Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

አስመራ ተጉዘው የነበሩት ሁለቱ የኢሳት ጋዜጠኞች ስለ ሞላ አስገዶም መክዳት ምን አሉ?

$
0
0

በአዲስ ዓመት ዋዜማ ኢሳት ያሰማው ሰበር ዜና አነጋጋሪ ሆኗል:: ውህደት ተፈጸመ የሚለው ዜና 3 ሌሊት ሳያልፍ ይህ ዜና ብዙዎችን እያነጋገረ ነው:: ስለታጋይ ሞላ አስገዶም አስመራ ሄደው አግኝተውት የነበሩት ሁለቱ የኢሳት ጋዜጠኞች ፋሲል የኔዓለም እና መሳይ መኮንን ምን ይላሉ? ያንብቡት::

ፋሲል የኔዓለም ስለ ሞላ አስገዶም:-

Mola asgedom copyየደሚህቱ ሞላ አስገዶም መክዳቱን ስሰማ በእጅጉ ተገርሜአለሁ። ከቀናት በፊት ሞላ ፣ ሰው አክባሪ፣ ተግባቢና አገሩን የሚወድ ሰው መሆኑን ጽፌ ነበር። ኤርትራ በነበርኩበት ጊዜ ደጋግሜ አግኝቸዋለሁ ፣ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ጊዜ ወስደን ተነጋግረናል። እስከዛሬዋ ቀን ድረስ ስለሞላ የነበረኝ አመለካከት ቀደም ብዬ የገለጽኩት ነው። ስለእውነት እመሰክራለሁ፣ ኤርትራ በነበርኩበት ወቅት አንድም ቀን በሰላይነት እንድጠረጥረው ወይም በወያኔነት እንድፈርጀው የሚያደርግ ነገር አላነበብኩም። ከህወሃት ጋር የሚጋራቸው አቋሞች ቢኖሩም፣ በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የማይናወጽ አቋም እንዳለው፣ ህወሃት ኢትዮጵያን ታሪክ አልባ በማድረጉ በጣም እንደሚያዝን ነግሮኛል። ከእርሱ ጋር የተግባባንበት የመጨረሻው ነጥብም ይህ ነበር- ህወሃት ኢትዮጵያን ከመበታተኑ በፊት እንድረስላት። ጥምረትን በተመለከተም በተወሰነ ደረጃ አስፈላጊነቱን ያምናል። ደሚት ያለውን የሰራዊት ብዛትና ሃብት ሲያስበው ደግሞ፣ ከደሚህት ያነሰ የሰራዊት ቁጥር ካላቸው ጋር ይጣመሩ የሚለውን ለመቀበል ሲቸግረው አይቻለሁ። በሌላ በኩል ደግሞ ወደ አማራው ክልል ዘልቆ ለመግባት አርበኞች አስፈላጊ ናቸው ብሎ ያምን ነበር፤ ለዚህም ሲል መጣመሩን ይፈልገዋል። እንደሰማሁት ከአርበኞች ግንቦት7ና ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በነበረው ድርድር፣ መጀመሪያ ላይ ባይደግፈውም፣ በራሱ አመራሮች በድምጽ ብልጫ ከተሸነፈ በሁዋላ ውሳኔውን ተቀብሎ ነበር ። ሞላ ” ጥምረቱን የደገፉት ጓደኞቼ በሂደት ያባርሩኝ ይሆናል” የሚል ስጋት ሳይገባው አልቀረም። እነ ፕ/ር ብርሃኑ ወደ ኤርትራ ወርደው ተቃዋሚዎችን ያስተባብራሉ ብሎ የጠበቀም አይመስለኝም። ምንም ይሁን ምን ሞላ የከዳው ከስልጣን ጋር በተያያዘ መሆኑን አምናለሁ። እኔ ኤርትራ በነበርኩበት ወቅት ከደሚህት ጋር የሚደረግ ድርድር ስላልነበር፣ ስለ ስልጣን ፍላጎቱ ልናገር አልችልም ። እንደሰማሁት በደሚት ውስጥ በርካታ አመራሮች አሁንም አሉ። የወጣው ሰራዊት ጥሎት ከወጣው ሰራዊት ጋር ሲነጻጸር ኢምንት መሆኑን አንዳንድ ሰዎች ነግረውኛል። ይህ ሰራዊት የአገር አድን ሰራዊቱ አካል ሆኖ የሚቀጥል ይመስለኛል። በነገራችን ላይ የደሚህት ሰራዊት ኢትዮጵያዊ ቅርጽ አለው፤ ሁሉንም ብሄረሰቦች አቅፎ የያዘ ነው። እንዲያውም ትዝ አለኝ፣ ደሚህት የተለያዩ ብሄረሰቦችን በአባልነት ይዞ እያለ እንዴት የትግራይ ነጻ አውጭ ተብሎ መጠራቱ ትክክል አይመስለኝም፣ ስማችሁ እየጎዳችሁ ነው ብየዋለሁ። ለማንኛውም፣ ፖለቲካ እንዲህ ነው። እስከመጨረሻው የጸና ብቻ እርሱ ያሸንፋል። መልካም አዲስ አመት።
መሳይ መኮንን ስለ ሞላ አስገዶም:-
ትግሉ የምር መሆኑን የሚያመላክቱ ምልክቶች እየታዩ ነው:: በባህላዊ መንገድ ሲታገሉ ስንዝር መሄድ ያልቻሉ የዕውነቱ ቀን ሲመጣ መንገዋለላቸው የሚጠበቅ ነው:: አዲሱ ንቅናቄ የሚያራግፈውን እያራገፈ ወደፊት ማለቱ አይቀርም:: ህወሀቶች በዚህ ከፈነጠዙ: የነጻነት ታጋዮችን የሚደግፉ ኢትዮጵያውንም በዚህ ከተሰበሩ ሁለቱም ተሳስተዋል:: ከግለሰብ የወረደ በድርጅት የሚመራ ትግል መስመሩን ይዟል:: ነገ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ወደ ህወሀት ቢገባ የሚቆም ትግል አይደለም እየተካሄደ ያለው:: ህዝብ ልቡ ለነጻነት ከቆመ: ህይወቱን ለመስዋዕት ካዘጋጀ ማን ያቆመዋል?


የዘ-ሐበሻ የዓመቱ ምርጥ ስፖርተኛ –ገንዘቤ ዲባባ

$
0
0

genzebe 1
የ23 ዓመቷ አትሌት ገንዘቤ ዲባባ የዘ-ሐበሻ የዓመቱ ምርጥ ስፖርተኛ ሆናለች:: ገንዘቤ በ2007 ዓ.ም አመርቂ የሆነ ውጤትን አስመዝግባለች:: ባለፉት 8 ዓመታት የአትሌትነት ቆይታዋም በርካታ ድሎችን አጣጥማለች:: ገንዘቤን ዘንድሮ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ በርካታ ትልቅ ስፖርተኞች መካከል የሚያደርጋት በአንድ ሳምንት ውስጥ ሁለት የዓለም ክብረ ወሰኖችን መስበሯ ነው::

ባለፈው ጥር ላይ በስዊድን ስቶክሆልም ከ1993 ዓ.ም ጀምሮ ያለተሰበረውን የ3 ሺህ ሜትር ሩጫ ሪከርድ ሰብራለች:: እንዲሁም ይህን ድል ካጣጣመች ከ4 ቀን በፊትም እንዲሁ በ1500 ሜትርን ሪከርድ ሰብራለች:: አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው በፓሪስ የአምስት ሺህ የዳይመንድ ሊግ ውድድር በአንደኝነት ያጠናቀቀችውም በዚሁ በተሰናባችሁ 2007 ዓመት ሰኔ ወር ላይ ነበር:: ሰኔ 27፣2007 ምሽት በተደረገው 8ኛው ዙር የዳይመንድ ሊግ ውድድር ገንዘቤ ርቀቱን በ14 ደቂቃ ከ15 ሰከንድ ከ41 ማይክሮ ሰኮንድ በመግባት ነበር ያጠናቀቀችው፡፡ ገንዘቤ የእህቷን ጥሩነሽን ክብረወሰን ትሰብራለች ተብሎ ቢጠበቅም ሳይሳካላት ቀርቷል። የጥሩነሽ ክብረ ወሰን ለመስበር 4 ሰከንድ ብቻ ነበር የቀራት።

አትሌት ገንዘቤ ዲባባ ሞናኮ ውስጥ በተካሄደ የዳይመንድ ሊግ ውድድር በ 1500 ሜትር አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ያስመዘገበችውም በዚሁ ዓመት ሰኔ ወር ላይ ነበር::

ገንዘቤ በዚሁ በተሰናባችሁ 2007 ዓ.ም ቤጂንግ ላይ በተደረገው የዓለም ሻምፒዮና ላይ አንድ ወርቅ እና አንድ ነሃስ ሜዳሊያ ለሃገሯ ያስገኘች ጠንካራ አትሌት ናት:: የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች የዓመቱ ምርጥ ስፖርተኛ በሚል መርጠዋታል:: እንኳን ደስ ያለሽ::

የዘ-ሐበሻ አመቱ ምርጥ አርቲስት –ቴዲ አፍሮ

$
0
0

teddy afro

የአመቱ ምርጥ አርቲስት – ቴዲ አፍሮ

ቴዲ አፍሮ “ሚስማር በመቱት ቁጥር ይጠብቃል” እንደሚባለው ሆኗል:: በመንግስት የሚደርስበት ጫና ይበልጥ ተወዳጅ እንዲሆን እያደረገው ነው:: በዚሁ ዓመት መጀመሪያ አካባቢ ላይ 70 ደረጃ የሚለውን ነጠላ ዜማ ከለቀቀ ወዲህ የሕዝብ ጆሮን አግኝቶ ነበር:: ጥቅምት 3 ቀን 2015 ዓ.ም ወደ ውጭ ሃገር ለኮንሰርት ዝግጅት ላይ በነበረበት ወቅት ድንገት ፖሊሶች አስረውት ነበር:: ምክንያታቸውም ከዚህ ቀደም ቴዲ አፍሮ- ከዓመታት በፊት የጎዳና ተዳዳሪ ገጭቶ ገድሏል የተባለበት ቢኤምደብሊው የቤት አውቶሞቢል ቀረጥ ሳይከፈልበት የገባ ነው በሚል በገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን መርማሪ ቡድን በቁጥጥር ሥር ዋለ:: በ30 ሺህ ብር ዋስም ተለቀቀ:: የሚገርመው ይህ ክስ ከብዙ ዓመታት በፊት መመስረቱ ብቻ ሳይሆን መኪናው በአሁኑ ወቅት በአርቲስቱ እጅ አለመኖሩም ጭምር ነው::

ቴዲ አፍሮ በዚህ ዓመት ‘አልሄድ አለ’ እና ‘ኮርኩማ’ አፍሪካ የተሰኙ መል ዕክት ያላቸውን ተወዳጅ ዘፈኖቹን አበርክቶልናል:: ሁለቱም ዘፈኖቹ እጅግ ተወዳጅ ሆነውለታል::

በዚህ ዓመት በቴዲ አፍሮ ላይ ከፍተኛ ጫና የተደረገበት ሲሆን ከዚህም ውስጥ የአውሮፓው ኮንሰርቱ እንዲስተጓጎል የተደረገበት ነው:: ከሃገር ሊወጣ ሲል ፓስፖርቱን ከሕግ ውጭ በደህንነቶች የተቀማው ቴዲ በአውሮፓ ማቅረብ የነበረበትን ኮንሰርት በዚህ ሳቢያ በመሰረዙ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል:: በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ሳይባል ደህነነቶች ‘ልክ እናስገባሃለን’ በሚል ፓስፖርቱን የተቀማው ቴዲ እየደረሰበት ያለውን ጫና ዘፈኑ ገልጾታል እየተባለ ነው:: “አልሄድ አለ” የሚለው ነጠላ ዜማውም ለራሱ የሰራው ነው እየተባለ ይነገራል::

ቴዲ በአዲስ ዓመት ዋዜማ በአዲስ አበባ ላፍቶ ሞል ሊያቀርበው የነበረው ኮንሰርቱ በፖሊስ ምክንያት እንዲሰረዝ ተደርጓል:: ለስርዓቱ ቅርብ የሆኑት ማዲንጎ አፈወርቅ እና አስቴር አወቀ ኮንሰርት እንዲያቀርቡ ሲፈቀድ ቴዲ በመከለከሉ የተቆጡት ኢትዮጵያውያን ኮንሰርቱን በፌስ ቡክ ለማድረግ ቆርጠው ተነስተዋል::

ቴዲ አፍሮ በዘ-ሐበሻ አንባቢዎች የአመቱ ምርጥ ሰው ሽልማትን አግኝቷል:: እንኳን ደስ ያለህ::

የማለዳ ወግ …በመካው የካዕባ መስጊድ የደረሰው ልብ ሰባሪ አሳዛኝ አደጋ! * ከ100 በላይ ሞተዋል ፣ ከ200 በላይ ቆስለዋል

$
0
0

meka

የሕወሓት መንግስት የሞላ አስገዶምን መኮብለል ተከትሎ የኤርትራ መንግስት ጉያ ውስጥ ሆኜ የተሳካ ሥራ ሰርቻለሁ አለ

$
0
0

Mola asgedom copy
ኢሳት የደህሚቱ መሪ ሞላ አስገዶም የተወሰኑ ግብረአበሮቹን አስከትሎ ኢትዮጵያ ገባ የሚለውን ዜና ማሰማቱን ተከትሎ የሕወሓት መንግስት በልሳኑ በኢትዮጵያ ፈርስት በኩል ባሰራጨው ዘገባ “የሻዕቢያ ጉያ ውስጥ ገብቼ በግንቦት 7 እና በኤርትራ መንግስት በኩል የሚደረጉትን ሁሉ በመከታተል የተሳካ ሥራ ሰርቻለሁ” አለ::

የሕወሓት መንግስት የሞላ አስገዶምን ከኤርትራ መኮብለል አስመልክቶ በኢትዮጵያ ፈርስት በኩል ባሰራጨው ዘገባ በኤርትራ ውስጥ የተለያዩ ሰዎችን በመመልመል አርበኞች ግንቦት 7 እየሰራ ያለውን ለመበታተን የተሳካ ሥራ ሰርቻለሁ ሲል ገልጿል::

ኢሳት ሞላ አስገዶም ኢትዮጵያ ገብቷል ሲል ኢትዮጵያ ፈርስት ደግሞ ሞላ አስገዶም ሱዳን ነው ያለው ሲል አስነብቧል::

የቴዲ አፍሮ የፌስቡክ ኮንሰርት ላመለጣችሁ የ4 ሰዓቱ ዝግጅት ቅጂ ይኸው

$
0
0

የቴዲ አፍሮ የፌስቡክ ኮንሰርት ላመለጣችሁ የ4 ሰዓቱ ዝግጅት ቅጂ ይኸው
የቴዲ አፍሮ በፌስቡክ የተጠራ ኮንሰርት በቀጥታ ወደ ኢትዮጵያና በውጭም በተሳካ ሁኔታ በህብር ሬዲዮ ተሰራጨ:: ሙሉ የኮንሰርቱን ዝግጅት ያዳምጡ::


11796256_1640024482947428_4244100396589286734_n

አርቲስት ሰብለ ተፈራ በመኪና አደጋ ሕይወቷ አለፈ

$
0
0
12004685_10153716875224587_6203966531896782357_n

ርቲስት ሰብለ ተፈራ

~በበርካታ ፊልሞች እና ድራማዎች ላይ ተውናለች በተለይም በኤፍቢሲ ሲተላለፍ በነበረው <<ትናናሽ ፀሀዬች>> በተሰኘው የሬድዮ ድራማ የእማማ ጨቤ የተሰኙ ገፅ ባህሪ በመወከል ተጫውታለች።

ቅዳሜ ምሽት በኢቢሲ እየተላለፈ በሚገኘው ቤቶች ድራማ ላይም ትርፌ በሚለውን ገፀባህሪዋ በርካታ ተከታታዮችን አፍርታለች አርቲስት ሰብለ ተፈራ።

መስከረም 1/2008 እንደደረሰን መረጃ ከሆነ ሳሪስ አካባቢ በደረሰ የመኪና አደጋ የአርቲስቷ ሂወት አልፏል። ለወዳጅ ዘመዶቿ እንዲሁም ለአድናቂዎቿ መፅናናትን እንመኛለን።

“ለዓመት በዓል ከቤት አትወጪም ብላ እናቴ በጣም ተቆጣችኝ”–አርቲስት ሰብለ ተፈራ

$
0
0

አርቲስት ሰብለ ተፈራ አዲስ አበባ ውስጥ ዛሬ 8 ሰዓት አካባቢ ከጎተራ ወደ ሳሪስ ጎዞ ስታደርግ ንፋስ ስልክ ቀለም ፋብሪካ አካባቢ በደረሰባት የመኪና አደጋ ህይወቷ ማለፉን መዘገባችን ይታወሳል:: መኪናውን ያሽከረክር የነበረው ባለቤቷ ሞገስ ሕይወቱ ተርፏል:: የሰብለ ሕይወትን የሚያስቃኘውና በቅርቡ አሜሪካ መጥታ በነበረበት ወቅት ከባውዛ ጋዜጣ ጋር አድርገው የነበረውን ቃለምልልስ ለትውስታ እናስነብባችሁ::

በቲያትር መድረክ ስራዎች ከኢትዮጵያ ውጭ እየተንቀሳቀስሽ ነው?
አዎ፡፡ አሜሪካ ግን ስመጣ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡ በአሜሪካ በተለያዩ ስቴቶች “የእኛ እድር” የሚል የመድረክ ድራማ ለማሳየት ግብዣ ተደርጎልኝ ነው የመጣሁት፡፡ የቲያትሩ ደራሲ መልካሙ ዘሪሁን ይባላል፡፡ ኢትዮጵያ እና እንግሊዝ አገር የተሰራ ቲያትር ነው፡፡

sebele tefera

ከቲያትር ይልቅ የሙዚቃ ስራዎች ከኢትዮጵያ ውጪ በተለያየ የዓለም ክፍሎች ይታያሉ?
ቲያትር ትልቅ ወጭ አለው፡፡ እንኳን በዚህ ደረጃ የክፍለ ሃገር እንቅስቃሴም በጣም ቀንስዋል፡፡ ድሮ ቲያትር ያለ ስፖንሰር የሚሰራ ስራ ነበረ፡፡ የተዋናይ ክፍያ ትንሽ ነው፤ አበል ትንሽ ነው፡፡ አሁን ግን ሁሉ ነገር ውድ በመሆኑ ኢትዮጵያ ውስጥም የምንቀሳቀሰው በስፖንስር ነው። ነገር ግን ከሁለትና ከሶስት ቲያትሮች ያልበለጠ ቲያትር ከኢትዮጵያ ውጭ ተጉዝዋል፡፡

የቲያትር ተመልካች ይለያል፡፡ ምን አልባት ቲያትር የሚመለከት ሰው የሙዚቃ ኮንሰርት ማያይ ወይንም የማያደምጥ ሊሆን ይችላል፡፡ አንዳንዴም ደግሞ ሁለቱንም የሚያይ ሊሆን ይችላል፡፡ የቲያትር ተመልካች ልዩ ነው፡፡ በቲቪ የሚያየውን ሰው በአካል መድረክ ላይ ማየቱ በራሱ ልዩ ነገር ይፈጥርለታል፡፡ ጉጉት፣አድናቆት አለ፡፡ በተዘዋወርኩባቸው የዓለም ክፍሎች የቲያትር ተመልካች ደስተኛ ሆኖ አዳራሽ እየሞላ ከተሰጠው ቀን ውጭ ተጨማሪ ቀን እየሰራን ነው ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰን የምንሄደው፡፡ እንቅስቃሴው አለ፡፡

በቲያትር ስራዎች ወደየት ሃገሮች ተጓዝሽ?
በተዋናይነትና በረዳት አዘጋጅነት በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ተዘዋውሪያለሁ፡፡ በዓለም ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ፕሮሞቶሮች “የትኛው ቲያትር ለተመልካች ይሆናል?”

በሚል ተመልክተው እና አጥንተው ገበያቸውን አማክለው የመረጡት ቲያትር ላይ ካስት ተደርጌ ተጉዣሁ፡፡ እንግሊዝ፣ ሳውዝ አፍሪካ፣ እስራኤል፣ ግሪክ፣ ሱዳን፣ አሜሪካ … ሃገሮች በተለያዩ ቲያትሮች ተጉዣለሁ፡፡ አሁን ደግሞ ካናዳ፣ ኳታር፣ ዱባይ ሌሎች ሃገሮች ካሉ ፕሮሞቶሮች ጋር ለመስራት እየተነጋገርን ነው፡፡ በተለይም ወደ ኢትዮጵያ ከተመለስኩ በኋላ ከሌሎች አርቲስቶች ጋር ለመጓዝም በእቅድ ላይ ነን፡፡

የመጀመሪያውን ጉዞ ለንደን ላይ ካደረኩ በኋላ ተመልካቹ ለቲያትር ያለውን ፍቅርና አድናቆት ሳይ ከመድረክ የወረዱ በርካታ ቲያትሮች አስብኳቸው፡፡ በተለይም የሃገራችን ኪነጥበብና ቲያትር ለማሳየት መድረኮች ቢፈጠሩ ሁሉ ብዬ ነው የተመኘሁ፡፡ ይህንንም ማለቴ የአገራችንን

ባህል የሚያሳዩ የገጠሩን ክፍል የሚያስቃኙ ቲያትሮች ከኢትዮጵያ ከወጡ ብዙ ዓመት የሆነቸው ቢያዩት ብዬ እመኛለሁ፡፡ ተሰርተው የወረዱ ጥሩ ጥሩ ቲያትሮች አሉ ከፕሮሞተሮች ጋር እየተነጋገርኩ ነው፡፡

“የፍቅር ካቴና” “ግይድ” የሚባሉ ቲያትሮች አሉ፡፡ ኮሜዲ አስተማሪ አገራችን ላይ ያለውን ትክክለኛ ነገር የሚንጸባርቅ፣ የባለገሩን ህይወት የሚያሳዩ እነ ባቢሎን በሳሎን ከመድረክ የወረዱ ሌሎች ቲያትሮች ከኢትዮጵያ ወጥተው የመታየት እድል ቢኖራቸው በውጭ የሚኖረው ተመልካች ደስተኛ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የሚሸቱ ቲያትሮች አሉ፡፡ የሚናፈቁ የትወና ጥበባቸው፣ አዝናኝና አስተማሪ የሆኑ በጥቂት ሰዎች የሚሰሩ ቲያትሮች፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ይደረግ ከነበረ ጉዞ አለምን መዞር

ተጀመረ ማለት ነው?
አዎ፡፡ አዲስ አበባ ያሉ ቲያትር ቤቶች፣ ትምህርትቤቶች ከዚያም በመላ ኢትዮጵያ ተዘዋውሪያለሁ፡፡ ቲያትር በጀመርኩ ወቅት፣ የከተማ አውቶብስ አስራ አምስት ሳንቲም በነበረ ጊዜ ነበር፡፡ ከጎተራ ጊወርጊስ ድረስ አስራ አራት ቁጥርን ይዤ እሄዳለሁ፡፡ ሰላሳ ሳንቲም ከተሰጠኝ ለእኔ ደስታ ነው ደርሶ መልስ፡፡ ሞያዬን እናቴም አባቴም አይወዱትም ነበር፡፡
“ግጥም ላነብ በትምህርት ቤቴ ተመርጬ ልሄድ ነው” ብዬ ቲያትር ለመስራት ሰላሳ ሳንቲም ተቀብዬ እሄድ ነበር አንዳንድ ጊዜ እናቴ ደሞዝ ስትቀበል የአንድ ሳምንት ትኬት በብር ከሃምሳ ሳንቲም ትኬት ትቆርጠልኝ ነበር አልፎ አልፎም በቤት ውስጥ ስራ ሰራቼ ያስደስትኳት ጊዜ ሳንቲም ተሰጠኛለች፡፡ እሷን እቆጥባለሁ፡፡ ካልሆነም ቲያትር ቤት የማገኛቸው ጓደኞቼን አምስት አምስት ሳንቲም ለምኜ ወደ ቤቴ እመለስ ነበር፡፡ ሳንቲም ከሌለን ደግሞ ከጊዎርጊስ እስከ ጎተራ ድረስ በእግራችን እንሄዳለን – እንቁጣጣሽ ከምትባል ጓደኛዬ ጋር፡፡ አልፎ አልፎም የአውቶብስ መጠበቂያ ስፍራ እቆምና ከአውቶብሱ የሚወርድ ሰው ጉዞውን ጨርሶ ሲወርድና ትኬት ጣል ሲያደርግ፣ የጣለውን አንስቼ አውቶብሱ ውስጥ እገባለሁ፡፡ በአውቶብሱ ውስጥ ተቆጣጣሪ ይዞኝ ጆሮዬን ቆንጥጦኛል፡፡
የመጀመሪያ ደሞወዝሽ ስንት ነበር?
ኢትጵዮጵያ ሬድዮ ለ“አውደ ገጠር” ፕሮግራሙ ድራማ ሰርቼ ሃይ ብር ተከፍሎኛል፡፡ በቀጣይ አንድ ስራ ሰርቼ መቶ ሃይ ብር ሲከፈለኝ ስልሳ አምስት ብር አውጥቼ ለእናቴ ሽቶ ገዛሁ፡፡ በብዛትም ችግሬ የአውቶብስ ትኬት ስለነበረ በርከት አድርጌ መግዛቴን አስታውሳለሁ፡፡በትምህርት

ቤት ሚኒ ሚድያ ውስጥ የተጀመረ ጋዜጠኛ የመሆን ፍላጎት እና ተሳትፎ ነው ወደ አርቲስትነት ያሸጋገረኝ፡፡ በእረፍት ሰዓትና ጠዋት ዜና አነብ ነበር፡፡ አልፎ አልፎም በአንድ ክፍል ውስጥ ለምንማር ተማሪዎች አስተማሪዎቻችን አስተምረውን ከክፍል ሲወጡ ዴስክ ላይ በመውጣት አስተማሪዎችን በመምሰል እቀልድ ነበር፡፡ በተለያዩ ቋንቋዎች በመቀለድ፣ በማስመሰል እጫዎትላቸው ነበር፡፡ እንዳጋጣሚ አንድ ጓደኛዬ ፋዘር/ተስፋዬ አበበ/ ጋር ይዛኝ ሄደች፡፡ ሳይ መድረክ ላይ ቲያትር እየተለማመዱ ነው። ከዚያን ቀን ጀምሮ ጋዜጠኝነቱ ቀረና ተዋናይ ሆንኩ። ሃያ ዓመታት አለፈ በዚህ ሁኔታ እንግዲህ፡፡ በነገራችን ላይ ጋዜጠኝነቱንም አልተወውም፡፡ እንደ ጋዜጠኛ የአየር ሰዓት ወስጄ ለመስራት እየተንቀሳቀስኩ ነው፡፡ መጻፍ ከሆነ ግጥም እጽፍ ነበር፡፡ አንድ ቀን ግጥሞቼን ሰብስቤ አሳትማለሁ ብዬ አስባለሁ፡፡ አሁን አሁን ደግሞ መድረክ እየመራሁ ነው፡፡ አንድ ቀን ደግሞ የጋዜጠኝነት ካራክተር ለመጫወት ፍላጎት አለኝ፡፡

sebele
ወቅቱ ፋሲካ ነው፣ ለቤተሰብ ለአውዳመት የሚያስፈልገውን አሟልተሸ ነው የመጣሽ?

ትዳር ይዤ እስከምወጥበት ጊዜ ድረስ ያለው በቤተሰብ ውስጥ አገልጋይ ትጉ ሰራተኛ ነበርኩ፡፡ የጉልበት ስራ ሳይቀር ባለሞያ ነበርኩ፡፡ ልብስ ማጠብ፣ አትክልት መኮትኮት…. የመሳሰሉትን፡፡ ከቤት አልፌ የተከራይ ቤቶችንም ልብስ፣ ልጆቻቸውን አጥብ ነበር፡፡ በዚህም እገረፍ ነበር፡፡ አሁን እንደ ድሮው አይደለም ስራ ቢዚ አድርጎኛል፡፡ ምን አልባት የበዓል ዕለት ሁሉ ቤት ላልውል እችላለሁ፡፡

የበዓል ዝግጅት፣ መድረክ መምራት፣ ጭውውት ሊኖረኝ ይችላል። አሁን ባለሁበት ደረጃ ቤትም ላልውል እችላለሁ:: ነገር ግን ለበዓል ቤት ከዋልኩ በቤት ውስጥ የምትሰራልኝ አለች አጋዥ አግኝቻለሁ አብረን እንሰራለን፡፡
አርቲስቶች ዓመት ባህልን በቤት ውስጥ አያከብሩም፣ አንችም ይሄው ፋሲካን በስራ ላይ እያሳለፍሽ ነው?
ፋሲካ ስትይ አንድ ነገር አስታወሽኝ፡፡ የመጀመሪያ መድረክ ስራዬ ነው፡፡ ገና ቲያትር ስጀምር የፋሲካ እለት አቃቂ ከተማ ቲያትር እናሳይ ነበር፡፡ የበዓል እለት እኛ ቤት አይወጣም…አይደለም ፋሲካ ስራና ትምህርት ከሌለ ከቤት አይወጣም፡፡ ፕሮግራም ተዘርግቶ አትሄጅም ተባኩ፡፡ መሪ ተዋናይ ነኝ። ከሁለትና ሶስት ወር በላይ ነበር ልምምዱን ያደረግነው፡፡ በዓመት በዓል ከቤት መውጣት የማይታሰብ ነው አይቻለም ተባለኩ፡፡ በህይወቴ እንደዛ ቀን አልቅሼ አላውቅም፡፡ ለቴዎድሮስ ተስፋዬ ወጥቼ ደወልኩለትና እናቴ ከቤት አትወጭም ተብያለሁ አልኩት:: ቴዲ ደወላላት

ነገራት፡፡ እነ ቴዲ ጋር እስከደርስ አላመንኩም እያለቀስኩ ነው የሄድኩት፡፡የዛሬ አስራ ስምንት ዓመት ነው በፋሲካ እለት ቲያትር ይዘን ወደ ጅማ እንሄድ ነበር፡፡ ቲያትር እየሰራን ከመድረክ ጀርባ ሴቶች ሽንኩርት እንከትፋለን፣ እናቁላላለን… ቲያትሩን ስንጨርስ የተቁላላውን ሽንኩርት ወደ አረፍንበት ሆቴል ይዘን ሄደን ዶሮውን ገነጣጥለን ሰርተን እንደ ደንቡ ለሊት ዘጠኝ ሰዓት ተነስተን ገደፍን… ፆመኙቹን አስፈታናቸው፣ ዓመት በዓልን አከበርን በዛው እለት የማልረሳው ቅቤ አንጥረን በብልቃጥ አስቀምጠን ነበር ከመድረክ ጀርባ … ሜካፕ ነበር የሽማግሌ(ጸጉርን ሽበት)ሚያስመስሉ…አንዱ ልጅ ጥንቁል አድርጎ ሽበት ለማስመሰል ተቀባው…ሺሸተው ነው የወጥ ቅቤ ሽበት ለማስመሰል እየተቀባ መሆኑን ያወቀው፡፡

በአንድ ወቅት ደግሞ “የሰው ሰው” የሚል ቲያትር ይዘን ወደ አስመራ ስንሄድ ታመምኩኝ፡፡ ለካ ባህር ዳር ነው ወባ የያዘኝ፡፡ መድረክ ላይ እየተደገፍኩ እንደሰራሁ ትዝ ይለኛል፡፡ “መድረክ መድሃኒት ነው” እንላለን እውነት ነው:: ልክ ከመድረክ ከወጣን በኋላ ግን ምን እያደረኩ እንደሆነ አላውቀውም ነበር፡፡ ከሰዓታት በኋላ ግን ብንን ስል ብዙ ሰው የተኛበት መካከል ነኝ፡፡ ነቅቼ ስመለከት ለአራት ቀን እንድተኛ ተጽፍዋል፡፡ ተዋናያኖቹ ያለ ስራ መቆየት ከባድ ነው። አበል፣ የመኪና ኪራይ ሁሉ ስላለ በቃ ወደ አዲስ አበባ እንመለስ የሚል ሃሳብ ቀረበ፡፡

በአውሮፕላን ብቻዬን ልላክ ነበር፡፡ ነገር ግን እሰራለሁ አልኩኝ፡፡ ጉሉኮሴን ወስጄ ጠነከርኩ ተነስቼ መድረክ ሰራሁ፡፡
ቤተሰብ ያወጣልሽ ስም እየተዘነጋ ነው?

አዎ:: ማንም ሰው ብቅ ስል “ትርፌ” ይሉኛል:: አንዳንዶቹ “ሰንሺ” ይሉኛል:: “ትርፌ” ብለው ሲጠሩኝ አቤት እላለሁ:: በሄድኩበት አገር ሁሉ እንደ ስጦታ ዳቦና አበባ ነው የሚሰጡኝ፡፡

በቀጣይ ምን እንጠብቅ?
“አልበም” የሚል ፊልም አለኝ ድርሰቱን ገዝቸው ነው አሳያለሁ የሚል እቅድ አለኝ፡፡ በሰብለ ፊልም ፕሮዳክሽን አማካኝነት ፕሮዲዩስ ያደረኩት እኔ ነኝ፡፡ እዚህ ያለኝን ከጨረስኩ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ስሄድ በሰብለ ፊልም ፕሮዳክሽን የሚሰራ የሬድዮ ፕሮግራም የአየር ሰዓት ይዤ መስራት እቅድ አለኝ፡፡
መልካም የስራ ዘመን፣ መልካም የፋሲካ በዓል ይሁንልሽ፡፡ ለመላው የክርስቲያ እምነት ተከታዬች በመሉ እንኳን ለፋሲካ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡ ለአድናቂዎቼ እወዳችኋለሁ፡


ሞላ ሌላ ደሚህት ሌላ

$
0
0

ከመሳይ መኮንን
እንኳን አደረሳችሁ:: የሞላ አስገዶም ወደ ህወሀት ካምፕ መግባት አዲሱን አመት በተለያዩ ስሜቶች እንድንቀበል አድርጎናል:: ይህን ያህል አጀንዳ ይሆናል ብዬ አልገመትኩም:: ስለሞላ እስከማውቀው ድረስ ጥሩ ኢትዮጵያዊ: እንደ ህወሀቶች ዘረኝነት የማይነካካው: በመግባባት ለመስራት ከልቡ የሚሻ ነበር:; መቼም ሰው እንደ እህል አይቀመስም:: መለኮታዊ ሃይል ኖሮ ልብ የቀበረውን ማወቅ አይቻል:: በሞላ ደም ውስጥ የሚንተከተከውና ዛሬ ላይ አደባባይ የወጣው ማንነት የሰው ልጅን ፈጽሞ አንብቦ እንደማይጨረስ አንዱ ማሳያ ሊሆን ይችላል:: ግን አንድ የማልደብቀው ሀቅ አለ:: ይህን የምናገረው ሞላ አሁን ወደ ህወሀት ጠቅልሎ በመግባቱ የተነሳ አይደለም:: ዕውነት ስለሆነ ነው:: ያኔ ያን ዕውነት ማፈንዳቱ ለትግሉ ጉዳት እንጂ ጥቅም አይኖረውም::

Mola asgedom copy
አዎን! ሞላ ባህላዊ መሪ ነው:: ለ5 ደቂቃዎች ከእሱ ጋር ፖለቲካ ለመጫወት አይቻልም:: ስለ ኢትዮጵያ ውስብስብ ፖለቲካ ያለው ግንዛቤ ያስደነግጣል:: ማለት ጥልቀት የለውም:: ቀናነቱና ገራገርነቱ ፖለቲካዊ ድክመቱን ባይሸፍኑለትም አብሮ ላለመስራት የሚጎረብጥ ሰው አልነበረም:: እርጋታውና ጨዋነቱም ሌላው ድክመቱን የሚጋርዱ ባህርያቱ ናቸው::
አሁን ሞላ የለም:: ደሚህት ግን ከነሙሉ ሰራዊቱ ትግሉን ተቀላቅሏል:: በደሚህት ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሰራዊቱ አባል ከተለያዩ የኢትዮጵያ አከባቢዎች የመጡ ናቸው:: የትግራይ የሚለው ስያሜ ቀድሞ ስለያዘ እንጂ ሰራዊቱ ሙሉውን ኢትዮጵያ የሚወክል ነው:: እኛም በኤርትራ ቆይታችን ይህን ታዝበናል:: የሰራዊቱ ስሜት ከሞላ አመራር ጋር የሚመጣጠን አይደለም:: አንድ ቀን ሰራዊቱ ፈተና እንደሚሆንበት ሞላ የተገነዘበው ይመስለኛል:: በደሚሀት ካምፖች በነበረኝ ተከታታይ ጉብኝቶች የተረዳሁት የሞላ አመራርና የደሚሀት ሰራዊት ፍላጎት ለየቅል መሆናቸውን ነው:: ይህን ጉዳይም አንድ ምሽት ላይ ባሬንቱ ከተማ ቢራ እየተጎነጨን አንስቼበታለሁ::
” ሰራዊቱ ኢትዮጵያዊ: ስያሜው ግን የትግራይ:: ምን ማለት ነው?”
ሞላ በወቅቱ ጥሩ መልስ ሰጠኝ:: አሁን ላይ ስገምት የማያምንበትን ነው የነገረኝ
” ቀላል ነው:: ስያሜው አያስጨንቅም:: “ት” ን በ”ኢ” የመቀየር ያህል ቀላል ነው:: ዋናው ተግባብቶ መስራት ነው” አለኝ::
ሞላ መግባባት አቅቶት ወይም በሌላ ምክንያት ወደ ህወሀት ሄዷል:: ኢትዮጵያዊ መልክ የተላበሰው ደሚህት ግን ከትግሉ ጋር ነው:: ግለሰብ በራሱ ውሳኔ መንገዱን መርጧል:: ጨርቅ ያድርግለት:: የኢትዮጵያ ትግል ከባህላዊው አመራር ካልተላቀቀ ለውጥ አይኖርም:: የሚንጠባጠበውን እያራገፉ ከመጓዝ ውጭ አማራጭ የለም:: በግለሰቦች ላይ የተንጠለጠለ ትግል ወደ መቃብሩ ወርዷል:: ሞላ ለጊዜው ጭረት ሊፈጥር ይችላል:: ከዚያ ያለፈ ጉዳት የለውም:: ደሚሀት መግለጪያ ያወጣል ተብሎ ይጠበቃል:: አዲሱ ዓመት ዘመናዊውና በዕውቀት ላይ የተመሰረተው የምር የሆነው ትግል የሚጀምርበት ይሆን ዘንድ ሁሉም የሚችለውን ያድርግ:: መልካም በዓል!!!

የትህዴን መሪ አቶ ሞላ አስገዶም ትግሉን ትቶ ለምን ኮበለለ?

$
0
0

mola

ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ

የትህዴን መሪ አቶ ሞላ አስገዶም ትግሉን ትቶ ለምን ኮበለለ ? ሊፈታ የሚገባ ጥያቄ የትህዴን መሪ አቶ ሞላ አስገዶም የተወሰኑ የትህዴን ሰራዊት ይዞ ሀገር ኢትዮጵያ ኮበለለ ይሄ ዜና ብዙዎቻችን እናዳስገረመ እና  አንዳንዶችንም እንዳሰደነገጠና፣ የተወሰኑ ግለሰቦችን እንደስደሰት እያየነው ያለ ነገርሲሆን የአቶ ሞላ  አስግዶም ከትግል ሜዳው መኮብለል እና ወደ ወያኔ ካምፕ መቀላቀል እኔን ባያስደነግጠኝ እና ባያስደስተኝም የአገር አድን ንቅናቄ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው በተሾሙ በማግስቱ ኮብልለው መጥፋታቸው   በጣም አገራሞትን ጭሮ ጥያቄ ስለፈጠረብኝ  ይችን ትንሽ ነገር ማለትን ወደድኩኝ:: በመጀመሪያ ልናውቀው የሚገባው ነገር እንደዚህ አይነት ነገር በትግል ውስጥ ሊያጋጥም እና ሊከሰት የሚችል እንደሆነ  መገንዘብ ያስፈልገናል::

እውነትና  ንጋትእያደር ይጠራል ቢሆንም ነገሩ እንደእኔ አመለካከት ግን አቶ ሞላ አስግዶም በመጀመሪያም ኤርትራ ተቀምጠው የየትግራይ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ እንቅስቃሴን (ትህዴን) በሊቀመንበርለ ሲመሩት የነበሩት በእርግጥ ጸረ ወያኔ አቋምና አላማ ኖሮቸው ነበር ወይስ ሌላ ስውርና የተደበቀ አጀናዳ በጉያቸው ደብቀው አስመሳይነትን ተላብሰው ውስጥ ውስጡን የየወያኔ ፖለቲካዊ አጀንዳ ሲያስፈጽሙ የነበሩ ሰው ነበሩ ወይ የሚለውን ነገር እንድጠረጥር ቢያደርጉኝም  ምንአልባትም ማን ያውቃል እኝህ ሰው የሆነ ጊዜያዊ ጥቅም መሻት አታሏቸው ይሆን የሚልም ነገር እንዳስብ አድርጎኛል:: ምክንያቱም ለእውነት እንዳንታገል ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል አንዱ ለጊዜያዊ  ጥቅም መታለል በመሆኑ። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንኮን ተዘግቦ እንደምናገኘው ኤሳው ለሆዱ ብሎ በምስር ወጥ ብኩርናውን አሳልፎ ለወንድሙ ለያዕቆብ እንደሸጠው ሁሉ ዛሬም በዚህ ዘመን ለጊዜያዊ ጥቅም ተብሎ ማንነትንና ሕሊናን በመሸጥ አስመሳይነትን ተላብሰው ለእውነት ከመቆም ይልቅ የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞችን ተቀብለው ከእውነት ጋር የተጣሉ በርካቶች ሰዎች እንዳሉ እናውቃለን።

 ሰው ለተለያዩ ጥቅሞች ሲል አስመሳይነትን ተላብሶ መኖርን የሚችል ፍጡር ነው::አስመሳይነት ዛሬ የጀመረ ብቻም ሳይሆን በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ አሉታዊ ተጽኖ ከፈጠሩ ጉዳዮች መካከል ትልቁን ስፍራ ይዞ እናገኘዋለን። በጥቅም ታውረው አስመሳይነትን ተላብሰው በጣሊያን ወረራ ዘመን መንገድ እየመሩ ወደ መሀል ሀገር ከማስገባት በተጨማሪም የንጉሠ ነገሥቱ የቅርብ ባልሙዋል ከነበሩ መኩዋንንቶች እና መሳፍንቶች መካከል ሳይቀሩ ለጣሊያን ያደሩ ሰዎችን እንደምሳሌ ማንሳት ይቻላል። እነዚህ በአስመሳይነት የተጠቁ ወገኖች ወይም ሹማምንቶች ህዝቡ ተቃውሞውን በማቆም መሰሪዋ ጣሊያን ይዛው የመጣችውን የይምሰል እውቀት እና ስልጣኔ በመቅሰም ሀገሩን ያለማ ዘንድ በሀሰት ለመሸንገል ሞክረዋል። መረጃ በመስጠት በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ደማቸው በግፍ እንዲፈስ ያደረጉት አስመሳዮች ወይም ጥቅመኞች ናቸው።

ዛሬም አስመሳይ ጥቅመኞች ጊዜያዊ ጥቅምን እና የወያኔን ትርፍራፊ ለመልቀም ቢኮበልሉ ድሩም ከትግል ጉራው የነበሩት  ታሪክን ለመበረዝ፣ የህዝብን ለመግደል ስለነበረ የሚያስደነግጥ ነገር አይኑርም ባይ ነኝ ምክንያቱም ነገም ሌላ ነገር ልንሰማ እንችል ይሆናልና ስለሆንም ማንኛችንም ከአስመሰይነት ተላቀን ማንነትንና ሕሊናን በጥቅም ሳንሸጥ እንደ ዜጋ ለሀገር በማሰብ ለነጻነት፣ ፍትህና ዲሞክራሲ በጽኑ መታገል ይኖርብናል በማለት ዘመኑን የድል ያድርግልን እላለው።መልካም አዲስ አመት

  ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!

የነ ኤፍሬም ማዴቦ ትንቢት ስለ ሞላ አስገዶም ከዳተኝነት –አብርሃም ታየኝ

$
0
0

Birhanu2qከአንድ ወር በፊት የአርበኞች ግንቦት 7 አመራር አባል ኤፍሬም ማዴቦ ኤርትራ ሂዶ ከዊሃ እስከ ኦምሃጅር ከአርበኞች ጋር በሚል ርዕስ የጻፈውና በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን የናኘው መልዕክት ትዝ ያለኝ የትህዴን   ሊቀመንበር የነበረው ታጋይ ሞላ አስገዶም ድርጅቱን ከድቶ ወደ ወያኔ ህወሃት ተመለሰ እንደተባለ ነው።

በተለያዩ የኤርትራ በረሃዎች ጫካዎች የመሸጉትን አርበኞች በጽሁፉ እያስቃኘን የትህዴን ካምፕ ደርሰው በነዓምን ዘለቀ ዲጄነት የተከፈተው የጥላሁን ገሰሰ ሙዚቃ ሲያዳምጡ በነበረበት ቅጽበት እንዲህ ሲል ሳያውቍም ይሁን አውቆት ተንብዮታል።

“አልማዝን አይቼ እልማዝን ሳያት”፤ “እንጉዳዬ ነሺ” “አመልካች ጣት” “መሳቁን ያስቃል” . . . ብቻ ምን አለፋችሁ የጥላሁን ሙዚቃ ተዥጎደጎደ። ጥላሁን ገሠሠ አስመራ ላይ የሚጠብቀንን ቀጠሮ ብቻ ሳይሆን ጭራሽ እኛነታችንን አስረሳን። ቢበዛ አንድ ሰዐት ብለን የመጣን ሰዎች ከሦስት ሰዐት በላይ ከደምህት ጓዶቻችን ጋር ቆየን። በመጨረሻ የጉዟችን መሪ “አንድ ለመንገድ” ብሎ ከተቀመጠበት ተነሳ። እሱ ሲነሳ “እንክርዳድ እንክርዳድ የተንከረደደ፤ ስንዴ መስሎ ገብቶ ስንቱን አሳበደ” የሚለዉ ዘፈን እያለቀ ነበር። ነአምን. . . ነአምን ብዬ ስጣራ . . . “One for the road” ይቀረናልኮ አለ ነአምን . . . እንሂድ የምለዉ መስሎት። ይህንን ሙዚቃ እንደ እንክርዳድ ተቀላቅሎን ለሚያሳብደን የዳያስፖራ ቱልቱላ መርጫለሁ አልኩት። ሳቅ አለና ከቴፑ ጋር መጫወቱን ቀጠለ። እርግጠኛ ነኝ ተቦርነ በየነ ወይም መሳይ መኮንን አንድ ቀን “እንክርዳድ እንክርዳድን” በኢሳት ያሰሙናል። አይደል ተቦርነ?

በመጨረሻ የኛም መሄጃ የሙዚቃዉም መገባደጃ ደረሰ። “One for the road” የተባለለት ሙዚቃ (ዘፈን) ገና ሲጀምር ሰማሁና ኢችንማ አምላክ ነዉ የመረጠልን አልኩ በልቤ። ያ በቁሙ “አጥንቴም ይከስከስ” ብሎ ያስተባበረን ጥላሁን ገሠሠ አሁንም ከላይ ከሰማይ ቤት “ቃልሽ አይለወጥ እባክሺ….ን” እያለ ቃል እንድንገባባ አደረገን። ተራ በተራ ከአርበኛ ሞላ አስገዶም ጋር እየተቃቀፍን “ቃልሽ- አይለወጥ- አባክሽን” ብለን ተለያየን። ቃል የዕምነት ዕዳ ነዉ ብዬ ነበር የጀመርኳችሁ፤ አሁንም ቃሌ ይሄዉ ነዉ። ቃላችን አይለወጥ! ቸር ይግጠመን።

ኤፍሬም ነኝ ከአርበኞች መንደር

 

አይ ሙዚቃ አመራረጥ ለነዓምን፤ አይ አጻጻፍ ለኤፍሬም !!! ቃልሽ አይለወጥ በሚለው የጥላሁን ገሰሰ ዘፈን ከዛሬው ከዳተኛ ከሞላ አስገዶም ጋር የተሰነባበታችሁት ቃሉን እንደሚያጥፍ ታይቷችሁ ነው ብዬ የነብይነት ማዕረግ ልሰጣችሁ ወደድኩ። “One for the road” የተባለለት ሙዚቃ ለሞላ አስገዶም መሸኛ  ይመስላል። እንክርዳዱ ማን እንደሆነ በውስጠ ወይራ አጻጻፉ ገባን።

የአፋር ሕዝብ ንቅናቄ፣ ትህዴን፣ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄና አርበኞች ግንቦት 7 የጋራ  አገር አድን ንቅናቄ መመስረታቸውን በተመለከተ  ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋም በኢሳት ራዲዮ  ተጠይቀው  በድርጅቶቹ አባላት መሃል ማፈግፈግ ቢከሰት እንኳ አገር አድን ሰራዊቱ እንደሚታደገው አብራርተዋል። ይቺንም ትንቢት ብያታለው። ለዚህም ካስረኛው የቃለመጠይቁ ደቂቃ በኋላ  እንደተረዳነው ከሁሉም ድርጅቶች ተውጣጥቶ ከተቋቋመው አገር አድን ሰራዊት ተመልሶ ወደ እናት ድርጅቱ ልመለስ ማለት አይቻልም። አራቱ ድርጅቶች  በጋራ ንቅናቄው ሰራዊት ይዋጣሉ እንጂ ለምሳሌ  ትህዴን  ብዙ ሰራዊት ያለኝ እኔ ነኝ እና በኔ ስም ተጠሩ ቢል የሚሰማው የለም።ሞላ አስገዶም ትግሉን የከዳውም ትህዴንን እንደንብረቱ ቆጥሮ  መሪ ካላደረጋችሁኝ ብሎ ከሌሎች ጋር ተጣልቶ ከሆነም ወደፊት የምናየው ነው።

ለማንኛውም የነፕሮፌሰር ብርሃኑ ምሁራዊ አካሄድ የህወሃትን ካባ ለብሰው ኤርትራ ለመሸጉት ቅጥረኞች አልተመቻቸውም። የተደላደለ የ አሜሪካ ኑሯቸውን ትተው እነ ኤፍሬም በረሃ ይወርዳሉ ብለው እነ ወዲ አስገዶም አልጠበቁትም። ህዝቡ ለውጥ እንደሚፈልግ ተረዱት።ነገም ዛሬም የሚወተውቱት ስለ እውነተኛ ዲሞክራሲ ነውና ሆዳሞች ጨነቃቸው።ስለዚህ ሳይነቃባቸው ፈረጠጡ።

በመጨረሻም የ አርበኖች ግንቦት ሰባት አመራሮች ኤርትራ ከገቡ የተሰበሩ ሁለቱን የህወሃት ሴራዎች እንይና  ለዛሬ ይብቃን።ዙሩ ከሯል።   ሃምሌ 10 እነ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ  ኤርትራ  ገብተው ሃምሌ 20 የኤርትሪያውንን መረጃ ሙሉ በሙሉ ለኢትዮጵያ ሲያቀብል ለበርካታ ዓመታት  የኖረ እና በኤርትሪያ የወያኔ ተቃዋሚ የነበሩ ሰዎችን  እያደነ ሲገድልና ሲያስር የነበረ የመላዋ ኤርትሪያ የፀጥታ ኃላፊ በቁጥጥር ስራ ውሏል።  ያኔ  ከአሜሪካ የሄዱት አመራሮች ያለደህንነት ስጋት እንዲንቀሳቀሱ የወያኔ ቀኝ እጅ የነበረው የጸጥታ ሃላፊ መያዝ ፍንጭ ሰጥቶ ነበረ። አሁን ደሞ  የተቃዋሚ ጦር ሰራዊት የት ህ ዴን መሪ በመሆን ለህወሃት ሲሰራ የነበረው ሞላ አስገዶም ተጋልጧል።ይህ እንግዲህ ብስሉ ከጥሬው ገና ከጅምሩ የተለየበት፤ ምርቱ ከ እንክርዳዱ በመጀመሪያው የውህደት ወንፊት የተጣራበት ወቅት ነው። በነዓምን የተጋበዝነውን ቃልሽ አይለወጥ እባክሽን የሚለውን የ ጥላሁን ገሰሰን ዘፈን ለሌሎቻችን እየጋበዝኩ ቃል የዕምነት ዕዳ ስለሆነ እንዳናጎድለው አሳስባለው።ቃል ብናጥፍ ግን የሚጎልብን ራሳችን ላይ መሆኑን ግልጽ ነው። ታጋይ እንጂ ትግል አይሞትም

 

አብርሃም ታየኝ

የሱባኤ አባትነት በቅድስና –ብጽዕና በብትህና በትህትና! (ሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 12.09.2015 /ሲወዘርላንድ –  ዙሪክ/

Ledet Message from His Holiness Abune Merkorios

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱሳን አሃዱ አምላክ አሜን! ሳይገባኝና ሳልመቸው፤ አሮጌውን ዓመት ሸኝተን የመንገድ ጠራጊውን የሰማዕቱን ቅዱስ ዮኋንስን ስንቀበል፤ በ2007 ዓ.ም ከተከወኑት ድንቅ ተግባራት – ለእኔ፤ አውራ የሆነው የኢትዮዽያ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖታችን ደማቅነት በሚመለከት፤ የውስጤን መንፈስ ለመግለጽ መፍቀድ ግድ አለኝ። በውነቱ ቁንጮ የሆነ ብሄራዊነትን ያበራ፤ ለልዕልቴ ለኢትዮጵያ አለንልሽ ያለ፤ ዕንባዋን የተጋራ ጉልላት ተግባር ስለሆነ።

እንዲህም ሆነ – የተግባር ቀጠሮ ሳይኖረን የሙያ አባቴና የሥራም አለቃዬ – ደወለልኝ።  ቃል ስጠብቅ ዘለግ አድርጎ በድምቀት „ዎህ“ አለ። ትንፋሼን ሰብሰብ አድርጌ „ምነው በደህና?“ ስል በድንጋጤ ግን በልስሉስ ለዛ ጠዬቅኩት „ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን አቡነ መርቀርዮዎስ ፓትርያርከ ዘኢትዮጵያ ፈጣሪ አምላካችን ጠብቆ በሰላም አሜሪካ መግባታቸውን – አበሰረኝ።  ሐሤታችነን ሳናባክን ስልኩ በሠናዩ ዜና ደወል ተጠናቀ።  ከሁለት ቀናት በኋላ አብሮ አደጌ ከካናዳ – ከአንኮቨር ደወለልኝ።  ታላቁ በዓለም ዓቀፋ ሰብዕዊ መብት አስከባሪ ድርጅት ቁልፍ ነበረችና ሂደቱን – አጫወተኝ። ሰንበት ላይ የቤቱ ሳተና – ሁለገብ አግልጋዩ፤ ረጋ ብሎ ታናሽ ወንድሜ ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን የሚገኙበትን ሁኔታ – ነገረኝ።  እግዜብሄርንም – አመሰገን። ከዛ በኋላም የሱባኤ አባትነት አብነትነታቸውን እማርበት፤ ነፍስ እገዛበት ዘንድ፤ አዝዬ ያሳደጉት ታናሽ ወንድሜ ሁለገቡን ሸክሜን እችልበት ዘንድ፤ እንደ ታላቅ ወንድም ታናሼ – ያስተምረኛል። ምሳሌነታቸው የብፁዕነታቸው ሊቅ ጉልትም ነውና።

ምስላቸው አድህኖዬ ነው።  ህይወታቸው ታምራቴ ነው። ታናሼ ወንድሜ በዚህ የመከራ ዘመን ለቤቱ መመረጡ፤ በጎንደር በገላእድ ተራራ ሥር፤ የአዳም ሰገድ እያሱ ቅርስ – ታቦቱን ንጉሠ ነገስቱ የተሸከሙለት፤ የሃይማኖት – የታሪክ እልፍኝ በሆነው በደብረ -ብርሃን ሥላሴ በሊቀ ሊቃውንትነት ጥንግ አገልጋይ የነበሩት አቨው አያቶቻችን ነዳያን፤ ሊለምኑ ላፈሩ ወገኖቻቸው ድንኳን ጥለው፤ አደግድገው እስከ 4 ፍሪዳ አርደው የልደተ ክርስቶስን ፆም መፍቻን በረከት ያፍሱ የነበሩት፤ የመላዕከብርሃናት ልሳነወርቅ ኃይለሥላሴ የትውፊት ወራሻቸው የመላዕከ ብርሃናት ገብረአጋይስት ልሳነወርቅ – ጸጋ ትንፋሽ በእርሱ በታናሽ ወንድሜ ላይ አርፎ፤ የተገፋው የሊቀ ሊቃውንታት ቅዱስ ዓውደ ምህረት ቤተኛ በስደት ሀገር ሥሉስ ቅዱስ አደረጉልን። ተመስገን።

ድምጻቸውን ለጾም፤ ሩሃቸውን ለሰጊድ፤ ጠረናቸውን ለዓለም ስምምነት – ለሰላም፤ ነፍሳቸዉን ለወንጌል ቀኖና እና ዶግማ ተገዢነት፤ ዘመናቸውን ለሱባኤ አባትነት – በቅንነት፤ የሰጡ ቅዱስ ሐዋርያ አባት ናቸው ቅዱስ አባታችን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቀርዮዎስ ፓትርያርከ ርዕሰ ሊቃነ ዻዻሳት ዘኢትዮጵያ ቅዱስ አባታችን ከምድረ አራዊት ሴራ ልዑል አምላካችን አውጥቶ፤ እንደ የበዛ ጭምትነታቸዉ፤ ቀሪ መዋለ እድሜያቸውን ያላዩትን የስደት መከራ እንደ ወዳጃቸው ውጽፍተ ወርቅ እንዲዩት ሲመርጥላቸው ለግዑፋን የወንጌል አርበኞች፤ ለሃይማኖታቸው ቀናዕይ ለሆኑት የኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ማህበረ ምዕመናን እንዲሁም በስደት ሐገር ለሚወለዱ የፍቅር ተስፋዎችና ለማግሥት ተረካቢዎች ሁነኛ የአብነት ሰብሳቢ ፊደል እንዲሆኑ መርቆ ነው የአብነት ሊቀ – ትጉኃን ቅዱስ አባታችን በቀስታ እየተራመ፤ዱ በፈርኃ እግዚአብሄር ልቅና እራሳቸውን እጅግ ዝቅ በማድረግ፤ ተዕቅቦን በተግባር በማበልጸግ፤ ዘመነ ሱባኤቸውን ለሐዋርያነትን የፈቀዱ መሆናቸው እኔ በግሌ ቅዱስነታቸውን የማየት ህልሜ ልክ የልጅነት ህልሜን እየሩሳሌም የማየት ያህል ነው ላያቸው እጅግ እምናፍቀው። ምክንያቱም የተመሰጠረው ፍጹም ልዩ ሥነ – ምግባር በራሱ የመዳኛ ጸበልና እምነት ነው። ገዳማዊ ህይወታቸው ሥርዬት ድህነት ነው። ብፁዕነታቸው የመንፈስ ቅዱስ ሥጦታ ናቸው ሚስጥርም ናቸው ኦርቶዶክስ ተዋህዶን አስከበሩት በረቂቁ ሰማያዊ ጸጋቸው።

ከዛ ከበላህሰቦች እጅ የወጡበት ማዕልትም ለእኔ ቅዱስ እለቴ ነው በሰለጠነው ዓለም እየኖሩ፤ በህግ  እግዚአብሄር እንዲህ ከሁሉ ነገር እርቆ እዩኝ እዩኝን ተጸይፎ ሌትና ቀን ዘግቶ በምነና መኖር – ለትውልዱ የድርሳን መጸሐፍ ነው ሰው የላትም እናት ሀገር ኢትዮዽያ ለሚሉት ይህ አመክንዮ የማዕዘን ድንጋይ ነው።

ብጽ ወቅዱስ አባታችን አቡነ መርቀርዮስ የህጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ ፓትርያርከ ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ  የሥም ክብርና ዝናን ለቅድስናቸው እንዳይመጥን ያደረጉት በድርጊት ነው አስተዳደራዊ የኃላፊነት ቦታውን ለፈቀዱት በመመረቅ፤ ቅዱስነታቸው የሱባኤውን ትጋት ወደዱት፤  ይህ ሰማያዊ ጸጋ ትውልድን በኤዶም መንፈስ ያበቅላል፤ መመካት አይገባም እንጂ እውነት የጥንት የጥዋቱ የዘመነ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ብርሃን ገድልና ታምራት ትውፊትን እንሆ በዘመናችን እያዬን ነው፤ የድምጻቸው ዜማ እጅግ ተናፋቂ የሆነውም የሃዲዱ ክህሎት ሚስጢር – ዓዕማድ ስለሆነ ነው ብፁዑነታቸው ማንንም አይጋፉም – ተመስገን

ይህ ፍጽምና በሸኘነው ዐመት ጉልሁን ትውልዳዊ ድርሻ በላቀ ጸጋ – ከወነ በሀገራቸው በኢትዮጵያ በሦስተኛ ዜግነት እንኳን መኖር ያልተፈቀደላቸው ምንዱባን በሊቢያ መሬት ደማቸው የአፈራቸውን መሬት በራሮት ሲጣራ ሰማእትነታቸው ኢትዮጵያዊ ዜግነትን ከወያኔ ሃርነት እግር ሥር ሲለምን ኢትዮጵያ ላይ ያለው የፓትርያርኩ ጽ/ቤት በመሪው በሰማዕትነት ላይ ዘና ያለ ስላቅን -አስደምጦናል ሎቱ ስብኃት  ለበላህሰብ ጥላነቱንም ዕንባ እየተራጨን  – በአርምሞና በተደሞ አድምጠናል የዘጠኙ ቅዱሳን የትናንት ቤተ ማዕዶት እንዴት ለማህጸኗ ነፍሶች ከዕንባቸው ጋራ ይጠቅጠቁ እግዚዖ፨

የቅዱስ አባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት ጥርኝ፤ የእናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ የገድል ባዕት፤ የነብዩ መሃመድ የልጆቻቸው የመካራ ማሳለፊያ ጥግ – የሆነች፤ የሁሉም ማዕድ፤ ማዕድነቷ ተደፍጥጦ ስሌቱ በዘውጋዊነት ተወራርዶ፤ ለሃይማኖታቸው ክብር ሲሉ እንደ ተሰውት ታላላቆች ከነመስቀላቸው ሲታረዱ፤ የእስልምና ዕምነት ተከታይ ወንድማቸው ሳይቀር እኔም ከእነሱ ጋር ብሎ አንገቱን ለቢላዋ ሲሰጥ፤ ዘመናትን በፍቅር በቃል ኪዳን ቀለበት ቃሉን ሲሰጥ፤ ኢትዮዽያዊነት ደምቆ – መራ ለምድራዊ ኑሮ የተጋ ኢትዮዽያ የሚገኘው  የፓትርያርኩ ቢሮ ሃዘንተኞቹ  በጭካኔ በሰለጠኑ የዞግ አንጋቾች ሲደበደቡ – ሲሳደዱ – ሲታሰሩ ለበደሉ ማካካሻ ልዩ ሥጦታ የአበጃችሁ ፊርማውን – ድል ባለ ድግስ በዕለ ሢመቱ ደም ደም እየሸተ አፈር እያነባች – አከበሩ። በቀደምቶቹ ሆነ በዛሬዎች ሰማዕታት ተዘመነ፤ ግራጫማ ክር የተላጠበት የፍቀት ዘመን ይህ ነው እንግዲህ የመሃል – የዳር – እየተባለ ማህበረ ምእመኑ በውጪ ሀገር በዘውገ ክታብ ተጠቅልሎ ሽፍን ዬህወሃት ተባባሪዎች ሲያምሱት የኖሩበት ዘመን – ንጹሁ ቅዱስ አምላክ ወርቅን ያነጠረበት፤ ሰማያዊ ታምራት እንዲህ – ተገለጠ። ንጽህና የት ላይ እንደሆነ ጆሮ ላለው አወጄ።

ፈጣሪ አምላካችን ተከታዮችን የሚያስተምረው በምሳሌ ነው ከእንቅልፉችን እንድንነቃ ከወደድን ታምር በማያቋርጥ ሁኔታ አሳይቶናል ለእርቅ ጉባኤ የተላኩት አራት ዐይና በትልልፍ ረግጠው የሄዱትን ጉባኤ ዜና ሳያቀርቡ፤ ቤታቸውም ሳይገቡ ነበር የቀሩት የአንድ የተመረጠ ብላቴና ታምራዊ ድምጽ ፍቅር እሰከ መቃብር – አድርጓል

ልዑል እግዚአብሄር ፍቅሩን ሰጥቶናል ይህ ፍቅር ጥጋችን ነው ስለሆነም ቀን በአማጠች ቁጥር እረኛ አባት ይሰጠናል የኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ታብብ – ትለመልም ዘንድ አብነቷን ሸልሟታል ለገሃዱ ዓለምም መሪ ሰጥቶናል ይህ ዐመት ለእኔ ልዩ ነው ለገሃዱም  – ለመንፈሳዊ ህይወቴ ቅኔ በዜማ ተቀኝቶልኛል

ቸርነቱ የማያልቅበት አምላካችን ወደ እኛ እንሆ ተመለከተ ሰምዕታት በሊቢያ ሥያሜው በህገ ቤተክርስቲያናችን ከብሮ ጸድቆ ታወጀ ፆመ ፍልሰቲት የወልዮሽ የሱባኤ ሰሞናት ሆና መከራውን ተጋራች ለልጆቻቻው አባት የሆኑት ቅዱስ አባታን „ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን አቡነ መርቀርዮዎስ  የህጋዊ ቅዱስ ሲኖደስ ፓትርያርከ – ዘኢትዮጵያ ሰፊ ዝግጅት የተደረገበትን የበዐለ ሢመት መሰናዶ የሰማእታቱ ክብር ብቻ እንዲበለጽግበት ፈቀዱ ለዚህ ላጠናቀቅነው ዐመት „የድንቅነት መብራት መሪ ኮከብ „ እኔ የሥላሴ ባርያ ሥርጉተ ሥላሴ – ብዬዋለሁ የሰማዕቱ ቅዱስ ሐዋርያ የዼጥሮስ ሃውልት ለባንዳነት ባደረ ዘረኛ ህወሃትና ተባባሪ የቅናት ተቋማት ቢነሳም፤ „የዼጥሮስ ያችን ሰዐት“ ቅኔ፤ የንጽህት ቅድስት እናታችን „ምነው እመብርሃን“ ተማህጽኖ ቢጠቀጠቅም፤ የእናታችን የተማህጽዕኖ ዘለዐለማዊ ክብር በመታበይ በህወሃት ቢነፈግም፤ የብላቴ ጌታ ጸጋየ ገብረመድህን ድምጽ ቢረገጥም፤ የእዮሩ አደባባይ ግን የተስፋ አባት አልነሳንም አሉን ንግሥተ ኢትዮጵያ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን እንደ ትናቱም ዛሬም ቅዱሳን አሏት። ይደልወን ውስጣቸው ያደረጉ ሰማዕትነትንም የዘከሩ የቅንነት እጬጌዎች።

 

ሌላው በአጋጣሚው ማንሳት የምሻው ቁም-ነገርበስደት ሀገር የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ በግራም በቀኝም በበታችነት ዲያቢሎሳዊ መንፈስ ላይ ታች ለምትሉ ወገኖቼ እናንተ እንደምታስቡት ማዕከላዊ አውደ ምህረታችን ቅጽር ግቪው – ደጀሰላሙ – አቃቤቱ ቤተ – መቅደሱ ሁለመናው በእንቁላል ውሃ የተገነባ፤ እጅግ በአጠረ ዕድሜ በልቅና እንደ ፈቃዱ የተራጀ፤ ቅዱስ መንፈሱን ለባንዳ ፍርፋሪ ያላስገዛ፤ የማንነቱ ጌታ መሆኑን በልበ ሙሉነት – እናገረዋለሁ እውነት ሁልጊዜም አሸናፊ ናት።

ቀሪዉ የአባቶቻችን ተግባራት ማህበረ ምእመኑን በዕንባ ዙሪያ የማሰባሰቡን ባሊህ ቢሉት መልካም ይሆናል ብትን አፈር ያሳጣቸው ይሄው ነውና ቢያንስ ለኢሳት ቤተ ክርስቲያናችን ኃላፊነቱን በሥሯ የተደራጅ የኢሳት ቤተሰቦች እንዲኖሩ እሷም ከምታገኘው በኲራት እራሷን ችላ እንደ አንድ ቤተሰብ የበረከቱ ተሳታፊ የምትሆንበት መርህ ነድፋ መንቀሳቀስ ይኖርባታል – በትህትና እና በአክብሮት በነፃነት የመኖር ትሩፋት ከቤተክርስትያናችን በላይ መምህር የለም እዛው ከጎረቤት እየኖሩ የኢሳት ብሄራዊ ተልዕኮ አይደለም መፈጠሩን ብዙወች አያውቁም ለዛውም የሚችሉ ስለዚህም በዚህ ዙሪያ ጠንካራ ማዕከላዊ የተግባር ዘመቻ ያስፈልጋል ጊዜ ሊሰጠውም አይገባም እንዲያውም ተዘግይቷል የኢትዮጵያ ሳትላይት ቴሌቪዥን ከሥሙ ጀምሮ ህብራችን – ክብራችንም ነው። ኢሳት ለቅድስት ቤተክርስትያናችን ልሣነወርቅ ሽልማቷ ነው።

ማህበረ ምዕመኑ ውርዴት እንዲገባቸው ማድረግ ያስፈልጋል  ከመንፈሱ ጋር ለሚኖር ኢትዮዽያዊ የበታችነት ውርዴ ነው  የተዋህዶ ልጆች የህጋዊ ሲኖዶስ ቤተኞች ከመረጃ ፍሰት እጥረት የተነሳ የህወሓት ዜና ማሰራጫ ሰለባ ሆነዋልና ቅዱሱ ማዕዳችን ከጥፋት ውሃ ያድናቸው ዘንድ እኔ የሥላሴ ባርያ ትቪያዋና ታናሿ ዝቅ ብዬ – አሳስባችሁአለሁ  እለምናችሁ – እማጸናችኋለሁ

በተጨማሪም አካል የሌለው የመዳህኒትዓለም አገልጋይ የቃለ ወንጌል ታሪክ የነፃነት ተጋድሎ ታሪክ መሆኑን የሳተ የተላለፈ ግድፈትም አዳምጣለሁ ይህም መንገዱ ልክ አይደለም እና ሃግ ልትሉት ይገባል – በትህትና እና በአክብሮት ህይወት ለሚገብረውም የአገር አድኑ ብሄራዊ ሠራዊታችን አስኳል የደጀንነት ተግባር ቀጠሮ ሊሰጠው አዬገባም ባይ ነኝ ማህበረ ምእመኑ በመረጠው ዘርፍ ተሳትፎውን በቋሚነት ይጀምር ዘንድ ቤተ ክርስቲያናችን ባለድርሻነቷን በግብር ማስጌጥ ይኖርባታል እንደ ትውፊቷ እንደ ጥንቱ እንደ ጥዋቱ

የራስ ባለአደራ፨

ድጓ ፆመ ድጓ፤  መጸሐፍ ከቅኔ – ርትህ ዝማሬ፤

ለወንጌል ገበሬ  – ለሰማዕታት ህብሬ፤

ሊቀ – ሊቃውንቱ  በኃቲ ሲያዜሙ

ትውፊት ትሩፋቱ ዳዊትን ሲደግሙ፤

ህዋስ ሆነው ኖሩ ቃሉን ሲመግቡ

የኪዳን አዝመራ የእኛ ደመ ግቡ

ማህሌት ተጠርታ ሃሌን አስቀድማ

ምስባክን አፍቅራ ቅዳሴን ቀምማ፤

ሰዕታት ባቋቋም  – መርጌታው በንግሡ

ብካብ በጽላቱ – ሙሴውም በአሃዱ፤

ደወሉ ተጣርቶ ጽናጽል ደጉ

ዕርግብ በር ይሆናል ሐሤትም መንኩሦ።

ስዋሰው ተራብቶ ግዕዝ ደጅ ተጠንቶ፤

ቅኝቱ ይወርዳል ብዕር ተባራይቶ፤

መንሹ ይርጋ ይላል ምርጥ ዘር አዝርቶ

ቃና ባይኑ ፈክቶ

ፆም ጸሎት ተዋዶ ስግደት በተደሞ፤

መታቀብ ተፈቅዶ ሱባኤ ባርዕምሞ፤

ሩህ ትሰክናለች ዉህድ በአንክሮ፤

ቅድስና ቤቷ  የኦርቶዶክስ ኑሮ

የሰማእታት ቁንጮ የሐዋርያት ዕርገት፤

የነበያት ንባብ ያንድምታ ሊቃውንት

የሠለስቱ ረቂቅ የአይነታ እትብት፤

አብነት

ሽብሸባው ሙሉወርድ  ዜማውም በጃኖ

እልልታው ጅረት ነው የህሊና መቅኖ

ሁልግዜም አሽታ አስብላ መግባ

በሰላማዊነት ጥናትን አዝምራ

አብራርታ ገምግማ ውስጡን ተመራምራ፤

ቀለሙን ጠጥታ፤ ሚስጢር አመሳጥራ፤

ዘመናት ቀናቱን በቅምረት አምራ

የእኛ የንብ አውራ የትውፊት ጎመራ

ብራናን አምርታ ሊቅነት በዕድምታ

ፈልቃ ትኖራለች ድንቅነት ገንብታ

ችግርን ተጋርታ እመቤቴን ጠርታ

ህይወት ትሆናለች ነባቢት አብርታ

የእሽት ባለብራ ትጉህ ባለ’ዝምራ

ገድፋ የማታውቀው የእኛ ባለ ቅኔ ከታምር ተምራ፤

መክሊት ተሰቷታል ከቅንነት ጎራ ሰንደቅ ልታበራ

መሆን ናት ነፃነት የመሆን ጎመራ የራስ ባለአደራ

ሥጦታ ለማተቤ ለቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ (ነሃሴ 23 . 2007 ሲዊዘርላንድ)

ለላይኛው ዕይታዬ የማጠናከሪያ ማጠቃለያ – በትህትና

፩ የኢሳት ቤተሰቦች ቅድስት ቤተክርስትያናችን በማዕዷ በቋሚነት ቢኖራት የታሪክ ታዳሚነት በሚዲያ ዙሪያ ይኖራታል   ብልህነትም – ይመስለኛል

፪ ለነፃነት አርበኞቻችን የሰብዕዊነቱን ድርሻ ብትወስድ – ይህም ማለት የቀይ መስቀል የደም ባንክን ኃላፊነት ድርሻ ቢኖራት፤ በሃይማኖታችን ጥቃት ሆነ፤ የቀደምቱን አዳራ በተግባርን ማብራት ሲሆን፤ ይህም ደም ለመስጠት የተዘጋጁ ቅዱሳን የደሙን ዋጋ በሽልንጓ እንዲያደርጉ ሁኔታውን ማመቻቸት፤ ለነፍስም ለስጋም ጸጋ ነው፤ በዚህም ቅድስት ቤተክርስቲያናችንም ለድል ዋዜማ ባይተዋር አትሆንም። ታተርፋለች።

፫ ተዋህዶ በሁለገብ ብቃት ሃብታም ናት ስለሆነም በዲፕሎማሲዉ መስክ ጉልህ ሚና ለመጫወት መሁራን ልጇቿን በአግባቡ የምታሰማራበት በር ቢኖራት ህልሜ ነው ይህን የከፋ ዘመን ዕንባ ለመጋራት የሃብት ሃብት የሆነውን የሰው ኃይሏን ለማንቀሳቀስ አለን የሚባልለት ስምሪት ቢኖራት መልካም – ይመስለኛል በልቶ ማደር ብቻውን ወይንም አማኝነት ብቻውን የሀገርን ክብር አይወክልም ውርዴትን ደማችን ሊጸየፈው ይገባል – እላለሁ ጠንከር ያለ፤ ቋት የሚገፋ ተግባር ከቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ጉልበታምና ሳቢ ተግባር ማዬትን – እናፍቃለሁ ነፃነት „ሰውን“ ማዕከሉ ያደረገ የኔነት የማንነት ሃይማኖት ነውና።

ዬእኔ ክብረቶች – ከስንብት በፊት የሰማዕቱ ቅዱስ አባታችን የአደራ ዓይን መስከረም 5. 2015 በሲዊዘርላንድ ዙሪክ ከተማ ቃናቸውን – ቃላቸውን ማድመጥ ለምትፈቅዱ Tsegay Radio or www.tsegaye.ethio.info Aktueall Sendung የ10.09.2015 የጸጋዬ ራዲዮ ዝግጅት አርኬብ ላይ ማዳመጥ ትችላላችሁ እርግጥ አዳራሽ ውስጥ የተቀዳ ስለሆነ ትእግስታችሁን – እጠይቃለሁ ተከታዩን በሚቀጥለው ዝግጅቴ – ይቀርባል ጉባኤው የመንፈስ ሃዲድ – ነበረው እንዲህ ዓይነት ሁለቱንም ፅኑ ፍላጎቶቼን ኪዳኑን የፈቀደልኝ ጉባኤ ገጥሞኝ – አያውቅም እኔ ብሄራዊ ብቻ ሳይሆን ዓለምዓቀፋዊዎችንም – ጉባኤዎችን አይቻቸዋለሁ የ05.09.2015 ፍጹም ልዩ ነበር – ለበጎ ነገሮች ራህብተኛዋ – ለእኔ

ለእኔስ ሰው መሆኔ ብቻ ይበቃኛል

ወስብሃት ለእግዚአብሄር

 

 

የአርቲስት ሰብለ ተፈራ ባለቤት ቀብሯ ላይ በፖሊስ ታስሮ ይገኛል * ለሞት ስለዳረጋት አደጋ ምክንያት ተናገረ

$
0
0

sebele tefera

(ዘ-ሐበሻ) በአዲሱ ዓመት በመኪና አደጋ ሕይወቷ ያለፈው ተወዳጇ አርቲስት ሰብለ ተፈራ የቀብር ስነስርዓት ነገ ሰኞ እንደሚፈጸም የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታወቁ::

የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንደሚሉት ከሆነ ባለቤቷ ሞገስ ተስፋዬ አደጋው ከተፈጸመ በኋላ በ እስር ላይ ይገኛል:: ፖሊስም ስለአደጋው አፈጣጠር ምርመራ እያደገበት ይገኛል::

ሞገስ ነገ ሰኞ በመንበረ ጸባኦት ቅድሥት ሥላሴ ካቴድራል ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት በሚፈጸመው የባለቤቱ የቀብር ሥነስርዓት ላይ በፖሊስ ታስሮ እንደሚገኝ የጠቆሙት የዘ-ሐበሻ ምንጮች ለፖሊስ አደጋው የተፈጸመ ሙዚቃ ለመቀየር ጎንበስ ሲል እንደሆነ ተናግሯል::

አርቲስት ሰብለ ተፈራ እና ባለቤቷ ሞገስ ተስፋዬ ይህ የመኪና አደጋ ከመፈጸሙ ከቀናት በፊት በአቡዳቢ እና በዱባይ ለእረፍት (ቫኬሽን) ወጥተው መልካም ጊዜ ማሳለፋቸውን ባለቤቷ በፌስቡክ ገጹ ለጥፎ ነበር::

ፓስተር ተከስተ ምላሽ ሰጠ –“ሆቴል ክፍል ውስጥ ገብታ በጣም ስትፈታተነኝ ሌላ ጊዜ ፍላጎትሽን አሟላልሻለሁ አልኳት እጂ አልነካኋትም”

$
0
0

ፓስተር ተከስተ እስካሁን ድረስ ለሚወራበት የወሲብ ክስ ጉዳይ በሰሜን አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ ከሚታተመው ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ ምላሽ ሰጥቷል:: ምላሹ እንደወረደ የሚከተለው ነው::

“እኔ ወ/ሮ ሆሳዕናን አስገድጄ አልደፈርኩም። በፍርድ ቤትም አልተከሰስኩም። ለዚህም ማስረጃ አለኝ።”

የወ/ሮ ሆሳዕና ባለቤት ባለፈው በቪ ኦ ኤ በቀረበው ፕሮግራም መግቢያ ላይ “በሚስቴ ላይ የጾታ ጥቃት ተፈጽሞባታል” ያለውና ወይዘሮ ሆሳዕናም በዚያው ፕሮግራም ላይ ቀርባ “ጉዳዩ በህግ የተያዘ ነገር ነው” ያለችው ነገር ሙሉ በሙሉ ውሸት ነው። እኔ ማንንም ሰው አስገድጄ አልደፈርኩም ምንም አይነት ክስም አልቀረበብኝም። ከወንጀል ነፃ መሆኔን የሚያሳይ ህጋዊ ማስረጃ በአሜሪካን አገር ጉዳዩ ከሚመለከተው መስሪያ ቤት በጠበቃዬ አማካይነት ያገኘሁት እሷ በአሜሪካን ድምፅ ሬድዮ ቀርባ ከስሸው ጉዳዩ በህግ ተይዟል ብላ በተናገረች በሚቀጥለው ቀን ነው።
pastor
ይባስ ብሎ በአሜሪካን ድምፅ ሬድዮ ፓስተር ተከሰተ ባለትዳር ሴት ደፍሮ ተከሰሰ የሚለውን ዜና ውሸት እና የፈጠራ ወሬ መሆኑን የሚያሳየው እኔ እነሱ ከሚኖሩበት ሚንያፖሊስ ከተማ እኔ ወደምኖርበት ወደ ዋሽንግተን ስመለስ ወደ አውሮፕላን ጣቢያ የሸኘችኝ እራስዋ ወይዘሮ ሆሳዕና ነች። በብዙ ጭቅጭቅ የ1000 (አንድ ሺህ) ዶላር የእጅ ሰዓት በራስዋ ክሬዲት ካርድ ገዝታልኛለች። ለዚህም ሌላ ህጋዊ ማሰረጃ አለኝ። በዚያን ሰአት እንኳን ልትከስኝ ቀርቶ ለወንድ ልጅ ሰዓት መስጠት እወዳለሁ ብላ እኔ ሰአት አልፈልግም እያልኳት እሷ ግን እኔ የወንድ ልጅ ሰዓት ስለሚስደስተኝ ልግዛልህ። አንተ ብትፈልግ ወደፊት በሌላ ነገር ቀይረው በማለት ከነደረሰኙ ሰጠችኝ።

አንተና ወይዘሮ ሆሳዕና እንዴት ተገናኛችሁ ጉዳዩስ እንዴት እዚህ ደረጃ ደረሰ? ብለን ላቀረብነው ጥያቄ የሰጠው ምላሽ፡ ወ/ሮ ሆሳዕናና የእኔ ባለቤት የአንድ ሰፈር ሰዎች ናቸው። ከዚያም በራስዋ በወይዘሮ ሆሳዕና ተደጋጋሚ ግፊትና ጥረት ተቀራረብን። የቤተሰባችን አካል ሆነችና አገልግሎትህን ስለምወድ እንድደግፍ ጌታ አሳሰበኝ በሚል መንፈሳዊ አካሄድ ለእኔና ለቤተሰቦቼ በተለያየ ጊዜ ስጦታ ሰጥታናለች። የቤተክርስቲያን አገልጋዮች በምዕመናን በጎ ፈቃድ የፍቅር ስጦታና የአገልግሎት ድጋፍ ማግኘት የተለመደ ስለሆነ እኔም በአገልግሎት ዘመኔ እኔንና አገልግሎቴን የሚደግፉ ብዙ ደጋግ ሰዎች ስላጋጠሙኝ ወይዘሮ ሆሳዕና ያለችውንም በቅንነት ተቀበልኩት። በመጨረሻም እኔ ባለቤትህና አንተ ለምን የጋራ ቢዝነስ አንጀምርም? እኔ ገንዘብ አለኝ፣ የቤተሰብ የቢዝነስ ልምዱም ስላለኝ አንተ ደግሞ ኢትዮጵያ ታዋቂ ስለሆንክ ሦስታችን አብረን ኢትዮጵያ ቢዝነስ ብንሰራ ሊሳካልን ይችላል ብላ ጠየቀችን። እኔም ማንኛውም ዘማሪ አንደሚመኘው ከቤተክርስቲያን ምንም ነገር ሳልጠብቅ ራሴን እና ቤተሰቤን በግሌ እየሠራሁ በማስተዳደር በነፃ የማገልገል ከፍተኛ ፍላጎት ስለነበረኝ እኔና ባለቤቴ በሀሳቡ ተስማማን። እኔ እነሱ ወደሚኖሩበት ከተማ የሄድኩት እና ሆቴል ያረፍኩት ራስዋ ወይዘሮ ሆሳዕና በአሜሪካን ድምፅ ሬድዮ ቀርባ እንደተናገረችው በጋራ ስለምንጀምረው ቢዝነስ ለመነጋገር ነበር። ይህን ሀሳብ ያመጣችው እራሷ ወይዘሮ ሆሳዕና ነች።

በራሷ ገንዘብ የአውሮፕላን ትኬት ቆርጣ እራሱዋ ሆቴል ይዛ፣ (ለዚህም ማስረጃ አለኝ)። ከዚያ በኋላ አሁንም ራሷ በአሜሪካን ድምፅ ቀርባ እንደተናገረችው ያረፍኩበት ክፍል ውስጥ ገብታ ልብሷን አወለቀች። ብዙ ተፈታተነችኝ። የምሄድበት መንገድ ትክክል እንዳልሆነና ሆን ተብሎ የገባሁበት ወጥመድ እንዳለ ሲገባኝ ፍላጎቱ ባይኖረኝም እሷን ሳላሳዝን ሞራልዋን ሳልነካ በሰላምና በእርጋታ ለመውጣት “በቃ አሁን እኔ መረጋጋት አልቻልኩም ፍላጎቱ የለኝም ሌላ ጊዜ ተመልሼ ልምጣና ያንቺን ፍላጐት አሟላለሁ” ብዬ ቃል ገባሁ። እሷም ተመልሼ ወደእሷ ከመጣሁና መሻቷን ከፈጸምኩ አብረን ልንሠራ ከተነጋገርንበት ቢዝነስ በተጨማሪ ለግሌ ዳጎስ ያለ ገንዘብ እንደምትሰጠኝ ነግራኝ ተለያየን። ካረፍኩበት ሆቴል ወደ አውሮፕላን ጣቢያ ስንሄድ ለወንድ ልጅ የሰዓት ስጦታ መስጠት ያስደስተኛል ብላ ከላይ እንደጠቀስኩት የአንድ ሺህ ዶላር ሰዓት መንገድ ላይ ወደሚገኝ ሞል ኦፍ አሜሪካ የገበያ ማዕከል ውስጥ ሜሲስ የሚባል ስቶር ወስዳ ገዛችልኝ።

አየር ማረፊያ አውርዳኝ ስንለያይ ለመጀመርያ ጊዜነጻነት ተሰማኝ። ዋሽንግተን ዲሲ ተመልሼ እቤቴ ስገባም የሆነውን ነገር ሁሉ ለባለቤቴ አንድም ነገር ሳልደብቅ ነገርኳት። ከዚያም እንደ አንድ ክርስቲያን እና እንደ አንድ አገልጋይ ከእኔ የማይጠበቅ ነገር አድርጌአለሁ ብዬ ያለማንም አስገዳጅነት በራሴ ፈቃድ ለቤተክርስቲያን ተናግሬ ወዲያውኑ ራሴ አገልግሎት አቆምኩ። በራሴ ቤተክርስቲያን ብቻ ሳይሆን በተለያዩ የአሜሪካን ክፍለግዛቶች በሚገኙ አብያተክርስቲያናት እንዳገለግል የተጋበዝኩባቸውን አገልግሎቶች በሙሉ በራሴ ፈቃድ ሰረዝኩ። እኔ ወደዋሽንግተን ከመጣሁ በኋላ ወይዘሮ ሆሳዕናም እኔን በስልክ ለማግኘት ተደጋጋሚ ሙከራ አደረገች ግን አልተሳካላትም። ከዚያ በኋላ የበቀል እርምጃው ግራ በሚያጋባ መልኩ መጣ።

መጀመሪያ ለእኔ ባለቤት ለወ/ሮ የምስራች ባለቤቱዋ አቶ መላኩ ደውሎ ሚስቴ ከአንቺ ባል ጋር አብራ ስለተኛች ይቅርታ ልትጠይቅሽ ነው ብሎ ስልኩን ለወይዘሮ ሆሳዕና ሰጣት። ወይዘሮ ሆሳዕናም እኔ ከባለቤትሽ ከተከስተ ጋር ተኝቻለሁ ይቅርታ አድርጊልኝ ብላ በስልክ ለእኔ ባለቤት የድምፅ መልእክት ተወችላት (ደውለው ለባለቤቴ የተውት የእሱም የእሷም የድምፅ መልዕክት ማስረጃው አለኝ)። ከዚያ ደጋግመው ደውለው ባለቤቴን አገኟትና ባልሽ ከሚስቴ ጋር ተኛ ብሎ ነገራት። ባለቤቴም በቃ ካጠፉ ይቅር እንበላቸው እና ነገሩ ይቁም አለችው።

ባለቤቴም ሁሉንም ነገር አልቀበል ስትል ወደ ቤተክርስቲያን ሄዱ። አቶ መላኩ ቤተክርስቲያን ሄዶ ፓስተር ተከስተ ከሚስቴ ጋር ተኝቷል አገልግሎት ማቆም አለበት ይቅርታ መጠየቅ አለበት አለ። እኔም የእግዚአብሔር ቃል እንደሚለው እና መንፈስ ቅዱስ እንደሚወቅሰኝ ከአንድ አገልጋይ የማይጠበቅ ጥፋት አጥፍቻለሁ። እግዚአብሔርንም በድያለሁ ለዛም እራሴን ከአገልግሎት አስቁሚያለሁ። እናንተንም ይቅርታ እጠይቃለሁ አልኩኝ። ሰዎቹ ዓላማቸው ክርስቲያናዊ ዕርቅ እንዳልሆነና አሳባቸውን በመቀየር ለሌላ ለተሻለ የበቀል እርምጃ ሊጠቀሙበት እንደሆነ አስቀድሜ ለሦስቱ ሽማግሌዎች ነግሬአቸው ነበር። ነገሩ በሰላም እንዲያልቅና ክርስቲያናዊ አካሄድ ነው ብዬ ስለማምን ሙሉ ኃላፊነት ወስጄ ይቅርታን ጠይቄአለሁ። አቶ መላኩ ግን የግብረሥጋ ግንኙነት ፈጽመሃልና እመን የሆነውንም ዝርዝር ነገር ንገረኝ ብሎ ጠየቀኝ። እኔም ሙሉ ኃላፊነት ወስጄ ይቅርታንም ጠይቄ የወይዘሮ ሆሳዕናን ስሜትና ስብእና የሚነካ ዝርዝር ነገር ውስጥ ግን እንደማልገባ አሳወቅሁኝ። ምክንያቱም እንደዚህ ዓይነት ነገር ያልተለመደ በመሆኑና አቶ መላኩ ማወቅ የሚፈልገውን መረጃ በሙሉ ከገዛ ሚስቱ ማግኘት ስለሚችል ነው። ቤተክርስቲያንም ፓሰተር ተከስተ ከአንድ አገልጋይ የማይጠበቅ ጥፋት አጥፍቻለሁ ብሎ
በራሱ ጥፋቱን አምኖ ንስሐ ገብቶአል አገልግሎትም አቁሞአል ፣አንተንም ይቅርታ ጠይቋል ነገሩ እዚህ ጋር ይለቅ ብለው ጠየቁት ። እነሱ ግን እኔን ለማጥፋት ቆርጠው ስለተነሱ ነገሩ እንዲቆም አልፈለጉም።

ቤተክርስቲያን መጥተው ያሰቡትን ያህል እኔን የጎዱኝ እና ያዋረዱኝ ስላልመሰላችው ቪ ኦ ኤ ሄደው ፓስተር ተከስተ አስገድዶ ደፍሮኛል ጉዳዩም በህግ ተይዞአል የሚል በሽምግልናው ወቅት በጭራሽ ያልተነሳ ሌላ ተጨማሪ የውሸት ታሪክ ፈጠሩ። ይህን አላማ እንዲያስፈጽም ጋዜጠኛ አዲሱ አበበን ይዘው መጡ። አቶ አዲሱ ጋር ስንነጋገር ሆን ብሎ እኔን ለማጥቃት እንዳሰበና እውነቱን ማወቅ እንደማይፈልግ ስለገመትኩ በጉዳዪ ለይ ምንም አይነት ኢንተርቪው ላንተ አልሰጥም፣ ጉዳዪም በቤተክርስቲያን ሽማግሌዎች ተይዟል አልኩት። የቤተክርስቲያን መሪዎች እና ጉዳዩን የያዙትም ሽማግሌዎችም አቶ አዲሱን ይሄ የቤተክርሰቲያን ነገር ነው በዚህ ነገር ላይ ምንም አይነት ፕሮግራም በሬዲዩ ላይ መሥራት የለብህም ብለው እየነገሩትና እየተለመነ በማን አለብኝነት ጉዳዩን አጣሞ ሁላችሁም እንደሰማችሁት እኔን በሚያዋርድ ፣ስሜን በሚያጠፋ፣ ሕይወቴንና አገልግሎቴን በሚያበላሽ መልኩ ፕሮግራሙን ሰርቶ በሬድዮ አቀረበው። አሁንም የምለው እኔ የበደሉኝን ሁሉ ይቅር ብያለሁ። እንደ ክርስቲያንና እንደ አገልጋይ አጉድዬ በተገኘሁባቸው ጉዳዮች ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ምህረትን ከባለቤቴና ከቤተክርስቲያኔ ደግሞ ይቅርታን አግኝቻለሁ። ዛሬ ደግሞ በእኔ ምክንያት ያዘናችሁትን ሁሉ ይቅርታ እጠይቃለሁ ብሏል።
አሁን እያሳየኸኝ ያለውን ማስረጃ ይዘህ ለማስተባበልና በሕግ ለመፋረድ እስከዛሬ ለምን ሙከራ አላደረግህም? ለሚለው ጥያቄም መልስ ሰጥቷል።

ሥሜንና ክብሬን በተመለከተ እኔ ሥምና የሚዋረድ ክብር የለኝም። እኔን ከጎዳና ላይ አንስቶ ሰው ያደረገኝ እግዚአብሔር ነው። ከእርሱ ውጭ በሰው የሚዋረድም የሚከብርም ማንነት የለኝም። ፍትህን በተመለከተ ደግሞ የምንኖርበት አሜሪካ የፍትህ አገር መሆኑን አውቃለሁ። የትኛውም ድርጅት፣ ባለሥልጣንም ሆነ ግለሰብ ከሕግ በታች መሆኑንም አውቃለሁ። ወንጌል አምኖ እንደዳነ ክርስቲያን ግን እግዚአብሔር ሁሉንም በጽድቅ ስለሚፈርድ ፍትህን ከእግዚአብሔር እንጂ ከማንም ሰው አልጠብቅም። ባለቤቴም ቢሆን ሁሉም ነገር በሰላምና በይቅርታ እንዲያልቅ ስለምትፈልግ ወደ ፍርድ ቤትም አልሄድንም። በዚህ አጋጣሚ ሳሚ በማያውቀውና በሌለበት ነገር በኔ ምክንያት ስለተሰቃየ ና በውሽት ስሙ ስለጠፋ በጣም ያዘንኩ መሆኔን እገልጻለሁ።

የቴዲ አፍሮ ምኞቶች

$
0
0

989TeddyAfro_NYC_26

ከያሬድ ኃይለማርያም

ዘረኝነትና ጥላቻ በመንግሥት ደረጃ በሚሰበክበት አገር፣ ድንቁርና እጅግ በተጫናቸው የወያኔ ቱባ ባለሥልጣናት ሕዝብ በሚዘለፍበት፣ ታሪክ ተጣሞ የአንድ ቋንቋ ተናጋሪን የሕብረተሰብ ክፍል በሌላው ላይ ለማነሳሳት ሌት ተቀን የሚደክሙና ጉርጓድ የሚምሱ ቡድኖችና ግለሰቦች ባሉበት አገር፣ ፍርሃትና ጥርጣሬ በነገሱበትና አፈና በበረታበት እንደ ኢትዮጵያ ባለ አገር እንደ ቴውድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ‹ ያሉ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች በማሕበረሰቡ ውስጥ ያላቸው ሚና በዘፈን ሕዝብን ከማዝናናት እጅግ ያለፈ ነው፡፡ የቴዲ ዘፈኖች ታሪክን ለሚክዱና ለሚያጣምሙ ማስተማሪያዎች ናቸው፡፡

በጥላቻ ጭንቅላታቸው ለናወዘና በጎጠኝነት በሽታ ለሚማቅቁም ፍቱን መድሃኒቶች ናቸው፡፡ የማንነት ቀውስ ለገጠማቸውም ጥሩ አስታዋሾች ናቸው፡፡ በፍርሃት ለሚማቅቁም ብርታት ናቸው፡፡ ከእውነት ለተጣሉም አስታራቂዎች ናቸው፡፡ በሥልጣን መባለግ ለሚናውዙም የማስጠንቀቂያ ደውሎች ናቸው፡፡ በፖለቲካ ቁርሾ ደም ለተቃቡም ፈዋሾች ናቸው፡፡ በፍቅር ለናወዙም የሃሳብ ሰረገሎች ናቸው፡፡ ቴዲ በዘፈኖቹ አገራዊና ግላዊ ሕይወታችንን የሚመለከቱ በርካታ ጉዳዮችን ዳሷል፡፡ ብዙዎች ያልደፈሯቸውን ጭብጥች ስሜትን በሚነካ መልኩ እያነሳ ውይይቶችን አጭሯል፡፡

በቁጥር ለመገመት የሚችግር አፍቃሪ ያለውን ያህል ስሙ ሲነሳ ወባ እንደነደፈው ሰው የሚያንዘፈዝፋቸውን ተቃዋሚዎችንም አፍርቷል፡፡ ይህም ነው ቴዲን ከዘፋኝነት አንድ ደረጃ ወደ ላይ ከፍ እንዲል የሚያደርገውም፡፡ ብዙ ዘፋኞች አንጋፋዎቹንም ጨምሮ ታሪካቸው በአድናቂ የተሞላ ነው፡፡ ምክንያቱም ቴዲ ያዜመባቸውን ፖለቲካዊ፣ ማሕበራዊና ኃይማኖታው ጭብጦች ፍጹም ሳይነኩና ሳይደፍሩ እድሜያቸውን የሚፈጁት ሁሉንም ለማስደሰት ነው፡፡ ሁሉንም ለማስደሰት ከራስ ጋር መፋታትን የግድ ይላል፡፡ ሕሊናን እንዳይነቃ አድርጎ ማስተኛትን ይጠይቃል፡፡

እራስን ሳይሆኑ ከሁሉም ጋር መስሎ የማደርን ወይም አድር ባይ የመሆን ክህሎትን ይጠይቃል፡፡ ከዛ በኋላ በልቶና ጠግቦ የሚያገሳውን እና ቁራጭ ዳቦ አሮበት በርሃብ ቁንጣን የሚሰቃየውን፣ ፍትሕ አጥቶና ነጻነቱን ተነፍጎ የሚማቅቀውንና በንጹሃን ደምና ስቃይ ኑሮውን የሚያደላድለውን፣ ዘመኑን የራሱ ብቻ ያደረገውንና አመታት ቢቀያየሩም ዘመን የራቀውን ሁሉ እኩል ማየት ይጀመራል፡፡ ቴዲ ከዚህ በሽታ በጊዜ ከተላቀቁ ጥቂት የኪነ-ጥበብ ሰዎች አንዱ ነው፡፡ እውነት በሁለት ተቃራኒ ጫፎች ላይ ለቆሙ ሰዎች እኩል አትመችም፡፡ የግድ ከሁለቱ አንዱ ለዛ እውነት በተቃሮኖ የቆሙ ናቸው፡፡

የቴዲ ዘፈኖችም ሁሉንም የማያስደስቱት ለዚህ ነው፡፡ ግፍ ይብቃ ብሎ የሚያዜመው ቴዲ ግፍ ፈፃሚዎቹንና ግፉአኑን እኩል ሊያስደስት አይችልም፡፡ ለዚህም ነው የተወሰኑ ዘፈኖቹ እየተመረጡ በሕዝባዊ መድረኮች እንዳይቀርቡ በወያኔ ባለሥልጣናት እገዳ የሚጣለው፡፡ ቴዲ ለእውነት፣ ለፍትህና ለፍቅር መቆም የሚያስከፍለውን ዋጋ እየከፈለ ያለ ብርቱ ሰው ነው፡፡ ስለሆነም በየማሕበረ ድረ-ገጾች ከአዲስ አመት ጋር ተያይዞ ስሙ ተደጋግሞ መነሳቱና መሞካሸቱ ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡ በዚህም የሚናደዱ ይኖራሉና መጪው ዘመን ልቦና የሚገዙበት ይሁን!

የቴዲን “ፍቅር ፈራን” ተጋብዛችኋል፡፡

መልካም አዲሰ አመት!!

ዘመኑ ቴዲ በዜማዎቹ የተመኘልን የፍቅር፣ የሰላም፣ የፍትህ፣ የአንድነትና የመተሳሰቢያ ይሁን!!!


የመንግስት ልሳን ፋና ራድዮ ሞላ አስገዶም ከሱዳን ኢትዮጵያ ገባ አለ

$
0
0

mola asgedom

Mola asgedom 2
ከአቤ ቶኪቻው

ሞላ አስገዶም የተባሉት የትህዴን ሸማቂ ቡድን መሬ፤ ዛሬ ኢትዮጵያ መግባታቸውን ራዲዮ ፋና ዘግቧል።
ራዲዮ ፋና እንዳለን ሰውዬው ወደ ሀገር ቤት የገቡት ሰባት መቶ የሚደርሱ ወታደሮቻቸውን ይዘው ነው። እርግጥ እኛ የደረሰን የፎቶ እና የሰው ማስረጃ የሚያሳየን የፋና ምንጮች ቁጥር እንደማይችሉ ነው። ሰውዬውን የተከተሏቸው ወይም ከመንገዱ ተርፈው ሱዳን ድንበር የደረሱት ታጣቂዎች ሰላሳ ከደረሱ ብዙ ናቸው።
ትላንት እና ከትላንት በስተያ የወጡ የመንግስት የስጋ ዘመድ የሆኑ ድረ ገጾች አቶ ሞላ አስገዶምን ‘ድሮውንም ስለላ ላይ ነበሩ… ከኢትዮጵያ ደህንነት እና መረጃ ክፍል ጋር ሲሰሩ ነበር…’ ብለውናል። ሰውዬው እውነትም ሰላይ ከነበሩ… እስከዛሬ የሰለሉት ነገር ቢኖር የገዛ ደህሚታቸውን ብቻ ነበር… አሁን አራት ጠመንጃ ያነገቱ ቡድኖች ሲጣመሩ እና ምክትል ሊቀመንበር ሲደረጉ ጥለው መውጣታቸው ዋና የስለላ አዝመራውን ትተውት እንደወጡ ሰነፍ ሰላይ ነው የሚቆጠሩት፤ (እና ቅጣት ይጠብቃቸዋል… ብለን እናላግጣለን!)

ራዲዮ ፋና እንዳለን ደግሞ ሰውዬው ‘ሀገሪቱን ለማተራመስ የሽብር ስራን ሲሰሩ የሰነበቱ’ ከሆነ… የመንግስትን አቀባበል አይተን የምናነሳው ጥያቄ ይኖረናል፤ አቶ ሌንጮ ለታ በሰላማዊ መንገድ አዲሳባ ሲገቡ ”ተመለሱ…” ብሎ የመለሳቸው መንግስት ዛሬ እነ ሞላ አስገዶምን ከነመሳሪያቸው እንኳን ደህና መጣችሁ ብሎ ከተቀበላቸው ያኔ በደንብ የምንጠያየቀው ይኖረናል::

የፋና ዜና ዘገባ እንደወረደ:-

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ራሱን የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደህሚት/ በማለት የሚጠራው እና በኤርትራ ውስጥ ሲንቀሳቀስ የነበረው የጦር ክፋይ ትናንት ወደ ሀገሩ ገባ።

ጦሩ የንቅናቄው መሪ በሆነው ሞላ አስገዶም እየተመራ ወደ ሀገር ውስጥ የገባው።

ቁጥራቸው ከ700 በላይ እንደሚሆኑ የተገመተው የደህሚት ጦር ከነ ሙሉ ትጥቁ ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ በሁመራ እና በመተማ አድርጎ ሰላማዊ በሆነ መንገድ መምጣቱን የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ምንጮች ተናግረዋል።

ጦሩ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ በመንገድ ላይ ትንኮሳ ሊፈጥሩበት ጥረት ያደረጉ የሻዕቢያ ሀይሎችን እየደመሰሰ ነው ወደ እናት ሀገሩ የገባው።

ጦሩ በሻዕቢያ እና ግንቦት 7 አስተባባሪነት በኢትዮጵያ ላይ የተለያዩ አደጋዎችን ለማድረስ ሲንቀሳቀስ መቆየቱ ይታወሳል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ መንግስት መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ጥቂት ስለ አርቲስት ሰብለ ተፈራ (እማማ ጨቤ)

$
0
0

በያሬድ ቁምቢና ውብዓለም ተስፋዬ

የአዲስ አመት ዋዜማ ጳጉሜ 5 ቱሉ ዲምቱ አቃቂ ደብረ ሰላም ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በመገኘት ‹የመዳን ቀን ዛሬ ነው› እና‹ የጅራፍ ንቅሳት› የተሰኙ ሁለት የራሷን ግጥሞች አቅርባለች፡፡
sebele tefera
ገና በስራዋ ስትታይ ድንቅ የትወና ብቃትና ፈጠራዋ የብዙዎችን ቀልብ መሳብ የቻለች ብርቅዬ ድንቅ አርቲስት ነበረች …ሰብለ ተፈራ፡፡ ፍጹም ባልተጠበቀ እና ድንገተኛ አደጋ ህይወቷ በማለፉ ቁጭትና ጸጸቱ የሚፋጅ ሆኗል፡፡ እጇ የነካው የጥበብ ስራ ሁሉ ያማረ የተዋጣለት ስለመሆኑ ሁሉም የሚስማማበት ጉዳይ ነው፡፡ አርቲስት ሰብለ ተፈራ (እማማ ጨቤ) አዲስ አበባ ከተማ ወሎ ሰፈር በተለምዶ አይቤክስ ሆቴል አካካቢ በ1968 ግንቦት 18 ዓ.ም ነው የተወለደችው፡፡በተወለደች በ40 ዓመቷ ትላንት ከሰዓት 10 30 ገደማ በድንገተኛ የመኪና አደጋ ህይወቷ አልፏል፡፡ ሰብለ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቷን በንፋስ ስልክ ትምህርት ቤት ያጠናቀቀች ሲሆን ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ደግሞ በንፋስ ስልክ አጠቃይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተምራለች፡፡ ዛሬ ላይ አብርቶና ደምቆ ለመታየት የበቃው የጥበብ አቅምና ብቃቷ የተጠነሰሰው ገና የ14 ዓመት ልጅ እግር እያለች ነበር፡፡ ከዚያም በ1984 ዓ.ም በዶክተር ተስፋዬ አበበ የቲያትር ሙያ ስልጠና አግኝታለች፡፡ የቲያትር ትምህርቷንም በመቀጠል በራክማኖፍ ኮሌጅ በትወና ዲፕሎማ በመያዝ ድንቅ ብቃቷን በትምህርት አግዛለች፡፡በዚህ ብቻ አላቆመችም እስክትለየን ድረስም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቲያትሪካል አርት ትምህርት ክፍል የዲግሪ ትምህርቷን እየተከታተለች ነበር፡፡ አርቲስት ሰብለ ከ20 በላይ ፊልሞች እንዲሁም ከ30 በላይ ቲያትሮች ላይ በመተወን ከመድረኮቹ ፈርጦች መካከል አንዷ ሆናለች፡፡ ጓደኛሞች ፣ላጤ፣ ሰቀቀን ፣ የሰርጉ ዋዜማ፣ ህይወት በየፈርጁ ፣እቡይ ደቀመዝሙር ፣ አምታታው በከተማ፣ የክፉ ቀን ደራሽ ፣አንድ ቃል፣ ወርቃማ ፍሬ፣ እንቁላሉ፣ 12 እብዶች በከተማ፣ ሩብ ጉዳይ፣ አብሮ አደግ፣ እነዚህ ቲያትሮች በሰብለ ተፈራም የተተወኑ ናቸው፡፡

አርቲስት ሰብለ ተፈራ በቲያትር አፏን የፈታችው ከአርቲስት ቴዎድሮስ ተስፋዬ ጋር በ‹ጭንቅሎ› ቲያትር ነው፡፡

ከተወነቻቸው ፊልሞች መካከልም ፈንጅ ወረዳ፣ ያረፈደ አራዳ፣ትንቢት፣ የሚሉት ፊልሞች ሰብለ ተፈራ ብቃቷን ያሳየችባቸው ናቸው፡፡

እንግሊዝ፣ አሜሪካ እና ሌሎች የአውሮፓ ሀገራት የእኛ ዕድር የሚለው ቲያትር በሰብለ ተፈራ ቀርቧል፡፡ በእስራኤል ‹ሴት ወንድሜ› የተሰኘ ቲያትር ይዛም ቀርባለች፡፡ አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ያውቀዋል ተብሎ በድፍረት የሚነገርለትና በዮናስ አብርሃም ተደርሶና ተዘጋጅቶ በፋና ብሮድካስቲግ ኮርፖሬት ለአምስት አመታት ገደማ በቀረበው ‹‹ ትንንሽ ፀሐዮች›› ተከታታይ የሬድዮ ድራማ እማማ ጨቤን አለማወቅ አይቻልም ፡፡ አዎ እማማ ጨቤ አራዳዋ፣ ዘመናዊዋ፣ ጨዋታ አዋቂዋ፣ ሞጃዋ ፣ጠርጣራዋ ፣ንግግር አዋቂዋ፣ ሆነው ይታወቃሉ፡፡ ‹እማማ ጨቤ› ያች ‹ሁሉ ሴት› ‹‹ብዙዋ ሴት›› ስጋ ለብሳ ነፍስ የዘራችው በአርቲስት ሰብለ ተፈራ ነው፡፡፡፡ በቤቶች የቴሌቭዥን ድራማ በመብልም በንግግርም አፏ ስራ የማይፈታው ድንቡሼዋ፣ ቦርቧራዋ፣ የማዕድ ቤቷ ንግስት ‹ ትርፌ › በሰብለ ተፈራ ውስጥ ነበረች፡፡ በአዲስ አበባ ባሉ ቲያትር ቤቶች የትወና አቅም ብቃቷን አሳይታለች፡፡ ልቆ የሚበልጠው የሰብለ ተፈራ ባለውለታነት ከአዲስ አበባ ውጪ ቲያትር ማቅረብ በማይታሰብበት፤ መንገዱ በሚፈትንበት፤ አዳራሽ እንደልብ በማይገኝበት፤ የጸሃዩ ሀሩር፣ ዝናቡ፣ ብርዱና ቆፈኑ መድረሻ በሚያሳጣበት በዚያን ወቅት በተለያዩ የክልል ከተሞች ለሚገኙ የጥበብ አፍቃሪዎች ቲያትርን እየተዟዟሩ ካሳዩት ለጥበብ ከተፈጠሩ ጥቂት አርቲስቶቻችን እና መስዋዕትነት ከከፈሉት መካከል አርቲት ሰብለ ተፈራ አንዷ ናት፡፡ አርቲስት ሰብለ ‹‹አልበም ›› የተሰኘውን ፊልም አዘጋጅታለች፡፡ ‹እርጥባን› በተሰኘው ቲያትርም ላይ በዳይሬክተርነት ሰርታለች፡፡ በርካታ የሬድዮና የቴሌቭዥን ማስታወቂዎች አርቲት ሰብለ ተፈራን ሲጋብዙ አይተናል ሰምተናል፡፡

sebele

ቅንነት፣ ደግነት፣ መልካምነት፣ አዛኝነት በተለይም ሰው መርዳት ለተቸገረ መድረስ የአርቲት ሰብለ ተፈራ የሰርክ ባህሪያት ናቸው፡፡አልችም አይሆንም የሚሉት ሃሳቦች በሰብለ ተፈራ ዘንድ የሉም፡፡ በተግባቢነት፣ በቀልድ አዋቂነት፣ ጥርስ ባለማስከደን ሰብለ ተፈራን የሚስተካከላት የለም፡፡

ሰብለ ተፈራ ከዓለማዊ ህይወቷ ይልቅ በመንፈሳዊ ህይወቷ የሚበልጥ ተሳትፎ ነበራት የሚባልላት አርቲስት ናት፡፡ በተለያዩ ቤተ ክስቲያናት በመገኘት በሙያዋ ታገለግል ነበር፡፡ የቅርቡን ብናነሳ የአዲስ አመት ዋዜማ ጳጉሜ 5 ቱሉ ዲምቱ አቃቂ ደብረ ሰላም ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በመገኘት ‹የመዳን ቀን ዛሬ ነው› እና‹ የጅራፍ ንቅሳት› የተሰኙ ሁለት የራሷን ግጥሞች አቅርባለች፡፡

አርቲስት ሰብለ ተፈራ ሚያዝያ 27 1999 ትዳር የመሰረተች ሲሆን ልጆች እንዳላፈራች ነው ለማወቅ የተቻለው፡፡

የአርቲት ሰብለ ተፈራ የቀብር ስነ ስርዓት ፡በካቴድራል ቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን ነገ ሰኞ መስከረም 3 2008 ከቀኑ 9 ሰዓት ወዳጅ ዘመዶቿና አድናቂዎቿ በተገኙበት ይፈጸማል፡
ለቅሶ ለመድረስ መልካም ፍቃድዎ ይሁንና፣ ላንቻ ግሎባልን አለፍ እንዳሉ ኮንኮርድ ሆቴል ሊደርሱ ጥቂት ሲቀርዎት በስተቀኝ ባለው መታጠፊያ ገባ እንዳሉ ያገኙታል ፡፡

ኢህአዴግ በረከት አይኖረውም!

$
0
0

ከዘኢትዮጵያ ጋዜጣ የተገኘ

አቶ በረከት ለትልቁ የኢህአዴግ ጉባኤ እንኳ ወደ መቀሌ አልሄዱም። የድርጅቱ አካሄድ የተያዘው አቅጣጫ አልተስማማኝም ብለው መቅረታቸው ተሰምቷል። ወዳጆቻቸው እነ አቶ አባይ ፀሐዬ በመተካካቱ የወጡ ሲሆን በረከት ግን በገዛ ፍቃዳቸው መልቀቃቸው ተነግሯል። በብአዴን (ብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ) ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት እንኳ ቢመረጡ ጨርሰው እንደማይቀበሉትና ከድርጅቱ ማናቸውም የፖለቲካ እንቅስቃሴ ተቆጥበው መቀመጥን መምረጣቸው ተገልጿል። አቶ መለስ ከሞቱ ወዲህ እንደነገሩ ሆነው ቢቆዩም፣ ራዕይ አስፈጻሚ፣ ወራሽ አውራሽ ሆነው ለመቀጠል ፍላጎቱ እንደነበራቸው አጀማመራቸው ያስታውቅ ነበር። አቶ መለስ ሲሞቱ እንዲህ ብለው ነበር፦
መለስን ሕይወቱ ከማለፉ ከአምስት ቀናት በፊት በስልክ አግኝቼ ስለ ጤንነቱ ጠይቄው ነበር፡፡ አስከፊውን ዜና የሰማሁት ሕይወቱ ባለፈ ጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ነው፡፡ በአጋጣሚ አጠገቡ አልነበርኩም፡፡ ተደወለልን፡፡ ከእንቅልፋችን ተቀስቅሰን ተሽሎታል የሚለውን ወሬ ሰምተን ስለነበር ተዝናንተን መተኛት ጀምረን ነበር፡፡ እና የመጨረሻዎቹ ቀናት ላይ ነው ችግር ያጋጠመው፡ ፡ ሲቀሰቅሱኝ ባልተለመደ ሰዓት ነበር፡፡ 5፡40 ላይ ሕይወቱ አልፎ 6፡10 ላይ ተቀሰቀስኩ፡፡ በዚህ ሰዓት ላይ የሚቀሰቅሰኝ ሰው ስላልነበረ “አቶ መለስ አርፏል” ማለት ነው የሚል ነገር ተሰማኝ፡፡ ያኔ በአንድ በኩል ባዶነት ተሰማኝ፤ በአንድ በኩል ደግሞ ትልቅ ኃይል ተሰማኝ፡፡ የዚህን ሰውዬ ራዕይ እንደ ኢሕአዴግ በቡድን ማሳካት አለብን የሚል ብርታት ሰጠኝ፡፡ እኔ አቶ መለስን እስከመጨረሻዋ ሰዓት ድረስ እየሠራ ነው የማውቀው፤ እየታገለ እየደከመ ራዕዩን እውን ለማድረግ ሲሠራ ነው የማውቀው፡፡ ሳጣው ባዶነት ብቻ አይደለም የተሰማኝ፤ ከፊቴ ሆኖ ሁሌም ወደፊት የሚጎትተኝ እንድሠራ የሚገፋፋኝ አሁንም ከጎኔ እንዳለ ነው የተሰማኝ፡፡

simon simon
አሁን ያ ስሜት ምን ሆነ? ምናልባት ለመለስብቻ ሲታዘዙ የኖሩት አቶ በረከት አሁን ከቀሩት የሕወሓት ኢህኢሃዴግ “ትርክምርኪዎች” ውስጥ ከፊት ሆኖ ወደፊት የሚጎትታቸው፣ ለሥራ የሚገፋፋቸው አንድም ሰው አላገኙ ይሆናል። እንኳን ብአዴን ወያኔ መባል ያኮራቸው የነበረው የኢህአዴጉ አቶ በረከት አሁን ዛሬ ላይ ደርሰው ሁሉ ነገር የደበራቸው መስልዋል። በፊትማ ለምሳሌ ሕወሃት 40ኛ ዓመቱን ሲያከብር፦

“እኛ ብአዴኖችም ሁሌም ቢሆን ራሳችንን ከህወሓት ነጥለን ያየንበት ጊዜ የለም። ሁላችንም “ወየንቲ ኢና” (ወያኔዎች ነን) ነው የምንለው።” ብለው የነበሩት አቶ በረከት ሰምዖን ወ/ገሪማ ዛሬ ማንንም መሆን አልፈለጉም።

ሰውየው በትውልድ ጎንደር በውልደት ከኤርትራ፣ በምልምል ከኢህአፓ፣ በድርጅት ከብአዴን በተጋድሎ ከወያኔ ሆነው እዚህም እዚያም እንደ ጆከር ሲሳቡ የኖሩ ሰው ናቸው።
ባንድ ወቅት፣ ህወሓቶች ጫካ በነበሩ ጊዜ፣ አቶ መለስ በሚገኙበት የፖለቲካ ጽ/ቤት ውስጥ፣ ከሳቸው ጋር የፖለቲካና በተለይም የፕሮፖጋንዳ ሥራውን በኃላፊነት የሚሠሩ ጥቂት ሰዎች ነበሩ። አቶ መለስ ዜናዊ፣ አቶ ዓለምሰገድ ገ/አምላክ (በክፍፍሉ ጊዜ የወጡት) አቶ አማረ አረጋዊና አቶ በረከት ሰምዖን ይገኙበታል። እንደሚባለው በአቶ መለስ ዜናዊና በአቶ በረከት ሰምዖን መካከል መቀራረቡ የተጀመረው ከዚያን ጊዜ አንስቶ ነው። ይበልጥ የተቀራረቡት ደግሞ በክፍፍሉ የፓርቲው የርዕዮተ ዓለም ሰው አቶ ዓለምሰገድ ከወጡ በኋላ ይመስላል።

ከዚያን ጊዜ አንስቶ አቶ መለስ የሚናገሩት አቶ በረከትን፣ አቶ በረከትም የሚያስፈጽሙት አቶ መለስን እየሆነ አንበደትና ጆሮ ሆነው ቀጥለዋል። ኢህአዴግ ውስጥ አቶ በረከትን ያለ አቶ መለስ ማሰብ አለመቻሉ እርግጥ እንደሆነ ሁሉ፣ አቶ መለስንም በረከት ማሰብ ቀላል አይደለም። መለስን በመሸጥ፣ በእያንዳንዱ ካድሬ ውስጥ በማስረጽ፣ አፈ ጮሌ ካድሬዎችን በመመልመል፣ የሕግ ባለሙያዎችን በተለይ ዳኞችን በመዘወር፣ የሚዲያ ተቋማትን በማሽከርከር፣ ባንኮችን በቦርድ በማስተዳደር፣ የኢህአዴግና የአቶ መለስ ትልቁ ባለውለታ ናቸው። አዳዲስ የሚበቅሉ የተቃዋሚ ድርጅቶችን ከስር ከስር እየተከታተሉ በመንቀል፣ በተለይም የግል ሚዲያዎችን በማዘጋትና ጋዜጠኞቻቸውን በማሰር ከአገር እንዲሰደዱ በማድረግ ነቃፊውን እየነቀሉ ደጋፊዎቻቸውን እየተከሉ የህወሓት ኢህአዴግን እድሜ ያሰነበቱ ሰው ናቸው። ያውቁታልና ግን አይሆኑ የሆኑለት ድርጅታቸው ካሁን በኋላ ብዙ ርቆ የሚሄድ አልመሰላቸውም።
simon

በረከት ትግርኛ ተናጋሪነታቸው ተጨምሮበት ብአዴንና ሕወሓት ውስጥ እየዘለሉ፣ መለስን ተደግፈው የሁለት ቤት ቤተኛ ነበሩ። አዛዥ ናዛዥ ሆነውም ኖረዋል። ወያኔዎቹ እኛ “ብአዴን” ነን አይበሉ እንጂ፣ እነ አቶ በረከት “ወያኔ ነን” ማለታቸው አይገርምም። በረከት ወያኔ ብቻ ሳይሆኑ ከተወሰነ ጊዜ በኋላም ወያኔዎችን ሳይቀር ሲያሾሩ የነበሩ ሰው ናቸው። በተለይ አቶ መለስ እንደቃታ ሲስቧቸው እንደ ጥይት እየተወነጨፉ ተቃዋሚዎቻቸውን ሲነድሉ ኖረዋል። ከበረሃ ጀምሮ የህወሃቶቹን አማርኛ ባማቅናት፣ የኢህአዴግ መግለጫዎችን በማዋዛት ቃል እያመነጩ ሲረጩ ሲያስረጩ የኖሩ ሰው ናቸው። “ኢሕአዴግ አስተዋይ እና አገሪቷን ከእንቅልፏ የቀሰቀሰ ድርጅት ነው” በማለትም ድርጅታቸውን የሚያሽሞነሙኑትን የአቶ በረከትን ውለታ ህወሓት/ ኢህዴጎቹ መቸም የሚረሱት አይሆንም። የኢህአዴጎቹ ክህደት እንደተጠበቀ ሆኖ በአገልግሎት ዘመናቸው አቶ በረከት ብዙ ጠላቶችን ያፈሩ በመሆናቸው ባላንጣዎቻቸው ብዙ ናቸው።

በተለይም በሕወሓት ካድሬዎችና ደጋፊዎች ዘንድ፣ በኤርትራ ተወላጅነታቸው ስለሚታወቁ፣ በሳቸው ላይ የሚሰነዘረውን ጭፍን ጥላቻ ለማንበብ የትኛውንም የህወሃት ካድሬ ጎተት አድርጎ ስለ አቶ በረከት መጠየቅ በቂ ነው።

በረከት ግን ለህወሓቶቹ እንደሱ አይደሉም። የማለዳው የትግል አጋራቸው አቶ ያሬድ ጥበቡ፣ ጥር 11/2004 ፍትህ ጋዜጣ ላይ እንዳስነበቡንና አቶ በረከትም በሁለት ምርጫዎች ወግ መጽሐፋቸው ቀዳሚ ገጽ ላይ እንደገለጸሉን፣ ካህሳሁን ገብረ ሕይወት የሚባል ታላቅ ወንድም ነበራቸው። በወያኔዎቹ ስለተገደለው ካሣሁን አቶ ያሬድ እንዲህ ብለዋል፦

ካሳሁንን በኢህአፓ ሰራዊት ውስጥ አውቀው ነበር ፡፡ እጅግ ተወዳጅ ሰው እንደነበር ትዝ ይለኛል ፡፡ ታዲያ ተሓህት ‹‹ትግሬ ለትግሬዎች ፣ የትልቋ ኢትዮጵያ (በትግርኛ ዓባይ ኢትዮጵያ ይሉታል) ህልመኞች ከሃገራችን ውጡ›› ብሎ ድንገት በከፈተብን ጥቃት ካሳሁን ውጊያ ላይ ተማረከ ፡፡ ከጠባቂዎቹ አምልጦ በአካባቢው ወደነበረችው የጀብሓ አሃዱ አስጥሉኝ ብሎ ሲሮጥ የወያኔ ዘቦች በጀርባው ባወረዱበት የመትረየስ ጥይት ተመትቶ እንደተሰዋ አሳዛኙ ዜና ደረሰን ፡፡ አዎን ካሳሁን ‹‹ትግራይ የኢትዮጵያ አይደለችም፣ የአማራና የትግሬ ለማኞች አብረው መለመን እንኳ አይችሉም›› ብለው የትግራይን ህዝብ ይቀሰቅሱ በነበሩ ጠባብ ብሄርተኞች እጅ ነበር የወደቀው ፡፡ ታዲያ በ1992 ህወሃት አመራር ውስጥ ክፍፍል ሲፈጠር፣ በረከት የመለስ አዳኝ ሆኖ የቆመ በመምሰል የወንድሙን ገዳዮች በከፊል የተበቀላቸው ነበር የመሰለኝ ፡፡ ሆኖም እዚህ የመጀመሪያ ገፅ ላይ ወንድሙን ካሳሁንን ‹‹እነሆ በተለምክልኝ መንገድ እጉዋዛለሁ›› ሲል፣ በረከት ከጠባብ ብሄርተኞች ጋር የሚያደርገው ትግል አሁንም የቀጠለ መሆኑን ነው ሹክ የሚለን ፡፡

ተስፋዬ ገ/አብ በሌላ ጽሑፍ እንደገለጸው ደግሞ የአቶ በከረት ስምዖን እውነተኛ ስም መብራህቱ ገ/ሕይወት ሲሆን አቶ በረከት ለራሳቸው ያወጡት ስም በኢህአፓ አባልነቱ ተገድሏል ብለው ካሉት ከእውነተኛው አቶ በረከት ሰምዖን የወሰዱት ስም ነው። እንደ አጻጻፉ ከሆነ ሞቷል የተባለው ሌላኛው በረከት ሰምዖን አሁንም አውሮፓ ውስጥ በህይወት ያለ ሲሆን ወንድምና እህቶቹም የኤርትራ ባለሥልጣናት ሆነው ይሠራሉ።

ከተወሳሰበው ህይወታቸው ሌላ፣ የተወሳሰበው የፖለቲካ ድርጅት ውስጥ ዋነኛ ተዋናይ የሆኑት አቶ በረከት፣ አቶ ያሬድ እንደሚጠቅሱላቸው በሙስና አይታሙም። “በረከትን ቀረብ ብለው ያዩት ሁሉ የሚመሰክሩለት አንድ ነገር ቢኖር ‹‹ከምቀበርባት ስድስት ክንድ መሬት በቀር ሌላ ሃብት አልፈልግም’ ማለቱን ነው” ካሉ በኋላ “የነዚህን ሁሉ አንድምታ ወደፊት የምናየው ይሆናል ፡፡” ብለዋል። አቶ ያሬድ እንዳሉትም የአቶ በረከት ሃብት ወደፊት የሚታይ ይሆናል። የጤና እክል እንዳለባቸው የሚነገረው አቶ በረከት ግን “እኔን የሚያሳስበኝ የጤናቸው ጉዳይ ነው፡ ፡” እያሉ ባለሥልጣናትን በኃላፊነት መንከባከባቸውን የሚገልጹት ሼኽ መሀመድ ሁሴን አል አሙዲ፣ በአቶ በረከት መጽሐፍ ምረቃ ላይ እንዲህ ብለው ነበር፦

“አቶ በረከት እንዳለው ደቡብ አፍሪካ ሄጄ ጠይቄዋለሁ፤ የጠየኩት ግን አመፀኛ እና ልውጣ
ብሎ ስለሚያስቸግር ነው፡፡ ታከም፣ እረፍ ሲባል እሺ አይልም፡፡ እኔ ደቡብ አፍሪካ ሄጄ መጀመሪያ ያደረኩት ክፍሉን በሴኪዩሪቲ ማስከበብ ነበር፡፡ እሱ ግን በኋላ የብአዴን 25ኛ ዓመት በዓል ላይ ካልተገኘሁ ብሎ አስቸገረ ቃል አስገብቼ ይዤው መጣሁ፡፡ በ48 ሰዓት ውስጥ አንጠልጥዬ መለስኩት፤ እኔን የሚያሳስበኝ የጤናቸው ጉዳይ ነው፡፡”
በሙስና የማይታሙት አቶ በረከት ያሻቸውን በፈለጉ ጊዜ ግን የሚያዙት ቢሊየነር አላቸው። “አላሙዲን ጠይቄው አሳፍሮኝ አያውቅም” በማለት በመጽሐፋቸው ምረቃ ቀን እንዲህ ብለው ነበር ፦

“የእኔ ሥራ መጽሐፉን መጻፍ ብቻ ነበር፡፡ አልአሙዲ እንዲያሳትመው መመሪያ ብቻ ነው የሰጠሁት፡
፡ ደወልኩ እና እነዚህን መጽሐፎች ታሳትማቸዋለህ አልኩት” በማለት መጽሐፉን ከኢትዮጵያ ውጪ ከማሳተም ጀምሮ እንዲያ ባለ በደመቀ ሥነ ሥርዐት እንዲመረቅ የማድረግ ወጪውን ሼኹ እንደሸፈኑ መግለጻቸው በወቅቱ በአዲስ አድማስ ተመዘግቧል፡፡ ህመም ገጥሞኝ ደቡብ አፍሪካ ለሕክምና በሄድኩ ጊዜ እዛ ድረስ መጥቶ ጠይቆኝ ነበር፡፡ የልብ ወዳጆች ነን፡፡ አሊ አልአሙዲ ወሬኛ ነው፡፡ ጨዋታ ይወዳል ውጭ አገርም ሄዶ ቢሆን ሦስት ቀን አያድርም፤ ይደውላል፤ ደውሎም ቀልድ አዋቂ ነው ተሳስቀን ነው የምንለያየው፡፡ አሊ አልአሙዲ ሣቅ እና ዕድሜህን ያብዛልህ” በማለት ምርቃቱን አውርደውት ነበር፡፡
እንግዲህ አሁን አቶ በረከት ፖለቲካውም በቃኝ ወደማለቱ መምጣታቸው ተሰምቷል። ወይም ፖለቲካውም እንደ እሳቸው ያሉትን በቃኝ ብሏቸው ሊሆን ይችላል። ለማንኛውም በዓይን ጥቀሻ ብቻ ይጠሯቸው የነበሩ ግልገል ካድሬዎቻቸው አገር ሲመሩ ወይም ሲያደናብሩ እያዩ የሥራ ፍሬያቸውን በትዝታ ይቃኙት ይሆናል። እስከማኩረፍ ያደረሳቸው የሁኔታዎች መበለሻሸት ግን፣ በቃ ከእንግዲህ ኢህአዴግ በረከት የለውም ሳያሰኛቸው አይቀርም።

አቡነ አትናቴዎስ በሚኒሶታ ለሚገኙት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ ምዕመናን ያስተላለፉት መልዕክት

$
0
0

አቡነ አትናቴዎስ በሚኒሶታ ለሚገኙት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ ምዕመናን ያስተላለፉት መልዕክት:-
abune
abune atnatwos

በኢትዮጵያ በፕሮቴስታንት ቤተክርስትያን ፓስተሮች እና ዘማሪዎች አማካኝነት በግልጽ እየተፈጸመ ያለ የዝሙት ጅሀዳዊ ሐረካት ኑዛዜ

$
0
0

“ፍሬም ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ፥ ይልቁን ግለጡት እንጂ፥ እነርሱ በስውር ስለሚያደርጉት መናገር እንኳ ነውር ነውና፤ ሁሉ ግን በብርሃን ሲገለጥ ይታያል፤ የሚታየው ሁሉ ብርሃን ነውና። ኤፌ 5:11-12

ቢንያም መንገሻ September 13,2015

የእግዚያብሔር ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ለእውነተኛ ክርስቲያኖች የየእለት እለት የህይወት አኗኗር የኑሮ ዘይቤ እንዲተዳደሩበት እና እንደተጻፈው ህግ እንዲኖሩበት ከእግዚያብሔር ዘንድ የተሰጠ ታላቅ የህግ እና ስርአት ያለው የዘላለም ህይወት የሚገኝበት መጽሐፍ ነው:: ይሁን እንጂ ዛሬዛሬ አያሌ የፕሮቴስታንት የቤተ እምነት አስተማሪዎች ( ሽማግሌዎች ፣ ፓስተሮች እና ነቢያቶች) እንዲሁም የተቋሙ ባለቤቶች በግልጽ ቃሉን በህገ ወጥ መልኩ አስጸያፊ ለሆነው ለስጋዊ ፍጆታቸው ሲጠቀሙበት ማየት ዛሬዛሬ እንደ አንድ የጸጋ ስጦታ ተደርጎ ተቆጥሮላቸዋል:: በዚህ ባለንበት በመጨረሻ የዘመን ፍጻሜ በኢትዮጵያ ያሉ የፕሮቴስታንት አገልጋዮች በአብዛኛዎቹ ማለት ይቻላል ስለመጨረሻው ዘመን ፍጻሜ መቅረብን አስመልክቶ ለምልክት እንዲሆን ከእግዚያብሔር ዘንድ ከተሰጡት እና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጻፉት የትንቢት ቃሎች ብዙዎቹ የተፈጸሙ ሲሆን ቀሪዎቹም በመፈጸም ላይ ናቸው:: ብዙዎቹ የትንቢት ቃሎች የሚፈጸሙት ደግሞ በእግዚያብሔር ስም እና የእግዚያብሔር ስም በሚጠራበት ቤት ውስጥ መሆኑ ደግሞ የዘላለም ህይወትን የሚገኝበትን የክርስቲያኖችን ፈተና እጅግ አክብዶታል:: ለዚህም ነው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በዘመኑ መጨረሻ እንደአሸን ፈልተው በስሙ የሚያስተምሩትን ሀሰተኛ አስተማሪዎች፣እረኞች እና ነቢያቶችን እንድንጠነቀቅ ብዙ ግዜ አበክሮ አስጠንቅቆናል:: “እንዳትስቱ ተጠንቀቁ፤ ብዙዎች። እኔ ነኝ፥ ዘመኑም ቀርቦአል እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ እነርሱን ተከትላችሁ አትሂዱ።” ሉቃ 21:8
rp_pastor-getenet-tekeste-zemari-sa.jpg
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በመጨረሻው ዘመን በስሙ ስለሚገለጡ ሀሰተኛ ከዲያብሎስ ወገን የሆኑ አስተማሪዎች፣እረኞች እና ነቢያቶችን የምናውቃቸው በፍሬያቸው ማለትም ተገልጦ በሚታይ ህይወታቸው እና ስራቸው እንደሆነ የእግዚያብሔር ቃል እንዲህ በማለት ያስተምረናል:: “የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ። ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን?” ማቴ 7:17_17“ብርሃንም ወደ ዓለም ስለ መጣ ሰዎችም ሥራቸው ክፉ ነበርና ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ስለ ወደዱ ፍርዱ ይህ ነው። ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፥ ሥራውም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም፤ እውነትን የሚያደርግ ግን ሥራው በእግዚአብሔር ተደርጎ እንደ ሆነ ይገለጥ ዘንድ ወደ ብርሃን ይመጣል።” ዮሐ3:19:21

በዛሬ ግዜ በኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያ ውጭ የሚገኙ የፕሮቴስታንት ቤተ እምነት ተቋማቶች ውስጥ የሚገኙ አገልጋዮች በአብዛኛዎቹ ለበጎ ነገር ምንም አይነት ፍቅር ሳይኖራቸው ለክፉ ነገር ግን ፍቅራቸውን ሲያየው ዲያብሎስ እራሱ እንኳ በእጅጉን ይቀናባቸዋል:: ዛሬ ዛሬ በግልጽ የፕሮቴስታንት አስተማሪዎች፣እረኞች እና ነቢያቶች ዋና መታወቂያቸው (ፍሬያቸው) ልቅ የዝሙት እርኩሰት፣ ያለመጠን ገንዘብን መውደድ ፣ ለበጎ ነገር እርስ በእርስ መጠላላት ፣ ውሸት ፣ እብሪት ፣ ቅናት ፣ አድመኝነት ከአለማውያን በላይ እየተንሰፈሰፉ አለምን የመውደድ ፍቅር በእጅጉን በግልጽ በየእለት እለት የስብከት ስጋ አገልግሎታቸው እና ህይወታቸው የሚታይ ሲሆን በተቃራኒው ደግሞ በጸያፍ የዝሙት ፣ የስርቆት ፣ የስካር ቅጥ ያጣ አለመኛ የሆኑ አስተማሪዎች ፣ እረኞች እና ነቢያቶች ጸያፍ የሀጢያት እርኩሰት ስራቸው ጸሐይ ላይ ሲወጣባቸው ደግሞ ጉድ በሚያስብል ፍቅራቸው በእግዚያብሔር ፊት ወድቀው ንስሀ ከመግባት ይልቅ ለስማቸው እና ለክብራቸው በመቆርቆርና ሰውእንዳይሰማ በማለት ከአዲስ አበባ እስከ ዋሽንግተን እንዲሁም ካናዳ ድረስ ሁሉም በተገለጠው ጸያፍ ሀጢያታቸው ላይ የተገለጠውን ህፍረተ ስጋቸውን ለመሸፈን ደራርበው “ብሉኮ” እና “ብርድ ልብስ” ሲያለብሱት ይታያል:: የእዚያብሔር ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስም እንደነዚህ አይነቶች ስላሉት አስተማሪዎች ፣ እረኞች እና ነቢያቶች በትንቢት ቃሉ እንዲህ በማለት ያስተምረናል:: “እንደ እነዚህ ያሉ ሰዎች የክርስቶስን ሐዋርያት እንዲመስሉ ራሳቸውን እየለወጡ፥ ውሸተኞች ሐዋርያትና ተንኮለኞች ሠራተኞች ናቸውና። ይህም ድንቅ አይደለም፤ ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣልና። እንግዲህ አገልጋዮቹ ደግሞ የጽድቅን አገልጋዮች እንዲመስሉ ራሳቸውን ቢለውጡ ታላቅ ነገር አይደለም፤ ፍጻሜአቸውም እንደ ሥራቸው ይሆናል።” 2ቆሮ11:13_15

“ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ።ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና፥ ገንዘብን የሚወዱ፥ ትምክህተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ የማያመሰግኑ፥ ቅድስና የሌላቸው፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኞች፥ ራሳቸውን የማይገዙ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን የማይወዱ፥ ከዳተኞች፥ ችኩሎች፥ በትዕቢት የተነፉ፥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ፤ የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ።” 2ጢሞ3:1-5“ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ መካከል ነበሩ እንዲሁም በመካከላችሁ ደግሞ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይሆናሉ፤ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው የሚፈጥንን ጥፋት በራሳቸው ላይ እየሳቡ የሚያጠፋ ኑፋቄን አሹልከው ያገባሉ፤ ብዙዎችም በመዳራታቸው ይከተሉአቸዋል በእነርሱም ጠንቅ የእውነት መንገድ ይሰደባል። ገንዘብንም በመመኘት በተፈጠረ ነገር ይረቡባችኋል፤ ፍርዳቸውም ከጥንት ጀምሮ አይዘገይም ጥፋታቸውም አያንቀላፋም።” 2ጴጥ2:1-3“እነዚህም ስለ ነውረኛ ረብ የማይገባውን እያስተማሩ ቤቶችን በሞላው ስለ ሚገለብጡ፥ አፋቸውን መዝጋት ይገባል።” ቲቶ 1:11“ወዳጆች ሆይ፥ ነፍስን ከሚዋጋ ሥጋዊ ምኞት ትርቁ ዘንድ እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ እለምናችኋለሁ፤ ስለሚመለከቱት ስለ መልካም ሥራችሁ፥ ክፉ እንደምታደርጉ በዚያ እናንተን በሚያሙበት ነገር፥ በሚጎበኝበት ቀን እግዚአብሔርን ያከብሩት ዘንድ በአሕዛብ መካከል ኑሮአችሁ መልካም ይሁን።” 1ጴጥ2:11-12“ፍሬም ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ፥ ይልቁን ግለጡት እንጂ፥ እነርሱ በስውር ስለሚያደርጉት መናገር እንኳ ነውር ነውና፤ ሁሉ ግን በብርሃን ሲገለጥ ይታያል፤ የሚታየው ሁሉ ብርሃን ነውና። ኤፌ 5:11-12

ዛሬዛሬ ማንም ፓስተር እና ነቢይ መሆን የፈለገ ሰው ከጫት ላይ ተነስቶ የቃመውን ጫት በጉንጩ እንደያዘ የእግዚያብሔርን መንግስት ቃልን ማስተማር ፣ እረኛ እና ነቢይ መሆን ይችላል:: ዛሬዛሬ ማንም ፓስተር እና ነቢይ መሆን የፈለገ ሰው ከሚጠጣው አስካሪ የአልኮል መጥጥ ላይ ተነስቶ የሚጨልጥበትን ብርጭቆ እንደያዘ የእግዚያብሔርን መንግስት ቃልን ማስተማር ፣ እረኛ እና ነቢይ መሆን ይችላል:: ዛሬዛሬ ማንም ፓስተር እና ነቢይ መሆን የፈለገ ሰው ከዝሙት አልጋ ላይ ተነስቶ የሚዘሙትበትን ኮንዶም በኪሱ እንደያዘ የእግዚያብሔርን መንግስት ቃልን ማስተማር ፣ እረኛ እና ነቢይ መሆን ይችላል:: ዛሬዛሬ በኢትዮጵያ ፕሮቴስታንት ቤተእምነት ውስጥ አብዛኛዎቹ አስተማሪዎች የሚያስተምሩት ሳይማሩ ነው:: አብዛኛዎቹ እረኞች እረኛ የሆኑት የራሳቸውን ቤተሰቦች መጠበቅ አቅቷቸው በትነው ነው:: አብዛኛዎቹ ዘማሪዎች የሚዘምሩት የዝማሬ ጸጋ ከእግዚያብሔር ዘንድ ተሰጥቶዋቸው ሳይሆን ድምጸ መርዋ ስለሆኑ እና በገንዘብም ረገድ ስለሚያዋጣ እና ጥሩ ገቢ ስለሆነ በሰዎች ተመስክሮላቸው እና ተመክረው ጭምር ነው:: አብዛኛዎቹ ሰባኪዎች የሚሰብኩት የእግዚያብሔርን ቃል አውቀውት እና ተረድተውት ሳይሆን ወሬ ማውራት ስለቻሉ ብቻ ነው:: ለዚህም አብዛኞቹ ሰባኪዎች ከሰበኩ ቡኋላ ነው መጽሐፍ ቅዱስን የሚያነቡት:: አብዛኛው ምእመና ሞቅ ተደርጎ በተሰበከው ስብከት የሞቀ “ሀሌሉያ!” እና “ኢየሱስ ጌታ ነው!” ብሎ በስሜት የሚጮኅውና የሚዘለው እንዲሁም እቃ የሚሰብረው የእግዚያብሔርን ቃል የመጽሐፍ ቅዱስን አውቀውት እና ተረድተውት ሳይሆን እንዲያው ካለምንም ማስረጃ በሉ ስለተባሉ ብቻ ነው:: ስለሆነም ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በትንቢት ቃሉ እግዚያብሔር ህዝቤ እውቀት ከማጣት የተነሰ ጠፋ (የገሀነም እሳት ማገዶ ሆኑ) ይለናል:: “ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል፤ አንተም እውቀትን ጠልተሃልና እኔ ካህን እንዳትሆነኝ እጠላሃለሁ፤ የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ። እንደ ብዛታቸው መጠን ኃጢአት ሠሩብኝ፤ እኔም ክብራቸውን ወደ ነውር እለውጣለሁ።” ትንቢተ ሆሴ 4:6-7 “ክፉውን መልካም መልካሙን ክፉ ለሚሉ፥ ጨለማውን ብርሃን ብርሃኑንም ጨለማ ለሚያደርጉ፥ ጣፋጩን መራራ መራራውንም ጣፋጭ ለሚያደርጉ ወዮላቸው! በዓይናቸው ጥበበኞች በነፍሳቸውም አስተዋዮች ለሆኑ ወዮላቸው! የወይን ጠጅ ለመጠጣት ኃያላን የሚያሰክረውንም ለማደባለቅ ጨካኞች ለሆኑ፤ በደለኛውን ስለ ጉቦ ጻድቅ ለሚያደርጉ፥ የጻድቁንም ጽድቅ ለሚያስወግዱበት ወዮላቸው!” ኢሳ 5:20_23

“እነዚህን አስተምርና ምከር። ማንም ልዩ ትምህርት የሚያስተምር ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ በሆነው ጤናማ ቃልና እግዚአብሔርን ለመምሰል በሚስማማ ትምህርት የማይጠጋ ቢሆን፥ በትዕቢት ተነፍቶአል አንዳችም አያውቅም፥ ነገር ግን ምርመራን በቃልም መዋጋትን እንደ በሽተኛ ይናፍቃል፤ ከእነዚህም ቅንዓትና ክርክር ስድብም ክፉ አሳብም እርስ በርስ መናደድም ይወጣሉ፥ አእምሮአቸውም በጠፋባቸው እውነትንም በተቀሙ፥ እግዚአብሔርን መምሰል ማትረፊያ የሚሆን በመሰላቸው ሰዎች ይገኛሉ። እንደነዚህ ካሉት ራቅ።” 1 ጢሞ 6:3-5 “ኑሮዬ ይበቃኛል ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤ ወደ ዓለም ምንም እንኳ አላመጣንምና፥ አንዳችንም ልንወስድ አይቻለንም፤ ምግብና ልብስ ከኖረን ግን፥ እርሱ ይበቃናል። ዳሩ ግን ባለ ጠጎች ሊሆኑ የሚፈልጉ በጥፋትና በመፍረስ ሰዎችን በሚያሰጥምና በሚያሰንፍ በሚጎዳም በብዙ ምኞትና በፈተና በወጥመድም ይወድቃሉ። ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፥ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ፥ ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ። አንተ ግን፥ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ ከዚህ ሽሽ፤ ጽድቅንና እግዚአብሔርን መምሰል እምነትንም ፍቅርንም መጽናትንም የዋህነትንም ተከታተል።” 1 ጢሞ 6:6-11

ዛሬ አብዛኞቻችን በእግዚያብሔር አይን ስንታይ አስጸያፊ በሆነ የሀጢያት እርኩሰት ውስጥ ተዘፍቀናል:: ለዚህም ደግሞ እንደ ዋና ምክንያት ተደርጎ የሚወሰደው እራሳቸውን በራሳቸው እና በኮሚቴ እርስ በእርስ የተሿሿሙት እና የተመራረጡት የፕሮቴስታንት የቤተ እምነት ባለቤቶች (ሽማግሌዎች ፣ ፓስተሮች እና ነቢያቶች) በግፍ እና በድፍረት ያለማንም ከልካይ በሀጢያት እርኩሰት ውስጥ በግልጽ ሲጨፍሩ እና ሲኖሩ ማየት እና መስማት ዛሬዛሬ በቤተ እምነቱ አማኝ ዘንድ የተለመደ የአምልኮ ህይወት ነው:: ለዚህም አገልጋዮች በክፉዋ የ“ኤልዛቤል” እርኩስ የዲያብሎስ መንፈስ ተይዘው የሚያስተምሩት እና በህይወታቸው የሚገልጡት ፍሬ መራራ ስለሆነ የእነሱም ተማሪዎች (ምእመናዎችም) ልዩ ልዩ የሀጢያት እርኩሰቶችን በግልጽ ተለማምደውት በተገለጠ ህይወታቸው ሲኖሩት ማየት አሁን አሁን በፕሮቴስታንት ቤተእምነት የሀጢያት እርኩሰት በተለይም “ዝሙት” እንደ ጸጋ ስጦታ የሚታይበት ዘመን ላይ መድረሳችን ያመላክታል:: የእግዚያብሔር ቃልም እንደነዚህ አይነት አገልጋዮችን እንደዚህ በማለት በትንቢታዊ ቃሉ ያስጠነቅቀናል::

“ቃል የሌለው አህያ በሰው ቃል ተናግሮ የነቢዩን እብድነት አገደ። ድቅድቅ ጨለማ ለዘላለም የተጠበቀላቸው እነዚህ ውኃ የሌለባቸው ምንጮች በዐውሎ ነፋስም የተነዱ ደመናዎች ናቸው። ከንቱና ከመጠን ይልቅ ታላቅ የሆነውን ቃል ይናገራሉና፥ በስሕተትም ከሚኖሩት አሁን የሚያመልጡትን በሥጋ ሴሰኛ ምኞት ያታልላሉ። ራሳቸው የጥፋት ባሪያዎች ሆነው። አርነት ትወጣላችሁ እያሉ ተስፋ ይሰጡአቸዋል፤ ሰው ለተሸነፈበት ለእርሱ ተገዝቶ ባሪያ ነውና።በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ከዓለም ርኵሰት ካመለጡ በኋላ ዳግመኛ በእርስዋ ተጠላልፈው የተሸነፉ ቢሆኑ፥ ከፊተኛው ኑሮአቸው ይልቅ የኋለኛው የባሰ ሆኖባቸዋል። አውቀዋት ከተሰጣቸው ከቅድስት ትእዛዝ ከሚመለሱ የጽድቅን መንገድ ባላወቋት በተሻላቸው ነበርና። ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል፥ ደግሞ። የታጠበች እርያ በጭቃ ለመንከባለል ትመለሳለች እንደሚባል እውነተኞች ምሳሌዎች ሆኖባቸዋል።”2 ጴጥ 2:16-22

እውነተኛ ክርስትያን ማንም ቢሰብከው እና ቢያስተምረው ትምህርቱ እውነት እንደሆነ ከእግዚያብሔር ቃል ጋር እየመረመረ ያመሳክራል እንጂ ስለተሰበከ ብቻ እውነት ነው ብሎ አይቀበልም:: የእግዚያብሔርም ቃል ሁሉንም የምንማራቸውን ትምህርቶች ከመጽሐፍ ቅዱስ በማስተያየት መመርመር እንዳለብን አብክሮ ያስጠነቅቀናል:: “ወዳጆች ሆይ፥ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፥ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ፤ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።” 1ዮሐ4:1 “እነዚህም በተሰሎንቄ ከሚኖሩት ይልቅ ልበ ሰፊዎች ነበሩና። ነገሩ እንደዚሁ ይሆንን? ብለው ዕለት ዕለት መጻሕፍትን እየመረመሩ ቃሉን በሙሉ ፈቃድ ተቀበሉ።” ሐዋ 17:11 “የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ትንቢት የሚናገሩላችሁን የነቢያትን ቃል አትሰሙ፤ ከንቱነትን ያስተምሩአችኋል፤ ከእግዚአብሔር አፍ ሳይሆን ከገዛ ልባቸው የወጣውን ራእይ ይናገራሉ።” ኤር 23:16 “ራሳችንን ብንመረምር ግን ባልተፈረደብንም ነበር፤ ነገር ግን በተፈረደብን ጊዜ ከዓለም ጋር እንዳንኮነን በጌታ እንገሠጻለን።” 1 ቆሮ 11:31-32 “በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ::” 2 ቆሮ 13:5

ለመግቢያ ከላይ በሰፊው እንደጠቀስኩት ስለ ፕሮቴስታንት የቤተ እምነት ባለቤቶች (ሽማግሌዎች ፣ ፓስተሮች እና ነቢያቶች) ጸያፍ የድፍረት ሀጢያት እርኩሰት የተገለጠ ህይወታቸውን መነሻ በማድረግ ይህን የዛሬውን መልእክቴን እንድጽፍ ካነሳሳኝ አንዱ እና ዋናው ነገር ከአንድ ሳምንት በፊት በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ አብዛኛዎቻችን ያነበብነው አንድ ዜና ነበር ያም ዜና ዘማሪ ተከስተ ጌትነት ወደ መደበኛው ስራው መመለሱን የሚናገር ዜና ሲሆን እኔ በግሌ እንደክርስቲያን ነገሩ በጣም አሳዝኖኛል:: ያዘንኩበትም አንዱ እና ዋናው ነገር ዘማሪ ተከስተ ወደ መደበኛው ስራው መመለሱ ሳይሆን እንዲመለስ የተደረገበት የአሰራር ሂደት ፍጹም አጋንንታዊ አሰራር መሆኑን ደግሞ ስረዳው እጅግ እጅግ ድርጊቱ ዘግንኖኛል:: እንደነዚህ ካሉት ሰዎች ጋር ምግብ እንኳን እንዳንበላ እንዲውም ከእነርሱም እንድንርቅ እንድንፈርድባቸውም እንኳ የእግዚያብሔር ቃል አበክሮ ያዘናል:: “ከሴሰኞች ጋር እንዳትተባበሩ በመልእክቴ ጻፍሁላችሁ። በጠቅላላው የዚህን ዓለም ሴሰኞችን፥ ወይም ገንዘብን የሚመኙትን ነጣቂዎችንም፥ ወይም ጣዖትን የሚያመልኩትን አላልሁም፤ ይህስ ቢሆን ከዓለም ልትወጡ ይገባችሁ ነበር። አሁን ግን ወንድሞች ከሚባሉት አንዱ ሴሰኛ ወይም ገንዘብን የሚመኝ ወይም ጣዖትን የሚያመልክ ወይም ተሳዳቢ ወይም ሰካር ወይም ነጣቂ ቢሆን ከእርሱ ጋር እንዳትተባበሩ እጽፍላችኋለሁ፤ እንደነዚህ ካለው ጋር መብል እንኳን አትብሉ። በውጭ ባሉ ሰዎች ላይ መፍረድ ምን አግዶኝ? በውስጥ ባሉ ሰዎች ላይ እናንተ አትፈርዱምን? በውጭ ባሉቱ ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል። ክፉውን ከመካከላችሁ አውጡት።” 1 ቆሮ 5:9-13

የእግዚያብሔር ቃል ሲናገር የሰው ሚስት የሚነካ አይምሮ የጎደለው ነው ይላል:: “ወደ ሰው ሚስት የሚገባም እንዲሁ ነው፤ የሚነካትም ሁሉ ሳይቀጣ አይቀርም። ሌባ በተራበ ጊዜ ነፍሱን ሊያጠግብ ቢሰርቅ ሰዎች አይንቁትም፤ ቢያዝም ሰባት እጥፍ ይከፍላል፥ በቤቱም ያለውን ሁሉ ይሰጣል። ከሴት ጋር የሚያመነዝር ግን አእምሮው የጐደለ ነው፤ እንዲሁም የሚያደርግ ነፍሱን ያጠፋል። ቍስልንና ውርደትን ያገኛል፥ ስድቡም አይደመሰስም። ቅንዓት ለሰው የቍጣ ትኵሳት ነውና፥ በበቀል ቀን አይራራለትምና። እርሱም ምንም ካሣ አይቀበልም፥ ስጦታም ብታበዛለት አይታረቅም።” ምሳ 6:29-35

ዘማሪ ተከስተ ጌትነት ይህንን ቃል በደንብ አብጠርጥሮ ያውቀዋል ብዬ አምናለሁ:: እርሱንም ከዘማሪ ወደ ዘመኑ ፓስተርነት በእድገት የሾሙት ኮሚቴዎችም የፓስተርነቱ የሹመት የፊርማ ቀለም ሳይደርቅ በለጋ በእንጭጩ በተሾመ በአራት ወሩ የሰውን ሚስት በተደጋጋሚ በማርከስ እና አጭበርብሮ የሰውን ገንዘብ እንደወሰደ ተመስክሮበት የቀረበበትን ክስ አሻፈረኝ አልቀበልም ብሎ የእርሱ ቢጤ የሀጢያት እርኩሰት ተባባሪዎቹ በሰሜን አሜርካ እና በኢትዮጵያ የሚኖሩ የፕሮቴስታንት የቤተ እምነት ባለቤቶች (ሽማግሌዎች ፣ ፓስተሮች እና ነቢያቶች) ፓስተር ተከስተ ይህንን በኢየሱስ ስም! አያደርግም! ፣ አይሰራም! እንዲሁም ቅራ ቅንቦ የሆነ የዲያብሎስ ማጣቀሻ ጥቅስ በመምዘዝ “የወንድሞች ከሳሽ ተጥሏል” በማለት ሊከላከሉለት ሲሞክሩ ተበዳይ እግዚያብሔር እና ህጋዊ የልጆቹ እናት ሚስቱ የተነወረችበት ወንድም መላኩ የሺዳኜ ግን በማስረጃ የተረጋገጠ ማስረጃ አለን እናንተ እንቢ ካላችሁ እንግዲህ ፍርዱን ወደ አለም ፍርድ ቤት ወስጄዋለሁ:: በሚባልበት ግዜ በእግዚያብሔር ፊት የንስሀ ይቅርታ ሳይሆን በሰው ዘንድ ስም እና ክብር ለመጠበቅ ሲባል ብቻ የእርቅ የሩጫ ሂደት እንደተሰራ ሁላችንም የምናውቀው የቅርብ ግዜ እውነተኛ ታሪክ ትዝታችን ነው:: ከዚያም ዘማሪ ተከስተን እርሱን ፓስተር ያደረጉት የእርሱ ቢጤ የሙያ አጋር ጓደኞቹ የቤተክርስትያን ፓለቲካቸውን ተከስተ ከማንኛውም አገልግሎት ለረዥም ግዜ ታግዷል:: በማለት መግለጫ ያወጡ ሲሆን መግለጫውን ባወጡ ስድስት ወር እንኳ ሳይሞላቸው ፓስተር ተከስተ ከአንድ አመት በላይ በእግዚያብሔር ፊት ወድቆ ንስሀ ስለገባ ወደ ቀድሞው አገልግሎቱ ተምልሷል:: ሀሌሉያ! የሚል ሰበር ዜና አበሰሩን:: በጣም ሰቅጣጭ ግፍ ነው:: በእግዚያብሔር ስም እየተሰራ ያለው:: ለዚህም ደግሞ የእግዚያብሔር ቃል ለእውነተኛ ክርስትያን ለወገኔ ይጠቅማል ብላችሁ አንዳች እንዳታደርጉ ብሎ ያዘናል:: “ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር፤ እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት፥ ለባልንጀራው ደግሞ እንጂ። በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን።” ፊሊ 2:3-5 “እናንተ ትበድላላችሁ ታታልሉማላችሁ፥ ያውም ወንድሞቻችሁን። ወይስ ዓመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዳይወርሱ አታውቁምን? አትሳቱ፤ ሴሰኞች ቢሆን ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች ወይም ቀላጮች ወይም ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሠሩ ወይም ሌቦች ወይም ገንዘብን የሚመኙ ወይም ሰካሮች ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ነጣቂዎች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።” 1 ቆሮ 6:8_10የእግዚያብሔርም ቃል ሲናገር እንዲህ ይላል:: “ከእርሱ ጋር ኅብረት አለን ብንል በጨለማም ብንመላለስ እንዋሻለን እውነትንም አናደርግም፤ ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል። ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም። በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው። ኃጢአትን አላደረግንም ብንል ሐሰተኛ እናደርገዋለን ቃሉም በእኛ ውስጥ የለም።” 1ኛ ዮሐ 1

Tekeste and sami

ዛሬዛሬ እውነተኛ ክርስትያኖች ከምንግዜውም በላይ በቤተክርስትያን ውስጥ የሚፈጠሩትን የተገለጡ እርኩሰቶች በሙሉ ስጋን የለበሰን ሰዎችን ሳይፈሩ ሀጢያቱን መግለጥ እና ስለእግዚያብሔር ቃል ቅንአት ብቻ ስንል አስጸያፊ አገልጋዮችን እኩይ ምግባራቸውን አይሆንም ማለት አለብን:: “ደመና ከምዕራብ ሲወጣ ባያችሁ ጊዜ፥ ወዲያው። ዝናብ ይመጣል ትላላችሁ፥ እንዲሁም ይሆናል፤ በአዜብም ነፋስ ሲነፍስ። ትኩሳት ይሆናል ትላላችሁ፥ ይሆንማል። እናንት ግብዞች፥ የምድሩንና የሰማዩን ፊት ልትመረምሩ ታውቃላችሁ፥ ነገር ግን ይህን ዘመን የማትመረምሩ እንዴት ነው? ራሳችሁ ደግሞ ጽድቅን የማትፈርዱ ስለ ምን ነው?” ሉቃ 12:54_57 “ፍሬም ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ፥ ይልቁን ግለጡት እንጂ፥ እነርሱ በስውር ስለሚያደርጉት መናገር እንኳ ነውር ነውና፤ ሁሉ ግን በብርሃን ሲገለጥ ይታያል፤ የሚታየው ሁሉ ብርሃን ነውና። ኤፌ 5:11-12

እንደ እውነቱ የእግዚያብሔር ቃል እንደሚያስረዳን በአሁን ግዜ በእግዚያብሔር ስም የተመሰረቱት አዛኛዎቹ በሰሜን አሜርካ እና በኢትዮጵያ የሚኖሩ የፕሮቴስታንት የቤተ እምነት ባለቤቶች (ሽማግሌዎች ፣ ፓስተሮች እና ነቢያቶች) እነሱም ምእመናውም ወደ እውነተኛው የእግዚያብሔር መንገድ ካልተመለሱ ፍጻሜያቸው የገሀነም እሳት ማገዶ መሆን ብቻ ነው:: “እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ፥ ወዮላችሁ እናንተ አትገቡም የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።” ማቴ 23:13 “ስለ ምን። ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ ትሉኛላችሁ፥ የምለውንም አታደርጉም?” ሉቃ 6:46 “ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ።” ዮሐ 14:15 “ለሰው ቅን የምትመስል መንገድ አለች፤ ፍጻሜዋ ግን የሞት መንገድ ነው።” ምሳ 16:25 ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነሥቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአልና፤ አስቀድሞም በእኛ የሚጀመር ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምን ይሆን? ጻድቅም በጭንቅ የሚድን ከሆነ ዓመፀኛውና ኃጢአተኛው ወዴት ይታይ ዘንድ አለው?” 1 ጴጥ 4:17-18

የዚህ መልእክት ዋና አላማ ሀጢያተኞች ላይ ጣታችንን ለመቀሰር ወይም ለመውቀስ አሊያም ድንጋይ ለመወርወርም አይደለም:: ማንም ሀጢያት የሰራን ሰውን ከክፉ ስራው እንዲመለስ እንድናስጠነቅቅ የእግዚያብሔር ቃል አበክሮ ስለሚያዘን ብቻ ነው::“እኔ ኃጢአተኛውን። በእርግጥ ትሞታለህ ባልሁት ጊዜ፥ አንተም ባታስጠነቅቀው ነፍሱም እንድትድን ከክፉ መንገዱ ይመለስ ዘንድ ለኃጢአተኛው አስጠንቅቀህ ባትነግረው፥ ያ ኃጢአተኛ በኃጢአት ይሞታል፤ ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ። ነገር ግን አንተ ኃጢአተኛውን ብታስጠነቅቅ እርሱም ከኃጢአቱና ከክፉ መንገዱ ባይመለስ፥ በኃጢአቱ ይሞታል፥ አንተ ግን ነፍስህን አድነሃል። ደግሞ ጻድቁ ከጽድቁ ተመልሶ ኃጢአት በሠራ ጊዜ እኔ በፊቱም ዕንቅፋትን ሳደርግ፥ እርሱ ይሞታል፤ አንተም አላስጠነቀቅኸውምና በኃጢአቱ ይሞታል ያደረጋትም ጽድቅ ነገር አትታሰብለትም፤ ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ። ነገር ግን ኃጢአት እንዳይሠራ ጻድቁን ብታስጠነቅቅ እርሱም ኃጢአት ባይሠራ፥ ተጠንቅቆአልና በእርግጥ በሕይወት ይኖራል፤ አንተም ነፍስህን አድነሃል።” ሕዝ 3:18-21 “የእግዚአብሔርን ቃል ቀላቅለው እንደሚሸቃቅጡት እንደ ብዙዎቹ አይደለንምና፤ በቅንነት ግን ከእግዚአብሔር እንደ ተላክን በእግዚአብሔር ፊት በክርስቶስ ሆነን እንናገራለን።” 2ቆሮ2:17

“ወዳጆች ሆይ፥ ነፍስን ከሚዋጋ ሥጋዊ ምኞት ትርቁ ዘንድ እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ እለምናችኋለሁ፤ ስለሚመለከቱት ስለ መልካም ሥራችሁ፥ ክፉ እንደምታደርጉ በዚያ እናንተን በሚያሙበት ነገር፥ በሚጎበኝበት ቀን እግዚአብሔርን ያከብሩት ዘንድ በአሕዛብ መካከል ኑሮአችሁ መልካም ይሁን።” 1ጴጥ2:11-12“ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል። እናንተ ኃጢአተኞች፥ እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ፥ ልባችሁን አጥሩ። ተጨነቁና እዘኑ አልቅሱም፤ ሳቃችሁ ወደ ኀዘን ደስታችሁም ወደ ትካዜ ይለወጥ። በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ ከፍ ከፍም ያደርጋችኋል።” ያቆ4:8-10“ወንድሞች ሆይ፥ እንመክራችኋለን፤ ያለ ሥርዓት የሚሄዱትን ገሥጹአቸው፤ ድፍረት የሌላቸውን አጽኑአቸው፤ ለደካሞች ትጉላቸው፤ ሰውን ሁሉ ታገሡ።” 1 ተሰ 5:14

እርስዎ እውነተኛ ክርስትያን ነኝ ብለው ያምናሉን? እንግዲያውስ ካመኑ በእግዚያብሔር ስም የሚነግዱትን ሸቃጭ አስጸያፊ የሀይማኖት ነጋዴዎችን ልክ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚያብሔር ቃል ቅናት ሲሉ ብቻ የትኛውንም ስጋ ለባሽ ሰውን ሳይፈሩ እና ሳያመቻምቹ የራሶትን ጅራፍ አዘጋጅተው በእግዚያብሔር ስም የሚነግዱትን ነጋዴዎች ከስፍራቸው ያባርሩ:: ይህንን በማድረግዎ በፍርድ ግዜ ከተጠያቂነት ፍርድ ነጻ ይሆናሉ:: “በመቅደስም በሬዎችንና በጎችን ርግቦችንም የሚሸጡትን ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠው አገኘ፤ የገመድም ጅራፍ አበጅቶ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም ከመቅደስ አወጣቸው፥ የለዋጮችንም ገንዘብ አፈሰሰ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ፥ ርግብ ሻጪዎችንም። ይህን ከዚህ ውሰዱ፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት አላቸው። ደቀ መዛሙርቱም። የቤትህ ቅናት ይበላኛል ተብሎ እንደ ተጻፈ አሰቡ።” ዮሐ 2:14_17

እኛም እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ “ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ” ብለናል::

ማራናታ!!!

“ሌሎቹ ደግሞ እንዲፈሩ፥ ኃጢአት የሚሰሩትን በሁሉ ፊት ገሥጻቸው። አንድን እንኳ በአድልዎ ሳታደርግ፥ እነዚህን ያለ መዘንበል እንድትጠብቅ በእግዚአብሔርና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በተመረጡትም መላእክት ፊት እመክርሃለሁ።” 1 ጢሞ 5:20-21

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live