጥጥርና ከፍተኛ የጨዋታ የበላይነትን በመያዝ እንደመሆኑ ብዛት ያላቸው ጎሎችን የማስቆጠር ዕድሎችን ለመፍጠር መቻል ነበረብን፣ ይህንን ኃላፊነታችንን በአግባ ለመፈፀም አለመቻላችን በግጥሚያው በቡድናችን የታየው ትልቅ አሳዛኝ አጋጣሚዎችን መሆኑን አምናለሁ፡፡ ወደ ሌሲስተር ሲቲ ሜዳ የመጣነው የማንቸስተር ዩናይትድ ተጨዋች ሆነን በመሀላችን ከእንደዚህ አይነቱ ሙሉ ሶስት ነጥቦችን የማግኘቱ ኃላፊነታችንን በአግባቡ  መፈፀም መቻል ነበረብን፡፡ በእርግጥ የሌሲስተር ሲቲ ተጨዋቾች አብዛኛውን ክፍለ ጊዜን ከራሳቸው የሜዳ ክልል ሳይወጡ በጠንካራ ሁኔታ የመከላከል ተግባርን መፈፀማቸው በቂ ክፍተትን እንድናገኝ ትልቅ ተፅዕኖን የፈጠረብን ሆኗል፡፡ ግን በሌሎች ግጥሚያዎች እንደዚህ አይነቱ በጠንካራ ሁኔታ የመከላከል ተግባራቸው የሚጠብቁን መሆኑን አምነን ተጋጣሚያችንን ለማስከፈት በዚህ ግጥሚያ ካሳየነውም በበለጠ የተቻለንን ሁሉ ከፍተኛ ጥረት ማድረግ ይኖርብናል›› የሚል አስተያየቱን አክሏል፡፡

የጀርመን ብሔራዊ ቡድን አምበል ሽዌንሲቲገር ለማንቸስተር ዩናይትድ ነጥቦችን የማስገኘት ተግባርን ሲፈፅም በሁለት ተከታታይ የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያዎች የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡ ከአንድ ሳምንት በፊትም ማንቸስተር ዩናይትድ ዋትፎርድን 2ለ1 በረታበት የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ ሁለተኛዋን የማሸነፊያ ጎል ትሮይ ዴልኒ በስህተት በራሱ መረብ ላይ ለማሳረፍ እንዲገደዱ ምክንያት የሆነች ጎል የማስቆጠር ሙከራን አድርጎን ነበር፡፡

በጉዳዩ ዙሪያ ሽዌንሲቲገር በመቀጠል አስተያየቱን የሰነዘረው ‹‹በማንቸስተር ዩናይትድ ተጨዋችነቴ ለመጀመሪያ ጊዜ በስሜ ያስመዘገብኳት ጎል በሌሲስተር ሲቲ ላይ ያስቆጠርኳት ነች፡፡ ለዚህ ክለብ የመጀመሪያዬ ጎል በመሆኗም አስደስታኛለች፣ ሆኖም ግን ደስታዬ የተሟላ ይሆን የነበረው ግጥሚያውን በሙሉ ሶስት ነጥቦች ለማጠናቀቅ ብንችል ነበር፡፡ ከዚህ አንፃር ለማንቸስተር ዩናይትድ የበለጠ ወሳኝ ተግባርን ፈፅሜያለሁ የምለው ዋትፎርድን ለመርታት በቻልንበት ግጥሚያ ለ2ኛዋ ጎል መገኘት የፈፀምኩትን ነው፡፡ ምክንያቱም ለማንቸስተር ዩናይትድ ካስቆጠርኳት የመጀመሪያዋ ጎሌ ይልቅ የቡድናችን ሙሉ ሶስት ነጥቦችን ማግኘትን እመርጥ ነበር›› በማለት ነው፡፡

በሌሲስተር ሲቲ በተደረገው ግጥሚያ ከማንቸስተር ዩናይትድ ተጨዋቾች ውስጥ የበለጠ ውጤታማ የጨዋታ እንቅስቃሴን ማሳየት ችሏል በሚል በበርካታ የፉትቦል ተንታኞች አድናቆትን ያተረፈው ሽዌንስቲገር ቡድናቸው ሌሲስተር ሲቲን በራሱ ሜዳ ለማሸነፍ በጠንካራ ሁኔታ ዝግጅቱን ሲሰራ መዝለቁን በማረጋገጥ በሰነዘረው አስተያየት ‹‹የሌሲስተር ሲቲ የዘንድሮ ሲዝን አቋም እጅግ ጠንካራ መሆኑን ከግንዛቤ በማስገባት ሙሉ ትኩረትን ሰጥተን ጠንካራ ዝግጅት ስንሰራበት የከረምነው ጨዋታ ነው፡፡ በተለይም ጃሚ ቬርዲ አደገኛ የማጥቃት እንቅስቃሴ ያለው ተጨዋች መሆኑን ከማመን በምን መልኩ እንደምንቆጣጠረው ዝግጅት ስንሰራ ዘልቀናል፡፡ ሆኖም ግን በዚህ ግጥሚያ በከፍተኛ ፍጥነት በታጀበ የካውንተር አታክ ጎል ሲያስቆጥርብን ታይቷል፡፡ ይህ ከእስካሁኑ ሲዝን በብዙ መልኩ በበለጠ በሜዳ ላይ ላለው ፉትቦላችን ሙሉ ትኩረትን የመስጠት ኃላፊነት እንዳለብን ሊያረጋግጥልን የሚገባ ጉዳይ ነው›› በማለት ነው፡፡

በቅዳሜ ምሽቱ ግጥሚያ ከማንቸስተር ዩናይትድ በኩል ከሽዌንስቲገር ጥሩ አቋም ባሻገር አንድ ሊጠቀስ የሚገባው መልካም ነገር ሆላንዳዊው አሰልጣኝ የዛሬ ዓመት በኪንግስ ፓወር ስቴዲየም በሌሲስተር ሲቲ 5ለ3 ከተሸፉበት የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ ትልቅ ትምህርትን ማግኘታቸው ነው፤ ምክንያቱም ቫንሃል የአሁኑ ግጥሚያን ሌሲስተርን 3-5-2 የጨዋታ ፎርሜሽንን በማመሳሰል መጀመራቸው ከጃሚ ቬርዲ ጎል በስተቀር በቡድናቸው የተከላካይ መስመር ላይ የዛሬ ዓመት እንደነበረው አይነት ከፍተኛ ጫና እንዳይፈጠርባቸው የረዳቸው ሆኗል፡፡ ሉዊ ቫንሃል ቡድናቸው ከሌሲስተር ሲቲ ጋር 1ለ1 ከተለያዩበት ግጥሚያ በኋላ የሰጡት ፖስት ማች ፕሬስ ኮንፈረንስ ከዚህ በታች ያለው ነው፡፡

ሉዊ ቫንሃል በግጥሚያው ስለ ተመዘገበው ውጤት

‹‹በሌሲስተር ሲቲ ሜዳ ነጥብ መጋራታችን የሚያስፀፅት ሆኖብኛል፤ ምክንያቱም በግጥሚያው 90 ደቂቃዎች ውስጥ በአብዛኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ የበላይነትን የያዝንበት የጨዋታ እንቅስቃሴን አሳይተናል፡፡ ሆኖም ግን የመጨረሻው እጣ ፈንታችን በድል ማጠናቀቅ የሚገባንን ግጥሚያን 1ለ1 በሆነ ውጤት ለማጠናቀቅ መገደድ ሆኗል፡፡ ከግጥሚያው መጀመር በፊትና በእረፍት ሰዓት ለቡድናችን ተሰላፊዎች የሰጠኋቸው መመሪያ ለእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንነት ክብር ለመብቃት የምንጓጓ ከሆነ እንደዚህ አይነቶቹ ግጥሚያዎችን የማሸነፍ ትልቅ ኃላፊነት አለብን ብያቸዋለሁ፡፡ በግጥሚያው ግን በበቂ ሁኔታ ጎሎን የማስቆጠር እድል ሳይኖራቸው ቀርቷል፡፡

ስለ ጃሚ ቬርዲ የመሪነት ጎል

‹‹የሌሲስተር ሲቲ ትልቁ ጠንካራ ጎን በረጅም ፓስ የመጣ ኳስን በአግባቡ በመጠቀም እንደዚህ አይነቱ ጎልን ማስቆጠር በመሆኑ ይህንን ለመቋቋም በልምምድ ወቅት ትኩረትን ሰጥተን መስራት ነበረብን፡፡ ይህንን ተግባርን ስንፈፅም ከርመናል፤ ሆኖም ግን ከሌሲስተር ሲቲ የመዓዘን ምት የተመለሰች ኳስን በማይታመን አይነት ከፍተኛ የካውንተር አታክ ሲስተም በመምጣት ጎሏን ሊያስቆጥሩብን ችለዋል፡፡ ጎሏ እንድትቆጠር የቡድናችን ተሰላፊዎች በተሻለ ሁኔታ የመከላከል ተግባርን በመፈፀም የጃሚ ቬርዲ አደገኛ የማጥቃት እንቅስቃሴን ሊቋቋሙት ይገባ ነበር፡፡

ይህንን ስል ግን ቬርዲ ጎሏን ለማስቆጠር ያደረገው በከፍተኛ ፍጥነት የታጀበ የማጥቃት እንቅስቃሴ ኳሊቲው ሊደነቅ እንደሚገባ በማመን ነው፡፡ የሌስተር ሲቱ የመዓዘን ምትን በተደራጀ የመከላከል ተግባር ለመቋቋም ከቻልን በኋላ ወዲያውኑ መረባችን በጎል ማስፈራችን አሳዛኝ ሆኖብኛል፡፡ ምክንያቱም ጎሏ የተገኘችው ተጨዋቾቹ ትልቁን ኃላፊነታቸውን ከፈፀሙ በኋላ ወዲያውኑ ነው››

ቡድናቸው የቆሙ ኳሶች ብቃቱን ስለማሳደጉ

‹‹ከቆሙ ኳሶች የማጥቃት እንቅስቃሴያችን ከዚህ በፊት ከነበረው አንፃር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተሻለ ሊሆንልን የቻለበት አንዱ ምክንያት ቅጣት ምቶችን የሚመቱልን ተጨዋቾች ብቃት አስተማማኝ ደረጃ ላይ መገኘቱ ነው፡፡ በሳምንቱ አጋማሽ ኮፒ ኤስ ቪ አይንድሆቨን ጋር ባደረግነው የቻምፒዮንስ ሊግ ግጥሚያም ዳሊ ብሊንድ በመአዘን ምት በትክክለኛው ቦታ ላይ ባስቲያን ሽዌንሲቲገርን ለማግኘት በመቻሉ የአቻነቷን ጎል እንድናገኝ ምክንያት ሆኖናል፡፡ የቆሙ ኳሶችን የሚመቱት ተጨዋቾችን ከአንዱ ግጥሚያ ወደ ሌላው በተሸጋገርን ቁጥር የመቀያየር ስትራቴጂ መያዛችንም ከዚህ መስፈርት ያለን ብቃት የተሻለ እንዲሆንልን ሌላኛው ምክንያት ሆኖናል፡፡

ቡድናቸው በርካታ እድሎችን ስላልፈጠረበት ጉዳይ

‹‹ይህንን ችግራችንን መቅረፍ ከቻልን ሁልጊዜም ሙሉ ትኩረትን ሰጥተን እየሰራንበት ያለው ጉይ መሆኑን ለማረጋገጥ እወዳለሁ፡፡ በዚህ ግጥሚያ ግን በምንመኘው መልኩ በበቂ ሁኔታ ጎል የማስቆጠር እድሎችን ለመፍጠር ሲሳነን ታይቷል፡፡ ለዚህ አንዱ ምክንያት የሌሲስተር ሲቲ ተጨዋቾች አብዛኛውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜን ከራቸው የሜዳ ክልል ሳይወጡ ማሳለፋቸው የፈጠረብን ተፅዕኖ  መሆኑን ግን አምናለሁ፡፡ ተስፋ የማደርገውም ከፊታችን ካሉት ግጥሚያዎች በርካታ ጎል የማስቆጠር እድሎችን ለመፍጠር ያልቻልንበት ችግራችንን በአግባቡ ለመቅረፍ እንችላለን ብዬ ነው››

ዋይኒ ሩኒን ስለቀየሩበት ውሳኔያቸው

‹‹በሁለት የተለያዩ ምክንያቶች የደረስኩበት ውሳኔ ነው፡፡ የመጀመሪያው መጠነኛ የሆነ የህመም ስሜት ሊፈጠርበት በመቻሉ ነው፡፡ በሜዳ ውስጥ ሲያነክስም ታይቷል፡፡ ሁለተኛው ምክንያቴ ደግሞ በፊት አጥቂ መስመራችን በተጋጣሚ ቡድን የተከላካይ መስመር ጀርባ በከፍተኛ ፍጥነት የሚገባ ተጨዋችን ለማግኘት የምንችልበት የስትራቴጂያዊ ለውጥ ስላስፈለገኝ መሆኑን ለማረጋገጥ እወዳለሁ››

The post Sport: ባስቲያን ሽዌንስታይገር ‹‹ማንቸስተር ዩናይትዶች በመሆናችን በእስካሁኑ የተሻለ ስኬት ሊኖረን ይገባል›› appeared first on Zehabesha Amharic.


Health: የጨጓራ ካንሰር ጉዳይ | 60 በመቶው ምልክት አልባ መሆኑን ያውቃሉ?!! –ይህን ህመም እንዴት በቀላሉ መከላከል፤ መከሰቱን ማወቅና ማዳን ይቻላል?

$
0
0

Gastric

60 በመቶው ምልክት አልባ መሆኑን ያውቃሉ?!!

ይህን ህመም እንዴት በቀላሉ መከላከል፤ መከሰቱን ማወቅና ማዳን ይቻላል?

የህክምና ባለሙያ በጉዳዩ ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተውበታል!!

 

ከእምብርት በላይ ያለው የሆድ ክፍል አካባቢ ህመም ሲሰማ ህመሙ ቁርጠት ወይም የቁስለት ስሜት ሊሆን ይችላል፡፡ አሊያም ምንነቱን በግልፅ ለማስረዳት የሚያስቸግር የህመም ስሜት ሊሆን ይችላል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም ማቅለሽለሽ፣ ማቃጠል፣ ማግሳትና ከምግብ በኋላ ሆድ የመንፋት ስሜቶች ካሉ ሁሉንም ነገር ከጨጓራ በሽታ ጋር የማያያዝ ጉዳይ በብዙ ሰው ዘንድ ተለመደ ሆኗል፡፡ ነገር ግን እነዚህ ምልክቶች ሲታዩ ሁልጊዜ የጨጓራ ህመም ነው ብሎ የተለያዩ ማስታገሻ መድሃኒቶችን መውሰድ አደገኛና ትክክል ያልሆነ ጉዳይ ነው፡፡

ምክንያቱም ሌሎች ተመሳሳይ ምልክት ያላቸውና ፈጥነው ካልተደረሰባቸው ህይወትን ለአደጋ የሚያጋልጡ በርካታ የበሽታ አይነቶች ስላሉ ነው፡፡ ከሞላ ጎደል የጨጓራ በሽታ የሚያሳያቸውን ምልክቶች ከሚያሳዩ በሽታዎች መካከል የጨጓራ ካንሰር በቀዳሚነት ይጠቀሳል፡፡ ለዛሬ በጨጓራ ካንሰር ምንነት፣ መንስኤ፣ አጋላጭ ምክንያቶች፣ የጨጓራ ካንሰር ከሌሎች በሽታዎች ጋር ባለው ትስስርና ለበሽታው ባሉ አማራጭ መፍትሄዎች ዙሪያ፣ አንድ የህክምና ባለሙያ ማብራሪያ ሰጥተውናል፡፡

ጥያቄ፡ጨጓራን በመጠኑ ያስተዋውቁንና ውይይታችንን እንጀምረው?

ዶክተር፡- ጨጓራ በምግብ መውረጃና በወተት አንጀት መካከል የሚገኝ ለሰውነታችን ጠቃሚ የሆነ የሰውነት ክፍል ነው፡፡ በሚበላና በሚጠጣ መልክ ወደ ሆዳችን የሚገቡ ነገሮችን የመቀበል፣ የማጠራቀም፣ የመፍጨትና ተፈጥሯዊ በሆነ የመቆጣጠሪያ ስርዓት አማካኝነት ሰውነት በሚፈልገው መጥን መጥፎ ወደ ትንሽ አንጀት የማስተላለፍ ስራን ያከናውናል፡፡ ጨጓራ ከሚያከናውናቸው ተግባራት አንፃር ሶስት ክፍሎች አሉት፡፡ እነሱም የላይኛው ወይም አናት አካባቢ የሚገኘው ክፍል (ፈንደስ)፣ በመሀል የሚገኘውና ሰፊ ቦታ የሚይዘው (ቦዲ) እና የታችኛው አካባቢ የሚገኘው ክፍል (አንትረም) ናቸው፡፡ ሶስቱ ክፍሎች የተነጣጠሉ ሆነው ሳይሆን ከአሰራራቸው አንፃር የሚለያዩ ስለሆነ ነው፡፡

ጨጓራ ላይ ሁለት ተቃራኒ ነገሮች አሉ፡፡ እነሱም ከጨጓራ ህመም የሚከላከሉልን ጉዳዮ በአንድ በኩል፣ እንዲሁም ለጨጓራ በሽታ የሚያጋልጡን ጉዳዮች ደግሞ በሌላኛው በኩል የተፋጠጡ ናቸው፡፡ ከጨጓራ ህመም ከሚከላከሉልን ነገሮች፣ ጨጓራ በተፈጥሮው ድርብና ጠንካራ ግድግዳ ያለው ከመሆኑ ባሻገር ጨጓራ በሚያመነጨው አሲድ እንዳይቃጠል ከላይ ንፍጥ መሰል ሽፋን ያለው ነው፡፡ አሲዱ ከመጠን በላይ እንዳይበዛ የሚከለከልልን አልካላይን ወይም ባይካርቦኔት የሚባል ንጥረ ነገርም አለው፡፡ እንዲሁም ከጨጓራችን የሚመነጨው አሲድ እንደፈለገው ወጥቶ ሰውነታችንን እንዳያቃጥለው ከላይና ከታች ያሉ የጨጓራ በሮች የመከላከል ተግባርን ያከናውናሉ፡፡

ጥያቄ፡የጨጓራን መደበኛ ተግባር ከሚያውኩ የጤና ችግሮች ዋና ዋና የሚባሉትን ቢገልፁልኝ?

ዶክተር፡- ማንኛውም ወደ ሆድ የሚገባ ነገር ከምግብ መውረጃ ቱቦ ቀጥሎ የሚያገኘው ጨጓራን ነው፡፡ በዚህም ሳቢያ ለተለያዩ በሽታዎች ተጋላጭ ይሆናል፡፡ ጨጓራን ከሚያጠቁ በሽታዎች መካከል በተፈጥሮ የጨጓራ መጥበብ (መኮማተር)፣ በምግብና በውሃ መበከል ሳቢያ የሚከሰት ኢንፌክሽ፣ የጨጓራ ግድግዳ መቆጣት፣ የጨጓራ ዕጢ፣ ከጨጓራ የሚነሱ ወይም ከሌሎች የሰውነት ክፍሎች የሚሰራጩ ካንሰሮችና መነሻ የሌላቸው አላርጂዎች፣ የጨጓራ በሽታን ከሚያመጡ የጤና ችግሮች መካከል ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ከላይ ከተዘረዘሩ የጤና ችግሮች በተጨማሪ ሌሎች በሽታዎች ማለትም የጉበት፣ የልብ፣ የኩላሊትና የሣንባ በሽታዎች የጨጓራ ህምምን ያመጣሉ፡፡

ጥያቄ፡ሌሎችን የጤና ችግሮች ወደ ፊት እንደ ሁኔታው በዝርዝር የምናያቸው ይሆናል፡፡ ለዛሬው ግን በጨጓራ ካንሰር ላይ እናተኩራለን፡፡ እስኪ ስለጨጓራ ካንሰር ምንነት የተወሰኑ ሐሳቦችን እናንሳ?

ዶክተር፡- ጨጓራ እንደማንኛውም አካል ያረጁ ሴሎችን በማስወገድ በአዳዲስ ሴሎች በመተካት፣ ሁልጊዜም ራሱን የሚያድስበት ተፈጥሯዊ ሂደት አለው፡፡ ከዚህ ተፈጥሯዊ የቁጥጥር ስርዓት ውጭ በሆነ መንገድ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሴሎች በዘፈቀደ ይራባሉ፡፡ የሴሎች ክምችት ደግሞ እብጠትን ይፈጥራል፡፡ እብጠቱ ካንሰር ሊሆን ይችላል ወይም ደግ ቅድመ ካንሰር (ወደፊት ካንሰር ሊሆን የሚችል) የሴሎች ክምችት (መከመርን) ያስከትላል፡፡ የጨጓራ ካንሰር በሁለት መልኩ ሊከሰት ይችላል፡፡ የመጀመሪያው ከጨጓራ ከራሱ ላይ የሚነሳ ካንሰር ሲሆን ሁለተኛው በደም ስሮች አማካኝነት ከሌሎች የሰውነት ክፍሎች ለምሳሌ ከአንጀት፣ ከጉበት፣ ከጡት፣ ከሳንባ፣ ከማህፀን፣ ከአጥንትና ከዘር ፍሬ የሚነሱ ካንሰሮች ጨጓራን ያጠቃሉ፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የሚከሰተው ግን ከራሱ ከጨጓራ ላይ የሚነሳው ካንሰር ነው፡፡

ጥያቄ፡የጨጓራ ካንሰር በዓለም አቀፍ ደረጃ በምን ሁኔታ ላይ ይገኛል?

ዶክተር፡- በዓለም ላይ በስፋት ከሚታዩ የካንሰር አይነቶች መካከል ከሳንባ ካንሰር ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ የሚታየው ከጨጓራ የሚነሳው ጋስትሪክ ካንሰር ነው፡፡ በዓለም ላይ ከ40 እስከ 50 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ለጨጓራ ካንሰር የተጋለጠ ነው፡፡ በተለይም በጃፓን፣ በቻይና፣ በራሺያ፣ በአርጀንቲና እና በብራዚል አካባቢ ባሉ ሀገሮች በስፋት ይታያል፡፡

ጥያቄ፡የጤና ችግሩ በሀገራችን በምን ሁኔታ ላይ ይገኛል?

ዶክተር፡- ከላይ በጠቀስኳቸው አገሮች መጠን ባይሆንም በሀገራችን የጨጓራ ካንሰር ከፍ ባለ ቁጥር ደረጃ ይታያል፡፡ በችግሩ ዙሪያ ሀገራዊ ጥናት ባይጠናም በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የኢንዶስኮፒ ምርመራ በተደረገላቸው ሰዎች ላይ የምግብ መውረጃ ቧንቧ፣ የጨጓራና የትንሹ አንጀት ካንሰሮችን መሰረት አድርጎ የተወሰነ ጥናት ተካሂዷል፡፡ በጥናቱ በባሌና በአርሲ ገጠራማ አካባቢዎች የምግብ መውረጃ ቱቦ ካንሰር በቀዳሚነት እንደሚታይ ተስተውሏል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ የታየው የጨጓራ ካንሰር ነው፡፡ ከፆታ አንፃር ከሴቶች ይልቅ ወንዶች በሁለት እጥፍ ለጨጓራ ካንሰር የመጋለጥ ዕድል አላቸው፡፡

ጥያቄ፡ለጨጓራ ካንሰር አጋላጭ ምክንያቶች የትኞቹ ናቸው?

ዶክተር፡- በቤተሰብ ውስጥ የካንሰር ታሪክ ያላቸው ሰዎች ከሌላቸው ሰዎች ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው፡፡ የአልኮል መጠጦችን የሚያዘወትሩ፣ ሲጋራ የሚያጨሱ፣ ቅባትና ቅመማ ቅመም የበዛባቸውን ምግቦች የሚመገቡ፣ ከፍተኛ የሰውነት ክብደት ያላቸው፣ በተደጋጋሚ የጨጓራ መቆጣት ያጋጠማቸውና ጨጓራ አካባቢ ተደጋጋሚ ቀዶ ህክምና ያደረጉ ሰዎች ለጨጓራ ካንሰር የመጋለጥ ዕድል አላቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ለቲቢ፣ ለቫይረስ እና ለተለያዩ የካንሰር በሽታዎች የሚሰጡ መድሃኒቶች ለጨጓራ ካንሰር መከሰት ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እንደዚሁም ለቤንዚን፣ ለጨረር፣ ለፋብሪካ ተረፈ ምርቶችና ለተለያዩ ኬሚካሎች መጋለጥ የጨጓራ ካንሰርን ያስከትላል፡፡

ጥያቄ፡የጤና ችግሩ ሲከሰት የሚያሳያቸው ምልክቶችስ?

ዶክተር፡- የጨጓራ ካንሰር ከፍተኛ ደረጃ ላይ እስኪደርስ ድረስ 60 በመቶው ምንም አይነት ምልክት አያሳይም፡፡ ስር ከሰደደና ደረጃው ከፍ ካለ በኋላ የሚያሳያቸው ምልክቶች የምግብ አለመፈጨት፣ የምግብ ፍላጎት ማጣት፣ ማቅለሽለሽ፣ የሆድ መነፋት፣ ከእንብርት በላይ ያለው የሆድ ክፍል መጎርበጥ (ህመም)፣ ቁርጠት፣ ማስታወክ፣ መድማትና የሆድ እብጠት ከሚታዩ ምልክቶች በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ፡፡

ጥያቄ፡ከጨጓራ ካንሰር ጋር ተመሳሳይነት ያላቸውን የህመም ምልክቶች የሚያሳዩ ሌሎች በሽታዎች ካሉ ቢገልፁልኝ?

ዶክተር፡- የጨጓራ ካንሰር ሲከሰት ከሚያሳያቸው ምልክቶች ተመሳሳይ የሆነ የጨጓራ ካንሰር፣ የሀሞት ከረጢት መቆጣት፣ የጣፊያ መቆጣት፣ አጣዳፊ የልብ ህመም፣ የትንሹ አንጀት ቁስለት፣ የሀሞት ጠጠር፣ የኩላሊት፣ የጉበት፣ የስኳርና የደም ብዛት በሽታዎች ጨጓራ መሰል የህመም ምልክት ያሳያሉ፡፡ ከእነዚህ በሽታዎች በተጨማሪ የምግብ ቱቦ መቆጣት፣ ከጨጓራችን የሚወጣው አሲድ ተመልሶ የምግብ ቱቦን ሲያቆስል፣ የሣንባ ምችና በሕፃናት ላይ የሚከሰት የሣንባ ኢንፌክሽን፣ የጨጓራ በሽታ ከሚያሳያቸው ምልክቶች ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው በመሆኑ ትኩረት ሳይሰጣቸው በመቅረቱ ብዙ ጊዜ የከፋ ጉዳት ሲያስከትሉ ይታያሉ፡፡ ከበሽታዎች ባሻገርም ሲጋራ የሚያጨሱ፣ ዕድሜያቸው የገፋ፣ የሰውነታቸው ክብደት ከሚጠበቀው በላይ የሆነባቸው ሰዎች፣ የጨጓራ ህመም መሰል ምልክቶች ሊያሳዩ የሚችሉ በመሆኑ፣ ማንኛውም ሰው ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል፡፡

ጥያቄ፡የጨጓራ ካንሰር ደረጃ ካለው ብናየው?

ዶክተር፡- የጨጓራ ካንሰር አራት ደረጃዎች አሉት፡፡ ደረጃ አንድ የሚባለው ካንሰሩ በተነሳበት ቦታ ላይ ተወስኖ የሚታይ ሲሆን፣ ደረጃ ሁለት ከጨጓራ ግድግዳ አልፎ ወደ አካባቢ መሰራጨት ሲጀምር ነው፡፡ ደረጃ ሶስት የምንለው በአካባቢው ያሉ አካላትን ማጥቃት ሲጀምር ማለት ነው፡፡ የመጨረሻው ደረጃ አራት ሲሆን በዚህ ደረጃ ላ ካንሰሩ በርቀት ወዳሉ የተለያዩ የአካል ክፍሎች ሲሰራጭ ነው፡፡ ለካንሰር በሽታ በህክምናው የሚሰጠው መፍት ውጤታማ የሚሆነውም ሆነ የማይሆንበት ጉዳይ የሚወሰነው ካንሰሩ ካለበት ደረጃ አንፃር ነው፡፡

ጥያቄ፡በአገራችን ከሚታዩ የካንሰር ህሙማን መካከል አብዛኛዎቹ ማለት ይቻላል ወደ ጤና ተቋማት የሚመጡት፣ ካንሰሩ ደረጃ 3 እና 4 ሲደርስ እንደሆነ ከጤና ተቋማት የተገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ምክንያቱ ምንድነው?

ዶክተር፡- ሐኪሞችን ጨምሮ በአብዛኛው ሰው፣ የጨጓራ በሽታን ቀለል አድርጎ ስለሚያየው ምልክቶችን መሰረት በማድረግ በግምት ማስታገሻ መድሃኒት ይወስዳል፡፡ የጤና ችግሩ ተገቢውን ህክምና ሳያገኝ ጊዜ ይሄል፡፡ በዚህም ምክንያት ካንሰሩ በጊዜው ሳይደርስበት ወደ ከፋ ደረጃ የሚሸጋገርበት ሁኔታ ይፈጠራል፡፡

ጥያቄ፡የጨጓራ ካንሰር በሽታ ለማረጋገጥ የሚቻለው እንዴት ነው?

ዶክተር፡- በህክምናው ሳይንስ የሚረጋገጥበት የተለያዩ የምርመራ ዘዴዎች አሉ፡፡ በደምና በሰገራ የካንሰር ጠቋሚ ምርመራ ይካሄዳል፡፡ የካንሰር ዕጢ መኖር አለመኖሩንና መራባት አለመራባቱን ለማወቅ የአልትራሳውንድ ምርመራ ይደረጋል፡፡ ለጨጓራ ካንሰር አስተማማኝ የሚባለው ምርመራ ኢንዶስኮፒ ነው፡፡ ኢንዶስኮፒ የጤፍ ፍሬ ከምታክለው እብጠት ጀምሮ እስከ ትልቁ እብጠት ድረስ በትክክል ለማየት ያስችላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የካንሰሩን አይነት፣ መነሻውን፣ የስርጭቱን ሁኔታ፣ ካንሰሩ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ በኢንዶስኮፒ የባዮብሲ ምርመራ በማድረግ የካንሰሩን ትክክለኛነት ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

ጥያቄ፡የካንሰሩ መኖር ከተረጋገጠ በኋላ በህክምናው ያለው መፍትሄ ምንድን ነው?

ዶክተር፡- የካንሰር እብጠቱ ከ214 ሳ.ሜ ከሆነ እና ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ካልተሰራጨ፣ በኢንዶስኮፒ አማካኝነት ቀረፎ (ቆርጦ) በማውጣት ማከም ይቻላል፡፡ ካንሰሩ ያለበት ደረጃ ከፍ ያለ ከሆነ በቀዶ ህክክና ማከም ይቻላል፡፡ በቀዶ ህክምናው ጨጓራ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ቆርጦ በማውጣት ለማከም ጥረት ይደረጋል፡፡ ከቀዶው ህክምና በኋላ ኪሞ ቴራፒና የጨረር ህክምናን ውጤት አስተማማኝ የሚሆነው ካንሰሩ የደረሰበት ደረጃ ነው፡፡ አስቀድሞ ከተገኘ ሙሉ በሙሉ ማዳን ይቻላል፡፡

ነገር ግን ካንሰሩ ወደ ሌላ ቦታ ከተሰራጨ በኋላ የሚደረግ የካንሰር ህክምና፣ የበሽተኛውን የአኗኗር ሁኔታ ጊዜያዊ በሆነ መንገድ ለማሻሻል እንጂ በዘላቂነት በየጊዜው ወቅታዊ የጤና ምርመራ በማድረግ በሽታው ካለ በጊዜው እንዲደርስበት ዕድል መፍጠር ይገባል፡፡ በተለይም ተደጋጋ የጨጓራ ቀዶ ህክምና ያደረጉ፣ በቤተሰብ ደረጃ የካንሰር ታሪክ ያላቸውና በተደጋጋሚ በኢንፌክሽ የተጋለጡ ሰዎች በየጊዜው ወቅታዊ ምርመራ በማድረግ ራሳቸውን ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡ ምክንያቱም ካንሰሩ ከፍ ወዳለ ደረጃ ሳይሸጋገር በጊዜው ማግኘት ማከም ስለሚያስችል ነው፡፡

ጥያቄ፡ቀደም ብለው ካንሰርን ለማከም ጨጓራ በቀዶ ህክምና ሙሉ በሙሉ እንዲወጣ ይደረጋል ብለዋል፡፡ ለመሆኑ የህመምተኛው የወደፊት ዕጣ ፈንታ ምንድነው የሚሆነው?

ዶክተር፡- ጨጓራ ሙሉ በሙሉ ቢወጣም መኖር ይችላል፡፡ ምንድነው የሚደረገው፣ የምግብ መውረጃ ቱቦንና አንጀትን በማገጣጠም ነው ህክምናው የሚሰራው፡፡ አንጀቱን በመሳብ ጨጓራን የሚመስል ነገር ይፈጠራል፡፡ ነገር ግን ህክክናው ምንም አይነት ችግር አያስከትልም ማለት አይደለም፡፡ እስከ ሁለት ዓመት ድረስ ብዙ ምግብ በአንድ ጊዜ መመገብ አይቻልም፡፡ ምግብ ከተባለ በኋላ ቶሎ ወደ አንጀት ስለሚገባ በተባለ ቁጥር ተቅማጥ ሊኖር ይችላል፡፡ እነዚህን ችግሮች ለመቀነስ የሚያስችሉ መድሃኒቶች ይሰጣሉ፡፡ ትንሽ ትንሽ ምግቦችን ቶሎ ቶሎ መመገብ ጠቃሚ ይሆናል፡፡

ጥያቄ፡ማንኛውም ምግብ መመገብ ይቻላል?

ዶክተር፡- ማንኛውንም ምግብ መመገብ አይቻልም፡፡ ፈሳሽና የተፈጩ ምግቦችን ነው መመገብ የሚገባቸው፡፡ እንደዚሁም ቅባት የበዛባቸውን ምግች በተቻለ መጠን መመገብ አይኖርባቸውም፡፡

ጥያቄ፡ከላይ የዘረዘሯቸው ህክምናዎች በሀገራችን ይሰጣሉ?

ዶክተር፡- ከሞላ ጎደል ሁሉም የህክምና አይነቶች በሀገራችን ሲሰጡ የሌለው የጨጓራ ካንሰርን በትንሽነቱ ስንደርስበት፣ ያለ ቀዶ ህክምና ካንሰሩን ቆርጦ ለማውጣት የሚያስችለው የኢንዶስኮፒ ህክክና በሀገራችን የለም፡፡ ነገር ግን ቀላል ነው፡፡ ጉዳዩ የመሳሪያ ጥያቄ ነው፡፡ መሳሪያው ከገባ ማንኛውም ኢንዶስኮፒ የሚሰራ ሐኪም ህክክናውን ሊሰጥ ይችላል፡፡ ሌላው ለካንሰር ተብሎ የሚሰጠው የጨረር ህክክና አለመስፋፋቱ ነው፡፡ በሀገራችን አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ አንድ ሰው፣ ለጨረር ህክምና እስከ ስድስት ወር ድረስ የሚጠብቅበት ሁኔታ አለ፡፡ ይሄን ችግር ለመቅረፍ በመንግሥት በኩል ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራበት እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ሐኪሞች እየሰለጠኑ ነው፡፡ መሳሪያዎችን በመንግሥትም ሆነ በግል ለማስገባት ጥረቶች እየተደረጉ ነው፡፡ ወደፊት ለውጥ ይመጣል ብዬ አምናለሁ፡፡

ጥያቄ፡የጨጓራ ካንሰርን ለመከላከል ምን ይደረግ?

ዶክተር፡- ትኩስነትና የማቃጠል ባህሪ ያላቸውን ምግቦች ማስወገድ፣ መጠጥና ሲጋራን በተቻለ አቅም ማስወገድ፣ የሰውት ክብደትን መቆጣጠር፣ ወቅታዊ የጤና ምርመራን በየጊዜው ማድረግና ከሁለት ሳምንት የዘለለ የጨጓራ ህመም ከተከሰተ ወደተገቢው የህክምና ባለሙያ በመሄድ ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል እላለሁ፡፡

The post Health: የጨጓራ ካንሰር ጉዳይ | 60 በመቶው ምልክት አልባ መሆኑን ያውቃሉ?!! – ይህን ህመም እንዴት በቀላሉ መከላከል፤ መከሰቱን ማወቅና ማዳን ይቻላል? appeared first on Zehabesha Amharic.

የማይንበረከክ መንፈስ (The Indomitable Spirit) |ገጣሚ፤ አንዱዓለም አራጌ –ከቃሊቲ ትርጉም፤ መስፍን ማሞ ተሰማ –ሲድኒ

$
0
0

andu-family-45

ይህ ከቃሊቲ መቀመቅ የወጣ የታጋዩ አንዱዓለም አራጌ የፅናት፤ የተስፋና የትግል ጥሪ ነው። ጥሪው ሥነ ቃል ነው። ሥነ ሕይወት። ሥነ ትግል! ቃል የዕምነት ዕዳ ነው – እንዲሉ። ይህ ሥነ ቃል አስቀድሞ የወረደው በፈረንጅ ቋንቋ በእንግሊዝኛ ነው። ሥነ ቃሉን ከሰፈረበት ድረ- ገፅ እንዳነበብኩት – ሰቀዘኝ። እያደር ደግሞ አስማጠኝ። ምናለ በሀገርኛ ቋንቋ ብመልሰው? ግና እንደገጣሚው ውስጠ ህመም ህመሙን ምን ያህል ማስተላለፍ እችላለሁ? እስከምንስ ጠልቆ ይሰማኛል? ወይስ አሞኛል?….ለማንኛውም እነሆ!

The post የማይንበረከክ መንፈስ (The Indomitable Spirit) | ገጣሚ፤ አንዱዓለም አራጌ – ከቃሊቲ ትርጉም፤ መስፍን ማሞ ተሰማ – ሲድኒ appeared first on Zehabesha Amharic.

በአሜሪካኖች ዘንድ እና በመላው ዓለም እየተሰፋፋ የመጣው አሳሳቢው የሴት ልጆች ግርዛት ሲቃኝ |ልዩ ዘገባ | Audio

ድሬዳዋ ከተማ የተቃውሞ መፈክር ወረቀቶች ተለጣጥፈው አደሩ

$
0
0

tekawimo 3

tekawimo

tekawimo2

tekawimo4
በኢትዮጵያ የተለያዩ ከተሞች የሚደረገው ተቃውሞ በቀጠለበት በዚህ ወቅት ዛሬ ሌሊት የካቲት 2/2008 በድሬዳዋ ከተማ በበርካታ ቦታዎች መፈክሮች ተለጥፈው ማደራቸውን ድምፃችን ይሰማ ዘገበ::
ድምፃችን ይሰማ እንደዘገበ በህዝበ ሙስሊሙ ላይ የሚፈጸሙ በደሎችን እና በኦሮሞ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግድያ በመቃወም በአማርኛ እና በኦሮሚፋ ቋንቋዎች የቀረቡት እኒሁ መፈክሮች በተለያዩ ስልክ እንጨቶች እና በግድግዳዎች ላይ ተለጥፈው ታይተዋል፡፡
በአማርኛ ከተለጠፉት መፈክሮች መካከል ‹‹ብሄራዊ ጭቆናው ይብቃ!››፣ ‹‹ኮሚቴው ይፈታ!››፣ ‹‹ድምጻችን ይሰማ!››፣ ‹‹የታሰሩት ይፈቱ!››፣ ‹‹ድራማው ይብቃ!››፣ የኦሮሞን ህዝብ መግደል ይቁም!››፣ ‹‹አምባገነን ፍርድ አንቀበልም!››፣ ‹‹ህዝብ ያልተቀበለው ማስተር ፕላን ተቀባይነት አይኖረውም!››፣ ‹‹የኢቢሲ ውሸት በቃን!›› የሚሉት የሚገኙ ሲሆን እኒሁ መፈክሮች በኦሮሚፋ ቋንቋም መለጠፋቸውን ሲል ድምፃችን ይሰማ አስታውቋል::

The post ድሬዳዋ ከተማ የተቃውሞ መፈክር ወረቀቶች ተለጣጥፈው አደሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

“በሃገራችን ላይ ነገ ከሚመጣው አደጋ ለመዳን ዛሬውኑ የቤት ሥራችንን እንስራ”ኦባንግ ሜቶ ወቅታዊ ቃለምልልስ | Audio

$
0
0

በአገራችን ሁለት ነገር ለውጥ ፈላጊውን ሀይል እያሳሰቡት የመጡ ይመስላሉ። በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ በብዙ መመዘኛዎች እየተዳከመ መምጣትና ይሄን ደካማ ስርዓት መቼና እንዴት በፍጥነት እንገላገለዋለን እና መጪውን ቀን ይህ ስርዓት የፈጠራቸው የጎሳና የሀይማኖት ፍጥጫዎችን ሕዝቡ በቀላሉ ይሻገራቸዋል ወይ? የሚሉት ዋነኞቹ ናቸው። ስርዓቱ ሕዝቡን በሳት አርጩሜ እየገረፈ ለመኖር አንዱን በሌላው እያስነሳ ዕድሜውን ለማራዘም የቆረጠ ነው። ኦባንግ ሜቶ ያንን ለመሻገር ከጎሳ ይልቅ ለሰብኣዊነታችን ቅድሚያ መስጠት ይገባል… ነገ ከሚመጣው ለመዳን ዛሬውኑ የቤት ሰራችንን እንስራ” ባይ ነው።ስለ ወቅታዊው የጋምቤላ ግጭትና ስለ ቀጣዩ <<እና ለእኛ>> ሕዝባዊ መድረክም አብራርተዋል። የህብር ራድዮ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ አነጋግሯቸዋል: ይህን ወቅታዊ ቃለ መጠይቅ እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።

“በሃገራችን ላይ ነገ ከሚመጣው አደጋ ለመዳን ዛሬውኑ የቤት ሥራችንን እንስራ” ኦባንግ ሜቶ ወቅታዊ ቃለምልልስ | Audio

The post “በሃገራችን ላይ ነገ ከሚመጣው አደጋ ለመዳን ዛሬውኑ የቤት ሥራችንን እንስራ” ኦባንግ ሜቶ ወቅታዊ ቃለምልልስ | Audio appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live