Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ኢትዮጵያ፡ በዘ-ህወሀት የተገደበች ሀገር (ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)

$
0
0

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

በዘ–ህወሀት የተወገዘችው ኢትጵጵያ

Security guards look at the construction of Ethiopia's Great Renaissance Dam in Guba Woredaባለፈው ሳምንት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እየተባለ የሚጠራው አዲስ ስምምነት የተፈረመበት የብዕር ቀለም ሳይደርቅ የግብጽ ፕሬዚዳንት ጀኔራል አብደል ፋታህ ኤል ሲሲ በአንድ ብሄራዊ የእርሻ ፕሮጀክት የምረቃ ስነስርዓት በዓል ላይ በመገኘት ለግብጽ ህዝብ እንዲህ የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፣ “ውኃ የህይወት ወይም የሞት ጉዳይ መሆኑን  እና ይህም የግብጽ ህዝብ ጭንቀት መሆኑን ሙሉ በሙሉ እገነዘባለሁ፡፡ እነርሱም መኖር እንደሚፈልጉ ሁሉ እኛም መኖር እንደምንፈልግ ከወንድሞቻችን ከኢትዮጵያውያን ጋር ስምምነት አድርገናል፡፡ ከዚህ ቀደምም በተሳሳተው መንገድ አልመራኋችሁም፣ አሁንም በተሳሳተው መንገድ አልመራችሁም፡፡“

ይኸ ነገር የጦርነት ወይስ የሰላም ንግግር ነው?

“ውኃ የህወይት እና የሞት ጉዳይ ነው?“ “እኛ ለመኖር እንደምንፈልግ ሁሉ እነርሱም ለመኖር ይፈልጋሉን? “አሁንም በተሳሳተው መንገድ አልመራችሁም?“

ጀኔራሎች (የሲቪል ልብስ ለብሰውም እንኳ ቢሆን) ስለህይወት እና ሞት እንዲሁም ስለመኖር እና በተሳሳተው መንገድ አልመራችሁም የሚል ንግግር ሲያደርጉ መስማት በእርግጠኝነት እኔን ያሳስበኛል፡፡ የወገናዊነት ስሜት አጥቅቶኝ ሊሆን ይችላል፣ ሆኖም ግን ጀኔራሎች ህዝቦቻቸውን በተሳሳተው መንገድ አንመራም ሲሉ ምክንያቱም አንድ መንገድ ብቻ ስለሚያውቁ ነው፡፡ የጦርነት መንገድ! ከጀኔራሎች የሚመጣ እንደዚህ አይነቱ ንግግር በእርግጠኝነት እጅግ በጣም እንድጨነቅ ያደርገኛል፡፡ በጣም ስሜታዊ ሆኘ ነውን?

ጀኔራሎች አብዛኛውን ጊዜ በመንታ ምላሳቸው ነው ንግግር የሚያደርጉት፡፡ ግልጽ በሆነ መልኩ ወደ አደባባይ በመውጣት “ይህንን ወይም ደግሞ ያንን በቦምብ እናጋያለን“ የሚል መልዕክት አያስተላልፉም፡፡ ስለአየር ጥቃት ዘመቻ ኢላማዎቻቸው ነው ንግግር የሚያደርጉት፡፡ ጀኔራሎች ሰዎችን በመያዝ ስለሚያደርጉት ማሰቃየት አይናገሩም፡፡ ስለአስገዳጅ ቃለ መጠይቆቻቸው ነው የሚናገሩት፡፡ በወገን ላይ ስለደረሰ ጉዳት ወይም ደግሞ ከጠላት ስለተተኮሰ ጥይት ይናገራሉ፣ ገድለናል ብለው በፍጹም አይናገሩም፡፡ ጀኔራሎች ስለፈጣን ወታደራዊ ጥቃት ይናገራሉ፣ ሆኖም ግን ስለእልቂት እና ሽብር አይናገሩም፡፡

ኤል ሲሲ ግለጽ የሆኑ እና ቀላል ቃላትን የተናገሩ አይመስልም፡፡ ለእኔ በጣም ጥልቅ የሆነ ንግግር ያደረጉ እንደሆኑ ነው የተሰማኝ፡፡ ሆኖም ግን በእርግጠኝነት ምን ማለታቸው ነው?

እርግጠኛ ለመሆን ኤል ሲሲ ለግብጽ ህዝብ በእርግጠኝነት ያስተላለፉት መልዕክት ምንድን ነው?

ኤል ሲሲ ለግብጽ ህዝብ የዓባይ ውኃ የሞት እና የህይወት ጉዳይ ነው ብለው ሲናገሩ አሁን በስልጣን እርካብ ላይ እንደ መዥገር ተጣብቆ ለሚገኘው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ዘ-ህወሀት) በእርግጠኝነት ምን ዓይነት መልዕክት እያስተላለፉ ነው?

ኤል ሲሲ “እነርሱም ለመኖር እንደሚፈልጉ ሁሉ እኛም ለመኖር እንፈልጋለን፣”  ሲሉ እኛ የማንኖር ከሆነ እነርሱም አይኖሩም ለማለት ነው?

“ለኢትዮጵያውያን ወንድሞች” መልዕክት ሲያስተላልፉ በእርግጠኝነት ምን እየተናገሩ ነው?!

ለቀጣናው ጎረቤቶች ምን መልዕክት እያስተላለፉ ነው? ለአሜሪካ እና ለአውሮፓ ኃያላን ምን እየተናገሩ ነው?

ኤል ሲሲ በአሁኑ ጊዜ እና ወደፊትም ምን ማድረግ እንዳለባቸው እንደሚያውቁ እና የግብጽ ህዝብ መጨነቅ እንደሌለበት መልዕክት እያስተላለፉ ነውን? ጭንቀቱስ ምንድን ነው?

የኤል ሲሲ አደጋን ያረገዙት ወታደራዊ ትችቶች ለእኔ አስጊዎች እና በቀጣይነት በሀገራችን ላይ አደጋን ሊያስከትሉ እንደሚችሉ በማሰብ የጄኔራሉን ስትራቴጂያዊ ዓላማ እና ብቃት ጥልቅ በሆነ መንገድ እንድመረምር አስገድዶኛል፡፡

ኤል ሲሲ የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ እየተባለ የሚጠራው ግድብ ሊገነባ የሚችለው ዓባይ ወደ በረዶ ክምርነት ሲቀየር እና ሰይጣን በበረዶው ክምር ላይ የሸርተቴ ጨዋታ መጫወት በሚጀምርበት ጊዜ ነው እያሉ የሚናገሩትን እሰማለሁ፡፡

ለመንደርደርያ ያህል አንዳንድ ነገሮችን ግልጥ ላድርግ፡፡

በመጀመሪያ በተለያየ መልኩ ከሰብአዊ መብት ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ሁኔታ ከፕሬዚዳንት ኤል ሲሲ ጋር አልስማማም፡፡ እ.ኤ.አ በ2011 በግብጽ ተከስቶ በነበረው ህዝባዊ አመጽ ምክንያት ተገኝቶ የነበረው የሰብአዊ መብት አጠባበቅ እንደገና እየተቀለበሰ ነው ከሚለው የዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ከሂዩማን ራይትስ ዎች ግምገማ ጋር እስማማለሁ፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ኤል ሲሲ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ወዳጅ ናቸው፡፡

እ.ኤ.አ ሚያዝያ 2015 እራሱን የኢራቅ እና የሌባነን እስላማዊ መንግስት/Islamic State of Iran and Levant (ISIL) እና ከዚህም በተጨማሪ የኢራቅ እና የሶርያ እስላማዊ መንግስት እያለ በሚጠራው አረመኔ እና አሸባሪ ወሮበላ ድርጅት የ30 ወጣት ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች በመሆናቸው ምክንያት አንገት በተቀላ ጊዜ  ኤል ሲሲ ፈጣን በሆነ መልኩ ወደ አደባባይ በመውጣት በግብጽ ህዝብ ስም በሊቢያ አሰቃቂ በሆነ መልኩ አንገታቸውን በተቀሉት ሰላማዊ ኢትዮጵያውያን የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸው ነበር፡፡

ኤል ሲሲ ከዚያ እልቂት የተረፉትን ኢትዮጵያውያን አንገት ከመቀላት ለመታደግ እና በሰላማዊ መንገድ በቻርተርድ አውሮፕላን ወደ ግብጽ ለማምጣት የግብጽ ወታደሮችን ወደ ሊቢያ የላኩ ሰው ነበሩ፡፡

የዘ-ህወሀት መሪዎች ኢትዮጵያውያን በሊቢያ ውስጥ አንገታቸውን መቀላታቸውን በሰሙ ጊዜ ያንን የመሰለ ኢሰብአዊ ድርጊት የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና ኢትዮጵያውያውን እንዲያውቁት እንኳ ይፋ አላደረጉም፣ ለድርጊቱም እውቅና አልሰጡም ነበር፡፡

በወቅቱ የዘ-ህወሀት አፈቀላጤ የነበረው ሬድዋን ሁሴን እንዲህ ብሎ ነበር፣ “አይሲስ  የኢትዮጵያውያንን አንገት እየቀላ ገድሏል እየተባለ በስፋት ሲዘገብ ይደመጣል፡፡ የጥቃት ሰለባዎቹ ኢትዮጵያውያን ስለመሆናቸው መንግስት የሚቻለውን ሁሉ በማድረግ ጉዳዩን በማጣራት ላይ ይገኛል“ ነበር ያለው፡፡

ዘ-ህወሀት ለዚያ አሰቃቂ እልቂት ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ በኃይል የለሾች እና በረዳት አልባዎች ኢትዮጵያውያን ላይ የተፈጸመውን እልቂት ጣቶቹን እያጣመረ እና እራሱን እያከከ ከዳር ቆሞ ሲመለከት በነበረበት ጊዜ ኤል ሲሲ ፈጣን እርምጃ በመውሰድ የበርካታ ኢትዮጵያውያንን ህይወት ታድገዋል፡፡

ኤል ሲሲ ከሞት አደጋ በመዳን ወደ ካይሮ ለመጡ ኢትዮጵያውያን በካይሮ አውሮፕላን ማረፊያ ቀይ ምንጣፍ አንጥፈው በክብር በመቀበል አንድ በአንድ እጆቻቸውን እየጨበጡ ሰላምታ በመስጠት የማጠናከሪያ ቃላት ተናግረዋል፡፡ በአቀባበል ስነስርዓቱ ላይ አንድም የዘ-ህወሀት ተወካይ አልታየም፡፡

ጥቂት ሰዎች ኤል ሲሲ የህዝብ ግንኙነት ስራ ጥቅም ዕድሎችን ከሚፈለገው በላይ ተጠቅመውበታል በማለት ሀሳብ ሊሰነዝሩ ይችላሉ፡፡

የእኔ መልስ ግን ቀላል እና እንዲህ የሚል ነው፡ “እየሰመጠ ያለ ሰው ማን ገመድ እንዳቀበለው ደንታው አይደለም! እንደዚሁም ሁሉ አንገቱን የመቀላት መጥፎ አጋጣሚ ባጋጠመው ጊዜ ህይወቱን ማን እንዳዳነው ወይም ደግሞ ህይወቱ በምን ምክንያት ከአደጋው እንደተረፈ ጉዳዩ አይደለም!“

ቀላሉ እውነታ ግን ፕሬዚዳንት ኤል ሲሲ ወጣት ኢትዮጵያውያንን ከሞት አደጋ ለማዳን ትዕዛዝ ሰጥተዋል ምክንያቱም እርሳቸው ይህንን ፈልገዋል፣ ምክንያቱም ያንን ማድረግ ችለዋልና፣ ምክንያቱም ትክክለኛውን ነገር ማድረግ ነው የሚል እምነት ነበራቸውና፣ ምክንያቱም ይኸ ጉዳይ በኢትዮጵያውያን እና በግብጻውያን መካከል መልካም ወንዳማማችነትን እና እህትማማችነትን ይመሰርታል ብለው ያምኑ ነበርና፣ ምክንያቱም ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች እንደ ክርስቲያን እና እንደ ሰብአዊ ፍጡር ፍትሀዊ በሆነ መልክ እና ክብራቸው ተጠብቆ መስተናገድ አለባቸው የሚል እምነት ስለነበራቸው ነው፡፡

ፕሬዚዳንት ኤል ሲሲ ድፍረት በተመላበት እና ፈጣን በሆነ መልኩ አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ በሊቢያ ውስጥ ታፍነው የነበሩ ኢትዮጵያውያንን ህይወት በመታደግ በሁለቱ የጥንታዊ ስልጣኔ ባለቤት ሀገሮች መካከል ለዘመናት ጸንቶ የቆየውን ወዳጅነት እና እህትማማችነት በጽኑ መሰረት ላይ እንዲገነባ አድርገዋል፡፡

ይህን ከዚህ በላይ ያልኩት የምቀጠለዉን ለማስገንዘብ ነው፡፡ ኤል ሲሲ  በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ጉዳት ለማድረስ ይመኛሉ ብዬ አላስብም፡፡ ከኢትዮጵያ ጋር ጦርነት ለማካሄድ ይፈልጋሉ ብዬ አላስብም፡፡ ኤል ሲሲ ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ እየተባለ ከሚጠራው የግድብ ግንባታ ጋር በተያያዘ መልኩ የሚከሰቱትን በርካታ ችግሮች ዴፕሎማሲያዊ በሆነ መልኩ እና ብቃት ባለው ቴክኒካዊ አካሄድ ይፈቱታል ብዬ አምናለሁ፡፡ ኤል ሲሲ ለችግሮቹ ሁሉ ከዘ-ህወሀት ጋር ምክንያታዊነትን መሰረት ባደረገ መልኩ በመወያየት ፍትሀዊ መፍትሄ ለመስጠት ይሞክራሉ ብዬ አምናለሁ፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ኤል ሲሲ ከዘ-ህወሀት ጋር የሚያደርጓቸው ዴፕሎማሲያዊ ጥረቶች በእብሪተኞቹ በዘ-ህወሀት መሪዎች ሰንካላ እና የድንቁርና አካሄድ ምክንያት ሙሉ በሙሉ  ይከሽፋል ብዬ አምናለሁ ፡፡

ችግሩ የፈለገውን ያህል ገፍቶ ቢመጣ እና በዓባይ የውኃ ፍሰት ላይ በሚመጣ የውኃ እጥረት ምክንያት በግብጽ ላይ ችግር ቢከሰት ኤል ሲሲ የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ እየተባለ የሚጠራው ግድብ ጉዳት እንዳያደርስባቸው ወይም ደግሞ የግብጻውያንን የእርሻ መሬቶች፣ የኃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ምርቶችን እና በየጊዜው እያደገ የመጣውን የግብጽን ህዝብ ለመመገብ የሚያስችሉትን የወደፊት የእርሻ መሬቶች ተግባራት በድርቀት የሚያስፈራራቸው ከሆነ የወታደራዊ አማራጭ እንጅ ሌላ አማራጭ እንደሌላቸው አምናሁ፡፡

የእኔ አስተያየት ከአዲሱ ስምምነት በኋላ ኤል ሲሲ ያሉት ነገር ከስልታዊ ዓላማ እና ብቃት እኳያ እና ከታሪካዊ ትስስር አንጻር ሲባል እንደገና ጥልቅ በሆነ መልኩ መመርመር አለበት፡፡

በሌላ አገላለጽ ወደፊት ለመጓዝ ግልጽ በሆነ እና በማያሻማ መልኩ መመለስ ያለባቸው ሁለት ጥያቄዎች ብቻ አሉ፡፡ እነርሱም፡

1ኛ) ውኃን በተመለከተ 97 በመቶ የሚሆነው የግብጽ ህዝብ የውኃ ምንጭ የሚገኘው ከዓባይ ወንዝ ስለሆነ ከዚህ ጋር በተያያዘ መልኩ እጥረት እና ችግር ቢፈጠር ኤል ሲሲ ጦርነትን በማስወገድ ወይም ደግሞ ከማናቸውም ወታደራዊ እርምጃ በመከላከል ጎልተው የወጡትን ችግሮች እና ጉዳዮች ሙሉ በሙሉ በዴፕሎማሲያዊ መንገድ ላይ ብቻ በመመስረት ሊፈቱት ይችላሉን?

2ኛ) ኤል ሲሲ በአሁኑ ጊዜ ወይም ደግሞ ወደፊት በመካከለኛ ጊዜ የውኃው ፍሰት ቀድሞ በነበረው ሁኔታ ያለምንም ችግር ወደ ግብጽ በእርግጠኝነት መፍሰስ እንዲችል ሊያደርግ የሚያስችል ወታደራዊ ብቃት አላቸውን?

በእኔ ትንታኔ ኤል ሲሲ እና የጦር አበጋዞቻቸው ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ እየተባለ የሚጠራው ግድብ በግብጽ ህዝብ ላይ የህይወት አደጋ ደቅኖ እንደሚገኝ እና የዚህ ታላቅ አደጋ ብቸኛ መፍትሄውም ወታደራዊ እርምጃ እንደሆነ ሊቀለበስ በማይችል መልኩ ከድምዳሜ ላይ የደረሱ ለመሆናቸው ጥያቄ የሚያስነሳ ጉዳይ አይደለም፡፡

ይህ ዓይነት አቋም ኤል ሲሲ እንዲሁ በባዶ አየር ላይ የፈጠሩት አይደለም፡፡ የወታደራዊ አማራጭ ሁልጊዜ በግብጽ ላይ የተፈራረቁት አገዛዞች ሁሉ በዓባይ ወንዝ ላይ የሚደረግ ማንኛውንም የግድብ ግንባታ በግብጽ ህዝብ ህይወት ላይ የማይቀር አደጋን የሚጋርጥ እንደሆነ አድርገው የሚቆጥሩት ስለሆነ በማናቸውም መንገድ እና አስፈላጊ ነው ተብሎ በሚታመንበት መንገድ ሁሉ መወገድ ያለበት ስልታዊ አማራጫቸው ነው፡፡

በአሁኑ ጊዜ ቂጥ ለቂጥ እየተያያዙ እያካሄዱት ያለው የዴፕሎማሲ ቸበርቻቻ አስረሽ ምችው  ዳንስ ወደፊት የማይቀረውን ነገር ለማዘግየት ካልሆነ በስተቀር ምንም ዓይነት የሚፈይደው ነገር በፍጹም የለም፡፡

እ.ኤ.አ በ2011 የመጀመሪያዎቹ ወራት የአረብ የጸደይ አብዮት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ዘ-ህወሀት የግብጽ ፖለቲካ እንዳይረጋጋ፣ በቋፍ ላይ እንዲቆይ እና የአገዛዝ ለውጥ እንዲኖር ሲፈልግ ቆይቷል፡፡ የዘ-ህወሀት መሪዎች በግብጽ ውስጣዊ ችግር ሳቢያ የግድብ ስራውን ማፋጠን እና የዓባይን ወንዝ የውኃ ፍሰት አቅጣጫ ማስቀየስ ከግብጻውያን የሚመጣ ጠንካራ ተቃውሞ የለም በሚል ጥቅም የሚያገኙ መስሎ ይታያቸዋል፡፡

ኤል ሲሲ እና የእርሳቸው ጀኔራሎች ያሉባቸውን ፖለቲካዊ አደጋዎች ተገንዝበዋል፣ እናም ላለፉት ሶስት ዓመታት ዴፕሎማሲያዊ ጨዋታ ሲጫወቱ ቆይተዋል፡፡

ኤል ሲሲ እና ጄኔራሎቻቸው ጊዜዎቻቸውን ለዴፕሎማሲያዊ ስራ ሲያውሉ ቆይተዋል፡፡ በአንድ ወቅት ሮጀርስ እዳሉት፣ “ዴፕሎማሲ ማለት አንድ ጥሩ አለት እስከምታገኝ ደረስ ተናካሽ ዉሻዉን ማባበል ሙከራ ማለት ነው“ እንዳሉት ነው፡፡

ከእኔ የሁኔታዎች ትንታኔ አንጻር በአሁኑ ጊዜ ኤል ሲሲ ከሁለት ዓመታት በፊት ከነበሩበት የበለጠ ጠንካራ አቋም አላቸው፡፡ እ.ኤ.አ ጥር 2011 እና ሰኔ 2013 በግብጽ ላይ ታይተው የነበሩት የፖለታካ አለመረጋጋት እና ህዝባዊ አመጽ በአሁኑ ጊዜ ምክንያት ሆኖ ሊነሳ አይችልም፡፡ በአሁኑ ጊዜ የኤል ሲሲን መንግስት በህዝባዊ አመጽ ለማስወገድ የሚደረግ ህዝባዊ ተቃውሞ የለም፡፡ ኤል ሲሲ በአሁኑ ጊዜ ኃይላቸውን ከማጠናከራቸውም በላይ ወታደራዊ አገዛዛቸው ውስጣዊ አንድነትን ፈጥሯል፡፡ በሙስሊም ወንድማማቾች ላይ ሲወሰድ የነበረው የኃይል እርምጃ በምሁራን፣ በወታደሩ፣ በቢሮክራሲው እና በሌሎች የሲቪል ተቋማት ሰፊ የድጋፍ መሰረት አለው ብዬ እጠርጥራለሁ፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ኤል ሲሲ ግብጽ ወደ እርስ በእርስ ጥላቻ እና የኃይማኖት ግጭት ውስጥ እንዳትገባ የተሻሉ ሰው ናቸው የሚል ሰፊ መግባባት አለ፡፡

በአሁኑ ጊዜ ኤልሲሲ ስለግድቡ ምንም ዓይነት ጭንቀት እንዳይኖርባቸው ለግብጻውያን ለመናገር በእራስ የመተማመን ስሜት አላቸው፡፡ ከመስመር በወጣ መንገድ ላይ አይመሯቸውም፡፡ ነገሮች ገፍተው ከመጡ በየትኛው መንገድ መጓዝ እንዳለባቸው በሚገባ ያውቃሉ፡፡ ህዝቦቻቸውን ወደ ውድቀት አይወስዱም፡፡ ኢትዮጵያውያን ወንድሞች የዓባይን ወንዝ በመገደብ በግብጻውያን ላይ አደጋን የሚጋብዙ ደደቦች አይደሉም፣ ምክንያቱም ግብጻውያን መኖር እንደሚፈልጉ ሁሉ እነርሱም መኖር ይፈልጋሉ፡፡

በሌላ አገላለጽ ኤል ሲሲ በአሁኑ ጊዜ የሮጀርን አለት አግኝተዋል፡፡ ከዚህ በኋላ ዘህወሀት ተናካሽ  ዉሾችአያባብሉም ፡፡ ብቸኛ ጥያቄሆኖ የሚቀርበው ግን ኤል ሲሲ አለቱን በሰራ ላይ የሚያዉሉት መቼ ነው የሚለውነው!

ስለኤል ሲሲ እና ስለወታደራዊ ዕቅድ አውጭዎቻቸው ያለኝ ትንታኔ ለማይቀረው ነገር ዘረፈ ብዙ እና የተሰላ የእርምጃ ደረጃ ያለው ታላቅ መሻሻሎችን አዘጋጅተው ተቀምጠዋል፡፡

የግብጾች ስልታዊ ዓላማዎች ታላቁ የህዳሴ ግድብ እየተባለ በሚጠራው ግድብ ላይ ጦርነትን እንደ ብቸኛ አማራጭ ይዘው የተቀመጡ እንደሆኑ አምናለሁ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ወታደራዊ ብቃት እንዳላቸው ወይም ደግሞ በግድቡ ከሚሰነዘርባቸው ማንኛውም አደጋ ለመከላከል እና ለወደፊትም ማንኛውንም ነገር ለመቆጣጠር እንደሚችሉ ያምናሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ አምካኝ የሆነ ወታደራዊ ኃይልን የመጠቀሙ አስፈላጊነት አልታያቸውም፡፡

የግብጾች ስልት በዚህ በሚቀርበው ቅደም ተከተል ባይሆንም የሚከተሉትን ነገሮች ለመከተል እቅድ አላቸው ብየ አምናለሁ፡

አንደኛ፡ ግብጻውያን ዓለም አቀፍ አበዳሪ እና ለጋሽ ድርጅቶችን ለግድቡ ግንባታ የሚውል  ገንዘብ ለዘ-ህወሀት እንዳይሰጡ በማግባባት ላይ እንደሚገኙ በርካታ ማስረጃዎች አሉ፡፡ ግብጽ በሁለት መንገድ ዘመቻዋን ጀምራለች፡ 1ኛ) የግብጽን የውኃ እና የውጭ ግንኙነት ሚኒስትሮችን ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ስብሰባ እንዲቀመጡ በማድረግ በዓባይ ተፋሰስ ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር ጥረት ማድረግ፣ 2ኛ) የግብጽ አምባሳደሮች ከእነዚህ ሀገሮች ለግንባታው የሚውል ገንዘብ እንዳይገኝ የማግባባት ስራ መስራት የሚሉት ናቸው፡፡ ይህ ስልት ዘ-ህወሀት ለግድቡ ግንባታ የሚውል ብድር ወይም ደግሞ ሌላ የገንዘብ እርዳታ እንዳያገኝ በማድረግ ስኬታማ ሆነዋል፡፡

ሁለተኛ፡  ኤል ሲሲ ማቋረጫ የሌላቸው የቴክኒካዊ እና የትንታኔ ጥናቶች መጠናት አስፈላጊ ነው በማለት የግድቡን የግንባታ ስራ የማዘግየት ተግባራትን ይሰራሉ ብዬ አምናለሁ፡፡

ባለፈው ሳምንት በተደረገው አዲስ ስምምነት መሰረት እ.ኤ.አ ከየካቲት 2016 ጀምሮ ለቀጣዮቹ 15 ወራት ግድቡ ስለሚያስከትለው ተጽዕኖ የቴክኒክ ጥናት ተጠንቶ ይቅረብ የሚለው ለዚህ ዓይነቱ ስልታዊ አካሄዳቸው የቅርብ ጊዜ ምሳሌ ነው፡፡ ያለምንም ጥርጥር ወደፊት ብዙ ጥናቶች ሊጠየቁ ይችላሉ፡፡ ቴክኒካዊ ጥናቶች በአሁኑ ጊዜ በርካታ ጥናቶች እንደሚያመላክቱት የግድቡ ግንባታ በግብጽ ላይ በበርካታ መንገዶች አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል የሚሉ የጥናት ግኝቶች ይቀርባሉ ብዬ አምናለሁ፡፡ እንደዚሁም ሁሉ በመጨረሻ በኤል ሲሲ እና ጀኔራሎቻቸው እነዚህን ቴክኒካዊ እና የምህንድስና ጥናቶች የጦርነት መንስዔ (ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ አሳማኝ ድርጊት) አድርገው ሊወስዱ እንደሚችሉ አምናለሁ፡፡

ሶስተኛ፡ ጊዜውን በማራዘም እና በሌሎችም አማራጮች ኤል ሲሲ በግድቡ ግንባታ ላይ የስራ ማስኬጃ ወጪዎች እጅግ በጣም እንዲንሩ የማድረግ አላማን በማራመድ በመጨረሻም ግድቡን ለመግንባት እና ለመጠገን ተግባራዊ ሊሆን የሚችል የገንዘብ አቅም እንዳይኖር ያደርጋሉ፡፡

በተለመደው አሰራር መሰረት ታላላቅ ግድቦች በሚገነቡበት ጊዜ የስራ ማስኬጃ ወጪዎች መናር የተለመደ ነው፡፡ እጅግ በጣም ግዙፍ በሆኑ እና የገንዘብ አዋጭነታቸው ላይ አጠቃላይ በሆነ መልኩ እስከ አሁን ድረስ ዝርዝር የሆነ ሳይንሳዊ ጥናት በተሰራላቸው ግድቦች ላይ የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች አቲፍ አንሳር፣ ቤንት ፍላይብጀርግ፣ አሌክሳንደር ቡዚየር እና ዳንኤል ሉን እ.ኤ.አ. በ1934 እና በ2007 መካከል በተገነቡ አስተማማኝ ወጭ እና የጊዜ ሰሌዳ ባላቸው ግድቦች ላይ ጥልቅ የሆነ ጥናት አካሂደዋል፡፡ የዚያ የጥናት ውጤት በግልጽ እንዳመላከተው ታላላቅ ግድቦች በሀገሩ ቋሚ የገንዘብ መለኪያ መሰረት 96 በመቶ የሚደርስ ከፍተኛ የሆነ የስራ ማስኬጃ ወጭ የሚጠይቁ መሆናቸውን ደምድመዋል፡፡ የፕሮክቱ ተግባራዊነት በአማካይ 44 በመቶ የመዘግት ችግር ይገጥመዋል፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የግድብ ግንባታ ወጭዎች የስራ ማስኬጃ ወጭዎች ከዚህ የተለዩ አይደሉም፡፡ ለምሳሌ ያህል በሰሜን ኢትዮጵያ የዓባይ ገባር በሆነው በተከዜ ወንዝ ላይ የተካሄደው የተከዜ ኃይድሮ ኤሌክትሪክ ግድብ ግንባታ ጠቅላላ ወጭ በመጀመሪያ ደረጃ 224 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ይፈጃል ተብሎ ነበር የተገመተው፡፡ ሆኖም ግን  ከተጀመረ ከስምንት ዓመታት በኋላ እ.ኤ.አ በ2008 ሲጠናቀቅ ዋጋው ወደ ሰማይ እንደሮኬት ተተኩሶ 360 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ሊሆን ችሏል፡፡ በምህንድስና ብቃት ማነስ ምክንያት ጥራት የሌላቸውን የግብዓት ቅሳቁሶች በመጠቀም እንደዚሁ የግንባታ ችግሮች/Structural problems የተለመዱ ችግሮች ናቸው፡፡ በኦሞ ወንዝ ላይ እ.ኤ.አ የካቲት 2010 በግልገል ጊቤ ሁለት ግድብ ላይ የተካሄደው ግንባታ እና በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ሁሉ የበለጠ ትልቅ የተባለው የግድብ ግንባታ የግድብ ስራው ተጠናቅቆ በተመረቀ 10 ቀናትን ሳያስቆጥር ተደረመሰ፡፡

አራተኛ፡ ኤል ሲሲ ግድቡ የሚጠናቀቅ ቢሆንም እንኳ ኃይል ማመንጨት እንዳይችል የስራ ማስኬጃ ወጭውን በዘ-ህወሀት ላይ በማናር የውኃ ማጠራቀሚያ ግድቡ እንዳይሞላ ረዥም ጊዜ በመውሰድ እንዲጓተት ያደርጋሉ የሚል እምነት አለኝ፡፡ በአንድ በኖርዌ ባለሙያዎች የተካሄደ የምህንድስና ጥናት እንደሚያመለክተው ሁሉም ነገር እንደታሰበው ይከናወናል ብለን ብናስብ እንኳ 67 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውኃ ለመሙላት ሰባት ዓመታትን ይፈጃል፡፡ ጥቂት ነገሮች ብቻ ናቸው በታቀደው መሰረት ከፍጻሜ የሚደርሱት፡፡

እጅግ ሲበዛ ድብቅ የሆነው ዘ-ህወሀት የኤሌክትሪክ ኃይል ምርቱን ግብ ለማሳካት እንዲቻል የውኃ ማጠራቀሚያው ግድብ በምን ያህል ጊዜ በውኃ እንደሚሞላ ግልጽ ያደረገው ነገር የለም፡፡ ያም ሆነ ይህ የመጀመሪያው የግድቡ የውኃ መሙላት ስራ እና ከዚህም ጋር ተያያዞ የሚከሰተው የውኃ ትነት ወደ ግብጽ በሚፈስሰው የውኃ መጠን ላይ ከፍተኛ የሆነ የውኃ ቅናሽ ያሳያል፡፡

ግድቡን በውኃ የመሙላት የስራ ሂደት ልዩ በሆነ ጥንቃቄ መያዝ እንዳለበት ከባለሙያዎች ግንዛቤ ወስጃለሁ፡፡ ግድቡን በውኃ የመሙላት ስራ በበርካታ ነገሮች ማለትም የመሙላት መጣኔን በመወሰን፣ በውኃው ወቅታዊ የመጠን ለውጦች፣ የግድቡን የመውጣት መጠን የመቆጣጠር ሁኔታ፣ በመጀመሪያው የግድብ ሙሌት ጊዜ ሊከሰቱ በሚችሉ ችግሮች ላይ በሚሰጥ መፍትሄ፣ በግድቡ የውኃ ሙሌት ሂደት ጊዜ ችግሮችን ለመለየት በሚደረጉ ዝርዝር የቴክኖሎጂ መመርመሪያዎች፣ ግድቡን ለመቆጣጠር በሚደረግ ዕቅድ እና በሸለቆው የታችኛው አካባዎች ላይ ግድቡ እየተሞላ ባለበት ሁኔታ በሚደርሱ ተለዋዋጭ ነገሮች እና በመሳሰሉት ተጽእኖ ፈጣሪ ነገሮች ላይ ይወሰናል፡፡ የውኃ ማጠራቀሚያ ግድቡ መሙያ ጊዜ በኢትዮጵያ እና በግብጽ መካከል ያለ ዋና የፍልምያ ጊዜ ሂደት ነው፡፡

አምስተኛ፡ ግድቡ የሚጠናቀቅ ቢሆን እንኳ ኤል ሲሲ የኤሌክትሪክ ምርቱ ገበያ እንዳይኖረው ጠንክረው በመስራት የገንዘብ ማነቆ እንዲፈጠር ያደርጋሉ፡፡ እንደ ዘ-ህወሀት ዕቅድ ከሆነ የግንባታ ስራው ከተጠናቀቀ በኋላ ከታላቁ የህዳሴ ግድብ የሚመነጨው የኤሌክትሪክ ኃይል ምርት ለሱዳን፣ ለግብጽ እና ለአረብ ፔንሱላ ሀገሮች ይሸጣል የሚል ነው፡፡

እ.ኤ.አ ጥቅምት 2015 በወጣው ዘገባ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለስልጣን ዋና ስራ አስፈጻሚ አዜብ አስናቀ እንዲህ ብለዋል፣ “የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለስልጣን አንድ ኪሎ ዋት (kwh) የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት ዘጠኝ የአሜሪካ ሳንቲሞች ወጭ ይደረጋሉ፡፡ ሆኖም ግን የሚሸጡት በስድስት የአሜሪካ ሳንቲሞች ነው፡፡“

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በአሁኑ ጊዜ 33 በመቶ ኪሳራ እየደረሰበት ሽያጩን ያካሂዳል፡፡ በዚህ መጣኔ ስሌት መሰረት ታላቁ የህዳሴ ግድብ እየተባለ የሚጠራው የኤሌክትሪክ ኃይል ተምኔታዊ የምጣኔ ሀብት ቀያሽ በነበረው እና በአሁኑ ጊዜ በህይወት በሌለው የአለቆች ሁሉ አለቃ በነበረው በመለስ ዜናዊ የዘ-ህወሀት ፕላኔት (ዓለም) ውስጥ ብቻ ነው ትርፋማ ሆኖ ሊቀጥል የሚችለው፡፡

በአፍሪካ በኃይል ምርት አቅርቦት ላይ በቀጣናው ሀገሮች መካከል መልካም ትብብር የሚደረግ ከሆነ እና አህጉር አቋራጭ ጥረትም ከታከለበት በአፍሪካ የኤሌክትሪክ ዋጋ ዝቅ ሊል እንደሚችል በርካታ ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡ ዋናው ቸግር እነዚህ ትብብሮች በአፍሪካ ሀገሮች መካከል ወጭን በመጋራት ባለ አለመተማመን ብቻ ሁኔታውን የሚያሳንሰው አይሆንም፡፡ ሆኖም ግን ለረዥም ጊዜ ዘላቂ የጋራ ጥቅም ሲባል በግድቦች ላይ ስለሚደረገው ቁጥጥር እና አስተዳደር ጭምር እንጅ፡፡

አስገራሚው ነገር ደግሞ በአሁኑ ጊዜ በዘ-ህወሀት እና በግብጽ መካከል ባለው የግድቡ ውዝግብ ምንም ዓይነት መተማመን የሚባል ነገር የለም፡፡ ሶስቱ ጎረቤት ሀገሮች አስተማማኝ የኃይል ዘርፍ መገንባት እንዲቻል እንደ ልማት አጋርነት ሊተባበሩ የሚችሉበት ምንም ዓይነት ድጋፍ ሊሰጥ የሚችል ማስረጃ የለም፡፡ ይኸ የማይካድ እውነታ ነው!

ስድስተኛ፡ የግድብ ስራው ከተጠናቀቀ እና ስራውን የሚጀምር ከሆነ ኤል ሲሲ የኃይል ግሪዶችን፣ የስርጭት እና የማከፋፈያ መስመሮችን፣ ቅርንጫፍ ጣቢያዎችን እና የመሳሰሉትን ከስራ ውጭ ለማድረግ የተለያዩ የአጭር ጊዜ ስልቶችን በመንደፍ ለማደናቀፍ ሙከራ ያደርጋሉ፡፡ እንደዚህ ዓይነት ድርጊቶች ለብዙ ጊዜ ለሚቆይ እና አስቸጋሪ ለሆነ የኃይል ችግር ብቻ የሚዳርጉ አይደሉም፡፡ ሆኖም ግን እንደዚህ ዓይነት ድርጊቶች በግደቡ የመሰረተ ልማት እና በምርታማነት አቅሙ ላይ ከፍተኛ የሆነ ችግርን ያስከትላሉ፡፡

ሰባተኛ፡ ኤል ሲሲ የመጨረሻ የሆነውን ወታደራዊ እርምጃ ከመውሰዳቸው በፊት ማንኛውንም ዴፕሎማሲያዊ እና ህጋዊ ማዕቀፎች በሽምግልና፣ በእርቅ፣ በፍርድ ቤት ሂደት እና በተባበሩት መንግስታት ጣልቃ ገብነት አማካይነት በግብጽ ላይ የተደቀነ አደጋ ነው ብሎ የሚያስበውን ነገር ለማስወገድ ጥረት ያደርጋሉ፡፡

ስምንተኛ፡ የግድብ ስራው ከተጠናቀቀ እና ስራውን የሚጀምር ከሆነ ኤል ሲሲ በግብጽ ላይ ምጣኔ ሀብታዊ የሆነ ጉዳት እስኪያመጣ ድረስ ዝም ብለው ምንም ዓይነት እርምጃ ሳይወስዱ ተቀምጠው ይቆያሉ ብዬ አላምንም፡፡ ግድቡ እንደተጠናቀቀ በቀናት ጊዜ ውስጥ ፈጣን የሆነ ጥቃት ይሰነዝራሉ ብየ አምናለሁ፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ምንም ዓይነት ጥርጣሬ የለኝም!

ዘጠነኛ፡ ሁሉም ሊቀበለው የሚችል እንዲህ የሚል አንድ እውነታ አለ፡ “ምንም ይሁን ምን ታላቁ የህዳሴ ግድብ እየተባለ የሚጠራው ግድብ ወደ ግብጽ ሀገር በሚፈስሰው የውኃ መጠን ላይ ከፍተኛ የሆነ ተጽዕኖ ሊያሳርፍ ይችላል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ግብጽ እያደገ በመጣው የህዝብ ብዛቷ የውኃ እጥረት ችግር እየተከሰተ ነው፡፡ ብዙ ውኃ ትፈልጋለች፡፡ ግድቡ ወደ ግብጽ ሀገር የሚፈስሰው የውኃ መጠን ላይ ከፍተኛ እጥረትን ያስከትላል፡፡“

እንደተባበሩት መንግስታት ዘገባ “ግብጽ ከተባበሩት መንግስታት የውኃ የድህነት መለያ መስመር በታች ናት፣ እናም እ.ኤ.አ በ2025 የተባበሩት መንግስታት ወደ “ፍጹም የውኃ እጥረት ቀውስ” ውስጥ እንደምትገባ ትንበያ ሰጥቷል፡፡ በሌላ አገላለጽ እ.ኤ.አ በ2025 ግብጽ በውኃ እጥረት ቸግር እጅ ከወርች ትያዛለች! በዓባይ ወንዝ የውኃ ፍሰት ላይ የሚደረግ ማንኛውም ዓይነት የውኃ ቅነሳ በግብጽ ላይ እልቂትን ይፈጥራል” ይላል፡፡

ባለፈው ሳምንት ግሎባል ኢንተሊጀንስ እንዲህ በማለት ደምድሟል፣ “ከዓባይ ወንዝ የውኃ መጠን በመቀነስ ወደ ማጠራቀሚያ ግድቡ የማስገባት ስራው ስድስት ዓመታትን የሚወስድ በመሆኑ የግብጽን የውኃ አቅርቦት በእጅጉይቀንሰዋል፡፡ በመጨረሻም በግድቡ ውስጥ የሚኖረው የማይንቀሳቀስ ውኃ በውኃ ትነት ምክንያት የውኃ መጠን መቀነስ ያስከትላል፣ ይህም በበኩሉ የውኃውን ጥራት ያበላሸዋል“ ብሏል፡፡

እ.ኤ.አ በ2012 በኖርዌዎች በተጠና ጥናት መሰረት በሰባት ዓመታት ጊዜ ውስጥ የውኃ ማጠራቀሚያ ግድቡን ለመሙላት 67 ቢሊዮን ኪዮቢክ ሜትር ውኃ መሞላት ያለበት ሲሆን ይህም ወደ ግብጽ ሀገር የሚፈስሰውን የውኃመጠን 25 በመቶ ሊቀንሰው ይችላል፡፡ እንደዚህ ያለው የውኃ ቅነሳ ለግብጽ ታላቅ መቅሰፍት ነው፡፡ የውኃ ማጠራቀሚያ ግድቡ አንድ ጊዜ ከሞላ ወደ ግብጽ ሀገር የሚፈስሰውን የውኃ መጠን በ50 በመቶ ይቀንሰዋል፡፡

እ.ኤ.አ በ2014 በማሳቹሴትስ የቴክኖሎጂ ተቋም በወጣ ዘገባ መሰረት በግድቡ ላይ ሊከሰቱ በሚችሉ በርካታ ችግሮች ላይ አጋሮቹ የሚሸጧቸው መፍትሄዎች እውነታን ያላገናዘቡ ናቸው በማለት እንዲህ በማለት ደምድሟል፡

“ግብጽ፣ ኢትዮጵያ እና ሱዳን በአሁኑ ጊዜ የገጠሟቸውን ችግሮች ለማስወገድ ዓለም አቀፍ አማካሪዎችን በመቅጠር ፈጣን የሆነ መፍትሄ ለማግኘት የጋራ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ ከእኛ እይታ አንጻር ይህ ጉዳይ ዝም ብሎ ባዶ ምኞት ብቻ ነው፡፡ ወደፊት የሚመጡት ጠንካራዎቹ ስምምነቶች ከእያንዳንዳቸው ሶስት ሀገሮች የውጭ ፖሊሲ እና የውኃ ባለሙያዎችን በማዋቀር በቴክኒክ ጉዳዮች ላይ የጋራ ግንዛቤ እንዲኖር እና ለስምምነት ፈቃደኝነቱ እንዲኖር የሚያግዙ ሲሆን ስለግድቡ አሰራር ዝርዝር አፈጻጸም ስምምነት፣ ስለኃይል ንግድ ስምምነት፣ ስለግድቡ ደህንነት እና ስለጨዋማነት አያያዝ ቁጥጥሩ የሚመለከቱ ስምምነቶች ወደ ፊት የሚመጡ ከባድ ጉዳዮች ናቸው“ ብሏል፡፡

ጉዳዩ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡

በአሁኑ ጊዜ በዓባይ ወንዝ ላይ እያስተጋባ ያለው የጦርነት ወሬ ነገ በዓባይ ወንዝ ላይ እውነተኛ ጦርነት ሊያስነሳ ይችላል፡፡ ዘ-ህወሀት ለግብጽ መጠነ ሰፊ የሆነ የውኃ መጠን በመከልከል በተጻራሪው ተቃውሞውን እያሰማ መሄዱን ብቻ እንደ ስልት የሚወስደው ከሆነ ጦርነቱ አይቀሬ እንደሚሆን አምናለሁ፡፡

ግብጻውያን ውኃ ለእነርሱ የህይወት እና የሞት ጉዳይ ነው በማለት ለብዙ ጊዜ ሲናገሩ ቆይተዋል፡፡ ..2025 በእርግጠኝነት ለእነርሱየህይወት እና የሞት ጉዳይ ይሆናል!

እ.ኤ.አ በ1979 የግብጽ ፕሬዚዳንት የነበሩት አንዋር ሳዳት እንዲህ ብለው ነበር፣ “ግብጽን እንደገና ወደ ጦርነት እንድትማገድ ሊያደርጋት የሚችል ብቸኛ ነገር ቢኖር ውኃ ነው፡፡“ የግብጽን ውኃ በ25 በመቶ ቀንስ እናም ጦርነት ይነሳል፡፡

እ.ኤ.አ በ2010 ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ ከኃይድሮ ኤሌክትሪክ ፋሲሊቲዎች ጋር በተያያዘ ሊነሱ ለሚችሉ ውዝግቦች ማስተንፈሻ አገልግሎት ሊውል የሚችል ወታደራዊ አደጋ ለመጣል እገዛ የሚያደርግ ትንሽ የአውሮፕላን ማረፊያ ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት ከኦማር አልባሽር ጋር ስምምነት አድርገዋል ተብሎ ይታመናል፡፡ በግብጽ ላይ የዓባይን ውኃ በ25 በመቶ መቀነስ በግብጽ ደቡባዊ የሀገሪቱ ጫፍ ላይ ግዙፍ የአየር ማረፊያ ግንባታን ያስከትላል፡፡

እ.ኤ.አ በ2013 በዚያን ጊዜ የነበሩት ፕሬዚዳንት መሀመድ ሙርሲ እንዲህ ብለው ነበር፣ “የግብጽ የውኃ ደህንነት በምንም ዓይነት መልኩ ሊሻር አይችልም፡፡ እንደ መንግስት ኃላፊነቴ ሁሉም ዓይነት አማራጮች ክፍት እንደሆኑ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ፡፡ የጦርነት ጥሪ እያሰማን አይደለም፣ ሆኖም ግን በውኃ ደህንነታችን ላይ አደጋ እንዲደቀን በፍጹም አንፈቅድም፡፡ አንዲት የውኃ ጠብታ ብናጣ ደማችን ተለዋጩንይይዛል፡፡“ የግብጽን ውኃ በ25 በመቶ (ወይም ደግሞ በአንድ አንድ የውኃ ጠብታ) መቀነስ ጦርነትን ያስከትላል፡፡

እ.ኤ.አ ሰኔ 2014 የግብጽ ሜጀር ጀኔራል የሆኑት ታላት ሞሳላም እንዲህ ብለው ነበር፣ “አሁን ያሉን አማራጮች በጣም ጥቂት ናቸው፡፡ ዴፕሎማሲ የመጀመሪያው ነው፣ ሆኖም ግን የግብጽ የማድረግ ብቃት ከዝቅተኛው ደረጃ ላይ ነው ያለው፣ እናም ሰላማዊ ንግግር ፍሬ የማያፈራ ከሆነ የግብጽ ወታደራዊ አዛዦች በውኃ ጥም ከመሞት ይልቅ በጦርነት መሞት ይሻላል የሚል ውሳኔ ሊያሳልፉ ይችላሉ፡፡“ የግብጽን የውኃ መጠን በ25 ከመቶ ቀንሱት እናም የግብጽ ወታደራዊ አዛዦች በውኃ ጥም ከመሞት ይልቅ በጦርነት መሞት ይሻላል የሚል ውሳኔ ሊያሳልፉ ይችላሉ፡፡

ጥቂት የግብጽ ምርጥ የፖለቲካ መሪዎች ግድቡን ለማፍረስ የተለያዩ መንገዶችን ማለትም ጸረ ዘ-ህወሀት የሆኑ ተቃዋሚዎችን መርዳት ጭምር የሚል ሀሳብ አቅርበዋል፡፡

እንደ አንድ የታመነ የስለላ ድርጅት ምንጭ ከሆነ ግብጽ ሁሉም ዴፕሎማሲያዊ አማራጮች ካለቁ እና ከከሸፉ በኋላ በዓባይ ወንዝ ላይ በሚገደብ ማንኛውም ግድብ ላይ ጦርነት የማካሄድ እንዲህ የሚል ዕቅድ አላት፡

“ቀውስ የሚመጣ ከሆነ ግድቡን የሚያፈርስ አንድ ጀት በመላክ በአንድ ቀን ውስጥ ግድቡን አፍርሶ እንዲመለስ እናደርጋለን፡፡ የዚያን ያህል ቀላል ነገር ነው፡፡ ወይም ደግሞ በግድቡ ላይ ሻጥር እንዲሰሩ የእኛን ልዩ ኃይሎች እንልካለን፡፡ ሆኖም ግን በአሁኑ ጊዜ ወታደራዊ አማራጭን እንደ ብቸኛ መፍትሄ አንወስድም፡፡ ይኸ የመጠባበቂያ ዕቅድ ነው፡፡ እስቲ ግብጽ እ.ኤ.አ በ1970ዎቹ ሁለተኛ አጋማሽ ላይ ያደረገችውን ወታደራዊ ግዳጅ ወደ ኋላ መለስ ብለን እናስተውል፡፡ እ.ኤ.አ በ1976 ኢትዮጵያ ታላቅ ግድብ ለመገንባት ሙከራ ያደረገችበት ጊዜ እንደነበረ አስባለሁ፡፡ መሳሪያው በባህር ላይ ወደ ኢትዮጵያ በመጓጓዝ ላይ እንዳለ ዶግ አመድ አደረግነው፡፡ ጠቃሚ የሆነ ልዩ ጥናት ነው“ ነበር ያሉት፡፡

የግብጽን ውኃ በ25 በመቶ ቀንሱ እና ኤል ሲሲ ግድቡን በቦምብ የሚያጋይ ጀት ይልካሉ፣ ወይም ደግሞ ልዩ ኃይላቸውን በመላክ በግድባችን ላይ አሻጥር ይፈጽማሉ፡፡

አስረኛ፡  በእኔ አስተያየት የግድቡ ግንባታ ለግብጻውያን በምንም ዓይነት መልኩ የስምምነት፣ የውይይት፣ የሽምግልና፣  የእርቀ ሰላም ወዘተ ጉዳይ ሊሆን አይችልም፡፡ ስለዚህ ጉዳይ በጥሞና አስቡበት፡፡ ግብጽ በምን ዓይነት ሁኔታ ነው በህይወት እና በሞት መካከል ስምምነት ልታደርግ የምትችለው?

አሁን በህይወት የሌለው እና የዘ-ህወሀት ቆንጮ አድርጊ ፈጣሪ የነበረው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት እንዲህ ብሎ ነበር፣ “ግብጻውያን በኢትዮጵያውያን ላይ በድንገት ወረራ ይፈጽማሉ የሚል ስጋት የለኝም፡፡ ያንን የሚሞክር ካለ ታሪኩ ሊነገረው ይገባል፡፡“

መለስ ብዙ ይናገራቸው ከነበሩት ጥቂት ጊዜዎች ውስጥ “ኢትዮጵያ” የሚለውን ቃል የተጠቀመ መሆኑን አምናለሁ፡፡ እርሱ ሁልጊዜ ኢትዮጵያን እንደ ሀገር ብቻ ነው የሚጠቅሳት፡፡ ኢትዮጵያ የሚለውን ቃል መጥራት የሚያሳፍረው መስሎ ይሰማኛል፡፡ መለስ እራሱን ኢትዮጵያዊ አድርጎ የጠራበትን ጊዜ ፍጹም የሰማሁበት ጊዜ የለም፡፡ በፍጹም! ማንም ቢሆን መለስ ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ የተናገረበት ጊዜ ቢኖር በመረጃ አስደግፎ የሚያቀርብልኝ ሰው ካለ ከስህተቴ እታረማለሁ፡፡

መለስ በኢትዮጵያ ወታደራዊ ብቃት ላይ ታላቅ ኩራት በማሳደሩ በጣም ደስ ይለኛል፡፡ በእርግጥ መለስ በታሪካዊ ምልከታው ትክክል ነው፡፡ ኢትዮጵያ ማንኛውንም ወራሪ አይቀጡ ቅጣት እየቀጣች በማባረር ከሶስት ሺ ዘመናት በላይ ሉዓላዊነቷን እና ነጻነቷን አስከብራ የኖረች ሀገር ናት፡፡

ዳግማዊ አጼ ምኒልክ የአውሮፓ ኃያላን አፍሪካን እንደ ቅርጫ ስጋ በመቀራመት በቅኝ ግዛትነት ለመያዝ የሚያስችላቸውን የበርሊን ኮንፈረንስ/ጉባኤ ካጠናቀቁ ከሁለት ዓመታት በኋላ እ.ኤ.አ በ1896 አደዋ ላይ የጣሊያንን ወራሪ ኃይል ድባቅ በመምታት አሳፋሪ ሽንፈቱን ተከናንቦ እንዲወጣ አድርገዋል፡፡ ከዚህ በተጻረረ መልኩ አሁን በህይወት የሌለው መለስ ከምንም በላይ በሚጠላቸው በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ላይ በዚህ ጀግንነታቸው ለምን ኩራት እንደማይሰማው የሚገርም ነገር ነው፡፡

ኢጣሊያ እ.ኤ.አ በ1935 ኢትዮጵያን ከወረረች በኋላ ኢጣሊያ ለሁለተኛ ጊዜ በመላው ኢትዮጵያ በዱር በገደሉ ተሰማርተው አመራር ይሰጡ በነበሩ እና በአልሞ ተኳሽ ጀግኖች ኢትዮጵያውያን አርበኞች ብርቱ ተጋድሎ ተሸንፋ ለመውጣት ተገድዳለች፡፡ ለዚህም ነው ኢትዮጵያውያን ተባበሩ በምንም ዓይነት መልኩ ለውጭም ሆነ ለውስጥ ጠላት እንዳተንበረከኩ የምለው፡፡

መለስ ይገምተው እንደነበረው ግብጽ ግድቡ ከተጠናቀቀ በኋላ በኢትዮጵያ ላይ ወረራ የመፈጸም ዕቅድ የላትም በሚለው አባባል ላይ እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ኤል ሲሲ ለጦር ኃይሉ ልዩ ትዕዛዝ በመስጠት በኢትዮጵያ ላይ የአውሮፕላን ጥቃት ወታደራዊ ግዳጅ ሊፈጽሙ እንደሚችሉ እገምታለሁ፡፡

ግብጽ ወታደራዊ ብቃት ስለሌላት በግድቡ ላይ ወታደራዊ ግዳጅ በመፈጸም ችግር ልትፈጥር አትችልም የሚል አስተያየት የሚሰጡ የፖለቲካ ትንታኔ የሚሰጡ ሰዎች አሉ (ለምሳሌ ያህልም በአየር ላይ ነዳጅ የሚሞላ ጀት)፡፡ በዚህም መሰረት ረዥም ርቀትን በመጓዝ ጥቃት ለማድረስ የሚያስችል አቅም የላቸውም ብለው ያስባሉ፡፡ ግብጻውያን ለእንደዚህ ዓይነቱ ዕቀድ የመጠባበቂያ ዕቀድ ሊኖራቸው ይችላል፡፡

እ.ኤ.አ መስከረም 2015 ኤል ሲሲ ሁለት የጦር አሮፕላን ተሸካሚ መርከቦችና እስከ 1850 ኪ/ሜ ርቀት በመብረር እና እስከ 50 ሺ ጫማ የመጨረሻ ከፍታ በመውጣት ጥቃት ሊሰነዝሩ የሚችሉ 24 ኦምኒሮል ተዋጊ ጀቶችን  መግዛታቸዉን ማስተዋል ጠቃሚ ነገር ነው፡፡

“በገንዘብ እጦት የተገደበ ግድብ?” በሚል ርዕስ ባዘጋጀሁት ትችት ላይ የእራሴን አመለካከት በማንጸባረቅ ግልጽ አድርጌ ነበር፡፡

በመርህ ደረጃ የግድቦችን መገንባት አልቃወምም፡፡ ሆኖም ግን “ዛፍ ተንከባካቢ” የሚል የማስታወቂያ ልብስ መልበስ ያኮራኛል፡፡ ባለም ላይ ሁሉ በአካባቢ ጥበቃ እና አያያዝ ላይ ሙሉ በሙሉ አምናለሁ: አካባቢ ጥበቃ ድረጅቶችንም ረዳለሁ፡፡ አካባቢ ጥበቃ ለወደፊት ተውልድ ተጠብቆ መቆየት አለበት:: ትናንሽ ግድቦች ከትላልቆቹ የተሻሉ እንደሆኑ አምናለሁ፡፡ የእኔ አመለካከት በብዙ ሳይንሳዊ ጥናቶች የተደገፈ ነው፡፡

ኃይል ለአፍሪካ በሚለው ለፖለቲካ እና ለኤሌክትሪክ በሚለው አጠቃላይ ጥያቄ ላይ የተለየ አመለካከት አለኝ፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ አፍሪካውያንን በቤታቸው እና በንግዳቸው ከማሻሻል በፊት በተሻሻለ አስተዳደር እና ተጠያቂነት ማጠናከር ጠቃሚ ነገር እንደሆነ አምናለሁ፡፡ የግድብ ግንባታ በአፍሪካ በተለይም በኢትዮጵያ ውስጥ በውድድር ላይ የተመሰረተ የጨረታ ኮንትራት በማይሰጥበት ሁኔታ በግድቡ ውስጥ የሚሰራው ብቸኛው ነገር ሙስና፣ ሙስና እና የበለጠ ሙስና ብቻ ነው፡፡

አሁን በቅርቡ በኮሎራዶ ወንዝ ላይ የተገነባ እጅግ በጣም ማራኪ የሆነ ግድብን  የመጎብኘት ዕድል አግኝቸ ነበር፡፡ ለእኔ ይኸ ነገር በጣም ትምህርታዊ የሆነ ልምድ ነው፡፡ እጅግ በጣም ግዙፍ የሆነ የኃይድሮ ኤሌክትሪክ ግድብ መገንባት እና ማስተዳደር ብዙ አደጋዎች  ያሉበት አስቸጋሪ ነገር እንደሆነ አምናለሁ፡፡

የግልገል ጊቤ ሶስትን ግድብ ማስተዳደር ያልቻሉ ሰዎች ከአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን ታላቅ ግደብ ማስተዳደር ስለመቻላቸው እርግጠኛ አይደለሁም፡፡

እ.ኤ.አ ሚያዚያ በ2014 “የቅንጦት ግድብ ወጭ“ በሚል ርዕስ ባቀረብኩት ትችት ላይ ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ምንም ዓይነት ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ የሌለው የቅንጦት ግድብ ነው በማለት ተችቼ ነበር፡፡ ዴቨሎፕመንት ቱደይ/Development Today የሚባለው የእርዳታ ነጻ መጽሔት እና በኖርዲክ እና በዘርፈ ብዙ እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች እየታገዘ በፖለቲካ፣ በቢዝነስ እና ከአካባቢ እና ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ የሚዘጋጀው መጽሔት የህዳሴውን ግድብ “ፖለቲካዊ እንደምታን የተላበሰ አሁን በህይወት የሌለው የመለስ ዜናዊ የቅንጦት ፕሮጀክት“ በማለት ጠርቶታል፡፡

ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ አየተባለ አሁን የሚጠራው እና ቀደም ሲል የሚሊኒየሙ ግድብ እየተባለ ይጠራ የነበረው ግድብ እንደሌሎቹ ቀደምቶቹ የታላቅነት ስሜት ይሰማቸው እንደነበሩት የአፍሪካ አምባገነኖች ሁሉ የአምባገነኑ የመለስ ዜናዊ የአዕምሮ ልጅ ነበር፡፡ በግብጽ ውስጥ ያለው የአስዋን ከፍተኛ ግድብ እንደ ጋማል አብደል ናስር ሀውልት ሆኖ ይቆጠራል፡፡ መለስ የማይሞት የኮንክሪት ስሚንቶ ማስታወሻ በመገንባት እራሱን ዝነኛ በማድረግ ትንሹ የአፍሪካ ታላቅ ለመባል ይፈልግ ነበር፡፡

ግድቡ በኢትዮጵያ እና በግብጽ መካከል የውኃ ጦርነት መንስዔ እንደሚሆን አምናለሁ፡፡

ስለታላቁ የህዳሴ ግድብ ሁልጊዜ ትችት በምጽፍበት ጊዜ የዘ-ህወሀት አነብናቢዎች፣ ሎሌዎች እና በጥላቻ የተሞሉ ግብዞች ብሄራዊ ስሜት የሌለው የዘ-ህወሀት ጠላት፣ ወዘተ በማለት ይጠሩኛል፡፡ ስለዘ-ህወሀት፣ ስለስኬቱ፣ እና በሀገሪት ውስጥ ልማት ለማምጣት በሚታገለው ድርጀት ላይ አሉታዊ ነገር ለመናገር ምንም ዓይነት አጋጣሚ የማያመልጠኝ አድርገው በመቁጠር ጥላሸት የመቀባት ሱሳቸውን ይወጡብኛል፡፡

የዘ-ህወሀት ሎሌዎች እና በጥላቻ የተሞሉ የዕኩይ ምግባር አራማጆች ሁል ጊዜ ሰኞ እያዘጋጀሁ የማወጣቸውን የትንታኔ ትችቶች አንበቦ መረዳት ይችላሉ ብዬ አላምንም፡፡ ቢችሉ በእውነታዎቹ እና በአመክንዮዎቹ ላይ በመመስረት እኔን በማፋጠጥ መሞገት ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን ይህንን በፍጹም አያደርጉትም!

ሆኖም ግን ማንም እውነታውን መሞገት ለሚፈልግ አድሉን አሰጣለሁ፡፡ ስለ “ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ”  የተለያዩ ጦርነት አያስከትልም የሚል ትንታኔ ቢሰጥ በጣም ጠቃሚ ነው ፡፡

የእራሴን አመለካከት አቅርቤአለሁ፡፡ ሌሎችም አስተያየታቸዉን አንድያካፈሉ አጋብዛለሁ!

በጉዳዮቹ ላይ ክርክር እናድርግ፡፡ እውነታዎችን እንመርምር፡፡ ህዝቡ መረጃ እንዲኖረው እናድርግ፡፡ በግድቡ ሊመጣ የሚችለው መዘዝ ምን ሊሆን እንደሚችል እናስጠንቅቃቸው፡፡ ህዝቡ ስለግድቡ ያለውን እውነት በሚገባ እንዲገነዘብ እናድርግ!

በበኩሌ ምንም ዓይነት የውኃ ጦርነት ወይም ደግሞ ሌላ ግጭት አለመኝም፡፡ በኢትዮጵያ፣ በሱዳን እና በግብጽ መካከል አህጉራዊ ትብብር እና ከዚያም ባለፈ መልኩ ጠቅላላ አህጉራዊ ትብብር ቢኖር ከምንም በላይ ደስታ የሚሰጠኝ ነገር የለም፡፡ እንደዚህ ዓይነት ትብብር በምኞት አላሚዎች ዓለም ውስጥ ብቻ እንጅ በሰሜን ምስራቅ የአፍሪካ አህጉር ሀገሮች ውስጥ ባሁን ጊዜ  ሊሰራ አይችልም፡፡ እንደ ወርቅ የጠራው እውነታ ይኸው ነው፡፡

በእኔ ትንታኔ ላይ ስምምነት የሌላችሁ ሰዎች ባለፈው ሳምንት በግሎባል ኢንቴሊጀንስ የተዘጋጀውን እና ይፋ የሆነውን እንዲህ የሚለውን ዘገባ ተመልከቱ፡

“…አህጉሩ ስለግድቡ የተለያየ አቋም በመያዝ ተለያይቶ እስከቀጠለ ድረስ እርግጠኛ የግንባታ ስራው በማንኛውም ጊዜ ሊሰናከል እና ሊቋረጥ ይችላል፡፡ ግድቡ በአሁኑ ጊዜ 50 በመቶው ተጠናቅቋል የሚል ዘገባ ቀርቧል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ የውኃ አቅጣጫ ማስቀየስ ስራ በግንባታ ቦታው አካባቢ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡ እስከ አሁን ድረስ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ግንባታው እየተካሄደ ቢሆንም ኢትዮጵያ ለፕሮጀክቱ ማስፈጸሚያ የሚውል የውጭ መዋዕለ ንዋይ ማግኘት አልቻለችም፡፡ የግድቡን ስራ ለማጠናቀቅ ከሚያስፈልገው ጠቅላላ ገንዘብ 4.8 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ እስከ አሁን ድረስ ሊገኝ የቻለው ገንዘብ ከ30 በመቶ በታች ነው፡፡ ኢትዮጵያ ቀሪውን ገንዘብ ለማግኘት ካልቻለች ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ ለበርካታ ዓመታት ሊዘገይ ይችላል፡፡ ለዚህ ነው ስምምነቶች አስፈላጊዎች ሊሆኑ የሚችሉት፡፡ የተሻሉ ስምምነቶች ከተካሄዱ ኢትዮጵያ ገንዘብ የማግኘት ዕድሏ የተሻለ ይሆናል፡፡“

ግድቡ ምን መሆን እንዳለበት ዕድሉ ያለው በኤል ሲሲ እጅ አይደለም፡፡

የዓባይ ወንዝ አስከፊ ዕድል ያለው በዘ-ህወሀት እጅ ላይ ነው፡፡

ይገርማል! ወይ ዳመና መዝገን!

ብር የለም ግድብ የለም!

አይገርምም! ግድብ በጦርነት ሳይሆን በገንዘብ ሲገደብ!

የሰኞ ትችቶቼን ለአስር ዓመታት ገደማ ያህል ስትከታተሉ ለቆያችሉ ለሁሉም ታማኝ አንባቢዎቼ (ወይም ደግሞጥቂቶች ፍቅርን የተላበሱየኃይማኖት ሰዎች እያሉ ለሚጠሯቸው) እንኳን ለፈረንጆች አዲስ ዓመት በሰላምአደረሳችሁ፡፡ 

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!         

ታህሳስ 26 ቀን 2008 .

The post ኢትዮጵያ፡ በዘ-ህወሀት የተገደበች ሀገር (ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም) appeared first on Zehabesha Amharic.


ሚሚየን እንዳያስሩብን ፈራሁ

$
0
0
እውነት ከ ምድር ቤት
እትየ ሚሚ በጋዜጠኞች ክብ ጠረቤዛ ላይ እሁድ ጃንዩሪ 3,2016 ላይ በኢትዮጵያ ታሪክ ለነጻነት የተደረገ ትግል አልነበረም ነገር ስልት ነበር፡፡ ያለፈውን ስረአት ለመጣል የተደረገው ትግል እራሱ የነጻነት ትግል አልነበረም፡፡ የኤርትራ ትግል ብቻ ነበር ለነጻነት ሲደረግ የነበረው በሚል ስትፈላሰፍ ሰማኋት፡፡ አይ ጆሮ ደጉ! ሰምቶ አይፈነዳም እኮ፡፡
Mimi
 
ከዚ በፊት ለሚሚ ጠረቤዛ ምን ያደርግላታል የሚል ጽሁፍ ማንበቤን አስታዉሳለሁ፡፡ በዛሬው ፕሮግራም ላይ ከሚሚየ ጋር አብሮ የነበረው አንድ አጋሯ ብቻ ነበር፡፡ ድሮ ድሮ ሌሎች ለምን መገኘት እንዳልቻሉ ትናገር ነበር፣ አንደኛው ስልጠና ሄዶ ሌላኛው መኪና አደጋ ሌላኛው ራቅ ያለ ቦታ ለመስክ ስራ ወጦ እየተባለ አንድ በአንድ ይልተገኙበት ምክንያት ይዘረዘር ነበር፡፡ዛሬ ግን ምንም ሳትለን ከፊቷ አንድ ሰውየ እንዳለ ነገራን ብቻ ነበር ወደ አበይት ጉዳዩቹ የገባቸው፡፡ እኔ ታድያ መቼም መስጋት ልማዴ ነውና ለቀጥታ ስርጭቱ ለመድረስ ሲሉ ያን ወደቢሮ የሚወስደውን ዳገት በሩጫ ሲወጡ መንግስት ሰላማዊ ሰልፍ ያለፈቃድ ወጡ በሚል እስኪጣራ አስሯቸው እንዳይሆን በሚል ልቤ ሲሸበር ነበር የቆየው፡፡በነገራችን ላይ አንድ የዛሚ ጋዜጠኛ ወደ ቢሮ የሚወስደውን ዳገት ጥድፍ ጥድፍ እያለች ስትወጣ ፖሊስ ተመልክቶ ኖሮ ሰላማዊ ሰልፍ እየወጣሽ ሊሆን ይችላል በሚል ጥርጣሬ ለስምንት ወር አስሮ ሲያጣራ ከቆየ በኋላ ባሳለፍነው ሳምንት ፍርድቤት ነጻ ብሎ ለቋታል፡፡ እና ወዳጄ ስትቸኩል እረጋ በል የሚለው ዘይቤ የሚሰራው ይሄኔ ነው፡፡ ዛሬ ይህ ጉዳይ ይነሳ ይሆናል ብየ ጠብቄ የነበረ ቢሆንም እነሱ ሆየ እንዳውም መንግስት እስሩ ላይ ለምንድን ነው የማይጠነክረው እስኪጣራ ሁሉም ተሰባስቦ ይግባ አይነት መፈክር እና ድንፋታ ነው ሲያሰሙን ያረፈዱት፡፡
 
ጋዜጦች ይዘጉ፤ መጽሄቶች ይታገዱ፤ ስልጠናዎች ይሰረዙ፤ የሚጽፉ እጆች ይቆረጡ አይነት ጥሪ ለማድረግ ማንም የማይቀድማት እትየ ሚሚ፤ በአንድ ወቅት የርሷን የሬዲዮ ጣቢያ የብሮድካስት ባለስልጣን ሊዘጋ እንደሆነ ደብዳቤ ሲጽፍላት፣ “ፍትህ በሃገሩ የለም እንዴ? ዛሚ የመንደር ሱቅ ነው እንዴ እንደዚ በአንድ ደብዳቤ የሚዘጋው?” የሚል ተጠቃሁ የደራሽ ያለህ የሚመስልን ጩኸት የሰማ በቃ ሚሚየ ትምህርት ወሰደች ብሎ ነበር፡፡ እርሷ እንደው ፍንክች የአባ ቢላዋ ልጅ ሆና ጭራሽ በሳለ ቢላዋ ሁሉም ካልተቆረጠ አይነት ጭልፊት ሆና ቀጠለች፡፡
 
በጠረቤዛው ዙርያ የነጻነት ትግል ጉዳይ እንደዚ የተካረረው አንዱ የተቃዋሚ ሊቀመንበር ትግሉ የነጻነት ትግል ይሁን የሚል ጥሪ አስተላልፏል በሚል ነው፡፡ መንግስት ምን እስኪሆን ነው የሚታገሰው ይላታል በጠረቤዛው ዙሪያ ያስቀመጠቸው(ወንበር መኖሩን እኔ እንጃ) ብቸኛው “ጋዜጠኛ”፡፡ በነገራችን ላይ ልሳሳት እችላለሁ ግን ጆሮየ ፈጥሮበት ነገር አያልፈውም እና ይህ ብችኛ ጋዜጠኛ እየዘላበደ እያለ ሲጋራ ለመለኮስ ላይተር ችር ችር ችር.. ሲል ይደመጣል፡፡ ይችን አንድ ሰአት እንኳን ብትታገስ ምናለ! አይ ክፉ አመል? ካልሆነ ደግሞ በአንድ ግዜ ቦግ አድርጎ ለሚለኩስ ላይተር በጀት እንዲያዝ ማድረግ፡፡ በቻይና እቃ እሷም ተንቃ እኛም ተሳቀን ከምናልቅ፡፡
 
ይህን ጥሪ በጋዜጣዊ መግለጫ አስተላልፈዋል በሚል እንደዚ ውግዝ የሚደርስባቸው የሰማያዊ ፓርቲ ለቀመንበር ናቸው፡፡ ታድያ እንደሚነግሩን ከሆነ እነዚህ በክቧ ጠረቤዛ የተሰባሰቡት ጋዜጠኞች የርሳቸውን ጋዜጣዊ መግለጫ ለመከታተልና አሉኝ የሚሉት ጥያቄም ካለ ለመጠየቅ በስፍራው አልተገኙም ነበር፡፡ እንግዴህ በስፍራው ያልተገኘነው ተከልክለን ነው አላሉንም፡፡ ስለዚህ ያልሄዱት በቦታው መገኘት ልማታዊነት መስሎ ስላልታያቸው ይሆናል ብሎ መጠርጠር ይቻላል፡፡ እናም ለዚህ ታላቅ ትችት መነሻ የሆናቸውን ዜና ያገኙት ከአንድ የህትመት ዉጤት ላይ እንደሆነ ነግረዉናል፡፡ ያንን ስሙን ሊነግሩን ያልፈለጉትን የህትመት ዉጤት ዋቢ በማድረግም ሊቀመንበሩን ኢትዮጵያ ነጻነቷን አስጠብቃ እንደኖረች አልሰሙም ወይ በሚል በጽኑ ሲወርፏቸው አርፍደዋል፡፡ ከራሳችን አልፈን ለአፍሪካ የነጻነት ተምሳሌት መሆናችንን ያራከሰ መግለጫ በሚል ሰውየውን በቃላት ሲያብጠለጥሉና የኢትዮጵያ ህዝብ በዚህ መግለጫ ተሰድቧል ሲሉ ተደመጡ፡፡ ማሳረጊያቸውም ያው በገደምዳሜው የይታሰርልን ጥሪ ሆኖ ተደመደመ፡፡
 
እንደነገርኳችሁ እኔ ስጋት ቶሎ ያጠቃኛል እና የዛሬን የክብ ጠረቤዛ ዉሎ ሲያዳምጡ የነበሩ ቀን ከሌት ሲዘመርላቸው ወይም ሲያዘምሩን የኖሩት “የነጻነት ታጋዮች” ምናልባትም በታላቅ ሃዘን ተዉጠው “እንዴት ነው እትየ? ምነው እሱ? እኛ ለ አስራሰባት አመት ለነጻነት ስንታገል ዉለን እንደዚ ባንዴ ያን የመሰለ መሪር የነጻነት ትግል እንዲህ እንደዋዛ በአንድ ጀምበር ፍጹም አልነበረም ብለሽ የካድሽው? እንደዚህ ስትይ ለዚህ ትግል የተሰውት ሰማእታት አጽም ትንሽ እንኳን አልጎረበጠሽም ወይ? እኛ የተረፍነው በህይወት እያለን እንደዚ ካልሽማ ትንሽ ዞር ብንል ምን ልትጨምሪ ነበር?” ብለው እስኪጣራ ከክቡ ጠረቤዛ ወደ ጠባቡ ቤት ተሸጋግረሽ ቀጣይ የምደባ ቦታሽን ተጠባባቂ የሚል የቃል ትዛዝ እንዳይመጣ ነው፡፡ እንግዴህ መቼም ባለፈው ግዜ በደብዳቤ አይቻልም ስላለች ነው ነገሩ ወደ ቀጭን የቃል ትዛዝ ይሆናል ተብሎ የተገመተው፡፡ ለእንደዚህ አይነቱ ትዛዝ ይግባኝ ብዙም የሚያስኬድ አሰራር እንዳልሆነ ይታወቃል፡፡ በግዜ ግለ ሂስ ማድረግ ነው የሚያዋጣው፡፡ ያለዚያ አሳሪዎቹን ከእሰሩልኝ ጥሪው ይልቅ የእሰሩኝ ጥሪው የበለጠ ሊያስጎመዥ ይችል ይሆናልና፡፡
 
በሌላ አጀንዳ ከተነሱ ጉዳዮች ዉስጥ አንዱ ሰሞኑን ተደረሰ የተባለው ስምምነት ነበር፡፡ እነ አልሲሲ እንደዚ አይነት ስምምነት ተስማማን ብለው በራሳቸው የመገናኛ ብዙሃን ለተናገሩትና የነሱ ሜይን ስትሪም ሚዲያ እይተቀባበሉ ለዘገቡት ዜና፤ ሚሚየ የኛዎቹን ሚዲያዎች የበሬ ወለደ ወሬ ፈጣሪዎች ብላ ውርጅብኙን ታወርድባቸው ገባች፡፡ አሁንማ በጣም ተደራጅተው እስከ ሳታላይት ቲቪ ድረስ አላቸው በማለት በቁጭት ስትንገበገብ ትደመጣለች፡፡ እንግዴ አገር ውስጥ ያሉት በሙሉ ተዘግተው ስላለቁ እከሌን ዝጉልኝና ለብጫየ ልጨፍር ማለት ስለማይቻል ነው ንዴቷ ብው ብሎ ላይተሯን ቦግ ያስደረጋት የሚል ጥርጣሬ አድሮብኛል፡፡ መጠርጠር በህግ ካልተፈቀደ ትቸዋለሁ፡፡
 
አንዱ ናይጀሪያዊ ኮን አርቲስ የተጫወተውን ድራማም እርሷ በተለመደ መልኩ መቀመጫውን አየርላንድ ያደርገ … በሚል አይናችሁን ጨፍኑ ላሞኛችሁን እና ሌሎችንም የተረጋገጡ ውሸቶችን በዚህ መረጃ እንደ ብርሃን ፈጥኖ በሚሰራጨበት ክፍለዘመን ያለ አንዳች ይሉኝታ ስታሽጎደጉዳቸው ለሰማ ወይ ግዜ ደጉ ስንቱን ታሰማናለህ ማለቱ አይቀርም፡፡ በዚህ አርስት ላይም ለፉክክር በሚመስል ድምጸት የዶ/ር ብርሃኑም በሌላ መቀመጫውን ጎረቤት አገር ባደረገ ሚዲያ የአመቱ ምርጥ ሰው መባላቸው ጉዳይ ተነስቶ በጽኑ ሲብጠለጠል ነበር፡፡ ሁኔታውን ያየ ጠ/ሚ ከ ዶ/ሩ ጋር ባደረጉት ውድድር አንድ እኩል የወጡ ነው የሚመስለው፡፡ ተቀማጭነቱን አዲስ አበባ ያደረገው የርሳቸው ሬዲዮ ግን ያመቱን ምርጥ ያስታቀፈው ለማን እንደሆነ አልነገሩንም፡፡
 
የሚገርመው ግን ውሸት እራሱ ያልቃል እንዴ? እኔ ከዚህ በፊት ባለኝ መረጃ እንደማያልቅ ነበር የማቀው፡፡ ወደመጨረሻ ላይ እኮ መጀመሪያ ተወርቶበት ያለቀን ጉዳይ በድጋሚ አንስተው የተናገሩትን ይደግሙት ገቡ፤ ይቺ አንድ ሰአት አልሞላ አለች፡፡ እነሱ እራሳቸው ፍጹም የመሰላቸት መንፈስ ታየባቸው፡፡ ልማታዊነትን በተሰላቸ መልኩ ማስቀጠል ስለማይችል ለሚቀጥለው ሳምንት የክብ ጠረቤዛ ዉሎ በርካታ አዳዲስ ዉሸቶችን የመፈብረክ ስራ ላይ ትኩረት ተሰጦ ሊሰራበት ይገባል የሚል ልማታዊ አስተያየት እንስጥ እንዴ?
 
ቸር እንሰንብት

The post ሚሚየን እንዳያስሩብን ፈራሁ appeared first on Zehabesha Amharic.

የኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ህብረት መግለጫ አወጣ –“ጣራ የለሽ እስር ቤት ከድጡ ወደ ማጡ”

$
0
0

United Ethiopian Muslims Peaceful Movement Support Group [UEM-PMSG]

የኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ህብረት

 

pastedGraphic.png

January 6, 2016
(PDF) ሁከት ፈጣሪ አሣሪና ገዳዩን የደርግ አገዛዝ ግንድ ፈንቅዬ የሰላም ችግኝ በምድረ ኢትዮጵያ አሰፍናለሁ፤ የሃሳብ ልዩነት ልዩነቶችን በጠመንጃ ቋንቋ ብቻ መፍታት የሆነውን የወታደር ስልት ቀልሼ በዘመኔ የክብ ጠረጴዛ ውይይት መደረክ እተካለሁ፤ እመኑኝ ቀን ይወጣላችኋል፤ ሰላም ትሰፍናለች እያለ ነብር ወያኔ ከሕዝብ የተቀላቀለው። የገባውን ቃል የግልብጥ ተርጉሞ በርግጥ ድብደባን፣ እስርን፣ ግድያና ሽብርን ማስፈኑን የዐይን እማኞች ነን። ነፍሰ ጡር፣ ወጣት የአገር ተስፋዎችን ደብድቧል፣ ሴትና አዛውንት አዋርዷል።እናት ስብእናዋንና ክብሯን ተገፋ ልጄን ልጄን እያለች በወታደር የተረሸነችበት የጭካኔ መድረክ እንጂ በክብ ጠረጴዛ በውይይት ችግር የመፍታት የሰከነ ሥልጡን ባህል በወያኔ መንግስት ሲተገበር አላስተዋልንም።
ጀግና ወላዲቷ እየተባለ የሚዘመርላት እናት ቀርቶ ውንድ ልጅ እንኳ በትግል ቆስሎ ወይም ተሸንፎ መሬት ከነካ እወደቀበት የማይመታበት ባህል ያለን ሕዝቦች ነበርን በየትም አገር ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ ሁኔታ የቢቢኤንና ኢሳትን ዜና አዳምጣችኋል በማለት ወታደሮች በሰው ቤት ጣራ ላይ እየወጡ የሳተላይት ዲሽ ሲነቅሉና ሲሰባብሩ ሰንብተዋል።

“ከድጡ ወደ ማጡ”ይሉታል አበው ከገጠር እስከ ከተማ ዱላ በጨበጡ ጠመንጃ በአነገቡ ወታደሮችና ጆሮ ጠቢዎች ሕዝቡን ማጠሩ የወያኔን ከልክ ያለፈ ፍርሃትና ከስልጣን መንጎጃው ወቅት መቃረቡን ከሚያመለክቱ ክስተቶች አንዱ ነው።

Muslim in ethiopia
የኢትዮጵያ ሙስሊም መሪዎች እነ አቡበከር፣ አህመዲን ጀበልና ሸህ መከተ ሙሄ መታሰርና በማእከላዊ መደብደብ የሕዝበ ሙስሊሙን ሞራል አጠናክሮ ወደ አንድ የትግል ጎራ እንደተሰበሰበ ሁሉ የኦሮሞ ሕዝብ መሬትን ነጥቀህ አሽከር አታደርገኝም በማለት የጀመረውን የመብት ፊልሚያ በመደገፍ  ወገናቸው ጎን የቆሙትን ጀግኖች እነ ኦቦ በቀለ ገርባ፣ አዲሱ ቦላና ደስታ ድንቃ፣ ደጀነ ጣፋ፣ ጌታቸው ሽፈራውና ዮናታን ተስፋዬ መታሰር፤ የኦሮሞ ኮንግሬስ ዋና ፀሃፊ ኦቦ በቀለ ነጋ ላይ የተፈፀመው ድብደባና ዛቻየኦሮሞን ህዝብ ብቻ ሣይሆን ድፍን የኢትዮጵያን ሕዝብ አስተባብሮ ለዘለቀ ትግል የሚያዘጋጅ ይሆናል። የጥቂት ታጋዮች መስዋእትነት የሺ ታጋዮች መፍለቂያ ምክንያት ነው፤ ታሪክም ይህንን ይመሰክራል።
ከወያኔ መንግስት ጋር ተሰልፋችሁ በህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን በደል በማራመድ ላይ የምትገኙ ካድሬዎች ለአንድ አፍታ ከራሳችሁ ጋር ተውያዩ፤ አስቡ፤ የዚያ ሁሉ ወጣት ደም ሲፈስ፤ የዩንቨርሲቲ ተማሪዎች በፌደራል ፖሊስ ተከበው ሲደበደቡ ያሰሙት የነበረውን

“ወየው፣ ወየው! ”የሰቆቃ ድምፅ ከሰማችሁ በኋላ ዳግመኛ ከወያኔ መንግስት ጋር ላለመስራት ቆራጥ ውሳኔ ማስተላለፍ በተገባችሁ ነበር። እንደ ሰው መሳሳት ያለ ነው ስህተትን ተርድቶ ከአጥፋት መመለስ ግን ትልቅነትና አዋቂነት ነው። እናንተም እንደ ህዝቡ በቃ በሉ። በቃ ብለው የወታደር ዩኒፎርም አቃጥለው ወደ ህዝብ ከገቡት ጋር ሁኑ ጊዜያዊ ጥቅም ከውያኔ መንግስት ጋር ያስተሳሰራችሁ፤ ገና ለገና ንግድ ቢጤ እሞክራለሁ በሚል ተስፋ ብቻ ዳር የተቀመጣችሁ ወገኖቻችን ሃብቱም ብልፅግናውም ሕዝብ ሰላም ሲያገኝ ነው። ለሐቅና ለፍትሕ ቁሙ። አዱኛውና ቱጃርነቱ ያኔ የአብሮነት ይሆናል።
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ሕብረት የወያኔ መንግስት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በተለይም በአሁኑ ወቅት ኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ እየፈፀመ ያለውን ጭፍጨፋና በደሉንም በመቃወማቸው ለእስር የተዳረጉት የኦሮሞ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ የሲቪል ድርጅቶች፣ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አካላት፣ ጋዜጠኞች፣ የኦሮሞ ወጣቶች፣ ቀደም ሲል በእስር በመማቀቅ ላይ የሚገኙ የሙስሊሙ መሪዎችና ጋዜጠኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ይጠይቃል።

በመላው የሃገሪቱ ሕዝብ ላይ የወያኔ መንግስት ያሰፈነው የሰቆቃ አገዛዝና የኢትዮጵያን መሬት ቆርሶ ለሱዳን ለመስጠት እያደርገ ያለውን ስምምነት በፅኑ የሚያወግዝ መሆኑን ይገልፃል።

ትግላችን እስከድል ደጃፍ ድረስ በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!

አላሁ አክበር!!!

የኢትዮጵያ  ሙስሊሞች  ሰላማዊ  ንቅናቄ  ደጋፊዎች  ሕብረት

The post የኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ህብረት መግለጫ አወጣ – “ጣራ የለሽ እስር ቤት ከድጡ ወደ ማጡ” appeared first on Zehabesha Amharic.

ዜና ፎቶ |በምዕራብ ሐረርጌ ሒርና ነዋሪው የፌደራል ፖሊሶችን ጠራርጎ ካስወጣ በኋላ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ከሰአታት በፊት ዘ-ሐበሻ ባቀረበችው ዘገባ የፌደራል ፖሊሶች በምዕራብ ሐረርጌ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ በመተኮስ በርካታ ወገኖችን ማቁሰላቸውን መዘገባችን ይታወሳል:: ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች እንዳመለከቱት ዛሬ ሙሉ ቀን ሂርና በጥይት እና በጭስ የጦር አውድማ መስላ ውላለች:: ነዋሪው ከፖሊሶች ጋር ትንቅንቅ ፈጥሮ ታጣቂዎቹን ከከተማዋ ጠራርጎ ያስወጣቸው ሲሆን መጨረሻ ላይም መንገዶችን ዘግቶ ነበር:: ሁኔታውን የሚያሳዩ ፎቶዎች ደርሰውናል – ተካፈሉ::

hirna 1 hirna 2 hirna 3 hirna 4

The post ዜና ፎቶ | በምዕራብ ሐረርጌ ሒርና ነዋሪው የፌደራል ፖሊሶችን ጠራርጎ ካስወጣ በኋላ appeared first on Zehabesha Amharic.

ኃይለማርያም ደሳለኝ ልጃቸውን የፊታችን እሁድ በቤተክርስቲያን እና በቤተመንግስት ይድራሉ

$
0
0

sosina

(ዘ-ሐበሻ) የሕወሓት መንግስት ታዛዥ ጠ/ሚኒስትር የሚባሉት ኃ/ማሪያም ደሳለኝ የመጀመሪያ ሴት ልጃቸውን ሊድሩ መሆኑ ተሰማ:: ኢሕ አዴግ ሃገሪቱን ከተቆጣጠረ በኋላ በስልጣን ላይ እያለ ልጁን በመዳር የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነዋል:: የአቶ ኃይለማሪያም ልጅ በሃዋሪያት ቤተክርስቲያን ጥር 1 ቀን 2008 ዓ.ም ትሞሸራለች::

የሃይለማርያም የመጀመሪያ ልጅ እንደሆነች የሚነገርላት ዶ/ር ሶስና ኃ/ማሪያም ከአቶ አቤል አየለ ጋር እሁድ ጥር 1 ቀን ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት በአዲስ አበባ በሚገኝ የሃዋሪያት ቤተክርስቲያን የቃል ኪዳን ሥነሥርዓታቸውን የሚፈጽሙ ሲሆን ከቤተክርስቲያን መልስ በታላቁ ቤተመንግስት በዶ/ር ሶስና ቤተሰቦች በአቶ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ እና በወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ እንዲሁም በአቶ አቤል አየለ ቤተሰቦች በአቶ አየለ ቡናሮ እና በወ/ሮ እልፍነሽ አቦታ የተዘጋጀ የምሣ ግብዣ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ እንደሚከናወን ከሃገር ቤት የወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል::

ሃይለማርያም ማርያም ደሳለኝ ከወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ በትዳር ሕይወታቸው ሦስት ሴት ልጆችን እንዳፈሩ የሕይወት ታሪካቸው ያስረዳል::

The post ኃይለማርያም ደሳለኝ ልጃቸውን የፊታችን እሁድ በቤተክርስቲያን እና በቤተመንግስት ይድራሉ appeared first on Zehabesha Amharic.

ነአምን ዘለቀ እና ጀዋር መሐመድ በጋራ በአንድነት ስለመታገል ተናገሩ |ሊደመጥ የሚገባ ቃለምልልስ

አባይ ጸሐዬ “በኦሮሚያ ክልል የመብት ጥያቄ ባነሱ ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ በቂ አይደለም” አሉ |አፈትልኮ የወጣ ምስጢራዊ ድምጽ

$
0
0

abay Tsehaye
የኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ የአባይ ጸሐዬን ምስጢራዊ ንግግር ይፋ አደረገ:: የቴሌቭዥን ጣቢያው እንዳሰማው ትናንት የኦሮሞን ሕዝብ ልክ እናስገባዋለን ያሉት አባይ ጸሐዬ ዛሬ ደግሞ “ተቃውሞ ባነሱት በኦሮሞዎች ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ በቂ አይደለም” ሲሉ መናገራቸውን ይፋ አድርጓል:: አፈትልኮ የወጣውን ድምጽ ያድምጡ::

The post አባይ ጸሐዬ “በኦሮሚያ ክልል የመብት ጥያቄ ባነሱ ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ በቂ አይደለም” አሉ | አፈትልኮ የወጣ ምስጢራዊ ድምጽ appeared first on Zehabesha Amharic.

የአርሰናል ተጫዋቾች በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ መልካም ገና ይሏችኋል | Video


ለቡ ድሮ እና ዘንድሮ፥ |በእለፋቸው ሞሲሳ

$
0
0

እድሜየን ሲሶ የኖርኩት ለቡ በምትባል በደቡብ አዲስአበባ በምትገኝኝ ቀበሌ ነው::….ድሮ ቀበሌ ገበሬ ማሕበር ነበር የምትባለው ….አሁን ለቁጥር ወግ በቅታ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ምንትስ ቀበሌ ዜሮ አንድ ተብላለች:: ለቡ ድሮ ድሮ…ሁርቡ የሚባል የክረምት ጀግና ወንዝ እየተገማሸረ ነዋሪውን የሚያሸብርባት….ጎረምሶች የወንዙን ፉከራ ከመጤፍ ሳይቆጥሩ እየዘለሉ ገብተው እወንዙ ዳር ሳር ሲግጥ ሳት ብሎት ገብቶ በ አለልቱ እግሮቹ የተተበተበ ወይፈን የሚታደጉባት …. የለቡ እና የማዶ ልጆች ክረምቱን ሙሉ እና በበጋው ቅዳሜ እና እሁድን ጠብቀው እግር ኩዋስ የሚጫወቱበት ሰፊ ሜዳ የያዘች….ጉርምስናን የተሻገሩት ህዳር ሃና እና ጥምቀትን እየጠበቁ ተሻግሮ ካሉት ገላን እና መኒሳ ቀበሌዎች ከሚመጡ ጎልማሶች ጋር የፈረስ ጉግስ ውድድር የሚያደርጉባት….

Lebu
ከመሃል ከተማ ልጆች በክረምት ለበዓል የሚበራ ለራሳቸውም …የሚሸጥም ችቦ በነፃነት ለቅመው “ገጠር ሄደን መጣን!” ብለው ጉዋደኞቻቸውን የሚያስቀኑባት… በማገዶ ሽያጭ የሚተዳደሩ የጨርቆስ እና ቄራ አካባቢ እናቶች ከቀበሌው የሚገዙትን እንጨት እና ቅጠል ተሸክመው መሬት ለመንካት ስንዝር እስኪቀራቸው አጎንብሰው በአንዲት ጨፈቃ እርዳታ የሚጉዋዙበትን አንጀት የሚበላ ትዕይንት የምታይበት …በፀደይ ወቅት ለማየት የሚያሳሳ የጤፍ ቡቃያ የሚሰራው ማዕበል ነፍስን ወሰድ የሚያደርግባት…ነዋሪዎች እንደይዞታቸው መጠን አርሰው…ዘርተው…አጭደው ከጎተራ የሚያስገቡባት….የሚበቃቸው እህላቸውን ሽጠው….የማይበቃቸው ጎን ለጎን ከከብት አዛባ እና ከጭቃ የሚሰሩትን አክንባሎ “ቆሼ” እየተባለ ወደሚጠራው አየርጤና አካባቢ ያለ ገበያ ወስደው ሽጠው….

…. ከከብቶች ግጦሽ የተረፈ ስንበሌጥ እና ባለሚ (የሱ ሳር ሽታ እስካሁን ልቤን በሃሴት ይሰውራታል) አጭደው ቄራ ወስደው ሽጠው….ጋዝ …ሳሙና…እና መሰል ሸቀጦችን እንዳቅማቸው ሸምተው የሚገቡባት የገጠር ቀበሌ ነበረች:: በአብዛኛው ኦሮሞዎች የሆኑ ነዋሪዎችዋ ….ከወሎዬዎች…ጎንደሬዎች…አንድ እድር ገብተው….አንድ ፅዋ ጠጥተው….ከአንድ ማዕድ ቆርሰው…. በእሳት የተያያዘ ጎጆን አብረው አትርፈው ….በሰላም የሚኖሩባት የገጠር ቀበሌ ነበረች:: ይሄ የሕይወት ዑደት ባይሻሻል ሳይብስበት ….ሳይደፈርስ እየዞረ መጥቶአል… ለዘመናት!

ይሄ እንደነገሩ የሳልኩት የለቡ ስእል መልካም ነው? የገጠር ኑሮ ሲያወሩት …ሲያነቡት…እንጂ ሲኖሩት አይመችም:: መብራት…ንፁህ ውሃ…ጤና….ትምህርት….እነዚህ ሁሉ ምስሉ ውስጥ ድራሻቸው የለም…. እነዚህ ነገሮች ለከተማ ነዋሪም የሚደርሱት ዕጣ በሚመስል ሁኔታ እንደሆነ እየቆየ አየሁ:: ነዋሪው ይህ ሁሉ ባይኖረው….አልፎ አልፎ ዓመት አዙሮ ለመግጠም እጅ አጥሮት አንድ በሬውን ቢሸጥ… ለድርድር የማያቀርበው አንድ ሀብት ግን አለው:: መሬት! ገበሬው “laffa kiyaa” ይላል:: እንደምንም መቀናጆ ገብቶ….ጅጊ ጠርቶ…ያርሳታል:: ልጆቹ ለጋብቻ ሲደርሱም እየቆረሰ ያወርሳታል…በመሬት ጉዳይ የተነሳ ጠብም እንዲህ በቀላሉ የሚበርድ አይደለም:: እድሜ ልክ ጠላት የሚያደርግ ጉዳይ ነው::

Lebu Revera hotelዘጠና አመተምህረትን አልፎ ነገር መጣ! አንዳንድ ፀጉረ ለውጥ ሰዎች ብቅ እያሉ ማሳው ውስጥ ጥቅል ሜትር ይዘው መንጎራደድ ጀመሩ…ገበሬው እና ልጆቹ “ምን ሊያደርጉ ነው?” በሚል ስሜት የሚሰራውን ሥራ በአርምሞ ያያል:: በአንድ የተረገመ በጋ የገበሬ ማህበሩ አስተዳዳሪዎች ከአስር ሺህ ብር ጀምሮ (ሀገር የሚያክል መሬት የነበራቸው ሰዎች ያገኙት ካሳ እስከ መቶ ሺህ እንደሚደርስ ሰምቻለሁ) እየወረወሩለት የእርሻ መሬቱን ነጥቀው ገበሬውን በ ጉዋሮው ወሰኑት! ያቺ ጥቂት ሺህ ብር እስክታልቅ ጠብቀውም ቀስ እያሉ ጉዋሮውንም ነጥቀው መቶ እና መቶ ሃምሳ ካሬ መሬት ከ ጥቂት ሺህ ብሮች ጋር ሰጡት:: አሁን …ማስተር ፕላን….የከተማ ልማት…መሬት የመንግስት ነው….ገለመሌ የሚሉ ነገሮችን እንተዋቸውና ለጊዜው…የገበሬውን ሕይወት ታይም ላይን እንይ::

….ማሳውን ተነጥቆ በተሰጠችው ብር የቤቱን የሳር ክዳን በቆርቆሮ ቀየራት….ከፍ ያለ ገንዘብ ያገኘው ታክሲ ገዝቶ ለከተማ ጮሌ ሹፌር እና ረዳት ሰጣት…እራሱ የተወሰደበት ማሳ ላይ ለሚሰሩ ቤቶች የማቴርያል ስቶር በወር መቶ ሃምሳ ብር እየተከፈለው ተቀጠረ… ልጆቹ የማቴርያሎቹ ጫኚና አውራጅ ሆኑ…. (ይሄንን ሥራ ማንም አይነካባችሁም ….ተደራጁና የናንተ ነው ስራው የምትል መደለያ ነበረች…..እውነቴን ነው!)….ሚስቱና ሴት ልጆቹ እዛው አካባቢ የሚሰሩ ቤቶች…ህንፃዎች….መንገዶች ላይ ድንጋይ ተሸካሚ ሆኑ…. ቀስ እያለ…የቤቶቹ የህንፃዎቹ ሥራ አለቀ…. እና በብስጭት ተቃጥሎ ከመሞት የተረፈው….ህንፃዎቹ ላይ አሁንም ዘበኛ ሆኖ ኑሮውን ይገፋል….

ጉዋሮው (ሁለት ሺህ….ሶስት ሺህ እና ከዛ በላይ የሚሆን ስፋት ያለው) ተወስዳ መቶ ካሬ እና ማፍረሻ የተሰጠችውም ባዶ ቁራጭ መሬት ታቅፎ ምንም ሊያደርገው አይችልም….እየሸጠ ወደ ዓለም ገና…ወደ ሰበታ…ዱከም…. (እዛም ደርሰው እስኪያባርሩት ድግሞ…) እየተገፋ ነው….ጎረምሶቹ…የሚወርደው ሲሚንቶም አልቆ….ቦዝነው … የልጆች አባት ሆነው….ያለ እድሜያቸው አርጅተው………በቁጭት …..በሱስ….በፀጥታ እየሞቱ ነው::

ለቡ ምን ትመስላለች አሁን? እረ አምሮባታል! ፒያሳ ምስጋና ትጣ! ወዝዋ ጨፍ ብሎአል! ወላ ሾፒንግ ሞል….ኢንዱስትሪ መንደር…ካልዲስ ካፌ….ደረጃውን የጠበቀ መንገድ….የመንገድ መብራት…ቪላዎች….አፓርትመንቶች……..እንደውሀ የሚፈሱ መኪኖች …ወዘተ ወረዋታል…:: አንድ የቀራት ነገር የለም!
እና ይሄው ነው! በመላ ሀገሪቱ በኦሮሞ ተማሪዎች የተቀጣጠለው አመፅ ይሄ ማብቃት አለበት! የሚል ነው:: ይሄ ማስተርፕላን በለቡ ….ሃናማርያም….ቱሉዲምቱ…ለገጣፎ የተጀመረው ሲስተሚክ የገበሬዎች መፈናቀል … በገዛ መሬቱ ላይ ባርያ የማድረግ ዘመቻ ማስቀጠያ መሳርያ ብቻ ነው! ተቃውሞውም ምንም ውስብስብ አጀንዳ የለውም! የመኖርና ያለመኖር ጥያቄ ነው! ይሄ ጥያቄም መኖርን ባረጋገጠ መልኩ እስካልተመለሰ ድረስ አመፁም እንደተቀጣጠለ ይቀጥላል!

The post ለቡ ድሮ እና ዘንድሮ፥ | በእለፋቸው ሞሲሳ appeared first on Zehabesha Amharic.

የገና በዓል ዛሬ የሚከበርባቸው 20 ሃገራት

$
0
0

chirstmss

እየሱስ ክርስቶስ የተወለደበት የገና በዓል በተለያዩ ሃገራት በተለያዩ ወቅቶች ይከበራል:: በአብዛኛው የዓለም ሕዝብ የሚያከብረው ዴሴምበር 25 ሲሆን ኢትዮጵያን ጨምሮ 20 ሃገራት ግን ጃንዋሪ 7 ያከብራሉ:: ለዛሬው እነዚህን ሃያ ሃገራት እናስተዋውቃችኋለን:: በነገራችን ላይ እስራኤል የገና በዓል 3 ጊዜ የሚከበርባት ሃገር ናት:: ዲሴምበር 25; ጃንዋሪ 7 እና ጃንዋሪ 18:: ጃንዋሪ 18 የሚያከበሩት የአሜሪካ ኦርቶዶክስ እስራኤላውያን ናቸው::

1ኛ. ቦስኒያና ሄርዞጎቭንያ
2ኛ. ሞልዶቫ
3ኛ. ቤላሩስ
4ኛ. ግብጽ
5ኛ. ኢትዮጵያ
6ኛ. ኤርትራ
7ኛ. ካዛኪስታን
8ኛ. እስራኤል
9ኛ. ኪርጊስታን
10ኛ. ሞንቴኔግሮ
11ኛ. ሜቄዶንያ
12ኛ. ሩሲያ
13ኛ. ጆርጂያ
14ኛ. ዩክሬን
15ኛ. ሰርቢያ
16ኛ. ኮሶቮ
17ኛ. ሩማንያ
18ኛ. ግሪክ
19ኛ. ቡልጋርያ

20ኛ. ሳይፕረስ

 

The post የገና በዓል ዛሬ የሚከበርባቸው 20 ሃገራት appeared first on Zehabesha Amharic.

በገና ወይም በጌታ ልደት በዓል ስጦታ የመሰጣጠት ባሕል የኛ ወይስ የሌላ?

$
0
0

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

3b8f71d0-f80f-4db0-ac05-fc4488a78c40ምዕራባዊያን ለገና ማለት ለጌታችን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል እርስ በእርሳቸው ስጦታ የመሰጣጣት በጣም ጥሩና ደስ የሚል ባሕል አላቸው፡፡ ይሄ ባሕላቸውም የጥበብ ሰዎች (ሰብአ ሰገል) ወይም የምሥራቅ ነገሥታት ጌታ በተወለደ ጊዜ ለጌታ ያበረከቱትን የወርቅ የዕጣን የከርቤ ስጦታን መሠረት ያደረገ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡

እንግዲህ ነጥቡ ያለው እዚህ ላይ ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ጌታ ከመወለዱ በፊት ጌታ እንደሚወለድና በተወለደ ጊዜም እነኝህ ነገሥታት እጅ መንሻ እንደሚያቀርቡለት ጌታ ከመወለዱ ከሽህ ዓመታት በፊት ጀምሮ በትንቢት ተነግሮ ነበር፡፡ አንዱን ብንጠቅስ፡-

“በፊቱም ኢትዮጵያ ይሰግዳሉ ጠላቶቹም አፈር ይልሳሉ። የተርሴስና የደሴቶች ነገሥታት ስጦታን ያመጣሉ የዓረብና የሳባ ነገሥታት እጅ መንሻን ያቀርባሉ። ነገሥታት ሁሉ ይሰግዱለታል። አሕዛብም ሁሉ ይገዙለታል”  መዝ. 72፤ 9-11

በትንቢቱም መሠረት በማቴ. 2፤1-11 ላይ እንደተገለጸው ትንቢቱ ተፈጽሟል፡፡ በዚህ ጥቅስ ላይ ስለእነዚህ ነገሥታት የተጻፈውን ስናይ ነገሥታቱን “የምሥራቅ ነገሥታት” ሲል ይጠራቸዋል፡፡ ነቢዩ ልበ አምላክ ዳዊት ስለ ነገሥታቱ አስቀድሞ በትንቢት ከተናገረው ቃል ጋር በማቴዎስ ወንጌል ላይ ነገሥታቱ የምሥራቅ ነገሥታት መሆናቸውን ከተናገረው ቃል ጋር ስናገናዝብ “የምሥራቅ” የሚለው ቃል የግብር (በቤተክርስቲያን ተምሳሌታዊ አገላለጽ ምሥራቅ የጽድቅ፣ የምሕረት፣ የሕይወት ተምሳሌትነት አለው) እናም “የምሥራቅ” ተብሎ መጠቀሱ ከነገሥታቱ ተግባርና አገልግሎት አኳያ የዚህ ተምሳሌታዊ አገላለጽ መግለጫ እንጅ የአቅጣጫ እንዳልሆነ እንረዳለን፡፡ ምክንያቱም ነገሥታቱ ከመጡባቸው የተጠቀሱ ሀገራትን የወሰድን እንደሆነ ተርሴስ ያለችው ከኢየሩሳሌም ወይም ከእስራኤል በስተምዕራም በኩል እንጅ በስተምሥራቅ በኩል አይደለችምና፡፡ ተርሴስ ብቻም ሳትሆን ኢትዮጵያም (ሳባም) ዓረብም ያሉት ከኢየሩሳሌም በስተደቡብ እንጅ በስተ ምሥራቅ በኩል ስላልሆነ፡፡

የቤተክርስቲያን መጻሕፍት ስለእነዚህ ነገሥታት ታሪክ በዝርዝር ጽፈዋል፡፡ የታሪክ ጸሐፍትም እንዲሁ፡፡ አንዳንዶቹ መረጃዎች እንደሚሉት አንደኛው ንጉሥ ኢትዮጵያዊ ሆኖ ሁለቱ ነገሥታት ግን በእርሱ ስር ያሉ እሱ የሾማቸው የግዛቱ ነገሥታቶች እንደሆኑ ይናገራሉ፡፡ ሌላው ቢቀር ግን ከሦስቱ አንዱ ኢትዮጵያዊ ለመሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም፡፡ መረጃውም አንዱ ከላይ የጠቀስኩት የመዝሙረኛው ዳዊት ጥቅስ ሲሆን ሌላኛው ትውፊታዊ መረጃዎች ናቸው፡፡ ትውፊታዊ መረጃን መሠረት አድርጎ የተሣለ ይሄ ኢየሩሳሌም ያለ ጥንታዊ ሥዕል ራሱ የሚያረጋግጠው ይሄንኑ ነው፡፡ በዚህ የምዕራባዊያን ሥዕል አንደኛው ንጉሥ ኢትዮጵያዊ (ጥቁር) ሆኖ ተሥሏልና፡፡

እዚህ ላይ “መጽሐፍ ቅዱስ ሳባ ብሎ ሲል ኢትዮጵያን ሳይሆን ዓረብን ነው” የሚሉ አሉና ለእነሱ ልንላቸው የምንችለው ነገር ቢኖር ሳባ ማለት ዓረብ ቢሆን ኖሮ ይህ የመዝሙረ ዳዊት ጥቅስ ሳባ ካለ በኋላ ዓረብ ብሎ ሌላ ባልጠራ ነበር፡፡ እርግጥ ነው ንግሥት ሳባ የዓረብን ምድር የገዛች ንግሥት ስለሆነች ዓረቦች እንደራሳቸው ንግሥት ይቆጥሯታል ከዚያም አልፈው የእኛ ናት እንጅ የኢትዮጵያ አይደለችም ይላሉ፡፡

የሚገርመኝ ነገር ቢኖር ንግሥተ ሳባ የዓረብ ናት ብለው የሚሉ ሰዎች ንግሥተ ሳባ የኢትዮጵያ ንግሥት እንደሆነች የሚናገረውን መጽሐፍ ክብረ ነገሥትን የጻፉት ዓረቦች ናቸው ማለታቸው ነው፡፡ እንደዛ ከሆነ ዓረቦቹ እራሳቸው ንግሥተ ሳባ የኢትዮጵያ ንግሥት መሆኗን መስክረዋል ማለት ነዋ! ደግሞስ እንዴት ጅል ቢሆኑ ነው “ዓረቦች ታሪካቸውን እንካቹህ ውሰዱት ድመቁበት እኛ ይቅርብን” ብለው የሚያስረክቡት?

የመጽሐፍ ቅዱስን መረጃ በመዳሰስ ንግሥተ ሳባ ኢትዮጵያዊት መሆኗን ማረጋገጥ እንችላለን፡፡ በእርግጥ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደተጠቀሱት እንደሌሎች ታላላቅ ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያዊ ተብሎ እንደተጻፈው ሁሉ ሳባንም “ኢትዮጵያዊት” ብሎ መጽሐፍ ቅዱስ አልጠራም፡፡ በአንጻሩም የመናዊት ወይም ዓረባዊትም አላላትም፡፡ እነኚህን ባይልም ዜግነቷን ወይም ሀገሯን በቀላሉ ልንለይ የምንችልበት ቀላል መንገድ ግን አለ፡፡

እንደሚታወቀው እንደ መጽሐፍ ቅዱሱ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በሀገርና በሕዝብ በመንግሥትም ደረጃ እግዚአብሔርን የሚያመልኩ ወይም የሚያውቁ እሱም የሚያውቃቸውና ሕዝቤ ልጆቼ የሚላቸው ሕዝቦች ወይም ሀገሮች ሁለት ብቻ ናቸው፡፡ እነርሱም ኢትዮጵያና እስራኤል ከእነዚህ ውጪ ማንም አልነበረም፡፡ ሌሎች ሀገሮች ከተነሡም በስደት ሔደው ምኩራባቸውንም  በዚያ ሠርተው እግዚአብሔርን ያመልኩ ከነበሩት አይሁዳውያን የተነሣ ካልሆነ በቀር በመጽሐፍ ቅዱስ ከእስራኤል ልጆችና ከኢትዮጵያ ልጆች ውጪ እግዚአብሔርን ያመልካሉ ተብሎ የተጻፈለት ሕዝብ አልነበረም፡፡ በት.አሞ.፱፣፯ ላይ እማ  እንዲያውም  በኩራት (የመጀመሪያ) ናቸው ከሚባሉት እስራኤላዊያንም ይልቅ እኛ ኢትዮጵያዊያኑ ከብረን እንታያለን፡፡ ቃሉ እንደሚለው “የእስራኤል ልጆች ሆይ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን? ይላል እግዚአብሔር”፡፡ እግዚአብሔር የእስራኤል ልጆችን እንደእኛ የኢትዮጵያጵያ ልጆች አድርጐ እንደሚያያቸው ከእኛ አሳንሶ እንደማያያቸው የእስራኤል ልጆችን በማጽናናትና በማረጋጋት የተናገረበት ጊዜ ነበር፡፡

እንግዲህ ቁልፉ ነገር ያለው እዚህ ላይ ነው፡፡ ሳባ በእግዚአብሔር የምታምን እንደነበረች ከተናገረችው ቃል መረዳት ይቻላል፡፡ አንደኛ ነገሥት 10፤1-13 ሁለተኛ ዜና መዋዕል 9፤1-12 ላይ ታሪኩ ተጽፎ እንደሚገኘው ሳባ ሰሎሞንን “አንተን የወደደ በእስራኤልም ዙፋን ያስቀመጠ አምላክህ እግዚአብሔር የተባረከ ይሁን፡፡ እግዚአብሔር እስራኤልን ለዘለዓለሙ ወዶታልና፡፡ ስለዚህ ጽድቅና ፍርድን ታደርግ ዘንድ ንጉሥ አድርጐ አስነሣህ” ብላዋለች፡፡

በንግግሯ እግዚአብሔር የጽድቅና የፍርድ አምላክ መሆኑን አስቀድሞ ከነበራት እምነት ተነሥታ መስክራለች፡፡ የተባረከ ይሁን ብላም ፈጣሪዋን አመስግናለች፡፡ ይሄንን ንግግር ለመናገር ስለእግዚአብሔር ጥልቅ የሆነ እውቀትና እምነት ጊዜ የወሰደ ትውውቅ ሊኖራት ግድ ይላል፡፡ ከእስራኤላዊያን ውጪም ይህንን ሊያደርጉ የሚችሉ ሌላ ሕዝብና መንግሥት ካለም ቀደም ሲል በቀረበው ማብራሪያ ወይም በመጽሐፍ ቅዱሱ መረጃ መሠረት ኢትዮጵያዊያን ብቻ ናቸው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን ስናነብ ከሳባም በፊት ኢትዮጵያ እግዚአብሔርን የምታመልክ ሀገር መሆኗን የሚያረጋግጡ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ መረጃዎች አሉ፡፡

እስራኤላዊያን ከሌላ ከማንም ወገን ጋር እንዳይጋቡ በእግዚአብሔር ተከልክለው በነበሩበት ወቅት ጭራሽ ሊቀነቢያት ሙሴ ግን ያገባው ኢትዮጵያዊቷን የካህንኑ የራጉኤልን (የዮቶርን) ልጅ ሲፓራን ነበር፡፡ ይህንን በማድረጉም ከእግዚአብሔር ዘንድ አንዳችም ተግሳጽ አልደረሰበትም፡፡ ይልቁንም ሙሴ ኢትዮጵያዊቷን በማግባቱ ያጉረመረሙት ወንድሙ አሮንና እኅቱ ማርያም እግዚአብሔር በባሪያዬ በሙሴ ላይ አጉረምርማችኋል በማለት ቁጣውን አወረደባቸው ማርያምንም በለምጽ ቀጣት እንጂ፡፡ ዘኁ.፲፪፣፩-፲፭ ዘጸ.፪፣፲፮-፳፪ ይህም የሆነበት ምክንያት ሌሎች ነቢያት ወደኋላ ግልጽ እንዳደረጉት የኢትዮጵያ ሕዝብ እግዚአብሔርን አምላኪና ሕዝበ እግዚአብሔር በመሆኑ ነው፡፡

ክብረ ነገሥት የሳባ አባቶች ዘንዶ አምላኪ እንደነበሩ ይናገራል፡፡ ይሄ ማለት ግን እግዚአብሔርን ጨርሶ አያውቁትም ነበር ማለት አይደለም፡፡ እስራኤላውያንም ከእግዚአብሔር ዘንድ ያ ሁሉ ተአምራት እየተደረገላቸውና እያወቁት ለጣኦት ያልሰገዱበትና ጣኦት ያላመለኩበት ዘመን አልነበረምና፡፡ ከነገሥታቶቻቸውም ከዳዊት በስተቀር ለጣኦት ያልሰገደ አልነበረምና፡፡ እንዲህ በመሆናቸው ግን እግዚአብሐየርን ጨርሶ የማያውቁ እንደሆኑ አላስቆጠራቸውም፡፡ እኛም ላይ እንደዛው ነው፡፡

እናም ተታለው ተወናብደው ጥልቅና ጠንቃቃ ንባብና መረዳትም ከማጣት የተነሣ ክብረ ነገሥትን የፈጠራና የተረት መጽሐፍ አድርገው ለሚያዩ እንዲታይም ለሚጥሩ ግለሰቦች ከላይ መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት በማድረግ ለመግለጽ ከሞከርኩት መረዳት እንደሚቻለው ሁሉ ክብረ ነገሥት ንግሥተ ሳባን ኢትዮጵያዊት መሆኗን አረጋግጦ ታሪኳን ሲተነትን ፈጥሮ አይደለምና ተረት ፈጠራ አለመሆኑን ሊያውቁ ይገባል፡፡ ይሄንን የሚጠራጠሩ ሰዎች ናይጄሪያ ቢሔዱ የንግሥተ ሳባን አፈ ታሪክ ሊሰሙ ይችላሉ ግዛቷ እንደነበረም ሊነግሯቸው ይችላሉ፡፡ ከሀገሯ ስትመጣ የመጣችበት ነው የሚሉትን የዋሻ መንገድም ሊያሳዩዋቸው ይችላሉ፡፡ የመኖች ንግሥተ ሳባን የኛ ንግሥት ናት የሚሉበት ምክንያትና የግእዝ አሻራዎችም እዛ የመገኘታቸው ምክንያት ከጥንት ዘመን ጀምሮ እኛ ከፋርሶች ጋር በመፈራረቅ ሳውዲ ዓረቢያንና የመንን ለረጅም ጊዜ ስንገዛው ስለነበረ ነው እንጅ ሳባ ዓረብ ስለነበረች አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ የመንን እንደገዛች ደግሞ እራሳቸው የመኖችም የሚያረጋግጡት ነገር ነው፡፡

ሌላኛው የሚያከራክር ነጥብ ደግሞ እነዚሁ በምዕራባዊያን የታሪክ ቀበኞች የተወናበዱ ዜጎቻችን “አይ! መጽሐፍ ቅዱስ ኢትዮጵያ የሚላት የምድያምን አሁን ሱዳን ተብሎ የሚጠራውን ምድር ነው እንጅ ኢትዮጵያን አይደለም” ይላሉ፡፡ እንዲህ ለሚሉ ግለሰቦች የምለው ነገር ቢኖር መጽሐፍ ቅዱስ “ኢትዮጵያ” ብሎ ሲል በእርግጥ ግዛቷ የምድያምን ምድር ጨምሮ ሰፊ የነበረ ቢሆንም እምብርቷ ግን ይህቺ አሁን ያለችው ኢትዮጵያ መሆኗን ሲያረጋግጥ “የሁለተኛውም ወንዝ ስም ግዮን ነው፡፡ እሱም የኢትዮጵያን ምድር ይከባል” ዘፍ. 2፤13 ብሎ ግዮን ወይም ዓባይ በምድሯ መንጭቶ ምድሯን የሚያካልላት ምድር መሆኗን በመናገር የኢትዮጵያን መልክዓምድራዊ አድራሻ (Geographical location) የት እንደሆነ ቁጭ አድርጎታልና መጽሐፍ ቅዱስ ኢትዮጵያ ብሎ ሲል የጥንት ግዛቷ ሰፊ የነበረ ቢሆንም ይህችን ኢትዮጵያችንን ማለቱ እንደሆነ ያለጥርጥር ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

ስለሆነም ወደቀደመው ነገራችን እንመለስና በዚህም መሠረት ጌታ ሲወለድ እጅ መንሻ ካቀረቡ ነገሥታት ውስጥ ከበዛ ሦስቱ ካነሰ አንዱ የኢትዮጵያ ንጉሥ እንደነበር እርግጠኛ መሆን ይቻላል ማለት ነው፡፡

እንግዲህ ምዕራባዊያኑ በጌታ ልደት በዓል እርስ በእርሳቸው ስጦታ የመሰጣጣት ባሕሉን የወሰዱት ወይም መሠረት ያደረጉት የጥበብ ሰዎችን ወይም ለጌታ የወርቅ የዕጣን የከርቤ እጅ መንሻ ያቀረቡትን ነገሥታት እንደሆነ ይናገራሉና ይህ ስጦታ የመሰጣጣት ባሕላቸው ፈጣሪ እኛ ነን ባሕሉም የእኛ እንጅ የእነሱ አይደለም ማለት ነው፡፡ እናም በጌታ ልደት በዓል ስጦታ የምትሰጣጡ ወገኖች ካላቹህ ይህን ውብ ባሕል ስታደርጉ የራሳቹህን ባሕል እንደፈጸማቹህ በማሰብ አድርጉት እንጅ የተውሶ ባሕል እያደረጋቹህ እንደሆነ እንዳይሰማቹህ እንዳታስቡ ማስገንዘብ እወዳለሁ፡፡

እንኳን አደረሳቹህ! በዓሉን የነጻነት፣ የይቅርታ፣ የምሕረት፣ የረድኤት፣ የበረከት፣ ያድርግልን! አሜን!!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com

The post በገና ወይም በጌታ ልደት በዓል ስጦታ የመሰጣጠት ባሕል የኛ ወይስ የሌላ? appeared first on Zehabesha Amharic.

“እንኳን ኣደረሳቹ”…! ( ከወይዘሮ ኣልጋነሽ ልጆች )

$
0
0

የተከበራቹ የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ውድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ለበዓለ ልደት በሰላም ኣደረሳቹ ኣደረሰን የሚሏቹ የጀግናዋ ወይዘሮ ኣልጋነሽ ገብሩ( ኣሸባሪነትና መንግስት በሃይል ለመገልበጥ በሚል ክስ ተፈርዶባት ለ3 ዓመት ወህኒ የወረደችው ) ልጆች ግርማነሽ ታደሰ፣ ዘነበ ታደሰ፣ ገብረሂወት ታደሰ ናቸው።

የጀግናዋ ልጆች ይሄ መልእክት ያስተላለፉላቹ ትናንት 27/ 04 / 2008 ዓ/ም በኣንድ በጎ ኣድራጊ ወጣት ኢትዮጵያዊ ልጆቹ በናታቸው መታሰር እንዳይከፋቸውና ለልደት በዓል መዋያ እንዲሆናቸው በማለት የላከው 1000 ብር ( ኣንድ ሺ ብር ) ብር ይዘን በኣካል እግሪሓሪባ ቀበሌ ተገኝተን ስንሰጣቸው ነው።

የጀግናዋ ልጆች ከዚ በፊት የተቻላቹ ድጋፍ ያደረጋቹላቸው ኢትዮጵያውያን በሙሉ ኣመስግነዋል።

እኛም በዚህ ኣጋጣሚ ወጣት ወገናችንና ሌሎቻቹ ከዚ በፊት ልጆቹ ለጎዳና ተዳዳሪነት እንዳይጋለጡ የገንዘብና የሞራል ድጋፍ ላደረጋቹላቸው በሙሉ በማመስገን ለክርስትና ሃይማኖት ከተከታዮች ወገኖቻችን መልካም በዓል ይሁንላቹ ለማለት እንወዳለን።

+ርሑስ በዓል ልደት+

+መልካም የገና በዓል+

አሜን…

The post “እንኳን ኣደረሳቹ” …! ( ከወይዘሮ ኣልጋነሽ ልጆች ) appeared first on Zehabesha Amharic.

የሰሞኑ ‹‹የኦሮምያ ግርግር›› ግራ ገብቶኛል –መስፍን ወልደ ማርያም

$
0
0

መስፍን ወልደ ማርያም
ታኅሣሥ 2008

በሁለት ደረጃ የሚቀርቡ ጥያቄዎች አሉኝ፤–
አንድ፡– ግርግሩ የኦሮምያ ነው? ወይስ የኢትዮጵያ? ወይስ ኦሮምያ ከኢትዮጵያ ተለይቷል?
ሁለት፡– የኢትዮጵያ የመሬት ጉዳይ ኦሮሞዎችን ብቻ የሚመለከት ነው? ወይስ የኢትዮጵያን ሕዝብ በሙሉ?

mesfinአንደኛ፣ ግልጽ ከሆነው እውነት እንነሣ፤ ኦሮምያ ከኢትዮጵያ አልተለየም፤ ስለዚህም ግርግሩ የኢትዮጵያ ነው እንጂ የኦሮምያ አይደለም፤ ጥንቱኑ ለማጋጨት የተሰጠውን ስያሜ በስምነቱ ከማጽደቅ በላይ ለታቀደው ዓላማ አመቺ መሣሪያ ማድረግ ነው፤ ይህ ደግሞ በቅድሚያ መሸነፍን የሚያረጋግጥ በመሆኑ ከወያኔ በቀር ደጋፊ ያለው አይመስለኝም፤ ቁርጠኛ ትግል ቁርጠኛ ዓለማና ቁርጠኛ ስልት ያስፈልገዋል፤ ስለዚህም ቁርጠኛ መሪ ያስፈልገዋል፤ የሕመሙን መርዝ እየተጎነጩ ከሕመሙ ፈውስ ለማግኘት አይቻልም፤ ግርግሩ የኦሮሞ ከተባለ ሁለት ውጤቶች ይከተላሉ፤ አንዱ ውጤት ከኦሮሞ በቀር ሌላውን ሕዝብ አያገባውም ማለት ይሆናል፤ ሁለተኛው ውጤት የልየነቱ በላቤቶችና ተፋላሚዎች ኦሮሞዎችና ወያኔዎች ብቻ ናቸው ማለት ነው፤ ይህ ትልቅ አደጋ አለበት፡፡
አደጋው ወደሁለተኛው ጥያቄ ይመራናል፤ ገብቶኝ እነረደሆነ የግርግሩ ምክንያት ሁለት ናቸው፤ አንዱ ከቤት-ንብረት መፈናቀል ነው፤ የዜግነት መብትና መገለጫ የሆነውን መሬት ማጣት ነው፤ ሁለቱም መሰረታዊ የሆኑ የኢትዮጵያዊነትን የዜግነት መብቶች ሚደፈጥጡ ናቸው፤ ልብ በሉ የኦሮሞን የዜግነት መብቶች ይደፈጥጣል አላልኩም፤ የኢትዮጵያውያንን ሁሉ መሠረታዊ መብቶች የሚደፈጥጥ ነው፤ ይህ የማያጠራጥር እውነት ነው፤ ይህንን ከተቀበልን ጉዳዩ የኦሮሞ ብቻ አይደለም፤ ግርግሩም የኦሮሞ ብቻ አይደለም፡፡
ትልቁ አደጋ ያሁንን ግርግር የኦሮምያ ብቻ ካደረግነው ወደፊት ያው ጉዳይ በሌሎች ጎሣዎች መሀከል ሊነሣ ነው፤ ሌሎች ግርግሮች ሊያስፈልጉ ነው፡፡
ጉዳዩ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሆነ ትግሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ ነው፡፡

The post የሰሞኑ ‹‹የኦሮምያ ግርግር›› ግራ ገብቶኛል – መስፍን ወልደ ማርያም appeared first on Zehabesha Amharic.

ለመላው የክርስትና ኃይማኖት ተከታይ ኢትዮጵያውያን በሙሉ! እንኳን ለ፪ሺ፰ኛው የጌታችን እና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ –ሞረሽ ወገኔ

$
0
0

ሐሙስ ታኅሣሥ ፳፰ ቀን ፪ሺህ፰ ዓ.ም.                                   ቅፅ ፬ ፣ ቁጥር

Moreshእንሆ ፈጣሪያችን ልዑል እግዚአብሔር ፍጹም አምላክ ሲሆን፣ በፈጠረው ፍጡር የማይጨክን፣ ርኅሩኅ የባህርይ አምላክ መሆኑን እናምናለን። እኛን ከኃጢያት ዕዳ ሊያድነን ስለፈቀደ፣ ፍጹም ሰው ሆኖ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደ። ስለዚህም  ዛሬ ታህሣሥ ፳፰ ቀን ፪ሺህ፰ ዓ.ም. የኢየሱስ ክርስቶስን ፪ሺ፰ኛ የልደት በዓል እናከብራለን። በዚህ አጋጣሚ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት መላው የክርስትና ኃይማኖት ተከታዮችን እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሣችሁ እንላለን።

ይህንን በዓል ስናከብር ማስታወስ ያለብን፣ በአሁኑ ዘመን ኢትዮጵያ አገራችን እና ሕዝባችን መስቀለኛ መንገድ ላይ መውደቃቸውን ነው። አገራችን ኢትዮጵያ ወደ መጨረሻው ጥፋት እና ውድቀት ፤ ሕዝባችንም ደግሞ ሊያባራ ወደማይችል የእርስ በእርስ እልቂት እንደከብት እየተገፉ እንደሆነ እናውቃለን። ስለሆነም የዘንድሮውን የጌታችንን እና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓልን በዚህ አስፈሪ ድባብ ውስጥ ሆነን እንደምናከብረው ወገኖቻችን ትገነዘቡታላችሁ የሚል ጽኑ እምነት አለን። የትግሬ-ወያኔ ዘረኛ አገዛዝ እግዚአብሔር በአምሣሉ የፈጠረውን እና ያከበረውን የሰው ዘር እንድ እንስሳ በመቁጠር ያለምንም ርኅራኄ ይጨፈጭፉታል። የአገራችንን ሉዓላዊ ግዛት በውጪ ኃይሎች በማስደፈር መሬታችንን ለሱዳኖች እና ለሌሎች ባዳን በማናለብኝነት በመቸብቸብ ላይ ናቸው። እንዲሁም የዐባይ፤ የባሮ፣ ፣ የአዋሽ ፣ የዋቢ ሸበሌ ፣ የገናሌ ፣ የተከዜ፣ የኦሞና የመሳሰሉት ታላላቅ ወንዞች ባለቤት፤ የጣና ፣ የአባያ ፣ የሻላ እና ከ32 የማያንሱ ኃይቆች ምድር ዜጎች ሆነን ሣለ፤ በየጊዜው በረሃብ አለንጋ እንገረፋለን። በተለይም ባለፉት 25 ዓመታት በትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ርሃብ እና ችጋር የኢትዮጵያውያን የመለያ ምልክት ለመሆን በቅተዋል። በዘንድሮውም ዓመት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ለርሃብ እና ለችጋር ተጋልጠዋል።

እግዚአብሔር በመልኩ እና በአምሣሉ ሲፈጥረን ያጎናጸፈን ፀጋዎች፦ ሁላችን የእርሱ ልጆች እንደሆንን፤ እንድንዋደድ እና እንድንፈቃቀር፤ እርስ በእርሣችን እንድንተዛዘን እና እንድንከባበር ነበር። ሆኖም በሃያ አምሥቱ ዓመት የትግሬ-ወያኔ ዘረኛ አገዛዝ ዘመን ሁላችንም ኢትዮጵያዊ ሆነን ሳለ በጥላቻ እና በዘር የመከፋፈል ፖለቲካ መርዝ ተመርዘን አብረን በጋራ በአንድነት ተፈቃቅረን እንዳንኖር ተደርገናል። ለዚህ የጥላቻ መርዝ መሻሪያው መድኃኒት ምን ይሆን? መርዙ የሚሽረው ምንጩ ሲደርቅ ብቻ ነው። ምንጩም የትግሬ-ወያኔ  የፖለቲካ ቡድን ሲሆን ማስፈጸሚያውም የኢትዮጵያ ሕዝብ በጎሣ እና በነገድ እንደ ቅርጫ ሥጋ በመመደብ ተከፋፈሎ እንዲተላለቅ በዚህ ቡድን የፖለቲካ መግለጫ አንቀጽ 39 የተደነገገው ነው። ስለዚህ ይህ የእርስ በእርስ ፍጅት እና መተላለቅ የሚያቆመው የትግሬ-ወያኔ ሥርዓት ከሥር መሠርቱ ተነቅሎ ሲወገድ ብቻ መሆኑ አያጠራጥርም።

የትግሬ ወያኔ ቡድን ለ17 ዓመታት በሽፍትነት፣ ለ25 ዓመታት ደግሞ በገዥነት ተፈናጥጦ የኢትዮጵያን ሕዝብ የደም እንባ ሲያስነባ ቆይቷል። በተለይ በዐማራ ሕዝብ ላይ ባደረሰው የዘር ማጥፋት ዘመቻ ክ5ሚሊዮን ያላነሱ አማሮች እንዳለቁ እና በዘር ማጽዳት ዘመቻው ደግሞ ከ10 ሚሊዮን የማያንሱ ዐማሮች መፈናቀላቸውን በየጊዜው የሚወጡ ዘገባዎች ያረጋግጣሉ። ይህ የአገዛዝ ቡድን ገና ሥልጣን በጠመንጃ ኃይል እንደተቆጣጠረ፣ በበደኖ ፣ በአርባጉጉ እንዲሁም በተለያዩ ቦታዎች የዐማራ ተወላጆች «ከእኛ ዘር አየደላችሁም» ተብለው ዐይናቸው በጨርቅ እየተሸፈነ በጭካኔ ከመቶ ሜትር ጥልቀት በላይ በሚሆኑ ገደሎች ውስጥ ከእነሕይዎታቸው ተወርውረዋል። ከእነዚያ የግፍ ሰለባዎች መካከል ነፍሰ ጡር እናቶች ፣ ጨቅላ ሕፃናት ፣ አቅመ ደካሞች እና አረጋውያን ይገኙበታል። በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ዐማሮችን ቤታቸውን በላያቸው ላይ እየዘጉ በእሣት አጋይተዋቸዋል። ግፉ እና አረመኔያዊ ጭፍጨፋው ያልደረሰበት የኢትዮጵያ ግዛት ክልል የለም። በሰሞኑ እንኳን የኦሮሞ ተወላጆች የአዲስ አበባ ከተማን ለማስፋፋት የወጣውን መሪ ዕቅድ በመቃወም ባስነሱት አመጽ፣ ጦሱ ምንም አይነት በደል ባልፈጸሙት ዐማሮች ላይ ከፍቷል። ሰሞኑን ዐማሮች በሁለት አቅጣጫ፣ ማለትም፦ በአንድ ወገን በቀጥታ በትግሬ-ወያኔ ካድሬዎች ታጣቂዎች እንዲሁም በሌላ ወገን «የትግሬ-ወያኔን መሪ ዕቅድ እንቃወማለን» በሚሉ ኃይሎች፣ ዐማራ ወገኖቻችን ቤታቸው እና አንጡራ ንብረታቸው ተቃጥሎ እንዲፈናቀሉ ከመደረጉም በላይ ብዙዎችም ተገድለዋል። ይህ ታሪክ ይቅር የማይለው አረመኔያዊ ግፍ የሚፈጸመው፣ በኢትዮጵያኖች እጅ ኢትዮጵያውያን በሆኑ የዐማራ ተወላጆች ላይ ነው። በመሆኑም የቂም በቀል ስሜት እና የዘረኝነት ደመና የአገራችንን ሰማይ እና የሕዝባችንን ልብ በሸፈነበት ወቅት፣ ፊታችንን ወደ እግዚአብሔር በንጹህ ልብ ማዞር እንድሚገባን አያጠያይቅም።

ባለፉት 25 ዓመታት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ የትግሬ-ወያኔ ያሣረፈው የማፈራረስ ዱላ ከአገር ቤት አልፎ በውጪ አገሮች በስደት ላይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን የኃይማኖት ነፃነት ሣይቀር በእጅጉ ጎድቶታል። ሲጀመር ወያኔ በፓትርያርክ ላይ ፓትርያርክ ሾመ። በዚያ ሣይገታ የቤተክርስቲያኒቱ ካህናት እና ምዕመናን ሊሸከሙት የሚከብድ የግፍ ጫና አወረደባቸው። አልፎ ተርፎም ውቅያኖሶችን ተሻግሮ በስደት ዓለም ያሉ ኢትዮጵያውያን ያቋቋሟቸውን አብያተክርስቲያናት የአመፅ እና የብጥብጥ አውድማ አደረጋቸው። በዘረጋው የካድሬ-ካህናት መዋቅር በመጠቀም፥ ምዕመናንን ከካህናት ፣ ካህናትን ከካህናት ፣ ምዕመናንንም ከሌሎች ምዕመናን ጋር እንዲበጣበጡ ያደርጋል። ለአብነትም ያህል በለንደን የርዕሰ-አድባራት ጽዮን ማርያም ፣ በቶሮንቶ ማርያም ፣ በዋሽንግተን ዲሲ የርዕሰ-አድባራት ቅድስት ማርያም ፣ በሴንት ፖል መድኃኒዓለም ፣ በዲሲ ቅዱስ ሚካኤል ፣ በቨርጂኒያ ኪዳነ ምሕረት ፣ በአትላንታ ቅድስት ማርያም ፣ ወዘተርፈ አብያተክርስቲያናት የተፈጸሙት እና በመፈጸም ላይ ያሉት የአመፅ ድርጊቶች ምንጫቸው አንድ ነው፦ የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ብቻ! መፍትሔው ያለው በምዕመናን እጅ ነው። ስለዚህ የቤተክርስቲያኒቱ ምዕመናን ለቤተክርስቲያናቸው ኅልውና ፣ አንድነት እና ሰላም መቀጠል ሲሉ ድምፃቸው እንዳይሰማ በኃይል ከታፈኑት እውነተኛ አባቶች ጎን ሊቆሙ ይገባል።

ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ በሳምራዊያን እና በአይሁዳዊያን መክካል የነበረውን የነገድ ልዩነት ግድግዳ እንዳፈረሰው ሁሉ ፣ በእኛ በኢትዮጵያውያንም መካከል በትግሬ-ወያኔ አገዛዝ የተረጭብንን የዘረኝነት መርዝ ሽሮ፣ የመከፋፋሉንም ግድግዳ ያፈርስልን ዘንድ የዘወትር ፀሎታችን ይሁን። ስለሆነም እውነተኛ ኢትዮጵያውያን በአንድነት ተረባርበን የትግሬ-ወያኔን የጥቁር አፓርታይድ የባርነት ሰንሰለት መበጣጠስ ይገባናል። ይህንን በማድረግ እግዚአብሔር የሰጠንን አንዲት ታላቅ ኢትዮጵያ ከጨርሶ ጥፋት እና መፍረስ አድነን ሕዝባችንንም ከታሪክ ውርደት እና ማቅ ነፃ ለማውጣት እንችላለን። በዚህ አጋጣሚ «ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች» የተባለው የተስፋ ቃል ይፈጸም ዘንድ፣ እኛ ኢትይጵያውያን እጆቻችንን ከልባችን ጋር ወደ ፈጣሪያችን ወደ እግዚአብሔር እንድንዘረጋ ሞረሽ ወገኔ የአደራ ጥሪዉን ያቀርባል።

 

ወስብሐተ እግዚአብሔር

 

The post ለመላው የክርስትና ኃይማኖት ተከታይ ኢትዮጵያውያን በሙሉ! እንኳን ለ፪ሺ፰ኛው የጌታችን እና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ – ሞረሽ ወገኔ appeared first on Zehabesha Amharic.

ጣራ የለሽ እስር ቤት: ከድጡ ወደ ማጡ –የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ሕብረት

$
0
0

January 6, 2016

 

1200056-thumb
ሁከት ፈጣሪ አሣሪና ገዳዩን የደርግ አገዛዝ ግንድ ፈንቅዬ የሰላም ችግኝ በምድረ ኢትዮጵያ አሰፍናለሁ፤ የሃሳብ ልዩነት ልዩነቶችን በጠመንጃ ቋንቋ ብቻ መፍታት የሆነውን የወታደር ስልት ቀልሼ በዘመኔ የክብ ጠረጴዛ ውይይት መደረክ እተካለሁ፤ እመኑኝ ቀን ይወጣላችኋል፤ ሰላም ትሰፍናለች እያለ ነብር ወያኔ ከሕዝብ የተቀላቀለው። የገባውን ቃል የግልብጥ ተርጉሞ በርግጥ ድብደባን፣ እስርን፣ ግድያና ሽብርን ማስፈኑን የዐይን እማኞች ነን። ነፍሰ ጡር፣ ወጣት የአገር ተስፋዎችን ደብድቧል፣ ሴትና አዛውንት አዋርዷል።እናት ስብእናዋንና ክብሯን ተገፋ ልጄን ልጄን እያለች በወታደር የተረሸነችበት የጭካኔ መድረክ እንጂ በክብ ጠረጴዛ በውይይት ችግር የመፍታት የሰከነ ሥልጡን ባህል በወያኔ መንግስት ሲተገበር አላስተዋልንም።
ጀግና ወላዲቷ እየተባለ የሚዘመርላት እናት ቀርቶ ውንድ ልጅ እንኳ በትግል ቆስሎ ወይም ተሸንፎ መሬት ከነካ እወደቀበት የማይመታበት ባህል ያለን ሕዝቦች ነበርን በየትም አገር ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ ሁኔታ የቢቢኤንና ኢሳትን ዜና አዳምጣችኋል በማለት ወታደሮች በሰው ቤት ጣራ ላይ እየወጡ የሳተላይት ዲሽ ሲነቅሉና ሲሰባብሩ ሰንብተዋል።

“ከድጡ ወደ ማጡ”ይሉታል አበው ከገጠር እስከ ከተማ ዱላ በጨበጡ ጠመንጃ በአነገቡ ወታደሮችና ጆሮ ጠቢዎች ሕዝቡን ማጠሩ የወያኔን ከልክ ያለፈ ፍርሃትና ከስልጣን መንጎጃው ወቅት መቃረቡን ከሚያመለክቱ ክስተቶች አንዱ ነው።
የኢትዮጵያ ሙስሊም መሪዎች እነ አቡበከር፣ አህመዲን ጀበልና ሸህ መከተ ሙሄ መታሰርና በማእከላዊ መደብደብ የሕዝበ ሙስሊሙን ሞራል አጠናክሮ ወደ አንድ የትግል ጎራ እንደተሰበሰበ ሁሉ የኦሮሞ ሕዝብ መሬትን ነጥቀህ አሽከር አታደርገኝም በማለት የጀመረውን የመብት ፊልሚያ በመደገፍ  ወገናቸው ጎን የቆሙትን ጀግኖች እነ ኦቦ በቀለ ገርባ፣ አዲሱ ቦላና ደስታ ድንቃ፣ ደጀነ ጣፋ፣ ጌታቸው ሽፈራውና ዮናታን ተስፋዬ መታሰር፤ የኦሮሞ ኮንግሬስ ዋና ፀሃፊ ኦቦ በቀለ ነጋ ላይ የተፈፀመው ድብደባና ዛቻየኦሮሞን ህዝብ ብቻ ሣይሆን ድፍን የኢትዮጵያን ሕዝብ አስተባብሮ ለዘለቀ ትግል የሚያዘጋጅ ይሆናል። የጥቂት ታጋዮች መስዋእትነት የሺ ታጋዮች መፍለቂያ ምክንያት ነው፤ ታሪክም ይህንን ይመሰክራል።
ከወያኔ መንግስት ጋር ተሰልፋችሁ በህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን በደል በማራመድ ላይ የምትገኙ ካድሬዎች ለአንድ አፍታ ከራሳችሁ ጋር ተውያዩ፤ አስቡ፤ የዚያ ሁሉ ወጣት ደም ሲፈስ፤ የዩንቨርሲቲ ተማሪዎች በፌደራል ፖሊስ ተከበው ሲደበደቡ ያሰሙት የነበረውን

 

“ወየው፣ ወየው! ”የሰቆቃ ድምፅ ከሰማችሁ በኋላ ዳግመኛ ከወያኔ መንግስት ጋር ላለመስራት ቆራጥ ውሳኔ ማስተላለፍ በተገባችሁ ነበር። እንደ ሰው መሳሳት ያለ ነው ስህተትን ተርድቶ ከአጥፋት መመለስ ግን ትልቅነትና አዋቂነት ነው። እናንተም እንደ ህዝቡ በቃ በሉ። በቃ ብለው የወታደር ዩኒፎርም አቃጥለው ወደ ህዝብ ከገቡት ጋር ሁኑ ጊዜያዊ ጥቅም ከውያኔ መንግስት ጋር ያስተሳሰራችሁ፤ ገና ለገና ንግድ ቢጤ እሞክራለሁ በሚል ተስፋ ብቻ ዳር የተቀመጣችሁ ወገኖቻችን ሃብቱም ብልፅግናውም ሕዝብ ሰላም ሲያገኝ ነው። ለሐቅና ለፍትሕ ቁሙ። አዱኛውና ቱጃርነቱ ያኔ የአብሮነት ይሆናል።
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ሕብረት የወያኔ መንግስት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በተለይም በአሁኑ ወቅት ኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ እየፈፀመ ያለውን ጭፍጨፋና በደሉንም በመቃወማቸው ለእስር የተዳረጉት የኦሮሞ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ የሲቪል ድርጅቶች፣ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አካላት፣ ጋዜጠኞች፣ የኦሮሞ ወጣቶች፣ ቀደም ሲል በእስር በመማቀቅ ላይ የሚገኙ የሙስሊሙ መሪዎችና ጋዜጠኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ይጠይቃል።

በመላው የሃገሪቱ ሕዝብ ላይ የወያኔ መንግስት ያሰፈነው የሰቆቃ አገዛዝና የኢትዮጵያን መሬት ቆርሶ ለሱዳን ለመስጠት እያደርገ ያለውን ስምምነት በፅኑ የሚያወግዝ መሆኑን ይገልፃል።

 

ትግላችን እስከድል ደጃፍ ድረስ በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!

አላሁ አክበር!!!

የኢትዮጵያ  ሙስሊሞች  ሰላማዊ  ንቅናቄ  ደጋፊዎች  ሕብረት

 

The post ጣራ የለሽ እስር ቤት: ከድጡ ወደ ማጡ – የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ሕብረት appeared first on Zehabesha Amharic.


ኢትዮጵያ ታሪክ ቅሚያና የዘርኝነት ሴራ –ደ .ሰርጸ ደስታ

$
0
0

ብዙ ጊዜ አስቤዋለሁ ግን መልስ ያላገኘሁለት ጥያቄ ነው፡፡ ብዙዎች ስለ ኢትዮጵያ ታላቅነት ሊያወሩ ይፈልጋሉ፡፡ ታላቅነታችን በምንድነው; ከዚህ በታች የማሳርፈው ሐሳብ ሁሉ የራሴ አስተያየት ነው፡፡ ምንዓልባት የሚቀየም ካለ ከልቤ ከወዲሁ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ ሰዎች ይገባቸው ይሆን በምለው ፊት ለፊት የሆኑ ቃላት ልጠቀም ስለምችል አሁንም ከምንም አንጻር ሳይሆን እኔን ስለመሰለኝ ነው፡፡ ከተስማማችሁ መልካም ስህትት ሆኖ ካገኛችሁት ግን ተሳስተሀል የምታስበው ትክክል አይደለም ብሎ ሊያርመኝና እኔም ያላወቅኩትን ሊያስተምረኝ የሚችል ካለ ከልብ እቀበላለሁ፡፡

  1. የጥንታዊው ስልጣኔና ታሪክ ቅሚያ፡

3116993112_racism_answer_2_xlarge


በእኔ አስተሳሰብ ጥንታዊ ስልጣኔ ታይቶበት የነበረው የኢትዮጵያ ታሪክ አሁን ያለንው ሕዝቦች (ይቅርታ የሕዝብ በራሱ ብዙ እንደሆነ አሳምሬ አውቀዋለሁ የዘመኑ ቋንቋ ስለሆነ ነው) የማንነታችን መገለጫ ሊሆን በፍጹም አይችልም፡፡ አክሱምም የትግሬ ላሊበላም የአማራ ሌላም በሉት አሁን ባለቤት እንደሆኑ የሚያስቡት ወገኖች አባቶቻቸው የሰሩት ሳይሆን የሌላ ሕዝብ በረከት እንደሆን አምናለሁ፡፡ ይህንንም ከልጅነቴ ጀምሮ አስተውለዋለሁ፡፡ ደግነቱ ግን ከውጭ በመጣ ሳይሆን አሁንም ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ አካል ሆኖ ባለ ሕዝብ እንደተሰራ ሳስብ እጽናናለሑ፡፡ የቀደመው የአክሱምም በሉት የኋለኛው የላሊበላ አስደናቂ የሰው ልጆች ጥበብ የኢትዮጵያውያን መጀመሪያ ነዋሪዎች የሆኑት ዛሬ አገው ብለን የምንጠራው ሕዝብ ታሪክ ነው፡፡ የዚሕ ሕዝብ ታላቅነት ደግሞ በኢትየጵያ ብቻ የተገደበ ሳይሆን የጥንታውያኑ ግብጾችም ታሪክ ባለቤት ነው፡፡ ፈርዖኖችና አክሱማውያን ወይም ዛሬ እኛ አገው የምንለው ሕዝብ አንድ ወገን እንደሆኑ እንገነዘባለን፡፡ ይህ ሕዝብ ግን ዛሬ በግብጽ በአረቦች በኢትዮጵያ ደግሞ ራሳቸውን ሰሎሞናውያን ነን በሚሉ ወገኖች ታሪኩ ተነጥቋል፡፡ የታሪክ ተመራማሪዎችም ይህን ጥንታዊ መሠረት የነበረውን ሕዝብ ታሪክ ከመዘከር ይልቅ የኢትየጵያን ጥንታዊ ጥበብ ያመከነውን ራሱን ሴማዊና የሰሎሞን ዘር እያደረግ የሚመጻደቀውን ሕዝብና መሪዎች ታሪክ ታላቅነት ሊነግሩን ብዙ ጥረዋል፡፡

ጥቂት እውነታዎችን እናንሳ በጥናዊቷ ኢትዮጵያ (አቢሲኒያ) (ምሳ. አክሱም፣ አዱሊስ)፣ ምስር (ግብጽ)፣ ኑቢያ (ሱዳን) ተንሰራፍቶ ይኖር የነበረው ይህ ነገድ (ወገን) በታላቅነቱ አለምን ያሰፈራና፣ ያስገርም እንደ ነበር ጥንታውያኑ የታሪክ ጸሐፊዎች መዝግበውታል፡፡ ከነዚህም አንዱ ዲዎከራተስ የተባለው ግሪካዊ ጸሐፊ ከክርስቶስ ልደት በፊት መዝግቦት ያለው ታሪክ ነው፡፡  ይህ ወገን ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም በአክሱምና አዱሊስ ታላቅና መሪ ሆኖ ሳለ የሰሎሞን ወገን ነን በሚሉና አረቦች ቀስ እያለ በመዳከሙ ስልጣኑ ስሎሞናውያን ነን በሚሉ እጅ ገባ፡፡ አዱሊስን ቀደም ብሎ በጦርነት አጣት አክሱምንም ለቀቀ፡፡ ለዘመናት ደንታ ቢስና የጥበብ አውዳሚ በነበረው የሰሎሞን ወገን ነኝ በሚለው አካባቢው ሲመራ ከቆየ በኋላ እንደገና ወደ ደቡብ በማፈግፈግ ዛሬ ላሊበላ ወይም ሮሃ የምትባለውን ቦታ ማዕል በማድረግ ያ የጥንቱ ባለታሪክ ሕዝብ ጉልበት አግኝቶ ሥልጣን ያዘ፡፡ ብዙዎቻችን ይህን ታሪክ የዛግዌ ሥርዎ መንግስት እያልን በትምሕርት ቤት ተምረንዋል፡፡ አስተማሪዎቻችን ግን የአክሱምን ታሪክ ከሰሎሞናውያኑ ጋር አጣምረው ነው የነገሩን፡፡ አዎ ታሪክን በመቀማት የተገኘ ታሪክ የመጀመሪየው የአክሱም ሰሎሞናዊ ለተባለው የጥበብ ጠላት መሰጠቱ ነው፡፡

ይህ ጥንታዊው የኢትየጵያ ሕዝብ እንደገና ሌላ ታሪክ በሮሃ (ዛሬ ድረስ አለምን የሚያስደምመውን) እያሳየ ሳለ ነገሮች ግራ በሚያጋባ ሆኔታ በሀይማኖት በሚመስል ማግባባት ሥልጣኑን አሳልፎ ሰሎሞናዊ ነኝ ለሚለው ወገን ሰጠ፡፡ የመጀመሪያውም ሰሎሞናዊ ነጋሲ ይኩኖ አምላክ ይባላል፡፡ ልብ በሉ ይህ ሕዝብ ሥልጣን አሳልፎ የሰጠው በሐይማኖታዊ ጉዳይ ስለነበር በሠላም ነው፡፡ ዛግዌዎች (አገዎች) እጅግ እግዚአብሔርን የሚያመልኩ ስለነበርም በዚህ ጉዳይ የተታለሉ ይመስለኛል፡፡ ይቅርታ እዝህ ጋር ያለው ሒደት ሐይማኖታዊ ጉዳይ ስላለው ግር ስላለኝ ብዙ መናገር አልፈለገኩም፡፡ የተሳሳትኩትም ካለ ሒደቱን አጥርቶ የሚያውቅ ሊያብራራልን ይችላል፡፡ እዝህ ጋር ግን መጥቀስ የምፈለገው ሥልጣኑን ለሰሎሞናውያኑ ሲያስረክብ የተገባለት የራስ ገዥነት ቃል ኪዳን ስለነበር ልብ ትሉት ዘንድ የአገው ገዥዎች እስከ አጼ ኃለስላሴ ዘመን ድረስ ዋግ ሹም የሚል ልዩ መጠሪያ እንደነበራቸው ይታወቃል፡፡ እንደ ውሉ ዋግ ሹም እንደ ራሶቹ ለንጉሱ የመታዘዝ ግዴታ የለበትም የመስማማት እንጂ፡፡

እንግዲህ ከይኩኖ አምላክ ጀምሮ ኢትየጵያን አንደገና አንድ ለማድረግ እስከተንቀሳቀሱት የአጼ ቴዎድሮስ፣ ዮሐንስ፣ ምኒሊክ ታሪክ ድረስ ያለውን የኢትዮጵያ ታሪክ ምን እነድሚመስል ሁላችሁም ትረዱታላችሁ፡፡ ሰለሞናውያኑ ለሁለሁለተኛ ጊዜ እድል ቢያገኙም አገሪቷን በየጎጡ ከፋፍለው በሚገዙ የዘመናታ ዱርዬ መሳፍንቶች መፈንጫ አደረጓት፡፡ በታሪክም ይህ ዘመን የጨለማው ዘመን ተብሎ ይታወቃል፡፡ ይህን እውነት አጉልቶ የሚነግረን የታሪክ ተመራማሪ አላገኘንም፡፡ አሁንም በዛው በተለከፍንበት የዘመናት ዝቅጠት በሆነው አስተሳሰብ እንዳክራለን፡፡ እዚህ ድረስ ያለውን አንኳር ታሪክ ከጠቆምኩ ይበቃኛል፡፡ ብዙ ማተት ይቻላል ውስጡን አለማወቅ ሳይሻል አይቀርም፡፡ ተሳስተሀል የሚል ያርመኝ

  1. የዘመናዊዋ ኢትዮጵያ ታሪክ ባለቤትነት ማሳጣትና ትውልድን በዘረኝነት ማምከን፡-

ይህ ታሪክ በአጼ ቴዎድሮስ ኋላም በዩሐንስ ተሞክሮ እውን የሆነው ግን በታላቁ ምኒሊክ ነው፡፡ እዚህ ታሪክ ላይ ዛሬ ያለው ትውልድ ብዙ የተመሰቃቀለ አመለካከት ስላለው በእርጋታ አንብቦ ከተረዳኝ በኋላ የምናገረው እውንት ካልሆነ በተጨባጭ ማስረጃ ያርመኝ፡፡ ይህ ታሪክ በይበልጥ ያሳተፈው ሕዝብ የትኛውን ነበር; በዚህ ታሪክ ሒደት ውስጥ ታሪክን የተቀማ ሕዝብ አለ; ከላይ ያነሳሁት የአገው ሕዝብ ታሪኩን በጉልበት ማጣት ተቀማ እንጂ ታሪኩን የራሱ እንደሆነ የሚያውቅ ይመስለኛል፡፡ ዛሬ በጎንደር አካባቢ እኛ የተለየን ነን ብሎ የተነሳው የቅማንት ሕዝብም ጥያቄ ከዚሁ መሠረት ጋር ሊያያዝ ይችላል፡፡ ብዙም ጠለቅ ብዬ ስለማላውቅ ግን ለመጠቆም ያህል እነጂ የምሰጠው መረጃ የለኝም፡፡ በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ግን ከፍተኛ አስተዋጾ የነበረው ሕዝብ  ታሪኩን መቀማት ብቻ ሳይሆን የአንተ አይደለም ተብሎ ከነጭርሱ የራሱን ታሪክ እንዲጠላና የጠላት ታሪክ እንድሆነ እንዲያስብ ተደርጓል፡፡

ወደዚህ ዝርዝር ከመገባቴ በፊት አንድ ቁም ነገር አዘል ተረት ትዝ ስላለኝ ላነሳው ወደድሁ፡፡ ሰወዬው በግ ተሸክሞ ገበያ ሊሸጥ ይሄዳል ሶስት ሌቦች ሰውዬውን በጉን ሊነጥቁት አስበው ተማከሩ፡፡ ምክራቸውም በተለያየ ቦታ መንገድ ላይ ሆነን በግ ሳይሆን ውሻ እንደተሸከመ ብንነግረው በጉን ይጥልልናል ብለው ተማከሩ እንደ ተማከሩትመ በተለያየ ቦታ ሆነው ገበያው መንገድ ላይ ይጠብቁት ጀመር፡፡ የመጀመሪያው ገና ባለበጉ ከሰፈሩ ወጥቶ የገበያውን መንግድ ሲጀምር ያገኘውና አያ እከሌ ምነው በዛሬው ቀን ውሻ ተሸክመህ ወዴት ትሄዳለህ ይለዋል፡፡ ባለበጉ ተናዶ እንዴ ወሻ ተሸከምክ ትለኛለህ ብሎ ሌባውን ዘልፎት ይሄዳል፡፡ መሀል መንገድ ላይ ሲደርስ ሌላው ሌባ ያገኘውና ከመጀመሪያው በባስ ምነው አያ እከሌ በገበያ ቀን ውሻ ተሸከመህ ወዴት ነው ይለዋል፡፡ ሰውይው ትንሽ መጠራጠር ጀመረ ግን ይሄንንም አልፎት ሄደ፡፡ ሶስተኛው ገበያው አቅራቢያ ሊደረስ ሲል ያገኘውና ራሱን ይዞ አቶ እከሌ ምነው በሠላም ነው በገበያ ቀን ውሻ ተሸክመሕ የመጣህው ይለዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ሰውዬው የተሸመው በግ ሳይሆን ውሻ እንደሆን ስላመነ ከትከሻው አውርዶ በጉን ይለቀዋል፡፡ ሌቦቹ በጉ የሄደበትን ተከትለው በዚህ ሁኔታ በጉን ይወስዱበታል፡፡ የኋለኛው የኢትየጵያ ታሪክ ቅሚያም እንዲሁ ነው፡፡

ከላይ በጠቀስኩት ተረት መሰል ቁምነገር አይነት የገዛ ታሪኩን በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ተነጥቆ እንደዜጋ እንኳን ሳይሆን እንደ ባዕድ ራሱን እንዲቆጥር የተደረገው ሕዝብ በዘመናዊኞቹ የኦሮሞ ሕዝብ እየተባለ የሚጠራው የኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝብ ነው፡፡ ከይቅርታ ጋር እዚህ ጋር የኦሮምኛ ተናጋሪ እንጂ ኦሮሞ የሚለውን ለመጠቀም አልፈለግኩም፡፡ ስለዝህ ጉዳይ ብዙ ራሱን በቻለ ርዕስ የማነሳው ይሆናል፡፡ ቢቻል በሌላ ፅሑፍ፡፡ ወደ ተነሳሁበት ልመልሳችሁ፡፡ የዘመናዊቷ ኢትየጵያን የፈጠሩት ምኒሊክ እንደሆኑ ሁላችንም የማንክደው ሀቅ ነው፡፡ የምኒሊክ ታሪክ ደግሞ ዋነኛ ተዋናዮቹ እነማናቸው ቢባል የኦሮምኛ ተናጋሪው በተለይም የሸዋ ኦሮሞ ታሪክ ነው፡፡ አስቀድሞ አገርን እንደ ከማድረግ ጀምሮ አፍሪካን ብሎም የጥቁርን ሕዝብ ሁሉ ታሪክ የለወጠው የአደዋው ታሪክ ይህ ታላቅ ሕዝብ በመሪነት የተሳተፈበት ድል ነው፡፡

የአገር አንድ ማድረጉን ሂደት ዛሬ ድረስ አስከሚኮነነው የአኖሌና ጨለንቆን ጦርነት ጨምሮ በኋላ ልምጣበት ግን እስኪ ሁላችንም ለሂሊናችን ዳኝነት ይረዳን ዘንድ በአደዋ ልጅምር፡፡ በአደዋው ድል ከሚታወቁ ጀግኖች ፊታውራሪ ገበየሁ ጎራና ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ ተወዳዳሪ የሚገኝላቸው አይመስለኝም፡፡ ከነጭረሱም ፊታውራሪ ገበየሁ በዚህ ጦርነት ራሳቸውን መስዋዕት ባያደርጉ ጦርነቱ ሽንፈት ሊሆን ይችል ነበር፡፡ ይህን ታሪክ ስናገር ብዙዎች የሚረዱት ስላልመሰኝ እያዘንኩ ነው፡፡ ገበየሁ የሚመሩት ጦር የመጀመሪያው ነበር፡፡ ጦሩ ከጣሊያን ጋር ሊገጠም ፈራ፡፡ ከዚህ በኋላ ገበየሁ ጦሩን በማዘዝ ሳይሆን እንዲህ የሚል ቃል ተናገሩ፡፡ “ሁላችሁም ተመለሱ ለምንሊክ ገበየሁ በእንዲህ ያለ ሁኔታ በጣሊያኖች ተገደለ ብላችሁ ንገሩት” ብሎ ወደ ጦርነቱ ብቻውን ገሰገሰ፡፡ በዚህን ጊዜ ነበር ወታደሩ የመሪያቸውን ቁረጠኛ ውሳኔ ሲያውቅ ፍርሀቱ ለቆት ጦርነቱን ከመሪው ጋር የተጋፈጠው፡፡ ይህ የታሪክ እውነት ነው! ይህ ባይሆን የአደዋ ጦርነት ምን ሊሆን እንሚችል ገምቱ፡፡ አደዋ የገበየሁ ደም ውጤት ነው፡፡ ስለ ገበየሁ ግን የረባ ታሪክ እንኳን አንብቤ አላውቅም፡፡ አባቴ ከነገረኝ በቀር፡፡ እንዳ ስላሴን ጣሊያን አረከሰው ገበየሁ በሞቴ ግባና ቀድሰው፣ የምትለው ስንኝ ግን በጣም ታስደስተኛለች፡፡ አደዋ የብዙዎች ተሳትፎ ቢኖርበትም እኝህ ታላቅ ሰው መስዋዕት ባይሆኑ ግን ታሪኩ ሌላ መልክ ሊኖረው እንሚችል አስባለሁ፡፡ በገበየሁ ሞት ጦሩ ሁሉ በእልህና በቆራጥነት ይዋጋ ነበርና፡፡ ሌላው በተለምዶ ባልቻ አባ ነብሶ የምንላቸው ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ በአደዋው ጦርነት በቀዳሚነት የሚታወቁት ጀግና ናቸው፡፡ ገበየሁ ቢሞት ተተካ ባልቻ …. የሚባለውም ከገበየሁ ጋር ተመሳሳይ የሆነ የጀግንነት ባሕሪ ስለነበራቸው ነው፡፡ በነገራችን ላይ ባልቻ ሳፎ በመጀመሪያው ጦርነት ወጣት ስለነበሩ ሁለቱንም የኢጣሊያ ጦርነት የተሳተፉ ሰው ናቸው፡፡ የሞቱትም በሁለተኛው ጦርነት ነው፡፡ ቅድም ኦሮሞ የሚባለው ሕዝብ በደም ይሁን በቋንቋ ለእኔ ግልጽ ስላለሆነልኝ ነው፡፡ ኦሮምኛ ተናጋሪ ያልኩት፡፡ ቋንቋ ባደግንበት ነውና፡፡ ኦሮሞ የሚባለው ሕዝብ እንደ አንድ መንደር ነዋሪ አይደለም፡፡ በጣም ውስብስብ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር እነ ራስ ሚካኤል የወሎው (ራስ አሊ መሰለኝ ይቅርታ አርሙኝ)፣ ራሳቸው እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሌሎችም የዚሁ የአደዋውና የምኒሊክ ዘመን ታላቅ ባለታሪኮች ከዚሁ ሕዝብ አካል ናቸው፡፡ ይህ እውነት ነው፡፡ የአደዋ ታሪክ በቀዳሚነት ሊዘከር የሚገባው ከዚህ ሕዝብ ጋር ነው፡፡ እውነት እንናገር ከተባለ ከትግራይ ራስ አሉላና መሪም ስለነበረሩ ራስ መንገሻ ዩሐንስ በቀር እዛ ቦታ ታሪኩ የሚታወቅ ሰው አልሰማሁም፣ አማራ ከሚባለውም ሕዝብ ከንጉስ ተክለሀይማኖት (ንጉስ ተክለሀይማኖትም ምን አልባት አማራ የሚባለው ሕዝብ አካል ከሆኑ ማለት ነው) በቀር ማን ተሳታፊ እንደነበር አላውቅም፡፡ እንግዲህ አማራ የተባለው ሕዝብ ተሳተፈ ከተባለ ራሳቸው ሚኒሊክና አጎታቸው ራስ መኮንን ናቸው፡፡  ይህም ባይሆን የሁለቱም መሪዎች ወታደሮች ኦሮሞ የሚባለው ሕዝብ ልጆች ሊሆኑ እንደሚችሉ እያሰብን፡፡  ለነገሩ ራሳቸው ምኒሊክ ሆኑ መኮንን የዘር (በደም ከሆነ) ሀረጋቸው ከየት እንደሆነ ማን ያውቃል; ሸዋ እንሆነ የተወሳሰበ ሕዝብ ነው፡፡ ይህን ታሪክ እንዲክድና እንሁም እንዲጠላው የተደረገው የዛሬው የኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝብ ትውልድ ለዚህ ባይተዋር ለአገሪቱም እነደዜጋ እነዳያስብ ሆኗል፡፡ ራስ መኮኒን የወልደ ሚካኤል ጉዲሳ ልጅ መሆናቸውን አንዘንጋ፡፡

አገርን እንድ የማድረጉ ሒደት ግልጽ ነበር፡፡ በዋነኝነት የመሩት አሁንም የኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝብ ልጆች ናቸው፡፡ ዛሬ ሆን ተብሎ የኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝብ ልጆች ያንን ታሪክ እንደ ልዩ የታሪክ ቁስል እንድቆጥሩ የተደረገብት ዋነኛ ምክነያት ያ ሂደት አሳፋሪ ሆኖ ሳይሆን ይህን ሕዝብ ራሱ የገነባትን ኢትዮጵያን እንዲጠላ በማድረግ እንደልባቸው በአገሪቱ ውስጥ ሊፈነጩ የሚችሉበትን እድል ለመፍጠር ባሰቡ አደገኛ ሴረኞች እንሆነ ብዙ ሰው አሁንም አልገባውም፡፡  በዚህ ጉዳይ ሴረኞቹ እንደጠበቁት ተሳክቶላቸዋል፡፡ የኦሮምኛ ተናጋሪውን ሕዝብ ልጆች ከታሪክ ባለቤትናቱ አልፎም ከኢትዮጵያዊነቱ ለይተውታል፡፡ ይህ ባይሆን አንድም ኃይል አለኝ የሚል አካል ያለዚህ ሕዝብ ይሁንታ እንኳን ዛሬ ሕዝቡ በሚኖርበት ኦሮምያ በሚባለው ክልል በሌሎችም ክልል እንደልብ መዘወር ባልቻለ ነብር፡፡ በኦሮምኛ ተናጋሪው ላይ የወጠኑት እቅድ ሙሉበሙሉ የተሳካላቸው ሲሆን ዛሬ ሌላውም ኢትዮጵያነቱን እንዲዘነጋና በቀበሌ እንዲያስብ በማድረግ አንድነቱን በመበታተን ሴረኞቹ ለራሳቸው አመቻችተውታል፡፡ ብዙ ሰው ጎሰኝነትን እጠላለሁ ይላል፡፡ ውስጡ ግን እጅግ ዘረኝነት ይነበባል፡፡ ጎጃሜው አማራ እንጂ ኢትየጵያዊነት ሁለተኛው ነው፣ ትግራዩም ትግሬ እንጂ እንደዚያው፣ ሌላውም እንደዚያው፡፡ እና ማን ነው በኢትየጵያነት ሁሉንም በአንድ አይቶ ሊመራ የሚችል; ዛሬ የሆነ ቦታ ሕዝብ ሲቸገር፣ ሲገደል፣ ሌላም ሲሆን ኢትየጵያዊ ተብሎ ማሰብ ቀርቷል፡፡ አማራ፣ ኦሮሞ ምናምነ ነው እንጂ፡፡ አንዳንዶች እንደውም ከሃይማኖትም ጋር አዳቅለውት ክርስቲያን አማሮች ምናምን ማለት የተለመደ ነው፡፡  ሰሞኑን በኦሮምያ ክልል ልጆቻችን ሲገደሉ ለብዙዎች የሞቱት ኦሮሞዎች ናቸው እንጂ ኢትየጰያውያን አይደሉም፡፡ ሰላማዊ ሰልፍም ወጭዎቹ ኦሮሞ፣ አማራ፣ ምናምን በሚል እንጂ በጋራ አጀንዳ አይደለም፡፡ እዚህ ላይ አሁን ለብዙ ልጆቻችን መሞት ምክነያት የሆነው አመጽ ሥሕተት እንደነበር ልናገር እወዳለሁ፡፡ ጥያቄው የኦሮሞ መሬት በሚል እንጂ የፍትሐዊነት አልነበረም፡፡ ጉዳዩን አንዳንዶች እንዳሉት የማንነት ጉዳይም አይደለም፡፡ ይህ ፕላን አንዱን ገፍቶ ለሌላው መሬት መስጠ ከሆነ የፍትሀዊነት ጉዳይ ነው፡፡ የፍትሐዊነት ጉዳይ ከሆነ ደግሞ ኦሮሞ ለተባለው ሕዝብ ልጆች ብቻ ሳየሆን ሁሉም በአንድነት ሊጠየቀው የሚገባ ጉዳይ በሆነ ጥያቄውም ጉልበት ባገኘ፡፡ ደግሞም ልማት በሚመስል ብዙም ጊዜ እንዳየንው ሆን ተብሎ የሆኑ ቡድኖችን ለመጠቀም ሊሆን ይችላል፡፡  ግን ኦሮሞ ለተባለው ሕዝብ የተለየ ባልሆነ ነበር፡፡ እንዲህ አንዱን የሚሰማው ሌላውን ደንታ የማይሰጠው የሕዝብ ጉዳት ብዙ ዓመት የተገነባ ዘረኝነት ውጤት እንደሆነ እናገራለሁ፡፡ ዛሬ የዩኒቨረሲቲ ተማሪዎች አመጸ ተነሳ ከተባለ የዘር ግጭት እንጂ የሕዝብ ጥያቄ ወይም በጋራ የተማሪዎች ጥያቄ አይደለም፡፡

አኖሌና ጨለንቆ ለምን በምኒሊክ ታሪክ ውስጥ ጎልተው እንዲታዩ ተፈለገ; እነዚህ ጦርነቶች የግድ ስለሆነ እንጂ ምኒሊክ ሆን ብለው ያደረጓቸው እንዳልሆን ግልጽ ነው፡፡ እውነት ነው አንድ ሕዝብ ሌላ አካል መጥቶ ሲወረው ራሱን መከላከል ጦርነት መግጠም ትክክለኛ ነው፡፡ ጦርነት ደግሞ ሁሌም ጉዳት አለው፡፡ ግን ጦርነት በታሪክ ሂደት ተከስቶ በሌላ ጊዜ እንደታሪክነቱ ቢዘከርም የሚነሳ ትውልድ  ያንን ታሪክ እያሰበ በቀል የሚያስብበት መሆን ባልተገባው፡፡ በአለም ላይ ያሉ አገራት በአብዛኛው ማለት ይቻላል ዛሬ ባላቸው ስፋት ያሉት በጦርነት ነው፡፡ አኖሌ ዛሬ ይህ ትውልድ እንደሚነገረው ሐርካ ሙራና ሐርማ ሙራ ተከስቶበት ከሆነ በግፈኝቱ ሊወሳ ይችላል፡፡ ተከስቶም ከሆነ ትውልዱን እንደዚያ ያሉ ክስተቶች በሌላ ታሪክ እንዳይደገም ሌላ በጎ አመለካከት እንዲኖረው ማነጽ ሲገባ ቂመኛና በቀለኛ እንዲሆን ማድረግ ባልተገባ ነበር፡፡ የሚያሳዝነው አዲሱ ትውልድ ሊያውም ደግሞ ታሪኩ ይመለከተዋል የተባለው የአኖሌ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን መላ የኦሮምኛ ተናጋሪው ባልተረጋገጠው የአኖሌ ታሪክ ተበክሏል፡፡ ይህንኑ ትውልድን በቂመኝነት መበከል ለማጠናከር መታሰቢያ በሚል በብዙ ሚሊዮን ገንዘብ ከመቶ ምናምን ዓመት በኋላ ሐውልት ቆሞለታል፡፡ ታሪኩ ሆኖ በትክክልም ቢረጋገጥ እንኳን ይህ ትውልድ አሁን ተሰራ በሚባለው ጥላቻን የሚያጸና ሐውልት ባልተደለለም ነበር፡፡ ይልቁን በመታሰቢየነትም ቢሆን ለሕዝቡ የሚጠቅም ት/ቤት ወይም ሆስፒታል ማሰብን በተቻለ ነበር፡፡ ከመቶ ዓመት በፊት ተደረገ ስለተባለ ታሪክ ይህ ትውልድ ቂመኛ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ ራሱን ግን ነጻ ማድረግ እንዳይችል አምክነውታል፡፡ ያስ ኋላ ቀር በነበረበት ዘመን ነው፡፡ ዛሬም ግን ለምን ከዚያ ባልተናነሰ ግፍ ይገደላል፡፡ አኖሌ የተባለው ግፍም ዛሬም ድረስ ሊሆኑ ከሚችሉ የጦርነት ግፎች አንዱ ነው፡፡ ይህ ግን በምኒሊክ ዕውቅና ሊሆን እንደማይችል ከምኒሊክ ባሕሪ አንጻር እረዳለሁ፡፡ ይልቁንም በጦርነቱ የአርሲ ሕዝብ እንደ ተጎዳ ያዩት ምንሊክ በጣም ስለ ሕዝቡ በማዘናቸው ወታደቶቻቸውን ከድል በኋላ መሬቱን እንዳየቀማው አዋጅ አስነግረው ነበር፡፡ ይህ እውነት ነው! ዛሬ ኦሮሞ ነኝ እያለ ወገኑን ለሞት ከሚማግደው በላይ ምኒሊክ ኦሮሞም በሉት ሌላ ሕዝብ አሳቢው ናቸው፡፡ እውነቱ ይሄ ነው! እና ዛሬ ከመቶ ምናምን አመት ነኋላ ይህ ሕዝብ ግፍ ቀረለት; ለዚህም ምኒሊክ ተጠያቂ ናቸው;

ጨለንቆ በምን ሒሳብ እንደ ታሪክ ቁስል እንደሚነሳ አይገባኝም፡፡ ልብ በሉ ጨለንቆ ላይ የተዋጉት አቡበከር ዋሬ እንደ ጀግና መታሰባቸው ባልከፋ፡፡ ይህን ምኒሊክ ራሳቸው ዛሬ ቢኖሩ በዚህ ቅር እንማይሰኙ እገምታለሁ፡፡ የሚኒሊክ ጦርነቶች የአላማ እንጂ ማንንም በጠላትነት የማየት አልነበረም፡፡ ምን አልባትም ዋሬ በጦርነቱ ባይሞቱ እንደ ወላይታው ጦና ድል ከተነሱ በኋላ የጨለንቆ መሪ ሆነው ይቀጥሉ እንደነበር እገምታለሁ፡፡ የምኒሊክ ዓማና ራዕይ ግልጽና ምንም ሸፍጥ ያለበት አልነበረም፡፡

ሌላው በስፋት በዘመንኛ አቀንቀኞች የሚነሳው ከምኒሊክ በፊት የኦሮሞ ሕዝብ የራሱ ታሪክ፣ አስተዳደር፣ ባሕል የነበረውና ምኒሊክ ሁሉን እንዳጠፉበት ነው፡፡ ከሜዳ ተነስቶ ታሪክ አይወራም፡፡ ችግሩ የኦሮምኛ ተናጋሪውን ሕዝብ ውስብስብ አሰፋፈርና ማሕበራዊ እውነታዎች በመካድና ሁሉንም ከመዳ ወላቡ ለመቀዳት ዝም ብሎ ኦሮሞ በሚል በአንድ ጎራ መድቦ ለራስ የሚመችን ሕዝብ ለመፈጠር ስለታሰበ ነው፡፡ እንግዲህ በምኒሊክ ጠፋ ከተባለው የዚህ ሕዝብ እሴት አንዱ የገዳ ሥርዓት ነው፡፡ በምኒሊክ ጊዜ ጨለንቆዎች በገዳ ሥርዓት መምራታቸው እጠራጠራለሁ፡፡ ይሕ ሕዝብ በዚያን ወቅት አሁንም የእስልምናን እምነት የሚከተል ሲሆን ብዙ ጊዜም ከአረቦች፣ ቱርኮችና ሌሎች ሙስሊም አገራታ ባለው ግንኙነት የአስተዳደር ዘይቤው የነዚሑንው አገራት የተከተለ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ አርሲ የገዳ ሥርዓት ተከታይ ለመሆኑ እጠራጠራለሁ፡፡ አብዛኛው የእስልምና እምነት ተከታይ የነበረው የኦሮምኛ ተናጋሪ ሕዝብ የገዳ ሥርዓት ተከታይ  እዳልነበረ አውቃለሁ፡፡ የልቁንም የገዳ ሥርዓት ለምኒሊክ ቅርብ በሁኑት የሸዋ ኦሮምኛ ተናጋሪ ሕዝብ ዛሬም ድረስ  የካሄዳል፡፡ የገዳ ልዩ ሥርዓት ዛሬ ድረስ በቦረና ሕዝብ ይካሄዳል፡፡ ይህ ባሕላዊ ሥርዓት ለዘመናዊው አስተዳደር ሊያበረክት የሚችለውን አስተዋጾ ብናውቅም እንደነበረ ግን ሊቀጥል እንደማይችልም ይታወቃል፡፡

ለምን ምኒሊክ ላይ ኢላማ ተደረገ ሲባል ማንም መልስ ባይኖረውም ሆን ተብሎ ሕዝቡን ከኢትዮጵያዊነቱ ለመነጠል የምኒሊክን ታሪክ ከትውልድ አእምሮ ውስጥ ማውጣትና በጥላቻ እንዲያየው ማድረግ ሁነኛ ብለሀት እንደሆነ ታስቦበት ነው፡፡ በምንም መስፈርት የምኒሊክን ታሪክ ጠንቅቆ የተረዳ ትውልድ አሁን ላሉት ዘረኞች እሽ ብሎ የሚገዛ አይሆንም፡፡ እውነታው በምኒሊክ ጊዜ ኦሮምያም በሉት ሌላ ከጥቂት ቦታዎች በስተቀር በአካባቢው መሪዎች ነበር የሚተዳደረው፡፡ ጅማ በአባ ጅፋር፣ ወለጋ በቦረዳ፣ ሌሎችም እንዲሁ፡፡ ይልቁንም ይህ ሥርዓት በሌሎች እንዲተካ ያደረገው የአጼ ኃ/ሥላሴ መንግስት ነው፡፡ ለሴረኞቹ ግን የአጼ ኃ/ስላሴ ነገር ብዙም አያሳስባቸው፡፡  በተቃራኒው ሴረኞቹ የኦሮሞም በሉት፣ ሱማሌ ወይም ሌላ ሕዝብ ከምኒሊክ ጋር የጠበቀ ታሪክ ስላለው በዚህ ሁኔታ እድል ስለማይኖራቸው ሕዝቡን የራሱ ከሆነው ከምኒሊክ ታሪክ መለየት ነበረባቸው፡፡ ታሪኩንም አማራ ለሚባለው ሕዝብ ሰጡት፡፡ ይህ የዘመናዊው ታሪክ ቅሚያ ነበር፡፡ በዚህ ሁሉ ሆን ተብሎ በተሴረ ትውልዱን ከራሱ ታሪክ ማጣላትና የማንነት መሠረቱን ዜግነቱን በማላላት የጎጥ አመለካከት ኖሮት ከቀበሌው እነዳይወጣ በማድረግ እነሱ እነድልባቸው እየፈነጩበት ባሉ ወገኖች እንደሚዘወር አሁንም አልገባንም፡፡

ከሁሉም የኢትዮጵያ ታሪክ ኦሮሞ የተባለው ሕዝብ ተወላጅ ከፍተኛ ስልጣን የነበራቸው በምኒሊክ ዘመን እንደሆነ ለብዙው የዛሬው ትውልድ አይገባውም፡፡ ከላይ በታላቁዊውና ታሪካዊው አደዋ ከጠቀስኳቸው በተጨማሪ በየቦታው አስተዳዳሪ የሆኑትን ሳይጨምር የምኒሊክን መንግስት በበላይነት የመሩት የዚሁ ሕዝብ ልጆች ነበሩ፡፡ የሚኒሊክ አጎት የተባሉት የኃ/ስላሴ አባት ከላይ የጠቀስኳቸው ራስ መኮንን ወልደ መስቀል ጉዲሳ፣ ሀብተጊዎረጊስ ቢነግዴ (አባ መላ)፣ ራሳቸው ጣይቱ ብጡል በምንሊክ መንግስት ከፍተኛውን ቦታ ከያዙትና አገሪቷን የመሯት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በዚህ ሁሉ ግን የኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝብ ብዙ በደል ነበረበት፡፡ የምኒሊክ ሥርዓት ግን በተቃራኒው ይህንን በደል የተዋጋ ነበር፡፡ ችግሩ በቤተክርስቲያን ተስግስገው ካሉ ጠንቋይ ደብተራዎች እና ሌሎች በፊትም ያሉ ከምኒሊክም በኋላ እንደልባቸው በሁኑ አደገኛ ቡድኖች ይህ ሕዝብ እንደተበደለ አያውቅም፡፡ ይልቁንም የራሱ የሆነውን ምኒሊክኒና ታሪኩን እነዲጥል ተደርጓል፡፡ ኢያሱ በምኒሊክ ለንግስና ሲመረጥ ምኒሊክ አስበውት የነበረው አሳቸው የጀመሩትን የኦሮምኛ ተናጋሪውም ሆነ ሌላውን ሕዝብ በፍትሐዊነት ያገለግላል ብለው ነበር፡፡ ኢያሱም የቱንም ያህል ወጣት ቢሆኑም አያታቸው ምንሊክ የመከሯቸውን ነበር የጀመሩት፡፡ ኢያሱም ግን በአደገኛ ደብተራዎችና ሴረኞቹ ወደቁ፡፡ ይህ ትውልድ ከዚህ እወነት ተጋረዷል፡፡ ጠላቶቹ የነገሩትን እየሰማ ራሱን አጥቷል ብዬ አስባለሁ፡፡

ይህ እኔ ያወቅኩት እውነት ነው፡፡ የሄ እውነት አይደለም የሚል ቢኖር ልታረም ፍቃደኛ ነኝ፡፡ አመሰግናለሁ!!

The post ኢትዮጵያ ታሪክ ቅሚያና የዘርኝነት ሴራ – ደ .ሰርጸ ደስታ appeared first on Zehabesha Amharic.

የነጻነት ቀን ቀርባለችና ጸንታችሁ ቁሙ! –እየሩሳሌም ተስፋው (ከቃሊቲ ማጎሪያ ቤት፣ አዲስ አበባ)

$
0
0

እነሆ በጨለማ ቤት ውስጥ ከታጎርን 311 ቀናት ሞሉን፡፡ ጊዜው እንዴት ይሮጣል ባካችሁ? የዛሬ አመት በዚህ ወቅት ከጓደኞቼ ጋር በዝዋይ እስር ቤት የሚገኙትን ጀግኖቻችንን ለመጠየቅና እንኳን አደረሳችሁ ለማለት የገና ዋዜማን በዝዋይ ወህኒ ቤት ተገኝተን ነበር፡፡ ግን ምኞታችን ቅዠት ሆኖ ያሰብነው ሳይሳካ አንድም የፖለቲካ እስረኛ ማግኘት ሳንችል በሩን ተሳልመን ተመለስን፤ መጠየቅ አትችሉም ተብለን፡፡…

iyarusየገና ዕለትም እንደለመድነው ከጀግኖቻችን ጋር ለማሳለፍ መጀመሪያ በቂሊንጦ ወህኒ ቤት፣ ቀጥሎ የስድስት ሰዓት ተጠያቂዎች ናቸውና የቃሊቲ ጀግኖቻችን ከእነሱ ጋር በማሳለፍ ለማስታወሻ ይሆነን ዘንድ እዚሁ ቃሊቲ በር ላይ ተሰባስበን ፎቶ ተነሳን፡፡ ያ በዓል ለእኔ እና ለአባሪዎቼ የመጨረሻ በዓላችን ነበር፡፡ ሆኖም በዓሁኑ ሰዓት በዚያ ፎቶ ላይ ተሰባስበን ከተነሳነው ስንት ሰው እንደሆነ በሰፊው እስር ቤት የቀረው እናንተው ማየት ትችላላችሁ፡፡ (ፎቶ ከተገኘ ማለቴ ነው)
ግማሾቻችን ቃሊቲ፣ ግማሾቹ ቂሊንጦ፣ ግማሾቹ ማዕከላዊ፣ ግማሾቹ ሸዋሮቢት ታጉረዋል፤ የቀሩትም ከሀገር ተሰደዋል፣ አንድ ሁለት ቆራጦች ደግሞ በፈታኝ ሁኔታ ውስጥ ሀገር ቤት ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ይህ ነው የኢትዮጵያ ፖለቲካ መጨረሻ! መታሰር አልያም ከሀገር መሰደድ! በቅርቡ የማደንቃቸውና የማከብራቸው ጓደኞቼ ወደ ማዕከላዊ መግባታቸውን ስሰማ በጣም አመመኝ፡፡ በእርግጥ ወያኔ በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ መታሰር አዲስ አይደለም፡፡ ከመታሰርም በላይ ወንድማችን ሳሙኤል አወቀ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድሏል፤ በኦሮሚያ ያለውን ግድያ የምናውቀው ነው፡፡ ግን እስከመቼ ግፉ ይቀጥላል? እስከመቼስ በዚህ ሁኔታ ጀግኖቻችንን እያስበላን እንቀጠላለን? እስከመቼስ መረጃ ምንጮቻችን የሆኑት ሚዲያዎች ሲታገዱ እንታገሳለን? እስከመቼ በፍርሃት ቆፈን ተቀፍድደን እንቀመጣለን? እስከመቼ እስሩና ግድያው የእኛን ቤት እስኪያንኳኳ እንጠብቃለን?
ለመሆኑ ቆርጠን ተነስተን ወያኔን ታግለን እንዳንጥል ያደረገን ምንድነው? ከአፍሪካ የስልጣኔ እና የነጻነት ፈር ቀዳጅ ተምሳሌት እንዳልነበርን ዛሬ ከጎረቤት ኬንያ እንኳን አንሰን ስንገኝ ምን ይባላል? አዎ በረባ ባረባው ለራሳችን የምንሰጠው ምክንያት ወደኋላ እየጎተተን ይገኛል፡፡ ልጄ፣ ሚስቴ፣ ባሌ፣ ልጄ፣ እናቴ፣ አባቴ…ስንል ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ከካርታ ላይ እንዳትጠፋብን እሰጋለሁ፡፡ የኢትዮጵያዊነት የጀግንነት ስሜቱ ወዴት ገባ? እድሜ ልክ በፍርሃት ከመኖር አንድ ቀን በጀግንነት መኖር አይሻልምን? ኸረ ንቃ ወገኔ…ተነስ! በቃ እኔ የምልህ ንቃ ነው!
ይህን የምልህ አንዳንድ የአዲስ አበባ ካድሬዎች በወያኔ ቴሌቪዥን እንደሚሉት አውሮፓ ተቀምጬ አይደለም፡፡ እዚሁ በግፍ እስር ላይ ሆኜ እንጂ! ተነስ የምልህ ፈርቼ በማፈግፈግ ሳይሆን ደፍሬ ከፊት በመቆም ነው፡፡ የጀመርኩት የነጻነት ትግል፣ የነጻነት መንገድ አለና ከዳር አድርስልኝ ነው የምልህ! በአንድ ወቅት የዛን ዘመኑ አሸባሪና የአሁን ዘመኑ የሰላም ኖቬል ተሸላሚ ኔልሰን ማንዴላ (ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልንና) እንዲህ ብለው ነበር፤ ‹‹ማንኛውም ህዝብ ሁለት ምርጫ ፊቱ ላይ የሚደቀንበት ጊዜ ይመጣል፡፡ እጅ መስጠት ወይም መሳሪያ ማንሳት? እኛም ሁለተኛውን ምርጫ እንድንመርጥ ተገድደናል›› ብለው ነበር፡፡ እኔም ኢትዮጵያዊነት አልደፈርም፣ አትንኩኝ ባይነት መሆኑን ተረድቼዋለሁና፣ እጅ መስጠት እንኳን ለእኔ ኢትዮጵያዊነት ገብቶኛል ለምለው ይቅርና ለአንድ ጨቅላ ህጻን ልጅ እጅ መስጠት ማለት ሞት ነውና ልክ እንደ ማንዴላ ሁለተኛውን ምርጫ እንድመርጥ ተገድጃለሁ፣…መሳሪያ ማንሳት!
ምንም እንኳ አሁን ላይ በወያኔ እጅ ወድቄ በዚህ ጨለማ ወህኒ ቤት ብገኝም ራዕዬ ትልቅ ነውና ብዙ በመንገዴ እየሄደበት ይገኛል፡፡ አዎ ዛሬ አካሌ እዚህ ቢገኝም ልቤ ባህርን ተሻግሮ ኤርትራ በርሃ ውስጥ ከጀግኖቹ መንደር ይገኛል፤ ወደ ኢትዮጵያ ከሚገሰግሱት ከነዚያ ልበ-ሙሉዎች ጋር የእኔ ልብ!
በመጨረሻም፣ ማንም ሰው ጀግና ነሽ፣ ጎበዝ ነሽ አይበለኝ! እኔ በሴትነቴ የጀመርኩትን እናንተም ተከተሉኝ፡፡ ልብ ከቆረጠ ሊገታው የሚችለው ምንም ኃይል የለምና! በዚያ በስቃይ ቤት ከማንም ሳትገናኙ መምሸቱንም መንጋቱንም ለምርመራ ስትወጡ ብቻ እያያችሁ በዓሉን የምታሳልፉት የምወዳችሁ ጓደኞቼ አይዟችሁ በርቱልኝ እላለሁ! የማያልፍ የለም!! የነጻነት ጊዜ ቀርባለችና ጸንታችሁ በአቋም ቁሙ! የኢትዮጵያ አምላክ ከእናንተ ጋራ ይሁን!!

The post የነጻነት ቀን ቀርባለችና ጸንታችሁ ቁሙ! – እየሩሳሌም ተስፋው (ከቃሊቲ ማጎሪያ ቤት፣ አዲስ አበባ) appeared first on Zehabesha Amharic.

በኢትዮጵያ ቢያንስ 140 ሰዎች ተገድለዋል- HRW (DW)

የሰላምና የፍትህ ጥሪ በኦሮሚያ –ወንጌላዊ ዳንኤል ጣሰው

$
0
0

c87d8e6b-eafd-4c86-90f4-6040d8a54ae8ሰሞኑን በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች እየደረሰ ያለው ሁኔታ በጣም የሚያሳዝን ሆኗል። ይህ ነገር ሲከሰት አሁን ለሁለተኛ ጊዜ ነው። ከአንድ አመት በፊት ተመሳሳይ ሁኔታ ተፈጥሮ እኛም በወቅቱ መልእክት አስተላልፈን ነበር።

ማሳሰቢያ፥ምክር፤ ተመልሶ እንዳይደገም። ታዲያ እንዴት ተመሳሳይ አደጋ ሊደገም ቻለ? አሁን ተባብሶ የብዙ ኦሮሞ ወገኖቻችን ህይወት ሊቀጥፍ ችሏል። ይህ ደግሞ እጅግ በጣም የሚያሳዝንና አሰቃቂ ነገር ነው።
በመጀመሪያ ለሟች ቤተሰቦች መጽናናት የቆሰሉትም እንዲያገግሙ እንጸልያለን፤ እግዚአብሔር መጽናናቱንና ብርታቱን ይስጣቸው።

ጉዳዩ ከማስተር ፕላኑ አልፎ የተጠራቀመ የመልካም አስተዳደር እጦትና የመብት ጥያቄዎችን ብሶት ያካተተ ሆኗል። በዚህ ጉዳይ ላይ በፍጥነት እርማት ካልተካሄደ ከፍተኛና ያልተጠበቀ አደጋ በሀገሪቷ ላይ ሊደርስ ይችላል። ይሄ ነገር ተባብሶ ከዚህም የባሰ የብዙ ወገኖቻችንን ህይወት ከመቅጠፉ በፊት ይታሰብበት።

የሰው ነፍስ ያለ አግባብ ያጠፉ፥ ከመጠን በላይ ሀይል የተጠቀሙ ሁሉ በህግ ይጠየቁ።
መንግስት ከህዝብ ለሚነሱ ጥያቄዎች በአግባቡ መልስ ይስጥ። ጉዳዩ በግልጽ ውይይት የሚፈታ በመሆኑ ከህዝቡና በሀገር ቤት ካሉ ህጋዊና ሰላማዊ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ውይይት ይደረግ። ባለፈው መንግስት ቃል እንደገባው በሀገሪቱ ጉዳይ ላይ ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እየተመካከርን እንሰራለን ብሏልና ቃሉን ይፈጽም።

የኢትዮጵያን ሰላምና ብልጽግና ለማይወዱ ሁሉ ይህ ጉዳይ ቀዳዳ እንዳይከፍት ወደ እርስ በርስ የከፋ አደጋም እንዳይሸጋገር ይታሰብበት።መብት የሚጠይቁ ወገኖችም በተቻለ መጠን በአግባቡ መብታቸውን እንዲጠይቁና “ግርግር ለሌባ ያመቻል” እንዲባል ወንጀል የሚሰሩ ሰዎች አጋጣሚውን ተጠቅመው ሀብት እንዳይዘርፉ፥ በሴቶችና በደካሞች ላይ ጥቃት እንዳይደርስ ጥንቃቄ ይደረግ እንላለን።

የሃይማኖት መሪዎችና ሌሎች ተቆርቋሪ ኢትዮጵያውያን ለተፈጠረው ችግር መፍትሄ በማፈላለግ መቀራረብና መነጋገር እንዲኖር ማድረግ አለባቸው።

አብያተ ክርስቲያናትና የሃይማኖት ተቋማት ሰላምን፥እርቅንና ፍትህን ማወጅ ይጠበቅባቸዋል። በዚህ ሰአት ድምጻቸውን ካላሰሙ መቼ ሊያሰሙ ነው? ሰው ሲሞት እያዩ ዝም ማለት አግባብ አይደለም። ጸሎት ያለ ስራ ሙት ነውና።

“ቤተ ክርስቲያን ለፍትህና ለሰላም ድምጿን ካላሰማች የሚሊዮኖችን ከበሬታና እምነት ታጣለች፤የሰላምና የፍትህ ዓላማ የሚያነሳሳ ታሪካዊና ትንቢታዊ ሃላፊነቷን መወጣት አለባት፤ያን ጊዜ የሰው ልጆች ቤተ ክርስቲያን በጨለማ ላሉ ብርሃን መሆኗን ይረዳሉ”። ሬቨረንድ ማርቲን ሉተር ኪንግ

ዳንኤል ጣሰው
ከኢትዮጵያ ተነሺ አብሪ
ዋሽንግተን ዲሲ

The post የሰላምና የፍትህ ጥሪ በኦሮሚያ – ወንጌላዊ ዳንኤል ጣሰው appeared first on Zehabesha Amharic.

የህዝብ መነሳሳት ሁሉን አሳታፊ የስርት ለውጥ ለማምጣት እንዲችል ምን ይደረግ?

$
0
0

ታህሳስ 30፣ 2008 (ጃንዋሪ 9፣ 2016)

shengoሕዝብ መብቱን ሲነፈግ፣ያገሩ ክብርና አንድነት ሲደፈር፣በሰላም ሠርቶ ማደር ሲሳነው፣በኑሮ ውድነትና በሥራ አጥነት ሲወጠር፣ጭራሽ የመኖር ተስፋው ሲጨልም ከትዕግስትና ከመንፈሳዊው የትግል ዘዴ ከጸሎት ወጥቶ በአደባባይ በሚገለጽ ተቃውሞ ውስጥ ለመሳተፍ ወይም ነፍጥ አንስቶ ለመፋለም ይገደዳል፡፤ በዚህም የትግል ሜዳ ውስጥ ሲገባ  አምባገነን መንግስት ጉንጉን አበባ ይዞ እጁን ዘርግቶ እንደማይቀበለው ያውቀዋል።ከመንግሥት ሊሰነዘር የሚችለውን የበቀል አመጽ አይዘነጋውም። መሞት፣መቁሰል፣መደብደብ፣መታሰርና መንገላታት እንደሚኖር ገና ከጥዋቱ  ቢረዳም ድምጹን አጥፍቶ፣አንገቱን ደፍቶ ከመኖር ይልቅ የመጣውን ለመቀበል ቆርጦ ያልሞት ባይ ተጋዳይ እርምጃ  ይወስዳል።

ሕዝብ ለሚወስደውና ለሚከተለው የትግል አቅጣጫ መሰረቱ መዋናነት የህዝቡን ጥያቄ ለመስማት የማይሻ፣በራሱ እብሪት የሚመራ አምባገነን መንግሥት በስልጣን ላይ መኖሩ ነው።ሕዝቡ በተደጋጋሚ ለሚያሰማው እሮሮ መልስ ካላገኘ ደፍሮ አደባባይ መውጣቱ የማይቀር መሆኑ በተደጋጋሚ በአገራችንና በሌሎች አገሮች የታዬ ሂደት ነው።የሂደቱ መደምደሚያ የሚሆነው ይዋል ይደር እንጂ የሕዝቡን ጥያቄ የማይቀበሉ መንግሥታት ተወግደው ስልጣኑ በሌሎች እጅ መውደቅ ይሆናል።

በሕዝብ ትግል ሳቢያ ሊመጣ የሚችለው ለውጥና የሥልጣን እርክክቦሽ በተለያየ፣ማለትም በጠቃሚና በጎጂ አቅጣጫ ሊሄድ ይችላል፤

አንደኛ ሕዝብ በቅጡ እንዲደራጅና ሁሉም በትግሉ ተሳታፊና የውጤቱ የጋራ ባለቤት እንዲሆን፣ከጎጠኝነት የራቀ በልበ ሰፊነት በቀልን አሶግዶ በመቻቻል፣አገር አድኖ ሕዝብ ለማዳን ጥረት የሚያደርግ  ከሁሉም የተውጣጣ ትግሉን የሚመራ አካል ከተፈጠረ የሚመጣው ለውጥ ተስፋ ሰጭና ለሁሉም የሚጠቅም ይሆናል።

በሌላው አቅጣጫ ደግሞ በሕዝቡ ትግል ጀርባ የሕዝቡን መብት እና ጥያቄ እያነሱ ግን ሁሉም ሕዝብ የሚሳተፍበትን መድረክ እያጠበቡ በተወሰኑ ሃይሎች ብቻ የሚመራ፣ሌሎችን ያገለለና ያራቀ፣ በጠባብ ቡድናዊ ስሜትና የተወሰኑ ክፍሎቸ ጥቅም ላይ ያተኮረ አመራር በመፍጠር መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ባይቻልም እንደ አጋጣሚ ስልጣን ለመያዝ ዕድሉና ሁኔታው ቢፈቅድ የሚመጣው ለውጥ የስርዓት ሳይሆን የባለስልጣኖች መቀያየር ይሆንና ሕዝቡን በአዲስ ጉልበተኞች ለቀጣይ ስቃይና ስርዓት የሚዳርግ  ይሆናል።የዚህም ሂደት ውጤት በተደጋጋሚ በተለያዩ አገሮች ሲከሰት የታዘብነውና የምናውቀው ነው የዚህ አይነቱ ለውጥ በአገራችን በኢትዮጵያ እንዲከሰት የሚሻ ቀና ልቦናና ጤነኛ አይምሮ ያለው ኢትዮጵያዊ ይኖራል ብለን አንገምትም። ይህ ማለት ግን በዛ አይነት አሰራር  ውጤት ለማምጣት የተሰለፉ የሉም ማለት አይደለም፤ አሉ።መኖራቸውም በተደጋጋሚ በሚያደርጉት የአግላይነትና የተንኮል ሴራ የተረጋገጠ ነው።

በአገራችን በሁሉም አቅጣጫ ይብዛም ይነስም ሕዝባዊ ተቃውሞ በተለያየ ደረጃና መልክ ሲገለጽ ቆይቷል።አሁን የዛ የተለያየ የሕዝብ ተቃውሞ እየሰፋና እየጠነከረ መንግሥትን ከሚያሰጋበት ደረጃ ላይ የደረሰ ይመስላል።ግምቱን ወደ ውጤት ለማሻገርር የሚቀረው ነገር ቢኖር ትግሉን አቅጣጫ የሚያሲዝና የሚመራ ሃይል  ከመፍጠሩ ላይ ነው።አሁንም በየፊናው ተከፋፍለው የሚጮሁ ድርጅቶች አልጠፉም እንደውም ቁጥራቸው ጨምሯል።

በአሁኑ እየተጋጋለ በሄደው ሕዝባዊ ተቃውሞ ምክንያት መኖራቸው የማይታወቅና ጠፍተው የነበሩ አንዳንድ ድርጅቶች ሳይቀሩ አንገታቸውን ብቅ ብቅ በማድረግ ውድድር ውስጥ እየገቡበት ነው።፣ ትላንት ከትላንት ወዲያ ኢትዮጵያንና ኢዮጵያዊነትን ሲያወግዙ የተደመጡ ሃይሎች ሳይቀሩ ለሕዝብ አንድነትና ጥቅም የቆምን ነን እያሉ መናገር ከጀመሩበት ጊዜ ላይ ደርሰናል።

ቀድሞም ሆነ አሁን ወደፊትም ቢሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ መብት፣የአገር ሰላምና አንድነት ሊጠበቅ የሚችለው ሁሉም ተባብሮ መታገል ሲችል ብቻ እንደሆነ ከታሪካችንና ከውድቀታችን ልንማር ይገባል።በተናጠል ወይም በውጭ ሃይሎች እርዳታና ድጋፍ  በጥቂቶች የሚመጣ ለውጥ ከድጡ ወደ ማጡ እንጂ ወደተሻለ ስርዓት አይወስድም።

የሁሉም ዜጋ ጥያቄና ፍላጎት በዋናነት ተመሳሳይ ነው፤የአማራው ከኦሮሞው፣ከትግራዩ፣ከአፋሩ፣ከደቡቡ፣ ከጋምቤላው፣ከጉራጌው…ወዘተ የተለየ ፍላጎት የለውም።ሰብአዊ መብቱ፣የዜግነት መብቱ ተከብሮለት በአገሩ ሊያገኝ የሚገባውን ድርሻ አግኝቶ እሱም የድርሻውን አበርክቶ በክብር መኖር ነው የሁሉም ፍላጎት።የየክልሉ አርሶ አደር ጥያቄ የሚያርሰው መሬት ባለቤትነትን፣መፈናቀል እንዲቀርለት በገፍ የሚከፍለው ግብርና የማዳበሪያ ዋጋ እንዲቀነስለት፣ልጆቹን አስተምሮ ለማሳደግና ለቁም ነገር ለማብቃት በሀገሩ ጉዳይ ላይም ሙሉ ተሳታፊ መሆን እንጂ ሌላ ምኞትና ፍላጎት የለውም።የየብሔሩ ወጣትም እንዲሁ ተምሮ የመስራትና በአገሩ ተከብሮ እየኖረ የበኩሉን ለአገሩ ለማበርከት እንጂ ሌላ ምኞት የለውም።ሁሉም ከችግርና ከመከራ ኑሮ ተላቆ መብቱ ተከብሮለት በሰላም መኖርን ይሻል።ትልቅና የበለጸገች ኢትዮጵያ፣ለዜጎቿ የምትመች ኢትዮጵያ፣የእራሷን ጥቅምና ክብር፣ዳርድንበር አሳልፎ የማይሰጥ መንግስት ያላት ኢትዮጵያ እንድትኖረው የማይመኝና የማይፈልግ የለም።

ይህ  የጋራ ሕዝባዊ ፍላጎት ወደ ተግባር ሊተረጎም የሚቻለው ሁሉንም በአንድነት አስተባብሮ ሊመራ የሚችል፣የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስ ከሕዝብ ጋር አብሮ የሚመክር መንግስት ሲኖር ብቻ ነው።ያ መንግስት ደግሞ በጥቂቶቸ ፍላጎትና ጥረት የሚፈጠር ሳይሆን ሁሉም አውጣጥቶ በጋራ የሚፈጥረው በተለይም እርስበርስ  ማጋጨትን፣ መከፋፈልን “እኛና እነሱ “ የሚል አግላይ መርሆና መርሃግብር ማጠንጠኛው ያላደረገ  የህብረተቡንም አመኔታ ያገኝ ስርአትና መንግስት ሲፈጠር ብቻ ነው።

በተመሳሳይ በጠባብና አግላይ አስተሳሰብ የሚመራ ተለያይቶ የቆመ ቡድን የሚያስተጋባው ጥሪና  የሚመራው ትግል የሚያመጣው ለውጥ ካለውና ሁሉም ከሚጠላውና ከሚታገለው የወያኔ ስርዓት የተሻለ አይሆንም። ስለሆነም የዚህ አይነት የትግል ሂደት ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ በቅድሚያ አውቆ አደጋው እንዳይከሰት መከላከያ ማበጀት ለጋራ ሕዝባዊ ጥቅምና ደህንነት የሚያስቡ ሁሉ ድርሻና አላፊነት ነው።በዝምታና በቸልታ ከዳር ቆመው የሚታዘቡት ድራማ አይደለም፣ነገ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ላይ ሊደርስ የሚችለውን ማጤኑና መዘጋጀቱ በተግባርም የትግሉ ተሳታፊ በመሆን የወደፊቱን አቅጣጫ ለሁሉም በሚበጅ መንገድ እንዲሆን የነቃ ተሳትፎ ማድረግ አስፈላጊ ነው።

እውነት ሁሉም የተቃዋሚ ሀይሎች የአምባገነንነትን ማብቃት የሕዝቡን አብሮ መኖር፣የአገራችን ኢትዮጵያን አንድነትና ልዑላዊነት የምንሻ ከሆነ በአንድነት አብረን የጋራ ሃይል የሚፈጠርበትን ዘዴ ባሰቸኳይ መሻት ይጠበቅብናል። ያ ደግሞ  በቀጠሮ የምናስቀምጠው ወይም ለተወሰኑ ቡድኖች በጎ ፈቃድ የምንተወው ሳይሆን ለዛሬው ያገራችን ሁኔታ  ሁላችንም የምንሰጠው አስቸኳይና ትክክለኛ መልስ ይሆናል።

እስከዛሬ ድረስ አግላይና ተከፋፍሎ የሚገኝ የፖለቲካ አካሄድ በሀገራችን ህዝብ አንድነትና የነጻነት ትግል ላይ ያሰከተለውን አሉታዊ ተጽእኖ ሁሉም የሚረዳው ነው፡፡ ይህ ሁኔታ ሰፊ አለመተማመንና ጥርጣሬን በወገኖቻችን ውስጥ ዘርቶ ይገኛል። ለግፈኛው ስርአት እድሜ መራዘምም ረድቷል። ይህን ለመስበር እና መተማመንን እንደገና ለመገንባት ሰፊ ስራ መሰራት ይኖርበታል። ለዚህም የድብቅብቆሽ ፖለቲካ ተላቆ በትግስት በግልጽነታና ባርቆ አሳቢነት፤ በሰጥቶ መቀበል መንፈስ መስራት አስፈላጊ ነው።

ሰሞኑን በአሜሪካና በሌሎች የአውሮፓ ከተሞች ቁጥራቸውና ስማቸው የበዛ የፖለቲካና የብዙሃን ድርጅቶች ለየአገራቱ መንግሥታት የድጋፍ መጠየቂያ ሰልፍ ለማድረግ እየጣሩ መሆናቸውን እናያለን። ሽንጎም የዚሁ እንቅስቃሴ አከል በመሆን ይንቀሳቀሳል፡ ከድርጅት ጉድጓዱ ወጥቶ በአንድ ላይ በሰልፍ ድምጽን ማሰማቱ ተገቢና አስፈላጊ መሆኑ ቢታመንም ይህ ብቻ መፍትሔ ያመጣል ማለት ግን አይደለም። መፈትሔ እንዲመጣ፣ችግሩ እንዲወገድ ከተፈለገ በአደባባይ ለመውጣት የሚሹት የተለያየ ድርጅቶች ከሰልፍ ባሻገር በአገር ቤት ካሉት ድርጅቶች ጋር በመተባበር ትግሉን ሊመራና ሊያቀናጅ የሚችል ግብረሃይል መፍጠር ይገባቸዋል። በተቃዋሚው ጎራ ብቻ የተሰለፈው ሳይሆን በመንግሥታዊ ዘርፍም ውስጥ የተሰለፈ ግን ስርዓቱ መለወጥ አለበት ብሎ የሚያምን ዜጋ የዚሁ ሕዝባዊ ትግል  አካል ሊሆን ይገባዋል። የሰው ህይወት እስካላጠፋና ሕዝብ እስካልበደለ ድረስ በመንግስት መዋቅር ውስጥ ሰርተሃል ተብሎ ሊገለል አይገባም።ወንጀል የፈጸመውም ቢሆን በማስረጃ በሕጋዊ መንገድ ሊጠየቅ ይገባል እንጂ በደም ፍላት ጥቃት ሊደርስበት አይገባም። ብሄራዊ መግባባትና አገራዊ እርቅ ለነገ የማይባል ተግባር ነው፡ ያ ካልሆነ አሁንም ዞሮ ዞሮ ዜሮ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ ለዚህ ወሳኝነት ላለው አደረጃጀትና  ትግል  ተባባሪና ደጋፊ መሆኑን አሁንም በድጋሚ ሊገልጽ ይወዳል።

ለእውነተኛ ለውጥ በመከባበር ላይ የተመሰረተ አንድነት ግንባር ወሳኝ ነው።በጥቂት የውጭ አገር መንግስታትና ድርጅቶች እርዳታና ድጋፍ ሃይል አደራጅቶ ሥልጣን ለመያዝ ከመሯሯጥ ይልቅ በራስ ሕዝብ ፍቃድ፣ተሳትፎና ድጋፍ ለውጥ ማምጣት ከመቅለሉም በላይ የሚያስከብርና የሚያኮራ ነው።

የምንሻው ለውጥ ከሳት ወደ እረመጥ ወይም  ከድጡ ወደማጡ እንዳይሆን እንጠንቀቅ!!!

ለመሰረታዊ ለውጥ ሁሉንም ያሳተፈ የተቀነባበረ የጋራ ትግል ወሳኝ ነው!!

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ

The post የህዝብ መነሳሳት ሁሉን አሳታፊ የስርት ለውጥ ለማምጣት እንዲችል ምን ይደረግ? appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live