Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የአንዋር መስጊዱን የቦምብ ጥቃት አስመልክቶ በእስር ቤት ከሚገኙ የኮሚቴው አባላት የተሰጠ መግለጫ

$
0
0

The post የአንዋር መስጊዱን የቦምብ ጥቃት አስመልክቶ በእስር ቤት ከሚገኙ የኮሚቴው አባላት የተሰጠ መግለጫ appeared first on Zehabesha Amharic.


ህገ-መንግስቱ ይከበር፤ የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ

$
0
0

አብራሃም ለቤዛ

 

“ህገ መንግስቱ የተጻፈበትን ወረቀት ያህል ዋጋ አያወጣም፡፡’’ ይህን ንግግር በ1997 ዓ/ም በተደረገው በምርጫ ዋዜማ በተደረገ የምርጫ ክርክር ላይ ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርየም የተናገሩት ነው፡፡ ፕሮፊሰሩ አክለውም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ህገ-መንግስት ሳይሆን ህገ- አራዊት ነው፡፡ መሬት ላይ እየተገዛን ያለው በህገ-መንግስት ሳይሆን አዉቀቱም ሆነ ክህሎቱ የሌላቸው የወያኔ ባለስልጣናት ህግን ተክተው በእውር ድምብራቸው በሚያስተላልፉት መመሪያ ነው፡፡

abebe Gelaw

እውን ወያኔ ለኢትዮጵያን የህገ-መንግስት ታሪክ እንዳስረከባት ፤ ከእርሱ ዘመን እንደተጀመረ አድረጎ የሚተርከው ወያኔ ይዞልን የመጣውን ህገ መንግስት እራሱ ያከብረዋል?

ወያኔ የምርጫ 1997 ዓ/ም ምርጫ ከፈጠረበት ድንጋጤ ማግስት ከህገ-መንግስቱ ጋር ተጻራሪ የሆኑ በርካታ ህገጎችን አውጥቶል፡፡ የወያኔ ፕሮፓጋንዳ ማሽን ቀን ከሌት ሀገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በሃይል ለመናድ እያለ ተቃዋሚዎችን የሚከስ ቢሆንም በተግባር ግን ህገ- መንግስቱን ወይንም ህገ-መንግስትን ማላገጫ ያረገ ቡድን ቢኖር ወያኔ ነው፡፡ መለስ ዜናዊ ከጫካ ይዞት በመጣው እውቀት 22 ዓመት የመራትን አገር የዩንቨርስቲን በር በትምህርት ከዚያም በመምህርነት የረገጡት ሃይለማርያም ደሳለኝ አገር መምራት አይችሉም ተብለው ወይም ሌላ ድብቅ አላማ ተረግዞ ህገ-መንግስት ተጥሶ (አንቀፅ 75) ሁለት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር ታኮ ተጨመረለት፡ድንቄም የማዕዘን ድንጋይ፤ አልሰማህም ይላል የአራዳ ልጅ አመንኪዮ አልባ ወይንም ሁለት መለኪያ ለአንድ ጉዳይ ሲያጋጥመው (double standard)፡፡

በቅርጽ ብቻ ፓርላመንታዊ ስርዓት የዴሞክረሲያዊ መንግስት መገለጫ ቢሆን ወያኔ የሚመራት ኢትዮጵያ ከአለም ቁንጮ ዲሞከራት አገር መባል በቻለች፡ የህግ ቋሚ ኮሚቴ፡ የማህበራዊ ቋሚ ኮመቴ እየተባለ ፐሮፊሽናል ፓርላማ ለማስመሰል የማስመሰያ ስም ይሸከማል፡፡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትን በዴሞክራሲያዊ ማእከላዊነት ፍልስፍና የሃሳቦች መንሸራሸሪያ መድረክ ሳይሆን የወያኔ ከበሮ ብቻ የሚደለቅበት የተዋረደ ቦታ ሁኖል፡፡

በአንጻሩ በንጉሱ ጊዜ የስልጣን ምንጭ ህዝቡ ሳይሆን መለኮታዊ ስልጣን በሆነበት ወቅት፤ ርዕስታቸውን ጋሻ አድርገው ወደ ምክር ቤት የመጡ የፓርላማ ተወካዮች በአንጻራዊ መንገደድ የመጡበትን አካባቢአዊ ቸግሮቻቸውንና ፍላጎታቸውን ለንጉሱ ምክርቤት ያለምንም መሸማቀቅ ያቀርቡ እንደነበር ታሪክ ይመሰክራል፡፡

ዛሬ ዛሬ ወያኔወች በህገ መንግስቱ ውስጥ ያሉትን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የረሱዓቸው ይመስላል፡፡ በኢትዮጵያ ምድር ሰለማዊ ሰልፍ ለማድረግ እንኳን የወያኔን ደጅ መጥናት ግድ ብሏል፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ የመሰረተ ልማት ስራዎችን ሰለሚያስተጓጉል የተከለከለ ነው፡፡ እንግዲህ ወይ ህገ-መንግስታዊ ማሸሻያ ያድርግ ወይስ ደግሞ ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ለመናድ የሚል አሰልች የሆነ የቅጥፈት ፕሮፓጋንዳ ይቁም፡፡

ከሶስት ሳምን ወዲህ በጊንጭ ተነስቶ በመላው ኦሮሚያ እየተቀጣጠለ ያለው ህዝባዊ አመጽ የመብት ጥያቄ ነው፤ ይህ ሰላማዊ የመብት ጥያቄ ግን ከአምባገነኑ ወያኔ ያገኘው የሃይል ምላሽ ሲሆን የብዙ ሰዎችን ሂዎት ቀጥፎል፡፡ ህዝብ ተማሪ፤ አርሶ አደር፤ ቀን ሰራተኛ፤ ጥቃቅን እና አነስተኛ ፤ ሲቪል ሰርቫንት፤ ከልጅ እስከ አዎቂ የተሳተፈበት ሰላማዊ የህዝብ ጥያቄ ጸረ-ሰላም ሃይሎች ከሆላ ሁነው የሚቀሰቀሱት የሽብረ ሴራ ማለት ወያኔ የመከበብ ስሜት ውስጥ ያለ ፈሪ እና ጠባብ ቡድን መሆኑን ያመለክታል፡፡

የዴሞክራሰ ስርኣት መገለጫ የሆኑት ሶስቱ አውዶች ህግ አውጭ፤ ህግ ተርጓሚ እና ህግ አስፈጻሚ ፤ አንዱ በአንዱ ጣልቃ ገብነትን አቁመው ነገር ግን ህጋዊ በሆነ መንገድ አንዱ አንዱን የሚቀቋጣጠርበትን መንገድ የተበጀ ሲሆን አገር ነጻ ህዝቦቾም እራሳቸውን መቻል ይችላሉ፤ ነጻነት ካለ ኮብልስቶን ዳቦ የማይሆንበት ምክንያት የለም፡፡ የፀጥታ ሃይለም ህዝብን ሳይሆን ዳር ድንበር (ወሰንን) መጠበቅ ይሆናል ተቀዳሚ ስራው፡፡

ዛሬ ወያኔ ከጎንደር እስከ ጋመምቤላ ያለውን ለም መሬት ለመስጠት እንደተዘጋጀ ይታወቃል፡፡ መለስ ዜናዊ ሞት ሳይቀድማቸው ለሚወዳቸውና ለሚወዱት ፓርላማ አባላት ሱዳን ከኢትዮጵያ አንዳችም መሬት አትፈልግም ነገር ግን የኢትዮጵያ አርሶአደር በወረራ ያዘውን መሬት ግን ለመመለስ ዝግጁ ነን ብለው ነበር፡፡ የወያኔ የስልጣን ጥም ለማርካት በህዝብ ድምጽ መተማመን ስለማይችን በጎረቤት አገራት ላይ መንጠላጠልን መርጦል፡፡ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ይሉሻል ይሄ ነው፡፡

በአሁኑ ሰዓት በአገራችን ያለው ህዝባዊ ቁጣ የተጠራቀመ የህዝብ ብሶት ነጸብራቅ ሲሆን ፤ የኦሮሚያ አርሶአደርና ተማሪ ብቻ ሳይሆን የአዲስ አበባ ጉሊት ሻጭ እናት ፤ በየከተሞች ስራፍለጋ የሚባዝነው የደቡብ ወጣት፤ በስሙ የሚነገድበት ነገር ግን ተጋዳላይ ጎረቤቶቹ ጮማ ሲቆርጡ የሚያዛጋው ትግሬ ፤ እንደ አበደ ውሻ እየታደነ ያለው አማራ ፤ በጋምቤላ በቤሻንጉል በኦሞ እና በአፋር የሚፈናቀለው አርብቶ አደር ብሶት ጭምር ነው፡፡

የኢትዮጵያ ወጣት ዥንጉርጉር የሆነውን ባህልህን፡ የሃማኖትና የቋንቋ ልዩነትህን እንደ ጌጥ ወስደህ ለዘረኞችና ለከፋፋዮች ሴራ ሳትንበረከክ ፤ የኢትዮጵያ መጻኢ ተስፋ በእኛው አጅ መሆኖነ ተገንዝበህ በህዘባዊ ፤ ሰላማዊ ትግል የስልጣን ባለቤትነታችንን ማረጋገጥ አለብን፡፡

አንድነት ሃይል ነው፤ ወራሪዎችን የመከተ ህዝብ ለባንዳዎች አያንስም፡፡ ኢትዮጵያን እ/ር ይጠብቃት፡፡

The post ህገ-መንግስቱ ይከበር፤ የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ appeared first on Zehabesha Amharic.

ዶሮ ብታልም ስለጥሬዋ |ለፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ እና ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም ‘አማራ የሚባል ሕዝብ የለም’አባባል የተሰጠ ምላሽ

$
0
0

በአበበ ተድላ፣ ሰኞ ታኅሣሥ 11 ቀን 2008 ዓም

 

የሰውን ስነልቦና ማወቅ ሰዎች የሚናገሩትና የሚሰሩት ለምን እንደሆነና የምን ሃሳብ ነፀብራቅ እንደሆነ ለመረዳት ይረዳል። ይሄንን ምእራባዊያንን ለምርጫም ለህክምናም ለሌላም ነገር ይጠቀሙበታል። ኢትዮጵያዊያን ምን ያህል እንደተጠቀምንበት አላውቅም ግን ወደ ዋና ጉዳዬ  ወደ ገደለው ልግባ።

mesfin

የሞተው ለገሰ ዜናዊ ወላጆቹ የጣልያን ባንዳ ሹምባሽ ስለነበሩ ከልጅነቱ ጀምሮ “አንተ ባንዳ” ሲባል ነው ያደገው። ስለዚህ ይሄንን ህመሙን ለማዳን ባንዳ ላለመባል መጀመሪያውኑ ቤተሰቦቹን ባንዳ ያሰኘው የወላጆቹ አላማ ሳይሳካ ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር መኖርዋ ስለሆነ፣ ኢትዮጵያን የማፈራረስ ስራ ዳር ማድረስ አለበት። በዚህም ምክንያት “የኢትዮጵያ መሪ” ተብሎ “ኢትዮጵያ” የሚባለውን ስም ሳይጠራ “ሃገሪቱ” እንዳለ፤ “ኢትዮጵያዊነት ላይ ሙጭጭ ብለዋል” ያላቸውን አማራ እስከህይወት ፍጻሜው ሲያጠፋ እና ሲያስጠፋ ኖሮ ከበሽታው ሳይድን ሞተ።

ፕ/ር መስፍን እና ፕ/ር ጌታቸውም እንዲሁ ከተለያየ ብሄር ስለተወለዱ ህይወታቸውን ሙሉ ምርምር አካሂደው በመጨረሻ ሰበር ዜና ብለው ያቀረቡልን ውጤት የነሱን ስሜት ሊያረጋጋ የሚችል የመሰላቸውን “አማራ የሚባል ህዝብ የለም” የሚለውን ሃሳብ ነው። ወገን እንግዲህ ሰው ከታመመ መርዳት ነው; የአእምሮ ህመም ደሞ ሲጀመር ችግር እንዳለባቸው ስለማይገባቸው ህክምናው ትንሽ አስቸጋሪ ቢሆንም፣ በቃ ታመዋል መታከም አለባቸው። ዝም ግን ሊባሉ አይችሉም፤ ምክንያቱም ጊዜ ወይንም አጋጣሚ ያገኘ እብድ በሽተኛ የሚያደርሰው ጉዳት ከፍተኛ ስለሆነ ከተቻለ ማከም አለበለዚያ ተይዘው እስከሚድኑ ከህዝብ መገለል አለባቸው፤ አለበለዚያ ጉዳታቸው የከፋ ነውና። ከምንም በላይ ጥፋታቸውን የሚያከፋው ደሞ ይሄንን የህይወት ሙሉ የጥናት ውጤት ልፋታችን ያሉትን (ለነገሩ ሳይለፋ የሚታወቅ ሃቅ ነው) ህዝቦች  በተለያየ ምክንያት ስለተቀላቀሉ “ይሄ ብሄር” ብሎ ጠርቶ “የሱ ቦታ እዚህ ነው በኢትዮጵያ ውስጥ” ማለት ስለማይቻል “የአማራ የኦሮሞ ወይም የትግሬ ወዘተ” ማለት አንችልም ብለው መደምደም ሲገባቸው (ያለጥናት ይሄም ማንም መንገደኛ ይነግራቸዋል) እነሱ ግን ይሄ አስተሳሰብ አማራ ላይ ብቻ እንዲሰራ አድርገው ሌሎችን ፈርተው ይሁን ምን ይሁን በማይታወቅ ምክንያት “አማራ የለም ሌላው ብሄር አለ” አሉን። ትልቅ ሰው በባህላችን ስለማይሰደብ እንጂ አሳፋሪዎች እላቸው ነበረ!

ሰው ያደገበት ሁኔታ ምን ያህል አስተሳሰቡን እንደሚቀይረው የታወቀ ቢሆንም ይቺን ምሳሌ ልጨምር። አንዱ አዲስ አበባ ሲያድግ በጣም የሽንት ቤት ችግር ያለበት ቦታ ስላደገ፤ በለስ ቀንቶት አድጎ ገንዘብ ኖሮት ቤት ሲሰራ መጀመሪ ያስጨረሰው ሽንት ቤቱን ነው። ትልቁ ደስታውም ሽንት ቤቱን ማየት እና ማሳየት እንደነበረ አንድ ወዳጄ አጫውቶኛል።

በተመሳሳይ ምሳሌ ብዙ አማራውች በትህነግ (ወያኔ) እና አጋሮቹ በደል ብዛት ምክንያት አሁን ላለው ስርአት ያለን ተቃውሞ ተመሳሳይ ቢሆንም በአብዛኛው አማራ ያለበት ቦታ ያደገ አማራ እና በተለይ አሁን ትህነጎች መስመር ሰርተው “ያለክልሉ ያለ” ተብሎ ያደገ አማራ ስለ ብሄር አከላለሉ የሚያደርገው ተቃውሞ ደረጃ ይለያያል፦ የደረሰበት ያውቀዋልና። በገዛ ሃገር አገር አጥቶ ከመኖር የበለጠ ህመም እንደሌለ ይሄ ስርአት ሚሊዮን አማራዎችን በገዛ ሃገራቸው ያል ክልላቸው የሚኖሩ እያሉ ሃገር እንዳሳጣ እና ለእልቂት እንደዳረገው ኖሮ አይቶታልና። ታዲያ ዶሮ ብታልም ስለጥሬዋ ይሄንን ርእስ አይገልጠውም ትላላቹ?

 

Getachew Haile“ምን ይሻላል ለምትሉ” ሁሌ የምንለውን አሁንም ደግሜ አቀርበዋለው። በፖለቲካ ብላቴናዎች ብንሆንም እነሱን እንደምንሰማው እኛንም ቢያዳምጡን፣ የምንለውን ቢሰሙን፣ ለዘመናት አጠናን ካሉት የተሻለ ሃሳብ ሊያገኙም ይችሉ ይሆናል። ጆሮ ይስጡን እንጂ መፍትሄውን እኛ ጋር ሊሆን ይችላል!

ሁሌም እንደምንለው ኢትዮጵያ ውስጥ አማራም፤ ትግሬም፤ ኦሮሞም ሌላም ወደ ሰማኒያ የሚጠጋ ብሄር አለ። በዛው ልክም ደግሞ ከተለያዩ ብሄሮች ተቀላቅለው የተወለዱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን አሉ። ለዚህም እኮ ነው “የትህነግን የአፓርታይድ አከላለል ልክ አይደለም፤ አንደኛ አማራ ተወካይ በሌለበት ነው የተሰራው፤ ሁለተኛ የተቀላቀሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያንን ሃገር ያሳጣል፤ አንዱን ወይንም ከዛ በላይ ወገናቸውን ክደው አንዱን እንዲመርጡ ህዝቦችን ያስገድዳል” ያልነው። የተቀላቀሉ ብሄሮች ኢትዮጵያ ውስጥ ስላሉ እና አማራም ከተቀላቀሉት አንዱ ሆኖ ሳለ “አማራ ብቻ የለም” ማለት ግን አይቻልም። አማራ ተቀላቅሎ ከጠፋ ሌላው ከአማራ ጋርም የተቀላቀለው ጠፍትዋል ማለት ነው እንጂ አማራ ብቻውን እንዴት ይጠፋል? የለም ይባላል? ብሄር መጥራት እናቁም የሚል የፖለቲካ አቅዋም ማራመድ ሌላ ጉዳይ ነው ግን “ብሄር መጥራት እናቁም” ማለት አማራን ብቻ ለይቶ “አማራ የለም” ማለት አይደለም። እንዲህ የሚያደርግ ሰው  በአማራ ላይ ትህነግ ለሚያደርሰው ጥቃት አባሪ እንደሆነ ነው የምንቆጥረው።

መፍትሄው እንዲህ ነው፤

“ኢትዮጵዮያ ውስጥ ብዙ የተቀላቀለ ብሄር አለና ብሄር ሳይጠራ ኢትዮጵያዊ ብቻ ተብለን እንኑር” የምትሉ መብታቹ ነው፤ ሃሳባቹን አራምዱ፤ ዲሞክራሲ ካለ ህዝቡ የወደደውን ይመርጣል። እንዲሁም “ብሄሬ እንዲጠራ” የሚለውን ቡድን “ፈጽሞ አይቻልም” እንዳትሉት። ነገር ግን “ብሄር የለም” ማለት አማራን ብቻ እንዲመለከት ማድረግ ለዚህም መረጃ “ድሮ አማራ ያልነበረ አማራ ሆነ” ብላቹ በተመሳሳይ ድሮ ኦሮሞ ያልነበረ ዳሞት፤ ፈጠጋር፤ አንጎት፤ እናራያ፤ ወዘተ ዛሬ ተቀይሮ “ኦሮሞ” የተባለ መሆኑን ለትግሬውም እንዲሁ ሌላውን ውጠው ትግሬ እንደተባለ አለመናገር ግን ሸፍጠኝነት ነው።

“ብሄራችን ቀድሞ እንዲጠራ እንፈልጋለን” ለምትሉም መብታቹ ነው። ይህንን አላማቹን አስፋፉ፣ ስበኩ፣ ችግር የለብንም። ግን አንድ ብሄር የራሱን መብት ይከበር ሲባል የሌሎች አብረው የሚኖሩ ብሄሮች መብት ተጥሶ ወይንም በገዛ ሃገራቸው በናንተ መልካም ፍቃድ እና ችሮታ ብቻ እንዲኖሩ የተፈቀደላቸው አይነት ስርአት ለመዘርጋት አትሞክሩ እንጂ።  “ምሁራን ነን፣ የሁሉም ኢትዮጵያዊ መብት እንዲከበር እንታገላለን፤” የምትሉ ኦሮሞውንም፣ ትግሬውንም፣ ገና እየተደራጀ ያለውንም አማራ፣ “የብሄሬ መብት ይጠበቅ ማለት ትችላላቹ። ግን የብሄሬ መብት ይጠበቅ ስትሉ የሌላውን ብሄርም ይሁን የተቀላቀሉትን መብት አለመጣሳቹን አስቡ” ነበር ማለት የነበራቸው እንጂ በደፈናው “አማራ የለም” በማለት ሰዎችን ከብሄርተኝነት ሃሳብ እናወጣለን ብላቹ እንዳታስቡ። ይሄ አማራው ተለይቶ በአማራነቱ በመላው ኢትዮጵያ ጥቃት እየደረሰበት “ድሮ ጨቋኝ ነበር” እየተባለ ጥላሸት የሚቀባበትን ህዝብ ራሱን ለማደራጀት ሲል አንዴ “የለም”፣ አንዴ “አማራ እንዴት ይጠባል”፣ እያሉ አማራን እንዳይደራጅ እና ራሱን ከጥፋት እንዳያድን ማድረግ አማራን ይጎዳል፣ ሌሎችን ይጠቅማል እንጂ ሌላ ምንም ጥቅም የለውም፤ አማራ በሆነው ባልሆነው ሲወዛገብ ጠባቦች የማጥፋት ስራቸውን ይቀጥላሉና። እንዴት ነው “ኦሮሚያ” ብለው የከለሉት ውስጥ ያለው መሬት “የኦሮሞ እንጂ በውስጡ ያሉ ህዝቦች አይደለም” ተብሎ ሌላውን እንግዳ ያደረገ ተፅፎ ያለን ስርአት ሳይቃወሙ ምሁራን ተብዬውች “አማራ አለ፣ የለም” የልጅ እቃ እቃ ጨዋታ  ውስጥ የሚገቡት? በኔ ይሄ እንዲያውም “አንድ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ መሬት የሆነ ብሄር ብቻ ነው” ማለት የአንድን ብሄር የበላይነት ስርአት መዘርጋት እንጂ እኩልነት አይደለም፤ ወይንም ቁርጥ ባለው “አገርህ አይደለህም” ልክ ሌላ ሃገር ኬንያ ወይንም ግብፅ እንዳለው ተደርጌ “ባልንህ እስከኖርክ አብረህ ትኖራለህ” ተብዬ በገዛ ሃገሬ ስደተኛ እንደሆንኩ በግልፅ ሊነገረኝ ይገባል፤ ከዛም ምላሼን ሰጣለው። አንድ ሰው ከሆነ ክልል ጋር ራሱን ካላስተሳሰረ ኢትዮጵያዊ መሆን በህገመንግስት ተብዬው መከልከሉን መቃወም ሲገባቸው ምሁራን የተባሉ፣ በተለይ አማራው ወደኃላ ተመልሶ “አማራ አለ፣ የለምን” ክርክር ከምሁር አንጠበቅም (ሌላውማ ህገመንግስት ተብዬውን ራሳቸው ስለፃፉት አፈፃፀም እንጂ ህገ መንግስቱ ችግር የለበትም ይሉናል አማራ በሌለበት እንዳፀደቁት እየታወቀ) ።  “አማራ ባህሉን ጫነብኝ” ብለው የተቆጡ መልሰው የአማራን ባህል ወስደው “ለምን አማራን አዲስ ባህል ተሰጠው” ብለው አማራ እንዲጠፋ እየተደረገ ያለውንና እየተወሰደበት ስላለው ባህሉ መጮህ ነው የሚገባቸው የአማራ ምሁራን ነን ተብዬዎች ወይንስ “አማራ አለ የለም” ወደሚል የጅል አታካራ ገብቶ አማራውን አወናብዶ ራሱን ከተደገነበት ጥፋት ማዳን እንዳይችል ነው ማድረግ ያለባቸው?

አማራነት ብቻ ነው በደም ውስጥ ያለውም እንበል፤ አማራ ከሌላ ብሄር ጋር የተቀላቀለብኝ ነኝ እንበል፤ “አማራ” ተብሎ አንድ ህዝብ ተለይቶ ሲጠቃ እንክዋንስ አማራነት እያለብኝ፤ ሰው በመሆኔም እታገላለው። “አማራ ነን” ወይንም “ለሰው ልጅ መብት እንከራከራለን” የሚሉ ኢትዮጵያዊያን፣ ሌሎች በብሄር የተደራጁ ኢትዮጵያዊያን አማራውን መብቱን ሳያከብሩ፣ ተወካይ እንክዋን ሳይኖረው፣ ያልነበረ መስመር  ትህነግ እና ወዳጆቻቸው አስምረው፤ “የብሄር ብሄረሰብ መብት አከበርን” ማለታቸውን ደጋግመው ሊቃወሙ ሲገባ፣ ይባስ በተለይ በዚህ ሰአት በማያስፈልግ “አማራ አለ፣ የለም” በሚል ጊዜያችንን ያባክናሉ።  የብሄር ብሄረሰብ መብት ሲባል አማራን አይጨምርም እንዴ? በኢትዮጵያ ውስጥ በእኩልነት መኖር “አማራን እኩል ሆኖ ይኑር” የሚል መብት ሊሰጥ አይገባም እንዴ? ይሄንን እውነት ተናግረን ችግሩን ከነመፍትሄው ብናቀርብም ከመስማት ይልቅ “ጠባቦች፣ የኢትዮጵያ ጠላቶች” ሌላም ሌላም እንባላለን፤  ዋናዎቹ ጠባቦች ራሳቸው ሆነው ሳለ።

እንግዲህ አማራውን ስቃዩን ያረዘመበት  “በኢትዮጵያዊነት ጎራ ስር ነን፤ በብሄር አንደራጅም” ያሉት “በኢትዮጵያ  ስም እንደራጅ” ይሉና የአማራን በደል ግን አይናገሩም። የአማራ ድርጅት ላለመባል “ኢትዮጵያን አልፈልግም” ብሎ መስመር አስምሮ ባንዲራ ፈጥሮ የሚታገለውን ግን ለማባበል ብዙ ርቀት ሄደው ስለሱ ቡድን አብረው ይጮሃሉ። ይሄም አልበቃ ብሎ አልፎ ተርፎም “አማራ የለም” ይሉታል። በብሄር የተደራጁት ደሞ የነሱን ብቻ መብት እንዲከበር ፈልገው አማራውን አገር አሳጥተው አንገቱን አስደፍተው ሊያጠፉት እየሰሩ ነው። ታዲያ የት አለ ኢትዮጵያዊነት? የታለ የብሄር መብት የተከበረው? እንዲህ ያለ ትክክለኛ ጥያቄ ከነመፍትሄው የምናነሳውን ፕ/ር ጌታቸውና ሌሎች “ጸረ-ኢትዮጵያ” አሉን እንግዲህ ማን እንደሆነ ጸረ-ኢትዮጵያ ልብ ያለው ልብ ይበል። ይሄ የሶሻሊስት አመለካከት “ከኔ ሃሳብ ውጪ ያለው ጠላቴ ነው፤ መጥፋት አለበት” አስተሳሰብ ካልለቀቀን ወደፊት መራመድ በጣም አስቸጋሪ ነው።

“ብሄራችን የተቀላቀለ ነው መደራጀት፤ ያለብን በኢትዮጵያዊነት ነው፤” ብለው የሚያምኑ ማለት የነበረባቸው ደግሞ “አሁን ያለው ስርአት ከተለያየ ብሄር ለተቀላቀሉ ህዝቦችን መብት የሚነፍግ እና አንድ ብሄር የግድ ስለሚያስመርጥ የተሳሳተና መቅረት ያለበት ነው፤” ማለት እንጂ ይሄንን ሃሳብ ለመናገር “አማራ የለም፣ ሌላው ብሄር አለ” ማለት ሚዛን አይደፋም። እኩልነት መብት ከሆነ አብረን ነን። ነገር ግን “የሁላችንም መብት የተከበረባት ሃገር ይኑረን” ብላቹ ነው መነሳት የነበረባቸው እንጂ፣ ገና ለገና ስትነሳ “በብሄር መደራጀት ልክ አይደለም” ብለህ አማራውን ብቻ ለይተህ “የለህም” ካልክ እንዴት ነው ከአማራው ጋር አብረን ሰርተን ነፃ እንውጣ የምትለው?  ወይ “ምንም ብሄር አንጥራ” ካላቹ ሁሉንም ብሄር አትጥሩ። ብሄር ጠርቶ አማራውን ለይቶ “የለም” ማለት ግን የትም አያደርስም፤ ምናልባት አማራውን ለመጉዳት ካላሰባቹ በስተቀር።

ስለዚህ ሲጠቃለል አማራም፤ ኦሮሞም፤ ትግሬም ሌላም አለ በጣም በርካታ ብዙ ሚሊዮን ከተለያየ ብሄር የተቀላቀሉም እንዲሁ አሉ። ከተቻለ “ብሄሬ ተጠርቶም” ይበል “ብሄሬ ሳይጠራ ኢትዮጵያዊ ነኝ” የሌሎችን መብት ባልነካ መልኩ ብዙሃን ድምፃቸው እየተከበረ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው በብዙሃኑ ተፅእኖ ሳይደርስባቸው ሁሉንም ኢትዮጵያዊ አስማምቶ አንዱ አንደኛ ዜጋ አንዱን ሁለተኛ ዜጋ ሳያደርግ የሚያስችል ስርአት መፍጠር ነው። ይሄ ስላልሆነ “ከአማራ በስተቀር ሌሎች በብሄር ስለተደራጁ ብቸኛ ከተለያየ ብሄር የተቀላቀልነው ሃገር ኖሮን ለመኖር የምንችለው አማራ የለም ብለን አማራው እየጠፋም አማራው ሳይደራጅ ኢትዮጵያ የሚለው ስም ይቆይልን” የሚለው አያስኬድም፤ አማራ ከጠፋ ኢትዮጵያም ትጠፋለችና። ይልቅስ “አማራውም ሌላውም ብሄር አለ፤ የተቀላቀሉም ብሄሮች አሉ፤ ስለሆነም አሁን ያለው ስርአት ለሁሉም መብት ስለማይሰጥ ልክ አይደለም” ብላቹ ስርአቱን ተቃወሙ እንጂ “አማራ የለም” በሚል ስርአቱ ሊያጠፋው የወሰነበት አማራ ላይ ሌላ አጥቂዎች አትሁኑ።

በተመሳሳይ መልኩ “በብሄር ተደራጅተን ብሄራችን ተጠርቶ እንኑር” ያላቹም እሰየው ቀጥሉ። ግን እናንተ የረገጣቹትን ሁሉ “የኛ” ብላቹ በሚሊዮን የሚቆጠር አማራ “ያለክልሉ የሚኖር” አስብላቹ እየገደላቹ እያሰደዳቹ፤ እናንተ “በአማርኛ አንማርም፣ አንሰራም፣ ቋንቋችን ስላልሆነ” ብላቹ በሚሊዮን የሚቀጠር አማራን በናንተ እንዲማር እንዲሰራ አስገድዳቹ፤ አማራው ባልተወከለበት የአፓርታይድ ድንበር አበጅታቹ፣ ምን አይነት እኩልነት እንደምታወሩ አይገባኝም። ስለዚህ እኩልነት ከተባለ አማራውም እኩል መብቱ የተከበረበት እና በገዛ ሃገሩ በሌሎች መልካም ፍቃድ ሳይሆን ሃገሩ ስለሆነ በራሱ መልካም ፍቃድ የሚኖርበት ሁኔታ እስካልተፈጠረ ምንም እኩልነት እንደሌለ እወቁት። እኩልነት ከሌለ ደሞ አመፅ፣ ጦርነት፣ ሞት ይቀጥላል። ይሄንን ደሞ የደም ጥማት ያለበት ሰይጣን ካልሆነ ሰው ይፈልጋል ብዬ አላስብም።

አማራው መውሰድ ያለበት እርምጃ መጀመሪያ መደራጀት ፤ በዚህ ሰአት “አማራ አለ፣ የለም” ብሎ የሚከራከሩትን ጅሎች ረስቶ፣ እንዲሁም የአማራ መደራጀት ለኢትዮጵያ መጥፋት ሳይሆን ለኢትዮጵያም ለአማራም እንደሚበጅ አስረግጦ፣ አማራ ተደራጀ ማለት ትህነግ እና ኦነግ ከኤህነግ ጋር ሆነው ያንተ ነው ብለው የሰሩለትን ድንበር ይቀበላል ማለት እንዳልሆነ ታውቆ፤ ከላይ እንዳልኩት የሁሉም ኢትዮጵያዊ መብት ተከብሮ አብረን እንኑር በሚለው ሃሳብ ይስማማል። ይሄንን እምቢ ብለው “አሻፈረኝ ደም የማፍሰስ አባዜ አለብን” ብለው “እኩል ሳይሆን የበላይ መሆን አለብን” ብሎ፤ “የኛ መሬት ሳይሆን የኔ ብቻ ነው” ብሎ ከገፋ መደራጀትህ ለመቼ ነውና ተገደህ ደም አፍስሰህ ያባቶችህን ድንበር አስከብረህ የ 3000 አመት ሌሎች አንፈልግም ያሉትን የኢትዮጵያ ታሪክን ተረካቢ መሆንህን አረጋግጠህ ለመኖር መቁረጥ ነው። ከዚህ ውጪ ስትልመሰመስ ምክንያት ስትደረድር ብትኖር የበለጠ መቀበሪያ ጉድጓድህን ትልቅ ታደርጋለህ እንጂ ለአማራም ለኢትዮጵያም አይበጅም።

አሁን እነ ፕ/ር መስፍን፤ ፕ/ር ጌታቸው ወይንም ሌሎች “ወይ አማራ ከተደራጀ ኢትዮጵያ ትፈርሳለች” የሚሉ ወይን ገፍተው “እንዲያውም አማራ የለም” የሚሉትን ትልቁን ስህተታቸውና ጦሱ በተለይ ለድሃው የሚያተርፈውን በዚህ መልኩ ላሳጥረው፥ ቢሆን ቢሆን የሁሉም ብሄር መብት ተከብሮ “ብሄር መጥራት መውረድ ነው” ለሚሉም “ኢትዮጵያዊ ብቻ” ብለው ራሳቸውን “ኢትዮጵያዊ” ብለው በተመሳሳይም ብሄሬ ይጠራ ለሚለውም በምርጫው ብሄሩ ሲፈልግ መታወቂያው ላይ ተፅፎለት (ምርጣው እስከሆነ) ለሁሉም ዜጋ መብት ተከብሮ የምንኖርባት ሃገር ቢኖረን ምንኛ ደስ ባለን። ይሄ ግን ትህነግ ስልጣን ላይ እያለና ከሱ በኋላ ለመተካት የሚንደረደሩትም ተመሳሳይ አቋም እስካላቸው ህልም ነው። ስለዚህ “አማራ ቢሸፍት እስከኢትዮጵያዊነት” ነውና አማራው ኢትዮጵያዊነቱን ሳይተው ኢትዮጵያ ሁሉም በእኩልነት የሚያምን በውስጥዋ ያለ ህዝብ ሁሉ ሃገር መሆንዋን ተቀብሎ ተደራጅቶ ራሱን ማዳን ነው። አማራው ከተደራጀ አሁን እንዲህ ያዙኝ ልቀቁኝ የሚለው ሁሉ ለመነጋገር ዝግጁ ይሆናሉ። አሁን ግን ማንን አይተው ማንን ፈርተው? “ኢትዮጵያ ውስጥ እኩልነት ይስፈን” ስንልም ሆነ “የብሄር ብሄረሰቦች እኩልነትይስፈን” ስንል ሰምተውን “አማራንም ይህ እኩልነት ይመለከተዋል” ይላሉ። አለም ጉልበት ላለው እንደምታሸረግድ አትርሱ። ስለዚህ አማራው ካልተደራጀ በአማራው ደም ሁሉም ጎጆውን እስኪያቀና ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር ስምዋ ብቻ ይቆያል። በዚህም አያበቃም ሁሉም በውስጡ ያሉትን በተለይ አማራውን እያጸዳ አዲስ ሃገር ለመስራት እየተንደረደሩ ስለሆነ ግፋ ቢል የድንበር ግጭት ይጠብቃቸዋል እንጂ ኢትዮጵያ ከተበታተነች እንደ ትንሽ ሃገር መቆም ይችላሉ። አማራ ግን ልክ ኤርትራ የተባለችው ለኢትዮጵያ እንዲህ የቤት ስራ ሰጥታን እንደምትስቅብን ትህነጎችም ሸርፈው ሸርፈው የአማራ ብለው ከልለው ያስቀሩት ወደፊት እንክዋን ትንሽ ሃገር ሆኖ መቆም እንዳይችል ልዩ ዞን እያሉ፤ ትንንሽ ቁጥር ያላቸውን ሌላ የከለሉት ውስጥ ሳያደርጉ “አማራ” ብለው የከለሉት ውስጥ በመስራት ረዥም የቤት ስራ እየሰጡን ነው። ሲጀመር አማራ በሌለበት ስለሆነ የተከለለው አማራን ተሸፍሽፎ የቀረ 4ቱ ክፍለ ሃገራት ላይ ብቻ ትህነግ እንደወሰነው እንዳለ ሆኖ አማራ ብለው ከከለሉት እንዳያቹት ጎንደርን ትግሬ፣ ቅማንት፣ ሌላም እያሉ ያፋርሱታል። ጎጃምን አገው፣ ቤኒሻጉል፣ አማራ ብለው ያፋርሱታል። አንጎትን/ላኮመልዛን (አሁን ወሎ) አገው፣ ትግሬ፤ኦሮሞ፣ አማራ ብለው ያፋልሱታል። ሸዋን አማራ፣ ኦሮሞ፣ ወዘተ ብሎ አጣልቶ እንዳያቹት አማራ ብሎ የከለለው ቦታ ሁሉ ግጭት ፈጥሮ መጨረሻ ይቺንውንም እንክዋን ሳይኖረን አማራ ተበትኖ ጠፍቶ ታሪክ ሊያደርጉን እየሰሩ ነው (አስታውሱ እነ ሃረር፤ ባሌ፤ ፈጠጋር፤ እናራያ እነሱ ባይሉም ሃገራችን እንደሆነ ግን ጠንቅቀን እናውቃለን)። ልብ በሉ ልክ ዩጎዝላቪያ ላይ ሰርቦች ላይ የምእራባዊያን ዱላ እንደበረታ ችግር ቢነሳ አማራ ላይ ከምእራባዊያን ዱላ እንደሚበረታ እንዳትረሱ። ሰርቦችን በመጨረሻ ዩጎስላቪያ የሚለውን ስም እንክዋን እንዳይጠቀሙ ተከልክለዋል። ምን ይታወቃል ኢትዮጵያ ድንበርዋ ሲሰፋ ሲጠብ ኖርዋል ብለን አነስ ያለች ኢትዮጵያ ይኑረን እንክዋን ብንል ኢትዮጵያ የሚለው የነፃነት ነፀብራቅ ስሙ ስለሚያማቸው አገራቸውን ዩጎስላቪያ እንዳይሉ እንክዋን እንደተከለከለት ኢትዮጵያ የሚለውን ስም እንክዋን መጠቀም መከልከል ሊጠብቀን እንደሚችልም አትዘንጉት። ስለዚህ አማራ ጠላቱ ብዙ ሆኖ ሳለ በገዛ ህዝቦቹ እንዳይደራጅ ሰንካላ እየተፈጠረበት ከቆየ አይደለም ኢትዮጵያ አማራ በራሱ እንደህዝብ መቀጠሉ ጥያቄ ውስጥ ይገባል እና ልብ ያለው ልብ ይበል። እናማ የአማራ ምሁር ነን የምትሉ አስቡበት።

እባካቹ ይቺን ፅሁፍ የፖለቲካ ብላቴና ምላሽ ብሎ ፅፎላቹሃል ብላቹ ለፕ/ር መስፍን እና ለፕ/ር ጌታቸው ላኩልኝ። የፌስ ቡክ ተከታያቸው ስላልሆንኩ ለነሱ መላክ አልችልምና።

ወገን መጀመሪያ አስተሳባችንን እናጽዳ እንጂ ፖለቲካን የልጅነት ህመማችንን እና ያለብንን የስነልቡና ችግር የምናድንበት፤ ወይንም ላንዳንዶቹ ደግሞ የሃብት ማግኘት ጥማት ፍላጎታቸውን ማርኪያ፤ በሌሎች ደም ሃብት ለማካበት የምንጠቀምበት ዘዴ አናድርገው። መነሻውን መድረሻውን በግልፅ ያላስቀመጠ፤ ሊነሱ የሚችሉ ጥያቄዎችን እና ቅሬታዎችን በግልፅ አቅርበን ሳንወያይ እንዲያው በድፍንፍኑ “አንድ ላይ ነን” ብለን ውጤታማ እንሆናለን ማለት ዘበት ነው። ስለጋና ዲያስፖራዎች ስለሃገራቸው ምን እንዳደረጉ እና አሁን ለሰፈነው አንጻራዊ ዲሞክራሲ በምን ውስጥ እንዳለፉ ምን እርምጃ እንደተወሰደ እንድታነቡ ጋብዤ ልሰነባበት።

ጆሮ ያለው ይስማ!

አበበ ተድላ

The post ዶሮ ብታልም ስለጥሬዋ | ለፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ እና ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም ‘አማራ የሚባል ሕዝብ የለም’ አባባል የተሰጠ ምላሽ appeared first on Zehabesha Amharic.

እነ ሀብታሙ አያሌው በጠቅላይ ፍ/ቤት የቃል ክርክር አደረጉ |አብርሃ ደስታ “ጭቆናን ካላጋለጥኩ ምኑን ተቃዋሚ ሆንኩት?”አብርሃ ደስታ

$
0
0

‹‹እኔ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል እንደመሆኔ መጠን የኢህአዴግን ጭቆና ማጋለጥ ግዴታዬም መብቴም ጭምር ነው! ይህን ካላደረጉ ምኑን ተቃዋሚ ሆንኩ?›› አብርሃ ደስታ

‹‹እኔ አሸባሪ አይደለሁም! የታሰርኩት በኢህአዴግ የፖለቲካ ሴራ ነው! እኔ የፖለቲካ እስረኛ ነኝ!›› ዳንኤል ሺበሺ

Abrha-Desta-Yeshiwas-Assefa-Daneil-Shibeshi-Habtamu-Ayalew

ኢዩኤል ፍሰሃ ዳምጤ በፌስቡክ ገጹ እንደዘገበው:-

በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረው በሥር ፍ/ቤት ውሳኔ በነፃ የተሰናበቱት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች የሆኑት አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ አቶ አብርሃ ደስታ፣ አቶ ዳንኤል ሺበሺ፣ አቶ የሺዋስ አሰፋና በተመሳሳይ የክስ መዝገብ ውስጥ ከአመራሮቹ ጋር የተከሰሰው አቶ አብርሃም ሰለሞን በፌደራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ዛሬ ታህሳስ 15 ቀን 2008 ዓ.ም በመቅረብ የቃል ክርክር አድርገዋል፡፡

በችሎቱ የተሰየሙት ግራ ዳኛ መዝገቡ ለዛሬ የተቀጠረው ታህሳስ 8 ቀን 2008 ዓ.ም ተከሳሾቹ የፍ/ቤቱ ሰብሳቢ ዳኛ የሆኑት አቶ ዳኜ መላኩ ከሰብሳቢነታቸው እንዲነሱ ባቀረቡት የፅሁፍ አቤቱታ ላይ መልስ ለመስጠት፤ የተከሳሾቹንና የአቃቤ ሕግን የቃል ክርክር ለማድመጥ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ተከሳሾቹ ‹‹ሰብሳቢው ዳኛ ይነሱልን!›› ብለው ያቀረቡት ጥያቄ ፍ/ቤቱ ስላላመነበት ውድቅ መደረጉን ገልፀዋል፡፡

አቃቤ ሕግ በችሎቱ ባቀረበው የይግባኝ አቤቱታው ተከሳሾቹ ከግንቦት ሰባት አመራር አባላት ጋር በተለያየ ጊዜ መገናኘታቸውን፤ ይህንንም የሚያስረዳ ማስረጃ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት ኤጀንሲ ማቅረባቸውን ነገር ግን የስር ፍ/ቤቱ እነዚህን ማስረጃዎች ሳይመዝን ‹‹በደፈናው ውሳኔ ስለሰጠ›› ይግባኝ መጠየቃቸውንና የስር ፍ/ቤቱ ውሳኔ ሲሰጥ ከጭብጥ መውጣቱን ገልጿል፡፡ ‹‹ፍ/ቤቱ ከፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ አንቀፅ 23 መሰረት የቀረበውን የሰነድ ማስረጃዎች በመመልከት የስር ፍ/ቤት ውሳኔን በመሻር ተከሳሾቹ የቀረበባቸውን ክስ እንዲከላከሉ ፍ/ቤቱ ይወስንልን ዘንድ እንጠይቃለን›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

1ኛ ተከሳሽ አቶ ሀብታሙ አያሌውና 5ኛ ተከሳሽ አቶ አብርሃም ሰለሞን በጠበቃቸው አምሃ መኮንን በኩል የመከራከሪያ ሃሳባቸውን አቅርበዋል፡፡ አቶ አምሃ መኮንን የስር ፍ/ቤቱ ደምበኞቻቸውን በነፃ ሲያሰናብታቸው የቀረቡትን ማስረጃዎች መዝኖ መሆኑን ለችሎቱ አስረድተዋል፡፡ አቃቤ ሕግ በክሱ ላይ ያቀረባቸው ነገሮች እንደመረጃ እንጂ እንደማስረጃ ሊያዙ እንደማይገባ የተከሳሾቹ የቀድሞ ጠበቃ በስር ፍ/ቤት ክርክር አድርገው የስር ፍ/ቤቱ ሐምሌ 2 ቀን 2007 ዓ.ም ‹‹በማስረጃ ሊያዙ ይገባል!›› ብሎ ብይን ማስተላለፉን አቶ አምሃ አውስተዋል፡፡ ጠበቃው ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት ኤጀንሲ በኩል የሚቀርቡ ማስረጃዎችም ፍ/ቤት ሊመረምራቸው እንደሚገባ ሲያስረዱ፡- ‹‹የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ኤጀንሲ በኩል የሚቀርቡ መረጃዎችን ፍ/ቤቱ ሙሉ ለሙሉ የሚቀበል ከሆነ የፍ/ቤቱ ሚና ምን ሊሆን ነው? ፍ/ቤቱ ከተቋሙ በኩል የሚቀርቡለትን መረጃዎች ሙሉ ለሙሉ የሚቀበል ከሆነም ፈራጁ ፍ/ቤት ሳይሆን ብሔራዊ መረጃና ደህንነት ኤጀንሲ ነው›› በማለት አስተያየታቸውን ሰንዝረዋል፡፡

ደምበኛቸው አቶ ሀብታሙ አያሌውም በክሱ ላይ ‹‹ዘመነ ካሴ›› ከተባለው የግንቦት ሰባት አባል ጋር በመነጋገር አብረው ለመስራት ተስማሙ ተብሎ ቢገለፅም ይህን የሚያስረዳ ማስረጃ አለመቅረቡን ገልፀዋል፡፡ ደምበኛቸው ከግለሰቡ ጋር ባደረጉት የስልክ ልውውጥ አንድም ቦታ ላይ አብረው ለመስራት መስማማታቸውን እንዳልገለፁ ጠበቃው ጠቁመዋል፡፡ በክሱ ላይ የአንድነት ፓርቲ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ የሆነው አቶ ሀብታሙ አያሌው ከዘመነ ካሴ ጋር ግንኙነት አደረጉ ተብሎ የተገለፀው ከእውነታ የራቀ መሆኑን ጠበቃው ገልፀዋል፡፡ በተጠቀሰው ጊዜ አቶ ሀብታሙ አይደለም የአንድነት ፓርቲ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሊሆኑ ቀርተው፤ የፓርቲው አባል እንዳልነበሩም አቶ አምሃ አስረድተዋል፡፡ አቶ ሀብታሙ በበኩላቸው በክሱ ላይ ተከሳሽ በዚህ የሞባይል ቁጥር ግንኙነት አድርጓል ተብሎ አለመገለፁን የስልክ ልውውጡም ምን እንደሆነ የሚያስረዳ አንዳች ነገር አለመቅረቡን ለፍ/ቤቱ አስረድተዋል፡፡

አቶ አምሃ ደምበኛቸው በሆነው 5ኛ ተከሳሽ አቶ አብርሃም ሰለሞን ላይ ምንም አይነት የሰነድ ማስረጃ አለመቅረቡን የግንቦት ሰባት አባል ነው ሲባልም፤ በግንቦት ሰባት መዋቅር ውስጥ እንዳለ የሚያሳይ ማስረጃ አለመቅረቡን ደምበኛው በምንም አይነት የሽብርተኝነት ተግባር ላይ እንደተሰማራ የሚገልፅ ምንም አይነት ማስረጃ አለመቅረቡን ገልፀዋል፡፡ አቶ አብርሃም ሰለሞን በበኩሉ ያለአንዳች ማስረጃ መታሰሩን ሲያስረዳ፡- ‹‹ከታሰርኩ በኋላ ነው ማስረጃ ሲፈለገብኝ የነበረው፤ ከታሰርኩ በኋላም ቤቴ እንኳ አልተፈተሸም፡፡ መንግስት አሰረኝ ብዬ አላምንም ያሰረኝ አንድ ግለሰብ ነው›› ሲል ተደምጧል፡፡

2ኛ ተከሳሽ አቶ ዳንኤል ሺበሺ፣ 3ኛ ተከሳሽ አቶ አብርሃ ደስታና 4ኛ ተከሳሽ የሺዋስ አሰፋ ያለጠበቃ በመቆም በግል ክርክራቸውን ያካሄዱ ሲሆን፤ ሶስቱም ተከሳሾች የአቃቤ ሕግ የይግባኝ ማመልከቻ ላይ እነሱን የሚመለከት ቅሬታ አለመቅረቡን ለፍ/ቤቱ ገልፀዋል፡፡ አቶ ዳንኤል ሺበሺ ‹‹እኔ አሸባሪ አይደለሁም! የታሰርኩት በኢህአዴግ የፖለቲካ ሴራ ነው! እኔ የፖለቲካ እስረኛ ነኝ!›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ የቃል ክርክር ለማድረግ ያዘጋጁት ወረቀትም በማረሚያ ቤቱ እንደተቀደደባቸው ለፍ/ቤቱ አሳይተዋል፡፡ ወረቀቱ ማህተም የተደረገበት ቦታ ተቀዶ መውጣቱን በችሎቱ ለነበሩ ታዳሚያን በግልፅ ታይቷል፡፡

3ኛ ተከሳሽ አቶ አብርሃ ደስታም ከታሰሩ በኋላ ማስረጃ ሲፈልግባቸው እንደነበርና በብሔራዊ መረጃና ደህንነት ኤጀንሲ የሚቀርብ መረጃ በፍ/ቤት ሳይመዘን ሙሉ ለመሉ ተቀባይነት የሚያገኝ ከሆነ ተቋሙ ከሳሽም፣ መስካሪም፣ ዳኛም ሆነ ማለት ነው፡፡ ይህ ከሆነ ዘንድ ደግሞ ፍ/ቤት መምጣትም አያስፈልግም ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ በክሱ ላይ ለኢሳት ቴሌቪዥን ቃለምልልሰ ሰጠ ተብሎ የቀረበው ክስ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ሲያስረዱ፡- ‹‹እኔ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል እንደመሆኔ መጠን የኢህአዴግን ጭቆና ማጋለጥ ግዴታዬም መብቴም ጭምር ነው! ይህን ካላደረጉ ምኑን ተቃዋሚ ሆንኩ?›› በማለት ለፍ/ቤቱ የገለፁ ሲሆን፤ በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ በመቅረብ ሃሳባቸውን ሲገልፁ የነበሩትም የኢህአዴግን ጭቆናን ማጋለጥ መብታቸው በመሆኑ እንደሆነ ለፍ/ቤቱ አስረድተዋል፡፡

4ኛ ተከሳሽ አቶ የሺዋስ አሰፋ በእሳቸው ላይ የቀረበ አንድም የሰው ምስክር እንደሌለ ገልፀው፤ ማዕከላዊ በነበሩበት ወቅትም በምርመራ ላይ አንድም ቀን ስለግንቦት ሰባት ተጠይቀው እንደማያውቁ ምርመራ ላይ ሲጠየቁ የነበሩትም ስለ ሰማያዊ ፓርቲ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ አቶ የሺዋስ የሰማያዊ ፓርቲ አባል በመሆናቸው ብቻ አያሌ መከራዎችን እየተጋፈጡ እንደሚገኙ ለፍ/ቤቱ አስረድተዋል፡፡ ያለፉትን 6 ወራት በማንም አለመጎብኘታቸውን ለፍ/ቤቱ ገልፀዋል፡፡

ፍ/ቤቱ የቃል ክርክሩ በፅሁፍ ተገልብጦ ከቀጣይ ቀጠሮ በፊት ከመዝገቡ ጋር ተያይዞ እንዲቀርብ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ 1ኛ ተከሳሽ አቶ ሀብታሙ አያሌው የሚገኙበት የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ተከሳሹ ባቀረቡት አቤቱታ ላይ ታህሳስ 19 ቀን 2008 ዓ.ም መልስ እንዲሰጥ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ የማረሚያ ቤት ተወካዩ በተጠቀሰው ቀን አቶ ሀብታሙን ይዞ እንዲቀርብ ፍ/ቤቱ አዟል፡፡

የፌደራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክር መዝኖ ውሳኔ ለመስጠት ለታህሳስ 29 ቀን 2008 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ እነ ሀብታሙ አያሌው ነሐሴ 14 ቀን 2008 ዓ.ም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ከተመሰረተባቸው የሽብርተኝነት ክስ መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ እንዲሰናበቱ ውሳኔ ማስተላለፉ አይዘነጋም፡፡

The post እነ ሀብታሙ አያሌው በጠቅላይ ፍ/ቤት የቃል ክርክር አደረጉ | አብርሃ ደስታ “ጭቆናን ካላጋለጥኩ ምኑን ተቃዋሚ ሆንኩት?” አብርሃ ደስታ appeared first on Zehabesha Amharic.

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን የመሰጠቱን ጉዳይ ዳግም አረጋገጡ |ንግግራቸው የሱዳን ጠ/ሚ/ር አስመስሏቸዋል

$
0
0

”በታሪካችን ያላየነው ረሃብ ላይ ነን” አቶ ኃይለ ማርያም

(ጉዳያችን ዜና)

ከግማሽ ክፍለዘመን በላይ ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ፓርላማ ማማ

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ዛሬ ታህሳስ 15/2008 ዓም በኢትዮጵያ ፓርላማ ቀርበው በሰጡት ማብራሪያ ላይ በተለይ በኦሮምያ ክልል ለተነሳው ሕዝባዊ አመፅ እና በሱዳን እና በኢትዮጵያ መካከል ስላለው የድንበር ጉዳይ ላይ  የተለመደ አወዛጋቢ እና የበለጠ አወሳሳቢ ንግግሮችን ተናግረዋል።
hailemariam
በኦሮምያ የተነሳውን ሕዝባዊ አመፅ ችግሩን፣መነሻውን እና መፍትሄውን የጠቆሙበት አገላለፅ የእራሳቸውን እና የመንግስታቸውን መፍትሄ ቢስነት በአደባባይ በድጋሚ ያጋለጠ ነው።ችግሩ ገበሬው መረጃ አለማግኘቱ ነው ማለታቸው እና በውጭ ኃይሎች ቅስቀሳ ነው የሚለው እርስ በርሱ የተቃረነ አነጋገር በእራሱ ለእራሳቸውም በአግባቡ የገባቸው አይመስልም።ችግሩን መንግስት ስለ ፕላኑ አለመንገሩ ነው ያሉት እና አሁን መንግስታቸው እያናገረ ያለው በጥይት መሆኑን ለሚያስተውለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ንግግራቸው በሕዝቡ ላይ ከመዘባበት ያለፈ አንዳች የሚሰጠው ፋይዳ የለም።በመፍትሄነት ያስቀመጡትም ምንም አዲስ ነገር የሌለው እና አሁንም መልሰን እንነግረዋለን የሚለው አባባል ንግግሩ በጥይት እንደሆነ አመላካች ነው።ሕዝብ የሚባለው እና የሚደረገው ስላልገባው ነው የሚለው አባባል በእራሱ ለሕዝብ ያለን የንቀት ደረጃ አመላካች ነው።በሰላማዊ ሰልፍ እጆቻቸውን ወደ ሰማይ እየሰቀሉ ድምፃቸውን ያሰሙ ታዳጊዎችን በጥይት አረር ከመቱ (እንደ አቶ ኃይለማርያም አነጋገር ‘ካናገሩ’) በኃላ አሁንም እናናግራለን እያሉ መዘባበት በእራሱ ህዝብን የአላዋቂነት ጥግ ነው።
በሌላ በኩል የሱዳን እና የኢትዮጵያን የድንበር ማካለል ጉዳይ ላይ የጀመሩበት አረፍተ ነገር እና በመካከል እና በመጨረሻ ላይ የደመደሙበት ንግግር ኢትዮጵያ በእዚህ አይነት ደረጃ የባዕዳንን ጉዳይ የሚያስፈፅም መንግስት ኖሯት እንደማያውቅ በግልፅ የሚያሳይ ነው።
”በመሬት ጉዳይ ላይ የተደረገ ድርድር የለም። በኢትዮጵያ እና በሱዳን መሃል ያለው ድንበር በደንብ ስላልተስተካከለ በእርሱ ላይ ነው እየሰራን ያለነው” ካሉ በኃላ የሱዳን ጠቅላይ ሚንስትር የሚናገሩ እስኪመስል ድረስ የኢትዮጵያን ክብር በሚነካ መልኩ ሱዳንን እየረበሽን ያለነው የእኛ ገበሬዎች ናቸው።አሁን የሚያርሱት መሬት የሱዳን መሬት ነው ብለው ለመከራከር ሞክረዋል።ይህ ማለት ባጭሩ ኢትዮጵያውያን ለዘመናት ሲያርሱት የነበረው መሬት በእራሳቸው አገር ጠቅላይ ሚኒስትር መሬቱ የሱዳን ነው እየተባሉ ነው ማለት ነው።በተለይ የሱዳን ወታደሮች ለስራ በወሰዷቸው ኢትዮጵያውያን ላይ ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ ብቻ እጅግ አሰቃቂ በሆነ መንገድ ስለመገደላቸው አንዳች ያልተነፈሱት አቶ ኃይለማርያም ይልቁንም የኢትዮጵያን ገበሬዎች በሱዳን ተገብተው ሲወቅሱ እንዲህ ብለዋል-
”ከእኛ አካባቢ እየሄዱ ሱዳናውያንን እየገደሉ የሚመለሱ” እንደሳቸው አገላለጥ ”ሽፍቶች”ናቸው ሲሉ ተደምጠዋል።በመቀጠል አቶ ኃይለማርያም እንዲህ አሉ: ”በርካታ ኪሎ ሜትሮች ሱዳን ውስጥ ገብተው የሚያርሱ እኛ የምናውቃቸው ኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮች እና ባለሀብቶች አሉ”  በማለት እነኝህ መሬቶች ለጊዜው ለሱዳን አይሰጡ እንጂ የሱዳን መሆናቸውን ባረጋገጡበት ንግግራቸው በቀጣዩ የድንበር ማካለልም መንግስታቸው የሱዳን መሆናቸውን እንደሚያውቅ አሁንም እንደ ኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ሳይሆን እንደ ሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትርነት ሲናገሩ ተደምጠዋል።
ባጠቃላይ ድንበሩን በተመለከተ ከተናገሩት መረዳት የሚቻለው ሁለት ጉዳይ ነው።አንዱ ኢትዮጵያ እና ሱዳን የድንበር ማካለል ሂደት ላይ ናቸው የሚለው ዜና ትክክል መሆኑን።በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ አሁንም እንደ ኢትዮጵያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳይሆን በሱዳን ወገን ተገብተው የኢትዮጵያን ገበሬዎች እና ባለ ሀብቶች የሱዳንን መሬት አረሱ እያሉ ይህ መሬት ለሱዳን እንደሚገባ በአንደበታቸው ሲናገሩ ተሰምቷል።በሌላ አነጋገር ለብዙ ትውልዶች መሬቱን ሲያርሱ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ከመሬታችን አንነቀልም ካሉ ከሱዳን ወታደሮች ጋር ተባብረው ገበሬዎቹን እና ባለ ሀብቶቹን የማባረር ሥራ እንደሚሰራ እየገለጡ ነው ማለት ነው።ምክንያቱም በአደባባይ መሬቱ የኢትዮጵያን አይደለም።ለጊዜው ነው ሱዳኖች የፈቀዱልን ካሉ በኃላ ይህንንም የሱዳን ውለታ መሆኑን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ለማስረዳት ሲውተረተሩ ተሰምተዋል።

በመጨረሻም አቶ ኃይለማርያም ”በምግብ እራሳችንን ችለናል” ብለው በተናገሩ በወራት ውስጥ በዛሬው እለት ደግሞ ካለ አንዳች እረፍት ”የገጠመን ድርቅ በታሪካችን ምናልባትም ባለፉት ሃምሳ ዓመታት ውስጥ አይተነው የማናውቅ በእኔ አመለካከት እጅግ የከፋ ድርቅ ነው” ሲሉ ተደምጠዋል።ለድርቁ የሰጡት መፍትሄ ግን የበለጠ አስቂኝ ነው።መፍትሄዎቹ የሚመጡ እርዳታዎችን መቀበል እና የውሃ ጉድጓድ በመቆፈር ነው ይላሉ አቶ ኃይለማርያም።ጥያቄው ግን  ከእሩብ ክ/ዘመን አምባገነናዊ እና የከፋፍለህ ግዛ የኢህአዴግ/ህወሓት አገዛዝ በኃላ ኢትዮጵያ በታሪክ ያላየችው ርሃብ ላይ ነች ማለት እና የውሃ እጥረት ችግር ለሆንባት አገር የውሃ ጉድጓድ መቆፈር መፍትሄ ነው ማለት ምን አይነት የአስተሳሰብ ድህነት ነው? የሚል ነው።ባጭሩ አቶ ኃይለማርያም ህወሃቶች ስልጣን እንዲለቁ እና የሽግግር መንግስት እንዲመሰረት ሿሚዎቻቸውን ቢመክሩ እና የመሸበት ቢያድሩ የተሻለ ነው።

ጉዳያችን GUDAYACHN
ታህሳስ 15/2008 ዓም (December 25/2015)

The post አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን የመሰጠቱን ጉዳይ ዳግም አረጋገጡ | ንግግራቸው የሱዳን ጠ/ሚ/ር አስመስሏቸዋል appeared first on Zehabesha Amharic.

ኃይለማርያም ደሳለኝ በፓርላማው ስለኦሮሞ ሕዝብ ወቅታዊ ጥያቄ ያደረጉት ንግግር –“ተቃውሞ ያነሱትን እንደከዚህ ቀደሙ እናደርጋቸዋለን”| Video

$
0
0


enqilf Hailemariam
ኃይለማርያም ደሳለኝ በፓርላማው ስለኦሮሞ ሕዝብ ወቅታዊ ጥያቄ ያደረጉት ንግግር – “ተቃውሞ ያነሱትን እንደከዚህ ቀደሙ እናደርጋቸዋለን”| Video

The post ኃይለማርያም ደሳለኝ በፓርላማው ስለኦሮሞ ሕዝብ ወቅታዊ ጥያቄ ያደረጉት ንግግር – “ተቃውሞ ያነሱትን እንደከዚህ ቀደሙ እናደርጋቸዋለን”| Video appeared first on Zehabesha Amharic.

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃዥተዋል “መሬት ቆርሰን አልሰጠንም…ነገር ግን ሱዳን ድንበር ውስጥ ገብተው የሚያርሱ የኢትዮጵያ ገበሬዎች አሉ”|ቪዲዮ

$
0
0

ዛሬ ፓርላማ ላይ የቀረቡት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ “ድንበር ቆርሰን አልሰጠንም… ግን በሱዳን መሬት ውስጥ ገብተው እያረሱ ያሉ የኢትዮጵያ ገበሬዎች አሉ” ሲሉ ተናገሩ:: በቅርቡ የድንበር ማካለል እናደርጋለን ያሉትና የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስተር ሆነው የቀረቡት አቶ ኃይለማርያም በሱዳን መሬት ላይ ገብተው እያረሱ ያሉትን ባለሃብቶች ድንበሩ እስከሚካለል ድረስ አትንኩብን ስንል የሱዳን መንግስትን ጠይቀናል ብለዋል:: ቭዲዮውን ይመልከቱ::

Hailemaria

The post ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃዥተዋል “መሬት ቆርሰን አልሰጠንም… ነገር ግን ሱዳን ድንበር ውስጥ ገብተው የሚያርሱ የኢትዮጵያ ገበሬዎች አሉ” | ቪዲዮ appeared first on Zehabesha Amharic.

“እንኳን ኃይለማርያም ይቅርና ነባሮቹ የብአዴን መሪዎች እነበረከትና አዲሱ እንኳ ከኤርትራና ሱዳን ጉዳይ የተገለሉ ነበሩ”ያሬድ ጥበቡ

$
0
0

Yared Tibebu

(ዘ-ሐበሻ) ትናንት አርብ በኢትዮጵያ ፓርላማ ቀርበው ስለኢትዮ-ሱዳን አወዛጋቢ የድንበር ማካለል ጉዳይ መግለጫ የሰጡት ሕወሓት የሚመራው መንግስት ጠቅላይ ሚ/ር ኃይለማርያም ደሳለኝ በድንበሩ ጉዳይ ያደረጉት ንግግር አነጋጋሪነቱ እንደቀጠለ ነው:: በርሳቸው ንግግር ዙሪያ የቀድሞው ኢህዲን (ብአዴን) ታጋይ የነበሩትና በአሁኑ ወቅት በሜሪላንድ አሜሪካ የሚገኙት ያሬድ ጥበቡ በፌስቡክ ገፃቸው ኃይለማርያም ዛሬ ካሰሙት ንግግር በኋላ ገስጸዋቸዋል::
“እንኳን እርሳቸው፣ ነባሮቹ የብአዴን መሪዎች እነበረከትና አዲሱ እንኳ ከኤርትራና ሱዳን ጉዳይ የተገለሉ ነበሩ” ያሉት አቶ ያሬድ ኃይለማርያም ከዚህ ጉዳይ እጃቸውን እንዲያወጡ መክረዋል::

የያሬድ ጥበቡ አስተያየት እንደወረደ ይኸው:-

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የሱዳን ኢትዮጵያን ወሰን ጉዳይ በታላቅ ጥንቃቄ ቢያዩትና፣ ምክርቤቱ ውስጥ የሰጡት አይነት የኢትዮጵያን አራሾች በድንበር ገፊነትና፣ በሽፍትነት የመሳል ምስክርነት ቢቆጠቡ ተመራጭ ነው ። አለመግባባቱ ወደፊት ወደአለምአቀፍ አርቢትሬሽን ቢላክ ይህ ቪዲዮ የሱዳኖችን የይገባኛል ጥያቄ የሚያጠናክርና ኢትዮጵያን የሚጎዳ በመሆኑ፣ ከዚህ መሰል ምስክርነት ቢቆጠቡ ተገቢ ነው ። በሁለተኛ ደረጃ፣ አቶ ኃይለማርያም ለኢህአዴግ መጤ መሆናቸውን መረዳት አለባቸው ። እንኳን እርሳቸው፣ ነባሮቹ የብአዴን መሪዎች እነበረከትና አዲሱ እንኳ ከኤርትራና ሱዳን ጉዳይ የተገለሉ ነበሩ። በወያኔ ፖሊትቢሮ ብቻ የተያዘ የውስጥ ጉዳይ ነበር ። በወያኔ 40ኛ አመት በአል ላይ መቀሌ ላይ ንግግር ያደረገው ሱዳናዊ፣ ” እኔም ወያኔ ነኝ” ብሎ ከፈከረ በኋላ፣ መለሰ ለመጨረሻው ከደርግ ጋር ድርድር ወደ ለንደን ከማቅናቱ በፊት፣ ካርቱም ላይ ፕሬዚደንቱ ቢሮ መሬት ላይ ፈርሸው ስላደረጓቸው ውይይቶች የነበረውን ትዝታ አካፍሏል ። በዚያ ወቅት፣ የጋራ ጠላታቸው የሆነውን የአማራ ህዝብ ለማዳከም መለስ የገባው ቃል ሊኖር ይችላል ። ምናልባትም አዲሱን መንግስት በማቋቋም ስም ወያኔ ከሱዳን የበላው መሃያ ሊኖርም ይችላል። ብዙ ያልተፈተሹና የማናውቃቸው ጉዳዮች ስላሉ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያለኝ ምክር፣ እጃቸውን ከዚህ ጉዳይ ውስጥ ማውጣትና፣ የወሰን ድርድር ለማድረግ የሚያሰገድድ ሁኔታ ፈፅሞ ባለመኖሩ፣ ጉዳዩ ባለበት እንዲቀጥል መተው የተሻለ ነው ብዬ አስባለሁ ። ሃገራቸውን የሚጎዳ ነገር ውስጥ እጃቸውን ባያስገቡ ይመረጣል ።
Screen Shot 2015-12-25 at 8.55.10 PM

The post “እንኳን ኃይለማርያም ይቅርና ነባሮቹ የብአዴን መሪዎች እነበረከትና አዲሱ እንኳ ከኤርትራና ሱዳን ጉዳይ የተገለሉ ነበሩ” ያሬድ ጥበቡ appeared first on Zehabesha Amharic.


እነ ጌታቸው ሺፈራው 28 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ተሰጠባቸው

$
0
0

10014992_814334035358923_3722530882798972632_nበሽብር ተጠርጥረው መያዛቸውን መርማሪያቸው ተናግሯል
‹‹ካሁን በፊት ይዝቱብኝ ነበር፤ ጋዜጠኛ በመሆኔ ነው የታሰርኩት›› ጌታቸው ሺፈራ

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

ትናንት ታህሳስ 15/2008 ዓ.ም በያሉበት ታድነው የታሰሩት ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው፣ የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው ዳንኤል ተስፋየ እና ሸዋታጠቅ ኃ/መስቀል ዛሬ ታህሳስ 16/2008 ዓ.ም አራዳ ፍርድ ቤት ቀርበው 28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ በሽብር ተጠርጥረው መታሰራቸውን በመግለጽ የ28 ቀን የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቆ ተፈቅዶለታል፡፡ ፖሊስ ታሳሪዎቹ የተጠረጠሩበትን ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዳው፣ ተጠርጣሪዎች ‹‹የአርበኞች ግንቦት 7 አባል በመሆን፣ በመመልመል፣ በኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ግንኙነት በመፍጠር የሽብር ወንጀል ሊፈጽሙ ሲሉ ተይዘዋል›› ብሏል፡፡
ተጠርጣሪዎች ስለተጠረጠሩበት ወንጀል እና ስለተጠየቀባቸው የጊዜ ቀጠሮ አስተያየት የሰጡ ሲሆን፣ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው ‹‹ካሁን በፊት በተደጋጋሚ ይዝቱብኝ ነበር፤ እኔ ጋዜጠኛ በመሆኔ ነው የተያዝኩት፡፡ ቤቴ ሲፈተሽ የተገኘውም የህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች (ሰማያዊና መድረክ) መግለጫዎችና ፕሮግራሞች ናቸው፡፡ ከተባለው ወንጀል ጋር ምንም ግንኙነት የለኝም፤ በነጻ ልሰናበት ይገባል›› ሲል ተናግሯል፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ አባሉ አቶ ዳንኤል ተስፋየ በበኩሉ ‹‹በፍተሻ የተያዙብኝ ባንዲራ፣ ሲዲ እና ስልክ ናቸው፡፡ ስለዚህ ለምርመራ የተጠየቀውን ያህል ጊዜ መፈቀድ የለበትም፤ አጭር ቀጠሮ ይሰጠን›› ሲል ጠይቋል፡፡
ሦስተኛው ተጠርጣሪ አቶ ሸዋታጠቅ ኃ/መስቀል ደግሞ ‹‹እኔ በቂርቆስ ክ/ከተማ በኢህአዴግ ተደራጅቼ የምሰራ ሰው ነኝ፡፡ ፖሊስ ከገለጸው ድርጅት ጋር ምንም ግንኙነት የለኝም፤ ድርጅቱን ጭራሽ አላውቀውም፤ የልጅ አባት ስለሆንኩ አጭር ቀጠሮ ይሰጠኝ›› በማለት አመልክቷል፡፡
ፍርድ ቤቱ ግን ፖሊስ የጠየቀውን 28 ቀናት የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ በመፍቀድ ለጥር 14/2008 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ በተመሳሳይ ከሁለት ወራት በፊት ከአርባምንጭ ተይዘው ወደማዕከላዊ የመጡት በአርባምንጭ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት እነ ሉሉ መሰለ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው 28 ቀናት ጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
በሌላ በኩል ትናንት ለእስር ከተዳረጉት መካከል የሆኑት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት አቶ ኤርሚያስ ጸጋየ፣ አቶ ፍሬው ተክሌ እና አቶ ቴዎድሮስ አስፋው ዛሬ ከሰዓት ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

The post እነ ጌታቸው ሺፈራው 28 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ተሰጠባቸው appeared first on Zehabesha Amharic.

ኢትዮጵያ የማን ናት? –ከአንተነህ መርዕድ

$
0
0

 

ታህሳስ2008 ዓ ም

“ኢትዮጵያ የማን ሆና ነው ኦሮሞ የሚገነጠለው” ( ኮሎኔል ዓለሙ ቂጤሳ)

“ኦሮሞ ግንድ ነው አይገነጠልም” (ጄኔራል ጀጋማ ኬሎ)

Ethiopiaባለፉት ሃያ አራት ዓመታት የብዙ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የልብ ህመም ሆኖ የቆየው የኦሮሞ ጥያቄ ነው። ዛሬም በኢትዮጵያ ህልውና ወሳኝ ጥያቄ ቢኖር የኦሮሞ ጥያቄ ነው። ኢትዮጵያን ለማጥፋት ሆነ በጨለማ ለመግዛት የተነሱት ጣልያንም ሆነ ወያኔ ለአላማቸው ማስፈፀምያ የዚህን ታላቅ ህዝብ ጥያቄ ነበር ኢትዮጵያን ለመጉዳት የሚጠቀሙበት። ከላይ በጥቅስ ያስቀመጥኋቸውን ሃሳቦች የተናገሩት በኦሮሞ ህብረተሰብ ውስጥ ትፅዕኖ ፈጣሪና ታላቅ ኢትዮጵያውያን ናቸው። ከአስራ አራት ዓመት በፊት በሞት የተለዩን ኮሎኔል ዓለሙ ቂጤሳን ንግድ ማተምያ ቤት አጠገብ ባለው መኖርያ ቤታቸው ለጦቢያ መጽሄት ቃለ መጠይቅ ልናደርግላቸው አንጋፋው ጋዜጠኛ አቶ ሙሉጌታ ሉሌ ጋር ሄደን ነበር። ሜጫና ቱሉማን በመመስረትና ለኦሮሞ መብት በመታገል ኢትዮጵያዊ መፍትሄ እንዲያግኝ በመልፋት የሚታወቁት እኒህ አንጋፋ አባት አመሻሽ እድሜአቸው ላይ ሆነው ያዩት ሁሉ አላስደሰታቸውም።

አክራሪ ፅንፍ የያዙ የኦሮሞ ኤሊቶች ከሌሎች ኢትዮጵያውያን መለየትን እንደመፍትሄ በግልፅ በሚሰብኩበትና ለተግባራዊነቱ በሚገፉበት፤ ወያኔም ይህንኑ አጀንዳ አስጨብጦ በሚያራግብበት ፈታኝ ወቅት ነበር የሄድንባቸው። አምቦ አካባቢ ግንደበረት ተወልዶ ከማደጉም በላይ የኦሮሞን ህብረተሰብ ጠንቅቆ የሚያውቀው ጋሽ ሙሉጌታ ከኮሎኔሉ ጋር ያላቸውን መግባባትና መከባበር ስመለከት ተገርሜያለሁ። በርካታ አገራዊና የግል ጥያቄዎችን ያቀረብንላቸው ቢሆንም በቁጣ ስሜት የመለሱት ለኦሮሞ ችግር ከኢትዮጵያ መገንጠል መፍትሄ ይሆናልን? የሚለውን ጥያቄአችንን ነበር። “ኢትዮጵያ የማን ሆና ነው ኦሮሞ የሚገነጠለው?” በማለት ነበር ጥያቄአችንን በጥያቄ የመለሱት።

ኦሮሞ የኢትዮጵያ እምብርት ብቻ ሳይሆን ከሰሜን ጫፍ እስከ ትግራይ፣ በደቡብ እስከ ኬንያ፤ በምስራቅ ኦጋዴንን ነክቶ በምዕራብ ሱዳን ድረስ ሲያጣቅስ በመሃል ከአብዣኛው ኢትዮጵያውያን ተዛንቆ፣ ተዋልዶ፣ ተዋህዶ በመኖሩ እድሉ የኢትዮጵያ ባለቤት መሆን እንጅ ጊዜው እንደወለዳቸው ፖለቲከኞች ቁራሽ መሬት ይዞ መወሰን አይደለም የህዝቡ ፍላጎት። ኮሎኔል ዓለሙ ቂጤሳም የገለፁት ይህንኑ የኦሮሞ ህዝብ ፍላጎት ነበር። ቃለ መጠይቁን ለህትመት አብቅተን ኮሎኔል ዓለሙን ደግመን ስናገኛቸው ያየሁትና የሰማሁት ለብዙ ጊዜ አሳዝኖኛል። የጊዜው የፖለቲካ አራጋቢዎች ትልቅ የመንፈስ ስብራት ፈጥረውባቸው ነበር። “ዛሬ በሽምግልናዬ ቤት ውስጥ ተወስኜ ሞቴን በጸጋ በምጠብቅበት ሰዓት የአገር ጉዳይ ጠልቆ ያልገባቸው ወንድሞቼ በእኔና በቤተሰቤ ያሳደሩብኝ ጫና ቀላል አይደለም። ቀሪ ጊዜዬን በሃዘን እንዳልቋጨው ታገሱኝ” አሉን። እኛም ታገስናቸው።

ዛሬ ኮሎኔል ዓለሙ ቂጤሳና አንጋፋው ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ በህይወት የሉም። ጋሽ ሙሉጌታ  ሊለየን ትንሽ ሰዓታት ሲቀረው “ለዘመናት ወጣቱ ላይ የነበረኝን ወቀሳ አንስቻለሁ፤ አገሩን የሚታደግ ወጣት በማየቴ ኮርቻለሁ። በሉ ተነሱ ሰልፍ የጀግና ነው፣ ድል የእግዜብሄር ነው” ሲል ተስፋውንና ጥሪውን ገልፆ አልፏል። የኦሮሞ ህዝብና ቀሪው ኢትዮጵያዊ ባንድ ቁሞ ታላቋን ኢትዮጵያን የመገንባቱ ተስፋ እየለመለመ ነው። የኦሮሞ ህዝብ የኢትዮጵያ ባለቤት ለመሆን አገራዊ አጀንዳ ይዞ እየተነሳ ነው። የኦሮሞ ፖለቲከኞች (ኤሊቶች) እንደ ኦሮሞ ህዝብ ሰፊ ልቦናና ኢትዮጵያዊ ባለቤትነትን ካላቀፉ ለጠባቡና ለጊዜአዊ የፖለቲካ ፍጆታ ራሳቸውን ወስነው መነሳት እንደማያዋጣቸው የተረዱ ይመስላል። ከአንጋፋ ፖለቲከኞች ሌንጮ ለታና ጓዶቻቸው፣ ከወጣቶቹም ጁአር ሞሃመድና ሌሎችም ሰሞኑን ያሳዩት ሁሉን አቃፊ (አኮሞዳቲቭ) አቋም  ያየ፤ የኦሮሞ ፖለቲከኞች የኦሮሞን ህብረተሰብ በሚመጥን ደረጃ ለመገኘት መንቀሳቀሳቸውን ወይንም መፈለጋቸውን ይገነዘባል። ያድርግልን። ከሰሞኑ የህዝብ አመፅ በኋላ የአማራውና የኦሮሞው አንድነት ጥሪ በሰፊው ተሰብኳል። አመፁን ተከትሎ የመጣ በረከት ይመስላል (ፈረንጆች ኤ ብሌሲንግ ኢን ዲስጋይዝ እንደሚሉት)። አመፁን ወደ እውነተኛ አንድነት እንዲያድግ ከተፈለገ አጀንዳው ከክልላዊነት ወጥቶ ወደ አገራዊነት መለወጥ  አለበት።

ለኢትዮጵያ ህልውናና እድገት የህዝቦቿ መተባበር፤ በተለይም የኦሮሞውና የአማራው በአንድነት መቆም ወሳኝ ነው። ለዚህም ነው የኢትዮጵያን ህዝብ ረግጠው ለመግዛት የሚያልሙ የውጭ ሆነ የውስጥ ጠላቶች እነዚህን ጉልህ የህዝብ ክፍሎችን የጥቃታቸው ኢላማ የሚያደርጉት። አድዋ ላይ አባቶቻችን ያንበረከኳትና በዓለም ፊት ያዋረዷት ጣልያን የሽንፈቷ ምክንያት የኢትዮጵያውያን ህብረት መሆኑን ከውድቀቷ ተምራለች። ከአርባ ዓመት በኋላ ቂም ቋጥራ ዳግም ስትመጣ፤ መጀመርያ የተሰማራችው ተባብረው የደቆሷትን አማራና ኦሮሞን በመለያየት ላይ ነው። ብዙ ክፍተት ለጊዜው ብትፈጥርም እንዳልተሳካላት ሌላውን የኦሮሞ የጀግንነት ምሳሌ የሆኑትን ኢትዮጵያዊ ታሪክእንቃኝ። የበጋው መብረቅ የሚባሉት የጀግናው የጄኔራል ጀጋማ ኬሎ አጎት ናቸው። ፊታውራሪ አባዶዮ ዋሚ ገሮ ይባላሉ። አባ ዶዮ የፈረስ ስማቸው ነው። ጣልያን አማራንና ኦሮሞን ለመከፋፈል በሰፊው ሠርቶ ስለነበር፤ ይህ ሰበካ እውነት የመሰላቸው ታላላቅ ሰዎች የፊታውራሪ አባ ዶዮ ዋሚ ገሮን ምክርና ይሁንታ ለመሻት ቤታቸው ሄዱ። “አማራ የሚበድለን ስለሆነ ከአካባቢያችን ልናስወጣ አስበናል ምን ይመክሩናል?” የሚል ሃሳብ አቀረቡላቸው። እንግዶቻቸውን አብልተው አጠጥተው፣ በነገሩም አሰላስለው ቆዩና ለእያንዳንዳቸው እፍኝ እፍኝ ሙሉ ሰርገኛ ጤፍ እንዲሰጣቸው አዘዙ። ጤፉም ለእንግዶቹ ተሰጠ። “በሉ ቀዩን ከነጩ ጤፍ ለዩልኝ” አሏቸው። ግራ የተጋቡት እንግዶች “አባ ዶዮ ይሄማ እንዴት ይቻላል?” በማለት እንደማይሆን ነገሯቸው። “ያቀረባችሁልኝ እኮ እንዲህ ያለ ጥያቄ ነው። ከአማራ ያልተጋባ፣ ያልወለደ፣ ያልተዛመደ ማን አለ? እንዝመት ካላችሁ በራሳችን፣ በቤታችን እንጀምር። ይህንን ደግሳ ያበላቻችሁ የልጆቼ እናት አማራ ናት። ልጆቼንና ልጆቿንም፣ እሷንም ጭምር ግደሉ፤ እናንተም በየቤታችሁም ሂዱና የአማራ ደም ያለበትን አጥፉ። ይህ እንዲሆን አይደል የምትጠይቁኝ” አሏቸው። በርግጥም ከአማራ ያልተዛነቀ ኦሮሞ፤ ከኦሮሞ ያልተዋለደ አማራ ጥቂት ነው። ጥፋታቸውን የተረዱት መልዕክተኞች የጣልያንን ተልዕኮ አከሸፉ። በነገራችን ላይ ዶክተር መረራ ጉዲናም አንዳንድ ፅንፈኛ የሆኑትን ፀረ አማራ የሆኑ የኦሮሞ ልሂቃንን “ማታ ቤታቸው አማራ ሚስቶቻቸውን ታቅፈው እያደሩ ቀን ስለእነዚህ ትልልቅ ህዝቦች መለያየት ይሰብካሉ” ሲሉ ከሃያ ዓመት በፊት መተቸታቸውን አስታውሳልሁ።

ታሪኩ በዚህ አያበቃም። የፊታውራሪ አባ ዶዮ ዋሚ ገሮ ወንድም የአባ ኬሎ ገሮ ልጅ ጀጋማ ኪሎ ጣልያንን ገና በአስራ አራት አመታቸው ጀምሮ ነው በጥይት እየቆሉ መውጫ መግቢያ አሳጥተው ነፃነታችንን ያጎናጸፉን። የጣልያንን ሴራ ብቻ ሳይሆን ሰላቶን ከነባንዳው አይቀጡ ቅጣት የቀጡት ጄኔራል ጀጋማ ኬሎ ከአምሳ አምስት ዓመት በኋላ የባንዳ ልጆች የሆኑ የወያኔ መሪዎች በአማራውና በኦሮሞው ልዩነት ፈጥረው ለማፋጀት ሲነሱ አጎታቸው ዘንድ ለምክር እንደሄዱ መልዕክተኞች የህወሃትን መርዝ ይዘው ኦሮሞን ከኢትዮጵያ ህዝብ ለመነጠል ሲያቀነቅኑ ልባቸው በሃዘን ተነክቷል። አዛውንቱ ፖለቲከኛ ቡልቻ ደመቅሳ “ለኦሮሞ መገንጠል ይበጀዋል ወይ?” ብለው ለጠየቋቸው “ኦሮሞ ግንድ ነው አይገነጠልም”  ቅርንጫፍ እንጂ ግንድ አይገነጠልም ብለው እንደመለሱላቸው ሰምቻለሁ። ዛሬ ጄኔራል ጀጋማ ኬሎ የ95 ዓመት አዛውንት ናቸው። የኦሮሞ አድባር፣ የኦሮሞ ዋርካ፣ የአጠቃላዩ የኢትዮጵያ ዋርካ በህይወት እያሉ ኢትዮጵያ በጠላቶቿ ስንት ጊዜ ተጠቃች? ስንት ጊዜ አፈር ልሳ ተነሳች?

አብዛኞቹ የህወሃት መሪዎች ለጣልያን ያደሩ የባንዳ ልጆች መሆናቸውን ከገብረመድህን አርዓያ የበለጠ ምስክር አንሻም። Rኡቅ ሳንሄድ የህወሃት ሴራ ባለቤት የመለስ ዜናዊ አያት የጣልያኑ ደጃዝማች አስረስ በርካታ ህዝብ ያስፈጁ አገር የሸጡ ባንዳ መሆናቸውን ሁሉም ያውቀዋል። ታድያ እነመለስና ጓደኞቻቸው ከአባቶቻቸው የተማሩት አገርን መታደግ ሳይሆን ማፍረስ ነው። ጀግናው አፄ ዮሃንስ ከበርካታ የኢትዮጵያ ጀግኖች ጋር(የትግራይን ጨምሮ) አንግታቸውን የተሰውበትን መሬት ሳይቀር ለሱዳን ሲሰጡ ሃፍረት የማያውቁ ከሃዲ ወንጀለኞች ናቸው። በመሆናቸውም ነው መሃል ኢትዮጵያን አፍኖ ለመግዛት አማራና ኦሮሞን ለመለያየት የባንዳ አባቶቻቸውን ጌቶች ፖሊሲ የተከተሉት። ይህ ተንኮል ከጣልያን የበለጠ ለእነሱ ሰርቷል። ባለፉት ሃያ አራት ዓመታት ከሁለቱ ህዝብ ፅንፈኛ የሆኑና ለፍርፋሪ የሚያድሩትን በማግኘታቸው ዙፋናቸው ላይ እስከአሁን ተደላድለዋል።

አማራው በየሄደበት እንደ አውሬ ታድኗል። ዐይኑ እያየ ገደል ላይ ተጥሏል። ይህንን ደግሞ ሃውዜን ላይ በትግራይ ህዝብ ሲፈፅሙት የተካኑ በመሆናቸው በፊልም እየቀረፁ “ኦሮሞው አማራውን እንዲህ አድርጎ ነው የገደለው” ብለው በአደባባይ በማሳየት እስከዛሬ የሠራላቸውን የመከፋፈል ሴራ ውጤታማ አድርጎታል። ተንኮላቸው በሁለት በኩል ስለት እንዳለው ቢላዋ ባንድ በኩል ኦሮሞውን ከአማራ ለመለያየት ሲያገለግላቸው፤ ሌላኛው ስለት ኦነግን የፖለቲካ ሞት እንዲሞትላቸው ማድረጋቸውን የዚህ ተንኮል መሃንዲስ ከሆነው መለስ ዜናዊ ጋር በቅርብ የሠሩትና አጥርተው የሚያውቁት ሊንጮ ለታ ዛሬ በአዛውንት እድሜአቸውና በሰከነ አእምሮአቸው ቢመሰክሩ ደስ ይለናል። ለትናንት የፖለቲካ ዓላማ ባይጠቅምም፤ ለዛሬውና ለነገው ትውልድ ትምህርት ይሆነዋል።

ኦሮሞው በየቦታው ሲሰደድ፣ ሲገደልና የአገሪቱን እስር ቤቶች ሲያጨናንቅ፤ አድር ባይ ልጆቹ ወያኔ የሰጣቸውን የመቶ ዓመት ታሪክ ሲቆፍሩና ተጠያቂ ሲፈልጉ፣ ዛሬ የሚፈጸመውን ዐይን ያወጣ በደልና ግፍ እነሱም ዐይተው እንዳላዩ፣ ህዝቡም እንዳያይ ብዙ የከፋ ወንጀል ሠርተዋል። ቢዘርፉ የማይጠረቁ የወያኔ መኳንንት አዲስ አበባን ጨርሰው የአካባቢውን ገበሬ ሲያፈናቅሉ “የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ” በሚል ጅል ተመክሮአቸው ህዝቡን አጥንቱ እስኪቀር ትንሽ ፍርፋሪ እያገኙ አስግጠውታል። ዛሬ ፅዋው ሞልቶ ሲፈስና ህዝቡ ከዳር ዳር ሲነሳ በድንገት ባነኑና የህዝብ ደጋፊ ነን ለማለት በአዳራሽ ተሰብስበው ወያኔ ላይ መፎከራቸውን ከኢሳት ሰምተናል። ልጃገረዷ አረገዘች የሚል ሃሜት ሲናፈስ “እስቲ ታገሱ፤ እህል ከሆነ ይጠፋል፣ ሽል ከሆነም ይገፋል” እንዳሉት ኦህዴዶቹ ከልባቸው ከሆነ የምናየው ነው።  ጌታቸው ወያኔ ሳይቀድሙት በመቅደም አባዜ የተካነ ነውና ቀበቶአቸውን ጠበቅ ሊያደርጉ ይገባል። የስምንት ዓመት ልጅ በጥይት ከሚደፋ፣ አስከሬን ለወላጅ በሺህ ብር ከሚሸጥ፣ አገርን ቆርሶ ከሚቸበችብ አምባገነን ጋር ከመስራት የከፋ ወንጀል አለ? ርህራሄ የሌለው ህወሃት ለዚህ ድፍረታቸው በመቶ ሺዎች አሳልፈው ከሰጧቸው፣ እስር ቤት ከሚገኙ ወንድሞቻቸው ጋር ለማጎር አይሳሳም። ደርግ መኢሶንን ተጠቅሞበት ደመኛ ጠላቶቹ ከሆኑት ኢህአፓዎች ጋር በአንድ እስርቤትና በአንድ ጉድጓድ እንዳገናኛቸው ሁሉ ወያኔም ይህንኑ እንደሚያደርግ ግልፅ ነው። ኦህዴድ ሆይ! በአገሪቱ በተለይ በኦሮሞው ላይ ለተሠራው ሁሉ ወንጀል ሃላፊነቱን በግልፅ በመውሰድና ከህዝብ ጎን በመቆም ዘላቂ ዴሞክራሲያዊ መፍትሄ ለማምጣት ካልታገላችሁ ይህ ሙት ስርዓት ይዟችሁ ይሞታል።

የኦሮሞ ህዝብ ልበ ሰፊ ነው። አስተዋይና አዋቂም ነው። ይህንን ትልቅነቱን ሰሞኑን በሚገባ አሳይቷል። በውስጡ ያሉትን አማሮችና ሌሎችንም እንዲተነኩስ ዘረኞች ቢሰብኩትም በልበ ሰፊነት ሰላማዊ ትግል እያደረጉ ልጆቹ ለሰላምና ለፍቅር ሲሉ ወድቀዋል። አምናም ዘንድሮም የወደቁ ጀግኖች የኢትዮጵያ ሰማዕታት ናቸው። ለጠባብ አላማ አልወደቁም። ይልቅስ ገዳዮቻቸው ወራዳ ታሪክ ፈፅመዋል። የኦሮሞ ህዝብ በትልቅነቱ ልክ አባቶቹ በደማቸው የአቆዩአትን አገር ባለቤት ሆኖ ነፃ ሊያወጣት ከወንድሞቹ ጋር ይሰለፋል እንጂ ፖለቲከኞች በሰፉለት አርቲፊሻልና ጠባብ ዓላማ ራሱን ወደ ትንሽነት አይቀይርም። ለዚያውም የትግራይን ህዝብ የካዱ የባንዳ ልጆች መጠቀምያ አይሆንም። ለኦሮሞ ህዝብ እንኳን ኢትዮጵያ ምስራቅ አፍሪካ ትጠበዋለች። “ኢትዮጵያ የማን ሁና ነው ኦሮሞ የሚገነጠለው” ያሉት ኮሎኔል ዓለሙ ቂጤሳ ዛሬ በህይወት ቢኖሩ ምንኛ ተስፋቸው በለመለመ። “ኦሮሞ ግንድ ነው አይገነጠልም” ያሉት ጀግናው ጄኔራል ጀጋማ ኬሎ እንደልብ መስማት ባዳገታቸው በዚህ የሽምግልና ወቅት አሁን በምልክትም ቢሆን የኦሮሞን ህዝብ እንቅስቃሴ መረዳታቸው አይቀርምና የመጨረሻ ዘመናቸው በሃዘን እንዳይቋጭ መትጋት ያስፈልገናል።

የእኛ ያልሆነን ሶሻሊዝም ለማፅደቅ የብዙ ኢትዮጵያውያን ደም ፈስሶ ስር ሳይሰድ ቀርቷል። የልዩነትና የጎሳ ፖለቲካም አፍላው ያለፈበትና የመሸበት አስተሳሰብ መሆኑን እንደሶሻሊዝሙ ብዙ ከፍለንበት ተምረናል። ኢትዮጵያውያን እጅ ለእጅ ተያይዘን ካለንበት ጨለማ ለመውጣት በጋራ ካልተነሳን ተስፋ የለንም። በተለይም ከአማራውና ከኦሮሞው የወጡ ጽንፈኞች በህዝቡ ስም በመነገድ አምባገነኑና ዘረኛው የውያኔ አገዛዝ እድሜ እንዲኖርው ከማገዝ እንዲቆጠቡ በግልፅ ሊነገራቸው ይገባል። በዘውግ ፖለቲካ ተጨፍነን እያለ፣ ለከተማ መሬት ስናዝን፣ የአግሪቱ ለም መሬት ለሱዳን እየተሰጠ ነው። በጉርሻ ስንጣላ የህልውናችን መሰረቱ  ራትና ምሳችን ሊሄድ ነው። መተማ ላይ የአፄ ዮሃንስን አንገት የቀላ ሰይፍ ድንበሯን አናስነካም ያሉትን ንፁሃን በመቁረጥ ላይ ነው። ሰይፉ ከሁለት አቅጣጫ ተደቅኖብናል። ከሱዳንና ከህወሃት። ሰሞኑን የሱዳኑ መሪ አልበሽር ሰራዊታቸው ወደ ኢትዮጵያ ድንበር እንዲንቀሳቀስ አዝዘዋል። በኢትዮጵያ ምንግስት በኩል ደግሞ ኃይለማርያም ደሳልኝ ኢትዮጵያውያንን ሱዳንን የሚያጠቁ ሽፍቶች ሲሉ በፓርላማው ፊት ወንጅለዋል። ይህም ይህወሃት ሰራዊት ከሱዳን ጋር ተባብሮ ዜጎቹን ለመውጋት መዘጋጀቱን ያመለክታል። ኢትዮጵያ በታሪኳ እንደዚህ ያለ ለህልውናዋ ጠላት የሆነ መንግሥት አጋጥሟት አያውቅም።

ይህን ጽሁፍ በማጠቃለል ላይ እያለሁ ወያኔዎች በቀለ ገርባንና ሌሎችንም እያደኑ ማሰራቸውን ሰማሁ። ይህ የሁሉም ኢትዮጵያዊ እጣ መሆኑን ያላወቀ ካለ አንድም የዋህ ነው፣ ያለዚያም የስርዓቱ አገልጋይ ነው። በቀለ ገርባን የመሰለ የተረጋጋ፣ ሰላም ፈላጊና ትልቅ የዓላማ ሰው አገሪቷ እንዳይኖራት ወያኔ ተግቶ መሥራት የጀመረው አሁን አይደለም። ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን፣ አሰፋ ማሩን፣ ተስፋዬ ታደሰን….ገድሏል፤ የቅንጅት መሪዎችን፣ አንዱዓለም አራጌንና ሺህ የኢትዮጵያ ተስፋዎችን አስሯል። በአራቱም ማዕዘናት ወጣትና ሽማግሌ ኢትዮጵያውያንን ገድሏል። አገርንና ህዝብን እንደጠላት ኢላማ አድርጎ ከተነሳ ስርዓት በጎ ነገር የመጠበቅ የዋህነት አብሮ የመግደልን ያህል ወንጀል ከሆነበት ደረጃ ላይ ደርሰናል። ኢትዮጵያውያን ሌት ተቀን መስራት ያለብን በቀለ ገርባንና ተመስገን ደስአለኝን ከመሰሉ ጀግኖች ጎን መቆምና እነሱን የመሰሉ ሺዎችን ከመካከላችን ማፍራትና መንከባከብ መሆን አለበት። ዳር ቆሞ ሌሎችን በመተቸት የተጠመደው ልሂቃን እውነተኛ ኢትዮጵያውያን ተገቢ ዋጋ እየከፈሉ ባለበት ሰዓት የጥርጣሬና ያለመተማመን ዲስኩሩን ያቁምና የትግሉ አካል ይሁን።

ኢትዮጵያ የቅን ልጆቿ ሁሉ የጋራ ናት!

በሁሉም አቅጣጫ መስዋዕት በሚከፍሉ ልጆቿም በቅርቡ ጨለማው ይገፍላታል!!

በአንድነት የተነሱ ታጋዮቿ ይታደጓታል!!

Amerid2000@gmail.com

 

 

 

 

 

 

The post ኢትዮጵያ የማን ናት? – ከአንተነህ መርዕድ appeared first on Zehabesha Amharic.

ተማሪዎች የአምቦ ዩኒቨርሲቲን ለቀው እየወጡ ነው |በወታደሮች ተገደው የተደፈሩ ሴቶች አሉ

$
0
0

ambo 2

ambo 3

ambo
(ዘ-ሐበሻ) በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች የተከሰተው የሕዝብ አመጽን ተከትሎ ይህን ለማረጋጋት ሁሉን ነገር እየፈነቀለ የሚገኘው ሕወሓት የሚመራው መንግስት የአምቦ ዩኒቨርሲቲን ከትናንና ምሽት ጀምሮ በፌደራል ፖሊስ መቆጣጠሩን ተከትሎ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲውን ለቀው እየወጡ መሆኑ ተሰማ::

ምንጮች ከስፍራው እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲውን ፌደራል ፖሊስ ከትናንት ማምሻውን ጀምሮ ከተቆጣጠረው በኋላ ተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል:: አንዳንድ ሴት ተማሪዎች መኝታ ክፍላቸው በፖሊስ ተሰብሮ በመግባት መደፈራቸውን ምንጮች ከስፍራው ገልጸዋል::

ፖሊሶች ሴት ተማሪዎችን መድፈራቸውን እና ግቢው መወረሩን ተከትሎ ተማሪዎች ወደየቤታቸውና ወደየመጡበት ከተማ እየሄዱ መሆኑን የገለጹት ምንጮች በአሁኑ ወቅት ዩኒቨርሲቲው የፌደራል ፖሊስ ካምፕ እንደሚመስል ገልጸዋል::

The post ተማሪዎች የአምቦ ዩኒቨርሲቲን ለቀው እየወጡ ነው | በወታደሮች ተገደው የተደፈሩ ሴቶች አሉ appeared first on Zehabesha Amharic.

ቴዲ አፍሮ እና ጎሳዬ ተስፋዬ በሲያትል “ኢትዮጵያ ሃገራችን”ሲሉ በአንድ መድረክ ሲዘፍኑ የሚያሳይ ቪድዮ

$
0
0

Teddy afro and Gosaye Tesfaye
(ዘ-ሐበሻ) ትናንት በሲያትል ዋሽግንተን የተደረገው የዝነኞቹ የቴዲ አፍሮ እና የጎሳዬ ተስፋዬ የሙዚቃ ኮንሰርት ባማረ ሁኔታ መጠናቀቁ ተሰማ:: ከአዘጋጆቹ አካባቢ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው በአቡጊዳ ባንድ እና በራስ ባንድ በመታጀብ ቴዲ አፍሮና ጎሳዬ በመድረኩ ላይ ነግሰው አምሽተዋል:: በቪድዮ ተደግፎ በተለቀቀው መረጃም ቴዲ አፍሮ እና ጎሳዬ በአንድ ላይ “ኢትዮጵያ ሃገራችን” የሚለውን ዘፈን በአንድ ላይ በመዝፈን ሕዝቡን አነቃቅተዋል:: ቪድዮው ይናገራል:-

The post ቴዲ አፍሮ እና ጎሳዬ ተስፋዬ በሲያትል “ኢትዮጵያ ሃገራችን” ሲሉ በአንድ መድረክ ሲዘፍኑ የሚያሳይ ቪድዮ appeared first on Zehabesha Amharic.

“ፍየል ወዲያ ቁዝምዝም ወዲህ!!” –ሸንጎ

$
0
0

ህሳስ 22 ቀን 2008 ዓ.ም.(26-12-2015)

በትናንትናው ዕለት የህወሃት/ኢሕአዴግ ጠ/ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ህወሃት በሚቆጣጠረው ፓርላማ ተገኝቶ መንግስቱ በወጠነው የአምስት ዓመት መመሪያና  በተለያዩ ርዕሶች ላይ ማብራሪያ ሰጥቷል።

shengoየታቀደውን የኤኮኖሚ ትራንስፎርሜሽንን በተመለከተ የግብር አሰባሰቡ በበለጠ እንዲያድግ የሚያስገድድ ሕግ እንደረቀቀ፣በገጠሩ የልማት እንቅስቃሴና መጠነኛ የእንዱስትሪ ተቋማት እንዲጎለብቱ የልማት ባንኩ ብዙ ካፒታል መድቦ ዘርፎችን በመዘርጋት ለመንቀሳቀስ እንደታሰበ ያብራራ ሲሆን በአለፈው የአምስት ዓመቱ ዕቅድ የባከነውን ገንዘብና የአገር ሃብት ከቁጥር ውስጥ ሳያስገባ እንዳልነበረ አድርጎ ሸፋፍኖ አልፎታል።የልማት ባንኩ ለህብረተሰቡ የሚሰጠውን ጥቅምና አገልግሎት ቢጠቅስም፣ብድርና ድጋፍ የሚያገኘው የህብረተሰብ ክፍል በግልጽ አልተቀመጠም።በማንኛውም አገር 90በመቶ የሚሆነውን የስራ ዕድል የሚፈጥረው የግል ክፍሉ ነው።የግል ክፍሉ ይህን ለማድረግ የሚችለው የሚሰራበት መሬት፣የአጭር፣የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ብድር በተፈለገው መጠን ለማግኘት ሲችልና በአገሪቱ ክፍሎች በሙሉ ያለምንም ገደብ ለመንቀሳቀስ ሲችል ነው።በተጨማሪ አገር ተከልና አገር ወለድ የግል ክፍል ከፍተኛ ሚና ሊኖረው የሚችለው መንግሥት ለውጭ ኢንቬስተሮች የሚሰጠውን አድላዊ ድጋፍና እንክብካቤ በመቆጠብ ለኢትዮጵያውያን ፊቱን ሲያዞር ነው።

ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት የታየው ግን ገዢው ፓርቲ ያልተቆጠበ ድጋፍ የሚሰጠው ለገዢው ፓርቲ ድርጅቶች፤ በተለይ ለህወሓት/ ኢሕአዴግ ለፓርቲውና ለመንግስት ለባለስልጣናቱ ቅርበት ላላቸው ነው። አሁንም እነዚህ ክፍሎች ዋና ተጠቃሚ እንደሚሆኑ አያጠራጥርም። በዚህ ዙሪያ የተሰጠው ማብራሪያ ለብዙ ዓመታት ተደጋግሞ የተለፈፈ በመሆኑ የማታለያ ባዶ ዲስኩር እንጂ ለሕዝቡ ኑሮና ለአገሪቱ ሰላም፣አንድነትና እድገት ታስቦ የተነደፈ፣በተግባር የሚተረጎም እንዳልሆነ ካለፉት ተመክሮዎች በመነሳት መናገር ይቻላል። በመጀመሪያውም የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የኢትዮጵያ ሕዝብ በቀን ሶስት ጊዜ በልቶ ለማደር    የሚያስችለው መመሪያ እንደሆነ የህወት መሪ በነበረው በመለስ ዜናዊ ተሰብኮበት ነበር።ውጤቱ ግን እንኳንስ በቀን ሶስት ጊዜ ቀርቶ አንድ ጊዜም በልቶ ለማደር የማይቻልበት አልፎ ተርፎም ከሌላው ጊዜ የበለጠ ከፍተኛ ቸነፈር የሰፈነበት ሰው ሰራሽ መቅሰፍት የወለደ ሆኖ ተገኝቷል።

የቸነፈር(ከፍተኛ እርሃብ) መከሰትና ስላደረሰው ጉዳት እንደ እስከዛሬው ዓይኔን ግንባር ያርገው ብሎ ለመካድ የሚፈቅድለት ሁኔታ ባለመኖሩ ያደጋውን ስፋትና ችግሩን ለማሶገድ ያሉትን መንግስታዊ ድክመቶችና መዋቅራዊ ችግሮች አምኗል። እርሃቡን ለመቋቋም ብዙ መንገዶችን እንደዘረጋ ቢተነትንም ከብዙ ጊዜ በፊት የተሰነዘረውን የሕዝብ አስተያየትና ምክር ባለመቀበሉ የተፈራው ችግር ለመንሰራፋቱ መንግስት እራሱ ተጠያቂ  እንደሆነ ቢታወቅም ድክመቱን አላመነም።  ምንም እንኳን የደርግ መንግሥት “የመሬት ለአራሹን አዋጅ” አውጥቶ፤ በሕዝብ ስም መሬትን ወደ መንግሥት እጅ ቢያዛውርም፤ ዛሬ ህወሓት/ኢህአዴግ ሰፊውን በግብርና የሚኖር ሕዝብ “ጭሰኛ” አድርጎታል። መሬቱን በፈለገው ዘዴ ለግል ክፍሎች ይቸረችረዋል።  የሕዝቡን በተለይም የአርሶ አደሩን የመሬት ባለቤትነት ጥያቄና የማምረት አቅም ግንባታን  አላመቻቸውም። የአገሪቱ ዜጋ በፈለገበት ቦታ ተንቀሳቅሶ ለመስራት የሚያስችለው መብት የለም። የክልል ገዢዎች ነዋሪዎችን በረባ ባልረባው ከቀያቸው እንዲባረሩ አድግቿዋል። ከተሜው ሆነ አራሹ በዜግነት መብቱ ማግኘት የሚገባውን መንግሥታዊ ድጋፍ በድርጅት አባልነቱና በብሔሩ የሚያገኝና የሚያጣው በመሆኑ ለርሃብና ለስደት እንዲጋለጥ አድርጎታል። የተፈጥሮ ድርቅ የሚያመጣውን ጉዳት እንደዋና ምክንያት አድርጎ በማቅረብ መንግስቱ ከሚኖርበት አላፊነትና ቀድሞ የመዘጋጀት ግዴታ ለማፈግፈግ ሞክሯል። ቀደም ሲል ለገጠሩ እድገትና የእርሻ መስክ የመስኖ ስራዎች መጎልበት ሲኖርባቸው በጠቅላይ ሚኒስትሩ አገላለጽ ለመስኖው ስራ መዳከምና ለርሃቡ ዝናብና  የቆቃ ግድብ ሳይቀር ተጠያቂ ሆኖ ቀርቧል። የአገር ውስጥና የውጭ አገር ባለሃብቶች ለሚያንቀሳቅሱት፣ ለውጭ አገር ገበያና አገልግሎት ለሚውሉ የአበባና የመሳሰሉት ምርቶች  እንዳለፈው ሁሉ ወደፊትም ትኩረትና ቅድሚያ እንደሚሰጥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጧል። ይህ ዕቅድ ለውጭ አገር ከበርቴዎች፤ ኪራይ ሰብሳቢዎችና አቀባባይ ነጋዴዎች ጥቅም የሚሰጥ ለገዥው ህወሀት/ኢህአዴግ ደግሞ ገንዘብ መሰብሰቢያ እንጂ ለደሃው የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይም ለሰፊው አርሶ አደር ጥያቄ መልስ የሚሰጥ አይደለም። እርሃብንም ለመዋጋትና ለማሸነፍ አያግዝም።ስለሆነም መዋቅሩን ለመለወጥ ፓሊሲውን መለወጥ አለበት።

በአገሪቱ ውስጥ የሚካሄደውን ሕዝባዊ ተቃውሞና እምቢ ባይነት በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጥቂት ስርዓተ አልበኞችና ሽብርተኞች ቅስቀሳ  ውጤት ነው በማለት ሲያጣጥለው፣እንዳለፉት ስርዓቶች በድንፋታ ተወጥሮ “ደካሞችና ነውጠኞች አቧራቸውን አራግፈው ብቅ ያሉበት፣የሕዝቡን እንቅስቃሴ ጠምዝዘው ለመጠቀም የቋመጡበት ነው” በማለት እንደለመደው ለማዳከምና በሃይል ለመደፍጠጥ  የሚመራው መንግስት መጠነ ሰፊ ዕቅድ እንደዘረጋ ለህወሓት/ኢሕአዴግ ምክር ቤት አስረድቷል። የሕዝብ ንቅናቄ መሆኑን ካመነ ዘንዳ ለምን ሕዝቡ ተነቃነቀ ብሎ መጠየቅና መልስ መሻት በተገባው ነበር። ለአገር እድገት፣ለሰላምና አንድነት፣ እንዲሁም የዲሞክራሲንና የመልካም አስተዳደርን ስርዓት ለመመስረት ቆርጦ የተነሳ ስብስብ እመራለሁ ከሚል ጠ/ሚኒስትር  የጥፋትና የጥቃት አዋጅ አይጠበቅም ነበር። አላፊነት የሚሰማው መሪ ቢሆን ኖሮ ሁሉንም የተቃዋሚ ክፍሎች የሚያሳትፍ ድርድር፣መግባባት፣መነጋገር የሚያስችል ሁኔታዎችን ፈጥሮ ለሰላምና ለእርቅ የሚጋብዝ ጥሪ ማድረግ በተገባው ነበር። ሆኖም ግን በጥፋት ላይ መሰረት ካደረገ መንግስትና ቡድን ቀናነትና የተሻለ አመራር ይገኛል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው። በጠቅላይ ምኒስትሩ የታወጀው የጥቃት እርምጃ አገሪቱንና ሕዝቡን ይበልጥ ወደቀውስ የሚከት አላፊነት የጎደለው፣የማንአህሎኝነትና ትእቢት የተመላበት አቋም ነው።

በእኩልነት ስም በሰሜን ጎንደር አካባቢ ለዘመናት በሰላም የሚኖረውን ሕዝብ ቅማንትና አማራ በማለት ሸንሽኖ ቀውስ ውስጥ የከተተው እራሱ በህወሃት/ኢሕአዴግ የበላይነት የሚመራው መንግስት መሆኑ እየታወቀ ለደረሰው የሕይወት መጥፋትና የንብረት መውደም ተጠያቂነቱን በሕዝቡ ላይ ጥሎታል። በዚህም በዚያም ብሎ በተቃዋሚው ላይ ዱላውን ለማሳረፍ ዝቷል። ሰሞኑን በኦሮሚያና በሙስሊሙ ማህበረሰብ የተቀሰቀሰው ሕዝባዊ ጥያቄ የጥቂት ነውጠኞችና ሽብርተኞች ደባ ነው ሲል ከማውገዝም በላይ የቅጣት እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁነቱን አረጋግጧል። በዚህ የበቀል እርምጃ በሰላማዊ ትግል አምነው የተሰለፉትን የፖለቲካ ድርጅቶችንና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማትን ለማጥፋትና ለመደምሰስ መታሰቡን ፍንጭ ከመስጠትም በላይ ለፖሊስና ለደህንነት ተቋማት ገደብ የሌለው ስልጣንና ትዕዛዝ መስጠቱን ይፋ አድርጓል። ከአገር ቤት ሾልኮ የሚወጣው መረጃ እንደሚያረጋግጠው በመቶ የሚቆጠሩ ዜጎች እንደተገደሉና ኦሮምያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ብቻ ከሶስት ሽህ በላይ የሚሆኑ ወገኖቻችን በእስርቤት እንደታጎሩ፣ቁጥራቸው ያልታወቁትም በመሰደድ ላይ  እንዳሉ ያመለክታል።የሕዝቡም ንቅናቄ ወደከፈተኛ የትጥቅ ትግል እንዳይሻገር በድንበር አካባቢ ያለውን ቁጥጥር ለማጠንከርና የትጥቅ ማስፈታትም እርምጃ በመላ አገሪቱ በሰፊው ለማካሄድ ያለውን ዕቅድ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በዝርዝር አስረድቷል። እዚህ ላይ የደርግ ተመሳሳይ ድርጊት ሲደገም ማየቱ የስርዓት ለውጥ አለመደረጉን ያሳያል።

ሙስናን በተመለከተ፣እራሱ በሚመራው መንግስት ውስጥ በጥልቀት መስፈኑን ባይክድም በደፈናው ሙስናን ለመዋጋት ደፍረን ከተነሳን ውሎ አድሯል ብሏል። ግን በእውነት ሙስናን የሚታገል መንግስት የሚመራ ቢሆን ኖሮ ለይስሙላ አብሮ ተካፍሎ ለመብላት ያስቸገሩትን ጥቂቶቹን ነካ ነካ አድርጎ ከማለፍ ባሻገር የሙስናው አውታር የሆኑትን የስርዓቱን ቀንደኛ መሪዎችና ተባባሪዎች ማጋለጥ፣ማሶገድና መቅጣት በተገባ ነበር።ግን ስርዓቱ ይገረሰስበታልና ያንን ለማድረግ አይደፍርም።ያንን ሊያደርግ የሚችለውና የሚደፍረው ለሕዝብ መብት የቆመ፣ሕዝብን ከዃላው ያሰለፈ መንግስት ብቻ ነው።

የድንበር መሬትን ቆርሶ ለሱዳን የመስጠቱን ጥያቄ በሚመለከት የሌለ ችግር እየፈጠሩ የሚያስተጋቡት ተቃዋሚዎች እንጂ መንግሥት በዚህ እረገድ ያደረገው ውልና ስምምነት የለም በማለት ዓይኔን ግንባር ያድርገው ብሏል። የድንበር መሬትን በሚመለከት ሱዳኖች ታጥቀው በገዛ መሬቱ ላይ ለዘመናት ሰፍሮ የሚኖረውን ኢትዮጵያዊ እንዳላባረሩት ሁሉ ምንም ችግር እንዳልተከሰተና እንደውም ኢትዮጵያውያኑ የሱዳኖችን መሬት ቀምተው የሚያርሱ ወንጀለኞች ናቸው በማለት ሱዳኖችን ታጋሾች ኢትዮጵያኑን ወንጀለኞች አድርጓቸዋል።  ለራሱ ሕዝብ ጠበቃ በመሆን ፋንታ ህወሓት/ኢህ አዴግ ለሱዳን መንግሥት ዋና ጠበቃ መሆኑ ይዘገንናል። ታላቅ ቁጣንም ይቀሰቅሳል። ድንበሩን ቆርሶ ለመስጠት በስተጀርባ ያደረገውን ውልና ስምምነት ተቃዋሚዎች፤ በተለይ የኢትዮጵያ የድንበሮች ኮሚቲ ላለፉት ስምንት ዓመታት በተከታታይ ያደረጉትን ከፍተኛ ጥረት የውሸት ቅስቀሳ ነው ከማለቱ ጋር አያይዞ እዛው በዛው በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን ድንበር ለመካለል ሥራ መጀመሩን አልካደም። አሁንም ደግመን ደጋግመን ህወሃት/ኢሕአዴግ በአጼ ምኒሊክ፣በአጼ ሃይለስላሴና በወታደራዊው መንግሥት ተከብሮ የቆየውን ዳር ድንበር ማስከበር ብሔራዊ ግዴታው ነው እንላለን።የሱዳን መንግሥት አጣዳፊ ጉዳይ ነው ብሎ አቤቱታ ያላቀረበበትን ጉዳይ ገዢው ፓርቲ እንዳጣዳፊ ጉዳይ ማድረጉ አግባብ የለውም።በእኛ ግምትና የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት ከሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሕገወጥ መንገድ የሱዳንን መሬት አልቀማም፤ለመቀማትም አያስብም።ድንበሩን አስከብሮ ከሱዳን ሕዝብ ጋር ከወያኔ በፊት እንደኖረው ወደፊትም ከወያኔ በዃላ ይኖራል። የሀገር ድንበር ጉዳይ ከፖለቲካ ጨዋታ በላይ ነው። በመሆኑም ይህ እጅግ ሀላፊነት የጎደለው ሀገርን ቀስበቀስ ቆራርሶ ለባእድ የማስረከብ ስራ ማስቆም ደግሞ የሁሉም ዜጋ ሀላፊነት ነው። ይህ አጥፊ ተግባር አሁኑኑ ሊቆም ይገባዋል።

ስለመልካም አስተዳደር፣እርቅና ሰላምም አንስቶ ነበር፡፤ግን ለሰላሙ መደፍረስና መልካም አስተዳደር እንዳይሰፍን እንቅፋት የሆኑት ተቃዋሚዎች ናቸው በማለት  ዋና ተጠያቂ  የሆነውን  እራሱ የሚመራውን መንግሥት ነጻ አድርጎ አቅርቧል።

ከዚህ በላይ በጠቅላይ ምኒስትሩ በአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ንግግር በተነሱት አንኳር የአገር ጉዳዮች ላይ ሸንጎ የተረዳውን ቀንጨብ በማድረግ ያቀረበ ሲሆን ይህ ጥልቀት ያለው ያገር ጉዳይ በአንድ ድርጅት ውሳኔና ፈቃድ የሚከናወኑ እንዳልሆኑ ሸንጎ ያምናል። በስልጣን ላይ ያለው ቡድን አላፊነት አለብኝ ብሎ የሚያምንና የሚቀበል ከሆነ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ፤በአገር ቤትና ከአገር ውጭ የሚገኙ ተቃዋሚ የፖለቲካ፣የማህበረሰብና የሙያ ስብስቦችን በሚያሳትፍ መልኩ በተግባር ሊተረጉመው ይገባል።እርቅና መግባባት የማይግባቡና በአቋም የተለያዩ ሃይሎችን የሚመለከት ጥያቄ ነው፣ማለትም መንግሥትንና ተቃዋሚ ሃይሎችን።ስለሆነም ተቃዋሚውን ሕዝብና ለሕዝቡ መብት ፣ለአገር አንድነት፣ለዴሞክራሲ ስርዓት መስፈንና ለሕግ የበላይነት የቆሙትን ድርጅቶችን፤ ስብስቦችንና ግለሰቦችን እያሳደደ፣እያገለለ፣ እየወነጀለና ሁሉንም በጠላትነት እየፈረጀ ለእርቅና ለመልካም አስተዳደር የቆምኩ ነኝ ማለት ተቀባይነት የለውም።ለጥያቄው ሁሉ የማይመጥን መልስ ያልቋጠረ ጉንጭ አልፋ የማደናገሪያ ስብከት ከመሆን ያለፈ አይደለም።በጠቅላይ ምኒስትሩ በአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝና በድርጅታቸው በህወሀት/ኢህአዴግ ለሕዝቡ ጥያቄ የተሰጠውና ለመስጠትም የተዘጋጀው የአመጽ መልስ “ፍየል ወዲያ ቅዝምዝም ወዲህ”የሚለውን የአገራችንን ነባር አባባል ያስታውሰናል።

ሸንጎ በአገራችን የተከሰተውን መጠነ ብዙ ችግር ለመፍታት የሚቻለው በአንድ ቡድን ፍላጎትና ጥረት አለመሆኑን ያምናል። ስለሆነም ሁሉም ተቃዋሚ ክፍሎች በነጻ ተሳትፎ አገሪቱ የተሻለ አቅጣጫ የምትከተልበትንና የተከሰቱት ችግሮች የሚወገዱበትን መንገድ ለመሻት ከሚፈልጉ ሁሉ ጋር ተባብሮ ለመስራት ፈቃደኛ  መሆኑን ይገልጻል። ይህንንም ሂደት ለመቀየስ የሚያስችል ስብሰባ በአስቸኳይ መደረግ አለበት ብሎ ያምናል፤ ያለንበት ወቅት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ስለደረሰ፣ለዚህ አገር አድን ተልእኮ ለሚሰለፉና ለሚደግፉ ሁሉ  ጥሪ ያደርጋል። ስብሰባው ቢቻል በኢትዮጵያ አለያም በውጭ አገር እንዲካሄድ የብዙሃኑ ውሳኔና ፍላጎት ከሆነ የበኩሉን ለማበርከት ዝግጁ ነው።

 

የሕዝብ ሰላማዊ ትግል ያሸንፋል!!

The post “ፍየል ወዲያ ቁዝምዝም ወዲህ!!” – ሸንጎ appeared first on Zehabesha Amharic.

የአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር አቶ ኤፍሬም ማዴቦ አሜሪካ ገብተዋል

$
0
0

Ephrem Madeno

(ዘ-ሐበሻ) የአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር አቶ ኤፍሬም ማዴቦ የነፃነት ሠራዊቱ ወዳለበት ኤርትራ በረሃ ባለፈው ኦገስት 2015 መጀመሪያ ላይ ከወረዱ በኋላ ሰሞኑን ወደ አሜሪካ እንደመጡ የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታወቁ::

የዘ-ሐበሻ ምንጮች የአርበኞች ግንቦት 7 አመራሩ አቶ ኤፍሬም ማዴቦ ለምን ወደ አሜሪካ እንደመጡ በማጣራት ላይ ይገኛሉ::

ሕወሓት በሚመራውና በሚያዝበት ፍርድ ቤት በአንዱዓለም አራጌ የክስ መዝገብ “በሃገሪቱ የመሰረተ ልማት አውታሮች ላይ፣ በሚዲያ ተቋማትና በባለስልጣናት ላይ አደጋን ለመጣል በሚል ክስ አቶ ኤፍሬም ማዴቦ እጃቸው ከተያዘበት እለት ጀምሮ በ25 ዓመት ዕኑ እስራት እንዲታሰሩ የተፈረደባቸው ፖለቲከኛ ናቸው:: በተጨማሪም ከእነ ብርጋዴር ጄነራል ተፈራ ማሞ ክስ ጋር በዕድሜ ልክ እስራት እንደተፈረደባቸው ይታወሳል::

The post የአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር አቶ ኤፍሬም ማዴቦ አሜሪካ ገብተዋል appeared first on Zehabesha Amharic.

ቦረንቲቻ ቡድን ሕወሓት የሚመራው መንግስት የሚጠቀምበት የኦሮሞ ቴሌቭዥን እና ራድዮ ድረገጽን ሃክ አደረገ

$
0
0
ይህ ሃኪንግ ቡድን መንግስታዊውን የኦሮሞ ቴሌቭዥንና ራድዮ ድረገጽን ሃክ አካደረገ በኋላ የራሱን መፈክሮች ለጣጥፎበታል

ይህ ሃኪንግ ቡድን መንግስታዊውን የኦሮሞ ቴሌቭዥንና ራድዮ ድረገጽን ሃክ አካደረገ በኋላ የራሱን መፈክሮች ለጣጥፎበታል

(ዘ-ሐበሻ) ራሱን ቦረንቲቻ ብሎ የሰየውመና የኦሮሞ ሕዝብ ተቃውሞ አራማጅ ቡድን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ራዲዮና ቴሌቭዥን ድረገፅን መጥለፉን (Hacked) አስታወቀ::

በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች የተጀመረው ሕዝባዊ ቁጣ በሳይበር በኩልም የቀጠለ ሲሆን ቦረንቲቻ የተባለው ቡድን የመንግስት ድረገጾችን ሃክ በማድረግ ተቃውሞውን በመግለጽ ላይ ይገኛል::

ይኸው የሃኪንግ ቦድን በቅርቡ የመከላከያ ሚንስቴርና የሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ ድረገፆች ተመሳሳይ ጠልፏቸው እንደነበር ይታወሳል::

The post ቦረንቲቻ ቡድን ሕወሓት የሚመራው መንግስት የሚጠቀምበት የኦሮሞ ቴሌቭዥን እና ራድዮ ድረገጽን ሃክ አደረገ appeared first on Zehabesha Amharic.


አዲስ አባባ ስለምን ታወዛግባለች? –በዘላለም ክብረት

$
0
0
ዘላለም ክብረት

ዘላለም ክብረት

ሕሩይ ሚናስ አስደናቂ ሰው ነው፡፡ የገበሬ ልጅ፣ በአስራዎቹ መጨረሻ አዲስ አበባ የገባ፡፡ ከዛም የአብነት ተማሪ ሆነና ቅዳሴና ቅኔ ሞካከረ፡፡ እሱ አልሆን ሲለው ጎዳና ወጥቶ ጎዳና አዳሪ ሆነ፡፡ ቀጠለና የለማኝ መሪ (sighted guide) ሆነ፡፡ እሱም ሲያልፍ ‹ለምን አልማርም?› ብሎ ትምህርት ተማረና ዩንቨርሲቲ በገባ በዓመቱ ‹ማርክሲስት› ሆነ፡፡ ትምህርቱንም ለአቢዮቱ ሲባል ተወውና መፅሃፍ ነጋዴ ሆነ፡፡ ማርክሲስት ነጋዴ! ‹ከወገብ በላይ ታቦት፣ ከወገብ በታች ጣኦት› እንዲሉ የትናንት ቀዳሹ ሕሩይ ዛሬ ማርክስዚምን ወደደ፡፡ የሕሩይ ማርክሲዝም ከትናንት ማንነቱ እጅግ በተለየ መንገድ ወሰደው፣ የመፅሃፍ አርታኢነት፡፡ መፅሃፍ ሲያነብ፣ ሲተረጉም፣ ሲፅፍና የአርትኦ ስራ ሲሰራ ውሎ ጫት ይቅማል፤ በዛ ላይ አረቄም ይሞካክራል፡፡ በመጨረሻ አበደ፡፡ ከዛ በኋላ ያለው የሕይወቱ ምዕራፍ ብዙ ያሳዝናል፡፡

በኋላ ከአዕምሮ ሕመሙ ሲያገግም ግን የሚገርም ነገር አደረገ፡፡ ‹እብድ› እያለ ሲያደርጋቸው ነበሩትንና የሚያስታውሳቸውን ነገሮች ሁሉ በተርታ ፅፎ ‹እብዱ› በሚል ርዕስ መፅሃፍ አሳተመ፡፡ ይህ መፅሃፉ ለሕሩይ ከብዙ ስራዎቹ አንዱ ነው፡፡ ስለ አዲስ አበባ ለመፃፍ ከሕሩይ የተሻለ ምሳሌ ማግኝት ይከብዳል፡፡ እሱም ‹ወይ ዐዲስ ዓበባ› በሚል ርዕስ (እውነትን መሰረት ያደረገ) መፅሃፍ ፅፎ አዲስ አበባ ከሩቅ ሲያይዋት ምን እንደምትመስል ይተርካል፡፡ በሕሩይ የገጠር ሕይወት አይን አዲስ አበባ ገነት ነበረች፡፡ ሕሩይ እንዲያውም በመደነቅ ‹‹ለካ የዐዲስ ዓበባን ሰው ፎቶ እያነሱ ነው ወደ ገጠር ‹ምስለ መላዕክትና ሰማዕት› እያሉ የሚልኩልን›› በማለት እሱ ከሚያውቀው ገጠርና ሕዝቡ አንፃር አዲስ አበባ ገነት፣ ነዋሪዎቿም መልዓክት እንደሆኑ ይገልፃል፡፡ ገነት ሆና ከሩቅ የታየችው አዲስ አበባ ሲገባባት ጎዳና ላይ አስተኝታዋላች፣ ‹አቢዮተኛ› አድርጋዋለች፣ አሳብዳ አስለፍልፋዋለች … በስተርጅናውም ‹ከጋራ ኮንዶሚኒየም ቤቶቿ› በአንዱ ይኖር ዘንድ ፈቅዳለታለች፡፡ ሕሩይ አዲስ አባባን ከሩቅ አይቶ ጎምጅቶባታል፡፡ አዲስ አበባን ጉያዋ ስር ሆኖም ተሰቃይቶባታል፡፡ ዛሬ ደግሞ አዲስ አበባ ሕሩይን እንከባከብኻለሁ እያለችው ነው፡፡ ሕሩይ ሚናስ – ራሱን ‹አውግቸው ተረፈ› ብሎ የሰየመ ሰው፡፡
ይህ የሕሩይ ብቻ ታሪክ አይደለም፡፡ የብዙ ኢትዮጵያዊያንም እንጂ፡፡ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባን ከከተማም በላይ የስልጣኔ ምልክት አድርጎ ነው የሚቆጥራት፡፡ እንዲያውም ሌሎች ከተሞች የሚለሙት ከአዲስ አበባ የሚመጡ ነዋሪዎች እንዲዝናኑባቸው ሁሉ እስኪመስል ድረስ የሌሎች ከተሞችን ዕድገት ሁሉ ወሳኟ አዲስ አበባ እየሆነች ነው፡፡ ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉ አካባቢዎች ‹የአዲስ አበባ እንግዶች መጥተዋል› ከተባለ ነገሩ ትልቅ ነው፡፡ አንዳንዴማ ‹እሷ እኮ አዲስ አበባ ቤት አላት› ሲባል ሁሉ ነው ሃብት የሚቆጠረው፡፡
አዲስ አበባ አንድ ከተማ ብቻ ነች ማለት ከባድ ነው፡፡ ከሀገሪቱ አጠቃላይ ሕዝብ 3.6 በመቶው ብቻ ቢሆንም አዲስ አበባ የሚኖረው ቀሪው የሀገሪቱ ሕዝብ ያለ አዲስ አበባ ምንድን ነው? እስኪባል ድረስ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ለተባለው ዓለም የስበት ማዕከል (center of gravity) ናት፡፡
1. “Addis Ababa: The 3rd most ‘Primate City’ on earth”
ጅኦግራፈሩ ማርክ ጀፈርሰን በጎርጎሮሳዊያን አቆጣጠር በ1939 አንድ የከተሞች እድገት ምጥጥን (balance) የሚገልፅ ሃሳብ ይዞ ብቅ አለ፡፡ የአውራ ከተማ (Primate City) ፅንሰ ሃሳብን፡፡ እንደ ጀፈርሰን አገላለፅ አንድ ከተማ በሀገሪቱ ውስጥ ካሉት ሌሎች ከተሞች መካከል በሕዝብ ቁጥር ትልቁ ሲሆንና የሕዝብ ቁጥሩም በሁለተኝነት ከሚከተለው ከተማ በእጥፍ ሲበልጥ ያ ከተማ ‹አውራ ከተማ› (Primate City) ይባላል፡፡ (በኋላ በጀርመናዊው ጅኦግራፈር ዋልተር ክራይስትለር የተፈጠረው የCentral Place Theory (CPT) በበኩሉ አውራነት የሚለካው አውራው ከተማ ከተከታዩ በሁለት ዕጥፍ ከበለጠ ነው በማለት ሌላ መከራከሪያ አቅርቧል)፡፡ ለማንኛውም ጀፈርሰን ይሄን የከተማ አውራነት መስፈርት (primacy rule) ካስቀመጠ ከአስር ዓመታት በኋላ በተለምዶ ‘Zipf’s law’ የሚባለውና በሳይንሳዊው አጠራር ‘Rank Size Rule’ እየተባለ የሚጠራው የምጥጥን (proportionality) ሂሳብ በአሜሪካዊው የስነ ቋንቋ ምሁር ጆርጅ ዚፒፍ ብቅ አለ፡፡ ዚፒፍ ምጥጥኑን ከቋንቋ ጋር አያይዞ ያቀረበው ቢሆንም በኋላ ወደሌሎች ጉዳዮችም አድጓል፡፡ በዚህም መሰረት እንደ ዚፒፍ ሎው የአንድ ሀገር የከተማ እድገት ጤነኛ ነው የሚባለው በአንድ ሀገር ውስጥ ካለው በሕዝብ ቁጥሩ ትልቁ ከተማ ቀጥሎ በሁለተኝነት የሚገኝው ሁለተኛው ከተማ በሕዝብ ትልቁ የሆነውን ከተማ ግማሽ ያክል ሕዝብ ያለው መሆን ይኖርበታል፡፡ ሶስተኛው ትልቅ ከተማ ደግሞ የትልቁን ከተማ ሲሶ ያህል ሕዝብ ሊኖርበት ይገባል፡፡ አራተኛው ትልቅ ከተማ ደግሞ የትልቁን ከተማ ሩብ ያህል ሕዝብ ሊኖርበት ይገባል… እያለ ምጥጥኑን ይቀጥላል፡፡
እንግዲህ ይሄን ህልዮታዊ መነሻ ይዘን፡፡ የአውራ ከተማ መኖር ምንን ያመላክታል የሚለውን ጉዳይ ስናይ ነው የሕልዮቶቹ መሰረት የሚገለፅልን፡፡ አንድ ሀገር አውራ ከተማ አላት ማለት አውራ የተባለው ከተማ የሀገሪቱ የትኩረት ነጥብ (national focal point) ነው ማለት ነው፡፡ ከዛም ባለፈ ያ ከተማ የሀገሪቱን ማሕበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች በዋነኛነት በያኝ (strong pull factor) ነው ማለት ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ሀገሪቱ የንጉሳዊ ግርማ (King Effect) ሰለባ ነች ማለት ነው፡፡ ስለ ሀገሪቱ ማውራት ማለት ስለ አውራው ከተማ ማውራት ነው፡፡ በዚህም ምክንያት በመዓከሉ (center) እና በዳር ሀገሩ (periphery) መካከል የእኩልነት ሚዛን እጅግ ተዛብቷል (imbalance) እንደማለት ነው፡፡
1.1. ሁለተኛ ከተማ (Secondary City)
በሌላ በኩል ደግሞ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአውራ ከተማን ፈተና ለመከላከልና ፍትሃዊ የከተማ እድገት እንዲኖር ሲባል የዓለም ባንክን ጨምሮ ብዙ ፖሊሲ አውጭዎች የሁለተኛ ከተማ (Secondary City) አማራጭን በማቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህም ማለት ከትልቁ ከተማ ባለፈ በሀገራት ውስጥ ከትልቁ ከተማ ብዙም ያልራቁ (አንዳንዶች ከ500,000 – 3,000,000 ነዋሪ ያለባቸው ከተሞች ሲሉ ሁለተኛ ከተማነትን ያብራራሉ) አማራጭ ከተሞችን መፍጠር ነው፡፡ ደቡብ ምስራቅ እስያ በዚህ በኩል በጣም የተሳካለት የዓለማችን ክፍል ነው፡፡
1.2. ኢትዮጵያስ?
የኢትዮጵያን ጉዳይ ስንመለከት ከላይ ከቀረቡት ሕልዮቶችና የፖሊሲ አውጭዎች ምክረ ሃሳብ እጅግ በተቃራኒው እናገኛታለን፡፡ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ባለስልጣን በሃምሌ 2007 ባወጣው ሪፖርት መሰረት ኢትዮጵያ 973 ከተሞች እንዳሏት የገለፀ ሲሆን፤ ከሀገሪቱ አጠቃላይ ሕዝብም 19 በመቶ የሚሆነው (ይህ አሃዝ አከራካሪ ነው) በከተማ ውስጥ ይኖራል ይላል ሪፖርቱ፡፡ ምንም እንኳን ኢትዮጵያ 973 ከተሞች ቢኖሯትም ከአምስቱ የከተማ ነዋሪዎች መካከል አንዱ በአዲስ አበባ ከተማ ነው የሚኖረው፡፡ በሌላ አነጋገር በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ (አዲስ አበባን ሳይጨምር) ከአንድ መቶ ሺህ ሕዝብ በላይ ያላቸው አስራ ስድስት ከተሞች ያሉ ሲሆን፤ የአስራ ስድስቱ ከተሞች ሕዝብ ተደምሮ ከአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ ጋር እኩል ነው፡፡
የማርክ ጀፈርሰንን የአውራነት ሕግ (primacy rule) እዚህ ላይ አምጥተን ስንመለከት አዲስ አበባን ከአውራም አውራ ሆና እናገኛታለን፡፡ ይሄም የሚሆነው በአንድ ሀገር ውስጥ ያለው ትልቅ ከተማ (አዲስ አበባ) በሀገሪቱ ውስጥ ካለው ሁለተኛ ትልቅ ከተማ (በሃምሌው የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ባለስልጣን ሪፖርት መሰረት አዳማ ከተማ ናት ሁለተኛዋ ብዙ ሕዝብ የሚኖርባት ከተማ) በእጥፍ ከበለጠ አውራ ከተማ እንደሚባል ከላይ ያየን ሲሆን፣ በዚህ ስሌት መሰረትም አዲስ አበባ ከተከታዩ አዳማ ወደ አስራ አንድ እጥፍ እንደምትበልጥና ይሄም አዲስ አበባ ከታይላንዷ፣ ባንኮክና ከፔሩዋ ሊማ ቀጥላ በዓለም ላይ ሶስተኛዋ አውራ ከተማ ሲያደርጋት በአፍሪካ ደግሞ አንደኛዋ ያደርጋታል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ይህ ግዝፈቷ የዚኮፍን የምጥጥን ሎው እንኳን መተግበር ማሰብም ከባድ ያደርገዋል፡፡ ይህ የተዛባ ምጥጥን አዲስ አበባ ከመመስረቷ ጀምሮ የተፈጠረ ነው ማለት ደግሞ ከባድ ነው፡፡ የአለፈውን የመቶ ዓመት እድገት እንኳን ብንመለከት በ1910 የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ 65,000 የነበረ ሲሆን ይህ ቁጥርም በጊዜው ከሀረር ከተማ ሕዝብ ጋር እኩል ነበር፡፡ ከሃያ አምስት ዓመታት በኋላ 1935 የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ 100,000 ሆነ፡፡ ከሌላ ሃያ አምስት ዓመታት በኋላ በ1961 የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ 443,728 ደረሰ፡፡ አሁንም ከሌላ ሃያ አምስት ዓመታትም በኋላ በ1984 የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ 1,423,111 ደረሰ፡፡ በመጨረሻም ከ35 ዓመታት በኋላ በ2015 የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ ከእጥፍ በላይ ጨምሮ ዛሬ 3,194,000 ደርሷል፡፡ ከመቶ ዓመታት በፊት በጊዜው በሕዝብ ቁጥር ሁለተኛ ከነበረችው የሀረር ከተማ ጋር ተመጣጣኝ ቁጥር የነበረው የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ ዛሬ በሁለተኝነት ከምትገኝው አዳማ ከተማ አስራ አንድ እጥፍ በልጣ በአውራ ከተማነት በሩቅ ተቀምጣለች፡፡
ስታንሊ ብሩን የተባሉ ፀሃፊ ‹‹የአውራ ከተማ መኖር በራሱ የሀገሪቱ እድገት ጤናማ እንዳልሆነና የተዛባ እንደሆነ ማሳያ ነው፡፡ ይሄም ማዕከሉ (center) ከዳሩ (periphery) አለመመጣጠናቸውን ያስገነዝበናል› ይላሉ፡፡ እንግዲህ የአሁኗ ኢትዮጵያን ፍትሃዊነት አዲስ አበባ በደንብ የምትገልፃት ይመስላል፡፡
አዲስ አበባ በታሪኳ ሶስት ጊዜ ከዋና ከተማነቷ የመቀየር እጣ ፋንታ ተጋርጦባት እንደምንም አልፋዋለች፡፡ የመጀመሪያው በአፄ ምኒልክ ዘመን በአካባቢዋ ያለው የማገዶ እንጨት በማለቁ ምክንያት ዋና ከተማው ወደ አዲስ ዓለም ለመቀየር በታሰበበት ወቅት ባህር ዛፍ ከአውስትራሊያ መጥቶ አዲስ አበባን ከመቀየር አድኗታል፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ ጣሊያን አዲስ አበባን በተቆጣጠረበት ወቅት አዲስ አበባ ተራራማ ከተማ ላይ በመሆኗ ጣሊያኖቹ የራሳቸውን የቅኝ ግዛት ዋና ከተማ (colonial city) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አካባቢ ለመመስረት ጥረት አድርገው በፋይናንስ እጥረት ምክንያት ሊተዉት ችለዋል፡፡ እንዲሁም አፄ ኃይለስላሴ የቀደመውን የተንቀሳቃሽ ዋና ከተማ (roving cities) ልምድ ለማስቀጠልና የራሳቸውን ዋና ከተማ ለማቋቋም በማሰብ ባህርዳርን ዋና ከተማቸው ለማድረግ አስበው እንደነበር ታሪክ ፀሃፊው በላይ ግደይ ‹አዲስ አበባ ያብባል ገና› ባሉት መፅሃፋቸው ላይ ይጠቁማሉ፡፡ ዛሬ አዲስ አበባ ዋና ከተማ ብቻ ሳትሆን ‹ሀገር› ናት፡፡ የበታቾቿን በሩቅ የምታይ ከተማ፡፡
በሌላ በኩል እነ ዓለም ባንክ እያስተዋወቁት የሚገኝው የሁለተኛ ከተማ (Secondary City) ፅንሰ ሃሳብም በአሁኗ ኢትዮጵያ ቦታ የሌለው ጉዳይ ነው፡፡ በፖለቲካና የንግድ ማዕከልነት የአውራዋን አዲስ አበባን ሚዛን የሚገዳደር አይደለም፤ ተስፋ እንኳን ያለው ከተማ አለ ማለት በጣም ከባድ ነው፡፡ ይህ የአዲስ አበባ አውራነትም ከተማዋን በሀገሪቱ ውስጥ በነዋሪ ደረጃ የመሰረታዊ አገልግሎቶች በቀላሉ የሚገኝባት (the highest concentration of basic service facilities per population) ቀዳሚ ከተማ አድርጓታል፡፡ ይሄም ከተማዋን ‘privileged position’ ያሰጣት ከመሆኑም ሌላ፤ አዲስ አበባን እጅግ ግዙፍና የማይደረስባት አይነት ከተማ አድርጓታል፡፡
ከአዲስ አበባ ምስረታ ጋር ተያይዘው ከሚነገሩ አፈ ታሪኮች አንዱ፣ የአፄ ምኒልክ ሃይለ መለኮት አያት የሆኑት ንጉሰ ሸዋ ሳህለስላሴ በአንድ ወቅት ጉለሌ የሚገኝ አንድ ዛፍ ስር ቁጭ ብለው ‹እዚህ አካባቢ የልጅ ልጆቼ ትልቅ ከተማ ሲመሰርቱ ይታየኛል› ብለው ነበር ይላል፡፡ ሳህለስላሴ የዛሬዋን አዲስ አበባ ቢያዩ ‹እንዴ እኔ በራዕይ ያየሁት እኮ ሀገር አይደለም ከተማ ነው› ብለው መደናገራቸው የሚቀር አይመስለኝም፡፡
የፌደራል ሀገሮች ተሞክሮ እንደሚያሳየን ፌደራሊዝም ‹አውራ ከተማን› (Primate City) ያጠፋል፡፡ የደቡብ ምስራቅ ተሞክሮ እንደሚያሳየን ደግሞ ልማታዊ መንግስት በዛ ያሉ ሁለተኛ ከተሞችን (Secondary Cities) ይፈጥራል፡፡ አውራዋ አዲስ አበባ የአውራዎች አውራ እየሆነች እየሄደች ሲሆን፡፡ አውራ ብቻ ሳትሆን ሁለተኛ ከተማም (Secondary City) ራሷ አዲስ አበባ ነች፡፡ አዲስ አበባ ብቻዋን እንዲህ ገዝፋ የአውራም አውራ እስክትሆን ድረስ ፖሊሲ አውጭዎቹ የት ሂደው ነው ብሎ መጠየቅ እዚህ ጋር ተገቢ ነው፡፡ የአሁኗ አዲስ አበባ ሕጋዊ (Legal status) ምንድን ነው ብለንም መጠየቅ ተገቢ ነው፡፡
2. አዲስ አበባ ምንድን ናት?
ኢትዮጵያ የፌደራል ስርዓትን በሕገ መንግስት ደረጃ ከተቀበለች ሁለት አስርት ዓመታትን አስቆጥራለች፡፡ የኢትዮጵያ የፌደራል ስርዓትም በሕገ መንግስት ደረጃ ዘጠኝ ክልሎችንና አዲስ አበባን እንደ አንድ የፌደራል ከተማ አስተዳደር (ድሬ ዳዋ በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች መካከል ያለው የይገባኛል ጥያቄ ‹ዘላቂ የሆነ ሕጋዊ መፍትሔ እስኪያገኝ› ለፌደራል መንግስቱ ተጠሪ በመሆን በአዋጅ ቁጥር 416/1996 የተቋቋመች የከተማ አስተዳደር ናት) በማድረግ ተቋቁሟል፡፡ በሕገ መንግስቱም ሆነ በኋላ ከተማዋን በሕግ ለማቋቋም በወጡት ቻርተሮች የከተማዋ ሕጋዊ ‹ስታተስ› (ከዋና ከተማነት ባለፈ) በግልፅ ባለመቀመጡም የከተማዋ ‹ስታተስ› ለተመሳሳይ ጥያቄ የተለያዩ መልሶችን እየሰጠ ቀጥሏል፡፡ ዓለም ላይ ባሉ የተለያዩ የፌደራል ስርዓቶች ዋና ከተማ ከዚህ በሚከተሉት ሶስት ጎራዎች በአንዱ ላይ ይመደባል፡፡ ራሱን የቻለ ክልል (City State)፣ በሕግ በፌደራል ቀጠናነት የተመደበ ከተማ (Federal District)፣ እና በአንድ ክልል ውስጥ የሚገኝ አንድ ከተማ (A City in A State)፡፡ ኢትዮጵያም በሕግ የፌደራል ስርዓትን ያቋቋመች ሀገር በመሆኗ ዋና ከተማዋ አዲስ አበባ በየትኛው ጎራ ትመደባለች ለሚለው ጥያቄ አንድ አይነት መልስ ማግኝት አስቸጋሪ ነው፡፡ ይህ አስቸጋሪ ሁኔታም ነው በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል መካከል ያለው ውዝግብ እንዳይፈታ አይነተኛ አስተዋፅኦ እያደረገ ያለው፡፡ ከላይ ከተጠቀሱት ሶስቱ መደቦች አንፃር የአዲስ አበባን ‹ስታተስ መመልከት› ጉዳዩን በበለጠ እንድንረዳው ይረዳናልና እሱን እንመልከት፡፡ ለመሆኑ አዲስ አበባ ምንድን ናት?
2.1. ራሷን የቻለች ክልል (City State) ናት
የፌደራል ስርዓትን ተግባራዊ ያደረጉ ሀገሮች ከሚያጋጥሟቸው ፈተናዎች አንዱ ዋና ከተማን መምረጥና መሰየም ነው (የስዊዘርላንድ ሕገ መንግስት በሕገ መንግስት ደረጃ ዋና ከተማ ከመሰየም የተቆጠበውም በዚህ ውዝግብ ምክንያት ነው)፡፡ የፌደራል ስርኣት የመንግስት ስራን በማዕከሉ መንግስትና በክልሎች መካከል የሚከፍል በመሆኑ ዋና ከተማዋን የትኛው ክልል ላይ ማድረግ አለብን የሚለው ጥያቄ አወዛጋቢ ነው፡፡ እንደ ጀርመን እና ቤልጅየም ያሉ የፌደራል ሀገሮች ለዚህ መፍትሔ ብለው ያቀረቡት ሀሳብ ዋና ከተማውን ራሱን የክልል ማዕረግ በመስጠት ከፌደራሉም ሆነ ከክልል መንግስታት ነፃ ማውጣትን ነው፡፡ በመሆኑም በርሊን በአሁኑ ወቅት ከአስራ ስድስቱ የጀርመን ክልሎች አንዷና ዋና ከተማ ስትሆን የቤልጀሟ ብራሰልስም ከቤልጅየም ሶስት ክልሎች አንዷ በመሆን የተፎካካሪዎቹ ፍሌሚሽና ዋሎን ክልሎች አስታራቂ ሁና በመሃል ትገኛለች፡፡
ታዲያ አዲስ አበባ ከዚህ ሞዴል ጋር ምን አገናኛት? በርግጥ አሁን በስራ ላይ ያለው ሕገመንግስት ያቋቋመው ዘጠኝ ክልሎችን ብቻ ነው፡፡ አዲስ አበባ ደግሞ ከነዚህ ክልሎች ውጭ ናት፡፡ ነገር ግን አዲስ አበባን በዋና ከተማነት ያቋቋመው የሕገ መንግስቱ አንቀፅ 49ን በጥልቀት ስንመለከት በንዑስ አንቀፅ ሁለት ላይ አዲስ አበባን ራሷን በራሷ የማስተዳደር ሙሉ መብት ይሰጣታል፡፡ ይህ አንቀፅም በሽግግር መንግስቱ ወቅት በአዋጅ ቁጥር 07/1984 እንደ ራስ ገዝ አስተዳደር በመሆን የተቋቋመችውን አዲስ አበባን መንፈስ ያጠናክራል፡፡ ይሄንም ስንመለከት አዲስ አበባ በተግባር (de facto) ራሷን የቻለች ክልል ትመስላለች፡፡ በነገራችን ላይ አዲስ አበባ ራሷን ችላ በሕግ ደረጃ (de jure) ክልል እንድትሆን ከሽግግሩ ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ የሚጎተጉቱ አካላት ብዙ ናቸው፡፡
2.2. የፌደራል ቀጠና (Federal District) ናት
በሌላ በኩል የፌደራል ዋና ከተማን የመምረጥ ፈተና ለማለፍ በዛ ያሉት ፌደራል ሀገሮች ዋና ከተማዋን በፌደራል ቀጠናነት (Federal District) በሕግ በመከለል ተጠሪነቷን ሙሉ ለሙሉ ለፌደራል መንግስት የማድረግን አሰራር ይጠቀማሉ፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆኑት አሜሪካና ሕንድ ናቸው፡፡ አሜሪካ ከሜሪላንድና ከቨርጅኒያ ግዛቶች መሬት በመውሰድ ዋሽንግተን ዲሲን በዋና ከተማነት ሰይማ (ስፋቱ ከአስር ማይል መብለጥ የለበትም የሚል ገደብ በማስቀመጥ) ተጠሪነቷን ለኮንግረስ አድርጋለች፡፡ ሕንድም ዴልሂን ዋና ከተማና የፌደራል ቀጠና አድርጋ ተጠሪነቱን ለምክር ቤት አድርጋለች፡፡ ይህ አይነት የዋና ከተማ አደረጃጀት የራሱ የሆነ (በተለይም ከምርጫ፣ ግብር እና የክልሎች መብት አንፃር) ችግሮች ያሉበት ነው፡፡ ከታች ለማየት እንሞክራለን፡፡
አዲስ አበባን ስንመለከት የህገ መንግስቱ አንቀፅ 49 (3) እና (4) አዲስ አበባ ተጠሪነቷ ለፌደራሉ መንግስት መሆኑን በመግለፅ የአዲስ አበባ ቀጠና የፌደራል ቀጠና እንደሆነ በተዘዋዋሪ ያስረዳል፡፡ ይህ ብዙ ሰዎች የሚስማሙበት ሃሳብ ቢሆንም ተያያዥ ችግሮች ግን በየጊዜው መነሳቸው አልቀረም፡፡
2.3. በአንድ ክልል የምትገኝ አንድ ከተማ (A City in a State) ናት
ሌላው ከፌደራል ዋና ከተማ አመሰራረት ጋር ተያይዞ የሚቀርበው መፍትሔ ደግሞ ዋና ከተማዋን ከክልሎች (States) በአንዱ ከተማ ላይ ማድረግና ክልሎች ተገቢውን ጥቅም እንዲያገኙ ማድረግ የሚለው ነው፡፡ የዚህ መፍትሔ ምሳሌ ተደርጋ የምትቀርበው ካናዳ ነች፡፡ የካናዳዋ ዋና ከተማ ኦታዋ ከካናዳ ስድስት ክልሎች አንዷ በሆነችው ኦንታሪዎ ግዛት ውስጥ የምትገኝ ከተማ ነች፡፡ ኦንታሪዎም እንደ ዋና ከተማ መቀመጫ ክልልነቷ ከኦታዋ ማግኝት የሚገባት ጥቅም በሕግ የተደነገገና የፀና ነው፡፡ ይህ አካሔድ በሌሎች ክልሎች ዘንድ ቅሬታ ይፈጥራል የሚል ትችት ይቀርብበታል፡፡
የአዲስ አበባን ጉዳይ ከዚህ አንፃር ስንመለከተው ደግሞ ከላይ በጠቀስነው የሕገ መንግስቱ አንቀፅ 49 (5) ላይ ‹የኦሮሚያ ክልል […] አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል መሃል ላይ የሚገኝ በመሆኑ […] ያለው ልዩ ጥቅም ይጠበቅለታል› ይላል፡፡ ይሄም ማለት በሌላ አነጋገር አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የምትገኝ አንድ ከተማ ነች እንደማለት ነው፡፡
2.4. ቻርተርድ ከተማ (Chartered City) ናት
አዲስ አበባ ሶስቱንም የፌደራል ዋና ከተማ ባህሪ አዳለ በመያዝ በየትኛው ሕጋዊ ‹ሰታተስ› ላይ እንዳለች ግራ የምታጋባ ከተማ ነች፡፡ ከዚህ በባሰ ደግሞ ከተማዋ በራሴ ቻርተር የምትተዳደር ከተማ (Chartered City) ነኝ በማለት ራሷን በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ቻርተር 87/1989 አቋቁማለች (ቻርተሩ በ1995 በአዋጅ ቁጥር 311/1995 እና በአዋጅ ቁጥር 361/1995 ሙሉ ለሙሉ ተሸሽሏል፡፡ እንዲሁም በ1996 በአዋጅ ቁጥር 408/1996 በከፊል ተሻሽሏል)፡፡ ይህ በዋናነት በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የከተማ ድህነትን ለመቀነስ እንደስትራቴጅ እየተወሰደ ያለ የአወቃቀር አይነት አዲስ አበባ ለምን እንደመረጠችው ብዙም ግልፅ ባይሆንም፤ በሁሉም ቻርተሮች ላይ ዋነኛ ዓላማው ‹የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ራሱን በራሱ የማስተዳደር ሙሉ ስልጣን እንዳለው […] በሕገ መንግስቱ በመደንገጉ› ምክንያት እንደሆነ ተገልፆ እናገኛለን፡፡ አዲስ አበባ ቻርተርድ ከተማ ነች ማለትም ከላይ 2.1 ላይ ለማመላከት የተሞከረውን የክልል ማዕረግ (status of state) የሚያጠናክር ሃሳብ ሆኖ የከተማዋን ስታተስ ለመወሰን ከላይ ያየናቸውን የዋና ከተማ ብያኔ ክርክር የበለጠ ያጦዘዋል፡፡
እንግዲህ አዲስ አበባ ራሷን የቻለች ክልል ናት፣ ተጠሪነቷ ለፌደራል መንግስቱ የሆነች የፌደራል ቀጠና ናት፣ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የምትገኝ አንድ ከተማ ናት እንዲሁም በራሷ የቆመች ቻርተርድ ከተማ ነች የሚሉ የራሳቸው አሳማኝ ምክንያት ያላቸው መከራከሪዎች ይቀርባሉ፡፡ ይህ ግልፅነት የጎደለው የከተማዋ ‹ስታተስም› አሁን ከተማዋን አስመልክቶ ለሚነሱ ውዝግቦች መነሻና መድረሻ ነው፡፡
3. ‹የአንተም ተው፣ አንችም ተይ ፌደራሊዝም› እና መዘዙ
[የኢትዮጵያ የሕገ መንግስት ኮሚሽን] ሰብሳቢ [አቶ ክፍሌ ወዳጆ] [የኮሚሽኑ] አባላት ተሳትፎና ኮሚሽን የሥራ ሒደት በተመለከተ አልፎ አልፎ አባላት በስብሰባ ላይ ያለመገኝት ሁኔታ በማሳየታቸው የስራ መጓተት እየተከሰተ መሆኑን፣ ከፓናሎች የሚጠበቁ ሪፖርቶች በተፈለገው ጊዜ ሊቀርቡ እንዳልቻሉና ይኸውም የፓናል አባላቶች በስብሰባ አለመገኘት ዋነኛው ምክንያት መሆኑን ገልፀው፣ ለመጪው ጊዜ በእያንዳንዱ ስብሰባ በሚነሱ ጉዳዮች ላይ በበቂ በመዘጋጀት ለውሳኔ የሚያበቃ ሰፈ ግንዛቤ በመጨበጥ መገኘት ከእያንዳንዱ አባል እንደሚጠበቅ አሳስበው፣ […] የአዲስ አበባን የመናገሻ ከተማነት ደረጃ (status) እና ወደፊት አከላለስ ሊኖራት የሚችለውን ቦታ አስመልክቶ በሚዘጋጀው የመወያያ ሰነድ (working paper) ውስጥ እንዴት ማስቀመጥ እንደሚቻል ውይይት ማድረግ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡፡››
ይህ ሐሳብ የተገለፀው የአሁኑን የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት ለማርቀቅ የተቋቋመው የሕገ መንግስት ኮሚሽን ሰብሳቢ በነበሩት አቶ ክፍሌ ወዳጆ ጳጉሜ 1- 1985 በኮሚሽኑ 39ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ነው፡፡ እንደ ሰብሳቢው ሐሳብ ከሆነ ሕገ መንግስትን ያህል ሰነድ ለማርቀቅ የተዋቀረው ኮሚሽን አባላት በኮሚሽኑ ስብሰባ ላይ አለመገኘታቸው አሳስቧቸውና የአዲስ አበባን ደረጃ (status) ገና ሳይወስኑ እስከ አሁን መቆየታቸው አሳስቧቸው ነው፡፡ ሰብሳቢው አቶ ክፍሌ ይሄን ቢሉም ይሄን ማስጠንቀቂያ በተናገሩበት እለት እንኳን ከ27 የኮሚሽኑ አባላት መካከል ስምንት የሚሆኑት አልተገኙም ነበር፡፡ አዲስ አበባን አስመልክቶ የቀረቡት ጉዳዮች በሕገ መንግስታዊው ጉባኤ የተወሰነ ውይይት ቢደረግበትም፣ በኮሚሽን ደረጃ ብዙም ውይይት እንዳልተደረገበት በጊዜው የኮሚሽኑ አባል የነበሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ይገልፃሉ፡፡ እንግዲህ ያ በቸልተኝነት የታለፈ ጉዳይ ነው አንዱ የዛሬው ችግር መነሻ፡፡ አዲስ አበባ የክልልም፣ የፌደራል ግዛትም እንዲሁም የአንድ ክልል ከተማ መልክ ይዛ ከሶስቱ አንዱን መሆን አለመቻሏ በጊዜው ሲሟገቱ የነበሩ ሁሉንም አካላት ለማስደሰት በሚል የታለፈ ጉዳይ ይመስላል፡፡
የተለያዩ ምሁራን አዲስ አበባን አስመልክቶ የተለያዩ ጥያቄዎችን እያነሱ ሕገ መንግስቱ መመለስ አለመቻሉን ሊያሳዩን ይሞክራሉ፡፡ መሰረታዊዎቹን ጥያቄዎች እዚህ ላይ ማንሳት ተገቢ ስለሚሆን አንስተን እንመልከታቸው፡፡
1. የአሜሪካ ዋና ከተማ የሆነችው ዋሽንግተን ዲሲ በተቋቋመችበት ወቅት መሬት ከሜሪላንድና ከቨርጅኒያ ስቴቶች ተቆርጦ ተሰጥቷት ነው የተቋቋመችው፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን ቨርጅኒያ መሬቴን መልሽልኝ በማለት መሬቷን በሕዝበ ውሳኔ መሬት የማስመለስ ሒደት (retrocession) መሰረት አስመልሳለች፡፡ ሜሪላንድም እስከ አሁን አልጠየቀችም እንጂ ብትጠይቅ ልታገኝ እንደምትችል የሕገ መንግስት ምሁራን ይገልፃሉ፡፡ አዲስ አበባ የምትገኝው በኦሮሚያ ክልል ውስጥ እንደሆነ ሕገ መንግስቱ በግልፅ ይደነግጋል፡፡ ታዲያ ኦሮሚያ ‹መሬቴን ራሴ አስተዳድራለሁ› ብትል በምን አግባብ ነው መልስ የሚሰጠው?
2. አሁንም እዛው ዋሽንግተን ዲሲ እንቆይና ባራክ ኦባማን ጨምሮ ብዙ የአሜሪካ ፖለቲከኞች ዋሽንግተን ዲሲ ራሷን የቻለች ሃምሳ አንደኛ የአሜሪካ ‹ስቴት› ብትሆን ፍላጎት እንዳላቸው (ከመራጭነት መብት አንፃር) ይገልፃሉ፡፡ ሐሳቡ ወደ ፊት ሊተገበር የሚችል ጉዳይ እንደሆነም ምሁራን እያስረዱ ይገኛሉ፡፡ አዲስ አበባ ራሴን ችዬ ክልል ልሁን ብትል በምን አግባብ ነው የሚስተናገደው ለሚለው ጥያቄ የራስን ክልል የመመስረት መብት የሚሰጠው የሕገ መንግስቱ አንቀፅ 47 (2) መብቱን የሚሰጠው ‹ለብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች› ሲሆን አዲስ አበባ በምን ጎራ ላይ እንደምታርፍ ምንም የተገለፀ ነገር የለም፡፡
3. አዲስ አበባ አሁን ባላት ቁመና ቻርተርድ ከተማ እንደሆነች ከላይ ለማየት ሞክረናል፡፡ ቻርተርድ ከተሞችን (Chartered Cities) ከሌሎች ከተሞች (General Law Cities) የሚለያቸው ዋነኛው ጉዳይ ደግሞ የፌደራልንም ሆነ የክልል መንግስታትን ጣልቃ ገብነትን የሚያስወግድ አሰራር መተግበራቸው ነው፡፡ ታዲያ አዲስ አበባ ቻርተርድ ከተማ እንደመሆኗ ‹የፌደራል መንግስቱን ጣልቃ ገብነት አልፈልግም› ብትል ሕገ መንግስቱ ምን መልስ ይሰጣል?
እነዚህን ሕልዮታዊ ጉዳዮች ያነሳነው የአሁኑ የኢትዮጵያ ፌደሬሽን በተግባር የሌለ ብቻ ሳይሆን በአወቃቀር ደረጃም የማይመልሳቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች መኖራቸውን ለማመላከት ነው እንጂ፤ ‹ጠያቂም መላሽም› እንደሌለ መረዳት ከባድ ሆኖ አይደለም፡፡
አዲስ አበባም ፖለቲካዊ፣ ሕጋዊ እንዲሁም መዋቅራዊ ችግሮቿ ሰንገው በያዟት በዚህ ወቅት ነው ‹የአዲስ አበባና ዙሪያዋ ኦሮሚያ ልዩ ዞን [የተቀናጀ] የጋራ ልማት ፕላን› ተብሎ የተሰየመው የሃያ አምስት አመታት ዕቅድ ብቅ ያለው፡፡
4. ‹[የተቀናጀ] የጋራ ልማት ፕላን› እና አዲስ አበባ
ስድስተኛው የዓለም የከተሞች ፎረም በጣሊያን ኔፕልስ ከሴፕቴምበር 02 እስከ 07 – 2012 ነበር የተካሔደው፡፡ ፎረሙ በተባበሩት መንግስታት ከተቋቋመበት ከ2002 ጀምሮ ባሉት አስር ዓመታት ውስት ለስድስተኛ ጊዜ ስብሰባ ማድረጉ ነበር፡፡ ከመላው ዓለም ከመጡ የተለያዩ ሀገር ተወካዮች አማካኝነት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የተወያየ ሲሆን የፎረሙ ዋነኛ አጀንዳም ‹Urban Future› የሚል ሲሆን በዋናነትም አራት መሰረታዊ ጉዳዮችን እንደመወያያ ይዞ ተካሂዷል፡፡ ከነዚህ አራት የውይይት ርዕሶች መካከል ቀዳሚው ‹Urban Planning: Institutions and Regulations› የሚል ነበር፡፡ በውይይቶቹ መጨረሻ ‹የዓለም የከተሞች ማንፌስቶን› ጨምሮ የተለያዩ የውይይቱ ውጤቶች ይፋ የተደረጉ ሲሆን፤ ከነዚህ የውይይቱ ውጤቶች መካከልም የዓለም ከተሞች የተቀናጀ የልማት ዕቅድን (Integrated Development Plan – IDP) ተግባራዊ እንዲያደርጉ የሚመክረው (recommendation) ይገኝበታል፡፡ ይህ በተባበሩት መንግስታት ደረጃ የቀረበው በ2012 ቢሆንም ከዛ በፊት በ2007 ‘Leipzig Charter on Sustainable European Cities’ የአውሮፓ ሀገሮች ይሄን የተቀናጀ አካሄድ በከተሞቻቸው ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸው ተስማምተው ነበር፡፡
ከዚህ ጊዜ ወዲህ አንዳንድ የአፍሪካ ሀገሮች የተቀናጀውን አካሄድ ተግባራዊ ሲያደርጉ ተስተውሏል፡፡ የደቡብ አፍሪካዋ ኬፕ ታውን (ከ2012 -2017) እና የኬኒያዋ ናይሮቢ (ከ2014 -2019) በዚህ ረገድ ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ደቡብ አፍሪካ እንዲያውም በሃገሪቱ ላሉ ከተሞች አጠቃላይ የተቀናጀ የልማት ዕቅድን ተግባራዊ እንዲያደርጉ መመሪያ እስከማውጣት ደርሳለች፡፡
4.1. የተቀናጀ የልማት ዕቅድ (Integrated Development Plan – IDP) ምን ለማለት ነው?
አንድ አይነት እና ወጥ የሆነ መልስ ማግኝት ባይቻልም የተለያዩ ከተሞች ከሰጡት የተለያየ ትርጉም አንፃር ሁለት መሰረታዊ ነገሮችን ማግኘት እንችላለን፡፡ 1. ሁሉም መሰረተ ልማት ላይ የሚሰሩ አካላት (የትራንስፖርት፣ የመብራት፣ የቤቶች ወዘተ) ተቀናጅተው ለተመሳሳይ ግብ እንዲተጉ ማድረግና 2. እቅዱን ያወጣው አካል ከእቅዱ ባለቤት (የከተማው ነዋሪ) ጋር አሳታፊ (participatory) በሆነ መንገድ በየጊዜው በመወያየት ተቀናጅቶ የሚሰራበት አካሄድ ነው፡፡ እንደ ናይሮቢ ያሉ ከተሞች በተቀናጀ የልማት ዕቅዳቸው የመሰረተ ልማት አገልግሎት (በተለይም ትራንስፖርት) በዙሪያው ካሉ አካባቢዎች (surroundings) ጋርም ለማቀናጀት ሙከራ አድርገዋል፡፡
በዚህ ጊዜ አዲስ አበባም በ1996 አዘጋጅታው የነበረው የከተማ ልማት እቅድ (ማስተር ፕላን) የትግበራ ጊዜው እያለቀ ነበርና የራሷን አዲስ ዕቅድ ለማዘጋጀት ቢሮ ከፍታ እንቅስቃሴ የጀመረችበት ጊዜ ነበር፡፡ መጀመር ብቻም ሳይሆን ስድስተኛው የዓለም የከተሞች ፎረም በተካሔደበት በመስከረም 2005 ለእቅዱ የሚያስፈልገውን መረጃ ለቀማ እንዳጠናቀቀች ይፋ አድርጋ እቅዱንም በጥቂት ወራት ውስጥ አጠናቅቄ ይፋ አደርጋለሁ ብላ ነበር፡፡ እንደተባለው እቅዱ በጥቂት ወራት ውስጥ እንደተጠናቀቀ ውስጥ ለውስጥ የተነገረ ሲሆን የመጀመሪያውንም ተቃውሞ በግንቦት 2005 ከኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) በወጣ መግለጫ አስተናግዳ ከዛ በኋላ የሆነውና እየሆነ ያለው ጉዳይ ሁሉም የሚያውቀው ነው፡፡ እዚህ ላይ ትክክለኛውን አከራካሪ ጉዳይ ለመለየት እንችል ዘንድ የእቅዱን መሰረት እና ይዘት ማየት ተገቢ ጉዳይ ነው፡፡
4.2. ‹ኢንደስትሪያላይዜሽን› ዘመነኛው ካርድ
‹‹የህዝባችን ኑሮ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚደርሰው አገራችን በኢንዱስትሪ የበለፀገች አገር ስትሆን ነው፡፡ አገራችን በአለም አቀፋዊው ኢኮኖሚያዊ ትብብር ውስጥ የሚኖራት ድርሻና ከዚሁ የምታገኝው ጥቅም በከፍተኛ ደረጃ ሊያድግ የሚችለው በኢንዱስትሪ የበለፀገች ስትሆን ነው፡፡ በመሆኑም የኢኮኖሚ ልማት እንቅስቃሴያችን ግብ በኢንዱስትሪ የበለፀገች አገርን መፍጠር መሆን አለበት፡፡ ሌላው ቀርቶ የግብርናና የገጠር ልማት እንቅስቃሴያችን የመጨረሻው ግብ አገራችን በኢንዱስትሪ የበለፀገች እንድትሆን ማድረግ ነው፡፡››
ይህ ሀሳብ የተገለፀው በ1994 በወጣው የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጅ ላይ ነው፡፡ ስትራቴጂው የግሉን ባለሃብት የኢንደስትሪያላይዜሽኑ መሰረት ማድረግና ግብርናው ኢንደስትሪውን እንዲመራው ማስቻል (Agriculture Development Led Industrialization – ADLI ) መሰረታዊ ጉዳይ እንደሆነ አስቀምጦ ያልፋል፡፡ ከዚህ ስትራተጅ የተከተሉት የእድገትና እና ትራንስፎርሜሽን እቅዶችም ዓላማቸው ግብርና የሚመራውን የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ወደ ኢንደስትሪ መር ማሸጋገርን (transformation) ዓላማ አድረገው የተቀረፁ ናቸው፡፡ ቁጥሮች እንደሚነግሩን ግን ኢሕአዴግ በኢንደስትሪው መስክ አልተሳካለትም፡፡ ኢንደስትሪው ያለፉት 50 አመታትን ተመሳሳይ መንገድ ይዞ የሚያዘግም ነው፡፡ ኢንደስትሪውን ይመሩታል የተባሉት ግብርና እና የግል ባለሃብቱም ከፕሮፓጋንዳ ባለፈ ብዙም በአካባቢው አይታዩም፡፡
ኢንደስትሪው የትም እንዳልደረሰ እና ‹ትራንስፎርም› የሆነ ብዙም ነገር እንደሌለ የተረዳው ኢሕአዴግ በድንጋጤ (frustration) የደቡብ ምስራቅ እስያ ተሞክሮ የሆነውን መንግስት መር (statist) ኢንደስትሪያላይዜሽን ተግባራዊ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ ከአስራ አምስት ዓመታት በፊት ኢንደስትሪውን ይመራዋል የተባለው ገበያና የግል ባለሃብትም ከአመራርነት ወርደው ቦታቸውን ለመንግስት አስረክበው ይገኛሉ፡፡
እንግዲህ በዚህ የኢሕአዴግ የኢንደስትሪያላይዜሽን ድንጋጤ ወቅት ነው ‹የአዲስ አበባና ዙሪያዋ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የጋራ [የተቀናጀ] የልማት ፕላንም› የመጣው፡፡ የፕላኑ ዋነኛ ግብ ‹ሀገሪቱ የሰነቀችውን የኢንደስትሪ ሽግግር ዕውን መሆን ወሳኝ አስተዋፅኦ የሚያደርግ የኢንዱስትሪ ልማት ማስተናገድ [የሚችል ክልል መፍጠር]› እንደሆነ በእቅዱ መግቢያ ላይ ተገልፆል፡፡ (ክልል የተባለው ምን እንደሆነ ወደታች የምናው ጉዳይ ነው)፡፡ በእቅዱ የተለያዩ ቦታዎች ላይ ‹‹ክልሉ የሀገሪቱን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በአጠቃላይ የዕቅዱ ዋና አካል የሆነውን የኢንደስትሪ ሽግግር በተለይም እውን በማድረግ ረገድ ወሳኝ ሚና መጫወት ይጠበቅበታል››፣ ‹‹ከግብርና ወደ ኢንደስትሪ የሚደረገውን ጥረት ማገዝ››፣ ‹‹በ2030 በምስራቅ አፍሪካ ተወዳደሪ የሆነና በኢኮኖሚ ውስጥ መሪ ሚና የሚጫወት ማዕከል መፍጠር››፣ ‹‹የከተማዋን እና የዙሪያ ኦሮሚያ አካባቢን በጋራ በአፍሪካ ቀንድ ቀዳሚ የኢንዱስትሪ ክልል ማድረግ›› ወዘተ የሚሉ የዕቅዱ ዋነኛ ትኩረት ‹ኢንደስትሪያላይዜሽን› እንደሆነ የሚያመላክቱ ጉዳዮችን እናያለን፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ኢሕአዴግ ስልጣን ከያዘ ወዲህ የአሁኑን ጨምሮ ለአዲስ አበባ ከተማ የተዘጋጁትን እቅዶች ስንመለከት ‹የዘመኑ መንፈስ› እንደሚመራቸው እናያለን፡፡ የመጀመሪያውና በ1986 የተዘጋጀው እቅድ ዋነኛ ትኩረቱ ‹ሰላማዊ ከተማ› መገንባት እንደነበር የተገለፀ ሲሆን፤ በ1996 የፀደቀው የከተማዋ የልማት እቅድ ደግሞ በጊዜው የኢሕአዴግ ዋነኛ ማጠንጠኛ የነበረውን ‹ኢንቨስትመንት› መሰረት ያደረገ ሲሆን በጊዜው የከተማዋን መሪ ፕላን ለማጽደቅ በከተማዋ አዲስ ነጋሪት ጋዜጣ ላይ በወጣው አዋጅ ቁጥር 17/1996 ላይም እንደተገለፀው ‹‹[…] ኢንቨስትመንትን በተሳለጠና ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማካሔድ [ማስቻል]…›› እንደሆነ ተገልፆ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ‹የዘመኑ መንፈስ› ኢንደስትሪያላይዜሽን ነውና እቅዱ ዋነኛ ትኩረቱን ኢንደስትሪ ላይ ማድረጉ የሚጠበቅና የሚገርም ጉዳይ አይደለም፡፡ ነገር ግን ከተማዋ የምስራቅ አፍሪካ የኢንዱስትሪ ማዕከል ለመሆን ኢንደስትሪ የምትገነባበት በቂ ቦታ የላትምና አወዛጋቢውን መስፋፋት ለማድረግ ተነሳች ማለት እንችላለን፡፡ ይሄ እንዴት ሆነ?
4.3. መሪ እቅድ (Master Plan) ወይስ አዲስ ክልል (New State)?
ሰኞ ግንቦት 18፣ 2000 በጊዜው የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ የነበሩት በአቶ መኩሪያ ሀይሌ እና ከአዲስ አበባ አስራ ሰባት እህት ከተሞች አንዷ በሆነችው የፈረንሳዩ፣ የሊዮን ከተማ ምክትል ከንቲባ Monsier Hubert Julien-Laferriere መካከል አንድ የትብብር ሰነድ ተፈረመ፡፡ የትብብር ሰነዱ በሁለቱ ከተሞች መካከል የተደረገው የአምስት ቀናት ውይይት ውጤት ነበር፡፡ ለውይይቱ የመነሻ ሃሳብ ያቀረበው የፌደራል የከተሞች ፕላን ኢንስቲትዩት በአዋጅ ቁጥር 450/1997 ከተሰጡት ስልጣኖች አንዱን በመጠቀም ሊዮን ከተማ አዲስ አበባን ልትረዳ የምትችልባቸው ሶስት አጀንዳዎችን አቀረበ፡፡ እነዚህም ሶስት አጀንዳዎች፡
1. የአዲስ አበባ ከተማን መሪ እቅድ (Master Plan) የመከለስ ስራ፣
2. በኦሮሚያ ክልል እና በአዲስ አበባ መካከል በጋራ ለመፍጠር ስለታሰበው ክልላዊ እቅድ (Regional Planning) እና፣
3. ስለ አዲስ አበባ ከተማ የውስጥ የልማት ስራ (Local Development Plan – LDP) ናቸው፡፡
በውይይቱ ማጠናቀቂያም በሶስቱ ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ በመደረሱ የሁለቱ ከተሞች አቻ ባለስልጣናት የትብብር ሰነዱን ተስማምተው ፈረሙ፡፡ የመሪ እቅዱ እና የውስጥ የልማት ስራው ከዚህ በፊት የተለመዱ ጉዳዮች በመሆናቸው ብዙም ግርታን የሚፈጥሩ አልነበሩም፡፡ ነገር ግን በኦሮሚያና በአዲስ አበባ መካከል ሊፈጠር የታሰበው ክልላዊ የልማት እቅድ የተለመደ ስላልነበር አፈፃፀሙን ለማየት የሚያጓጓ ነበር፡፡ የዚህ ክልላዊ እቅድ መነሻ ግን አሁንም ወደኋላ ወደ 1996 ይወስደናል፡፡ በ1996 የወጣው የአዲስ ነጋሪቱ ‹የአዲስ አበባ ከተማ መሪ ፕላን አዘገጃጀትና አወጣጥ› አዋጅ ቁጥር 17/1996 በአንቀፅ 8 (2) ላይ ‹የአዲስ አበባ መዋቅራዊ ፕላን ከመዘጋጀቱ በፊት [ከኦሮሚያ ክልል ጋር] በፈቃደኝነት በጋራ ስምምነት ላይ የተመሰረተ የአዲስ አበባና አካባቢዎች ፕላን እንዲዘጋጅ አስተዳደሩ ሁኔታዎችን ያመቻቻል› በማለት ክልላዊ እቅድ መታቀድ ከጀመረ ቆየት ያለ ጊዜ እንዳስቆጠረ ያመላክተናል፡፡
አሁን መንግስት ያዘጋጀው የተቀናጀ የጋራ የልማት እቅድ ሰነድም (የዚህ ፅሁፍ ፀሃፊ እዚህ ላይ ያገኘው ሰነድ) እነዚህን የኋላ ታሪክ በመያዝ ክልላዊ እቅድን (Regional Planning) ከመሪ እቅድ (Master Plan) በመቀየጥ የተዘጋጀ ነው፡፡ ያለውን የፌደራል ስርዓት አይተን ትግበራው ምን ሊመስል ነው ብለን ማሰብ የሚከብደን አይነት እቅድም ነው፡፡ የእቅዱ ስያሜ እንኳን መሪ እቅድ (Master Plan) ሳይሆን ክልላዊ እቅድ (Regional Plan) ነው፡፡ ግቡም አዲስ አበባን በ 100 ኪሎ ሜትር ሬዲየስ የሚከብ ሰፊ ክልልን ማልማት ነው፡፡ 36 ከተሞችን እንደሚያካትትም ተጠቅሷል፡፡ ከአዲስ አበባ ሌላ በስም በእቅዱ ላይ ተጠቅሰው የምናገኛቸው ከተሞችም ዱከም፣ ገላን፣ ሰበታ፣ አዋሽ፣ ለገዳዲ፣ ለገጣፎ (ሁሉም በኦሮሚያ ክልል፣ የፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን ከተሞችን ማለት ነው) ናቸው፡፡ በልማት እቅዱ ውስጥ የተካተተው አካባቢም 85 በመቶው ገጠር እንዲሁም 15 በመቶው ደግሞ የከተማ አካባቢ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ እንዲሁም በአምስቱ ኦሮሚያ ክልል፣ የፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን አምስት ከተሞችን ውስጥ በ25 ዓመታት ውስጥ ከ30 ሺህ እስከ 40 ሺህ ነዋሪዎችን ማስፈርን በእቅድነት ይዟል፡፡ ይሄም ዓላማ ያደረገው ‹የክልሉን ነዋሪ ከአስከፊ ድህነት ማላቀቅ› ነው የሚል ሲሆን፤ እዚህ ላይ የየትኛውን ክልል ነዋሪ ማለታችን ተገቢ ነው፡፡
እነዚህን ጉዳዮች ስንመለከትም እቅዱ በዋናነት ክልላዊ እቅድ እንጂ የከተማ መሪ እቅድ እንዳልሆነ ለመረዳት ብዙም አያዳግተንም፡፡ ሰፊ የገጠር አካባቢን (85 በመቶው የእቅዱ አካባቢ) አካልሎ ግቡን ኢንደስትሪያላይዜሽን ማድረጉንም ስናይ ‹ግዙፏ አዲስ አበባ በተግባር ደረጃ (de facto) የራሷ የሆነ ክልል (አስረኛዋ የኢትዮጵያ ክልል) ለመመስረት ጥረት እያደረገች ነው እንዴ?› ብለን እንድንጠይቅ ያደርገናል፡፡ ከላይ የጠቀስነው አደናጋሪው በፌደራል ስርዓቱ ውስጥ የአዲስ አበባ ‹ስታተስ› ጉዳይም እዚህ ላይ መሰረታዊው የጥያቄ ነጥብ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡
4.4. ኦሮሚያ፣ አዲስ አበባ እና ‹እቅዱ›
ከላይ በተራ ቁጥር 3 ላይ ሕገ መንግስቱ በተረቀቀበት ወቅት የነበረው የአዲስ አበባን ‹ስታተስ› ግልፅ ያለማድረግ ችግርና አዲስ አበባ ከምትገኝበት ኦሮሚያ ክልል ጋር የሚኖራትን ግንኙነት ግልፅ ያለማድረግ ችግር ሕልዮታዊ ጥያቄዎችን ለማንሳት ሙከራ አድርገናል፡፡ እዚህ ላይ ደግሞ በተግባር እያጋጠሙ ያሉ ቸግሮችን በማንሳት የወደፊቱን ሁኔታ ለማየት እንሞክር፡፡
አብዛኛው የአዲስ አበባ ከተማና የኦሮሚያ ክልል ውዝግቦች የሚነሱት ከድንበርና ከሉዓላዊነት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ነው፡፡ አዲስ አበባ ያለ ቅጥ እየተስፋፋች ነው፣ የኦሮሞን ባህልና ቋንቋ እያጠፋች ነው፣ በሕገ መንግስቱ ለኦሮሚያ ክልል የተሰጣት ልዩ ጥቅም እስከ አሁን በሕግ ባለመወሰኑ ጉዳዩን አወሳስቦታል ወዘተ የሚሉ ትችቶች እየቀረቡ እስከ አሁን ቀጥሏል፡፡
4.4.1. ድንበር
የአዲስ አበባ ስፋት ባለፉት ሃምሳ አመታት ከእጥፍ በላይ አድጓል፡፡ በ1953 በሔክታር 21,800 የነበረው የአዲስ አበባ የቆዳ ስፋት በ1986 ወደ 53,014 ሔክታር ሰፍቶ፤ አሁን ያለውን የ54,000 ሔክታር ስፋት ደግሞ በ1996ቱን በከተማዋ መሪ ዕቅድ የተሰፈረላት ነው፡፡ በሀምሳ ዓመታት ውስጥ ከተማዋ በእጥፍ ያደገች ቢሆንም በአለፉት ሃያ ዓመታት ውስጥ ግን አሁን ካላት ስፋት ብዙም የተለየ ነገር አላሳየችም፡፡ የከተማዋ ከኦሮሚያ ጋር ያላት የድንበር ውዝግብ ዋነኛ መነሻ የሆነው የድንበሩ አለመካለል (demarcation ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የተለያዩ ውዝግቦች በጊዜው እንደሚነሱ ይሰማል፡፡ ተሾመ ያሚ የተባሉ የሕግ ባለሙያም በጉዳዩ ላይ ባደረጉት ጥናት የኮልፌ-ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ከቡራዩ ከተማ አስተዳደር ጋር እንዲሁም የንፋስ ስልክ-ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከሰበታ ከተማ አስተዳደር ጋር በቅርብ ጊዜያት ውስጥ የድንበር ይገባኛል ውዝግብ ውስጥ እንደገቡ ይገልፃሉ፡፡ እንዲሁም የገቢ ምንጭን አስመልክቶ የኦሮሚያ ክልል የማዕድን ኤጀንሲ ቢሮ ከአዲስ አበባ አቻው ጋር የተወዛገበባቸው አካባቢዎች እንዳሉ አያይዘው ይገልፃሉ፡፡ እነዚህን ችግሮች ግን መንግስት ሕጋዊ መፍትሔ ከመስጠት እና የሕግ አፈታቱን ከማሳደግ ይልቅ ተለመደውን ፖለቲካዊ መፍትሔ እየሰጠ ችግሩ አሁንም በዘላቂነት ያልተፈታ ጉዳይ እንደሆነ ቀጥሏል፡፡
አዲስ አበባ አሁን ካላት ቦታ ውጭ (54,000 ሔክታር ወይም 527 ኪሜ ስኩየር) መስፋት አትችልም ወይ? ለሚለው ጥያቄ ሕጋዊ መፍትሔ የሚሰጠን በ1996 የወጣው የአዲስ ነጋሪቱ ‹የአዲስ አበባ ከተማ መሪ ፕላን አዘገጃጀትና አወጣጥ› አዋጅ ቁጥር 17/1996 ሲሆን አዋጁም ‹‹[የአዲስ አበባ የ] መስፋፊያ አካባቢ [የሚባለው] በማስተር ኘላኑ የቦታ ደረጃ በአዲስ አበባ ከተማ ተከልሎ ባለ የአርሶ አደር ወረዳዎች ስር የሚገኝ የለማ እና ወደፊት የሚለማ መሬት የሚገኝበት አካባቢ ነው፡፡›› በማለት ከተማዋ አሁን ካላት ቦታ ውጭ እንደማትስፋፋ ይገልፃል፡፡ ከኦሮሚያ ክልል ጋር ያለው ግንኙነት አስመልክቶ በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር የመመስረቻ ቻርተር 87/1989ም ሆነ ይሄን ቻርተር ሙሉ ለሙሉ ያሻሻሉት አዋጅ ቁጥር 311/1995 እና በአዋጅ ቁጥር 361/1995 የድንበሩ ጉዳይ ‹ወደፊት በውይይት ይካለላል› ከማለት በስተቀር ያስቀመጡት ነገር የለም፡፡ በሌላ በኩል የአዲስ አበባ መለጠጥ ያሳሰበው እና ይሄም መገታት አለበት ብሎ ያሰበው የኦሮሚያ ክልል በ2000 የፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን በሚል አዲስ ዞን የአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ክልልን ግንኙነት ለማሳለጥ በሚል ሰበብ አቋቁሟል፡፡ አሁን የቀረበው ‹የልማት እቅድ› ደግሞ የልዩ ዞኑን ከተሞች ሙሉ ለሙሉ በማስገባት ሌላ አዲስ መካረር ፈጥሯል፡፡
4.4.2. ቋንቋ
የአሜሪካዋ ቨርጂኒያ ስቴት ለዋና ከታማዋ ዋሽንግተን ዲሲ የሰጠሁት መሬት ይመለስልኝ በማለት መሬቷን በ1846 አስመልሳለች፡፡ በሌላ በኩል አሁን ያለችውና መሬት ከሜሪላንድ ‹ስቴት› ወስዳ የቆመችው ዋሽንግተን ዲሲ ‹ራሷን የቻለች ክልል ትሁን የሚለውም› ሃሳብ ብዙም ተቃውሞ አይቀርብበትም፡፡ ለዚህም ለስላሳ ግንኙነት ዋነኛው መሰረትም የዋሽንግተን እና የዙሪያዋ ያለው የባህልና ቋንቋ መመሳሰል ነው፡፡
በተቃራኒው አዲስ አበባ የምትናገረው ቋንቋ በዙሪያዋ ካለው ቋንቋ የተለየ ነው፡፡ አዲስ አበባ አማርኛን ታወራለች ዙሪያዋ ደግሞ ኦሮምኛን ይናገራል፡፡ የቋንቋ ምሁሩ ፕሮፌሰር ባየ ይማም ‹አዲስ አበባ ለአማርኛ፣ አማርኛ ለአዲስ አበባ› ባሉት ፅሁፋቸው የአማርኛንና የአዲስ አበባን ግንኙነት ሲያስረዱ፡
ከአዲስ አበባ ከተማ ምሥረታ በኋላ የተለያየ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በየምክንያቱ ወደ ከተማዋ በመግባት በጉርብትና አብረው መኖርና መሥራት ጀመሩ፡፡ ይህም ሁኔታ ሕዝቦችን ከተለያየ ቋንቋ ተናጋሪነት ወደ አንድ የጋራ ቋንቋ ተጠቃሚነት አሸጋገረ:: ልሳነ ዋህድ የነበረው ብሄረሰብ ልሳነ ክልዔ እየሆነ መጣ። አማርኛ ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ከተመኛውን ሁሉ የሚያገናኝ የጋራ ቋንቋ ሆነ፡፡
አዲስ አበባና አማርኛ፣ ለርስበርሳቸው ብሎም ለመላው ኢትዮጵያ የለውጥ ተምሳሌት ናቸው፡፡ እያንዳንዱ ብሄረሰብ በቤቱም ሆነ በአደባባይ የሚናገረው የራሱን ቋንቋና አማርኛን ነው ለማለት ይቻላል፡፡ የአዲስ አበባ ሕዝብ ግን ከዚህ ይለያል፡፡ በአደባባይ ሁሉም የሚናረው አማርኛን ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ መርካቶ የሚሰማው ቋንቋ ሌላ ሳይሆን አማርኛ ነው፡፡ አዲስ አበባ የሕብረ-ብሔራዊነት ተምሳሌት እንደሆነች ሁሉ፣ አማርኛም የዚሁ መግለጫ ነው፡፡ ከሁሉም ይወስዳል፣ መልሶ ለሁሉም ያሰራጫል፡፡ ሁሉንም ያገናኛል፣ ከሁሉም ቃል ይወስዳል፣ ለሁሉም ቃል ይሰጣል፡፡
በማለት ይገልፃሉ፡፡ ፕሮፌሰሩ እንደሚሉት አዲስ አበባን ያለ አማርኛ ማሰብ በፍፁም የማይቻል ነው፡፡ በተቃራኒው ደግሞ በዙሪያዋ ያሉት የአዲስ አበባ ከባቢዎች ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ናቸው፡፡ በመሆኑም ‹ይህች እንደ አንድ ከተማ ብቻ ሳይሆን እንደ ኢትዮጵያ ስልጣኔ ምልክት እየተደረገች የምትታይ ከተማ የምትናገረው ቋንቋ በዙሪያዋ ያለውን ኦሮምኛ ቋንቋ ያጨቁነዋል› የሚለው ሃሳብ የሚሰነዝሩ ሰዎች ብዙ ናቸው፡፡ አሁን ደግሞ ክልላዊ የልማት እቅድ ቀርቧል፡፡ እቅዱም ከቋንቋ ጋር በተገናኝ ያለውን ተቃውሞና ውዝግብ የበለጠ አክርሮታል፡፡
4.4.3. የገበሬ መሬት ለከተሜ?
ከአዲስ አበባ መስፋፋት ጋር ተያይዞ ሌላው እየቀረበ ያለው ጉዳይ አዲስ አበባ በሰፋች ቁጥር ገበሬዎችን እያፈናቀለች ቤት አልባ ታደርጋለች የሚለው ሲሆን፡፡ የተለያዩ ጥናቶችም ይሄን ያመላክታሉ፡፡ ፈየራ አብዲ የተባሉ አጥኝ አዲስ አበባ ከምስረታዋ ጀምሮ አሁን ያለችበትን ስፋት ለሜድረስ በዓመት በአማካኝ 400 ሔክታር ያህል ስትሰፋ ነበር ይላሉ፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ግን ከተማዋ በሕግ አግባብ ልትሰፋ የምትችለው ከተማዋ በቻርተር ከተማነት በተቋቋመችበት አዋጅ ቁጥር 87/1989 ላይ የተገለፀውን ‹የአዲስ አበባ ከተማ የከተማውን ክልል እና በመስተዳደሩ ክልል ውስጥ የሚገኙትን ሃያ ሶስት የገጠር ቀበሌዎች ያጠቃልላል›› ተብሎ በተገለፀው አግባብ ወዳሉት ሃያ ሶስት የገጠር ቀበሌዎች ብቻ ነው ሊሆን የሚችለው፡፡ በኢፌዴሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 40 (4) ላይ ‹‹የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች መሬት በነፃ የማግኝትና ከመሬታቸው ያለመነቀል መብታቸው የተከበረ ነው፡፡›› ተብሎ የተከበረውን የገበሬዎችን መብት ይጥሳል የሚሉ ብዙ ወገኖች አሉ፡፡ ነገር ግን በዚሁ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 8 ላይ ‹‹መንግስት ለሕዝብ ጥቅም አስፈላጊ ሁኖ ሲያገኝው ተመጣጣኝ የካሣ ክፍያ በቅድሚያ በመክፈል […] [መሬቱን] ሊወስደው ይችላል›› ተብሎ በመደንገጉ ይህ የገበሬዎች መብት ገደብ ያለው ነው የሚለው ሃሳብም እዚህ ላይ መሰረታዊ ነገር ነው፡፡
ነገር ግን አሁን እየቀረበ ያለው ‹የተቀናጀ የጋራ እቅድ› ዓላማው ኢንደስትሪያላይዜሽን እንደሆነ ያስቀመጠ ሲሆን 1.1 ሚሊዮን ሔክታርን ያቀፈና 17 የሚሆኑ ወረዳዎችን የያዘ እንደሆነ ተገልፆል፡፡ ይሄም እጅግ ብዙ የገጠር ቀበሌዎችን እንደሚያካትት ግልፅ ነው፡፡ ኢንደስትሪያላይዜሽንን መሰረት ያደረገ እቅድ በዚህ ያህል ቦታ ሲታቀድ ገበሬዎችን በገፍ አያፈናቅልም ብሎ ማሰብ ራስን ከማሞኘት ባለፈ ፋይዳ ያለው ነገር አይደለም፡፡ መፈናቀሉንም ‹ለሕዝብ ጥቅም አስፈላጊ ሁኖ ስለተገን› ነው ብሎ ማሰብ የባሰ ሞኝነት ነው የሚሆነው፡፡
ሲጠቃለልም አዲስ አበባ በተሳሳተ የከተማ ልማት ፖሊሲ ሌሎች ከተሞች በሀገሪቱ ውስጥ የሉም እስኪባል ድረስ ያለልክ ገዝፋለች፡፡ በዚህም ምክንያት አዲስ አበባ ላይ የሚደረግ ማንኛውም እቅድ አካባቢያዊ እቅድ ከመሆን ይልቅ ሀገራዊ እቅድ ነው ማለት ይቻላል፡፡ በመሃሉና በዳር ሀገሩ መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ ከመስራት ይልቅ አሁንም በፖሊሲ ደረጃ የአዲስ አበባን ግዙፍነት በበለጠ የማስቀጠል አካሔድ ነው አሁን እየተካሔደ ያለው፡፡ ይህ አካሔድ ደግሞ በፌደራል ስርዓት ሊኖር የሚገባው ግልፅ የሆነ ድንበር እና ‹ስታተስ› ካለመኖሩ ጀምሮ የተነሳ ሲሆን፤ በተግባርም ችግሮችን በፖለቲካዊ ውሳኔ አድበስብሶ የማለፍ ውጤት ሲጠራቀም ቆይቶ አሁን ላይ የደረሰ ጉዳይ ነው፡፡ እንዲህ የገዘፈ እቅድን (ያውም ‹መሪ እቅድ› ይሆን ‹ክልላዊ እቅድ› በግልፅ ያልተቀመጠ እቅድ) ከአንድ ከተማ ጋር አያይዞ ማቅረብም ለጉልበተኛው የከተማ ገዥ ልሒቅ ተጨማሪ ሃይል በመስጠት ገበሬውን ከራሱ መሬት ወደ ጭሰኝነት የሚገፋ ነው የሚሆነው፡፡ ላልተሳካ ኢንደስትሪያላይዜሽን መሰረታዊ መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ የፌደራል ስርኣቱን በግዴለሽነት በመግፋትና በመሰለኝ ለማሳካት መሞከር ነገም ሌላ ችግር ነው የሚመዘው፡፡ ሕሩይ ሚናስን ከሩቅ ገነት ሁና በመግነጢሳዊ ሃይሏ ስባ ቤተኛ ያደረገችው አዲስ አበባስ እስከ መቼ ነው ሀገሪቱ በፖሊሲ ክሽፈት እየወደቀች ያለችውን የተለያየ ፈተና ለማለፍ መሳሪያ የምትሆነው? የፌደራል ስርዓቱስ እስከ መቼ ነው ሕጋዊነትን ሳይተዋወቅ የሚዘልቀው?

The post አዲስ አባባ ስለምን ታወዛግባለች? – በዘላለም ክብረት appeared first on Zehabesha Amharic.

Sport: ኢንተርናሽናል የእግር ኳስ ዳኛው ለሚ ንጉሴ ለአንድ አመት ታገዱ

Next: ፕ/ር መረራ ኢሕአዲግ በኦሮሚያ ከልላዊ መንግስት የተቀሰቀሰውን ሕዝባዊ አመጽ ሊያዳፈነው እንደማይችል ገለጹ |ኤርትራ የየመኑን አካባቢያዊ ጦርነትን መቀላቀሏን በይፋ አሰታወቀች፣ |አገዛዙ የቅማንት ብሔር የማንነት ጥያቄን ውዝግብን ለማብረድ ልዩ ኮሚቴ አዋቅርኩ ይላል፣ የቅማንት የማንነት ጥያቄ ህወሃት ሆን ብሎ ተጨማሪ መሬት ለመውሰድ ያለመበት አጀንዳ ነው የሚሉ አሉ |ቃለ መጠይቅ ቃለ መጠይቅ ከአቶ አለሙ ያይኔ የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ሊቀመንበር እና ከጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ ጋር እና ሌሎችም አሉን
$
0
0

lemi  Niguse

ኢትዮ-ኪክ እንደዘገበው ኢንተርናሽናል አልቢትር ለሚ ንጉሴ ትላንት ኢትዮጵያ ቡና ከደደቢት ባደረጉት የፕሪምየር ሊጉ ጨዋታ በፈፀሙት የዳኝነት ስህተት ለ1 አመት ከስራቸው ታግደዋል። በጨዋታው ኢትዮጵያ ቡና ያገኝውን የፍፁም ቅጣት ምት በቅርበት አስተውለው ጨዋታውን እንዲቀጠል ማድረጋቸውን ተከትሎ ደደቢቶች በፈጣን የመልሶ ማጥቃት ኳሷን ኢትዮጵያ ቡና መረብ ላይ አሳርፈዋል። ኢንተርናሽናል አልቢተር ለማ 2015 በCAF የክለቦች ሻምፒዮንስ ሊግ የመጀመሪያ ዙር የሱዳኑን አል ማላኪያ እና የናጄሪያውን ካኖ ፒሊራ ጨዋታ መርተዋል፤ ከዚህ በተጨማሪም በ2015 የCAF ከ20 አመት በታች ግብፅ እና ኮንጎ ያደረጉትን ጨዋታ በ4ኛ ዳኛንነት ተሳትፈዋል።

The post Sport: ኢንተርናሽናል የእግር ኳስ ዳኛው ለሚ ንጉሴ ለአንድ አመት ታገዱ appeared first on Zehabesha Amharic.

ፕ/ር መረራ ኢሕአዲግ በኦሮሚያ ከልላዊ መንግስት የተቀሰቀሰውን ሕዝባዊ አመጽ ሊያዳፈነው እንደማይችል ገለጹ |ኤርትራ የየመኑን አካባቢያዊ ጦርነትን መቀላቀሏን በይፋ አሰታወቀች፣ |አገዛዙ የቅማንት ብሔር የማንነት ጥያቄን ውዝግብን ለማብረድ ልዩ ኮሚቴ አዋቅርኩ ይላል፣ የቅማንት የማንነት ጥያቄ ህወሃት ሆን ብሎ ተጨማሪ መሬት ለመውሰድ ያለመበት አጀንዳ ነው የሚሉ አሉ |ቃለ መጠይቅ ቃለ መጠይቅ ከአቶ አለሙ ያይኔ የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ሊቀመንበር እና ከጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ ጋር እና ሌሎችም አሉን

$
0
0

 Caption የህብር ሬዲዮ ዋና አዘጋጅ፣ከላይ አቶ አለሙ ያይኔ የድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ሊቀመንበር፣ ካርታ፣ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው፣ከታች ፕ/ር መረራ ጉዲና፣የተማሪዎቹ ተቃውሞ.ጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ


Caption የህብር ሬዲዮ ዋና አዘጋጅ፣ከላይ አቶ አለሙ ያይኔ የድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ሊቀመንበር፣ ካርታ፣ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው፣ከታች ፕ/ር መረራ ጉዲና፣የተማሪዎቹ ተቃውሞ.ጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ


<...> የአቶ ዓለሙ ያይኔ የኢትዮጵያ የድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ሊቀመንበርለህብር ሬዲዮ ከሰጡት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

<... ...> ጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ በወቅቱየአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ከአገር ቤት ከሰጠውት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

ለወደብ አልባዋ ኢትዮጵያ የወጪ እና የገቢ ንግድ የጀርባ አጥንት የሆነችው ጅቡቲ ውስጥ ሰሞኑንየተከሰተው ፖለቲካዊ ቀውስ ሲዳሰስ (ልዩ ዘገባ)

ሌሎችም
ዜናዎቻችን

ፕ/ር መረራ ጉዲና ኢሕ አዲግ በኦሮሚያ ከልላዊ መንግስት የተቀሰቀሰውን ሕዝባዊ አመጽ ሊያዳፈነው እንደማይችል ገለጹ

“የሚሊዮኖች ደጋፍ ያለው ሰላማዊ እና ሕዝባዊ ተቃውሞን ማስቆም በጭራሽ አይቻልም”ፕ/ር መረራ ጉዲና

የአምቦ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የአገዛዙ አጋዚ ወታደሮችበዩኒቨርስቲው ውስጥ ገብተው የሚያደርሱባቸውን ጥቃትበመቃወም ወደ ቤተሰቦቻቸው ሄዱ

ሴት ተማሪዎች መደፈራቸው ተገለጸ

ኤርትራ የየመኑን አካባቢያዊ ጦርነትን መቀላቀሏን በይፋአሰታወቀች

ሸንጎ የአገዛዙ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ የድንበሩንጉዳይ ጨምሮ ያቀረቡትን የተምታታ ሪፖርት አጣጣለ

አገዛዙ የቅማንት ብሔር የማንነት ጥያቄን ውዝግብን ለማብረድ ልዩኮሚቴ አዋቅርኩ ይላል

የቅማንት የማንነት ጥያቄ ህወሃት ሆን ብሎ ተጨማሪ መሬትለመውሰድ ያለመበት አጀንዳ ነው የሚሉ አሉ

የነገረ ኢትዮጵያ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው እና ሁለትየሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላይ የአገዛዙ ፍርድ ቤት 28 ቀን ፈቀደ

ዛሬ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ለመወያየት ወደ ካርቱም የተጓዙትየኢትዮጵያ ልዑካኖች ከሰብሰባው ቦታ አርፍደው ደረሱ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

The post ፕ/ር መረራ ኢሕአዲግ በኦሮሚያ ከልላዊ መንግስት የተቀሰቀሰውን ሕዝባዊ አመጽ ሊያዳፈነው እንደማይችል ገለጹ | ኤርትራ የየመኑን አካባቢያዊ ጦርነትን መቀላቀሏን በይፋ አሰታወቀች፣ | አገዛዙ የቅማንት ብሔር የማንነት ጥያቄን ውዝግብን ለማብረድ ልዩ ኮሚቴ አዋቅርኩ ይላል፣ የቅማንት የማንነት ጥያቄ ህወሃት ሆን ብሎ ተጨማሪ መሬት ለመውሰድ ያለመበት አጀንዳ ነው የሚሉ አሉ | ቃለ መጠይቅ ቃለ መጠይቅ ከአቶ አለሙ ያይኔ የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ሊቀመንበር እና ከጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ ጋር እና ሌሎችም አሉን appeared first on Zehabesha Amharic.

ድምፃዊ ዓለማየሁ እሸቴ፤ በሜልበርን የሥነ-ጥበብ ማዕከል ስለሚያቀርበው የሙዚቃ ዝግጅቱ ይናገራል | Audio

Previous: ፕ/ር መረራ ኢሕአዲግ በኦሮሚያ ከልላዊ መንግስት የተቀሰቀሰውን ሕዝባዊ አመጽ ሊያዳፈነው እንደማይችል ገለጹ |ኤርትራ የየመኑን አካባቢያዊ ጦርነትን መቀላቀሏን በይፋ አሰታወቀች፣ |አገዛዙ የቅማንት ብሔር የማንነት ጥያቄን ውዝግብን ለማብረድ ልዩ ኮሚቴ አዋቅርኩ ይላል፣ የቅማንት የማንነት ጥያቄ ህወሃት ሆን ብሎ ተጨማሪ መሬት ለመውሰድ ያለመበት አጀንዳ ነው የሚሉ አሉ |ቃለ መጠይቅ ቃለ መጠይቅ ከአቶ አለሙ ያይኔ የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ሊቀመንበር እና ከጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ ጋር እና ሌሎችም አሉን
$
0
0

SBS Amharic: ድምፃዊ ዓለማየሁ እሸቴ፤ በሜልበርን የሥነ-ጥበብ ማዕከል ስለሚያቀርበው የሙዚቃ ዝግጅቱ ይናገራል። የዓለማየሁ የሙዚቃ ትዕይንት ለሕዝብ የሚቀርበው ጃኑዋሪ 9, 2016 ነው።

ድምፃዊ ዓለማየሁ እሸቴ፤ በሜልበርን የሥነ-ጥበብ ማዕከል ስለሚያቀርበው የሙዚቃ ዝግጅቱ ይናገራል

The post ድምፃዊ ዓለማየሁ እሸቴ፤ በሜልበርን የሥነ-ጥበብ ማዕከል ስለሚያቀርበው የሙዚቃ ዝግጅቱ ይናገራል | Audio appeared first on Zehabesha Amharic.

ዛሬ በምዕራብ ሐረርጌ ሕዝቡ ቁጣውን ሲያሰማ ውሏል |ቪዲዮም ይዘናል

$
0
0


(ዘ-ሐበሻ) የኦህዴድ ባለስልጣናት ሕዝቡን ያረጋጉ መስሏቸው ተመልሰው ወደ ሕዝቡ ላይ ጥቃት መሰንዘራቸው በቀጠለበት በዚህ ወቅት በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች የሕዝቡ ቁጣ ቀጥሏል:: ዛሬ በም ዕራብ ሃረርጌ ሂርና ከተማ የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን እንዲሁም የሕወሓት ወታደሮች በሕዝቡ ላይ ያደረሱትን ግድያና ንብረት ነጠቃ በመቃወም አደባባይ ወጥተው ውለዋል::

በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች መንገዶችን በመዝጋት ሕዝቡ ተቃውሞውን እየገለጸ ይገኛል::

ዛሬ በምዕራብ ሃረርጌ የተሰማው ተቃውሞ ወደ ሌሎችም ከተሞች እንደሚቀጥል ይጠበቃል:: ፖሊስ ሰልፈኛውን ለመበተን የሃይል እርምጃዎችን እንደወሰደ ቢሰማም እስካሁን ለዘ-ሐበሻ ስለተጎዱ ሰዎች የደረሱ መረጃዎች የሉም::

Zehabesha News

The post ዛሬ በምዕራብ ሐረርጌ ሕዝቡ ቁጣውን ሲያሰማ ውሏል | ቪዲዮም ይዘናል appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live