Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

በቡታጅራ ከተማ ታላቅ ህዝባዊ ተቃዉሞ ተደረገ |የሳዲቅ አህመድ የቪድዮ ዘገባ ከጽሁፍ ጋር

$
0
0

በደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን በመሰቃን ወረዳ በዛሬዉ እለት ህዝባዊ እምቢተኝ ተስተዋለ።ፓሊሶች ተደብድበዋል።ፖሊሶች ተጎድተዋል። የመንግስት ታጣቂ ሐይላት ክላሽ ኢንኮቫቸዉን ተቀምተዋል።

መንግስት ያወጣዉን የመሬት ይዞታ አዋጅ በመቃወም ዛሬ በድንገት የተደረገዉ ሰልፍ ፖሊሶች ህዝቡን መቆጣጠር ተስኖአቸዉ በህዝብ ቁጥጥር ስር የዋሉበት አጋጣሚ እንደነበር የሰልፉ ታዳሚዎች ያስረዳሉ። መንግስት ከአያት ቅድመ አያቶቻችን የወረስነዉን መሬት እየቀማ ለኢንቨስተሮች ይሰጥብናል የሚሉት የቡታጅራና የአካባቢዉ ነዋሪዎች ተወልደን ባደግነበት ቀዬ እንድንፈናቀል ተደርገናል ሲሉ ቅሬታን ያሰማሉ።

የአካባቢዉ ነዋሪዎች ለቢቢኤን እንደገለጹት ልክ የአዲስ አበባዉን የሚመስል ማስተር ፕላን በድብቅ ተሰርቶ ስራ ላይ እየዋለ ነዉ። በህወሃት የሚመራዉ መንግስት የመስቃንን ማህበረሰብ መሬት በተቀናጀ መልኩ ለመዝረፍና ጥቅሙን ለሚያስከብሩ አካላት ለመስጠት የምስጢር ፕላኑን ወደ መሬት ላይ ለማዉረድ ሲሞክር ነዉ ዛሬ በፖሊሶችና በህዝብ መካከል ግጭት የተነሳዉ።

የተቦን፣ዊጣ፣ወዶ፣ጆሌ ሐሙስ ገበያ በሚባሉት የመስቃን ወረዳ ቀበሌ ገበሬ ማህበራት ያሉ አርሶ አደሮች መሬታቸዉ እየተቀማ ህወሃት መራሹ መንግስት ለሚፈልጋቸዉ አካላቶች መሰጠቱን የሚያስረዱት አርሶ አደረሮች ጉዳዩ የህልዉና ጉዳይ ስለሆነ ለአቤቱታ ወደ ቡታጅራ ከተማ በመጡበት መታሰራቸዉን ይገልጻሉ።

በገዛ መሬታቸዉ ቤት የሰሩ አርሶ አድረሮች ከተማዎች በሚስፋፉበት ወቅት ቤቶቻቸዉ እንደሚፈርሱ በምሬት ይናገራሉ።እንደ ቅርስ የያዙት ቤትና ንብረት እንደመከነ የሚገልጹት አርሶ አደሮች ከከተማ ራቅ ወዳሉ የገጠር ቀበሌዎች የመሰቃን ወረዳ እና የቡታጀራ ከተማ አሰተዳደር ባለስልጣናት ከታጣቂ አጃቢዎች ጋር በመጓዝ የገጠር ቤቶች ከመንግስት ፍቃድ ዉጪ የተሰሩ በመሆናቸዉ መፍረስ አለባቸዉ ቤቶቹን ለማፍረስ ያደረጉት ሙከራ በዉርደት መጠናቀቁን ነዋሪዎቹ ለቢቢኤን ገልጸዋል።

“እኛ የገጠር ነዋሪዎች ነን፤ በገጠር ዉስጥ ልክ እንደ አያት ቅድመ አያቶቻችን ቤት እንሰራለን፤ ይህንንም ለማድረግ የማንም ፍቃድ አያሻንም!” በማለት ባለ ሰልጣናቱ የታጀብቡበትን ክላሽ-ኢንኮቭ በመንጠቅ ከየቀበሌ ገበሬ ማህበራቱ እንዳባረሯቸዉ የመስቃን ወረዳ ነዋሪዎች ለቢቢኤን ገልጸዋል።

በመሬት ነጠቃዉ የተንገፈገፉ የቡታጅራ ነዋሪዎች በዛሬዉ እለት ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ አደባባይ መዉጣታቸዉን የገለጹልን የቡታጅራ ነዋሪዎች በከተማዋ ዉስጥ እየዞሩ የተቃዉሞ ድምጽ ማሰማታቸዉን ለቢቢኤን ገልጸዋል።ሰላማዊ ሰላፍ አድራጊዎቹ “መንግስት ሌባ፣ ፖሊስ ሌባ፣መብታችን ይከበር፣የታሰሩት ይፍቱ፣ጥያቄያችን ይመለስ!” እያሉ ድምጻቸዉን ሲያሰሙ ከአገር ሽማግሌ በስተቀር ሊያቆማቸዉ የሞከረ የፖሊስ ሐይል አለመኖሩ ለማወቅ ተችሏል።

ተቃዉሞዉ በሚደረግበት ሰዓት ባንክ ቤቶች፣ቤንዚን ማደያዎች፣ሱቆች ምግብ ቤቶች የተዘጉ ሲሆን ከተማዉን ከሆሳእና፣ከአዲስ አበባ እና ከዝዋይ የሚያገናኘዉ ዋና መንገድ ተዘግቶ እንደነበርም ለማወቅ ተችሏል።ማምሻዉን በደረሰን መረጃ መሰረት ፈዴራል ፖሊስ ከወልቅጤ ከተማ ቡታጅራ ድረስ በመምጣት ሰፍሯል። ዉጥረት ቡታጅራ ዉስጥ ነግሷል። ይህ ዉጥረት ወዴት እንደሚያመራ ባይታወቅም፥ የታወቀዉ ነገር ቢኖር ባልተጠበቀ መልኩ በየተኛዉም የኢትዮጵያ ክፍል ህዝባዊ እምቢተኝነት ሊከሰት እንደሚችል ነዉ። ዛሬ ቡታጅራዎች ይህንን አስመስከረዋል::

Sadik Ahemed Journalist

The post በቡታጅራ ከተማ ታላቅ ህዝባዊ ተቃዉሞ ተደረገ | የሳዲቅ አህመድ የቪድዮ ዘገባ ከጽሁፍ ጋር appeared first on Zehabesha Amharic.


ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የኦሮሞዎችን ተቃውሞ በተመለከተ የተናገሩት 4 ወሳኝ ነጥቦች

$
0
0

ግርማ ካሳ

ዶክተር ብርሃኑ ነጋ በዋሺንገትን ዲሲ ባደረጉት ንግግር በኦሮሚያ በተነሳው እንቅስቃሴ ዙሪያ 4 ነጥቦችን አንስተው ትምህርት ሰጪ ሃተታዎችን አድርገዋል።

ሲጀምሩ በኦሮሚያ የተደረገው ነገር ለርሳቸው emotional እንደሆነ ነበር የገለጹት። “ሕጻናት፣ እርጉዞች፣ አሮጊቶችን መግደል፣ መርገጥ ….. ፣ እርሱ ለማወገዝ ኢትዮጵያዊ መሆን የለብንም። ሶሪያ ላይ ይሄ ነገር ሆነ ብለን እናዝን የለም እንዴ ? “ ያሉት ዶክተሩ፣ ከምንም ነገር በላይ ፣ ሌላ ስሌቱን ቀርቶ፣ የሰው ልጆች ናቸውና፣ በምንም መልኩ፣ ማንም ያድርገው መወገዝ እንዳለበት ነው የገለጹት።
Screen Shot 2016-02-01 at 10.37.13 PM

“በወገኖቻን ላይ መሆኑ ደግሞ፣ የሚጥልብን እዳ አለ። ከከንፈር መምጠት ወዲያ ማድረግ ያለብን ነገር አለ። ወገኔ ከሆነ፣ ዝም ብዬ ከንፈር መምጠት ከሆነ፣ ምኑ ላይ ነው ወገንንቱ ። ይሄ ነገር እንዲቆም ማድረግ ያለብንን ሁሉ ማድረግ አለብን” ሲሉ ነው ያሰመሩበት።

በመቀጠል በሁለተኛነት የችግሩን መንስኤ መረዳት አንደሚያስፈለግም ያስረዱት ዶር ብርሃኑ የተቃዉሞው መንስኤ ማስተር ፕላኑ እንደሆነ ገልጸው፣ ከማስተር ፕላኑ ጀርባ ግን ጥያቄው የመሬት ጥያቄ እንደሆነ ነው ለማሳየት የሞከሩት። “የማስተር ፕላኑ ጥያቄ ማስተር ፕላን የሚለው አውጥታችሁ ብታዩት፣ የመሬት ነጠቃ ነው” ነበር ያሉት።“የአዲስ አበባ ነዋሪዎችም ተባረዋል፤ ለወያኔ ሃብታሞች ቦታ ለመልቀቅ” ሲሉ፣ ይህ የመሬት ጥያቄ፣ ከማስተር ፕላኑ በፊት በአዲስ አበባ የነበረ ችግር እንደሆነም አስረድተዋል።፡በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በጋምቤላ 300 ሺህ ወገኖች በላይ ከሚኖሩበት ቦታ እንደተባረሩ፣ ለስኳራ ምርት ተብሎ ፣ በአፋር ክልል በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች መንጋቸውን የሚያሰማሩበት መሬት እንደተነጠቁ በመግልጽ፣ ችግሩ ትግራይ ዉስጥም ጨምሮ በሁሉም ቦታቸው እንዳለ ነው ያስረዱት። ስለትግራይ ሲናግሩ “ በትግራይ በራያና አዘቦ የዚያ አካባቢ ለካድሬዎች ቤት ለመስራት ድሃው አፈናቅለዋል፤ በመቀሌ የአፓርታይድ መንደር የሚባል አለ አይደለም እንዴ ? ድሃዉን አባራው እነርሱ የሰሩበት ? “ ነበር ያሉት።

የመሬት ነጠቃው ችግር በሁሉም ቦታ ያለ፣ የአንድ ብሄረሰ ጥያቄ ሳይሆን የመደብ ጥያቄ እንደሆነ የገለጹት ዶር ብርሃኑ በሌሎች ቦታዎች ያለውና በኦሮሚያ ያለው ልዩነቱ አንድ ብቻ እንደሆነ ጠቁመዋል። እርሱም፣ ኦሮሞዎች ለመታገል መወሰናቸው ። “እነርሱ ተነስተው፣ መንገድ ላይ ወጥተው ተቃዉመዋል። እኛ ይሄን የማንደገፈው ለምንድን ነው ? ቅናት ነው ? እንደ ጥያቄ ያነሱት የመሬት ጥያቄ፣ ይሄን ትግል እንድንደግፈው እንጂ እንድናቀወመው የሚይደርግ አይደለም” ሲሉም ተቃዉሞ መደገፍ እንዳለበት አጥንክረው አሳስበዋል።

“ጥያቄ የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ ነው” ያሉት ዶር ብርሃኑ፣ “ አሁን ያለውን ስሪት፣ ማንንም ከማንም ቢታ ለማስነሳት የሚያስቸል ስሪት ነው ያለው። መሬት የመነግስት ነው ስለሚሉ በፈለጉ ጊዜ ምንንም ሊያስነሱ ይችላሉ ሲሉ ችግሩ ከመሬት ባለበትነት ጋር እንደሆን አስረድተዋል።

በሶስተኛ ደረጃ ዶር ብርሃኑ ሌላውም ማህበረሰብ ሙሉ ለሙሉ ልባችን ሰጥተን ለምን የኦሮሞዎችን እንቅስቃሴ መደገፍ እንዳልተቻለ ሲያስረዱ፣ “ችግሩ የማንነት ፖለቲካ የፈጠረብን ስሜት አለ” በማለት ነበር።
የግላቸው እንጂ የደርጅታቸው አቋም እንዳለሆነ የገለጹት ዶር ብርሃኑ “ዘላቂ የመረጋጋት እና እዉነተኛ ዲሞክራሲ ከመፍጠር አኳያ የማንነት ፖለቲካ አይጠቅመን ብቻ ሳይሆን በዜግነት ላይ ወደ ተመሰረት ፖለቲካ ነው ዘላቂ መረጋጋት የሚሰጠን ብዬ ነው የማምነው” ነበር ያሉት። “ በማንነት ፖለቲካ ላይ ተመሰርቶ የተረጋጋ አገር መፍጠር አይቻልም ብዬ አማናለሁ።የወደፊቷ ኢትዮጵያን ስናስብ ከዚህ ከማንነት ፖለቲካ እንዴት እንደምንወጣ ማሰብ አለብን” ሲሉም አክለዋል።

“ይሄ ስንል ግን የማንነት ፖለቲካ ለምን እንደተፌጥረ መረዳት አለብን” ያሉት ዶር ብርሃኑ አሁን ያለዉን የማንነት ፖለቲክ እንዲሁ እንዳልመጣ በመረዳት በጊዜያዊነት accommodate በማድረግ በሂደት ማሻሻል እንደሚገባም ለማሳየት ሞክረዋል። “የማንነት ፖለቲካን ከዚህ በፊት የነበረው ችግር ያመጣው በመሆኑ ፣ በማንነት ፖለቲካ ዉስጥ ያለውን ማህበርሰብ እንዴት ነው የምንቀይረው ካለን የሽግግር ስትራቴጂ ያስፈልገናል” ብለዋል ዶር ብርሃኑ።

ስለኦሮሞዎች እንቅስቃሴ ዶር ብርሃኑ ሲትነትንኑ ከአክራሪነት የጸዳ እንደሆነ፣ መገንጠል የሚለው ጥያቄ እዚህ ትግል ዉጥ እንደሌለ፣ ወያኔዎች እየተነኩስትም፣ የሌሎችን ብሄር ሰዎች attack ለማድረግ ሙከራ እንዳልተደረገና የኦሮሞ ቡድኖች ሌላው ኢትዮጵያ እንዲቀላቀላቸው ለመጀመርያ ጊዜ ጥሪ ማቅረባቸው በመጥቀስ ነበር በጎነቱን አጉልተው ያሳዩት።

በአንጻሩም “የዚያኑ ያክል ግን፣ በኦሮሚያ የሚደረገው ትግል ደግፎ ፣ ሌላው አካባቢ ያለው ባለመነሳቱ የፈጠረው ችግር አለ” ሲሉም ሌላ ኢፌክት በተቃራኒው እንዳለ ገልጸዋል።

ከኦሮሞ የፖለቲካ ሃይሎች ጋር በጋራ ለመንቀሳቀስና ፣ የማንነት ፖለቲካ ትራዚሽናል በመሆኑ፣ አሁን ትግሉ ለማቀናጀት፣ በተግባር የተጀመሩ ስራዎች በቶሎ መጀምር እንዳለባቸው የገለጹት ዶር ብርሃኑ “የአክራሪ ዱላ ተፈርቶ ትግል አይቆምም፤ የያዝነው የአገር ጉዳይ ነው” ነበር ያሉት። “ሰዎችን ማስጮህ ቀላል ነው። ማህበረሰብ አሰባስቦ ዉጤት ማምጣትት ከባድ ነገር ነው” ያሉት ዶር ብርሃኑ ከኦሮሞ ሞደሬት ሃይሎች ጋር በመሆን፣ እዉነተኛ ዴሞክራሲ የሰፈነባት አገር ለመገንባት ፍላጎት አላቸው ብለው ከሚያምኗቸው ጋር ዉይይቶች መጀመሩን ለተሰብሳቢው ገልጸዋል።

The post ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የኦሮሞዎችን ተቃውሞ በተመለከተ የተናገሩት 4 ወሳኝ ነጥቦች appeared first on Zehabesha Amharic.

የወቅቱ አንገብጋቢ ጥያቄ –ከደጀኔ አያኖ

$
0
0

ከደጀኔ አያኖ

Ethiopiaመቼ ነው በሐገራችን ውስጥ እረሃብ የሚጠፋው? ሰርተን፤ በልተን፤ ጠግበን የምንኖረው?

መቼ ነው በተማርነው መሰረት ያለዘመድ ሥራ የምናገኘው?

መቼ ነው ዘረኝነት የሚጠፋው? እኩልነት የሚሰፍነው?

መቼ ነው ዝርፊያው፤ ሙስናውና ብዝበዛው የሚቆመው?

መቼ ነው የሐገሪቷ ሀብት ወደ ውጭ ሀገር የሚሰረቀው? ገንዘቧ የሚራቆተው? የመግዛት አቅሟ የደቀቀው?

መቼ ነው በሐገራችን ኮርተን መኖር የምንችለው?

መቼ ነው በሐገራችን ውስጥ እንደልባችን ሃሳባችንን መግለፅ (በአፍ፤ በፅሁፍ፡ በራዲዮ፤ በቲቪ) የምንችለው? በተነፈስን ጊዜ ሁሉ ግራና ቀኝ የማናየው?

መቼ ነው በሐገራችን ዲሞክራሲን ዕውን የምናደርገው? በነፃ የመወዳደራችን መብት የሚከበረው? በፈልግንበት የፖለቲካ ድርጅት ሥር ለመሥራት የምንችለው? የፈልግነውን ተወዳዳሪ መምረጥ የምንችለው?

መቼ ነው “አምስት ለአንድ” ተደራጅተህ እኔን ብቻ ምረጠኝ የሚለውን የዲሞክራሲ ባላንጣ በፈቃዳችን መገርሰስ የምንችለው? መቼ ነው ድምፃችን በዲሞክራሲ ሕግ እንደ መራጭ ሕዝብ የሚሰማው?

መቼ ነው በሐገራችን ውስጥ በሰላም የምንኖረው? ያለፍርሃት ወጥተን ያለፍርሃት ተመልሰን ወደ ቤታችን የምንገባው?

መቼ ነው በሐገራችን ውስጥ የሕግ የበላይነት የሚከበረው/የሚሰፍነው? መቼ ነው ሕዝብ ያፀደቀው ሕገ መንግሥት የሐገሪቱን ሕዝብ መብት የሚጠብቀው?

እስከመቼ ነው ተምረን እንዳልተማረ፤ የአምባገነኖች ቅጥር በመሆን፤ በዪና አስበዪ የምንሆን? የአምባገነኖች ፖሊሲ አቀንቃኞች፤ ጠበቆች፤ ዳኞች፤ አስተዳዳሪዎችና ወታደሮች የምንሆን?

መቼ ነው ልጆቻችን እናት ኃገራቸውን ለቀው፤ ሞትን መርጠው፤ ወደማያውቁት ህገር መሰደድ የሚያቆሙት? መቼ ነው እንደአያቶቻቸው በኩራት ኃገራቸው/ቀያቸው ውስጥ በኩራት የሚኖሩት? እንደልባቸው ወጥተው እንደልባቸው የሚገቡት?

መቼ? መቼ? መቼ? መቼ? መቼ? መቼ? መቼ? መቼ ነው።

የፖለቲካ እንካ ሰላምታ ያብቃ

ሰሞኑን፤ የአ/አባባን ማስተር ፕላንን በመቃወም በኦሮምያ አካባቢ የተጀመረውን የሕዝብ አመፅና እንቅስቃሴ እንደምክንያት በመጠቀም፤ ብዙ የተቃዋሚ ድርጅቶች እርሰ በርሳቸው መነጋገር መጀመራቸው በጣም የሚያስደስት ነው። ሁላችሁም በአንአድነት፤ ለዲሞክራሲ፤ ለፍትህ፤ ለፍቅርና ለብልፅግና ለመሥራት መነጋግርችሁ ታላቅ ጅማሬ ነው። እግዚአብሔር ይርዳችሁ።

እንግዲህ ከሃምሳ አመት በላይ የተካሄደው “የፖለቲካ እንካ ሰለምታ” ይቁም። ዶ/ር በያን አሶባ በቅርቡ በአዲስ ድምፅ እሬድዮ “ሁሉም የተቃዋሚ ድረጅቶች የጋራ ፕላትፎርምና ስምምነት አድረገን ዲሞክራሲያዊ ትግል ማካሄድ አለብን። …70% የሚሆነው ኢትዮጵያዊ እድሜው በሰላሳ ዓመት ቤት ነው። … የኛ ትውልድ አሁን ይሄን ትብብር ካላደረገና የዲሞክራሲ ትግል ካላካሄደ ጊዜው ያልፍበታል … በጥድፍፊያ እስከዛሬ ያልሰራንውን ሰርተን ለመጪው ትውልድ የማስረከብ ግዴታ አለብን …” ብለዋል። እንደዚህ አይነት የሚያረካ ንግግር ከተቃዋሚዎች አፍ መስማት ትልቅ ነገር ነው። ዛሬ ነገ ሳንል አንድነታችንን እናጠንክር።

እስካሁን የነበረው አካሄዳችን በጣም የሚያስዝን ነበር። ትላንትና በዳይፐር ተጠቅልልለው በቅኝ አገዛዝ ስርዓት ይድሁ የነበሩት የአፍሪካ አገሮች እንኳን፣ እኛ “የፖለቲካ እንካ ሰላምታ” ቁጭ ብለን ስንለዋወጥ፣ በአጭር ግዜያቶች ጥለውን በርረዋል። እኛ ከቅኝ ግዛት እንዲላቀቁ የረዳናቸው ብዙ ሃገሮች ዲሞክራሲን ሲገነቡ እኛ ወደኋላ ተመልሰን በራሳችን ልጆች ተገዚዎች ሆነናል። እኛ ለመሰረትነው የአፍሪካ እግር ኳስ ድርጅት፤ ቋሚ ተመልካቾች ሆነናል። አያችሁ፤ ከአያቶቻችን እንሻላለን እንላለን። እነሱ ግን ከና ከድሮው “የተናቀ ይስረግዛል” ብለው ጨርሰውታል።

አያቶቻችን ባቆዩልን የሺህ ዓመታት ነፃነት ውስጥ፤ እንኳንስ የቴክኖሎጂ እድገት ልናመጣ ይቅርና ጠግበን ለማደርም አልቻልንም። በየሰላሳና በየሃምሳ ዓመታቶች ሕዝባችን በከፋ የረሃብ ሰቆቃ ውስጥ በተደጋጋሚ እየተዘፈቀ የዓለም ለማኞች ሆነን ቀርተናል።

በእንደዚህ አይነት ጉዞዋችን፡ የጎንደር፤ የአክሱምና የላሊበላ ታሪካችን ለዓለም ሕዝቦች “የልብ ወለድ ታሪክ” ሊመስላቸው የሚችልበት ወቅት እሩቅ አይመስልም። ለዚህ ሁሉ ድክመት (ክሽፈት እንዳሉት ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም) በኔ አስተሳሰብ፤ ከአፄ ኃ/ሥላሴ ጀምሮ የነበረው ትውልድ ነው። ከዚያ በፊት የነበረውን ትውልድ ዘመናዊ መንግሥትና ዘመናዊ የትምህርት ስርዓት ካለመኖር ጋር አያይዘን ከተጠያቂነቱ ብናላቅቀው ይሻል የመስለኛል።

እንግዲህ፤ በአፄ ኃ/ሥላሴ ጊዜ የነበረው ትውልድ፤ በየተማሪ ቤቶች ቅጥር ግቢ ውስጥ፤ በቀ ኃ/ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እየተመራ የነደፈውን አብዮታዊ ትግል አጫጭሶ የገዢውን መደብ ለመገርሰስና ተራማጅ የሕዝብ መንግሥት ለመገንባት ታላቅ መስዋእትነት ከፍሏል።

ይሄው አብዮቱን በቀደምተኝነት በዩኒቨርስቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ ይመራ የነበረው ተማሪ፤ ግቢውን ለቆ ከወጣ በኋላ ግማሹ በከተማ ሆኖ፤ ሌላው ደግሞ ወደሜዳ ወርዶ የአብዮቱን አቅጣጫ በተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ሥር እየቀየሰ ታግሏል።

አሁን ኢትዮጵያና ኤርትራ ወስጥ ያሉት የገዢ መደቦችም በዚያን ወቅት ተረግዘው ጭንጋፍ የሆኑ የኢትዮጵያ ተማሪዎች አብዮት ናቸው። በደርግ ጊዜም የሰፊውን ሕዝብ አብዮት ያኮላሹት ከነዚህ ጭንጋፎች ያልተሻሉ ዩኒቨርስቲው የወለዳቸው የአብዮቱ የእንግዴ ልጆች ናቸው። ከ40 ዓመታት በበለጠ የፖለቲካ እንካ ሰላምታ ተፋጥጠው በኤርትራና በኢትዮጵያ ውስጥ ላሉት ጭንጋፎች፡ የዕድሜ ማራዘምያ ዋስትና በሚያስገርም መንገድ እየሰጡ ያሉትም አሁንም ከዚያው ከቀ.ኃ.ሥ ዩኒቨርስቲ የበቀሉት ተራማጅ ተማሪዎች ናቸው። ይሄ “የአፄ ኃ/ሥላሴ እርግማን ይሆን?” ያሰኛል።

ስለዚህ፤ እርግማንም ከሆነ ጠበል እንረጭና፤ ለሁሉም የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት፤ ፍትህ፤ መብትና ብልፅግና፤ ነገ ዛሬ ሳንል፤ በጋራና በትብብር እንስራ።

ከአብዮቱ አበይት ጥያቄዎች ሁለቱን ለመጥቀስ

መሬት ላራሹ አማሮችን በተመለከተ

በወቅቱ የነበረው ታላቁ ጥያቄ ከመሬት አስተዳደር ጋር የተቆራኘ ነበር። መሬት ለአራሹ ይሰጥ። የመሬቱ ባለቤት ጭሰኛ ሆኖ ሳለ፤ በላዩ ላይ ተመርቶ ለመጣው ሰው ገባሪ ሆኖ ከሚያመርተው ሰብል አንድ ሶስተኛውን ይገብራል።

ለመሆኑ ይህ የመሬት አያያዝ እንዴት እንደነበርና በምን አኳኋን እንደተያዘ በአጭሩ ብንመለከት፡

1ኛ  በእርስት መልክ የተያዘ መሬት። ይህ መሬት ከአባት ወይንም ከእናት የተወረሰ፤ ሲወርድ ሲዋረድ በውልደት የተገኘ መሬት ነው።

2ኛ  በጉልት የተያዘ መሬት። ይህ መሬት የመንግሥት ሆኖ አራሹ ግብር እየገበረ የሚተዳደርበት መሬት ነው።

3ኛ  የማደሪያ መሬት። ይህ መሬት መንግሥት በድሮ ጊዜ ለሰራተኞቹ (ለምሳሌ ወታደሮች) እንደ ደምዎዝ የመደበላቸው መሬት ነበር።

4ኛ  ከማደሪያ መሬት የሚመሳሰለው ሌላው የመሬት አያያዝ ደግሞ የርሻ መሬት በመመራት ነበር። በአፄ ኃ/ሥላሴ አገዛዝ ጊዜ ማንኛውም አርሳለሁኝ የሚል ኢትዮጵያዊ ግማሽ ጋሻ የመንግሥት መሬት መመራት ይችል ነበር። የመንግሥት ሰራተኛ ከሆነ ደግሞ ሙሉ ጋሻ መሬት መመራት ይችል ነበር። የመንግሥት መሬት ማለት በመንግሥት ቁጥጥር ስር ያለና በግለሰብ እጅ ያልገባ መሬት ማለት ነው። ነገር ግን ይህንን ሕጋዊ መንገድ በመጠለል ብዙ እራሳቸው አራሽ ያልሆኑ ግለሰቦች ተጠቃሚ ሆነዋል። በብዙ የኢትዮጵያ ክልልሎች ውስጥ እርቆ የሚኖረው ገበሬም፤ በቋንቋም ሆነ በመገናኛ እጥረቶች ምክንያት ሰለመሬት ግብርና አዋጅ ጠንቅቆ ሰለማያወቅ ለመሬት ንጥቂያው በሰፊው ተጋልጧል። አዲስ መጪው ሰው መሬቱ ግብር እንዳልተከፈለበት ካረጋገጠ በኋላ በቀያሽ አስለክቶ ለመሬቱ ግብር በመክፈል፤ በመንግሥት አዋጁ መሰረት ይህን ግማሽ ወይንም ሙሉ ጋሻ መሬት ሕጋዊ ያደርጋል ማለት ነው። በዚህም እረገድ አማራውም ትግሬውም (በትንሹ የሌሎች ብሄረሰብ ተወላጆችም) ተጠቃሚዎች ሆነዋል።

5ኛ  የግል መሬት። ይህ መሬት ለገዢው መደብ እንደሹመቱና እንደቅርበቱ ከመንግሥት የተሰጠ መሬት ነው። አገር አቅንተዋል የተባሉትንና፤ ለሐገር ነፃነት ጦር ግንባር የዘመቱትን ይጨምራል። ከዚህም ጨምሮ በገዢው መደብ መሪዎች በዝርፊያ መልክ በአስተዳዳሪነት ሹመት (አገረ ገዢዎች) በየጠቅላይ ግዛቱ የተላኩ የአፄ ኃ/ሥላሴ መሳፍንቶችና ባላባቶች በራሳቸውና በጭፍሮቻቸው ሥም ያጠቃለሉት በሺህ የሚቆጠር ጋሻ መሬት ነው። ለምሳሌ በጨርጨር አካባቢ በአንድ ባለስልጣን ብቻ ከ 900,000 ሄክታር በላይ ተይዞ ነበር (SILESHI WOLDETSADIK, Land Ownership In Hararge Province  Imperial Ethiopian College of Agricultural and Mechanical Arts Experiment Station Bulletin No. 47, 1966). ከዚህ ከተያዘው መሬት ውስጥም በመንግሥት ለቀረጥ የተመዘገበው 1.1% ወይንም 9,900 ሄክታር ብቻ ነበር። በጣም ብዙ መሬት እንደያዙ በስፋት የሚነገርላቸው ራስ መስፍን ስለሺ ነበሩ. እነዚህን የመሳሰሉ ትልቅ ባለሃብቶች፤ በትራክተር ማረስ ሲጀምሩ ደግሞ መሬቱ ላይ ሰፍሮ የነበረውን ጭሰኛ እያባረሩ መጡ። በአካባቢው ያለውን የገበሬ መሬትም በገንዘብ ሃይል እየገዙ ሰበሰቡ።

6ኛ መንግሥት ለቤተክርስትያኖች ለመተዳደሪያ የሰጠው መሬት

7ኛ  መንግሥት በሰፈራ የሰጠው መሬት። ይህ መሬት በፊት ሰፋሪ ያልነበረበት የመንግሥት መሬት ነው። ይህ ገበሬዎችን ከተጨናነቀ ቦታ በማስነሳት ወደ ሌላ የመንግሥት መሬት የማስፈር ፕሮግራም የተጀመረው 1958 ዓ.ም ጀምሮ ነው። ከ1974 አብዮት በኋላ ደርግ ከ600,000 የሚበልጡ ሰዎችን በተለያዩ ቦታዎች አስፍሮ ነበር። በ1985 ዓ.ም ባወጣውም የመደርተኛነት (Villagization) ፕሮግራም፤ እስከ 1986 ዓ.ም 4.6ሚ የሚሆኑ ሰዎች፤ በ4500 መንደሮች፤ በሸዋ፣ በአርሲና በሐረርጌ አስፍሯል። በዚህ ፕሮግራም በመቀጠልም ፤ 1989 ዓ.ም ከማለቁ በፊት እስከ 13ሚ ሕዝቦች በመንደርተኝነት አስፍሯል(Thomas P. Ofcansky and LaVerle Berry, editors Library of Congress Federal Research Division (1991)።

የመሬት ይዞታ ተጠቃሚዎች ገዢው መደብና ከገዢው መደብ ጋር የተሳሰሩት ናቸው። እነዚህም መውሳፍንቶች፤ አገረገዢዎች፤ ባላባቶች ሹሞችና ወታደሮች ናቸው። አማሮችን፤ ትግሬዎችንና ኦሮሞዎችን በብዛት ያካትታል።

የሆነ ሆኖ፤ ከመሬት ላራሹ ጥያቄ ጋር ተያይዞ፤ የአማራው ሥም ብቻ ተገንጥሎ የሚነሳበት ምክንያት፦

1ኛ የትግሬውም ሆነ ከሌላ ብሄር የመጣው ባለመሬት ሥም ከአማራ ሥም ጋር ስለሚመሳሰል።

2ኛ ትግሬውም ሆነ ከሌላ ብሄር የመጣው ባለመሬት የአማርኛ ቋንቋን በየሄዱበት (በየሰፈሩበት) ስለሚናገሩ፤ በአካባቢው ነውሪ እንደ አማራ ስለሚቆጠሩ ነው።

በብዙ የሚቆጠሩ የትግራይና (ኤርትራንም ጨምሮ) የኦሮሞ ተወላጆች መሬትና ጭሰኞች ነበራቸው። በወረዳና አውራጃ አስተዳድሪነትም የስርዓቱ አካል በመሆን የመሬት ንጥቂያ ተጠቃሚዎች ሆነዋል።

በመጀምሪያ ደረጃ ግን በመሬት አስተዳደር ችግር ወይም “በመሬት ላራሹ ጥያቄ” በጣም የተኮነነው የአማራው ብሔር ብቻ ነበር።ተራው አማራ፣ ግማሽና አንድ ጋሻ መሬት ተመርቶ ከራሱ ብሔር ውጭ በሌላ ክልል የሚኖረው፣ ምን ያህል መሬት ይዞ እንደነበረ የወጣ ቆጠራ (ስታትስቲክስ) የለም።

እንግዲህ ለምን አማራ ብቻ እንደጠላት እንደሚታይ አይታወቅም። ይህንን የመሬት ላራሹ ጥያቄ ከግብ ለማድረስ ትግሉን በቀደምትነት ከጀመሩት የኢትዮጵያ ታጋዮች አንጋፋዎቹ የአማራ ወጣቶች ለመሆናቸው አያጠያይቅም። በአ/አበባ፣ በጎንደር፣ በደ/ማርቆስ፣ በባህርዳር፤ በደሴና በመሳሰሉት አደባባዮች የወደቁት የኢትዮጵያ/የአማራ አርበኞች ቁጥር ስፍር አልነበራቸውም። ታሪክም አይከዳውም።

መሬት ላራሹ ከታወጀበት ከ1975 ዓ.ም ጀምሮ በሌላው ክልል ይኖር የነበረው የአማራ ሕዝብ፣ (በተለይም በገጠሩ) ሙሉ በሙሉ ለመፈናቀሉ ጥርጥር የለውም። የተፈናቀለው የአማራ ገበሬ በኢትዮጵያዊነቱ በሕግ የተመራውንና (ማለትም በፊት ገበሬ ያልሰፈረበት ቦታ የተመራውን) መንግሥት ከሌላ ቦታ አምጥቶ በመንግሥት ባዶ መሬት ላይ ያሰፈረውን አማራ ይጨምራል። የወያኔ ሕገ መንግስት ነሐሴ 15 ቀን 1987 (21 August 1995) ከፀደቀ በኋላ ከሚኖሩበት ኅገር የተፈናቀሉትና የተጨፈጨፉት አማራዎች ቁጥር በትንሹ ከሚሊዮን ይበልጣል።

አዲስ አበባ ነሐሴ 15 ቀን 1987 (21 August 1995) በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ የወጣው ወያኔ ያፀደቀው ሕገመንግሥት እንዲህ ይላል።

“አንቀጽ 32 – የመዘዋወር መብት

  1. ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወይም በሕጋዊ መንገድ ሀገሪቱ ውስጥ የሚገኝ የውጭ ዜጋ በመረጠው የሀገሪቱ አካባቢ የመዘዋወርና የመኖሪያ ቦታ የመመስረት እንዲሁም በፈለገው ጊዜ ከሀገር የመውጣት ነፃነት አለው።”

“አንቀጽ 40 – የንብረት ደንብ

  1. የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች መሬት በነፃ የማግኝትና ከመሬታቸው ያለመነቀል መብታቸው የተከበረ ነው። አፈፃፀሙን በተመለከተ ዝርዝር ሕግ ይወጣል።”

“አንቀጽ 9 – የሕገመንግሥት የበላይነት

  1. ማንኛውም ዜጋ፤ የመንሥት አካላት፤ የፖለቲካ ድርጅቶች፤ ሌሎች ማህበራት እንዲሁም ባለሥልጣኖቻቸው፤ ሕገ መንግሥቱን የማክበርና ለሕገ መንግሥቱ ተገዢ የመሆን ኃላፊነት አለባቸው።”

እንግዲህ በሌላ የብሔር ክልል (ኢትዮጵያ) ውስጥ፤ በሕገ መንግሥቱ አዋጅ በአንቀጽ 32 ንዑስ 1፤ የመዘዋወርና የመኖር መብቱ የተረጋገጠለት አማራ ሲባረር…

በሕገ መንግሥቱ አዋጅ በአንቀጽ 40 ንዑስ 4፤ የንብረት ደንብ መሰረት፤ ከመንግሥት ካገኘው መሬት አማራ ብቻ የሆነው ሲፈናቀል…

የመንግሥትም አካላትም ሆነ ወይንም ወንጀለኞቹ፤ ሕገ መንግስቱን ተፃራሪ በመሆን የአማራን ሕዝብ ከሚኖርበት ቤቱ በማባረራቸውና በማፈናቀላቸው፤ በሕገ መንግሥቱ አዋጅ አንቀጽ 9 ንዑስ 2 መሰረት ሃላፊነት አለባቸው።

መሬት ላራሹ ከታወጀስ በኋላ በሌላው ክልል ውስጥ (አሁን በከተማዎች ውስጥ ማለት ነው) ስንት አማራዎች ይኖራሉ? እርሻ ውስጥ አሁን እንደሌሉበት የታወቀ ነው (ካሉም ቁጥር ውስጥ የማይገቡ ናቸው)። የሚተዳደሩትስ በምን ዘርፍ ነው? በንግድና በመንግሥት ሥራ ተሰማርተው መሆን አለበት። ኢትዮጵያዊነት እንደከሰል እየከሰመ በመጣበት (የወያኔ መንግሥት)፤ በአሁኑ ወቅት ደግሞ በሌላ ክልሎች ውስጥ አማራ ሆኖ የመንግሥት ሥራ ማግኘት ለዘበት ይመስላል። ስለዚህ በብዛት በሌላ የኢትዮጵያ ክልል ውስጥ የሚኖሩት አማሮች፤ አያትና ቅድም አይቶቻቸው ተወልደው ባደጉበት ክልል እንደሌላ ዜጋ ወደ ዳር ተገለው በየከተማው ሥር ተሸጉጠው ተቀምጠዋል።

ታድያ መሬት ላራሹ ከታወጀ ከ40 ዓመት በላይ ሆኗል። አሁንም ቢሆን እነዚህ እንደ ባዕድ ተቆጥረው መብታቸው የተገፈፈው ኢትዮጵያኖች በአማራ ሥም ግፍ እየተሰራባቸው ነው። ለዚሁም ተጠያቂው ዘረኛው የወያኔ መንግሥት ነው። በብሔር እልቂትና (genocide) አገርን በማጥፋት ወንጀል ተጠያቂ ነው። ይህ እልቂት አሁንም በቅርብ በቤንሻንጉል ክልል ውስጥ አገርሽቶበት ብዙ ሰዎች አልቀዋል።

 

የብሔሮች ጥያቄ፤ አማሮችን በተመለከተ

በተመሳሳይ ሁኔታ ሌላ የተነሳው የተማሪዎች ጥያቄ ደግሞ “የብሔር ብሔረሰቦች ጥያቄ” ነበር። የዚያን ጊዜ፤ ይህን ጥያቄ ለመፍታት በጋራ ቀደምትነት የቆመው ተማሪ ዘረኛነትን የማያወቅ፤ ለቅንና ለእኩልነት የቆመ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙት ብሔር ብሔረሰቦች ነፃነት ሕይወቱን ለመሰዋት የተዘጋጀ ነበረ።

እንደሚታወቀው ሁሉ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ፤ የብሔርን ጥያቄ በፅሁፍ አቅርቦ በቀ. ኃ/ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ወስጥ ያነበበና በዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች መፅሔት ላይ በ1969 ያሳተመው ዋለልኝ መኮንን ነበር። ብዙዎቹ ተማሪዎች ከአማራ ከትግሬና (ኤርትራውያንን ጨምሮ) ከኦሮሞ አካባቢ የመጡ ነበሩ። ከነዚህ ለሰፊው ሕዝብ ሕይወታቸውን ለማሳለፍ ከአብዮቱ ግንባር ከተሰለፉት ተማሪዎች መካከል ቤተሰቦቻቸው በገዢው መደብ ውስጥ ትላልቅ ስልጣን ያላቸውም ነበሩ። እንግዲህ እነዚህ የኦሮምያ፤ የአማራ፤ የትግራይ፤ ወዘተ ተማሪዎች ነበሩ በግንባር ቀደምትነት የኢትዮጵያ ጭቁን ሕዝቦችን ከጭቆና ቀንበር ለማላቀቅ፤ ለሰብአዊ መብቶች፤ ለብሔር ብሔረሰቦች እኩልነትና ነፃነት ደመ ከልብ ሆነው የቀሩት። ዘር ያልነበራቸው፤ ለዘር እኩልነት የቆሙ፤ በየአደባባዩ ለሰፊው ሕዝብ መስዋዕትነት የከፈሉ።

ይህንን ለመጥቀስ የፈለኩት ባሁኑ ግዜ በአንዳንድ አካባቢ፤ የዘር መርዘኛ ፕሮፓጋንዳ እየረጩ፤ ገና ዛሬ ከዕንቅልፋቸው ብንን ብለው ስለ ብሔር ብሔረሰቦች ጥያቄ “ሊቆች” ሆነው (ይህን ሁሉ ችግር የፈጠረው አማራው እንደሆነ በማስመሰል) ጠበብተኝነትን ሲያራምዱ ስላየሁ ነው። እነዚያ በዩኒቨርስቲውና በየከፍተኛው ት/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የበቀሉት፤ ዘር ያልነበራቸው፤ የኢትዮጵያ ተማሪ አርበኞች ስም ሲጎድፍ ሳይ ደሜ ይፈላል። ከነዚህ “ልብ ወለድ የፖለቲካ ደራሲዎች” ውስጥ አንዳንዶቹ ደግሞ የአርበኛውን የኢትዮጵያ ተማሪ ታሪክ እንኳን ያላነበቡ፤ የፖለቲካ ጥልቀት የሌላቸው፤ ለራሳቸውም ይሁን ለሀገራቸው ክብር ብለው እውነተኛ ትግልን ያልቀመሱ “የብዕር ነብሮችና የዘረኞች ደወል” ብቻ ናቸው።

አንድ አማራ፤ አንድ ኦሮሞ ወይንም አንድ ትግሬ የዛሬ ሀምሳ ዓመት ሰደበኝ ወይንም አንቋሸሸኝ ብሎ አንድ ብሔረሰብን በጠቅላላ መወንጀል ትልቅ ሥህተት ነው። በየብሔረሰቡ ስንት መረን የወጣ ባለጌ ሰው አለ? በኢትዮጵያ ውስጥ ከባለሞያዎች እኩል የተሰደበ ሰው ነበር እንዴ? በየብሔረሰቡ ሸክላ ሰሪው “ፉጋ”፤ ብረት ሰሪው “ቀጥቃጭ”፤ እንጨት ሰሪው “አናጢ” እየተባለ ይሰደብ አልነበረም? ይሄ ለምን መጣ? ከትምህርት ማነስ ነው። ስንቱ ነው ኢዚህ ሰሜን አሜሪካን እንኳን መጥቶ አፍሪካ አሜሪካዎችን “እነዚህ ጥቁሮች” የሚለው (ይህን ከፍተኛ ትምህርት ያለው ሰው ሲናገር ሰምቻለሁ) አንዳንዱ ደግሞ “እነዚህ ባሪያዎች” ይላል። አዳንድ ጊዜ ከቀለም ትምህርት ደግሞ ኮመንሴንስ ያለው ሰው ይሻላል። አንዳንዱ ሲናገር ጭቃ ነው። እንደዚህ አይነቱን ጭቃ ከየአህጉሩ ለቅሞ ማውጣት አይቻልም። ዘወትር የሚወልዳቸው ቤት አይጠፋምና።

ስለዚህ፤ እኛ ከተማርን፡ ሕዝባችንን ካስተማርን (መጥፎ መጥፎውን ሳይሆን ጥሩ ጥሩውን ነገር) በፊት የነበረው መጥፎ ቋንቋ በጥሩ ቋንቋ ይቀየራል። ዛሬ አንድ ዘረኛ “ኒገር” ብሎ ቢሰድበኝ፤ አለቃዬ ደግሞ በቀለሜ የተነሳ ተፅዕኖ ቢያደርግብኝ፤ መብቴን ለማስከበር በህግ እጠይቀዋለሁኝ እንጂ የነጭን ዘር በጠቅላላ አልኮንንም። በጭፍንና በደምፍላት መራመድ አደገኛ ነው።

ስለዚህ ሐገራችን ውስጥም ይሄንንው የሕዝብ ህልውና የሚያስከብር የሕግ የበላይነት ያስፈልጋል። የሕግ የበላይነት እንዲነግስ በትብብር ከሰራን፤ መከባበር፤ መፈቃቀር፤ መረዳዳትና አንድነት ሳይወዱ በግድ ይዛመዱናል። የዘረኝነት ሰንሰለት ይሰበራል።ሰሞኑን በአዲስ ድምፅ ራዲዮ ዶ/ር አረጋዊ “ላለፈው ቤት ክረምት አይሰራለትም” ብለዋል። ያለፈውን፤ ጊዜ የጣለውን ስርዕት እያነሳን ወርቃማ ጊዜያችንን በከንቱ ከማጥፋት፤ እስቲ መጀመሪያ የየራሳችንን አቋም በደምብ ገምግመን ትልቋን ኢትዮጵያ ለመገንባት አብረን እንነሳ። ትብብራችንን ዛሬ እንጀምር። ማንኛውም ቅራኔ በንግግርና በመደማመጥ ይፈታል።

 

የገዢው መደብች ከብሔር ጋር ያላቸው አሰላለፍ ምን የመስላል?

የባላባቱ የገዢ መደብ

ኢትጵያን በዚያ ወቅት የሚያስተዳድረው የገዢ መደብ፤ በብዛት የተውጣጣው ከኦሮሞ፤ ከአማራና ከትግሬ ብሔረሰቦች ነበር። የዚህ የገዢ መደብ ያገዛዝ ስርዓት ባላባታዊ (ፊውዳላዊ) ነበር። ይህ ባላባቲዊ አገዛዝ፤ ለብዙ ዓመታት የሁሉም ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ብሔረሰቦች የአገዛዝ ስርዓት ሆኖ ቆይቷል። ወላሞ በወላሞ ባላባቶች፤ ከፋ በከፋ ባላባቶች፤ ኦሮሞ በኦሮሞ ባላባቶች፤ ከምባታ በከምባታ ባላባቶች፤ አማራ በአማራ ባላባቶች፤ ትግሬም በትግሬ ባላባቶች ተገዝተዋል። ወ.ዘ.ተ።

በባላባታዊ አገዛዝ ሥር የሁሉም ብሔረሰብ ጎሳዎች ተገዢዎች ነበሩ። በዚህ አገዛዝ መሰረት፤ አነስተኛ ሕዝብና ግዛት ያላቸው ባላባቶች፤ መብታቸውንና ጥቅማቸውን ለማስከበር ሲሉ ለትላልቆቹ ባላባቶች ይገብራሉ (በገቢያቸው መጠን እንደቀረጥ ማለት ነው)። ትላልቆቹ ባላባቶች በተራቸው ደግሞ፤ ግዛታቸውን ለማስስፋፋትና ሃይላቸውን ለማጠናከር በጊዜው ላሉ ሃይለኛና ገናና ባላባት ይገብራሉ። ጊዜ ሲሳካላቸው ደግሞ እነሱም ያስገብራሉ።

በየብሔሩ ወስጥ ያለው ባላባትዊ ሽኩቻ በዚህ መልከ ገፅታው እንደ አይነት ባህሪ የነበረው ነበር። አንድ ብሔር ሌላውን ብሄር ሊያንበረክክ የቻለውም በሃይል ነበር። አማራውም፤ ኦሮሞውም፤ ክርስትያኑም፤ እስላሙም ይህንን የመሰለ ባህርይ አሳይቷል።

በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ አንድ ብሔረ ወጥ የሆነ የባላባት (የመሳፍንት) ሥርዓት ኢትዮጵያን መርቶ አያውቅም፤ ከሌላ በመቀላቀል እንጂ። አፄ ተዎድሮስ እንኳን ቢሆኑ፡ ምንም እንኳን የመሳፍንት ዘር ባይኖራቸውም (አላቸው የሚል ሰው ቢኖርም)፤ ጎንደርን፤ ትግሬን፤ ውሎንና ሸዋን በማስገበር ነው ኢትዮጵያን አንድነት ጠቅልልለው ለመግዛት የቻሉት።

በዚያን ወቅት ኢትዮጵያን ለመግዛት “ሃይልና ሃይማኖት” ትልቅ ሚና ተጫውተዋል። ይህንን ሃይል ለማግኘት ባላባቱ በጥቅም የመደጋገፍንና በጋብቻ የመተሳሰርን ዘዴዎች ለብዙ ዓመታት ተጫውቷል። ለዚህም የአፄ በዕደ ማርያም ሚስት የነበረችውን ንግሥት ዕሌኒንና (1450-1500) በየጁ መሳፍንቶች ግዜም (1670-1845; በነራስ ዐሊ፣ ራስ አሊጋዝ፣ ራስ ጉግሳ፤ ወዘተ) በጣም ጎልቶ የታየውን በጋብቻ የተገመደ ሀይል መጥቀስ ይረዳል። ንግሥት ዕሌኒ፤ ገራድ መሐመድ የተባለው የደዋሮ ገዢ ልጅ ነበረች። አፄ በዕደ ማርያም በ1470 ዓ.ም ሲሞቱ ልጆቻቸው (አፄ እስክንድር፤ ያዕቆብና ልብነ ድንግል) ለአቅመ አዳም ስላልደረሱ ንግሥት ዕሌኒ እስዋ እራሷ እንደራሴ በመሆን ለብዙ ዓመታት እንደንግሥት ገዝታለች። በዙርያው ካሉ የስላም ገዥዎች ጋር የቤተሰብ ግንኙነት ስለነበራት ሁለቱንም ክፍሎች በማስማማትና በማስተባበር ጠቅማለች።

ስለዚህ የገዢው መደብ (የባላባታዊ የአገዛዝ ስርዕት) ከራሱ ብሔርና ሀይማኖት ውጭ ይቅርና፤ በራሱ ብሔርና ሀይማኖት ውስጥ ካሉትም ባላባቶችና መሳፍንቶች ጋር፤ ጥቅሙን ለማስከበር በጋብቻ ተሳስሯል። ሰፊውን ሕዝብ ለብዙ አመታት በጭቆና የገዛው በየራሱ ብሔር ውስጥ ያለው ባላባት እንጂ ከሌላ ብሔር የመጣ ባላባት አይደለም። በጦርነት ቢሸነፍም ተሸናፊው ባላባት (በዚያው ክልል ያለው) ለአሸናፊው (ከሌላ ክልል ወይንም ከዚያው ክልል ለመጣው) ይገብር እንጂ ተራው ሕዝብ ግን ሁልጊዜ የሚገብረው ጊዜ ለሾመው ባላባት ነበር።

የደርግ የገዢ መደብ

በደርግም ጊዜ፣ የገዢው መደብ አማራ ነው እየተባለ (የተለያዩ የፖለቲካ ቡድኖች የፕሮፖጋንዳ ጨወታ ሆኖ ቆይቷል) ይወራ ነበር። እውነተኛው ሀቅ ግን ደርግ ዘር አልነበረውም። ቢኖረውም እንኳን አገሪቱን ይመሩ ከነበሩት ሃይሎች ውስጥ 60% የሚያክሉት የኦሮምያ ተወላጆች ነበሩ ይባላል (አንዳንዶቹ በእናት ወይ በአባት፣ እንደ ኮሎኔል መንግስቱ)። ይህ እንግዲህ በቁጥር ጥናት መረጃ (እስታትስቲክስ) የተረጋገጠ አይደለም ።

የሆነ ሆኖ፤ ቀደም ብሎ እንደተገለፀው፤ መሬት ተወርሷል። በሌላው የኢትዮጵያ ክልል የሚኖረው አማራ ተፈናቅሏል። ግማሹሁም ተቃጥሏል። ሌላውም ከየገደሉ ተወርውሮ ተሰባብሯል። በራሱም ሆነ በሌላ ክልሉ ውስጥ የሚኖረውም አማራ፡ የአብዮቱን መፈክር በልጆቹ ክንድ አስይዞ፤ የትግሉ ግንባር ቀደም በመሆን መስዋእት ከመክፈል በስተቀር ያገኘው ፋይዳ የለም። ታድያ የአማራ ሥም ከደርግ የገዢ መደብ ጋር ምን አገናኘው?

ኢሕአፓና መኢሶን ከአማራ የገዢ መደብ ጋር ነው እንዴ የታገሉት? መኢሶን (በኃይሌ ፊዳ መሪነት) ያጠናከረውና የገነባው የደርግን እንጂ የአማራ የገዢ መደብን ነበር?  አሁንም ይሄው መከረኛው የአማራ ሥም፣ በልብ ወለድ ፖለቲከኞች፣ ከአፈር ጋር እንደታሸ ነው። ስለዚህ የገዢው መደብ ከዚህ ብሔር ነው የመጣው ለማለት አይቻልም። ደርግ የተለየ እንክብካቤና ጥቅም ለአንድ ብሔር ብቻ ሲሰጥ አልታየምና። የአማራ ብሔር፤ እንደሌሎቹ የኢትዮጵያ ብሔሮች (እንዲያውም ከሌሎቹ በላይ) የተጨቆነ ነበር።

የወያኔ የገዢ መደብ

የወያኔ የገዢ መደብ ደግሞ ከሁሉም በግልፅ የተለየ ነው። የገዢው ቡድን መቶ ፕርሰንት ከትግራይ ብሔር ነው። በፓርላማ ውስጥ፤ ከዚህ የገዢ ቡድን ጎን የተቀመጡት የሌላ ብሔር ተወካዮች የገዢውን ቡድን በዓለም ዓቀፍ ሕብረተሰብ ፊት ኅጋዊ ለማስመሰል ብቻ የተቀመጡ ተዋናዮች ናቸው። ጠቅላላው የሀገሪቱ መመሪያዎችና ደንቦች ይህንን የገዢ መደብ በስልጣን ኮርቻ ላይ ለማቆየት የተነደፉ ናቸው። ከነዚህም በዋነኝነት የሚቀመጠው መመሪያ “ብሔር ብሔረሰቦችን በዘር ከፋፍሎ፤ እርስ በርስ እያናከሱ” የመግዛት ፖሊሲ ነው።

በገዢው የወያኔ መደብ ውስጥ ሥርዐቱን ተቆጣጥሮ ዓላማውን ለማራመድ የተሰማራው (የተቀጠረው ወይም በጥቅም ላይ ያለው) ሕዝብ ምን ያህል ነው? 10 ሺህ? 50 ሺህ? ወይም 100 ሺህ? (ይሄ ማለት እንግዲህ ከ6.1ሚ የትግራይ ሕዝቦች ውስጥ 0.16%፣ 0.41% ወይም 1.64% ማለት ነው)። እንግዲህ ወያኔ የአምባገነን ክንዱን በቀረው 99ሚ ሕዝብ ላይ ጭኖ በአፈሙዝ የሚመራው ከ1% ባነሱት የትግራይ ተወላጅ ወበዴዎችና ቅጥረኞች እንጂ በመላ የትግራይ ሕዝብ ድጋፍ አይደለም። ይህ በደንብ መታወቅ አለበት። አራት ነጥብ።

የገዢው መደብ በትግሬ ጠበብተኝነት (ዘረኛ) የሚመራ አምባገነናዊ መንግሥት ነው። ስለዚህ ሰፊው የትግራይ፣ የአማራም፣ የኦሮምያ፣ የሱማሌም፤ ወዘተ ሕዝብ ለመቶ ዓመታት እንደተጨቆነው ሁሉ፤ አሁንም የገዢው መደብ ጭዳ ሆኖ ቀርቷል። ለዚህ ነው ወያኔ የትግራይን ሕዝብ በጭራሽ አይወክልም የምለው።

የገዢው መደብ ወያኔ ግን በለመደው የዘረኝነት አንደበቱ የትግራይን ሕዝብ ከጎኑ ለማሰለፍ “እኔ ከወረድኩኝ አለቀልህ”፤ “ለዘለዓለም ተበዳይ ሆነህ ትቀራለህ”፤ “ይሄ የትግራይ ሕዝብ ፓርቲ ነው”፤ “በሜዳ ያመጣንውን ድል ከማንም አንጋራም፤ የትግራይ ሕዝብ ድል ነው” እያለ መሸንገሉን አላቆመም። ለትግራይ ሕዝብ ግን የወያኔ መንግሥት “ታላቅ የታሪክ ጠባሳ” ነው። በትግራይ ሕዝብ ሥም የሚነግድ፤ የትግራይ ሕዝብን ከሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር የሚያቃቅር፤ ኢትዮጵያ የምትባለውን ሀገር ለመገነጣጠል የጥላቻ መርዝ እየበጠበጠና እያሻማ የሚገኝ አደገኛ የገንዘብ ቅጥር ነፍሰ ገዳይ ነው።

ወያኔ ዘርን በዘር ላይ ለማስነሳት ያጧጧፈው ፕሮፓጋዳና የወለዳቸው ውጤቶች

በአማራ ላይ ጥላቻ መጀመሪያ የቀሰቀሰው ጣልያን ነው። “ከፋፍለህ ግዛው” የሚለውን የቅኝ ግዛት መርሆውን እውን ለማድረግ ከሰማይ ላይ ወረቀት እያበተነ “አማራ ጠላትህ ነው። አትተባበረው። አባርረው። ግደለው” እያለ በየከተማውና በየባላገሩ ይበትን ነበር። የተባበረውን ሁሉ ሾሟል። ከተሾሙት ውስጥም “ባንዳው” የመለስ ዜናዊ አባት ይገኙበታል።

ወያኔ በአማራ ላይ የተነጣጠረ የዘር ጥላቻ ፕሮፓጋንዳውን የጀመረው ገና ሜዳ በነበረበት ወቅት “አማራ የትግራይ ሕዝብ ጠላት ነው” እያለ እንደነበር አቶ ገ/መድህን አርዓአያ በማያወለውል ማስረጃ ገልፀውታል (ኢሳት ቲቪ)። ይህ እንግዲህ ከጣልያን የተወሰደ ግልባጭ ፕሮፓጋንዳ ነው።

ይህ የዘር ጥላቻ ፕሮፓጋንዳ የሚሰበከው ለትግራይና ለኦሮምያ ሕዝብ ነው። ወያኔ የትግራይ ሐዝብ እንዲያቅፈው የኦሮሞ ሕዝብ ደግሞ እንዲደግፈው ይፈልጋል። በትግራይ ሕዝብ ድጋፍ ብቻ ኢትዮጵያን ለመግዛት አይችልምና።

ኦሮሞና አማራ ትላልቅ ብሄሮች ናቸው። እነሱ በአንድነት ከቆሙ፤ ወያኔ አለቀለት ማለት ነው። የወያኔ መረዎች የኦሮምያ መሪዎችን በቀላሉ ሸንግለው አንጃ እንደሚፈጥሩ እርግጠኞች ነበሩ፤ የታወቀ ንቀት ስለነበራቸው። ስለዚህ አንጃ ፈጥረው ኦሮሞና አማራን ደም ማቃባቱ ትልቁ የወያኔ እስትራቴጂ ነው።

ለዚህ ነው ወያኔ እሱ እራሱ በአዋጅ ያወጣው ሕገ መንግሥት ባላንጣ ሆኖ፤ የአማራው ሕዝብ ሲባረር፤ ሲፈናቀል፤ ገደል ውስጥ ሲወረወር፤ ሲቃጠልና ሲጨፈጭፍ አይኑን ጨፍኖ፤ ጆሮውን ደፍኖ ቁጭ ያለው።

አቶ ጅዋር መሃመድ ደግሞ (ከእንጀራ አባቱ ከሊቀ መኳስ መለስ ዜናዊ የተማረውን ቲወሪ እንዳለች ገልብጦ) “መጀመሪያ ኦሮሞ ነኝ፤ ኢትዮጵያን በሰከንደሪ ደረጃ ነው የማያት” ይለናል። “ኢትዮጵያን ከመቀበሌ በፊት የኦሮሞን አቅምና ጡንቻ መጨመር ያስፈልጋል” እያለ ይፎክራል። ጡንቻው ማንን ለምስፈራራት እንደሆነ የሚያውቀው እሱ ብቻ ነው። ይህ አባባል ግልፅ የሆነ፤ ዘርን ከዘር ለማጋጨት የተጠነሰሰ “የዘረኝነት ፕሮፓጋንዳና ሴራ” ነው።

አቶ ጅዋር መሃመድ በሲ.ቢ.ኤስ ተጠይቆ ከሰጣቸው መልሶች መካከል አንዱ እንዲህ ይላል። “በመቶ የሚቆጠሩ የኦሮሞ ወጣቶች በየቀኑ በሊቢያ በኩል አውሮፓ እየገቡ ነው። እነሱን እየተቀበልን በፍጥነት ተደራጅተው ወደ ትምህርትና ወደ ሥራ መስክ እንዲገቡ ጥረት እያደረግን ነው”። ሌሎቹንስ የኢትዮጵያ ወጣቶች ማነው የሚረዳቸው? አማራውም፤ ትግሬውም፤ ሲዳማውም፤ ሀድያውም፤ ወላሞውም የየራሱን ብሔር ከፈለገ ይርዳ ማለት ነው? እነዚህ የኢትዮጵያ ልጆች በአውሮፓም ሆን በአሜሪካ የሚታወቁት በብሔር ስማቸው ነው ወይስ በኢትዮጵያዊነታቸው ነው? ሐገርህ ማነው አቶ ጅዋር? ከዚህ የበለጠ ጎስኝነትና ብሔረሰብኝት አለ? ይህ አስተሳሰብ ብቻ አቶ ጅዋር መሐመድን እንደኢትዮጵያ ጠላት ሊያስቆጥረው ይገባል።

“ኢትዮጵያ የምትባለውን ሐገር እኛ ላይ እንደጫና ነው ያስቀመጡብን። የራሳችንን የብሔር መታወቂያና (አይዴንቲቲ) ቋንቋ  እንድናወግዝ (ዴናውንስ እንድናደርግ) እንገደዳለን። ካላወገዝን ደግሞ እንታሰራለን” ይላል። “ይሄ ባባቴም ባያቴም ጊዜ ተደርጓል” ይላል። አቶ ጅዋር! በአያትህ ጊዜ ባልኖር፤ በአባትህ ግዜ አንተ ያልደረስክበትን (ያላየህውን) ብዙ የኦሮሞ ክልልሎች ተዘዋውሬ አይቻለሁኝ። ኦሮሞ በመሆኑ ብቻ፤ የኦሮሞ ቋንቋ በመናገሩ ብቻ! ይታሰራል የምትለውን ግርድፍ ውሸት ከየት እንዳመጣህውም አላውቅ። በዚያን ጊዜ እኮ ስንት በሥማቸውና በብሔራቸው የኮሩ የኦሮሞ ጄኔራሎች፤ ሚኒስቴሮች፤ መሳፍንቶችና ባላባቶች ነበሩ። ይሄ እኮ የኦሮሞን ሕዝብ መሳደብ ነው። እንደዚህ እየተሳደብክ እንዴት ያሁኑን ሃላፊነት ሰጡህ? ከየት ጉድጓድ ወስጥ ነው ብቅ ያልከው አቶ ጅዋር? የየትኛው የአረብ ሐገር ቅጥረኛ ነህ? ማነው ደሞዝህን እየከፈለ፤ አልጃዚራ ላይ መድረክ እየሰጠ (ካታር?) “ኢትዮጵያን ገነጣጥልልን” ያለህ? ወያኔም የዚህ ደመወዝ ከፋይ ይሆን?

ገና የስልጣን ኮርቻ ላይ ሳንቀመጥ፣ በጎሳ የተመሰረተ አደረጃጀትና አወቃቀር በውጭ አገር ሆነን ከጀመርን፣ ሃገር ቤት ሥልጣን ይዘን ብንገባ እንዴት ልንሆን ነው? “አሁን ደግሞ የኛ ተራ ነው። አርፈህ ተቀመጥ” ነው?

አቶ ጅዋር! አትሳሳት። በዘር የበላይነት የተመሰረተ አገዛዝ በኢትዮጵያ ውስጥ ከአሁን ወዲያ ጨርሶ ቦታ አይኖርም። ሰፊው ሕዝብ ሞኝ አይደለም። አንድ ጊዜ በጥፊ ተመቷል። ለሁለተኛ ጊዜ ግን አይመታም።

 

የባላገሩ ጥያቄና የብሔሮች አንድነት ውጤት

አበው ሲተርቱ “ድር ቢያብር አንበሳ ያስር” ይላሉ። ትብብራችንና አንድነታችን፤ እድገታችንና ኩራታችን ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ጨዋ ነው። በባህሉና በልምዱ ተፋቅሮና ተጋግዞ መኖር እንደሚችል ያስመሰከረ ሕዝብ ነው።

እድሉን አንግኝቼ፣ ሌሎች የአፍሪካ ሃገሮች እንዳደረኩት፤ ወደ ብዙ የኢትዮጵያ ከተሞችና ገጠሮች ሄጃለሁኝ። የብዙ ቀን መንገድ በበቅሎ፣ በፈረስና በመኪና ተጉዣለሁኝ። ተራ ኢትዮጵያዊ ነኝ። የተለያዩ ቋንቋዎች፣ ባህሎችና ሃይማኖቶች አጋጥመውኛል። ግን በየደረስኩበት ሁሉ ለእንግዳ የሚሰጠው ክብር ተለይቶኝ አያውቅም። ይሄ ነው እንግዲህ እኔ የማውቀው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጨዋነት።

የባላገሩና የከተሜው ጥያቄ

ሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ አንገብጋቢ ጥያቄ ምንድነው? የከተሜው/የገበሬው ጥያቄ ምንድነው? እስቲ ከምትኖሩበት ቪላ ቤት ወይም አፓርትመንት ወደ በረንዳ ወጣ ብላችሁ በሚመች ወንበር ላይ ተመቻችታችሁ ተቀመጡ። ከዚያም ወደ ውድ አገራችሁ ኢትዮጵያ ውስጠ ኅሊናችሁን ልካችሁ ባንድ ክፍል ከተማ ቤት ወስጥ ከአራትና አምስት ልጆቻቸው ጋር የሚኖሩትን ወላጆች፤ በገጠር ደግሞ ወደ ባላገር ወረድ ብላችሁ ያችን ጭስ ያፈናትን ጎጆ ከታች ተመልከቷት።

እስቲ መጀመሪያ ኦሮምያ፤ ከምባታ፤ ወላይታ፤ ሱማሌ፤ አፋር፤ ትግሬ፤ ጉራጌ፤ አማራ  ውስጥ ውዳለችዋ ትንሿ የኢትዮጵያ ጎጆ ቤት እናምራ።

ምን ይታያችኋል? ጭስ ያቀለመውን የሣር ኮፍያ ደፍታ፤ ለሺህ ዓመታት ጠብቃ ያቆየችውን የጭቃ ቤት ንድፍ ጥበብ ከርሻው በስተጥግ ሆና እያስመረቀች፤ የገበሬው ኩራትና ዞሮ መግቢያ ሆና ተቀምጣለች። ወደ ጓዳዋ ገባ ስትሉ ደግሞ፤ ባንድ በኩል የቤት እቃዎች፤ በሌላ በኩል ደግሞ የዕንግዳ መቀበያና የመኝታ ሥፍራ አቅፋ፤ መሃል የቆመውን ምሰሶ ተደግፋ ቆማለች።

ጤናይስጥልኝ የገበሬው ጎጆ። እስቲ ምን ትፈልጊያለሽ? ምን ጎደለሽ ብላችሁ ጠይቋት? ስለ እግዚአብሔር ብላችሁ፤ ምነው በርሽ ተጣመመ? የማገርሽ ምርጊት ምነው ተበላ? ለምን የሳር ኮፍያሽ በጭስ ቀለመ? ለምን ክፍልሽ እበት እበት ይሸታል ሪፍረሽነር እናምጣልሽ እንዴ? እስቶቩና ፍሪጁ የት ነው የተቀመጠው? ብላችሁ እንዳትጠይቋት። “አይ ልጆቼ ትናንትና ፈረንጅ ሀገር ብትሄዱ በአጭር ግዜ ውስጥ ያሳደገች እናታችሁን ኑሮ እረሳችሁ?” በማለት ልቧ እንዳይሰበር።

ለጠየቃችኋት ጥያቄዎች እንዲህ በማለት ትናገራለች። እናት ከልጆቿ አትደብቅምና።

1ኛ ከቀን እቀን ጦም ማደሩ ገደለኝ። አምናና ዘንድሮ ዝናም ጠፍቷል። እንዴት ልሁን? መሬቱም እንደድሮው ካለ ማዳበሪያ አያፈራም። እሱን ለመግዛት ደግሞ አቅም የለኝም።

2ኛ ከቅድም አያት ወደ አያት፤ ከአያት ወደ አባት፡ እያለ የሚዋራረሰው መሬት ቁራጭ እየሆነ መጥቷል። በዚህች ኩርማን በምታክል መሬት እንኳን ቤተሰብን ይዞ ለአንድ ለራስም መኖር አይቻልም። መቼ ነው ኢንደስትሪው ተስፋፍቶ ልጆቻችን ሰርተው መብላት የሚችሉት? ምንድነው የናንተ የልጆቻችን እቅድ? አለበለዚያማ ሀገሩ በሙሉ ለማኝ መሆኑ አይደል? ትላለች

3ኛ ልጆቼን የት ላስተምር? ት/ቤት ያለው ከቀን ጉዞ በኋላ ነው። እናንተ እንኳን በፈረንጅ ሀገር ልጆቻችሁን ባውቶሞቢል እያንቀባረራችሁ ታስተምሩ የለ? ምነው እኔን እናታችሁን እረሳችሁኝ?

4ኛ መብራቱን እንኳን ተውት የከተማውንም ሰምተናል። ሃኪም ቤት እኮ በአካባቢው ጨርሶ የለም፤ ሴቶቹ በምጥ ምክንያት እያለቁ ነው። ሃኪም በቅርብ ቢኖር ይድኑ ነበር። እንዴ አስክናልቅ ድረስ ነው እንዴ እናንተ የምትጠብቁት?

5ኛ አካባቢው ያለው ወንዝ በጣም እሩቅ ነው። ወንዙ ትንሽ ስለሆነ ውሃው ደግሞ ለመጠጥ አይሆንም። ሰው በወስፋትና በትል በሽታ እያለቀ ነው። እንዲያው የጉድጓድ ውሃ የምናገኘው መቼ ነው? እንዲያው የናንተን ቅዘን አጥበን አሳድገን በውሃ ጥም እስክንሞት ትጠብቃላችሁ?

እንዳያችሁት፤ አንገብጋቢው የጎጆዋ ጥያቄ ከመገንጠል ጋር አይያያዝም። ተገነጠለችም፤ አልተገነጠለችም “ይህ የሕልውና ጥያቄዋ ቀጠሮ አይሰጣትም” ነገ ተነገወዲያ ሳይባል መመለስ አለበት።

ከዚህ ከገጠር ጉብኝት በኋላ ደግሞ ወደከተማ ተመለስ። በየጎዳናውና በየመንደሩ ሰው እንደሰርዲን ታጭቋል። የመኪና መንገዱ በተሽከርካሪዎች ተጨናንቋል። ዋናውን መንገድ ለቀህ፤ ቀጭን የግር መንገዷን ተከትለህ ቁልቁል ስትወርድ፤ ከአንድ ትልቅ ቤት ጀርባ ተለጥፋ የተቀመጠች የአንድ ክፍል ቆርቆሮ ቤት ትደርሳለህ። አንኳኩተህ ግባ።

እንደገባህ በስተቀኝህ በኩል ሁለት አነስተኛ አልጋዎች በሰያፍ ተገጣጥመው ተንጋለዋል። ከፊታቸው አግዳሚ ወንበሮች ተኮልኩለዋል። በግራ በኩል ደግሞ ዳርና ዳሩ የሚታይ በመጋረጃ የተከለለ ተለቅ ያለ አልጋ ይታያል። ከአልጋው በስታግርጌ ግድግዳውን ተደግፎ ትልቅ የኮመዲኖ ሳጥን አንጋጦ ቆሟል።

ሰላምታ ከተለዋውጥክ በኋላ፡ “ምንድነው ችግርህ? ብሶትህ? ምን ቢደረግልህ መልካም ይመስልሃል ብለህ ትጠይቀዋለህ።

“አይ ወንድሜ እሱስ ምኑ ቅጡ” ብሎ ይጀምራል።

1ኛ ከቀን ወደ ቀን የልጆቻችንና የራሳችንን ሆድ እንኳን ለመሸፈን እየከበደን መጥቷል። የምግብ ዋጋ ቀን ከቀን ወደ ላይ እየናረ ነው። የዛሬ ዓመት በቀን ሶስቴ በሽሮውም፤ በጎመኑም አድርገን እንበላ ነበር። ስጋውንማ በአመት በዓል እንኳን ለመቅመስም አልቻልንም። በዚህ ዓመት ደግሞ ቁርሱንም አቁመናል። የሚመጣውን ዓመት እንግዲህ እግዜር ይወቅ።

2ኛ የቤቱም ኪራይ ከኑሮ ወድነት ጋር አብሮ እያደገ ሄዷል። ደሞዜ ከምግብና ከቤት ኪራይ አያልፍም። ለኮንዶምንየም ካመለከትን ዓመታት አልፈዋል። ዕጣው ግን ሊደርሰን አልቻለም። ቤቶቹ ለራሳቸው የወያኔ ዘመዶችና ካድሬዎች ነው የሚከፋፈለው። ለኛ እንግዲህ ከመቶ አንድ ይደርሰን ይሆናል። እጣውም እንኳን በአሁኑ ጊዜ ቢደርሰን እንዴት አድርገን የመጀመርያ ክፍያውን እንደምንከፍል አናውቅም።

3ኛ ሥራ የለም። ባለቤቴ በሂሳብ ሥራ የዩኒቨርሲቲ ምሩቅ ናት። እንኳን በትምህርቷ የሚሆን ሥራ ይቅርና ማንኛውንም ሥራ ቢሆን እስካሁን አላገኘችም። ሥራ ለማግኘት ካድሬ መሆን ወይንም የመንግስት ዝምድናን ይጠይቃል። አሁንማ ሁሉም ሥራ ለማግኘት ብሎ ካድሬ ስለሆነ እሱም አልተገኘም። ለዚህ ነው ወጣቱ ተምሮም ሥራ በማጣቱ በነፍሱ ቆርጦ ሀገሩን ትቶ በገፍ ወደውጭ ሐገር የሚሰደደው።

4ኛ ልጆቼ ተራቁተዋል። በምን አቅሜ ላልብሳቸው? ጓደኞቻቸው ጥሩ ጥሩ ለብሰው ሲያዩ ይሳቀቃሉ። በስልጣን ዝርፊያና በሙስና ስለከበሩ፤ እንደዚያ የሚለብሱት የባለጊዜዎቹ የወያኔዎችና የካድሬዎቻቸው ልጆች ናቸው። እነሱ ለአንድ ምሳ የሚያጠፉት እኔ በወር ከማገኘው ደምወዝ በላይ ነው።

5ኛ ልጆቼ ቢታመሙ፤ እኔና ባለቤቴ ብንታመም ሞተን መቅረታችን ነው። መታከምያ እንኳን ገንዘብ በእጃችን የለም።

6ኛ የትራስፖርት ችግሩ ይሄ ነው ብዬ ለመንገር ቃላቶች ያጥሩኛል። ጧት ስሄድ ቀደም ብዬ ከቤት ብወጣም ከሰው ብዛት የተነሳ ከአንድ ሰዓት ያላንሰ ተሰልፌ ተራ መጠበቅ አለብኝ። ስመለስማ እንዲያውም ከጧቱ ይብሳል፤ እጥፍ ሰዓት ነው የሚወስድብኝ። ምን ብዬ ልንገርህ ወንድሜ! እያለቅን ነው። ዋና ዋናውን ነገርኩህ እንጂ መከራችን ብዙ ነው። እናንተም ትረዱናላችሁ፤ ለችግራችን መፍትሄ ይዛችሁ ትመጡ የሆናል ብለን ስንጠብቅ ዓመታት አለፉ። ተዳክመናል በቶሎ ካልደረሳችሁልን ማለቃችን ነው ብሎ ለተጠየቀው ጥያቄዎች መልስ የሰጣል።

እስኪ አሁን ይህን ሁሉ ከሰማህ/ሽ በኋል ከሰሜን አሜሪካ ወደ ኃገር ቤት የላከውን/ሺውን ውስጠ ኅሊና መለስ አድረገህ/ሽ እውን አለም ትገባለህ/ቢያልሽ ማለት ነው።

ታዲያ የህዝቡ አንገብጋቢ ጥያቄ ምንድነው?

የከተማዋም አንድ ክፍል የቆርቆሮ ቤት ሆነች የገጠሯ ጎጆ፤ መሰረታዊው ጥያቄያቸው “የሕልውና” ጥያቄ ነው። ይህ የሕልውና ጉዳይ ቀጠሮ የማይሰጥ አንገብጋቢ ጥያቄ ነው። የሚውል የሚያድር አይደለም።

የኢትዮጵያ ጭቁን ሕዝብ መገንጠል አይደለም አንገብጋቢ ጥያቄው። ይሄ እንደረቀቀ ቲወሪ “በልብ ወለድ ፖለቲከኞች” መፅሀፍ ወስጥ፤ ከነማርክስና ከነሌኒን ተግልብጦ በመጀመሪያ ገፅ ላይ የተፃፈ መፈክር ነው። የሌላ ሀገር ሰዎች ከራሳቸው የኢኮኖሚና የማህበራዊ ኑሮ አቋሞችና ስርዐአቶች ጋር በማያያዝ ያካሄዱትን አብዮት በካርቦን ከመገልበጥ፤ የራሳችን የምንለው፤ ከራሳችን የኢኮኖሚና የማህበርዊ ኑሮ ጋር የሚጣጣም ወቅታዊ መፍትሄ ማምጣት አለብን።

አማራም ተነስቶ ዛሬ ለመገንጠል ይችላል። ኦሮምያም እንደዚሁ። ትግራይም እንደዚሁ። ወዘተ። ከዛስ በኋላ? ኦሮምያ ከተገነጠለች የትኛው ክፍል ነው ሥልጣን የሚይዘው? ክርስቲያኑ? እስላሙ? ነቀምቴው? አርሲው? አምቦው? ቦረናው? የትኛው የፖለቲካ ድርጅት? በኦሮሚያ ውስጥ የሚኖሩት ጎሳዎችስ እንዴት ሊሆኑ ነው። ሕዝቡ ከፈለገ ደግሞ ትንሹም ብሄር መገንጠል ይችላል። ትልቅ ብሔር ለሆነ ለኦሮሚያ ክልል ግን ከመገንጠል ጥቅሙ፤ ጉዳቱ ይብሳል። ትልቅ ብሔር እንደመሆኑ መጠን በአንድነት ግንባር ውስጥ ትልቅ ድርሻ በመውሰድ ብዙ ለሐገር የሚጠቅሙ ሚናዎች መጫወት ይችላል።

ችግሩን የሚያባብሰው ተማርኩኝ ያለው “የልብ ወለድ ፕሮፖጋንዳ” ፀሃፊው ነው። ኦሮሞን እንገንጥል። ትግሬን እንገንጥል። ሲዳማን እንገንጥል። ወዘተ ይለናል። እንዴት ነው የምንገነጣጠለው? አንተስ/አንቺስ የምትገነጠለው/የምትገነጠዪው? እስቲ እንዴት እንደምትገነጠል፤ ክልልህ ውስጥ ካሉት የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር እንዴት መተባበር እንድምትችል፤ ምን አይነት መግሥት እንደምትመሰርት፤ የመገንጠልህ ጥቅምና ጉዳቱ፤ መገንጠል የሚያመጣው የኢኮኖሚ ጥቅምና ጫና፤ ከጎረቤቶችህ ጋር ያለህ ግንኙነት፤ ወዘተ. ወዘተ… በድንብ ተጠንቷል? የባእድ ቲዎሪ ከመፍተልና ወያኔ ያቀበለህን የዘረኝነት ልቃቂት ከማጠንጠን ይልቅ ወረድ ብለህ መሰረትህን እወቅ። ማንንነትህን እወቅ።

እንግዲህ መገነጣጠል ከተጀመረ ማለቂያ ላይኖረው ነው። በማንኛውም ክልል ውስጥ አደጋው ይሄ ነው። ሌኒንን እንዳንጠይቀው ሞቶብናል። የራሳችን ሌኒን “መለስ ዜናዊ” ደግሞ እሱኑው ስለዚሁ ጉዳይ ለመጠየቅ በድንገት ሄዶ በትሮትስኪ ሰዎች ተጠልፎ ግምገማ እየተደረገበት ነው ይባላል።

የሰፊው ሕዝብና የሐገራችን ጎጆ ወቅታዊ ጥያቄ መገንጠል አይደለም።

እኩልነት። መብት። ነፃነት። ፍትህ። ይህን ለማስከበር ደግሞ አንድነት። የሁሉም ጭቁን ሕዝቦች ጥያቄና ፍላጎት አንድ አይነት ነው።

 

በትብብር ሆኖ ጠንካራ ኢትዮጵያን ለመገንባት ምን ያስፈልጋል ለሚለው ጥያቄ የራሴን አስተያየት እንሚቀጥለው አቀርባለሁ።

  1. እስካሁን የነበረውን የፖለቲካ እንካ ሰለምታ ጨርሶ ማቆም።
  2. በአንድ የጠርጴዝያ ዙርያ ተቀምጦ የሁሉንም ድርጅቶችና ግለሰቦች አስተያየትና ሃሳቦች በዝርዝር መፃፍ (ማስቀመጥ)።
  3. የቀረቡት ሃሳቦች ላይ፤ በታላቅ ትዕግሥትና በመደማመጥ፡ ተነጋግሮ፤ እያንዳዱን ነጥብ በጥሞና አኝኮና አብላልቶ፤ በየአንገብጋቢ መልካቸው ቅደም ተከተል ማስያዝ።
  4. ጊዜያዊ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ (ከየድርጅቱ) መምረጥ። የዚህ ኮሚቴ አባሎች በብቃታቸው፤ በልምምዳቸውና በብስለታቸው ብቻ የሚመረጡ መሆን አለባቸው።
  5. ለዚህ ጊዜያዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ፤ የወከላቸው የፖለቲካም፤ የሲቪክናም ሆነ የሀይማኖት ድርጅት ሁሉ የማያወላውል ድጋፍ በመስጠት ከኋላቸው መሰለፍ አለባቸው።
  6. በጊዜያዊው ኮሚቴው ሥር የሚሰራ የድርጅቱ አፈቀላጤ (የሚድያ አቋም) ማቋቋም።
  7. ጊዜያዊው የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው፤ በወከሉት ድረጅቶችና በራሱ ሚድያ በኩል ዲያስፖራውን በማስተባበር የሰውና የማቴርያል አቅም ለመገንባት፤ ሌት ተቀን ሳይሉ በአስቸኳይ በሥራ ላይ እንዲሰማሩ ማድረግ።
  8. ጊዜያዊው የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው፤ በወከሉት ድርጅቶች እየተረዳ ሀገር ውስጥ ካሉ የፖለቲካ፤ የሲቪክና የሃይማኖት ድርጅቶች ጋር ጠንካራ ግንኙነቶችን መፍጠርና መተባበር።
  9. በጊዜያዊ ሥራ አስፈፃሚው ኮሚቴ ስር ሆኖ የሚካተት፤ ከአሜሪካና ከአውሮፓ መንግሥታት ጋር የሚያግባቡ (lobby) ግለሰቦችን የሚመራና የሚከታተል፤ በፖለቲካና ፐብሊክ ሪሌሽን ጥሩ ልምምድና ችሎታ ያለው ቡድን ተቋቁሞ አግባቢዎቹን (lobby group) ከፍትኛ ክትትል እዲያደርግ (ይህ የሎቢ ግሩፕ እንደ አንገብጋቢ ጥያቄ መታየት ይኖርበታል)። ከትግሉ ክፍል አንደኛው ትልቁ ምዕራፍ ነውና።
  • እነዚህ የተባበሩት የፖለቲካ፤ የሲቪክና የሃይማኖት ድርጅቶች ሀገር ውስጥ በመዝለቅ ሕዝብን በመቀስቀስ ሥራ ላይ በመሰማራት ታላቅ ግፊት ማድረግ መቻል አለባቸው (በሰላማዊ ሰልፍ፤ በሥራ ማቆም አድማ፤ የገጠር መንገዶችን በመዝጋት፤ የመሳሰሉትን በማድረግ …)
  • ከላይ የተገለፀው ግፊት ወያኔን በጠረጴዛ ዙርያ ለማምጣትም ሆነ በሕዝብ አመፅ ለማንበርከክ የጠቅማል።
  • ጊዜያዊው የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በየጊዜው ስብሰባ በመጥራት፤ በትብብሩ ውስጥ ላሉት ድርጅቶች ሥራው ያለበትን ደረጃ በተመለከተ ማብራርያ መስጠት። ለሕዝብም በሚድያው በኩል ተከታታይ ገለፃዎች መስጠት (to foster transparency).
  • ወ.ዘ.ተ…..

 

Dayano65@outlook.com

The post የወቅቱ አንገብጋቢ ጥያቄ – ከደጀኔ አያኖ appeared first on Zehabesha Amharic.

የኢትዮጲያ ብሄራዊ ቋንቋ በኢህዴግ ዕይታ –ብሩህ ቦጋለ

$
0
0

LanguagePartners5በየትኛው የአለም ሕዝብ ዙሪያ በአንድ ሕብረ መንግስት ወይም በአንድ መንግስት ሥር የሚኖሩ ብሐር ብሔረሠቦች በእምነት፣በጎሳ፣በቋንቋ የግድ አንድ አይነት ሆነው መገኘት አይጠበቅባቸው ሊሆኑም አይችሉም፡፡ለምን የሚባል ጥያቄም አይኖረውም በሁሉም አንድ አይነት ሆነው ቢገኙም እንኳ የትውልድ ሐረግ አመጣጣቸው ከተለያዩ የግንድ ሐረግ ከተለየ ቦታ መሆኑ አይቀሬ ነው፡፡ ለአብነት ያክል በአንድ ሕብረ ብሔር ውስጥ አንድ አይነት ቋንቋ ተናጋሪ አምስት ሚሊዮን ብሔረሠቦች ቢኖሩ አምስቱም ሚሊዮን ሕዝቦች ጥንት ከአንድ አይነት ጎሳ፣ ከአንድ አይነት ቋንቋ ተናጋሪ፣ ወንዴና ሴቴ የመጡ ናቸው ብሎ ማመን ድንቁርና ነው ምክንያቱም የሕብረተሠብ ዕድገት አመጣጥን ሥርዓት ያልተከተለ ኢሳይንሳዊ ይሆናልና፡፡

እዚህ ላይ ስለሕብረተሠብ ታሪክ አመጣጥ ለማስረዳት ሳይሆን አካሄዴ ስለብሔራዊ ቋንቋ  አንድነት ጠቀሜታ የታዬኝን አስተያየት ለማምልከት እንጂ፡፡ ምንም እንኳን ጥንት መንግስት አልባ በነበረበት የሕብረተሠብ ስብጥር አኗኗር ወክት የአናሳዎች ጎሳዎች ቋንቋ በአብላጫዎቹ ቋንቋዎች  እየተዋጡ የአንዱ ጎሳ ቋንቋ ከአንደኛው እየተወራረሰ በሐደ ቁጥር የባሕል ፣ የጋብቻ ፣ የሥነ ተዋልዶ ስብጥር በዚያው ልክ እያሠፋ መጥቶ አንድ አይነት ቋንቋ ለመናገር መንስኤ ከመሆን ውጭ እያንዳንዱ ጎሳ በያንዳንዱ ጎጥ ውስጥ ለያንዳንዱ ቋንቋ  ከመሬት  የፈለቀለት ነገር አይደለም፡፡ ይህ ማለት በህብረተሠብ ስብጥር አኗኗር አንደኛው ከሌላኛው ቋንቋ  ተወራርሶ የመጣ የጋራ ቋንቋ  አንጂ እንደ ኮምፒይተር አንድ ግለሠብ የፈጠረው ወይም ሌላይኛው በፍልስፍና ያገኘው የፈጠራ ውጤት አለመሆኑ መታወቅ ይኖርበታል፡፡

የቋንቋ ጥቅሙ ለመግባቢያ ብቻ ሆኖ ለማህበራዊ ግንኙነትም ፋይዳ አለው ይህን አካሄድ ገዥ መደቦች አይወዱትም ይህ የጎሳ ስብጥር ሕብረት አኗኗር ግንኙነት የተቋረጠው መንግስት የሚባለው ሥርዓት እምነትን  መዕከል አድርጎ በያለበት መሥፋት ከጀመረ በኃላ በየጎጥ ክልል ውስጥ የሚኖር ሕብረተሠብ በጎጥ ወይም በከል የጎሳ አለቃ ቁጥጥር ሥር ስለወደቀ የሕብረተሠብ ስብጥር ማህበራዊ ግንኙነት ተገደቦ የየጎጡ ወይም ክልል አለቆች ገዥዎች እየበዘ በሄዱ ቁጥር አንዱ ጎሳ ከንድ ጎሳ እያጋጩ የጦር ጅብደኝነት  አንዱ በአንዱ ጎሳ ላይ ጥላቻ እየፈጠሩ ቋንቋን መሠረት ያደረገ አገዛዝ ቦታውን ተረክቦ የቋንቋ መስፋፋት ለገዥ መደቦች መበራከት አስተዋፅአ አድረጎል በአንጻሩም  በቋንቋ መሰፋፋት ምክንያት  አንዱ ጎሳ በአንደኛው  ቋንቋ ተናጋሪ ላይ ያጎሪጥ በጥላቻ የመታየት ችግር ሲፈጥር ሲያናቁር እንደኖረ የሚታወቅ የታሪክ ሐቅ ነው፡፡

ይሁን እንጂ አንዱ ቋንቋ ከአንዱ የሚበልጥበት ወይም የሚያንስበት መገለጫ የለውም ሁሉም ቋንቋ  በራሱ የራሱ ምሳሌ፤ተረት ፣ቅኔ፣ ተረብ፣ ውስጠ ወይራ ቀልድና አዝናኝ ጫወታዎች አሉት አንዱም ብሔረሰብ የሌላውን ቋንቋ ያከብራል፤ያፈቅራል፡፡አንዱ ቀንቃ ከአንዱ የሚናቅ  እንዲናቅ ሌላው ቃንቃ እንዲከበር የሚያደርጉት ማንም ሆነ ማን ምን የገዥ መደቦች ናቸው አንጂ ሕብረተሰቡ እንዳይደለ እንዳልነበረም ይበልጥ የሚያውቁት ፖሊቲከኞችና የፖለቲካ አቀንቃኞች እንደሆኑም ድሮም እንደነበሩ ሠፊው ሕዝብ በውል ያውቃቸዋል በአደባባይ ላይ ለይስሙላ ሲለፈፋም ንቀቱም ጥላቻውም ከራሳቸው የሚመነጭ ለፖለቲካ መሰሪያነት ለያይተው ለማየት የሚያደርጉት የውል ጥበብ ውጠት ድምር ነው፡፡ማናቸውም ብሄርብሄረሰቦች በአፍ መፍቻ ቃንቃቸው መማር መዳኘት መመራመር ባህላቸውንና ቋንቋቸውን መንከባከብ ዕና ማሳደግ፤ለጋራ መገናኛ ቋንቋ ማደግና መጎልበት ታላቅ የማነይናቅ አስተዋፅዖ እንዳለው ሰፊው ሕዝብ ያምንበታል፡፡ምክንያቱም የያንዳንዱ ብሔረሰብ በዐፍ መፍቻ ቋንቋው  ተምሮ መመራመር መታርጎም ከቻለ ለጋራ መገናኛ ቋንቋ መግባባት መንገዱን ቀላል አመቺ ስለሚያደርገው በእጅጉ ሠፊው ብዘኃኑ ሕዝብ ይደግፈዋል ቢቻለውም በተጨማሪ ቋንቋውን አውቆ መናገር ቢችል ደስታው ነው፡፡ ይህ ሐቅ መሆኑን ብዙኃኑ ሕዝብ እርስ

በርዕሱ ይታወቃል ማናቸውም የፖለቲካ ክፍል ግን ለያይተህ ግዛ መርህ ሚስጢር በውስጥ አጀንዳ ይዞ በአደባባይ ሰፊው ህዝብ አንዱ የአንዱን ቋንቋ እንደሚንቅ አስመስሎ በተዘዋዋሪ የአባዬን ወደ እማዬ እንዲሉ ቋንቋን ተንቆ ነበር ብሎ የሚኮንነው ማንን ነው?ይህ ሁሉ ማናበብ ሰፊ የፖለቲካ ሽፋን ምስጋና ለማግኘት እንደ መሳሪያነት መጠቀሚያ ማታለያ ከማድረግ ያለፈ ልባዊ እውነታነቱ ትዝብትን ያጭራል፡፡ አናግሮ አናጋሪ ይሉኋችዋል ይህ ነው፡፡ አጥብቆ ጠያቂ የእናቱን ሞት ይረዳል እንዲሉ የሰሜን ኢትዮጲያችን ተጎራባች የሆኑትን የዋሁን ገበሬ ከነቋንቋው ለብዙ ዓመታት በጥላቻ አይን የሚያየና ቋንቋውን በጆሮው መስማት የጠላና ደንቅ የነበረውን የቅርብ ጊዜ ትዝታ ህዝብ አካል ማን ነበር? ከዚያህም አልፎ ከርሱ ቋንቋ በስተቀር የሌሎችን ቋንቋ ታሪክ የለሽ አድርጎ በንቀት ሲመለከት በአደባባይ ይታይ የነበረው የየትኛው ህብረተሰብ የፖለቲከ አቀንቃኝ እንደነበረ እራሱ አያውቀ በድፍረት ለህዝብ ቋንቋ ማስከበር ነው፡ የቆምኩት ማለት ከንቀት በላይ ንቀት መሆኑ ነው፡፡ ዳሩ ምን ያድርግ ፖለቲከኛ ማለት ለጥቅሙ ማሰከበሪ ስልጣን የቆመ የዛሬ ጊዜሃዊ ምቾቱን እንጂ ያለፈው በወገኞቹ ላይ የነበረውን የታሪክ አሻራ ጥላቻ ደንታ አይሰጠውም፡ሆዱ ከሞላ ከጠላቶቹ ጎን ያለ ይሉኝታ ይሰለፋልና ዛሬ ከዚህ ኢህሀዲግ ወያኔ ጋር የተሰለፉት የሰሜን ወያኔ አጎራባች ክልል ህዝቦች የፖለቲካ አጋሮች እና ካድሬዎች ከዚህ በላይ የተፃፈውን እውነተኛ ታሪክ ከኛ ይበልጥ ያውቁታል ዳሩ ሆዱን የወደደ ማእረጉን ይጠላል፡እንዲሉ ሆነና ነው እንጂ፡፡

ከዚህ በላይ የተሰነዘሩትን አስተያየቶች እውነታነት ለታዛቢዎች ትተን ወደ ዋናው የቋንቋ አንድነት ጠቀሜታ እንመለስ፡ቋንቋ በመንገድ ይመሰላል መንገድ ሁሉንም አገናኝ ነው፡መንገድ ከሌለ የሁልም ግንኑኝነት ይቋረጣል ታዲያ ቋንቋን ከመንገድ ጋር ካመሳሰልን እያንዳዱ ብሄረሰብ በአፍ መፍቻ ቋንቋው መማር እና ቋንቋውን ማዳበር እንደተጠበቀ ሆኖ እነዚህ ብዙሃን ህብረተሰቦች በአንድ ህብረ ብሄር ውስጥ በሚኖሩበት ጊዜ አንድ የጋራ መገናኛ ቋንቋ መኖር ግድ ይላል፡፡ ስለዚህ የጋራ ቋንቋውን የነዚህ ሁሉ መገናኛ ስለሚሆን እንደ ራሳቸው ቋንቋ ተደርጎ መታየት በራሱ እንደመብት እና ግዴታ ሆኖ ብሄርብሄረሰቦች እንደራሳቸው ቋንቋ የማወቅ ግዴታ ሊኖረው ይገባል፡፡ ለምን መብትና ጥቅሙ የጋራ ነውና እትዮጲያ በአሁኑ የኢአዴግ መንግስት የጋራ ብሄራዊ ቋንቋ አልባ ሆና ትገኛለች፡፡ የፌደራላዊ ቋንቋ ተብሎ አይታሰብም፡፡ ይህ በራሱ የብሄር ብሄረሰቦች ግኙኝነት እንዳይኖራቸው ከፋፍሎ ለመግዛት አመቺ እየሆነላቸው ሄዶ ቀስ በቀስ የጋራ የሆነ ቋንቋ እየተመናመነ ሄዶ ጠባብ ደረጃ ላይ ከደረሰ በኃላ እነዚያ ብልጣ ብልጦች የፈየዱትን ቋንቋ የራሳቸው እና በራሳቸው ካቢኔዎች ብቻ እንዲነገር ለማድረግና ሌሎቸ ብዙኋን የፌዴራል ቋንቋ ተናጋሪ ብሔርብሔረሰብም ተወላጆች ውስን ይሆኑና እነሱና መሰሎቻቸው ብቻ በቋሚነት እየተለዋወጡ ለመምራት አመቺ ሁኔታ ስለሚፈጥርላቸው ሆን ተብሎ በኢህዴግ የተንኮል ክፋፍለህ ግዛ ስልት ውጤት መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡ በዚህ ዓይነት የሰፊውን ህዝብ መገናኛ መንገዱን ቀስ በቀስ ከዘጉት በኋላ ብዙሃኑ በየክልሎች ውስት ተወስኖ ሲቀር የፌዴራል ቋንቋ ባለቤት እራሳቸው እና መሰል አጋሮቻቸው ብቻ ሆነው ለለሌላው ብዙሃን አማራጭ እድል ይነፍገዋል ማለት ነው፡፡ ለዚህ ነው ይህ ስውር የተንኮል አካሄድ እንዳይነቃባቸው ቋንቋን መሰረት ያደረገ የፌዴራለዊ አወቃቀር የህዝብ መብት አስመስለው 24 ሰዓት ሙሉ የሚለፍፉት፡፡ ይህ ሲባል ፖለቲከኞች በይፋ በአደባባይ ከራሳቸው ቋንቋ በስተቀር አትማሩ፣ አትናገሩ ይላሉ ማለት አይደለም፡፡ እንዲህማ በይፋ ካሉ የእነሱ ሁለቱንም ቋንቋ አጣርቶ ማወቅ ላይ ህዝባዊ አሉታዊ ተፅህኖ ስለሚያሳድርባቸው በይፋ አያወግዙም ግን በየግሉ ቋንቋ መማርና መናገር ብሎም እስከ መጨረሻው መዝለቅ መብትና ግዴታው መሆኑን ሲያሰምሩበት በአንፃሩ ደግሞ የሌላውን የብዙሃኑን የመገናኛ ቋንቋ መማርና መናገር አለመፈለግ መብት አስመስለው እየለፈፉ የብሔራዊ ቋንቋ ሰፊው ህዝብ በስፋት እንዳያውቅ ተዘዋዋሪ፣ ቁሳዊና ሰብሃዊ አገልግሎት እንዲነካም ለማድረግ ብለው ኢትዮጲያ በተለምዶ የፌዴራላዊ ቋንቋ እንጂ ብሔራዊ ቋንቋ የላትም የሚሉት ወደፊትም እንዳይኖራት ለማድረግ ድብቅ አጀንዳቸው መሆኑን በገሃዱ ያሳያል፡፡

ይህ አካሄድ የፌዴራሉ ቋንቋ ባለቤትነት ተረክበው ለጥቂት ሹማምንት ካድሬ ውስን አካላት ብቻ ተገልጋይና በአማርጭነት ተጠቃሚዎች እየሆኑ የብዙሃኑን ከሀገር ሀገር የመዘዋወር እድል መብትና ጥቅሙን ይገድቡታል፡፡ የዚያን ጊዜ ነው የብሔር ብሔረሰቦች ቋንቋ ግኑኝነት እየላላ ሄዶ እድገትና ፍቅር ሆድና ጀርባ ሆኖ በክልል የሚወሰነው፡፡ ያን ጊዜ ነው እያንዳዱ ክልል በያንዳንዱ ገዢዎች እጅ የምትወድቀው፡፡ ያን ጊዜ ነው የመጨረሳው የብዙሃን መብትና ጥቅም በጎጥ የሚወስነው፡፡ ያን ጊዜ ነው የየክልል ገዢዎች በዲፕሎማሲ ግኙኝነት ከሀገር ሀገር ሲንደላቀቁ ብዙሃን በቋንቋ ተገድበው የሚረገጡት፡፡ ይህን መሰል አሳብ አድርባዮች ጥቂት ባለጥቅሞች ገና በተስፋ የሚጋዙ ጥቂት የወግ የፖለቲካ እቀንቃኞች አይቀበሉትም፡ብዙሃኑ ደግሞ በንቃት ህሊና ክህሎት አለመዳበር የተነሳ የፖለቲካ ድብቅ አጀንዳ ሚስጢር ማወቅ ይሳነዋል ይህን ለማስፈፀም አቅምም አንድነትም አይኖረውምና፡፡

The post የኢትዮጲያ ብሄራዊ ቋንቋ በኢህዴግ ዕይታ – ብሩህ ቦጋለ appeared first on Zehabesha Amharic.

እውን ወልቃይት ትግሬ ነው !! –ይገረም አለሙ

$
0
0

welkayet - satenawወቅቱ 1994 ክረምት ነው፡፡  በየአመቱ ት/ት ቤቶች ሲዘጉ መምህራንን አንደም በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ለማጥመቅ ሁለትም ስራ ፈተው ከዋሉ የሚሰሩት ስለማይታወቅ ጠርንፎ ለማቆየት የሚዘጋጀው ስብሰባ ጎጃም ደብረ ማርቆስ በሶስት አዳራሾች እየተካሄደ ነው፡፡ ቤተ መንግሥት አዳራሽ ሲኒማ ቤትና መንገድ ትራንስፖርት አዳራሽ፡፡

በሲኒማ ቤቱ  ስብሰባ በአወያይነት ከተመደቡት አንዱ ከአንደኛ እስከ አራተኛ ክፍል ድረስ በእንድ መምህር  ስለሚካሄደው የትምህር አሰጣጥ የሚያውቀውን ሳይሆን የተነገረውን በተረዳው መጠን ለተስባሳቢው ገለጸ፡፡ ይሄው የትምህርት አሰጣጥ አማራ ክልልን ጨምሮ በመላ ሀገሪቱ ውጤታማ ሆኗል ያለው  አወያይ በትግራይ ክልል ብቻ ተግባራዊ አለመሆኑ ጠቅሶ ምክንያት ተብሎ የተነገረውንም  ሲናገር በዚህ ደረጃ የተመደቡት በአብዛኛው ሴቶች ነበሩ፣ ከእነዚህ አብዛኛዎቹ ደግሞ በተመሳሳይ ውቅት በማርገዛቸው ፕሮግራሙን ማስቀጠል አልተቻለም  አለ ፡፡ በዚህ ግዜ አዳራሹ በሳቅ ተሞላ፡፡ መድረኩ ለውይይት ክፍት መሆኑ ሳይገለጽም  ለአስተያየትና ለጥያቄ በርካታ እጆች በአየር ላይ ታዩ፡፤

እውያዩ ገለጻውን አብቅቶ ( የተነገረውን ተናግሮ) ቀጣዩ ሰአት የውይይት መሆኑን ገልጾ ቅድሚያ ለሴቶች በሚል የመጀመሪያውን የመናር እድል ለሴት ሰጠ፡፡ እድሉ የተሰጣት መምህርትም ከአንድ እስከ አራተኛ ክፍል በአንድ መምህር ማስተማር በአማራ ክልል ውጤታማ ሆኗል ተብሎ ከመድረክ የተገለጸው  እኛ በተግባር ከምናውቀው ጋር የሚገናኝ አይደለም በማለት ከአወያዩ ገለጻ በተቃራኒ የሆነ አስተያየት ከሰጠች በኋላ አንድ ጥያቄ አለኝ እሱም ምንድን ነው በትግራይ ክልል በዚህ ደረጃ የተመደቡት  አብዛኛዎቹ ሴት መምህራን በመሆናቸውና ከእነርሱም ብዙዎቹ በተመሳሳይ ወቅት በማርገዛቸው ፕሮግራሙ ተግባራዊ አለመሆኑና ወደ ቀድሞው አሰራር መመለሱ ተገልጻል፡፡ እዚህ አማራ ክልል እኛ ሴቶቹ ማርገዝ አልችል ብለን ነው; ወይንስ ወንዱ ማስረገዝ አቅቶት; ጥያቄየ ያሄ ነው ብላ ስትቀመጥአዳራሹ በጭብጨባ በሳቅ በውካታ ተናጋ፡፡ አወያዩ የሚይዝ የሚጨብጠው ጠፍቶት ተደነጋግሮ እየተርበተበተ ቀልዱን አቁሙና ወደ ቁም ነገር አንግባ ማለት ጀመረ፡፤

መምህርቷ አጋጣሚውን በመጠቀም አጠቃላይ ፖለቲካዊ መልእክት ለማስተላለፍ አስባ ያደረገችው ይሆን ወይንም በመድረክ የተነገረው ስሜቷን ነክቶት ለዚሁ ምላሽ ለመስጠት  ብላ የተናገረችው  የምታውቀው እሷ  ብቻ ብትሆንም የተናገረችው ቃል ግን  ጥልቅ መልእክት ያለው ነበር፡፡  የአማራ ወንዶች ማስረገዝ አቃታቸው ወይ; ከባድ ጥያቄ ነው፡፡

ከአስር ዓመታት በላይ ወደ ኋላ ሄጄ ይህን እንዳስታውስ ያደረገኝ አቶ አቦሆይ የተባሉ የህውሀት ሰው ሰሞኑን ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ጋር  ባደረጉት ቃለ ምልልስ  ያለምንም ማንገራገር  በድፍረት ወልቃይት ትግሬ ነው ሲሉ መስማቴ ነው፡፡ ሰውየው በዚህ አላበቁም ወልቃይት ትግሬነቱን ለማስከበር የትጥቅ ትግል ማካሄዱን  አሁን በትግራይ ክልል ስር በመሆኑ ደስተኛ መሆኑን ኮሚቴ የሚባሉት ሰዎች ህዝቡን የማይወክሉ እንደሆኑ ወዘተ ተናገሩ፡፡ ንግግራቸው ፈር የለቀቀና ከእውነት የራቀ  መሆኑ ሳያንስ ድፍረታቸው ያስገረማት ጋዜጠኛ (ትዘታ)  ጥያቄዋን ጠንከር ስታደርግባቸው አሁን ትንሽ ስራ አለብኝ ሌላ ግዜ ደውለው እንነጋር በማለት  ጥያቄዋን ከዛ በላይ አንዳትገፋ  አደረጓት፡፡

ግለለሰቡ የአንድ ወረዳ ሹም ቢሆኑም የተናገሩት የተነገራቸውንና ርሳቸው በቦታው ተሸመው እያስፈጸሙት ያለውን የድርጅታቸውን እምነት በመሆኑ በአነስተኛ ሥልጣን ለይ ያለ ሰው የተናገረው ተብሎ ተቃሎ የሚታይ አይደለም፡፡

ታሪክን ሽረው እውነትን ክደው ወልቃይት ትግሬ ነው ሲሉ ንግግራቸው ሳይሆን ንቀታቸው ያበግናል፣ ማንአለብኝነታቸው  ስሜትን ይፈታተናል፤  ድፍረታቸው እልህ ያሲዛል፡፡ የአማራ ወንድ ማስረገዝ ኣቃተው እንዴ  የሚለውን ከላይ የጠቀስናትን መምህርት ጥያቄም ያስታውሳል፡፡ ወልቃይት በብልሀትም በጉልበትም  መሬቱን ተነጥቆ፣   ማንነቱ ተለውጦ ያለአባቱ ትግሬ ተብሎ ሀያ አራት አመት በትግራይ ክልል ስር  መገዛቱ ሳያንስ  ወያኔዎች ደፍረው ወልቃይት ከጥንትም ትግሬ ነው ለማለት የበቁት የወልቃይትን አማራነት የሚያረጋገጥ ወንድ ጠፍቶ ነው ; የሚያሰኝም  ነው፡፡ (በቅርብ ግዜ ተጠናክሮ የቀጠለውን የኮሚቴዎች እንቅስቃሴ ሳይጨምር ነው ታዲያ)

ከላይ ከአፋፉ ላይ ካልከሉት ጠላት አይን የለውም ይገባል ከቤት በማለት ድንበር የሚገፋን ሆነ ግዛት የሚያስፋፋን

ገና ሲጀማምር  ማስቆም እንደሚገባ  በቀረርቶ የሚገልጸው አማራ በምን መንገድ ተታሎ ወይንስ በምን ያህል ጫና ተረቶ ት ነው እንዲህ በገዛ መሬቱ እሱ አንደ ጭሰኛ  ቀማኛው  አንደአባቢድራ ለመኖር የበቃው የሚያሰኝም ነው፡፡ መምህሯ አንዳለችው ማስረገዝ አቅቶት ይሆን!

እንደምንሰማው ከሆነ በወሰዱት ለም መሬት ያረኩት ይበልጡኑ የጎመዡት ወያኔዎች ከወሰዱት የሚበልጥ መሬት እንደሚቀራቸውና ያንንም ለመጠቅለል  እንደሚያልሙ ነው፡፡  ይህም አያያዙን አይተው ጭብጦውን ቀሙት አይነት መሆኑ ነው፡፡

የጥምቀትን በዐል በተለይም የጃንሆይ ሜዳ ክብረ በአልን በልዮ አጨፋፈራቸው በማድመቅ የሚታወቁት የቀድሞው ሰሜን ወሎ የአሁኑ ደቡባዊ ትግራይ ዞን ነዋሪዎች (ራያዎች) በሆታቸው የሚሉት ግጥም በአብዛኛው ፖለቲካዊ ነው፡፡ታዲያ ገና የወያኔ መንግስት ባልረጋ ባልተረጋገባት ግዜ አንስቶ እስከ ቀርብ ግዜ ድረስ ራያ እንጨት ስበር ቆቦ ውኃ ቅዳ ፣ላስታ አንጨት ስበር ጎንደር ውኃ ቅዳ እያሉ ወያኔ ወደመሀል አገር የተንደረደረባቸውን አካባቢዎች ይጠቃቅሱና ወዴት ትሸሻለህ ጎትተህ ጎትተህ ባመጣኸው እዳ  በማለት የአካባቢውን ፖለቲካዊ ሁኔታ ይገልጡት ነበር፡፡

ወያኔ ከደርግ አይብስም ብሎ በተለይም በመላኩ ተፋራ አረመኔያዊ ድርጊት ተማሮ ለወያኔ ድጋፉን የሰጠው ጎንደር መሬቱን ተነጠቀ፤  የጫርኩት እሳት እኔኑ ፈጀኝ ብሎ በድርጊቱ ተቆጭቶ ይህን  ለልጆቼ አላስተልፍም በማለት አማረነቴ ይታወቅ ድንበሬ ይከበር ሲል  ወልቃይት ከጥንትም ትግሬ ነው ተባለ፤ አረ እንዴት ሆኖ በማለት ትግሉን ሲያጠናክር  አማራና ቅማንት የሚል የማዳከሚያ ልዩነት ተፈጠረበት ይህም አልበቃ ብሎ የሱዳንን መሬት ወሮ የሚያርስ ሽፍታ ተብሎ ተወግዞ ጥቃት ታወጀበት፡፡ በወያኔ ስለተቀማው መሬት ሲከራከር ምን ታመጣለህ ተብሎ ቀሪው ለም መሬቱም ለሱዳን ሊሰጥበት ነው፡፡ ይህን ሲያደርጉ ሱሪውን ተጠራጥረውት ወንድነቱን ንቀውት ይሆን፡፡ …እነርሱ ምን ያርጉ ከእኛ ሰው ሲታጣ ነው ያለው ያ ድምጻዊ፡፡

ራያዎች በሆታቸው እንዳሉት  አሁን ያለው ትውልድ ይበጃል ብሎ ጎትቶ ያመጣው  በመሆኑ አንድ ውል ሳያሲዝ ከነገሩ መሸሽ ስለሌለበት ስለማይችል፤ ሁለትም የአካባቢው ሁኔታ በዚህ መልኩ ለመጪው ትውልድ መተላለፍ የሌለበት በመሆኑ የወልቃይትን አማራነት  የድንበሩንም ተከዜነት ማረጋገጥ የዚህ ትውልድ ግዴታ ነው፡፡ ወያኔዎች በብልሀትም በጉልበትም ተከዜን ተሻግረው መሬት መውረር ግዛት ማስፋፋታቸውን በተለያየ መንገድ የተቃወሙ የአካባቢው ተወላጆች የደረሱበት እንደማይታወቅ ሰሞኑን እየሰማን ነው፡፡ ከቅርብ ግዜ ወዲህም ነገሩን የምር ይዘው በህግ ለማስፈጸም የሚጣጣሩትን የኮሚቴ አባላት ከማወከብ አልፎ አዲስ አበባ እንዳይገቡ  እስከማገት ተደርሷል፡፡ይህ ሁሉ ንቀት ነው ማናለብኝነት፡፡

ቢሆንም ግን ይህና መሰል የወያኔ አድራጎት  ምሬቱን አክፍቶትና ብሶቱን አብሶት ነገሮች እነርሱ ወደሚፈልጉት ለኢትዮጵያውያን ግን ወደማይበጅ  አቅጣጫ እንዳያመሩ ቁስለቱን ሁሉ ችሎ፣ ንቀቱን ታግሶ፣ ጥቃቱን ተቋቁሞ ከእነርሱ በላይ ማሰብን ይጠይቃል፡፡ የገበያ ግርግር ለሌባ ያመቻል አንዲሉ እነርሱ ተጠቃሚ የሚሆኑት ህዝብ ተፋቅሮ ተከባብሮ ሲኖር ሳይሆን ርስ በርሱ ሲጋጭ መተማመን አጥቶ የጎሪጥ ሲተያይ ወዘተ በመሆኑ ነገሮች ወደዛ እንዳያመሩ ብርቱ ጥንቃቄ ያሻል፡፡ከምንም በላይ ትግርኛ ተናጋሪውን ወገን ከሌላው ኢትዮጵያዊ አቆራርጠው የህውሀት ምርኮኛ ለማድረግ የሚዘሩት መርዝ ፍሬ እንዳያፈራ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ አማራ አንጂ ትግሬ አይደለሁም ድንበሬም ተከዜ ነው ማለት ራሱ የወያኔው ሕገ መንግሥት የሚደግፈው ጥያቄ በመሆኑ ነገሮች ወያኔዎች ወደሚጎትቱት አቅጣጫ ሳይሆን ህዝብ ወደሚፈልገው አቅጣጫ እንዲያመሩና ዘላቂ ሰላም ሊያስገኙ በሚያስችል መልኩ መፍትሄ አንዲያገኙ ቆራጥና የሰከነ ትግል ማካሄድ የግድ ይላል፡፡ አለበለዚያ ዳሩ ካልተከበረ መሀሉ ዳር ይሆናል እንደሚባለው የወልይት ጎንደሬነት ታሪክ ሆኖ ይቀራል፡፡ አለያም ግዜ እየጠበቀ የሚፈነዳ ፈንጅ ይሆናል፡፡

የወልቃይትን አማራነትና የድንበሩንም ተከዜነት ለማረጋገጥ የሚካሄደው ትግል ከወያኔ ጋር ብቻ አይደለም፡፡ ኦህዴድ በአዲስ አበባው ማስተር ፕላን እንደተፈተነው ሁሉ ብአዴንም በዚህ ወሳኝና ወቅታዊ ጉዳይ መፈተን አለበት፡፡ ወልቃይት አማራ ነው ትግሬ ፤  ከጎንደርና ከወሎ ወደ ትግራይ የሄደው መሬት ቋንቋን መሰረት ባደረገው የፌዴራሊዝም አከላለል ነው ወይንስ ከጥንትም የትግራይ መሬት በመሆኑ ነው፡ ለሱዳን የሚሰጠው መሬት የኢትዮጵያ ነው  ወይንስ አቶ ኃይለማሪያም እንዳሉት የጎንደር ሽፍቶች በኃይል የያዙት የሱዳን መሬት ነው፡፡  ከብአዴኖች መልስ የሚሻ ጥያቄ ፡፡

The post እውን ወልቃይት ትግሬ ነው !! – ይገረም አለሙ appeared first on Zehabesha Amharic.

የዓለማችን ትልቁ ስጋት ዚካ ቫይረስ –ሊያደምጡት የሚገባ ጠቃሚ መረጃ |በቴክሳስም ተገኘ

$
0
0

ከ3ሺ በላይ ሰዎች በብራዚል ተይዘዋል:: ይህ በሽታ ለመጀመሪያ ጊዜ በቴክሳስ በአንድ ሰው መገኘቱን ሲኤን ኤን ትናንት አረጋግቷል:: ለመሆኑ ይህ የዓለማችን ትልቁ ስጋት የሆነው ዚካ ቫይረስ ምንድን ነው? ከየት መጣ? የታምሩ ገዳን ዘገባ ያድምጡት::

የዓለማችን ትልቁ ስጋት ዚካ ቫይረስ – ሊያደምጡት የሚገባ ጠቃሚ መረጃ

The post የዓለማችን ትልቁ ስጋት ዚካ ቫይረስ – ሊያደምጡት የሚገባ ጠቃሚ መረጃ | በቴክሳስም ተገኘ appeared first on Zehabesha Amharic.

“ሁላችን ያለ  ልዩነት በአንድ ላይ አገራችን ኢትዮጵያን ነጻ ለማውጣት ካልታገልን ግድያው ተራ በተራ ይቀጥላል”   ኢ/ር ኦዶል ኦጁሉ በወቅታዊው የጋምቤላ ጉዳይ ይናገራሉ

$
0
0

ኢ/ር ኦዶል ኦጁሉ በቅርቡ የተቋቋመው የታህሳስ ሶስት መታሰቢያ ዴሞክራሲአዊ እንቅስቃሴ ናቸው:፡ በሰሞኑ ከ30 በላይ ኢትዮጵአውአን የአኙዋክ ብሄር ተወላጆች ላኢ እየተፈጸመ አለው የዘር በስልታን ላይ ባለው አገዛዝ ሆን ብሎ ከጀርባ ያቀነባበረው ድርጊት እንጂ የአኙዋክና የኑዌር ጎሳ ግጭት አይደለም ይላሉ። ኑዌሮችን አስታጥቆ ጭፍጨፋ ሲካሄድ ቆመ ወታደሮቹ የሚያዩት ለምንድነው፡ በእነዚህና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ አናግረናቸዋል።

Hiber_radio_interview_cover_020216

The post “ሁላችን ያለ  ልዩነት በአንድ ላይ አገራችን ኢትዮጵያን ነጻ ለማውጣት ካልታገልን ግድያው ተራ በተራ ይቀጥላል”   ኢ/ር ኦዶል ኦጁሉ በወቅታዊው የጋምቤላ ጉዳይ ይናገራሉ appeared first on Zehabesha Amharic.

Health: ከማህፀን ውጭ የሚፈጠር እርግዝና (Ectopic Pregnancy) |በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር

$
0
0

Dr Honilet
ከማህፀን ውጭ የሚፈጠር እርግዝና በአብዛኛው የሚከሰተው እንቁላልን ከእንቁላል ማቀፊያ ወይም እንቁልጢ ወደ ማህፀን በሚወስደው ቱቦ (Fallopian tubes) ውስጥ ነው፡፡
ከዚህ በተጨማሪ የማህፀን ውጭ እርግዝና በሆድ ውስጥ፤ በእንቁላል ማቀፊያ ከረጢት (እንቁልጢ) እና በማህፀን አንገት ላይም ሊከሰት ይችላል፡፡
ከማህፀን ውጭ ሚፈጠር እርግዝና በአፋጣኝ ሕክምና ካልተደረገለት ከፍተኛ ለሆነ እና ሕይወትን አደጋ ላይ ሊጥል የሚችል የደም መፍሰስን ያስከትላል፡፡
✔ ለሕመሙ ተጋላጭነት የሚዳርጉ ሁኔታዎች
• ከዚህ ቀደም የተከሰተ ከማህፀን ውጭ እርግዝና
• ኢንፌክሽን፡- በማህፀን ቱቦዎች ላይ የሚከሰት ኢንፌክሽን በአብዛኛው በአባላዘር በሽታዎች ምክንያት የሚመጡ ናቸው፡፡
• ተፈጥሮአዊ የማህፀን ቱቦ አቀማመጥ ወይንም በቀዶ ጥገና ጊዜ የሚደርስ የቱቦ ጉዳት
✔ የሕመሙ ምልክቶች
• በመጀመሪያ ሕመሙ ምንም ዓይነት ምልክት ላያሳይ ይችላል ወይንም ደግሞ ከማህፀን ውስጥ ካለ እርግዝና ጋር ተመሳሳይነት ያለው ሊሆን ይችላል፡፡
ይህም፡-
• የወር አበባ አለማየት
• የጡት ሕመም
• ማቅለሽለሽ እና እርግዝና ምርመራ ላይ እርግዝና እንዳለ የሚጠቁም ውጤት ናቸው፡፡
✔ በቀጣይነት የሚከሰቱ ምልክቶች
• የሆድ ሕመም
• ቀላል የሆነ ደም በማህፀን መፍሰስ
• እርግዝናው በእንቁላል ማስተላለፊያ ቱቦ ውስጥ ከተፈጠረ እና ቱቦው እንዲቀደድ ካደረገ ለከፍተኛ የደም መፍሰስ ስለሚያጋልጥም ራስን እስከመሳት ሊያደርስ ይችላል፡፡
• ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች በሚያጋጥምዎ ጊዜ ወደ ሕክምና ቦታ መሄድ ያስፈልጋል፡፡ በሕክምና ቦታም ከማህፀን ውጭ ያለ እርግዝና መፈጠሩን ለማረጋገጥ የደም ምርመራዎችና የአልትራ ሳውንድ ምርመራ እንዲያደርጉ ይጠየቃሉ፡፡
• አንዳንዴም እርግዝናውን በአልትራሳውንድ ለማየት የማይቻልበት ጊዜ ላይ ከሆነ በሐኪም ጥብቅ ክትትል እየተደረገ እና የደም ምርመራዎች እየተደረጉ በአልትራ ሳውንድ እስኪረጋገጥ ድረስ ይጠበቃል፡፡
• ከማህፀን ውጭ በተፈጠረ እርግዝና ምክንያት ከፍተኛ የደም መፍሰስ ከተከሰተ ግን በአፋጣኝ የቀዶ ጥገና ሕክምና ሊደረግ ይገባል፡፡
✔ ህመሙን እንዴት መከላከል ይቻላል?
• ከማህፀን ውጭ የሚከሰትን እርግዝና መከላከል ባይቻልም ተጋላጭነት የሚጨምሩ ሁኔታዎችን ማስወገድ ግን ይቻላል፡፡ ለምሳሌ አንድ ለአንድ በመወሰን እንዲሁም በግብረ ሥጋ ግንኙነት ጊዜ ኮንዶምን በመጠቀም ከአባላዘር በሽታዎች እራስን መከላከል ይቻላል፡፡
• ከዚህ ቀደም ከማህፀን ውጭ እርግዝና ካጋጠመዎ ከቀጣይ እርግዝና በፊት ሐኪምዎን ማማከር ከእርግዝና በኋላም ቢሆን ሐኪምዎ ጋር ክትትል ማድረግ ተገቢ ነው፡፡
• ወዲያውኑ የሚደረጉ የደም ምርመራዎችና የአልትራ ሳውንድ ምርመራ የእርግዝናውን ሁኔታ ስለሚያሳውቁ ወደ ሕክምና ተቋም በመሄድ ምርመራውን ማድረግ ተገቢ ነው፡፡
ጤና ይስጥልኝ

The post Health: ከማህፀን ውጭ የሚፈጠር እርግዝና (Ectopic Pregnancy) | በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር appeared first on Zehabesha Amharic.


በነሃብታሙ ጉዳይ ሰበር ችሎት የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዉሳኔ የሕግ ስህተት አለበት አለ

$
0
0

habitamuትላንት ጥር 24 ቀን 2008 ዓ.ም፣ እነ ሃብታሙ አያሌው፣  በሁለት ፍርድ ቤቶች ፣ በጠቅላይ ፍርድ ቤት እነ ከዚያ በላይ በሆነው በሰበር ችሎት ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር።

የአንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት ፣ አቃቢ “ሽብርተኞች ናቸው” በሚል ላቀረበው ክስ በቂ መረጃ አላቀረበም በሚል መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ እንዲለቀቁ ቢወሰንም፣ ማረሚያ ቤቱ የፍርድ ቤትን ትእዛዝ በመናቅ እስረኞች ሳይፈታ መቆየቱ ይታወሳል። ቀናቶች ካለፉ በኋላ፣ አቃቢ ሕግ ለጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ይግባኝ በማለቱ፣ የአንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት የወሰነዉን ዉሳኔ ታግዶ፣ እነ ሃብታሙ በወህኒ እንዲቆዩ ተደርጓል።

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ፣ የታችኛውን ፍርድ ቤት ውሳኔ ማገዱን በመቃወም፣  ለሰበር ፍርድ ቤት በቀረበው ክስ መሰረት፣ ለሶስት ወራት ጉዳዩ ከታየ በኋላ፣ ሰበር ፍርድ ቤቱ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዉሳኔ መሰረታዉ የሕግ ጥሰት እንዳለበት ያረጋገጠ ሲሆን፣ ጉዳዩን ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ እንዲመለከተው  ወደዚያ አስተላልፎታል።

በሌላ በኩል በጠቅላይ ፍርድ ቤት ፣ ከአሥራ አምስት ቀናት በፊት፣ አቃቢ ሕግ እነ ሃብታሙ አያሌዉን ለመክሰስ ያቀረበዉን የኦዲዮ መረጃዎች ይዞ እንዲያቀርብ ተጠይቆ፣   አቃቢ ሕግም  15 ቀናት  ይሰጠኝ ባለው መሰረት፣ ለዛሬ ጥር 24 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረ ቢሆን፣  አቃቤ የተጠየቀዉን ማስረጃ ሳያቀርብ ቀርቷል።

ፍርድ ቤቱ  ለሚቀጥለው ሳምንት መረጃው እንዲቀርብ ያዘዘ ሲሆን፣  በዚያን ጊዜ መረጃው ካልቀረበ፣  ዉሳኔ እንደሚወስኑ በመግልጽ ተለዋጭ ቀጠሮ ለየካቲት አንድ ቀን ተሰጥቷል።

በሁለቱም ፍርድ ቤቶች የነበረዉን ሁኔታ የአሜሪካ ድምጽ ዘጋቢ መለስካቸው አመሐ እንደሚከትለው አቅርቦታል፡

 

The post በነሃብታሙ ጉዳይ ሰበር ችሎት የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዉሳኔ የሕግ ስህተት አለበት አለ appeared first on Zehabesha Amharic.

ማኅበረ ቅዱሳን ለፓትሪያርኩ ደብዳቤ ጻፈ |“የፓትርያርኩ መመሪያ የእውነት ጠብታ የለበትም”

$
0
0

§ ቅዱስ ሲኖዶስ እርምት እና አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጥበት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱን ተማፅኗል

§ ከአስተዳደር በደል እና ከዝርፊያ የተነሣ የቤተ ክርስቲያኒቱ ወቅታዊ ሁኔታ እንዳሰጋው ገልጧል

§ አግባብነቱን የጠበቀ ወቅታዊ እርምትና መተማመኛ ያለው አሠራር ተግባራዊ እንዲኾን ጠይቋል

በአዲስ አበባ ዛሬ ታትሞ የወጣው ሰንደቅ ጋዜጣ እንደዘገበው:-

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አባ ማትያስ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ መንፈሳዊ ኮሌጆች በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የማያቋርጥ ትግል እንዲያካሒዱ በደብዳቤ ላስተላለፉት ክሥ እና ወቀሳ አዘል መመሪያ ማኅበሩ የጽሑፍ ምላሽ ሰጠ።

mahibere-kidusan-logo

የማኅበሩ ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ፥ በኮሌጆቹ ውስጥ በስውር የሚካሔደው “የተሐድሶ መናፍቃን” እንቅስቃሴ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን በመጥቀስ ያቀረበውን ተከታታይ ዘገባ ተከትሎ ፓትርያርኩ ባለፈው ሳምንት ሰኞ ለቅድስት ሥላሴ፣ ለሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ እና ለቅዱስ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጆች በአድራሻ በጻፉት ደብዳቤ፥ ማኅበሩ የቅዱስ ሲኖዶስን ሥልጣን በመጋፋት በቤተ ክርስቲያንና በት/ቤቶቿ ላይ የጥፋት ጣቶቹን መቀሰሩን በመግለጽ ለሕግ ተገዥ እስኪሆን ድረስ እንዲታገሉት ኮሌጆቹን አሳስበዋል።

ክሡን በግልባጭ እንኳ እንዲያውቀው አለመደረጉንና የደብዳቤው ዓላማና ተልእኮው ምን እንደሆነ ለመገመት መቸገሩን የገለጸው ማኅበረ ቅዱሳን በበኩሉ፤ ፓትርያርኩ ያስተላለፉት መመሪያ ፍጹም እውነትነት በሌለው መረጃ ላይ የተመረኮዘና ማኅበሩን የማይገልጽ እንደኾነ በመጥቀስ ዝርዝር የጽሑፍ ምላሽ ሰጥቷል። በዘገባው በተነሡት ሐሳቦችና ስለማኅበሩ አሠራር መወያየት አስፈላጊ ሲሆንም መገሠጽ እየተቻለ ሰዎችን በሚያስቆጡ ቃላት መሸንቆጥ የምእመናኑን ትዕግሥት እየተፈታተነ እንዳለ በምላሹ ተገልጧል።

ማኅበሩ፥ ጥር 24 ቀን 2008 ዓ.ም. በቁጥር ማቅሥአመ/239/02/ለ/08 ለፓትርያርኩ፣ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት እና ለብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በአድራሻ በጻፈውና ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱና ለተለያዩ መንግሥታዊ አካላት ደግሞ በግልባጭ ባሳወቀው ደብዳቤ፤ አባታዊ መመሪያና ቡራኬ ለመቀበል፣ በሚነሡበትም ክፉ ጉዳዮች ለመወያየት በአካል በመቅረብ፣ ለስድስት ጊዜያት ደብዳቤ በመጻፍ እንዲሁም ብፁዓን አባቶችን ጨምሮ በተለያዩ አካላት በኩል ፓትርያርኩን ለማነጋገር ቢጠይቅም ጊዜ ሰጥተው ሊያወያዩት እንዳልቻሉ አውስቷል።

abune matias

በአንጻሩ ማኅበሩን በመክሰስ ለሚቀርቡ የተለያዩ አካላት ፓትርያርኩ ጊዜ እየሰጡ እንደሚያነጋግሩ የጠቀሰው ደብዳቤው፣ “ለአንድም ቀን እንኳን በተከሰስንበት ጉዳይ ቀርበን ቃላችንን እንድንሰጥ አለማድረግዎ አስደንቆናል፤” ብሏል። “የተሐድሶ እምነት አራማጆች” በሚያዘጋጇቸውና በሚመሯቸው ድረ ገጾችና ብሎጎች ማኅበሩን ለመክሰስ የሚያወጧቸው ሐሳቦች በፓትርያርኩ መመሪያም ተጠቅሰው መታየታቸው እንዳሳዘነውና እንዳስገረመው ማኅበሩ ገልጾ፣ ከሳሾች ባቀረቡት ቃል ላይ ብቻ ተመሥርቶ ፍርድ መስጠት እውነተኛውን ሕግ በምትተረጉመው ቤተ ክርስቲያናችን ፍጹም እንግዳ ሥርዓት እንደኾነ ተችቷል፤ እውነታውን ለማወቅና ለሚነሡ ችግሮች መፍትሔ ለመስጠት የጉዳዩን ባለቤቶች ጠርቶ ፊት ለፊት በማነጋገርና በመመካከር መፍታት እንጂ አንድ ጩኸት በተሰማ ቁጥር ደብዳቤ መጻፉ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እንደማይበጅ ማኅበሩ አስገንዝቧል። (የማኅበረ ቅዱሳን ደብዳቤ ሙሉ ቃል ከዚህ በታች ተያይዟል)

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ቁጥር ማቅሥአመ/239/02/08

ቀን 24/05/2008

ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ

ፓትርያርክ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም፣

ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

አዲስ አበባ ፤ ኢትዮጵያ

ለብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በሙሉ

በያላችሁበት

ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት

አዲስ አበባ ፤ ኢትዮጵያ

ጉዳዩ፡- በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ስለተጻፈና የተሳሳተ መረጃ

የያዘ ደብዳቤን ይመለከታል

ቅዱስ አባታችን ሆይ፡-

በደብዳቤ ቁጥር ል/ጽ/179/338/2008 ጥር 16 ቀን 2008 ዓ.ም ከቅዱስነትዎ የተጻፈና ለቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ፣ ለሰዋሰወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ እና ለቅዱስ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ በአድራሻ የተጻፈ፤ ማኅበረ ቅዱሳንን አስመልክቶ ፍጹም እውነትነት የሌለው መረጃ ላይ በመመርኮዝ መመሪያ ያስተላለፉ መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ በተለያዩ ሚዲያዎች ተሰራጭቶ ተመልክተናል። ይህም ጉዳይ እኛን የቤተ ክርስቲያን አካል የሆንን ልጆችዎን እጅግ አሳዝኖናል። የደብዳቤው ዓላማና ተልእኮም ምን እንደሆነ ለመገመት አስቸግሮናል። ምንም እንኳ በደብዳቤው የሰፈረው ሃሳብ ፍጹም እኛን የማይገልጸን ቢሆንም ስለተከሰስንበት ጉዳይ በግልባጭ እንኳ እኛ እንድናውቀው አልተደረገም። ይሁንና እንደ ቤተ ክርስቲያን ልጅነታችን ካሁን ቀደም በተደጋጋሚ እንዳደረግነው እውነቱን ለማስገንዘብ አሁንም ይህንን ደብዳቤ ለመጻፍ ተገደናል።

ማኅበረ ቅዱሳን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ስር ሕጋዊ በሆነ ሥርዓት፣ በቅዱስ ሲኖዶስ ሙሉ ዕውቅናና ፈቃድ ተዋቅሮ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ እነሆ 23 ዓመታትን አሳልፏል። ማኅበሩ የሚመራበትና የሚተዳደርበት ደንብም በመጀመሪያ በማደራጃ መምሪያው በኩል በኋላም በ1992 ዓ.ም በቅዱስ ፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት በኩል በዝርዝር የሚያጠኑ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሚመሩት ኮሚቴ ታይቶና ተመርምሮ የጸደቀለት እንዲሁም በ1994 ዓ.ም በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ደረጃ ቀርቦ የታየ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሚመሩት፣ የተለያዩ የቤተ ክርስቲያናችን ሊቃውንት እና የሕግ ባለሙያዎች የተሳተፉበትና ከ6 ወራት በላይ የፈጀ ጥናት የተደረገበት የማኅበሩ መተዳደሪያ ደንብ እንደገና ታይቶና ተፈትሾ በምልዓተ ጉባኤው የጸደቀና ሁሉም ሊቃነ ጳጳሳት ፊርማቸውን ያስቀመጡበት መሆኑን ቅዱስነትዎ ጠንቅቀው ያውቁታል ብለን እናምናለን። ይህንንም ማድረጋቸው ብፁዓን አባቶቻችን ዘመኑን በመዋጀት በዘመናዊ ትምህርት የሚመረቁ ወጣቶች በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማድረግ አርቀው በማሰባቸው ነው። እውነታው ይኽ ሆኖ ሳለ በደብዳቤዎ ላይ ማኅበሩን «ጥቅሙና ጉዳቱ በሚገባ ሳይጠና ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንጻር የሚያስከትለው የሃይማኖትና የሥርዓት ተፋልሶ ሳይፈተሽ በአንድ ወቅት ራሱ አርቅቆና አዘጋጅቶ ባቀረበው ደምብ በቅዱስ ሲኖዶስ የተፈቀደልኝ ሕጋዊ ማኅበር ነኝ ይላል$ በማለት መግለጽዎ ለምን እንደሆነ አልገባንም። ይህ ሀሳብም ከቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔና አሠራር የተቃረነ ሆኖ አግኝተነዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በ2004 ዓ.ም የማኅበሩ አገልግሎት እየሰፋ በመሄዱ እና በወቅቱ ከሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ኃላፊዎች ጋር የነበረውን አለመግባባት ቅዱስ ሲኖዶስ በምልዓተ ጉባኤ ደረጃ በአጽንኦት ከተመለከተ በኋላ ለጊዜው የማኅበሩ ተጠሪነት ለብፁዕ ዋና ሥራ አሥኪያጅ እንዲሆንና ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ ይቻል ዘንድ እና ማኅበሩን ከነበረበት ደረጃ የበለጠ ሊያሠራው የሚችል ደንብ እንዲኖረው በማሰብ ቅዱስ ሲኖዶስ እርስዎም በተገኙበት ጉባኤ ደንቡን የሚያሻሽል (የጉዳዩ ባለቤት የሆኑ የማኅበሩ አባላትም የተካተቱበት) ኮሚቴ መሰየሙ ይታወሳል። ይኸው ማሻሻያ ተሠርቶ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ ግን ማኅበሩ በ1994 ዓ.ም ጸድቆ የተሰጠው መተዳደሪያ ደንብ ሕጋዊ ሆኖ እንደሚቀጥልም አጽንኦት ተሰጥቶበት መታለፉ ግልጽ ነው። ቅዱስነትዎ በመንበሩ ከተሰየሙ በኋላም ይኽው አጥኚ ኮሚቴ ሥራውን አጠናቅቆ ቢያቀርብም ቅዱስነትዎ በተደጋጋሚ አልቀበልም በማለትዎ መዘግየቱን የሚዘነጉት አይመስለንም። እንዲያውም ከዚህ አንፃር በርስዎ በኩል የቀረበ እና በየትኛውም አሠራር ቢሆን እንግዳ የሆነ ውሳኔን ማኅበሩ ይሁን ብሎ ተቀብሎታል። ይኸውም በመንግሥታትም አሠራር ቢሆን አንድ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሊሰጥ የሚደራጅን ማኅበር ሊያገለግልበት የፈለገበትን አቅጣጫና የሚመራበትን ውስጠ ደንብ ከተቋሙ ሕግ አንፃር አርቅቆ በማቅረብ በፈቃድ ሰጪው አካል ያስጸድቃል እንጂ ፈቃድ ሰጪው አካል ራሱ ሕገ ደንብ አርቅቄ ካልሰጠኹህ አይልም። ሆኖም ግን ቀደም ሲል ቅዱስ ሲኖዶስ የሰየመውና በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት መሪነት ከአንድ ዓመት በላይ የደንብ ማሻሻያውን ጥናት ሲሠራ የቆየው ኮሚቴ ያዘጋጀውን ጥናት አልቀበልም ብለው እንግዳ በሆነ መልኩ አንድም የማኅበረ ቅዱሳን ተወካይ የሌለበት ሌላ አዲስ ኮሚቴ እንዲቋቋም መደረጉን ሲሰማ ማኅበሩ በይሁንታ ነው የተቀበለው። ይህንንም ያደረግንበት ምክንያት በብፁዓን አባቶቻችን ላይ ካለን አመኔታና ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ታዛዥ ከመሆናችን የተነሣ ነው። ይሁንና ቅዱስነትዎ ይህንን በአዲስ መልክ የተቋቋመውን ኮሚቴ አባላቱ እነማን እንደሆኑ እንኳ ለኛ ባላሳወቁበት ሁኔታ “በቅዱስ ሲኖዶስ የተወሰነውን የደንብ ማርቀቅ ሥራ ሆን ብሎ በማሰናከል ያለ ደንብ እየሠራ ይገኛል” በማለት በደብዳቤዎ ላይ ማስቀመጥዎ እጅግ አስገራሚ ነው።

ይህ ሁሉ ቢሆንም ማኅበረ ቅዱሳን በአባቶች ምክር፣ ጸሎት እና ድጋፍ ምንም ዓይነት የሕግም ሆነ የሥርዓት ተፋልሶ ሳያስከትል ለአባቶች እየታዘዘ አሁንም አገልግሎቱን ግልጽ በሆነ አሠራር እያከናወነ ይገኛል። ከእርስዎ ከቅዱስ አባታችንም ዘንድ ቀርበን አባታዊ ቡራኬና መመሪያ ለመቀበል፣ እንዲሁም አንዳንድ ለቤተ ክርስቲያናችን ቅን የማያስቡ ወገኖች የማኅበሩን ስም በክፉ ባነሱበት ጊዜ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በተደጋጋሚ ከእርስዎ ጋር ለመወያየት በአካልም እየቀረብን በደብዳቤም ከስድስት ጊዜ በላይ (በቁጥር ማቅሥአመ/80/02/ለ/06 ቀን 21/1/06 ዓ.ም፣ በቁጥር ማቅሥአመ /118/02/ለ/06 ቀን 9/5/06 ዓ.ም፣ በቁጥር ማቅሥአመ/127/02/ለ/06 ቀን 25/6/06 ዓ.ም፣ በቁጥር ማቅሥአመ /138/02/ለ/06 ቀን 24/8/06 ዓ.ም፣ በቁጥር ማቅሥአመ/165/02/ለ/07 ቀን 01/02/07 ዓ.ም፣ በቁጥር ማቅሥአመ /212/02/ለ/07 ቀን 3/13/07 ዓ.ም) ለቅዱስነትዎ በቀጥታ ጽፈን መጠየቃችን ይታወሳል። ከዚህም በተጨማሪ ከብፁዓን አባቶች ጀምሮ የተለያዩ አካላትንና ግለሰቦችን ከርስዎ ጋር እንዲያወያዩን በተደጋጋሚ ጠይቀን ነበር። ነገር ግን እርስዎ ጊዜ ሰጥተው ሊያነግግሩን አልቻሉም። በአንጻሩ ማኅበሩን ከቅዱስነትዎ ዘንድ ከስሰው የሚቀርቡ የተለያዩ አካላትን ጊዜ እየሰጡ ማነጋገርዎ ብቻ ሳይሆን አንድ ቀን እንኳን በተከሰስንበት ጉዳይ ቀርበን ቃላችንን እንድንሰጥ እንኳ አለማድረግዎ አስደንቆናል። ክስ የቀረበበትን አካል አቅርበው ሳይጠይቁ ከርሱም ሳይሰሙ ከሳሾች ባቀረቡት ቃል ላይ ብቻ ተመስርቶ ፍርድ መስጠት በማንኛውም አካል ዘንድ በተለይም እውነተኛውን ሕግ በምትተረጉመው ቤተ ክርስቲያናችን ፍጹም እንግዳ የሆነ ሥርዓት ነው።

ቅዱስ አባታችን ሆይ፡-

የቤተ ክርስቲያንን ልዕልና የሚያስጠብቀው ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅምት 2007 ዓ.ም ባደረገው ጉባኤ ከተወያየባቸው ጉዳዮች መካከል ተሐድሶን በተመለከተ በቃለ ጉባኤው ያሰፈረው እንደሚከተለው ይነበባል “… የተሐድሶ መናፍቃን መገኛ ምንጫቸው ከየት እንደሆነ ጉባኤው በመወያየት ደቀ መዛሙርቱ ከየአኅጉረ ስብከቱ ሲላኩ ጤናማ እንደሆኑ ነገር ግን ተመርቀው ሲመለሱ ግን ከነችግራቸው ሌላ ሰው ሆነውና መስለው ይመለሳሉ። ለዚህ የችግሩ ምንጮች ኮሌጆቹ እንደሆኑ ያመለክታል። ምክንያቱም መንፈሳዊ ኮሌጆች ተልከው መናፍቃን ሆነው ሲመለሱ እያንዳንዱን ኮሌጅ ጥርጣሬ ውስጥ ያስገባዋል። ስለዚህ ሁሉም ኮሌጆች ሊፈተሹና ሊመረመሩ ይገባል …“ ካለ በኋላ ቃለ ጉባኤው የሚከተለው ውሳኔ መተላለፉን ይገልጻል። “… የመምህራን ክህሎት እና የሃይማኖታቸው ጉዳይ፣ የኮሌጆች የትምህርት ካሪኩለም አቀራረጽ፣ የመማሪያ መጻሕፍት ዝግጅት ምን እንደሚመስል ታይተውና ተፈትሸው ሊሠራባቸው ይገባል” የሚል ውሳኔ ማስተላለፉና ይህንንም የሚያጠና አንድ ኮሚቴ ማቋቋሙ ይታወቃል። ይህንን ውሳኔ ለተቋቋመው ኮሚቴ ለማሳወቅ ቅዱስነትዎ ኅዳር 4 እና 11 ቀን 2007 ዓ.ም በጻፏቸው ደብዳቤዎች ላይ “መናፍቃንና የተሐድሶ አራማጆች በቤተ ክርስቲያናችን ኮሌጆች ተምረው ስውር ዓላማቸውን በማካሄድ ሕዝበ ክርስቲያኑን በመከፋፈል ላይ ስለሚገኙ ከኮሌጆቻችን ጀምሮ … በማስረጃ የተደገፈ ጥናት እንድታቀርቡ” በሚል አጽንኦት ሰጥተው መግለጽዎ ይታወሳል። ከዚህ በተጨማሪ ባለፉት ሁለት ዓመታት በተደረጉት የሰበካ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ ከተለያዩ አኅጉረ ስብከት የቀረቡ ሪፖርቶችና አስተያየቶች ከየመንፈሳዊ ኮሌጆች የተመረቁ አንዳንድ መምህራን የተሐድሶ መንፈስ እያራመዱ እንዳስቸገሯቸውና የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ማወካቸውን በግልጽ ማቅረባቸው፣ እነዚህም ሀሳቦች በጉባኤዎቹ ሲቀርቡ በተሰብሳቢዎቹ ከፍተኛ ድጋፍ ሲሰጣቸው እንደነበር ይታወሳል።

የማኅበረ ቅዱሳን ሚዲያ የሆነችው ስምዐ ጽድቅ ዘኦርቶዶክስ ጋዜጣም ይህንን የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔና የአኅጉረ ስብከት ሪፖርቶች መነሻ በማድረግ ከመስከረም ወር 2008 ዓ.ም ጀምሮ በተከታታይ ንቁ በሚለው አምዷ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ መልኩን እየቀያየረ እና በረቀቀ መልኩ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕልውና አደጋ ውስጥ እየከተተ የመጣውን የተሐድሶ መናፍቃኑን አጠቃላይ የኅቡዕ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ዘገባ እየሠራች መረጃ መስጠት ቀጥላለች። በተለይም በኅዳር እና በታኅሣሥ አጋማሽ እትሞቿ ተሐድሶዎች ቤተ ክርስቲያናችን በምትመካባቸው መንፈሳዊ ኮሌጆቻችን ውስጥ በስውር ምን እያደረጉ እንደሆነ እና ለነርሱም መግቢያ ቀዳዳ ሊሆኑ የሚችሉ ጉዳዮችን በማሳያነት በመጥቀስ ዘገባ ማቅረቧ እውነት ነው። ለዚህም ዘገባ የተለያዩ አካላት ያወጧቸውን ሪፖርቶች ጋዜጠኛው ወይም ጸሐፊው በመጠቀም በኮሌጆቹ አካባቢ የተሐድሶ መናፍቃንን እንቅስቃሴ የሚያመላክት የዳሰሳ ጥናት ማድረጉ ተገልጿል። በንጹሕ ስንዴ መካከል እንክርዳድ መገኘቱ ፍጹም እንግዳ ባይሆንም ቁጥሩ እየጨመረ መምጣቱ ግን አሳሳቢ መሆኑ በጽሑፉ ተዳስሷል። በሌላ መልኩ ደግሞ ቤተ ክርስቲያናችን እጅግ የምትኮራባቸው መምህራንና ሊቃውንት ከነዚሁ ኮሌጆች በብዛት መገኘታቸውን እና የየኮሌጆቹ የሥራ ኃላፊዎችም ሆኑ እውነተኞቹ ደቀ መዛሙርት ይህንን የተሐድሶዎችን እንቅስቃሴ ተረድተው ምን ዓይነት ተጋድሎ እያደረጉ መሆኑን፣ ችግሩ ግን ሰፊ ሆኖ ከዐቅማቸው በላይ እንዳይሆን የሁሉም የቤተ ክርስቲያን አካላት የነቃ ተሳትፎና ርብርብ እንደሚያስፈልግ በጋዜጣዋ በሰፊው ታትቶ ቀርቧል። ማኅበረ ቅዱሳንም ችግሩን በአጠቃላይ አሠራር ደረጃ እንዲፈታ ማድረግ ላይ ማተኮር እንጂ በቤተ ክርስቲያናችን የሚመለከተው አካል ውሳኔ ሳይሰጥባቸው አንዳንድ የችግሩ መገለጫ የሆኑ ግለሰቦችን በስም እየጠቀሱ በጋዜጣ የማውጣት ዓላማ የለውም።

ሆኖም ግን ይኸው መረጃ በይፋ መውጣቱና ጉዳዩም ከቅዱስ ሲኖዶስ ጀምሮ በየደረጃው ባሉ እውነተኛ የቤተ ክርስቲያናችን አካላት ሁሉ ዘንድ ትኩረት በማግኘቱ የተደናገጡት የተሐድሶ እምነት አራማጆች የሰርጎ ገብ እንቅስቃሴያቸው እንዳይገታባቸው ማዘናጊያ መፍጠር ነበረባቸው። ለዚህም እንዲረዳቸው ማኅበረ ቅዱሳን በስምዐ ጽድቅ ዘኦርቶዶክስ ጋዜጣው “መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶቹን በጅምላ በሕፀፀ ሃይማኖት ከሰሰ” በማለት የጋዜጣዋን አንድ እትም አንጠልጥለው ከአንድ ወር በኋላ ወሬውን በአዲስ መልክ በየኮሌጆቹ አካባቢ በስፋት ማናፈስ ጀመሩ። ይህንን ወሬ የሰሙ አንዳንድ እውነተኛ ሰዎችም ሳይቀር ሙሉውን ተከታታይ ጽሑፍ ሳያነቡት ቅሬታ ተሰምቷቸው ቀርበው አነጋግረውናል ፤ አንዳንዶቹም የተወሰነውን ጥቅስ በማንሳት ለምን እንዲህ እንደተገለጸ እንድናብራራላቸው በደብዳቤ የጠየቁንም አሉ። ከእነዚህ ጋር ጥሩ ውይይት አድርገን መግባባት ላይ ደርሰናል። ነገር ግን ይህንን የተሐድሶዎቹን ድብቅ ዐላማ ያልተረዱ አካላት አንዳንድ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን ጭምር በማሳሳት የዚህ የስውር እንቅስቃሴያቸው ደጋፊ እንዲሆኑ አድርገዋቸዋል። እንግዲህ በዚህ ሁኔታ ከየኮሌጆቹ ከሚማሩ ደቀ መዛሙርት መካከል በውድም ሆነ በግድ እንዲፈርሙ ተደርገው ለቅዱስነትዎ የቀረበልዎትን የቅሬታ ጥያቄ ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነው ውሳኔ መሆኑ ተዘንግቶና የማኅበረ ቅዱሳን አንድ ተወካይ እንኳ ተገኝቶ ማብራሪያ እንዲሰጥ ሳይደረግ እንዲህ ዓይነት ብያኔ በርስዎ በቅዱስ አባታችን መሰጠቱ በከፍተኛ ሁኔታ አሳዝኖናል። ጥቂት የተሐድሶ እምነት አራማጆችን “በርቱ፣ ተቃውሟችሁንና ማደናገራችሁን ቀጥሉበት” የሚል የሚመስል መልእክት የያዘ ሐሳብ በቅዱስነትዎ ፊት መሰጠቱም እጅግ አስደንቆናል። እንደ እውነቱ ከሆነ በጋዜጣው ላይ የወጣው አጠቃላይ የጽሑፉ ጭብጥ ሲታይ ቅዱስ ሲኖዶስ ከወሰነው ውሳኔ የተለየ ስምዐ ጽድቅ የጻፈችው ምን አለ? በጥሞና ከታየ የቀረበውን መረጃ ወስዶ በቅዱስ ሲኖዶስ እንደገና የተቋቋመው ኮሚቴ እንዲያጠናው ማድረግ የሚገባ እንጂ ሊያስከስስም ሆነ እንዲህ ዓይነት ደብዳቤ ሊያስጽፍ የሚችል ነገር ለመኖሩ በፍጹም አልታየንም።

ቅዱስ አባታችን ሆይ፡-

የማኅበረ ቅዱሳን አደረጃጀት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚማሩ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን የመንፈሳዊ ትምህርት ሥርዓት ለመከታተል፣ አባላቱ በሙያቸውና በበጎ ፈቃዳቸው ለቤተ ክርስቲያን የሚሰጡትን የትሩፋት አገልግሎት ለማስተባበር ተብሎ በሀገረ ስብከትና በወረዳ ደረጃ ብቻ መዋቅር የተዘረጋለት መሆኑ ይታወቃል። በአጥቢያ ደረጃ ማኅበሩ ምንም ዓይነት ተቋማዊ አደረጃጀት እንደሌለውም የተገለጠ ነው። ይኽ አደረጃጀቱም በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ የተሰጠው መሆኑ ለሁሉም የቤተ ክርስቲያን አካላት ግልጽ ነው። ከዚህም በተጨማሪ የማኅበሩ አባላት በፍጹም ታዛዥነት ቀርበው በቤተ ክርስቲያን መዋቅር እየተመራንና ብፁዓን አበው መመሪያ እየሠጡን እንሥራ ብለው ወደ ቤተ ክርስቲያን ለበጎ ፈቃድ አገልግሎት መቅረባቸው የሚያስመሰግን እንጂ የሚያስወቅስ አልነበረም።

በቤተ ክርስቲያናችን የአገልግሎት ማኅበር ሲቋቋም ማኅበረ ቅዱሳን የመጀመሪያው አይደለም። ቤተ ክርስቲያን እውቅና ሰጥታቸው የተቋቋሙ፣ የራሳቸው ጠቅላላ ጉባኤ ፣ የራሳቸው ውስጠ ደንብ ፣ የራሳቸው አመራር ያላቸው ብዙ ማኅበራት በቤተ ክርስቲያናችን ነበሩ፤ አሁንም አሉ። ሆኖም ግን በእንዲህ ዓይነት መንገድ የተቋቋሙትና የቤተ ክርስቲያን የቅርብ ክትትል ያልተለያቸው ማኅበራት ለቤተ ክርስቲያን አንድነት ሲጠቅሙ እንጂ ጉዳት ሲያደርሱ ታይቶ አይታወቅም። በርግጥ ቤተ ክርስቲያን የማታውቀውና በቤተ ክርስቲያንም ሥርዓት የማይመራ ማኅበር ለቤተ ክርስቲያን ጠቃሚ ሊሆን እንደማይችል ግልጽ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለእምነታቸው ቀናዕያን የሆኑ አንዳንድ ወጣቶች በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ተሰባስበው ሃይማኖታቸውን ለመማር መነሳሳታቸው፣ በተማሩትም ትምህርት መሠረት ስለወንጌል መስፋፋት እገዛ ማድረግና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለመስጠት መጀመራቸው እንዳሻቸው መሆን ለለመዱት ተሐድሶዎች እና ጥቅመኞች ነገሩ ስላላማራቸው ‹‹ማኅበራት በሌላ ቦታ እንጂ በቤተ ክርስቲያን አመራር ሥር መዋቀራቸው ቀኖና የጣሰ ነው›› የሚል ሀሳብ ይዘው ብቅ አሉ። ይህ አባባል እንደ እውነታ ተወስዶ በእርስዎ ደብዳቤም መጻፉ ቅር የሚያሰኝ ነው። ለቤተ ክርስቲያናቸው ቀናዒ ሆነው የድርሻቸውን ለመወጣት የሚደራጁ ማኅበራት ለአንዲት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት መሳካት እስከሆነ ድረስ ማኅበረ ቅዱሳን ስለነዚህ ማኅበራት መደራጀት በጎ አመለካከት ቢኖረውም ማኅበረ ቅዱሳን ከራሱ ውጪ ለየትኛውም ማኅበር መቋቋምም ሆነ መክሰም ኃላፊነት የለበትም።

ማኅበረ ቅዱሳን ከቀድሞ ጀምሮ የዓመት ዕቅዱንና በየስድስት ወሩ ደግሞ የአፈጻጸም ሪፖርቱን ተጠሪ ለሆነለት አካል በጽሑፍ ሲያስገባ ቆይቷል። እንዲሁም የፋይናንስ (የገቢና የወጪ) አሠራሩን ዘመናዊ በሆነ መንገድ በመመዝገብ ገለልተኛ በሆኑና በመንግሥት በተፈቀደላቸው የውጭ ኦዲተሮች ጭምር በየዓመቱ እያስመረመረ ሪፖርቱን ለሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያናችን አካላት እያቀረበ መጓዙ ለማንም ግልጽ ነው። በ2007 ዓ.ም የጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ላይ ለቤተ ክርስቲያን ቁጥጥር የተሻለ እንዲሆን በቤተ ክርስቲያን ሥር የተቋቋሙ ማኅበራት ሁሉ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ተፈቅዶ በሚሰጣቸው የገቢና የወጪ ደረሰኝ እንዲጠቀሙ በተወሰነው መሠረት ማኅበረ ቅዱሳን የዚህ ውሳኔ አፈጻጸም ፋና ወጊ በመሆን ይህንኑ ካርኒ አሳትሞ መጠቀም መጀመሩ ይታወቃል። ይህንኑም በያዝነው ዓመት በቀረበው የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዓመታዊ ሪፖርት ላይ የቁጥጥር መምሪያውም ማረጋገጡን በግልጽ መስክሯል። ማኅበሩ የአገልግሎትና የፈቃድ ማኅበር እንደመሆኑ አባላቱ እንደየገቢያቸው መጠን የአባልነት አስተዋጽኦ ይከፍላሉ። የማኅበሩም ዋናውና ቋሚው የገቢ ምንጭ ይኸው በመሆኑ ማንኛውም የማኅበሩ የሥራ ማስኬጃ የሚሸፈነው በአባላቱ መዋጮ ነው። የማኅበሩ አመራር አባላትም አገልግሎታቸው የበጎ ፈቃድ በመሆኑ ጊዜአቸውን መስዋዕት አድርገው ከመስጠታቸው በተጨማሪ ለትራንስፖርትም ሆነ ሌሎች ወጫአቸውን ሁሉ የሚሸፍኑት ከኪሳቸው አውጥተው ነው። እንዲያውም ብዙ ጊዜ ለሥራ ማስኬጃ የሚሆን ገንዘብ ሲያነስ ተጨማሪ መዋጮ እንዲያዋጡ ኃላፊነት ይኖርባቸዋል። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ማኅበሩ በተለየ ሁኔታ ገንዘብ እየሰበሰበ ለማይታወቅ አገልግሎት ያውላል ተብሎ መገለጹ ፍጹም ከእውነት የራቀ ውንጀላ ከመሆኑም በላይ ከአንድ ቅዱስ አባት የማይጠበቅ በመሆኑ በእጅጉ ያሳዝናል።

ማኅበሩ በመተዳደሪያ ደንቡ ላይ በግልጽ በተፈቀደለት መሠረት አባላቱ ሙያቸውንና ዕውቀታቸውን አስተባብረው ገዳማትን በልማት ራሳቸውን እንዲችሉና የአብነት ትምህርት ቤቶች በደጋፊ ማጣት የትምህርት አሰጣጣቸው እንዳይስተጓጎልና እንዳይበተኑ ለማድረግ ፕሮጀክት ቀርፀው ለቤተ ክርስቲያናችን አባላት ለሆኑ በጎ አድራጊዎች በማኅበሩ በኩል ያቀርባሉ። ለፕሮጅክቱ የሚሆን ገንዘብም ሲገኝ ማኅበሩ በሥራ ላይ አውሎ ለሚመለከተው አካል (ለገዳማቱ ወይም ለአብነት ትምህርት ቤቱ ኃላፊዎች) ያስረክባል። ይህም የሚፈጸመው በቅድሚያ በገዳማቱ በደብዳቤ ሲጠየቅ ወይም በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ወይም በሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች ሲታዘዝ (ሲጠየቅ) ነው። የእነዚህ ፕሮጀክቶች አፈጻጸማቸውንም ሆነ የፋይናንስ አወጣጣቸውን የሚያሳየውን ሪፖርት በየጊዜው እየተዘጋጀ ገንዘቡን ላዋጡት ምእመናን (ወይም ማኅበራት) እንዲሁም ፕሮጀክቱ ለሚተገበርላቸው የቤተ ክርስቲያን አካላት የሚቀርብላቸው ሲሆን ይህም በየዓመቱ በውጭ ኦዲተሮች እየተመረመረ ሪፖርቱ ለሚመለከታቸው የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አካላት እየቀረበ ይገኛል። በመሆኑም አገልግሎቱ የየሀገረ ስብከቱ ሊቃነ ጳጳሳት የቅርብ ክትትል አይለየውም። እንግዲህ በዚህ አሠራር መጓዝ የትኛውን የቤተ ክርስቲያን ቀኖና እንደሚጥስ ለእኛ አልገባንም። እንዲሁም “ከቤተ ክርስቲያን የሚሰጠውን አመራር አይቀበልም፣ አባቶችን ይዳፈራል” ተብሎ በእርስዎ ደብዳቤ መገለጹ አግባብነት አለው ብለን አናምንም።

የማኅበሩ አባላት በአብዛኛው ወጣቶች የሆኑ የቤተ ክርስቲያናችን አማንያን ናቸው። ከነርሱ መካከልም የመንፈሳዊ አገልግሎት ዝንባሌ ያላቸው የአብነት ትምህርቱን ከትምህርታቸው ጎን ለጎን እየተማሩ፣ በየሊቃነ ጳጳሳቱ እየተፈተሹና መሥፈርቱን እያሟሉ ክህነት ይቀበላሉ። ቅዱስ አባታችን እርስዎም በአሜሪካ በነበሩ ጊዜ በዚሁ መንገድ ለአንዳንዶቹ ክህነት መስጠትዎን አይዘነጉትም። ይህ ደግሞ በሁሉም ብፁዓአን አባቶች የታወቀ ጉዳይ ሆኖ ሳለ በደብዳቤዎ ላይ “ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ውጪ … ለአባላቱ በጅምላ ክህነት እያሰጠ …” ብለው መግለጽዎ በምን ምክንያት እንደሆነ ግልጽ አይደለም። መቼም ክህነት የሚሰጠው በእናንተ በብፁዓን አባቶች እንጂ በሌላ አካል እንዳልሆነ ይታወቃል። ታዲያ በዚህ ጉዳይ ቀኖና ተጥሶስ ከሆነ የጣሰው ማን ነው ለማለት ነው; ምናልባት ካሁን ቀደም ብፁዓን አባቶችን ለማንቋሸሽ ሲባል አንዳንድ ሰዎች በየመድረኩ ሲናገሩት የነበረውን ድጋፍ ለመስጠት ታስቦ ካልሆነ በስተቀር ማኅበረ ቅዱሳን የሚከሰስበት አንዳች ምክንያት የለውም። ደግሞም አሁን ባለው ሁኔታ የዘመናዊውን ትምህርት መስፋፋት ተከትሎ ብዙ ብሩኅ አእምሮ ያላቸው ወጣቶች ከአብነት ትምህርቱና ከቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አገልግሎት ተለይተው እንዳይቀሩ መሥራት የቤተ ክርስቲያናችን ድርሻ ነው። በአሁኑ ሰዓትም በርከት ያሉ የአብነት ትምህርት የተማሩና በትምህርቱም የገፉ ወጣቶች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እየገቡ በመሆኑ ገና ብዙ አብነቱን እና የአስኳላውን ትምህርት ያጣመሩ ምሁራን ቤተ ክርስቲያናችን ይኖሯታል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። ይህም አርቆ ላሰበ ሰው ለቤተ ክርስቲያን አንድ ሰፊ የአገልግሎት አቅጣጫ ነው።

በውጭ ሀገር ስላለው የቤተ ክርስቲያን አገልግሎትም ምናልባት ያለፉት ሦስት ዓመታት አስረስተዎት ካልሆነ በቀር የማኅበሩ አባላት ስለቤተ ክርስቲያን አንድነት በሚያደርጉት ከፍተኛ ተጋድሎ እንደ ገና ዳቦ ከሁሉም አቅጣጫ እሳት እየነደደባቸው የሚታገሉ መሆኑን በየጊዜው ለቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ከውጪ ሀገር በመጡ ቁጥር ይመሰክሩት የነበረ ነው። በቅርቡም በአሜሪካ ሄደው በነበረ ጊዜ የተጋበዙባቸው አብያተ ክርስቲያናት እንዴት እዚያ ደረጃ እንደደረሱና ማን መሥዋዕትነት እንደከፈለባቸው፣ አሁንም ቢሆን በቅዱስነትዎ ጉዞ ወቅት ማን እንዳስከበርዎ ልቡናዎ ያውቀዋል። ከዚህም በላይ በሀገር ውስጥ ለተለያዩ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎቶች በሚዘዋወሩበት ጊዜ በየቦታው በደመቁ ሰልፎች ተሰልፈው እየዘመሩ በማጀብ የሚቀበሉዎ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ማኅበረ ቅዱሳን ቤተ ክርስቲያናቸውን እንዲያውቁና አባቶቻቸውን እንዲያከብሩ ስላስተማራቸው መሆኑ ግልጽ ነው።

ቅዱስ አባታችን ሆይ፡-

በተጨማሪም በደብዳቤዎ ላይ አንዱ ዋና ወንጀል ተደርጎ የተገለጸው «በሌለው ሥልጣን የጾም አዋጅን እስከማወጅ ደርሷል” የሚል ይገኝበታል። በአጭር ቋንቋ ለመግለጽ ማኅበረ ቅዱሳን ያወጀው ጾም የለም። ጾም በቅዱስ ሲኖዶስ እንደሚታወጅም ጠንቅቆ ያውቃል፤ ያስተምራልም። ለጾም አድሉ ብላ በምታስተምር ቤተ ክርስቲያናችን ተጨማሪ ጾም ታውጃላችሁ ተብሎ የቀረበብን ክስ በቤተ ክርስቲያን ጾም በዝቷልና ካልተቀነሰ እያሉ በከንቱ የሚደክሙትን ተሐድሶዎች ሀሳብ ለምን አትደግፉም የሚል ያስመስለዋል።

በአጠቃላይ ካሁን ቀደም በተለያዩ የተሐድሶ እምነት አራማጆች በሚያዘጋጇቸውና በሚመሯቸው ድረ-ገጾችና ብሎጎች ላይ በተደጋጋሚ ማኅበረ ቅዱሳንን ለመክሰስ ሲያወጧቸው የነበሩትና አንድም የእውነት ጠብታ እንኳ የሌላቸውን ሀሳቦች በርስዎ ደብዳቤ በአጭር በአጭሩ ተጠቅሰው ማየታችን እጅግ አሳዝኖናል፤ አስገርሞናል። እነርሱ ሁል ጊዜም እውነት መናገር ልማዳቸው እንዳልሆነ በሁሉም ዘንድ ስለሚታወቅ ንቀን መልስ ሳንሰጣቸው ቆይተናል። በርስዎ ደረጃ ይህ እንደገና ሲስተጋባ ግን ዝም ማለቱ ተገቢ ስላልሆነ ነው ይህን ምላሽ ለመስጠት የተገደድነው። ይህ ለመንፈሳውያን ኮሌጆቹ በአድራሻ የተጻፈላቸው ደብዳቤም ዓላማው በእውነት ግልጽ አይደለም። ስለዚህ አሁንም ቢሆን እውነታውን ለማወቅና ለሚነሱ ችግሮች መፍትሔ ለመስጠት የጉዳዩን ባለቤቶች ጠርቶ ፊት ለፊት በማነጋገር እና በመካከር መፍታት እንጂ አንድ ጩኸት በተሰማ ቁጥር ደብዳቤ መጻፉ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚበጅ አይመስለንም። በርስዎ ስም የሚጻፉ ደብዳቤዎችም ቤተ ክርስቲያንን የሚወክሉና ክብርዋን የሚያስጠብቁ፣ በሁሉም አካላት ተአማኒነት ኖሯቸው ትኩረት ሰጥተው የሚመለከቷቸው እንዲሆኑ ቢደረግ እጅግ ደስ ይለናል።

ክቡራን ንዑዳን ብጹአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ሆይ፡-

ማኅበረ ቅዱሳን በናንተ ቡራኬና መመሪያ ሰጪነት በብዙ ገዳማውያን አባቶቻችን ጸሎት እና በምእመናን ከፍተኛ ድጋፍ ቤተ ክርስቲያንን በአገልግሎቱ ለመደገፍ ላለፉት 23 ዓመታት የዐቅሙን ያህል ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። የነበረው አገልግሎት አልጋ በአልጋ ባይሆንም በተለይ በአሁኑ ወቅት ያለው የቤተ ክርስቲያናችን ሁኔታ እያሰጋን መጥቷል። የተሐድሶ መናፍቃኑ በማን አለብኝነት የቤተ ክርስቲያናችንን ትምህርተ ሃይማኖት እና ቀኖና በሚጻረር መልኩ የእምነት መግለጫቸውን በይፋ በመጽሐፍ መልክ አሳትመው እያሰራጩ ባሉበት ወቅት፣ ጥቅመኝነት በአንዳንድ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ውስጥ ክብር ተሰጥቶት በይፋ ዝርፊያ በሚፈጸምበት እና አገልጋዮች ካህናት በየቦታው በሚበደሉበት በዚህ ጊዜ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ርዕሰ መንበር ደረጃ በቅዱስነታቸው እንዲህ ዓይነት ለቤተ ክርስቲያን የማይበጁ ደብዳቤዎች እየተፈረሙ ሲወጡ ማየት እጅግ ከባድ አደጋ እንዳለው ይሰማናል። ምንም እንኳ ማኅበሩን አጥጋቢ ሥራ ሠርቷል ወይም አልሠራም፣ ስሕተቶችንም ይፈጽማል አይፈጽምም ብሎ መከራከር መውቀስና በሀሳቦቹም መወያየት፣ አስፈላጊም ሲሆን መገሠጽ እየተቻለ ከአንድ ቅዱስ አባት ቀርቶ ከየትኛውም የተቋም ሓላፊ በማይጠበቁና የሰዎችን ስሜት በሚያስቆጡ ቃላት መሸንቆጥ በእጅጉ የሚያሳዝን ሆኖ ተሰምቶናል። ለአብነት ያህልም ማኅበሩን ከሳሾቹ እንኳን በማይሉት መንገድ “የቤተ ክርስቲያንን ቀኖና በመጣስ ታሪክ ይቅር የማይለው ጥፋት እየፈጸመ ይገኛል” የሚለው ሊጠቀስ ይችላል። ይህ አገላለጽ ለማኅበሩ አመራርና አባላት ቀርቶ ደብዳቤውን በየሚዲያዎቹ ያዩት ሁሉ ትዕግሥትን የሚፈትን እንደሆነ እየገለጹልን ይገኛሉ። የጥቅምቱን ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ተከትሎም ማኅበሩ የቤተ ክርስቲያናችንን ስብከተ ወንጌል ለዓለም የሚያሰራጭበት የቴሌቪዥን መርሐ ግብር ሲቋረጥ ለሚመለከተው የቤተ ክርስቲያናችን አካል ብናመለክትም በቅዱስነታቸው ደብዳቤ እንዲቆም መደረጉም ሌላው አሳዛኝ ተግባር ነው። ከዚህም በላይ በዘመናችን ባለው ቴክኖሎጂ ምክንያት የትኛውም መረጃ ወይም ጉዳይ በሚዲያ ለሕዝቡ በከፍተኛ ፍጥነት የሚዳረስ መሆኑ አይዘነጋም። ይህንም ተከትሎ ብዙ ዓይነት ስሜቶችና አጸፋዎች ከምእመናን ይደመጣሉ። በመሆኑም በወቅቱ አግባብነቱን የጠበቀ ዕርምትና ለወደፊቱም መተማመኛ ያለው አሠራር ተግባራዊ እስካልሆነ ድረስ የሚከተለው አደጋ ትልቅነት ይታየናል።

ስለዚህ ቅዱስ ሲኖዶስ በጉዳዩ ላይ በአንክሮ እንዲወያይበት እና እርምት እንዲሠጥበት ለእኛም ከዚሁ አንፃር አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጠን እንድታደርጉልን ከእግረ መስቀላችሁ ሥር ወድቀን በፍጹም ትሕትና እንጠይቃለን።

የቅዱስነትዎ ቡራኬ ይድረሰን

የብፁዓን አባቶቻችን የጸሎታችሁ ረድኤት አትለየን

ግልባጭ፡-

Ø ለኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት

Ø ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት

Ø ለኢ.ፊ.ዲ.ሪ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ጽ/ቤት

Ø ለኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ጽ/ቤት

Ø ለኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን

Ø ለብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት

Ø ለውስጥ ደኅንነት ጥበቃ ዋና መምሪያ

Ø ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት

አዲስ አበባ

Ø ለትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርእሰ መስተዳድር ጽ/ቤት

Ø ለትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን

Ø ለትግራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፍትሕ ቢሮ ጽ/ቤት

መቐሌ

Ø በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚገኙ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ለሚመሩት አህጉረ ስብከት

በያሉበት

Ø ለማኅበረ ቅዱሳን ለሁሉም ማእከላት

በያሉበት

Ø ለኦዲትና ኢንስፔክሽን አገልግሎት

Ø ለዋና ጸሐፊ ቢሮ

ማኅበረ ቅዱሳን

ቀሲስ ዶ/ር ሰሙ ምትኩ

የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ

ፊርማና ማህተም አለው¾

The post ማኅበረ ቅዱሳን ለፓትሪያርኩ ደብዳቤ ጻፈ | “የፓትርያርኩ መመሪያ የእውነት ጠብታ የለበትም” appeared first on Zehabesha Amharic.

ሕወሓት የሚመራው የመከላከያ ሠራዊት አባላት ለኦሮሞ ሕዝብ ትግል ድጋፉን እየሰጠ ነው –ሰራዊቱ ድጋፉን ያሳየባቸው ፎቶዎች እየተለቀቁ ነው

$
0
0

wetader 1

(ዘ-ሐበሻ) በኦሮሚያ የተቀሰቀሰውን ሕዝባዊ አመጽ ተከትሎ ሕወሓት ከላይ የሚመራው የመከላከያ ሠራዊት አባላት ለኦሮሞ ህዝብ ትግል ድጋፋቸውን በመስጠት ላይ ይገኛሉ:: በሠራዊቱ ውስጥ በተለይ የኦሮሞና የአማራ ተወላጅ የሆኑ የጦር ሰራዊቱ አባላት አንድነት በመፍጠር ላይ እንደሚገኙ ከመከላከያ ምንጮች ያገኘናቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ::

በቅርቡ ሕብር ራድዮ ላይ ቀርቦ ቃለምልልስ የሰጠው ጀዋር መሐመድ “በሰራዊቱ ውስጥ የማደራጀት ሥራ ሰርተን ጨርሰናል:: በኦህ ዴድ ውስጥም እንዲሁም:: ሠራዊቱ መተኮስ ባለበት ወቅት ወደ ስር ዓቱ መተኮስ የሚችልበትን ሥራ ሰርተናል” ማለቱ የሚታወስ ሲሆን… ዛሬ በሶሻል ሚድያዎች እየተለቀቁ ያሉት ፎቶዎች እንደሚያሳዩትም የተለያዩ የሠራዊቱ አባላት እጃቸውን ወደላይ አድርገው በማጣመር ለኦሮሞዎቹ ትግል ያላቸውን አጋርነት በመግለጽ ላይ ናቸው::

wetader 2

ሕወሓት የሚመራው መንግስት በግድ ሕዝቡ እንዲቀበለው እያስገደደው የሚገኘውን ባንዲራም እየቀደዱ የሚያሳዩ ፎቶዎች ተለቀዋል::

ከመከላከያ ያገኘናቸው መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በአሁኑ ወቅት ውስጥ ውስጡን የኦሮሞና የአማራ ተወላጆች የሆኑ ወታደሮች በ ስር ዓቱ ግፍ በመንገብገብ የተደራጁ ሲሆን የሕወሃት ባለስልናት እርስ በ እርሳቸው እንዲከፋፈሉ ያዘጋጁትን ወጥመዶች እየበጣተሱ እንደሚገኙም ታውቋል::

wetader

በተለይ የኦሮሞና የአማራ ወታደሮች በአንድ ላይ ሕብረት መፍጠራቸው ያሰጋው ሕወሃት ሊያስተባብሩ ይችላሉ የሚላቸውን ወታደሮች በግድ የዓመት ፈቃድ እንዲወጡ እንዲሁም እያሰረም እየገመገመም እንደሚገኝ የዘ-ሀበሻ ምንጮች ገልጸዋል::

The post ሕወሓት የሚመራው የመከላከያ ሠራዊት አባላት ለኦሮሞ ሕዝብ ትግል ድጋፉን እየሰጠ ነው – ሰራዊቱ ድጋፉን ያሳየባቸው ፎቶዎች እየተለቀቁ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

አንዳርጋቸው በምናቤ –ከተስፋዬ ገብረአብ

$
0
0

andargachew Tisge

እነሆ! ቅዳሜ ዞሮ መጣ። በዚህች የቅዳሜ ምሽት ስለ አንዳርጋቸው ጥቂት አወጋ ዘንድ መንፈሴ መራኝ። አዲስ ነገር አትጠብቁ። ከቀንዱም ከሸኾናውም ዝም ብዬ አወጋለሁ። የምትሰሩት ሌላ አስቸኳይ ጉዳይ ካላችሁ ይህን ፅሁፍ ለማንበብ ጊዜአችሁን አታቃጥሉ። እንደው ዘና ብላችሁ ከሆነ ግን ብታነቡት ምንም አይላችሁም።

(ተስፋዬ ገብረአብ)

(ተስፋዬ ገብረአብ)

አንዳርጋቸውን ለመጀመሪያ ጊዜ የተዋወቅሁት በደርግ ውድቀት ማግስት አዲስአበባ ላይ ሲሆን፣ እለቱ ቅዳሜ እኩለ ቀን ነበር። በዚያን ጊዜ አበበ ባልቻ እና ባለቤቱ መአዛ ብሩ ጓደኞቻቸውን አልፎ አልፎ ቅዳሜ ከመኖሪያ ቤታቸው ይጋብዙ ነበር። ማለትም ምሳ እንበላለን፤ ውስኪና ቢራም ይኖራል። ስነጥበብ እና ፖለቲካ እየቀላቀልን እናወጋለን። አማረ አረጋዊና መአዛ ብሩ የልጅነት የትምህርት ቤት ጓደኛሞች ነበሩ። እንግዲህ እኔም የዚህ የቅዳሜ ማህበር አባል የሆንኩት በአማረ በኩል ነበር። ካልተሳሳትኩ ስለዚህ ጉዳይ ከዚህ ቀደም በጨረፍታ የፃፍኩ ይመስለኛል።

አንዳርጋቸው ወደዚያች የቅዳሜ ማህበር መምጣት ጀመረ። ቀጭን ነበር። ትዝ ይለኛል እንደዛሬው ሰከን ያለ አልነበረም። ስሜታዊነት ይታይበት ነበር። ፀጉሩ ጥቁር ነበር። ጢም አልነበረውም። መንፈሱም ቁመናውም የጎረምሳ ነበር። ከቅዳሜ ማህበሩ አባላት መካከል ነቢይ መኮንን፣ እሸቱ ጥሩነህ፣ ተፈሪ አለሙ፣ ማንያዘዋል እንደሻው፣ ፍቃዱ ተክለማርያም እንደነበሩ አስታውሳለሁ። ተድላ (?) የሚባል መንዜም በመካከላችን ነበር። ቀዌ ነገር ነው። ግጥም፣ ሙዚቃ ምናምን አይወድም። እያሽሙዋጠጠ ይሄን ፖለቲካ በጭንቅላቱ ያስኬደዋል።

ቃል በቃል ባይሆንም አንድ ቀን አማረን እንዲህ አለው።

“የኢትዮጵያ ስልጣኔና ስልጣን የትግሬ እና የአማራ መሆኑን አምናለሁ። እንግዲህ አሁን ለመግዛት ተራችሁ ሆኖአል። ያው አሸንፋችሁዋል መቸስ። እስክትሸነፉ ደግሞ ትገዛላችሁ። አንድ ነገር ግን በጥብቅ ማወቅ አለባችሁ። የምትወድቁበት ዘመን ሲደርስ ስልጣኑን መልሳችሁ ለኛ መተው ነው። OLF በመካከሉ ከገባ እናንተም እኛም የምንሊክን ቤተመንግስት  ለዘልአለሙ አናገኘውም። … ቆይ አታቋርጠኝ …. የለም! የለም! ስማኝማ … ብሄር ብሄረሰብ … እሱን እርሳው! ምንድነው የምታወራው?”

ተድላን በቁምነገር የሚሰማው አልነበረም። የማህበሩ ማጣፈጫ ነበር። አማረ አረጋዊ በወቅቱ የቴሌቪዥን መምሪያ ሃላፊ እንደመሆኑ፣ “ሰዎች ምን ይላሉ?” የሚል ተወዳጅ ፕሮግራም ጀምሮ ነበር። አንዳንድ ጊዜ እዚያ የምናወጋት ወግ ተፅፋና ተከሽና በፕሮግራሙ ላይ ትቀርባለች። አማረ ደጋግሞ ተድላን፣ “እዚህ የምትናገረውን ፃፈውና በቴሌቪዥን ይቅረብ” ይለዋል። አንድ ጊዜ በቁምነገር እንዲህ ሲናገረው ተድላ ሳቀ። ድምፁን ቀንሶም እንዲህ አለው፣

“ይሄ እኮ የቤተሰብ ጨዋታ ነው።” ከዚያም የአማረን ትከሻ ይዞ ሊያግባባው ሞከረ፣ “…የትግሬ ህዝብ ወንድማችን ነው። እየተፈራረቅን ገዝተናል፤ አይደለም እንዴ? ‘የሞትንም እኛ – የነገስንም እኛ’ እንዲሉ። የናንተ ችግር መቶ አመታት በተራራ መሃል ተቀብራችሁ መኖራችሁ ነው። አሁን ባነናችሁ። ‘ምኒልክ ዮሃንስን ሸውዶ ነው ዙፋን የያዘው’ ምናምን ብላችሁ እየተቆጣችሁ ስለመጣችሁ እንግዲህ ቤተመንግስቱንም ባንኩንም ትተንላችሁዋል። ርግጥ ነው፤ በአድዋ ጦርነት ከምኒልክ ጋር የመጣን ጊዜ አንዳንድ ጉዳት አድርሰናል። ብዙ ዛፎች ቆርጠናል። ብዙ ዶሮዎች ፈጅተናል። መቸም ይሄ በክፋት የተደረገ አይደለም። ካሳ ባለመደረጉ ብትቀየሙ እንገነዘባለን። ዋናው ነገር አሁን ረጋ በሉና አስቡ። መለስ ዜናዊን ታገኘዋለህ አይደለም? በግልፅ ንገረው። ሸዋን ስትለምዱ ጨዋታው ይገባችሁዋል። … ህዝብ … ህዝብ የምትሉትን ብትቀንሱ ይሻላችሁዋል። እውነት አይደለም። ህዝብ የሚባል ነገር የለም። ህዝብ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ልንገርህ? ስለራሱ ብቻ የሚያስብ የግለሰቦች ጥርቅም ነው። ….መስሏችሁ ነው… እስክትለምዱት ነው። ገበሬ … አርሶአደር … እሱን ተወው!…ስማኝ ልንገርህ! …ገበሬ ማለት አቃጣሪ ማለት ነው።”

ፍቃዱ ተክለማርያም ክራር አንስቶ ማዜም ሲጀምር ከተድላ ሽሙጥና ፍልስፍና አረፍ እንላለን። ሰአሊው እሸቱ ጥሩነህ አንድ አሪፍ ግጥም ሲያነብ መንፈሳችን በቅኔ ውቅያኖስ ላይ ይንሳፈፋል። ነቢይ መኮንንም እጁን ወደ ኪሱ ሰዶ አንድ ቅጠል ወረቀት መምዘዙ የማይቀር ነበር። ጥቂት ወርቃማ ስንኞች አያጣም። የእሸቱ የስነ ግጥም ፍቅር ልክ እንደ መአዛ ብሩ ነው። ያበዱ ናቸው። እና ታዲያ ይህን የመሰለውን ውብ የቅዳሜ ማህበር ያፈረሰው አንዳርጋቸው ፅጌ ነበር። “ውስኪ እየጠጡ ግጥም ማንበብ፤ ዝባዝንኬ መስማት አልፈልግም!” ብሎ በሚቀጥለው ቅዳሜ እንደማይመጣ አሳወቀ። የፅጌ ልጅ ማህበራችንን ሲንቅብን እኛም ቀስ በቀስ ተውነው።

ከዚያ ወዲያ አንዳርጋቸው ቀልቤን የሳበው፣ “አማራ ከየት ወዴት?” በሚል ርእስ መፅሃፍ ፅፎ ሲያሳትም ነበር። ወዲያው መፅሃፉን ገዝቼ አነበብኩት። አንብቤ ስጨርስ በጣም ገረመኝ። አንዳርጋቸው ለመለስ ዜናዊ የቅርብ ሰው እንደነበር ይሰማ ነበር።  የጓደኝነታቸው መነሻ የአላማ አንድነት ነው ብዬ አምን ነበር። የተፈራ ዋልዋ ሚስት የአንዳርጋቸው እህት ናት። በመሆኑም አንዳርጋቸው ከአላማ አንድነት በተጨማሪ በጋብቻም ከኢህዴን (ብአዴን) ጋር በጥብቅ መተሳሰሩ ይሰማኝ ነበር። ከወያኔ ስርአት ጋር ተጣብቀው ሊቆዩ ከሚችሉ ባለስልጣናት ዋናው አንዳርጋቸው ነው የሚል እምነት ነበረኝ። “አማራ ከየት ወዴት?” የሚለውን መፅሃፍ ሳነብ ግን አንዳርጋቸውን በትክክል አወቅሁት። በጠባዩ ነፃ እና አፈንጋጭ መሆኑን ተረዳሁ። ብዙም አልቆየ። ወያኔን አውግዞ እንደገና ወደ እንግሊዝ አገር ተሰደደ። ከዚያም ለረጅም ጊዜ ድምፁ ሳይሰማ ቆየ።

በመቀጠል ስለአንዳርጋቸው የሰማሁት በምርጫ 97 ለመሳተፍ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ ነበር። ብዙም አልቆየ የቅንጅት አመራር ከመታሰሩ በፊት ወያኔ አንዳርጋቸውን በፖሊስ  ይዛ እየደበደበች ዝዋይ አሰረችው። የቅንጅት አመራር ሊታሰር ጥቂት ሲቀረው ደ’ሞ አንዳርጋቸው ከእስር ተፈትቶ ወደ ለንደን ተመልሶ ኮበለለ። ግንቦት 7ን እስኪመሰርት ድረስም በስደት ላይ ሆኖ የተቃዋሚውን ትግል በመምራት ግንባር ቀደም ነበር።

አንድ ጊዜ ለአንድ ወር እረፍት ከሆላንድ ወደ ኤርትራ ሄጄ ሳለ አንዳርጋቸው አስመራ መኖሩን ሰማሁ። ላገኘው መጓጓቴ ትዝ ይለኛል። እሱም አስመራ መሄዴን ሰምቶ ኖሮ ቀድሞ ስልኬን አገኘና ደወለልኝ። ኤክስፖ ሆቴል ተቀጣጠርን። ሳገኘው በአካል ብዙ ተለውጦ አገኘሁት። ጠጉሩ ገብስማ ሆኖአል። ጥቂት ክብደት ጨምሮአል። ንግግሩ ግን አልተለወጠም ነበር። እንደቀድሞው ፊት ለፊት ይናገራል። ጉራ የለበትም። ሰዎችን በቀላሉ ጓደኛው የማድረግ ችሎታውም አብሮት ነበር።

ያን ቀን እስከ እኩለ ሌሊት ቆየን። በብዛት እሱ ነበር የሚናገረው። የማልስማማባቸው የፖለቲካ አመለካከት ቢኖሩትም የፅጌ ልጅ የስልጣን ጉጉት እንደሌለው መረዳት ችዬ ነበር። “ለሚቀጥለው ትውልድ ምንድነው የምንተውለት? ቅርሳችን፣ ባህላችን፣ ታሪካችን…” እያለ በምሬትና በቁጭት ይናገር ነበር። ከዚያ በሁዋላ ከአንዳርጋቸው ጋር በአስመራ እና በአምስተርዳም በተደጋጋሚ ተገናኝተናል። በወያኔ ተጠልፎ እስኪወሰድ ድረስም መልካም ግንኙነት ነበረን።

ጊዜ ሰውን ቆሞ አይጠብቅም። የአምስት ኪሎ ባለቅኔ “መንገዱ ፈጣን ነው – የሰው ህይወት ጉዞ፤ ይጋልባል እንጂ – ቆሞ አያይም ፈዞ” እንደሚለው ነው። አንዳርጋቸው በወያኔ ሲጠለፍ የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ሊፈረስ እንደሚችል ገምቼ ነበር። ወያኔም እንዲሁ ነበር ያሰበው። አንዳርጋቸውም ቢሆን ከታሰረበት ቦታ ሆኖ ሲናገር እንደሰማነው የግንቦት 7 የትጥቅ ትግል የመቀጠል ተስፋ እንደሌለው ነበር የተነበየው። እሱን ተክቶ፣ በረሃ ወርዶ፣ ትግሉን የሚያስተባብር አመራር ማግኘት ስለመቻሉ ጥርጣሬ ነበረው። ብርሃኑ አንዳርጋቸውን ተክቶ በረሃ ይገባል ተብሎ የሚታሰብ አልነበረም። ፕሮፌሶር ብሬ ሁዋላ አፋችንን አስያዘን እንጂ፤ በሃሜት ቦጫጭቀነው ነበር። ብርሃኑ አሜሪካ ላይ ከቤተሰቡ ጋር መኖሩ፤ የመምህርነት ቋሚ ስራ መጀመሩ፤ አንዳርጋቸውም ተስፋ የቆረጠ መስሎ መታየቱ ተደማምሮ ብርሃኑን እንድናማው አደፋፍሮን የነበረ ይመስለኛል።

በዚህም ተባለ በዚያ የአንዳርጋቸው መጠለፍ የግንቦት ሰባትን ትግል አጠናከረው እንጂ አላዳከመውም። ከዚህ አንፃር ወያኔ ከስራለች። አሳምራ ተሸውዳለች። አሁንም ቢሆን ለወያኔ የሚሻላቸው አንዳርጋቸውን በሚቀጥለው አውሮፕላን ወደ ለንደን መላክ ነው። ምክንያቱም አንዳርጋቸው ለታጋዮች የብርታት ሻማ ሆኖ እያገለገለ ነው። ትግሉን ለመቀላቀል ወደ ኤርትራ የሚጎርፉት ወጣቶች አንዳርጋቸውን በአእምሮአቸው መያዛቸው እውነት ነው። አንዳርጋቸው የነገ የአመፅ መነሻም ሊሆን ይችላል። ስብሃት ነጋ ይህችን በጎ ምክር እንደሚያጤናት ተስፋ አደርጋለሁ።

ብርሃኑ ነጋን አጊንቼው አላውቅም። በአጋጣሚ ያዩት ሰዎች ይነግሩኛል። አንድ ጊዜ ግን (ከ60 ቀናት በፊት) ቀይባህር ዳርቻ መንገዶች በጎርፍ ተዘግተውበት ብርሃኑ ሌሊቱን በረሃ ላይ ማደሩን ሰምቻለሁ። እኔም በአካባቢው ነበርኩ። ከውጭ አገር ከመጣ እንግዳ ጋር ወደ አዱሊስ ከተማ እየተጓዝኩ ነበር…

በነገራችን ላይ የዘንድሮው የምፅዋ ክረምት በፍፁም ታይቶ የሚታወቅ አይነት አይደለም። ከህዳር መጨረሻ ጀምሮ እንደ ጉድ ይረግጠዋል። ምፅዋ ላይ ፀሃይ የለችም። ቀይባህር ቀዝቅዟል። ከባድ ማእበልም አለ። በዚህ አይነት የአየር ጠባይ መዋኘት ብዙም ደስ አይልም። የምፅዋ ነዋሪዎች ብርድ ልብስ ተከናንበው የመተኛት አጋጣሚ በማግኘታቸው ተገርመዋል። በቆሎና ማሽላ፣ እንዲሁም ቡልቱግ ጥሩ ይዘዋል። በርግጥ ዝናቡ ከመበርታቱ የተነሳ ጎርፉ ጥቂት የገበሬ ጎጆዎችን እንደ ዘንቢል አንጠልጥሎ ቀይባህር ጨምሯቸዋል። ሂርጊጎ ወይም ገልአሎ አካባቢ ስድስት ሰዎች በተኙበት በጎርፍ መወሰዳቸውም አቢይ ዜና ሆኖ ሰንብቶ ነበር።

… አሳባችን እንኳ ከእንግዳው ጋር ፎሮ ከተማ አድረን ስናበቃ በማለዳው ወደ አዱሊስ ለመሄድ ነበር። ሳይቻል ቀረ። እንዳልኩት ሃይለኛ ጎርፍ መንገዱን ዘግቶ ጠበቀን። ባለ ከባድ ማርሽ መኪና ይዘው ጎርፉን ለመሻገር የሚሞክሩ፤ የኤርትራን ወታደራዊ ዩኒፎርም የለበሱ ሰዎችም አፋፉ ላይ ነበሩ። ብርሃኑ ነጋ ያለበት ቡድን በሁለት ጎርፎች መካከል መያዙን አንደኛው ወታደር ነገረኝ። እንዳጫወተኝ ከሆነ ይህ ጎርፍ መንገዱን ከመዝጋቱ በፊት ነበር እነ ብርሃኑ የተሻገሩት። ከፊታቸው ግን ሌላ አደገኛ ጎርፍ መንገድ ዘግቶ እንደ ፈረሰኛ እየተገላበጠ ወደ ቀይባህር ሲገባ ጠበቃቸው። እነ ብርሃኑ ወደፊት መቀጠል ስላልቻሉ ወደ ምፅዋ ለመመለስ ፊታቸውን አዞሩ። ከሁዋላቸውም ግን መንገዱ በአዲስ ደራሽ ፈረሰኛ ጎርፍ ተዘግቶ ጠበቃቸው። በመካከሉ የጎርፍ እስረኛ ሆኑ።

“ለእርዳታ እየሄዳችሁ ነው?” ስል ጠየቅሁት።

“ችግር እንዳይኖር ለማየት ነበር። ማለፍ አልቻልንም።”

“እነ ብርሃኑ ወዴት እየሄዱ ነበር?”

“እሱን አላውቅም።”

“ወደ አሰብ ነው ወይስ ወደ ዊኣ?”

“አላውቅም በእውነቱ” ብሎ ገልመጥ አደረገኝ።

“ስንት ናቸው?” ስል ጥያቄየን አራዘምኩ።

መልስ ሳይሰጠኝ ዝም በማለቱ፤ ጥያቄየን ማቆም እንዳለብኝ ተረዳሁ።

በዚያን ሌሊት ሴንትራል ሆቴል ነበር ያደርኩት። በረንዳው ላይ ቁጭ ብዬ የባህሩን የማእበል ድምፅ እየሰማሁ ነበር። ባህሩ ላይ በርቀት መብራት ይታያል። መርከብ መሆን አለበት። በፀጥታዬ ውስጥ ሳለሁ ታዲያ እግዚአብሄርን እንዲህ አልኩት፣

“ታታሪ ነጋዴ ወይም ብርቱ ግንበኛ ልታደርገኝ እየቻልክ፣ ያለእውቅናዬ ፀሃፊ ያደረግኸኝ አምላክ ሆይ! በል እስኪ የምር ፈጣሪ ከሆንክና ችሎታው ካለህ የምናቤን ሻማ ለኩስና አንዳርጋቸው ምን እያደረገ እንዳለ ገልጠህ አሳየኝ?”

ፈጣሪ በምናቤ በኩል መጣና፣ “አይንህን ጨፍን!” አለኝ። እንደታዘዝኩት አይኖቼን ጨፈንኩ። አይኖቼን ስጨፍናቸው የምናቤ መስኮቶች ተከፈቱ። አንዳርጋቸውንም አየሁት።

….ቀጭን አልጋ ላይ በጀርባው ጋደም ብሎ ነበር። ከግድግዳው ጥግ ላይ ቡኒ ጠረጴዛ ይታያል። አንዳርጋቸው ከአልጋው ብድግ ብሎ በር ከፍቶ ወጣ። ከትንሿ ደጃፍ ላይ አንዲት የእንጨት ወንበር አለች። ቁጭ አለ። ሰማዩን ቀና ብሎ አየው። እጁን አነሳና ጢሙን ሞዠቀ። ጢሙና ጠጉሩ ሃጫ በረዶ መስሎአል። ጥርሶቹ አይታዩም። እንደ አውሮፓውያን ስስ የሆኑት ከንፈሮቹ እንደ ኪዊ የቀለም ቆርቆሮ ግጥምጥም ብለው ተዘግተዋል። ቅንድቦቹ የጥርስ ቡሩሽ ይመስላሉ። ከተቀመጠበት ተነሳና ወደ እስር ክፍሉ ገባ። ጠረጴዛው ላይ ቁጭ ብሎ ኮምፕዩተር ከፈተ። ምንም አልፃፈም። ዘጋውና ተነሳ። ወደ ደጅ ወጣና በረንዳው ላይ ቁጭ አለ። ሰማዩ ላይ መልሶ አፈጠጠ። ከጥቂት ደቂቃዎች ማፍጠጥ በሁዋላ አይኖቹን ጨፈናቸው። በዚያ መልኩ ብዙ ቆየ። በመካከሉ የበር መከፈት ድምፅ ሰማ። አይኖቹን ግን አልከፈተም። ማን እንደመጣ ማየት አላስፈለገውም። የራት ሳህን የያዘ ፖሊስ ነበር። አንዳርጋቸው አይኖቹን ከፈተ። ፖሊሱ ሳህን እና ውሃ ካስቀመጠለት በሁዋላ ቁጭ አለ፣

“ምን አለ አዲስ ነገር?” ሲል ጠየቀው።

“ምንም የለም።”

“የኦሮሞዎች አመፅ እምን ደረሰ?”

“ቀጥሎአል። ብቻ እየቀዘቀዘ ነው የሚሉም አሉ።”

“የሞቱትስ ስንት ደረሱ?”

“ብዙ ነው! ከመቶ በላይ ይሆናል…”

“በሌላ አካባቢ አመፅ የለም?”

“ምንም የለም።”

“ስለ ብርሃኑስ ምን ወሬ አለ?”

“ምንም የለም። እዚያው ነው።”

ከጥቂት ዝምታ በሁዋላ ፖሊሱ ጠየቀው፣

“የምትፈልገው ነገር አለ?”

“ምንም የለም።”

“ትበሳጫለህ እንዴ?”

አንዳርጋቸው በስሱ ሳቀ፣

“አሳሪም ታሳሪም በቅርቡ ተያይዘን እናልፋለን። ታሪክ እና ትእዝብት ብቻ ይቀራሉ።”

ከጥቂት ደቂቃዎች በሁዋላ ፖሊሱ ተሰናብቶ ወጣ። አንዳርጋቸው አይኖቹን ወደ ሰማይ ተከለ። ጨረቃዋን በሩቅ ርቀት አያት። የልጃገረዶች የፊት መመልከቻ መስታወት መስላ ሰማዩ ላይ ተለጥፋለች። እና አንዳርጋቸው እንደገና አይኖቹን ጨፈነ።

The post አንዳርጋቸው በምናቤ – ከተስፋዬ ገብረአብ appeared first on Zehabesha Amharic.

የሀገር አድን ጥሪ ለወጣቱ!(ከአርበኞች ግንቦት7 ወጣቶች መምርያ )

$
0
0

ማክሰኞ ፣2 ፌብሩወሪ 2016

12042873_868355303254893_5731700769108826326_nወጣቶች በሃገራችን ላይ የተጫነብን የወያኔ የመርገምት አገዛዝ ያጎሳቆለን፤ በኑሮ የተበደልንና በሰላም ለመኖር ያልታደልን ፍጡሮች ብንሆንም ህዝባችን ነጻነቱን ሲቀማ፣ መብቱ ሲደፈር፣ ክብሩ ሲዋረድ ከዳር ቁመን የምንመለከትበት አንዳች ምክንያት ሊኖረን አይገባም። ወቅቱ ለነፃነታችንና ለመብታችን ባላንጣ የሆነውን አምባገነን የወያኔን ስርዓት ፊት ለፊት ተጋፍጠን፣ በትግላችን ደቁስን ማንነታችንን የምናስመስክርበት ወቅት እንጂ በፍርሃትና በዝምታ ተውጠን ወደኋላ የምንልበት ስዓት አይደለም። ደግሞም እኛ ወጣቶች ለመብት እና ነፃነታችን ተፈጥሮ የለገሰችንን እምቅ ኃይልና ጉልበት ተጠቅመን በቁርጠኝነት ተነስተን ካልታገልን የሥርዓቱን አምባገነናዊ የጭቆና አገዛዝ በፍርሃትና በዝምታ እንደተቀበልን ተደርጎ መወስዱ የማይቀር ነው።
ከምንግዜውም በላይ እኛ ወጣቶችን ዛሬ ሁለት አበይት ጉዳዮች በጉልህ ያሳስቡናል፤ ሊያሳስቡንም ይገባል። እነዚህም ሃገራችን ያለችበት አሳሳቢ ሁኔታና የኛ የተተኪው ትውልድ የወደፊት ተስፋ ምን ሊሆን ይችላል? የሚሉት ናችው። በቀደመው ጊዜ በሃገራችን የተፈራረቁት አምባገነን ገዥዎች ለወጣቱ ተስፋና የተሻለ ነገር ከመስጠት ይልቅ በጠላትነት ፈርጀው በሽብር እየገደሉና ጥቃት እየፈጸሙበት ሲያሳድዱት ኖረዋል። የወጣቱ ሰቆቃ አሁን በወያኔ ዘመን ደግሞ እጅግ በጣም በከፋ ሁኔታ ተባብሶ ቀጥሏል።
የወያኔ መሪዎች ለኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ማዕከላዊን፡ ቃሊቲን፤ ሽዋሮቢትን፣ ዝዋይን እና የመሳስሉ የሰቆቃ እስር ቤቶችን ሲያሰፉ እንጂ የሥልጠናና የምርምር ተቋም ሲያድሱና ሲገነቡ ለማየት አልታደልንም። የሚገነቡ የትምህርት ተቋማትም ለሥርዓቱ የእድሜ ማራዘሚያ እንጂ የእውቀት ማስጨበጫ ተቋም እንዳልሆኑ ተግባራቸውንና ውጤታቸውን መመልከት ይቻላል። በአደባባይ ያለፍትህ የሚገደለው ወጣት ባንክ ሲዘርፍ ተገኘ፣ ወንጀል ሲሰራ ተያዘ የሚሉ የሀሰት ምክንያቶች እየተለጠፉበት ያለኃጢአቱ የሀሰት ስም በመቀባት ዳግም ይገሉታል።
የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ከሚፈራበት የትምህርት ተቋም ድረስ በመግባት የአማራ ህንጻ፣ የኦሮሞ ህንጻ፣ የትግሬ ህንጻ…ወዘተ እያሉ የትምህርት ሥርዓቱን ከጠባቡ የፓለቲካ ግባቸው ጋር በማያያዝ በነገ ተስፋችን ላይ ዘምተው የልዩነት ግድግዳ ባሳፋሪ መልክ እየገነቡ ቀጥለዋል። አላማው ደግሞ በጎስኝነት በሽታ ተውጠን ከእህቶቻችንና ከወንድሞቻችን ጋር እየተባላንና እየተገዳደልን የምንኖርበት ሲኦል ለመፍጠር መሆኑ አያጠያይቅም። በዚህም ሳቢያ ብሔራዊ ሰሜታችን እየደበዘዘ ሄዷል። ብሔራዊ ሰሜት ከሌለን ደግሞ አገር አለን ማለት ጨርሶ የሚታስብ እንደማይሆን ግልጽ ነው።
በነገራችን ላይ ዛሬም ድረስ ወያኔዎች ለእድገትና ለልማት መዘጋጀታችውን እየደሰኮሩ ህዝብን በማታለል የስልጣን ዘመናቸውን ለማርዘም መውተርተራቸውን አላቆሙም። በየጊዜው ኢትዮጵያ ተመነደገች፤ ልማቱ ተፋጥኗል እያሉ በሃሰት ህዝብን ለማወናበድ ይሞክራሉ።እውነታው ግን በእጅጉ ተቃራኒ መሆኑን የህዝቡን የኑሮ ሁኔታን በመመልከት መረዳት ይቻላል። ዛሬ የፋሽስቱ ወያኔ አገዛዝ በፈጠረው የተወሳሰበ ችግር በሀገሪቱ የወጣት ሥራ ፈትና ተጧሪ ሞልቶና ተትረፍርፎ በሚታይበት፤ ሥራ የማግኘት እድል በፓለቲካ ታማኝነት ብቻ በሆነባት ሃገርና ወያኔ የፓለቲካ ሥልጣኑንና ወታደራዊ ኃይሉን ተጠቅሞ የሀገሪቷን ሀብት እያጋበስ በሚዘርፍበት ሁኔታ ላይ ቆመን ልማትና እድገት ማለት ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ተራ ማጭበርበሪያና ዲስኩር ካልሆኑ በስተቀር ፈጽሞ ትርጉም የሚሰጥ አይደለም።
ለነገሩ ወያኔ ከመጀመሪያው ጀምሮ ያዘጋጀልን ቃሊቲ፤ ማዕከላዊ፤ ሁርሶን፤ ሽዋሮቢትንና የመሳሰሉትን የማሰቃያ ማጎሪያዎች መሆኑን የተረዳን ስለሆነ በዚህ የምንደናገር አይደለም። ለዚህም ነው በአሁኑ ወቅት እኛ ወጣቶች ተሰባስበንና ተደራጅተን ከመታገል ውጪ ሌላ ምርጫ የለንም ብለን በድፍረት የምንናገረው።
አምባገነንነት ስርዓት ካልተገታ የአገር ሰላም ሆነ የህዝብ ህልውና እና አንድነት ዋስትና አያገኝም። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ሥልጣን የጨበጡት ወንበዴ ግለሰቦች የኢትዮጵያ ህዝብን ሀብት እየተቀራመቱ ለግል ጥቅማቸው የሚያውሉ፣ ህዝቡን የሚገሉ፤ የሚረግጡና የሚበድሉ በተለይ ደግሞ ለባእድ ጥቅም የተገዙ ናቸው። እነዚህ ግለስቦች ብሔራዊ ስሜታችውን አሽቀንጥረው የጣሉ፤ የራሳችውን ባህል፤ ወግ፤ ታሪክና ሕዝብ አምርረው የሚጠሉ ከራሳቸውና ሥልጣን ላይ ካስቀመጧቸው መንግሥታት ጥቅም ውጪ ሌላ ምንም የማይታያቸው ናችው።
ታዲያ የሃገራችን ህልውና ከመቼውም በላይ ለከፋ አደጋ ተጋልጦ ባለበት በአሁኑ ወቅት በተለይ የእኛ የወጣቶች ግዴታና ድርሻ ምን መሆን አለበት ብለን ራሳችንን መጠየቅና ብሎም መልስ ለመስጠት መዘጋጀት ሀገራዊ ግዴታንና ኃላፊነትን ለመወጣት የመጀመሪያው እርምጃ መሆን ይኖርበታል።
ጭቆናንና በደልን በመታገል ረገድ ደግሞ የቀደምት የታላላቅ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን አኩሪ ገድል ለዛሬው ትግላችን ትልቅ የትምህርት ማእከል ሆኖ ያገለግለናል። ሀገራችን ከኋላቀር ሥርዓትና ከብልሹ አገዛዝ ተላቅቃ፤ ድህነትን አሸንቀጥራ ጥላ በልማት ጎዳና እንድትራመድ፤ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እውን እንዲሆን፤ ማህበራዊ ፍትህ እንዲስፍን ባጠቃላይም ተጨባጭና ዘላቂ ለውጥ በሃገራችን እንዲመጣ ጽኑ እምነት ሰንቀው ለሕዝባዊ ትግሉ ሕይወታቸውን መስዋእት በማድረግ ሲታገሉ የነበሩ ጀግና ወጣቶች እንዳሉ ታሪክ ያስገነዝበናል።
ዛሬም ጭምር ግንባራችውን ሳያጥፉ መስዋእትነትን በመክፈል እያስመስከሩ ያሉ መኖራቸውን ስንመለከት ጀግና የሚያፈራው ጀግናን ነውና እኛም ወጣቶች አንገታችንን ቀና አድርገን ዛሬም እንደ ትናንቱ ለሃገራችንና ለህዝባችን ነፃነት መታገል ብሔራዊ ግዳጃችን ብቻም ሳይሆን ታላቅ ክብርም ጭምር መሆኑን ተገንዝበን ለሞት ሽረቱ ትግል በቁርጠኝነት መነሳት ይኖርብናል። ከፊታችን ለሚጠብቀንና ሃገራችን እያሰማች ላለው የሀገር አድን ጥሪ መልስ ለመስጠት እኛ የኢትዮጵያ ወጣቶች ከሃገር ቤት እስከ ውጪው አለም ድረስ የተቀናጀና የተቀነባበረ ንቅናቄ በመፍጠር ምላሽ ልንሰጥ ይገባል።
በኅብረትና በጽናት ከታገልን ደግሞ የወያኔን የሰቆቃ አገዛዝ አሰወግደን የሕዝባችንን ሮሮ የማናስቆምበት እና ተጨባጭ ለውጥ በሀገራችን ለማምጣት የማያስችለን አንዳች ምድራዊ ሃይል እንደማይኖር በእርግጠኛነት መናገር ይቻላል። ዛሬ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ እንዳለ ብልጭ ብልጭ እንደሚል ኮኮብ ብንመስልም በርግጠኝነት ነገ ከፀሐይ ደምቀን ከአሽዋ በርከትን የምንታይበት ጊዜ ይመጣል፤ እየመጣም ነው።
በመጨረሻም የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ወጣቱን ትውልድ መብቱንና የዜግነት ክብሩን ለመጎናጸፍ እንዲችል ብሎም የሀገር እና የወገን ነፃነትን ለማምጣት ወያኔን ታግሎ ማሸነፍና ከስልጣኑ ማውረድ ግድ ነው ብሎ በጽኑ ያምናል። በአገር ውስጥም ሆነ በመላው ዓለም ተበታትኖ የሚገኘውን ወጣት በአገሩ ተከብሮ እንዲኖር የተለየና የተቀደሰ አማራጭ አለው። ይኸውም እየተደራጁ መታገል፣ እየታገሉ መደራጀት ነው ብሎ ንቅናቄያችን ያምናል።
የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ የነደፈውን ጊዜ የማይሽረውን ሁለገብ የመታገያ ስልትና አላማን ከግብ ለማድረስ ትግልን በጽናት መቀጠል የሚለው መርሁ ሲሆን ተደራጅቶ በጽናት መታገልን በተግባር ለማዋል ደግሞ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ወጣት ንቅናቄውን እንዲቀላቀል ጥሪ ያደርጋል። ተደራጅቶ ሊያጠፋን የተነሳን ጠላት በተደራጀ ሃይል ማንበርከክና ከስር መሰረቱ ማስወገድ ይቻላልና። ስለዚህ የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ በአረመኔው የወያኔ አገዛዝ ላይ የሚካሄደውን ትግል አጠናክሮ በመቀጠል በአገር ውስጥ ወጣቱን በህቡዕ ከማደራጀት ጀምሮ በውጭው ዓለም በየአህጉሩ በተዋቀሩ የንቅናቄው መዋቅሮች አማካኝነት ወጣቱን አደራጅቶ በማንቀሳቀስ አስፈሪ የሆነ የነፃነት ማዕበል ፈጥሯል። አሁንም የንቅናቄውን ዓላማ የሚደግፉና በነፃነት ትግሉ ለመሳተፍ የቆረጡ ወጣቶች እንዲቀላቀሉ የአርበኞች ግንቦት7 ወጣቶች መምርያ በድጋሚ ሃገራዊ ጥሪ ያቀርባል!

ፈሪዎችንና ባንዳዎችን ወደ ጎን በመተው እውነተኛ ታጋዮችን ይዘን ትግላችንን እንቀጥላለን!!!

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

The post የሀገር አድን ጥሪ ለወጣቱ!(ከአርበኞች ግንቦት7 ወጣቶች መምርያ ) appeared first on Zehabesha Amharic.

የወልቃይት የአማራ ብሔር የማንነት አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ታስረው ተፈቱ

$
0
0

Zehabesha News

ጥር 20 ቀን 2008 ዓ.ም. ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ የታገዱት የወልቃይት የአማራ ብሔር የማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴዎች፣ የኃይማኖት አባቶችና የአካባቢ ሽማግሌዎች ሰኞ ጥር 23 ቀን 2008 ወደ መዲናችን መግባት ችለው ነበር፡፡ የትግራይ ክልል ኮሚቴዎቹና ኅበረተሰቡ በወጡበት ይቅርታ ጠይቀው በቶሎ ካልተመለሱ እርምጃ እንደሚወስድ በትግርኛ ቴሌቪዥን ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ መስጠቱም ይታወሳል፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ ዛሬ ቁጥራቸው 22 የሚሆኑ ተወካዮች ለፌደሬሽን ምክር ቤትና ለፌደራል ጉዳዮች ቢሮ አቤቱታቸውን ለማሰማት ከቀኑ 7፡00 ላይ ሃያ ሁለት አካባቢ ከጓደኞቻቸው ተለይተው ሒደው ነበር፡፡ እነዚሁ የኮሚቴ አባላት እስከ ምሽት 2፡00 ከታፈኑ በኋላ ይህን ዜና ለሕዝብ ያሰራጨው የወልቃይት ጠገዴ ሰሜን አርማጭሆ ድምጽ ታስረው መፈታታቸውን ዘግቧል::

ታስረው የነበሩት የወልቃይት የአማራ ብሔር የማንነት አስተባባሪ ኮሚቴዎች:-

1. ኮ/ል ደመቀ

2. አቶ አታላይ ዛፌ

3. አቶ ተሰማ ረታ

4. አቶ ይለፍ በየነ

5. አቶ አደራጀው ዋኘው

6. አቶ አባይ ግርማይ

7. አቶ ሸፈቀ አደም

8. አቶ ሙሉ ንጉሤ

9. አቶ ለገሠ ሐጎስ

10. አቶ አማረ ዓለሙ

11. አቶ መንግሥቱ እንዳለው

12. አቶ ካሣ ጥሩ

13. አቶ ፈጠነ ገብሩ

14. አቶ አታላይ ገብረእግዜር

15. አቶ ኢብራሒም መሐመድ

16. አቶ ማእዛ ገብሩ

17. አቶ ልዩእሸት አስፋው

18. አቶ ጌታቸው አደመ

19. አቶ ጣሒር

20. ወ/ሮ ኪሮስ

21. አቶ መብራቱ

22. አቶ አዲሱ ናቸው፡፡

The post የወልቃይት የአማራ ብሔር የማንነት አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ታስረው ተፈቱ appeared first on Zehabesha Amharic.

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ለቪኦኤ ቃለምልልስ ሰጡ |ስለአንዳርጋቸው ጽጌ፣ ስለኦሮሞ ሕዝብ ተቃውሞ፣ ስለሚያደርጉት ጥንቃቄ ተናገሩ


ማኅበረ ቅዱሳን ለፓትርያርኩ ምላሽ ሰጠ |መልካም ሞላ

$
0
0

በቅርቡ ማኅበሩን አስመልክቶ በቅዱስ ፓትሪያሪኩ የተጻፈው መመሪያ/ ደብዳቤ አሳዝኖናል የደብዳቤው ዓላማ እና ተልእኮ ምን እንደሆነ መገመት አስቸግሮናል ያለው ማኅበረ ቅዱሳን፤ የተከሰስንበት ጉዳይ መሰረት የሌለው እና እኛን የማይወክለን ነው ሲል ለቀረበበት ክስ በቁጥር ማቅሥአመ/239/02/ለ/08 በቀን 24/05/2008 ዓ/ም በተጻፈ ደብዳቤ ምላሽ ሰጥቷል፡፡

ጋዜጠኛ መልካምሰላም ሞላ

ጋዜጠኛ መልካምሰላም ሞላ


‹‹ማኅበረ ቅዱሳን ጥቅሙና ጉዳቱ በሚገባ ሳይጠና ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንጻር የሚያስከትለው የሃይማኖት እና የስርዓት ተፋልሶ ሳይፈሽ ራሱ አርቅቆ ባጸደቀው ደንብ በቅ/ሲኖዶስ የተፈቀደልኝ ህጋዊ ማኅበር ነኝ ይላል …›› ለሚለው የፓትሪያርኩ ክስ፤ ማህበሩ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃና መምሪያ ስር ህጋዊ በሆነ ስርዓት በቅዱስ ሲኖዶስ ሙሉ እውቅናና ፈቃድ ተዋቅሮ የሚመራበት ደንብ በመጀመሪያ በማደራጃ መምሪያው በኩል በኋላም በ1992 ዓ/ም በቅዱስ ፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት በኮሚቴ ታይቶና ተመርምሮ የጸደቀለት እንዲሁም በ1994 በቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ደረጃ ቀርቦ የታየ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት እና ሊቃነ ጳጳሳት የተሳተፉበት ለ 6 ወር የፈጀ ጥናት የተደረገበት የማኅበሩ ደንብ በምልዓተ ጉባኤው የፀደቀና ሁሉም ሊቃነ ጳጳሳት የፈረሙበት መሆኑን ጠቅሰው ምላሻቸውን ሰጥተዋል፡፡ በ2004 ዓ/ም ከማኅበሩ አገልግሎት መስፋት ጋር ተያይዞ ከማደረጃ መምሪያው ጋር በነበረ አለመግባባት ለጊዜው ማኅበሩ ተጠሪነቱ ለብጹዕ ዋና ስራ አስኪያጅ እንዲሆን እና ማኅበሩን የበለጠ እንዲሰራ የሚያደርገው ደንብ ማሻሻያ እንዲያደርግ ኮሚቴ ተቋቁሞ ስራውን አጠናቆ ቢጨርስም ፓትርያርኩ በተደጋጋሚ አልቀበልም በማለታቸው መዘግየቱን በደብዳቤ ተገልጧል፡፡
abune matias

ቀደም ሲል በቅዱስ ሲኖዶስ የተሰየመው ኮሚቴን ጥናት አልቀበለም በማለት ሌላ የማኅበረ ቅዱሳን ተወካይ የሌለበት ኮሚቴ እንግዳ በሆነ መልኩ ቢያቋቁሙም ለቤተ ክርስቲያን ካለን አመኔታ አኳያ ይሁን ብለን ብንቀበልም ‹‹ በቅዱስ ሲኖዶስ የተወሰነውን ደንብ ማርቀቅ ስራ ሆን ብሎ በማሰናከል ያለ ደንብ እየሰራ ይገኛል›› የሚለው ወቀሳ እንዳስገረመው ማኅበረ ቅዱሳን ገልጧል፡፡ ከስድስት ጊዜ በላይ ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር ቀርበን ለመወያት ብንሞክርም ፍቃደኛ አልሆኑልንም ሲል ማኅበሩ ቅሬታውን በደብዳቤው አትቷል፡፡

በ2007 ዓ/ም ቅዱስ ሲኖዶስ ተሀድሶን በተመለከተ በቃለ ጉባኤው ‹‹የተሀድሶ የችግር ምንጭ ኮሌጆቹ እንደሆኑ ያመለክታል›› በማለት በኮሌጆች ውስጥ ያለው አሰራር መታየት እና መፈተሸ አለበት የሚል ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወቃል፡፡ ቢሆንም ኮሌጆቹ ላቀረቡት የሀሰት ክስ እኛ ተገኝተን ሳንጠየቅ ውሳኔ ማሳለፍዎ ቅር አሰኝቶናል፤ በበጎ ፍቃድ ቤተ ክርስቲያንን ማገልገላችን የሚያስመሰግን እንጂ የሚያስወቅስ አይደለም ብለዋል፡፡

ማኅበሩ የዓመቱን እቅድና በየስድስት ወሩ የአፈጻጸም ሪፖርት ተጠሪ ለሆነለት አካል ሲያስገባ እንደቆየ እና የገቢ እና የወጭ አሰራሩንም በመንግስት በተፈቀደላቸው የውጭ ኦዲተሮች ጭምር በየዓመቱ እያስመረመረ ሪፖርት ያቀርባል ያለው ደብዳቤው፤ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ተፈቅዶ በሚሰጣቸው ደረሰኝ መጠቀም እንደጀመረ አስረድቷል፡፡ ማኅበሩም በበጎ ፈቃድ የተመሰረተ በመሆኑ የማህበሩ የስራ ማስኬጃ በአባላቱ እንደየገቢያቸው መጠን በሚከፍሉት የአባልነት አስተዋጾ ይሸፈናል፡፡ ተጨማሪም ወጭ ሲኖርም አባላቱ አዋጥተው እንደሚሸፍኑ ቢታወቅም ‹‹ማኅበሩ በማይታወቅ ሁኔታ ገንዘብ እየሰበሰበ ለማይታወቅ አገልግሎት ያውላል›› ተብሎ መገለጹ የውሸት ውንጀላ ከመሆኑም በላይ ከአንድ ቅዱስ አባት የማይጠበቅ ተግባር ነው ሲል በደብዳቤው ተገልጧል፡፡ ማኅበሩ ገዳማት ራሳቸውን እንዲችሉ፣ የአብነት ተማሪዎች ድጋፍ አጥተው እንዳይበተኑ ለማድረግ ፕሮጀክት ቀርጾ ግልጽ እና ተጠያቂነት በሰፈነበት አሰራር ለሚመለከተው ክፍል አቅርቦ ስራ ላይ ያውላል፡፡ ስራውም በየሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳሳት የቅርብ ክትትል እንደማይለየው እየታወቀ ‹‹ከቤተ ክርስቲያን አባቶች የሚሰጠውን አመራር አይቀበልም ፤ አባቶችን ይዳፈራል›› ተብሎ መገለጹ አግባብነት አለው ብሎ እንደማያምን ማኅበሩ አስታውቋል፡፡

አብዛኛው የማኅበሩ አባላት ወጣት በመሆናቸው ተምረው መስፈርቱን እያሟሉ ክህነት እንደሚቀበሉ እና እርስዎም አሜሪካ እያሉ ክህነት መስጠትዎ አይዘነጋም ያለው ደብዳው፤ ክህነቱ የሚሰጠው በብጹዓን አባቶች በመሆኑ ቀኖና ቢጣስ እንኳን ማኅበሩ የሚጠየቅበት ምክንያት የለም ሲሉ ‹‹ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ውጭ በጅምላ ክህነት እያሰጠ›› በማለት የተገለጸው አግባብነት እንደሌለው አስረድተዋል፡፡

‹‹ባለፉት ሶስት አመታት እረስተውት ካልሆነ በቀር የማኅበሩ አባላት ለቤ/ን አንድነት በሚያደርጉት ከፍተኛ ተጋድሎ እንደ ገና ዳቦ ከሁሉም አቅጣጫ እሳት እየነደደባቸው የሚታገሱ መሆኑን በየጊዜው ለቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ከውጭ ሀገር በመጡ ቁጥር ይመሰክሩ ነበር፡፡ በቅርቡም አሜሪካ ሄደው በነበረ ጊዜ የተጋበዙባቸው አብያተ ክርስቲያናት እንዴት እዚያ ደረጃ እንደደረሱና ማን መስዋዕትነት እንደከፈለባቸው ፤አሁንም ቢሆን በቅዱስነትዎ ጉዞ ወቅት ማን እንዳስከበርዎ ልቦናዎ ያውቀዋል፡፡ … በሀገር ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ጉዞ ሲያደርጉ በደማቅ ሰልፍ የሚቀበሎት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ማኅበረ ቅዱሳን ቤተ ክርስቲያናቸውን እንዲያውቁና አባቶቻቸውን እንዲያከብሩ ስላስተማራቸው መሆኑ ግልጽ ነው›› ሲል አቡነ ማትያስ ፓትሪያሪክ ከመሆናቸው በፊት ለማኅበሩ ሲያደርጉት የነበረውን እገዛ እና ቀና አስተሳሰብ በማስታወስ አሁንም ማኅበሩ ወጣቶች ላይ እየሰራ ያለውን እንቅስቃሱ ገልጦ ጽፏል፡፡
‹‹በሌለው ስልጣን የጾም አዋጅ እስከማወጅ ደርሷል ›› ለሚለው ውንጀላም ማኅበረ ቅዱሳን እስከዛሬ ያወጀው ጾም የለም ያለ ሲሆን ክሱ ‹በቤተክርስቲያን ጾም በዝቷል ካልተቀነሰ› የሚሉት ተሀድሶዎችን ሀሳብ ለምን አትደግፉም የሚል ይዘት አለው ብሏል፡፡ በተሃድሶ እምነት አራማጆች በሚያዘጋጇቸው እና በሚመሯቸው ድረ-ገፆች እና ብሎጎች ማህበሩን ጥላሸት ለመቀባት ይነሱ የነበሩ ሃሳቦች በእርስዎ ደብዳቤ ማየታችን አሳዝኖናል አስገርሞናልም፡፡ እነሱን ንቀን መልስ ሳንሰጣቸው የቆየን ቢሆንም በእርስዎ ደረጃ ይህ በመነሳቱ ለመመለስ ተገደናል ሲል የገለጠው የማኅበሩ ደብዳቤ አሁንም ተነጋግረን መፍትሄ ማምጣት የተሻለ አካሄድ መሆኑን ጠቁሟል፡፡

ማኅበሩ አጥጋቢ ስራ ሰርቷል ወይም አልሰራም፤ ስሕተቶችንም ይፈጽማል አይጽምም ብሎ መከራከር መውቀስ እና በሃሳቦም መወያየት አስፈላጊም ሲሆን መገሰጽ እየተቻለ ከአንድ ቅዱስ አባት የማይጠበቅ የሰዎችን ስሜት በሚያስቆጡ ቃላት መሸንቆጠረ በእጅጉ አሳዝኖናል ብለዋል፡፡

ስለዚህ ጉዳዩን ቅዱስ ሲኖዶስ ተመልክቶ ተወያይቶ እርምትና መፍትሄ እንዲሰጥበት እንጠይቃል በማለት የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ የሆኑት ቀሲስ ዶክተር ሰሙ ምትኩ ደብዳቤውን በፊርማቸው አረጋግጠዋል፡፡

The post ማኅበረ ቅዱሳን ለፓትርያርኩ ምላሽ ሰጠ | መልካም ሞላ appeared first on Zehabesha Amharic.

“አውዳሚ የምላቸውን ሐሳቦች ለመፋለም ሞክሬያለሁ” –በዕውቀቱ ስዩም

ሴቶች የቀድሞ ልማዶቻቸውን ከትዳራቸው ጋር እንዴት አጣጥመው ማስኬድ ይችላሉ? |ለወንዶች ማንበብ በፍፁም የተከለከለ ነው

$
0
0

በሊሊ ሞገስ

ወንዶች ትዳር ከመሰረቱ በኋላ ከዚያ በፊት ያደርጓቸው የነበሩትን ማህበራዊ መስተጋብር ወይም ተጨማሪ ገቢን ለማግኘት ሲያከናውኗቸው የነበሩ ተግባሮችን በጠቅላላ ያቆማሉ፡፡ ይህ አካሄድ በሴቶችም ላይ ጎልቶ ይስተዋላል፡፡ ባለቤታቸው ጠቀም ያለ አስቤዛ የሚሰጥ ከሆነም ስራቸውን አቁመው ተጧሪ የሚሆኑ ሴቶችም ከብዙ በጥቂቱ አይጠፉም፡፡ እናም እንደ ቀድሟቸው ከጓደኞቻቸውም ሆነ ከቤተሰቦቻቸው ጋር መገናኘትና ራሳቸውን መንከባከብን ያቆማሉ፡፡ ይህ ብዙ ሴቶች ካገቡ በኋላ የሚፈፅሙት ስህተት እንደሆነ ይገመታል፡፡

‹‹ትዳር ሙሉ ሰው ያደርጋል›› ከሚለው በተቃራኒ፣ ብዙዎቹ በትዳቸው ግማሽ ሰው ሆነው ደስታ እንዲያጡም ይህ አካሄድ የራሱ የሆነ አሉታዊ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡
አንዲት ሴት በትዳር ህይወቷ ስላጋጠማት ችግር ያወጋችኝን ላካፍላችሁ ወደድኩ፡፡
Cheating

‹‹…ከባለቤቴ ቢኒያም ጋር ስንጋባ ውጭ ውጭ የምትል ሴት ለትዳር አትረባም በሚል፣ ባለቤቴን በሚገባ ለመንከባከብ እንዲመቸኝ ስራዬን አቆምኩ፡፡ ጓደኞቼንም ተውኳቸው፡፡ ትዳር ከመያዜ በፊት ለረጅም ጊዜ በሳምንት አንድ ቀን ከጓደኞቼ ጋር ተራራ የመውጣት ፕሮግራም ነበረኝ፡፡ ይህ ተግባር ፍፁም ደስታን ይስጠኝ ነበር፡፡ ከመደበኛ ስራዬም ውጪ ባለኝ ትርፍ ጊዜ ስፖርት አዘውትሮ ነበር፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በተለያዩ የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴዎች ላይ መሰተፌ ውስጣዊ እርካታን ስለሚፈጥርልኝ፣ በህይወቴ በጣም ደስተኛና ምቹ ባህሪ ያለን ሰው ነበርኩ፡፡ ሆኖም ትዳር ከመሰረትኩ በኋላ እነዚህን እንቅስቃሴዎች በሙሉ እርግፍ አድርጌ በማቆም ሙሉ ጊዜዬንና ትኩረቴን ለባለቤቴ መስጠት ጀመርኩ፡፡

ከጓደኞቼ ጋር ከማሳልፈው ጊጊ ይልቅ ከባለቤቱ ጋር እራት በልቼ የፍቅር ፊልም ለማየትና በቤት ውስጥ እየተዝናኑ ለማሳለፍ ወሰንኩ፡፡ ባለቤቴም ምርጫዬን አልተቃወመም፡፡ እንዲያውም በመጀመሪያ ለትዳራችን ስምረት ስል ከጓደኞቼ ጋር መገናኘት ማቆሜን ስነግረው፣ አብረን ብዙ ጊዜ ለማሳለፍ መምረጤና ለትዳሬ ዋጋ በመክፈሌ ተደስቶ እጅግ አመስግኖኝ ነበር፡፡ ከጥቂት ወራት በኋላ ግን ባለቤቴ ለእኔ ያለው ፍቅር ባይቀንስም አዳዲስ ባህሪያትን ማንፀባረቅ ጀመረ፡፡ ከእራት በኋላ ከእኔ ጋር ሆኖ ፊልም ከማየት ለብቻው ሆኖ መጽሐፍ ማንበብ መረጠ፡፡

ይባስ ብሎ በሳምንት አንዴ ከጓደኞቹ ጋር እየተጨዋወተ ለማምሸት ፕሮግራም አደረገ፡፡ ይህ የባለቤቴ ተግባር በጣም አናደደኝ፡፡ ስሜቴን የማረግብበት ምንም መፍትሄ ስላጣሁ እቤት ቁጭ ብዬ በመብሰልሰሌ በጣም ተጎዳሁ፡፡ ባለቤቴም ከጓደኞቹ ጋር ተዝናንቶ ሲመጣ ሰላም ልሰጠው አልቻልኩም፡፡ በዚህም ምክንያት በቤታችን ሰላም ከጠፋ ሰነባብቷል፡፡

አሁን አሁን ሳስበው፣ የመጀመሪያ ውሳኔዬ እጅግ የተሳሳተ መሆኑ ይሰማኛል፡፡ በመሆኑም ማንኛውም ሰው ለትዳሩ የሚገባውን ትኩረት እና እንክብካ መስጠቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ትዳሩን አደጋ በማይከት መልኩ ራሱን ማዝናናትም ሆነ ማህበራዊ ግንኙነቶቹን ማስፋት ከዚህም በተጨማሪ ምርጫው በሆኑ መዝናኛዎች ላይ መሳተፍ አለበት ብዬ አምናለሁ›› በማለት ተሞክሮዋን አካፍላናለች፡፡

እርግጥ ነው ከትዳር በኋላ ቀደምት እንቅስቃሴዎቻቸውን የሚተዉ ወንዶች ባይጠፉም፣ በአብዛኛው በዚህ መንገድ ሲጓዙ የሚታዩት ሴቶች መሆናቸው የዛሬው ጽሑፌም ሴቶች ላይ ያተኩራል፡፡ በዚህም መሰረት እንደ ሄለን ያሉ ሴቶች ከትዳር በኋላ የግል ምርጫዎቻቸውን እርግፍ አድርገው በመተው ቤት ቤት ማለት ሲያበዙ ከሚገጥሟቸው ተግዳሮቶች በመነሳት ከነገሩን መካከል የተወሰኑትን ጠቅለል ባለ መልኩ አቅርቤዋለሁ፡፡
የግል ፍላጎት (እንቅስቃሴን) መተው ያለው ትዳራዊ አንድምታ!

– እንደ ሃና ባለቤት ብዙዎቹ በትዳር መባቻ ሚስቶቻቸው ጓደኞቻቸውንና ሌሎች በግላቸው የሚያከናውኗቸውን እንቅስቃሴዎች ትተው ከእነሱ ጋር ብቻ ጊዜያቸውን ሲያጠፉ ደስ ይላቸዋል፡፡ እንዲያውም አንዳንዴ ሚስቶቻቸው ከጓደኞቻቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት ማቆም እንዳለባቸው ያስጠነቅቋቸዋል፡፡ ትንሽ ቆይተው ግን ባሎች ራሳቸው አዲስ ነገር ፍለጋ ውጭ ውጭ ማለት ይጀምራሉ፡፡

– ባሎች ሚስቶቻቸው በራሳቸው ስራ ሲጠመዱ ማየት የበለጠ ይመቻቸዋል፡፡ ቤታቸው መምጣት የሚናፍቃቸው ሚስታቸው ከእነሱ የተለየ የግል ህይወት ሲኖራት ነው፡፡ አንዲት ሴት ባሏ ወደ ቤት ሲገባ መጽሐፍ እያነበበች፣ ድርሰት እየፃፈች ወይም የግል ስራዋን እየሰራች ከጠበቀችው፣ ወይም ‹እስካሁን ጥለኸኝ ጠፋህ አይነት…› ወቀሳ ይልቅ አብረዋት ስሚሩ ባልደረቦቿ የምታጫውተው ወይም አዳዲስ ሐሳቦችን የምታካፍለው ከሆነ የተሻለ ነፃነት እንደሚሰማው ብዙዎች መስክረዋል፡፡ ሠራተኛ ሚስት ያለቻቸው ባሎች እነሱ የማያውቁትን ነገር ባለቤታቸው ስታጫውታቸው፣ በመካከላቸው ያለው ጓደኝነትና የውይይት አጀንዳ ስለሚጎሉበት ይበልጥ ይደሰታሉ፡፡

– እስቲ እርስዎ ባለትዳር ከሆኑ ከባለቤትዎ ጋር ያለዎትን የቀን ተቀን ግንኙነት ልብ ብለው ያጢኑ፡፡ ባለቤትዎ ከእርስዎ ጋር መነጋገር የሚፈልገው መቼ ነው? ለረጅም ሰዓት ስልክ ሲያነጋግሩ ወይም ስራ ሲይዙ አልያም አስቸኳይ ቀጠሮ ይዘው ለመውጣት ሲጣደፉ? ከዚህ በተቃራ እርስዎ ባለቤትዎን ለማዋራት ቁጭ ብለው ያለምንም ስራ ሲጠብቁት እሱ በስራ ተጠምዶ የማውራት ፍላጎቱ ሲቀንስ ማስተዋል የተለመደ ነው፡፡

በተመሳሳይ መልኩ በመጀመሪያው ትዳር ዓመት ስህተት እንደፈፀመች የምትናገረው ኑኑ እንዲህ ትላለች፡- ‹‹አብዛኞቹ ወንዶች የሚስቶቻቸው አትኩሮት በእነሱ ላይ ብቻ ሲሆን ደስ ይላቸዋል የሚል የተሳሳተ እምነት ነበረኝ፡፡ በመሆኑም ስራዬን በመልቀቅ ባለቤቱን ለመንከባከብ ወሰንኩ፡፡ ይህ በሆነ በሁለት ዓመቱ ግን ከባለቤቴ ጋር መሰለቻቸት ላይ ደረስን፡፡ ይሄን ስገነዘብም የመንግሥት ሠራተኛ መሆኔን ባቆምም በግሌ ሌላ ስራ ጀመርኩ፡፡ በመሆኑም ከባለቤቴ ውጭ ከጓደኞቼ ጋር አብሬ መዝናኛ ቦታዎች እሄዳለሁ፤ ለአራት ዓመት ያህል በሳምንት ሁለቴ ቴኒስ እጫወት ነበርና ይህም የተስተካከለ አቋም እንዲኖረኝ ከማድረጉም በላይ ንቁ፣ ደስተኛና መንፈሰ ጠንካራም አድርጎኛል፡፡

በቤተክርስቲያን በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ላይ ከመሳተፍ ባሻገር፣ በማታ ፈረቃ የኮሌጅ ትምህርት መከታተል ጀምሬም ነበር፡፡ የማከናውነው ነገር በበዛ ቁጥር ባለቤቴ ለእኔ ያለው ፍቅር እየጨመረ መምጣቱን አስተውያለሁ፡፡ እሁድ፣ እሁድ ቴኒ ለመለማመድ ስሄድ ባለቤቴ እንደሚናፍቀኝ ማወቅ ያስደስተኝ ነበር፡፡ አንዳንዴ እኔ ሳልጤቀው ባለቤቴ ቴኒስ ስለማመድ መጥቶ ያየኛል፡፡ እኔም ብሆን ከቀድ ይበልጥ ለራሴና ለማንነቴ የምሰጠው ግምት ጨምሯል፡፡ ባለቤቴም ለእኔ ያለው አትኩሮት ከበፊቱ መጨመሩን ተገንዝቤያለሁ፡፡ በተደጋጋሚም አድናቆን ገልፆልኛል›› ስትል ትናገራለች፡፡ በመጨረሻም ማንኛዋም ትዳር የያዘች ሴት ከባልና ሚስትት ተጨማሪ ህይወት ሊኖራት ይገባል ባይ ነኝ በማለት ልምዷን አካፍላለች፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ የስነ ልቦና ተመራማሪዎች የሚሉት ነገር አለ፡፡ አንድ ሰው ሌላውን ለመውደድና ለመንከባከብ በቅድሚያ ራሱን መጠበቅ እና ማዳን እንዳለበት ሲሆን፣ አንዲት ሴት ጤናዋን እና ስነ ልቦናዋን ከጠበቀች ባለቤቷን በኢኮኖሚ ከመደገፍ በተጨማሪ ትዳሯ እንዲባረክ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ታበረክታለች፡፡ ከዚህ በተቃራኒ ያለ ስራ የተቀመጡ ሚስቶች ብቻቸውን መሆን ስለሚሰለቻቸው በየሰዓቱ ባለቤታቸው ጋ እየደወሉ መነጫነጭ ወይም ጠብ መፍጠር ይቃጣቸዋል፡፡

– በአጠቃላይ ሴቶች መረዳት ያለባቸው ነገር ወንዶች ራሳቸውን በራሳቸው ለመንከባከብ ብቁ መሆናቸውን ነው፡፡ ወንዶች በተፈጥሯቸው ለራሳቸው ፍላጎት ቅድሚያን ይሰጣሉ፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ሴቶች ለሌላው መኖር እና ለስሜታዊ ቅርርቦሽ አብዝተው ይጨነቃሉ፡፡ የራሳቸውን ፍላጎት ሳያሟሉ ሌሎች ያሟላሉ፡፡ ለዚህ ተግባራቸው ምስጋና ሳያገኙ ወይም ዕውቅና ሳይቸራቸው ምስጋና ሳያገኙ ወይም እውቀት ሳይቸራቸው ሲቀር ስሜታቸው ክፉኛ ይጎል፡፡ ይህ ሲባል ግን ሚቶች በግል ተግባራቸው ተወጥረው ከባለቤታቸው ጋር የሚያሳልፉት ጊዜ ሊኖራቸውአይገባም ማለት አይደለም፡፡ ባለትዳር ሴቶች ከባለቤቶቻቸው ጋር ለመዝናናት፣ ጥሩ የፍቅር ጊዜትን ለማሳለፍ ብሎም በጋራ ጉዳዮ ላይ ለመምከር በቂ ጊዜ ሊኖራቸው ይገባል፡፡

እንደዚሁም ቀደም ሲል ከጓደኞቻቸው ጋር ያደርጉት የነበረውን ለምሳሌ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ኮሌጅ መማርና የግል ስራ መስራት የመሳሰሉትን ካገቡ በኋላም መቀጠል ይገባቸዋል ነው፡፡ ባለቤትዎ በህይወትዎ ትልቅ ቦታ ያለው ሰው ቢሆን፣፣ ህይወትዎን በሙሉ ለባለቤትዎ መስዋዕት በማድረግ ከልክ በላይ መጣበቅ ግን ሸክሙን ሊያከብደው ስለሚችል፣ በውህደት ውስጥ ላለመጥፋት ጥንቃቄ በማድረግ ሚዛናዊ አካሄድ መከተል ተገቢ ነው፡፡

– ባሎች፣ ሚስቶቻቸው ነፃ ሆነው በግላቸው ሲንቀሳቀሱና የሚያከናውኑት ነገር ሲኖራቸው የበለጠ ደስተኛ እንደሚሆኑ ይታመናል፡፡ ሆኖም ባለትዳር ሴቶች ስራ መስራት ያለባቸው ባለቤታቸው ደስተኛ እንዲሆን፣ እንዲናፍቃቸው ወይም በእሱ ላይ የሙጥኝ እንዳይሉ ብቻ አይደለም፡፡ የግል ህይወት ሊኖራቸው የሚገባው ራሳቸውን  ለማስደሰትና የተሻለ ህይወት ለመምራት ብሎም ለተፈጠርንለት አላማ ለመቆም መሆን አለበት፡፡

አንዲት ሴት ከትዳር በፊት ስራ ከነበራት ትዳር ስትይዝ አስገዳጅ ሁኔታዎች ካልተፈጠሩ በቀር ስራ ማቆም የለባትም፡፡ ከትዳር በፊት ጎበዝ ሃይማኖተኛ፣ አስተዳዳሪ፣ ፖለቲከኛና በሌሎችም የሥራ መስኮች ተሳትፎ ያደርጉ የነበሩ ሴቶች ካገቡ በኋላ የቀድሞ ተግባራቸውን ሲያቆሙ እናያለን፡፡ ምናልባትም አንዲት ታዋቂ ፖለቲከኛ የነበረች ሴት ካገባች በኋላ የፀጉሯ ምክትል ጠ/ሚኒስትር ማን እንደሆነ ላታውቅ ትችላለች፡፡ በመሆኑም ለአንዲት ሴት ትዳሯ ራሷን አስራ አዕምሮዋን እንድትገድል የሚያደርጋት ተቋም እንዳልሆነ ልታወቅ ይገባል እላለሁ፡፡

የትኛውንም አይነት እንቅስቃሴ ለብቻ ማከናወን አለመፈለግ

ሌላው የባለትዳር ሴቶች ችግር ደግሞ፣ ትዳር ከያዙ በኋላ ሁሉንም ነገር ከባለቤታቸው ጋር አብረው ማድረግ ያለባቸው ይመስላቸዋል፡፡ ሳያገቡ በፊት በግላቸው ያደረጉት የነበረውን ነገር ትዳር ከመሰረቱ በኋላ ለብቻቸው መስራት የተራራ ያህል ሲከብዳቸወ ይታያል፡፡

ሄለን የተባለች ሴት ትዳር ከያዘች በኋላ እንዲህ አይነት ችግር እንደገጠማት ትናገራለች፡፡ ‹‹ሳላገባ በፊት ማንኛውንም ነገር በግሌ እሰራ ነበር፡፡ መግዛት ያለብኝን ዕቃ፣ የምመርጠውን የዕቃ አይነት፣ የፀጉሬን ሰራርና የልብስ ምርጫዬን ወዘተ… በግሌ እወስን ነበር፡፡ ካገባሁ በኋላ ከተወሰኑ ወራት በኋላ ግን ስለምሰራው ነገር ሁሉ ባለቤቴን ማማከር ጀመር፡፡ በግ ማከናወን የምችለውን ነገር ባለቤቴን ሳላማክር ማድረግ ያስፈራኝ ጀመር፡፡ ቤታችን ቀለም እንዲቀባ ስፈልግ ባለቤቴ አብሮ ጥሩ ቀለም እንዲመርጥ እጠይቀዋለሁ፡፡ ጠረጴዛና ወንበር መግዛት ሲያስፈልግም እንዲሁ ባለቤቴ እንዲመርጥ እፈልጋለሁ፡፡

ሌላው ቀርቶ የፀጉሬ አሰራርና አለባበሴን ባለቤቴ እንዲመርጥ እጠይቀው ጀመር፡፡ ሁልጊዜ ባለቤቴ ስራውን እየተወ አብሮ ሲያማርጠኝ ቆየ፡፡ አንድ ቀን ግን ባለቤቴን የቤት ዕቃዎችን እንዲያገዛኝ ስጠይቀው፣ ብዙ ስራ እንዳለበትና እኔ የመሰለኝን ወይም ከጓደኞቼ ጋር ሄጄ እንድገዛ ሐሳብ ሰጠኝ፡፡ ምርጫዬ እንደሚስማማውም ገለፀልኝ፡፡ ሆኖም ግን ብቻዬን ሄጄ የቤት ዕቃ ለመግዛት አልደፈርኩም፡፡ በቤት ውስጥ ያሉ ዕቃዎችን መለወጥ ቢያስፈልግም ስህተት ከመስራት ያለቁ ወንበሮችና ጠረጴዛዎችን ለስድስት ወር ያህል መጠቀም መረጥኩኝ፡፡

የሄለን አይነት ችግር በብዙ ባለትዳሮች ላይ የሚታይ ነው፡፡ ሄለን ለመስራት የምትፈልገውን ነገር ባሏን ማማከሯ ከአንድ መልካም ሚስት የሚጠበቅ ተግባር ቢሆንም፤ ነገር ግን ባሏ ዕቃ የማጋዛት ፍላጎት እንደሌለው ወይም ሌላ የሚያከናውነው ተግባር እንዳለው ሲገልፅላት ለብቻዋ መንቀሳቀስና ለራሷ ምርጫና ፍላጎት ዋጋ መስጠት ነበረባት፡፡ ይህ አይነቱ አካሄድ በሂደት በራስ የመተማመን መንፈስ ይቀንሳል፡፡

ለባለቤትዎም ሁሌ እርዳታን የሚጠብቅ ሸክም ይሆናሉ፡፡ ጥሩ ትዳር የሚፈጠረው ጥንዶች በግላቸውና በጋራ የሚሰሩትን ማመጣጠን ሲችሉ ነው፡፡ ብዙዎቹ ትዳር የያዙ ሴቶች ግን ያላቸውን ተሰጥኦ መጠቀም ትተው በባለቤታቸው ሐሳብ መመራት ይጀምራሉ፡፡ የግል ህይወታቸውንም አቁመው በጠቅላላ ከባለቤቶታቸው ጋር የተቆራኘ ያደርጋሉ፡፡ ከዕለታት በአንዱ ቀን ባለቤታቸው የግል ህይወቱን መምራት እንደሚፈልግ በተረዱ ጊዜም የመክዳት፣ የመተው፣ የሐዘንና የተበዳይነት ስሜት ይሰማቸዋል፡፡ እርስዎም እንዲህ አይነቱን ስህተት እንዳይፈጽሙ ጥንቃቄ ያድርጉ፡፡

The post ሴቶች የቀድሞ ልማዶቻቸውን ከትዳራቸው ጋር እንዴት አጣጥመው ማስኬድ ይችላሉ? |ለወንዶች ማንበብ በፍፁም የተከለከለ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

Sport: ሊዮኔል ሜሲ የዓለማችን ምርጡ ተጫዋች

$
0
0

ከ2008 ወዲህ ባሉት ዓመታት የፊፋ ባሎን ደ ኦር ሽልማትን ሁለት ተጨዋቾችን ብቻ ማለትም ሊዮኔል ሜሲ እና ክርስቲያኖ ሮናልዶ በየተራ ሲፈራረቁበት መዝለቃቸው ይታወሳል፤ ሆኖም ግን እስካሁንም ድረስ ከሁለቱ አርጀንቲናዊው የዓለማችን እጅግ ምርጡ ተጫዋች ማነው? የሚለው ጉዳይ መወያያ ርዕስ ሆኖ መዝለቁ አልቀረም፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ የዓለማችን ምርጥ የፉትቦል ተንታኞች ሰሞኑን ካስነበቡት ፅሑፍ ውስጥ ግን ከዚህ በታች ያለው ሙያዊ ዳሰሳቸው የ26 ዓመቱ አርጀንቲናዊ የባርሴሎና ኮከብ መጠነኛ የሆነ ብልጫን መያዙን የሚጠቁም ሆኗል፡፡

mesi2

ባለፉት 10 ዓመታት ውስጥ የያዘውን ከፍተኛ ብቃትን በሜዳ ላይ እንዲወጣ በማስቻልና በዙሪያው ከሚገኙት የቡድን ጓደኞች በተገቢው መልኩ ተጠቃሚ በመሆን ብልህነቱ ሊዮኔል ሜሲ ከዋነኛ ተቀናቃኙ ክርስቲያኖ ሮናልዶ አንፃር የተሻለ ምርጥ ተጫዋች ሆኖ ዘልቋል ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ በእርግጥ ሮናልዶ በ2014/15 ሲዝን በ54 ግጥሚያዎች ላይ 61 ጎሎችን ለማስቆጠር የቻለበት ሪከርዱን ሜሲ በተመሳሳይ የውድድር ዘመን በ57 ግጥሚያዎች 58 ጎሎን ለማስቆጠር ከቻለበት ሪከርዱ አንፃር የተሻለ የሚባል ነው፤ ሆኖም ግን አርጀንቲናዊው  ኢንተርናሽናል በ2015 ከባርሴሎና ጋር የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ድልን ለመቀዳጀት ከመቻልም አልፎ ለስፓኒሽ ላሊጋ ሻምፒዮንነትና ለኮፓ ዴል ሬይ ድሎችም መብቃቱ ሲታወስ የሚኖር አይነት ተደናቂ የውድድር ዓመትን ለማሳለፍ ችሏል፡፡ ሜሲ ከባርሴሎና ጋር የሶስትዮ ዋንጫ ድልን ሉዊስ ሱዋሬዝ እና ኔይማር ከጎኑ ሆነው ያበረከቱለት እገዛን ከፍተኛነት ችላ ሊባል የማይገባው ነው፡፡

ጋሬዝ ቤል፤ ሀሜስ ሮድሪጌዝ እና ካሬም ቤንዜማ ግን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ የሰጡት ድጋፍ ያነሰ የሚባል ነው፡፡ ሪያል ማድሪድ በእያንዳንዱ የውድድር ዓመት ትልቅ ስም ያላቸው ተጫዋቾችን በስኳዱ የመያዝ ባህል ያለው ቢሆንም ክርስቲያኖ ሮናልዶ በ2009 ፕራሲዝን ማንቸስተር ዩናይትድን በመልቀቅ ሳንቲያጎ በርናባው ከደረሰ ወዲህ ግን ከአንድ በላይ የስፓኒሽ ላ ሊጋ ሻምፒዮንነት ክብርን ለመቀዳጀት አልቻለም፡፡ ይህ በዚህ ወቅት አትሌቲኮ ማድሪድ ካስመዘገበው ሪከርዱ ጋር ተመሳሳይነት ያለው መሆኑም ሮናልዶ ከያዘው ትልቅ ደረጃ አንፃር በዙሪያው የሚገኙት ተጫዋቾችን ለዋንጫ ድሎች የማነሳሳት አስተዋፅኦን ከሊዮኔል ሜሲ አንፃር አነስተኛ የሚባል መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡

ሮናልዶ ከቡድኑ ጋር ከሚቀዳጃቸው የዋንጫ ድሎች ይልቅ በግሉ ለሚያገኛቸው ሽልማቶች ከፍተኛ የሆነ ጉጉት እንዳለውም በቅርቡ ባወጣው የራሱን ህይወትን የሚዳስስ ዶክመንተሪ ፊልም ላይ በሰጠውመግለጫ ያንፀባረቀ ሆኗል፡፡ በወቅቱ ፖርቹጋላዊው ኢንተርናሽናል በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየቱን የሰዘነረው ‹‹ከ2009 እስከ 2012 ድረስ ባሉት አራት ተከታታይ ዓመታት ሊዮኔል ሜሲ የባሎን ደ ኦር ሽልማትን ሲያገኝ ራሴን እንድወቅሰው ምክንያት ሆኖኝ ነበር የሚል ነው፡፡

ይህ የክርስቲያኖ ሮናልዶ አስተያየት እግር ኳስ የቡድን ስፖርት መሆኑን እስከመዘንጋት ደረጃ ደረሰ የመሰለበት ተደርጎ ተቆጥሮበታል፡፡ ሜሲን ከሮናልዶ በላይ የዓለማችን ትክክለኛው እጅግ ምርጡ ተጫዋች የሚያስብለውም ዋነኛው መስፈርት ለቡድን ስራ የሚሰጠው ከፍተኛ የሆነ ከበሬታ ነው፡፡ በ2015 ዓመት ሊዮኔል ሜሲ ለቡድን ጓደኞች የፈጠራቸው ጎሎችን የማስቆጠር እድሎች ሮናልዶ በተመሳሳይ ወቅት በስ ካስመዘገባቸው ጋር በጭራሽ የማይደራረስ መሆኑን የሚያንፀባርቅም ጭምር ነው፡፡ አርነጅቲናዊው ኮከብ በኢንተርናሽናል ደረጃም ከፖርቹጋላዊው አንፃር በብዙ መልኩ የሚሻል ሪከርድን በ2015 የውድድር ዓመት ለማስመዝገብ ለመቻሉ የአገሩ ዋናው ብሔራዊ ቡድንን በአምበልነት ለመምራት በቺሊ አዘጋጅነት በተካሄደው የኮፓ አሜሪካ ውድድር የፍጻሜ ጨዋታ ያደረሰበት በቂ ማስረጃ ነው፡፡ በዛ የፍፃሜ ግጥሚያ ሜሲ አርጀንቲናን ለዋንጫ ሽልማት ባለቤትነት ለማብቃት ያልቻለው ቡድኑ የመለያ ምቶች ዕድለቢስ ስለነበር እንደሆነ ይታወሳል፡፡

The post Sport: ሊዮኔል ሜሲ የዓለማችን ምርጡ ተጫዋች appeared first on Zehabesha Amharic.

Sport: ‹‹የተከላካይ ክፍሉ በዚህ ጥንካሬው ከቀጠለ ዩናይትድ የውድድር ዘመኑን በስኬት የማጠናቀቅ ዕድሉ የሰፋ ነው›› ዳቪድ ደ ሂያ

$
0
0

 

ምንም እንኳን ማንችስተር ዩናይትድ ከሊጉ መሪ አርሰናል በዘጠኝ ነጥቦች ርቀት ላይ ቢገኝም የግማሽ የውድድር ዘመን የቀያዮቹ ሰይጣኖች አቅም ሲመዘን አሁንም ዩናይትድ የሊጉ ሻምፒዮን አሊያም በቻምፒዮንስ ሊግ የሚያሳትፈውን ደረጃ ይዞ ለማጠናቀቁ ዋስትና የለውም፡፡

David de Gea

ግብ ለማስቆጠር የሚቸገረው የሉዊ ቫን ሃል ቡድን በመጀመሪያው ሮክ ግማሽ የውድድር ዘመን ጥሩ ጎኑ ይነሳ ከተባለ የተከላከይ ክፍሉ በየጨዋታው በአማካይ ከአንድ ጎል በታች የሚያስተናግድበት መልካም ሪከርዱ ነው፡፡ ስፔናዊው ግብ ጠባቂ ዴቪድ ደ ሂያ አሁንም ምርጥ ብቃቱን ይዞ መዝለቁ ጉልህ ድርሻ አለው፡፡ ታዲያ ግብ ጠባቂው በውድድር ዘመኑ ዩናይትድ አንድ አይነት ዋንጫን አንስቶ ማጠናቀቅ ከፈለገ ይሄን የመከላከል ሪከርዱን ጠብቆ መጓዝ እንደሚኖርበት ሂያ በአፅንኦት ያስረዳል፡፡

በስፔን ብሔራዊ ቡድን ውስጥ የአኪር ካሲያስ የረዥም ጊዜ ተተኪ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው ዳቪድ ደ ሂያ በሰጠው ቃለ ምልልስ ይሄንና ሌሎችን ጉዳዮች ዳስሷል፡፡

ጥያቄ፡- ተደጋጋሚ ጉቶች የፈጠረው ተፅዕኖ እንዳለ ሆኖ የጣላችኋቸው ቁልፍ ነጥቦች ተስፋ እንድትቆርጡ አድርጓችሁ ይሆን?

መልስ፡- ይመስለኛል፡፡ ሁልጊዜም ቁልፍ ተጨዋቾች ጉዳት የሚያስተናግዱ ከሆነ ጨዋታዎችን ማሸነፍ ይከብዳል፡፡ እኛም በዚህ አይነት ሁኔታዎች ያለፍንባቸው አጋጣሚዎች ነበሩ፤ ነገር ግን ይሄ በተለይ ደረጃው ከፍ ባለ ሊግ የሚያጋጥም ነገር ነው፡፡ ኣዲሶቹ ወጣቶች ልምድ ያላቸውን ተጨዋቾች ተክተው የሚችሉትን ያህል አገልግሎት ሰጥተዋል፡፡ የአንጋፋዎቹን ያህል አስተዋፅኦ ከወጣቶቹ መጠበቅ ግን ተገቢ አይመስለኝም፡፡

ጥያቄ፡- ከዘንድሮው ዩናይትድ ጥሩ ነገር ይነሳ ከተባለ የተከላካይ ክፍሉ ሪከርድ ይጠቀሳል፡፡ በሙሉ ጥንካሬው ላይ ሲገኝ የውድድር ዘመኑን በስኬት ለማጠናቀቅ ምን ያህል አስተዋፅኦ ይኖረዋል?

መልስ፡- የተከላካይ መስመራችን ከአምናው በተሻለ ዘንድሮ ጠንካራ ይመስልሃል፡፡ ይሄ ደግሞ በጣም ወሳኝ እና አስፈላጊ ነው፡፡ ጎሎችን እንደ አምናው አብዝተን እያስተናገድን አይደለም፡፡ በማጥቃት ሚና ያለንን ጥራት በሚገባ ተጠቅመን ጎሎችን ካስቆጠርንና የተከላካይ ክፍሉ በዚህ ጥንካሬው ከቀጠለ ዩናይትድ የውድድር ዘመኑን በስኬት የማጠናቀቅ ዕድሉ የሰፋ ነው፡፡

ጥያቄ፡- ከዚህ ቀደም በኦልድ ትራፎርድ መጫወት የሚከብዳቸው በተለይ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ዩናይትድን እየፈተኑት ነው፡፡ ምናልባት የትኩረት እና የመደራጀት ችግር ይሆን?

መልስ፡- ይመስለኛል፤ ብዙ ጊዜ በኦልድ ትራፎርድ ስንጫወት ኳስን አብዝተን ስለምንቆጣጠር፤ በትኩረት ማጣት ጎሎችን አስተናግደን ነጥብ የጣልንባቸው ጨዋታዎች ነበሩ፡፡ አንዳንድ ቡድኖች ለረዥም ደቂቃ የጎል ዕድል ሳይፈጥሩ ቆይተው በድንገት መዳኛ መከላከል ቀጠና ይደርሳሉ፡፡ በዚህ ጊዜ የመከላከል ቅርፃችን ከተበላሸና ትኩረታችንን ካጣን ጎል ይቆጠርብናል፡፡

ጥያቄ፡- አንተ ወደ ኦልድ ትራፎርድ በመጣህበት ዓመት በሜዳችሁ ስትጫወቱ የነበረውን ሁኔታ ከዘንድሮው ጋር ስታነፃፅረው ምን አይነት ምስል ይሰጥሃል?

መልስ፡- ወደ ኦልድ ትራፎርድ መጥተው የሚጫወቱ ክለቦች ሁልጊዜም አዕምሯቸው ውስጥ የሚይዙት ከግዙፍ ክለብ ጋር እንደሚጫወቱ ነው፡፡ እነዚህ ክለቦች በራሳቸው ሜዳ ላይ ጥቅጥቅብለው መጫወትን ይመርጣሉ፡፡ ግን እንደ የክለቦቹ ይለያያል ክፍተቶችን ፈልገው ጎል ሊያስቆጥሩብን የሚመጡ ቡድኖችም ነበሩ፡፡ አሁን የዚህ አይነት ቡድኖች በርክተዋል፡፡

ጥያቄ፡- በማንቸስተር ዩናይትድ አምስተኛ ዓመትህን ይዘሃል፡፡ ከቆይታህ አንፃር አሁን የበለጠ ኃላፊነት ይሰማሃል?

መልስ፡- አሁን በዩናይትድ በርካታ አዳዲስ ወጣቶችን እየተመለከትኩ ነው፡፡ በርካታ ጨዋታዎችን ታደርጋለህ፡፡ ይሄ ደግሞ ተፅዕኖህ ከፍ እያለ እንዲሄድ ያደርገዋል፡፡ እንደ ግብ ጠባቂነቴ በተለይ የተከላካይ ክፍሉን መምራት ይጠበቅብኛል፡፡ ተከላካዮቻችን ከጫና ነፃ ሆነው እንዲጫወቱ ያደርጋቸዋል፡፡

ጥያቄ፡- በቻምፒዮንስ ሊግ ከምድብ ጨዋታዎች ማለፍ አለመቻላችሁ ምን ስሜት ፈጠረባችሁ? ዩሮፓ ሊግ መፅናኛ ይሆናችኋል?

መልስ፡- ዩሮፓ ሊግ ለእኔ ጥሩ ስሜት የሚሰጠኝ ፉክክር ነው፡፡ በተለይ በ2010 ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር ሆኜ ይሄን ዋንጫ አጣጥሜዋለሁ፡፡ ነገር ግን ይሄ በቻምፒዮንስ ሊግ ታሪክ ደማቅ አሻራ ያለው ማንቸስተር ዩናይትድ ነው፤ አሁን በሌላ ውድድር ውሰጥ ነን፤ ዩሮፓ ሊግን በዜይቢያዊ መንገድ ለማሸነፍ ጥረት እናደርጋለን፡፡ የማክሰኞ እና ረቡዕ የቻምፒዮጀንስ ሊግ ምሽቶችን ለለመደው ዩናይትድ ግን እንግዳ ነገር መሆኑ እርግጥ ነው፡፡ ቢሆንም ግን የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎችን በበቂ ዝግጅት ማድረግ ይኖርብናል፡፡ የምንገጥመው ትንሽ የሚመስለውን የዴንማርኩን ሚዲቲላድን ነው፤ ነገር ግን የደርሶ መልሱን ጨዋታ አሸንፈን በድል መንገድ እንደምንጓዝ ሙሉ ተስፋ አለኝ፡፡

ጥያቄ፡- ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር የዩሮፓ ሊግን ዋንጫ ያነሳው ከቻምፒዮንስ ሊግ ውጭ ከሆናችሁ በኋላ ነበር፡፡ ድሉን ያከበራችሁት ግን ለየት ባለ ሁኔታ ነበር፡፡

መልስ፡- በጣም ትክክል፡፡ ዋንጫዎችን ማሸነፍ የተለየ ስሜት ይሰጣል፡፡ እግርኳስ የቡድን ስፐርት እንደ መሆኑ ደስታውን በጋራ ማጣጣም ልዩ ነው፡፡ ለእኔ ግን የእንግሊዙን ፉልሃም አሸንፈን ዋንጫውን ያነሳንበትን ቀን የማልረሳው ነው፡፡

ጥያቄ፡- ከፊትህ የዩሮ 2016 ሻምፒዮና ይጠብቅሃል፤ ከፈረንሳይ ጉዞ በፊት ምን እያሰብክ ነው?

መልስ፡- ውድድሩ የሚጀምረው ገና ሰኔ ወር ላይ ነው፡፡ የመጀመሪያው ከዚያ በፊት በርካታ ፈተናዎች በክለቤ ይጠብቀኛል፡፡ ጊዜው ሲደርስ ግን ልዩ ስሜት የሚፈጥር ውድድር ይሆናል፡፡ ከስሜን ጋር የዩሮ 2012 ክብራችንን ለማስጠበቅ ከቡድኑ ጋር ተካትቼ መጓዝ ያስደስተኛል፡፡

The post Sport: ‹‹የተከላካይ ክፍሉ በዚህ ጥንካሬው ከቀጠለ ዩናይትድ የውድድር ዘመኑን በስኬት የማጠናቀቅ ዕድሉ የሰፋ ነው›› ዳቪድ ደ ሂያ appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live