Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

በዛሬዉ እለት በአንዋር መስጊድ የተከሰተዉን ፍንዳታ አስመልክቶ የተዘጋጀዉን ፕሮግራም ያዳምጡ። –ሳዲቅ አህመድ


በወገኖቻችን ላይ የሚካሄደው አፈናና ጭፍጨፋ ባስቸኳይ ይቁም –ሸንጎ

$
0
0

The post በወገኖቻችን ላይ የሚካሄደው አፈናና ጭፍጨፋ ባስቸኳይ ይቁም – ሸንጎ appeared first on Zehabesha Amharic.

የአርበኞች ግንቦት ሠራዊት በሕወሓት አገዛዝ የጦር ኃይል ላይ የሽምቅ ጥቃት ሰንዝሬ ድልን ተቀዳጀሁ አለ

$
0
0

“አርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በህወሓት አገዛዝ የጦር ኃይል ላይ ጥቃት በመሰንዘር ከፍተኛ ድልን ተቀዳጀ!!” ሲል ንቅናቄው ባሰራጨው ዘገባ ተደጋጋሚ የሽምቅ ውጊያዎችን በማድረግ የህወሓትን መከላከያ ሰራዊት፣ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ጦር አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት የህዝብ አለኝታነቱን እያስመሰከረ ይገኛል ብሏል::
AG7

እንደ ድርጅቱ መግለጫ ከሆነ “ባለፈው ሳምንት ህዳር 21/2008 ዓ.ም ጀግናው ሰራዊታችን በዋልድባ በጠላት ሰራዊት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን አሁን ደግሞ ከዋልድባ ወደ አዲ-አርቃይ በመወርወር ማክሰኞ ህዳር 28/2008 ዓ.ም አዲ-አርቃይ ላይ ከወያኔ መከላከያ ሰራዊትና የሚሊሻ ታጣቂ ኃይል ጋር ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ እስከ ምሽቱ 1፡00 ለሶስት ተከታታይ ሰዓታት የዘለቀ ከባድ ውጊያ በማድረግ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የጠላት ጦር በመግደልና በማቁሰል ድልን ተጎናፅፏል፡፡” ይላል::

ድርጅቱ መረጃውን በመቀጠል:-
“ሰራዊታችን በጦር ሜዳ ውሎው፣ ከጥልቅ የሀገር ፍቅር ስሜት በተቀዳ ወኔ፣ እስከ አፍንጫው ታጥቆ የመጣውን የህወሓትን መከላከያ ሰራዊትና የሚሊሻ ታጣቂ ኃይል በጦር ሜዳው ላይ በጥይት ቆልቶና አሳሮ አስቀርቶታል፡፡
ፍልሚየው በማግስቱ ረቡዕ ህዳር 29/2008 ዓ.ም ከጥዋቱ 1፡00 ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ሰዓታት ማለትም እስከ ረፋዱ አራት ሰአት በዚያው አዲ-አርቃይ ላይ የቀጠለ ሲሆን ፣ ወያኔ ከሌላ ቦታ አጓጉዞ ለጦርነት ያሰለፈውን ተጨማሪ የመከላከያ ሰራዊት ጀግኞቹ የአርበኞች ግንቦት ሰባት የነፃነት ፋኖዎች የጠላትን ጦር ድባቅ መትተውታል፡፡” ብሏል::

አርበኞች ግንቦት 7 እንዳስታወቀው ለነፃነት የሚደረገው ጦርነት አሁንም ቀጥሏል፡፡ የወያኔ ባለስልጣናት የሚይዙት የሚጨብጡት አጥተው በተለይ በኤርትራና በኢትዮጵያ መካከል የሚገኘውን ድንበር የበለጠ ከፍተኛ ቁጥር ባለው ሰራዊት ለመዝጋት ቢሯሯጡም ድንበር ላይ የተመደበው ወታደር ከወያኔ እየከዳ የነፃነት ትግሉን ከነትጥቁ እየተቀላቀለ ይገኛል፡፡ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሰራዊት በተቀዳጀው ድል የአካባቢው ህዝብ ጮቤ እየረገጠ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ይህ በ እንዲህ እንዳለ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት የአርበኞች ግንቦት 7 ወታደሮች የሆኑ ጥቃት ሊያደርሱ ወደ ከተማ ሊገቡ ሲሉ በሰሜን በኩል ይዣቸዋለሁ ሲል በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ ከመናገሩ ውጭ ስለ ተደረገ ውጊያ ያለው ነገር የለም::

The post የአርበኞች ግንቦት ሠራዊት በሕወሓት አገዛዝ የጦር ኃይል ላይ የሽምቅ ጥቃት ሰንዝሬ ድልን ተቀዳጀሁ አለ appeared first on Zehabesha Amharic.

ተቃውሞው በተለያዩ ከተሞች ቀጥሏል |አምቦ ዛሬም የወጣቶች ሕይወት አለፈ |በተለያዩ ከተሞች የተደረጉትን ተቃውሞዎች ዘገባ ይዘናል

$
0
0

ambo

(ዘ-ሐበሻ) መነሻውን የአዲስ አበባን አዲሱ ማስተር ፕላን አድርጎ ወደ ሌሎች የመብት ጥያቄዎች የተሸጋገረው የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞ ዛሬም በተለያዩ ከተሞች እንደቀጠለ ነው:: ዛሬ በአምቦ ከተማ ቀበሌ 06 አካባቢ በተነሳው ተቃውሞ የመንግስት ወታደሮች በነዋሪው ላይ እርምጃ መውሰዳቸው ተሰምቷል:: አምቦ ልክ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ የወጣቶች ደም አደባባይ ላይ የፈሰሰባት ሲሆን በዛሬው ተቃውሞ የሁለት ወጣቶች ሕይወት እንዳለፈ እየተነገረ ነው:: ለዘ-ሐበሻ መረጃ ያደረሱት ወገኖች እንዳሉት አምቦ ከተማ ውስጥ በተለይ በቀበሌ 06 የአጋዚ ጦር እየወሰደ ያለው እርምጃ የሚዘገንን ነው::

የተማሪዎቹ ተቃውሞ ዛሬም በተለያዩ ከተሞች ቀጥሏል:: በአጫጭሩ የየከተማውን ውሎ እናስቃኛችሁ::

ሰሜን ሸዋ

በፍቼ ከተማ በተደረገ ተቃውሞ ፖሊስ እርምጃ ከመወሰዱም በላይ ከ50 በላይ የአካባቢውን ነዋሪ እንዳሰረ ተሰምቷል:: የአካባቢው ነዋሪ እስሩም ግድያውም አያቆመንም በሚል ተቃውሞው ላይ በርትቶበታል:: በዚሁ በሰሜን ሸዋ በዋራ ጃርሶ ወረዳ ቱሉ ሚልኪ ከተማ በወታደሮች ተከባለች::

ምዕራብ ሸዋ
በወንጪ ከተማ በተደረገ ተቃውሞ አጋዚ ጦር ወደ ሕዝቡ ተክሶ ሁለት ሰዎች ዛሬ መግደሉ ተሰምቷል:: የሟቾች ማንነት እየተጣራ ሲሆን አካባቢው በውጥረት ውስጥ ነው::
ምዕራብ አሪሲ (አዳባ)

በምዕራብ አሪሲ በተደረገ ከፍተኛ ተቃውሞ ወደ ሕዝብ የተኮሱት የአጋዚ ጦር ወታደሮች 2 ሴት ተማሪዎችን ማቁሰላቸው ተሰምቷል:: የአንዷ ወጣት ስም ጀምሊና ሁሴን ቅባቶ እንደምትሰኝም ለማወቅ ተችሏል:: በሌላ በኩልም በጋርደሎ ሚስራ በተደረገው ተቅውሞ ገበሬዎች እና አስተማሪዎችም የተማሪዎቹን ተቃውሞ ተቀላቅለውታል::
በዶዶላም ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ ተነስቷል::

አዳማ

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ በአዳማ የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎ በርካታ ወጣቶች መታሰራቸው ተሰማ:: ከነዚህም መካከል የአዳማ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆነው ታደሰ ቱፋ መታሰሩ ታውቋል::

Jima University

ጅማ
የጅማ ዩኒቨርሲቲ በታጠቁ የአጋዚ ጦር ወታደሮች መከበቡ ታወቀ:: የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተጫኖ ኮሌጅ ተማሪዎች ምግብ አንበላም የሚል ተቃውሞ በማንሳታቸው ዋናው ካምፓስ በወታደሮች መከበቡና አለመረጋጋቱ እንዳየለ ተሰምቷል::

ምስራቅ ሃረርጌ

በቃርሳ ወረዳ ላነጌይ ከተማ የአካባቢው ነዋሪና ተማሪዎች በአንድ ላይ በመቀላቀል ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ ሲያሰሙ መዋላቸው ተሰምቷል:: ምስራቅ ሃረርጌ ለነጌይ ከተማ ውጥረት ውስጥ ነች::

ወለጋ

በወለጋ ዩኒቨርሲቲ ፖሊስና የደህንነት ኃይሎች በሰላማዊ ሰልፎች ላይ ተሳትፈዋል ያሏቸውን ተማሪዎችን አንድ በአንድ እየወሰዱ በማሰር ላይ እንደሚገኙ ተሰማ:: ተማሪዎች ራሳቸውን ለመከላከል እየሞከሩ ሲሆን እስካሁን ከ200 የማያንሱ ተማሪዎች መታሰራቸው ተዘግቧል::

ምዕራብ ሃረርጌ

በም ዕራብ ሃረርጌ አሰቦት ከተማ በወጣቶች ተቃውሞ ሙሉ ቀን ውጥረት ውስጥ መዋሏ ተዘገበ:: ተማሪዎቹ ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በተጨማሪ ላለፉት 25 ዓመታት በስር ዓቱ እየደረሰባቸው ያለውን ጭቆናና በደል ሲያወግዙ እንደነበር የአይን እማኞች ይናገራሉ::

The post ተቃውሞው በተለያዩ ከተሞች ቀጥሏል | አምቦ ዛሬም የወጣቶች ሕይወት አለፈ | በተለያዩ ከተሞች የተደረጉትን ተቃውሞዎች ዘገባ ይዘናል appeared first on Zehabesha Amharic.

ሰልፈኞች በምዕራብ ሸዋ ግንደበረት የመለስ ዜናዊን ፓርክ በእሳት አነደዱት –አጋርፋና ወሊሶ በተኩስ ድምጽ ተናውጠዋል

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) እየተካረረ የመጣውና በኦርሚያ ክልል ትናንሽ ከተሞችን ጨምሮ እየተደረገ ያለው ሕዝባዊ ቁጣ በኦሮምያ ክልል በምእራብ ሸዋ ዞን በአቡነ ግንደበረት ደርሶ በዚሁ ከተማ ውስጥ ያለውንና ካለ ሕዝቡ ፍላጎት በሟቹ ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ስም ተሰይሟል ያሉትን ፓርክ አቃጠሉት::

abune gindeberet

በምእራብ ሸዋ አቡነ ግንደበረት ከተማ የሕዝቡ ቁጣ ገንፍሎ ከወጣ ወዲህ በስፍራው የተሰማራው የአጋዚ ኮማንዶ እንኳ ሊያስቆመው እንዳልቻለ የገለጹት ምንጮች ፓርኩን የሟቹን የቀድሞው ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊን ስም በእርግማን መልክ እያነሱ ሲያቃጥሉት እንደነበር ምንጮች ዘግበዋል::

ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በአምቦ አሁንም አለመረጋጋቱ ያለ ሲሆን በወሊሶ ዛሬም በተፈጠረው ግርግር ሰዎች እየሞቱ መሆኑን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ይጠቁማል:: በወሊሶ ንግድ ቤቶች ሱቆቻቸውን ዘግተዋል:: አካባቢው በተቃውሞ እና በአጋዚ ጦር ጥይት ተናውጣለች::

በአጋርፋም ከፍተኛ ተቃውሞ መነሳቱ ተሰምቷል:: አካባቢው በጥይት ድምጽ እየተናወጠ ነው::

The post ሰልፈኞች በምዕራብ ሸዋ ግንደበረት የመለስ ዜናዊን ፓርክ በእሳት አነደዱት – አጋርፋና ወሊሶ በተኩስ ድምጽ ተናውጠዋል appeared first on Zehabesha Amharic.

በምዕራብ ሸዋ የተለያዩ መንደሮች ከ100, 000 ሕዝብ በላይ ለተቃውሞ አደባባይ ወጣ –ፎቶዎች ይናገራሉ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በምዕራብ ሸዋ በጊንዶ ከተማና በአካባቢዋ የሚገኙ መንደሮች በአጠቃላይ ከ100 ሺህ ህዝብ በላይ ወጥቶ ስርዓቱን በመቃወም ላይ ይገኛል:: ዛሬ ዴሴምበር 12, 2015 የተደረገውን ተቃውሞ ትላልቅ እናት እና አባቶች ሳይቀሩ ተቀላቅለውታል::

በጊንዶ ከተማ የተለያዩ ቃጠሎች በየአደባባዩ እየታዩ ሲሆን የአጋዚ ጦር አካባቢውን በሁለት አቅጣጫ እንደከበበው የተገኘው መረጃ ይጠቁማል:: ቀጣይ ፎቶዎች ይናገራሉ::

ከዚህ ቀደም በነበረው የዘ-ሐበሻ ዜና በጅማ ከተማ የተፈጠረው ተቃውሞ አሁንም እንዳልበረደ ከስፍራው የደረሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ::

በባሌ ደንበል ታውን የተነሳው ተቃውሞም እንደቀጠለ ነው::

Ginbo mom

gGinbo Ginbo 1

The post በምዕራብ ሸዋ የተለያዩ መንደሮች ከ100, 000 ሕዝብ በላይ ለተቃውሞ አደባባይ ወጣ – ፎቶዎች ይናገራሉ appeared first on Zehabesha Amharic.

‹‹ሰልፍ ለመጠበቅ የፖሊስ ዕጥረት አለብን አሉን፤ ሰው ለመደብደብ ግን የፖሊስ እጥረት የለባቸውም›› አቶ በቀለ ገርባ – [የኤልያስ ገብሩ ዘገባ ስለ አዳማ]

$
0
0

bekele gerba
ዛሬ አዳማ በጸጥታ ሃይሎች ተወጥራ መዋሏን ተመልክቻለሁ
ከናዝሬት አዲስ አበባ ሲገባ ጥብቅ ፍተሻ እየተደረገ ይገኛል
—-


ትናንት እና ዛሬን ያሳለፍኩት በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ዋና ከተማ በሆነችው አዳማ ከተማ ነበር፡፡
ትናንት ከአቶ በቀለ ገርባ ጋር በአዩ ኢንተርናሽናል ሆቴል በአካል ተገናኝተን፣ ከሁለት ሰዓታት በላይ ተጨማሪ ቃለ ምልልስ (ለ‹‹አዲስ ገጽ›› መጽሔት) አድርገን እና በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ኢ-መደበኛ ሀሳቦችን በስፋት ተወያተናል፡፡


አቶ በቀለ ነጻ አመለካከት ያላቸው፣ ሀሳባቸውን በቀላሉ ማሰረዳት የሚችሉ፣ ነገሮችን በተለያዩ ቀላል መንገዶች ማስረዳት የሚመርጡ፣ ሰውን በአስተውሎት የሚያዳምጡ፣ በጨዋታ መሀል ቀልዶች ጣል የሚያደርጉና ጨዋነትን የተላበሱ ኢትዮጵያዊ መሆኑን ተረድቻለሁ፡፡ በተለይ አቶ አባዱላ ገመዳን በሚመለከት የተናገሯትን ቁም ነገር አዘል ቀልድ መቼም ቢሆን አልረሳትም፡፡ በድንገት ስቄያለሁ፤ አብረንም ስቀናል፡፡

File Photo (Adama City)

File Photo (Adama City)


……በዛሬው ዕለት መድረክ በአዳማ የጠራውን ሰልፍ እንደጋዜጠኛ ለመመልከት ከጥዋቱ 02፡30 ጀምሮ ከተማዋን ለመቃኘት ጥረት አድርጌአለሁ፡፡ በጥዋቱ ወደከተማዋ መግቢያ አካባቢ፣ በዋናው መንገድ ግራና ቀኝ፤ ዱላ የያዙ ፖሊሶችን ማየት ጀምሬ ነበር፡፡ ከቁርስ በኋላ፣ ሠዓቱ ገፋ ብሎ፣ ቀኑ መረፋፈድ ሲጀምር፣ በከተማዋ በርካታ ፖሊሶችን መመልከት በጣም ቀላል ነበር፡፡ ዋናውን መንገድ በእግሬ በመጓዝም ስቃኘው፣ የፖሊሶች ቁጥር በጣም እየጨመረ መጣ፡፡ ከዋናው መንገድ ግራና ቀኝ ወደውስጥ በሚስገቡ የአስፋልትና ፒስታ መንገዶች ውስጥም ፖሊሶች ተሰብስበው አካባቢውን በንቃት ይከታታላሉ፡፡ ሁለት የፖሊስ መኪኖች፣ በአንዱ መኪና ላይ አድማ በታኝና ከላይ እስከታች የመከላከለያ ጭንብል የለበሱ (ቁጥራቸው 8 የሚሆን)፣ መሳሪያ የታጠቁ ወታደሮች በግራ በቀኝ መሳሪያቸውን አነጣጣረው በመቀመጥ በዋና መንገዱ ላይ በፍጥነት ይሽከረከራሉ፡፡ በሌላኛው መኪና ደግሞ ወታደራዊ ልብስ የለበሱ አልሞ ተኳሾች (8 የሚሆኑ) ተጭነው በሁለት ረድፍ እንደተቀመጡ መሳሪያቸውን በማነጣጠር ከተማዋን ይዞሯት ነበር፡፡ እነዚህን ወታደሮች በጥቂት ሜትሮች ርቀት ላያቸው ችያለሁ፡፡ እጃቸው የመሳሪያ ቃታ ላይ አርፎ ፊታቸው ቅጭም ብሎ እንደተኮሳተረ ነበር፡፡ በግሌ የጭካኔ ስሜት በገጽታቸው ላይ አንብቤያለሁ፡፡ ሌሎች የፖሊስ እና የመንግሥት መ/ቤት መኪኖችም ፖሊሶችን ጭነው ከተማዋን ሲቀኙ አስተውያለሁ፡፡
ዱላ ሳይሆን ‹‹ወፍራም አጠና የያዙ›› ብል የሚቀለኝ በርካታ ፖሊሶች አዳማን ከረፋዱ ጀምሮ እስከቀትር ድረስ ሲያስጨንቋት ነበር፡፡ የጎማ ዱላ የያዙ ፖሊሶች ቁጥራቸው አነስተኛ የነበረ ሲሆን ፖስታ ቤት አካባቢም ፌሮ ብረት የያዘ አንድ ፖሊስ በአይኔ ተመልክቻለሁ፡፡ ሰልፉ ይደርግበታል ወደተባለው ቦታ መግባት ግን እጅግ አስቸጋሪ ነበር፡፡


የሰልፉ አንዱ አስተባባሪ የነበሩትን አቶ በቀለ ገርባን ቀጥር አካባቢ በሞባይል ስልካቸው ላይ አገኘኋቸውና ስለጉዳዩ ጠየኳቸው፡፡ ሰልፉ መበተኑን ከጠቆሙኝ በኋላም፣ ‹‹ሰልፍ ማድረግ አትችሉም፡፡ አልተፈቀደላችሁም፡፡ ሰልፉን የሚጠብቅ በቂ የፖሊስ ሃይል የለንም፡፡ ከላይ የለበስከውን ቲ-ሸርት አውልቅ …›› ተብዬ ነበር በማለት አስረዱኝ፡፡ አያይዘውም ‹‹ሰልፍ ለመጠበቅ የፖሊስ ዕጥረት አለብን አሉን፤ ሰው ለመደብደብ ግን የፖሊስ እጥረት የለባቸውም›› ሲሉ በከተማው አስተዳደር ድርጊት ማዘናቸውን ነገሩኝ፡፡


…ከሰዓት በኋላ በከተማዋ የነበሩት ፖሊሶችና ወታደሮች ቁጥር ቢያንስም አልፎ አልፎ በከተማዋ ጎዳናዎች ላይ ይታዩ ነበር፡፡ ከወዳጄ ፍቃዱ በቀለ ጋር አመሻሽ 11፡00 ሰዓት ገደማ በአዳማ አዲስ አበባ የፍጥነት መንገድ ከአዳማ ተጉዘን የአዲስ አበባውን መግቢያ መንገድ እንደጨረስን፣ በርካታ መኪኖች ተደርድረው ሁሉም ሳፋሪዎች ከመኪና እየወረዱ ሲፈተሹ ተመለከትን፡፡ እኛም የተሳፈርንበት መኪናም ቆሞ ከወረድን በኋላ ተፈትሸን በመግባት ሲመሽ አዲስ አበባ ገብተናል፡፡


እንግዲህ በሁለት ቀናት በአዳማ በነበረኝ ቆይታ እንደጋዜጠኛ የታዘብኩትን በአጭሩ እንዲህ አስነብቤያችኋለሁ፡፡
መልካም ምሽት

The post ‹‹ሰልፍ ለመጠበቅ የፖሊስ ዕጥረት አለብን አሉን፤ ሰው ለመደብደብ ግን የፖሊስ እጥረት የለባቸውም›› አቶ በቀለ ገርባ – [የኤልያስ ገብሩ ዘገባ ስለ አዳማ] appeared first on Zehabesha Amharic.

Sport: የዩሮ 2016 ድልድል ወጣ (የምድብ ድልድሉን ይዘናል)

$
0
0

euro 2016

(ዘ-ሐበሻ) በፈረንሳይ ከጁን 10 እስከ ጁላይ 10, 2016 ዓ.ም ለሚደረገው የአውሮፓ ዋንጫ የምድብ ድልድል ዛሬ ዲሴምበር 12, 2015 ዓ.ም ወጣ:: በዚህም መሠረት

በምድብ 1
– ፈረንሳይ
– ሩማንያ
– አልባኒያ
– ስዊዘርላንድ

በምድብ 2
– እንግሊዝ
– ሩሲያ
– ዌልስ
– ስሎቫኪያ

በምድብ 3

– ጀርመን
– ዩክሬን
– ፖላንድ
– ሰሜን አየርላንድ

ምድብ 4

– ስፔን
– ቼክ ሪፐብሊክ
– ቱርክ
– ክሮሺያ

ምድብ 5
– ቤልጂየም
– ጣሊያን
– ሪፐብሊክ አየርላንድ
– ስዊድን

ምድብ 6
– ፖርቱጋል
– አይስላንድ
– ኦስትሪያ
– ሃንጋሪ

በ እጣ ተደልድለዋል::

በጥሎ ማለፍ በቼክ ሪፐብሊክ 3ለ2 የተሸነፈችው ሆላንድ በዘንድሮው የአውሮፓ ዋንጫ  እናያትም:: በወጣው ድልድል ስፔን; ቼክ ሪፐብሊክ; ቱርክና ክሮሺያ የተደለደሉበት ምድብ እና ቤልጂየም; ጣሊያን; ሪፐብሊክ አየርላንድ እና ስዊድን የተደለደሉባቸው ምድቦች ከባድ ምድቦች ተብለው ተወስደዋል::

The post Sport: የዩሮ 2016 ድልድል ወጣ (የምድብ ድልድሉን ይዘናል) appeared first on Zehabesha Amharic.


የአርበኞች ግንቦት 7 የመጀመሪያ ምክርቤት ስብሰባውን ካጠናቀቀ በኋላ መግለጫ አወጣ

$
0
0

nega 2 nega 3 nega

መግለጫ

አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ከህዳር 26 ቀን 2008 ዓ.ም እስከ ህዳር 30 ቀን 2008 ዓም ድረስ ሰራዊቱ በሚገኝበት የትግል ቦታ የመጀመሪያውን የምክር ቤት ስብሰባ አድርጎ በስኬት አጠናቋል::
ይህ ስብሰባ የቀድሞዎቹ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባርና ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ተዋህደው አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ከተሰኘ ወዲህ የተደረገ የመጀመሪያው የምክር ቤት ስብሰባ ነው::
ይህ ስብሰባ፦
1. ውህደት ከተደረገበት ከጥር 2 2007 ዓ.ም ወዲህ የስራ አስፈፃሚውን የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አድምጧል፤
2. ከውህደት ወዲህ ንቅናቄው የፈጸማቸውን ተግባራት በጥልቀት መርምሯል፤
3. የንቅናቄውን ህገ-ደንብና አሰራሮችን መርምሮ ማሻሻያዎችን አድርጓል፤
4. የምክር ቤቱ ልዩ ልዩ ኮሚቴዎችን አቋቁሟል
5. ተተኪና ወጣት የአመራር አባላት ምክር ቤቱ ውስጥ እንዲካተቱ አደርጓል፤
6. የሃገራችንን የወቅቱን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ሁኔታዎች በጥልቀት መርምሯል፤
7. በወቅቱ ሁኔታዎች ጥናት ላይ ተመርኩዞ የወደፊት የትግል አቅጣጫውን ቀይሷል፣ ግልጽ የሆነ የትግል ስትራቴጅ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፤
8. ከስብሰባው በኋላ መከናወን የሚገባቸውን ተግባራት ቅደም ተከተል አውጥቶ ለስራ አስፈጻሚው መመሪያዎችን አስተላልፏል፡፡
የአርበኞች ግንቦት 7 ምክር ቤት፣ የኢትዮጵያ ህዝብ የህወሓትን አምባገነን አገዛዝ አስወግዶ በምትኩ ፍትህ የነገሰባት፣ የዜጎች እኩልነት የተረጋገጠባት፣ ዴሞክራሲያዊት አገር ለመገንባት የሚያደርገውን ትግል በግንባር ቀደምትነት ለማስተባበርና ለመምራት ከመቸውም ጊዜ በላይ በቁርጠኝነት መነሳቱን ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ይገልጻል::
አርበኞች ግንቦት 7 የኢትዮጵያ ህዝብ ትግል ወደ አዲስ ደረጃ ተሸጋግሯል ብሎ ያምናል:: ለውጥ ፈላጊ ኢትዮጵያዊያን ዜጎችና ድርጅቶች በሙሉ በሚያመቻቸው መንገዶች እየተደራጁ ከንቅናቄያችን ጋር ግንኙነት በመፍጠር በጋራ ትግል አምባገነኑን ወያኔ ከስልጣን እንድናስወግድና በምትኩ ፍትህ፣እኩልነትና የሃገርን አንድነት የሚያረጋግጥ የፖለቲካ ስርዓት እንድናቋቁም ጥሪ ያደርጋል::
ድል ለ ኢትዮጵያ ህዝብ!

The post የአርበኞች ግንቦት 7 የመጀመሪያ ምክርቤት ስብሰባውን ካጠናቀቀ በኋላ መግለጫ አወጣ appeared first on Zehabesha Amharic.

አምባሳደር ግርማ ብሩ በቺካጎ ከተማ በኢትዮጵያውያን ብርቱ ተቃውሞ ሲደርስበት የሚያሳይ ቪዲዮ

ኢትዮጵያውያን በቺካጎ በወያኔ የተጠራውን ስብሰባ ሳይካሄድ በሕብረት በተኑት |ሐተታ ከቪዲዮ ጋር

$
0
0

girma biruu

(ዘ-ሐበሻ) በቺካጎ የወያኔ ”የስለላ አምባሳደር እና የደህንነት ሰራተኛ” ሆኖ እንዲያገለግል የታጨውን አቶ በፍቃዱ ረታ ለመሾም በቺካጎ ትሩማን ኮሌጅ ውስጥ የነበረው ስብሰባ የኢትዮጵያ ትውልድ ባላቸው ዜጎች መበተኑ ተሰማ::

ለዚህ የአምባሳደርነትት ሽልማት የመጡት በዲሲ የሚገኙት የወያኔ አምባሳደር የሆኑት አቶ ግርማ ብሩ ሲሆኑ አንድም ንግግር ሳያደርጉ በኢትዮጵያ የሚገኘውን ድርቅ እና በተማሪዎች ላይ የተፈጸመውን አስከፊ ግድያ እስካልቆመ እና የሚላላኩለት መንግስታቸው ከስልጣን እስካልወረደ ድረስ ማንም ሰው አምባሳደርም ሆነ ኢትዮጵያዊ ነን ብለው የማይወክሉበትን ኢትዮጵያዊነት ሊያሳዩ አይችሉም በማለት ስብሰባው እንዲበተን አድርገዋል::

አቶ በፍቃዱ እረታ በቅጽል ስማቸው (ስልሳ ጎራሽ) እየተባሉ የሚጠሩት እኝህ ግለሰብ በችካጎ ከተማ የወረዳ 46 የአልደርማንነት ተወዳዳሪ ለመሆን ሲጥሩ የነበረ ሲሆን ሳይሳካላቸው በዝረራ የወደቁ እና ከዚያም በሁዋላ በወያኔ መደብ ላይ የልጥቀምህ ጥቀመኝ ስራ የሚሰሩ አገልጋይ መሆናቸውን ከቺካጎ የኦሮሞ ማህበረሰብ ደረሰን ዘገባ ያመለክታል::

ይህን አይነት የተቃውሞ ሰልፍ በወያኔ መንግስት ላይ በችካጎና አካባቢዋ ሲደረግ የመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን በተለያዩ አጋጣሚዎች ህብረተሰቡ ወያኔ የሚያደርገውን የቺካጎ ስብሰባ በአጽንኦ ከመመልከታቸውም በላይ አንድም ነገር የማያደርጉ ዜጎች የነበሩ ሲሆን በአሁን ሰአት በሃገሪቱ ላይ እየደረሰ ያለው አስከፊ አገዛዝ ግን ቁጣቸውን ሊቀሰቅሳቸው እንደቻለ የዚህ የተቃውሞ ሰልፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ገልጾአል።

አቶ በፍቃዱ ረታ ለአልደርማንነት በ2011 በችካጎ እና አካባቢዋ የተወዳደሩ ሲሆን ከዚያም በፊት የወያኔ መንግስት የገለልተኛ የምርጫ አጣሪ ኮሚቴ ብሎ ጠርቷቸው; በአዲስ አበባ በመሄድ; “የወያኔ መንግስት ፍትሃዊ እና የተሳካ ምርጫ አድርጓል በማለት በኢትዮጵያ ውስጥ አንድም የተገደለ ዜጋ የለም” ብለው የሸመጠጡ ሰው ናቸው ተብሎ ይነገርላቸዋል::

The post ኢትዮጵያውያን በቺካጎ በወያኔ የተጠራውን ስብሰባ ሳይካሄድ በሕብረት በተኑት | ሐተታ ከቪዲዮ ጋር appeared first on Zehabesha Amharic.

“ትግሉን ከዳር ለማድረስ የጋራ አመራር የሚኖርበትን ሁኔታ እየተወያየንበት ነው”–ጃዋር መሀመድ ልዩ ቃለምልልስ ከሕብር ራድዮ ጋር

$
0
0

Jawar Mohamed
(ዘ-ሐበሻ) አክቲቭስት ጃዋር መሐመድ ከላስቬጋስ ከተማ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚሰራጨው ሕብር ራድዮ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ በሰሞኑ የኦሮሞ ተማሪዎች ባነሱት የመብት ጥያቄና በየከተማው እየተቀጣጠለ በሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ዙሪያ ቃለ ምልልስ አደረገ:: “ትግሉን ከዳር ለማድረስ ሁሉንም ወገን ያሳተፈ የጋራ አመራር የሚኖርበተን ሁኔታ እየተወያየንበት ነው” ብሏል::

ሙሉውን ቃለምልልስ በላስቬጋስ ሰዓት አቆጣጠር ዛሬ ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት ጀምሮ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች ማዳመጥ ይቻላል:: ቃለምልልሱ ካመለጣችሁ ከሰዓታት በኋላ ሙሉን በዘ-ሐበሻ ድረገጽ ላይ እንቀዋለን::

በአሜሪካና ካናዳ ለምትኖሩ በ712 -432-8451
በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140
በአውስትራሊያ 0280725172 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል።

ከጃዋር በተጨማሪ ጋዜጠኛና አክቲቭስት ሳዲቅ አህመድም በሕብር ራድዮ ላይ ታገኙታላችሁ:: ሳዲቅ በወቅቱ ትግል ዙሪያ “ኢትዮጵያውያን ይህ ወርቃማ ጊዜ እንዳያልፈን መተባበር አለብን” ሲል ጥሪውን አቅርቧል::

The post “ትግሉን ከዳር ለማድረስ የጋራ አመራር የሚኖርበትን ሁኔታ እየተወያየንበት ነው” – ጃዋር መሀመድ ልዩ ቃለምልልስ ከሕብር ራድዮ ጋር appeared first on Zehabesha Amharic.

“ጎንደር ቋራ አካባቢ ህዝባችንን ለመከፋፈል የሚወስደው እርምጃ ጊዜ የሚሰጠው ባለመሆኑ አፋጣኝ አጸፋዊ እርምጃ ወስደናል”–አማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ

$
0
0

Amara Democratic Force

ከአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ (አዴሃን)የተሰጠ መግለጫ

የወያኔ ዘረኛው ቡድን በጎንደር ቋራ አካባቢ ህዝባችንን ለመከፋፈል በሚወስደው እርምጃ ጊዜ የሚሰጠው ባለመሆኑ አፋጣኝ አጸፋዊ እርምጃ ወስደናል፡፡
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ(አዴሃን) ከተመሰረተበት ዋና አላማ አማራን ከጥፋት ለመታደግ በመሆኑ ይህ ከሰሞኑ አንድን ህዝብ በመክፈል ነጣጥሎ ለማጥቃት ሲራወጡ የነበሩ ህወሓት እና የህወሓት ቅጥረኞች ላይ እርምጃ ወስደናል።

በዘረኛው የወያኔ ቡድን በመላው ኢትዮጵያ የሚያደርሰው ማፈናቀል፡ ማጥፋት፡መግደል፡ወዘተ አልበቃ ብሎት አሁን ደግሞ ድብቅ ሴራዉን በመርዝ በመለወስ እርስ በርስ ለማፋጀት የሚያደርገው ሙከራ መቼም ቢሆን አይሳካለትም። ይህን የህውሓት የረከሰ አላማ የሚፈጽም፡የሚያስፈጽም በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የተባበረ ከተጠያቂነት አይድንም።ከሰሞኑ በቋራና መተማ አካባቢ የህውሓት ባለ ሃብቶች የዚህ እኩይ ተግባር ሲፈጽሙ እና ሲያስፈጽሙ ስለተገኙ ንቅናቄያችን እርምጃ ወስዷል። አሁንም እርምጃው ተጠናክሮ ይቀጥላል:
ዛሬ በሃገራችን እንደ ሰደድ እሳት የሚቀጣጠለው ህዝባዊ አመጽ ከኛ የጦር ተጋድሎ ጋር ተደምሮ ሲታይ የህወሓት
ውድቀት ቅርብ ጊዜ እንደሆነ መገንዘን አያዳግትም፡፡

ይሁን እንጂ ህወሓት ከመነሻው ጀምሮ ይዞት የተነሳውን ዕቅድ አማራ ከምድረ ገጽ ለማጥፋት የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ይገኛል፡፡ ንቅናቄያችን ከህዝብ ጋር በመሆን ይህን ዕቅድ ያከሽፋል:: ህወሓትንም ይደመስሳል፡ብሎም ለኢትዮጵያ ነጻነት ጥግ ድረስ ይጓዛል፡፡
ዛሬ ንቅናቄያችን ከመቼውም ጊዜ በላቀ ሁኔታ ሃይሉን አጠናክሮ ህዝባችንን ለመታደግ ከፍተኛ ተጋድሎ በማድረግ ላይ ነው።ይህንን ህዝብን እና አገርን ከጥፋት ለመታደግ የሚደረግን ትግል በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሃገር የምትገኙ ኢትዮጵያዊያኖች ንቅናቄያችንን በመቀላቀልና በማንኛውም መንገድ በማገዝ ህዝባችንን ከጥፋት እንታደግ ዘንድ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

የአማራ ህዝብ ትግል ያሸንፋል!
አንዲት ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ታህሳስ 3፡2008 ዓ.ም

The post “ጎንደር ቋራ አካባቢ ህዝባችንን ለመከፋፈል የሚወስደው እርምጃ ጊዜ የሚሰጠው ባለመሆኑ አፋጣኝ አጸፋዊ እርምጃ ወስደናል” – አማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ appeared first on Zehabesha Amharic.

መንግስት በምዕራብ ሸዋና በደቡብ ም ዕራብ ሸዋ ዛሬ ብቻ 25 ሰዎች ገደለ

$
0
0

Zehabesha News

(ዘ-ሐበሻ) በኢትዮጵያ በተለይም በኦሮሚያ የተለያዩ ቦታዎች የተነሳው የሕዝብ ቁጣ አሁንም እንደቀጠለ ነው:: ዛሬ ብቻ በም ዕራብ ሸዋና በደቡብ ምዕራብ ሸዋ 25 ሰዎችን መንግስት መግደሉ ተሰማ::

አንደኛ ወሩን ያስቆጠረው የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞ በርትቶ በቀጠለበት በዚህ ሰዓት በዛሬው ዕለት የመንግስት ወታደሮች በተጠቀሱት ሁለት ቦታዎች ብቻ 25 ሰዎችን መግደላቸው የሕዝቡን ቁጣ ይበልጥ እንዲያይል እነሚያደርገው ተገልጿል::

በአሁኑ ወቅት የኦሮሞ ክልልን ይመሩ የነበሩ ባለስልጣናት ሁሉ ምንም ዓይነት አመራር እንዳይሰጡ ከመደረጉም በላይ ከደህነነት መስሪያ ቤትና ከመከላከያ በተውጣጣ ኮማንድ ፖስት ክልሉ እንዲተዳደር እየተደረገ ይገኛል::
ዝርዝር መረጃ ይዘን እንመለሳለን::

The post መንግስት በምዕራብ ሸዋና በደቡብ ም ዕራብ ሸዋ ዛሬ ብቻ 25 ሰዎች ገደለ appeared first on Zehabesha Amharic.

በወገኔ ላይ አልተኩስም ያሉ ወታደሮች ዩኒፎርማቸውን እያቃጠሉ ሕዝቡን እየተቀላቀሉት ነው ተባለ

$
0
0

mekelakeya

(ዘ-ሐበሻ) በኦሮሚያ እና በ150 የኦሮሚያ ከተሞች የተቀሰቀሰው ሕዝባዊ ቁጣን ለማብረድ መንግስት ወታደሮቹን አሰማርቶ ትናንት ብቻ በም ዕራብ ሸዋ እና በደቡብ ም ዕራብ ሸዋ 25 ሰዎችን መግደሉን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም:: ዛሬ ከሃገር ቤት የሚወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ወደ ሕዝቤ አልተኩስም ያሉ ሕወሓት የሚያዘው መከላከያ ሚ/ር ወታደሮች በየቦታው ዩኒፎርማቸውን በአደባባይ በማቃጠል ሕዝቡን እየተቀላቀሉ ነው::

በኦሮሚያ የተነሳው ከፍተኛ የሕዝብ ቁጣ ዛሬም ቀጥሎ በም ዕራብ ሸዋ ባኮ እንዲሁም በም ዕራብ ወለጋ በነጆ ወረዳ በወራ ጅሩ; አቹማ ጎሪ እና ጊዳ ከተሞች ተቃውሞ ሲሰማ ውሏል;; ቡራዩ ከተማ የመለስተኛ ሁልተኛ ደረጃ ተማሪዎች ወታደሮች እንዳይገቡ በድንጋይ መንግዱን አጥረውታል::

The post በወገኔ ላይ አልተኩስም ያሉ ወታደሮች ዩኒፎርማቸውን እያቃጠሉ ሕዝቡን እየተቀላቀሉት ነው ተባለ appeared first on Zehabesha Amharic.


የአዲስ አበባ መስፋፋት በተመለከተ የተሰጠ አስተያየት –ተፈራ ድንበሩ

$
0
0

ሰሞኑን የኦሮሞ ፈዴራሊስት ኮንግሬስ ባለሥልጣን የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ በፖርቲው ስም ያወጡትን መግለጫ ይመለከታል።

abune gindeberetበመሠረቱ ፖርቲያቸው ሕዝባዊ ዓላማዎችን አንግቦ ሕዝባዊ ጥያቄዎችን ቢያነሣ መብቱ ስለሆነ እንደሕዝብ ፖርቲ የመንቀሳቅስ መብቱን ሊከበርለት ይገባል። ሆኖም በመግለጫው ላይ የሠፈሩት ሐሳቦች ኦሮምንና ኦሮሚያ የሚባለውን አዲስ አገር ከሌላው ሕዝብና አገር ለይተው አስቀምጠዋል፤ እንዲዚሁም የአዲስ አበባን ከፈዴራላዊ አመለካከት ጋር በሚቃረን ሁኔታ የከልሉ መብት ተጥሷል ብለው አቅርበውታል። ሆኖም መሠረታዊ ችግሩ ላይ ባለማተኮራቸው ኢሕአዴግ የሚፈልገውን ጨዋታ እየተጫወቱለት ነው።-– [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—-

The post የአዲስ አበባ መስፋፋት በተመለከተ የተሰጠ አስተያየት – ተፈራ ድንበሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

ሕብር ራድዮ ልዩ ቃለምልልስ ከጃዋር መሐመድ እና ሳዲቅ አህመድ ጋር –“ይህ ዕድል እንዳያመልጠን እንጠቀምበት”| Audio

Next: Hiber Radio: አንድ የካናዳ ኩባንያ ኢትዮጵያን እና ግብጽን በአወዛጋቢው ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ሊሸመግል ነው ተባለ፣ የሱዳኑ ፕ/ት አልባሽር ካይሮን እና አ/አበባን ለመዳኘት መሬት ይሰጠኝ ማለታቸው ተሰማ፣ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ባለቤት የእንግሊዝ የው/ጉ/ሚ/ርን ለመጀመሪያ ጊዜ በግንባር አነጋገሩ፣ ሳውዲ አረቢያ አትዮጵያዊያን የቤት ሰራተኞችን ወደግዛቷ ዳግም ለማስገባት ሕዘበ ውሳኔ ልታካሄድ ነው፣ የአማራ ዴሞክራሲ ሀይል ንቅናቄ የአገዛዙን ዘረኛ እንቅስቃሴ በመቃወም በጎንደር ወታደራዊ ጥቃት ፈጸምኩ አለ፣ ሰማያዊ ፓርቲ በኦሮሞ ተወላጅ ተማሪዎች ላይ የተወሰደውን ግፍ ተቃውሞ አጋርነቱን ገለጸ፣ ከመድረክና ከሌሎቹም ጋር ለመስራት ወሰነ…ሌሎችም ወቅታዊ ዝግጅቶች አሉን:-
$
0
0

የተጀመረው የተማሪዎች ተቃውሞ እንደ ሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ ከአንዱ ወረዳ ወደ ሌላው ከአንዱ ከተማ ወደ ሌላው በፍጥነት እየተሸጋገረ ነው:: ተቃውሞው የቀሰቀሰው ሕዝባዊ ቁጣ በቀላሉ ወደሌሎች አካባቢዎች ተዛምቶ ብሄራዊ መልክ በፍጥነት ለምን አልያዘም? የተቃውሞው መሪዎች በይፋ አለመታወቅ ይሆን? የአገዛዙ የአንዋር መስጊድ ጥቃት ለምን በዚህ ወቅት? ኢትዮጵያውያን ዛሬ ካልተባበርን መቼ ነው አንድ ላይ ለለውጥ የምንቆመው? ጋዜጠኛና አክቲቪስት ሳዲቅ አህመድና ከኦሮሞያ ሚዲያ ኔትወርክ ዋና ስራስኪያጅና የፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ ከሆነው ጃዋር መሐመድ ጋር ጋዜጠኛ ሐብታሙ አሰፋ ከሕብር ራድዮ ተወያይቷል:: ያድምጡት።

ሕብር ራድዮ ቃለምልልስ ከጃዋር መሐመድ እና ሳዲቅ አህመድ ጋር – “ይህ ዕድል እንዳያመልጠን እንጠቀምበት” | Audio

The post ሕብር ራድዮ ልዩ ቃለምልልስ ከጃዋር መሐመድ እና ሳዲቅ አህመድ ጋር – “ይህ ዕድል እንዳያመልጠን እንጠቀምበት” | Audio appeared first on Zehabesha Amharic.

Hiber Radio: አንድ የካናዳ ኩባንያ ኢትዮጵያን እና ግብጽን በአወዛጋቢው ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ሊሸመግል ነው ተባለ፣ የሱዳኑ ፕ/ት አልባሽር ካይሮን እና አ/አበባን ለመዳኘት መሬት ይሰጠኝ ማለታቸው ተሰማ፣ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ባለቤት የእንግሊዝ የው/ጉ/ሚ/ርን ለመጀመሪያ ጊዜ በግንባር አነጋገሩ፣ ሳውዲ አረቢያ አትዮጵያዊያን የቤት ሰራተኞችን ወደግዛቷ ዳግም ለማስገባት ሕዘበ ውሳኔ ልታካሄድ ነው፣ የአማራ ዴሞክራሲ ሀይል ንቅናቄ የአገዛዙን ዘረኛ እንቅስቃሴ በመቃወም በጎንደር ወታደራዊ ጥቃት ፈጸምኩ አለ፣ ሰማያዊ ፓርቲ በኦሮሞ ተወላጅ ተማሪዎች ላይ የተወሰደውን ግፍ ተቃውሞ አጋርነቱን ገለጸ፣ ከመድረክና ከሌሎቹም ጋር ለመስራት ወሰነ…ሌሎችም ወቅታዊ ዝግጅቶች አሉን:-

$
0
0

Hiber Radio: አንድ የካናዳ ኩባንያ ኢትዮጵያን እና ግብጽን በአወዛጋቢው ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ሊሸመግል ነው ተባለ፣የሱዳኑ ፕ/ት አልባሽር ካይሮን እና አ/አበባን ለመዳኘት መሬት ይሰጠኝ ማለታቸው ተሰማ፣ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ባለቤት የእንግሊዝ የው/ጉ/ሚ/ርን ለመጀመሪያ ጊዜ በግንባር አነጋገሩ፣ ሳውዲ አረቢያ አትዮጵያዊያን የቤት ሰራተኞችን ወደግዛቷ ዳግም ለማስገባት ሕዘበ ውሳኔ ልታካሄድ ነው፣ የአማራ ዴሞክራሲ ሀይል ንቅናቄ የአገዛዙን ዘረኛ እንቅስቃሴ በመቃወም በጎንደር ወታደራዊ ጥቃት ፈጸምኩ አለ፣ ሰማያዊ ፓርቲ በኦሮሞ ተወላጅ ተማሪዎች ላይ የተወሰደውን ግፍ ተቃውሞ አጋርነቱን ገለጸ፣ ከመድረክና ከሌሎቹም ጋር ለመስራት ወሰነ፣ ቃለ መጠይቅ ከጃዋር መሐመድና ከጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ ጋር በወቅታዊ የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞና ትግሉ ወደ ብሄራዊ ተቃውሞ ስለሚያድግበት ሁኔታ ሌሎችም ወቅታዊ ዝግጅቶች አሉን:-

Hiber

የህብር ሬዲዮ ታህሳስ 3 ቀን 2008 ፕሮግራም

ጃዋር መሐመድ ለህብር ሬዲዮ ከሰጠው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

ጋዜጠኛና አክቲቪስት ሳዲቅ አህመድ(ስለ ወቅታዊው ተቃውሞ ለህብር ሬዲዮ ከጃዋር ጋር ከሰጠው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ)

የዘ-ሐበሻ ድህረ ገጽ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ሔኖክ አለማየሁ በሚኒሶታ ስለተደረገው ሰልፍ ለህብር ከሰጠው ማብራሪአ(ሙሉውን አዳምጡት)

ቢላል ኦሮሞ በሚል ስያሜ በማህበራዊ ሚዲያ ፓል ቶክ የወያኔን ሴራ ለማክሸፍ እንቅስቃሴ የሚያደርገው አክቲቪስት ስለ ሰሞኑ በኦሮሚያ ክልል የተነሳ ተቃውሞ እና በውጭ አገራት ስለሚነሱ ተቃውሞዎች ከሰጠን ቃለ መጠይቅ (ሙሉውን ያድምጡት)

ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የተቀሰቀሰው ሕዝባዊ የተቃውሞ አመጽን ተከተሎ የተሰጠው አለማቀፋዊ ድጋፍ ሲዳሰስ (ልዩ ዘገባ)

ኦሮሞ ተማሪዎች ጀመሩት ሕዝባዊ ተቃውሞን ሁሉም እንዲቀላቀለው ቀረበው የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ጥሪና ማስተንቀቂያ

በቬጋስ ታክሲ አሽከርካሪዎች እንቅስቃሴን በማህበር ለማደራገት ስለ ተጠራ ስብሰባ ቃለ መጠይቅ(ሙሉውን ያዳምጡት)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

በሕዝባችን ላይ አንተኩስም አሉ ኦሮሞ ብሔር ተወላጅ ኮሎኔሎች ከሰራዊቱ ውስጥ መታሰር መጀመራቸው ተገለጸ

አንድ የካናዳ ኩባንያ ኢትዮጵያን እና ግብጽን በአወዛጋቢው ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ሊሸመግል ነው ተባለ

የሱዳኑ ፕ/ት አልባሽር ካይሮን እና አ/አበባን ለመዳኘት መሬት ይሰጠኝ ማለታቸው ተሰማ

በ ታላቁ አንዋር መሰጊድ የደረሰው የቦንብ አደጋ አነጋጋሪ ሆኗል፣

እንግሊዝ ዜጎቿ ወደ መርካቶ እና መሰል ስፍራዎች እንዳይሔዱ አሰጠነቀቀች፣ ዘረኞች በአሜሪካው የካሊፎርኔያ ግዛት መስጊድ አቃጠሉ

የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ባለቤት የእንግሊዝ

የው/ጉ/ሚ/ርን ለመጀመሪያ ጌዜ በግንባር አነጋገሩ፣የውይይቱንም ውጤት እና አቋማችውን ገልጸዋል

እንግሊዝ በአንዳርጋቸው ጉዳይ ቁርጥ ያለ ውሳኔ አሻለሁ ስትል ለኢትዮጵያ ባለሰላጣናት ጥያቈ አቀረበች

” አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በኢትዮጵያ እስር ቤት ውስጥ መሞት የለባቸውም” አንግሊዛዊቷ የሕዝብ እንደራሴ

ሳውዲ አረቢያ አትዮጵያዊያን የቤት ሰራተኞችን ወደግዛቷ ዳግም ለማስገባት ሕዘበ ውሳኔ ልታካሄድ ነው

የሪያድ ነዋሪዎች ኢትዮጵያዊያን የቤት ሰራተኞች በጸባያቸው ምቹዎች ናቸው ሲሉ አደናቆታቸውን መስጠታቸ ታውቋል

የአማራ ዴሞክራሲ ሀይል ንቅናቄ የአገዛዙን ዘረኛ እንቅስቃሴ በመቃወም በጎንደር ወታደራዊ ጥቃት ፈጸምኩ አለ

ሰማያዊ ፓርቲ በኦሮሞ ተወላጅ ተማሪዎች ላይ የተወሰደውን ግፍ ተቃውሞ አጋርነቱን ገለጸ

ከመድረክና ከሌሎቹም ጋር ለመስራት ወሰነ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

The post Hiber Radio: አንድ የካናዳ ኩባንያ ኢትዮጵያን እና ግብጽን በአወዛጋቢው ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ሊሸመግል ነው ተባለ፣ የሱዳኑ ፕ/ት አልባሽር ካይሮን እና አ/አበባን ለመዳኘት መሬት ይሰጠኝ ማለታቸው ተሰማ፣ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ባለቤት የእንግሊዝ የው/ጉ/ሚ/ርን ለመጀመሪያ ጊዜ በግንባር አነጋገሩ፣ ሳውዲ አረቢያ አትዮጵያዊያን የቤት ሰራተኞችን ወደግዛቷ ዳግም ለማስገባት ሕዘበ ውሳኔ ልታካሄድ ነው፣ የአማራ ዴሞክራሲ ሀይል ንቅናቄ የአገዛዙን ዘረኛ እንቅስቃሴ በመቃወም በጎንደር ወታደራዊ ጥቃት ፈጸምኩ አለ፣ ሰማያዊ ፓርቲ በኦሮሞ ተወላጅ ተማሪዎች ላይ የተወሰደውን ግፍ ተቃውሞ አጋርነቱን ገለጸ፣ ከመድረክና ከሌሎቹም ጋር ለመስራት ወሰነ… ሌሎችም ወቅታዊ ዝግጅቶች አሉን:- appeared first on Zehabesha Amharic.

ሕዝብን ከመጨፍጨፍ እየዘመተ ያለው ጦር – የሚሊዮኖች ድምጽ

Previous: Hiber Radio: አንድ የካናዳ ኩባንያ ኢትዮጵያን እና ግብጽን በአወዛጋቢው ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ሊሸመግል ነው ተባለ፣ የሱዳኑ ፕ/ት አልባሽር ካይሮን እና አ/አበባን ለመዳኘት መሬት ይሰጠኝ ማለታቸው ተሰማ፣ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ባለቤት የእንግሊዝ የው/ጉ/ሚ/ርን ለመጀመሪያ ጊዜ በግንባር አነጋገሩ፣ ሳውዲ አረቢያ አትዮጵያዊያን የቤት ሰራተኞችን ወደግዛቷ ዳግም ለማስገባት ሕዘበ ውሳኔ ልታካሄድ ነው፣ የአማራ ዴሞክራሲ ሀይል ንቅናቄ የአገዛዙን ዘረኛ እንቅስቃሴ በመቃወም በጎንደር ወታደራዊ ጥቃት ፈጸምኩ አለ፣ ሰማያዊ ፓርቲ በኦሮሞ ተወላጅ ተማሪዎች ላይ የተወሰደውን ግፍ ተቃውሞ አጋርነቱን ገለጸ፣ ከመድረክና ከሌሎቹም ጋር ለመስራት ወሰነ…ሌሎችም ወቅታዊ ዝግጅቶች አሉን:-
$
0
0

soldersበነሶሞራ የሚመራው እዝ፣ ህዝብን ለመጨረስና በሃይል አንገትን ለማስደፋት ሁለት ዲቪዝን ጦር ወደ ምራብ ሸዋና ወለጎ እየወሰደ ነው። ይህ አይነቱ እንቅስቃሴ አገዛዙ ሊወስደው የሚችለው የመጨረሻ ተግባር ነው። ጎንደር ላይ ከሰፈረው ጦር በተጨማሪ ወደ ኦሮሚያ እየተሰማራ ያለው ሲደመርበት በሌሎች ከተሞች የሚኖረው ጦር በጣም የተመናመነ ነው።

በመሆኑም በአዲስ አበባ. በጎጃም፣ በወለኦ፣ በሰሜን ሸዋ፣ እና በደቡብ ክልል ሕዝቡ ለነጻነትና ለመብት ድምጹን ማሰማት ቢጀመር ይሄ ስርዓትን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለመገርሰስ አመቺ ሁኔታን ይፈጥራል ተብሎ ይገመታል።

በመሆኑም ሌላው ማሀበረሰብ ድምጹን ያሰማ ዘንድና በኦሮሚያና በጎንደር ለመብታቸው ከቆሙ እየተገደሉ ካሉ ወገኖቻችን ጎን እንዲቆም ያስፈልጋል።

እስከአሁን በጎንደር ከ150 በላይ ዜጎንች የተገደሉ ሲሆን በኦሮሚያ የዛሬን ቀን ሳይጨመር ከሰባ በላይ ሕይወታቸው አልፏል።

The post ሕዝብን ከመጨፍጨፍ እየዘመተ ያለው ጦር – የሚሊዮኖች ድምጽ appeared first on Zehabesha Amharic.

ከአዲስ አበባዉ ማስተር ፕላን ወደ አዲስ አበባዉ ቤተ መንግስት? |አዘጋጅ: ሳዲቅ አህመድ | Audio

$
0
0

Sadik Ahemed Journalist
የከተማ ልማት እና ህገ ደንቦችን ያጠኑ ምሁር፣ ኢኮኖሚስት፣የማህበረሰብ መሪዎችና ያገባኛል ያሉ ያገር ሽማግሌዎችን በማናገር የተዘጋጀ ልዩ ፕሮግራም። አገር ዉስጥ የኦሮሞ ማህበረሰብ የጀመረዉ የነጻነት ንቅናቄ የኦሮሞ ማህበረሰብ ብቻ ወይስ የመላዉ ኢትዮጵያዉያን? እነዚህንና ሌሎች ተዛማጅ ጥያቄዎችን የኦሮሞ ምሁራን፣የማህበረሰብ መሪዎችና ያገር ሽማግሌዎች መልስ ይሰጣሉ።

አዘጋጅ: ሳዲቅ አህመድ
(ቢቢኤን ሬድዮ)

The post ከአዲስ አበባዉ ማስተር ፕላን ወደ አዲስ አበባዉ ቤተ መንግስት? | አዘጋጅ: ሳዲቅ አህመድ | Audio appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live