Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ተጠያቂው ማን ነው?

$
0
0

ከደብረጊዮርጊስ
ኢትዮጵያ ዳግም ወደ እርስ በእርስ ጦርነት እየሔደች መሆኗ እጅግ ያሳዝናል። የደርግ መንግሥት የሰላምና የለውጥ በሮችን ሁሉ ዘግቶ ሁሉንም በኃይልና በጉልበት በመግደል እና በማሰር ጨርሶ ሰላም የሚያገኝ መስሎት ነበር። ግን አልሆነም። የሰላምና የለውጥ አማራጭ በሮች ሁሉ የተዘጋባቸው ኃይሎች ምንም ምርጫ ስላልነበራቸው ወደ ጦርነት አማራጭ ለመሄድ ተገዋል። አሁን ሥልጣን ላይ ያለውን ኃይል ጨምሮ። በዚህ ለረጅም ዓመታት በተካሔደ የእርስ በርስ ጦርነትም ቁጥሩ እጅግ ብዙ የሆነ ኢትዮጵያዊ በሁሉም ወገን ተሰውቷል የአካል ጉዳተኛ ሆኗል። ብዙ የኢኮኖሚ መሻሻል ልታሳይ ትችል የነበረች ሃገራችንም ሕዝቧ በሚያሳዝን የኑሮ ደረጃ ላይ እንዲገኝ አድርጎታል።
clash
ይህ አሳዛኝ ሁኔታ ዛሬም በኢትዮጵያ ላይ ሊደገም አንዣቧል። ልክ እንደ ደርግ በሥልጣን ላይ ያለው ኃይል በሮችን ሁሉ ዘግቶ የአገዛዙን ስህተት የተቹትን ሁሉ በማሰር በመግደልና ስደተኛ በማድረጉ ምክንያት ዳግም ወደ ጦርነት እየገሰገስን መሆናችን እጅግ ያሳዝናል። ለዚህም አሁን ሥልጣን ላይ ያሉት ደርግን ተጠያቂ እንደሚያደርጉት ዛሬም ተጠያቂው በስልጣን ላይ ያለው ኃይል ነው። ይህ ጦርነት ከቀድሞው ጦርነትም በበለጠ መሠረቱ ሰፋ ያለ ጅማሬ ያለው የጦርነት ክተት ውጤቱም እንዲሁ ሰፊና አስከፊ እንደሚሆን ስልጣን ላይ ያሉት ብቻ ሳይሆኑ በተለያየ ምክንያት መንግስት የሆነውን ኃይል የሚደግፉ ሁሉ ሊያጤኑት ይገባል። ለምን? ለምን? ለምን? በጥቂቶች እምቢ ባይነትና ትእቢት ለምን ሃገር ወደ ጦርነት ትገባለች? ይህ ደም የመፋሰስ እና የሃገር ጥፋት ወደማይመለስበት ደረጃ ከመድረሱ በፊት ሁላችሁም ምከሩ ዝከሩ!!!

100% አሸንፈናል እያሉ በሃገርና በህዝብ ላይ ማላገጥ ዋጋ እንደሚያስከፍል እና ዘላቂ የሃገርና የሕዝብ ጥቅምና ሰላም እንደሚያሳጣ ደጋፊና ወዳጅ ነን ያላችሁ ምከሩ ዝከሩ። ሁሉም ኢትዮጵያዊ በባህሉ ተዋጊ ነው። ጀግናም ነው። የህዝብ ቁጣ ከገነፈለም የተከማቸ መሳርያ ወይንም ገዢ መሬት አያድኑም። ባሳለፋችሁት የጦርነት ልምድ ይህን እውነታ እናንተ ይበልጥ ታውቁታላችሁ። ደርግ በሰው ኃይል በመሳርያና ገዢ ቦታዎችን ይዞ ይበልጣችሁ ነበር። ግን ያ በቁጣ የተነሳውን ህዝብ ሊያቆመው አልቻለም። በህዝቡ ውስጥ ያለውን ብሶትና ስሜትም በሚገባ ታውቁታላችሁ። ነገር ግን ልክ እንደ ደርግ አሁን በመሳሪያ ተማምናችኋል። ነገር ግን ልክ እንደደርግ ጠባችሁ ከፈጣሪም ጋር ነውና አወዳደቃችሁም እንደዛው እንደሚሆን አትርሱ። ወደልቦናችሁ ከተመለሳችሁ ግን አሁንም ግዜ አላችሁና ተመከሩ።

በተለይም በሃይማኖት አባትነት ቦታ ላይ የተቀመጣችሁ በፍርሃትና በአድርባይነት ተሸብባችሁ የሃገራችሁ ህዝብ በጥቂቶች እምቢ ባይነትና እብሪት ዳግም ወደ ጦርነት ሲገባ እያያችሁ ሊገሰጽ የሚገባውን ክፍል ባለመገሰጻችሁ እግዚአብሔር በነፍስ ብቻ ሳይሆን በሥጋም የከበደ መከራ እንደሚያመጣባችሁ አትርሱ። እግዚአብሔር ይህ መጪው አዲስ አመት እብሪተኞች ወደልቦናቸው ተመልሰው በኢትዮጵያ ላይ የለውጥ ሂደት የሚታይበት እንዲሆን እና የሰላምን ወሬ የምንሰማበት እንዲሆን ያድርግልን።


ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ከአስመራ ለመጀመሪያ ጊዜ ለጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ተናገሩ –“ጆሮ ሰጥቼ ስከታተለው አልነበረም”

$
0
0

ብረት አንስተው የሕወሓትን መንግስት እጥላለሁ ብለው አስመራ የዘመቱት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ከአንድ ወር በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ጋር ቆይታ አድርገዋል:: ዶ/ር ብርሃኑ እርሳቸው ከዘመቱ በኋላ ሕዝብ እያወራው ስላለው ነገር ሲናገሩም “ጆሮ ሰጥቼ ስከታተለው አልነበረም” ብለዋል:: ሙሉውን ያድምጡት::

nega

የኢትዮጵያ አገር አንድ በዴሞክራሲ የጋራ ንቅናቄን ምስረታ በማስመልከት የወጣ ድርጅታዊ መግለጫ

$
0
0

(ማክሰኞ ጳጉሜ 3 2007 ዓ.ም)
የኢትዮጵያ ህዝብ የአገሩን ሉአላዊነት እና አንድነት አስከብሮ የኖረ ብቻ ሳይሆን አፍሪካዊያን ወንድሞቹና እህቶቹ ከቅኝ አገዛዝ ነፃ እንዲወጡ የራሱን አስተዋፅኦ ያደረገ ጀግና ህዝብ ነው፡፡ ሆኖም ይህ ጀግኛ ህዝብ ከአብራኩ በወጡ ገዥዎች ነፃነቱ ተገፎ፣ መብቶቹ ተረግጠው የመከራ ኑሮ እየገፋ አያሌ ዘመናት ኖሯል፡፡ ይህ የመከራና የሰቆቃ ኑሮ ዛሬም አላበቃም፣ እንዲያውም “ከጭቆና ነፃ አወጣንህ” እያሉ የሚሳለቁበት ግፈኛ ገዥዎች የጫኑበትን የስቃይ ቀንምበር ተሸክሞ የውርደት ኑሮ እየኖረ ነው፡፡
Birhanu
የኢትዮጵያ ህዝብ የአገር ውስጥ ገዥ መደቦች የጫኑበትን የስቃይና የመከራ ቀንበር ሰባብሮ ለመጣል፣ ፍትህ፣ ሰላምና እኩልነት የሰፈነበት ኑሮ ለመኖር ዓመታት የፈጀ ከፍተኛ መስዋዕትነት የተከፈለበት ትግል አድርጓል፡፡ እስካሁን ትግሉን በአሸናፊነት ተወጥቶ የናፈቀውን ፍትህ፣ ሰላምና ብልፅግና ማግኘት አልቻለም፡፡ ለዚህ በርካታ ምክንያቶች ያሉት ቢሆንም ዋናው ምክንያት ህዝባዊ ትግሉን በተባበረና በተቀናጀ መልክ መስራት አለመቻሉ ነው፡፡ ይህ ስር የሰደደ ያለመተባበር ችግር በህወሓት/ኢህአዴግ ዘመን ተባብሷል፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ ሆን ብሎ የፈጠረው የመለያየት እና የከፋፍለህ ግዛው ፖሊሲ ለጋራ ድል አብሮ መታገልን በጭራሽ አስቸጋሪ ጉዳይ አድርጎት ቆይቷል፡፡

ዛሬ ግን ይህ ሁኔታ ተቀይሯል፡፡ በጋራ አብሮ በመታገል የሚገኘው ዘርፈ ብዙ ጥቅም የገባቸውና ካለፈው ተደጋጋሚ የታሪክ ስህተት የተማሩ፣ በአገራችን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲመሰረት በምድር ላይ በመንቀሳቀስ ላይ ያሉ አራት ድርጅቶች በጥምረጥ ተሳስረው በጋራ ለመታገል ወስነዋል፡፡ እነዚህ አራቱ ድርጅቶች ለብዙ አመታት የአብሮ መታገል ፍላጎት እንቅፋት የሆነውን የገዢ መደቦች የከፋፍለህ ግዛው ሴራ በጣጥሰዋል፡፡ ይህ ዛሬ በጥምረት የተጀመረው ትብብር እያደገ ሄዶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ውህደት እንዲያድግ ይደረጋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ንቅናቄው ከሌሎች ለዴሞክራሲ ስርዓት መመስረት ከሚታገሉ ኢትዮጵያዊያን ድርጅቶች ጋር ተጣምሮ ለመስራት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ ይገፋበታል፡፡
በዚህም መሰረት፣

1ኛ) የአፋር ድርጅቶች የጋራ ንቅናቄ
2ኛ) የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣
3ኛ) የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ እና
4ኛ) አርበኞች ግንቦት 7 ለአድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ፣
የኢትዮጵያ አገር አድን በዴሞክራሲ የጋራ ንቅናቄ (በአጭሩ “የአገር አድን ንቅናቄ”) የሚባል ድርጅት ዛሬ በአዲስ ዓመት መባቻ ጳጉሜ 3 ቀን 2007 ዓ.ም ፈጥረዋል፡፡ የንቅናቄውን ምክርቤት፣ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴና የተለያዩ መምሪያዎችን ከማቋቋሙም በላይ ዶክተር ብርሃኑ ነጋን ሊ/መንበር፣ ታጋይ ሞላ አስገዶምን ም/ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል፡፡
የኢትዮጵያ አገር አድን በዴሞክራሲ የጋራ ንቅናቄ ከአራቱ አባል ድርጅቶች የተውጣጣ አገር አድን ሰራዊት አቋቁሟል፡፡ይህ አገር አድን ሰራዊት በሚያደርጋቸው የትግል እንቅስቃሴዎች ሁሉ የአራቱ አባል ድርጅቶች ሰራዊቶች አባላት ሁሌም ከጎኑ አብረው በመሰለፍ ይታገላሉ፡፡
ባለፉት ሃያ አራት ዓመታት ከህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ በሰላማዊ መንገድ ለመገላገል የኢትዮጵያ ህዝብ ከፍተኛ ጥረት አድርጓል፣ ሁኖም ለእነዚህ ጥረቶች ከአገዛዙ የተገኘው ምላሽ እስር፣ ስደት፣ ውርደትና ሞት ብቻ ነው፡፡ ይህ በመሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ሳይወድ የህዝባዊ አመፅ አማራጭን እዲቀበል ተገዷል፡፡ በዚህም ምክንያት አሁንም ለሰላም የዘረጋውን እጅ ሳያጥፍ የህወሓት/ኢህአዴግን አገዛዝ በህዝባዊ አመፅ ለማስወገድ እንቅስቃሴውን ጀምሯል፡፡

በጋራ የሚደረገው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ በትግሉ ሜዳ ከሚደረገው ሕዝባዊ አመጽ በተጨማሪ የፖለቲካ፣የዲፕሎማሲና የሕዝብ ግንኙነት ዘርፎችን ያካተተ ይሆናል፡፡ ይህ አዲስ ጅምር የህወሓት/ኢህአዴግን አገዛዝ ዕድሜ ለማሳጠር በሚደረገው ሕዝባዊ ትግል ውስጥ የመጀመሪያውና ወሳኝ ምዕራፍ ሲሆን በዚህ አዲስ ጅምር ውስጥ አገር አድን ሰራዊቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጉያ ውስጥ እየገባ፣ ዕዝብን እያነቃና እያደራጀ ወገኑ ከሆነው ሕዝብ ጋር የሚያደርገው የትግል እንቅስቃሴ በመጪው አዲስ ዓመት በተጠናከረ መልኩ ይቀጥላል፡፡
የኢትዮጵያ አገር አድን በዴሞክራሲ የጋራ ንቅናቄ አገር አድን ሰራዊት መመስረቱን በዚህ መግለጫ ሲያሳውቅ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጎኑ እንዲቆም ያደርጋል፡፡እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሰብዓዊ መብቶቹና ነፃነቱ ተከብረው በኢትዮጵያ ውስጥ በሰላም ሰርቶ መኖር የዜግነት መብቱ እንጂ የገዢዎች ችሮታ አለመሆኑን ማስመስከር አለበት፡፡ እኛ ኢትዮጵያዊያንን ለእስራት፤ለስደትና ለሞት የዳረገን የውርደት ኑሮ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ማብቃት አለበት፡፡
ይህንን ብሩህ ዓላማ እውን የሚያደረግ ሁለንተናዊ የአገር አድን ትግል ተጀምሯል፡፡

የኢትዮጵያ ገበሬ ሆይ !
መሬት የህዝብ ነው እየተባልክ ህወሓት/ኢህአዴግ ሲያሰኘው አንተንና ቤተሰብህን ከመሬትህ እያፈናቀለና መሬቱን ለባእዳን እየሸጠ፤ አለዚያም በገዛ መሬትህ ላይ እንደ ገባር ተቆጥረህ አገሪቱ የዝናብ እጥረት ባጋጠማት ቁጥር የዕርዳታ ሰጭዎችን እጅ ተመልካች ሆነሃል፡፡
ዛሬ ልጆችህ በአገር አድን እንቅስቃሴ ዙሪያ ተሰባስበው ከዚህ የውርደት ኑሮ ነፃ ሊያወጡህ ቆርጠው ተነስተዋል፡፡ ይህ ትግል አንተ በምትኖርበት አካባቢ፣በአንተ ድጋፍና አንተም ተሳትፈህበት የሚደረግ ትግል ነው፡፡ ስለዚህ ልጆችህ ከህወሓት/ኢህአዴግ ጋር በሚያደርጉት ትንንቅ መሸሸጊያ ጫካቸው አንተ ነህ፡፡ ውሃ ሲጠማቸው ውሃ እያጠጣህ፤ ሲርባቸው ቤት ያፈራውን እያበላህ፤ ይህንን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚደረግ የመብት፣ የነፃነትና የእኩልነት ትግል ከልጆችህ ጋር አብረህ እድትታገል በአገር አድን እንቅስቃሴ ዙሪያ የተሰባሰቡ ልጆችህ አገራዊ ጥሪ ያቀርቡልሃል፡፡

የኢትዮጵያ ወጣት ሆይ!
“የወደፊቷ ኢትዮጵያ ተረካቢ ነህ” እየተባለ በተደጋጋሚ እየተነገረህ ነው፡፡ አንተ በራስህ ዓይን እደምትመለከተው የዛሬዋም ኢትዮጵያ ለአገርና ለህዝብ ደንታ በሌላቸው ሰዎች እጅ ገብታ እፈረሰች ነው፡፡ የዛሬዋ ኢትዮጵያ ከህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ ነፃ ካልወጣች የነገዋ ኢትዮጵያ አትኖርም፡፡ የነገዋን ኢትዮጵያ የመገንባት ባአንተ በወጣቱ ጀርባ ላይ የወደቀ ኃላፊነት ነው፡፡ ይህ ስራ የሚጀምረው ህወሓት/ኢህአዴግን ከስልጣን በማባረር ነው፡፡ የስደት ኑሮ አብቅቶ በገዛ አገርህ ውስጥ ባሰኘህ ቦታ ያሰኘህን ስራ እየሰራህ የክብር ኑሮ የምትኖርበትን ጊዜ አንተው ራስህ ታግለህ ማምጣት አለብህ፡፡ ስለዚህ ዛሬ ራሳቸው አደራጅተው ከህወሓት/ኢህአዴግ ጋር ከሚፋለመው የአገር አድን ሰራዊት ጋር ዛሬውኑ ተቀላቀል፤ ይህንን ማድረግ የማትችል ደግሞ በምትኖርበት ቦታ ከምታምናቸው ጓደኞችህ ጋር ሆነህ ራስህን እያደራጀህና የመረጃ ማሰባሰብ ስራዎችን እየሰራህ በየአካባቢህ የሚገኘውን የህዝባዊ እቢተኝነት ቡድን ተቀላቀል፡፡

በአገር ውስጥና በውጭ አገሮች ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የምትታገሉ ድርጅቶች ሆይ !
ኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ተገንብቶ ማየት የሚሹ የተለያዩ ድርጅቶች ህወሓት/ኢህአዴግ ስልጣን ከመያዙ በፊትና ሥልጣን ከያዘም በኋላ በርካታ ዓመታት የፈጀ እልህ አስጨራሽ ትግል አካሂደዋል፤ዛሬም እያካሄዱ ነው፡፡ ይህ በተናጠል እየተካሄደ ያለው ትግል በመካከላችን የልዩነትና ያለመተማመን አጥር ሰርቶ ስላራራቀን ህወሓት/ኢህአዴግን ማሸነፍ ቀርቶ ጠንካራ ጡንቻ እንድናሳርፍበት እንኳን አላስቻለንም፡፡ ይልቁንም የምንታገልለት ህዝብ በየቀኑ ይታሰራል፤ ሰቆቃ ይደርስበታል፤ ይገደላል፡፡ ከዚህ ሁሉ ያመለጠው ደግሞ አገሩን ለቅቆ ይሰደዳል፡፡ በመካከላችን ያሉትን መለስተኛ ልዩነቶች ለህዝብ አቅርበን በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለመፍታት እስከተማመን ድረስ የአሁኑ ትግላችን ይህንኑ ለማድረግ ነውና ለዚህ እንቅፋት የሆነብንን የህወሓት/ኢህአዴግ ሥርዓት አብረን የማንታገልበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ ስለሆነም ሁላችንም ፍሬያማ ለሆነ ትብብር ራሳችንን እናዘጋጅ፤እንተጋገዝ፡፡

የኢትዮጵያ ምሁር ሆይ !
አገራችን ኢትዮጵያ ሁለት እጆቿን ዘርግታ ከምንግዜውም በላይ ያንተን የምሁር ልጆቿን የነቃ የትግል ተሳትፎ የምትፈልግበት ጊዜ አሁን ነው፡፡የኢትዮጵያ ምሁር ለኢትዮጵያ ሕዝብ መብትና ነፃነት መከበር ከፍተኛ አስታውጽኦ አድርጓል፤ ግን ይህ በአብዛኛው በተናጠል አንዳዴም ድርጅታዊ መልክ ይዞ የተካሄደው ትግል የኢትዮጵያን ሕዝብ መብትና ነፃነት ማስከበር አልቻለም፡፡ በዚህ ተስፋ ቆርጠህ ከዳር ቆመህ የአገርህን ውርደት ዝም ብለህ እያየህ ከነበርክ ይህ ከዳር ሆኖ የመመልከቻ ጊዜ አሁን አብቅቷል፡፡ ስለዚህ አገር ውስጥና አገር ውጭ የምትኖረው ኢትዮጵያዊ ከወንድሞችህና እህቶችህ ጋር በመሆን ይህን የተቀጣጠለ ሕዝባዊ ትግል ተቀላቅለህ ዝንት ዓለም ስተመኝው የነበረውን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመመስረት ድርሻህን እንድታበረክት አገራዊ ጥሪ ቀርቦልሃል፡፡

የህወሓት/ኢህአዴግ አባላት ሆይ!
አንዳንዶቻችሁ ከልባችሁ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የምትታገሉ መስሏችሁ፤ ከፊሎቻችሁ ደግሞ በሁኔታዎች ተገድዳችሁ፤ ሌሎቻችሁ ደግሞ አማራጭ አጥታችሁ ባለፉት ሃያ አራት ዓመታት ከለየለት የአገር ጠላት ድርጅት ጋር ተስልፋችሁ እናት አገራችሁን ስትበደሉ ቆይታችኋል፡፡ ብዙዎቻችሁ የሕዝብ ስቃይና መከራ ተሰምቷችሁ የበደላችሁትን ሕዝብ ለመካስ አመች ጊዜ እየጠበቃችሁ ነው ብለን እናምናለን፡፡ ደስ ይበላችሁ! የምትጠብቁት ጊዜ ደርሷል፡፡ መጭው እውነተኛ ዴሞክራሳዊ ስርዓት እናንተንም ነፃ የሚያወጣ ስርዓት ነውና ሁላችሁም በያላችሁበት ትግሉን ተቀላቀሉ፤መቀላቀል የማትችሉ ደግሞ መረጃ በማቀበልና ስርዓቱን ከውስጥ ሆናችሁ በማፍረስ ሕዝባዊውን ትግል ደግፉ ከህሊና እና ከታሪክ ተጠያቂነት ራሳችሁን ታደጉ፡፡

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሆይ !
ያንተ ኃላፊነት የአገረህን ዳር ድንበር ከጠላት መጠበቅ ሆኖ ሳለ ህወሓት/ኢህአዴግ በአገርህ አንድነት ላይ የሚሸርባችው ሴራዎች አስፈፃሚ አድርጎህ ጭራሽ ደህንነቱን ለመጠበቅና ለመንከባከብ ቃል ከገገባለት ሕዝብ ላይ መሳሪያህን እንድታነሳ እያደረገህ ነው፡፡ አንተ የወጣኸው ከኢትዮጵያ ሕዝብ አብራክ ውስጥ ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ወልዶ ባሳደገህ ወገነህ ላይ “ተኩስ” የሚል ፀረ-ሕዝብ ትዕዛዝ ሲሰጥ በፍጹም አትቀበል፣ ይልቁንም በጠላትህ ህወሓት/ኢህአዴግ ሰርዓት ላይ አዙር ወይም መሳሪያህን እየያዝክ ወገኖችህን ተቀላቀል፡፡ እኛ ወገኖችህ ለነፃነት የምናደርገው ትግል በዘረፋና በሙስና ከከበሩ ዘራፊ ወታደራዊ መሪዎች ነን ባይ ሽፍቶች ጋር ነው እንጂ በፍጹም ካንተ ከወገናችን ጋር አይደለም፡፡ የእኛ ትግል አንተ የአገርህን ዳር ድንበር ለመጠበቅ የሚያስችልህን ብቃት ለመፍጠርና እውነተኛ የሕዝብ ሰራዊት እንድትሆን ለማድረግ ነው እንጂ አንተን ወገናችንን ለመበታተን የመጣን ጠላቶች ወይም አንተን በመግደል የምንደሰት አይደለንም፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ!
አንድን ጨቋኝ አምባገነን ስርዓት ታግለህ በደመሰስክ ማግስት ከቀድሞው የባሰ የሚረግጥህና የሚጨቁንህ ስርዓት በላይህ ላይ እየተጫነ ተቆጥረው የማያልቁ የስድት፣ የሰቆቃና የውርደት ዓመታት ዓሳልፈሃል፡፡ አባቶችህ በደማቸው አስከብረው ያስረከቡህ የአገር አንድነት ላልቷል፤ አንተ ታግለህ ከቅኝ አገዛዝ ነፃ ያወጣሃቸው አገሮች በዕድገት ወደ ኋላ ጥለውህ ሄደዋል፤ የወለድካቸው ልጆችህ እስር ቤት ውስጥ ናቸው አልያም አንተንና አገራችውን ጥለው ተሰደዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! “አምላኬ! አምላኬ! ይህ የመከራና የውርደት ዘመን መቼ ይሆን የሚያበቃው?” እያልክ ሰማይ ሰማዩን እየተመለከትክ ፈጣሪህን ጠይቀሃል፤ ለምነሃልም፡፡ ፈጣሪ አልረሳህም፡፡ የወለድካቸው ልጆችህ ተሰባስበውና ተደራጅተው የናፈቀህን የሰላምና የነፃነት ኑሮ የምታገኝበትን ቀን ለማቅረብ በአገር አድን ሰራዊትነት ተደራጅተው እየተፋለሙ ነው፡፡ የአገር አድን የጋራ ንቅናቄ ዓላማ አገራችን ኢትዮጵያ ፍትህ፣ ሰላምና እኩልነት የሰፈኑባት አገር እንድትሆን ነውና የምትችል በአካል ትግሉ ሜዳ ተገኝተህ በጉልበትህ፤ ይህን ማድረግ የማትችለው ደግሞ በገንዘብህ፣ በእውቀትህና ለዚህ ከጠላትጋር ለሚደረገው ትንንቅ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ለወገን ኃይሎች በማቀበል ትግሉን ተቀላቀል፡፡
አንድነት ኃይል ነው!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

የሕወሓት አስተዳደር የመከላከያ ሰራዊት ለአባይ ግድብ መስሪያ ገንዘብ አናዋጣም አሉ

$
0
0

የወያኔ ኢህአዴግ ስርአት መከላከያ ሰራዊት ለአባይ ግድብ መስሪያ ገንዘብ እንዲያዋጡ ለቀረበላቸው ጥሪ እንዳልተቀበሉት የትህዴን ድምጽ ምንጮች ከመከላከያ ውስጥ ገለፁ::

Photo File

Photo File


በምንጮቹ መረጃ መሰረት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እንደ አዲስ ለአባይ ግድብ መስሪያ የሚሆን በሚል ገንዘብ እንዲያዋጡ በአመራሮቻቸው ለቀረበላቸው ጥሪ አንቀበልም ማለታቸውን የገለፀው መረጃው ለቀረበው ጥሪ ሳይቀበሉት የቀሩበት ምክንያትም “ ባለፉት ጊዚያት በተደጋጋሚ የከፈልነውን ገንዘብ ቦንድ ይሰጣቸኋል ተብለን እስከ አሁን ድረስ ግን ሳይተገበር አንከፍልም” እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል::

መረጃው በማከል።- የሰራዊቱ ከፍተኛ አዛዦች በሰራዊቱ ውስጥ አጋጥሞ ያለውን ለአባይ ግድብ ገንዘብ አንከፍልም የማለቱ የመበታተን አደጋ። እንዴት አድርገን ለሰራዊቱ እናሳምነው በሚል በከባድ ውጥረት እንደሚገኙ የተገኘው መረጃ ጨምሮ አስረድቷል ሲል የትህዴን ድምጽ ዜናውን ቋጭቷል::

የአይኤሱ ከፍተኛ ኮማንደር በአንዲት የወሲብ ባሪያው ተገደለ

$
0
0

ከታምሩ ገዳ

ኢራቅ እና ሶሪያ ውስጥ በሰፋት የሚነቀሳቀሰው ፣ እራሱን “የእስላሚክ መንግስት” Islamic State ) በማለት የሚጠራው ፣ ነገር ግን ሃይማኖት እና መልካም ሰነ ምግባሮች የለሹ አክራሪ ቡደን በቁጥጥር ሰር ካደረጋቸው በርካታ የወሲብ ባሪያ (Sex slaves) እህቶች መካከል አንዷ በአክራሪው ቡድን ላለፉት ሶስት ወራት ከደረሱባት ተደጋጋሚ የወሲብ ጥቃቶች የተነሳ የቡድኑ ከፈተኛ ኮማንደር የነበረ ግለሰብን መግደሏ ተነገረ ።
isis
የኩርዲስታን ዲሞክራሲ ፓርቲ አፈቀላጢ የሆኑት ሳይድ ሙሞዚኔ ሰኞ እለት አልሱማሪያ ከተባለው የኢራቅ የግል ቴሊቭዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ሰሟ ያልተጠቀሰው ነገር ግን አናሳ የሆኑት የኢዛዲ ጎሳ ተወላጅ እንደሆነች የተገመተች አንዲት በ አይኤስ ታጣቂዎች እጅ የወደቀች ሴት የቡድኑ ቁልፍ ሰው የሆነ እና በበረሃ ሰሙ አቡ አናስ የተባለ ኮማንደር ለተለያዩ ተዋጊዎች የወሲብ ፍላጎታቸው መወጣጫ ሲያደርጋት በመክርሙ ከደረሰባት ግፍ እና በደል የተነሳ ተጠቃሹ ኮማንደርን የኢራቅ ሁለተኛ ከተማ በሆነችው ሞሱል አቅራቢያ ቅዳሜ እለት መግደሏን ተናገረዋል።ምንም እንኳን አፈቀላጤው የአይኤስ የወሲብ ባሪያ የነበረችው እህት ኮማንደሩን እንዲት እንደገደለችው ባይናገሩም አንዳንድ ዘገባዎች ግን በጥይት ተኩሳ እንደገደለችው ገምተዋል። የዚህች ምስኪን ሴት እጣ ፈንታ ምን እንደሆነ ለጊዜው አልተገለጸም ።

ካለፈው 2014 እኤአ ጀምሮ በርካታ የኢራቅ እና የሶሪያ ከተሞችን የተቆጣጠረው አይኤስ ለወሲብ ባርነቱ መጠቀሚያ አንሆንም(አሽባሪዎችን አናገባም ) ያሉ ከ 150 በላይ ሴቶችን (እርጉዞችን ጨምሮ) እንደገደለ የተባበሩት መንገስታት ድርጅት ልዪ ተወካይ በቅርቡ ያወጣው ዘገባ ያትታል። አይ ኤስ እድሜያቸው ከ9 እስከ 40 አመታት የሚገመቱ የሺያት ሙስሊሞች፣ኢዚይድ እና ከርሲቲያኖችን ሴቶችን እርቃናቸውን በአደባባይ እንዲቆሙ በማደረግ መጀመሪያ ለቡድኑ መሪዎች፣ቀጥሎም ለኢሚሪዎች(ኮማንደሮች)፣ በሰተመጨረሻም ለተራ ተዋጊዎች ከ 165 ዶላር እሰከ 41 ዶላር ( እዚህ ላይ የትናንሾቹ ሴቶች ዋጋቸው ከፍ ይላል) እና እንዳንድ ሴቶች እሰከ 22 ጊዚያት እንደተሸጡ ተዘግቧል።አይ ኤስ ባለፈው ሜያዚያ መባቻ ላይ 28 ኢትዮጵያዊያን ሰደተኞችን ሊቢያ ውስጥ እጅግ ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ አንገታቸውን በሰይፍ ቀልቶ ፣ በጥይት ደብድቦ መግደሉ እና ድርጅቱም ከፍተኛ ሕዝባዊ ቁጣ መቀስቀሱ አይዘነጋም።ይህ እቁይ ቡድን በሚሊዮን ለመቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎች መፈናቀል እና በመቶ ሺዎች ሞት ምክንያት ሲሆን ቡድኑን ከሚዋጉት መካከል የሴቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑ ይነገራል።

ችግሩ ወያኔን በማስወገድ ብቻ የሚፈታ አይደለም ! –ካለፈው የቀጠለ

$
0
0

ፈቃዱ በቀለ፣ ዶ/ር     

መስከረም 8፣  2015

መግቢያ

የተፈጠርነው እንደ እንስሳ  ለመኖር ሳይሆን ፣ የትክክለኛውን ዕውቀትና  የታታሪነትን    መንገድ ለማግኘትና ለመቀዳጀት ነው ።“ ዳንቴ

ዳንቴ ይህንን ያለው በ13ኛው ክፍለ-ዘመን የኢጣሊያን ህዝብ በድህነት፣ በተስቦ በሽታና በጦርነት፣ እንዲሁም ኑሮው ሁሉ ስለጨለመበት ደጉን ከክፉ መለየት ባልቻለበት ወቅትና፣ ማንኛውንም ለሰው ልጅ የሚሰቀንን አጸያፊ ድርጊት በሚያደረግበት ዘመን በአንክሮ ከተመለከተ በኋላ ነው። በእሱ ዕምነትም፣ ለዚህ ሁሉ ዋናው ምክንያት የሰው ልጅ አዕምሮ በጊዜው በነበረው ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፈ በመጣው ባህላዊ የአኗኗር ስልትና በመጥፎ ነገሮች ስለተወጠረና ደጉን ከክፉ ለመለየት የሚያስችለው ዕውቀት ስለሌው ነው። በዚህም ምክንያት የማሰብ ኃይሉ እጅግ ደካማ ስለነበር አርቆ ማሰብና ለምን በእንደዚህ ዐይነት ሁኔታ ውስጥ ለመኖር ተገደድኩ ብሎ ራሱን ለመጠየቅ አይችልም ነበር። በዳንቴ ምርምርና ዕምነት የሰው ልጅ ግን ራሱ በሚሰራው አፀያፊ ሁኔታና አልፎ አልፎ በሚከሰት የተፈጥሮ አደጋ መሰቃየት ያለበት ሳይሆን፣ መንፈሳዊ ኃይል ያለውና የሚኖርበትንም ሁኔታ መለወጥ እንደሚችልና አካባቢውንም ገነት እንደሚያደርጋት የአምላኮች ኮሜዲ በሚለው ግሩም ስነ-ጽሁፉ ውስጥ ያመለክታል።

የዳንቴን ጥቅስ ትምህርታዊ አባባል ለመጥቀስ የተገደድኩበት ዋናው ምክንያት አንዳንድ ጊዜ ከምኖርበት፣ ከዚሁ ከአንድ የምዕራብ አውሮፓ ከተማ ወጣ ብዬ የገጠሩን ህዝብ የኑሮ ሁኔታ ስመለከትና ከአገራችን የገጠር ሁኔታና የህዝባችንን አኗኗር ጋር ሳወዳድር ነው። ራሴንም የምጠይቀው፣ እኛ በእግዚአብሄር አምላክ ተፈጥረናል በምንባለው በጠቅላላው የሰው ልጅ ዘንድ የአስተሳሰብና የድርጊት ለውጥ መኖሩን ሳወጣና ሳወርድ፣ አንደኛው አካባቢውን ወደ ገነትነት መለወጥ ሲችል፣ ሌላው ደግሞ እግዜአብሄር የለገሰውን የተፍጥሮ ጸጋ በማውደም ከእንስሳ ያላነሰ ኑሮ መኖሩን ስመለከትና በጭንቅላቴ ውስጥ ሳወጣ ሳወርድ ነው።  ጀርመን አገር ስኖር ብዙ ዐመታት ባስቆጥርም፣ በመጀመሪያዎቹ አስር ዐመታት ይህንን ያህልም የአገራችንን ሁኔታ ከጀርመኑ ወይም ከአንዳንድ የአውሮፓ አገሮች ጋር ለማወዳደር ሃሳቡም ሆነ ግንዛቤውም አልነበረኝም። ከትምህርቴ ዓለም ባሻገር ራሴን ከተለያዩ ዕውቀቶችና ቲዎሪዎች ጋር የማገናኘትና፣ እስከተወሰነ ደረጃም ድረስ ዕውቀቱን ለመረዳት ዕድል ቢያጋጥመኝም፣ ተጨባጭ ከሆነው የቀን ተቀን ህይወቴ ጋር የተያያዘውን የቤትና የመንገድ አሰራር፣ የመናፈሻና የልጆች መጫወቻ ቦታዎች፣ የመብራትና የውሃ  እንዲሁም የመጸዳጃ  ጉዳይና፣ አያሌ የሰውን ልጅ ህይወት የሚነኩ ጉዳዮችን ጭንቅላቴ ውስጥ አስገብቼ ለማውጣትና ለማውረድ እስከዚህም ድረስ ደንታ አልነበረኝም። ጀርመን አገር ከመጣሁ ከሰላሳ ዐመታት በላይ ሲሆነኝ፣ በእነዚህ ዐመታት ውስጥ አንድም ጊዜ መብራት የተቋረጠበትና የውሃ ዕጥረትም የተከሰተበት ጊዜ በፍጹም አላጋጠመኝም። ቀኑ እየረዘመ ሲሄድ፣ ከቲዎሪ አልፌ በቴዎሪና በተጫባጩ የሰው ልጅ ኑሮ መሀከል ያለውን ሁኔታ ስመለከት የዕውቀት ትርጉሙ የመጨረሻ መጨረሻ ሌላ ነገር ሳይሆን የሰውን ልጅ ኑሮ ማሻሻልና፣  ለዚህ ደግሞ እያንዳንዱ ግለሰብ የመንፈስ ነፃትን በመቀዳጀት በሰማይ ላይ ሳይሆን በምድር ላይ ገነትን መመስረት እንዳለበት ልገነዘብ ችያለሁ።  ስለሆነም፣ ነጩ የአውሮፓና የአሜሪካ ህዝብ ብቻ ሳይሆን፣ ጥቁር አፍሪቃዊም፣ እኛንም ጨምሮ በማሰብ ኃይሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመስራት የኑሮውን ሁኔታ መለወጥና፣ አካባቢውንም ገነት ማድረግ አለበት የሚል ውሳኔ ላይ ከደረስኩኝ ከአስር ዐመታት በላይ ሆኖኛል። ይህ ብቻ ሲሆንም አንድ ግለሰብም ሆነ አንድ ህዝብ ነፃነቱን መቀዳጀት እንደሚችል ለመረዳትና ለመገንዘብ ችያለሁ።  በመሆኑም የሰው ልጅ ከእንስሳ የሚለየው ሞራላዊ፣ ስነ-ምግባራዊ፣ ባህላዊ፣ ጥበባዊና ከዚህም በመነሳት ተዓምር በመስራት በዕቅድና በተቀነባበረ መልክ የኑሮውን ሁኔታ ማሻሻል እንዳለበት በፈላስፋዎችና በሊትሬቸር ሰዎች ተመዝግቧል፤ በተግባርም ታይቷል። ታዲያ እኛን ምን ተሳነን? ምንስ ጎደለን?  የሚለት ጥያቄዎች ሁልጊዜ ያብከነክኑኛል።

ራሴን ከአውሮፓው የህብረተሰብ አወቃቀር ታሪክና ፍልስፍና ጋር ይበልጥ ማስተዋወቅ ከጀመርኩኝ  ከሃያ ዐመታት በላይ ሲሆነኝ፣ በዚያው መጠንም በአገሮች መሀከል ያለውን ልዩነት የማወዳደር ዕድል ይበልጥ አጋጥሞኛል ብል እንደግብዝነት አይቆጠርብኝም። ይሁንና ግን የባህል ሁኔታና የታሪክ ሂደት ለአንድ ህብረተሰብ ዕድገት ወሳኝ ሚናን እንደሚጫወቱ ሙሉ በሙሉ ባምንም፣ በሌላ ወገን ግን ራሴን እንደጠረጥር የሚያስገድደኝ ሁኔታ አለ። አንዳንድ የተበሳጩ ኢትዮጵያውያን ወንድሞቼ ጋር በምጫወትበት ጊዜ በእኔ አባባል ይህንን ያህልም አይረኩም። ምክንያትም እንድደረድርላቸው አይፈልጉም። በምሁር „መፈላሰፍም“ ስለማያራከቸው፣ በነጩና በኛው ዓለም መሀከል ያለውን ልዩነት ለመረዳት የሚፈልጉት በሌላና ብዙም ውጣ ውረድን በማይፈልግ ስሌት ነው። በአብዛኛዎቹ ዕምነት ወይም ግምት የነጭ ዘር ከስልጣኔ ጋር የተወለደ ሲሆን፣ እኛን ደግሞ እግዚአብሄር በድሎናል የሚል ነው። በእዚህ ዐይነቱ ማረጋገጫ የሌለው አባባል ባልስማማም፣ አንዳንድ ውጭ አገር ሰላሳና አርባ ዐመታት ኑረው ወደ አገራቸው የተመለሱ ኢትዮጵያውያን ለአገራቸው ያላቸውን አመለካከትና ደንታ-ቢስነት ስመለከት ራሴን እንድጠረጥር ተገድጃለሁ። አንድ ሰው ውጭ አገር ሰላሳና አርባ ዐመታት ከተቀመጠ በኋላ የግዴታ የአስተሳሰብ ለውጥ ያመጣል ብዬ ስለማምን፣ ወደ አገሩ በሚመለስበት ጊዜ እስከተወሰነ ደረጃም ድረስ የአገሩ ሁኔታ እንዲቀየር አስተዋጾዖ ሊያበረክት ይችላል የሚል ዕምነት ነበረኝ። ለብዙ ዐመታ ሁኔታዎችን ከተከታተልኩኝና፣ ካወጣሁና ካወረድኩኝ በኋላ የተገነዘብኩት ነገር፣ ከውጭው ዓለም ወደ አገሩ የሚመልስ ኢትዮጵያዊ ራሱን አግሎ ከመኖር በስተቀር ለአገሩ ምንም ዐይነት አስተዋጽዖ እንደማያበረክት ነው።  የማነሳው ጥያቄ፣ ለመሆኑ እኛ ኢትዮጵያውያን  አንድን ነገር ተኮር አድርጎ የመመልከትና የማገናዘብ ኃይል አለን ወይ? ሁለተኛ፣ ከራሳችን ባሻገር ለአገራችን ዕድገትና እንዲሁም ለህዝባችን የኑሮ መሻሻል ምኞትና ፍላጎት አለን ወይ?  መልሱ ባጭሩ በራሳችን ዓለም የምንኖርና ለለውጥም ያልተዘጋጀን ነን የሚል ነው። ይሁንና ግን በሌላ ወገን ኢትዮጵያ አገሬ እያልን መዝሙርም እንዘምራለን፤ ባንዲራውንም ለብሰን እንጎድራደዳለን። እንደሚታወቀው ባንድ በኩል ለአገር ዕድገትና ስልጣኔ ደንታ-ቢስ መሆን፣ በሌላ ወገን ደግሞ ባንዲራ ማውለብለብና አገሬ አገሬ እያሉ መዘመር፣ አብረው ሊሄዱ የሚችሉ ነገሮች አይደሉም።

ስለሆነም ለአገሬ እታገላለሁ የሚልና፣ የዛሬውን አገዛዝ የሚጠላ አገር ወዳድ ነኝ ባይ ኢትዮጵያዊ ማንሳት ያለበት ጉዳይ አለ።  ይኸውም አንድ ሶስት ሺህ ዐመት ታሪክ ያለው አገርና ከአጭር ጊዜ በስተቀር የውጭ አገር ቅኝ ግዛት ያለሆነ ለምን የስልጣኔና የዕድገት ባለቤት ለመሆን አልቻለም? አገራችን ለምንስ ባለፉት አርባ ዐመታት በድህነትና በረሃብ እንድትታወቅ ተገደደች? የሚለውን አንስቶ መወያየት የሚያስፈልግ ይመስለኛል። ወደ አርዕስቱ ጋ ልመለስና፣ አብዛኛዎቻችን ዛሬውኑ ወያኔ ቢወገድ ችግሩ የሚፈታ የሚመስለን አለን። በእግዚአብሄርም ቁጣም ቢሆን የሁላችንም ዕምነት  የዛሬው ሰይጣናዊ አገዛዝ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ ላይ እንዲላቀቅ እንመኛለን። መወገድም እንዳለበት ታሪካዊ ግዴታ እንደሆነ ይህ ጸሀፊም ያምናል። ይሁንና ግን መመለስ ያለብን፣ ለመሆኑ የችግሩን ምንጭ በደንብ ተረድተናል ወይ?  ሁለተኛስ፣ ደረጃ በደረጃ ህዝባችን የሚፈልገውን ነገር ለመመለስ በቂ ዝግጅት አድርገናል ወይ?  ችሎታውስ አለን ወይ?  እነዚህን መሰረታዊ ጥያቄዎች መመለስ ያለብን ይመስለኛል። እነዚህን መሰረታዊ ጥያቄዎች መመለስ ሳንችል፣ ይህ አገዛዝ ዛሬውኑ መወገድ አለበት ብንልና እንዳጋጣሚም ቢወገድ ፍጥጫ ውስጥና፣ ሌላ ችግር ውስጥ መውደቃችን አይቀርም። ስለዚህም እነዚህን የመሳሰሉትንና ሌሎችን ለአገር ግንባታ አስፈላጊ ናቸው የምንላቸውን ነገሮች አንስተን መወያየትና መልስም ለመስጠት መዘጋጀት መቻል አለብን ብሎ ይህ ጸሀፊ ያምናል። ይህንን ስናደርግ ብቻም ትግላችን የተሟላና ግቡንም ሊመታ እንደሚችል ግልጽ መሆን አለበት።

በዚህ ረገድ የህብረተሰባችንን ዋና ችግርና ዘለዓለማችንን በድህነትና በረሃብ እንድንታወቅና፣ መሳቂያና መሳለቂያ ያደረጉንን ነገሮች ለመረዳት እንድንችል ዘንድ የሰው ልጅ በጠቅላላው ሃሳብን የማፍለቅ ችሎታ እንዳለው ፣ ይሁንና ግን ደግሞ በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ ይህንን ሊያደርግ እንደማይችል ጠጋ ብለን መመልከቱ ግንዛቤ ሊሰጠን ይችላል። በስልጣኔና በህብረተሰብ ዕድገትና ለውጥ ታሪክ ውስጥ ሃሳብን የማፍለቅና ሃሳብን ተግባራዊ ማድረጉ የቱን ያህል ለአንድ ህዝብና አገር በሰላምና በነፃነት መኖር እጅግ አስፈላጊዎች መሆናቸውን በህብረተሰብ ታሪክ ውስጥ የተረጋገጠ መሆኑን መረዳት እንችላለን።  በሌላ ወገን ደግም በየጊዜው አዳዲስ ሃሳቦችን ማፍለቅና በተግባርም መተርጎም የማይችል ህዝብ የድህነትና የኋላ-ቀርነት ሰለባ መሆኑን እንመለከታለን።

ሃሳብን ማፍለቅና ሃሳብን ወደ ተግባር መተርጎም የስልጣኔ ዋናው ቁልፍ መሆኑን የመረዳቱ ጉዳይ !

በመጀመሪያው ጽሁፌ ላይ የአዕምሮንና የመንፈስን ሚና እስከተወሰነ ደረጃ ድረስ ለመተንተን ሞክሬያለሁ። አዕምሮና መንፈስ በጭንቅላታችን ውስጥ የሚገኙ፣ አውቀንም ሆነ ስናውቅ የተለያዩ ሃሳቦችን ማፍለቅ እንደሚችሉ ለመጠቆም ሞክሬያለሁ። ይሁንና ግን አዕምሮና መንፈስ ዕውቀትንና ጥሩ ሃሳብን የማፍለቅ ችሎታ ቢኖራቸውም፣ በአጠቃላይ ሲታይ የሰው ልጅ በስሜት፣ አልፎ አልፎ ደግሞ በደመ፟-ነፍስ የሚመራ ነው። ይህም ማለት በጣም ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው በመንፈሳቸው ኃይል በመመራት አርቆ-አሳቢነትን በማስቀደም ደጉን ከክፉ መለየት የሚችሉት። ትክክለኛ ዕውቀትንም በማፍለቅ የሰው ልጅ በመንፈስ ኃይሉ ራሱን ነፃ ማውጣትና የተፈጥሮ አደጋ ሰለባ እንዳይሆን መንገዱን የሚያሳዩት በመንፈሳቸው የበላይነት የሚጠቀሙና አርቆ-አሳቢነትን የሳይንስ ግኝት መሳሪያ ማድረግ የሚችሉ ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው። የስልጣኔን ታሪክ በምናገላብጥበት ጊዜና፣ ካለብዙ ውጣ ውረድ ራሳችንን ስንጠይቅ የምንገነዘበው ነገር ፍልስፍናንና ጥበብን ማፍለቅ የቻሉት ልዩ ዐይነት ተሰጥዖ ያላቸው ሰዎች ብቻ ናቸው።  በሌላ ውገን ግን እንደፈላስፋዎችም ባይሆን የሰው ልጅ በደመ-ነፍስ በመመራት አዳዲስ መሳሪያዎችን መፍጠር እንደሚችልና የአኗኗር ስልቱን እንደሚለውጥ መገንዘብ ይቻላል።  ይሁንና ግን በአንድ አካባቢ የህዝብ ቁጥር እየጨመረ ሲመጣና ሀብትም በጥቂት ሰዎች ቁጥጥር ሲውል አንድ ህዝብ በመጀመሪያው ዕድገቱ ሊገፋበት አይችልም። ባህላዊ የአኗኗር ልምድና ርዕዮተ-ዓለም፣ በተለይም ደግሞ በተለያዩ ነገሮች ማምለክና፣ የራስንም ዕድል ከአምልኮት ጋር ማያያዝ በአንድ አካባቢ የሚኖር ህዝብ የማሰብ ኃይሉን እንዳይጠቀም አግደው እንደሚይዙት በጥናት የተረጋገጠ ነው። ስለሆነም ከአንድ አካባቢ ወይም ከአንድ የህብረተሰብ-ክፍል የሚፈልቁ ልዩ ልዩ አስተሳሰቦች እንደየጥራታቸውና እንደየአተረጓገማቸው የሰውን ልጅ የማሰብ ኃይል መቆጣጠር ይችላሉ፤ ወይም የማሰብ ኃይሉን በማዳበር ታሪክን እንዲሰራ ያግዙታል። ስለሆነም የሰውን ልጅ ዕውቀት አመጣጥና አፈላለቅ በመረዳትና የተፈጥሮንም ምንነት በመተርጎም ረገድ በፈላስፋዎች ዘንድ ከፈተኛ ክርክር ተካሂዷል። በተለይም በአሁኑ ዘመን የሰው ልጅ ቁጥር በበዛበትና የተለያዩና የተዘበራረቁ ኤንፎርሚሽኖች፣ እንደዚሁም ገንዘብና የፍጆታ አጠቃቀም የሰውን ልጅ አዕምሮና መንፈስ ወጥረው በያዙበት ዘመን በጣም ጥቂት ሰዎች ብቻ ነው በአርቆ-አሳቢነት ሃይል የሚመሩና ራሳቸውን መቆጣጠር የሚችሉት።

ይህ በእንደዚህ እንዳለ፣ የሃሳብን አፈላለቅና ተግባራዊነት መረዳቱ ላለንበት የተወሳሰበ ችግር እስከተወሰነ ደራጃ ድረስ መልስ ሊሰጠን ይችላል ብዬ እገምታለሁ። በፍልስፋና ዓለም ውስጥ ሃሳብ(Idea) ከፍተኛ ትርጉም አለው። ይህም ማለት በአጠቃላይ ሲታይ በተግባር ሊመነዘር የሚችለው ተጨባጭ ነገር ሁሉ ከአዕምሮአችን በመንፈስ ኃይል የሚፈልቅ ነው። ለምሳሌ ካለብዙ መጨነቅ(Intuitively ) የሰው ልጅ የፈጠራቸውን ነገሮች ሁሉ ስንመለከት ከተፈጥሮና በተፈጥሮ ውስጥ ካሉት ነገሮች በስተቀር ሁሉም ነገሮች በሰው ልጅ የማሰብ ኃይል ነው የተፈጠሩት። ለምሳሌ ከብዙ መቶ ሺህ ዐመታት በፊት የሰው ልጅ ዝም ብሎ በጫቃ ውስጥና በዛፍ ላይ በሚኖርበት ዘመን ጎጆ የመቀልበስ ነገር ታየውና ራሱን ከብርድና ከአደጋ ለመከላከል ሲል መጠለያን መስራት ተገደደ። ቀስ በቀስም ሌሎችን ነገሮች መስራት እንደሚችል ሲረዳ የተፈጥሮ ተገዢ ከመሆን ይልቅ እስከተወሰነ ደረጃ ድረስ ተፈጥሮን እንደሚቆጣጠር ወይም በተፈጥሮ ውስጥ ያሉ ነገሮችን እያወጣና መልክና ቅርጽ በመስጠት ኑሮውን እንደሚያሻሽል ተገነዘበ። እንደዚሁም ጠረቤዛና ወንበር እንዲሁም አልጋ ሳያይ በራሱ የማሰብ ኃይል መፍጠር ቻለ። ባጭሩ፣ ይህ የሚያሳየን የሰው ልጅ ሃሳብን ወይንም ዕውቀትን ከጭንቅላቱ በአዕምሮውና በመንፈስ ኃይሉ ማፍለቅና ሃሳቡንም ወደ ተግባር ለመመንዘር እንደሚችል ነው። በዚህ መልክ የሰው ልጅ የቋንቋ፣ የፊደልና የጽሁፍም አፍላቂ ነው። ስለሆነም ርስ በርሱ በመገናኘትና ሃሳብ ለሃሳብ በመለዋወጥ ከድሮው በተሻለ ሁኔታ አዲስ ህብረተሰብ መፍጠር ይችላል። እንዲህ እያለ እየሄደ አዳዲስ መሳሪያዎችንና የፍጆታ ዕቃዎችን በማምረትና የስራ-ክፍፍልን በማዳበር ወደ ንግድ ልውውጥ የሚያመራና ገንዘብን በመፍጠር የንግድ ግኑኝነትና ልውውጥ እንዲፋጠን የሚያደርግ ነው።  ይህ ሁሉ ነገር የተፈጠረው እንደዛሬው የአካዳሚ ዕውቀትና ዩኒቨርሲቲዎች ባልተስፋፉበት ዘመን ነው።

ይሁንና ግን አንድ ህብረተሰብ የተወሰኑ ነገሮችን ከፈጠረና ወይም ካገኘ በኋላ ከዚያ በላይ ገፍቶ ሊሄድ እንደማይችል ደግሞ በታሪክም የታየ ነው። ለምን አንድኛው ከሌላው ቀድሞ እንደሚሄድ፣ በመጀመሪያ የስልጣኔ ባለቤት የሆነው በሌላው እንደሚቀደምና፣ ኋላ ብቅ ያለው ከፍተኛ ምጥቀትን በማግኘት የተሻለ ህብረተሰብን እንደሚመሰርትና ህግና ስርዓትንም በማውጣትና በመደንገግ ለሰው ልጅ ኑሮ መልክ እንደሚሰጠው በተለያዩ ተመራማሪዎች በተለያየ መልክ ይተረጎማል። በተጨማሪም በተለያዩ ህዝቦችና ህብረተሰቦች ዘንድ የተለያየ የአኗኗር ስልትና ነገሮችን በመረዳት ረገድ ለምን ልዩነት ይኖራል ? በሚለው ሃሳብ ላይ የተለያየ ትርጓሜ ይሰጣል።

በፍልስፍናና የህብረተ-ባህል(Socio-Cultural studies) ጥናት መሰረት ለዚህ የተለዩየ ምክንያቶች ይሰጣሉ። ብዙ ጥናቶች እንደሚያረጋግጡት ከሆነ፣ አንዳንድ ዘረኛ ፈረንጆች እንደሚሉት የዘር ልዩነት ጉዳይ ሳይሆን የተለያዩ ሃሳቦች ሲገናኙና የተለያዩ ህዝቦችም ሲጋቡና ሲዋለዱ የተሻለ ሃሳብና ዕውቀትን ማፍለቅ እንደሚችሉ ነው። እንደሚባለውና እንደተረጋገጠውም የመጀመሪዉ የሰው ልጅ የተገኘው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው። ዲዮዶርስ የሚባለው የግሪኩ የታሪክ ጸሀፊ እንደሚነግረን ከሆነ ለግብጽ ስልጣኔ መነሻ ዋናው ምክንያት ኢትዮጵያውያን እንደሆኑና፣ የመጀመሪያውም የግብፅ ፋራዖኖች ከኢትዮጵያ ፈልሰው የሄዱ እንደሆኑ ይነግረናል። የመጀመሪያዎቹ ኢትዮጵያውያን ፋራዖኖች ከኢትዮጵያ ፈልሰው ሲሄዱ ህግንና የሂሳብንም ሆነ ሌሎችን ዕውቀቶችን ይዘው እንደሄዱ በሚገባ ሰፍሯል። ይህ ከሆነ በኋላ ግን ኢትዮጵያ በዚያው እንዳለች ስትቀር የግብጽ ስልጣኔ ከፍተኛ ደረጃ በመድረስ፣ ፍልስፍና፣ አስትሮኖሚና ማቲማቲክስ፣ እንዲሁም የአርክቴክቸር ዕውቀቶች እዚያ ሊዳብሩና ሊስፋፉ ችለዋል። የግብጽ ስልጣኔ ለብዙ ሺህ ዐመታት የበላይነትን ከያዘ በኋላ ውስጡ ባለው የታፈነ ስርዓት የተነሳና ዕውቀት ከቀሳውስጡ ወጥቶ መነጋገሪያና መከራከሪያ እንዲሆን ባለመደረጉና፣ ከዚህ በላይ ደግሞ የህዝቡም ቁጥር አነስተኛ ስለነበር ስልጣኔው በዚያው መልክ ሊቀጥልና ከፍተኛ ደረጃ ላይ ሊደርስ አልቻለም።

ወደ ግሪክ ስንመጣ ግን ሁኔታው የተለየ ይሆናል። በመጀመሪያ ደረጃ የመጀመሪያዎች የግሪክ ፈላስፋዎች፣ ፕይታጎራስ፣ ታለስ፣ ሶሎንና ፕላቶ ዕውቀታቸውን ግብፅ ሄደው እንደቀሰሙ ማርቲን በርናልና የሴኔጋሉ ምሁር አንታይ ዲዮፕ በሚገባ አረጋግጠዋል። ሌሎችም እንደዚሁ በዚህ ማስረጃ ይስማማሉ። ይህ በእንደዚህ እንዳለ ከተለያየ ቦታ ፈልሰው የመጡ ህዝቦች የሚገናኙባት አዮን የምትባለው ደሴት ላይ የመጀመሪያው የግሪክ ስልጣኔ መዳበርና አዲስ ዕምርታን እንዳገኘ በታሪክ የተረጋገጠ ነው። በዚህ መልክ የግሪኩ ስልጣኔ የተጠነሰሰው ከህንድና ከግብጽ በመጣው ፍልስፋና አማካይነትና፣ ግሪክም የተለያዩ ህዝቦች መናኸሪያ እንደነበረችና፣ በተለይም ደግሞ ከግብፅ የመጡ ጥቁር አፍሪቃውያን ለስልጣኔው ዕምርታ እንደሰጡት የተረጋገጠ ጉዳይ ነው።

ለግሪክ ስልጣኔ መነሾ ይህ ብቻ አይደለምም ዋናው ምክንያት።  በግብጽ ስልጣኔ ዘመን ዕውቀት ከቀሳውስቱ የሚያልፍ አልነበረም። እንደ ምስጢር የተያዘና ህዝቡ እንዳያውቀው በመደረጉ የግብጽ ስልጣኔ እምርታን ሊያገኝ አልቻለም። ወደ ግሪክ ስንመጣ ግን፣ የግሪክ ፈልሳፎች ፍልስፍናውን ወደ ውጭ በማውጣት ወጣቱን ማስተማሪያና መከራከሪያ አደረጉት። በአንድ ነገር ላይ ብቻ ረክቶ እንዳይቀር ጥያቄን በጥያቄ እንዲያነሳ በማድረግ ዕውነትን  ከውሸት ሊለይ የሚችልበትን ዲያሊክቲካዊ የምርምር ዘዴ እንዲቀዳጅ አደረጉት። ከእንግዲህ ወዲያ በስሜት የሚገፋ መሆኑ ቀርቶ በሎጂክና በምርምር በመመራት የተሻለ ነገር ማግችትና መፍጠር እንደሚችል አስተማሩት።  አንድን ማዕከለኛ ነገር ከአንድ ነገር ነጥሎ በማውጣትና እንደገና ደግሞ በነገሮች መሀከል መተሳሰር እንዳለ በማሳየት ይህ የምርምር ዘዴ ለሳይንስ መሰረት እንዲጥል ተደረገ። ከዚህ በኋላ የግሪክ ሳይንቲስቶች ከዚያ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ አዳዲስ መሳሪያዎችን መፍጠርና ለመጀመሪያ ጊዜ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ጥበባዊ የከተማ ዕቅድ በማውጣት  ዘመናዊ የአኗኗር ዘዴን ፈጠሩ። ለመጀመሪያ ጊዜ መሻሻልና (Progress) ዘመናዊነት (Modernity) በማሰብና በምርምር ኃይል እንደሚደረስባቸው አረጋገጡ። አርኪሜዲስና ከሱ በፊት የነበሩ ሊቃውንት በመንፈስና በማሰብ ኃይል እየተመሩ ከምንም በመነሳት አዳዲስ መሳሪያዎችን ሲፈጥሩና እንደ አሊክሳንደሪያ የመሳሰሉትን ከተማዎች ሲገነቡ ማረጋገጥ የቻሉት ገንዘብ ሳይሆን የዕድገት መነሾ የሰው ልጅ የማሰብ ኃይል መሆኑን ነው። የሰው ልጅ የማሰብ ኃይሉን ማንቀሳቀስ ከቻለና ለመሻሻልም ፍላጎት ካለው ምንም ሳይኖር አዲስ ነገር መፍጠር እንደሚችል የግሪክ ፈላስፎች ማረጋገጥ ችለዋል። ከዚያ በኋላ በጋሊልዮና በኒውተን የተፈጠሩት መሳሪያዎችና ግኝቶች በግሪክ ስልጣኔና፣ በተለይም ደግሞ በአርኪሜዲስ  ዕውቀት ላይ የተመሰረቱ ናቸው። ይሁንና የአውሮፓው ስልጣኔ ከመነሳቱና ዕምርታን ከማግኘቱ በፊት ከክርስቶስ ልደት በኋላ በስምንተኛው ክፍለ-ዘመን ባግዳድ የሳይንስና የፍልስፍና መዲና እንደነበረችና፣ በዚያ ዘመንም አንድ ሚሊዮን ህዝብ ይኖርባት እንደነበር የታወቀ ነው።  የአውሮፓ ስልጣኔ አነሳስ እነዚህን መሰረት ያደረገና እየዳበረ የመጣ ለመሆኑ ቀደም ብለው የወጡም ሆነ አዲስ ጥናቶች ያረጋግጣሉ።

ክዚህና ከአውሮፓው ስልጣኔ የምንማረው ምንድን ነው፟?  በአንድ አካባቢ አዲስ ዕውቀት ወይም ስልጣኔ ቢገኝም ከፍተኛ ዕምርታን ሊቀዳጅና ህብረተሰብአዊ ለውጥ ሊገኝ የሚችለው የተለያዩ ህዝቦች ስልጣኔን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ይዘው ሲሄዱና አዲሱ ቦታ ተቀማጭ ሲሆኑና ከኗሪው ህዝብ ጋር በመጋባት ሲቀላቀሉ ነው።  ይህ እንግዲህ የመጀመሪያው ግሎባላይዜሽን ሲሆን፣ ጤናማ አስተሳሰብ በነበረበትና፣ አንደኛው ህዝብ ሌላውን በበላይነት በመቆጣጠር ሀብቱን በመዝረፍና በመጨቆን ዕድገትን በተወሰነ ቦታና የህብረተሰብ ክፍል ብቻ እንዲሽከረከር በማያደርግበት ዘመን ነበር። በሌላ አነጋገር፣ ተንኮል በማይታሰብበት ዘመንና፣ ጥበብንና ሳይንስን ለሰው ልጁ ሁሉ ማካፈል ያስፈልጋል ተብሎ በሚታሰብበት ጤናማ አስተሳሰብ በሰፈነበት ዘመን ነው። ወደ አውሮፓው ታሪክና ዕድገት ስንመጣ ግን፣ በተለይም እንግሊዝ የበላይነትን መቀዳጀት ስትጀምርና በአዲስ የፍልስፍና አስተሳሰብ ስትመራና የሌሎች አውሮፓን አገሮች ምሁራን ስትመርዝ ዕውቀት በተወሰነ ክልል ብቻ እንዲሽከረከር ይደረጋል። በተለይም ከአስራስምንተኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ የዘረኝነት ቲዎሪ በመስፋፋት የጥቁር ዘር ሳይንስንና ፍልስፍናን ሊያፈልቅ አይችልም የሚለው በመስፋፋት የነጭ-ዘር የበላይነት እንዳለው ለማረጋገጥ ጥረት ይደረጋል። ይህ ጉዳይ በሳይንስ ያልተረጋገጠ ቢሆንም የነጭ ዘር እንደ አምላክ እንዲታይ አብቅቶታል። በሁላችንም ዘንድ የህሊና ተጸዕኖ በማሳደር እስከዛሬ ድረስ ሲያሰቃየንና የዝቅተኛ ስሜት እንዲያድርብን በማድረግ ለመሸማቀቅ በቅተናል። በራሳችን ላይ ዕምነት እንዳይኖረን ተደርገናል። በተለይም በአውሮፓው ምድር ውስጥ ብሄረተኝነት(Nationalism) መስፋፋት ከጀመረበት ከ19ኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮና የአፍሪቃን የጥሬ-ሀብት ለመቀራመት ስትራቴጂ ከተቀየሰ ወዲህና፣ ብዙ የአፍሪቃ አገሮች በቅኝ-ግዛት አስተዳደር ውስጥ እንዲወድቁ ከተደረጉ በኋላ የተወሰደው እርምጃ ሁሉ የአፍሪቃን ህዝብ የኑሮ ሁኔታ ማዘበራረቅና የማሰብ ኃይሉንም በማዳከም ዘለዓለሙን በዝቅተኝነት ስሜት ወድቆ እንዲኖር ማድረግ ነው። ይህ ዐይነቱ ስትራቴጂ ለኛም በመትረፍ የማሰብ ኃይላችን እንዲጠብና ለዕድገትና ለስልጣኔ የሚሆነውን መሰረት በመጣል ከድህነትና ከረሃብ እንዳንላቀቅ ተደርገናል። በቡሃ ላይ ጆር ደግፍ እንዲሉ ፊዩዳላዊ አስተሳሰብና የተበጣጠሰ የካፒታሊዝም የፍጆታ አጠቃቀምና የምርት ክንዋኔ አንድ ላይ በመጣመር የአስተሳሰብ አድማሳችንን ለማጥበብ በቅተዋል።

 

የማሰብ ነፃነት፣ ሃሳብን መግለጽና የአስተሳሰብ  አንድነት ህብረተስብአዊ ኃይል መሆናቸውን መረዳት !

በአውሮፓ ታሪክ ውስጥ የግሪክ ስልጣኔ ብቅ ካለና ከዳበረ ወዲህ በነጻ ማሰብ፣ ሳይፈሩና ሳይቸሩ ሃሳብን መግለጽ፣ መከራከርና ለማሳመንም ሆነ ለማመን መሞከር፣ ከዚያም በኋላ ወደ አንድ አስተሳሰብ ላይ መድረሰ መሰረታዊ የስልጣኔ ጉዳይ ሆኗል።  ስለሆነም ለሶክራተስም ሆነ ለፕላቶ፣ እንዲሁም ለአርስቲቶለስ በተከታታይ ደቀ መዝሙሮችን ማፋራት ከባድ አልነበረም። በየጊዜው ብቅ የሚሉት ፈላሳፋዎችና ሳይንቲስቶችም በመንፈስ ኃይል ተውጠው የሰውን ልጅና ተፈጥሮን በማገናኘት ሚዛናዊ የሆነ ስርዓት ለመገንባት ችሎታም ሆነ ፍላጎት ነበራቸው። ዋናው ምኞታቸውም ሆነ ምርምራቸው በመጀመሪያ ደረጃ የራሳቸውን ፍላጎት ለሟሟላት ሳይሆን፣ የሰው ልጅ አርቆ-የማሰብ ኃይሉን በመጠቀም በመስማማትና በመተባበር ጤናማና ጥበባዊ ህብረተሰብ ለመገንባት እንደሚችል መንገዱን ማሳየት ነበር። ስለሆነም መንፈሳዊውና የማቴርያላዊ ዓለም አንድ ላይ ሊጓዙ የሚችሉበትና፣ የሰው ልጅም በመንፈስ ኃይል እየተመራ ራሱን በመቆጣጠር አዲስና ሚዛናዊ የሆነ ህብረተሰብ መመስረት እንዳለበት ማስተማር ነበር። በተለያየ ጊዜ ብቅ ባሉት የግሪክ ፈላስፎች ዘንድ የአመለካከት ልዩነት ቢኖርም የሚስማሙበት ነገር አንድ ህብረተሰብ ልክ እንደኮስሞስ የተሰተካከለና በስርዓት የሚመራ ህብረተሰብ መመስረት አለበት በሚለው ላይ ነው። ሌላው የሚስማሙበት ነገር፣  በአጠቃላይ ሲታይ የሰው ልጅ አርቆ-የማሰብ ኃይሉን ለመጠቀምና ራሱን በራሱ ለማግኘት ብዙ መቶ ዐመታት እንደሚፈጁበት ነው። ይሁንና አንድ ህብረተሰብ ትክክለኛውን ዕውቀት ካገኘና አርቆ-የማሰብ-ኃይሉን ካስቀደመ ስልጣኔን በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊቀዳጅ እንደሚችል በአንዳንድ የህብረተሰብ ታሪክ ውስጥ የተረጋገጠ ነው። በሌላ ወገን ግን  በአንድ አገር የሚኖር ህዝብ እንደ አንድ ኃይል የሚታይ ቢሆንም፣ ዋናው መነሻቸው ግለሰብአዊ  ነፃነትና ራስን በራስ ማግኘት የሚለው መሰረተ-ሃሳብ ለስልጣኔ ቁልፍ እንደሆነ ያሰምሩበታል። ይህ ዐይነቱ ግለሰብአዊ ነፃነት ግን ስግብግብነትንና የራስን ፍላጎት ማሟላት የሚለውን የሚያስቀድም ሳይሆን፣ የየግለሰቡን ነፃ አስተሳሰብ አፍላቂነትና የአዕምሮንና የመንፈስን የበላይነት ለማሳየት ነው። በመሆኑም ግለሰቦች ነፃና ሃሳብ አፍላቂዎች እንዲሁም በራሳቸው የሚተማመኑ መሆናቸውን የሚያመለከት ከዕብነ-በረድ የተሰራ የሰው ምስል ሀውልት በግሪክ ስልጣኔም ሆነ በሬናሳንስ ዘመን የተስፋፋ ነበር።

ይህ የማሰብ ነፃነት ግን በካቶሊክ ሃይማኖት የበላይነት ከሰባት መቶ ዐመታት በላይ ይታፈናል። ውጤቱም በአውሮፓ ምድር ውስጥ የተስቦ በሽታ መስፋፋትና በድህነት ዓለም ውስጥ መኖር ነበር። ይህ ሁኔታ ግን በሬናሳንስና በሬፎርሚሽን ኃይል ይለወጣል። በተለይም በጀርመን ምድር ማርቲን ሉተር በመነሳትና የካቶሊክ ኃይማኖትን የበላይነት በመቃወም እያንዳንዱ ግለሰብ መጽሀፍ ቅዱስን ማንበብና በራሱም አርቆ የማሰብ ኃይል መመራት እንዳለበት ያውጃል። ለመጀመሪያ ጊዜም መጽሀፍ ቅዱስን ከላቲን ወደ ጀርመንኛ ተርጉሞ በማሰራጨት ለጀርመን ቋንቋ ከፍተኛ ዕምርታን ይሰጠዋል። እስከ አስራአምስተኛው ክፍለ-ዘመን ድረስ በየክልሉ በራሱ ዲያሌክት ብቻ ይግባባ የነበረውና በሃይማኖት ይበጣበጥ የነበረው የጀርመን ህዝብ አንድ የመግባቢያ ቋንቋ ያገኛል። በጀርመንኛ የተተረጎመውን መጽሀፍ ቅዱስን ሲያነብ የማሰብ ኃይሉ ከፍ ይላል። ዐይኑ ይከፈታል። ዝም ብሎ የሚነዳ ህዝብ ሳይሆን ማሰብ የሚችልና የሚጠይቅ፣ እንዲሁም በምድር ላይ የራሱ ነፃነት ያለው መሆኑን ይገነዘባል።

በጀርመን ምድር የተከሰተው የማሰብ ነፃነትን መቀዳጀት ቀስ በቀስ ለጀርመን ሊትሬቸርና ለአዲሱ የጀርመን አዲያሊስት ፍልስፍና መንገዱን ይከፍታል። የተለያዩ ፈላስፋዎች ብቅ ብቅ በማለት የተፈጥሮንና የህዋን ምንነት በመመርመር ለጀርመን ህዝብ አዲስ የአስተሳሰብና የኑሮ ፈለግ ይቀዱለታል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ኑሮ በዘፈቀደ መሆኑ ቀርቶ በአርቆ አስተዋይነት እየታሰበና እየታቀደ፣ መንደሮችም ሆነ ከተማዎች በዕቅድ እየተሰሩ የሰው ልጅ በሰማይ ላይ ሳይሆን በምድር ላይ ገነትን እንደሚመሰርት ያረጋግጣሉ። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ጀርመን የአሳቢዎችና የገጣሚዎች አገር በመሆን አዲስ ዕምርታ ይታይባታል። በተለይም በቫይማር ከተማ ግንባታ የተረጋገጠው ይህ ዐይነቱ የማሰብና የግጥም ኃይል አንድ ላይ በመጣመራቸው ነው። በዚህ ዐይነቱ ሂደት ውስጥ የተለያዩ አስተሳሰቦች ቢከስቱም፣ እነዚህ የተለያዩ አስተሳሰቦች ወደ ርስ በርስ ግጭት ያመሩበት ሁኔታ አልነበረም። በተቻለ መጠን ለመግባባትና ለመደማመጥ መሞከር፣ በዚያም መሰረት በአንድ መሰረታዊና ሳይንሳዊ በሆነ ነገር ላይ በመስማማት ቲዎሪን ወደ ተግባር መመንዘር ነበር። በግሪኩም ሆነ በጀርመኑ የፍልስፍናና የሳይንስ ታሪክ ውስጥ ካለ ፕሪንስፕል መመራት ቦታ አልነበራቸውም። ተንኮለኝነት፣ ምቀኝነትና በሆነው ባልሆነው ወደ ግጭት ማምራት የሚታወቁ አልነበሩም። ማጭበርበርና ለራስ ጥቅም ብቻ መሽቀዳደምና ሌላውን ማዳካም የኑሮአቸው ፍልስፍና አልነበረም።  ሃሳባቸው ወደ እግዚአብሄር የሚጠጋ በመሆኑ በልዩ የመንፈስ ኃይል እየታገዙ ህብረተሰብአዊ ኃላፊነታቸውን መውጣት ነበር ዋናው ዓላማቸው። በአገራችን የተለመደው ዐይነት ሽወዳና እጅግ የደቀቀ አስተሳሰብ እንዲሁም ህብረተሰብን አዘበራርቆ ጥሎ መጥፋት የሚታወቅ አለነበረም። ፈላስፋዎችና ሳይንቲስቶቹ በልዩ መንፈስ የሚመሩ ስለነበር ዘለዓለማዊ ዕምነታቸውና ዓላማቸው የሰውን ልጅ የመንፈስ ኃይል ማዳብርና አርቆ አሳቢም መሆኑን እንዲገነዘብ ማድረግ ነበር። በተለይም የካንትን የህይወት ታሪክና ስራውን ያነበበ ሰው የሚረዳው፣ ይህ ታላቅ ፈላስፋ በእርግጥም ህይወቱን በሙሉ በምርምር ያሳለፈና፣ የህይወት ዕቅዱም ስነ-ስርዓትን የያዘና በሌላ ዓለም ውስጥ ይኖር የሚያስመስለው ነበር። የላይብኒዝም የሞናድ(Monad) ቲዎሪ የሚያረጋግጠው የሰውን ልጅ የማሰብ ኃይል ነው። በተለይም የእንግሊዝ ኤምፕሪሲስቶችን ወይም በዛሬው አባባል የሊበራል አስተሳሰብ ያላቸውን ምሁሮች የተሳሳተ አመለካከት ለመጣል የደረሰበት ማረጋገጫ የሰው ልጅ ጭንቅላት ውስጣዊ-ኃይል እንዳለውና ራሱን በራሱ በማንቀሳቀሰ አንድን ነገር እንደሚፈጥር ነው። ስለሆነም በእሱ የሞናድ ቲዎር መሰረት ትንሿ ህዋስ ብትሆንም ውስጣዊ-ኃይል ያላትና በራሷ ውስጣዊ የመንቀሳቀስ ኃይል ከሌለች ህዋሶች ጋር በመተሳሰር ልዩ ነገር እንደምትፈጥር ነው ለማረጋገጥ የቻለው። በሌላ አነጋገር ዕውቀት ከውጭ ወደ ወደ አዕምሮአችን ውስጥ የሚገባ ሳይሆን በማሰብ ኃይልና በምርምር ከውስጥ የሚፈልቅ ነው። የላይብኒዝ የሞናድ ቲዎሪ የፕላቶንን የዕውቀት አፈላለቅ ያረጋገጠ ነው ማለት ይቻላል።

ከዚህ ሁሉ የምንረዳው ምንድ ነው? በመጀመሪያ የሃሳብ ነፃነት በማንም ኃይል የሚሰጥ ሳይሆን ከሰው ልጅ ጋር የተፈጠረ ነው። ስለዚህም የሰው ልጅ የሚናገርበትና ሃሳቡን የሚገልጽበት አንደበት አለው። ሁለተኛ፣ ማንኛውም ሰው በአርቆ-አሳቢነትና በፕሪንስፕል በመመራት ወደ አንድ የጋራ አስተሳሰብ ላይ መድረስ ይችላል። በሳይንስና በፍልስፍና ዓለም ውስጥ የተለያዩ ሀቆች ወይም ዕውነተኛ ነገሮች የሉም። ሁል ጊዜ ሊኖር የሚችለው አንድ ሀቅ ወይም አንድ ዕውነት ብቻ ነው። ይሁንና ግን የተለያዩ ፈላስፋዎች የሃሳብና የዕውቀትን የመፍለቅ ጉዳይ በተለያየ መልክ ስለሚተረጉሙትና፣ በሃሳብ ወይም በዕውቀት ምንጭ ላይ ስምምነት ስለሌለ የሃሳብ ልዩነቶች ይፈጠራሉ። ለምሳሌ የሰው ልጅ ከዕውቀት ጋር የተፈጠረ ነው፣ ይህንንም በማሰብ ኃይሉ ወደ ውጭ ማውጣት አለበት በሚለው ፕላቶናዊ አስተሳሰብና፣ የለም የሰው ልጅ ዕውቀት ከውጭ በሚታየው ነገር ላይ የተመሰረተና እሱም ወደ አዕምሮ ውስጥ በመግባትና በመብላላት እንደገና ወደ ዕውቀት የሚመነዘር ነው በሚለው ላይ የአስተሳሰብ ልዩነት ይኖራል። ይህ ጉዳይ በተለይም በአስራስድስተኛውና በአስራሰባተኛው ከፍለ-ዘመንና፣ ከዚያም በኋላ እስከ አስራዘጠነኛው ክፍለ-ዘመን ድረስ ፈላስፋዎችን ሲያከራክር የቆየና፣ የመጨረሻ መጨራሻም በካፒታሊዝም አሸናፊነት የሶፊስቶች የበላይነት የነገሰበትን ሁኔታ እነመለከታለን። ይህ ማለት ግን ሶፊስቶች ወይም የማቴርያላዊ ዓለም ትክክለኛ ነው ማለት ሳይሆን፣ በኃይል አሰላለፍ ለውጥ የተነሳ የበላይነትን የተቀዳጀው ኃይልና ከሱ ጋር ያበሩ ወይም ጠበቃ የቆሙ ምሁሮች ሌላውን የህብረተሰብ ክፍል ተገዢያቸው ለማድረግ  የሚጠቀሙበት መሳሪያና በዓለም አቀፍ ደረጃ አማራጭ የሌለው ሆኖ የተወሰደ ነው። ዛሬ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን ድህነት መስፋፋት፣ የሀብት ዘረፋና ጦርነት፣ እንዲሁም የህዝቦችን መፈናቀል ስንመለከት በዓለም አቀፍ ደረጃ ላይ የተስፋፉት አገዛዞች በዚህ ዐይነቱ የሰውን ነፃነት በሚያፍን ሶፊስቲያዊ አስተሳሰብ ስለሚመሩ ነው። በዚህ አመለካከት ማንኛውም ግለሰብ እንደ አንድ ግለሰብ የሚታይና የራሱም ውስ|ጣዊ ነፃነት እንዳለው አይወሰድም።  ማንኛውም ግለሰብ በአንድ አካል የሚወጣ ህግንና ደንብና እንዲሁም አስተሳሰብን ጥያቂ ሳይቀርብና ሳይከራከር ዝም ብሎ መቀበል አለበት። የየአገሮችን ህገ-መንግስት ስንመለከት የምንገነዘበው፣ ህገ-መንግስቶች በየአገሩ የሰፈኑትን የኃይል አሰላለፎች የሚያንፀባርቁ እንጂ በምንም ዐይነት የህዝብን ጥቅምና ፍላጎት እንዲሁም ዕውነተኛ ነፃነት የሚያስቀድሙ አይደሉም። በዚህም ምክንያት ራሱ ህገ-መንግስት የተዛባ የሀብት ክፍፍልና ክምችት እንዲሁም የድህነት ምንጭ በመሆን በየአገሩ የተስተካከለ ዕድገት እንዳይመጣ እንቅፋት ሆናል ማለት ይቻላል።

አስቸጋሪውን የኢትዮጵያ ሁኔታና የህዝብ አስተሳሰብ የመረዳት ጉዳይና አስፈላጊነት !

በአውሮፓ የህብረተሰብ ታሪክ ውስጥ አንድ የተለመደ አሰራር አለ። ከግሪክ ስልጣኔ ጀምሮ ብቅ ያሉት ምሁራን ጥረታቸው ሁሉ በጊዜው የነበረውን የየህብረተሰባቸውን የተመሰቃቀለ የኑሮ ሁኔታና የገዢ መደቦችን ባህርይ በቅጡ መረዳት ነበር። ከዚያም በመነሳት ከጨለማ በመውጣት እንዴት ብርሃንን ማየት ይቻላል? ብለው የተቻላቸውን ጥረት ማድረግ ነበር። ደጋግሜ ለማሳየት እንደ ሞከርኩት፣ አሁንም ቢሆን አዕምሮና መንፈስ ያላቸውን ልዩ ቦታ በመረዳትና የነበረውን አስቸጋሪ ሁኔታ በሳይንስ የትንተና ዘዴ በመጋፈጥ፣ አገዛዙና ህዝቡ በዘልማድ ላይ ከተመሰረተ ኑሮ ተላቀው የማሰብ ኃይላቸውን በመጠቀም አዲስ ህብረተሰብ ለመፍጠር ያልተቆጠበ ትግል ማድረግ ነበር።  በዚህም መሰረት የአውሮፓ ምሁራን ህይወታቸውን ለዕውቀት በመሰዋት ለሳይንስና ለቴክኖሎጂ ዕድገት መሰረት መጣል ችለዋል ማለት ይቻላል። ይሁንና ግን በአስተሳሰባቸው ውስጥ ሳይንስንና ቴክኖሎጂን የተረዱትና የፈጠሩትም የሰውን ልጅ ከጨለማ ኑሮ ለማላቀቅና ኑሮውን ለማሻሻል እንጂ ወደ መጨቆኛ መሳሪያ በመለወጥ ጦርነት እንዲስፋፋ አይደለም። ይህ ዐይነቱ አስተሳሰብ ግን በካፒታሊዝም ዕድገትና በኃይል የአሰላለፍ ለውጥ የተነሳ ልዩ ባህርይና መልክ እየያዘ ይመጣል። ሳይንስና ቴክኖሎጂ የጥቂት አገሮች ሞኖፖሊ በመሆን ዓለምን መበወዣና ጦርነትን ማስፋፊያ ሊሆኑ በቅተዋል። የዕድገትና የስልጣኔ ምንጮችና መሰረቶች ከመሆን ይልቅ የአገዛዝ መሳሪያዎች በመሆን ህዝብን ማፈናቀያና ሀብቱንም መዝረፊያ ሊሆኑ በቅተዋል ማለት ይቻላል።

ወደ አገራችን ሁኔታ ስንመጣ እስከዛሬ ድረስ የህብረተሰብአችንን ኋላ-ቀርነት፣ የሳይንስና የቴክኖሎጂ መሰረት እንዳይጣልና፣ ህዝባችንም የስልጣኔ ቀማሽ እንዳይሆን አግደው የያዙትን ነገሮች ለማጥናት የሞከረ የለም ብል እንደ ግብዝነት አይቆጠርብኝም። በመጀመሪያው እትሜ ላይ ለማሳየት እንደሞከርኩት፣ የፊዩዳሉ ስርዓትና ሃይማኖት ማነቆ በመሆን ለአዲስ አስተሳሰብና የአኗኗር ስልት መፈናፈኛ መንገድ ለመስጠት እንዳልቻሉ ነው። ይህንን አጥብቄ የማነሳው በዚያው በድሮው መልክ መኖር የለብንም፣ መሻሻል አለብን የምንል ከሆነ ብቻ ነው። የለም በዚያው በዘልማዳችን መኖር እንፈልጋለን የምንል ከሆነ ደግሞ ምንም መከራከር አያስፈልግም። ስርዓቱንና ሃይማኖትን በጥያቄ ውስጥ ማስቀመጥ የለበንም። በሌላ በኩል ግን ሃይማኖት በራሱ የሰው ልጅ ኑርውን ማሻሻል የለበትም አይልም። የትም ቦታ አልተጻፈም። በብሉይ ኪዳንም ሆነ በአዲሱ መጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ የሰው ልጅ በእግዚአብሄር አምሳል የተፈጠረና ራሱንም መለወጥ እንዳለበት ያመለክታል። ለምሳሌ በብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ „ብዙ ተባዙ ተፈጥሮንም በቁጥጥራችሁ ስር አድርጓት ይላል።“ በዚህ አባባል ሙሉ በሙሉ ባልስማም፣ የሰው ልጅ በማሰብ ኃይሉና በስራው ኑሮውን እንደሚያሻሽል  መጽሀፍ ቅዱሱ ያስተምረናል። ሌላው ደግሞ በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ እንደመሰረታዊ ነገር የተጻፈው፣ „ጠይቅ ይመለስልሃል፣ ፈልግ ታገኛለህ፣ አንኳኳ በሩ ይከፈትልሃል፣“ የሚሉት አባባሎች የሚያረጋግጡት መጽሀፍ ቅዱስ በራሱ የሰውን ልጅ የማሰብና የመፍጠር ኃይል በፍጹም እንደማይቃወም ነው። የሰው ልጅም በእግዚአብሄር አምሳል ነው የተፈጠረው ብሎ ቁልጭ አድርጎ ይነግረናል። ይህም ማለት በማሰብ ኃይላችን ገነትን መስራት እንደምንችል ነው የሚያረጋግጥልን።  አስቸጋሪው ግን የተወሰኑ ነገሮች ብቻ ተወስደው እንደ ቀኖና ሲደገሙና፣ የሰው አዕምሮ ውስጥ ሲገቡ የሰው ልጅ መሰረታዊ ነገሮችን እንዲረሳና፣ ጭንቅላቱ በባልባሌ ነገሮች እንዲጠመድ ይደረጋል። የኖይሮ ባይሎጂና የሶስዮሎጂ ምሁራን እንደሚያስተምሩን ከሆነ፣ በመሰረቱ የሰው ልጅ አዕምሮ ወግ-አጥባቂ (Conservativ) ነው። የተወሰኑ ነገሮችን እንደዶግማ ከተቀበለ በኋላ ከዚያ አልፎ ራሱን ለመጠየቅም ሆነ ራሱን ለማስጨነቅ አይፈልግም። በዚህም ምክንያት የራሱ ውስን አስተሳሰብ ተገዢ በመሆን በድንቁርና ዓለም ውስጥ እንዲኖር ይገደዳል። ፍልስፋና ከክርስትና ሃይማኖት የቀደመ ቢሆንም የሰው ልጅ ራሱን በመፈላሰፍ ከማስጨነቅ ይልቅ ብዙም ማረጋገጫ የማይጠይቀውን የተወሰኑ ነገሮችን ብቻ ከመጽሀፍ-ቅዱስ ውስጥ በመውሰድ የኖሮው መመሪያ ያደርጋቸዋል። ስለዚህም መጽሀፍ ቅዱስና ሃይማኖት በራሳቸው ሳይሆኑ የሰውን የማሰብ ኃይል የሚያግዱት፣ እንዴት እንደሚተረጎሙና በተግባርም እንደሚውሉ ነው። በተጨማሪም በሰው ልጅ በተወሰኑ ነገሮች ብቻ በመርካትና ራስን ካለማስጨነቅ የተነሳ ነው ህብረተሰባዊ ችግሮች ሊፈጠሩ የሚችሉት።

ያም ሆነ ይህ በአውሮፓ ታሪክ ውስጥ የፊዩዳሉ ስርዓት የራሱ የሆነና በአወቃቀሩ የተወሰነ ውስጠ-ኃይል ስለነበረው እስከተወሰነ ደረጃ ድረስ ለአስተሳሰበ ለውጥ መፈናፈኛ ስጥቷል ማለት ይቻላል። በተለይም ስርዓቱ ከኛው ጋር ሲወዳደር በጣም ጨቋኝ ስለነበር የግዴታ ገበሬው እንዲያምጽና እንዲደራደርም አስችሎታል። ከዚህም በላይ በተለይም አንዳንድ የሃይማኖት መሪዎች ራሳቸውም ምርምር ስለሚያደርጉና በምድራዊና በመንፈሳዊ ዓለም ያለውን የቀሳውስት አኗኗር እንዲለይ ይጎተጎቱ ስለነበር፣ ሃማኖት ከውስጥ ቅራኔ ተነስቶበታል ማለት ይቻላል። በተጨማሪም፣ በሩቅ ንግድ አማካይነት በአንድ በኩል ወደ ውስጥ የገንዘብ ሀብት መከማቸት፣ በሌላ ወገን ደግሞ አሪስቶክራሲውና የባላባቱ መደብ ከአዲስ የፍጆታ አጠቃቀም ጋር መተዋወቅና፣ ራሱ የባላባቱ መደብ በዕዳ መተብተብ የግዴታ ስርዓቱን ላላ እንዲያደርገውና ለአዳዲስ ኃይሎችና አስተሳሰብ በሩን እንዲከፍት ማድረግ ተገዷል። ከዚህም ባሻገር ገንዘብ ማካበት የጀመረው በሩቅ ንግድ የተሰማራው ነጋዴ ወደ ውስጥ የዕደ-ጥበብ ስራን መቆጣጠር ይጀምራል። አንጥረኛው ከነጋዴው የሚመጣለትን ትዕዛዝ በመቀበልና ምርትን በማምረት(Putting-Out System) የፍጆታ አጠቃቀም እንዲለወጥና የውስጥ ንግድም እንዲስፋፋ ያደርጋል ። ለአውሮፓው የካፒታሊዝም ዕድገት መዓት የተጋጠጠሙና እንደምክንያት የሆኑ ነገሮች ስላሉ በእነሱ ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ለመስጠት አልፈልግም።

ወደ አገራችን ስንመጣ ስርዓቱ ይህንን ሁሉ ዕድል አላገኘም። ከውስጥ አንጥረኛው ከነጋዴው ጋር የመገናኘት ዕድል አልነበረውም። በውጭ ንግደ ላይ የተሰማራው ነጋዴ ወደ ውስጥ ተቀማጭና የሰራ-ክፍፍልን የሚያዳብር አልነበረም። ከዚህም በላይ በባላባቱ ስርዓት ንግድና የዕደ-ጥበብ ስራዎች እንደ አፀያፊ ተግባራት ነበር የሚቆጠሩት። በዚህም ምክንያት በንግድና በዕደ-ጥበብ ሙያ የተሰማሩት „የህብረተሰብ ክፍሎች“ ከክርስቲያኑ ህዝብ ጋር በጋብቻም ሆነ በሌላ ነገር የሚጋቡና የሚገናኙ አለነበሩም። ይህም በራሱ ህብረተሰቡ አዳዲስ አስተሳሰብ እንዳያፈልቅና እንዳይስፋፋ አድርጎታል ማለት ይቻላል። ከውጭም የሚመጣ አስተሳሰብም ስላልነበረ ስርዓቱ ለብዙ መቶ ዐመታት ተንሰራፍቶ የመኖር ዕድል አጋጥሞታል። እንደነ ማርቲን ሉተርና ካንትን የመሳሰሉ ስዎች ብቅ ማለትም ስላልቻሉ አዲስ ፍልስፍናና ሳይንሳዊ አስተሳሰብ ሊዳብሩ አልቻሉም።  በዚህ ላይ፣ የርስት መሬት የተሰጠው የክርስቲያኑ ገበሬ ባለው ረክቶ የሚኖር ስለነበር የተቃውሞ ባህል ማዳበር አልቻለም። ግፋ ቢል የሚያደርገው በተናጠለ መሸፈት ነበር። ይህ ጉዳይ እስከዛሬ ድረስ እንደ ባህል ተወስዶ ምሁሩም ሲመረው ወደ ውጭ የሚሽሽና ከውጭ ሆኖ ለመታገል የሚጥር አድርጎታል። በሌላ አነጋገር፣ ከውስጥ ሆኖ ስርዓቱን በምሁራዊ ኃይል ለመጋፈጥ የሚያስችል ባህል ስላልተመደ ስርዓቱ ራሱ ካለብዙ ግፊት ለብዙ መቶ ዐመታት እንዲቆይና ኋላ-ቀርነትና ድህነት መለዮአችን እንዲሆን ለማድረግ ችሏል ማለት ይቻላል። ከዚህ በተረፈ የገበሬው የማምረት ኃይል ደካማ ስለነበር ብዙ በማምረት ወደ ገበያ አውጥቶ የመሸጥ ኃይል አልነበረውም። ለባላባቱና ለቤተክርስቲያን ከገበሬው የሚሰጠው ድርሻ ከራስ ጥቅም ስለማያልፍ በአጠቃላይ ሲታይ ሀብት እንዳይከማችና እንደገና ለመዋዕለ-ነዋይ እንዳይውል አግዶታል። በፖለቲካ-ኢኮኖሚክስ ህግ መሰረት ከፍጆታ በላይ ተጨማሪ ምርት(Surplus-product) የማያመርቱ ህዝቦች ለማደግ አይችሉም። በሌላ አነጋገር፣ ከእጅ ወደ አፍ ብቻ በሚውል የአሰራርም ሆነ የአስተራረስ ዘዴ የሚኖር ህዝብ የማደግ ኃይሉ በጣም ደካማ ነው ማለት ነው።  በሌላ ወገን ግን በአገራችን ውስጥ ምንም ዐይነት ቴክኖሎጂያዊ ወይም የአሰተሳሰብ ለውጥ የለም ብሎ መናገር በፍጹም አይቻልም። ለምሳሌ የጠላ፣ የጠጅንና የካቲካላን አጠማመቅ ካለብዙ ውጣ ውረድ ስንመረመር እናቶቻችን በደመ-ነፍስ እየተመሩ አዲስ የአኗኗር ስልትን ማዳበር እንደቻሉ ነው የምናየው። በመሰረቱ፣ በተለይም የካቲካላ አጠማመቅ ባይሎጂያዊ፣ የኬሚካላዊና የፊዚክስ ክንውን ነው። ከምርት ክንዋኔ እስከ ብቅል ማብቀልና ድፍድፍ መስራትና ይህንንን በእሳት አማካይነት ወደ ፈሳሽነት መለወጥ ሳይንሳዊ ክንዋኔ ለመሆኑ የተረጋገጠ  ጉዳይ ነው። ይህ ሁሉ ሊሆን የቻለው እናቶቻችን ምንም ዐይነት ሳይማሩ በደመ-ነፍስ በመማራቸውና እስከተወሰነ ደረጃም ድረስ የማሰብ ኃይላቸውን መጠቀም በመቻላቸው ነው።  እንደዚህ ዐይነቱ አመራረትም በአውሮፓ ምድር ውስጥም በማዕከለኛው ዘመን  የተለመደ ነበር። እነሱ ግን መመራመርና መፍጠር ስለቻሉ ቴክኖሎጂውና የአሰራር ዘዴው በዚያው ሊቀር አልቻለም። የሽማኔንም ባህል ስንመለከት እናቶቻችንና አባቶቻችን ከውጭው ዓለም ጋር ሳይገናኙ በራሳቸው የማሰብ ኃይል የልብስ አሰራር ቴክኒክን ሊያዳብሩና፣ እስከዛሬ ድረስ ይህ እንደ ባህል ሊወሰድና መለዮአችንም ሊሆን በቅቷል።፡ ይህም የሚያመለክተው የተለያዩ ህበረተሰቦች በራሳቸው የማሰብ ኃይል አንደኛው ከሌላው ሳይኮርጅ የተወሰነ ቴኮኖሎጂያዊ ለውጥንና የአመራረት ሁኔታን እንደሚፈጥርና እንደሚያዳብር ነው።

እዚህ ላይ መተንተን ያለበት ሌላ መሰረታዊ ነገር አለ። በመጀመሪያ ማንም ሰው ፊይዳል ልሁን ብሎ አይነሳም። ፊዩዳሊዝም የህብረተሰብአዊ ክንውን ውጤት ሲሆን፣ በስ13ኛው ክፍለ-ዘመን በአሸናፊነት ከወጣው የሰለሞናዊው አገዛዝ ጋር በጥብቅ የተያያዘ ስርዓት ነው። አዲሱ ንጉሳዊ አገዛዝ ህብረተሰቡን ለመቆጣጠርና ለማስተዳደር ሲል መሬትን ለባላባቱ መደብና ለገበሬው እንደየህብረተሰብአዊ አቀማመጣቸው አከፋፈለ። በዚህ ዐይነቱ የመሬት አደላደልና ህብረተስብአዊ አወቃቀር ቤተክርስቲያን የራሷ ድርሻ ተሰጣት። በዚህ መልክ የህብረተሰቡ የርስ በርስ ግኑኝነት መሬትን በሚቆጣጠሩና ከመሬት በሚገኝ ሀብት በሚተዳደሩና አርሶ በሚያድረውና፣ ጠቅላላውን የአገዛዘ አወቃቀር በሚደግፈው ሰፊ ገበሬ መሀከል የሚገለጽ ነበር። እንደዚህ ዐይነቱ ስርዓት በገዢና ተገዢ፣ በአስገባሪና በገባሪ መሀከል የሚገለጽ ስለነበር ገበሬው መጠየቅ የሚችልና ለመብቱም የሚከራከረ አልነበርም። ስርዓቱ ተፈጥሮአዊ ሆኖ በመወሰዱ የህብረተሰቡን ኑሮና አስተሳሰቡን የሚደነግግና የምርት ኃይሎችም እዚያው ባሉበት ቀጭጨው እንዲቀሩ የማድረግ ኃይሉ ከፍተኛ ነበር ማለት  ይቻላል። ስለሆነም የሰው የማሰብ ኃይል ውስንና በራሱ የማሰብ ኃይል የኑሮውን ሁኔታ ማሻሻልና መለወጥ የማይችል ሆኖ ይሰማው ነበር። በህብረተሰቡ ውስጥ የሚከሰቱ ማንኛውም ቀውሶች፣ ረሃብ፣ የወረርሽኝ በሽታና ሌሎችም እንደ እግዚአብሄር ቁጣ የሚታዩና በጸሎት ሊወገዱ የሚችሉ መስሎ የሚታይበት ሁኔታ ለብዙ መቶ ዐመታት ስፍኗል።  ከዚህ በተጨማሪም፣ በሆነው ባልሆነው ነገር ማመንና በፍርሃት መዋጥ የህብረተሰቡ የማሰብ አካልና አስተሳሰቡንም ወጥሮ የያዘው ነበር። ስለዚህም የገበሬውም ሆነ የአገዛዙ በተለያየ መልክ የሚገለጹ ባህሪዎች በሚሆንና በማይሆን ነገሮች የተጠመዱና ለሳይንስንና ለቴክኖሎጂ ፈጠራ የማያመቹ አስተሳሰቦች ነበሩ።

ያም ሆነ ይህ የፊዩዳሉ ስርዓት አ.አ እስከ 1974 ድረስ መቆየቱና፣ ራሱ ደግሞ እጅግ ተሰበጣጥሮ የገባው በተለይም በገንዘብና በፍጆታ አጠቃቀም የሚገለጸው ካፒታሊዝም የማሰብ ኃይላችንን ሊወስነው ችሏል። ይህም ማለት በረቀቀና በተወሳሰበ መልክ እንዳናስብ፣ ሎጂካዊና አርቆ አስተሳሰብን እንዳናዳብር፣ ንቃተ-ህሊናችንን በማዳበር ለህብረተሰባችን ኃላፊነት እንዳይሰማን፣ በአገራችንና በራሳችን ላይ ከመመካት ይልቅ በውጭው ዓለም ላይ ጥገኛ እንድንሆን ለማድረግ በቅቷል ማለት ይቻላል። በተጨማሪም ሂስን ለመቀበልና ለመሰንዘርም ዝግጁ መሆን አልቻልንም። ካለምንም ውጣ ውረድ አንድ „ከበድ ያለ ሰው“ ስናይ በሱ ሃሳብ መመራት አስቸጋሪው ባህርያችን እየሆነ መጥቷል። ይህም ማለት ዕውቀትንና ጥበብን አሳዳጆች ሳንሆን ሰውን በማሳደድና በሱ ጥገኛ በመሆን የአዳዲስ አስተሳሰብና የዕድገት እንቅፋት ለመሆን በቅተናል።  በዚህ ላይ ደግሞ በዕምነትና በፕሪንስፕል ላይ አለመመራትና አለመስራት፣ እንዲሁም ተንኮልና አድርባይነት አስቸጋሪው ባህርያችን በመሆን ለችግራችን ልዩ ገጽታ በመስጠት ህብረተሰብአችን እንዲመሰቃቀል አድርገውታል። ስለሆነም፣ ለፈጠራ የሚያመቹ አዳዲስ ሃሳብን የማፍለቅና ችግርን የመፍታት ባህልን ማዳበር አልቻልንም። በአንድ ሃሳብ ዙሪያ ለመደራጀት አለመቻል፣ በዕቅድ መመራትና የተሰጠንን ኃላፊነት በስራ ላይ ማዋል አለመቻል፣ ተጠያቂ መሆንና በአጠቃላይ ሲታይ ለህብረተሰብአችን ኃላፊነት እንዳለበን አለመረዳት ሌላውና አስቸጋሪው ባህርያችን ሆነዋል። በተለይም የተለያዩ የፍልስፍናና የሳይንስ አስተሳሰቦች እንደመከራከሪያ ነጥቦች ስለማይቀርቡና ጥናትም ስለማይካሄድ አብዛኛዎቻችን የተሰማራናው ብዙም ጥያቄን ወደ ማያስከትለው ግን ደግሞ ለአንድ ህብረተሰብ የመኖርና ያለመኖር ወሳኝ በሆነው  ፖለቲካ(ቦለቲካ) በሚባለው ነገር ላይ ነው።

እንዲሁም የአንድን ህብረተሰብ ዕድገት የሚጎትቱና ህብረተሰባዊ ትርምስም እንዲፈጠር የሚያድረጉ አስተሳሰቦች በመስፋፋት የማሰብ ኃይላችንን ለመቆጣጠር በቅተዋል። ይህ በራሱ ደግሞ በጠቅላላው በአደረጃጀት፣ በዕቅድ ላይና በጠቅላላው ለህብረተሰብ ዕድገት በሚያስፈልጉ ነገሮች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ በማድረግ ለዛሬው ትርምስ ምክንያት ሆነዋል ማለት ይቻላል። ይህ ብቻ ሳይሆን፣ ሁሉም በየፊናው የሚሮጥ እንጂ ለመተባበር የሚፈልግ አይደለም። ሁሉም ስልጣን ላይ ቁጥጥ ለማለት የሚፈልግ እንጂ ለማስተማርና ደቀ-መዝሙሮችን ለማፍራት የሚፍልግ አይደለም። እያንዳንዱ ግለሰብም ሆነ ድርጅት አለኝ የሚል በራሱ ብቻ ኢትዮጵያን የመሰለ ትልቅ አገር የሚገነባ ነው የሚመስለው። ብዙ ዕውቀትና ኃይል እንዲሁም መቻቻል ለአገር ግንባታ አስፈለጊዎችና መሰረተ-ሃስቦች እንደሆኑ አይረዳም። ኢትዮጵያ ትላንትና የሃምሳ ሚሊዮን ህዝብ አገር፣ ዛሬ ደግሞ የዘጠና ሚሊዮን ህዝብ አገር እንደሆነች የሚረዳው በጣም ጥቂቱ ብቻ ነው። የህዝብ ቁጥር በዚህ መልክ እየጨመረ ሲሄድ የግዴታ አዳዲስ ፍላጎቶችም እንደሚከሰቱና፣ እየጨመረ የመጣውን የህዝብ ቁጥር ለማስተናገድ በየጊዜው ማሰብና ማቀድ አስፈላጊ መሆኑን የሚረዳው በጣት የሚቆጠር ነው።  ስለሆነም አንድን አገር ለመገንባት ኃይልንና ሃሳብን መሰበሰብና በጋራ ለመሰራት አስፈላጊ መሆኑን የተገነዘብን አይመስለኝም። በተለይም ባለፈው አርባ ዐመታት ቡዳናዊ ስሜት አይሎ በመውጣቱና፣ በዚህ ላይ ደግሞ እንደ ሃይማኖትና የብሄረሰብ ጥያቄዎች ተጨማሪ አጀንዳ ሆነው በመወሰዳቸው አስተሳሰባችን ችግርን ለመፍታት ወደ ሚያስፈልጉ ነገሮች ላይ ከማዘንበል ይልቅ በችግራችን ላይ ችግርን በመጨመር ወደ ትርምስና መፍቻ ወደ ማይገኝለት ዓለም ውስጥ የምንጓዝ ለመሆን በቅተናል። እስከዛሬ ድረስ ሁላችንም ቢሆን ችግራችንና የችግራችንን ምንጭ ከሳይንስና ከፍልስፍና አንፃር መመርመር አልቻልንም። ሁላችንም ብንሆን ይበልጥ የምንመራው በስሜታዊነት እየተገፋን እንጂ የማሰብ ኃይላችንን በማንቀሳቃስ  አይደለም። እንደ አንድ ጥቁር ህዝብና የተወሳሰበ ችግር እንዳለበት በአንድ መንፈስና በአንድ ዓላማ ከመነሳትና ከመመራት ይልቅ ቡድናዊ ስሜትን በማዳብርና ሳይንሳዊ መሰረት የሌላቸውን ነገሮች በማንሳት በምስኪኑ ህዝብ ላይ እናሾፍበታለን። ለምሳሌ ከሳይንስና ከፍልስፍና አንፃር የምርምር መሰረተ-ሃሳቦች የሰው ልጅ፣ ተፈጥሮና ኮስሞስ ብቻ ናቸው። ስለሆነም የሰውን ልጅ የማሰብ ኃይል በማዳበር የሰው ልጅና ተፈጥሮ በመደጋገፍ በምድር ላይ ሚዛናዊ ስርዓት መመስረት የሚለው የሳይንስና የፍልስፍና መሰረተ-ሃሳቦች ናቸው። እኛ ግን ሳይንሳዊ መሰረት የሌለውን የብሄረሰብ ጥያቄን በመፍጠር ለችግራችን ልዩ ዕምርታን ሰጥተነዋል።  በአስራሰባተኛው፣ በአስራስምንተኛውና በአስራዘጠነኛው ክፍለ-ዘመን ብቅ ያሉት የአውሮፓ ምሁራን ልክ ዛሬ እኛ እንደምናስበውና እንደምንጨቃጨቅበት ትግላቸውን ቢጀምሩ ኖሮ የሳይንስና የቴክኖሎጂ ዓለምን ባላየን ነበር። ጫካ ውስጥ እየተተራመስን የምንኖር ነበርን። ስለሆነም የሰውን ልጅና ተፈጥሮን እንደመፈላሰፊያ ነጥብ የወሰዱት የአውሮፓ ምሁራን የሳይንስና የቴክኖሎጂ ባለቤት ለመሆን ሲበቁ፣ እኛ ደግሞ ከሳይንስና ከፍልስፍና ውጭ የማይሆን ነገር በመፍጠር በመጠራጠርና በመፈራራት ዓለም ውስጥ እንኖራለን። የሰው ልጅ ሌላውን አምሳሉንና በእግዚአብሄር አምሳል የተፈጠረውን እንዲጠላና እንዲገደል እናደርጋለን። የዕውቀትና የአስተሳሰብ ችግር መሆኑን ከመረዳት ይልቅ ችግሩ ሁሉ ከአንድ ብሄረሰብ የተፈጠረ በማስመስል ህብረተስብአዊና ባህላዊ ትርምስ እንፈጥራለን። ይህም የሚያረጋግጠው ምንድ ነው፟? የቀጨጨ አስተሳሰብ ያለንና አምላክ የለገሰንን የማሰብና የመመራመር ኃይል ሁሉ ለመጠቀም እንደማንችል ነው።   ስለሆነም፣ እኛው ራሳችን የረሃብና የድህነት ምክንያቶች ልንሆን በቅተናል። ዕድገትና ስልጣኔ እንዳይኖር እንቅፋት በመሆን የጥቁር ህዝብ በጨለማ ዓለም ውስጥ እንዲኖር ባለማወቅ የምንሰራው ስራ ሁሉ የታሪክ ወንጅል እየሆነ መጥቷል።

ሌላው አስቸጋሪው ጉዳይ ደግሞ ሁሉም ፖለቲከኛ ሆኖ ለመታየት መፈለጉና ስለሚሯሯጥም አስቸጋሪ ሁኔታን እየፈጠረ ነው። እስከሚገባኝ ድረስ ፖለቲካ እንደማንኛውም የትምህርት ዘርፍ ዕውቀትን ይጠይቃል። እንደ ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ ባይሎጂና እንደህክምናና ሌሎችም ችግር መፍቻ ዘዴዎች የሆኑት እንደ ኢንጂነሪግ የመሳሰሉት ዕውቀቶች ሁሉ ፖለቲካ ሰፋ ያለ ዕውቀትን የሚጠይቅ ነው። ለምሳሌ አንድ ሰው የፓይለት ኮርስ ወስዶ በደንብ ሳይሰለጥንና ፈተናውን ሳያልፍ አውሮፕላን መንዳት እንደማይችል ሁሉ ፖለቲካ አንድን ህብረተሰብ ማስተዳደሪያና አገርን መገንቢያ መሳሪያ እንደመሆኑ መጠን ማንኛውም በፖለቲካ ዓለም ውስጥ እሳተፋለሁ የሚል አስፈላጊውን ጥናትና ምርምር ማድረግና በተግባርም ለማሳየት መቻል አለበት። ማንም እየተነሳ ፖለቲከኛ ነኝ የሚል ከሆነ ፖለቲካ የወንበዴዎችና የገዳዮች መጫወቻ ይሆናል ማለት ነው። ይህ ዐይነቱ በአገራችን የተስፋፋ አጉል ባህል እስካልተወገደ ድረስና፣ ፖለቲካም ሳይንሳዊና ፍልስፍናዊ፣ ሶሶይሎጂያዊና ሳይኮሎጂያዊ፣ እንዲሁም ልዩ ልዩ ዕውቀቶችን መሰረት ያደረገ መሆኑ እስካልታየ ድረስ ሁሉም ፖለቲከኛ ነን እያለ ህዝብን ይበጠብጣል።  ስለሆነም ሁሉም በየዝንባሌውና በሰለጠነው ፊልድ ቢሰራና አስተዋፅዖ ቢያደርግ ለአገርና ለህዝብ ይበጃል።  እስካሁን የማይገባኝ ነገር፣ ለምሳሌ ፊዚክስ ወይም ባይሎጂ የተማሩ ምሁራን በዚህ ጠለቅ ያለ ምርምር ከማድረግና ለአገራቸውም ዕድገት አስተዋፅዖ ከማበርከት ይልቅ ፖለቲካ ዓለም ውስጥ ገብተው ዕውቀታቸውን እንድሚያባክኑ ነው።

ይህ ሁሉ የሚያረጋግጠ ምንድነው ? የሃሳብ ነፃነት ተሰምቶን ሃሳብን የምናፈልቅና በሱ ላይ ክርክር ለማድረግ የማንችል መሆናችንን ነው። የሌላውንም ሃሳብ የማናዳምጥና በንቀት የምናይ ነን። እንደ አ.አ በ1906 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ የሄደ ጀርመናዊና አዲስ አበባና አርሲ እስከ ጣሊያን ጦር መጨረሻ ድረስ የኖረ ጀርመናዊ የኢትዮጵያ አገር ወዳድ በቅጡ ባህርያችንን እንደተመለከተው፣ አብሲኒያኖች 1ኛ) መመልከትና መኮረጅ አይችሉም፣ 2ኛ) የሰውን ንግግር ሳይሆን የራሳቸውን ንግግር ብቻ ነው የሚያዳምጡት ያለው እስከዛሬ ድረስ ቋሚነት አለው። ልዩ ዐይነት ባህርያችንና ለውዝግብ አንዱ ምክንያት ነው ማለት ይቻላል። ሃሳብን ማፍለቅ አለመቻል ብቻ ሳይሆን ማዳመጥና መደማመጥንም አንችልም። ይህ ዐይነቱ ባህርይ እስካለ ድረስ ደግሞ ስለ አገርና ዕድገት ማሰብም ሆነ ማውራት አንችልም። ከዚህ ስንነሳ የግዴታ ሁለንተናዊ  የአስተሳሰብ ለውጥ ለማድረግ መቻል አለብን። ራሳችንን እየመላለስን ለመጠየቅና ለመመርምር ዝግጁ መሆን አለብን። ይህ እስካለሆነ ድረስ  የወያኔ መወገድ በራሱ ብቻ ምንም ለውጥ ሊያመጣ የሚችለው ነገር የለም።  ከዚህ በመነሳት ደግሞ ወደ ሌላው አስቸጋሪው ነገር እንሻገር።

ለምን ዐይነት ህብረተሰብ እንደምንታገል ያለማወቁ ጉዳይ !!

ድሮም ሆነ ዛሬ ሲያተራምሰን የኖረው ለምን ህብረተስብ እንደምንታገል ያለማወቃችን ነው። ለምሳሌ በአውሮፓ ህብረተሰብ የትግል ታሪክ ውስጥ ከግሪኩ ስልጣኔ ጀምሮ በየኤፖኩ ብቅ ያሉት ምሁራን ምን ምን ነገሮች እንደሚፈልጉና ምን ዐይነትስ ህበረተሰብ መመስረት እንዳለበት በደንብ የተገነዘቡ ነበር። ስለሆነም ከመንግሰት አወቃቀር ጀምሮ፣ እስከ ፖለቲካ ምንንነትና ሞራልና ስነ-ምግባር መወያያ ነጥቦች ነበሩ። በግሪክ ስልጣኔም ሂደት ውስጥ ለአንድ ህብረተሰብ መኖርና ማበብ የግዴታ የስራ ክፍፍልና የንግድ ልውውጥ አስፈላጊው መሰረተ-ሃሳቦች እንደሆኑ ክርክር ይደረግ ነበር።

ኋላ ደግም ወደ አውሮፓ ስንመጣ የመንግስትን ሚና በኢኮኖሚ ውስጥና፣ የነቁ የህብረተስብ ክፍልሎችን በሃስባና በቁሳቁስ መርዳት፣ እንዲሁም ደግሞ ማኑፋክቱርና የውስጥ ንግድ እንዲስፋፋ አስፈላጊው እርምጃዎች ስለመወሰዳቸው ጉዳይ በምሁራን ዘንድ በሰፊው ውይይትና ክርክር ይደረግባቸው ነበር። ይህ ብቻ ሳይሆን፣ ለአንድ ህዝብ መሰባሰብ የግዴታ መንደሮችና ከተማዎች በዕቅድ መስራት እንዳለባቸውና፣ ምን ምን እርምጃዎች መወሰድ እንዳለባቸው፣ እንዴትስ ገንዘብንና የሰውን ኃይል መሰብሰብና ማደራጀት እንደሚያስፈልግ ሌላው መነገጋሪያ ነጥብ ነበር። ከተማዎች፣ መንደሮች፣ የመናፈሻ ቦታዎች፣ የገበያ አዳራሾችና ልዩ ልዩ ለአንድ አገር የሚያስፈልጉ ነገሮች ሳይነጠፉና ሳይሰተካከሉ ስለ ኢኮኖሚና ስለአንድ ህብረተሰብ ማውራት እንደማይቻል ለአውሮፖው ምሁራን ግልጽ ነበር። ስለሆነም የአውሮፓው ምሁራን አስተሳሰብ ሁለንታዊና፣ አንዱ ነገር ከሌላው ተነጥሎ ሊታይ እንደማይችል መመሪያ ዘዴና የአሰራር ባህል ነበር።

ወደ አገራችን ስንመጣ ግን፣ በተለይም ወያኔ ስልጣን ከጨበጠ ወዲህ ተቃዋሚ ነኝ ከሚለውና መጠኑ ከማይታወቀው ኃይል፣ ህዝባችን ምን ዐይነት ስርዓት እንደሚያሰፈልገውና በምንስ መልክ እንደሚደራጅ ግልጽ ውይይት ሲካሄድ ታይቶ አይታወቅም። ከአብዮቱ በፊትና በአብዮቱ ወቅት በዚያን ጊዜ ተራማጅ ነኝ ይል ከነበረው ኃይል ዘንድ ቢያንስ አንድ ዐይነት ስምምነት ነበር። ወዛደሩንና ገበሬውን ያቀፈ ዲሞክራሲያዊና ሶሻሊስታዊ ስርዓት መገንባት ያስፈልጋል የሚለው ላይ ስምምነት ነበር። በዚያን ጊዜ ከተማሪው ንቅናቄ የወጡ ተራማጅ ኃይሎች በጊዜው የነበረውን ስርዓት ከመመረመሩ በኋላ የደረሱበት መደምደሚያ ዲሞክራሲያዊና ሶሻሊስታዊ ስርዓት ነው የሚያስፈለገው የሚል ነበር። ይህ ዐይነቱ ግምገማና ድምዳሜ ትክክል ነው ትክክል አይደለም በሚለው ላይ መነታረኩ ከዚህ ጽሁፍ አቅም በላይ ነው። ለማለት የተፈለገው አንድን አገዛዝ እቃወማለህ ስንል አገዛዙን ብቻ ሳይሆን የስርዓቱንም ምንነት መረዳትና፣ ለምንስ ህብረተሰብ እንደምንታገልና፣ ምን ምንስ እርምጃዎች ተግባራዊ መሆን እንዳለባቸው ማመልከት ያስፈልጋል።

በተቃዋሚው ዘንድ ያለው ሌላው አስቸጋሪ ነገር ወያኔ ስልጣን ከጨበጠ ጀምሮ የዘረጋውን ስርዓት በሚገባ አለመመርመር ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን፣ በአብዛኞቻችን ዘንድ አገዛዙ እስከዛሬ ድረስ የተከተለውን የኢኮኖሚ ፖሊሲ አለመመርመርና ለመረዳት አለመቻል ለወደፊቱ ህብረተሰብአዊ ፕሮጀክት አስቸጋሪ ሁኔታ መፍጠር ችሏል። እንደሚታወቀው ለአንድ አገር ነፃነት እታገላለሁ የሚል ድርጅትም ሆነ ድርጅቶች የስርዓቱን ምንነትና ስንኩልነት በሚገባ መረዳት አለባቸው። ለምሳሌ ሲያመን  ሃኪም ቤት በምንሄድበት ጊዜ ሀኪሙ ምርመራ ከመጀመሩ በፊት ምንና የት ቦታ እንደሚያመን፣ ከመቸስ ጀምሮ እንደሚያመን ሲጠይቀን መመለስ እንዳለብን ሁሉ፣ ለአገራችንም እንታገላለን ስንል በቅድሚያ በሽታውንና ለዕድገት ማነቆ የሆነውን ሁኔታ በሚገባ መመርመርና ወደ ውጭ አውጥተን መወያየትና መከራከር አለብን። እንዲያው በደፈናው ነፃነት ነው የሚያስፈልገን፤ ሌላውን ከዚያ በኋላ እንወያይበታለን የሚለው አባባል ለችግራችን መፍትሄ ሊሆን የሚችል አይደለም። በተለይም ደግሞ ከህብረተስብ ግንባታ፣ ፈጠራና በሳይንስና በቴክኖሎጂ፣ እንዲሁም ደግሞ ውብ ውብ ከመሳሰሉ ከተሞች አንፃር ስንነሳ በቅድሚያ የዛሬውን የአገራችንን ሁኔታ፣ የአገዛዙን ፖሊሲና ከውጭ ኃይሎች ጋር ተቆላልፎ ለዕድገትና ለስልጣኔ ከፍተኛ ጠንቅ መሆኑን እያነሱ መወያየት ያስፈልጋል። ከዚህ ስንነሳ ለምንድን ነው ይህንን አገዛዝ የምንታገለው?  ብለን ጥያቄ ማቅረብ አለብን።

በአጭሩ ይህንን አገዛዝ የምንታገለው ፋሺሽታዊ መዋቅር በመዘርጋት ህዝባችንን ርስ በርሱ እንዲጫረስ የተቻለውን ሁሉ ስለሚያደርግ ነው። የውጭ ኃይሎች ታዛዥ፣ በተለይም የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ታዛዥ በመሆንና የጦር ካምፕ እንዲቋቋም በማድረግ የውክልና ጦርነት በማካሄድ የጥቁር ህዝብ ርስ በርሱ እንዲጫረስና ለዘለዓለሙ የስልጣኔ ባለቤት እንዳይሆን ስለሚያደርግ ነው። አገራችን ብቻ ሳይሆን፣ በአካባቢው ያለው ጠቅላላው ጥቁር ህዝብ ስልጣኔን እንዳያይ በጦርነት ታምሶ እንዲኖር ስለሚያደርግ ነው። አገራችን ታሪክ እንዳይሰራባት፣ ህዝቦቿ የቀን ብርሃንን እንዳያዩና ዘለዓለም ተመጽዋች ሆነው እንዲኖሩ ስለሚያደርግ ነው። ባጭሩ የአገዛዙ ተልዕኮ ፀረ-ስልጣኔ፣ ፀረ-ሳይንስና ፀረ-ቴክኖሎጂ፣ ፀረ-ህዝብና የተፈጥሮ ጠንቅ ስለሆነ ነው አጥብቀን የምንዋጋው። ስለሆነም ትግላችን የዛሬው እጅግ አስከፊ ስርዓት እንዲወገድና ህዝባችንም ዲሞክራሲያዊ ነፃነቱን እንዲቀዳጅና ታሪክን ለመስራት እንዲችል ነው ደፋ ቀና ይምንለው። ባጭሩ የዛሬው አገዛዝ የድህነት፣ የረሀብ፣ የጦርነት፣ የስደት፣ የትርምስና ያለመረጋጋት ምንጭ ስለሆነ አጥበቀን እንታገለዋለን። አገዛዙን የምንታገለው በትግሬዎች ስለሚመራ ሳይሆን ይህንን እንደ ሽፋን በመጠቀም በጠቅላላው ህዝባችን ላይ ስለዘመተ ነው። የትግሬን ኤሊት የበላይነት አሰፍናለሁ በሚል የራሱንና ከሱ ጋር በጥቅም የተሳሰሩ ጥቂት ሰዎችን ጥቅም የሚያሰጠብቅ ነው። በዚህም ምክንያት በአገሪቱ ውስጥ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ሰፋ ያለና ጠቅላላውን ህዝብ የሚጠቅም ኢኮኖሚ እንዳይዳብር አግዶ ይዟል። ሰፋ ያለ ህዝቡን ሊያስተሳሰር የሚችልና በሳይንስ የተጠና ባህል እንዳይዳብርና አገራዊና ብሄራዊ ስሜት እንዳያድጉ በዕውቅ ይሰራል።  አገዛዙ  የውጭ ቅምጥ ስለሆነና በነሱም ስለሚደገፍ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት ብቻ ሳይሆን የጠቅላላው ጥቁር ህዝብ ጠላት ማለት ይቻላል።

ስለሆነም የኛ ትግል ደግሞ የሰለጠነችና በቴክኖሎጂና እንዲሁም በሳይንስ ላይ የተደገፈች ኢትዮጵያን መገንባት ይሆናል። ውብ ውብ ከተማዎችና መንደሮችን በመገንባት ህዝባችን ዕውነተኛ ነፃነቱን ሊጎናጸፍበት የሚችልባትን ኢትዮጵያ ለመገንባትና ለመጭው ትውልድ ለማስተላለፍ ነው ዋናው ትግላችን። በዚህም ሺህ በሺህ የሚቆጠሩ የሊትሬቸርና የፈላስፋ ስዎች፣ እንዲሁም የሳይንስና የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች የሚበቅሉባትና የሚስፋፉባት አገር ለመመስረት ነው። ይህ ዐይነቱ ህብረተሰብ በመንግስት፣ በህብረተሰቡና በግል ተሳትፎ የሚገነባና የሚደጋገፍ፣ ግን ደግሞ የገበያን ኢኮኖሚ የማይጻረር፣ የገበያ ኢኮኖሚ ጤናማ በሆነ መልክ ሊገነባ የሚችልበትን መሰረት ለመጣል የሚያስችል መሆን አለበት። ህዝባችን ከድህነትና ከረሃብ የሚላቀቀውና ዕውነተኛ ነፃነቱን ሊቀዳጅ የሚችለው በሳይንስና በቴክኖሎጂ አማካይነት ብቻ መሆኑን በመረዳታችን ለዚህ ለተቀደሰ ዓላማ እንታገላለን። ዋናው ትግላችንም የተከበረችና የምትፈራ፣ እንዲሁም ብሄራዊ ነፃነቷ በማንም ኃይል የማይደፈር ኢትዮጵያን መገንባት ይሆናል።

ከዚህ ስነሳ የሚቸግረኝ ነገር  የወያኔን ባህርይ የማወቁ ጉዳይ ሳይሆን ተቃዋሚው ኃይል ምን እንደሚፈልግና ለምንስ ህበረተሰብ እንደሚታገል ለመረዳት አለመቻሌ ነው። ይህ ዐይነቱ ግልጽ የትግል አካሄድ ከምን የመነጨ ነው? በእኔ ዕምነት የተቃዋሚው ኃይል የሚመራበት ፍልስፍናና ሳይንስ የለውም። በመሆኑም በቅጡ የአገዛዙን ባህርይም ሆነ ስርዓቱን፣ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ኮሙኒቲው የተደገሰልንን የጥፋት ፖለቲካ በሚገባ የተገነዘበና ሊገነዘብም የሚፈልግ አይደለም። እንዲያው በደፈናው ብቻ እኛ ስልጣን ከጨበጥን ሁኔታውን እንለወጠዋለን የሚል አጉል ፖለቲካ በማካሄድ ስፊውን ህዝብና፣ በተለይም ደግሞ ወጣቱን እያዘናጋውና እያታለለው ነው። ይህ ከሆነ ደግሞ ለምንስ ወያኔን እንደምታገል ግልጽ አይደለም። ለምንስ ዕድሜዬን በሙሉ እኔ ብቻ ሳልሆን የኢትዮጵያ ህዝብም እንደሚሰቃይ አይገባኝም። ስለሆነም የስርዓቱን ምንነት ብቻ ሳይሆን ጠላቶቹንም ጠንቅቆ ማወቅ የሚያስፈልግ ይመስለኛል። ለዕድገታችን ጠንቅ የሆኑ ኃይሎችን በሚገባ መረዳት ከቻልንና፣ በቲዎሪ ደረጃ ተንትነን ማስረዳት ከቻልን ለችግሩ መፍትሄ አንድ መልስ አገኘን ማለት ነው።

ሌላው አስቸጋሪው ጉዳይ ደግሞ የተሰበጣጠሩ ኃይሎችና ዓላማቸውስ ምን እንደሆኑ የማይታወቁ በትግል ውስጥ እንሳተፋለን ስለሚሉና እዚህና እዚያ ስለሚሯሯጡ የአገራችንን ሁኔታ እንዳንረዳና ርዕይም እንዳይኖረን ለማድረግ በቅቷል። በተለይም ውጭ አገር የሚኖረውና እዚህና እዚያ የሚሯሯጠውና፣ ይኸኛውን ወይም ያኛውን ድርጅት እደግፋለሁ ወይም አባል ነኝ የሚል በዓለም ውስጥ ምን ነገር እንደሚካሄድ የሚያውቅ አይመስለኝም። ከዘጠና በመቶ በላይ የሚሆነው በውጭ አገር የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ከሊትሬችሮችና ከጋዜጦች ጋር ግኑኝነት የለውም። ይህ ዐይነቱ ኃይል ነው ልባችንን የሚያደርቀውና ለትግሉ እንቅፋት የሚሆነው። በዚህ መልክ ደግሞ አገርን ነፃ ማውጣትና ጠንካራ አገር መገንባት አይቻልም። ስለሆነም ትግሉ የግዴታ ጥራት ማግኘት አለበት። ለዚህ ደግሞ ሰፊ ጥናት ማካሄድ ያስፈልጋል። መንፈስን የሚያድስና ጥራትን የሚያመጣ የፍልስፍናና የሳይንስ መመሪያ ሊኖረን ይገባል። ይህ ሲሆን ብቻ ነው የታሪክ አስተዋፅዖአችንን ልንወጣ የምንችለው። አገራችንና ህዝባችን ታሪክ እንዲሰራ መንገዱን ማሳየት ብቻ ሳይሆን የምናግዘውም የጠራ አስተሳሰብና፣ አነሰም በዛም አንድ ሁላችንንም ሊያሰራ የሚችል የጋር አመለካከት ያፈለቅንና እንደመመሪያ መውሰድ ከቻልን ብቻ  ነው። ፕሉራሊዝምና ሊበራሊዝም የሚባሉት የቅንጦት ፅንሰ-ሃሳቦች ለችግራችን መፍትሄ ሊሆኑ አይችሉም። የአውሮፓው ህዝብም በነዚህ ፅንሰ-ሃሳቦች ወደ ጠንካራ ህብረተሰብና ህብረ-ብሄር አልተሽጋገረም። ይህ ማለት ግን የሃሳብ ነፃነት አይኑር ማለቴ አይደለም። ወደድንም ጠላንም ፕሉራሊዝም የተፈጥሮ ህግ ነው። በሌላ ወገን ግን አንድ ድርጅትም ሆነ አንድ ግለሰብ የጠራና መፍትሄ አምጭ አስተሳሰብ ሳይኖረው ስለፕሩላሪዝምና ሊበራሊዝም ቢሰብክ ውዠንብርን ብቻ ነው የሚነዛው። ህዝባዊ ፍላጎትን ሳይሆን የራሱን ጥቅም ብቻ ነው ተግባራዊ ለማድረግ የሚታገለው። አሁን ባለው የአገራችን የተወሳሰበና የተመሰቃቀለ ሁኔታ የግዴታ ስራ ሊያስራና መፍቴሄ ሊሰጥ የሚችል የሁላችንም መመሪያ የሆነ የጋራ ሃሳብ ማዳበር የሚያስፈልግ ይመስለኛል።

በመሆኑም ማንኛውም ስለ አገሬ ያገባኛል የሚል ግለሰብም ሆነ የፖለቲካ ድርጅት ማንሳትና መመለስ የሚገባቸው ጥያቄዎች አሉ። 1ኛ) በአገራችን የተንሰራፋውን ረሃብና እንደ ባህል የተወሰደውን እንዴት አድርጎ በአምስት ዐመት ጊዜ ማጥፋት ይቻላል? ብሎ መመለስ ያስፈልጋል። 2ኛ) ከዚህ በመቀጠል በምን ዘዴና መሳሪያ ድህነትን በሃያ ዐመት ጊዜ ውስጥ ማስወገድ ይቻላል? ብሎ መጠየቅና ተገቢውን መልስ ለመስጠት መዘጋጅተ ያስፈልጋል። 3ኛ) እንዴት አድርጎ ቀስ በቀስ ለላይኛው ጥያቄዎች መልስ ሊሰጡ የሚችሉ ቀልጣፋ ኢንስቲቱሽኖች መገንባት ይቻላል ? የሰው ኃይልንም እንዴት ማሰልጠንና ማሰማራት ይቻላል ? በሚለው ላይ በበቂው መነጋገር ያሻል። 4ኛ) ከዚህ ስንነሳ እንዴት አድርጎ ያሉትን የሰውም ሆነ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማንቀሳቀስ አንድ ጠንካራ ህብረተሰብ ገንባት ይቻላል? ብሎ መጠየቅና ለመልስ መዘጋጅት የማይታለፍ መሰረታዊ ሃሳብ ነው። 5ኛ) ከዚህ ስንነሳ በመንግስት፣ በህብረት ስራና በግለሰብ ተሳትፎ መሀከል የስራ-ክፍፍል በመፍጠር እንዴት አድርጎ የተሳሰረ ኢኮኖሚ መገንባት ይቻላል? ለሚለው በቂ መልስ መስጠት የምሁሩ የቤት ስራ ነው። 6ኛ) መንደሮችን፣ ከተማዎችናን የመኖሪያ ቦታዎችንና ልዩ ልዩ ለንግድና ለፋብሪካ የሚሆኑ ቤቶችንና መደብሮችን በምን ኃይልና በምን ሀብት መስራት እንችላለን?  በሚለው ላይ መነጋገሩ ሌላው አንገብጋቢ ጥያቄ ነው። ባጭሩ በሰላሳና በሃምሳ ዐመታት ውስጥ ልዩ መልክ የምትይዝና ውስጠ-ኃይሏ ጠንካራ የሆነ  ኢትዮጵያን በምን ዘዴና በምን ኃይል፣ እንዲሁም ሀብት መገንባት ይቻላል፟? የሚለውን ጥያቄ ተቃዋሚው ኃይል መመለስ ያለበት ይመስለኛል።  በዚህ መልክ ብቻ ትግላችን መልክ ሊይዝ ይችላል። መልካም ንባብ !!

 

ፈቃዱ በቀለ

                                                                                 fekadubekele@gmx.de

 

የጠቢባን አባባል፣     ጓደኛህን ንገረኝና ማንነትህን እነግርሃለሁ !!

comment pic

                                                               

 

ጦማሪያኑ ለአራተኛ ጊዜ ለብይን መቀጠራቸውን ተቃወሙ

$
0
0

9f63d0258a66cac66fe763a18892b271_L‹‹አንድ ዳኛ ምንም ማድረግ አይችልም›› ዳኛ ዘሪሁን ደሳለኝ

‹‹ከዳኞች ጋር ምንም ችግር የለብንም ከማን ጋር እንደተጣላን ገብቶናል›› በእስር ላይ ያሉ ጦማሪያን

በተጠረጠሩበት የሽብር ተግባር ወንጀል ክስ ከተመሠረተባቸው በኋላ የከሳሽ ዓቃቤ ሕግ የሰውና የሰነድ ማስረጃ ቀርቦባቸው ለብይን የተቀጠሩት አራት ጦማሪያን፣ ለአራተኛ ጊዜ ጳጉሜን 2 ቀን 2007 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱን ተቃወሙ፡፡

ተከሳሾቹ ጦማሪያን ናትናኤል ፈለቀ፣ አቤል ዋበላ፣ አጥናፍ ብርሃኔና በፍቃዱ ኃይሉ ጳጉሜን 2 ቀን 2007 ዓ.ም. ብይን እንደሚሰጥ የጠበቁ ቢሆንም፣ ጉዳያቸው በሦስት ዳኞች የሚታይ ከመሆኑ አንፃር በዕለቱ አንድ ዳኛ አቶ ዘሪሁን ደሳለኝ ብቻ የተገኙ በመሆናቸው ብይኑ ሳይሰጥ ቀርቷል፡፡ ብይኑ ተሠርቶ የተጠናቀቀ ቢሆንም፣ ዳኞች ባለመሟላታቸውና በመዝገቡ ላይ ባለመፈረማቸው ብይኑ ሊነገር እንደማይችል ዳኛ ዘሪሁን ገልጸዋል፡፡

በዳኞች አለመሟላት ለሁለተኛ ጊዜ መቀጠሩ ያበሳጫቸው ተከሳሾቹ፣ ‹‹እኛ ከዳኞች ጋር ምንም ችግር የለብንም፡፡ ከማን ጋር እንደተጣላን ገብቶናል፡፡ የምንፈልገው ቁርጥ ያለው እንዲነገረን ነው፡፡ ወይ በነፃ እንሰናበት ወይም ተከላከሉ እንባል፡፡ ብይን ለመስጠት በሚቀጠሩት ቀናት መካከል ያለው ጊዜ ለእኛ ሕመም ነው፤›› በማለት ቅሬታቸውን ተናግረዋል፡፡

የጦማሪያኑ ጠበቃ አቶ አመሀ መኰንን ‹‹ዳኞች እንዲሟሉ መተባበር ያለብን ነገር ካለ እንተባበር ወይም ለፍርድ ቤቱ አስተዳደር እናመልክት፤›› የሚል ሐሳብ ለዳኛ ዘሪሁን አቅርበዋል፡፡ ዳኛው በሰጡት ምላሽ፣ ‹‹የሚቻል ከሆነ ሞክሩ፤›› ብለዋል፡፡ እሳቸውም ብይኑ ቢሰጥ እንደሚመርጡ፣ ተጠርጣሪዎቹን ዓይናቸውን ባያዩ ደስ እንደሚላቸውና (በተደጋጋሚ በመመላለሳቸው) በግላቸው እንደሚከብዳቸው ተናግረዋል፡፡

ያልተሟሉት ዳኞች በተለያዩ ምክንያቶች መቅረታቸውን በመጠቆም፣ እንደተሟሉ እስከ መስከረም 10 ቀን 2008 ዓ.ም. ድረስ ለማረሚያ ቤቱ ተነግሮ ብይኑ ሊሰጥ እንደሚችል በጽሕፈት ቤት አስታውቀዋል፡፡

Source:: Ethiopian Reporter

መንግስት የቴዲ አፍሮን ኮንሰርት ቢከለክልም ኢትዮጵያውያን በፌስቡክ ኮንሰርቱን ሊያደርጉት ነው

$
0
0

የአዲስ አመት ዋዜማ የቴዲ አፍሮ ዘፈኖችን በፌስቡክ ሁሉም ሰው ሼር እንዲያደርግ ተጠይቋል

ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ለኢትዮጵአ አዲስ ዓመት ዋዜማ ሊያቀርብ የነበረውን ኮንሰርቱን በአገዛዙ ባለስልታናት የቀጥታና የተዘዋዋሪ ቻና እንዳአካሂድ መደረጉን ተከትሎ በሚሊኦን የሚቆጠሩ አድናቂዎቹ ከአገር ውስጥና ከውጪ በዕለቱ የዋዜማውን ምሽት በቴዲ ሙዚቃዎች በቀጥታ ለማሳለፍና ለድምጻዊው፣ለፍቅር ያላቸውን ድጋፍ ለስርኣቱ አፈና ቦታ እንደማይሰጡ ለማሳት የተለያዩ ወጣቶች በማህበራዊ ሚዲያው ጥሪ አቀረቡ።
teddy afro
ያልተደራጁ ነገር ግን በየበኩላቸው በሚያቀርቡት ጥሪ የበዓሉን ዋዜማ በአካል የተከለከለውን ኮንሰርት በማህበራዊ ሚዲያው በስፋት በጋራ ሚዚቃዎቹን በማዳመጥ የቀጥታ ስርጭት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር አርብ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ጀምሮ እንዲሆን ጥሪ እያደረጉ ሲሆን ድምጻዊ ቴዲ አፍሮም መረጃው ደርሶት የቀጥታ ስርጭት እንዲከታተል በየገጻቸው ጥሪ አቅርበዋል።

<<ቴዲ አፍሮን ያለስፖንሰር ~ አርብ ምሽት!>> በሚል ከአድናቂዎቹ አንዱ በማህበራዊ ሚዲያው ከአገር ቤት በመጻፍ ከሚጠቀሱት የትነበርክ ታደለ የተጀመረው ጥሪ ብዙዎችን አስከትሎ የቴዲ አፍሮ የበዓል ዋዜማ የሙዚቃ ዝግጅት በሶሻል ሚዲያው በአገር ቤት ያለ ስፖንሰር በፍቅር ስለ ፍቅር እየቴዜመ የአገርና የወገን ተቆርቋነት የሚያደርሰውን አፈና አልፎ ስርጭቱ ያለ ከልካይ ይቀርባል የሚለው የማህበራዊ ሚዲያው ጥሪ እየተስፋፋ ነው።

ለአርብ ምሽት የቴዲ አፍሮ የማህበራዊ ሚዲያው ኮንሰርት መነሻ የሆነውን የትነበርክ ታደለ ከአገር ቤት ያቀረበውን ጥሪ ሙሉውን ተከትሎ ቀርቧል።
ቴዲ አፍሮን ያለስፖንሰር ~ አርብ ምሽት! (የትነበርክ ታደለ) ከልጅነታችንም በምንወደው ነገር እያስፈራሩን ነው ያሳደጉን! የኛ የምንለውን እየነጠቁን “አርፈህ ቁጭ በል! ያለዝያ አታገኛትም!” እያሉ አሳደጉን። ይሄው አድገንም አልቀረልንም። ለቴዲ አፍሮ የሰጠነው ፍቅር ከነሱ ላይ የቀነስነውን መስሏቸው ወሰዱት! ነጠቁን!

ለበአል ዋዜማ ሰብሰብ ብለን የሆድ የሆዳችንን እያወጋን (እየዘመርን~እየዘፈን~እየጨፈርን) አዲሱን አመት እንዳንቀበል አንዴ ስፖንሰሮችን ሲገላምጡ አንዴም ፈቃድ ሲከለክሉ ይሄው ህዝብ የወደደውን ይህን ሰው “ቤትህ ተከተት!” ተብሎ ትእዛዝ ወጣበት።

እኔ በጣም ግርም ይለኛል! አሁን አፍሪካ “ጭለማ” ትባል? ምን በወጣትና? የትኛው የአፍሪካ ሀገር ነው አንድን ዘፋኝ እግር ለእግር እየተከታተለ፣ አመት ካመት ሳይሰለች መከራ የሚያበላ? የቱ ሀገር ነው አንድን ዘፋኝ በህዝብ ፊት ዘፈኑን እንዳያቀርብ እንቅፋት የሚሆን? ጨለማ? ሆ!ሆ!

ስንት በዝሙት የረከሱ፣ በሀሺሽ የደነዘዙ፣ በወንጀል የተጨማለቁ ዘፋኞች እንኳ ይህን ያህል ፈተና ሲደርስባቸው አላየንም። እንኳን ቴዎድሮስ ካሳሁን ግርማሞ…..ከልጅ እስከ አዋቂ የሚያሸረግድለት፣ የልብን ሚስጥር ነጋሪ፣ ችግርን ተጋሪ እንቁ የህዝብ ልጅ ቀርቶ…..

….እኔ ቴዲን ለማንቆለጳጰስ ምንም አቅም የለኝም። እሱም የሚፈልገው አይመስለኝም።

..እና…… ለማንኛውም ለእንቁጣጣሽ ዋዜማ ከምሽቱ ሁለት ሰአት ጀምሮ በዘ-ሐበሻ እና በሕብር ራድዮ ፌስ ቡክ ገጻችን ላይ የቴዲ አፍሮን ሙዚቃዎች በተለያዩ ዝግጅቶች አስውበን ለማቅረብ ዝግጅት ላይ ነን::

የቴዲ አፍሮ የአዲስ ዓመት ዋዜማ ኮንሰርት


ከዓመት በዓሉ ጋር ተያይዞ የሸቀጦች ዋጋ እየናረ ነው

$
0
0

Ethiopian-grain-shopጷግሜን ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለለስልጣን ሰሞኑን የአዲስ ኣመት በዓልን አስመልክቶ በሸቀጦች ላይ ዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቱን ቢናገርም፣ የሸቀጦች ዋጋ ከንረት ሊታደገው አለመቻሉን ያነጋገርናቸው የአዲስአበባ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡
በአዲስአበባ በሳሪስና በሾላ ገበያዎች ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች እንደጠቆሙት ሰሞኑን የሸቀጦች ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡ በገበያዎቹ የአበሻ በመባል የሚታወቀው ሽንኩርት በኪሎ ከ17- 18 ብር፣ የፈረንጅ ሽንኩርት ከ21- 22 ብር በኪሎ በመሸጥ ላይ ነው፡፡ ከአንድ ሳምንት በፊት የሽንኩርት የአንድ ኪሎ ዋጋ ከ8 – 17 ብር የነበረ መሆኑ ሲታወስ የዋጋው ንረት ከፍተኛ መሆኑን መረዳት እንደሚቻል አስተያየት ሰጪዎቹ ተናግረዋል፡፡
የምግብ ቅቤ በኪሎ ከ270- 290 ብር እየተሸጠ መሆኑን፣ የአንድ ዕንቁላል ዋጋ ከ3 ብር ከ75 ሳንቲም እስከ 3 ብር ከ85 ሳንቲም መናሩን ነዋሪዎቹ ጠቁመዋል፡፡ የሌሎችም ሸቀጦች ዋጋ ንረት መታየቱንም አረጋግጠዋል፡፡
ባለፉት ወራት ከፍተኛ የዋጋ ንረት ያሳዩት የበርበሬና የምስር ምርቶችንም በተመለከተ መንግስት በተደጋጋሚ የአቅርቦት ችግር የለም ቢልም ዋጋቸው ግን አንዳችም መረጋጋት ማሳየት አልቻለም፡፡
የሥጋ ምርቶችንም በተመለከተ የበሬ ሥጋ በአማካይ በኪሎ ከ120 – 170 ብር በመሸጥ ላይ ሲሆን፣ የበግ ስጋ በኪሎ ከብር 90 – 140 ብር እየተሸጠ ነው፡፡ በአንዳንድ የቁርጥ ሥጋ አቅራቢ ሉካንዳ ቤቶች የአንድ ኪሎ ሥጋ ዋጋ በአማካይ ከ200 – 250 ብር ነው፡፡ የሥጋ የችርቻሮ ዋጋ ካለፉት አንድ ወር ወዲህ የከብት አቅራቢዎች በደረሰኝ እንዲገበያዩ መገደዳቸውን ተከትሎ ዋጋው ቀስ በቀስ እየጨመረ መምጣቱን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡
የዶሮ ዋጋም በአማካይ ከ180 እስከ 300 ብር የሚሸጥ ሲሆን መካከለኛ በግ ከ1 ሺ 800 እስከ 2 ሺ 500 ብር ዋጋ እየተጠየቀበት ነው፡፡ የዶሮና የበግ ዋጋ በቀጣይ ሁለት ቀናት በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል የሚል ሥጋት እንዳላቸው ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡
የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን ሰሞኑን በሰጠው መግለጫ ኢኮኖሚያዊ መነሻ የሌላቸው የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ከሚመለከታቸው መ/ቤቶች የተውጣጣ ግብረሃይል መቋቋሙን በመግለጽ ነጋዴዎችን አስጠንቅቆአል፡፡
አንድ በዕንቁላል ንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ግለሰብ ስለባለስልጣኑ ማስጠንቀቂያ ተጠይቀው የዕንቁላል ዋጋ የናረው ከመኖ እጥረት ጋር በተያያዘ የአቅርቦት ማነስ በመከሰቱ ሲሆን፣ ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚረከቡበት ዋጋ ውድ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ መንግስት ዋጋ እንዳትጨምሩ ስላለ ብቻ ለመክሰር የምንነግድበት ሁኔታ ሊኖር አይችልም በማለት ማስጠንቀቂያውን አጣጥለውታል፡፡

 

Source:: Ethsat

  ባለራዕዩ መሪያቸው ሲታወሱ! – ገ/ጻዲቅ አበራ

$
0
0

meles zenawi የቀድሞው ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ ይህቺን ዓለም ከተሰናበቱ ሦስት ዓመታት የተቆጠሩ ቢሆንም፣ ሀገሪቱን በሙት መንፈስ የሚያምሱት  ገዢዎችና ተከታዮቻቸው ደጋግመው እያነሷቸው ይገኛሉ። ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካ የተረፈ ራዕይ የነበራቸውና ዓለምንም ያጎደሉ ስለመሆናቸው አብዝተው እየተናገሩላቸው ቢሆንም፣ ጥላቻ ያመቀና ዘረኝነትን በልቡ የሰነቀ እንዴት ሀገራዊ እንደምንስ አህጉራዊ  ራዕይ ይኖረዋል?  በመንደሩ ፍቅር የወደቀና ጽልመትን አውርሶን፣ በተግባር የዓለም ግርጌ አድርጎን የሄደ፣ እንደምንስ ሃገራዊ ሕልም ይኖረዋል ብሎ መጠየቁ፣ ከሙት ጋር ሙግት መግጠም ሳይሆን፣ በሙት መንፈስ ሀገሪቱን ለሚያምሱ መልዕክት ይሆናል።

 

ከግንቦት ሃያ 1983 ዓ/ም ጀምሮ፣ አንዴ በጊዜያዊነት፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ በሽግግር ጊዜ ፕሬዚዳንትነት፣ በመቀጠልም በጠቅላይ ሚንስትርነት እስከ ዕለተ-ሞታቸው  የኢትዮጵያን የመሪነት መንበር የጨበጡትና በቁጥር አንድነት ለሃያ አንድ ዓመታት ከሁለት ወራት የቆዩት፤ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እንደገለጸልን ደግሞ ለተጨማሪ አንድ ወር በመንፈስ ከቤልጂየሙ ሴንት ሉክ ሆስፒታል መንበራቸው ላይ የቆዩት መለስ ዜናዊ፣ የኢትዮጵያ ሲባሉ ኖረው፣  በተግባር ግን የኢትዮጵያ መሪ ሳይሆኑ፣ የትግራይ ክልል ተጠሪ ሆነው ማለፋቸው ለሚያይ የተገለጠ፤ ለሚያስተውል ያልተሰወረ የመሆኑን ያህል፣ አቶ መለሰም በድርጊት ብቻ ሳይሆን፣ በቃላትም ይህንኑ ሲያራጋግጡልን ኖረው አልፈዋል።

 

የካቲት 11 ቀን 1984 ዓ/ም፣ እንዲሁም በመስከረም ወር 1999 ዓ/ም፣ በትግራይ-መቀሌ በአደባባይ እና በስብሰባ አዳራሽ የተናገሩትን ማስታወሱ፣ በምርጫ 2002 ዓ/ም ለትግራይ ሕዝብ ያስተላለፉትን መልዕክት መጥቀሱ፣ እንዲሁም ሕወሃትን በአስተሳሰብና በትግርኛ ተናጋሪነት ብቻ ሳይሆን፣ የትግራይ ተወላጅነትን ደም የግድ ወደሚል ደረጃ ያወረዱበትን ፍፁም ጫፍ የረገጠ ዘረኝነት ማንሳቱ፣ ለአንዳንዶች የአዋጁን በጆሮ ያህል ቢሆንም፣ ኢትዮጵያ በአፍሪካ በሃብት ግንባር-ቀደም ሆናለች የሚባለውን የድንቁርና ተረት ሳያላምጡ የሚውጡና ግራ-ቀኝ ለማየት ያልታደሉ፣በጉድጓድ ውስጥ ተጥለው በጠባቧ ቀዳዳ ልክ ዓለምን የሚመለከቱ የዋሆች መኖራቸውንም ታሳቢ ማድረጉ ተገቢ ነው።

 

ሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ፣ የኢሕአዲግነትን ካባ አጥልቆ፣ በሻዕቢያ ሜካናይዝድ ኃይል ድጋፍ፣ ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ/ም አዲስ አበባን ሲቆጣጠር፣ የግዜያዊ መንግስት ፕሬዚዳንት መሆናቸው የተነገረን ባለ ራዕዩ መሪያቸው መለስ ዜናዊ፣ ስለባንዲራ ጨርቅነት አውርተው፣ የአክሱም ሐውልት ባለመብትነት የትግራይ ሕዝብ ብቻ ስለመሆኑ ተናግረው፣ ወላይታው ስለአክሱም ሐውልት ምን አገባው የሚል ምሳሌ ሲሰጡ ታዲያ የአደዋ ሰው አዲስ አበባ ቤተ-መንግስት ምን ይሰራል? የሚል ሃይ ባይ የለምና፣  ከወር በኋላ የኢትዮጵያ የሽግግር መንግስት ፕሬዚዳንት መሆናቸው ተገልፆ በመንበራቸው ቀጠሉ። የሽግግሩ መንግስት ፕሬዚዳንትም ለሕወሃት 17ኛ ዓመት በዓል ወደ መቀሌ ተጓዙ። የኢትዮጵያው ፕሬዚዳንት መለስ ዜናዊ፣ የካቲት 11 ቀን 1984 ዓ/ም በሕወሃት 17ኛ ዓመት በዓል ላይ ለትግራይ ሕዝብ ፣ “እንኳን ከናንተ ተወለድኩኝ! እንኳንም የሌላ አልሆንኩኝ..” ሲሉ ከፍተኛ ጭብጨባ ተከተለ።

የፖለቲካው ስንክሳር የማይገባውና አቶ መለስ የሁሉም ነኝ የሚሉበት ወንበር ላይ መሆናቸውን ያልተረዳው ሕዝብ ማጨብጨቡ ተፈጥሯዊ ቢሆንም፣ የሕወሃት መሪዎችም እጃቸውን ማውለብለባቸው ህመም ካልሆነ፣ ዘረኝነት መሆኑ ግን ግልጽ ነው። ንግግሩን ያልሰሙ እንዲሰሙም በአማርኛ ቋንቋ ተተርጉሞ  በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ጋዜጣ ላይ ታተመ፤ የኢትዮጵያው ፕሬዚዳንት እንኳን ከትግራይ ተወለድኩኝ ያሉበት በሌላ እነጋገር፣ ኦሮሞ፣ አማራ፣ ሲዳማ፣ ወላይታ፣ ወዘተ ባለመሆናቸው መደሰታቸውን የገለጹበት “ታሪካዊ” ንግግር፣ ሞራልና የሕግ የበላይነት ባለበት ከሥልጣን የሚያሽር፣ የሚያሳፍርና የሚያስወቅስ ቢሆንም፣ አቶ መለስ ግን ከነ ሙሉ ስልጣናቸው  ስያሜ ቀይረው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው መመረጣቸውን፣ ነሐሴ 17 ቀን 1987 ዓ/ም ፓርላማው ነገረን። በፓርላማው 178 ወንበር የያዙት ኦሕዴዶች፣ 136 ወንበር የታደላቸው ብአዴኖች፣ እንዲሁም 123ቱ የተለቀቀላቸው ደኢሕዴኖች – እንኳን ከትግሬ ተወለድኩ ያሉትን መለስ ዜናዊን በሙሉ ድምጽ ሲመርጡ ራሳቸውን እየሰደቡ መሆናቸው ግልጽ ቢሆንም፣ ጠመንጃውን የያዘውና ቀለብ የሚሰፍርላቸው ሕወሃት በመሆኑ፣ እጅ አውጥቶ ራስን ከመዝለፍ ባሻገር፣ እየተከፈላቸው በመልዕክተኝነት ሲገድሉና ሲያስገድሉ መኖራቸውም እውነት ነው።የቀድሞው ፕሬዚዳንት መንግሥቱ ኃይለማሪያም እየተሸነፉ ሲሄዱና ሥልጣን እየከዳቸው፣ ሁሉ ነገር ከእጃቸው እየወጣ በነበረበት የ1983 ዓ/ም መጀመሪያ ፣ በደብረብርሃን ከተማ ተገኝተው፣ የሰሜን ሸዋ ሕዝብ ሲዘምት እንጂ ሲዘመትበት አላየንም በማለት የተናገሩትን ሲተቹና ሲያብጠለጥሉ የሰማናቸው የሕወሃት ሰዎችና ደጋፊዎቻቸው፣ የሌላውን ኃላፊነት የጎደለው ንግግር ለማውገዝ ደጋግመው ሲጽፉና ሲሰብኩ እንዳልሰማናቸው፣ ኃላፊነት የጎደለው ብቻ ሳይሆን ከመሪ የማይጠበቅ ዘረኛ ንግግር ከነርሱ ሰው ሲመጣ ባለራዕይ እያሉ ያለሃፍረት እያንቆለጳጵሱ ቀጥለዋል።

 

አቶ መለስ ዜናዊ ሥልጣን በያዙ በወራት ጊዜ ውስጥ መቀሌ ተገኝተው የተናገሩትን ኃላፊነት የጎደለው ንግግር፣ አንዳንዶች የሥልጣን ሙቀት የፈጠረው ስካር ስለሚሆን፣ ሲውል-ሲያድር ይሰክናሉ በሚል ዕድል እንስጣቸው በማለት ነገሩን በረጋ ሁኔታ ለማየት የሞከሩ ቢሆንም፣ አቶ መለስ በሥልጣን ሙቀት ሳይሆን፣ የሚያምኑበትን አስበው እንደተናገሩ ለአሥመራው መፅሔት ሕውየት ማረጋገጫ የሰጡት በጥቂት ዓመታት ልዩነት ነበር። በኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ስር የሚታተመው ሕውየት የትግርኛ መፅሔት፣ስበኢትዮጵያ አቆጣጠር 1989 ዓ/ም በምዕራባዊያኑ በ1997 ከአቶ መለስ ጋር ባደረገው ቃለ-ምልልስ “አንተ የኢትዮጵያ መሪ ሆነህ እንዴት እንኳን ከትግራይ ተወለድኩ ትላለህ፤ ይህ አባባል ሌሎችን አያስከፋም ወይ?” በሚል ላነሳባቸው ጥያቄ፣ በአባባላቸው እንደማይፀፀቱ፣ የተናገሩትም ተገቢ መሆኑን  ማረጋጋጫ ሰጡ። በእሳት ተፈትኖ ወርቅነትን ካስመሰከረ ሕዝብ መወለዴ ያኮራኛል ብል ምን ነውር አለው? ሲሉም መልሰው ጠየቁ። “በእሳት ተፈትኖ፣ ጨርቅ ሳይሆን ወርቅ የሆነ” በማለትም፣ በርሳቸው አባባልና አስተሳሰብ በእሳት ያልተፈተኑትን ወይም ተፈትነው ጨርቅ የሆኑትን እየቀጠቀጡ፣ እያሰሩና እየገደሉ፣ እያሰደዱና እየዘረፉ ቀጠሉ።

በየካቲት ወር 1984 ዓ/ም መቀሌ ላይ የተናገሩት ሥልጣን በፈጠረው ስካር ነው በማለት ሰለርሳቸው ሆነው የተጨነቁት፣ ከአምስት ዓመታት በኋላ አቶ መለስ የኢትዮጵያን ሕዝብ በወርቅና በጨርቅ ፈርጀው ራሳቸውን የወርቁ አካል መሆናቸውን ሲያውጁ፣ የሥልጣን ስካር “ሃንጎቨር” ወይም ያደረ ስካር ከእርሳቸው ጋር አብሮ አምስት ዓመታት ስለዘለቀ ነው በማለት ይሉኝታ-አልባ ሙግት ሲያነሱ ባናይም፣ ሲቆዩ ጥላቻቸው እየረከሰ፣ ባይተዋርነቱ እየቀነሰ ሁሉንም የራሴ የሚል ስሜት የድርባቸው ይሆናል በሚል ተስፋ ያደረጉ መኖራቸው ግን እውነት ነው። ሆኖም ተስፋቸው በአቶ መለስ ዘረኛ አመራር እየሟሸሸ፣ የይሉኝታን ገደብ ባለፈው የሥልጣን፣ የዘረፋና የስግብግብነት ጉዞ እየተሟጠጠ ቢሄድም፣ በኢትዮጵያ ምድር፣ በኢትዮጵያውያን የጋራ ሃብትና ሲሣይ ዓለሙን እየቀጨ፣ ሁለት አሥርተ-ዓመታት በሥልጣን ላይ የቆየ መሪ፣ በ2000 ዓ/ም የትግራይ ወጣቶችን ለብቻ ሰብስቦ የትግሬነት የአደራ ቃል ኪዳን ይጭንባቸዋል ብሎ የሚጠብቅ፣ እርሱ እንደነርሱ ዘረኝነቱ ወደ ሕመም የተቀየረበት፣ እልያም ጥልቅ የፖለቲካ ልሂቅ መሆን ይኖርበታል።

 

የኢትዮጵያን ማዕከላዊ ሥልጣን በተቆጣጠሩ በ10ኛው ወር መቀሌ ከተማ ላይ እንኳን ከናንተ ተወለድኩኝ በማለት ብዙዎችን ያሳዘነና ያሳቀቀ ንግግር ያደረጉት መለስ ዜናዊ፣ በሥልጣናቸው ላይ 15 ዓመታት ያህል ተደላድለው ቆይተውም፣ ሕመሙ አብሯቸው እንደቀጠለ መስከረም 9 ቀን 1999 ዓ/ም መቀሌ ላይ ከድርጊት ባሻገር በቃላትም አረጋገጡት፤ የተግራይ ወጣቶችን ሰብስበው የሚከተለውን መልዕክት አስተላለፉ። “ወደዳችሁም ጠላችሁም የአያቶቻችሁን ዓላማ ትረከባላችሁ፤ ጥያቄው ከአያቶቻችሁ ይበልጥ ትሰራላችሁ ወይ? የሚለው ነው፤ የትግራይ ተስፋ ባለፉት ላይ ሳይሆን በእናንተ እጅ ነው።” በማለትም አሳሰቡ።

 

በቮይስ ኦፍ አሜሪካ የአማርኛው አገልግሎት በወቅቱ የተዘገበው ይህ የአቶ መለስ ዜናዊ ንግግር፣ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊ መሪ የግድ እንደሚላትና የዘረኝነት ልክፍት በፍቅር፣ በሃብትና በሥልጣን እንደማይረክስ ከማመልከቱ ባሻገር፣ የጥላቻ ቫይረስ የተሸከሙ ብዙ ሺህዎች እየተቀፈቀፉ ለመሆናቸው ፣ ማኀበራዊ መድረኮችን ዛሬ በጥላቻ የወረሩት የርሳቸው ደቀ-መዛምርት በቂ ማሳያ ናቸው።እነዚህ ከአጥማቂው በላይ ጥላቻ ደማቸው ውስጥ የሚንተከተከው ወጣቶች፣ ባለራዕይ የሚሏቸው መሪያቸው፣ የጥላቻ እና የዘረኝነት ማጣቀሻ ወይንም ሪፈረንስ ሆነው በኢትዮጵያ የትምህርት ካሪኩለም ውስጥ በምሳሌነት ሲጠቀሱ፣ እነርሱ የድርጊት ምሳሌ ሆነው ጭለማ ውስጥ የነበሩበትን የጥላቻ ዘመን በፍቅር ሲናዘዙም እናያለን፤ እንሰማለን!አቶ መለስ ይህችን ምድር ሊሰናበቱ ሁሉት ዓመት በቀራቸው ወቅት በተደረገው የ2002 ዓ/ም ምርጫ “ትግራይ ውስጥ ምንም አይነት ልዩነት እንዳይኖር ወይንም ስንጥቅ እንዳይታይ ጥሪ ማድረጋቸውን የአንድ ወቅት የርሳቸው የትግል አጋር አቶ ገብሩ አሥራት በመስከረም 2005 ዓ/ም በታተመው ሎሚ መፅሔት ላይ የተናገሩትንም ማስታወሱ፣ ጥላቻው ወይንም ሕመሙ እስከ መቃብር አብሮ እንደዘለቀ ማሳያ ነው።

 

የሕወሃቶች ባለ ራዕይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን በክፋት፣ በዘረኝነትና በአድላዊነት የሚያስታውሳቸው፣ በርግጥም በንግግር ችሎታቸውም የማይረሳቸው፣ በአደባባይ ዘለፋቸውና ፀያፍ ቃላታቸውም የሚታሰቡት መለስ ዜናዊ፣ ሥልጣንና ሃብት፣ ወደ አንድ አካባቢ ሲገፉ መኖራቸውም የአደባባይ ምስጢር ሆኖ ቀጥሏል።በሥልጣንና በሃብት ጋራ ላይ በሰፊው የተዘረጉት የአንድ አካባቢ ሰዎች የመሆናቸውን ያህል፣ በስማቸው የሚነገድባቸው፣ከነጉስቁልናቸው የሚኖሩ የትግራይ  ተወላጆች መኖራቸውም የማይካድ እውነት ነው። የሀገሪቱን ወታደራዊና የጸጥታ መዋቅር፣ እንዲሁም የኢኮኖሚ አውታር፣  መወሰኛውን የፖለቲካ ጡንቻ በአንድ ሰፈር ሰዎች እጅ አስገብተው፣ ከየጎጡ የተመረጡ የሌላ ቋንቋ ተናጋሪዎችን ለምልክት አስቀምጠው ኢትዮጵያን ሲቀጠቅጡ፣ ሲዘርፉና ሲያስዘርፉ ያለፉት መለስ ዜናዊ፣ ትግራይን የኢንዱስትሪ ማዕከል የማድረግ ህልማቸውን መልክ- መልክ አስይዘው ማለፋቸውን ባለቤታቸው በአደባባይ በድምጽና በምስል መስክረዋል።

 

ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለምንም መያዣ አንድ ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ብር አስወስደውና ከነወለዱ የተበለሸ ብድር በሚል  አንዲሠረዝ አርገው፣ የሃገሪቱ የልማት ባንክም የሕወሃት ካዝና እንዲሆን መንገዱን በውጉ ጠርገው፣ የሕወሃቱን ኢሣይያስ ባሕረን በቁንጮ አስቀምጠው ሄደዋል።  የኢትዮጵያ ንግድ ባንክንም በነ አቶ ስየ ቤተሰብ ሥር አቆይተው፣ ወደነ አቶ ዓባይ ፀሐዬ ቤተሰብ አሸጋግረው፣ ባለራዕዩ መሪያቸው ተሰናብተዋል። በሕወሃቱ ኤፈርት እንዲሁም በግለሰቦች ስም የሚደረገው ዘረፋ ሳይበቃ፣ የሃገሪቱን የመከላከያ ተቋም በንግድና ኮንስትራክሽን ዘርፍ እንዲሰማራ መንገዱን ጠርገው የሕወሃት ሰዎችን አደላድለዋል። የመከላከያ ሚኒስቴር ንግድ ውስጥ መግባቱ በዐይን የሚታይና በግልጽ የተነገረ ቢሆንም፣ ኦዲት እንዳይደረግም መንገዶች ተጠርገዋል፡፡ ይህ የመከላከያ ተቋም አማራ ወይንም ኦሮምያ ወይንም ሶማሊያ ወይንም ደቡብ ውስጥ አንድ የመርፌ ሱቅ ሳይከፍት፣ ትግራይ ውስጥ በርካታ ፋብሪካዎች ተክሏል። የፓወር ኢንጂን ኤሌክትሪክ ዎርክሾፕ፣ የኧርዝ ሙቪንግ ማሽን መገጣጠሚያ እንዲሁም የፀረ-ተባይ ኬሚካል ፋብሪካ ጨምሮበ አጠቃላይ ወደ ሰባት ፋብሪካዎችን በመቀሌ የገነባ ሲሆን፣ የመለዋወጫ ዕቃዎች ፋብሪካ በማይጨው፣ ውቅሮ፣ አዲግራት፣ አክሱም፣ ሽሬ ወዘተ.. የገነባ ሲሆን፣ በአጠቃላይ ከአንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ  አስራ ሰባት ፕሮጀክቶችን በትግራይ ክልል በመከናወን ላይ መሆኑንም ከክልሉ ኢንቬስትመንት ቢሮ የተገኘው መረጃ ያስረዳል። ይህም የውጭ ባለሃብቶች በክልሉ የመለዋወጫ ችግር እንዳይገጥማቸው መሆኑ ተመልክቷል። ቬሎሲቲ የተባለ የተባበሩት አረብ ኢምሬት አንዲሁም ቢ. ዲ. ኤል. የተባለ የባንግላዴሽ ኩባንያዎች ወዘተ.. በጨርቃ-ጨርቅ ዘርፍ እንዲሰማሩ ዕድሉ በመመቻቸቱ፣ ትግራይን የኢንዱስትሪ ማዕከል የማድረጉ ተግባራዊ ጉዞ ቀጥሏል።

 

አቶ መለስ ዜናዊ በቃልም ፣ በድርጊትም ለተነሱበት ዓላማ ቆመው፣ በታገተው ሕዝብና ክልሎች ኪሣራ ዘረኛ ፖሊሲ ሲቀርጹ፣ ሲፈጽሙና ሲያስፈጽሙ የነበሩ፣ በጥቅሉ ኢትዮጵያዊ አጀንዳ ሳይኖራቸው፣ በተግባርም ኢትዮጵያዊ መሪ ሳይሆኑ ያለፉ በመሆናቸው በጥቅል ለኢትዮጵያውያን እንኳን ባለራዕይ፣ በመሪነት መዝገብ ውስጥ በወጉ ያልተጻፉ መሆናቸውም ሊሰመርበት ይገባል።

አቶ መለስ ዜናዊ ከሰላሣ ቢሊዮን ዶላር በለይ የውጭ ብድር ጭነውብን፣ ከአርባ ቢሊዮን ዶላር በላይ ዕርዳታ እየጎረፈ፣ በዓለም ላይ ከኒጀር ቀጥሎ ሁለተኛ ደሃ አድርግወን የሄዱ፣ ከቴክኖሎጂ ነጥለውን፣ከመንግስት አልባዋ ሶማሊያ ጋር አስተካክለውን ያለፉ፣ በቃላት እያፋፉን፣ በተግባር አቀጭጨው፣ በድርጊት አድቅቀው፣ በብልጭልጭ ቅብ ጉስቁልናችንን ሸፍነው፣ ደሃ አበራክተው፣ ድህነትን አስታቅፈውን የሄዱ የጭለማ ዘመን ተምሳሌት ናቸው። የሃገሪቱን የትምህርት ሥርዓት የገደሉ፣ የሥልጣንን ክብርና ዋጋ ለሞራል አልባዎችና ዕውቀት ላይ ለሸፈቱ መንገደኞች ስጥተው ልጆቻችንን ተምሳሌት የነሱ፣ ከዛሬ አልፈው ለነገ ዕዳ የተዉብን፣ የኢትዮጵያን ሃያ አምስት ዓመታት በከንቱ ያባከኑና ከነገም ተጨማሪ ዓመታትን ያበላሹ፣ ታሪክ በዕኩይ ድርጊታቸው ሲያስታውሳቸው የሚኖር፣ ለስደትና ለጥቃት ያጋለጡን ፣ የገደሉንና ያስራቡን ፣ የሰው ልጅን የክፋት መጠን ያየንባቸው ፣ የዘረኝነት አክሊል የደፉና ክፋትን የሰነቁ በታሪካችን በዕኩይ ድርጊታቸው ሲታወሱ የሚኖሩ ናቸው።

 

አቶ መለስ ዜናዊ ላይመለሱ ከሄዱ ከሦስት ዓመታት በኋላ የማነሳቸው፣ በሙት ወቃሽነት መንፈስ ሳይሆን፣ በሙት መንፈስ የሚመሩት ተከታዮቻቸው ካረፉም ከሦስት ዓመታት በኋላም ሥጋ ለባሽነታቸውን እንድንጠራጠር አብዝተው ሲለፉ፣ እውነቱን በመፈንጠቅ በዘረኝነት የተለወሱ፣ በአካባቢ ልጅነት የተበከሉ በድን ሃሳቦች፣ ከጠባቧ ኩሬ ከዘረኞቹ ማኀበር ባሻገር ቦታ እንደሌለው ለማስገንዘብ ጭምር ነው። እነዚህ የርሳቸው አምላኪዎች ህሊናቸው የለበሰው የዘረኝነት ሞራ የሚገፈፈው በሃሳብ ልዕልና ሳይሆን፣ በኃይል ልዕልና ወይንም በጉልበት ብቻ መሆኑም ሊሰመርበት ይገባል። ይህንን በተገቢው ተገንዝበው፣ ግራና ቀኙን አንብበው፣ ግላዊና ቤተሰባዊ ምቾታቸውን ጥለው በረሃ የወረዱት የነፃነት አርበኞች፣ በለጋ ዕድሜያቸው ፍትህና ነፃነትን ሽተው መሳሪያ ያነሱ ጉብሎች፣ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን አክብሮታቸውን የማይነፍጓቸው፣ በዘረኝነት፣ በአፈናና በድንቁርና ላይ የተነሱ፣ ፍትህ፣ ነፃነት፣ እኩልነትና ዴሞክራሲን ያነገቡ፣ በጨለማው ላይ ብርሃን የሚረጩ ተስፋዎቻችን ናቸው።፡ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊ መሪ የምታገኝበት፣ በቀለም ላይ የሸፈቱ፣ በገንዘብ የድንቁርና ቆብ የጫኑ በድንቁርና ሃገር የሚያምሱበት፣ ዘረኞች ኢትዮጵያን የሚያተረማምሱበት ሁኔታም ያበቃል። ኢትዮጵያችን ትነሳለች፤ ከሀገራት ግርጌም ትወጣለች።

 

 

 

ከኢሳት የሃሳብ መንገድ ወደ ጽሁፍ የተመለሰ

 

 

ተስማምታችሁ ተርኩልን! (በልጅግ ዓሊ)

$
0
0

መነአልወድም ነበረ እርግማን ጨርሶ፣
ግን ላንተ ወዳጄ ሆዴ በጣም ጢሶ ፣
ዛሬስ ተራገምኩኝ ይሁን ብዬ ጮህኩኝ ይኸው በገሃድ፣
የወሬው ፈጣሪ ሰብቀኛው አመድ ።

ዮሐንስ አድማሱ

ኀብርና ምርምር /1966/

“ . . . የ13 ወራት የፀሐይ ብርሃን (13 Months of Sunshine) በሚለው ፖስተር ላይ ቡና ስታፈላ የምናውቃት ቆንጆ ወ/ሮ ውቢት አመንሲሳ ከባሕል ምኒስቴር ወደ ቱሪዝም ኮምሽን በፍስሃ ገዳ ልዩ ትዕዛዝ ተዛወረች። . . . “

የደርግ ዘመን የአራዳ ሹክሹክታ !

3000በአሁኑ ወቅት ብዙ ጽሁፎች በመፅሐፍት አለያም በድረ ገጽ ለንባብ ሲቀርቡ ይታያሉ። ከነዚህም መሐከል ብዙዎቹ ታሪክ ቀመስ ናቸው። በተለይም ደግሞ በኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ፣ በኢሕአፓ፣ በደርግና ኢሠፓ ብሎም በቀድሞው ሠራዊት፣ በወያኔና ሻዕብያ ላይ የሚያተኩሩ ይበዙባቸዋል። እነዚህ የዘመኑ ጦማሮች የሰነቁት ታሪክ የሚያጠነጥነው በግለሰብ፣ በድርጅት ታሪኮች፣ በአንድ ወቅት የተፈጸሙ ክስተቶችና እንቅስቃሴዎች ላይ ነው። ጽሁፎቹ በተለይ አዲሱ ትውልድ ስለሃገሩ እንዲያውቅ “እንደሚረዱ“ አያጠራጥርም። እንደሚረዱ የሚለውን በትምህርተ ጥቅስ ያስቀመጥኩት አንዳንዶቹ ለማስተማር ሳይሆን ለማደናገር የተዘጋጁ እንደሆኑ ከሚያቀነቅኗቸው የተፋለሱ ጭብጦች በግልፅ መረዳት ስለሚቻል ነው።

ይህን ለማለት የደፈርኩት አንዳንዶቹን ጽሁፎችን በሃቅ ሚዛን እየሰፈርን ስንመለከታቸው በውስጣቸው እንደዋዛ ሊታለፉ የማይገቡ የገዘፉ ስህተቶችን ደጉሰው እናገኛለን። ማንኛውንም ታሪክ-ነክም ሆነ ፖለቲካዊ ይዘት ያለውን ጽሁፍ ለሕዝብ ንባብ የሚያቀርቡ ግለሰቦች ስለሚያነሷቸው ጭብጦች ትክክለኛ መረጃ የመስጠትና ለታሪኩ ዋቢ ሆኖ የመቅረብ ሃላፊነት ብቻ ሳይሆን የትረካ ሚዛናዊነቱንም ጭምር መጠበቅ እንዳለባቸው ሊያስተውሉ በተገባ ነበር። ነገር ግን ይህ ሳይሆን ቀርቶ በተቃራኒው ከእውነት ያፈነገጡ በርካታ ትረካዎች በሃገራችን ስነ-ጽሁፍ ዘርፍ እንዳሻቸው ሲናኙ እየተስተዋለ ነው።

በአንድ ጽሁፍ ውስጥ የሚተላለፈው መልዕክት ሃላፊነት የጎደለው ከሆነ ታሪክን በማዛባት ረገድ የሚያስከትለውን ጉዳት አስቀድሞ ማጤን አያዳግትም። የመረጃና ኢንፎርሜሽንን ደህንነት/ትክክለኝነት የመጠበቅ ሃላፊነት ደግሞ ከእያንዳንዳችን የሚጠበቅ የዜግነትና የሙያ ሃላፊነት ጭምር ነው የሚሆነው። ይህም አሳሳቢ የሚሆነው ጽሁፎቹ የማታ ማታ በታሪክነት እየተዘገቡ ነገ ህያው ምስክር ሆነው እንደሚቀጥሉ ስለምንረዳ ነው። ምናልባት ታሪክ ከዚህ በላይ የተሻለ የራሱ አጻጻፍ ዘዬ ሊኖረው ይቻላል። ቢሆንም ግን ዛሬ እነዚህ በየቦታው በመጻሐፍት ስም የሚወጡት መደብሎች ነገ ለትናንትናውም ሆነ ለዛሬው ታሪካችን እንደ ትክክለኛ የመረጃ ምንጭ ተወስደው መጠቀሳቸው አይቀሬ ነው። ሃላፊነት የጎደላቸው ጻሐፊዎች እስካሉ ድረስ ዛሬም ሆነ ነገ ሚዛኑን ያጋደለ አለያም እውነትን ያደበዘዘ ጽሁፍ ማንበባችን አይቀሬ ነው። ለእያንዳንዱ ጽሁፍ ግድፈት አግባብ ያለው የማረሚያ ምላሽ በወቅቱ መስጠት ተገቢ ቢሆንም ቅሉ ዘወትር ይህን ማድረግ ግን አይቻልም።

ለአብነት አንዳንድ ጭብጦችን እናንሳ። በአንድ ወቅት ባንድ እንቅስቃሴ ላይ የተሳተፉ እንኳን ስለ ሁኔታው የተዘበራረቀ መረጃ ነው የሚያቀርቡት። እንቅስቃሴው የተደረገበት ቦታ፣ ሰዓት፣ የነበሩ ግለሰቦች በተተዘበራረቀ ሁኔታ ተጽፈው ይገኛሉ። ለምሳሌ ዘነበ ፈለቀ በጻፈው “ነበር“ በሚለው መጽሐፍ ላይ (ገጽ 17 – 26) የደርግ አባላት 109 መሆናቸውን ነው የዘረዘሩት። በሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ “እኛና አብዮቱ“ መጽሐፍ ላይ (ገጽ 68 – 74 ) የደርግ አባላት ቁጥር 108 ነው። በዚህ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ቦታ ባለው ኮሚቴ ውስጥ የተረሳ ወይም የተጨመረ ሰው አለ ማለት ነው። የአንድ ሰው መጨመር ወይም መቅረት ቀላል ሊመስል ይችላል። እውነታው ግን ከባድ ስህተት ነው። አለአግባብ የተጨመረ ካለ ቢያንስ ለ60ዎቹ የቀዳማዊ ሃይለሥላሴ መንግሥት ባለስልጣናት ግድያ በታሪክ ተጠያቂ ሊሆን ነው። በስህተት ካልተጨመረ ደግሞ በዚህ ግዙፍ ታሪክ ላይ ያደረገው አስተዋጽዖ ተረሳ ማለት ነው።

በሌላ በኩል ደግሞ የቀድሞውን የኢትዮጵያን መከላከያ ሠራዊት አስመልክቶ አንዴ እየተጋነነ፣ ሌላ ጊዜ እየተኮነነ፣ ከከፍተኛና ዝቅተኛ መኮንኖች እስከ ባለሌላ ማዕረጎች ድረስ የሚጻፉትን የወቅቱን መድብሎች ካስተዋልን፣ እርስ በራሳቸው የሚቃረኑ አያሌ የአፃፃፍ ግድፈቶች ያሉባቸው ከመሆናቸውም ባሻገር የታሪክ መዛባት የሚታይባቸውም ጭምር እንደሆኑ እንገነዘባለን። የማዕረግ እድገት የከለከላቸውን አጋነው እየኮነኑ በአንፃሩ ደግሞ ለእነርሱ ቀረቤታ አለያም ጠቀሜታ ያለውን አላግባብ ሲክቡ ይስተዋላሉ። እንዲህ ያለው ሌጣና የተዛባ፣ ሚዛን የሌለው አፃፃፍ፣ የግል ጥላቻንና ቂምን ማወጃ፣ መድብል ከመሆን ባለፈ እውነት በማቋት ረገድ የሚፈይደው አንዳች ነገር አይኖረውም።

በቀበሮ ጉድጓድ ታፍኖና ለዓመታት ደሙንና ሕይወቱን እየገበረ ለሃገር ሉዓላዊነት አብሮ ሲወድቅ ሲዋደቅ የኖረን ሠራዊት ታሪክ ከግል ጥቅም አንፃር እየመነዘሩ ዋጋ ማሳጣት የሠራዊቱን ገድል ማዛባት ነው የሚሆነው። የዚህ ዓይነቱ ቅኝት ዞሮ ዞሮ በስተመጨረሻው እውነቱ ሲጋለጥ ራስን የሚያስገምትና ዋጋ የሚያሳጣ ሊሆን ስለሚችል አስቀድሞ ሊጤንበት ይገባል። ሥራ ሠራተኛውን አክባሪ እንደመሆኑ መጠን፣ የሰው ልጅ እሱ ስለራሱ ከሚደረድረው ስንክሳር ይልቅ ሥራው ራሱ ሲናገርለት በሁሉም ዘንድ ይበልጥ ይከበራል። ከዚህ ውጭ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘትና ራስን ለማስከበር ሲባል የግል ገድል ክበው እየፃፉ በማስነበብ የአንድን ታሪክን ፍሰት ለማዛባት መሞከር ጸያፍ ተግባር ይመስለኛል።

የቀድሞውን የኢትዮጵያን ተማሪዎች እንቅስቃሴንም በሚመለከት ደግሞ ሁኔታው የከፋ ሆኖ እናየዋለን። የራስን ወንጀል ለመሸፈን ሲባል የኋሊት ተጉዞ ያንን በቆራጦች የተገነባን ትግል ጥላሸት መቀባት ሃላፊነት የጎደለው ብቻ ሳይሆን ታሪካዊ ስህተትም ጭምር ነው የሚሆነው። የኢሕአፓን ታሪክ በሚመለከት ሁኔታው ከዚህ የተሻለ ሆኖ አይታይም። አንዳንድ የቀድሞ አባላት በዘንድሮ መነጽር የጥንቱን ታሪክ ለመተንተን የሚያደርጉት ጥረት ውሃ የማይቋጥር ነው። ችግሩ ግን እውነተኛውን የድርጅቱን ታሪክ ለማግኘት በሕቡዕ የሚንቀሳቀስ ስለነበር አስቸጋሪ ነው። ቢሆንም ግን በአንኳር ጥያቄዎች ላይ አሁን በሕይወት የሚገኙ የቀድሞ አመራር አባላት መልስ የሚሆን በመተባበር መጻፍ ይችሉ ነበር። ግን ለዛ አልታደልንም።

በአሁኑ ወቅት በሕይወት የሚገኙ ኢሕአፓ አመራር አባላትም ቢሆኑ እውነተኛውን ታሪክ ጽፎ ለሕዝብ ንባብ፣ ለታሪክ ማጣቀሻ እንደማብቃት ይባስ ብለው የግል መቆራቆሻ መድረክ ማድረጋቸው ሌላው አሳፋሪ ተግባር ነው። ይልቁንም ለሚቀጥለው ትውልድ ትምህርት ይሆን ዘንድ እውነትን በእውነትነቱ፣ ድክመትን በማስተማሪያነቱ፣ ጥንካሬን ደግሞ በአብነቱ ወስዶ በሃቅ ለሕዝብማሳየትና ለቀጣዩ ትውልድ የትግል ማመላከቻ በማድረግ ሌላ ታሪካዊ ስህተት እንዳይደገምና ቀጣዩ ትውልድ የማይገባ የመከራ አዙሪት ውስጥ እንዳይዘፈቅ ታሪካዊና ሕዝባዊ ሃላፊነትን መወጣት ነው የሚበጀዉ። ከዚህ ውጭ “ከእኛ ወዲያ ፉጨት . . . “ በሚል፣ ሌሎችም እንዳይጽፉ ዝም ለማሰኘት የሚደረገው ግትር አስተሳሰብና ጭፍን ትችት በድርጅቱና በቀደምት ታጋዮቹ ፅኑ የመስዋዕትነት ትግል ታሪክ ላይ ሸፍጥ የመስራት ያህል ነው።

እስቲ ለእማኝ ያህል ይህ ከላይ የጠቀስኩትን በሚመለከት አንዳንድ ሁኔታዎችን አብረን እንመልከት።

1ኛ . በአንድ ርዕስ ላይ አንዱ የካበውን ሊላው ሲንደው መታየት የተለመደ ሆኗል። ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው በአለፉት ሳምንታት አቶ አሰፋ ጫቦ በተለያዩ ድረ ገፆች ላይ “ኦ አዳም አንተ !!“ በሚል ርዕስ ስለ ደርግ ባለስልጣኑ ሻለቃ ፍስሃ ገዳ ያስነበቡንን ጽሁፍና በወቅቱ የኢሠፓ አባል የነበሩት ዶክተር አያሌው መርጊያው ጎበና “እናት ሀገር ! የኢሕአፓ እንቆቅልሽ“ በሚል መድብላቸው ያሰፈሩትን ጽሁፍ እንመለክት።

አቶ አሰፋ ጫቦ በጽሑፋቸዉ ጓደኛቸው የነበሩትን የደርግ ባለስልጣን ሻለቃ ፍሰሃ ገዳን “ምርጥ ተተኪ የማይገኝላቸው ዜጋ“ አድርገዉ ሲስሏቸው፣ በተቃራኒ ገጽታው በወቅቱ አብረው ይሠሩ የነበሩት ዶክተር አያሌው መርጊያ ደግሞ የመጥፎ ባህል አቀንቃኝ እንደነበሩ ይገልጻሉ። ስለሆነም ሻለቃ ፍስሃ ገዳ በዶክተሩ ድርሰት የአሸሼ ገዳሜ አቀነባባሪ ፣ የዝሙትና የዋልጌነት፣ የስርቆትና የብኩንነት፣ እንዲሁም የዝርፊያና የጦፈ የጥቁር ገበያ ንግድ አስተባባሪ አድርገው አቅርበዋቸዋል።

አቶ አሰፋ ጫቦ ፡ –

“አንድ አራት አመት ያክል ደርግ ጽሕፈት ቤት ቢሮ ነበርንና ፍስሐ ገዳን በየቀኑም ባይሆን ብዙ ጊዜ የማግኘት እድል ነበረኝ። ብዙም የምንነጋገረው አልነበረም። አስፈላጊ በሆኑ ነጥቦች ብቻ ካልሆነ በስተቀረ። የቀረውን ሳንነጋር የምንግባባ (Given) ይመስለኛል። የታውቀ ነው በሚሉት መልክ። ከማስታውቂያ ኮምቲ በኋላ የፕሬዚዳንቱ፤የመንግስቱ ኃይለ ማርያም፣ የፕሮቶኮል ሹም ሆነ። ይህ የሚሰማማው ስራ መሆኑን የነገርኩት ይመስለኛል። የፕሮቶኮል ሹም ስራ አሻማ ነው ብዬ ስለማምን።ከዚያ እኔ ማእከላዊ ከወርድኩ በኋላ የሆቴልና ቱሪዝም ኮሚሽነር ሆኖ መሾሙን ሰማሁ። ዋናውን የአሻም ስራ አገኘ አልኩኝ በልቤ። በሆቴሊና ቱሪዝም ዘርፍ ከመስራቹ አቶ ኃብተ ስላሴ ታፈሰ ጋር የሚነጻጸር ምናልባትም ሊበልጥ የሚችል ለውጥ ያመጣ ፍስሽ ገዳ መሆኑን ዛሬ ወዳጅም ጠላትም አምኖ ተቀብሎ በዚያ ላይ ተንተርሶ ወደሚቀጡለት ደርጃ ያደረሱት ይመስለኛል። ወዳጅም ጠላትም ከማለት ሁሉም ተቀብሎ ብል የሚሻል ይመስለናኛል። ፍስሀ ጠላት ያለው ሊኖረውም የሚችል ስለማይመስለኝ ነው።

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46038

የዶክተር አያሌውን ደግሞ ምንም ሳልቀንስ ሳልጨምር ከመጽሀፉ ገጽ 33 ላይ የሰፈረውን አንድ አንቀፅ እነሆ፡

“በደርግ ጊዜ በተለይም በአስረሽ ምችው ሻምበል ፍስሐ ገዳ ዘመን ቱሪዝምና ሆቴሎች ኮሚሽን የስካር የዝሙት፣ የዋልጌነት፣ ስርቆት፣ የብኩንነት ፣ የዝርፊያ ፣ የጦፈ የጥቁር ዶላር ንግድ ማካሄጃ ዋሻና ግቢ ነበር። ወጣት ሴቶቻችንን ለአረቦች ዶላር ማግኛ እንደሸቀጥ ለመጠቀም ማስተባበርና ማስተናገድ ሙያው የሚጠይቀው ከፍተኛ የችሎታ መመዘኛ ነበር። ሻምበል ፍሰሐ ገዳ ወይም የደርግ ባለስልጣናትንና ወዳጆቻቸውን ላንጋኖ ሶደሬና ወንዶ ገነት ለመዝናናት ሲሄዱ በተቀናጀ በተደራጀ መልክ ወጣትና ውብ የሴት

አስተናጋጆችን ለአዝናኝነት እያስተባበሩ በመላክ ሽር ጉድ ማለት ሌላው ከፍተኛ የብቃትና የችሎታ መመዘኛ ነበር ። ይህን ተግባራት የሚያከናውኑና የሚያስተባብሩ ነበር ታማኝ ትጉ ታታሪ አዋቂ ባለሙያ የሚያስቆጥረው።“

እዚህ ላይ ማንን እንመን ? አቶ አሰፋ ጫቦን ወይስ ዶክተር አያሌውን ? ተስማምታችሁ ተርኩልን ማለት እንግዲህ ይህ ነው። ሻለቃ ፍሰሃ ገዳን በጥፋታቸዉ መኮነን፣ በልማታቸዉ መመስግን ይገባቸዋል። በሁለቱም ጽሁፍ የምናጣው ይህንኑ ነው። አቶ አሰፋ ጫቦ ጓደኛቸውን ለማመስገን የተጓዙበትን መንገድ በትዝብት አልፈን የደርግን አሠራርና ባህርይ ስናስብ ለሥርዓቱ ታማኝነት እንዲሁ በቀላሉ የሚገኝ ሳይሆን በሌሎች ላይ በሚፈፀም ግፍ የሚገኝ እንደነበር መረዳት አያዳግትም። ታማኝነት ከሌለ ደግሞ በሥልጣን ላይ መቆየት ከቶ የሚቻል አልነበረም። የመንግስቱ ኃይለ ማርያም፣ የፕሮቶኮል ሹም ለመሆን መቼም ምን እንደሚያስፈልግ ማንም መገመት ይችላል። ታማኝ ለመሆን ታማኝ ያልሆኑትን ማጋለጥ ወይም ማግለል አስፈላጊ ነበር። በሥልጣን ላይ እስከ ደርግ መጨረሻ ለመቆየት ደግሞ ቢያንስ በሌሎች ላይ ግፍ ሲፈጸም ዝም ማለት ወይም መደገፍን ይጠይቃል። በተለይ በደርግ አባልነት በመጀመሪያው ረድፍ ተሰልፈው የነበሩ ግለሰቦች ገና ከጅምሩ በ60ዎቹ የንጹሃን ደም እጃቸው የተነከረ ለመሆኑ አያሌ ማስረጃ ማቅረብ ይቻላል። ንፁሃን ዜጎችን ይገደሉ ብሎ እጅ መቀሰር ለግድያው ተባባሪነት ትልቅ ማረጋገጫ ነው የሚል እምነት አለኝ። ይህንና ይህንን በመሳሰሉ ሌሎች በርካታ ምክንያቶች ናቸው በደርግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ዘመን አቶ አሰፋ ጫቦ ሊስሏቸው እንደፈለጉት ገፀ-ባህሪይ ዓይነት ፍሰሃ ገዳን ፈልገን የምናጣቸው።

ከግል ወዳጅነትና ትስስር ይሁን ወይም ከጥቅም ተጋሪነት ስሌት በውል ባይታወቅም፣ ከደርግ ባህሪይ አንፃር ዛሬ ሻለቃ ፍሰሃ ገዳ “ጀግና” ተብለው ቢሰየሙ ከቶ ሊያስደንቀን አይገባም። የትልልቆቹን ወንጀል በብዕር ጸበል ለማፅዳት ከተቻለ የትንንሾቹም በዚያው ፀበል ፈውስ ሊያገኝ እንደሚችል ታሳቢ አድርጎ ከሆነ ቆንጆ ስህተት ነው። ነገር ግን መደከም ያለበት አዲሱ ትውልድ ካለፈው ስህተት እንዲማር እስከተፈለገ ድረስ እውነቱን እንዲያውቅና የታሪክ ሚዛን እንዳይዛባ ከማድረግ ባለፈ ሌላ የተሻለና አማራጭ መንገድ አይኖርም።

2ኛ. አንዳንድ ታሪኮች ከመቸኮልም ይሁን ጥናት ባለማድረግ ትልልቅ ስህተቶች፣ ዝርክርክነት ይነበብባቸዋል። ለዚህ እንደ መረጃ የሚሆነን አስደናቂው ታሪክ የጥላሁን ገሠሠ ታሪክ ነው። ጥላሁንን በተመለከተ በሁለት መድብሎች ውስጥ የተለያየ የታሪክ ገፅታ ይዞ እናነባለን። አንደኛው በዘካሪያ መሐመድ “የሕይወት ታሪኩና ምሥጢር“ ሲሆን ሌላኛው “የኢትዮጵያ የሙዚቃ ንጉስ“ በሚል በኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር የተዘጋጀው ነው። ይህንን ትልቅ ውዝግብ ያስነሳ የተዛባ የታሪክ ቅኝት አስመልክቶ ራሱን ለእውነት በማንበርከክ በአደባባይ ወጥቶ አንዱ የሌላኛው ጭብጥ በመቀበል መረጃዬ የተሳሳተ ነው፣ ከይቅርታ ጋር በዚህ አርሙት ለማለት የደፈረ እሰከአሁን አላነበብኩም። ካለ ግን እታረማለሁ።

በሁለቱ መጽሐፍት ውስጥ ያለው ልዩነት ጥልቀት ያለው ጥናት ሳይደረግ ከሚሰራ ስህተት የመነጨ ይመስለኛል። በደራሲያኑ ማሕበር መጽሐፍ (ገጽ 4 -5) ጥላሁን የተወለደው ጠበንጃ ያዝ ሰፈር ነው በሚል ይነበባል። በዘካሪያ ማህመድ መጽሐፍ (ገጽ 29 – 30) ጥላሁን ገሠሠ የተወለደው ጎሮ/ሶየማ የገጠር ቀበሌ ነው። ሁለቱን መጽሐፍት ስናነብ ግራ ሊገባን ይችላል። ጥላሁን የተወለደው ወሊሶ ወይስ አዲስ አበባ ጠበንጃ ያዥ ሰፈር? ተራ ጥያቄዎች እንኳን መልስ አላገኙም። ይህ ዓይነቱ ስህተት በአሁኑ ጊዜ በተደጋጋሚ መጽሐፍት ውስጥ ጎልቶ የሚታይ ችግር ነው። እነዚህ እንኳን ከጊዜ ቅርበታቸውና ከመረጃ አቅርቦት አንፃር ስህተት ሊፈጠርባቸው ባልተገባ ነበር።

3ኛ. በጥላቻና ሕዝብን ለማሳሳት የተጻፉ መጽሐፍት በአሁኑ ወቅት በብዛት ይገኛሉ። ይህ ደግሞ ሆነ ተብሎ የሚደረግ በመሆኑ እንደ ወንጀልም ይቆጠራል። በተለይ በወያኔ የሚተዳደሩ ግለሰቦች ታሪክን ለማበላሸት በሰፊው የተያያዙት ነው። በጥላቻና የሌሎችን ታሪክን ለማበላሸት ከተጻፉት ውስጥ በሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ ተደርሶ በጸሐይ አሳታሚ ድርጅት የታተመው “እኛና አብዮቱ“ ከፍተኛውን ቦታ ይይዛል። በውስጡ ሳይሰልቅ ገርድፎ ያቋታቸው ውሸቶች በመብዛታቸው አያሌ ትችቶች በድረ ገፆች ሲያስተናግድ ከርሟል። ለእማኝ ያህል በገጽ 230 ላይ ያለውን እነሆ፡ –

“. . . ዝግጅቱ ከሞላ ጎደል በዚህ ሁኔታ ከተጠናቀቀ በኋላ የሕዝብ ድርጅት ጉዳይ ጊዜያዊ ጽ/ቤት ጉባኤ አባላት ሁነው የተመረጡት ሰዎች ተጠርተው በ1968 ታህሣሥ ወር መጨረሻ አካባቢ ጽ/ቤቱን እንዲያቋቁሙ ተደረገ። መሥራች የጉባኤ አባላትም ፦

አቶ የወንድወስን ኃይሉ
አቶ መሥፍን ካሡ
ደ/ር ሰናይ ልኬ
ዶ/ር ነገደ ጎበዜ
አቶ ኃይሌ ፊዳ
ዶ/ር ፍቅሬ መርዕድ
አቶ አሰፋ መድህኔ
አቶ እሸቱ ጮሌ
ዶ/ር መለስ አያሌው
አቶ ተስፋዬ ሸዋዬ
አቶ ባሮ ቱምሳ
ዶ/ር በዛብህ ማሩ
አቶ ዮሐንስ አድማሱ ናቸው።

የተመረጡት የጉባኤ አባላት የመጀመሪያ ስብሰባ ባካሄዱበት ቀን ዮሐንስ አድማሱ በኢሕአፓ ራሱን እንዲያገል በተሰጠው መመሪያ ምክንያት በስብሰባው ሳይገኝ ቀረ ። . . .“

በቁጥር 13 የሚገኘውን ዮሐንስ አድማሱን ለአብነት እንመልከት። ይህ ሆነ የተባለው በ1968 ታህሣሥ ወር መጨረሻ ገደማ ነበር።

የአዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ ፕረስ 2004 ዓ. ም. ባሳተመው “ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ አጭር የሕይወትና የጽሑፍ ታሪክ“ በዮሐንስ አድማሱ ተጽፎ በወንድሙ ዶ/ር ዮናስ አድማሱ የተሰናኘው መጽሐፍ መቅድም ላይ ስለ ዮሐንስ አድማሱ እንዲህ ይላል፡ –

“ በ1967 ዓ. ም. በወታደራዊ መንግሥት የታወጀውን የ1967ቱ የዕድገት በሕብረት ዘመቻ በሂርና ተመድቦ ሲሰራ በነበረበት ጊዜ ነው ሕይወቱ ያለፈው። ሰኔ 7 ቀን ፣ 1967 ከዕድገት በሕብረት መምሪያ በተጻፈ ባለ ሦስት ገጽ ዘገባ መሠረት ዮሐንስ ነፍሱ ከስጋው የተለየችው በሰኔ 3 ቀን 1967 ዓ. ም. ከአንድ ቀን በፊት የጀመረው ሕመም ስለጠናበት ወደ አሰበ ተፈሪ ሆስፒታል ሲወስዱት በመንገድ ላይ፣ መጣቀሻ በምታባል መንደር ነው። . . .“

ሰኔ 3 ቀን 1967 ዓም ያረፈው ዮሐንስ አድማሱ በታህሳስ 1968 ዓ.ም. በኢሕአፓ ስብሰባው ላይ እንዳይገኝ ተደረገ ብሎ መጻፍ የሚያስከፋ ነውረኛ ተግባርና የጥላቻ እርሾ ውጤት ነው የሚመስለው። ታላቁን ደራሲ ዮሐንስ አድማሱን በተደጋጋሚ በአብዮቱ ወቅት በተሰለፉ የተለያዩ ቡድኖች ውስጥ ለመመደብ የሚደረገው ጥረት ብዙ ነው። ሻምበል ፍቅረሥላሴ በኢሕአፓነት ሲከሱት ሌሎች ወጣት ፀሐፊዎች በመኢሶንነት ሲመድቡት ተነበዋል። እነዚህ ሁሉ ሃሜቶች የተፈጠሩት ዮሐንስ አድማሱ ላይ በጠቀስኩት ግጥም የወሬ ፈጣሪ ፣ ሰብቀኛ ብሎ በሰማቸው ወሬ ፈጣሪዎች ነው።

እነዚህ ከላይ የጠቀስኳቸው ከብዙዎቹ በጣም ጥቂቶቹ ነጥቦች ሲሆን ሌሎች በየመጽሐፉ በብዛት ይገኛሉ። እነዚህን የመሳሰሉ የተሳሳቱ መረጃዎች በማንበብ የነጻው ፕረስ ወጣት ጋዜጠኞች ሳይቀሩ ከፍተኛ የሆነ ስህተት እየጻፉ ይነበባሉ። ችግሩ የተጻፈ ሁሉ እውነት እየመሰለን የምንቀበል ብዙ መሆናችንም ጭምር ነው።

ጊዜና ጉልበት ይጠይቃል እንጂ ብዙ ብዙ እንደዚህ ዓይነት የታሪክ ግድፈቶችን እየነቀሱ ለሕዝብ ማቅረብ ይቻላል። ይህን ያነሳሁት ስህተቶች ለምን ተሰሩ ለማለት ሳይሆን ዓላማው ለምን? የሚለው ጥያቄ ሊጤን ይገባል ብየ ስለማምን ነው። ፍቅረሥላሴም ሆኑ ሌሎች መሰል ጓዶቻቸዉ በማርክሲዝም – ሌኒንዝም ካባ ሽፋን በጥላቻና ግፍ በዜጎች ላይ ጣት እየቀሰሩ በደቦ የከፋ ወንጀል ሲሰሩና ሲያስጨፈጭፉ እንዳልኖሩ ሁሉ ዛሬም ቢሆን እንደልማዳቸው ጣት የመቀሰር ውንጀላቸውን እንዳልተዉ ያረጋግጥልናል። ድሮ ጣት ቀስረዉ በአፈሙዝ ንፁሃን ወገኖችንን ሲያስጨፈጭፉ የኖሩ የደርግ ባለስልጣናት፣ ዛሬ ደግሞ ብዕር ቀስረው ዳግም ታሪኩን ለመጨፍለቅ ሲማስኑ እየተመለከትን ነው። ቀደም ሲል በሃገርና በወገን ላይ በሰሯቸው ግፎች በአዕምሯቸው ውስጥ የተፈጠረውን ጭንቀት ለማለዘብ ግፉ የተፈጸመባቸውን ወገኖች ዳግም በመክሰስ የወንጀል ሸክማቸውን ለመቀነስ እንደ ዓይነተኛ መሳሪያ ለመጠቀም ቆርጠው የተነሱ ይመስላል። ደርጎች ዛሬም በቀብራቸው አፋፍ ላይ ቆመው ሃቁን ተናግረው ንስሃ ለመግባት ዝግጁ አይደሉም። ከነወንጀላቸው ወደ ግብአተ መሬት መግባት ደግሞ የሞት ሞት ነው። ኢትዮጵያዊ እምነትም ባህልም አይደለም። እግዚአብሔር ለንስሃ ሞት ያብቃቸሁ ብለን እንመርቃቸው ?

አንድን ሀገራዊ ክስተት በሰከነ አይምሮ እውነትን ቃኝቶ፣ ጭብጡን በህሊና መዝኖ በመጻፍ ለሕዝብ ንባብ ማቅረብ እየተቻለ፣ ያለምንም አስገዳጅ ሁኔታ፣ ሃላፊነት በጎደለው መልኩ፣ በታሪክ መስክ ላይ እንዳሻቸው ሽምጥ በሌጣ ብዕር መጋለብ ምን ያህል ዳግም ሕዝብን መናቅና ሃገርን መበደል እንደሆነ፡ ፀሃፊዎች ሁሉ በውል ሊረዱት ይገባል። ሜዲያው ስለተመቸ ብቻ ውል እንደጠፋዉ ልቃቂት መያዣ መጨበጫ ያጣ ድርሰት መቸክቸክ ስምን በፃህፍት ተርታ ለማስመዝገብ ይፈይድ እንደሁ እንጅ ከታሪክ ተወቃሽነት ከቶ አያስመልጥም። አንዳንዶች ትላንት አብረው የሠሩትን ጥፋት በሌሎች ሲያሳብቡ የሚታዩ ሲሆኑ፣ ሌሎቹ ደግሞ የበሉበት ሌማት የአለላው ቀለም ገና ስላልረገፈ ባዲስ ቆዳ ለጉመው ታሪኩን ቀጥለው ለማስኬድ ይፍገመገማሉ። ከዚህ ውጭ የሆኑት እዝያም እዚህም እየዘለሉ የታሪክ ቃርሚያዎችና ያሉባልታ ስብስቦች የሚያቀርቡ ናቸው።

አንድን ታሪካዊ ክንውን ለመፃፍ መድፈር በራሱ የሚያስመሰግን ነገር ቢሆንም፣ እውነትን መግለጥ ደግሞ እጅጉን የላቀ፣ የሚያስከብርና የሚያስመሰግን ተግባር ነው። ለመጭውም ትውልድ ልናስተላልፈው የሚገባ ጭብጥና መልዕክት ዘላቂነት ከእኛ ሃቀኝነትና ሃገራዊና ህዝባዊ እይታ ይመነጫል። እኛ ሃላፊዎች ነን፣ ነገር ግን ሥራችን በመልካምም ይሁን በበጎ ጎኑ ተዘግቦና ህያው ሆኖ ይኖራል። ወደድንም ጠላንም፣ አለማንም አጠፋንም ታሪክ እየሠራን ነው። ስለዚህም ነው ለሃገርና ለሕዝብ ብሎም ለትውልድ ትክክለኛውንና እውነትን በማሳወቅ ረገድ ፃህፍት ታላቅ የሙያና ሃላፊነት ሚና የሚጠበቅባቸዉ።

ስለ ሃገራችን የሚያስቡ ሁሉ በሰላም ይክረሙ!

beljig.ali@gmail.com

ፍራንክፈርት 09.09.2015

\

አሥተማሪዏች ወደ ትውልድ መርዝ የዘሩ ተባሉ – (አስገደ ገ/ስላሴ)

$
0
0

dscf2632-e1282840457239ሓይለማርያም ደሣለኝ የሥርዓታችነን እንቅፋት ሁነውብን ያሉ ትምክሕት ጠባብነት ጽንፈኝነትት ናቸው አሉና ለእነዚህ እንቅፋቶች የሚያባብሱ ደግሞ አሥተማሪዏች
በዚህ ትውልድ ብቁ ዜጎች ማፍራት ሣይሆን የሚሠሩ በትውልድ ላይ መርዝ የሚዘሩ ናቸውብሎዋቸዋል  ዋዋ አቶ ሓይለማርያም አሁንም አሁን ያለው የትምሕርቲ የተባላሸ ውጤት በተግባር የሚያዩት ያሉት የራሣችሁ ትውልድ ገዳይ የትምሕርት ፖሊሲ በዜጎቻችን የዘራቹሑት መርዝ እያለ ወደ አስተማሪዎች ማስጠጋችሁ
ምንያህል በአሥተማሪዎች ላይ ያላችሁ ንቀት ያረጋግጣል
የትምሕርት ጥራትና ተማሪዎች የበላሸው እኮ
1 ኛትምሕርት ቤቶች የህ ወ ሓ ትና አጃቢ ፓርቲዎችና
አጋሮች አባሎች በመሆናቸው
2 ኛ አስተማሪዎች ማሰተማር አቋርጠው የገዥ ፓርት ስራ
እንዲሰሩ ሥለሚገደዱ መመዘኒያቸው ለፓርት ባላቸው
ተሳትፎ ስለሚጠይቅ
3 አስተማሪዎች በሙያቸው የሚመራቸው የቀበሌ ተመራጭና ምንም የፔዳጎጅ ሙያ የለለው መሀይም በመሆኑ
4 ወደ አሥተማሪነት የሚመደቡ ወገኖች የትምህርት ውጤታቸው ዝቅተኛ ሆኖ ብቁ ስልጠና ስለማይሰጣቸው
5 ኛንሮዋቸው በአንስተኛ ክፍያ ምክንያት እጅጉን የወረደ
በመሆኑ ቤት የቤት ቁሳቁሥ ስለሌለው ቤት ተካራይቶ
ለመኖር እንኳን ታማኝነት ሥለሌለው ሚስት እንኳን አያገ
ኝም ከአንድ አስተማሪ ንሮ የአንድ መሓይም የቀበሌ መሪ
ይበልጣል ቤት ትዳር ነጻነት አለው
አስተማሪ ግን የትምህርት ነጻነት የሙያ ነጸነት የለውም ሌላ
ቀርቶ ለተማሪዎቹ በትምህርታቸው መዝኖ ሊያሳልፍ ወይ
ሊያሥወድቅ አይችልም ቀበሌዎች ናቸው የሚወሱኑት
ስለዚህ ሁኔታው ያባለሸው ራሱ ኢህአደግ እያለ ለአሁኑ
ትውልድ መርዝ የሚረጭ ወዴት ወደጭቁኑ አስተማሪ
ጠጋጠጋ ማለቱ በመሆነ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ለአስተማሪዎች ከመወንጀል የራስዎና ፓርቲዎ መርዛማና
ትውልዲ ገዳይ ፖሊሲ ይፈትሹ

በ2007 ዓ.ም የተፈጸሙ 21 ዋና ዋና ክስተቶች

$
0
0

በ2007 ዓ.ም የተለያዩ ክንውኖች ተካሂደውበታል:: አሳዛኝ አሳፋሪና ብሔራዊ ውርደትን ያስከተለ ጭምር ነው። አዲስ ዓመት ብሄራዊ በኣል ስለሆነ እንደተለመደው 21 ጊዜ መድፍ ይተኮሳል። በኣመቱ ውስት ከተከናወኑት በርካታ ክንውኖች እናም 21ንዱን ዋና ዋና ጠቀስ አድርገን ለማለፍ ወደድን ::

ከሃብታሙ አሰፋና ታምሩ ገዳ

ethiopians isis
1. 28 ኢትዮጵያውያን በሊቢያ ታረዱ ፣ በጥይትን ተደፉ ። ይህን የኢትዮጵያውያን መታረድ ተቃውመው በሃገር ቤት ሰልፍ የወጡ ሰዎች በኢትዮጵያ መንግስት ታስረዋል:: በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያውያን በያሉበት ሃገር አብረው አልቅሰዋል::
2. በደቡብ አፍሪካ ወገኖቻችን በግፍ ተገደሉ ። በእሳት ተቃጠሉ ።በሊቢያ ያሉ ወገኖች ወይታ በየመን የድረሱልን ጥሪና አገር ጥለው የወጡና ዛሬም መሔጃ አጥተው በጭንቅ ላይ ያሉ::
south africa ethiopians
3.ይህን ግፍ ለመቃወም አደባባይ የወጡ በሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵአውያን ታሰሩ ተደበደቡ የዛሬ ምሽት እንግዳችን አቶ ማሙሸት አማረ ሕጋዊው የመኢአድ ፕሬዝዳንት ።በዚህ ሳቢያ የታሰሩ የሰማያዊ ፣የመኢአድ አባላት በእስር ላይ ያሉ የተፈረደባቸው ጭምር አሉ በስም የማናውቃቸው አሉ
mamushet
4.. በሜድትራልያን ባህር ከአንድ መንደር የተሰደዱ 11 ወጣቶች ሰመጡ ።

5.ትልቅ የፕሮፖጋንዳ ፍጆታ የሆነው ቀላል ባቡር ተመረቀ ተብሎ ምነው እንደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተመርቆ ምነው ስራ አይጀምርም ተባለበት:: ባቡሩ እስካሁን ሥራም አልጀመረም::
car accident
6. ለሙስሊሙ ማህበረስብ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ላይ ፍርድ ተበየነባቸው:: የ18 ዓመት ወጣት 22 ዓመት ተፈረደበት ።
muslim dim
7. የመንግስት ተቃዋሚ የነበረው ወጣት ሳሙኤል አወቀ በድንጋይ ተቀጥቅጦ ተገደለ ። የአረና አመራር አባል እንዲሁ ሑመራ ላይ ቤታቸው ሊገቡ ሲሉ ተገደሉ::
Samuel Aweke
8. የተጭበረበረውን ምርጫ ተከትሎ የመድረክ አባል የሆነው የኦሮሞ ሕዝብ ፌዴራሊስት ንቅናቄ(ኦፌዴን ) ምርቻ ታዛቢዎችና አባላት ጭምር ተገደሉ- በአርሲና ኮፈሌ:: እንዲሁም ታዋቂው ፖለቲከኛ አቶ በቀለ ገርባም የተፈቱት በዚሁ ዓመት ነበር:: ምርጫው ከመደረጉ አስቀድሞ መንግስት የፖለቲካውን ምህዳር በማጥበቡም ከ25 እላይ ጋዜጠኞች ወደ ጎረቤት ሃገራት ተሰደዋል::
bekele gerba
9. ፍርድ ቤት ነፃ ያላቸው የህሊና እስረኞች ህውሃት አልፈታም አለ ። መንግስት አልፈታም ካላቸው ተቃዋሚዎች መካከልም ሃብታሙ አያሌውና አብርሃ ደስታ ይገኙበታል::
habitamu
ዊንዲ ሼርማን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ የአፍሪካ ጉዳኢ ከሚመለከታቸው ባለስልታናት አንዷ የሆኑት ወይዘሮ አዲስ አበባ ላይ ግንቦት ሰባትን ወያኔ የሚያቀርብበትን ክስ ከማጽደቅ አልፈው የዓለም መሳቂአ የሆነው የመቶ በመቶ የተጭበረበረ ምርጫን አስቀድመው ዲሞክራሲአዊ ነው ማለታቸው ።ምርጫው 100% ተሰረቀ::

10..በምርጫው ቢያንስ አገዛዙን ለማንገዳገድ ሕዝባዊ መነቃነቅ ለመፍጠር ሰፊ ግምት ከተሰታቸው ቀበሌ ድረስ ወርዶ በማደራጀት ጎልቶ የወጣው አንድነት እና ጠንካራ አመራርና አባላት ጭምር ያሉት መኢአድ በሕገ ወጥ ውሳኔ ለአንድነት ተለጣፊ አንድነትና አመራር ለመኢአድ ተለጣፊ አመራር ተሰጠበት:: የአገር ቤቱ የሰላማዊ ትግል ቢአንስ በፖለቲካ ፓርቲዎች ስም የሚደረግ እንቅስቃሴ የት ድረስ እንደሚሄድ የታየበት ብዙዎች ከዚህ አገዛዝ ጋር በተቃዋሚነት በሕጋዊ መንገድ ተመዝግቦ የሚደረግ ትግል መጨረሻው ይሄ ነው ያሉበት::
udJ&AEUP
11. ሰማያዊ ፓርቲና መድረክ ምርቻውን እንደ መታገያ ወስደናል ብለው ምርቻ ውስጥ የገቡበትና ከምርጫ በሁዋላ ራሳቸውም በሰጡት ቃለ ምልልስ ባለባቸው ጫና ሳቢያ ትግሉን የረሱት መስለው የምርጫውን ውጤት በመቃወም ጉልህ ተቃውሞ የአደባባይን መውጣት ጨምሮ አለማድረጋቸውና የዝምታ ፖለቲካው::

12..የፕ/ት ኦባማ ወደ ኢትዮጵያ መሄድን ተከትሎ የጋዜጠኛ ርዮት ዓለሙና ከጦማሪያኑና ከጋዜጠኞቹ በአጠቃላይ አምስቱ ተለይተው መፈታት:: የአንድ ጋዜጠኛን ጨምሮ የሌሎች መታሰር::

ርዕዮት ዓለሙ ከእህቷ እስከዳር ዓለሙ ጋር ከ እስር ከተፈታች በኋላ

ርዕዮት ዓለሙ ከእህቷ እስከዳር ዓለሙ ጋር ከ እስር ከተፈታች በኋላ


13.የቀሩት ጦማሪያን ብይን መጓተት:: የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ፍርድ እና ይግባኝ ጠይቆም ፍርዱ እንዲጸና መደረጉ የዓመቱ አበይት ጉዳይ ነበር::
14. የአሜሪካን ፕሬዝደንት ኦባማ ኢትዮጵያን ጎበኙ ። የአፍሪካን መሪዎች ሰብስበው በስልጣን ለምን መቆየት ትወዳላችሁ ። ያውም ብዙ ገንዘብ እያላችሁ ሲሉ ጠየቁ ። ግንቦት ሰባት አሸባሪ አይደለም ሲሉ የህወሓት ኢህአዴግን አገዛዝ ክስ ውድቅ ማድረጋቸው የ2007 ትውስታ ነበር::
obama
15.የአርበኞች ግንቦት ሰባት የደፈታ ውጊያ በይፋ መጀመሩን ማወጁና ውጊያውን ተከትሎ ብዙ ሳይቆይ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ እና ሌሎች ከፍተና አመራሮች አቶ ነአምን ዘለቀና አቶ ኤፍሬም ማዴቦ ወደ ኤርትራ በረሃ ትግሉን ለመምራት መውረድና የፈጠረው ሰፊ መነቃቃት::
Birhanu Nega
16.የት እንዳሉ ያልታወቀው እንግሊዝን የዘገየ ቁጣ ያስከተለው የነጻነት ታጋዩ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ካልታወቀ እስር ቤት ወደ ቃሊቲ መቃወር እና በአባታቸው መጎብኝት፣ ለልጆቻቸው ስልክ መደወላቸውና በስማቸው መጽሐፍ እየተጻፈ ለመሆኑ የአገዛዙ ውጭ ጉዳይ ሚ/ር ፍንጭ መስጠታቸው እና ተያያዥ ውሸታቸው
17.የሕወሓት መሪዎች የስልጣን ሽኩቻ:: በአዲስ አበባውና በመቀሌው ቡድን መካከል የነበረው ሽኩቻ በመቀሌው ቡድን አሸናፊነት መጠናቀቁ::
18 . የረሃብ አደጋው በሰውና በእንስሳ ላይ ጉዳት ማድረሱና የአገዛዙ የተለመደ የሀሰት መግለጫ::
19. ኢህአዴግዬ እኔ ከሌለሁ ትጠፋላችሁ ብሎ ለሚቀጥለው 5 ዓመት ራሱን መረጠ ።
election board
20 .የቴዲ አፍሮ የአዲስ ኣመት ኮንሰርት መሰረዝ እና ስርኣቱ የተቀበላቸው አርቲስቶች ዝግጅት :: ቴዲ አፍሮን መንግስት በዚህ ዓመት ብቻ 4 የሃገር ቤትና የውጭ ኮንሰርቶቹን እንዲሰርዝ ቭዛ እና ጥበቃ በመከልከል አሰናክሏል::

21. እየተባባሰ የመጣው የሰብኣዊ መብት ጥሰትና የኑሮ ውድነት ብልሹ አሰራር ዛሬም ዜጎችን ብዙሃኑን አማርራል:: አገዛዙ የዲያስፖራ በዓል ሲል በውጭ የሚገኘውን ኢትዮጵያዊ ለመደለል ለመከፋፈል የሞከረበት::

በነገራችን ላይ የ13 ወር ጸጋ በሚባልባት አገር አስራሶ ስተኛዋ ወር ጳጉሜ ዘንድሮ ስድስት ቀን ነች ለመንግስት ሰራተኛው ደሞዝ የማይከፈልበት ወር ናት። ለዚህ ይመስላል ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ከአገር ቤት > ሲል በአገር ቤት ጳጉሜን ጠቀስ አድርጓታል::

በ2007 ዓ.ም ሞት የነጠቀን 4 አርቲስቶች

$
0
0

ከቅድስት አባተ

daniel kuncho
ኮሜዲያን ዳንኤል ቁንጮ

ወዳጁ ኮሜዲያን ዳንኤል ቁንጮ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየውም በዚሁ ዓመት ነበር:: በ አንድ ወቅት ስመ ገናና የነበረውና በ ኤግዚቢሽን ማዕከል በሚደረጉ ዝግጅቶች እና በቲቪ ፕሮግራሞች ላይ ኣጫጭር ጭውውቶችን ያቀርብ የነበረው ዳንኤል ቁንጮ ራሱን ወደ ዲጄነት ቀይሮም ፒያሳ ኣካባቢ በሚገኘው በኣካል ጸ ክለብ ውስጥ ለረዥም ዓመታት ኣገልግሉኣል። – See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/40122#sthash.4tvTPHrC.dpuf 

shambel Mekonen Mersha

አርቲስት ሻምበል መኮንን መርሻ

በዘፋኝነት; በሙዚቃ አቀናባሪነትና በሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋችነት የሚታወቁት ታዋቂው አርቲስት ሻምበል መኮንን መርሻ ያረፉት በዚሁ ዓመት ነበር:: በፖሊስ ኦርኬስትራ ውስጥ የትራንፔት ሙዚቃ ተጫዋች የነበሩትና “አደሉላ (የዘማች እናት)” በሚለው ታዋቂ ዘፈናቸው የሚታወቁት ሻምበል ወደ ሙዚቃው ዓለም ከመግባታቸው በፊት የወርቅ ሰራተኛ ነበሩ:: ሻምበሉ በአንድ ወቅት ለዘ-ሐበሻ ዘጋቢ እንደገለጹት ወርቅ ሰሪነት የተቀጠሩት በወቅቱ 15 ብር ነበር:: – See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/41691#sthash.ahQfaDAV.dpuf

seyfe areaya
አርቲስት ሠይፈ አረአያ
በኢትዮጵያ ትያትር እና ፊልም ኢንዱስትሪ ውስጥ ትልቁን ድርሻ ያበረከተው አንጋፋው አርቲስት ሠይፈ አረአያ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት በዚሁ ዓመት ነበር: – See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/41497#sthash.EuAEo9oR.dpuf

selamawit gebresilase
በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሴት ተዋናይት ሰላማዊት ገብረሥላሴም ያረፈችው በዚሁ በ2007 ዓ.ም ነበር

‹‹እኔ ቲያትር ከመጀመሬ በፊት፣ ወንዶች ጢማቸውን እየተላጩና ጡት እየቀጠሉ የሴትን ገጸባህሪ ይጫወቱ ነበር›› ትል ነበር የመጀምሪያዋ ኢትዮጵያዊት ሴት ተዋናይ:: ከ1944 እስከ 1986 ዓ.ም ድረስ እጅግ በርካታ ቲያትሮችን ሰርታለች። ዳዊትና ኦሪዮን፣ አልሞትም ብዬ አልዋሽም፣ ቴዎድሮስ፣ ጦጢት፣ ፍልሚያ፣ ንግስተ-ሳባ፣ የሺ በጉለሌ እና የመሳሰሉትን በብቃት ተውናለች፡፡ ሴት ተዋናይ ባልነበረበት ጊዜ ወንዶችን ሱሪ ያስታጠቀች ቀዳማዊት አርቲስትም ናት። – See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/36980#sthash.juQVe8xe.dpuf

darios modi

ጋዜጠኛ ዳርዮስ ሞዲ

ግንቦት 13 1983 ዓ.ም የቀድሞው ፕሬዚዳንት ኮለኔል መንግስቱ ኃይለማርያም ወደ ዙምባብዌ ሲሸሹ ዜናውን በኢትዮጵያ ራድዮ በማንበቡ በታሪክ ውስጥ የሚጠቀሰው ጋዜጠኛ ዳርዮስ ሞዲ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየውም በዚሁ ዓመት ነበር: – See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/44503#sthash.OmJhgn24.dpuf

የተደበቀው የህወሓት ማንነት ከደደቢት እስከ ቤተመንግስት (ክፍል 6)…ዘረኝነት በህወሓት የመከላከያ ሰራዊት ውስጥ

$
0
0

samora Yenus
ህወሓት ለዕለት ጉርሳቸው ብቻ ሲሉ የመከላከያ ሰራዊቱ አባል የሆኑ የደሃው የኢትዮጵያ ህዝብ ልጆችን በገፍ እየገበረ በእነሱ ደም እና አጥንት ነግሶ ረግጦ ሲገዛ ለመኖር በመከላከያው ውስጥ ከሚጠቀምባቸው ስልቶች ዋነኛው እና ቁልፉ የትግራይ ብሄር ተወላጆችን ከታች እስከ ላይ በሚገኙ የአዛዥነትና የሓላፊነት ቦታዎች በማስቀመጥ ነው፡፡
የህዝብ ልጅ የሆነው ሰራዊት የህወሓትን የስልጣን እድሜ ለማራዘም ሲባል ብቻ በየበረሃው እንደቅጠል እየረገፈ የሚገኘው እና የቀረውም አስተዳደራዊ በደል እየደረሰበት መብቱን እንዳይጠይቅ ተደርጎ በመቀፍደድ መላዎሻ አጥቶ የሰቆቃ ህይወት እየገፋ የሚገኘው ከጓድ መሪ ጀምሮ እስከ ኤታማጆር ሹሙ ድረስ ለህወሓት ታማኝ በሆኑ የአንድ ብሄር ተወላጆች መሪነት ተጠርንፎ በመያዙ ነው፡፡
ይህ በህወሓት የመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ተንሰራፍቶ የሚገኘው የለየለትና ዓይን ያወጣ ዘረኝነት ሰራዊቱን ከገጠሙት በርካታ የወቅቱ ችግሮች ዋነኛው ይሁን እንጂ የኋላ ኋላ የሚብሰው ራሱን ህወሓትን ነው፡፡
በመከላከያ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በመላው የኢትዮጵያ ምድር አፈር ላይ የበተነው የዘረኝነት ዘር በቅሎ በማደግ በጊዜ ሂደት ጥሻ ሆኖ ህወሓትን በቁሙ ውጦ ደብዛውን እንደሚያጠፋው የተረጋገጠ ነው፡፡
ህወሓት በየጎጡ የቀበረው የመንደርተኝነት አውዳሚ ፈንጅ ከወዲሁ በአፋጣኝ ካልከሸፈ ከእሱ አልፎ ኢትዮጵያን በጣጥሶ ሊያፈርሳት እንደሚችል እርግጠኛ ሆኖ መናገር ይቻላል፡፡
ህወሓት የትግራይ ብሄር ተወላጅ ብቻ የሆኑ ታማኝ ሰዎቹን በመሾም በዘር የዕዝ ሰንሰለት እግር ከወርች አስሮ ለስልጣኑ አድባር መሰዋዕት ሊያቀርበው ለዕርድ ያዘጋጀው ሰራዊት የህወሓት ጀምበር ልትጠልቅ ስታዘቀዝቅ የጠብመንጃውን አፈሙዝ ወደራሱ ወደ ህወሓት አዙሮ የሚተኩስ መሆኑን ለመናገር ነብይ መሆን አያሻም፡፡ በርና መስኮቱ በተዘጋ ቤት ውስጥ በባለቤቱ የሚደበደብ ውሻ መሹለኪያ ቀዳዳ ስለሌለው ብቸኛው አማራጩ በስለታም ጥርሶቹ ደብዳቢ ባለቤቱን ዘነታትሮ መጣል ስለሆነ፡፡
ህወሓት በመከላከያ ኃይሉ ውስጥ ያሰፈነውን ገደብ የለሽ ዘረኝነት ለማረጋገጥ ዋና ዋና የሚባሉ የአዛዥነትና የአስተዳደር ቦታዎችን በዝር ዝር መመልከት ይቻላል፡፡
• የመከላከያ ኤታማጆር ሹም ጀነራል ሳሞራ የኑስ (ህወሓት)
• የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽንና ኮምዩኒኬሽን ዋና ዳይሬክተር ብ/ጀ ገ/ኪዳን ገ/ማሪያም (ህወሓት)
•የመከላከያ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮ/ል ፍፁም ገ/እግዚአብሄር (ህወሓት)
•የመከላከያ በጀትና ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮ/ል ምዑዝ አብረሃ (ህወሓት)
•የመከላከያ የኪነ-ጥበባት ስራዎች ኃላፊ ኮ/ል ክብሮም ገ/እግዚአብሄር(ህወሓት)
•የመከላከያ መገናኛና ኢንፎርሜሽን መምሪያ የግንኙነት መምሪያ ኃላፊ ኮ/ል ነጋሲ ትኩ (ህወሓት)
•የመከላከያ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮ/ል ገ/ትንሳይ ሀጎስ (ህወሓት)
•የመከላከያ ትምህርትና ስልጠና መምሪያ ዋና አዛዥ ሌ/ጀነራል ሳዕረ መኮንን (ህወሓት)
•የመከላከያ ሎጀስቲክ መምሪያ ዋና አዛዥ ሜ/ጀነራል ኢብራሂም አብዱል ጀሊድ (ህወሓት)
•የመከላከያ ኢንደስትሪ ኃላፊ ሜ/ጀነራል ክንፈ ዳኛው (ህወሓት)
•የመከላከያ ዩኒቨርስቲ ኮማንዳንት ብ/ጀነራል ኃለፎም እጅጉ (ህወሓት)
•የመከላከያ ዩኒቨርስቲ ኢንጅነርኢንግ ኮሌጅ ኃላፊ ኮ/ል ሃጎስ ብርሃነ (ህወሓት)
•የብርሸለቆ መሰረታዊ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ት/ቤት ዋና አዛዥ ብ/ጀነራል ገ/እግዚአብሄር በየነ (ህወሓት)
•የብርሸለቆ መሰረታዊ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ት/ቤት የስልጠና ኃላፊ ኮ/ል ግርማይ ገ/ጨርቆስ (ህወሓት)
•የብርሸለቆ መሰረታዊ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ት/ቤት የኢንዶክትሪኔሽንና ኮምዩኒኬሽን ኃላፊ ኮ/ል ጌታሁን ካህሳይ (ህወሓት)
•የብላቴ ማሰልጠኛ ዋና አዛዥ ኮ/ል ዮሃንስ ካህሳይ(ህወሓት)
•በልዩ ኃይል ማሰልጠኛ ማዕከል የልዩ ኃይልና ፀረ-ሽብር ማሰልጠኛ ት/ቤት አዛዥ ሻለቃ ተክላይ ወ/ገብርኤል (ህወሓት)
•የሜ/ጀነራል ሃየሎም አርአያ ወታደራዊ አካዳሚ ዋና አዛዥ ኮ/ል ጎይቶም ፋሩስ (ህወሓት)
•የጦላይ የበታች ሹም ማሰልጠኛ ዋና አዛዥ ኮ/ል አደም ትኩ (ህወሓት)
•የሜ/ጀነራል ሙሉጌታ ቡሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና አዛዥ ኮ/ል ብርሃነ ተክሌ(ህወሓት)
•የሆሚቾ አሙኒሽን ኢንጅነርኢንግ ኢንደስትሪ ዋና ኃላፊ ኮ/ል ሀድጉ ገ/ጊዮርጊስ (ህወሓት)
•የኢትዮጵያ ፓወር ኢንጅነርኢንግ ኢንደስትሪ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ አሰፋ ዮሃንስ (ህወሓት)
•የመከላከያ የኮንስትራክሽንና ኢንጅነርኢንግ ማሽነሪ ኢንደስትሪ ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ካህሳይ ክዕሽን (ህወሓት)
•የመከላከያ መሰረታዊ ልማትና ግንባታ ዘርፍ የኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ወልዳይ በርሄ (ህወሓት)
•የታጠቅ ትራንስፎርመር ማምረቻ ኢንደስትሪ ም/ስራ አስኪያጅ ሻለቃ አማኑኤል አብረሃ (ህወሓት)
•የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንደስትሪ ፋይናንስ ኃላፊ ሌ/ኮ ለተብርሃን ደመወዝ (ህወሓት)
•የመከላከያ ጤና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮ/ል ሓጎስ አስመላሽ (ህወሓት)
•የመከላከያ ሚዲያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮ/ል ፀጋዬ ግርማይ(ህወሓት)
•የመከላከያ መገናኛና ኢንፎርሜሽን ዋና መምሪያ የግንኙነትና ስርአት ደህንነት መምሪያ ኃላፊ ኮ/ል በርሄ አረጋይ(ህወሓት)
•የመከላከያ ፋውንዴሽን ኃላፊ ብ/ጀነራል ያይኔ ስዩም (ህወሓት)
•የሽሬ ከተማ ኮሪደር ሜንተናንስ ኃላፊ ኮ/ል አብረሃ ገ/መድህን(ህወሓት)
•የብሄራዊ ተጠባባቂ ኃይል ዋና አዛዥ ሜ/ጀ ማሞ ግርማይ (ህወሓት)
•የኢንሳ /ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ/ ዳይሬክተር ሜ/ጀነራል ተ/ብርሃን ካህሳይ
•የኢንሳ ም/ዳይሬክተር እና የጂኦ ስፓሻል /Geo-spatial/ ደህንነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮ/ል ታዜር ገ/እግዚአብሄር

………………….
በዕዞች፣ በክፍለ ጦሮችና በሬጅመንቶች ደረጃ እንዲሁም በአየር ኃይል ውስጥ የሚገኙትን በአንድ ብሄር ተወላጆች የተያዙትን የኃላፊነት ቦታዎች ደግሞ ሳምንተ በክፍል 7 በዝር ዝር እንመለስባቸዋለን፡፡


ስለቴዲያችን – (ማርታ መኮንን)

$
0
0

teddy afro
• የቴዲ ወላጅ አባት ካሳሁን_ግርማሞ እና እናቱ ጥላዬ_አራጌ ( ራዬ ) ለጥበብ የተሰጡ ናቸው። እናቱ ጥላዬ አራጌ የመድረክ ተወዛዋዥ ስትሆን አባቱ ካሳሁን ግርማሞ መድረክ እያዝናና በማስተዋወቅ ተወዳጅ እና ተደናቂ ነበር። በተጨማሪም በሬድዮ ጋዜጠኝነት በሚያገለግልበት ወቅት በሚያቀርባቸው ወንጀል ነክ የፖሊስ ተከታታይ የምርመራ ታሪኮች ብዙ አድማጭ እና አድናቂ አፍርቷል።

እንዲሁም የመድረክ ተወዛዋዧ ጥላዬ አራጌ ቴዲን ስትጸንሰው 16 የአስራ ስድስት አመት ወጣት ነበረች። ቴዲን እርጉዝ እያለች ደብረ ዘይት(ቢሾፍቱ) ጎራ ብላ በነበረበት ወቅት ታላቁ ሰአሊ ለማ ጉያ በልዩ ሁኔታ የሳለውን የአፄ ቴዎድሮስን ስዕል ያበረከተላት። ስዕሉን አተኩራ እየተመለከተች ባለቤቷን “ካሳሁን…ካሳ” ብላ ጠርታው የምትወልደውን ልጅ ስሙን ቴዎድሮስ … ቴዎድሮስ_ካሳሁን እንደምትለው የነገረችው።

ሀምሌ 7/1968 ዓ.ም ወንድ ልጅ ከነቃጭሉ ዱብ አለ።…የኢትዮጵያ ሙዚቃም አዲስ ንጉስ አገኘች። ቴዎድሮስ የስድስት አመት ልደቱን ሲያከብር እናቱ ራዬ አልተገኘችም። የወላጆቹ ትዳር ሊዘልቅ የቻለው እስከ አምስት አመቱ ነበር። ቴዲም ከአባቱ ጋር አደገ።

ታዳጊው ቴዲ የሙዚቃ ፍቅር በውስጡ ተንሰራፍቶ ልቡን አሸፈተው…ጥበብ ገዛው!! ከወላጆቹ ግን ተቃውሞ ነበር የጠበቀው። ለሙዚቃ ያለውን ፍቅር ለአባቱ ለማሳየት በተደጋጋሚ ቢሞክርም ከአባቱ አበረታች ምላሽ አላገኘም።

ወላጆቹ ከጥበብ የልፋታቸውን ያላገኙ ሰዎች ስለሆኑ ወይም ከጥበብ ያተረፉት የሰውን አድናቆት እና ፍቅር ብቻ ስለሆነ የነሱ ጉዳት በልጃቸው እንዲደገም አልፈቀዱም። የወላጆቹ ተቃውሞ ቀጠለ። ነገር ግን ቴዲ ለራሱ ፍቃድ ሰጥቶ ወደ ጥበብ ባህር ጭልጥ ብሎ ገባ።

በአንድ አስገራሚ እለት እናቱ ራዬ በህመም አልጋ የያዘችውን እህቷን እያስታመመች ሳለ ፊቷን ወደ ተከፈተው ቴሌቪዥን ዞር ስታደርግ አይኖቿ የሚያዩትን ልታምን አልቻለችም። ልጇ ቴዲ “ትዝታ” የሚለውን ሙዚቃ እየተጫወተ ነበር። ተደነቀች!

ዘፈኑ ሲያበቃ እራስዋን ቴሌቭዥኑ ስር ተንበርክካ ነበር ያገኘችው። አባቱ ደግሞ ለስራ ጉዳይ ከአዲስ አበባ ውጪ ቆይቶ እንደመጣ የሜነጃይተስ ህመም አጋጥሞት የህክምና ክትትል አድርጎ ሻል ብሎት እንዳገገመ ነበር የአንድ ብቸኛ ልጁን ሙዚቃ ለመጀመሪያ ጊዜ ያዳመጠው።
በእርጋታ ደስታውን ገለፀ። በወዳጆቹ ልጁ ሲደነቅ ሲያይ ኩራት ተሰማው። ይሁን እንጂ አባቱ ካሳሁን ግርማሞ ቴዎድሮስ ካሳሁን በዘፈኖቹ ሀገር ሲነቀንቅ ለማየት አልታደለም።

ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ – 78 (PDF)

$
0
0

በሰሜን አሜሪካ ትልቁ የኢትዮጵያውያን ጋዜጣ የሆነችው ዘ-ሐበሻ የ8ኛ ዓመት ጉዞዋን ልትጀምር ነው:: እነሆ በአዲሱ ዓመት ዋዜማ በ32 ገጾች መረጃዎችን ይዛ በሚኒሶታና አካባቢው በሁሉም የኢትዮጵያውያን እና የምስራቅ አፍሪካ ንግድ ቤቶች ውስጥ ተቀምጣለች:: በዓለም አቀፍ ደረጃ በድረገጻችን ለምታነቡንም በፒዲኤፍ (PDF) ይዘንላችሁ ቀርበናል::

Zehabesha 78

ዘ-ሐበሻ – እውነት ያሸንፋል

የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት በሰፊው አደባባይ !! (አሌክስ አብርሃም)

$
0
0

የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት በሰፊው አደባባይ !!
ከኮንሰርቱ ጎን ለጎን ያለና የነበረውን እንጨዋወት ዘንድ ….
(አሌክስ አብርሃም)

11796256_1640024482947428_4244100396589286734_nእነሆ የጥበብ አጋርነታችንን ልንገልፅ ከብዙ መቶ ሽዎች ወገኖቻችን ጋር ቁመናል ….የድምፃዊ ቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ኮንሰርት በፌስቡል ዛሬ ማታ ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ ይከበራል !! በሚሊየን የሚቆጠሩ በመላው አለም የሚገኙ የፌስቡክ የቲውተር ተርቲበኞች ባሉበት ሰፊ እጅግ በጣም ሰፊ አደባባይ ላይ … የሰራን ልናሞግስ ኪነጥበብ ከየትኛውም የሰው ልጆች ተራ ጥላቻና ተንኮል በላይ መሆኗንም ልናሳይ ዘር ሃይማኖት ቦታ ሳይለየን በአዲስ አመት ዋዜማ ይሄው ፌስቡክ ላይ ሽክ ብለን ተገኝተናል !ቴዲ አፍሮን በስራው እንወደዋለን !! ይሄው ነው …ለምን ወደድነው ግን …??? ተዲ ዘፋኝ ስለሆነ ብቻ ነው ?….አይደለም!! ቴዲ ምርጥ ገጣሚ ስለሆነ ብቻ ነው ?….አይደለም !! ቴዲ በጥረቱ ታዋቂ ስኬታማ ስለሆነ ብቻ ነው ?… አይደለም !! ቴዲና ብዙሃኑ ኢትዮጲያዊ ወዳጆቹ ከዚህም የመረረ ትስስር ከዚህም ያለፈ የነብስ ወዳጀነት እንዲኖረን ያደረጉ ብዙ ምክንያቶች አሉን ……ከሙሉ ፍቅርና አክብሮት በድክመቱ እየወቀስን ብቃቱንም እናውጃለን …..

ማነህ ቁጠርልኝ …..አንድ በል ….እኛ ደሃ ህዝቦች ነን …ለስኳር የምንሰለፍ …ለታክሲ የምንሰለፍ በሊሞንዚን የምንታለፍ … ኪነጥበብ እኛን ለማስቀናት የተፈጠረች እስኪመስለን ሙዚቃዎቻችን ውስኪ መራጫ የቆንጆ ሴትና ሃብታም ኑሮ መፈንጫ ሁነው ሆድ ሲያስብሱን ይሄ ቴዲ አፍሮ የሚባል ልጅ መጣና ድህነታችንን ዘፈነው… እኛም ዘፋኞቻችንን ዝፈኑልን ሳይሆን እኛን ራሳችንን ዝፈኑን ነበር ያልነው ቴዲ ዘፈነን !! እኛን ሁኖ እኛን መስሎ ፍቅራችንን እንዳፈቀርናት አስቀመጣት ! ደስም አለን !!
ና ወዲህ ተባብለው በደላው መድረክ ተጋብዞ ተራምዶት እኛ ደሆቹ ጋር ባዶ ሜዳ ላይ ቁሞ ከድሃ ወገኖቹ ጋር …ብሶታችንን ሆድ ብሶት ዘፍኖልናል …. !! ብትፈልጉ ‹‹አርት ፖለቲክስ›› በሉት ቢያሻችሁ ያሻችሁን በሉት …ብቻ ቴዲ መድረክ ላይ እኛ ከስር ሳይሆን ….ቴዲ መሃላችን ተገኘ …እኛን ሆነ እኛም እሱን መሰለን !! ውቡን አዳራሽ ግድግዳና ጣራውን ትቶት መጣና….‹‹እደጅ አድራለሁ ኮከብ ስቆጥር !!›› አዳራሽ ውስጥ ተሁኖ ‹‹ኮከብ ሰዎች…ሃብታም ሰዎች ›› እንጅ የግዜር ኮከብ አይቆጠርማ ! ይመስክር ስቴዲየም …ውጭ አድረን ኮከቡን ከነጨረቃው ከነእግዜሩ እያን ደስስስስ ብሎን አመሸና ማን ጋር ቴዲ ጋር ! ያኔ ከወደዛ ግድም ርችት ወደሰማይ ሲተኮስ ከወደስቴዲየም የሽዎች የሃሴት ፈገግታ ምድሩን አንቆጥቁጦት ነበር …ደግሞኮ አላኮረፍንም … የኑሮ ልዩነቱን ወደአንድነት ጠራውና አስጠራን እንጅ …..እንዲህ ነበራ ቅኔው
‹‹ብንኮራረፍ ጠላት ይቃል
ያገርህ ሰርጓስ በማን ይደምቃል
አሳልፈናል ክፉ ደጉን …
ቃል ኪዳን አለን እንዳይለየን›› !
ሁለት በልልኝ …..መሸብን …ምሽታችን ሲከፋ ቴዲ በተሰጠው መክሊት ኤሎሄ ብሎ ኤሎሄ አስባለና …. ‹አይነጋም ወይ › ሲል …ከምር ግን አይነጋም እንዴ ብለን አብረነው ጮኸናል … ኤችሁ በተለይ ለአንዳንድ ልማታዊ ዘፋኞች ጨለማ ጥሩ ነው ክለብ እንዲሰሩ ይረዳቸዋል …የክለብ መብራት ንጋት መስሎት የማይዘናጋ ከክለቡ ውጭ ያሉ ሚሊየን ህዝቦች ጨለማ ውስጥ መቆማቸውን አስቦ ‹‹አይነጋም ወይ ›› የሚል የህዝብ ልጅ ነው አልን ….እሱማ ለቀን ጉርሱ ላመት ልብሱ አልጨለመበት ስለእኛ እንጅ !! እና ወደድነው ! በቃ ወደድነዋ!

ሶስት በልልኝ ….(ቁጥር እንዳታሳስት አንተ ልጅ ) ….ዘራፍ አሉና ስለእኛ የቆሙት ከእኛ ከራሳችን ጋር አጋጩን ….እልፍ ደም ፈሰሰ ህዝብ ከህዝብ ተለያየ …ሌሎችን ሊጫን የሚዳዳው ፖለቲካችን ጉልበቱ ይሄው ነው …..እልቂትና ማለያየት ! ባለትዳሮች ተለያዩ ሚስት ከባል ባሎች ከሚስት …. ልጆች ከወላጆቻቸው እናቶች ከልጆቻቸው ….ፍቅረኞች ከፍቅረኞቻቸው ተለያዩ ግማሹ እዛ ግማሹ እዚህ መሃል ላይ የፖለቲካ ተራራ …የናፍቆት እንባ ከድንበር ወዲያና ወዲህ ….ልክ በዚህ ሰዓት ወጣቱ የኪነጥበብ ሰው ቴዲ መጣና መለያየትን በዜማ ግሬደሩ ጠራርጎ በተለያየ ህዝብ መሃል የኪነጥበብ ሃዲዱን ዘረጋው….. እናም የፍቅር ባቡሩን ሸከተፍ እያደረገ ያውም ህዝቡን ጢም አድርጎ ጭኖ ዳህላክ ላይ ዝርግፍ !ከነፍቅር ቤት መስሪያው …… ቢያንስ በመንፈስ አገናኘን …እና ….ወደድነው …ወደድነዋ !!

አራት በል ቆጣሪ ….ግን ግዴለም አረፍ እያልን …ማታ ከመቶ ሽዎች ጋር ዘና ብለን እንጨዋወታለን ….እኔ የምልህ ግና አደባባዩን ሰፋ ሰፋ እድርገው ዛሬ ማታ ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ላይ ኮንሰርቱ እንደሚጀመርም ….በደንብ አሳውቅ …ቆይ እዚህ ላይ አንድ ነገር ልብ በል…ማንንም ከማንም ሳትለይ ሁሉንም ጋብዝ …ኪነጥበብ በፍቅር ሁሉንም መሳብ እንጅ መግፋት …አንዱን ስባ ሌላውን መግፋት አይሆንላትማ ጃ ! ወደፊት !!

ተሰፋ የቆረጡ ሰደተኞችን “የደበደበች’ ጋዜጠኛ

$
0
0

ከታምሩ ገዳ

ከርስ በርስ ጦርነት እና ከ አክራሪው የ አይ ኤስ ጥቃቶች ሸሽተው በምእራብ አውሮፓ ወስጥ ለመጠለል ሰሞኑን እንደጎርፍ የሚተሙት እና ተሰፋ ሰንቀው ቢጓዙም የተለያዩ በደሎች የገጠሟቸው የመካከለኛው ምስራቅ እና የአፍሪካ ሰደተኞች ሁናቴን በቴሊቭዥን መሰኮት ለተመለከተ ልቡ የማይነካ ሰብ አዊ ፈጡር ያለ አይመሰልም።

Journalist journalist 2

በተለይ ደግሞ ይህንን የዘመናችን ታላቅ የሰበአዊ ቀውስ እና ሰቆቃን ከሰፈራው ደረስ በመገኘት በምስል እና በደምጽ ቀረጸው ለተመልካቾች ፣ለአድማጮች እና ለአንባቢዊያን የሚያደረሱ ጋዜጠኞች ሃላፊነታቸው እና ሃዘናቸው ድርብ ድርብርብ ነው።ታዲያ በምስራቅ አውሮፓዊቷ ( በሃንጋሪይ) በኩል ወደ ምእረብ አውሮፓዎቹ እነ ጀርመን፣እንግሊዝ ፣ስዊድን የመሳሰሉት አገሮች ለመሸጋገር በደንበር ላይ የተኮለኮሉት በመቶዎች የሚገመቱ ተሰፋ የቆረጡ የሶሪያ ሰደተኞች ባለፈው ማክሰኞ ከሃንጋሪ ፖሊሶች ጋር በተፋጠጡበት ወቅት ሁኔታውን ለመዘገብ በርካታ አለም አቀፍ ጋዜጠኞች በሰፈራው ተገኝተው ነበር።

ይሁን እና ለሃንጋሪው በሄርተኛ እና ጸረ ሰደተኞች ለሆነው ቴለቪዥን( N1 TV ) ጋዜጠኛ እና ምስል ቀራጭ የሆነችው ፔትራ ላሳዛሎ አንድ ከሶሪያው ጦርነት ያመለጡ ዳግም ከሃንጋሪ ፖሊሶች ጋር የተጋፈጡ አባት ጨቅላ ልጃቸውን ታቅፈው ከፖሊሶቹ በመሸሽ ላይ ሳሉ የመቅረጫ ካሜራውን በምስኪኑ ስደተኛ ላይ ያነጣጠረች ጋዜጠኛ ተብዮዋ ፔትራ እግሯን (እንደ ካራቲስት) በመሰንዘር በሽሽት ላይ የነበሩ ሶርያዊው አባትን በመጥለፍ ሰደተኛው አባትም በጨቅላው እና በብርቅዩው ልጃቸው ላይ በመውደቃቸው ልጃቸው ምርር ብሎ ሲያለቅሰ እርሻቸውም ሲራገሙ ጋዜጠኛ ተብዩዋ ካሜራዋን ወድራ መቅረጿን አላቆመችም ነበር ።ከዚያም በሁዋላ ከፖሊስ ከበባ እና ወከባ ለማምለጥ የሞከሩ ሌላ አንዲት ልጃገርድ እና አንድ ጨቅላ ህጻንን በጠረባ በመምታት መጣሉዋን በምስል የተደገፉ ማሰረጅዎች አጋልጠዋታል።ግለሰቧ ቀደም ሲልም በርካታ የሶሪያ ሰደተኞችን ሳትደበደብ እና በእግሯ ሳትጠልፍ እንዳልቀረች ተገምቷል።

ይህንን 20 ሰኮንዶች የፈጀው ነገር ግን አሳዛኝ እና ሞራላዊነት የጎደለው ትውኔትን የጀርመኑ RTL ቴሌቭዥን ጋዜጠኛ ስቲፋን ሪቸር ምስሉን በቲዊተር አካውንቱ ላይ መለጠፉን ተከትሎ ደርጊቱ በመላው አለም በመሰራጨቱ የተገፉ ወገኖች አይን እና ጆሮ መሆን የነበረባት ነገር ግን በተቃራኔው በመቆም ፍጹም ሰበዊነት እና እርህራሄ የጎደላት ፔትራ ከተቀጠረቸበት የቴሊቭዥን ጣቢያ ጋር የነበራት የስራ ኮንትራትም ያለ ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ (በቅጽበት) ተቋርጧል ። ቀጣሪዋ ጣቢያም “አሳፋሪ እና ተቀባይነት የጎደለው ምግባር “ በማለት የውግዘት መግለጫ ወዲያውኑ አውጥቷል ። በርካታ ወገኖች ነዴታቸውን በግለሰቧ ላይ ያሰሙ ሲሆን በኣንድ ቀን ውስጥ ብቻ ከ 16ሺህ በላይ የፊስ ቡክ ተጠቃሚዎች “የማፈሪያ ግድግዳ “በሚል አዲስ አካዋንት ላይ በገለሰቧ ላይ የተሰማቸውን ቅሬታቸወን አስፍረዋል። ፔትራም ይህንን እኩይ ተግባር ለመፈጸም ምን እንደገፋፋት ኣስከ አሁን ድረስ አስተያየት አለሰጠችም። የአገሪቱም አቃቢ ህግም ግለሰቧን እንዴት እንደሚከሰስ ጉዳዩን “ሃሙስ እለት እያጠናው መሆኑን ይፋ አድርጓል።ጋከአገሪቱ ፖሊሶች በላይ የሰብአዊ መብት ረጋጭ ሆና የተገኘችው ጋዜጠኛ ተበዩዋ ጥፋተኛ ሆና ከተገኘች ሰዎች ላይ አካላዊ ጥቃት በመሰንዘር ወንጀል እስከ 5 አመት ወደ ኣስር ቤት ልትወረወር ትችላለች። የቀበጡ እለት ,,,, ይሉሃል ይሄኔ ነው።

የዘ-ሐበሻ የዓመቱ ምርጥ ሰው –ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ * አህመዲን ጀበል፣ ቴዲ አፍሮና ገንዘቤ ዲባባም በየዘርፉ አሸንፈዋል

$
0
0

ዘ-ሐበሻ ድረገጽ የዓመቱ ምርጥ ሰው በሚል አንባቢዎቿን በማሳተፍ ምርጫ ስታደርግ ይህ ለአምስተኛ ጊዜ መሆኑ ነው:: እስካሁን መምህር የኔሰው ገብሬ; ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ; ታጋይ አንዱአለም አራጌና አብርሃ ደስታ በተከተታይ ዓመታት የአመቱ ምርጥ ሰው ሽልማቶችን አግኝተዋል::

ዘንድሮ ለአንድ ወር ያህል ዘ-ሐበሻ የሕዝብ ድምጽን በስልክ; በቫይበር; በፌስቡክ; በኢሜይል እና በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ስትቀበል ነበር:: በሺህዎች የሚቆጠሩ የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች የ2007 የዓመቱ ምርጥ ሰው ይሁንልኝ ሲሉ ድምፃቸውን የሰጧቸው ሰዎች በርካቶች ነበሩ:: የዘ-ሐበሻ ኤዲቶሪያል ቦርድ ሁሉም የሕዝብ ድምጽ ቆጠራ ካደረገ በኋላ የሚከተሉት 10 ሰዎች ከፍተኛውን ድምጽ አግኝተዋል::

1ኛ. አህመዲን ጀበል
2ኛ. አንዳርጋቸው ጽጌ
3ኛ. ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
4ኛ. አቶ ነአምን ዘለቀ
5ኛ. አቡነ መቃሪዮስ
6ኛ. ገንዘቤ ዲባባ
7ኛ. ቴዲ አፍሮ
8ኛ. ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
9ኛ. ወይንሸት ሞላ
10ኛ. ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ናቸው::

ከ10ሩ እጩዎች ውስጥ ከፍተኛውን ድምጽ ያገኙትን በየዘርፉ ከፋፍለን አቅርበናቸዋል:: በዚህም መሠረት የዘ-ሐበሻ የዓመቱ ምርጥ ሰው የሚከተሉት ናቸው::

nega

የዓመቱ ምርጥ ሰው ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

በዘ-ሐበሻ አንባቢዎች ዘንድ ከፍተኛውን ድምጽ ያገኙትና የአመቱ ምርጥ ሰው የተሰኙት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ናቸው:: “ካሁን በኋላ ሰዎችን ሰብስቤ ማውራት ላቆም ነው” ባሉ በሁለተኛው ቀን ለነፃነታችን እየወደቅን እንታገላለን ብለው ጥሩ ኑሯቸውን ትተው በርሃ ወርደዋል::

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በ1958 ዓ.ም ደብረዘይት አካባቢ የተወለዱ ሲሆን ምንም እንኳ የተወለዱት ከሃብታም ቤተሰብ ቢሆንም አስተዳደጋቸው ግን ራሳቸውን ችለው እንዲያድጉ እየተማሩ ነው:: ይህንን ፕሮፌሰር ብርሃኑ በሃገር ቤት ለሚታተም ጋዜጣ በ1997 ዓ.ም ሲናገሩ “አባቴ ነጋ ቦንገርን ልጅ እያለሁ ሲኒማ ራስ ጥሩ የህንድ ፊልም ወጥቶ ለማየት ሳንቲም ስጠኝ ስለው ራስህ ሰርተህ ስታገኝ ትገባለህ ይለኝ ነበር” (ቃል በቃል የተወሰደ አይደለም) ይላሉ:: አባታቸው አቶ ነጋ ቦንገር ሲያሳድጓቸው በማሞላቀቅ ሳይሆን ራሳቸውን መቻል እንዳለባቸው በማስተማር ነበር:: ይህም ለፕሮፌሰሩ ስኬት ጠቅሟቸዋል::

ፕሮፌሰሩ ወደ ሳሪስ አካባቢ ግሎባል የሚባል ደረጃውን የጠበቀ ሆቴል ከፍተው የነበረ ቢሆንም በሽብርተኛነት በኢትዮጵያ መንግስት ከተከሰሱ በኋላ ይህ ሆቴል ተወርሷል::

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ወደ ትግሉ ዓለም የገቡት ገና የ17 ዓመት ወጣት በነበሩበት ወቅት ነው:: ያን ጊዜ ከኢህ አፓ ጋር በሚሰሩበት ወቅት ብዙ ምስጢሮች ባይነገራቸውም መኪና ይነዱ ስለነበር የኢሕአፓ አመራሮችን ከቦታ ቦታ በመውሰድ አገልግሎት ይሰጡ እንደነበር አብረዋቸው ይታገሉ የነበሩ ሰዎች ለዘ-ሐበሻ ይናገራሉ:: እንዲሁም ፕሮፌሰር ብርሃኑ በወቅቱ በኢህአፓ አመራሮች እርምጃ ሊወሰድባቸው ሲል በሱዳን በኩል አምልጠው እንደጠፉ ከታሪካቸው ያሰባሰብነው መረጃ ያመለክታል::

በሱዳን በኩል አድርገው አሜሪካ ከገቡም በኋላ ትምህርታቸው ላይ በማተኮር በከፍተኛ ማዕረግ የተመረቁ ሲሆን ኢህአዴግ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ ኢትዮጵያ ጠቅልለው በመግባት ሃገራቸውን ማገልገል ጀምረዋል:: ፕሮፌሰር በቅድሚያ ኢሕ አዴግን ለመለወጥ አዳዲስ ሃሳቦችን ቢያቀርቡም ኢህ አዴግ ግን የሚለወጥ ድርጅት ሊሆን አልቻለም:: በዚህም ተስፋ ሳይቆርጡ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች ማህበርን በመመስረት ብዙ አስተዋጽኦ አበርክተዋል::

ከምርጫ 2007 በፊት ፕሮፌሰር ብርሃኑ እና ፕሮፌሰር መስፍን በብሄራዊ ሎተሪ አዳራሽ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በመሰብሰብ ስለ ነፃነትና መብት ምንነት በሰፊው በሕዝባዊ ስብሰባ ይሰብኩ ነበር:: በርካታ ተከታዮችን እያፈሩ መምጣታቸው ያስፈራው መንግስት ሁለቱንም ታዋቂ ፖለቲከኞች ሕገመንግስቱን በኃይል ለመናድ በሚል አስሮ ሲያንገላታቸው ቆይቷል::

ምርጫ 1997 እየቀረበ ሲመጣ በየወሩ በሂልተን ሆቴል ኢትዮጵያ በ2020 በሚል ምሁራን እየተሰባሰቡ ኢትዮጵያ በ2020 ዓ.ም ምን መሆን እንዳለባት እንዲመካከሩ ያደርጉ የነበሩት ፕሮፌሰር ብርሃኑ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር በነበሩበት ወቅት ደመወዛቸውን ለችግረኛ ተማሪዎች ያከፋፍሉ እንደነበር ይነገራል::

ፕሮፌሰሩ ቀስተዳመና የተሰኘ ፓርቲ አቋቁመው ከኢድሊ ጋር በመተባበር ታላላቆቹን መኢአድና ኢዴፓ-መድህንን አንድ በማድረግ ቅንጅት ፓርቲ እንዲፈጠርና በምርጫ 97 ኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ ለውጥ እንዲፈጠር ጥረው ነበር:: በዚህም የአዲስ አበባ ከንቲባ ሆነው በሕዝብ ተመርጠው የነበረ ቢሆንም መንግስት በሃይል ያመጣሁትን ስልጣን በስኪብርቶ አለቅም በሚል የፖለቲካውን ምህዳር ዘግቶታል::

በዚህ ምርጫ ሰብሰብም ፕሮፌሰር ብርሃኑ እስር ቤት ተወርውረው ነበር:: ከ እስር ቤት ከወጡ በኋላም ሰላማዊ ትግል ብቻውን ለውጥ አያመጣም በሚል ወደ ሁለገብ ትግል በመሸጋገር ግንቦት 7ን መሰረቱ:: ግንቦት ሰባት በአሁኑ ሰዓት ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር እየተዋሃደ ትግሉ ወደ አንድ አቅጣጫ እንዲሸጋገር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ሰርተዋል:: ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ2007 የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች የአመቱ ምርጥ ሰውን ክብር ስላገኙ እንኳን ደስ ያለዎ::
genzebe 1
የዓመቱ ምርጥ ስፖርተኛ – ገንዘቤ ዲባባ

የ23 ዓመቷ አትሌት ገንዘቤ ዲባባ የዘ-ሐበሻ የዓመቱ ምርጥ ስፖርተኛ ሆናለች:: ገንዘቤ በ2007 ዓ.ም አመርቂ የሆነ ውጤትን አስመዝግባለች:: ባለፉት 8 ዓመታት የአትሌትነት ቆይታዋም በርካታ ድሎችን አጣጥማለች:: ገንዘቤን ዘንድሮ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ በርካታ ትልቅ ስፖርተኞች መካከል የሚያደርጋት በአንድ ሳምንት ውስጥ ሁለት የዓለም ክብረ ወሰኖችን መስበሯ ነው::

ባለፈው ጥር ላይ በስዊድን ስቶክሆልም ከ1993 ዓ.ም ጀምሮ ያለተሰበረውን የ3 ሺህ ሜትር ሩጫ ሪከርድ ሰብራለች:: እንዲሁም ይህን ድል ካጣጣመች ከ4 ቀን በፊትም እንዲሁ በ1500 ሜትርን ሪከርድ ሰብራለች:: አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው በፓሪስ የአምስት ሺህ የዳይመንድ ሊግ ውድድር በአንደኝነት ያጠናቀቀችውም በዚሁ በተሰናባችሁ 2007 ዓመት ሰኔ ወር ላይ ነበር:: ሰኔ 27፣2007 ምሽት በተደረገው 8ኛው ዙር የዳይመንድ ሊግ ውድድር ገንዘቤ ርቀቱን በ14 ደቂቃ ከ15 ሰከንድ ከ41 ማይክሮ ሰኮንድ በመግባት ነበር ያጠናቀቀችው፡፡ ገንዘቤ የእህቷን ጥሩነሽን ክብረወሰን ትሰብራለች ተብሎ ቢጠበቅም ሳይሳካላት ቀርቷል። የጥሩነሽ ክብረ ወሰን ለመስበር 4 ሰከንድ ብቻ ነበር የቀራት።

አትሌት ገንዘቤ ዲባባ ሞናኮ ውስጥ በተካሄደ የዳይመንድ ሊግ ውድድር በ 1500 ሜትር አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ያስመዘገበችውም በዚሁ ዓመት ሰኔ ወር ላይ ነበር::

ገንዘቤ በዚሁ በተሰናባችሁ 2007 ዓ.ም ቤጂንግ ላይ በተደረገው የዓለም ሻምፒዮና ላይ አንድ ወርቅ እና አንድ ነሃስ ሜዳሊያ ለሃገሯ ያስገኘች ጠንካራ አትሌት ናት:: የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች የዓመቱ ምርጥ ስፖርተኛ በሚል መርጠዋታል:: እንኳን ደስ ያለሽ::

teddy afro

የአመቱ ምርጥ አርቲስት – ቴዲ አፍሮ

ቴዲ አፍሮ “ሚስማር በመቱት ቁጥር ይጠብቃል” እንደሚባለው ሆኗል:: በመንግስት የሚደርስበት ጫና ይበልጥ ተወዳጅ እንዲሆን እያደረገው ነው:: በዚሁ ዓመት መጀመሪያ አካባቢ ላይ 70 ደረጃ የሚለውን ነጠላ ዜማ ከለቀቀ ወዲህ የሕዝብ ጆሮን አግኝቶ ነበር:: ጥቅምት 3 ቀን 2015 ዓ.ም ወደ ውጭ ሃገር ለኮንሰርት ዝግጅት ላይ በነበረበት ወቅት ድንገት ፖሊሶች አስረውት ነበር:: ምክንያታቸውም ከዚህ ቀደም ቴዲ አፍሮ- ከዓመታት በፊት የጎዳና ተዳዳሪ ገጭቶ ገድሏል የተባለበት ቢኤምደብሊው የቤት አውቶሞቢል ቀረጥ ሳይከፈልበት የገባ ነው በሚል በገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን መርማሪ ቡድን በቁጥጥር ሥር ዋለ:: በ30 ሺህ ብር ዋስም ተለቀቀ:: የሚገርመው ይህ ክስ ከብዙ ዓመታት በፊት መመስረቱ ብቻ ሳይሆን መኪናው በአሁኑ ወቅት በአርቲስቱ እጅ አለመኖሩም ጭምር ነው::

ቴዲ አፍሮ በዚህ ዓመት ‘አልሄድ አለ’ እና ‘ኮርኩማ’ አፍሪካ የተሰኙ መል ዕክት ያላቸውን ተወዳጅ ዘፈኖቹን አበርክቶልናል:: ሁለቱም ዘፈኖቹ እጅግ ተወዳጅ ሆነውለታል::

በዚህ ዓመት በቴዲ አፍሮ ላይ ከፍተኛ ጫና የተደረገበት ሲሆን ከዚህም ውስጥ የአውሮፓው ኮንሰርቱ እንዲስተጓጎል የተደረገበት ነው:: ከሃገር ሊወጣ ሲል ፓስፖርቱን ከሕግ ውጭ በደህንነቶች የተቀማው ቴዲ በአውሮፓ ማቅረብ የነበረበትን ኮንሰርት በዚህ ሳቢያ በመሰረዙ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል:: በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ሳይባል ደህነነቶች ‘ልክ እናስገባሃለን’ በሚል ፓስፖርቱን የተቀማው ቴዲ እየደረሰበት ያለውን ጫና ዘፈኑ ገልጾታል እየተባለ ነው:: “አልሄድ አለ” የሚለው ነጠላ ዜማውም ለራሱ የሰራው ነው እየተባለ ይነገራል::

ቴዲ በአዲስ ዓመት ዋዜማ በአዲስ አበባ ላፍቶ ሞል ሊያቀርበው የነበረው ኮንሰርቱ በፖሊስ ምክንያት እንዲሰረዝ ተደርጓል:: ለስርዓቱ ቅርብ የሆኑት ማዲንጎ አፈወርቅ እና አስቴር አወቀ ኮንሰርት እንዲያቀርቡ ሲፈቀድ ቴዲ በመከለከሉ የተቆጡት ኢትዮጵያውያን ኮንሰርቱን በፌስ ቡክ ለማድረግ ቆርጠው ተነስተዋል::

ቴዲ አፍሮ በዘ-ሐበሻ አንባቢዎች የአመቱ ምርጥ ሰው ሽልማትን አግኝቷል:: እንኳን ደስ ያለህ::

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

የዓመቱ ምርጥ ጋዜጠኛ – ሃብታሙ አሰፋ

የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች የዓመቱ ምርጥ ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ ሆኗል:: የኢትዮጵያ ነፃ ጋዜጠኞች ማህበር ከፍተኛ አመራር የነበረውና በሃገር ቤትም እንደነ መብረቅ/መብሩክ; ሩሕ; ሪፖርተር እና ሌሎችም ሚድያዎች ውስጥ ሲሰራ የነበረው ጋዜጠኛ ሃብታሙ በስደት ካይሮ ከቆየ በኋላ ወደ አሜሪካ ላስቬጋስ ከተማ ኑሮውን ካደረገ በኋላ ሕብር የተሰኘች ራድዮ መስርቶ ሙያውን ቀጥሎበታል::

ሃብታሙ አሰፋ ካለምንም የሕዝብ እርዳታ; በራሱ ጥረት በየሳምንቱ የሚያዘጋጃት ሕብር ራድዮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳጅ ሆና በአሁኑ ወቅት እንደ አማራጭ የመረጃ ምንጭነት ተቀምጣለች:: ከኪሱ እያወጣ በየሳምንቱ የተለያዩ ጉዳዮችን በማንሳት ከሃገር ቤትም ሆነ ከውጭ ሃገር ቃለምልልሶችን በማቅረብ ለኢትዮጵያ ህዝብ መረጃዎችን በማድረስ አኩሪ ሥራ ሰርቷል::

ሕብር ራድዮ በ2007 ዓ.ም እድገት ካሳዩ ሚዲያዎች መካከል አንዷ ስትሆን በድረገጽ; በሳውንድ ክላውንድ; በዩቲዩብ; በጎግል እና በአፕል አፖች እንዲደመጡ ጋዜጠኛ ሃብታሙ ትልቁን ሥራ ሰርቷል::

ከራድዮው ሥራ በተጨማሪም በተለይ ለተሰደዱና ለተጎዱ ጋዜጠኞች ሞራል በመስጠት; በማስተባበር ከጎናቸው በመቆም ያደረገው አስተዋጽኦ ይጠቀስለታል::

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋና ሕብር ራድዮ ሕዝቡ በቁሳቁስ ሊያግዛቸው ከቻለ እስካሁን ከሰሩት የበለጠ ሥራዎችን መሥራት እንደሚችሉ በየሳምንቱ እሁድ የሚያቀርቡት ፕሮግራሞች ይነግሩናል::

የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች የ2007 የዓመቱ ምርጥ ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ – እንኳን ደስ ያለህ::

hqdefault

የዓመቱ ምርጥ የሃይማኖት መሪ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል

ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በ1972 አ.ል በጂማ ከተማ ተወለደ፡፡ ኡስታዛችን ለቤተሰቦቹ የአራተኛ ልጅ ሲሆን ከህፃንነቱ ጀምሮ በሰዎች ዘንድ ፍፁም ዝምተኛና በፀባዩ ተወዳጅ ነበር፡፡ ኡስታዝ አህመዲን ከሰባ ወንድምና እህቶቹ ለወላጆቹ የተለየ ፈቅር ያለው ሲሆን በተለይ ለእናቱ ያለው ፍቅርና ታዛዥነት ከሌሎቹ ለየት ያደርገዋል፡፡

ኡስታዝ እድሜው ለትምህርት ሲደርስ 1ኛ ደረጃ ትምህርቱን ቄራ መለስተኛ ት/ቤት ይማራል፡፡ ኡስታዝ ከትምህርት ይልቅ የ mechanic ሙያን ይወድ ስለነበር ወደ እዚያው ያደላል፡፡ በዚህም የአስረኛ ክፍል ማትሪክስ ውጤት በመድገሙ አባቱ ከሙያ ትምህርቱ እንዲቆም በማድረግ ሙሉ ትኩረቱን ወደ መደበኛው ት/ት እንዲያደርግ ይመክሩታል፡፡ እናም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ጂማ high school እስከ 12ኛ ድረስ በመማር በከፍተኛ ውጤት አጠናቀቀ፡፡ ከፍተኛ ትምህርቱን በአዲስ አበባ 4 ኪሎ campus በ chemistry የትምህር ክፍል የመጀመሪያ ዲግሪውን የያዘ ሲሆን በመቀጠልም በ Arabic and litrecher ማስተርስ ዲግሪውን ይዟል፡፡

ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በ campus ውስጥ ለ6 አመታት የቆየ ሲሆን በነዚህ አመታት ውስጥ ከመደበኛ ትምህርቱ ጎን ለጎን የሙስሊም ተማሪ ጀመዓ አሚር በመሆን አገልግሏል፡፡ እንዲሁም ሙስሊሙ ህብረተሰብ ዘንድ ታዋቂና ተወዳጅ ያደረገውን “ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች” የሚለውን መፅሃፍ በግቢ ቆይታው አዘጋጅቷል፡፡ ኡስታዛችን በ6 ኪሎ campus በ history ማስተርሱን ሰርቷል፡፡ ከዚያ በኋላ ‹በሙስሊሞች ጉዳይ መፅሄት› እና በተለያዩ ድርጅቶች ሲሰራ ቆይቷል፡፡ በዚህም ብዙ መፅሃፎችን ለህትመት አብቅቷል፡፡ በራሱ ካሳተማቸው ውስጥ ‹የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የጭቆናና የትግል ታሪክ፤ የሴቶች መብት በመፅኃፍ ቅዱስና በቁርአን እንዲሁም 303 በክርስትና ዙርያ የሚነሱ ጥያቄዎች› የሚሉት ይገኙበታል፡፡ እንዲሁም ኡስታዝ አህመዲን ጀበል አሁን ላለው ኡማ እና ለቀጣዩ ትውልድ ብዙ መፃህፍቶችን በመተርጎም ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡

ኡስታዝ አህመዲን ጀበል የመጀመሪያ የዲን ቂርአቱን በጂማ ፍትህ መስጂድ በተለያዩ ኢማሞች ቀርቷል፡፡ እንዲሁም አዲስ አበባ እያለ በኡስታዝ ሸኽ ሀሰን ሀሚዲን እና ኡስታዝ ሀሚድ ሙሳ የተለያዩ የዲን ትምህርቶችን የቀሰመ ሲሆን በራሱም የተለያዩ ኪታቦችን በማገላበጥ እውቀቱን አዳብሯል፡፡

በአጠቃላይ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ከህፃንነቱ አንስቶ አሁን እስካለው የእድሜ ደረጃ ድረስ በባህሪው እጅግ ተወዳጅና የተከበረ ግለሰብ ነው፡፡ ለሰዎች ያለው አክብሮት፣ ለተቸገሩ ያለው አዘኔታ፣ ለታላቆቹ ያለው ታዛዥነትና ለታናናሾቹ ያለው አክብሮት በስነ-ምግባሩ የላቀ ያደርጉታል፡፡ ሲናገር በእርጋታ፣ ሲያስረዳ የማይቆጣ፣ ክርክርና ጥላቻን ከቀልቡ ያራቀ ድንቅ ግለሰብ ነው፡፡

ይህ ድንቅ የኢስላም ልጅ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ከአስራ ሰባቱ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች አንዱ ሲሆን ለሙስሊሙ ኡማ በትምህርት መልክ ሲሰጥ የነበረውን ዛሬ ላይ በተግባር እያሳየ ይገኛል፡፡ ኡስታዝ አህመዲን አሁን በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚገኝ ሲሆን በረመዳን ወር ላይ ከፍተኛ የሆነ ስቃይንና ፊትናን ቀምሷል፡፡ ኡስታዝ ዛሬ ለሁላችንም የሚሆን አርአያ መምህራችን ነው፡፡ ፈተና በመጣ ሰአት ከራሱ የበለጠ ለሙስሊሙ ኡማ የሚጨነቅ፣ ከነፍሱ ይበልጥ ለዲኑ የሚጨነቅና ከህይወቱ በላይ ኢስላምን የሚወድ ድንቅ መምህር፡፡ ይህንንም ዛሬ በተግባር እያሳየ ይገኛል፡፡ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በአንድ ወቅት እንዲህ ሲል ተናግሮ ነበር….
“ታሪክ ሰሪ እንጂ ታሪክ አንባቢ መሆን የለብንም…!”

አዎ! ዛሬ እርሱ ታሪክ ሰሪ ሁኗል፡፡ በኢስላም ላይ ያንዣበበውን አደጋ በመጋፈጥ፤ ለልጆቻችን ኢስላምን እንጂ አናወርስም በማለት የመጀመሪያው ድንቅ ሰው ነው፡፡ ማንም ያልሆነውን ስም ቢለጥፉበትም (አሸባሪ፣ አክራሪ፣ መንግስት ለመገልበጥ የሚሮጥ፣…..ሌላም ሌላም) እያሉ ቢጠሩትም ይህን አለመሆኑን ግን ራሳቸው ጠሪዎቹ ያውቁታል፡፡ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ሰላምን ተምሮ ሰላምን ያስተማረ፣ ሰላምን አውቆ ስለ ሰላም ያሳወቀ፣ ሰላምን በማሻተማር ላይ ህይዉን የመራ ድንቅ የኢስላም ልጅ ነው፡፡ በሰላም አደፍራሾች በተደበዱ ጊዜም፣ ኢስላም ላይ ዘመቻ በተከፈተበት ጊዜም፣ ጠላቶች በሃይል ኢስላምን ካልለቀክ እያሉ በሚያሰቃዩበት በዚህ በጭንቅ ጊዜም ሰላምን እንጂ ሌላን ያልሰበኩ ባለ ድንቅ ስብእና::

አህመዲን ጀበል እንኳን ደስ ያለህ::

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live