Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ወያኔ በራሱ ወጥመድ –መስፍን ወልደ ማርያም

$
0
0

Prof. Mesfin
ኅዳር 2008

ራስን ሳያታልሉ ሌላውን ማታለል አይቻልም፤ ለራስ ካልዋሹ ለሌላ ሰው መዋሸት አይቻልም፤ ዞሮ ዞሮ ወደቤት እንደሚባለው ዞሮ ዞሮ ማታለልም ሆነ ውሸት ማደሪያ ሲያጡ ወደቤታቸው ይመለሳሉ፤ ያኔ ፈጣሪና ፍጡር ይፋጠጣሉ፤ ፍጡር የማታለያ ልብሱን አውልቆ በዓለም ፊት ራቁቱን ይቆማል፤ በከመረው ውሸት መጠን ነቀፌታ ተሸክሞ ያቃስታል፡፡
የታወሩት ዓይኖቹ ይከፈቱና ሕይወት ነጠላ አለመሆኑን፣ በማኅበራዊ ሕይወት ውስጥ ውጣ-ውረድ መኖሩን፣ ጥላቻና ፍቅር፣ ጤንነትና ሕመም፣ ደስታና ሐዘን መፈራረቃቸውን፣ የግለሰብ ሕይወት በሞት ተሸንፎ መሻሩን፣ ገንዘብ የማይገዛው ነገር መኖሩን፣ ገንዘብ በከበደ መጠን ማቅለሉን አለማወቅ፣ ገንዘብ የማይመክተው ጦርና በገንዘብ ሊታጠቀው የማይችል መሣሪያ መኖሩን አለማወቅ፣ የደከመ እንደሚያይልና ያየለ እንደሚደክም፣ ዓለማችን በጣም የተያያዘና የተቆራኘ በመሆኑ አንዱን ሲያስነጥሰው ሌላውን እንደሚነዝረው የወያኔ ጎረምሶች አልተረዱም፡፡

ዛሬ ፈጣሪና ፍጡር ተፋጠጡ፤ ፍጡር የማታለያ ልብሱን አውልቆ በዓለም ፊት ራቁቱን ቆሟል፤ በከመረው ውሸት መጠን ውርደትን ተሸክሞ ያቃስታል፤ እያታለሉ ውሸትን መጠምጠም እያታለሉ ውሸትን እንደመተርተር ቀላል አይደለም፤ ውሸት ያከሳል፤ ውሸት ያዋርዳል፤ ውሸት መደገፊያ ያሳጣል፤ ውሸት ወዳጆችን ያሳፍራል፤ ጠላቶችን ያፈነድቃል፡፡
በውሸት ለሌሎች የተገነባው ወጥመድ ሲከፈት ማንም፣ ምንም የለበትም፤ ባዶ ግን አይደለም፤ ባለቤቱ አለበት! ባለቤቱ በገዛ ወጥመዱ ውስጥ! ታለለ የተባለው ሁሉ ዳር ቆሞ አታላዩ መታለሉን እያየ ይስቃል፤ አታላዩ የውሸት ምሰሶው መውደቁን ገና አልተረዳም፤ ውሸቱን አይቶ ወዳጁ እንደከዳው አታላዩ አልገባውም፡፡

ማታለልና መዋሸት በሃያ አምስት ዓመታት ጉዞ ዙሪያውን ገደል አደረገው፤ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የአስታራቂነት ጥረት ከብዙ ዓመታት ጦርነት ወጥቶ በሰላም የነበረው ሱዳን አሁን ለሁለት ተገመሰ፤ ለሁለት መገመሱ አልበቃ ብሎ እንደገና ሊገማመስ እየተደባደበ ነው፤ የሶማልያ ትርምስ እየባሰበት ሄደ እንጂ አልተሻለውም፤ ኢትዮጵያና ኤርትራ እንደተኳረፉ ናቸው፤ ከዚያም በላይ በውክልና እየተቆራቆዙ ነው፤ የኢትዮጵያና የኬንያ ወታደሮች መጋጨታቸውና ጥቂቶች መሞታቸው አዲስ የሰላም ጠንቅ ነው፤ ጂቡቲ በፈረንሳይና በአሜሪካ ጦር የምትጠበቅ ስለሆነ አይበገሬ ትሆናለች፤ ሆኖም የአዲስ አበባ-ጂቡቲ ባቡር መቆም በጂቡቲ ሕዝብ ላይ የሚያስነሣው ግም ስሜት የለም ለማለት ያስቸግራል፡፡

የምዕራባውን ኃይሎች ፍላጎት ኢትዮጵያ ሰላም የሰፈነባት፣ ከነሱ ምጽዋት የማትወጣ ፍጹም ደሀ፣ ያለምንም ስጋት አካባቢውን በሞላ ለመቆጣጠር የሚያስችላቸው ሁኔታ የተመቻቸበት እንድትሆንላቸው ነበር፤ አሁን ግን ሰላም የሰፈነባት አገር እንደማትሆን ምልክቶችን እያዩ ነው፤ እንዲያውም በመሀከለኛው ምሥራቅ በግልጽም ይሁን በስውር እየበረታ የሚሄደው ጸረ-አሜሪካን ስሜት በአፍሪካ ቀንድ ላይ የተተከለ እንደሆነ ምዕራባውያን በመሀከለኛው ምሥራቅ ዘይት አምራች አገሮች ላይ ያላቸውን ጥቅም ሁሉ ክፉ ስጋት ላይ የሚጥልባቸው ሊሆን እንደሚችል የተገነዘቡ ይመስላል፤ በተጨማሪም ከኤርትራ ጋር በጠላትነት የተፋጠጠች ኢትዮጵያ ለምዕራባውያን የምትመች አለመሆንዋንም እየተገነዘቡ ነው፤ ስለዚህም ከኢትዮጵያ አገዛዝ ጋር በመሆን አሻክረውት የነበረውን ግንኙነት ለማለስለስ እየሞከሩ ነው፤ ይህ ሁሉም እየሆነ የኢትዮጵያ አገዛዝ ገና አልነቃም፤ በአፍሪካ ኅብረት በኩል ቀስቃሽ ተልኮለታል፡፡

በኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት ለወግም እንኳን መጥፋቱን የአፍሪካ ኅብረት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የተገነዘበው ይመስላል፤ በኢትዮጵያ ፍርድ ቤት ለዓመታት የማይቋጭ ሆኖ የቆየውን የእስላሞች ጉዳይ ለማየት ውሳኔ ላይ ደርሷል፤ በኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት አለመኖሩን የአፍሪካ ኅብረት ውሳኔ ዋና ማረጋገጫ ነው፤ ዙሪያው ገደል መሆኑ የምዕራባውያን (አሜሪካና አውሮፓ) ኃይሎች ተማምነውበት የነበረውን የኢትዮጵያ አገዛዝ ጥያቄ ውስጥ ይጥለዋል፤ ዙሪያው ገደል መሆኑ የኢትዮጵያ አገዛዝ የሰላም አራማጅ መስሎ እንዳይታይ አድርጎታል፤ እንዲያውም የኢትዮጵያ አገዛዝ በአካባቢው ካሉት አገዛዞች ጋር የሻከረ ዓይነት ግንኙነት ስለሚያሳይ አሜሪካና አውሮፓ የሚወድዱት አይመስልም፤ ይህ ውጪውን ሲታይ ነው፡፡

ከውስጥ ሲመለከቱት ደግሞ ሌሎች የግጭት መድረኮችና ሌሎች ጉዳዮች ይታያሉ፤ ዋናውና መሠረታዊው ግጭት አገዛዙ በሕገ መንግሥቱ የተደነገጉትን ነጻነቶችና መብቶች ሰርዞ ምንም ዓይነት ልዩነት በቃልም ይሁን በጽሑፍ መግለጽ እንደሽብርተኛነት የሚያስቆጥርና የሚያስወነጅል መሆኑ ነው፤ ፕሮፌሰር ስርግው ሐብለ ሥላሴ ዓጼ ምኒልክ፣ የአዲሱ ሥልጣኔ መሥራች በሚለው መጽሐፉ ኢትዮጵያውያን አእምሮ የሚባለውን ጋዜጣ መግዛት እንዲለምዱ በማለት አጼ ምኒልክ ጋዜጣውን ይዘው በአደባባይ እንደሚወጡ ይነግረናል፤ ዛሬ በአዳፍኔ አገዛዝ፣ መቶ ዓመታት ወደኋላ ሄደን ታዋቂ ጋዜጠኞች ሁሉ በእስር እየማቀቁ ጋዜጦች ሁሉ ጠፍተዋል፤ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተከልክለውና ታፍነው ባሉበት የወያኔ አገዛዝ፣ የፖሊቲካ ቡድኖች ተኮላሽተው አልጋ ላይ በዋሉበት ሁኔታ፣ ፖሊሶች፣ ዓቃቤ ሕጎች፣ ዳኞችና የወህኒ ቤት አዛዦች እንደፈለጉ በሚሠሩበት አገር ግጭቶች ያለማቋረጥ እንደሚፈጠሩ ሳይታለም የተፈታ ነው፤ የፖሊቲካ ውይይት፣ ክርክርና ንግግር በተከለከለበትና አንድ ድምጽ ብቻ ለማዳመጥ በተፈቀደበት ሥርዓት ብዙ እምቢ-ባዮች ይኖራሉ፤ አዳፍኔ ጎራዴውን እየሳለ በሄደ ቁጥር ሰላማዊ የፖሊቲካ ውይይትም በተስፋ-ቢስነት አላስፈላጊ አማራጭ ውስጥ ይገባል፤መለስ ዜናዊ ‹‹መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ›› ብሎ ተቀናቃኝ ቡድኖችን ከመረቀ ሃያ አምስት ዓመታት ተቆጠሩ፤ አሁን ምርቃቱ የደረሰ ይመስላል፤ ዛሬ ላይ ሆኖ ሲታሰብ መለስ ዜናዊ ራሱን የረገመ ይመስላል፡፡

ወሬው ሁሉ የኢትዮጵያን ሕዝብ አለመረጋጋት የሚያመለክት ነው፤ ከጎንደር አስከቦረና ከኦጋዴን አስከጋምቤላ ወሬው ሁሉ የግጭት ነው፤ አንድም ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ፣ በውይይትና በስምምነት መደምደሚያ ሲያገኝ አይታይም፤ አይሰማም፤ ሁሉንም ነገር በጡንቻ በማስገደድ ለማስፈጸም የሚደረገው ሙከራ ያረጀና ያፈጀ መሆኑን ለማስታወቅ ተቀዋሚውም የጡንቻውን መንገድ እየተላመደው ነው፤ ጡንቻ ለጡንቻ መቆራቆዙ ደም እያፋሰሰ ጡንቻን ያነግሣል እንጂ ሕዝብን አይገነባም፤ በኢትዮጵያ ውስጥ የጡንቻ ግጭት መስፋፋት በሰሜን በኤርትራና በትግራይ፣በትግራይና በጎንደር፣ በትግራይና በወሎ፣ በምሥራቅ በሱማሌና በኦሮሞ፣ በሱማሌና በሐረሬ፣ በኦሮሞና በሐረሬ ፣ በደቡብና በምዕራብ በተለያዩ ጎሣዎች መሀከል የተጫረው እሳት ሲቀጣጠል ማብረዱ እንደማቀጣጠሉ ቀላል አይሆንም፤ ተንጋሎ የተፋ ለራሱ ከፋ እንደሚባለው ይሆናል፤ በምዕራብና በምሥራቅ፣ በሰሜንና በደቡብ የሚቀጣጠለው እሳት ድንበር ጥሶ የሚወጣና ጦሱ የማይበርድ ይሆናል፤ወያኔም ሆነ ለወያኔ ወንበር ያሰፈሰፉ ሁሉ፣ በጎሠኛነት ስሜት እየነደዱ የማመዛዘን ችሎታቸውን ያጡ ሁሉ የሰነዘሩት የጥላቻ ስለት በነሱው ላይም ሲያርፍ የተመኙትን ትርፍ ሳይሆን ኪሳራ እንደሚያጋጥማቸው ከመሸ በኋላ ይረዱታል፤ ለሌሎቹ አዲስ ይሆናል እንጂ ለወያኔ ከመሸ በኋላ መረዳት የባሕርይ ነው!

ከሶርያ በሶማልያና በኬንያ በኩል እያደፈጠ የሚገሰግሰው የሽብር ቡድን ወደኢትዮጵያ አይደርስም ማለቱ አውቀውም ይሁን ሳያውቁ እንደተለመደው ለከመሸ በኋላ ማሰብ ማስተላለፉ የመጨረሻው ስሕተት ሊሆን ይችላል፤ የመጨረሻው ስሕተት የተሠራውን አሰፋልት መንገድ አፍርሶ የባቡር ሀዲድ እንደመሥራት አይቀልም፤ የውጮቹን አካባቢ ኃይሎች እንደውስጡ አመራር በጡንቻ (የአሜሪካን ድጋፍ ቢኖርበትም) ለማስተናገድ ማሰብ ማሰብ አይደለም፤ ማሰብ የጎደለው መሆኑም በገሃድ እየታየ ነው፤ በኢትዮጵያ ዙሪያ ያሉ አገሮች በሚከተለው ሰንጠረጅ ተዘርዝረዋል፡፡

ወደአሥራ አንድ የሚጠጉ ጎረቤቶች እንኳን ለአላዋቂዎች አምባገነኖችና ለአዋቂ መሪዎችም ቢሆን በጣም ፈታኝ ነው፤ የኢትዮጵያ አገዛዝ አሜሪካንን ከመጠን በላይ በመተማመን የውጩን አመራር ልክ እንደውስጡ በጉልበትና በማታለል ላይ የተመሠረተ አድርጎታል፤ ይህ ሁኔታ ከአጋም የተጠጋ ቁልቋል አድርጎታል፤ በዚህም ምክንያት እንዳይደርስ ከተባለበት ከጂቡቲ በቀር ከኢትዮጵያ ጋር በግጭት ያልተላከፈ አገር የለም፤ የኃያል አሽከር መሆን ኃያል የሆኑ የሚያስመስል ሕመም አለ፤ ጃንሆይ አማኑኤል ሆስፒታልን ሲጎበኙ አንዱን ያገኙትና ስሙን ይጠይቁትና ይነግራቸዋል፤ ቀጥሎም በተራው ያንተስ ስም ይላቸዋል፤ የኛማ ግርማዊ ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ነው ብለው ሲመልሱለት ከት ብሎ ይስቅና እኔንም ሲጀምረኝ እንዲህ ነበር ያደረገኝ ይላቸዋል! መማር የፈለገ አምባገነን እብድ ከተባለ ሰውም መማር ይችላል! አሜሪካኖች የኢትዮጵያን አገዛዝ የአካባቢው ሰላም ጠባቂነት በጥርጣሬ እንዲመለከቱት ያደረጋቸው ይኸው ሳይሆን አይቀርም፤ አንዱና ዋናው የማሰብ ችግር ነው፡፡

ኢትዮጵያና ጎረቤቶችዋ
2008 ዓ.ም.
ተ፣ቁ. አገሮች የኢትዮጵያ ጦር ከኢትዮጵያ ጋር ግጭት የውስጥ ሰላም

1 ኢትዮጵያ የለም
2 ሱዳን1 አለ አለ የለም
3 ሱዳን2 አለ የለም
4 ሱዳን3? ?
5 ኬንያ ? አለ አለ
6 ሰማልያ አለ የለም
7 • ስባሪ1 የለም
8 • ስባሪ2 የለም
9 • ስባሪ3 የለም
10 ጂቡቲ አለ
11 ኤርትራ አለ አለ

ምናልባት ከባሕር ማዶ ያለው ጎረቤታችን፣ የመን በአፍሪካ ቀንድ አገሮች ላይ የተለየ መዘዝ ይዞላቸው ይመጣ ይሆናል፡፡
አሁን ደግሞ ከሁሉም የባሰው መጋለጥ መጣ፤ ማንም በማይደርስበት ፍጥነት እያደገ ነው የተባለው ኢኮኖሚ አከርካሪቱን ተመታ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ በችጋር ጥቃት ስር ወደቀ፤ የወያኔ የኢኮኖሚ እድገትም ሆነ የአገሩን ሕዝብ ያቀጨጨው የወያኔ ጡንቻ ውሀ ሆኑ፤ ኢኮኖሚ በጡንቻ አያድግም፤ ችጋር በጡንቻ አይገፋም፤ ሕጸናትንና አሮጊትና ሽማግሌዎችን የገጠር ነዋሪዎች እያመነመነ በመጣል የሚጀምረው ችጋር አይደበቅም፤ ከወራት በኋላ ማምለጥ ያልቻሉትን ሁሉ ችጋር እየበላ በያለበት ሲጥላቸው በዓለም ጋዜጦች ይወጣል፤ ያኔ መዋሸትና ማታለል ዋጋ ያጣሉ! ያኔ ጡንቻ ዋጋ ያጣል! ያኔ ስለእድገት ማቅራራት ዋጋ ያጣል!

ዓላማው ሁሉ ታወቀ፤ ዘዴው ሁሉ ታወቀ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዓላማውም ዘዴውም ሰለቸው፤ ምዕራባውያን ኃይሎች ውሸትን መጠገን ሰለቻቸው፤ የአፍሪካ ሕዝቦች የጎሠኛነት በሽታ እንዳይተላለፍባቸው ፈሩ፡፡

The post ወያኔ በራሱ ወጥመድ – መስፍን ወልደ ማርያም appeared first on Zehabesha Amharic.


በምዕራብ አርሲ አዳባ ከተማ የሚገኙ ተማሪዎች አደባባይ ወጡ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) የአዲስ አበባን ማስተር አዲሱን ማስተር ፕላን በመቃወም በመላው የኦሮሚያ ክልል የቀጠለው ተቃውሞ በአዲስ ከተሞችም እንዲሁ እየተቀጣጠለ እንደሚገኝ ተዘገበ::

arsi arsi1 arsi2

እንደ ዘ-ሐበሻ የመረጃ ምንጮች ከሆነ መንግስት 2ኛ ሳምንቱን በያዘው የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞ ከ7 የማያንሱ ሰላማዊ ዜጎችን ተቃውሟቸውን ለማብረድ ሲል ገድሏል:: ይህም የተማሪዎቹን ጥያቄ ከማስተር ፕላኑ በተጨማሪ ግድያውን የማውገዝም ጭምር እንዲሆን አድርጎታል::

ዛሬ በአዳባ ታውን በተደረገው የተማሪዎች ተቃውሞ ላይ ከተማሪዎች በተጨማሪ እንዲሁ የመንግስት ሠራተኞች እና ሌሎች የማህበረሰቡ አባላት መሳተፋቸውን የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገልጸዋል::

ፖሊስ የተማሪውን ስብስብ ለመበተን የሃይል እርምጃ ቢወስድም አሁንም ቁጣው እንዳየለ ምንጮች ዘግበዋል::

The post በምዕራብ አርሲ አዳባ ከተማ የሚገኙ ተማሪዎች አደባባይ ወጡ appeared first on Zehabesha Amharic.

Health: በ40ዎቹ ውስጥ ያሉ ወንዶችና ሴቶች ሊጠነቀቋቸው የሚገቡ 9 ዋነኛ የጤና ችግሮች

$
0
0

በ40ዎቹ ውስጥ ያሉ ወንዶችና ሴቶች ሊጠነቀቋቸው የሚገቡ 9 ዋነኛ የጤና ችግሮች ምን እንደሆኑ በርካታ አንባቢዎች በተለያየ መልኩ በጠየቃችሁን መሰረት የህክምና ባለሙያችን ጠቅለል ያለ ምላሽ ሰጥቷል፡፡

back pain

‹‹ገንዘብ የሚገኘው በ20፣ ልብ የሚገኘው በ40›› ይላሉ አባቶች፡፡ 40 ዓመት ታዲያ ማስተዋልና ልብን ብቻ አይደለም ይዞ የሚመጣው፣ አሳሳቢ የጤና ችግሮችንም እንጂ! የጤና ባለሙያዎች ሰዎች ጤናማ አመጋገብን፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴንና አጠቃላይ የጤና ክብካቤን ከልጅነታቸው ጀምረው እንዲተገብሩ ቢመክሩም፣ ብዙዎች ጤና ሲታወክና ዕድሜ ሲገፋ ብቻ ይህን ምክር ያስታውሳሉ፡፡ የደም ቧንቧ እና ልብ ህመሞች፣ የመተንፈሻ አካላት ህመም፣ የወሲብ ድካም፣ የመውደቅና መሰበር አደጋዎችን መቋቋም አለመቻል፣ በአጠቃላይ የበሽታ መከላከል አቅም መዳከም ከ40 ዓመት በኋላ ይበረታሉ፡፡ ለመሆኑ ከ40 ዓመት በኋላ የብዙዎች ስጋት የሚሆኑት እነዚህ የጤና ችግሮች የትኞቹ ናቸው፡፡ ምንስ በማድረግ ቀድሞ መከላከልና መቆጣጠር ይቻላል? ጥቂቶቹን አነሳስተን የባለሞያዎቹን ምክር እናስከትላለን፡፡

1. የከፍተኛ የደም ግፊት መዘዝ

ከፍተኛ የደም ግፊት፣ በርካታ ሰዎችን በኢትዮጵያም ሆነ በተቀረው የዓለም ክፍል የሚያጠቃ ከፍተኛ የጤና ችግር ነው፡፡ ችግሩ ታዲያ የግፊቱ መጨመር ብቻ ሳይሆን ይህን ተከትለው የሚመጡት እንደ ልብ ህመም፣ ስትሮክ፣ የኩላሊት ሥራ መቆም፣ የስንፈተ ወሲብና ሌሎችም ናቸው፡፡ የደም ግፊትን መቆጣጠር ካልቻ በረጅም ጊዜ እነዚህ የጤና ቀውሶች መከተላቸው አይቀርም፡፡ ከፍተኛ የደም ግፊትን የሚያመጡት እንደ ከፍተኛ የኮሌስትሮል መጠን በደም ውስጥ መገኘት፣ በዘር የሚተላለፍ ደም ግፊት፣ እንዲሁም በደም ቧንቧዎች ላይ የሚደርስ ጉዳት ቀዳሚዎቹ ናቸው፡፡ በተለይ ዕድሜ እየገፋ ሲመጣ ተጋላጭነት እየጨመረ የሚመጣባቸው፣ የልብና የደም ቧንቧ ህመሞች ክትትልና ህክምና ካልተደረገላቸው ህይወትን እስከመውሰድ የሚደርስ አደጋ አላቸው፡፡ ከፍተኛ የደም ግፊትን ለመቆጣጠር በባለሙያዎች የተቀመሙ መድሃኒቶችን ሰዎች ለረጅም ጊዜ መውሰድ ግዴታቸው ሲሀን፣ ግፊቱን የሚጨምሩ የምግብ አይነቶችንና መጠጦችን ከመውሰድ እንዲቆጠቡም ይመከራል፡፡

2. የልብ ህመም

‹‹ብር የሚገኘው በልጅነት፣ ልብ የሚገኘው በ40 ዓመት›› የተሰኘው የአባቶች ብሂል፣ በወጣትነት ጊዜ የብር አጠቃቀማችንን ግዴለሽነት ለመግለፅ የተነገረ ይመስላል፡፡ አባባሉ ከጤና አንፃር ደግሞ የሚያስከትላቸው ተጨማሪ ሐሳቦችም አይጠፉም፡፡ ብር በልጅነት ብቻ ሳይሆን በ40 ዓመትም ይገኛል፡፡ ነገር ግን ብሩ የልብ ጤና ጠንቅ የሆኑ የአኗኗር ስልቶችንም ይዞ ይመጣል፡፡ እንቅስቃሴ የጎደለው የሥራ ጠባይ፣ ቅባትና ስኳር የሚያጠቃቸው ምግቦችን ማዘውተር፣ መጠጥና በምቾት ስም የሚመጡ ስልቶች ለጤና ጠንቅ ይሆናሉ፡፡ በተለይ ከ40 ዓመት በኋላ፣ እነዚህ ችግሮች ተጠናክረው የሚመጡ በመሆኑ ጥንቃቄው ግድ ነው ይላሉ ባለሙያዎች፡፡ ኮሮነሪ አርተሪ የሚባለው ቧንቧ ሥራው ይስተጓጎላል፡፡ ሌሎች ለተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ደም በስርዓት የማድረስ ስራዎችም፣ ከ40 ዓመት በኋላ በሚከሰቱ የኑሮ የሰውነት ፊዚዮሎጂ ለውጦች ምክንያት ይመጣሉ፡፡

3. የስኳር ህመም

ከ2 ሚሊየን በላይ የስኳር ህሙማን ባሉባት ኢትዮጵያ፣ ተጨማሪ 3 ሚሊዮኖች ደግሞ ቅድመ ስኳር በሚባለው ደረጃ ይገኛሉ አሊያም ተጋላጭ ሆነው ይገኛሉ፡፡ ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገራት ናይጄሪያንና ደቡብ አፍሪካን ተከትላ፣ ኢትዮጵያ በስኳር ህሙማን ብዛት በሶስተኛነት ተቀምጣለች፡፡ የስኳር ህመም ሁልጊዜ ከ40 ዓመት በኋላ የሚመጣ ችግር አይደለም፡፡ በህፃናት ላይ የሚከሰትበትም አጋጣሚ ጥቂት አይደለም፡፡ ነገር ግን አጋላጭ የሚባሉት እንደ ከፍተኛ ደም ግፊትናልብ ህመም እንዲሁም ከእንቅስቃሴ መራቅ በርክተው የሚታዩት ከ40 ዓመት በኋላ በመሆኑ፣ ስኳርን ከ40 በኋላ በመሆኑ፣ ስኳርን ከ40 በኋላ የሚመጣ ፈተና በሚለው በዚህ ዝርዝር ልናካትተው ወደናል፡፡

የኢኮኖሚ ዕድገትና ከተሜነት እየተስፋፋ መምጣት፣ የብዙዎቹ ኢትዮጵያ ክልሎች እውነታ እየሆነ ነው፡፡ ታዲያ የከተሜነት ህይወቱ ይዞት የሚመጣው ስልጣኔና የተሻለ የኑሮ ዘዬን ብቻ አይደለም፡፡ ለጤና ጠንቅ የሆኑ የአመጋገብ፣ መጠጥና እንቅስቃሴ ለውጦችም ይመጣሉ፡፡ ከጤናማው አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ፋይበር ነክ ምግቦች ይልቅ ስጋና ቅባት ነክ ምግቦችን ማዘውተር፣ ከእግር ጉዞ ይልቅ እየተጋፉም ቢሆን ትራንስፖርት መጠቀም፣ የሆነለትም መኪና ላይ የሙጥኝ ማለት እንዲሁም ከእንቅስቃሴ ሙሉ ለሙሉ መራቅ የዘመናዊነቱ ክፋቶች ሆነዋል ይላሉ ባለሙያዎቹ፡፡ መጠጥና ሲጋራም የራሳቸው አስተዋፅኦ አላቸው፡፡ ይህ በአብዛኛው በከተሞ አካባቢ እየተስፋፋ ያለ የኑሮ ዘዬ ለውጥ፣ በክልሎችም እየተስፋፋና ለስኳር ህመም በአስደንጋጭ ሁኔታ መጨመር መንስኤ ሆኖ እየተነሳ ነው፡፡ ለዚህ የኑሮ ዘዬ ለውጥ መፍትሄውና ከስኳር ህመም መጠበቂያው መፍትሄ፣ አንድ ጊዜ ቁጭ ብሎ ራስን መፈተሽና ዘላቂውን የጤና ቀውስ ማሰብ እንደሆነ ባለሞያዎቹ ይጠቅሳሉ፡፡

ሥጋና ጮማ ማንም በየቀኑ ቢያገኝ አይጠላም፡፡ የባለሞያዎችም ምክር ይህን እርግፍ አድርጋችሁ ተዉ አይደለም፡፡ ምጣኔ እናበጅለት ነው፡፡ በርካሽ የምንገዛቸው አትክልቶችና ፍራፍሬዎችን፣ ጥራጥሬዎችንና መሰል የእህል ዘሮችን በብዛት ብናዘወትር፣ በየዕለቱ ቢያንስ ከ20-30 ደቂቃ እንቅስቃሴን ብናደርግና በቢሮ ውስጥም ለረጅም ሰዓት ተቀምጦ መስራት፣ የስራው ጠባይ ከሆነ በየተወሰነ ሰዓት እየተነሳን ብንንቀሳቀስ፣ ከሊፍት ይልቅ ደረጃውን በእግር ብንወጣው እና ንቁ የኑሮ ዘዬን ብንለመድ የስኳር ህመምን ብቻ ሳይሆን ኩላሊት፣ ካንሰር፣ ጉበት፣ ኮሌስትሮል እና መሰል ጉዳይ መንስኤዎችን መቆጣጠር እንደሚቻል ነው ባለሞያዎቹ የሚያሳስቡት፡፡

 

4. ስትሮክ

ስትሮክ ከልብ ጤና ጋር ጥብቅ ትስስር አለው፡፡ የልብ ደም ቧንቧዎች በቂ ደም ወደ ጭንቅላት መውሰድ ሲሳናቸው ወይም ጭንቅላት ውስጥ ያሉትም የደም ቧንቧዎች በከፍተኛ ደም ግፊት ሲፈነዱ የሚፈጠረው የጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ ስትሮክን ያስከትላል፡፡ ይህ የጤና ችግርም እንዲሁ ዕድሜ ሲጨምርና አርባዎቹን ሲዘል የሚጎበኝ በጥንቃቄ ሊታይ የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ የደም አቅርቦቱ ወደ ጭንቅላት መድረስ ሲያቆም ወይም በከፍተኛ ሁኔታ ሲቀንስ የተለያዩ አካላት ስራቸውን ያቆማሉ፡፡ ራስ ምታት፣ እይታ መደብዘዝ፣ ግራ መጋባት፣ መናገር ማቃት እና የመሳሰሉት መገለጫዎች ስትሮክን ይናገራሉ፡፡ ስትሮክን ከማከም መከላከሉ ቅድሚያ የሚሰጠውና ውጤታማው ስትራቴጂ መከላከሉ እንደሆነ በማዮ ክሊኒክ ከፍተኛ ኤክስፐርት የሆኑት ዶ/ር ዴቪድ ሊ ለሪደርስ ዳይጀስት ገልፀዋል፡፡

5. የጀርባ ህመም

የጀርባ ህመም፣ ዓለም የቆመች ያህል እንዲሰማን የሚያደርግ ህመሙን መቋቋምም የሚያስቸግር የጤና ጉዳይ ነው፡፡ የጀርባ ህመም በተለያዩ የጡንቻ፣ ነርቭ እና ዲስክ ችግሮች ሊከሰት የሚችል ሲሆን፣ ዕድሜ ሲገፋ አጥንት እና ጡንቻዎች ከመዳከማቸው አንፃር 40ዎቹን ሲያልፉ የጀርባ ህመምን ሊጠብቁት ይችላሉ፡፡ የጀርባ ህመምን በጊዜ ለሐኪም ማሳየት ቀዳሚው ውጤታማ ችግሩን የማሸነፊያ ዘዴ ነው ይላሉ ሪደርስ ዳይጀስት ያነጋገራቸው ኤክስፐርት፡፡ ስለሆነም መውደቅን የመሰለ አደጋ ካለ እና ማናቸውንም ለጀርባ ህመም የሚዳርግ የበሽታ ምክንያት በፍጥነት ታከሙት ይላሉ ባለሙያው፡፡

6. የወሲብ ድክመት

እንደተቀሩት የአካል ክፍሎቻችን ሁሉ፣ ስኬታማ ወሲብ ለመፈፀም በቂ የደም አቅርቦት፣ ጤናማ ስሜትና አካላዊ ሁኔታዎች ወሳኝ ናቸው፡፡ ዕድሜ ሲገፋ ይበረታሉ ያልናቸው እንደ ልብ ህመም፣ ከፍተኛ የደም ግፊትና ስኳር ህመሞች በወሲህ ሕይወት ላይ ከፍተኛ ጫናን ያደርሳሉ፡፡ በቂ የደም ፍሰት እጥረት ምክንያት፣ ብልትን እንደ ልብ ማቆም አለመቻል በወንዶች፣ በብልት መድረቅ ደግሞ በሴቶች ከዚህ አንፃር በብዙ ሰዎች ዘንድ የሚታዩ ችግሮች ናቸው፡፡ በስራ ውጥረትና በቤተሰብ ጉዳዮ የሚነሱ፣ የአዕምሮ ሰላምን የሚነሱ ጉዳዮችም ስነ ልቦናዊ ጫናቸው ከበድ ስለሚል በወሲብ መደሰትን ፈተና ውስጥ ሲከትቱት ይታያል፡፡ እንደ ሌሎች ከበድ አድርገን እንደምናያቸው የጤና ችግሮች፣ ወሲብ ላይ ችግር ሲኖር በግልፅ ተነጋግሮ ለመፍታት መጣርን ኤክስፐርቶች ይመክራሉ፡፡ ከትዳር ወይም ፍቅር ጓደኛ በተጨማሪ የስነ ልቦና ምክርና ሌሎች አካላዊ ችግሮችን ለመፍታት ዕድሜው አይረፍድምና ችላ አይበሉት የባለሞያው ምክር ነው፡፡

7. የዕይታ መድከም

በዚህ ዕድሜ ውስጥ ተዘውትሮ የሚታየው ጉዳይ የዕይታ መዳከም ነው፡፡ ይህ በልዩ መጠሪያው ፕሪስባዮፒያ የሚባለው የማየት መዳከም፣ በተለይ በዓይን ሌንስ ብርሃን ማንፀባረቅ ድክመት ጋር ተያይዞ የሚከሰት ሲሆን፣ ከዚህ ዕድሜ ጀምሮ እንደ ልብ የማንበቡ ነገር መጽሐፍም ሆነ ኮምፒዩተር ወይም የምግብ የሬስቶራንት ሜኑ ንባብ እየተዳከመ ይመጣል፡፡ ይህ ደግሞ በየጊዜው እየጨመረም ይመጣል፡፡ ይህ ደግሞ በየጊዜው እየጨመረም ሊመጣ ይችላል፡፡ ከዚህ አንፃር አርቀን ለማንበብ ጥረት ልናደርግ እንችላለን፡፡ በርቀት የማየት ችግር ኖሮባቸው መነፅር ሲያደርጉ የነበሩ ደግሞ ከዚህ ዕድሜ ጀምሮ በቅርበት ለማንበብ ከመነፅራቸው ይልቅ ባዶ ዓይናቸው የተሻለ ሆኖ ሊያገኙት ከቻሉ ችግሩ ጀምሯቸዋል ማለት ነውና ማንኛውም ሰው፣ ከዚህ ዕድሜ በኋላ በየሁለት ዓመቱ አንዴ የዓይን ምርመራ በማድረግ ተገቢ መነፅሮችን ለመጠቀም መዘጋጀት አለበት፡፡

8. የትውስታ መድከም

ከአሁን ቀደም የተለያዩ ነገሮችን የማስታወስ ብቃታችን ከዕድሜ ይከሰታል ተብሎ የሚጀምረው ከ60 ዓመት ጀምሮ ነበር፡፡ በቅርቡ ይፋ የሆኑ አዳዲስ ጥናቶች ግን ለማስታወስ መቸገር፣ ለውጡ ከ40 ዓመት ጀምሮ ሊታይ እንደሚችል ነው፡፡ ለ10 ዓመታት ያህል በ2200 ሴቶች ላይ በተደረጉ ጥናቶች ያመለከቱትም፣ የሰዎች የአዕምሮ ብቃትና የትውስታ አቅም ከ45 ዓመት ጀምሮ መቀነስ ይጀምራል፡፡ ይህ ማለት ደግሞ በተቻለ መጠን ሁኔታውን ተረድተን የአዕምሮ ትኩረትንና የማስታወስ ብቃትን የሚጨምሩ፣ የአካል ብቃትና የአዕምሮ ስፖርቶችን (እንደ ሜዲቴሽና ዮጋ) መከወን ያስፈልጋል፡፡ እንዲሁም ልብን መከላከል ጭንቅላትን መጠበቅ ነውና፣ በተለይ የልብ ጤናማነት ላይም አጥብቆ መስራት ሌለው ምክር ነው፡፡

loer back

7. ሜኖፓዝ

ይህ በተለይ በ40ዎቹ በሴቶች ላይ ብቻ የሚከሰት ችግር ነው፡፡ ይህም የወር አበባ ማቆምን ተከትሎ በሴቶች ላይ የስነ ልቦና ለውጦች መንፀባረቅ የሚጀመርበት ጊዜ ነው፡፡ በአማካይም ከ45ኛው ዓመት ዕድሜ ጀምሮ የአብዛኛዎቹ ሴቶች የወር አበባ መቆራረጥና የሴትነት ሆርሞን ምንጮች መዛባት የሚጀመርበት በመሆኑ፣ ለዚህ መሰል ተፈጥሯዊ ዑደት መዘጋጀትና በሐኪም ትዕዛዝ ሊወሰዱ የሚችሉ የሴትነት ሆርሞን አረጋጊ ክኒኖችን እንዲሁም እንደ ካልሲየም የመሰሉ የማዕድን እንክብሎች መውሰዱ መልካም ነው፡፡ ለማንኛውም እነዚህ የዕድሜ ለውጦችን ተከትለው የሚጀምሩ ናቸው ለማለት እንጂ እርጅና ጀመረ ማለታችን አይደለምና ተስፋ የሚያስቆርጥ አይደለም፡፡ ሌላ 40፣ 50 እና 60 ዓመት እንጠብቃለንና፡፡

አጠቃላይ ምክር 

ለልብና ደም ቧንቧዎች ጤና የምናደርገው ክብካቤ፣ እስከ ወሲብ ህይወታችን የሚደርስ ጠቀሜታን ስለሚሰጥ እዘህ ላይ ትኩረት ማድረግን ባለሞያዎቹ ይመክራሉ፡፡ እንደ ችግሩ ተጨባጭ ሁኔታ ከሐኪም ጋር በመነጋገር፣ ከ40ዎቹ በኋላ የሚመጡትን የጤና ችሮች በምክክርና ህክምና ማስወገድ ይቻላል፡፡ ከህክምናው በፊት ግን ቢተገበሩ ውጤት ያመጣሉ ሲሉ ባለሞያው የተወሰኑ ምክሮችን ይዘረዝራሉ፡፡

ቋሚ የሆነ ኦክስጅንን የሚጠቀም፣ ደከም የሚያደርግ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ልምድ ማድረግ አርባዎቹ ውስጥም ይቻላል፡፡ ይህም በሰውነት የተጠራቀመ ቅባትን በፍጥነት በማቃጠል፣ ከስብ መከማቸት የሚመጡትን የደም ቧንቧ መጥበብና በዚህ መነሻነት የሚመጡ በሽታዎችን ለማራቅ ይረዳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ጡንቻን የሚገነቡ እንቅስቃሴዎችም ጥሩ ናቸው፡፡ መንፈስን ዘና የሚያደርግ የእግር ጉዞ፣ ሜዲቴሽ፣ ብዙ ፈሳሽ መጠጣት (አልኮልን አይጨምርም)፣ ቅባት እና ስኳር ነክ ምግቦችን በልኩ ማድረግና ቀለል ወዳሉት የአትክልትና ፍራፍሬ፣ ዓሣ እና ጥራጥሬ ነክ ምግቦች ማዘንበል፣ በ40ዎቹ ዕድሜ የሚመከሩ ሌሎች ብዙ 40 ዓመቶችን መጨመር የሚያስችሉ የባለሞያዎቹ ምክሮች ናቸው፡፡

The post Health: በ40ዎቹ ውስጥ ያሉ ወንዶችና ሴቶች ሊጠነቀቋቸው የሚገቡ 9 ዋነኛ የጤና ችግሮች appeared first on Zehabesha Amharic.

ጊዜዉ መተባበርን እና መናበብን የሚጠይቅበት ወቅት ላይ ነን –ነፃነት በለጠ

$
0
0

 

tumblr_inline_n407i5d6ch1qersu1በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን መነሻነት በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ አርሶ አደርች መፈናቀላቸዉን በመቃወም በኦሮሚያ ክልል ዉስጥ ባሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ የሁለተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች አማካኝነት የተነሳዉ ተቃዉሞ መጠኑ እየጨመረ እና ተቃዉሞዉ እየተጠናከረ በመካሄድ ላይ ነዉ፡፡ ይህንን ተቃዉሞ ለማዳፈን የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች እየወሰዱ ያሉት የሃይል እርምጃ ጭካኔ የተሞላበትና ለድብደባ፣ ለግርፋት፣ ለስቃይ እና ለግድያ የዳረገ ነዉ፡፡

ህወሃት (ወያኔ) ገና ከምስረታዉ ጀምሮ የጨነገፈ እና የዲሞክራሲ ባሕርይ ያልነበረዉ ድርጅት ለሥልጣን ሲበቃ ከዚህ ባሕርይዉ ሳይላቀቅ ላለፉት 24 ዓመታት በዜጎች ላይ ግፍና በደል እየፈፀመ ይገኛል፡፡ በዚህ ሰሞን እየተቀጣጠለ ያለዉን የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃዉሞ የኃይል ርምጃ በመዉሰድ ለመከላከል ቢሞክርም እንዲያዉም የተቃዉሞዉ አድማስ እየሰፋ እና እያደገ ሊሄድ ችሏል፡፡ የወያኔ መንግስት እያደረሰ ያለዉ በደል በሁሉም ክልሎች ባሉ ኢትዮጲያዉያን ላይ እየደረሰ ያለ እንጂ የተወሰኑ አካባቢዎችን ብቻ የሚሸፍን አይደለም፡፡ የግፍ አገዛዙ ያስከተለዉ ፖሊቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ባህላዊ ቀዉስ ከዳር እሰከዳር ያዳረሰ ጉዳይ ነዉ፡፡

ይህ በጎሳ ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ ስርዐት ያስከተለዉ መዘዝ እርስ በርሳችን እንዳንግባበ፣ በጎሳችንን ማንነት ዉስጥ ብቻ ተደብቀን ሀገራዊ ስሜት እንዳይኖረን በመደረግ ላይ መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነዉ፡፡ ስለሆነም አሁን በኦሮሚያ ክልል ዉስጥ እየተካሄደ ያለዉን ተቃዉሞ ሰርዐቱ ለነደፈዉ የጎሳ ፖሊቲካ የተመቻችን በመሆናችን በኦሮሚያ እና በጎንደር እየተካሄደ ያለዉን ተቃዉሞ የኛም ተቃዉሞ ነዉ በማለት ድጋፍ ስንሰጥ ብዙም አይታይም፡፡ ለወያኔ መሰሪ ስራ ተመቻችተናል ማለት ነዉ፡፡ በወያኔ ካምፕ የሚፈለገዉ ይህ እርስ በርስ አለመናነበብ፣ አለመተባበር መሆኑ እየተረጨ ላለዉ በጎሳ እና በሃይማኖት የመከፋፈል እስትራቴጅ ራሳችን አዘጋጅተን የወያኔን የስልጣን እና የግፍ አገዛዝ ዕድሜ እያራዘምን ነዉ ማለት ነዉ፡፡

የኦሮሚያ ተማሪዎችና በጎንደር ያለዉን ተቃዉሞ የእኛም ተቃዉሞ መሆን ስለአለበት በምንችለዉ መንገድ አጋርነታችንን ማሳየት አለብን፡፡ ይህ የአዲስ አበባ ማስፋፈያ ማስተር ፕላን ያስነሳዉ ተቃዉሞ ሰብብ እንጂ ዋናዉ ምክንያታችን ለላፉት 24 ዓመታት በዲሞክራሲ ጭምብል የወያኔ መንግሰት እየፈፀመ ያለዉ ማለቂያ የሌለዉ ጭቆና ድምር ዉጤት ነዉ፡፡ ስለዚህ የኦሮሞ ተማሪዎች እና የጎንደር ህዝብ የመረረ ተቃዉሞ የሁላችንም ተቃዉሞ ስለሆነ ከጎናቸዉ በመሆን ትግላቸዉን ልናጠናክር ይገባል፡፡

ይህ ካልሆነ ግን የበዛ ጥፋት፤ እንግልት እና መበታተን ሊያስከትልብን ይችላል፡፡ ለመጥቀስ ያህል ለወያኔ ከፋፈልለህ ግዛዉ ፖሊሲ የተመቻቸን እንሆናለን፣ ቀጥሎም በህዝቦች የእርስ በርስ ግንኙነት መጥፎ ጠባሳ ጥሎ ያልፋል፣ በተጨማሪም በጋራ የኢትዮጲያን ብሄራዊ አንድነት ለማስጠበቅ በሚደረገዉ እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ ጋሬጣ እንሆናለን ፡፡ አልፎም ለኢትዮጲያ የዉጭ ጠላቶች በቀላሉ እንጋለጣለን፡፡ ስለዚህ ወቅቱ መተባበርን፣ እርስ በርስ መደጋገፍን የሚጠይቅበት ወቅት ላይ ነን፡፡ የወያኔ አገዛዝ ዕድሜዉ እያጠረ መሆኑን የተለያዩ ምልከቶች ተጠናክረዉ እየታዩ ስለሆነ ሁሉም ኢትዮጲያዊ ለሐገራችን መፃኢ ዕድል መቃናት፣ የተሻለች እና ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጲያን ለመመስረት የበኩሉን አስተዋፅዎ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ ይህንን የህዝብ ትብብር ዕዉን እንዲሆን የሚከተሉት ማህበራዊ ኃይሎች ከፍተኛ ኃላፊነት ይጠበቅባቸዋል፡፡

ለተቃዋሚ ኃይሎች

የተቃሚዉ ክፍል በራሱ ዉስጣዊ እና ዉጫዊ ምክንያቶች በመነጩ ችግሮች ተተብትቦም ቢሆን  የራሱን ድርሻ ለመወጣት በመንገዳገድ ላይ ይገኛል፡፡ ወያኔ በመሰሪ ተግባሩ የራሱን ሰዎች አስርጎ በማስገባት ትርምስ በመፍጠር ለሁለት እንዲከፈሉ በማድረግ ጠንካራ ናቸዉ የሚባሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ተዳክመዉ እና መኖራቸዉ የሚረሳበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል፡፡ በምርጫ ወቅት ብቻ ድምፃቸዉ የሚሰማዉ አንዳንድ አደርባይ ተቀዋሚዎች ለዚህ የፖሊቲካ ሴራ ድርሻቸዉን በመወጣት አስከአሁን ዘልቀዋል፡፡ አሁንም በኦሮሚያ ክልል ዉስጥ  እየተካሄደ ያለዉን የተቃዉሞ እንቅስቃሴ አስከአሁን ባለኝ መረጃ የሰማያዊ ፓርቲ ካወጣዉ የተቃዉሞ መግለጫ በስተቀር ሌሎቹ ድምፃቸዉ እየተሰማ አይደለም፡፡ ጊዜዉ ተቀናጅተን የተጀመረዉን ትግል ተጠናክሮ እንዲቀጥልና አድማሱ እየሰፋ እንዲሄድ የተቃዋሚ የፖለቲካ ኃይሎች ሰፊ ሚና ይጠበቅባቸዋል፡፡ ወያኔን ለማንበርከክ ለወያኔ ምቹ የሆነዉን እርስ በርስ መናቆር እና መናናቅ ጥለን በጋራ መንፈሰ ስንፋለም ነዉ ጨለማዉ ተገፎ የተሻለች ኢትዮጲያን እዉን ማድረግ የሚቻለዉ፡፡ ልዩነትን አቻችሎ በመተባበር የእግር እሳት የሆነብንን አምባገናነዊ መንግሰት በጋራ ከስሩ ስንመነግለዉ ነዉ ኢትዮጲያ ወደተሻለ የታሪክ ምዕራፍ የምትሸጋገረዉ፡፡ ስለዚህ የተቀዋሚዉ ጎራ ህዝብን በማሰባሰብ ወደ ተጠናከረ ትግል ማሸጋገር ይጠበቅበታል፡፡

ለመከላከያ፣ ለፌደራል ፖሊስ፣ ለልዩ ኃይል እና ለፖሊስ አባላት

በኦሮሚያ እና በጎንደር የተቀጣጠለዉን የተቃዉሞ እንቅስቃሴ በአለቆቻችሁ ታዛችሁ የምትፈፅሙት ግድያ፣ ድብደባ፣ ግርፋት እና ማሰቃየት በገዛ ወገናችሁ ላይ መሆኑን ዘንግታችሁታል ማለት አይቻልም፡፡ የሌሎች ሃገር የፀጥታ ኃይሎች የጉዞ መንገድ በመከልከል፣ ዉሃ በመርጨት፣ ዙሪያ ከቦ እንዲቀመጡ ማድረግ፣ ከፋ ከተባለ አስለቃሽ ጢስ በመጠቀም ተቃዉሞን ለማብረድ ይሞከራሉ፡፡ ነግ ግን ከአብራኩ ወጥታችሁ የገዛ ወንድሞቻችሁን እና እህቶቻችሁን በአጠቃላይ ወገናችሁን ርህራሄ በጎደለዉ መንገድ የምትፈፅሙት ተግባር ታሪክ ይቅር የማይለዉ ነዉ፡፡

ከመካከላችሁ ከጥቂቶቹ ተጠቃሚ ክፍሎች በስተቀር እናንተ የበይ ተመልካች እንጂ ድህነቱ እና በኑሮ መንገላታቱ በእናንተም እየደረሰ ያለ ነዉ፡፡ ስለሆነም የወያኔን ዕድሜ ከማራዘም እና ወገናችሁን ለስቃይ ከመዳረግ በመቆጠብ የወገን አጋርነታችሁን በተለያየ መልኩ መግለፅ ይጠበቅባችኃል፡፡ አፈሙዙን ወደ ስርዐቱ ላይ በማዞር የወያኔን ዕድሜ በማሳጠሩ ትግል የበኩላችሁን ደርሻ መወጣት ይጠበቅባችኃል፡፡

ለኃይማኖት መሪዎች

በሰላማዊ መንገድ ለተቃዉሞ የወጡ ወጣቶች እና የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ያልተመጣጠነ የኃይል ርምጃ ሲወሰድ እና የሰዉ ልጅ ነፍስ ሲጠፋ እናንተ ዝምታን መምረጣችሁ ምን ይባላል? ተገቢስ ነዉ? ለእዉነት በመቆም፣ ትክክል ያልሆነ ነገር ሲፈፀም በግንባር ቀደምትነት ቤዛ መሆን የሚጠበቀዉ ከእናንተ ከኃይማኖት መሪዎች ነበር፡፡ በብዙ መንገድ ከስርዐቱ ጋር ላለመላተም አይታችሁ እንዳላያችሁ አልፎም ለስርዐቱ አገልጋይ በመሆን መስለፍን የመረጡ የኃይማኖት መሪዎች በመካከላችሁ እንዳሉ ይታወቃል፡፡

በኦሮሚያ በሰላማዊ መንገድ እየተካሄደ ያለዉን እንቅስቃሴ ለመግታት የመንግሰት የፀጥታ ኃይሎች በምላሹ እየወሰዱት ያለዉ የሃይል ርምጃ በማዉገዝ መንግሰት ከዚህ አሳፋሪ ተግባሩ እንዲታቀብ ማሳሰብ እና ማስጠንቀቅ ይጠበቅባችሁ ነበር፡፡ ግን ምንም የተፈጠረ ስለማይመስለን ለወገኖቻችን ያለን ተቆርቋሪነት ደረጃ እጅግ ዝቅተኛ ነዉ፡፡ አሁንም ጊዜዉ ስላልረፈደ ሁሉም እምነቶች መከፋፈልን የሚሰበኩ ባለመሆኑ ተከታዮቻችሁን በዘር እና በኃይማኖት መከፋፈልን ትተዉ እንዲተባበሩ የራሳችሁን ድርሻ ልትወጡ ግድ ይላል፡፡

ለዲያስፖራ ኮሚኒቲ

በሀገራችን ዉስጥ ያለዉ የዘር ፖሊቲካ ያመጣዉ ጣጣ ለእናንተም ተርፎ በእናንተ ካምፕ ዉስጥ ያለዉን መቆራቆስ ከተለያዩ መረጃዎች እንከታተላለን፡፡ በልማት የተሻለ ደረጃ ባሉ ሀገሮች እየኖራችሁ እና የሰለጠነዉ ዓለም በመተባበር እየሰሩ ያሉትን ነገር እያሰተዋላችሁ የምትገኙ ዲያስፖራዎች የሀገራችንን ሰዎች እንዲተባበር እና ልዩነትን እንዳያራግብ ታስተምራላቸሁ ሲባል ወደ መንደር ደረጃ ወርዳችሁ እርስ በርስ ስትናቆሩ መስማት ለእኛ በሀገር ቤት ላለን ምን ያህል እንደሚያመን ልትገነዘቡት ይገባ ነበር፡፡ ሆኖም መሬት ላይ ያለዉ ዕዉነታ ግን ለወያኔ መሰሪ ፖለቲካ ተመቻችታችሁ በሰለጠነ መንገድ በመነጋገር ችግሮቻችሁን ከመፍታት ይልቅ ጎራ ለይታችሁ በመናቆራችሁ በሀገር ቤት ላለዉ የፀረ-ወያኔ ትግል መሳሪያ በመሆን እያገለገላችሁ መሆኑን ልትገነዘቡት ይገባል፡፡ ወያኔን ማንበረክክ የሚቻለዉ ስንተባበር ነዉ፡፡ ሰለዚህ በኦሮሚያ እና በጎንደር የተጀመረዉን ትግል ባላችሁበት ቦታ የትግል አጋርነታችሁን መግለፅ ይጠበቅባችኃል፡፡ ላላችሁበት መንግስት እየተፈፀመ ያለዉን ግድያ፣ ድብደባ እና ማሰቃየት እንዲሁም በደርቅ ሳቢያ የተከሰተዉን የከፋ የረሃብ አደጋ ለአለም ህብረተሰብ ልታሳወቁ ይገባል፡፡ ለመንግስታት መሪዎች በአገራችን ያለዉን መከራና ግፍ በማስገነዘብ በኩል ድርሻችሁ የላቀ ነዉ፡፡

በመጨረሻም እናንተ ለእኛ አርአያ በመሆን ያለባችሁን የፖለቲካ ልዩነት በመነጋገር፣ ልዩነቶቻችሁ የማይታረቁ ከሆነ በሚያግባባችሁ በጋራ በመስራት እዉነተኛ እና ዜጎች በእኩልነት የሚኖሩባትን ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጲያን ለመመስረት የሚደረገዉን እልህ አስጨራሽ ትግል በማገዝ የበኩላችሁን ድርሻ ልትወጡ ይገባል፡፡ በአስተሳሰብ፣ በአመለካከት መለያየት ጠላትነትን አያሳይም፡፡ ከዘር ብሔረተኝነት ወጥተን የህዝቦች እኩልነት እና ነፃነት የተከበረባት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጲያን በመመስረት ወደ ገበያ ብሔረተኝነት እንድንሸጋገር የእናንተ ሚና ሊናቅ አይችልም፡፡ እናንተም ለኢትዮጲያ ባለድርሻ ናቸሁና፡፡

ማጠቃለያ

ወያኔ / ኢህአዴግ የሚመራዉ ሰርዐት ኢትዮጲያን ያዋረደ፣ የዘር ፖሊቲካን የፖሊቲካ ሰርዐቱ ዋና ምስሶ በማድረግ ልብ ለልብ እንዳንገኛ ተግቶ እየሰራ ያለ እና ኢኮኖሚዉ በ11 ፐርሰንት አደገ በማለት በዘረፋ ለተሰማሩት ጥቂት የህብረሰተብ ክፍሎች ያመቻቸ እና ህዝቡን ግን ወደከፋ ድህነት የከተተ አስነዋሪ ስርዐት ነዉ፡፡ ይህ ግፈኛ ስርዐት በተቃዉሞ የሚመጣን ማንንም ክፍል በጉልበት ለማዳከምና ለማንበርከክ የሚሞከር አሁንም በጫካ ህግ እየተመራ ያለ መንግሰት ነዉ፡፡ ከዚሁ ጎን በሎሌነት ያሰለፋቸዉ ሆድ አደር ባለስልጣናት የዚሁ የክፋት ስራ ተባባሪ በመሆን ጌቶቻቸዉን ለማስደሰት አደርጉ የተባሉትን በመፈፀም እና ጥቅማቸዉ እንዲቀጥል በማድረግ ስርዐቱ ዕድሜዉ እንዲራዝም የሚቻላቸዉን ያህል እየተፍጨረጨሩ ይገኛሉ፡፡ በተለይ የኦሮሚያ  ባለስልጣናት በክልሉ ወጣቶች ላይ ወያኔን ለማስደሰት እየወሰዳችሁት ያለዉ ጭካኔ የተሞላበት ርምጃ ጊዜ ይወስዳል እንጂ የኢትዮጲያ ህዝብ እንደሚፋረዳቸሁ መጠራጠር የለባችሁም፡፡ ሆኖም ህዝብ ተባብሮ ከተነሳ የሚገታዉ አንዳችም ኃይል እንደሌለ በዓለም የተፈፀሙ የህዝባዊ መነሳሳቶች እና አብዮቶች ታሪክ ያስተምሩናል፡፡

የኢትዮጲያ ህዝብ ሆይ!! በኦሮሚያ፣ በጎንደር እና በሌሎችም አካባቢ እየተቀጣጠለ ያለዉን ህዝባዊ ተቃዉሞ በመደገፍ ሁላችንም ያለብንን የዜግነት ኃላፊነት ልንወጣ ጊዜዉ ይጠይቀናል፡፡

በህብረት እንነሳ !!!

ድል ለኢትዮጲያ ህዝብ !!!

ኢትዮጲያ በነፃነት፣ በሠላም እና በህብረት ለዘላለም ትኑር !!!

እግዚአብሔር ኢትዮጲያን ይጠብቅ !!!

 

The post ጊዜዉ መተባበርን እና መናበብን የሚጠይቅበት ወቅት ላይ ነን – ነፃነት በለጠ appeared first on Zehabesha Amharic.

ከ 10 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊያኖች ለረሃብ ሰለባነት ተጋልጠዋል |ድርቁ ከ 50 አመት ወዲህ በአስከፊነቱ ግዙፍ መሆኑ ተነግሯል

$
0
0

ከታምሩ ገዳ

ሞረሃብ ፣ድርቅ እና ሰቆቃው ከኢትዮጵያ ጋር የነበራቸውን ቁርኝት ዛሬም የፋቁት አይመሰልም። ዛሬም እንደቀደሞው ሁሉ አገራችን በምእራባዊያን የዜና ማሰራጫዎች ዘንድ ከረሃብ እና ከደርቅ ጋር በተያያዘ ስሟ እየተጠራ ይገኛል።ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአገሪቱ በሚገኙ በተለያዩ ክልሎች ላይ ያንጃበበው የረሃብ አደጋ ወደ 10.1 ሚሊዮን የሚገመት ሕዝብን ሊያጠቃ አንደሚችል የአለማቀፉ የሕጻናት ነፍስ አድን ድርጅት (Save the Children) በትላንትናው እለት (ታህሳስ 8 2015 አኤአ) ባወጣው ማሰጠንቀቂያው አስታውቋል።

ግብረሰናዩ ድርጅት በዚሁ መግለጫው ብዛታቸው 400 000 ህጻናት ለከፍተኛ የምግብ እጦት አደጋ ይጋለጣሉ ሲል ስጋቱን የገለጸ ሲሆን ይህ አይነቱ አደጋ ደግሞ አገሪቱ ካልፈው 50 አመት ወዲህ አይታው የማታውቀው ቁጣ ይሆናል ተብሎ ተሰግቷል።ለድርቁ መባባስ የኋላ ቀር የግብርና መርህ መከተል፣ የ መልካም አስተዳደር (ፖሊሲ)እና ገደብ የለሽ የሕዝብ ቁጥር መጨመር ምክንያቶች ኣንደሆኑ የሚተቹ ወገኖች የመኖራቸውን ያህል የአከባቢ አየር ተመራማሪዎች በበኩችአው የሞቀ አየር በውቂያኖስ ላይ መንሰራፋት እና ዝናብ ተኮር ለሆኑ የእርሻ አካባቢዎች በቂ እርጥብ አየር ከውቅያኖስ ወደ መሬት ያለመንፈሱ (ኢሊኖ)ዋንኛ ችግር ነው ይላሉ።

ከዚሁ ጋር ችግር በተያያዘ በአንድ ወቅት ከራሳቸው ተርፈው ለሸማቾች ይተርፉ የነበሩ አርሶ አደሮች የሚቀምሱት እና የሚልሱት በማጣታቸው ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ጠያቂነት የተዳረጉ ሲሆኑ የህይወታቸው ዋልታ እና ምሰሶ የሆኑት የቀንድ እና የጋማ ከብቶችም በገፍ በመሞት ላይ መገኘታቸውን ከድርቁ አካባቢዎች የሚወጡ ዘገባዎች ያሳያሉ።ምንም እንኳን እስከ አሁን ድረስ ድርቁ በሰው ሕይወት መቀጠፍ ላይ ያደረሰው አደጋ አለመኖሩን ፣ የተረጂዎችም ቁጥር ከ 8 .2 ሚሊዮን በላይ ከፍ እንዳላለ እና ድርቁም ከቁጥጥር ውጪ እንደማይሆን ገዢው መንግስት በተለይ ደግሞ አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ በቅርቡ “ጋሶች ለፈትኑን አሰበዋል እና ግን ድርቁን በራሳችን እንቋቋማለን ማለታቸው የሚታወስ ሲሆን የአደጋው መጠነሰፊነት በተመለከተ አለማቀፍ ጣልቃ ገብነት እንደሚያሰፈልገው (ሲቭ ዘ ች ልድረን) በመግለጫው አጥብቆ ሳያስጠነቅቅ አላለፈም።
ይህ ከ አምስት አስርት አመታተ ወዲህ በአይነቱ የከፋ ነው የተባለው ድርቁን አና ተያያዥነት ያላቸው ችግሮችን ለመቋቋም ቢያንስ የ$4.1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር አንደሚያሰፈልግ በአኢቶጵያ የግብረ ሰናዩ ድርጅት ተጠሪ ጆህን ግርሃም “በሁዋላ የከፋ አደጋ ተከስቶ ከምንጸጸት በፊት ለተጎጂዎቹ አፋጣኝ ምላሽ እንሰጥ “ሲሉ ምእራባዊያን ለጋሾችን ተማጸነዋል። እዚህ ላይ ከየአቅጣጫው የሚሰነዘሩት የቁጥር ጫዎታዎች እና የፖሊቲካዊ ፍልሚያዎች በዙም እንደማይጠቅሙ የሚናገሩት የፖለቲካ ተንታኞች ፖሊቲካውም ሆነ ሽኩቻዎቹ ሕዝብ የሚበላው እና የሚጠጣው ሲኖርው ብቻ ነው የሚያምረው በማለት መምከራቸው እና ቅድሚያ ለደርቁ እና ለተጎጆዎቹ ወገኖች ማለታቸው

The post ከ 10 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊያኖች ለረሃብ ሰለባነት ተጋልጠዋል | ድርቁ ከ 50 አመት ወዲህ በአስከፊነቱ ግዙፍ መሆኑ ተነግሯል appeared first on Zehabesha Amharic.

ለወያኔ ድርጊት፣ ምን ስም እናውጣለት-ይገረም ዓለሙ

$
0
0

ወገንን ጨፍጫፊ ቆዳው የነጣ ነው

በአበሻ የሚጨክን ፈረንጅ ብቻ ነው፤

እያለ የሚያስብ የዋህ ፍጡር ማነው

ጨፈጫፊ ከሆነ አበሻም ጣሊያን ነው

እንቶኔም በተግባር ሲኞር እንቶኔ ነው፤

Woyaneበየግዜው እየከፋ የሄደውን የወያኔ አረመኔነትና የሀገራችንን ጉዞ ወዴትነት ሳስብ ትውስ ያለችኝን ይህችን ስንኝ ወደ ማስታወሻየ ገልብጬ ያኖርኳት በ1980ዎቹ መጨረሻ ግድም ለንባብ ይበቁ ከነበሩት መጽሄቶች ከአንዱ ነው፡፡ ወያኔ ዴሞክራት መስሎ ለመታየት በሞከረበትና ትክክለኛ ማንነቱ ገሀድ ወጥቶ  ብዕርን ከጠመንጃ አስበልጦ መፍራት ባልጀመረበት በዛ ወቅት እንዲህ የጻፉት ሰው ዛሬ በህይወት ካሉ ምን ሊሉ እንደሚችሉ መገመት ይቸግራል፡፡

ወያኔዎች ደርግን በጨፍጫፊነት በማውገዝ ዛሬም ድረስ  ፈሺስት ናዚ ወዘተ በማለት ይገልጹታል፡፡ በዘመነ ደርግ የተፈጸመውን ቀይ ሽብርም ለአንድ ሰሞን የፖለቲካ ፍጆታ ሊጠቀሙበት ሞክረዋል፡፡ ግን ካወገዙት ተግባር ተምረው ከተጸየፉት ድርጊት ርቀው ሊገኙ አልቻሉም፡፡ በርግጥም ከጅምሩ ስለ ቀይ ሽብር የነበራቸው አያያዝ ሊማሩበት ሳይሆን ሊያደናግሩበት፤ ለተበዳዮች ፍትህ ሊያስገኙበት ሳይሆን ጥላቻን ሊያነግሱበት እንደነበረ መለስ ብሎ በማስታወስ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡  ከቀይ ሽብር ቢማሩ ኖሮ ራሳቸው ያቋቋሙት የቀይ ሽብር ኮሚቴ ይዞት የነበረውን “ያለመቻቻል ፖለቲካ ሰማዕታት፣መቼም እንዳይደገም የሚለውን መርህ  ተግባራዊ ባደረጉና  እንዲህ የለየላቸው ጨፍጫፊ  ባልሆኑ ነበር፡፡

የቀይ ሽብር ነገር ለወያኔ የፖለቲካ ካርድ በነረበት ወቅት የቀይ ሽብር ኮሚቴ ባዘጋጀው አንድ የውይይት መድረክ ላይ የጥናት ወረቀት ያቀረቡት ፕ/ር ባህሩ ዘውዴ የፖለቲካ ልዩነቶችንም በተመለከተ አንዱ ወገን ምንግዜም ቢሆን ፍጹማዊ እውነትን ሊታደል እንደማይችል ተገንዝቦ የሌላውን ወገን ሀሳብ እህ ብሎ ማዳመጥ መቻል ይኖርበታል፡፡ የተቀዋሚ ወገን አየለ ብሎ ቃታ ለመሳብ መጣደፍ ዞሮ ዞሮ ሀገርን በብርቱ የሚጎዳ መሆኑን ከ « ቀይ» ሽብር ያተረፍነው ትልቁ ትምህርት ነው” ብለው ነበር፡፡ ነገር ግን ወያኔዎች ቀይ ሽብርን ያራገቡት ፖለቲካ ሊቆምሩበት እንጂ ሊማሩበት ያለመሆኑን ውለው ሳያድሩ በጀመሩት የሁሉም ነገር መፍትሄ ከጠመንጃ ይመነጫል አይነት ተግባራቸው  አሳይተውናል፡፡

ሌላው ተናጋሪ የነበሩት ዶ/ር የራስ ወርቅ አድማሴ ባቀረቡት ጽሁፍ ደግሞ ከኛ ትውልድ ስህተት በመማር የልጆቻችንን ትውልድ ከፖለቲካ ግድያ፣ከዘር ማጥፋት ፍጅትና ከስጋትም ጭምር ነጻ በሆነችና ፍትህ በነገሰባት ኢትዮጵያ እንዲኖሩ እንመኛለን፡፡ ይህን ምኞታችንን እውን ካደረግን ደግሞ እሱ ጊዜ የማይሽረውና የማያደበዝዘው ዕውነተኛው የሰማዕታት መታሰቢያ ይሆንልናል፡፡» በማለት ዋናው ቁም ነገር የድንጋይ ሀውልት ማቆሙ ሳይሆን ካለፈው ተምሮ መሰል ጥፋት እንዳይደገም ማድረጉ እንደሆነ ነበር የገለጹት ፡፡ግና አንደ አለመታደልም ሆነና ወያኔን ሀይ የሚለውም ጠፋና ይሄው ዛሬ ድረስ ስጋቱም ፍጅቱም እንዳለ አለ፡፡

ባለፉት ሀያ አራት ዓመታት ወያኔ ከምንይልህ ቤተ መንግሥት ሆኖ የፈጸማቸው ኢ- ሰብአዊ ተግባሮቹን ለታሪክና ለትውልድ ፍርድ ትተን ዛሬም በእብሪትና በማን አለብኝነት የሚፈጽማቸውን ተግባራት ስናስተውል ጨፍጫፊ ከሆነ  ሀበሻም ጣሊያን ነው የሚያሰኙ ናቸው፡፡ታዲያ እኒህን ከእለት እለት እየባሱ የመጡ አረመኔያዊ ድርጊቶቹን ምን ስም አንስጣቸው፡፡ ይመጥ አይመጥነው ባይታወቅም  አንድ ሰሞን አንዳንድ ሰዎች ጥቁር ሽብር ማለት ጀምረው ነበር፡፡

ከወራት በፊት አቶ ኤፍሬም ማዴቦ #አይኔ እያየስ እዚህ ውስጥ አልገባም መሠረት ሙሴ$ በሚል ርዕስ ባስነበቡን ጽሁፍ ስሙ የተጠቀሰው ወጣት  ከሌሎች ሁለት ወጣቶች ጋር ጎነደር መተማ ላይ ተያዘ፡፡ ሁመራ ተወስደው ጫካ ውስጥ ሊረሸኑ ጉድጓድ አፍ ላይ ቆመው  ገዳዮቹ አንደኛውን ወጣት  በጥይት መትተው ወደ ጉድጓድ ሲከቱት አይኔ እያየስ እዚህ ውስጥ አልገባም ያለው መሰረት እግሬ አውጪኝ ብሎ ሮጦ አካሉ በጥይት ቢነዳደልም አምልጦ በሻዕቢያ ወታደሮች እጅ መውደቁንና ታክሞ ድኖ ግንቦት ሰባትን መቀላቀሉን ነግረውናል፡፡( ይህን አንብበን ዝም ማለታችን ራሱ አስገራሚ ነው)

ወጣቱ በፈጣሪ ቸርነት በማምለጡና አቶ ኤፍሬምንም በማግኘቱ የአይን ምስክርነቱን ሊሰጥ ቻለ፡፡ ባይሆን ኖሮ ይኑሩ ይሙቱ ሳይታወቅ ቤተሰብም እርሙን ሳያወጣ ጫካ እንደተጣሉ ይቀሩ ነበር፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በየደረጃው ባሉ ዘመንኞች እየተረሸኑ  በጅምላ የተቀበሩና በየጫካው የተጣሉ  ዜጎችን ቤት ይቁጠራቸው ማለት ይቻላል፡፡ አንድ ቀን ግን መጋለጡ  አይቀርም፡፡

እዛው ጎንደር ውስጥ የወንድሞቹ በረሀ መግባት በሰላም ለሚኖረው ክብሩ አሰፋ ወንጀል ሆኖ 18 ዓመታት አስፈርዶበት  በጎንደር ወህኒ ቤት ስድስት ኣመታትን ካሳለፈ በኋላ ከእስር ቤት ተወስዶ መረሸኑን  ከአርበኞች ግንቦት ሰባት መግለጫ አንብበናል፡፡ይህም ወያኔዎች ጠላታችን የሚሉትን ሰው አስረው እንኳን እንቅልፍ የማይወስዳቸውና ካልገደሉ የማይረኩ መሆናቸውን የሳየ ነው፡፡ በዚህ መልክ የተረሸኑ ወገኖቻችንስ  ምን ያህል ይሆኑ;

ከሁለት ዓመት በፊት አዲስ አበባ ውስጥ ከስድስት ኪሎ ወደ ፈረንሳይ የሚሄደው መንገድ ሲሰራ ሶስተኛ ሻለቃ በመባል ይታወቅ የነበረውና ወያኔ ስሙን እየቀያየረ የሚጠቀምበት የጦር ሰፈር  ጫፉ ላይ አጥሩ ፈርሶ ሲቆፈር የቅርብ ግዜ አስክሬን ከነተጠቀለለበት ብርድ ልብስ መገኘቱ ይታወሳል፡፡ በማህበራዊ ድረ ገጽም ምስሉ ተለቆ ለአንድ ሳምንት መነጋገሪያም ሆኖ ነበር፡፡ (ንዴት ቁጣችን፣ ተቃውሞ ፉከራችን ከአንድ ሳምንት አይዘል አይደል!) ሳይታሰብ በመንገድ ስራ ቁፋሮ ምክንያት  ለእይታ የበቃው ያ የወገን አጽም የወያኔ የጦር ካምፖች ለወታደራዊ ተግባር ብቻ ሳይሆን ታፍነው ለሚሰወሩ ዜጎች ማሰቃያ መግደያና መቀበሪያነትም የሚያገለግሉ መሆናቸውን ያጋለጠ ነው፡፡ በዚህ መልክስ ስንት ወገኖቻችን በአረመኔዎች እየተገደሉ በየቦታው ተቀብረው ይሆን; ጠያቂ ጠፍቶ ጯሂ አልተገኝቶ ሆኖ እንጂ ቁፈራው ሰፋ ተደርጎ ቢቀጥል ብዙ ጉድ በተጋለጠ ነበር፡፡

የፖለቲካ ትርፍ አገኛለሁ ብሎ በደርግ እየተገደሉ በየቦታው የተቀበሩ ወገኖቻችንን አጽም እያወጣና በቴሌቭዥን እያሳየ ሲያስለቅሰንና ሲያላቅሰን የነበረው ወያኔ እሱ በተራው ሀያ አራት ዓመት ሙሉ አስሮ አሳቃይቶና ገድሎ ሊረካ አልቻለም፡፡  መታሰር መሰቃየትና መገደል በቃን ብለን ካላመረርንና ካልተባበርን አለበለዚያም ለወያኔ ሰጥ ለጥ ብለን ካላደርን በስተቀር  ወያኔ ከዚህ አድራጎቱ መቼም የሚገታ አይመስልም፡፡ ግና ዘላለማዊ ምድራዊ ኃይል የለምና አንድ ቀን የጨለመው ሲበራ ህሊናቸው ፋታ ነስቶአቸው ወይንም ህግ አስገድዷቸው ወያኔ በዘመነ ሥልጣኑ እየገደለ በየቦታው ስለቀበራቸው  ኢትዮጵያውያን  የአይን እማኝነታቸውን የሚሰጡ ሰዎች መኖራቸው አይቀርም፡፡

ይሄው ሰሞኑን ደግሞ በየመድረኩ ስለፍትህ ስለ መልካም አስተዳደር ተቃውሞን በሰላማዊ መንገድ መግለጽ ስለመቻል ወዘተ እየደሰኮሩ በተግባር ግን በሰላማዊ መንገድ ጥያቄ ባቀረቡና ተቃውሞ ባሰሙ ወጣቶች ላይ ነብሰ ገዳይ ወታደሮቻቸውን አሰማርተው እያስደበደቡ እያሳሰሩና እያስገደሉ ነው፡፡ ለሀያ አራት አመታት በስልጣን ለመቆየት የቻሉት በማናቸውም ወገን የሚነሳን ማናቸውንም ጥያቄና ተቃውሞ በእስር በድብደባና በግድያ ጸጥ በማሰኘት በመሆኑ ሌላ ለጥያቄ መልስ መስጫ ዘዴም ሆነ ተቃውሞን ማስተናገጃ መንገድ አያውቁም፡፡

የአረመኔነታቸው ክፋት ጎንደር እስር ቤት ተቃጥሎ እስረኞች  ህይወታቸውን ለማትረፍ ሲሮጡ እየተኮሱ ገድለዋል፡፡ ያለህበት ቤት ሲቃጠል  አይንህ እያየ ዝም ብለህ ተቃጠል የሚሉ ነው የሚመስለው፡፡ እንደው እነዚህ ከእሳት የሚያመልጥን ዜጋ ተኩሰው የሚገድሉ ነብሰ በላዎች ከምን አይነት ማህጸን የተፈጠሩ ይሆኑ! ወይስ ወያኔዎች ሲያሰለጥኑዋቸው ከምግብ ወይንም ከሚጠጣ ነገር ጋር ቀላቅለው የሚሰጡዋቸው ከሰውነት ወደ አንስሳነት የሚቀይር፣ ሰዋዊ አስተሳሰብን አደድቦ ህሊና ቢስ የሚያደርግ ነገር ይኖር ይሆን፡፡

ወያኔዎች የአረመኔነታው ክፋትና የንቀታቸው ብዛት አንድም ገደሉ መቶ ለአፋቸው ይህል እንኳን  በተፈጠረው ነገር እናዝናለን አይሉም፡፡ እነርሱ የሚያውቁት በሟች ቁጥር ላይ መሟገት ነው፡፡ ሰሞኑን የምንሰማውም ይህንኑ ነው፡፡

በሰላም ተቃውሞ በሚያሰሙ ( ቢቢስ ድንጋይ  ይወረውሩ ይሆናል) ወጣቶች ላይ እንዲህ በየግዜው ግድያ የሚፈጽሙት ወያኔዎች ደርጎች ላይ እንደሆነው በአዲስ አበባ ከተማ በትላልቆቹ ባለሥልጣኖች ላይ ቢተኮስባቸው፣ ከመካከላቸው ቢቆስልና ቢሞትባቸው ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉ መገመት አይከብድም፡፡ አብርሀ ደቦጭና ሞገስ አስግዶም የጣሊያኑን ጀነራል በቦምብ ካቆሰሉ በኋላ ጣሊያኖች በአዲስ አበባ የፈጸሙት ጅምላ ፍጅት መቼም የሚረሳ አይደለም፡፡ ወያኔዎች ከእስከዛሬ ተግባራቸው እንዳወቅናቸው  ከመካከላቸው አንድ ሰው ቢገደል ወይንም ቢቆስል ተመሳሳይ ተግባር ከመፈጸም ወደ ኋላ እንደማይሉ ፡፡ ታዲያ ይህን በቀይ ሽብር ለተጨፈጨፉ ወገኖች ሀውልት አቁሞ ጭፍጨፋ የሚፈጽም አረመኔ ቡድን ለእሱም ሆነ ለድርጊቱ ምን ስም እናውጣለት፡፡

 

The post ለወያኔ ድርጊት፣ ምን ስም እናውጣለት-ይገረም ዓለሙ appeared first on Zehabesha Amharic.

ለወያኔ ድርጊት፣ ምን ስም እናውጣለት –ይገረም ዓለሙ

$
0
0

ወገንን ጨፍጫፊ ቆዳው የነጣ ነው

በአበሻ የሚጨክን ፈረንጅ ብቻ ነው፤

እያለ የሚያስብ የዋህ ፍጡር ማነው

ጨፈጫፊ ከሆነ አበሻም ጣሊያን ነው

እንቶኔም በተግባር ሲኞር እንቶኔ ነው፤

በየግዜው እየከፋ የሄደውን የወያኔ አረመኔነትና የሀገራችንን ጉዞ ወዴትነት ሳስብ ትውስ ያለችኝን ይህችን ስንኝ ወደ ማስታወሻየ ገልብጬ ያኖርኳት በ1980ዎቹ መጨረሻ ግድም ለንባብ ይበቁ ከነበሩት መጽሄቶች ከአንዱ ነው፡፡ ወያኔ ዴሞክራት መስሎ ለመታየት በሞከረበትና ትክክለኛ ማንነቱ ገሀድ ወጥቶ  ብዕርን ከጠመንጃ አስበልጦ መፍራት ባልጀመረበት በዛ ወቅት እንዲህ የጻፉት ሰው ዛሬ በህይወት ካሉ ምን ሊሉ እንደሚችሉ መገመት ይቸግራል፡፡

 

ወያኔዎች ደርግን በጨፍጫፊነት በማውገዝ ዛሬም ድረስ  ፈሺስት ናዚ ወዘተ በማለት ይገልጹታል፡፡ በዘመነ ደርግ የተፈጸመውን ቀይ ሽብርም ለአንድ ሰሞን የፖለቲካ ፍጆታ ሊጠቀሙበት ሞክረዋል፡፡ ግን ካወገዙት ተግባር ተምረው ከተጸየፉት ድርጊት ርቀው ሊገኙ አልቻሉም፡፡ በርግጥም ከጅምሩ ስለ ቀይ ሽብር የነበራቸው አያያዝ ሊማሩበት ሳይሆን ሊያደናግሩበት፤ ለተበዳዮች ፍትህ ሊያስገኙበት ሳይሆን ጥላቻን ሊያነግሱበት እንደነበረ መለስ ብሎ በማስታወስ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡  ከቀይ ሽብር ቢማሩ ኖሮ ራሳቸው ያቋቋሙት የቀይ ሽብር ኮሚቴ ይዞት የነበረውን “ያለመቻቻል ፖለቲካ ሰማዕታት፣መቼም እንዳይደገም የሚለውን መርህ  ተግባራዊ ባደረጉና  እንዲህ የለየላቸው ጨፍጫፊ  ባልሆኑ ነበር፡፡

 

የቀይ ሽብር ነገር ለወያኔ የፖለቲካ ካርድ በነረበት ወቅት የቀይ ሽብር ኮሚቴ ባዘጋጀው አንድ የውይይት መድረክ ላይ የጥናት ወረቀት ያቀረቡት ፕ/ር ባህሩ ዘውዴ የፖለቲካ ልዩነቶችንም በተመለከተ አንዱ ወገን ምንግዜም ቢሆን ፍጹማዊ እውነትን ሊታደል እንደማይችል ተገንዝቦ የሌላውን ወገን ሀሳብ እህ ብሎ ማዳመጥ መቻል ይኖርበታል፡፡ የተቀዋሚ ወገን አየለ ብሎ ቃታ ለመሳብ መጣደፍ ዞሮ ዞሮ ሀገርን በብርቱ የሚጎዳ መሆኑን ከ « ቀይ» ሽብር ያተረፍነው ትልቁ ትምህርት ነው” ብለው ነበር፡፡ ነገር ግን ወያኔዎች ቀይ ሽብርን ያራገቡት ፖለቲካ ሊቆምሩበት እንጂ ሊማሩበት ያለመሆኑን ውለው ሳያድሩ በጀመሩት የሁሉም ነገር መፍትሄ ከጠመንጃ ይመነጫል አይነት ተግባራቸው  አሳይተውናል፡፡

 

ሌላው ተናጋሪ የነበሩት ዶ/ር የራስ ወርቅ አድማሴ ባቀረቡት ጽሁፍ ደግሞ ከኛ ትውልድ ስህተት በመማር የልጆቻችንን ትውልድ ከፖለቲካ ግድያ፣ከዘር ማጥፋት ፍጅትና ከስጋትም ጭምር ነጻ በሆነችና ፍትህ በነገሰባት ኢትዮጵያ እንዲኖሩ እንመኛለን፡፡ ይህን ምኞታችንን እውን ካደረግን ደግሞ እሱ ጊዜ የማይሽረውና የማያደበዝዘው ዕውነተኛው የሰማዕታት መታሰቢያ ይሆንልናል፡፡» በማለት ዋናው ቁም ነገር የድንጋይ ሀውልት ማቆሙ ሳይሆን ካለፈው ተምሮ መሰል ጥፋት እንዳይደገም ማድረጉ እንደሆነ ነበር የገለጹት ፡፡ግና አንደ አለመታደልም ሆነና ወያኔን ሀይ የሚለውም ጠፋና ይሄው ዛሬ ድረስ ስጋቱም ፍጅቱም እንዳለ አለ፡፡

 

ባለፉት ሀያ አራት ዓመታት ወያኔ ከምንይልህ ቤተ መንግሥት ሆኖ የፈጸማቸው ኢ- ሰብአዊ ተግባሮቹን ለታሪክና ለትውልድ ፍርድ ትተን ዛሬም በእብሪትና በማን አለብኝነት የሚፈጽማቸውን ተግባራት ስናስተውል ጨፍጫፊ ከሆነ  ሀበሻም ጣሊያን ነው የሚያሰኙ ናቸው፡፡ታዲያ እኒህን ከእለት እለት እየባሱ የመጡ አረመኔያዊ ድርጊቶቹን ምን ስም አንስጣቸው፡፡ ይመጥ አይመጥነው ባይታወቅም  አንድ ሰሞን አንዳንድ ሰዎች ጥቁር ሽብር ማለት ጀምረው ነበር፡፡

 

ከወራት በፊት አቶ ኤፍሬም ማዴቦ #አይኔ እያየስ እዚህ ውስጥ አልገባም መሠረት ሙሴ$ በሚል ርዕስ ባስነበቡን ጽሁፍ ስሙ የተጠቀሰው ወጣት  ከሌሎች ሁለት ወጣቶች ጋር ጎነደር መተማ ላይ ተያዘ፡፡ ሁመራ ተወስደው ጫካ ውስጥ ሊረሸኑ ጉድጓድ አፍ ላይ ቆመው  ገዳዮቹ አንደኛውን ወጣት  በጥይት መትተው ወደ ጉድጓድ ሲከቱት አይኔ እያየስ እዚህ ውስጥ አልገባም ያለው መሰረት እግሬ አውጪኝ ብሎ ሮጦ አካሉ በጥይት ቢነዳደልም አምልጦ በሻዕቢያ ወታደሮች እጅ መውደቁንና ታክሞ ድኖ ግንቦት ሰባትን መቀላቀሉን ነግረውናል፡፡( ይህን አንብበን ዝም ማለታችን ራሱ አስገራሚ ነው)

 

ወጣቱ በፈጣሪ ቸርነት በማምለጡና አቶ ኤፍሬምንም በማግኘቱ የአይን ምስክርነቱን ሊሰጥ ቻለ፡፡ ባይሆን ኖሮ ይኑሩ ይሙቱ ሳይታወቅ ቤተሰብም እርሙን ሳያወጣ ጫካ እንደተጣሉ ይቀሩ ነበር፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በየደረጃው ባሉ ዘመንኞች እየተረሸኑ  በጅምላ የተቀበሩና በየጫካው የተጣሉ  ዜጎችን ቤት ይቁጠራቸው ማለት ይቻላል፡፡ አንድ ቀን ግን መጋለጡ  አይቀርም፡፡

 

እዛው ጎንደር ውስጥ የወንድሞቹ በረሀ መግባት በሰላም ለሚኖረው ክብሩ አሰፋ ወንጀል ሆኖ 18 ዓመታት አስፈርዶበት  በጎንደር ወህኒ ቤት ስድስት ኣመታትን ካሳለፈ በኋላ ከእስር ቤት ተወስዶ መረሸኑን  ከአርበኞች ግንቦት ሰባት መግለጫ አንብበናል፡፡ይህም ወያኔዎች ጠላታችን የሚሉትን ሰው አስረው እንኳን እንቅልፍ የማይወስዳቸውና ካልገደሉ የማይረኩ መሆናቸውን የሳየ ነው፡፡ በዚህ መልክ የተረሸኑ ወገኖቻችንስ  ምን ያህል ይሆኑ;

 

ከሁለት ዓመት በፊት አዲስ አበባ ውስጥ ከስድስት ኪሎ ወደ ፈረንሳይ የሚሄደው መንገድ ሲሰራ ሶስተኛ ሻለቃ በመባል ይታወቅ የነበረውና ወያኔ ስሙን እየቀያየረ የሚጠቀምበት የጦር ሰፈር  ጫፉ ላይ አጥሩ ፈርሶ ሲቆፈር የቅርብ ግዜ አስክሬን ከነተጠቀለለበት ብርድ ልብስ መገኘቱ ይታወሳል፡፡ በማህበራዊ ድረ ገጽም ምስሉ ተለቆ ለአንድ ሳምንት መነጋገሪያም ሆኖ ነበር፡፡ (ንዴት ቁጣችን፣ ተቃውሞ ፉከራችን ከአንድ ሳምንት አይዘል አይደል!) ሳይታሰብ በመንገድ ስራ ቁፋሮ ምክንያት  ለእይታ የበቃው ያ የወገን አጽም የወያኔ የጦር ካምፖች ለወታደራዊ ተግባር ብቻ ሳይሆን ታፍነው ለሚሰወሩ ዜጎች ማሰቃያ መግደያና መቀበሪያነትም የሚያገለግሉ መሆናቸውን ያጋለጠ ነው፡፡ በዚህ መልክስ ስንት ወገኖቻችን በአረመኔዎች እየተገደሉ በየቦታው ተቀብረው ይሆን; ጠያቂ ጠፍቶ ጯሂ አልተገኝቶ ሆኖ እንጂ ቁፈራው ሰፋ ተደርጎ ቢቀጥል ብዙ ጉድ በተጋለጠ ነበር፡፡

 

የፖለቲካ ትርፍ አገኛለሁ ብሎ በደርግ እየተገደሉ በየቦታው የተቀበሩ ወገኖቻችንን አጽም እያወጣና በቴሌቭዥን እያሳየ ሲያስለቅሰንና ሲያላቅሰን የነበረው ወያኔ እሱ በተራው ሀያ አራት ዓመት ሙሉ አስሮ አሳቃይቶና ገድሎ ሊረካ አልቻለም፡፡  መታሰር መሰቃየትና መገደል በቃን ብለን ካላመረርንና ካልተባበርን አለበለዚያም ለወያኔ ሰጥ ለጥ ብለን ካላደርን በስተቀር  ወያኔ ከዚህ አድራጎቱ መቼም የሚገታ አይመስልም፡፡ ግና ዘላለማዊ ምድራዊ ኃይል የለምና አንድ ቀን የጨለመው ሲበራ ህሊናቸው ፋታ ነስቶአቸው ወይንም ህግ አስገድዷቸው ወያኔ በዘመነ ሥልጣኑ እየገደለ በየቦታው ስለቀበራቸው  ኢትዮጵያውያን  የአይን እማኝነታቸውን የሚሰጡ ሰዎች መኖራቸው አይቀርም፡፡

 

ይሄው ሰሞኑን ደግሞ በየመድረኩ ስለፍትህ ስለ መልካም አስተዳደር ተቃውሞን በሰላማዊ መንገድ መግለጽ ስለመቻል ወዘተ እየደሰኮሩ በተግባር ግን በሰላማዊ መንገድ ጥያቄ ባቀረቡና ተቃውሞ ባሰሙ ወጣቶች ላይ ነብሰ ገዳይ ወታደሮቻቸውን አሰማርተው እያስደበደቡ እያሳሰሩና እያስገደሉ ነው፡፡ ለሀያ አራት አመታት በስልጣን ለመቆየት የቻሉት በማናቸውም ወገን የሚነሳን ማናቸውንም ጥያቄና ተቃውሞ በእስር በድብደባና በግድያ ጸጥ በማሰኘት በመሆኑ ሌላ ለጥያቄ መልስ መስጫ ዘዴም ሆነ ተቃውሞን ማስተናገጃ መንገድ አያውቁም፡፡

gonder

የአረመኔነታቸው ክፋት ጎንደር እስር ቤት ተቃጥሎ እስረኞች  ህይወታቸውን ለማትረፍ ሲሮጡ እየተኮሱ ገድለዋል፡፡ ያለህበት ቤት ሲቃጠል  አይንህ እያየ ዝም ብለህ ተቃጠል የሚሉ ነው የሚመስለው፡፡ እንደው እነዚህ ከእሳት የሚያመልጥን ዜጋ ተኩሰው የሚገድሉ ነብሰ በላዎች ከምን አይነት ማህጸን የተፈጠሩ ይሆኑ! ወይስ ወያኔዎች ሲያሰለጥኑዋቸው ከምግብ ወይንም ከሚጠጣ ነገር ጋር ቀላቅለው የሚሰጡዋቸው ከሰውነት ወደ አንስሳነት የሚቀይር፣ ሰዋዊ አስተሳሰብን አደድቦ ህሊና ቢስ የሚያደርግ ነገር ይኖር ይሆን፡፡

ወያኔዎች የአረመኔነታው ክፋትና የንቀታቸው ብዛት አንድም ገደሉ መቶ ለአፋቸው ይህል እንኳን  በተፈጠረው ነገር እናዝናለን አይሉም፡፡ እነርሱ የሚያውቁት በሟች ቁጥር ላይ መሟገት ነው፡፡ ሰሞኑን የምንሰማውም ይህንኑ ነው፡፡

 

በሰላም ተቃውሞ በሚያሰሙ ( ቢቢስ ድንጋይ  ይወረውሩ ይሆናል) ወጣቶች ላይ እንዲህ በየግዜው ግድያ የሚፈጽሙት ወያኔዎች ደርጎች ላይ እንደሆነው በአዲስ አበባ ከተማ በትላልቆቹ ባለሥልጣኖች ላይ ቢተኮስባቸው፣ ከመካከላቸው ቢቆስልና ቢሞትባቸው ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉ መገመት አይከብድም፡፡ አብርሀ ደቦጭና ሞገስ አስግዶም የጣሊያኑን ጀነራል በቦምብ ካቆሰሉ በኋላ ጣሊያኖች በአዲስ አበባ የፈጸሙት ጅምላ ፍጅት መቼም የሚረሳ አይደለም፡፡ ወያኔዎች ከእስከዛሬ ተግባራቸው እንዳወቅናቸው  ከመካከላቸው አንድ ሰው ቢገደል ወይንም ቢቆስል ተመሳሳይ ተግባር ከመፈጸም ወደ ኋላ እንደማይሉ ፡፡ ታዲያ ይህን በቀይ ሽብር ለተጨፈጨፉ ወገኖች ሀውልት አቁሞ ጭፍጨፋ የሚፈጽም አረመኔ ቡድን ለእሱም ሆነ ለድርጊቱ ምን ስም እናውጣለት፡፡

 

The post ለወያኔ ድርጊት፣ ምን ስም እናውጣለት – ይገረም ዓለሙ appeared first on Zehabesha Amharic.

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምግብ ቦይኮት አደረጉ

$
0
0

(የሚሊዮኖች ድምጽ)  የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በስፋት ተቃዉሟቸውን እያሰሙ ነው። በወያኔ ግፈኛ ታጣቂዎች በጎንደር እና በኦሮሚያ በግፍ ለተገደሉ ወገኖቻችን ሃዘናቸውን በመግለጽ፣ እህቶቻችንም ጥቅር በመልበስ፣ በካፌቴሪያ ምሳ አንበላም ብለው ቦይኮት አደርገዋል።

addis ababa 2 addis ababa

እንቅስቃሴ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ወደ አዲስ አበባ እየገባ ። እንቅስቃሴው በኦሮሞ ተማሪዎች በማስተር ፕላኑ ዙሪያ ቢጀመርም፣ መልኩን በስፋት ቀይሮ፣ አሁን የሁሉም ዜጎች እንቅቃሴና ሆኗል። ለመሰረታዊ የመብት፣ የነጻነት የእኩልነትና የዲሞክራስ ጥያቄ ሆኗል።

በኦሮሚያ የተለያዩ ቦታዎች እየተደረጉ ያሉ እጅግ በጣም ብዙ እንቅስቃሴዎች እንደተጠበቁ፣ በተመሳሳይ ሁኔታ በሃረር ከተማ (ሃረሬ ክልል)፣ በዲላ ( ደቡብ ክልል፣ ጌዶ ዞን ዋና ከተማ) እንዲሁም በአዋሳ (የደቡብ ክልል ዋና ከተማ) ተቃዉሞዎች ተደረገዋል።

በተለይም በአዲስ አበባ ህይ ስኩሎችን በቅርብ ይቀላቀላሉ ተብሎ ይጠበቃል።

The post በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምግብ ቦይኮት አደረጉ appeared first on Zehabesha Amharic.


በዋሽንግተን ዲሲ ዛሬ የተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የተሰማውን መፈክሮች የሚያሳይ ቪዲዮ

ፕ/ር ኤፍሬም ይስሐቅ፤ ክርስትና ኢትዮጵያ ውስጥ እንደምን እንደተመሠረተ ይናገራሉ | Audio

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስመራ ወርደው የያዩትን 3 ተግዳሮቶች ተናገሩ | Video

$
0
0

የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር የሆኑት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በቅርቡ ብራሰልስ ላይ ከኢሳት ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ በወቅታዊ ጥያቄዎች ላይ ወቅታዊ ምላሾችን ሰጥተዋል:: ቭዲዮውን ይመልከቱት::

birhanu nega

The post ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስመራ ወርደው የያዩትን 3 ተግዳሮቶች ተናገሩ | Video appeared first on Zehabesha Amharic.

የኦሮሞ ህዝብ ብሶት፥ ወደ የጋራ ነጻነት: – ፃዲክ አህመድ

$
0
0

Sadik Ahmed

“ከአዲስ አበባዉ የእርሻ መሬት እስከ አሜሪካዊ ቤተ መንግስት፥መብትን የማስከበር ጣምራ ሒደት!”
 
በአሜሪካዉ ቤተ መንግስት እና በዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የኢትዮጵያ መንግስት በሰላማዊ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ የሚያደርገዉን ግድያ፣ድብደባ፣ እስር፣ወከባና ማፈናቀልን በመቃወም በተደረገዉ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በመገኘት ሳዲቅ አህመድ ያዘጋጀዉ ልዩ ፕሮግራም።

The post የኦሮሞ ህዝብ ብሶት፥ ወደ የጋራ ነጻነት: – ፃዲክ አህመድ appeared first on Zehabesha Amharic.

አለማቀፉ ማህበረሰብ እነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን እንዳይዘነጋ ተማጽኖ ቀረበ

$
0
0
Eskinder Nega

Eskinder Nega

ከታምሩ ገዳ

በተለያዩ ጊዜያት ሰለ ሰብአዊ መብት መከበር ፣ሰለ ፍትህ ፣እኩልነት እና ሃሳብን በነጻነት ስለመግለጽ ሲጽፉ እና ሲሰብኩ የአወዛጋቢው የጸረ ሸብር ህግ ሽፋን ለከባድ ቅጣት እና እሰራት የተዳረጉት የኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ አባላት የሆኑት እነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ተመሰገ ደሳለኝ፣ ውብሸት ታዮ፣ሰለሞን ከበደ፣የሱፍ ጌታቸው ፣ሳሌህ አድሪስ ተስፋ ልደት ኬዳኔ አና የመሰሳሰሉት ጋዜጠኞች ለአፍታ እንኳን ሊዘነጉ አይገባም ሲል አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት አሚኒስቲ ኢንተርናሽናል (Amensty International) የተማጸኖ ጥሪውን አቅርቧል።
webshet taye
የመብት ተሟጋቹ ድርጅት በተላንትናው እለት የተከበረው አለማቀፍ የሰብ አዊ መብት ቀንን በማሰመልከት ባወጣው መግለጫው ከላይ የተጠቀሱት ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት አርበኞቹ እነ አሰክንደር ነጋ እና ሰማቸው ያለተጠቀሱት ነገር ግን በተለያዩ የአገዛዙ ማጎሪያ ቤቶች ውስጥ ተወርውረው እየማቀቁ የሚገኙትን ወገኖች ሰለ ተጋድሏቸው እና ሰለ ከፈሉት መሰዋትነት ልንዘነጋቸው አይገባም ብሏል።ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በአረቡ አለም ተቀሰቅሶ የነበረው የለውጥ ማእበልን በተመለከተ እና ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ጋር ሰለሚኖረው ተዛማጅነት ሰፊ ትንታኔ ማቅረቡን ተከተሎ በአገዛዙ የጸረሽብር ህግ ክስ ቀርቦበት የ18 አመታት እስራት የተዳረገ ሲሆን ጋዜጠኛ ውብሸት እንዲሁ የኢሃአዲግ የሁለት አሰርት አመታት ጉዞን በመንቀፉ ለ14 አመታታ በዘዋይ ማረሚያ ቤት ተወርውሯል።በአሁኑ ወቅት ከእስራቱ ባሻገር በጤና መታወክ ምክንያት በእስር ቤት አየማቀቀ የሚገኘው ጋዜጠኛ ተመስገንም የተለያዩ ክሶች ቀርበውበት ለእስራት ተዳርጓል። በቅርቡ የአሜሪካው ፕ/ት ባራክ ኦባማ የአ/አ ጉብኝታቸውን ምክንያት በማድረግ የ ዞን 9 ማህበራዊ ድህረ ገጽ ጦማሪያኖች እና ጻፊት ሪዮት አለሙ ከእስራት መለቀቃቸውን ያወሳው ዘገባው ኢትዮጵያ ባለፈው የፈረንጆቹ 2014 አመት ከ17 በላይ ጋዜጠኞችን በማሰር እና ብዛት ያላቸውን ደግሞ አገራቸውን ፣ ቤተሰባቸውን እና ሙያቸውን ጥለው እንዲሰደዱ በማድረግ በአለም በ4ኛ ደረጃ ትገኛለች ሲል ያወሳል።

በጎረቤት ግብጽ በቅርቡ የተደረገውን ህዝባዊ ቁጣን እና የመንግስት ለውጥን ለአልጀዚራ ቲሊቭዥን ሲዘግቡ በካይሮ ባለሰልጣንት ለተወሰኑ ወራቶች ለእስራት ተደርገው የነበሩት ፒተር ግረስቲ ፣መሃመድ ፋሂም እና ባሂር ሞሃመድ በመላው አለም ማህበረሰብ ዘንድ እለታዊ የመወያያ ርእሶች ሲሆኑ ከ10 አመታት በላይ በእስር ቤት አንዲማቀቁ የተበየነባቸው እነ እስክንድር ነጋ የከፈሉት መሰዋትነት እና የአለማቀፉ ማህበረሰብ ለችግራቸው ትኩርት ሰጪነት እና በአገዛዙ ላይ ጫና የመስፈጠር ሚዛኑ የተዛባ (አናሳ )ነው ተብሏል። ጋዜጠኛ አሰክንደር እና የተወሰስኑት በእስር ላይ የሚገኙት የሙያ አጋሮቹ ለፈጸሙት ሙያዊ ኣና ሰነምግባራዊ ተጋድሎ የተለያዩ አለማቀፋዊ ሽልማቶችን እና አክብሮት ማግኘታቸው አይዘነጋም።

temesgen1

በዚህ አጋጣሚ ኢትዮጵያዊያን በተለይ ደግሞ በነጻው እና በሰለጠነው አለም የሚኖረው የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ በአገር ቤት ውስጥ ሰላም ፣ ዲሞክራሲ እና የሃሳብ ነጻነት እንዲከበር ከፍተኛ መሰዋትነት በመክፈላቸው እራሳቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን ለ ከፍተኛ አደጋ ያጋለጡት እነ እስክንደር ነጋ ሆነ ለሰደት እና ለተለያዩ ችግሮች የተዳረጉት ቤተሰቦቻቸውን በሞራል እና በገንዘብ በመታደግ በአሰር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞች የከፈሉት መሰዋትነት ከንቱ አልመሆኑን ለአገዛዙ ጭምር በተግባር ማሳየት እንደሚገባቸው በርካቶች ይመክራሉ።

The post አለማቀፉ ማህበረሰብ እነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን እንዳይዘነጋ ተማጽኖ ቀረበ appeared first on Zehabesha Amharic.

የአ. አበባን ማስተር ፕላንን በመቃወምና ለተገደሉት ተማሪዎች አጋር ለመሆን በአውስትራሊያ ቪክቶሪያ የተደረገ ሰላማዊ ሰልፍ | Audio

$
0
0

በቪክቶሪያ የኦሮሞ ማኅበረሰብ ማኅበር አባላት፤ የአዲስ አበባን ማስተር ፕላንን በመቃወምና ኦሮሚያ ክልል ውስጥ በተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች ሳቢያ ህይወታቸውን ላጡት ወጣቶች ድጋፋቸውን በመቸር ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል። የተቃውሞና የድጋፍ ሰልፉ የተካሄደውም ዓርብ፤ ዲሴምበር 11 2015 ሜልበርን ከተማ ውስጥ ነው።

የአ. አበባን ማስተር ፕላንን በመቃወምና ለተገደሉትን ተማሪዎች አጋር ለመሆን በአውስትራሊያ ቪክቶሪያ የተደረገ ሰላማዊ ሰልፍ | Audio

The post የአ. አበባን ማስተር ፕላንን በመቃወምና ለተገደሉት ተማሪዎች አጋር ለመሆን በአውስትራሊያ ቪክቶሪያ የተደረገ ሰላማዊ ሰልፍ | Audio appeared first on Zehabesha Amharic.

ሰበር ዜና: በአንዋር መስጊድ ውስጥ ምንነቱ ያልታወቀ ፈንጂ ፈነዳ

$
0
0

Zehabesha News
(ዘ-ሐበሻ) ዛሬ አርብ ዲሴምበር 11, 2015 በታላቁ አንዋር መስጊድ ፈንጂ መፈንዳቱ ተሰማ:: ምንነቱ ያልታወቀና ማን እንዳፈነዳው ያልተገለጸው ይኸው ፍንዳታ በበርካታ ሰዎች ላይ ጉዳት አድርሷል ሲሉ የዘ-ሐብሻ ምንጮች ዘግበዋል::

በአሁኑ ወቅት በፖሊስ እና በአምቡላንስ መስጊዱ መከበቡን ያስታወቁት የአይን እማኞች በርካታ ቁስለኞች ወደ አካባቢው የሚገኙ ሆስፒታሎች እየተወሰዱ ነው::
ዘገባዎች እንደሚሉት ይህ ፍንዳታ ከመከሰቱ አስቀድሞ በአካባቢው ረብሻ ተነስቶ እንደነበር የደረሰን መረጃ ጠቁሟል::

ዝርዝር መረጃ ይዘን እንመለሳለን::

The post ሰበር ዜና: በአንዋር መስጊድ ውስጥ ምንነቱ ያልታወቀ ፈንጂ ፈነዳ appeared first on Zehabesha Amharic.


የወያኔ እንቆቅልሽ (ይገረም ዓለሙ)

$
0
0

woyaneወያኔ አዲስ አበባ የመግባት ፈቃድ ባኘበት የለንደኑ ስመ ድርድር ላይ ተዋናይ ከነበሩት አሜሪካዉያን አንዱ ኢትዮጵያ ወደብ ያስፈልጋታል የሚል ሀሳብ ሳነሳ መለስ አያገባህም አለኝ በማለት ነገሩ ካለፈ በኋላ መናገራቸውን እናስታውሳለን፡፡የኤርታር ጉዳይ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት መድረክ ክርክር ይካሄድበት በነበረበት ወቀት ኤርትራ ራሷን የቻለች ሀገር አንድትሆን ይከራከር የነበረው ጣሊያን ሳይቀር ኢትዮጵያ በአሰብ በኩል ወደብ እንድታገኝ ይደግፍ ነበር፡፡አቶ መለስና ድርጅታቸው ግን ከጣሊያንም ብሶ ኤርትራን በማስገንጠል ሳይወሰን ኢትዮጵያ በየትም አቅጣጫ የባህር በር እንዳይኖራት አደረጉ፡፡

ወደብን የሚያህል ነገር የግመል መጠጫ ብለው አናንቀው አሳልፈው የሰጡ ለሀገር ክብርና ሉአላዊነት፤ ለዳር ድንበር መጠበቅ ወዘተ ደንታ የሌላቸው ሰዎች ባድመ በኤርታራ ተወረረ ብለው ሁለት መላጣዎች በማበጠሪያ ሲጣሉ የሚል ስላቅ ላስከተለ ጦርነት ኢትጵያውያንን ሲማግዱ ነገሩ እንቆቅልሽ ነበር፡፡ የጦርነቱ ሂደትና አፈጻጸም በተለይም  በፊሽካ አንደሚቆም የስፖርት ውድድር ጦርነቱ  በአቶ መለስ ትዕዛዝ የቆመበተ ምሲጢር ፣ከዚህ በኋላም ይግባኝ የሌለው ውሳኔ ለመቀበል በመስማማት ወደ አለም አቀፍ ፍርድ ቤት የተኬደበት ሁኔታ በአቶ መለስ ብቻ የሚታወቅ እንቆቅልሽ ነበር፡፡

የኢትዮፕን ሕዝብ ምንም አንደማያውቅ አድርገው ተፈርዶባቸው ተፈረደለን ብለው የአለም አቀፍ ፍርድ ቤት የወሰነው ውሳኔ ምስጢር ተደርጎ የሚያዝ ወይንም ከሕዝብ ተደብቆ የሚቀር ይመሰል ህዝቡ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ወጥቶ ደስታውን እንዲገልጽ ጥሪ ማስተላለፋቸውም ሌላኛው አንቆቅልሽ ነበር፡፡

አድበስብሰው ለማለፍ ያደረጉት ሙከራ ሁሉ ከሽፎ ከየአቅጣጫው በተለይ ከትግራዊያን ተቃውሞ ሲበረታባቸው በውሳኔው መሰረት  በመሬት ላይ ችካል ቸክሎ የድንበር ማካለል ለማካሄድ ሰዎችን ያለ ፍላጎታቸው ወደዛና ወደዚህ የሚያደርግ ስለሆነ ውሳኔውን አንቀበላለን ስለ አፈጻጸሙ ግን አንነጋገር የሚል ጥያቄ አነሱ፡፡ ይህ ጥያቄ በሻዕቢያ በኩል ተቀባይነት ባለማግኘቱም በሁለቱ ሀገሮች መካከል ይሄው እስከ ዛሬ ሰላምም ጦርነትም የለም፡፡

ይን ያነሳሁት ስለ ባድመ ለማውራት ፈልጌ አይደለም፡፡ለሱዳን መሬት ለመስጠት የተነሳሱበት ምክንያት አንቆቅልሽ ቢሆንብኝ እንጂ፡፡ሱዳኖች የመሬት ይገባኛል ጥያቄ አነስተው በጉልበትም ይሁን በህግ ያደረጉት ነገር ስለመኖሩ አልሰማንም፡፡በአካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም ተጠይቀው ፈቃደኝነታቸውን አልገለጹም፡፡ በዚህ ሁኔታ ወያኔዎች ከመሬት ተነስተው አለያም ውስጥ ለውስጥ ተነጋግረው ለም መሬት ለሱዳን ለመስጠት መነሳታቸው ለኢትዮጵያውያን አንቆቅልሽ ነው፡፡ አቶ መለስ የቋጠሩትና ለጥቂት ታማኝ ወዳጆቻቸው በአደራ ያስተላለፉት ምስጢር እንደሆነ የሚገመት የድንበር ጉዳይ በኢህአዴጋውያን ቀርቶ ህውኋቶችም ሁልም የሚያውቁት ስለመሆኑ ያጠራጥራል፡፡

ያ ባድመ ላይ የታየ የአለም አቀፍ ፍርድ ቤትን ውሳኔ ተግባራዊ እስካለማድረግ የዘለቀ ወኔ የት ገባ፡፡ ነው ወይንስ ለወያኔ ከትግራይ የሚወሰድና ከቀሪው የኢትዮጵያ ክፍል የሚወሰድ መሬት ልዩነት አለው፡፡ ነው ወይንስ ሰሞኑን እየተነገረና እየተጻፈ እንዳለው ኢትዮጵያ መግዛት የማይችሉበት ደረጃ ሲደርሱ ትግራይን ገንጥለው ወደ ሚመሰርቱት ሀገር ለማጠቃለል እስከዛ በሱዳን እጅ  በአደራ እንዲቀመጥላቸው ነው፡፡

ወያኔዎች ከወያኔዎቹም የተለዩት ወያኔዎች በተለይ አቶ መለስ እስከ 1991 ዓ.ም የፈጸሙዋቸው የኢትዮጵያን ጥቅሞች የማሳጣትና የመጉዳት ተግባር ሁሉንም በሻዕቢያ በኩል እናገኘዋለን ከሚል እቅድ ይመስል ነበር፡፡ የሞታችሁለትን ኤርታራን የማስገንጠል ዓላማችሁን ተግባራዊ ስታደርጉ ቢያንስ ኢትዮጵያ የባህር በር እንዳታጣ አሰብን አትስጡባት ሲባሉ ጦረኞች የቀድሞ ሥርዓት ናፋቂዎች ህዝቡን ሳይሆን መሬቱን የሚፈልጉ ወዘተ እያሉ የውግዘት መአት ሲያወርዱና ከሻዕቢያ ብሰው ጠያቂዎቹን ሲያጠቁ  ለነጋ ትግራይ ወደብነት አሰብ በወዳጃችን እጅ ትቆይልን ብለው ያደረጉት ነው በማለት ብዙ ኢትዮጵያውያን ጥርጣሬአቸውን ይገልጹ ነበር፡፡ ግና ፈጣሪ ኢትዮጵያን አይረሳትምና ያሰቡት ሁሉ እንዳይሆን ሆኖ ጸባቸው ከራሳቸው አልፎ ለመላው ኢትዮጵያውያን ተረፈ፡፡ ወያኔዎች ግን መቼም በምንምና ከምንም የማይማሩ ናቸውና ዛሬም የኢትዮጵያን ሉዐላዊነት እየተፈታተኑ ዳር ድንበሯን እያስደፈሩ ለም መሬቷን( በአደራ ለማስቀመጥም ይሁን፣ በሽፍትነት ዘመናቸው ለተደረገላቸው ውለታም ይሁን  በሽያጭም ይሁን ) ለመስጠት ሽር ጉድ እያሉ  ነው፡፡

ብሶት ደስታውን ቁጭት ፍላጎቱን በቀረርቶ በመግለጽ የሚታወቀው የሀገሬ አርሶ አደር መሬት እግር አለው ይሄዳል እንደ ሰው፣ ጀግና ልጅ ተወልዶ ቦታው ካልመለሰው ይላል፡፡ አባቶቻችን በየዘመናቱ ከየአቅጣጫው ከመጡ ወራሪዎች ጋር ተፋልመው ወድ ህይወታቸውን ሰውተው ያቆዩአት ሀገር በሀገር በቀል እንቆቅልሽ ፍጥረቶች አለም የሚያውቃት መልኳ ተቀይሯል፡፡ አልባ ብሎአቸው ዛሬም ድንበሯን አስገፍተው በአለም ካርታ ላይ ሌላ ቅርጽ ሊያሰጧት ነው፡፡ለነገ ያሰቡትን ደግሞ አናውቀቅም፡፡

ሀገር እግ አለው ይሄዳል አንደ ሰው አንደተባለው ያለፈው ሲቆጨንና ዛሬም ሌላ ሊሄድ ነው፡፡ በባለፈ ከመቆጨት የአሁኑን እኩይ ሴራ በመግታት ባለበት በነበረበት እንዲቆም ማድረግ የዚህ ትውልድ ታሪካዊ ኃላፊነት ነው፡፡ኮረኔል ምግሽቱ በቅርቡ አንደተናገሩት በርሳቸው የሥልጣን ዘመን ሱዳኖች አንድም ግዜ የድንበር ማካለል ጥያቄ አቅርበው አያውቁም፡፡ አሁንም ወያኔ በድንበር ማካለል ስም መሬት ለመስጠጥ የጠነሳው በሱዳኖቹ ጥያቄ ስለመሆኑ በቂ ማረጋገጫ የለም፡፡ ቢሆንም ደግሞ መሬት የተስካር ዳቦ አይደልም ለጠየቀ ሁሉ እየተቆረሰ የሚሰጥ፡፡

የድንበር ማካለል በድብቅ ጓዳ ለጓዳ በሚደረግ ስምምነት የሚካሄድ አይደለም፡፡ ሁለት ወዳጃሞች ወይንም ባለውለታዎች እዛና እዚህ ሥልጣን ላይ ሥላሉ የሚከናወንም አይደለም፡፡ የራሱ ሂደትና የአፈጻጸም  ሕግና ስርዓት አለው፡፡ ይህ ሁሉ እንቆቅልሽ ሲጠቃለል ምክንያቱ አንድ ነገር ነው፡፡ የወያኔ ኢትዮጵያዊ አጀንዳ አለመኖር፡፡ ሀገራዊ ስሜትና ኢትዮጲያዊ አጀንዳ ሳይዙ ሀገር መግዛት ደግሞ ቅኝ ግዛት ይሆናል ፣ሌላ እንቆቅልሽ፡፡

 

The post የወያኔ እንቆቅልሽ (ይገረም ዓለሙ) appeared first on Zehabesha Amharic.

በአንዋር መስጊድ የፈነዳው ምንነቱ ያልታወቀውን ፈንጂን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ

$
0
0

anwarከቢቢኤን ራድዮ የተገኘው ተጨማሪ መረጃ እንደሚያመለክተው በዛሬው ዕለት በታላቁ አንዋር መስጊድ የፈነዳው ያልታወቀ ፈንጂን ደህንነቶች የ ኤሌክትሪክ ፍንዳታ ነዉ የሚል የተሳሳተ መረጃ እያሰራጩ ነዉ ሲሉ እማኞች ገልጸዉልናል ብሏል:። ራድዮው ምንጮቼ ገለጹልኝ እንዳለ መዉሊድን አስመልክቶ ይበተን ከነበረ ከረሜላ ጋር አብሮ በሶፍት ወረቀት የተጠቀለለ ነገር ሰዎች ላይ ወድቆ ነዉ ፍንዳታዉ የተከሰተዉ።

ራድዮው እንደዘገበው ከሰዉነት ላይ የተቆረጠ ስጋ የፈሰሰ ደም ያለበት ፎቶ ግራፍ በሶሻል ሚድያዎች የተለቀቀ ሲሆን ፍንዳታዉ እንደተከሰተ ደህንንነቶች ግቢዉን የመቆጣጠራና የማጽዳት ስራ ላይ ነበሩ። ግቢዉ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዉሉ ከተጠረገ በሗላ ከጠረጋ የተረፈ የሰው ስጋ (ሙዳ ስጋ)አግኝተዉ ፎቶ ማንሳታቸዉን እማኞቻችን ነግረዉናል ሲል ራድዮው ዘገቧል::

በዚህ ምንነቱ ያልታወቀና ከወደላይ ተወርውሮ የመጣ ነው በተባለው ፈንጂ የተነሳ 6 ሰዎች ቆስለው ተክለሃይማኖት ሆስፒታል ህክምና ላይ ናቸው::

1 የሞተ ሰውም አለ እየተባለ ሲሆን ዘ-ሐበሻ ይህን ለማጣራት እየሞከረች ነው::

The post በአንዋር መስጊድ የፈነዳው ምንነቱ ያልታወቀውን ፈንጂን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ appeared first on Zehabesha Amharic.

“መሬት ለአራሹ”ተረስቶ “መሬት ለካድሬ”–ከአምዶም ገብረሥላሴ

$
0
0

oromo

“መሬት ለኣራሹ” የሚል 60ዎቹ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች መፎክር ነበር።
የጃንሆይ ዙፋን መገርሰስ ዋነኛ ምክንያት ሆነ። ደርግም ጥያቄው ህዝቡ በሚፈልገው መልኩ ኣልመለሰውም።

ህወሓት ደርግ ገርስሶ 4 ኪሎ ከገባ በኋላም የመሬት ጥያቄ “መሬት የህዝብና መንግስት ናት። መንግስት ማለት ህዝብ ሰለ ሆነ እኔ ራሴ የመሬት ባለቤት ነኝ” ብሎ በማወጅ ህዝባችን መሬት ኣልባ ኣደረገው።

“መሬት ለኣራሹ” ትቶ መሬት ለካድሬ የሚል ውስጣዊ መፎክር ለ25 ዓመታት ተግባራዊ ኣድርገዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘ እስቲ ሰሞኑ በውቕሮ የተጋለጠ ጉድ እንደምሳሌ ላቅርብ።

የውቕር ከተማ ከንቲባ ኣቶ ዘርኡ ገብረመስቀል እያሉ ኣቶ ገብረዝሄር ገብረመድህን የተባሉ ባለ ሃብት “ማድያ ለመክፈት ስለምፈልግ በኣውራ ጎዳና መስመር መሬት ይሰጠኝ” ኣሉ።

ማድያ እንዲሰሩበት የመረጡት መሬት 1200ካ/ሜ ሲሆን በውቕሮ ከተማ ገበያ ለካሬ ሜትር 700 ብር በሊዝ ገበያ የተወሰነለት ነው።

ባለሃብት በሊዝ ዋጋ ከገዛው 840 000 ብር መክፈል ነበራቸው ይሁን እንጂ ይሄ ብር ከመክፈል ከውቕሮ ከንቲባ ኣቶ ዘርኡ ገብረመስቀል ጋራ ተደራደሩ በድርድራቸውም ስምምነት ላይ ደረሱ። ከከንቲባው ጋር 4 ሰዎች ከባለ ሃብቱ ተደራደሩ።

oromo2

በድርድሩ ወደ መንግስት ካዝና ሊገባ የነበረውና በባለሃብቱ ሊከፈል የታሰበው 840 000 ብር ግማሹ እንዲቀርና ግማሹም ለኣምስት ሰዎች እንዲካፈሉት ወሰኑ። በዚህ መሰረት

1) ኣቶ ዘርኡ ገብረመስቀል 250 000 ብር

2) ምክትል ከንቲባ ገብረመድህን ስዩም 70 000

3) ተኽለ ኣብርሃ የመሬት ማልማት ፅፈት ቤት ሓላፊ( መዛገጃቤት) 50 000 ብር

4) ጊደና በርሀ የውቅሮ መሃንዲስ 50 000 ብር ተካፈሉት።

በዚህ መሰረት ኣቶ ገብረዝሄር ገብረመስቀል ሊከፍሉት ከነበረው ዋጋ በግማሽ ቀንሰው ለካሬ ሜትር በ23 ብር 420 000 ብር ለባለስልጣናት በመክፈል ከግማሽ በላይ ቅናሽ ኣግኝተዋል።

ሰሞኑ በትግራይ የህወሓት ካብኔ ኣባላት ግምገማዎች እያካሄዱ ይገኛሉ። በስብሰባው የተለያዩ ኔትወርኮች ያሉት ሲሆኑ ራስ በራስ እየተጠላለፉ ይገኛሉ።

በውቕሮ ከተማ እየተካሄደ ያለው ግምገማ የካቢኔ ባለስልጣናት ይሄ ሙስና ኣጋለጡ። በዚህ መሰረትም ከንቲባው ኣቶ ርኡ፣ የማዘጋጃቤት መሬት ማልማት ሓላፊ ተኽለ ፣ የውቕሮ ከተማ መሓንዲስ ጊደና በርሀ ሲታሰሩ ምክትል ከንቲባ ገብረመድህን ስዩም 70 000 ብር ሙሰኛ ባልታወቀ ምክንያት ኣልታሰረም።

መሬቱ ከኣራሹ ተቀምቶ ለካድሬው ጥቅም እየዋለ ይገኛል።
ኣቶ ሓየሎም በላይ 1200 ካ/ሜ መሬታቸው በከንቲባና ባለ ሃብቱ ያለ ካሳ ክፍያና የመሬት ልዋጭ ተነጥቀዋል። ኣብየቱታቸው እስከ ዞን ድረስ ቢያሰሙም ምንም መፍትሄ ኣልተሰጣቸውም።

tigrai

በተያያዘ ዜና የመቐለ ከንቲባ ነበርና የማእከላዊ ኮሚቴ ኣባል የነበሩ ጉምቱ ባለ ስልጣንም ደብሪ በተባለ የገጠር ቀበሌ በሚስታቸው ስም ከኣንድ ገበሬ መሬት ቀምተው ኣርሶ ኣደሩ መሬት ኣልባ ሲያደርጉት ከቀበሌ እስከ ክልል ኣብየት ቢል ሰሚ እንዳላገኘ በሓድነት ክፍለ ከተማ በህዝብ ግምገማ ተጋልጠዋል።

የኣይናለም፣ እግሪሓሪባ ወዘተ ገበሬዎች በካድሬዎችና ባለስልጣናት ያለኣግባብ መሬታቸው እመተቀሙ መሬት ኣልባ ሁነዋል።

እንደነ ወይዘሮ ኣልጋነሽ ገብሩ የመሳሰሉ ጀግኖች ደግሞ መሬታችን ኣሳልፈን ኣንሰጥም በማለታቸው ለእስር ተዳርገው ይገኛሉ።

ይሄው ኣርሶ ኣደሩ ባገሩ መሬት ኣልባ ሲሆን ካድሬው ግን ከገበሬው እየቀማ ባለሃብት እየሆነ ነው።

የኦርሞ ህዝብ “የኣዲስ ኣበባ ማስፋፍያ ማስተር ፕላን ገበሬው መሬት ኣልባ ያደርግብናል” በማለት እየተቃወመው ይገኛል። ይሄ ተቃውሞ ከ25 ዓመታት የኢህኣዴግ ኣገዛዝ ልምድ ተነስተን መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሊደግፈው ይገባል።

መንግስትም ህዝቡ ያልተቀበለው እቅድ በመሰረዝና ሰልፉ ለመበተን የተጠቀመው ያልተመጣጠነ የሃይል እርምጃና ላደረሰው ጉዳት በድፍረት ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባዋል።

ኢህኣዴግ የመሬት ፖሊሲዎቹ መቀየር ኣለበት። መንግስት የኦሮሞ ህዝብ ሰለማዊ ተቃውሞ በኣግባቡ መመለስ ብቻ ሳይሆን ከመሬት ባለቤትነቱም መራቅና የማስተዳደር ስራ ብቻ እንዲታቀብ እንመክረዋለን።

ህወሓትና የትግራይ ህዝብ መለየት ያቃታቹ የህወሓት ካድሬዎችና ፅንፈኛ በጥላቻ ዓይናቹ የታወረው ተቃዋሚዎች ኣትድከሙ።

የትግራይ ህዝብ ከኦሮሞና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ጎን በኣንድነት ተሰልፎ ለውጥ እውን ያደርጋል። ህዝባችን በተግባር የሚደግፈው ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እንጂ በስሙ የሚነግድለት ኣምባገነን ስርዓት ኣያስፈልገውም።

ነፃነታችን በእጃችን ነው።

‪#‎Ethiopian_Famine‬
‪#‎ክፉ_ቀን‬
‪#‎ዘበን_ኣካሒዳ‬

The post “መሬት ለአራሹ” ተረስቶ “መሬት ለካድሬ” – ከአምዶም ገብረሥላሴ appeared first on Zehabesha Amharic.

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ በአዳማ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ነገ ጠዋት ይደረጋል

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በኢትዮጵያ በተለይም በኦሮሚያ እና በጎንደር ከፍተኛ ያለ ውጥረት በተከሰተበት በዚህ ወቅት የአዲስ አበባን አዲሱን ማስተር ፕላን በመቃወም እና መንግስት በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የጥይት ዝናብ ማውረዱን በማውገዝ ኦፌኮን የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በአዳማ ከተማ እንደሚካሄድ ለዘ-ሐበሻ የተላከው መረጃ አመለከተ::

File Photo (Adama City)

File Photo (Adama City)

ነገ ቅዳሜ ጠዋት (ዲሲምበር 11, 2015) የሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ መነሻው በከተማው መስቀል አደባባይ መሆኑ ታውቋል:: ይህ ሰላማዊ ሰልፍም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት የሚደረግ ከመሆኑም በተጨማሪ ሁሉም ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ እንዲሳተፍ ጥሪ ተላልፏል::

በአዳማ ከተማ መስቀል አደባባይ በተጣራው በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የኦፌኮ ከፍተኛ አመራሮች ዶ/ር መረራ ጉዲና እና ኦቦ በቀለ ገርባ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል::

The post የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ በአዳማ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ነገ ጠዋት ይደረጋል appeared first on Zehabesha Amharic.

የአጋዚ ሰራዊት በምዕራብ አሪሲ አዳባ ከተማ ወታደራዊ ጥቃት ፈጸመ –አንድ ወጣት መገደሉ ተሰማ

$
0
0

adaba

(ዘ-ሐበሻ) በምዕራብ አሪሲ አዳባ ከተማ ለሰላማዊ ሰልፍ በወጡ የህብረተሰቡ ክፍል ላይ የአጋዚ ጦር ወታደራዊ እርምጃ መውሰዱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ:: በከተማዋ የአጋዚ ጦር በወሰደው እርምጃ የጥይት ድምጽ እና ጭስ ከተማዋን ሞልቶት እንደዋለ ነዋሪዎቹ አስታውቀዋል::

እንደ ነዋሪዎች ገለጻ ከሆነ በአዳባ ከተማ በአጋዚ ጦር በተወሰደው ወታደራዊ እርምጃ አንድ ወጣት ተገድሏል:: በአዳባ የተገደለው ወጣት ስም ነስረዲን መሀመድ እንደሚባልም ታውቋል::

በአሁኑ ሰዓት ወደ አዳባ ከተማ መግባትም ሆነ መውጣትም የማይቻል ሲሆን ወታደሮች ከተማዋን አጥረዋታል:: በአጋዚ ጦር ጥቃት የቆሰሉት ወገኖች በሃዋሳ እና ኩረያ ሆስፒታል እያታከሙ መሆኑም ተሰምቷል::

The post የአጋዚ ሰራዊት በምዕራብ አሪሲ አዳባ ከተማ ወታደራዊ ጥቃት ፈጸመ – አንድ ወጣት መገደሉ ተሰማ appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live