Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የኦጋዴን ነፃነት ግንባር 2 ከፍተኛ አመራሮች በአልሸባብ አንገታቸው ተቀልቶ ተገደሉ * ግንባሩ የኢትዮጵያ መንግስት እጅ አለበት ሲል ከሰሰ

$
0
0

Zehabesha News

(ዘ-ሐበሻ) የኦጋዴን ነፃነት ግንባር ሁለት ከፍተኛ አመራሮቼ ከሶማሊያ ባይዶዋ ወደ ኦጋዴን ሲጓዙ በአልሸባብ ታጣቂዎች ታፍነው ተወስደው ተገደሉብኝ ሲል ከሰሰ። ለዚህም ተጠያቂው በስልጣን ላይ ያለው የኢትዮጵያ መንግስት ነው ብሏል::

የኦጋዴን ነፃነት ግንባር ከቅርብ ወራት ወዲህ በጠቅላላው ከአስር የማያንሱ አባሎቼ ሶማሊያ ውስጥ በአልሸባብ ታጣቂ ቡድን ታፍነው ከተወሰዱ በኋላ አንገታቸው ታርዶ ተገድለውብኛል ብሏል ።

እንደ ግንባሩ ክስ ከሆእ የኢትዮዽያ መንግስት የደህንነት ሰራተኞች በስውር ከአልሸባብ ንዑስ ቡድን ጋር በመገናኘት ግድያው እንዲፈፀም አሲረዋል።

በስልጣን ላይ ያለው የኢትዮጵያ አገዛዝ እስካሁን ምንም ዓይነት ምላሽ ባይሰጥም ከዚህ ቀደም መንግስት የኦጋዴን ነፃነት ግንባር ከአልሸባብ ጋር ግንኙነት ያለው አሸባሪ ድርጅት ነው ሲል መክሰሱ ይታወሳል:: አማጺው ቡድንም ሆነ መንግስት እርስ በራሳቸው ከአልሸባብ ጋር ግንኙነት አላቸው እየተባባሉ መካሰሳቸው ለብዙዎች ግርምታን ፈጥሯል;;


Sport: ከወላጅ አባቱ ጋር በዘረኛዋ ጋዜጠኛ የተደበደበው ታዳጊ ስደተኛ ከክርስቲያኖ ሮናልዶ እቅፍ ገባ

$
0
0

Ronaldo
ከታምሩ ገዳ
በቅርቡ የሶሪያውን የእርስ በርሰ ጦርነት ከሸሹት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰደተኞች መካከል እንድ ሰደተኛ አባት በምስራቅ አውሮፓ(ሃንጋሪ ውስጥ) ከፖሊስ ለማምለጥ ሲጥሩ በአንዲት ጋጠወጥ ሃንጋሪያዊት ጋዜጠኛ(ፔትራ ላሳዛሎ) ከእነ ወንድ ልጃቸው ተጠልፈው መወደቃቸውን ተከትሎ ጋዜጠኛዋ ወዲያውኑ ከሰራዋ ሰትባረር አሳዛኙም በደል የደረሰባቸው ሶሪያዊው አባት(ኦሳማ አብዱል ሞሸን)እና የ 7 አመቱ ለጃቸው ዛይድ የአለም መገናኛ ብዙሃናት ትኩረትን ስበው ሰንበተዋል።

ታዲያ ሰሞኑን ከ ወደ ስፔን የተሰማው መልካም ዜና እንደሚያበሰረው ከሆነ የአባት እና የልጅዩው ሰደተኞች ገተመኝ ከልባቸው የዘለቀው የሰፔን እግር ኳስ አካዳሚባለፈው ሳምንት የ ስደተኝነት ፍቃድ እንዲያገኙ አመቻችቶላቸዋል። እኛ በዚያች ምግባረ ብልሹ ጋዜጠኛ እግር ተጠልፈው ከእነ ልጃቸው መሬት ላይ የወደቁት አባት(ኦስማን) በትውልድ አገራቸው ሶሪያ የ ቀደሞ እግር ኳስ አሰልጣኝ በመሆናቸው የሰፔንም መንግስት መተነኛ ልምምድ አደረገው ስፔን ወስጥ ወደቀደሞ ሰራቸው (አሰለጣኝነት )እንዲመለሱ እና አዲስ ህይወታቸውንም እንዲገነቡ ተሰፋ ሰጥቷቸዋል ።አባት እና ልጅም በሳምንቱ ማብቂያ (ቅዳሜ)እለት ወደ ስፔኑ በርናቡ ተጉዘው እወቁ የሪያል ማድሪድ ክለብ ከግራንዳ ከለብ ጋር ባደረጉት ውድድር እና 1ለ0 ባሸነፉበት ግጥሚያ ላይ በከብር እንግድነት ተገኝቷዋል ። ጨቅላው ዛይድም ከታዋቂው የአለማችን ፣የማድሪድ አጥቂ እና ፖርቱጋል ቡድን ተጨዋች ከክርስቲያን ሮናልዶ ጋር እጅ ለእጅ በመያያዝ ቡድኑ ወ ደ ሜዳ ሲገባ ሮናልዶን አጅቦታል። በነገራችን ላይ የ ማድሪድ ክለብ በዚህ አመት ወስጥ ከሶሪያ ለተፈናቀሉ እና ስፔን ለተጠለሉ የ አንድ ሚሊዮን ዮሮ እርዳታ ለግሷል።

ከልጅነቱ አንስቶ ሲመኘው የነበረው የሪያል ማድሪድ ከለብ እና ከተአምረኛው ሮናልዶ ጋር በአካል ለመገናኘት አድሉን ያገኘው ዛይድ በሺዎች የሚቆጠሩ የማድሪድ ክለብ ደጋፊዎች የቡድኑን መለያ ሹራብ ላጠለቀው ለታዳጊው ለዛይድ ያላቸውን ልዩ ፍቅር አሳይተዋል። እርሱም በመላሹ “ከልጅነቴ አንስቶ ልጎበኝው ሰመኘድው የነበርው ሪያል ማድሪድን ለመጎበኘት ታደልኩ”ብሏል።ነገር ሁሉ ለበጎ ነው ማለት ይሄን ጊዜ ነው።

የደም ማነስ (Anemia)

Next: Hiber Radio: አይሲስ ኢትዮጵያዊኖችን ለጦርነት እየመለመለ መሆኑ ተጋለጠ፣ አንዳርጋቸው እንዲፈቱ የደገፉት የእንግሊዝ ፖለቲከኛ ከፍተኛውን የፓርቲ ስልታን አገኙ፣ የአቶ አንዳርጋቸው ባለቤት ደስታቸውን ገልጸዋል፣ኢትዮጵያ በሶማሊያ የሞቱ ወታደሮቿን ቁጥር ለመግለጽ ፈቃደኛ አለመሆኗ ተገለጸ፣ በሶማሊያ የህብረቱ ጦር ከአንድ ሺህ በላይ ወታደሮችን ማጣቱ ተገለጸ፣ በማዕከላዊ በደረሰባቸው ድብደባ አካል ጉዳተኛ የሆኑት የመኢአድ የውጭ ግንኙነት ሀላፊ አቤቱታቸው ሳይሰማ ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ ተፈቀደባቸው ፣ሰማያዊ ፓርቲ አዲሱን ካቢኔ አቋቋመ እና ሌሎችም
$
0
0

የደም ማነስ በደምዎ ውስጥ በቂ የሆነ ጤናማ ቀይ የደም ሴሎች ወይም ሄምግሎቢን ሲያንስ የሚከሰት በሽታ ነው፡፡ ሄሞግሎቢን ዋናው የደም ሴሎቻችን ክፍል ሲሆን ከኦክስጅን ጋር ይጣመራል በጣም ጥቂት ወይም ጤናማ ያልሆኑ ቀይ የደም ሴሎችን ካሉን ወይም ጤናማ ያልሆነ ጥቂት ሄሞግሎቢን ካለን በሰውነታችን ውስጥ ያሉት ሴሎች በቂ ኦክስጅን አይደርሳቸውም፡፡ የደም ማነስ ምልክቶች ከሆኑት አንድ የሆነው የድካም ስሜት የሚከሰተው የሰውነት አካሎቻችን በትክክል ለመስራት የሚፈልጉትን ያክል ኦክስጅን ስለማያገኙ ነው፡፡

animia
ሴቶች ህፃናት እና ከባድ በሽታ ያለባቸው ሰዎች ለደም ማነስ የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ነው፡፡

ልናስታውሳቸው የሚገቡ ጠቃሚ ነገሮች እነሆ፦
✔አንዳንድ የደም ማነስ አይነቶች በዘር የሚተላለፉና በወሊድ ጊዜ ህፃናትን የሚያጠቁ ናቸው፡፡
✔ለአቅመ ሂዋን የደረሱ ሴቶች በብረት እጥረት ለሚከሰተው የደም ማነስ በተለየ ሁኔታ የተጋለጡ ናቸው ምክንያቱም በወር አበባ ጊዜ የደም መፍሰስ እና በእርግዝና ወቅት የደም ፍላጎት ስለሚጨምር ነው፡፡
✔በእድሜ የገፉ ሰዎች በደም ማነስ የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ነው ምክንያቱም በምግብ እጥረት እና የተለያዩ የህክምና ችግሮች ስለሚኖሩባቸው ነው፡፡
የተለያዩ የደም ማነስ አይነቶች አሉ ሁሉም የተላያዩ መነሻ እና የተለያየ ህክምና አላቸው፡፡ በብረት እጥረት የሚከሰተው የደም ማነስ በጣም የተለመደ በሽታ ነው አመጋገባችንን በመቀየር እና የብረት ንጥረ ነገር በመዉሰድ በቀላሉ መታከም እንችላለን፡፡ አንዳንድ የደም ማነስ አይነቶች ለማሳሌ በእርግዝና ወቅት የሚከሰተው ጤናማ ነው አንዳንዶቹ ደግሞ እስከ እድሜ ልክ የሚዘልቁ ናቸው፡፡

የደም ማነስ መነሻ ምክንያቶች
ከ400 የሚበልጡ የደም ማነስ አይነቶች አሉ እነሱም በሶስት መደቦች ይከፈላሉ፦
1. በደም መፈሰስ የሚከሰት
2. ቀይ የደም ሴሎች ምርት መቀነስ ወይም የማምረት ችግር
3. በቀይ የደም ሴሎች ውድመት/ጥፋት የሚከሰት የደም ማነስ አይነቶች ናቸው፡፡

1. በደም መፍሰስ የሚከሰት የደም ማነስ
ደም በሚፈሰን ጊዜ ብዙ ቀይ የደም ሴሎችን እናጣለን ይህም የሚከሰተው በትንሹ ለረጂም ሰዓት ደም ስለሚፈሰን ሲሆን ይህን ነገር ብዙ አናስተዉለውም፡፡ እንደዚህ አይነቱ ከባድ የደም መፍሰስ በሚከተሉት መንገዶች ይከሰታል
✔ ከጨጓራና አንጀት ጋር የተያያዘ በሽታዎች (ክንታሮት፣ቁስለት፣የጨጓራ ህመም እና ካንሰር)
✔ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶች(አስፕሪን ወይም አይቡፕሮፊን)
✔ የወር አበባ እና በወሊድ ጊዜ(በተለይ በወር አበባ ጊዜ የደም ፍሰት ከመጠን በላይ ከሆነ እና በተደጋጋሚ እርግዝና ከተከሰተ)

2. ቀይ የደም ሴሎች ምርት መቀነስ ወይም የማምረት ችግር
በዚህ አይነት የደም ማነስ ጊዜ ሰዉነታችን በጣም ጥቂት የደም ሴሎች ማምረት ወይም የደም ሴሎቻችን በትክክል ተግባራቸውን መወጣት ሲያቅታቸው ሲሆን በሁለቱም አጋጣሚዎች የደም ማነስ ይከሰታል፡፡ ቀይ የደም ሴሎች ችግር ይኖርባቸዋል ወይም በቁጥር ይቀንሳሉ የዚህ ምክንያት ጤናማ ያልሆኑ የደም ሴሎች ሲኖሩ ወይም ተግባራቸውን በብቃት ለመወጣት የሚያገለግሉ ሜኔራሎችና ቫይታሚኖች እጥረት ሲኖር ነው፡፡ ለዚህ አይነቱ የደም ማነስ መነሻ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፦
✔ ሲክል ሴል የደም ማነስ(አኒሚያ)
✔ በብረት እጥረት የሚመጣ የደም ማነስ
✔ በቫይታሚን እጥረት
✔ በመቅኒ እና አባት/መነሻ ሴል ችግር
✔ ሌላ የጤና ችግሮች ናቸው
በሲክል ሴል የሚከሰት የደም ማነስ በዘር የሚተላለፍ ሲሆን ቀይ የደም ሴሎች የጨረቃ ቅርጽ እንዲኖራቸው ያደርጋል ስለዚህ በቂ ኦክስጂን ወደተለያዩ አካሎች ማድረስ ያቅተዋል፡፡ የጨረቃ ቅርጽ ያላቸው የደም ሴሎች በጥቃቅን የደም ቧንቧዎች ውስጥ ይቀረቀራሉ ይህም ህመም ያስከትላል፡፡
በብረት እጥረት ምክንያት የሚከሰተው የደም ማነስ ብረት በተባለው ሚኒራል እጥረት ሲኖር ነው፡፡ በአጥንታችን ውስጥ ያለው መቅኒ ኦክስጂን ወደተለያዩ የሰውነት ክፍል የሚደርደውን ሄሞግሎቢን ለመስራት ብረት ያስፈልገዋል፡፡ በቂ የሆነ የብረት ሜኔራል ከሌለ በቂ የሆነ ሄሞግሎቢን አይመረትም የዚህ ውጤት በብረት እጥረት የሚከሰት የደም ማነስ ነው፡፡ የዚህ አይነቱ የደም ማነስ መነሻ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው
✔ የብረት እጥረት ያለባቸው ምግቦችን የመመገብ ዘይቤ
✔ እርግዝና እና ማጥባት የእናትን የብረት ክምችት መጠን ይቀንሳል
✔ የወር አበባ
✔ በተደጋጋሚ የደም ልገሳ ማድረግ
✔ ከባድ ስፖርታዊ ልምምዶች
✔ የምግብ መፍጨት ችግሮች
✔ አንዳንድ መድሃኒቶች
በቫይታሚን እጥረት የደም ማነስ የሚከሰተው በቫይታሚን ቢ 12 እና ፎሌት እጥረት ነው፡፡ እነዚህ ሁለት ቫይታሚኖች ቀይ የደም ሴሎችን ለመስራት ያገለግላሉ፡፡ ለዚህ ችግር መነሻ ምክንያቶች
✔ ሜጋሎብላስቲክ አኒሚያ፡ የቫይታሚን ቢ12 እና ፎሌት እጥረት
✔ ፐረንሸስ አኒሚያ፡ የቫይታሚን ቢ12 በጨጓራ የመመጠጥ ችግር ነው
✔ የምግብ እጥረት፡ ትንሽ ስጋ ወይም ሙሉ ለሙሉ ስጋ አለመመገብ
✔ እርግዝና፣ አንዳንድ መድሃኒቶች፣ የአልኮል ሱሶች፣ የአንጀት በሽታዎች
አፕላስቲክ አኒሚያ፡ አባት(መነሻ)ቀይ የደም ሴሎች በቁጥር ሲቀንሱ ነው
✔ ታላሲሚያ የሚከሰተው ቀይ የደም ሴሎች በትክክል መብሰል እና ማደግ ሲያቅታቸው ነው
✔ ሊድ ለተባለው መርዛማ ማዕድን መጋለጥ የአጥንት መቅኒ እንዲጎዳ ያደርገዋል
በተለያዩ ምክንያቶች የሚከሰት የደም ማነስ መነሻው ለቀይ የደም ሴሎች ምርት የሚጠቅሙ ሆርሞኖች እጥረት ሲሆን በዚህ አይነት ምክንያት የሚከሰቱት የሚከተሉት ናቸው::
✔ ከባድ የኩላሊት በሽታ
✔ የታይሮይድ እጥረት
✔ የተለያዩ በሽታዎች(ስኳር፣ ካንሰር፣ ሪህ፣ ኢንፌክሽን)
✔ የእድሜ መግፋት

3. በቀይ የደም ሴሎች ውድመት/ጥፋት የሚከሰት ደም ማነስ
ቀይ የደም ሴሎች በሚሰባበሩበት ጊዜ እና የደም ዝዉዉር ውጥረት መቋቋም ሲያቅታቸው ያለ እድሜያቸው ይፈነዳሉ ከዚያም ሄሞላይቲክ አኒሚያ ይከሰታል፡፡ ይህ ችግር ስንወለድ ወይም ካደግን በኃላ ሊከሰት ይችላል አንዳንድ ጊዜ መነሻ ምክንያቱ አይታወቅም፡፡

መልካም ጤንነት!!!

Hiber Radio: አይሲስ ኢትዮጵያዊኖችን ለጦርነት እየመለመለ መሆኑ ተጋለጠ፣ አንዳርጋቸው እንዲፈቱ የደገፉት የእንግሊዝ ፖለቲከኛ ከፍተኛውን የፓርቲ ስልታን አገኙ፣ የአቶ አንዳርጋቸው ባለቤት ደስታቸውን ገልጸዋል፣ኢትዮጵያ በሶማሊያ የሞቱ ወታደሮቿን ቁጥር ለመግለጽ ፈቃደኛ አለመሆኗ ተገለጸ፣ በሶማሊያ የህብረቱ ጦር ከአንድ ሺህ በላይ ወታደሮችን ማጣቱ ተገለጸ፣ በማዕከላዊ በደረሰባቸው ድብደባ አካል ጉዳተኛ የሆኑት የመኢአድ የውጭ ግንኙነት ሀላፊ አቤቱታቸው ሳይሰማ ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ ተፈቀደባቸው ፣ሰማያዊ ፓርቲ አዲሱን ካቢኔ አቋቋመ እና ሌሎችም

$
0
0

Habitamu

የህብር ሬዲዮ  መስከረም 9 ቀን 2008 ፕሮግራም

 <… በተቃዋሚ ስም የተቀመጡት አንዳንዶች የአቶ ሞላን ክህደት መደገፋቸው ራሱን የቻለ ክህደት ነው። መንግስትሰጠኝ ያለውን ተልዕኮ የፈጸመ ሰው ተመልሼ ወደ መንግስት ገባሁ ሲል ተቃዋሚ ሆነህ ምን ብለህ ነውየምታመሰግነውክህደት ነው ያልኩት ይሄንን ነውየሕዝቡ መሰረታዊ ጥያቄ የዲሞክራሲ ጥያቄ እስካልተመለሰአንዱ ከዳ ሌላው ለስርዓቱ ጊዜያዊ ድል መስሎ ካልታየ በስተቀር ህዝቡ አንዱንም ቅስቀሳቸውን አልተቀበለውም ደገፉ የተባሉትም   …>   አቶ ይድነቃቸው ከበደ የሰማያዊ ፓርቲ የም/ቤት ሰብሳቢ በግል የአገር ቤቱን የከዱትን አቶ ሞላን  በተመለከተ ለስርዓቱ ቅስቀሳ ሕዝቡ ያለውን ስሜት  ከህብር ሬዲዮ ተጠይቆ ከሰጠው ማብራሪያ (ሙሉውን ያዳምጡ)

<…ምርጫ ቦርድ ለእነ አቶ አበባው የሰጣቸው መኢአድ ጽ/ቤቱን ብቻ ነው አባላቱ ከእኛ ጋር ናቸው። ብዙ ጠንካራ አደራጆች አባላት በየቦታው ታስረውብናል።ትግላችን ይቀጥላል  …ፖለቲካው በቲፎዞ መሆን የለበትም። በአገሪቱ ያለው ኢፍትሐዊ ስርዓት እስኪለወጥ አቅማችንን አስተባብረን መታገል አማራጭ የለውም። የኢትዮጵየያ የተቃውሞ ፖለቲካ ያው እስሩንም መገደሉንም እያስተናገድን የምንሄድበት ነው። የታሰሩትን አለመርሳት ይገባል…>   አቶ ማሙሸት አማረ የመኢአድ ሕጋዊው ፕሬዝዳንት ለህብር  ከሰጡት   ምላሽ የተወሰደ ክፍል ሁለት (ሙሉውን ያዳምጡ)

በእንግሊዝ አቶ አንዳርጋቸው እንዲፈቱ ትልቅ ጥረት ያደረጉት አዛውንቱ ፖለቲከኛ በፖለቲካው አደባባይ አሸናፊ የሆኑበት ሂደትና የወደፊቱ ጉዞዋቸው  (ልዩ ጥንቅር)

በቬጋስ የኢትዮጵያውያን ታክሲ አሽከርካሪዎች የመብት ሙግት የፍርድ ቤት ሂደት  (ቃለ መጠይቅ)

ሌሎችም 

ዜናዎቻችን

የሊቢያው አክራሪ ቡድን አይሲስ ኢትዮጵያዊኖችን ለጦርነት እየመለመለ መሆኑ ተጋለጠ

የሃይማኖት ነጻነታችን ተደፈረ ያሉ ስድስት ኢትዮጵያዊያንክርስቲያኖች ስልጤ ዞን ውስጥ “በአሽባሪነት ክስ‘ ለከባድ እስራትተዳረጉ

የተባበሩት አረብ ኢሜሪት  ለኢድ አልደሃ  በአል ከአንድ ሺህ በላይኢትዮጵያዊያንን ነዳዮችን ስጋ ልታበላ ነው  ተባለ

አቶ አንዳርጋቸው  ጽጌ አንዲፈቱ  ከፈተኛ ጥረት ያደረጉት የእንግሊዙፖለቲከኛ ሰሞኑን  ታላቅ ስልጣን አገኙ

ኢትዮጵያ ሶማሊያ ውስጥ ሰለሞተ ሆነ ሰለቆሰለ የመከላከያ ሃይልአሃዝ  መግለጫ አልሰጥም አለች በሶማሊያ የሚገኘው ህብረቱ ከአንድሺህ በላይ ወታደሮቹን ማጣቱን ወታደራዊ መረጃዎች ገለጹ

ከምርጫ በኋላ ድምጹ የጠፋው ሰማያዊ ፓርቲ አዲሱን  ካቢኔውንአዋቀረ

በማዕከላዊ በደረሰበት ድብደባ የአካል ጉዳተኛ የሆነው የህጋዊውየመኢአድ የውጭ ግንኙነት ሀላፊ አቤቱታውን /ቤት ሳይሰማው ቀረ

የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ዘመነ ምህረት እንደይጠየቅእንደታገደ ነው

 ሌሎችም ዜናዎች አሉ

“በኤርትራ መንግስት ላይ ሙሉ እምነት አለን”–አቶ ነአምን ዘለቀ ከአስመራ መልስ

Previous: Hiber Radio: አይሲስ ኢትዮጵያዊኖችን ለጦርነት እየመለመለ መሆኑ ተጋለጠ፣ አንዳርጋቸው እንዲፈቱ የደገፉት የእንግሊዝ ፖለቲከኛ ከፍተኛውን የፓርቲ ስልታን አገኙ፣ የአቶ አንዳርጋቸው ባለቤት ደስታቸውን ገልጸዋል፣ኢትዮጵያ በሶማሊያ የሞቱ ወታደሮቿን ቁጥር ለመግለጽ ፈቃደኛ አለመሆኗ ተገለጸ፣ በሶማሊያ የህብረቱ ጦር ከአንድ ሺህ በላይ ወታደሮችን ማጣቱ ተገለጸ፣ በማዕከላዊ በደረሰባቸው ድብደባ አካል ጉዳተኛ የሆኑት የመኢአድ የውጭ ግንኙነት ሀላፊ አቤቱታቸው ሳይሰማ ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ ተፈቀደባቸው ፣ሰማያዊ ፓርቲ አዲሱን ካቢኔ አቋቋመ እና ሌሎችም
$
0
0

ኤርትራ ከሄዱ በኋላ በ3ኛ ወራቸውው ወደ አሜሪካ የተመለሱት አቶ ነአምን ዘለቀ ከኢሳት ጋር ቃል ተመላልሰዋል:: በቃለምልልሳቸውም በኤርትራ መንግስት ላይ ሙሉ እምነት አለን አሉ:: ቃለምልልሱን አድምጡት::

Neamen zeleke zehabesha

የመቀሌ አማርኛ በአዲስ አበባ

$
0
0

mekele
ከአቻምየለህ ታምሩ

ከዚህ ጽሁፍ ጋር አያይዤ የለጠፍኳቸውን የባቡር ጣቢያ ስሞች ስመለከት አዲስ አበባ ወደ መቀሌ የሄደች መስሎ ተሰማኝ። መቀሌ ብዙ ድርጅቶች ከትግርኛ ይልቅ በአማርኛ ማስታወቂያ መለጠፍ ይቀናቸዋል። መቀሌ ውስጥ አማርኛ የቢዝነስ ማስታወቂያ መጻፊያ ቋንቋ ነው። መቀሌ በአማርኛ የቢዝነስ ማስታወቂያ እንደመጻፏ መጠን ለቃላትና ለሆሄያት ግድፈት ግን ግድ የላትም። መቀሌን ለአመታት ለሚያቃት ሰው የአማርኛ ሆሄያትን በማሳከር ባለሁለት ዲጂት እድገት እያስመዘገበች ያለች ከተማ ልትመስለው ትችላለች።

ምስጉን ተስፋይ የሚባል ጎበዝ የአዲግራት ልጅ አንድ የግጥም መድበል አሳትሟል። የግጥም መድበሉን ያሳተመው በአማርኛ ነው። የምስጉንን ግጥሞች አንብቦ መረዳት የሚችል ቢኖር እንደኔ አይነት በአማርኛ አፉን የፈታ ሳይሆን የትግራዋይ አማርኛ [Tigrian Amharic ] የሚችል ሰው ብቻ ነው። ምስጉን ተስፋይ መጽሀፉን ሲጽፍ አማርኛውን በማረም ያገዘውን ወንድሙን አመስግኗል። ግን ወንድሙም ልክ እንደ ምስጉን የትግራዋይ አማርኛ ተናጋሪ በመሆኑ የተነሳ የግጥም መድበሉ የአማርኛ እርማት የተደረገለት ሳይሆን የአማርኛ መፋለስ ተደርጎለት ለመታተም የበቃ ነው የሚመስለው። ሁለቱም የትግራዋይ አማርኛ ጽሁፍ «ጸሀፊዎች» በመሆናቸው ለምስጉን ያልታየው የአማርኛ እርማት ችግር ለወንድሙ ሊታየው አይችልም።

መቀሌ ከተማ በየንግድ ተቋሙና በየአደባባዩ ከተለጠፉ የንግድ ማስታወቂያዎች መካከል ባልተሳካ አማርኛ ከተጻፉት ውስጥ የሚከተሉት ይገኙባቸዋል፤«ሞቫይል ቆፎ ንሸጣለን»፤ «ካራ ቡላ ናጫወታለን»፤ «ሞቫይል ካርድ አሎ»፤ «ሞቫይል ቆፎ ንጠግናለን» «ተራንስ ፎርሜሽኑ ይሳካል» «ኤመይል ንከፍታለን»፤ «ፍስ ቡክ ናስጠቕማለን»፤ «ባለማጮሶ ንመስግንናለን»፤«ዃረንቡላ አንጫወታለን»፤«የተዘጋ ዋሃ ንሸጣለን» [የታሸገ ውሀ እንሸጣለን ለማለት ነው] ወዘተ።

መቀሌ በአማርኛ ለሚጻፉ ማስታወቂያዎች ብቻ ሳይሆን በእንግሊዝኛ ቋንቋም ለሚጻፉ ማስታወቂያዎች ግድ የላትም። የቢዝነስ ማስታወቂያዎችን በእንግሊዝኛ ቋንቋ ጽፈው የሚለጥፉት አብዛኛውን ጊዜ የአውሮፓን የእግር ኳስ ጨዋታዎችን የሚያሳዩ የDSTV ቤቶችና ፊልም የሚያከራዩ ሙዚቃ ቤቶች ናቸው። «Prison Break» የተሰኝውን የእንግሊዝኛ ፊልም የሚያከራዩ አራት መደዳውን የተሰደሩ ሙዚቃ ቤቶች ማስታወቂያውን የሚያስቅ እንግሊዝኛና አማርኛ ቀላቅለው ጽፈውት ተመልክቻለሁ። የመጀመሪያው «ድንኳን [በትግርኛ ሱቅ ማለት ነው» ማስታወቂያውን <«prison brike» ዚህ ይገኛሉ> ብሎ ለጥፎታል። ሁለተኛው ቪዲዮ አከራይ ደግሞ <«perison braik» በዝካረ ይገኛሉ> ይላል። ሶስተኛው ቪዲዮ ቤት ሙሉ በሙሉ «የእንግሊዝኛ» ቃላትን ተጠቅሞ «price break four rent» ይላል። አራተኛው ነጋዴ ደግሞ በፋንታው <«prisim brek» ፊልም ናከራያለን> ሲል ለጥፏል።

ሌላ መቀሌ የማውቀው የንግድ ድርጅት በተለምዶ ሀውዜን አደባባይ ከሚባለው የከተማይቱ አነስተኛ አደባባይ በስተቀኝ አቅጣጫ በግምት አንድ መቶ ሜትር ያህል ገባ ብሎ በግራ በኩል «ናቲ ምሿለኪያ ካፌና ሬስቶራንት» ይሰኝ የነበረን ቤት ነው። እኔና ጓደኛዬ «ናቲ ምሿለኪያ ካፌና ሬስቶራንት» በተደጋጋሚ እየተገናኘን የቤቱን «ስፔሻል ምግብ» ተመግበናል። አዲስ አበባ ላይ «ምሿለኪያ» የሚል የባቡር መተላለፊያ ተጽፎ ሳነብ ቀጥታ ወደ ጭንቅላቴ የመጣው መቀሌ ከተማ የማቀው «የናቲ ምሿለኪያ ካፌና ሬስቶራንት» ነበር። ለዚያም ነው የጽሁፌን ርዕስ «የመቀሌ አማርኛ በአዲስ አበባ» ብዬ የሰዬምሁት።

የመቀሌን «ድድ ማስጫዎች» ተዘዋውሮ ለጎበኘ በመቀሌ ከተማ የንግድ ማስታወቂያዎችን ከፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ «ባነር» መለየት ይቸግረዋል። በተለይ ዋናው የህወሀት ጽህፈት ቤት አካባቢ በሚገኙ የንግድ ቤቶች ላይ የሚለጠፉ የንግድ «ማስታወቂያዎችን» ላስተዋለ ንግድ ቤቶቹ እቃና አገልግሎት መሸጣቸውን ትተው ፕሮፓጋንዳ መሸጥ የጀመሩ ነው የሚመስሉት። ሰላሳ ዘጠነኛው የህወሀት ልደት መቀሌ ከተማ ሰማህታት አዳራሽ ሲከበር ህወሀት ጽህፈት ቤት ፊት ለፊት ባለ አንድ ካፌ ደጅ ተቀምጠን እኔና ጓደኛዬ ሻይ ቡና እያልን ባካባቢው የሚካሄደውን እንቅስቃሴ እየታዘብን ነበር። ሻይ ቡና በምንልበት ካፌ በር ላይ «መለስ ጅግና እዩ፤ጀግና አይሞትም» ከሚል መፈክር ስር «Meles is alive» የሚል የእንግሊዝኛ ፍቺ ተሰጥቶት መፈክሩ ተሰቅሎ ነበር። ይህ መፈክር ዋናው ህወሀት ጽህፈት ቤት ውስጥም ተሰቅሎ እንደነበር ለማወቅ ችያለሁ።

በአጠቃላይ መቀሌ የተቀመጠ አንድ ለአቅመ ፖለቲካ የደረሰ ሰው ትናንትና የተለቀቁትን የአዲስ አበባ ባቡር ጣቢያ ስሞች ሆሄያት መጣመምን ሲመለከት አዲስ አይሆንም። ይልቁንም ድርጊቱ አዲስ አባባ ላይ ሊፈጸም የቻለው አንድም የባቡር ጣቢያ ስሞቹ መቀሌ ሄደው የተጻፉ መሆን አለባቸው ብሎ ሊያስብ ይችላል፤ አልያም የመቀሌን ማስታወቂያዎች የሚያትሙ ባነር ጻፎች አዲስ አበባ መጥተው የጣቢያ ስሞችን ለመጻፍ የተደረገውን ውድድር «አሸንፈው» ከመቀሌ ይዘው በመጡት የሆሄ መቅረጫ የአዲስ አበባን የባቡር ጣቢያ ስሞች ወደ ማተሙ ገብተዋል ብሎ ያስባል።

በአዲስ አበባና በመቀሌ በተፈጸሙ የሆሄያት ግድፈቶች መካከል ግን አንድ ልዩነት ይታየኛል። የመቀሌ ማስታወቂያዎች ግድፈት የአማርኛ ሆሄያት ብቻ አይደለም፤ የመቀሌ ማስታወቂያዎች ለእንግሊዝኛ ፊደሎችም ግድ የላቸው። የአዲስ አበባዎቹ ግን የአማርኛ ሆሄያቱ ስህተትም ቢሆኑ የእንግሊዝኛ ስሞች ግን በስህተት የተጻፉትን የተሳከሩ የአማርኛ ሆሄያት ተከትሎ በትክክል የተቀረጹ ናቸው። አዲስ አበባ በተሳከረ አማርኛ ተጽፈው ወደ እንግሊዝኛ ሲለወጡ ግን ወጥነት የሚባል ነገር ገደል ገብቷል። ሲያሻቸው ሙሉውን በupper case letters ሌላ ጊዜ ሲፈልጉ ደግሞ በsentence case ጽፈውታል። ይህንን መፋለስ አጸደ ህጻናት ያሉ ልጆች እንኳ አይፈጽሙትም።

በመጨረሻ ከማስታወቂያ ሆሄያቱ ግድፈት ጀርባ ስላለው እውነት አንድ ሞያዊ ቁምነገር ላክል። አንድ የመሰረተ ልማት አውታር ተሰርቶ ሲጠናቀቅ አገልግሎት መስጠት ከመጀመሩ በፊት የጥራት ፍተሻ [ Quality Control] ይካሄድበታል። ፍተሻው የመሰረተ ልማቱ ፊዚካል ግንባታ ደረጃውንና ጥራቱን በጠበቀ መልኩ መካሄዱን ብቻ ሳይሆን በየቦታው የሚሰቀሉ የአውታሩ ምልክቶችና የማስታወቂያ ሄሆያትን ትክክለኛነትም ያካትታል። በአንድ ባቡር አውታር ላይ የሚካሄድ የማስታወቂያ ሆሄያትና የምልክቶች ፍተሻ የመጨረሻው ደረጃ ፍተሻ ነው። ይህንን ደረጃ ያላለፈ አውታር የጥራት ደረጃ ፍተሻውን እንዳላለፈ ይቆጠራል። በዚህ መሰረት ትናንትና ስራ ጀመረ የተባለው የአዲስ አበባው ቀላል ባቡር ፕሮጀክት የመጨረሻውን የጥራት ፍተሻ ምዘና አላለፈም ማለት እንችላለን። የመጨረሻውን የጥራት ፍተሻ ምዘና ያላለፈ አውታር ማስተካከያ ተደርጎበት ካልሆነ በስተቀር እንዳለ በቁሙ ስራ እንዲጀምር አይደረግም። ይህ ምክረ ሀሳብ የEconomics of infrastructure ሀ ሁ ነው። ትናንትና ኢትዮጵያ የሳተችው ይህንን ምክረ ሀሳብ ነው። ለነገሩ በኢትዮጵያ የሚሆን ነገር እንዳይሆን ሆኖ መደረጉ አዲስ ነገር አይደለም። በኢትዮጵያ እውቀት ከትምህርት ቤት ሳይሆን ከወያኔ ወንበር ስለሚፈልቅ መቆርቆዝና መዝቀጥ ባህላችን ከሆነ ውሎ አድሯል።

እኔን የገረመኝ ግን ከውጭ ማንም ሰው አይቶ የሚለየውን የሆሄያት ግድፈት እንኳ ተመልክቶ ማስተካከል ያልቻለ የጥራት ማረጋገጥ ምዘና፤ ውስብስብ የሆነውን፣ ጥልቅ ሞያዊ ክህሎት የሚጠይቀውን፣ ባይን የማይታየውንና ከባዱን የባቡሩን መስመር ፊዚካላዊ ጥንካሬ ጉድለት ፈትሾ የባቡር መስመሩ ግንባታ ደረጃውን መጠበቁን አለመጠበቁን እንዴት ብሎ ማረጋገጥ ይችላል? በእውነት ስራ ጀመረ የተባለው የባቡር መስመር ፕሮጀክት የጥራት ፍተሻ ተካሂዶበታልን? እንዴት ተብሎ ስንት መሀንዲሶች ባሉባት አገር ውስጥ የባቡሩ አውታር በአይን የሚታየውን የጥራት መመዘኛ [ማለት መስመር አመላካች ሆሄያት በሚገባ ያልተሟሉለት ሆኖ ሳለ] ፈተና ማለፍ ሳይችል በአይን የማይታዩ የጥራት ፍተሻዎችን እንዳለፈ ተቆጥሮ የመጨረሻውን የጥራት ደረጃ ምዘና ባላሟላ ሀዲድ ላይ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት እንዲጀመር ይደረጋል?

በወያኔ ዘመን ሁሉ ነገር ፖለቲካ ሆኖ እውቀት፣ጥራትና ልቀት የሚባል ነገር ሁሉ በኢትዮጵያ ምድር አፈር ድሜ በላ። አውሮፓና አሜሪካ ቀርቶ የትም ሶስተኛ አለም ውስጥ የመጨረሻውን የጥራት ምዘና ደረጃ ያላሟላ የባቡር አውታር እንደኛ አገር ሀላፊነት በጎደለው መልኩ ስራ እንዲጀመር አይደረግም። በእውነት የባቡሩ አውታር ላይም የተደረገ ፍተሻ በተሰቀሉ የአውታሩ ምልክቶችና የማስታወቂያ ሄሆያት ልክ ከሆነ፤ ከጣራው በላይ ዳንኪራ የተደለቀለቱ የባቡር ትራንስፖርት በቅርቡ ከአገልግሎት ውጭ ሆኖ ሰባራ ሀዲድ ብቻ ታቅፈን እንቀራለን። ይህንን እድሜ ያለው ያያል!

መንግሥት እርዳታ ፈላጊነቱን በይፋ አመነ

$
0
0

ከይድነቃቸው ከበደRedwan

“መንግሥት እርዳታ ፈላጊነቱን በይፋ አመነ !” መባሉ  ምን አዲስ ነገር አለው ፣ለዛውም የኢትዮጵያ መንግስት በማለት እንዳትሸወዱ ! የህውሓት/ኢህአዲግ ገዥው መንግሰት የምግብ እርዳት እና ድርቅን ለመከላከል ፣ሞቼ ነው በቁሚ የምለምነው ሲል ነበር፡፡
በአገራችን በኢሊኒኖ ምክንያት በተከሰተው ድርቅ፣ በሰው ሕይወት እና በእንስሳት  ላይ እየደረሰ ያላው አደጋ አሳሳቢነት አስመልክቶ ፤የመንግሰት ኮሚኒኪሽን ጉዳይ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሬዲዋን ሁሴን “ሰባት ሞቶ ሚሊይን ብር በጀት የያዝን በመሆኑ ችግሩን መቆጣጠር እንችላለን ፣ ምንም አይነት የዉጪ እርዳታ አያስፈልገንም፣ የዚህን ያህል አሳሳቢ ደረጃ አልደረሰም” በማላት የመንግስታቸውን አቋም ነሐሴ ወር 2007 ዓ.ም መግለፃቸው የሚታወስ ነው፡፡

አቶ ሬዲዋን መግለጫውን በሰጡ ሳምንት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ   ዳያስፓራ ነን ባዩችን በሚሊኒየም አዳራሽ ሰብስበው “አሁን በክረምቱ በምስራቁ የሀገራችን ክፍል ከላይ እስከታች ድርቅ አጋጥሞናል……፣ወዳጆችን በዚህ ሰዓት ተሯሩጠው መጥተው እርዳታ ይሰጡን ነበር ፣አሁን እስኪ እናያቸዋለን በማለት ዳር ነው የቆሙት……. ፣አቅማችን እየጎለበተ ስለመጣ እራሳችን ገዝተን እራሳችን አቅርበን ህዝባችን እንዳይራብ እናደርጋለን ።” በማለት በድፍረት ተናግረዋል፡፡ይህ የድፍረት ንግግራቸው በቀጥታ ስርጭት በኢቲቪ ተላልፏል፡፡

“ጉድ እና ጅራት ….” እንደሚባለው ሆነና አቶ ሬዲዋን ሁሴን ዛሬ ማለትም መስከረም 10 ቀን 2008 ዓ.ም የመንግስታቸውን አቋም ሲገልፁ ፤በኢሊኒኖ ምክንያት በተፈጠረው የዝናብ እጥረት የተጎዱ ዜጎች ቁጥር ቀድሞ ከተገመተው 2ነጥበ9 ሚሊየን ህዝብ በማሻቀብ ከ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ደርሷል፣ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የተጠበቀው ድጋፍ በሚፈለገው መልኩ አልተገኘም፣ይህም በመሆኑ ለልማት ከያዘው በጀት እንጠቀማለን “አሉ”፡፡

ይሄ መንግሥት ነኝ ባይ ህውሓት/ኢህአዲግ በዚህ ደረጃ፣ በአገር እና በህዝብ ላይ መቀልዱ የወደፊት የታሪክ ተጠያቂነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ፤አሁን ላይ የሥርዓቱ ውድቀት እየተፋጠነ ለመምጣቱ ከምክንያቶች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ “የተራበ ህዝብ መሪውን ይበላል” መባሉ ቀርቶ መሆኑ ይመጣ ይሆን ? መልሱን አብረን እንጠብቃለን፡፡

አሁንም ግን በአገራችን በሰሜን ምስራቅ እና በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ መጠኑ እየጨመረ መጥቷል፡፡ በተለይ በእንስሳት ላይ እየደረሰ ያለው አደጋ እጅግ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል፣ ወገኖቻችን በምግብ እጥረት እየተሰቃዩ ለሞት እየተዳረጉ ነው፡፡የችግሩ አሳሳቢነት ደረጃ ከፍ ማለቱ ገዥው ህውሓት/ኢህአዲግ መንግስት ለመሸሸግ አልቻልም፡፡ በግልፅ ቋንቋ “ከውጭ የሚጠበቀው ድጋፍ ካልተገኘ መንግስት ለልማት የመደበውን ሀብት በማዞር ለዜጎች ምግብና ለእንስሳት የሚሆን መኖ ለማቅረብ እግደዳለው” በማላት በአቶ ሬዲዋን ሁሴን በኩል ገልፆዋል፡፡እንዲህ አይነቱ መንግስታዊ ማስፈራራት ምክንያቱን እና ውጤቱን ለመገመት ቀላል ነው፡፡

ከአንድ ወር በፊት እኔ በግሌ እንዲሁም የተለያዩ ግለሰቦች እና ተቋማት፣ ከመገናኛ ብዙሃን ኢሳት እና የውጪ ሃገር ሚዲያዎች፣ የችግሩን አሳሳቢት በተቻለ አቅም ለመግለፅ ተችሎአል፡፡በተለይ መንግሰት “ሰባት ሞቶ ሚሊይን ብር በጀት የያዝን በመሆኑ ችግሩን መቆጣጠር እንችላለን ፣ ምንም አይነት የዉጪ እርዳታ አያስፈልገንም፣ የዚህን ያህል አሳሳቢ ደረጃ አልደረሰም” በማላት በድፍረት ሲናጋር ፣ይሄ ነገር ተገቢ አይደለም ፣የሚመጣው ነገር አይታወቅም ከአጉል ቀረርቶ እና ባዶ ሽለላ መቅረት አለበት፡፡

ስለዚህም ከችግሩ አሳሳቢነት እና ወደፊት ከሚያስከትለው አደጋ አንጻር፣ ለዓለም አቀፍ ማህብረሰብ እንዲሁም ለለጋሽ ድርጅቶች እርዳታ መጠየቅ አለበት፡፡በማለት የችግሩ አሳሳቢነት ለገለፁ ለአገር ወዳድ እና ተቆርቋሪ ኢትዮጵያዊያን የተሰጠው ምልሽ “አቅማችን እየጎለበተ ስለመጣ እራሳችን ገዝተን እራሳችን አቅርበን ህዝባችን እንዳይራብ እናደርጋለን ።” በማለት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በአደባባይ ተዘባበቱ፡፡

ይሄን በተናገሩ ሁለት ወር ሳይሞላ የሚረዳን አጣን፣ለዚህ ጉዳይ የያዝነው ገንዘብ እያለቀ ነው፤ከዚህ በኋላ ለልማት የያዝነውን ገንዘብ ነው የምንጠቀመው፤ሲሉ መስማት ያሳፍራል፡፡ነገ ደግሞ ለልማት የያዝነው ገንዘብ ድርቁን ለመከላከል ያወጣነው ስለሆነ፣ አገር የምናስተዳድርበት ገንዘብ የለንም ይሉ ይሆን ? ያኔ ጊዜ “የተራበ ህዝብ መሪውን ይበላል” መባሉ እርግጥ ይሆናል፡፡

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!

አፕል በኤሌክትሪክ የምትሠራ መኪና ሊያመርት ነው

$
0
0

በምናለ ብርሃኑ

በዚህ ዘመን በወደዱት ድርጅት ወይም ተቋም የተሰራን ምርት ገበያ ላይ ፈልጎ መጠቀም ልማድ እየሆነ መጥቷል፤ የተጠቃሚዎችና የኩባንያዎች የመፈላለጊያ መንገድም በዝቷል። ታዲያ ተቋሞችም ፈላጊዎቻቸውንና አድናቂዎቻቸውን ላለማጣት እና ላለማስቀየም ብሎም ተሽሎ ለመገኘት ሌት ተቀን በመልፋት እና የተሻለ እና አዳዲስ ነገር በማቅረብ ገበያውን ሲቆጣጠሩት ይስተዋላል።

apple car New

በተለይም በዚህ ዘመን የኤሌክትሮኒክስ ገበያውን የተቆጣጠሩት ታላላቅ ኩባንያዎች ይህን ያደርጋሉ፤ የአሜሪካው አፕልም ከእነዚህ ድርጅቶች አንዱና ተጠቃሹ ነው። ይህ ኩባንያ በዘመናዊ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎቹ በተለይም ደግሞ በተንቀሳቃሽ ስልኮችና ሰዓቶቹ ይታወቃል፤ አሁን ደግሞ እጅግ በዘመነ ተሽከርካሪ ወደ ገበያ ልመጣ ነውና ጠብቁኝ እያለ ነው።

ኩባንያው በኤሌክትሪክ የምትሰራ አነስተኛ እና ዘመናዊ ተሽከርካሪን በፈረንጆቹ 2019 መንገድ ላይ እሞክራታለሁ ማለቱን ወል ስትሪት ጆርናል ላይ የወጣ መረጃ ያትታል።

በአራት አመታት ውስጥ ተገጣጥማ መንገድ ላይ ትወጣለች ያላትን ተሽከርካሪ ጉዳይን በተመለከተም ከካሊፎርኒያ ባለስልጣናት ጋር መምከሩም ነው የተነገረው።

ታይታን የሚል ሚስጥራዊ መጠሪያ በተሰጠው ፕሮጀክት ያለውን ስራ ለማቀላጠፍም ተቋሙ የሰራተኞቹን ቁጥር ለመጨመር ማሰቡም ተነግሯል።

ከዚህ በተጨማሪም የዘርፉን ኢንጅነሮች የቀጠረ ሲሆን ይህ አዲስ የኤሌክትሪክ መኪና ፕሮጀክቱም የተቋሙ ትልቁና ዋናው አጀንዳ ነው ተብሏል።

አዲሷ ተሽከርካሪ ያለ ሾፌር ላትሰራ እንደምትችል ተጠቅሷል፥ ምናልባትም ከዚህ እጅግ የዘመኑትና ራሳቸውን ችለው የሚሄዱ ተሽከርካሪዎች የኩባንያው የረጅም ጊዜ እቅድ እንደሆኑም ነው የተነገረው።

ከዚህ ቀደም ጎግል ተመሳሳይ ተሽከርካሪን ያመረተ ሲሆን፥ የመኪና አምራች ኢንዱስትሪውን ከመቀላቀል ይልቅ ለተሽከርካሪ መገጣጠሚያ እና አምራች ኩባንያዎች ሶፍትዌሮችን አሻሽሎ ማቅረብ ቀጣይ ተግባሩ መሆኑን ኩባንያው መግለጹም ይታወሳል።
ምንጭ፥ fossbytes.com


Sport: ባርሴሎና ዘንድሮ የሚቸገርባቸው ምክንያቶች

$
0
0

የተጫዋቾች ጊዜያዊ የዝውውር እገዳ፣ የትኩረት ማጣት እና የዣቪ ኸርናንዴዝ አለመኖር ባርሴሎና በአዲሱ የውድድር ዓመት ያለፈውን ዓመት ስኬት ለመድገም እንዲቸገር ያደርገዋል፡፡ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን የካታላኑ ክለብ እንደ 2008/09 የውድድር ዘመን የሶስትዮሽ ዋንጫ ባለቤት ሆኗል፡፡ የላሊ ጋ፣ ቻምፒዮንስ ሊግ እና ኮፓ ዴል ሬይ ድሎችን አሳክቶ ዓመቱን በስኬት ፈፅሟል፡፡
ሶስቱ አጥቂዎች (ሉዊስ ሱዋሬዝ- ሊዮኔል ሜሲ- ኔይማር) በጋራ 122 ጎሎችን ባስቆጠሩበት የውድድር ዘመን ባርሴሎና ለእነኚህ ክዋክብት የሚመች አጨወወት ተከትሏል፡፡ ፈጣን፣ መልሶ ማጥቃት እና ቀጥተኛ እግርኳስን ተጫውቶ ከፔፕ ጋርዲዮላ ቲኪ-ታካ የመሩት ፍልስፍና መውጣቱን አረጋግጧል፡፡ በአዲሱ ዓመትም ቢሆን ይሄ የጨዋታ ፍልስፍና የሚለውጥ አይመስልም፡፡

barcelona FC 2015
ባርሴሎና ዘንድሮ ይሄንን ታሪካዊ ስኬት መድገም ይችላል? የካታላኑ ክለብ በስፔን ሱፐር ካፕ በአትሌቲክ ቢልባኦ በደርሶ መልስ 5-1 በመሸነፉ ምክንያት በ2008/09 እና 2009/10 የውድድር ዘመን በነበሩት ዓመታት እንዳሳካው አይነት የስድስት ዋንጫ ባለቤት መሆን አይችልም፡፡
የሉዊስ ኤንሪኬ ቡድን ያለፈው ዓመት ጥንካሬ ዘንድሮ አብሮት ያለ አይመስልም፤ ቡድኑ ከወዲሁ የተዳከመ ይመስላል፡፡ የተከላካይ መስመሩ ደግሞ በቀላሉ ተሰባሪ ይመስላል፡፡ በአውሮፓ ሱፐር ካፕ ቤቲስ ሴቪያን እስከ 57ኛው ደቂቃ ድረስ 4-1 እየመራ 4ለ4 ተለያይቶ ፔድሮ 115ኛው ደቂቃ ላይ ኳስ እና መረብን አገናኝቶ ቡድኑን አሸናፊ አደረገው እንጂ የተከላካይ መስመሩ ጉዳይ አሳሳቢ ነው፡፡ ባርሴሎና ዘንድሮ የሚቸገርባቸው ምክንያቶች ምንድናቸው?

የዣቪ አለመኖር፡-
ዣቪ ወደ ኳታር መጓዝ ለባርሴሎና ትልቅ ኪሳራ ነው፡፡ ምርጡ አምበል፣ የቲኪ ታካ ምልክት እና የቡድኑ ልብ የነበረው ዣቪ በመልበሻ ክፍል ውስጥ አለመኖሩ ቡድኑን እንደሚጎዳው ጥርጥር የለውም፡፡ የእርሱ መልቀቅ በባርሴሎና ታሪክ ተጠቃሽ አጋጣሚዎች መሀከል አንዱ ነው፡፡
ከአንድ ዓመት በፊት ከቤቲስ ሴቪያ ወደ ባርሴሎና የመጣው ኢቫን ራኪቲች ቦታውን ተክቶ ቢጫወትም ሉዊስ ኤንሪኬ የቡድኑን የጨዋታ አቅጣጫ መለወጥ ሲፈልግ ዣቪን በእርሱ ቦታ ተክቶ ያስገባ ነበር፡፡ ዣቪ በ19 የላ ሊጋ ጨዋታዎች የመጀመሪያ ተሰላፊ ነበር፡፡ በዚህ ዕድሜው እንኳን እስከ መጨረሻው ጨዋታ ድረስ ተፅዕኖ ፈጣሪ ለመሆን አልተቸገረም፡፡
በአውሮፓ ሱፐር ካፕ ቤቲስ ሴቪያ ከአንድሬስ ኢንዬስታ ተቀይሮ መውጣት በኋላ ሁለት ጎሎችን አስቆጥሮ አቻ መሆኑ የአጋጣሚ ጉዳይ አይደለም፤ ባርሴሎና ስኬታማ ለመሆን ‹‹በባርሴሎና መንገድ›› መጫወት ግድ ይለዋል፡፡ የዣቪ ተፅዕኖ ደግሞ ጎልቶ ይወጣል፡፡

የዝውውር እገዳ
የቡድኖች መዳከም በአዳዲስ የተጨዋቾች ዝውውር ሊጠናከር ይችላል፤ ክለቡ ህግን ረስቶ እና ርትዕን ወደ ጎን ብሎ ከ18 ዓመት በታች ተጨዋቾችን በማስፈረም እስከ ጃንዋሪ 2016 ድረስ እገዛ ተጥሎበታል፡፡ ያም ቢሆን ባርሴሎና ቀድሞ ለዣቪ ምትክ ኢቫን ራኪቲችን አስፈርሟል፤ ኧረ እንዲያውም እስከ ውድድር ዓመቱ አጋማሽ ድረስ የማይጠቀምባቸውን አርዳ ቱራን እና አሌክስ ቪዳልን አስፈርሟል፡፡
አዳዲስ ተጨዋቾችን አስፈርሞ ነበር፡፡ ተጨዋቾችን አለማንቃት እና ለፉክክር ዝግጁ አለማድረግ ምን ያህል ዋጋ እንደሚያስከፍል የዘንድሮ ቼልሲ ቁልጭ አድርጎ አሳይቶናል፡፡ አሰልጣኝ ጆዜ ሞውሪንሆ ባለፈው ዓመት የፕሪሚየር ሊግ እና ካፒታል ዋን ካፕ ሻምፒዮን መሆን ቢችሉም ዘንድሮ ይህንን ለማሳካት እጅግ በጣም ተቸግረዋል፡፡ ኧረ እንዲያውም ስቃይ ውስጥ ገብተው የክለቡን ዶክተር ኤቫ ካርኔይሮን ክብር የሚነካ ስድብ ተሳድበው ‹‹ጆዜ ምን ነካቸው?›› አስብለዋል፡፡
የባርሴሎናም ጉዳይ ተመሳሳይ ይመስላል፤ ሊዮኔል ሜሲ ብቻውን ሆኖ ዓመቱን ሙሉ የካታላኑን ክለብ ውጤታማ ማድረግ ይከብደዋል፡፡ በቀጣይ በአዳዲስ ተጨዋቾች ዝውውር ቡድኑን ማጠናከር ግድ ይላል፡፡

የተወሰኑ ተጨዋች ጥገኛ መሆን
ባርሴሎና አንድን ጨዋታ በድል ለመወጣት የሜሲ፣ ኔይማር እና ሱዋሬዝ ጥገኛ ነው፤ አማካይ ክፍሉ ሰርጂዮ ቡስኬት እና አንድሬስ አንዬስታን ቢይዝም የእነኚህ ተጨዋቾች ተፅዕኖ ከቀደሙት ዓመታት አንፃር ወርዷል፡፡
በሪያል ማድሪድም ቢሆን ነገሩ ተመሳሳይ ነው፡፡ ሮናልዶ፣ ቤንዜማ፣ ቤል፣ ሞድሪች እና ራሞስ ከሌሉ የስፔኑ ክለብ መቸገሩ አይቀርም፡፡
ያም ቢሆን ባርሴሎና የቡድን ጥልቀቱ ደካማ ይመስላል፣ ከላ ሜሲያ ያደጉ ተጨዋቾች ዋናውን ቡድን ቢቀላቀሉም በዚህ ወቅት እምነት የሚጣልባቸው አይደሉም፡፡ ሰርሂ ሮቤርቶ፣ ሳንድሮ እና ሙኒር ኤል-ሃዳዲ በቀጣይ ቋሚ ተሰላፊ ለመሆን መፎካከራቸው እርግጥ ነው፡፡
የቻምፒዮንስ ሊግ የዓለም ዋንጫ አይደለም፣ ሆኖም የሶስትዮሽ ዋንጫ ባለቤት መሆን ቢያስደስትም ስኬቱን መድገም ይከብዳል፡፡ ‹‹ዋንጫዎችን እያነሳህ በቀጠልክ ቁጥር ለማሸነፍ ያህል ስሜት ይሞታል›› በማለት ጊለም ባለጌ በፔፕ ጋርዲዮላ ቡድን ላይ የሰጠው አስተያየት ሁሉንም ነገር ሊነግረን ይችላል፡፡

አጭር እና አድካሚ ዝግጅት
ባርሴሎና በስፔን ሱፐር ካፕ የመልስ ጨዋታ ከአትሌቲክ ቢልባኦ ጋር 1-1 ሲለያይ በባርሴሎና ተጨዋቾች ፊት ላይ የድካም ስሜት ያስተውል ነበር፡፡ የጄራርድ ፔኬ በቀይ ካርድ መውጣት የዚህ አንድ አካል ተደርጎ ሊወሰድም ይችላል፡፡ ግዙፉ ተከላካይ በጨዋታው የመስመር ዳኛውን እናት ክብር የሚነካ ስድብ መሳደቡ ደግሞ ለረጅም ሳምንታት ያህል እንዲቀጣ አድርጎታል፤ ይሄ ደግሞ የተከላካይ መስመሩን አሳስቶታል፡፡ በቀጣይ ባርሴሎና የገጠመውን ችግር አስወግዶ ‹‹ከክለብም በላይ›› የሚለውን አባባል በተግባር ማረጋገጥ ግድ ይለዋል፡፡

ከዳባት አጅሬ ጠገዴ ሊሰራ ታቅዶ የነበረው መንገድ በአገዛዙ ከፍተኛ ባለስልጣናት ውሳኔ መታጠፉ ተገለፀ

$
0
0

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ) የህወሓት አገዛዝ ከዚህ ቀደም መንገዱ የሚገነባበትን አካባቢ ህዝብ ማለትም ከዳባት እስከ ጠገዴ ለሚገኘው ነዋሪ መንገድ ሊገነባለት ዕቅዱ እና በጀቱ አልቆ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንደሚገባ ቃል ከመግባት አልፎ ሰፊ የፕሮፓጋንዳ ቅስቀሳ አድርጎ ነበር፡፡ የይስሙላሁ ጠ/ሚንስትር ኃ/ማሪያም ደሰላኝም በተመሳሳይ ሁኔታ ከአንድ ዓመት በፊት ጎንደር ተገኝቶ “ከዳባት-አጅሬ ጠገዴ የሚደርስ መንገድ በፌድራል መንግስቱ ወጭ እንገነባለን…” ሲል ቃል ገብቷ፡፡ ነገር ግን ከሰሞኑ ዕቅዱ መሰረዙ ለወረዳው ባለስልጣናት ከፌድራል አገዛዙ ባለስልጣናት በቀጥታ ተገልፆላችዋል፡፡
news
ከዳባት-አጅሬ ጠገዴ ድረስ ሊሰራ የተከለለው መንገድ ግንባታ ዕቅድ የታጠፈው መንገዱ ጠገዴ ከደረሰ በቀላሉ ከወልቃይት ጋር ይገናኛል በሚል ምክኒያት እንደሆነ ታውቋል፡፡ የህወሓት አገዛዝ የወልቃይትን ህዝብ ያለፍላጎቱ ከጎንደር ገንጥሎ ከትግራይ ጋር በመቀላቀል በኃይል አፍኖ ረግጦ እየገዛው መሆኑ የሚታወቅ ነው በመሆኑም መከረኛው የወልቃይት ህዝብ ከማንም እንዳይገናኝ ለማድረግ እና ነጥሎ ለማቆየት ከዳባት-አጅሬ ጠገዴ ሊሰራ የታቀደው መንገድ ተሰርዟል፡፡
ከዳባት-አጅሬ ጠገዴ ሊሰራ በዕቅድ ተይዞ የወልቃይትን ህዝብ ለመነጠል ሲባል ብቻ የተሰረዘው መንገድ እንዲገነባ በህዝቡ የተጠየቀው ከ1997 ዓ.ም በፊት ነበር፡፡

የአካባቢው ህዝብ መንገዱ አይሰራም በመባሉ ብቻ ሳይሆን አገዛዙ ዕቅዱን ለመሰረዝ የተነሳሳበት ምክንያት እጅግ በጣም እያበሳጨው እንደሆነ እና ለለውጥ ለመታገል ውስጥ ለውስጥ መደራጀት መጀመሩን የአርበኞች ግንቦት 7ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች የላኩልን መረጃ ያረጋግጣል፡፡

አሜሪካ ሙስሊም መሪ “አያስፈልጋትም “ ያሉ እጩ ፕ/ታዊ ተወዳዳሪ ተቃውሞ ገጠማቸው (ከታምሩ ገዳ)

$
0
0

12036537_10154338576224298_4988585076349569315_n
ጥያቄው በዚህ ብቻ አልተቋጨም ወረድ ሲልም “ታዲያ የእስልምና ሐይማኖት ከአሜሪካ ሕገ መንግሰት ጋር ይጣጣማል ብለው ያምናሉ?” የሚል ጥያቄ ቀረበላቸው። የቤን ካርሰን ምላሽ”ነው ብዩ በፍጹም ነው ብዩአላስብም ። አገሪቱን ሙስሊም ፕ/ት ይምራ ብዮ አልቀሰቅስም፣ በዚህ ሃሳብ በጭራሽም አልስማማም” የሚል ነበር ። የ64 አመቱ ጸሃፊው፣ፖለቲከኛው ፣ ጡረተኛው የእንጎል ቀዶ ጥገና ስፐሻሊስቱ(እዚህ ላይ የእርሳቸውም የእንጎል ሰራስር ትንሽ ላላ ያለ ይመሰላል) እና ወግ አጥባቂ ክርስቲያን የሆኑት ቤን ካርሰን ወዲያውኑ ከተለያዩ ወገኖች ተቃውሞዎች የገጠማቸው ሲሆን በተለይ የአሜሪካ የሙስሊም ካውንስልዳይሬክተር የሆኑት ኒሃድ አዋድ “ካርሰን በዚህ አንጋገራቸው ብቻ ብቁ ፕ/ት መሆን አይችሉም፣ከውድድር በቅድሚያ ሊባረሩ ይገባል፣ለእጩ ፕ/ታዊ ተወዳዳሪዎች የምመክራቸው ነገር ቢኖር የአሜሪካ ህገ መንግስት ምን እንደሚል በቅድሚያ አንዲያነቡት ነው ።”በማለት ተችተዋል፣መክረዋል።

የካርሰን የምረጡኝ ቅስቀሳ ቡደን በበኩሉ” የ እጩ ፕ/ታዊው የ ካርሰን አስተያየት ተጣሟል /ተጋንኖ ነው የቀረበው” ሲል መላሽ በመሰጠት የካርሰን አስተያየት የነበረው”አሜሪካ በአሁኑ ወቅት ሙስሊም ፕ/ት ለመቀበል ዝግጁ አይደለችም የሚል ነበር ፣ካርሰን በቅርቡ የሙስሊሙን ማህበረሰብ ለማነጋገር ዝግጁ ናቸው።” በማለት አልሸሹም ዞር አሉ አይነት ምልሹን ሰጥቷል። ዛሬ ማክሰኞ የምረጡኝ ዘመቻውን ኦሃዮ ውስጥ ያካሄዱት ካርሰን ከቀደመው አቋማቸው ፈቀቅ እንዳላሉ “ይልቁንም ሃይማኖታዊ ተጽእኖ ለማሳደር የሚሻ ክርሰቲያናዊ መሪም ቢሆን ቦታ የለውም።”ሲሉ ተደምጠዋል።ካርሰን በአሁኑ ወቅት 20% ቅደመ ምርጫ ደጋፍ በማግኝት በረፖብሊካኑ ጎራ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

ከዚህ ቀደም “ ፕ/ት ኦባማ ትውልዳቸው አሜሪካ አይደለም ፣የልደት ካርዳቸውም ቢሆን አሜሪካዊነታቸውን ሰለ መጠቆሙ እጠራጠራለሁ ።”ያሉት (የሪፐብሊካኖችን እጩዎች እየመሩ ያሉት) ቱጃሩ ዶናልድ ትራምፕ በዚህ ሰሞን ደግሞ “ከተመረጥኩ የሜክሲኮ ሰደተኞች ወደ ግዛታችን (አሜሪካ ) ዝር እንዳይሉ በአለም ትልቁ የሆነ አጥር በድንበራችን ላይ እገነባለሁ፣ፕ/ት ኦባማ የክርስትና እምነትን እያጠፉ ነው። “ በማለታችው ከዲሞክራቶች ታላቅ ተቃውሞ ገጥሟቸው ሰንብተዋል ።

ሲኦል እንገናኝ!!! ሲኦል እንገናኝ –ከተማ ዋቅጅራ

$
0
0

 

የአቶ ኃይለማርያም ዛቻ የት ያደርሳቸው ይሆን?

Haile Mariam -- Satenawእኛም አሉ ሲኦል ያሉት ከሲኦል መልዕክታቸውን ሲያስተላልፉ፡- እኛም መሪ ነበርን እኛም ትእቢተኛ ነበርን እኛም ትምክህተኛ ነበርን እኛም የንጹሃንን ደም በከንቱ እናፈስ ነበረ እኛም ህዝብን በመበደል፣ በማሰቃየት እና  በማስለቀስ እንደሰት ነበረ እኛም እናስፈራራ፣ እንዝት፣ እንፎክር፣ እናቅራራም ነበረ እኛም እናጠፋለን፣ እንደመስሳለን፣ አይቀጡ ቅታት እንቀጣለን፣ የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን፣ እንል ነበረ አዲሱ መሪው ሆይ ያንተ ግን የሚያሳዝነው የጻፉልህን እያነበብክ ያዘዙህን እየፈጸምክ እኛው ጋር መምጣትህ ነው።

እንዴት የታደሉት ናቸው የመጠፋፋት ስራን ስሩ ስንላቸው እንቢ ያሉ ለእውነት የቆሙ በውስጣቸው ክፋት የሌለባቸው፣ የሰው ደም በከንቱ የማያፈሱ፣ ለሃብት እና ለስልጣን ብለው ህዝብን ከህዝብ አገርን ከሃገር የማያጋጩ እንደዚ አይነቶቹ እዚህ የሉም። ክፉ አትሁኑ፣ ገዳይ አትሁኑ፣ በዳይም አትሁኑ ሲባሉ አልሰማ ብለው በክፋታቸው የቀጠሉ እንደነዚ አይነቶቹ ሰዎች  የክፋት ተባባሪዎች ሁሉ መኖሪያቸው ለዘላለም እኛ ጋር ነው።አዲሱ መሪ አንተም ወደኛ መምጫህን እያደላደልክ እና እያፋጠንከው ነውና በቅርቡ እንገኛለን።

ይቺን የስልጣን ወንበር በእውነት ካልተቀመጡበት ህዝብን በመልካም ካላገለገሉበት ፍቅርና መስማማትን ካላስተማሩበት እንዴ አይነት መከራ ነው። የስልጣን ወንበር አልፈልግም የሚሉ እንዴት የታደሉ ናቸው። ግን… ግን ስልጣንን ሁሉም ይፈልጓታል ሁሉም ይባልጉባታል። በስልጣን ወንበር ለመቆየት ሲባል የአይናቹ ቀለም አላማረንም አስወግደው ስንል፣ ይሄኛው ደግሞ በስልጣናችን የመጡ ናቸውና ደምስሳቸው ስንል፣ እውነተኞችን ስናሰቃይ ንጹሃኑን ስናጠፋ ምስኪኑን ህዝብ ስነቀጣው ይኸው ዛሬ እኛ በማይጠፋው ቅጣት እየተቀጣን ነው።

አዲሱ መሪ ሰሞኑን እኛው እንደምንለው አንተም ዛቻህን መዛትህን ስንሰማ አንተም በቅርቡ ከኛ ጋር ሊያገናኘን የሚያስችልህን መንገድ መከተልህ አያስደንቅም ምክንያቱም እኛም እንዲሁ ያደርገን ነበር።በዙሪያችን ብዙ አስተዋሾች ነበሩን እንዲህም ይሉን ነበረ፡- ተዉ የምትሰሩት ስራ ጥሩ አይደለም፡- ተዉ የንጹሃንን ደም በከንቱ ማፍሰስ ግፍ ነው፡- ተዉ ህዝብን መበደል መከራው ለናንተ ነው፡- መልካም ስሩ፣ መልካም ሁኑ፣ እውነትን ተናገሩ፣ እውነትን ተግብሩ፣ እውነተኛም ሁኑ፣ በእውነትም ኑሩ፤ እያሉ የሚነግሩንን ጩኸታቹ በዛብን ወይ ዝም በሉ አልያም የናንተ ንግግር የተኛውን ህዝብ ይቀሰቅሳል እና እናሶግዳችኋለን እያልን ስናጠፋቸው እና ስናጠፋፋቸው የጥፋት ስራችንን እንሰራለን እንጂ ከቶውኑ ድምጻቸውን ለመስማት ፍላጎት እንኳን የለንም ነበረ።እናም ዛሬ አንተም በዙሪያህ እየተነሱ በተለያየም መንገድ  የሚናገሩትን  እውነትን እንድትመለከት የሚጠቁሙህን ሰዎች ባትሰማ አይደንቅም ወንበሩ ላይ የተቀመጡትም ሆኑ በወንበሩ ዙሪያ የተሰበሰቡት በሙሉ እውነትን የመቀበልም ሆነ የሚመለከት ልቦና የላቸውም። ታዲያ ደግመህ… ደግመህ ተናገር እናጠፋችኋለን፣ እንደመስሳችኋለን፣ አሸባሪ፣ ተጠርጣር፣ የልማት አደናቃፊ፣ የአገር እድገት ጸር፤ እያልክ ንጹሃንን ለማጥፋት እና ለማጠፋፋት ስትዝት ጥፋቱ ወንበሩ ላይ ያሉትን የማይነካ ስለሚመስላችሁ  ስትቀባጥሩ እና ሲያስቀባጥሩህ ወደኛ በቅርቡ ትመጣለህ።

አዲሱ መሪ የውድቀትህ ዋዜማ ለይ ነህና  አብዝተህ ጩህ የመውደቂያህ ዘመን ደርሷል እና በዙሪያህ ያሉትን ሁሉ መንከስና ማነካከስ ያምርሃል። እናም ከሲኦል ሆነን የምንነግርህ መልእክት ግዜህ አጭር ነውና ካለችህም አጭር ግዜ አንተ በጣም አሳጥረከዋልና በቶሎ ወደኛ ትመጣለህ ታዲያ ስትመጣ በርከት ብላችሁ እነ አቦይንም ይዘህ ና እኛ የበላናትን እሳት እናተም ትበላላችሁ።

ከተማ ዋቅጅራ

22.09.2015

Email- waqjirak@yahoo.com

 

 

እውነተኛ ፍላጎታችን ኢትዮጵያን መታደግ ከሆነ ለኢትዮጵያ ስንል ሁሉን እናድርግ

$
0
0

ናትናኤል በርሔ

Ethiopia ስለ ታላቅዋ የአፍሪቃ እንቆቅልሽ፤ ስለ ሥልጣን አያያዝና ሥልጣን ላይ መውጣት፣ ሥልጣንም ላይ መሰንበትና ከእሱም አልወርድም ማለት ምን እንደሆነ እንድናስብ እንድናውቀው ተጨባጩ ሁኔታ እንደሚያሳየው ለአንድ አምባገነን ለዚያም አስተሳሰብ ልቡን ለሸጠ ሰው ይህ ሆድ አደር ትልቅ ቦታ አለው። ያለመታደል  ሆኖ ሗላቀር የሆኑ አገሮች በተለይ በአፍሪካ በመሪነትና በወሳኝነት ቦታዎች ላይ የሚቀመጡበት አብዛኞች በልምድና በስነምግባር የተራቆቱ ስለሚበዙባቸው በራሳቸው ስለማይተማመኑ ገንዘብ ማጋበስና በስልጣን ለመቆየት ሲሉ ውሸትና ማታለል ይበዛሉ። ዛሬን እንጂ ነገንና ለነገው ትውልድ ደንታ ስለሌላቸው ከወገንና ከሀገራቸው ሕዝብ ይልቅ ከውጭ መንግስት ፍላጎት ጋር ግንባር ቀደም ትብብር ያደርጋሉ  ከመላው አለማት በአምባገነት ቅድሚያ ከሚሰጣቸው አገራት መሀከል ግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው  የወያኔ አገዛዝ አንዱ ነው።  ላለፉት 24 ዓመታት እየተጨቆነች እና እየተረገጠች ላለችው አገሬ ኢትዮጵያ እኛ ኢትዮጵያውያን ወያኔ ከሥልጣን ላይ ከወጣ ጊዜ አንስቶ በእያንዳንዷ ዓመት የተባበረ እንቅስቃሴ የምናደርግበትን መተማመንና መከባበርን በወያኔ ጋሻ ጃግሬዎች እርዳታ የብሔር ፖለቲካ ከፋፍለህ ግዛ እነሆ ዛሬ ወያኔ ባዘጋጀልን ወጥመድ ወድቀን በመንፈራገጥ ላይ እንገኛለን።

ኢትዮጵያ ብዙ ውስብስብ ችግሮች ያለባት አገር ናት። በተለያዪ ጊዜዎች እነዚህ ለራሳቸው የግል የቡድን ፍላጎት መጠቀሚያ ለማድረግ የፈለጉ ወይም እነዚህን ችግሮች ዲምክራሲያዊ ባልሆነ መንገዶች በህዝብ ስም እንፈታለን ብለው የተነሱ አምባገነን ሀይሎች የሀገራችንን ችግሮች የበለጠ አወሳስበው በመጨረሻ እራሳቸውም አይወድቁ አወዳደቅ ሲወድቁ አይተናል ይሄውም በቅርብ ጊዜ በሰሜን አፍሪካ ሆነው ማንሳት በቂ ነው። ሕወሃት ስልጣን ከጨበጠ ከጅምሩ በኢትዮጵያ የዘረጋዉ ፖለቲካ በዘር ላይ የተመሰረተ ከፋፋይ ፖለቲካ ነዉ። ኢትዮጵያ የብዙ ብሄረሰብ አገር ናት። በታሪኳ የተሰሩ ብዙ ስህተቶችና በደሎች አሉ። በአንጻሩም ደግሞ ኢትዮጵያዉያን ከተለያዩ ቋንቋዎችና ክልሎች በሰላም በፍቅር ኖረዋል፣ ተዋደዋል፣ ተደባልቀዋል። በጋራ የዉጭ ወራሪ ኅይላትን መክተዋል። ወያኔ/ኢሕአዴግ ከደደቢት በረሃ ተነስቶ አዲስ አበባ ገብቶ በመንገሥ በአባቶቻችን መስዋዕትነት ተከብሮ የቆየውን ድንበራችን በማፍረስ፣ ከቤቶቻችን በማፈናቀል፣ መሬታችንን ለባዕድ በመስጠት ያደረሰብን በደል ጣሊያን ከአውሮፓ በመምጣት ከተቃጣብን ወረራ ካደረሰብን ጉዳት በልጦ ይገኛል። በሽፋን ስሙ ኢሕአዴግ ተብዮው ወያኔ/ሕወሐት ዕድሜውን ለማራዘም ይመቸው ዘንድ በውስጣችን ቅራኔን በማስፋት በዘር እያደራጀ፤ ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት ሕዝብን በእሥራት፥ በግድያ፥ በበሽታ፣ በረሐብ እየፈጀና እያስፈጀ ፋሽስታዊ ሥርዓቱን ከጫነብን  ላለፉት ሁለት አስር አመታት በላይ አልፎናል። የተቃዋሚው ጎራም ባልረቡ ልዩነቶች እርስ በርስ ባለመግባባትና ተለጣፊውም በዝቶ ትግላችን ግብና ዓላማውን ከመሳቱም አልፎ ወያኔ የኢትዮጵያን ሕዝብ አስፈራርቶና አሽብሮ ለመግዛት በሚያደርገው ትግል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ድጋፍ እያበረከትን ነው። ከወያኔ ጋር መደራደር በሀገራችን የዴሞክራሲን ሥርዓት መመሥረት አያስችልም። ወያኔ በታሪኩ ሁኔታዎች ወጠር ሲያደርጉት ለማዘናጋት እንደራደር ቢልም በመጨረሻ ቅራኔዎችን የሚፈታው በኃይል ብቻ ነው። ከወያኔ መደራደር የሕዝቡን ትግል እጅ ለማሰጠት ብቻ ነው። በኢትዮጵያ ለሚደረገው የዴሞክራሲያዊ ትግል መሳካት ዋነኛው መሠረት የኃይል ሚዛንን ወደ ሕዝብ ወገን እንዲያጋድል የሚያደርግ ሕዝባዊ ጉልበት በጥንቃቄና በቁርጠኝነት ሲገነባ ብቻ ነው። ከዚያ ባነሰ አቅም መደራደር ሽንፈትን ለማረጋገጥ ነው።

በጎንደር በኩል ያለ የኢትዮጵያ ሰፊ ለም መሬት ከህዝብ ደብቆ ለሱዳን መንግስት በገጸ በረከትነት በማቅረብ የውሃውን ጥልቀት ሞክሮ ዛሬ ደግሞ በምዕራቡ የኢትዮጵያ ክፍል ኢትዮጵያውያንን ከሀገራቸው መሬት በሃይል እያፈናቀለ የቤልጀየምን የቆዳ ስፋት ያክል መሬት እየቆረሰ ለተለያዩ ሀገሮች ሀገራችንን እየሸነሸነ በመሸጥ ላይ ያለ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ሌት ተቀን የሚሰራ ቡድን ነው።  ይህ የኢትዮጵያ የሆነን ነገር ሁሉ ብዙ መስዋዐትነት የከፈሉት አርበኞች አባቶቻችን የሚሸጥና የሚለውጥ አፋኝ ወሮበላ መንግስት ኢትዮጵያዊነትን ሸርሽሮ በጎሳ የተከፋፈለ ደካማ ህዝብና ደካማ ሀገር ለማድረግ ይዞ የተነሳውን ዓላማ ሲሰራበት ቆይቶዋል። ይህ አፋኝ የኢትዮጵያ ጠላት የህዝቡን የሰውነት መብቱን ገፎ ከመኖር በታች ከሞት በላይ አድርጎት በረሃብ ከሚታመሰው ህዝብ ጉሮሮ እየነጠቀ ከመሬት ሽያጭ የሚያገኘውን ገንዘብ በተለያዩ የውጭ ባንኮች የሚያሸሸውንና የሚያጉረው አልበቃ ብሎት ዛሬ ደግሞ የአምስት አመት  ሁለተኛው  እቅድና ትራንስፎርሜሽን በሙሉ የሚነደፈውና የሚጠነጠነው ከሀገሪቱ ጥቅም አኳያ እንጅ ከእውነትና ከሀሰት ከሰብአዊነትና ከዴሞክራሲ ጋር በተዛመደ መልክ ስላልሆነ የምታወሩት ሌላ የምታደርጉት ሌላ ብለን ብናሳጣቸው ብንወቅሳቸው ለኛ ጠብ የሚል ነገር አይኖርም ።

ይህ እንዲሆን ከተፈለገ  ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ራዕይ አንግበው ሕዝቡን የሥልጣን ባለቤት
ለማድረግ ፤ በኢትዮጵያዊነት ላይ በማንኛውም ዓይነት መልኩ በማንም ግፊት ሳይደራደሩ በጽናት የሚከፈለውን መስዋዕትነት እየከፈሉ ለሚያታግሉ ኢትዮጵያዊ ድርጅቶችም ሆነ ግለሰቦች ከፍተኛ አክብሮትና ድጋፍን ከመስጠት ወደ ኋላ
ማለት የለብንም። የተያያዝነው ትግል የዴሞክራሲ ብቻ ሳይሆን ሀገር አድንም መሆኑን ጠንቅቀን ማወቅ አለብን።  እንዴት ከዚህ ልንደርስ ቻልን ብለን እያንዳንዳችን ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ራሳችንን ብንጠይቅና ጊዜ ሳንፈጅ መተማመንና መከባበርን እንዳ ሀገሬ ወጌሻ ለቃቅምን ከቦታው እንዲገባ መጠገን መጀመር ይኖርብናል። ይህ ጥረት ደግሞ እያንዳዳችን ትከሻ ላይ ወድቋል።

ይኄው የአሜሪካ መንግስት ነው በአንድ በኩል ሰብዓዊ መብትና ዲሞክራሲ እያለ ሲለፍፍ በሌላ ወገን ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ ስቃይ መከራና የሰብዓዊ መብት ረገጣ አይቶ እንዳላየ ሰምቶ እንዳልሰማ በመሆን እንደ ሰሜን ኮርያው አይነት በዓለም በዕኩይነቱ አቻ የሌለው አምባገነን መሪ የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ሲደግፈው የሚታየው ለጥቅም እንጂ ሰብዓዊ መብት፣ ዲሞክራሲ ወይም የሰው ልጅ ጣዕርና ዕልቂት ምኑም ያልሆነው የአሜሪካ መንግስትና የዚሁ ፖሊሲ አራማጅ መሪዎቹ  የሶርያው ፣ የአፍጋኒስታኑ ፣ የሩዋንዳ የእርስ በርስ ፍጅት ዳር ሆነው ሲያዩ ዓለም ታዝቧል።

ኢትዮጵያ፡ እንደሀገር፡ እንድትቀጥልና፡ የኢትዮጵያ፡ ህዝብም፡ ከተጫነበት፡ የመከራ ቀንበር፡ እንዲገላገል፡ ከልብ፡ የምንናፍቅ፡ ከሆነ ምኞት፡ የሚጭበጠው፡ በሥራ ነውና፡ ያለምንም፡ ማቅማማት፡ እያንዳንዳችን፡ የዜግነት ድርሻችንን፡ የምናበረክትበት፡ ቀን ቢኖር፡ ዛሬ ሥአቱም፡ አሁን፡ ነው፡ በካሀዲው፡ ጎራ ከተሰለፉትና፡ በመሀል፡ ከሰፈሩት፡ ጥቂት፡ ሰዎች፡ ውጭ ሁሉም፡ ኢትዮጵያዊ፡ ማለት፡ ይቻላል፡ የወያኔን፡ ሀገር፡ አጥፊነት

ከነዚህ ወጥመዶችና የተንኮል ተግባራቱ መካከል አንዱ ሰላዮቹን ለተቃዋሚዎች እጃቸውን እንደሰጡ በማስመሰል የሚታወቁ መረጃዎችን በመድገም ወይም አሳሳች መረጃ በመስጠት ባለስልጣን ነበርኩ፤ ብዙ ነገር አውቃለሁ በማለት አልፎ ተርፎም የኢትዮጵያውያን ትግል ለማዳከም  አንድነትን ወገን ለመከፋፈልና የሕዝቡን ትግል ለማኮላሸት የሚጠቀሙበት ስልት ነዉ። እኛም ሁለት አማራጭ ነዉ ያለን ከዚህ በፊት ከሰራናቸዉ ስህተቶች ተምረን ልዩነቶቻችን አቻችለን የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች በኛ ላይ የሚዘረጉትን ወጥመዶች ሰባብረን፣ ይህ ችቦ የበለጠ እንዲቀጣጠል ማድረግ አንደኛዉ አምራጫችን ነዉ። ሁለተኛዉና ሌላዉ አማራጭ የሕወሃት መንግስትን እድሜ የሚያራዝም፣ የተለኮሰዉን ችቦ የሚያዳፍን፣ አገራችን ኢትዮጵያውም ከድጥ ወደ ማጡ እንድትሄድ የሚያደርግ የርስ በርስ የመከፋፈልና አብሮ ያለመሥራት አጉል ኀላ ቀር ልማዳን መቀጠል ነዉ።

አንድ ግን ለማሳረጊያ ማንሳት የምንፈልገው ነገር ቢኖር፣ እኛ ተከባብረንና ተፋቅረን አብረን በሰላም ለመኖር ከአወቅንበት እንደሚባለው እንደ አውሮፓውያኖች ገና ብዙ አመታት መጠበቅ ሳይሆን ነገ ማድረግ የምንችለው ነገር ነው። ያገኘነው ልምምድ የቀመስናቸው መከራዎች በቂ ትምህርቶች ናቸው። ነጻነትና ነጻ አስተሳሰብ ማለት ደግሞ ማንኛውንም ዓይነት “ባርነትን” አልፈልግም ማለት ነው።

 

ቸር እንሰንብት።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያ አገራችንን ይጠብቅልን፡፡

 

ናትናኤል በርሔ

 

tewodrosdagmawi@gmail.com

በአዲስ አበባ የመብራቱ ችግር ተባብሷል –እሁድ ዕለት በካይሮ ከተማ ለፈነዳው ቦምብ ከአይሲስ ጋር በቅርብ የሚሰራው ቡድን ኃላፊነቱን ወሰደ

$
0
0

ፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ በሳተላይት የሚሰራጭ የራዲዮ ፕሮግራም FINOTE DEMOCRACY VOICE OF ETHIOPIAN UNITY SATELLITE RADIO

eprp# በአዲስ አበባ የመብራቱ ችግር ተባብሷል
# በኬኒያ በአስተማሪዎች አድማ ትምህርት ቤቶች እንደተዘጉ ነው
# በቡርኪና ፋሶ መፈንቅለ መንግስት ያካሄዱት ወታደሮች ስልጣኑን እስከሚቀጥለው ምርጫ እንይዛለን አሉ
# በናይጄሪያንና በካሜሮን ሽብርተኞች ባፈነዱት ቦምብ በርካታ ሰዎች ሞቱ
# እሁድ ዕለት በካይሮ ከተማ ለፈነዳው ቦምብ ከአይሲስ ጋር በቅርብ የሚሰራው ቡድን ኃላፊነቱን ወሰደ
ለዝርዝር ዜናዎች > ከታች ይጫኑ (to listen detail news click below)

Part 1

Part 2

የማለዳ ወግ …”ነቢይ በሀገሩ አይከበርም! ”ከያኒው በበጎ ስራው ተሸለመ!

$
0
0

Josy Gebre
* እንኳን ደስ ያለህ ጆሲ ገብሬ
Jossy In Z House በሚለው ስሙ የሚታወቀው ጆሲ ገብሬ በምድረ አሜሪካ , ባልቲሞር Baltimore ውስጥ Deedee Africa Entertainment Award የተባለው ክብር ለሚገባው ክብር የሚሰጥ ድርጅት ባካሔደው ሥነ ሥርዓት ለሰብዕና ዙሪያ ለሰራው በጎ ስራ የክብር ሽልማት ማግኘቱን ሰምተናል ! እንኳን ደስ አለህ ከያኒ ጆሲ :)
ጆሲ ለበርካታ አመታት EBS በተባለው የቴሌቪዥን ፕሮግራም እስካቋረጠበት ቀን ድረስ በሚያቀርባቸው ማራኪ ዝግጅቶቹ በይበልጥ ይታወቃል ። ወጣቱ ከያኒ ጆሲ በዚህ ፕሮግራሙ የተዘነጉ ፣ የተረሱ ፣ የተገፉ ወገኖችን በመደገፍ ፣ ለመደገፍ በማነቃቃት ያደረገውን አርአያነት ያለው ስራ እንማርበት ዘንድ ልዩ በዝግጅቱ አስመስክሯል ብየ አምናለሁ ! ጆሲ በአይነቱ ልዩ በነበረው የመድረክ ዝግጅቱ የጥበብ ሰዎችን በመጋበዝ ባደረጋቸው ውይይቶች ጠቃሚ መረጃንም ያበረከተ ቅን ወጣት የጥበብ ሰው ነው ። በመድረክ አቀራረቡ ፣ በሚያቀርባቸው ቀልብን የሚስቡ የተመጠኑ ጥያቄዎች ፣ ዝግጅቶች በተጨማሪ የመድረክ ፕሮግራም መምራት አሉን ከሚባሉት ጋዜጠኞች የተሻለ ክህሎቱን ያስመሰከረ አርቲስት ነው ባይ ነኝ !
ብዙ የጥበብ ሰዎች ገንዘብ ለማጋበስ ወጥነው በሚለቋቸው ስራዎቻቸው እየተመጻደቁ ” ሀብቴ የህዝብ ፍቅር ነው ፣ ህዝቤን እወዳለሁ! ” የሚሉትን ህዝብ ድምጽ መሆኑ ቢገዳቸው ከሰብዕና ሸሽተው የከረሙት ቁጥር የትየለሌ ነው ፣ ከእኒህ ከያንያን መካከል ጆሲ ባወጣቸው የተለያዩ የጥበብና የመድረክ ስራዎቹ ጆሲ አስተማሪና አርአያነት ያለው በጎ የስራ ዘርፍ ተሰልፎ ፈር ቀዳጅ የሆኑ ስራዎችን ከሰሩ ጥቂት ከያንያን መካከል አንዱ ነው ባይ ነኝ ።
ወጣቱ ከያኒ ጆሲ ገብሬ ” በሚያቀርበው ዝግጅት በጎ ስራውን ለራሱ ክብር መቆለያ ተጠቅሞበታል !” የሚል ወቀሳና ዘመቻ ሲሰነዘርበት አዝኛለሁ። ወቀሳ ዘለፋው በተሰነዘረበት ማግስት ለበጎ ስራ አርአያነት ያለው ወጣት በ EBS ከሚያቀርበው ዝግጅት መገለሉ አስከፍቶኛል ። ያስከፋኝና በገደምዳሜ የሰማነውን የ EBS ቴሌቪዥንን እርምጃ የማልደግፈው ጣቢያው ጆሲ ከተወነጀለበት የግል ዝና ግንባታ ባለፈ በችጋር የተገረፉ ፣ በድህነት ማጥ የወደቁ ፣ የተሰበሩ ልቦችን መጽናኛ መሆን ከግምት ውስጥ ያስገባ ባለመሆኑ ነው ! ይህ የግል ምልከታየ ነው!
ቅዱስ መጽሐፉ ” ነቢይ በሃገሩ አይከበርም ” እንዲል አለመታደል ሆኖ ወገኖቻችን የሚሰሩትን ትልቁን መልካምና በጎ ምግባር እየዘነጋን በተራ ኩነቶች ላይ ተፈናጠን ክብር ለሚገባውቸው ለእኛ ሰዎች እኛ ክብር አንሰጥም ። ዛሬ በዚህ እኛነታችን የተከፋች ነፍሴና ውስጡ የደማ ልቤ ትፍስህት አግኝታለች ። ለወገናችን በጎ ምግባር የእኛ ያልሆኑት ክብር ሲሰጡ መመልከት የሚፈጥረው ደስታ ነፍሴ ታውዳለች !
ወደድንም ጠላንም ወጣቱ ከያኒ ጆሲ ገብሬ ሌላው ቀርቶ አሁን አሁን አልፎ አልፎም ቢሆን ጉምቱ ታዋቂ ከያንያን ወደ በጎው ሰብአዊነት ጎዳና ይመጡ ፣ ይቀላቀሉ ዘንድ አርአያ እንደሆነ ይሰማኛል ! እናም ለጆሲ ሰብአዊነትን መሰረት ያደረገ ድንቅ ስራው አድናቂ ነኝ !
ለወጣቱ ከያኒ ለጆሲ ገብሬ ክብር እሰጣለሁ!
ክብር ለሚገባው ክብር እሰጣለሁ !
ነቢዩ ሲራክ
መስከረም 12 ቀን 2008 ዓም


“አዲስ አበባ ውሸት የሚነገርበት መዲና ሆናለች” (በኤፍሬም ማዴቦ – ከአርበኞች መንደር)

$
0
0

የተናገሩት ከሚጠፋ…

ባለፈዉ መጣጥፌ “ቃል የእምነት ዕዳ ነዉ” ብዬ ጀምሬ “ቃላችን አይለወጥ” ብዬ ነበር የተለየኋችሁ። አለምክንያት አልነበረም እንዲህ ያልኳችሁ፤ በአንድ በኩለ ቃል መከበርም መከፈልም ያለበት ዕዳ ስለሆነ በሌላ በኩል ደግሞ ቀትር ላይ የገባዉን ቃል ሳይመሽ እንደ ጴጥሮስ ሦስቴ የሚክድ ብዙ ቃላ አባይ ሰላለ ነዉ። አገሬን ከወያኔ አጸዳለሁ ብሎ ቃል የሚገባ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዕዳ አለበት።
Madebo
ዕዳዉ ደግሞ ገንዘብ ወይም ንብረት አይደለም። ቃሉን መጠበቅ ወይም ቃሉን ማክበር ነዉ።
ደግሞም አንድ ሰዉ የተናገርዉን ቃል ሰብሮ የእምነት ባለዕዳ ከሚሆን ዕድሜ ልኩን የገንዘብ ባለዕዳ ቢሆን ይሻለዋል። የገንዘብ ዕዳ ቆይቶም ቢሆን ይከፈላል ወይም አበዳሪዉ ሊምረን ይችላል፤ የዕምነት ዕዳ ግን የማይሽር ጠባሳዉ እየቆረቆረን አብሮን ይኖራል እንጂ አይጠፋም። ማንም ሰዉ ለአገሬ ህይወቴን እሰጣለሁ ብሎ ቃል ሲገባ መሃላዉ ከህዝብና ከአገር ጋር ብቻ አይደለም፤ እንዳዉም የሰዉ ልጅ ቃል የሚገባዉ መጀመሪያ ከራሱ ጋር ነዉ። ለራሱ የገባዉን ቃል የማያከብርና ቃሌ ቃል ነዉ ብሎ የገዛ ራሱን የእምነት ዕዳ ያልከፈለ ሰዉ ለህዝብና ለአገር ቃል መግባት አይችልም። ዛሬ ወያኔን እናጥፋ ብሎ ካራ ጨብጦ አብሮኝ የቆመ ሰዉ ነገ ከወያኔ ጋር ሆኖ ካራዉን እኔዉ ላይ አዙሮ ባየዉ እሱ ቀድሞዉንም ካራ የጨበጠዉ ወያኔን ለማጥፋት ሳይሆን ስጋ ሊቆርጥብት ነዉና ብዙ አይገርመኝም። እንዲህ አይነቱን ለቁም ነገር ሲፈልጉት አልሰማ ብሎ ሆዱ ሲሞላለት ግን ሳይጠሩት አቤት የሚል ስጋ ወዳድ ሆዳም ደግሞ ኢትዮጵያ በየዘመኑ አፍርታለችና ብዙ ሊገርመን አይገባም። ከሰሞኑ ከምድረ ኤርትራ የነፈሰዉ ነፋስ ያስተማረን አንድ ትልቅ ቁም ነገር ቢኖር እንዲህ አይነቱን ሞላ ጎደለ የሚባል የካራና የስጋ ጨዋታ ነዉ። አዎ! የካራ ጨወታ – ወዲህ ማዶ ስጋ ሊቆርጡበት ወዲያ ማዶም ስጋ ሊቆርጡበት።

“የተናገሩት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ” . . . ገዢዎቻችን በተለይ የዛሬዎቹ ቃል አባዮች እንደቆሻሻ ዕቃ መሬት ላይ ጣሉት እንጂ ቃል የዕምነት ዕዳ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ዘመን አይሽሬ የአገራችን አባባል ነዉ። አባቶቻችን የተናገሩትን ወይም ቃል ገብተዉ የተማማሉትን ነገር ከሚያጥፉ የወለዱትን ማጣት ይቀላቸዋል። እኛ ልጆቻቸዉ ግን ከዬት የመጣን ጉዶች አንደሆንን አላዉቅም ቃል አባይነታችን እኛን፤ ልጆቻቸንና አገራችንን ሲያጠፋ በአይናችን እያየን ቅር እንኳን አይለንም። “እመጣለሁ ብሎ ሰዉ እንዴት ይዋሻል፤ ማበል እንኳን አንቺን ምድር ያበላሻል” መሬት ላይ ጠብ የማይል ትክክለኛ አባባል ነዉ። አገራችን ኢትዮጵያ ትናንት እንሞትልሻለን ብለዉ ዛሬ በሚገድሏት ቃል አባይ ልጆቿ እየተበላሸች ነዉ። እነዚህ ቃልአባዮች የኢትዮጵያን የምድር ላይና የምድር ዉስጥ ኋብቷን አንጂ የገረጣዉን ፊቷን ማየት አይፈልጉም- አዎ ወያኔ የሚያየዉ ኃብትሽን፤ የሳዑዲዉ ሰዉ ወርቅሽን፤ ባዕድ ከበርቴዉ ለምለም መሬትሽን . . . ወይኔ ኢትዮጵያ ማን ይሆን የሚያየዉ የጠቆረዉ ፊትሽን፤ ማን ይሆን የሚያብሰዉ እምባሽን፤ እኮ ማን ይሆን የሚያቆመዉ መከራሺን . . . ማን ይሆን?. . . ማን ይሆን?

የዛሬዋ ኢትዮጵያ አንድ ትዉልድ ዉሸት ብቻ እየሰማ ያደገባት የዉሸት መዲና ሆናለች። ጳጳሱ፤ ቄሱና ፓስተሩ “እኔ መንገድ፤ አዉነትና ህይወትና ነኝ” ያለዉን የሰማዩን አምላካቸዉን ረስተዉ ለምድር ዉሸታሞች አደሩ። ሂዱና ዋሹ ሲባሉ ሄደዉ ዋሹ፤ እዉነትን በዉሸት አስተባብሉ ሲባሉ አስተባበሉ፤ በሀሰት መስክሩ ሲባሉ አፋቸዉን ሞልተዉ በሀሰት መሰከሩ። “ታላቁ መሪ” እየዋሸን ኖሮ እየዋሸን ሞተ። መታወቂያዉ ዉሸት ነዉና ሞቶም አልሞተም ተብሎ ተዋሸለት። ከአህያ ጋር የዋለች ጊደር ምን ለምዳ ትመጣለች እንዲሉ ሌላ ሁሉ ቢቀር ዉሸትን ይፀየፋል ተብሎ የተነገረለት የዛሬዉ ጠ/ሚኒስቴር ጭራሽ “ታላቁን መሪ” እንደዋቢ እየጠቀሰ ስራዉ ሁሉ ዉሸት፤ ዉሸት፤ ዉሸት ብቻ ሆኖ ቀረ። የኢትዮጵያ ሬድዮ ሲከፈት ዉሸት ይናገራል፤ ሲዘጋ ደግሞ ነገ ስለሚዋሸዉ ዉሸት ያስባል። ጋዜጦች በስህተት አንኳን እዉነት አይጻፍባቸዉም። የኢቲቪ ዜና አንባቢ ተመስገን በየነ ግማሽ ሰዐት የዋሸዉን ዉሸት ለማካካስ ዜናዉን አንብቦ ሲጨርስ ለ15 ደቂቃ ጎንበስ ብሎ ይሰግዳል።

ለረጂም ግዜ ተማምነን ጀርባችንን የሰጠነዉ ሰዉ ለጠላት እጁን ሰጥቶ ጦርነት ሲያዉጅብን አንዳንዴ በትግሉ ዉስጥ ማንን አምነን ጀርባችንን እንደምንሰጠዉ ግራ ሊገባን ይችላል። ከሰሞኑ የሰማነዉ ዜና እንዲህ ግራ የሚያጋባ ዜና ነዉ። ሆኖም ሳንተማመን ትግል ብሎ ነገር የለምና የትግል ጓዶቻችንን ማመን ብርታት እንጂ ደካሞች እንደሚሉት ሞኝነት ወይም የዋህነት አይደለም። በጓዶቻችን ላይ ክህደት ፈጽመን ከምናሰቃያቸዉ እኛ ብንሰቃይ ይሻላል፤ ደግሞም ጓዶቻችንን ማመን አቅቶን በጥርጣሬ ተፋጥጠን ባለንበት ከምንረግጥ አንዳንዴ አዉቀንም ቢሆን ብንታለል ብዙ መንገድ መጓዝ እንችላለን። ትግል በተለይ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል ከሚያስተምረን ትምህርቶች ዉስጥ አንዱና ዋነኛዉ ሌሎች በኛ ላይ እምነት እንዲኖራቸዉ ከፈለግን እኛ አስቀድመን ልናምናቸዉ አንደሚገባን ነዉ። አለዚያ ሁለታችንም አንተማመንም። አለመተማመን ደግሞ ያጠፋፋናል እንጂ አንድ ቤት ዉስጥ አብሮ አያኖረንም። እንደኔ እንደኔ የወያኔን ስርዐት ደምስሰን ኢትዮጵያን የእኩሎች አገር የምናደርጋት እያንዳንዳችን ለትግል ጓዶቻችን የገባነዉን ቃል ሰብረን ረጂም ህይወት ከመኖር ቃላችንን አክብረን ዛሬዉኑ መሞትን ስንመርጥ ብቻ ነዉ። ወያኔ አንደ እሳት የሚፈራዉና በፍጹም የማያሸንፈዉ አንዲህ አይነቱን ከብረት የጠነከረ ጽኑ አቋማችንን ብቻ ነዉ። ለዚህ ነዉ እንዲህ አይነት ጽናት የሌላቸዉን ደካማ ግለሰቦች ፈልጎ እያማለለ ጽናታችንን የሚፈታተነዉ። ከሰሞኑ ለህዝብ ከመታገል ህዝብን መታገል መርጦ ከለየላቸዉ የህዝብ ጠላቶች ጋር የተቀላቀለዉ ሞላ አስገዶም ለዚህ ዉሳኔ የበቃዉ ህዝባዊዉ ትግል የሚፈልገዉ የአለማ ጽናት የሌለዉ ደካማ ግለሰብ ስለሆነ ብቻ ነዉ። ዉድ ኢትዮጵያዉያን ክህደት ትናንት ነበር፤ ዛሬ አለ፤ ነገም ይኖራል። ስለዚህ ክህደት ሊያስተምረን እንጂ በፍጹም ሊያስበረግገንና አንገታችንን ሊያሰደፋን አይገባም። ክህደትና ከሀዲዎችን እያሰላሰልን የምንኖር ከሆነ የበለጠ እንዲጎዱን ተጨማሪ ዕድል እንሰጣቸዋለን እንጂ ሌላ ምንም የምንፈይደዉ ፋይዳ የለም።
ሞላ አስገዶም እሱን የመሰሉ ደካማ ጓደኞቹን ከተቀላቀለ በኋላ መቀሌ፤ አዲስ አበባና አዳማ ዉስጥ ክህደቱን አስመልክቶ እርስ በርሳቸዉ የሚጣረሱ ሦስት ጋዜጣዊ መግለጫዎችን ሰጥቷል። እርግጠኛ ነኝ ይህ ቁርስ ላይ የተናገረዉን ምሳ ላይ የማያስታዉስ ግለሰብ በተያዘለት የጉብኝት ሰሌዳ መሠረት ዘጠኙን ክልሎች የሚዞር ከሆነ ዘጠኝ የተለያዩና እርስ በርሳቸዉ የሚጣረሱ ምክንያቶችን መደርደሩ አይቀርም። የወያኔ የመረጃና የደህንነት መ/ቤት ተብዬዉም ቢሆን ምን ያህል የዉሸትና የጉራ ቤት ለመሆኑ መረጃ ብሎ የለቀቃቸዉን ዉሸቶችና ቱልቱላዎች መጥቀሱ ይበቃል። ለምሳሌ የመረጃና ስለላ ድርጅቱ ከአንድ አመት በላይ ከሞላ አስገዶም ጋር በሚስጢር ይሰራ እንደነበር ተናግሯል። ይህ እዉነት ከሆነ የደምህት ታጋዮች በዚህ አንድ አመት ግዜ ዉስጥ በወያኔ ታጣቂዎችና ወታደራዊ ጣቢያዎች ላይ ለወሰዷቸዉ እርምጃዎች በተለይ እግር ኳስ ጨዋታ በመከታተል ላይ እንዳሉ ለወሬ ነጋሪ ሳይቀር እንዳለ ለተደመሰሱት የኢትዮጵያ ወታደሮች ተጠያቂዉ ከሞላ አስገዶም ጋር ይሰራ የነበረዉ የወያኔ የመረጃና የስለላ ድርጅት ነዉ ማለት ነዉ።

ሞላ አስገዶም ትናንት ከኛ ጋር ሆኖ እኛ ሲል ነበር፤ ዛሬ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጠለቶች ጋር ሆኖ እኛ ይላል። ይህ ሰዉ “እኛ” ሲል የሱ እኛ እነማንን እንደሚያጠቃልል አይታወቅም፤ እሱ እራሱም የሚያዉቀዉ አይመስለኝም። ሞላ አስገዶም ወያኔን እንደተቀላቀለ አፉን ሞልቶ ጥምረቱን የፈጠርነዉ “እኛ” ነን ብሎ ሲናገር በተደጋጋሚ ተደምጧል። ጥምረቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ፍላጎትና ህዝባዊ ትግሉ የደረሰበት የዕድገት ደረጃ ዉጤት ነዉ እንጂ ሞላ አስገዶም ስለፈለገዉ የሚፈጠር አለዚያ የሚቀር የሞላ አስገዶም የቤት ዉስጥ ዕቃ አይደለም። ደግሞም እንደ ሞላ አስገዶም ፍላጎት ቢሆን ኖሮ የደምህት ጥምረቱ ዉስጥ መግባት ለግዜዉም ቢሆን ሊዘገይ ይችል ነበር። ደምህት ጥምረቱ ዉስጥ ገብቶ አገር አድን የጋራ ንቅናቄዉ የተፈጠረዉ የደምህት ሠራዊትና ከሞላ አስገዶም ዉጭ ሁሉም የደምህት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ከሌሎች ኢትዮጳያዉያን ወገኖቻቸዉ ጋር ሆነዉ በጋራ ለመታገል በመወሰናቸዉ ነዉ። የሞላ አስገዶም ፈርጥጦ ወያኔ ጉያ ዉስጥ የመሸጎጡ ዋነኛዉ ምክንያትም የዚህ ዉሳኔ ዉጤት ነዉ እንጂ የወያኔ መረጃና ስለላ ድርጀት ሚስጥራዊ ግንኙነት ዉጤት አይደለም። ሌላዉ እርስ በርሱ የሚጋጭ የወያኔ ዉሸት – በአንድ በኩል ሞላ አስገዶምና የደምህት ሠራዊት ሙሉ ትጥቃቸዉን እንደታጠቁ ጠቅልለዉ ወደ አገራቸዉ ተመለሱ የሚለዉ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ቁጥሩ ወደ 700 የሚጠጋ የደምህት ሠራዊት ወደ አገሩ ተመለሰ የሚለዉ የተምታታ ዘገባ ነዉ። እዚህ ላይ የደምህትን ሠራዊት ብዛት መናገሩ አስፈላጊ ባይሆንም ግንዛቤ ማግኘት የፈለገ ሰዉ ግን ተመድ ያወጣቸዉን ሪፖርቶች መመልከቱ የሚበቃ ይመስለኛል። ደግሞም ሞላ አስገዶም አታልሎ መንገድ ካስጀመረዉ ሠራዊት ዉስጥ ገሚሱ ወደ ትግሉ ሜዳ ተመልሷል፤ የተቀረዉ ደግሞ ወደ ትግሉ ሜዳ ካልተመለስኩ እያለ ከሱዳን ባልስልጣኖች ጋር እየተደራደረ ነዉ። በነገራችን ላይ የዚህ ጽሁፍ ጸሀፊ ሞላ አስገዶም አታልሎ ሀምዳይት ከወሰዳቸዉ በኋላ ትግል ወይም ሞት ብለዉ ተመልሰዉ ከትግል ጓዶቻቸዉ ጋር ከተቀላቀሉ ጀግኖች ኢትዮጵያዉያን ጋር አብሮ ቡና ጠጥቷል።

ጓዜን ጠቅልዬ ትግሎ ሜዳ ከመግባቴ በፊትም ሆነ ከገባሁ በኋላ የደምህት ስም በተነሳ ቁጥር አብረዉ የሚነሱ ሁለት መላምቶች አሉ። አንደኛዉ መላምት ደምህት የኤርትራ መንግስት ሆን ብሎ የፈጠረዉና ጭራሽ ኤርትራ ዉስጥ የመንግስት የጸጥታ ሀይሎችን ተክቶ በመንግስታዊ ተቋሞች ጥበቃና ደህንነት ስራዎች ላይ የተሰማራ ድርጅት ነዉ የሚል መላምት ሲሆን ሁለተኛዉ መላምት ደግሞ ሞላ አስገዶም በኤርትራ መንግስት ድጋፍ ሁለተኛዉ መለስ ዜናዊ ሆኖ ህወሃትን ተክቶ አትዮጵያን ይመራል የሚለዉ መላምት ነዉ። ደግነቱ የነዚህ መላምቶች የማዕዝን ራስ የሆነዉ ሞላ አስገዶም ኮብልሎ ወያኔን መቀላቀሉና ከተቀላቀለ በኋላ የሰጣቸዉ ጋዜጣዊ መግለጫዎች ሁለቱንም መላምቶች እንዳልነበሩ አድርጓቸዋል። እኔን አልገባ ያለኝና በጣም የሚገርመኝ ግን በአንድ በኩል የኤርትራ መንግስት የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ድርጅቶች ትብብር እንዲፈጥሩ አይፈልግም ይባላል፤ በሌላ በኩል ደግሞ ጥምረቱ የተፈጠረዉ በሻዕቢያ ግፊት ነዉ ይባላል። መቼም ገና በልጅነቴ ካልጃጀሁ በቀር ሻዕቢያና የኤርትራ መንግስት መሃል ልዩነት ያለ አይመስለኝም። ሌላዉ የሰሞኑ አስቂኝ ድራማ ደግሞ ሞላ አስገዶም ጥምረቱን የፈጠርነዉ እኛ ነን ሲል የሱን መኮብለል አስመልክቶ የሚሰጠዉ አስተያያት ደግሞ ሞላ አስገዶም ጨርቁን ጠቅልሎ ወያኔን የተቀላቀለዉ ብርሀኑ ነጋ በኤርትራ መንግስት ግፊት የጥምረቱ ሊ/መንበር መሆኑ አልዋጥ ብሎት ነዉ ይባላል።

ሌላዉ አሁን በቅርቡ ወይም ከሞላ አስገዶም መኮብለል በኋላ የተጠነሰሰዉ መላምት ደግሞ ደምህቶች እራሳቸዉ ኤርትራ ዉስጥ የሚገኙ ተቃዋሚ ድርጅቶች በወያኔ ስርዐት ላይ ወታደራዊ እርምጃ መዉሰድ እንዳይችሉ ሆን ተብለዉ በወያኔ የተፈጠሩ እንቅፋቶች ናቸዉ የሚለዉ መላምት ነዉ። በኔ ግምት ይህኛዉ መላምት ከሁሉም መላምቶች የከፋና እጅግ በጣም አደገኛ የሆነ ጽንፈኛ መላምት ነዉ። እንደዚህ መላምት ፈጣሪዎች አባባል የትግራይ ህዝብ በህወሃት አመራር በደል አይደርስበትም ወይም የትግራይ ህዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያዉያን ወንድሞቹና እህቶቹ ጋር ሆኖ የህወሃትን ግፈኛ ስርዐት አይታገልም ማለት ነዉ። እንዲህ አይነቱ ጭፍንነትና ጠባብነት የሚመነጨዉ ደግሞ ሞላ አስገዶምንና ደምህትን ወይም ህወሃትንና የትግራይን ህዝብ ለያይቶ ማየት ካለመቻል አባዜ ነዉ። በደርግ ስርዐት ዉስጥ ጭቆናዉና በደሉ በዛብኝ ብሎ ጠመንጃ ያነሳዉ ጀግናዉ የትግራይ ህዝብ ህወሃት ከሌሎች ኢትዮጵያዉያን ወገኖቹ ተነጥሎ እንዲታይ ለማድርግ የሚሸርብበትን ሤራና የሚያደርስበትን ግፍና መከራ አፉን ዘግቶ የሚቀበልበት ምንም ምክንያት የለም። ስለዚህ ደምህት የትግራይ ህዝብ ብሶትና ምሬት አምጦ የወለደዉ ፀረ ህወሃት ንቅናቄ ነዉ እንጂ ወያኔ የፈጠረዉ ድርጅት አይደለም፤ሊሆንም አይችልም። ሞላ አስገዶምም ቢሆን የራሱ የተጠረቃቀመ ድክመት ከንቅናቄዉ ሊ/መንበርነቱ እንደሚያስነሳዉ ሲያዉቅ የፈረጠጠ ፈርጣጭ እንጂ እሱና ወያኔ እንደሚሉት የአንድ አመት ቀርቶ የአንድ ወርም ተከታታይ ግንኙነት አልነበራቸዉም።

ወደ ኢትዮጵያ ፖለቲካ መድረከ ብቅ ብለዉ የጠፉትንም ሆነ ዛሬም ድረስ ያሉትን የፖለቲካ ድርጅቶች ባህልና ድርጅታዊ አሰራር ስንመለከት የድርጅቶች ህልዉና መመዘኛና የማንነታቸዉ መለኪያ ቆምንለት የሚሉት አላማ ሳይሆን የመሪዎቻቸዉ በተለይ የዋናዉ መሪ ተክለሰዉነት ነበር። የድርጅት ወይም የፓርቲ ሊ/መንበር ከድርጅቱ ባለይ ነዉ፤ እሱ ይሁን ያለዉ ይሆናል፤አይሁን ያለዉ አይሆንም። ብዙ ግዜ የድርጅት/ፓርቲ ሊ/መንበር ድርጅቱን የማፍረስ አቅም ጭምር አለዉ። ይህንን ደግሞ በቅርብ ግዜ ታሪካችን በተደጋጋሚ አይተናል። አንድን ድርጅት ወይም ፓርቲ አባላት ሲቀላቀሉ የሚመለከቱት የፓርቲዉን ሊ/መንበር እንጂ የፓርቲዉን የፖለቲካና የኤኮኖሚ ፕሮግራም አይደለም። የፓርቲ ሊ/መንበርም ቢሆን የኔ የሚላቸዉን ሰዎች ነበር እየመረጠ የሚያሰባስበዉ። እንደዚህ አይነቱ የፓርቲ አደረጃጀትና አሰራር አሁን እየተቀየረ የመጣ ቢሆንም ለረጂም ግዜ የፖለቲካ ትግላችን ችግር ሆኖ ቆይቷል። ሞላ አስገዶም በቅርቡ የደምህትን ሠራዊት ከነሙሉ ትጥቁ ይዤ ኢትዮጵያ ገባሁ ብሎ በድፍረት የተናገረዉ ንግግር ይሄዉ የድርጅት ሊ/መንበር ያሰኘዉን ሁሉ ማድረግ ይችላል የሚለዉ የቆየ የፖለቲካ ባህላችን በሽታ ተጠናዉቶት ነዉ። “ዝንጀሮዉን ከጫካ ያዉጡታል እንጂ ጫካዉን ከዝንጀሮዉ ዉስጥ አያወጡትም” የሚል ብህል አለ፤ ትክክለኛ ብህል ነዉ። ሞላ አስገዶም ህወሃት/ወያኔ የኢትዮጵን ህዝብ በአጥር እየለያየ በትናናንሽ ጎጆዎች ዉስጥ ማኖሩ አልዋጥ ብሎት ሁሉንም የሚያቅፍ ሰፊ ቤት ሰርተን ኢትዮጵያን የዲሞክራሲ አገር እናደርጋለን ብሎ ለብዙ አመታት የታገለ ሰዉ ነዉ። ችግሩ ሞላ አስገዶም ነዉ ከነዚያ ትናንሽ የወያኔ ጎጆዎች የወጣዉ እንጂ ትናንሽ ጎጆዎቹ ከሞላ አስገዶም ዉስጥ ስላልወጡ እንደ ማግኔት እየሳቡት ወደነበረበት ቦታ መልሰዉታል። ለሁሉም የሞላ አስገዶም ታሪክ ሲጻፍ – መጣና ሄደ ከሚሉ አምስት ሆሄያት የዘለለ ምንም ቁም ነገር የለዉም። እየመጡ መሄድና እየሄዱ መምጣት ደግሞ ትናንሽ ቤት የሚናፍቃቸዉ ትናንሽ ሰዎች እስካሉ ድረስ ይቀጥላል።

ሁለት ሺ ሰባት ሊጠናቀቅ ሦስት ቀን ሲቀረዉ አንድ የብዙ ኢትዮጵያዉያንን ጆሮ የሳበ ዜና ቴሌቪዥኑን፤ ሬድዮኑን፤ ጋዜጣዉንና ድረገጹን ተቆጣጠረዉ። ዜናዉ የወያኔ/ህወሃትን ስርዐት በመሳሪያ ኃይል የሚታገሉ አራት ድርጅቶች አገር አድን የጋራ ንቅናቄ ፈጠሩ የሚል የአዲስ አመት የምስራች ነበር። የኢትዮጵያ ህዝብ ለረጂም ዘመን የናፈቀዉ የምስራች ነበር። ግን ምን ያደርጋል – በጥባጭ እያለ ንጹህ ዉኃ አይጠጣምና ይሀንን የአዲስ አመት የምስራች ሰምተን ሳናጣጥም ነበር የሞላ አስገዶምን ዜና ክህደት የሰማነዉ። አስደንጋጭ ዜና ነበር። በእርግጥም የአራት ድርጅቶች ጥምረት ተፈጠረ የሚል ዜና በተሰማ ማግስት የጥምረቱ ምክትል ሊ/መንበር ሠራዊት እየመራ ሄዶ ወያኔን ተቀላቀለ የሚል ዜና መስማት የሚያስደነግጥና በመጀመሪያዉ ዜና ላይ ቀዝቃዛ ዉኃ የቸለሰ ልብ ሰባሪ ዜና ነዉ። ደግነቱ ሁሉም ነገር ለበጎ ነዉ። የሞላ አስገዶም መክዳት ተራ ዜና ነዉ ማለቴ አይደለም። ግን ሞላ አስገዶምና የወያኔ መረጃ ድርጅት በትብብር ሠራነዉ ያሉት አዲስ ድራማ ተዉኔቱ ሳይጻፍ አየር በአየር የተከወነ ምናቡ ያልተባ ድራማ በመሆኑ ድራማዉ ከያኒዉን ሳይሆን የኢትዮጵያን ህዝብና ለአንድነቱና ለነጻነቱ የሚታገሉ ልጆቹን በከፍተኛ ደረጃ የጠቀመ መሆኑን ማሳዉቁ አስፈላጊ ይመስለኛል።
ደምህት በዚህ የወያኔ ድራማ ዉስጥ በእሳት ተፈትኖ ወርቅነቱን አረጋግጧል። ሞላ አስገዶም የደምህትን ሠራዊት ለወያኔ አስረከብኩ ብሎ በተናገረ ማግስት የደምህት መሪዎች የሰጡት አርቆ አስተዋይነት የታየበት አመራርና ያሳዩት ቆራጥነት የፖለቲካ ድርጅቶቻችን የደረሱበትን የዕድገት ደረጃ በግልጽ አሳይቷል። ደምህት እራሱም እንደ አንድ የትግል ድርጅት የተደቀነበትን አደጋና ፈተና በጣጥሶ በመዉጣት በትናንሾችና በደካሞች ሴራ በፍጹም የማይናጋ ጠንካራ ድርጅት መሆኑን በተግባር አሳይቷል። የዛሬዉ ደምህት ዉስጡን ከአድርባዮች ያፀዳ ሁለትና ሦስት እርምጃዎች ወደፊት የተራመደ ጠንካራ ድርጅት ነዉ። እርግጠኛ ነኝ ይህ የደምህት መሪዎች ያሳዩት አስተዋይነት፤ ጽናትና ቆራጥነት እኔ የምፈልገዉ ነገር ካልሆነ ድርጅቱን በአፍጢሙ እደፋዋለሁ ብለዉ ለሚያስቡ ዕብሪተኛ መሪዎች ጥሩ ትምህርት ነዉ። ሌላዉ የሞላ አስገዶም ክህደት በግልጽ ያሳየን ነገር ቢኖር የኢትዮጵያ ፖለቲካ መድረክ የሀዝብ መብትና ነጻነት ይከበር በሚሉ የነጻነት ሀይሎችና ህዝብን ረግጠን እንገዛለን በሚሉ ፀረ ህዘብ ሀይሎች ለሁለት መከፈሉን ነዉ። ወደድንም ጣላን ካሁን በኋላ ያለን አማራጭ ሁለት ብቻ ነዉ፤ ወይ ወያኔ ሆኖ ከህዝብ ጋራ መዋጋት ወይም ከህዘብ ጋር ሆኖ ወያኔንና ስርዐቱን መዋጋት። ሞላ አስገዶም ጎራዉን ለይቷል፤ እኛም ጎራችንን እንለይ። መኃል ቆሞ መመልከት አብቅቷል።

ጠላቴን አግዝፌ መመልከት አልወድም፤ ትንሽ ነዉ ብዬም ጠላቴን በፍጹም አልንቅም። በቅርቡ የወያኔ የመረጃና ደህንነት መ/ቤትና ሞላ አስገዶም ከአንድ አመት በላይ አብረን ሠራን ያሉትን የጀማሪዎች ስራ ስምለከት ግን ወያኔ/ህወሃት “የምትሰሩትን ብቻ ሳይሆን የምታስቡትን ጭምር የሚያይ አይን አለኝ” እያለ የኢትዮጵያን ህዝብ ከማስፈራራት ዉጭ የረቀቀ የመረጃ ስራ መስራት ቀርቶ አረፍተነገሮችን አገጣጥሞ ለጆሮ የሚጥም ንግግር ማድረግ የሚችል አዋቂ የሌለበት የባዶዎች ድርጅት መሆኑን ነዉ የተረዳሁት። ሞላ አስገዶምም በወዶገባነት ሄዶ የተቀላቀለዉ ይህንኑ አዋቂ የሌለበትን እሱን የመሰለ ድርጅት ነዉ። ይህንን ደግሞ እስከዛሬ በሰጣቸዉ ቃለመጠይቆች በግልጽ አይተናል። ህወሃት/ወያኔን እስከዛሬ በሥልጣን ላይ ያቆዩት ሁለት ነገሮች ቢኖሩ አንዱ ጠመንጃ ሁለተኛዉ የኛ የነጻነት ኃይሎች መበታተን ብቻ ነዉ።

ነገ የምንፈልጋት ኢትዮጵያ እንደ መኪና ተገጣጥማ አትጠብቀንም – የዛሬዉ ጥረታችንና ድካማችን ዉጤት ናት። ኢትዮጵያና ህዝቧ ከወያኔ ሲፀዱ የሚነፍሰዉ የነጻነት አየር ሁላችንንም ቢያስደስትም ደስታዉ የሚገለጸዉ በግለሰብ ደረጃ ነዉ። ዛሬ ከጠላት ጋር ተፋልመን የተቀማነዉን ነፃነት ማስመለስና እንደገና እንዳንቀማ ነቅቶ መጠበቅ ግን የሁላችንም የጋራ ሀላፊነት ነዉ። እንግዲህ ወገን ወገባችንን ጠበቅ የምናደርግበት ግዜ አሁን ነዉና ሁላችንም በየተሰለፍንበት መስክ እንበርታ። ጠላታችን ጠንካራ መስሎ የሚታየዉና ያለ የሌለ ጡንቻዉን የሚያሳርፍብን የማይቀረዉን ድል ማሽተት ስንጀምር ነዉ። የድል መአዛችንን የምናሸትበት ግዜ ደግሞ ሩቅ እንዳይመስለን ነገና ከነገ ወዲያ ነዉ። ከወላዋይና እዚህም እዚያም እየዘለለ ከሚያዘናጋን አጉል ጓደኛ አንዱኑ የለየለት ጠላት ይሻላልና የሞላ አስገዶም ክህደት ትግላችንን ሊያጠራዉና መንገዳችንንም ሊያሳጥረዉ ይገባል እንጂ በፍጹም ግራ ሊያጋባን አይገባም። አይዞን. . . ሞኝ ከዘመዱ ከሚያገኝዉ ጥቅም አዋቂ ከጠላቱ የሚያገኘዉ ጥቅም ይበልጣልና ጠላቶቻችን የፈጠሩልንን አጋጣሚዎች ሁሉ በሚገባ እንጠቀምባቸዉ እንጂ ለጠላት አንመቻች። ጠላታችን እየተሳሳተልን ነዉ፤ ጠላት ሲሳሳት ማቋረጥ ነዉር ነዉ። ቸር ይግጠመን!!!
አፍሬም ነኝ ከአርበኞች መንደር

  የኣንድነት ችቦ እየተንቦገቦገ ነው –ከአቶ ቸሩ ላቀው

$
0
0

 

unityከወያኔ የዘር ኣገዛዝ በፊት የኢትዮጵያ መለዮ ለባሾች ከሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች የተውጣጡ ስለነበሩ ከሥልጠና ቦታቸው ጀምሮ በየደረሱበት የውጊያ ዐውደ ግንባርና የጦር ሠፈር ኑሮኣቸው እንደ ወንድማማች፣ እህትማማችና ጓደኛሞች የሚተያዩ  ነበሩ እንጂ የዘር ቆጠራ ውስጥ ኣይገቡም ነበር። ኣብሮ መብላትና መጠጣት፣ ኣብሮ መዝናናትና ለሞትም ሆነ ለድል ኣብሮ መሰለፍን ዓላማቸው ኣድርገው የሚንቀሳቀሱ ነበሩ። የትግል ኣጋራቸውን ሕይወት ከተቃራኒው ጦር ኣረር ለማዳን እንጂ ጓደኛቸውን መግደልና ማስገደል እንኳን ሊደረግ ታስቦም ኣያውቅም ነበር።

ወያኔ ሥልጣን ከያዘ በኋላ ችግር ሳይኖር ራሱ በራሱ ላይ ችግር በመፍጠሩ ሁለት ኣጣብቂኝ ውስጥ ገባ። ሌሎችን ማመን ስለኣልቻለ ማንኛውንም እንቅስቃሴ በትግራይ ተወላጆች ብቻ ለማንቀሳቀስም ዓላማው ነበር። መለዮ ለባሾቹንም በትግራይ ተወላጆች ብቻ እንዳያዋቅር በቂ ሊሆኑለት ኣልቻሉም። ስንቱ ቦታ ይሰለፋሉ። በሆኑለት ደስ ባለው ነበር። ስለሆነም ሌሎችን በሁለተኛ ዜጋነት ቀጥሮ  ማሠራቱ ኣይቀሬ ሆነበት። የትግራይ ተወላጅ የሆኑት ግን በመሪነት እንዲያገለግሉ ኣደረገ።

ይኸ የትግሬዎችን በበላይነት የማየቱ ተንኮል ሌሎችን እንዳያስነሳበት እያንዳንዱን ብሔር በጥርጣሬ እንዲተያዩ  የዘር ልዩነት መርዝ ጋታቸው። ስለሆነም ሁሉም እንደ ጭዳ በግ ወደ እርድ መነዳት ሆነ። ኣትግደለኝ፣ ኣታግለኝ፣ ኣታንገላታኝ፣ መብቴን ጠብቅልኝ፣ ወዘተ የሚል የመብትና የዜግነት ጥያቄዎች በራቸው ተዘጋ። የጋራ ጠላታቸውን ለመፋለም መዘጋጀት ሳይሆን እርስ በርስ እንዲፋጠጡ ሆነ። ሲዘምቱ ግን ወርቃማዎቹ ከኋላ ሆነው ወደፊት እያሉ ይነዱኣቸዋል፣ ወደ እሳቱ ይማግዱኣቸዋል። እንደ እንስሳ የተጠመዱ ፈንጂዎች ላይ እንዲሔዱ ኣደረጉኣቸው። የፈንጂ መሞከሪያ ኣደረጉኣቸው። የጠላት ጦር ሳይገድላቸው ራሱ ወያኔ ገዳያቸው ሆነ። እኔ ልቅደም፣ እኔ ልቅደም ይባባሉ ነበር እንጂ ኣንዱ ሌሎችን ወደ እሳት ወላፈን የሚገፈትርበት ጊዜ ኣልነበረም። ያንን ጊዜ ወያኔ እንደ ኋላቀር ቆጠረው።

በወርቃማው ዘር ላይ ተንተርሶ  በመሣሪያ ኃይል ሀገሪቱን የሚያሽከረክረው የወያኔ መንግሥት በሰሜን ጎንደር፣ በሰሜን ወሎና በሰሜን ኣፋር እያደረገ እንዳለው ጨርቆቹ ቢያልቁለት መሬቱ ስለሚለቀቅለት ወርቃማዎቹን ያሰፍርበታልና ጦርነትን ይፈልጋል፣ በሰበቡ ጨርቆቹ እንዲያልቁለት ይፈልጋል። “የማትረባ ፍየል ዘጠኝ ትወልዳለች፣ እነርሱም ያልቃሉ እርሷም ትሞታለች።” እንደተባለው ወያኔ መራሹ መለዮ ለባሽ እስከ ዛሬ ባየው የዘር ፖለቲካና የነርሱ መገለል ቆም ብለው እንዲያስቡ እያደረጋቸው ጀርባቸውን እየሰጡ ናቸው። ወያኔዎቹ በለኮሱት እሳት ራሳቸው ይቃጠሉበት እንጂ እኛ በምን ተዕዳችን እያሉ ናቸው። ወያኔ የማይሆንና ሊሆንም የማይችል መርዝ ላለፉት 24 ዓመታት ቢረጩም ለጊዜው ትንሽ ተሳክቶለት ቢፈነጩም ዘለቄታ ኣላገኘም። ኣሁን ወደ ዜሮ እየወረደ ነው።

ወያኔ ላለፉት ኣርባ ዓመታት የኢትዮጵያውያንን ኣንድነትና ኣብሮነት ለማፍረስ እየጣረና እያስገደደም እስከ ዛሬ ቢለፋም ሊሳከለት ኣልቻለም። እንዲያውም ራሱን እየለበለበው ከመሆንም ኣልፎ በሰሜኑ ኢትዮጵያችን በኩል የሚያቃጥለው የኣንድነት መሠረት ተጥሎ  ወደርሱ እየገሠገሠ ነው። ይህ ወያኔን እንደ ጎርፍ ውሃ ጠራርጎ  የሚወስደው በጠንካራ መሠረት ላይ የተጣለው የኣንድነት ኃይል በቅርቡ እንደታየው የተቃዋሚው  ሕዝባዊ ኃይል ከየብሔረሰቡ የተውጣጣ ሆኖ ተገኝቷል። የኢትዮጵያን ሕዝብ ኣብሮነት ሊያለመልም ነው። ዱብ ዕዳ ሆኖበት ሊዋጥለት ያልተቻለውን ኣንድነትን የማፍረስ ዘመቻ የሚያፈርሱ ኃይሎች መፈጠራቸው የወያኔን መንደር እያፈራረሰው ነው። ይህ የሚያሳየን ወያኔ ለማፍረስ ደፋ ቀና ሲል የቆየውን የኣርባ ዓመት ትግል ድባቅ መታበት።

ወያኔ ከሰውም፣ ከእንስሳቱና ከደኖቹም ጋር የተጣላ ስለሆነ ተግባሩ መቀበሪያ ቦታም ሊያሳጣው ነው። ግዑዟንም መሬታችንን ደኖቿን ኣቃጥሎ ያራቆጣትና ያጎሳቆላት ስለሆነ ሲሞቱም ለመቃብራቸው ኣትመቻቸውም። ትተፋቸዋለች። ሬሳቸውን ኣውሬዎችና ኣሞራዎችም ኣይበሉም። እነርሱንም መከለያ ወይም መጠለያ ኣሳጥተዋቸዋልና ይጠየፉኣቸዋል።

ቸሩ ነኝ

ቸር ይግጠመን

abatemsas@gmail.com.

ኢሕአዴግ በአዲስ አበባ አስተዳደር ሹም ሽር እያካሄደ ነው

$
0
0

(ሪፖርተር) የአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት አብዛኛዎቹን የክፍላተ ከተሞችና የወረዳ አመራሮች በማንሳት፣ በአዳዲስ አመራሮች እየተካ መሆኑ ታወቀ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሁለተኛውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ለማሳካትወረዳዎችና ክፍላተ ከተሞች መመራት ያለባቸው ዲፕሎማና ከዚያ በላይ የትምህርት ደረጃ ባላቸው መሆን አለበት የሚል አዲስ አቋም መያዙ፣ ለሹም ሽሩ ምክንያት መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

Photo File

Photo File

በዚህ መሠረት በአሥሩም ክፍላተ ከተሞችና በሥራቸው በሚገኙ 116 ወረዳዎች የሚገኙ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አመራሮች ተነስተዋል፡፡ በተጨማሪም ሹም ሽሩ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰፈነውን የመልካም አስተዳደርና የሙሰኝነት ችግር ለመቅረፍ መንግሥት ከያዘው ዕቅድ ጋር የሚያያዝ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

ይህን ችግር ለመቅረፍ በቅድሚያ ይህ ችግር ያለባቸው አመራሮች ተገምግመው እንዲነሱ መደረጉም ተገልጿል፡፡ ለማሳያ ያህል በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከሚገኙ 12 ወረዳዎች ከዲፕሎማ በታች ያላቸው አመራሮች 70 የሚጠጉ ሲሆን፣ እነዚህ ሁሉ እንደተነሱ ተገልጿል፡፡ በሙስናና በተለያዩ ግድፈቶች ደግሞ 30 አመራሮች እንዲነሱ መደረጉም ተመልክቷል፡፡

በሌሎች ክፍላተ ከተሞችና በሥራቸው በሚገኙ ቀበሌዎችም በተመሳሳይ ከ100 ያላነሱ አመራሮች በእነዚህ ሁለት ምክንያቶች መነሳታቸው ተገልጿል፡፡ ይሁንና ከዲፕሎማ በታች የትምህርት ደረጃ ኖሯቸው አመራር ሲሰጡ የቆዩ አባላት ቅሬታ አቅርበዋል፡፡ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉት እነዚህ አመራሮች ትምህርት ለመማር ጥያቄ  በሚያቀርቡበት ወቅት መንግሥት ቅድሚያ ሥራችሁን ሥሩ የሚል ምላሽ የሰጣቸው በመሆኑ ትምህርት መማር እንዳልቻሉ አስታውሰው፣ ውሳኔው ፍትሐዊ እንዳልሆነ ጠቁመዋል፡፡

በአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ይህንን አለመግባባት ለማስቀረት የውይይት መድረኮች ፈጥሮ እንደነበርም ታውቋል፡፡ በዚህም ያላቸው የትምህርት ደረጃ ዝቅተኛ በመሆኑ የተነሱ አመራሮች የሦስት ወራት ደመወዝ፣ በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅተው ሥራዎችን እንዲሠሩ ወይም ዕድሜያቸው ለጡረታ የደረሰው ደግሞ በጡረታ እንዲገለሉ ሐሳብ ቀርቦ፣ ከሞላ ጎደል መግባባት ላይ መደረሱ ተመልክቷል፡፡

ዋነኛው የአዲስ አበባ ከተማ ችግር የመልካም አስተዳደር እጦትና ኪራይ ሰብሳቢነት [ሙስና] እንደሆነ ነዋሪዎች ባገኙት አጋጣሚ ሲገልጹ ቆይተዋል፡፡ ይህ ችግር የ2007 ዓ.ም. የሥራ አፈጻጸም በሚገመገምበት ወቅት በሰፊው ተነስቷል፡፡ በተለይ በመሬት፣ በንግድና በአገልግሎት መስጫ ዘርፎች ላይ ኅብረተሰቡ ከፍተኛ እሮሮ በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡

በእነዚህ ዘርፎች ለተገልጋዮች ተገቢውን አገልግሎት አለመስጠት፣ ተገልጋዮችን ለማስተናገድ ዝግጁ አለመሆን፣ ለሚቀርቡ ቅሬታዎች አፋጣኝ ውሳኔ አለመስጠት፣ ‹‹ጉዳዩ አልታየም›› በማለት ተገልጋዮችን ማጉላላትና ጉቦ መጠየቅ ከሚቀርቡት ቅሬታዎች መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡

በንግድ በኩል የንግድ ፈቃድ ዕድሳት፣ የንግድ ስያሜ አሰጣጥ፣ የንግድ አድራሻ ማረጋገጫ አሰጣጥ፣ ሕገወጥ ንግድ በሰፊው የሚታዩ ችግሮች ከመሆናቸውም በተጨማሪ፣ በአጠቃላይ የንግድ ሥርዓቱ የተተረማመሰ እንደሆነ ቅሬታ ይቀርባል፡፡

በእነዚህ ሁሉ ችግሮች ሙስና ዋነኛ መገለጫ መሆኑ ከኅብረተሰቡ በሰፊው የሚነሳ ጉዳይ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ይህንን የኅብረተሰብ ሮሮ በመቀበል፣ የራሱን ግምገማ አካሂዶ ችግሩ እንዳለ አምኗል፡፡ ችግሩን ለመቅረፍ ከሕዝብ ጋር ተወያይቶ ወደ ተግባር እንደሚገባ ገልጾ ነበር፡፡

ይህንን ችግር ለመፍታት በተካሄዱ ተከታታይ ግምገማዎች ግድፈት እንዳለባቸው የተለዩ አመራሮችን ከክፍላተ ከተሞችም ሆነ ከወረዳዎች ማንሳት ዋነኛ ዕርምጃ ሆኗል፡፡

በዚህ መሠረት ቢያንስ ችግሩ ጎልቶ በሚታይባቸው ክፍላተ ከተሞች ከ30 በላይ አመራሮች፣ በወረዳ ደረጃም በተመሳሳይ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አመራሮች እንደተነሱ ምንጮች ተናግረዋል፡፡

ይሁንና በአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ባለቤትነት የሚካሄደው ይህ ሹም ሽር ባለፈው ሳምንት መገባደዱን መረጃዎች አመልክተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተወልደ ገብረ ፃድቃን ሥራው እየተካሄደ መሆኑን ለሪፖርተር አረጋግጠው፣ ሥራው ባለመጠናቀቁ መረጃ ለመስጠት እንደማይችሉ ገልጸዋል፡፡

ከዚህ በመቀጠል የአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት በማዕከል ደረጃ የሚገኙ ቢሮዎችንና ኤጀንሲዎችን የሚመሩ አመራሮች ላይ ሹም ሽሩን እንደሚቀጥልም ተገልጿል፡፡ ሹም ሽሩ በርካታ አመራሮችን ከካቢኔ የሚያስወጣና በምትካቸው አዳዲስ የካቢኔ አባላትን እንደሚሾም ምንጮች ተናግረዋል፡፡

የካቢኔ አባላቱ ሹም ሽር በቅርቡ ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ቀርቦ ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ትህዴን በአንድ ሳምንት ብቻ 19 ከትግራይ ክልል የመጡ ወጣቶች እንደተቀላቀሉት አስታወቀ

$
0
0
Photo File

Photo File

የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ እንዳስታወቀው በአንድ ሳምንት ብቻ 19 የትግራይ ተወላጆች እንደተቀላቀሉት አስታወቀ:: በዚህ ሳምንት ውስጥ የህወሃት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግን ስርዓት በመቃወም በርካታ ወጣቶች ወደ ትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ድርጂት መቀላቀላቸውን ከማሰልጠኛ ማዕከል የደረሰን መረጃ አመለከተ።

ደህሚት በድረገጹ እንዳስታወቀውና ከድርጅቱ ደረሰኝ ባለው መረጃ መሰረት የወያኔን ከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ በመቃወም በርካታ ወጣቶች ወደ ማሰልጠኛ ማዕከል መቀላቀላቸውን የገለፀ ሲሆን የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል
1 ተክላይ ታፈረ ገብረዋሂድ ከትግራይ ማዕከላዊ ዞን ናዴር አዴት ወረዳ አዲ ላኪያን ቀበሌ አዲ በዛ አካባቢ
2 በሪሁ ገብረየሱስ ሃድጉ ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን ጉሎ መከዳ ቀበሌ አዲስ ተስፋ ሰፈር ደንጎሎ ከተባለው መንደር
3 ነፀረ-አብ አባዲ ፍስሃ ከሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ታህዳይ አድያቦ ወረዳ ገመሃሎ ቀበሌ ሁመር ከተባለው ሰፈር
4 ፍስሃ ገብረስላሴ ገብረ መድህን ከማዕከላዊ ዞን አህፈሮም ወረዳ ቤተ ገበዝ ቀበሌ ዝባን እንዳቦይ ገብራት ከተባለው አካባቢ
5 ጉዑሽ ሃይለ ገብረስላሴ ከስሜን ምዕራብ ዞን ታህታይ ቆራሮ ወረዳ ማይ አድራሻ ከተባለው ቀበሌ
6 አወት ገዛኢ ፈዳይ ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን ጉሎመከዳ ወረዳ ዛላንበሳ ከተማ
7 ክብሮም ገብረ ፃድቅ ረዳ ከማዕከላዊ ዞን መረብ ለኸ ወረዳ አድፍታው ቀበሌ አዲ ቀረዲሂም ከተባለ መንደር
8 በሪሁ አብረሃ ተላ ከትግራይ ደቡባዊ ዞን አምባላጀ ወረዳ ስስት ቀበሌ ከታረ ከተባለው ሰፈር
9 በረከት ገብረ ኪዳን ወልደማሪያም ከትግራይ ማኦከላዊ ዞን ናአዴር አዴት ወረዳ አዲ ለኪያን ከተባለው ቀበሌ
10 ሚኪኤሌ ካህሳይ በርኸ ከትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ታህታይ አድያቦ ወረዳ አዲ ፀፀር ከተባለው ቀበሌ
11 ፀጋይ ሃፍታይ ከምስራቃዊ ዞን ክልተ አውላሎ ወረዳ ፅጌረዳ ቀበሌ
12 ከድር ወህበይ አብራር ከሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ታህታይ ቆራሮ ወረዳ አድ ብዘት ከተባለው ቀበሌ ብዘት አካባቢ እምቢሉ ከተባለው መንደር
13 ሃጎስ ገብረ ዮሃንስ ንጉሴ ከማዕከላዊ ዞን መረብ ለኸ ወረዳ አወት ቀበሌ
14 ግደይ ወልደሚካኤል ወልደማሪያም ከሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ሽረ ወረዳ ሰመማ ቀበሌ
15 አሸናፊ ገብረየሱስ ወልዱ ከምስራቃዊ ዞን ጉሎ መከዳ ወረዳ አዲስ አለም ቀበሌ አዲ ገናህ ከተባለው አካባቢ
16 ዘነበ አለም ገብረ ሚካኤል ከሰሜን ምዕራብ ታህታይ አድያቦ ወረዳ ባድመ ቀበሌ
17 ገብረ ሂወት ጉዕሽ ገብረ መስቀል ከማዕከላዊ ዞን መረብ ለኸ ወረዳ ራማ ቀበሌ ሰፈር 03
18 መብርሃቶም ሃዲሽ ተክለ ከሰሜን ምዕራብ ዞን ላእላይ አድያቦ ወረዳ አድክልተ ቀበሌ ገዛ ስቃ ከተባለው መንደር
19 ክብሮም ተሾመ ክንፈ ከማዕከላዊ ዞን መረብ ለኸ ወረዳ ማይ ወዳምበራይ ቀበሌ አዲገባ እና ሌሎችም ሲሆኑ በተለይ ፍስሃ ገብረ ስላሴ ስርዓቱን እንዲቃወም ያስገደደውን ምክንያት ሲናገር ስርዓቱ አገዛዙን ለማስረዘም ሲል ብድር በመስጠት ሞዴል ተሸላሚ ናችሁ ብሎ ሲያበቃ እንደገና ተገልብጦ በተላላኪዎቹ ተጠቅሞ አቶ ገብረእግዜር ጋዕሲ የተባለውን ንፁህ ዜጋ የቀፎ ንቡን በማላታይን ሲያጠፉ በማየቱ መሆኑን ገልፀዋል።
ሰልጣኝ ጉዕሽ ሃይሉ ገብረስላሴ በበኩሉ ባለፈው ምርጫ አረና የተባለውን ድርጂት የመረጡ ዜጎች ከመሬት እደላ እንደተከለከሉ ከገለፀ በኋላ ቀደም ሲልም በብድር የተሰጡ ወገኖችን ጊዜው ሳይደርስ መልሱ እያሉ እያሰሩ ያሰቃዩአቸው እንደነብር ገልፀዋል።

ለመላው የእስልምና ዕምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፥እንኳን ለ፲፬፻፴፮(1436)ኛው የኢድ አል-አድሃ በዓል አደረሳችሁ!

$
0
0

moresh

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት                                 

ረቡዕ መስከረም ፲፪ ቀን ፪ሺህ፰ ዓ.ም.

ለአላህ (ፈጣሪ) ቃል መገዛት የሕይዎት መስዋዕትነትን እስከመክፈል ድረስ ተገቢ መሆኑን ለሚያስገነዝበው ታላቁ የአረፋ በዓል እንኳን አደረሣችሁ፤ ኢድ ሙባረክ! የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ በመላው ኢትዮጵያዊ በተደረገበት የማያቋርጥ ተፅዕኖ ምክንያት በዚህ ዓመት መጀመሪያ ከፍትኅ አፈላላጊ ኮሚቴ አባሎች መካከል ጥቂቶቹን መፍታቱ ይታወቃል። ሆኖም አሁንም ቢሆን ምንም ወንጀል ሳይፈፅሙ በትግሬ-ወያኔ አገዛዝ የእሥር ጉሮኖ የሚማቅቁ አያሌ ሙስሊም ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን ስላሉ እነርሱ በሙሉ ከእሥር እስኪፈቱ ድረስ ሰላማዊ ተቃውሞው መገታት አይኖርበትም።

የትግሬ-ወያኔዎች ግፈኛ እና ዘረኛ አገዛዝ ባለፉት ዓመታት የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈፀመባቸውን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን አስታውሷቸው፤ ደማቸውም ደመ-ከልብ ሆኖ እንዳይቀር ድምፃችንን ለዓለም ማኅበረሰብ ከፍ አድርገን እናሰማ። የአረፋ በዓል ላጡ፣ ለነጡ ወገኖች ችሮታ የሚደረግበት በዓል ነውና፣ በዚህ የጉግ-ማጎግ አገዛዝ የዘር ማጽዳት ዘመቻ ለሚፈናቀሉት ኢትዮጵያውያን ሁሉ ሰብዓዊ የዕርዳታ እጆቻችሁን ዘርጉላቸው። በዚህ አጋጣሚ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት በዓሉ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን የደስታ እና የታላቅ ተስፋ ዕለት እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቱን ይገልፃል።

ኢድ ሙባረክ!

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live