Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

አላሙዲ ለአርቲስት ገነት ንጋቱ የውጭ ህክምና የሚሆን የትራንስፖርት ወጪ ለመቻል ቃል ገቡ

$
0
0

Alamudi and Genet
(ዘ-ሐበሻ) ተወዳጇ አርቲስት ገነት ንጋቱ ከህመሟ አገግማ ከሆስፒታል እቤቷ መግባቷን ዘ-ሐበሻ ከቀናት በፊት መዘገቧ ይታወሳል:: በአሁኑ ወቅት በሞጋቾች ድራማ ላይ በመተወን ላይ የምትገኘውና ሕመሟም ካልተሻላት ወደ ሙያዋ እንደማትመለስ የተነገረላት ይህችው ተወዳጅ አርቲስት ወደ ውጭ ሃገር ሄዳ መታከም እንዳለባት የተነገራት ሲሆን ይህን ወጪ ለመሸፈን እንዲቻል ሕዝብ እንዲረባበረብ ጥሪ ቀርቦ ነበር::

ሼህ መሀመድ አላሙዲ በሰይፉ ፋንታሁን እና በሰራዊት ፍቅሬ በኩል በላኩት መልዕክት መሰረት ወደ ውጭ ሃገር ሄዳ እንድትታከም የትራንስፖርት ወጪዋን እንደሚሸፍኑ ቃል ገብተዋል:: ሰይፉና ሠራዊት ዛሬ ገነትን እቤቷ ሄደው አላሙዲ የገቡትን ቃል መግለጻቸውንም ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ያመለክታል::

አላሙዲ ለአርቲስቷ የውጭ ህክምና መጓጓዣ ይሆን ዘንድ ቃል የገቡት ገንዘብ 800,000 ብር ነው::

The post አላሙዲ ለአርቲስት ገነት ንጋቱ የውጭ ህክምና የሚሆን የትራንስፖርት ወጪ ለመቻል ቃል ገቡ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

↧

ቴዲ አፍሮ በዋሽንግተን ዲሲ በተሳካው የሙዚቃ ኮንሰርቱ ላይ “ጃ ያስተሰርያል”ን ሲዘፍን የሚያሳይ ቪዲዮ

$
0
0

teddya fro
(ዘ-ሐበሻ) ቴዲ አፍሮ እና ጎሳዬ ተስፋዬ ትናንት ምሽት ጃንዋሪ 2, 2016 ዓ.ም የተሳካ የሙዚቃ ኮንሰርት በዋሽንግተን ዲሲ አደረጉ:: ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር በተመዘገበበት በዚሁ ትልቁ ኮንሰርት ላይ ሕዝቡ በከፍተኛ ሁኔታ መደሰቱን በሶሻል ሚድያዎች ከሚሰጣቸው አስተያየቶች መረዳት ተችሏል:: ቴዲ አፍሮ በሰሜን አሜሪካ የጀመረው ኮንሰርት ከቀናት በኋላ በላስቬጋስ እና በሌሎች ከተሞችም ይቀጥላል ተብሏል:: ለዛሬው ትናንት በዋሽንግተን ዲሲው ኮንሰርት ያስተሰርያልን ሲጫወት የሚያሳየውን ቪዲዮ ይመልከቱ::

The post ቴዲ አፍሮ በዋሽንግተን ዲሲ በተሳካው የሙዚቃ ኮንሰርቱ ላይ “ጃ ያስተሰርያል”ን ሲዘፍን የሚያሳይ ቪዲዮ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

የመጨረሻዉ መጀመሪያ -ከሳዲቅ አህመድ

$
0
0

 

አሜሪካ ለምን የአርባ ምንጭ የሰዉ አልባ አይሮፕላን ማስነሻ ጣቢያዋን መተዉ አስፈለጋት?

 

(ሳዲቅ አህመድ)

(ሳዲቅ አህመድ)

ወደ አለም አቀፉ የዲፕሎማሲ መንደር ቀረብ ቀረብ ማለት ከጀመሩ ወራት ተቆጥረዋል።ከሐያላኑ አገራት ጋር የቀጥታ ሳይሆን የእጅ አዙር የዲፕሎማሲ ጉዞን ሳይጀምሩ አልቀሩም የሚሉም አሉ። በጠመዝማዛዉ መንገድ የሚጓዙት የዲፕሎማሲ ጉዞ ከሚፈልጉበት ቦታ እስኪያደርሳቸዉ ድረስ እምብዛም አትኩሮት አልሳቡም። እርሳቸዉ ግን እየተጓዙ ነዉ። ፕሬዝዳንት ኢሳያስ

አፈርቂ።

 

ዜናዉ፦

 

አሜሪካ አርባ ምንጭ ዉስጥ ያላትን የሰዉ አልባ አይሮፕላን ማብረሪያ ጣብያ መጠቀም ማቆሟ ታወቀ

 

በሱማሊያ ያሉትን አል-ሸባቦች ለማጥቃት አሜሪካ እንደ ኢሮጵያዉያን አቆጣጠር ከ2011 ጀምሮ ትጠቀምበት የነበረዉን የሰዉ አልባ አይሮፕላን ማስነሻ ጣብያ መጠቀም ማቆሟን አሶሽየትድ ፕሬስ አዲስ አበባ ያለዉን የአሜሪካ ኤምባሲ ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

 

ዴቪድ ኬኔዲ የተባሉት የኤምባሲዉ ቃል-አቀባይ ለአሶሽየትድ ፕሬስ በኢሜይል በላኩት መልእክት ሁለቱ አገራት ባደረጉት ስምምነት አሜሪካ በአርባ ምንጭ የምታደርገዉ ቆይታ አስፈላጊ አይደለም።የኤምባሲዉ ቃል አቀባይ ይህንን ቢሉም የኢትዮጵያና የአሜሪካን ግንኙነት የሚከታተሉ ባለሙያዎች ክስተቱ አሜሪካ የፖሊሲ ለዉጥ ማረግ መጀመሯን አመላካች ዱካ ሊሆን ይችላል ሲሉ ይጠቁማሉ።

 

 ለጋሽ አገራትና ፍላጎታቸዉ

 

የቀድሞዉ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ቡሽ  ሽብር ፈጠራን የመዋጋት ዘመቻ ማወጃቸዉ የሚዘነጋ አይደለም።ኢትዮጵያ የዚሁ ሽብር ፈጠራን የመከላከል ሚና ተሰጥቷትበምላሹ  ከለጋሽ አገራት ድጎማን ስትቀበል መቆየቷ ይታወቃል።መረጃዎች እንደሚያመላክቱት አሜሪካ ለኢትዮጵያን በደንብ አርጋ ትለግሳለች። በ2008እንደ አዉሮፕያዉያኑ አቆጣጠር አሜሪካ ለኢትዮጵያ 969ሚሊዮን ዶላር ለግሳለች። በ2009 916 ሚሊዮን ዶላር፣በ2010 የለገሰችዉ ወደ 513 ሚሊዮን ዝቅ ማለቱ ይታወቃል።

 

አሜሪካ ኢትዮጵያን የምትለግሰው አገሪቷ ዉስጥ የሚከሰተዉን የድርቅና የርሃብ አደጋ ለመከላከል፣ድህነትን ለመቋቋም፣ ለመልካም አስተዳደር፣ ማህበራዊ ሁናቴዎች ላይ ያሉ መመሪያዎችን ለማሻሻልና ለወታደራዊ ስልጠና መሆኑን መረጃዎች ያመላክታሉ። የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የሆኑ ድርጅቶች ኢትዮጵያ ዉስጥ ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብት ረገጣ በመኖሩ አሜሪካ እና ሌሎች ለጋሽ አገራት የሚለግሱት ገንዘብ የአገሪቱን ዜጎች ህልዉና አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን ያስጠነቅቃሉ።

 

አኩሪ ስራን ሰሪ ወይስ ሽብርን ፈጣሪ?

 

የአሜሪካዉ ፕሬዝዳት በራክ ኦባማ በሐምሌ 20/2007 ወደ ኢትዮጵያ በተጓዙበት ወቅት “ኢትዮጵያ ሽብር ፈጠራን በመከላከል ጽኑ የአሜሪካ አጋር ናት፣ ኢትዮጵያዉያን ጠንካራ ተዋጊዎች ናቸዉ” ማለታቸዉ ይታወሳል። ኦባማ ይህንን ቢሉም፤ የኢትዮጵያ መንግስትን የሚቀናቀኑ ቡድኖች በህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ የሚመራዉ መንግስት ‘ሽብር ፈጠራ በሱማሌ ዉስጥ እንዲስፋፋ ከአልሸባብ ጋር ግንኙነት ያደርጋል፣የሶማሊያን የጦር አበጋዞች እያስታጠቀ ሽብር ፈጠራን መነገጃ አድርጓል፣የኢትዮጵያ ወታደሮችን ሶማሊያ እየላከ ያስፈጃል ሲሉ መንግስትን ተጠያቂ ያደርጋሉ።ጄከብ ጁማ የተባሉ ኬንያዊ ቱጃር በመጋቢት 25/2007 በትዊተር ገጻቸዉ ላይ በለቀቁት መረጃ “የኢትዮጵያ መንግስት አሸባሪዉን አል-ሸባብ ያስታጥቃል።አዲስ አበባ ለአፍሪካ ቀንድ አለመረጋጋት ተጠያቂ ናት።የኬንያዉ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የአፍሪካዉ ህብረትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ መንግስትን እንዲመረምሩ ግፊት ማድረግ አለባቸዉ!” ብለዉ ነበር። የቱጃሩ መረጃ አነጋጋሪ ሆኖ መሰንበቱ ይታወሳል።ለኢትዮጵያ መንግስት ቅርበት ያላቸዉ የመገናኛ ብዙሃን ጉዳዩን ለማስተባበል ስሯሯጡ መታየታቸዉ የሚዘነጋ አይደለም።

 

የእጅ አዙር ዲፕሎማሲ?

 

በህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ የሚመራዉ የኢትዮጵያ መንግስት ተቀናቃኝ አጎራባች አገራት ስለመጡበት ለምእራቡ አገራት የሚኖረዉ ስልታዊ አጋርነት እየቀነሰ ነዉ በማለት የሚገልጹም አሉ።የአሜሪካ ስልታዊ አጋር የሆኑ የባህረሰላጤዉ ሱኒ ሙስሊም አገራት የአሰብ ወደብን መገልገያ ለማድረግ መወሰናቸዉ አነጋጋሪ ሆኗል።

 

በአሜሪካ የዉጭና የዲፕሎማሲ ጉዳዮች 38 አመታትን ያገለገሉት አምባሳደር ሐርማን ኮህን በአፍሪካ ቀንድ እየተከሰተ ስላለዉ ፈጣን ለዉጥ በታህሳስ 18/2008 በግል ገጻቸዉ ላይ ጽፈዉ ነበር።…”እናንተ አቢሲኒያዉያን ሆይ!” ብለዉ የተጣሩት አምባሳደር ኮህን “እናንተ በእርስ-በርስ ግጭት ስትጣሉ…ስትጯጯሁና…ሳትነጋገሩ… የባህረ ሰላጤዉ መንግስታት ምሳቹን እየበሉባቹ ነዉ” ብለዉ አስጠንቅቀዋል። ኮህን አክለዉም የተባበሩት አረብ ኤምሬት አይሮፕላኖች ከአሰብ ያለማቋረጥ መንቀሳቀሳቸዉንና ሳዑዲ አረቢያ በአሰብ ላይ የ50 አመታት ኪራይ መዉሰዷን አመላካች ሪፖርቶች መኖራቸዉን ገልጸዋል።

 

የባህረ ሰላጤዉ የሱኒ ሙስሊም አገራት በየመን በኩል ያለዉን የኢራንንና የሺዓ መስፋፋት ለመከላከል ኤርትራ ላይ አትኩሮት ማድረጋቸዉ የሚታወቅ ነዉ። እነዚህ በነዳጅ ዘይት ገንዘብን ያካበቱ አገራት ከአሜሪካ ጋር ስልታዊ አጋሮች ናቸዉ። ከአሜሪካ ጋር በኢኮኖሚዉና በወታደራዊ ግንኙነት የዉዴታ ግዴታ ቁርኝት አላቸዉ። ወደ አሰብ መዘንበላቸዉና አሰብን መከራየታቸዉ ያለአሜሪካ ይሁንታ በራሳቸዉ ፍላጎት ብቻ የተደረገ ነዉ ለማለት አያስደፍርም።

 

ሽብር ፈጠራን ለመከላከል በሚል መርህ በሳዑድ አረቢያ የሚመራ የ34 አገራት ጥምር ጦር በታህሳስ 5/2008ተመስርቷል። ይህ ጥምር ጦር የኪራዩን የአሰብ ወደብ አይጠቀምም ማለቱ አስቸጋሪ ነዉ። የጥምር ጦሩ አላማ ISIS እና ሌሎችን በኢስላም ስም የተነሱ አሸባሪዎችን ማመናመን መሆኑ እየተነገረ ነዉ።የአገራቱ ጣምራ ጦር የተዋቀረዉ ለፕሮፓጋንዳ ካልሆነና አላማዉ ተግባር ላይ ከዋለ፤ ISIS ብቻ ሳይሆን በሶማሊያ ያለዉም አል-ሸባብ የጣምራ ጦሩ ተጠቂ የሚሆንበት እድል የሰፋ ነዉ።ስለዚህ አሜሪካ ለምን አርባ ምንጭ ላይ የሰዉ አልባ አይሮፕላን ማስነሻ ይኖራታል? ስልታዊ አጋሬ የምትላቸዉን አገራትን በጅ አዙር ከመጠቀም ምን ይከለክላታል? ለምን የጠገበዉን አሳማ (ህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ) ትቀልባለች? ለአሜሪካ በጅ አዙር የተራበችዉን ኤርትራ ማብላት አይሻላትም ?

 

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወቂ ለምን በአንድ አመት ሁለት ግዜ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ተጓዙ?

 

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወቂ መጀመሪያ በሚያዚያ 21/2008 ወደ ሳዑዲ አረቢያ በመጓዝ ከአገሪቱ ንጉስ ሰልማንቢን አብዱል አዚዝ አል-ሱዑድ ጋር መገናኘታቸዉ በአረቡ አለም በሰፊዉ የተዘገበ ቢሆንም ኢትዮጵያዉያን እምብዛም አትኩሮት የቸሩት አይመስልም ነበር። ኢሳያስ አፈወርቂ ዳግም በታህሳስ 10/2008 ወደ ሪያድ ሳዑዲ አረቢያ የሁለት ቀን የስራ ግብኝት ለማድረግ ማቅናታቸዉ በአገራቱ መካከል የጠበቀ ስልታዊ ግንኙነት መመስረቱን አመላካች ነበር።የኢሳያስን የዑኡዲ ሁለተኛ ጉዞ ተከትሎ ኤርትራ ጣምራ የ34 ጦርን አገራትን ሐይል ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንደምትደግፍ ከአገሪቱ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዉጡ መረጃዎች አመላክተዋል።

 

ህወሃት መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት ለጸረ ሽብር ተግባር ከለጋሾች እርዳታ የሚቀበልበት አል-ሽባብ የጣምራ ጦሩ አባልና ደጋፊ በሆኑ አገራት ተከቧል። ሶማሊያ፣ጅቡቲ እና ኤርትራ ጣምራ ጦሩን ደጋፊ ናቸዉ።ስለዚህ አሜሪካ ለምን የሰዉ አልባ አዉሮፕላን ማስነሻዋን አርባ ምንጭ ማቆየት ያሻታል?

 

ማስጠንቀቅና ልመና

 

በጋምቤላ እና በኦሮሚያ ያሉ አርሶ አደሮችን እያፈናቀለ መሬትን ለሳዑዲ አረቢያና ለሌሎች አገራት ሲያከራይ የነበረዉ የኢትዮጵያ መንግስት አስመራም ተመሳሳይ ስራ በመጀመሯ ደስተኛ አለመሆኑን እየገለጸ ነዉ። በባለፍዉ የህዳር ወር መገባደጃ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለማሪያም ደሳለኝ ሳዑዲ አረቢያና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን ማስጠንቀቃቸዉ ታዉቋል። ለአገር ዉስጥ ጋዜጣ ቃለ መጠይቅ የሰጡት ሐይለማርያም ደሰላኝ  በአሰብ ወደብ ላይ የሚያደጉትን እንቅስቃሴ ተከትሎ ኢትዮጵያ ለሚኖራት ምላሽ ሐላፊነቱን ሳዑዲ አረቢያና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ይሸከማሉ ብለዋል።

 

የጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለማሪያም ደሳለኝ ማስጠንቀቂያ ሳይሻር በከፍተኛ የኢትዮጵያ የመንግስት ባለስልጣናት የሚመራ የልዑካን ቡድን ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በታህሳስ23/2008 በመግባት አቡ ዳቢ ፈንድ ፎር ዴቨሎፕመንት የሚባል የተራድኦ ድርጅትዘንድ በማምራት በሁለትዮሽ የእድገት፣ የመዋእለ ንዋይ እና የእርዳታ ጉዳዮች መነጋገራቸዉ ተዘግቧል።

 

እየቀረበ ያለዉ ለዉጥ

 

ህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ በጅ አዙር አሸባሪን የመዋጋት የገበያ እሽቅድም ከጁ እየተፈተለከበት ይመስላል። ኤርትራ እና የ34 አገራት ጣምራ ጦር እየተፎካከሩት ነዉ። ስርዓቱ በከፍተኛ አጣብቂኝ ዉስጥ ገብቷል። ከዚህ አጣብቂኝ ለመዉጣትም እንደ አማራጭ የወሰደዉ የጅምላ ግድያንና እስር ነዉ። ተሰሚነት ያላቸዉ ሰዎች፣አክቲቪስቶች፣ጋዜጠኞች፣የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች፣ተማሪዎች፣ መምህራንና ሌሎችም የስ ርዓቱ ሰለባ እየሆኑ ነዉ። የማሰቃያ እና የማጎሪያ እስር ቤቶች መሙላታቸዉ እየተነገረ ነዉ። በጥቅሉ በህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ የሚመራዉ መንግስት አይደለም አሸባሪነትን ሊከላከል እራሱ አሸባሪ በመሆን ለዜጎች ህልዉና ስጋት መሆኑን የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁናቴ መቃኘቱ በቂ ነዉ።

 

አዲሱ የኢትዮጵያ አመት ከገባበት ግዜ ጀመሮ በተለያዩ ቦታዎች ቦምብ መፈንዳት ጀምሯል። በታላቁ አንዋር መስጊድ ዉዳሴ (መንዙማ) ሲያሰሙ በነበሩ ምእምናን ላይ በታህሳስ 1/2008 የቦምብ ጥቃት ደርሷል። በጥቃቱም  እስከ 18 የሚደርስ ሰዉ ተጎድቷል።ተመሳሳይ የቦምብ ጥቃት በታህሳስ 22/2008 በዲላ ዩንቨርስቲ ተከስቶ 3 ሰዎች ሲሞቱ 6 መቁሰላቸዉ ታዉቋል። ዜጎች በነቂስ ድርጊቱ የህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ነዉ የሚል መግባባት ላይ የደረሱ ይመስላል። ይህንኑ ለማረጋገጥ እስኪመስል ድረስ ዊኪ ሊክስ የተባለዉ የመረጃ አነፍናፊ ድረ ገጽ በበመስከረም5/2004 የኢትዮጵያ መንግስት እራሱ ቦምብ አፈንድቶ በኤርትራና በኦነግ እንደሚያላክክ አዲስ አበባ ከሚገኘዉ የአሜሪካ ኤምባሲ አፈትልኮ የወጣ መረጃን ዋቢ በማድረግ ለአለም ህዝብ አሳዉቋል። ታዲያ ህወሃት ወራሹ መንግስት እንደምን በጸረ ሽብር ዘመቻ ሁነኛ ስልታዊ አገር ሊሆን ይችላል?

 

ከብሔራዊ ጭቆና ወደ ብሔራዊ ድል

 

ህወሃት መራሹ መንግስት በእምነት ጉዳይ ጣልቃ እንደሚገባ ክስ ይቀርብበታል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ጣልቃ ገብቷል የሚል ለአመታት የዘለቀ ብሶት አለ። ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች መጤ አንጃ አምጥቶ ጫነብን ብለዉ በመቃወም አለም አቀፍ ሰላማዊ ንቅናቄን ጀምረዉበታል።ህወሃት  የአገሪቷን ሐብት ተቀራመተዉ፣ጥቂቶች ሐብታም ሲሆኑ ሚሊዮኖች በድህነት ማቀቁ የሚለዉ እሮሮ በሰፊዉ ይሰማል። አገሪቷ ዉስጥ የተንሰራፋዉ የርሃብ አደጋ በተፈጥሮ ክስተት የመጣ ቢሆንም የመልካም አሰተዳደር እጦት ርሃቡን የከፋ እንዲሆን አድርጎታል የሚለዉ ህዝባዊ ብሶት በሐዘና በሲቃ የሚሰማ ነዉ።  የኢትዮጵያን ድንበር ቆርሶ ለሱዳን ለመስጠት የኢትዮጵያ መንግስት መስማማቱ የአገርን ሉዓላዊነት አስደፈረ የሚል ብሔራዉ ቁጭትን ፈጥሯል።በአገሪቷ ላይ የተንሰራፋዉ የመሬት ቅርምት ዜጎች በጫንቃቸዉ ላይ ሊሸከሙት ከሚችሉት በላይ ሆኖ እየተንገፈገፉበት ነዉ።

የኦሮሞ ተማሪዎች “መሬቴን አላስነጥቅም!” የሚለዉ ንቅናቄ አገራዊ ሆኖ ስርዓቱን ለመናጥ የበቃ ነዉ።ህወሃት ይህንን ሰላማዊ ንቅናቄ ለመቀልበስ በሰላማዊ ዜጎች ላይ አጋዚ በሚባለዉ ቅልብ ጦሩ የሚወስደዉ ዘግናኝ እርምጃ ህዝቡ ወደ “ህዝባዊ እንቢተኝነት” እንዲያመራ እየዳረገዉ ነዉ። ወልቃይት ጸገዴዉ ተገድጄ ትግራይ ዉስጥ ተካለልኩ ወደ አማራ ክልል ልመለስ በማለት የማንነት ንቅናቄን ጀምሯል። የጎንደሩ ገበሬ በደሙ የዋጀዉ መሬት ለሱዳን ሊሰጥ በመሆኑ እምቢኝ አሻፈረኝ ብሎ እየተነሳ ነዉ። አኝዋኩ መሬቴ ለባእዳን ተሽጦ በግፍ ተገደልኩ፣በግፍ ተፈናቀልኩ እያለ ነዉ። አርበኞች ግንቦት 7 በጦርነት ህወሃት መራሹን መንግስት እጥላለሁ ብሎ እየተዋደቀ ነዉ።

ብሶት የማይሰማበት የኢትዮጵያ ክልል የለም።ዜጎች ህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ለ25 አመታት ባንሰራፋዉ አምባገነናዊ ስርዓት ተንገፍግፈዋል።

የማይቀር ህዝባዊ እምቢተኝነት ከፊት ለፊት ተጋርጧል። አሜሪካንም ሆነች ሌሎች ሐያላን አገራት ለህዝባዊ ጩኸት ‘ጆሮ ዳባ ልበስ’ ያለዉን ህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ጣል-ጣል ቢያረጉ አይገርምም። የሚገርመዉ ‘ከማይታወቅ መልአክ… የሚታወቅ…’ ብለዉ በህወሃት ላይ ተስፋ ቢያረጉ ነዉ። አሜሪካንም ሆኑ ሌሎች በኢኮኖሚ የበለጸጉ አገራት ቅድሚያ ለብሔራዊ ጥቅማቸዉ ነዉ የሚሰጡት። አገራቱ ብሔራዊ ጥቅማቸዉ ህወሃት ጋር አለመኖሩን ቢረዱትም ያቺን የመጨረሻዋን ሰዓት የሚጠብቁ ይመስላል። ታዲያ!…ዉድና ጠቃሚ የጦር መሳሪያዎቻቸዉን ወደ ሌላ ቦታ መዉሰዱ መጨረሻዉ እየጀመረ አይመስልምን? “የመጨረሻዉ መጀመሪያ!” ለማንኛዉም ልብ ያለዉ ልብ ይበል።

The post የመጨረሻዉ መጀመሪያ -ከሳዲቅ አህመድ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

የዲላ ዩኒቨርሲቲ የወንዶች ማደሪያ ህንፃ በእሳት እየነደደ ነው

$
0
0

Zehabesha News
(ዘ-ሐበሻ) በዲላ ዩኒቨርሲቲ ለ4ኛ ቀን አለመረጋጋቱ እንደቀጠለ ነው:: ከቀናት በፊት ቦምብ መፈንዳቱ እንደዚሁም 3 ተማሪዎች በመጸዳጃ ቤት ውስጥ ታርደው መገኘታቸው በዘ-ሐበሻ መዘገቡ አይዘነጋም::
ዛሬ ከስፍራው ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ እንደሚጠቁመው የዩኒቨርሲቲው የወንዶች ማደሪያ ህንፃ እየተቃጠለ ነው:: የ እሳቱ መነሻ ምን እንደሆነ አልታወቀም::

ይህ ዜና እየተጠናቀረ ባለበት በዚህ ወቅት አካባቢው በተኩስ እየተናወጠ ሲሆን ተማሪዎችም ግቢውን ለቀው እየወጡ እንደሆነ ታውቋል::

ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን እንመለሳለን::

The post የዲላ ዩኒቨርሲቲ የወንዶች ማደሪያ ህንፃ በእሳት እየነደደ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

ጥያቄአችን አንድ ይሁን –ይገረም አለሙ

$
0
0
hands holding each other in unity  cartoon vector  illustration

hands holding each other in unity cartoon vector illustration

ወያኔዎች የኢትዮጵያን የመንግሥትነት ሥልጣን እንደያዙ በርካታ  ኢትዮጵያውያን ወያኔዎቹ ራሳቸው ዓላማችን ብለው በሰነድ ያሰፈሩትንም ሆነ ስለ እነርሱ የሚያውቁ ሰዎች የመሰከሩትን  ወደ ጎን በማለት እነዚህ ሰዎች ከጫካ ነው  የመጡት እንኳን የሰው ልጅ አውሬ እንኳን ከጫካ ወጥቶ በአግባቡ ከተያዘ ተለማምዶ ከሰው ጋር ይኖራልና ግዜ ልንሰጣቸውና ልናግዛቸው ይገባል  በማለት   በቅርብም በሩቅም ሆነው እንደውም አንዳንዶች እነርሱው ጋር ገብተው  ይበጃል ያሉትን ለመምከር ጠቃሚ ያሉትንም መንገድ ለማሳየት ብዙ ጥረዋል፡፡

 

ብረት አንስቶ መታገልና መንግሥት  ሆኖ ሀገር መምራት የተለያዩ ናቸውና ወያኔዎች ይህን ተረድተው  ከጠመንጃ አምላኪነት ወደ ለህግ ተገዢነት እንዲያድጉ ፣ ከአብዮተኝነት ወደ ዴሞክራሲያዊነት እንዲለወጡ ከታጋይነት ወደ ሀገር መሪነት እንዲሸጋገሩ  የዘር ጥብቆአቸውን አውልቀው ኢትዮጵያዊ ካባ እንዲለብሱ ወዘተ ለማስቻል አመቺ ሆኖ ባገኙት መንገድና ዘዴ ሁሉ  የቻሉትን ያደረጉ ወገኖች ያስገኙት ውጤት በማይለወጠው የወያኔ  ሕገ አራዊት መበላት ነው፡፡

 

ወያኔ  በሀይል የያዘውን ሥልጣን በህዝብ ፈቃድ ለማረጋገጥና ሀገሪቱን ወደ ዴሞክራሲያዊ አቅጣጫ ለማምራት በጠመንጃ የተገኘ ሥልጣን በሀይል ይጠበቃል ከሚለው እምነት ወጥቶ  ምርጫ ለማካሄድ ፈቃደኛ እንዲሆን አለበለዚያም በተለያየ መንገድ አስገድዶ    ነጻ ምርጫ በኢትዮጵያ አንዲለመድ ለማድረግ በርካታ ኢትጵያውያን ጥረዋል፤ ሕዝቡም በየግዜው መስዋዕትነት ከፍሏል ፡፡ የመጀመሪያው የ1987 ምርጫ መአህድና ኦነግ በመጨረሻ ሰአት ራሳቸውን ከምርጫ  አግልለው ይሄ ነው የሚባል የምርጫ ሂደት ሳይታይ ብዙ ህዝብም ምርጫ መኖሩን አንኳን ሳያውቅ ምንም አሻራ ሳያኖር  አለፈ፡፡

በሁለተኛው የበ1992 ምርጫ ከ10 በላይ  የሚሆኑ የተቀዋሚ ፓርቲ አባላት  የፓርላማ  ወንበር በማግኘታቸው  ጥረቱ መስመር ሊይዝ ወያኔም እየተማረ ሊሄድ ነው  አሰኝቶ  ተቀዋሚዎች ጠንክረው ቢሰሩ ወያኔን በምርጫ ማሸነፍ ካልሆነም ሥልጣን መጋራት ይቻላል  የሚለው አስተሳሰብ እንዲጎለብት አስችሎ ነበር፡፡ በዚህ መነቃቃት የተነሳሱ ወገኖች በተቻለ አቅም ያለፉ ችግሮችን በተለይ ተለያይቶ ለምርጫ መቅረብን ለማስወገድ ቅንጅትን መስርተው ባካሄዱት  ምርጫ 97 በአጠቃላይ ተቀዋሚው በወያኔ የታመነ ከ200 በላይ ወንበር ለማግኘት ሲችል ውጤቱን ተከትሎ በተፈጠረው አለመግባባት አያሌ ኢትዮጵያውያን ተገደሉ፣ ታሰሩ ተሰደዱ ንብረት ወደመ፡፡ ይህ የምርጫ 97 ሂደት አንድም ህዝቡ ለወጥ መፈለጉንና  ነጻ ምርጫ ቢካሄድ በድምጹ ለውጥ ማምጣት  መቻሉን ሁለትም ወያኔ በሀይል የተገኘ ስልጣን በስመ ዴሞክራሲ አይለቀቅም (በጠመንጃ ይጠበቃል) ከሚለው አምነቱ የሚላቀቅ አለመሆኑን ያሳየ ነበር ፡፡

 

በምርጫ ስልጣኑን ማስጠበቅ እንደማይችል ከምርጫ 97 በግልጽ የተማረው ወያኔ ምርጫ 97ትን ያየ እንከን የለሽ ምርጫ እያለ አይጫወትም ያለ በሚመስል ሁኔታ  ምርጫ በኢትዮጵያ የሱን ስልጣን ለማደስ የሚውል ብቻ እንዲሆን የሚያበቃውን  ስራ ሲሰራ  የምርጫ 97  ውጤት መክሸፍ እንዴትነትና ምንነት በውል ሳይመረምሩ  የተገኘውን ወንበር ብቻ በማየት ወይንም የየራሳቸው ምክንያት ኖሮአቸው    በምርጫ 2002 የተወዳድሩ  አንድ ወንበር ብቻ አገኙ፡፡ ወያኔ ከዚህም ልምድ ተምሮ በሀይል የተገኘ ሥልጣን በሀይል የጠበቃል መርሁን አጠንክሮ የፓርላማውን ወንበር ለመጠቅለል በበቂ ተዘጋጅቶ በምርጫ 2007 ተቀዋሚ የሚባል ፓርላማ ደጅ እንዳይደርስ ለማድረግ ቻለ፡፡ በመሆኑም ወያኔን ምርጫ ለማለማመድ ሀያ አራት አመት ሙሉ የተደረገው ጥረት ውጤቱ ዜሮ ሆነ፡፡ ከሀያ አራት ዓመቱ ልፋት ከንቱነት በላይ የሚያሳዝነውና የሚያስቆጨው  በየምርጫው በተለይ በምርጫ 97 የተከፈለው መስዋዕትነት ነው፡፡

 

ጦርነትን ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን ጦርነትን መስራትም እንችላለን የሚሉትንና  የሰላማዊ ትግል ልምድም እውቀትም የሌላቸውን ወያኔዎች ሰላማዊ ትግልን በተግባር በማለማመድ ሀገራችን ለዘመናት ከተጓዘችበት የጠመንጃ ትግል ማላቀቅ ይኖርብናል ያሉ ወገኖች ፓርቲ እየመሰረቱ ለመንቀሳቀስ ሞክረዋል፡፡ በርግጥ ፖለቲከኞቹ  ራሳቸው ሰላማዊ ትግል ብለው ፓርቲ ሲመሰርቱ  የሀገሪቱን የቀደመ ታሪክ የወቅቱን ነባራዊ ሁኔታ የህዝቡን ሥነ- ልቦና ስልጣን ላይ ያለውን ሀይል ማንነት በሚገባ አጥንተው ከዚህ አንጻር በሀገራችን ደረጃ በደረጃ ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ የሰላማዊ ትግል አይነቶችን ለይተው  አውቀውና  በበቂ ተዘጋጅተው የጀመሩ ባይሆኑም የወያኔ ባህርይ ግን በዚህ ደረጃ ላይ ያሉ ፓርቲዎችን እንኳን በህጋዊ አግባብ  ማስተናገድ አልቻለም፡፡ በሂደት እያደጉና እየጎለበቱ እንዳይሄዱ ማድረግ አይደለም ሲጀምሩ የነበራቸውን አቅም አንኳን ይዘው እንዳይቀጥሉ በህግም በጉልበትም እያዳከመ ጠንካራ ተቀዋሚ ቢኖር መሀል መንገድ ድረስ ሄደን እንቀበለው ነበር በማለት ሲሳለቅና ሲመጻደቅ ኖረ፡፡ በመሆኑም  በሀያ አራት ኣመታት ውስጥ  ወያኔን ከሰላማዊ ትግል ጋር ለማለማመድ የተደረገው ጥረት ያስገኘው ውጤት  ወያኔን የለየለት አምባገንን ማድረግና ግንባር ቀደም የህዝብ ታጋዮችን ጨምሮ አያሌ ኢትዮጵያዉያንን በእስር በስደት በሞት ማጣት ነው፡፡

 

ወደ ኋላ መለስ በማለት ለማንም ግልጽ የሆነውን ይህን ጉዳይ ማንሳቴ፤

አብዛኛው ኢትዮጵያዊ  ወያኔዎችን የሚቃወመው  እነርሱን በመጥላት ወይንም  እነርሱ እንደሚሉት የቀድሞውን ሥርዓት በመናፈቅ ወይንም  እነርሱ የሚሉትን የብሄር ብሄረሰቦች መብት መረጋገጥ በመጥላት ሳይሆን ከኢትዮጵያዊነት ያፈነገጠው ተፈጥሮአቸው በምክርም በተሞክሮም የማይለወጥ በመሆኑ እንደሆነ ለማሳየት፡፡ ወያኔዎች  የምሁራንን ምክር ተቀብለው ፣ የህዝብን ጩኸት አዳምጠው፣ የፖለቲከኞችን  ተቃውሞ ሰምተውና አማራጭ ሀሳብ ተቀብለው  ከደደቢት ህልማቸው ቢወጡና እንደ ኢትዮጵያ መንግስት ማሰብና መስራት ቢጀምሩ ከዴሞክራሲም ጋር እርቅ ቢፈጥሩ  ከሚቃወማቸው የሚደግፋቸው በበዛ ነበር፡፡  ከዛ በኋላ ሊኖር የሚችለው ተቃውሞም ቢሆን በሌሎች ዴሞክራቲክ ሀገሮች እንደሚታየው በተወሰኑ ጉዳዮች በተለይም በአፈጻጸም ላይ የተመሰረተና በሰለጠነ የፖለቲካ አካሄድ የሚከናወን በሆነ ነበር፡፡

 

ሌላው ይህን ጉዳይ ወደ ኋላ ሄጄ ማንሳቴ  ወያኔ በምንም ሁኔታ ከተነሳበት ዓላማም ሆነ  ወደ ግቡ ከሚያደርገው ጉዞ ዝንፍ የማይል መሆኑ በተግባሩ የተረጋገጠ መሆኑን  ለማስታወስና  ከዚህ በኋላ በወያኔ አገዛዝ የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ ፣ሰብአዊ መብትን ማስከበር፣ምርጫን የህዝብን ድምጽ ወደ ስልጣን መቀየሪያ መሳሪያ ማድረግ፣ በጥቅሉ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ይቻላል የሚል ተስፋ የተሟጠጠ በመሆኑ ጥያቄአችን አንድ እሱም ነጻነት የሚል መሆን አለበት  የሚል አጽንኦት ለመስጠት ነው፡፡

 

ከላይ በጥቂቱ ለማሳየት የተሞከሩት ወያኔን ከበርሀ ፋኖነት ወደ መንግስትነት ለመለወጥ የተደረጉ ጥረቶችና ያስገኙት ውጤቶች የሚያሳዩት ወያኔ ከደደቢት  እሱነቱ መቼም በምንም የማይለወጥ መሆኑን ነው፡፡  ኢትዮጵያውያን ደግሞ ራሳችንን ለውጠን ወያኔን ለመቀበልና ለአገዛዙ ይሁንታ ለመስጠት  አይቻለንም፡፡ ይህን ለማድረግ ኢትዮጵዊነታችንን  ከውስጣችው አንጠፍጥፈን ማውጣት ያስፈልገናል ፤  ህሊናቸንና ሆዳችንን ቦታ ማቀያየር ይጠበቅብናል፤ ከዴሞክራሲ  ከህግ የበላይነት ከሰብአዊ መብት ወዘተ ጋር መለያየት ግድ ይላናል፡፡ ይሄ ደግሞ የማይሆን ብቻ አይደለም ፈጽሞ የማይታሰብ በመሆኑ ነው  አትዮጵያውያን ሀያ አራት ዓመታት ሙሉ የሚገደሉት የሚታሰሩት የሚሰደዱት በተለያዩ የወያኔ ባዶ ስድስት የጭካኔ ዘዴዎች የሚሰቃዩት፡፡

 

በርግጥ ከላይ የተጠቀሰውን  አድርገው አዲስ ማንነት ፈጥረው  ለወያኔ ያደሩ አልፎ ተርፎም ከጳጳሱ ቁሱ እንዲሉ ሆነው በወያኔ ተልእኮ አስፈጻሚነት የተሰለፉ ቀላል የማይባል ቁጥር ያላቸው በሀገር ውስጥም በውጪም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አሉ፡፡ ወያኔ ከዓላማው ዝንፍ ከመስመሩም ፈቀቅ እንዳይል  የእነዚህ ሰዎች ተግባር አስተዋጽኦ አድርጓል ማለት ይቻላል፡፡ እንደውም ከዓላማው ዝንፍ አለማለቱና የሚፈጽማቸው ኢ-ሰብአዊ ተግባራት ሲታዩ ለተለያየ ዓላማና ፍላጎት በተለያየ መንገድ እጅ  የሰጡትን ሰዎች በማየት   ሌላውስ ለምን እጅ አይሰጥም ወይንም ሰጥ ለጥ ብሎ አይገዛም በሚል  የእልህ አስተሳሰብ  እየተጓዘ ያለ ነው የሚያስመስሉት፡፡

 

ታዲያ ወያኔ ራሱን ለውጦ የህዝብ አካል መሆን ካልቻለ፤ ህዝቡ ወያኔን መሆን አይደለም መምሰል ቀርቶ በመንግስትነት እንዲቀበለው የሚያስችል ምንም ነገር ከሌለ አንድና ብቸኛ ምርጫው መገላገል ነው፡፡  በወያኔ አገዛዝ ስር የፍትህ፣ የሰብአዊ መብት፣ የሀብት ተጠቃሚነት የዴሞክራሲ ወዘተ  ጥያቄዎች  ማንሳት ግዜው አልፎበት አሁን ጥያቄው የነጻነት ጥያቄ ሆኗል፡፡ በሆኑም ወያኔን ለመለወጥም ለማለማመድም እቅጣጫ ላማሳየትም ከተደረገው የሀያ አራት አመታት ጥረት መክሸፍ በኋላ  በሁሉም የሀገሪቱ ማዕዘን በሁሉም ኢትዮጵያዊ ( ከወያኔዎች በስተቀር ) መነሳት ያለበት ጥያቄ የነጻነት  ጥያቄ መካሄድ ያለበት ትግል ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የመመስረት ትግል መሆን ይገባዋል፡፡  ይህን ማድረግ ካልቻልን ዛሬም ካለፈው አልተማርንም ለወደፊትም ምንም ራእይ የለንም ማለት ነው፡፡

The post ጥያቄአችን አንድ ይሁን – ይገረም አለሙ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
↧

ዝምታ ሰላም አይደለም ፕሮፓጋንዳም እድገት አይሆንም!!! –ግረማ ሠይፉ ማሩ

≫ Next: Hiber Radio: የኢትዮጵያው አገዛዝ በአወዛጋቢው በሕዳሴ ግድብ ግንባታ ዙሪያ ሕዝባዊ ተቃውሞ እንዳይቀሰቀስበት ስጋት እንዳለው የግብጽ ሚዲያዎች አጋለጡ ፣በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ተቃውሞው እንደገና ተጠናክሮ እየቀጠለ ነው፣በጅማ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ተሰቅሎ ተገኘ፣አገዛዙ በተቃዋሚዎች ላይ የሽብር ጥቃቱን ቀጥሏል –የንጹሃን ሞት ጨምሯል፣ ከኢትዮጵያ የሄዱ የደህነት አባላት የኬኒያ ድንበርን ተሻግረው የአፈና እና የጦር መሳሪያ ዝርፊያ አድርሰዋል ስትል ናይሮቢ ወቀሳዋን አሰማች እና ቃለ መጠይቅ ከዶ/ር አክሎግ ቢራራና ከሰማያዊ ፓርቲ ም/ሊቀመንበር ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ሌሎችም
$
0
0

girmseifu32@yahoo.com, girmaseifu.blogspot.com
Girma Siefuሰሞኑን በማሕበራዊ ሚዲያ ላይ ተሳትፎ የሚያደርገው ሰው ጤና መሆኑን መጠራጠር የግድ ብሎኛል፡፡ አንዱ ውጭ ሀገር ሆኖ እንደእርሱ ካላቅራራህ ይለኛል፡፡ ሌላው ማንነቱ እንዳይታወቅ መሸጎ እየፃፈ ይፎክርና እንደ እኔ ፎክር ይለኛል፡፡ ለማነኛውም ሁላችንም እንደየ አቅማችን እና ችሎታችን፣ ምን አልባትም ድፍረታችን ያህል ለምናደርገው የነፃነት ትግል ክብር ብንሰጣጥ ጥሩ ይመስለኛል፡፡ ፈሪ መሆንም እኮ መብት ይመስለኛል፣ ሰው ለምን ትፈራለህ ለምን ይባላል!! ባይሆን ፈሪ እንደ እኔ ፍሩ ሲል ነው አይ ሊባል የሚገባው፡፡ በእኔ እምነት የዚህች ሀገር የወደፊት ዕጣ ፈንታ ሊወሰን የሚገባው በሃሰብ ክርክር እና በዚሁ በሚገኝ የበላይነት ብቻ መሆን አለበት ብዬ አምናለሁ፡፡ ለዚህም ነው ሁሉም የማይሰማማበት ቢሆን እንኳን የእኔ ሃሳብ ይህ ነው ብዬ ለመግለፅ የምወደው፡፡ ይህን አካሄድ ያለመውደድ መብት ቢሆንም የእኔን ውደድ ብሎ ማስገደድ አይቻልም፡፡ ይህን ከሰሞኑ የፌስ ቡክ የፅሁፍ ምልልሶች መነሻ አድርጌ ካልኩኝ፤ ለዛሬ ፅሁፍ መነሻ ያደረጉት ደግሞ ለአንድ ሳምንት በምክር ቤት ወጉ እንዳይቀር “ሲመከርበት” የከረመው የሁለተኛው ዙር የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ እና የሰሞኑ “የተቀናጀ ማስተር ፕላን እንቢ” በሚል መነሻ በኦሮሚያ አካባቢ የተቀሰቀሰው ንቅናቄ፣ በጎንደር የተፈጠረው ግጭት እንዲሁም ድርቅ መነሻ ሆኖ የተከሰተው ርሃብ እንደምታ ምን ሊመስል እንደሚችል በአጭሩ የግል እይታዬን ለማስቀመጥ እሞክራለሁ፡፡

ገዢዎቻችን አፍረት የሚባል ነገር እንደሌለባቸው የሚያስታውቀው የመጀመሪያውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ በስኬት ማጠናቀቃቸውን ሲነግሩን አፋቸውን አንኳን ጎልደፍ ያለማድረጋቸው ብቻ ሳይሆን በምክር ቤት ውስጥ ለተሰበሰቡት እጅ በማውጣት ደሞዝ ለሚከፈላቸው ሳይሆን በሚዲያ ለሚከታተላቸው ህዝብም ያላቸውን ንቀት የሚያሳይ ነው፡፡ በመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽኝ ዕቅድ በዋነኝነት ከተቀመጡት ግቦች የተሳከ የሚባል አንድም ነገር የለም እንዳይባል (ጥራት በሌለው ትምህርትና ጤና የቁጥር ስኬት መኖሩ አይካድም)፣ ከዚህ በስተቀር መብራት 10 ሺ ሜጋ ዋት ብለው ሶሰት ሺ ያለመድረሳቸው፣ ባቡር 2395 ኪ.ሜ ታቅዶ እሰከ አሁን ስራ ያልጀመረውን የአዲስ አበባ ድሬዳዋን ብንወስድ 700 ኪሎ ሜትር እንደማይሞላና ይህም ዕቅዱ የውሸት ህዝብ ማማለያ እንደ ነበር ነው፡፡ በግብርና ዘርፍ በብዙ ሚሊዮን የውጭ ምንዛሬ ያስገኛል የተባለው እቅድ የተያዘለት፣ የተገላቢጦሽ መንግሰት በውጭ ምንዛሬ ሰንዴ መግዛት ውስጥ መግባቱ ይታወቃል፡፡ ባለፈው አምሰት ዓመት ከፍተኛ የእድገት ምጣኔ አስመዝግቦዋል የተባለው ግብርና ነው ብለው ሚሊየነር አርሶ አደር ብሎ መሸለሙን ሳይጠናቀቅ በድርቅ ተሳቦ 15 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ የሚላስ የሚቀመስ ማጣቱ መሬት የያዘ አቅ ነው፡፡ እነዚህ ለማሳያ የቀረቡት እና ሌሎችም እራሳቸው ያመኑት የውጭ ንግድ ዘርፍ ያለመሳካት ተጨምሮ ከወረቀትና ፉከራ ያላለፈው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ በስኬት አጠናቀናል ይሉናል፡፡ ይህ እቅድ አልተሳካም የሚሉት ምን ቢሆን እንደነበር ግን ሊነግሩን አልቻሉም፡፡  ቢሆንም በስኬት ተጠናቋል እያሉን ነው፡፡ በአንድ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትምህርት አግኝተንበታል ማለታቸው የሚታወስ ሲሆን እቅዱ ግን ለትምህርት መቅሰሚያ ነው አላሉንም ነበር፡፡

ቀጣዩ ዕቅድ በሚመለከት በመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን ከነበረው ሁኔታ በተለየ በጅምሩ የታየው እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ደግሞ በኦሮሚያ እና በጎንደር አካባቢ የዜጎችን ህይወት እስከመቅጠፍ የደረሰው ህዝባዊ እንቅስቃሴ ሲሆን በመላ ሀገሪቱ የተከሰተውም ድርቅ መነሻ ያደረገው ርሃብ አንዱ ነው፡፡ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ሲገለፅ የነበረወ ነገር “የፀጥታ/ዝምታ መኖር፣ የሰላም ምልክት እንዳልሆነ” ነበር፡፡ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት በኢትዮጵያ ነብስ ዘርቶ ያለው ቋንቋ መሰረት ያደረገ ፌዴራሊዝም፣ እንዲሁም በተለያየ ወቅት የነበሩ የእርስ በእርስ ግጭቶች፣ አሁንም በሀገሪቱ ለመድበለ ፓርቲ እንዳይመሰረት ገዢው ፓርቲ የዘጋው በር፣ ሀገራዊ መግባባት ለመፍጠር የሚያሰችል ከተለያየ መሰመር የሚቀርቡ ብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄዎች፣ ወዘተ ተገቢው ምላሽ ያለማግኘታቸው በሀገራችን ዘላቂ ሰላም ለማምጣት አስቸጋሪ እንደሆነም ተገልፆዋል፡፡ ዘላቂ ሰላም በሌለበት ደግሞ እድገት የሚባል ነገር ሊታሰብ የሚችል አይደለም፡፡ በቅርቡ በኦሮሚያ አካባቢ በተፈጠረው እንቅስቃሴ ምክንያት ወደ ሀገር ውስጥ መዋለ ንዋይ ካፈሰሱት ግንባር ቀደም የሆነው የዳንጎቴ ሲሚኒቶ ፋብሪካ ላይ አንዣቦ ነበር የተባለው አደጋ እና ሌሎች ችግርች ለሌለች በዚህ ሀገር ኢንቨስት ለማድረግ ለሚፈልጉ ኢንቨሰተሮች መልዕክቱ ምን ሊሆን እንደሚቸል ግልፅ ነው፡፡ ከፍተኛ የውጭ መዋለ ንዋይ ፍላጎት ያላት ሀገራችን እሰከ አሁን ያለውን ያህል የውጭ ገንዘብ ለማገኝት በሚቀጥለው አምስት ዓመት የምትችልበት ሁኔታ አይኖርም የሚል ግምት አለኝ፡፡ ይህ ደግሞ የሚሆነው የውጭ ኢንቨስተሮች መረጃ የሚያገኙት ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሳይሆን ዓለም አቀፍ ባለሞያዎች ከሚሰጡት ትንታኔ ነው፡፡ መንግሰት እንደሚለው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች የሚሰጡት መግለጫ እና የሚያወጡት ሪፖርት ዋጋ ቢስ አይደለም፡፡ እነዚህ ባለሀብቶች የት ሀገር ቢሄዱ በሰላም እንደሚነግዱ እና የተሻለ ትርፍ እንደሚያገኙ መረጃ የሚያገኙበት ምንጭ ነው፡፡

የውጭ ኢንቨስተሮች ብቻ አይደለም ከአሁን በኋላ የሀገር ውስጥ ባለሀብትም ቢሆን ዘላቂ ሰላም በሌለበት ሁኔት ኢንቨት የሚያደርጉበት ሁኔታ እጅግ ዝቅተኛ ነው የሚሆነው፡፡ ከዚህ በፊትም ሲያደርጉ ከነበረው ያነሰ ይሆናል ማለቴ ነው፡፡ ከዚህ በፊትም ቢሆን ቀላል የማይባሉ ኢትዮጵያዊያን ከሀገራቸው ውጭ መስራትን በተለይ በምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ሀገሮች አካባቢ ምርጫቸው እንደሚያደርጉ ይታወቃል፡፡ አሁን ያለው ሁኔታ ደግሞ የበለጠ ገፊ ነው፡፡ ባለፈው የገቢዎችና ጉምርክ ባለስልጣን ሹም በሙስና ሲታሰሩ ከሀገር ተገፍተው የወጡ ነጋዴዎች ያሳዩትን የደስታ ምንጭ ትዝ ይለኛል፡፡ ትንንሾቹ ሲታሰሩ ለውጥ የሚመጣ መስሏቸው፡፡

በኢትዮጵያ ኢንቨስትምንት ውስጥ መንግሰት እጁን በማስረዘም በከፍተኛ ደረጃ ኢንቨስትመንት ውስጥ ይሳተፋል፡፡ ይህ የመንግሰት ተሳትፎ ደግሞ መስረት ያደረገው ከውጭ መንግሰታት እና ዓለም አቀፍ አበደባሪዎች ከሚገኝ ብድር እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በሀገር ውስጥ የተፈጠረው ህዝባዊ እንቅስቃሴ በግልፅ ወጥቶ ከመታየቱ በፊትም ሀገሪቱ ያለባት የብድር ጫና ከፍተኛ መሆኑን ሪፖርት እያደረጉ እና ጥንቃቄ እንዲወሰድ ሲመክሩ ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ ላይ እንደከዚህ ቀደሙ ከፍተኛ ብድር ይስጣሉ የሚል ግምት መውሰድ የዋህነት ነው፡፡ ይልቁንም ይህ አጋጣሚ ተጠቅመው ብድሮቹን ከማግኘት በፊት አንድ አንድ የማሻሻያ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ግፊት ያደርጋሉ፡፡ አሁን በግልጽ እያየነው ያለው እውነትም ዜጎች በረሃብ አደጋ ላይ ሆነው እያለ እርዳታው በቁጥ ቁጥ የሆነበት ሁኔታ በምግብ እራሳችንን ችለናል የሚለውን መንግሰት ከወገቡ ጎንበስ ብሎ እስኪለምን ድረስ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በቅርቡ እንደሰማነው ፉከራ ከሆነ ደግሞ መንግስት በራሱ አቅም እርዳት እንደሚሰጥ ነው፡፡ ወጤቱን አብረን የምናየው ይሆናል፡፡

የረሃቡን ጉዳይ ካነሳን “ኤሊኖ” ወቅታዊ ክስተት ስለሆነ ማለፉ አይቀርም ጥሎት የሚሄደው ጠባሳ ግን በእንድ እና ሁለት ዓመት የምንወጣው አይደለም፡፡ ለእድገትና ትራንሽፎርሜሽን እቅድ ትግበራ 15 ሚሊዮን ህዝብ ከዚህ ውስጥ ከግምሻ በላይ የሚሆነው አምራች ዜጋ ምንም ሚና የለውም ሊባል አይችልም፡፡ ይህ ህዝብ ለህድገት እሴት ከመሆን ይልቅ ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የመቋቋሚያ ጊዜው ነው የሚሆነው፡፡ የጠፉበትን እንሰሳት ተክቶ ወደ ትርፍ እና ቁጣባ ለማምራት በዚህ አምስት ዓመት ውስጥ አይችለም፡፡ ይህ ደግሞ በእድገት ላይ የራሱ ጫና ይኖረዋል፡፡ መንግሰት ይህም ሆኖ ግን እድገታችን እንደተለመደው በአስማት በሁለት አሃዝ አድጎዋል ማለቱ አይቀርም፡፡ የነብስ ወከፍ ገቢያችንም እንዲሁ ይጨምራል፡፡

ሰለዚህ ቀጣዩ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አሁን ሀገሪቱ ካለችበት ያልተረጋጋ ሁኔታ፣ አዚህም እዚያም የሚከሰቱ ግጭቶች እና ግጭቶቹን መንግሰት የሚፈታበት ሀይልን መሰረት ያደረገ አካሄድ ለሀገሪቱ እጅግ አስፈላጊ የሆነው የውጭ ኢንቨስተምንት በሚጠበቀው ያህል ሊመጣ አይችለም፡፡ የሀገር ውስጥ ባለሀብቶችም ቢሆኑ ተሳትፎዋቸው በአጭር ጊዜ ውጤት ከሚያመጡ ንግዶች ሊዘል አይችልም፣ ቢኖርም በተለመደው አዲስ አበባ እና አካባቢዋ ብቻ ይሆናል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ አሁን ከፍተኛ አደጋ ጋርጦ ያለው የዜጎች የሚላስ የሚቀመስ ማጣት አጠቃላይ ሀገራዊ አቅምን በሚፈትን መልኩ ለልማት የሚውልን ገንዘብ ወደ እለት ደራሽ እርዳት እንዲውል ከማድረጉም በላይ አጭር ለማይባል ጊዜ የሚቀጥል የማቋቋሚያ ወጪን ይጠይቃል፡፡ እነዚህ በቀጣይ ፈታኝ ሁኔታዎች ሲሆኑ በተለይ በተፈጠረው ህዝባዊ እንቅሰቃሴ ሀገር አለን፣ መንግሰት አለ ብለው በሰላም ሃሳባቸውን ለመግለፅ ወጥተው ሳይመለሱ የቀሩ ዜጎች ደምና ህይወት በተራ የፎረም ፕሮፓጋንዳ ሰብሰባ በሚሰጥ የአቋም መግለጫ የሚፈወስ አይደለም፡፡ በዚህች ሀገር ህዝብን ያማከለ ልማትና እድገት እንዲኖር ካሰፈለገ፣ ዜጎች ሃሳባቸውን በመግለፃቸው የህይወት መሰዋዕትነት መክፈል ማቆም ይኖርባቸዋል፡፡ ለእሰከ ዛሬው የተከፈለው መሰዋዕትነትም ተገቢውን ማካካሻ በማድረግ ብሔራዊ እርቅ እንዲሰፍን መስራት ይኖርብናል፡፡ ሀገራችን የጋራችን ሃሳባችን የግላችን ነው፡፡

ቸር ይግጠመን!!!!!!!

The post ዝምታ ሰላም አይደለም ፕሮፓጋንዳም እድገት አይሆንም!!! – ግረማ ሠይፉ ማሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

Hiber Radio: የኢትዮጵያው አገዛዝ በአወዛጋቢው በሕዳሴ ግድብ ግንባታ ዙሪያ ሕዝባዊ ተቃውሞ እንዳይቀሰቀስበት ስጋት እንዳለው የግብጽ ሚዲያዎች አጋለጡ ፣በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ተቃውሞው እንደገና ተጠናክሮ እየቀጠለ ነው፣በጅማ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ተሰቅሎ ተገኘ፣አገዛዙ በተቃዋሚዎች ላይ የሽብር ጥቃቱን ቀጥሏል –የንጹሃን ሞት ጨምሯል፣ ከኢትዮጵያ የሄዱ የደህነት አባላት የኬኒያ ድንበርን ተሻግረው የአፈና እና የጦር መሳሪያ ዝርፊያ አድርሰዋል ስትል ናይሮቢ ወቀሳዋን አሰማች እና ቃለ መጠይቅ ከዶ/ር አክሎግ ቢራራና ከሰማያዊ ፓርቲ ም/ሊቀመንበር ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ሌሎችም

$
0
0
የኢትዮጵያው አገዛዝ በአወዛጋቢው በሕዳሴ ግድብ ግንባታ ዙሪያ ሕዝባዊ ተቃውሞ እንዳይቀሰቀስበት ስጋት እንዳለው የግብጽ ሚዲያዎች አጋለጡ ፣በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ተቃውሞው እንደገና ተጠናክሮ እየቀጠለ ነው፣በጅማ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ተሰቅሎ ተገኘ፣አገዛዙ በተቃዋሚዎች ላይ የሽብር ጥቃቱን ቀጥሏልቀጥሏል፣የንጹሃን ሞት ጨምሯል፣የእርዳታ እህልና ዘይት በባለስልጣናት ተዘርፎ እየተሸጠ ነው፣ የአሜሪካ መከላከያ ሚ/ር በኢትዮጵያ ውስጥ የሚያደርገውን የሰው አልባ አውሮፕላኖች የጸረ ሽብር ዘመቻውን ማቋረጡን አስታወቀ፣ ከኢትዮጵያ የሄዱ የደህነት አባላት የኬኒያ ድንበርን ተሻግረው የአፈና እና የጦር መሳሪያ ዝርፊያ አድርሰዋል ስትል ናይሮቢ ወቀሳዋን አሰማች እና ቃለ መጠይቅ ከዶ/ር አክሎግ ቢራራና ከሰማያዊ ፓርቲ ም/ሊቀመንበር ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ሌሎችም

የህብር ሬዲዮ አዘጋጅ፣ ከላይ የግድቡ ግንባታ፣ ዶ፣ር አክሎግ ቢራራ፣ከታች በረሃብ ችግር ላይ ሆኑ ወገኖች፣ተቃውሞውን ተከትሎ በቦንብ የተመታችው ህጻን ሀና እና የሰቀሉት ጅማ ዩኒቨርስቲ ተማሪ አስከሬን የሚያሳይ

የህብር ሬዲዮ ታህሳስ 24 ቀን 2008 ፕሮግራም
እንኳን ለአዲሱ ዓመትና ለኢትዮጵያውያን የገና ዋዜማ አደረሳችሁ!

<በረሀብ ሳቢያ ችግር ውስጥ ላለው ወገናችን መድረስ አለብን። ከሕዝቡ የሚዋጣውን ገንዘብ በቀጥታ የረሃብ አደጋ ለደረሰባቸው ወገኖቻችን እንዲደርስ ገንዘቡን ሰብስበን ከምናስረክበው ወርልድ ቪዥን ጋር ተስማምተናል። የቀረው ሕዝቡ ተባብሮ ለወገኖቹ የራሱን አስተዋጽዎ ማድረግ ብቻ ነው። ይህ ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵአውያን መብት በሳውዲ ዜጎቻችን የግፍ ሰለባ በሆኑ ጊዜ ተቋቁሞ በርካታ ጠቃሚ ስራዎችን ሰርቷል…በአባይ ጉዳይ ላይ የሰሞኑ ፊርማ ብቻ ሳይሆን ባለፈው ማርች ላይ የተደረገው ስምምነት የኢትዮጵያን ጥቅም የማያስጠብቅ የራሷን መብት ለግብጽ አሳልፎ የሚሰጥ ትልቅ ብሄራዊ ክህደት ነው ብዬ ጽፌ ነበር ሰሞኑን ሱዳን ላይ ያደረጉት ያንን ኢትዮጵያን አሳሪ ስምምነት የሚያጸና የአባይ ግድብን ወደ ውሃ የሌለበት ህንጻ ወይም ጉድጓድ ብቻ አድርጎ የሚያስቀር አደገኛ ነው። ይሄን ነው አገዛዙ ጥቅም አስጠባቂ የሚለው?… > ዶ/ር አክሎግ ቢራራ የዓለም አቀፍ ለኢትዮጵያውያን(ግሎባል አሊያንስ) የውጭ ግንኙነት ሀላፊ እና የቀድሞ የዓለም ባንክ የኢኮኖሚ አማካሪ በወቅታዊ ጉዳይ ለህብር ሬዲዮ ከሰጡት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)
<…በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ ለማንኛውም ሰላማዊ ጥያቄ ወይ እስር ወይ ድብደባ እና ጥይት ነው ሁኔታው አደገኛ እየሆነ ነው። የሁሉም አገራት ዲፕሎማቶች እያነጋገሩን ነው በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ መንግስት እየወሰደ ያለው የሀይል እርምጃ አደገኛ ሁኔታ ሊያስከትል እንደሚችል ገብቷቸዋል። አንድ ከአሜሪካ ኤምባሲ የመጡ ዲፕሎማት መንግስት ለፕ/ት ኦባማ የገባውን ቃል አልተገበረም ብለዋል። ሕዝቡም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም ተስፋ የቆረጠበት ስርዓት ነው …ሕዝቡ አገሩን እንዲያስተዳድር ብሄራዊ መንግስት እንዲመሰርት በጥቅሉ ያቀረብነው ጥሪ ሆን ብለን ነው።አንድ ታርጌት ቡድን እየነጠልን ለከሌ ለከሌ ብንል የጥቃት ሰለባ ይሆናሉ እኛ ግን በቻልነው መጠን አፈናው በርትቶም ሁሉንም ወገኖች ያሳተፈ ነገር ለማድረግ በክተኛ ጫና በደህነት ክትትል ውስጥ በእነሱ አጃቢዎች ተከበን እየዋልን ሰብስበው እስኪያስሩንም ሆነ ማንኛውንም እርምጃ እስኪወስዱብን ሰላማዊ ትግላችንን ቀጥለናል… > የሰማያዊ ፓርቲ ም/ሊቀመንበር አቶ ለገሰ ተፈረደኝ ለህብር ሬዲዮ ከሰጡት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)
አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝን <<የዓመቱ የአፍሪካ ታላቅ ሰው>> ብሎ የሰየማቸው አውሮፓ ላይ የተቀመጠው ናይጄሪያዊ ማንነትና ድህረ ገጹ ሲፈተሽ (ልዩ ዘገባ)
ሌሎችም
ዜናዎቻችን
የኢትዮጵያው አገዛዝ በአወዛጋቢው በሕዳሴ ግድብ ግንባታ ዙሪያ ሕዝባዊ ተቃውሞ እንዳይቀሰቀስበት ስጋት እንዳለው የግብጽ ሚዲያዎች አጋለጡ
በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ተቃውሞው እንደገና ተጠናክሮ እየቀጠለ ነው
በጅማ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ተሰቅሎ ተገኘ
በሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ በየቀኑ የንጹሃንን ሕይወት እየቀጠፈ ነው
የእርዳታ እህልና ዘይት በባለስልጣናት ተዘርፎ እየተሸጠ ነው
የአሜሪካ መከላከያ ሚ/ር በኢትዮጵያ ውስጥ የሚያደርገውን የሰው አልባ አውሮፕላኖች የጸረ ሽብር ዘመቻውን ማቋረጡን አስታወቀ
ከኢትዮጵያ የሄዱ የደህነት አባላት የኬኒያ ድንበርን ተሻግረው የአፈና እና የጦር መሳሪያ ዝርፊያ አድርሰዋል ስትል ናይሮቢ ወቀሳዋን አሰማች
የሰማያዊ ፓርቲ አባል የመግደል ሙከራ ተደረገባቸው
በመላው ዓለም የሚገኙ ኤርትራውያን የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ም/ቤትን በመቃወም ወደ አደባባዮች ወጡ
ሌሎችም ዜናዎች አሉ

The post Hiber Radio: የኢትዮጵያው አገዛዝ በአወዛጋቢው በሕዳሴ ግድብ ግንባታ ዙሪያ ሕዝባዊ ተቃውሞ እንዳይቀሰቀስበት ስጋት እንዳለው የግብጽ ሚዲያዎች አጋለጡ ፣በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ተቃውሞው እንደገና ተጠናክሮ እየቀጠለ ነው፣በጅማ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ተሰቅሎ ተገኘ፣አገዛዙ በተቃዋሚዎች ላይ የሽብር ጥቃቱን ቀጥሏል – የንጹሃን ሞት ጨምሯል፣ ከኢትዮጵያ የሄዱ የደህነት አባላት የኬኒያ ድንበርን ተሻግረው የአፈና እና የጦር መሳሪያ ዝርፊያ አድርሰዋል ስትል ናይሮቢ ወቀሳዋን አሰማች እና ቃለ መጠይቅ ከዶ/ር አክሎግ ቢራራና ከሰማያዊ ፓርቲ ም/ሊቀመንበር ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ሌሎችም appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

የእኔና አየርመንገዳችን ክርክር –የኢ-ፍትሓዊነት ማሳያ?! –በአቤል ዋበላ

≪ Previous: Hiber Radio: የኢትዮጵያው አገዛዝ በአወዛጋቢው በሕዳሴ ግድብ ግንባታ ዙሪያ ሕዝባዊ ተቃውሞ እንዳይቀሰቀስበት ስጋት እንዳለው የግብጽ ሚዲያዎች አጋለጡ ፣በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ተቃውሞው እንደገና ተጠናክሮ እየቀጠለ ነው፣በጅማ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ተሰቅሎ ተገኘ፣አገዛዙ በተቃዋሚዎች ላይ የሽብር ጥቃቱን ቀጥሏል –የንጹሃን ሞት ጨምሯል፣ ከኢትዮጵያ የሄዱ የደህነት አባላት የኬኒያ ድንበርን ተሻግረው የአፈና እና የጦር መሳሪያ ዝርፊያ አድርሰዋል ስትል ናይሮቢ ወቀሳዋን አሰማች እና ቃለ መጠይቅ ከዶ/ር አክሎግ ቢራራና ከሰማያዊ ፓርቲ ም/ሊቀመንበር ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ሌሎችም
$
0
0

ያኔ ይደብረኝ ነበር፡፡ መሥሪያ ቤቱ ይደብረኛል፡፡ አለቆቼ ይደብሩኛል፤ የሚጠገ’ኑት አውሮጵላኖች ሽታ ይደብረኛል፡፡ አቧራ የጠገቡት የጥገና መሳሪያዎቼ ይደብሩኛል፡፡ ለምን ይህንን ስህተት ሠራሁ እያልኩኝ ራሴን እጠይቃለሁ፡፡ ለምን በኮሌጅ የተማርኩትን የመሀንዲስነት ሙያ ትቼ ስለምን የአውሮጵላን ጥገና ሙያ ውስጥ ገባሁኝ እያልኩኝ ራሴን እጠይቃለው፡፡ ከኮሌጅ እንደወጣሁኝ ሥራ የጀመርኩት በቢሾፍቱ ከተማ ነበር፡፡ በኋላ ደግሞ የተወሰኑ ወራት ጫንጮ የሚገኝ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሠርቻለው፡፡ ጥግ ጥግ ከመዞር ገላግሎ አዲስ አበባን እንድከትምባት ዕድሉን ያመቻቸልኝ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው፡፡ያኔ የትውልድ ከተማዬ ውስጥ፣ አዲስ አበባ መሆን እፈልግ ነበር፡፡ አራት ኪሎ ከቤተ መንግሥቱም፣ ከቤተ ክህነቱም መራቅ አልፈልግም ነበር፡፡ ምክንያቴ ደግሞ የማወቅ የመማር ነበር፡፡ ጫንጮ ብርዳማ ናት፡፡ እንደ አየር ንብረቷ የዐሳብ ገበያዋም ለእኔ ፍላጎት የሚያመረቃ አልነበረም፡፡ በወቅቱ በስስት የምትነበበውን አዲስ ነገር ጋዜጣን ለማግኘት እንኳን ወደ መዲናዋ የሚመላለሱ ሹፌሮችን መለማመጥ ግዴታዬ ነበር፡፡

ጦማሪ አቤል ዋበላ

ጦማሪ አቤል ዋበላ

ህወሓት መራሹ ስርዓት እንዳይሆን-እንዳይሆን ካደረጋቸው ነገሮች አንዱ የሀገሪቱ ኢንዱስትሪ ነው፡፡ የዚህ የተሳከረ ፖሊሲ ግንባር ቀደም ሰለባ ከሆኑት መካከል የቴክኖሎጂ ተማሪዎች ይገኙበታል፡፡ የሀገሪቱ ኢንዱስትሪዎች የተማረ የሰው ኃይል ፍላጎት መጠንና ዓይነት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ በገፍ ከሚያስመርቁት ተማሪ ጋር ሊጣጣም ባለመቻሉ በቴክኖሎጂ ምሩቃን እና ቀጣሪዎቻቸው መካከል የተዛባ ግንኙነት በግልጽ ይታያል፡፡ ከተማሪዎች መካከል በኮሌጅ በብዙ ትጋት የቀሰሙትን ወደ ንድፈ ሐሳብ የሚያደላ ትምህርት በተግባር የሚያውሉበት ዕድል የሚያገኙት እጅግ ጥቂቶች ብቻ ናቸው፡፡ አብዛኛው ግን የዕለት እንጀራውን ለማብሰል በተገኘው የሥራ መስክ መሰማራት ዕድል ፈንታው ነው፡፡ አንዳንድ ቀጣሪዎች ይህንን ዕድል ተጠቅመው ለሥራ መደቡ ከሚያስፈልገው በላይ የሰለጠነ (overqualified) ምሩቅን በዝቅተኛ ክፍያ ይቀጥራሉ፡፡ ‘ስለአፈር እና ድንጋይ ምንነት አጥንተው በሲቪል ምህንድስና የተመረቁ ልጆች ኮብል ስቶን ለመጥረብ መርቴሎ ጨበጡ’ ተብሎ በከተማው መነጋገሪያ ከመሆኑ በፊት ብዙ ምሩቃን ከሠለጠኑበት የቴክኖሎጂ ዕውቀት እጅግ በጣም ጥቂቱን ብቻ በሚሻ የሥራ መደብ ተሰማርተው ነበር፡፡ ከነዚህ overqualified የሆኑ ምሩቃንን ባልተገባ መልኩ ከሚቀጥሩ ድርጅቶች መካከል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይገኝበታል፡፡ አየር መንገዱ በርካታ ባለዲግሪዎችን ከቴክኒክና ሙያ ተቋማት ብቻ በሚገኝ ዕውቀት በሚሠሩ የሥራ መደቦች ላይ ቀጥሮ ያሠራ ነበር፡፡ አሁንም ይህ ተቀይሯል ብዬ አልገምትም፡፡

እኔም አዲስ አበባ መሆንን አጥብቄ ፈለግሁኝ፡፡ማስታወቂያ ሲወጣ ጠብቄ አመለከትኩኝ፡፡ አየር መንገዱም ወግ ወጉን ይችልበታል፡፡ የጽሑፍ፣ የቃልና የህክምና የመሳሰሉ ፈተናዎችን አሳልፎ የአውሮጵላን ጥገና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱን እንድቀላቀል ፈቀደልኝ፡፡ በትምህርት ቤቱ የሚሰጠውን የዐሥራ አንድ ወራት ሥልጠና ተከታትዬ አየር መንገዱን ለሰባት ዓመታት እንዳገለግል ይህን ባልፈጽም ግን ከሰባ ሺሕ በጥቂቱ ከፍ የሚል የኢትዮጵያ ብር ለመክፈል ተስማምቼ ፈረምኩኝ፡፡ ሥልጠናው ተጀመረ፡፡ ሁሉም ነገር የዓይን አዋጅ፤ ጽዱው የትምህርት ቤቱ ግቢ፣ የደንብ ልብስ ለብሰው አጀብ ሠርተው የሚጓዙ ተማሪዎች፣ ቆነጃጅቱ እጩ የበረራ አስተናጋጆች . . . ምኑ ይወራል ሁሉም ነገር አዲስ ሆነብኝ፡፡ ስለትምህርት ቤቱና አየር መንገዱ ገለጻ ተደረገልን፡፡ ዎርልድ ክላስ ኩባንያ እንደተቀላቀልን ተደሰኮረልን፡፡ ጀብድ የሚወደው ልቤ የምር ነገር የተገኘ መስሎት ቋመጠ፡፡ ትምህርት/ሥልጠና ተጀመረ፡፡

በሥልጠናው የመጀመሪያ ሁለት ሳምንታት የተማርነው አንድ ክብደት ያለውን ነገር ከመሬት ከፍ በማድረግ አየር ላይ ማንቀሳቀስና መቆጣጠር እንዴት እንደሚቻል የሚያስረዳው የኤሮዳይናሚክስ (aerodynamics) ትምህርት ነበር፡፡ በጣም የሚያስደስትና የሰው ልጅን አእምሮ ምጥቀት እንድናደንቅ የሚያስገድድ ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ የወሰድናቸው ትምህርቶች ግን የኔን ቀልብ የሚስቡ ሆነው አልተገኙም፡፡ በአብዛኛው ከጥገና ጋር የተያያዙ መሰረታዊ ዕወቀቶችን የሚያስጨብጡ ተደጋጋሚና ውስብስብነት የሌላቸው ነበሩ፡፡ ይህ ደግሞ አስቸጋሪ የምህንድስና ችግሮችን ከነመፍትሔዎቻቸው ለቃረመ አእምሮ እዚህ ግባ የሚባል አልነበረም፡፡ ከእኔ ጋር አቪየሽን ትምህርት ቤት ከነበሩ ሀያ አምስት ተማሪዎች መካከል ካልተዘነጋኝ ሀያ ሶስቱ በሀገሪቱ ውስጥ ከሚገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በምህንድስና የተመረቁ በመሆናቸው ስለጥገናው ትምህርት ያላቸው ግንዛቤ ከኔ ብዙም የሚርቅ አልነበረም፡፡ ከአንዳንድ እድሜያቸው ከገፋ መምህራን በስተቀር መምህራኑ የኛን ሥነ ልቦና ስለሚረዱ ብዙም አላስጨነቁንም፡፡ እኛም ጥሩ ታዛቢዎች ነበርን፡፡ ዳግም ሥራ ፍለጋ መውጣትን በመስጋት የትምህርት ቤቱ መምህራንና አስተዳደርን ላለማስቆጣት ተጠንቅቄ በምርቃት መርሐ ግብሩ ላይ ባልገኝም ትምህሩቱን አጠናቅቄ በአውሮጵላን ስትራክቸር ጥገና ክፍል ተመድብኩኝ፡፡
ወደሥራ ገበታ ስሄድ በሁለት ጉዳዮች ላይ የራሴን ግምት ወስጄ ነበር፡፡ ከመጀመሪያውና ልክ ከሆነው ግምቴ ልጀምር፡፡ ከልጅነት ጀምሮ መጽሐፍ ከማንበብና ኳስ ከመጫወት በዘለለ የአካልና የአእምሮ ቅልጥፍናን በሚጠይቁ ሥራዎች ደካማ ነበርኩኝ፡፡ እናታችንን በመርዳት የቤት ወስጥ ሥራዎች የሚያከናውኑት ታላላቅ እህቶቼ ነበሩ፡፡ አሁን ሳስበው በሚያሳፍረኝ ሁኔታ ያኔ ግቢያችን የቧንቧ ውሃ በሌለበት ጊዜ ከቦኖ ውሃ በባሊ ሲቀዱ እንኳ አላግዛቸውም ነበር፡፡ ስለዚህ ይህ የአውሮጵላን ጥገና ባለሙያነት አካላዊ ብቃትና ዲሲፕሊን እንዲኖረኝ ያደርገኛል ብዬ አስብ ነበር፡፡ ይህ ግምቴ ልክ ነበር፡፡ በብዙ መልኩ ተለውጫለው፡፡ በትዕግስት መካኒካል ችግሮችን የመፍታት ክህሎት አዳብሪያለሁ፡፡ ምን አልባት አንድ ባለሙያ የሆነ ሰው አሁን ነገሮች የምሠራበት አኳኋን ላይጥመው ይችላል፡፡ እኔ ግን የነበርኩበትን አውቃለውና በአሁኑ ቅልጥፍናዬ ደስተኛ ነኝ፡፡
ሁለተኛው ግምቴ የሥራው ከባቢ ባለሙያነት የሚበከበርበትና ከስልጠናው ደግሞ የተሻለ ሳቢ ይሆናል የሚል ግምት ነበረኝ፡፡ ይህ ግምቴ ፈጽሞ ከእውነታው እጅግ የራቀ ነበር፡፡ በአለቆችና የበታች ሠራተኞች መሐል ያለው ግንኙነት ያለሁት ያ ስመ ገናናው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው ወይስ ሌላ ቦታ ያሰኛል፡፡ ይህን ጤናማ ያልሆነ የሥራ ግንኙነት ተከትሎ ሠራተኛውም በሥራው የሚለግም፣ አለቆቹን ሲያይ ብቻ ሠራተኛ ለመምሰል የሚሞክር ሀሜተኛና ብሶት የሚያበዛ ነው፡፡ አለቆቹም ከበታች ሠራተኛ የተሻለ ስብዕና ስለሌላቸው ጎበዝ ሠራተኛን ሳይሆን ወሬ የሚያቀብልን የሚወዱ፣ በጥቅማጥቅም እየደለሉ የራሳቸውን አንጃ የሚያደራጁ፣ ሰራተኛ የተመቸው ሲመስላቸው የሚከፋቸው፣ ትልቅ የሚመስሉ ነገር ግን የህጻናት ተግባር ሲፈጽሙ የሚገኙ ናቸው፡፡ በእርግጥ ይህ ገለጻ የማይመለከታቸው ጥቂት ደህና ሰዎችን እንዳያሰከፋብኝ እሰጋለሁ፡፡ ነገር ግን እነዚህ ሰዎች በዚያ ስፍራ ጥሩ ለመሆን ሲሞክሩ ከእኔ በላይ ችግር ገጥሟቸዋል ብዬ ስለማምን መግለጽ የፈለግኹትን ዐሳብ ይርረዱኛል ብዬ ተስፋ አደርጋለው፡፡ በዚህ በተበከለ የሥራ ከባቢ ከሠለጠኑበት የሙያ ዘርፍ ያነሰ ብዙ የአእምሮ ጉልበት የማይጠይቅ ሥራን መከወን ከባድና ስለ አስቸጋሪነቱ የሥነ ልቦና ባለሙያዎች የሚስማቡበት ነው፡፡ ይህ ሁኔታ አብዮተኛው ልቤን ምቾት ሊሰጠው አልቻለም፡፡ ይህን ቅሬታዬን በአንድ በዲፓርትመንት ደረጃ በተደረገ ስብሰባ ላይ አነሳኹት፡፡በዚያ ቀን በአለቆቼ ጥርስ ውስጥ ገባሁኝ፡፡ በቅንነት መሥሪያ ቤቱን ሀገራችንን የምናገለግልበት፣ ለብዙ ዓመት በሥራ ላይ ከነበሩ አንጋፋ ሠራተኞች ልምድ የምንቀስምበትና የምንማርበት፣ እኛም የምንጠቀምበት ምቹ ስፍራ እናድርገው ባልኩኝ ጠላት አፈራኹኝ፡፡ ከዚያ እኔም ደበረኝ ከአየር መንገዱም ጋር ሆድና ጀርባ ሆንን፡፡ አየር መንገድ ትቼ የምወጣበትን ቀን መናፈቅ ጀመርኩኝ፡፡
በዚህ በደበረኝ ወቅት ነበር አየር መንገዱ ሥራ ላይ ለሚገኙ ሠራተኞቹ ከዘመኑ የአቪየሽን ኢንዱስትሪ ጋር በየጊዜው እንዲተዋወቁ (Recurrent) ሲል ያዘጋጀውን ሥልጠና እንድወስድ የታዘዝኩት፡፡ አለቆቼ ለእኔ አስበው ሳይሆን የፎርማሊቲ ጉዳይ ሆኖባቸው ይህንን ሥልጠና እንድከታተል ፈቀዱ፡፡ እኔም ከዚያ ከማልወደው የሥራ አከባቢ ገለል ማለትን ፈልጌ ስለነበር በደስታ ወደ ሥልጠናው አመራኹኝ፡፡ በሥልጠናው ከዚህ በፊት እንዳሠለጠኑኝ መምህራን ከዚህ በፊት የማውቀውን ነገር በተሰላቸ መንገድ የሚደግም ሰው አልገጠመኝም፡፡ ሰውየው ዓለም ዐቀፍ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ በሚገባ የተረዳ ነው፡፡
በዚህ ውድድር በበዛበት መድረክ አየር መንገዱ ውጤታማ እንዲሆን እያንዳንዱ ሠራተኛ በተመደበበት የሥራ መደብ ምን እንደሚጠበቅበት በመተንተን ያስረዳል፡፡ የኢንዱስትሪውን ፓለቲካ፣ የተቆጣጣሪ ድርጅቶችን ጸባይ፣ እንደ አይካዎ ያሉ አለም አቀፍ የአቪዬሽን ማኅበራት ፍላጎቶች፣ አየር መንገዱ ያሉበትን ተግዳሮቶች፣ ኢንዱስትሪው በዘመኑ የደረሰበትን ዕውቀት በከፍታ(experts with excellence)የሚያውቁ ሠራተኞች እንዴት ለአየር መንገዱ ጉልበት እንደሚሆኑ ነገር ግን አየር መንገዳችን የነጠረ (refine) ዕውቀት ያላቸው ባለሙያዎች እጥረት እንዳለበት ተጨባጭ በሆነ መልኩ አስረዳን፡፡ ያን ጊዜ ከእንቅልፌ እንደመባነን አልኩኝ፡፡ ተዳፍኖ የነበረውን ሀገሬን በባለሙያነት የማገልገል ስሜቴን ቆሰቆሰው፡፡ ወደቢሮው ሄጄ ላመሰግነው ብቋምጥም አየር መንገዱን ከተቀላቀልኩኝ ጀምሮ ያዳበርኩት የባይተዋርነት ስሜት ቀፍድዶ ያዘኝ፡፡ ለራሴ ግን ያለሁበትን ሁኔታ ለመቀየር ቃል ገባኹኝ፡፡
የምህንድስና ክፍል ክፍት የሥራ ቦታ ሲያወጣ ተወዳድሬ ለማለፍ በቦሌም በባሌም መንገድ ጥረት አደረግኹኝ፡፡ ዕድል ዘግይታም ቢሆን ከእኔ ጋር ሆነች፡፡ አስፈላጊውን ፈተና እና ቃለ መጠይቅ በማለፌ በአየር መንገዱ የአውሮጵላን ጥገና እና ዕድሳት ክፍል የጥገና መሳሪያዎች አስተዳደር እና ምህንድስና ክፍል በመሀንዲስት እንዳገለግል ተመደብኩኝ፡፡ በአጋጣሚ የቅርብ አለቃዬም የሚሠራውን የሚያውቅ፣ ትጉሕና የሚመራው ክፍል የሚጠበቅበትን ሚና በአግባቡ የተረዳ ነበር፡፡በርካታ ሥራዎችን ለመከወን ዕቅድ ያዝን፡፡ እኔም ለመጀመሪያ ጊዜ ቢሮዬ ይናፍቀኝ ጀመር፡፡ ጠዋት ቀድሞ መግባት፣ ማታ ደግሞ አርፍዶ መውጣት እና በእረፍት ቀኔም ወደቢሮ መሄድ ልማዴ ሆነ፡፡ የተወሰኑ ወራት ደስ ብሎኝ ሠራሁ፡፡ አለቃዬም ስገምት በሥራችን ከሞላ ጎደል ደስተኛ የነበረ ይመስለኛል፡፡
በዕለተ ዓርብ ሚያዝያ 17/2006 ዓ.ም. ከ ቀኑ 10፡30 አከባቢ ነው፡፡ የተለመደ ሥራዬን ለማከናወን ኮምፒዩተሬ ላይ አፍጥጫለው፡፡ የመሥሪያ ቤቱ ደኅንነት ከሁለት የማላውቃቸው ሰዎች ጋር ወደቢሮ ገብተው “አቤል ዋበላ . . . አንዴ ውጭ ፈልገንህ ነው” ሲሉ ጠሩኝ፡፡ ሕገ-መንግሥቱን እና ሕገ-መንገሥታዊ ስርዓቱን በኃይል ለማፍረስ በመሞከር ተጠርጥሬ በፌደራል ፓሊስ ቁጥጥር ስር መዋሌ ነው፡፡ ዞን ዘጠኝ ላይ ከሚጽፉ አምስት ጦማሪዎች እና ሌሎች ሦስት ጋዜጠኞች ጋር በአባሪነት የፌደራል ወንጀል ምርመራ ዘርፍ (ማዕከላዊ) ገባን፡፡ በሂደት ፓሊስ ጥርጣሬውን ወደ ሽብር አሳደገው፡፡
ጭራሽ ይግረማችሁ ብሎ በፌደራል ዐቃቤ ሕግ ታግዞ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ክስ መሠረተ፡፡ ክሱ እንኳን ለዳኞቹ እና ለእኛ ለተከሳሾቹ አይደለም ለራሱ ለዐቃቢ ሕጉም የሚገባ ስላልሆነ በጠበቆቻችን አማካኝነት የክስ መቃወሚያችንን አቀረብን፡፡ ዳኞቹ ፈራ ተባ እያሉ የተወሰነ ነጥቦች ብቻ እንዲያስተካከል አድርገው አሻሽል ያሉት ነጥብ ሳይሻሻል ክሱ እንዲቀጥል ወሰኑ፡፡ እኛም በፀረ-ሽብር አዋጁ አንቀጽ ፫/፪ “የኅብረተሰቡን ወይም የኅብረተሰቡን ክፍል ደኅንነት ወይም ጤና ለከፍተኛ አደጋ” ለማጋለጥ “በመሞከር፣ በማሴር፣ በማነሳሳት” በሚል ተከሰን ፍርዳችንን መጠባበቅ ያዝን፡፡ ከዚያም ዐቃቤ ህግም አስቂኝ የሆነውን የሰውና የሰነድ ማስረጃውን አቀረበ፡፡ ይህ ሂደት አንድ ዓመት ከስድስት ወር ገደማ ፈጅቶ ጥቅምት 05/2008 ዓ.ም. መከላከል ሳያስፈልገን በነጻ ተለቀቅን፡፡
ከፍርድ ቤት በቀጥታ ለአየር መንገዱ የተጻፈ በነጻ መለቀቄን የሚገልጽ ማስረጃ ጥቅምት 10/2008 ዓ.ም. ተቀብዬ ድርጅቱ በነጻ መሰናበቴን ተመልክቶ ወደ ሥራ እንዲመልሰኝ ጥቅምት 15/2008 ዓ.ም. አመለከትኩኝ፡፡ ውሳኔ ላይ አልደረስንም በሚል ሲያመላልሱኝ ከቆዩ በኋላ ሕዳር 16/2007 ዓ.ም. ከዓመት በፊት በኖቨምበር 4/2015(ጥቅምት 25/2007 ዓ.ም.) የተጻፈ ከሥራ መታገዴን የሚገልጽ የስንብት ደብዳቤ ሰጡኝ፡፡ ደብዳቤው የሥራ ውሌ እንዲቋረጥ ምክንያት የሆነው ለስድስት እና ከዚያ በላይ ለተከታታይ ወራት በእስር ምክንያት ከሥራ ገበታዬ መቅረት መሆኑን ጠቅሶ ይህ ከሆነ ደግሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የኢ.አ.መ. መሠረታዊ የሠራተኞች ማኅበር 10ኛ የኅብረት ስምምነት አባሪ 1 ክፍል አንድ ተ.ቁ 6(111) እና የአሠሪ እና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 377(2003) አንቀጽ 27(1)(ተ) አንድ ላይ በመሆን የሥራ ቅጥር ውል ወዲያው እንዲቋረጥ ያደርጋል ይላል፡፡
በሕግ ከኅብረት ሥምምነቶች በላይ ተቀባይነት ያለው የአሠሪ እና ሠራተኛ አዋጅ አንቀጽ ፳፯ ያለማስጠንቀቂያ የሥራ ውል ስለማቋረጥ በቁጥር (፩) “በኅብረት ስምምነት ካልተጠቀሰ በሌላ አኳኋን ካልተወሰነ በስተቀር የሥራ ውልን ያለማስጠንቀቂያ ማቋረጥ የሚቻለው በሚከተሉት ሁኔታዎች ብቻ ነው፡፡” ይልና ከፊደል ተራ ሀ-ቀ ከእስራት ጋር ያልተያያዙ የሥራ ውልን የሚያቋርጡ ሕገ-ወጥ ድርጊቶችን ይዘረዝራል፡፡ በፊደል ተራ (በ) ደግሞ “በሠራተኛው ላይ ፴ ቀናት ለሚበልጥ ጊዜ የእስራት ፍርድ ተወስኖበት ከሥራ ሲቀር” ይላል፡፡ እኔ በሕግ አንድም ቀን እንድታሰር ‹የጥፋተኝነት ብይን› ስላልተላለፈብኝ አይመለከተኝም፡፡ በድርጅቱ የተጠቀሰው በፊደል ተራ (ተ) “ያለማስጠንቀቂያ የሥራ ውል ለማቋረጥ ያስችላሉ ተብለው በኅብረት ስምምነት የተወሰኑ ሌሎች ጥፋቶች መፈጸም” የሚለው ነው፡፡ በዚህ መሠረት አዋጁ ሥልጣኑን ለኅብረት ስምምነቱ ስለሚሰጥ ያንን መመልከቱ አስፈላጊ ነው፡፡
የኅብረት ስምምነቱ አባሪ 1 ክፍል አንድ “ያለማስጠንቀቂያ ከሥራ የሚያሰናብቱ ከፍተኛ የሥነ-ስርዓት ግድፈቶች/ጥፋቶች እና የሥነ-ስርዓት እርምጃዎች” ይልና ከ ተ.ቁ 1-30 ያሉ ከወሲብ ትንኮሳ አንስቶ በድርጅቱ ቅጽር ግቢ ውስጥ ጠብና አምባጓሮ እስከመጫር የሚደርሱ የጥፋት ዓይነቶችን ይዘረዝራል፡፡እኔን የሚመለከተው 6(111) “ወንጀል ፈጽሞ የ6 ወር እስራት ወይም ከዚያ በላይ እስራት ተፈርዶበት በፍርዱ መሠረት የሚታሰር መሆኑ ሲታወቅ ወይም በማንኛውም ምክንያት ሳይፈረድበት 6 ወር ወይም ከዚያ በላይ ታስሮ የቆየ ”የሚለው ነው፡፡ እዚህ ጋር ነው እንግዲህ ሕገ-መንግሥታዊ መብቴ የተጣሰው፡፡ አዋጁ ለኅብረት ስምምነቱ ሥልጣን ቢሰጥም አሠሪዎች የሠራተኛ ማኅበራትን እየጠመዘዙ የዜጎችን ሕገ-መንግሥታዊ መብት በሚጥስ መልኩ የፈለጉትን ነገር በኅብረት ስምምነት እያሰፈሩ ሠራተኛውን እንዲድበሉ አይፈቅድም፡፡ የኅብረት ስምምነቱ ሕገ-መንግሥቱንና ሌሎች የሀገሪቱን ሕጎች የማይጥስ፣ በመንፈሱ ፍትሓዊ ሊሆን ይገባዋል፡፡ በሕገ-መንግሥቱ በግልጽ አንድ ሰው በፍርድ ቤት እስካልተወሰነበት ድረስ እንደ ነጻ ሰው እንደሚቆጠር በአንቀጽ 20 ላይ ሰፍሯል፡፡ በመጠ’ርጠሬ ምክንያት ብቻ የሥራ ውሌን ማቋረጥ ሕገ-መንግሥታዊ ታዛዥነትን ያፈረሰ ነው፡፡ ‹በማንኛውም ምክንያት ሳይፈረድበት 6 ወር እና ከዚያ በላይ የቆየ› የሚለው የሀገራችንን የፍርድ ቤቶች ‹ፍትሕን ከሰጡ አዘግይተው የመስጠት› ተጨባጭ ሁኔታ ያላገናዘበ ነው፡፡
ይህንን የመብት ጥሰት ከሕግ ባለሙያው አመሐ መኮንን ጋር ተማክሬ ሕዳር 24/2008 ዓ.ም. በፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ደረጃ ፍ/ቤት ቦሌ ምድብ ሥራ ክርክር ችሎት ወደ ሥር እንድመለስ ወይም ድርጅቱ ወደሥራ የምልመለስበት በቂ ምክንያት አለ ሚባል ከሆነ ከሕግ ውጭ ለተቋረጠው የሥራ ውል በሕጉ መሠረት አስፈላጊውን ክፍያ እንዲፈጽም በመጠየቅ ክስ መስርቻለሁ፡፡ ይህን ክሴን ተከትሎ መሥሪያ ቤቱ በደረሰው መጥሪያ መሠረት በታኅሣሥ 22/2008 ዓ.ም. የጽሑፍ ምላሽ ሰጥቷል፡፡ በዚህ መልሱም የሌባ ዓይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ እንዲሉ ድርጅቱ ስህተቱን ለማረም ዝግጁነት እንደሌለው አሳይቷል፡፡ የሚገርመው በማይመለከተው ጉዳይ ላይ በመግባት የፌደራል ዐቃቤ ሕግ በእኔ እና ጓደኞቼ በጠቅላይ ፍርድ ቤት የጠየቀውን ይግባኝ በማንሳት ከሳሽ ገና ለገና ተከሳሽ በድጋሚ ሊታሰር ይችላል በሚል ወደ ሥራ ልመልሰው ልገደድ አይገባኝም ብሏል፡፡ ሰሚት የሚገኘው ፍርድ ቤትም ክርክሩን ለመስማት ለየካቲት 24/2008 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ቀጠሮ ይዟል፡፡
ጉዳዩ በዚህ ቢያበቃ መልካም ነበር፡፡ ድርጅቱ በሕገ-ወጥ መንገድ የሥራ ውሌን አቋርጦ ሳለ ድርጅቱ የሚሰጠውን ሥልጠና ስወስድ ቃል የገባኹት የሰባት ዓመት አገልግሎት በግሌ ያልተወጣኹኝ በማስመሰል ሰባ ሺ የኢትዮጵያ ብር ከነወለዱ እንድከፍለው ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የካ ምድብ ችሎት ክስ መስርቶብኛል፡፡ ይህ የሚያሳየው ድርጅቱ ምን ያህል ኢ-ፍትሓዊነት ቀለባቸው በሆኑ ሰዎች እንደሚመራ ነው፡፡ ከሥራ ለምን ቀረው? በእስራት ምክንያት እስራቱ የማን ስህተት ነው? የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዳረጋገጠው የፖሊስ ሐሰተኛ ክስ ነው:: የሥራ ውሌን ማን አቋረጠው? የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሥራ ገበታ ለምን ቀረህ በማለት በመጨረሻም የገባኸውን ቃል አልፈጸምክም በሚል የከሰሰኝ ራሱ አየር መንገድ ሆኖ አዙሪት ውስጥ ገብቼያለሁ፡፡ ከዚህ ቀደም የልደታውን፣ የአራዳውን፣ የስድስት ኪሎውን ፍርድ ቤት ነበር የማውቀው አሁን ደግሞ የካ ፍርድ ቤት በታህሳስ 26/2008 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 እንድቀርብ ታዝዣለው፡፡ የምቆመው ብቻዬን ከመሰላቸው ተሳስተዋል፡፡ የምቆመው እንደ አየር መንገዱ ከሕግ በላይ በሆኑ አሠሪዎች በደል ከደረሰባቸው ሠራተኞች ጋር ነው፡፡ የምቆመው ኢ-ፍትሓዊነት በሀገራችን እንዲወገድ ከሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ጋር ነው፡፡ ከዚህ በፊት አየር መንገዱ ብዙ ሠራተኞችን በድሎ በዝምታ እንደታለፈው(የጽሑፉ ዓላማ ይሄ አይደለም እንጂ ስለበደሉ ብዙ ማለት ይቻላል) ከእኔ ዝምታን ቢፈልግ አያገኛትም፡፡ ከእስር እንደወጣኹኝ አንዳንድ ወዳጆቼን ሥራ እንዴት ነው ብዬ ጠይቄ ነበር የብዙዎቹ ምላሽ “ቀንበሩ ከበዷል” የሚል ነው፡፡ ይህንን መሰል ዘመናዊ ባርነቶች እንዲወገዱ ምኞቴ ነው፡፡ እኔ ግን ፍትሕ ባላገኝ እንኳን ለታሪክ ተመዝግቦ እንዲቀመጥ ስል ይህን እናገራለሁ፡፡

The post የእኔና አየርመንገዳችን ክርክር – የኢ-ፍትሓዊነት ማሳያ?! – በአቤል ዋበላ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

የወልቃይት ጠገዴ መሬቱን እንጂ…! |ሳምሶን ኃይሌ

$
0
0

በሐገር ቤት ከሚታተመው የቀለም ቀንድ ጋዜጣ የተገኘ

ከአንድ ሳምንት በፊት የወልቃይት አማሮች የማንነት ጥያቄ አስተባባሪዎቹ ሊያገኙኝ እንደሚፈልጉ ገልጸውልኝ በቀጠሯችን መሠረት ተገናኘን። ለኢፌዴሪ የፌደሬሽን ምክር ቤት ያስገቡትን የማንነት ጥያቄ ማመልከቻ እንዲሁም 116 የት እንደደረሱ የማይታወቁ ወገኖቻቸውን ስም ዝርዝር የያዘ ሰነድ ፎቶ ኮፒ ሰጡኝ። ሰነዱ በራሱ ገላጭ ቢሆንም የአካባቢውን ተወላጆች መሠረታዊ ጥያቄ በሚገባ ለመረዳት በዕድሜና በተመክሮ በሳል የሆኑ ሰዎችን ማነጋገሩ የተሻለ መስሎ ስለተሰማኝ ሐሳቤን ገለጽኩላቸው። እነሱም ጥያቄየን ተቀብለው ከአንድ የ70 ዓመት አዛውንት ጋር አገናኙኝ።

welkaiyt

ያገኘዋኋቸው አባት ታሪክን ጠንቅቀው የሚያውቁ የቤተ ክህነት ሊቅ ናቸው። እኚህ አዛውንት ስለወልቃት ጠገዴ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵና ሱዳን ጉዳይ ላይ ያላቸው ዕውቀት ከፍተኛ ነው። ይህ ከዚህ ቀጥሎ የቀረበው የዕድሜ ባለጸጋው የወልቃይት ተወላጅ የነገሩን ነው።

የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ወንዱም ሴቱም ጅግና ነው። በጣሊያን ወረራ ዘመን እናቶቻችን ልጆቻቸውንና ባሎቻቸውን አልጋ ሥር ጠመንጃ አቀባብለው እንዲደበቁ ያደርጋሉ። እነርሱ ደግሞ በርበሬ (ሚጥሚጣ) ድቁሱን በውኃ በጥብጠው ያስቀምጣሉ። ከዚያም የጠላት ወታደር በውበታቸው ማርከው ወደ ቤት ያስገቡታል። የወልቃይቷን ሴት ውበት ዓይቶ በስስት የሚገባው ፈረንጅ ፊትና ዓይን ላይ ያን የተበጠበጠ በርበሬ ይደፉበታል። ያ ወታደር ሲደናበር አልጋ ሥር የተደበቀው ባለነፍጥ አናቱን ብሎ እየሸለለ የጠላትን ትጥቅ ቀምቶ ጫካ ይገባል።

ኢሕአፓና ሕወሓት ታኅሣሥ 21 ቀን 1972 ዓ.ም. በወልቃይት ደጀና ከተባለ ቦታ ላይ ጦርነት ገጠሙ። ‹‹ግንብ›› የተባለ ጎድጓዳ ቦታ አለ። ግንብ ውስጥ ሰው ቢጮህ ማንም አይደርስለትም። ጥይት ቢተኮስም ርቀት ቦታ አይሰማም። ደጀና ላይ ሲዋጉ የነበሩ የኢሕአፓ ወታደሮች ሁሉ ግንብ ውስጥ ዶግ አመድ ሆኑ። አስከሬን ቀባሪ አጥቶ ለአሞራ ቀለብ ሆነ። የሰው ልጅ ለካ ያን ያክል ስብ ይሸከማል? ስቡ ቀልጦ የሚፈሰው መሬቱን ሁሉ አጥቁሮት ነበር። የጥይት ድምጽ አፍኖ የሚይዘው ግንብ አስከሬኖቹ የሚተፉትን መጥፎ ጠረን ግን አፍኖ መያዝ ተሳነው። ድፍን ወልቃይትን በመጥፎ ጠረን አሰከረው።

ከሞት ያመለጡት የኢሕአፓ ሠራዊት አባላት ወደ ሱዳን ተሰደዱ። የወልቃይት ጠገዴ ጣዕር ከዚህ ጊዜ ይጀምራል። ሕወሓቶች ወልቃይት ጠገዴን ዙረው ሲመለከቱ በመሬቱ ለምነት ጎመዡ። በዚህ ምክንያት መሬቱን ለመውሰድ ሕዝቡን በልዩ ልዩ መንገድ ማሰቃየትና ከአካባቢው ማፈናቀልን ሥራዬ ብለው ተያያዙት። በዚህ መንገድ ሕወሓት ‹‹ኢሕአፓን አስጠልላችኋል›› በማለት በወልቃይት ሕዝብ ላይ መከራውን አንድ ብሎ ጀመረ። ያኔ የተጀመረው መከራ አሁንም ይበልጥ ተጠናክሮ ቀጠለ እንጂ አልቆመም። ኢሕአፓን አስጠግተዋል ያላቸውን አማሮችን ቤትና ንብረት ማቃጠል የጀመረው ሕወሓት ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የወልቃይት ወጣቶችን ሰበብ እየፈለገ መግደል ሥራው ሆነ፤ የግፍ አገዛዝ በሕዝቡ ላይ ተጫነ። ለዚህ ደግሞ የሱዳን መንግሥት ታላቅ ሚና ተጫውቷል። አሁንም ቢሆን የሱዳን መንግሥት የጥፋት እጆች አልተሰበሰቡም።
የወልቃይት ጠገዴ አማሮች የተከፈተባቸው ጥቃት ሁለንተናዊና ከብዙ አቅጣጫ ነው። የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊና የሥነ ልቦናዊ ጦርነት ሰላባ ናቸው። በመንግሥት መሥሪያ ቤት ቅድሚያ የሚሰጥ ከመሐል አገር ለሚመጣ የትግራይ ተወላጅ ነው። የወልቃይት ልጆች ትምህርት በአማርኛ መማር አይችሉም፤ ትምህርት ቤት ውስጥ በአማርኛ ቋንቋ ማውራትም አይችሉም። ክልክል ነው። ሕወሓት በዚያ አካባቢ መንቀሳቀስ ከጀመረበት ጊዜ አንሰቶ ከሰላሳ በላይ ለሚሆኑ ዓመታት የኢትዮጵያም ሆነ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ያላወቅ ብዙ በደል ደርሷል። አያሌ የወልቃይት ተወላጆች ተገድለዋል፤ ተሰደዋል። ቁጥራቸውን የማናውቀው ልጆቻችን የት እንደወደቁ ሳይታወቅ ደብዛቸው ጠፍቷል።

የሕወሓቶች ግፍ ወልቃይት ጠገዴ አማሮች የተፈጥሮ ስሜታቸውን እንኳ በወዱ እንዳይገልጹ ነው የሚያስገድዷቸው። የዳንሻ ከተማ ከንቲቫ ሕዝቡን ሰብስቦ ‹‹ልጆቻችሁ ስለምን አማርኛ ያወራሉ!›› በማለት በአደባባይ ሕዝቡን ማስፈራራቱ የአደባባይ ሚስጥር ነው። አማርኛ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች ‹‹የኢሕአፓ ቅሪቶች›› በመባል ይታወቃሉ። አማርኛ የሚናገሩ ሰዎች ምንም ዓይነት መብት የላቸውም። የሕግ አካላት የአማራ ተወላጆችን አያስተናግዱም። የወልቃይት ተወላጆች ከትግራይ ብሔረሰብ አባላት ጋር ተጋጭተው ወይም ሌላ በደል ደርሶባቸው ለሚመለከተው የፍትሕ አካል ቢያመለክቱ የፍትሕ አካሉ ለትግራዩ እንደሚያዳላ ማንም ያውቃል። የተለመደ ነው።

ትግርኛ በአግባቡ ባለመናገራቸው በደል የሚደርስባቸው የወልቃይት አማሮች ብዙ ናቸው። ለናሙና አንድ እናንሳ። የአካባቢው ሕዝብ ባህሉም ሥነ ልቦናውም ምርጫው አማራነት ነው። ሕዝቡ ለትግራይና ኤርትራ ቅርብ በመሆኑ እንደሌሎች በአዋሳኝ አካባቢዎች እንደሚኖሩ ሕዝቦች የተለያየ ቋንቋ ይናገራል። የዚህ ዓይነት ሁኔታ በየትም አካባቢ ያለና ተፈጥሯዊ ነገር ነው። የድሬዳዋ ሕዝብ ከአማርኛ ሌላ ሶማሊኛም ኦሮምኛም እንደሚናገር ይታወቃል። ኢትዮጵያውያን በሌሎች የአገራችን ጥአካባቢዎችም እንዲሁ ነው። የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብም ከአማርኛ ሌላ ትግርኛ ይናገራል። ዐረብኛ ቋንቋ የሚናገሩም ብዙዎች ናቸው። ሕዝቡ ትግርኛ ይናገር እንጂ የአካባቢው ትግርኛ የተለየ ነው። ወደ አማርኛ በእጅጉ ይቀርባል። የትግራይ ብሔረሰብ አባላት ይህን በሚገባ ያውቃሉ። በዚህ ምክንያትም ብዙ በደል አለ። ትምህርት ቤት ሞክሼ የአማርኛ ፊደላትን የሚጽፉ ተማሪዎች ካሉ በጣም ይወገዛሉ። ለምሳሌ ኀ፣ ሠና ፀ የአማርኛ ፊደላት ናቸው ተብለው ስለሚታሰቡ መምህራን ለፊደላቱ ያላቸው ጥላቻ የበዛ ነው። እንደሚታወቀው ጉራጌ ዞን ውስጥ ለምሳሌ ለኦሮሚያ ክልል ቅርብ በሆነው ሶዶ ወረዳ ውስጥ ብዙዎች ኦሮምኛ ቋንቋ ይችላሉ። ኦሮምኛ ስለሚናገሩ ኦሮሞ ናቸው በሚል ወደኦሮሚያ ክልል ለመጠቅለል ጥረት ቢደረግም ሕዝቡ ማንነቱን አሳልፎ አልሰጠም።

መታወቅ ያለበት የብሔረሰቦች መብት ተከብሯል እየተባለ ድቢ በሚመታበት ዘመን የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ያለታሪኩና ፍላጎቱ ወደትግራይ ክልል እንዲጠቃለል የተደረገው በሕወሓት ውሳኔ በመሣሪያ አፈሙዝ ነው። ሕዝቡ ፈጽሞ አልተጠየቀም፤ ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድልም አልተሰጠውም። አካባቢው በትግራይ ክልል ሥር እንዲሆን ከተወሰነ ጀምሮ የመብት ጥያቄ የሚያነሱ ልጆቻችንን ስንቀብር ኖረናል። ጥያቄው ወደፊት እንዳይቀርብና ለአንዴና ፋይሉን ለመጨረሻ ጊዜ ለመዝጋት ሲባል በሺህዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆችን በአያት ቅድመ አያቶቻችን ርስት ላይ በማስፈር የትግራይን የበላይነት ለመፍጠር ያልተሞከረ ነገር የለም። የሕዝባችን በደል ድርብ ድርብርብ ነው የምንልበት ምክንያት በደሉ በባለመሣሪያው ሕወሓት የሚፈጸም በመሆኑ እንደሌሎች ሕዝቦች ጥያቄ በኢትዮጵያ ሕዝብና በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ እስካሁን ጎልቶ ባለመውጣቱ ነው። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የተሻለ ሁኔታ ቢኖርም ከደረሰብን በደል ጋር ስናወዳድረው በጣም የሚያሳዝን ነው።

የሱዳን መንግሥት ለኢትዮጵያ የአጥንት ቲቢ ነው!

የሱዳን መንግሥት እኮ ለአገራችን የአጥንት ቲቪ ነው። የሱዳን መንግሥት የወልቃይትን አማሮች ከሕወሓት ጋር እንዴት አድርገው እንደፈጇው በሚገባ እናውቃለን። ከ1972 ጀምሮ ሕወሓቶች አስቀድመው የሚያጠና ሰው ይልካሉ። ሰላይ መሆኑ ነው። አስቀድመው የሚመጡት ሰላዮች በራሱ መተማመን ያለውንና ቆይቶም ለሕወሓቶች ተቃውሞ ያነሳል የሚሉትን ወጣት በስም ዝርዝር ይልካል። ሕወሓቶች ለሱዳኖች ይናገራሉ። ሱዳኖች መኪና ይዘው ይገባሉ። ወጣቶቹን ይይዙና ወደ ግዛታቸው ይወስዷዋል። ‹‹ዛሬ እከሌ ጠፋ! ዛሬ እከሌ በሱዳኖች ተወሰደ!›› ሁልጊዜም የሚሰማ እሮሮ ነው። ይህ እሮሮ በሕወሓቶች የሽፍትነት ዘመን ብቻም ያቆመ አይደለም። እስካሁን ድረስ የቀጠለ ደረቅ ሐቅ እንጂ። ሱዳን ድንበር ከገቡ በኋላ በጥይት ተደብድበው ይገደላሉ። ትልልቅ ከተማዎች አደባባይ ላይ ይሰቀላሉ። ከተማ አደባባይ ላይ የሚሰቀሉትን በተመለከተ ሱዳኖቹ የሚሉት ‹‹ሐበሻ ራሱን አጠፋ›› ነው። ሕወሓቶች ራሳቸው የወልቃይት አማራ ወጣቶችን ጉድጓድ እንዲቆፍር ካደረጉ በኋላ በቆፈሩት ጉድጓድ ይቀብሯቸዋል። ‹‹የትግሬ እናት ሐዘን ተቀምጣ አንተ ጠግበህ ትበላለህ?›› በማለት ውኃ በቀጠነ ይገድሏቸዋል።

ሕወሓቶች እንዲህ ይላሉ። መሬቱ እንጂ ሕዝቡ አያስፈልገንም። የሱዳን ዜጎች ድንበር አካባቢ የሚያገኟቸውን ኢትዮጵያውያን ሳይጠይቁ የማያልፉት ነገር አለ። ይኸውም ‹‹አማራ ነህ ትግሬ!›› የሚል ነው። ለሱዳኖች ሰው ማለት ትግሬ ነው። አማራ የሱዳን ጠላት አድርገው ይቆጥሩታል። የሱዳን ደህንነቶች የፈለጉትን የወልቃይት ተወላጅ በፈለጉት ጊዜ መጥተው መውሰድ ይችላሉ። የህወሓትም ደህንነቶች እንዲሁ። የወልቃይት ተወላጆች ወደ ሱዳንም ቢገቡ እዚህ ቢቀመጡ ያው ነው። የወልቃይት ተወላጆችን ግፍ ሊያስረዳ የሚችል አንድ ምሳሌ እንጥቀስ። ቄስ ተገን እንየው የሚባል ካርቱም እስጢፋኖስ የሚያገለግል የወልቃይት አማራ አለ። ቄስ ተገን በቤተ ክህነት ትምህርት ከዚህ ቀረህ የማይባል ምሁር ነው። በግዕዝ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ በዐረብኛ ደግሞ ከግብጥ ኮፕቲክ ቤተ ክርስቲያኖች ይቀድሳል። ቄስ ተገን ያለውን ለአገሩ ልጆች አካፍሎ ይበላል። ሕወሓቶች ቄስ መስፍን አገር ውስጥ ላሉ ለሚማሩ ልጆች ገንዘብ እንደሚረዳ ደረሰቡት። ለተቸገረ ገንዘብ መለገስ የሚያስመሰግን እንጅ የሚያስወቅስ ሆኖ አልነበረም። ባለፈው መጋቢት ወር 2007 ዓ.ም. ካርቱም የተላከ የወያኔ ደህንነት ይዞት መጣ። ማዕከላዊ እስከ ጥቅምት 2008 ዓ.ም. ከማንም ከምንም ጋር ሳይገናኝ ጨለማ ቤት አቆይተው ‹‹ለማንም እንዳትናገር›› ብለው ለቀቁት። ቄስ ተገን ምንም አማራጭ ስላልነበረው አሁን ወደ ካርቱም ተመልሷል።

የወልቃይት ልጃገረዶች በትምህርት ቤት የሚደርስባቸው አበሳም ከፍተኛ ነው። ሐሙስ ሐሙስ ሴት ተማሪዎች የመምህራንን መኖሪያ ያጸዳሉ የሚባል ያልተጻፈ ሕግ ነበር። ገና ለአቅመ ሔዋን ያልደረሱ ሕፃናት የመምህራኖቻቸውን ቤት ለማጽዳት በተራ ሁልጊዜ ሐሙስ ‹እነ ጋሽዬ› ቤት ይሄዳሉ። ሕፃናቱ በመምህራኖቻቸው ይደፈራሉ። ያረግዛሉ ይወልዳሉ። በሕግ ሊያገቡ የታጩ ልጃገረዶች ሁሉ እየተደፈሩ ያገባሉ። ምክንያቱ ደግሞ አማሮችን ትግራዊ ለማድረግ ብቻ ነው።

የወልቃይት አባቶች ተጨነቁ። ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት ላለመላክ ወሰኑ። በዚህ ጊዜ ደግሞ ለትምህርት የደረሰ ልጁን እቤት ያስቀመጠ ሰው ይቀጣል የሚል ሕግ መጣባቸው። ወላጆች አሁን ሌላ አማራጭ ፈለጉ። ‹በመምህራን› ልጆቻቸው ከመደፈራቸው በፊት በልጅነታቸው መዳር። መጨነቅ ነው። ይህም ሌላ ጣጣ አስከተለ። በሴቶችና ሕፀናት ጉዳይ ‹‹ያለ ዕድሜ ጋብቻ›› በሚል ክስ ይመሰረትባቸዋል። ያለ ዕድሜያቸው በሚደፍሯቸው መምህራን ላይ ግን ማንም ምንም አይልም። ይህ ሁሉ ችግር የሚደራረብባቸው ወልቃይቴዎች ያላቸው አማራጭ ሁለት ብቻ ነው። አንደኛው ልጆቻቸውን ወደ ጎንደርና ሌሎች አካባቢዎች ወስዶ ማስተማር ሲሆን ሁለተኛው ግን የመምህሮቹን ‹‹ዲቃላ›› ማሳደግ።

መታወቅ ያለበት አንድ መሠረታዊ ነገር አለ። የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ጥያቄ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ አይደለም። ይህ ማለት ሕዝቡ የመልካም አስተዳደር ችግር የለበትም ማለት አይደለም። በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች እንደሚታየው በእኛ አካባቢም የመልካም አስተዳደር ችግረ አለ። የእኛ ዐቢይ እና የሕወሓት ሰዎች የቱንም ያህል ቢገድሉንና ቢያሳድዱን የማንተኛለት፤ እኛ መፈጸም ባንችል ጉዳዩን ለልጅ ልጆቻችን የምናወርሰው ጥያቄ የማንነታችን ጉዳይ ነው። አማሮች ነን። ትግራይ አይደለንም። የደረሰብንና እየደረሰብን ያለውን ያልተነገረለት በደል ኢትዮጵያውያንና የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እንዲገነዘብልን እንፈልጋለን።

The post የወልቃይት ጠገዴ መሬቱን እንጂ…! | ሳምሶን ኃይሌ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
↧

የትህዴን ወታደሮች በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ዙሪያ ያደረጉት ውይይት |“ኢሕአዴጎች አታላዮች ናቸው…አትመኗቸው”– Video

$
0
0


የትህዴን ወታደሮች በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ዙሪያ ያደረጉት ውይይት | “ኢሕአዴጎች አታላዮች ናቸው… አትመኗቸው” – የትህዴን ወታደሮች በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ዙሪያ ያደረጉት ውይይት | “ስርዓቱ ካልተወገደ ችግር አይጠፋም” – Video

The post የትህዴን ወታደሮች በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ዙሪያ ያደረጉት ውይይት | “ኢሕአዴጎች አታላዮች ናቸው… አትመኗቸው” – Video appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

በላስቬጋስ ከ8 ወር በላይ ራሷን ሳታውቅ የቆየችው ኢትዮጵያዊቷ ወጣት ኤደን ኃይሉ አረፈች |ቤተሰብ የህክምና ስህተት ተፈጽሟል ባይ ነው

$
0
0

eden hailu
(አድማስ ራድዮ) ኤደን ቬጋስ ለትምህርት ከመሄዷ በፊት የአትላንታ ነዋሪ ነበሬች።

የአትላንታና የቬጋስ ነዋሪ የነበረችው 20 ዓመቷ ወጣት ኤደን ሃይሉ ያረፈችው ትናንት ጃንዋሪ 4 /2016 ነው። ኤደን ኃይሉ ከስምንት ወራት በፊት በአንድ የቬጋስ ሆስፒታል ለሆድ ህመም የገባችው ኤደን ከዚያ ወዲህ ከሆስፒታሉ አልወጣችም። ቤተሰብ ለአድማስ ሬዲዮ እንደገለጸው ፣ ሆዷ አካባቢ የሚሰማትን ህመም ለመታየት ገብታ ሳለ፣ ሃኪሞች በምርመራ ወቅት የሰጧትን ግሉኮስ ሰውነቷ መቀበል ስላቃተው፣ ዶክተሩ ቀዶ ጥገና በማድረግ ምክንያቱን ለማወቅ ይወስናል፣ ከዚያ በኋላ ግን የተፈጠረው ሳይታወቅ፣ ሙሉ በሙሉ አዕምሮዋ መስራቱን በማቆሙ ህይወቷ ባያልፍም፣ አካሏ ግን በድን እንደሆነ 8 ወር ያህል ቆይታለች።

ሃኪሞች አትተርፍም እና ፈርማችሁ ህይወቷ እንዲያልፍ አድርጉ ቢሉም፣ ቤተሰብ ምን እንደተደረገችና እንዴት ይህ ቀላል ሰርጀሪ ለዚህ ሊዳርጋት በቃ የሚለውን ሳናውቅ ህይወቷን ያቆየውን ቱቦ እንዲነቀል አናደርግም በማለት ሲከራከሩ ቆይተዋል። ሆስፒታሉም በህጉ መሰረት የህክምና ዝርዝር የምንሰጠው ፣ “በሽተኛው ህክምናውን ጨርሶ ሲወጣ ” በመሆኑ ፣ መስጠት አንችልም በማለቱ ለዚህ ሁሉ ወራት የህክምናው ዝርዝር መረጃ ሳይወጣ ቆይቷል። ቤተሰብ የህክምና ስህተት ተፈጽሟል ባይ ነው።

The post በላስቬጋስ ከ8 ወር በላይ ራሷን ሳታውቅ የቆየችው ኢትዮጵያዊቷ ወጣት ኤደን ኃይሉ አረፈች | ቤተሰብ የህክምና ስህተት ተፈጽሟል ባይ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

Sport: ትውልደ ኢትዮጵያዊው ታዳጊ ወጣት ለባርሴሎና ክለብ ፈረመ

$
0
0

anwar madera

[በተሻገር ጣሰው]

አንዋር ማዴራ ይባላል በፈርነጆቹ አቆጣጠር ማርች 2003 ላይ ነበር በመዲናችን አዲስ አበባ የተወለደው ::
ገና ታዳጊ ህፃን እያለ በማደጎ ወደ ስፔን ተጎዘ በስፔን ቆይታውም ገና ከህፃንነቱ ጀምሮ ለእግር ኳስ ልዩ ፍቅር በመኖሩ ከኢትዮጵያ ወስደው የሚያሳድጉት ቤተሰቦቹ ፍላጎቱን ለማሞላት ወደ እግር ኳስ አካዳሚ አስገቡት ::ልክ አስራ አንድ አመቱ ሲሆነው ከአስራ ስድስት አመት በታች ሴልታ ቪጎን ክለብ ተቀላቅሎ መጫወት ጀመረ::

አንዋር አሁን አስራ ሶስት አመቱ ነው:: ከወደ ስፔን የተሰማው ዜና እንደሚያስረዳው በትውልድ ኢትዮጵያዊው የሆነው አንዋር ማዴራ የባርሴሎና ክለብ የበላይ ጠባቂዎችን በአጨዋወት ጥበብ በመማረኩ የተነሳ ሴልታ ቪጎን ክለብ ለቆ ከ16 አመት በታች ለባርሴሎና ክለብ እንዲጫወት ማስፈረማቸውን ነው የተዘገበው::

ተጫዋቹ በያዝነው በፈረንጆቹ አዲስ አመት ጨዋታውን እንደሚጀምርና ከ3 አመት በሆላ ለዋናው ባርሴሎና ክለብ መጫወት እንደሚፈልግ ምኞቱን ተናግሯል::

ለትውልደ ኢትዮጵያዊው አንዋር ማዴራ ያሰበው እንዲሳካለት መልካም ምኞታችን ነው

The post Sport: ትውልደ ኢትዮጵያዊው ታዳጊ ወጣት ለባርሴሎና ክለብ ፈረመ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

በአወዳይ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው ወጡ |ወታደሮች ትምህርት ቤታቸውን ለቀው ካልወጡ አንመለስም ብለዋል

$
0
0

Zehabesha News
(ዘ-ሐበሻ) የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ተከትሎ የተነሳውና ጋብ ብሎ የነበረው የተማሪዎች ቁጣ እያየለ መጥቶ ዛሬ በምስራቅ ሐረርጌ በምትገኘው አወዳይ ከተማ የሚገኙ ተማሪዎች ቁጣቸውን በመግለጽ ትምህርት ቤታቸውን ለቀው መሄዳቸው ተሰማ::
በአወዳይ ከተማ ከኢለመንተሪ እስከ ፕሪፓራቶሪ ደረጃ ተማሪ የሆኑ ወጣቶች ለትምህርት ቤታቸው አስተዳደር “ወታደሮች ግቢያችንን ለቀው ካልወጡ…. ተማሪዎችን ማሰር እና መፍታታቸውን እስካላቆሙ ድረስ እንዲሁም ወገኖቻችንን የገደሉ ወታደሮች ለፍርድ ካልቀረቡ በስስተቀር ወደ ትምህርት አንመለስም” በሚል ጊቢያቸውን ለቀው ወደየመጡበት ሄደዋል::
በምስራቅ ሐረርጌ እና በም ዕራብ ሐረርጌ የሕዝቡ ቁጣ በከፍተኛ ሁኔታ ቀጥሏል::

The post በአወዳይ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው ወጡ | ወታደሮች ትምህርት ቤታቸውን ለቀው ካልወጡ አንመለስም ብለዋል appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
↧

በሚኒሶታ የሚገኘው ቅዱስ ዑራኤል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በኦሮሚያና በጎንደር ለተገደሉት ወገኖች የጸሎት እና የሻማ ማብራት ጥሪ አቀረበ

$
0
0

st Paul

በሚኒሶታ አካባቢ ለምትገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሙሉ።
በቅርቡ በሀገራችን ኢትዮጵያ:-
1ኛ/ በኦሮሚያ ክልል ድንጋይ ሳይጨብጡ ዱላ ሳይዙ መሳሪያ ሳያነሱ ሰላማዊ ጥያቄ ያቀረቡ ወገኖቻችን አረመኔው ወያኔ በሰራዊቱ ያለርህራሄ በወሰደው የማስጨፍጨፍ እርምጃ የብዙ ንጹሃን ዜጎቻችን ደም ያላግባብ ፈሷል፤ አሁንም ግፍና ጭፍጨፋው እንደቀጠለ ነው።
2ኛ/ በጎንደር እራሱ ወያኔ በተለመደ የማበጣበጥ ተንኮሉ ቅማንትና አማራ በሚል የመለያያ ተንኮል በቆሰቆሰው ግጭት እንዲሁ የብዙ ንጹሃን ወገኖቻችን ደም በከንቱ ፈሷል። ብዙ ሰላማዊ ሕዝብም ከመኖሪያው እየተፈናቀለ ይገኛል።
የደብረ ብርሃን ቅዱስ ኡራኤል የኢት/ኦ/ተ ቤተ ክርስቲያን ይህን በማስመልከት SATURDAY፤JANUARY 9TH 2016 ከ5:00PM እስከ 7፡0 PM በግፍ ደማቸው ለፈሰሰው ወገኖቻችን በጸሎተ ፍትሀት ለማሰብና የሻማ ማብራት ስርዓት ስለምናደርግ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በሰዓቱ በመገኘት እንዲሳተፉና የሟች ወገኖቻችን ቤተሰቦች አብረን በአንድ ላይ እንድናጽናና ተጋብዛችሗል።
ሲመጡ ሻማ መያዘወትን እንዳይዘነጉ።
አድራሻ፡ 1144 EARL STREET, SAINT PAUL, MN 55106

The post በሚኒሶታ የሚገኘው ቅዱስ ዑራኤል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በኦሮሚያና በጎንደር ለተገደሉት ወገኖች የጸሎት እና የሻማ ማብራት ጥሪ አቀረበ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ለዓለም የጤና ድርጅት መሪነት ሊወዳደሩ መሆኑ ተሰማ

$
0
0

Tewodros Adhanom
(ዘ-ሐበሻ) ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በስልጣን ላይ እያሉ “ትኩስ ኃይል” በሚል ያሞኳቸው የነበሩትና ዛሬ ሕወሓት የሚመራው መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ለዓለም የጤና ድርጅት መሪነት ሊወዳደሩ መሆኑ ተሰማ::

ምንጮች እንደሚሉት በአንድ ወቅት የጠቅላይ ሚኒስተሩን ቦታ ይይዛሉ ተብለው በሰፊው ሲወራላቸው ቆይተው ከጫካ በመጡት ታጋዮች የተገፉት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የውጭ ጉዳይ ሚንስተርነት ሥራቸውን ለቀው ለአለም የጤና ድርጅት መሪነት ሊወዳደሩ እንቅስቃሴ ጀምረዋል::

በቅርቡ ወደ ጀኔቫ ይሄዳሉ ተብሎ የሚነገርላቸው ዶ/ር ቴዎድሮስ በዚያውም የምረጡኝ ቅስቀሳ ያደርጋሉ እየተባለ ነው::

ቴዎድሮስ አድሃኖም የውጭ ጉዳይ ሚኒስተርነቱን ቦታ ትተው ለዓለም ጤና ድርጅት መሪነት ለመወዳደር የወሰኑት በአዲስ አበባውና በመቀሌው የሕወሓት ቡድኖች መካከል በተፈጠረው ልዩነት በከፍተኛ ሁኔታ ከተበሳጩ በኋላ ነው የሚሉት ምንጮች በተለይ ጠቅላይ ሚኒስተር ለመሆን ያላቸው ፍላጎት ከተሰናከለ በኋላ በተደጋጋሚ ይሄን ስልጣን መልቀቅ እንደሚፈልጉና በሥራው እንደተሰላቹ እንደሚናገሩ የቅርብ ምንጮች ይናገራሉ::

 

ቴዎድሮስ  በሕወሓት ታሪክ በትጥቅ ትግሉ ሳይሳተፉ ወይም በረሃ ሳይወርዱ ወደ ፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ እንዲገቡ የተደረጉ እሳቸው ብቻ መሆናቸው ይነገራል። ቴዎድሮስ አድኻኖም ገብረየሱስ በ1986 ከአስመራ ዩኒቨስቲ በባዮሎጂ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን እንዳገኙ ሲገለጽ በተለያዩ የጤና ትምህርቶች ከሁለት የእንግሊዝ ዩኒቨስርቲዎች ከፍተኛ ዲግሪዎቻቸውን ማግኘታቸውን የህይወት ታሪካቸው ያስረዳል። ኢህአዴግ ከተሸነፈበት የምርጫ 97 በኋላ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሆነው እስኪሾሙ ድረስ ሚኒስቴሩን በረዳትነት ሲመሩ ቆይተዋል።

The post የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ለዓለም የጤና ድርጅት መሪነት ሊወዳደሩ መሆኑ ተሰማ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

ጉዞ ወደ ዘመነ መሳፍንት |በልጅግ ዓሊ

$
0
0

 “ተው ልጓሙን ያዘው ፡ ቀዳማ¹ ለቀህ፣

 በሁዋላ እንዳይከፋ ፡ አወዳደቅህ።”

የሕዝብ ግጥም

የፈረንጆቹም ዓመትም ባተ ። አሮጌው በአዲስ ተቀየረ ። እኛ ግን “ወይፍንክች ያባ ቢላዋ ልጅ” እንደተለመደው እኛው ነን። የሚገርመው ነገር የሸሚዛችን ቅድ እንኳ አልተቀየረም። ወያኔን ከማውገዝ ያለፈ ፋይዳ ያልው ሥራ አልሠራንም፦   1991  . . .   1992 . . .  1993 . . .  2015  . . .  2016  . . . . እያልን ዓመታት እንደቆጠርን እዚህ ደረስን። … መድረሻ የሌለው ተሰፋ ሰንቀን፣ ውል የሌለው የትግል ስልት ነድፈን፣ ቋት የማይሞላ ፖለቲካ ገርድፈን፣ ወንዝ የማይሻገር እጅና እግር ይዘን፣  እልባት የሌለው ጥላቻ እያጃጃለን አለናት! አለን!

የሃገሬ ገበሬ በደርግ ዘመን በደረስውን ድርቅ ተማሮ በግጥም እንዲ ብሎ ነበር ።

ይህንን 77 እሰሩት በገመድ ፤

ወደ 78 እንዳይረማመድ።

አንዳንድ ዓመቶች ወደሚቀጥለው ዓመት ባይሸጋገሩ ፣ እንደቆሙ ቢቀሩ እንዴት ደስ ይላል።

2015 መጥፎ ወይስ ጥሩ ነበር እንበል ? ለነገሩ  ሁለቱም  ነበር ማለት ይቻለል። ብዙ አውርተን፣ ብዙ ተስፋ አንግበን፣ ሳንጠግብ ተስፋችን ጠውልጎ፤ ብዙ  አስተዛዝቦን አልፏል “ተዛዚብና” እንዲል ያገር ሰው ። ለማንኛውም እንኳን ለፈረንጆቹ አዲስ ዓመት አደረሰን! በእኛም በእነርሱም ብንቆጥረው እኛ’ እኛው ነን ። የሚለውጠን ነገር ይኖር ብላችሁ ?

ያለፈን ወቃሽ አያድርገንና 2015 በእውነትም መጥፎ ነበር ። 30 ዜጎቻችንን ሊቢያ ላይ ገብረናል ። በዚያም እጅግ አዝነናል ፣ አልቅሰናል ፣ አንብተናል ፣ ዝክራቸውን ረስተናል ። እነርሱ ሳይሆኑ እኛ የቁም ሙቶች እንደሆንን አስመስክረናል ። ደግሞም ተመልሰን ልማታዊ ቱሪስቶች ሆነናል።  አቦ! እኛ’ እኛ ነን ! ያኔ! ማለዳ በዘመን መለወጫ የቀመስነው ፌጦ አለት ድንጋይ ላይ ቆመን ነው መሰል፣ ዓመታት እያስወነጨፈ ይሰዳል እንጅ እኛ ምን በወጣን የምንቀየር? ይኸው ራሳችንን ”አስከብረን” እየኖርን ነው። እነዚያን ምስኪኖች ወዲያው ረስተን ወያኔ በጠራው  የዲያስፖራ ስብስባ ከወያኔ ጋር  አሸሼ ገዳሜ ስንል ፣ ዳንኪራ ስንረግጥ ከርመን ተመልሰን የለ ።  ወያኔ ደሃውን እያፈናቀለ መሬት ለእኛ እንዲሰጠን ለምነናል ። መሬት ላራሹን አውግዘን ፣ መሬት ለመራሹ! ብለናል። ይህ ታላቁ 2015 ድላችን ነው ብንለውስ? ያንስበት ይሆን?

ወያኔማ እንዳለው ረዥም መንገድ መጥቶ ይኸው እየተቀበለን አይደል እንዴ? ቀጣዩ ማን እንደሆነ ባናውቅም የመን ድረስ ሄዶ አንዳርጋቸው ፅጌን አንከብክቦ ተቀብሎ የለ። በዚያ ሰሞን እኔም አንዳርጋቸው ነኝ ብለን በፌስ ቡክና በመግለጫ አንደኛ ሆነን ነበር ። ትንሽ ቆይተን ያው

¹ ቀዳማ – የኮርቻ ቀዳማ – በፊት የሚገኝ – እንቢአጉስ የሚገባበት ።

እንዳመላችን ረሳነው ። እንኳን አንድ ሰው የወያኔ ሰለባ ይሆኑ ብዙ መቶዎችን፣ ብዙ ሽዎችን እረስተን የለ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ረሃብተኞችን እንደረሳነው ዓይነት፣ . . .  ሌሎች ብዙ ብዙ ነገሮችን እንደምንረሳው ዓይነት፣ 2015 ሳያልቅ የፖለቲካ እስረኞችን ጉዳይ እርግፍ አድርገን ከተውን ሰነበት እኮ ።

እኛ አንዱን መጨበጥ ፣ የጨበጥነውን መልቀቅ የለመደብን የዘመን ፖለቲከኞች መሆናችን አይደል ትልቅነታችን ። በኤርትራ በኩል መሄዱ ያዋጣል አያዋጣም ክርክሩስ ቢሆን እንደው አንድ ሰሞን! አንድ ሰሞን! አዘፍኖን ነበር እኮ ። የመረጃዋች ጋጋታ፣ እሰጥ አገባው እንቅልፍ አሳጥቶን ነበር ። እሱም አሁን ፋሽኖ አልፎበታል መሰል ፣ ሮጠው የሄዱት ሮጠው ሲመለሱ እየታየ ነው ። ችግር የለም እኛ ፣ እኛ ነን።

በዚህ ሁሉ እኔ የዓመቱ ታላቅ ቀልድ ብዬ የወሰድኩት የካሳ ከበደን ቀልድን ነው።   ባለፈው ቪዥን ኢትዮጵያና ኢሳት ባዘጋጁት የውይይት መድረክ ላይ “ ኢሳያስ አፈወርቂ ለኢትዮጵያ አንድነት ይታገላል “ ያሉት። እንዴት ደስ የሚል የዓመቱ ታላቅ አባባል ነው። በሻዕብያ አንቀልባ የኢትዮጵያ አንድነት ሲጠበቅ ! ደስ አይልም! … ያውም ተስፋዬ ገብረ እባብ (የኢሳያስ አፍወርቂ የኢትዮጵያ ጉዳይ አማካሪ) ልቡ ራርቶልን ለኢትዮጵያ አንድነት ሲያስብ ታየኝ! በተለይም አማራ ለሚባለው የህብረተ-ሰብ ክፍል ። … እውነት እውነት እላችኋለሁ ተስፋዬና ጓደኞቹ ቢችሉ ቆዳችንን ገፈው በቁም ስጋችንን ቢቸበችቡት ምንኛ ደስ ባላቸው። … “ እባበ ሲወድም ሲጠላም በሰው ላይ ይጠመጠማል ” እንዲሉ።

ድሮም ካሳ ከበደ ተጫዋች ናቸው።  ወያኔ ሲገባ በበሽተኛ ወሳንሳ ሆነው ነው ከፈላሻዎች ጋር ከአዲስ አበባ የፈለሱት ። ከዚህ የበለጠ ምን ቀልድ አለ ? የኢሠፓው ማዕከላዊ ኮሚቴ አባሉ ግንባራቸው ላይ የቤተ እሥራኤሎች ታርጋ ተለጠፎላቸው ታሪክ የሰሩ ሰው ናቸው ። … እንዴት ይረሳል? …  እንማ እንዴ! እንማ …?

መቼም ካሳ የምራቸውን ከሆነና እኛም ካመንን በኤርትራ የተሰዋው የኢትዮዮጵያ ሠራዊት አጥንት ይወጋናል ። ይህን ሊያምንም የሚችል በነዋይ ሃገሩን የሚቸበችብ ብቻ ነው ። ከዛ ውጭ ማንም አያምንም ። የዓመቱ ቀልድ ብለን እንለፈው ። … እኛ ብናልፈውስ 2015 እንደገና“መሰባሰብ“የጀመረው የኢሠፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ይህን ቀልድ ያምናል? ምን ይታወቃል የሚገኘው ነዋይ አዕምሮን መሸበብ ከቻለ  ለይሉኝታ ደግሞ መከላከያ ጭንብል አይጠፋለትም።

2015 እውነትም ጥሩ ነበር ። ለሃያ ከምናምን ዓመታት ዋሽንግቶን ዲሲን ያማከለው ትግላችን ወደ ሃገራችን ጠጋ ብሏል። ይክፋም ይልማም አሥመራ ደርሷል። ከ24 ዓመታት በኋላ አሥመራ በመድረሱ ድልን አውጀናል፣ በሳምንት ፣በወር አዲስ አበባ የሚደርስ መስሎን ነበር ። አለመሆኑን ስናውቅ ቀኝ ኋላ ዙር ያልን አለን። ምን ችግር አለ ሌላ ጥሩ ልብ ወለድ ታሪክ መጻፍ ነው ። የሚያስለቅስ ፣ የሚያዝናና ። መቸም “ ጡትና መንግሥት ጊዜውን ጠብቆ መውደቁ አይቀር “ ምን ጣጣ አለው።  ዛር እንደቆመ ነው መቆመር!!!

2015 መልካም ምግባር የነበራቸው ሰዎችም ይዞ ሄዷል ። ሙሉጌታ ሉሌ ፣ ዘውዴ ረታ ፣ አስማማው ኃይሉ (አያ ሻውል) . . . ሌሎችም ። አሁንስ እንኳን ተገላገሉ ያስብላል ። ዩኒቨርስቲ በዘር ተከፋፍሎ ግማሹ ሲያምጽ፣ ግማሹ ሲማር ከሚያዩ ፣ ምሁር እንዲህ ሲዘግጥ ከሚታዘቡ፣  እኛ በክልል ተገዝተን፣ በክልል ነገሮች ስንተነትን ከሚመለከቱ፣ ትላንት ለኢትዮጵያ አንድነት የሚሉ ዛሬ ለክልል መጠናከር ሲያሸረግዱ ከማየት መገላገል ሳይሻል አይቀርም ። ከዚህ የደም ግፊትን፣ ስኳር … ገለመሌ ከሚያባብስ ንዴት ፣ በጊዜ ማለፉ መልካም ነው።

በ2015 ስንት አሪፍ አሪፍ መጽሐፎች ለንባብ በቅተዋል  ። የፍስሐ ደስታ ቀዳሚውን ቦታ ይዟል ። ፍሰሐ ደስታ አራዳ ናቸው ። የዘመኑ ምሁሮቻችን መጽሐፍ እንደማያነቡና ከሽፋኑ እንደማያልፉ የተረዱና የገባቸው የደርግ አባል ሆነው አግኘቻቸዋለሁ። በመጽሐፉ ውስጥ ሙልጭ አድርገው የሚሰድቡትን ሕዝብ በሽፋኑ ላይ የይስሙላ ይቅርታ ይጠይቃሉ ። አቤት ያድናቂው ብዛት ፣ አቤት የቃለ መጠይቁ ብዛት . . .  ። አንድ የኢሕአፓ መሪ ነኝ የሚሉ ግለስብ አልፈው ተርፈው “ሚዛን የደፋ” ብለውት ነበር ። ለመሆኑ በየትኛው ሚዛናቸው መዝነውት ይሆን ? የእኛ ምሁሮች ከሽፋን ባሻገር መጽሐፍ ገልበው እንደማያነቡ ጸሐይ አሳታሚ በውል የተረዳው ይመስለኛል ። ለማ በገበያ የአማርኛ መማሪያን ያላነበበው የወያኔ አሽቃባጭ ሰይፉ ፋንታሁን የሚባል እንኳን ሳይቀር ቃለ ምልልስ ከፍስሐ ደስታ ጋር አድርጎ ነበር ። መቸም አንዳንዱ መኖሩ ለማንም ካልጠቀመ መሞቱ ማንንም አይጎዳም።  ቪቫ ፍስሃ ደስታ በመጸሀፉ ሽፋን ላይ ይቅርታ መጀመሩ አንድ እርምጃ ነው። የሚሻለው ግን በእርስዎ ትዕዛዝ የተገደሉትን ንፁሃን በማሰብ ቄስ ፈልጎ ንስሃ መግባት ነው ። እዚህ ላይ ነበር ጥፋቴ ብሎ መጀመር ነው ታላቅነት። የጅምላ ይቅርታ ብዙም አያስኬድም።

2015 አሪፍ ነበር ። በተለይ መጨረሻው ላይ ። ዳግማዊ ታዕሳስ ግርግር ታይታ ነበር ። የመንግስቱ ነዋይን ታዕሳስ ግርግር ከዚህችኛዋ ታህሳስ ግርግር የሚያመሳስለው ብዙ ነገር ነው። ሁለቱም ብዙ ሊሰሩ የሚችሉ ኃይሎችን አሳጥተውናል ። የመንግሥቱ ነዋይ ግርግር ክቡር ዘበኛን ብቻ በመያዙና ሌሎች ክፍሎችን ባለማካተቱ ሲከሽፍ፣ የሰሞኑ ደግሞ ክልላዊ ስለነበር ውጤቱመ ያው ተከልሎ ቀረ።

በሌላ በኩል 2015 እንዴት የሚያሳዝን ዘመን ነው። ከአምቦ ዮንቨርሲቲ የኦሮሞ ተማሪዎች አመፁ። የእከሌ ዩንቨርስቲ ኦሮሞ ተማሪዎች ተነሱ! የሚለው ዜና በጣም የሚገርም ነው ። ሌሎቹስ ? አንድ የተሳሳተ ነገር አለ። ወያኔ በቀረጽው የክልል ክፍፍል መገዛት ራሱ ስህተት ነው። ይህ ነውአሳዛኙ የ2015 ክስተት ። ይህ ክስተት ጃዋርና ተስፋዬ ገብረ እባብ ትንቢታችን ተሳካ ፣ ኢትዮጵያ ፈረሰች ብለው ጮቤ እንዲረግጡ አድርጓል ። እኛም እኛ ነን፣ ከበሮቻንን ይዘን አብረን ደልቀናል። ምን ጣጣ አለው! “ዘሎ የወረደ ዋጋው ይቀንሳል” ዓይነት የወያላ ጨዋታ ተጫወትን አይደል።

እኛ 25 ዓመታት ታግለን ምንም አልተማርንም። አሁንም ከጠላቶቻችን ጋር አብረን እንጨፍራልን ። ከሕዝብ በሰበሰብነው ገንዘብ በከፈትነው የመገናኛ ዘዴ ለሕዝብ ጠላቶች መድረክ እንሰጣለን። እኛ እኛ ነን፣ ዓመት ቢቀያየር የማንቀየር ። ሃላፊነት የማይሰማን የሠለጠን ዘመናዊ መሪዎች፣ ፖለቲከኞች፣ አክቲቪስቶች፣ ታጋዮች ።… አቤት ስማችን መብዛቱ ፣ ተግባራችን መክሳቱ።

የዓመቱ ታላቅ ቃለመጠይቅ ሳይሆነ ይቀራል ብላቸሁ ነው? . . . መሳይ ለጃዋር በኢሳት ያቀረበው ። በጣም ያስቅም ያናድድም ነበር ። መሳይ ጥያቄው እየጠፋው በፍርሃት  ሲርበተበት ለተመለከተ ተጠያቂው ጥያቄውን ያወጣው ይመስላል። ። ጃዋር ግን ጥያቄውን ቀድሞ እንደተነገረው ሳይደነግጥ ፣ ሳይሸበር  ነበር የሚመልሰው ።  በእኔ በኩል የዓመቱ ታላቅ ቃለ መጠይቅ ብየዋለሁ ።

ለነገሩ መሳይ ደስ የሚል እሳት የላሰ የኢሳት ጋዜጠኛ ነው (ተከታታዩ ስልሆንኩ እንደማይቀየመኝ ተስፋ አለኝ)። መሳይ ለጃዋር ካቀረበው ጥያቄ መካከል “በእኔና በአንተ እድሜ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደዚህ ዓይነት እንቅስቃሴ ” ብሎ የሚጀምረው ጥያቄው ሌላ ጥያቄ አጫረብኝ ። ውድ መሳይ ለመሆኑ እድሜያችሁ ስንት ነው? የ97 ምርጫ ጊዜ ኩፍኝ አልወጣላችሁም ነበር ? አየህ መሳይ ጃዋር ስንዝሮ ፖለቲከኛ የሚባለው ለዚህ ነው። ሰኞ ተረገዝኩ፣ ማክሰኞ ተወለድኩ የሚለው ተረት ተረት ዓይነት። አንዳንዴ እድሜን በመልክ መገመት ይከብዳል። ውድ መሳይ ለኢንፎርሜሽን ያህል በ1997 ምርጫ ከዚህ የበለጠ እንቅስቃሴ ነበር ።

2015 ብዙ ነገሮችን ሳንረሳ ስላስታወሰን “ልናመሰግነው” ይገባል። ተስፋዬ ገብረ-እባብንና ጃዋርን ከሰመመናቸው ነቅተዋል፣ 56 ድርጅቶችን መኖራቸውን ሰምተናል ፣ የተለያዩ መግለጫዎችን ፣ አዳዲስ ስሞችን ፣ አዳዲስ ዓርማዎችን . . .ውዘተ አይተናል። የ56 ድርጅቶች መሪዎች ሱዳን ድንበር ላይ ሄደው ቢደረደሩ ኖሮ ስጋት ከቶ ባልገባን ነበር ። ድርጅቶቹ ግን “ለስሟ መጠሪያ ምን ሰፋች” እንደሚባለው ቢጤ እንዳይሆኑ ከወዲሁ አንድ ቢባል ጥሩ ነው።

ከአስር ሚሊዮን ሕዝብ በላይ በርሃብ አለንጋ እየተገረፈ ሳለ፣ በዚህ በታህሳሱ ግርግር ሰሞን ስለድርቁ ማውራት የተረሳ ነበር ። ይህ ወያኔን ሳይመቸው አልቀረም። ድርቁ የተረሳው የሰሞኑ ፖለቲካ ስላልሆነና ለሥልጣን ስለማያበቃ ይመስላል። በሌላ በኩል ስለድርቅ ማውራት እንደ አፍሮ ፣ እንደ ቤል ቦተም ሱሪ በፖለቲካው ፋሽን የተረሳ ነው። በልምድ እንደምናውቀው የራበው ሰው ይሞታል እንጂ በምን ጉልበቱ መንግሥት ላይ አምጾ ድንጋይ ይወረውራል! ከየትስ አምጥቶ ለፖለቲካ ድርጅቶች የኢኮኖሚ ተቋማት የማዳበሪያ እዳ ይከፍላል! ከየትስ አምጥቶ ገንዘብ ለመሪዎቹ ፌሽታ ያዋጣል ! እንደው ለታዘበው የአንድ ሳምንት ዜና የሆነው ድርቅ የጠፋ ነው የሚመስለው ። እነዚያ በረሃብ የሚሰቃዩ ዜጎቻችንን ምግብ ዘነበላቸው እንዴ ? “ጉድ ያለው ገንፎ አድሮ ይፋጃል” እንዲሉ መቼም ለታዕምር ነው የፈጠረን ። ድርጅቶችስ ምነው መግለጫቸው በረሃቡ ጉዳይ አነሰ ?  እኛ ካፒታሊዝምን ስለምንወድና ካፒታሊዝም ደግሞ ለደሃው ግድ ስለሌለው? አይ መከራችን መብዛቱ ። ምነው ሶሻሊስት ፣ ኮምኒስት ሆነን እንዳማረብን በሞትን ኖሮ።

2015 ደግ ዘመን ነው። ስማቸውን የረሳናቸው እነ መኢሶን እንኳን መግለጫ አወጡ። የመኢሶን አርማ መቀየሩ አሁን ነው ልብ ያልኩት። ማጭድና መዶሻው በአበባ ተቀይሯል ።  ሶሻሊስቶች ማጭድና መዶሻን ጣሉ እንዴ? ። ስለ ድርቁ መኢሶን መግለጫ ያላወጣው ማጭዱን ከአርማው ስላነሳ ይሆን? የገበሬው ጉዳይ አይመለከተኝም ዓይነት! ጋሼ ነገደ ጎበዜን ማጭድና መዶሻውን እንዳይጥለው በቅርብ ስለማገኘው እነግረዋለሁ። የካፒታሊዝም ወዳጅነታችን ካከተመ ምናልባት ተመልሶ ፍለጋው እንዳያስቸግረን ባይሆን በቅርብ ያስቀምጥልን እንጅ ። ዓርማው ላይ  ስለሚታዮት  13 ከዋክብት ትርጓሜም ቢነግረን ደስ ይለናል ። እኛ እንደሁ አንዱም አልሆነልን።

ያም ሆኖ ግን እኛም እኛ ነን ። ከ1991 እስከ አሁን ምንም ያልተቀየርን ። ይችም ታዕሳስ ግርግር ሆና ስንት አዳዲስ የፖለቲካ ድርጅቶች አየን። ስንት የመሳሪያ ትግል የጀመሩ እንዳሉ ሰማን።  ከሁሉ በላይ ደግሞ ታሪካዊው ነገር 56 ድርጅቶች አንድ ላይ ሆነው መግለጫ አወጡ የሚለው ዜና መስማታችን አስደሰተን። እስከዛሬ ከተፈጠሩት ሕብረቶች ሁሉ ከፕሮፖጋንዳው ጥቅሙ አንጻር  ግዙፉና በዓይነቱ ልዩ ነው መሰለኝ ። በተግባር ወደፊት የምናየው ነው ። ብራቮ! ጥሩ ጅምር በ2015 ።

በመግለጫው ውስጥ በእከሌ የሚመራው ኦነግ ፣ በእከሌ የሚመራው ኢሕአፓ ፣ በእከሌ የሚመራው የአማራ ድርጅት፣ የሚለው ግን “ደስ አይልም” ። 2015 ትልቁ ግባችን ይህ ነው መሰለኝ ። ወደ መሳፍንት ዘመን ለምናደርገው ጉዞ ከአሁኑ ደጅአዝማቾቹን ፣ ፊት አውራሪዎቹን ፣ ቀኝ አዝማቾቹን፣ አጋፋሪዎቹን እና ሌሎቹንም  እየተዋወቅን መሄዳችን ጥሩ ነው ። ስለድርጅቶች ስናነሳ ለአማራ የተቋቋሙ ድርጅቶች ፣ ለኦሮሞ የተቋቋሙ ድርጅቶች . . .  እንደው ሌሎቹም፣ ሌሎቹም… አንድ ላይ ወደ መሳፍንት ዘመነ መንግሥት ጉዞ እየተጣደፍን አይመስልም ። ሥልጣን ላይ ቢደርሱስ እንዴት ነው የሚስማሙት? ሁሉም ክልሉን ይዞ ሊታኮስ?… ስለ ኢትዮጵያ አንድነትና ሉዓላዊነት ጉዳይ ወያኔ ከወረደ በኋላ እንወስናለን የሚለው ነጠላ ዜማ  የማይጥመው እዚህ ላይ ነው።

እኔ እንደሚመስለኝ በ2015 ግለሰብ ሆነን የቀረን በጣም ጥቂት ነን። እንዳንዶች ድርጅት ነን የሚሉ ከግለሰብነት አያልፉምና ይህ ቀልድ ሊቆም ይገባል ። አለበለዚያ በቅርብ ጊዜ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጋ ድርጅት እንዳይኖረን ሰጋቴ ነው ።  .. እየተስተዋል እንጅ!

2016 ቀልዶቻችን ትተን ወደ እኛነታችን ተመልሰን ያላረስነውን ለማፈስ፣ ያልዘራነውን ለማጨድ እንደ ሰሞኑ መግለጫ ባንሞክር ጥሩ ነው ። በሕዝባችን ላይ እምነት ጥለን ፣ ከሕዝባችን ጋር ተደራጅተን መታገልን ነው መመኘትና መሥራት ያለብን ። ቆቡን ጣለ እንጅ መኢሶን አንቅሮ የተፋው መፈክር ዛሬ ነበር የሚሰራው “ ለነቃ ፣ ለተደራጀና ለታጠቀ የሕዝብ ትግል” የሚለው። ይህ መፈክር 1967 አይሰራም ነበር ። ጠንካራ ሠራዊት ፣ ጠንካራ የሠራተኛ ማህበር ፣ መኢሶን ፣ ኢሕአፓ ፣ ደርግ ፣ኢዲዩ ሌሎችም በነበሩበት ወቅት ጊዜያዊ ሕዝባዊ መንግስት ሊሠራ ይችላል። ዛሬ ሃገሪቷ በክልል ተከፋፍላ፣ ተቃዋሚ ድርጅቶች በደከሙበት ወቅትና አደገኛ አዝማሚያ ባለበት ሁኔታ፣ በሕዝብ አመጽ ብቻ ወደ ሕዝባዊ መንግሥት መጓዝ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል ። ይቻላል ከተባለ ቀመሩን ምሁራን ሊያሳዩን ይገባል። እኔ በበኩሌ የሽግግር መንግሥት ፣ ጊዜያዊ ሕዝባዊ መንግሥት የሚለው በዚህ በለየለት ከፍፍል ወቅት ይሰራል የሚል እምነት የለኝም ። ምክንያቱም በድርጅቶች መካከል እንኳን አንድ ዓይነት ዓላማ አይታይም ።

በአንድነት ላይ የተመሰረተ እምነት ያለው ንቃት ፣ በዚህ እመነት ላይ ዴሞክራሲን ግቡ ያደረገ ድርጅት ወይም ሕብረት ፣ በዚህ ድርጅት ወይም ሕብረት ሥር የሚደረግ የመሣሪያ ትግል ብቻ ነው መፍትሔው ። ይህንን ወደ ጎን አድርገን በየጎጡ ፣ በጎበዝ አለቃ የሚመራ ፣ ወደ መሳፍንት ዘመን የሚመራ ትግልን መቀስቀስ ሃገር ከማፈራረስ ባሻገር ምንም ፋይዳ አይኖረውም የሚል እምነት አለኝ ።  … ልብ ያለው ልብ ይበል !

ስለ ሃገራቸን በጎ የሚያስቡ ሁሉ መልካም ዓመት ይሁንላቸው ።

ፍረንክፈርት 01.01.2016

beljig.ali@gmail.com

The post ጉዞ ወደ ዘመነ መሳፍንት | በልጅግ ዓሊ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

አዲስ አበባና በተለያዩ ከተሞች ከጥር 6 እስከ ጥር 8, 2008 የሚካሄድ ሕዝባዊ ተቃውሞ !!

$
0
0

The post አዲስ አበባና በተለያዩ ከተሞች ከጥር 6 እስከ ጥር 8, 2008 የሚካሄድ ሕዝባዊ ተቃውሞ !! appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
↧

ተማሪዎች ዛሬ በገብረ ጉራቻ ያደረጉት ተቃውሞን የሚያሳይ አጭር ቪዲዮ

↧

ስደት የፍርሃት ውጤት ነው –ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም

$
0
0

Pro Mesfinከሁለት ቀኖች በፊት ስለበእውቀቱ ሥዩም አድናቆታቸውን በፌስቡክ ላይ የገለጹ ሁለት ሰዎች ነበሩ፤ ለበእውቀቱ ያላቸውን አድናቆት እኔም እጋራቸዋለሁ፤ ነገር ግን የእነዚህ ሰዎች አድናቆት በእውቀቱ ራሱንና ማንነቱን እንዲከዳ ይቃጣቸዋል፤ አንዱን አውቀዋለሁ፤ ከፖሊቲካና ከትጥቅ ትግል ወደስደት ‹‹ነጻነት›› የተሸጋገረ ያሬድ ጥበቡ የሚል የሚያኮራ ስም ይዞ የስደት መምህር የሆነ ነው፤ ሁለተኛው ሚስተር ቴዲ ገብርኤል ይባላል፤ እነዚህ ሁለት ስደተኞች በእውቀቱ ሥዩምን በጣም ስለሚወድዱትና ስለሚያከብሩት በአሜሪካ ስደተኛ ሆኖ እንዲቀርላቸው ይፈልጋሉ፤ በዚህ ብቻ ለኢትዮጵያ ያላቸውን ስሜት መገመት በጣም የሚያሳዝን ነው፤ ወደዝርዝር አልገባም፡፡

በዚያው እነሱ አስተያየታቸውን በጻፉበት ገጽ ላይ የራሴን አስተያየት ለጥፌ ነበረ፤ በበነጋታው ባየው የሁላችንም አስተያየቶ ድራሻቸው ጠፍቷል፤ አንድ ቀን ሙሉ ፈልጌ አጣኋቸው፤ ያሬድ ጥበቡና ቴዲ ልዩ ዘዴ እንዳላቸው አላውቅም፤ ሌላም ሰው ያንን ጽሑፍ ለማጥፋት ምን ምክንያት እንዳገኘ አላወቅሁም፤ ለማናቸውም ያንን ሀሳቤን እንዲያውም አስፋፍቼ ለማቅረብ ዕድል አገኘሁ፡፡

ያሬድ ጥበቡና ቴዲ በእውቀቱን በአሜሪካ ለማስቀረት የሚፈልጉበት ምክንያት ምንድን ነው? ምክንያቱን በትክክል እንኳን እኔ እነሱም የሚያውቁት አይመስለኝም፤ ግምቴን ግን ላቅርብና አይደለም ካሉ እንሟገትበት፤ አንደኛ ሊክዱት በማይችሉት ሐቅ ልጀምርና ሁለቱም ሰዎች በጣም ፈሪዎች ናቸው፤ ስለዚህም ፍርሃታቸውን ወደበእውቀቱ አዛምተው ጨለማን ተጋፍጦ በነጻነት ከቆመበት የማይመችና የማይደላ የእናቱና የአባቱ ዓለም ወደአሜሪካ የምቾትና የስድነት ባዕድ ዓለም ከእነሱ ጋር እንዲደባለቅ ይፈልጋሉ፤ ለምን እንዲደባለቃቸው ይፈልጋሉ? ትልቁ ጥያቄ ይሄ ነው፤ መልሱም እኔ እንደምገምተው እሱ እነሱን ሲሆን፣ እነሱ አሱን የሆኑ ስለሚመስላቸው ነው፤ ትንሽ ቢያስቡበት (ፍርሃት ለማሰብ ጊዜ አይሰጥም እንጂ!) በእውቀቱ እነሱን ሲሆን አሁን ያለውን ለነጻነት የመቆም ዋጋ እንደሚያጣና እንደሚያንስ መገንዘብ ጊዜ አይፈጅባቸውም ነበር፤ ቴዲም ሆነ ያሬድ ለበአውቀቱ ‹‹የቸሩት›› ፍርሃታቸውን ነው፤ የኢትዮጵያ ወጣቶች ወኔ የሌላቸው የሚሆኑት እንደዚህ ያሉ የፍርሃት ጠቢባን በሰላ ዘዴ እየነደፏቸው ነው፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ‹‹አርቲስት›› እያለ ከሚጠራቸው ሰዎች ውስጥ በአንድ እጅ ጣቶች የሚቆጠሩ መኖራቸው አጠራጣሪ ነው፤ እኔ እርግጠኛ ሆኜ የማውቀው ቴዎድሮስ ካሣሁንን ነው፤ አሁን ደግሞ በእውቀቱ ብቅ ቢል በመንፈስ ከከሰሩት ከአላሙዲን ስብስብ ውስጥ ሊያስገቡት ይጥራሉ፡፡ (አላሙዲን በገንዘቡ ወርቅም ይግዛበት ወይም ሰው ገበያው ከፈቀደለት (በጎንደርኛ አማርኛ ወርቅ ባሪያ ማለት ይሆናል ሲባል ሰምቻለሁ፤) በብሩም ሆነ በወርቁ ላይ ባለመብት ነው፡፡

ፍርሃት የግል ነውና በፍርሃት ተገንዞ መኖርን አልቃወምም፤ አጥብቄ የምቃወመው ግን ፍርሃትን (ሕመምን) ወደሌላ ሰው ማስታለፍን ነው፤ ፍርሃት እንደማናቸውም ተላላፊ ሕመም በንክኪም ሆነ በንግግር ይተላለፋል፤ አጥብቄ የምቃወመው ወኔ ያለው ኢትዮጵያዊ ሁሉ በፍርሃት ቆፈን እየተጠፈረ ስደተኛ እንዲሆን መገፋፋትን ነው፤ አጥብቄ የምቃወመው ለመብቱና ለነጻነቱ ግፉን እየተቀበለ የግፈኞቹን አረመኔነት በመንፈሳዊ ወኔው የሚጋፈጠውን ከምድረ ኢትዮጵያ እንዲጠፋ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት ነው፤ እኔ አጥብቄ የምቃወመው ኢትዮጵያን በሀብት ደሀ የሆነች አገር ብቻ ሳትሆን በሰውም፣ በአእምሮም፣ በመንፈስም ደሀ የሆነች አገር እንድትሆን በማወቅም ባለማወቅም የሚደረገውን ጥረት ነው፤ የፈረንጅ አገር ኑሮ እንደሚደላና እንደሚጥም እያየን ነው፤ በፈረንጅ አገሮች ላይ የሚውለው የኢትዮጵያ አካል፣ አእምሮና መንፈስ በኢትዮጵያ ላይ ቢውል ኢትዮጵያም የምትደላና የምትጥም አገር ልትሆን ትችል ነበር፤ ጠፍሮ የያዘንን ሰንሰለት በጣጥሰን ችሎታችንን ሁሉ በግንባታ ላይ እንዳናውለው ባንድ በኩል ፍርሃት በሌላ በኩል የሥልጣን ፉክክር አደንዝዞናል፡፡
ቴዲ ገብርኤል በእውቀቱ ‹‹በኢትዮጵያ ውስጥ በመፈጠሩ አኮራለሁ›› ይልን ወዲያውኑ ያንን በኢትዮጵያ ውስጥ በመፈጠሩ የኮራበትን በእውቀቱን ለስደተኛነት ያጨዋል፤ በእውቀቱ በአሜሪካ ስደተኛ ሆኖ ቢቀር በቁሙ ሞቶ ኢትዮጵያ አላጣችውም?አያድርግበትና በእውቀቱ አገሩ ገብተ ወያኔ ቢገድለው ወይም ቢያስረው በወያኔ አረመኔነት በእውቀቱ ሕያው አይሆንም?
ሌላው ያልታሰበው ጉዳይ በሚስተር ቴዲ አስተሳሰብ ‹‹የሚያኮሩ›› ኢትዮጵያውያን ሁሉ ከአገር ከወጡ አገሩ በሙሉ የነሚስተር ቴዲ መሆኑ አይደለም እንዴ! እግዚአብሔር ያውጣን! በእውቀቱንም በደህና ይመልሰውና በአገሩ በሰላም ያኑረው!
ለቀልድ የተባለነው ማለት ‹‹ቢያዩኝ እስቃለሁ፤ ባያዩን እሰርቃለሁ›› የሚለውን ዘዴ መከተል ነው፡፡

ኢትዮጵያውያን በተለይ በደርግና በወያኔ የአገዛዝ ዘመናት በብዛት ለስደት መደረጋቸውን ማንም የሚያውቀው ነው፤ የስደቱ ምክንያት ብዙ ነው፤ ስደተኛው ሁሉ አይወቀስም፤ ነገር ግን የሚወቀሱ ሞልተዋል፤ ምናልባትም የኢትዮጵያን ስደተኞች ልዩ የሚያደርገው ስደተኛውና አሳዳጁ በአንድ አገር ስደተኞች ሆነው፣በአገራቸው ተከባብረው መኖር ያቃታቸው ሰዎች በሰው አገር በግዳቸው ተከባብረው መኖራቸው ነው፤ መቻቻል ማለት እንዲህ ነው!

The post ስደት የፍርሃት ውጤት ነው – ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

ዮናታን ተስፋየ እና ጌታቸው ሺፈራው ከጠበቆቻቸው ጋር እንዳይገናኙ ተደረጉ

$
0
0

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

Yonatan Tesfaye Semayawi Party PRNegere Ethiopia edtor Getachew-Assefa-300x200በማዕከላዊ ፌደራል ወንጀል ምርመራ በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው እና የሰማያዊ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበረው አቶ ዮናታን ተስፋዬ ከጠበቆቻቸው ጋር እንዳይገናኙ መደረጋቸውን ሊያነጋግሯቸው ወደ ማዕከላዊ አምርተው የነበሩት ጠበቆቻቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

የሁለቱ ወጣቶች ጠበቆች የሆኑት ጠበቃ አምሃ መኮንን እና ሽብሩ በለጠ ዛሬ ታህሳስ 27/2008 ዓ.ም ደንበኞቻቸውን ለማግኘት ወደ ማዕከላዊ ሄደው የነበር ቢሆንም ‹‹ሰራተኞች ስብሰባ ላይ በመሆናቸው መግባት አትችሉም›› በሚል ከበር መልሰዋቸዋል፡፡

በማዕከላዊ በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችን ጠበቆች ማግኘት የሚችሉት በሳምንት ሁለት ቀናት፣ ማለትም ዕሮብ እና አርብ መሆኑን ያስታወሱት ጠበቃ አምሃ፣ በእነዚህ ቀናትም እንኳ ደንበኞቻችንን ማግኘት መከልከላችን ግልጽ የህገ-መንግስት ጥሰት ነው ብለዋል፡፡

‹‹ህገ-መንግስቱ በእስር ላይ ስለሚገኙ ሰዎች መብት በግልጽ የሚናገረው በየትኛውም ቀን ከጠበቆቻቸው፣ ከወዳጆቻቸው፣ ከሀይማኖት አባቶቻቸው እና ከወላጆቻቸው ጋር መገናኘት እንደሚችሉ ነው፡፡ ይህ ሆኖ እያለ በሳምንት ሁለት ቀናት ብቻ ደንበኞቻችንን ለማግኘት መገደቡ ሳያንስ ዛሬ ከበር ላይ መከልከላችን የሚያሳየው በግልጽ ህገ-መንግስቱን ለማክበር ቁርጠኝነት እንደሌለ ነው›› ብለዋል ጠበቆቹ፡፡

ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው እና ዮናታን ተስፋዬ ከታሰሩ ከሳምንት በላይ ቢሆናቸውም እስካሁን በአንድም ሰው እንዲጎበኙ አልተፈቀደም፤ በወቅቱ በተመሳሳይ ለእስር የተዳረጉ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትም በቤተሰብ እንዳይጎበኙ ተደርገዋል፡፡ በዚህም ታሳሪዎቹ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ባለመቻሉ ቤተሰቦቻቸውንና ወዳጆቻቸውን እንዳሳሰባቸው ለመረዳት ተችሏል፡፡

The post ዮናታን ተስፋየ እና ጌታቸው ሺፈራው ከጠበቆቻቸው ጋር እንዳይገናኙ ተደረጉ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live




Latest Images