Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

Sport: ለዓለም ዋንጫና ለቻን ማጣሪያ ጨዋታ የሚሰለፉት 19 የብሔራዊ ቡድናችን ተጫዋቾች ታወቁ

$
0
0

ethiopian national tea
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ቀጣይ ላለባቸው የዓለም ዋንጫና የቻን ማጣሪያ ጨዋታ የ19 ተጫዋቾችን ስም ዝርዝር ይፋ አደረጉ።

የተመረጡት ተጨዋቾች መስከረም 19 ቀን 2008 ዓ.ም ከቦትስዋና ጋር በሚያደርገው የአቋም መለኪያ ጨዋታ ይሳተፋሉ ሲሉ መንግስታዊ ሚዲያዎች ዘግበዋል::

ለ2018ቱ የዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ እንዲሁም ለ2016ቱ የአፍሪካ አገሮች እግር ኳስ ዋንጫ /ቻን/ ከቡሩንዲ ጋር ለሚደርገው ጨዋታ ቅድመ ዝግጅት ያደርጋሉ።

ሁሉም ተጫዋቾች መስከረም 10 ቀን 2008 ዓ.ም በፌዴሬሽኑ ጽህፈት ቤት ተገኝተው ሪፖርት በማድረግ ወደ ሆቴል የሚሰባሰቡ ሲሆን፥ ልምምዳቸውንም የሚጀምሩ ይሆናል።

ተጨማሪ ተጨዋቾች ከ2007 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች በኋላ እንደሚለዩ የኢትዮጵያ ብሄራዊ እግር ኳስ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ መግለፃቸውን ፌዴሬሽኑ የላከው መግለጫ ያመለክታል።

በአሰልጣኙ የተመረጡት ተጨዋቾችም ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናችው።

ግብ ጠባቂዎች፦

1. ታሪክ ጌትነት

2. ለዓለም ብርሃኑ

3. አቤል ማሞ

ተከላካዮች፦

1. ስዩም ተስፋዬ

2. ተካልኝ ደጀኔ

3. አሰቻለው ታመነ

4. አንተነህ ተስፋዬ

5. ሙጂብ ቃሲም

6. ዘካርያስ ቱጂ

አማካዮች፦

1. ኤፍሬም አሻሞ

2. ጋቶች ፓኖም

3. ሙሉ ዓለም መስፍን

4. ብሩክ ቃልቦሬ

5. ቢኒያም በላይ

6. በረከት ይስሃቅ

7. አሰቻለው ግርማ

አጥቂዎች፦

1. ባዬ ገዛሀኝ

2. ዳዊት ፈቃዱ

3. ራምኬል ሎክ

↧

↧

ዶ/ር አረጋዊ በርኸ ስለ ትሕዴን ሁኔታ

$
0
0

[Must-Listen] Dr. Aregawi Berehe Answers Your Questionsየትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ መሪ አቶ ሞላ አስገዶም ብዛታቸው በመቶዎች የተቆጠረ የድርጅቱን ታጣቂዎች ይዘው ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው ድርጅቱን “ከመጉዳት ይልቅ ያጠናክረዋል” ብለዋል የቀድሞ የሕወሓት ታጋይ ዶ/ር አረጋዊ በርኸ ለቪኦኤ በሰጡት የሰሞኑ ሁኔታ ትንተና፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ከወጡት መካከል አሁንም ሱዳን ውስጥ ያሉትን ለመመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የትሕዴን ምክትል ሊቀመንበር አቶ መኮንን ተስፋዬ ተናግረዋል፡፡ የሱዳን ባለሥልጣናት ከስድስት መቶ ከሚበልጡ ታጣቂዎች ላይ ትጥቅ መረከባቸውን ሱዳን ትሪቡን የሚባለው የኢንተርኔት ጋዜጣ አመልክቷል፡፡ ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Source:: voanews

↧

Sport: ፔድሮ!!! የጆዜ ሞውሪንሆ ትክክለኛ ውሳኔ

$
0
0

pedr

ከማንችስተር ዩናይትድ ይልቅ የቼልሲ ጥሪን ለመቀበል አንድ የጆዜ ሞውሪንሆ የስልክ ጥሪን መስማት በቂው ይሆንለታል፡፡ ለምዕራብ ለንደኑ ክለብ በ21 ሚሊየን ፓውንድ የዝውውር ሂሳብ ከፈረመ ጥቂት ቀናት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለቼልሲ በተሰለፈበት ግጥሚያ አንድ ጎል በማስቆጠርና ሌላ አንድ የጎል አሲስትን በስሙ በማስመዝገብ ማን ኦፍ ዘ ማች ፐርፎርማንስን ለማበርከት ችሏል፡፡ ከዚህ አንፃር የቼልሲው አሰልጣን ስፔናዊውን ኢንተርናሽናል አጥቂ ‹‹በትክክል ዲያጎ ማራዶና አይደለም፡፡ ሆኖም ግን ማራዶናን ለመሆን የተቃረበ ነው›› በማለት ቢገልፁት አስገራሚ አይሆንም፡፡

ቼልሲ የዘንድሮውን ሲዝን ከስዋንሲ ሲቲና ከማንችስተር ሲቲ ጋር ያደረጋቸው የመጀመሪያዎቹ ሁለት የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያዎች ለማሸነፍ ተስኖት ከጀመረ በኋላ በሀውዝሮን ስቴዲየም ዌስትብሮም አልቢዮንን 3ለ2 በሆነ ውጤት ለማሸነፍ እንዲችል ምክንያት ከሆኑት ጎሎች ውስጥ ፔድሮ የመጀመሪያዋን በ20ኛው ደቂቃ ላይ ከመረብ ለማሳረፍ ችሏል፡፡ ከዛም ዲያጎ ኮስታ የጎል መጠኑን ሶስት አድርሶታል፡፡

ከዚህ አንፃር የ28 ዓመቱ ስፔናዊ አጥቂ ቼልሲ ፊርማውን ለማግኘት ለባርሴሎና የፈከለበትን 21 ሚሊየን ፓውንድ በአግባቡ መክፈል ጀምሯል ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ከግጥሚያው በኋላ ፔድሮ በተሰባበረ የእንግሊዝኛ ቋንቋ በሰጠው መግለጫውም ለቼልሲ በተሰለፈበት የመጀመሪያው ግጥሚያው ጎልን በማስቆጠር የታጀበ ታላቅ ፐርፎርማንስን ለማበርከት በመቻሉ የተሰማው ደስታ ከፍተኛ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

‹‹ለአዲሱ ክለቤ ለመጀመሪያ ጊዜ በተሰለፍኩበት ግጥሚያ ጎል ማስቆጠሬ ትልቅ ደስታን ፈጥሮልኛል›› በማለት ለስካይ ስፖርትስ ቲቪ መግለጫውን መስጠት የጀመረው የቀድሞው የባርሴሎና የአጥቂ መስመር ተጨዋች በመቀጠልም ‹‹ወደዚህ ተወዳጅ ክለብ የመጣሁት በርካታ ጎሎችን ለማስቆጠር የምችልበት አስተማማኝ ብቃትን መላበሴን እርግጠኛ በመሆን ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ገና በመጀመሪያው የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያዬ ጎል ለማስቆጠር መቻሌ አጠቃላዩ የቼልሲ ቆይታዬ በስኬት የታጀበ እንደሚሆን ሙሉ ለሙሉ እርግጠኛ አድርጎኛል፡፡ ምክንያቱም ገና በመጀመሪያው ግጥሚያዬ ጎልን ማስቆጠር መቻሌ አጠቃላዩ በራስ የመተማመን መንፈሴን እጅግ ያማረ እንደሚያደርገው አውቃለሁ፡፡ ተስፋ የማደርገውም ለቼልሲ የተሰለፍኩበትን የመጀመሪያውን ሲዝኔን በርካታ ጎሎችን በማስቆጠር ለማጠናቀቅ እችላለሁ ብዬ ነው›› የሚል አስተያየቱን አክሏል፡፡
ከዚህ በፊት ከፔድሮ ጋር ለባርሴሎና እና ለስፔን ብሔራዊ ቡድን በበርካታ ግጥሚያዎች አብሮት የተሰለፈው የቼልሲው አማካይ ሴስክ ፋብሪጋስ በበኩሉ ‹‹ፔድሮ በክለባችን ቆይታው ትልቅ ስኬት እንደሚኖው ሙሉ ለሙሉ እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ ባሰብኩትም መልኩ በታላቅ ፐርፎርማንስ የታጀበ አስገራሚ አጀማመርን አድርጎልናል፡፡ የፔድሮ ወደ ክለባችን መምጣትን ከልብ የወደድኩት ቡድናችን ከሌላው የተለየ አይነት ጥቅምን እንደሚሰጠን ስለማምንበት ነው፡፡ ምክንያቱም ከተጋጣሚ ቡድን የተከላካይ መስመር ጀርባ የሚገባበት እጅግ ከፍተኛ የሆነ ፍጥነት አለው፡፡ ያለማቋረጥ በርካታ ድሪብሊንጎችን ለማድረግ የሚችልበት አስተማማኝ ብቃትንም ተላብሷል፡፡

ይህ ሌሎቹ የቡድናችን ተሰላፊዎች በማጥቃቱ እንቅስቃሴ እንዲሳተፍ በቂ ክፍተትን የሚያስገኝላቸው መሆኑን አምናለሁ፡፡ በእርግጥ ቡድናችን ሌሎች ከፍተኛ ፍጥነት ያላቸው የፊት አጥቂዎችን በሎይክ ሬሚና በዲያጎ ኮስታ አማካይነት ይዟል፡፡ ሆኖም ግን በክንፍ በኩል አጠቃላይ የቡድናችን የማጥቃት እንቅስቃሴን ከፍተኛ ፍጥነትን ለማስገኘት የሚችልበት እንደ ፔድሮ ያለ ተጨዋችን አጥብቀን እንፈልግ ነበር፡፡ የፔድሮ መምጣት ይህንን ፍላጎታችንን በትክክል እንዳሳካልንም በዚህ ግጥሚያ ያበረከተው ታላቅ ፐርፎርማንስ በቂ ማስረጃ ሆኖልናል፡፡ እርግጠኛ ሆኜ የምናገረውም ፔድሮ በሰፊው ሲዝን በሌሎች በርካታ ግጥሚያዎች ለቡድናችን ታላቅ ፐርፎርማንስን ማበርከቱን እንደሚገፋበት ነው›› በማለት የ28 ዓመቱ ስፔናዊ ኢንተርናሽናል የቼልሲ የፉትቦል ሕይወት አጀማመርን አወድሶታል፡፡

የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንነት ክብርን የማስከበር አላማን በመያዝ የዘንድሮውን ሲዝን የጀመረው ቼልሲ ሶስቱ ስፔናዊያን ኢንተርናሽናሎች ማለትም ፔድሮ፣ ዲያጎ ኮስታና ሴዛር አዝፕሊኩዌታ አማካይነት ባስቆጠራቸው ጎሎች ዌስትብሮምን 3ለ2 የረታበት ግጥሚያ የዘንድሮ የውድድር ዘመን የመጀመሪያው ድሉ ነው፡፡ ሆኖም ግን በእስካሁኑ ሶስቱ ግጥሚያዎች በአጠቃላይ በስምንት ጎሎች መረቡን ማስደፈሩ በቡድኑ የተከላካይ መስመር ላይ ከፍተኛ የሆነ የመሳሳት ችግር መፈጠሩን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ሆኗል፡፡
በተለይም በሀውዝሮን ስቴዲዮም በተደረገው ግጥሚያ የቡድኑ አምበል ጆን ቴሪ በ2ኛው ግማሽ የቀይ ካርድ ሰለባ መሆኑ ይህ ችግር በቀጣዮቹ ግጥሚያዎች ላይም ተባብሶ እንደሚቀጥልበት የሚጠቁም ሆኗል፡፡ ሆኖም ግን አሰልጣኝ ጆዜ ሞውሪንሆ ቡድናቸው የዘንድሮው ሲዝንን የመጀመሪያው ድሉን ለማስመዝገብ ከቻለበት የእሁዱ ግጥሚያ በኋላ በሰጡት መግለጫ ባልተለመደ መልኩ በቡድናቸው የተከላካይ መስመር ከታየው ክፍተት ይልቅ አዲስ ፈራሚያቸው ፔድሮ ሮድሪጌዝ ወደ አዲስ የሊግ ውድድር መምጣቱ ምንም አይነት ችግር ሳይፈጥርበት ማን ኦፍ ዘ ማች ፐርፎርማንስን ለማበርከት በመቻሉ የተሰማቸው ደስታ ከፍተኛነትን ማንፀባረቁን ምርጫቸው አድርገውታል፡፡

‹‹ትክክለኛው ዲያጎ ማራዶና ነው አልልም፡፡ ሆኖም ግን ማራዶናን ለመሆን የተቃረበ ተጨዋች ነው›› በማለት ለቼልሲ ቲቪ መግለጫቸውን መስጠት የጀመሩት ሞውሪንሆ በመቀጠልም ‹‹ወደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ በመጡበት ሲዝን ያልተሳካላቸው በርካታ ታዋቂ ተጨዋቾች በመኖራቸው ፔድሮ ከቡድናችን ጋር የፕሪ ሲዝን ዝግጅት ባልሰራበት ሁኔታ ወደ ክለባችን በመግባት ገና የመጀመሪያው ሳምንት ውስጥ በመደበኛ ቋሚ ተሰላፊነት የሰጠሁበት ውሳኔዬ ስጋትን የፈጠረባቸው ሰዎች መኖራቸውን አውቃለሁ፡፡ በእርግጥም ከሌላ ሀገር የሊግ ውድድር መጥተው ገና በመጀመሪያው የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያቸው የሚጠበቅባቸውን ውጤታማ ፉትቦልን ለማበርከት ያልቻሉ ተጨዋቾች በርካታ መሆናቸውን ከዚህ በፊት በራሳችን ክለብ ካጋጠመን እውነታ አንፃር የምናውቀው ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ፔድሮ ለቡድናችን በተሰለፈበት የመጀመሪያው ግጥሚያው ጎልና አሲስትን በስሙ ለማስመዝገብ መቻሉ ከፍተኛ የሆነ የኩራት መንፈስን የፈጠረብኝ ሆኗል፡፡

በዚህ የመጀመሪያው ግጥሚያ የወትሮውን ውጤታማ እንቅስቃሴውን በተሟላ ሁኔታ አሳይቷል፡፡ ይህንን ስል ግን ለባርሴሎናና በተሰለፈባቸው የፕሪ ሲዝን ግጥሚያዎችና ሶስት የነጥብ ጨዋታዎች ላይ ጥሩ አቋም ስለነበረው ለቡድናችን በፍጥነት ትልቅ ስኬት እንደሚኖረው አምንበት እንደነበር ለማረጋገጥ ከፈረመ ገና ከሶስት ቀናት በኋላ በመደበኛ ቋሚ ተሰላፊነት የመጀመር እድልን በመስጠት ላልተፈለገ ከፍተኛ ጫና ልዳርገው አልመኝም ነበር፡፡ ዝውውሩን ካደረገ ወዲህ ባሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በቡድናችን ካለው ሁሉም አይነት የጨዋታ ስታይልና ታክቲካል ጉዳዮች ጋር ራሱን ለማዋሃድ ያደረገው ያለሰለሰ ጥረቱ ስኬታማ እንዲሆንለት በዚህ ግጥሚያ ካሳየው እጅግ የላቀ ውጤታማ ፐርፎርማንሱ በቀላሉ ለመረዳት ችያለሁ፡፡ ከዚህ አንፃር ፔድሮን ከፊታችን ባሉት በእያንዳንዱ የቡድናችን ግጥሚያዎች ላይ በመደበኛ ቋሚ ተሰላፊነት የመጫወት እድልን ልሰጠው የማልጓጓበት ምክንያት አይኖረኝም›› የሚል አስተያየት አክለዋል፡፡

የፔድሮ ስታምፎርድ ብሪጅ መድረስ በማንቸስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ሉዊ ቫንሃል ላይ ከፍተኛ ትችትን ማስከተሉ ይታወቃል፡፡

ምክንያቱም ባንሃል በእጃቸው ሊያስገቡት የተቃረቡትን ተጨዋች ለዋነኛ ተቀናቃኛቸው ቼልሲ አሳልፈው ለመስጠት ተገድደዋል፡፡ ይህንን ስህተታቸውን ለመሸፋፈን ሲሉም ቫንሃል ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በሰጡት መግለጫ ‹‹ፔድሮን ያላስፈረምኩት በራሴ ውሳኔ ነው›› ብለዋል፡፡ በእሁዱ ግጥሚያ በተግባር የታየው ጉዳይ ግን የማንቸስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ፔድሮን ለማግኘት ባለመቻላቸው ለቼልሲ በአንድ ሲዝን ከ20 ጎሎች በላይ ለማስቆጠር የሚችልበት ውጤታማ ተጨዋችን አሳልፈው የሰጡበት ትልቅ ስህተትን መስራታቸውን ነው፡፡

ይህንን በማመንም የጎል ድረገፅ የፉትቦል ተንታኝ ላይም ትዌሜይ በፔድሮ ሮድሪገዝ በማን ኦፍ ዘ ማፕ ፐርፎርማንስን በታጀበ የቼልሲ የፉትቦል ህይወት አጀማመር ዙሪያ ከዚህ በታች ያለውን ሙያዊ ትንተናውን አስነብቧል፡፡ ማንቸስተር ዩናይትድ ለድፍን ሁለት ወራት ፔድሮን ለማግኘት ያደረገው ፍሬ አልባ ጥረትን ለማሳካት 24 ሰዓታት እንኳን የማይሞላ ነው፡፡ የተጨዋቹ ኤጀንት አንቶኒዮ ሳንዜ ባለፈው ሳምንት ውስጥ ስፔናዊው አጥቂ በሚጠበቀው መልኩ ለምን ወደ ኦልድ ትራፎርድ አልተጓዘም በሚል ለቀረበለት ጥያቄ ምላሹን የሰጠውም ‹‹ምናልባትም ማንቸስተር ዩናይትድ ማንቀላፋቱን በመምረጡ ይመስለኛል›› በማለት ነው፡፡
ራሱ ፔድሮም ‹‹የቼልሲ ጥሪ ግልፅነትና ታማኝነት የተሞላበት በመሆኑ ጥያቄውን ለመቀበል የወሰደብኝ ጊዜ 630 ሰኮንዶች ብቻ ነው›› ብሏል፡፡ ለታማኞቹ ቀጣሪዎቹ ምን አይነት ውጤታማ ግልጋሎትን እንደሚሰጣቸው ለማረጋገጥ በሀውዝሮን ስቴዲየም በተደረገው ግጥሚያ ጎል በማስቆጠር የታጀበ ታላቅ ፐርፎርማንስን በማበርከት ለማስመስከር ችሏል፡፡

ከዌስትብሮም ጋር በተደረገው ግጥሚያ በመጀመሪያው ግማሽ የመሪነቷ ጎልን በማስቆጠርና ለ2ኛዋ መገኘት ምክንያት የሆነ የጎል አሲስትን በስሙ በማስመዝገብ የጆዜ ሞውሪንሆ ቡድንን የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንነት ክብርን የማስከበር አላማን እንደ አዲስ አቀጣጥሎታል፡፡ ይህንን ያደረገው ገና ስታምፎርድ ብሪጅ ከደረሰበት ሶስት ቀናት ብቻ ባስቆጠረበት ሁኔታ መሆኑም በፍጥነት የሞውሪንሆ ታክቲካል መመሪያን ጠንቅቆ መረዳቱን ያረጋገጠ ሆኗል፡፡

ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝም ፔድሮ በሜዳ ላይ ካሳየው ውጤታማ ፉትቦሉ በበለጠ ታክቲካል መመሪያቸውን በፍጥነት ተግባራዊ ለማድረግ የቻለበት ፈጣን አዕምሮውን አድንቀውለታል፡፡ ለሞውሪንሆ የበለጠ ትልቅ ደስታን ሊፈጥርባቸው የሚገባውም ፔድሮ ገና በመጀመሪያው ግጥሚያው ከቡድናቸው ኮከብ ተጨዋች ኤን ሃዛርድ ጋር ያማረ የማጥቃት እንቅስቃሴን መፍጠር መቻሉ ነው፡፡

በጨዋታው 20ኛው ደቂቃ ላይ ላስቆጠራት ጎል ሃዛርድ ቆንጆ ፓስን አድርሶለታል፡፡ ከዛ በኋላም በሁለቱ መካከል የነበረው የጨዋታ እንቅስቃሴ መናበብ የገለልተኛው ፉትቦል አፍሪቃን ሳይቀር ስሜትን የሚስብ ሲሆን ታይቷል፡፡ በተለይም የፔድሮ በከፍተኛ ፍጥነት የታጀበ የማጥቃት እንቅስቃሴ የዌስትብሮም የተከላካይ መስመር ተጨዋች ከሆኑት ክሬግ ዳውሰንና ክሪስ በርንት ግራ የመጋባት መንፈስን ሲፈጥርባቸው ታይቷል፡፡

ፔድሮ በሁለቱም ክንፎች በኩል በሜዳ ላይ በቆየባቸው 83 ደቂቃዎች ያደረገው በከፍተኛ ፍጥነት የታጀበ ውጤታማ የማጥቃት እንቅስቃሴ በሰፊው ሲዝን በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ለሚገኙት የግራ የቀኝ ተመላላሽ ሚና ባለቤቶች ትልቅ ፈተናን የሚፈጥርባቸው እንደሚሆን ያስገነዘባቸው ሆኗል፡፡
ዲያጎ ኮስታ ላስቆጠራት ጎል ካደረገለት ፓስ ባሻገር ከዊልያን በደረሰው ቆንጆ ኳስ የግጥሚያው 2ኛው የጎል አሲስቱን ማስመዝገብ በቻለ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ብራዚላዊው ኢንተርናሽናል የፔድሮ ግሩም ፓስን በደካማ የጎል አጨራረስ አባክኗታል፡፡ በአጠቃላይ ፔድሮ ታክቲካልም ሆነ ቴክኒካሊ እንከን የማይወጣለት ውጤታማ ፉትቦልን ለቼልሲ በተሰለፈበት የመጀመሪያው ግጥሚያ ላይ ለማበርከት ችሏል፡፡

ይህ ቅዳሜ ማንቸስተር ዩናይትድ ከኒውካስል ጋር 0ለ0 በተለያየበት ግጥሚያ የተጋጣሚ ቡድን የተከላካይ መስመርን ለማስከፈት ያልቻለበት ችግሩን ፔድሮ ሙሉ ለሙሉ ይቀርፉለት እንደነበር ለማረጋገጥ ሆኗል፡፡ በኦልድ ትራፎርድ ግጥሚያ ሁን ማታ በቀኝ ክንፍ በኩል ከፍተኛ ፍጥነትን ለማመንጨት ሲቸገር ታይቷል፡፡
ፔድሮ ግን ይህንን ጠቀሜታን በቦታው ላይ በተሟላ ሁኔታ ከመስጠትም አልፎ ባለፉት ሁለት ግጥሚያዎቹ የአቋም አለመረጋጋት የተከሰተበት የቼልሲው ቀኝ ተመላላሽ ብራኒስላቭ ኢቫኖቪች ላይ የሚፈጠረውን የማጥቃት ጫናን ቀንሶለታል፡፡ ከዚህ አንፃር ፔድሮ በቼልሲ ካምፕ ዳግም ከፍተኛ የሆነ የመነቃቃት መንፈስ እንዲፈጠርበት አስችሎታል ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡

የፔድሮ የቼልሲ የመጀመሪያው ግጥሚያ በደቂቃዎች
20ኛ ደቂቃ
ከሴስክ ፋብሪጋስ ጋር የአንድ ሁለት የኳስ ቅብብል ካደረገ በኋላ በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ዌስትብሮም የሜዳ ክልል ዘልቆ ገብቷል፡፡ ከዛም ከኤደን ሃዛርድ ጋር ፓሶችን ከተለዋወጠ በኋላ በፔናሊቲ ቦክስ ውስጥ ያገኛት ኳስን በፍጥነት በመምታት በቼልሲ ማሊያ የመጀመሪያውን ጎሉን አስቆጥሯል፡፡
30ኛው
ከዌስትብሮም መዓዘን ምት የተመለሰችውን ኳስ ከዊሊያን ጋር በመቀባበል የቼልሲ ፈጣን የካውንተር አከታክ እንቅስቃሴ አስጀምሯል፡፡ ከዛም በቀኝ ክንፍ በኩል ዲያጎ ኮስታን ትክክለኛው ቦታ ላይ አግኝቶት የቼልሲ 2ኛው ጎል ተገኝታለች፡፡
40ኛ
የዌስትብሮሞቹ አልካንና ዊልትዘን በከፍተኛ ፍጥነት በታጀበ ድብሪሊንግ በማለፍ ቆንጆ ፓስን ለዊሊያን አድርሶታል፡፡ ሆኖም ግን ብራዚላዊው ያገኛት ጎል የማስቆጠር እድልን ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡
80ኛ
ተቀይሮ ለገባው ራዳሜል ፉልካኦ ያለቀለት ጎል የማስቆጠር እድልን ፈጥሮለታል፡፡ ሆኖም ግን ኮሎምቢያዊው አጥቂ በደካማ አጨራረስ አጋጣሚውን አባክኖታል፡፡ በሶስት ደቂቃዎች ከኋላም ፔድሮ ተቀይሮ ሲወጣ ከቼልሲ ተጓዥ ደጋፊዎች የጋለ የአድናቆት ጭብጨባ ተደርጎለታል፡፡

↧

የህወሓት አገዛዝ ለሱ ታማኝ በሆኑ የመከላከያ ሰራዊቱ አባላት አማካኝነት የጠገዴን ገበሬ እየጨፈጨፈው መሆኑ ታወቀ

$
0
0

clash
(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ) የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች አካባቢውን ይንቀሳቀሱበታል በሚል ጥርጣሬና ስጋት እጅግ በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያለው የመከላከያ ሰራዊት ኃ ይል በጠገዴ ምድር ላይ ያፈሰሰው እና የጠበቀውን ድጋፍ ከህዝቡ ማግኘት ያልቻለው ህወሓት የአርበኞች “ግንቦት 7 ታጋዮችን ታስጠልላላችሁ እና መረጃ ስጡን…” በሚል ሰበብ ነው ደሃውን ገበሬ በጥይት እየጨፈጨፈው የሚገኘው፡፡

ባለፈው ሳምንት ጳጉሜ 5 2007 ዓ.ም የህወሓት መከላከያ ሰራዊት በጠገዴ ሳርና ነዋሪ ገበሬዎች ላይ በከፈተው ተኩስ አቶ አቡሃይ መኩሪያ የተባሉት ገበሬና ወንድ ልጃቸው እሸቴ አቡሃይ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ታውቋል፡፡

↧

የተደበቀው የህወሓት ማንነት ከደደቢት እስከ ቤተ መንግስት – (ክፍል 7) በመከላከያ ሰራዊት ዕዞች እና ክ/ጦሮች ያለው ዝረኝነትና ስም ዝርዝር

$
0
0

mekelakeya
የተከበራችሁ አንባብያን! ባለፈው ሳምንት በክፍል 6 ዝግጅት በአንድ ብሄር ተወላጆች የህወሓት አባላት ብቻ የተያዙትን በመከላከያ መምሪያ፣ በመከላከያ ስልጠና መምሪያ እና በመከላከያ ኢንደስትሪ ውስጥ የሚገኙ ዋና ዋና ቦታዎች በጥቂቱ ለመዳሰስ ተሞክሯል፡፡
በዛሬው የተደበቀው የህወሓት ማንነት ከደደቢት እስከ ቤተ መንግስት ክፍል ሰባት ጽሁፍ ደግሞ በህወሓት መከላከያ ሰራዊት ዕዞች እና ክ/ጦሮች ውስጥ ያለውን የስልጣን መዋቅር በጨረፍታ ለማሳየት እንሞክራለን፡፡
• የሰሜን ዕዝ አዛዥ ሜ/ጀነራል ገብራት አየለ (ህወሓት)
• የሰሜን ዕዝ ምክትል አዛዥና የሎጀስቲክ ኃላፊ ብ/ጀነራል አብረሃ አረጋዊ (ህወሓት)
• የሰሜን ዕዝ ምክትል አዛዥ እና የኦፕሬሽን ኃላፊ ብ/ጀነራል ማዕሾ በየነ (ህወሓት)
• የሰሜን ዕዝ 4ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ዋና አዛዥ ኮ/ል ነጋሲ ተስፋዬ (ህወሓት)
• የሰሜን ዕዝ 4ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር የኢንዶክትሪኔሽንና ኮምዩኒኬሽን ኃላፊ ሌ/ኮሎኔል ሙሉ አብረሃ(ህወሓት)
• የሰሜን ዕዝ 4ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ምክትል አዛዥ እና የኦፕሬሽን ኃላፊ ኮ/ል ገ/ስላሴ በላይ (ህወሓት)
• የሰሜን ዕዝ ጤና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮ/ል ላዕከ አረጋዊ (ህወሓት)
• የሰሜን ዕዝ መሀንዲስ አዛዥ ኮ/ል ተስፋዬ ብርሃኔ (ህወሓት)
• የሰሜን ዕዝ ዋና አዛዥ ፅ/ቤት ኃላፊ ኮ/ል ገ/ዩሃንስ ተክሌ (ህወሓት)
• የሰሜን ዕዝ አጠቃላይ የትምህርት አገልግሎት ኃላፊ ኮ/ል ግደይ ኃይሌ (ህወሓት)
• የሰሜን ዕዝ የመዳኃኒትና አቅርቦት አገልግሎት ኃላፊ ኮ/ል አሰገደ ገ/መስቀል (ህወሓት)
• የሰሜን ዕዝ የኢንዶክትሪኔሽንና ኮምዩኒኬሽን ኃላፊ ኪሮስ ወ/ስላሴ (ህወሓት)
• የሰሜን ዕዝ ዘመቻ ኃላፊ ኮ/ል ታደለ ገ/ህይወት (ህወሓት)
• የሰሜን ዕዝ የሰው ኃይል አመራር መምሪያ ኃላፊ ኮ/ል መሃሪ አሰፋ (ህወሓት)
• በሰሜን ዕዝ የብ/ጀነራል በርሄ ወ/ጊዮርጊስ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል ዋና አዛዥ ኮ/ል ጀማል መሃመድ (ህወሓት)
• በሰሜን ዕዝ የብ/ጀነራል በርሄ ወ/ጊዮርጊስ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል ሆስፒታል ጤና ኃላፊ ሌ/ኮሎኔል ተክላይ ገ/መድህን (ህወሓት)
• የሰሜን ዕዝ የጤና ሙያተኞች ማሰልጠኛ ማዕከል ዳይሬክተር ሻለቃ ነጋሲ ሃጎስ (ህወሓት)
• የማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜ/ጀነራል ዮሃንስ ወ/ጊዮርጊስ (ህወሓት)
• የማዕከላዊ ዕዝ ምክትል አዛዥና የኦፕሬሽን ኃላፊ ብ/ጀነራል አብርሃ ተስፋዬ (ህወሓት)
• የማዕከላዊ ዕዝ የትምህርት ክትትል ኃላፊ ሌ/ኮሎኔል ሀጎስ ኃይሌ (ህወሓት)
• የማዕከላዊ ዕዝ የዘመቻ መምሪያ አዛዥ ኮ/ል ገ/ሚካኤል ኪዳነ ማሪያም (ህወሓት)
• በማዕከላዊ ዕዝ የፋና ማሰልጠኛ ማዕከል ምክትል አዛዥ እና የኦፕሬሽን ኃላፊ ኮ/ል ገ/እግዚአብሄር ገ/ሰላማ (ህወሓት)
• በማዕከላዊ ዕዝ የፋና ማሰልጠኛ የወታደራዊ ተሸከርካሪ እና ማመላለሻ ዲፓርትመንት ኃላፊ ሻለቃ ተክላይ ካህሳይ (ህወሓት)
• የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜ/ጀነራል ፍሰሃ ኪዳኑ (ህወሓት)
• የምዕራብ ዕዝ ምክትል አዛዥ እና የሎጀስቲክ ኃላፊ ብ/ጀነራል አብድራህማን ኢስማኤል (ህወሓት)
• የምዕራብ ዕዝ ኢንስፔክሽን ኃላፊ ኮ/ል ዮሃንስ ገ/ሊባኖስ (ህወሓት)
• የምዕራብ ዕዝ ሲግናል ሬጅመንት አዛዥ ኮ/ል ተክላይ ገ/ፃድቃን (ህወሓት)
• የምዕራብ ዕዝ ጤና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮ/ል ገ/ኪዳን ቸኮል (ህወሓት)
• የምዕራብ ዕዝ የስልጠና ኃላፊ ኮ/ል በርሄ ኪዳነ (ህወሓት)
• የምዕራብ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ምክትል አዛዥ እና የስልጠና ኃላፊ ኮ/ል ንጉሴ ኃይሌ (ህወሓት)
• የደቡብ ምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌ/ጀነራል አብርሃ ወ/ማሪያም (ህወሓት)
• የደ/ምስራቅ ዕዝ ም/አዛዥ እና የሎጀስቲክ ኃላፊ ብ/ጀነራል የማነ ሙሉ (ህወሓት)
• የደ/ምስራቅ ዕዝ የትራንስፖርት ኃላፊ ኮ/ል ቀለህ ገ/ስላሴ (ህወሓት)
• የደ/ምስራቅ ዕዝ የህግ ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮ/ል ገ/ሚካኤል ገብራት (ህወሓት)
• የደ/ምስራቅ ዕዝ ጤና ት/ቤት ዳይሬክተር ሻምበል ሀፍቱ ሰበሩ (ህወሓት)
• የ5ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ዋና አዛዥ ኮ/ል ሃጎስ (ህውሓት)
• የ5ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ምክትል አዛዥ እና የአስተዳደርና ፋይናንስ ኃላፊ ኮ/ል ተ/ብርሃን አለማየሁ (ህወሓት)
• የ7ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር የወንጀል ምርመራ ኃላፊ አምሳ አለቃ ኃይለአብ ፍሰሃ (ህወሓት)
• የ8ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ዋና አዛዥ ኮ/ል ገ/እግዚአብሄር ዘሚካኤል (ህወሓት)
• የ8ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ኢንዶክትሬኔሽንና ኮምዩኒኬሽን ኃላፊ ሌ/ኮሎኔል ሃጎስ ታረቀኝ (ህወሓት)
• የ12ኛ ክ/ጦር ምክትል አዛዥ እና የሎጆስቲክ ኃላፊ ኮ/ል ምሳሁ ገ/ተክሌ(ህወሓት)
• የ20ኛ ክ/ጦር ምክትል አዛዥ እና የኦፕሬሽን ኃላፊ ኮ/ል ሰመረ ተክሉ(ህወሓት)
• የ22ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ ኮ/ል ወ/ጊዮርጊስ ተክላይ(ህወሓት)
• የ23ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ ብ/ጀነራል በላይ ስዮም (ህወሓት)
• የ24ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ ብ/ጀነራል ፍስሃ ወርቅነህ (ህወሓት)
• የ24ኛ ክ/ጦር የጤና ኃላፊ ሌ/ኮሎኔል ዘሚካኤል ብርሃኔ (ህወሓት)
• የ25ኛ ክ/ጦር አዛዥ ብ/ጀነራል አሰፋ ቸኮል (ህወሓት)
• የ25ኛ ክ/ጦር ምክትል አዛዥ እና የሎጆስቲክ ኃላፊ ኮ/ል ገ/ሊባኖስ ገ/ጊዮርጊስ (ህወሓት)
• የ32ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ ብ/ጀነራል ገ/መስቀል ገ/እግዚአብሄር (ህወሓት)
• የ32ኛ ክ/ጦር ም/አዛዥ እና የፋይናንስ ኃላፊ ኮ/ል መሃሪ በየነ(ህወሓት)
• የ32ኛ ክ/ጦር የጤና ኃላፊ ሌ/ኮሎኔል ተክሊት ገ/ህይወት (ህወሓት)
• የ33ኛ ክ/ጦር አዛዥ ብ/ጀነራል ጋይም ሺሻይ (ህወሓት)
• የ33ኛ ክ/ጦር የኢንዶክትሪኔሽን ኃላፊ ሻምበል መብራሃቶም አብርሃ (ህወሓት)
• የተዋጊ ማሀንዲስ ክ/ጦር ዋና አዛዥ ብ/ጀነራል ሙሉ ግርማይ (ህወሓት)
• የተዋጊ መሀንዲስ ም/አዛዥ ኮ/ል ሰመረ ገ/እግዚአብሄር (ህወሓት)
• የተዋጊ መሀንዲስ ክ/ጦር ማሰልጠኛ ዋና አዛዥ ኮ/ል አደም ትኩ (ህወሓት)
……………………….
ውድ አንባቢዎቻቸን በቀጣዩ ሳምንት ደግሞ በክፍል ስምንት በአየር ኃይሉና በሰላም ማስከበር ተልዕኮው ያሉትን በአንድ ብሄር የተያዙ የአዛዥነት ቦታዎችን በመጠኑ እንፈትሻለን፡፡

↧
↧

የስንፈተ ወሲብ –ከ10 በላይ ምክንያቶችና ከ10 በላይ መፍትሄዎች!!

$
0
0

 

ይህ ጽሁፍ በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ላይ ታትሞ ወጥቷል::

በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት የሚፈጠር ችግርን በግልፅ ተነጋግሮ፣ መፍታትን ባህሉ ባደረገ ማህበረሰብ ውስጥ የስንፈተ ወሲብ ችግር የትዳር አደጋ የመሆኑ ጉዳይ ብዙም አሳሳቢ ላይሆን ይችላል፡፡

ሀገራችንን ጨምሮ በአፍሪካና በኤዢያ በትዳር ተጣማሪዎች መካከል በግልፅ የመነጋገር ባህል የዳበረ እንዳልሆነ በስነ ማህበረሰብ ሙያተኞች የተጠኑ ጥናቶች ያረጋግጣሉ፡፡ ስንፈተ ወሲብ ፆታና ዕድሜ ሳይለይ ይከሰታል፡፡ አደጋ የሚሆነው ችግሩ መከሰቱ ሳይሆን፣ ጥንዶች በተፈጠረው ችግር ዙሪያ በግልፅ ተወያይተው መፍትሄ ለማፈላለግ ዝግጁ አለመሆናቸው ነው፡፡

sexual-dysfunction copy

በፍቅረኞችም ሆነ በባለትዳሮች መካከል የሚፈፀም ወሲብ፣ ለሁለቱም የእርካታ (የደስታ) ምንጭ መሆኑ ሲቀር ‹‹ለምን?›› ብለን መጠየቅም ሆነ ርዕሰ ጉዳዩን በጠረጴዛ ዙሪያ አምጥቶ አለመነጋገር ብዙዎቻችን አንደፍርም፡፡ ፈቃደኝነቱም የለንም፡፡ ችግሩ እየተባባሰ ሲመጣ፣ ግንኙነቱ በፍቅረኝነት ደረጃ ላይ ያለ ከሆነ በቃሽኝ (በቃኸኝ) በሚል ይቋረጣል፡፡ ትዳር ከሆነም የፍቺ ጥያቄ ማቅረብ በሀገራችን የተለመደና በየጊዜው ቁጥሩ እየጨመረ የመጣ ክስተት ሆኗል፡፡ የሚገርመው ግን በፍቅረኞች (በትዳር) ደረጃ የተመሰረተው ግንኙነት፣ በአንድ ጀንበር ለማፍረስ ሲወሰን እውነተኛው ምክንያት ከመጋረጃ ጀርባ የተደበቀ ነው፤፤ ፍቺ የጠየቀችው ሴቷ ከሆነች ‹‹ይሰክራል፣ ይደበድበኛል፣ ገንዘብ ይደብቀኛል፣ ከእኔ ሌላ ሴት ወዷል ወዘተ…›› በሚል የውሸት ጭንብል ትሸፍነዋለች፡፡ የትዳር ይፍረስ ጠያቂው ወንዱ ከሆነ ደግሞ ‹‹ትጨቀጭቀኛለች፣ ገንዘብ ታባክናለች፣ ከእኔ ይልቅ የምትሰማው ወላጆቿን ነው ወዘተ…›› በማለት ለግንኙነቱ መሻከር ቁልፍ ምክንያት የሆነውን ችግር ወደ ጎን ሲገፋው ይስተዋላል፡፡ ‹‹ችግሩን የደበቀ መድሃኒት አያገኝም›› እንደሚባለው፣ የስንፈተ ወሲብ ጉዳይን በሀገራችን ባህል ለውይይት የማይቀርብ አጀንዳ በመሆኑ፣ የብዙ ትዳሮችን መፍረስ ከመጋረጃ ጀርባ ያለ አብይ ምክንያት ሆኖ ዛሬም ድረስ ቀጥሏል፡፡

በዘርፉ ጥናት ያካሄዱ ሙያተኞች ስንፈተ ወሲብ መፍትሄ ያለው የስነ ልቦና፣ የአካላዊና የአዕምሯዊ ጤና ችግሮች ውጤት ነው ይላሉ፡፡ በዛሬው ዝግጅት የስንፈተ ወሲብ ችግር ምንነትን፣ መንስኤን፣ አጋላጭ ምክንያቶችን፣ በሀገራችንና በዓለም ላይ ያሉ አማራጭ መፍትሄዎችን እንደዚሁም ከርዕሰ ጉዳዩ ጋር በተያያዘ፣ መታወቅ አለባቸው በምንላቸው ሐሳቦች ዙሪያ፣ ሙያዊ ማብራሪያ እንደሚከተለው እናቀርባለን፡፡

ጥያቄ፡- ስለስንፈተ ወሲብ ችግር ምንነት፣ የተወሰነ አጠቃላይ ሐሳብ ብናነሳና ውይይታችንን በዚሁ ብንጀምረው ጥሩ ይመስለኛል?

ዶ/ር፡- ስንፈተ ወሲብ የሚለውን ቃል፣ ጠበብ ባለው ዐውዱ ሲታይ፣ የወንድም ሆነ የሴት ብልት አለመነቃቃትንና ለግንኙነት ዝግጁ ካለመሆን ጋር የቀጥታ ቁርኝት ያለው ነው፡፡ ነገር ግን ስንፈተ ወሲብ ብልት ለግንኙነት ዝግጁ አለመሆን ማለት ብቻ አይደለም፡፡ ከዚህም ሰፋ ያለ ትርጓሜ ያለው ነው፡፡ የስንፈተ ወሲብ ችግር በሁለት መንገድ የሚከሰት ነው፡፡ የመጀመሪያው ተፈጥሯዊ በሆነ የአፈጣጠር ችግር ማለትም በክሮሞዞን፣ የሴትነትና የወንድነት መገለጫ በሆኑት የኦቫሪና የቴስትሮን አፈጣጠር ችግር ምክንያት የሚፈጠር ሲሆን፣ ሁለተኛው ከውልደት በኋላ በዕድገት ሂደት በአካላዊ፣ በአዕምሯዊ፣ በስነ ልቦናዊና በአካባቢያዊ ምክንያቶች የሚፈጠር የስንፈተ ወሲብ ችግር ነው፡፡ በዚህ ወቅት የሚፈጠረው ችግር ለግብረ ስጋ ግንኙነት ፈፅሞ ዝግጁ አለመሆንን፣ ጭራሹኑ ስሜት ማጣትን፣ ፍላጎት አለመኖርን፣ የመጨረሻው እርካታ ላይ አለመድረስን፣ የሌላኘውን ስሜት ሳይጠብቁ ፈጥኖ መርካትን፣ ለግንኙነት ዝግጁ ያለመሆንን ሁሉ ያጠቃልላል፡፡

ጥያቄ፡- በተፈጥሮም ሆነ ከውልደት በኋላ የሚከሰተው የስንፈተ ወሲብ ችግር፣ በወንዶችም ሆነ በሴቶች ተመሳሳይ ነው ማለት ይቻላል?

ዶ/ር፡- በወንዶችና በሴቶች ላይ የሚከሰተው የስንፈተ ወሲብ ችግር አንድና ተመሳሳይ ነው ማለት ግን አይደለም፡፡ ለምሳሌ በተፈጥሮ ሴት ሁና የተፈጠረች ቢሆንም፣ ወንድ የመሆንና ሴትን ለማግባት የመፈለግ በሌላም በኩል በአንድ ሰው ላይ የሴትነትና የወንድነት ብልቶች በአንድ ላይ በመፈጠር ምክንያት የስሜት መሳከር በሁለቱም ፆታዎች፣ በተመሳሳይ መልኩ የሚከሰትበት አጋጣሚ እንዳለ መገንዘብ ተገቢ ይሆናል፡፡

ከውልደት በኋላ ከሚፈጠር የወሲብ ችግሮች አንፃር ሲታይ፣ በግብረ ስጋ ግንኙነት ጭራሹኑ ስሜትም ሆነ ፍላጎት ማጣት ብዙውን ጊዜ በሁለቱም ፆታዎች ላይ ይከሰታል፡፡ በአንፃሩ ደግሞ የወሲብ አካል አለመነቃቃት (ዝግጁ ያለመሆን) ችግር በስፋት በወንዶች ላይ የሚታይ ሲሆን፣ ከሚፈፀመው የወሲብ ግንኙነት እርካታ (ደስታን) ማጣትና የመጨረሻው እርካታ ላይ አለመድረስ ሁለቱም ፆታዎች ይጋሩታል፡፡

ሴቶችም ቀደም ሲል ከነበራቸው ጥሩ ያልሆነ የወሲብ ግንኙነት ምክንያት ወሲብ ለመፈፀም ይፈራሉ ወይም ከነጭራሹ ግንኙነቱን ሊጠሉት ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም በፍቅር ከማይመርጡት ሰው ጋር ትዳር የመሰረቱ ሴቶች ወሲብ የደስታ ምንጭ ሳይሆን እንደ አንድ ስራ ይመለከቱታል፡፡ በመሆኑም ከግንኙነቱ እርካታን አይጠብቁም፡፡ ይህ ሁኔታ በወቅቱ ካልተፈታ ወደ ስር የሰደደ ስነ ልቦናዊ ችግርነት መሸጋገሩ አይቀርም፡፡

ጥያቄ፡- የችግሩ መንስኤ ምንድነው ይላሉ?

ዶ/ር፡- የስንፈተ ወሲብ መከሰቻ ምክንያቶች እነዚህና እነዚያ ብቻ ናቸው የሚባልበት አይደለም፡፡ የችግሩ መንስኤ ከወሲብ መፈፀሚያ አካላት ለውጦች እስከ ስነ ልቦናዊ ቀውሶች ድረስ የሚዘልቅ ነው፡፡ ለዚህም ነው የስንፈተ ወሲብ ችግር መምጫ ምክንያቶች አንድና አንድ የሚባሉ ሳይሆን ድርብርብ ናቸው የሚባለው፡፡

አንዱና ዋናው ምክንያት፣ አካላዊ የጤና ችግሮች ማለትም በአደጋ ምክንያት ወገብ አካባቢ መሰበርና እሱን ተከትሎ የሚከሰት የነርቭ ስርዓት መቃወስ፣ የኩላሊት፣ የጉበት፣ የስኳር፣ የደም ግፊት፣ የካንሰርና የልብ በሽታዎች በተጨማሪም በወንዶች የዘር ፍሬ ማመንጫና በሴቶች የእንቁላል ማኳቻ አካባቢ የሚፈጠሩ የተለያዩ አካላዊ በሽታዎች፣ የደም ስር ችግሮችና የኮሌስትሮል መጠን መጨመር ለስንፈተ ወሲብ ችግር መከሰት መንስኤ ይሆናሉ፡፡ ሌላው መንስኤ የስነ ልቦና መዛባት (መቃወስ) ነው፡፡ ስነ ልቦናዊ መዛባቱ በውጥረት፣ በጭንቀት፣ በድብርት፣ በጫና ውስጥ በመውደቅ፣ በፍርሃትና ከአይናፋርነት ጋር የተያያዙ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ከስነ ልቦና ምክንያቶች ቀጥሎ ለስንፈተ ወሲብ ችግር መከሰት፣ ከአዕምሮ ጀምሮ እስከ ታችኛው ቅርንጫፍ የነርቭ ስርዓት ድረስ ያለው አካባቢ በከፊል አልያም ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ፣ የነርቭ ስርዓት ጤና መቃወስ ካለ ለችግሩ መከሰት በቂ ምክንያት ይሆናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የወንድ ብልት ለግብረ ሥጋ ግንኙነት ዝግጁ መሆን የሚችለው፣ የታችኛው የወንድ ብልት ክፍል በደም ሲሞላ ነው፡፡ ነገር ግን የደም ስሮች በተለያየ ምክንያት ችግር ውስጥ ሲወድቁ በቂ የደም መጠን ወደ ወንዱ ብልት አይደርስም፡፡ ካልደረሰ ደግሞ የወንድ ብልት ተነቃቅቶ ለወሲብ ዝግጁ የሚሀንበት ዕድል የለም ማለት ነው፡፡

ቴስቴስትሮን የተባለው ስሜት ቀስቃሽ ሆርመን፣ በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ሥራውን በአግባቡ መስራት ሳይችል ሲቀር፣ በብልት አካባቢ በሚሰራ ቀዶ ህክምና ሳቢያ እዚያ አካባቢ ያሉ ነርቮችና ደም ስሮች ሲጎዱ እንዲሁም ለረጅም ጊዜ ባይስክል መንዳት ለስንፈተ ወሲብ ችግር ያጋልጣል፡፡ በሌላኛው ገፅ ደግሞ ሌሎች ህመሞችን ለመፈወስ ተብለው የሚሰጡ መድሃኒቶች ለአብነት የደም ግፊት፣ ለአዕምሮ ህመም፣ ለጨጓራ፣ ለሽንት መሽናት፣ የኮሌስትሮልን መጠን ዝቅ ለማድረግ የሚወስዱትና ለሌሎች የጤና ችግሮች የምንወስዳቸው መድሃኒቶች፣ ለስንፈተ ወሲብ ችግር መከሰት መንስኤም የመሆን ዕድል አላቸው፡፡ በተለይም ከ25 በመቶ በላይ የሚሆነው የወንዶች የስንፈተ ወሲብ ችግር ምክንያቶች፣ ለሌሎች ህመሞች ተብለው ከሚሰጡ መድሃኒቶች ጋር ይቆራኛል፡፡ ከ10 እስከ 20 በመቶ የሚሆነው ምክንያት ስነ ልቦናዊ ሲሆን፣ ከ40 እስከ 80 በመቶ የሚሆነው የስንፈተ ወሲብ ችግር ከአካላዊ ጤና ጋር የተያያዘ በቂ ምክንያቶች አሉት፡፡

ከላይ በስንፈተ ወሲብ መከሰት በምክንያትነት ከተዘረዘሩት ውጭ በመጠኑ የበዛ አልኮል መውሰድ፣ ሲጋራ ማጨስና ለመዝናኛ ተብለው የሚወሰዱ ሱስ የማስያዝ አቅም ያላቸው መድሃኒቶች ሁለቱንም ፆታዎች ለስንፈተ ወሲብ ችግር ያጋልጣቸዋል፡፡ ሌላውና ለስንፈተ ወሲብ መፈጠር እንደ አንድ ምክንያት መገለፅ ያለበት፣ ሰውነትን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ሽባ የሚያደርገው ፓርኪንሰን የተባለው በሽታ ነው፡፡

ጥያቄ፡- የስንፈተ ወሲብ ችግር በሀገራችንና በዓለም አቀፍ ደረጃ በምን ሁኔታ ላይ የሚገኝ ነው?

ዶ/ር፡- ችግሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ አድማሱንና መጠኑን በማስፋት ላይ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በአሜሪካ ማቹሲስተስ ሆስፒታል የተደረገው ጥናት እንዳመላከተው፣ ከ40 እስከ 70 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሰዎች 52 በመቶ፣ በድህነት ውስጥ ያሉ 14 በመቶ፣ ትዳር የፈቱ 14 በመቶና የግንዛቤ ችግር ያለባቸው ሰዎች 13 በመቶ ለችግሩ የመጋለጥ ዕድል ይኖራቸዋል፡፡ በቦስትሰን የተካሄደ ሌላ ጥናት እንዳመለከተው ደግሞ 30 ሚሊየን የሚሆኑ የስንፈተ ወሲብ ችግር ያለባቸው ወንዶች በአሜሪካ ብቻ ይኖራሉ፡፡ በጥናቱ ውስጥ ከተካተቱና ዕድሜያቸው 70 ዓመት ከሞላቸው ወንዶች ደግሞ 70 በመቶ የሚሆኑት የስንፈተ ወሲብ ችግር እንዳለባቸው ተረጋግጧል፡፡

የስንፈተ ወሲብ ችግር በሀገራችን በምን ደረጃ ላይ እንዳለ የሚያመለክት ጥናት ማግኘት ባለመቻሉ፣ የችግሩን ስፋት በአግባቡ መገንዘብ አልተቻለም፡፡ ነገር ግን ጤና ተቋማትን መሰረት አድርገው የሚወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ የስንፈተ ወሲብ ችግር በአገራችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ በመሄድ ላይ ነው፡፡ ለምሳሌ በየዓመቱ ግልፅ ምክንያት ሳይቀመጥላቸው የሚፈርሱ ትዳሮች እየጨመሩ እንደሆነ የሚያሳዩ መረጃዎች አሉ፡፡ በኤዢያ፣ በላቲን አሜሪካ፣ በደቡብ አፍሪካና በሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች ትዳርን የሚያናጉ ምክንያቶችን ለማወቅ በተጠኑ ጥናቶች ከ65 በመቶ በላይ የሚሆነው ምክንያት አንደኛው ወገን ሌላኛውን በወሲብ ግንኙነት ወቅት መርዳት ካለመቻሉ (ካለማስደሰቱ) ጋር የተያያዘ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በሀገራችን በግልፅ የወጣ ምክንያት ሳይኖራቸው የሚፈርሱም ሆነ በግጭት የሚናጡ ትዳሮች ሁሉም ባይሆኑ አብዛኞቹ ምክንያታቸው የስንፈተ ወሲብ ችግር እንደሆነ ይገመታል፡፡

የስንፈተ ወሲብ ችግር የስነ ልቦና፣ የአዕምሮና የአካላዊ ጤና ችግር ብቻ ሳይሆን፣ ከግለሰቡ እስከ ቤተሰባዊ ሕይወት ድረስ የሚዘልቅ ማህበራዊ ችግርም ጭምር ነው፡፡ አንደኛው ወገን በስንፈተ ወሲብ ችግር ውስጥ አለ ማለት ሌላኛው ወገንም ተጠቂ ከመሆን የሚያመልጥ አይሆንም፡፡ እንዲህ ያለው ሁኔታ ደግሞ የትዳር መፍረስንና የልጆችን መበተን ያመጣል፡፡ ልጆቹን የሚረዳቸው ቤተሰብ ከሌላ ለረሃብና ለእርዛት ይጋለጣሉ፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ በስንፈተ ወሲብ ችግር ሳቢያ ከፈረሱ ትዳሮች የተገኙ ልጆች የማህበረሰቡ ችግር ወደ መሆን ተሸጋገሩ ማለት ነው፡፡

ጥያቄ፡- ችግሩ ያለበት ሰው ከሚያሳያቸው ምልክቶች ዋና ዋና የሚባሉትን ቢገልፁልኝ?

ዶ/ር፡- ወንዶችም ሆኑ ሴቶች የስንፈተ ወሲብ ችግር ሲከሰትባቸው፣ በጋራ ወይም በተናጠል ከሚያሳዩዋቸው ምልክቶች ዋና ዋና ተብለው የሚታወቁት ቀጥሎ የምገልፃቸው ናቸው፡፡

– የወሲብ ፍላጎት ማጣት (ለሁለቱም)

– የወሲብ መፈፀሚያ አካላት ለወሲብ ዝግጁ አለመሆን (በወንዶች)

– ለግንኙነት ዝግጁ የሚያደርግ ፍሳሽ በበቂ መጠን አለመመንጨት፣ የሚደረገውን የወሲብ ግንኙነት ደረቅና ህመም የበዛበት ያደርገዋል (ለሴቶች)

– የመጨረሻው የእርካታ ደረጃ ላይ አለመድረስ የሚሉት ዋና ዋናዎቹ የስንፈተ ወሲብ ምልክቶች ናቸው ተብሎ ይወሰዳል፡፡

ጥያቄ፡- አንዳንድ ሰዎች የስንፈተ ወሲብ ችግርን ፈጥኖ እርካታ ላይ ከመድረስ በተጨማሪም ከወንዶች ብልት ማነስና ከሴቶች ብልት መስፋት ጋር ሲያያይዙት ይታያል፣ ይህ አስተሳሰብ ሳይንሳዊ መሰረት አለው ማለት ይቻላል?

ዶ/ር፡- የተጠቀሱ ጉዳዮች ከስንፈተ ወሲብ ጋር የሚያያዙ አይደሉም፡፡ በእርግጥ ፈጥኖ የዘር ፍሬን የማፍሰስ ችግር ያለባቸው በርካታ ቁጥር ያላቸው ወንዶች እንዳሉ ግልፅ ነው፡፡ የዚህ ምክንያቱ ለወሲብ ጉጉ መሆን፣ ዘር ፍሬዬ ፈጥኖ ሊፈስብኝ ነው ብሎ መጨነቅና ተጣማሪዬና በወሲብ ማርካት አልችልም በሚል ስሜት ዝግጁ አለመሆን ጋር የተያያዙ ችግሮች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እንዲህ ያሉ ሰዎች የስነ ልቦና ሙያተኛ ምክር ከተደረገላቸው በቀላሉ ከችግራቸው የሚላቀቁበት ዕድል ሰፊ ነው፡፡ ፈጥኖ የዘር ፍቼን ማፍሰስ ከላይ ከዘረዘርናቸው ምክንያቶች ሌላጋር የሚተሳሰሩበት ሁኔታም እንዳለ መገንዘብ ይገባል፡፡ በሌላም በኩል የወንድ ብልት ማነስም ሆነ የሴት ብልት የመስፋት ጉዳይ፣ ለስንፈተ ወሲብ ችግሮች ጋር የሚያስተሳስረው ምንም አይነት ምክንያት እንደሌለው በመገንዘብ አጠረብኝ ብሎ መጨነቅን ማስወገድ ጠቃሚ ይሆናል፡፡ ሰፋብኝ ብሎ ከመሸማቅም ራስን ነፃ አድርጎ በነፃነት ስሜትን ሰጥቶ፣ ስሜትን ለመቀበል ዝግጁ መሆን አስፈላጊ ይሆናል፡፡

ጥያቄ፡- ችግሩን ለይቶ ለማወቅ ተግባራዊ የሚደረጉ ምርመራዎች የትኞቹ ናቸው?

ዶ/ር፡- ትልቁና የመጀመሪያው ምርመራ ሐኪሙ ከበሽተኛው ጋር ስለ ህመሙ አጠቃላይ ሁኔታ በቂ መረጃ ለማግኘት የሚያደርገው ጥልቅ ውይይት ነው፡፡ በውይይቱ የተገኘውን መሰረት በማድረግ የደም፣ የሽንት፣ የሆርሞንና ተያያዥነት ያላቸው ምርመራዎች ይካሄዳሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በኤምአርአይ እና በሌሎችም ቴክኖሎጂ አመጣሽ መሳሪያዎች፣ የስንፈተ ወሲብ ችግሩን በትክክል መኖሩን እንዲሁም የችግሩን ስፋትና አይነት በትክክል ለይቶ ለማወቅ የሚያስችል ምርመራ እናደርጋለን፡፡

ጥያቄ፡- ለመሆኑ የስንፈተ ወሲብ ችግርን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችሉ ሳይንሳዊ መፍትሄዎች ካሉ ቢገልፁልኝ?

ዶ/ር፡- የመጀመሪያው አማራጭ መፍትሄ በስነ ልቦና ባለሙያ በተጋገዝ ጭንቀትን፣ ፍርሃትን፣ ውጥረትን፣ ድብርትን፣ ስጋትንና ቀድሞ ተሸናፊ የመሆን ስነ ልቦናዊ ችግሮችን ማስወገድ ይቻላል፡፡ ለዚህ ችግር መፍትሄ የሚሰጡ ሳይኮሎጂካል ቴራፒዎች አሉ፡፡ ስለሆነም የስነ ልቦና ባለሙያዎችን ምክር ተቀብሎ በመተግበር፣ ህክምናውን በአግባቡ መፈፀም ከተቻለ በአጭር ጊዜ ውስጥ አስተማማኝ መፍትሄ ማግኘት ይቻላል፡፡ በዚህ ሂደት ደስተኛ የመሆንና በራስ የመተማመን መንፈስም በዚያው መጠን ይዳብራል፡፡ ነፃነት ያለው፣ ከስጋትና ከጭንቀት የፀዳ ግንኙነት በመፈፀም የመጨረሻው እርካታ ላይ የሚደርስበትን ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል፡፡ የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ ጠብቆ ለመዝለቅም የሁለቱን ጥንዶች በአግባቡ ለመደጋገፍ የሚያስችል የቅንነት ባህልን እንዲገነቡ ያስፈልጋል፡፡ ከስነ ልቦናዊ መፍትሄዎች ባሻገር ለስንፈተ ወሲብ ችግር መከሰት ምክንያት ናቸው ብለን ያነሳናቸውን በሽታዎች፣ ለምሳሌ ስኳርንና ደም ግፊትን በአግባቡ በቁጥጥር ስር ማዋል እንዲሁም ሌሎችን የውስጥ ጤና ችግሮችን ጊዜ ሳይወስዱ መታከም ተገቢ ይሆናል፡፡ ለሌሎች በሽታዎች ተብለው የሚሰጡ መድሃኒቶችን በተቻለ አቅም ማስወገድ ይገባል፡፡ በሌላም በኩል የስንፈተ ወሲብ ችግርን በጊዜያዊነት ቢሆን መፍትሄ ለመስጠት የሚችሉ መድሃኒቶች አሉ፡፡ ለምሳሌ ሲልደናፊል (በንግድ ስያሜው ቪያግራም)፣ ቮርድናፍና ታላፌን የሚባሉት በዓለም ላይ የሚታወቁ ናቸው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ሲልደናፊል (በንግድ ስያሜው ቪያግራም) የሚባለው መድሃኒት በሀገራችንም ይገኛል፡፡ ይህ መድሃኒት በዋጋው ተመጣጣን የሚባል ነው፡፡ እዚህ ላይ ማንኛውም ሰው መገንዘብ ያለበት፣ መድሃኒቱ መወሰድ ያለበት ሌሎች ስነ ልቦናዊ ችግሮችን ለማስወገድና መፍትሄ ማምጣት ሳይቻል ሲቀር ብቻ ይሆናል፡፡

ሌላው አማራጭ ህክምና፣ በሆርሞን እጥረት የተነሳ የስንፈተ ወሲብ ችግር ለአጋጠማቸው ሰዎች፣ የሆርሞን መተኪያ ህክምና ይሰጣቸዋል፡፡ ይህ የህክምና ዘዴ በሀገራችንም የሚሰጥ ነው፡፡ ከላይ በገለጽናቸው አማራጭ ህክናዎች መፍትሄ ላላገኙ ሰዎች፣ ምንም እንኳን የህክምና ዘዴዎች በሀገራችን ባይገቡና ጥቅም ላይ ባይውሉም በሌላው ዓለም የሚሰራባቸው ሌሎች ተጨማሪ መፍትሄዎች አሉ፡፡

– ቫኪዩም ዲቫይስ የሚባል ዘዴ አለ፤ ይህ ዘዴ የወንድ ብልት እንዲቆም በማድረግና ቫኪዩም ዲቨይሱን ብልት ላይ በመግጠም ወዲያውኑ ውጤታማ ግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈፀም ያስችላል፡፡

– ብልት በበቂ መጠን ወሲብ መፈፀም እንዲችል የተነቃቃና ለወሲብ የተዘጋጀ፣ የወንድ ብልት ላይ የሚወጉ መድሃኒቶች በዓለም ገበያ ላይ አሉ፡፡

– ውጤታቸው አስተማማኝነቱ የሚያጠራጥር በመሆኑ፣ የጎንዮሽ ጉዳታቸው ጠንካራ ስለሆና አንዳንድ ጊዜ ተመልሶ የማይተኛ የብልት መቆምን የሚያመጡ በመሆናቸው፣ አማራጭ ካልጠፋ በስተቀር ጥቅም ላይ አይውሉም እንጂ በሽንት ቧንቧ ወደ ውስጥ የሚጨመሩ የስንፈተ ወሲብ ችግር መድሃኒቶች በሌሎች የዓለም ሀገሮች በስፋት ይሸጣሉ፡፡

– በቀዶ ህክምና ብልትን በመሰንጠቅ፣ ሰው ሰራሽ በሆነ መንገድ ማቆሚያ በማስገባት፣ ውጤታማ ወሲብ መፈፀም የሚያስችል ዘዴ ነው፡፡

– የስንፈተ ወሲብ ችግሩ ዋነኛ መንስኤ በደም ስር ላይ የተከሰተ የጎላ ጉዳት መሆኑ በምርመራ ከተረጋገጠ፣ ደም ስሮቹን በማይክሮ ሰርጀሪ የማስተካከልና ጤናማ የሚያደርግ የህክምና ዘዴም በሌላው ዓለም ወደ ተግባር ከተሸጋገረ ከርሟል፡፡

ጥያቄ፡- አንዳንድ ሰዎች ያለ ሐኪም ትዕዛዝ ቪያግራምንም ሆነ ሌሎች መድሃኒቶችን በራሳቸው ሲወስዱ ይስተዋላል፣ እንዲህ ያለው ተግባር ችግር አያስከትልም?

ዶ/ር፡- ቪያግራም ማንኛውም ሰው የሚወሰደው መድሃኒት አይደለም፡፡ መድሃኒቱ የስኳር፣ የደም ግፊት፣ የልብና የኩላሊት በሽታዎችን ያባብሳል፡፡ እንደዚሁም የደም ስሮችን በማጥበብ ስትሮክንና ደም ማነስን ያመጣለ፡፡ እነዚህ የጤና ችግሮች ያሉባቸው ሰዎች በምንም ምክንያት ቪያግራን መውሰድ የለባቸውም፡፡ ስለሆነም በምንም መንገድ ቢሆን ቪያግራም ያለ ሐኪም ትዕዛዝ መወሰድ የለበትም፡፡ መድሃኒቱ በሐኪም ትዕዛዝ ቢሆንም ለረጅም ጊዜ ከተወሰደ ሱስ የመሆን ዕድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ ሱስ ከሆነ መድሃኒቱ ካልተወሰደ በስተቀር ወሲባዊ ግንኙነት መፈፀም የማይቻልበት ደረጃ ላይ ያደርሳል፡፡ ሌሎችም መድሃኒቶች ተመሳሳይ የሆነ የጎንዮሽ ጉዳት ስላላቸው በተቻለ አቅም አግባብ ያለው ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

ጥያቄ፡- ለማጠቃለያ ማንሳት የሚፈልጉት ሐሳብ ካለ ያንሱትና እንሰነባበት?

ዶ/ር፡- የስንፈተ ወሲብ ችግር ሊታከምና ሊድን የሚችል የጤና ችግር መሆኑን ሁሉም ሰው ቢገነዘብ ጠቃሚ ይሆናል ብዬ አምናለሁ፡፡ ሁለቱ ተጣማሪች የተሰማቸውን ጥሩ ያልሆነ ስሜት ከደመባበቅና ወደ ተባባሰ የስነ ልቦና ችግር ከማምራት ይልቅ በግልፅ መነጋገር ይኖርባቸዋል፡፡ መፍትሄ ባለው ችግር ግንኙነታቸውን ጤናማ ወዳልሆነ አቅጣጫ መምራት አይኖርባቸውም፡፡ ስለሆነም በተፈጠረው ችግር ዙሪያ መደማመጥና መከባበር በሰፈነበት አግባብ፣ የመነጋገር ልምድን ማዳበር ይጠበቅባቸዋል፡፡ የስንፈተ ወሲብ ችግር ከተከሰተ በኋላ ማከም ብቻ ሳይሆን ችግሩን አስቀድሞ መከላከል የሚያስችሉ ዘዴዎችም እንዳሉ መታወቅ ይኖርበታል፡፡ ለአብነት ጭንቀትን፣ ድብርት፣ መረበሽንና ፍርሃትን መቀነስ ከተቻለም ጭራሹኑ ማስወገድ ይገባል፡፡ በተጨማሪም አልኮልን አዘውሮ ከመውሰድ መታቀብ፣ ጫት መቃምና ሲጋራ ማጨስን በተቻለ መጠን ማስወገድ ያስፈልጋል፡፡ በተፈጥሮ የተከሰተ የስንፈተ ወሲብ ችግር መኖን አለመኖሩን ለማረጋገጥ፣ ልጆች 18 ዓመት ሳይሞላቸው ቢመረመሩና ችግሩ ካለ ቢታከሙ ጠቃሚ ይሆናል፡፡

↧

የሞላ አስገዶም ነገር! –በተስፋዬ ነጋ (ዋሽንግተ ዲሲ)

$
0
0

 

Asgdom

የሞላ አስገዶም ነገር

ኢቲቪ ስለትህዴን መክዳት የለፈለፈው፣ አቶ ሞላ ስለ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ ስለተቃዋሚዎቹ፣ የሻብያን ጦር “እየደመሰሱ” ስለመምጣት በግነት የተናገረው፣ ሌላው የትሄዴን ጊዜያዊ ሃላፊ ኮማንድር መኮንን ተስፋዬ ስለከዳው የትህዴን ጦር እና ስለውጊያው የተናገረው እና የተለያዩ ሌሎች አስተያየቶች ሰሞኑን በማህበራዊ ድህረገጾች ተለቀዋል፣ ኢትዮጵያውያን በነቂስ ተወያይተውባቸዋል። እኔም ውይይቱን መልሼ መድገም አልፈልግም፥ የእኔ አላማ የአቶ ሞላ አስገዶም በተለያዩ አካላትና ሁኔታዎች መዳፍ ስር ቢወድቅ ኖሮ  በጥትቅ በሚታገሉ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች፣ በኢትዮጵያ መንግስትና፣ በኤርትራ መንግስት ላይ የሚፈጥረው አዎንታዊና አሉታዊ ተፅዕኖዎች በአጭሩ መዳሰስ ነው።

አቶ ሞላ በኤርትራ ትግል ሜዳ ውስጥ ቢቆይ ኖሮ

አቶ ሞላ በኤርትራ ውስጥ በትግል ላይ መቆየት፣ ለነጻነት የሚደረገውን ትግል እጅግ ረጅም እና እልህ-አስጨራሽ ያደርገው ነበር። ብዙ የሰው ህይወትና እልቂት ሊከተልም ይችላል። ትግሉም ወደኋላ ይጎተት ነበር። አቶ ሞላና አብረውት ወደኢትዮጵያ የተጓዙት በትግሉና በህብረቱ ያልተደሰቱ “አርበኞች” እነሱ እንደሚሉት ከሆነ ሰነድ በመሸጥና፣ የስለላ መረብ በመዘርጋት ለኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ የውስጥ አርበኝነት ስራ መስራት በቻሉ ነበር። እነዚህ የኢትዮጵያ መንግስት ባንዳዎች በሁለት ልብ ሆነው ጦርነቱን በቁርጠኝነት ሊያካሄዱ አይችሉም። ስለዚህ በህወሃት ላይ ነፍጥ ያነሱት የህብረቱ አባል ኢትዮጵያውያን በህወሃት ካሊበር ጥይት መታጨዳቸው አይቀርም ነበር። በሌላ አነጋገር አቶ ሞላ አሁን ከነበረው የስልጣና የዕዝ ሃላፊነት አንጻር እያንዳንዷን የአማጺያንን እንቅስቃሴ ለህወሃት አለቆቹ አሳልፎ መስጠቱ አይቀርም። ይህ ደግሞ በተቃዋሚው ላይ የሚያደርሰውን እልቂት እድግ ከባድ ያደርገዋል። ከዚያም የኤርትራና የተቃዋሚ ሃይሎች “ከተደመሰሱ” በኋላ አቶ ሞላና ግብረ-አበሮቹ የ”ጀግኖች ጀግና” ተብለው በተወደሱ ነበር። በመሆኑም አቶ ሞላና ግብረ-አበሮቹ ከትጥቅ ትግል ሃላፊነት ገለል ማለት  በነፍጥ ለሚታገሉ ተቃዋሚ ሃይሎች ከፍተኛ ድልና እፎይታ ነው። ተቃዋሚዎች አንድ ከፍተኛ የ”ወገን” ጠላት ነው የተገላገሉት! አቶ ሞላ በመሸሹ አሸናፊዎቹ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎችና የኤርትራ መንግስት ናቸው።

አቶ ሞላ ኤርትራ ውስጥ ቢገደል ኖሮ!

አቶ ሞላ በሽሽት ላይ እያለ ሱዳን ሳይደርስ ቢገደል ኖሮ ምን ይፈጠር ነበር? ያው እንደተለመደው የህወሃትም ይሁን አብዛኞቹ የተቃዋሚ ሃይል አባላት አቶ ሞላን የኤርትራ መንግስት እንደገደለው ማውራታቸው አይቀሬ ነበር። ይህም ኤርትራ ላይ ከፍተኛ ጥላሸት ከመቀባቱ በተጨማሪ ኤርትራ የገባ ተቃዋሚ ሁሉ እንደሞተ ለሚቆጥሩ ተቃዋሚዎችና ለህወሃት አገዛዝ ልሂቃን ከፍተኛ የዕልልታ ዜና ፍጆታ ይሆን ነበር። “ኤርትራ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች እንዲጠነክሩ አትፈልግም፣ ህወሃትና ሻዕቢያ አንድ ናቸው” ለሚሉ ተቃዋሚዎችና ጥርጣሬ ውስጥ ላሉ ወገኖች የሰውየው ኤርትራ ውስጥ መገደል አስተማማኝ የመረጃ ፍጆታ ይሆን ነበር። በተለይም ለእነ አቶ ኤሊያስ ክፍሌ ዜናው አስደሳች ይሆን እንደነበር ጥርጥር የለኝም። በሌላ መልኩ የኢትዮጵያ መንግስት የትህዴንን የመሰለ “ጠላት” ስለተገደለላቸው ደስታቸው ወደር አይኖረውም፥ ህወሃት ስለግድያው ኤርትራን መውቀሱ ግን አይቀርም። እናም አቶ ሞላ አስገዶም ወደ እናት ፓርቲው ህወሃት በሰላም መቀላቀሉ ለተቃዋሚው ትግል ስኬት ቀላል የማይባል ፋይዳ ይኖረዋል። አቶ ሞላ በመቶ የሚቆጠር ሃይል ይዞ ወደሱዳን ያለምንም ችግር መሄድ መቻሉ የሚያሳየው በኤርትራ ያሉ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ያለምንም ገደብ የመንቀሳቀስ መብት እንደተቸራቸው ነው። የአቶ ሞላ ኤርትራ ውስጥ መገደል ለተቃዋሚዎችም፣ ለኤርትራ መንግስትም ከፍተኛ ኪሳራ ይሆን ነበር። ከዚህ አይነት ድርጊት አትራፊው የኢትዮጵያ መንግስት ብቻ ይሆን ነበር።

አቶ ሞላን ህወሃት ኤርትራ ውስጥ ቢገለው ኖሮስ?

አቶ ሞላን የህወሃት መንግስት ቢገድለውስ ኖሮስ? ይህም ሁኔታ በትግሉ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ይፈጥር ነበር። በፊት አቶ አንዳርጋቸውን ከየመን ጠልፎ ያመጣ የህወሃት ቡድን፣ በተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ላይ ግድያ ቢፈፅም ለህወሃት ከፍተኛ ድል፣ ለተቃዋሚዎች እና ለኤርትራ መንግስት ግን አንገት የሚያስደፋ ሽንፈት ይሆን ነበር። በሉዓላዊት አገር ኤርትራ የጠላት አገር ሃይል ገብቶ ተቃዋሚ ፓርቲ ሃላፊን ከገደለ፣ ኤርትራ በደህንነት ጥበቃ ንዝህላልነት ተጠያቂ መሆኗ አይቀርም። ያ ሳይሆን ቀርቶ ህወሃት አውቆም ይሁን ሳያውቅ ለተቃዋሚ ትግል ስኬት ከፍተኛ እገዛ ሊያደርግ የሚችል ስራ ሰርቷል። የአቶ ሞላ ኤርትራ ውስጥ በህወሃት ደህንነት አለመገደል ለአማጺው ሃይልና ለኤርትራ መንግስት ከፍተኛ እፎይታ ነው።

አቶ ሞላ ወደ ኢትዮጵያ ባይመለስስ?  

አቶ ሞላ ሱዳን ወይም ሌላ አገር ውስጥ ጥገኝነት ቢጠይቅስ ወይም ወደሌላ አገር ተላልፎ ቢሰጥስ? ይህ ድርጊት ለህወሃት ከፍተኛ ጥቅም ይኖረው ነበር። ህወሃት ጥሩ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻም ይሰራበት ነበር። በተለይም ኤርትራ አሁን ካላት አለም አቀፋዊ ተሰሚነት አንጻር፣ ሁኔታው ለተቃዋሚዎች አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረው ነበር። አቶ ሞላም ቢሆን ከህወሃት ጋር ሳይወግን፣ ተቃዋሚ ሃይሎችንና የኤርትራ መንግስትን ማውገዝና በተወሰነ መልኩም ቢሆን ተፅዕኖ ሊፈጥር ይችል ነበር። ሰውየው ኤርትራ ውስጥ በትግል ካሳለፈው ጊዜ አንጻር እሱ ሊናገር የሚችለው አብዛኛው ነገር በተወሰነ ደረጃም ቢሆን በአገር ውስጥም ይሁን ከአገር ውጭ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ተአማኒነት ይኖረው ነበር። ያም ሆነ ይህ፣ አቶ ሞላ ይህንን ዕድል ሳይጠቀምበት ቀርቷል።

አቶ ሞላ በተቃዋሚዎች ኤርትራ ውስጥ ቢታሰርስ/ ቢገደልስ?

አቶ ሞላ በራሱ በትህዴን ሰዎች ቢታሰር ወይም ቢገደል ኖሮ ለተቃዋሚዎቹ ለራሳቸው ጥሩ ሁኔታ አይፈጥርም ነበር። እስሩን ወይም ግድያውን የፈጸሙት ጓዶቻቸው ሳይሆኑ የሻዕቢያ መንግስት እንደፈጸመው በመገመት ዳር ላይ የቆሙ ሰዎች ብዙ ሊያወሩ ይችሉ ነበር። እንግዲህ በትጥቅ ትግል የሚያምኑ የተቃዋሚ መሪዎች የኢሳያስን መንገድ በመከተላቸው በጥርጣሬ መታየታቸው፥ በዋነኝነትም የሻቢያን ጉዳይ በማስፈጸም መታማታቸው አይቀርም። ሞላ አስገዶምና ግብረ-አበሮቻቸው በራሳቸው በትሂዴን ሰዎች በጣም ሊወደዱ የሚችሉበት፣ በውጭ የሚኖረውም ሆነ በአገር ውስጥ ያለው ተቃዋሚ እንደጀግናም ሊቆጥራቸው የሚችልበትን ሁኔታ ሳይሆን ቀርቷል። የእሱ መታሰር በትጥቅ ትግሉ ላይ እጅግ ከፍተኛ ጉዳት ያደርስ ነበር። አቶ ሞላ አስገዶም ብቸኛ ጀግና ተደርጎም ሊቆጠር ይችል ነበር።

አቶ ሞላ ወደ ኢትዮጵያ መግባትስ?

የአቶ ሞላ ወደህወሃት ጉያ መግባት ለኢትዮጵያ መንግስትና፣ ለራሱ ለሞላ አስገዶም ከፍተኛ ኪሳራ ነው። አቶ ሞላ የዘር ካርድ በመምዘዝ እንደቀድሞ ጓዶቹ ተመልሶ ወደህወሃት አፎት ገብቷል። አሁን  በአገርም በውጭም ያለ ተቃዋሚ ሁሉ አቶ ሞላ “ጓደኞቹን ጥሎ የፈረጠጠ” ከሃዲ አድርገው ያየዋል። አስራ አራት አመት ሙሉ ራሱ የመለመላቸውንና ያሰለጠናቸውን ወታደሮች በኤርትራ በረሃ በትኖ ነፍሴ አውጪኝ ብሎ ወደ ኢትዮጵያ ሸሽቷል።

አቶ ሞላ ይህን አስነዋሪ ድርጊት በማድረጉ ከህዝቡ ያገኘው ንቀት እንጂ ጀግንነትና ክብር አይደለም። ክህደት የራስ ወዳድነት መገለጫ ነው። እሱ ወደ ኢትዮጵያ ሸሽቶ ገባ፣ በእሺ የሚቆጠሩ ጓዶቹስ? የሚል ጥያቄ በብዙሃን ኢትዮጵያውያን ዘንድ ሲብላላ ቆይቷል። እንግዲህ አቋም የሌለው ሰው በህዝብ ኪሎ በጣም ትንሽ ይመዝናል፥ ሞላም ከዚህ አላመለጠም።

የህወሃት ሃላፊዎችም የሰውየውን ወደ ኢትዮጵያ መኮብለል እንደጥሩ የፖለቲካ ትርፍ ማየታቸው የሚገርም ነው። የፖለቲካ ትርፍ የሚገኘው አማጺ የነበረን ሰው አበባ ይዞ ምንጣም አንጥፎ በመቀበል አይደለም። የፖለቲካ ትርፍ የሚኖረው ማህበራዊ ችግሮችን በመቅረፍ፣ የፖለቲካ ምሕዳር በማስፋት፣ ለዜጎች ዴሞክራሲና ነጻነት በማጎናጸፍ፣ የስልጣንና የሃብት ከፍፍል በማመጣጠንና እኩልነትን በማስፈን እንጂ፣ አንድ ያውም መሳሪያው ሱዳን ውስጥ አስረክቦ የመጣን ሽፍታ የንጉሳን አቀባበል በማድረግ አይደለም። አሁን አቶ ሞላ ምንም የፖለቲካ ተፅዕኖ የመፍጠር አቅም የለውም። ምናልባት የውጊያ ልምድ ሊኖረው ይችል ይሆናል፥ ለ14 አመት ግን አልተዋጋም። በመሆኑም፣ አቶ ሞላም በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ንቀት አስመዘገበ፣ የኢትዮጵያ መንግስትም እንኳን የፖለቲካ ትርፍ መሳሪያ እንኳን ሳያገኝ ቀረ። የኤርትራ መንግስት አማጺያንን በነጻነት እንዲንቀሳቀሱ በመፍቀድ፣ ከኢትዮጵያውያን ከፍተኛ አክብሮት ተቸረ። አማጽያንም ትግሉን በተጠናከረ፣ በተዋሃደ መንገድ ጀመሩት!

↧

እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ለህዳር 21 ተቀጠሩ

$
0
0

‹‹የሽብር ተከሳሽ በመሆናችን ህክምና ተከልክለናል›› ተከሳሾቹ

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

12036883_770479663077694_3137358405184060069_nየኢትዮ-ኤርትራ ድንበርን አቋርጠው ኤርትራ የሚገኘውን ግንቦት ሰባት የተባለ በተወካዮች ም/ቤት ሽብርተኛ የተባለ ድርጅትን ሊቀላቀሉ ሲሄዱ ተይዘዋል በሚል የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ በድጋሜ ለብይን ቀጠሮ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
ዛሬ መስከረም 5/2008 ዓ.ም የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የቀረቡት ብርሃኑ ተ/ያሬድ፣ እየሩሳሌም ተስፋው፣ ፍቅረማርያም አስማማው እና ደሴ ካህሳይ በድጋሜ ለህዳር 21/2008 ዓ.ም ብይን ለመስማት ተቀጥረዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ዛሬ የአቃቤ ህግን ምስክርና የሰነድ ማስረጃ መርምሮ ብይን ይሰጣል ተብሎ ይጠበቅ ነበር፡፡
ተከሳሾቹ በማረሚያ ቤት እየደረሰብን ነው ያሉትን አቤቱታ ለፍርድ ቤት ያሰሙ ሲሆን፣ በተለይ ‹‹የሽብር ተከሳሽ ስለሆንን ብቻ ህክምና ተከልክለናል፤ በማንነታችን ጥቃት እየተፈጸመብን ነው›› ሲሉ ችሎት ፊት ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም ፍርድ ቤቱ እነዚህን ችግሮች በተመለከተ ለማረሚያ ቤቱ ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው ጠይቀዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ የማረሚያ ቤት ተወካይ ያለውን በማስጠራት ‹‹ማስታወሻ ያዝና አጣራ›› በማለት አልፎታል፡፡
በሌላ መዝገብ የሽብር ተከሳሽ የሆነው በአርባ ምንጭ የሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪ በፍቃዱ አበበ በበኩሉ ቀሪ የመከላከያ ምስክሮቹን ለማሰማት ለህዳር 16/2008 ዓ.ም ተቀጥሯል፡፡

↧

በአዲስ አበባ ዛሬ ቦሌ ሚካኤል አካባቢ ፈንጂ ተገኘ በሚል የወያኔ ደህነቶችና ፖሊሶች ወከባ ሲፈጥሩ ዋሉ

$
0
0

አምባሳደር ቪኪ ሐልድስተን ከዚህ ቀደም የስርኣቱ ደህነቶች ራሳቸው ፈንጂ ጠምደው ማፈንዳታቸውን መናገራቸውን ዊክሊክስ አጋልጦ ነበር

Photo File

Photo File

ህብር ሬዲዮ-ላስ ቬጋስ) በአዲስ አበባ ከተማ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 01 በልዩ ስሙ ቦሌ ሚካኤል ታክሲ ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፊት ለፊት በሩ አካባቢ ዛሬ አርብ መስከረም 7 ቀን 2008 ከቀኑ 5 ሰዓት ተኩል ጀምሮ አነስተኛ ፈንጂ ተገኘ ተብሎ ህዝቡ በፖሊሶች ከአካባቢው እንዲርቅ በማድረግ ብዛት ያላቸው ደኅንነቶችና ፖሊሶች አካባቢው ተቆጣጥረውት መዋላቸውን የህብር ሬዲዮ ምንጮች ከስፍራው ገለጹ።

ህዝቡም ግማሹ በድንጋጤ ሲሯሯጥ አንዳንዱ ‹‹ይሄማ የተለመደ ድራማ ነው!›› በማለት ችላ ብሎ ውሸት በመሆኑ ተጠግቶ ለማየት ሲሞክር ፖሊሶቹም ግማሾቹ እየሳቁ ‹‹ እረ ሂዱ ›› በማለት በፌዝ ህዝቡን ሲያባሩ ማየታቸውን እነዚሁ ምንጮግ ገልጸው በዚህ ሳቢያ ንጹሃን ተወንጅለው ቢታሰሩ ያስገርማል ሲሉ ከወዲሁ ምንጮቻችን ስጋታቸውን ገልጸዋል።

የደኅንነት አባሎችና የአካባቢው የቀበሌ ሰራተኞች ከፈንጂ መከላከያ ልዩ ልብስ የተሰራላቸው ይመስል ፈንጂው አጠገብ በመቆም ለፈንጂውም ለኢህአዲግም ታማኝነታቸውን ለማሳየት የሚጥሩ አስመስለውት ነበር፡፡ በአካባቢው በድብቅ ለኢህአዲግ ሲሰሩ የነበሩ ሰዎችም በዛሬው ቀን ሰፊው ህዝብ እያንዳንዱን ባንዳ ለመለየት ችሏል ያሉት እነዚሁ ምንጮች አንዳንዶቹም አውቀውትም ሆነ ሳያውቁት ከደኅንነቶችን ጋር ሰላም በመባባል ማንነታቸውን አጋልጠዋል ሲሉ የታዘቡትን ጭምር ተቅሰዋል።

ፈንጂ የተባለውን ማን እንዳየው ለማጣራት የህብር ምንጮች ተጨማሪ የማጣራት ሙከራ ባገኙት መረጃ ፈንጂ ተብሎ የነበረው አረንጓዴ ከለር ያለውና አይተውት የማያውቁት ነገር ከሳይክል አጠገብ በማየታቸው በዕለቱ ተረኛ የነበሩት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጥበቃ ደንግጠው መናገራቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ የፀረ ሽብር ሃይል በፍጥነት መጥቶ ካሜራውን ደግኖ የተመከሩ ፖሊሶችና ደኅንነቶችን በመቅረጽ ህዝቡ ላይ የስነ ልቦና ጫና ለማድረግ ሞክረዋል፡፡ በዕለቱም የቦሌ ክፍለ ከተማ አየር መንገድ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ዋና ኃላፊ የሆኑት እና ፈላጭ ቆራጭ እየሆኑ የመጡት ኮማንደር ታፈረ ተጠምቀ ከወትሮው ለየት ባለ ሁኔታ አዲስ በአይነቱም በይዘቱም ልዩ ልብስ ለብሰወው ቦታው ላይ በመገኘት ቃለ መጠይቅ ሲደረግላቸው ነበር፡ ያሉት እነዚሁ የዜና ምንጮቻችን ህዝቡና ፖሊሶች እንዲህም ደኅንነቶች በዚህ ሁኔታ ሰዉ ተፋጠው ቢቆሙም ከፎቁ ላይ ልጅ እግር ወጣት በመውረድ ወደ አቆማት ሳይክል ሲሄድ ሁሉም ሲጮህ ነሁኔታው ግራ የተጋባው ወጣት ‹‹ምንድን ነው?›› ብሎ ወደ ህዝቡ ቢያይ ‹‹ ከሳይክል ስር ፈንጂ አለ ዘወር በል›› ቢሉት ካሳይክል በታች ያለው የተቀመጠውን የሚያውቀው እቃ በመሆኑ ፈንጂ አይደለም ቀለል ያለ ኤሌክትሮኒክስ መሆኑን በአደባባይ ሲናገር ፖሊሶችና ደኅንነቶች በፍጥነት ያለምንም ጥያቄ ሳይክሉንና ልጁን በፖሊስ መኪና ይዘውት ወደ አልታወቀ ቦታ ሄደዋል፡፡ ነገሩ እንደታወቀ ሲያዩ እና ሁኔታው አላምር ሲላቸው ህዝቡን በታትነውታል፡፡

የፕ/ት ኦባማን የኢትዮጵያ ጉዞ ተከትሎ <<የሽብር ጥቃት ታቅዷል ከአልሸባብ ጋር ግንኙነት አለህ>> በሚል ሀሰተኛ ክስ የታሰረውን ጋዜጠኛ ሀብታሙ ምናለ ላይ አስቀድሞ ጭምር ክትትል ሲያደርጉና ከቤትም አስውጥተው እስር ቤት የወሰዱት ምርመራ ሲያደርጉበት የነበሩ ደኅንነቶች የዛሬው <<የፈንጂ ተገኘ>> የድራማው መሪ ተዋናይ ሆነው መዋላቸውን እነዚሁ የህብር ምንጮች ጨምረው ገልጸዋል ፡፡

ስለ ሁኔታው ከአካባቢው እማኞች መካከል አንዳንዶች ሁኔታውን በመታዘብ ደግሞ ይሄን አሳበው ማንን ለማሰር እንደፈለጉ አልታወቀም፡፡ እንደለመዱት ሱማሌያውያንና ማፈሳቸው አይቀርም ለእራሳችንም ግን ያሳጋል ሲሉ ከወዲሁ ድራማው የተፈለገው ለአፈና መሆኑን ግምታቸውን ሰጥተዋል። ፈንጂ ተገኘ የተባለበት አካባቢ በአሁኑ ሰዓት የተለመደውን ተግባሩን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
bole
ሰሞኑን ከኤርትራ የከዱትን የትህዴን የቀድሞ ሊቀመንበር ታጋይ ሞላ አስግዶም መዋሰት አቅቷቸው በተደጋጋሚ ሲደናገሩ በታየበት መግለጫ ላይ የኤርትራ መንግስት ግንቦት ሰባትን ጨምሮ በአገሩ ያሉ በኢትዮጵያ ለውጥ እንዲመጣ ነፍጥ ያነሱ የነጻነት ተዋጊዎችን በማሰማራት ለሽብር ይልካል ሲሉ መክሰሳቸውን ተከትሎ ስርዓቱ የሆነ ነገር እንዳያፈነዳ የሚል ግምት ሲሰጥ መቆየቱ ይታወሳል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ እ.ኤ.አ ሴፕተምበር 16 ቀን 2006 በአዲስ አበባ ካራ ቆሬ አካባቢ በቤት ውስጥ የኦነግ አባል ሳይሆኑ ናቸው የተባሉና በቤት ውስጥ በያዙት ፈንጂ ፈንድቶባቸው ሞቱ የተባሉትና ኦነግና የኤርትራ መንግስት አፈነዱት በተባለው ሶስቱም በሕጋዊ መንገድ የተቋቋመውና በጊዜው ዶ/ር መረራ ጉዲና የሚመሩት የኦሮሞ ሕዝብ ኮንግረስ(ኦብኮ) አባል በመሆናቸው አስቀድሞ በስርዓቱ በፈጠራ ወንጀል የታሰሩ ሲሆኑ የፈነዳውን ሆን ተብሎ በህወሃት-ኢህአዴግ አገዛዝ መሆኑን ዊክሊክስ የአሜሪካ ኤምባሲ የጊዜው ጉዳይ ፈጻሚ ሆኑት ቪኪ ሐድልስተን(Vicki J. Huddleston) ለመንግስታቸው የላኩትን የምስጢር መረጃ ማጋለጡ ይታወሳል።

በዛሬው የአዲስ አበባ የፈንጂ ተገኘ ድራማ የአገዛዙ መገናኛ ብዙሃን ምን ብለው የስርዓቱን የፈጠራ ውሸት እንደሚያቀርቡ እየጠበቅን ነው ሲሉ የህብር ሬዲዮ ምንጮች ከስፍራው ገልጸዋል።

↧
↧

ዜጐችን ከቀያቸው ማፈናቀል የልማታዊነት መገለጫ አይሆንም !!

$
0
0

ዳዊት ደምመላሽ ( ኖርዎይ )

(ከዚህ ቀደም ከጉራ ፈረዳ የተፈናቀሉ አማሮች፡ ፎቶ ፋይል)

(ከዚህ ቀደም ከጉራ ፈረዳ የተፈናቀሉ አማሮች፡ ፎቶ ፋይል)

የህወሃት/ኢህአዴግ/ መራሹ መንግስት ዜጐችን ከቀያቸው እያፈናቀለ ልማታዊ መንግስት ነኝ እያለ ነጋ ጠባ ይደሰኩርልናል አንድ መንግስት እንደ መንግስት መናገር የሚችለው ህዝቦቹን ከድህነትና ከኌላ ቀርነት እንዲሁም ከስደት ሲያላቅቅና የህዝቦችን አንድነት መልካም ግንኙነት ሲያጠናክር የሀገር ሉሃላዊነትንና ዳር ድንበርን ሲያስከብር ነው ።

ህዝቡ በኑሮ ውድነት የሚሰቃይበትና የበይ ተመልካች በሆነበት ቁርሱን በልቶ ምሳውን በማያገኝበት ወጣቱንና አገር ተረካቢውን ትውልድ ለስደት በመዳረግ በሰሃራና በሜድትራንያን ባህር እንዲሁም በተለያዩ ጐረቤት አገራት በእስር ቤት ውስጥ ታጉረው የመንግስት እያሉ ሰሚ ሳያገኙ ለአደጋዎች በተጋለጡበት የጐሳ ስሜት ተንሰራፍቶ አንዱ የበላይ ሌላኛው የበታች አንዱ ጐሳ አንዱን እንዲጠላና ሰላሙ እንዲናጋ ህዝቡ ወልዶ ከብዶ ከኖረበት መንደሩ በሐይል እየተፈናቀለ እንዲበታተን የሚያደርግ ቡድን የሚመራው መንግስት ጥፋታዊ እንጂ ልማታዊ ተብሎ ሊጠራ አይገባውም ።

የህዝብን መብት ገፎ የሚፅፉ ጋዜጠኞችንና የተቃዋሚ ፖለቲካ አመራሮችንና አባላቶችን አገሪታ ውስጥ ባሉ እስር ቤቶች አጉሮ የአገሩን ሀብትና ለም መሬት ጭምር ቆርሶ ለባዕድ አሳልፎ እየሰጠና ተባብሮ የአገሪታን አንጡራ አብት እየመዘበሩ በውጭ አገራት ባሉ ትላልቅ ባንኮች በልጆቻቸውና በቤተሰቦቻቸው በመቶ ቢሊዬን ዶላሮችን ዘርፈው እያስቀመጡ ባሉበት አገር ውስጥ ልማታዊ መንግስት አለ ብሎ ማመን ቀርቶ መናገሩ የስህተት ስህተት ነው ።

ለራሱ ህዝብ አክብሮትና ብሔራዊ ስሜት የሌለው ቡድን ከድሃው የኢትዬጵያ ህዝብ በተዘረፈው ገንዘብ የውጭ አገር ተባባሪዎቹን ለማስተናገድና ለመሳብ በአገሪቷ ውስጥ ትላልቅ ሆቴሎችንና መንገዶችን በመገንባቱ ብቻ ልማታዊ መንግስት ነው ብሎ መቀበልና ማስተጋባት ድንቁርና መገለጫ ነው።

በአጭሩ ልማት ሲተረጐም የህዝብ ኑሮ መሻሻልን፣ የሰብዓዊ መብት መከበርን፣ የዜጐችን ደህንነትና ሰላማዊ ኑሮ ዋስትና መኖርን ፣የዲሞክራሲና የዜጐች መብትን መረጋገጣቸወን ማሳየት ይኖርበታል ።

ህዝቡ በሀገሩ ጉዳይ የማይመክርበት ፣ የማይወስንበት ሁኔታ ካለ ትርጉም የሚሰጥ ልማት ሊሆን አይችልም ልማት ማለት የጥቂቶቹን ከርስ ሞልቶ ማደር ብቻ ሳይሆን በህዝብ ውስጥ የመንፈስ እርካታም ጭምር ሲኖርና የሀገር ዜግነትና ባለቤትነት ሲገለጽ ብቻ ነው  ።

ይህ ከዚህ በላይ በአጭሩ ጠቅለል አድርጌ በዝርዝር የጠቀስኩት ሐሳብ የህወሃት / ኢህአዴግን ፖሊሲዎችን ምንነት ቁልጭ አድርጎ ከሚያሳየን መገለጫዎቹ አንኳር ነጥቦች ከብዙዎቹ ጥቂቶቹ ናቸው በቀጣዩ ጽሁፌ ተመልሼ እስክንገናኝ ቸር እንሰንብት ።

ኢትዬጵያ ለዘላለም

ትኑር !!

↧

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ሞላን ነገሩት (ያድምጡት)

$
0
0

የቀድሞው የትህዴን መሪ የሕወሓት መንግስትን ከተቀላቀሉ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ምላሽ ሰጡ:: – ያድምጡት

Birhanu Nega

↧

  ጥቂት ስለ ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ፡ ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ እስከ ቂሊንጦ እስር ቤት –  በሱፍቃድ ደረጄ

$
0
0

 

(besufekadereje@gmail.com)                                                        

ኡስታዝ ካሚል ሸምሱተግባቢና በሳል ነው፤ ረጋ ባለ አንደበቱ የሚሰማውን በጥሞና መናገር ልዩ ያደርገዋል ፡፡ እምነቱን አጥበቆ ይወዳል፤ የእስልምና ሃይማኖት የሚያዛቸውን ተግባራት (ሶላት መስገድ፣ መጾም…) ፈጽሞ ሌሎች መሰሎቹ እንዲፈጽሙ ማድረግን ያውቅበታል፡፡ ከሌለች  የእምነት ተከታዮች ጋር የመግባባቱና ከሁሉም ጋር በአብሮነት መኖሩ ባጠቃላ ማህበራዊ ኑሮ የሚጠይቀውን ግዴታ የመወጣት ልዩ ችሎታ አለው፡፡ ከማንም ሰው ጋር የመግባባት፣ ተጫውቶ የማጫወት ክህሎት አለው፡፡ ከቀለሙ በተጓዳኝ ሀይማኖታዊ እውቀቱም የተመሰከረለት ነው፡፡ ሙስሊም ተማሪዎችን በመሰብሰብ በስነ ምግባር እንዲታነጹና ለሀገራቸው ተቆርቋሪ እንዲሆኑ ያስተምራል፡፡ በግቢው ውሰጥ ተሰሚነት ካላቸው የሀይማኖት ሰዎች አንዱ ነበር

፡፡

ካሚል ሽምሱን መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ሳለ አውቀው ነበር፤ አንድ ባችም ነበርን፤ በህግ ፋከልቲ ተደልድለን ለአምስት አመታት በቆየንባቸው ወራት ደጉንም ከፉንም አብረን አሳልፈናል፡፡ ካሚል ሸምሱ ጽንፈኛ የሆነ አመለካከት ሲያራምድ ለአንዲት ቀናት  እንኳን አላየነውም፣ አልሰማነውም፤ በግቢው ውሰጥ ከነበረው ተወዳጅነት ተነስቶም እንዲህ አይነት ሀሳብ የነበራቸውን ተማሪዎች ሊገስጽ ይችል ይሆናል እንጂ አንዲትም ቀን ክፉ ሲወጣው አልሰማንም፡፡  ከዚህ ይልቅ በሳል አስተሳሰቦችንና አንድ የሚያደርጉ ስራዎችን ማከናውን ይቀናዋል – ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ፡፡ እንደውም እኛም ክርስትያንነታችን እርሱም ሙስሊምነቱ ሳይገድበን እንደ አንድ የአዳም ልጆች እንጨዋወታለን ቀልዶችን እያነሳን እንሳሳቃለን እንጂ ላንዲትም ቀን እርሱ የኛን እኛም የርሱን እምነት የተንተራሰ እሰጥ አገባ ወይንም መከፋፈል መሰረት ያደረግ ጉዳይ አንስተን አናውቅም ፡፡ እንደውም አንተ የዚህ እኔ የዛ ነኝ የሚለው አስተሳሰብ ትዝም ብሎን አያውቅም፡፡ በዚህ መልኩ የህግን ሀ ሁ ፣ ሰብአዊ መበቶችን፣ የህግ ሙያን ተምረን ወጣን፡፡ አገቱኒ፡፡

ሰብአዊ መብት ማለት የማይሸራረፍ አንድ ሰው ሰው ስለሆነ ብቻ የሚያገኘው መብት ማለት ነው፡፡ ሰብአዊ መብት አንዱ ባንዱ ካልተደገፈ፣ አንዱን አክብሮ ሌላዉን ቸል ያሉት እንደሆነ፣ አንዱን በአደባባይ አውሎ ሌላውን ጓዳ ውስጥ ከቆለፉበት ምንም ትርጉም አይኖረውም፣ ግንጥል ጌጥ የሚሉት አይነት ይሆናል፡፡ በአገራችን ዛሬ ዛሬ እየደመቀ የመጣው ሰብአዊ መብቶችን መቆራረጥና መሸራረፍ ችግር አንዱ አንዱን እየወለደ አገሪቷን ልትወጣው የማትችለው አዘቅት ውስጥ እየከታት እየመጣ እንደሆነ በሂደት ክስተቶች እያሳዩን መጥተዋል ፡፡

መንግስት የእምነት ነጻነት ተረጋጧል እንደፈለግክ እምነትህን ማራመድ ትችላለህ ይልና በሌላ በኩል ደግሞ የእምነት መሮዎችህን የምመርጥልህ ግን እኔ ነኝ ይላል፡፡ የህዝበ ሙስሊሙ ተቃውሞው ከዚህ ይጀምራል፤ በታህሳስ 21 ቀን 2004 አ.ም. ጀማል መሀመድ የተባለው የመጅሊስ አመራር አወሊያ ትምህርት ቤት አንድ ደብዳቤ ይጽፋል፤ ደብዳቤው በርካታ የመስጂድ ኢማሞች፣ የትምህርት ቤቱ መምህራን እና የአረብኛ ተማሪዎች ከተቋሙ እንደተባረሩ ይገልጻል፤ ይህ ደብዳቤ መጅሊሱ ሙሉ በሙሉ ፓለቲካዊ ማስፈጸሚያ ወደ መሆን እንደተሸጋገረ ግልጽ ማሳያ ሆነ፡፡ ሀይማኖታቸው እንዲህ የካድሬ ማላገጫ መሆኗ ያበገናቸው ሰዎችም ተሰበሰቡ፣ አስራ ሰባት አባላትን ያቀፈ ኮሚቴ ሰየሙ፡፡ “የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ” በተሰኘው በዚህ ኮሚቴ አባል ለመሆን ከተመረጡት አንዱ ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ ነበር፡፡ ስራ ድልድል ላይም የኮሚቴው የህግ ተጠሪ ሆኖ ተመረጠ፡፡

ከዚህ በኋላ ኮሚቴው ስብሰባዎችን በሚያካሄድበት ቦታ ሁሉ የኮሚቴው አካሄድ ፍጹም ሰላማዊ እንደሆነ ህገ መንግስቱ ላይ የተካተቱ መብቶቻችን ይከበሩ ሲል ካሚል ሸምሱ ይናገር ነበር፡፡ ጥያቄያቸውም ሀይማኖታዊ ብቻ እንደሆነ ሳያሰልስ ለማስረዳት ሞክሯል፡፡ ባንዳንድ መስጊዶች ስብሰባ ላይም (ለምሳሌ በሻሸመኔ እንዲህ ማድረጉን ከአሌክስ አብርሀም የጌስቡክ ገጽ ላይ የተያያዘውን ፎቶ ማየት ይቻላል፡፡) የህገ መንግስቱን አንቀጾች እየጠቀሰ ጥያቄያቸው ህግንና ህግን የተከተለ መንገድ እንደሆነ አንደበተ ርትኡ የሆነው ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ ተናግሯል፡፡ በግንቦት 8 ቀን 2004 አ.ም ኮሚቴው ስለተቋቋመበት አላማና የህዝበ ሙስሊሙ ወቅታዊ ጥያቄዎች ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡ በዚህ ቃለ ምልልሱም ህዝበ ሙሲሊሙ ያነሳው ህገ መንግስታዊ ጥያቄዎች መሆናቸውንና ባእድ የሆነው የአህባሽ አስተምሮም በግድ ላያቸው ላይ ሊጫን በመሞከሩ መቃወማቸውን ተናግሯል፡፡ አያይዞም አህባሽ ለሙስሊሙ ብቻ ሳይሆን ፣ ለክርስትያኑ ባጠቃላይ ለሀገር ጸር የሆነ ሙስናን የሚያበረታታ አስተምህሮ ነው ሲልም ተናግሯል፡፡ በሌላ አነጋገር አህባሽ ጸረ ኢትዮጵያ አስተምህሮ ከሆነ የነካሚል ሸምሱ ትግልም ይህንን ባጭሩ ለመቅጨት ከሆነ ትግላቸው አገርን ማዳንም ጭምር ነበር ማለት ነው፤ በመሆኑም ለመስዋእትነታችሁ ታላቅ ዋጋ መስጠት ብቻ ሳይሆን እዳም እንዳለብን ተገንዝበናል፡፡ ነገሩ አስቀድሞ የገባቸው የሚመስሉ እንዳንድ ክርስትያኖች ኮሚቴው በሚጠራው ስብሰባ ላይ ይገኙ ነበር፡፡

መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴው ለጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ ድረስ ደብዳቤ በመጻፍ ጥያቄያቸው ገለልተኛ መጅሊስ እንዲቋቋም፣ የአወሊያ ትምህርት ቤት አስተዳደር እንዲከለስ፣ የሀይማኖት ነጻነታቸው እንዲጠበቅ የሚያሳስብ ብቻ እንደሆነ ገልጧል፡፡ ይህ ቢሆንም ቅሉ በጥር የተቋቋመው ኮሚቴ አባላት በሀምሌ ወር 2004 አ.ም ለእስር ተዳረጉ፡፡ ለአገሩም ለእምነቱም ብዙ መስራት የሚችለው ካሚል ሸምሱ ከልጆቹና ከባለቤቱ ተነጥሎ ወደ እስር ቤት ተጋዘ፡፡ ለአራት ወራትም ያለ ፍርድ በማእከላዊ ታሰሮም ስቃየ ስቃያትን ተቀበለ፡፡ ጂሀዳዊ ሀረካት ተብሎ በወያኔ የተቀነባበረው ዶክመንተሪ ፊልም ላይም ካሚል ሸምሱን ሲያቀርብ መከራ እየደረሰበት መሆኑን ከገጽታው ማንበብ ይቻል ነበር ፡፡ ማእከላዊ እንዲታሰሩ የተደረጉበት ቦታም ሳይቤሪያ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን በበጋም በክረምትም እጅግ ቀዛቃዛ በመሆኑ እችክእችክ ያስብላል፡፡በማእከላዊ ቆይታቸውም አካላዊም ሆነ ስነ ልቦናዊ ጥቃቶችን ለማስተናገድ ተገደዋል፡፡ ከመርማሪዎቹ አንዱም‹‹ዓለም ላይ ያለን ጠበቃ ብታመጣ አታሸንፈንም ፖሊሱም የእኛ! አቃቤ ህጉም የእኛ! ዳኛውም የእኛ!›› ሲል እነደደነፋ ካሚል ሸምሱ ለፍርድ ቤቱ ተናግሯል፡፡ ከዚህ ባለፈም በፍርድ ሂደቱ ጊዜ ፈታኝ የሆኑ ጥያቄዎችን ለአቃቤ በማቅረብ ሀሰት ራቁቱን እንዲቀር አድርጓል፡፡

ደፋር የሆነውና በመንግስት የሚደገፈው መጅሊስ ግን የህዝበ ሙስሊሙን መሪዎች አሳስሮ ሲያበቃ ምርጫ አካሂዳለሁና ተሳተፉ ሲል ቱሪናፋነቱን ሊያስመሰክር በቅቷል፡፡ መስከረም 27 2005 በማደርገው ምርጫም ተሳተፉ ሲልም መለፈፍ ጀመረ፡፡ ካሚል ሸምሱም በጠበቃው አማካይነት መጅሊሱን በመክሰስ ምርጫውን እንዳያካሂዱ እግድ ይተላለፍ ዘንድ ጠይቆ ነበር፡፡ ወደ ቂሊንጦ እስር ቤት ከተዛወረ ወደህ በእስረኞቹ ከፍተኛ ተወዳጅነትን በማትረፉ በከፍተኛ ድምጽ የታሳሪዎች ተወካይ ተደርጎ ተመርጧል፡፡ የሙስሊሞች ድምጽ፤ የቂሊንጦ ድምጽ፤ የድምጽ አልባዎች ድምጽ – ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ፡፡ በቂሊንጦ አስሩ በዞን 1 ታሰሮ የነበረ ሲሆን ወደ ዞን ሶስት እንዲዛወር ተደርጓል፤ የእስር ቤቱ ምክንያትም ሰዎችን እየሰበሰብክ ቁራን እንዲቀሩ ታደርጋለህ የሚል ነበር፡፡

እንደ ማራቶን በረዘመው የሶስት አመታት የፍርድ ቤት ምልልስና እንግልት በኋላ ካንጋሮው ፍርድ ቤት ጥፋተኛ ናቸሁ ሲል በየነ፡፡ የሙስሊሙ ህጋዊ ተወካይ የሆኑትን ኮሚቴዎችም ከ 7 እስከ 22 አመት በሚደርስ እስራት እንዲቀጡ ወሰነ፡፡ ከኮሚቴው አባላት መሀል 22 አመት የተፈረደባቸው አራት ሲሆኑ ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ አንዱ ነው፡፡ እውነትና ፍትህ አገራቸው የት ይሆን ፍርዱን ተከትሎም ባንድ ክፍል አብረው ይማሩ ከነበሩ ጓደኞቹ ሁለቱ እንዲህ ብለዋል፣

  • Law school friend, Kamil Shemsu, fall prey to the constitution he studied! 22 yrs of sentencing for simply demanding constitutional rights?
  • Kamil was the most mature, intelligent, down to earth classmates I’ve ever had. As far as I am considered one cannot get as far from being a religious terrorist as Kamil. He was a good man.

 

ዛሬ የሙስሊሙ ማህበረሰብ በሀገርም በውጭም ያለው ካሚል ሸምሱን አንተ ብሎ አይጠራውም፤ ሰውን የሚያስከብረውም ሆነ የሚያወርደው ስራው ነውና ላመነበት ጉዳይ እስከ መጨረሻው በጽናት በመጓዙ አንቱ ተብሏል፡፡እንዲህ አንቱታን ካተረፈ፣ ቃሉን ጠባቂ፣ ስለ እውነት እስከመጨረሻው ድረስ መስዋእት ከሆነ ሰው ጋር ባንድ ወንበር ቁጭ ብዬ መማሬ ታላቅ ኩራት ይሰማኛል፤ በሌላ በኩል ደግሞ 22 አመታትን ያለ ሀጥያቱ እንዲታሰር በዝንጀሮው ፍርድ ቤት የተበየነበትን ወንድም ኡስታዝ ካሚል ሸምሱን ሳስበው እንባ ይተናነቀኛል፡፡ ህግን አሳምሮ ለሚያውቅ ግለሰብ ህጋዊ መብቶቹ ሲጣሱ መመልከት እጅግ የሚያደማ እንደሆነ እንገነዘባለን፤ ቢሆንም የዛሬ መስዋእትህ ለሀገርህ፣ ለልጆችህ፣ ከታሪክ ተጠያቂነት ለመዳን ያደረግው መሆኑ ያጽናናኛል፤ እውነት ግን መቼም ተሸፍና አትቀርም፣ ዋጋ የከፈላችሁለት አላማችሁም ጠብ አይልም፤ እውነት ነጻ ታወጣችኋለች፤ ወንድም ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ አንተም ሆንክ ፍትህ የተጠማው መላው ህዛባችን ከእውነተኛ ዳኛ ፍትህ የሚያገኙበት ቀን እጅግ ቅርብ ናት፡፡

አዲሱ አመት በጎ በጎውን የምንሰማበት ያድርግልን!

ተጻፈ፤ መስከረም 02 2008 አ.ም

↧

Health: በኢስላም ማህፀንን ማከራየትና መከራየት እንዴት ይታያል? –ዳኢ መንሱር ሁሴን ይነግሩናል

$
0
0

ዳኢ መንሱር ሁሴን ስለ ማህፀን ማከራየት ከኢስላም አስተምህሮ አንፃር እንደሚከተለው አብራርተውልናል፡፡

ምስጋና ለአሏህ (ሱ.ወ) የተገባ ነው፡፡ ሶላትና ሰላም በአሏህ መልዕክተኛ በሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ ይስፈን፡፡
ወደ ዋናው ርዕሳችን ከመግባታችን በፊት እንደ ኢስላም አስተምህሮ የሰው ልጆች የተፈጠሩባቸውን አራት መንገዶች እንመልከት፡፡

የመጀመሪያው መነሻችን የሆኑት የአባታችን አደም (ዐ.ሰ) አፈጣጠር ሲሆን፣ እርሳቸውም ያለ እናትና አባት በአሏኅ ችሎታና ጥበብ ከአፈር መፈጠራቸው ነው፡፡ በመቀጠልም እናታችን ህዋ ደግሞ ያለ ሴት ከአባታችን አደም ጎን ተፈጠሩ፡፡ በሶስተኛ የምናገኘው የነቢዩሏህ ዒሳ (ዐ.ሰ) ከእናት ብቻ ያለ አባት በአሏህ (ሱ.ወ) የ‹‹ሁን›› ቃል የተወለዱበት ተአምራዊ አፈጣጠር ነው፡፡ በመጨረሻ የምናገኘው ብዙሃኑ የአደም ልጆች ከእናትና አባት የተወለድን የምንራባበት መንገድ ነው፡፡
የሰው ልጆች ምድር ላይ የተገኘንባቸውን መንገዶች ካየን፣ በርዕሳችን ስላነሳነው ልጅ ምናልባትም ከሶስት ወላጆች እንዲገኝ ‹‹ሰለጠንኩ›› የምትለው ዓለም ስላመቻቸችው፣ ‹‹የማህፀን ኪራይ›› ኢስላም የሚለውን ትንሽ እንበላችሁ፡፡
እንደሚታወቀው ይህ ጉዳይ፣ በቀደሙት ጊዜያቶች የማይታወቅና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተጀምሮ ዓለም ላይ እየተስፋፋ ያለ ነገር ነው፡፡ ከዚህ በፊት ስላልነበረ ቀደምት የኢስላም ምሁራን በጉዳዩ ላይ የተናገሩት ነገር የለም፡፡ በተጨማሪም ታዋቂ የሙስሊሙ ማህበረሰብ መሪዎች (የመዝሃብ ባለቤቶች) የነበሩ፣ ይህን ጉዳይ በኢስላም መፈቀዱን ወይም አለመፈቀዱን የዘገቡትም የተናገሩትም ነገር የለም፡፡
pregnancy-facts04
እዚህ ላይ ልብ ልንል የሚገባን ነገር ቢኖር፣ የሙስሊሙ የመዝሃብ መሪዎች ከቁርአን እና ከሐዲስ (የነብዩ ሙሐሙድ አስተምህሮ) ባገኙት ትንተና ሰጥተዋል፡፡ ይህ አይነቱ ትንታኔ ደግሞ ከቁርአን እና ከሐዲስ ቀጥሎ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ ትልቅ ቦታ አለው፡፡ ሕይወቱንም እዚያ ላይ ባገኘው ሕግ ነው የሚመራው፡፡
ለዚህም ነው ከላይ በጉዳዩ ላይ ከነርሱ የተገኘ ማብራሪያ አለ? ወይስ የለም የሚለውን ለማስቀመጥ የሞከርነው፡፡ እነሱ የሰጡት ትንታኔ የለም ማለት ግን ኢስላም ስለዚህ ጉዳይ የሚሰጠው ብያኔ የለም ማለት አይደለም፡፡ አሏህ (ሱ.ወ) ከቁርአኑ ላይ እንዲህ ብሏል፡-
‹‹በመጽሐፉ (በቁርአን) ውስጥ ምንም (ስለምንም) ነገር (ሳንገልፅ) አልተውንም›› (አል አንአም 38) በሌላ ምዕራፍ ላይም፣ ‹‹ዕውቀቱ ከሌላችሁ የዕውቀት ባለቤቶችን ጠይቁ›› (አል አንቢያእ 7)
ይህ ማለት፣ የትኛውም አዲስ ነገር ቢፈጠር የሚፈጠረው ነገር ጠቅለል ብሎ በተቀመጠው የአሏኅ (ሱ.ወ) ቃል (ቁርአን) እና የመልዕክተኛው ንግግር (ሐዲስ) ሕግ ስር በጊዜው በሚኖሩ ምሁሮች ጥልቅ እይታ እና ግንዛቤ በሚኖሩ ምሁሮች ጥልቅ እይታ እና ግንዛቤ መሰረት ተገቢ የሆነ ትንተና እና ብያኔ ይሰጥበታል፡፡ ከላይ እንደተጠቀሰው፣ ይህ ጉዳይ መጤ ከመሆኑም ጋር አንዳንድ ሰዎች ስለ ጉዳዩ ሰፊ ጥናት ሳያደርጉ፣ በደፈናው ችግር እንደሌለውና ለሰዎች ጥሩ የሕይወት መቀጠያ ዘዴ አድርገው ይገልፁታል፡፡ ነገር ግን ይህ አመለካከት እንደማያዋጣና ጉዳዩን ትኩረት ሰጥተን ልናየው እንደሚገባ በዚህ ጽሑፍ ለመጠቆም እንሞክራለን፡፡
ማህፀንን ስለማከራየትም ሆነ መከራየት አሁን ላይ ያሉ ሙስሊም ምሁራ የሰጡትን ትንታኔ እና ብያኔ ከማየታችን በፊት አላህ (ሱ.ወ) ስለ ሀፍረተ ገላችን ምን እንደተናገረ አጠር ባለ መልኩ እንመልከት፡፡
አንደኛ፡- ‹‹(አማኞች) እነዚያ ብልቶቻቸውን (ከሐራም) የሚጠብቁት…›› (አል ሙእሚኑን፤ 5-6)
ከአንቀፁ እንደምንረዳው፣ አላህ (ሱ.ወ) አንድ ወንድ በሸሪዓዊ መንገድ ከተፈቀደችለት ሴት ውጭ የሚያደርገውን የግብረ ሥጋ ግንኙነት እርም አድርጓል፡፡
ሁለተኛ፡- አሏህ (ሱ.ወ) የሰውን ልጆች ዘራቸውን እና ልጆቻቸውን እንዲጠብቁ አደራ ብሏል፡፡

ሀፍረተ ገላችንን እና ክብራችንን እንዴት መጠበቅ እንዳለብን በአጭሩ ይህን ካልን፣ ወደ ዋናው ርዕሰ ገዳይ ስንገባ ማህፀን ማከራየት ካለምንም የሐሳብ ልዩነት በኢስላም ክልክል (ሐራም) ነው ይሉናል- ሙስሊም በኢስላም ክልክል (ሐራም) ነው ይሉናል- ሙስሊም ምሁራኑ፡፡ ለዚህም የሚከተሉትን ምክንያቶች ያቀርባሉ፡፡

1. የሚወለደው ልጅ የእናት፣ የአባት ብሎም የዘር እውቅናን ሙሉ በሙሉ ይህ ነው ለማለት ብዥታ ውስጥ ይከተላል፡፡ ይህ ብዥታ በኪራይዋ እናት እና በዋናዋ እናት መካከል ወደ ፀብ ይወስዳል፡፡ የሚወለደው ልጅ ከሁለቱ እናቶች የአንዷ እንደሆነ እርግጠኛ ብንሆንም፣ በእርግጠኝነት የዚህች ነው ብሎ መወሰን ግን አንችልም፡፡ ከሳይንሱም ጋር ተያይዞ በዘርፉ ሰፊ ጥናት ያደረጉት ዶክተሮችና ፕሮፌሰሮች ስለ ችግሩ ብዙ የሚሉት ስላለ ያንን ፈልጎ መረዳት ከእኛ የሚጠበቅ ይሆናል፡፡ ስለዚህ እንደ ኢስላም ህብረተሰቡ ይህን እንዲርቀው ይመከራል፡፡

2. ይህን ጉዳይ ከወንዱ ፍትወት እንዲሁም ከሴቷ እንቁላል ለመውሰድ ሂደቱ የእሷንም የሱንም ሀፍረተ ገላ ማየት ይጠይቃል፡፡ በተጨማሪም የኪራይዋ እናት ሀፍረተ ገላን ማየት ግድ ይላል፡፡ ይህ ደግሞ ከላይ ከተጠቀሰው የኢስላም አስተምህሮ ጋር ይጋጫል፡፡ የሌላን ወገን ሀፍረተ ገላን ማየት ክልክል ስለሆነ (ባል የሚስትን ሚስት የባልን ሐፍረተ ገላ ማየት ሲቀር)

ይህን በተመለከተ አሏህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡- ‹‹ለአማኝ ወንዶች እይታቸውን እንዲቆጣጠሩና ብልቶቻቸውንም እንዲጠብቁ ንገራቸው›› (አን ኑር 30)
ይህም አንዱ የሌላውን ሀፍረተ ገላ አይመልከት፡፡ ለዚያም እይታውን ወደ ታች ይመልስ፣ የራሱንም ሀፍረተ ገላ ይሸፍን ማለት ነው፡፡ ከፊል ሙስሊም ምሑራን በጣም ለከፋ ችግር ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ፣ (ሴት ከሆነች አባቷ፣ ባሏ፣ ለአቅመ አዳም የደረሰ ወንድሟ ወይም ልጇ ባሉበት) መታየት እንደሚቻል ብይን ይሰጣሉ፡፡
ይህ አይነቱ ጥንቃቄ ያስፈለገውም፣ ሰይጣን የሰው ልጆች ከአምላካቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት በማቋረጥ የራሱ ግብረ አበሮች እንዳያደርጋቸው በማሰብ ነው፡፡ ተቃራኒ ፆታዎች ከተፈጥሮ መሳሳቡ ጋር የሰይጣን ጉትጎታ ሲጨምር፣ ህገ ወጥ የሆኑ መነካካትና መተያየት ወደ ዝሙት እንዳያመራቸው ነው፡፡

3. የማህፀን ኪራይ የምዕራቡ ዓለም ‹‹ስልጣኔ›› የፈጠረው ግኝት ነው፡፡ በተለይ ከሃይማኖት ህግጋት አንፃር ስልጣኔቸው ደግሞ በከፊል ሰይጣኔ መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ ኢስላም ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ጋር ሰፊ ግንኙነት ቢኖረውም ሰዎች ከተፈጠሩለት አሏህን የማምለክና ለትዕዛዙ እጅ የመስጠት አላማ ጋር የሚያጋጭን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ውጤት አያስተናግድም፡፡

ጠቅለል ባለ መልኩ፣ በስልጣኔ ስም ሁሉንም መከተል ሳይሆን ጥሩና መጥፎ ጎጂና ጠቃሚውን ለይተን ልንጠቀምበት እንደሚገባ ኢስላም ያስተምራል፡፡
ኢስላም እንደ እምነት፣ ለስነ ምግባርና ባህሪ በጥቅሉ ለመልካም ማህበራዊ እሴቶች ትልቅ ዋጋ ይሰጣል፡፡ በተቃራኒው ምዕራቡ ዓለም ደግሞ ለዚህ ጉዳይ ትኩረት ሲሰጥ አይታይም ይላሉ ምሁራኑ፡፡ ስለ ማህፀን ኪራይ ክልክልነት ለማስረዳት ከተነሱት ምክንያቶች፣ ማህበረሰባዊ ቀውሶችን ስለሚያስከትል ሸሪዓዊ (ኢስላማዊ ሕግ) መነሻ የለውም የሚል ነው፡፡ ይልቁንም ማህፀን የሴቷ ሀፍረተ ገላ ስለሆነ ለሕጋዊ ባሏ እንጂ ህጋዊ ባሏ ያልሆነ ወንድ ፍትወት ተቀብላ ልታሳድግበት አይፈቀድላትም፤ ሸሪዓ አምርሮ ይቃወመዋል፡፡

እንደ ኢስላም አንድ ወንድ ያላገባትን ሴት ባይተዋር ለሆነ እርግዝና የመጠቀም መብት የለውም፡፡ በሌላ አገላለፅ አንዲት ሴት ማህፀኗን ላላገባት ወንድ ስታከራይ ሀፍረተ ገላዋን በጋብቻ ላልተሳሰራት ወንድ እየፈቀደች ነው፡፡ እርሷም ለእርሱ እርሱም ለእርሷ ስለማይፈቀዱ ሙሉ ዝሙት ይሆናል ባይባልም ተግባሩ ግን ሙሉ በሙሉ ሐራም ነው፡፡
የእርሱን ፍትወት በእርሷ ውስጥ እንዲያሳድግ ከማድረጉም በላይ፣ ፅንሱ የሚመገበውና የሚያድገው በማህፀን ውስጥ ስለሆነ በጎም ሆነ መጥፎ ተፅዕኖ የሚያርፍበት ከኪራይዋ እናቱ ነው፡፡ ስለሆነም ይህቺ ሴት የጎጂ ልማዶች (መቃም፣ ማጨስ፣ አልኮል መጠጣት ወዘተ…) ተጠቂ ብትሆን ፅንሱ ከጅምሩ ገና ለአደጋ ተጋላጭ ሊሆን ይችላል፡፡ በዚህ ሂደት ላይ ጽንሱን የሚከታተለው ዶክተር፣ ፅንሱ ላይ የአካል ጉዳት ይታያልና የወሊድ ጊዜሽ ከመድረሱ በፊት በቀዶ ጥገና ወጥቶ ጽንሱ መታከም አለበት ቢላት ፈቃደኛ ትሆናለች? የእኔ ለማትለው የሰው ልጅ ትክክለኛዋ እናቱ ብትሆን፣ ልታደርገው የምትችለውን የራሷን ሕይወት ቤዛ የማድረግ ጥያቄ ትቀበላለች?

እዚህ ላይ ሌላ ሳንጠቅስ የማናልፈው ሐሳብ ቢኖር፣ በሕጋዊ ባልና ሚስቶች መካከል በተፈጠረ አንዳች ውስጣዊ ችግር ምክንያት፣ ሚስቲቱ መፀነስ ካልቻለች በሕክምና ድጋፍ የባሏን ፍትወትና የራሷን እንቁላል ውጭ ላይ አሳድጎ ፅንሱን ወደ ራሷ ማህፀን አስገብተው ቢወልዱ የራሳቸው እስከሆነ ድረስ ችግር እንደሌለው ሙስሊም ምሑራን ይገልፃሉ፡፡
4. በእርግዝና ወቅት ያልተጠበቁ እንደ ስኳር፣ የደም ግፊት ያሉ ከባባድ ህመሞች የሚገጥሟቸው ሴቶች አሉ፡፡ እነኚህ በሽታዎች በአፋጣኝ ህክምና ካላገኙ የነፍሰ ጡሯን ህይወት ሊቀጥፉ ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም ፅንሱን ለመጠበቅ (ለማዳን) ቀዶ ህክምና (ኦፕራሲዮን) የግድ ሊሆን ይችላል፡፡ ይሁን ኃላፊነትስ የሚወጣው ማን ነው? ይህቺው
የኪራይ እናት ወይስ የእንቁላሏ ባለቤት?

ከዚህ ሂደት ጋር ተያይዘው የተለያዩ እንግዳ ነገሮችም ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ እነዚህን የባህል፣ የስነ ልቦና እና ሌሎች ማህበራዊ ቀውሶች እንዴት ነው የምንፈታቸው? ኃላፊነቱን ለየትኛይቱ እናት እንስጣት?
ከዚህ በመነሳት አንድ ድምዳሜ ላይ እንደርሳለን፡፡ ይኸውም ፅሱ በዚያችው በእውነተኛ እናቱ ማህፀን አሏህ (ሱ.ወ) እንደፈቀደለት ይኑር፡፡ እናቱም ጽንሱን የመጠበቅና የመንከባከብና በአሏህ ፈቃድ ጊዜው ሲደርስም የመውለድ ሰብአዊ፣ ሃይማኖታዊና ህጋዊ ግዴታ ይኖርባታል፡፡
‹‹ማህጸን መከራየት ሞግዚት እንደመቅጠር ነው›› የሚሉ አንዳንድ ወገኖች አሉ፡፡ ፍየል ወዲያ… እንዲሉ፣ ይህ ጤነኛ አዕምሮ ሊቀበለው የማይችል ሐሳብ ነው፡፡ አንድን የተወለደ ልጅ ሞግዚት ብትንከባከበው፣ ጡቷን ብታጠባውና ብታሳድገው ልጁ በኪራይ ማህፀን እንደሚያድገው ፅንስ ያለ ተፅዕኖ አይገጥመውም፡፡ ከሞግዚቷ ጋር አለመግባባት ቢፈጠር ወይም በሆነ ምክንያት ጡት ማጥባት ብትከለክለው (ብታቆም)፣ ልጁ በቀላሉ ወደ ወላጅ እናቱ ተመልሶ አስፈላጊውን እንክብካቤ ማግኘት ይችላል፡፡ ህይወቱም ያለምንም እንከን መቀጠል ትችላለች፡፡

5. የማህፀን ኪራይ፣ በትዳር ህይወት ውስጥ በባልና ሚስት መካከል ሌላ ሶስተኛ ሰው ጣልቃ እንዲገባ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፡፡ ባል ወደ ኪራይ እናት የሚሳብበት ክፍተት ይፈጠራል፡፡ ይኸው መጤ ፍልስፍና በምዕራቡ ዓለም ውስጥ ብዙ ቀውሶችን እያመጣ ይገኛል፡፡ አንድ ክስተት እንደ አብነት ብናነሳ፡፡ እንግሊዝ ሀገር ውስጥ ዋናዋ እናት ለኪራይዋ እናት ለመክፈል የተስማማችውን 20 ሺ ፓውንድ የማህፀን ኪራይ ጊዜው ደርሶ ልጇ ከተወለደላት በኋላ አልከፍልም በማለት ጭቅጭቅ አስነስታ ነበር፡፡ የኪራይዋ እናትም ‹‹ብሩን ካላመጣሽ ልጁ የእኔ ነው፣ እውቅና አልሰጥሽ›› ብላ ክስ እንደመሰረተችባት ተሰምቷል፡፡ ይህ ወረርሽኝ በእኛ ሀገር ደረጃ ደግሞ ከዚህ የከፋ ችግሮችን ይዞ እንደማይመጣ ምን ያህል እርግጠኞች ነን? ስለዚህ ልብ ያለው ልብ ይበል ነው ነገሩ፡፡

የወንድ ዘር (ስፐርም) ልገሳ

ስለማህፀን ኪራይ ካነሳን ዘንዳ፣ ጉዳዩ ተቀራራቢነት ስላለው የወንድ ዘር (ስፐርም) ልገሳን በተመለከተ ትንሽ ማለት ወደድን፡፡ እርስዎ እስካሁን ከሰሟቸው ልገሳዎች ‹‹የደም፣ የልብ፣ የኩላሊት፣ የዓይን ልገሳ ወዘተ…›› ባለፈ ወንዶች ፍትወታቸውን በመለገስ ላይ ናቸው፡፡ በዚህ ሂደት ደግሞ አንድ ‹‹ቸር›› የሆነ ወንድ፣ በዚህ ልገሳ ከተሰማራ ስለማንነታቸውና ስለዚህች ምድር ዕጣ ፈንታቸው የማይጨነቅላቸውን ጭራሹንም የማያውቃቸውን የትየለሌ ልጆች ሊያፈራ እንደሚችል መገመት አያዳግትም፡፡
ይህ የማስተዋል አቅሙ ላልከዳው ሰው፣ እጅግ ከባድና ዘግናኝ በመሆኑ ለመስማት እንኳን የሚከብድ ጉዳይ ነው፡፡ ኢስላም በተለይ ወንድ እንደ አባት ለልጆቹ፣ የምድራዊም ሆነ ሰማያዊ ዓለም ሁለንተናዊ ዕጣ ፈንታቸው የሚበጃቸውን የማመላከት፣ የመንከባከብና መሰል ኃላፊነቶች አስረክቦታል፡፡ ወንዱ የአባትነት ሚናውን ለማይወጣበት ይህ አይነት የዘር (ስፐርም) ልገሳ ክልክል ነው፡፡

↧
↧

የጠንቋይ ፖለቲካ  -ከከተማ ዋቅጅራ

$
0
0

ethiopia_detail_mapሰይጣን በባህሪው ፍቅር፣ መስማማት፣ መዋደድ፣ መከባበር፤ አይወድም። በተገላቢጦሽ ጥላቻን፣ መለያየትን፣ መጣላትን፣ በገዳደልን፤ ይወደዋል። ጠንቋይ የሰይጣን አገልጋይ ስለሆነ ወደሱ የሚመጡትን በሙሉ ዙሪያቸው በጠላት እንደተከበቡ አድርጎ ይነግራቸዋል። በግራ በኩል ያሉት ጎረቤትህ  አንተን ለማጥፋት የተነሱ ናቸውና ተጠንቀቃቸው ይለዋል። በቀኝ በኩል ያሉት ጎረቤቶችህ ያንተን እድል ጥርግ አድርገው ወስደውብህ እንዳታድግ  ያደረጉህ እነሱ ናቸውና ማርከሻው እኔ ጋር ስላለ እሰጥሃለው ሌላ ግዜ ግን ወደነሱ መንደር እንዳትሄድ እራቃቸው ይለዋል። በፊለፊት ያሉት ጎረቤቶችህ ደግሞ ሃብት እንዳይኖርህ ሰርተህ እንዳታድግ ተምረህ እንዳትራቀቅ በማድረግ አስረውህ የያዙህ እነሱ ናቸውና ሽሻቸው ይለዋል። በኋላ በኩል ያሉትን ጎረቤቶቹን ደግሞ በልጆችህ እንዳትደሰት ባለህ ባህል እንዳትኮራ በትዳርህ ደስተኛ እንዳትሆን ቤትህን የሚያተራምሱት እነሱ ናቸውና ሽሻቸው አሽሻቸው ይለዋል። ከፊት ከኋላ ከግራና ከቀኝ ከምስራቅ ከምዕራብ ከደቡብ ከሰሜን ያሉት በሙሉ ጠላት ናቸውና እራቃቸው፣ አርቃቸው፤ አትቅረባቸው፣ ተጠንቀቃቸው፣ አጥፋቸው፤እያለ ጠንቋዩ ደጋግሞ ስለሚነግረው ምንም የማያውቀው የጎረቤት ሰዉ በገቡ በወጡ ቁጥር ከጠንቋዩ በተነገረው የማጠፋፋት መልዕክት የመበታተን አጀንዳ ጥርስ እየተነከሰባቸው የጎሪጥ እየታዩ እንዲኖሩ ይደረጋሉ። ከባዱ ነገር እና ትልቅ ስህተት የሚሆነው በጠንቋይ ፖለቲካ አራማጆች የሚተላለፈው መልዕክት በመቀበል ወዳጅ የሆነውን ህዝብ ጣላት፣ አንድ የሆነውን ህዝብ ሁለት፣ የተቀራረቡትን ህዝብ ማራራቅ፣ የተዋደዱትን ህዝብ ማጣላት፣ አደጋው ለራስ ነው። ወዳጅ የሆነው ህዝብ በፍቅር የሚኖረውን ህዝብ በግድ ጠላት ነህ ጠላት ነህ እየተባለ ሲነገረው ዝም ያለውን ህዝብ በመነካካት የተነሳ እንደሆነ ጥቂት የጠንቋይ ፖለቲካ አራማጆች እና ተከታዮቹ ከፍተኛ ዋጋ የሚያስከፍል ነውና በጥልቀት ሊታሰብበት ይገባል።

ወያኔና ሻብያ በጠንቋይ ፖለቲካ አካሄዳቸው ለግዜው በሆነ ከሁለት አስር አመታት በላይ በስልጣን ቆይተውበታል። እዚህ ጋር ለኤርትራ ህዝብ ጥቂት ጥያቄዎችን ጣል አድርጌ ልለፍ። ሻብያ የኤርትራ ጠላት ኢትዮጵያ እንደሆነ ደጋግሞ ለትውልዱ ይነግራቸዋል ኢትዮጵያ ከኤርትራ የሚፈልጉት ወርቋንና ቀይ ባህርን ነው ህዝቧን ግን አይፈልጉም በማለት ህዝቡ ለኢትዮጵያ መጥፎ አመለካከት እንዲኖረው አድርጓል። በቅርብ ኢሳያስ አፍዎርቄ በኢሳት ጋዜጠኖች በቀረበለት ጥያቄ ግን የንስሃ ያህል ትንሽ ተናግሯል የኢትዮጵያ ህዝብ እና የኤርትራ ህዝብ የትኛውም ፖለቲከኛ ቢመጣ አይለያዩም የሚል ጣል በማድረግ አስምቶን የኤርትራ ጠላት ወያኔ ነው እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብ አይደለም ብሏል። ይሄ ጥሩ ጅማሬ ነው የኢትዮጵያም የኤርትራም ጠላት ወያኔ ከሆነ አንድ የጋራ ጠላት አለን ማለት ነውና መደጋገፍ ይቻላል ማለት ነው። ጥላቻን በማስተማር የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚደረግ ሩጫ ጉዳት ለራስ ነው ይታሰብበት።

ጥያቄ፡- የኤርትራ አባት  እና  እንቶቼ ወንድም እና እህቶቼ ኤርትራ ነጻ ወታለችን? የጀብሃ እና የሻቢያ የ30 አመት የትግል ውጤት ሊያመጣ የተፈለገው ነጻነት እንደዚ አይነቱን ነውን? ኤርትራ  ውስጥ ደርግ ስልጣን ላይ በነበረበት ግዜ ከሚሞተው ህዝብ ቁጥር አሁን በዘመነ ሻብያ ግዜ መቶ እጥፍ ለምን ጨመረ? በደርግ ዘመን ተቸግሮ አገሩን ጥሎ ከሚሰደደው ኤርትራዊ በዘመነ ሻብያ ግዜ በመቶ እጥፍ ለምን ጨመረ? በደርግ ግዜ በዩኒቨርስቲ ደረጃ ተምረው ከሚመረቁ የኤርትራ ተማሪዎች በዘመነ ሻብያ ግዜ ለምን በመቶ እጥፍ ቀነሰ? ተተኪው ትውልድ ካልተማረ  ነገ አገሪቷን የሚረከባት ዜጋ ምን አይነት ሊሆን ይችል ይሆን? በኤርትራ አገር ላይ ወደፊት ሊመጣ የሚችለውን ቀውስ ቆም ብሎ ያስተዋለ  ኢርትራዊ ይኖር ይሆን? ካለስ ዝምታን የተመረጠው እስከመቼ ነው?  እዚህ ጋር ደርግ ይሻላል እያልኩኝ ሳይሆን በሁለቱ መንግስት ዘመን ያለውም በህዝቡ ላይ የነበረውን ሁኔታ ማነጻጸሬ እንደሆነ ይታወቅልኝ። ብቻ ብዙ አልገባበትም ምናልባትም በሌላ ግዜ አስፈላጊ ሆኖ ከታየኝ በሰፊው ልመለስበት እችላለው አሁን ግን የኛ ችግር ገዝፎ እና ጎልቶ ስላለ ወደዛ እሄዳለው።  ልናገር የምፈልገው ኢትዮጵያኑ ስለ ኤርትራ መናገር የምንፈልገው የኤርትራን የማእድን ሃብቷን ፈልገን አይደለም የራሳችንንም ሃብት በአግባቡ አልሰበሰብን እንኳን የሰው ልንመኝ ነገር ግን የወንድም እና የእህትነት ፍቅር ግድ ብሎን እንጂ ሃብትና ንብረቷን የሚመኝ ማንም ኢትዮጵያዊ የለም።

የጠንቁይ ፖለቲካ በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ውስጥ ለማስረጽ ሃያ አራት አመት ሙሉ እየተሰራበት ጉዳይ ነው። ወያኔም ስልጣኑ ላይ እስካለ ድረስም ይገፋበታል። የትግሬ ጠላት አማራ፣ ኦሮሞ፣ ደቡቡ፣ ሱማሌው፣ አፋሩ፣ ጋንቤላው፣ ነው። የኦሮሞ ጠላት አማራ፣ ሱማሌው፣ ደቡቡ፣ ጋንቤላው፣ አፋሩ፣ ነው። የአማራው ጠላት ኦሮሞው ፣ ሱማለው፣ ደቡቡ፣ አፋሩ፣ ጋንቤላው ነው። የደቡቡ ጠላት ኦሮሞ፣ አማራ፣ ሱማለው፣ ጋንቤላው፣ አፋሩ ነው ……. ይሉናል።  በሰላምና በፍቅር ይኖር የነበረውን ህዝብ በጠላትነት እየሰየሙ ባሰመሩት የሞት መስመር ውስጥ እንዲገቡ በማድረግ ወዳጅ የነበሩት ህዝቦች እና አንድ የነበረውን ህዝብ እንደ ጠላት እንዲተያዩ  የሚያደርግ  የጠንቋይ ፖለቲካ አካሄድ ነው።

ውሸት ሲበዛ ተደጋግሞም ሲነገር እውነት ይሆናል ብለው የሚያምኑ ሰዎች የጠንቋይ ፖለቲካቸውን ሲነግሩት ምንም በማያውቀውን ህብረተሰብ ላይ ብዝታን መፍጠሩ አይቀሬ ነው። በአሁኑ ሰዓት እውነት ዝምታን መምረጥ የለበትም። ዝምታ መልስ በማይሆንበት ቦታ ላይ የግድ መናገር ያስፈልጋል። እውነትን እየሻሩ በምትኩ ውሸትን የሆነውን የጠንቋይን ፖለቲካ በአንድም በሌላም ሁኔታ ለህብረተሰቡ እየተሰበከለት ባለበት  ሁኔታ እውነተኞች ዝምታ ከቶውኑ መልስ ሊሆን አይችልም። እውነትን እና እውነተኞችን እያጠፉ ሃሰት  እና ሃሰተኞችን በተለያየ መድረክ አግዝፎ መናገር ምን ያህል ከባድ ግዜ ላይ እንደደረስን የሚያሳይ ነውና ያልነቃህ ንቃ የተኛህም ተነሳ እውነትን ይዘህ ዝምታ ይብቃ። በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ አንድ ህብረተሰብ በሌላው ህብረተሰብ ላይ ጠላት ሆኖ የተነሳበት ወይንም ለመጠፋፋት የሞከሩበት ግዜ የለም። የጠንቋይ ፖለቲካ አራማጆች እንደሚሉት አንዱ ህብረተሰብ ሌላውን ህብረተሰብ የማጥፋት ፍላጎት ኖሮት ቢሆን ኖሮ ዛሬ ኢትዮጵያ  ውስጥ ከሰማኒያ በላይ ቋንቋ ተናጋሪ ሊገኝ ባልቻለ  ነበረ መላው ኢትዮጵያዊ አንድ ቁንቋ አንድ እምነት አንድ ዘር ሆኖ በቀረ ነበረ። ነገር ግን የሚታየው እውነት ግን የጠንቋይ ፖለቲከኞች አራማጆች እንደሚሉት ስላልሆነ እውነቱ ሊገለጽ በሰፊውም ሊነገር ይገባል። የጠንቋይ ፖለቲካ አራማጆች በሙሉ ላደረሱት ጉዳትም  በህግ ሊጠየቁ ይገባል።

ግዜው ወሳኝ የትግል ሰዓት ላይ አድርሶናል። ስንዴው ከገለባው እውነተኛው ከሃሰተኛው የሚለይበት ግዜ ላይ ነን። ጣልያን ኢትዮጵያን መውረር በምትፈልግበት ግዜ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ ስትደርስ ዋና ዋና የተባሉትን ሰዎች በአደባባይ በመግደል ህዝቡ ፈርቶ ይገዛልኛል በሚል ህሳቤ አረመኔአዊ ድርጊት በንጹሃን እና በጀግኖች ኢትዮጵያዊያን ላይ በአደባባይ በመፈጸም እንዳሰቡት ሳይሆን ጭራሽ በመላው ህዝብ መሃል ቁጣና እልህ ተቀጣጠለ። በኢትዮጵያን መሃል ባንዳዎችን መልምለው የክብር ሊሻን በመሸለም የኢትዮጵያን ህዝብ ለማሸማቀቅ ቢሞክሩም ጣልያንም ድረስ ወስደው የስልጣን ካባ በመደረብ አሞግሰው ህዝባችንን እንዲሰልሉላቸው በመላክ መረጃዎችን ቢያገኝም የኢትዮጵያኑን ጀግንነት ግን ሊቋቋሙት ባለመቻላቸው ከሽንፈት አላዳናቸውም።

አሁን የኢትዮጵያ ሁኔታ መጨረሻው ምዕራፍ ላይ እየተቃረብን ስለመጣ የጠንቋይ ፖለቲካ በኢትዮጵያ  ውስጥ መቀበሪያው አፋፍ ላይ መድረሱን ምልክቶች እየታዩ  ነው። እውነት በአደባባይ የሚነገርበት ሃሰትም በአደባባይ የሚገለጽበት ግዜ ተቃርቧል። ከአሁን በኋላ የተጀመረው ትግል ወደፊት እንጂ ወደኋላ የሚል የለም። የኢትዮጵያ እውነተኛ ታጋዮች እና የጠንቋይ ፖለቲካ አራማጆች ሁለት የትግል አምድ ተተክለዋል። አንዱ ሊወድቅ የተቃረበው ሌላው  በጽናት ሊቆም የተቃረበው። ግዜው የምርጫ ነውና  በተግባር ተገልጾ የሚታይ ምርጫ። ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን በሰላም፣ በደስታ፣ በፍቅር ማኖር አልያም ኢትዮጵያን እያዘረፉ፣ እያበጣበጡ፣ እንዲኖሩ የመፍቀድ ምርጫ። ከዘላለም ባርነት ታግሎ ለራስ እና ለአገር ነጻነት የምናመጣበት ግዜው አሁን ነው።

ሞላ አስግዶም ከተወሰኑ ሰራዊቶች ጋር ከጠንቋይ ፖለቲካ አራማጆች ዘንድ ተቀላቀለ ተብሎ መነገሩ ምንም አይነት መረበሽን አይፈጥርም። ምክንያቱም ሰዓቱ የምርጫ ነውና ወይ ኢትዮጵያዊ መሆን አልያም የጠንቋይ ፖለቲካ ተከታይ መሆን ምርጫው ይሄ ነው። ምነዋ ጀነራል ከማል ገልቹ ሰራዊቶችን አስከትሎ  ወያኔን አልከዳም እንዴ። የአየር ኃይል አባላቶች ከተዋጊ ሄልኮፕተር ጋር ክደው አልሄዱም እንዴ ዛሬስ ወያኔ ውስጥ ያለው መከላከያ ሰራዊት አጋጣሚውን እየጠበቀ የጠንቋይ ፖለቲካ ጥለው በመውጣት ከኢትዮጵያ ታጋዮች ጋር በመሆን ትግሉን በአጭር ግዜ  ውስጥ የኢትዮጵያ የነጻነት ብስራት መንገሪያ የጠንቋይ ፖለቲካ መጥፊያ በጋራ እንደሚያደርሱት የማያውቅ ማንም ኢትዮጵያዊ የለም። ያኔ የጠንቋይ ፖለቲካ  አራማጆችን ማየት ነው  እውነት በነገሰበት ሃሰት ለመቆም ሃይል የለውምና ሁሌም ኢትዮጵያ እና ህዝቧ አሸናፊዎች ናቸው።

ከእንግዲህ ጥቂት ጥቅመኞች ለመጥቀም ተብሎ በሱማሌ አገር  የሚገደል ንጽህ የኢትዮጵያ ወታደር እንዳይኖር፣ ከእንግዲህ አገር ጥሎ  በመሰደድ በየበረሃው የሚሞት ወገን እንዳይኖር፣ በአረብ አገር በስቃይ እና በግፍ የሚገደሉ ወገኖች እንዳይኖሩ፣ ጥቂቶች ጠግበው ብዝኋኑ ተርበው የሚኖርበት አገር እንዳይኖረን፣ ታናሽ ታላቁን ታላቅ ታናሹን፣ ባለስልጣን ተራውን ተራውም ባለስልጣኑን በማክበር በህግ በመተዳደር የህግ የበላይነት ተከብሮ ማየት ከፈለግን…..ወታደር፣ አስተማሪ፣ ተማሪ፣ ገበሬ ፣ ሰራተኛ፣ ነጋዴ፣ ሴት፣ ወንድ፤ ሳንል ትግሉን በመቀላቀል በገጠር በከተማ፣ ከመሃል እስከ ዳር ተነስተን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ግዜ የጠንቋይ ፖለቲካን በኢትዮጵያ ምድር ማጥፋት ያለብን ግዜ አሁን ነው። የተጀመረው ትግል  ማንም ቢከዳ ታላላቅ ታጋዮችን ይዘው የፖለቲካ ስራ ቢሰሩባቸው የጠንቋይ ፖለቲካ የጣር ጩኽት ነውና ከእንግዲ በኋላ ወደ ኋላ ሳይሆን ወደ ፊት … ወደ ፊት… ወደ  ፊት… ነው።

ፍቅር እና እውነት የሰው ልጅን  ሁል ግዜ በነጻነት የሚያኖሩት ናቸው። ትግሉን በመደገፍ መሰናክሎችን በማስወገድ ህዝባችንን ከጠንቋይ ፖለቲካ ነጻ እናውጣ።

 

ከተማ ዋቅጅራ

19.09.2015

Email- waqjirak@yahoo.com

 

 

 

 

 

↧

አረማሞ (ሥርጉተ ሥላሴ )

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 19.09.2015 /ሲወዘርላንድ –  ዙሪክ/

እንዴት ናችሁ ቤቶች? ደህና ናችሁን? እኔ  እህታችሁ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ።

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ - ዙሪክ)

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

ዛሬ በጋዜጠኛ ደምስ በለጠ  ዙሪያ የሚሰጡ አስተያዬቶችን ለመግራት አባ ቅንይ ጸሐፊ አቶ ይገርም አለሙ „መፈራረጅ አይገባም“ ሲሉ ላቀረቡት የመከላከያ ጹሁፍ – መልስ መስጠት ግድ አለኝ። የማከብረወት እንደ ሃሳበወት ቢሆን መልካም ነበረ። ዘመቻው ገንቢ ቢሆን ኖሮ፣ አቅማቸው ብቁ ነው ዬሚቃወማቸው ተቋማት። ጠረባውን ለማስተናገድ። ነገር ግን የነጠረው የሂደት መስታውት ዬጉዞው ምርጫ አረማሞነት ክትር እንዲሰራለት – አላደረገውም። ሃቅን አላይህም ቢሉት፣ ህሊና ማንዘርዘሪያውን ይዞ – ያፋጥጣል። ተወደደም – ተጠላም፣ ተፈቀደም – አልተፈቀደም። የአቋም ልዩነትንና ዬአሰተሳሰብ ልዩነት ለሳይንሳዊ ተፈጥሯቸው ዕውቅና ለመስጠት – ከፈቀድን።

በቅድሚያ አረማሞ የነገር ሥምን ነው የሚወክለው። የዕሳቤ አረማሞ ለማለት ነው። አረማሞ ማለት እንደ ዘር ተዘርቶ በቅሎ – አስብሎ – በቁመናው – ያድጋል። ይጎለምሳል። ሸበላ ሆኖ ነው – ዬሚበቅለው። ውስጡ የሚገኘው እድገቱን ከጨረሰ በኋላ ነው። ለዚህም ነው እንደ አረም እድገቱን ሳይጨርስ ተነቅሎ – የማይጣለው። የመዳህኒተዓለም አስተምህሮ ተምሳሌን እንድናስተውለው ነው፤ የአምላካችን ረቂቅ ጥበቡ ከሊቅ እስከ ደቂቅ በትርጉም ነው – የተፈጠረው። አረማሞ በሽፉኑ ምንም ልዩነት ሳይኖር፣ ሽፋኑ ሲሸለቀቅ – እንደ ሌሎቹ  አፍርቷል ተብሎ ሲገለጥ የተቃጠለ የአፈር ዱቄት፣ የጭስ አቧራ፣ መሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ ጠረኑ ሆነ አጠቋቈሩ ሥም የለሽ ነው። አረማሞ ከየትኛውም የእህል ዘር ብቻ ሳይሆን፣ ከወገነ – ፅጽዋትም ለምሳሌ፣ ከእሳር ሆነ ከእንዶድ ሊፈጠር – ይችላል። አንድ የሚያደርጋቸው የአረማሞ ፍሬ የተቃጠለ፣ የተፈጬ የአፈር ጭስ፣ አቧራ መሆኑ ነው። እርእሱ ብቻውን pilar ሆኖ ዬብሄራዊ ነፃነታችን ቀበኛ ሆነ፣  ተቀናቃኝ ቂመኛ ዕሳቤዎች ውስጣዊ ጭብጥ፤ ተፈጥሯዊ ባህሪ ዙሪያ – ገብ ቀልቡን ግልጥ አድርጎ ያሳዬናል። ከአረማሞ ተፈጥሮ ጋር መደማመጥ – ከቻልን፤

በተረፈ ዬኔዎች – መቅደም የነበረባቸው ጹሁፍ ስለነበሩብኝ፣ ትንሽ የዘገየሁ ቢመስልም፣ ቁስሉ አሁንም ንፍርቅርቅ ብሎ ስለ ቀጠለ፣ በቅንነት ተነሳስተው በዚህ እርዕስ የማከብራቸው  ጸሐፊ አቶ ይገርም አለሙ የጻፋትን ግርም እያለኝ ነበር – ያነበብኩት፤ ከሥርም በአጭሩ የምለውን – ብያለሁ። በዝርዝር ግን ማህበራዊ ድህረ ገጽ ለይ ስለ ተለቀቀ፣ የግድ መታረቅ አለበት ሥራዬ ነው – ዘበኝነት። ዬፀሐፊ አቶ ይገርም አሉሙ ዬተነሱባቸው ጹሑፍ ….

  1. „ፐ!ፐ!ፐ! ኢትዮጵያ እንዴት ያለ ትንታግ ጋዜጠኛ አላት በል!“ August 31, 2015 ፀሐፊ ነፃነት ዘለቀ
  2. „ጽሁፍህ ወያኔ፣ ወያኔ ይሸታል” ይድረስ ለደምስ በለጠ September 2, 2015 ፀሐፊ ቢላል አበጋዝ፣ ዋሽግቶን ዲሲ
  3. ለእነኝህ ጹሑፎች መልስ ለመስጠት ነበር ፀሐፊ አቶ ይገርም አለሙ „መፈራረጅ ለምንም አይበጅ“  September 2, 2015 ዬፃፉት።

በዚህ አጋጣሚ በድካም ዕውቅና ያገኙ የትምህርት ደረጃዎች ጥሰት በግራ ቀኙ ግድፈት – አያለሁ። ይህም ሁላችነን ዬሚያስገምት ይመስለኛል። ብናርመው መልካም ነው። ስለዚህም ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ ጋዜጠኝነቱን በሥልጠና ነው ያገኘው። በጋዜጠኛ ደምስ በለጠ በኩልም የመጨረሻው እርከን ላይ የሚገኙት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፕሮፌሰር መሆናቸውን ሆን ብሎ በተደጋጋሚ ዶር. እያለ ነበር የገለጠው። ይህ ዓለምዓቀፍ ዕውቅና ያገኘ የዕውቀት የክብር ልዕቅና ሥያሜ ያልተገዛ ስለሆነ ተሞልቶ መገለጽ አለበት።

ማያያዣ

እህ – እጅግ በርካታ ግራሞቶች በሰንበት መታደሚያ ቤቴ ኢትዮ ሚዲያ በልኮንዳ ቤት ተግባር ቅርጥምጣሚዎችን፣ ቅንጥብጣቢዎችን በያይዶ በሚቀርበው በአቶ አንለይ ከበደ (ቤኒ) ደመ ነፍስ የቢዲዮ ቅንብር መማረኩ፣ በፍቅር  እብድ ማለቱ ለካንስ የፋሽስቱ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ቱባ ቱባ ባለስልጣኖች ዝክረ – ጀግንነት ሽሽት መሆኑ – አስተውዬበታለሁ። እንደ ነበረኝ አክብሮትም እግዚአብሄር ይማራችሁ እላለሁ። አያያዛችሁ – አላማረኝም፣ ዬተቀናላችሁ ሕዝባዊ ፍቅር እንዲህ በግፍ ከገፋችሁት፣ አንቴና ወደ ጠረን ብቻ እንዲያደርግ – ይገደዳል። እንደ ጣዖት ዬምታመልኩትን ቤተ – ነገዳችሁን የማዳን ጸጋችሁም ፉርሽ ሆነ። በሰሞናቱ ደስታችሁን የመቆጠብ አለመቻላችሁ አቅምም አቅልም ስስ መሆኑ፣ በእናንተ ላይ የነበረኝን ጽኑ እምነቴን ለዳጥ – ገበራችሁት። እግዚአብሄር – ይይላችሁ። መጠራጠርን ዘውድ ደፋችሁለት። ዬታሪክ አሻሮ እሮ – አሮ።

 http://www.ethiomedia.com/1000parts/7253.html “Now hailed as hero by Ethiopia, TPDM leader Molla Asgedom has been a TPLF implant for over one year, an official source said on Sunday.” የማከብራችሁ የኢትዮ ሚዲያ ቦርድ አባላት – የነፍስ ወከፍ ዬጥበብ ፍቅረኛ ሜዳ ላይ ዬሚታፈስ – መስሏችኋል። ቀረባችሁ። ልብ ያለው ሽብ። ቀን ጥሩ ነው የታጬቀ ገመና – ተዘክዝኳል። አቶ ሞላ አስገዶም ገለበጥኩ ብለው ተገልብጠዋል። እንዲህ ሲሉ „ህወሃትን አርጅታችኋል፣ ተተኪዎችን ወጣቶች አለን፣ በሙስናም በክታችኋል ሲሉ በአሽሙር ሾጥ አድርጓቸዋል። ስለ ልማታቸውም ኤርትራን ትራስ አድርገው ጎሸም” በማድረግ ቀዳዳ – በቀዳዳ። ከእንግዲህ በኋላ አቶ ሞላ አስገዶምን በሚዲያ ለማየት – ይቸግራል።

ውዴ አብርሽ ዬተመረጠ ለዚህ – ነበር። እንኳንም ዬአሉላ ዬአደራ ልጅ – ታሰረ። አሁን ነው ዬአዳኜ ሚስጢር – ዬታዬኝ።

በተረፈ ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ “ዬደምህቱ መሪ ሞላ አስገዶም ከትናንት በስትያ እስከ ዛሬ“ ሲል ለአዲስ አመት ውስጡን አሳይቶናል። እኔ እንደማስበው ብዕሩና ብራናው ብቻ ሳይሆን ከውጊያ ወረዳ ላይ ዬነበረው ዬልብ ማዳመጫ ይዞ ስለ ነበረ የተዋጊዎች ልብ ድም … ድም ሲል ልባቸውን – አስደምጦናል። ወንዳታ¡ የላስቤጋሳው ሰው አልባ ምርጥ ትራፊክ (navigation) „ … በዚህም የነፃነታቸውን  ብስራትና  የአዲሱን አመት ችቦ ኤርትራና ሱዳን ደንበር ላይ ተዋጊዎች በጥይት ለኮሱ።“  ነፃነት ኢትዮዽያ ስላለ ነው ዬሙያ አጋሮቹ እስር ቤት ዬወጣትነት ዘመናቸውን – የሚገብሩት። ማለፊያ ነው¡ ሚሊዎኖች በስጋት -በፍርሃት በባእታቸው የታፈኑት – ለጋዜጠኛው እንደ ዜጋ ለመታየት ማመልከቻ ማስገባት – አለባቸው። በህወሃት ፉሽስታዊ ሥርዓት ወይንም ፖለቲካ የምትመራው ኢትዮጵያ በእርሱ ግምት ነፃነት በገፍ የሰፈነባት መሆኑን በተደጋጋሚ አስረግጦ ነግሮናል። ይህው ነው የጉዳዩ – አስኳል።

አስኳል።

የማከብረወት ጸሐፊ አቶ ይገርም ሃሳብን ለማስታረቅ የፈቀዱትን የአሸማጋይነት ተግባር – አከብራለሁ። ይህ ማለት ግን የእርሰዎን ዕይታ እሸምታለሁ ወይንም እሸከማለሁ ማለት አይደለም። እኔም በቅንነት መንገዱን “ውስጤ” በሚል ሂጀበት ነበር። ለማንኛውም መረጃ አቅርቡና ተሟገቱ ስላሉ፣ ፍላጎተዎት ተንጠልጥሎ እንዳይቀር – ትንሽ ልል ፈለግሁኝ። አውራንባ ታይምስ አዘጋጅ ቤተ – ትግራይ ስለሆነ ነው የተወገዘው ወይንስ ወጣት ጆዋር ቤተ – ኦሮሞ? ድፍረት ይኑረን፣ የምናከብራቸው ወንድሞቻችን ሆነ እህቶቻችን ለግድፈታቸው ጥብቅና መቆሙ መጠን ሊኖረው – ይገባል። ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ ሰብዕናውን ሳንነካ ከእኛ ጠረን በፍጹም ሁኔታ እዬራቀ ዬሄደውን የሃሳብ ጉዞውን ልንጸዬፈው – ይገባል። የእኔ ስለሆነ ብቻ ይህን ያህል በሙሉ ትጥቅ ተስፋን ሲያደቅ ታከብረው ከነበረ እህቱ የብዕር ጦር – ይታዘዛል። ይህ ዬነሲብ ትረካው ለአቶ ወንድም ከነበረኝ ግንዛቤ ጋር – ተጣላ።

የማከብረወት – ለመሆኑ በጠላት ወረዳ ተገኝቶ ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ የሰጣቸውን ሦስት ቃለ ምልልሶችን – አዳምጠዋል? ትጥቁን የፈታው ከማን ጋር? የትኛው ቤት? አለማለቱ ብቻ ሳይሆን፣ ከ95 ሚሊዮን ሕዝብ ስቃይ በእጅጉ እርቆ ነው ያዬሁት። መማሩ እራሱ አሳዘነኝ፣ በህዝብ ስቃይ ዘመቻ ነው ዬተያያዘው። ሰፋ – አላለም። ለእኔ ዕንባ የማበስ አቅም የላቸውም – ጹሁፎቹ። ለዕንባዬ  እርቅ ያላደረገ – ጥንቃቄ የጎደለው የቂም ኩትኩት። ጠብታ ለዕንባዬ ማስታገሻ ዬለውም። ይዘረገፋል ያለው ገመና ዬትረካ ባህሬ ከማያዙ በሰተቀር ካሴቱ ገልብጦ – ተገልብጦ – ተገለባብጦም ጭብጡ ከሌሎች ከሰማናቸው ውጪ፣ የመረጃ ጥማትን ረጠብ የማድረግ፣ ተጽእኖ ዬመፍጠር፣ መንፈስን ዬመግዛት አቅሙ ጥግ ስላላገኜ ስደት ጠይቋል።

ሁለት ዘለላዎችን ላንሳ፣ አደኛው „ገመና እዘረግፋለሁ“ አለ፣ ቁምጥ አሉ የህወሃት ደጋፊዎች፣  እውነቱን ለማወቅ የሚሹም ቅኖች ጠበቁ። እንደ የሰለጠነ  (professional )ጋዜጠኛ በቪዲዮዎ፣ በቃል መቅጃ፣ በተደራጀ የፎቶ ቅንብር፣ ሲጠበቅ ክፍል አንድ ተጀምሮ ክፍል ሁለት ተዘሎ ክፍል ሦስት ቀረበ። ከዛ በኋላ በክፍል መጀመሩን መዝለሉ ብቻ ሳይሆን የጹሁፍን ተካታይ ባህሪ ውልብሊቢቱን በመያዝ በጭብጡ ማእከል ዙሪያ ለመከተም – አልተቻለም። የሆነ ሆኖ የጀግና አንዳርጋቸው ጽጌ ጠለፉ የሀገር ጥቃት ነበር። በህወሃት ዬተቆራረጡ ቪዲዎች ዬወገኖቻችን ዬሰቆቃ ድምጽ እንኳንስ ለእኛ፣ ሰውን ለመተረጎመ ፍጡር መራር ነበር። ያን ጊዜ ዬት ነበር? እኛ የማናውቀው መረጃ 2014 በስቃያችን ውስጥ ሳይኖር ዬምናውቀውን ለእኛ መልሶ ይነግረናል። እምንጠብቀው የተመላለሰትን ወደ ኤርትራ „ገመና“ ያለውን ነበር። ማጣፊያ አጠረ …

ሁለተኛው በመጨረሻ ምን ትላለህ? ተብሎ ሲጠዬቅ እዬተሳለቀ „መሪያችሁን ሂድ ወደ ወንዶቹ በሉት። ወኔ ከኖረው „ ነበር ያለው። በዚህ ፈጣሪ አምላካችን የመጀመሪያ ሰው አድርጎ የፈጠረው አዳምን ነው ያላገጠበት። አዳምን ሲፈጥረው አሳስቶ – አልነበረም። አዳም ወንድ ሆኖ ነው – የተፈጠረው። ተባእት ሁናችሁ የተፈጠራችሁት እራሳችሁን ፈትሹ – በአክብሮት፤ ህመሙን ልቡን ታገኙታላችሁ። ይህ ሽቅብታ የፈላስማውን ማስተር ፒስ የሊወናርዶ ዳቬንች የአዳምና የፈጣሪው መንፈስ እስኪ ጉግል አድርጉና ተመልከቱት – በትህትና። ፍጹም አምላክ በፍጽምና ስልጣኑ የፈጠረውን የወንድነት ረቂቅ ተፈጥሮ የደፈረ ነበር የቃለ ምልልሱ  – እድምታ።። በስማ በለው ሳይሆን ቁጭ ብዬ ነው – ያዳመጥኩት። ወንድም ላለው፣ አጎት ላለው፣ የትዳር አጋር ላላት አንስት ሁሉ ዬምጥ ቀን ነበር። ከዚህም ሌላም ማንሳት ይቻላል። ጫካ ጥርሱን የነቀለበት ስለመሆኑ – ያላገናዘበ ነበር። ፕሮፌሰር ዶር. ብርሃኑ ነጋ (ሥህነ – ቤዛ) በቅጡ 17 ዓመት አልሞላው ዱር ቤቴ ሲል። እንዲሁም ፕሮፌሰር ዶር ብርሃኑ ነጋ ዓለምዓቀፋዊ ትንፋሽ፣ አኽጉራዊ የሩህ መናህሪያ ቀለማም መዲና በሆነችው በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያው በህዝብ ፈቃድ የተመረጠን „ቀበቶ የለውም“ ብሎ መሳለቅ ያን የህዝብ ድምጽ መናቅም – መጠቅጠቅም ነው።

ሌላው አንድ ዬፖለቲካ ድርጅት ሆነ ንቅናቄ ከፕሮግራምና ከደንቡ ተነስቶ መረህ – ግብር አለው። ጊዜውን የሚተምነው፣ ዬሰው ኃይል እንደ ወቅቱ የሚያሰማራው በመርኻ ግብሩ ነው። ይህ ማለት ትጥቅን የመረጠው ፕሮግራሙን ያጸደቀ ዕለት ነው። ያልተገባ ዘለፋው ለዛውም ለመሥራቹ – ለቀባሪው አረዱት ነበር። የንቅናቄው መሪ ጋዜጠኛ ደምስ ስላባጨለው አልነበረም „የሚታዩ ነገሮች ለማምጣት የማይታዩ ነገሮችን መሥራትን ይጠይቃል“ „ ከእንግዲህ ሰው ሰብስቤ ማነጋገር ላቆም ነው“ ዬአርበኝነቱ መንገድ ጠራጊ መርህ ነበር። ይሄን እንደ አንድ ከፍተኛ ሙሁር አቶ ወንድም ለመተንተን ሆነ አስቀድሞም ለመተንበይ አቅም – አልነበረው። ይህ ቅላፄ የማን ትንፋሽ እንደሆነ ከህሊናው ጋር ለሚኖረው ነፃነት ፈላጊ አሳምሮ ያውቀዋል። ስለዚህም ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ ዬማን አምሳያ ነው? በማን ቁስል ነው የሚረማመደው? ዕንባን እዬረገጠ ወይንስ እዬጠረገ? ለዚህም ነው የግንዛቤ ወለምታው ራቁቱን የሆነው።

ስለዬትኛው ዬህግ እረገጣ ነው ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ ዬፃፈው? ዛሬ እስር ቤት ውስጥ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እንዲገለል ብቻ ሳይሆን አንድ ጆሮው ተደፍኖ ዬዱካ ማስቀመጫ – ተክልክሏል። ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በጽንሱ እስር ቤት ከነበረው አንድያ ልጁ ትዳሩ መለየት አልበቃ ብሎ፣ መጽናኛውን ቅዱሱን መጸሐፍ – ተነጥቋል። ጋዜጠኛ ውብሸት ታየ በእንኩላሊት በሽታ እዬተሰቃዬ ከአንድያ ልጁ ከትዳሩ ተለይቶ ለዛውም ቤተሰቦቹ የረባ መተዳደሪያ – የላቸውም። መምህርና ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ በምን ስቃይ ሁኔታ እንደ ነበረች – ይታወቃል። ሲፈቷት በቁም እስር ስለመሆኑ የአፓርታይድ አግናባት ጨለማዊ የአያያዝ ሁኔታ ሰሞኑን እሷንና የነገን ተስፋ በሰነቅኩበት ጹሑፏ – ተረድቻለሁ። መምህርና ጋዜጠኛ አብርሃም ደስታ ስንቅ አቀባይ አልባ ከቤተሰቦቹ ተነጥሎ – በሥነ ልቦናው ሳይቀር ልዮ ደባ እየተደረገበት ነው።። ዬዞን ዘጠኝ ቤተሰቦች ወጣትነታቸውን ሲነጠቁ ምን አለ? ምን ተናገረ? ምን ፃፈ? ሊያስረዱኝ ይችላሉ ጸሐፊ ይገርም አለሙ – በትህትና?

የእስልምና እምነት አቨው አስታራቂ ሽማግሌዎች መፍትሄ አመንጭዎች በግፍ ሲታሰሩ፣ ፍፁም ልዩ የሆነ የሰላማዊ ትግል ለእኛ ዬማርቲን ሉተር የትግል ተመክሮ – ሰልጥኖና ደምቆ ትዕይንቱ – ሲታይ፣ ዬት ነበሩ የአቶ ወንድም ብዕርና ብራና? ማገዶዎች የአንድነት፣ የሰማያዊ፣ የመኢህድ መሪዎች ሲታሰሩ (አቶ አንዱአለም፣ አቶ ናትናኤል መኮነን፣ አቶ ሃብታሙ አያሌው፣ አቶ ዳንኤል ሺበሺ) እንዲሁም ሺዎች ሁሉንም የመስዋእትነት መፈተኛ ዬሆኑለት አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ብሄራዊ ፓርቲ በትእቢት በህወሃት ሲፈርስ የብዕሩ ትንፋሽ ለመሆኑ የት ነበረች? የሰላማዊ ትግል ደቀ መዝሙር እንደሆነ እየነገረን ነው፣ አራባና ቆቦ የሆነ ነገር፣

ለመሆኑ የብዕሩ ባዕት ዬትኛው ፕላኔት ነው – ያለችው? የወያኔ ሃርነት ትግራይ ዞጋዊ አስተዳደር የ2007 ምርጫ በደም ተለውሶ ሲያላግጥ፣ የደም ዋጋ ሥጋና ደሞቻችን ሲከፍሉ፤ በህዝብ ዕንባ ሲጬፈር፣ ከቶ ለአቶ ወንድም የሰርግ ቅልቅል ሆኖለት ይሆን? የሰማያዊ መሪ ኢንጂነር ይልቃል ስንት ጊዜ ታሰሩ – ተፈቱ? የአንቦ ወጣቶች የነገ የኢትዮዽያ ተስፋዎች ባሩድ ሲበላቸ – ሺዎች የውቅያኖስ ስንቅ ሲሆኑ – ሳውዲ ላይ እህቱ በሰባት እንሰሳ ተደፍራ ሰንደቋን እንደ ለበሰች ድፍት ስትል – ደቡብ አፍሪካ ላይ ወንድሞቹ ሲቃጠሉ – ሲነዱ – የሥጋቸው ጥብስ ሽታ ለብዕሩ ለምን ራቀ? የእርሱ ብዕር ዬአርበኞች ትግል ለመፍለጥ ብቻ ነው የተፈጠረችውን? ይንገሩኝ አቶ ይገርም …

ከነማተባቸው ሊቢያ ላይ ሰማዕትነት በኢትዮጵያዊ – ዜግነት ሲደምቅ ሃዘንተኛ በጠገበ አጋዚ – ሲወቃ፤ የዘመናት ዬትውፊት – ታሪክ ዬማተብ አውደ ምህረት ቅዱስ ዋልድባ አብረንታንት – ስቋር ገዳማት ሲደፈሩ፣ ቅዱሳኑ ሲደበደቡ፣ ሲገፈተሩ፣ ከአርምሞ ቤታቸው ሲነቀሉ፣ የሰለጠነው ጋዜጠኛ  (professional journalist ) የወንድም ደምስ በለጠ ብራና ሃኪም ቤት ወይንስ ጫጉላ ቤት? ወይንስ ኮማ ላይ ነበረችን?

ዬኮፐን ሃገኑ ዬድል ጎመራ ዕለቱ 2014 በዓለም ዙሪያ በፍሰሃ – ሲናኝ፣ ዬሴቶች ቀንዲል ዬንግስት ጣይቱ፣ ምንቴ፣ ዘውዴ ልጆች  በአጋዚ ቆመጥ ተቀጥቅጠው ወደ እስር ሲጋዙ፣  እስር ቤት ለሴቶች ካቴና ብቻ – አይጠብቃቸውም፣ ብዕር ሊያው ዬማይችለው፣  ዓለምም ዬማያውቀው፣ የዘለዓለም የመንፈስ ግዞት ይጠብቃቸዋል። ከእስር ሲለቀቁ ኢትዮዽያን ቢለቁ እንኳን ተልጦ መጣል – አይቻልም። እነኝህን መከረኞች በሆነ ባልሆነው ቁሙ ተቀመጡ ሲባሉ፣ ሳስብ ምነው አምላኬ በህልማቸው እንኳን ብትነግራቸው እላለሁ። እንደ ሰው መቆማቸው በእሱ በባለቤቱ ታምር ብቻ ነው። ወላጆቻቸው እራሱ ሊያውቁት አይችሉም፣ ታዲያ በዚህ ዙሪያ ቂም አምራች ብዕሩ ምነው እስከዛሬ ለፋሽስት መሞከሪያ ፆታዊ ማንነት በሚመለከት ዝምታን መረጠ? ረመጥ …

ቁስሌና ውስጤ ዬዬኔሰው ገብሬ ሰማእትነት – ተረሳ፣ ዬትዳር አጋርሽ መሳሪያ ደብቋል ተብላ ዬባለቤቷን ዬዘር ማፍርያ ባደገችበት ባዕት በጥርሷ እንድትጎትት – ሲደረግ፣ ዓለምን የማያውቀው ዕንቡጥ ሞት – ሲፈረድበት፣ ከእህል ጋር ለመገናኘት ቅኖችን ወገኖቿ ሁሉ በተሳነን አሳንጋላ ወቅት ምን ሲል – ተደመጠ? ጋዜጠኛው ለምን ገለልተኛ ሆነ? ነፍሰጡሯ ታጋይ ወይንሸት ሞላ መርዝ – ስትወጋ፣ በነጋ በመሼ ቁጥር ካቴና ስንቋ ሲሆን፣ እሱ ለደላዉ የህወሓት ካድሬ ለአቶ ሄኖክ ሰማእግዚር ጥብቅና ቆሞ አዬነው፣ ያ አልበቃው ብሎ ለአንድ ካህዲ የትግራይ ህዝብን ክብር ዬቀነሰ የአቶ ሞላ አስገዶም ፈን ሆኖ – ተገኘ፣

ያ … ብቁ ጀግና ካፒቴን ሃይለመድህን አበራ ሁለት መቶ ሁለት ነፍስን የታደገ፣ ዬሀገሩን ክብር ደም – ሳያጋባ፣ በሙሉ ጀግንነት ሲዊዘርላንድ ጄኔባ በድል ሲገባ፣ ሰው አልባው ትራፊኩ ለእሱ ለምን አልሰራም? ልክ እንደ አቶ ሞላ አስገዶም ስለምን መልካም አልተመኘም? በርካታ ጋዜጠኞች የዓለሞቹ ሳይቀር የእውነት አርበኛ ጋዜጠኞች ያደነቁት የሁሉ ነገር አብነትና ሞዴል ታናሹ ጀግንነትን ሲያደምቅ ለምን ድፍረቱ የእንቧይ ካብ ሆነ? ከዛ በኋላ ስንት የአውሮፕላን አደጋ ገጠመ? በእነ አንድርያስ ሉቢስ Andreas Lubitz በ2015 የጀርመን ዊንግ ረዳት አብራሪ ሆነ የማላዢያውን ጀርመን ለተሳፋሪዎች ለያንዳዳቸው ካሳውን እስከ 50.000 ሃምሳ ሺህ ኢሮ ለተጎዱ ቤተሰቦች ከፈለች  – የሦስት ሳምንት የፈረንሳይ፣ የጀርመን፣ የስፔን የወል የሌትና ቀን ዘመቻ ጠቅላላ ወጪ – ሳይጨምር። ሰቀቀኑ እጅግ መራራ ነበር፣ የእኛ ብልህ ግን ከሁሉም ነገር ያዳነ የጀግኖች ቁንጮ ሆኖ ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ  „ወንድሜ ሞላ አስገዶም አንተም ሆንክ አብረውህ ያሉ ተዋጊዎች፣ እንኳን ከሻብያ ገሃነም ወጣችሁ። ለነፃነት በቃችሁ። አዲሱ አመት የሰላም እንዲሆንላችሁ ምኞቴ ነው። እግዚአብሄር የምታስቡትን ሁሉ ያሟላላችሁ ዘንድ እፀልያለሁ“ ሲል በተማህጽኖ ደጅ ጥናቱን – አሳየን። ኢትዮጵያ ገነት ሆናለች ይለናል – ተረበኛው አቶ ወንድም — ሎቱ ስብሃት ነው።

ከቶ ዬት ነበር ይህ ሰው? ዬእኛ ነው ወይንስ ዬሌላ? ለማን ነው ዬቆመው? ሊለምኑ ያፈሩ ሚሊዎኖች ናቸው። ትራፊ እንዲኖር ዬሚማጸኑት ሚሊዎን ልጆቻችን ድልድዬ – ጉድጓድ ውስጥ የሚኖሩ ሺዎች ናቸው። ትምህርት – ህክምና – መጠለያ ያጡ ሚሊዎኖች ናቸው። መሬታቸው ተሽጦ – አልቋል። ዕዳው ለዘመነኞች-  መዳነሻ፣ የነገ የፈተና ዳገት ነው። ይህ ሥም ዬለሽ ህመም ለጋዜጠኛ ደምስ በለጠ የህሊና ሰሌዳ ባዕድ ነው።  እኛ አይደለነም እራሱ የመረጠው መንገድ ነው። —- ተግባቶ? አቶ ይገርም።

እንደ ጦር ልክ እንደ ወያኔ ሃርነት ትግራይ የሚፈራው ደግሞ ኢሳትን ሲሆን፣ ይህ ከሚሊዮኖች መንፈስ ጋር መጣላት ነው። የኢሳት ቲ ሸርት የለበሰ ያንገበግበዋል – ለምን? የሚገርመው በአሁኑ ፁሁፍ „ለመጀመሪያ ጊዜ ኢሳት ሰበር ዜና እውነቱን ሲናገር“ አለ። ጠቅላላ ሁኔታው – ሆድ እቃው – አሮጌ ቆረንጮ ሆኖ ነው ያገኘሁት። ኢሳት እኮ የመጀመሪያው አፍሪካዊ – ኢትዮጵያዊ – ዓለማቀፋዊ ሚዲያ ነው። ለአፍሪካ ሀገሮች ዬሚዲያ ታሪክ በስደት ሀገር ዬአብነት አዲስ መዲና ነው። ኢሳት ዬሚሊዎኖች ነው። በታሪካችን ወላዊ ተስፋችን ያበራ ህሊናች ነው። ከስድስት ኮሮች በላይ የፀሐይ ጉልበት ያለው ዬጥራት የጥረት ዓውዳችን። ኢሳት ዬእሱን ሃላፊነት መከራውን ሁሉ ታግሶ ስለተወጣ በቅናት ተጠምዶ ምን – ያሳብደዋል? ሲሆን በሙያው ሊረዳ የሚችልበትን ትብብር ማሰናዳት ሲገባው፣ ዬታላቋ ትግራይ አረማሞ ቡቃያ ዕሳቤ ማዳበሪያ መሆን ምን – ይሉታል? ከቻለም አማራጮችን ዘርግቶ ክፍተት ነው በሚለው ቦታ ላይ መትጋት – ይችላል። ከሁሉ በላይ ሲያከብሩት ለነበሩት መንፈሶች ሁሉ ዬማይጠነቀቀው ለምንድን ነው? ስለምንስ አስተውሎ – አይራመድም? የትምህርት ጸጋ – ዕድሜ ዬሚለግሱትን ሥነ – ምግባሮች ለማዳመጥ ስለምን ቀና አይሆንም?

ጥላቻ ዬጎረሰ ዘመቻው በአርበኞች ግንቦት፣  ዬሚያወርደው ናዳ የፖለቲካ ድርጅቶችን የመመስረት ሙሉ ዓለምዓቀፍ ነፃነትን ይጋፋል። ህልውናቸውን እንዲህ መፈታተን ዬፍልስፍናው – ዬዶክትሪን እጥረት ያለበትም – ይመስለኛል። አሁንም አቅሙ ካለ ማን ከለከለ? መብት ነው -ነፃነት ነው። ጀምሮ ማዬት – ማሳዬት። ደጋፊ – አይገዛም። የዓላማ ብቃትና ተፅዕኖ ፈጣሪነት ነው ፍቅርን  ዬሚያሳፍስ። ለተደማጭነት በጥላቻ የበከተ ዘመቻ ሳይሆን – ተግባርን ጨበጥ ያደረገ ዬትእግስት ሰጋር በቅሎ። መጀመር አይደለም ቁም ነገሩ መጨረስ – ተጽዕኖ ከማሳደር አቅም ጋር መቀባትንም  – ይጠይቃል። ሌላው ደግሞ እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ መክሊት ይዞ ነው ዬሚወለደው፣ መክሊትን ያለማወቅ ችግርም ካለቦታ  – ይቀረቅራል። በሥነ – ምግባርም በሰብዕናም ዳጥ ያባዛል። ፖለቲካ የተርቲም ጉዳይ አይደለም። ፖለቲካ – ሳይንስ ፍልስፍና እና ጥበብ ነው። ንጹህ አዬሩ ማስተዋልና ሆደ ሰፊነት ይጠይቃል። የህዝብን ስሜት ውስጡ ነው።

የአዲሱን ትውልድ ብቃት – ፈሪነት።

ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ አዲሱን ትውልድ ብቃት እንደ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ፈርቶታል። አጋጣሚ ቢኖረው ሃብትሽን ለካቴና  እንደ ዳረገው ፋሽስቱ ወያኔ ሃርነት ትግራይ የአርበኞች ግንቦት የውጭ ሀገር ከፍተኛ መሪ አካሉ ወጣት አቶ እዮኤል ሙሉነህን እስር ቤት ነበረ – የሚከተው። ለእኔ ለዘመኑ የምርጥ – ምርጥ ንግግር ነበር። እጅግ ብቁ ነበር። የንግግር ህገ-ሥርዓት የአድማጭን ቀልብ ድንበር አልባ ገዝቶ፤ በውጤታማ አኃታዊ መንፈስ ማስከን አንድን ተናጋሪ ብቁ ያደርገዋል፤ ይህን ደግሞ ትንታጉ – ከውኖታል። አይደለም አዳራሽ ውስጥ ያለውን ኦዲየንስ ውጭ ያለውን ታዳሚ በፍቅር – በወኔ – በእውነት ዙሪያ የማሰባሰብ አቅሙ ዓፄ ነበር። የተነሳበት የጭብጥ አናት በሙሉ የተደማጭነት አቅም – ቋጭቶታል። እውነት ለመናገር ዕልፍ የነገ ተስፋዎች እሱን ባደረገኝ ስለሚሉ የመልካም ምሳሌ ለመሆን ያስቻለ ታሪካዊ ድንቅ ንግግር ነበር። ሰውን በድንበር አልቦሽ የፍጥረት አብይነት የተረጎመ መምህር ንግግር ነበር። „ሰው“ ማለት ኢትዮዽያዊ ብቻ አይደለም። ድንበር አልቦሽ ዓለም አቀፍ የፍጥረት ጠበቃዎች የተደራጁበት አመክንዮ ይሄው ሆኖ ለጋዜጠኛ ባእድ ሲሆን ሪህ ነው።

በነሲብ አይደለም የምናገረው – የንግግር ሥነ ጥበብን ንድፈ- ሃሳቡን ተምሬዋለሁ። በተጨማሪም የድምጽ ቃናን ውጪ ሀገር ኮርስ ወስጃለሁ። ጋዜጠኛ ደምስ ባለበት ከተማ በነፃነት ግብር ልቆ መታዬት ህመሙ – ሆኗል። እውነት ለመናገር ለዛውም ለጋዜጠኛ የሚበልጥ በቅሎ ማየት አለመፍቀድ የበሽታ ነው። ለምን ከእስር ተፈተህ? ለምን ተደማጭ ሆንክ ነው ቁጭ አድርጎ – ሲኮልም ያሳደረው። አስተማሪ ሊያስተምር፣ ሃኪም ሊያክም፣ ጋዜጠኛ ደግሞ ሊዘግብ – የህዝብን ስሜት ለመለካት ከማህበረሰቡ የተሳትፎ ዓውዶች መገኘት የተሰለጠነበት ሙያ ባህሪም – ተፈጥሮም ነው። አበባ ያዙልኝ ሆኖም – አያውቅ። እንዲህ የሚጸጽተው ከሆነ ማመልከቻ ያስገባለት – የለም። በወቅቱ መቅረት ይችል ነበር። በጸጸት ቁርሾ – ከአስር አመት በኋላ – ከሚባክን።

አቶ ወንድም በፋሽስት ወያኔ ሃርነት ትግራይ የታሰሩት የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችም ይሁን ግፉ ያሰደዳቸው ወጣት መሪዎቻችን አንደባታቸው አንገት አያስደፋነም „በምንም ተጀምሮ በምንም የተጠናቀቀው“ የአንተ መንፈስ የረበበት አቶ ሞላ አስገዶም ደጋግመህ ተመልከታቸው አንገት ያስደፋል – ሙጃ። የገረፍታ ምችን የሙጥኝ የምትለው ብዕርህ እራሷን ለመግለጥ – አሳፋሪውን ጋዜጣዊ መግለጫ የተለመደውን ልበ ወለድ ለመስራት ሙሽሽ አለች። ይልቅ ለአቶ ሞላ አስገዶም ትንሽ የጣት ጥፍር ቀለም ብትልክላቸው የአዲስ አመት ስጦታ ማሟሻ በሆነልህ ነበር። ለማንኛውም መልካም አዲስ ፍቅር ….

አሁን ወደ ቀደመው የአቶ ይገርም የማጠቃለያ ሙግቴ፣ ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ እንዲህ ትክን እያለ ኢሳት – አርበኛ ግንቦት ከሚል ወራሪው የህወሃት ጠ/ሚር ለኃይለማርያም ደስአለኝ በሚያደርሱት በደል ዙሪያ ሆነ የትልልፍ ተራጋጭ አንደበት ለመግራት  አይተጋም? ትንፋሽ ለማሰማት – ተሳነው? ባለሟልነቱን እያየን ስለሆን ጆሮ ዘንበል – ይባልለታል። ቢያንስ በደንበራችን ጉዳይ ብዕሩ ኮተት ብትል ምን አለ?

ቃል ሲተረትር የሚውሉት ለፌስ ቡኩ ጄኒራሉ ለዶር ቴወድሮስ አዳህኖም ለምን  – አይሰራበትም? ለልብ ወለድ የነሲብ ትረካ የአፃፃፍ ዘይቤው ለህወሃት የለበጣ ጉዞ ብጡል ነው¡። ኮከብ – ለኮከብም ግጥምጥም ብሎ እየታየ ነው። ፍቅር እስከ መቃብሩ – ከዘለቀ? አቀራረቡ በትረካም ይሁን ሆነ በተረት ትርትር ለመነካካት ምን – አስፈራው? አርበኞች ግንቦት፤ ኢሳት ስለምን ዬስጋቱ ምንጭ ሆኑ? ይሄ መፈተሽ – አለበት። በቅንነትና በንፁህ ህሊና ሆድ እቃው ዝርግፍግፍ ብሎ ላንመለስበት እልባት ማግኘት – አለበት። በነሲብና በግምት ሳይሆን ከፍሬ ነገሩ ጋር ፊት ለፊት በእውነት (fact ) መድረክ መጋጠም አለብን።

ክወና።

ብልሁ ኢሳት ልጆቹን ቀድሞ ወደ ኤርትራ መላኩ ብቻ ሳይሆን፤ ያገኘውን መረጃ በቁጠባ መያዙ፤ ለበስ አድርገው ቁስል ሲረግጡ ሃዘን ካልፈጠረላቸው ከዶር. አረጋይ በርኽ ጋር ያደረገው ቃለ- ምልልስ የስጋቱን ቂመኛ ትልም መፈናፈኛ እንዲያሳጣ – አድርጎታል። ይህ እውነትን ለማግኘት ለሚተጉ ሰዎች የመፍትሄ መንገድ ይመስለኛል። ቀደም ብሉ ከVOA ጋር የተደረገው ቃለ – ምልልስ ወገንተኝነቱ የአደባባይ ሲሳይ አድርጎልናል። በአጃቢነት የተሰለፋችሁ የመከረኛው ቤተሰቦች ልብ ይስጣችሁ – ፈጣሪዬ። እነሱም እንደ ካቦ ነው የሚያዮችሁ።

ወቅትን በማቅለል፣ በማዛል፤ በማግነን ወይንም በማሳጠር ሳይሆን፤ በብልህነት ዬምትገኘውን ብጣቂ መረጃ ዋጋ እንዲኖራት በማድረግ፤ ጥቅም ላይ እንዲውል በማድረግ እረገድ ዬፀበል ያህል መዳህኒት ነው። ብዙ ስጋቶችን ጥበቡ መልክ – አስይዞታል። ጥንቃቄ ያተርፋል እንጂ – አያከስርም። ብዙ ዬሚዲያ ተግባራት በአቶ ሞላ አስገዶም የተደረገው ቃለ ምልልስ ለለውጥ ፈላጊው ዬፖለቲክ ዬሥነ ልቦና ዬበላይነት ለእኛ – አትርፏል። አረማሞ ሆድ እቃዎች ካለ ሽፋን አደባባይ ስለዋሉ ዘመኑ የእኛ ነው፤ „አለ ነገር“ አቮላችን ከሆነ። አርበኛው ሻንበል በላይነህ „እንቢበል“ ሽልሞናል፤ እኔም የማከብረው መሪዬ የኢትዮዽያ አገር አድኑ ብሄራዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ (ሥህነ – ቤዛ) በግንቦት 2009 ፍራንክፈርት አማይን ለገላጭነት መጥቶ በነበረበት ጊዜ እርእሱ „እንቢበል“ የሚል ሥነ -ግጥም አቅርቤ ነበር። ለህትምት ከበቁትም መጸሐፍቶቼ በአንዱ አለ። መከረኛውም እንቢበል።  የአሻሮ መጠቅለያ – አትሁን። እንደ ክብርህ ዘመኑን – አንብበው። ውርደት ውርዴ – ለጉርድነት ነው። አንተ ግን የውርሰ – ጽናትን ጥቁር አንበሳን – ተከተል። ድሪቶ – ክፍልህ አይደለም። ሰንደቅን ለሚመራው ብቻ ልብህን ስጥ። ሙቀትህን “ለፍትህ” አርበኛ።

ክብሬ ዘሃበሻን አመስግኜ – ለናፍቆቶቼ የጹሑፌ ታዳሚዎች መሸቢያ ሳምንትን ተመኘሁ።

*ፎቶው ላይ ያለው ግጥም ዬእኔ ሃብት አይደለም።

ምንጭ http://ecadforum.com/Amharic/archives/15560/

http://ecadforum.com/Amharic/archives/15559/

http://ecadforum.com/Amharic/archives/15555/

 

ለእኔስ ሰው መሆኔ ብቻ ይበቃኛል።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ። ኑሩልኝ።

 

 

↧

አስመራ የገቡት አቶ ነአምን ዘለቀ በሚኒሶታው የአርበኞች ግንቦት 7 ገቢ ማሰባሰቢያ ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ

$
0
0

neamin zeleke zehabesha

(ዘ-ሐበሻ) ለአርበኞች ግንቦት 7 የሚደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ በቀጠሉበት በዚህ ወቅት በሚኒሶታም የፊታችን ኦክቶበር 17, 2015 ዓ.ም እንደሚካሄድ አስተባባሪዎቹ ለዘ-ሐበሻ ገለጹ::

በሚኒሶታ የአርበኞች ግንቦት 7 የገቢ አሰባሳቢ አስተባባሪ ኮሚቴ ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫው እንዳስታወቀው አቶ ነአምን ዘለቀ ከአስመራ መልስ በሚኒሶታው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ ይገኛሉ:: ኦክቶበር 17 ቅዳሜ ከቀኑ 3:00 ሰዓት ጀምሮ በሚደረገው በዚህ የገቢ ማሰባሰብ ዝግጅት ላይ ከአቶ ነአምን በተጨማሪም ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች እንደሚኖሩ አስተባባሪው አስታውቋል::

አቶ ነአምን ዘለቀ የአስመራ ቆይታቸውን በዚህ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ እንደሚያካፍሉ በርካታ ሕዝብ ተስፋ እንዳለው ይጠበቃል:: ስብሰባው የሚደረግበት አድራሻን እና ቦታን ለማወቅ አዘጋጅ ኮሚቴው ለዘ-ሐበሻ የላከውን በራሪ ወረቀት ይመልከቱ::

↧

በተከታዮቹ 5 ስቴቶች ውስጥ የምትኖሩ፤ የስቴት የመንጃ ፈቃድ ከስቴት ስቴት በአውሮፕላን እንዳትበሩ ምክንያት ሊሆናችሁ ነው

$
0
0

Close up of thief's hand in black glove stealing driver's license, studio shot. Image shot 2012. Exact date unknown.

(ዘሐበሻ) በሕዝብ ብዛት የዓለማችን ሦስተኛ ሃገር የሆነችው አሜሪካ ከ322 መቶ ሚሊዮን ሕዝቦቿ ውስጥ 38% የሚሆኑት ፓስፖርት የላቸውም:: ታዲያ ሰሞኑን ትራቭል ኤንድ ሌዠር የተሰኘው ድረገጽ ያወጣው መረጃ ለነዚህ 38% ለሚሆኑት አሜሪካውያን ዱብ እዳ ነው::

ድረገጹ እንደሚለው ከሆነ አሜሪካ ካሏት ስቴቶች ውስጥ 5ቱ ስቴቶች የመኪና መንጃ ፈቃዳቸውን እንደ መታወቂያ የሚጠቀሙ ሰዎች በዚህ መታወቂያ ከዚህ ቀደም የትኛውም ስቴት በአውሮፕላን ሲበሩ ቆይተዋል:: ከ2016 ጀምሮ ግን ይህ የማይታሰብ ነው ይለናል – ድረ ገጹ::

“Driver’s licenses from New York, Louisiana, Minnesota, American Samoa, and New Hampshire will no longer be enough to get on a domestic commercial flight” ሲል ያስነበበን ድረገጹ የኒውዮርክ; የሉሲያና; የሚኒሶታ የአሜሪካን ሳሞአ እና የኒውሃምፕሻየር መንጃ ፈቃድ ያላቸው ሰዎች በአውሮፕላን ለመሳፈር አስቸጋሪ የሚሆኑት መታወቂያዎቹ የሆምላንድ ሴክዩሪቲን “REAL ID Act” ደረጃ አያሟሉም::

ይህ ሕግ በ2016 ሲጸድቅ ከላይ የተጠቀሱት ስቴቶች ውስጥ የሚኖሩት ወገኖች በአውሮፕላን ከስቴት ወደ ስቴት ለመዘዋወር ከመንጃፈቃድ የዘለለ መታወቂያ ያስፈልጋቸዋል:: ቀኑ አይወሰን እንጂ የስቴት መታወቂያ ይዞ አውሮፕላን ማረፊያ ለመሳፈር የሚሄድ ሰው ከመታወቂያ የዘለለ ፓስፖርት ወይም እንደ ግሪን ካርድ ያሉ መታወቂያዎችን ካልያዘ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዳይሳፈር አይከለከልም ሆኖም ግን የ3 ወር የይቅርታ ጊዜ ይሰጠውና በነዚህ ጊዜያቶች ውስጥ የሚጠየቀውን መታወቂያ ካላሟላ በአውሮፕላን መሳፈር አይችልም::

በነዚህ 5 ስቴቶች ውስጥ የምትኖሩ ወገኖች ሕጉ በ2016 ተግባራዊ ይሆናል ይባል እንጂ ቀኑ አልተገለጸም:: በመሆኑም ካሁኑ ተዘጋጁ::

↧
↧

በአያት ሁለት ኮንዶሚኒየም ያልተከደነ ቱቦ የሰው ሕይወት አጠፋ

$
0
0

(ሪፖርተር ጋዜጣ እንደዘገበው) በተለምዶ አያት አደባባይ እየተባለ በሚጠራው አያት ቁጥር ሁለት ኮንዶሚኒየም አካባቢ፣ ባልተከደነ ቱቦ ምክንያት የአራት ዓመት ሕፃን ሕይወት መስከረም 5 ቀን 2008 ዓ.ም. አለፈ፡፡
condominum hayat ethiopia
በአካባቢው በሚገኙት ኮንዶሚኒየም ቤቶች ውስጥ በአብዛኛው የሚኖሩት በመልሶ ማልማት ከአራት ኪሎና ከተለያዩ አካባቢዎች የተነሱ ነዋሪዎች ሲሆኑ፣ አደጋው የደረሰው ከእነዚህ መካከል አንዱ በሆኑት አቶ እንግዱ ዘለቀ ሕፃን ልጅ ላይ ነው፡፡

የሕፃኑ ሕይወት የተቀጠፈውም የቤቶቹ ግንባታ ባለመጠናቀቁና የተከፈቱ ቱቦዎች በመኖራቸው እንደሆነ ቤተሰቦቹ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የሟች ሕፃን አጐት አቶ አበበ ለውጠኝ ስለጉዳዩ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ፣ አካባቢው ለመኖሪያ በጣም አደገኛ እንደሆነና በየቦታው ተቆፍረው ያልተከደኑ ቱቦዎች በብዛት አሉ ብለዋል፡፡ ከእነዚህም አንዱ ሟች ሕፃን ኢዮብ እንግዱ የገባበት ቱቦ ሦስት ሜትር ጥልቀት እንዳለውና ከመኖሪያ ቤታቸው ጀርባ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡

ሕፃኑ ጠፋ ተብሎ ሲፈለግ ከቆየ ከአንድ ሰዓት ፍለጋ በኋላ ወደ ቤታቸው ሲመለሱ አስከሬኑ ቱቦው ውስጥ ተንሳፎ እንዳገኙትም ገልጸዋል፡፡

የሟች ሕፃን ወላጆች በድንጋጤ ምክንያት ሰውን ማናገር እንደማይችሉም አቶ አበበ አክለው ገልጸዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ የአካባቢው ኅብረተሰብ መስከረም 7 ቀን 2008 ዓ.ም. ሰላማዊ ሠልፍ ማድረጉን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ጉዳዩንም ፖሊስ ይዞታል፡፡ የሟች ሕፃን ኢዮብ የቀብር ሥነ ሥርዓት መስከረም 6 ቀን 2008 ዓ.ም. በአባ ኪሮስ ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል፡፡

↧

የአንዱዓለም ተፈራ የአገር አንድነት አስተሳሰብ እና  የቅማንት ህዝብ መፃኢ ዕጣ-ፈንታ

$
0
0

ከብርቱካን ወለቃ

eskemecheአንዱዓለም ተፈራ የሚባሉና የኢህአዴግንና የፌደራል ሥርዓቱን የሚቃወም ጹህፍ በ‹‹እስከመቸ›› የሚባል ድህረ-ገጽ የሚያዘጋጁ ‹‹ፀኃፊ››  በቅማንት ህዝብ ላይ ኢትዮሚዲያ ዶት ኮም (www.ethiomedia.com ) ላይ በተደጋጋሚ የሚለቋቸውን ፁህፎች ለመጀመሪያ ጊዜ ስመለከት እንደሌሎች ሁሉና በተለመደው መንገድ ግላዊ ስሜታቸውን ለማርካት የሞነጫጨሩት ስለመሰለኝ ምንም ነገር ሳልል ረዘም ላለ ጊዜ አልፌው ነበር፡፡ ጉዳዩ እየተደጋገመ ሲመጣ ግን ዝም ስለተባሉ ‹‹እትንን እትን ካላሉት—›› እንደሚባለው የሚሉትን ተግንዝቦ ሀይ የሚላቸው ሰው የሌለና እሳቸው የሚሉት ነገር ብቻ ትክክል የሆነ እንዳይመስላቸው ይህን መልስ ለመስጠት ተገድጃለሁ፡፡ እኝህ ግለሰብ በመጋቢት 21/2007 ‹‹የቅማንትን ክልል መመስረት በሦስት መንገዶች›› በሚል ርዕስና በነሀሴ ወር 2007 በዚሁ ድህረ-ገፅ ላይ ‹‹የማይለቀን የቅማንት ጉዳይ፤ ብለው ብለው ለአቤቱታ ወደእኛ መጡ›› በሚል ርዕስ ፅፈዋል፡፡ በዚህ ጸህፌ በመጀመሪያ በፃፉት ርዕሰ-ጉዳይ ላይ መልስ ይሆን ዘንድ ይህን አጭር ፁህፍ ለመፃፍ ተግድጃለሁ፡፡ እርግጥ ነው ለእንዲህ አይነት የወረደ አስተሳሰብ መልስ መስጠት ጊዜን ማባከንና እንደሳቸው ሀሳብ የወረደ ሊመስል ቢችልም ግለሰቡ ራሳቸውን አዋቂና የፖለቲካ ተንታኝ  አድርገው እንዳይመለከቱ መልስ  ለመጻፍ ተገድጃለሁ፡፡ በእርግጥ ለሁለተኛ ጊዜ በፃፉት መጣጥፍ ላይ እጅግ በሚምር ቋንቋ ተከሽኖ መልስ ተሰጥቷቿል፡፡ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ እኔም በቀጣይ የግሌን ሀሳብ እጨምራለሁ፡፡

ግለሰቡ ‹‹የቅማንትን ክልል መመስረት በሦስት መንገዶች›› በሚል ርዕስ የፃፉት ፁህፍ ማጠንጠኛው ጊዜ ባለፈበትና በ19ኛው ክ/ዘመን የፖለቲካ ርዮት ዓለም (political ideology: Establishing strong and united nation through putting multiethnic people together) ላይ የተቃኘ ለመሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡ ለእኝህ ግለሰብ የኢትዮጵያ አንድነት የሚረጋገጠው አንድ ህዝብ፣ አንድ ሀይማኖት፣ አንድ  ቋንቋ በሚለው የአፍሪካ አገሮች ከቅኝ ተገዥነት በ1960ዎቹ አካባቢ ነፃ ሲወጡ በመሬት ላይ የነበረውን ተጨባጭ ሁኔታ ሳይገነዘቡ ያራመዱት የነበረው አገር የመገንባት አስተሳሰብ ቀጥታ ነፀብራቅ ነው ማለት ይቻላል፡፡

እኝህ ግለሰብ አማራ እና ቅማንት የሚባል ህዝብ መኖሩን በራሳቸው አንድበነት ስለአንድ የጭልጋ አካባቢ ግለሰብ ሲያወሩ ‹‹በአባታቸው ከቅማንት በእናታቸው ደግሞ ከአማራ የተወለዱ ግለሰብ እንደሆኑ ይነግሩንና ከዚህ ግለሰብ የተወለዱት ልጆች ደገሞ የቅማንት ዝርያ ቢኖራቸውም የሚያደሉት ለዐማራነታቸው ነው›› ይላሉ፡፡ ይህን ካሉ በኋላ ቀጠል ያደርጉና  እንዲህ ይላሉ‹‹በእርግጥ ለእኔ ቅማንት ከአማራ የሚለየው በምንድነው?›› ብለው ራሳቸውን ይጠይቃሉ፡፡ ይሁን እንጅ አማራ የሚባለው ህዝብ ከቅማንት የሚለይበትን ምክንያት ፈፅመው ማወቅም ሆነ ጠይቆ መረዳትን አይሹም፡፡ ምክንያቱም ለእሳቸው በኢትዮጵያ የሚገኙ ሁሉም ህዝቦች በተለይ ደግሞ የአገው አካል የሆነው ቅማንት የአማራ ተቀጥላ እንጅ ራሱን የቻለ ህዝብ ነው ብሎ ማሰብ እጅግ ከመክበድም አልፎ የራሳቸውን ዘር ዝቅ ማድረግ መስሎ ይሰማቸዋል፡፡ ለእኝህ ግለሰብ በኢትዮጵያ የሚገኙ ህዝቦች በሙሉ መጤ ሲሆኑ ነገር ግን እራሳቸው ተገኘሁበት የሚሉት ህዝብ ግን ኢትዮጵያ የምትባልን ምድር ጠፍጥፈው የሰሩና በካስማ ወጥረው የዘረጉ ያክል ብቸኛ ባለመበት እንደሆኑ አድርገው ይቆጥራሉ፡፡ ‹‹ኦሮሞ ፣ቅማንት ትገሬ ፣ ሲዳማ፣አፋር ነኝ›› የሚል ህዝብ ካለ ደግመ ወደ ማዳጋስካር ወደ ግብፅ  ወደ የመን እንዲመለሱ ይመክራሉ፡፡

የአማራ ክልል ለምን እንደተቋቋመ ምንም ነገር ሳይተነፈሱ ‹‹የቅማንት ራስን በራስ ማስተዳደር በወያኔ/ኢህአዴግ/ የተጠነሰሰ አማራን የማዳከም ሴራ ነው›› ይሉናል፡፡ ለዚህ ግለሰብ ለእሱ መብት የሆነው ለሌላው ግን ወንጀል እንደሆነ ይነግሩናል፡፡ህወሀት በዚች አገር ከመምጣቱ በፊት የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እንዴት ሲኖሩ እንደነበር የኢትዮጵያ ህዝቦች ህያው ምስክር ናቸው፡፡  ቅማንት የሚባል ህዝብ በማንነቱ ምክንያት እንዴት እየተዋረደ፣ እየተሰደበ እንደኖረና በዚህም ምክንያት ቋንቋውንና ማንነቱን ረስቶ በደባል ማንነት ስር ሲርመጠመጥ እንደነበር ሊነግሩን አይመኙም፡፡ለእነሱ ያ በህዝብ ላይ ሲደርስ የነበረ ግፍ ኢትዮጵያ የምትባልን አገር አንድ ለማድረግ ስለነበር የተደረገው ሁሉ ትክክል ነበር፡፡  እነሱ ‹‹የደጉ ዘመን›› ብለው የሚጠሩት ዘመን ለአብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ የመከራ፣ የስቃይ፣ የግፍ ዘመን ነበር፡፡ ቋንቋቸው ከሰው ፊት እንዳይነገር ‹‹የወፍ ቋንቋ›› ሲባልና አማርኛ ለመናገር የሚኮላተፈው ሁሉ ገመድ አፍ፣ ተብታባ ሲባል እንደነበር ለእዚህ ግለሰብ አይገባውም፡፡

ቅማንት የሆነ ግለሰብም ይሁን ሌላ በዘሩ የተነሳ በነበረው ሥርዓት ተፅዕኖ ምክንያት ሆዱ እያወቀ ያለሆነውን ‹‹አማራ ነኝ›› ሲል እንደነበር ለዚህ ሰውየ መናገር ለቀባሪ ማርዳት ይሆናል፡፡ ሁሉም የሰው ልጅ በስላሴ ዓምላክ መፈጠሩ ተዘንግቶ ከእንጨትና ከእሬት የተገኘ ፍጡር በማድረግ ለዘመናት በማንነቱ ሲሸማቀቅ የነበረው ይህችን አገር አንድ ህዝብ አንድ ቋንቋ አንድ ሀይማኖት እያሉ ህዝቡን ረስተው ሲገዙት የነበሩ ገዥዎች እነማን እንደሆኑ ሊነግሩን አይፈልጉም፡፡ ለዚህ ግለሰብ ግን ያ ዘመን ሁሉም ህዝብ ተዋርዶ ገዥዎችና የዚያ ሥርዓት ደጋፊዎች የበላይ እንዲሆኑ የተደረገበት ዘመን  የአንድነትና የመልካም ዘመን ነበር፡፡ ራሳቸው የሚሰድቡትና ኢትዮጵያን ከፋፈለ ብለው የሚጠሩት የፌደራል ሥርዓትና የትግራይ ነፃ አውጭ ብለው የሚኮንኑት የፖለቲካ ድርጅት  ግን ሁሉም ኢትዮጵያዊ በእኩልነት ተከባብረው እንዲኖሩ መፍቀዱ ለእሳቸውና እሳቸው ለተገኙበት ህዝብ ትልቅ ስደብ እና ያን ‹‹ታላቅ›› የሚሉትን ህዝብ ያዋረደ ከሌሎች በእኩል አይን እንዲታይ ያደረገና ለኢትጵያ መፃኢ ዕድልም አደገኛ እንደሆነ ሳያሰልሱ ይነግሩናል፡፡

 

እኝህ ግለሰብ የቅማንትን የራስ አስተዳደር ህገ-መንግሥታዊ ጥያቄ በሦስት መንገዶች እመለከተዋለሁ ይላሉ፡፡

ይህውም፣

1ኛ ከህገ-መንግሥቱ አንፃር

‹ኦሮሞ  ነኝ›  ፣ ‹ቅማንት ነኝ› ‹ወላይታ ነኝ› ማለት  ኢትዮጵያዊነትን የሚደመስስ አስተሳሰብ ነው ይሉና አማራ ነኝ ብሎ መቀጠል ግን ኢትዮጵያዊነት የሚያስቀጥል አስተሳሰብ በመሆኑ ተመራጭና ጤነኛ አስተሳሰብ እንደሆነ ሊነግሩን ይሞክራሉ፡፡ በራሱ የነገድ ሥም የሚጠራ ህዝብ ኢትዮጵያዊነቱን እንደካደ ሊያስረዱን ይሞክራሉ፡፡‹‹ቕማንት ቕማንት ነኝ ብሎ ኢትዮጵያዊነቱን ከሚያጣ ይልቅ አማራ ነኝ ብሎ ኢትዮጵያዊ መሆን ይሻለዋል›› ይላሉ (ገጽ 1 ፓራግራፍ 4 መስመስር 4 እና 5)፡፡ ቅማንት ነኝ፣ ኦሮሞ ነኝ፣ ሽናሻ ነኝ ማለት ኢትዮጵያዊነትን ስለሚደፈጥጥ ኢትዮጵያዊ  ብቸኛው የዘር ሀረግ ‹አማራ› ብቻ እንደሆነ በግልፅ ይነግሩናል

ለቅማንት ህዝብ ቅማንት ነኝ ማለት.፣ ለኦሮሞው ኦሮሞ ነኝ ማለት ፣ለትግሬው ትግሬ ነኝ ማለት ወዘተ ነውርና ፀረ-አንድነት ሲሆን ለአማራ አማራነ ነኝ ማለት ግን ኢትዮጵያዊነትን የሚያጠነክር አስተሳሰብ እንደሆነ ሊሰብኩን ይሞክራሉ፡፡ ለእኝህ ሰው ኢትዮጵያ አንድ የምትሆነው ሁሉም ማንነቱን ረስቶ አማራ ነኝ ሲል ብቻ እንደሆነ ይመክሩናል፡፡ ይህን  በተመለከተ መጋቢት 21/2007 ዓ.ም ‹‹የቅማንትን የክልል አስተዳደር በሦስት መንጎዶች›› ባሉበት መጣጥፋቸው ላይ በግልጽ  እንዲህ ይሉናል፡፡ ‹‹—— ለአንድ የቅማንት ተወላጅ ቅማንት ነኝ ማለቱ እንጅ ኢትዮጵያዊ ነኝ ማለቱ ዋጋ የለውም›› ይላሉ፡፡ ስለዚህ አንድ ቅማንት ኢትዮጵያዊ ለመሆን ከፈለገ ማንነቱን ረስቶ በኢትዮጵያዊነቱ ይጠራ እንደማለት ነው፡፡ እኝህ ግለሰብ ጎንደር ውስጥ ሲያድጉና ወላጆቻው ራሳቸው በፈጠሩት ስለቅማንት ማንነት የተዛባ ተረት ተረት ሲግቷቸው በማደጋቸውና በኢትዮጵያ ስለ አንድ ብሔረሰብ ታላቅነትና የኢትዮጵያ ብቸኛ ባለቤትነት አጣመው ስላሳደጓቸው በምንም መልኩ የቅማንትን ማንነት መቀበል አይፈልጉም፡፡ በተቃራኒው እርሳቸው የተገኙበት ብሔር ሲጠራ በኩራት ደረታቸውን በትቢት ይወጥራሉ፡፡  የቅማንት ህዝብ የራስ አስተዳደር ‹‹ለምን ጠየቀ?›› ብለው በተቆረቆሩበት አስተሳሰብ ስለአማራ የራስ አስተዳደር መመሥረት ምንም ነገር ማለት አይፈልጉም፡፡ ለዚህ ግሰብ ለአማራ ይህ ተፈጥሯዊ መብት ሲመስላቸው ለቅማንት ግን የማይገባ ጉዳይ ነው፡፡ ወረድ ይሉና እርሳቸውን ያናደደቻቸው ሌላው ነገር በአማራ ክልል የሚገኘው ቅማንት አማራ እንዲሆን አለመደረጉ እንጅ በትግራይ ክልል የሚገኙ ኩናማዎች፣ ሳሆች ኢሮቦች በስማቸው መጠራቸውን አይቃወሙም፡፡ እንዲያውም ይህ አለመደረጉ እጅግ እንደሚያማቸው ይገልጣሉ፡፡ እገረ-መንግዳቸውን ግን አማራ እየተባለ የሚጠራው ህዝብ የጋፋት የሽናሻ፣ የወይጦና የሌሎች ህዝቦች ስብስብ መሆኑን ሳይደብቁ በጹህፋቸው በሌላ አስተሳሰብም ቢሆን ነግረውናል፡፡

2ኛው ትግራይን ከማስፋፋት አንፃር

እኝህ ግለሰብ የቅማንት ቅማንት ነኝ ማለት የህዝቡ መብት መሆኑን በመዘንጋት የቅማንት ጥያቄ መነሻውና መድረሻው የትግራይን ግዛት ከማስፋፋት ጋር ለማያያዝ ይሞክራሉ፡፡ ለእኝህ ግለሰብ ቅማንት ቅማንት የመሆን ተፈጥሯዊ መብቱን በግልፅ ይደመስሱታል፡፡ ቅማንት ጥንታዊ ኢትዮጵያዊ መሆኑን ሙሉ በሙሉ በመደምሰስ የቅማንት ህዝብን የውስጥ አስተዳደር ጥያቄ የሚያይዙትና የሚያዩት ከትግራይ የቦታ መስፋፋት ድብቅ ዓላማ ጋር ያቆራኙታል፡፡ ይህ ማለት ቅማንት የሚባል ህዝብ በኢትዮጵያ ያልነበረ ነገር ግን ወያኔ/ኢህአዴግ/ ለግዛት ማስፋፋት ዓላማው ሲል ብቻ ከ20 ዓመት ወዲህ  የፈጠረው ህዝብ እንደሆነ በግልፅ ይነግሩናል፡፡ የዛሬን አያድርገውና እኝህ ግለሰብ ጎንደር ውስጥ ሲያድጉ ቢያንስ በ24 ሠዓት ውስጥ ቅማንትን የሚያንቋሽሽ ፀያፍ ቃል ወይ ራሳቸው ይሉታለ አለያ ከቤተሰቦቻቸው ወይም ከጎረቤታቸው ሲነገር ሲሰሙ እንዳደጉ የሚዘነጉት አይመስለኝም፡፡ አሁን እያራመዱት ላለው ጭፍን የዘር ጥላቻም መሰረቱ ያደጉበት ቤተሰብና ማህበረሰብ ለመሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡ ታዲያ በዚህ መንግድ ያደገ ግለሰብ የቅማንትን ህዝብ የመብት ጥያቄ በተንሸዋረረ አመለካከታቸው ቢያዩት የሚያስገርም አይደለም፡፡የሚገርመው ግን ዛሬም የኢትዮጵያን አንድነት በ1960ዎች በነበረው አስተሳሰብ ለማስቀጠል ታች ላይ ማለታቸው ነው፡፡ ግለሰቡ ማወቅ አይፈልጉም እንጅ ከአሁን በኋላ የኢትዮጵያን አንድነት በአንድ ህዝብ ሥም አስቀጥላለሁ ብሎ ማሰብ ቐዠት ብቻ  ሳይሆን የጤንነት መጓደል ጭምር ነው፡፡

አቶ አንዱዓለም ‹‹ተስፋፊው የትግራይ ገዥ ከተከዜ አልፎ አስከአባይ ድረስ ለመቆጣጠር ያለውን ዓላማ ለማሳካት ቅማንትን አንደመሸጋገሪያ ድልዲይ ለመጠቀም ሲል ከተኙበት ቀስቅሶ የራስ አስተዳደር ጥያቄ እንዲያነሱ አደረጋቸው›› ይሉናል፡፡ ይሁን እንጅ ገዥው የአማራ ክልል መንግሥት የቅማንትን ህዝብ ያለፈቃዱ ‹‹ከዛሬ ቀን ጀምሮ አማራ ሆናችኋል›› ብሎ ከህዝብና ቤት ቆጠራ ሲሰርዛቸው ያ ለዚያ ታላቅ ህዝብ ለሚሉት መስፋፋት አልነበረም ይሆን?፣ ዘር ማጥፋትም አይደለም?፡፡ ይህን ድርጊት ተገቢና ትክክል አደርገው ስለሚያስቡ የአማራ መንግሥትን መክሰስ ፈፅሞ አይፈልጉም፤ በተቃራኒው ተገቢና  በልባቸው ጀግኖች እያሉ የሚያወድሷቸው ይመስለኛል፡፡ እስኪ እርሳቸው የተገኙበት ህዝብ የቅማንት ዕጣ ፈንታ ቢገጥመው ምን ይሰማቸው ይሆን? አማራ የሚባል ህዝብ ተሰርዞ ኦሮሞ ወይም ትግራዋይ ሆነሀል ቢባል አፈሙዝ ከማዞር የሚያግዳቸው ነገር ይኖር ነበር? ይህ ሆኖ አይደለም ሥልጣን የህዝብ በመሆኑ ከውጭ አገር ሆነው እያስነሱ ያሉትን አቧራ እያሸተትን ነው፡፡ ቁም ነገሩ  ግን ከአቧራነት የሚያልፍ አይደለም፡፡ ‹‹የቅማንት ክልል ለማን ይጠቅማል?›› ብለው በጠየቁበት አንድበታቸው የአማራ ክልል መመስረት ‹‹ለማን ይጠቅማል?›› ብለው ለመጠየቅ ድፍረቱን አላገኙም፡፡ ያሉት ምንድነው ‹‹የቅማንት ክልል ከተመሰረት የአማራ ክልል የቱ ሊሆን ነው? ነበር ያሉት፡፡ ቀጠል በማድረግ ‹‹የቅማንት ደካማ ክልል መመስረት ምን ጊዜም የማያባራ ንትርክ ከአማራው ጋር ይፈጠራል›› በማለት ስጋት አስመስለው ጎንደሬ አማራ የቅማንት ክልል ከተመሰረተ ለጦርነት እንደሚዘጋጅ ሊያስፈራሩን ይሞክራሉ፡፡ ከዚህ የአማራ ህዝብ ቁጣ እና ወረራ ለመዳን የቅማንት ህዝብ ትግሬዎችን አድኑኝ ለማለት ይገደዳሉ በማለት ትንቢታቸውንና ስጋታቸውን ይነግሩናል፡፡ ስለዚህ ነገ የራስክን ክልል በመመስረትህ በአማራ ህዝብ ሊደርስብህ ከሚችለው ቁጣ ለመዳን የራስ አስተዳደር ጥያቂያችሁን ቅማንቶች አቁሙ ይላሉ፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ከእኛ አንኳ ብታመልጡ በመጨረሻ በትግሬዎች ተደፍጥጣችሁ እስከውዲያኛው  ከምደረ-ገጽ መጥፋታችሁ አይቀርምና እነሱ ከሚያጠፏችሁ እኛ እንደጀመርነው እንጨርሳችሁ ለማት ይዳዳቸዋል፡፡ በክልሉ ለሚኖሩ ሌሎች ህዝቦችም ማለትም ለአገው ለሽናሻ ለወይጦ  ለሻንቅላ ህዝቦች በቅማንት ሊደረስ የሚችለው እንዳይደርሰባችሁና የመምጫችን ቀን ስለማይታወቅ  ከአሁኑ ንስሀ ግቡ በማለት ይመክራል፡፡ የሚያሳዝነው ከወላጆቻው የወረሱት ፀያፍ የህዝብ ስም አጠራር አንኳ አላስተካከሉም፡፡ አሁንም የሌለን ህዝብ ‹‹ሻንቅላ›› እያሉ ለኢትዮጵያ ህዝቦች ያላቸውን ንቀት ይነግሩናል፡፡ ሻንቅላ ማነው ‹ነብዩ› አንዱዓለም?

‹‹የቅማንት ክልል መመስረት ዋና ምክንያቱ የትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር የፖለቲካ ቅማራ ነው፡፡›› ይላሉ፡፡ ግን በነካ ብዕራቸው የአማራ ክልል መመስረት የየትኛው ተፈጥሯዊ ህግ ውጤት እንደሆነ ቢነግሩን? አቶ አንዱዓለም በአግባቡ አልተረዱተም እንጅ  ወያኔ/ኢህአዴግ/ ያልነበረን የአማራ ህዝብ ራሱን የቻለ ብሔረሰብ ነው ብሎ አንድ ደረጃ ከፍ አድርጎታል፡፡  የደርግ ፕረዚዳንት የነበሩት መንግሰቱ ኃ/ማሪያም‹‹ እውን አማራ የሚባል ህዝብ አለ?›› ያሉትን ሀቅ ኢህአዴግ ደምሰሶታል፡፡ እውነታው ግን የመንግሥቱ ኃ/ማሪያም ጥያቂያዊ ንግግር ነበር፡፡

3ኛው ዐማራውን ከማዳከምና ከማጥፋት አንፃር

የቅማንተን ክልል መመስረትን ያየበት ሦስተኛው መንገድ ወያኔ አማራን ለማጥፋት ካለው ዓላማ ጋር ያያዙታል፡፡ ይህን በተመለከተ እንዲህ ይላሉ፡፡ ‹‹የትግሬዎች ነፃ አውጭ ሲቋቋም ከመጀመሪያዎች አራቱ ግቦች አንዱ በአማራው መቃብር ላይ የትግራይን ሪፑብሊክ እንመስርታለን የሚል ነው›› ይላሉ (ገፅ 3 ፓራግራፍ 2)፡፡ ቀጠል በማድረግ ‹‹ይህ የቅማንት ክልል መመስረት የትግሬዎች ነፃ አውጭ ግንባር ትግራይን ለማስፋፋት እንደሆነ ከላይ በተራ ቁጥር 2 አሳይቻለሁ ይላሉ፡፡

ለእኝህ ግለሰብ በኢትዮጵያ የፀደቀው ህገ-መንግሥት የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ሲደርሳባቸው ከነበረው ግፍ አውጥቶ በእኩልነትና በመከባበር ላይ የተመሰረተ አንድነት እንዲያመጣ ታስቦ በህዝቦች ይሁንታ የመጣ ሳይሆን አማራ የሚባልን ታላቅ ህዝብ ለማዳከምና ብሎም ለማጥፋት  በወያኔ የተጠነሰሰ ሴራ ነው ይሉናል፡፡ ምክንያቱም ይላሉ ‹‹ለወያኔ ከደርግ ይልቅ መሰረታዊ ጠላቱ አድርጎ የሚያየው የአማራን ህዝብ ነው›› ይላሉ፡፡  ነገር ግን ሰው በላው ደርግ የወያኔ ጊዚያዊ ጠላት ነበር በማለት ያስቀምጣሉ፡፡ ይህን ዐማራን የማጥፋት  ተልዕኮውን ለማሳካት ‹‹ወያኔ ቅማንትን ጠፍጥፎ ሰራው›› ይላሉ፡፡ በክልሉ የተለያዩ ህዝቦችን በመፍጠር የአማራን ቁጥር አሳነሰ ይላሉ፡፡ ለአቶ አንዱዓለም ትልቁ ጭንቀት የአንድ ብሔረሰብ እንደህዝብ ራሱን አሳውቆ መቀጠልና ራሱን በራሱ ማስተዳደሩ ተፈጥሯዊ የሆነውን መብቱን ረስተው የቅማንት ህዝብ የራስ አስተዳደር መመስረት የአማራን ህዝብ ቁጥር ማሳነሱ ላይ ያንገበግባቸዋል፡፡ የወያኔ የቅማንት ህዝብ የራስ አስተዳደር መፍቀድ አማራን ለማጥቃት ነው ባሉ አንደበታቸው የቅማንትን ዘር ለማጥፋት እየተደረገ ያለውን ግፍ ለምን ማንሳት አልፈለጉም? ለአንድ ህዝብ ብቻ መቆርቆር እውን የኢትዮጵያን እነድነት ያረጋግጣል?

ለዚህ ግለሰብ አንድነት ማለት ቦታ እንጅ ሰው አይደለም፡፡ ይህን እውነታ እንዲህ በማለት ራሳቸውን ይጠይቃሉ፡፡ ወያኔ ‹‹ከየትኛው ቦታ አማራ ተባሮ የቅማንት ህዝብ እንዲሰፍር ይደረጋል?›› ብለው ሲጠይቁ አሁን ቅማንት ሰፍሮ የሚገኝበት ቦታ የአማራ ቦታ እንጅ የቅማንት አይደለም ማለታቸው እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡ ይህም ማለት ቅማንት አገር የሌለው በእነአንዱዓለም በጎ መግባር የተቀመጠ ህዝብ ነው ማለታቸው ለመሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡ ምክንያቱም እንአንዱዓለምና መሰሎቹ ያደራጇቸው የአማራ ህብረት አባላት (በኢትዮጵያ)  ‹‹ቅማንት አገር ስለሌለው ወደመጣበት ግብፅ እንመልሰዋለን እንዳሉት ማለት ነው፡፡ የቅማንት ጥያቄ የመብት እንጅ የቦታ ማስፋፋት እንዳልሆነ እያወቁ ቅማንት የሚባል ህዝብ በጎንደር ምድር ላይ ፍፁም ቦታ አንደሌው አድርገው ይነግሩናል፡፡ ምን ይደረግ ‹‹በኋላ የበቀለ ቀንድ በፊት የበቀለውን ጆሮ በለጠው›› አይደል ከእነተረቱ፡፡ ምን ይሁን! የቅማንቶች ምድር ጎንደር ለዚህ ግለሰብ ያለፈ ታሪክ ሆነባቸውና ከነአካቴው የቅማንትን በጎንደር ምድር ቦታ የሌለው ህዝብ እንደሆነ ሊነግሩን ሞከሩ፡፡ የዛሬን አያድርገውና እንኳን የጎንደር ምድር ራሳቸውም የተገኙበት ህዝብ መሰረቱ ቅማንት አንደሆነ የሚጠፋቸው አይመስለኝም፡፡ በአንድ ወቅት በተደረገ የሀይማኖትና የፖለቲካ ተፅዕኖ ተገዶ ማንነቱን የቀየሩትን የአቶ አንዱዓለም ዘመዶች ሥርወ-ግንዱ ቅማንት ነበር፡፡

በፁህፋቸው መጨረሻ ‹‹በትግሬዎች ነፃ አውጭ ግንባር የቅማንት ክልል ተፈጥሯል፤ ታዲያ ይህን እንዴት መታገል ይቻላል?›› ብለው ይጠይቁና  የህን አገር አፍራሽ ተግባር መቃወም  የሁሉም ግዴታ እንደሆን መልሱን ራሳቸው ይመልሱታል›፡፡ መፍትሄውም ‹‹የትግሬን ነፃ አውጭ ድርጅት ተባብሮ መደምሰስ ነው›› ይላሉ፡፡ የትገሬ ነፃ አውጭ ከተደመሰሰ የቅማንት ማንነትም አብሮ ይደመሰሳልና ማለታቸው ነው፡፡

በዚህ ፁህፋቸው አቶ አንዱዓለም ሁለት ትልልቅ ስህቶችን ፈፅመዋል፡፡

1ኛውና የመጀመሪው  ስህተታቸው የቅማንት ህዝብ እንደህዝብ በራሱ የማይነቀሳቀስ በድን አካል አድርገው በማየታቸው የቅማንት ህዝብ ማንም ሲፈልገው በባዳነት የሚጠቀምበት አስመስለው መሳላቸው ነው፡፡ ግን እኝህ ግለሰብ የዘነጉት አብይ ቁም ነገር ቢኖር ራሳቸው አስር ጊዜ የትግራይ ነፃ አውጭና ከፋፋይ ብለው በሚጠሩት ድርጅት ተመሰረተ በሚሉት የፌደራል ሥርዓት ውስጥተሸቀዳድሞ ስልጣን ላይ ፊጥ ያለው እርሳቸው የተገኙበት ህዝብ አካል የሆነው ቡድን እንደሆነ ረስተውት ሳይሆን ‹‹በብቸኝነት ለምን እኛ ብቻ አገሪቱን አልተቆጣጠርንም›› ከሚል ጭፍን የሥልጣን አባዜ ነው፡፡ ዛሬ የአማራን ክልል የሚመራው በመንደርና በጎጥ በተሰባሰቡ ቡድኖች መሆኑን እያወቁ ስለዚህ ጉዳይ ምንም ማለት አይፈልጉም፡፡ ባንዳነት የራስን መብት ማስከበርና በፌደራል ሥርዓቱ መሳተፍ  ከሆነ የመጀመሪያወ ባንዳ ማን እንደሆን ለማወቅ ምንም አይነት የሂሳብ ቀመር አያስፈልገውም፡፡ ለእኝህ ግለሰብ ቁም ነገሩ የህዝብ ቁጥር ብቻ ስለሚመስላቸው የቅማንትን ህዝብ ከአማራው ህዝብ ጋር በማነጣጠር ‹‹የትም አትደረሱም›› ለማለት የሞክራሉ፡፡ ቁም ነገሩ ቁጥር ቢሆን ኑሮ እስራኤል የምትባል አገር እና አስራኤል የሚባል ህዝብ ከፍተኛ ቁጥር ባለው የአረብ ህዝብ ተከቦ ህልውናውን ባላስከበረ ነበር፡፡ ከፈለጉ እኝህ ግለሰብ የሚናፍቁትን ጦርነት ጊዜ ሳይወስዱ ማወጅ ይችላሉ፡፡ ይህ የሚናፍቁት ጦርነት የቅማንትን ህዝብ ብቻ ለብልቦ የሚቆም መስሏቸው ከሆነ ተሳስተዋል፡፡ በጎንደር ምድር ላይ ወይ አብረንና ተከባብረን እንኖራለን አለያ ደግሞ በግፍ የሚመጣ ጦርነትን መመከት የሚያቅተው ያለ ህዝብ ያለ አይመስለዎት፡፡

2ኛውና ሌላው ስህተታቸው የዚህ ፁህፍ ማጠንጠኛቸው ህወሀት/ኢህአዴግ/ የአማራን ህልውና ለመፈታተን የተፈጠረ ድርጅት በማስመሰል የሚደስኩሩትና የዚህ ህዝብ ህልውና መደፈር ለኢትዮጵያ አንድነት መደፈር ብቸኛ ምልክት አድርገው የሚያራምዱት የተሳሳተ አስተሳሰብ ነው፡፡ ‹‹ተደፈረ፣ በወያኔ የጥፋት በትር ሥር ወደቀ›› የሚሉት ህዝብ ከጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብ  20 በመቶ  ሊሆን ቢችል ነው፡፡ ሌላውን በማግለል እንደገንጣይና ከፋፋይ መመለልከት ጊዜው ያለፈበትና ውኃያማይቋጥር አስተሳሰብ መሆኑን የተገነዘቡት አይመስልም፡፡ የእንዲህ አይነት የተቸካይነት (inflexible) አመለካከት ይበልጥ የኢትዮጵያን ህዝብ ይከፋፍል ካልሆነ በስተቀር የአነድነት ስሜትን ማምጣት አይችልም፡፡

ለአንዱዓለምና ለመሰሎቹ የራሳቸውን የተንሸዋረረ አመለካከት አስተካክሎ ወደ አማካኝ ቦታ ከመምጣት ይልቅ ይህ አመለካከት ወያኔነትና የወያኔነት አቀንቀኝነት ሊመስላቸው ይችላል፡፡ ግድ የለኝም፡፡ በኢትዮጵያ ብሔር. ብሔረሰቦችና ህዝቦች እኩልነት የሚያምን ድርጅት ሁሉ ደጋፊ ነኝ፡፡ እኝህ ግለሰብ አልተረዱትም እንጅ ወያኔ/ኢህአዴግ/ የሚሉት ድርጅት ለዐማራ ህዝብ የማንነት እውቅና በመስጠት የቅማንትን ህዝብ ከአማራ መንግሥት ደጅ እንዲጠና እንዳደረገው የተገዘቡ አይመሰልም፡፡ ለሳቸው ጥያቄ የሆነባቸው አማራ ባለመብት መሆኑ ሳይሆን ቅማንት መብቱን መጠየቁ ብቻ ነው፡፡ ምክንያቱም ይህ መብት ለእነሱ ተጥሯዊ  መብት ሲሆን ለቅማንት ግን የማይታሰብ እውነታ አድርገው ያዩታልና፡፡

ይህን በዚህ ላብቃና ግለሰቡ ለሁለተኛ ጊዜ ‹‹የማይለቀን የቅማንትጉዳይ፤ ብለው ብለው ብለው ወደእኛ ለአቤቱታ መጡ›› በሚል ርዕስ www.ethiomeida.com ላይ በፃፉት ዙሪያ ሰፊ መልስ ይዠ አስክመለስ ድረስ ቸር ይግጥመን!

ከብርቱካን ወለቃ

ይህን ፀሁፍ መነሻ አድርጎ መልስ መፃፍ የሚፈልግ ሁሉ በፌስ ቡክ አድራሻየ ወይም birtukanwoleka@gmail.com በሚለው አድራሻ ሊፅፈልኝ ይችላል፡፡

 

 

↧

Health: ለባለትዳሮች 10 በሽታን መከላከያ ምክሮች!!

$
0
0

በጋብቻ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች፣ በላጤነት ከሚኖሩት ይልቅ ረዥም ዕድሜ የመኖር ዕድል እንዳላቸው ነው ፊትነስ መጽሔት የምርምር ውጤቶችን ዋቢ የሚያደርገው፡፡ ‹ከአንድ ብርቱ…› እንደሚባለው፣ ጥምረቱ የሚያመጣቸው መተሳሰቦች፣ ጫና እና ኃላፊነት በመሰረታዊነት የሰዎችን ደስታና ዕድሜን ይቀጥላል ነው የጥናቱ ሐሳብ፡፡ ትዳር በጥቅሞቹ ብዛት የተከበበ ቢሆንም፣ በጤና እና በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ላይ እንቅፋት ከሚሆኑ ችግሮች ሙሉ ለሙሉ ነፃ ሊሆን አይችልም ይላሉ ባለሙያዎቹ፡፡

fast food

በአሁኑ ወቅት የበርካቶቹ ባለትዳሮች፣ የጤና ችግሮች መንስኤ ተብሎ የሚቀመጠው ከልክ ያለፈ ውፍረት ሲሆን፣ ከዓለም አቀፍ ጦርነቶች ባልተናነሰ መልኩ የሰው ልጅ ከፍተኛው ስጋት ሆኗል፡፡ ውፍረት ለደም ግፊት፣ ለስኳር፣ ለልብ ህመም፣ እና ለሌሎች በሽታዎች ጠንቅ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ግን ትዳርን ከዚህ የጤና ጠንቅ ጋር በቀጥታ ምን አገናኘው? የሚል ጥያቄ ሊቀርብ ይችላል፣ የተለያዩ ጥናቶች የሰዎችን አመጋገብ ከትዳር በፊትና በትዳር ውስጥ ያለውን ልዩነት ፈትሸዋል፡፡ በትንሹ ለሁለት ዓመታት በጋብቻ ውስጥ የቆዩ ጥንዶች፣ ከጋብቻ ውጪ ተጋላጭነታቸው የሰፋ ነው፡፡ በ20ዎቹ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያለች አንዲት ሴት፣ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት በትዳር ላይ ስትቆይ በአማካኝ 24 ፓውንድ ክብደት ታከማቻለች ይላል 2012 ላይ በጉዳዩ ላይ የወጣው ጥናት፡፡

ትዳር እንዴት ከልክ ላለፈ ውፍረት ያጋልጣል?

ትዳር ለውፍረት ምክንያት የሚሆንባቸው ምክንያቶች በርካታ ናቸው፡፡ የትዳር አጋሮች ካላገቡት አንፃር ብዙ ጊዜ ምግቦቻቸውን በጋራ ይመገባሉ፡፡ ለመመገብ ረዥም ጊዜ መጠቀማቸው ሌላው የሚጠበቅ ተግባር ነው፡፡ ይሄ ለምሳሌ ያለምንም መጣደፍ ቴሌቪዥን በመመልከት፣ ሞባይል በመነካካት፣ በማውራት እንዲሁም ከሌሎች ተግባራት ጎን ለጎን መመገባቸው፣ አውቀውትም ሆነ ሳያውቁት ከፍተኛ የምግብ ክምችት ወደ ሰውነታቸው እንዲያስገቡ ሊያደርጋቸው ይችላል፡፡

በሌላ በኩል በቤት ውስጥ የሚሰናዱ ምግቦች ስብ እና ሌሎች ውፍረት አመንጪ ንጥረ ነገሮችን በሰፊው ይከተትባቸዋለ፡፡ በዚህም የቤተሰቡ አባላት ከፍተኛ ክብደት ለማከማቸት ብዙ መመገብ እንኳን ላያስፈልጋቸው ይችላል፡፡

በጋራ መመገብ ትዳር ለሚያመጣው ከልክ ያለፈ ውፍረት ሌላው መንስኤ ነው፡፡ የትዳር ተጣማሪዎች በቤት ውስጥ ለመመገብ እስከቀረቡ ድረስ በጋራ መመገባቸው በተለይ እንደኛ ባሉ ሀገራት የተለመደ ነው፡፡ ይሄ ደግሞ በርታ በርቺ በመባባል የቀረበውን ምግብ በጋራ ለማጥቃት ይረዳል፡፡ ሁኔታው በተለይ የአፒታይት ችግርና የምግብ ጠበኝነት ላለበት ሰው መልካም ሲሆን፣ ወትሮም የምግብ ነገር ለማይሆንላቸው ደግሞ ይዞባቸው የሚመጣው ጣጣ ሊኖር እንደሚችል ማሰብ ተገቢ ነው፡፡ አዎ ውፍረት ከጤና ጠንቅነቱ ባለፈ ብዙ የተደከመበትንና ዕድሜ የተከፈለበትን ትዳር ይረብሻል እና በእርግጥም መፍትሄ ያሻዋል፡፡

– በተለይ ያላገቡ ሴቶች አዘውትረው የሚለብሱት ሱሪ ጠበብ ማለት ሲጀመር ቶሎ መፍትሄ የመሰላቸውን ተግባር በሙሉ ለመፈፀም ወደኋላ አይሉም፡፡ አመጋገብን መግራት ልምምዶችን ማድረግ ደግሞ መሰረታዊ እርምጃዎች ናቸው፡፡ ነገር ግን እነዚህ ሴቶች ወደ ትዳር ሲገቡ እና በተመሳሳይ በውፍረት ሳቢያ ሱሪያቸው የመጥበብ ምልክት ቢያሳያቸው ሌላ መግዛት ነው ቀዳሚው ምርጫቸው፡፡

– ባለትዳሮች ከላጤዎቹ አንፃር በህይወታቸው የተረጋጉ ናቸው፡፡ ይሄ የሚመጣው በተለይ የምወደው የምወዳት ቀሪውን ህይወቴን አብሮኝ የሚኖር ሰው አግኝቻለሁ ከሚል አስተሳሰብ ነው፡፡ ይሄ ታዲያ አንዳንዶች ራስን መጠበቅ ተጨማሪ ሥራ አድርገው እንዲመለከቱ ያደርጋል፡፡ ውፍረት አመንጪ ሁኔታዎችንም ቤታቸው ውስጥ መፍጠር ይጀምራሉ፡፡ የፊትነስ ባለሙያዎች ችግሩ በሴቶች ላይ ይበረታል ነው የሚሉት፡፡

በትዳር ውስጥ ከልክ ያለፉ ውፍረቶችን መከላከያ 10 ውጤታማ መንገዶች

1. በራስ ስኬት እና ለውጥ ላይ መጀመሪያ ትኩረት ማድረግ

በትዳር አጋርህ ወይም አጋርሽ መጥፎ ልማዶች (በአመጋገብ እና በእንቅስቃሴዎች) በምንም መንገድ መዘናጋት አያስፈልግም፡፡ የትዳር አጋርህን ወይም አጋርሽን የምታነሳሽትና ወደ ውፍረት መቀነሻ ተግባሮች የምናመጣበት ብቸኛው አማራጭ የሚሆነው ምሳሌ ሆኖ መገኘት ነው፡፡

2. የውስጥ ማንነት እንጂ አካላዊ ገፅታ

ለእኔ ቦታ የለውም የሚለውን አመለካከት ማራቅ ያስፈልጋል፡፡ ቀደም ሲል ወደ ትዳር ሲገባ ምክንያት የነበረው ውበት በግንኙነት ሂደት ውስጥ ሲጠፋ ድብርት፣ ስሜት ማጣትና አለመግባባት ይከተላል፡፡ ስለዚህ በግንኙነት ውስጥ ሁሉም ነገር ወሳኝ ናቸውና ግዴለሽነትን በቅድሚያ ማስወገድ አለብን ነው ባለሙያዎች የሚሉት፡፡

3. ከትዳር አጋር ጋር ሰፊ ጊዜን በምግብ ላይ አለማሳለፍ

ከሁለቱም የሚመጡ የእንቅስቃሴ ግብዣዎች ሩጫና የዳንስ ክፍለ ጊዜ መፈቃቀሩ ዕድሜ እንዲኖረው ያደርጋል የምትለው ጄኔፌር ኮኸን ነች፡፡ የተስተካከለ አካላዊ ቁመና በትዳር ውስጥ የወሲብ ህይወትን፣ በራስ መተማመንን እንዲሁም ኃይልን በማቆየት ረገድ ቀዳሚው ባለድርሻ ነው፡፡

4. ለራስ ጊዜ መስጠት፡- የቅርብ ጊዜ ጥናቶች እንደሚያሳዩት፣ ጭንቀት በሰውነት ላይ ቀጥተኛ የቅርፅ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል፡፡ አድሬናሊን እና ኮንቲሶል የሚባሉ ሆርሞኖች፣ በሰውነት ውስጥ እንዲሰራጩ በማድረግም፣ የደም ግፊት ከማስተካከል ባለፈ ልብ ከመደበኛው መጠንም በላይ በፍጥነት እንዲመታ በማድረግ፣ ራሳችንን ለአደጋ እናጋልጣለን፡፡ ስለዚህ በትዳራችን ውስጥለጭንቀትና ለአለመረጋጋት የሚያጋልጡንን ምክንያቶች መቅረፍ ያስፈልጋል፡፡

5. ዮጋ፡- ከፍተኛ ኃይል፣ ጥሩ ቅርፅ፣ ተጣጣፊነት፣ የተሻለ መንፈስና ዝቅተኛ ጭንቀት እንዲኖረን የሚረዳንን ዮጋን ማዘውተር ይመከራል፡፡ ባለሙያዎች ዮጋን ስንሰራ በአዕምሯችንና በሰውነታችን መካከል ትስስር እንዲኖር ያደረጋል ነው የሚሉት፡፡ በተቻለ መጠን እንቅስቃሴውን አሁንም ከትዳር አጋራችን ጋር በጋራ እንድንሰራ ይመከራል፡፡ ዮጋ የውስጥ እና የውጭ ሰውነታችን በአካል ደረጃ የሚያሰራ በመሆኑ ተመራጭ ያደርገዋል፡፡

6. ፍራፍራችን ማዘውተር፡- የሮማን ፍሬ ጁስ እጅግ ዝቅተኛ የኮሌስትሮል መጠን ያለውና የደም ግፊትን በመቀነስ ትልቅ ጥቅም ሲያስገኝ፣ ውፍረትን ደግሞ ይቆጣጠርልናል፡፡ ሌሎች ፍራፍሬዎችንም በአመጋገብ ዝርዝራችን ውስጥ ማካተት ያስፈልገናል፡፡

7. አረንጓዴ ሻይን ማዘውተር

የዚህ ቅጠል የጤና ጥቅሞች በየጊዜው እየተበራከቱ መጥተዋል፡፡ አረንጓዴ ሻይ ለከፍተኛ ውፍረት መንስኤ የሆነውን ኮሌስትሮልን ከመከላከል ባለፈ የተለያዩ የካንሰር በሽታዎችን ይታገላል፡፡

8. እንደ ሌሎች የሥራና የኑሮ ቀጠሮዎች ሁሉ ለስፖርታዊ እንቅስቃሴ በቀላሉ የማይሰረዙ ፕሮግራሞችን መቅረፅ ነው የሚያስፈልገው፡፡ ባለሙያዎች ዓርብ ምሽትና ቅዳሜ ጠዋትን በተለይ ባለትዳሮች ለስፖርታዊ እንቅስቃሴ ምርጫቸው ቢያደርጓቸው የተሻ ነው ይላሉ፡፡

9. ለትዳር አጋር ውለታ መዋል፡- የውፍረት ችግር የሌለባቸው ሰዎች ባሎች ወይም ሚስቶች በአንፃሩ ከውፍረት ጋር የሚኖሩ አጋሮቻቸውን መርዳት አለባቸው ነው የባለሙያዎች ምክር፡፡ በተለይ ትዳር ለዘለቄታው ለማቆየት ራስን በወዳጅ ጫማ ውስጥ ከቶ ስሜቶቻቸውን በመጋራት ከዛም የመፍትሄ አካል በመሆን ወደ መደበኛ ሰውነት ቅርፅ ለማምጣት መረዳት ያስፈልጋል፡፡

10 የትዳር ተጣማሪዎች ከልክ ላለፈ ውፍረት የሚያጋልጡ እርምጃዎችን ለመወሰን አንዱ በአንዱ ላይ ጫና እንደሚያሳድሩት ሁሉ ጤናማ አመጋገብ በጎጇቸው ውስጥ እንዲኖር እና የእንቅስቃሴ ልማድም የዘወትር ተግባራቸው እንዲሆን መተጋገዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡

↧
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live