Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የሕወሓት መንግስት የአውሮፕላን አብራሪውን ኃይለመድህን አበራን መኪና ለጨረታ አቀረበ

$
0
0

(ሪፖርተር) በጥር 2006 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ ወደ ሮም ጣሊያን ሲበር የነበረውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 767 አውሮፕላን ጠልፎ ጄኔቫ ስዊዘርላንድ ያሳረፈው ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን አበራ ንብረት የሆነች የቤት መኪና በሐራጅ ለጨረታ ቀረበች፡፡
Haile Medhin Abera

የሰሌዳ ቁጥር አአ 2-A32521 መኪና ጨረታ ያቀረበው ዘመን ባንክ ነው፡፡ ረዳት አብራሪው ለመኪና ግዢ ከዘመን ባንክ የተበደረው ብድር ስላልተከፈለው ባንኩ ተሽከርካሪዋን በጨረታ ለመሸጥ መገደዱን አስታውቋል፡፡

ባንኩ ተሽከርካሪዋን ለጨረታ ያቀረበው በሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 261,503.37 ነው፡፡ ጨረታው የሚካሄደው በመስከረም ወር 2008 ዓ.ም. ነው፡፡ ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን መኪናዋን የገዛው ከአውሮፕላን መጥለፉ ጥቂት ወራት ቀደም ብሎ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡

ኃይለ መድኅን ስዊዘርላንድ ውስጥ የፖለቲካ ጥገኝነት ቢጠይቅም የአገሪቱ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አውሎት ፍርድ ቤት አንድ ጊዜ የቀረበ ሲሆን፣ ከዚያ በኋላ ጉዳዩ በምን ደረጃ ላይ እንዳለ አይታወቅም፡፡ ለስዊዘርላንድ ኢሚግሬሽን ባለሥልጣን በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢቀርብም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በግለሰቡ ላይ ክስ መሥርቶ፣ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሌለበት 19 ዓመት ፅኑ እስራት እንደተፈረደበት ይታወሳል፡፡


አስመራ የሚገኘው ትህዴን መግለጫ አወጣ –“የሸሹት የግል ጥቅማቸው የቀረባቸው ናቸው”

Next: ሞላ አስገዶም ከኤርትራ የከዱት ከሰባቱ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ብቻቸውን በስምንት ላንድ ክሩዘር ከወታደሮች ጋር መሆኑ ተገለጸ፣ አገዛዙ አስቀድሞ ግንኙነት እንደነበረው መግለጹ ለሞራሉ የፈጠረው መሆኑም ተጠቆመ፣ የህወሓት ባለስልጣናት ሲያደርጉት የቆዩትን የስልጣን ሽኩቻ ተከትሎ በደህነቱ መ/ቤት አንዱ የአንዱን ደጋፊ ወደ ማጥቃት መሸጋገራቸው፣ በአገር ቤት የበዓል ገበያው ማሻቀብና የነገሰው ውጥረት መላ ካልተበጀለት አገሪቱን ወደ አደገኛ ሁኔታ ሊከት ይችላል መባሉ፣ የመንግስታቱ ድርጅት ወደ ኢትዮጵያ ለሚሄዱ የውጭ አገር ሰዎች ያወጣው ማስጠንቀቂያ፣ ቃለ መጠይቅ ከቴዲ አፍሮ የፌስ ቡክ ኮንሰርት አዘጋጆች አንዱ እና ከጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ በአገር ቤት ስላለው ሁኔታ እና ሌሎችም
$
0
0

ከትህዴን የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

ድርጅታችን ትህዴን በየካቲት 1993 ዓ/ም ብረት አንስቶ ትግል ሲጀምር አላማው ግልፅና የማያሻማ ነበር።

(photo File)

(photo File)

እሱም በሃገራችን የገነነው አፋኝ ስርዓት ህዝባችንን ከፋፍሎ ሰብኣዊ መብቱን ረግጦ ለመግዛት በሚያመቸው መንገድ ይጓዝ ስለነበር ድርጅታችን ትህዴን ችግሩን ለመፍታት ኩሁሉም በኢትዮጵያ አንድነት ከሚያምኑ ድርጅቶች በመተባበር ህዝባዊ ስርአት ለመትከልና አንድነቷ የተጠበቀ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ መገንባት የሚል አላማ አንግቦ የህወሓት-ኢህ አዴግ ስርዓትን በመቃወም ነፍጥ አንስቶ በትጥቅ ትግል መፋለም ከጀመረ 14 ዓመታት ሆኖታል።

በነዚህ 14 ዓምታት የትግል ጉዞ ድርጅታችን ትህዴን በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ወታደራዊ መስክ ከፍተኛ ድሎችን እያስመዝገበ መጥቷል። ትግል ሲባል ቀላል እንዳልሆነ ካሳለፍነው የትግል ታሪክ እየተማርን መጥተናል። ድርጅታችን ትህዴንም በዚህ አጭር እድሜው ክፍተኛ ድሎችን ሲጎናጸፍ የተለያዩ መስናክሎችን በመሻገር ነው።
በቅርብ ጊዜ የተወሰኑ በትግሉ የቆዩና ግላዊ ጥቅማቸው የተነካባቸው ግለስቦች ትግሉን ባሻቸው መንገድ ሊጠመዝዙት ስላልቻሉና በአብዛኛው ታጋይ በመድረክ ተይዘው መፈናፈኛ ስላጡ ተስፋ ቆርጠው ከትግሉ ጎራ ሸሽተዋል።

የተከበርከው ሰፊው ህዝባችን እነዚህ ጥቂት ግለሰቦች ለግል ጥቅማቸው ያደሩ እንጂ ትህዴንን የሚወክሉ አይደሉም። የእነዚህ ስዎች ከትግሉ መክዳት ደግሞ ድርጅታችን ትህዴን የቆሸሸውን በመጥረግ ጥንካሬውን ከመቸውም ጊዜ በላይ ያጎለብተዋል እንጂ ትግሉን ለሰክንድም ቢሆን አያደናቅፈውም።
ትህዴን ይዞት የተነሳ ዓላማ የመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ፍላጎት ስለሆነ ሊቅበለውም ውይም ላይቅበለውም የሚችለው ህዝብ እንጂ ግለሰቦች አይደሉም። ትግላችን ደግሞ በሃገራችን ያለውን ፀረህዝብ ስርዓት ከስልጣኑ ተወግዶ ህዝባችን የጀመረውን የትጥቅ ትግል ግቡን ሳይመታ ለአፍታም ቢሆን አይቆምም።
ስለሆነም መላው የኢትዮጵያ ስፊ ህዝብ ይህንን ተረድተህ እንደበፊቱ ሁሉ በልጆችህ እይተካሄደ ባለው ህዝባዊ ትግል ጎን እንድትሰለፍ መላው የትህዴን ታጋይ ጥሪውን ያቀርባል።
ፍኖተ ትህዴን ፍኖተ ድል ነው!
ድል ለጭቁኖች!!

ሞላ አስገዶም ከኤርትራ የከዱት ከሰባቱ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ብቻቸውን በስምንት ላንድ ክሩዘር ከወታደሮች ጋር መሆኑ ተገለጸ፣ አገዛዙ አስቀድሞ ግንኙነት እንደነበረው መግለጹ ለሞራሉ የፈጠረው መሆኑም ተጠቆመ፣ የህወሓት ባለስልጣናት ሲያደርጉት የቆዩትን የስልጣን ሽኩቻ ተከትሎ በደህነቱ መ/ቤት አንዱ የአንዱን ደጋፊ ወደ ማጥቃት መሸጋገራቸው፣ በአገር ቤት የበዓል ገበያው ማሻቀብና የነገሰው ውጥረት መላ ካልተበጀለት አገሪቱን ወደ አደገኛ ሁኔታ ሊከት ይችላል መባሉ፣ የመንግስታቱ ድርጅት ወደ ኢትዮጵያ ለሚሄዱ የውጭ አገር ሰዎች ያወጣው ማስጠንቀቂያ፣ ቃለ መጠይቅ ከቴዲ አፍሮ የፌስ ቡክ ኮንሰርት አዘጋጆች አንዱ እና ከጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ በአገር ቤት ስላለው ሁኔታ እና ሌሎችም

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


የህብር ሬዲዮ መስከረም 2 ቀን 2008 ፕሮግራም

እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ!

<... ...> ጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ ከአገር ቤት የበዓሉን አከባበርን የብዙሃኑን ሕይወት በተመለከተ ከህብር ሬዲዮ ተጠይቆ ከሰጠው ማብራሪያ (ሙሉውን ያዳምጡ)

<... ...> የትነበርክ ታደለ የቴዲ አፍሮ የፌስ ቡክ ኮንሰርት ዋና አስተባባሪ ስለ ስለ > ከሰጠው ምላሽ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡ)

የታጋይ ሞላን መክዳትና የመገናኛ ብዙሃን ዘገባ ሲቃኝ (ልዩ ጥንቅር)

የኢትዮጵያ ቀን በላስ ቬጋስ አከባበር(ቃለ መጠይቅ)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

ሞላ አስገዶም ከትህዴን ሰባት ከፍተኛ አመራሮች ብቻቸውን ተከታዮቻቸውን ይዘው በስምንት ላንድ ክሩዘር መክዳታቸው ተገለጸ

ከወያኔ ጋር ቀድመው ግንኙነት ነበራቸው የሚለው ስርዓቱ ሞራሉን ለመገንባት የፈጠረው ነው ተባለ

የህወሓት ባለስልጣናት የስልጣን ሽኩቻ በደህንነቱ መ/ቤት አንዱ የአንዱን ደጋፊ ወደ ማሳደድ ተሸጋገረ

በአገር ቤት ዘንድሮም በኑሮ ውድነቱ መባባስ ሳቢያ ለብዙሃኑ በዓሉ በዓል እንዳልመሰለ ተገለጸ

በአገሪቱ በሕዝቡ ውስጥ የታፈነው ውጥረት ፈጥኖ ሰላማዊ ሽግግር ካልተደረገ አደገኛ ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል ተገለጸ

የመንግስታቱ ድርጅት ወደ ኢትዮጵያ ለሚጓዙ የውጭ አገር ሰዎች ማስጠንቀቂያ አወጣ

ካይሮ ደቡብ ሱዳን ላይ ሰፊ የግብርና መሬት ወሰደች

የሆላንዱ ኩባንያ ራሱን ከአወዛጋቢው የህዳሴ ግድብ ጥናት ማግለሉነረ አስታወቀ

የመብረቅ አደጋ ኢትዮጵያ ውስጥ በተጠለሉ የደ/ሱዳን ስደተኞች ላይ የህይወት እና የአካል ጉዳት አደረሰ

በሑመራ በበረከት ከተማ በበዓሉ ዋዜማ የከባድ መሳሪያ ተኩስ መካሄዱን ነዋሪዎች ገለጹ

የኡጋንዳው ፕ/ት ዩኤሪ ሙሴቬኒ ሰሞኑን ሶማሊያ ውስጥ ለሞቱት ወታደሮቻቸው ተጠያቂዎቹ > መኮንኖች ናቸው አሉ

ሶማሊያዊው የኦሎምፒክ ሻምፒዮን ሞሕ ፋራህ የተከለከለ እጽ ይጠቀም እንደነበር አመነ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

ዛሬ መስከረም 3/2008 እስከንድር ነጋ ከታሰረ 4 ዓመት ሞላው

Previous: ሞላ አስገዶም ከኤርትራ የከዱት ከሰባቱ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ብቻቸውን በስምንት ላንድ ክሩዘር ከወታደሮች ጋር መሆኑ ተገለጸ፣ አገዛዙ አስቀድሞ ግንኙነት እንደነበረው መግለጹ ለሞራሉ የፈጠረው መሆኑም ተጠቆመ፣ የህወሓት ባለስልጣናት ሲያደርጉት የቆዩትን የስልጣን ሽኩቻ ተከትሎ በደህነቱ መ/ቤት አንዱ የአንዱን ደጋፊ ወደ ማጥቃት መሸጋገራቸው፣ በአገር ቤት የበዓል ገበያው ማሻቀብና የነገሰው ውጥረት መላ ካልተበጀለት አገሪቱን ወደ አደገኛ ሁኔታ ሊከት ይችላል መባሉ፣ የመንግስታቱ ድርጅት ወደ ኢትዮጵያ ለሚሄዱ የውጭ አገር ሰዎች ያወጣው ማስጠንቀቂያ፣ ቃለ መጠይቅ ከቴዲ አፍሮ የፌስ ቡክ ኮንሰርት አዘጋጆች አንዱ እና ከጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ በአገር ቤት ስላለው ሁኔታ እና ሌሎችም
$
0
0

Eskinder-Nega
(ዘ-ሐበሻ) ታዋቂው ጋዜጠኛ እስከድር ነጋ ዛሬ ከታሰረ 4 ዓመት ሞላው:: እስክንድር በ2004 ዓ.ም መስከረም 3 የታሰረ ሲሆን 4 ዓመቱን በጥንካሬ ደፍኗል::

ጋዜጠኛ እስከንድር በሕወሓት መንግስት 18 ዓመት ተፈርዶበት ይግኛል:: ኢትዮጵያውያን በየጊዜው የዚህን ታዋቂ ፎቶ በመያዝ እንዲፈታ መንግስትን ቢጠይቁም ጆሮ ዳባ ልበስ ተብለዋል::

የጋዜጠኛ እስከንድር ነጋ ባለቤት እና እስር ቤት የተወለደው ልጁ ናፍቆት በአሜሪካ ቨርጂኒያ ይገኛሉ::

ሰርካለም የ እስክንድርን 4 ዓመት እስር ቤት ቆይታ በማስመልከት በፌስቡክ ገጿ የሚከተለውን ጽፋለች::

“እነሆ ዛሬ ድፍን 4 ዓመት!! ከመስከረም 3/2004 ዓ.ም-መስከረም 3/2008!
ለቆምክለት ዓላማ እስር አይደለም የህይወት ዋጋም ካስከፈለህ ፣የአንተ መስዋዕትነት ለሌሎች ፈውስ ከሆነ፣ መቼም በማይሸረሸር አቋሜ ከጎንህ እቆማለሁ!
ውዴ የብቸኝነት ህይወት እንደእሬት ቢመረኝም፣ አልፎ አልፎ ቢፈታተነኝም፣ ምርጫዬ ለራሴ ማድላት ሳይሆን ምርጫህ መሆኑን ቃል እገባልሃለው!! ድል ለነፃነት ናፋቂዎች!!
አንድ ቀን ልጅህን ወይ ታቅፈዋለህ አልያም….”

እስክንድር ነጋ ን ፍቱት

ከመግለጫው በስተጀርባ

$
0
0

(ጌታቸው ሺፈራው)

የትህዴን ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ሞላ አስግዶም ከኤርትራ መውጣታቸውን ተከትሎ በህወሓት/ኢህአዴግ እና በተቃዋሚዎች በኩል ያልተጠበቁ ስሜቶች ተስተናግደዋል፡፡ ከተቃዋሚዎች በላይ ግን ራሱ ስርዓቱና ደጋፊዎች በክስተቱ ስሜታዊ ሆነው፡፡ ለዚህም በስርዓቱ ደጋፊ ሚዲያዎችና በደህንነት ተቋሙ እየተላለፉ ያሉትን መረጃዎች ማየት በቂ ነው፡፡ ያልጠበቁትን የሆነላቸው የሚመስሉት የስርዓቱ ደጋፊዎች በርካቶች በእሱ ስም በአሸባሪነት ተከሰሰው አሁንም ድረስ ፋዳቸውን የሚያዩበትን ድርጅት መሪ ‹‹ሀገር ወዳድ፣ ጀግና….›› እያሉ አሞግሰውታል፡፡ ይህ ያልተጠበቀ ‹‹ድል›› እንዳያመልጠው የፈለገው ህወሓት/ኢህአዴግም ሰውዬው ከኤርትራ የወጡት ለአንድ አመት በተደረገ ሚስጥራዊ ግንኙነት ነው ብሎ ‹‹ድሉን›› የራሱ አድርጎታል፡፡ የሻዕቢያ ተላላኪ ሲላቸው የነበሩትን ሰው በአንዴው የራሱ ተላላኪ አድርጓቸዋል፡፡ በተለያዩ አጋጣሚዎች አሸባሪ ተደርጎ ሲቆጠር ‹‹ወደ ሀገር የገባው ትህዴን›› አሁን ሀገር ወዳድ ተደርጎም የጀግንነት አቀባበል እየተደረገለት ነው፡፡

Mola asgedom

ከደጋፊዎቹና ከሚዲያዎቹም በላይ ስርዓቱ በተቋማቱ ደረጃም ስሜታዊና ሁኔታው ድንገተኛና ያልተጠበቀ እንደነበር የሚያሳይ መግለጫ አውጥቷል፡፡ ‹‹የብሄራዊ የመረጃና የደህንነት አገልግልግሎትና ከፌደራል ፖሊስ የጋራ ፀረ ሽብር ግብረ ሃይል›› ተሰጠ የተባለው መግለጫም የሚያሳየው ይህንኑ ነው፡፡ እንደ ተቋም በተለይም እንደ መረጃ ተቋም ተከሰቱ ያላቸውን ጉዳዮች በመረጃ መግለፅ ሲገባው ከአንድ መንግስት ብቻ ሳይሆን ስርዓትን በፕሮፖጋንዳ ለማጥቃት ከሚፈልግ ጀማሪ ተቃዋሚ እንኳን ያልተሻለ የተጋነነ ፕሮፖጋንዳን በመግለጫነት አውጥቷል፡፡ ‹‹ሀገር ወዳድ፣ እጅግ አኩሪ በሆነ መንገድ፣ እናት ሃገራቸው፣ ብርሃኑ ነጋ ሳይወድ ተገዶ ወደ አስመራ እንዲገባ፣ በተላላኪዎቹ ብዙ ዳንኪራ ከተደለቀበት በኋላ፣ ወሽመጣቸው እንዲቆረጥ፣ በአንድ የሻዕቢያ ቅጥረኛ ከሃዲ አማካይነት፣ የኤርትራ መንግስት ሰራዊት ሙሉ በሙሉ በመደምሰስ፣ ……..›› የመሳሰሉት መግለጫው ውስጥ የተካተቱ ስሜታዊ አገላለፆች ከአንድ መረጃ ተቋም ብቻ ሳይሆን ከመንግስትን ጋር የፕሮፖጋንዳ ጦርነት ውስጥ የገባ ተቃዋሚ ድርጅት ቢያወጣቸው እንኳን የሚያስተዛዝቡ ናቸው፡፡
ከዚህ ባሻገር አብዛኛው የመግለጫው ‹‹የሀገሪቱን ሰላም የማይፈልግ፣ ተላላኪ፣ አሸባሪ፣ ፀረ ሰላም….›› ይለው የነበረውን ቡድንና ግለሰብ የሚያሞካሽ ነው፡፡ መግለጫው ‹‹ታጣቂ ሀይሉ የሻዕብያ ቅጥረኛና የኢትዮጵያ ፀረ ሰላም ሃይል የሆነው አሸባሪው ግንቦት 7 ኢትዮጵያ ላይ ያነጣጠረውን የጥፋት ሴራ ባለመቀበል ነው ወደ እናት ሀገሩ የተመለሰው።›› ሲል አሞካሽቶታል፡፡ (በዚህ ‹‹እናት ሀገር›› የሚልን አገላለፅ እንደ ትምክት በሚያይ ስርዓት ውስጥ ምን አልባትም ከደርግ ውድቀት በኋላ በመግለጫ ደረጃ ስለ ‹‹እናት ሀገር›› እየተወራላቸው ያሉት አቶ ሞላ አስግዶም ብቻ ይመስሉኛል፡፡)

‹‹ድሉን›› ወደ መንግስት ጥረት ለመለወጥ የጣረው ስሜታዊ መግለጫ ‹‹ሀይሉ በጉዞ ወቅት ከሻዕብያ የተሰነዘረበትን ጥቃት ተቋቁሞ በአንፃሩ የሻዕብያን ሰራዊት እየደመሰሰ ወደ እናት ሀገሩ ሊመለስ ችሏል።›› ሲልም ‹‹ጀብዱን›› አውርቶለታል፡፡ ‹‹ብዙ መስዋዕትነት በመክፈል ነው ከነሙሉ ትጥቁ እና ሎጀስቲክ መሳሪያው አገሩ የገባው።›› ሲልም አወድሶታል፡፡ የደህንነት መስሪያ ቤቱ መግለጫውን ምሽት ላይ ያስተላለፈው ቢሆንም ፋና ግን ከመግለጫው ጋር ተመሳሳይነት ያለው ዜና ትናንት መስከረም 2/2008 ዓ.ም አስተላልፏል፡፡ ይህም መግለጫውን ከአንድ ደህነንት ተቋም ነኝ ከሚል ይልቅ ከስርዓቱ የፕሮፖጋንዳ ቅርንጫፍ የወጣ ስለመሆኑ የሚጠቁም ነው፡፡

የደህንነት መስሪያ ቤቱ በመግለጫው መግቢያ ‹‹በኤርትራ መንግስት አማካኝነት ለበርካታ ዓመታት ሲደራጅ የነበረው›› ብሎ ታጣቂ ቡድኑ ግዙፍ አቅም እንደነበረው ቢገልፅም ወረድ ብሎ ‹‹በአሁኑ ወቅት ኤርትራ ውስጥ የቀሩት እና መውጣት ያልቻሉ የቡድኑ አባላት በሽተኞች፣ በየቦታው የነበሩ እስረኞች፣ የኪነት ቡድን አባላትና ሌሎች አቅመ ደካሞች ብቻ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡›› ሲል ይህ ለበርካታ አመታት የተደራጀ ቡድን አባላት 700 ብቻ ናቸው ብሎ ፕሮፖጋንዳ አይሉት ፌዝ በመግለጫነት አስተላልፎልናል፡፡

ለትህዴን ለምን?

በዚህ ደረጃ ባይሆንም በተለያዩ ጊዜያት አሸባሪ ተብለው የተፈረጁ ቡድኖች አመራሮች ከስርዓቱ ጋር ታርቀው ወደ ሀገር ቤት ገብተዋል፡፡ ለዚህ ‹‹ውለታቸውም›› ቢያንስ እየተሸማቀቁም ቢሆን የቅንጦት ኑሮ መግፋት ችለዋል፡፡ እነዚህ ቡድኖች በተለይም የኦነግና የኦብነግ አመራሮች በገቡበት ወቅት ‹‹የአሸባሪ ቡድን፣ የአጥፊ ቡድን….›› አባላት እየተባሉ ከመወቀስ አልዳኑም፡፡ በቴሊቪዥን ዶክመንተሪዎችም ስርዓቱ ደግሞ ደጋግሞ ከሚወቅሳቸው በላይ ራሳቸው ቀርበው ራሳቸውን እንዲወቅሱ እየተገደዱ ነው፡፡ አቶ ሞላ አስግዶም ግን ገና ከጅምሩ፣ ገና ወደ ሀገር ቤት ሳይገቡም ጀምሮ ከዚህ የተለየ እየተደረገላቸው ነው፡፡ ምን አልባት ሞላ አስግዶም ያደረጉትን ጀኔራል ከማል ገልቹ ቢያደርጉት ከእንደዚህ አይነት ሙገሳ ይልቅ ከአሁን ቀደም ይደረግ እንደነበረው ፍረጃ ሊያመልጡ ይችላሉ ብሎ መገመት የዋህነት ይሆናል፡፡ ይህም በመሰረታዊነት ህወሓት/ኢህአዴግ ከሚከተለው ጎሰኛ ፖሊሲው እንደተቀዳ መገንዘብ አያዳግትም፡፡

በዚህ ፕሮፖጋንዳ የትግራይ ህዝብ ከህወሓት ውጭ ሌላ አማራጭ እንደሌለው፣ የትግራይን ህዝብ ወክለናል የሚሉት ተቃዋሚዎች የስርዓቱ መጠቀሚያና ከስርዓቱ ጋር ተባብረው ሌሎች ቡድኖችን ከማጥቃት ውጭ ለተቃዋሚው ጎራ እንደማይታመኑ ማሳየት ይፈልጋል፡፡ ለዚህም መግለጫው ‹‹በዚህ አጋጣሚ ይህ ኦፐሬሽን በድል እንዲጠናቀቅ ከጅምሩ የትግራይ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ ተሳትፎ ነበረው›› ማለቱን በዋቢነት መጥቀስ ይቻላል፡፡ ይህ አመለካከት በህዝብ ውስጥ አለ ተብሎ ስለሚገመት አጋጣሚውን በመጠቀም ህወሓትና የትግራይን ተቃዋሚዎችን የማይጨካከኑ እንደሆኑ ለማሳየት ተፈልጓል፡፡ እውነትም በሌሎቹ ታጣቂ ቡድኖች ላይ እንደሚጨከነው እነ አቶ ሞላ ላይ አልተጨከነባቸውም፡፡

ከአዋጭነት አንፃር

ክስተቱ ለስርዓቱ ድንገተኛ እና ያልተጠበቀ እንደሆነ በዋነኝነት የሚያሳየው የደህንነቱ ተቋምን ጨምሮ ሚዲያዎቹ የግንቦት ሰባት አመራሮችን ወደ ኤርትራ መምጣትን የስርዓቱ ትልቅ ስኬት እንዲሁም የግንቦት ሰባት ትልቅ ውድቀት አስመስለው ማቅረባቸው ነው፡፡ እንደ መግለጫው ለግንቦት ሰባት ትልቅ ስኬት የነበረው፣ እንዲሁም ስርዓቱ ይጎዳ የነበረው አመራሮቹ አሜሪካን ሆነው ድርጅቱንና ቅንጅቱን/ትብብሩን በርቀት ቢመሩ ነው፡፡ በተቃራኒው ግን አመራሮቹ አሜሪካን ውስጥ ሆነው ድርጅቱን መምራታቸው ትልቅ ጫና እንደነበረባቸው የሚታወስ ነው፡፡ ወደ ኤርትራ በሄዱበት ማግስት በርካቶች ለትጥቅ ትግሉ ቆርጠው መግባታቸውን የሚያሳይ ነው ሲሉም ተደምጠዋል፡፡ የ‹‹ኦፕሬሽኑን›› ድራማ እውነት ለማስመሰል በችኮላ የወጣው መግለጫ ግን ለግንቦት ሰባት ስኬት ነው የተባለውንም የስርዓቱ ስኬት አድርጎ ገልብጠው አነብንቦታል፡፡ በችኮላ! ምን አልባትም ያልተጠበቀው ‹‹ድል›› በፈጠረላቸው ደስታ፡፡

መግለጫ ለበርካታ አመታት ሲደራጅ ነበር ያለውን ቡድን አባላት ስርዓቱ በቁጥር ከእሱ ያንሳሉ ለሚላቸው ሰላይ አድርጓቸዋል፡፡ አቶ ሞላ አስግዶምን ጨምሮ 700 የሰራዊቱ አባላት የስርዓቱ ሰላዮች ነበሩ ማለት ነው፡፡ በመግለጫው በዋነኝነት አቶ ሞላን ጨምሮ ይህ ሁሉ ሰራዊት አሳካው የተባለው ቅንጅቱ/ትብብሩ እንዳይሳካ ማድረጉን ነው፡፡ የመግለጫው ዋና አንጓ ግንቦት ሰባትን ከሌሎች ታጣቂዎች መነጠል ይመስላል፡፡ ለአንድ አመት ተደረገ ያለው ሚስጥራዊ ስራ ተሳካ ሲልም ትብብሩ እንዳይደረግ መሰናክል ሆኗል በሚል ነው፡፡

በእርግጠኝነት የአቶ ሞላ አስግዶም ‹‹ተልዕኮ›› በስርዓቱ የተመራ ቢሆን ኖሮ ከትብብሩ ከማፈንገጥ ይልቅ ትብብሩ ውስጥ ቆይቶ እንዲሽመደመድ ማድረግን ቅድሚያ በተሰጠው ነበር፡፡ ምክንያቱም አቶ ሞላ አስግዶም ወደ ኢትዮጵያ ከመግባት ይልቅ ምክትል ሆነው ለስርዓቱ ጠቃሚ ስራን መስራት ይችሉ ስለነበር ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር የመግለጫውን (ፕሮፖጋንዳውን) ትልቅ ትኩረት የሳቡት ፕ/ር ብርሃኑና ድርጅታቸው ግንቦት ሰባት ናቸው፡፡ ፕ/ር ብርሃኑን ጨምሮ 90 በመቶ የሚሆነው የግንቦት ሰባት አመራር ኤርትራ እንደሚገኝ ተገልጾአል፡፡ ከአመራሩ መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ኤፍሬም አዴቦ ከሳምንታት በፊት ባስነበቡት ፅሁፍ አሁን ስርዓቱ የራሱ ተላላኪ አድርጎ ያቀረባቸው አቶ ሞላ አስግዶምን ጨምሮ አብዛኛውን የትህዴን ታጋይ ጋር መገናኘት ችለዋል፡፡

በመሆኑም ይህን ‹‹ኦፕሬሽን›› ስርዓቱ የመራው ቢሆን ኖሮ ‹‹አሻፈረኝ›› ብሎ ወደ ኢትዮጵያ ከመመለስ የግንቦት ሰባት አመራሮች ላይ ጉዳት ማድረስ እጅግ ትልቅ ጥቅም ይሰጠው እንደነበር መገንዘብ ቀላል ነው፡፡ በእርግጠኝነት በመግለጫው ‹‹አሸባሪው›› የተባሉት ብርሃኑ ነጋ፣ ውይክሊክስ ስርዓቱ ‹‹የጀኔራል ዘለቀን ልጅ መረጃ ማግኘት እንፈልጋለን›› እያለ እያደናቸው ነው የሚባልላቸው አቶ ንዓምን ዘለቀና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ላይ አደጋ ማድረስ ወደ ሀገር ከሚገባው 700 ይሁን 7000 የትህዲት ሰራዊት በላይ ስርዓቱ የሚቋምጥበት ነበር፡፡
የትህዴን ካምፕ ድረስ እየሄዱ ከሰራዊቱ ጋር የሚገናኙትን፣ ይህ እንኳ ባይሆን ከእነ ሞላ ጋር ተሰብስበው ሲመክሩ የነበሩትን የግንቦት ሰባት ከፍተኛ አመራሮች ላይ አደጋ መጣሉ አዋጭና ምን አልባትም የእነ ሞላ አስግዶም ጠባቂዎች የሚፈፅሙት ቀላል ተልዕኮ ነበር፡፡ ምን አልባትም ራሳቸው አቶ ሞላ አስግዶም ጭምር፡፡
ይህ ሁሉ ድንገተኝነት የሚያመለክተው አቶ ሞላ አስግዶም በትብብሩም ይሁን በሌላ ጉዳይ በነበራቸው ቅሬታ ከኤርትራ ለመውጣት ያደረጉትን ሂደት ስርዓቱ የራሱ በማድረግ እንደተጠቀመበትና እሳቸውንም ‹‹ሳይሸነፉ›› ወደ ሀገር እንዲመለሱ በችኮላ መወሰኑን ነው፡፡ አሁን እየተደረገ ያለው የችኮላ ፕሮፖጋንዳ ማንን እንደሚጠቅም እየቆየ የሚታይ ይሆናል፡፡

የአርቲስት ሰብለ ተፈራ ቀብር ተፈጸመ * ባለቤቱቷ በ15 ሺ ብር ዋስ ተለቀቀ

$
0
0

የ አርቲስት ሰብለ ተፈራ ቀብር ተፈጸመ * ባለቤቱዋ በ15 ሺ ብር ዋስ ተለቀቀ::

የአርቲስት ሰብለ ተፈራ የቀብር ስነሥርዓት ብዙ ሺህ አድናቂዎቿ እና ወዳጅ ዘመዶቿ በተገኙበት ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ በቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ተፈጸመ::

ባለቤቷ የሚያሽከረክረው መኪና ከቆመ መኪና ጋር ተላትሞ የአርቲስቷ ሕይወት በአዲሱ ዓመት ያለፈ ሲሆን ባለቤቷ ሞገስ ተስፋዬ ላለፉት 3 ቀናት እስር ቤት ቆይቷል:: ዛሬ ጠዋት ፍርድ ቤት የቀረበው ሞገስ በ15 ሺህ ብር ዋስ የተለቀቀ ሲሆን በቀብር ስነስርዓቷ ላይም የርሷን ፎቶ ግራፍ የያዘ “ሰብልዬ ሁሌም እወድሻለሁ” የሚል ቲሸርት ለብሶ ተገኝቷል::

sebele 1`

sebele 2

sebele 3

sebele 4

sebele 5

sebele tefera

አርበኞች ግንቦት 7 ሞላ አስገዶምን አስመልክቶ መግለጫ ሰጠ –“ተስፋ የመቁረጥ የክህደት እንቅስቃሴ”አለው

$
0
0

መስከረም 3 ቀን 2008 ዓ.ም
================================================
በኢትዮጵያ የቅርብ ጊዜ የፖለቲካ ትግል ታሪክ ውስጥ ባጠቃላይና በተለይ ደግሞ ህወሓት/ኢህአዴግ የፖለቲካ ስልጣኑን በተቆጣጠረባቸው ባለፉት ሁለት አስርት አመታት ውስጥ ህወሓት/ኢህአዴግን እንቃወማለን በሚለው ወገን ገንነው የመጡ ሁለት አፍራሽና ኋላቀር የፖለቲካ አዝማሚያዎች (trends ) አሉ። ከነኝህ ውስጥ አንደኛው ራስን በፖለቲካ አመለካከት ዙሪያ ከማሰባሰብ ይልቅ በጎጥና በዘውግ ደረጃ የመመልከትና ሀገራዊ ፖለቲካን በደም ቆጠራ የመመንዘር አባዜ ነው። ሁለተኛውና ከዚሁ ያልተናነሰው ችግር የፖለቲካ ድርጅት በመሰረታዊ ያመለካከት መርሆች ዙሪያ ሰፋ ያለ የማህበረሰብ ክፍልን የማሰባሰቢያ ድንኳን መሆኑ ቀርቶ፤ በስራ ሳይሆን ድንገተኛ አጋጣሚን በመጠበቅ ትርፍ ለማጋበስ በሚቋምጡ ሰነፍ “ነጋዴዎች“ የተቋቋሙ ሩቅ የማይሄዱ የንግድ ድርጅቶች ይመስልበ ተግባር ምንም የማይፈይዱ ”የፖለቲካ ድርጅቶች“ እንደ አሸን የመፍላታቸው ፈሊጥ ነው። እነኝህ ሁለቱም አዝማሚያዎች የህወሓት/ኢህአዴግን ህይወት ከማራዘም አልፈዉ ማህበረሰቡን ወደሚመኘው እውነተኛ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት አንድ ጋት እንኳን ፈቀቅ አላደረጉትም። ይልቁንም ዴሞክራሲን የሚናፍቁ ታጋዮች ተሰባስበውና ተጠናክረው ስርዓቱን ከመግፋት ይልቅ በግለሰብ ደረጃ ወይንም በትናንሽ ቡድኖች በመሰባሰብ የሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች በስርዓቱ በቀላሉ እየተመቱ ብዙ ታጋዮች ለሞት፤ ለስቃይና ለእስር ተዳርገዋል። አሁንም እየተዳረጉ ነው።
Mola asgedom
የዚህ አይነት የትግል አካሄድ ሩቅ እንደማያስኬድ የኢትዮጵያ ህዝብ ከተገነዘበው ቆይቷል። ይህ አካሄድ እንዲቀየርና የፖለቲካ ሀይሎች ተሰባስበው ይህንን በስልጣን ላይ ከሚገባው በላይ የቆየና አገሪቱን ለውርደት የዳረገ የጥቂት ዘራፊዎች ቡድን ከጫንቃው ላይ እንዲያነሱለት ሲማጠን ቆይቷል።ምንም እንኳን በመሪዎች ድክመት የሚመኘውን ዳር መድረስ ባይችልም ባጭር ጊዜ ልምዱ በትንሹም ቢሆን የተባበረ ትግል ሊያስገኝ የሚችለውን ጥቅም በመጠኑም ቢሆን አይቶታል።
ይህ የህዝብ ፍላጎት መኖር ግን በራሱ ይህንን የተባበረ ሰፊ ማህበራዊ እንቅስቃሴ መፍጠርን ቀላል ያደርገዋል ማለት አይደለም። በብዙ ስራ፤ በብዙ ድካምና ያላሰለሰ ጥረት የሚፈጠር እልህ አስጨራሽ ሂደት ነው። ባንድ በኩል እንዲህ አይነት ሰፊ የህዝብ እንቅስቃሴ በስልጣኑ ለመቆየት የሚፈጥርበትን ችግር የሚረዳው በስልጣን ላይ ያለው የዘራፊዎች ቡድን ይህን እንቅስቃሴ ከወዲሁ ለማምከን ያለ የሌለ የገንዘብ፤ የስለላና የተንኮል ሀይሉን ይጠቀማል። በተቃዋሚ ድርጅቶች ውስጥ ሰርጎ በመግባትና ደካማ ሀይሎችን በገንዘብ በመግዛት ወይንም በማስፈራራት እንዲህ አይነት ትብብሮች እንዳይፈጠሩ ከውስጥ ለመቦርቦር ተግቶ ይሰራል። በሌላ በኩል ደግሞ የትም የማያደርሳቸውን “የራሳቸውን ድርጅት” የሙጢኝ ብለው ለትልቅና አገራዊ አላማ እራሳቸውን ላለማስገዛት የቆረጡ ደካማ “የድርጅት መሪዎች” እንዲህ አይነቱን የጋራ እንቅስቃሴ በራሳቸው ግብዝነትና ስግብግብነት ምክንያት ብቻ ሊያሰናክሉት መሞከራቸው አይቀርም።

ይህ ግን ጊዜው ያለፈበት አዝማሚያ ነውና የሚሳካ ሙከራ አይሆንም። የተናጠል ትግል ሂደት ማብቂያው ጊዜ ተቃርቧል። የኢትዮጵያ ህዝብም ሆነ ለእውነተኛ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ የሚታገሉ ኃይሎች እንዲህ አይነቱን ፋይዳ ቢስ ሂደት የመቀበል ትዕግስታቸው ተሟጧል። በቅርብ ጊዜ የሞላ አስገዶምን መክዳት በማስመልከት የትህዴን አመራር ባወጣው መግለጫ“ኢትዮጵያን እውነተኛ ዴሞክራሲያዊት ሀገር ለማድረግ ከሁሉም ኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ጋር አብሮ መስራት የድርጅታችን መሰረታዊ መርሆ ነው” እንዳለው ይህ መሰረታዊ መርሆ በሀገራችን የጸረ ህወሓት/ኢህአዴግ ትግል የበላይነት ይዞ እየመጣ ያለ እጅግ አስፈላጊና ለድሉም ወሳኝ የሆነ የጊዜው የፖለቲካ አዝማሚያ ነው። አርበኞች ግንቦት 7 ይህን መሰረታዊ መርሆ ከምር ወስዶ የሚንቀሳቀስ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ነው።

ይህአዲስ የፖለቲካ አዝማሚያ ምቾት የማይሰጣቸው የፖለቲካ ኃይሎች መኖራቸው የሚጠበቅ ነው። የህወሓት/ኢህአዴግ የስለላ ድርጅት ከሰሞኑ ሞላ አስገዶምን በማስመልከት ባወጣው መግለጫ በግልጽ እንዳስቀመጠው ኢትዮጵያውያን የዴሞክራሲ ኃይሎች ተሰባስበው እንዳይታገሉና ስርዓቱን እንዳይፈታተኑ የማያደርገው ጥረት የለም። በዚህ በህወሓት/ኢህአዴግ መሰሪ እንቅስቃሴ ደግሞ በቀላሉ መጠቀሚያ የሚሆኑት በጋራ የሚደረግ ትግል በግለሰብ ደረጃ ያሳጣናል ብለው የሚፈሩት “የግል ጎጆና” ጥቅም የሚያስጨነቃቸው ደካማ የፖለቲካ መሪዎች ነን ባዮችን ነው። ባንጻሩ በየድርጅቶቹ ውስጥ በሚገኙት ብዙሀኑ ሩቅ አሳቢ መሪዎች ጥረትና በተለይም ደግሞ ይህን ትግል ለአላማ እንጂ ለሌላ ምንም አይነት የግል ጥቅም ያልተቀላቀሉና በትግሉ ሂደትም ትልቁን ሚና በሚጫወቱት ብዙሀን ታጋዮች አልበገር ባይነት እንዲህ አይነት ደካማ መሪዎች ተከታይ በማጣት ሲዳከሙና በሚያደርጉት እንቅስቃሴ በድርጅታቸው ውስጥ የሚነሳባቸውን ተቃውሞ መቋቋም ባለመቻላቸው በቀላሉ እየተፍሸለሸሉ ከመራገፍ በስተቀር በድርጅቶቹ ላይ ከባድ ጉዳት ሳያደርሱ ይከስማሉ።

በህወሓት/ኢህአዴግ “የስለላ ድርጅት አቀናባሪነት” በሞላ አስገዶም መሪነት ከሰሞኑ የተሞከረው የማፍረስ ንቅናቄ ከሽፎ ወደ ተስፋ መቁረጥ የክህደት እንቅስቃሴ የተቀየረው የሰሞኑ ሙከራም የዚህ አጠቃላይ ሂደት አካል ነው። በዚህ የከሸፈ ሙከራ ውስጥ እጅግ የሚገርመውና የትህዴንን ብዙሀን አመራሮች ብስለት፤ የድርጅቱን መዋቅራዊና ድርጅታዊ ጥንካሬ፤ እንዲሁም ብዙሀኑ ታጋይ ለጋራ ትግል ያለውን ቆራጥ አቋም ያስመሰከረው፤ ይህንን የማፍረስ ሙከራ የመራውና ሳያሳካለት በመጨረሻም በጣም ጥቂት ተከታዮቹን ብቻ ይዞ የከዳው ለረጅም ጊዜ የድርጅቱ ሊቀመንበር የነበረው ሞላ አስገዶም መሆኑ ነው። እንዲህ አይነት የመክዳት ሂደት ባጭር ጊዜ በማህበረሰባችን ላይ የሚፈጥረውን አስጨናቂ ስሜት የምንረዳው ቢሆንም ከዚያ በላይ ልንረዳው የሚገባው ግን በእንዲህ አይነት ከፍተኛ ያመራር ቦታ የነበረ ሰው ሙከራ አለመሳካት በእርግጥም የሀገራችን ፖለቲካ እየበሰለ፤ ከግለሰብ አመራሮች ተጽእኖ እየተላቀቀ፤ አዲስ የተባብሮ መታገል አቅጣጫን እያበሰረ እየሄደ መሆኑንና በትናንሽ ሰዎች መግተርተር ይህ ሂደት የማይቀለበስ መሆኑን የሚያመለክት የረጅም ጊዜ ግኝት መሆኑን ነው።

አርበኞች ግንቦት 7 በዚህ አጋጣሚ ለትህዴን ብዙሀን አመራርና ለሰፊው ታጋይ በመርህ ላይ ለተመሰረተው አቋማቸውና መርሃቸውን ለማስጠበቅ ለሚያደርጉት ቆራጥ ትግል ያለውን ጓዳዊ አክብሮት ይገልጻል። በመግለጫቸው ላይ በግልጽ ያስቀመጡት መርሆአቸው የኛም መርሆ መሆኑን ስንገልጽላቸው በታላቅ ኩራት ነው። ድርጅታቸውን እያጸዱ የተመሰረቱበትን መርሆ ጠብቀው ለመጓዝ ባሳዩት ቁርጠኝነትና ወደፊትም በሚያደርጉት ትግል ምንጊዜም ከጎናቸው መሆናችንንና ጓዳዊ ድጋፋችን ምንጊዜም እንደማይለያቸው በዚህ አጋጣሚ ደግመን ልናረጋግጥላቸው እንወዳለን። በመግለጫቸው ላይ እንዳሉትም ይህ ትግል ኢትዮጵያን ዴሞክራሲያዊ ሳያደርግ የማይቆምና እንዲያውም ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ለኢትዮጵያ ህዝብም በየጊዜው በሚፈጠሩ እንቅፋቶች ላይ ሳያተኩር ትግሉን በሙሉ ልብ እንዲደግፍ ያደረጉት ጥሪ የኛም ጥሪ ነው።

አንድነት ኃይል ነው!!!
አርበኞች ግንቦት 7: ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ

ጽናት። –ከሥርጉተ ሥላሴ

$
0
0

14.09.2015 /ሲወዘርላንድ –  ዙሪክ/

እንዴት ናችሁ ወገኖቼ ደህና ናችሁ ወይ?

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ - ዙሪክ)

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

ዛሬ ያለንበት ወቅት የወሳኝ ዓይን ነው። ጥንካሬ የሚያንገዋልላቸው እጅግ ውስብስብ ብንታወች – ይኖራሉ። ብሄራዊ የነፃነት ትግል ለዛውም የእርስ – በእርስ ሲሆን ረቂቅና ማስተዋልን የሚጠይቁ አመክንዮች  – ይኖራሉ። በፖለቲካ ህይወት ውስጥ አንጃ የተለመደ በመሆኑ የጥንካሬም የድክመት መለኪያ ሊሆን – አይችልም። ሂደቶች በራሳቸው ሊፈጥሩት – ይችላሉ።

ይህ እርምጃ ከግል ስሜት፦ ከጥላቻ፦ ከግል ኢጎ፦ ከኮፒ ራይት፦ ከበታችነት ስሜት፦ ተወጥቶ የፍላጎታችን ማዕከላዊ መዋቅር ማዬት ከተፈለገ በርግጥም የራዕያችን ጥርጊያ መንገድ ፍንትው ብሎ – ይታያል። አቅም ከፍላጎት ጋር ብቻ ሳይሆን ከዘመን ፈቃድ ጋር – ተጋብቷል። ለዚህም ነው የእንቅልፍ ክኒን ወስደው የነበሩ ብዕሮች ሁሉ አቧራቸውን አራግፈው የቂም ቋጠሮ ዳንቴሎችን ሲተረትሩ – የሚታዩት። የጠበቅነው ይዘረገፋል የተባለው ገመና የባለቤቱን ሆድእቃ ያለ ይግባኝ በቂም በቀል ተለውሶ የበለጠ እንድንመረምረው አጋጣሚ – ሸለመን። ሌት ተቀን የሚባዘንበት ምክንያት በህልም ውስጥ ለመኖር አለመቻል የፈጠረው ድቀት ይመስለኛል።

ሰማይና መሬት የተደባልቅ ያህል ጉሮ ወሸባዬ የሚባልለት አቶ ሞላ አስገዶም የአቋም ለውጥ ወሽኔ እርምጃ ሲል ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ ኢትዮ ሚዲያ ላይ አስነብቦናል። የመልካም ምኞት መግለጫም – ተፈርሞበታል። ትግል ማለት ይሄ ነው። በሃስብ ልዩነት እየተባለ ጊዜ ማጥፋት የለብንም ያልኩትም ለዚህ ነበር። የነፃነት ትግል በተራመደ ቁጥር እንዲህ መንገድ – ይጠርጋል። ጫጫታው፦ ሁካታው ይሄው ነበር።

አቶ ሞላ አስገዶም በሚመለከት ከፈረንሳይ ጋዜጠኞች ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ ብቻ አዳምጫለሁ። ከዛ ውጪ አንድም ቀን ብዕሬም ብራናዬም ምንም ብለን አናውቅም። አሁንም ምንም አልልም። ለምን? አጀንዳዬ ስላልሆኑ። ሌላው ከእኛ በተጻራሪ ወገን ያሉት የአሸናፊነት ስሜት ያገኙ – መስሏቸዋል።  አቶ ሞላ አስገዶም ምንም ሳይጽፉ በራሳቸው ሽጉጥ አለምን ቢሰናበቱ ኖሮ ዲል ያለ ድግስ ደግሰው – አታሞዋን ቢደልቁ ይችሉ ነበር። አሁን ግን ድርብ ኪሳራ ነው። የእኛ ሥነ – ልቦና ግን ገዢ መሬት ነው ያለው ማስተዋልን – ከፈቀድንለት።

እኔ በግሌ የመንፈስ እንቅፋት በፈቃዱ ሳይገፋ፣ እራሱን መፈንገሉ – ይታመሱ የነበሩት ግልብ ስሜቶችን ጠራርጎ አሮጌው ዓመት አቃጥሏቸዋል። ስለዚህም ደስተኛ ነኝ። ጥበብ – አይቼበታለሁ። ነገም፣ ከነገ ወዲያም፣ ከዚያ ወዲያም ማፈንገጥ – መክዳት አንጃ ሊኖር ይችላል። ብቁ አመራር መሬት ላይ ስለአለ። አብዛኛው ህዝብ ደግሞ መንፈሱን – ይጠብቃል።

ጽናት ሁልጊዜም ስንቅና ትጥቅ ሊሆን ይገባል። የነፃነት ትግል መራራ ጉዞ አረሙን ያንጠባጥባል። ፈተናን እዬጣሰ የሚሄደው ጽናት የድል ዋዜማን ያቀርባል። ሌላው ነፃነት የራበው ወገን የጠላት ጎራ ሚዲያ ሰለባ መሆን የለበትም። የጠላት መረጃ ያዳመጥኩት በሙሉ ዬዘበጠስ – ወጥ ያልሆነ – ችኩል ነበር። ስለሆነም ቀልብ ሊሰጠው አይገባም። ያልተጠበቀው ብቁ አመራር መሬት ላይ ሲገኝ እስተ ጎመራው – ፈነዳ። ቀለጦው ጠራረገው – ቀጣውም። እኛ መጠበቅ ያለብን የእኔ ከምንላቸው ሚዲያወች መሆን ይገባል። የነፃነት አርበኛው ሆነ ደጀኑ ቃናውን መጠበቅ – ይገባዋል። በዚህ ዝብርቅ – ሙርቅርቅ የሰመጠ መርከብ ትጥቅን መፍታት – አይገባም።

በጣም የገረመኝ ነገር ጥምረቱን የሚያቅልል ዕይታወች – አዳምጫለሁ። የሚፈራ ጉልበታም አቅም መኖሩ እንዲህ – ያፍረከርካል። አንድነት እንዲህ የእንፋቅቅ ያስኬዳል። ይህ የድል መንገድ ባይሆን በደቡብ ዞን ያሉት አንድ ለመሆን ምን አንደፈደፋቸው? ይህ በሀገረም በውጪ ሀገር የሚታይ አመክንዮ ነው። ሌላው ግን ከኢትዮጵያ መልስ ሰተት ብሎ የገባ አዲስ አጀንዳ አለ – የወያኔ የክብር እንግዶች።  ይህን በተቃጠለ ካርቦን ፁሑፌ ገልጭው ነበር። ኮተት እያሉ ከወዳደቁበት እዬተነሱ ያሉት ጥምረቱ የትግራይን ልጆች ማግለል ይገባል ይላሉ። ኢትዮጵያን ከነችግሮቿ የመሸከም አቅም ብልህነት ነው። መውደቅን የፈቀዱ እንዲህ እንደ አቶ ሞላ ሲኖሩ ደግሞ መቃብራቸውን – ይቆፍሩ። ታጥቦ – ጭቃ።

ዛሬ ትግሉ ዬሁሉም ነው። ባለቤትነቱም የሁሉም ነው። ጥበቃውም የሁሉም ነው። እግዚአብሄርንም እንመን። የእምነት ጽናትም ይኑረን። ፈተናችን ብዙ ነው። ትእግስትና ጽናትን – ይጠይቃል። ጽላታችን ኢትዮጵያን እናድርግ። መንገዱ አቀበት፣ ዳጥ፣  ጨቀጨቅ ነው። ሆድ – አይባሳን። እሩቅ እንሰብ። ብርሃንን – እንናፍቅ። ዘመኑ እራሱ ፈተና ውስጥ ነው። ባለቤት ግን አለው። ሁሉም ለመልካም ነው። በጎ ነገሮችን ለማጣጣም መራራ ሂደቶችን መፍቀድን ይጠይቃል። እንጽና። እውነት ከእኛ ዘንድ ነው። አምላካችንም አድምጦናል። „በመከራ ጽና“ ይላል የእግዚአብሄር ቃል።

ኢትዮጵያዊነት ያሸንፋል።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 

 

 

 

 


የአቶ ሞላ አስገዶም ክህደትና ህወሀትና የግንቦት ሰባት ጠላቶች ጉሮ ወሸባዬ

$
0
0

በበላይ አካሉ: belayakalu@yahoo.com

አቶ ሞላ አስገዶም ጥቂት ተከታዮቹን ይዞ ተመልሶ ወደ ህወሃቶች ካምፕ መቀላቀሉን በኢሳት ሰበር ዜና ከተነገረበት እለት ጀምሮ በጣም አሳዛኝና አሲቂኝ አስተያየቶችን ሰምተናል:: የገበያ ግርግር ለሌባ ሰርጉ ነው::
mola
ህወሀት/ወያኔ በጣም አሲቂኝ በሆነ መልኩ እንዲህ ብሎናል: “ለበርካታ አመታት በኤርትራ መንግስት አማካይነት ሲደራጅ የነበረ የጥፋት ሀይል ብሔራዊ የመረጃና የደህንነት አገልግሎት በዚህ ሀይል ውስጥ ከነበሩ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ጋር ምስጢራዊ የሆነ የግንኙነት ስርዓት በመመስረት በተሰራው የተቀናጀ የኦፐሬሽን ስራ አማካይነት በተደራጀ መልኩ ከነሙሉ ትጥቁና የሰው ሀይሉ ጋር መስከረም 1 ቀን 2008 ዓ. ም. ወደ ሃገሩ እንደገባ የጋራ ፀረ ሽብር ሀይሉ አስታውቋል፡፡”
እንደ ህወሀት አባባል እነሞላ 10 ዓመት በላይ ወደ ኤርትራ የተላኩት ተዝናንተው እንዲመጡ ነበር ማለት ነው? ለነገሩ የህወሀትን አሲቂኝ መግለጫ ወደ ጎን እናድርገውና፡ ከህወሀት መግለጫ በስተጀርባ ያለውን በጥቂቱ በአጭሩ እናስቀምጠው::

ህወሀት ይሄንን የተለመደ ቀዳዳ ዲስኩሩን ያስተላለፈልን አንደኛ የስለላ ድርጅቴ አቅም ከፍተኛ ነው ማንኛውም አይነት የተቃውሞ እንቅስቃሴ ውስጥ እጄ አለበት ብሎ ኢትዮጵያዊያን ላይ የስነ ልቦና ሽብራዊ ተጽእኖ ለማድረግ: ሁለተኛ ነገር አሁንም የትግራይ ህዝብን በሙሉ የህወሀት ደጋፊ በማስመሰል ከዚህ ቀደም የነበረውን የከፋፍለህ ግዛ ፓለቲካ ይበልጥ በማስፋት ሌላው ኢትዮጵያዊ በትግራይ ህዝብ ላይ ያለውን ጥላቻ ለማስፋትና: በአንፃሩ ደግሞ የትግራይ ህዝብን ከህወሀት ውጪ ምንም አማራጭ እንዳይኖረው ማድረግ: በሶስተኛ ደረጃ በራሱ በህወሀትና በአንዳንድ የምቀኛ የተቃዎሚ ሀይሎች ግንባር ሲጮህበት የከረመውን የቁራ ጩሀት ደረቅ ተራ ፕሮፓጋንዳ “ሻኧቢያ የኢትዮጵያ ጠላት ስለሆነ በሻኧቢያ በኩል የሚደረገው ትግል አያዋጣም” የሚለውን ለማስተላለፍ ነው።
በመጀመሪያ ደረጃ እውነታው አሁን ህወሀት እንደሚቀባጥረው ሳይሆን እውነት እነ የአቶ ሞላ አስገዶም የተላኩት ከ10 አመት በላይ ለብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ወቅታዊ መረጃ እንዲደርስ ለማድረግ ሳይሆን የህወሀትን አስከፊ የገዳይ ስርዓት ለመታገል ስለመሆኑ ለማወቅ የፓለቲካ ጠቢብ መሆን ወይንም የግድ እንደነ ኤልያስ ክፍሌ: ክንፉ አሰፋ: አበበ በለውና ሌሎችም “ድሮም ብዪ ነበር” ባዮች የምቀኛው የተቃዎሚ ሀይሎች ግንባር አባል መሆንን አይጠይቅም::

ምክንያቱም እነ አቶ ሞላ አስገዶም ከህወሀት ጋር በውስጥ ቢሰሩ ኖሮ ቢያንስ ቢያንስ እንዴት ፕሬዝደነት ኢሳያስ አፍወርቂንና ሌሎች ከፍተኛ የኤርትራ ባለስልጣናት ላይ 10 ዓመት ሲቀመጡ አንድ ጊዜ እንኳን የመግደል ሙከራ አላደረጉም? እሺ እሱም ይቅር ለካስ በምቀኛው የተቃዎሚ ሀይሎች ግንባር መዝገበ ቃላት መሰረት ወያኔና ሻእቢያ አንድ ናቸው:: እሺ ቢያንስ ቢያንስ እነ ዶ/ር ብርሀኑና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ላይ የመግደል ሙከራ አላደረጉም? ወይስ አዝነውላቸው ነው?

ሀሰትና ስንቅ እያደር ያልቅ እንደሚባለው ከሰሞኑ ጉሮሮዋቸው ደርቆባቸውና ብእራቸው ዶልድሞባቸው የከረሙት የምቀኛው የተቃዎሚ ሀይሎች ግንባር አባሎች አዲስ ስራ አግኝተዋል:: ስለዚሁም በተለያየ ቀለማቶች የያዝዋቸውን አዲስ የማደንቆሪያ የጭቃ ጅራፋቸውን ይዘው የፈረደበትን ግንቦት 7ትን ለመውቀጥ እንደ ጀት ተተኩሰው “ድሮም ብዪ ነበር” የሚባለውን ቦንብ እያዥጎደጎዱት ይገኛሉ። እንደሚታወቀው አባላቱ ሻእቢያን በመቃወም ስም ለረጅም ጊዜ ሲያራምዱት የነበረው ፀረ_ግንቦት 7 ፕሮፓጋንዳ ዘመቻ በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች በቅርብ ጊዜያት በተደረጉ የአርበኞች ግንቦት7 የድጋፍ ማሰባሰቢያ ስብሰባዎች ላይ ኢትዮጵያዊያን በነቂስ ወተው ስብሰባዎችን መካፈል ብቻ ሳይሆን ገንዘባቸውንና አንጡራ ሀብታቸውን ለትግሉ በማዋጣት ደጀንነታቸውንና ለሚደረገው ትግል ቁርጠኝነታቸውን በማሳየት እንኳን የጥቂት የዲያስፓራ የተልባ ቢንጫጫ ህልመኞች የምቀኛው የተቃዎሚ ሀይሎች ግንባር አባሎች ተራ የአሉባልታ ጋጋታ ብቻ ሳይሆን እራሱን የህወሀት/ወያኔን የወንጀለኛ ቡድን አንገት አስደፍትዎል::

ሌላው አሳዛኝ ሁኔታ አንዳንድ ፅንፈኛ ኢትዮጵያዊያኖች ህወሀት/ወያኔ በቀደደው የዘረኝነት ቀዳዳ ውስጥ ወድቀው የተከበረውን የትግራይ ህዝብን ከአንድ ግለሰብ ጋር በማገናኘት ዘርን ሲሳደቡና ልዩነቶችን ከወያኔ በላይ እያሰፉ የራሳቸውን ጠባብነትና ባዶ ጭንቅላት አሳይተዋል:: ለመሆኑ ልደቱ አያሌው በጠራራ ፀሀይ ህዝብን ሲከዳ ጠቅላላ የአማራ ህዝብ ባንዳ ነው መባል ነበረበትን? እንዴ ስንት ኦሮሞ: ጉራጌ: ወላይታ: አማራ: ከንባታ: አፋር: አደሬ: ሶማሌ: ወዘተ በየጊዜው እየከዳ የህወሀት/ወያኔ አገልጋይ ሲሆን አይተን የለ እንዴ? ታዲያ የትኛው ግለሰብ ነው ዘሩ ተጠቅሶ የተረገመው? ለማንኛውም እነዚህን ጥቂት በዘረኝነት ልክፍት ያበዱ በሽተኞችን የአቶ ሞላ አስገዶምን ክህደት ከጠቅላላው የትግራይ ህዝብ ጋር እያገናኙ የዘረኝነት አጀንዳቸውን የሚነዙትን ከህወሀት/ወያኔና ከምቀኛው የተቃዎሚ ሀይሎች ግንባር አባሎች እኩል መታገል አለብን:: ምክንያቱም እንደዚህ አይነት ፍጹም ጥላቻ ላይ የተመሰረተ አንድን ማህበረሰብ በአንድ ከረጢት ዉስጥ አሰስገብቶ መፈረጅ በጣም ከዘቀጠ አስተሳሰብ የሚመጣ ድርጊት ነው ::

እንደሚታወቀው በእውነተኛ ትግል ውስጥ መውደቅ: መነሳት: መታሰር: መቁሰል: መክዳት: መሞትና ወዘተ ይኖሩበታል:: ስለዚህም ዛሬ ብቻ ሳይሆን ትናንትም ዛሬም ነገም ሌሎች ሞላ ይኖራሉ:: ይሄንን የማያውቅ ካለና በነ የምቀኛው የተቃዎሚ ሀይሎች ግንባር አባሎች ተራ የአሉባልታ ፕርፓጋንዳ የሚታለል አለ ብዬ አላስብም:: ዋናው ነገር እንጨት ካልነፈጉት እሳት አይጠፋም እንደሚባለው: የዘረኛው የወያኔ አስከፊ አገዛዝ ጭቆናውን እስካላቆመ ድረስ በዛች አገር ላይ የነፃነት ትግል አይቆምም::

ስለዚህም አሁንም ቢሆን ደጋግመን ለህወሀት/ወያኔና ለምቀኛው የተቃዎሚ ሀይሎች ግንባር አባሎች የምንነግራቸው አህያ ሞተች ተብሎ ጉዞ አይቀርም:: ኢትዮጵያዊያኖች የምንታገለው አቶ ሞላ ስለገባ ወይም ስላልገባ ሳይሆን ወይንም ዶ/ር ብርሀኑ ስለገባ ወይም ስላልገባ ሳይሆን ወይንም ጀነራል ከማል ገልቹ ስለገባ ወይም ስላልገባ ሳይሆን በአገራችን ኢትዮጵያ ምድር ላይ ሰላም: ፍትህና ዲሞክራሲ በነውጠኛውና በዘረኛው የወያኔ የጉጅሌ ስርዓት ስለተነፈግንና በሀገራችን ላይ እንደ ማርያም ጠላት እየተደበደቡ: እየታረዙ: እየታሰሩና እየተገደሉ መኖር ስላንገሸገሸን ነው::

የሰካራም ግጥም ሁል ጊዜ ቅዳ ቅዳ: ስለዚህም ዛሬ የህወሀት/ወያኔና የምቀኛው የተቃዎሚ ሀይሎች ግንባር አባሎች ባዶ ጉሮ ወሸባዬ እና አሁንም ላንቃቸው እሲኪላቀቅ የሻእቢያን ጠላትነን ሊነግሩን አፍንጫችሁን ቆርጠን ለአፋችሁ እናጉርሳችሁ አይነት ፓለቲካ ቢጫወቱ ማንም አይሰማቸውም:: ምክንያቱም እንደ ተረቱ “ብርሌ ከነቃ አይሆንም እቃ ነው:” ዛሬ ለየትኛውም ኢትዮጵያዊ ከህወሀት/ወያኔ የገለማ አገዛዝ ውጪ ማንም ጠላት የለውም፡ ስለዚህም ይሄንን አስከፊ ስርዓት ለመታገል ኢትዮጵያዊያን ከኤርትራ ብቻ ጋር ሳይሆን ገና ከሰይጣንም ጋር ቢሆን ያብራሉ::

ድል ለኢትዮጵያዊያን::

የሞላ ኣስገዶም ጉዳይ ስርዓቱ የቆመበትን መሰረት ማሳያ ነው (ገለታው ዘለቀ)

$
0
0

 

Molla Asgdom 3ከኣመታት በፊት በምርጫ ዘጠና ሰባት ኣካባቢ ኣዋሳ ከተማ ውስጥ የገጠመኝ ነገር ትዝ ይለኛል ። በኣዋሳ ከተማ  ቆይታየ ጊዜ ከኣንድ ታዋቂ የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት ውስጥ እሳተፍ ነበር። በዚህ ድርጅት መሳተፍ እንደጀመርኩ ብዙም ሳልቆይ  የወጣቶች ጉዳይና የድርጅት ጉዳይ ሆኘ ተመደብኩ።ታዲያ  በዚያ ኣጭር ጊዜ ቆይታየ  የመንግስትን የስለላ ስራና ተፈጥሮ እንድረዳ እድል ስለሰጠኝ  ያ ጊዜ ኣስተማሪየ ሆኖ ይሰማኛል ። በውነት ለመናገር  ያ የኣዋሳ ቆይታየ ስለ ወያኔ ያለኝን መረዳት ኣራምዶት ነበር።

ዛሬ የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (TPDM) መሪ የነበረው ኣቶ ሞላ የተወሰኑ ታጋዮችን ይዞ ወደ ኢትዮጵያ ገባ የሚለው ዜና ከተሰማ በሁዋላ ያ የኣዋሳው ትዝታየ የኋሊት በምናብ ታወሰኝ። በተለይም የኣቶ ሞላ ኣስገዶምን ኢንተርቪው ሳይ “እኛ  ከመንግስት ጋር ስንሰራ ቆይተናል። ግንኙነት ነበረን” ሲሉ የኣዋሳ ገጠመኘን በጣም ኣጉልቶ ኣሳየኝ።

እስቲ ኣዋሳ የሆነውን ላውጋችሁ። ኣዋሳ ከተማ ውስጥ እሳተፍበት በነበረው የፖለቲካ ድርጅት ውስጥ ከኮሚቴዎቹ መካከል ኣንዱ ማለትም የህዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊው በጣም ይቀርበኝ ነበር። ኣቶ ኤልያስ ይባላል። ይህ ሰው ትሁት፣ ተቆርቋሪ፣ ለኣገር ኣሳቢ ነው። ኣቶ ሞላን ይመስላል። በስብሰባዎች ወቅት ማስታወሻ መያዝ ይወዳል። ስብሰባዎችን ስንጨርስ ኣቀፍ እያደረገ ወደ ጎን ወሰድ ያደርገንና ለድርጅቱ ያለውን ፍቅር፣ የእኛን ኣስተዋጾ ያደንቃል። እኔም እውነቱን ለመናገር ኣመንኩት። ታዲያ ከእለታት ኣንድ ቀን  የተለመደውን ስብሰባችንን ኣጠናቀን ስንጨርስ

“ የማወራህ ብርቱ ሚስጥር ኣለኝና ኣብረን ወጣ እንበል”  ኣለኝ ለስላሳው ኣቶ ኤልያስ

በደስታ። እንዴውም እኔም ዛሬ የማካፍልህ ኣሳብ ኣለኝ::

በተለይ በኣዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኣካባቢ ልዘረጋው ያሰብኩትን መዋቅርና ፕላን ለማሳየት ፋይሌን ከፈትኩና ኣንድ ገጽ ወረቀቴን ይዤ ወጣሁ። እንደተለመደው ኣቶ ኤልያስ ኣቀፍ ኣርጎኝ እየመራኝ ከጽህፈት ቤቱ ግቢ ወጥተን ጉዞ ጀምረናል። ወደየት እንደምናመራ ኣልገባኝም፣ ኣልጠይቅምም። የኣዋሳው ዩኒቨርሲቲ ፕላኔ መስጦኝ ስለነበር በዚያ ዙሪያ ኣንዳንድ ኣሳብ እያነሳሁለት እንጓዛለን። ከጥቂት ጉዙ በኋላ ወደ ኣንድ የማይመች ኣጣብቂኝ ቦታ ይዞኝ ገባ።

ወደ ተሻለ ቦታ ሄደን ሻይ ቡና እያልን ብናወራ ኣይሻልም ኣቶ ኤልያስ?

ኣንድ ርምጃ ፈንጠር ብሎ ቆመና ጥቂት ዝም ኣለ።  ግብዣየን እያሰበበት መስሎኝ ደግሜ ጠየኩት።

ኣቶ ኤልያስ ቀና ኣለና

“ኣይ! ሌላ ጊዜ ይሻላል ኣሁን ግን የማጫውትህ  ብርቱ ምስጢር ኣለኝ “

ኣጫውተኝ፣ ምን ችግር ኣለ……….።   ፈርጠም ብየ። የመሰለኝ ያው ከድርጅቱ እቅድ ጋር የተያያዘ ጉዳይ ነውና ።

“ችግር ገጥሞኛል እባክህ”    ኣለ ኣቶ ኤልያስ ተስፋ እንደቆረጠ ሰው ፊቱን ኣቀጭሞ።

ምን ችግር ገጠመህ?   መልሱን ሁሉ በኪሱ እንደሞላ ሰው ዘና ብየ

“ተይዣለሁ”

ማን ነው የያዘህ ….  ማለቴ ኣልገባኝም??…..

“ይዘውኛል”

እነማን ናቸው የያዙህ ኣቶ ኤልያስ?

“ደህንነት ይዞኛል”

ኣልገባኝም?

“የመንግስት ደህንነት ይዞኝ ለነሱ እየሰራሁ እገኛለሁ”

ግራ ገባኝ በውነት።

ለነሱ እየሰራሁ ነው ስትለኝ ምን ማለት ነው?

“በቃ የደህንነቱ ዋና ሃላፊ ይዞኝ ለኛ ሰላይ ሁን ኣለኝ፣ ለኛ የማትሰልል ከሆነ በኣንተና በቤተሰብህ ላይ ፍረድ ስላለኝ ለነሱ እየሰራሁ እገኛለሁ። ቀን ቀን ከናንተ ጋር ተሰብስቤ ማስታወሻ ስይዝ እቆይና ማታ ማታ በሚኖረን ስብሰባ ላይ ሪፖርት ኣደርጋለሁ። በተለይ ኣንተ ወደዚህ ከመጣህ በሁዋላ የኣንተን ንግግሮች በሚገባ ማስታወሻ ይዤ ሪፖርት እንዳደርግ ታዝዤ ይህንን በማድረግ ላይ እገኛለሁ። ደህንነቱ ይከታተልሃል።”

ስንት ጊዜ ሆነህ እንዲህ ስታደርግ?

“ከዓመት በላይ ይሆነኛል”   ልክ ኣቶ ሞላ ኣስገዶም ከዓመት በላይ ከመንግስት ጋር ስሰራ ነበር እንዳሉት::

ይህንን ጉዳይ ለድርጅቱ መሪዎች ኣሳውቀሃል?

“በፍጹም:!”  ምላሱን ጎልጉሎ

ኣቶ ኤልያስ ቀጠለ …….“ ላንተ ብቻ ነው የምነግርህ…. ላንተ የምነግርህም በተለይ ስብሰባዎች ላይ የምትናገረውን እንድትጠነቀቅ፣ ይህንን የኣዋሳ ዩኒቨርሲቲ እቅድህን እንድታዘገየው ነው። “

እውነቱን ለመናገር በጣም ግራ ተጋብቼ ነበር። ይሁን እንጂ ይህ ሰው ኣሁን ይህን የሚነግረኝ ለእኔ ኣሳቢ ስለሆነ ነው ብየም ኣሰብኩ። ሁለታችንም መሬት መሬት እያየን ነገሮችን በማላመጥ ላይ እያለን። ኣንድ የቸኮለ ሰው የሚመስል በጎናችን ሲያልፍ

 

“ሰላም ኤልያስ” ኣለ።

ሰውየው በጎኔ ሲያልፍ ኣየሩን ቀዝፎት ነበር። ለምን በዚያ መጠጋጋት በስራችን እንዳለፈ ኣላውቅም። ለማስፈራርትም ሊሆን ይችላል።

የኣየር ላይ ሰላምታ ተለዋውጠው ሲያበቁ ኤልያስ ጠበብ ያለ ሳቅ ጀመረ።

“ይሄም የኛ ሰው ነው….ሰላይ ነው…  ማታ ማታ ሁሌ እንገናኛለን”

 

ኣሁን ጨዋታ በቃኝ። ብቻየን መሆንና ማሰብን መረጥኩ።

ጥሩ ኣቶ ኤልያስ ስለ ሰጠኸኝ መረጃ ኣመሰግናለሁ። ሌላ ጊዜ እንጫወታለን። እጄን ዘረጋሁ። ለሰላምታ።

“ኣንተንም በቅርቡ ሊያነጋግሩህ ሊጠሩህ እንደሚችሉ እገምታለሁ።”

እኔን?

“ኣዎ! ” ደሞ ይስቃል

 

ውስጤ በሸቀ። ዛሬ ማታደህንነቱን ስታገኘው ወደኔ ኣትምጡ በልልኝ ብየ የማመናጨቅ ያህል ሰላም ብየው ተለየሁ።

ጉዳዩን ሮጦ ለሌሎች ከመናገር በፊት መመርመር መረጥኩና ጋሪ ተሳፍሬ ወትሮም ወደምወደው የኣዋሳ ሃይቅ ዳር ኣመራሁ። በዛ ቁጭ ብሎ የኣዋሳን ግርማ እያዩ ማሰቡ ይረዳል።

ኣዋሳ ሃይቅ ዳር ቁጭ ብየ ማሳብ ጀመርኩ።

ይህ ሰው እንዴት ይህን ብርቱ ምስጢር ሊነግረኝ ቻለ?

ለምንስ እኛን ሰላማዊ ታጋዮችን በዚህ ደረጃ መሰለል ኣስፈለገ?

ምን የተደበቀ ነገር ኣለን?

ምን ስለላ ያስፈልገናል? ብዙ ጥያቄዎች ያለ ወረፋ በኣይምሮየ በፍጥነት ይጎርፋሉ። ኣንድ ደረጃ ከፍ ብየ ማሰብ እንዳለብኝ ተሰማኝ።

ያኔ ኣገሩ ኣንጻራዊ የሆነ ሰላም ነው። ብዙ የፖለቲካ ድርጅቶች በተሻለ ኣንጻራዊ ነጻነት ይሰራሉ ፣ ምንድነው ይሄ ነገር?……… ኣሳብ ሳወጣ ሳወርድ ከቆየሁ በሁዋላ የወያኔን ዘዴ ለመረዳት ብዙ ኣልተቸገርኩም። የኣዋሳ ጀምበር ደህና እደር ኣዋሳ ስትል፣ የሃይቁ ፍጡራን እነ ጉማሬ በውሃ ሲጫውቱ ከተቀመጥኩበት ተነሳሁ። ከሃይቁ ዳር ዳር ቀጥፌ የነበረውን ሳር ወደ ውሃው ወረወርኩና ሽቅብ ወደ ማረፊያየ ኣቀናሁ።

ግምቴን ይዤው ጥቂት ቀን ቆየሁና የሚቀጥለው የኮሚቴው ስብሰባ ላይ ተገኘሁ። ስብሰባው ቅዝቅዝ ብሏል። ኣዲስ ኣሳብ ኣይሰነዘርም። ጥቂት የኮሚቴው ኣባላት ላይ ምክንያት የለሽ ደረቅ ፈገግታ ኣያለሁ። እርስ በርስ መተያየት ተያይቶ ሲያበቁ ፈገግ ማለት ሆነ ስራችን። እንዲሁ የሆነ ያልሆነውን ጥቂት ኣወራንና የመለያያ ጊዜ ደረሰ። ኣቶ ኤልያስን ሰረቅ እያደረኩ ኣይ ነበር::  ለሌሎችም ተመሳሳይ ነገር ነግረው እንደሆነ ከኣይምሮኣቸው መረጃ ለመስረቅ ጥረት ኣደረኩ። ለማናቸውም ኣንዱን የኮሚቴ ኣባል መጨረሻ ላይ በጎን በጎን ኣድርጌ በማውራት ለሌሎችም ይህን ለኔ የነገረኝን መንገሩን ለመረዳት ኣስቤ ጠየኩት። በርግጥም ለእኔ የደረሰኝን ኣይነት መረጃ ለዚህ ሰውም እንደደረሰው ገባኝ።

ነገሩ እያደር እየበራልኝ መጣ። ኣቶ ኤልያስ በርግጥ የስለላ ስራ ይሰራል። የስለላ ስራውን የሚሰራው ግን እንገልሃለን ስለተባለ ሳይሆን ለረጅም ጊዜ የወያኔ ኣባል ነው። ኣሁን የተሰጠው ሚሽን በዚህ እኔ በምሳተፍበት የፖለቲካ ድርጅት ውስጥ በሃላፊነት ቦታ ሰርጎ በመግባት በዚህ  ቀጣና ያለውን ሰላማዊ ትግል ማፍረስ ነው። ኣቶ ኤልያስ ደምበኛ ወያኔ ሲሆን ለእኔ ያንን ምክር መሳይ ማስፈራሪያ የሚነግረኝ በስብሰባዎች ላይ ኣሳብ እንዳላቀርብ፣ ፈርቼ ቶሎ ከዚያ ድርጅት እንድወጣ ነው። ይህ ሰው ተልእኮው ይሀ ነው።  ኣቶ ኤልያስ ጥሩ ሰው ይምሰል እንጂ እየተቅለሰለሰ ስራ ይጎትት እንደነበር ኋላ ላይ መገምገም ችየ ነበር።

ወያኔ  የተቃዋሚ ድርጅቶችን ለመምታት የሚጠቀማቸው ስልቶች ብዙ እንደሆኑ ይህ ጉዳይ ያሳየኝ ጀመር። ተገረምኩ። ኣብሪ ጉዳይ ሆኖ ታየኝ። ጉዳዩ ኣገራዊ ሆኖ ገዝፎ ታየኝ። በርግጥ በማእከላዊ ደረጃ፣ በሁሉም ፓርቲዎች ዘንድ ይህ ኣይነቱ የወያኔ ኣሰራር ወጥነት ሊኖረው እንደሚችል ኣመንኩ።  በውነት ኢትዮጵያ ያሳዘነችኝ ያን ቀን ነው። ኣሳዘነችኝ። ሚናው ያለየለት ትግል ውስጥ ሆና ግራ ተጋብታ ታየችኝ። ወያኔ ትግሉን እንዴት እንዳወሳሰበው ሳይ ኢትዮጵያን ለቆ የመውጣቱ ጉዳይና የታጠቁ ሃይሎችን የመቀላቀሉ ጉዳይ በውስጤ ሲደምቅ ይሰማኝ ነበር። የታጠቁት ሃቀኛ ናቸው፣ ወያኔ ሰርጎ ኣልገባባቸውም የሚለውን እምነት ከየት እንዳፈስኩት ባላውቅም የተሻለ ኣማራጭ መስሎ ግን ታየኝ።

ከሁሉ በላይ ግን የወያኔ ስርዓት በምን ላይ እንደቆመ የመመርመሩ ጉዳይ ዝንባሌየን ሳበው። ይህ ጥያቄየም የሃገሬን የፖለቲካ ችግር የሚያስረዳኝ  ለወደፊት ተሳትፎየም በመረዳት ላይ ያተኮረ ድጋፍ ለመስጠት የሚረዳኝ መሰለኝ።

ብዙ ሰው እንደሚረዳው የወያኔ መራሹ መንግስት በትግል ሂደቱም ሆነ ኣሁን ስልጣን ከያዘ በሁዋላ የሚጠቀምበት ስልት ጠለፋ (haijacking)መሆኑ በመረጃ ተደግፎ ገባኝ ። በሰፊው ኣገራዊ ችግርም ሆኖ ስለታየኝ ኣዲስ ነገር መሰለኝ።

ህወሃት ራሱ “ኢሃዴግ” ብሎ የሚጠራውን ካባ ለመልበስ ሲል የተለያዩ የብሄር ድርጅቶችን የፈጠረ ሲሆን እነዚህ ድርጅቶች በወያኔ ሙሉ በሙሉ የተጠለፉ ናቸው። እንቅሳቃሴዎቻቸው ሁሉ በህወሃት የተጠለፈ፣ መጠለፍ ብቻ ሳይሆን በቁጥጥር ስር የዋሉ ናቸው። ህወሃት እነዚህን ድርጅቶች ጠልፎ  ጠልፎ ኣንድ “ኢሃዴግ” የሚባል ካባ ይለብስና መንግስት ሲመሰርት ደግሞ መንግስትን ራሱን በሙሉ ሲጠልፈው እናያለን። ሰኪዩሪቲው፣ወታደሩ፣ ሲቪል ሰርቪሱ በሙሉ የመንግስት ተቋማት በህወሃት ተጠልፈው እናያለን። ይህ ብቻ ሳይሆን የተቃዋሚውን ክፍል ሰላማዊውን ትግልና የትጥቅ ትግሉንም መጥለፍ ለዘላቂ ስልጣን ይጠቅመኛል ብሎ ስለሚያስብ ኣንዳንዴ ራሱ መንግስት ተቃዋሚ ነን የሚሉ ድርጅቶችን እየፈጠረ ኣንዳንዴ በእውነተኛ ተቃዋሚ ድርጅቶች ውስጥ እስከ ሃላፊነት ደረጃ የሚደርሱ ኣስመሳይ ወያኔዎችን እየሰገሰገ የጠለፋውን ስራ ሲሰራ እናያለን። ይህ የሚያሳየው ራሱ መንግስት በጠለፋ ላይ የተዋቀረ መሆኑን ነው። ይህ የህወሃት መሰረታዊ ት በስልጣን ላይ የመቆያ እምነትና ዘዴ ነው። ህወሃት ወደ ስልጣን ሲመጣም ከመጣም በሁዋላ የማይለወጥ ይህ የጠለፋ ዘዴው በዜጎች ሁሉ ዘንድ መታወቅና መጋለጥ ኣለበት። እውነተኛ የተቃዋሚ ድርጅቶችም በተለይ ኣመራር ኣካባቢ ያሉ ሰዎች ትግሉ እንዳይሄድ ሲያደርጉ ይህን የወያኔን የጠለፋ ተፈጥሮ  በመገንዘብ ኣባላት ኣመራሮቹን ወጥሮ ሊይዝ ይገባል። በየጊዜው ትግሉ የት ደረሰ? ብሎ ወጥሮ ሊይዝ  ይገባል። የየፖለቲካ ፓርቲ ኣባላትና ንጹሃን ኣመራሮች ድርጅታቸው ወደ ኣንድነት የማያመራበትን ምክንያት ኣጥብቀው መጠየቅ ወደ ኣንድነት የማያመራ ከሆነ መልቀቅና ማጋለጥ ያስፈልጋል።

ለዛሬው ጽሁፌ መነሻ ወደ ሆነኝ ጉዳይ ልመለስና በትህዴን ሊቀመንበሩ በኣቶ ሞላ ኣስገዶም ጉዳይ ልንደነቅ ኣይገባም ለማለት ነው የቆምኩት።ይህ ጉዳይ የስርዓቱ መሰረት መገለጫ ነው ለማለት ነው። ኣቶ ሞላ ኢትዮጵያ ከገቡ በኋላ የሚነግሩን ከመንግስት ጋር ስንሰራ ኣንድ ኣመት ኣልፎናል  ረዘም ላለ ጊዜ ስንሰራ ነበር ይላሉ። ይህ ማለት ኣቶ ኣንዳርጋቸውንም ያሳፈኑት እነሱ ናቸው ማለት ነው። ኣንዳርጋቸውን ሲያታልሉ ሲሰልሉ ነው የከረሙት። ያሳዝናል።

ሲሰልሉ የቆዩበት ጊዜ ግን ውሸት ነው። ወያኔ በጣም ይፈራ የነበረው የታጠቁ ሃይሎችን ሲሆን እነዚህን ሃይላት ለመጥለፍ  እንደ ትህዴን ኣይነቱን መጥለፍ ወሳኝ መስሎ ነው ይሚታየውነው።ከስልጣን የሚያስለቅቀው ሃይል ሲፈጠር ደግሞ ለመጨረሻ ጊዜ ኣማራጭ (worst case scenario) የሚያገለግል ሃይል ኣድርጎም ነበር የሚያየው።

በመሆኑም በዚህ ድርጅት ውስጥ ከመሪው ጀምሮ እንደ ኣዋሳው ኣቶ ኤልያስ ኣይነት ሰው ኣስቀምጦ የትጥቅ ትግሉ እንዳይራመድ ማድረግ፣ የትጥቅ ትግሉ እንዳይራመድ ብቻ ሳይሆን  በስርዓቱ ተማረው በትጥቅ ትግል ወያኔን ለመጣል ከኢትዮጵያ የሚመጡትን ኢትዮጵያዊያንን ይዞ በማቆየት፣ ወይም በማጥፋት ወይም ኣሳልፎ በመስጠት ስራቸውን ሲሰሩ ቆይተዋል። ኣቶ ኣንዳርጋቸው ኣንዱ ሰለባ ናቸው።

ልብ በሉ …..ትህዴን ከተቋቋመ ረጅም ጊዜው ሲሆን ብዙ ወታደር ኣለው ተብሎ  ይወራል። የሚገርመው ግን ኣንድ ቀበሌ እንኳን ሲይዙ የትጥቅ ትግሉን ሲያጠናክሩ ኣይታይም።ህወሃት በተቋቋመ በስድስት ወሩ ከፍተኛ ውጊያዎችን ኣድርጎ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ነጻ መሬት እያሰፋ ነበር የሄደው። እነ ሞላ  ኤርትራ ቁጭ ብለው ሌሎች ተቃዋሚ ሃይላትን እያዳከሙ የወያኔ ደጀን ሆነው ቆይተዋል። እነዚህ ሃይሎች የትጥቅ ትግሉን የሚጠልፉ ቡድኖች ናቸው። ይህ ማለት ግን ኣብዛኛውን የዋህ የትህዴንን ኣባል ኣይወክልም። በየትኛውም የተቃዋሚ ድርጅት ውስጥ ወያኔ ግዙፉን ህዛባዊ ድጋፍ ኣያገኝም። ህዝቡ ተቃዋሚዎች ኣለን የሚሉትን መርህ ስለሆነ የሚደግፈው ወያኔ ይህን ሃይል መቼም ቢሆን ሊጠልፈው ኣይችልም። ይሁን እንጂ ኣመራር ላይ ያሉትን ኣንዳንዶችን እንዲህ እየጠለፈ ትግሉን ማጓተቱ ኣንዱ የስርዓቱ እምነትና መሰረት መሆኑን መረዳት ኣለብን። ለዚህ ነው ሰፊው ህዝብና ኣባላቱ ድርጅቶቹን ውጤት ተኮር ግምገማ ሊያደርግባቸው ይገባል የሚያስብለን።

 

ወያኔን ከጠለፋ ስራው የምናጋልጠውና ትግሉ የሚ ጠናከረው ፓርቲዎችን ወደ ተግባር በምንገፋው የግፊት መጠን ነው።  የወያኔ መርህ የሆነውጠለፋ በመንግስት፣ በተቃዋሚዎች ደረጃ ብቻ ሳይሆን በኣለም ኣቀፍ ተቋማት ኣካባቢ የሚቃወሙትን፣ የሰባዊ መብት ረገጣውን በሚያጋልጡ ድርጅቶች ሁሉ ላይ ያነጣጠረ ሊሆን እንደሚችል እገምታለሁ። የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ጠብቀው ሲያጋልጡትና ርዳታ ሲያስቀሩበት ወያኔ ዝም ይላል ብሎ ማሰብ የወያኔን ቂመኛ ባህሪ ያለማወቅና የዋህነት ነው። ስለዚህ እኛ ኢትዮጵያውያን ለነዚህ ተቋማትና ለለጋሽ ኣገራት የወያኔን የህዝብ ግንኙነት ስራና ተንኮል ማጋለጥ ኣለብን።

ኢትዮጵያውያን የወያኔን ስርዓት ኣወቃቀር በሚገባ ልንረዳ ይገባናል የሚያስብለን ትግሉን ወደፊት ለማራመድ ዘዴኛ እንድንሆን እንጂ ሁሉን እንድንጠረጥርና ተስፋ እንድንቆርጥ ኣይደለም። ስርዓቱ የቆመበት ይህ የማታለልና የጠለፋ ድርጊት መፍረስ ኣለበት። በሌላ በኩል ስለ ወያኔ ተፈጥሮ ስናወራ መርሳት የሌለብን ወያኔ ራሱ ድርጅቱ እንደ ፖለቲካ ድርጅት የሚታይ ኣይደለም። ህወሃት የማህበራዊ ኢኮኖሚ ተቋም   ሲሆን ይህ ተቋም መንግስትን በተለይም ወታደሩንና ሰኪዩሪቲውን ጠልፎ የሚኖር ነው። የህወሃት ውስጣዊ ማንነት ኤፈርት ነው። ምንም ኣይነት የጠራ የፖለቲካ ርእዮት የማናየው፣ ኣገሪቱ ወደ ተሻለ መድብለ ፓርቲ ስርዓት የማትራመደው የወያኔ ተፈጥሮ ፖለቲካዊ ዝንባሌ ያለው ሳይሆን የሶሺዮ ኢኮኖሚክ ተቋምነት ባህርይ ያለው በመሆኑ ነው።  ይህንን ስርዓት የሚቃወሙ ሃይላት በፍጹም በጎሳ ላይ መደራጀት የለባቸውም። ጎሳ ተኮር የሆነ ትግል በመርህ ደረጃ ከወያኔ ኣይለይም።

ምን ኣልባት በየዋህነት ለውጥ በዚህ መንገድ ይመጣል ብለው የተነሱ ሃይለት ኣሁን የሚረዱበት ዘመን ይመስላል። ከመጣመድ ከግንባር ወጥተው መዋሃድ ኣለባቸው። ጎሳዊ ስም ይዞ በኣንድ በኩል በኢትዮጵያ ኣንድነት ኣምናለሁ የሚለው ፍልስፍና በሚገባ መጤንና ስህተትነቱ ሊገባን ይገባል። ሚናው የለየለት ትግል ውስጥ ካልገባን ወያኔ ለጠለፋ ስራው የሚጠቅመውን ሁኔታ እናመቻቻለን።

የኣቶ ሞላ መኮብለል የሚያሳየው ሃቀኛ ትግል እያየለ መምጣቱን ሲሆን ኣሁንም ቢሆን ፓርቲዎች እያጠሩ ቶሎ ወደ ውህደት መራመድ ኣለባቸው። ውህደት በራሱ የሚያፈርሰው ብዙ የወያኔ ሴራ ኣለ። በሌላ በኩል ወያኔ ኣደገኛነቱ ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለኤርትራውያንም ነው። ኣጠቃላይ የሃበሾችን መጻኢ እድል እያወሳሰበ ያለ መጥፎ ሰርዓት ነው።

እዚህ ላይ ኣንድ ነገር በግልጽ መናገር ጥሩ ነው። ይሄ  “ወያኔ” የሚለው ኣጠራር ትርጉሙ ፈጽሞ ከትግራይ ተወላጆች ጋር መያያዝ የለበትም። የትግራይ ወጣቶችም ይህን ስያሜ ከባህላዊ ቡድናቸው ማንነት ጋር ማያያዝ የለባቸውም። ወያኔ የብሄር መጠሪያ ኣይደለም። ወያኔ ማለትራሱ ስርዓቱና የስርዓቱን ተዋንያን የሚያሳይ ሲሆን ኣዲሱ ለገሰም፣ በረከት ስምዖንም፣ ኣባዱላ ገመዳም፣ ሃይለማርያም ደሳለኝም፣ ቴድሮስ ኣድሃኖምም፣ ወያኔዎች ናቸው።እነሱም ሁላችንም ወያኔዎች ነን ብለዋል።   የትግራይ ወጣቶችም ሆኑ ሌሎች ወገኖች ከዚህ ከማንነት ፖለቲካ መራቅ ኣለብን። ሃበሾች ለነጻነታችን ስንል ከዚህ ከፋፋይ ኣስተሳሰብ ጋር መታገል ኣለብን። የተባበረችውን ኢትዮጵያን የምንገነባው ወጣ ባለ ኣሳብ ነው።ከሁሉ በላይ የወያኔን የጠለፋ ስርዓት ስንረዳው በየጊዜው የሚከዱ፣ ትግሉን ሲጎትቱ የሚያዙ የተቃዋሚ መሪዎችን ነገር ግን የወያኔ ሰላዮችን ስናይ ግራ ሳንጋባ የበለጠ የዴሞክራሲ ትግላችንን እናቀጣጥላለን።   ጉዳያችን ከመርህ ጋር የተጣበቀ፣ ከኢትዮጵያ ኣንድነት ጋር የተጣበቀ ይሁን። ሚናው የለየለት ህብረት እንመስርት። ሚናው የለየለት የትግል ኣውድማ ውስጥ እንግባ። ከዚያ ብዙ ህዝብ የሚጠብቀው የትግል ፍሬ ይታያል።

 

የተባበረችውን ኢትዮጵያን እንገንባ

 

እግዚኣብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ

 

geletawzeleke@gmail.com

የግብጹ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎድሮስ ካልዕ ለመስቀል በዓል አዲስ አበባ ይገባሉ

$
0
0

(ሪፖርተር፤ ነአምን አሸናፊ፤ መስከረም ፪ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም.)

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት እና ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታዎድሮስ ካልዕ የኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የእስክንድርያነ ፖፕ እና ፓትርያርክ ዘመንበረ ማርቆስ

his-holiness-abune-tawodros-and-his-holiness-abune-mathiasየግብጽ ኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፖፕ እና የመንበረ ማርቆስ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎድሮስ ካልዕ፣ በመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ላይ ለመታደም እና የአራት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ፣ መስከረም ፲፭ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም. ከቤተ ክርስቲያኒቱ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጋር በመኾን አዲስ አበባ ይገባሉ፡፡

ፓትርያርክ አቡነ ቴዎድሮስ አራት ቀናት በሚወስደው ቆይታቸው፣ መስከረም ፲፮ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም. በሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ላይ ከመታደማቸው በተጨማሪ፣ ወደ አኵስም እና ላሊበላ አቅንተው ታሪካዊ እና ሃይማኖታዊ ሥፍራዎችን እንደሚጎበኙም ታውቋል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በሚኖራቸው ቆይታ፣ በአዲስ አበባ የሚገኙ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላትን፣ እንዲኹም ከኢትዮጵያ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት እና ከታዋቂ ግለሰቦች ጋር እንደሚነጋገሩ ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ጉዟቸውን አስመልክቶ ቅዱስነታቸው ከሳምንት በፊት ከግብጽ የውኃ ሀብት ሚኒስትር ሆሳም አል ሞጋሃዚ ጋር መነጋገራቸው የተዘገበ ሲኾን፣ በውይይታቸውም ወቅት ግብጽ በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ላይ ያላትን ጥያቄዎች አንሥተው ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት እና ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ጋር ውይይት እንዲያደርጉ ሚኒስትሩ መጠየቃቸውና የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው ተዘግቧል፡፡

ፖፕ አቡነ ቴዎድሮስ በበኩላቸው ለዚህ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ ኹለቱ አብያተ ክርስቲያናት ባላቸው ታሪካዊ ግንኙነት፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በዚኽ ረገድ እየተባበሯቸው እንደኾነና አስተዋፅኦዋቸውም ከፍተኛ እንደኾነ ገልጸዋል፤ በማለት ስታር አፍሪካ በተሰኘ ድረ ገጽ ላይ የወጣ ዘገባ ያትታል፡፡

የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ባለፈው ጥር ወር ግብጽን ለስድስት ቀናት በይፋ በጎበኙበትና በካይሮ ፕሬዝዳንታዊ ቤተ መንግሥት ከፕሬዚዳንት አልሲሲ ጋር በተወያዩበት ወቅት ፕሬዚዳንቱ፣ የዓባይ ወንዝ ለኢትዮጵያውያን የልማት ምንጭ ቢኾንም ለግብጽ ግን ልማት ብቻ ሳይኾን የደም ሥር መኾኑንም መናገራቸው ይታወሳል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስም በበኩላቸው፣ በጠንካራ ትስስር ላይ የተመሠረተው የኹለቱ አገሮች ግንኙነት፣ ከዓባይ የሚመነጭ ውኃ የማያቋርጥ የጋራ ሀብት በመኾኑ በፍትሐዊነትና በእኩልነት ተጠቃሚ የሚኮንበት ይኾናል ማለታቸውም አይዘነጋም፡፡

ፖፕ አቡነ ቴዎድሮስ ዳግማዊ፣ እ.ኤ.አ. በ፲፱፻፶፪ ማንሱራ በተሰኘ የግብጽ ከተማ የተወለዱ ሲኾን፣ በ፲፱፻፸፭ ከኤሌክሳንደርያ ዩኒቨርሲቲ በፋርማሲ የመጀመሪያ ዲግሪ አግኝተዋል፡፡ ለጥቂት ዓመታት በመንግሥት ቁጥጥር ሥር የሚገኝ መድኃኒት ፋብሪካን ከአስተዳደሩ በኋላ፣ ቅዱስ ፒስሆግ የተባለ ገዳም በመግባት የሥነ መለኰት ትምህርት በማጥናት እ.ኤ.አ. በ፲፱፻፹፱ ተመርቀዋል፡፡

ከሦስት ዓመት በፊት ያረፉትን የቀድሞውን ፓትርያርክ አቡነ ሺኖዳን በመተካት በአኹኑ ወቅት ፻፲፰ኛው የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ በመኾን በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡

ቤተ ክርስቲያናችን ለታሪካዊው የቅዱስነታቸው ጉብኝት፣ በፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት የሚመራ ዘጠኝ አባላት ያሉት ኮሚቴ በማቋቋም ዝግጅት በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡

Source:: haratewahido

የዞን ፱ ጦማሪያን የዓለማቀፉን የፕሬስ ነጻነት ሽልማት ተሸላሚ ሆኑ

$
0
0

zone 9 bloggers“ስለሚያገባን እንጦምራለን” በሚል መሪ ቃል ከዛሬ አራት ዓመት በፊት የተቋቋመው የዞን ፱ ዐምደ መረብ ጸሃፍት የሕገመንግስቱ የመጻፍ ነጻነት በሚፃረረው መልኩ እንደ ሌሎቹ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች በአሸባሪነት ተከሰው ካለ ፍትሕ በእስር ቤት የሚገኙት ጦማሪያኑና የቡድኑ አባላት ለፕሬስ ነፃነት ላደረጉት አስተዋፆ ዓለማቀፉን የፕሬስ ነጻነት ሽልማት ተሸላሚ አድርጓቸዋል።
የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ሲፒጄ እንዳስታወቀው የመገናኛ ብዙሃንና የጋዜጠኞች መብትን በማፈንና በማሰር ኢትዮጵያ ከአስር የዓለማችን አገራት ውስጥ እንደምትገኝና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ውብሸት ታዬን ጨምሮ የዞን ፱ ጦማሪያኑ ናትናኤል ፈለቀ፣አቤል ዋበላ፣በፍቃዱ ኃይሉ አሁንም በእስር ላይ የሚገኙ መሆናቸውን አክሎ ገልጽዋል።
ኢትዮጵያ የጸረ ሽብር አዋጁን ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረችበት እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር ከ2009 ጀምሮ በርካታ ቁጥር ያላቸው ጋዜጠኞች ታስረዋል። በ2014 17 ጋዜጠኞች የታሰሩ ሲሆን፣ በዚህ አመት ጋዜጠኞችን በማፈን አገሪቱ በአለም የ4ኛ ደረጃን ይዛለች።
የዞን 9 ጸሃፊዎች በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ጭቆና፣ ሙስናና የማህበራዊ ፍትህ እጦት ሲያጋልጡ መቆየታቸውን የገለጸው ሲፒጄ፣ በጋራ የሚጽፉዋቸው ጽሁፎች በኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይነበቡ ሲታፈኑ ቆይተዋል ብሎአል። የዞን 9 ጸሃፊዎች መገናኛ ብዙሃን በገንዘብ እንዲሁም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ በመንግስት በሚደርስበት አፈና በተደከሙበት ወቅት፣ ላደረጉት አስተዋጽኦ ሲፒጄ እውቅና እንደሰጣቸው በመግለጫው አስታውሷል።

Source:: Ethsat

ይህን መንግሥት እንዳትነኩት ይወድቃል!

$
0
0

hailemariam
ከዘኢትዮጵያ ጋዜጣ የተገኘ

ኢህአዴግ በየሁለት ዓመቱ የጠቅላላ ጉባኤውን ያካሂዳል። በዚህ ጉባኤ የድርጅቱን ዋናና ም/ሊቃነመናብርት ይመርጣል። ድርጅቱ የሚጓዝበትን
ሁሉን አቀፍ የፖሊስ ሰንድም ያዘጋጃል። ያለፈውንም ዓመት መርምሮ ያጸድቃል። እነዚህ እንደተጠበቁ ሆነው፣ ድርጅቱ እክል በገጠመው ወይም በድርጅቱ
አባላት መካከል መቃቃር የተፈጠረ በመሰለው ጊዜ ግን፣ ጉባኤን ራስን እንደ መፈወሻ ስፍራ (ፎርም) በመፍጠር፣ ግምገማና ሹም ሽሮችን በማድረግ ተሐድሶ ያደርጋል። አሁን አሁን ያን መሳይ ነገር ብዙ አይታይም። ምክንያቱም ጉባኤው ያን መሳይ አቅም እንዲኖረው ድርጅታዊ ሥራ የሚሠራና የሚመራ ጠናካራ አመራርና መሪ ይፈልጋል። ኢህዴግ ከአቶ መለስ ሞት በኋላ ያን መሳይ መሪ ማጣቱ መነገር ከጀመረ ሰንብቷል። ግምገማዎች የሚደርጉ ቢሆን ግምገማዎቹ ለውጦች የሚካሄዱባቸው ወይም ሥር ነቀል ሹም ሽሮች የሚታዩባቸው አይደሉም። ምክንያቱም የሚሻር የሚሽር ሰው የለም። እንኳን ድርጅቱ እንዲህ የአመራር ንቅዘትና ድክመት ሞልቶት ቀርቶ፣ ደህና እየሠራን ነው ተብሎ በሚፎከርበት ዘመን እንኳ፣ አቶ መለስ ዜናዊ፣ የውሸታቸውን በስብሰናል ገምተናል እያሉ፣ የሚያስቸግሯቸውን ሰዎች የሚያባርሩበት፣ የፈለጓቸውን እሚሾሙ እሚሽሩበት ሁኔታ ነበር። በዘንድሮ የኢህአዴግም ሆነ የአባልድ ድርጅቶቹ ጉባኤ ላይ ግን ይህ አልታየም። ብዙዎቹ ባሉበት ሲጸኑ ብዙ ችግር አለበት በተባለበት ህወሓት ዘንድ ብቻ መጠነኛ ለውጥ ታይቷል። ያ ም ቢሆን የአራቱም ድርጅቶች ሊቀመንበርና ም/ሊቀመንበሮቻቸው በድጋሚ ተመርጠዋል።

ያም ሆኖ የድርጅቶቹ ሁሉ አስኳልና የሥልጣን ማዕከል በሆነው፣ የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕውሓት) ውስጥ ግን፣ አንጻራዊም ቢሆን ግብ ግቦችና መጠነኛ ለውጦች ታይተዋል። በዚህ ስብሰባ ልክ አቶ መለስ እንደሚያደርጉት ቢያንስ እንደ ልቡ መናገር የቻለና ሁሉም ላይ ቁጣና ተግሳጹን ማስፈን የቻለ አንድ ሰው ታይቷል። በህወሓቱ ጉባኤ የሥራ አስፈጻሚነቱን ሥፍራ የተረከበውና የአገሪቱ ቁልፍ ቦታ የሆነውን የደህንነት መ/ቤት የተቆጣጠረው ሚኒስትሩ አቶ ጌታቸው አሰፋ አዳራሹን በሙሉ እንደ ልባቸው ሲወርዱበትና አመራሮችን በሰላ ወቀሳና ክስ ከፍ ዝቅ ሲያደርጓቸው መዋላቸው ተሰምቷል። የአመራር ጉድለትና ሙስፍና መንሰራፋቱን፣ በአመራር አባላቱ ዘንድ ዝሙትና መጠጥ ያለ ቅጥ መበራክታቸውን፣ የማስተዳደር አቅምና ችሎታ መጥፋቱን ሁሉ በማንሳት የሰላ ትችት አቅርበዋል። አቶ ጌታቸው አመራሩ የትግራይን ህዝብ የበደለ መሆኑን ሁሉ በማንሳት፣ ይቅርታ መጠየቅ የሚያስፈልግበትን አግባብ ሁሉ መመሪያ ቢጤ መስጠታቸውና አስተያየታቸውን በቁጣ መግለጣቸው ተሰምቷል። ከአቶ መለስ ሞት በኋላ እንደዚያ ባለ ኃይለ ቃል ህወሓቶችን የተቆጣ የህወሓት ሰው መኖሩን እንጃ!

ያም ሆኖ ግን የአዲስ አበባውና የትግራዩ ቡድን እየተባለ ለሁለት መከፈሉ የሚነገርለት ህወሓት፣ አንዳች ለውጥ ሳያታይበት የውድቅትና የድክመት ምንጭ ናቸው የተባሉትን አቶ አባይ ወልዱን የድርጅቱ ሊቀመንበር አድርጎ እንደገና መርጧቸዋል። በአቶ ስብሐት ነጋ በአቶ አርከበና ደጋፊዎቻቸው አማካይነት በትግራይ ባለው አመራር ላይ ሲዘንብ የሰነበተው ፕሮፖጋንዳ፣ ምንም ለውጥ ሳይስገኝ፣ አቶ ጌታቸውን ብቻ በሥራ አስፈጻሚነት አስመርጦ፣ የተቀረውን በሙሉ ለባለድሎቹ መቀሌዎች አስረክቦ ተመልሷል። ያ ማለት ግን ጉዳዩ አልቆለታል ማለት አይደለም። ምክንያቱም በፓርቲው አባላት መካከል የተፈጠረው መናናቅና መረን የተለቀቀው ሙስና ይበልጥ መንሰራፋቱ አስግቷል። ያ ሁሉ ኃጢአት ተወርቶ፣ ከፓርቲው አመመራ አባላት ይመለከተዋልና እምርጃ ይወሰድበት መባሉ ቀርቶ፣ በትህትና እስኪ ይቺን ሂስህን በዚች ውሃ ዋጣት የተባለ ባለሥልጣን አንድም የለም። በአጉል የመተካካት ጨዋታ እንኳ የተሰናበቱትም ቢሆን በክብር ተሸኙ ተባል እንጂ በድክመት ተባረሩ አልተባለም። በአቅም ማነሰ የተገመገሙ ሰዎች ያቺኑ አቅማቸውን እንደያዙ ቀጥለዋል።

የተባለውማ ለምሳሌ የትግራይ ህዝብ ከአባይ ወልዱ ይልቅ እሳቸውን ፈልጓል በሚል ወከባ፣ ወደ ፓርቲው አመራር ተመልሰው እንዲመጡ ታሰበው የነበሩት አቶ አርከበ እቁባይ ነበሩ። ግን ምን ያደርጋል እንኳን ሊመረጡ በእጩነት እንኳ ሊቀርቡ የሚችሉበት አግባባ ባለመፈቀዱ የመቀሌው አንጃ ባዶአቸውን እንዲመለሱ አድርጓቸዋል። ለመቀሌዎቹ ይብላኝላቸው እንጂ አርከበ እንደሆነ ፕላን ቢ አላቸው። እንዲያውም ትክክለኛውና ጥቅም የሚያስገኘው ሥልጣን፣ በፓርቲ ሳይሆን በመንግሥት መዋቅር ውስጥ እየሆነ በመምጣቱ፣ ፓርቲውን ጥርስ አልባ በማድረግ የመንግሥት ተቋማትን ለመቆጣጠር ሀሳብ መኖሩ ተሰምቷል። ለምሳሌ አቶ አርከበ ከአማካሪነት ይልቅ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በሚኒስቴር ደረጃ የሚቋቋም የራሳቸው መዋቅር ሠርተው፣ በሚኒስትር ማዕረግ፣ የኢንደስትሪ ፓርኮች ኃላፊ ለመሆን መዘጋጀታቸው ተነግሯል። ይህ ከፍተኛ ገንዘብና ጥሪት ሊያንቀሳቅስ የሚችል ተቋም ለብቻው ወጥቶ የሚደራጅበት ምክንያት ምንድነው? ከሆነስ ለምን በኢንደስትሪ ሚኒስትር ስር አይጠቃለልም ይህስ ከጥቅማ ጥቅም ሙስና ወደ መዋቅር ወደ መዘርጋት ሙስና መሸጋገሩ አይደለም ወይ? የመሳሰሉ ጥያቄዎች ተነስተው ግብግብ መኖሩም እየተሰማ ነው። በፓርቲው መስመር የሹመት ቦታ ያጡት አቶ አርከበ የራሳቸውን መዋቅር አስጠንተውና ሚኒስቴር መ/ቤት ዘርግተው ለዚህ ድፍረት መብቃታቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩን አቶ ኃ/ማርያምን ንቀው ነው ብሎ የሚከሷቸውም አሉ። ኃይለማርያም ተንቀዋል ብሎ ክስ እንኳ እንዲያው ስራ መፍታት ነው።

ለማንኛውም አቶ አርከበ፣ ሲሆን ሲሆን ህዝቡ ጠይቋቸዋል በሚል ሰበብ፣ መቀሌ ወርደው፣ ከወ/ሮ አዜብ ላይ የኤፈርት ድርጅቶችን አስለቅቀው፣ ድርጅታዊ ሥራ እየተሰጣቸው፣ ድምጾቻቸውን የሚሸጡ ካድሬዎችን በቁጥጥር ሥር በማድረግ፣ አላግባብ ተባረናል የሚሉትን እነ ስዩም መስፍንና ስብሐት ነጋን ወደ ፓርቲው መዋቀር መመለስ ት የሚቻልበትን የምርጫ መስመር መክፈት፣ ሲመከርበት የሰነበተ ዘዴ ነበር። ያ ሳይሆን ቀርቶ ከባለቤታቸው የተማሩትን ዘዴ የተጠቀሙት ወ/ሮ አዜብ ሁሉም እስኪደነግጡ ድረስ ከደብረጽዮን በቀር፣ ከሁሉም የላቀ ድምጽ አግኘተው፣ በሥራ አስፈጻሚነት እንደገና ሊመረጡ ችለዋል። እነ አርከበ፣ አባይ ፀሐዬ፣ ስብሐትና ስዩም መስፍን እንኳን ሊመረጡ የምርጫ ጨዋታ ውስጥ እንኳ መግባት አልቻሉም። ለነገሩማ ወደጉባኤ አዳራሾችም እንዲገቡ የተፈቀደላቸው የኢራኑ ኑዩክሌር ድርድር ያህል ጊዜ ፈጅቶ ነው ይባላል።

ሌላው የሥልጣን ማማ ናቸው የሚባሉት የሠራዊቱ ኤታማዦር ሹም ጀኔራል ሳሞራ የኑስ፣ እነ ወ/ሮ አዜብን የሚደግፉ ሲሆኑ፣ በዘንድሮ የጉባኤ ስብሰብዎችም ላይ፣ ሲቭል ለብሰው ሲንጎራደዱ ከርመዋል።

በህገመንግሥቱና በይስሙላው ልማድ መሠረት፣ የሠራዊቱ አባላት ተጠሪነታቸው ለሕገመንግሥቱ ብቻ ነው ስለሚባል፣ፖለቲካ ወገንተኝነት በሚያሳየው የፓርቲ ስብሰባ ላይ መገኘት አይኖርባቸውም። ድሮም አቶ የነበሩት ጄኔራል ሳሞራ ግን አቶ ሆነው ሰንብተዋል። ለዚህም ምክንያት ሳይኖራቸው አይቀርም።

በአገሪቱ ዛሬ የላቀውንና ተቀራራቢ የሆነውን ሥልጣን ያላቸው ጄኔራል ሳሞራና የደህንነት ሹሙ አቶ ጌታቸው አሰፋ መሆናቸው ይታመናል። አቶ ጌታቸው ወደ ፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ በመግባት ራሳቸውን በማስመረጣቸው አንዲት እርከን ወደላይ ከፍ ማለታቸው ለሳሞራ ሳይገባቸው አልቀረም። አቶ ጌታቸውም የሥራ አስፈጻሚነቱን ቦታ የሞሉት የሳሞራ ሰዎች በስብሰባቸው ላይ ምን እንደሚያወሩ፣ ምን እንደሚወስኑ ለማወቅ ቀረብ ብለው መመልከቱን ካስፈለገም በወሳኝነት መሳተፉን ሳይፈልጉ አልቀረም። ይህ ከሆነ ደግሞ ምንም ነገር ሊደረግ በሚችልባት አገር፣ ወታደሩ ሳሞራ ድንገት ብድግ ብለው፣ ከዛሬ ጀምሮ በፓርቲዎቹ የሥራ አስፈጻሚ እ ስብሰባዎችም ላይ መገኘት አለብኝ እንዳይሉ መስጋቱ ተገቢ ሳይሆን አይቀርም። ጌታቸውንም ሆነ ሳሞራን ከሥልጣን ላይ ሊያነሳቸው የሚችል አንዳች ኃይል ቢኖር ሊሆን የሚችለው ፓርቲው ብቻ ስለሚሆን ፓርቲውን ጥርስ እንዲኖረው ወይም ወላቃ ሆኖ እንዲቀጥል ማድረጉ ከማንም በላይ በሁለቱ ባለሥልጣናት ላይ የወደቀ ኃላፊነት መሆኑን ሁለቱም ሳይረዱት አልቀሩም።

በሌላ በኩልም ቀደም ባለው መዋቅር፣ የደህንነት ሚኒስትሩ በፓርቲው አንጻር ተጠሪነታቸው ለሥራ አስፈጻሚው ለዶ/ር ለደህንነቱ አማካሪ ለአለቃ ጸጋዬ የነበረ ሲሆን፣ ከአሁን በኋላ ግን፣ ደብረጽዮንም ሆኑ ጌታቸው እኩል ሥራ አስፈጻሚዎች ስለሚሆኑ አለቃ ፀጋይም ስለተሸኙ፣ ጌታቸው ለማንም ሳይጠሩ ሥልጣናቸውን ሊሠሩ ይችላሉ። መቸም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ለኃ/ማርያም ሪፖርት ያደርጋሉ ተብሎ መጃጃል አይኖርም።

በቀር ማለት ነው። ጨዋታውን አጓጊ የሚያደርገው ግን ካሁን በኋላ ጀኔራል ሳሞራ ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉ ማሰቡ ላይ ሲሆን፣ ስብሐትን የተመረኮዙት አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ ሳሞራን ጥለው ጀነራል ሰዓረን ለማምጣት እየዶለቱ መሆኑ ከተሰማ ሰንብቷል።

ለማንኛውም ካሁን በኋላ ከትግራይ የመጣ ሰው ጠቅላይ ሚኒስትር አይሆንም እየተባለ መነገሩ፣ ቦታውን ለሌሎች ብሄረሰቦች ከመልቀቅ ቸርነት ሳይሆን፣ ያ ጠቅላይ ሚኒስትር እውነተኛ ባለሥልጣን ሊሆን ስለሚችል የመጀመሪያ ተጎጂዎች የሚሆኑት ደህንነቱና ኤታማዦር ሹሙ ናቸው። በዚያች አገር ቀርቶ በየትኛውም አገር ላይ፣ አንድ መሪ ሥልጣን ጨበጠ የሚባለው ቢያንስ እነዚህን ሁለት ነገሮች መሾምና መሻር ሲችል ብቻ ነው። ለማንኛውም ካሁን በኋላ ከትግራይ የመጣ ሰው ጠቅላይ ሚኒስትር አይሆንም እየተባለ መነገሩ፣ ቦታውን ለሌሎች ብሄረሰቦች ከመልቀቅ ቸርነት ሳይሆን፣ ያ ጠቅላይ ሚኒስትር እውነተኛ ባለሥልጣን ሊሆን ስለሚችል የመጀመሪያ ተጎጂዎች የሚሆኑት ደህንነቱና ኤታማዦር ሹሙ ናቸው። በዚያች አገር ቀርቶ በየትኛውም አገር ላይ፣ አንድ መሪ ሥልጣን ጨበጠ የሚባለው ቢያንስ እነዚህን ሁለት ነገሮች መሾምና መሻር ሲችል ብቻ ነው።

በዚህ የሥልጣን ሽኩቻና ፍትጊያ መካከል፣ እየተላተመ ያለው ሕወሓት/ኢህአዴግ፣ በዚያ ላይ እንደ አቶ በረከት ሰምዖን ያሉትን ሰዎቹን አጥቶ፣ ምን ያህል እድሜ ሊኖረው
እንደሚችል ማየቱ የሚያጓጓ ነገር ነው። የዘንድሮውን የህወሓት ጉባኤ ያዳነውም አንዱ ይሄ እባካችሁ ይሄን ድርጅት በጣም አትነካኩት ሊወድቅ የሚችል ተሰባሪ ነገር ነው የሚል መራራት መኖሩ ነው። ሌላኛው ደግሞ የኢህአዴግ ጉባኤ ከህወሃት ጉባኤ በኋላ የሚካሄድና ቀን ተቆርጦለት በዚያ ላይ እዚያው መቀሌ ላይ ሊደረግ እንግዶች ተጠርተው አገር እየጠበቀው ያለ ነገር በመሆኑ ነው። ያም ሆኖ እንኳ መግባባት እየጠፋ እረባካችሁ ቶሎቶሎ በሉ እየተባለ ገመናን አሳልፎ ላለመስጠት ውጥረት ቀብሮ በውጥረት ስር የተካሄደ ጉባኤ ነው። ሌላ ጊዜ እንመለስበታለን የተባለ!

የሆኖ ሆኖ የመቀሌውም ይሁን የአዲስ አበባው ወገን አሸነፈም ተሸነፈም ሁለቱም ህወሓትን ከመጠጋገን የተረፈ ሌላ ጥቅም አይኖራቸውም። የጀመርኳትን ቤት እስክጨርስ ወይም አዲስ አበባ ደርሼ እስክመጣ ኢህአዴግን አትነካኩብኝ ይወድቅብኛል የሚሏት ጨዋታም ሌላዋ ጥቅም ናት። የባለ ሥልጣኑን እድሜን ያረዘመች ጥቅም!

“ሞላ ለጥቂት አመለጠን…ሲያመልጥ የተዋጋው ከሻዕቢያ ጋር ሳይሆን ከኛ ጋር ነው”–የትህዴን ጊዜያዊ ሊቀመንበር ታጋይ መኮንን ተስፋዬ (Audio)

$
0
0

ከኢሳት ጋር የተነጋገሩት የትህዴን ጊዜያዊ ሊቀመንበር ታጋይ መኮንን ተስፋዬ “ሞላ ለጥቂት አመለጠን” አሉ:: ሲያመልጥ የተዋጋው ከሻዕቢያ ጋር ሳይሆን ከኛ ጋር ነው አሉ:: በቃለምልልሳቸውም ”ከሚያዚያ ወር ጀምሮ የ7ዓመት ግምገማ እያደረግን ቆይተናል። በዚህም ሞላ በፖለቲካ አመራር ድርጅቱን አዳክሞታል የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰናል። ሰራዊቱ የአመራር ለውጥ በሚፈልግበት ጊዜ ላይ በተካሄደው በዚሁ ግምገማ ሞላ ከፍተኛ ተቀውሞ ከድርጅቱ አመራሮችና አባላት ደርሶበታል። ” ብለዋል:: ሙሉ የድምጽ ቃለምልልሱን ያድምጡ::

mola

የጥምረቱ ፍሬ እና ገለባ በቶሎ መለየት።እየጠራ ገፋ ትግሉ –ከቢላል አበጋዝ

$
0
0

ዋሽግቶን ዲ ሲ

ማክሰኞ ፣ ሴፕቴምበር 15 ቀን 2015

Molla Asgdom 3ነጎደ እየጠራ ገፋ ትግሉ።ይህ እውነትተኛ አባባል ከቀድሞው የኢህአፓ የትግል መዝሙር ነው።ለአገራቸው ቀድሞ እንደተሰዉት ሁሉ የዛሬዎቹ አርበኞችም ደምሂቶችም ሁላችንም  ልንዘምረው የሚገባ ነው።ከታሪክ መማር ማለት በተግባር ይህ ነው ብል ስተት አይሆንም።ከዚህ ወዲያ እየጠራ ይገፋል እንጂ ትግሉ ወደኋላ አይቀለበስም።ጥምረቱን ምንም ሀይል አይገታውም።ህዝባዊ ስለሆነ!የዚህ ጽሁፍም ዓላማ ትግላችን እየጠራ ይገፋል፤የህወሃት ክስረት እየጨረ ይሄዳል ለማለት ነው።

ወያኔ ህወሃት ወሰን የሌለው በጀት መድቦ አቀናበርኩት ብሎ ይፋ ያወጣው “የተቀነባበረ” ሴራ በነሞላ አስገዶም መክዳት ምክንያት መግለጫ ተሰጥቶበታል።ወያኔ ህወሃት “አቀናበርኳቸው” ያላቸው ድርጊቶችን፤በኤርትራ ውስጥ የአቶ አንዳርጋቸውን ግድያ፤በሰንአ የመን የአቶ አንዳርጋቸውን መታገት፤አሁን ደግሞ የነሞላን አንድ ጋንታ ይዞ ወደ ሱዳን ቀጥሎም ኢትዮጵያ መግባት እንቆጥራለን።ይህ ሁሉ የወያኔ ህወሃት መንግስት ጥረት ያላሰለሰ ውጣ ውረድ የትጥቅ ትግል ተጀምሮ፤ጎልብቶ የህወሃት ስንብት እንዳይረጋገጥ ነው።የወደፊቱም መውተርተር ከትጥቅ ትግል መጠናከር ፍራቻ ነው እንጂ ሌላውን ጨብጧል ።ውሉን የሚፈታው ብረት መሆኑን ወያኔ ስቶት አያውቅም።

ሰምኑ በተፈጠረው ሁኔታ ከሁሉም ይልቅ ወያኔ የህወሃትን ስለላ እርባና ቢስ የሚያደርገው ለድርጊቱ  ቸኩሎ አላፊነት መውሰዱ ነው።በጣም የረቀቀ ይሆን የነበረው እነሞላ አስገዶም በኢትዮጵያ አንድነት ጉዳይ ኤርትራ ጋር ጥርስ ተናከሱ ብሎ በስደት ወደ ሱዳን ቢያወጣቸው ኖሮ በሁኔታው ብዙ የፕሮፓጋንዳ ሸመት ይገዛበት ነበር።ስለላ ትልቅ የአእምሮ እሴትን የሚሻ ተግባር ነው። ለወያኔ ህወሃት የሚሆን የስራ ምድብ አይደለም።(ለስለላ የቀጠሯቸው ፈረንጆች ደደቦች ብለዋቸዋል) የወያኔ ህወሃት ስለላ፤ተቧዳኙ የይዘትና የጥራቱ ደረጃው ዝቅ ያለው አይጋ ፎረም፤ ተራ ተላላኪው ኢትዮጵያ ፈርስት፤በዳያስፖራም ወሬ አናፋሽ የሆኑት ኢትዮ ሚዲያ ከነቃጭሉ ደምስ በለጠን ጨምሮ አንዴ ተንጫጩ።እለቱን ጥምረቱን በትነዋል።በኤርትራ ያለ ተዋጊን አተራምሰዋል አሉ በነሱ ቤት። በኢትዮጵያ ውስጥና በዓለም ተሰራጭቶ ያለው ዜጋ ተስፋ ያረገበት፤የለፋበት ሁሉ በወያኔ ህወሃት ቤት የእንቧይ ካብ ነው ማለት ነው። ስለላ የእለት ትንሽ ድል ማግኘት አይደለም።ይህ ሳይገባቸው ከአራት ኪሎ ይባረራሉ ማለት ስለህወሃት ማጋነን አይደለም።በሞላ መክዳትም ወያኔ ተቻኮለ። ይህ ነው የወያኔ ህወሃት ብልሃት።ከንቱ ልፋት! የጅብ ችኩል ይሏል ይህ ነው።የኢትዮጵያ አምላክስ የት ሄዶ?

ሞላ አስገዶም ወታደራዊ መሪ እንጂ ፖለቲከኛ አይደለም ቢባል እንኳን ሊያስከዳው የቻለውን ምክንያት ቅልብጭ አድርጎ መናገር አለመቻሉ ከነጻ አውጭ መሪ ይልቅ አንዱን የወያኔ ተራ ጄኔራል አስምስሎታል።ፖለቲካው ቀርቶ ስለ አመላለጡ ማቅረብ አለመቻሉ ቢሄድ አያጎዳም የሚለውን አባባል የሚደግፍ ነው።ድርጅቱ ደምሂት ሞላ ሊቋቋመው ያልቻለ የውስጥ እንቅስቃሴ ነበር ላለው ብዙ መረጃ እንድመኝ አድርጎኛል።ሞላ አስገዶም ወያኔ እሱ ለትግል ከተነሳበት ጊዜ በኋላ ምን በጎ አድርጓል?ላነሳውስ የአገራችን አንድነት ምን ፈይዷል? ዳር ድንበሯስ ?እሱ ከሸሸበት ሳይርቅ ለሱዳን በወያኔ የተሰጠውን መሬት ወሬውን አልሰማም ?መሪ መሆኑ ዜና ይከታተላል እንድንል ያስገምታል።ታዲያ ስለረሃብና ስደቱ፤ ሞቱ ውርደቱ አይሰማም ?ስለ ትግራይ ህዝብ የሌላው ይቅር አይሰማም?ይህ ሰው በአስራ አራት ዓመታ አእምሮ አጎልባች ምን ነገሮችን አርጎ ይሆን?ደምሂት ካለው ስልጣንን የማጣት ብሎም የግል ጥቅም በተቀር ሌላ ሞክንያት የሚጥም አይሆንም።ያለውን የጠላት ጦር እንኳን እንዴት “እደጠራረገው” በቂ ወታደራዊ መግለጫ አልሰጠም። በተፈጠረው ሁኔታ ደምሂት አዲስ የተሻለ መሪ የሚያወጣበት እድል ማግኘቱ ለድርጅቱ ብሎም ለጥምረቱ የጠና መሰረት ላይ መቆም ወሳኝ ነው።ሳይደግስ አይጣላም ይሏል ይህ ነው።

በሰጠው መግለጫ ሞላ አስገዶም የሚመስል ነገር እንኳን ሊያቀርብ አልቻለም።የነበረችውን ታሪካዊ እድል አባከናት ለመጨረሻ ጊዜ።”ጥምረቱ ትርጉም የለውም” “ጥምረቱን እኛ ነን ያመጣነው”እነዚህ አባባሎች ስለ ሞላ አስገዶም እና ስለላከው ወያኔ ብዙ ይናገራሉ።ጥምረቱ እንደምናውቀው በአራት ድርጅቶች መላከል የሆነ ነው።መሪዎችን ተከታዮችን ይዞ ማለት ነው።እኒይን ሁሉ ሞላ አስገዶም ሲዘውራቸው ነበር ማለት ነው! ሞላ እንግዲህ በአስራ አራት ዓመታት ያካበተው ምትሃታዊ ሀይል ነበረው? የማይካደው የጦር መሪ መሆኑ የሚሰጠው ያሻውን ሀይል ባሻው ጊዜ ማንቀሳቀስ መቻሉ ነበር።ይህን ተጠቅሞ አምልጦበታል።ሞላ የጥምረቱ አላማ ከደምሂትም ከሱም ከማንም ሌላ ድርጅትና መሪ የገዘፈ መሆኑን ሳይረዳ ይቀራል ማለት አይቻልም።ግን የስልጣንን ማጣት ፍርሃት አየለበት።የደምሂት መግለጫ እንዳቀረበው ሁሉ። የሻቢያ “ኢትዮጵያን መበታተን” ተቃራኒም የመጨረሻው ገቺው ጥምረት\ውህደት ነውና ለክጂው ያቀረበው ምክንያት እንዲያ የወያኔ ስለላ ወደሱ አፍ የዶለውን ነው። “የሻቢያን ጦር መጠራረግ” ብዙ ማለት ያስችል ነበር።እንደ አንድ የጦር መሪ።

ከሞላ አስገዶም የሁለት ቀናት ወሬ በኋላ ወያኔ ህወሃት ምን ይዞልን ይመጣል ?ከኤርትራ እስከ ዋሽንቶን ዲሲ በረቀቀው ስለላ ስራው፤ጥምረቱን አመከንኩት።አለቀ።ደቀቀ።እያለ ሊያዝናናን መሞከሩ ይጠበቃል።መጽሀፍም ታተመ መባል ፤ቃለ መጠይቆች፤ይቀጥላሉ። ለውጊያ እንዘጋጅ፤ኤርትራ ዘመቻ ብዙ ድግሶች ይኖራሉ። ከልማት ወሬ በራብ መምጣት እፎይ ስንል ስለ ኤርትራ ደግሞ የምንታክትበት ሁሉ ከፊታችን ነው። ወያኔ መከራውን እያየ ነው።ሙስና ስቅ ስቅ ያሰኘዋል።ኢኮኖሚው ውሉ ጠፍቷል።አሻንጉሊት ድርጅቶቹ ተዳፍረውታል።ተጠልቷል።ከሁሉም ይበልጥ ሰሜን ኢትዮጵያን ጎንደር፤ትግራይ፤ወሎን ብቻ ከላይ የሚመጣን ይበልጥ ይሰጋል። ይህና ይህ ብቻ ነው የህወሃት እንቅል ነሺ ቅዥት።

የትግሉን ሂደት ስናስተውል ዋናው በዚህ አጋጣሚ ጎልቶ እየሄደ የሚወጣው የጎሳና የክልል ድርጅት አመለካከት መክሰሚያው መዳረሳችን፤ ከወያኔም እንገላገል ካልን በጠባቡ ከማሰብና ከማየት ለዓላማም የጎሳና የክልል መሰረት ከመስጠት ርቆ ጥምረት ውህደት አስቦ “አገራችንን ማዳን” በትልቁ የተጻፈበት ባቡር ሳያመልጥ ቶሎ መሳፈር ነው። ይህ ባቡር ከአስራ አራት አመታት በኋላ እድሉን ያባከነውን ሞላን ጥሎት ገስግሷል።ሌሎች ድርጅቶችን ይህ ፈጣን  ባቡር ማምለጥ የለበትም።ከዚህ ወዲያ ጥምረት ወይም የሞላ መንገድ ነው።ካልሆነ የጎሳና የክልል ድርጅት በቃኝ። ተውኩትም ማለት የኮራ አማራጭ ነው።በግሌ ወደፊት በታሪክ ያስመሰግናል ባይ ነኝ።

የጥምረቱ ፍሬ እና ገለባ በቶሎ ለየ።እየጠራ፤ ገፋ ትግሉ።ፈጠነም እላለሁ።ኢትዮጵያን አምላክዋ እንደታረቃት ትልቁ ምልክት የጥምረቱ እንቅፋት ብዙ ዋጋ ሳያስከፍል ራሱ በገዛ እግሩ ሹልቅ ማለቱ ነው።ሹልክ እንደ ሞላ አስገዶም።ወገኔ የትግራይ ሰው የሚገጥምበትን ለማሰማት ያብቃን።አሁን የጥምረቱን የስራ ውጤት እንስማ።ስለ ሞላ በዚህ ይቁም ከናካቴው::እየጠራ ገፋ ትግሉ።ፋሽስቱን ባንዳውን እያስወገደ። ነጎደ ጠራ ትግሉ!

 

አነድነት ሀይል ነው!

ድል ለመብቱ ለነጻነቱ እየታገለ ላለው የኢትዮጵያ ህዝብ!

ኢትዮጵያ  በህዝቦችዋ አንድነትና ፍቅር ለዘለዓለም በነጻነት ትኑር!


“ከእንካሰላንታው ባሻገር”–ኤርሚያስ ለገሰ

$
0
0

ermias copy
የሰሞኑን የኢትዬጲያ ፓለቲካ ለተከታተለ ሰው የትግሉ ጫፍ ወዴት እየሔደ እንደሆነ ለመገመት አያዳግተውም። …በአንድ በኩል ላለፋት ሁለት አስርተ አመታት የበላይነቱን ያስጠበቀው አናሳ እና ዘረኛ ቡድን አሁንም ከማንም በላይ የደም ሀረጉን በመምዘዝ ለመሰባሰብ እየተጋ ያለበት ነው። …በሌላ በኩል ሁሉን አቀፍ ትግል የመረጡ በብሔርም ሆነ በሕብረ ብሔራዊነት የተደራጁ ሀይሎች ሀይላቸውን በማቀናጀት በጋራ ለመስራት እየተመካከሩ ያለበት ሁኔታ ነው። እነዚህ ሁለት እንቅስቃሴዎች ከፓለቲካ ፓርቲ እና የድርጅት ህልውና ባሻገር ከኢትዬጲያ ህዝብ የነጳነት ትግል መቀጠልና ወደ ኃላ መመለስ ጋር የተቆራኙ ናቸው። ርግጥም የእነዚህ ሁለት አካላት የፍልሚያ ውጤት የወደፊቱን የኢትዬጲያ እጣ ፋንታ የመወሰን እድሉ ከፍተኛ ነው።

1• ” አናሳ እና ዘረኛው ቡድን”

የመጀመሪያው እድል ከፓለቲካ ፕሮግራም እና ብቃት ይልቅ የማንነት ደም ያስተሳሰራቸው አናሳ ቡድኖች በኢትዬጲያ ህዝብ ጫንቃ ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው፣ እንደ በረሮ(?) ከክብደታቸው በላይ የሚበሉበት ሁኔታ መፈጠሩ ነው። ያለማጋነን የዛሬይቱ ኢትዬጲያ በጥቁር ደም በተሞሉ መዥገሮችና ቁንጣን በያዛቸው በረሮዎች ተወራለች። የአናሳው ቡድን ተስፈኞችም ህዝባችን ላይ የተጋረጠ አደጋ በማለት ወደዚህ ቡድን እየተሰባሰቡ ነው። የትግራይን ህዝብ ካባ በማጥለቅ የራስን የስልጣን ፍላጐት ለማርካት ጥረት እየተደረገ ነው። በተባራሪ እንደሰማነው የተቃዋሚ አመራሮች ነን የሚሉና ብሄራዊ ማንነታቸው ሁሌም የበላይ እንደሆነ እንዲቀጥል የሚፈልጉትም በዚህ ጐራ የሚካተቱ ናቸው። አንዳንድ ምልክቶችም እየታዩ ነው።በህውሀት ጉባኤ አንዱ ተነስቶ ውይይት የተደረገበት እነዚህን ተቃዋሚዎች ( አቤ ቶኪቻው “የስጋ ዘመዶች ” ይላቸዋል) በመለየት ቢያንስ የማለዘብ ስራ የመስራት አስፈላጊነት መሆኑ የውስጥ መረጃዎች ያመላክታሉ። መጀመሪያ በሀገር ውስጥ ያሉ የተቃዋሚ ስያሜ የተሰጣቸው ቡድኖች የቅድሚያ ትኩረት አግኝተዋል። በማስከተል ወደ ተለያዩ ሀገሮችም አማላይ ቡድኖችን ለመላክ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ያለበት ሁኔታ ነው። በቅርቡ ወደ ሰሜን አሜሪካ መጥተው የነበሩ ግብረሀይሎች አንዱ ተልእኮ ይህ እንደነበረ ይገመታል። ወደ አውሮፓም የሚሄዱ ( በተለይም የቀድሞ ህውሀት አመራሮችን የሚያናግሩ) የህውሀት ቡጅሌዎች እንደሚኖሩ ይጠበቃል።

ይሔ በአናሳ ብሔር ስም የተሰባሰበ ቡድን በአሁን ሰአት እየተከተለ ያለው ስትራቴጂ ዋነኛ ማጠንጠኛ የትግራይ ህዝብ እና ሌላው የኢትዬጲያ ማህበረሰብ በባላንጣነት እና ጠላትነት እንዲተያይ ማድረግ ነው። ይሄ ቡድን ለዘር ማጥፋት እንደ አንድ ምልክት ተደርጐ የሚቆጠረውን ” እኛ እና እነሱ!” የሚለውን አባባል ወደ ተግባር ለመለወጥ ወገቡን ታጥቆ እየሰራ ነው። ይህ አናሳ ቡድን ኃላቀር በሆነ የፓለቲካ ባህል የተተበተበ በመሆኑ የትግራይን ህዝብ ለማደናገር በዘረኝነት እየቀሰቀሰ ነው። የትግራይን ህዝብ ከሌላው ኢትዬጲያዊ በመለያየት እና በማናቆር አገዛዛቸውን ለማራዘም ወገባቸወን ጠበቅ አድርገው እየሰሩ ነው። ይህ አናሳ ቡድን የተቀረው የኢትዬጲያ ህዝብ እንዲያውቅላቸው የሚፈልጉት ነገር አለ። ይኸውም እርስ በእርሳቸው ቅራኔ ቢፈጠር እንኳን ” በአንድ ጐጆ ስር” የተፈጠረ ልዩነት አድርጐ የኢትዬጲያ ህዝብ እንዲወስድ ይፈልጋሉ። ለዚህም ነው ከአስርተ አመታት በላይ በኤርትራ የመሸገውን የትግራይ ንቅናቄ በአሸባሪነት በፓርላማ እንዲፈረጅ ያላደረገው። በተቃራኒው ከእሱ ያነሰ እድሜ ያለው ግንቦት ሰባት በአሸባሪነት እንዲመደብ ያደረገው። …

…ለዚህም ነው ኤርትራ የመሸገውን ደህሚት “የኤርትራ ሀይል ( የኢሳያስ ጠባቂ)” የሚል ስያሜ እንዲሰጠው ያደረገው። …ለዚህም ነው ደህሚት ያሉት አባላት ከ300 አይበልጡም የሚል አሰልቺ ፕሮፐጋንዳ ለተራዘመ አመታት እንዲስተጋባ ያደረገው።…ለዚህም ነው አይኑን በጨው አጥቦ በግላጭ የተናገረውን በማጠፍ ዛሬ ደግሞ በሶስት እጥፍ ቁጥራቸውን አሳድጐና አጀግኖ ነገሪት እየጐሰመ ተቀበልኳቸው የሚለን። …ለዚህም ነው እነዚህ ትግሉን ወደ ተሻለ ደረጃ ማሻገር ያቃታቸው ” የጦጣ ዘር አቀባዬች” መንገዋለላቸውን አውቀው ቅሬታ ሲያዝሉ መንገድ ላይ አፈፍ አድርጐ ” ለእኛ እና እነሱ” የውድመት ስትራቴጂው የተጠቀመበት። …

…ለዚህም ነው በተቀረው ኢትዬጲያውያን ዘንድ ” ዘሮች ሁሉ እኩል ናቸው፣ አንዳንድ ዘሮች ግን የበለጠ እኩል ናቸው” የሚለው አባባል ገዥ አስተሳሰብ እንዲሆን ያደረገው። …ለዚህም ነው ” ፕሮፌሰሩ ወደ ጫካ እንዲገባ ያደረግነው እኛ ነን!” ያለው አንደበታቸው ሳይዘጋ ” ኢሳያስ ፕሮፌሰሩን ወደ ሜዳ እንዲወርድ አደረገው” የሚል ቅጥፈት ሲናገሩ የማይሸማቀቁት። እኔ እምለው ኢሳያስ አፈወርቂና አባይ ወልዱ (ዶክተር ደብረጲዬን) እየተመካከሩ መስራት ጀመሩ እንዴ?…መቼስ ” የአህያ በሬ!” የሆነው “ደ -ሳአ -ለ -ኝ!” እና ሌሎች ባለሟሎች የዚህ አካል ነው ብሎ ማመን ከቧልት አይዘልም ብዬ ነው።

ነገርን ነገር ያነሳዋል እንዲሉ አንዳንድ በሚኒስትር እና ፓርላማ ደረጃ ያሉትን ባለሟሎች ሁለት ጥያቄ ልጠይቅ። ክቡር ሚኒስትሮች! ለመሆኑ ” የፀረ ሽብርተኝነት ግብረሀይል አባላት” እነማን እንደሆኑ ታውቃላችሁ?… ክቡራን ሚኒስትሮች እና የሸንጐ አባላት ደእሚት የሽብርተኝነት አዋጁ ከመውጣቱ ስድስት እና ሰባት አመት በፊት የተቋቋመ እንደሆነ መንገር ለቀባሪው ማርዳት ይሆንብኛል። ታዲያ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት፣ በወይዘሮ አስቴር ማሞ አንባቢነት፣ በተከበረው ፓርላማ አጵዳቂነት ለምን በሽብርተኝነት አልተፈረጀም??

2• ” The Law of the Few!”

ሁለተኛው እድል አምባገነናዊ ስርአቱ እየደቀነ ያለውን አደጋ በአግባቡ በመረዳት የስርአት ለውጥ መምጣት እንዳለበት ያመኑ ሀይሎች ቅሌን ጨርቄን ሳይሉ በትብብር የሚሰሩበት ሁኔታ መፍጠር ነው። ትብብርም እንበለው ንቅናቄ የመጨረሻው ግቡ በጠመንጃ ስልጣን ያለመያዝ፣… በኢትዬጲያ ዲሞክራሲያዊ ስርአት ለመገንባት መደላድል መፍጠር፣ …ሁሉን የሚያቅፍ ምቹ ሁኔታ መፍጠር እስከሆነ ድረስ በጋራ ለመስራት የሚያስቸግረው አይደለም። የትብብር አላማ እና ግቡ ግልጵ እስከሆነ ድረስ በጥቂቶች ቢጀመርም (“The Law of the few”) ነገ እልፎችን የሚያሰልፍ ጥቂቶችን እያራገፈ የሚሄድ መሆኑ ሳይንሳዊ ነው። በተጨባጭም እየታየ ያለው እውነታ የዚህን ሳይንሳዊ አባባል የሚያፀና ነው።

እንደ እውነቱ ከሆነ የሰሞኑን የጥቂት የለውጥ ሀይሎች እንቅስቃሴ ስመለከት የሚያስታውሰኝ የማልኮም ግላድዌል የሚባለው ፀሀፊ የጳፈው የሊደርሺፕ መጵሀፍ ነው። ማልኮም ” Tipping point: How little Things make Big Differences” በሚለው መጵሀፋ ህዝባዊ ንቅናቄ (ማእበል) የሚቀሰቀሰው በጥቂት የቆረጡ ሰዎች እንደሆነ ያስረዳል። በእሱ እምነት መሰረት መሰረታዊ የለውጥ ሂደት ( ህዝባዊ ንቅናቄ) ለማቀጣጠል ወሳኞቹ ጥቂቶች ናቸው። ርግጥ እነዚህ ህዝባዊ ንቅናቄ ፈጣሪዎች ራእይ ያላቸው፣ ራእያቸውን ለማስፈፀም ስትራቴጂና አቅጣጫ የመንደፍ ክህሎት፣ የማደራጀት ብቃት፣ በህዝባዊ ማእበል ሊያነሷሷቸው ከሚፈልጉት ማህበረሰብ ጋር የተሻለ ተቀባይነት፣ እንዲሁም አለም አቀፍ እና አገራዊ ሁኔታውን ለመተንተን የሚያስችላቸው ብቃት ያላቸው ሊሆን ይገባል።

ከላይ የተቀመጠውን ሀልዬት መሰረት በማድረግ እነዚህ ጥቂት የለውጥ ሀይሎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ሶስት አበረታች ውጤቶችን ያስመዘገቡ ይመስለኛል። እነዚህም፣

2•1 ምን አይነት ትግል

በእነዚህ ጥቂት የለውጥ ሀይሎች ከአመታት በፊት ሲቀነቀን የነበረው ” በኢትዬጲያ ውስጥ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ሁሉን አቀፍ ትግል መካሔድ አለበት” የሚለው የፀና አቋማቸው በኢትዬጲያ ምድር ላይ ገዥ መሬት ተቆናጦ የአብዛኛው አስተሳሰብ ወደ መሆን ተቀይሯል። በዛሬይቱ ኢትዬጲያ አናሳው ዘረኛ ቡድን የበላይነቱን እስከያዘ ድረስ የምርጫ ፓለቲካ እንደ እባብ አፈር ልሶ የመነሳት እድሉ አልቦን በአልቦ የማባዛት ያህል ሆኗል። ከእንግዲህ በኃላ ብረት እና ህዝባዊ እንቢተኝነት ተዋህደው (Synergy) ፈጥረው እስካልተንቀሳቀሱ ድረስ በሌላ መንገድ ለውጥ አመጣለው የሚለው አካሄድ የተዘጋ ፋይል ሆኗል። እንደ እውነቱ ከሆነ በአሁኑ ጊዜ ” ብሔራዊ መግባባት”፣ ” ህገ መንግስት”፣ ” ምርጫ ቦርድ”፣ ” ተፎካካሪ ፓርቲ” …ወዘተ የሚሉ አባባሎችና ተቋማት ” ከኢቲቪ እና የመለስ አካዳሚ” ከሚባሉት ስፍራዎች የዘለለ ቦታ የላቸውም። ዛሬ በኢትዬጲያውያን ዘንድ ያለው አስተሳሰብ በጉልበት ረግጦ የሚገዛ ሀይል የሚወገደው በጉልበት ብቻ እንደሆነ መግባባት ላይ ተደርሷል።

2•2 የለውጥ ሀይሎችን ማብዛት

እነዚህ ጥቂት የለውጥ ሀዋርያዎች በወሰዱት እርምጃ ባልተጠበቀ ሁኔታ የደጋፊያቸውን ሀይል ማሳደግ ችለዋል። በርካታው ህዝብ ( የሚቃወሟቸውን ሳይቀር) በወሰዱት እርምጃ አክብሮት እንዳለው ማሳየት ችለዋል። እነዚህ የለውጥ ሀይሎች የሚታመኑ እና የሚሰሙ በመሆናቸው መላውን ኔትወርክ ለመቆጣጠር ችለዋል። ዛሬ አብዛኛው ማህበራዊ ድረገጶችና ሚዲያዎች የተሸፈኑት በእነዚህ ሰዎች የእለት እንቅስቃሴ ሆኗል። በመላው አለም እነሱን ለመደገፍ የሚጠሩ ስብሰባዎች የህዝብ ማእበል እያጋጠማቸው ነው። እናቶች የጣት ወርቃቸውን አውልቀው እስከመስጠት ደርሰዋል። በየአህጉሩ ጠንካራ ተከታዬችን በማፍራት ላይ ናቸው። ባጭሩ ትንሹ መዘውር ትልቁን ማንቀሳቀስ ጀምሯል። ትልቁ መዘውር በተሟላ ሁኔታ መንቀሳቀስ ከጀመረ የሚያቆመው አይኖርም…The law of few!

እዚህ ላይ አንድ ነገር ላንሳ። እነዚህ በአናሳ ብሔር ገዥ መደብ ዙሪያ የተሰባሰቡ ዘረኞች እና ባለሟሎቻቸው ዘወትር ከአፋቸው የማትጠፋ የፕሮፐጋንዳ ቃል አለች። ይህቺም ” የዲያስፓራወን ገንዘብ አታሎ ለመውሰድ! ” ትላለች። እንደ እውነቱ ከሆነ ይሕቺን ቃል ከድሮ የትግል ጓደኞቼ አፍ ስሰማ ከመጠን በላይ እሸማቀቃለሁ። በአንድ በኩል አዳራሽ እየሞላ የሚፈሰውን ዲያስፓራ (በውጭ የሚኖር ኢትዬጲያዊ) ማገናዘብ የማይችል በነዱት የሚነዳ ማህበረሰብ አድረገው እየቆጠሩት ነው። ርግጥ ነው አዲሳአባን ተራራ ላይ ሆኖ ሲያያት በምሽት ፀሀይ የወደቀችበት መሰለኛ ያለው የትላንት ታጋይ ( የዛሬው በአሜሪካ ኤምባሲ ንግግር ለማድረግ የሚጋበዝ ኮረኔል) ይህንን ቢል የሚያስከፋ አይደለም። ነገር ግን የውጭውን አለም ከሚያውቁት እነ አምባሳደር ግርማ ብሩ አፍ ሲወጣ ግን ያሸማቅቃል። በነገራችን ላይ በቅርብ ጊዜ የለውጥ ሀይሎቹን ለመደገፍ በተጠራ ህዝባዊ ስብሰባ ተገኝቼ ነበር። እናም በስብሰባው ላይ የለውጥ ሀይሉን ለመደገፍ ከመጡት ኢትዬጲያውያን ሁለቱ የህግ ዶክትሬት ነበራቸው።… ሁኔታው ስለገረምኝ ወደ አዱገነት በሀሳብ ሄድኩኝ። መልስ ባጣ አምባሳደሬን መጠየቅ ፈለኩ። እንዲህ በማለት ብጠይቅስ፣

ጋሽ አምባሳደር ግርማ ብሩ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ስንት የህግ ዶክትሬት ያላቸው መምህራን እንዳሉ እንድትነግረን ከማክበር ጋር እጠይቃለሁ!!

2•3 የለውጥ ተውሳኮችን ማንገዋለል
ጥቂቶቹ የለውጥ ሀይሎች ያስመዘገቡት ሁለተኛ ውጤት ትግሉን ወደ ፊት ማራመድ የተሳናቸውን የበረሀ አመራሮች በአጭር ጊዜ ማንገዋለል መቻላቸው ነው። ሞላ አስክዶም እንደነገረን ላለፋት አስራ ምናምን አመታት በወር ሀያ ምናምን ሺህ ብር እየተከፈለው፣ የፈለገውን ምግብ እየበላ፣ ከአንደኛው አልጋ ወደ ሌላኛው እየተዘዋወረ ( ስንት ጊዜ ከአልጋ እንደወደቀ የህማማት እለት እንደምንሰማ ተስፋ አድርጌ!) የኖረ ሰው ነው። በሌላ በኩል በእሱ ስር ባሉት ሰፊ ጦር ምክንያት በሌለው አቅሙ የወታደራዊነት (Militarism) አመለካከት እንዲያዳብር አድርጐታል። በመሆኑም ትግሉን ፈቀቅ ማድረግ ተስኖት በቁጥር ተኮፍሶ የመኖር ሂደቱትን ገፍቶበታል። የዘር ምንጩም ሆነ አስተዳደጉ ከህውሀት ነውና ለእሱ የትምህርት፣ችሎታና ብቃት ጉዳይ ከግምት የሚገባ አይደለም። ሁሉም ዘሮች እኩል ናቸው፣ ሌሎች የበለጠ እኩል ናቸው እንዲሉ!…እንግዲህ ይህ የጓድ ሞላ አይብን( cheese) ጠብቆ የመኖር ህልውና በለውጥ ሀይሎች ተሰናከለ። የእሱን አባባል እንደ ወረደ ልውሰደውና ሀያ ምናምንቴ ሺህ ብር የነበረችው ደሞዝ ልትቀር ሆነ! …በየጊዜው የምትታረደው ጥቦት ልትቀር ነው!…ከአልጋ አልጋ እየተገላበጡ መውደቅ ልትቀር ነው! …ታዲያ ምን ይዋጠው!…ለማንኛውም “Who moved Molla’s cheese?” ብዬ ብሰናበት ምን ይለኛል??

ኤርሚያስ ለገሰ ( በፈረንጂኛ ከለሊቱ ሶስት ሰአት)

ግንቦት 7ን ሊቀላቀሉ ነው ተበለው የተያዙት እነብርሃኑ ለህዳር 21 ተቀጠሩ ‹‹የሽብር ተከሳሽ በመሆናችን ህክምና ተከልክለናል›› ተከሳሾቹ

$
0
0

birhanu tekle
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
የኢትዮ-ኤርትራ ድንበርን አቋርጠው ኤርትራ የሚገኘውን ግንቦት ሰባት የተባለ በተወካዮች ም/ቤት ሽብርተኛ የተባለ ድርጅትን ሊቀላቀሉ ሲሄዱ ተይዘዋል በሚል የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ በድጋሜ ለብይን ቀጠሮ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
ዛሬ መስከረም 5/2008 ዓ.ም የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የቀረቡት ብርሃኑ ተ/ያሬድ፣ እየሩሳሌም ተስፋው፣ ፍቅረማርያም አስማማው እና ደሴ ካህሳይ በድጋሜ ለህዳር 21/2008 ዓ.ም ብይን ለመስማት ተቀጥረዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ዛሬ የአቃቤ ህግን ምስክርና የሰነድ ማስረጃ መርምሮ ብይን ይሰጣል ተብሎ ይጠበቅ ነበር፡፡
ተከሳሾቹ በማረሚያ ቤት እየደረሰብን ነው ያሉትን አቤቱታ ለፍርድ ቤት ያሰሙ ሲሆን፣ በተለይ ‹‹የሽብር ተከሳሽ ስለሆንን ብቻ ህክምና ተከልክለናል፤ በማንነታችን ጥቃት እየተፈጸመብን ነው›› ሲሉ ችሎት ፊት ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም ፍርድ ቤቱ እነዚህን ችግሮች በተመለከተ ለማረሚያ ቤቱ ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው ጠይቀዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ የማረሚያ ቤት ተወካይ ያለውን በማስጠራት ‹‹ማስታወሻ ያዝና አጣራ›› በማለት አልፎታል፡፡
በሌላ መዝገብ የሽብር ተከሳሽ የሆነው በአርባ ምንጭ የሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪ በፍቃዱ አበበ በበኩሉ ቀሪ የመከላከያ ምስክሮቹን ለማሰማት ለህዳር 16/2008 ዓ.ም ተቀጥሯል፡፡

ዘለቀ ገሠሠ:- ወደ ሃገሩ ሲመለስ ችካጎ “እፎይ…እፎይ…!”ተነፈሰች የተባለለት ቤዝ ጊታር ተጨዋች!

$
0
0

እመቤት ጸጋዬ ከቺጋጎ

በዚህ በያዝነው ወር የመጀመሪያው ሳምንት ላይ የአዲስ አድማስ ጸሃፊ አቶ መንግስቶ አበበ የተሰኘው የአዲስ አድማስ የድህረ ገጹ እና የጋዜጣው አምደኛ በአንድ እውነታን ባልጨበጠ እና በሬ ወለደ አይነት የመንደር ወሬ ይዞ ብቅ ማለቱ አንዲቱን ብቻም ሳይሆን ግዙፉን አለም አስገርሞ አስደንግጦአልም። ይኸውም የነገሩ እውነታን ማጣት እና የበሰለ የወሬ ቅንብር አለመኖሩ ለዘመናት አዲስ አድማስ ያካበተውን ትልቁን ዝና በተለይም ከእነ አቶ አሰፋ ጎሳዬ ጠንካራ ጀርባ የነበራቸውንም ስራም ሆነ በነ ነብይ መኮንን ስልታዊ ጥበብ የነበረውን እድገት ይዞ በአንድ ጊዜ ወደ ከንቱ ጉድጓድ እንዲጠልቅ እና እንዲቀበር አድርጎታል ፤ምክንታያዊ ሁነቶቹ ምንድናቸው ተብሎ ቢጠየቅ ምርምራዊ ጋዜጠኝነት የጎደለው እና ስነ ምግባራዊ ሂደት ያልታከለበት የለብለብ ጋዘጠኛ ስራ ሆኖ መቅረቡ ሲሆን ምናልባትም ይህንን ስራ እንዲቀርብለት የፈለገው ግለሰብ በተወሰነች አልባሌ በሆነች ጉርሻ ስሙን ለማግዘፍ እና የህብረተሰብ ትኩረትን ለማግኘት ሲል የሰራው ትልቅ ሴራ እንደሆነ ለመረዳት ይቻላል ፤ እንዲህም ሆኖ ግን ጋዜጠኛውን አያስተችም ተብሎ ሊያሰኝ አይችልም ፣በሚገባ ሊያስተች እና ሊያስገመግም ወይንም የጋዜጠኝነቱ ሚና ምን እንደሆነ እና ከየት የተማረው የትምህርት ማእረጉ ምን እንደሆነ ሊያሳውቅ ወይንም ሊያስጠይቅ የሚገባው መንገድ እንደሆነ የሚያመላክት ጎዳና ነው ።
zeleke Gesese
ስለ ጉዳዩ ጠለቅ ብለን ከማየታችን በፊት ጋዜጠኝነት ምን ማለት እንደሆነ መዳሰሳችን ጥሩ ነገር ነው ፣ምክንያቱም በየትኛውም ሃገር የሚከበረው እና ከመንግስት በላይ ሊፈራ እና ሊወደስ የሚገባው የጋዜጠኝነት ሙያ በኢትዮጵያ ውስጥ ግን በመግስት ሲረገጥ እንዲሁም በሙያተኞቹ ሲገለበጥ እና ሲረገጥ ሲናቅ እና ሲወድቅ የሚታይበት ሙያ መሆኑ አንዳንድ ጊዜም ሙያውን እንዲጠላ ያደርገዋል ፣በተለይም በአፍሪካ ይበልጡኑም በአፍሪቃ ቀንድ አካባቢ ፣ይህም የሆነው የመንግስታቶች እንቢተኝነት እና ጨለምተኝነት ስሜት ፤ በውስጣቸው ያለውን ድብቅ ሴራም ፣ ሆነ በሃገሪቱ ላይ የሚፈጸመውን ድብቅ ደባ ፤ አልያም የሃገሪቱን ሃብት ምዝበራ ፤ ሆነ የመንግስት ጉልበት መንኮታኮትን ፤ የመረጃ ማእከሎች ከሰሙት ወደ ክፉኛ ደረጃ ያደርሱታል፤ የሚለው ስጋታቸውም ብቻም አይደለም መረጃ ማእከሎችን እንዲዘጉ እና ጋዜጠኞች ለእስር ወይንም ለስደት እንዲበቁ የሚያደርጉት ፣የስልጣን እድሜአቸውን ለማራዘም እንዲረዳቸውም ጭምር ነው ። ታዲያ የእኛ አገሮቹ ማስ ሚዲያ ግን ናሮ ካስቲንግ ናቸው ይህም ማለት በተወሰኑ ሰዎች ላይ ብቻ ትኩረት አድርጎ ስለዕነዚያ ስዎች ብቻ የሚያወራ የሚለፈልፍ አጋኖ የሚያወራ የሚል አይነት ትርጉዋሜ ይሰጠዋል።

በማስ ሚዲያም ሆነ ብሮድካስቲንግ ወይንም ናሮ ሚዲያ ያለው ልዩነት ሰፊ ነው ፣ ናሮ ሚዲያ የሚባሉት ብዙውን ጊዜ በውጭው አለም በስፖርቱ ላይ ትኩረት ሰጥተው የሚዘግቡት ሚዲያ ብቻ ናቸው እነዚህም እንደ ኢ ኤስ ፒ ኤን ኤ (ESPNA) የተሰኘው የስፖርት ጋዜጠኞች ድርጅት ነው ። ማስ ሚዲያ የሚባሉት ደግሞ የሬዲዮን ቴሌቪዥን፣ጋዜጣ እና ኦንሊን ላይ ድህረ ገጽ ኖሮአቸው በተለያዩ መልኩ መረጃን ለአለም የሚያቀብሉ ሲሆኑ በአሁኑ ሰአትም የሶሻል ኔትዎርኮችንም በመጠቀም ዘገባዎችን በቀላሉ ለአለም ማሰራጨት ስለሚችሉ የሶሻል ኔትዎርኮችንም የሚጠቀሙትንም ያካልላል፣ ወደ ብሮድካስቲንግ ደግሞ ከመጣን ቴሌቪዥን እና ሬዲዮ ከህትመት ድርጅቶች ጋር ብቻ በመፎካከር ሊሰሩ የሚችሉ ድርጅቶች ናቸው ስያሜውን የሚያገኙት አሰራራቸውም ሆነ የስራ ደረጃቸውም ፈቃዳቸውም ሁሉም ይዘታቸው ልክ እንደየ ስማቸው የሚለያይ ሆኖ ሳለ ። ይህንን ጥሬ ትርጉዋሜአቸውን ይዤ ያቀረብኩት ሲሆን ስለ እያዳንዱ ጥልቀት ያለውን ስራ ይዤ ልቅረብ ብል ሃሳቡን በሙሉ ስቶ ወደ ሌላ አቅጣጫ ይገባል እና በተወሰነ መልኩ ብቻ ለማስረዳት እሞክራለሁ ።

ሆኖም ታዲያ ልክ በብዙ ጥቃቅን እንደተሞላ ጋዜጠኛ በእንግሊዘኛው (Embedded journalists) (የጦር ሜዳ ዘጋቢ) ወይንም ኢምቤድድ ጆርናሊስትስ የእኛ አገሮቹም በጉርሻ የተሞሉ ሆነው የማይሆን እና አላስፈላጊ ነገሮችን ሲሰሩ ይታያሉ ፤ብዙ ጊዜ የወታደራዊ ጋዜጠኞች የሃገርን ክብር እና የውስጣዊ ደህንንነት ስጋት ለመጠበቅ ሲሉ ያልሆነውን ነገር ሆነ ብለው እንደሚያወሩት ሁሉ የእኛ አገር በገንዘብ ተኮር የሆኑ ጋዘጠኞቻችን financial target journalists እየሰሩበትን ያለውን ስራ አዘጋጆቻቸው ትኩረት ሰጥተው አለማየታቸው ይበልጡኑ መገናኛ ብዙሃኖችም ጭምር የንግድ ጥቅማቸውን ብቻ ያተኮሩ እንጂ የአንባቢያኖቻቸውን ህልውና ያተኮረ አለመሆኑን ያስረዳል ፤ ለዚህም ነው መርምራዊ ጋዜጠኝነት አስፈልጎ ጥልቀት ባለው ነገር ላይ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ የሚገባው ዋነኛ ስራ ከመውጣቱ በፊት ትልቅ አርትኦት የሚጠይቀው ፣አለበለዚያ ማንኛውም ሰው ቢሆን ከተጠያቂነት አይድንም ።

ምርምራዊ ጋዜጠኝነት ትርጉሙ ምንድነው የሚለውን በቀጥተ ከእንግሊዘኛው ቃል ላይ ብናየው ምንም ሳልጨምር ሳልቀንስ ትርጉሙን ላስቀምጥላችሁ “ Investigative means journalism the use of in-depth reporting to unearth scandals, schemes, which at times put reporters closer to political leaders.” ጋዜጠኞች በጥልቅ ምርምራዊ ስራ ልዩ የሆነን ተሰምቶ የማይታወቅን እና የሚያስገርሙ ጉዳዮችን ፈልፍሎ የሚያወጣ በተለይም የተለያዩ የባለስልጣናቶችን ጉቦ ቅሌትcorruption scandal ፣ወይንም የወሲባዊ ቅሌት sex scandal ,እፈረታዊ ድርጊቶችን ፣በሃገር ህልውና ላይ በድብቅ ሴራ የሚደረጉ ጥፋቶችን ወይንም ሃገርን አሳልፎ ለሌላ ችግር የሚሰጡ የባለስልጣናትንም ሆነ የግለሰቦችን ሴራ ፣ስለ ተደበቁውይንም ጠፉ አለበለዚያም በሚስጥራዊ ስለተያዙ ስራዎች በመመራመር እና በመፈለግ በቅርበት ከፖለቲከኞች ጎን በመሆን እየተከታተለ ሙሉ ሚስጥራዊ ዘገባን በማንኛውም ወቅት እና ሰአት ለህዝብ ምንም ሳያወላዳ የሚያቀርብ ንጹህ ጋዜጠኝነት ነው ።

በኢትዮጵያ ውስጥ የጎደለው ይህ ነው ፣ይህንን ደግሞ ለማወቅ ከተፈለገ አሁንም ባሉት የህትመት ድርጅቶች ላይ ማየት የሚቻል መሆኑን በግልጽ እና በገሃድ ከመንግስት ከሚያስተዳድራቸው ጋዜጦች እና ሌሎች የሬዲዮ እና የቴሌቪዝን ባሻገር እንደ እነ ሪፖርተር እና አዲስ አድማስ ወይንም ፎርቹን አልያም ሌላ በግለሰብ የሚታተሙ ወይንም በሬዲዮ ስርጭት የሚሰራጩ መገናኛ ብዙሃኖች ምንም የምርምራዊ ስራ ብቃት የሌላቸው ወይንም ሃይሉ ያነሳቸው አለበለዚያም በመንግስት ጫና ስራውን እንዳይሰሩ የተገደቡ ሆነው ስናያቸው በሌላም ጎዳና ስንሄድ ሙያተኞቻቸው ከሙያ ጋር ሳይሆን ከጥቅም ጋር የተሳሰሩ ግለሰቦች መሆናቸውን ሁላችንም እንረዳለን ።

ከዚህ በላይ ያለውን ሃሳብ እንደ መንደርደሪያ ሃሳብ አድርጌ ስለጋዜጠኞቻችን የሙያ ባህርይ ጉድለት መነሻ ሃሳብ ሆኖ እና ላሉበት መንገድ ፍንትው ያለ ነገር መግለጽ የማልችልበት ጥቃቅን እና የተሰባበሩ እነዚህ ሃሳቦች ተጠግነውም ቢሆን የነገውን እየወደቀ ያለውን የመገናኛ ብዙሃን ጉዞ ሰሩ ተነቅሎ ከተጣመመበት ቀና ከማይልበት ቦታ ላይ ሸከፍ አድርጎ እንዲይዘው ሊያደርገው የሚችል ባላ ለማስደገፍ የተሞከረች እንጂ ጥልቀት ያለው እውቀት ኖሮኝ አይደለም፣ነገር ግን ይህንን ሃሳብ ባላቀርብ የመገናኛ ብዙሃኑ ውድቀት በሰፋ ጊዜ ሁልጊዜም ሊከነክነኝ ስለሚችል ይህንን ነገር መናገርን መርጫለሁ ታዲያ ለዚህ መነሻ የሆነኝ ዋነኛ ምንጭ በአቶ ዘለቀ ገሰሰ ላይ የተሰራው ናሬሽን ስቶሪ ቴሊንግ ድምቀታዊ ታሪካዊ ንግርት ስለሆነ ወደ ቁምነገሩ ምን እንደተከናወነ እኔም የበኩሌን ለመናገር ቃጣሁ !
ወደ ዋናው ቁምነገር ልምጣ እና በሳለፍነው ሳምንት አዲስ አድማስ ያሳተመው የድህረገጹ ስራ ላይ በንግድ እና ኢኮኖሚ አምዱ ላይ “ወደ አገሩ ሲመለስ “አዲስ አበባ አሸነፈች፤ ቺካጐ ተሸነፈች” የተባለለት አርቲስት” አስገራሚ ስራን አይተን ተደነቅን መቼም ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው እንደሚባለው ፣ለሰሚው ግራ ገብቶታል ፣ተናጋሪውም ከብዶታል ማንነቱንም ቆልሎአል ፤ እሱነቱንም እረስቶአል ጋዜጠኛውም ለተሰጠው መረጃም ምንም አሳማኝ መረጃ ሳይጠይቅ በስራዎቹ ተደንቆአል ፤በእርሱም ኮርቶአል ከብሮአል ጋዜጠኝነቱንም አስመስክሮአልም ። እንዲህ ነው የኛ ጀግና ጋዜጠኛ ፤ እንዲህ ነው የኛ ባለሃብት አሰኝቶልናል ። እንኳን ደስ ያላችሁ ደስ ይበለን እስኪ እኛም ታሪክ ይዘን መጣን አብረን እልል እንበል ብለን እኛም ፣ማን ይናገር የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ ብለን እውነታውን እንዲህ ልናቀርበው ከእናንተ ጋር ተፋጠናል እስኪ እናንተም እውነታውን ይዛችሁት ኑ እኛም ይሄው ብለን ዛሬ ብእራችንን ልናሾል ወደድን።

ከመጀመሪያው አረፍተ ነገር ለመነሳት ያህል በቁጥራቸው ከ30 በላይ ለተዘዘሩት የትምህርት ቤት ማሰራት እና የተሰሩበት ቦታዎች ያልተገለጹበት እና በማን ሃይል እንደተሰሩ እና ገንዘቡ ከየት ተገኘ የሚለውን የማያካትት ጥያቄ ሳይነሳ 225 ሺህ ዜጎችን የፈራበትን ትምህርት ቤት የት እንደተመሰረቱ ፣መቼ እንደተመሰረቱ ፣የተመሰረቱት ትምህርት ቤቶች የንግድ ፈቃዳቸው በማን ነው ፣ያሰራቸውስ ሰው ወይንም ድርጅት ማን ይባላል ብለን በጥልቅ ማወቅ እና መረዳት ተገቢ ነው ፣ለዚህም ለእያንዳንዱ ግብረ ሰናይ ድርጅት NGO ሊሰጣቸው የሚገባውን የስራ እና የስም ድርሻ ሳይዘነጋ አቶ ዘለቀ ገሰሰ የሰሩት ተብሎ እንዴት ሊሰየምላቸው ተሰኘ ? ለመሆኑ የንግድ ፈቃዱ በእጃቸው ይገኛልን ? በሌላም አቅጣጫ ሊያስጠይቅ የሚችል ጥያቄ ቢኖር በየአመቱ ለ15 አመታት እንኳን በየ አንዳንዱ ክፍል ማለትም ከአንደኛ ክፍል እስከ ስምንተኛ ደረጃ ድረስ 375 ተማሪዎች ቢኖሯቸው እስካሁን ድረስ 45.000 የሚሆኑ ተማሪዎችን ለማስተማር ይችላሉ ሆኖም ግን አሃዝ ተሳስታችሁ ይሆን ወይንስ እያንዳንዳቸው ክፍሎች በተናጠል ከ 500 በላይ የሚይዙ ክፍሎች ነበሯቸው ?አለበለዚያ ግን ልክ እንደ ጋዜጠኛው እና እንደ አቶ ዘለቀ ስታትስቲክ ስሌታዊ አካሄያድ በአንድ ክፍል ውስጥ 2000 ተማሪዎችን የሚያስተናግድ ክፍል ነበራቸው ያም ማለት ለእያንዳንዱ ከ 1 እስከ ስምንተኛ ክፍል ድረስ ማለት ነው ይህም ሲሆን በጠቅላላው በ 15 አመታቱ 240.000 የሚሆኑ ተማርዎችን አስተምረዋል ማለት ነው ?

ለመሆኑ ግን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲስ በአንድ ክፍል ውስጥ 2000 የሚይዝ የተማሪውች ቦታ አለውን እንዴ ብለን እንድንጠይቅ ያስገድደን ይሆናል ? በዚህም መሰረት ላይ በአንድ ክፍል ውስጥ 200 መቶ ተማሪዎች እንኳን ቢቀመጡ ምን ያህል ትምህርት ቤቶች እንዳሉ እና በትምህርት ገበታቸው ላይ ሊኖሩ የሚችሉትን ተማሪዎች እንኳን ብናነጻጽር በአስራአምስት አመታት ከምን ያህል ትምህርት ቤቶች 225.000 ተማሪዎች ሊወጡ እንደሚችሉ ማስላት የሚቻል ይመስለኛል ለዚህም ይህንን ከግንዛቤ እንዲገባ ማድረግ ይቻላል ይህንን በትክክለኛው የስታትስቲክስ አሰራር በግራፍ አቅርብልን የምትሉም ከሆነ ምን ያህል ሊመጣ እንደሚችል እያንዳንዷን ቁጥር በግላጭ በሚያሳይ ዳታ ሰርቼላችሁ ልልከው እችላለሁ ። በሌላው አቅጣጫም እንመልከተው ከተባለ ለ 30 ትምህርት ቤቶች ውስጥ አሉ የተባሉትን የአሃዝ ቁጥር ከተመለከትነው በእያንዳንዱ ትምህርት ቤት ውስጥ 7500 ተማሪዎች አሉ ማለት ነው ፣በሚገርም ሁኔታ በአመት ይህን ያህል የሚያፈራ ትምህርት ቤት ካለን ሃገሪቱ ካላት ህዝብ ብዛት አንጻር እና የትምህርት ማግኘት የተሳናቸው እጥረት ቢያንስ 0.355 ፐርሰንት ቀንሶልናል ማለት ነው ። ይህንም በትክክል ካሰላነው በጣም ትልቅ እድል ነው ምክንያቱም የሃገሪቱ መንግስት እንኩዋን በ 25 አመታት ውስጥ ባስገነባቸው የትምህርት ቤቶች ላይ እንዲህ አይነት ፈጣን የሆነ ለውጥ ለማሳየት ያልቻለበትን ሁኔታ አቶ ዘለቀ ፈጥነው ደርሰውበታል ። ታዲያ ይህም ሆኖ ግን አንድ አባባል ትዝ አለኝ “ዝም የምለው ሳላውቅ ቀርቼ አይደለም ሁልግዜ ትርጉም ከሌለው ቃላት ምክንያት ያለው ዝምታ ስለሚበልጥ ነው” እንዲህም ሲባል ሞኝነት ያለ ይመስላችሁ ይሆን ዝምታን ብንመርጥ አቶ ዘለቀ ገሰሰ እንዲህ አይነት ወሬ ሊያወሩን የቻሉት?

በሌላም በኩል ከ30 በላይ ጋንግስተር ብለው ለተናገሩት አሁንም በግልጽ ልናገር የምችለው እውነታ እንዳለ ይረዳሉ ይህንን እውነታ ደግሞ አልሆነም አልተደረገም አይኔን ጨለማ ያድርገው ብለው እንደማይሉ አውቃለሁ ፣ምክንያቱም እውነተኛውን ታሪክ ወደ ጋንግስተር ስለለወጡት እንጂ ፣ምናልባትም መስመሩን ባልቀው በሳለፍነው ሁለት አመታት ተመልሰው ወደ ችካጎ አቅንተው በመምጣት በከተማዋ የጃማይካውያን አባላቶች በክፉኛ ተደብድበው በጩቤ ተጫጭረው በድብቅ ሆስፒታል ከርመው ከሆስፒታል የተኙበት መረጃዎች ያመለክታሉ ፣ለዚህም ደግሞ በቅርበት እርስዎን ወደ ሆስፒታል እንዲሄዱ የረዳዎትን ግለሰብ ጠንቅቀውት የሚረዱት ይመስለኛል እንዴት አምቡላንስ አስጠርቶ ህይወትዎን እንዳተረፈልዎ ይህንን እንደ ምስክር ማቅረብ ከተቻለ እናቀርባለን ሆኖም ግን ለአደረጉት ውለታ ጀማይካውያኖች አደረግነው የሚሉት ጉዳይ ቢሆንም የምእራብ አፍሪካውያኖችም እጅ አለ የሚባለውም ነገር እንዳለ አይዘንጉት።

ከዚያም ውጭ ቆዳው ጥቁር ውስጡ ነጭ እየተባለ የሚጠራው እና ከፍተኛ የዘረኝነትን መንፈስ የሚያራምደው ይሄው ግለሰብ እንደመሆኑ መጠን እና በእራሱ በወገኖቹ በኢትዮጵያኖች ላይ አይናቸው ላይ ከፍተኛ ሃይል ያለውን የባትሪ መብራት በማብራት እና በጥቁር የሰኩሪቲ ጋርዶች እየተገፉ እንዲደበደቡ የሚያደርገው ይሄው አቶ ዘለቀ ገሰሰ ፤ እራሱን እንደጲላጦስ ከደሙ ንጹህ ነኝ እኔ መልካም አድራጊ እና ፈጣሪ ነኝ ብሎ እንደ ጣኦት አምልኩኝ ብሎ መነሳቱ በጣም አስገራሚ የታሪክ ብዥታ ነው ። ለእንደዚህ አይነቱ ድርጊቶቹ ደግሞ የሃገርን ልጅ በሃገር ልጅ ብለው የዳሎል ባንዶች ያቁዋቋሙትን የዋይልድ ሄር ባር ወይንም ቡናቤትን የእኔ የብቻዬ ነው እናንተን እንደፈለገኝ አደርጋለሁ እያለ ሲዝብት በዝምታ እየታየ እና ወንዱን ቀሚስ አስለብሶ ሴቱን ወንድ ባደረገበት በዚህ በሰሜን አሜሪካ ዝምታን የለበሰው ወጣት የኢትዮጵያ ወንድ ፤ምን ያህል ትእግስተኛ እና ፍቅር ለበስ ህዝብ ሆነን እንደተፈጠርን ያሳዩበት ትልቅ አጀንዳ እንዳለ መረሳት የለበትም ለዚህ ደግሞ ለቀድሞው ለዳሎል ባንድ አባላት ለአቶ አስራት እና ሩፋኤል ወልደማርያም ይግባቸው እና ዋይልድሄር በቁሞ ለረጅም ዘመን እንዲጓዝ አድርገውታል አሁንም እያደረጉት ይገኛሉ ። ታዲያ ኢትዮጵያኖቹ እንደ መዝናኛ እና እንደራሳቸው ሃብት ተጠቅመው የሃገራቸውን ልጆች ያቋቋሙትን ትልቅ ድርጅት ለመርዳት እና ለመዝናናት ሲሄዱ ከፍተኛ ግፊት እና እንግልት የደረሰባቸው ኢትዮጵያኖች ብቻ የትየለሌ ናቸው ፣እንደዚህ ልንጠቁማችሁ የወደድነው ግን ለምን ጃማይካኖች እና የምእራብ አፍሪካውያኖች በአቶ ዘለቀ ገሰሰ ላይ ጥቃት ሰነዘሩ የሚለውን እንደመጠይቅ ካነሳን በራሱ ወገኖች ላይ የለመደውን ድርጊት በሌሎቹም ላይ መፈጸሙ ሲሆን ፣ በከንቲባው ጸሃፊም ላይ ፈጽሞት ድርጅቱ እንዲዘጋ ፒትሽን ሁሉ እንደተፈረመበት እና አጣብቂኝ ውስጥ ገብቶ እንደነበር የሚረሳው አይመስለንም።ሌላው ልናሳውቃችሁ የፈለግነው የዘለቀ ውሸት ለኢትዮጵያን ወገኖች በጣም አዲስ እንደመሆኑ መጠን የተወራው ሁሉ እውነት ሳይሆን ሃሰት ነው የሚለውን እና ፣ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ የሚለውን ሃሳብ ለመሰንዘር ሲሆን ፣አገራችንንም ከእንደነዚህ አይነቶቹ ዳግም ዶ/ር ኢንጂነር ዘሚካኤል ዓይነቶቹ ለመታደግ ስንል እውነታውን አፍረጥርጠን መናገሩን ወደድን።

በሌላም በኩል በችካጎ ፖሊስ ዲፓርትመንት አባላት ለጥበቃ በተሰማሩ ፖሊሶች በአደንዛዥ እጽ ተጠቃሚነቱ ተይዞ ማን እንደሚሸጥለት የማይጠቁም ከሆነ በአደገኛ ሁኔታ ወደ መቀመቅ ውስጥ ሊገባ እንደሚችል በፖሊሶች ተነግሮት እና በእጃቸው ላይ ከወደቀበት ጊዜ ጀምሮ የእጽ አዘዋዋሪ ሃይሎችን እየጠቆመ ከፖሊስ ጀርባ የአዘዋዋሪዎች ሰላይ ሆኖ እንዲሰራ መሰየሙን አገር ያወቀው ጸሃይ የሞቀው ታሪክ ነው ፤ ይህንን አሉባልታ ሳይሆን እውነታውን ለመናገር ያህል መስመር ለማስያዝ እንጂ ከዚያ ውጭ ከማንኛውም ነፍሰ በላ ሰው ጋር እንዳለገጠሙ ያውቁታል ፤ እንዲያውም በአንድ ወቅት በቡሽቲዎች(ጌይ) ባር ለመዝናናት ገብተው ፤ቆነጃጅቶችን አገኘን ብለው የወንድ ወይዘሮዎችን አቅፈው እየሳሙ ሲደንሱ ቆይተው በመጨረሻው ወቅት ላይ ድምጾቻቸውን ሲሰሙ እና ከእንቅስቃሴ ብዛት መደባበስ እና ስሜት ውስጥ መገባባት ሲጀምሩ በዳንስ ክፍሉ ውስጥ የወንዱን ብልት አፈፍ አድርገው ይዘው ማንነታቸውን ሲያውቁ እግሬ አውጭኝ የፈረጠጡበትን እና ጌዎቹም ያዙልን እያሉ እንደተከተሉዋቸው በገሃድ የሚታወቀውን ታሪክ ጋንግስተሮች ናቸው ብሎ ማደናበር ተገቢ አይደለም እና ይህንን እውነት ባንደብቀው ጥሩ ነው ።
ወደ ሌላው አረፍተ ነገር ስንገባ የዋይልድ ሄር ባር በወቅቱ የነበረው የደንበኞች ኮታ በመጀመሪያው ፎቅ ላይ 75 ሰው ከዚያም በምድር ላይ ያለው ላይ ደግሞ 300 ሰው በኢሊኖይ ስቴት ዲፓርትመንት የሲቲ ኦፍ ሺካጎ የንግድ ፈቃድ ላይ የተመዘገበው የቀድሞው ፈቃድ በግልጽ እንደሚያሳይ ጠንቅቀው የሚያውቁት ነው ፤ ይሄው የዳሎል ባንድ ክለብ እንዴት ተብሎ ቢገመት ይሆን አንድ ሺህ ሰው የሚይዝ ተብሎ ሊነገር የበቃው ? በነገራችን ላይ የዋይልድ ሄር ክለብ የአቶ ዘለቀ ገሰሰ ክለብ ሳይሆን ዳሎል ባንድን አንድ ጣልያናዊ ሲያሰራቸው ቆይቶ በህግ ጉዳይ ቤቱ እንዲዘጋ ሲደረግ እንደገና ዳሎል ባድ የሼር ኩባንያ በመፍጠር በጋራ የከፈቱት እና በአቶ ዘለቀ ገሰሰ የስም ማጭበርበር ስሌት የተነጠቁበት ሁኔታ ያለ ሲሆን እስከመጨረሻው የሽያጭ ወቅት ድረስ አባሎቹ የድርሻቸውን አግኝተው የተለያዩ መሆናቸውን በግልጽ በቅድሚያ ለመጠቆም እወዳለሁ፣ለዚህም ደግሞ በተደጋጋሚ በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ የእኔ ክለብ ነው ብለው የገለጹት ይሄው ክለብ በአባልነት ማን ማን እንደነበረ የሚገልጸውን ስም ዝርዝር ወደ ሁላ ይዤ እቀርባለሁ እና ይህንን ጉዳይ በጥሞና ይከታተሉት ዘንድ የአክብሮት ግብዣዬ ከወዲሁ ነው ።

ለዚህም ክለብ መውድቅ እና የገንዘብ መጥፋትም ሆነ የገንዘብ ኪሳራ መዳረግ ዋነኛ ተጠያቂው አቶ ዘለቀ ከጥቂት አመታት በፊት ከ 50% በላይ የሼር ሆልደርነቱን በቅምጣቸው (እማማ) አማካይነት ገንዘብ ተሰጥቶአቸው ሲቆናጠጡ ከሁለቱ የዳሎል ባንዶች በአሁን ሰአት በህይወት የሌሉትን ወንድሞች የሼር ሆልደርነታቸውን መሸጥ ሲፈልጉ ገዝተው መሆኑ እንዲታወቅ ያሻል ፤እንዲህ ሆኖ ሳለ በህጉ መሰረት ከ50 % በላይ ሼር ሆልደርነቱን የያዘው ሃላፊ ይሆናል የሚለውን ቦታ ተረከቡ ከዚያም የተለያዩ ነገሮችን በስማቸው ለማድረግ እንዲያስችላቸው እና ውሳኔ አሳላፊ ሆነው እንዲረዳቸው እድሉን ተጠቀሙበት በዚህም ሁኔታ ፣ በወቅቱ ቅምጣቸው የነበሩት እና ቢሊየነሯ አሮጊት እናት በየጊዜው ብድር እያበደሩ ስራቸውን እንዲያስኬዱ ያደርጉላቸው ነበር ሆኖም ግን ለስም እንጂ ገንዘቡ የሚውለው ለሌላ ተግባር መሆኑን ያልገባቸው ሼር ሆልደሮቹ ምንም ከመናገር ተቆጥበው ኖረዋል።

አሁን ድረስ በዚህ ጉዳይ ላይ ባንዱን ለማናገር የሚነሳ የመገናኛም ብዙሃንም ሆነ ግለሰብ ቢኖር አንደበታቸው ዝም ነው የሚለው። ዝምታ ነው መልሴ ብለው የውስጣቸውን በውስጣቸው ይዘው እንዲሄዱ የተደረገበት ዋነኛ ሴራ በተለያዩ አጋጣሚዎች የተሰሩት ድብቅ የሆኑ ተንኮሎች እና በህግ እንዲደነገጉ የተደረጉት አንዳንድ ቴክኒክ እና ታክቲኮች በመሆናቸው ማናቸውንም የመገናኛ ብዙሃን በዚህ ጉዳይ ላይ ለማናገር በራቸው ዝግ ነው። ይህንንም ጉዳይ የሚያውቀው አቶ ዘለቀ አንደበቱን ከፍቶ ክለቡ የኔ ነው ለማለት ያስደፈረበትም ክንያት ይህ ሳይሆን እንዳልቀረ በችካጎ የሚገኘው ህብረተሰብ እንደመነጋገሪያ አድጎ ሰሞኑን ሲወያይበት ከርሞአል ፤በእርግጥም በየመጠጥ ቤቱ እና ቡና መጠጫ ቤቱ የውሸቱ ልሂቅነት ልዩ መወያያ ርእስ ሆኖ መክረሙ እኔ ዶክተር ነኝ እያለ የመንግስትን መስሪያቤት ጭምር ሲያጭበረብር ከነበረው ዘሚካኤል የሚበልጥ ትልቅ ውሸት የውሸት መናሃሪያ ሲሉት ተሰምተዋል።

በእዳ መብዛት መንግስት ከቀድሞው የቅምጥ ሚስትዎት (እማማ) ጋር አብሮ በእዳ እጅዎት ተጨማልቆበት የነበረውን ገንዘብ ለማጥራት ሲሉ የዳሎል ባንድ ለዘመናት ያፈራውን ድርጅት የግሌ ነው በማለት ከሴትዮዋ ጋር እየተበደሩ በእኩይ ተግባርም ሆነ በእድሳት ወይንም በስራ ማስኬጃ መልክ ያጠፉትን ገንዘብ ፣በመያዦነት እንዲወረስ እና እንዲሸጥ ሲወሰንብዎት እርስዎ ግን በሙሉ አፍዎት ሸጨው ነው ብለው ማለትዎ እውነት በችካጎ ያለው ህዝብ አይፋርድዎትም ፣›?
የፔን ፕሪስከር የኤክስፕረስ ኢን ሆቴል ኮርፖሬት ባለቤቶች ለተወሰነ ጊዜ የመጡበት ምክንያት በቀድሞው ጊዜ ዘለቀ ገሰሰ ይዞአት የነበረችው የእድሜ እና የገንዘብ ባለጸጋ ሴትዮ የቅርብ ወድጆች በመሆን ክለቡን ለማየት በቅተዋል ።

ከዚያ ባሻገር ግን የአሜሪካው ፕረዚዳንት ሴናተር በነበሩበት ወቅት እንኩዋን አይደለም ሊጎበኙት ቀርቶ የሴናተርነት ስራቸውን ተጠምደው በቆዩበት ስፕሪንግ ፊልድም ሆነ በስተት ዲፓርትመንት ጊዜአቸውን በመሰዋእትነት ማሳለፋቸውን ማንም የሚረዳው ሲሆን ለክለብ መዝናናት ጊዜም ያለነበራቸው ናቸው ለዚህም ደግሞ በክለቡ ውስጥ በአባልነት ወይም ሽርክና የነበራቸው የዳሎል ባንድ አባላት እንኳን የመጡበትን ጊዜ የማስታወስም እድሉ እንዳልነበራቸው ለማወቅ ችያለሁ ።
በሌላም ጉዳይ ልይ እንምጣ እና አቶ ዘለቀ ገሰሰ ያልገለጻቸው እና የባንዱ አባል የነበሩት እነማን እንደነበሩ ለማሳወቅ የሚያስገድደኝ ሲሆን እነዚህንም አንድ ባንድ የስም ዝርዝራቸውን ማቅረቡ ተገቢ ሆኖ አግኝቸዋለሁ ። ዋና ዋናዎቹ አስራት አምሮ ስላሴ የዋይልድ ሄር የሼር ሆልደር የነበረ አሁንም ዋይልድ ሄርን በመምራት ላይ ያለ ፣ሩፋኤል ወልደማርያም የዋይልድ ሄር የሼር ሆልደር የነበረ አሁንም ዋይልድ ሄርን በመምራት ላይ ያለ ፣መላኩ ረታ የዋይልድ ሄር የሼር ሆልደር የነበረ (በህይወት የሌለ) ሙሉገታ ገሰሰ፣ ደረጀ መኮንን (በህይወት የሌለ) የዋይልድ ሄር የሼር ሆልደር የነበረ ፣ ዘለቀ ገሰሰ፣ ንጉሴ አስፋው ችካጎ ላይ የተቀላቀለ እና ጴጥሮስ መኩሪያ በችካጎ የሚኖር ፣በዚህ ዝርዝር ውስጥ የአቶ መላኩን እና ደረጀ መኮንን የሼር ሆልደርነት በመግዛት ከፍተኛውን ድርሻ በመያዝ ከ 51% በመቶ በላይ ይዞ ሃላፊነቱን ለመያዝ የበቃው አቶ ዘለቀ ገሰሰ በሃላፊነት ተቀመጠ እንጂ የድርጅቱ ባለቤት በመሆን በማንኛውም ዘመን አልመራም ፣ለዚህም እንደምሳሌ ሆኖ ጠቀስ የሚችለው ክዋይልድ ሄር ሼር ሆልደር በመሆን የነበረው አንዱን አካል የህግ ባለሙያ የነበረው አሜሪካዊውን ባለሃብት( በህይወት የሌለ )ብቻ መጥቀስ ተገቢ ነው ፣ምክንያቱም በዚህ ጉዳይ ላይ የዳሎል ባንዶችን እንደ ባለቤትነት አባል ለመጥቀስ ያልወደደውን አቶ ዘለቀን ለማሳመን እና እውነታውን ለማውጣት ትልቁ ምሳሌ እና ሊጠቀስ የሚገባው ሰው መሆኑን ማወቅ የገባናል ።

ይህም ብቻም አይደለም ዋይልድ ሄርን ወደ ውድቀት የዳረገውንም አቶ ዘለቀ ሸጥኩት ያለበትን ምክንያት ዝርዝር ሲተነተን በእዳ ተይዞ በባዶ ወደ ሃገሩ ተሸኘ የሚለውን ቃላት ብንመነዝረው የሚያወጣ ትርፍ እና ኪሳራ ያለው ሲሆን በአሁን ሰአት ላይ ግን ዋነኛ ትግሉ በሃገሪቱ ላይ በኢንቨስተርነት ስም የተመዘገበው ይሄው ባለ እዳ በሃገሪቱም ውስጥ ገብቶ ባንኮችን ለማጭበርበር የሚያመቸውን ስትራቴጂ እየነደፈ እንጂ በማናቸውም ሁኔታዎች ዘለቀ ገሰሰ ዋይድ ሄርን በባለቤትነት አልመራም። በሼር ሆልደር የአባልነት ስምምነት ግን የድርጅቱ አመራር አካል ወይንም ማናጀር በመሆን አገልግሎአል ይህንን በምንም መልኩ የማይታበይ እውነተኛ ቃል ነው ።

ለዚያም በባንካራብሲ bankruptcy ሰበብ የኢሊኖይስ የታክስ ኢንቬዥን (ታክስ ማጭበርበር )መዝገብ ላይ እንዲሰፍር የተደረገበት እና ከፍሎ ያልጨረሰውን እዳ እና ከስሬአለሁ ድርጅቱንም ዘግቻለሁ ብሎ ያለበትንም በመላው አሜሪካ ብቻ የሚደመጠውን የችካጎ ፐብሊክ ሬዲዮ በወቅቱ በኪሳራ የዘጉ ድርጅቶችን የ3 ደቂቃ የአየር ሰአት ሰጥቶ ጠቅለል አድርጎ በአወራበት ሰአት ስለ ዋይልድ ሄር የተገለጸውን ሃሳብ ብቻ መጠቆም ይበጃል።

ሆኖም ግን ዛሬም ቢሆን ዋይልድ ሄርን አስተዳድረዋለሁ የባለቤትነቱም ዘርፍ የኔ ነው ብሎ የሚለው አቶ ዘለቀ ፣ በቀድሞዋ የቅምጥ ሚስቱ እዳ መብዛት እና ይህችው ሴትዮ ገንዘቤን እፈልጋለሁ ክፈለኝ በማለት ወጥራ በመያዟ ምክንያት እንዲሸጥ ከተደረገ በሁዋላ እና በአሁን ሰአት ምግብ ቤት የሆነ ሲሆን ፣የሼር ሆልደሮቹ የሚገባቸውን ገንዘብ ወስደው እስከ ወዲያኝው የሄደበትን መንገድ ላይረግጡ ተሰነባብተው ዛሬ ስማቸውንም በክፉም ሆነ በደግ ማንሳት እስኪቀፈው ድረስ እና እራሱ የሰራው በደል እና ክፉ ሴራ ለእራሱ እስኪከረፋው ድረስ ሆኖ ሳለ በሌላው ወገን ደግሞ እነርሱ ስሙንም እንደገና በማደስ ዛሬ ከቀድሞው በተሻለ ሁኔታ ህይወቱን ዘርተውበት ዋይልድ ሄር ችካጎ ከሚገባው በላይ ያለመለመ ትልቅ ባር መከፈቱን ማብሰራችን የማይቀር ነው ። ለዚህም ደግሞ በባለቤትነት የሚመሩትን ሰዎች ሙሉ በሙሉ ከመጥቀስ ይልቅ በቀድሞው የዋይልድሄር አባሎች እና የዳሎል ባንድ ቀዳሚ ሰራዊት የሚባሉትን አቶ አስራትን እና የቴዲ አፍሮ ባንድ ላይ በከበሮ መችነት የሚያገለግለውን ሩፋኤል ወልደማርያምን ብቻ መጥቀሱ ምስክርነትን ሊሰጥ ይችላል።

በሌላም መስመር ወድ ዳሎል ባንድ መለስ ብለን የኋላ ትዝታ እንዲህ በቀላሉ እንጫር ካልን ፣ዳሎል ባንድ እንዲፈርስም ዋነኛ ምክንያት የሆነው እራሱ አቶ ዘለቀ መሆኑን የሚረሳ አይደለም ።መቸም ሙት አይወቀስም ወይም አይከሰስም አለበለዚያም ለምስክርነት አይጠራም እንጂ ሟች ደረጀ መኮንን አቶ ዘለቀን ካለው አንድ አጭር አረፍተ ነገር ለትውስታው ያህል እንዲታወሰው ማድረጋችን ተገቢ ነው “ዘለቀ ይህንን ትልቅ ህብረተሰብ እና ይህንን ትልቅ ባንድ ምስቅልቅሉን የምታወጣው እና የምትበጠብጠን አንተ ነህ ፤አንተ ቤዝ ጊታር ተጨዋች እንጂ ዘፋኝ አይደለህም ! ዘፋኝ ነኝ እዘፍናለሁ ካልክ እኔ ባንተ ድምጽ ሙዚቃን ሰርቼ አላበላሽም እና ካንተ ጋር አልሰራም ! የሙዚቃም ችሎታውም የለህም” የምትለዋን አጭር መስመር ቃል በዚያች ትንሽዬ አዳራሽ ውስጥ በመናገሩ ጥርስ ተነከሰበት ከዚያም ዳሎል ባንድን በዓንድ እግሮ ቆሞ እንዲፈርስ ተደረገ እና ተለያይተው ጊዜ ባንድ እንዲፈጠር ተደረገ ።

ስለ ዳሎል ባንድ ከ ዚጊ ማርሌ እና ሜሎዲ ሜከርስ ጋር የነበራቸውን ጉዞ ለማስታወስ ያህል ከአስር አመታት በላይ ሳይሆ የተጓዙት ከ1986 እ.ኤ.አ እስከ 1990 ሲሆን ሁለት አልበም አሳትመዋል እነሱም conscious party 1988 One bright day..1989 Both won Grammies And sold over a million copies of each ከዚያም 3ኛውን ሙዚቃ በ1996 የተሰራው ሲሆን የግራሚ አዋርድ አሸናፊ የሆኑበት እንደሆነ ይታወቃል በዚህም የዳሎል ሙሉ ባንዱ እና የዚጊ ማርሌ ባንዶች በጋራ በሚሰሩት ስራ የዚህ ሽልማት ባለቤቶች ሆነዋል ። ከዚያም በመቀጠል እስከ 2000 እ.ኤ.አ ሩፋኤል ወልደማርያም (የአሁኑ የቴዲ አፍሮ ከበሮ ተጨዋች) ከዚጊ ማርሌይ ጋር አውሮጳ እና አሜሪካ ቱር ያደረገ ሲሆን ሌሎቹ በተለያዩ አጋጣሚዎች ተገለው ነበር ከዚያም ቀጥሎ grateful dead.. የተሰኘ ግሩፕ መቋቋሙ የሚታወስ ነው ።

ወድ ኢትዮጵያ ኮሙኒቲ እንምጣ እና የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ የተመሰረተው ከ32 አመታት በፊት ሲሆን ምክንያቱም አቶ እስክንድር ወይሳ የተባለ ሰው በድንገተኛ ሞት በመነጠቃቸው ምክንያት ኮሙኒቲውን ለመመስረት በቺካጎ እና አካባቢው የነበሩ ጥቂት ኢትዮጵያኖች እና ኢትዮጵያን ወዳጆች ተሰባስበው መክረው ያደረጉት ሲሆን በዚህ ተሳትፎ ላይ ግን ዶ/ር እርቁ በዶክትሬት ዲግሪያቸው ላይ ዴዘርቴሽን (የመመረቂያ ስራቸውን) በመስራት ላይ ሳሉ እያለ መሆኑ ያለኝ መረጃ ያመለክታል።

እርሳቸውም በሚሽጋን ስቴት ዩኒቨርሲቲ የነበሩ ሲሆን በመስራችነት ላይ የተመዘገቡ አይደሉም በዚህም መሰረትም አቶ ዘለቀም በዚሁ መስራችነት ላይ አልነበረም ፣ዶ/ር አብርሃም ደመወዝም የተቀላቀሉት ከተመሰረተ ረዘም ካለ አመታት በሁዋላ እንደሆኑ ታሪካዊ ስራዎቹ ያስረዳሉ ። ታዲያ እንዲህ ያሉት ዝባዝንኬዎችን እንዲጠቀሱ እና አቶ ዘለቀ ገሰሰን ሰማይ እንዲደርስ የሚያደርጉት እነዚህ የቃላታዊ እጀባ ስራዎች ያልሰራቸውን ስራዎች ሰርቶል በማለት ተአማኒንነትን በህብረተሰቡ ውስጥ በመፍጠርም ሆነ በባንኮች አካባቢ ትልቅ ትኩረትን በመስጠት በሚገኙት የሃገሪቱ የእድገት መሰረት እና የኢንቨስተሮች ግብዣ ሳጥን ውስጥ በመግባት የገንዘብ ብድር እዳ እንዲያገኝ የሚያስችል ስልት ነው እንጂ ዘለቀ ገሰሰ ሰራሁዋቸው የሚላቸው ትክክለኛ እና አንጡራ የሆኑ ስራዎች አይደሉም።
በእርግጥ ነው በእውነተኝነት እና በተአማኒነት የሰራ ሰው ይመሰገናል ፣ይሞገሳል ፣ይካባል ፤ይደገፋል፤ክብር ያገኛል ። ለዚያም ነው ተበዳዮቹ የዳሎል ባንድ አባላቶች ዛሬም ድጋሚ በከፈቱት በዚህ ትልቅ የሙዚቃ አዳራሽ ውስጥ በችካጎ የሚገኙት ኢትዮጵያኑ እየሄዱ እንኳን እናንተ ሆናችሁልን በሰላም ዳግም ዋልድሄርን መለሳችሁልን የሚሉዋቸው ፣በእርግጥም ወደ ሃገሩ ሲመለስ ችካጎ ተሸነፈች ሳይሆን የተባለው ፣ችካጎ ተነፈሰች ፣እዳ በኪነጥበቡ ቀለለላት መሆኑንስ ትገነዘቡት ይሆን …….ሁላችንም እፎይ ተመስገን ብለን ማለታችንንስ እንዴት ታውቁት ይሆን ….?

የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ በየአመቱ በሚያደርገው የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮራም ላይ በሚደረገው የድጋፍ ጥሪ ላይ አቶ ዘለቀ ገሰሰ ብዙውን ጊዜ ከ10.000 በላይ የአሜሪካ ዶላር እለግሳለሁ እያለ ለዘመናት የኮሙኑቲውን አመራር አካላት እና አባላቶች በማጭበረበር አንድም ቀን ለ32 አመታት ሲጓዝ የነበረውን ኮሙኒቲ ቃሉን ጠብቆ 1000 የአሜሪካን ዶላር ያልሰጠ መሆኑን እና እስከዛሬ ድረስ ቃል የገባውንም የገንዘብ ስሌት ኮሙኒቲው በመዝገቡ ውስጥ አስፍሮት የሚገኝ መሆኑን እና ብዙውን ጊዜ ለእራሱ አቤቱታቸውን ማቅረባቸውንም ጠንቅቆ የሚያወቀው ጉዳይ ነው ታዲያ እንዲህ ሆኖ ዛሬ ለ33 አመታት መሰረቱን ይዞ የሄደውን እና ከተለያዩ አለማት ስደተኞችን ወደ ሶስተኛ ሃገራት እንዲመጡ ከፍተኛ ጥረት በማረግ ከኢሚግሬሽን አካላቶች ጋር በጥምረት በመስራት ታላቅነቱን እና አጋርነቱን አግኝቶ በኢሚግሬሽን ዲፓርትመት አመታዊ በጀት የሚንቀሳቀሰውን ይሄንኑ ኮሙኒቲ ከመስራቾቹ አንዱ ነኝ ብሎ ላለው ጉዳይ ፤ከመስራቾቹም ዋና ዋና የሚባሉት በአሁን ሰአት በቦርድ አባልነት ያሉ ሲሆን ታላቅ የቤቱ ሃውልት እና ምስክሮች ናቸው እና፣ውሸትን ደበቅ እናድርገው ይሉናል ።

በሌላው በኩል ስለ ጀሲ ጃክሰን የፖለቲካ ሂደት እና የፑሽ ኪሚቴ ተብሎ የተወራው የንፋስ መንገድ በጣም አስገራሚ በመሆኑ የአሜሪካን የፖለቲካ መንፈስ ለማይረዱ ሰዎች ወደ ፖለቲካው ለመግባት እንዲህ ተባልኩኝ ብሎ ማውራት በጣም የሚያስቅ በመሆኑ ዝርዝር ሃሳብ መስጠቱ ተገቢ ስላልሆነ በይለፍ ብናልፈው ተገቢ ነው ፤ለምን ቢባል አሜሪካኖች ስለ እራስቸው ፖለቲካ እንኩዋን የውጭ ሰው የራሳቸውንም ጥላ የማያምኑ ዜጎች ናቸውና ነው !።

ማጠቃለያ ፤ ባሳለፍነው 2007 የኢትዮጵያ ሃገራዊ ምርጫ ላይ የቅንጅት አመራሮች እና ጋዜጠኞች በገዢው መንግስት በወያኔ ክስ ተመስርቶባቸው ወደ ማረምያ ቤት ከተወረወሩ በሁዋላ ፣ጋዜጠኞችንም ሆነ የተቃዋሚ ፓርቲውን በነበረው ሁኔታ ከቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ጋር የሰላማዊ ድርድር በማለት የሃገር ሽማግሌዎች በመሆን ሽምግልናውን የጀመሩትን ሰዎች ዕነማን እንደሆኑ መጥቀስ የሚያሻ አይመስለኝም ሆኖም ከተፈለገ አንድ ሶስቱን እና ዋነኞቹን መጥቀሱ ተገቢ ነው ሻለቃ አትሌት ሃይሌ ገብረ ስላሴ ፣ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅ ፣አቶ ውብሸት ወርቃለማሁ ዋናዎቹ በመሆን አጀንዳውን ይዘውት ይነቀሳቀሱ የነበሩ ሲሆን ከሙስሊሙ ማህበረሰብ እና ክክርስትናውም ማህበረሰብ የተውጣጡ የእምነቱ አመራር አካላቶችም በጋራ በመሆን መስራታቸው የሚታወስ ነው ታዲያ አቶ ዘለቀ ገሰሰ በየትኛው የሽምግልና መስመር ላይ ነው የሃገር ሽማግሌ በመሆን አቶ መለስ ዜናዊን ለማነጋገር የበቁት ? እስኪ የአዲስ አድማስ ጋዘጣ የቀድሞ 2007/2008 እነደ ኤሮጳውያን አቆጣጠር ያላችሁን የጋዜጣ ማህደራችሁን ፈተሽ አድርጋችሁ በዳኛ አድል መሃመድ የተፈረመውን ደብዳቤ የያዘውን ሪፖርታችሁን አይታችሁ ለማንበብ ሞክሩት እና የሃገር ሽማግሌዎች እነማን እንደ ነበሩ መስክሩ ። የኢትዮጵያ ባንክች መቼም እንዲህ አይነቱን ታሪክ እያያችሁ የእዳ መዝገባችሁን ከፍታችሁ እንኩዋን ደህና መጣችሁ እንደማትሉ አምናለሁ ስለሆነም እውነትኛ ባለሃብት የሚሰራውን ያውቃል እና በእውነት መንገድ እንጓዝ
“ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር” እግዚአብሄር ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
የእውነት መንገድ ብትቀጥንም አትበጠስም
የውሸት ጋሪዎች ግንበእውነተኛው መንገድ በቀን እየተደናበሩ በጨለማ በጭንብል እንደተገፉ ይኖራሉ !
አበቃሁ ቸር እንሰንብት

ወጣቷን በመግደል የተጠረጠረው የፌዴራል ፖሊስ አባል በራሱ ላይ የግድያ ሙከራ አደረገ

$
0
0

የወጣት ሰሎሜ የቀብር ሥነ ሥርዓት ማክሰኞ መስከረም 4 ቀን 2008 ዓ.ም. በለቡ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል፡፡

አንድ የፌዴራል ፖሊስ አባል ለቡ አካባቢ በሚገኝ መዝናኛ ቤት ውስጥ ሰኞ ምሽት አንዲት ወጣት መግደሉ ተሰማ፡፡ ግለሰቡ ራሱን ለማጥፋት ቢሞክርም ተርፎ በሕክምና ላይ ይገኛል፡፡
selome
ሰሎሜ ጉልላት የተባለችው የ20 ዓመት ወጣት ከጓደኛዋ ጋር በመሆን በለቡ ኮንዶሚኒየም ቤቶች አካባቢ በሚገኝ የጓደኛቸው መዝናኛ ውስጥ በመዝናናት ላይ እያሉ ነው ከተጠርጣሪው ገዳይ ጋር የተገናኙት፡፡

ለጊዜው ስሟን መናገር ካልፈለገችው ጓደኛዋ መረዳት እንደተቻለው፣ የፖሊስ የደንብ ልብስ የለበሰው ግለሰብ ከዚህ ቀደም ሰሎሜን አስቸግሮ ከሚያውቅ ግለሰብ ጋር በሚዝናኑበት ባር ውስጥ እንደነበር ትናገራለች፡፡ ሁለቱ ሴት ጓደኛሞች መዝናኛ ባሩ ውስጥ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ከመውጣታቸው በፊት፣ ወደ መፀዳጃ ቤት ለመግባት ተስማምተው መሄዳቸውን ታስታውሳለች፡፡ ክፍሉ ራሱን የቻለ መዝጊያ ኖሮት መፀዳጃ ክፍሎቹም ራሳቸውን የቻሉ መሆናቸውን የገለጸችው የዓይን እማኟ፣ አንዱን ክፍል በሚከፍቱበት ወቅት ዩኒፎርም የለበሰው ፖሊስ ውስጥ ሆኖ ስላዩት ይቅርታ መጠየቃቸውን ትገልጻለች፡፡

ይቅርታቸውን ተቀብሎ እንደወጣ እነሱ ወደ መፀዳጃ ክፍሎቹ ገብተው ከደቂቃ በኋላ ሲወጡ የዋና ክፍሉን በር ቆልፎ ፖሊሱ መፀዳጃ ክፍል ውስጥ እንደጠበቃቸው አስረድታለች፡፡ ወደ ሰሎሜ ተጠግቶ ‹‹አንቺ ሰው የማታናግሪው ለምንድነው?›› ብሎ በጥፊ እንደመታትና እንደወደቀች የገለጸችው የሟች ጓደኛ፣ እሷ በሁኔታው ተደናግጣ ወደ መፀዳጃ ክፍሉ ገብታ መቆለፏን ትናገራለች፡፡ በክፍሉ ውስጥ እንዳለች የተኩስ ድምፅ መሰማቱን፣ የማቃሰት ድምፅ ስትሰማ መውጣቷን ገልጻለች፡፡

ጓደኛዋ ሰሎሜም ሆነች ፖሊሱ ወድቀው እንዳየቻቸው ሰው እንዲደርስላት ብትጮህም፣ ለደቂቃዎች ያህል ማንም እንዳልደረሰ ትናገራለች፡፡

በኋላ ከደረሰችላት አንዲት እንስት ጋር በመሆን እስትንፋሷ የነበረውን ጓደኛዋን ለመርዳት እየሞከረች ሳለ፣ ፖሊሶች እንደደረሱና በሥፍራው ወደሚገኝ ጤና ጣቢያ በፒክ አፕ መኪና ይዘዋት መሄዳቸውን፣ ነገር ግን የጓደኛዋ ሕይወት ማለፉን ገልጻለች፡፡

ተጠርጣሪው የፖሊስ ባልደረባ ጭንቅላቱን በጥይት መትቶ ራሱን ለማጥፋት ቢሞክርም ሕይወቱ ባለማለፉ የሕክምና ዕርዳታ እየተደረገለት ነው፡፡

ጉዳዩን በተመለከተ ከፖሊስ መረጃ ለማግኘት የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡ ይሁን እንጂ ተጠርጣሪው ገና በሕክምና ላይ በመሆኑ ፖሊስ ቃሉን እንዳልተቀበለ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

የወጣት ሰሎሜ የቀብር ሥነ ሥርዓት ማክሰኞ መስከረም 4 ቀን 2008 ዓ.ም. በለቡ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል፡፡

Source:: Ethiopian Reporter

በዕውቀቱ ስዩም በፍቅር ስም በፖሊስ ስለተገደለችው ወጣት ጻፈ

$
0
0

በፍቅር ሰበብ; ሴት ስለሚገድሉ ወንዶች የሚወጡ ዜናዎችን እንሰማለን፡፡ በወጣትነታቸው የተቀጠፉ ጽጌሬዳዎች ያሳዝናሉ፡፡

ነፍስ ይማር!!

በፍቅር ሰበብ መግደል በተለይ የወንዶች ችግር ይመስለኛል ፡፡ ሴቶች በወደዱት ሰው መገፋትን በእንባቸው ያጥቡታል፡፡ ለወንድ ግን ደም ካልፈሰሰ ስርየት የለም፡፡

Beweketu Seyoun joke about African leaders summit [Very Funny]ለብዙ ወንዶች ከሴት ጋር የሚደረግ ግኑኝነት የፍቅር ጉዳይ ብቻ ኣይደለም፤ የክብር ጉዳይ ጭምር ነው፡፡ ኣንድ ሴት ፈልገው እምቢ ስትላቸው ሰማይ እንደ ብረት ቁና የሚደፋባቸው ወንዶች ጥቂት ኣይደሉም፡፡ ኣልፈልግህም መባል ተንቄ ነው የሚል ስሜት ያሳድራል፡፡ ሰው መገፋቱን ለብቻው ይዞ እንዳያስታምም ማህበረሰብ ኣስተያየት ከባድ ቀንበር ሆኖ ይወድቅበታል፡፡ ” ጠይቋት ጥምብ ርኩሱን ኣውጥታ ”ኣባረረችው የሚል ሽሙጥ ኣርፈህ እንድተኛ ኣያደርግም፡፡ ኣብዛኛው ያለም ህብረተሰብ ኣሸናፊውን የሚቀድስ ተሸናፊውን የሚያራክስ ነው፡፡ እኛም“ የወደቀ ዛፍ ምሳር ይበዛበታል” ብለን ዘግተነዋል ፡፡ ኣንድ ሰው እምቢ ያለችውን ሴት ሲቀጥፍ ብቻውን ኣይደለም፡፡ ሽንፈትን የሚያጋንን ማህበረሰብም ኣባላትም የሆንነው እኛም በስውር ተባብረነዋል፡፡

ኣፍቅራችሁ የተገፋችሁ ወንዶች መገፋታችሁን በጸጋ የምትቀበሉበት ጽናቱን ይስጣችሁ፡፡“ንቃኝ ነው፡፡” ከማለት“ እኔ ምርጫዋ ስላልሆንኩ ነው፡፡ እኔን የምትፈልገኝ ሴት ደግሞ የሆነ ቦታ ኣለች ፤የሆነ ጊዜ ላይ ትመጣለች” ብሎ ማሰብን ተለማመዱ፡፡ በርግጥ ሰዎች በተቆጡበት ወቅት በቀልን እንጅ ጠቃሚ ምክር የሚያስታውስ ልቦና እንደሌላቸው ይገባኛል፤ እንዲያው ቢቸግረኝ ነው፡፡

selome

የዛሬ ኣበባዎች የነገ ሰለባዎች ሴቶች ሆይ ! ልባችሁ ያልፈቀደውን ሰው በይሉኝታ ወይም ለእናት ኣገራችሁ ስትሉ የማቀፍ ግዴታ የለባችሁም፡፡ ለእናት ኣገራችሁ ስል ኣንድ የሰነበተ ወግ ትዝ ኣለኝ፡፡ በመንጌ ጊዜ ኣንዲት ቆንጆ ሴተኛ ኣዳሪ ነበረች፡፡ የኣፍሪካ ኅብረት ስብሰባ በተደረገ ጊዜ ካፍሪካ ኣምባገነኖች ኣንዱ ከጀላት፡፡ ይህን ያወቁ የመንጌ ቦዲጋርዶች መኖርያዋ ድረስ መጥተው “የሴራሊዮን ፕሬዚዳንት ስለወደዱሽ ተኝላቸው ” ብለው ኣባበሏት፡፡ እሷም እሺ ብላ የፕሬዚዳንቱን ወቀጣ ጥርሷን ነክሳ ስትቀበል ኣደረችና ማለዳ እያነከሰች ወደ ቤቷ ተመለሰች፡፡ በማግስቱ ምሽት እንደገና ልኡካኑ መጥተው ሊወስዷት ሲያግባቧት“ ኧረ ምን በወጣኝ !! ትናንትም ለእናት ኣገሬ ስል ነው የተረዳሁ ”በማለት መለሰች፡፡(” የተረዳሁ“ የሚለው ቃል የዋናው ቃል ምትክ ሆኖ ገብቷል፡፡ )

እና ቆነጃጅት ለእናት ኣገራችሁ ሲባልም ቢሆን የማትፈልጉት ወንድን እሺ የማለት ግዴታ የለባችሁም፡፡ ግን በተቻላችሁ መጠን ኣለመፈለጋችሁን በተለሳለሰና በተሽሞነሞነ ቃል ለመግለጽ ሞክሩ፡፡“ እኔ ደግሞ የሚገጥመኝ ሙጀሊያም ሙጀሊያሙ ነው ”ኣይነት መልክት ያለው ፊት ላለማሳየት ተጠንቀቁ፡፡ በለሰለሰ ቃል የተገለጸ እምቢታ ከእሽታ ልተናነሰ በጎ ስሜት ይፈጥራል፡፡

የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለን ሴት ተማሪዎችን ኣስቁመን ባንድ እጃችን በላብ ያደፈ ደብተራችንን፤ በሌላ እጃችን የተፈቃሪዋን እጅ ጨብጠን “ ኣበባው ግሮሰሪ ገብተን ብንጫወት ምን ይመስልሻል?” ስንል የሚመለስልን መልስ ኣይረሳኝም፡፡“ ይቅርታ ! እኔ ኣላማ ኣለኝ፤ በእህትና በወንድምነት ከሆነ ግን ችግር የለውም” ይሉን ነበር፡፡ በጊዜው ኣላማ የሚለው ቃል ትልቅ ክብደት ያለው ቃል ነበር፡፡ ህብረተሰብን ከመሃይምናትና ከኋላቀርነት የማውጣት ኣላማ፤የኣገር ኣንድነት ኣላማ ምናምን የሚባሉ ግዙፍ ቃሎች ጋር የተያያዘ ነበር፡፡እና ከልጅቷ ኣላማ ጋር ሲነጻጸር የኛ ሽፍደት ኢምንት ሆኖ ይታየናል፡፡ በዚያ ላይ፤ ያችን በመሰለች ልጅ በወንድምነት መታጨታችን ያጽናናል፡፡ እናም በመጣንበት እግራችን በሰላም እንመለሳለን፡፡

ከላይ ያስቀመጥኳቸው የግጭት መፍቻ ሀሳቦች ከችግሩ ትልቅነት ኣንጻር ኣቅመቢስ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እንግዲህ በተረፈ “ ኣይድረስ” ማለት ነው፡፡

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live